You are on page 1of 744

[Date]

ያልታተሙ የሰበር ውሳኔዎች በአንድ


ተሰብስበው የተዘጋጁ ከቅፅ 1-8
ስብስብ
በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃና የህግ አማካሪ)
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

…….CASSATION DECISIONS.....

….2013-2014 E.C...….

COMPILED BY-DANIEL FIKADU


/ATTORNY OF LAW/
Join us
https://t.me/joinchat/TDlwVN4QoPeK8
94b

https://m.facebook.com/groups/1928323
943874057/?ref=bookmarks

https://wordpress.com/home/lawethiopi
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 188271

ሀምሌ 27 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፊ

ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

ቀነአ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

አመልካቾች ፡-1ኛ. ወ/ሮ አስካለ ዘለቀ

2ኛ. ወ/ሮ ጽጌ ተስፋዬ ጠበቃ ዋቤ ሐጂ ከ1ኛ አመልካች ጋር ቀረቡ

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጽጌ ዘለቀ፡- ወኪል በቀለ ጉታ ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች በቀን 24/04/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ

ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 178872 በቀን 26/01/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ

ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የጀመረው በስር የፌደራል

መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካቾችና በዚህ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ያልሆኑት ዋና ሳጅን ደረሰ

ዘለቀ ከሳሾች ነበሩ፤ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ፡፡

ከሳሾች በቀን 07/03/2010 ዓ.ም በተፃፈ የውርስ ይጣራልን አቤቱታ የሟቾች አቶ ዘለቀ በቀለ እና

ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማ የመጀመሪያ ደረጃ እና ተተኪ ወራሾች መሆናቸውን፤ በመግለጽ ውርስ እንዲጣራላቸው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ 190228

ቀን ሀምሌ 26 2013ዓ.ም

ዳኞች፡ ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካቾች፡ 1ኛ. አቶ ቶፊቅ መሀመድ

2ኛ. አቶ ሽኩር ረዲ ጠበቃ ወንድወሰን ሂርጶ ቀረቡ

ተጠሪ፡ የኢፌዲሪ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን፡- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ የቀረበው አመልካቾች የፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ
አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 00027 በ26/4/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 169910 በ30/4/12ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ19/5/12ዓ.ም በተጻፈ
የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ በስር የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዳኝነት ችሎት በአመልካቾች
ላይ ባቀረበው ክስ የግል ተበዳይ የሆነው የK.C.J ካምፓኒ ወኪል ጆሽ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የድርጅቱን እቃዎች ከሌሎች ለመለየት የሚያስችል EVEREST (ኤቨረስት) የሚል የማይዳሰስ ንብረት ምስል
ባለቤት ነው፡፡ EVEREST የንግድ ምልክት በቃላት ብቻ ያልተገደበ የቅርጽና የምስል ነጻነትን ምናባዊ ይዘት
በመፍጠር ከምርትና አገልግሎት ጋር ካለው ጥምረት አንጻር ከ1982ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ መገበያያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስፍራዎች በመግባት በገነባው መልካም ስም የሸማቹ ማህበረሰብን ምርጫ የመምራት አቅም ፈጥሯል፡፡
ሆኖም የኤቨረስት የንግድ ምልክትና የአመልካቾች የምርት ማሸጊያ መጠን፤ በማሸጊያው ላይ ባረፈው የሴት
ምስል እና በአብዛኛው ደረጃ አደናጋሪ ሆኖ እያለ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥበቃ ያልተደረገለትን የምርት ማሸጊያ
ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት 1ኛ አመልካች ከ2006ዓ.ም ጀምሮ ተስመስ ቆንጆ የሚባል የምርት ማሸጊያ
ዲዛይን አመሳስሎ በማምረት እንዲሁም 2ኛ አመልካች የዚሁን አይነት ተመሳሳይ ምርት ከ2008ዓ.ም ጀምሮ
ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ሸማቹ ማህበረሰብን የሚያደናግር ምርት በመሸጥ ላይ የሚገኙ በመሆናቸውና
የምርት ማሸጊያው እቃው ምልክት እና የሚኖረው አገልግሎት ተመሳሳይና አደናገሪ በመሆኑ ምክንያት
አመልካቾች እየፈጸሙ የሚገኘው ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተግባራቸውን እንዲያቆሙ ትእዛዝ
እንዲሰጥልን እንዲሁም አመልካቾች ለፈጸሙት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተግባር ከአመታዊ ሽያጭ
ገቢያቸው 10% እንዲቀጡ ውሳኔ እንዲሰጥልን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችንም
አያይዞ አቅርቧል፡፡

አመልካቾች ባቀረቡት መልስ በK.C.J ካምፓኒ ተመዝግቧል የተባለው EVEREST (ኤቨረስት) የተሰኘው
የቃል የንግድ ምልክት ነው፡፡ በክሱ በምስልና በቃል ብቻ ያልተገደበ የቅርጽ ነጻነትንም ያካተተ ነው በሚል
የቀረበው በማስረጃ ያልተደገፈ ነው፡፡ የምዝገባ የምስክር ወረቀቱ ላይ ምስልና ቅርጹ ጥበቃ አልተሰጠውም፡፡
በንግድ ምልክትና ጥበቃ አ/ቁ 501/98 አንቀጽ 4 መሰረት የንግድ ምልክት ባለቤትነት የሚገኘውና በ3ኛ
ወገን ላይ ተፈጸሚነት የሚኖረው ሲመዘገብና የምስክር ወረቀት ሲሰጥ ነው፡፡ K.C.J ካምፓኒ የተጣሰበት
የጸጉር ማቅለሚያ ሂና ማሸጊያ ምስልና ቅርጽ ላይ መብት የለውም፡፡ በአ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(1)፤ 8(2)
ሀ እና ለ መሰረት ያልተገባ የንግድ ውድድር አለ የሚባለው ከሀቀኝነት ውጪ የማታለል ስራ፤ የተወዳዳሪን
ጥቅም ሊጎዳ የሚችል ተግባር መፈጸም ፤የማደናገር ተግባር እንዲሁም የማደናገር ድርጊት ወይም የሌላውን
ነጋዴ መረጃ ማውጣት እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም አመልካቾች በህጋዊ የምዝገባ ሂደት ባገኙት ህጋዊ
የንግድ ምልክት እቃዎችን ከመሸጥ ባለፈ የፈጸሙት ህገወጥ ድርጊት ስለመኖሩ ማስረጃ አልቀረበም፡፡
የቀረበው ክስ አመልካቾች በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ለማድረግና ተጠሪ በመስኩ ብቸኛ ነጋዴ ሆኖ
ለመቆየት አልሞ ያቀረበው በመሆኑ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል፡፡ ክስ የተነሳበት ምርት በማሸጊያው ላይ
ያለው ምስል እና ቅርጽ ለጥበቃ ብቁ አይደለም፡፡ በአመልካቾች የንግድ እቃዎች ጥቅም ላይ የዋሉት ተስመስ
ቆንጆ እና መልካማ የተሰኙት የንግድ ምልክቶች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኙና ህጋዊ ጥበቃ ያላቸው
ናቸው፡፡ ተስመስ ቆንጆ፤ ኤቨረስት እና መልካማ በሚሉት የንግድ ምልክቶች መካከል የአጻጻፍም ሆነ
በትርጉም ሊያሳስት የሚችል ተመሳሳይነት የለም፡፡ የጸጉር ማቅለሚያ ሂናዎችን የሚጠቀሙ አብዛኛው
የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ያላቸውና የሚፈልጉትን የምርት አይነት ለይተው የሚያውቁ እንደሆኑ
ይገመታል፡፡ ስለሆነም በንግድ ምልክቶቹ መካከል መመሳሰል የሌለ በመሆኑ ሸማቹን አያደናግርም፡፡ ተጠሪ
ያቀረበው የውጪ ሀገር የምዝገባ ምስክር ወረቀት በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት እስካልተመዘገበ
ድረስ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የሰጣቸው ማብራሪያዎች በአዋጁ
እንዲያስፈጽመው ከተሰጠው ስልጣን ጋር የማይሄድ ከመሆኑም በተጨማሪ የንግድ ምልክቶች ያደናግራሉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወይም አያደናግሩም ብሎ የመወሰን ስልጣን የአንድ አስፈጻሚ ስልጣን ሳይሆን የፍርድ ቤቶች ስልጣን ነው፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በመ.ቁ 145383 በ24/8/10ዓ.ም አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት ጉዳይ
በመሆኑ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ጠይቀዋል፡፡ የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎችንም አያይዘው
አቅርበዋል፡፡

ችሎቱም 1ኛ. አመልካቾች አ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(1) እና 8(2)(ሀ) እና (ለ)ን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ
የንግድ ውድድር ፈጽመዋል ወይስ አልፈጸሙም? 2ኛ. አመልካቾች ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር
ፈጽመዋል የሚባል ከሆነ ሊሰጥ የሚገባው ዳኝነት ምን መሆን አለበት? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ
ግራቀኙን በቃል ካከራከረ፤ የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የመጀመሪያውን ጭብጥ
በተመለከተ በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(1) ማንኛውም ነጋዴ በንግድ ስራ
ሂደት ውስጥ ማናቸውም ሀቀኛ ያልሆነ፤ አሳሳች ወይም አታላይነት ያለበትና የተወዳዳሪን የንግድ ጥቅም
የሚጎዳ ወይም ሊጎዳ የሚችል ተግባር መፈጸም እንደማይችል ከደነገገው አንጻር በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ
የግል ተበዳይ ብሎ ያቀረበው የK.C.J ካምፓኒ ወኪል ጆሽ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የጸጉር
ማቅለሚያ ምርቶችን ከውጪ እያስመጣ የሚሸጥ ሲሆን ለምርቱ የንግድ ምልክት የቃል ጥበቃ ከኢትዮጵያ
አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በ1/9/08ዓ.ም ተሰጥቶታል፡፡ በተመሳሳይ 1ኛ አመልካች TSMSSKONJO የሚል
የቃልና የምስል የንግድ ምልክት ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በ22/9/08ዓ.ም እንዲሁም 2ኛ
አመልካች MELKAMA የሚል የቃል የንግድ ምልክት በ4/10/08ዓ.ም ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት
ጥበቃ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የንግድ ስራቸውን እያከናወኑ ያሉትም ይህንኑ የንግድ ስማቸውን
እየተጠቀሙ መሆኑን አመልካቾች ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪም ያቀረበው ክርክርና ማስረጃ ይህንኑ የሚያረጋጋጥ
በመሆኑ ከዚህ አንጻር አመልካቾች ተጠሪ ጥበቃ ያገኘበትን EVEREST የሚል የንግድ ምልክት
እንዳልተጠቀሙ ያስገነዛባል፡፡

ግራቀኙ ካቀረበት ክርክር አንጻር ተጠሪ በተባለው የምርት ማሸጊያ ላይ ሌሎች እንዳይጠቀሙበት ለመከልከል
እና በብቸኝነት ለመጠቀም የሚያስችል መብት አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለው ነጥብ ሲታይ በንግድ
ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አ/ቁ 501/98 መሰረት የንግድ ምልክት ምዝገባ ያገኘ ማንኛውም ባለመብት ሌላ 3ኛ
ወገን በንግድ ምልክቱ እንዳይጠቀም ለማገድ መብት እንደሚያስገኝለት ከደነገገው አንጻር በተያዘው ጉዳይ
ተጠሪ ለምርቱ መለያ በንግድ ምልክትነት ያስመዘገበው የምርቱን ስያሜ የሚያመላክት Everest የሚል ቃል
እንጂ የምርት ማሸጊያውን ዲዛይን እና በምርቱ ላይ ያለውን ምስል አይደለም፡፡ ምንም እንኳ የተጠሪ
ምስክሮች የማሸጊያ ዲዛይኑና ምስሉ ተመዝግቦልናል ያሉ ቢሆንም ተጠሪ ይህን የሚያስረዳ የሰነድ ማስረጃ
አላቀረበም፡፡ ተጠሪ ያቀረበው ማስረጃም Everest የሚል የቃል ጥበቃ ያገኘበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት
ነው፡፡ ሌላው ተጠሪ ያቀረበው ማስረጃ ከህንድ ሀገር የተሰጠ የጥበቃ ሰርተፍኬት በኢትዮጵያ ውስጥ
ለኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ቀርቦ ያልጸደቀ በመሆኑ ህጋዊ ማስረጃ ነው ተብሎ አይወሰድም፡፡
በአንጻሩ አመልካቾች እና የአመልካቾች ምስክሮች ማሸጊያው የወል ወይም የጋራ መጠቀሚያ መሆኑን
መስክረዋል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ በ3ኛ ወገኖች ላይ ክስ ሊያቀርብ የሚችለው ጥበቃ ያገኘበት የቃል የንግድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ምልክት ተጥሶ ሲገኝ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ተጠሪ አመልካቾች Everest የሚለውን የቃል የንግድ ምልክት
እየተጠቀሙ የጸጉር ማቅለሚያ ምርትን ለገበያ እያቀረቡ ስለመሆኑ አላስረዳም፤ በሌላ በኩል አመልካቾች
ለምርቱ እየተጠቀሙ የሚገኙት TSMSSKONJO እና MELKAMA የሚሉ መጠሪያዎችን በመጠቀም
መሆኑን የተጠሪ እና የአመልካቾች ምስክሮች አስረድተዋል፡፡

የአመልካቾች ድርጊት ሸማቹን ያደናግራል ወይስ አያደናግርም የሚለውን ነጥብ በተመለከተ በዋናነት የጸጉር
ማቅለሚያ የሚጠቀመው የህብረተሰብ ክፍል የትኛው ነው የሚለው ሲታይ የተጠሪ ምስክሮች ሁሉም
አይነት ሸማች ምርቱን ይጠቀመዋል ያሉ ሲሆን የአመልካቾች ምስክሮች የጸጉር ማቅለሚያ መሰረታዊ
የሚባል ሳይሆን የቅንጦት እቃ ነው፤ ምርቶቹንም የሚጠቀሙት የህብረተሰብ ክፍሎች በአብዛኛው የተሻለ
የግንዛቤ ደረጃ ያላቸውና ምርቶችን በማሸጊያው ብቻ አይተው የሚገዙ ሳይሆን በስም ለይተው የሚገዙ
ናቸው የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡ በዚህ ረገድ ምርቱን የሚጠቀሙት የህብረተሰብ ክፍሎች ወይም
ሸማቾች የትኞቹ ናቸው የሚለው ሲታይ የጸጉር ማቅለሚያ መሰረታዊ ፍላጎትን ለማማላት የሚውል ምርት
ሳይሆን ለተጨማሪ ውበት መጠበቂያነት የሚውል እንደመሆኑ ምርቱን የሚጠቀሙት የህብረተሰብ ክፍሎች
በሚጠቀሙት ምርት ምንነት ላይ ግንዛቤ ያላቸው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ
የሚፈልጉትን ምርት በስም ለይተው ለመግዛትና ለመጠቀም የሚችሉ ናቸው፡፡ ተጠሪም ቢሆን የአመልካቾች
ድርጊት ሸማቹን የሚያደናገር ነው ከማለት በስተቀር ያቀረበው ማስረጃ የለም፡፡ ስለሆነም የአመልካቾች
ድርጊት ሸማቹን የሚያደናግር ድርጊት ነው የሚባል ባለመሆኑ አመልካቾች የንግድ ውድድርና ሸማቾች
ጥበቃ አ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(2)(ሀ)ን በመተላለፍ የፈጸሙት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር የለም፤
በመሆኑን ወደ ሁለተኘው ጭብጥ መግባት ሳያስፈልግ ተጠሪ አመልካቾች ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር
ፈጽመዋል በሚል ያቀረበውን ክስ በማስረጃ ስላላስረዳ በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡

ተጠሪ ከላይ በተገለጸው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ
አስተዳደራዊ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ የግራቀኙ ክርክርን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ
ከአእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለው የጽ/ቤቱ የንግድ ምልክትና ኢንዱስትሪ ንድፍ
ልማት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት የንግድ ምልክት ምርመራ ከፍተኛ ባለሙያ እንዲቀርብ በማድረግ ምዝገባ
ሳያደርግ የመጠቀም መብትን በሚመለከት ሙያዊ ምስክርነት እንዲሰጥ ከፍ/ቤቱ ለቀረበለት የማጣሪያ ጥያቄ
ባለሙያው የሰጠውን ምላሽ ተቀብሎ እንዲሁም በስር ፍ/ቤት በማስረጃ ዝርዝር ፊደል (ለ) ላይ የተገለጸው
ኤግዚቢት በፍ/ቤት ቀርቦ እንዲታይ ካደረገ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የስር ፍ/ቤት የተጠሪን ክስ ውድቅ
በማድረግ ለደረሰበት ድምዳሜ መነሻው ተጠሪ የንግድ ምልክት ጥበቃ ያገኘው ኤቨረስት በሚል ስም ሲሆን
በተመሳሳይ የንግድ ዘርፍ ተሰማርተው ማደናገር ፈጽመዋል የተባሉት የአመልካቾች ድርጀት ስም ደግሞ
ቆንጆ እና መልካማ የሚል መጠሪያ ነው ያላቸው፤ ስለዚህ ስማቸው ኤቨረስት ከሚለው ስም ጋር ምንም
አሳሳች ነገር የለውም፤ በተጨማሪም ይህን የጸጉር ማቅለሚያ ምርት የሚጠቀሙ ሸማቾች ከመደበኛ
ማህበረሰብ የተሻለ ግንዛቤ እና አቅም ያላቸው በመሆኑ የሚገዙትን ምርት በሚገባ የተረዱ ናቸው፡፡ ስለዚህ
በምርቱ ዙሪያ መደናገር አይገጥማቸውም፤ የምርቱ ማሸጊያ መልክና ቀለም ምዝገባ ያልተሰጠው በመሆኑ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጥበቃ አለው ሊባል አይችልም በሚል ነው፡፡ በስር ፍ/ቤቱ የተሰሙት የተጠሪ ምስክሮች የኤቨረስት የጸጉር
ቀለም ማሸጊያ ከቆንጆና መልካማ የጸጉር ቀለም ማሸጊያ ጋር በጣም የሚመሳሰል በመሆኑ በሸማቾች ላይ
ማደናገር እያስከተለ መሆኑን እንደ አንድ ሸማች ጭምር እንደሚያውቁ እና ሸማቾችም ችግር
እንደገጠማቸው እንደገለጹላቸው መስክረዋል፡፡ በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በቁ.
አጠ28/662-11 በ26/12/08ዓ.ም ለአዲስ አበባ ፓሊስ እንዲሁም በቁ. አጠ28/119-660/08 በ26/12/08ዓ.ም
እና በቁ. አጠ28/560-104/08 በ1/11/08ዓ.ም ለንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ዋና ባለስልጣን በዋና
ዳይሬክተሩ የተጻፉት ደብዳቤዎች የኤቨረስት የጸጉር ቀለም ማሸጊያ ከቆንጆና መልካማ የጸጉር ቀለም ማሸጊያ
ጋር አብሮ ቀርቦ ቢታይ በአብዛኛው በሚባል ደረጃ የመጠን፤ የፊደላት ቀለማትና በአጻጻፍ ዘዴ በመደቦች
ቀለማት፤ በማሸጊያው ላይ ባረፈው የሴት ምስል… እንዲሁም በአጠቃላይ የቀለም ቅንጀት ተመሳሳይ
በመሆኑ በገበያ ውስጥ ቢገባ ሸማቹን ሊያደናግር እንደሚችል በዚህም ምክንያት የአንድ ድርጀት ምርት
እንደሚመስሉ ይገልጻሉ፡፡

ተጠሪ ባቀረበው ክስ በአ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(2)(ሀ) መሰረት መደናገር በስም ብቻ ሳይሆን በማናቸውም
ሁኔታ ስለመሆኑ፤ እንዲሁም ኤቨረስት የጸጉር ቀለም የምርቱን ማሸጊያ ከ1982ዓ.ም ጀምሮ ከቆንጆ እና
መልካማ በፊት በቀደምትነት የሚጠቀምበት በመሆኑ በመጠቀም የጥበቃ መብት አለኝ በማለት የተከራከረ
ሲሆን በአመልካቾች በኩል ደግሞ ጥበቃ የሚገኘው በአ/ቁ 501/98 አንቀጽ 4 መሰረት በማስመዝገብ ስለሆነ
ያልተመዘገበ የንግድ ምልክት ሌላው እንዳይጠቀምበት ለመከላከል የሚያስችል መብት አይሰጥም በሚል
ተከራክሯል፡፡ ሆኖም በስር ፍ/ቤቱ በጽሁፍ ማስረጃነት ከአእምሯዊ ንብረት ምዝገባ ጽ/ቤት በቁ. አጠ28/560-
104/08 በ1/11/08ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በንግድ ምልክት ላይ ያለ መብት በመሰረታዊ ደረጃ ከመመዝገብ
የሚመነጭ ቢሆንም ሳይመዘገብ ለረጅም ግዜ ግልጋሎት ላይ የዋለ የንግድ ምልክትም ቢሆን ለባለቤቱ
መብትን የሚያጎናጽፍ መሆኑ በንግድ ምልክት አዋጁ ላይ የተለያዩ ቦታዎች ተጠቅሶ እንደሚገኝ እና የንግድ
ምልክት ህግ ሳይንስም ይህን እንደሚያረጋግጥ የተመለከተ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም በይግባኝ
ሰሚው ፍ/ቤት በማጣሪያ ምስክርነት የቀረቡት ባለሙያ ይህንኑ ሃሳብ በሚያጠናክር መልኩ የምስክርነት
ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የኤቨረስት የጸጉር ቀለም ማሸጊያ ባለቤት K.C.J ካምፓኒ ከ1982ዓ.ም
ጀምሮ በማሸጊያው ይጠቀም እንደነበር ሲታይ በ2006ዓ.ም እና 2008ዓ.ም የኤቨረስት ባለቤት K.C.J መብት
እንዳለው ያስገነዝባል፡፡ በኤግዚቢትነት ለፍ/ቤቱ የቀረቡት የኤቨረስት፤ የመልካማ እና የቆንጆ የጸጉር ቀለም
መያዣ ምርቶች ማሸጊያዎች ፍ/ቤቱ እንደተመለከተው ከስማቸው መለያየት በስተቀር በሌላው ይኅውም
በማሸጊያው መጠን፤ የፊደላት ቀለማት፤ የመደቦች ቀለማት፤ የማሸጊያው ቀለም፤ በማሸጊያው ላይ ያረፈው
ፎቶ… ተመሳሳይነት እንዳለው እና አንዱን ከአንዱ ለመለየት አስቸጋሪ መሆኑን ያስገነዛባል፡፡

የአመልካቾች ምስክሮች የጸጉር ማሸጊያ ቢመሳሰሉም የፈለጉትን የምርት አይነት በስሙ ለይተው መግዛት
እንደሚቻል የገለጹ ሲሆን 3ኛ ምስክራቸው የተጠሪ የጸጉር ቀለም ማሸጊያ ከአመልካቾች የጸጉር ቀለም
ማሸጊያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚመሳሰሉ እና በዚሁ ምክንያትም ሊያደናግሩ እንደሚችሉ
እንደሚያደናግሩ የገለጹ ከመሆኑም በተጨማሪ ከላይ የተገለጹት የአእምራዊ ንብረት ጽ/ቤት በተለያዩ ቀናት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በጻፋቸው ደብዳቤዎች ላይ የአመልካቾች የምርት ማሸጊያ ከተጠሪ የምርት ማሸጊያ ሙሉ በሙሉ


የሚመሳሰሉ እና ሸማቹንም የሚያናግሩ፤ ሊያደናግሩ የሚችሉ መሆኑን ዝርዝር ማብራሪያ ገልጿል፡፡ ሆኖም
የስር ፍ/ቤት ይህን የጽሁፍ ማስረጃ ለምን እንዳልመዘነው ወይም እንዳልተቀበለው በውሳኔው ላይ
አልገለጸም፡፡ በአመልካቾች በሰነድ ማስረጃነት የቀረቡትን በወንጀል ጉዳይ የተሰጡትን ውሳኔዎች በተመለከተ
የወንጀልና የአስተዳደራዊ ጉዳዮች የማስረጃ ምዘና የሚለያይ ከመሆኑም በተጨማሪ በወንጀል ነጻ መባል
ከአስተዳደራዊ ተጠያቂነት ነጻ እንደማያደርግ የወንጀል መርህ ከደነገገው አንጻር ማስረጃው ሚዛን የሚደፋ
ሆኖ አልተገኘም፡፡

የስር ፍ/ቤቱ የምርቱ ተጠቃሚዎች የተሻለ ግንዛቤ ያላቸው ያላቸው በመሆኑ በምርቱ ማሸጊያ መመሳሰል
መደናገር አይኖርም የሚለው መደምደሚያ የሀገሪቱን ማህበረሰብ ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘበ እና በጥናት
ላይ ያልተመሰረተ በግለሰብ ሀሳብ ላይ ብቻ የተመሰረተ ከመሆኑ አንጻር፤ የተሻለ አረዳድ ያለው የመንግስት
መስሪያ ቤት የሰጠውን መረጃ ሳይመዝን የደረሰበት በመሆኑ እንዲሁም የአ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(2)(ሀ)ን
ድንጋጌ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ተጠሪ ክሱን በሚገባ አላስረዳም ሲል የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፡፡
ስለሆነም በተጠሪ በስር ፍ/ቤት በቀረቡት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሁም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት
በኤግዚቢትነት ባስቀረባቸው ምርቶች እና የባለሙያ ምስክርነት አመልካቾች በአ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8 (1)
እና 2(ሀ) የተደነገገውን በመጣስ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር የፈጸሙ መሆናቸውን ተጠሪ በበቂ ማስረጃ
ያስረዳ ስለሆነ አመልካቾች ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ተግባር ፈጽመዋል በማለት እንዲሁም
አመልካቾች ጥፋተኞች ናቸው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የስር የዳኝነት ችሎቱ የተጠሪን ክስ
ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የግራቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ በአ/ቁ 813/2006
አንቀጽ 42(3) መሰረት አመልካቾች እያንዳንዳቸው የአመታዊ የሽያጭ ገቢያቸውን 5%(አምስት በመቶ)
የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ በማለት ወስኗል፡፡ እንዲሁም የአመልካቾች ድርጅቶች የሚጠቀሙበት የጸጉር
ቀለም ማሸጊያዎች ከኤቨረስት የጸጉር ቀለም ማሸጊያ በመጠን፤ በፊደላት፤ ቀለማትና በአጻጸፍ ዘዴ፤
በመደቦች ቀለማት፤ ማሸጊያው ላይ ባረፈው የሴት ምስል …. በአጠቃላይ የቀለሞች ቅንጅት ተመሳሳይነት
ያለው በመሆኑ በገበያ ውስጥ ሸማቾችን የሚያደናግርና ሊያደናግር ስለሚችል እንዳይጠቀሙ በማለት
ወስኗል፡፡

አመልካቾች ከላይ በተገለጸው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ስሚ ችሎት
አቅርበው ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አ/ቁ 813/2006 መሰረት
አመልካቾች የማደናገር ሁኔታ ያስከተለ ተግባር ፈጽመዋል አልፈጸሙም የሚለው የማስረጃ ጉዳይ በመሆኑ
የባለስልጣኑ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በቁ. አጠ28/662-11
በ26/12/08ዓ.ም ፤ በቁ. አጠ28/119-660/08 በ26/12/08ዓ.ም እና በቁ. አጠ28/560-104/08 በ1/11/08ዓ.ም
የተጻፉትን ደብዳቤዎች፤ ከንግድ ምልክትና ኢንዱስትሪ ንግድ ልማት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሰጠውን
ምስክርነት እና ምርቶችን በኤግዚቢትነት በማስቀረብ የ EVEREST የጸጉር ቀለም ማሸጊያ ከቆንጆና መልካማ
የጸጉር ቀለም ማሸጊያ በአብዛኛው ደረጃ የመጠን፤ የፊደላት፤ ቀለማትና የአጻጻፍ ዘዴ በመደቦች ቀለማት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በማሸጊያው ላይ ባረፈው የሴት ምስል… ተመሳሳይ መሆናቸውን ያረጋገጠ መሆኑን ከችሎቱ ውሳኔ መረዳት
የተቻለ በመሆኑ የባለስልጣኑ ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካቾች የአ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(1) እና 8(2) ሀ
እና ለን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ፈጽመዋል በማለት የአመታዊ ሽያጭ ገቢያቸውን
5%(አምስት በመቶ) የገንዘብ ቅጣት እና አመልካቾች የሚጠቀሙበትን የጸጉር ቀለም ማሸጊያዎች
እንዳይጠቀሙ መወሰኑ አግባብ ነው በማለት የስር የፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ
ሰሚ አስተዳደራዊ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል፡፡

የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከላይ የተገለጹትን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም በአጭሩ ተጠሪ
አላግባብ ተበዳይ ነኝ ያለው የኬሲጄ ካምፓኒ ያስመዘገበውን EVEREST በሚለው የጸጉር ቀለም ምርት ላይ
የተረጋገጠለትን መብት የስር ፍ/ቤት ሳያረጋገጥ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ፈጽማችኋል በማለት
የሰጠው ውሳኔ፤ ለክርክር መነሻ የሆነውን ምስል እና ማሸጊያ እንዳንጠቀም እንዲሁም አመልካቾች
እያንዳንዳችን የአመታዊ ሽያጫችንን 5% እንድንቀጣ የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮ የስር የንግድ ውድድርና
የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዳኝነት ችሎት የሰጠው ውሳኔ እንዲጸናልን፤ ወጪና ኪሳራም እንዲከፈለን
እንዲወሰንልን የሚል ነው፡፡

ይህ አቤቱታቸው በሰበር አጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ አመልካቾች አከራካሪው የንግድ ምልክት በህጋዊ አካል
ተመዝግቦላቸው ባለበት እና ምንም ተቃውሞ ባልቀረበበት ሁኔታ፤ የንግድ ስራቸውን እየሰሩ ባለበት ሁኔታ፤
ከሌላው ተመሳሳይ የንግድ ምልክት ካለው በተለየ እነሱ ብቻ ተለይተው የንግድ ስራ መስራት አትችሉም
የተባለበት ከአዋጁ አንቀጽ 2፤ 12 እና 4 እንዲሁም ከህገመንግስቱ አንቀጽ 41(1) አንጻር ለማጣራት ለሰበር
ችሎቱ ይቅረብ ተብሎ በ15/11/12ዓ.ም በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ተጠሪ በ17/2/13ዓ.ም በተጻፈ
ባቀረበው መልስ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(2)(ሀ) ማንኛውም ነጋዴ
በሌላው ነጋዴ ወይም በነጋዴው ተግባራት በተለይም ነጋዴው ከሚያቀርበው የንግድ እቃ ጋር በተገናኘ
ሁኔታ ማደናገርን ያስከተለ ተግባር ወይም ሊያስከትል የሚችል ማንኛውም ድርጊት መፈጸም እንደማይችል
ከደነገገው አንጻር የስር የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ስሚ ችሎት አመልካቾች የ K.C.J ካምፓኒ ለረዥም አመታት
ሲጠቀምበት የነበረውን ማሸጊያ ሆን ብለው በምስልና በዲዛይን በማሳሰል ማቅረባቸውን በስር የዳኝነት ችሎቱ
ከቀረቡት ከተሰሙት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች፤ በባለስልጣኑ የይግባኝ ሰሚ ችሎት ዘንድ በኤግዚቢትነት
ከቀረቡት ምርቶች እና የባለሙያ ምስክርነት በማረጋገጥ ይህም ሀቀኛ ያልሆነ አሳሳችና የተወዳዳሪን ጥቅም
የሚጎዳ ሸማቹንም የሚያሳስት ተግባር ነው በማለት አመልካቾች ከዚህ ተገቢ ካልሆነ የንግድ ውድድር
ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ
እንዲደረግ በማለት ጠይቋል፡፡

አመልካቾች በ17/3/13ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

ይህ የሰበር ችሎትም የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ፤ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢዎቹ የህግ
ድንጋጌዎች አንጻር የስር የፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍ/ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ስሚ ችሎት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈመበት
መሆን አለመሆኑን እንደሚከተለው መርምሯል፡፡

1ኛ አመልካች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘበት ተስመስ ቆንጆ( TSMSSKONJO) የተሰኘው የጸጉር
ቀለም የንግድ ምልክት እና 2ኛ አመልካች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘበት መልካማ( MELKAMA)
የተሰኘው የጸጉር ቀለም የንግድ ምልክት ብቻ ሆኖ ሳለ ለጸጉር ቀለማቱ የሚጠቀሙት ማሸጊያዎች በተጠሪ
በተወከለው የግል ተበዳይ K.C.J ካምፓኒ ካስመዘገበው EVEREST ከተሰኘው የጸጉር ቀለም ማሸጊያ
በሁሉም መልኩ ይኅውም በቅርጽ፤ በመጠን፤ በፊደላት፤ በቀለማትና በአጻጻፍ ዘዴ እንዲሁም በማሸጊያው
ላይ ባለው የሴት ምስል የሚመሳሰሉ እና ሸማቹን ህብረተሰብ የሚያደናግሩ እና ሊያደናግሩ የሚችሉ
መሆናቸውን በዚህም የተነሳ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አ/ቁ 813/2006 አንቀጽ 8(1) ማንኛውም
ነጋዴ በንግድ ስራ ሂደት ውስጥ ማንኛውም ሀቀኛ ያልሆነ፤ አሳሳች፤ ወይም አታላይነት ያለበት እና
የተወዳዳሪን የንግድ ጥቅም የሚጎዳ ወይም ሊጎዳ የሚችል ድርጊት ለመፈጸም የማይችል ስለመሆኑ
የደነገገውን እንዲሁም የአዋጁ አንቀጽ 8(2) ሀ እና ለ በሌላው ነጋዴ ወይም በነጋዴው ተግባራት በተለይም
ነጋዴው ከሚያቀርበው የንግድ እቃ ወይም አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሁኔታ ማደናገርን ያስከተለ ወይም
ሊያስከትል የሚችል ማንኛውም ድርጊት፤ የመረጃው ባለቤት ከሆነው ነጋዴ ፈቃድ ውጪ ከሀቀኛ የንግድ
አሰራር ተጻራሪ በሆነ ሁኔታ የሌላውን መረጃ የማውጣት፤ የመያዝ ወይም የመጠቀም ማናቸውም ድርጊት
ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ሆነው እንደሚቆጠሩ የደነገጉትን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር
የፈጸሙ ስለመሆናቸው ማስረጃዎችን የመስማት፤ የመመርመር እና የመመዘን በህግ ስልጣን የተሰጠው
የፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍ/ቤት በስር የንግድ ውድድርና
የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዳኝነት ችሎት ዘንድ የተሰሙትን የግራቀኙን ምስክሮች ቃል፤ ከሌሎች የሰነድ
ማስረጃዎች በተጨማሪ ኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በቁ. አጠ28/662-11 በ26/12/08ዓ.ም፤ በቁ.
አጠ28/119-660/08 በ26/12/08ዓ.ም እና በቁ. አጠ28/560-104/08 በ1/11/08ዓ.ም የጻፋቸውን ደብዳቤዎች
በመመርመር እና በመመዘን እንዲሁም አከራካሪዎቹን EVEREST፤ ተስመስ ቆንጆ እና መልካማ
የተሰኙትን የጸጉር ቀለም ምርቶች ማሸጊያዎች በኤግዚቢትነት በማስቀረብ እና በመመልከት የምርቶቹ
ማሸጊያዎች ከስማቸው መለያየት በቀር በማሸጊያው መጠን፤ የፊደላት ቀለማት፤ የመደቦች ቀለማት፤
የማሸጊያው ቀለም፤ በማሸጊያው ላይ ያለው ፎቶ… ተመሳሳይነት ያለው እና አንዱን ከአንዱ ለመለየት
የሚያስቸግሩ መሆናቸውን ግንዛቤ በመውሰድ፤ በተጨማሪም ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ከጉዳዩ
ጋር ግንኙነት ያለውን የጽ/ቤቱን የንግድ ምልክት እና ኢንዱስትሪ ንድፍ ልማት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት የንግድ
ምልክት ምርመራ ከፍተኛ ባለሙያ በማስቀረብ እና ምዝገባ ሳያደርግ የመጠቀም መብትን በሚመለከት
የሙያ ምስክርነቱን እንዲሰጥ በማድረግ የሰጠውን የምስክርነት ቃል በመመርመር እና በመመዘን አመልካቾች
ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር የፈጸሙ መሆናቸውን በፍሬነገር ደረጃ በማረጋገጥ ፤ የስር የዳኝነት ችሎቱ
የተጠሪን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ በመሻር አመልካቾች ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር
ፈጽመዋል፤ ጥፋተኞች ናቸው በማለት የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አ/ቁ 813/2006 አንቀጽ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

42(3) የአዋጁን አንቀጽ 8 ድንጋጌዎች የተላለፈ ማንኛውም ነጋዴ የአመታዊ ሽያጭ ገቢውን ከ5% እስከ
10% የገንዘብ ቅጣት የሚቀጣ ስለመሆኑ በደነገገው መሰረት የግራቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ
እያንዳንዳቸው አመልካቾች የአመታዊ ሽያጭ ገቢያቸውን 5% የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ በማለት የሰጠው
ውሳኔ እንዲሁም የአመልካቾች ድርጅቶች የሚጠቀሙት የጸጉር ቀለም ማሸጊያ ከኤቨረስት የጸጉር ቀለም
ማሸጊያ በመጠን፤ በፊደላት፤ በቀለማት እና በአጻጻፍ ዘዴ፤ በመደቦች ቀለማት፤ በማሸጊያው ላይ ባረፈው
የሴት ምስል… በጥቅሉ በቀለሞች ቅንጅት ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ በገበያ ውስጥ ሸማቾችን
የሚያደናገርና ሊያደናገር ስለሚችል እንዳይጠቀሙ በማለት የሰጠውን ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ ጉዳዩን
በይግባኝ ያየው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በማጽናት የሰጠውን ውሳኔ ይህ የሰበር ሰሚ
ችሎት የፌደራል ፍ/ቤቶች አ/ቁ 1234/2013 አንቀጽ 10(1) እና የኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ)
ከደነገጉት አንጻር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘውም፡፡ ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 00027
በ26/4/11ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ
169910 በ30/4/12ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ የሰበር ችሎት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡
3. የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ፡፡
4. በሰበር አጣሪ ችሎቱ በ15/11/12ዓ.ም የኢፌዲሪ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን
በቁጥር አ/ም/ክስ/አ/ዳ/199/2012 ጥር 26 ቀን 2012ዓ.ም ለጉምሩክ ኮሚሽን የሰጠው ትእዛዝ
ከመፈጸም ለግዜው ታግዶ እንዲቆይ የሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ፡፡
5. በዚህ የሰበር ችሎት በ12/12/12ዓ.ም በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ዳኝነት ችሎት
በመ.ቁ 000103 የተጀመረው አፈጻጸም ታግዶ እንዲቆይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል፡፡
ይጻፍ፡፡
6. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ በማስረጃነትም ሟች አቶ ዘለቀ በቀለ በ16/01/1996 ዓ.ም እና ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማ

በ14/03/2008 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የሚገልፅ የወራሽነት ማስረጃ አቅርበዋል፡፡

ተጠሪ ለክሱ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቶ ዘለቀ በቀለ የሞቱት ከሳሾች እንደጠቀሱት

በ1996 ዓ.ም ሳይሆን በ1991 ዓ.ም ነው፤ ከዚህ አንፃር የሟች አቶ ዘለቀ በቀለ ውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ ከ19

አመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) መሰረት በይርጋ የሚታገድ ነው፤ በሌላም በኩል ወ/ሮ

ደደፌ ዱጉማን በሚመለከት አቶ ዘለቀ ከመሞታቸው በፊት ለረጅም አመታት ተለያይተው የነበረ መሆኑንና

የውርስ ሃብት ነው በሚል በተጠቀሰው ቤት ውስጥም ኖረው የማያውቁ መሆኑን በመግለጽ የቀረበው የውርስ

ይጣራልኝ አቤቱታ በሙሉ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን በማንሳት ተከራክረዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት የይርጋ ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ሟች አቶ ዘለቀ የሞቱበትን ጊዜ በተመለከተ

በከሳሶች በኩል በወራሽነት ማስረጃቸው ላይ በ1996 ዓ.ም በሞት የተለዩ ስለመሆኑ ከሚገልጸው ውጭ ሌላ

ማስረጃ አልቀረበም፤ በአንፃሩ ተከሳሽ የወራሽነት ማስረጃን ጨምሮ የቀብር ስርዓቱ ከተፈፀመበት

ቤተክርስቲያን የተፃፈ ደብዳቤ እና ምስክሮችን በማቅረብ ሟች አቶ ዘለቀ በ1991 ዓ.ም የሞቱ ስለመሆኑ

አስረድተዋል፡፡ ይርጋውም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሊቆጠርይገባል፡፡ ስለሆነም ሟች አቶ ዘለቀን በተመለከተ

በአመልካቾች የቀረበው የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000 (1) መሰረት በ 3 ዓመት ውስጥ

ያልቀረበ ከመሆኑም በላይ ይህንን የይርጋ ጊዜ የሚያቋርጥ ምክንያት ስላላቀረቡ ጥያቄው በይርጋ የሚታገድ

ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማን በተመለከተ በሞት የተለዩት በ14/03/2008 ዓ.ም መሆኑ አከራካሪ

ባይሆንም አሁን የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ የቀረበበት ከሟች አቶ ዘለቀ ጋር የተፈራ መሆኑ የተገለጸውን ንብረት

በሚመለከት በህጉ በተቀመጠው ግዜ ውስጥ ከሟች አቶ ዘለቀ ጋር ከተለያዩ በኋላ በ10 አመት ግዜ ውስጥ

ሳይጠይቁ የቆዩ መሆናቸውን የቀረበው ማስረጃ የሚያረጋግጥ በመሆኑ የሟች መብት ቀድሞውኑ በይርጋ ቀሪ

የሆነ በመሆኑ አመልካቾች በዚሁ መነሻነት ያቀረቡት የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ ቀድሞውኑ ሟች ባላረጋገጡበት

መብት ላይ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚህ ብይን ቅር በመሰኘት አመልካቾች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርበዋል፡፡ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን

መርምሮ የሟች ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማ ውርስን በሚመለከት በንብረቱ ላይ ኖረው የሚያውቁ ስለመሆናቸው

ባለመረጋገጡ፤ ሟች አቶ ዘለቀ በቀለ ከመሞታቸው በፊት ተለያይተው የኖሩ መሆኑ በማስረጃዎች

በመረጋገጡ፤ እንዲሁም በህይወት እያሉ ንብረቱ ላይ ያላቸውን መብት ያላስከበሩ መሆኑ በመረጋገጡ ሟች

የሌላቸውን መብት ከሳሾች ሊያገኙ የማይገባ ከመሆኑ አኳያ የስር ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን ክስ በይርጋ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቀሪ ማድረጉ ህጉን የተከተለ ነው በማለት ይህን የውሳኔ ክፍል አፅንቷል፡፡ በሌላ በኩል ሟች አቶ ዘለቀ በቀለን

በሚመለከት የአሁን አመልካቾች አውራሽ ሟች ወ/ሮ ብዙነሽ ዘለቀ ከዚህ ቀደም በፌ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት

በመ/ቁ 23047 ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበው የነበረ በመሆኑ ይህ ጥያቄያቸው ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1851(2) ድንጋጌ

አንፃር የክርክሩ መዝገብ እስከተቋረጠበት ጥር 2000 ዓ.ም ድረስ የይርጋ ጊዜውን አቆጣጠር የሚያቋርጥ ነው፤

ከጥር 2000 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው አቤቱታ 10 ዓመት ከመሙላቱ በፊት ህዳር 2010

ዓ.ም የቀረበ ነው፤ ውርስ እንዲጣራና ድርሻ ክፍፍል ኢንዲፈፀም የሚቀርብ ክስ የይርጋ ጊዜ የሚወስወነው

የፍ/ብ/ህ/ቁ 1080(3) ሟች ከሞቱበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር 10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ ጥያቄው ውድቅ

ይሆናል በማለት ይደነግጋል፤ ስለሆነም የአሁን አመልካቾችን በተመለከተ ጥያቄያቸው በይርጋ ሊታገድ

አይገባም በማለት በዚህ ረገድ የተሰጠውን ብይን ሽሮ በፍሬ ነገሩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን ለስር ፍርድ ቤት

መልሷል፡፡

ይህን በመቃወም ተከሳሽ (የአሁን ተጠሪ) ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበዋል፡፡ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን

መርምሮ ለግራ ቀኙ ክርክር አግባብነት ያለው የይርጋ ድንጋጌ የፍ/ብ/ህ/ 1000(1) እንጂ 1080 (3) አይደለም፤

የአመልካቾች አውራሽ ከሞቱ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ ሲቆጠር 3 አመት ያለፈ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) ክሱ

በይርጋ ሊታገድ የሚገባ ነው፤ በመ/ቁ 23047 ቀርቦ የነበረው ክርክር መቋረጡ ከተረጋገጠበት ጥር 2000 ዓ.ም

ጀምሮ ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው ጥያቄ በስር ፍ/ቤት እስከቀረበበት ህዳር 2010 ዓ.ም ድረስ ያለው ጊዜ

ሲቆጠርም 3 አመት ያለፈ በመሆኑ ጥያቄው ከዚህ አንጻርም ሲታይ በይርጋ የሚታገድ ነው፤ በመሆኑም

ይ/ሰሚው ከፍተኛው ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት የሰጠው ውሳኔ ክፍል ስህተት የተፈፀመበት ነው

በማለት ሽሮ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በውጤት ደረጃ አጽንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካቾች ባቀረቡት ማመልከቻ ተፈፀመ የሚሉትን የህግ

ስህተት ዘርዝረው ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲሻርና ንብረት ማጣራቱ

በተጠየቀበት አግባብ እንዲፈጸምልን በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ የአመልካቾች የውርስ መብት በይርጋ ቀሪ ነው ተብሎ

የተወሰነበትን አግባብ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1000 እና 1852 እንዲሁም የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ

31185 እና 17937 ከሰጠው ትርጉም ጋር በማገናዘብ ለማጣራት በሚል ጉዳዩ ለዚህ ችሎት እንዲቀርብ እና

ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ባቀረቡት መልስ የስር ክርክራቸውን አጠናክረው የአመልካቾች የውርስ ይጣራልን ጥያቄ በህጉ

አግባብ በይርጋ የታገደ በመሆኑ የጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲጸና ጠይቀዋል፡፡ አመልካቾችም የመልስ መልስ

አቅርበዋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን ለሰበር ችሎቱ የተያዘውን ጭብጥ ከግራ ቀኙ

ክርክር፤ ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በውሳኔው የተፈጸመ የህግ

ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው የአመልካቾች ቀዳሚ ቅሬታ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 23047 ምን እንደተሰራ

ማጣራት ሲገባው ሳያጣራ በዝምታ ማለፉን የታዘበው የከፍተኛው ፍ/ቤት ስህተት ነው ብሎ ተችቶ

በተጠቀሰው መዝገብ ውስጥ የውርስ ንብረትን ለማጣራት ከተካሄደው ርቀት አኳያ ተፈጻሚነት ያለው አንቀጽ

የፍ/ብ/ህ/ቁ 1080(3) ነው ማለቱ ትክክል ሆኖ እያለ የፌ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ተፈጻሚነት ያለው አንቀጽ 1000(1)

ነው ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፤ እንዲሁም የሟች አቶ ዘለቀ የውርስ ንብረት ማጣራት ይርጋ በመ/ቁ

23047 ላይ በተደረሰው እንቅስቃሴ መቋረጡን ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ተቀብሎ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ቀጥሎ አዲሱ

የይርጋ ዘመን 3 አመት ነው ያለው የፍ/ብ/ህ/ቁ 1852(1)ን ጠቅሶ ነው፤ ይሁንና የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2)

አዲሱ የይርጋ ዘመን 10 አመት ነው እያለ ጠ/ፍ/ቤቱ የሁለቱን ንዑስ አንቀጾች ተያያዥነት ባለማጤን የሰጠው

ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው በሚል እየተከራከሩ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ተጠሪ በበኩላቸው በመ/ቁ 23047 እንዲጣራ ከተሰጠው ትዕዛዝ ውጭ ምንም አይነት የውርስ

ማጣራት ባልተካሄደበትና የውርስ አጣሪ ሪፖርት ባልቀረበበት ግራ ቀኙም ባለመቅረባቸው መዝገቡ ተዘግቷል

በተባለበት ሁኔታ በዚህ መዝገብ የውርስ ድርሻ እንደተለየና ሪፖርት እንደቀረበ በማስመሰል አሁን ያቀረቡት

መከራከሪያ ሀሰተኛ፣ የህግና የማስረጃ ድጋፍ የሌለው እንዲሁም አዲስ መከራከሪያ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግ፤

እንዲሁም አመልካቾች ያቀረቡት የ10 አመት የይርጋ ክርክር በፍ/ብ/ህ/ቁ 1846፣ 1852(1) እና 1000(1)

መሰረት ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡

እንደተመለከትነው የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ሟች አቶ ዘለቀ በቀለን በተመለከተ የአሁን

አመልካቾች አውራሽ ሟች ወ/ሮ ብዙነሽ ዘለቀ አስቀድመው በመ/ቁ 23047 ጥያቄ አቅርበው የነበረ በመሆኑ

ይህ ጥያቄያቸው ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1851(2) ድንጋጌ አንፃር የክርክሩ መዝገብ እስከተቋረጠበት ጥር 2000 ዓ.ም

ድረስ የይርጋ ጊዜውን አቆጣጠር የሚያቋርጥ ስለመሆኑ፤ ከጥር 2000 ዓ.ም ጀምሮ ሲታሰብ ደግሞ ለዚህ

ክርክር መነሻ የሆነው አቤቱታ 10 ዓመት ከመሙላቱ በፊት ህዳር 2010 ዓ.ም መቅረቡን፤ ውርስ እንዲጣራና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ድርሻ ክፍፍል ኢንዲፈፀም የሚቀርብ ክስ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1080(3) መሰረት በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሊቀርብ

እንደሚችል በመዘርዘር የአመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ በይርጋ ሊታገድ እንደማይገባ ወስኗል፡፡

ይሁንና የፍ/ብ/ህ/ቁ 1080(3) የውረስ መከፋፈሉን አሰራር በሚደነግገው ክፍል ውስጥ የተካተተ ሲሆን

የውርስ ክፍፍልን በሚመለከት በወራሾች መካከል በተደረገው ስምምነት ወይም የክፍያ ሃሳብ ያልተስማማ

ወራሽ ይህን ለማስፈረስ የሚያቀርበው ጥያቄ በይርጋ የሚታገድበትን ጊዜ የሚደነግግ እንጂ የውርስ ማጣራት

ጥያቄን የሚመለከት የይርጋ ጊዜ አይደለም፡፡ የውርስ ማጣራትን ጥያቄ የሚመለከተው የይርጋ ደንብ

በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) ስር የተመለከተው ሶስት አመት ጊዜ ሲሆን በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ

25567 እና በሌሎችም መዛግብት የሰጠው ትርጉም በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 መሰረት ለተያዘው

ጉዳይም በተመሳሳይ ተፈጻሚነት ያለው ነው፡፡ ስለሆነም ይኸው ተጠቅሶ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ

በጠቅላይ ፍርድ ቤት መታረሙ በአግባቡ ነው ብለናል፡፡

የሟች አቶ ዘለቀ የውርስ ንብረት ማጣራት የይርጋ ጊዜ መቆጠር በመ/ቁ 23047 ላይ በተደረገው

እንቅስቃሴ ተቋርጦ ነበር መባሉን በተመለከተም ከመነሻው የአመልካቾች አውራሽ በመ/ቁ 23047 ጥያቄ

አቅርበው የነበረ ከሆነ አዲስ ፋይል ከማስከፈት ይልቅ በክርክሩ ተተክተው ማስቀጠል የሥነ ሥርዓት ህጉን

የተከተለ ይሆን የነበረ ሲሆን የስር ፍርድ ቤቶች በመ/ቁ 23047 የተደረገውን ክርክር በይርጋ ማቋረጫነቱ

የተቀበሉት ስለሆነና በዚህ ረገድ የቀረበ ቅሬታ ባለመኖሩ በዚህ ላይ ይህ ችሎት ውሳኔ የሚሰጥበት አይሆንም፡፡

ይሁንና ይኸው መዝገብ የይርጋ ጊዜ መቆጠርን ያቋርጣል ከተባለ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1852(2) መሰረት አዲሱ የይርጋ

ዘመን 10 አመት ሊሆን ይገባል በማለት አመልካቾች መከራከራቸው ተገቢ መሆን አለመሆኑን መርምረናል፡፡

የውርስ ህጉ የውርስ ጉዳይን የተመለከቱ ልዩ የይርጋ ድንጋጌዎች የያዘ ሲሆን በሌላ በኩል በህጉ ላይ

የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ሲቋረጥ እንደ አዲስ ስለሚቆጠረው የይርጋ ጊዜ የውርስ ህጉ አይደነግግም፡፡ ይህ

ጉዳይ በውርስ ህጉ ካልተሸፈነ ደግሞ የጠቅላላ ህጉ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1677

መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚህ መሰረት የይርጋ መቋረጥ ውጤትን የሚደነግገው ጠቅላላ ድንጋጌ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1852

ሲሆን በንኡስ (2) ስር የአዲሱ ይርጋ ዘመን 10 አመት እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ የዚህን ድንጋጌ ተፈጻሚነት

በተመለከተ ይህ ሰበር ችሎት በመ/ቁ 31185 እና በሌሎችም ተመሳሳይ መዛግብት በሰጠው ትርጉም

“ድንጋጌው የሚገኘው ጠቅላላ የውሎች ህግ በሚለው ክፍል ከመሆኑም በላይ ውልን አስመልክቶ የሚቀርብ ክስ

በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ እንደሚሆን በፍ/ብ/ህ/ቁ 1845 ላይ ስለተመለከተ ከዚሁ ከጠቅላላ ውል ጋር በተያያዘ

አንድ የይርጋ ጊዜ ሲቋረጥ ሌላ አዲስ የ10 ዓመት ይርጋ ጊዜ ሊኖር እንደሚችል ከሚያስገነዝብ በስተቀር በልዩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ህግ የይርጋ ጊዜው ከ10 ዓመት ዝቅ ብሎ የሚገኘው ሁሉ ተቋርጦ በሚገኝበት ወቅት አዲሱ የይርጋ ጊዜ 10

ዓመት ነው ማለት እንደማይቻል” ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ከዚህ አንጻር በተያዘው ጉዳይ የይርጋ ጊዜ መቆጠር

ይቋረጣል ከተባለ በኃላ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1852(2) መሰረት አዲሱ የይርጋ ዘመን 10 አመት ሊሆን ይገባል በማለት

አመልካቾች የሚያቀርቡት መከራከሪያ ህግ አውጭው ለተለያዩ ክሶች የወሰነውን የተለያየ የይርጋ ጊዜ መሰረት

ያላደረገና በሰበር ችሎቱም የተሰጠውን አስገዳጅ ትርጉም ያላገናዘበ በመሆኑ ክርክራቸው ተቀባይነት የለውም፡፡

በአጠቃላይ በግራቀኙ መካከል ያለው ክርክር በወራሾች መካከል መሆኑን በማረጋገጥና ለጉዳዩ

ተፈጻሚነት ያለው የፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) መሆኑን መሰረት በማድረግ የአመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ በይርጋ

የሚታገድ ነው ተብሎ በተሰጠው ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 178872 በቀን 26/01/2012 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ፍርድ ቤት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ፡፡

3. የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

4. የስር ፍርድ ቤት መዛግብት በመጡበት መልኩ ይመለሱ፡፡

5. ውሳኔው ዛሬ ነሐሴ 3/2013 ዓ.ም ተነቧል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ.2ዐ3746
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

ብርሃኑ መንግስቱ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- ታሪኩ ኬዶ ኬሪ

ተጠሪ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካችና በዚህ መዝገብ ያልቀረቡ ሌሎች 9
ተከሣሾችን ጨምሮ ያቀረበው የእርስ በእርስ ጦርነት የማነሳሳት ወንጀል የአሁን አመልካች በተከሰሰበት 5
ክሶች እንዲከላከል ብይን ሰጥቶ ክስና ማስረጃውን አልተከላከልክም ተብሎ ጥፋተኛ ተደርጐ በ16 ዓመት ጽኑ
እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ እና በይግባኝም ውሣኔው ያለመታረሙ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ላይ
መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲሉ አቤቱታ በማቅረባቸው
መነሻነት ነው፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላይው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካችን 9ኛ ተከሣሽ በማድረግ፣
ሌሎች 9 ተከሣሾችን ጨምሮ በአጠቃላይ 6 ክሶች የቀረቡባቸው ሲሆን፣ አመልካች ግን 6ኛ ክስ ላይ
አልተጠቀሰም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዐቃቤ ሕግ አቅርቦት የነበረው ክስ በአጭሩ፡-

1ኛ ክስ በሁሉም ተከሣሾች ላይ ሆኖ የወ/ሕ/አ/35/32 ( 1)(ሀ) 24ዐ/3 ስር የተደነገገውን ተላልፈው የእርስ


በእርስ ጦርነት ለማነሳሳት ካልታወቁ ቡድኖች ሀሳብ በመቀበል መስከረም 6/2ዐ11 ዓ.ም. በግምት ከምሽቱ
12፡45 ሰዓት ሲሆን በወረዳ ዐ1 ሴቄ ማርያም ሞሪንታ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው ሰፈር የጋሞ ብሔር
ተወላጅ የሆኑ ድንጋይ፣ ዱላ፣ገጀራ፣ አካፋ እና የተለያየ ስለት ያላቸው መሳሪያዎች በመያዝ “ጋሞን ማን
ነካ” እና የኦሮሞን ቤት እየለዩ ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ እየፎከሩ የኦሮሞ ተወላጆች እኛን ገድለው
እንዴት ይኖራሉ እያሉ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነውን ሰው በያዙት ዱላና ድንጋይ ቀጥቅጠው በመግደል
በፈፀሙት በተሳሳተ እንቅስቃሴ ውስጥ በራሳቸው ፍቃድ ተካፋይ በመሆን የእርስ በእርስ ጦርነት በማስነሳት
ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

2ኛ ክስ በሁሉም ተከሣሾች ላይ፣- የወ/ሕ/አ/35፣ 32/1/ሀ/ 539/1/ሀ ተላልፈው ሰውን ለመግደል አስበው
መስከረም 6 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. በግምት ከምሽቱ 12፡ዐዐ ሰዓት ሲሆን በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ ዐ1 ልዩ ቦታው ሱቄ
ማርያም ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የኦሮሞ ተወላጆች እኛን ገድለው እንዴት ይኖራሉ እያሉ በጤፍ ማሳ
ውስጥ ያለውን ዳኜ ፈየራ በያዙት ዱላና ድንጋይ ቀጥቅጠው የገደሉት በመሆኑ በፈፀሙበት ከባድ የሰው
ግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

3ኛ ክስ በሁሉም ተከሣሾች ላይ፡- የወ/ሕ/አ/35፣32/1/ሀ እና 69ዐ/3/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ


ተከሣሾች በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ አስበው መስከረም 7 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. በግምት 12 ሰዓት
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ወ/ዐ1 የአቶ ብሩ ኢዶ ንብረት የሆነ የተለያዩ ንብረቶች ጠቅላላ ግምታቸው 112,8ዐዐ.ዐዐ ብር፣
የአቶ ተሾመ መንገሻ ንብረት የሆነውን ኮድ 2-73289 አ.አ. ቪታራ መኪና ግምቱ ብር 3,ዐዐ0.00 ብር፣
የወ/ሮ ብርቄ ገብሬ የሆነውን ንብረት ጠቅላላ ግምቱ ብር 8,ዐዐዐ.ዐዐ ብር፣ የአቶ ወርቁ ኢዶ ንብረት ጠቅላላ
ግምቱ ብር 425,ዐዐዐ.ዐዐ በሆኑት ንብረቶች ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

4ኛ ክስ በሁሉም ተከሣሾች ላይ፡- የወ/ሕ/አ/ 35፣32/1/ሀ/ 555/ሀ/ ተላልፈው በ1ኛ ክስ በተጠቀሰው ጊዜ እና


ቦታ አቶ እስራኤል ተመስገን የተባለውን በያዙት ድንጋይና ዱላ ደብድበውት ሲወድቅ ጥለውት የሄዱ
በመሆናቸው ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

5ኛ ክስ በሁሉም ተከሣሾች ላይ፡- የወ/ሕ/አ/35፣ 32/1/ሀ/ 555/ሀ/ ተላልፈው ወ/ሪት ባንቱ ድናግዴን በያዙት
ድንጋይና ዱላ ወርውረው በተለያየ የሰውነት አካሏ ላይ ሲመቷት ስትወድቅ ጥለዋት በመሄዳቸው በፈፀሙት
የሰው አካል ላይ ጉዳት መድረስ ወንጀል ተከሰዋል በሚል ክስ አቅርቧል፡፡ 6ኛ ክስ አመልካችን የሚመለከት
ባለመሆኑ መመዝገብ አላስፈለገም፡፡

አመልካች ክሱን ክዶ በመከራከሩ ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን የሰማ ሲሆን የዐቃቤ ሕግ 1ኛ፣ 2ኛ፣ 4ኛ፣
5ኛ፣6ኛ፣8ኛ፣9ኛ እና 1ዐኛ ምስክሮች በአመልካች ላይ ያስረዱት ነገር የለም፡፡ ነገር ግን 3ኛ፣7ኛ ምስክሮች
በአመልካች ላይ የሰጡት ምስክርነት ፡- 3ኛ ምስክር አመልካች ገጀራና ድንጋይ ይዘው ከሚያልፉ መሀል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እሱም የነበረ መሆኑን፣ ዳኜ ፈይራ የተባለው ሰው ተገድሎ መገኘቱን ማን እንደገደለው ግን እንደማያውቅ፣


አመልካች ንብረት ማውደሙን እና ወደ ተጠለሉ ሰዎች እየመራ የወሰደ መሆኑን መስክሯል፡፡ 7ኛ የዐቃቤ
ህግ ምስክር በበኩሉ የአሁን አመልካችን በችሎት ለይቶ ማሳየቱን፣ በጊዜው የኦሮሞ ልጆችን ሲያሯሩጥ
የነበረ መሆኑን ማሳ ውስጥም ሰው ሞቶ መገኘቱን እና በተጠለሉ ሰዎች ላይም ጉዳት የደረሰ መሆኑን
አውቃለሁ ሲል መስክሯል፡፡

ፍ/ቤቱም የቀረበውን ክስ እና ማስረጃን መርምሮ በ1ኛ ክስን አስመልክቶ የቀረበው ማስረጃ የእርስ በእርስ
ጦርነት ድርጊትን ሊገልጽ የሚችል አይደለም በሚል የቀረበውን ክስ ወደ አምባጓሮ ወይም በጠብ ተካፋይ
ሆኖ መገኘትን የሚያሳይ ነው በማለት ድንጋጌውን ወደ 577/3/ በመቀየር አመልካችን ጨምሮ
1፣2፣5፣7፣1ዐኛ ተከሣሾች እንዲከላከሉ፣ በ2ኛ ክስ አመልካችን ጨምሮ 2ኛ፣5ኛ፣7፣8ኛ፣ እና 1ዐ የስር
ተከሣሾች በ539/1/ሀ/ ስር እንዲከላከሉ፣3ኛ ክስን አስመልክቶ በድርጊቱ ሰው ያልሞተ መሆኑ ስለተረጋገጠ
በሚል የቀረበውን ድንጋጌ ወደ 69ዐ/1/ለ/ በመቀየር አመልካችን ጨምሮ 1ኛ፣2ኛ፣5ኛ፣7ኛ፣8ኛ እና 1ዐ የስር
ተከሣሾች እንዲከላከሉ፣4ኛ ክስን አስመልክቶም ድንጋጌውን በመቀየር በ556/2/ሀ ስር አመልካችን ጨመሮ
1ኛ፣2ኛ፣5ኛ፣8ኛ እና 1ዐኛ የስር ተከሣሾች እንዲከላከሉ፣ 5ኛ ክስንም እንዲሁ ወደ 556/2/ሀ በመቀየር
አመልካችን ጨምሮ ሌሎች ተከሣሾች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡ ከዚህ ውጪ ያሉ የስር ተከሣሾችን
መከላከል ሳያስፈልጋቸው ከቀረበባቸው ክስ በነፃ አሰናብቷል፡፡

በዚሁ መሠረት አመልካች የመከላከያ ማስረጃውን አቅርቦ ያሰማ ሲሆን ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ
አመልካች ክስና ማስረጃውን አልተከላከለም በሚል እንዲከላከል ብይን በተሰጠበት የህግ ድንጋጌዎች ስር
ጥፋተኛ ነው ሲል የጥፋተኝነት ውሣኔ በመስጠት ቅጣቱን አስልቶ በ16/ አስራ ስድስት ዓመት/ ጽኑ እስራት
እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

አመልካች በስር ፍ/ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታውን ያቀረበ
ቢሆንም ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሣኔ አጽንቷል፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሣኔ
በመቃወም ነው፡፡

አመልካች መጋቢት 1 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. በጠበቃው አማካይነት የተፃፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን፣
ይዘቱም በአጭሩ፡- አመልካች በተከሰሰባቸው የወንጀል አይነቶች ላይ የወ/ሕ/አ/35 ተፈፃሚ ሊሆን የሚገባው
ያለመሆኑን፣ በአመልካች ላይ በተጠቀሰው ከባድ ወንጀል ቅጣቱም እድሜ ልክ ወይም ሞት በሚያስቀጣ ላይ
በህብረቱ ውስጥ ተገኝተሀል በሚል ምክንያት ብቻ አመልካች ምን እንዳደረገ ተለይቶ ባልተከሰሰበት እና
ባልተመሰከረበት ጥፋተኛ ተደርጉ ቅጣት መጣሉ፣ ዳኜ ፈየራ የተባለው ሰው በተገደለበት በ6/1/2ዐ11 ዓ.ም.
አመልካች በቦታው የነበረ ስለመሆኑ ባልተመሰከረበት፣ የዐቃቤ ሕግ 1ኛ፣2ኛ፣4ኛ፣ ምስክሮች አመልካች ከላይ
በተጠቀሰው ቀን እንደሌለ መስክረው ባለበት፣ 5ኛ፣5ኛ፣7ኛ፣8ኛ፣1ዐኛ ምስክሮችም በአመልካች ላይ
የመሰከሩት ነገር በሌለበት፣ በ3ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክርም ላይ ከአመልካች ጋር ጠበኛ በመሆኑ
እንዳይመሰክር አመልክተን እያለ ጥፋተኛ መደረጉ፣ ተመስክሮበታል እንኳን ቢባል በወ/ሕ/አ/54ዐ መሆን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሲገባው በ2ኛ ክስ 539/1/ሀ ጥፋተኛ ተደርጐ መቀጣቱ መሠረታዊ የህግ ስህተት በስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ
የተፈፀመ መሆኑን ስለሚያሳይ ስህተቱ እንዲታረምልኝ ሲል ጠይቋል፡፡

አቤቱታው በአጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ አመልካች በወ/ሕ/አ/ 35/32/1/ሀ እና 577/3/፣ 539/2/ሀ፣69ዐ/1/ለ/


እና 556/2/ሀ/ን ተላልፎ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ በስር ፍ/ቤት የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሣኔ
የተወሰነበትን አግባብነት ከተጠቀሰው ድንጋጌና ከወንጀል ህግ አንቀጽ 23/2/ አንፃር ለመመርመር መዝገቡ
ለችሎቱ እንዲቀርብ በመታዘዙ ሊቀርብ ችሏል፡፡

ለተጠሪ መጥሪያ እንዲደርሰው ተደርጐም በ22/11/2ዐ13 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም፡-እንደ
አድማና አምባጓሮ የመሳሰሉ ወንጀሎች በአንቀጽ 35 2ኛ ሃሣብ አገላለጽ ከዐ/ሕግ የሚጠበቀው በህብረቱ
ውስጥ ተከሣሽ መገኘቱን እንጂ ወንጀል አለመፈፀሙን የማስረዳት ሸክም ወደ ተከሣሽ የሚዞር መሆኑን፣
ያቀረብነውን ክስ ከጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ያስረዳን በመሆኑ፣ ዳኜ ፈየራ የተባለው ሰው ግድያ ላይ አመልካች
ከሌሎች ጋር አብሮ ስለመኖሩ በምስክር ያረጋገጥን መሆኑን፣ 3ኛ፣4ኛ እና 7ኛ ምስክሮች የኦሮሞ ወጣቶችን
አመልካች ከሌሎች ጋር በመሆን እያባረረ ወደ በቀለ ኢዶ የጤፍ ማሳ የወሰዱ መሆኑ፣ ማሳ ውስጥም ዳኘ
ፈየራ ሞቶ መገኘቱ መመስከሩን፣ የወ/ሕ/አ/539/1/ሀ ወደ 54ዐ ይቀየርልኝ ያለውንም አስመልክቶ አመልካች
ከሌሎች ጋር በመስማማት ድርጊቱ የፈፀመ በመሆኑ ድንጋጌውን የሚያቋቁም ከሆነው አንዱ የተሟላ
በመሆኑ ሊቀየር የሚገባው አለመሆኑን፣ በማንሳት የስር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፋተኝነትም
ሆነ የቅጣት ውሣኔ ተገቢ በመሆኑ አቤቱታው ውድቅ ይደረግልኝ ብሏል፡፡

የአመልካች ጠበቃም የቀደመው የሰበር አቤቱታን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገብ
ተያይዞ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ልውውጥ በዚሁ ተጠናቋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭር በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ መልስ እና
የመልስ መልስ በስር ፍ/ቤቶች ከተሰጠው ውሣኔ እና አጠቃላይ ከማስቀረቢያ ነጥቡ አኳያ ከጉዳዩ ጋር
አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡

የክርክሩ ሂደት የሚያሳየው በአመልካች ላይ ዐቃቤ ህግ 5 ክሶችን ጠቅሶ ከሌሎች ተከሣሸች ጋር ወንጀል
ፈጽሟል ሲል ክስ የመሰረተበት መሆኑን፣ የተጠቀሱት ክሶችም 24ዐ/3፣ ለጦርነት የማነሳሳት
ወንጀል፣539/1/ሀ/ ከባድ የሰው ግድያ፣69ዐ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፣555/ለ/ በሰው አካል ላይ ከባድ
ጉዳት ማድረስ ወንጀል ፈጽሟል ሲል ክስ ያቀረበ ሲሆን አመልካች ክሱን ክዶ የተከራከረ በመሆኑ ምስክሮች
ተሰምተው ለጦርነት የማነሳሳት ወንጀሉ ድንጋጌን እና በአካል ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ወንጀል ድንጋጌን
ወደ አምባጓሮ እና ቀላል አካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል በመቀየር ሌሎቹ ክሶች በነበሩበት ሁኔታ አመልካች
እንዲከላከል ፍ/ቤቱ ብይን የሰጠ በመሆኑ አመልካች የመከላከያ ማስረጃ በማድረግ ምስክሮችን አቅርቦ
አሰምቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በአጣሪ ችሎቱ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በጭብጥነት ተይዞ ሊመረመር የሚገባው
ዐቃቤ ሕግ እንዳቀረበው ክስ በማስረጃ ስለማስረዳት አለማስረዳቱና አስረድቷል ከተባለም አመልካች ክሱና
ማስረጃውን ተከላክሏል ወይንስ አልተከላከለም የሚለውን እና ተጠቅሰው የቀረቡት ድንጋጌዎች በተደራራቢ
ክስ የመቅረባቸውን አግባብነት ከወ/ሕ/አ/23/2/ /35 ፣6ዐ፣61 እና 141፣577/3/፣ 69ዐ ድንጋጌዎች ጋር
ሊመረመር የሚባው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የወ/ሕ/አ/23/2/ በግልጽ የሚደነግገው፡- “ አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀሉን የሚያቋቁሙት


ሕጋዊ፣ግዙፋዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው፡፡” በሚል ነው፡፡

ከወንጀል ጉዳዮች የክስ ሂደት ጋር በተገናኘ ዓቃቤ ሕግ ሊያከናውናቸው ከሚገቡ ተግባራትና ኃላፊነቶች
ዋናው የተከሰሰን ሰው የወንጀል ድርጊቱን በቀረበው ክስ አይነት ስለመፈፀሙ በበቂና አሳማኝ ማስረጃ
የማስረዳት ሸክሙን መወጣት ያለበት ስለመሆኑ ከወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 141 እና 142/1/ ድንጋጌ መረዳት
እንችላለን፡፡

የወ/ሕ/አ/577/3/ ፡- “ በአምባጓሮ ወቅት ከነበረው ሁኔታ የተነሳ በተለይም በጠበኞች መካከል በነበረው
ቂም፣የጠብ ማጫር ወይም የስካር ሁኔታ ወይም የጦር መሣሪያዎችን፣ ድንጋዩችን ወይም ማቁሰል ወይም
መግደል የሚችሉ ሌሎች ነገሮችን የያዙ ወይም እነዚሁ ነገሮች የተሰጧቸው በመሆኑ በጠቡ መካከል ሰው
የቆሰለ ወይም የተገደለ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ከፍተኛው መደበ ቅጣት ሊደርስ ይችላል፡፡” በሚል ይደነግጋል፡፡

በመሰረቱ ተደራራቢ ወንጀሎች በአጠቃላይ በአንድ ጊዜ(ሀሳባዊ መደራረብ) ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ
ጊዜያት የተፈፀሙ ድርጊቶችን(ቁሳዊ መደራረብ) የሚመለከቱ ሲሆኑ መደጋገም የቁሳዊ መደራረብ መለያ
ባህሪ በመሆኑ ተመሳሳይ ድርጊቶች በተለያዩ ጊዜያት ቢፈፀሙ ወይም የተለያዩ ድርጊቶች በተለያዩ ጊዜ
ተፈፅመው ቢገኙ ቁሳዊ መደራረብ አለ ለማለት የሚቻል ሲሆን፣ በአንድ ነጠላ ድርጊት ከአንድ በላይ የሆኑ
ወንጀሎች መፈፀማቸው የሀሳባዊ መደራረብ መለያ ባህሪ መሆኑን ከወ/ህ/አ.60(ሀ)እና(ለ) ድንጋጌ ይዘት
ለመረዳት ይቻላል፡፡

ወደ ያዝነው ጉዳይ ስንመለስ አመልካች ላይ ዐቃቤ ሕግ ጠቅሶ ያቀረበውን ክስ ስንመለከት በፍ/ቤቱ ባይለወጥ
ኑሮ 1ኛው ክስ የእርስ በእርስ ጦርነት ማነሳሳት የነበረ ሲሆን ይህን ግን የስር ፍ/ቤት የቀረበው ክስ እና
ማስረጃ የተጠቀሰውን መስፈርት አያሟላም በሚል ወደ አምባጓሮ ድንጋጌ የቀየረው መሆኑን ነው፡፡

ከላይ እንደተመለከትነው የወ/ሕ/አ/577/3/ ተጠቅሶ አመልካች ጥፋተኛ የተባለ ሲሆን አመልካች በድንጋጌው
ጥፋተኛ ሊደረግ የበቃው የወ/ሕ/አ/35 እና 32/1/ሀ ተጠቅሶ ከሌሎች ጋር በህብረት ወንጀሉን ፈጽሟል
በሚል በመሆኑ የወ/ሕ/አ/35 በግልጽ የሚደነግገው ደግሞ አድማና አምባጓሮ በተደረጉ ጊዜ በህብረቱ ውስጥ
መገኘቱ የተረጋገጠበት ሰው የማይቀጣው በወንጀሉ ተካፋይ አለመሆኑን ሊያስረዳ ከቻለ ብቻ መሆኑን
ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም አመልካች አምባጓሮው መፈፀሙ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ
ቁጥራቸው ትንሽ ይሁኑ እንጂ በቀረቡት ምስክሮች በዚህ ህብረት ውስጥ ስለመገኘቱ የመሰከሩበት በመሆኑ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች አብረውት የተከሰሱት ሰዎች ድንጋይ፣ ዱላ እና ሌሎች ማቁሰል የሚችሉ መሳሪያዎችን በመያዝ
እየፎከሩ የኦሮሞ ልጆች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ እሱም የተጠለሉ ሰዎች ያሉበትን ቦታ ይመራ የነበረ
መሆኑን፣ የኦሮሞ ልጆችን ያባርር የነበረ መሆኑን፣ እንዲሁም መስከረም 6 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. በነበረው ረብሻ
ላይ የነበረ ስለመሆኑ እና በዚህ የአመልካቾች ድርጊት የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ንብረትም የወደመ መሆኑ
በምስክሮች በፍሬ ነገር ደረጃ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል፡፡

አመልካች ከላይ በተጠቀሰው ቀን ሰዓትና ቦታ በአምባጓሮው መካከል ስላለመኖሩ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ


ጥርጣሬን በሚፈጥር መልኩ ባቀረባቸው ማስረጃዎች አልተከላከለም፡፡ በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የቀረበውን
1ኛ ክስ ወደ 577/3/ ቀይሮ ጥፋተኛ ማድረጉ ተገቢ እንጂ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡

ነገር ግን የስር ፍ/ቤት የወ/ሕ/አ/577/3/ ወንጀል ተፈጽሟል ብሎ ያመነ ከመሆኑ አንፃር ዐቃቤ ሕግ
የወ/ሕ/አ/539/1/ሀ/ ጠቅሶ በዛው በተፈጠረ አምባጓሮው ድርጊት ምክንያት ሰው የሞተ መሆኑን በመጥቀስ
አመልካች የሰው መግደል ወንጀል ፈጽሟል በማለት ያቀረበውን ክስ ድርጊቱ የተደራራቢ ወንጀልን መስፈርት
የማያሟለ መሆኑን በመረዳት 2ኛው ክስ በ1ኛው ክስ ውስጥ የሚጠቃለል ነው ብሎ መወሰን ሲገባው በአንድ
ወንጀል የመስራት ሃሣብ የተፈፀመን ድርጊት ወንጀሉ እንደተደራረበ አድርጐ በ2ኛ ክስ ጥፋተኛ ማለቱ
መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

መስከረም 7 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. አመልካችን ጨምሮ የስር ሌሎች ተከሣሾች የወ/ሕ/አ/35/32/1/ሀ/ እና


69ዐ/1/ለ/ ተላልፈው በተለያዩ ሰዎች ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን አስመልክቶ በአመልካች ላይ ድርጊቱን
ስለመፈፀሙ በማስረጃ የተረጋገጠበት በመሆኑ እንዲሁም ወንጀሉ የተፈፀመበት ቀን አምባጓሮ ከተፈፀመበት
ቀን የሚለይ በመሆኑ በዚህ ድንጋጌ አመልካችን ጥፋተኛ በማድረግ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ ላይ
የተፈፀመ መሠረታዊ የህግ ስህተት የሌለ በመሆኑ ሊፀና የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በስር ፍ/ቤት
ውሣኔ ላይ የተፈፀመው መሠረታዊ የህግ ስህተት ሊታረም የሚገባው በመሆኑ የበላይ ፍ/ቤትም የስር
ፍ/ቤትን የህግ ስህተት ሳያርም ማለፉ ተገቢ ባለመሆኑ ውሣኔውን በማሻሻል ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1) የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 1886ዐ5 በ27/5.2ዐ13


ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 227ዐ15 ጥቅምት 24
ቀን 2ዐ12 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው የጥፋተኝነት ውሣኔ እና ህዳር 3ዐ ቀን 2ዐ12 ዓ.ም.
የተሰጠው የቅጣት ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 195/2/ለ/2 መሠረት ተሻሽሏል፡፡
2) አመልካች ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ሊወሰንበት የሚገባው በወ/ሕ/አ/35፣32/1/ሀ እና
577/3 እና 69ዐ/1/ለ/ በአምባጓሮ እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነው ብለን ወስነናል፡፡
አመልካች በወ/ሕ/አ/539/1/ሀ እና 556/2/ሀ ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣት ሊወሰንበት አይገባም ብለን
ወስነናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

3) አመልካች ጥፋተኛ የተባለበት የወ/ሕ/አ/577/3/ የአምባጓሮ ወንጀል


ድንጋጌ፡- “ በአምባጓሮ ወቅት ከነበረው ሁኔታ የተነሳ በተለይም በጠበኞች መካከል በነበረው
ቂም፣የጠብ ማጫር ወይም የስካር ሁኔታ ወይም የጦር መሣሪያዎችን፣ ድንጋዬችን ወይም
ማቁሰል ወይም መግደል የሚችሉ ሌሎች ነገሮችን የያዙ ወይም እነዚሁ ነገሮች የተሰጧቸው
በመሆኑ በጠቡ መካከል ሰው የቆሰለ ወይም የተገደለ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ከፍተኛው
መደበኛ ቅጣት ሊደርስ ይችላል፡፡” በሚል ይደነግጋል፡፡
በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ወንጀልን የሚደነግገውና አመልካች ጥፋተኛ የተባለበት
የወ/ሕ/አ/69ዐ/1/፡- “ ወንጀሉ በወንጀል ክስ አቅራቢነትና ከሰባት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ
እሥራትና መቀጮ ሊያስቀጣ በሚችል ፡- ለ/ ወንጀሉ የተፈፀመው በዛቻ፣በኃይል ወይም
በብዙ ሰዎች ይልቁንም ሁከት፣ የሥራ መዝጋት ወይም የሥራ ማቆም አድማ በተነሳ ጊዜ
በሠራተኞች ወይም በአሰሪዎች እንደሆነ----” በሚል ይደነግጋል፡፡

ከላይ በተገለፀው ድንጋጌ መሠረት በተፈፀመው የአምባጓሮ ወንጀል ምክንያት ሰው የተገደለ


እንደሆነ አጥፊው በወ/ሕ/አ/577/3/ ስር በተደነገገው መሠረት ቅጣቱ እስከ ከፍተኛው
መደበኛ ቅጣት ሊደርስ ይችላል”፡ ይህም ማለት በወንጀል ህጉ አንቀጽ 539/1/ ስር
እንደተደነገገው ሰው በመግደል ወንጀል ከፍተኛ መደበኛ ቅጣት ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት
ወይም ሞት ነው፡፡ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 577/3/ ስር በሞት ወይም በእድሜ
ልክ እስራት ሊያስቀጣ በሚችል ወንጀል ጥፋተኛ ስለተባሉ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 69ዐ/1/
ስር ጥፋተኛ የተባሉበት ቅጣት በወንጀል ህጉ አንቀጽ 184/1/ሀ/ መሠረት ከፍተኛው መደበኛ
ቅጣት ውስጥ የተጠቃለለ ነው፡፡
በመሆኑም የሞት ቅጣት ወይም የእድሜ ልክ እስራት ቅጣት በሌሎች ተደራራቢ ወንጀሎች
ምክንያት ሊጣሉ የሚገባቸውን የቅጣት ዓይነቶች ሁሉ አካቶ የሚይዝ ስለመሆኑ በወ/ሕ/አ/
184/1/ሀ/ ስር የተደነገገ በመሆኑ አመልካች ጥፋተኛ የተባለበትን ተደራራቢ ወንጀል
ማለትም የወ/ሕ/አ/69ዐ/1/ለ/ ቅጣቱ ሲሰላ ታሳቢ አይደረግም ብለን ወስነናል፡፡
4) አመልካች ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ የቅጣት መነሻው እድሜ ልክ
እስራት በመሆኑ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2ዐዐ6 መሠረት ደረጃ 38 ተይዞ
ቅጣቱ መሰላቱ እና ቅጣት መወሰኑ ተገቢ ነው ብለን ወስነናል፡፡
ሆኖም ግን በስር ፍ/ቤት ከተያዘው 3 የቅጣት ማቅለያ በተጨማሪ ከአጠቃላይ ክርክሩ
እንደተገነዘብነው አመልካች ይህን ድርጊት እንዲጸትም የገፋፋው አስቀድሞ በጋሞዎች ላይ
ተፈጽሞ የነበረው ጉዳት መሆኑን መረዳት የሚቻል በመሆኑ ቅጣቱም ሊጣል የሚገባው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍትህን ሊያሰፍን በሚችል መልኩ ሆኖ ስላገኘነው ይህን ወንጀል ለመፈፀም ያነሳሳውን


ምክንያት እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ በመውሰድ 4 የቅጣት ማቅለያ እንዲያዝና ከተያዘው
የቅጣት መነሻ ደረጃ ላይ መቀነስ ተገቢ ነው ብለን የቅጣት ደረጃውን ወደ ደረጃ 34 ዝቅ
አድርገን በ15/ አስራ አምስት/ ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተደርጐ ቅጣቱ ተሻሽሎ
ተወስኗል፡፡
ትዕዛዝ
 የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች እና አመልካች ለታሰረበት
ማረሚያ ቤት እንዲደርስ ታዟል፡፡
 አመልካች የታሰረበት ማረሚያ ቤትም አመልካች ከዚህ ቀደም በዚህ
ጉዳይ የታሰረው ታሳቢ ተደርጐ በተሻሻለው ውሣኔ መሠረት ቅጣቱን ተከታትሎ
እንዲያስፈጽም ታዟል፡፡
 የውሣኔው ግልባጭ አመልካች ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት በፍ/ቤቱ
መልእክት ክፍል በኩል እንዲደረስ ታዟል፡፡
 መዝገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል፡፡
የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
ሠሰ/መ/ቁ. 190307

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- መዓዛ አሸናፊ

ሰለሞን አረዳ

ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች- የካ ክ/ከተማ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት

ተጠሪዎች-

1. አቶ አበበ በቀለ
2. ሻለቃ ደሳለኝ ኃይሌ
3. ፻ አለቃ ሻሜ አስቻለዉ
4. ፶ አለቃ ኃ/ስላሴ አደራ
5. አቶ አሰፋ ክፍሌ
6. አቶ መንግስቱ ይታፈሩ
7. አቶ ሁንዴሳ ጎሴ
8. አስር አለቃ አራርሳ ደገፉ
9. አቶ ቡልቶ ስሜ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍርድ

ጉዳዩ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ


የሚስተናገድበትን አግባብ የሚመለከት ነዉ፡፡ የጉዳዩም አመጣጥ ሲታይ ተጠሪዎች በየካ ክ/ከተማ
ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ ባቀረቡት ክስ ቤትና ንብረታቸዉን ያላግባብ አፍርሶ በመዉሰድ
ጉዳት ያደረሰባቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ ካሳ እንዲከፈላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ጉዳዩን የተመለከተዉ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩን መርምሮ የተለያዩ ንብረቶች ዋጋ ብር
443,215.00 ንብረቱ ከተወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ተከሳሽ እንዲከፍል ዉሳኔ
ሰጥቷል፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ ተከሳሽ በነበረዉ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ
የተሰጠዉ ዉሳኔ ሊሻር ይገባዋል በማለት አመልካች አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም የፌዴራል ከፍተኛ
ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ የሚቀርበዉ
ለአቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ ያረፈዉ የክርክሩ ምክንያት በሆነዉ ንብረት ላይ ሆኖ በክርክሩ
ተካፋይ ያልሆነ ወገንን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ሲረጋገጥ ሲሆን፣ በተያዘዉ ጉዳይ ተከሳሽ
መጥሪያ ደርሶት ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ክርክሩን ማሰማት ባለመፈለጉ ምክንያት በሌለበት ዉሳኔ
በተሰጠበት ሁኔታ አመልካች ተከሳሹ ክርክሩን አላሳወቀንም የሚል ምክንያት በመጥቀስ ዉሳኔዉ
ይሻርልን በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ የፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉን አንቀጽ 358 ዓላማ ያገናዘበ አይደለም
በማለት ዉድቅ አድርጎታል፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህንኑ በትዕዛዝ አጽንቶታል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበዉም በዚሁ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ሲሆን አመልካች


የካቲት 02 ቀን 2012 ዓ.ም አዘጋጅቶ ያቀረበዉ አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር የአፈፃፀምና ማዘጋጃ አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣዉ አዋጅ ቁጥር
35/2004፣ አዋጅ ቁጥር 64/2011 ላይ በተመለከተዉ መሠረት አመልካች የከተማ አስተዳደሩ
ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር በማናቸዉም ዳኝነት አካል ዘንድ የመቃወሚያ አቤቱታ
የማቅረብ መብት አለዉ፤ ተከሳሽ የነበረዉ ተቋም እና አመልካች በአንድ መንግስታዊ መዋቅር ስር
መገኘታቸዉ ብቻ አከራካሪዉን ጉዳይ በተመለከተ ተመሳሳይ ጥቅምን የሚወክሉ አካላት ናቸዉ
ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም፤ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በሰ/መ/ቁጥር 37502 ላይ በሰጠዉ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ይህንኑ አረጋግጧል፤ ይህ ሆኖ እያለ
አመልካች በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት ያቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ
በማድረግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የጸናዉ
ዉሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል የሚል ነዉ፡፡

የሰበር አቤቱታዉ በአጣሪ ችሎት ተመርምሮም አመልካች የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ


የከተማ አስተዳደሩን መብትና ጥቅም ማስከበር እንደሚችል በህግ ስልጣን ተሰጥቶት እያለ
አቤቱታዉን ዉድቅ በማድረግ የተሰጠዉን ዉሳኔ አግባብነት ግራ ቀኝ በተገኙበት አጣርቶ ለመወሰን
ሲባል ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪዎች በተደረገላቸዉ ጥሪ መሠረት ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም
አዘጋጅተዉ በሰጡት መልስ አመልካች በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ያቀረበዉን የመቃወም አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ በተሰጠ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የህግ
ስህተት ያለመኖሩን ጠቅሰዉ ጸንቶ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ከስር ጀምሮ የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ
ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችሎትም የሰበር አቤቱታዉን ለማስቀረብ የተያዘዉን ጭብጥ
ከግራ ቀኝ ክርክር እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን
እንደሚከተለዉ መርምሮታል፡፡ እንደመረመረዉም አመልካች በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ
አንቀጽ 358 መሠረት ላቀረበዉ የመቃወም አቤቱታ መሠረት ያደረገዉ ተጠሪዎች በስር ተከሳሽ
በነበረዉ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ ያቀረቡትን ክስ መሠረት በማድረግ ብር
443,215.00 ከወለድ ጋር ለተጠሪዎች እንዲከፈል ፍርድ ቤቱ የሰጠዉ ዉሳኔ የአስተዳደሩ
ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም የሚነካ በመሆኑ እና አመልካች በፍርድ ቤት ክርክር አቅርቦ ይህን
መብት ለማስከበር በህግ ስልጣን የተሰጠዉ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ፡፡ በእርግጥ አመልካች በፍርድ
ቤት ክርክር አቅርቦ የክፍለ ከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም የማስከበር ስልጣን
በህግ የተሰጠዉ መሆኑ አላከራከረም፡፡ አከራካሪዉ እና የዚህን ችሎት እልባት የሚያሻዉ ጭብጥ
አመልካች በፍርድ ቤት ክርክር በማድረግ የከተማዉ ነዋሪዎችን/የህዝብና የመንግስትን መብትና
ጥቅም ለማስከበር ያለዉ መብት/ስልጣን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣንና ኃላፊነት
ባለዉ ሌላ የከተማዉ አስተዳደር አካል ክርክር ተደርጎበት ዉሳኔ ያረፈበት ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ
በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ ያስችለዋል ወይ?
የሚለዉ ነዉ፡፡

እንደሚታወቀዉ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸዉን የጽሑፍ ክርክር መርምረዉ፣ በቃል የሚቀርቡ


ክርክሮችን አዳምጠዉ፣ ማስረጃዎችን መዝነዉ እና መሠረታዊ ህጎችን ተርጉመዉ ዉጤት ላይ
መድረስ ይችሉ ዘንድ ሥርዓት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ክርክሮች የሚመሩባቸዉ ሥርዓት እና ደንቦች
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ተቀርጸዉ ስራ ላይ እንዲዉሉ የሚደረግበት ምክንያትም ይሄዉ
ነዉ፡፡ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ የፍትሐብሔር ክርክሮችን አስመልክቶ የምንከተለዉ ስርዓት
ሲሆን አጠቃላይ ዓላማዉም የፍትሐብሔር ጉዳዮችን ፍትሐዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ቀልጣፋ በሆነ
ሁኔታ በመምራት ፍትሐዊ ዉሳኔ እንዲያገኙ ማስቻል ነዉ፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት ይቻል ዘንድም
የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ የተለያዩ ደንቦች እና መርሆዎችን ይደነግጋል፡፡ ክርክሮች በዘፈቀደ
ሳይሆን ሥርዓት ባለዉ ሁኔታ እንዲመሩ በማድረግ የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት መብትን፣
ብሎም ክርክሮች ባነሰ ወጪ እና ጊዜ መቋጫ እንዲያገኙ በማድረግ በፍርድ ቤት እና በተከራካሪ
ወገኖች ላይ ያላግባብ የሚደርሰዉን የገንዘብ እና የጊዜ ብክነት በማስቀረት የክርክሩ ሂደትም ሆነ
ዉጤቱ ፍትሐዊ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ የሚኖረዉ ሚና
ከፍተኛ በመሆኑ በህጉ ላይ የተመለከቱትን ደንቦች እና መርሆዎች በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲዉሉ
የማድረጉ አስፈላጊነትም የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡

በዚህ ረገድ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጋችን ዕዉቅና ከተሰጣቸዉ ደንቦች ዉስጥ አንዱ
በከሳሽነት እና በተከሳሽነት ከተሰየሙት ወገኖች ዉጪ ያሉ ሦስተኛ ወገኖች የክርክር ተሳታፊ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚሆኑበትን ሁኔታ የሚመለከተዉ ደንብ ነዉ፡፡ በከሳሽነት እና በተከሳሽነት ከተሰየሙት


ተከራካሪዎች ዉጭ የሆነ ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ተሳታፊ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ፍትሐዊ
ዉሳኔ ለመስጠት የማይችል ዓይነት (indispensable party) ከሆነ በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ወይም
መብት ባለዉ ሰዉ አቤቱታ አቅራቢነት፣ እንዲሁም ዉጤቱ መብቴን ሊነካ ይችላል በሚል ወገን
(interested party) አቤቱታ አቅራቢነት ሦስተኛ ወገን በተጀመረ ክርክር ተሳታፊ የሚሆንበትን
ሥርዓት የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ ይዘረጋል (አንቀጽ 40 እና 41 ይመለከቷል)፡፡
ዓላማዉም የጉዳዩ አመራር ፍትሐዊ እንዲሆንና በሥርዓት እንዲከናወን ለማስቻል ሲባል ነዉ
ተብሎ ይታመናል፡፡ ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ከላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ክርክሩ
በሂደት ላይ እያለ በክርክሩ ተሳታፊ ሆኖ መብቱን ማስከበር ይችል የነበረ ሰዉ ተሳታፊ ባልሆነበት
መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም
በህግ የዳኝነት ስልጣን ባለዉ አካል በተሰጠ ዉሳኔ መብቴ ተነክቷል የሚል ሦስተኛ ወገን
አቤቱታዉን በማቅረብ ዉሳኔዉን በመቃወም መብቱን ሊያስከብር የሚችልበትን ሥርዓት
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ የድንጋጌዉ ሙሉ
ይዘትም፡-

በክርክሩ ዉስጥ ተካፋይ መሆን የሚገባዉ ወይም በክርክሩ ዉስጥ ለመግባት


የሚችልና እንዲሁም ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠዉ ፍርድ መብቱን
የሚነካበት ማናቸዉም ሰዉ ራሱ ወይም ጠበቃዉ ወይም ነገረ ፈጁ ተካፋይ
በልሆነበት ክርክር የተሰጠዉ ፍርድ ከመፈጸሙ በፊት መቃወሚያዉን ለማቅረብ
ይችላል የሚል ሲሆን የዚህ ድንጋጌ የእንግሊዝኛዉ ቅጅም Any person who should or
could or could have been a party to a suit and whose interests are affected by a
judgment in the suit may, if he was not a party to such suit either in person or through
a representative, file an opposition to such judgment at any time before such judgment
is executed በማለት ይደነግጋል፡፡

ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለዉም ክርክሩ መጀመሩን ሳይረዳና ሳያዉቅ በከሳሽነትና


በተከሳሽነት በተሰየሙት ወገኖች መካከል የተደረገዉ ክርክር ተጠናቆ መወሰኑ እንኳ ቢታወቅ
ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ይረዳ ዘንድ በዉሳኔዉ መብቴ ተነክቷል የሚለዉ የክርክሩ ተካፋይ
ያልነበረዉ ሰዉ ይህንኑ ዉሳኔ መቃወም የሚችል መሆኑን ነዉ፡፡ በተለይም በድንጋጌዉ ማናቸዉም
ሰዉ ራሱ ወይም ጠበቃዉ ወይም ነገረ ፈጁ ተካፋይ ባልሆነበት ወይም በእንግሊዝኛዉ if he was not
a party to such suit either in person or through a representative በሚል የተገለጸዉ የሚያሳየዉ
ሦስተኛ ወገን የሚያቀርበዉ አቤቱታ ተቀባይነት የሚኖረዉ አቤቱታ አቅራቢዉ ለአቤቱታዉ
በምክንያትነት የጠቀሰዉ ጉዳይ በቀደመዉ የክርክር ሂደት በመቃወም አመልካቹ በእራሱ ወይም
በወኪሉ ወይም ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ሰዉ ክርክር ያልቀረበበት
ሲሆን ነዉ፡፡ በሌላ አገላለጽ የመቃወም አመልካቹ ለአቤቱታዉ መሰረት ያደረገዉ ክርክሩ በሂደት
ላይ በነበረበት ወቅት ጉዳዩ የሚያገባዉ ሰዉ የክርክሩ ተሳታፊ በሆነበት ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበት
ጉዳይ ከሆነ እና የመቃወም አመልካቹ ዉሳኔዉ ‘በግል’ መብቱን የሚነካ መሆኑን በአቤቱታዉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ካላሳየ በስተቀር አቤቱታዉ ተቀባይነት የሚኖረዉ አይደለም፡፡ የመቃወም አመልካች ለመቃወሚያዉ


ምክንያት የሆኑትን ዝርዝር ምክንያቶች እና የሚጠይቀዉን ዳኝነት በአቤቱታዉ በዝርዝር መግለጽ
እንዲሁም አቤቱታዉ ለሌሎች ተከራካሪ ወገኖች እንዲደርስ ተደርጎ ክርክሩም የሚሰማዉ
የመጀመሪያዉ ክርክር በተሰማበት ሂደት ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 359 እና 360 ላይ የተመለከቱት
ድንጋጌዎችም የሚያሳዩት ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ የመቃወም አመልካቹን
መብትና ጥቅም በግል የሚነካ መሆን ያለመሆኑ ጉዳይ የመቃወም አመልካቹ እና በክርክሩ ተሳታፊ
የሆኑ ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች የሚያቀርቡትን ክርክር እና ማስረጃ መሠረት በማድረግ ታይቶ
ዉሳኔ የሚሰጥበት መሆኑን ነዉ፡፡ ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠዉ የዳኝነት
አካል የተሰጠን ዉሳኔን መቃወም የሚቻልበትን ሥርዓት አስመልክቶ በሥነ ሥርዓት ህጉ
የተመለከተዉ ድንጋጌ በዉሳኔዉ መብቱ ‘በግል’ የተነካበት ሰዉ መቃወሚያዉን አቅርቦ መብቱን
ለማስከበር እንዲችል እንጂ አንድን መብትና ጥቅም ለማስከበር የተለያዩ ሰዎች ተፈራርቀዉ
የሚያቀርቡትን አቤቱታ ለማስተናገድ ያለመሆኑን መገንዘቡ ተገቢ ነዉ፡፡ ይልቁንም የመቃወም
አቤቱታ የሚቀርብበትን ሁኔታ አስመልክቶ በድንጋጌዉ ላይ ከተመለከቱት መስፈርቶች አንፃር
ሲታይ የድንጋጌዉ ዓይነተኛ ዓላማ በአንድ በኩል በከሳሽነት እና በተከሳሽነት በተሰየሙ ወገኖች
መካከል በተደረገ ክርክር መነሻነት የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሰዉ ዉሳኔዉን በመቃወም
ተከራክሮ መብቱን እንዲያስከብር በማድረግ ፍትሕ የማግኘት መብቱን በማረጋገጥ፣ በሌላ በኩል
በከሳሽነት እና በተከሳሽነት በተሰየሙት ወገኖች መካከል ክርክር ተደርጎበት እልባት ባገኘ ጉዳይ ላይ
በድጋሚ ክርክር በማቅረብ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር በሚል በሦስተኛ ወገን የሚቀርብ
አቤቱታ ተቀባይነት እንዳይኖረዉ በማድረግ በአንድ ጉዳይ ላይ ወይም ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን
ለማስከበር በሚል ክርክሮች በተደጋጋሚ ሊቀርቡ የሚችሉበትን ሁኔታ በማስቀረት ክርክሮች
በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጪ መቋጫ እንዲያገኙ ብሎም የፍርድ ሂደቱም ሆነ ዉጤቱ ተገማች
እንዲሆን ማድረግ ነዉ፡፡ ስለሆነም በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የቀረበ
የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን አስመልክቶ በፍርድ ቤቶች የሚሰጠዉ
ትርጉም ይህንኑ ያገናዘበ ሊሆን ይገባል፡፡

ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ስንመለስ፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ በተጠሪዎች ከሳሽነት በስር


ፍርድ ቤት በተከሳሽነት የተሰየመዉ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ሲሆን ለቀረበዉ ክስ
ምክንያት የሆነዉም የተጠሪዎችን ቤት አፍርሶ ንብረታቸዉንም ያላግባብ በመዉሰድ ጉዳት
ያደረሰባቸዉ መሆኑ ነዉ፡፡ ተጠሪዎች ይህ ድርጊት በስር ተከሳሽ መስሪያ ቤት የተፈጸመ እና
ለጉዳቱ ኃላፊነቱን የሚወስደዉም መስሪያ ቤቱ ስለመሆኑ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ
33(3) እና 92 መሠረት አረጋግጠዉ ክስ ያቀረቡ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ በመሆኑም
አመልካች በህጉ አንቀጽ 33(3) መሠረት በቀጥታ ተከሳሽ ሆኖ ሊቀርብ የሚችልበት ሁኔታ
አይኖርም፡፡ በተከሳሽነት የተሰየመዉ የወረዳዉ አስተዳደር ጽ/ቤት ቀርቦ ባለመከራከሩም ዉሳኔ
በሌለበት ተሰጥቷል፡፡ አመልካች የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ ተቋም በመሆኑ የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ
የመንግስት ወይም የግል ተቋም እንደሚያደርገዉ ሁሉ በቀጥታ ተቋሙን በሚመለከተዉ ጉዳይ ላይ
በከሳሽነት፣ በተከሳሽነት፣ በጣልቃ ገብነት ወይም በመቃወሚያ አቤቱታ አቅራቢነት በፍርድ ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠዉ የዳኝነት አካል ቀርቦ የክርክሩ ተሳታፊ በመሆን እንደ ተቋም
ያለዉን መብት የማስከበር መብትም ግዴታም አለዉ፡፡ ይሁንና በተያዘዉ ጉዳይ ላይ አመልካች
በተጠሪዎች የቀረበዉ ክስ ይመለከተኛል ወይም በህጉ አንቀጽ 33(3) መሠረት በተከሳሽነት መጠራት
የነበረብኝ እኔ ነኝ የሚል ክርክር የለዉም፤ ይልቁንም በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ
358 ያቀረብኩት የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት ሊኖረዉ ይገባል በማለት የሚከራከረዉ በስር
ተከሳሽ የነበረዉ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር እንዲከፍል የተወሰነበት ገንዘብ የክፍለ
ከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑን እና የክፍለ ከተማዉን ነዋሪዎች መብትና
ጥቅምን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መከራከር እንዲችል በህግ ስልጣን
የተሰጠዉ መሆኑን ነዉ፡፡ በእርግጥም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና
ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 5 የዐቃቤ ሕግ ቢሮ የተከተማዉ አስተዳደር መስሪያ
ቤቶች የአስተዳደሩና የነዋሪዉ መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ እንደሚከራከር የተመለከተ ሲሆን፣
አመልካች የክፍለ ከተማ አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በመሆኑ ስለ ክፍለ ከተማ የሥልጣን አካላት
ሥልጣንና ተግባር በሚደነግገዉ ክፍል አንቀጽ 78 መሠረት የክ/ከተማዉንና የክፍለ ከተማዉን
ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ወኪል ሆኖ ለፍርድ ቤት ወይም በህግ
የዳኝነት ስልጣን በተሰጠዉ አካል ቀርቦ ክርክር የማቅረብ ስልጣን ይኖረዋል፡፡

በዚህም መሠረት በክፍለ ከተማዉ እና በስሩ የተደራጁት መስሪያ ቤቶች ከክፍለ ከተማዉ
ነዋሪዎች መብትና ጥቅም ጋር በተያያዘ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ተሳታፊ በሆኑበት ጉዳይ ላይ
አመልካች ወኪል ሆኖ መከራከር ይችላል፡፡ እንዲሁም እነዚህ መስሪያ ቤቶች የክርክሩ ተሳታፊ
መሆን ሲገባቸዉ ተሳታፊ ባልሆኑበት የተሰጠ ዉሳኔ ሲኖር እና ዉሳኔዉም የክ/ከተማዉን ነዋሪዎች
መብትና ጥቅም የሚጎዳ ከሆነ የሚመለከተዉን የክፍለ ከተማዉን መስሪያ ቤት በመወከል
በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡
ይህ እንዳለ ሆኖ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ወይም በጣልቃ ገብነት ወይም በመቃወም
አመልካችነት የክርክር ተሳታፊ ሲሆን መስሪያ ቤቱ በእራሱ የህግ ባለሙያ ወይም ነገረ ፈጅ
ክርክሩን ማቅረብ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ የሚታወቅ ነዉ፡፡ ይህም የሚያሳየዉ በፍርድ ቤት
ክርክር አድርጎ አንድን መብትና ጥቅም በማስከበር ሂደት አመልካች (ዐቃቤ ህግ) እና ጉዳዩ
የሚመለከተዉ መስሪያ ቤት ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ነዉ፡፡ ይህ ማለት ግን
ሁለቱ ተቋማት አንድን መብትና ጥቅም ለማስከበር በጋራ ተከራካሪ በመሆን ይቀርባሉ ወይም
ከሁለቱ አንደኛዉ መስሪያ ቤቱን በመወከል ክርክር አድርጎ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ ሌላኛዉ ወገን
ተመሳሳይ መብትን የማስከበር በህግ ስልጣን/መብት ስላለዉ ብቻ ዉሳኔዉን ለመቃወም አቤቱታ
ያቀርባል ማለት እንዳልሆነ መገንዘቡ ተገቢ ነዉ፡፡ ይልቁንም የከተማዉን/የክፍለከተማዉን ነዋሪዎች
መብትና ጥቅም ከማስከበር ጋር በተያያዘ ክርክር ሲኖር የሚመለከተዉን መስሪያ ቤት ወክሎ
ክርክሩን ማቅረብ የሚችል አካል ከአቃቤ ህግ እና ከመስሪያ ቤቱ የህግ ባለሙያ ማን መሆን
እንዳለበት የአቃቤ ህግ መስሪያ ቤት እና መስሪያ ቤቱ ተነጋግረዉ የሚወስኑት ነዉ፡፡ በዚህ መልኩ
ተነጋግረዉ ጉዳዩን አቃቤ ህግ እንዲይዝ ከተወሰነ ሌላ የተለየ ዉክልና እንዲያቀርብ ማድረግ
ሳያስፈልግ ጉዳዩን የሚመለከተዉ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ የሚያቀርበዉን ክርክር መቀበል እንዲችል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተመለከተ ድንጋጌ ነዉ፡፡ ከዚህ ዉጪ ዐቃቤ ህግ ጉዳዩ የከተማዉ ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም
የሚመለከት በመሆኑ ብቻ የሚመለከተዉ መስሪያ ቤት የክርክሩ ተሳታፊ በመሆን በተደረገ ክርክር
መሠረት ዉሳኔ ያገኘዉን መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን አለኝ በሚል ብቻ ተመሳሳይ መብትና
ጥቅም ማስከበርን መሠረት ያደረገ አቤቱታ በፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም
አቤቱታ ማቅረብ አይችልም፡፡ ዐቃቤ ህግ ክርክር በማቅረብ የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም ማስከበር
እንደሚችል ስልጣን የሚሰጠዉ ከላይ የተመለከተዉ የአዋጁ ድንጋጌ አተገባበርም ይህን እዉነታ
ባገናዘበ መልኩ ሊሆን ይገባል፡፡

ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዳይ ስንመለከት ክሱ የቀረበበት የየካ ክፍለከተማ ወረዳ 1


አስተዳደር ጽ/ቤት ለፍርድ ቤት ቀርቦ ባለመከራከሩ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠ ሲሆን፣
ክርክር ሳይደረግ የተሰጠ ዉሳኔ የክፍለ ከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም የሚጎዳ ነዉ የሚል
ከሆነ እና ተከሳሹ መስሪያ ቤት ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ ክርክሩን ሊያቀርብ ያልቻለበት በቂ እና አሳማኝ
ምክንያት አለዉ የሚል ከሆነ ከተከሳሽ መስሪያ ቤት ጋር በመነጋገር አቤቱታዉ በፍትሐብሔር ሥነ
ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 78 መሠረት ማቅረብ ይችል ነበር፡፡ አመልካች ይህን ሳያደርግ እና በዚህም
ምክንያት በተከሳሽነት የተሰየመዉ መስሪያ ቤት በሌለበት ክርክሩ እንዲቀጥል ተደርጎ የተሰጠ ዉሳኔ
ሥነ ሥርዓታዊ ነዉ ተብሎ በሚገመትበት ሁኔታ ዉሳኔዉን በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ
አንቀጽ 358 መሠረት ያቀረበዉ አቤቱታ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም፡፡

ሲጠቃለል በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ


የክርክሩ ተሳታፊ ባልሆነበት በተደረገ ክርክር የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሦስተኛ ወገን
የመቃወም አቤቱታዉን አቅርቦ የክርክሩ ተሳታፊ በመሆን ተከራክሮ መብቱን ማስከበር እንዲችል
ታስቦ የተዘረጋ ነዉ፡፡ በመሆኑም አቃቤ ህግ ወኪል ሆኖ ሊከራከር የሚችልበት መብትና ጥቅም
ክርክር በማድረግ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ጉዳዩ በሚመለከተዉ
መስሪያ ቤት ክርክር ቀርቦበት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ አቃቤ ህግ ዉሳኔዉን በፍትሐብሔር ሥነ
ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት ሊቃወም የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡ በዚህ አግባብ
ለመወሰን ለክርክሩ ምክንያት ከሆነዉ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሁለቱም (ዐቃቤ ህግ እና ጉዳዩ
የሚመለከተዉ መስሪያ ቤት) የሚያስከብሩት መብትና ጥቅም አንድ እስከሆነ ድረስ የአቃቤ ህግ
መስሪያ ቤት እና በክርክሩ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት የተሰየመ መስሪያ ቤት የየራሳቸዉ
ስልጣንና ኃላፊነት ያላቸዉ መሆን ያለመሆኑ ጉዳይ በጭብጥነት ሊያዝ የሚገባዉ ጉዳይም
አይደለም፡፡ ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘ አመልካች የሚያቀርበዉ ክርክር ተገቢነት የለዉም፡፡
በእርግጥ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 37502 በቅጽ 8 ላይ
በታተመዉ ዉሳኔ ሁለት ራሳቸዉን የቻሉና የህግ ሰዉነት ያላቸዉ ተቋሞች በአንድ የመንግስት
መዋቅር ሥር የሚገኙ በመሆናቸዉ ብቻ ተመሳሳይ ጥቅምን የሚወክሉ አካላት ናቸዉ ወደሚል
መደምደሚያ የሚያደርስ አለመሆኑን በመጥቀስ ከከተማ አስተዳደሩ አንዱ አካል የክርክሩ ተሳታፊ
በሆነበት ክርክር ተደርጎ ዉሳኔ መሰጠቱ የአመልካች መስሪያ ቤት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ
አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ እንዳያቀርብ የሚከለክል አይደለም የሚል ይዘት ያለዉ
የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ይሁንና ይህ የህግ ትርጉም በሦስተኛ ወገን አቤቱታ የሚቀርብበትን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሁኔታ አስመልክቶ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ


ዓላማ ያገናዘበ ባለመሆኑ ሊለወጥ የሚገባዉ የህግ ትርጉም ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በዚህ ሁሉ
ምክንያት ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ዉሳኔ

1. የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት


በመ/ቁጥር 210662 ላይ ሐምሌ 02 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የተሰጠዉ ዉሳኔ
እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 181686 ላይ
ታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ ትዕዛዝ በፍትሐብሔር ሥነ
ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንተዋል፡፡
2. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 37502 (ቅጽ 8 ላይ
እንደታተመዉ) የሰጠዉ የህግ ትርጉም ተለዉጧል፡፡
3. የአዲስ አበባ ከተማ ዐቃቤ ህግ ቢሮ (በየደረጃዉ ያሉ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤቶችን ይጨምራል)
ወኪል ሆኖ ክርክር በማቅረብ የነዋሪዉን መብትና ጥቅም እንዲያስከብር በአስፈፃሚ
አካላት ማቋቋሚያ አዋጁ ስልጣን የተሰጠዉ ቢሆንም፣ ይህ ስልጣኑ ብቻዉን ተመሳሳይ
መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣን ያለዉ የሚመለከተዉ የከተማዉ አስተዳደር አካል
የክርክሩ ተሳታፊ በሆነበት ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ መሠረት አድርጎ እንደገና
ክርክር ለማድረግ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም
አቤቱታ እንዲያቀርብ ምክንያት አይሆንም፡፡
4. በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን
ይቻሉ፡፡
5. የሰበር አጣሪ ችሎት የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ እግድ
ተነስቷል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የሰባት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መ/ቁጥር 191095

ሐምሌ29/2013 ዓም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱአለም

አመልካች/ቾች፡- አቶ ከተማ ኑኔ

ተጠሪ/ዎች፡- ወ/ሮ መረጠች ለማ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ በሊዝ ውል የተገኘ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር
አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ/14021 ላይ ታህሳስ 17/2012 ዓም በዋለው ችሎት
የስር ፍቤቶችን ውሳኔ የሻረበትን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡

የክርክሩ ስረ ነገር አመጣጥ እንዲህ ነው፡፡ አቶ ባላይ ላጲሶ የተባሉት የአሁን ተጠሪ የቀድሞ
ባለቤት ከተጠሪ ጋር የነበራቸውን ጋብቻ በፍቺ መፍረሱ ተከትሎ ቦታ እና አዋሳኙ በክስ አቤቱታው
ውስጥ የተዘረዘረውን እና ጋብቻቸው ፀንቶ በነበረበት ወቅት በሊዝ ውል ያገኙትን 4000 ካሬ ሜትር
ይዞታ ለመካፈል በሆሳና ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡
የአሁን ተጠሪም ቀርበው ንብረቱ የጋራ በመሆኑ ቢካፈሉ አልቃወምም የሚል መልስ
በመስጠታቸው የተጠቀሰው ይዞታ የጋራ ንብረት መሆኑ ተጠቅሶ እንዲካፈሉ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ይህ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከሆነ በኋላ የአሁን አመልካች ባልና ሚስቱ እንዲካፈሉ ተብሎ ውሳኔ ያረፈበት ይዞታ ተጠሪና
ባለቤታቸው በጋብቻ አብረው በነበሩበት ወቅት ተጠሪ ለባለቤታቸው በሰጡት ውክልና መሰረት
መጋቢት 29/2008 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ያስተላለፉላቸው መሆኑን፤ በውሉ መሰረት ጉዳዩ
በሚመለከተው አስተዳደር ክፍል ቀርቦ ተገቢውን ክፍያ ፈፅመው በስም ዝውውር ደረጃ ላይ ያለ
መሆኑን በመግለፅ ንብረቱን ባልና ሚስቱ በሽያጭ ያስተላለፋት በመሆኑ እንዲካፈሉ የተሰጠው
ውሳኔ ሊሻር ይገባል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡

በዚሁ የመቃወም አቤቱታ ላይ ተጠሪ እና ባለቤታቸው መልስ እንዲሰጡ በታዘዘው መሰረት


ሁለቱም ቀርበው የተጠሪ ባለቤት ይዞታውን በሽያጭ ሲያስተላልፍ ይህንን ለማድረግ
የሚያስችላቸው ተገቢን የውክልና ስልጣን የሌላቸው በመሆኑ ውሉ ፈራሽ ነው፤ የሽያጭ ውሉም
በአዋጅ ቁጥር 721/2004 የተመለከተውን የሊዝ ውል ማስተላለፊያ ስርአትን ያልተከተለ በመሆኑ
ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ለክርክር
ምክንያት የሆነው የሊዝ ይዞታ የተሸጠበት ውል በተፈረመበት መጋቢት 29/2008 ዓም የአሁን
ተጠሪ ባለቤት ውክልና አለኝ ብለው በውሉ የፈረሙ ቢሆንም የነበራቸው ውክልና ውሉን ለመፈረም
የሚያስችላቸው ያልነበረ መሆኑን፤ በወቅቱ የአሁን ተጠሪ ወልደው ተኝተው የነበረ በመሆኑ እና
የሽያጭ ውሉም ለክፍሉ አስተዳደር ከቀረበ በኋላ የተጠሪ ባለቤት ተገቢ ውክልና የላቸውም በመባሉ
ምክንያት ተጠሪ ሚያዚያ 03/2008 ዓም ሙሉ ውክልና ለባለቤታቸው ሰጥተው አስተዳደራዊ ሂደቱ
የቀጠለ መሆኑን፤ በዚሁ ተጠሪ እና ባለቤታቸው በሽያጭ ውሉ ተጎድተናል በማለት ይዞታው
ቀድሞ ከተሸጠበት ዋጋ በተጨማሪ ብር 100.000(አንድ መቶ ሺህ) ከአመልካች የተቀበሉ መሆኑን፤
አመልካችም ይዞታውን እና ይዞታውን የሚመለከቱ ሰነዶችን በሙሉ ተረክበው በእጃቸው አድርገው
የሚገኙ መሆኑን እና በአስተዳደር አካል ተጀምሮ የነበረው የስም ዝውውር ሂደትም በአሁን ተጠሪ
ተቃውሞ የቆመ ስለመሆኑ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ የሽያጭ ውሉ እና
የውክልና ውሉ ፊትና ኋላ ቢሆኑም ተጠሪ ስለ ሽያጩ ሙሉ እውቀት እና ፈቃድ የነበራቸው
በመሆኑ የአመልካች መብት የሚያሳጣ አይደለም፤ የሽያጭ ውሉ በሊዝ አዋጁ መሰረት
አልተከናወነም የሚባል ከሆነም ድርጊቱን መቃወም እና ማስቆም የሚገባው የሚመለከተው
አስተዳደር አካል ነው፤ ሆኖም የክፍሉ መሬት አስተዳደር የሽያጭ ውሉን ተቀብሎ እና አስፈላጊውን
ክፍያ አስፈፅሞ ሂደቱን የጀመረ በመሆኑ ከተጠሪ እና ባለቤታቸው በኩል የቀረበው ክርክር ከቅን
ልቦና ውጭ የቀረበ ነው፤ ቀደም ሲል ተጠሪ እና ባለቤታቸው እንዲካፈሉ የተባለው ይዞታው
በሽያጭ ለአሁን አመልካች ባስተላለፉት ይዞታ ላይ የተሰጠ ውሳኔ ነው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቁጥር 360(2) መሰረት ሽረዋል፡፡ በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የሃድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ
ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ዘግቷል፡፡

የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በበኩሉ የግራቀኙ ክርክር ከሰማ በኃላ በሰጠው ውሳኔ በሊዝ ውል በተገኘ
ይዞታ ላይ ያለ የሊዝ መብት ሊተላለፍ የሚችለው በሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 24(2)
ስር በተመለከተው አግባብ ግልጽ የሽያጭ ውል ከአሁን ተጠሪ እና ባለቤት ተላልፎልኛል ቢሉም
ውሉ በአዋጁ በተመለከተው ሥርዓት የተፈፀመ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ነገር የለም፤ ውሉም
የተደረገው በባዶ መሬት ላይ ሲሆን ባዶ መሬትን መሸጥ በህገ መንግስቱ የተከለከለ በመሆኑ ውሉ
ህጋዊ ውጤት የለውም ሲል የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ሽሯል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች በጠበቃቸው በኩል
የካቲት 13/2012 በተጻፈ ዘጠኝ ገፅ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያሉትን
መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ መሰረታዊ ይዘቱም
የአሁን ተጠሪ ባለቤታቸው ያለህጋዊ ውክልና ለክሱ ምክንያት የሆነውን የሊዝ ይዞታ መብትን
አስመልክቶ ከአሁን አመልካች ጋር ያደረጉት የሽያጭ ውሉ እዲፈርስላቸው በሃድያ ዞን ከፍተኛ
ፍርድ ቤት በመ/ቁ15511 ላይ ክስ አቅርበው ያለፍርድ ቤቱ ፈቃድ ክሱን ያነሱ በመሆኑ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 279 እና 5 መሰረት የውሉን ህጋዊነት አስመልክቶ ድጋሚ ክርክር
ሊያቀርቡ አይችሉም አመልካች ለክሱ ምክንያት የሆነውን ይዞታ እላዩ ላይ ከነበረው ጅምር ቤት
ጋር ገዝተው ግንባታውን ያፈረሱ እንጂ ባዶ መሬት አልገዙም፣ የክፍሉ አስተዳደርም የሽያጭ
ውሉን ህጋዊነት አረጋግጦ እላዩ ላይ የነበረውን ግንባታ ግምት በማስላት አመልካች መክፈል
የሚገባቸውን ክፍያ አሳውቆ በማስከፈል ከአመልካች ጋር የሊዝ ውል የፈረመ በመሆኑ ውሉ ህጋዊ
ነው፤ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶችም ይኽው ለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋግጠው ወስነው
እያለ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በህግ ባልተሰጠው ስልጣን ማስረጃን መዝኖ ውሳኔዎቹን መሻሩ
የኢ/ፌ/ድ/ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 80/3/ለ/ እና ይኽው ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 32220 ላይ
የሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተላለፈ ነው፤ የሽያጭ ውሉም የተደረገው በሊዝ ውል በተገኘ
መብት ላይ በመሆኑ እና ይህም በህግ መንግስቱ አንቀፅ 40/6/ እና በሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004
አንቀፅ 14 መሰረት የተፈቀደ ሆኖ እያለ ውሉ ከመነሻው ፈራሽና እንዳልተደረገ ይቆጠራል ተብሎ
መወሰኑ አግባብ አይደለም፤ ስልጣን ያለው የክፍሉ አስተዳዳር ውሉን ተቀብሎ የመዘገበ በመሆኑ
ሽያጩ በአዋጁ መሰረት አልተደረገም ሊባል አይችልም፤ በአዋጁ መሰረት አልተደረገም ቢባል
እንኳን ውሉ ጉድለት ያለበት ውል ነው ከሚባል በቀር ከመነሻው እንዳልተደረገ የሚያስቆጥር
ባለመሆኑ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የውሉ ህጋዊነት የተረዳበት እና የተረጎመበት መንገድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የፍ/ብ/ህ/ቁ 1716፣1717 እና 1718 እንዲሁም ይኽው ሰበር ሰሚ ችሎት ይህንኑ ጉዳይ


አስመልክቶ በመ/ቁ 43226 ላይ የሰጠው አስገዳጁ የህግ ትርጉም የተከተለ አይደለም፤ የሽያጭ ውሉ
ጉድለት የለበትም እንጂ ቢኖርበት እንኳን በአዋጁ መሰረት አልተደረገም የሚለውን መቃወሚያ
ማቅረብ ያለበት እና የሚችለው ጉዳዩ የሚመለከተው የክፍሉ አስተዳደር እንጂ መብታቸውን
በሽያጭ ያስተላለፉት ተጠሪ አይደሉም፤ ውሉ ከተደረገ ከአራት ዓመት በላይ በመሆኑ እና ከውሉ
በኋላም አመልካች በቦታው ላይ ከፍተኛ መሻሻል ያደረጉ በመሆኑ ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት
ሊመለሱ የሚችሉበት ሁኔታ የለም፤ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም ውሉ ህጋዊ አይደለም ውሉ
ከመወሰን ውጭ በውጤቱ ላይ ውሳኔ ያልሰጠ እንዲሁም ከውሉ በኋላ በቦታው ላይ ስለተደረገው
መሻሻል ሳይወሰን ማለፋ ከህግ አግባብ ውጭ በመሆኑ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ውሳኔ ውድቅ ተደርጎ
የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ሊፀና ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የክልሉ የሰበር ችሎት የሰጠው ውሳኔ የኢ/ፌ/ድ/ሪ ህገ
መንግስት አንቀፅ 80/3/ለ/፣ 4ዐ /6/፣ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 14/2/ ድንጋጌዎችን
በተገቢው ያገናዘበ ስለመሆኑ ግራቀኙ በተገኙበት በዚህ ችሎት እንዲመረመር በአጣሪ ችሎት
በመታዘዙ ተጠሪ የፅሁፍ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡

በዚህ መሰረት ተጠሪ በጠበቃቸው አማካኝነት ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም የተፃፈ ሁለት ገፅ መልስ
አቅርበዋል፡፡ ፍሬ ቃሉም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በሊዝ ውል የተገኘ ባዶ መሬት ሽያጭ የሊዝ
አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 24/2/ እና /3/ ድንጋጌን የተከተለ መሆን ስላለመሆኑ በጭብጥነት
ይዞ በመመርመር ውሉ በአዋጁ መሰረት ያልተደረገ መሆኑን አረጋግጦ የወሰነ በመሆኑ ውሳኔው
የሚነቀፍ አይደለም፤ በሽያጭ ውሉም የተላለፈው ባዶ መሬት በመሆኑ ከህግ መንግስቱ አንቀፅ
40/6/ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ይልቁንም ውሉ በባዶ መሬት ላይ የተደረገ እና የሊዝ
አዋጁንም ድንጋጌ ያልተከተለ ስለመሆኑ ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
ውሳኔ የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ሊፀና ይገባል የሚል ነው፡፡ የአመልካች
ጠበቃም ህዳር 10/2013 በተፃፈ የመልስ መልስ የሰበር ቅሬታቹውን የሚያጠናክር መከራከሪያ
በማከል የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሊሻር ይገባል በማለት ሞግተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም
የግራ ቀኙን ክርክር ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አኳያ አግባብነት
ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል፡፡

በመሠረቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራልም ሆነ የክልል ፍርድ ቤቶች


የዳኝነት ሥልጣን የሚመነጨው ከፌደራሉ ህገ መንግስት ስለመሆኑ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 78
ይደነግጋል፡፡ በህገ መንግስት አንቀፅ 8ዐ/3/ መሠረት በፌደራልም ሆነ በክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሥር ለማቋቋም የሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው የዳኝነት ስልጣን በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ
ውስጥ መሠረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞ ሲገኝ በሰበር አይቶ የማረም ሥልጣን ነው፡፡ ህገ
መንግስቱን መሠረት አድርገው በፌደራልም ሆነ በየክልሉ የታወጁት የፍር ድ ቤት ማቋቋሚያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አዋጆችም በህግ መንግስቱ በተገለፀው አግባብ ተመሳሳይ የዳኝነት ስልጣን ለሰበር ሰሚ ችሎት
የሰጡ ለመሆኑ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2ዐ13 አንቀፅ 1ዐ ድንጋጌ
እንዲሁም አሁን ለቀረበው ጉዳይ አግባብነት ካለው ከተሻሻለው ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና
ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 43/1994 አንቀጽ 5/3
ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡

በፌዴራልም ሆነ በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሥር የተቋቋመው የሰበር ሰሚ ችሎት በህገ


መንግስቱ እና ህገ መንግስቱን ተከትለው በወጡ አዋጆች የተሰጣቸው የሰበር ሰሚነት ስልጣን
ተግባራዊ ሲያደርጉ ፍሬ ነገርን በተመለከተ በዋናነት መነሻ የሚያደርጉት ስልጣን ባላቸው የበታች
ፍርድ ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ነው፡፡ እናም የሰበር ችሎት ቀዳሚ ተግባር
የሚሆነው የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ በማስረጃ የተረጋገጠውን መሠረት በማድረግ
በሰጡት የህግ ትርጉም ውስጥ የፈፀሙት መሠረታዊ የህግ ስህተት ካለ ለይቶ በህግ አግባብ ማረም
ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ሰበር ሰሚ ችሎት በሥር ፍርድ ቤት ተመዝኖ አቋም የተያዘበትን ጉዳይ
በተመለከተ በዝምታ በማለፍ አልያም በራሱ ማስረጃውን መዝኖ ውሳኔ ለ መስጠት የሚያስችለው
የህግ አግባብ የለም፡፡

ይህ ማለት ግን የበታች ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸውን ማስረጃዎችን ይዘት በአግባቡ ሳይመለከቱ


ሲቀሩ፤ ወይም በማስረጃ የተረጋገጠው እና ፍርድ ቤቱ የደረሰበት ድምዳሜ የተለያዩ ሆኖ በተገኝ
ጊዜ ሰበር ሰሚ ችሎት ይህንን መሰል ጉዳይ ማየት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ የዚህ ዓይነት
ሁኔታ ሲያጋጥም ጉዳዩ የማስረጃ ምዘና ጉዳይ ሳይሆን ማስረጃን እና ህግን በማዋሃድ ረገድ
የሚፈፀም ግድፈት በመሆኑ ጉዳዩ የማስረጃ ሳይሆን የህግ ነጥብ በመሆኑ ስልጣን ያለው የሰበር
ሰሚ ችሎት ጉዳዩን አይቶ ከማረም የሚከለክለው አይደለም፡፡

አሁን በቀረበው ጉዳይ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን ወሳኔ ለመሻር የጠቀሰው
ሁለት ምክንያቶችን ነው፡፡ አንዱ ውሉ በራሱ በባደ መሬት ላይ የተደረገ በመሆኑ ከመነሻውም ውሉ
ኢ-ህገ መንግስታዊ ነው የሚል ሲሆን ሌላው ደግሞ የሽያጭ ውሉ በሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2ዐዐ4
አንቀፅ 24/2/ እና /3/ መሠረት አልተደረገም የሚል ነው፡፡ እንግዲህ በሥር ፍርድ ቤቶች
ከተደረገው የግራ ቀኙ ክርክር መረዳት እንደሚቻለው የውሉ ጉዳይ በሊዝ ውል የተገኘ ሙብትን
በሽያጭ ማስተላለፍ ስለመሆኑ ከመገለፁ ውጭ በሽያጭ የተላለፈው ባዶ መሬት ይሁን

አልያም ግንባታ ያለበት መሆኑ የክርክር ጭብጥ አልነበረም ፡፡ የሽያጭ ውሉ በባዶ መሬት ላይ
የተደረገ ነው የሚለው ጉዳይ የተነሳው በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ነው፡፡ ከወሉ ህጋዊነት አኳያ
በአሁን ተጠሪ አና ባለቤታቸው ሲቀርቡ የነበረው መከራከሪያዋ ውሉ በባልና ሚስት የጋራ መብት
ላይ ያለተጠሪ ፈቃድ እና ህጋዊ ውክልና የተደረገ ነው፤ እንዲሁም በሊዝ አዋጁ መሠረት የተደረገ
አይደለም የሚል ነው፡ ከዚህ ባለፈ ውሉ በባዶ መሬት ላይ የተደረገ ነው በሚል የቀረበ ክርክር
የለም፡፡

በእርግጥ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የመዋዋል ነፃነት ከሚገደብባቸው ልዩ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ
የውሉ ጉዳይ ህጋዊ መሆን እንደ ሆነ እና በውጤት ደረጃም ለህግ ተቃራኒ የሆነ ውል ፈራሽ
ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ/1711 እና 1716 ድንጋጌ ያስገነዝባል፡፡ ከዘህ አንፃር በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ
መንግንት አንቀፅ 4ዐ/3/ የገጠርም ሆነ ከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት መብት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመንግስትና የህዝብ ብቻ መሆኑን እና መሬት የማይሽጥ የማይለዋጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፤


ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት መሆኑ ተደንግጓል፡፡ እናም በፍርድ ቤት በቀረበ ክርክር
በተከራካሪ ወገኖች የቀረበው ውል የውሉ ጉዳይ የህገ መንግስቱን እና የመሠረታዊ ህግ መንግስታዊ
ህግ ድንጋጌን የሚቃረን መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ስለ ውሉ ህጋዊነት ከተከራካሪዎች የሚቀርብ
መቃወሚያን መጠበቅ ሳያስፈልግ ፍርድ ቤት በራሱ ጊዜ አንስቶ መመርመር ያለበት ጉዳይ ነው፡፡
ከዚህ አኳያ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሽያጭ ውሉን ህጋዊነት አንስቶ መመርመሩ የሚነቀፍ
ተግባር አይደለም፡፡

ሆኖም በግራ ቀኙ መካከል ተደረገ የተባለው ውል የውሉ ጉዳይ በእርግጥም በህግ የተከለከለ
ስለመሆኑ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ እንግዲህ ግራ ቀኙ የሚከራከሩት የሊዝ መብት
ከማስተላለፍ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው የሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2ዐዐ4 ነው፡፡
በዚህ አዋጅ መሠረት የሊዝ ባለመብት የሆነ ሰው በአዋጁ በተመለከተው ሥርዓት መሠረት የሊዝ
መብቱን በሽያጭ ለማስተላለፍ አልያም በዋስትና ለማስያዝ የሚችል ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀፅ 24
ተመልክቷል፡፡ መብቱም ግንባታ ከመጀመሩ አልያም በግማሽ ከማጠናቀቁ በፊት ሊተላለፍ የሚችል
ስለመሆኑ በዚህ አንቀፅ በንዑስ አንቀፅ 2 ሥር ተመልክቷል፡፡ በእርግጥ በዚህ መልኩ
የሚተላለፈው የሊዝ መብት አግባብ ባለው አካል በሚደረግ ቁጥጥር መፈፀም የሚገባው ስለመሆኑ
ተመልክቷል፡፡ እናም ከአፈፃፀም አኳያ የተቀመጠው ሥርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ የሊዝ
በላመብት የሆነው የሊዝ መብቱን ግንባታ ከመጀመሩ በፊትም ቢሆንም ማስተላለፍ እንደሚችል
የተፈቀደ በመሆኑ የዉሉ ጉዳይ በህግ የተከለከለ ነው ሊባል የሚችል አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር
የክልሉ ሰበር ሲሚ ችሎት ጉዳዩን የተረዳበት መንገድ በሊዝ ባለመብቶች የተረጋገጠውን የመብት
አድማስ ያላገናዘብ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፡፡

የሽያጭ ውሉ በሊዝ አዋጁ በተመለከተው አግባብ አልተፈፀመም የተባለውን በተመለከተ ጉዳዩ


በመጀመሪያ የዳኝነት ሥልጣኑ የተመለከተው የከተማው መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሉ ጉዳዩ
ለሚመለከተው ለክፍሉ አስተዳደር ቀርቦ እና አስተዳደሩም ውሉን ተቀብሎ በውሉ መሠረት
አስፈላጊ ክፍያዎችን አስከፍሎ በስም ዝውውር ሂደት ላይ እያለ የአሁን ተጠሪ ተቃውሞ
በማቅረባቸው ምክንያት ሂደቱ የቆመ ስለመሆኑ ማረጋገጡን በፍርድ ሀተታው ውስጥ በግልፅ
አስፍሯል፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው በሊዝ ውል በተገኝ ይዞታ ላይ ግንባታ ከመጀመሩ አልያም
ግንባታው በግማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የመብት ማስተላለፍ ሂደቱን የመከታተል እና የመቆጣጠር
ሥልጣን የተሰጠው አስተዳደር ክፍል በውሉ ይዘትና አፈፃፀም ላይ ተቃውሞ የሌው መሆኑን
ነው፡፡ ከውሉ ሂደት እና አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ጉድለት ቢኖር እንኳን ውሉን አልቀበልም ብሎ
የመመለስ አልያም አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ ተሟልቶ እንዲቀርብ የማዘዝ ስልጣን ያለው ይኸው
አካል፡፡ ሆኖም ከዚህ አኳያ ውሉ የተነቀፈ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክርም ሆነ የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡
ይህ ከሆነ ደግሞ ውሉ በአዋጁ በተመለከተው ሥርዓት አልተፈፀመም የሚባልበት ምክንያት
የለም፡፡ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም ቢሆን የሽያጭ ውሉ በሊዝ አዋጁ በተመለተው አግባብ
አልተከናወነም ከማለት በዘለለ የሥር ፍርድ ቤቶች ከዚህ አንፃር በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጡትን እና
ያን መሠረት አድርገው የደረሱበትን ድምዳሜ ያልተቀበሉበትን ምክንያት አልገለፀም፡፡ ወሉ በአዋጅ
መሠረት አልተፈፀመም በሚል በጥቅሉ ከመገለፁ ውጭም ምን ማሟላት ሲገባ እንዳልተፈፀመ
በግልፅ ተጠቅሶ የተሰጠ ትችት የለም፡፡ ይህ በሌለበት የሥር ፍርድ ቤቶች ወሳኔን መሻሩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በእርግጥም የሚነቀፍ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ ተከታዩ ውሳኔ


በአብላጫ ድምፅ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

1. የደቡብ ብሔር ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝባች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 14ዐ21 ላይ ታህሳስ 17/2ዐ12 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ
ቁጥር 348/1/ መሠረት ተሽሯል፡፡
2. የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 254ዐ2 ላይ ሰኔ 28/2ዐ11
ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔን በማፅናት የሃድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
በመ/ቁ 2ዐ174 ላይ መስከረም 13/2ዐ12 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር
348/1/ መሠረት ፀንቷል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡
2. መዝገቡ ተዘግቷል
የማይነበብ የሶሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የልዩነት ሃሳብ

ስማችን በተቁ. 1 እና 3 ላይ የተገለጸው ዳኞች አብላጫው ድምጽ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ ለመሻር በሰጠው ምክንያት ስላልተስማማን የሀሳብ ልዩነታችንን
እንደሚከተለው አስፍረናል፡፡

ከመዝገቡ ይዘት በግልጽ መገንዘብ እንደሚቻለው የተጠሪ የቀድሞ ባለቤት የነበሩት አቶ በላይ
ላጲሶ ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ ጸንቶ በነበረበት አከራካሪ የሆነውን ንብረት ለአሁን አመልካች
ሸጡ የተባሉት መጋቢት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ግለሰቡ ጠቅላላ የአስተዳደር
የውክልና ስልጣን የነበራቸው ቢሆንም ንብረቱን በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚያስችል የውክልና
ስልጣን እንዳልነበራቸው በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው፡፡ የተጠሪ ባለቤት የነበሩት
ግለሰብ ንብረቱን በሽያጭ ለአሁን አመልካች ባስተላለፉበት ጊዜ የውክልና ስልጣን ካልነበራቸው
ከመነሻውም ቢሆን ስልጣን ሳይኖራቸው የተደረገ የሽያጭ ውል በመሆኑ ውሉ ሕጋዊ ውጤት
አይኖረውም፡፡ ስለሆነም ይህን ህጋዊ ውጤት የሌለውን የሽያጭ ውል በመያዝ ስመ ሀብቱን
ለማዘዋወር በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ቤት ሲቀርቡ ግለሰቡ ይህንኑ ለማድረግ የሚያስችል
የውክልና ስልጣን የሌላቸው መሆኑ ተነግሮአቸው የሽያጭ ውሉ ከተደረገ በኋላ ሚያዝያ ዐ3 ቀን
2008 ዓ.ም. የተሰጣቸው የውክልና ስልጣን ወደኋላ ተመልሶ አስቀድሞ መጋቢት 29 ቀን 2008
ዓ.ም. የተደረገውን የሽያጭ ውል ህጋዊ የማድረግ ውጤት አይኖረውም፡፡

ምንም እንኳን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሉ የተደረገው በባዶ መሬት ላይ
ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ የሻረ ቢሆንም ከላይ በጠቀስነው ሕጋዊ ምክንያት
የሽያጭ ውሉ ህጋዊ ውጤት ሊኖረው አይገባም የሚል እምነት ያለን በመሆኑ በውጤት ደረጃ
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ ሊጸና ይገባ ነበር በማለት በሐሳብ
ተለይተናል፡፡

የማይነበብ የሁለት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰ/መ/ቁ፡-191430
ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር - አልቀረቡም

ተጠሪዎች ፡- 1ኛ. አቶ ታምሩ ደብሩ አልቀረቡም

2ኛ. አቶ አንተነህ ደበበ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ክርክሩ የአክሲዮን ድርሻ ትርፍ እንዲከፈል የቀረበ ክስን መሰረት ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የምእራብ
ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተጠሪ ከሳሽና 1ኛ የከሳሽ ተከሳሽ፣ አመልካች ተከሳሽና የተከሳሽ ከሳሽ
እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ 2ኛ የተከሳሽ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

1ኛ ተጠሪ ጥቅምት 23 ቀን 2009 ዓ.ም ፅፎ ባቀረበው ክስ በአመልካች ኩባንያ ውስጥ በልዩ ቁጥር 1457
የተመዘገበ የአክሲዮን ድርሻ ያለኝ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ ሒሳብ ተሰርቶ ሊከፈለኝ ሲገባ ከ2006 እስከ
2008 ያልተከፈለኝ የአክሲዮን ትርፍን ፍርድ ቤቱ ሂሳቡን በማስመርመር በግምት ብር 30,000 እንዲከፈለኝ
ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች ህዳር 13 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ እና የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል፡፡ በመከላከያ መልሱ
1ኛ ተጠሪ የኩባንያው ባለአክሲዮን ስለመሆኑ ያቀረበው የድርሻ ሰርተፊኬት ወይም የአክሲዮን ድርሻ
ስለመግዛቱ የሚገልፅ ማስረጃ ስለሌለ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33 መሰረት ክስ የማቅረብ መብት የለውም፡፡
ዳኝነት የተጠየቀበት ገንዘብም ከምን ያህል የአክሲዮን ድርሻ ላይ እና በእያንዳንዱ አመት ምን ያህል
የአክሲዮን ትርፍ እንደተገኘ ስለማይገልፅ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 216 መሰረት ተቀባይት የለውም የሚል
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል፡፡ በፍሬ ጉዳይ ላይ በሰጠው መልስ 1ኛ ተጠሪ የሚከፈለው
የአክሲዮን ትርፍ የለም እንጂ አለ እንኳ ቢባል የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ.ም
ያሳለፈውና በፌደራል ሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተመዘገበውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ
የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥር HT/FIND/245/15 ባወጣው መመሪያ
መሰረት የሚከፈለው ገንዘብ የለም፡፡ 1ኛ ተጠሪ በኩባንያው ምስራቅ ዲስትሪክት ጭሮ አካባቢ ፅ/ቤት በሽያጭ
ሰራተኝነት ሲሰራ ብር 301,792.50 ለግል ጥቅሙ ያዋሉ ስለሆነና በእጁ ያለውን ሰነድ አስረክቦ ክሊራንስ
እስካላቀረበ ድረስ የሚከፈለው ክፍያ እንደሌለ እያወቀ ያቀረበው ክስ የህግ መሰረት የለውም ተብሎ ውድቅ
ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል፡፡

በሌላ በኩል አመልካች በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ 1ኛ ተጠሪ በድርጅቱ ከሰኔ 12 ቀን
2003 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 2007 መጨረሻ በሽያጭ ሰራተኝነት ተቀጥሮ ሲሰራ ከተረከበው መጠናቸው
የተለያዩ የሞባይል ካርዶች እና ዲምላይት የሚባል የሶላር መብራት ሽያጭ በኩባንያው የባንክ ሒሳብ
ማስገባት ሲገባው ብር 301,972.50 ለግል ጥቅሙ በማዋል ማጉደሉ ሐምሌ 6 ቀን 2007 ዓ.ም በተደረገ
የኦዲት ምርምራ ተረጋግጧል፡፡ 2ኛ ተጠሪም ጥቅምት 21 ቀን 2004 ዓ.ም በተፈረመ የዋስትና ውል 1ኛ
ተጠሪ በአመልካች ንብረት ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት እስከ ብር 100,000 ለመክፈል ተስማምቷል፡፡ ስለሆነም
1ኛ ተጠሪ ይህን ገንዘብ ወለድን ጨምሮ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ በገባው ዋስትና መሰረት ወለድን ጨምሮ
ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በአንድነት እና በነጠላ እንዲከፍሉ እንዲወሰን እንዲሁም የ1ኛ ተጠሪ አክሲዮን በጫረታ
ተሽጦ ለእዳው ለአከፋፈል እንዲውል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡

1ኛ ተጠሪ በተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ላይ ህዳር 23 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል፡፡ በመልሱም
ያጎደልኩት ሒሳብ የለም፡፡ በ1ኛ ተጠሪ እጅ ያሉ የተለያዩ ደረሰኞች ሳይመረመሩ በአመልካች ፍላጎት ብቻ
የተሰራው የውስጥ ኦዲት ተቀባይነት የለውም፡፡ ከዚህ በፊት በወረዳው ፍርድ ቤት በነበረን ክርክር ተቀባይት
ያጣ ስለሆነ በገለልተኛ የሂሳብ ባለሞያ ተጣርቶ በነፃ ልሰናበት ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

2ኛ ተጠሪ በበኩሉ አመልካች ተጠሪን የተለያዩ ክፍያዎችን ከፍሎ ከስራ ሲያሰናብተው እዳ ካለበት ተቀናሽ
ሊያደርግ ይገባ ነበር፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያጎደለው ንብረት የለም፡፡ አለ እንኳ ቢባል በቂ ንብረት ያለው በመሆኑ አኔ
ላይ የቀረበው ክስ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክርና የሰው ማስረጃ ከሰማ በኋላ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች ኩባንያ የአክሲዮን ድርሻ
ያለው መሆን አመሆኑንና ያለው ከሆነ ሊያገኝ ሲገባው የቀረበት ጥቅም እንዲሁም 1ኛ ተጠሪ ያጎደለው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሒሳብ ካለ በባለሞያ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት በቁጥር wmm00606 ግንቦት
16 ቀን 2009 ዓ.ም የቀረበው ሪፖርት 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ኩባንያ ከተቀበለው ጠቅላላ መጠኑ ብር
9,848,456 የሆነ የሞባይል ካርድ እና ዲምላይት ዋጋ በላይ ብር 10,194,395.25 ገቢ ማድረጉን ገልጿል፡፡
አመልካች 1ኛ ተጠሪን ያለአግባብ ከስራ በማሰናበቱ ምክንያት 1ኛ ተጠሪ የተለያዩ ክፍያዎችን ለማስከፈል
በመ/ቁጥር 29811 ክስ ሲያቀርብ አመልካች 1ኛ ተጠሪ ገንዘብ ያጎደለ መሆኑን ገልፆ ያቀረበው ክርክር
የለም፡፡ የ1ኛ ተጠሪ ምስክሮች እና የአመልካች 1ኛ ምስክር ተጠሪው ገንዘብ ማጉደሉን አናውቅም በማለት
የመሰከሩ በመሆኑ 2ኛ የአመልካች ምስክር ተጠሪው ገንዘብ አጉድሏል በማለት የሰጠውን ምስክርነት
ተዓማኒነት የሚያሳጣው ሲሆን የቀረበው የባለሞያው ማስረጃም ተጠሪው በብልጫ ብር 347,939.25
መክፈሉን የሚያረጋግጥ ስለሆነ በአመልካች የቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ተገቢነት የለውም፡፡ የቀረበው
የባለሞያ ሪፖርትም በ2006 እና 2007 ዓ.ም 1ኛ ተጠሪ ያልተከፈለው ብር 25,804.33 የአክሲዮን ድርሻ
ትርፍ ያለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ስለሆነ እና የካቲት 9 ቀን 2007 የተደረገው የባለአክሲዮኖች ስብስባ እና
የን/ሕ/ቁጥር 452 አክሲዮን ድርሻ ክፍያን ስለማይከለክል ይህን ገንዘብ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ይክፈል
በማለት ወስኗል፡፡

አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኙን ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ አመልካች በስር ፍ/ቤት የቀረበው የኦዲት ሪፖርት የአዲት ስርዓትን ጠብቆ ያልተሰራ እና አንድ
ደረሰኝ ለሒሳብ ስሌቱ ሁለት ጊዜ በመያዝ የተፈጸመ ነው ይህንንም ቅሬታ በስር ፍ/ቤት አቅርቤ መታለፉ
ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረበውን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የምእራብ ሀረርጌ ዞን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ
ፅ/ቤት በድጋሜ ኦዲት አድርጎ ውጤቱን እንዲገልጽ ያሳወቀ ሲሆን ፅ/ቤቱም የባንክ እስቴትመንት እና የባንክ
እስሊፕን መሰረት በማድረግ አጣርቶ በቁጥር WMMDO06/06/2/85 መጋቢት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበ
ውጤት የብር 198,719.25 ጉለት በ1ኛ ተጠሪ ላይ መገኙትን ሰላረጋገጡ የስር ፍ/ቤት የአመልካችን ክስ
ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም ይህን ገንዘብ 1ኛ ተጠሪ ይክፈል፤ 2ኛ ተጠሪም ዋስ እስከሆነበት የገንዘብ
መጠን ብር 100,000 ድረስ ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በአንድነት እና በነጠላ ይክፈል በማለት ወስኗል፡፡

አመልካች የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ጉዳዩን በመጀመሪያ በተመለከተው ፍ/ቤት ከጠየኩት
ዳኝነት ላይ ብር 103,253 ተቀናሽ ተደርጎ መወሰኑ አግባብ አይደለም፤ በኦዲት ሪፖርት ተቀናሽ የተደረገው
ብር 292,125 ገቢ ስለመደረጉ በባንክ እስቴትመንቱ የማይታይ እና ደረሰኞቹ ላይ በእጅ የተፃፈው እና በባንኩ
ማህተም ላይ የተገለፀው ቀን ልዩነት የሚታይበት በመሆኑ ትክክለኛነቱ ከባንኩ እንዲጣራ ያቀረብኩት
አስተያየት ታልፎ ዳኝነት ከጠየቀበት የገንዘብ መጠን ብር 103,253 አለመወሰኑ አግባብ አይደለም በሚል
ይግባኙን ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቧል፡፡ ፍ/ቤቱም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ባይ ዳኝነት
ከጠየቀበት የገንዘብ መጠን ብር 198,719.25 እንዲከፈለው የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በማሻሻል
ሲወስን አሁን ይግባኝ የተጠየቀበትን ቀሪውን ብር 103,253 በተመለከተ የከፍተኛ ፍ/ቤት ከወሰነው ጋር
ተመሳሳይ አቋም መያዙን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ የክልሉ ፍ/ቤቶች በውክልና ስልጣናቸው የሰጡት ውሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተመሳሳይ በሆነበት በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 9 አመልካች የተሰጠው ሌላ የይግባኝ መብት የለም በማለት
ቅሬታውን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቶታል፡፡

አመልካች የካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው ይህን የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ
በመቃወም ነው፡፡ የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ የክልሉ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካችን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ
ሙሉ ለሙሉ ውድቅ በማድረግ ሲወስን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሒሳቡን በገለልተኛ የሂሳብ ባለሞያ
እንዲመረመር አድርጎ 1ኛ ተጠሪ የሚታይበትን ጉለት ብር 198,719.25 እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ በገባው
ዋስትና መሰረት በአንድነት እና በነጠላ እንዲከፍል የስር ፍ/ቤቱን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ በመሻር ወስኖ እያለ
ውሳኔዎቹ ተመሳሳይ ናቸው በሚል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታውን ለ2ኛ
ጊዜ የቀረበ ይግባኝ ነው በሚል ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም፡፡ በተጨማሪም የምስራቅ ሀረርጌ ዞን
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት ኦዲተሮች ምርመራው የተሰራበትን አግባብ በሚመለከት የአመልካች የባንክ
ሒሳብ 1000014402091፣ 1000032664176 እና 1000024461468 መሰረት አድርገው ምርመራ
ከተደረገበት የባንክ እስቴትመንት ላይ የማይታይ ብር 292,125.00 1ኛ ተጠሪ ገቢ ያደረጉበት ደረሰኝ ላይ
ይታያል በሚል ተቀናሽ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም በሚል ያቀረብነው መቃወሚያ ሳይታይ ታልፎ የክልሉ
ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

አቤቱታው በሰበር አጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ ጉዳዩ የተጀመረው በዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ይግባኝ
ሰሚው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የዞኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ሽሮታል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው
ውሳኔ ላይ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲያቀርብ የስር ፍ/ቤቶች ሁለቱም ተመሳሳይ ውሳኔ
እንደሰጡበት ተደርጎ ለ2ኛ ጊዜ ይግባኝ ማቅረብ አይቻልም ተብሎ መዘጋቱ ከአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ
9(2) አንፃር ለማጣራት ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪዎች መልሳቸውን እንዲያቀርቡ ታዟል፡፡

ተጠሪዎች በጋዜጣ ጥሪ ተደርገው መልስ ባለማቅረባቸው መልስ የማቅረብ መብታቸው ታልፏል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
የአመልካች ይግባኝ አቤቱታ ለ2ኛ ጊዜ የቀረበ ነው ብሎ ውድቅ የማድረጉን እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ
ፍ/ቤት አመልካች በስር ፍ/ቤት ዳኝነት ከጠየቀበት የገንዘብ መጠን ብር 301,792.50 ውስጥ ብር
198,719.25 ብቻ እንዲከፈለው የመወሰኑን አግባብነት በስር ፍ/ቤት ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ
ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዲሁም ከፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 9 እና ሌሎች ለጉዳዩ
ተገቢነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

በመጀመሪያም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች የይግባኝ መብቱን ስለጨረሰ ይግባኝ ማቅረብ
አይችልም የማለቱን አግባብነት ስንመለከት በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 80(2)(4) መሰረት የክልል ፍርድ
ቤቶች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን ስር የሚወድቁ ጉዳዮችን
በውክልና ስልጣን መመልከት የሚችሉ መሆኑ፤ የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤቶችም የዞን ፍ/ቤቶች በውክልና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የዳኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔን በይግባኝ የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ጉዳዮችን በተወካይነቱ በይግባኝ ሰሚ ስልጣኑ ተመልክቶ ክልሉ
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ የሠጠ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን
በይግባኝ የመመልከት ስልጣን ያለው ስለመሆኑ በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 9 ላይ
ተመላክቷል፡፡

አመልካች በፌደራል መንግስት የተመዘገበ ተቋም በመሆኑ የምእራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን
የተመለከተው በውክልና ስልጣኑ መሆኑ አላከራከረም፡፡ በዚህ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ በመሰረተው ክስ
በአመልካች ኩባንያ ውስጥ በልዩ መዝገብ ቁጥር 1457 የተመዘገበ የአከሲዮን ድርሻ ያለው መሆኑን ገልጾ
ከ2006-2008 ዓ.ም ያልተከፈለ የአክሲዮን ድርሻ ትርፍ ብር 30,000 እንዲከፈለው ዳኝነት ጠይቋል፡፡
አመልካች ክሱን ክዶ የተከራከረ ሲሆን በአንጻሩ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል፡፡ በዚህም ክስ ተጠሪ
በአመልካች ኩባንያ የምስራቅ ዲስትሪክት በሽያጭ ሰራተኝነት ተቀጥሮ ባገለገለበት ጊዜ ብር 301,792.50
ማጉደሉን ገልጾ ይህንን ገንዘብ 1ኛ ተጠሪ እንዲከፍል እንዲወሰንለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን
ምስክር ከሰማ በኋላ በጉዳዩ ላይ የባለሞያ ሪፖርት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ተጠሪ ገንዘብ አለማጉደሉን
ይልቁንም በብልጫ ብር 347,939.25 ለአመልካች ኩባንያ ገቢ ማድረጉ እንዲሁም ያልተከፈለው የአክሲዮን
ድርሻ ትርፍ ብር 25,804.3 መኖሩን አረጋግጦ የአመልካችን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውድቅ አድርጎ አክሲዮን
ድርሻ ትርፉን ለተጠሪ እንዲከፍል ወስኗል፡፡ አመልካችም በስር ፍ/ቤት የቀረበውን የባለሞያ ሪፖርት
በመቃወም ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ጉዳዩ በድጋሚ በባለሞያ እንዲጣራ ተደርጎ ተጠሪ ብር
198,719.25 ማጉደሉ በመረጋገጡ በዚሁ አግባብ ተጠሪዎች ኃላፊነት አለባቸው በማለት ወስኗል፡፡ በዚህም
ምክንያት አመልካች ቀድሞ ዳኝነት ከጠየቀበት ብር 301,792.5 ውስጥ ውሳኔ ባልተሰጠበት ብር 103,253
ላይ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኙን አቅርቦ በዚህ ገንዘብ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ
ከዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ለ2ኛ ጊዜ የቀረበ ይግባኝ ነው በሚል ውድቅ
አድርጎታል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የክልሉ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን
የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውድቅ ሲያደርግ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ዳኝነት ከተጠየቀበት
የገንዘብ መጠን ውስጥ ውድቅ ያደረገውን እና አመልካች ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበበትን
የገንዘብ መጠን ብር 103,253 ትክክል ነው በሚል ተቀብሎ መጉደሉ የተረጋገጠው ገንዘብ ብር 198,719.25
እንዲከፈለው ወስኗል፡፡ ይህም በሁለቱም ደረጃ ያሉት የክልሉ ፍርድ ቤቶች ብር 103,253 በሚመለከት
በአመልካች የቀረበውን የዳኝነት ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን የሚያሳይ ነው ወይም ይህን ገንዘብ
በሚመለከት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ከዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ጋር በውጤት ደረጃ
ልዩነት የለውም ወይም አፅንቶታል የሚያስብል ነው፡፡ በመሆኑንም አመልካች በክልሉ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ
ላይ መሰረታው የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ካለ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር
አቤቱታ ከሚያቀርብ በቀር ለ2ኛ ጊዜ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሚያቀርብበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አግባብ ስለሌለ መዝገቡ መዘጋቱ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 9 ን መሰረት ያደረገ
ስለሆነ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበውን ቅሬታ አልተቀበልነውም፡፡

በመቀጠል አመልካች የምእራብ ሐረርጌ ዞን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በድጋሜ ለክልሉ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት በላከው ሪፖርት ላይ ቅሬታ አቅርቤ እያለ ተገቢነት ባለው ማስረጃ እንዲጣራ ሳይደረግ መወሰኑ
ተገቢ አይደለም በሚል የሚያቀርበውን መቃወሚያ ስንመለከት አመልካች በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበውን
የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማጣራት እንዲቻል ለባለሞያ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ባለሞያው ተጠሪ ሒሳብ አለማጉደሉን
ይልቁንም በብልጫ ለአመልካች ገቢ ያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ በአንጻሩ አመልካች ይህን የባለሞያ ሪፖርት
መሰረት ተደርጎ የተሰጠውን ውሳኔ የኦዲት ስርዓትን የተከተለ አይደለም በማለት በመቃወሙ በድጋሜ
እንዲጣራ ትዕዛዝ ተሰጥቶ የምእራብ ሐረርጌ ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤትም የባንክ እስቴትመንት
እና ደረሰኝን መሰረት አድርጎ በማጣራት ተጠሪ ብር 198,719.25 ማጉደሉን በማረጋገጡ በዚሁ አግባብ
ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ ይህም ፍ/ቤቱ በጉዳዩ ላይ ትክክለኛ ውሳኔ መስጠት እንዲቻለው ተገቢውን ማጣራት
ያደረገ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ ሰበር ችሎት ኢ.ፌ.ድ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ
80/3/ሀ መሰረት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸውን ውሳኔዎች ማረም ነው፡፡
ከዚህ ውጪ ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ማስረጃን መዝነው የሚደርሱበትን የፍሬ
ነገር ድምዳሜ የማስረጃ አቀባበል እና ምዘና መርህ ጥሰት እስካልተፈጸመበት ድረስ ይህ ችሎት የማረም
ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ አመልካች ከባንክ እስቴትመንት እና ከባንክ እስሊፕ አንጻር የሚያነሳው ክርክር
የማስረጃ ምዘናን የሚመለከት የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት የኦዲት ሪፖርቱን መርምሮ የደረሰበትን ድምዳሜ እንዳለ የሚቀበለው ይሆናል፡፡በመሆኑ የክልሉ ጠቅላይ
ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ቋሚ ችሎት በመ/ቁጥር 276775 በቀን 01/09/2011
ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 193168
ቀን ፡- ሕዳር 29 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- 1. ወ/ሮ መሠለች ደስታ

2. ወ/ሮ ወሰንየለሽ መንክር

3. አቶ ቀደሰ መንክር

4. አቶ አክሊሉ መንክር

5. ወ/ሪት ፎቶ መንክር

6. ወ/ሮ ፀሐይ መንክር

7. ወ/ሮ ሒሩት መንክር

8. አቶ ናርዶስ መንክር

9. አቶ ነብዩ መንክር

ተጠሪ ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ
የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ
እንደተረዳነው አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተከሳሽ እና ተጠሪ የመቃወም አመልካች ነበሩ፡፡ አመልካቾች በዚህ ችሎት ደረጃ ተከራካሪ ባልሆነው የአዲስ
ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 582 በሆነ ይዞታ
ላይ ያላቸው ካርታ እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ሲሉ የጠየቁት ዳኝነት በፍርድ ቤቱ ውደቅ
በመደረጉ ይግባኝ አቅርበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ተመልክቶ አመልካቾች በዕጃቸው
በሚገኘው 783.82 ካሬ ሜትር ይዞታ በመሆኑ ካርታውን እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ
ወስኗል፡፡

ተጠሪ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት ፍርዱን በመቃወም ማመልከቻ ያቀረበ ሲሆን ይዘቱም ተከሳሽ
የነበረው የወረዳ አስተዳደር ካርታ የማስተካከል ሥልጣን የለውም፣ በዚህም የከተማው አስተዳደር ሆነ
የነዋሪዎች መብትና ጥቅም ተነክቷል፡፡ አመልካቾች በ773 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ዳኝነት ጠይቀው
ባልተጠየቀ ዳኝነት በ783.82 ካሬ ሜትር ላይ መወሰኑ ተገቢ አይደለም፡፡ ይዞታ ማረጋገጫ እንዲሰጠኝ
በማለት በፍርድ ቤት ዳኝነት የሚጠየቅበት አይደለም ተብሎ ፍርዱ እንዲሰረዝ የሚል ነው፡፡ አመልካቾች
ባቀረቡት መልስ የወረዳውን አስተዳደር ወክሎ ዐቃቤ ሕግ ሲከራከር ስለነበር ተጠሪ ባለው አደረጃጀት ጉዳዩን
ቀድሞ የሚያውቀው ነው፡፡ ሁለት ጊዜ ታይቶ ውሳኔ ካገኘና ከጸና በኋላ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት
የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1/1195፣
2/1995፣ 18/1997፣ 4/2000 እና 64/2011 እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመዝገብ ቁጥር 37502 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተጠሪ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት
መቃወሚያ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ቀደም ሲል የተሰጠውን ፍርድ በማሻሻል የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት የፈጠረውን ሁከት እንዲያስወግድ የተሰጠው የውሳኔ ከፍል በማጽናትና ካርታው
እንዲስተካከል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ግን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤትን
የሚመለከት ባለመሆኑና በፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኝነት የሚጠየቅበት ባለመሆኑ ፍርዱ በከፊል ሊሰረዝ ይገባል
በማለት ወስኗል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የአመልካቾችን ይግባኝ ባለመቀበል
ሠርዟል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የአዲስ ከተማ ክፍለ
ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤትን ወክሎ የክፍለ ከተማው ዐቃቤ ሕግ ሲከራከር የነበረ በመሆኑ በአንድ
አደረጃጀት ሥር ያለው ተጠሪ ተቃዋሚ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፤ ተጠሪ ጉዳዩን በአስተዳደራዊ አቤተታ ሆነ
በፍርድ ቤት ክርክር ሂደት የሚያውቀው ነው፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱም በመዝገብ ቁጥሮች 165372 እና
165750 ላይ ትርጉም የሠጠበት ነው፡፡ ተጠሪ ያነሳው የፍሬ ነገር ክርክርም ቀደም ሲል ክርክር ተደርጎበት
ውሳኔ የተሰጠበትና ተጠሪን መብትና ጥቅም የሚነካ አይደለም የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን
ተመልክቶ ይዞታው የአመልካቾች መሆኑ በተረጋገጠበት እና መስተዳድሩ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ባልተካደበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤት ካርታን አስመልክቶ ውሳኔ ያልሰጠበት አግባብ ለማጣራት ተጠሪ መልስ
እንዲያቀርቡ በማዘዙ ተጠሪ ያቀረበው መልስ የወረዳ ሆነ በክፍለ ከተማ ደረጃ ያለ ዐቃቤ ሕግ እና ተጠሪ
የተለያየ ነው፤ በአንድ መዋቅር የተደራጀም አይደለም፤ የተለያየ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ነው፡፡ የተጠቀሱት
የሰበር ውሳኔዎች ለጉዳዩ አግባብነት የላቸውም፡፡ ተጠሪ መብትና ጥቅሙ በመነካቱ ተቃዋሚ ሆኖ መከራከሩ
ተገቢ ነው፤ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊጸና ይገባል በማለት ክርክሩን አቅርቧል፡፡ አመልካቾች የመልስ
መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ተጠሪ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት ተቃዋሚ
ሆኖ ማመልከቻ ማቅረቡ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ
መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመረዉም ተጠሪ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት ላቀረበዉ የመቃወም


አቤቱታ መሠረት ያደረገዉ አመልካቾች በስር ተከሳሽ በነበረዉ የአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር
ጽ/ቤት ላይ ያቀረቡትን ክስ መሠረት በማድረግ ካርታ እንዲያስተካክልና ሁከት እንዲያስወግድ ፍርድ ቤቱ
የሰጠዉ ዉሳኔ የአስተዳደሩ ነዋሪዎችን መብትና ጥቅም የሚነካ በመሆኑ እና ተጠሪ በፍርድ ቤት ክርክር
አቅርቦ ይህን መብት ለማስከበር በህግ ስልጣን የተሰጠዉ መሆኑን በመጥቀስ ነዉ፡፡ በእርግጥ ተጠሪ በፍርድ
ቤት ክርክር አቅርቦ የከተማ አስተዳደሩን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም የማስከበር ስልጣን በህግ የተሰጠዉ
መሆኑ አላከራከረም፡፡ አከራካሪዉ እና የዚህን ችሎት እልባት የሚያሻዉ ጭብጥ አመልካች በፍርድ ቤት
ክርክር በማድረግ የከተማዉ ነዋሪዎችን/የህዝብና የመንግስትን መብትና ጥቅም ለማስከበር ያለዉ
መብት/ስልጣን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣንና ኃላፊነት ባለዉ ሌላ የከተማዉ አስተዳደር
አካል ክርክር ተደርጎበት ዉሳኔ ያረፈበት ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358
መሠረት የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ ያስችለዋል ወይ? የሚለዉ ነዉ፡፡

እንደሚታወቀዉ ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸዉን የጽሑፍ ክርክር መርምረዉ፣ በቃል የሚቀርቡ ክርክሮችን
አዳምጠዉ፣ ማስረጃዎችን መዝነዉ እና መሠረታዊ ህጎችን ተርጉመዉ ዉጤት ላይ መድረስ ይችሉ ዘንድ
ሥርዓት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ክርክሮች የሚመሩባቸዉ ሥርዓት እና ደንቦች በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ
ተቀርጸዉ ስራ ላይ እንዲዉሉ የሚደረግበት ምክንያትም ይሄዉ ነዉ፡፡ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ
የፍትሐብሔር ክርክሮችን አስመልክቶ የምንከተለዉ ስርዓት ሲሆን አጠቃላይ ዓላማዉም የፍትሐብሔር
ጉዳዮችን ፍትሐዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ቀልጣፋ በሆነ ሁኔታ በመምራት ፍትሐዊ ዉሳኔ እንዲያገኙ ማስቻል
ነዉ፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት ይቻል ዘንድም የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ የተለያዩ ደንቦች እና
መርሆዎችን ይደነግጋል፡፡ ክርክሮች በዘፈቀደ ሳይሆን ሥርዓት ባለዉ ሁኔታ እንዲመሩ በማድረግ የተከራካሪ
ወገኖችን የመሰማት መብትን፣ ብሎም ክርክሮች ባነሰ ወጪ እና ጊዜ መቋጫ እንዲያገኙ በማድረግ በፍርድ
ቤት እና በተከራካሪ ወገኖች ላይ ያላግባብ የሚደርሰዉን የገንዘብ እና የጊዜ ብክነት በማስቀረት የክርክሩ
ሂደትም ሆነ ዉጤቱ ፍትሐዊ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ የሚኖረዉ ሚና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከፍተኛ በመሆኑ በህጉ ላይ የተመለከቱትን ደንቦች እና መርሆዎች በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲዉሉ የማድረጉ


አስፈላጊነትም የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡

በዚህ ረገድ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጋችን ዕዉቅና ከተሰጣቸዉ ደንቦች ዉስጥ አንዱ በከሳሽነት እና
በተከሳሽነት ከተሰየሙት ወገኖች ዉጪ ያሉ ሦስተኛ ወገኖች የክርክር ተሳታፊ የሚሆኑበትን ሁኔታ
የሚመለከተዉ ደንብ ነዉ፡፡ በከሳሽነት እና በተከሳሽነት ከተሰየሙት ተከራካሪዎች ዉጭ የሆነ ሦስተኛ ወገን
በክርክሩ ተሳታፊ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት የማይችል ዓይነት
(indispensable party) ከሆነ በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ወይም መብት ባለዉ ሰዉ አቤቱታ አቅራቢነት፣
እንዲሁም ዉጤቱ መብቴን ሊነካ ይችላል በሚል ወገን (interested party) አቤቱታ አቅራቢነት ሦስተኛ
ወገን በተጀመረ ክርክር ተሳታፊ የሚሆንበትን ሥርዓት የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ ይዘረጋል (አንቀጽ
40 እና 41 ይመለከቷል)፡፡ ዓላማዉም የጉዳዩ አመራር ፍትሐዊ እንዲሆንና በሥርዓት እንዲከናወን
ለማስቻል ሲባል ነዉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች ከላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች
መሠረት ክርክሩ በሂደት ላይ እያለ በክርክሩ ተሳታፊ ሆኖ መብቱን ማስከበር ይችል የነበረ ሰዉ ተሳታፊ
ባልሆነበት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም
በህግ የዳኝነት ስልጣን ባለዉ አካል በተሰጠ ዉሳኔ መብቴ ተነክቷል የሚል ሦስተኛ ወገን አቤቱታዉን
በማቅረብ ዉሳኔዉን በመቃወም መብቱን ሊያስከብር የሚችልበትን ሥርዓት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት
ህጉ አንቀጽ 358 ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ የድንጋጌዉ ሙሉ ይዘትም በክርክሩ ዉስጥ ተካፋይ መሆን
የሚገባዉ ወይም በክርክሩ ዉስጥ ለመግባት የሚችልና እንዲሁም ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠዉ
ፍርድ መብቱን የሚነካበት ማናቸዉም ሰዉ ራሱ ወይም ጠበቃዉ ወይም ነገረ ፈጁ ተካፋይ በልሆነበት
ክርክር የተሰጠዉ ፍርድ ከመፈጸሙ በፊት መቃወሚያዉን ለማቅረብ ይችላል የሚል ነው፡፡

ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለዉም ክርክሩ መጀመሩን ሳይረዳና ሳያዉቅ በከሳሽነትና በተከሳሽነት
በተሰየሙት ወገኖች መካከል የተደረገዉ ክርክር ተጠናቆ መወሰኑ እንኳ ቢታወቅ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ
ይረዳ ዘንድ በዉሳኔዉ መብቴ ተነክቷል የሚለዉ የክርክሩ ተካፋይ ያልነበረዉ ሰዉ ይህንኑ ዉሳኔ መቃወም
የሚችል መሆኑን ነዉ፡፡ በተለይም በድንጋጌዉ ማናቸዉም ሰዉ ራሱ ወይም ጠበቃዉ ወይም ነገረ ፈጁ
ተካፋይ ባልሆነበት ወይም በእንግሊዝኛዉ if he was not a party to such suit either in person or
through a representative በሚል የተገለጸዉ የሚያሳየዉ ሦስተኛ ወገን የሚያቀርበዉ አቤቱታ ተቀባይነት
የሚኖረዉ አቤቱታ አቅራቢዉ ለአቤቱታዉ በምክንያትነት የጠቀሰዉ ጉዳይ በቀደመዉ የክርክር ሂደት
በመቃወም አመልካቹ በእራሱ ወይም በወኪሉ ወይም ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ
ሰዉ ክርክር ያልቀረበበት ሲሆን ነዉ፡፡ በሌላ አገላለጽ የመቃወም አመልካቹ ለአቤቱታዉ መሰረት ያደረገዉ
ክርክሩ በሂደት ላይ በነበረበት ወቅት ጉዳዩ የሚያገባዉ ሰዉ የክርክሩ ተሳታፊ በሆነበት ታይቶ ዉሳኔ
የተሰጠበት ጉዳይ ከሆነ እና የመቃወም አመልካቹ ዉሳኔዉ ‘በግል’ መብቱን የሚነካ መሆኑን በአቤቱታዉ
ካላሳየ በስተቀር አቤቱታዉ ተቀባይነት የሚኖረዉ አይደለም፡፡ የመቃወም አመልካች ለመቃወሚያዉ
ምክንያት የሆኑትን ዝርዝር ምክንያቶች እና የሚጠይቀዉን ዳኝነት በአቤቱታዉ በዝርዝር መግለጽ እንዲሁም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አቤቱታዉ ለሌሎች ተከራካሪ ወገኖች እንዲደርስ ተደርጎ ክርክሩም የሚሰማዉ የመጀመሪያዉ ክርክር
በተሰማበት ሂደት ስለመሆኑ በህጉ አንቀጽ 359 እና 360 ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎችም የሚያሳዩት
ለመቃወም አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ የመቃወም አመልካቹን መብትና ጥቅም በግል የሚነካ መሆን
ያለመሆኑ ጉዳይ የመቃወም አመልካቹ እና በክርክሩ ተሳታፊ የሆኑ ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች የሚያቀርቡትን
ክርክር እና ማስረጃ መሠረት በማድረግ ታይቶ ዉሳኔ የሚሰጥበት መሆኑን ነዉ፡፡

ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠዉ የዳኝነት አካል የተሰጠን ዉሳኔን መቃወም
የሚቻልበትን ሥርዓት አስመልክቶ በሥነ ሥርዓት ህጉ የተመለከተዉ ድንጋጌ በዉሳኔዉ መብቱ ‘በግል’
የተነካበት ሰዉ መቃወሚያዉን አቅርቦ መብቱን ለማስከበር እንዲችል እንጂ አንድን መብትና ጥቅም
ለማስከበር የተለያዩ ሰዎች ተፈራርቀዉ የሚያቀርቡትን አቤቱታ ለማስተናገድ ያለመሆኑን መገንዘቡ ተገቢ
ነዉ፡፡ ይልቁንም የመቃወም አቤቱታ የሚቀርብበትን ሁኔታ አስመልክቶ በድንጋጌዉ ላይ ከተመለከቱት
መስፈርቶች አንፃር ሲታይ የድንጋጌዉ ዓይነተኛ ዓላማ በአንድ በኩል በከሳሽነት እና በተከሳሽነት በተሰየሙ
ወገኖች መካከል በተደረገ ክርክር መነሻነት የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሰዉ ዉሳኔዉን በመቃወም
ተከራክሮ መብቱን እንዲያስከብር በማድረግ ፍትሕ የማግኘት መብቱን በማረጋገጥ፣ በሌላ በኩል በከሳሽነት
እና በተከሳሽነት በተሰየሙት ወገኖች መካከል ክርክር ተደርጎበት እልባት ባገኘ ጉዳይ ላይ በድጋሚ ክርክር
በማቅረብ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር በሚል በሦስተኛ ወገን የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት
እንዳይኖረዉ በማድረግ በአንድ ጉዳይ ላይ ወይም ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር በሚል ክርክሮች
በተደጋጋሚ ሊቀርቡ የሚችሉበትን ሁኔታ በማስቀረት ክርክሮች በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጪ መቋጫ
እንዲያገኙ ብሎም የፍርድ ሂደቱም ሆነ ዉጤቱ ተገማች እንዲሆን ማድረግ ነዉ፡፡ ስለሆነም በፍትሐብሔር
ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የቀረበ የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት ያለዉ መሆን ያለመሆኑን
አስመልክቶ በፍርድ ቤቶች የሚሰጠዉ ትርጉም ይህንኑ ያገናዘበ ሊሆን ይገባል፡፡

ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ስንመለስ፣ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ፣ በአመልካቾች ከሳሽነት በስር ፍርድ ቤት


በተከሳሽነት የተሰየመዉ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ክርክር ተደርጎ ውሳኔ
ተሰጥቶበታል፡፡ ተጠሪ የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ ተቋም በመሆኑ የህግ ሰዉነት የተሰጠዉ የመንግስት ወይም
የግል ተቋም እንደሚያደርገዉ ሁሉ በቀጥታ ተቋሙን በሚመለከተዉ ጉዳይ ላይ በከሳሽነት፣ በተከሳሽነት፣
በጣልቃ ገብነት ወይም በመቃወሚያ አቤቱታ አቅራቢነት በፍርድ ቤት ወይም በህግ ስልጣን በተሰጠዉ
የዳኝነት አካል ቀርቦ የክርክሩ ተሳታፊ በመሆን እንደ ተቋም ያለዉን መብት የማስከበር መብትም ግዴታም
አለዉ፡፡ ይሁንና በተያዘዉ ጉዳይ ላይ ተጠሪ በአመልካቾች የቀረበዉ ክስ ይመለከተኛል ወይም በህጉ አንቀጽ
33(3) መሠረት በተከሳሽነት መጠራት የነበረብኝ እኔ ነኝ የሚል ክርክር የለዉም፤ ይልቁንም በፍትሐብሔር
ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ያቀረብኩት የመቃወም አቤቱታ ተቀባይነት ሊኖረዉ ይገባል በማለት
የሚከራከረዉ በስር ተከሳሽ የነበረዉ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ የተወሰነው
ውሳኔ የከተማ አስተዳደሩን ሆነ የከተማዉን ነዋሪዎች መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑን እና የነዋሪዎች
መብትና ጥቅምን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመቃወም አቤቱታ አቅርቦ መከራከር እንዲችል በህግ ስልጣን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተሰጠዉ መሆኑን ነዉ፡፡ በእርግጥም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ
አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 5 የዐቃቤ ሕግ ቢሮ የከተማዉ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአስተዳደሩና
የነዋሪዉ መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ እንደሚከራከር የተመለከተ ሲሆን፣ ተጠሪ የከተማ አስተዳደሩ ዐቃቤ
ሕግ ቢሮ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩን አካላት ሆነ የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ
ወኪል ሆኖ ለፍርድ ቤት ወይም በህግ የዳኝነት ስልጣን በተሰጠዉ አካል ቀርቦ ክርክር የማቅረብ ስልጣን
ይኖረዋል፡፡

ተጠሪ የሚከራከረው በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበረው የወረዳ አስተዳደር ካርታ ለማስተካከል ሥልጣን
የለውም፣ ካርታ ይስተካከል የሚለው በፍርድ ቤት ዳኝነት ሊጠየቅበት አይችልም የሚል በመሆኑ ከተከሳሹ
መብትና ጥቅም አኳያ የቀረበ ክርክር ነው፤ የተለየ ሳይሆን ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ወክሎ እየተከራከረ
መሆኑንም ያስገነዝባል፡፡ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ጉዳዩ በሚመለከተዉ መስሪያ
ቤት ክርክር ቀርቦበት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ አቃቤ ህግ ዉሳኔዉን በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ
358 መሠረት ሊቃወም የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡ የሥር ፍርድ ቤት ለውሳኔው መሠረት
ያደረገው የሠበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37502 የተሰጠው የሕግ ትርጉምም በሰበር መዝገብ ቁጥር
190307 የተለወጠ እና መሥሪያ ቤቱ ተከራክሮ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ወክሎ
ዐቃቤ ሕግ ሊከራከር እንደማይችል አስገዳጅ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡ በተጨማሪም በተያዘው ጉዳይ ተከሳሽ
የነበረውን የወረዳ አስተደዳር በዐቃቤ ሕግ ተወክሎ ሲከራከር የነበረ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት የተረዳን
ሲሆን የወረዳ ዐቃቤ ሕግ፣ የክፍለ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ሆነ በቢሮ ደረጃ ያለው ዐቃቤ ሕግ በተመሳሳይ
አደረጃጀት ያለ እና አንዱ ለአንዱ ተጠሪ ሆኖ የተዋቀረ በመሆኑ የተለያየ የሕግ ሰውነት አለን በሚል
ምክንያት ብቻ ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ወክለው አንድን ጉዳይ ሁለትና ከዚህ በላይ ጊዜ ክርክር
እንዲደረግበት መብት የሚሰጥ አይደለም፡፡ ስለሆነም ተጠሪ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሠረት ያቀረበውን
ተቃውሞ መሠረት ተደርጎ ቀደም ሲል ተሰጠው ፍርድ መሻሻሉ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተዘረጋውን ሥርዓት
ያልተከተለና መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ዉሳኔ

1. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 188696 የካቲት 13 ቀን 2012
ዓ/ም እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 196817 ሕዳር 30 ቀን 2012 ዓ/ም የሰጡት
ዉሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን ይቻሉ፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 መዝገቡ ተዝግቷል ወደመዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 193443

ሀምሌ 30 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

ቀነአ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች፡- አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ፡- ጠበቃ ዳንኤል ደጉ ቀረቡ

ተጠሪዎች፡- 1ኛ. አቶ ጌትነት አለማየሁ

2ኛ. ደስታዬ አለማየሁ ጠበቃ መብራቱ ማሞ ቀረቡ

3ኛ. አቶ ፍቃዱ አለማየሁ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍ ር ድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 28/11/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል
መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 83577 በቀን 09/11/2011 ዓ.ም እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ
ፍ/ቤት በመ/ቁ 243422 በቀን 01/07/2012 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በስር ፍርድ ቤት ሲጀመር
የአሁን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሾች ነበሩ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪዎች በቀን 02/04/2010 ዓ.ም ባቀረቡት የክስ አቤቱታ እህታችን ወ/ሮ አልማዝ
አለማየሁ የካቲት 03/2009 ኣ.ም በሞት ተለይተዋል፤ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ልጅ አልወለዱም፤
እናትና አባታችንም ከሟች ቀድመው ሞተዋል፤ ሟች ኑዛዜም አላደረጉም፤ ከሳሾች የሟች እህታችን
ምትክ ወራሾች ስንሆን ተከሳሽ ሟች እህታችን ስለተናዘዘችልኝ የኑዛዜ ወራሽ ነኝ በማለት ከሳሾች
በመ/ቁ 74433 አቅርበን በነበረው ውርስ ይጣራልኝ አቤቱታ ላይ ጠልቃ ልግባ በማለት ባቀረቡት
አቤቱታ ምክንያት ተከሳሽ ሟች ተናዛልኛለች ማለታቸውን ለማወቅ ችለናል፤ ተከሳሽ ሟች
ተናዛልኛለች ከሚሉበት ጥር 21/2009 ዓ.ም ቀደም ከአንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ ከዚህ አለም
በሞት እስከተለየችበት እለት ድረስ ህይወቷን ስታ የኑዛዜ ቃል ለመስጠት የማትችል በመሆኑ
ምክንያት ሟች ሰጥታለች የተባለው የኑዛዜ ቃል በፍ/ብ/ህ/ቁ 881 መሰረት ሟች የኑዛዜውን ቃል
እየተናገረች የተጻፈ ወይም በሟች የእጅ ጽሁፍ የተጻፈ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ አይደለም፤ ስለሆነም
ሟች ሰጥታለች የተባለው የኑዛዜ ቃል በግልጽ ስለሚደረግ ኑዛዜ የተመለከተውን ፎርም የማያሟላ
በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 881 መሰረት ፈራሽ ነው እንዲባልልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተከሳሽ በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው በብይን ውድቅ የተደረገ
ሲሆን በፍሬ ነገር መልሳቸው የተከሳሽ አሳዳጊ ሟች ወ/ሮ አልማዝ የካቲት 03/2009 ዓ.ም ሞተው
በማግስቱ መቀበራቸው እውነት ነው፤ ሟች ተከሳሽን ከህጻንነቴ ጀምሮ በመውሰድ ያሳደገችኝ እና
ስታስተምረኝ የቆየች ሲሆን ከመሞቷም በፊት ይህንኑ ኑዛዜ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጠችው የማደጎ
ልጇ ነኝ፤ ከሳሾች ምትክ ወራሽ ነን በማለት የማደጎ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ እና የኑዛዜ ወራሽ
የሆንኩት ተከሳሽ እያለሁ ለተከሳሽ የተደረገ ኑዛዜ ይፍረስልን በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ
ሊደረግ ይገባል፤ ሟች በህይወት እያለች ያላትን ቤትና የቤት ቁሳቁስ በሙሉ ተናዛልኝ ሞታለች፡፡
ሟች ኑዛዜ ባደረገችበት ወቅት ብዙም ህመም ያልነበራት መንቀሳቀስ ሆነ መናገር የምትችል
በትክክለኛ አእምሮ ላይ የነበረች የምትሰራውንና የምታደርገውን የምታውቅ ነበረች፡፡ ሟች ለተከሳሽ
በትክክለኛ አእምሮዋ ማንም ሳያስገድዳት በራሷ አነሳሽነት የንስሀ አባቷ እና ምስክሮች ባሉበት
ኑዛዜውን ያደረገች ሲሆን እነሱም ሟች የሰጠችውን የኑዛዜ ቃል እሷ እየተናገረች በጽሁፍ ካሰፈሩ
በኋላ ሟች የሰጠችው ቃል ወዲያው በኮምፒውተር በመጻፍ አምጥተውላት ካነበቡላት በኋላ
በምስክሮች ፊት የፈረመችና ምስክሮችም ይህ ኑዛዜ ሲደረግ በቦታው ሆነው ያዩ መሆኑን
አረጋግጠው የፈረሙበት ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ 881 መሰረት ኑዛዜው ሊከተል የሚገባውን ፎርም
አሟልቶ የቀረበ ኑዛዜ በመሆኑ ሊፈርስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት ክርክሩንና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ
የኑዛዜው ሰነድ ሲመረመር በኑዛዜው ላይ አራት ምስክሮች የፈረሙ ሲሆን ተደረገ የተባለው ኑዛዜ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ግን በምስክሮች ፊት ስለመነበቡና ይኸው ስርአት ስለመፈጸሙ የሚገልጽ አይደለም፤ ሟች


በህይወት እያሉ በፍላጎታቸው ኑዛዜ ያደረጉ መሆናቸው በተከሳሽ ምስክሮች የተረጋገጠ ቢሆንም
ሟች ያደረጉት የኑዛዜ ቃል በህጉ ላይ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟላ አይደለም፡፡ ስለሆነም ሟች
ጥር 21 ቀን 2009 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ የፍ/ብ/ህ/ቁ 881 ስር የተቀመጡትን መስፈርቶች
(ስርአቶች) ያላሟላ በመሆኑ ፈራሽ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት
ተከሳሽ ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ውሳኔው ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች በቀን 28/11/2012 ዓ/ም ባቀረቡት
ማመልከቻ ሟች አልማዝ አለማየሁ ለአመልካች ጥር 21/2009 ዓ.ም ያደረገችው ኑዛዜ አናዛዥ
በሆኑት ምስክሮች የተነበበላት ስለመሆኑ በግልጽ ተጠቅሶ ያለ ከመሆኑም ውጪ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት
እነዚህን በኑዛዜው ላይ ያሉትን ምስክሮች በችሎት አስቀርቦ ኑዛዜው ለሟች በምስክሮች ፊት
ስለመነበቡ አረጋግጦ እያለ ኑዛዜው በምስክሮች ፊት ስለመነበቡና ይኸው ስርአት ስለመፈጸሙ ሰነዱ
አያመላክትም በማለት ፈራሽ ማድረጉና ከፍተኛ ፍ/ቤቱ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናት ውሳኔ
መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ እንዲታረምልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡

ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ የስር ፍ/ቤት ሟች ለአመልካች ያደረጉት ኑዛዜ
ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብነት ከፍ/ብ/ህ/ቁ 881 እና በሰበር መ/ቁ 17429 ከተሰጠው
አስገዳጅ ውሳኔ አንጻር ለመመርመር በሚል ጉዳዩ ለዚህ ችሎት እንዲቀርብ እና ተጠሪዎች መልስ
እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡

ተጠሪዎች በቀን 20/02/2013 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ ሟች ሰጠች የተባለውን ኑዛዜ


በኮምፒውተር ለማጻፍ የወሰዱት ምስክሮች ሳይሆኑ አመልካች ናቸው፤ ከወሰዱ በኋላ በህግ
ባለሙያ ታግዘው ሟች ከሰጠችው ቃል ውጭ አስጨምረው በማጻፍ ያመጡ መሆኑን አመልካች
በስር ፍ/ቤት ያቀረቧቸው ምስክር በመስቀለኛ ጥያቄ ላይ አረጋግጠው መልስ ሰጥተዋል፤ ይህም
የኑዛዜው ቃል ከመጀመሪያውኑም ከአጻጻፍ ጀምሮ የፍ/ብ/ህ/ቁ 881 እና 882 ላይ የተደነገገውን
የግልጽ ኑዛዜ አጻጻፍን ያላሟላ ስለነበር ከጅምሩም የፈረሰ ነው፤ ሰበር ችሎት በመ/ቁ 70057
በሰጠው ትርጉም ኑዛዜው ለተናዛዥ እና ምስክሮች ስለመነበቡ በሰነዱ ላይ ያለመገለጹ ብቻ የኑዛዜ
ሰነዱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 881(2) እና 882 ስር የተመለከተውን ፎርማሊቲ አያሟላም ተብሎ ፈራሽ
እንዲሆን የግድ የሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ኑዛዜው በግልጽ ስለመነበቡ ኑዛዜው ላይ
የተገለጸ ቃል ባለመኖሩ የስር ፍ/ቤቶች ኑዛዜው ፈራሽ ነው በማት የሰጡት ውሳኔ የሚነቀፍበት
ምክንያት ባለመኖሩ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዲጸና በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካችም በመልስ
መልሳቸው አቤቱታቸውን በማጠናከር አቅርበዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከፍሲል ባጭሩ የገለጽነው የክርክሩን አመጣጥ ነው፡፡ በበኩላችን የግራቀኙን ክርክር ቅሬታ
ከቀረበበት ውሳኔና ተገቢነት ካላቸው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማያያዝ መርምረናል፡፡

እንድመረመርነው የፌ/መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የኑዛዜውን ሰነድ ይዘት መርምሮ ሟች


ወ/ሮ አልማዝ አለማየሁ ለአመልካች ጥር 21/2009 ዓ.ም አደረጉት የተባለው ኑዛዜ በግልጽ
የሚደረግ የኑዛዜ አይነት መሆኑን መገንዘብ መቻሉን፤ በኑዛዜው ላይ አራት ምስክሮች የፈረሙበት
መሆኑን፤ ነገር ግን ኑዛዜው በምስክሮች ፊት ስለመነበቡና ይኸው ስርአት ስለመፈጸሙ የሚገልጽ
አለመሆኑን፤ በአጠቃላይ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በህጉ ላይ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟላ
አለመሆኑን በማረጋገጥ ወስኗል፡፡ ይህ መደምደሚያ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ተቀባይነት
አግኝቷል፡፡

በመሰረቱ በግልጽ ስለሚደረግ ኑዛዜ ፎርም ከሚደነግገው የፍ/ብ/ህ/ቁ 881 ይዘት መገንዘብ
እንደሚቻለው በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ማናቸውም ሌላ ሰው ወይም ተናዛዡ
ራሱ የሚጽፈው ነው፡፡ ኑዛዜው በተናዛዡ እና በአራት ምስክሮች ፊት ካልተነበበና ይህም ስርዓት
(ፎርማሊቲ) መፈፀሙንና የተፃፈበትንም ቀን የሚያመለክት ካልሆነ በቀር ፈራሽ ነው፡፡ በእርግጥ
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 17429 እና ሌሎችም ተመሳሳይ መዛግብት በሰጠው
ትርጉም መሰረት በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ኑዛዜው መነበቡን የሚያመለክት ከሆነ በግልፅ “ተነቧል”
የሚል ቃል አለመኖሩ ኑዛዜውን ፈራሽ የሚያደርግ ስላለመሆኑ ወስኗል፡፡

በተያዘው ጉዳይ ግራቀኙ የሚከራከሩበት ወ/ሮ አልማዝ አለማየሁ ትተውት አልፈዋል


የተባለው ኑዛዜ በግልጽ የሚደረግ የኑዛዜ አይነት መሆኑና አራት ምስክሮች የፈረሙበት መሆኑን
የሚያሳይ ቢሆንም ኑዛዜው በምስክሮች ፊት መነበቡን የሚያመለክት እንዳልሆነ በስር ፍርድ ቤት
ተረጋግጧል፡፡ የስር ፍርድ ቤት ይኸን የማስረጃና የፍሬ ነገር መደምደሚያ በማረጋገጥ ኑዛዜው
በፍ/ህ/ቁ 881 የተመለከተውን ፎርም የተከተለ ስላለመሆኑ ወስኗል፡፡

አመልካች በቅሬታቸው በኑዛዜው ላይ ያሉት ምስክሮች በስር ፍርድ ቤት ቀርበው ኑዛዜው


ለሟች በምስክሮች ፊት ስለመነበቡ አረጋግጠው እያለ ኑዛዜው በምስክሮች ፊት ስለመነበቡና ይኸው
ስርአት ስለመፈጸሙ ሰነዱ አያመላክትም ተብሎ መወሰኑ አላግባቡ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡
ይሁንና የማስረጃውን አይነት በተመለከተ በፍ/ብ/ህ/ቁ 897 ስር እንደተደነገገው በግልጽ የተደረገ
ኑዛዜ የሚረጋገጠው የኑዛዜውን ጽሁፍ በማቅረብ ሲሆን ኑዛዜውን ለማስፈፀም በማናቸውም ሌላ
መንገድ ለማስረዳት አይቻልም በማለት የሚደነግግ በመሆኑ ክርክራቸው ህጉን መሰረት ያደረገ ሆኖ
አላገኘነውም፡፡ ከዚህም ሌላ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 17429 በሰጠው ትርጉም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ኑዛዜው መነበቡን የሚያመለክት ከሆነ በግልፅ “ተነቧል” የሚል ቃል
አለመኖሩ ብቻ ኑዛዜውን ፈራሽ የሚያደርግ ስላለመሆኑ የተወሰነበት እንጂ ይህ ትርጉም ኑዛዜው
ከመነሻው በምስክሮች ፊት መነበቡን የሚያመለክት እንዳልሆነ በተረጋገጠበት እንደተያዘው ጉዳይ
ባለ ሁኔታ ላይ ተፈፃሚነት የሚኖረው አይደለም፡፡

በአጠቃላይ ወ/ሮ አልማዝ አለማየሁ ትተውት አልፈዋል የተባለው ኑዛዜ በግልፅ የሚደረግ
ኑዛዜ ፎርምን ተከትሎ የተሰጠ አለመሆኑን የስር ፍርድ ቤቶች በማጣራትና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ
የወሰኑ በመሆኑ ውሳኔው የህግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም ብለናል፡፡ ተከታዩንም ወስነናል፡

ው ሣ ኔ

1. የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 83577 በቀን 09/11/2011 ዓ.ም እንዲሁም
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 243422 በቀን 01/07/2012 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. ዕግድ ካለ ተነስቷል፡፡

3. የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሠበር መዝገብ ቁጥር 195656

ሀምሌ 29 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንከር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ከሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1ኛ ወ/ሮ የጌራወቅ አንጋጋው

2ኛ ወ/ሮ ትዕግስት አንጋጋው

3ኛ ወ/ሮ በለጡ አንጋጋው

4ኛ አቶ አንበርብር አንጋጋው

5ኛ አቶ ናኦድ አንጋጋው

6ኛ ወ/ሮ አስቴር አንጋጋው

7ኛ አቶ ምኒልክ አንጋጋው

8ኛ አቶ አግደው አንጋጋው

9ኛ ወንደወሰን አንጋጋው

ተጠሪዎች፡- 1ኛ የካ /ክ/ከ ወረዳ ዐ6 አሰተዳደር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2ኛ ሲስተር ብርሃኔ ሰማኝ

3ኛ አቶ አስራት ገብረ ቃል

4ኛ ወ/ሮ አሰገደች ደበበ

5ኛ አቶ አምባቸው ታረቀኝ

6ኛ አቶ ደበበ ዘውገ

7ኛ አቶ ተክላይ ካሳ

8ኛ አቶ ገዛኸኝ ሽጉጤ

9ኛ አቶ ካሳ ፍሰሃ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚህ አግባብ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ይዞታ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 251ዐዐ7 በቀን ሰኔ 15/2ዐ12 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሥር
ፍ/ቤቱን ውሳኔ በማጽናት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረገበትን ትዕዛዝ በመቃወም ነው፡፡

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካቾች በተጠሪዎች ላይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የካ ምድብ ፍታብሄር


ችሎት ባቀረቡት ክስ አውራሻችን ቦታውና አዋሳኙ በክሱ ውስጥ የተገለፀዉን 513 ካ.ሜ የሆነው
የቤት ቁጥር 39ዐ ጎን ያለውን ይዞታ በውል ከባለቤቶቹ በመግዛት ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያ እንዲሆን
አንድ ጣራ ግርግዳ የሚጋሩትን እና በአንድ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን ቤቶች በመሥራት እስከ
1969 ዓ.ም ድረስ አምስቱን ደጃፍ ቤቶች ለተለያዩ ሰዎች ሲያከራዩ ቆይተው እነዚህን ቁጥራቸው
ከ391-395 ድረስ ያሉ ቤቶች 1ኛ ተጠሪ ትርፍ ነው በማለት በመውረስ በህገ-ወጥ መንገድ
በመውሰድ ከ2ኛ-6ኛ ላሉ ተጠሪዎች በማከራየት እንዲሁም ቤቱን በእነዚህ ተከራዮች ስም ለማዛወር
በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ 1ኛተጠሪ ቁጥሩ 391Aኤ የሆነው ለልጆች መኘታ ቤት
የምንጠቀምበትን አንድ ክፍል ቤት በ1981 ዓ.ም በሩን በመስበር ለ9ኛ ተጠሪ አከራይቶ ያለግባብ
ጥቅም እያገኘ መሆኑ፤ እንዲሁም 7ኛ ተጠሪ የ9ኛ ተጠሪ ልጅ በቤቱ እየኖረ የሚገኝ በመሆኑ፤

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

8ኛ ተጠሪ ደግሞ ለጥበቃ ሠራተኛ የተሠራውን የቤት ቁጥር 39 B በማያውቁት መንገድ በመያዝ
እየተገለገለ የሚገኝ መሆኑን በመጥቀስ የቀበሌው መስተዳደር አምስት አባላት ያሉት ቡድን ጥቅምት
2ዐ ቀን 1968 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ 11 ክፍል ቤቶች ለአውራሻችን የተፈቀደ መሆኑን ገልፆ ነገር
ግን ጋራዥና የእንጀራ መጋገሪያ ቤቶች በጋራ እንድንጠቀም በመወሰኑ አውራሻችን ውሳኔውን
በመቃወም ለመስተዳደሩ የንዑስ ወረዳ ዐ4 አዝማች ቡድን በማቅረብ ኮሚቴው ህዳር 23 ቀን 1968
ዓ.ም በሰጠው ውሳኔም ትርፍ ናቸው የተባሉት ከመኖሪያ ቤቱ ጋር የተያያዙት አራት ክፍል ቤት
ከነሰርቪሱ ስለሆኑ በትርፍነት ስለማይቆጠሩ በይዞታቸው ሥር እንዲቆዩ ሌላ ትርፍ ሆኖ የተገኘውን
አራት ክፍል ከነሰርቪሱ እንዲያስረክቡ በማለት የወሰነ ቢሆንም 1ኛ ተጠሪ ሊያስረክበን ስላልፈቀደ
ቤቱን ለቀው እንዲወጡና ያላግባብ ያገኙትን ገቢ እንዲከፍሏቸው አመልክተዋል፡፡

ተጠሪዎች ከ9ኛ ተጠሪ ውጭ መልሳቸውን ያቀረቡ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ በቀን ሐምሌ 5/2ዐ1ዐ ዓ. ም
በተጻፈ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቀወሚያ በማለት አመልካቾች ቤቱ አላግባብ በትርፍነት
ተወስዶብኛል የሚሉ ከሆነ ለኘራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 11ዐ/87 መሠረት በሰዓቱ
ከሚያቀርቡ በስተቀር ለፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ሊያቀርቡ ስለማይገባ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል፤
ክርክር የቀረበባቸውን ቤቶች መንግስት ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ እያስተዳደራቸው የሚገኝ በመሆኑ
አመልካቾች ክስ የማቅረብ መብትና ጥቅም የላቸውም በማለት ተከራክሯል ፡፡ ከ2ኛ-6ኛ
የተመለከቱት ተጠሪዎች በበኩላቸው አመልካቾች ቤቶቹ በአዋጅ ቁጥር 47/67 ለአመልካቾች አባት
ተፈቅዶላቸው ባለንብረት የሆኑባቸውን ማስረጃዎች ስላላቀረቡ ክሱን ለማቅረብ መብትና ጥቅም
የላቸውም ፤ አመልካቾች ቤቶቹ የተወረሱ መሆናቸውን የሚያምኑ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 11ዐ/87
በአንቀፅ 3/1/ አግባብ ቤቶቹ የተወረሱት በቀላጤ በመመሪያ ወይም ደግሞ በቃል ትዕዛዝ መሆኑን
በማስረዳት ውሳኔ በማሰጠት ያልቀረቡ በመሆኑ ክሱ የክስ ምክንያት የለውም ተበሎ ውድቅ
ይደረግልን በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማቅረብ ተከራክረዋል፡7ኛ ተጠሪ ደግሞ የቤት
ቁጥር 391A አመልካቾች 7ኛ ተጠሪን ሊከሱ የማይገባቸው መሆኑን፤ ቤቱ ውስጥ የሚኖረው
በጥገኘት መሆኑን፤ አሁን 9ኛተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ አስረክቦ የታሸገ መሆኑን ገልጾ ተከራክሯል፡፡
8ኛ ተጠሪ በበኩሉ የቤት ቁጥር 391B ቤቱን ያገኘው በስጦታ ውል ከአመልካቾች አባት መሆኑን
በመጥቀስ ክሱ የቀረበው ከ4ዐ ዓመት በኋላ በመሆኑ በይርጋ ሊታገድ የሚገባ መሆኑን ፤ የቤቱ
ግምት በአግባቡ ያልተገመተ መሆኑን ጠቅሰው ክሱ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በማለት
ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክር ተመልክቶ ህዳር 5 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም በዋለው ችሎት
በሰጠው ብይንም ቤቶቹ ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ ትርፍ ናቸው በሚል በ1ኛ ተጠሪ ተወርሰው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መያዛቸው በአመልካቾች የታመነ መሆኑን ፤ በመንግስት እጅ ለረጅም ጊዜ የተያዘ ቤት ይመለስልኝ


ጥያቄ ለፍ/ቤት የሚቀርበው በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተጠቅሶ ከሚመለከተው አካል የተረጋገጠ ከሆነ
ወይም በአዋጅ ቁጥር 11ዐ/87 መሠረት በኘራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቀርቦ ባለመብትነቱ ተረጋግጦ
የተወሰነ ከሆነ ለዚህ ማስረጃ ሲቀርብ መሆኑን አመልካቾች ግን ከሚመለከተው አካል ተረጋግጦ
የተሰጣቸው ካርታ መኖሩን ወይም በአዋጅ ቁጥር 11ዐ/87 መሠረት ባለመብት የሆኑበትን ውሳኔ
አለማቅረባቸውን በመጥቀስ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም በማለት በብይን ዘግቶታል፡፡
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤቱም የሥር ፍ/ቤቱን ውሳኔ አፅንቶታል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው አመልካች መስከረም 8/2ዐ13
ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያሉትን መሠረታዊ የህግ
ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎቱ እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍሬ ቃሉም 1ኛ ተጠሪ በሰጠው
መልስ ክርክሩ ቁጥራቸው 391-395 እና 390 ኤ፣ 390 ቢ ቤቶችን በተመከተ መሆኑን ገልጾ
አቅርቦ እያለ ፍ/ቤቱ የቤት ቁጥር 391 ኤ እና 391 ቢ በሆኑ ቤቶች ላይ ምንም አይነት ክርክር
ባልቀረበበት ብይን መስጠቱ ስህተት መሆኑን፣ ክስ የቀረበባቸው ቤቶች የአመልካቾች እንደሆኑ
በማስረጃ አስደግፈን አቅረበን እያለ የስር ፍ/ቤት በአዋጁ ቁጥር 47/67 መሰረት ያልተፈቀደ
በመሆኑ በፍ/ቤቱ ከሰው ሊጠይቁ አይችሉም ማለቱ ስህተት መሆኑን፣ ጥያቄው ያላግባብ
ተወረሰብን ሳይሆን ያላግባብ የተወሰዱ ቤቶች እንዲመለሱ የመፋለም ዳኝነት ሆኖ እያለ፣ በቅፅ 003
ላይ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የወረሰው ከአውራሻቸው ሳይሆን አውራሽ አባታቸውን አስረው ከእናታቸው
በማስገደድ መሆኑን በመጥቀስ ማስረጃዎች እንዲቀርቡ ለፍ/ቤቱ ያመለከትን ቢሆንም ማስረጃዎቹ
ሳይሰሙ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑን፣የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉዳዩ በፕሪቬታይዜሽን ኤጀንሲ ሊታይ
ማለቱ ኤጀንሲው የፈረሰ በመሆኑ ጉዳዩን ያለ ፍትህ የሚያስቀር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣
የስር ፍ/ቤት አዋጅ ቁጥር 47/67ን የተረጎመበት አግባብ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በስር ፍ/ቤት አላግባብ የተያዘባቸው ቤት


እንዲለቀቅላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ የስር ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት የዳኝነት ስልጣን የለኝም በማለት
የወሰነበትን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 47/67 እና 110/87 እንዲሁም በሰ/መ/ቁ 31682 በሆነ
መዝገብ ከተሰጠ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ለዚህ ሰበር ችሎት ቀርቦ
እንዲታይ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

1ኛ ተጠሪ በቀን ታህሳስ 24/2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ በስር ፍ/ቤት የቀረበው ክስ
በፍ/ቤቱ ሊታይ የማይችል ስለመሆኑ በተመሳሳይ ጉዳይ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ 45161

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቅፅ 10 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠበት መሆኑን፣ሁሉንም ብይን የተሰጣባቸውን ቤቶች በቃል


ክርክር ወቅት አንስተው የተካራከሩበት መሆኑን፣ ለክርክር የቀረቡት ቤቶች በአዋጁ
ስላለመወረሳቸው አመልካቾች ማስረጃ ያላቀረቡና 1ኛ ተጠሪ ግን ማስረጃ ያቀረበ መሆኑን፣ የቤት
ቁጥር 391 በአዋጁ 47/67 ከተወረሰ በኋላ ቤቱን ሀእና ለ በማለት በመከፍፈል እያስተዳደረው
የሚገኝ መሆኑ ቤቶቹ በመንግስት እንደተወረሰ አመልካቾች ያመኑ መሆኑን በመግለፅ የስር
ፍ/ቤት ብይን ሊፀና ይገባል በማለት የተከራከረ ሲሆን ከ 2ኛ-6ኛ ያሉ ተጠሪዎች በበኩላቸው
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ቤቶቹ ከተወረሱ 4ዐ ዓመት ስለሆናቸው በአዋጅ ቁጥር
47/67 የተወረሱ ንብረቶች የባለቤትነት ሁኔታ አጣርቶ የመወሰን ስልጣን የተሰጠው በአዋጅ ቁጥር
110/87 አንቀፅ 4/1/2/ መሰረት ለኢትዮጲያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ መሆኑን፣ ቤቶቹ በአንድ
ጣራና ግድግዳ ስር የተሰሩ 5 ደጃፍ ቤቶች መሆናቸውንና የአመልካቾች አውራሽ ትርፍ ቤት
ስላለው መርጦ በመውሰድ ሌሎቹ በህጉ መሰረት የተወረሱ መሆናቸውን በመጥቀስ የስር ፍ/ቤት
ብይን ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

8ኛ ተጠሪ ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካቾች ቤቱ ከአዋጅ ውጭ ያላግባብ


ተወርሶ ከሆነ መብታቸውን ተጠቅመው ስልጣን ለነበረው አካል ያላቀረቡና ያልጠየቁ መሆኑን፣
በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት መ/ቁ 31682 በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተወርሰዋል ተብለው
በመንግስት ተቋማት ቁጥጥር ስር ያሉ ቤቶች ጋር በተያያዘ ይመለሱልኝ በሚል የሚቀርቡ
አቤቱታዎችን መሰረት በማድረግ ፍ/ቤቶች መውረስና አለመውረስን በተመለከተ ማስረጃዎችን
መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን ያልተሰጣቸው መሆኑን፣ 8ኛ ተጠሪ የያዙት ቤት አባታቸው
አቶ ሽጉጤ ቡሌ ከአመልካቾች አባት በስጦታ ያገኙት መሆኑ በቀበሌው ማስረጃ መቀበያ መረካከቢያ
ደረሰኝ ላይ በማህተም ተረጋግጦ ማህደር ላይ የተቀመጠ መሆኑን፣ ስለሆነም የሚጠየቁበት አግባብ
እንደሌለ ተከራክረዋል፡፡ 7ኛ እና 9ኛ ተጠሪ በፍ/ቤቱ መጥሪያ ቢላክላቸውም መልስ ያላቀረቡ
በመሆኑ ችሎቱ በቀን መጋቢት 16 ቀን 2013 በዋለው ችሎት መልስ የማቅረብ መብት ቀሪ
በማድረግ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

የጉዳዩን አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሉቱም
ከሰበር ቅሬታው አኳያ እና ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ይዘት አንፃር አግባብነት ካለው ህግ ጋር
በማገናዘብ ተመርምሮአል፡፡ በመሰረቱ ለረዥም ጊዜ በመንግስት ቁጥጥር ስር የነበረን ቤት
ይለቀቅልኝ በሚል አቤቱታ የሚያቀርብ ወገን ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ
ወይም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል ከሆነም ለሚመለከተው አካል ጥያቄውን አቅርቦ ውሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አግኝቶ ባለመብት መሆኑን ማስረዳት ያለበት ስለመሆኑ ከመስረዳት ሸክም ከመክሰስ መብት አንፃር
በሰ/መ/ቁ 14094 እና 45161 አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ ይህንን ማስረጃ የሚሰጠውን በጉዳዩ ላይ
የዳኝነት ስልጣን ያለውን አካል በተመለከተ አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከአዋጁ ውጪ
ተወስዶብኛል የሚል ወገኝ ጉዳዩን ማቅረብ ያለበት ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ስለመሆኑ አዋጅ
ቁጥር 110/87 እና ይህንኑ አዋጅ ለማሻሻል የወጡት አዋጅ ቁጥር 193/92 እና 572/2000
የሚያሳዩ ሲሆን በዋነኛነትም የአዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀፅ 4/2/ /ሐ/ ከአዋጁ ውጪ የተወሰደን
ንበረት ባለቤትነት በተመለከተ በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ መረጃዎችን እያጣራ ተገቢውን ውሳኔ
የሚሰጠው ይኽው አካል መሆኑ በግልፅ ተመልክቷል፡፡

በዚህ አግባብም በሰበር መዝገብ ቁጥር 30631፤30701 እና በተመሳሳይ መዝገቦች በተሰጠው


አስገዳጅ ውሳኔም ለረዥም ጊዜ በመንግስት ቁጥጥር ስር የነበረን ቤት ከአዋጅ ውጪ ወይም በህገ
ወጥ መንገድ በመንግስት የአስተዳዳር አካል ተወስዶብኛል በሚል የሚቀርቡ አቤቱታዎችን
እንዲሁም ከምርጫ ቤት ጋር በተያያዘ የምርጫ ቤቴን፤ በቀላጤ፣በቃል ትዕዛዝ ወይም በመመሪያ
ከህግ ውጪ ተወሰደብኝ በሚል የሚቀርቡ አቤቱታዎች መርምሮ የመወሰን ስልጣን ያለው
የፕራይቬታዜሽን ኤጀንሲ ለመሆኑ አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ አሁን በያዝነው ጉዳይ አመልካቾች
ክሳቸውን ያቀረቡት 1ኛ ተጠሪ ቁጥራቸው ከ391-395 ድረስ ያሉ ቤቶችን ትርፍ ነው በማለት
በመውረስ በእገ-ወጥ መንገድ በመውሰድ ከ2ኛ እስከ 6ኛ ለተመለከቱት ተጠሪዎች ማከራየቱን የቤት
ቁጥር 391Aን በተመለከተም ከ1981 ዓም ጀምሮ በህገወጥ መንገድ በመውሰድ ለ9ኛ ተጠሪ
በማከራየት እየተጠቀመ መሆኑን በመግለፅ ሲሆን አመልካቾች አውራሽ አባታችንን በማሰር
እናታችንን በማስፈረም የተዘጋጀ ነው ቢሉም ቁጥራቸው ከ391-395 ያሉት ቤቶች የተረከበበትን
በ24/03/1968 ዓም የተዘጋጀውን ቅፅ 003 በማቅረብ ቤቶቹ ለረዝም ጊዜ በአስተዳደር አካሉ
ቁጥጥር ስር የቆዩ መሆኑን አሳይቷል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ የስር ፍርድ ቤት አከራካሪዎቹን
ቁጥራቸው ከ391-395 የተመለከቱትንና ቁጥሩ 391A የሆነው ቤት አስመልክቶ ለፕራይቬሽን
ኤጀንሲ ቀርቦ ባለመብትነታቸው ተረጋግጦ ወይም በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት በወቅቱ
በተቋቋመው አካል ተረጋግጦ የተሰጠው ውሳኔ በሌለበት በቀጥታ ቤቶቹ በህጉ አግባብ ተወርሰዋል
ወይስ አልተወረሱም በማለት የመወሰን ስልጣን የለኝም በማለት የአመልካቾችን ክስ ከነዚህ ቤቶች
አንፃር ውድቅ ማድረጉ የሚነቅፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡

በ8ኛ ተጠሪ ቁጥጥር ስር የሚገኘውን የቤት ቁጥር 391B በተመለከተ በሰበር መዝገብ ቁጥር
37281 በተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ አግባብ ቤቱ ተወርሶ ለረዝም ጊዜ በመንግስት የአስተዳደር አካል
ቁጥጥር ስር ለመሆኑ አመላካች ማስረጃዎች ያአልቀረቡ በመሆኑና አመልካቾች ክስ ሲያቀርቡም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሆነ 1ኛ ተጠሪ መልስ ሲሰጥ በዚሁ አግባብ ያልተከራከረ ሆኖ እያለ 8ኛ ተጠሪም የአመልካቾች


አውራሽ ለአባታቸው በስጦታ የሰጧቸው የግል ቤታቸው መሆኑን ጠቅሰው እየተከራከሩ የስር
ፍርድ ቤት ይህንን ቤት አስመልክቶ የቀረበውን ክርክር ከላይ ከተመለከቱት ቤቶች ክርክር ለይቶ
በማየት የግራቀኙ የመፋለም ክርክር በመመርመር ተገቢውን ውሳኔ ሊሰጥ ሲገባ ከላይ
ከተመለከተው ክርክር ጋር አጠቃልሎ በማየት የአመልካቾችን በቤትቁጥር 391B ላይ ያቀረቡትን
ክስ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለው ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1.የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት በኮመ/ቁ 134862 በ05/03/2012


ዓ.ም በዋለው ችሎት አከራካሪዎቹን የቤት ቁጥራቸው ከ391-395 የተመለከቱትንና ቁጥሩ391A
የሆነውን ቤት አስመልክቶ የሰጠውና እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ251009 በቀን
15/10/2012 ዓም በዋለው ችሎት ይህንን የውሳኔ ክፍል በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ
በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል

2. አመልካቾች በየካ ክ/ከ/ወረዳ 06 የሚገኘውን የቤትቁጥር 391B የሆነውን ቤት አስመልክቶ በ8ኛ


ተጠሪ ላይ ያቀረበውን ክስ ጥያቄው ለፕራይቬታዜሽን ኤጀንሲ ቀርቦ ባለመብትነታቸው
ተረጋግጦ ወይም በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት በወቅቱ በተቋቋመው አካል ተረጋግጦ የተሰጠ
ውሳኔ በሌለበት በቀጥታ ቤቱ በህጉ አግባብ ተወርሰዋል ወይስ አልተወረሱም በማለት የመወሰን
ስልጣን የለኝም በማለት የግራቀኙን የመፋለም ክርክር ውድቅ ማድረጉና ይህ ውሳኔ በከፍተኛው
ፍርድ ቤት መፅናቱ መሰረታዊ የህግ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው የውሳኔ ክፍል
ተሸሯል፡፡ የስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የጉዳዩን መዝገብ በማንቀሳቀስ አመልካቾችና 1ኛ ተጠሪ
አከራካሪውንቤት አስመልክቶ ያቀረቡት የመፋለም ክርክር 8ኛ ተጠሪ ካቀረቡት መቃወሚያ
በመነሳት መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ341(1) መሰረት
መልሰንለታል፡፡

3. የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ በመጣበት አኳኃን ይመለስ፡፡

4. ሚያዝያ 04 ቀን 2013 ዓም በዋለው ችሎት በየካ ክ/ከ/ወ/06 የቤ/ቁ391A እና392 የሚገኙ


ቤቶች አስመልክቶ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ እንዲነሳ ታዟል፡፡

5. ግራቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ

ጉዳዩ ተገቢውን እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ8/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 195919

ቀን ፡- ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- 1. ወ/ሮ ጌጤ ዶሪ

2. ወ/ሮ አበራሽ ዶሪ

3. ወ/ሮ ባዩ ዶሪ

4. ወ/ሮ ዘሪቱ ዶሪ

ተጠሪ ፡- 1. አቶ ዶሪ ሻሎ

2. አቶ ዓለሙ ጉጆ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የሠጠው ውሳኔ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበር፡፡ አመልካቾች
ያቀረቡት ክስ ወላጅ እናታችን ወ/ሮ ማሬ በዳኔ በ21/08/1990 ዓ/ም የሞቱ ሲሆን አመልካቾች የሟች
ልጆችና ወራሾች ነን፤ በይርጋ ጨፌ ወረዳ በአዳሜ ቀበሌ አስተዳደር ክልል ሥር ከአባታችን ከ1ኛ ተጠሪ
ጋር በጋራ ያፈሩት ቤት አላቸው፡፡ ንብረቱን ወራሾች በማናውቀው ሁኔታ በ15/05/2010 ዓ/ም በተጻፈ ውል
1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ በሽያጭ መኖሪያ ቤቱን ከነይዞታው አስተላልፏል፡፡ በፍ/ሕ/ቁ. 1715(2) መሠረት
ውሉ ፈርሶ ንብረቱን ለወራሾች እንዲመልሱ እንዲወሰንልን ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

1ኛ ተጠሪ የሠጡት መልስ ይዘት ውሉ የተደረገው በ21/09/2009 ዓ/ም ነው፡፡ የተሸጠውም 20 በ17 ሜትር
ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ነው፡፡ የሽያጭ ውሉ ከባለቤቴ ወ/ሮ ምትኬ ደሮ እና ከሌሎች ሦስት ወራሾች
ጋር በብር 50,000.00 የተደረገ ነው፡፡ 2ኛ ተጠሪም ንብረቱን ከገዛ በኋላ ማሻሻያ ሥራ ሰርቶበታል፡፡
የእናታቸው ድርሻ ከተሸጠ ውርሱ ተጣርቶና ድርሻ ተለይቶ ሊቀርብ ሲገባ በዚህ አግባብ ያልቀረበ ክስ
ተቀባይነት የለውም የሚል ነው፡፡ 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ንብረቱን ገዝቻለሁ፡፡ የኔ ባይ ከመጣ ለመከራከርና
ለማስቀረት ተዋዋዮች ግዴታ ገብተዋል፡፡ ንብረቱን የማደስና የማሻሻያ ሥራ ሰርቻለሁ፡፡ አመልካቾች
ድርሻቸውን ከሻጮች ይጠየቁ እንጂ ውሉ ሊፈርስ አይገባም ብለዋል፡፡ የይርጋ ጨፌ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግራቀኙን አከራክሮ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 41857 እና 47378
ላይ በቅጽ 10 እንደታተመ በሠጠው ትርጉም መሠረት ጠንቃቃ ገዥ ያደረገው የሽያጭ ውል ሊፈርስ
አይገባም፡፡ ወራሾች ድርሻቸውን ከሽያጭ ገንዘቡ ከሻጮች ሊቀበሉ ይገባል በማለት ወስኗል፡፡ በየደረጃው
የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን አጽንተዋል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በተጠቀሱት የሰበር
ችሎት ውሳኔዎች ወራሾች ብቸኛ ወራሽ ነን በማለት ንብረቱን በስማቸው አዛውረው ያደረጉትን ሽያጭ
የሚመለከት ነው፤ በተያዘው ጉዳይ የንብረቱ ሻጭ ወራሾች ሳይሆኑ 1ኛ ተጠሪ ናቸው፡፡ የንብረቱ ሥመ-
ሀብትም አልተዛወረም፤ በጋራ ስናስተዳድረው የነበረን ንብረት ነው 1ኛ ተጠሪ የሸጡት፡፡ በውል አዋዋይ ፊት
የተደረገ ውል አይደለም፤ ውሉም ሕገ-ወጥ በመሆኑ ሊፈርስ ይገባል የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት
ጉዳዩን መርምሮ የሠበር ውሳኔዎች ተጠቅሰው ውሉ ሊፈርስ አይገባም መባሉ ሕጋዊነቱን ለመመርመር
ተጠሪዎች መልስ እንዲያቀርቡ አዟል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ይዘትም በሥር ፍርድ ቤቱ የተጠቀሰው
የሠበር ውሳኔ ለጉዳዩ ተፈጻሚነት ያለው ነው፡፡ አመልካቾች ንብረቱ ሲሸጥ ያውቃሉ፡፡ ውሳኔው ተገቢ ነው
የሚል ነው፡፡ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ አመልካቾች ውሉ ሲፈጸም እያወቁና ንብረቱ ማሻሻያ ሥራ ሲሰራበት እያዩ
ቆይተው ያቀረቡት ክስ ተገቢነት የለውም፡፡ የተሸጠው ቤት እንጂ ቦታ አይደለም፤ ውሉ ሕጋዊ ስለሆነ
ሊፈርስ አይገባም፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊጸና ይገባል ብለዋል፡፡ አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ
የሠበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ በሰበር አጣሪ ችሎት የተያዘው
ጭብጥ፣ በሥር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደመረመርነው አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ወላጅ እናታችን ሟች ወ/ሮ ማሬ በዳኔ ልጆችና ወራሾች ነን፤
በይርጋ ጨፌ ወረዳ በአዳሜ ቀበሌ አስተዳደር ክልል ሥር ከአባታችን ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በጋራ ያፈሩት ቤት
አላቸው፡፡ ንብረቱን ወራሾች በማናውቀው ሁኔታ በ15/05/2010 ዓ/ም በተጻፈ ውል 1ኛ ተጠሪ ለ2ኛ ተጠሪ
በሽያጭ መኖሪያ ቤቱን ከነይዞታው አስተላልፏል፤ ውሉ ፈርሶ ንብረቱን ለወራሾች እንዲመልሱ
እንዲወሰንልን የሚል ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ 20 በ17 ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ለ2ኛ ተጠሪ
መሻጣቸውን ገልጸው ውርሱ ተጣርቶና ድርሻ ተለይቶ ያልቀረበ ክስ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ
በበኩላቸው ንብረቱን ገዝቻለሁ፡፡ ንብረቱን የማደስና የማሻሻያ ሥራ ሰርቻለሁ፡፡ አመልካቾች ድርሻቸውን
ከሻጮች ይጠየቁ እንጂ ውሉ ሊፈርስ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ውል ሊመሠረት የሚገባው ችሎታ ባላቸው፣ በተዋዋዮች ነጻ ፈቃድ፣ የሚቻልና ሕጋዊ በሆነ ዓላማና ጉዳይ
ላይ በሕግ የተመለከተውን የውል አጻጻፍ ፎርም ተከትሎ ሊሆን እንደሚገባ በፍ/ሕ/ቁ. 1678 ላይ
ተመልክቷል፡፡ ውሉ የአመሠራረት ጉድለት ካለበት ተዋዋዮች/መብት ያገኙ ሰዎች ሥምምነቱ ፈራሽ
እንዲሆን በፍ/ሕ/ቁ. 1808 አግባብ ክስ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ አመልካቾችም በዚህ አግባብ ውል ሰጭ የሆኑት
አባታቸው በሙሉ ንብረቱ ላይ ውሉን ለመፈጸም መብት የላቸውም፣ በንብረቱ የሟች እናታችን ግማሽ ድርሻ
ላይ ወራሾች ሳንፈቅድና ሳንስማማ የተደረገው ውል ፈራሽ እንዲሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች የንብረቱ
ግማሽ ባለድርሻ ወራሾች የሆኑት አመልካቾች አይደሉም የሚል ግልጽ ክርክር የላቸውም፡፡ የሥር ፍርድ
ቤትም አመልካቾች በንብረቱ ላይ ድርሻ ያላቸው መሆኑን በማረጋገጥ ከሽያጭ ገንዘቡ 1ኛ ተጠሪ ድርሻቸውን
እንዲከፍሏቸው ወስኗል፡፡ አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ከሽያጭ ገንዘቡ ሳይሆን ውሉ ፈርሶ
ንብረቱን መረከብ አለብን በሚል ነው፡፡

2ኛ ተጠሪ በዚህ ችሎት ደረጃ የሚከራከሩት አመልካቾች ውሉ ሲፈጸም እያወቁና ንብረቱ ማሻሻያ ሥራ
ሲሰራበት እያዩ ቆይተው አሁን ያቀረቡት ክስ ተገቢነት የለውም በማለት ነው፡፡ ከዚህ ክርክር በመነሳት 2ኛ
ተጠሪ መብቱ የተላለፈላቸው ጥበቃ ሊደረግለት በሚገባ ግብይት መሆን አለመሆኑን መመልከት ተገቢ ነው፡፡
2ኛ ተጠሪ ግዥ ሲፈጽሙ አንድ ጠንቃቃ ገዥ በሕግ ሆነ በአሠራር ሊያደርገው የሚገባውን ጥንቃቄ
የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ሕግ የተለየ ጥበቃ ስለሚያደርግ የሀብትነት ሠነድ
ስለሚወጣበት፤ ሠነዱ ስለሚገኝበት የሥራ ክፍል፣ ውሉ ስለሚፈጸምበት እና ንብረቱ ስለሚተላለፍበት
ሥርዓት የተገለጸውን መከተል ዴታ ይጥላል፡፡ ሽያጭ ውል የሚፈጸምበት ንብረት ላይ በሕግ መብት
ያላቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑ፣ ቦታው ላይ ቤት ያረፈበትና ስለቤቱ የሚመለከቱ ሠነዶች በቤቱ ባለሀብት
ሥም በማይንቀሳቀስ ሀብት ምዘገባ ክፍል መገኘቱና ውሉ የፍ/ሕ/ቁ. 2878 በሚያዘው አግባብ ንብረቱ
በሚገኝበት ሥፍራ ባለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ምዘገባ ክፍል እንዲመዘገብ ይጠበቃል፡፡ 2ኛ ተጠሪ ውሉን
የፈጸሙት ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ሲሆን የንብረቱ ግማሽ ባለድርሻ ወራሾች የሆኑት አመልካቾች በሽያጭ ውሉ
አለመሳተፋቸው ከትክክለኛው ባለመብት ያልገዙ መሆኑን ያሳያል፡፡ አመልካቾች የሽያጭ ሂደቱን በጊዜው
ያውቁ ነበር የሚለው የ2ኛ ተጠሪ ክርክርም ሌሎች ወራሾች እንዳሉ እያወቁ ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ
የገዙት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ ውሉም በማይንቀሳቀስ ሀብት ምዘገባ ክፍል የተመዘገበ አይደለም፡፡ ስለሆነም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተደረገው የሽያጭ ውል ተገቢውን ሕግና አሠራር ተከትሎ የተፈጸመ ባለመሆኑ ውሉ ፈራሽ ሊሆን ይገባል
ብለናል፡፡

በሥር ፍርድ ቤት የተጠቀሱት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 41857
እና 47378 የሠጣቸው ውሳኔዎችና አስገዳጅ ትርጉሞች የሽያጭ ውሉ ጥበቃ እንዲደረግለት የሚያዘው
ንብረቱ በሻጭ ስም ተዛውሮ የነበርና ገዥው ተገቢው ጥንቃቄ አድርጎ በሕግ በተመለከተው ሥርዓት
ለተፈጸመ ግብይት ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ 2ኛ ተጠሪ ተገቢው ጥንቃቄ አድርገው የፈጸሙት የሽያጭ ውል
ባልሆነበት ሁኔታ ውሉ ሊፈርስ አይገባም ተብሎ መወሰኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

1. የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 76667 የካቲት 24 ቀን 2012
ዓ/ም፣ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 15110 ታህሳስ 03 ቀን 2012 ዓ/ም እና የይርጋ
ጨፌ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 012032 መስከረም 06 ቀን 2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. በይርጋ ጨፌ ወረዳ በአዳሜ ቀበሌ አስተዳደር ክልል ሥር የሚገኘው ቤት በተጠሪዎች መካከል


የተደረገው የሽያጭ ውል ፈራሽ ነው በማለት ወስነናል፡፡ 2ኛ ተጠሪ ንብረቱን ለአመልካቾችና ለ1ኛ ተጠሪ
እንዲያስረክቡ ተወስኗል፡፡

3. 2ኛ ተጠሪ የሽያጭ ገንዘቡንና ለማሻሻያ ሥራ ያወጡት ወጪን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪን ከመጠየቅ ይሕ


ውሳኔ አያግድም፡፡

4. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡ የይርጋ ጨፌ ወረዳ ፍርድ ቤት በውሳኔው
መሠረት እንዲያስፈጽም አዘናል፡፡ ይጻፍ
 በዚህ ችሎት የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ/ም የተሰጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 196128
ቀን ፡- ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ወ/ሮ መቅደስ ወልደማርያም ፡- ጠበቃ ነብዩ ምክሩ ቀረቡ

ተጠሪ ፡- አቶ ታምሩ በቀለ፡- ጠበቃ ዘውዱነህ ዘኪዮስ ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው
አመልካች ተቃዋሚ ሲሆኑ ተጠሪ የስር አፈጻጸም ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ከወ/ሮ ኤደን ወንድይፍራው እና
ኤድሰን ካርጎ ኃ/የተ/የግል ማሕበር ጋር ተከራክረው ገንዘብ እንዲከፈላቸው በመወሰኑ ምክንያት ውሳኔውን
ለማስፈጸም የአፈጻጸም ክስ አቅርበዋል፡፡ ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የሚሆን በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ
ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 1137 የሆነ የ1ኛ የፍርድ ባለዕዳ ወ/ሮ ኤደን ወንድይፍራው ንብረት ነው
በማለት ለእዳው መክፈያ እንዲሆን ጠይቀው አፈጻጸም ችሎቱ ንብረቱ እንዲከበር ያደረገ ሲሆን አመልካች
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሠረት ንብረቱ እንዲለቀቅ የተቃውሞ ማመልከቻ አቅርበዋል፡፡ ይዘቱም በአፈጻጸም
የተከበረው ንብረት የሟች ወንድይፍራው መንገሻና የእኔ ያልተከፋፈለ የጋራ ሀብት ነው፡፡ የሟች የውርስ
ሀብትም በፍርድ ቤት በመጣራት ላይ ያለ ስለሆነ የውርስ ድርሻ አልተለየም፡፡ በመሆኑም ንብረቱ ተሸጦ
ለፍርዱ ገንዘብ ማስፈጸሚያ ሊውል አይገባም ብለዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር የንብረቱ ስመ-ሀብት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወደወራሾች ዞሯል፣ ካርታውም በስማቸው ይገኛል፤ ይሕም የውርስ ድርሻቸው መለየቱን ያሳያል፡፡ ስለሆነም
በ1ኛ የፍርድ ባለዕዳ ድርሻ ላይ የአፈጻጸም ትዕዛዝ መሰጠቱ ተገቢ ነው የሚል ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን
አከራክሮ የውርስ ንብረት ያልተከፋፈለ የወራሾች የጋራ ንብረት ነው፡፡ ንብረቱ በአመልካች እና በሌሎች
ወራሾች ስም መመዝገቡ ተረጋግጧል፡፡ ይሕ በሆነበት ሁኔታ የውርስ ሀብት ማጣራት ሂደት ይጠበቅ መባሉ
ተገቢ አይደለም፡፡ አፈጻጸሙ ንብረቱ ላይ ሊቀጥል ይገባል በማለት ወስኗል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የአመልካችን ይግባኝ ባለመቀበል ሠርዟል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የውርስ ሀብቱ
በመጣራት ላይ ያለ ነው፡፡ የ1ኛ የፍርድ ባለዕዳ የውርስ ድርሻ አልተለየም፡፡ ስለሆነም የአፈጻጸም ክርክሩ
የውርስ ማጣራት ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሊጠብቅ ይገባል የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን
ተመልክቶ የውርስ ድርሻው ተለይቶ ባልታወቀበትና አመልካች ይሕንን እየተቃወመ አፈጻጸሙ በንብረቱ ላይ
መቀጠሉ ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ በማዘዙ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ንብረቱ ላይ የሚስትነትና
የወራሽነት ማስረጃ ወጥቶ ስመ-ሀብቱ ተዛውሯል፡፡ የውርስ ማጣራት አቤቱታ ያቀረበ ሰው ካለ በራሱ
የሚከራከር እንጂ አመልካች ሌሎች ሰዎችን ወክለው ሊከራከሩ አይችሉም፡፡ የፍርዱ ገንዘብ ብር
173,283.00 ነው፤ የ1ኛ የፍርድ ባለዕዳ የውርስ ድርሻ ከዚህ ገንዘብ በላይ ነው፡፡ በድርሻቸው ላይ አፈጻጸሙ
መቀጠሉ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር
ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ የሠበር አጣሪ ችሎት ከያዘው
ጭብጥና በሥር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪ ከወ/ሮ ኤደን ወንድይፍራው እና ኤድሰን ካርጎ ኃ/የተ/የግል ማሕበር ጋር


ተከራክረው ገንዘብ እንዲከፈላቸው በመወሰኑ ምክንያት ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የሚሆን በአዲስ አበባ ከተማ
ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 1137 የሆነ የ1ኛ የፍርድ ባለዕዳ ወ/ሮ ኤደን ወንድይፍራው
ንብረት ነው በማለት ለእዳው መክፈያ እንዲሆን ጠይቀው አፈጻጸም ችሎቱ ንብረቱ እንዲከበር አድርጓል፡፡
አመልካች በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሠረት ንብረቱ እንዲለቀቅ የተቃውሞ ማመልከቻ ያቀረቡት የተከበረው
ንብረት የሟች ወንድይፍራው መንገሻና የእኔ ያልተከፋፈለ የጋራ ሀብት ነው፡፡ የሟች የውርስ ሀብትም
በፍርድ ቤት በመጣራት ላይ ያለ ስለሆነ የውርስ ድርሻ አልተለየም፡፡ ስለሆነም በአፈጻጸም ሊከበር አይገባም
የሚል ነው፡፡ ለፍርድ ማስፈጸሚያ የተከበረ ንብረት ላይ መብቴ ተነክቷል ያለ ሰው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418
መሰረት የተቃውሞ ማመልከቻ አቅርቦ በንብረቱ ላይ ያለውን መብት በማሳየት ንብረቱ ከአፈጻጸም ውጭ
እንዲሆን የመጠየቅ መብት አለው፡፡ በድንጋጌው ንዑስ ቁጥር 3 ላይ አመልካች የሆነው ወገን ንብረቱ ላይ
የተቀዳሚነት ሆነ የባለይዞታነት መብቱን የሚያረጋግጥለትን ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 419(1) መሠረት ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን እና ማስረጃውን መርምሮ ንብረቱ እንዲያዝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወይም እንዲከበር የሚያደርግ በቂ ምክንያት አለመኖሩን ሲረዳ የተያዘው ንብረት እንዲለቀቅ ትዕዛዝ
ይሠጣል፡፡

አመልካች ያቀረቡትን የተቃውሞ ማመልከቻ ተከትሎ ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር የንብረቱ ስመ-ሀብት
ወደወራሾች ዞሯል፣ ካርታውም በስማቸው ይገኛል፤ ይሕም የውርስ ድርሻቸው መለየቱን ያሳያል፡፡ ስለሆነም
በ1ኛ የፍርድ ባለዕዳ ድርሻ ላይ የአፈጻጸም ትዕዛዝ መሰጠቱ ተገቢ ነው የሚል ነው፡፡ ከክርክሩ የተገነዘብነው
በአፈጻጸም የተከበረው ቤት ባለንብረት አመልካችና አቶ ወንድይፍራው መንገሻ ነበሩ፡፡ አቶ ወንድይፍራው
መንገሻ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ሥመ-ሀብቱ በአመልካች ስምና በሟች ወራሾች ስም መዛወሩን
የሥር ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ፍሬ ነገር ነው፡፡ አመልካችም ንብረቱ በአመልካና በወራሾች ስም መዛወሩን
ክደው አይከራከሩም፡፡ 1ኛ የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት ወ/ሮ ኤደን ወንድይፍራው የሟች ወራሽና ባለድርሻ
መሆናቸውም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው፡፡ አፈጻጸም ችሎቱ በተለይም ሐምሌ 02 ቀን 2011 ዓ/ም በሠጠው
ትዕዛዝ ዕዳው የሚፈጸመው የፍርድ ባለዕዳ በንብረቱ ባላቸው የውርስ ድርሻ ልክ ስለመሆኑ ገልጿል፡፡ ንብረቱ
ወደ ወራሾች ሲዛወር በቤቱ ግማሽ ሀብት ላይ መብት ያላቸው ሰዎች የተለዩ በመሆኑ የውርስ ድርሻው ላይ
አፈጻጸሙን ማስቀጠል የሚያስችል ነው፡፡ አመልካች በንብረቱ ላይ ያላቸው ግማሽ ድርሻ ለዕዳው መክፈያ
እንዲውል ያልተደረገ በመሆኑ አፈጻጸም ሂደቱ መብታቸውን የነካ አይደለም፡፡ ሌሎች ወራሾች ውርስ ሀብት
እንዲጣራ የጠየቁ ካሉና አፈጻጸሙ መብታቸውን የሚነካ ከሆነ መብታቸው የተነካባቸው ሰዎች በራሳቸው
የተቃውሞ ማመልከቻ ሲያቀርቡ የሚመረመር ይሆናል፤ አመልካች ውክልና ሳይኖራቸው በራሳቸው ስም
ስለሌሎች ሰዎች ሊከራከሩ አይችሉም፡፡ ስለሆነም የሥር ፍርድ ቤቶች በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 418 መሰረት
አመልካች ያቀረቡትን የተቃውሞ ማመልከቻ ያልተቀበሉት የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ተከትለው ስለሆነ
የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 253896 ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ/ም እና የፌዴራል


የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 267544 ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

1. የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡

2. አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የመ.ቁ. 196174
መስከረም 28/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡ አቶ ጋትዴት ኛቾም የቀረበ የለም

ተጠሪ፡ አቶ ኒያል ደጆክ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም
የአሁን ተጠሪ ጥር 05/2012 ዓም ፅፈው በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ ተጠሪ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዉ የነበረው ክስ ጭብጥም
ለአስር ተከታታይ ዓመታት በእጃቸው አድርገው ሲገለገሉበት የነበረውን ይዞታ የአሁን አመልካች
በራሳቸው ሥልጣን ይዘውባቸው ቤት የሰሩበት መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ሁከቱ ተወግዶ
ይዞታው እንዲለቀቅላችው ዳኝነት የሚጠይቅ ነው፡፡

በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት አመልካች ክስ የቀረበበት ይዞታ በከተማው ማስተር
ፕላን ምክንያት በተወሰደብኝ ይዞታ ምትክ በከተማው አስተዳደር ተሰጥቶኝ የይዞታ ማረጋጋጫ ምስክር
ወረቀት ጭምር ወስጄበት የያዝኩት ይዞታዬ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት
ተከራክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ክስ የቀረበበት
ይዞታ የአሁን ተጠሪ ስለመሆኑ ተጠሪው ባቀረቧቸው የሰው ምስክሮች የተረጋገጠ መሆኑን፤ በአሁን
አመልካች በኩል የቀረቡ ምስክሮች ደግሞ ይዞታ የከተማ አስተዳደሩ የቀበሌ 01 ምክር ቤት በኩል
የተሰጣቸው እንደሆነ መናገራቸውን፤ ሆኖም የቀበሌ ምክር ቤት የከተማ ይዞታን ለመስጠት ሥልጣን
ያልተሰጣቸው መሆኑን፤ አመልካች በማስረጃነት ያቀረቡት የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም
በክርክር ሂደት የተሰጠ በመሆኑ ህገ ወጥ ነው በማለት የአመልካችን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎ
ይዞታውን ለተጠሪ ሊለቁ ይገባል ብሏል፡፡

ይህንኑ ውሳኔ በይግባኝ የተመለከተው የጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩሉ ክስ በቀረበበት
ይዞታ ላይ ለአሁን አመልካች የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቀርቦ እያለ ይህ ወደ ጎን
ተደርጎ በሰው የምስክርነት ቃለ ብቻ አመልካች ይዞታውን እንዲለቁ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑን ተችቶ
የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሯል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደግሞ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ
በመሻር የወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔን አጽንቷል፡፡ አመልካች በዚሁ ውሳኔ ላይ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች መስከረም 15/2013
ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያሉትን መሰረታዊ
የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ
ተመርምሮ ለክርከሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ለአመልካች የሰጠው መሆኑን
በስር ፍ/ቤት ውሳኔ በተገለፀበት ሁኔታ አመልካች ሁከት ፈጥረዋል በማለት የተሰጠውን ውሳኔ
አግባብነት ከፍ/ህ/ቁ 1149 አኳያ በዚህ ሰበር ችሎት እንዲመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር
እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም በሰበር አጣሪው
ችሎት ሊጣራ ይገበዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው
የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል፡፡

እንግዲህ ከክርክሩ አጀማመር መረዳት እንደሚቻለው ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ለአስር ተከታታይ ዓመታት
በእጄ አድርጌ ስለገለግለብት የነበረውን ይዞታዬን አመልካች በሥልጣኑ ይዞት ቤት የሰራበት በመሆኑ
ሁከቱ ተወግዶ ይዞታው ሊለቀቅልኝ ይገባል የሚል ነው፡፡ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለአንድ ንብረት
ባለይዞታ ንብረቱን አስመልክቶ በህግ ከተረጋገጡት መብቶች ውስጥ አንዱ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁጥር
1149(1) ይደነግጋል፡፡ በዚህ መልኩ ክስ የሚያቀርብ ሰው ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች
ሁከት ተፈጠረበት የተባለውን ንብረት/ሀብት/ ባልተጭበረበረ መንገድ በእጁ አድርጎ በእውነት
የሚያዝበት መሆኑን እና በዚሁ ይዞታው ላይ በተከሰሰው ሰው ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሁከት
የተፈጠረበት ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህ/ቁ/1140፣ 1146 እና 1149 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መረዳት
ይቻላል፡፡ በዚህ አግባብ በቀረበ ክስ ላይ ሁከት ተፈጥሯል ተብሎ ውሳኔ የሚሰጠውም የተከሰሰው ሰው
የሌላ ሰው ይዞታ መያዙ አልያም በይዞታው ላይ ሁከት መፍጠሩ ሲረጋገጥ እና የሁከት ክስ የቀረበበት
አካልም የሥራውን አደራረግ የሚፈቅድ ለእርሱ የሚናገርለት መብት መኖሩን በፍጥነት እና
በማይታበል ዓይነት ሁኔታ ሳያስረዳ ሲቀር ስለመሆኑ ከዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 1 እና 3 ይዘት
መረዳት ይቻላል፡፡

አሁን በቀረበው ጉዳይ ተጠሪ ያቀረቡትን የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማስረዳት ያቀረቡት የሰው ምስክር
ብቻ ነው፡፡ የተሰሙት ምስክሮችም ቢሆኑ ይዞታው የተጠሪ ነው የሚል የምስክርነት ቃል
ከመስጠታቸው ባለፈ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ይዞታ ተጠሪ በእጃቸው አድረገው በእውነት
እያዘዙበት እያለ አመልካች በሁከት ተግባር የያዙባቸው ስለመሆኑ ያረጋገጡት ነገር የለም፡፡ በአንፃሩ
የአሁን አመልካች በዚሁ ይዞታ ላይ የተሰጣቸውን የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እና ከ2009 ዓ.ም
ጀምሮ ግብር ሲገብሩበት የነበረውን ማስረጃ ስለማቅረባቸው ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ይዘት መረዳት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይቻላል፡፡ በእርግጥ አመልካች ያረቀቡት የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ግራ ቀኙ በክርክር ላይ


እያሉ የተሰጠ ነው በሚል ውድቅ ተደርጓል፡፡ ሆኖም የይዞታ ማረጋጫ ምስክር ወረቀቱ ለአመልካች
የተሰጠው ህዳር 03/2012 ሲሆን ተጠሪ ክስ ያቀረቡት ደግሞ ጥር 05/2012 ዓ.ም ስለመሆኑ የስር ፍርድ
ቤት መዝገብ የሚያሳይ በመሆኑ ማስረጃው በክርክር ሂደት የተገኘ ነው የሚባል አይደለም፡፡ በክርክር
ሂደት የተገኘ ነው ቢባል እንኳን ማስረጃው የተሰጠው ከህግ እና የአሰራር ደንብ ውጭ ስለመሆኑ
እስካልተረጋገጠ ድረስ ውድቅ የሚደረግበት የህግ አግባብ የለም፡፡

ሲጠቃለል ተጠሪ ለክሱ መነሻ የሆነውን ይዞታ በእጃቸው አድርገው በእውነት እያዘዙበት እያለ በአሁን
አመልካች በሁከት ተግባር የተያዘባቸው ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት፤ ይልቁንም አመልካች በይዞታው
ላይ ቢያንስ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ግብር እየገበሩበት ያለ እና በይዞታው ላይም ሥልጣን ባለው
አስተዳደር አካል የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ
አመልካች በይዞታው ላይ ሁከት ፈጥረዋል ተብሎ እንዲለቁ መወሰኑ በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር
መሰረት ያላደረገ እና የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149 ድንጋን መሰረታዊ ይዘት ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

1. የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት


በፍ/ፋ/መ/ቁ/02517/2012 ላይ ሐምሌ 28/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የክልሉ ሰበር ሰሚ
ችሎት ይህንኑ ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ እንዲሁም የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር
መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/007/6/12 ላይ የካቲት 27/2012 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል፡፡

2. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/መ/ቁ/20105 ላይ ሚያዝያ


16/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በውጤት ደረጃ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት
ፀንቷል፡፡

ትዕዛዝ

1. የዚህን ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡


2. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-196340

ቀን፡-29/02/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ ማኅበር - ጠበቃ ነጋ ጌታነህ ቀረቡ

ተጠሪ ፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን- ነ/ፈጂ ደመቀ ሞልዬ ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
ጉዳዩ የኮንስትራክሽን ሥራ ዉል አፈጻጸም መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ የተጀመረዉ
አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረተዉ ክስ ነዉ፡፡በግራ ቀኙ መካከል በቀን
10/05/2008ዓ/ም የመገጭ ግድብ የዉሃ ማማ የመሰረት ምሰሶ ጉድጓድ ቁፋሮ ግንባታ ሥራ ዉል
ተደርጓል፡፡የግንባታ ዉሉ ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) ጨምሮ ብር 57,500,9200.00
ነዉ፡፡ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች የዉሉ አካል እንዲሆን ስምምነት ተደርጓል፡፡ተጠሪ ብር 11,500,184.00
ለአመልካች ቅድመ ክፍያ ፈጽሟል፡፡አመልካች ግንባታዉን በ360 ቀናት በማጠናቀቅ ለተጠሪ ለማስረከብ
ግዴታ ገብቷል፡፡ተጠሪ የግንባታ ሥራ ቦታ ለአመልካች በቀን 29/06/2008ዓ/ም አስረክቧል፡፡

ሆኖም ግንባታዉ የዘገየዉ የግንባታ ሥራዉ በሚከናወንበት ወቅት በሃገሪቱ በተለይ በአማራ ክልል ጎንደርና
አካባቢ በተነሳዉ የሕዝብ አመጽ በተፈጠረ ሁከት መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀበት ጊዜ ስለነበር
ከቀን 30/12/2008ዓ/ም እስከ ቀን 14/02/2009ዓ/ም ለ79 ቀናት የግንባታ ሥራዉ ተቋርጧል፡፡ይህም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 1 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1793 መሰረት ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ከመሆኑም በተጨማሪ በጠቅላላ የዉል
ሁኔታዎች ቁጥር 18.6 መሰረት ከአመልካች ቁጥጥር ዉጭ ነዉ ተብሎ የሚወሰድ ነዉ፡፡ይህንን ምክንያት
በመጥቀስ አመልካች በቀን 04/12/2008ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ የ102 ቀናት የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ ለተጠሪ
ቢያቀርብም ተጠሪ በዉል ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ 18.6፣73(1/ረ እና ሸ) ከዉልና ከሕግ የመነጨ
ምክንያት በመጥቀስ ለአመልካች ጊዜ ይራዘምልኝ ጥያቄ በ21 ቀን ዉስጥ ምላሽ ስላልሰጠ የማስረከቢያ ጊዜዉ
በዉል ተለይቶ እንዳይሰን በማድረጉ የማስረከቢያ ጊዜዉ በአእምሮ ግምት በቂ የሆናል ተብሎ
ስለሚወሰን(time at large) በዉሉ የተመለከተዉ የማስረከቢያ ጊዜ የማይፀና ሆኗል፡፡ አመልካች ለግንባታ
ሥራዉ መዘግየት ተጠያቂነት ሳይኖርበት ተጠሪ ዉሉን በሕገ-ወጥ መንገድ አቋርጧል፡፡የተፈጠረዉ ከአቅም
በላይ ምክንያት ከ60 ቀናት በላይ ስለቆየ በዉሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ 21.3/መ መሰረት አመልካች
ዉሉን መቋረጥ መብት ቢኖረዉም አላቋረጠም፡፡ይልቁንም ግንባታዉ በተፈጠረዉ የጸጥታ ችግር ምክንያት
ተቋርጦ ከቆየ በኋላ አመልካች ሥራዉን እንዲቀጥል አማካሪዉ በቀን 01/04/2009ዓ/ም ጽፎ ለአመልካች
በግልባጭ አሳዉቋል፡፡ አመልካች ሥራዉን በቀን 24/12/ 2009ዓ/ም በቁጥር የኢኮስኮ/8390/09 በጻፈዉ
ደብዳቤ አመልካች ሥራዉን በታቀደዉ የማስረከቢያ ጊዜ በቀን 20/07/2009ዓ/ም አላጠናቀቀም በሚል ቀኑን
ወደኋላ በማድረግ ዉሉን አቋርጧል፡፡

ስለሆነም አመልካች ለዉሉ መዘግየት ተጠያቂነት ሳይኖርበት ተጠሪ ዉሉን በሕገ-ወጥ መንገድ አቋርጧል
ተብሎ እንዲወሰን፡፡ ዉሉ በተቋረጠበት ጊዜ አመልካች ከሚቆፈረቱ 64 ጉድጓዶች ዉስጥ 21 የቆፈረ በመሆኑ
አመልካች ለሰራዉ ሥራ ብር 12,794,644.30 ሊከፈለዉ ስለሚገባ ከዚህ ላይ በቅድመ ክፍያ መልክ
የከፈለዉ ብር 11,500,184.00 ተቀንሶ የሚቀረዉን ብር 1,294,460.30 ዉሉ ሲቋረጥ መክፈል ሲገባዉ
ስላልከፈለ ከቀን 22/04/2008ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ተጠሪ ለአመልካች እንዲከፍል
እንዲወሰንበት፡፡ዉሉ የተቋረጠዉ አመልካች ተጠያቂ በሚሆንበት ምክንያት ባለመሆኑ ተጠሪ ከአመልካች
ተከፋይ ሂሳብ ላይ በቅጣት መልክ የቀነሰዉን ብር 5,750,000.00 ለአመልካች ተመላሽ እንዲያደርግ
እንዲወሰንበት፡፡አመልካች ለግንባታዉ መዘግየት ተጠያቂ ነዉ የሚባል ከሆነ በዉሉ አንቀጽ 87.1 መሰረት
ቅጣት የሚቀነሰዉ ላልተሰሩ ሥራዎች መጠን ብቻ ነዉ ተብሎ እንዲወሰን፡፡ተጠሪ ዉሉን ሲያቋርጥ
የአመልካች የግንባታ መሳሪያዎች አግቶ በመያዝ አመልካች በንብረቱ እንዳይገለገል በማድረጉ አመልካች
ከማሽኖቹ ያጣዉን ገቢ እስከ ቀን 23/10/2010 ዓ/ም ድረስ በተወሰደ የዋጋ ጥናት የተጣራዉን ከተ.እ.ታ
በፊት ብር 59,136,000.00 እንዲከፍል እንዲወሰንበት፡፡ ተጠሪ ዉሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያቋርጥ ከጊዜ
ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ተጨማሪ የክፍያ ጥያቄዎች በዉሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ
18.6፣69.1፣74.1/ተ መሰረት ከተ.እ.ታ በፊት ብር 8,1666,798.15 ተጠሪ ለአመልካች እንዲከፍል
እንደወሰንበት፡፡ እንዲሁም ተጠሪ በቅድመ ክፍያ ዋስትና እና በመልካም አፈጻጸም ዋስትና ላይ የማዘዝ
ሥልጣን የለዉም እንዲባልና ለአመልካች እንዲለቅ እንዲወሰንለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡

ተጠሪ ለክሱ በሰጠዉ መልስ አመልካች በክሱ የተጠቀሰዉን የግንባታ ሥራ በብር 57,500,920.00
ለመሥራት ከተጠሪ ጋር ዉል ተፈራርሟል፡፡አመልካች በዉሉ መሰረት ቅድመ ክፍያ ብር 11,500,184

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 2 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከተጠሪ ላይ ተቀብሏል፡፡አመልካች በዉሉ መሰረት አመልካች ቅድሚያ ክፍያ በተፈጸመለት በ20 ቀናት
ዉስጥ ሥራዉን ጀምሮ በ360 ቀናት ግንባታዉን አጠናቆ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ለግንባታ ሥራዉ
የተጓተተበት ምክንያት አመልካች ባለዉ የፀጥታ ችግር ሳይሆን የአመልካች የማሽን ብልሽት እና ለፕሮጀከቱ
ሥራ የሚሆን በቂ የሰዉ ኃይል እና ግብአት ባለመቅረቡ ነዉ፡፡ይሁን እንጂ ድጋሚ ጨረታ ማዉጣት የበለጠ
የግድብ ሥራዉ ጊዜ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል በሚል አመልካች ያሉበትን የአቅም እና የተለያዩ ችግሮች
በአስቸኳይ እንዲያርም መግባባት ላይ በመድረስ ላቀረበዉ የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ በቀን 08/05/2009ዓ/ም
የ33 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ተጠሪ ለአመልካች ሠጥቷል፡፡አመልካች የፀጥታ ችግር ስለመኖሩና ይህም
ሥራዉን እንዳይሰራ ፍፁም እክል የሆነበት መሆኑን በማስረጃ አላስረዳም፡፡የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የግንባታ
ሥራዉ በሚሰራበት አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምክንያት የታወጀ አይደለም፡፡ስለሆነም በፍ/ብ/ሕግ
ቁጥር 1792 መሰረት ከአቅም በላይ የሆነ ኃይል ሊባል የሚችል ካለመሆኑም በተጨማሪ የግንባታ ሥራዉን
ሊያስተጓጉል የሚችል የፀጥታ ችግር ባለመኖሩ አመልካች በወቅቱ ሥራዉን ሲሰራ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ
ግንባታዉን እንዲያጠናቅቅ በተደጋጋሚ ተጠሪ ለአመልካች ማስጠንቀቂያ የሰጠ ቢሆንም አመልካች ችግሩን
ቀርፎ ግንባታዉን ማጠናቀቅ ባለመቻሉ ከጊዜና ከገንዘብ አንጻር በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ
ምክንያት ተጠሪ ዉሉን መቋረጡን ለአመልካች በጽሁፍ አሳዉቋል፡፡

አመልካች በቀን 04/12/2008ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ለወደፊት የጊዜ ማራዘሚያ እንደሚጠይቅ ገለጸ እንጂ
በዚህ ቀኝ የጊዜ ማራዘሚያ አልጠየቀም፡፡የጊዜ ማራዘሚያ በቀን 09/03/2009ዓ/ም እና በቀን
03/04/2009ዓ/ም በተጻፉ ደብዳቤዎች ጠይቆ በአምስት ቀን ዉስጥ ማለትም በቀን 14/03/2009ዓ/ም መልስ
በመስጠት የሥራ መርሀግብር አዉጥቶ ተጨማሪ ማሽነሪና የሰዉ ኃይል አስገብቶ በተጨማሪ 33 ቀናት
ዉስጥ እንዲያጠናቅቅ ተጨማሪ ጊዜ ስለተሰጠዉ በ21 ቀን ዉስጥ ላቀረበዉ ጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ ተጠሪ
መልስ እንዳልሰጠዉ አድርጎ ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም፡፡አመልካችም ይህንን መሰረት በማድረግ
ሥራዉን እስከ ቀን 16/08/2009ዓ/ም ድረስ ለማጠናቀቅ በሚያስችለዉ መልኩ የሥራ መርሀ ግብር
አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡የ33 ቀናት ጊዜ ማራዘሚያ ስለተሰጠዉ ተጠሪ ለጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ መልስ ሳይሠጥ
ዉሉን እንዳቋረጠ አድርጎ ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይኘት የለዉም፡፡በአጠቃላይ አመልካች የገነባዉ 21
ምሶሰዎች ሲሆኑ ይህም በዉሉ መሰረት ስለመገንባቱ ተሞክሮ አለመረጋገጡ እንደተጠበቀ ሆኖ አፈጻጸሙ
ከ1/3ኛ ያነሰ ነዉ፡፡ይህም የአቅም ችግር እንዳለበት ስለሚያሳይ ተጨማሪ 360 ቀናት ቢጨመርለትም ቀሪዉን
ሥራ ማጠናቀቅ አይችልም፡፡ስለሆነም ዉሉ የተቋረጠዉ በአግባቡ ነዉ፡፡ተጠሪ ዉሉን ከመቋረጡ በፊት
ለተጠሪ የ60 ቀናት ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ ዉሉ ተጠሪን አያስገድደዉም፡፡በዉሉ አንቀጽ 21.2 ላይ ተጠሪ
ለአመልካች የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠዉ በፈቃጅ መልክ የተቀመጠ ነዉ፡፡በዚህ መሰረት ማስጠንቀቂያ
መስጠት አስፈላጊ የሚሆነዉ በዉሉ አንቀጽ 21.2/ሀ መሰረት ተጠሪ ዉሉን በራሱ አነሳሽነትና ምክንያት
የሚያቋርጥ ሲሆን ነዉ፡፡ ግንባታዉን ማጠናቀቂያ ጊዜ በዉሉ በግልጽ ስለተመለከተ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1775
መሰረት ተጠሪ ዉሉን ከማቋረጡ በፊት ለአመልካች ማስጠንቀቂያ ለመስጠት አይገደድም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 3 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች የ21 ጉድጓዶች ግንባታ ስለፈጸምኩ ብር 1,294,460.03 ይከፈለኝ በማለት የጠየቀ ቢሆንም በዉሉ
መሰረት ግንባታ መፈጸሙንና ለታለመለት ዓላማ የሚዉል መሆኑን አስመርምሮ ለተጠሪ ያላስረከበ
በመሆኑና በዉሉ አንቀጽ 59.3 መሰረት በአማካሪ መሀንዲሱ አስመርምሮ ይሕንን የሚያሳይ በማስረጃ
ባለማቅረቡ ይህንን ገንዘብ ተጠሪ ልከፍል አይገባም፡፡ተጠሪ ከአመልካች ክፍያ ላይ ብር 5,750,000.00
በቅጣት መልክ ቀንሶ ያስቀረዉ በዉሉ አንቀጽ 5 መሰረት አመልካች በዉሉ በተመለከተዉ ጊዜ ግንባታዉን
ባለማጠናቀቁ ምክንያት ግንባታዉ ለዘገየበት ጊዜ በዉሉ አንቀጽ 27 መሰረት የበሰለ ጉዳት ኪሳራ(liquidated
damage) በየቀኑ 0.1% የዉሉ ዋጋ 10% እስከሚሆን ድረስ ከተከፋይ ሂሳቡ ላይ ቆርጦ ለማስቀረት ዉሉ
በሚሰጠዉ መብት መሰረት የተፈጸመ በመሆኑ አለአግባብ ተቀንሶብኛል ሲል ያቀረበዉ ጥያቄ ዉድቅ ሊሆን
ይገባል፡፡አመልካች ግዴታዉን ሳይወጣ ሲቀር በዉሉ አንቀጽ 58 መሰረት ያስያዘዉ ዋስትና እንዲከፈለዉ
ተጠሪ ዋስትናዉን ለሰጠዉ ባንክ ጥያቄ አቅርቦ ገንዘቡን የመዉረስ መብት ስላለዉ ተጠሪ አንደዋና ተቋረጭ
ለፕሮጀክቱ ባለበት የግንባታ ሥራዉ ለዘገየበት በየቀኑ ብር 4,927,939.79 እየታሰበ ግንባታዉ ለዘገየባቸዉ
ቀናት በቅጣት መልክ እንዲከፍል አመልካች ምክንያት ስለሆነና ተጠሪ ክፍያ እንዲፈጸምለት ለባንክ ደብዳቤ
ስለጻፈ አመልካች ከዋስትና ጋር በተያያዘ ያቀረበዉ ጥያቄ ዉድቅ ሊሆን ይገባል፡፡ አመልካች ከጊዜ ጋር
ተያያዥነት ላላቸዉ ተጨማሪ ወጪ ተዳሪጌያለሁ ብሎ በዉሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ 18.6፣69.1 እና
74 መሰረት የሥራ ዉሉ የተቋረጠዉ ከአቅም በላይ ሁኔታ ወይም ሥራዉን ለማስቀጠል የማያስችል ሁኔታ
ገጥሞ አሠሪዉ ወይም ተጠሪ የሥራ ዉሉን ያቋረጠ እንደሆነ በመሆና በተያዘዉ ጉዳይ የሥራ ዉሉ
የተቋረጠዉ በዚህ አግባብ ካለመሆኑም በተጨማሪ አመልካች ያወጣዉ ወጪ ባለመኖሩና ለወጪ መዳረጉን
የሚያሳይ ማስረጃም ያላቀረበ በመሆኑ ከዚህ ጋር አያይዞ ብር 8,166,798.55 እንዲከፈለዉ ያቀረበዉ ጥያቄ
ዉድቅ ሊሆን ይገባል፡፡

እንዲሁም አመልካች ተጠሪ የግንባታ መሳሪያዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ አግቶ ስላቆየ ብር 59,136,000.00
እንዲከፈለኝ በማለት የጠየቐዉ ዳኝነት በአጠቃላይ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ መጠን ብር 80,181,307.57
ስላደረገዉ ይህም አመልካች ከዉሉ ዋጋ በላይ ዳኝነት እንደጠየቐ ስለሚያሳይና በዉሉ መሰረት ከዉሉ
ጠቅላላ ዋጋ በላይ ካሳ መጠየቅ ስለማይቻል ከዚህ አኳያ የጠየቐዉ ዉድቅ ሊሆን ይገባል፡፡ተያዙብኝ ያላቸዉ
ንብረቶች ንብረቶቹ እንደሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ተጠሪ አንዳች የአመልካች ንብረቶች
አልያዘም፡፡በጠቅላላ የዉሉ ሁኔታዎች አንቀጽ 23 እና በዉሉ ልዩ ሁኔታ አንቀጽ 64.2 መሰት ዉሉ በሥራ
ተቋራጩ ምክንያት ሲቋረጥ በግንባታ ቦታ ላይ ያሉ ሁሉም የግንባታ እቃዎች፣መሳሪያዎች እና ጊዜያዊ
የግንባታ ሥራዎች የተጠሪ(የአሰሪ) ንብረት እንደሚሆኑ ስለተደነገገ አመልካች ንብረቶቹን የማስመለስም ሆነ
አከራይቶ የሚያገኘዉን ጥቅም የመጠየቅ መብት የለዉም፡፡ እንዲሁም አመልካች ማሽኖቹን ወደ ግንባታ
ስፍራዉ ያመጣቸዉ ተከራይጦ ይሁን በሌላ መንገድ ስለመሆኑ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ለቆሙበት ጊዜ የከፈለዉ
ክፍያ ስለመኖሩ ያቀረበዉ የኪራይ ክፍያ ሰነድ የለም፡፡ሊከፈለዉ ይገባል እንኳን ቢባል መከፈል ያለበት ዉሉ
ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለዉ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ንብረቱን ተከታትሎ በወቅቱ በመሰብሰብ ጉዳት የመቀነስ
ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ በራሱ ጥፋት ጥያቄ ሳያቀርብ ለቀረበት ጊዜ ሁሉ ክሱን ከማቅረቡ በፊት ያለዉን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 4 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወደኋላ ሄዶ መጠየቁ ተገቢነት የለዉም፡፡እንዲሁም የጠየቀዉ ካሳ ተመጣጣኝ አይደለም በማለት ክሱ ዉድቅ


እንዲደረግለት በመጠየቅ ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 220306 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና በግራ ቀኙ የቀረቡለትንና ራሱ ያስቀረበዉን


ማስረጃዎች ሰምቶና መርምሮ በቀን 10/02/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ በግራ ቀኙ መካከል ለክሱ መነሻ
የሆነዉ የመገጭ ግድብ የዉሃ መቆጣጣሪያ ማማ የመሰረት ምሰሶ ጉድጓድ ቁፋሮ የግንባታ ሥራ ዉል
መፈራረማቸዉ፣የግንባተታዉ አጠቃላይ ዋጋ ከተ.እ.ታ ጋር ብር57,500,920.00 እንደሆነ፣ በጠቅላላ የዉል
ሁኔታዎች የተመለከቱትን የዉል ግዴታዎች ለመፈጸመ ግዴታ መግባታቸዉን እና ተጠሪ ለአመልካች
ቅድመ ክፍያ ብር 11,500,184.00 መክፈሉ በግራ ቀኙ የታመነ ነዉ፡፡ግራ ቀኙ የተካካዱበትን ጭብጦች
በመለየት በግራ ቀኙ መካከል ያለዉን የግንባታ ዉል ተጠሪ ያቋረጠዉ በአግባቡ ነዉ ወይስ አይደለም የሚል
ጭብጥ በተመለከተ አመልካች በአካባቢዉ በገጠመዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት
ሥራ መስራት ባለመቻለ ጊዜ መባከኑን ገልጬ የጊዜ ማራዘሚያ የጠየቅሁ ቢሆንም ተጠሪ መልስ በመንፈግ
ከሕግ ዉጭ የሥራ ዉል አቋርጧል በማለት የተከራከረዉን ተጠሪ ዉሉ የተቋረጠዉ በዉሉ የተመለከተዉ
ጊዜ ተጠናቆ አመልካች በጠየቀዉ መሰረት ተጨማሪ የ33 ቀን ጊዜ የተራዘመለት ቢሆንም አመልካች
የመሳሪያና የሰዉ ኃይል ችግር ስላለበት በራሱ ጉድለት የግንባታዉ ጊዜ በመጓተቱ ምክንያት የሥራ ዉል
በሕግ አግባብ የተቋረጠ ነዉ በማለት የተከራከረ ቢሆንም አመልካች አቅርቦ ባሰማቸዉ ምስክሮች ከቀን
19/11/2008ዓ/ም እስከ ህዳር 2009ዓ/ም ድረስ ክፕሮጀክቱ አካባቢ ጎሳን ለይቶ የማጥቃት ሁከትና ብጥብጥ
በአካባቢዉ እንደተከሰተ፣በተለይም አመልካችና ሠራተኞች የተጠሪ ሠራተኞች ወደሚገኙበት ወደመገጭ
ካምፕ እንዲገቡ በተጠሪ ባለመፈቀዱ ምክንያት ከሳይጡ ወጣ ብሎ በሚገኘዉ ጠዳ ከተማ ላይ አመልካች
ለሠራተኞቹ ተከራይቶ በነበረዉ ቦታ ላይ ከፍ ያለ ረብሻ ተፈጥሮ ንብረቱ ተዘርፎ ሠራተኞቹ ለነፍሳቸዉ
ሸሽተዉ ማምለጣቸዉን ከዚያም በኋላ ወደሥራ ተመልሰዉ ለመግባት የግርግር ጊዜ እስከሚያልፍ ሲጠበቅ
የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜዉ እንዳለፈ ይህም በዉሉም ሆነ በፍትሐ ብሔር ሕግ መሰረት ከአቅም በላይ የሆነ
ሁኔታ አመልካች እንደገጠመዉ አመልካች ከተጠሪ የተሻለ ማስረጃ በማቅረብ አስረድቷል፡፡

በሌላ በኩል አመልካች ላቀረብኩት የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄ ተጠሪ በ21 ቀን ዉስጥ መልስ አልሰጠኝም
በማለት የተከራከረ ቢሆንም አመልካች እ.ኤ.አ በቀን 18/11/2016ዓ/ም ላቀረበዉ ጥያቄ በአማካሪዉ በ5 ቀን
ዉስጥ በቀን 23/11/2016 ዓ/ም በተሰጠ መልስ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጠዉ እንደማይገባና በዉሉ በተመለከተዉ
ጊዜ እንዲያጠናቅቅ ተገልጾ መልስ ተሰጥቶታል፡፡ አመልካች እ.ኤ.አ በቀን 18/11/2016ዓ/ም ከአቅም በላይ
የሆኑ ሁኔታዎች እንደገጠሙት ገልጾ ለወደፊት የጊዜ ማራዘሚያ እንደሚጠይቅ አሳወቀ እንጂ የጊዜ
ማራዘሚያ ጥያቄ ከዝርዝር መግለጫ ጋር በዉሉ አንቀጽ 73/2 መሰረት አልጠየቀም፡፡አመልካች በአማካሪዉ
ዉሳኔ ቅሬታ ካለዉ በጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች(GCC) ወይም (FIDIC) ላይ በተመለከተዉ መሰረት ደረጃዉን
ጠብቆ ቅሬታ አላቀረበም፡፡ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አመልካች እ.ኤ.አ በቀን 12/12/2016 ጽፎ ለ102 ቀናት
የጊዜ ማራዘሚያዉ እንዲሰጠዉ በድጋሚ ያቀረበዉን ጥያቄ ተከትሎ ተጠሪ በቀን 08/05/2009ዓ/ም በተያዘ
ቃለ ጉባኤ ለአመልካች ጠቸማሪ ጊዜ የሠጠዉ ሲሆን ይህ ጊዜ በቂ አይደለም በማለት ይግባኝ ለሥራና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 5 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከተማ ልማት ሚኒስቴር ካለማቅረቡም በላይ በተሰጠዉ ጊዜ ግንባታዉን ለማከናወን የሥራ መርሀ-ግብር
አቅርቦ ወደ ሥራ የገባ ቢሆንም በታቀደዉ ማስረከቢያ ጊዜ ባለማጠናቀቁ ተጠሪ በቀን 15/12/2009ዓ/ም
ዉሉን ሊያቋርጥ ችሏል፡፡ከዚህም ፍርድ ቤቱ የተረዳዉ እስከ ቀን 08/05/2009ዓ/ም ድረስ ያለዉን ጊዜ
በተመለከተ በግራ ቀኙ በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት ለአመልካች የ33 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመሰጠቱ
መቋጫ አግኝቷል፡፡ ሆኖም አመልካች የተራዘመለትን ጊዜ ተጠቅሞ እስከ ቀን 16/08/2009ዓ/ም ድረስ
ሥራዉን ማጠናቀቅ ይቅርና የዉል ማቋረጫ ደብዳቤ ተጽፎ እስከተሰጠበት ቀን 15/12/2009ዓ/ም ድረስ ከ7
ወር በኋላም ቢሆን ሰርቶ አጠናቅቆ አላስረከበም፡፡ ተጠሪ ለአመልካች ከቀን 08/05/2009ዓ/ም በኋላ ዉሉን
ከማቋረጥ በፊት ከተከታታይ 6 ጊዜ ሲያስጠነቅቅ ቆይቶ በቀን 15/12/2009ዓ/ም ዉሉን ያቋረጠዉ አመልካች
የግንባታ ሥራዉን በማዘግየቱ ምክንያት በመሆኑ ተጠሪ ዉሉን በአንቀጽ 22(2/ሀ እና መ) መሰት በሕግ
አግባብ የተቋረጠ ነዉ ሲል ወስኗል፡፡

አመልካች በዉሉ 64 የዉሃ መቆጣጠሪያ ማማ የመሰረት ምሰሶ ለመስራት ተስማምቶ የግንባታ ዉሉ


ሲቋረጥ አመልካች 21 የዉሃ መቆጣሪያ ማማ የመሰረት ምሰሶ በዉሉ መሰረት መስራቱ በማስረጃ
እንደተረጋገጠ ገልጾ ለዚህ ሥራዉ ለቅድመ ክፍያ የተከፈለዉ ተቀንሶ ተ.እ.ታ ጨምሮ ቀሪ ብር
1,294,460.30 ተጠሪ ለአመልካች እንዲከፍል ወስኗል፡፡እንዲሁም ዉሉ በአመልካች ምክንያት ስለተቋረጠ
በዉላቸዉ አንቀጽ 19(2 እና 3) እና 27 መሰረት ዉሉ በጊዜዉ ባለመጠናቀቁ ለሚደርሰዉ ጉዳት ተጠሪ
ባልተሰራ ሥራ መጠን ልክ በየቀኑ የዉሉን ዋጋ 0.1% የዉሉ ዋጋ 10% እስከሚደርስ ድረስ ለአመልካች
ከሚከፈል ክፍያ ላይ የመቀነስ መብት አለዉ፡፡በዚህ መሰረት ተጠሪ ከአመልካች ሊቀንስ የሚገባዉ የጉዳት
ካሳ ብር 5,620,645.00 ነዉ በማለት ወስኗል፡፡

እንዲሁም ተጠሪ የግንባታ ዉሉን ሲያቋርጥ የአመልካችን የግንባታ መሳሪያዎች ከቀን 08/12/2009ዓ/ም
ጀምሮ ይህ ክስ እስከቀረበበት ጊዜ በኃይል አግቶ በመያዝ አመልካች በንብረቱ እንዳይገለገል በማድረጉ
ተገቢነት የሌለዉ ዉሳኔ በመሆኑ አመልካች በንብረቶቹ ባመለመገልገል ያጣዉን ጥቅም ብር 45,000,000.00
ተጠሪ ለአመልካች ሊከፍል ይገባል፡፡ሆኖም ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ተጠሪ ከአመልካች የሚፈለገዉ እዳ
ብር 5,620,645.00 ሲቀነስ ብር 39,379,355 ከተጠሪ የሚጠበቅ ሲሆን አመልካች ለሰራዉ ሥራ
ለአመልካች ሊከፈል ይገባል የተባለዉ ብር 1,294,460.30 ሲጨመር በድምሩ ብር 40,673,815.00 ከቀን
05/06/2010ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ተጠሪ ለአመልካች እንዲከፍልና የአመልካችን
መሳሪያዎች/ማሽነሪዎች እንዲሁም የቅድመ ክፍያ ዋስትና ለአመልካች ሊመለስለት ይገባል በማለት ሌሎች
አመልካች የጠየቃቸዉን ዳኝነት ጥያቄዎች ዉድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡

ተጠሪ በዉሳኔዉ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ችሎቱም
በመ/ቁጥር 187031 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 25/12/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ በግራ ቀኙ መካከል
በተፈጸመ ዉል መሰረት ዉሉ በአመልካች ምክንያት በዉሉ በተመለከተዉ ጊዜ ሳይጠናቀቅ በመቅረቱ ዉሉ
የተቋረጠ እንደሆነ ተጠሪ የአመልካችን መሳሪያዎች/ማሽነሪዎች በባለቤትነት ተረክቦ በዉሉ የተጠቀሰዉ ሥራ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 6 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አስኪጠናቀቅ እንዲጠቀምባቸዉ መብት ተሰጥቶታል፡፡በዚህ መሰረት ተጠሪ በዉሉ የተሰጠዉ መብት


ማሽኖቹን ሥራዉ እስኪያልቅ ለመጠቀም የይዞታ መብት እንጂ የባለቤትነት መብት አልተሰጠዉም በሚል
አመልካች ያቀረበዉ መከራከሪያ ተቀባይነት ያለዉ አይደለም፡፡ዉሉ በአመልካች ጥፋት መቋረጡ ተጠሪ
የማሽኖቹ ባለቤት እንዲሆን በዉሉ ግራ ቀኙ እንደተስማሙ የምንገነዘበዉ ጉዳይ ቢሆንም የተሰጠዉ
ባለቤትነት ግን ከዉሉ አጠቃላይ ዓላማ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ በዉሉ ለተጠቀሰዉ ሥራ ማጠናቀቂያ ሰፊ
መብት የሚሰጥ እንጂ በዉሉ የተጠቀሰዉ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚቀጥል አይደለም፡፡ስለሆነም
መሳሪያዎቹ/ማሽኖቹ የአመልካች በመሆናቸዉ በዉሉ መሰረት አመልካች ያላጠናቀቀዉን ሥራ ተጠሪ
በአመልካች ማሽኖች ተጠቅሞ የማጠናቀቅ እና ካጠናቀቀ በኋላ ማሽኖቹን ለአመልካች ሊመልስ ይገባል
በማለት የዉሉን ጠቅላላ ሁኔታ አንቀጽ 23.2፣21፣64.2/ሠ እና 83.3ን ጠቅሶ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ
አመልካች በማሽኖች ማግኘት እየቻልኩ ተጠሪ ማሽኖቹን በመያዙ ያጣሁት ነዉ ያለዉን ገቢ ተጠሪ
እንዲከፍል መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሮ አመልካች መክፈል ከሚገባዉ ቅጣት ከብር
5,620,645.00 ላይ አመልካች ለሰራዉ ሥራ የሚከፈለዉ ብር 1,294,460.30 ተቀንሶ አመልካች ብር
4,326,184.70 ለተጠሪ ሊከፍል ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ አሻሽሎ ወስኗል፡፡

አመልካች የኮንስትራክሽን ሥራ ዉሉ ሲቋረጥ ተጠሪ የአመልካችን ማሽኖች ባለማስረከቡ ማሽኖቹ ያለሥራ


በመቆማቸዉ አመልካች ያጣዉን ገቢ እንዲከፍልና ማሽኖቹን/መሳሪያዎቹን እንዲመልስ አመልካች የጠየቀዉን
ዳኝነት በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት የደረሰዉን ጉዳት አረጋግጦ በርትእ ብር 39,375,355.00 ተጠሪ
ለአመልካች እንዲከፍል የወሰነዉ ጉዳዩን ከጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች አንቀጽ 21.5፣83.1፣83.2፣83.3
እንዲሁም ከፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1205 አንጻር በመመርመር ተጠሪ ማሽኖቹን የመዉረስ መብት እንደሌለዉ
ጭምር በማረጋገጥ ስለሆነ ተገቢነት ያለዉ ነዉ፡፡ሆኖም ይግባኝ ሰሚዉ ችሎት ተጠሪ ዉሉ ከተቋረጠ ከ3
ዓመታት በኋላ ማሽኖቹን የመዉረስ መብት አለኝ በማለት አግቶ የያዛቸዉን ጊዜያት አመልካች በንብረቶቹ
ሳይገለገል የቆየበትን ጊዜያት ከግምት ዉስጥ ሳያስገባ አመልካች ያጣዉን ጥቅም ተጠሪ ሊከፍል አይገባም
በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ፡፡ይግባኝ ሰሚዉ ችሎት በፍርድ ሀተታዉ
ላይ ተጠሪ የአመልካችን ንብረቶች መያዝ የሚችለዉ አመልካች ያልጨረሳቸዉን ሥራዎች ለመጨረስ ብቻ
ነዉ በማለት የአመልካችን ክርክር የሚያጠናክር ምክንያት ከገለጸ በኋላ ከዚህ አግባብ ዉጭ ተጠሪ ማሽኖቹን
ከ3 ዓመት በላይ አግቶ ላቆየበት ጊዜ የታጣ ገቢ ሊከፍል አይገባም ማለቱ ዉሳኔዉ እርስ በእርስ የሚቃረንና
ሚዛናዊነት የጎደለዉ ነዉ፡፡የተሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ በአመልካች ንብረት ማብቂያ ለሌለዉ ጊዜ ይዞ እንዲቆይ
የሚያደርግና አግቶ ያቆየዉን ጊዜ ከግምት ያላስገባና በአመልካች ላይ የደረሰዉንና እየደረሰ ያለዉን ጉዳት
ያላገናዘበ በመሆኑ ሕግንና ሞራልን የሚቃረን ስለሆነ አመልካች ያጣዉን ገቢ ተጠሪ እንዲከፍል የተወሰነዉ
አለአግባብ ስለተሻረ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ይጽናልኝ በማለት አቤቱታዉን አቅርቧል፡፡

ሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታዉን መርምሮ ተጠሪ የግንባታ ሥራ በዉሉ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ
ባለመጠናቀቁ የቀረዉን ሥራ ሠርቶ እስከሚጨርስ ድረስ የግንባታ ሥራ መሳሪያዎችን እንዲይዙና ሥራዉ
ሲጠናቀቅ እንዲመልስ ዉላቸዉ መሰረት ተደርጎ ሲወሰን በዉሉ ላይ ሥራዉን የሚጨርሱበት ጊዜ በዉላቸዉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 7 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ባይቀመጥም ከጠቅላላ ዉል ይዘት መሰረት ተጠሪ ባለበት እንዲመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን
01/06/2013ዓ/ም የተጻፈ የሚከተለዉን መልስ አቅርቧል፡፡

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በነበረዉ ክርክር ተጠሪ ማሽኖቹን ሊያዝ የሚገባበትን ጊዜ በተመለከተ ያደረገዉ
ክርክር የለም፡፡ ስለሆነም ተጠሪ ማሽኖቹን ማብቂያ ለሌለዉ ጊዜ እንዲጠቀምባቸዉ መወሰኑ ተገቢ አይደለም
በማለት ያቀረበዉ መከራከሪያ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 329/1 መሰረት ተቀባይነት የለዉም፡፡ ይግባኝ ሰሚዉ
ችሎት በዉሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ 23.2 እና 83.3 እንደዚሁም የዉሉ ልዩ ሁኔታ አንቀጽ 64.2/ሠ
ላይ ዉሉ በሥራ ተቋራጭ/አመልካች ጥፋት ከተቋረጠ ተጠሪ የአመልካች ጥፋት ከተቋረጠ ተጠሪ
የአመልካችን ማሽኖች አመልካች የጀመረዉ ሥራ እስኪጠናቀቅ ድረስ መጠቀም ይችላል የሚል በመሆኑ
ዉሳኔዉ የተጠሪን ከዉል የመነጨ መብት መሰረት ያደረገ ዉሳኔ ነዉ፡፡እንዲሁም በዉሉ አንቀጽ 23.2
በግልጽ እንደተመለከተዉ ዉሉ በአመልካች ምክንያት ከተቋረጠ በግንባታ ቦታ ላይ ያሉ ማሽኖቹን ተጠሪ
የመዉሰድ መብት እንጂ ተጠቅሞ የመመለስ በመሆኑ አመልካች ጀምሮ የነበረዉ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላም
ቢሆን ተጠሪ የመመለስ ግዴታ የለበትም፡፡በግራ ቀኙ ዉል ጠቅላላ ሁኔታዎች አንቀጽ 83/3 ላይ ዉሉ በስር
ተቋራጩ(አመልካች) ምክንያት የተቋረጠ እንደሆነ አሠሪዉ(ተጠሪ) ንብረቱን ሥራዉ እስኪጠናቀቅ ድረስ
ለመጠቀም እንደሚችል ይጠቀሳል፡፡ስለሆነም ተጠሪ ማሽኖቹን የመዉረስ ከዉል የመነጨ መብት እያለዉ
ይህንን መብት ባለመቀበል ሥራዉ እስኪጠናቀቅ ድረስ የመጠቀም መብት አለዉ ብሎ መወሰኑ ተጠሪን
የሚጎዳ ዉሳኔ በመሆኑ ተጠሪ ለአመልካች የሚከፍለዉ የጉዳት ካሳ የለም ተብሎ በመወሰኑ የተፈጸመ
ስህተት የለም፡፡በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔም አመልካች እንዳለዉ እርስ በእርሱ የሚጣረስ
አይደለም፡፡ዉሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ የአመልካች ማሽኖች ተጠሪ የግንባታ ሥራዉን በሚያሰራበት ቦታ
ላይ ያሉ ቢሆንም የማሽኖቹ ቁልፍ አመልካች እጅ ስለሚገኙና ተጠሪ ቁልፎቹ እንዲሰጠዉ በተደጋጋሚ
ተጠይቆ ባለማስረከቡ ማሽኖቹ ላለፉት ሶስት አመታት ማሽኖቹ በተጠሪ ተይዘዋል ቢልም ተጠሪ
ተጠቅሞባቸዉ ስለማያዉቅ እስካሁን ተጠሪ በማሽኖቹ እየተገለገለ እንደሚገኝ አድርገዉ ያቀረበዉ ተቀባይነት
ያለዉ አይደለም፡፡በዚህ ምክንያት በማሽኖቹ አልተጠቀምንም እንጂ ብንጠቀም እንኳን ለአመልካች
የምንከፍለዉ ክፍያ አይኖርም፡፡ስለሆነም ተጠሪ ማሽኖቹንን እንዲወርስ ዉሳኔዉ ሊሻሻል ይገባል እንጂ
ለአመልካች ካሳ የሚከፈልበት የሕግ መሰረት የለም ተብሎ ዉድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም
የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘዉን ማስቀረቢያ ነጥብ ከግምት በማስገባት በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ
የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ
መርምረናል፡፡

እንደተመረመረዉም ለግራ ቀኙ ክርክር መነሻ የሆነዉ ተጠሪ አመልካችን የመገጭ ግድብ የዉሃ መቆጣጠሪያ
ማማ የመሰረት ምሰሶ ጉድጓድ ቁፋሮ የግንባታ ሥራ ለማሰራት በቀን 10/05/2008 ዓ/ም ወይም እ.ኤ.አ
ጃንዋሪ 19 ቀን 2016 ዓ/ም የተፈራረሙት ዉል ነዉ፡፡የግንባታዉ አጠቃላይ ዋጋ ከተ.እ.ታ ጋር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 8 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ብር57,500,920.00 እንደሆነ፣ ግንባታዉን በ360 ቀናት ዉስጥ ለማጠናቀቅና በጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች
የተመለከቱትን የዉል ግዴታዎች ለመፈጸም ግዴታ መግባታቸዉ በግራ ቀኙ የታመነ ነዉ፡፡እንዲሁም በዉሉ
መሰረት ተጠሪ ለአመልካች ቅድመ ክፍያ ብር 11,500,184.00 በቀን 24/06/2008ዓ/ም መክፈሉ፣አመልካች
ቅድመ ክፍያ ከተከፈለዉ ቀን ጀምሮ በ20 ቀን ዉስጥ ግንባታ ለመጀመር የዉል ግዴታ መግባቱን፣አመልካች
ግንባታ በሚፈጽምበት አካባቢ በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠዉ ጠይቆ ከአቅም
በላይ የሆነ ሁኔታ እንደገጠመዉ ተረጋግጦ በተጠሪ የ33 ቀናት ጊዜ ተጨምሮለት ግንባታ መፈጸሚያ ጊዜ
ተራዝሞለት አመልካች ወደ ሥራ እንደገባ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡ በተራዘመዉ ጊዜ
አመልካች የሉበትን የሰዉ ኃይልና የማሽነሪ(ግንባታ የመፈጸም አቅም)ችግር መቅረፍ ባለመቻሉ ተጠሪ
በዉልና በሕግ አግባብ ዉሉን መቋረጡ፤ዉሉ በተቋረጠበት ጊዜ በዉሉ መሰረት አመልካች መገንባት
ከሚጠበቅበት 64 የዉሃ መቆጣጠሪያ ማማ የመሰረት ምሰሶ ጉድጓድ ዉስጥ 21 ብቻ እንደሰራ በግራ ቀኙ
የታመነና በስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸዉ፡፡እንዲሁም ዉሉ በሚቋረጥበት ጊዜ
ግንባታ በሚፈጸምበት ቦታ የአመልካች ንብረት የሆኑ የግንባታ መሳሪያዎች/ማሽነሪዎች በግንባታ ቦታ
በተጠሪ ይዞታ ሥር እንደቀሩም የተረጋገጡ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡ግራ ቀኙን ያከራከረዉና የዚህን ችሎት ምላሽ
የሚሻዉ ጭብጥ ዉሉ ሲቋረጥ በግንባታ ቦታ የነበሩትን የአመልካችን መሣሪያዎች/ማሽኖች ቀሪ የግንባታ
ሥራ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተጠሪ ተጠቅሞባቸዉ ግንባታዉን የማጠናቀቅ መብት አለዉ ተብሎ መወሰኑ እና
ግንባታዊ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለሚኖረዉ ጊዜ አመልካች በማሽኖች ማግኘት እችል የነበረዉንና ያጣሁትን
ገቢ ተጠሪ ሊከፍለኝ ይገባል በማለት ጠይቆ በከፍተኛ ፍርድ ቤት የተወሰነለትን ይግባኝ ሰሚዉ ችሎት
ዉደቅ በማደረጉ የተፈጸመ በዚህ ችሎት ደረጃ ሊታረም የሚችል ስህተት መኖር አለመኖሩን የሚመለከት
ነዉ፡፡

በኮንስትራክሽን ሕግጋትና በልማድ የዳብረዉና ተቀባይነት አግኝቶ ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች ወይም የሲቪል
ሥራዎች ኮንስትራክሽን ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች (Standard conditions of contract for Construction of civil
works) በሚል በሚታወቁ ደንቦች ላይ የሚታወቁ የኮንስትራክሽን ሥራ በዉሉ ላይ ተወስኖ በተቀመጠዉ
የግንባታ ሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ዉስጥ እንዳያልቅ ወይም ግንባታዉ ሳይጠናቀቅ እንዲዘገይ የሚያደርጉ
የተለያዩ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን እነዚህም በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ እንደተመለከተዉ በአራት የኃላፊነት
ገጽታዎችና ኃላፊነት በሚያስከትሉ ሁኔታዎች(risk) ምንጮች ላይ በመመስረት የሚታወቁ ናቸዉ፡፡እነዚህም
አንደኛ ሙሉ በሙሉ አሰሪዉን በሚመለከቱ ምክንያቶች ወይም ሁኔታዎች(employer's risk event) የሚከሰት፣
ሁለተኛዉ ሙሉ በሙሉ ሥራ ተቋራጩን(ንኡስ ተቋራጩን ይጨምራል) በሚመለከቱ ሁኔታዎች
(contractor's risk event) የሚከሰት፣ሶስተኛዉ አሰሪዉን፣ ሥራ ተቋራጩንና አማካሪ መሀንዲሱን በሚመለከቱ
ሁኔታዎች (concurrent risk event/Common risk) የሚከሰት ሲሆን አራተኛዉ ደግሞ በግንባታ ዉሉ ተሳታፊ
የሆኑ ወገኖችን በማይመለከት እና ከእነዚህ አካላት ቁጥጥር ዉጭ በሆኑ ሁኔታዎች(special risk event)
የሚከሰት በሚል የሚገለጹ ናቸዉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 9 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ግራ ቀኙ በተፈራረሙት ዉል አንቀጽ 23.2 እና በዉሉ ልዩ ሁኔታ አንቀጽ 64.2/ሠ እና አንቀጽ 83.3 ስር


ዉሉ የተቋረጠዉ በሥራ ተቋራጩ ጥፋት ከሆነ ሁሉም የግንባታ ቁሶች፣መሳሪያዎች፣ጊዜያዊ የግንባታ
ሥራዎች እና የግንባታ ሥራዎች የአሠሪዉ እንደሚሆኑ ተደንግጓል፡፡ በሌላ በኩል የዉላቸዉ አካል ባደረጉት
የሲቪል ሥራዎች ኮንስትራክሽን ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች (Standard conditions of contract for Construction
of civil works)ላይ አንቀጽ 63(1/ሠ) ስር ባለዉ የመጨረሻ ፓራግራፍ ላይ የሥራ ተቋራጭ የዉል
ግዴታዉን አለመወጣት (Default of contractor) ወይም በሥራ ተቋራጩ ጥፋት ዉሉ በሚቋረጥበት ጊዜ
የሚያስከትለዉን ዉጤት በተመለከተ እንደተደነገገዉ ደግሞ አሠሪዉ ከግንባታ ቦታ ሥራ ተቋራጩን
በማሰናበት ለግንባታ ሥራዉ ተብለዉ በግንባታ ቦታዉ ገብተዉ የሚገኙ መሳሪያዎችንና ማሽኖችን
(construction plant)፣ ጊዜያዊ ግንባታዎችንና ቁሶችን የግንባታ ሥራዉን ለማጠናቀቅ የመጠቀም መብት
እንዳለዉና ተገቢ ነዉ ብሎ ሲወስን ከሥራ ተቋራጩ ለሚፈልገዉ ከዉሉ ለመነጨ የበሰለ እዳ እነዚሁኑ
ንብረቶች በመሸጥ ገንዘቡን ማስመለስ(ለዕዳዉ ማካካሻ ማድረግ) እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ በዚህ አግባብ ግራ
ቀኙ በተፈራረሙትና በዉሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች ላይ የተመለከተዉ ሀሳብ በአንድ በኩል ዉሉ የተቋረጠዉ
በሥራ ተቋራጩ ምክንያት(ጥፋት) የተነሳ እንደሆነ በግንባታ ቦታ ላይ ያሉ ንብረቶች ላይ አሠሪዉ
የባለቤትነት መብት እንዲያገኝ በሚያደርግ መልኩ የተቀረጸ ሲሆን በሌላ በኩል በግንባታ ቦታዉ ላይ ባሉት
በስራ ተቋራጩ ንብረቶች እና/ወይም በጊዜያዊነት በሥራ ተቋራጩ በተሰሩ ግንባታዎች አሠሪዉ
ተገልግሎባቸዉ የቀረዉን ሥራ ያጠናቅቃል በሚል በንብረቶቹ የመገልገል መብት አሰሪዉ እንዲኖረዉ
በሚያደርግ መልኩ በሚጣረስ አኳኋን የተደነገገ ነዉ፡፡በአንድ ዉል ላይ ባሉ የዉል ቃላት (Provisions)
መካከል በዚህ መልኩ አለመጣጣም ሲኖር በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1732 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ
የተመለከተዉን የዉል አተረጓጎም መርሆዎች ተከትሎ በመተርጎም ተፈጻሚነት ያለዉን የዉሉን ሀሳብ
መለየት ይገባል፡፡

በፍ/ብሕግ ቁጥር 1734 ስር እንደተደነገገዉ የዉሉ ቃል(the provision of contract)የሚያሻማ በሆነ ጊዜ


ተዋዋዮቹ ዉላቸዉን ከመዋዋላቸዉ አስቀድሞ ወይም ከተዋዋሉ በኋላ የነበሩበትን ሁኔታ በማመዛዘን
የተዋዋዮቹ ሐሳብ ምን እንደነበር በመፈለግ አሻሚ ለሆነዉ የዉል ቃል ትርጉም መስጠት ይገባል፡፡እንዲሁም
በዚሁ ሕግ በቁጥር 1732 ስር ደግሞ ዉሎች የቅንነት፣የመተማመንን ግንኙነት መሰረት በማድረግና
በጉዳዮቹ ዉስጥ ያለዉን ልማዳዊ ሥርዓት በመከተል በቅን ልቦና ሊተረጎሙ እንደሚገባም ተመልክቷል፡፡

በያዝነዉ ጉዳይ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገዉ ዉል ጉዳይ(object) በዉሉ የተመለከተዉን ግንባታ በዉሉ
በተመለከተዉ አግባብና ጊዜ አመልካች እንዲገነባ ግዴታ የሚጥል ተጠሪ ደግሞ የዉሉን ዋጋ ለአመልካች
መክፈልና በዉሉ የዉሉን ጉዳይ ለመፈጸም የተቀመጡ ሌሎች ተግባራትን መወጣት ነዉ፡፡ከጠቅላላ የዉል
ሁኔታዎችና ደንቦች፣ በኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ ከዳበሩ ልማዶች መገንዘብ እንደሚቻለዉ አመልካች በዚህ
ዉል የተመለከተዉን ግዴታዉን በዉሉ በተመለከተዉ ጊዜ ወይም በስምምነት በተራዘመዉ ጊዜ ሠርቶ
በማጠናቀቅ ባያስረክብ ተጠሪ እንደ ዋና ተቋራጭ የሚኖረዉ መብት ግንባታዉ ለዘገየበት ጊዜ በዉሉ
አስቀድሞ የተወሰነ ኪሳራ(liquidated damage) ማስከፈል፤ እንደነገሩ ሁኔታ በዉላቸዉና በሕግ አግባብ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 10 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ግንባታዉ በጊዜ ባለመጠናቀቁ ምክንያት የሚደርስበትን ሌላ ወጪ ወይም የተረጋገጠ ኪሳራ(actual damage)


ማስከፈል እና/ወይም በግንባታ ቦታ ላይ ባሉት የሥራ ተቋራጩ ንብረቶች በመጠቀም ቀሪዉን የግንባታ
ሥራ በሌላ ተቋራጭ አሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚያስችል በዉል ባገኘዉ መብት መሰረት በራሱ ተግባራዊ
ማድረግ ወይም በፍርድ ቤት በአመልካች ላይ እንዲወሰንለት መጠየቅ ነዉ፡፡ ይህም የሚያሳየዉ የዉሉ
ጉዳይም ሆነ የሥራ ተቋራጩ የዉል ግዴታ ያለመወጣት ወይም በተቋራጩ መዘግየት ምክንያት ዉሉ
በተቋረጠ ጊዜ የሚከተለዉ ዉጤት የተቋራጩን የንብረት ባለቤትነት መብት ወደ አሠሪ ወይም ወደ ዋና
ሥራ ተቋራጭ ማስተላለፍ እንዳልሆነ ነዉ፡፡ከዚህ የምንገነዘበዉ ግራ ቀኙ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት
በተፈራረሙት ዉል ላይም ሆነ የዉላቸዉ አካል ባደረጉት ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች የተደነገገዉን
የተስማሙት በአመልካች ጥፋት ዉሉ ሲቋረጥ በግንባታ ቦታ ላይ የነበሩትን ንብረቶች ባለቤትነት መብት
ለተጠሪ ለማስተላለፍ በማሰብ ሳይሆን በአመልካች ምክንያት ዉሉ በመቋረጡ ተጠሪ ቀሪዉን ሥራ በራሱ
ሰርቶ ለማጠናቀቅ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ አሊያም ሌላ የሥራ ተቋራጭ አስገብቶ ለማጠናቀቅ በሚያደርገዉ
እንቅስቃሴ ለሥራዉ አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎችን/ማሽኖችን እየፈለገ እና ዋናዉን ግንባታ ለማከናወን
የሚያስፈልጉ ጊዜያዊ ግንባታዎችን በመገንባት ተጨማሪ ጊዜ እንዳያባክን እና በአመልካች ጥፋት ለተጨማሪ
ወጪ እንዳይዳረግ ለማድረግ፤ እንዲሁም ከሥራ ተቋራጩ የሚፈልገዉ ገንዘብ ካለም እነዚሁኑ የተቋራጩን
ንብረቶች እንደመያዣ (lien right) በመጠቀም ማስከፈል እንዲችል መብት ለመስጠት ነዉ፡፡ስለሆነም ይግባኝ
ሰሚዉ ፍርድ ቤት ዉሉ በተቋረጠበት ጊዜ በግንባታ ቦታ የሚገኙትን መሳሪያዎችን/ማሽኖችን ቀሪ ግንባታ
እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተጠሪ ይዞ የመገልገል መብት አለዉ በማለት ለዉሉ የሰጠዉ ትርጉም የተዋዋዮችን
ሀሳብና የዘርፉን ልማድ ከግምት ያስገባ በመሆኑ ከዚህ አንጻር የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም፡፡

እንዲሁም ተጠሪ ይህንን መብት ያገኘዉ ዉሉ አመልካች ኃላፊ በሆነበት ጥፋት(ጉድለት) ምክንያት
በመቋረጡ ስለሆነ ተጠሪ ዉሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ቀሪዉ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አመልካች
በማሽኖቹ/በመሳሪያዎቹ ማግኘት የሚችለዉን ገቢ ለመተካት የሚገደድበት የዉልም ሆነ የሕግ መሰረት
የለም፡፡ምክንያቱም ከላይ በተመለከተዉ መሰረት ተጠሪ በመሳሪያዎቹ/በማሽኖቹ የመገልገል መብት አለዉ
የሚለዉ የዉሉ ጠቅላላ ሁኔታ ዉጤት የሚኖረዉ ተጠሪ በመሳሪያዎቹ/በማሽኖቹ ያለክፍያ መገልገል ሲችል
ነዉ፡፡ተጠሪ ለመሳሪያዎቹ ክፍያ እየፈጸመ እንዲገለገል በዉሉ ታስቦ የነበረ ቢሆን ኖሮ መሳሪያዎቹ/ማሽኖቹ
በተጠሪ እጅ በሚቆዩበት ጊዜ ተጠሪ ስለሚከፍለዉ ክፍያ አመላካች ድንጋጌ ያስቀምጡ ነበር፡፡በዚህ መልኩ
በዉሉ ተጠሪ በመሳሪያዎቹ/በማሽኖቹ በሚገለገልበት ጊዜ ለአመልካች ስለሚከፍለዉ ክፍያ የሚገልጽ የዉል
ቃል አለን በማለት ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር የለም፡፡በዚህ አግባብ በዉሉ ያልተመለከተዉ ዉሉ በአመልካች
ጥፋት በተቋረጠበት ሁኔታ እንዲህ አይነት የሁለቱን ግንኙነት የሚያስቀጥል ሀሳብ በዉሉ ለማኖር ሀሳብ
ነበራቸዉ ለማለት የሚያስችል አሳማኝ አመክኒዮ ባለመኖሩና በአመልካች ላይ እንዲህ አይነት ኃላፊነት
የመጣበት ዉሉ በሱ ጥፋት በመቋረጡ ምክንያት ስለሆነ ነዉ፡፡

ስለሆነም ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ተጠሪ በዉሉ መሰረት በግንባታ ቦታ በሚገኙት የአመልካች
መሳሪያዎች እና/ ወይም ማሽኖች ቀሪዉ ግንባታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የመገልገል መብት ስላለዉ አመልካች

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 11 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመሳሪያዎቹ እና/ ወይም በማሽኖቹ ማግኘት እችል የነበረዉን ገቢ አጣሁኝ በማለት እንዲከፈለዉ የጠየቀዉን
ተጠሪ ሊከፍል አይገባም በማለት የስር ፍርድ ቤት ከዚህ አኳያ የወሰነዉን በመሻር የሰጠዉ ዉሳኔ ዉሉንና
ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም፡፡ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የእነዚህ
መሳሪያዎች እና/ ወይም ማሽኖች ባለቤትነት መብት የአመልካች በመሆኑ ቀሪዉ የግንባታ ሥራ በተጠሪ
ምክንያት ወይም በአሰሪዉ ዉሳኔ ወይም በሌላ ምክንያት እንዲቀር ከተደረገ(ከተተወ) አመልካች በስር ፍርድ
ቤት ባቀረበዉ ክስ ላይ ዘርዝሮ ያቀረባቸዉ መሳሪያዎች እና/ ወይም ማሽኖች እንዲመለሱለት ከመጠየቅ ይህ
ዉሳኔ የሚያግደዉ አይደለም ብለናል፡፡ በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል፡፡

ው ሳ ኔ

1. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 187031 ላይ በቀን 25/12/2012ዓ/ም


የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት የወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

1. በዉሳኔዉ መሰረት እንዲፈጽም የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ለግራ ቀኙም


ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 12 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ ማኅበር -

ተጠሪ ፡-የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ተጠሪ በቀን 01/06/2013 ዓ/ም ጽፎ ያቀረበዉን መስቀለኛ የሰበር አቤቱታ መርምረን የሚከተለዉን ትእዛዝ
ሰጥተናል፡፡

ት እ ዛ ዝ

የተጠሪ መስቀለኛ አቤቱታ ዉሉ ሲቋረጥ በግንባታ ቦታ የነበሩትን የአመልካችን መሳሪያዎች/ማሽነሪዎች


በዉሉ መሰረት እንዲወርስ አለመወሰኑ መሰሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ የሚል ነዉ፡፡ ጉዳዩን
እንደመረመርነዉ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገዉ የኮንስትራክሽን ሥራ ዉል ተጠሪ ቀሪዉን ሥራ
በመሳሪያዎቹ/በማሽኖቹ እየተገለገለ እንዲያጠናቅቅ መብት የሚሰጠዉ እንጂ በመሳሪያዎቹ/በማሽኖቹ ላይ
የባለቤትን መብት የሚሰጠዉ ባለመሆኑ ከዚህ አንጻር ይግባኝ ሰሚዉ ችሎት በመ/ቁጥር 187031 ላይ በቀን
25/12/2012ዓ/ም እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 220306 በቀን 10/02/2012 ዓ/ም የሰጡት
ዉሳኔ ጉድለት ስለሌለባቸዉ አቤቱታዉን ሰርዘናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 13 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

?? /? /? ? ? 196346
? ? 26/11/2013 ? /?
ዳኞች ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች - አቶ በፍቃዱ ጌታቸው፣- ጠበቃ ከፋለኝ ደጉ ቀረቡ


ተጠሪ - 1. አቶ ዮናስ ጌታነህ 2. ወ/ሮ ብዙነሽ ጌታነህ 3. አቶ ተስፋዬ ጌታነህ
4. ወ/ሮ ሸዋዬ ጌታነህ 5. ወ/ሮ ዘነበች ጌታነህ 6. ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ጌታነህ
7. አቶ በየነ ደረሰ 8. አቶ አዲሱ ጌታነህ ፡- ተወካይ ዘነበች ጌታነህ ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መስከረም 22 ቀን
2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 182644
ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት
የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት
በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ ያከራከረን ቤት በእናቴ ስም
የተመዘገበ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ጣልቃ ገብዎች ቤቶቹን ሰራን የሚሉት 1ኛ ጣ/ገብ አያቴ
ሞግዚቴ ሆኖ ባለበት ጊዜ መሆኑ እየታወቀ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
ያላደረኩትን እርቅ መሰረት አደርጎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ
ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡

በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን
የአሁን አመልካች ባቀረበው አቤቱታ እናቴ ወ/ሮ ዓለምነሽ ጌታነህ በ1989 ዓ/ም ሞታለች፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወራሽነቴን በ2009 ዓ/ም አረጋግጫለሁ፡፡ እናቴ በህይወት እያለች ያፈራችው ንብረት በን/ስልክ
ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ውስጥ ያለ የቤት ቁጥር 1711 የሆነው ቤት የእናቴ ውርስ ሀብት ስለሆነና
አጣርቼ ያቀረብኩት በመሆኑ እንዲጸድቅልኝ ሲል ጠይቋል፡፡ ጣልቃ ገብዎች 1. አቶ ጌትነት
አበበ፣ 2. አቶ ዮናስ ጌትነት፣ 3. ብዙነሽ ጌታነህ፣ 4. አቶ ተስፋዬ ጌታነህ 5. ሸዋዬ ጌታነህ 6.
ዘነበች ጌታነህ 7. ሙሉብርሃን ጌታነህ 8. ፈቴን በየነ 9. አቶ አዲሱ ጌታነህ ባቀረቡት አቤቱታ
ቤቱ በሟች ወ/ሮ ዓለምነሽ ጌታነህ ስም ይመዝገብ እንጂ ቦታው ላይ ያሉት ቤቶች በጣልቃ
ገብዎች የተሰሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም አቤቱታው ውድቅ ይሁንልን በሚል ተከራክረዋል፡፡
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ቁጥር 124770 ታህሳስ 1 ቀን 2011 ዓ/ም
በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ያከራከረው የቤት ቁጥር 1171 የሆነው ቤት ቦታው በአመልካች
እናት ስም የተመዘገበ መሆኑን በቀረበው የሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ ቢሆንም በቦታው ላይ ጣልቃ
ገብዎች ቤት የሰሩበትና ሲኖሩበት የነበሩ መሆኑን፣ ቤቱን ሲሰሩ የተቃወማቸው የሌለ መሆኑ
በመረጋገጡና አመልካችም ያላስተባበለው በመሆኑ፣ የንብረት ባለቤት ነኝ የሚል በሀብቱ በገንዘቡ
በዕውቀቱ ያፈራው ንብረት መሆኑን ማረጋገጥ የሚገባውና ይህንንም አመልካች ባለማረጋገጡ
የውርስ ንብረት ነው ለማለት የሚቻል አይደለም ሲል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ
ወስኗል፡፡ የአሁን አመልካች ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ አከራክሮ
በመ/ቁጥር 222293 ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ያከራከረው የቤት
ቁጥር 1171 የሆነው ቤት በአመልካች እናት ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በመሆኑና እናቱ ስትሞት
1ኛ ጣልቃ ገብ አያቱ የአመልካች ሞግዚት መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ፣ 1ኛ ጣልቃ ገብ
የአመልካች ሞግዚት ሆኖ ሀብቱንም ጭምር ሲያስተዳድር ባለበት ጊዜ ከ2ኛ እስከ 9ኛ ያሉት
ጣልቃ ገብዎች በቦታው ላይ ቤት በመስራታቸው የተቃወማቸው የለም ሊባል የሚችል
አይደለም፡፡ በመሆኑም ቤቱ የውርስ ንብረት ነው፡፡ ጣልቃ ገብዎች ሰራን ለሚሉት ቤት ግምቱን
መጠየቅ ይችላሉ ሲል የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር ወስኗል፡፡ ጣልቃ
ገብዎች ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው አከራክሮ በመ/ቁጥር 182644 ሰኔ
12 ቅን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ያከራከረው የቤት ቁጥር 1171 የሆነው ቤት
በአመልካች እናት ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቢሆንም ይዞታውን ያገኙት 1ኛ ጣልቃ ገብ አባቷ
ናቸው፡፡ በጊዜው አባቷ 1ኛ ጣልቃ ገብ ሌላ ቤት ስለነበረው በአመልካች እናት (በልጁ) ስም
ያስመዘገበ መሆኑና በይዞታው ላይ ቤቶች የተሰሩትም በጣልቃ ገብዎች መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
እንዲሁም ግራ ቀኙ በ30/8/2002 ዓ/ም በሽማግሌዎች ባደረጉት እርቅ ይህንኑ ፍሬ ነገር በማስፈር
ጣልቃ ገብዎች የሰሩት ቤት የራሳቸው ሆኖ አመልካች የሰራውን 9*16 = 144 ካ/ሜ ይዞታ
እንዲወስድ የተስማሙ መሆኑንም ያሳያል፡፡ ይሁንና አመልካች የእርቁ የመጀመሪያ ገጽ ላይ
አልፈረምኩም፣ ሽማግሌዎች በመጨረሻው ገጽ ላይ አልፈረሙም ከሚል ክርክር ውጪ እርቁን
አላደረኩም የሚል ክርክር የለውም፡፡ በዚሁ እርቅ መሰረት መፈጸም ሲገባ የከፍተኛው ፍ/ቤት
የሞግዚትነቱን ሁኔታ ብቻ በማየት የሰጠው ውሳኔ ስህተት ነው ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት
ውሳኔ ሽሮ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናት ወስኗል፡፡

የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል፡፡ መዝገቡም ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤትና ይዞታ በአሁኑ አመልካች እናት ስም ተመዝግቦ እያለ የውርስ
ሃብት አይደለም ተብሎ ለተጠሪዎች የተወሰነበትን አግባብ ለመመርመር ሲባል ቀርቧል፡፡
መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል፡፡ ተጠሪዎች ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ
የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዳልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልን ሲሉ
ተከራክሯል፡፡ አመልካችም የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን
በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና


የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ
ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር
ግራ ቀኙን ያከራከረው ቤት በአሁን አመልካች እናት ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን፣ ቤቱ
በአሁን አመልካች እናት ስም የተመዘገበው በተለያየ ምክንያት ከቦታቸው ለተነሱ ነዋሪዎች
መንግስት ምትክ ቦታ ሲሰጣቸው ለስር ፍ/ቤት 1ኛ ጣልቃ ገብ የተሰጠና 1ኛ ጣልቃ ገብ ሌላ
ቤት ስለነበረውና በወቅቱ ለከተማው ነዋሪ ሁለት ቤት ስለማይፈቀድ በልጁ በአሁን አመልካች
እናት ስም ያስመዘገበ መሆኑን፣ እንዲሁም በይዞታው ላይ ያሉት ቤቶች በጣልቃ ገብዎች የተሰሩ
መሆኑንም ማስረጃ የመስማትና የመመዘን ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት አረጋግጦ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የአሁን አመልካች አቤቱታ ቅሬታ ያከራከረው ቤት የውርስ ንብረት መሆኑ በቀረቡት ማስረጃ
ተረጋግጦ እያለ አቤቱታዬ ውድቅ መሆኑ ተገቢ አይደለም የሚል የፍሬ ነገርና የማስረጃ ምዘና
ጉዳይ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10(1) መሰረት
ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከተሰጠው ስልጣን ውጭ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ
የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም፡፡ በዚሁ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት
ይግባኝ ሰሚው ችሎት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
አልተገኘም፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 182644 ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ/ም


በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል፡፡
4. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የመ.ቁ.196871

ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡ አቶ ሀብታሙ ዝናቡ ፡- ቀርበዋል

ተጠሪ፡ አቶ ታሪኩ አየለ ፡- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር
አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁ/333779 ላይ ጥቅምት 03/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔን
በማፅናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለማስለወጥ ነው፡፡

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ ሐምሌ 05/2011 ዓ.ም ፅፈው በአሁን አመልካች ላይ በጅማ
ወረዳ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ ፍሬ ቃሉም ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር ውስጥ
የተጠቀሰውን 200 ካሬ ሜትር የከተማ ይዞታ ነሐሴ 06/2011 ዓ.ም ተሰጥቷቸው አስፈላጊውን
ክፍያ ፈፅመው እና የግንባታ ፈቃድ አውጥተው በቦታው ላይ ግንባታ ለማከናወን ሲሄዱ
ባላወቁት መንገድ የአሁን አመልካች ትንሽ ሰርቪስ ቤት ሰርተዉበት የያዙባቸው መሆኑን
በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው በቦታው ላይ የሰሩትን ቤት አፍርሰው እንዲለቁላቸው ዳኝነት
የሚጠይቅ ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች ለዚሁ ክስ በሰጡት መልስ ይዞታውን በ1987 ዓ.ም በሽንሻኖ ያገኘሁት ህጋዊ
ይዞታዬ ነው፤ ተጠሪ ከክሳቸው ጋር ያቀረቡት ማስረጃም ይዞታውን የሚመለከት አይደለም፤
ተጠሪ ከአካባቢውም ምንም ይዞታ የሌላቸው በመሆኑ ልለቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት እና ስለጉዳዩም


ከአስተዳደር ክፍሉ ተጣርቶ እንዲቀርብለት በማድርግ እንዲሁም ይዞታው ለተጠሪ ሲሰጥ ነበሩ
የተባሉትን የክፍሉ መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች የይዞታውን ማህደር ይዘው በመቅረብ
ስለይዞታው አሰጣጥ እንዲያስረዱ ካደረገ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ለክርክር ምክንያት የሆነው
ይዞታ ቀደምት ይዞታነቱ የአሁን አመልካች ቢሆንም ይዞታው ከአምልካች ላይ በህጋዊ መንገድ
ተወስዶ ለአሁን ተጠሪ በሽንሻኖ የተሰጠ መሆኑን፤ ይህ ሲሆንም በዞታው ላይ ዛፍ ብቻ እንጂ
በአመልካች የተሰራ ቤት ያልነበረበት ስለመሆኑ አረጋግጫለሁ በማለት አመልካች በቦታው ላይ
የሰሩትን ቤት አፍርሰው ይዞታውን ለተጠሪ ሊለቁ ይገባል በማለት ወስኗል፡፡ ይኸው ውሳኔ
እስከ ክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ፀንቷል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች ጥቅምት
11/2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል
ያሉትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለክርክር መነሻ የሆነው ይዞታ ለአሁን ተጠሪ
ከመሰጠቱ በፊት የአመልካች ቤት የነበረበት መሆኑ ባልተካደበት አመልካች ቤቱን አፍርሰው
ይዞታውን ለተጠሪ ያስረክቡ ተብሎ የተወሰነበት አግባብ ግራ ቀኙ በተገኙበት ለዚህ ችሎት
ቀርቦ እንዲመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ይህንን ሲመስል ችሎቱም የግራ ቀኙን ክርክር
ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ እና በስር ፍርድ ቤት በማስረጃ ከተረጋገጠው
ፍሬ ነገር አንፃር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ መርምሯል፡፡

እንግዲህ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ይዘት መረዳት እንደሚቻው ለክርክሩ ምክንያት የሆነው
ይዞታ ቀደምት ይዞታነቱ የአሁን አመልካች ቢሆንም ስልጣን ባለው አስተዳደር አካል
ከአመልካች ተወስዶ አስተዳደር እጅ ከገባ በኋላ በህጋዊ መንገድ ለአሁን ተጠሪ በሽንሻኖ
የተሰጠ ለመሆኑ ማስረጃን የመመርመር እና የመመዘን ስልጣን ባለው የወረዳው ፍርድ ቤት
ተረጋግጧል፡፡ የይዞታውን አወሳሰድ በተመለከተም በይዞታው አካባቢ በተደረገ አሰሳ ከአንድ
ሰው በቀር አመልካችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በአካባቢው ያለምንም ህጋዊ መብት መሬት
ይዘው የነበረ በመሆኑ መንግስት ሰዎቹን በማሳመን ተቀብሏቸው በሽንሻኖ ለሌሎች ሰዎች
የሰጠ መሆኑን እና በዚሁ አግባብ አሁን ክስ የቀረበበት ይዞታ ለተጠሪ የተሰጣቸው ስለመሆኑ
በክፍሉ መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች በዝርዝር መገለፁን የወረዳው ፍርድ ቤት መዝገብ
ያሳያል፡፡ በይዞታው ላይ ለተጠሪ የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ህጋዊነትን አስመልክቶ
ትክክለኛው እና ህጋዊ ሰነድ በተጠሪው እጅ ያለው ሲሆን በመሬት አስተዳደሩ ጽ/ቤት
በሚገኘው ቀሪ ላይ በጽ/ቤቱ ሰራተኛ ሆነ ተብሎ JU30P1 የነበረው 1 ቁጥሩን በካርቦን ፅሁፍ
ወደ 4 ተለውጦ የተተካ ስለመሆኑ ተደርሶበት ሰራተኛው በስነ ምግባር የተረከሰሰ ስለመሆኑንም
መረጋገጡ ተገልጿል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከእነዚህ በፍሬ ነገር ደረጃ ከተረጋጡት ነጥቦች በግልፅ መረዳት የሚቻለው የአሁን አመልካች
ለክርክር ምክንያት በሆነው ይዞታ ላይ ቀድሞውንም ቢሆን በህግ ጥበቃ የሚደረግለት የይዞታ
መብት ያላቋቋሙ ሲሆን ይዞታው ስልጣን ባለው አስተዳደር አካል ከአመልካች ላይ ተወስዶ
ለተጠሪ በሰነድ ተረጋግጦ የተሰጣቸው መሆኑን ነው፡፡ በፍሬ ነገር ደረጃ ይህ ከተረጋገጠ የስር
ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ማስረጃን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ
ስህተት የለም፡፡ በመሆኑም የአመልካች የሰበር ቅሬታ ውድቅ ተደርጎ ተከታዩ ውሳኔ
ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት


በመ/ቁ/333779 ላይ ጥቅምት 03/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን
ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

ትዕዛዝ

1. የዚህን ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡


2. በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል፡፡ ይፃፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-196963

ቀን፡-04/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ ደሣለኝ ሲሳይ

ተጠሪ ፡- 1. ወ/ሮ ድማም ተክሉ አልቀረቡም

2. አቶ መንግስቱ አዘነ

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

የሰበር አቤቱታ የቀረበው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ
የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በሚል ነው፡፡ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ
ከሳሽ እና 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከባለቤቴ አቶ
አዘነ በየነ ጋር የባንክና የዕቁብ ዕዳ ስለነበረብን በቡራዩ ከተማ ዉስጥ የነበረንን ቤት በቀን 24/08/1999 ዓ/ም
በተደረገ ዉል ሽጠን በሱሉልታ ከተማ ቁምቡሬ በተባለ ቦታ በካርታ ቁጥር ሱል/243/2005 ሆኖ
የሚታወቀዉን ቤት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ልጃችን ስለሆነ በስሙ ከአቶ ዳዊት አለሙ ላይ ገዝተናል፡፡ ይሁን
እንጂ ባለቤቴ በሞት ሲለይ አመልካች ቤቱን ስለያዘብኝ ቤቱንና ሰነዱን እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በራሴ ገንዘብ የገዛሁት
እንጂ የ1ኛ ተጠሪ አይደለም ብለዋል፡፡ አመልካች በክርክሩ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 41 መሰረት ጣልቃ
በመግባት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት በቀን 28/01/2011ዓ/ም በተደረገ ዉል በብር 443,594.25 ከ2ኛ
ተጠሪ ላይ ገዝቼ በስሜ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር ሱል/562/11 ከቀን 06/02/2011ዓ/ም ጀምሮ
አስመዝግቤ የያዝኩት ነው፡፡ ክርክር ያስነሳውን ቤት በግዥ ያገኘሁት ስለሆነ ሊከራከሩበት አይገባም ብለዋል፡፡
1ኛ ተጠሪ ለጣልቃ-ገብ ማመልከቻ ባቀረቡት መልስ ቤቱን አመልካች የገዛው ክስ ካቀረብኩና እግድ እንዲሰጥ
ከጠየቅሁ በኋላ ነው፡፡ 2ኛ ተጠሪም ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ነው የሸጠው፤ አመልካች መብት የሌለው መሆኑን
እያወቀ የገዛው ስለሆነ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ንብረቱን
ለአመልካች መሸጣቸውን በመግለጽ መልስ አቅርበዋል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት ለክርክሩ መነሻ
የሆነዉን ቤት የ2ኛ ተጠሪ አባት(የ1ኛ ተጠሪ ባለቤት) በ2ኛ ተጠሪ ስም ለራሳቸዉ ጥቅም በገንዘባቸዉ የገዙ
ስለመሆኑ ምስክሮቻቸዉ አላስረዱም፡፡ ቤቱ የተገዛዉ በ2ኛ ተጠሪ ስም በመሆኑና ተመዝግቦ የሚገኘዉም
በ2ኛ ተጠሪ ስም ስለሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195 መሰረት 2ኛ ተጠሪ የቤቱ ባለቤት እንደሆኑ ይገመታል፡፡
1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ መብት ለማግኘት ቤቱ በ1ኛ ተጠሪ እና በባለቤታቸዉ ገንዘብ በአሁን 2ኛ ተጠሪ ስም
መገዛቱን በማስረጃ በማረጋገጥ ግምቱን ማስተባበል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ማስረጃዉ ሲመረመር
የቤቱ ባለቤት 2ኛ ተጠሪ እንደሆኑ የሚያስቆጥረዉን ግምት በማስረጃ አላስተባበሉም በማለት ክሱን ዉድቅ
በማድረግ ወስኗል፡፡

ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ ሚዛን በሚደፋ
ሁኔታ ማስረጃዎቹ የሚያሳዩት 1ኛ ተጠሪ ከባለቤታቸዉ ጋር የነበራቸዉን እዳ ለመሰወር በማሳብ
የነበራቸዉን ቤት ሽጠዉ በ2ኛ ተጠሪ ስም ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ቤት መግዛታቸዉን ነዉ፡፡ በሕብረተሰቡ
ዉስጥ ባለዉ ተጨባጭ ሁኔታ አባት በልጁ ስም ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሚገዛ መሆኑ የተለመደ ነዉ፡፡
በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች 1ኛ ተጠሪ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1195 መሰረት ቤቱ በ2ኛ ተጠሪ ስም ሊመዘገብ
የቻለበትን ምክንያት በማስረዳት ግምቱን አስተባብለዋል፡፡ አመልካች ንብረቱ በቅን ልቦና ከ2ኛ ተጠሪ
አልገዙትም፤ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት በቀን 23/01/2011 ዓ/ም ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ደግሞ
አከራካሪዉን ቤት ለአመልካች በሽያጭ ያስተላለፉት በቀን 28/01/2011 ዓ/ም ክሱ ከተመሰረተ ከ5ቀን በኋላ
እንደሆነ የቀረበዉ ማስረጃ ስለሚያሳይና አስቀድሞ ከብር አንድ ሚሊዮን በላይ በሆነ ገንዘብ የተገዛዉን ቤት
2ኛ ተጠሪ ለአመልካች በብር 445,000.00 እንደሸጡ በመግለጽ መከራከራቸዉ ሲታይ በአመልካች እና በ2ኛ
ተጠሪ መካከል በድብቅ ግንኙነት መኖሩን ያሳያል፡፡ ስለሆነም ክርክር ያስነሳዉን ንብረት 1ኛ ተጠሪ በሞት
ከተለዩት ባለቤታቸዉ አቶ አዘነ በየነ ጋር ያፈሩት ንብረት ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር
አመልካች ቤቱን ለመግዛት ለ2ኛ ተጠሪ የከፈሉትን ገንዘብ ከ2ኛ ተጠሪ ላይ ከማስመለስ ዉሳኔዉ
እንደማያግድ ገልጾ ወስኗል፡፡ አመልካች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡትን የሠበር
አቤቱታ ባለመቀበል ሠርዟል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም 2ኛ ተጠሪ በስሙ
ካርታ መያዙን፣ የሊዝ ውል መዋዋሉን አይቼ በውል አዋዋይ ፊት በተደረገ ውል ገዝቼና ስመ-ሀብት
አዛውሬ የያዝኩት ንብረት ነው፡፡ የ2ኛ ተጠሪ አባት በሕይወት እያለ 2ኛ ተጠሪ የሊዝ ውል ተዋዋሎ
ያዛወረውን ድብቅ ግንኙነት መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ ንብረቱን በምገዛበት ጊዜ በፍርድ ቤት እግድ
አልተሰጠበትም፡፡ የቤቱ ዋጋ ብር 445,000.00 የተባለው የመሐንዲስ ዋጋ ግምት ነው፤ ቤቱን የሸጠልኝ
በብር 1,200,000.00 ነው፡፡ ተጠሪዎች ያላቸውን ግንኙነት አላውቅም፤ በንብረቱ ላይ ያለኝ መብት ሊከበር
ይገባል የሚል ነዉ፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት 2ኛ ተጠሪ
በስሙ የሚገኘውን ለአመልካች በሽያጭ አስተላልፈው ባለበት ሁኔታ ቤቱን እንዲለቁ የመወሰኑ አግባብነትን
ተጠሪዎች ባሉበት እንዲጣራ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ
ንብረቱ ላይ ክስ ካቀረብኩ በኋላ እገድ እንዲሰጥበት ጥያቄ አቅርቤ በእግድ ማመልከቻው ላይ 2ኛ ተጠሪ
አስተያየት እንዲሰጡበት ትዕዛዝ ተሰጥቶ፤ 2ኛ ተጠሪ ትዕዛዙን አልቀበልም ካሉ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ
ባላቸው ግንኙነት፣ 2ኛ ተጠሪን ለመርዳት በዝቀተኛ ዋጋ የተሸጠው ንብረቱን ለማሸሽ ነው፡፡ በማጭበርበርና
ከቅን ልቦና ውጭ የተደረገ ሽያጭ ስለሆነ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ
በበኩላቸው ንብረቱ የራሴ ነው፤ ውል ለመዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፊት የባንክ ዕዳ እና የፍርድ ቤት
እግድ እንደሌለው ተረጋግጦ ለአመልካች በሽያጭ ውል የተላለፈና በስሙ አዛውሮ ባለሀብት የሆነበት ንብረት
ነው ብለዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሠበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የግራ ቀኝ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘዉን
ማስቀረቢያ ነጥብ መሰረት በማድረግ ዉሳኔው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን
አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በሱሉልታ ከተማ ቁምቡሬ በተባለ ቦታ በካርታ ቁጥር


ሱል/243/2005 በ2ኛ ተጠሪ ስም ያለው ንብረት የ1ኛ ተጠሪና የሟች ባለቤቴ ስለሆነ ቤቱን ከነሰነዱ 2ኛ
ተጠሪ ሊያስረክበኝ ይገባል በሚል ባቀረቡት ክርክር መነሻነት የተጠሪዎች ክርክር እስከ ፌዴራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ በመዝገብ ቁጥር 196173 ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ/ም በሠጠው ውሳኔ
ንብረቱ በ2ኛ ተጠሪ ስም የተገዛ ቢሆንም የተገዛበት ገንዘብና ባለቤትነቱ የ1ኛ ተጠሪና የባለቤታቸው
ስለመሆኑ በመረጋገጡ ለ2ኛ ተጠሪ በሕግ የተሰጣቸው የባለሀብትነት ግምት ስለመስተባበሉ በሥር የክልሉ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በማስረጃ ተረጋግጦ ንብረቱ የ1ኛ ተጠሪና የባለቤታቸው ተብሎ
የተሠጠውን ውሳኔ አጽንቷል፡፡ በዚህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ላይ አመልካች በክርክር ያልተሳተፉ በመሆኑ
ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ መግዛታቸው ውጤቱ በጭብጥነት ተይዞ አልተመረመረም፡፡ በዚህም ምክንያት
አመልካች አሁን በተያዘው መዝገብ ላይ የሠበር አቤቱታቸውን ያቀረቡ በመሆኑ በተጠሪዎች ክርክር
ንብረቱን ገዝቻለሁ በሚል ያቀረቡት የጣልቃ ገብነት ማመልከቻና ሕጋዊ ውጤቱን በቀጣይነት
እንመለከታለን፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 41 መሠረት ጣልቃ የሚገባ ተከራካሪ ክርክሩ መብቱን የሚነካው እና በጉዳዩ ላይ


የተረጋገጠ መብት ያለው መሆኑን ማሳየት አለበት፡፡ አመልካችም ጣልቃ የገቡት ክርክር ያስነሳውን ንብረት
2ኛ ተጠሪ በስማቸው ካርታ አውጥተው የያዙትን መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ ውል
ገዝቼዋለሁ፡፡ ውሉም ሥልጣን ባለው አካል የተመዘገበና ስመ-ሀብቱ ተላልፎ የባለቤትነት ማረጋገጫ
ያወጣሁበት ነው፡፡ ስለዚህ የ1ኛ ተጠሪ ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ የሚከራከሩት
አመልካች ቤቱን የገዛው ክስ ካቀረብኩና እግድ እንዲሰጥ ከጠየቅሁ በኋላ ነው፡፡ 2ኛ ተጠሪም ፍርድ ቤት
ሳይቀርብ ነው የሸጠው፤ አመልካች መብት የሌለው መሆኑን እያወቀ የገዛው ስለሆነ ክርክሩ ተቀባይነት
የለውም በሚል ነው፡፡ ከክርክሩ የተረዳነው 2ኛ ተጠሪ ቤቱን በስማቸው ከገዙ በኋላ ለአመልካች ውል
ለመዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ሽያጭ ውል በማድረግ ባለሀብትነት መብትን አስተላልፈዋል፡፡

አመልካች መብቱ የተላለፈላቸው ጥበቃ ሊደረግለት በሚገባ ግብይት መሆን አለመሆኑን መመልከት ተገቢ
ነው፡፡ አመልካች ግዥ ሲፈጽሙ አንድ ጠንቃቃ ገዥ በሕግ ሆነ በአሠራር ሊያደርገው የሚገባውን ጥንቃቄ
የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ሕግ የተለየ ጥበቃ ስለሚያደርግ የሀብትነት ሠነድ
ስለሚወጣበት፤ ሠነዱ ስለሚገኝበት የሥራ ክፍል፣ ውሉ ስለሚፈጸምበት እና ንብረቱ ስለሚተላለፍበት
ሥርዓት የተገለጸውን መከተል ግዴታ ይጥላል፡፡ ሽያጭ ውል ሊፈጸምበት በሚችል የከተማ ክልል ውስጥ
ያለ፣ ቦታው ላይ ቤት ያረፈበትና ስለቤቱ የሚመለከቱ ሠነዶች በቤቱ ባለሀብት ሥም በማይንቀሳቀስ ሀብት
ምዘገባ ክፍል መገኘቱና ውሉን የፍ/ሕ/ቁ. 1723(1) በሚያዘው አግባብ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል
ፊት ማድረግ ይጠበቃል፡፡

አመልካች ውሉን የፈጸሙት 2ኛ ተጠሪ ቤቱን ገዝተው ሕጋዊ ሠነድ በቤቱ ላይ ካወጡበት በኋላ ሕጋዊ
ባለቤት እንዳለው በማረጋገጥ በውል አዋዋይ ፊት መሆኑ ሲታይ ግብይቱ ሕግን መሠረት ያደረገ በመሆኑ
የሕግ ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ ነው፡፡ አመልካች ውሉን የማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ እንዲጻፍ በማድረግ
ካርታ ያወጡበት በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 2878 እንደተመለከተው ውሉ ሦስተኛ ወገኖችን ላይም ውጤት ያለው
ነው፡፡ ሕግን መሠረት ላደረገ ግብይት ፍርድ ቤት ሕጋዊ ጥበቃ በመስጠት ገበያው በሕግ እንዲመራ ሆነ
የኢኮኖሚ እንቅሳቀሴው ጤናማ በሆነ ሁኔታ እንዲመራ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡ ንብረቱ በ2ኛ ተጠሪ
ስም ከመመዝገቡ እና ወደ አመልካች በሽያጭ ውል በሠነድ ከመዛወሩ በፊት መብቱ የማን ነው የሚለውን
አመልካች የማጣራት ኃላፊነት በሕግ የለባቸውም፡፡ ንብረቱ ላይ በፍርድ ቤት እግድ ከመሰጠቱ በፊት
የተዛወረ ከመሆኑ አኳያ አመልካች ክስ ካቀረቡ በኋላ ሽያጭ ውሉ መደረጉ ሆነ የተሸጠበት ዋጋ የተደረገውን
ግብይት ቀሪና ውጤት አልባ አያደርገውም፡፡ ምንም እንኳን 1ኛ ተጠሪ በንብረቱ ላይ መብት ያላቸው
ስለመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠላቸው ቢሆንም ይህ መብታቸው ከመረጋገጡ በፊት 2ኛ ተጠሪ በስማቸው
የነበረውን ንብረት ለሦስተኛ ወገን ለሆኑት ለአመልካች ያስተላለፉ በመሆኑ፤ ከሦስተኛ ወገን መብት አኳያ
ንብረቱን 1ኛ ተጠሪ ሊረከቡ አይችሉም ብለናል፡፡ ሥለሆነም ክርክር ያስነሳው ንብረት ሕጋዊ ባለመብት
አመልካች በመሆናቸው 1ኛ ተጠሪ ንብረት ለመረከብ ያቀረቡት ክስ ውድቅ ሊደረግ ሲገባ ይሕ ታልፎ
የተሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ

1. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 333206 ነሀሴ 07 ቀን 2012 ዓ/ም
እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 322981 ሚያዚያ 20 ቀን
2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሏል፡፡

2. በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 33894 ጥር 27 ቀን 2012 ዓ/ም
የሠጠው ውሳኔ በውጤት ደረጃ ጸንቷል፡፡

3. 1ኛ ተጠሪ የሽያጭ ገንዘቡን ከ2ኛ ተጠሪ ለመጠየቅ ሆነ ወይም በሕግ አለኝ የሚሉትን መብት ክስ
አቅርበው ከመከራከር ይሕ ውሳኔ አያግድም ብለናል፡፡

4. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-197008

ቀን፡- 05/02/2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን - ጠበቃ መኮንን ይማም ቀረቡ

ተጠሪ ፡- ፀጋ ረታ አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር - አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ክርክሩ የሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው
ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ
ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት እቃዎቹ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም
ኬብሎቹን እንዲያቀርብ ወይም በወቅቱ የገበያ ዋጋ የእቃዎቹን ግምት ብር 182,900 ወጪና ኪሳራን
ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች እቃዎቹ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ካወቀበት
ጊዜ ጀምሮ በ1 አመት ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመቃወሚያው ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ግንኙነታቸው የሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ ስለሆነ
ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለው ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው የፍ/ሕ/ቁጥር 1845 ሳይሆን የሽያጭ ውልን
የሚመለከተው የፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረትም በሻጩ አጭበርባሪነት ካልሆነ በቀር
ገዢው ጉድለቱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ ማቅረብ አለበት፡፡ አመልካች የተጠሪ
አጭበርባሪነት ያለበት ስለመሆኑ በክሱ ያልገለፀ ሲሆን ተጠሪው የእቃዎቹን ጉድለት እንዲያስተካክል
ያሳወቀው ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲሁም ለተረከባቸው እቃዎች ክፍያ የፈጸመው ጥቅምት 25 ቀን
2009 ዓ.ም በመሆኑ ክሱ የቀረበው ሁለት ኣመት ካለፈው በኋላ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ነው፡፡ የተጠሪ
ሰራተኛ ሰኔ 10 ቀን 2009 ዓ.ም UPS 5kg ለቼክአፕ መውሰዱ ጉድለቱን በግልፅ አምኗል አያስብልም፡፡
አምኗል ቢባል እንኳ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በ1 ዓመት ውስጥ ክሱ ስላልቀረበ በይርጋ ይተጋዳል በማለት ብይን
ሰጥቷል፡፡

አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኙን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ውሳኔን
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት በማፅናቱ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን
አቅርቧል፡፡ የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ አመልካች በክሱ ላይ ፍሬ ነገርን ከመግለፅ በዘለለ ተጠሪው መቃወሚያ
ሊያቀርብ ይችላል ብሎ በማሰብ በክስ መስማት ወቅት ሊያቀርብ የሚችለውን መከራከሪያ አስቀድሞ ማቅረብ
ግዴታ በሌለበት ተጠሪው የማታለል እና የማጭበርበር ተግባር ስለመፈፀሙ አመልካች በክሱ አልገለፀም
መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ ተጠሪ እቃዎቹን አስተካክላለው ብሎ መውሰዱን አልካደም፡፡ የወሰደውም እቃውን
ባስረከበ በአንድ ዓመት ውስጥ ሲሆን እቃውን በእምነት በመውሰድ በተግባር የማታለል እና የማጭበርበር
ተግባር የፈፀመ ሲሆን እቃዎቹን አስተካክሎ የሚያቀርብበት ጊዜም ስላልተወሰነ እና እቃዎቹን አስተካክሎ
እንዲያስረክብ በተደጋጋሚ በአመልካች ሲጠየቅ ከዛሬ ነገር አስተካክዬ እመልሳለው ማለቱ ስላልተካደ አስፈላጊ
ከሆነም ምስክሮቻችንን በመስማት ሊጣራ ሲገባ ክሱ በይርጋ ይታገዳል መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ ውሉ
የሽያጭ ብቻ ሳይሆን የጥገና ማደስና መለዋወጫ ማቅረብ መሆኑ በሰነድ ተረጋግጦ እያለ ሽያጭ ብቻ ነው
ተብሎ የሽያጭ ሕግ የይርጋ ድንጋጌ ተግባራዊ መደረጉ እንዲሁም እቃው በተጠሪ እጅ ያለ በመሆኑ
አመልካች በማንኛውም ጊዜ ንብረቱን መጠየቅ የሚችል ሁኖ እያ ክሱ በይርጋ ይታገዳል መባሉ የፍ/ሕ/ቁጥር
1206 እና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 63600 ቅፅ 10 የሰጠውን ውሳኔ
የሚቃረን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው፡፡

አቤቱታው በአጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ ተጠሪ የእቃውን ጉድለት አምኖ መልሶ መቀበሉን ለክሱ በሰጠው
መልስ አምኖ እያለ ክሱ በአንድ አመት ይርጋ ይታገዳል ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት ከፍ/ሕ/ቁጥር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2298(1) እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ ለመመርመር ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪ
መልሱን እንዲያቀርብ ታዟል፡፡

ተጠሪም ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል፡፡ የመልሱ ይዘት ባጭሩ ተጠሪ ለክሱ በአማራጭ
በሰጠው መልስ አመልካች የመለሳቸውን እቃዎች አስመልክቶ ክትትል አላደረገም በሚል መቀመጡ
አማራጭ ክርክር ከሚሆን በቀር በፍ/ሕ/ቁጥር 1851(ሀ) መሰረት እዳውን አምኗል አያስብልም፡፡ እቃው
ጉድለት አለበት በሚል ማሳወቅም ሆነ ጉድለት አለ በሚል እቃ መመለሱ መታመኑ በውጤት ደረጃ አንድ
ስለሆነ በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) መሰረት አመልካች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ
ይታገዳል መባሉ ተገቢ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡

አመልካች የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልሱን ያቀረበ ሲሆን የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር
ተከራክሯል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የአመልካች ክስ በይርጋ ይታገዳል ተብሎ የመወሰኑን
አግባብነት በስር ፍ/ቤት ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዲሁም ለጉዳዩ ተገቢነት
ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡

እንደመረመርነውም አመልካች በዋናነት የሚከራከረው ተጠሪው ክርክር ያስነሳውን እቃ መልሶ መረከቡ እና


በተለያዩ ጊዜያትም ከዛሬ ነገ አስተካክዬ አስረክባለው እያለ እንደነበር ባልተካደበት አስፈላጊ ከሆነም ምስክር
ሊሰማ ሲገባ እንዲሁም ውሉ ሽያጭ ብቻ ሳይሆን የጥገና እና የመለዋወጫ እቃ አቅርቦት ጭምር ሆኖ እያለ
ክሱ በአንድ አመት ይርጋ ይታገዳል መባሉ ተገቢ አይደለም በማለት ነው፡፡ ተጠሪ በበኩሉ እቃውን መልሶ
መቀበሉን በአማራጭ ክርክር ማቅረቡ እዳውን አምኗል የማያስብል እና አመልካች ጉድለት አለበት በሚል
ማሳወቁም ሆነ እቃውን መመለሱ በውጤት ደረጃ ልዩነት ስለሌለው ክሱ በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) መሰረት
በይርጋ ይታገዳል ተብሎ መወሰኑ ተገቢ መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል፡፡

ገዢው ክስ ማቅረቡን የከለከለው የሻጩ አጭበርባሪነት ካልሆነ በቀር እቃው እንደ ውሉ ትክክል አለመሆኑን
ወይም ጉድለት ያለበት መሆኑን ካስታወቀበት ቀን አንስቶ እስከ አንድ አመት ውስጥ ክስ ያላቀረበ እንደሆነ
እቃው ጉድለት አለበት ወይም እንደ ውሉ የቀረበ አይደለም በማለት ክስ ማቅረብ የማይችል መሆኑ
በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) ላይ ተመላክቷል፡፡ ይህም ማለት አንድ ገዢ የገዛው እቃ ላይ ጉድለት ያለበት ከሆነ
ጉድለቱ ለሻጩ ባሳወቀ በአንድ አመት ውስጥ ጉድለቱ እንዲስተካከልለት ክስ ካላቀረበ ክሱ በይርጋ
ይታገዳል፡፡ ነገር ግን ገዢው በዚህ አንድ አመት ውስጥ ክስ እንዳያቀርብ የሻጩ አጭበርባሪነት ከልክሎት
ከሆነ ገዢው ጉድለት መኖሩን ካሳወቀ ከአንድ አመት በኋላም ቢሆን ጉድለቱ እንዲስተካከልለት ክስ ማቅረብ
ይችላል፡፡ በሌላ አባባል የሻጩ የማጭበርበር ድርጊት የአንድ አመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ የሚያቋርጥ
ምክንያት ይሆናል፡፡ የዚህ ድንጋጌ አላማ ሻጩ በፈጸመው የማጭበርበር ተግባር የወንጀል ድርጊት በመሆኑ
በአንድ አመት ውስጥ ክስ አልቀረበም በሚል በወንጀል ድርጊቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን ለመከላከል ነው፡፡ ይህ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማለት ግን የማጭበርበር ድርጊት ከተፈጸመ ምንም አይነት የክስ ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ አይኖረውም ማለት
አይደለም፡፡ የማጭበርበር ድርጊቱ እንደ ይርጋ ማቋረጫ ጊዜ ተወስዶ የአንድ አመቱ የይርጋ ጊዜ
የማጭበርበር ድርጊቱ ከተፈጸመ ጊዜ ጀምሮ እንደአዲስ መቁጠር የሚጀምር ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
ሌላው መታየት ያለበት የሻጩ አጭበርባሪነት የሚለው አገላለጽ ምን አይነት እና መቼ የሚፈጸም የሻጩን
ድርጊት የሚያመለክት ነው? የሚለው ሊሆን ይገባል፡፡ በፍ/ህ/ቁጥር 2297 ሻጩ የሸጠውን ነገር ጉድለቶች
ያሉበት መሆኑን ገዢው እንዳያውቃቸው በተንኮል ደብቋቸው ከሆነ ሻጩን ከሀላፊነት የሚያድኑ የውል
ቃሎች ቢኖሩ ሻጩ ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችል ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት ሻጩ ለገዢ በሸጣቸው
ነገሮች ላይ ጉድለት መኖሩን እያወቀ በተንኮል በሽያጭ ወቅት ምንም አይነት ጉድለት እንደሌለባቸው
አስመስሎ ከሸጠ ወይም ከሽያጭ በኋላም ቢሆን ጉድለቱ እንዳይታወቅ ለማድረግ ሻጩ የማጭበርበር ድርጊት
የፈጸመ በመሆኑ ተጠያቂ የማያደርገው የውል ቃል እንኳን ቢኖር ውሉ ተፈጻሚ እንደማይሆን እና ሻጩ
በኃላፊነት እንደሚጠየቅ የሚያመለክት ነው፡፡ የፍ/ህ/ቁጥር 2298/1 የፍ/ሕ/ቁጥር 2297 ተከታይ እንደመሆኑ
ተጣምረው ሲነበቡ ሻጩ እቃውን ወይም የሚሸጠውን ነገር ለገዢ በሚሸጥበት ወይም በሚያስረክብበት
ወቅት እቃው ጉድለት ያለበት መሆኑን እያወቀ ጉድለት እንደሌለ አድርጎ ወይም ጉድለቱ እንዳይታወቅ
አድርጎ በማጭበርበር ለገዢ መሸጡ ወይም ማስረከቡ ከተረጋገጠ ክስ የማቅረቢያ ጊዜው በአንድ አመት
ይርጋ የማይገደብ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በተቃራኒው ሻጩ በሽያጭ ወይም በርክክብ ወቅት
የፈጸመው የማጭበርበር ድርጊት ከሌለ ጉድለቱን ገዢው ለሻጭ ባሳወቀ በአንድ አመት ውስጥ ክስ ካላቀረበ
ክሱ በይርጋ ይታገዳል ማለት ነው፡፡

በተያዘው ጉደይ አመልካች ተጠሪው ከዛሬ ነገ እቃውን እጠግናለው በማለት የማጭበርበር ተግባር ስለፈጸመ
ክሱ በይርጋ ተቋርጧል መባሉ ተገቢ አይደለም በማለት የሚከራከር ቢሆንም ከላይ እንደተገለጸው
በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) የተገለፀው የማጭበርበር ተግባር እቃውን ከሚመለከት ዝርዝር መግለጫ ወይም
በግብይቱ ጊዜ እቃው ጉድለት ያለበት መሆኑ እየታወቀ ይህን በመደበቅ ከተፈጸመ ተግባር ጋር የሚገናኝ
ነው፡፡ ተጠሪ ከዛሬ ነገ እቃውን አስተካክላለሁ እያለ ቆይቶ ቢሆን እንኳን ተጠሪ የዋቢነት ሃላፊነቱን
አለመወጣቱን የሚያሳይ እንጂ በግዢ ወቅት በእቃው ላይ ያለው ጉድለት በአመልካች እንዳይታወቅ
የማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙን የሚያመለክት አይደለም፡፡ ከግብይቱ በኋላ የተጠሪ ሰራተኛ ሰኔ 10 ቀን
2009 ዓ.ም UPS 5kg ለቼክአፕ መውሰዱ ጉድለቱን በግልፅ አምኗል የሚያስብል ካለመሆኑም በላይ ተጠሪ
ጉድለቱን ለማስተካከል እቃውን ተቀብሏል ቢባል እንኳ በዚህ አግባብ ባለማስተካከሉ አመልካች ተጠሪ
እቃውን ለማስተካከል ከተቀበለበት ጊዜ ጀምሮ በሕግ በተገለፀው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ክስ በመመስረት
ዳኝነት ሊጠይቅ ይገባ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አመልካች ተጠሪው ከዛሬ ነገ እቃውን አስተካክላለው በማለት
ያጭበረበረኝ ስለመሆኑ ምስክሮቼ መሰማት ነበረባቸው በማለት የሚከራከር ቢሆንም በፍትሐብሄር ክርክር
ማስረጃ የሚሰማው እና ፍሬ ነገር እንዲነጥር የሚደረገው ለጉዳዩ አወሳሰን የግድ አስፈላጊ ሲሆን ብቻ
ስለመሆኑ ከፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለሆነም አመልካች ምስክሮቼ ሊሰሙ ይገባ ነበር
በማለት የሚያቀርበው ቅሬታ ተገቢነት የለውም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመጨረሻም አመልካች ለክሱ መነሻ ያደረገው የገዛዋቸው እቃዎች በውሉ መሰረት ተሟልተው የቀረቡ
ባለመሆኑ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም የሚል ሁኖ እያለ እና ውላችን የጥገና እና
የመለዋወጫ አቅርቦትን ስለሚጨምር የፍ/ሕ/ቁጥር 2298 ለጉዳዩ ተፈጻሚነት የለውም በማለት የሚያነሳው
መከራከሪያ ተገቢነት ስንመለከት አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ተጠሪው ጥገና እንዲያደርግልኝ
ይወሰንልኝ የሚል ግልጽ ዳኝነት አልጠየቀም፡፡ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከመለዋወጫ እና ጥገና ውል ጋር
የተያያዘ ክስ ባላቀረበበት የተጠቀሰው የይርጋ ድንጋጌ ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም በሚል የሚያቀርበው
መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበው የሽያጭ ውልን መሰረት
አድርጎ በተሸጠው እቃላይ አለ የሚለው ጉድለት በገንዘብ ወይንም በአይነት እንዲስተካከልለት በመሆኑ
ለጉዳዩ የፍ/ሕ/ቁጥር 2298/1 ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

በመሆኑም አመልካች ተጠሪ እቃውን እንዲያስተካክል ያሳወቀው ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም መሆኑ እና
ክሱ የቀረበው የካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም መሆኑ ተረጋግጦ በይርጋ ይታገዳል ተብሎ በስር ፍ/ቤቶች
በተሰጠው ብይን ላይ እና ብይኑን በማጽናት በተሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም
በማለት ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁጥር 65181 ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው
ብይን እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 239590 ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው
ችሎት ሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡
3. አመልካች ለተጠሪ እንዲስተካከል ሰጥቻለሁ የሚለውን እቃ በተመለከተ ባለበት ሁኔታ ለማስመለስ
ክስ ከማቅረብ ይህ ውሳኔ አያግደውም፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁጥር 197009

ሀምሌ 28 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ ኃይለጊዮርጊስ ይልማ፡- አልቀረቡም

ተጠሪ፡- አቶ አዲስ እሸቱ፡- አልቀረቡም

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ይህ የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ የቻለው አመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት
ተከሳሾች አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት የስር የጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት
የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ
ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን ተጠሪ በጣርማ
በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን አመልካች 1ኛተከሳሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ በተመለከቱት ተከሳሾች ላይ
ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ላይ የተመለከተውን 400 ካሜ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ከነሰርቪሱ
የካቲት 27 ቀን 2011 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከተመለከቱት ተከሳሾች በብር
200,000.00 ገዝቼ ካርታ በስሜ የተሰጠኝ ቢሆንም ቤቱን ከአመልካች ነፃ በማድረግ ያላስረከቡኝ
በመሆኑ ፤አመልካችም በአደራ ይዤ የምጠቀመው ነው በማለት ምንም መብት ሳይኖረው ለማስረከብ
ፍቃደኛ ስላልሆነ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች ቤትና ይዞታውን ከ3ኛ ወገን ነፃ አድርገው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዲያስረክቡኝ አመልካችም የፈጠረውን ሁከት አቁሞ ቤትና ቦታውን እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ


በማለት አመልክተዋል፡፡

አመልካች በሰጡት መልስም አዋሳኙ በክሱ ላይ በተጠቀሰው ቦታ ላይ ያለውን ሰርቪስ ቆርቆሮ ቤትና
ለሱቅ እና ለሻይ ቤት አገልግሎት የሚውለውን ከ28 አመት በላይ ከእሸቴ ወዳጆ ጋር በቤተሰብ
አባልነት ስኖር እንድሰራ ፈቅደውልኝ የሰራሁት ከመኖሪያ ቤቱ አዋሳኝ ሆኖ የተለየ መግቢያና መውጫ
ያለው የቤት ቁጥራችንም ቢሆን የኔ 151 ሆኖ የሟች 153 በመሆን የተመዘገበ በመሆኑ ግንባታውን
ሳከናውንም የተቃወመኝ ባለመኖሩ ፤የስር ተከሳሾች በውርስ ያላገኙትን ለተጠሪ መሸጣቸው አግባብ
ባለመሆኑ ፤ለ28 አመት በእጄ በቆየው ንብረት ላይ ክስ ለማቅረብም ይርጋ ስለሚያግዳቸው በግል
የያዝኩትን ቤትና ቦታ ላስረክብ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቶ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ በሰጠው ውሳኔም ማዘጋጃ
ቤቱ በሰጠው ምላሽ 400 ካሜ ላይ ያረፈው ቤትና ቦታ ስመ ንብረቱ በሟች እሸቴ ወዳጆ ስም
የነበረ፤አቶ እሸቴ ከሞቱ በኋላም ከ1ኛ እስከ 3ኛ በተመለከቱት ተከሳሾች ስም የተመዘገበና ግብሩም
በነዚሁ ተከሳሾች ስም የሚከፈል መሆኑን የገለፀ መሆኑ አመልካች ቤቱን በማያሻማና ግልፅ በሆነ ሁኔታ
የግሌ ነው ብሎ አለመያዙንና አለመገልገሉን የሚያሳይ መሆኑን ፤ተጠሪ ቦታውንና ቤቱን ሲገዛ በስር
ተከሳሾች ስም መሆኑን አረጋግጦ መሆኑን የሰነድ ማስረጃዎቹ የሚያሳዩ መሆኑን ፤ማዘጋጃ ቤቱ የሰጠው
ምላሽም ሽያጩ አመልካች የግሌ ነው የሚለውን ቤትና ቦታ የሚጨምር ፤መግቢያና መውጪያውም
አንድ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ፤አመልካችና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት
ተከሳሾች ክስ የቀረበበትን ቤትና ቦታ ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት ወስኗል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ


ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት የሠረዘው ሲሆን ፤የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር
አጣሪ ችሎትም በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት የአመልካችን
የሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም ምስክሮቼ ቤቱን ወላጅ አባቴ
በ1984 ዓም መስራቱን አስረድተው እያለ የተጠሪ ምስክሮች ይህንን ባላስተባበሉበት የስር ፍርድ ቤት
በህጉ የተቀመጠውን የማስረጃ ምዘና መርህ ሳይከተል ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈፀመበት ነው፤አባቴ ከ1984 ዓም ጀምሮ አከራካሪውን ቤትና ቦታ ውሳኔው እስከተሰጠበት የካቲት
12 ቀን 2012 ዓም ድረስ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የሚጠቀምበት ሆኖ እያለ የይርጋ መቃወሚያው በስር
ፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይሰጥበት መታለፉ አግባብነት የለውም፤ማዘጋጃ ቤቱ መውጪያና መግቢያው አንድ
ነው በማለት የሰጠው ምላሽ እውነታውን የደበቀ በመሆኑ ሊያዝ አይገባም በማለት የተከራከርኩ በመሆኑ
በገለልተኛ ባለሙያ ሊጣራ ሲገባ ጥያቄዬ ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም፤ባለመሬቱ ሳይቃወም
በሌላ ሰው መሬት ላይ ህንፃ የሰራ ሰው የዚህ ህንፃ ባለቤት ሊሆን እንደሚገባ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1179(1)

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተመለከተ ሆኖ እያለ ሟች አባቴ ግንባታውን ያከናወኑት ሟች እሸቴ ፈቅደውለት ሆኖ እያለ ፤በሰበር


መ/ቁ.96628 በተሰጠ አስገዳጅ ውሳኔበዚህ አግባብ የተገነባ ቤት የውርስ ሀብቱ አካል ሊሆን እንደማይገባ
ተመልክቶ እያለ ለኔ በውርስ ሊተላለፍ የሚገባውን ሟች አባቴ በስጦታ ያገኘውን ቤትና ቦታ በማካተት
የተደረገው የሽያጭ ውል የህግ መሰረት የለውም ተብሎ ሊፈርስ ይገባል ተብሎ የስር ፍርድ ቤቶች
ውሳኔ ተሸሮ አከራካሪው ቦታና ቤት ለአመልካች ሊተላለፍ ይገባል ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት
አመልክተዋል፡፡

በስር ፍርድ ቤቶች የስር 1ኛ ፤2ና እና 3ኛ ተከሳሾች አውራሽ የአመልካችን አባት በህይወት እያለ
ሳይቃወሟቸው ቤት ሰርተው ሲኖሩበት የነበረ መሆን አለመሆኑ የተረጋገጠበትን እና አመልካች ቤቱን
ለቀው ለተጠሪ እንዲያስረክቡ የተወሰነበትን አግባብ ከማስረጃ ምዘና መሰረታዊ መርህ እና ከፍ/ብ/ህ/ቁ
1179 እና ተከታታይ ድንጋጌዎች አንፃር ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪ
መጥሪያ ደርሷቸው መልሳቸውን ሰጥተዋል፡፡

ተጠሪ በሰጡት መልስም የቀረበው አቤቱታው ውድቅ ሊደረግ ይገባል የሚሉባቸውን ዝርዝር ሁኔታዎች
በመዘርዘር የሰበር አቤቱታው ውድቅ ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊፀና ይገባል በማለት
ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ ከተገቢው ህግና፤ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡ በመሰረቱ
አንድ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ወገኖች የተለያዩበትን የህግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ምን እንደሆነ
በመለየት ለጉዳዩ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለውን ጭብጥ መያዝ ያለበት መሆኑን
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.246(2) የሚደነግግ ሲሆን እነዚህ የተያዙ ጭብጦችን አስመልክቶ የአንዱ ጭብጥ መወሰን
ሌሎቹንም ያጠቃልላቸዋል ብሎ ፍርድ ቤቱ ካልገመተ በስተቀር እየአንዳንዱ ጭብጥ በህጉ አግባብ
ተመርምሮ እልባት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ከፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.182(3) ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡አሁን
በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ ክርክር በተነሳበት ቤት ላይ በግዢ ያገኙት መብት እንዲከበርላቸው ላቀረቡት
ክስ አመልካች በህግ የተቋቋመ መብት ያላቸው መሆኑን በመግለፅ የተከራከሩ ሲሆን ለዚህም መሰረቱ
ቤቱን አባታቸው የሰሩት አቶ እሸቴ ወዳጆ ፈቅደውላቸው መሆኑን የቤቱን ግንባታ ሲያከናውኑም
የተቃወማቸው ሰው አለመኖሩን በመግለፅ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1179(1) አግባብ ክርክር ያቀረቡ መሆኑን የስር
ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክር የሚያሳይ ቢሆንም የስር ፍርድ ቤት በዚህ አግባብ የቀረበውን ክርክር
መሰረት አድርጎ ተገቢውን ጭብጥ በመያዝ ለግራ ቀኙ ክርክር እልባት መስጠቱን የስር ፍርድ ቤት
መዝገብ አያሳይም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የስር ፍርድ ቤት የአመልካች አባት አከራካሪውን ቤት የሰሩ መሆኑን ግንባታውን ሲያከናውኑም በስር
ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች አውራሽ ተፈቅዶላቸው መሆኑን ገልፀው የተከራከሩ በመሆኑ የግራ ቀኙ
ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል ከዚሁ ክርክር አንፃር በመመርመር የአመልካች አባት
አከራካሪውን ቤት ሰርተዋል? ወይስ አልሰሩም? ሰርተዋል ከተባለስ የሰሩት በአቶ እሸቴ ወዳጆ
ተፈቅዶላቸው ነውን? ተፈቅዶላቸው ከሰሩስ ግንባታውን ተፈቅዶላቸው መስራታቸው በተለይም በግዢ
ውል ይዞታውን ካገኙት ተጠሪ አንፃር በገነቡት ቤት ላይ የሚያገኙት መብት ይኖራልን? ተፈቅዶላቸው
ያልሰሩ ከሆነስ ግንባታውን ሲያከናውኑ የቀረበ ተቃውሞ ነበርን? ውጤቱስ ምን ሊሆን ይገባል?
የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ለግራ ቀኙ ክርክር ተገቢውን እልባት ሊሰጥ ሲገባ የግራ ቀኙን መሰረታዊ
የክርክር ነጥብ ሳያጣራ ማዘጋጃ ቤቱ በሰጠው ምላሽ 400 ካሜ ላይ ያረፈው ቤትና ቦታ ስመ ንብረቱ
በሟች እሸቴ ወዳጆ ስም የነበረ መሆኑን ፤አቶ እሸቴ ከሞቱ በኋላም ከ1ኛ እስከ 3ኛ በተመለከቱት
ተከሳሾች ስም የተመዘገበና ግብሩም በነዚሁ ተከሳሾች ስም የሚከፈል መሆኑን የገለፀ መሆኑን መነሻ
በማድረግ አመልካች ቤቱን በማያሻማና ግልፅ በሆነ ሁኔታ የግሌ ነው ብሎ አለመያዛቸውንና
አለመገልገላቸውን በመጥቀስ ፤ተጠሪ ቦታውንና ቤቱን ሲገዛ በስር ተከሳሾች ስም መሆኑን አረጋግጦ
መሆኑን የሰነድ ማስረጃዎቹ የሚያሳዩ መሆኑን ፤ማዘጋጃ ቤቱ የሰጠው ምላሽም ሽያጩ አመልካች የግሌ
ነው የሚለውን ቤትና ቦታ የሚጨምር መሆኑንና መግቢያና መውጪያውም አንድ መሆኑን በመጥቀስ
አመልካች ከፍ/ብ/ህ/ቁ.1179 አንፃር ያቀረቡትን ክርክር በአግባቡ ሳይመረምር አከራካሪውን ቤትና ቦታ
ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ
ስላገኘነው የሚከተለው ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1. የጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.0120263 በ12/06/2012 ዓም የሰጠው ፍርድና ይህንን


ፍርድ በማፅናት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.0133151 ግንቦት 25 ቀን 2012
ዓም እንዲሁም የአ/ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.03-11754 ጥቅምት 06 ቀን
2012 ዓም የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸረዋል፡፡
2. የጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት መዝገቡን እንደገና በማንቀሳቀስ የአመልካች አባት አከራካሪውን
ቤት ሰርተዋል? ወይስ አልሰሩም?ሰርተዋል ከተባለስ ቤቱን የሰሩት በአቶ እሸቴ ወዳጆ
ተፈቅዶላቸው ነው? ወይስ አይደለም? ተፈቅዶላቸው ከሰሩስ ግንባታውን ተፈቅዶላቸው
መስራታቸው በተለይም በግዢ ውል ይዞታውን ካገኙት ተጠሪ አንፃር በገነቡት ቤት ላይ
የሚያጎናፅፋቸው መብት ይኖራልን? ተፈቅዶላቸው ያልሰሩ ከሆነስ ግንባታውን ሲያከናውኑ
የቀረበ ተቃውሞ ነበርን? ተቃውሞ ካልቀረበስ ተቃውሞ ሳይቀርብባቸው የገነቡትን ቤት
ለተጠሪ ለቀው ሊያስረክቡ ይገባል?ወይስ አይገባም? የሚሉትንና ተያያዥ ጭብጦች በመያዝ
ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች አስቀርቦ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመመርመር በህጉ አግባብ የመሰለውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343(1)


መሰረት መልሰንለታል፡፡
3. በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.01- 20263 በተጀመረው አፈፃፀም ላይ ጥቅምት 27 ቀን
2013 ዓም የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ እና ታህሳስ ዐ7 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም አከራካሪው ይዞታና
ቦታ ላይ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡
4. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

በግራ ቀኙ መሃል ያለው ክርክር ተገቢውን እልባት ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ


ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ. 197106
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት- አልቀረቡም

ተጠሪዎች፡- 1. ወ/ሮ አማረች ባሳ ጠበቃ ነብያት ግርማ ቀረቡ

2. ወ/ሮ ሰብለ ወንጌል ዮናስ

መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 022929 በሕዳር 25 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ
ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 807 የሆነውን የመንግስት ቤት ላይ በመመሪያ ቁጥር 5/2011
አንቀጽ 16(1)ሀ መሰረት ተጠሪዎች የተከራይነት መብት እያላቸው አመልካች ሊለቁ ይገባል ማለቱ
በፍታብሔር ህግ ቁጥር 1149(3) መሰረት የሁከት ተግባር ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ
በማጽናት በየደረጃው ባሉ የከተማው አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ
ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች ተከሳሽ፤
የአሁን 2ኛ ተጠሪ ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት
ያቀረበችው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 8ዐ7 የሆነውን
የመንግሥት ቤት ከሟች ባለቤቷ አቶ ዬናስ አንጎሌ ጋር ተከራይተው ሲኖሩ ባለቤታቸው በጠና በመታመሙ
ለህክምና ውጪ ሀገር ይዞው በሄደችበት በሞት መለየቱን፣ ሚስትነቷን በመ/ቁ.1143 ሚያዝያ 8 ቀን 2ዐ1ዐ
ዓ.ም. አረጋግጣ ለአመልካች ብታሳውቅም የቤቱን ኪየራ ተቀብሎ 1ኛ ተጠሪ ከውጭ ሀገር እስክትመለስ
ድረስ ለተወካይ አላዋውልም በማለት የሟች ልጆች እና ወራሾች በቤቱ ውስጥ እየኖሩበት ባለበት ጥቅምት
13 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም. ቤት ድረስ በመምጣት ቤቱን ልቀቁ አሽጋለሁ በማለት ሁከት የፈጠረባቸው መሆኑን
በመግለጽ እንዲሁም መልቀቂያ ሳይወስዱ ከ4ዐ ዓመታት በላይ1ኛ ተጠሪ የያኩት እና የሟች ልጆች ጭምር
የሚኖሩበት ቤት ላይ እየፈፀመ ያለው ሁከት እንዲከም ይወሰንልን ሲሉ ዳኝነት መጠየቋን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን አመልካች በሰጠው መልስ 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ ከኪራይ ውልም ሆነ ከህግ የመነጨ መብት እና
ጥቅም የላትም፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት 1ኛ ተጠሪ ለቃ ባለቤቷን ለማሳከም ወደ ውጪ ሀገር
መሄዳቸውን አልካደችም፤ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን በእውነት በእጇ ይዛ የምታዝበት አይደለም፤ 1ኛ ተጠሪ
በመመሪያው መሰረት ለሚመለከተው አካል በአደራ ማስረከብ ሲገባት ከህግ ውጪ በተወካይ የኪራይ ውል
አዋውሉን ማለቷ ህገወጥ ተግባር ነው፤1ኛ ተጠሪ ባለቤታቸው ከሞተ በኋላ ሚስትነቷን አረጋግጣ አዲስ
ውል ሳትዋዋል እና የስም ዝውውር ሳትፈጽም ቤቱን በመያዟ አመልካች ቤቱ እንደሚታሸግ ማስጠንቀቂያ
መስጠቱ አስተዳደራዊ ኃላፊነቱን ተወጣ እንጂ የሁከት ተግባር አለመሆኑን በመግለጽ የ1ኛ ተጠሪ ክስ ወድቅ
ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ለመግባት ጠይቃ ተፈቅዶላት ባቀረበችው መከራከሪያ የሰጠችው መልስ አመልካች
እየፈጠረ ያለው የሁከት ተግባር በ1ኛ ተጠሪ እና በሌሎች ላይ ብቻ ሳይሆን በ2ኛ ተጠሪ ላይ ጭምር ነው፤
2ኛ ተጠሪ ህጋዊ የነዋሪ መታወቂያ ተሰጥቷት እና እየኖረችበት መሆኗን በመግለጽ የአመልካች የሁከት
ተግባር ሊቆም ይገባል በማለት ተከራክራለች፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተጠሪዎች መብት እና ጥቅም ያላቸው መሆኑን ያረጋገጡ በመሆኑ በዚህ ረገድ
የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል፡፡ በፍሬነገር ላይም የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ እና
ከሚመለከተታቸው አካላት የአከራከሪውን ቤት ማህደሮች እንዲቀርቡ ካደረገ በኋላ በአከራካሪው የመንግስት
ቤት ውስጥ እየኖሩ ያሉት የ1ኛ ተጠሪ ምስክር የሆነው አቶ አዲስ ቤካ እና ባለቤቱ ወ/ሮ ፋሲካ ጉልላት
ከልጆቻቸው ጋር እንጂ ተጠሪዎች አለመሆናቸው ተረጋግጧል፤1ኛ ተጠሪ ውል ላለመዋዋሏ ምክንያት
አመልካች በተወካይ አናዋውልም በማለቱ እንደሆነ ተረጋግጧል፤ 1ኛ ተጠሪ በአከራከሪው የቤት ቁጥር 807
ላይ የጸና የቤት ኪራይ ውል እንደሌላቸው አልተካደም፤ 1ኛ ተጠሪ የሟች አቶ ዮናስ አንጎሌ ሚስት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስለመሆናቸው የተረጋገጠ በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀጽ 16/1/ሀ መሰረት ከህግ የመነጨ
የተከራይነት መብት አላቸው፤ በፍታብሔር ህግ ቁጥር 1140 መሰረት 1ኛ ተጠሪ ከሟች ባለቤታቸው ጋር
ተከራይተው ለረጅም አመታት የኖሩበት እና ባለቤታቸው ለህክምና ውጪ ሄዶ በመሞቱ ሚስትነታቸውን
በማረጋገጥ የተከራይነት መብቱ እንዲተላለፍላቸው መጠየቃቸውን እና ቤቱ በአመልከች ይዞታ ስር
አለመሆኑ ተረጋግጧል፤ በመሆኑም አመልካች ቤቱን ልቀቁ ማለቱ የሁከት ተግባር በመሆኑ ሁከት ሊወገድ
ይገባል በማለት ወስኗል፡፡ ይኸው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ የከተማው ፍርድ ቤቶች ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- ተጠሪዎች በአከራካሪው ቤት የማይኖሩበት እና ለ3ኛ ወገን ማስተላለፋቸው የተረጋገጠ በመሆኑ
በመመሪያው መሰረት መንግስት ቤቱን መረከብ ይችላል፤ተጠሪዎች ውል ሳይዋዋሉ የቀሩት ክርክር
በተነሳበት ቤት ውስጥ ስለማይኖሩበት እንጂ በአመልካች ችግር አይደለም፤ 2ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ
የተከራይነት መብት እንደሌላት አረጋግጠናል፤ ተጠሪዎች ውሉን ያላሳደሱት በአመልካች ምክንያት ስለመሆኑ
አልተረጋገጠም፤ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለክርክር መነሻ የሆነው የመንግስት የኪራይ ቤት ተጠሪዎች በቤቱ
ውስጥ የማይኖሩ እና ለሌሎች 3ኛ ወገኖች ያስተላለፉ መሆናቸው ተገልጾ ባለበት በአመልካች የተሰጠው
ማስጠንቀቂያ ሁከት ፈጥሯል በሚል የተወሰነበት አግባብነት ከመመሪያ ቁጥር 5/2011 አንፃር ለመመርመር
ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪዎችም ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ
ተደርጓል፡፡

የተጠሪዎች መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች 1ኛ ተጠሪ ኑሮአቸው በአሜሪካ እና በ3ኛ ወገን እጅ ለመሆኑ
በምስክር ተረጋግጦ ማስጠንቀቂያ ሰጠን በማለት የሚያቀርበው ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያላቀረበው አዲስ
ክርክር በመሆኑ ውድቅ ሊደረግ ይገባል፤ 2ኛ ተጠሪ የነዋሪነት ማስረጃ ያቀረበች እና በአከራካሪው ቤት
ውስጥ እንደምትኖር ተረጋግጧል፤1ኛ ተጠሪ ቤቱን ያልተዋዋሉት በአመልካች ምክንያት ስለመሆኑ
ተረጋግጧል፤1ኛ ተጠሪ ሚስትነት ያረጋገጠችበትን ማስረጃ ቀርቦ እያለ አመልካች ከመመሪያው ውጪ
ውሉን ለማማዋል ፍቃደኛ አልሆነም፤ሟች በመካኒሳ አካባቢ ይኖር እንደነበር አልተረጋገጠም፤1ኛ ተጠሪ
ለህክምና ውጪ ሄደው እስከሚመለሱ የኪራይ ውሉን ለመዋዋል ለልጃቸው ውክልና ሰጥተው ባለበት ቤቱን
በአደራ አላስረከቡም በሚል ሚያቀርበው ክርክር ተገቢነት የለውም፤ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት
ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት የአሁን 1ኛ ተጠሪ አቅርበውት የነበረው ክስ የሁከት ሆኖ ባለቤታቸው


ተከራይተውት የነበረውን ቤት ባለቤታቸውን ውጭ ለማሳከም በሄዱበትና በሞት ተለይተው እያለ እሳቸውም
በሕክምና ላይ በመሆናቸው በወኪል እንዲያዋውለኝ ጠይቄ ሊያዋውለኝ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ እንድለቅ
ማስጠንቀቂያ የተሰጠ መሆኑ ሁከት በመሆኑ ሁከት ይወገድልኝ በሚል ሲሆን አመልካችም በበኩሉ በቤቱ
ላይ ከኪራይ ውልም ሆነ ከህግ የመነጨ መብት እና ጥቅም የላትም፤ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት 1ኛ
ተጠሪ ለቃ ባለቤቷን ለማሳከም ወደ ውጪ ሀገር የሄዱ በመሆኑ የሚያምኑ በመሆኑ በእጃቸው ይዘው
በእውነት የሚያዙበት አይደለም፣ በእውነት የማያዙበት ወይም መደበኛ ኑሮ የማይኖሩበት ከሆነ ደግሞ
ሁከት ተፈጽሮብኛል ብለው ክስ ሊያቀርቡ አይችሉም፣ቤቱን በአደራ ለመንግሥት ከማስረከብ ይልቅ ከህግ
ውጭ በተወካይ የኪራይ ውል አዋውሉን ማለታቸው አልካደችም፤ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን በእውነት በእጇ ይዘው
የሚያዙበት አይደለም፤ 1ኛ ተጠሪ በመመሪያው መሰረት ለሚመለከተው አካል በአደራ ማስረከብ ሲገባት
ከህግ ውጪ በተወካይ የኪራይ ውል አዋውሉን ማለታቸው ህገወጥ ተግባር ነው፤የአሁን አመልካች ከአንድ
ከተማ ወደ ሌላ ከተማ በሚሄዱበት ጊዜ በርክክብ ሰነድ ለሚመለከተው መንግሥት አካል ማስረከብ ሲገባቸው
ከህግ ውጭ ሳያስክቡ በመሄዳቸው ባለቤታቸው ከሞቱ ሚስትነታቸውን አረጋግጠው መመሪያ ቁጥር 5/2ዐዐ9
አንቀጽ 15/1/ሀ/ አዲስ ውል መዋዋል ሲገባቸው ያለኪራይ ውል እና የስም ዝውውር ሣይፈጽሙ ቤቱን
መያዛቸውን መሠረት በማድረግ ቤቱ እንደሚታሸግ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አስተዳደራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ
እየተወጣ እዳ የሁከት ተግባር አይደለም የሚል ነው፡፡
ከአጠቃላይ ክርክሩ ከማስቀረቢያ ነጥቡ አንፃር በጭብጥነት ተይዞ ሊመረመር የሚገባው 1ኛ ተጠሪ
የሚያከራክረውን ቤት የመከራየት መብት አላቸው የላቸውም የሚለውን ከመመሪያ ቁጥር 5/2ዐ11 አንፃር
ሊመረመር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 329/1/ እንደደነገገው፡- “ በዚህ ሕግ በቁጥር 345 የተደነገገው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ


በጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ያልተነሳውን ክርክርና ያልቀረበውን አዲስ ነገር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት
ለመቀበል አይችልም፡፡” ይላል፡፡

አመልካችም ለህክምና ወደ ውጭ መሄዳቸውን ገልፀው 1ኛ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ሲከራከሩ ሙሉ ለሙሉ


ኑሯቸውን በውጭ አድርገዋል በሚል ያልተከራከረና ይህን የሚያሳይም ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ
በውጭ አገር ለመኖር ስለማሄዳቸው በስር ፍ/ቤት ሳይከራከር በሰበር ደረጃ የሚያነሳው ክርክር ተቀባይነት
የሌለው ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መመሪያ ቁጥር 5/2011 አንቀጽ 16/1/ሀ በግልጽ የሚደነግገው “ የቀበሌ ቤትን የተከራየ ማንኛውም ሰው
በሞት ሲለይ ወይም ከአካባቢው በተለያየ ምክንየት ሲለቅ ቤቱን ለቢሮው እንዲመልስ ይደረጋል፣ ሆኖም
ሟች በተከራየው ቤት ውስጥ የሚከተሉት፡-
ሀ. የተከራዩ ባል ወይም ሚስት ለመሆኑ ሕጋዊ የጋብቻ ማስረጃ ሲቀርብ፣ ----” በሚል የቀበሌ ቤትን
ማስተላለፍ እንደሚቻል ይደነግጋል፡፡

1ኛ ተጠሪ እና ሟች ባለቤታቸው በዚህ በሚያከራክረው ቤት ውስጥ በጋብቻ አብረው ሲኖር የነበረ ስለመሆኑ
አመልካች በመካድ የሚከራከር ሳይሆን ሟች የቤቱ ተከራይ የነበሩ እና እሳቸው መሞታቸውን ነገር ግን 1ኛ
ተጠሪ በወኪል ውል አዋውለኝ ብለውት በወኪል መዋዋል የማይቻል መሆኑን በመግለጽ እምቢተኝነቱን
የገለፀና በቤቱ ውስጥም ሌሎች ሰዎች እየኖሩበት ያሉ መሆኑን በማንሳት ቤቱን አስረክበው መሄድ
ነበረባቸው የሚል ክርክር ነው የሚያቀርበው፡፡
በሚያከራክረው ቤት ውስጥ ያሉት ሰዎች በምስክርነት ቀርበው 1ኛ ተጠሪ ባለቤታቸውን ሊያሳክሙ ሄደው
ባለቤታቸው በሞት የተለዩና አ/አ/ አምጥተው የቀበሩ መሆኑን፣ እሳቸውም ለህክምና ውጭ አገር
መሆናቸውን በመግለጽ የመሰከሩ ሲሆን በቤት ውስጥ እየኖሩ ያሉት ቤቱን 1ኛ ተጠሪ አስተላልፈውላቸው
ስለመሆኑ አልተረናጋገጠም፡፡

በመመሪያ ቁጥር 5/2ዐ11 አንቀጽ 14/1 በማንሳት ውሉን ተጠሪ አላሳደሱም በመሆኑም እንዲለቁ
መስጠንቀቂያ መስጠቴ ተገቢ ነው በሚል ያነሳውን ክርክር በተመለከተም ህጉ ያስቀመጠው ውል ሳያሳድሱ
የኪራይ ቤትን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን እንጂ እንደ 1ኛ ተጠሪ ያሉ ውል በውክልና ይታደስልኝ ብለው
አመልክተው ተቀባይነት ያጡትን የሚመለከት አይደደም፡፡ በሌላ በኩል እንዲሁ በመመሪያው አንቀጽ 49
መሠረት የመንግሥት ቤትን ለ3ኛ ወገን ያስተላለፉ ግለሰቦችን በሚመለከት የተደነገገውን ድንጋጌ ተጠሪ ቤቱ
ላይ ወኪል አድርገው ለህክምና የሄዱ ግለሰቦችን በሚመለከት መልኩ የተቀረፀ ባለመሆኑ እንዲሁ
የአመልካች ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም፡፡
በመሆኑም የስር ፍ/ቤት የሚያከራክረው ቤት ላይ የመከራየት መብት አላቸው በሚል ሁከት እንዲወገድ
የሰጠው ውሣኔም ሆነ የበላይ ፍ/ቤቶች የስር ፍ/ቤት ውሣኔን ማጽናታቸው ህግና መመሪያን መሠረት
ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት የማያበቃ በመሆኑ ሊፀና
ይገባል በሚል ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ
1. የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 32235 መስከረም 5 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. በዋለው
ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ፣ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 31644 መጋቢት 16 ቀን 2ዐ12
ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ እና የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/
ዐ22929 ህዳር 25 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ፀንቷል፡፡.

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡


መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰ/መ/ቁ፡-197405

ቀን፡- 29/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1ኛ. የቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 አስተዳደር ጽቤት አልቀረቡም

2ኛ. የቂ/ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽቤት

ተጠሪ፡- የኢትዮጵያና ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት- ነ/ፈጂ ወይንሸት እንድሪስ ቀረቡ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም
በተፃፈ ማመልከቻ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 247606 ግንቦት 17
ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ
ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፀው በሰበር ችሎት ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረቡት
ማመልከቻ መነሻነት ነው፡፡አመልካቾች በስር በፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ተከሳሾች የነበሩ
ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ ተጠሪ በኢትዮጵያ ጅቡቲ መንግስት መካከል
በተደረገው ዓለም አቀፍ ስምምነት መሰረት በተቋቋመ የሁለቱ መንግስታት ንብረት የሆነ የዓለም አቀፍ
ድርጅት ሲሆን በሁለቱ መንግስታት የመሬት ይዞታ ተለክቶ ተሰጥቶታል፡፡በአዋጅ ቁ. 47/67 አንቀጽ
43 እና 5 (3) መሰረት የዓለም አቀፍ ድርጅት ቦታ የማይወረስ ሲሆን የተጠሪ ቤትና ይዞታ ያልተወረሰ
መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤም በወቅቱ ከነበረው የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር ተሰጥቶታል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ለአጣደፊ ስራ ለሚፈልጉ ሰራተኞች ቤት ስለሚሰጥ በቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘውን የቤት


ቁጥር 159 ለአቶ ነጋሽ ተፈራ ሰጥቶ ነበር፡፡የእኚህ ግለሰብ የስራ ግንኙነት በሞት ምክንያት የተቋረጠ
ሲሆን በህይወት እያሉ ቤቱን ከሕግና ከድርጅቱ አሰራር ውጪ ኃ/ማሪያም አስራት ለተባለ ሰው
አስተላልፈው አቶ ኃ/ማሪያም አስራት ደግሞ ቤቱን የቀበሌ በማስመሰል በወቅቱ ከአመልካቾች ጋር
ውል ተዋውሏል፡፡ግለሰቡ አሁን በህይወት የሌለ ሲሆን ወራሾች ኮንዶሚንያም ደርሷቸው ወረዳው ቤቱን
ተረክቦ አሽጎት በነበረ ጊዜ ጥቅምት 27/2010 ዓ.ም ቤቱን እንዲያስረክቡ ማስጠንቀቅያ ቢሰጣቸውም
ለማስረከብ ፈቃደኛ አይደሉም፡፡በመሆኑም አመልካቾች በአዋጁ ያልተወረሰ ቤት የያዙ ስለሆነ ቤቱን
እንዲያስረክቡ ይወሰንልን በማለት አመልክተዋል፡፡

አመልካቾች መቃወሚያ አቅርበው ፍርድ ቤቱም መቃወሚያዎቹን መርምሮ ውድቅ በማድረግ ብይን
የሰጠ ሲሆን በፍሬ ጉዳዩ ላይ በሰጡት መልስም የቤት ቁጥር 159 በአዋጅ ቁ.47/67 መሰረት ተወርሶ
መንግስት የሚያስተዳድረው የመንግስት ቤት ነው፡፡ የተወረሰውም ከአቶ ነጋሽ ተፈራ ላይ ሲሆን ቤቱ
ለአቶ ኃ/ማሪያም አስራት ተከራይቶ ቆይቶ አሁንም ለሌለ ሰው ተከራይቶ ያለ ነው፡፡ስለዚህ የተጠሪ ክስ
ውድቅ ይደረግልን በማለት ተከራክረዋል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር እና የቀረበውን የሰነድ ማስረጃ መርምሮ በሰጠው
ውሳኔም ተጠሪ አለም አቀፍ ድርጅት ሆኖ በሁለቱ መንግስታት ተለይቶ የተሰጠውን ይዞታ
የሚያመለክት የአየር ካርታና በዚህ በተለየው ቦታ ውስጥ የሚገኙትን ቤቶች ዝርዝር ያቀረበ
መሆኑን፤ተጠሪ ለንብረቱ ካርታ ማቅረብ የማይጠበቅበት መሆኑን በሰበር መዝገብ ቁጥር 21684
ከተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ መገንዘብ የሚቻል መሆኑን፤አከራካሪውን ቤት በተመለከተ ከአቶ አስራት
ኃ/ማሪያም ጋር የኪራይ ውል በማድረግ የአስተዳደር አካሉ ኪራይ ሲሰበስብበት የነበረ ቢሆንም
አመልካቾች ለተጠሪ ተለይቶ የተሰጠው ይዞታ የለም ይህ ቤትም በዚህ በተለየ ይዞታ ውስጥ አይገኝም
በተጠሪም አልተሰራም በማለት ያቀረቡት ክርክር ባለመኖሩና ባለንብረትነትን የሚያፀድቀው የስራና
ቤት ሚኒስቴር ለተጠሪ በተሰጠው ክልል ውስጥ ያለ ይዞታና ንብረት ሊወረስ እንደማይችል፤የተወሰደ
ይዞታና ንብረት ካለም እንዲመለስለት የተፃፈውን ደብዳቤ በማቅረብ ያስረዳ ስለሆነ አመልካቾች
ክርክር የቀረበበትንና በቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘውን የቤት ቁጥር 159 ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል
በማለት ወስኗል፡፡ይህ ውሳኔ ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፀንቷል፡፡

አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ባቀረበው
ክስ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንፃር ያቀረቡት ክርክር የፌደራል ቤቶችን ለማቋቋም በወጣው ሕግ አዋጅ
ቁጥር 25/88 አንቅጽ 11(2) መሰረት ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት በመሆኑ ጉዳዪን የማየት የስረ
ነገር የዳኝነት ስልጣን ያለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆኖ ሳለ የስር የመጀመሪ ደረጀ ፍርድ
ቤት ከፍርድ ቤቱ የስረ ነገር ስልጣን የዳኝነት ስልጣን ሳይኖረው የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የተፈፀመበት ነው፤ አከራካሪው የቤት ቁጥር 159 የሆነው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት
የተወረሰ በመሆኑ አስተዳደሩ ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ጉዳዮች በአዋጅ
ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41 መሰረት የከተማ የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የስረ ነገር የዳኝነት
ስልጣን ያለው ስለመሆኑ ጠቅሰን ለፍርድ ቤቱ ያቀረብነውን አቤቱታ አልፎ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ
የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤ ተጠሪ ክርክር ባስነሳው ቤት ላይ ያቀረበው ቃለ ጉባኤ ፤የአየር ካርታ
፤ዓለም አቀፍ ስምምነት ክርክር ባስነሳው ቤት መብት ያለው ስለመሆኑ ያቀረበው የቤት ባለቤትነት
ማስረጃ ወይም የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በሌለበት ባለመብት መሆኑን የሚያሳይ ባልሆነበት
የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረበውን ክስ ተቀብሎ የሰጠው ውሳኔ የማስረጃ መርህ ያልተከተለና
መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ስለሆነ ሊሻር ይገባል በማለት አመልክተዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለክርክር መነሻ የሆነው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 በመንግስት የተወረሰ ስለመሆኑ በተገለፀበትና ተጠሪ
የቤቱ ባለቤት ሆነው ለአቶ ነጋሽ ተፈራ ያስተላለፉት ስለመሆናቸው ተረጋግጧል በሚል አመልካቾች
ቤቱን ለተጠሪ እንዲያስረክቡ የተወሰነበትን አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ
በኋላ ተጠሪ መጥሪያ ደርሶት መልስ እንዲያቀርብ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ በሰጠው መልስም አንድ ክርክር በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 11(2)(ሀ) መሰረት ለፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊቀርብ የሚችለው ድርጅቱ አለም አቀፍ ስለሆነ ሳይሆን ጉዳዩ የአለም አቀፍ ህግን
የሚመለከት ሆኖ ሲገኝ በመሆኑ፤የከተማ አስተዳደሩን ፍርድ ቤት ስልጣን አስመልክቶም ፍርድ ቤቱ
በጉዳዩ ላይ ስልጣን የሚኖረው የከተማው አስተዳር ስለመሆናቸው ክርክር ባልቀረበባቸው
የይዞታ፤የኪራይና ተመሳሳይ ክርክሮች ላይ በመሆኑ አመልካቾች ይህንን በተመለከተ ያቀረቡት የሰበር
አቤቱታ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፤አመልካቾች ክርክር የተነሳበትን ቤት አከራይቼ ይኖሩ ነበር
ያላቸው አቶ ኃ/ማሪያም አስራት ሲሞቱ ባለቤታቸው ወ/ሮ እቴነሽ ነጋሽ ቤቱ የተጠሪ መሆኑን አውቀው
ቤቱን እንድንረከባቸው ለተጠሪ ድርጅት የፃፉትን ደብዳቤ ለስር ፍርድ ቤት አያይዘን
አቅርበናል፤ከዚህም በተጨማሪ የተጠሪ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ሊወረሱ እንደማይችሉ
የስራና ከተማ ልማት ቤት ሚኒስቴር የፃፈውን ማስረጃ በማቅረብ ክርክራችንን ያስረዳን ስለሆነ ይህም
ክርክር የተነሳበት ቤት በሕግ አግባብ ያልተወረሰ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ እያለ አመልካቾች የቤት
ቁጥር የማይገልጽ ተዓማኒነት የጎደለውን ቅጽ በማቅረብ ቤቱ ተወርሷል ለማስባል ያቀረቡት ማስረጃ
እና መከራከሪያ ፍፁም ከእውነት የራቀ እና በሕግ የተደገፈ ስላልሆነ ፍርድ ቤቱ አመልካቾች
ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊያፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፣፣

አመልካቾች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡አመልካቾች
ከስር ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን አንፃር ሁለት ክርክሮችን ያቀረቡ ሲሆን የመጀመሪያው አዋጅ ቁጥር
25/88 አንቀፅ 11(2) ን መሰረት ያደረገ ሆኖ ተጠሪ ከአለም አቀፍ ህግ አንፃር ያቀረበውን ክርክር
የማየት ስልጣኑ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆኖ እያለ የስር ፍርድ ቤት ተቀብሎ ማስተናገዱ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን በመጥቀስ የቀረበ ነው፡፡ተጠሪ በኢትዮጲያና ጅቡቲ
መንግስታት መካከል በተደረገ ስምምነት መሰረት የተቋቋመ የሁለቱም መንግስታት ንብረት የሆነ
ድርጅት መሆኑ ግራ ቀኙ የተማመኑበት ነጥብ ነው፡፡

የግል አለም አቀፍ ህግን የሚያስነሱ ጉዳዮችን የማስተናገድ ስልጣን የተሰጠው ለፌደራል ከፍተኛ
ፍርድ ቤት ስለመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 11(2)(ሀ) ድንጋጌ ተመልክቷል፡፡በዚህ
ድንጋጌ መሰረት ጉዳዩ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር እንዲወድቅ የሚያደርገው
መሰረታዊ ጉዳይ ተጠሪ በኢትዮጲያና ጅቡቲ መንግስታት መካከል በተደረገ ስምምነት መሰረት
የተቋቋመ የሁለቱም መንግስታት ንብረት የሆነ ድርጅት መሆኑ ሳይሆን ለክርክር የቀረበው ጉዳይ
የሁለቱን ሀገሮች ህጎችን ገፋ ሲልም የአለም አቀፍ ህግን የተፈፀሚነት ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ ሲገኝ
ነው፡፡(በተመሳሳይ ጉዳዮች በሰበር መዝገብ ቁጥሮች 100290፤152590 እና በሌሎች ተመሳሳይ
መዝገቦች የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ይመለከቷል፡፡)

አሁን በያዝነው ጉዳይ በግራ ቀኙ መሃል የተያዘው ጉዳይ የሁለቱን ሀገሮች ህጎችን አልያም የአለም
አቀፍ ህግን የተፈፀሚነት ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ በዚህ አግባብም እነዚህ ህጎች ለክርክር የቀረበውን
ጉዳይ የሚፈቱበትን አግባብ መለየትን፤ለክርክር የቀረበውን ጉዳይ በመፍታት ረገድ በእነዚህ ሀገር
ህጎችና አለም አቀፍ ህግ መሃል አለመጣጣም መኖር አለመኖሩን መለየትን፤አለመጣጣም የሚኖር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከሆነም አለመጣጣሙ የሚፈታበትን አግባብ መለየትን በመጨረሻም ለጉዳዩ አወሳሰን አግባብነት


ያለውን ህግ መምረጥን የሚጠይቅ የክርክር አመራር ሁኔታ ባልተፈጠረበት ከዚህ ይልቅ በግራ ቀኙ
መሃል ያለው የመፋለም ክርክር የሌሎች ህጎችን የተፈፀሚነት ጥያቄ የማያስነሳ በሀገራችን የንብረት
ህግና ሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች አግባብ እልባት የሚያገኝ ሆኖ እያለ ተጠሪ በኢትዮጲያና ጅቡቲ
መንግስታት መካከል በተደረገ ስምምነት መሰረት የተቋቋመ የሁለቱም መንግስታት ንብረት የሆነ
ድርጅት ስለሆነ ብቻ አመልካቾች በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 11(2)(ሀ) መሰረት ፍርድ ቤቱ
ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም በማለት መከራከራቸው ከላይ በተመለከተው አግባብ ለአዋጁ አንቀፅ
11(2)(ሀ) የተሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም መሰረት ያደረገ ሆኖ አላገኘነውም፡፡

አከራካሪው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሰ ሆኖ አስተዳደሩ የሚያስተዳድረው በመሆኑ


በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41 መሰረት በጉዳዩ ላይ የዳኝነት ስልጣን ያለው አስተዳደሩ
ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ጉዳዮችን የማየት ስልጣን የተሰጠው የአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ነው በማለት አመልካቾች ከፍርድ ቤቱ ስልጣን ጋር
በተያያዘ ያቀረቡትን መቃወሚያ በተመለከተ በግራ ቀኙ መሃል ያለው ክርክር የቤት ቁጥር 159
የሆነው ቤት ይገባኛል በሚል የቀረበ የመፋለም ክርክር መሆኑ ግራ ቀኙ የተማመኑበት ነጥብ ነው፡፡
በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41(1)(ረ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የከተማ
አስተዳደሩ ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች ጋር በተያያዘ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የሚኖራቸው የቤቱ
ባለቤትነት የከተማው አስተዳደር ስለመሆኑ ክርክር ሳይኖርበት ከባለቤትነት በመለስ የሚነሱ ክርክሮችን
አስመልክቶ ነው፡፡(በሰበር መዝገብ ቁጥሮች 32376፤33841 እና በተመሳሳይ መዝገቦች ላይ የተሰጠውን
አስገዳጅ የህግ ትርጉም ይመለከቷል፡፡)ይህ ከሆነ ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ፍርድ ቤቶች
ግራ ቀኙ በሚያካሂዱት የመፋለም ክርክር ላይ የዳኝነት ስልጣን አላቸው ሊባል የሚችልበት የህግ
አግባብ ባለመኖሩ አመልካቾች ከፍርድ ቤቱ የዳኝነት ስልጣን ጋር በተያያዘ ያቀረቡትን መቃወሚያ
አልተቀበልነውም፡፡

ግራ ቀኙ በፍሬ ጉዳዩ ያቀረቡትን ክርክር በተመለከተ ተጠሪ ለንብረቱ ካርታ ማቅረብ የማይጠበቅበት
ህዝባዊ ድርጅት ከመሆኑ አንፃር በሁለቱ መንግስታት ተለይቶ የተሰጠውን ይዞታ የሚያመለክት የአየር
ካርታና በዚህ በተለየው ቦታ ውስጥ የሚገኙትን ቤቶች ዝርዝር ያቀረበ መሆኑ ማስረጃን
የመስማት፤የመመርመርና የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ነጥብ ሲሆን ፤
ለተጠሪ ተለይቶ የተሰጠው ይዞታ የለም ይህ ቤትም በዚህ በተለየ ይዞታ ውስጥ አከራካሪው ቤት
አይገኝም ቤቱ በተጠሪም አልተሰራም በማለት አመልካቾች ክርክር ባላቀረቡበት፤ይህም አከራካሪው ቤት
በተጠሪ የተሠራና ለተጠሪ ተለይቶ በተሰጠው ይዞታ ውስጥ የሚገኝ ለመሆኑ በአመልካቾች የታመነ
መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ እያለ፤ ባለንብረትነትን የሚያፀድቀው የስራና ቤት ሚኒስቴር ለተጠሪ በተሰጠው
ክልል ውስጥ ያለ ይዞታና ንብረት ሊወረስ እንደማይችል፤የተወሰደ ይዞታና ንብረት ካለም
እንዲመለስለት የፃፈው ደብዳቤ መቅረቡም ተጠሪ በአከራካሪው ቤት ላይ ከአመልካቾች የተሻለ መብት
ያለው መሆኑን እንዳስረዳ የሚያሳይ በመሆኑ፤ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀፅ 12(2) መሰረት
የከተማ ቤት ባለንበረትነትን በወቅቱ በነበረው አወቃቀር የሚያፀድቀው የስራና ቤት ሚኒስቴር የአዋጁን
አንቀፅ 43 በመጥቀስ እና በሁለቱ ሀገሮች መሀከል የተደረገውን ስምምነት በመጥቀስ ለተጠሪ የተሰጠው
ይዞታ ውስጥ የሚገኝ ይዞታና ንብረት ሊወረስ እንደማይገባ ፤የተወሰደ ንብረትና ይዞታ ካለም ሊመለስ
እንደሚገባ መግለፁ በስር ፍርድ ቤቶች መረጋገጡ አመልካቾች አከራካሪው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67
ተወርሶ የሚያስተዳድሩት መሆኑን በመግለፅና ቅፅ 003 እና ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎችን በማቅረብ
በቤቱ ላይ የሚያቀርቡት ክርክር አዋጁንና አዋጁን መሰረት በማድረግ የተፃፈውን የስራና ቤት
ሚኒስቴር መግለጫ መሰረት ያላደረገ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ይህም የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን
በመስማት በመመርመርና በመመዘን የደረሱበት መደምደሚያ ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን ህጎች እና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሰረታዊውን የማስረጃ ምዘና መርህ መሰረት ያደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት መሆኑን
ስለሚያሳይ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ
1. የፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.60123 በቀን 24/02/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት
አመልካቾች አከራካሪውነን ቤትን ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት የሰጠው ፍርድ እና
ይህንን ፍርድ በማፅናት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.247606 በቀን 17/09/2012 ዓ.ም
በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
2. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስለገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ 197432
ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ

ተጠሪ፡- መልካሙ ዳታ ደሴ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 192545 ሐምሌ 27 በቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው
ነው፡፡

ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን አመልካች
በአሁን ተጠሪ ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 670
ድናጋጌን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሡ ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ በቀን
08/03/2012 ዓ.ም ከሌሊቱ በግምት 11፡00 ሠዓት ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ክልል ልዩ ቦታው
ሸገር ሕንጻ አካባቢ በሚገኘው የግል ተበዳይ አቶ ብሌን ጎይትኦም ብርክሰትን ክለብ ውስጥ አበባየሁ ከተባለው
ካልተያዘ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን የበሩን ቁልፍ ፈልቅቀው በመግባት ክለብ ውስጥ የነበረውን 2ኛ
የዓቃቤሕግ ምስክር ቃለአብ ቱፋን በተኛበት መጥተው ተጠሪ ቢላዋ በመያዝ ከተንቀሳቀስክ እወጋሃለሁ
በማለት ካስፈራራው በኋላ አፉን በፎጣ ሲያፍነው ያልተያዘው ግብረአበሩ ደግሞ በሲባጎ ገመድ አንገቱን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አንቆ ከአልጋው ብረት ጋር በማሰር ራሱን እንዲስት ካደረጉ በኋላ አጠቃላይ ግምቱ ብር 202,000.00 /
ሁለት መቶ ሁለት ሺሕ / የሆነ የሙዚቃ ማጫወቻ ሚክሰር፤ የሙዚቃ ማጫወቻ፤ ላፕሮፕ እና ሞባይል
በመውሰድ ከተሰወሩ በኋላ በክትትል ተይዞ በምሪት የተገለጹት ንብረቶች ተመላሸ በማድረግ በፈጸመው
የውንብድና ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡

ተጠሪ ክሱ ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ክሱን ሳይቃወም የእምነት ክሕደት ቃሉን ሲጠየቅ ዕቃዎቹን
የወሰድኩት ድርጅቱ የሠራሁበትን የአምስት ወር ደመወዝ እና የሁለት ዓመት የአገልግሎት ክፍያ
ስለከለከለኝ ነው በማለት መብቱን ጠብቆ ቃሉን መስጠቱ ፍርድ ቤቱ በክሕደት መዝግቦ የዓቃቤ ሕግን
ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተጠሪ የወንጀል ድርጊቱን መፈጸሙ የተመሰከረበት በመሆኑ ክሱን እንዲከላከል ሲል
ብይን ሰጥቷል፡፡ ተጠሪም መከላከያ ማስረጃ የሌለው መሆኑን በመግለጹ ፍርድ ቤቱ ተጠሪን በወንጀል ሕግ
አንቀጽ 670 መሠረት ጥፋተኛ ብሎ በአራት ዓመት ከአምስት ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ አቅርቧል፡፡
ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ በዓቃቤሕግ ምስክሮች በኩል ሳይቀር
የተነገረው ተጠሪ በግል ተበዳይ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ እንደነበር እና በወቅቱም ከስራ ተሰናብቶ
ባለበት ወቅት ያልተከፈለው ደመወዝ ክፍያ የነበረው መሆኑን ነው፤ ተጠሪ ወሰደ የተባለውን ንብረት ሙሉ
ለሙሉ ለግል ተበዳይ የመለሰ ስለመሆኑም አልተካደም፤ ይህም የሚያሳየው የግል ተበዳይን ንብረት ሕገወጥ
በሆነ መንገድ የወሰደው ውንብድና ለመፈጸም ሳይሆን ያልተከፈለውን ክፍያ ለማስፈጸም ስለመሆኑ ግልጽ
በመሆኑ ተጠሪ የነበረው የወንጀል ሐሳብ ውንብድና ሳይሆን መብቱን በሕገወጥ መንገድ ማስከበር ወንጀል
ነው በማለት ጥፋተኛ የተባለበትን የሕግ አንቀጽ ቀይሮ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 431/ለ / ይህ አንቀጽ
በስሕተት የተጠቀሰ እና አንቀጽ 436/ለ ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ ግንዛቤ ተወስዶበታል / መሠረት ጥፋተኛ
ብሎ በስድስት ወር ቀላል እሥራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- የወንጀል ድርጊቱ በተፈጸመበት ጊዜ ተጠሪ ከስራ ተሰናብቶ እንደነበር እና ያልተከፈለው ደመወዝ
እንደነበረው የተሰጠ የምስክርነት ቃል የለም፤ ተጠሪ ንብረቱን ለግል ተበዳይ መመለሱ የውንብድና ወንጀል
ለመፈጸም ሀሳብ እንደሌለው ያሳያል መባሉም ተገቢ አይደለም፤ የተወሰደውን ሐብት የመመለስ ጉዳይ
በአድራጊው ፈቃደኝነት የተፈጸመ ቢሆንም የተፈጸመውን ወንጀል አያስቀረውም፤ ተጠሪ ንብረቱን የመለሰው
በራሱ ፈቃደኝነት ሳይሆን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ነው፤ ስለሆነም እነኚህ ሁኔታዎች ከግንዛቤ
ሳይገቡ በስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 670 ሥር የተመለከተውን ወንጀል
በመተላለፍ የውንብድና ወንጀል የፈጸመ ስለመሆኑ በተገለጸበት ሁኔታ በሕገ ወጥ መንገድ መብቱን
ለማስከበር የተደረገ ድርጊት ነው በሚል በወንጀል ሕግ አንቀጽ 436/ለ ጥፋተኛ የመባሉን አግባብነት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ
ተደርጎለት ስላልቀረበ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፏል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይሕ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

በመሠረቱ አንድን ሰዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 670 የተመለከተዉን የዉንብድና ተግባር ፈጽሟል ብሎ


ጥፋተኛ ለማድረግ ድርጊቱ ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት አስቦ፤
የሌላ ሰዉ ንብረት የሆነዉን ተንቀሳቃሽ ዕቃ ለመዉሰድ እንዲያመቸዉ ወይም በሚወስድበት ጊዜም ሆነ
ከወሰደ በኃላ የገጠመዉን ተቃዉሞ ዉጤታማነት ለማስቀረት ሲል በሌላ ሰዉ ላይ የኃይል ድርጊት ወይም
ከባድ የሆነ የማንገላታት ተግባር ወይም ዛቻ የፈጸመ ወይም በማናቸዉም ሌላ መንገድ ይህንን ሰዉ
ለመከላከል እንዳይችል ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤት በስር ፍርድ
ቤት የተሰሙትን የዓቃቤሕግ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል መርምሮ እና መዝኖ ተጠሪ ድርጊቱን
የፈጸመው በተከሰሰበት ድንጋጌ ላይ የተገለጹትን የወንጀል ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች መሠረት ሳይሆን
ያልተከፈለውን ደመወዝ ለማስከፈል ስለመሆኑ አረጋግጧል፡፡ ስለሆነም የአመልካች አድራጎት የወንጀል ሕግ
አንቀጽ 670 ድንጋጌን የሚያቋቁም አይሆንም፡፡
በሌላ በኩል ተጠሪ የሀይል ተግባር በመጠቀም የራሱ ያልሆነውን ንብረት የወሰደ ስለመሆኑ የተረጋጠ
በመሆኑ ጥፋተኛ ሊባል የሚገባው አድራጎቱ ሊሸፍነው በሚገባው የሕግ አንቀጽ ሥር ነዉ፡፡ የተጠሪን
አድራጎት የሚሸፍነዉ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 436/ለ ማንም ሰው መብት ሳይኖረው ወይም ሕግን ተቃራኒ
በሆነ መንገድ ሊከፈለው የሚገባውን ክፍያ ለማግኘት ሲል የባለዕዳው ንብረት የሆነውን ማናቸውንም
ተንቀሳቃሽ ዕቃ የወሰደበት እንደሆነ ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እሥራት ይቀጣል በማለት
ይደነግጋል፡፡

በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ አልተከፈለኝም የሚለውን ክፍያ እንዲከፈለው ለማድረግ ሲል ድርጊቱን የፈጸመ
በመሆኑ ጥፋተኛ ሊባል የሚገባው አድራጎቱ በሚሸፍነው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 436/ለ ድንጋጌ ነው፡፡
ስለሆነም የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህንኑ መሠረት በማድረግ ተጠሪን በወንጀል ሕግ አንቀጽ
436/ለ መሠረት ጥፋተኛ በማለት ቅጣቱን አሻሽሎ መወሰኑ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ
መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አልተፈጸመበትም፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 192545 ሐምሌ 27 በቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሠረት ጸንቷል፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሰ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የሰ/መ/ቁጥር 198071
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሀምሌ 27 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡-እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ፡- ቀረቡ

ተጠሪ ፡- አቶ ወርቁ ዋበሎ፡- አልቀረቡም

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርምራ ሲሆን በዚህ አግባብም ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ቦታን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው
የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች አከራካሪውን ይዞታ በመልቀቅ ለተጠሪ ሊያስረክብ ይገባል
በማለት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ስላመለከቱ ነው፡፡አመልካች በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር
ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪ የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ውስጥ
የተጠቀሰውን በቢቾ ቀበሌ የሚገኘውን ይዞታ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በስጦታ አግኝቼ ቆርቆሮ ቤት ሰርቼ
የምጠቀምበትን በ2008 ዓም በተደረገው ህገ ወጥ ይዞታን ስርአት የማስያዝ አሰራር ይዤ ካለሁበት 6
ሜትር መንገድ በመውሰዱ ወደ አመልካች ይዞታ ውስጥ ሲያስገባኝ አመልካችም ከኋላ ለኔ ለቅቆ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወደፊት እንዲሸጋሸግ ሲደረግ ለኔ በተሰጠኝ ይዞታ ላይ ቤት ገንብቶ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆነ በራሱ
ወጪ አፍርሶ እንዲለቅልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዲሰጡ በታዘዙት መሰረት አመልካች በሰጡት መልስም ለተጠሪ ተለክቶ
ድንጋይ ተተክሎ 200 ካሜ የሰጠ አካል ስለሌለ ፤አመልካች ከአቶ አለማየሁ ቃልቤ 260 ካሜ በውል
አግኝቼ ቤት ሰርቼና ንብረት አፍርቼ ባለሁበት በ2008 ዓም ሽንሻኖ ሲደረግ በአካባቢው ካለው ችግር
አንፃር ባለንበት እንድንቆይ ከማድረግ ባለፈ ድንጋይ ተተክሎ ተለክቶ የተሰጠ ይዞታ ባለመኖሩ የተጠሪ
ክስ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በአካል ቦታው ተገኝቶ ምልከታ
አድርጎ ተገቢውን ማጣራት አድርጎ በሰጠው ውሳኔም የአመልካች ምስክሮች በስፍራው ምንም አይነት
ሽንሸና አለመደረጉን ሁሉም እንደያዘ እንዲቆይ የመንገድ መለያ ድንጋይ ብቻ ተተክሎ መታለፉን
ማስረዳታቸውን፤በምልከታም ይኸው መረጋገጡን፤ማዘጋጃ ቤቱ በሰጠው ምላሽም ግራ ቀኙ በህገ ወጥነት
ይዞታውን የያዙ ሆኖ ሰነድ እየተጠባበቁ ያሉ እንጂ አንዱ በአንዱ ይዞታ ውስጥ የሚገባበት አካሄድ
የለም በማለት መግለፁን በመጥቀስ አመልች ይዞታውን ለተጠሪ የሚለቅበት የህግ አግባብ የለም በማለት
የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጓል፡፡

ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ
ቀኙን አከራክሮ በሰጠው ውሳኔም የተጠሪ ምስክሮች እንደ ክስ አቀራረባቸው ሲያስረዱ የአመልካች
ምስክሮች ደግሞ በሽንሻኖ ወቅት ሁለቱ በመጣላታቸው ምክንያት መሀንዲሶቹ ድንጋይ ሳይተክሉ
ወጥተዋል በሚል ያስረዱ መሆኑን፤ተጠሪ በሊዝ አዋጁ መሰረት ይዞታውን ህጋዊ ለማድረግ በ2008 ዓም
ቅጣት ለመንግስት ገቢ ያደረጉ ለመሆኑ የሰነድ ማስረጃ መቅረቡን ፤የክፍለ ከተማው ማዘጋጃ ቤት
ለተጠሪ ይዞታ ማህደር ሲኖር ለአመልካች ይዞታ ማህደር የሌለው መሆኑን መግለፁን ፤የግራ ቀኙ
ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል በስፍራው ሽንሻኖ መኖሩን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ
አጠቃላይ ማስረጃዎቹ እንደ ተጠሪ ክርክር የሚያስረዱ መሆኑን በመጥቀስ አመልካች ምንም እንኳ
በእጁ ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ ባይኖረውም ተጠሪ ይልቀቅልኝ ለሚለው ማካካሻ ከፊት ለፊት
መንገድ የሆነውን ያገኘ ስለሆነ 6 ሜትር ለተጠሪ ለቆ ያስረክብ በማለት ወስኗል፡፡ይህ ውሳኔ በክልሉ
ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በሰበር ሰሚ ችሎቱ ፀንቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ህዳር 08 ቀን 2013 ዓም በተፃፈ ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም
የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ባለይዞታ መሆኔን፤በይዞታውም ላይ ንብረት መኖሩን፤ይዞታውም
ያልተሸነሸነ መሆኑን ከሰውና ከሰነድ ማስረጃ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤቱ ምላሽ አረጋግጦ እያለ፤ተጠሪ
ንብረቱ በእጃቸው መኖሩን ሳያረጋግጡ ይመለስልኝ በማለት ሊጠይቁ የሚችሉበት የህግ አግባብ ሳይኖር
፤በአስተዳደር አካል ያልተሰጠውን መብት ፍርድ ቤቶቹ ለተጠሪ መስጠታቸው አግባብነት
የለውም፤በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረት ቢፈፀም የቤቴን ሙሉ ሳሎን በመሰንጠቅ ቤቴን ሙሉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለሙሉ የሚያፈርስ ሆኖ ከመኖሪያ ቤቴ የሚያፈናቅለኝ በሆነበት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከማዘጋጃ


ቤቱ ማብራሪያ ውጪ ቦታው ተሸንሽኗል በማለት ተጠሪ ድንጋይ ቢተከል እዚህ ጋር ይሆናል በማለት
ያሳየውን በመቀበል የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤

አመልካች ይዞታዬን ለማጣት የምገደደው የከተማ መሬት በሊዝ ስለመፍቀድ በወጣው ደንብ ቁጥር
123/2007 ለማስፈፀም ተሸሽሎ በወጣው መመሪያ ቁጥር 08/07 መሰረት ስታንዳርዱ 200 ካሜ ተደርጎ
መብቴ ተጠብቆ ፤መሬትም የሚሰጠኝ ከሆነ ድርሻዬ ተሰጥቶኝ የሽንሸና ድንጋይ ተተክሎ ሊሆን ሲገባ
ይህ ባልተደረገበት ፤ምልከታውንም በተመለከተ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለምልከታ ግራ ቀኛችን
እንድንገኝ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ከፍርድ ቤት አንድም ተወካይ ሳይኖር የተፈፀመ በመሆኑ የሀዲያ ዞን
ከፍተኛ ፍርድ ቤትና በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ተሸሮ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር
የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲፀና ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ግራ ቀኙ ያላቸው ይዞታ ሰነድ አልባ ስለመሆኑ ከተገቢው
የአስተዳደር አካል በመጣው ምላሽ ተገልፆ እያለ አመልካች አልፎ የያዘውን የተጠሪን ይዞታ እንዲለቅ
የተወሰነበትን አግባብ ለማጣራት ለዚህ ሰበር ችሎት ቀርቦ እንዲታይ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ
ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ የጎፈር ሜዳ ክ/ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቀድሞ
የያዝኩትን 6 ሜትር ከፊት ለፊት እንድለቅና ወደ ኋላ እንድሄድ ድንጋይ ሲተከል በዚህ በተወሰደብኝ
ምትክ የአመልካች በምስራቅ በኩል 6 ሜትር የተሰጠኝ ሲሆን አመልካችም በዚሁ በሚለቀው ቦታ
ምትክ በስተምዕራብ በኩል 6 ሜትር ተሰጥቶት የያዘ በመሆኑ ለመልቀቅም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ፤ይዞታዬ
የሆነውን 200 ካሜ ህጋዊ ለማድረግ ተገቢውን ክፍያ የፈፀምኩኝ በመሆኑ፤አመልካች ለኔ የተሰጠኝንና
ለራሱ በምትክ የተሰጠውን ይዞታ ይዞ ከመደበኛው የቦታው አሰጣጥ 200 ካሜ በላይ በድምሩ 353.08
ካሜ ይዞ የሚገኝ በመሆኑ ፤አመልካች ለይዞታው ህጋዊ የሆነ ምንም አይነት ማስረጃ ያላቀረበ በመሆኑ
የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዲፀናላቸው ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም
ከሰበር ቅሬታው አኳያ እና ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ይዘት አንፃር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ
ተመርምሯል፡፡በመሰረቱ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ክሳቸውን ያቀረቡት ማዘጋጃ ቤቱ በ2008 ዓም
ባደረገው ህገ ወጥ ይዞታን ስርአት የማስያዝ አሰራር ይዘው ካሉበት 6 ሜትር መንገድ በመውሰዱ ወደ
አመልካች ይዞታ ውስጥ ሲያስገባቸው አመልካችም ከኋላ ለቅቆላቸው ወደፊት እንዲሸጋሸግ የተደረገ
መሆኑን ነገር ግን በሽግሽግ የደረሳቸውን ይዞታ አመልካች ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልፀው
በፍርድ ሀይል ለቅቆ እንዲያስረክባቸው በመጠየቅ ነው፡፡የተጠሪ የይገባኛል ጥያቄ መነሻው በማዘጋጃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቤቱ እውቅናና ፍቃድ መሰረት የሚደረግን ሰነድ አልባ ይዞታን በህግ አግባብ ስርአት በማስያዝ ሂደት
የተፈጠረን ሽግሽግ መሰረት ያደረገ በመሆኑ በዋነኝነት በማዘጋጃ ቤቱ እውቅናና ክትትል የተፈፀመ
ሽግሽግ መኖር አለመኖሩ ላይ ግራ ቀኙ የተካካዱ በመሆኑ የሂደቱ ባለቤት የሆነው ማዘጋጃ ቤቱ ለክሱ
መነሻ የሆነውን ሽግሽግ ማድረጉን ተጠሪ ሊያስረዱ ይገባል፡፡

የተጠሪ ምስክሮች የተጠሪን ቦታ 6 ሜትር ያህል መንገድ ስለወሰደው ማዘጋጃ ቤቱ ድንጋይ ተክሎ ወደ
አመልካች ይዞታ 6 ሜትር ገብተው ሰነድ አልባ ይዞታውን ህጋዊ ስርዓት የማስያዙ ሂደት የተጠናቀቀ
መሆኑን ያስረዱ ቢሆንም ማስረጃን የመስማት ፤የመመርመርና የመመዘን ስልጣን ያለው የከተማው
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባደረገው ማጣራት ማዘጋጃ ቤቱ ተጠሪ የያዙት ይዞታ ቀድሞውኑ በቂ
በመሆኑ አንዱ ወደ አንዱ ይዞታ ውስጥ ገብቶ ሽግሽግ የተደረገበት ሁኔታ አለመኖሩን በ17/10/2011
ዓም በሰጠው ምላሽ እንዳረጋገጠ በውሳኔው ላይ አመልክቷል፡፡ይህም በግልፅ በማዘጋጃ ቤቱ እውቅና
የተሰጠው ለተጠሪ መብት የሚፈጥር ሽግሽግ አለመኖሩን ያሳያል፡፡ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ
በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሲሽሩ ለተጠሪ መብት መፈጠር መነሻ የሆነውን
ለስር ፍርድ ቤት ከተሰጠው የተለየ የማዘጋጃ ቤቱ ምላሽ መኖሩን በውሳኔያቸው ላይ አላመለከቱም፡፡

የተጠሪ ክስ መነሻው ማዘጋጃ ቤቱ በፈፀመው ሽግሽግ ምክንያት የተፈጠረን መብት መሰረት ያደረገ
ሆኖ እያለ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ማዘጋጃ ቤቱ ያደረግኩት ሽግሽግ የለም እያለ ምስክሮቹ ሽንሻኖ እና
ሽግሽግ መኖሩን በሚያሳይ መልኩ አስረድተዋል የሚል መነሻ በመያዝ ክርክሩ በይዞታው ላይ በህግ
የተረጋገጠ የቀደመ መብት አለኝ የሚል ባልሆነበት ተጠሪ በሊዝ አዋጁ መሰረት ይዞታውን ህጋዊ
ለማድረግ በ2008 ዓም ቅጣት ለመንግስት ገቢ ያደረጉ ለመሆኑ የሰነድ ማስረጃ መቅረቡን ፤የክፍለ
ከተማው ማዘጋጃ ቤት ለተጠሪ ይዞታ ማህደር ሲኖር ለአመልካች ይዞታ ማህደር የሌለው መሆኑን
መግለፁን በመጥቀስ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ መሻሩና በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች በዋነኝነትም ሰበር
ሰሚ ችሎቱ የግራ ቀኙን የይዞታ ስፋት ልክ በማወዳደር አመልካች ለችሎቱ የገለፀውና በአካል ሲለካ
የተገኘው ልዩነት አለው በማለት ለግራ ቀኙ ክርክር መሰረታዊ ነጥብ የሆነውን በማዘጋጃ ቤቱ እውቅና
የተደረገ ሽንሻኖና ሽግሽግ መኖሩን የጉዳዩ ባለቤት ከሆነው ማዘጋጃ ቤት በማጣራት ከስር ፍርድ ቤት
የተለየ ምላሽ ሳያገኙ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ መሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ
ስላገኘነው የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

1.የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.20670 ነሀሴ 23 ቀን 2011 ዓም የሰጠው ውሳኔ እና ይህንን


ውሳኔ በማፅናት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.14065 ጥር 27 ቀን 2012 ዓም እንዲሁም
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.14731 ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓም የሰጡት
ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2.የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.28508 ሀምሌ 05 ቀን 2011 ዓም


የሠጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

3.ጥር 17 ቀን 2013 ዓም በዋለው ችሎት በአፈፃፀም መዝገብ ቁጥር 29719 በተያዘው አፈፃፀም ላይ
የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡

4.ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ክርክሩ ተገቢውን እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ክራሲያዊ ሪፐብሊክ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ 198400
ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- መሀመድ አባ ቡልጉ

ተጠሪ፡- የጌምቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሕዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 51111 ጥር 5 ቀን 2012
ዓ.ም የስር ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር አመልካች ይዞታው የእኔ ነው የሚል ከሆነ በአዋጅ
ቁጥር 721/2004 እና ደንብ ቁጥር 182/2008 መሠረት ለሚመለከተው አካል አቤቱታ አቅርቦ እንዲከፈለው
ማድረግ ሲገባው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ
በማጽናት በየደረጃው ያሉት የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጅማ
ዞን ጎማ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን
ተጠሪ ተከሳሽ፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌለው የጌምቤ ከተማ መምሕራን ማህበር እነ አቶ ደሳለኝ አበበ / 14
ሰዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በአጭሩ፡- አመልካች በሕጋዊ መንገድ የያዝኩት አንድ ፈጫሳ የቡና ችግኝ እና አንድ ፈጫሳ ባህር ዛፍ በ
2004 ዓ.ም ተክለው ጸድቆ የነበረ መሆኑን፤ ተጠሪ ምንም ካሳ ሳይሰጣቸው ከአመልካች ወስዶ ለሰዎች
ሲሰጥ የቀረውን አንድ ፈጫሳ በጌምቤ ከተማ ከሶ በር አካባቢ ተብሎ በሚጠራው አዋሳኙ በክሱ ላይ
በተገለጸው ይዞታ ውስጥ በቀን 23/09/2011 ዓ.ም በመግባት አጠቃላይ ግምቱ ብር 3830 የሚያወጣ አራት
ደጃፍ 3*4 የሆነ 10 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት፤ መሪ እንጨት እና ማገር እንዲሁም ከንች ያፈረሰባቸው መሆኑን
በመግለጽ አፍርሶ የወሰደውን የንብረት ግምት ብር 3830 / ሶስት ሺሕ ስምንት መቶ ሠላሳ ብር /
እንዲከፍላቸው እና በይዞታቸው ላይ የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን
የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን ተጠሪ በሰጠው መልስ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መሬት በከተማው አስተዳደርም ሆነ በአመልካች
ቁጥጥር ስር አለመሆኑን፤ መሬቱ ሳይት ፕላን ወጥቶበት በሕጋዊ መንገድ ለሌሎች ሰዎች የተሰጠ እና
አመልካች መብት ሳይኖራቸው ክስ ያቀረቡ መሆኑን በመግለጽ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 33/2 መሠረት ክሱ
ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

የሥር ጣልቃ-ገብ ባቀረበው የጣልቃገብነት ክርክር በክሱ ላይ የተገለጸው መሬት በቀን 26/07/2011 ዓ.ም
ተጠሪ ተሰጥቶአቸው ለቤት መስሪያ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን አጠራቅመው ባሉበት ሁኔታ አመልካች ሁከት
በመፍጠራቸው ቤቱን ለመስራት እንዳልቻሉ በመግለጽ በይዞታው ላይ ቤት እንዲሰሩበት እና የንብረቱን
ግምት የማግኘት መብታቸው እንዲጠበቅ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት ጠይቋል፡፡

የስር ጣልቃገብ ላቀረበው መከራከሪያ አመልካች በሰጡት መልስ ይዞታው ለጣልቃ ገብ መሰጠቱን
አላውቅም፤ ጣልቃገብ የሰጠውን አካል ከመጠየቅ በቀር ከአመልካች ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ይዞታው
የአመልካች እንጂ የቀበሌ አስተዳደር አይደለም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ በበኩሉ ጣልቃገቡ ላቀረበው መከራከሪያ በሰጠው መልስ፡- ይዞታው በሕጋዊ መንገድ ለጣልቃ ገብ
የተሰጠ ነው፤ አመልካች ይዞታውን ኮሎኔል ለማ ዋሚ ከሚባሉ ግለሰብ በምን አግባብ እንዳገኙ ያልገለጹ
ሲሆን ግብር የገበሩበትንም ሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ አላቀረቡም፤ ቦታው ለሕዝብ ሲሰጥም
አልተቃወሙም በማለት መልሰ ሰጥቷል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ እና ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ስለጉዳዩ
ተጣርቶ እንዲቀርብለት ካደረገ በኋላ አመልካችን ጨምሮ ክስ በቀረበበት ይዞታ ላይ በአካባቢው ላለ
ለማንኛውም ባለይዞታ የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ያልተሰጠ መሆኑ ተረጋግጧል፤ አንድ ይዞታ ለልማት
ሲፈልግ አስፈላጊው ካሳ ለባለይዞታው ሊከፈለው እና ምትክ መሬት ሊሰጠው ይገባል፤ ተጠሪ ከሕግ ውጪ
የአመልካችን የግል ይዞታ የወሰደ እና ሁከት በመፍጠር ብር 3830 / ሶስት ሺሕ ስምንት መቶ ሰላሳ /
የሚገመት ንብረት ያወደመበት በመሆኑ ይህንኑ ገንዘብ ከፍሎ የፈጠረውን ሁከት በማቆም ይዞታውን ለቆ
እንዲወጣ በማለት ወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
አቅርቧል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም አመልካች ይዞታውን የገዛበትን ውል እና ይዞታውን ሸጠለት
የተባለው ግለሰብ መብት ያለው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም፤ አመልካች ይዞታው የእኔ ነው
የሚል ከሆነም በአዋጅ ቁጥር 721/2004 እና ደንብ ቁጥር 182/2008 መሠረት ለሚመለከተው አካል
አቤቱታ አቅርቦ እንዲከፈለው ማድረግ ሲገባው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት
የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል፡፡ ይህም ውሳኔ በየደረጃው ባሉ የክልሉ ፍርድ ቤቶች ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- አመልካች አከራካሪውን ይዞታ በሕገወጥ መንገድ የያዝኩት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፤ የስር
ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተጠየቀው ዳኝነት ውጪ በመውጣት እና በአግባቡ በማስረጃ ሳያረጋገጥ አዋጅ ቁጥር
721/2004 እና ደንብ ቁጥር 182/2008 መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ አመልካች ባቀረቡት ምስክሮች እና
በሚመለከተው የመሬት አስተዳደር ጽ/ቤት የሐገር ሽማግሌዎችን ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ ተጠሪ
የአመልካችን ይዞታ ከሕግ ውጪ ለጣልቃ ገብ የሰጠ ስለመሆኑ ተገልጾ ባለበት ሁኔታ ተጠሪ የፈጠረው
ሁከት የለም በሚል የመወሰኑን አግባብነት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ለማጣራት ሲባል ጉዳዩ በዚህ
ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች ኮሎኔል ለማ ዋሚ ከሚባል ግለሰብ በሽያጭ ያገኘበትን የሽያጭ
ውልም ሆነ ይዞታውን በሌላ አግባብ ያገኘ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም፤ ለክርክሩ ምክንያት
የሆነው ይዞታ ለሕዝብ ሲሰጥ አመልካች ለየትኛውም የአስተዳደር አካላት ቅሬታ አላቀረበም፤ ማሕበሩ ቤት
ለመስራት ሲል አመልካች በሕገ ወጥ መንገድ ቤት መስራቱ አግባብ አይደለም፤ አመልካች ከሽማግሌዎች እና
ከሰው ማስረጃ በቀር የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እና የግብር ደረሰኝ አላቀረበም፤ መሬትን መሸጥ መለወጥ
አይቻልም፤ አመልካች ያቀረበውን የአላባ ጥያቄ ለዚሁ ጉዳይ ለተቋቋመው የአስተዳደር ክፍል ማቅረብ
ይችላል፤ የግንባታ ፍቃድ ሳይኖረው የገነባውን ቤት ተጠሪ ለማፍስም ሆነ ለማገድ የሚያስችል ሙሉ
ስልጣን ስላለው የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

በመሠረቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(4) ማናቸውም ኢትዮጲያዊ አርሶአደር የመሬት

ባለይዞታ የመሆን እና ከይዞታው ያለመፈናቀል መብት ያለው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የዚሁ ሕግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አንቀጽ 40(1)እና(7) ድንጋጌዎችም ማንኛውም ኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆን የተከበረለት/ላት
መሆኑን፤ በጉልበቱ፣ ወይም በገንዘቡ በመሬቱ ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል
ሙሉ መብት እንዳለው፤ይህ መብትም የመሸጥ፤የመለወጥ፤ የማውረስ፤የመሬት ተጠቃሚነቱ ሲቋረጥ ንብረቱን
የማንሳት፤ባለቤትነቱን የማዛወር ወይም የካሳ ክፍያ የመጠየቅ መብትን የሚያካትት እና ዝርዝር አፈጻጸሙም
በሕግ የሚወሰን መሆኑን ይደነግጋሉ፡፡ የዚሁ አንቀፅ ንኡስ አንቀጽ ስምንት ደግሞ የግል ንብረት ባለቤትነት
መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፋላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ
በመክፈል የግል ንብረትን ለመውሰድ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡

ሕገ-መንግሥቱን ተከትለው የወጡት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን እና የንብረት ካሣ
የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/ 1997 እና የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው
አዋጅ ቁጥር 721/2004 ድንጋጌዎችም የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መንግስት ለሕዝብ
ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ካሳ በቅድሚያ በመክፈል የግል ንብረትን ለመውሰድ እንደሚችል
በተመሳሳይ ሁኔታ ይደነግጋሉ፡፡

በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ አከራካሪ በሆነው ይዞታ ላይ አመልካች መብት ያለው ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ
አላቀረበም፤ ቦታውም ለሕዝብ ተሰጥቷል በማለት የሚከራከር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በሚመለከተው የመሬት
አስተዳደር እና በአካባቢው ሽማግሌዎች ጉዳዩ ተጣርቶ እንዲቀርብለት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት አመልካችን
ጨምሮ በአካባቢው ላሉ ባለይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ያልተሰጣቸው ቢሆንም አመልካች ይዞታውን
በሰነድ አልባ ለረጅም ጊዜ ይዘውት የነበረ መሆኑን እና ተጠሪ ከሕግ ውጪ የአመልካችን ይዞታ በመውሰድ
ሁከት የፈጠረባቸው እና ንብረታቸውን ያወደመባቸው ስለመሆኑ ተረጋግጧል፡፡ አመልካች በዚህ አግባብ
ይዞታውን ይዘው ሲጠቀሙበት የነበረ ስለመሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ አግባብነት ባላቸው ሕጎች እና የአፈጻጸም
መመሪያዎች መሠረት ከመሬት አለመነቀልን እና ካሳን አስመልክቶ ሰነድ አልባ ይዞታዎች በልዩ ሁኔታ
ሊስተናገዱ የሚችሉበት ስርዓት ስለመኖር አለመኖሩ በቅድሚያ ተጣርቶ እንዲቀርብ ካልተደረገ በቀር በጉዳዩ ላይ
ፍትሐዊ ውሳኔ መስጠት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ይህ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች
የየራሳቸውን ምክንያት በመስጠት የሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ
አግኝተነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ
1. በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጎማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 44184 ሕዳር 12 ቀን 2012
ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 51111 ጥር 5
ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 222416
ጥር 22 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ
332900 መጋቢት 03 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት
ተሽሯል፡፡
2. የጎማ ወረዳ ፍርድ ቤት አግባብነት ባላቸው ሕጎች እና የአፈጻጸም መመሪያዎች መሠረት ከመሬት
አለመነቀልን እና ካሳን አስመልክቶ ሰነድ አልባ ይዞታዎች በልዩ ሁኔታ ሊስተናገዱ የሚችሉበት
ስርዓት ስለመኖር አለመኖሩ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ተጣርቶ እንዲቀርብለት በማድረግ እና
ጉዳዩን ለማጣራት የሚያስችለውን ተገቢ ነው ያለውን ትዕዛዝ በመስጠት ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢ ነው
ያለውን ውሳኔ እንዲሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1 መሠረት ጉዳዩ ተመልሶለታል፡፡
3. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሠ/መ/ቁጥር 198669
ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ/ም
ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ ወንድማገኝ ታደሰ- ቀረቡ

ተጠሪ ፡- አጋር የጥበቃ አገለግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር - አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ የስራ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካች በሐረር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ
በመሰረቱት ክስ ተጠሪ ለጥበቃ ስራ ከቀን 01/02/2010 ዓ/ም ጀምሮ በወር ብር 1,293.00 ደመወዝ
እየከፈለ ሊያሰራቸዉ ቀጥሯቸዉ እስከ ቀን 13/02/2011 ዓ/ም ድረስ እየሰሩ ቆይተዉ በስራ
መመዝገቢያ ላይ ፈርሜ የተረከብኩት ጥበቃ ቀጠና ውጪ ሌላ ቀጠና ላይ ሄደህ የጥበቃ ሥራ
እንዲሰሩ ሲያዛቸዉ በሥራ መመዝገቢያ ላይ ፈርሜ የተረከብኩት ጥበቃ ቀጠና ላይ ችግር ቢፈጠር
ተጠያቂ እሆናለሁ በማለታቸዉ ብቻ በቀን 13/02/2011 ዓ/ም ከሥራ እንዳሰናበታቸዉ ገልጸዉ
ሥንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ ተብሎ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን በድምሩ ብር
22,487.08 ተጠሪ እንዲከፍላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪ በሰጠው መልስ ተጠሪ የአመልካችን መብት ሳይነካ በተመሳሳይ ቦታ ላይ ተዛውረዉ እንዲሰሩ
አዘዛቸዉ እንጂ ተጠሪ አመልካችን አላሰናበታቸዉም፡፡ተጠሪ በተዛወሩበት ቦታ እንዲሰሩ በጽሁፍ
ቢታዘዙም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ተጠሪ የዓመት እረፍት ተጠቅመዋል፡፡ስለሆነም እንዲከፈላቸዉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የጠየቁት ክፍያዎች አይገባቸዉም፡፡የሸምዝና የጫማ በሚል እንዲከፈላቸዉ የጠየቁት 6000.00 ብር


ያለአግባብ የጠየቑትና የተጋነነ ስለሆነ ዉድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 50384 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 03/07/2012


ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ የተመደብኩበትን ቦታ ትቼ ወደሌላ ምድብ ብሄድ ፈርሜ በተመደብኩበት
ቦታ ችግር ቢፈጠር ተጠያቂ ስለምሆን በሌላ ምድብ አልሰራም በማለቱ አመልካች የተጠሪን የሥራ
ዉል ማቋረጡ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ስር የተደነገገዉን መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ የአመልካች
የሥራ ዉል ከሕግ-ወጭ ተቋርጧል ሲል ወስኗል፡፡ይህንን ተከትሎም የአገልግሎት ክፍያ የ2 ዓመት
ብር 1,724.00፣ የካሳ ክፍያ ብር 1,293.00 ፤ የሥራ ውሉ በተጠሪ አነሳሽነት ከሕግ-ዉጭ ስለተቋረጠ
በአንቀጽ 41/1 መሰረት የአንድ ወር ደመወዝ ካሳ ብር 1,293.00 ፣ በአንቀጽ 43 መሰረት ከሕግ-
ውጪ የስራ ዉሉ በመቋረጡ የአመልካች የቀን ደመወዝ በ180 ተባዝቶ ካሳ ብር 7,758.00 ፣ የ28
ቀን የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ብር 1,206.60፣ ክፍያ ለዘገየበት ብር 3,879.00 ፤ የጥበቃ
ደንብ ልብስና ጫማ በአመት 2 ጊዜ የ2010 እና 2011 ዓ/ም በግራ ቀኙ ያልተካደ ቢሆንም የዋጋ
ዝርዝር በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ በአማካይ ብር 3,000 እንዲሁም ወጪ ኪሳራ በቁርጥ 500 ብር
አጠቃላይ ብር 19,360.00 ተጠሪ ለአመልካች እንዲከፍል ወስኗል፡፡

ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሀረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ
በመ/ቁጥር 20027 ላይ በቀን 30/10/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር
337 መሰረት ሰርዞባቸዋል፡፡ በመቀጠል ተጠሪ አቤቱታውን ለሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ
ችሎቱ በመ/ቁጥር 00101 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 26/02/2013 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ለሥራ
ውሉ መቋረጥ መነሻ የሆነው ጉዳይ አመልካች በቀን 13//02/2011 ዓ/ም በተመደቡበት የሥራ ቦታ
በሥራ ሰዓት ባለመገኘተቻዉ በቦታቸው ሌላ ሠራተኛ ተመድቦ አመልካች አርፍደዉ በመምጣቱ
ተጠሪ አመልካችን በሌላ ቦታ ጥበቃ ቀጠና በዚያው በተቀጠረው ቅጥር ግቢ ምንም አይነት የደመወዝ
ቅነሳ ሳያደርግ በያዘው ደመወዝ መብትና ጥቅም ጋር ያዛወረውን አመልካች ባለመቀበላቸዉ እንደሆነ
ከክርክሩ መረዳት ችለናል፡፡ተጠሪ የአመልካችን ለሥራው አመቺ በሆነ ቦታ አዘውሮ ማሰራቱ
አስተዳደራዊ ስልጣኑ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር በአመልካች በኩል ቅን ልቦና አለመኖሩን ለመረዳት
ችለናል፡፡በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የጉዳዩን አመጣጥና የተጠሪን የአስተዳደር ስልጣን ግምት
ውስጥ ሳያስገባ እና አመልካችን ከስራ አላሰናበትኩም አሁን ተመልሶ መስራት ይችላል የሚል ክርክር
አቅርቦ እያለ ተጠሪ በሕገ-ወጥ መንገድ የሥራ ውል አቋርጧል በማለት የሠጠዉ ዉሳኔ አበዋጅ ቁጥር
1156/2011 ከአንቀጽ 23 እስከ 45 የተደነገገዉን ያላገናዘበ በመሆኑ አግባብ አይደለም በማለት ሽሮ
ወስኗል፡፡

አመልካች በቀን 03/03/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡- የሥር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካች የሥራ ዉል የተቋረጠዉ በተጠሪ ጥፋት መሆኑን


አረጋግጧል፡፡ተጠሪ ምንም ዓይነት የዝውውር ደብዳቤ ሳይሰጠኝ እና ሳይደርሰኝ በሌላ ቀጠና ሄጄ
እንድሰራ ሲያዘኝ አስቀድሞ ፈርሜ የተረከብኩት ንብረት ቢጠፋ ተጠያቂ ስለሚሆን የፈረምኩት
ፊርማ እንዲሰረዝልኝ በማለቴ ፈቃደኛ አልሆነም በማለት ያለማስረጃ ያቀረበዉን ክርክር የክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት መቀበሉና የሥር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ መሻሩ ስህተት ስለሆነ ተሽሮ የመጀመሪያ
ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲፀናላቸው በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ የሰበር ችሎት አምስት ዳኞች የሚሰየሙበት ከመሆኑ
አኳያ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በሶስት ዳኞች ተሰይመዉ የወሰኑበትን አግባብ ሰበር አምስት ዳኞች
የሚሰየሙበት ችሎት ከመሆኑ አኳያ የሀረር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሶስት
ዳኞች ብቻ ጉዳዩን አይቶ የወሰነበት አግባብ እንዲመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን
26/11/2013 ዓ/ም የተፃፈ መልሱን አቅርቧል፡፡ የመልሱም ይዘት በአጭሩ፡- የሚከተለው ነው፡፡

ተጠሪ አመልካችን ከሥራ ያሰናበተው አመልካች እንደሚሉት ሳይሆን አመልካች ሥራ ከገቡ በኋላ
የተመደቡበትን ሥራ ቦታ ላይ እየሰራ እያለ ሌላ ክፍተት ያለበት ቦታ ላይ ሄደዉ እንዲሰሩ ሲመደቡ
አልሄደም ከዚህ ከተመደብኩበት ቦታ ውጪ አልሰራም በማለታቸዉ ነው፡፡ ተጠሪ አመልካችን ሌላ
ቦታ ላይ የመደበዉ አመልካችን ተጠያቂ ለማድረግ ሳይሆን የሥራ ክፍተትን ለመሸፈን
ነው፡፡በተጨማሪም በኃላፊው ታዞ በሌላ ስራ ላይ የተመደበ ሰራተኛ ተጠያቂ የሚሆነው ለተመደበበት
ቦታ እንጂ በኃላፊው ታዞ ለተነሳበት ቦታ አለመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ የሀረሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው ውሳኔ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል፡፡

ከዚህ በላይ በአጭሩ የተመለከተዉ የግራ ቀኙን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች
ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት ጭብጥ በተጨማሪ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር በሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር
አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

በመጀመሪያም የሐረሪ ሕዝብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሦስት ዳኞች በተሰየሙበት ሰበር ሰሚ ችሎት
ጉዳዩን በሰበር ለማለየት የቻለበትን የሕግ መሰረት መርምረናል፡፡ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ጉዳይ የክልል ጉዳይ
መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ለ) ላይ እና በሐረሪ ሕዝብ ክልል ሕገ
መንግስት አንቀጽ 70(2/ሐ) ላይ እንደተመለከተዉ ዝርዝሩ በሕግ በሚወሰነዉ መሰረት የሐረሪ ክልል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትን በክልል ጉዳይ ላይ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ ለማረም
በሰበር ችሎት የማየት ስልጣን እንዳለዉ ተደንግጓል፡፡ይህንን ተከትሎ በወጣዉ ሕግ በሐረሪ ሕዝብ ክልል
ፍርድ ቤቶችና የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መቋቋሚያ አዋጅ ለማሻሻል በወጡ አዋጆችና እንደገና ለማሻሻል
በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 68/1999 አንቀጽ 7(ሀ እና ለ) (ይህ አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 107/2004 እንደገና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቢሻሻልም ይህ አንቀጽ አልተለወጠም) ስር ከተደነገገዉ መረዳት የሚቻለዉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት


የሚኖሩት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችሎቶች ሦስት ዳኞች (አንድ ሰብሳቢ ዳኛና በሁለት ተጨማሪ ዳኞች)
ተሰይመዉ እንደሚዳኙ ደንግጓል፡፡በሌላ በኩል በቀድሞዉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር
25/1988(በአዋጅ ቁጥር 454/1997 እንደተሻሻለዉ) አንቀጽ 10/4 እና ይህንን አዋጅ ከነማሻሻያዉ በሻረዉ
የፌደሬል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10/2 ላይ በተደነገገዉ መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚያስችለዉ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት እንደሆነ የተደነገገ
ቢሆንም ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነዉ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ላይ እንጂ
በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ላይ አይደለም፡፡ይህም ታሳቢ ያደረገዉ የክልል ጠቅላይ ፍርድ
ቤቶች የየክልላቸዉን ሕገ መንግስትና የክልሉን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የክልሉ ሰበር ሰሚ
ችሎት ላይ የሚሰየሙትን ዳኞች ብዛት የመወሰን ሥልጣን እንዳላቸዉ ነዉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ
ቀደም በሰ/መ/ቁጥር 185278 ላይ በቀን 25/01/2013 ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ ላይ እና በሌሎች መዝገቦች ላይ
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሦስት ዳኞች በተሰየሙበት ሰበር ችሎት ዉሳኔ
በመስጠቱ የተፈጸመ ስህተት እንደሌለ ተገልጾ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡ በመሆኑም የሐረሪ ሕዝብ ክልል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከላይ በተጠቀሱት ሁለቱም ሕገ መንግስታት በተፈቀደዉ መሰረት ባወጣዉ ሕግ ላይ
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሦስት ዳኞች እንደሚያስችል በተደነገገዉ መሰረት ይህንን
ጉዳይ ሦስት ዳኞች ተሰይመዉ በሰበር አይተዉ በመወሰናቸዉ ከአሰያየም አንጻር በዚህ ችሎት ደረጃ ሊታረም
የሚችል የተፈጸመ ስህተት የለም ብለናል፡፡

ዋናዉን ጉዳይ በተመለከተ የተያዘዉን ጭብጥ እንደመረመርነዉ የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ
ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን መርምሮና መዝኖ የሥራ ዉል ማቋረጫ ምክንያት ነዉ ተብሎ በሕግ የተደነገገ
በቂ ምክንያት ሳይኖር ተጠሪ አመልካችን የሥራ ዉል ማቋረጡን ማረጋገጡን ገልጾ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ
ሲል ወስኗል፡፡ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔ ላይ እነደተመለከተዉ ተጠሪ እንደ አሠሪ ሠራተኛዉን ሥራ
ወዳለበት አዛዉሮ የማሰራት መብት ያለዉ መሆኑ አከራካሪ አይደለም፡፡ ሆኖም ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት
ለክሱ በሰጠዉ መልስ ያቀረበዉ ክርክር አመልካችን አላሰናበትኩም የሚል እንጂ ስንብቱ ሕጋዊ ነዉ የሚል
አይደለም፡፡አመልካች ደግሞ ለስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ማስረጃ ተጠሪ እንዴት በሕገ-ወጥ መንገድ
እንዳሰናበታቸዉ አስረድተዉ ፍርድ ቤቱም ተጠሪ በሕግ ከተመለከተዉ አግባብ ዉጭ ተጠሪ አመልካችን
እንዳሰናበታቸዉ የቀረቡለትን ማስረጃዎች መርምሮና መዝኖ አረጋግጦ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ የሚል
ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡በሐረሪ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 70(2/ሐ) ላይ እንደተደነገገዉ የክልሉ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት በክልሉ ፍርድ ቤቶች በተወሰነ የክልል ጉዳይ የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ የሚገኝ መሰረታዊ የሕግ
ስህተት ከማረም ባለፈ ማስረጃ መዝኖ የአንድን ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር አረጋግጦ የፍሬ ነገር ድምዳሜ
ላይ በመድረስ ዉሳኔ እንዲሰጥ ሥልጣን አልተሰጠዉም፡፡በተያዘዉ ጉዳይ ተጠሪ አመልካችን ከሕግ ዉጭ
አላሰናበተም የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ የሥር ፍርድ ቤቶች የሠጡትን ዉሳኔ የሻረዉ ማስረጃ
በመመዘን ጭምር በመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ብለናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሥንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ ካለ በኋላ የወሰናቸዉ ክፍያዎችን


እንደመረመርነዉ አመልካች ክሱን ያቀረቡት ተጠሪ ከሕግ-ዉጭ ከሥራ አሰናብቶኛል በሚል ሆኖ እያለና
በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 32/1 ስር በተመለከቱ ምክንያቶች የሥራ ዉሉ እንደተቋረጠ
ባልተረጋገጠበት የሥር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ለአመልካች በአዋጁ አንቀጽ 41/1 መሰረት
የአንድ ወር ደመወዝ በካሳ መልክ እንዲከፍል የሠጠዉ ዉሳኔ የሕግ መሰረት ስለሌለዉ ሊታረም ይገባል
ብለናል፡፡እንዲሁም የጥበቃ ደንብ ልብስና ጫማ በአመት 2 ጊዜ የ2010 እና 2011 ዓ/ም አልተሰጠኝም
በሚል አምላከች ብር 6000.00 እንዲከፈላቸዉ ጠይቀዉ የሥር ፍርድ ቤት በርትዕ 3000.00
እንዲከፈላቸዉ የወሰነዉም ቢሆን የደንብ ልብስ የሚሰጠዉ በሥራ ላይ ተገኝቶ ለሚሰራ ሠራተኛ
በመሆኑ የሥራ ዉሉ ሲቋረጥ አብሮ የሚቋረጥ እንጂ ሕገ-ወጥ ስንብት በተፈጸመ ጊዜ አሠሪዉ ወደ
ገንዘብ ለዉጦ እንዲከፈል የሚገደድበት ጥቅማጥቅም ባለመሆኑ ከዚህም አንጻር የተሠጠዉ ዉሳኔ
ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ ስህተት በመሆኑ የሚከተለዉን ወስነናል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 00101 ላይ በቀን 26/02/2013ዓ/ም
የሠጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል፡፡

2. የሐረሪ ክልል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 50384 ላይ በቀን 03/07/2012ዓ/ም የሰጠዉ
ዉሳኔ እና የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 20027 ላይ በቀን 30/10/2012ዓ/ም የሰጠዉ
ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሻሻለዋል፡፡

3. የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ለአመልካች በአዋጁ አንቀጽ 41/1 መሰረት የአንድ ወር
ደመወዝ በካሳ መልክ እንዲከፍል እና የደንብ ልብስና የጫማ በሚል በርትዕ ብር 3000.00 እንዲከፍል
የወሰነዉ ብቻ ተሽሮ ሌላዉ የዉሳኔ ክፍል ፀንቷል፡፡

4. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ 198703
ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፡- አልቀረቡም

ተጠሪ፡- አበባየሁ ተዘራ፡- ከጠበቃ ነቢያት ግርማ ጋር ቀረቡ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሕዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 183756 ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው
ችሎት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በመሻር ተጠሪን
ከተከሰሰችባቸው ሁለት ክሶች በነፃ በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡
አመልካች በተጠሪ ላይ በሥር ፍ/ቤት አቅርቦአቸው የነበሩት ክሶች ሁለት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡-

1ኛ ክስ፡- ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 543(3) እና ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 26 ድንጋጌዎች
በመተላለፍ የሌላውን ሰው ሕይወት፣ ጤንነት እና ደሕንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለባት ባለመወጣት
በቀን 23/07/2010 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡30 ሠዓት ሲሆን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-57534 አ.አ የሆነ
ተሸከርካሪ እያሽከረከረች ከስድስት ኪሎ ወደ መገናኛ አቅጣጫ ስትጓዝ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው
ኮከበ ፅባሕ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ስትደርስ ለእግረኛ ቅድሚያ በመከልከል በእግረኛ ማቋረጫ መንገድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ላይ ስታቋጥ የነበረችውን ሟች አስምረት ንጉሴን በመኪናው የፊት ለፊት አካል ገጭታ በጭንቅላቷ ላይ
ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ራሷን ስታ ወድያውኑ ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በፈጸመችው በቸልተኝነት
ሰውን መግደል ወንጀል ተከሳለች የሚል ነው፡፡

2ኛ ክስ፡- ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 575/2(ሀ) ድንጋጌን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ ላይ በተጠቀሰው ጊዜ፣
ቦታ እና አፈጻጸም ሁኔታ በእግረኛ መንገድ ላይ ስታቋርጥ የነበረችውን ሟች አስምረት ንጉሴን በመኪናው
ፊት ለፊት አካል ገጭታ ከጣለቻት በኋላ ምንም ዓይነት እርዳታ ሳታደርግላት ስታመልጥ በአካባቢው ሰዎች
የተያዘች በመሆኑ በፈጸመችው በአደጋ ላይ የሚገኝን ሰው አለመርዳት ወንጀል ተከሳለች የሚል ነው፡፡

ተጠሪ ክሱ ተነቦላት እንድትረዳው ከተደረገ በኋላ መቃወሚያ ያቀረበች ሲሆን መቃወሚያው በብይን ውድቅ
ተደርጓል፤ የእምነት ክሕደት ቃሏን ስትጠየቅም ድርጊቱን አልፈጸምኩም በማለት ክዳ በመከራከሯ ፍርድ
ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ተጠሪ በተከሰሰችበት በሁለቱም ክሶች እንድትከላከል ሲል ብይን
ሰጥቷል፡፡ ተጠሪም በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 142/3 መሠረት ቃሏን የሰጠች ሲሆን መከላከያ ምስክሮቿንም
አቅርባ አሰምታለች፡፡ ፍርድ ቤቱም የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ ሟችን በእግረኛ
መንገድ ላይ እያቋረጠች እያለች ተገቢውን ጥንቃቄ ባለማድረግ እና ሟችን ቅድሚያ በመከልከል በመግጨት
እና ከገጨችም በኋላ ምንም ዓይነት እርዳታ ሳታደርግ ጥላ ለማምለጥ የሞከረች ስለመሆኑ የዐቃቤህግ
ምስክሮች በመግለጽ ያረጋገጡትን ፍሬ ነገር ተጠሪ አላስተባበለችም በማለት በተከሰሰችባቸው ሁለቱም ክሶች
ጥፋተኛ ብሎ በሦሥት ዓመት ከሦሥት ወር ጽኑ እሥራት እና በብር 2,500 የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ
ሲል ወስኗል፡፡

ተጠሪም ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታዋን
አቅርባለች፡፡ ይግባኙ የቀረበለትም ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የምስክርነት
ቃል እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው፤ በመኪና ግጭት አደጋ የሟች ሕይወት ማለፉ ቢረጋገጥም አደጋው
የደረሰው በተጠሪ መኪና መሆኑን የተሰጠው የምስክርነት ቃል አጠራጣሪ ነው፤ ተጠሪ ባቀረበቻቸው
ምስክሮች በይግባኝ ባይ መኪና ላይ የደረሰ ጉዳት ያልነበረ እና ግጭቱ በደረሰበት ቦታ ላይ ግን የመኪና
ፍሬቻ እና መስታወት ስብርባሪ የነበረ መሆኑን፤ ተጠሪ በወቅቱ የደሰች እርጉዝ እና ሶስት ሕጻናት ልጆችዋን
የጫነች መሆኑን መስክረዋል፤ ተጠሪ የነበረችበት ሁኔታ መኪናውን በፍጥነት ታሽከረክራለች ለማለት
የሚያሳምን አይደለም፤ ተገኘ የተባለው የመኪና አካል ስብርባሪ የእኔ መኪና አይደለም በትእዛዝ ቀርቦ
ይታይልኝ በማለት ብትጠይቀም ጥያቄዋ ውድቅ ተደርጓል፤ በራሺያ ኤምባሲ በደህንነት ካሜራ ተቀርጾአል
የተባለውን አደጋው የደረሰበት አካባቢ እንቅስቃሴ ማስረጃ ፖሊስ እንዲያቀርብ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም
ማስረጃውን ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግ በጋራ ማየታቸውን ነገር ግን ዐቃቤሕግ በክሱ የማስረጃ ዝርዝር ውስጥ
ያላካተተው እና ማስረጃው በፍላሽ ላይ የነበረ በመሆኑ በቫይረስ ችግር የተበላሸ መሆኑን በመግለጽ ማስረጃው
ሳይቀርብ መቅረቱ ሲታይ ዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ለክሱ የሚረዳው ሆኖ ባለማግኘቱ በተቃራኒው ለተጠሪ
ሊጠቅም የሚችል ከመሆኑ አንፃር የተወው ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፤ ስለሆነም ዓቃቤ ሕግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በወቅቱ በደረሰ የመኪና አደጋ ሟች ተገጭው ሕይወታቸው ማለፉን እንጂ ግጭቱ የደረሰው በተጠሪ መኪና
መሆኑን ባላስረዳበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪን ክሱን አላስተባበለችም በማለት የሰጠው የጥፋተኝነት
እና የቅጣት ውሳኔ አግባብ አይደለም በማለት ሽሮ ተጠሪን ከተከሰሰችባቸው ሁለቱም ክሶች በነፃ በማሰናበት
ወስኗል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- በራሽያ ኤምባሲ ደህንነት ካሜራ የተቀረጸው በፍላሽ የነበረ በመሆኑ በቫይረስ የተጠቃ እና
ማስረጃውን ዐቃቤ ሕግ እና ፖሊስ በጋራ ያዩት መሆኑና ማስረጃውም የአደጋው አደራረስ የማያሳይ
ስለመሆኑ ፖሊስ በቀን 06/10/2011 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ በፃፈው ደብዳቤ ተረጋግጧል፤ ዐቃቤ ህግ ይህን
ማስረጃ በክሱ የማስረጃ ዝርዝር ውስጥ በማስረጃነት አለመጥቀሱ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የዓቃቤሕግ
የማስረጃ የመምረጥ እና ለክሱ የሚጠቅመውን የመለየት መብት ግምት ውስጥ ያላስገባ እና የማስረጃ ምዘና
ስነ ስርዓት ሕግን ያልተከተ ነው፤ ተጠሪ የወንጀል ድርጊቱን እንደ አቃቤ ህግ ክስ አቀራረብ ባቀረባቸው
ማስረጃዎች የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ተጠሪ አላስተባበለችም፤ በመሆኑም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተጠሪን ከሁለቱም ክሶች በነፃ በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ
ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪን ከተከሰሰችባቸው ሁለት ክሶች በነጻ
በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ አግባብነት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 89676
ከሰጠው ውሳኔ አንጻር ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም
ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠችው መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የፍሬ ነገር እና የማስረጃ ምዘና
ክርክር በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ሊቀርብ አይገባም፤ አመልካች እንደ ክሱ አቀራረብ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ
በላይ አላስረዳም፤ ተጠሪ ባቀረብኩት ማስረጃ ክሱን አስተባብያለሁ፤ በኤግዚቢትነት የተያዘው የመኪና
ስብርባሪ ተጠሪ እንዲቀርብ ያቀረብኩትን ጥያቄ ውድቅ ተደርጎብኛል፤ በራሺያ ኤምባሲ የደህንነት ካሜራ
የተቀረጸው የአካባቢው እንቅስቃሴ ማስረጃ የአደጋውን ሁኔታ የሚያሳይ እንደመሆኑ መጠን እንደ ማንኛውም
ማስረጃ በጥንቃቄ ሊያዝ ሲገባው ዐቃቤ ህግ ክሱን ውድቅ ስለሚያደርገበት ብቻ በክሱ በቫይረስ ጠፍቷል
በሚል ምክንያት እንዲቀርብ አላደረገም፤ ስለሆነም የስር ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪነ በነጻ በማሰናበት
የሰጠው ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች ለዚህ ችሎት ባቀረበው ክርክር ተጠሪ የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸሟ በበቂ ሁኔታ በተረጋገጠበት
ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተጠሪን ከተከሰሰችበት ክስ በነጻ በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ
አይደለም በማለት የሚከራከር ቢሆንም በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጡትን ፍሬነገሮች የመመርመር፤ ማስረጃን
የመመዘን እና ያልተጣራ ፍሬነገር ካላ ራሱ የማጣራት ወይም እንዲጣራ የማድረግ ስልጣን ያለው ጉዳዩን
በይግባኝ የተመለከተው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች
የምስክርነት ቃል እርስ በእርሱ የሚጋጭ እና በመኪና ግጭት አደጋ የሟች ሕይወት ማለፉ ቢረጋገጥም
አደጋው የደረሰው በተጠሪ መኪና መሆኑን የተሰጠው የምስክርነት ቃል አጠራጣሪ መሆኑን፤ ተጠሪ
ባቀረበቻቸው ምስክሮች በይግባኝ ባይ መኪና ላይ የደረሰ ጉዳት ያልነበረ እና ግጭቱ በደረሰበት ቦታ ላይ ግን
የመኪና ፍሬቻ እና መስታወት ስብርባሪ የነበረ መሆኑን፤ ተጠሪ በወቅቱ የነበረችበት ሁኔታ መኪናውን
በፍጥነት ታሽከረክራለች ለማለት የማያሳምን መሆኑን፤ ተጠሪ ተገኘ የተባለው የመኪና አካል ስብርባሪ የእኔ
መኪና አይደለም በትእዛዝ ቀርቦ ይታይልኝ በማለት ብትጠይቀም ጥያቄዋ ውድቅ የተደረገ መሆኑን፤
በደህንነት ካሜራ ተቀርጾአል የተባለውን የአካባቢውን እንቅስቃሴ ማስረጃ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ቢሰጥም
ዐቃቤሕግ በክሱ የማስረጃ ዝርዝር ውስጥ ያላካተተው እና በቫይረስ ችግር ተበላሽቷል በሚል ምክንያት
ያልቀረበ መሆኑን፤ ዓቃቤ ሕግ በወቅቱ በደረሰ የመኪና አደጋ ሟች ተገጭው ሕይወታቸው ማለፉን እንጂ
ግጭቱ የደረሰው በተጠሪ መኪና መሆኑን ያላስረዳ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ
10/1 መሠረት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው ስልጣን መሠረታዊ የሆነ የሕግ
ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን
ስልጣን የለውም፡፡
በያዝነው ጉዳይ የዓቃቤሕግ ማስረጃዎች እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ እና ዓቃቤ ሕግ በወቅቱ በደረሰ የመኪና
አደጋ ሟች ተገጭው ሕይወታቸው ማለፉን እንጂ ግጭቱ የደረሰው በተጠሪ መኪና መሆኑን ያላስረዳ
መሆኑ፤ ተጠሪም ባቀረበችው መከላከያ ማስረጃ በዓቃቤሕግ ማስረጃ ላይ ጥርጣሬን የፈጠረች ስለመሆኑ በስር
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተረጋገጠ እና ይህ ችሎትም መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበትን
የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የሌለው በመሆኑ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተጠሪን ከቀረበባት ክስ በነጻ በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ
በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አልተገኘበትም፡፡ ስለሆነም ተከታዩን
ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 183756 ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2//ሀ/ መሠረት ጸንቷል፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት


ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-198805

ቀን፡-29/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል

ተጠሪ ፡- አቶ ከበደ ደስታ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ
ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት
ክስ ከሟች አባታቸው አቶ ደስታ አድማሱ በውርስ የሚተላለፍ የሚንቀሳቀስ እና በዚህ ችሎት ደረጃ አከራከሪ
ሆነ የቀረበውን የገጠር እርሻ መሬት አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች
ስለመሬቱ ያቀረቡት መልስ ይዞታው የሟች ደስታ አድማሱና የባለቤቱና የአመልካች አያት የሆኑት የወ/ሮ
እህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ሲሆን አያቴ ወራሽ ስለሆን የሟች ደስታ አድማሱን ድርሻ በኑዛዜና በሥጦታ
አስተላፈውልኛል፡፡ በድጋሜ ከልጆቹ ጋር መሬቱን አውርሰውኛል፡፡ የሟች ደስታ ድርሻ ሊተላፍልህ
አይችልም ቢባል እንኳን የአያቴ የቤተሰብ አባል ስለሆንኩ ግማሽ ድርሻውን ተጠሪ ሊጠይቁኝ አይገባም
ብለዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ መሬቱ የሟች ደስታ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/3
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አድማሱና የእህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ይዞታ ነበር፤ ለአመልካች የተሰጠ ኑዛዜ ሆነ ሥጦታ የነበረ ቢሆንም
በወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ደረጃ አልጸደቀም፡፡ ስለሆነም ግማሹ የሟች ደስታ ድርሻ
ለተጠሪ በውርስ የሚገባቸው ሲሆን የሟች እህተጊዮርጊስን ድርሻ በውርስ ለአመልካች የሚተላለፍ ነው፡፡
ከመሬት ውጭ ያሉ ንብረቶች ለአመልካች ኑዛዜ ስላላቸው ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት
ወስኗል፡፡ በየደረጃው የሚገኙ ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የይግባኝና የሠበር
አቤቱታ ባለመቀበል ሠርዘዋል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ግንቦት 09 ቀን 2009
ዓ/ም ሥጦታ ውል የተደረገ ስለመሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ውሉ በወረዳ ጽ/ቤት ደረጃ በራሱ ቸልተኝነት
ባለመጽደቁ ውጤት የለውም መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ ነሀሴ 08 ቀን 2010 ዓ/ም ለአመልካች እና ለሁለቱ
ልጆቼ አቶ ደስታ አድማሱ ኑዛዜ አድርገውልን ስም ባለመዛወሩ ብቻ ውድቅ መደረጉ ሕጋዊ አይደለም፡፡
የሟች ደስታ አድማሱን ደርሻ መሬት ላስረክብ አይገባም የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን
ተመልክቶ ስጦታ ውሉ ባይመዘገብ እንኳን አመልካች የኑዛዜ ወራሽ ከመሆናቸው አኳያ በግማሽ ድርሻ
መሬቱ ላይ መብት የላቸውም መባሉ ተገቢነቱን ለመመርመር ለሰበር ሰሚ ችሎቱ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ
መልስ እንዲያቀርቡ ያዘዘ ሲሆን ተጠሪ ያቀረቡት መልስ የተደረገ ኑዛዜ ሆነ ስጦታ ውል የለም፤ ሟች
ከሞተ በኋላ ተጠሪን ከውርስ ለመንቀል የተዘጋጁ ሠነዶች ናቸው፡፡ እውነት ቢሆን ኖሮ ኑዛዜ እንዲሁም
የሥጦታ ውልም ተደርጎልኛል ሊል አይችልም፡፡ በሕግ አግባብ የተደረገና የተመዘገበ ውል ባለመኖሩ
ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ
የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙ ክርክር፣ የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘውን
ጭብጥ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪ ከሟች አባታቸው አቶ ደስታ አድማሱ በውርስ የሚተላለፍ የገጠር እርሻ መሬት
አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ላቀረቡት ዳኝነት አመልካች ሟች ደስታ አድማሱ ድርሻቸውን
በ08/12/2010 ዓ/ም በተደረገ ኑዛዜና በ09/09/2009 ዓ/ም በተደረገ ሥጦታ አስተላፈውልኛል፡፡ ተጠሪ ግማሽ
ድርሻውን ሊጠይቁኝ አይገባም በማለት ነው፡፡ ግንቦት 09 ቀን 2009 ዓ/ም ተደረገ የተባለው የሥጦታው
ውል ሕጋዊነት ውሉ በተደረገበት ጊዜ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት ሊመረመር የሚገባ ሲሆን በአማራ
ክልል የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 17(6) መሠረት የገጠር መሬት ላይ የሚደረግ
የሥጦታ ውል መሬቱ በሚገኝበት የወረዳ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ሊመዘገብ እንደሚገባ
ተመልክቷል፡፡ ኑዛዜው ደግሞ የክልሉ ገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ነሀሴ
08 ቀን 2010 ዓ/ም የተደረገ በመሆኑ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 17(4) መሠረት በተመሳሳይ መሬቱ በሚገኝበት
የወረዳ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ አለበት ተብሎ ተመልክቷል፡፡ የሥር ወረዳ ፍርድ ቤት
በሕግ አግባብ የተመዘገበ ሥጦታ ወይም ኑዛዜ የሌለ መሆኑ በማረጋገጥ ድምዳሜ ላይ ድርሷል፡፡ የፌደራል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/3
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ
በተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሠበትን የፍሬ ነገር ድምዳሜ ላይ
እንዲመለከት ሥልጣን አልተሠጠውም፡፡ አመልካች በ2009 ዓ/ም መሬቱ በሥጦታ ተሰጥቶኛል ካሉ በኋላ
እንደገና በ2010 ዓ/ም በኑዛዜ አግኝቼዋለሁ የሚለው ክርክርም እርስ በእርሱ የሚቃረን አሳማኝ ያልሆነ
በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤትን ድምዳሜ ተቀብለናል፡፡ ስለሆነም መሬቱ የሟች ደስታ አድማሱና
የእህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ይዞታ ተጠሪ የአባታቸውን ግማሽ ድርሻ እና አመልካች የሟች እህተ
ጊዮርጊስን ወራሽ ስለሆነ ግማሽ ድርሻ ሊካፈሉ ይገባል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ
የሆነ የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-11784 ጥቅምት 23 ቀን 2013
ዓ/ም፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 013366 ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ/ም እና
የሞጃና ወደራ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 0114235 ታህሳስ 16 ቀን 2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/3
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-198891

ቀን፡-02/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ አክሉሉ ካሕሳይ - ቀረቡ

ተጠሪ ፡- አኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር - በሌለበት የሚታይ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው
አመልካች የስር ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር ጥር 25 ቀን 2005
ዓ/ም በተደረገ የመኪና ኪራይ ውል ስምምነት መሠረት የሠሌዳ ቁጥር 3-83597 አ.አ. የሆነ ተሽከርካሪ ለ10
ወራት ከ15 ቀናት ለሰራው ብር 346,500.00 ተጠሪ መክፈል ሲገባው ብር 100,000.00 ብቻ ከፍሎ ቀሪ
ገንዘብ ስላልከፈለ ብር 246,500.00 ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረበው
መልስ የሠዓት መቆጣጠሪያ ሳያቀርቡ ብር 136,147.00 ከፍለናል፡፡ በውሉ መሠረት ታይምሽት ሳይቀርቡ
ክፍያ መጠየቃቸው አግባብነት የለውም፡፡ የቀረበው ማስረጃም በአመልካች መኪና ሥራ መስራታችን
አያሳይም፤ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል ብሏል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግራቀኙን ማስረጃ በመስማት በውሉ መሠረት የተሰራውን ስራ
በሠዓት መቆጣጠሪያ ማስረዳት አለበት፡፡ በአመልካች የቀረበው የሠዓት መቆጣጠሪያ ለክሱ መነሻ በሆነው
መኪና የተሰራ ስራ ስለመኖሩ አያስረዳም፡፡ የቀረቡት ምስክሮችም መኪናው መከራየቱን እንጂ ስለክፍያው
የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ በሌላ በኩል ተጠሪ ከብር 100,000.00 በላይ መክፈሉን አስረድቷል፡፡ ቀሪ ክፍያ
ያለበት ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፤ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል፡፡ አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለመቀበል ሠርዟል፡፡

ይህ የሠበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሠበር አቤቱታ ይዘትም በግራቀኛችን
የተደረገው ውል እና የቀረበው የሠዓት መቆጣጠሪያ ክፍያው ብር 346,500.00 መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
መክፈሉን ማስረዳት ያለበት ተጠሪ ነው፤ ብር 346,500.00 መክፈሉን አላስረዳም፡፡ ስለሆነም ውሳኔው
ይሻርልኝ የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን መርምሮ የሠዓት መቆጣጠሪያ ቀርቦ እያለ በሥር ፍርድ
ፍርድ ቤት አልቀረበም ተብሎ ክሱ ውደቅ መደረጉ ተገቢነቱን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ያዘዘ
ሲሆን ተጠሪ ተጠርቶ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቷል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ የሠበር አጣሪ ችሎት የያዘው
ጭብጥ፣ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር ጥር 25 ቀን 2005 ዓ/ም በተደረገ የመኪና ኪራይ


ውል ስምምነት መሠረት የሠሌዳ ቁጥር 3-83597 አ.አ. የሆነ ተሽከርካሪ ለ10 ወራት ከ15 ቀናት ለሰራው
ተጠሪ መክፈል ሲገባው ያልከፈለው ቀሪ ገንዘብ ብር 246,500.00 ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፈላቸው ሲሆን
ተጠሪ በበኩሉ የሚከራከረው በውሉ መሠረት የሠዓት መቆጣጠሪያ ሳያቀርቡ ክፍያ መጠየቃቸው አግባብነት
የለውም፡፡ የቀረበው ማስረጃም በአመልካች መኪና ሥራ መስራታችን አያሳይም፤ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል
በማለት ነው፡፡ ግራቀኙ ባላቸው የመኪና ኪራይ ውሉ ስምምነት መነሻ ያደረገ ክርክር የሥር ፍርድ ቤቶች
አመልካች ያቀረቡትን ክስ በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት ወስነዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ
የተመለከተው የሥር ፍርድ ቤት ሆነ ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በሕግ ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው
ናቸው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ላይ
በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሠበትን የፍሬ
ነገር ድምዳሜ ላይ እንዲመለከት ሥልጣን አልተሠጠውም፡፡ ነገር ግን ማስረጃ ለመመዘን ሥልጣን
የተሠጠው ፍርድ ቤት ማስረጃ ሲቀበል የተከራካሪዎችን እኩል የመደመጥ መብት ካላከበረ፣ የማስረዳት
ሸክም (burden of production) የማን ነው የሚለውን ካልለየ፣ የማስረጃ ተቀባይነትና ተገቢነት ላይ
መከተል የሚገባውን ሥርዓት ካልተከተለ፣ በምዘና ጊዜ የሁሉንም ተከራካሪዎች ማስረጃ አብሮ ካልመዘነ፣
የተለየ የማስረዳት ደረጃ (standard of proof) የሚጠይቁ ጉዳዮችን በሚጠይቀው ደረጃ ልክ መረጋገጡን
ካላሳየ እና በመሠረታዊ ሕግ ሆነ በሥነ-ሥርዓት ሕግ ያሉትን የማስረጃ ሕጎችና መርሆች ካላከበረ ጉዳዩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማስረጃ ምዘና ሳይሆን የሕግ አተረጓጎምና አተገባበር ስህተትና ፍርድ ቤት ያለበትን ኃላፊነት አለመወጣት
ስለሚሆን የሰበር ሰሚ ችሎቱ የሚመለከተው ጉዳይ ይሆናል፡፡

በያዘነው ጉዳይ የግራቀኙ የመኪና ኪራይ ውል አንቀጽ 9 እና 10 መሠረት የሠዓት መቆጣጠሪያ ማስረጃ
በአከራይ እና ተከራይ ተወካይ ተሞልቶ በፕሮጀክቱ ኃላፊ ተረጋግጦና ፀድቆ ለክፍያ መቅረብ እንዳለበት
ተመልክቷል፡፡ አመልካችም በሥር ፍርድ ቤት የሰዓት መቆጣጠሪያ ሠነድ እና የሠው ማስረጃዎች
አቅርበዋል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት ማስረጃውን የመዘነ ሲሆን የሠዓት መቆጣጠሪያ ሠነድ መቅረቡን ገልጾ ነገር
ግን ሠነዱ አመልካች ክስ ያቀረቡበት የሠሌዳ ቁጥር 3-83597 አ.አ. የሆነ ተሽከርካሪ የሚመለከት
አይደለም፣ የሠው ምስከሮችም ስለክፍያው መጠን አያውቁም በሚል ውድቅ ያደረገው ስለመሆኑ
ተገንዝበናል፡፡ ይህም ውሳኔ ላይ የተፈጸመ የማስረጃ አቀባበል ሆነ ምዘና መርሕ ስህተት አለመኖሩን
ያሳያል፡፡ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው መክፈሉን ማስረዳት ያለበት ተጠሪ ነው ያሉ ቢሆንም አመልካች
በውሉ የተመለከተው መኪና ምን ያህል ሰዓት እንደሰራ ባላስረዱበት ሁኔታ የማስረዳት ግዴታው ወደተጠሪ
የሚዞርበት ሕጋዊ ምክንያት የለም፡፡ ስለሆነም ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም
ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 256601 ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ/ም እና የፌደራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 83281 የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ አመልካች የራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ. 199004
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ ዘውዱ ሽፈራው

ተጠሪ፡- አቶ ፍሬው በቀለ

መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 57013 በሕዳር 11 ቀን
2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
በመ.ቁ. 329068 ጥር 28 ቀን 2012 ዓ.ም እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.
332581 በመጋቢት 07 ቀን 2012 የሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ
ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ
ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን
አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት
ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በ460 ካ.ሜ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት በ12/03/2011 ዓ.ም በተፃፈ ውል
ከተጠሪ ላይ በብር 250.000 ገዝቶ ሙሉ በሙሉ ገንዘቡን የከፈለ መሆኑን፤ በስሙም በካርታ ቁጥር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

4378/2011 ማስረጃ የተሰጠው መሆኑን፤ ተጠሪ በውሉ መሰረት ቤቱን እስከ 12/03/2011 ዓ.ም. ለመልቀቅ
የተስማማ ቢሆንም ቤቱን የለቀቀው በ03/09/2011 ዓ.ም መሆኑን፤ ተጠሪ በቤቱ ላይ የነበረውን ባለ 3 ፌዝ
መብራት ቆጣሪ የወሰደ መሆኑን በመግለጽ ቆጣሪው የቤቱ አካል ስለሆነ እንዲመልስለልኝ እና የቤቱን ኪራይ
ብር 30,000 እንዲከፍል ይወሰንልኝ በሚል ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን ተጠሪ በሰጠው መልስ በግራ ቀኛችን መካከል የኪራይ ውል የለም፤ ባለ 3 ፌዝ መብራት ቆጣሪ
የተባለው ከቤቱ ጋር ለአመልካች አልሸጥኩም፤ ቆጣሪው ለንግድ ቤት በኢትየጵያ ልማት ባንክ እና መብራት
ሀይል በጻፉልኝ ድጋፍ ለዳቦ ቤት ተብሎ የተሰጠው ነው፤ የዳቦ ማሽኑ ያለቆጣሪው ስለማይሰራ እና የቤቱ
አካል አለመሆኑን በመግለጽ የአመልካች ክስ ወድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ባለ 3 ፌዝ የተባለወ ቆጣሪ ተጠሪ የሸጠው ዳቦ
ቤት ላይ የነበረ እና ተጠሪ ሲጠቀምበት የቆየ ነው፤ተጠሪ ዳቦ ቤቱን በሚሸጥበት ጊዜ ከ3 ፌዝ ቆጣሪ ጋር
አብሮ መሸጡ ተረጋገጧል፤ በግራ ቀኙ መካከል የኪራይ ውል መኖሩ ተረጋግጧል፤ በመሆኑም ተጠሪ ከዳቦ
ቤቱ ላይ ነቅሎ የወሰደውን ባለ 3 ፌዝ ቆጣሪ እንዲመልስ እና ከ12/04/2011 ዓ.ም እስከ 03/09/2011
ዓ.ም ያለውን የ5 ወር የቤት ኪራይ በወር 6,000 ታስቦ በአጠቃላይ ብር 30,000 ለአመልካች ይክፈል
በማለት ወስኗል፡፡

ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
አቅርበዋል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤትም አመልካች ከተጠሪ በግዥ ያገኘው መኖሪያ ቤት የራሱ የሆነ ቆጣሪ
ያለው መሆኑን በግራቀኙ አልተካደም፤ በፍታብሔር ህግ 1132(1) መሰረት የመኖሪያ ቤት የተፈቀደው
ቆጣሪ መብራት ከቤቱ ጋር ለአመልካች ተላልፏል፤ ክርክር ያስነሳው ቆጣሪ ግን የንግድ ቤቱ መሆኑ ግራ
ቀኙ ባልተካካዱበት የስር ፍርድ ቤት በግራ ቀኙ የሽያጭ ውል ላይ የሌለውን ተጠሪ ዳቦ ቤቱን ሲሸጥ
ቆጣሪውንም ጭምር እንደሸጠ የሚቆጠር ነው እንዲሁም የሽያጭ ውሉ በ12/04/2011 ዓ.ም ከተደረገበት
ጀምሮ አመልካች በዚህ ቤት ውስጥ ለመቆየት መብት የለውም፤ የቤት ኪራይ ውል ስለመኖሩ በሰው
ምስክሮች ተረጋግጧል፤ አመልካች ከቤቱ ውስጥ በ12/04/2011 ዓ.ም ለመውጣት የተስማሙ እና
03/09/2011 ዓ.ም ድረስ የቆየ ሲሆን ይህም አራት ወር ከ21 ቀናት ሲሆን የአንድ ወር በ6,000 ሺህ ብር
ሲታሰብ 28,200 ስለሚሆን አመልካች ለተጠሪ ሊከፍል ይገባል በማለት በማሻሻል ወስኗል፡፡ ይህንኑ ውሳኔ
በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችሎት ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- ክርክር ያስነሳው ቆጣሪ የንግድ ቤት መሆኑ ግራ ቀኙ ያልተካካዱ እና በማስረጃ ጭምር
የተረጋገጠ ነው፤ ተጠሪ ቤቱን በሚሸጥልኝ ጊዜ ዳቦ ቤትም ሆነ የዳቦ ስራ አልነበረውም የዳቦ ማሽኑ የገዛው
ቤቱን ሸጦልኝ ስም ካዛወረልኝ በኋላ በባንክ ብድር ነው፤ በመሆኑም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት እና ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ
በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት ክርክር ያስነሳው ቤት ላይ ያለው ባለ 3 ፌዝ ቆጣሪ
የቤቱ አካል አይደለም በማለት የወሰነበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ
ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ክርክር ያስነሳው ባለ 3 ፌዝ ቆጣሪ የዳቦ ማሽን አካል እንጂ የተሸጠው
ቤት አካል አይደለም፤ በቀን 12/03/2011 ዓ.ም የተደረገው ውል የቤት ሽያጭ እንጂ የዳቦ ማሽን ድርጅት
ሽያጭ ውል አይደለም፤ የዳቦ ማሽኑ ቀድሞ የነበረ ነው፤በመሆኑም የስር ከፍተኛ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጡት ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

ከክርከሩ ሒደት መገንዘብ የቻልነው የሚያከራክረው በሽያጭ ከተላለፈው ቤት ላይ ያለው ባለ 3 ፌዝ ቆጣሪ


ከቤቱ ጋር አልተሸጠም በመሆኑም ተጠሪ ከቤቱ ላይ ነቅሎ መውሰዱ ተገቢ አይደለም የኪራይ ገንዘብም
ያልተከፈለ ይከፈለኝ ሲል የአሁን አመልካች ክስ ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ ቤቱ ራሱን የቻለ ቆጣሪ
ያለውና ባለ 3 ፌዝ ቆጣሪው ግን የተሸጠው ቤት አካል ሆኖ ባለመሆኑ ልመልስ አይገባም በሚል
ተከራክረዋል፡፡አከራካሪውን ቤት አመልካች ህዳር 12 ቀን 2011 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ሲገዙ ውሉ
የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ተብሎ መዘጋጀቱ ግራ ቀኙ ያልተካካዱበት ነጥብ ሲሆን ማስረጃን
የመስማት፤የመመርምርና የመመዘን ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ማረጋገጣቸውን
በውሳኔያቸው ላይ አመልክተዋል፡፡

አመልካች ቤቱን ሲገዙ አከራካሪውን ባለ ሶስት ፌዝ የመብራት ቆጣሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዚህም
ተገቢውን ክፍያ በመጨመር የገዙ መሆኑን፤የቤቱ አንድ ክፍልም(ሰርቪሱ) የመብራት ቆጣሪውን የሚጠቀም
የንግድ ቤት መሆኑን ገልፀው የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ቤቱን ሲሸጡ አከራካሪው ባለ ሶስት ፌዝ የመብራት
ቆጣሪ በቤቱ ላይ ያልነበረ መሆኑን ፤የቤቱ አንድ ክፍል ባለ ሶስት ፌዝ መብራት የሚጠቀም የንግድ
እንቅስቃሴ የማይደረግበት መሆኑን በመግለፅ ተጠሪ በግልፅ ያቀረቡት ክርክር የለም፡፡ከዚህ ይልቅ ተጠሪ
ያቀረቧቸው ምስክሮች ተጠሪ የሸጡት የመኖሪያ ቤትና የዳቦ ቤት መሆኑን ከሽያጩ በኋላ ተጠሪ በመኖሪያ
ቤቱ ለ3 ወር በዳቦ ቤቱ ደግሞ ቤት እስኪያገኝ ድረስ እንዲጠቀሙበት የተስማሙ መሆኑን ማስረዳታቸው
የሽያጭ ውሉ ሲከናወን በውሉ ላይ ከተመለከተው ባለፈ የተነጠለ የንግድ ስራ የሚከናወንበት የንግድ
ድርጅት መኖሩን ሁለቱ ቤቶችም ተነጣጥለው ርክክብ ሊፈፀምባቸው እንደሚችል የተጠሪ ምስክሮች
ማስረዳታቸውን ያሳያል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተዋዋይ ወገኖች ውላቸውን ከመዋዋላቸው አስቀድመው ወይም ከተዋዋሉ በኋላ የነበሩትን


ሁኔታዎች፤የፈፀሙትን ተግባር በማመዛዘን ሀሳባቸው ምን እንደነበረ ለማወቅ መሞከር ለውሉ ጉዳይ አግባብ
ያለው ትርጉም ለመስጠት ተገቢ መሆኑን በፍ/ብ/ህ/ቁ.1734(1) የተመለከተ ሲሆን ይህንኑ ድንጋጌ መሰረት
በማድረግ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር 38544 አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡ተጠሪ የሽያጭ
ውሉ ላይ የመኖሪያ ቤት የሽያጭ ውል በሚል መመልከቱን መሰረት በማድረግ ቤቱ ሌላ የመብራት ቆጣሪ
ያለው መሆኑን በመጥቀስ አከራካሪው ባለ ሶስት ፌዝ የመብራት ቆጣሪ የሽያጩ አካል አለመሆኑን በመጥቀስ
ቢከራከሩም ስለ ውሉ ቀርበው ያስረዱት የተጠሪ ምስክሮች ራሳቸው ከውሉ በኋላ የተጠሪን አቆያየት
አስመልክቶ ግራ ቀኙ ሲስማሙ የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዱ ሽያጩ በርግጥም በመኖሪያ ቤት ላይ ብቻ
አለመደረጉን በግልፅ እያመለከቱ “ተጠሪ የሸጡት የመኖሪያ ቤትና የዳቦ ቤት መሆኑን ” ማስረዳታቸው
በወቅቱ የንግድ ድርጅትን ባካተተ መልኩ የሽያጭ ውል መደረጉን ያሳያል፡፡

ከመነሻውም በአከራካሪው የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ወቅት የዳቦ ቤት የንግድ ስራው ከነበረ ፤ይህ የንግድ ስራ
የሚከናወነው በዚሁ የቤቱ አካል ከሆነ ደግሞ ይህ ለንግድ ስራው መሰረት የሆነው አከራካሪው ባለ ሶስት
ፌዝ የመብራት ቆጣሪ የሽያጩ አካል አለመሆኑን በውል የተገለለበትን ማስረጃ በማቅረብ ተጠሪ
አላስረዱም፡፡ወይም በንግድ ህጉ አንቀፅ 127(2)(ሠ) አግባብ አከራካሪው ባለ ሶስት ፌዝ የመብራት ቆጣሪ
ነጋዴውን የሚከተል እንጂ የንግድ መደብሩ ሽያጭ አካል ሆኖ የማይጠቃለል መሆኑን ተገቢውን ማሳያ
በማቅረብ አላስረዱም፡፡ከዚህ ይልቅ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1732 አግባብ በጉዳዮች ውስጥ ያለውን ልማዳዊ ስርአት
በመከተል ውሉን ስንተረጉመው አከራካሪው ባለ ሶስት ፌዝ የመብራት ቆጣሪ ነጋዴውን የሚከተል የንግድ
መደብር ሽያጭ ቢከናወንም ነጋዴውን ተከትሎ የሚሄድ የንግድ መደብሩ አካል ባልሆነበት ከዚህ ይልቅ
ከነጋዴው ተነጥሎ የንግድ መደብሩ አካል ሊሆን የሚችል ሆኖ እያለ የስር የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ
ቤት አከራካሪውን ባለ ሶስት ፌዝ የመብራት ቆጣሪ ተጠሪ ለአመልካች ሊመልስ አይገባም በማለት የስር
የሎሜ ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር መወሰኑና በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች ይህንን ውሳኔ
ማፅናታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.57013 በ11/03/2012 ዓም የሠጠው ውሳኔና


ይህንን ውሳኔ በማፅናት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.
329068 ጥር 28 ቀን 2012 ዓ.ም እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

332581 በመጋቢት 07 ቀን 2012 የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት


ተሸረዋል፡፡
2. የሎሜ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.86641 ሰኔ 24 ቀን 2011 ዓም የሰጠው ውሳኔ ከውጤት አንፃር
ፀንቷል፡፡
3. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ

የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-199400 ቀን፡

03/02/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ አበበ አድገህ-ጠበቃ ዘመኑ ተሰጋ ቀረቡ

ተጠሪዎች ፡- 1. ወ/ሮ ዘሪቱ ደርሰህ

2. አቶ ፍሬዉ ተገኘ

3. አቶ በቃሉ ተገኘ

4. አቶ መስፍን ተገኘ

5. አቶ መልሰዉ ተገኘ ጠበቃ፡- አሊ መሀመድ ቀረቡ

6. አቶ መኮንን ተገኘ

7. አቶ አያሌዉ ተገኘ

8. አቶ ሽታ ተገኘ

9. ወ/ሮ እቴነሽ ተገኘ

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ በተካደ ጊዜ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚገባዉን ዉል አይነት የሚመለከት
ነዉ፡፡አመልካች በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ከ1ኛ ተጠሪ እና
ከተራ ቁጥር 2-5 ድረስ የተጠቀሱ ተጠሪዎች አባት ከሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ጋር በቀን 13/10/1987 ዓ/ም
በተጻፈ የቤት ሽያጭ በደንበጫ ከተማ ዉስጥ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን ስፋቱ 5 ሜትር በ10 ሜትር
ወይም 50 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ በሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን 32 ዚንጎ የቆርቆሮ
ቤት በብር 10,000.00 ሽጠዉልኛል፡፡ገንዘቡን በእለቱ ተረክበዉ የሽያጭ ዉሉን በደንበጫ ከተማ አገልግሎት
ጽ/ቤት አስገብተነዉ በፋይሉ ዉስጥ ይገኛል፡፡ቤቱን በግዥ ያገኘሁ ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜ የታመነ እና
የተረጋገጠ ቢሆንም አሁን ላይ በቤቱ ለመጠቀም ስፈልግ የተለያዩ ተግባራትን እንዳላከናዉንና የቤቱ ስመ
ሀብት በስሜ ዞሮ እንዳይመዘገብ ተጠሪዎች ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ስለሆነም ተጠሪዎች በሚመለከተዉ
አካል ፊት ቀርበዉ የቤቱን ስመ ሀብት በስሜ እንዲያዛዉሩልኝ እንዲወሰንልኝ፡፡ዉሉ የሚፈርስበት ምክንያት
አለ ከተባለም ቤቱ በአሁኑ ጊዜ የሚያወጣዉን የዕለት ዋጋ ብር 200,000.00 እንዲከፍሉኝ ይወሰንልኝ
በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ለክሱ በሰጡት መልስ የቤት ሽያጭ ዉል የለም፡፡ዉሉ
አለ እንኳን ቢባል ስመ ንብረት የማዛወር ጉዳይ አስተዳደራዊ ጉዳይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የመዳኘት
ሥልጣኝ የለዉም፡፡አመልካች ዉል ይፈጸምልኝ ዳኝነት የጠየቁት ዉሉ ከተደረገ ከ23 ዓመት በኋላ በመሆኑ
ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ የታገደ ነዉ፡፡ዉል ነዉ ተብሎ የቀረበዉ ሰነድ 1ኛ ተጠሪም ሆኑ ከተራ ቁጥር 1-5
የተጠቀስን ተጠሪዎች ወላጅ አባት ያልፈረሙበት ነዉ፡፡ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ሆነዉ እያለ በእጅ ጽሁፍ
ተፈርሞ በሀሰት የተዘጋጀ በመሆኑ እንደረቂቅ የሚቆጠር ነዉ፡፡የሚጸና የቤት ሽያጭ ዉል የለም፡፡የቤት
ሽያጭ ዋጋ አልተከፈለም፡፡አመልካች ቤቱን አልተረከቡም፡፡ዉሉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት በዉል
አዋዋይ ተቋም ያልጸደቀና ያልተመዘገበ በመሆኑ ፈራሽ ነዉ፡፡ብር 10,000.00 ገዝቻለሁ እያሉ ብር
200,000.00 ይከፈለኝ ማለታቸዉ የሕግ መሰረት የለዉም፡፡ከ6ኛ እስከ 9ኛ ከተጠቀስን ተጠሪዎች
የሚጠይቁት ዳኝነት ግልጽ አይደለም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 01-73063 ላይ አስቀድሞ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ዉሳኔ በመስጠት
ዉድቀ ካደረገ በኋላ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በቀን 05/03/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ
በቀን 13/10/1987ዓ/ም የተጻፈ የቤት ሽያጭ ዉል በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ እና በተጠሪዎች አዉራሽ
በሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ መካከል ተደርጎ የሽያጩን ገንዘብ መቀበላቸዉ በምስክሮች ቃልና በሰነድ ማስረጃዎች
ተረጋግጧል፡፡ሆኖም ተጠሪዎች ዉሉ የለም በማለት ክደዉ ስለተከራከሩ የቤት ሽያጭ ዉሉ በፍ/ብ/ሕግ
ቁጥር 1723 አኳያ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ያልተመዘገበ ወይም በፍርድ ቤት ፊት
ያልተፈጸመ በመሆኑ አመልካች ዉል እንዲጸናላቸዉ ወይም ስመ ንብረት እንዲዞርላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ
ተቀባይነት የለዉም፡፡ነገር ግን አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች አስረክበዉ በሽያጭ ዉሉ ምክንያት አመልካች
ለ1ኛ ተጠሪ እና ለሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ የከፈሉትን ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር) ተጠሪዎች በአንድነት
ሊመልሱላቸዉ ይገባል በማለት በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ
በመ/ቁጥር 50815 ላይ በቀን 27/05/2012ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞባቸዋል፡፡እንዲሁም ለክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ችሎቱ በመ/ቁጥር 03-97032 ላይ በቀን 05/10/2012 ዓ/ም
በሰጠዉ ትእዛዝ ሰርዞባቸዋል፡፡

አመልካች በቀን 06/04/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ
ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡-ለክርክሩ መነሻ
የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉሉ 1ኛ ተጠሪና ሟች ከ2-9 የተጠቀሱ ተጠሪዎች አባት ቤቱን ከሸጡልኝ በኋላ በቤቱ
ማህደር ዉስጥ ተያይዞ የባለስልጣኑ ማህተም አርፎበት ጸድቆ የሚገኝ ስለሆነ ዉሉ የዉል ምዝገባ ሂደቱን
በሚመለከተዉ ባለስልጣን አካል ፊት ተደረጎና ተመዝግቦ ያለፈና የቀረዉ የሥም ማዞር ሂደት ብቻ እንደሆነ
ተረጋግጧል፡፡ስመ ንብረት ማዞር ደግሞ ከቤት ሽያጭ ዉል ምዝገባ በኋላ ያለ ቀሪ የሥራ ክንዉን ሂደት
እንጂ ምዝገባ አይደለም፡፡የቤት ሽያጭ ዉል ተመዝግቧል ወይም ሥርዓቱን ጠብቆ የማይንቀሳቀስ ንብረት
ሽያጭ ተከናዉኗል ሊባል የሚችለዉ በሰ/መ/ቁጥር 16109 እና 36740 ላይ በተሰጠዉ አስገዳጅ ትርጉምና
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723፣1680፣1681 እና 2878 መሰረት ተዋዋዮች የሽያጭ ዉሉን ይዘዉ ቀርበዉ የሽያጭ
ስምምነታቸዉ ሲገልጹና ዉሉ ከማህደሩ ጋር ሲያያዝና የባለስልጣኑ ማህተም ሲያርፈበት በመሆኑ
አከራካሪዉ ዉልም በዚህ አግባብ የተፈጸመ ሆኖ እያለ በዉል አዋዋይ ፊት ተርጎ የተመዘገበ ዉል ስላልሆነ
ረቂቅ ነዉ በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሠጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ፡፡ከዚህ
ቀደም በነበረዉ የሑከት ይወገድልኝ ክርክር የተጠሪዎች አባት ቤቱን የሸጡልኝ መሆኑን አምነዋል፡፡ስለሆነም
የቤት ሽያጭ ዉሉ በሚመለከተዉ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ የተመዘገበና ፀድቆ ማህተም የተደረገበት ስለሆነ
ተጠሪዎች እንደዉሉ እንዲፈጽሙ አለመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ተብሎ ይታረምልኝ በማለት
አቤቱታቸዉን አቅርበዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ሽያጭ ዉል ስለመኖሩ በአመልካች
የቀረቡ ምስክሮች አስረድተዉ ባለበትና ዉሉም በሚመለከተዉ ማዘጋጃ ቤት ቀርቦ ማህተም ተደርጎበት ከቤቱ
ማህደር ጋር የተያያዘ መሆኑን ተከትሎ አመልካች ቤቱን ተረክበዉ እየተጠቀሙ መሆናቸዉ በተገለጸበት
ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት አልተመዘገበም በሚል ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት እንዲመለሱ የተወሰነበት
አግባብነት ተጠሪዎች ባሉበት እንዲመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 08/07/2013 ዓ/ም የተፃፈ
በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል፡፡

ተጠሪዎች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ዉል ከመካድ ባለፈ በሰነዱ ላይ ያለዉ ፊርማ የሟች እንዳልሆነ
በመግለጽ በግልጽ ክደን ተከራክረናል፡፡በዉሉ ላይ ያለዉ ፊርማ በፎረንሲክ ቢመረመርም ፊርማዉ የሟች
መሆን አለመሆኑ አልተረጋገጠም፡፡እንዲሁም ዉሉ በዉል አዋዋይ ፊት ያልተደረገና ያልተመዘገበ
ነዉ፡፡እነዚህን ምክንያቶች ተቀብሎ የስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 ስር የተደነገገዉን መሰረት
አድርጎ የሰጠዉ ዉሳኔ የሰ/መ/ቁጥር 21448 የተሰጠዉን አስገዳጅ ትርጉም መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡ዉሉ በቤቱ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማህደር ዉስጥ የተያያዘዉና ማህተም ያረፈበት ያለሟች ፈቃድና እዉቅና ዉጭ በሕገ ወጥ መንገድ
በአመልካች ጠያቂነት ነዉ እንጂ በአመልካችና በሟች መሆኑ አልተረጋገጠም፡፡ አመልካች ክስ የቀረበበትን
ቤት በፀናና ሕጋዊ ዉጤት ባለዉ የሽያጭ ዉል የገዛዉ መሆኑን የማስረዳት ግዴታ ያለባቸዉ አመልካች
ሆነዉ እያለ ሕጋዊ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለዉን ማስረጃ በማቅረብ ያላስረዱ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት
በሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካችም በቀን
27/07/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች
ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ሲል የያዘዉን ጭብጥ መሰረት
በማድረግ በክልሉ ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን
አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነውም ማስረጃዎችን መርምሮና መዝኖ ፍሬ ነገርን የማረጋገጥ ሥልጣን የተሰጠዉ የስር ፍርድ
ቤት እንዳረጋገጠዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል በማዘጋጃ ቤት ዉስጥ በሚገኝ ማህደር ዉስጥ
የሚገኝ መሆኑ ቢረጋገጥም ዉሉ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሆነዉን ቤት በሽያጭ ማስተላለፍን የሚመለከት
እንደመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር በተደነገገዉ አግባብ በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት
ያልተደረገ (ያልተረጋገጠ) እና ያልተመዘገበ(non-authenticated) እንደሆነ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡
እንደሚታወቀዉ በአገራችን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሕዝቡ ዘንድ ካለዉ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
የተነሳ የፍትሐ ብሔር ሕጋችንና የፍትሐ ብሔር ፍትህ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ለዜጎች የማይንቀሳቀስ
የንብረት መብት ልዩ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ከዚህ አንጻር ከዘረጋዉ የጥበቃ ሥርዓት ዉሰጥ አንዱ በፍትሐ
ብሔር ሕጉ የተለያዩ አናቅጽ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማስተላለፍ የሚደረጉ ዉሎች መከተል ያለባቸዉ
ፎርማሊቲዎች እና ስለ ምዝገባ የተደነገገዉ ነዉ፡፡ (አንቀጽ 1553-1646 እንዲሁም 1723፣ 2878 እና 3052
ይመለከቷል)፡፡ እነዚህ ድንጋጌዎች የየራሳቸዉ የሆኑ ዓላማዎች ያላቸዉ ቢሆንም፤ አጠቃላይ ዓላማቸዉ ግን
ለማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ልዩ ጥበቃ በመስጠት እነዚህን ንብረቶች በተመለከተ ባለይዞታዉ መብቱን ሲያገኝ
ወይም ንብረቱ በሆነ ምክንያት ወደ ሌላ ሦስተኛ ወገን በሚያስተላልፍበት ወቅት የመመዝገብ ስልጣን
በተሰጠዉ መንግስታዊ አካል ካልተመዘገበ ሕግ ፊት የሚጸና መብት እንዳይኖረዉ በማድረግ ዜጎች በዚህ
ግዙፍነት ባለዉ ንብረት ላይ ያላቸዉን መብት ከፍላጎታቸዉ ዉጪ በሆነ መንገድ እንዳያጡ ጥበቃ
ለመስጠት፤ ብሎም ንብረቱ ወይም ንብረቱን የሚመለከቱ መብቶች በዉል ሊተላለፉ የሚችሉ መሆን
ያለመሆኑንም በማጣራት የዉሉን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ ጭምር ስለመሆኑ ከየድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ
የምንገነዘበዉ ነዉ፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ ከሚከናወኑት ሕጋዉያን ተግባራት ጋር በተያያዘ ምዝገባ ወይም ዉሉ


በሚመለከተዉ አካል ዘንድ እንዲረጋገጥ የግድ ከሚልባቸዉ ዉስጥም አንዱ በፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ
1723(1) ስር የተመለከተዉ ድንጋጌ ሲሆን፣ በዚህ ድንጋጌ መሠረት የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚደረጉ ዉሎች በጽሑፍና ዉል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት መሆን አለበት፡፡ ሕግ አዉጪዉ
ይህ እንዲሆን የፈለገበት ምክንያትም ዉሉ በተዋዋዮች መካከል ስለመደረጉ ለማረጋገጥ (certainty in
transactions) ስለመሆኑ በዙሪያዉ ከተፃፉት አንዳንድ ጽሑፎች መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፤ ይህ ሰበር
ችሎትም በሰ/መ/ቁጥር 36887 ላይ በሰጠዉ የህግ ትርጉም በዚህ ድንጋጌ መሠረት የሚከናወን
የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ምዝገባ ዓላማ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ዉል መኖሩን ለማስረዳት ስለመሆኑ
ወስኗል፡፡

ከላይ እንደተመለከተዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገዉ ፎርማሊቲ በተዋዋዮች መካከል በፀና
አኳኋን የተደረገ ዉል መኖሩን ለማረጋገጥና በዋናነት የተዋዋዮቹን መብት ለመጠበቅ የተደነገገ ሲሆን
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2878 እና በሌሎች ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተመለከተዉ ምዝገባ (Registration)
ደግሞ ተዋዋዮች የማይነቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ለማስተላለፍ ወይም ባንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ
የአላባ ጥቅም መብት ወይም የመያዣ ወይም የሌላ አገልግሎት መብት ለመቋቋም ወይም በድንጋጌዎቹ ላይ
የተመለከቱትን ሌሎች መብቶችን ለመመስረት ዉል በመዋዋላቸዉ የሦስተኛ ወገኖች መብትና ጥቅም
እንዳይነካ ለሦስተኛ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ ነዉ፡፡ይህ አይነት ምዝገባ (Registration) የሚከናወነዉም
ንብረቱ ተመዝግቦ በሚገኝበት አስተዳደር አካል ዘንድ በሚገኘዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ላይ
ነዉ፡፡በመሆኑም ተዋዋዮች የቤት ሽያጭ ዉል የለም በሚል ዉሉን ተካክደዉ በሚከራከሩበት ጊዜ በእርግጥም
በፀና አኳኋን የተደረገ ዉል ማድረግ አለማድረጋቸዉን ? ዉሉ የተደረገዉ መቼ ነዉ? የሽያጭ ዉል ከሆነ
በምን ያህል ዋጋ ነዉ የተደረገዉ? ለዉሉ ምክንያት የሆነዉ ምን ዓይነት ንብረት ነዉ? የትስ የሚገኝ ነዉ?
የሚሉና ንብረቱን ለማስተላለፍ መብት ባለዉ ሰዉ መፈረም አለመፈረሙን የሚመለከትና መሰል የይዘት
ክርክሮች የተነሱ እንደሆነ ይህን ለማጣራት ሊቀርብ የሚገባዉ ማስረጃ ዓይነትም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1
ስር በተደነገገዉ አግባብ በጽሑፍ ሆኖ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን ባለዉ አካል ፊት የተደረገ ዉል ሊሆን
ይገባል፡፡ ይህን አስመልክቶም ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 78398 በሰ/መ/ቁጥር 188881 እና
በሌሎችም ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

በተያዘዉም ጉዳይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል በመካከላችን አልተደረገም በማለት 1ኛ ተጠሪ
በራሳቸዉ ሌሎች ተጠሪዎች ደግሞ አባታቸዉን ወርሰዉ ባገኙት የወራሽነት መብት ክደዉ መከራከራቸዉ
የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡አመልካች ደግሞ የቤት ሽያጭ ዉል አለ ብለዉ ክስ በማቅረብ እንደዉሉ
እንዲፈጸምላቸዉ ዳኝነት መጠየቃቸዉ ግልጽ ነዉ፡፡አንድን ፍሬ ነገር ማስረጃ አቅርቦ የማስረዳት ሸክምን
ከሚመለከተዉ መሠረታዊዉ መርህ (Basic Principle of Burden of Proof) መረዳት እንደሚቻለዉ አንድ
አከራካሪ ፍሬ ነገር አለ ወይም የለም ብሎ የሚከራከር ሰዉ ፍሬ ነገሩ መኖሩን ወይም አለመኖሩን በማስረጃ
የማስረዳት ሸክም(ግዴታ) አለበት፡፡ (የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 258-260 እና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001
ይመለከቷል)፡፡በዚህ መሰረት አመልካች ይህንን ፍሬ ነገር ለማስረዳት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት
በዉል አዋዋይ ፊት ተደርጎ የተመዘገበ (authenticated) ዉል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ሆኖም አመልካች በዚህ
አግባብ የተደረገ ዉል ለስር ፍርድ ቤት አላቀረቡም፡፡ዉሉ በማዘጋጃ ቤት በሚገኝ ማህደር ዉስጥ ስለሚገኝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደተመዘገበ ይቆጠራል ብለዉ ያቀረቡት ክርክርም ቢሆን ይሕ ተግባር ተፈጽሞ ቢሆን እንኳን በፍ/ብ/ሕግ
ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገዉን የፎርም ስርዓት የሚተካ ካለመሆኑም በላይ ይህ ተፈጸመ ያሉት ስርዓት
የተዋዋዮቹን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የተዘረጋ ስርዓት ባለመሆኑ ይህ መከራከሪያቸዉ በክልሉ ፍርድ
ቤቶች ተቀባይነት በማጣቱ የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም፡፡

ስለሆነም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት በዉል አዋዋይ ፊት
ተደርጎ የተመዘገበ የቤት ሽያጭ ዉል በማስረጃነት አቅርበዉ ባለማስረዳታቸዉ ተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ዉል
አልተደረገም በማለት ክደዉ የተከራከሩትን ክርክር ተቀብሎ አመልካች በዉሉ መሰረት እንዲፈጸምላቸዉ
ያቀረቡትን ዳኝነት ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ እና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝና በሰበር
ይሄዉ ዉሳኔ መጽናቱ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን
ወስነናል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 01-73063 ላይ በቀን 05/03/2012ዓ/ም የሰጠዉ


ዉሳኔ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 50815 ላይ በቀን 27/05/2012ዓ/ም የሰጠዉ
ትእዛዝ እና የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 03-97032 ላይ በቀን 05/10/2012 ዓ/ም የሰጠው
ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንቷል፡፡

2. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-199400 ቀን፡

03/02/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ አበበ አድገህ-ጠበቃ ዘመኑ ተሰጋ ቀረቡ

ተጠሪዎች ፡- 1. ወ/ሮ ዘሪቱ ደርሰህ

2. አቶ ፍሬዉ ተገኘ

3. አቶ በቃሉ ተገኘ

4. አቶ መስፍን ተገኘ

5. አቶ መልሰዉ ተገኘ ጠበቃ፡- አሊ መሀመድ ቀረቡ

6. አቶ መኮንን ተገኘ

7. አቶ አያሌዉ ተገኘ

8. አቶ ሽታ ተገኘ

9. ወ/ሮ እቴነሽ ተገኘ

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ በተካደ ጊዜ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚገባዉን ዉል አይነት የሚመለከት
ነዉ፡፡አመልካች በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ከ1ኛ ተጠሪ እና
ከተራ ቁጥር 2-5 ድረስ የተጠቀሱ ተጠሪዎች አባት ከሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ጋር በቀን 13/10/1987 ዓ/ም
በተጻፈ የቤት ሽያጭ በደንበጫ ከተማ ዉስጥ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን ስፋቱ 5 ሜትር በ10 ሜትር
ወይም 50 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ በሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን 32 ዚንጎ የቆርቆሮ
ቤት በብር 10,000.00 ሽጠዉልኛል፡፡ገንዘቡን በእለቱ ተረክበዉ የሽያጭ ዉሉን በደንበጫ ከተማ አገልግሎት
ጽ/ቤት አስገብተነዉ በፋይሉ ዉስጥ ይገኛል፡፡ቤቱን በግዥ ያገኘሁ ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜ የታመነ እና
የተረጋገጠ ቢሆንም አሁን ላይ በቤቱ ለመጠቀም ስፈልግ የተለያዩ ተግባራትን እንዳላከናዉንና የቤቱ ስመ
ሀብት በስሜ ዞሮ እንዳይመዘገብ ተጠሪዎች ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ስለሆነም ተጠሪዎች በሚመለከተዉ
አካል ፊት ቀርበዉ የቤቱን ስመ ሀብት በስሜ እንዲያዛዉሩልኝ እንዲወሰንልኝ፡፡ዉሉ የሚፈርስበት ምክንያት
አለ ከተባለም ቤቱ በአሁኑ ጊዜ የሚያወጣዉን የዕለት ዋጋ ብር 200,000.00 እንዲከፍሉኝ ይወሰንልኝ
በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ለክሱ በሰጡት መልስ የቤት ሽያጭ ዉል የለም፡፡ዉሉ
አለ እንኳን ቢባል ስመ ንብረት የማዛወር ጉዳይ አስተዳደራዊ ጉዳይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የመዳኘት
ሥልጣኝ የለዉም፡፡አመልካች ዉል ይፈጸምልኝ ዳኝነት የጠየቁት ዉሉ ከተደረገ ከ23 ዓመት በኋላ በመሆኑ
ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ የታገደ ነዉ፡፡ዉል ነዉ ተብሎ የቀረበዉ ሰነድ 1ኛ ተጠሪም ሆኑ ከተራ ቁጥር 1-5
የተጠቀስን ተጠሪዎች ወላጅ አባት ያልፈረሙበት ነዉ፡፡ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ሆነዉ እያለ በእጅ ጽሁፍ
ተፈርሞ በሀሰት የተዘጋጀ በመሆኑ እንደረቂቅ የሚቆጠር ነዉ፡፡የሚጸና የቤት ሽያጭ ዉል የለም፡፡የቤት
ሽያጭ ዋጋ አልተከፈለም፡፡አመልካች ቤቱን አልተረከቡም፡፡ዉሉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 መሰረት በዉል
አዋዋይ ተቋም ያልጸደቀና ያልተመዘገበ በመሆኑ ፈራሽ ነዉ፡፡ብር 10,000.00 ገዝቻለሁ እያሉ ብር
200,000.00 ይከፈለኝ ማለታቸዉ የሕግ መሰረት የለዉም፡፡ከ6ኛ እስከ 9ኛ ከተጠቀስን ተጠሪዎች
የሚጠይቁት ዳኝነት ግልጽ አይደለም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 01-73063 ላይ አስቀድሞ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ዉሳኔ በመስጠት
ዉድቀ ካደረገ በኋላ ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በቀን 05/03/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ
በቀን 13/10/1987ዓ/ም የተጻፈ የቤት ሽያጭ ዉል በአመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ እና በተጠሪዎች አዉራሽ
በሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ መካከል ተደርጎ የሽያጩን ገንዘብ መቀበላቸዉ በምስክሮች ቃልና በሰነድ ማስረጃዎች
ተረጋግጧል፡፡ሆኖም ተጠሪዎች ዉሉ የለም በማለት ክደዉ ስለተከራከሩ የቤት ሽያጭ ዉሉ በፍ/ብ/ሕግ
ቁጥር 1723 አኳያ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ያልተመዘገበ ወይም በፍርድ ቤት ፊት
ያልተፈጸመ በመሆኑ አመልካች ዉል እንዲጸናላቸዉ ወይም ስመ ንብረት እንዲዞርላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ
ተቀባይነት የለዉም፡፡ነገር ግን አመልካች ቤቱን ለተጠሪዎች አስረክበዉ በሽያጭ ዉሉ ምክንያት አመልካች
ለ1ኛ ተጠሪ እና ለሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ የከፈሉትን ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር) ተጠሪዎች በአንድነት
ሊመልሱላቸዉ ይገባል በማለት በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ
በመ/ቁጥር 50815 ላይ በቀን 27/05/2012ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞባቸዋል፡፡እንዲሁም ለክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ችሎቱ በመ/ቁጥር 03-97032 ላይ በቀን 05/10/2012 ዓ/ም
በሰጠዉ ትእዛዝ ሰርዞባቸዋል፡፡

አመልካች በቀን 06/04/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በተሰጠ
ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ፡-ለክርክሩ መነሻ
የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉሉ 1ኛ ተጠሪና ሟች ከ2-9 የተጠቀሱ ተጠሪዎች አባት ቤቱን ከሸጡልኝ በኋላ በቤቱ
ማህደር ዉስጥ ተያይዞ የባለስልጣኑ ማህተም አርፎበት ጸድቆ የሚገኝ ስለሆነ ዉሉ የዉል ምዝገባ ሂደቱን
በሚመለከተዉ ባለስልጣን አካል ፊት ተደረጎና ተመዝግቦ ያለፈና የቀረዉ የሥም ማዞር ሂደት ብቻ እንደሆነ
ተረጋግጧል፡፡ስመ ንብረት ማዞር ደግሞ ከቤት ሽያጭ ዉል ምዝገባ በኋላ ያለ ቀሪ የሥራ ክንዉን ሂደት
እንጂ ምዝገባ አይደለም፡፡የቤት ሽያጭ ዉል ተመዝግቧል ወይም ሥርዓቱን ጠብቆ የማይንቀሳቀስ ንብረት
ሽያጭ ተከናዉኗል ሊባል የሚችለዉ በሰ/መ/ቁጥር 16109 እና 36740 ላይ በተሰጠዉ አስገዳጅ ትርጉምና
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723፣1680፣1681 እና 2878 መሰረት ተዋዋዮች የሽያጭ ዉሉን ይዘዉ ቀርበዉ የሽያጭ
ስምምነታቸዉ ሲገልጹና ዉሉ ከማህደሩ ጋር ሲያያዝና የባለስልጣኑ ማህተም ሲያርፈበት በመሆኑ
አከራካሪዉ ዉልም በዚህ አግባብ የተፈጸመ ሆኖ እያለ በዉል አዋዋይ ፊት ተርጎ የተመዘገበ ዉል ስላልሆነ
ረቂቅ ነዉ በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሠጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ፡፡ከዚህ
ቀደም በነበረዉ የሑከት ይወገድልኝ ክርክር የተጠሪዎች አባት ቤቱን የሸጡልኝ መሆኑን አምነዋል፡፡ስለሆነም
የቤት ሽያጭ ዉሉ በሚመለከተዉ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ የተመዘገበና ፀድቆ ማህተም የተደረገበት ስለሆነ
ተጠሪዎች እንደዉሉ እንዲፈጽሙ አለመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ ተብሎ ይታረምልኝ በማለት
አቤቱታቸዉን አቅርበዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት ሽያጭ ዉል ስለመኖሩ በአመልካች
የቀረቡ ምስክሮች አስረድተዉ ባለበትና ዉሉም በሚመለከተዉ ማዘጋጃ ቤት ቀርቦ ማህተም ተደርጎበት ከቤቱ
ማህደር ጋር የተያያዘ መሆኑን ተከትሎ አመልካች ቤቱን ተረክበዉ እየተጠቀሙ መሆናቸዉ በተገለጸበት
ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት አልተመዘገበም በሚል ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት እንዲመለሱ የተወሰነበት
አግባብነት ተጠሪዎች ባሉበት እንዲመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 08/07/2013 ዓ/ም የተፃፈ
በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ አቅርበዋል፡፡

ተጠሪዎች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን ዉል ከመካድ ባለፈ በሰነዱ ላይ ያለዉ ፊርማ የሟች እንዳልሆነ
በመግለጽ በግልጽ ክደን ተከራክረናል፡፡በዉሉ ላይ ያለዉ ፊርማ በፎረንሲክ ቢመረመርም ፊርማዉ የሟች
መሆን አለመሆኑ አልተረጋገጠም፡፡እንዲሁም ዉሉ በዉል አዋዋይ ፊት ያልተደረገና ያልተመዘገበ
ነዉ፡፡እነዚህን ምክንያቶች ተቀብሎ የስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723 ስር የተደነገገዉን መሰረት
አድርጎ የሰጠዉ ዉሳኔ የሰ/መ/ቁጥር 21448 የተሰጠዉን አስገዳጅ ትርጉም መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡ዉሉ በቤቱ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማህደር ዉስጥ የተያያዘዉና ማህተም ያረፈበት ያለሟች ፈቃድና እዉቅና ዉጭ በሕገ ወጥ መንገድ
በአመልካች ጠያቂነት ነዉ እንጂ በአመልካችና በሟች መሆኑ አልተረጋገጠም፡፡ አመልካች ክስ የቀረበበትን
ቤት በፀናና ሕጋዊ ዉጤት ባለዉ የሽያጭ ዉል የገዛዉ መሆኑን የማስረዳት ግዴታ ያለባቸዉ አመልካች
ሆነዉ እያለ ሕጋዊ ተቀባይነትና ተዓማኒነት ያለዉን ማስረጃ በማቅረብ ያላስረዱ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት
በሰጠዉ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካችም በቀን
27/07/2013 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች
ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ሲል የያዘዉን ጭብጥ መሰረት
በማድረግ በክልሉ ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን
አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነውም ማስረጃዎችን መርምሮና መዝኖ ፍሬ ነገርን የማረጋገጥ ሥልጣን የተሰጠዉ የስር ፍርድ
ቤት እንዳረጋገጠዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል በማዘጋጃ ቤት ዉስጥ በሚገኝ ማህደር ዉስጥ
የሚገኝ መሆኑ ቢረጋገጥም ዉሉ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሆነዉን ቤት በሽያጭ ማስተላለፍን የሚመለከት
እንደመሆኑ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር በተደነገገዉ አግባብ በሕግ ሥልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት
ያልተደረገ (ያልተረጋገጠ) እና ያልተመዘገበ(non-authenticated) እንደሆነ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡
እንደሚታወቀዉ በአገራችን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሕዝቡ ዘንድ ካለዉ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ
የተነሳ የፍትሐ ብሔር ሕጋችንና የፍትሐ ብሔር ፍትህ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ለዜጎች የማይንቀሳቀስ
የንብረት መብት ልዩ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ከዚህ አንጻር ከዘረጋዉ የጥበቃ ሥርዓት ዉሰጥ አንዱ በፍትሐ
ብሔር ሕጉ የተለያዩ አናቅጽ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማስተላለፍ የሚደረጉ ዉሎች መከተል ያለባቸዉ
ፎርማሊቲዎች እና ስለ ምዝገባ የተደነገገዉ ነዉ፡፡ (አንቀጽ 1553-1646 እንዲሁም 1723፣ 2878 እና 3052
ይመለከቷል)፡፡ እነዚህ ድንጋጌዎች የየራሳቸዉ የሆኑ ዓላማዎች ያላቸዉ ቢሆንም፤ አጠቃላይ ዓላማቸዉ ግን
ለማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ልዩ ጥበቃ በመስጠት እነዚህን ንብረቶች በተመለከተ ባለይዞታዉ መብቱን ሲያገኝ
ወይም ንብረቱ በሆነ ምክንያት ወደ ሌላ ሦስተኛ ወገን በሚያስተላልፍበት ወቅት የመመዝገብ ስልጣን
በተሰጠዉ መንግስታዊ አካል ካልተመዘገበ ሕግ ፊት የሚጸና መብት እንዳይኖረዉ በማድረግ ዜጎች በዚህ
ግዙፍነት ባለዉ ንብረት ላይ ያላቸዉን መብት ከፍላጎታቸዉ ዉጪ በሆነ መንገድ እንዳያጡ ጥበቃ
ለመስጠት፤ ብሎም ንብረቱ ወይም ንብረቱን የሚመለከቱ መብቶች በዉል ሊተላለፉ የሚችሉ መሆን
ያለመሆኑንም በማጣራት የዉሉን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ ጭምር ስለመሆኑ ከየድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ
የምንገነዘበዉ ነዉ፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ ከሚከናወኑት ሕጋዉያን ተግባራት ጋር በተያያዘ ምዝገባ ወይም ዉሉ


በሚመለከተዉ አካል ዘንድ እንዲረጋገጥ የግድ ከሚልባቸዉ ዉስጥም አንዱ በፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ
1723(1) ስር የተመለከተዉ ድንጋጌ ሲሆን፣ በዚህ ድንጋጌ መሠረት የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚደረጉ ዉሎች በጽሑፍና ዉል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠዉ አካል ፊት መሆን አለበት፡፡ ሕግ አዉጪዉ
ይህ እንዲሆን የፈለገበት ምክንያትም ዉሉ በተዋዋዮች መካከል ስለመደረጉ ለማረጋገጥ (certainty in
transactions) ስለመሆኑ በዙሪያዉ ከተፃፉት አንዳንድ ጽሑፎች መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፤ ይህ ሰበር
ችሎትም በሰ/መ/ቁጥር 36887 ላይ በሰጠዉ የህግ ትርጉም በዚህ ድንጋጌ መሠረት የሚከናወን
የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ምዝገባ ዓላማ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ዉል መኖሩን ለማስረዳት ስለመሆኑ
ወስኗል፡፡

ከላይ እንደተመለከተዉ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገዉ ፎርማሊቲ በተዋዋዮች መካከል በፀና
አኳኋን የተደረገ ዉል መኖሩን ለማረጋገጥና በዋናነት የተዋዋዮቹን መብት ለመጠበቅ የተደነገገ ሲሆን
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2878 እና በሌሎች ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተመለከተዉ ምዝገባ (Registration)
ደግሞ ተዋዋዮች የማይነቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ለማስተላለፍ ወይም ባንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ
የአላባ ጥቅም መብት ወይም የመያዣ ወይም የሌላ አገልግሎት መብት ለመቋቋም ወይም በድንጋጌዎቹ ላይ
የተመለከቱትን ሌሎች መብቶችን ለመመስረት ዉል በመዋዋላቸዉ የሦስተኛ ወገኖች መብትና ጥቅም
እንዳይነካ ለሦስተኛ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ ነዉ፡፡ይህ አይነት ምዝገባ (Registration) የሚከናወነዉም
ንብረቱ ተመዝግቦ በሚገኝበት አስተዳደር አካል ዘንድ በሚገኘዉ የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ላይ
ነዉ፡፡በመሆኑም ተዋዋዮች የቤት ሽያጭ ዉል የለም በሚል ዉሉን ተካክደዉ በሚከራከሩበት ጊዜ በእርግጥም
በፀና አኳኋን የተደረገ ዉል ማድረግ አለማድረጋቸዉን ? ዉሉ የተደረገዉ መቼ ነዉ? የሽያጭ ዉል ከሆነ
በምን ያህል ዋጋ ነዉ የተደረገዉ? ለዉሉ ምክንያት የሆነዉ ምን ዓይነት ንብረት ነዉ? የትስ የሚገኝ ነዉ?
የሚሉና ንብረቱን ለማስተላለፍ መብት ባለዉ ሰዉ መፈረም አለመፈረሙን የሚመለከትና መሰል የይዘት
ክርክሮች የተነሱ እንደሆነ ይህን ለማጣራት ሊቀርብ የሚገባዉ ማስረጃ ዓይነትም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1
ስር በተደነገገዉ አግባብ በጽሑፍ ሆኖ ዉል ለማዋዋል ሥልጣን ባለዉ አካል ፊት የተደረገ ዉል ሊሆን
ይገባል፡፡ ይህን አስመልክቶም ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 78398 በሰ/መ/ቁጥር 188881 እና
በሌሎችም ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

በተያዘዉም ጉዳይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የቤት ሽያጭ ዉል በመካከላችን አልተደረገም በማለት 1ኛ ተጠሪ
በራሳቸዉ ሌሎች ተጠሪዎች ደግሞ አባታቸዉን ወርሰዉ ባገኙት የወራሽነት መብት ክደዉ መከራከራቸዉ
የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡አመልካች ደግሞ የቤት ሽያጭ ዉል አለ ብለዉ ክስ በማቅረብ እንደዉሉ
እንዲፈጸምላቸዉ ዳኝነት መጠየቃቸዉ ግልጽ ነዉ፡፡አንድን ፍሬ ነገር ማስረጃ አቅርቦ የማስረዳት ሸክምን
ከሚመለከተዉ መሠረታዊዉ መርህ (Basic Principle of Burden of Proof) መረዳት እንደሚቻለዉ አንድ
አከራካሪ ፍሬ ነገር አለ ወይም የለም ብሎ የሚከራከር ሰዉ ፍሬ ነገሩ መኖሩን ወይም አለመኖሩን በማስረጃ
የማስረዳት ሸክም(ግዴታ) አለበት፡፡ (የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 258-260 እና የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2001
ይመለከቷል)፡፡በዚህ መሰረት አመልካች ይህንን ፍሬ ነገር ለማስረዳት በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት
በዉል አዋዋይ ፊት ተደርጎ የተመዘገበ (authenticated) ዉል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ሆኖም አመልካች በዚህ
አግባብ የተደረገ ዉል ለስር ፍርድ ቤት አላቀረቡም፡፡ዉሉ በማዘጋጃ ቤት በሚገኝ ማህደር ዉስጥ ስለሚገኝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደተመዘገበ ይቆጠራል ብለዉ ያቀረቡት ክርክርም ቢሆን ይሕ ተግባር ተፈጽሞ ቢሆን እንኳን በፍ/ብ/ሕግ
ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገዉን የፎርም ስርዓት የሚተካ ካለመሆኑም በላይ ይህ ተፈጸመ ያሉት ስርዓት
የተዋዋዮቹን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የተዘረጋ ስርዓት ባለመሆኑ ይህ መከራከሪያቸዉ በክልሉ ፍርድ
ቤቶች ተቀባይነት በማጣቱ የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም፡፡

ስለሆነም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት በዉል አዋዋይ ፊት
ተደርጎ የተመዘገበ የቤት ሽያጭ ዉል በማስረጃነት አቅርበዉ ባለማስረዳታቸዉ ተጠሪዎች የቤት ሽያጭ ዉል
አልተደረገም በማለት ክደዉ የተከራከሩትን ክርክር ተቀብሎ አመልካች በዉሉ መሰረት እንዲፈጸምላቸዉ
ያቀረቡትን ዳኝነት ጥያቄ ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ እና በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝና በሰበር
ይሄዉ ዉሳኔ መጽናቱ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ ስህተት ባለመኖሩ ተከታዩን
ወስነናል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 01-73063 ላይ በቀን 05/03/2012ዓ/ም የሰጠዉ


ዉሳኔ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 50815 ላይ በቀን 27/05/2012ዓ/ም የሰጠዉ
ትእዛዝ እና የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 03-97032 ላይ በቀን 05/10/2012 ዓ/ም የሰጠው
ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንቷል፡፡

2. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 199518
ቀን ፡- ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- 1. ወ/ሮ ከጆ ሆዕለሞ

2. አቶ አብሬ ክበሞ አልቀረቡም

ተጠሪ ፡- አቶ ብርሃኑ ሸንቆ፡- ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰ/መ/ቁ. 199518
ቀን ፡- ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች ፡- 1. ወ/ሮ ከጆ ሆዕለሞ

2. አቶ አብሬ ክበሞ አልቀረቡም

ተጠሪ ፡- አቶ ብርሃኑ ሸንቆ፡- ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት የሠጠው ውሳኔ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ
ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ተከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ደግሞ የአፈጻጸም
ከሳሽ ነበሩ፡፡ ለአፈጻጸም መነሻ የሆነው አመልካቾች ሁለት ጥማድ የይዞታ መሬት ለቀው ለተጠሪ
እንዲያስረክቡ ተብሎ የተሠጠው ውሳኔ ነው፡፡ ተጠሪ የአፈጻጸም ክስ ያቀረቡትም በዚህ መሠረት
እንዲፈጽምላቸው ሲሆን አመልካቾች በበኩላቸው ለተጠሪ የተወሰነው በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር
ከተመዘገበው በላይ የእኛን የይዞታ መሬትና መኖሪያ ቤት ቤትን ጭምር ለተጠሪ አሳልፎ የወሰነ በመሆኑ
በተጠሪ ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በተመለከተው አግባብ ፍርዱ እንዲፈጸም ጠይቀዋል፡፡ የአፈጻጸም
ክርክሩን ሲመራ የነበረው የሻሸጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ቤት አመልካቾች እንዲለቁ የተወሰነው መውጪያ
መግቢያ ላይ የሠሩትን ቤት ጨምሮ ስለመሆኑ በውሳኔው የተመለከተ በመሆኑና አመልካቾችም ቤቱን
ለማንሳት ጊዜ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቆይተው ቤቱ ያለበት መሬት የእኛ ነው ማለታቸው ተገቢነት የሌለው
ነው በማለት ቤቱ ተነስቶ እንዲፈጽም ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ በይግባኝ እና በሠበር የተመለከቱት በየደረጃው
የሚገኙ ፍርድ ቤቶች የአፈጻጸም ችሎት ውሳኔን አጽንተዋል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ከተወሰነው ሁለት
ጥማድ መሬት ውጭ መወጪያ መግቢያ በሚል አራት ጥማድ መሬታችን አስረክቡ መባላችን ሆነ ቤት
አፍረሱ መባሉ ከፍርዱ ውጭ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለሆነ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት
ጉዳዩን መርምሮ ቤት ያፍርሱ መባሉ በውሳኔውና በአፈጸጻም ክሱ መሠረት የተጠየቀ መሆን አለመሆኑን
ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ በማዘዙ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ይዘቱ አመልካቾች በያዙት ሁለት
ጥማድ መሬት ቤት ሰርተው የሚገኙ መሆኑ ተረጋግጦ በውሳኔው መሠረት እንዲፈጸም የተወሰነ ነው፡፡
ስለሆነም ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተብሎ ሊፀና ይገባል ብለዋል፡፡
አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የአፈጻጸም ክርክሩ ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነውን ፍርድ
እና የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ተከትሎ የተመራ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን
መርምረናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደመረመርነው ለአፈጻጸም መነሻ የሆነው አመልካቾች ሁለት ጥማድ የይዞታ መሬት ለቀው ለተጠሪ
እንዲያስረክቡ ተብሎ የተሠጠው ውሳኔ ነው፡፡ ተጠሪ የአፈጻጸም ክስ ያቀረቡትም በዚህ መሠረት
እንዲፈጽምላቸው ነው፡፡ አሁን አከራካሪ ሆኖ የዚህን ችሎት ምላሽ የጠየቀው አመልካቾች ቤት እንዲያፈርሱ
ተብሎ በአፈጻጸም ትዕዛዝ መሠጠቱ በፍርዱ መሠረት እየተፈጸመ ያለ መሆን አለመሆኑ ነው፡፡ በዋናነት
ሥነ-ሥርዓት ሕግ የተቀረጸው ሠዎች ግጭቶችን ሠላማዊ በሆኑ ሁኔታ እንዲፈቱ ለማስቻል (peaceful
resolution of disputes)፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበት ዘዴ እንዲኖርና ፍርድ ቤቶች ክርክርን ፍትሐዊ
እና ወጭ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት እንዲችሉ ነው፡፡ የአፈጻጸም ችሎት ጉዳዩን መምራት ያለበት
የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎችና ለአፈጻጸም መሠረት የሆነውን ውሳኔ መሠረት
በማድረግ ሲሆን ውጤቱም ሠዎች በፍርድ ያገኙትን መብት ማስፈጸም ነው፡፡ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 212
መሠረት የሥነ-ሥርዓት ግድፈት ያለበት ፍርድ በይግባኝ ካልተለወጠ የጸና እና ሊፈጸም የሚችል ፍርድ
እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በህግ የተቋቋመ የዳኝነት አካል ከነግድፈቱም ቢሆን የሰጠው ውሳኔ መከበር እና
መፈጸም አለበት፡፡ ፍርድ የማይፈጸም ከሆነ የሕግ የበላይነት መገለጫ የሆነውን ዋናውን የፍርድ ቤቶች
ኃላፊነት አለመወጣት ይሆናል፡፡ ዜጎች በፍትሕ ሥርዓቱ የሚጠቀሙት መብታቸውን ለማስከበር ነው፡፡
የመብት ማስከበር መሠረቱ ደግሞ ፍርድን ከማናቸውም መሠናክል ነጻ በማድረግ ማስፈጸም ነው፡፡ ፍርድ
ቤቶች በዚህ አግባብ ኃላፊነታቸውን ካልተወጡ ዜጎች በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ያገኙት ፍትሕ
የማግኘት መብትን ማረጋገጥ እና ማስፈጸም አይቻልም፡፡ ውጤቱ ደግሞ መብት ካለመከበሩም በተጨማሪ
ፍርድ ቤቶች ላይ እምነት (public trust) እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ሰብዓዊ መብቶችን
ከማስከበር እና የሕግ የበላይነት እንዲኖር ያላቸውን የማይተካ ሚና የመወጣት ግዴታ ያለባቸው በመሆኑና
አንዱ መገለጫ የወሰኑትን ውሳኔ ማስፈጸም በመሆኑ ተከራካሪዎች በፍርድ ያረጋገጡትን መብት
ሳይፈጸምላቸው ፍርዱ ያለውጤት ቀሪ እንዳይሆን የመከላከል የፍርድ ቤቶች ኃላፊነት ነው፡፡

በሌላ በኩል የአፈጻጸም ችሎት በመርህ ደረጃ የቀረበን ውሳኔ የማስፈጸም ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም
ለአፈጻጸም የቀረበው ውሳኔ በህግ ዳኝነት ለመሥጠት ሥልጣን ባለው አካል የተሰጠ፣ የዳኝነት አካሉ በሕግ
አግባብ የተቋቋመ እና የውሳኔው መሠረት የሆነው ነገር ሕልውና ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጥና በአጠቃላይ
ለአፈጻጸም የቀረበው ውሳኔ የጸና እና የሚያስገድድ መሆኑን መመርመር አለበት፡፡ ዋነኛው የፍርድ መገለጫ
የተከራካሪዎችን የፍሬ ነገር ሆነ የሕግ ክርክር ልዩነትን በጭብጥነት በመያዝ ለጉዳዩ የመጨረሻ እልባት
መስጠት ነው፡፡ የአፈጻጸም ችሎት ተግባርም በፍርድ እልባት ያገኘውን መብት ማስፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ
ለአፈጻጸም የሚቀርበው ውሳኔ በዚህ ደረጃ ክርክሩን የቋጨና የአፈጻጸም ችሎቱን ወደሙግት ሂደት
የማያስገባ መሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም አፈጻጸም ችሎት የተከራካሪዎችን መብት በራሱ እየወሰነ
ሊያስፈጽም ስለማይችል ነው፡፡

በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረቡት ክስ ካለኝ 0.306 ሄክታር መሬት በቤተዘመድ ፊት
የሠጠሁትን ሁለት ጥማድ የአደራ መሬት ሊያስረክቡኝ ይገባል ሲሆን የሻሾገ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ
ቁጥር 02179 ታህሳስ 06 ቀን 2010 ዓ/ም በሠጠው ውሳኔ አመልካቾች በአደራ የያዙትን ሁለት ጥማድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሬት ለቀው ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ወስኗል፤ ለአፈጻጸም መሠረት የሆነው ውሳኔም ይኸው ነው፡፡
አመልካቾች በውሳኔው መሠረት ሁለት ጥማድ መሬቱን የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፤ ይህንን ካልፈጸሙ
አፈጸጻም ችሎቱ በውሳኔው በተመለከተው መሠረት ይዞታውን እንዲያስረክቡ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
አመልካቾች በሰበር አቤቱታቸው ሁለት ጥማድ መሬቱ ላይ የተወሰነው ውሳኔ ቢፈጸም ተቃውሞ የሌላቸው
መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሠበር አቤቱታው መሠረት ከፍርድ ውጭ ቤትና አራት ጥማድ መሬት ላይ
እየተፈጸመ ነው የሚል ነው፡፡ አፈጻጸም ችሎቱም የቆርቆሮ ክዳን ቤት አንሰተው ፍርዱን እንዲፈጽሙ
ማዘዙን ከአፈጻጸም ትዕዛዙ ግልባጭ ይዘት ተገንዝበናል፡፡ ተጠሪ ዋናውን ክስ ያቀረቡ ጊዜ ቤት
እንዲፈርስላቸው ዳኝነት የጠየቁ ስለመሆኑ የፍርዱ ይዘት አያሳይም፡፡ ፍርድ ቤቱም በውሳኔ መልክ
ያስቀመጠው ሁለት ጥማድ መሬት እንዲለቀቅ ነው፡፡ በሌላ በኩል ለአፈጸጻም መነሻ የሆነው ፍርድ ገጽ 09
ሁለተኛ አንቀጽ ላይ አመልካቾች ቤት ሰርተው የተጠሪን መውጪያ የከለከሉ ስለመሆኑ መረጋገጡን
አስፍሯል፡፡ በፍርድ የሠፈረው ነጥብ ዳኝነት ያልተጠየቀበትና በፍርዱ ውሳኔ ክፍል ላይ ያልተመለከተ
በመሆኑ የሚፈጸመው የውሳኔ ክፍል አካል ነው ሊባል አይችልም፡፡ ቤት እንዲፈርስ ለመወሰን በይዞታው
ላይ ቤት መሠራቱ ተገልጾ ቤቱ ላይ ግልጽ ዳኝነት ሊጠየቅበት ይገባል፡፡ ቤቱን የሠራው ወገንም ራሱን
የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት ቤቱ በማን ይዞታ ላይ ተሰራ? በፈቃድ የተሰራ ነው ወይስ አይደለም? ሕጋዊ
ውጤቱስ ምንድን ነው? የሚሉና ተያያዥ ጭብጦች ተይዘው ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባ ነው፡፡ አመልካቾች
ቤት እንዲያፈርሱ በዚህ ረገድ ዳኝነት ያልተጠየቀበትና ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ቤት እንዲፈርስ
የተሠጠ ውሳኔ ስለሌለ ቤቱን እንዲያነሱ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ ከፍርዱ ውጭ የሆነና የአመልካቾች
መብት የሚጎዳ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡

በሌላ በኩል አመልካቾች አራት ጥማድ መሬት እንድንለቅ በአፈጻጸም እየተገደድን ነው በሚል ያቀረቡትን
ክርክር በተመለከተ ክርክሩ ቤቱ ያለበት ይዞታን የሚጨምር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ቤቱ ያለበት ይዞታ
በአመልካቾች እጅ ሲቀር ለተጠሪ የሚያስረክቡት ይዞታ መጠን ምን ያህል ይሆናል የሚለው ለአፈጻጸም
መነሻ የሆነው ፍርድ ላይ የተመለከተው አዋሳኝ እንዲሁም በውሳኔው የተገለጸው ሁለት ጥማድ መሬት
ከሚለው ጋር ተጣርቶ ሊፈጸም የሚችል በመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 14137 ግንቦት 14 ቀን
2012 ዓ/ም፣ የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 20779 መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ/ም
እና የሻሾጎ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 02179 ነሀሴ 15 ቀን 2011 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. አመልካቾች ቤት እንዲያነሱ/እንዲያፈርሱ በአፈጻጸም ሊገደዱ አይገባም በማለት ወስነናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

3. የሻሾጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ለአፈጻጸም መነሻ በሆነው ውሳኔ ላይ የተመለከተውን ሁለት ጥማድ ይዞታ
አመልካቾች ቤት ከሰሩበት ውጭ ያለውን በማጣራት እንዲያስፈጽም ጉዳዩን መልሠናል፡፡

4. ተጠሪ በይዞታቸው ላይ ቤት ከተሰራ መብታቸውን ክስ አቅርበው ከማስከበር ይህ ውሳኔ አያግድም፡፡

5. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡ የሻሾጎ ወረዳ ፍርድ ቤት በዚህ ውሳኔ
መሠረት ያስፈጽም፡፡ይጻፍ
 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠ እገድ ካለ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ
ተጠሪ የአፈጻጸም ክስ ያቀረቡትም በዚህ መሠረት እንዲፈጽምላቸው ሲሆን አመልካቾች በበኩላቸው ለተጠሪ
የተወሰነው በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ከተመዘገበው በላይ የእኛን የይዞታ መሬትና መኖሪያ ቤት ቤትን
ጭምር ለተጠሪ አሳልፎ የወሰነ በመሆኑ በተጠሪ ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በተመለከተው አግባብ ፍርዱ
እንዲፈጸም ጠይቀዋል፡፡ የአፈጻጸም ክርክሩን ሲመራ የነበረው የሻሸጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ቤት አመልካቾች
እንዲለቁ የተወሰነው መውጪያ መግቢያ ላይ የሠሩትን ቤት ጨምሮ ስለመሆኑ በውሳኔው የተመለከተ
በመሆኑና አመልካቾችም ቤቱን ለማንሳት ጊዜ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ቆይተው ቤቱ ያለበት መሬት የእኛ
ነው ማለታቸው ተገቢነት የሌለው ነው በማለት ቤቱ ተነስቶ እንዲፈጽም ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ በይግባኝ እና
በሠበር የተመለከቱት በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶች የአፈጻጸም ችሎት ውሳኔን አጽንተዋል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ከተወሰነው ሁለት
ጥማድ መሬት ውጭ መወጪያ መግቢያ በሚል አራት ጥማድ መሬታችን አስረክቡ መባላችን ሆነ ቤት
አፍረሱ መባሉ ከፍርዱ ውጭ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለሆነ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት
ጉዳዩን መርምሮ ቤት ያፍርሱ መባሉ በውሳኔውና በአፈጸጻም ክሱ መሠረት የተጠየቀ መሆን አለመሆኑን
ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ በማዘዙ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ ይዘቱ አመልካቾች በያዙት ሁለት
ጥማድ መሬት ቤት ሰርተው የሚገኙ መሆኑ ተረጋግጦ በውሳኔው መሠረት እንዲፈጸም የተወሰነ ነው፡፡
ስለሆነም ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተብሎ ሊፀና ይገባል ብለዋል፡፡
አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የአፈጻጸም ክርክሩ ለአፈጻጸሙ መነሻ የሆነውን ፍርድ
እና የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ተከትሎ የተመራ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን
መርምረናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደመረመርነው ለአፈጻጸም መነሻ የሆነው አመልካቾች ሁለት ጥማድ የይዞታ መሬት ለቀው ለተጠሪ
እንዲያስረክቡ ተብሎ የተሠጠው ውሳኔ ነው፡፡ ተጠሪ የአፈጻጸም ክስ ያቀረቡትም በዚህ መሠረት
እንዲፈጽምላቸው ነው፡፡ አሁን አከራካሪ ሆኖ የዚህን ችሎት ምላሽ የጠየቀው አመልካቾች ቤት እንዲያፈርሱ
ተብሎ በአፈጻጸም ትዕዛዝ መሠጠቱ በፍርዱ መሠረት እየተፈጸመ ያለ መሆን አለመሆኑ ነው፡፡ በዋናነት
ሥነ-ሥርዓት ሕግ የተቀረጸው ሠዎች ግጭቶችን ሠላማዊ በሆኑ ሁኔታ እንዲፈቱ ለማስቻል (peaceful
resolution of disputes)፣ መብታቸውን የሚያስከብሩበት ዘዴ እንዲኖርና ፍርድ ቤቶች ክርክርን ፍትሐዊ
እና ወጭ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት እንዲችሉ ነው፡፡ የአፈጻጸም ችሎት ጉዳዩን መምራት ያለበት
የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 378 እና ተከታዮቹን ድንጋጌዎችና ለአፈጻጸም መሠረት የሆነውን ውሳኔ መሠረት
በማድረግ ሲሆን ውጤቱም ሠዎች በፍርድ ያገኙትን መብት ማስፈጸም ነው፡፡ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 212
መሠረት የሥነ-ሥርዓት ግድፈት ያለበት ፍርድ በይግባኝ ካልተለወጠ የጸና እና ሊፈጸም የሚችል ፍርድ
እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በህግ የተቋቋመ የዳኝነት አካል ከነግድፈቱም ቢሆን የሰጠው ውሳኔ መከበር እና
መፈጸም አለበት፡፡ ፍርድ የማይፈጸም ከሆነ የሕግ የበላይነት መገለጫ የሆነውን ዋናውን የፍርድ ቤቶች
ኃላፊነት አለመወጣት ይሆናል፡፡ ዜጎች በፍትሕ ሥርዓቱ የሚጠቀሙት መብታቸውን ለማስከበር ነው፡፡
የመብት ማስከበር መሠረቱ ደግሞ ፍርድን ከማናቸውም መሠናክል ነጻ በማድረግ ማስፈጸም ነው፡፡ ፍርድ
ቤቶች በዚህ አግባብ ኃላፊነታቸውን ካልተወጡ ዜጎች በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 37 ያገኙት ፍትሕ
የማግኘት መብትን ማረጋገጥ እና ማስፈጸም አይቻልም፡፡ ውጤቱ ደግሞ መብት ካለመከበሩም በተጨማሪ
ፍርድ ቤቶች ላይ እምነት (public trust) እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ሰብዓዊ መብቶችን
ከማስከበር እና የሕግ የበላይነት እንዲኖር ያላቸውን የማይተካ ሚና የመወጣት ግዴታ ያለባቸው በመሆኑና
አንዱ መገለጫ የወሰኑትን ውሳኔ ማስፈጸም በመሆኑ ተከራካሪዎች በፍርድ ያረጋገጡትን መብት
ሳይፈጸምላቸው ፍርዱ ያለውጤት ቀሪ እንዳይሆን የመከላከል የፍርድ ቤቶች ኃላፊነት ነው፡፡

በሌላ በኩል የአፈጻጸም ችሎት በመርህ ደረጃ የቀረበን ውሳኔ የማስፈጸም ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም
ለአፈጻጸም የቀረበው ውሳኔ በህግ ዳኝነት ለመሥጠት ሥልጣን ባለው አካል የተሰጠ፣ የዳኝነት አካሉ በሕግ
አግባብ የተቋቋመ እና የውሳኔው መሠረት የሆነው ነገር ሕልውና ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጥና በአጠቃላይ
ለአፈጻጸም የቀረበው ውሳኔ የጸና እና የሚያስገድድ መሆኑን መመርመር አለበት፡፡ ዋነኛው የፍርድ መገለጫ
የተከራካሪዎችን የፍሬ ነገር ሆነ የሕግ ክርክር ልዩነትን በጭብጥነት በመያዝ ለጉዳዩ የመጨረሻ እልባት
መስጠት ነው፡፡ የአፈጻጸም ችሎት ተግባርም በፍርድ እልባት ያገኘውን መብት ማስፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ
ለአፈጻጸም የሚቀርበው ውሳኔ በዚህ ደረጃ ክርክሩን የቋጨና የአፈጻጸም ችሎቱን ወደሙግት ሂደት
የማያስገባ መሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም አፈጻጸም ችሎት የተከራካሪዎችን መብት በራሱ እየወሰነ
ሊያስፈጽም ስለማይችል ነው፡፡

በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረቡት ክስ ካለኝ 0.306 ሄክታር መሬት በቤተዘመድ ፊት
የሠጠሁትን ሁለት ጥማድ የአደራ መሬት ሊያስረክቡኝ ይገባል ሲሆን የሻሾገ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ
ቁጥር 02179 ታህሳስ 06 ቀን 2010 ዓ/ም በሠጠው ውሳኔ አመልካቾች በአደራ የያዙትን ሁለት ጥማድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሬት ለቀው ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ወስኗል፤ ለአፈጻጸም መሠረት የሆነው ውሳኔም ይኸው ነው፡፡
አመልካቾች በውሳኔው መሠረት ሁለት ጥማድ መሬቱን የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፤ ይህንን ካልፈጸሙ
አፈጸጻም ችሎቱ በውሳኔው በተመለከተው መሠረት ይዞታውን እንዲያስረክቡ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
አመልካቾች በሰበር አቤቱታቸው ሁለት ጥማድ መሬቱ ላይ የተወሰነው ውሳኔ ቢፈጸም ተቃውሞ የሌላቸው
መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሠበር አቤቱታው መሠረት ከፍርድ ውጭ ቤትና አራት ጥማድ መሬት ላይ
እየተፈጸመ ነው የሚል ነው፡፡ አፈጻጸም ችሎቱም የቆርቆሮ ክዳን ቤት አንሰተው ፍርዱን እንዲፈጽሙ
ማዘዙን ከአፈጻጸም ትዕዛዙ ግልባጭ ይዘት ተገንዝበናል፡፡ ተጠሪ ዋናውን ክስ ያቀረቡ ጊዜ ቤት
እንዲፈርስላቸው ዳኝነት የጠየቁ ስለመሆኑ የፍርዱ ይዘት አያሳይም፡፡ ፍርድ ቤቱም በውሳኔ መልክ
ያስቀመጠው ሁለት ጥማድ መሬት እንዲለቀቅ ነው፡፡ በሌላ በኩል ለአፈጸጻም መነሻ የሆነው ፍርድ ገጽ 09
ሁለተኛ አንቀጽ ላይ አመልካቾች ቤት ሰርተው የተጠሪን መውጪያ የከለከሉ ስለመሆኑ መረጋገጡን
አስፍሯል፡፡ በፍርድ የሠፈረው ነጥብ ዳኝነት ያልተጠየቀበትና በፍርዱ ውሳኔ ክፍል ላይ ያልተመለከተ
በመሆኑ የሚፈጸመው የውሳኔ ክፍል አካል ነው ሊባል አይችልም፡፡ ቤት እንዲፈርስ ለመወሰን በይዞታው
ላይ ቤት መሠራቱ ተገልጾ ቤቱ ላይ ግልጽ ዳኝነት ሊጠየቅበት ይገባል፡፡ ቤቱን የሠራው ወገንም ራሱን
የመከላከል መብቱ ተጠብቆለት ቤቱ በማን ይዞታ ላይ ተሰራ? በፈቃድ የተሰራ ነው ወይስ አይደለም? ሕጋዊ
ውጤቱስ ምንድን ነው? የሚሉና ተያያዥ ጭብጦች ተይዘው ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባ ነው፡፡ አመልካቾች
ቤት እንዲያፈርሱ በዚህ ረገድ ዳኝነት ያልተጠየቀበትና ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ቤት እንዲፈርስ
የተሠጠ ውሳኔ ስለሌለ ቤቱን እንዲያነሱ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ ከፍርዱ ውጭ የሆነና የአመልካቾች
መብት የሚጎዳ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡

በሌላ በኩል አመልካቾች አራት ጥማድ መሬት እንድንለቅ በአፈጻጸም እየተገደድን ነው በሚል ያቀረቡትን
ክርክር በተመለከተ ክርክሩ ቤቱ ያለበት ይዞታን የሚጨምር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ቤቱ ያለበት ይዞታ
በአመልካቾች እጅ ሲቀር ለተጠሪ የሚያስረክቡት ይዞታ መጠን ምን ያህል ይሆናል የሚለው ለአፈጻጸም
መነሻ የሆነው ፍርድ ላይ የተመለከተው አዋሳኝ እንዲሁም በውሳኔው የተገለጸው ሁለት ጥማድ መሬት
ከሚለው ጋር ተጣርቶ ሊፈጸም የሚችል በመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 14137 ግንቦት 14 ቀን
2012 ዓ/ም፣ የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 20779 መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ/ም
እና የሻሾጎ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 02179 ነሀሴ 15 ቀን 2011 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. አመልካቾች ቤት እንዲያነሱ/እንዲያፈርሱ በአፈጻጸም ሊገደዱ አይገባም በማለት ወስነናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

3. የሻሾጎ ወረዳ ፍርድ ቤት ለአፈጻጸም መነሻ በሆነው ውሳኔ ላይ የተመለከተውን ሁለት ጥማድ ይዞታ
አመልካቾች ቤት ከሰሩበት ውጭ ያለውን በማጣራት እንዲያስፈጽም ጉዳዩን መልሠናል፡፡

4. ተጠሪ በይዞታቸው ላይ ቤት ከተሰራ መብታቸውን ክስ አቅርበው ከማስከበር ይህ ውሳኔ አያግድም፡፡

5. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡ የሻሾጎ ወረዳ ፍርድ ቤት በዚህ ውሳኔ
መሠረት ያስፈጽም፡፡ይጻፍ
 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠ እገድ ካለ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ8/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ.199542
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1. አቶ ዳዊት ወ/ዮሐንስ ፋሪስ ጠበቃ መስፋን መኮንን ቀረቡ

2. ወ/ሪት ሰርካለም ወ/ዮሐንስ ፋሪስ

3. አቶ ዳንኤል ቸርነት

ተጠሪ፡- አቶ ገዛኸኝ ቢራ ዱቤ - ጠበቃ አድማሱ አለማየሁ -ቀረቡ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች ታሕሳስ 08 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር
አቤቱታ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 242906 መጋቢት 08 ቀን 2012 ዓ.ም የስር ፍርድ ቤት
የሰጠውን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 260 ውስጥ
የሚገኙትን ስድስት ክፍል ቤቶች ለአመልካቾች ሊያስረክብ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ
በማጽናት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 194433 ጥቅምት 11 ቀን 2013
ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ
በማቅረባቸው ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡
በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ፤ በዚህ የሰበር
ክርክር የሌሉ ወ/ሮ ፈንታዬ ወ/ዮሐንስ ደግሞ 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካቾች በሥር
ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 260 ካርታ
ቁጥሩ ኮ/ቀ/የማ/ን/መ/341/18371/02 የሆነ ቤት እና ይዞታ ወ/ሮ አልማዝ ኤርኮ እና አሥር አለቃ ወ/ዩሐንስ
ፋሪስ በውርስ የተላለፈላቸው መሆኑን እና ቀሪው ይዞታ በካርታ እንዲካተትላቸው በሂደት ላይ የሚገኙ
መሆኑን፤ ሟች እናታቸው ወ/ሮ አልማዝ ኤርኮ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ
ስድስት ክፍል ቤት ሰርተው እንዲኖሩበት የተፈቀደላቸው መሆኑን፤ የውርስ ሐብት በተጣራበት የመ.ቁ.
33448 በሆነው መዝገብ በቀን 03/11/06 ዓ.ም በጸደቀው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ የተከሳሾች መብት
ስድስት ክፍል ቤት መሆኑን እና በይዞታው ላይ መብት የሌላቸው መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ
የቤቱን ግምት በመክፈል ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ ቤቱን እና ይዞታውን ለቀው እንዲወጡ ይወሰንላቸው
ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን ተጠሪ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ነገሩ ላይ ደግሞ
አመልካቾች የወሰዱት ካርታ መክኗል፤ ሟች ወ/ሮ አልማዝ ኤርኮ በሕይወት እያሉ ቦታውን ሰጥተዋቸው
ቤት ሲሰሩ አመልካቾች አልተቃወሙም፤ 1ኛ ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ ቤቱን ከሰሩበት ቦታ ውጪ ባለው
ይዞታ ላይ ካርታ ለማሰራት አመልክተው በሂደት ላይ እያሉ በአመልካቾች እንቢተኝነት ተቋርጧል፤ የአሁን
ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ መብት በውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ የተረጋገጠ በመሆኑ ክሱ ወድቅ ሊደረግ
ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

የስር 2ኛ ተከሳሽ በሰጡት መልስ ከተጠሪ ጋር ባል እና ሚስት መሆናቸውን እና የአመልካቾች ወላጅ እናት
በህይወት እያሉ ሶስት ክፍል ቤት ሰርተው ከሞቱ በኋላ ደግሞ ሌላ ተጨማሪ 3 ክፍል ቤት መስራታቸውን
አመልካቾች የሚያውቁ መሆኑን፤ የአመልካቾች እናት ተጠሪ እና 2ኛ ተከሳሽ ወደፊት ቤት ሲሰሩ
እንደሚለቁ እንደነገረቻቸው እና ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በ 820 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ግብር እየተገበረበት የቆየ
መሆኑን እና አመልካቾች መብት ካላቸው ቢወሰንላቸው የማይቃወሙ መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በብይን ውድቅ ያደረገ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ
ደግሞ የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ እና ከሚመለከታቸው የአስተዳድ አካላት በአመልካቾች እና በተጠሪ ስም
የሚገኙ ማሕደሮች እንዲቀርቡለት እና ስለጉዳዩ ተጣርቶ ምላሽ እንዲላክለት ካደረገ በኋላ በአመልካቾች
አውራሽ ፍቃድ በይዞታው ላይ ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ ስድስት ክፍል ቤት መስራታቸው እና
የአመልካቾች አውራሽ በ820 ካ.ሜ ላይ ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸው ተረጋግጧል፤ ተጠሪ ይዞታው በስጦታ
የተላለፈለት ስለመሆኑ አላስረዳም፤ በይዞታው ላይ የሰፋ መብት ያላቸውም የአመልካቾች አውራሽ እንጂ
ተጠሪ አይደለም፤ ተጠሪ እና የስር 2ኛ በአመልካቾች አውራሾች ይዞታ ላይ ስድስት ክፍል ቤት ሲሰሩ
አመልካቾች ያልተቃወሙ በመሆኑ በመሐንዲስ በተረጋጠው መሠረት የቤቱን ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ብር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

142,201 / አንድ መቶ አርባ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ አንድ / ከፍለዋቸው ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ
በአመልካቾች አውራሽ ይዞታ ላይ የሰሩትን ስድስት ክፍል ቤቶች ለቀው እንዲስረክቡ በማለት ወስኗል፡፡

የአሁን ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
አቅርበዋል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የአመልካቾች አውራሾች በፈቀዱላቸው ባዶ ቦታ ላይ
የአመልካቾች አውራሽ ከመሞታቸው በፊት ሶስት ክፍል ቤት መስራታቸውን እንዲሁም ወ/ሮ አልማዝ ኤርኮ
ከሞቱ በኋላም አመልካቾች ሳይቃወሙ ተጨማሪ ሶስት ክፍል ቤቶችን መስራታቸው ተረጋግጧል፤ በእነ
ፋንታዬ ወልደዩሐንስ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው የቦታ ስፋቱ 366 ካ.ሜ እንደሆነ ለተጠሪ እና ለስር 2ኛ
ተከሳሽ የተፈቀደላቸው ይዞታ በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኝ የይዞታ ይካተትልኝ ጥያቄ ተነስቶ በጽ/ቤቱ
በኩል ስራው እንዳልተከናወነ ተረጋግጧል፤ ተሰሩ የተባሉት ቤቶች የሚገኙት የውርስ ሐብት ክርክር
በተነሳበት ቤት ውስጥ መሆኑን በፍርድ ቤት የጸደቀው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ያመለክታል፤ ለባልና ሚስቱ
የተፈቀደላቸው ቤት እንዲሰሩ ብቻ ሳይሆን ባዶ ቦታ ጭምር መሆኑን እና የውርስ ሀብት አካል አለመሆኑ
ተረጋግጦ ባለበት የስር ፍርድ ቤት የተፈቀደላቸው ይዞው ላይ ቤት እንዲሰሩ እንጂ ይዞታውን ጭምር
አይደለም ሲል የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሮ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን ስድስት ክፍል
ቤቶች ለቀው በመውጣት ሊያስረክቡ አይገባም በማለት ወስኗል፡፡ ይህንኑ ውሳኔ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- ተጠሪ እና የስር 2ኛ ተከሳሽ በወቅቱ የነበረባቸውን የመጠለያ ችግር እስኪፈቱ ድረስ 3 ክፍል ቤት
ሰርተው በይዞታው ላይ እንዲጠቀሙ ለጊዜው የመጠቀም መብት የተሰጣቸው መሆኑን የስር 2ኛ ተከሳሽ
አምነዋል፤ የአመልካቾች እናት ከሞተች በኋላ አመልካቾች ልጆች በመሆናችን በእህታችን በ2ኛ ተከሳሽ
ሞግዚትነት እና አስተዳዳር ስር በመሆናችን 3 ክፍል ቤቱን እንዲሰሩ ፍቃድ አልሰጠንም፤ የስር ከፍተኛ
ፍርድ ቤት የስር 2ኛ ተከሳሽ በስር ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ ባላቀረቡበት በተጠሪ የቀረበውን
የይግባኝ ቅሬታ ብቻ መሰረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የለውም፤ በመሆኑም የስር ይግባኝ ሰሚ
ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም
ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ የክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት
እንደሚለቁ ከሟች እናታቸው ጋር የተስማሙ ስለመሆናቸው በመግለጽ መልስ በሰጡበት እና በተሰጠው
ውሳኔ ላይም ይግባኝ ባላቀረቡበት ሁኔታ ተጠሪ ስድስት ክፍል ቤቶች ለቀው ሊያስረክቡ አይገባም በማለት
የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም
ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 33448 በቀን 02/11/2006
ዓ.ም የቀረበው የውርስ አጣሪ ሪፖርት ጸድቋል፤ አከራካሪ የሆኑት ስድስት ክፍል ቤቶች በተጠሪ እና በስር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2ኛ ተከሳሽ ያለምንም ተቃውሞ ስለመስራታቸው አመልካቾች አልካዱም፤ አከራካሪው ይዞታ ተጠሪ ቤት


ሰርቶ እንዲጠቀምበት የተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል፤ የስር 2ኛ ተከሳሽ ቤቱ በጊዜያዊነት ስለመሰጠቱ
የሚያቀርቡት ክርክር በማስረጃ አልተረጋገጠም፤ አመልካቾች በተጠሪ እና በስር 2ኛ ተከሳሽ እህታቸው ላይ
ባቀረቡት ክስ መነሻነት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በጋራ በተሰራው 6 ክፍል ቤት ላይ በመሆኑ ተጠሪ
በዚህ ረገድ ይግባኝ መጠየቄ ተገቢ ነው፤ አመልካቾች 3 ክፍል ቤት ያለፈቃዳችን ተሰራ በማለት
የሚያቀርቡት ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዲስ ክርክር በመሆኑ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤቶች
የተሰጠው ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

አመልካቾች በአሁን ተጠሪ እና ባለቤታቸው በሆኑት የስር 2ኛ ተከሳሽ ላይ አቅርበውት በነበረው ክስ ሟች


እናታቸው ወ/ሮ አልማዝ ኤርኮ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ተጠሪ እና የስር 2ኛ አከራካሪ በሆነው ይዞታ
ላይ ቤት ሰርተው እንዲጠቀሙበት የፈቀዱላቸው ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ተጠሪ እና ባለቤታቸው የሆኑት የስር 2ኛ ተከሳሽ
የአመልካቾች አውራሾች በፈቀዱላቸው ባዶ ቦታ ላይ የአመልካቾች አውራሽ ከመሞታቸው በፊት ሶስት ክፍል
ቤት መስራታቸውን የአመልካቾች እናት ከሞቱ በኋላም አመልካቾች ሳይቃወሙ ተጨማሪ ሶስት ክፍል
ቤቶችን ክርክር በተነሳበት ይዞታ ውስጥ የሰሩ ስለመሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ
10/1 መሠረት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው ስልጣን መሠረታዊ የሆነ የሕግ
ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን
ስልጣን የለውም፡፡
አከራከሪ የሆኑት ስድስት ክፍል ቤቶች በአመልካቾች አውራሽ ፈቃድ ተጠሪ እና ባለቤታቸው የሆኑት የስር
2ኛ ተከሳሽ የሰሯቸው መሆኑ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ይግባኝ
ሰሚ ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ እና ለዚህ ችሎት የተሰጠው ስልጣን መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን
ያልተሰጠው በመሆኑ የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠውን ፍሬነገር መሠረት በማድረግ ተጠሪ
ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ስድስት ክፍል ቤቶች ለቀው በመውጣት ሊያስረክቡ አይገባም በማለት የሰጡት
ውሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1179/1 ድንጋጌን እና ይህንኑ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 30101፤ 36636፤ 105125 እና በሌሎችም መዛግብት ላይ የሰጠውን አስገዳጅ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሕግ ትርጉም መሠረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት
አላገኘንበትም፡፡ ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 242906 መጋቢት 08 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 194433
ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የመ.ቁ.199901
መስከረም 27/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ዘውዴ እረዳ

2ኛ. ወ/ሮ ጥሩወይ በላይ እረዳ

3ኛ. አቶ ጌታሁን ተረፈ እረዳ

4ኛ. ወ/ሮ እመቤት አማረ እረዳ

ተጠሪ፡ ወ/ሮ የሹምነሽ ስዩም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የውርስ ንብረት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአሁን
አመልካቾች በሰቆጣ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን ተጠሪ ላይ ጥቅምት 14/2011 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ
ነው፡፡ የክሱም ጭብጥ ከአያታቸው ቄስ ረዳ ተክለሃይማኖት በውርስ የተላለፈላቸውን ቦታ እና አዋሳኙ
በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን በ245.8 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ አንድ ህድሞ ክብ ቤት የአሁን
ተጠሪ ከነበረባቸው የቤት ችግር በመነሳት እንዲኖሩበት ፈቅደዉላቸው በኋላም በቤቱ ላይ በ2007 ዓ.ም
በወራሾች ስም ካርታ አስወጥተው ለመከፋፈል ተጠሪ እንዲለቁላቸው ሲጠይቋቸው ያለምንም መብትና
ጥቅም አለቅም ብለው ይዘው የሚገኙ መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው እንዲለቁላቸው ዳኝነት
የሚጠይቅ ነው፡፡

በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ተጠሪ ጥቅምት 23/2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና አመራጭ የስረ ነገር ክርክር አቅርበዋል፡፡ መቃወሚያውም ሁለት
ነው፡፡ የመጀመሪያው ቄስ ረዳ ተ/ሓይማት ከሞቱ በኋላ 1ኛ አመልካች፣ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያሉት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካቾች ወላጆች እና ወላጅ እናቴ ወ/ሮ ውዴ ረዳን ጨምሮ በሰባት ወራሾች መካከል የውርስ ሀብት
ክፍፍል ተደርጓል፤ በክፍፍሉም ወላጅ እናቴ ቀድሞኑም ከአባቸው ቄስ ረዳ ጋር ክስ በቀረበበት ቤት
ውስጥ ይኖሩ የነበረ ሲሆን አባታቸውን ጦረው፣ ሲታመሙም አስታመው፤ ከሞቱ በኋላ ደግሞ
አስፈላጊውን ሃይማኖታዊ ስርዓት ሁሉ የፈፀሙላቸው መሆኑ ከግንዛቤ ገብቶ አሁን ክስ የቀረበበት ቤት
ለእናቴ በክፍፍል እንዲደርስ እና ቀሪውን ንብረት ሌሎች ወራሾች እንዲካፈሉት በአስማሚ ሽማግሌዎች
ፊት ስምምነት ፈፅመዋል፤ በስምምነቱ መሰረት ወላጅ እናቴ ክስ የቀረበበትን ቤት ለ25 ዓመታት
ኖረውበት እርሳቸው ከሞቱ በኋላም በውርስ ተላልፎልኝ ለ7 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረ ነው፤
በመሆኑም ክሱ በወራሾች መካከል በስምምነት ባለቀ ጉዳይ ላይ የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ሊደረግ ይገባል
የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የውርስ ሀብት ክፍፍል ከተደረገ ከሶስት ዓመት በኋላ ክስ/መቃወሚያ
ሊቀርብበት የማይችል በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዳል የሚል ነው፡፡ በአማራጭ የስረ ነገር ክርክር
ደግሞ ክስ የቀረበበት ንብረት ከእናቴ በውርስ የተላለፈልኝ ሆኖ እያለ አመልካቾች በመመሳጠር ሆነ
ብለው የተጠሪን የውርስ ሃብት አካተው ካርታ ያወጡበት በመሆኑ ልለቅ አይገባም የሚል ነው፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም ክሱ የቀረበው በስምምነት ባለቀ ጉዳይ ላይ ነው? ወይስ አይደለም? በሚል
ጭብጥ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ሰምቷል፡፡ በዚሁ መሰረት በተጠሪ በኩል የቀረቡት
ምስክሮች የውርስ ክፍፍል ስምምነቱን መርተዋል የተባሉት ሽማግሌዎች መሆናቸውን፤ በሰጡት ቃልም
የግራ ቀኙ አያት በሞቱ ጊዜ የግራ ቀኙን ወላጆች ጨምሮ በሰባት ወራሾች መካከል በስምምነት የውርስ
ሀብት ክፍፍል ያደረጉ መሆኑን፤ በስምምነቱ መሰረትም አሁን ክስ የቀረበበትን ቤት ለአሁን ተጠሪ
ወላጅ እናት እንዲደርስ እና የተቀረውን የውርስ ሀብት ሌሎች ወራሾች ለመካፈል ተስማምተው በዚሁ
መሰረት ጉዳዩን በስምምነት የጨረሱ ስለመሆኑ ሲመሰክሩ በአመልካቾች በኩል የቀረቡት ምስክሮች
ደግሞ ክፍፍል መደረጉን አናውቅም በማለት የተናገሩ ስለመሆኑ መዝግቦ በሰጠው ብይን “የክፍፍል
ስምምነቱ በቃል የተደረገ ቢሆንም በግራ ቀኙ ወላጆች መካከል የውርስ ሀብት ክፍፍል ስምምነት
የተደረገ ስለመሆኑ ተረጋግጧል፤ የውርስ ሀብት ክፍፍልን አስመልክቶ በህግ ተለይቶ የቀመጠ
ፎርማሊቲ የለም፤ ክሱም በስምምነት በተጠናቀቀ ጉዳይ ላይ የቀረበ ነው” በማለት ውድቅ አድርጓል፡፡

ይህንኑ ብይን በይግባኝ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩሉ ስምምነቱ በማይንቀሳቀስ
ንብረት ላይ የተደረገ ሲሆን የፍ/ብ/ህ/ቁ/1567፣ 1568 እና 1723 በሚደነግገው መሰረት በፅሁፍ የቀረበ
ስምምነት ባለመኖሩ ተቀባይነት የለውም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሮ በይርጋ መቃወሚያው
ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ እንዲወስን፤ ክሱ በይርጋ የማይታገድ ከሆነ በክሱ ስረ ነገር ክርክር ላይ
አከራክሮ የመሰለውን እንዲወስን በነጥብ መልሷል፡፡ የአሁን ተጠሪ በተራቸው ይህንን ውሳኔ በመቃወም
ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን
ክርክር ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ለውርስ ሀብት ክፍፍል ስምምነት በህግ ተለይቶ የተቀመጠ ልዩ
ፎርማሊት የለም፤ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተጠቀሱት የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1567፣ 1568 እና 1723
የውል ጉዳይን እንጂ የውርስ ጉዳይን የሚመለከቱ ባለመሆናቸው ለጉዳዩ አግባብነት የላቸውም በማለት
የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር የወረዳ ፍርድ ቤት ብይን አፅንቷል፡፡ ይኸው ውሳኔ
በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች ህዳር 30/2013 ዓ.ም
በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያሉትን መሰረታዊ የህግ
ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍሬ ቃሉም አመልካቾች የሟቹ ወራሽ
ስለመሆናችን የወራሽነት ማረጋገጫ በማውጣት እነ ቄስ ተረፈ እረዳ በሚል በ2007 ዓ.ም በስማቸው
በማዞር ካርታ አሰርተው እስከ 2012 ዓ.ም ግብር እየገበሩ በጋራ የያዙት እና ያልተከፋፈለ የውርስ
ሀብት ስለመሆኑ የሰነድና የሰው ማስረጃ አቅርበው አሰምተው እያለ በአግባቡ ሳይታይ የወረዳው ፍ/ቤት
በብይን መዝጋቱ ትክክል ነው በሚል መወሰናቸው አግባብ አይደለም፤ ተጠሪ ቤት ስለሌላቸው ቤቱን
እየጠበቁ እንዲኖሩበት የተደረገ እንጅ ከቤቱ ላይ መብት የላቸውም፤ ተደረገ የተባለው ስምምነትም
በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የተደረገ ሲሆን ስምምነቱን የሚገልፅ የቀረበ የሰነድ ማስረጃ የለም፤ ይህ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በሌለበት ወንድም እና የአባታቸውን ወገን አቅርበው ስምምነት ነበር በመባሉ ብቻ ጉዳዩ በስምምነት
ያለቀ ነው ተብሎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ያስቀርባል በመባሉ ምክንያት ተጠሪ የፅሁፍ መልስ
እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡ በዚሁ አግባብ ተጠሪ መጋቢት 22/2013 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል፡፡
ፍሬ ቃሉም አንድን ፍሬ ነገር ለማስረዳት ተለይቶ የተመለከተ ማስረጃ እንዲቀርብ ህጉ ካላስገደደ በቀር
ፍሬ ነገሩን በማንኛውም የማስረጃ አይነት ማስረዳት የሚቻል ስለመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/47551 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፤ የውርስ ሀብት ክፍፍል ስርዓትን
አስመልክቶ በወራሾች መካከል በሚደረግ ስምምነት ብቻ ሊፈፀም የሚል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር
1079 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ስር ከመገለፁ ውጭ ክፍፍሉ ሊፈፀም ስለሚገባበት የተለየ ፎርማሊቲ
አልተመለከተም፤ የአያታችን የውርስ ሀብት ክፍፍል አስመልክቶ ወላጆቻችን በራሳቸው በመረጧቸው
ሽማግሌዎች ስምምነት ተደርጎበት ክስ የቀረበበት ንብረት ለወላጅ እናቴ ስለመድረሱ የወረዳው ፍርድ
ቤት በማስረጃ አረጋግጦ ወስኗል፤ ስለ ውርስ ሀብት ክፍፍል በህግ ተለይቶ የተመለከተ ፎርማሊቲ
በሌለበት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አግባብነት የሌላቸውን እና ስለ የማይንቀሳቀስ ሀብት ርስት
ምዝገባ የተመለከቱትን የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1567 እና 1568 ድንጋጌዎችን ጠቅሶ የወረዳ ፍርድ ቤት
ውሳኔን መሻሩ አግባብ ባለመሆኑ የክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ይህንኑ ተረድተው በማረማቸው
የፈፀሙት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም፤ አመልካቾች ክስ ያቀረቡት የውርስ ሀብት ክፍፍሉ ከተደረገ
ሶስት ዓመት በኋላ በመሆኑ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1106 መሰረት ከመነሻው በይርጋ የሚታገድ በመሆኑ
የሰበር አቤቱታው ውድቅ ሊደረግ ይገባል የሚል ነው፡፡ አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን
የሚያጠናክር የመልስ መልስ በመስጠት ሞግተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ይህ ችሎትም
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ክስ በስምምነት ባለቀ ጉዳይ ላይ የቀረበ ነው በሚል በመወሰኑ
የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመኖሩ ለጉዳዩ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ
ተመርምሯል፡፡

እንግዲህ ከክርክሩ አመጣጥ መረዳት እንደሚቻለው የስር ፍርድ ቤቶች የተለያዩት የማይንቀሳቀስ
ንብረትን በተመለከተ በወራሾች መካከል የውርስ ሀብት ክፍፍል ስምምነት ሊፈፀም የሚገባበትን
ፎርማሊትን አስመልክቶ ነው፡፡ በመሰረቱ የውርስ ንብረት ክፍፍል አሰራር በወራሾች መካከል በሚደረግ
ስምምነት፣ በወራሾቹ መካከል ስምምነት ከሌለ ደግሞ ከእነርሱ መካከል አንዱ ተግቶ ያሰናዳውን የክፍያ
ሐሳብ ለዳኞች አቅርቦ በማፀደቅ ሊከናወን እንደሚችል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1079 ይደነግጋል፡፡ በእርግጥ
ህጉ የውርስ ሀብት ክፍፍል በዚህ መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ከመደንገጉ ውጭ በወራሾች መካከል
የሚደረገው የክፍፍል ስምምነት ሊፈፀም ስለሚኖርበት ፎርማሊቲ በግልፅ አላስቀመጠም፡፡ እናም
ስለክፍፍሉ የተለየ ፎርም አለመቀመጡ የስምምነቱ ፎርም አፈፃፀም ለወራሾች የተተወ ነፃነት ነው
ሊባል ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም በዚህ መልኩ የሚደረገው ስምምነት በተስማሚዎቹ መካከል መብትና
ግዴታን የሚፈጥር ውል እንደመሆኑ መጠን የስምምነቱ ፎርማሊቲ ስምምነት ከሚደረግበት ንብረት
ዓይነት እና ባህሪ አኳያ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በዚሁ አግባብ በፍትሐብሔር ህጉ አምስተኛ መፀሓፍ ውስጥ ስለልዩ ውሎች የተደነገገው ልዩ ድንጋጌ
እንደተጠበቀ ሆኖ ከውልም ሆነ ከውል ውጭ የሚመነጭ ማናቸውም ስምምነት በፍትሐብሔር ህጉ
አራተኛ መፀሀፍ ውስጥ ስለውሎች በጠቅላው በተደነገገው መርህ መሰረት የሚመራ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ
ቁጥር 1677 ድንጋጌ ይዘት ያሳያል፡፡ ስለውሎች በጠቅላላው ከሚደነግገው የህጉ ክፍል ውስጥ
ከተመለከቱት መሰረታዊ መርሆዎች ውስጥ አንዱ በቁጥር 1719 ስር የውል ፎርማሊቲን አስመልክቶ
የተቀመጠው መርህ ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት በህግ በልዩ ሁኔታ የውል ፎርም ካልተመለከተ በቀር
ተዋዋይ ወገኖች ስምምነታቸውን በተስማሙበት አኳኋን ሊፈፅሙ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡ የተዋዋይ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወገኖች የስምምነታቸውን ፎርማሊት የመወሰን ነፃነት ከሚገደብበት ልዩ ሁኔታ ወይም በስተቀር ውስጥ
አንዱ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ስምምነትን አስመልክቶ ስለመሆኑ በቁጥር 1723 ስር
ተመልክቷል፡፡ በዚሁ አግባብ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስምልክቶ የሚደረግ የክፍፍል ወይም የማዛወር
ስምምነቶች ሁሉ በጽሑፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን
በተሰጠው አካል ፊት መደረግ እንደሚገባው የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1723(2) ድንጋጌ ያስገነዝባል፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስምልክቶ የሚደረግ ስምምነት በዚህ አይነቱ ጥብቅ የአፈፃፀም ስርዓት
መሰረት እንዲመራ የተፈለገበት የራሱ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ ምክንያት እንዳለው መረዳት ይቻላል፡፡
ከህግ አኳያ ንብረቱ በተፈጥሮው ዘለቄታዊ ባህሪ ያለው በመሆኑ ምክንያት በእንደዚህ ዓይነት ንብረት
ላይ የሚፈጠር ማናቸውም መብት የሶስተኛ ወገኖችን መብት እንዳይጎዳ ተገቢን ቁጥጥር እና ጥንቃቄ
ለማድረግ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ከአስተዳደር አንፃር ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም
የማይንቀሳቀስ ንብረት በህግ አግባብ በተቋቋመ መንግስታዊ አስተዳደር ክፍል ዘንድ መመዝገብ ያለበት
እና በንብረቱ ላይ የሚደረግ ማናቸውም የመብት መለዋወጥ መረጃዎች ሁሉ በሰነድ መደራጀት ያለበት
ስለመሆኑ ስለ የማይነቀሳቀስ ንብረት መዝገብ በሚደነግገው የፍትሐ ብሔር ህጉ አንቀፅ 10 ከቁጥር
1553 ጀምሮ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡

በእርግጥ የፍትሐብሔር ህጉ አንቀፅ 10 ስራ ላይ የሚውልበት ቀን በነጋሪት ጋዜጣ እስኪታወጅ ድረስ


ተፈፃሚ እንደማይሆን በፍ/ብ/ህ/ቁር 3363(1) ስር ተመልክቷል፡፡ ይህ እስከሚሆን ድረስም በምትኩ
በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 3364 - 3367 ድረስ የተመለከቱት ልማዳዊ ደንቦች ተግባራዊ የሚደረጉ ስመሆኑ
በቁጥር 3363(2) ስር ተመልክቷል፡፡ በጊዜ ሂደትም መሬትን እና ሌሎች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን
ምዝገባ እና አስተዳደር የሚመለከቱ የአስተዳደር መዋቅሮች በህግ እንዲቋቋሙ ተደርጎ የማይንቀሳቀስ
ንብረትን የሚመለከቱ ስምምነቶች ላይ አስተዳደራዊ ቁጥጥር እየተደረገበት ያለ ለመሆኑ በችሎት
ግንዛቤ ሊወሰድበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ አግባብ ያላቸው የአስተዳደር አካላት በማይንቀሳቀስ ንብረት
ላይ የተደረገን ስምምነት ተቀብለው ለመመዝገብ እና በስምምነቱ መሰረት በንብረቱ ላይ ተጓዳኝ
መብት ለመፍጠር ስምምነቱ በህጉ በተመለከተው ልዩ ፎርም ተፈፅሞ ሊቀርብላቸው ይገባል ማለት
ነው፡፡

አሁን በቀረበው ጉዳይ ለክርክር ምክንያት የሆነው የማይንቀሳቀስ ንብረት ከ1ኛ አመልካች አባት
እንዲሁም ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለት እና ከተጠሪ አያት በተዋረድ የመጣ የውርስ ሀብት ስለመሆኑ ግራ
ቀኙን ያከራከረ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቁም የሚከራከሩት ንብረቱን አስመልክቶ በወራሾች መካከል
የተደረገ የክፍፍል ስምምነት ስለመኖሩ ላይ ነው፡፡ የተጠሪ መከራከሪያ ክስ የቀረበበት ቤት የአያታችን
የውርስ ሀብት ቢሆንም የውርስ ሃብቱን አስመልክቶ በወራሾች መካከል በቃል ስምምነት ክፍፍል ተደርጎ
ቤቱ ለእናቴ ደርሷቸው ከእናቴ የተላለፈልኝ ነው የሚል ነው፡፡ አመልካቾች በበኩላቸው ስምምነት
ስለመኖሩ ክደዋል፡፡ እንዲያውም በንብረቱ ላይ በወራሾች ስም በጋራ የባለሀብትነት ማረጋገጫ ምስክር
ወረቀት አውጥተው ግብርም በስማቸው እየገበሩ የሚገኙ መሆኑን ገልፀው ይከራከራሉ፡፡ እንግዲህ ተጠሪ
የሚጠቅሱት ስምምነት የተደረገው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በመሆኑ ከላይ በተሰጠው የፍርድ ትችት
መሰረት ስምምነቱ ቢያንስ በፅሁፍ የተዘጋጀ እና በሚመለከታቸው ወራሾች የተፈረመበት ሊሆን
ይግባል፡፡ በዚህ መልኩ የቀረበ ስምምነት በሌለበት እና ስምምነት ስለመኖሩም ከሌሎች ባለመብቶች
ጭምር መከራከሪያ ቀርቦ ባለበት በህግ ረገድ እውቅና የሚሰጠው እና ህጋዊ ውጤት የሚኖረው
ስምምነት አለ ለማለት አይቻልም፡፡ ክስ የቀረበበትን ንብረት አስምልክቶ ቀድሞ የተደረገ እና ህጋዊ
ውጤት የሚኖረው ስምምነት ከሌለ ደግሞ በዚሁ ምክንያት የአመልካቾች ክስ በመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ የሚዘጋበት አግባብ የለም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ ይህ በሆነበት የወረዳው ፍርድ ቤት የአመልካቾችን ክስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መዝጋቱ


እና የክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ መቀበላቸው ስምምነት ተደርጎበታል የተባለውን የውርስ
ሀብት ባህሪ እና ከዚያው አኳያ የተቀመጠውን ተጓዳኝ አስገዳጅ የህግ ፎርማሊትን መሰረት ያላደረገ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ
1. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁ/03-27166 ላይ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡
2. በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር ዞን ከፍተኛ
ፍርድ ቤት በመ/ቁ/01037 ላይ ጥር 29/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዚህን ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡
2. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ.200144

ቀን፡- 02/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ እማሆይ አዛል አይናለም

ተጠሪ፡ አቶ ምህረት በላይ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የስጦታ ውል እንዲፈርስ የቀረበ ክስ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ
ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ
ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ እንዲሁም የቡሬ ወረዳ መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጽ/ቤት 2ኛ
ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የአመልካች ክስ ይዘት ባጭሩ ለተጠሪ ያደረግሁለት የሥጦታ
ውል በመንፈስ ልልነት እና በዕድሜ የገፋሁ አቅመ ደካማ በመሆኔ ምክንያት ከፈቃዴ ውጭ
ህጉን ሳይከተል ያደረግሁት በመሆኑ እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር
የስጦታ ውሉን ያፀደቀ በመሆኑ የስጦታ ውሉ ይፍረስልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ
ባቀረበዉ መልስ አመልካች በፈቃዷ ስጦታውን ያደረገችለት መሆኑን እና ክሱ የቀረበው
የአመልካች ልጆች ከቅን ልቦና ውጭ በሆነ ሁኔታ መሬቱን ለመውሰድ በማሰብ ነዉ፤የስጦታ
ውሉ የሚፈርስበት የህግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡የስር 2ኛ ተከሳሽም አመልካች

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የራሷን ይዞታ በሙሉ ፈቃዷና ፍላጎቷ በወቅቱ በነበሩ ሽማግዎችና የመሬት ባለሙያዎች
ባሉበት ግልጽ የስጦታ ውል በህጉ መሰረት የተደረገ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም
በማለት መልስ መስጠቱን መዝገቡ ያሣያል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች በቀን 24/06/2005 ዓ.ም በቀበሌ
ጽ/ቤት የመሬት ስጦታ ውል ላይ መፈረሟን አልካደችም፣የስጦታ ውሉ በሙሉ ፍላጎት
ማመልከቻ አቅርባ እንዲታሰብበት ተደርጎ በቀበሌውም ማስታወቂያ ተለጥፎ ዉሉ የተፈፀመ
መሆኑን በተጠሪ ምስክሮች በተገቢው ሁኔታ ተረጋግጧል፣ የአመልካች ምስክሮች ግን ስለስጦታ
ውሉ የሚያውቁት የሌለ በመሆኑ ክሱን ማስረዳት አልቻሉም፣ስለዚህ አመልካች ስጦታ
ያደረገችዉ በሙሉ ፍላጎቷና ፍቃዷ መሆኑን እንዲሁም የስር 2ኛ ተከሳሽም ስጦታውን
ተቀብሎ ያፀደቀው በህጉ አግባብ በመሆኑ የስጦታ ውሉ ሊፈርስ አይገባም በማለት ውሳኔ
ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለምዕ/ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባ


ፍ/ቤቱም ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ የተጠሪ ምስክሮች የቀበሌ
መሬት አስተዳደር ኮሚቴ የሆኑት አመልካች ለተጠሪ መሬት ለመስጠት ፍላጎት ኖሯት
ያቀረበችው ማመልከቻ እንደሌለ እና መሬቱ ባለበት ቦታ ያጣሩት ነገር እንደሌለ ገልፀው
በተለይ 1ኛ ምስክር ተጠሪ ስጦታ ልትሰጠኝ ነው ብሎ ወረቀት ይዞ መጥቶ አመልካች አብራ
ካልመጣች በሚል እንደመለሰው እና በዛው ሳይመጣ እንደቀረ የሰጠዉ ቃል እንዲሁም ተጠሪ
የሚጠበቅበትን ቢያንስ 3(ሶስት) ዓመት አመልካችን ስለመጦሩ ማረጋገጫ ሳይቀርብ እና
የወረዳው መሬት አስተዳደር ተጠሪ ያቀረቡት ማመልከቻ ላይ ተቃዋሚ ካለ እንዲቀርብ
የለጠፈው ማስታወቂያ ማግኘት እንዳልቻሉ የገለፁ በመሆኑ የተደረገው የስጦታ ውል ህግና
መመሪያውን ተከትሎ የተፈፀመ ነው ለማለት የሚያስችል ባለመሆኑ ስጦታው ሊሻር ይገባል
በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሽሯል፡፡

የአሁኑ ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን
ፍ/ቤቱም ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ የአመልካች ምስክሮች ስጦታ
ሲደረግ እንደማያውቁ መናገራቸዉን፤ስጦታ ሲደረግ የነበሩት የተጠሪ ምስክሮች ቃል
የሚያስተባብል ባለመሆኑ በህጉ የተቀመጠውን መስፈርት በማሟላት ስጦታ ተደርጓል የተባለው
አነጋገር የተሻለ ተቀባይነት ያለው ነው፣ ተጠሪ የህጉን መስፈርት አሟልቶ ስጦታ ተጠቃሚ
ከሆነ በኋላ ሌሎች ደጋፊ ማስረጃዎች አግባብ ባለው አካል አለመገኘታቸው ስጦታውን
ሊያፈርስበት የሚገባ አይደለም፣ የመጦር ግዴታ የከፍተኛ ፍ/ቤት በራሱ አንስቶ የሰጠው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዳኝነት ሲታይ አግባብ ሆኖ አልተገኘም በማለት የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በመሻር
የወረዳው ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል፡፡

አመልካች ይህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ይታረምልኝ በማለት ለክልሉ


ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ችሎቱም ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኝ
ክርክር መርምሮ የስጦታ ውሉ በመስፈርት ረገድ ጉድለት ያለበት አይደለም፤አመልካች
ስጦታውን ለማድረግ ያመለከተችበት ማመልከቻ እና ቃለጉባኤ ማግኘት ባይቻልም አመልካች
በወረዳው መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ቀርባ ስጦታውን ያደረገች መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ
እና ውሉ በማጭበርበር ወይም ከአመልካች ፈቃድ ውጭ በሆነ ሁኔታ ስለመፈፀሙ በማስረጃ
እስካልተረጋገጠ ድረስ የስጦታ ውሉ የሚፈርስበት ሁኔታ የለም በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ
አጽንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ሲሆን የአመልካች አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሲታይ፤
የስጦታ ውሉ የመሬት አስተዳደር ደንብ ቁ.51/99 እና የአፈፃፀም መመሪያ አንቀጽ 12/7/ ላይ
የተመለከተውን ሂደት ሳይከተል፣የፍ/ህ/ቁ 881 መሰረት ስጦታው የግልጽ ኑዛዜ ስርዓትን
ያልተከተለ በመሆኑ በፍ/ህ/ቁ 2443 መሰረት ተቀባይነት የሌለው እና በስጦታ ቅጽ ላይ
ተጎትቼ እንዲፈርም ተደርጎ የአንድ ዓመት ቆይታ ጠብቆ ሳይመዘገብ ለስጦታ ተቀባይ
ማረጋገጫ ደብተር መስጠቱ እየታወቀ ውሉ የጸና ነው ሲል ውሳኔ መስጠቱ ስህተት በመሆኑ
ውሳኔው ተሽሮ የስጦታ ውሉ እንዲፈርስ በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ የአሁኑ አመልካች መሬት በስጦታ
ለተጠሪ ለመስጠት ለሚመለከተው አካል ማመልከቻ ባልሰጡበት እንዲሁም ተጠሪ የመጦር
ግዴታ መወጣቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የስጦታ ውሉ ሕጋዊ ነው ሊፈርስ አይገባም ተብሎ
በስር ፍ/ቤት የተወሰነበትን አግባብ ከፍ/ሕ/ቁ 881 እና 2443 እንዲሁም ከክልሉ ገጠር መሬት
አዋጅ ጋር በማገናዘብ መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት
ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ታዟል፡፡

ተጠሪ ያቀረበው መልስ ባጭሩ አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ተጠሪ በማባበልና
በማስፈራራት ያለፈቃዴና ፍላጎቴ ወደ ቢሮ ወስዶኝ እጄን ጎትቶ ያስፈረመኝና ስጦታውም
የጸደቀ ስለሆነ ውሉ ይፍርስልኝ የሚል እንጂ ተጠሪ ግዴታውን አልተወጣም ወይም አበል
ከለከኝ አልተባለም፣ስለዚህ ግዴታውን አልተወጣም የሚል በስር ፍ/ቤት ያልተነሳ አዲስ ክርክር
ስለሆነ አጣሪ ችሎቱ የመጦር ግዴታውን መወጣት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የሚለው ጭብጥ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተቀባይነት የለውም፤አመልካች በክልል ሰበር ሰሚ ችሎት የእርሷ ቤተሰብ አባል በመሆን ከ3


አመት በላይ በነፃ ሳገለግልና ስጦር እንደቆየሁ በግልጽ በማመን የስጦታ ውሉ እንዲደረግ
በማመልከቻ ጠይቃ የተደረገ መሆኑ በአዋዋይ ሽማግሌዎች በመረጋገጡ፤ የስጦታ ውል በህግ
የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልቶ የተደረገ መሆኑ ተረጋግጦና ተመዝግቦ ውሉ ፀድቆ
የባለይዞታነት መብት በተጠሪ ስም የተላለፈ ስለመሆኑ አዋዋይ ሽማግሌ በሆኑት ምስክሮችና
በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም ተብሎ
እንዲፀና በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ
አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘበንዉ አመልካች
ለተጠሪ ያደረጉት የገጠር መሬት ስጦታ ዉል በመሬት አስተዳደር አካል ተመዝግቦና በመሬቱ
ላይ የይዞታ መረጋገጫ ደብተር ለተጠሪ መሰጠቱ የተረጋገጠ ፍሬነገር ጉዳይ ሲሆን ይህ ዉል
እንድፈርስ አመልካች ዳኝነት የጠየቁት የሥጦታ ዉሉ በመንፈሰ ልልነትና አቅመ ደካማነት
የተደረገ ነዉ በሚል ምክንያት ስለመሆኑ መዝገቡ ያሣያል፡፡

የስጦታ ዉል ማለት ሰጪዉ ለሌላ ሰዉ ችሮታ በማድረግ ሃሳብ ከንብረቶቹ አንዱን የሚለቅበት
ወይም ግዴታ የሚገባበት ዉል ስለመሆኑና ስጦታ ማድረግ የሰጪዉ የግል ተግባር ስለመሆኑ
የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2427 እና 2434 ይደነግጋል፡ከዚህ እንደምንገነዘበዉ ስጦታ ዉል የጸና ዉል
እንዲሆን እንደማናቸዉም የዉል ጉዳዮች በዉል ህግ የተደነገገዉን መሰረታዊ መስፈርት
አሟልቶ መገኘት ያለበት መሆኑን ነዉ፡፡የስጦታ ዉሉ በህግ የተመለከተዉን መሰረታዊ
መስፈርት እና ስለስጦታ ዉል የተደነገጉትን ደንቦች አላሟላም በሚል መብትና ጥቅሙ
የተነካበት ወገን ዉሉ እንዲፈርስ ሊጠይቅ እንደሚችል ከዉል ህጎች ጠቅላላ ድንጋጌ እና
ስለስጦታ ዉሎች ከተደነገገዉ ልዩ ከፍል መገንዘብ ይቻላል፡፡በመሰረቱ አንድ ዉል እንዲፈርስ
የሚደረገዉ ዉሉ የተቋቋመበት ሁኔታ ከመሰረቱ ግድፈት ሲኖርበት ነዉ፡፡ይኸዉም የተዋዋይ
ወገን ለመዋዋል ችሎታ ወይም ፈቃድ ጉድለት ሲኖር ወይም የዉለታዉ ጉዳይ ህግን ወይም
ግብረ ገብነት/ሞራል/ የሚጻረር ሲሆን ወይም በህግ የተደነገገዉን ፎርም ሳያሟላ ሲቀር
ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1808 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ከእነዚህ ምክንያቶች
በአንዱ ወይም በሌላ ሁኔታ ዉሉ ጉድለት አለበት በሚል ዉሉ እንዲፈርስ መጠየቅ የሚችለዉ
ወገን ማንነት እንደየምክንያቱ የሚለያይ መሆኑም በዚሁ ድንጋጌ ላይ ተመልክቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይህ እንደ አጠቃላይ ሆኖ የስጦታዉ ዉል ሊፈርስ የሚችልባቸዉ ልዩ ሁኔታዎች በህጉ አንቀጽ


2437 እስከ 2440 ላይ ተዘርዝረዋል፡፡በዚህም መሠረት የስጦታ ዉል ሊፈርስ የሚችለዉ
ስጦታዉ በተደረገበት ወቅት ስጦታ አድራጊዉ የአእምሮ ችግር እንዳለበት ታዉቆ በፍርድ
ክልከላ የተደረገበት (judicial interdiction) ወይም ስጦታዉ የተደረገዉ ስጦታ ሰጪዉ የፍርድ
ክልከላ እንዲደረግበት ለፍርድ ቤት ጥያቄ ከቀረበ በኋላ ወይም ስጦታዉ ሲደረግ የስጦታ
ሰጪዉ አእምሮ ጤነኛ አለመሆኑን የዉሉ ይዘት የሚያሳይ ሲሆን፣ ስጦታዉን ለማድረግ መነሻ
የሆነዉ ምክንያት ከህግ ወይም ከሞራል ተቃራኒ ከሆነ፣ ስጦታዉ ሲደረግ ስጦታ ሰጪዉ
በመንፈስ ጫና (undue influence) ስር መሆኑ ከተረጋገጠ ስለመሆኑ ከድንጋጌዎች ይዘት
መገንዘብ ይቻላል፡፡ስለሆነም የስጦታ ዉል እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ የሚያቀርብ ሰዉ
ከእነዚህ ሁኔታዎች ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሁኔታ መኖሩን የመግለጽ እና ይህንኑ የማረጋገጥ
ግዴታ ይኖርበታል፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ ተጠሪ ስጦታዉ እንዲፈርስ የጠቀሱት ምክንያት ስጦታ ያደረጉት በመንፈስ
ልልነትና አቅመ ደካማነት በተጠሪ ጫና ተደርጎባቸዉ መሆኑን በመግለጽ ሲሆን የሥር ፍርድ
ቤቶች የግራቀኙን ማስረጃ መርምረዉ እና አመዛዝነዉ በዚህ ረገድ የአመልካች ምስክሮች
ያስረዱት አሳማኝ ምክንያት አለመኖሩን አረጋግጠዋል፡፡በመሰረቱ የስጦታ ዉሉ የተደረገዉ
በመንፈስ መጫን ነዉ የሚለዉን ፍሬነገር ጉዳይ የማስረዳት ሸክም የአመልካች ስለመሆኑ ህጉ
ያስገነዝባል፡፡የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2439፤2001/1/ እና የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 259 ድንጋጌዎችን
ይመለከታል፡፡ይሁንና አመልካች በክሱ የጠቀሱት ሁኔታ ስለመኖሩ ወይም በስጦታ አድራጊዉ
አእምሮ ላይ ተፅዕኖ ስለመኖሩ የተረጋገጠ ነገር የለም፡፡ስለዚህም እንደክሳቸዉ አቀራረብ ዉሉ
በጫና የተደረገ መሆኑን ማስረዳት ባልቻሉበት ሁኔታ በዚህ ምክንያት ዉሉ እንዲፈርስ
ያቀረቡት ቅሬታ ተገቢነት የለዉም፡፡ሌላዉ አመልካች መከራከሪያ የሥጦታ ዉሉ ፎርም
የሚመለከት ነዉ፡፡ አከራካሪዉ የሥጦታ ዉል የተደረገዉ በ24/06/2005ዓ.ም መሆኑን መዝገቡ
ያሣያል፡፡ የገጠር መሬት ባለይዞታ የይዞታ መብቱን በስጦታ ሌላ ሰዉ ሊያስተላለለፍ የሚችል
ስለመሆኑና መሟላት ያለባቸዉ ሁኔታዎች አስመልከቶ በወቅቱ ስራ ላይ የነበረዉ አማራ ክልል
የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 133/98 አንቀጽ 15 እና 17 በዝርዝር ደንግጓል፡፡ የዉሉን ፎርም
አስመልከቶ የስጦታ ዉሉ በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት ተመልክቷል፡፡የአዋጁን
አንቀጽ17/5/ይመለከታል፡፡እንዲሁም ስምምነቱ መሬቱ በሚገኝበት ወረዳ ባለዉ የባለስልጣኑ
ቅርንጫፍ መ/ቤት ቀርቦ መመዝገብ እንዳለበትም ያመለክታል፡፡በተያዘዉም ጉዳይ ማስረጃ
የመመርመርና ፍሬነገር ማረጋገጥ ሃላፊነት የተሰጣቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች እንዳረጋገጡት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመሬት ስጦታ ዉሉ የተደረገዉ በአካባቢ ሽማግሌዎችና በቀበሌዉ ጽ/ቤት ፊት በጽሁፍ


የተደረገ ስለመሆኑና በአዋጅ እና የአዋጁን ማስፈጸሚያ ደንብ ተከትሎ ተገቢዉን ሂደት
ተከትሎና ፎርማሊቲ ተሟልቶ ምዝገባና የይዞታ ማረጋገጫ በተጠሪ ስም የተከናወነ መሆኑን
ያረጋገጡት ጉዳይ ስለመሆኑ ዉሳኔዉ ያሣያል፡፡ስለሆነም የገጠር መሬት ስጦታ ዉል አፈጻጸም
በሚመለከት በልዩ ህጉ የተደነገገዉ ፎርምና ምዝገባ ስርዓት ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑ
በተረጋገጠበት ሁኔታ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 881 እና 2443 የተደገገዉን አላሟላም የምባልበት
ምክንያት የለም፡፡በዚህም ረገድ አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

በሰበር አጣሪ ችሎት የተያዘዉ ሌላዉ ጭብጥ ተጠሪ አመልካችን ስለመጦሩ ባልተረጋገጠበት
ሁኔታ የሥጦታ ዉሉ ሊፈርስ አይገባም መባሉ ተገቢ መሆን አለመሆኑን በሚመለከት
ነዉ፡፡በመሰረቱ ይህ የክርክር ነጥብ በስር ፍርድ ቤት ዳኝነት ያልተጠየቀበት አዲስ ክርክር
ነዉ በሚል በሰበር ላይ የቅሬታ ነጥብ ሆኖ መቅረቡ ተገቢነት እንደሌለዉ በመግለጽ ተጠሪ
ተከራክሯል፡፡ከመዝገቡ እንደሚታዉ ተጠሪ አመልካችን የመጦር ግዴታ አልተወጣም በሚል
ምክንያት የሥጦታ ዉሉ እንዲፈርስ አመልካች በግልጽ ዳኝነት ስለመጠየቃቸዉ መዝገቡ
አያሣይም፡፡በዚህ ረገድ አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዉሳኔ
እንደሚያሣየዉ የመጦር ግዴታ አስመልከቶ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት በራሱ ጊዜ ያነሳዉ እንጂ
የአመልካች የክስ ምክንያት አለመሆኑን አረጋግጧል፡፡ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የስር ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ዉሳኔ የሻረበት አንዱ ምክንያትም የመጦር ግዴታን በሚመለከት በስር ፍርድ ቤት
ያልቀረበ የክርክር ነጥብ በመሆኑ ነዉ፡፡በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 329/1/ እንደተደነገገዉ በስር
ፍርድ ቤት ያልተነሳ ክርክርና አዲስ ነገር በይግባኝ ሰሚ ችሎት ተቀባይነት የለዉም የሚለዉ
የክርክር አመራር መርህ ይህንኑ የሚያስገነዝብ ነዉ፡፡ይህ መርህ ለሰበር ችሎትም ተፈጻሚነት
እንዳለዉ እሙን ነዉ፡፡ስለሆነም ተጠሪ አመልካችን ለመጦር ከስጦታ ዉሉ ወይም ከህግ
የመነጨ ግዴታ ስለመኖሩ ገልጸዉ ዳኝነት ባልጠየቁበት ብሎም ግዴታዉን ማጓደል
አለማጓደሉ የክርክር ምክንያት ሆኖ በስር ፍርድ ቤት ተጣርቶ ዉሳኔ ባልተሰጠበት ሁኔታ ይህ
ሰበር ችሎት የክርክር ጭብጥ አድርጎ የምወስንበት ስነስርዓታዊ መሰረት የለዉም፡፡ይሁንና
የመጦር ግዴታን አስመልክቶ በማንኛዉም ጊዜ ዳኝነት ከመጠየቅ የሚገድብ አለመሆኑ
ሊታወቅ ይገባል፡፡

ሲጠቃለል የሥጦታ ዉሉ በጽሁፍ የተደረገ እና በሚመለከተዉ አካል የተመዘገበ መሆኑን


በማረጋገጥ ዉሉ የሚፈርስበት ሌላ ህጋዊ ምክንያት መኖሩን አመልካች በተገቢዉ ማስረጃ
ባለማስረዳታቸዉ ክርክራቸዉን ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በግራቀኙ የቀረበዉን ክርክርና በማስረጃ የተረጋገጠዉን ፍሬነገር መሰረት በማድረግ መሆኑን


መገንዘብ ችለናል፡፡በመሆኑም በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፌዴራል ፍርድ
ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4/ እና 10 ድንጋጌዎች መሰረት ለሰበር
ችሎቱ ከተሰጠዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን አንጻር ሲታይ ዉሳኔዉ ህጉንና እና
ስለገጠር መሬት ስጦታ ዉል አፈጻጸም በክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር ህግ የተደነገገዉን
ያገናዘበ ነዉ ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት
ምክንያት አላገኘንም፡፡በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ዉሳኔ

1ኛ/የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/48692 ላይ


በ28/05/2011ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ እና ይህንኑ በማጽናት ሰበር ችሎቱ በመ/ቁ/03-84881 ላይ
በ27/11/2012ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ ህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ጸንቷል፡፡ 2ኛ/በዚህ
ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

ሄ/መ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 200178
ቀን ፡- ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ወ/ሮ ህብስት ምሕረቴ፡- ጠበቃ ባንታምላክ ብናልፍ ቀረቡ

ተጠሪ ፡- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ፡- ዐ/ህግ ማዘንጊያ ደምሴ ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ
እንደተረዳነው አመልካች የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን በወንጀል
ተጠርጥረውና ተከሰው የነበረ ሲሆን በኋላም ከወንጀል ክሱ በፍርድ ቤት በነጻ በመሰናበታቸው ወደሥራ
ለመመለስ አመልክተዋል፡፡ መሥሪያ ቤቱ በሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41
መሠረት በወንጀል ተጠርጥሮ ሥልጣን ባለው አካል በእስር ላይ የነበረና እስከ ሦስት ወር ጊዜ ውስጥ
ከወንጀል ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ወደሥራ ካልተመለሰ አገልግሎቱ ይቋረጣል በሚል በግልጽ የተቀመጠ
በመሆኑና አመልካች በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ጥያቄውን ያላቀረቡ በመሆኑ ተቀብለን መድበን ለማሰራት
አንችልም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን
የአስተዳደር ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ የአማራ ክልል የተሻሻለው የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር
253/2010 አንቀጽ 85(3) መሠረት ከወንጀል ክስ ነጻ የተባለ ሠራተኛ ወደሥራ የሚመለስበትን የጊዜ ገደብ
አያስቀምጥም፡፡ ደንብ ቁጥር 79/2003 አዋጁን ሊጻረር አይችልም፡፡ አመልካች ወደሥራ ሊመለሱ ይገባል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በማለት ወስኗል፡፡ ተጠሪ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ
የአማራ ክልል የገቢዎች አዋጅ ቁጥር 168/2002 ተከትሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 79/2003 መሠረት ተጠሪ
ሠራተኞቹን ያስተዳድራል፡፡ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 44(1) መሠረት የመንግስት ሠራተኞች አዋጅና
ተያያዥ ሕጎች በደንቡ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ብቻ ተፈጻሚ ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ በወንጀል የታሰረ
ሠራተኛን አስመልክቶ ስለሚመለስበት ሁኔታ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 ላይ ስለተሸፈነ በዚህ
ጉዳይ የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ተፈጻሚነት የለውም፡፡ መመሪያ ቁጥር 1/2011 ከአቅም በላይ በሆነ
ምክንያት በሥራ ቦታ አለመገኘትን አስመልክቶ ገቢዎች ቢሮ ያወጣው መመሪያ በወንጀል ተጠርጥሮ ታስሮ
ነጻ የተባለን ሠራተኛ የሚመለከት አይደለም፡፡ አመልካች በሦስት ወር ውስጥ ከወንጀል ክሱ ነጻ መባላቸውን
አረጋግጠው ወደሥራ ለመመለስ ያላመለከቱ በመሆኑ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 መሠረት ወደሥራ
ሊመለሱ አይገባም በማለት የአስተዳደር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሽሯል፡፡ የክልሉ ሰበር ችሎት የአመልካችን
የሠበር አቤቱታ ባለመቀበል ሠርዟል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም በወንጀል ነጻ የተባለ
ሰው እንኳን ቀድሞ የነበረውን ሕጋዊ መብት ቀርቶ አላግባብ ለታሰርኩበት ካሣ ከመጠየቅ ሕጉ
አይከለክልም፡፡ ደንብ ቁጥር 79/2003 በመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 ተሽሯል፡፡ አዋጅ
ቁጥር 253/2020 አንቀጽ 85(3) ታስሮ ከስድስት ወር ጊዜ በላይ የቆየ ሠራተኛ እንኳን በፍርድ ቤት ነጻ
ከተባለ ወደሥራ መመለስ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ደንብ ቁጥር 79/2003 ተፈጻሚ ነው ቢባል እንኳን
በመመሪያ ቁጥር 1/2011 እስር ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ ከወንጀል ክሱ በነጻ
እንደተባልኩ ወደሥራ ለመመለስ ስለጠየቅሁ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎኝ ወደሥራ እንድመለስ ሊወሰን
ይገባል የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ አመልካች ከሥራ ቦታ ያልተገኙት በእስር
ምክንያት ከአቅማቸው በላይ በሆነ ምክንያት ከመሆኑ አኳያ ወደሥራ ሊመለሱ አይገባም መባሉ ከአዋጅ
ቁጥር 253/2010 ድንጋጌዎችን ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ለሰበር ችሎት ያስቀርባል በማለት
ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተጠሪ የሠጠው መልስ የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜው
አልፏል፡፡ ተጠሪ ሠራተኞችን የሚያስተዳድረው ከሲቪል ሰርቪስ ሕጉ ውጭ በተለየ ደንብ ቁጥር 79/2003
ነው፡፡ አመልካች ስድስት ወር በላይ ታስረዋል፡፡ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 መሠረት የታሰረ
ሠራተኛ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ነጻ መሆኑን አረጋግጦ ካልተመሰለ አገልግሎቱ እንደሚቋረጥ
ተደንግጓል፡፡ መመሪያ ቁጥር 1/2011 አንቀጽ 7 ላይ በደንቡ መሠረት አገልግሎቱ የተቋረጠ ወይም
የተፈረደበት ሠራተኛ ወደስራ ለመመለስ የሚያቀርበው ጥያቁ ተቀባይነት እንደሌለው የሚገልጽ በመሆኑ
አመልካች ወደሥራ ሊመለሱ አይገባም ተብሎ መወሰኑ ተገቢ ስለሆነ ሊጸና ይገባል ብሏል፡፡ አመልካች
የመልስ መልስ በማቀረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም አመልካች ወደሥራ ሊመለሱ አይገባም መባሉ ሕጋዊ
መሆን አለመሆኑን? የሚለውን በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደመረመርነው አመልካች የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን
በወንጀል ተጠርጥረውና ተከሰው የነበረ ሲሆን በኋላም ከወንጀል ክሱ በፍርድ ቤት በነጻ በመሰናበታቸው
ወደሥራ ለመመለስ አመልክተዋል፡፡ አመልካች ለክርክር መሠረት ያደረጉት የአማራ ክልል የተሻሻለው
የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀጽ 85(2) በተመለከተው መሠረት የታሰረ ሠራተኛ
የሥራ መደቡ እስከ ስድስት ወር ጊዜ ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚጠብቀውና በንዑስ ቁጥር ሦስት ላይ ደግሞ
ከወንጀሉ ነጻ ተብሎ ከስድስት ወር በኋላ ከመጣ ባለው ክፍት የሥራ መደብ እንደሚመደብ የሚገልጸውን
በመያዝ ነው፡፡ በሌላ በኩል የተጠሪ የክርክር መሠረት የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሠራተኞችን
የሚያስተዳድረው በአዋጅ ቁጥር 253/2010 ሳይሆን በተለየ ሕግ በመሆኑና ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ደንብ
ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 ላይ ከሦስት ወር በላይ የታሰረ ሠራተኛ አገልግሎቱ ይቋረጣል ስለሚል
አመልካች ከሦስት ወር በበለጠ ጊዜ ታስረው የቆዩ በመሆኑ ወደሥራ ሊመለሱ አይገባም የሚል ነው፡፡
ይሕም ጉዳዩ የሚገዛበት ሕግ ላይ የክርክር ልዩነት ያላቸው መሆኑን ያሳያል፡፡

በመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 171/2002 ሆነ ይህን አዋጅ የሻረው አዋጅ ቁጥር 253/2010
የተፈጻሚነት ወሰኑ በአንቀጽ 4 እንደተመለከተው በመንግስት መሥሪያ ቤትና በመንግስት ሠራተኞች ላይ
ነው፡፡ በመርሕ ደረጃ ማንኛውም የክልሉ የመንግስተ ሠራተኛ የሚተዳደረው በዚሁ ሕግ መሠረት ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል ሕግ አውጪው ሲፈቅድና በተለየ ሕግ ሲደነገግ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞቻቸውን
በተለየ ሕግ ሊያስተዳድሩ ይችላሉ፡፡ የአማራ ክልል የገቢዎች ባለስልጣን ተግባራትን እንደገና ለማቋቋም
በወጣው አዋጅ ቁጥር 168/2002 አንቀጽ 14 እና 8(1) መሠረት መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞቹን በአዋጁና
አዋጁን ለማስፈጸም በሚወጣው ደንብ መሠረት እንደሚያስተዳድር ተመልክቷል፡፡ ይህን ተከትሎም ደንብ
ቁጥር 79/2003 የተደነገገ ሲሆን ሠራተኞቹን የሚተዳደሩበትን ዝርዝር ድንጋጌዎች ይዟል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ
መሥሪያ ቤት ሠራተኞችን የሚያስተዳድረው በተለየ ሕግ ስለመሆኑ ተገንዝበናል፡፡ በደንቡ አንቀጽ 44(1)
ላይ የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ተፈጻሚነቱ በደንቡ ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡

በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 ላይ አንድ የባለስልጣኑ ሠራተኛ በወንጀል ተጠርጥሮ ሥልጣን ባለው
አካል በእስር ላይ ከዋለና እስከ ሦስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከወንጀሉ ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ወደሥራው
ካልተመለሰ አገልግሎቱ ይቋረጣል ሲል ይደነግጋል፡፡ ድንጋጌው በአንድ በኩል ወንጀል ያልፈጸመ ሠራተኛ
የሥራ መደቡ ምን ያህል ጊዜ ክፍት ሆኖ እንደሚጠብቀው የተመለከተ ሲሆን በሌላ በኩል መሥሪያ ቤቱ
ከምን ያህል ጊዜ በላይ የሥራ መደቡን ክፍት አድርጎ ሠራተኛ ሳይቀጥረበት ሥራውን ማስቀጠል ይችላል
የሚለው ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ይሕም የሠራተኛው መብትና ጥቅም እና በሕዝብ/መንግስት ጥቅም መካከል
ሁለቱን ጥቅሞች ለማስታረቅ ታስቦ መቀረጹን ያሳያል፡፡ አመልካች በሕጉ እንደተመለከተው በሦስት ወር ጊዜ
ውስጥ ከወንጀሉ ነጻ ተብለው ወደመሥሪያ ቤቱ ያላመለከቱ በመሆኑ የሥራ አገልግሎታቸው ተቋርጧል፡፡
አመልካች መመሪያ ቁጥር 1/2011 ጠቅሰው ጉዳዩ ለአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ነው በማለት ያቀረቡትን
ክርክር በተመለከተ መመሪያው ሊያስፈጽም የወጣው ደንብ ቁጥር 79/2003 ሲሆን በደንቡ ስለታሰረ ሠራተኛ
ግልጽ ድንጋጌ ያለ በመሆኑ ለጉዳዩ መመሪያው ተፈጻሚነት የለውም ተብሎ ክርክሩ በሥር ፍርድ ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው፡፡ በአጠቃላይ ተጠሪ ሠራተኞቹን በሚስተዳድረበት ሕግ መሠረት አመልካችን
ወደሥራ የሚመልስበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ
የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 97087 ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ/ም
እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 52577 ታህሳስ 14 ቀን
2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መ/ቁ/200247

ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ አቶ ታሪኩ ዮናስ

ተጠሪ ፡ ዳንጎቴ ኢትዮጵያ ሲምንቶ ፋብሪካ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የአሰሪና ሠራተኛ የስራ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል
ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ
ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ፡፡አመልካች 02/06/2012 ዓ.ም ባቀረበው ክስ ተጠሪ
በሰው ኃይል አስተዳደር የሥራ ዘርፍ በደብዳቤ ቁጥር DI-HR-009-14 ሕዳር 24 ቀን 2007
ዓ.ም በወር ደመወዝ ብር 7,100 የቀጠረኝ ሲሆን የሥራ ብቃት ምዘናዬ ከፍተኛ ስለሆነ
በተለያየ ጊዜ እድገት ሰጥቶኝ በመጨረሻ በወር ደመወዝ ብር 29,980.14 እየሰራዉ እያለ
ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ያለአንዳች ጥፋት ከስራዬ ስላሰናበተኝ በአዋጅ ቁ/1156/2011
መሰረት ወደ ስራዬ እንዲመልሰኝ ወይም ካልመለሰኝ የተለያዩ ክፍያዎች በድምሩ ብር
435,711.34 እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በቀን
12/06/2012 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካች ከፍተኛ የኦፊሰር ስራ ዘርፍ እና
የድርጅታችን የሰው ኃይል መመሪያ ኃላፊ በመሆን ሲሰራ ቆይቷል፣ሃላፊነቱ ሥራ አስኪያጅ
የሆነ ሰው ደግሞ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 3(2ሐ) መሰረት በአሰሪና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሰራተኛ አዋጅ መክሰስ ስለማይችል ክሱ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ እንዲሆን


ጠይቋል፡፡

ፍ/ቤቱም የመጀመሪያ መቃወሚያ ላይ የግራ ቀኝ ክርክር በመስማት አመልካች የተቀጠሩበት


የስራ ዘርፍ የድርጅቱን የዓመት ዕቅድና በጀት ማውጣት፣ መከታተል፣ የሚቆጣጠርና
የሚያቀናብር እንደሆነ የጽሁፍ ማስረጃ የሚስገነዝብ ነው፣ የስራ ቅጥሩም የሚያሳየው በሥራ
አስኪያጅነት የስራ ዘርፍ ላይ ተቀጥሮ እንዳለ ስለሚገልፅ ሥራ አስኪያጅ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀጽ 3(2)(ሐ) መሰረት በአሰሪና ሰራተኛ ክርክር የሚታይ አይደለም በማለት
በብይን ክሱን ውድቅ አድርጓል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ


ቢሆንም ፍ/ቤቱ አመልካች የአስተዳደር መመሪያ ኃላፊ ሥራ አስኪያጅ ሆኖ እያለ የአሰሪና
ሰራተኛ አዋጅ ጠቅሶ መብቱን መጠየቁ አግባብነት የለውም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337
መሰረት ይግባኙን ሰርዟል፡፡

አመልካች ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል እንዲታረምልኝ በማለት ለክልሉ


ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ችሎቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ
አመልካች መጀመሪያ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን አምኖ በክሱ ላይ ስለገለፀ ተጠሪው በታመነው
ጉዳይ ላይ ማስረጃ ለማቅረብ አይገደድም፣አመልካች በፊት ከነበረበት የስራ ዘርፍ ወደ ሌላ ስራ
ዘርፍ ተቀይሮ ከስራ መሰናበቱ ያቀረበው ማስረጃ የለም፣አመልካች በተመደበበት የሥራ ዘርፍ
ላይ ደመወዝ ሲጨመርለት እንደቆየ ክሱ ያሳያል፣በተጨማሪም አመልካች ለተለያዩ መ/ቤቶች
የፃፈዉ ደብዳቤ ስራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፣ሥራ አስኪያጅ መሆን የግድ
ሰራተኛ መቅጠርና በጥፋት ከስራ ማሰናበት ብቻ አይደለም፣ስለዚህ የስር ፍ/ቤት አመልካች
ሥራ አስኪያጅ እንጂ ሠራተኛ አይደለም በማለት የደረሰበት አቋም የህግ ስህተት የለዉም
በማለት አጽንቷል፡፡

አመልካች ለዚህ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ባጭሩ መጀመሪያ በተሰጠኝ
የስራ ቅጥር ደብዳቤ ስልጣን አልሰጠኝም እንጂ ቢሆንም እንኳ ተጠሪ ከስራ ሲያሰናብተኝ
ከአስተዳደር የሥራ ዘርፍ ወደ ማህበራዊ ጉዳይ የስራ ዘርፍ(corporate social responsibility
officer) ሚባል ቀይሮኛል፣ በዚህ ስራ ዘርፍ ደግሞ የሚቆጣጠረው፣
የሚቀጥረው፣የማያስተዳድረው ወይም የምወስደው የስነ ምግባር እርምጃ የለም፣በመጀመሪያ
የስራ ዘርፍም የዓመት ስራ ዕቅድ እንዳወጣ፣ የዓመት በጀት እንዲመድብም ሆነ ሰራተኛ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለመቅጠሪም ሆነ ለማባረር ስልጣን አልተሰጠኝም፣በሥራ አስኪያጅነት የፈረምኩት የፅሁፍ


ማስረጃም አልቀረበም፣የስራ ደረጃዬም 9ኛ እርከን ሲሆን፣ ታህሳስ 1 ቀን 2018 እ.ኤ.አ ሥራ
ላይ በዋለው የድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ደግሞ ሥራ አስኪያጅ የሚባለው የሥራ ደረጃው
ከእርከን 12 በላይ ከ13 አስከ 17ኛ እንደሆነ በስር ፍ/ቤት እየተከራከርኩ በማስረጃ ሳያጣራ
በግምት አመልካች ሥራ አስኪያጅ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
በመሆኑ ውሳኔው ተሽሮ አመልካች ሰራተኛ ነዉ ተብሎ ውሳኔ እንዲሰጥ በማለት አመልክቷል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካች የሥራ መሪ ነው
ተብሎ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ስለ ስራ መሪ በህጉ የተመለከቱትን ዝርዝር ድንጋጌዎችን
ያገናዘበ መሆኑን አለመሆኑን ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል
ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ታዟል፡፡

ተጠሪ ያቀረበው መልስ ባጭሩ አመልካች በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በከፍተኛ የሰው ሀብት
ኦፊሰር ስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ ሲሰራ የቆየ መሆኑን ለስር ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ላይ
ገልፀዋል፣ በዚህ ስራ መደብ ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ደግሞ የአመራር ስራ በመሆኑ የዓመት
ስራ ዕቅድ ማውጣት፣ አስፈላጊውን በጀት መመደብ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ መደገፍና
ማቀናጀት እንደሆነ መጋቢት 2011ዓ.ም በተፈረመው መመሪያ ተገልፀዋል፣ አመልካች
በተጨባጭ ይህንን ሲሰራ ቆይቷል፣ይህም በተለያየ ጊዜ አመልካች ሲጽፍ ከነበረው ደብደዳቤ
መረዳት ይቻላል፣አመልካች በማስረጃ አልተደገፈም የሚለው ሀሰት ነው፣በስር ፍ/ቤት
ባቀረብነው መልስ ላይ ማስረጃ በዝርዝር አያይዘን በማቅረብ አመልካች የስራ መሪ መሆኑን
አስረድተናል፣ስለዚህ አመልካች የሥራ መሪ ነው መባሉ የህግ ስህተት የለውም፡፡አመልካች
ከስራ ሲሰናበት የስራ መደቤ ተቀይሯል የሚለው በስር ፍ/ቤት ያልተነሳ አዲስ ክርክር በመሆኑ
ተቀባይነት የለውም፣የሥራ መደቡ ቢቀየርም እንኳ የስራ መደቡ ተመሳሳይ የአመራር መደብ
ነው፣ አመልካች በመተዳደሪያ ደንብ ታህሳስ 01/2018 መሰረት ሥራ አስኪያጅ ከእርከን 12
በላይ ነው የሚለው፣አመልካች ይህ ደንብ ከመውጣቱ በፊት ስለተቀጠረ ደንቡ ወደ ኋላ
ተመልሶ አይሰራም፣ ደንቡ ተፈፃሚ ይሆናል ቢባል እንኳ ይህንን ክርክር በስር ፍ/ቤት አንስቶ
አልተከራከረም፣ስለዚህ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 329 መሰረት ክርክሩ ውድቅ ተደርጎ የስር ውሳኔ እንዲፀና
በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካች በመልስ መልሱ ላይ አሁን የተነሱት ክርከሮች በስር ፍርድ
ቤት የተነሱ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ብይን ያሳያል በሚል አቤቱታዉን በማጠናከር
ተከራክሯል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ በአመልካች
እና በተጠሪ መካከል የሥራ ዉል ግንኙነት እንደነበር አላከራከረም፡፡አከራካሪዉ ጉዳይ
አመልካች ከስራ ሲሰናበት ሲሰራ የነበረዉ የሥራ መሪ የሥራ መደብ ላይ ነዉ ወይሥ
አይደለም የሚለዉ ነዉ፡፡

በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 10/2/ እንደተመለከተዉ የሥራ መሪ ማለት
በህግ ወይም እንደድርጅቱ የሥራ ጠባይ በአሰሪዉ በተሰጠዉ የዉክልና ስልጣን መሰረት
የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማዉጣትና የማስፈጸም ስልጣን ያለዉ ወይም ሰራተኛን
የመቅጠር፤የማዘዋወር፤የማገድ፤የማሰናበት ወይም የመመደብ ተግባሮችን የመወሰን ስልጣን
ያለዉ ግለሰብ ሲሆን፤እነዚህ የሥራ አመራር ጉዳዮችን አስመልከቶ የአሰሪዉን ጥቅም
ለመጠበቅ አሰሪዉ ሊወስደዉ ስለሚገባዉ እርምጃ በማንም ሳይመራ የራሱን የዉሳኔ ሃሳብ
የሚያቀርብ የህግ አግልግሎት ሃላፊን ይጨምራል፡፡ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ የሚቻለዉ
አንድን ሰራተኛ የሥራ መሪ የሚያሰኘዉ ተግባር ሁሉንም በዝርዝር የተገለጹ ተግባራትን
የማከናዉን አለማከናወን ጉዳይ ሳይሆን እንደድርጅቱ የሥራ ጠባይ የሥራ አመራር ስራ
ተብለዉ የተለዩ ተግባራትን እንዲፈጽም ሃላፊነት የተሰጠዉ መሆን አለመሆኑን የመለየት
ጉዳይ ነዉ፡፡ስለዚህም አንድ ሰራተኛ የድርጅቱ የሥራ መሪ ነዉ ወይሥ አይደለም የሚለዉን
ለመወሰን ከድርጅቱ የሥራ ባሕርይ አንጻር የተሰጠዉ ሃላፊነትና ተግባር መታወቅ አለበት፡፡

በተያዘዉም ጉዳይ የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች የስራ መሪ ነዉ ከሚል ድምዳሜ ላይ


የደረሱት በድርጅቱ የሥራ ጠባይ የተሰጠዉ ሃላፊነት በከፍተኛ የሰው ሀብት ኦፊሰር ስራ
መደብ የዓመት ስራ ዕቅድ ማውጣት፣ አስፈላጊውን በጀት መመደብ፣ ክትትልና ቁጥጥር
ማድረግ፣ መደገፍና ማቀናጀት በተጨባጭ ሲሰራ ቆይቷል በማለት ነዉ፡፡

አመልካች የሥራ መሪ አይደለሁም ብሎ የሚከራካረዉ ሁለት ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ


ስለመሆኑ ክርክሩ ያሣያል፡፡አንደኛዉ ምክንያት የተቀጠረበት የሥራ ዘርፍ የሥራ መሪ
የሚያሠኝ ነዉ ቢባል እንኳን በተጨባጭ ሰራተኛ መቅጠር፣ ማሰናበት እና የዲስፕሊን እርምጃ
መዉሰድ ስልጣን አልነበረኝም ስለዚህም የሥራ መሪ አይደለሁም የሚል ሲሆን ሁለተኛዉ
ምክንያት ቀደም ሲል የነበረበት የሥራ መደብ የሥራ መሪ ነዉ የሚባል ቢሆን እንኳን ከስራ
ሲሰናበት የስራ መደቡ ተለዉጧል በማለት ነዉ፡፡እነዚህ የፍሬ ነገር ክርክሮች በስር ፍርድ
ቤት የተነሱ ጉዳዮች ስለመሆኑ መዝገቡ ያሣያል፡፡የመከራከሪያ ነጥቦቹን አግባብነት በቅደም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተከተል እንመለከታለን፡፡ የመጀመሪያዉ ነጥብ አመልካች ሲሰራ የነበረበት የሥራ መደብ


የሥራ መሪ የሚያሰኘዉ ነዉ ወይሥ አይደለም የሚለዉን በሚመለከት ማስረጃ በመመዘን
የክርክሩን ፍሬነገር የማጣራት ሃላፊነት የተሰጣቸዉ የሥር ፍርድ ቤቶች እንዳረጋገጡት
አመልካች ከፍተኛ ኦፍሰር የሥራ ዘርፍ /HCM and Administration/ ሆኖ ሲሰራ የዓመት ስራ
እቅድና አስፈላጊ በጀት ማዉጣት፣መቆጣጠር፣መከታተልና መደገፍ ሲስራ እንደነበር የተረጋገጠ
ፍሬነገር ጉዳይ ነዉ፡፡የድርጅቱን የበጀት ጉዳዮች ማቅድና ማስፈጸም ስራ በማናቸዉም
ሰራተኛ የሚከናወን መደበኛ ስራ ሳይሆን የሥራ አመራር ስራ ስለመሆኑ አዋጁ ስለስራ መሪ
ከሰጠዉ ትርጉም መገንዘብ ይቻላል፡፡ይህን የሚያሣየዉ አመልካች በድርጅቱ የስራ አመራር
ተግባር ሲያከናዉን የነበረ መሆኑን ነዉ፡፡በእርግጥ የድርጅቱ የሰዉ ሃይል መምሪያ ሃላፊ ሆኖ
ሲሰራ እንደነበር እንጂ የሰዉ ሃይል በመቅጠር፣በማስተዳደርና የዲስፕሊን እርምጃ በመዉሰድ
ረገድ ያከናወነዉ ተግባር ስለመኖሩ በማስረጃ አልተረጋገጠም፡፡ይሁንና አመልካች ሌሎች
የድርጅቱን የሥራ አመራር ተግባራት ሲሰራ እንደነበር ከተረጋገጠ ሰራተኛ ቅጥር እና
አስተዳደራዊ ተግባራት አለመስራቱ ብቻዉን የሥራ መሪ ከመባል የሚያሥቀር አለመሆኑን
መገንዘብ አስፈላጊ ነዉ፡፡ምክንያቱም ከላይ እንደተገለጸዉ የህጉ ይዘት ሲታይ ሰራተኛን
የመቆጣጠር ጉዳይ በተጨማሪነት ወይም ራሱን ችሎ የሚቆም የሥራ አመራር ተግባርና
ሃላፊነት መለያ ሆኖ ሊወሰድ እንደሚችል አመልካች በመሆኑ ነዉ፡፡የአዋጁን አንቀጽ 3/1/ሐ
ይመለከታል፡፡በመሆኑም የመጀመሪያዉ የክርክር ምክንያት በስር ፍርድ ቤቶች ዉድቅ
መደረጉ ስህተት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የቀረበዉ መከራከሪያ አመልካች ከስራ ሲሰናበት የሥራ መደቡ ማህበራዊ
ጉዳይ የስራ ዘርፍ(corporate social responsibility officer) የሚለዉ ላይ እንደነበር እና ይህ
የሥራ ዘርፍ የስራ አመራር የሥራ ዘርፍ አለመሆኑን ገልጾ ስለመከራከሩ መዝገቡ
ያሣያል፡፡በዚህ ረገድ በተጠሪ በኩል የቀረበዉ ክርክር የሃላፊነት ደረጃዉ ተመሳሳይ ነዉ የሚል
ነዉ፡፡ይሁንና የሥር ፍርድ ቤቶች ይህንኑ አከራካሪ ጉዳይ በጭብጥነት ይዘዉ በማስረጃ
አጣርተዉ እና ከድርጅቱ የሥራ ደንብ ጋር አገናዝበዉ ያረጋገጡት ፍሬነገር ባለመኖሩ የሥራ
መደቡ መለወጥ የሥራ ሃላፊነቱ ላይ ያስከተለዉን ለዉጥ ምንድነዉ የሚለዉንና ህጋዊ
ዉጤቱን በዚህ ሰበር ችሎት ለመወሰን የሚቻል ሆኖ አላገኘንም፡፡በመሆኑም በዚህ ረገድ
የቀረበዉን ፍሬነገር ክርክር የሥር ፍርድ ቤት በማስረጃ አጣርቶ እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ
ሆኖ አግኝተናል፡፡በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉሳኔ

1ኛ/የአደኣ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ/41550 ላይ በ10/07/2012ዓ.ም የሰተዉ ብይን እና


ይህንኑ በማጽናት የም/ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት እንደቅደም ተከተላቸዉ በመ/ቁ/31966 እና በመ/ቁ/333425 ላይ የሰጡት ዉሳኔ
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ተሸሯል፡፡

2ኛ/አመልካች ከስራ ሲሰናበት የሥራ ዘርፍ ለዉጥ ተደርጓል ወይሥ አልተደረገም?ለዉጥ


ተደርጓል ከተባለ የተመደበበት የሥራ ዘርፍ የሥራ መሪ ነዉ ወይሥ አይደለም የሚለዉን
በማስረጃ በማጣራት ተገቢዉን ዉሳኔ እንዲሰጥበት በማለት መዝገቡን በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር
343/1/ መሰረት ለአድኣ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት መልሰናል፡፡ይጻፍ፡፡

3ኛ/ በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ.200480

ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

2. ቀነዓ ቂጣታ

3. ፈይሳ ወርቁ

4. ደጀኔ አያንሳ

5. ብርቅነሽ እሱባለዉ

አመልካች፡…….አቶ በድሩ አባገላን - ቀርበዋል

ተጠሪ፡…………. የሟች አቶ አባድጋ አባጎጃም ወራሾች ወ/ሪት አልፋ አባድጋ አባጎጃም እና

አቶ ሀምዛ አባድጋ አባጎጃም- ወ/ት አልፍያ አግድጋ- ቀርበዋል

ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍርድ

ይህ የእርሻ መሬት ክርክር የተጀመረዉ በየም ልዩ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች
የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ
የቻለዉ የአሁን አመልካች የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.14976
በ1/9/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን
በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በሟች አባቴ አቶ
አባገላን አባጊቤ እጅ ለ56 ዓመታት የቆየን ባህር ዛፍ ይዞታ ከዚህ ቀደም በመ.ቁ.09921 ላይ
ባህር ዛፍ የሟች አባቴ ነዉ ተብሎ የተወሰነዉ የዉርስ ይዞታዬን በጉልበት ስለያዘብኝ የአሁን
ተጠሪ ይዞታዉን እንዲለቅልኝ፣ የወደመዉን ንብረት ግምትና በክሱ ምክንያት የወጠዉን
ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብት እንዲጠበቅልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡

የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ አመልካች ይህ መሬት በመ.ቁ.09921 ላይ


ተወስኖልኝ በንብረት ክፍፍል አግኝቻለሁኝ በማለት ያቀረበዉ ክርክር ሀሰት ነዉ፤ ይህን ይዞታ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከደርግ መንግስት ጀምሮ ስንገብርበትና ለሶስት ዙር ያስለካን ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ነዉ በማለት


ተከራክሯል፡፡

ከዚህ በኋላ የወረዳዉ ፍ/ቤት የአመልካችን የሰዉ ምስክሮች በመስማት፣ ከሚመለከተዉ አካል
በማጣራት ባሳለፈዉ ዉሳኔ ለክርክር መነሻ የሆነዉ የእርሻ መሬት የአሁን ተጠሪ አባት
የአባጎጃም አባቂጤ መሆኑ እና በተጠሪ ወንድም በሟች አቶ አባጊዲ አባጎጃም ስም ግብር
ሲገበር የቆየ መሆኑን በማስረጃ የተረጋገጠ ስለሆነ፣ በመ.ቁ.09921 ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን
አመልካች አባት ከተጠሪ አባት ጋር በይዞታዉ ላይ ባህር ዛፍ በጋራ ተክለዉ ሲጠቀሙበት
ስለነበር አመልካች መሐመድ አባጊዲ ላይ ክስ አቅርቦ የተወሰነዉ ባህር ዛፍ እንጂ ይዞታዉ
አይደለም፣ አሁን ባህር ዛፉ ሸጠዉ ገንዘቡነሰ የተካፈሉ ሆኖ ቦታዉ መንገድ ዳር ስለሆነ ጉቶዉ
ደርቆ ተጠሪ እህል ዘርቶ የሚጠቀመዉ በመሆኑ፣ በመሆኑም የአሁን ተጠሪ ይዞታዉን
ለአመልካች የሚለቅበት እና ካሳ የሚከፍልበት አግባብ የለም በማለት ወስኗል፡፡ ከዚህ በኋላ
የአሁን አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም በየደረጃዉ ላሉት የክልሉ ፍ/ቤቶች ቅሬታዉን
ያቀረበ ቢሆንም ፍ/ቤቶቹ ቅሬታዉን በትዕዛዝ በመሰረዝ የሥር የወረዳዉን ዉሳኔ በማጽናት
ወስኗል፡፡ የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ፡፡

የአሁን አመልካች በ26/4/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ የአመልካች አባት በ1954 ዓ.ም
ባህር ዛፍ ተክሎ እስከ 2000 ዓ.ም ሲጠቀምበት የቆየዉና በመ.ቁ.09921 ላይ በተሰጠዉ ዉሳኔ
መሰረት በክፍፍል የባህር ዛፍ ይዞታ ለአመልካች ደርሶ እያለ እና ተጠሪ ይዞታዉን በጉልበት
መያዙ ተረጋግጦ እያለ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት
የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲሻርልኝ፣ በጉልበት የተቀመሁት ባህር ዛፍ እንዲመለስልኝ
የተጨፈጨፈዉ ባህር ዛፍ ግምት እንዲጠይቅ እንዲወሰንልኝ በማለት በዝርዝር አመልክቷል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን በማየት ፣የሥር ፍ/ቤቶች በዚህ ጉዳይ የሰጡት ዉሳኔ አስቀድሞ
አመልካች በመ.ቁ.09921 ላይ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተከራክሮ ያስፈረደዉን ፍርድ በአግባቡ
ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ሲባል የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ
እንዲሰጥ ባዘዘዉ መሰረት የተጠሪ ወራሾች ባቀረቡት መልስ የሥር ፍ/ቤቶች ይህን ጉዳይ
በማስረጃ በማጣራት የሰጡት ዉሳኔ ተገቢ ስለሆነ እንዲጸናልን ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ
መብታችን እንዲጠበቅልን በማለት በዝርዝር ተከራክሯል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ
አቅርቧል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት


ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንዲሁም የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል
ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል፡፡ እንደመረመርነዉ የአሁን አመልካች
ባቀረበዉ ክስ የጠየቀዉ ዳኝነት የመሬት ይዞታን የሚመለከት እና ተጠሪ ይህን መሬት
በጉልበት ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ የሚል ነዉ፡፡ የአሁን ተጠሪ በዚህ ረገድ ባቀረቡት ክርክር
ለክርክር መነሻ የሆነዉ ይዞታ የአመልካች አባት ይዞታ ሳይሆን የሟች አቶ አባጎጃም አባቂጤ
መሆኑን ገለጸዉ ተከራክሯል፡፡ የሥር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ ፍሬ
ነገር የማጣራት እና ማስረጃን የመስማት የመመርመርና የመመዘን በሕግ የተሰጠዉን ስልጣን
መሰረት በማድረግ የሰዉ ምስክሮችን በመስማት ከሚመለከተዉ አካል ተጣርቶ እንዲቀርብ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በማድረግ ባሳለፈዉ ዉሳኔ ለክርክር መነሻ የሆነዉ የእርሻ መሬት የሥር ተከሳሽ አባት የአቶ
አባጎጃም አባቂጤ መሆኑን እና በሥር ተከሳሽ ወንድም ስም ተገቢ የመንግስት ግብር ሲከፈል
እንደነበር መረጋገጡን የሥር ፍ/ቤት የዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል፡፡

በዚህ ይዞታ ላይ የሥር ተከሳሽ አባት አቶ አባጎጃም አባቂጤ እና የአሁን አመልካች አባት
አባገላን አባጊቤ ባህር ዛፍ ተክለዉ ሲጠቀሙበት እንደነበር እና የአሁን አመልካች የዉርስ
ይዞታን በተመለከተ በሌሎች ወራሾች ላይ ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ መሐመድ አባጊዲ ላይ አሁን
ለክርክር መነሻ በሆነዉ ይዞታዉ ላይ ያለዉን ባህር ዛፍ በተመለከተ ክስ ማቅረቡን
የመ.ቁ.09921 ላይ የተደረገዉ ክርክር ያመለክታል፡፡ የየም ልዩ ወረዳ ፍ/ቤት በመ.ቁ.09921
ግራ ቀኙን በማከራከር በ15/6/2008 ዓ.ም ባሳለፈዉ ዉሳኔ አከራከሪዉን ባህር ዛፍ 7ኛ ተከሳሽ
መሐመድ አባጊዲ ከአመልካች አባት ጋር የእኩል ነዉ በማለት መወሰኑን የዉሳኔዉ ግልባጭ
ያሳያል፡፡ ከዚህ ዉሳኔ ይዘት መረዳት የሚቻለዉ ለአሁን አመልካች የተወሰነዉ ባህር ዛፍ
እንጂ ባህር ዛፉ ያረፈበት ይዞታ እንዳልሆነ ነዉ፡፡

አሁን በተያዘዉ ክርክር ደግሞ የአመልካች አባት ባህር ዛፉን አብረዉ ከተከሉት ሰዉ ጋር
ባህር ዛፍ ሸጠዉ ገንዘቡን የተካፈሉ መሆኑንና በአሁኑ ወቅት በይዞታዉ ላይ ጉቶዉ እንኳን
ተነስቶ የሌለ መሆኑንና በመሬቱ ላይ እህል የተዘራ መሆኑን በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬ
ነገር ነዉ፡፡ ይህ ማለት ለክርክር መነሻ በሆነዉ ይዞታ ላይ ቀድሞ የነበረዉ ባህር ዛፍ አሁን
የሌለ እና ይዞታዉ ለእርሻ ሥራ እያዋለ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በመሆኑም ለአመልካች
በመ.ቁ.09921 ላይ ተወስኖ የነበረው ባህር ዛፍ እንጂ የመሬት ይዞታ አይደለም፤ ባህር ዛፉም
ቢሆን አሁን በይዞታዉ ላይ እንደሌላ የሥር ፍ/ቤቶች በማስረጃ አጣርተዉ ያረጋገጡት ጉዳይ
ነዉ፡፡ አመልካች በኦሮሚያ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999
አንቀጽ 6 (1) መሰረት በዚህ ይዞታ ላይ የመሬት የባለይዞታነት መብት ያለዉ መሆኑን በሥር
ፍ/ቤት የረጋገጠዉ ነገር የለም፡፡ በመሆኑም አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉ ቅሬታ
ተቀባይነት የለዉም፡፡ ይህ ችሎት በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80 (3፣ ሀ) እና በአዋጅ
ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 (1) መሰረት ከተሰጠዉ ስልጣን አንጻር የአሁን አመልካች
ያቀረበዉ ቅሬታ የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መፈጸማቸዉን
የሚያመለክት ስላልሆነ ተቀባይነት የለዉም ብለናል፡፡

ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች ለክርክር ምክንያት የሆነዉን የገጠር መሬት
ተጠሪ በጉልበት ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ በማለት ያቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ያሳለፉት
ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ዉሳኔ

1. የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.14976 በ1/9/2012 ዓ.ም


የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348
(1) መሰረት ጸንቷል፡፡
2. የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ፡፡
3. ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻሉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡

የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

-የሰ.መ.ቁ.200482

ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

2. ቀነዓ ቂጣታ

3. ፈይሳ ወርቁ

4. ደጀኔ አያንሳ

5. ብርቅነሽ እሱባለዉ

አመልካች፡……. ወ/ሮ ሐቢባ ሸምሱ ስሩር - ቀርበዋል

ተጠሪ፡…………. አቶ ቴዎድሮስ ገብሩ ብዛ- ቀርበዋል

ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍርድ

ይህ የፍቺ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች
እና የአሁን ተጠሪ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን
አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251802 ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከተጠሪ ጋር ግንቦት
12 ቀን 2001 ዓ.ም በግብጽ ሀገር ጋብቻ ፈጽመን አብረን ሲንኖር ህጻን ሊና ቴዎድሮስ
የተባለችዉን ልጅ የወለድን ቢሆንም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ግንኙነታችን ተቋርጦ በጋብቻ
መቀጠል ስላልቻልን ጋብቻችን እንዲፈርስልን በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡

የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ከአመልካች ጋር ጋብቻ አልፈጸምንም፣ በጋብቻ


ሰነዱ ላይም አልፈረምኩም፣ አመልካች ጋብቻ እንደሌላቸዉ ስለመሆኑ ማስረጃ ተሰጥቷል፤
በግብጽ አገር ጋብቻ የሚፈጸመዉ በፍ/ቤት ነዉ፤ ከአመልካች ጋር በነበረን የግብረ ስጋ
ግንኙነት የተጠቀሰችዉን ልጅ ከመዉለዳችን ዉጭ በጋብቻም ሆነ ጋብቻ ሳይፈጽም እንደባልና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሚስት አለመኖራቸዉን ገልጸዉ ጋብቻ በሌለበት የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት


ተከራክሯል፡፡

ከዚህ በኋላ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በመስማት፣ ከሚመለከተዉ አካል
በማጣራትና የቀረበዉን የሰነድ ማስረጃ በመመርመር ባሳለፈዉ ዉሳኔ በአመልካች እና በተጠሪ
መካከል በግብጽ አገር ጋብቻ ስለመፈጸማቸዉ አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ባለመረጋገጡ
አመልካች የጋብቻ ፍቺ እንዲወሰን ያቀረበችዉ የዳኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለዉም፤
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተፈጸመ ጋብቻ የለም፣ የሚሰጥ ፍቺ የለም በማለት
ወስኗል፡፡ ይህ ጉዳይ በይግበኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.254606
በ20/4/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ግራ ቀኙን በማከራከር የሥር ፍ/ቤትን ዉሳኔ በማጽናት
ወስኗል፡፡ የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማለወጥ ነዉ፡፡

የአሁን አመልካች ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ አመልካች እና ተጠሪ
መንግስትን ተቃዉመን ከአገር ተሰደን ለብዙ ጊዜ እንደባልና ሚስት አብረን ሲንኖር ዕድሜዋ
10 ዓመት የሆናትን ልጅ ሊና ቴዎድሮስ የተወለደች ሲሆን በግብጽ አገር የጋብቻ ዉል
ያደረግን ሲሆን እኛ በግብጽ አገር በስደት የሚንኖርና ሕጋዊ ነዋሪዎች ባልሆንበት በአገሪቱ
በሕጋዊ መንገድ እንደሚኖር ዜጋ የጋብቻ ዉሉ በፍ/ቤት አልተመዘገበም በማለት የጋብቻ ዉል
የለም በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ፡፡ አመልካች
ይህን ክርክር ለማስረዳት የሰዉ ምስክሮችን ቆጥረን እያለ የሥር ፍ/ቤቶች ምስክሮቹን
ሊቀበሉን አልቻሉም፣ ተጠሪ የጋራ ሀብት ነዉ በማለት በአመልካች ስም ለኮንዶሚኒየም
የተቆጠበዉን ገንዘብ ማሳገዱ ጋብቻ መኖሩን እያመነ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ ሳለ የሥር
ፍ/ቤቶች ጋብቻ የለም በማለት የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ
እንዲታረምልኝ በማለት በዝርዝር አመልክታለች፡፡

ይህ ችሎት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲሰጥ ባዘዘዉ መሰረት
ሚያዚያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ አመልካች እና ተጠሪ በግብጽ አገር በስደተኞች
ካምፕ ጋብቻ ስለመኖሩ የጋብቻ ሰነድ መፈረሙ ተረጋግጧል ይበሉ እንጂ ሰነዱ ወደ
ኢትዮጵያ ሲገባ በኢፌዴሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕጋዊነቱ ተረጋግጦ የገባ ስላልሆነ ሕጋዊ
ሆኖ የቀረበ ሰነድ አይደለም ተቀባይነት የለዉም፤ የሥር ፍ/ቤት ከግራ ቀኙ ክርክር አንጻር
የሰዉ ምስክሮችን መስማት እንደማያስፈልግ ስላመነበት ማለፉ ትክክል ነዉ፤ አመልካች
ከተጠሪ ጋር እንደባልና ሚስት አብረን ኖረናል ያሉት በሥር ፍ/ቤት ያልተነሰ ክርክር ስለሆነ
ተቀባይነት የለዉም፤ ለኮንዶሚኒየም የተቆጠበዉን ገንዘብ ያሳገድኩት የጋራ ሀብት ነዉ በሚል
ሳይሆን በዚህ ክርክር ምክንያት ለሚደርስብኝ ወጪና ኪሳራ የሚወሰንልኝ ከሆነ ይህን ገንዘብ
ለመዉሰድ እንዲችል ነዉ፡፡ ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በአግባቡና ሕጋዊ ስለሆነ የቀረበዉ
አቤቱታ ዉድቅ እንዲሆንልኝ ወጪና ኪሳራ እንዲወሰንልኝ በማለት በዝርዝር ተከራክሯል፡፡
አመልካች የሰበር አቤቱታዋን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርባለች፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት


ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል፡፡ እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዳይ
ምላሽ የሚሻዉ ፣ይህ ጉዳይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ነዉ ወይስ አይደለም?

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ህግን የሚመለከት ከሆነ ክርክሩን ለማየት የሥረ-ነገር የዳኝነት
ያለዉ የትኛዉ ፍ/ቤት ነዉ? የሚሉት ነጥቦች መሆናቸዉን ተገንዝበናል፡፡ በዚህ መሰረት
አመልካች ካቀረበችዉ ክርክር እና የሥር ፍ/ቤቶች በዉሳኔያቸዉ እንዳመለከቱት አመልካች
ከተጠሪ ጋር ጋብቻ ፈጽመናል የሚትለዉ በግብጽ አገር በስደተኞች ካምፕ መሆኑን ጠቅሳ
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ጋብቻቸዉን በምስክሮች ፊት አስፈጽሟል
ያለችበትን የጋብቻ የምስክር ወረቀት የሰጠ መሆኑን እና ተጠሪም ይህን ሰነድ መፈረሙን
በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርመራ ክፍል መረጋገጡን ነዉ፡፡ ተጠሪ ግን
ከአመልካች ጋር በግብጽ አገር ጋብቻ አለመፈጻቸዉን፣ በግብጽ አገር ተጋቢዎች ጋብቻ
መፈጸም ያለባቸዉ በፍ/ቤት መሆኑን፣ የተባለዉ የጋብቻ ሰነድ አግባብነት ባለዉ ሕግ መሰረት
በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረጋግጦ ወደ አገር ያልገባ መሆኑንና ተቀባይነት
ሊኖራዉ እንደማይገባ ገልጾ መከራከሩን መዝገቡ ያሳያል፡፡ በግራ ቀኙ መካከል ከሚነሳዉ
የፍሬ ነገር እና የህግ ክርክር አንጻር ጉዳዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን [Private International
Law] የሚመለከት ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡

እንደሚታወቀዉ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ የዉጭ አካል ተካፋይ የሆነበትን የህግ ክርክር
የሚመለከቱ መርሆዎችና ደንቦችን የሚያካተት ነዉ፡፡ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ ወይም የሕግ
ግጭት [Conflict of laws] የሚመለከተዉ በተያዘዉ የህግ ክርክር የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት
እንዳላዉ እና የትኛዉ ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን እንዳለዉ የሚወስኑ የህግ መርሆችን
ነዉ፡፡ የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 (1፣ ሀ)
መሰረት የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱ የፍትሕ ብሔር ጉዳዮችን ለማየት
የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን ይደነግጋል፡፡

በዚህ አግባብ አሁን የተያዘዉ ጉዳይ ሲታይ አመልካች ባቀረበችዉ ክርክር ከተጠሪ ጋር ጋብቻ
ፈጽመናል ያለችዉ በግብጽ አገር በሚገኘዉ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ካምፕ
በከፍተኛ ኮሚሽንና በምስክሮች ፊት መሆኑን ገልጻ ተከራክራለች፡፡ ይሁን እንጂ አመልካች
ከተጠሪ ጋር አድርገናል የሚትለዉ ጋብቻ እንዲፈርስላት ክስ አቅርባ ዳኝነት የጠየቀችዉ
በኢትዮጵያ ፍ/ቤት መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ በዚህ መሰረት ከግራ ቀኙ ክርክር አንጻር
በአመልካች እና በተጠሪ መካከል በግብጽ አገር በሚገኘዉ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች
ካምፕ አመልካች ተፈጽሟል የሚትለዉ ጋብቻ በተመለከተ ሕጋዊ ጋብቻ ተፈጽሟል ለማለት
የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል? የሚለዉ ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ጉዳይ ሆኖ
እናገኛለን፡፡ እንዲሁም በግራ ቀኙ መካከል በግብጽ አገር በሚገኘዉ የተባበሩት መንግስታት
የስደተኞች ካምፕ ተፈጽሟል የተባለዉ ጋብቻ፣ በሕግ አግባብ የተፈጸመ ጋብቻ ነዉ የሚባል
ከሆነና ጋብቻቸዉ በፍቺ ዉሳኔ እንዲፈርስ የሚወሰን እንደሆነ የፍቺ ዉጤት በምን አግባብ
ይታያል? የሚለዉ ነጥብ ሊነሳ እንደሚችል ሌላዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙን
የጋብቻ ይፍረስልን ክርክር በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ የትኛዉ ነዉ? የሚለዉን ነጥብ
መወሰንን ይጠይቃል ማለት ነዉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙ ክርክር የግለሰብ ዓለም አቀፍ
ሕግን የሚመለከት ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ እናገኛለን፡፡ ይህ ጉዳይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን
የሚመለከት ከሆነ ደግሞ በኢትዮጵያ ዉስጥ የትኛዉ ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት የሥረ-ነገር
የዳኝነት ስልጣን አለዉ? የሚለዉ አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር ታይቶ ምላሽ ሊሰጥበት
የሚገባዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ በዚህ መሰረት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

(1፣ ሀ) መሰረት የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከቱ የፍትሕ ብሔር ጉዳዮችን የማየት
የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ-ነገር የዳኝነት ስልጣን ያለዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን
ይደነጋገል፡፡ ስለሆነም ፍ/ቤት አንድን ጉዳይ ለማየት የሥረ-ነገር የዳኝነት ስልጣን አለዉ
ወይስ የለዉም? የሚለዉን አስመልክቶ ተከራካሪ ወገኖች ከዚህ አንጻር የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ባያነሱም ፍ/ቤት በራሱ ተነሳሽነት በማንሳት ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሊሰጥበት
እንዲሚገባዉ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.9 (1)፣ 231 (1፣ ለ)፣ 244 (3) እና 245 (2) ድንጋጌዎች
ይዘትና ዓላማ መረዳት ይቻላል፡፡ በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ይህ ጉዳይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ
ሕግ ጥያቄን የሚያስነሳ መሆኑን እና ጉዳዩን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ-ነገር የዳኝነት
ስልጣን ያለዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን በመገንዘብ የአሁን አመልካች ያቀረበችዉን
ክስ ዉድቅ በማድረግ ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ጉዳዩን ማቅረብ እንደሚትችል በማመልከት
መወሰን ሲገባቸዉ ይህን ባለማድረግ ያሳለፉት ዉሳኔ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ሕጎች አንጻር
ተቀባይነት የለዉም ብለናል፡፡

ሲጠቃለል የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ይህን ጉዳይ ለማየት የሥረ-ነገር የዳኝነት
ስልጣን ሳይኖረዉ ጉዳዩን አይቶ ያሳለፈዉ ዉሳኔ እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን ዉሳኔ
ማረም ሲገባዉ በማጽናት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ
የሚከተለዉ ተወስኗል፡፡

ዉሳኔ

1. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251802 ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ


ዉሳኔ እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.254606 በ20/4/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ
መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1)
መሰረት ተሽሯል፡፡
2. ይህ ጉዳይ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ስለሆነ ጉዳዩን ለማየት
የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ-ነገር የዳኝነት ስልጣን ያለዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንጂ
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አይደለም ብለናል፡፡
3. ግራ ቀኛቸዉ ይህን ጉዳይ ስልጣን ላለዉ ፍ/ቤት ከማቅረብ ይህ ዉሳኔ የሚከለክላቸዉ
አይሆንም ብለናል፡፡
4. የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ፡፡
5. ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻሉ፡፡
6. ይህ ዉሳኔ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ተነቧል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

?? /? /? ? ? 200492
? ? 27/3/2014 ? /?
ተፊሪ ገብሩ /ዶ/ር/

ዳኞች ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች - አቶ እንዳለማው ተመስገን


የቀረበ የለም
ተጠሪ - አቶ ሀብታሙ መላኩ
ቀርበዋል
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ታህሳስ 26 ቀን
2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር
89392 ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ
ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 01-75094 ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና
የቁጭ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 01-02393 ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት
የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ
በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች
የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል
የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የአሁን አመልካች ቀደም ብሎ ከአቶ በልስቲ ተመስገን ጋር
ተከራክሬ ተጠሪ ወደ ክርክሩ መግባት ሲገባው ትቶ በፍርድ ባለቀ ጉዳይ በአዲስ ክስ ማቅረብ
አይችልም፡፡ ይርጋን በተመለከተ መሬቱ ከመቼ ጀምሮ እጄ እንደገባ ታስቦ መወሰን ሲገባ የከሳሽ
እድሜ ታይቶ መወሰኑ ተገቢ አይደለም፡፡ መሬቱ የኔ ስለመሆኑ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የምስክር ወረቀት አቅርቤ እያለ ታልፎ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡

በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከአብክመ. የቁጭ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን
ከሳሽ የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ተከሳሽ የአሁን አመልካች የወላጅ አባቴን 45*50 የሆነ
የመሬት ይዞታ ከ2007 ዓ/ም ጀምሮ የያዘብኝ በመሆኑ ይልቀቅልኝ ሲል ጠይቋል፡፡ ተከሳሽም
በዚህ መሬት ላይ አቶ በልስቲ ተመስገን በመ/ቁጥር 00544 ከሶኝ የተወሰነልኝ ስለሆነ እና ከሳሽ
በዛን ሰዓት ጣልቃ ገብቶ ያልተከራከረ በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5 መሰረት ክሱ ውድቅ
ይሁንልኝ፡፡ መሬቱ የከሳሽ አባት አይደለም፡፡ ይህን ይዞታ ከ1989 ዓ/ም ጀምሮ ይዤ ስለምገኝ
ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው፡፡ ይዞታው በኔ ተመዝግቦ የሚገኝና የኔ መሬት በመሆኑ ክሱ ውድቅ
ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥቷል፡፡ የቁጭ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤትም በመ/ቁጥር 01-02393 ግንቦት
22 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ከሳሽ ጉዳዩ ካሁን በፊት ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ
ነው ላለው ቀደም ብሎ በነበረው ክርክር የአሁኑ ከሳሽ ተከራካሪ ባለመሁኑ የከሳሽ ክስ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 5 ውድቅ የሚሆን ባለመሆኑ የተከሳሽ ተቃውሞ ተቀባይነት ያለው
አይደለም፡፡ ይርጋን በተመለከተ የምስክር ቃልና አግባብነት ያለውን የህግ ድንጋጌዎችን ከግንዛቤ
ውስጥ አስገብተን ተከሳሽ ያነሳው የ10 ዓመት ይርጋ ውድቅ ነው፡፡ በፍሬ ነገሩ ላይ የከሳሽ
ምስክሮች ይህ ክስ የቀረበበት መሬት ለከሳሽ አባት የተደለደለ መሆኑን መስክረዋል፡፡ የተከሳሽ
ምስክሮች መሬቱ ከ1989 ዓ/ም ጀምሮ በተከሳሽ እጅ ያለ መሆኑን መስክረዋል፡፡ ቀበሌው
ይዞታው በ1996/97 ዓ/ም በአቶ መላኩ ተመስገን የተቆጠረ መሆኑን አጣርተው ገልፀዋል፡፡ የቡሬ
ወረዳ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ጽ/ቤትም በ1989 ዓ/ም ለከሳሽ ወላጅ አባት የተደለደለ
መሆኑን አጣርቶ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ይህ መሬት ለከሳሽ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ሊሰራለት
ሲገባ ባልታወቀ ሁኔታ ለተከሳሽ የተሰራለት መሆኑ ታውቋል፡፡ ይዞታው የከሳሽ አባት መሆኑ
የተረጋገጠ በመሆኑ ተከሳሽ ለከሳሽ መሬቱን ይልቀቅለት ሲል ወስኗል፡፡ ተከሳሽ ለምስራቅ ጎጃም
ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ በመ/ቁጥር 01-75094 ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ/ም
በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ የወረዳ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈተመበት ባለመሆኑ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ተከሳሽ
የአሁን አመልካች ለአብክመ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ አቅርቦ አከራክሮ
በመ/ቁጥር 89392 ተህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ የከፍተኛ እና
የወረዳ ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናት ወስኗል፡፡

የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል፡፡ መዝገቡም ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ
ያከራካሪው መሬት ባለቤትነት ደብተር ለአሁን አመልካች ተሰጥቶ ያለው ባልተሰረዘበት ሁኔታ
ታልፎ መሬቱ የተጠሪ ነው የተባለበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ቀርቧል፡፡ መልስና
የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል፡፡ ተጠሪ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት
የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዳልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል
ተከራክሯል፡፡ አመልካችም የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን
በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና


የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን
የሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ
ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም በስር
ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ግራ ቀኙን ያከራከረው የመሬት ይዞታ በ1989 ዓ/ም ለአሁን ተጠሪ
አባት የተደለደለ መሆኑንን፣ በ1996/97 ዓ/ም ለአሁን ተጠሪ አባት የተመዘገበ መሆኑን የወረዳ
የመሬት አስተዳደርና አጣቃቀም ጽ/ቤት አጣርቶ ሪፖርት አድርጓል፡፡ የወረዳ የመሬት
አስተዳደርና አጣቃቀም ጽ/ቤት ለአሁን አመልካች የመሬት ባለይዞታነት ማረጋገጫ የምስክር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወረቀት የተሰራለት ባልታወቀ ሁኔታ መሆኑንና የመሬት ባለይዞታነት ማረጋገጫ የምስክር


ወረቀት ለአሁን አመልካች ሊሰራለት የማይገባ መሆኑንም ገልጿል፡፡ በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች
በቀረበው ማስረጃ መሰረት አጣርተው ያከራከረው የመሬት ይዞታ የአሁን ተጠሪ መሆኑን ውሳኔ
ሰጥተዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የአሁን አመልካች ባከራከረው የመሬት ይዞታ ላይ የመሬት ይዞታ
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰራለት በህጉ አግባብ እንዳልሆነና ሊሰራለት የማይገባ መሆኑን፣
ይዞታውም ለአሁን አመልካች እንዳልሆነና የአሁን ተጠሪ ወላጅ አባት ይዞታ መሆኑ ተጣርቶ
መወሰኑ ቅር የሚያሰኝ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁጥር 44634 ላይ በሰጠው ውሳኔ በፍ/ብሔር ክርክር አንድ መብት ወይም ግዴታ አለ ብሎ
የሚከራከር ወገን መብቱ ወይም ግዴታው ስለመኖሩ የማስረዳት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ አስገዳጅ
የህግ ትርጉም ሰጥቶበት ይገኛል፡፡ የአሁን አመልካች ያከራከረው የመሬት ይዞታ የሱ ስለመሆኑ
ባላስረዳበት ሁኔታ ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት ያላው ሆኖ ያልተገኘ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች
የሰጡት ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም፡፡

ውሳኔ

1. የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 89392 ታህሳስ 14 ቀን


2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 01-
75094 ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የቁጭ ንዑስ ወረዳ
ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 01-02393 ግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው
ውሳኔበፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ታህሳስ 28 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የቁጭ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት
የመ/ቁጥር 01-01393 ላይ የሰጠው የአፈጻጸም እግድ ተነስቷል፡፡ ይፃፍ፡፡
3. በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
4. የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል፡፡
5. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-200555

ቀን፡-29/02/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ መሐመድ አበራ- አልቀረቡም

ተጠሪዎች ፡-1. አቶ ታጁ ጌታዬ

2. ሀሰን አሊ አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ የገጠር እርሻ መሬት ተጠቃሚነት መብት የሚመለከት ነዉ፡፡በስር በወግድ ወረዳ ፍርድ ቤት ተዋበች
አስናቀዉ ከሳሽ የአሁን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ በዚህ መዝገብ ላይ በተከራካሪነት ያልተሰየሙት ካሳዉ
መንግስቱ 2ኛ ተከሳሽ የአሁን ጣልቃ ገቦች ከሌሎች ስድስት ጣልቃ ገቦች ጋር በመሆን በጣልቃ ገብነት
ተከራክረዋል፡፡ የክሱም ይዘት በወረዳዉ 02 ቀበሌ ዉስጥ በክሱ በተጠቀሱት አዋሳኞች የሚታወቅ
በ1983ዓ/ም የተመራሁበትንና በደብተር ያስመዘገብኩትን 4 ገመድ የእርሻ መሬት አመልካች ይዞብኝ ለስር
2ኛ ተከሳሽ በመሸጡና 2ኛ ተከሳሽ ቤት ሊገነባ ስለሆነ የያዙብኝን መሬት እንዲለቁልኝ ይወሰንልኝ በማለት
ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአሁን አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ መሬቱ የከሳሽ ሳይሆን ከሟች አሊ ፈለቀ ጋር በ1983ዓ/ም አብረዉ
ተመርተዉ አቶ አሊ ፈለቀ በ2003ዓ/ም ሲሞት እኔ ከሟች ጋር በቤተሰብ አባልነት አብሬ ያደኩ በመሆኔ
ወራሽነቴን አረጋግጬ ለሁለት ከከሳሽ ጋር ሁለት ሁለት ገመድ ተካፍለናል፡፡በደረሰኝ መሬት ላይ ቤት ልሰራ
እንጨትና ድንጋይ አራግፌያለሁ እንጂ የከሳሽን አልነካሁም በማለት ተከራክረዋል፡፡የስር 2ኛ ተከሳሽም
መሬቱን አልገዛሁም፤የአሁን አመልካች ቤት ሊሰራ ነዉ በማለታቸዉ ድንጋይና እንጨት አራግፌያለሁ
በማለት ለክሱ መልስ ሰጥቷል፡፡

የአሁን ተጠሪዎች በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 41 መሰረት በክርክሩ ጣልቃ በመግባት ክስ የተመሰረተበት መሬት
የሟች አባታችን አሊ ፈለቀ ሲሆን የአሁን አመልካች 2 ገመድ መሬት መብት ሳይኖራቸዉ በመያዝ ለሌላ
ሰዉ በሽያጭ አስተላልፈዉ ቤት ሊያሰሩበት ስለሆነ ወርሰን የያዝነዉን መሬት እንዲያስረክበን ይወሰንልን
በማለት ጠይቀዋል፡፡በዚህ የጣልቃ ገቦች አቤቱታ ላይ የስር ከሳሽ በሰጡት መልስ መሬቱ የጣልቃ ገቦች
መሆኑን በመግለጽ የተከራከሩ ሲሆን የአሁን አመልካች ደግሞ የሟቹ የቤተሰብ አባል በመሆን ወራሽነቴን
አረጋግጬ የያዝኩት ነዉ በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 28616 ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶና መርምሮ በቀን 12/05/2012
ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ለክርክሩ መነሻ ከሆነዉ 4 ገመድ መሬት ዉስጥ 2 ገመድ መሬት የሟች አሊ ፈለቀ
እንደሆነና አመልካች የሟች የአቶ አሊ ፈለቀ የቤተሰብ አባል በመሆን መሬቱን ሊይዙ እንደቻሉ በማስረጃ
ስለተረጋገጠና ይሕም በአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 17/5
መሰረት የሕግ ድጋፍ ያለዉ በመሆኑ አመልካች መሬቱን በሕግ አግባብ ስለያዙ ሊለቁ አይገባም ሲል
ወስኗል፡፡ የአሁን ጣልቃ ገቦች ከሌሎች የሥር ጣልቃ ገቦች ጋር በመሆን ይግባኝ ለደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ
ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 45606 ላይ በቀን 18/05/2012ዓ/ም በሰጠዉ ብይን
ይግባኙን ሰርዞባቸዋል፡፡

በመቀጠል ተጠሪዎች የሰበር አቤቱታቸዉን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበዉ ችሎቱ
በመ/ቁጥር 03-28591 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 07/04/2013ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ክርክሩ አዲሱ
የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 252/2009 ተፈጻሚ በሆነበት ጊዜ የተጀመረ እና በቀድሞዉ አዋጅ መሰረትም
ተወርሶ ሕጋዊ መብት የተቋቋመበት ስላልሆነ በአሁን አዋጅ መሰረት ቅድሚያ ሊወርስ የሚገባዉ
ማነዉ?የሚለዉ ዉሳኔ ማግኘት ያለበት ጭብጥ ነዉ፡፡በአዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 17/5 መሰረት የሟች
መሬት በቅድሚያ ለመዉረስ መብት ያለዉ የሟች ልጆች ሲሆኑ ልጆች ሞተዉ ከሆነ ደግሞ የልጅ ልጅ
ምትክ ሆነዉ እንዲወርሱ ሊደረግ የሚቻል ስለመሆኑ በንዑስ አንቀጽ 6 ተደንግጓል፡፡ የአሁን ተጠሪዎችም
የቀድሞ አዋጅ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ወራሽነታቸዉን ያሳወጁ ቢሆንም ቀድመዉ ወርሰዉ ያልያዙ በመሆኑ
በአሁን አዋጅ የሚስተናገድ ከመሆኑ አንጻር ከአሁን አመልካች ቀድመዉ የሟች አሊ ፈለቀን መሬት
የመዉረስ መብት ያላቸዉ የአሁን ተጠሪዎች ስለሆኑ አመልካች የሟችን ሁለት ገመድ መሬት ለተጠሪዎች
ሊያስረክብ ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ በመሻር ወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በቀን 27/04/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት
በአጭሩ፡- ለክሱ መነሻ ከሆነዉ መሬት የስር ከሳሽ ድርሻቸዉን መዉሰዳቸዉ ከመረጋገጡም በተጨመሪ
ክሳቸዉን በማስረጃ ባለማስረዳታቸዉ ክሱ ዉድቅ መደረግ ነበረበት፡፡ለተጠሪዎች(ለጣልቃ ገቦች) ሕጉ
የወራሽነት መብት የሚጠብቅ ቢሆንም ተጠሪዎች የራሳቸዉ የሆነ መሬትና መተዳደሪያ ደንብ ያላቸዉ ሲሆኑ
በአንጻሩ አመልካች ከሁለት ዓመቶ ጀምሮ እዚያዉ አድጌ አያቴ አቶ አሊ በሞት እስከተለዩበት 2003ዓ/ም
ኖሬ ያደኩኝ ነኝ፡፡ለመሬቱ በተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ላይ በቤተሰብ አባልነት ተመዝግቤያለሁ፡፡አያቴ
ከሞቱበቱ በኋላ ከ2003ዓ/ም ጀምሮ በስሜ ግብር እየገበርኩ እገኛለሁ፡፡የክልሉ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር
252/2009 አንቀጽ 17/5 የራሱ የሆነ መሬት የሌለዉ የቤተሰብ አባል መሬቱን በቅድሚያ እንዲወርስ መብት
የሚሰጥ ነዉ፡፡ስለሆነም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የቤተሰብ አባል መሆኔ ተረጋግጦ እያለ የያዝኩትን መሬት
እንዲለቅ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች መሬቱን የያዙት የቤተሰብ አባል በመሆን በሕጋዊ
መንገድ ነዉ ተብሎ የተወሰነዉን የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የመዉረስ መብት የላቸዉም በማለት የሻረበትን
አግባብነት ከአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 አንቀጽ 17/5
አንጻር ተጠሪዎች ባሉበት እንዲመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 26/09/2013 ዓ/ም የተፃፈ
መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡የመልሳቸዉም ይዘት በአጭሩ፡-ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት በ1983 ዓ/ም
የተደለደለዉ ለሟች አቶ አሊ ፈለቀ እና ለስር ከሳሽ ወ/ሮ ተዋበች አስናቀዉ ነዉ፡፡ሆኖም አቶ አሊ ፈለቀ
ከሞቱ በኋላ ከ2003ዓ/ም ጀምሮ 1ኛ ተ|ጠሪ እናቴን ወ/ሮ ዘነበች አሊን በመተካት እንዲሁም ሁለተኛ ተጠሪ
የወላጅ አባቴ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ መሆኔን ከሌሎች ወራሾች ጋር በማረጋገጥ መሬቱን ከስር ከሳሽ ጋር
በመሆን አከራካሪዉን መሬት ስንጠቀም ቆይተናለ፡፡በ2011ዓ/ም ወ/ሮ ተዋበች አስናቀዉ ሰባት ሰዎች በሚል
የመሬት ማረጋገጫ ደብተር በስማችን አዉጥተን እየተጠቀምን እንገኛለን፡፡ክርክሩ የተጀመረዉ የክልሉ
የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/2009 ጸድቆ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በመሆኑ፣አመልካች
በመሬቱ ላይ ቀድመዉ የመሬት ባለይዞታነት ደብተር በማዉጣት ያቋቋሙት መብት ባለመኖሩ፣አዋጅ ቁጥር
252/2009 አንቀጽ 17/5 ላይ ባስቀመጠዉ የወራሽነት ቅደም ተከተል መሰረት የቀድሞዉ አዋጅ ቁጥር
133/1998 አንቀጽ 16/5 እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣዉን ደንብ ቁጥር 51/1999 አንቀጽ 11/7
ስለወራሽነት ቅደምተከተል አካሄድ ለዉጦ ቅድሚያ መዉረስ የሚገባዉ የቤተሰብ አባል ሳይሆን የሟች ልጆች
ናቸዉ በማለት ደንግጓል፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቅድሚያ የመዉረስ መብት
ያላቸዉ የሟች ልጆች ናቸዉ በማለት የአመልካችን ክርክር ባለመቀበል የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ በመሻሩና
አመልካች መሬቱን እንዲለቁ በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች
ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ሲል የያዘዉን ጭብጥ በማሻሻል
የክልሉ ፍርድ ቤቶች ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት ለአመልካች አይገባቸዉን በማለት ሲወስኑ ለጉዳዩን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተገቢዉን ሕግ መሰረት በማድረግ ነዉ ወይስ አይደለም የሚል ጭብጥ በመያዝ በስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ
ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ
እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነውም የስር ከሳሽ ወ/ሮ ተዋበች አስናቀዉ በክሱ የተጠቀሰዉና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ 4 ገመድ
መሬት በአጠቃለይ የእሳቸዉ እንደሆነ በመግለጽ አመልካችና የስር 2ኛ ተከሳሽ እንዲለቁላቸዉ ዳኝነት
መጠየቃቸዉን የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ግልባጭ ያሳያል፡፡ የአሁን ተጠሪዎች እና ሌሎች አራት ሰዎች
በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 41 መሰረት በጣልቃ ገብነት መከራከራቸዉን ከክርክሩ ተገንዝበናል፡፡ ከቀረበዉ
ክርክርና ማስረጃዎች ለክሱ መነሻ ከሆነዉ ስፋት 4 ገመድ ከሆነ መሬት 2 ገመድ የስር ከሳሽ ይዞታ እንደሆነ
ቀሪዉ ግማሽ መሬት ደግሞ የሟች አቶ አሊ ፈለቀ ይዞታ እንደሆነ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠና በግራ
ቀኙም የታመነ ነዉ፡፡እንዲሁም አመልካች የሟች ቤተሰብ አባል እንደሆኑና የስር ጣልቃ ገቦችን ጨምሮ
የአሁን ተጠሪዎች(የአሁን 1ኛ ተጠሪ የሟች አቶ አሊ ፈለቀ ሚስት ወራሽ እንደሆኑ ለዚህ ችሎት ባቀረቡት
መልስ ላይ ገልጸዋል) የሟች አቶ አሊ ፈለቀ ወራሾች እንደሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር
ነዉ፡፡ ግራ ቀኙን ያከራከረዉና የዚህን ችሎት ምላሽ የሚሻዉ ጭብጥ አከራካሪዉ የሟች አቶ አሊ ፈለቀ
መሬት የሟቹ የቤተሰብ አባል ለሆኑት አመልካች ሊተላለፍ የሚገባ ሳይሆን ለአሁን ተጠሪዎች ሊተላለፍ
የሚገባ ነዉ ተብሎ መወሰኑ እና ለጉዳዩ ተፈጻሚነት ያለዉ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት
የወጣዉ ደንብ ቁጥር 51/1999 ሳይሆን የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መወሰኛ
አዋጅ ቁጥር 252/2009 ነዉ ተብሎ በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን
የሚመለከት ነዉ፡፡
እንደሚታወቀዉ ሕግ በዜጎች መካከል ያለዉን ግንኙነት ለመቆጣጠር ሲባል በሕግ አዉጪዉ አካል የሚወጣ
መሣሪያ ነዉ፡፡ በዚህ አግባብ የሚወጣዉም ሕጉ በሥራ ላይ ባለበት ወቅት በዜጎች መካከል ያለዉን ወይም
ወደ ፊት የሚፈጠረዉን ግንኙነት ለመቆጣጠር ወይም ለመዳኘት በመሆኑ ሕጉ ከመዉጣቱ በፊት ወይም
ከተሻረ በኋላ በተፈጠረ/በሚፈጠር ግንኙነት ላይ ሕግን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም፡፡ ይህም ሕግ ወደ ኋላ
ተመልሶ አይሰራም ከሚለዉ አጠቃላይ መርህ (the principle of non-retroactivity of laws) ጋር የተያያዘ
ነው፡፡ ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለዉም መርህ መሠረተ ሃሳቡም ሕጉ በስራ ላይ ከዋለ በኋላ
ለተፈጠረ መብትና ግዴታ ወይም ፍሬ ነገር ላይ ተፈጻሚ መሆን ስላለበት እና ዜጎች በሚያዉቁት ሕግ
መተዳደር አለባቸዉ የሚለዉን ታሳቢ ያደረገ ነዉ፡፡እንዲሁም አንድ ሕግ የሚጸናበትን ጊዜ አስመልክቶ በሕግ
አዉጪዉ ከተደነገገዉ ቀን በፊት ለተፈጠሩት ክስተቶች ወይም መብትና ግዴታዎች ተፈፃሚነት አይኖረዉም
የሚል ሃሳብ ያለዉ ነዉ፡፡ የዚህ መርህ ተግባራዊነት የሕግ የበላይነት ከሚረጋገጥባቸዉ መገለጫዎች
መካከል አንዱ ነዉ፡፡ ስለሆነም አንድ መሠረታዊ ሕግ (substantive law) ወደ ኋላ ተመልሶ እንዲሰራ ሕግ
አዉጪዉ በሕጉ ላይ በልዩ ሁኔታ ካላመላከተ በስተቀር ፍርድ ቤት ወይም ሌላ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠዉ
አካል ለያዘዉ ጉዳይ ተፈፃሚነት ያለዉን መሠረታዊ ሕግ ሲወስን መሠረት ሊያደርግ የሚገባዉ ወይም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሠረት እንዲያደርግ የሚጠበቅበት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ጉዳይ በተፈጠረበት ጊዜ ተፈጻሚ ሲሆን
የነበረዉን ሕግ ሊሆን ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት አንድ ሕጋዊ ዉጤት ያለዉ ተግባር (Juridical act) ወይም
መብትና ግዴታ በተፈጠረበት ጊዜ የነበረዉ ሕግ በሌላ ሕግ የተተካ ሆኖ ሲገኝ እና ክርክሩ ለፍርድ ቤት
ወይም ለዳኝነት ሰጪ አካል የቀረበዉ አዲሱ ሕግ በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ሆኖ ከተገኘ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን
መምራት እና ዉሳኔ መስጠት ያለበት በመብትና ግዴታው በተፈጠረበት ጊዜ ተፈጻሚ ሲሆን በነበረው ሕግ
መሠረት ይሆናል፡፡ ክርክሩ አዲሱ ሕግ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ለፍርድ ቤት መቅረቡ ጉዳዩ በአዲሱ ሕግ
መሠረት እንዲመራ ምክንያት ሊሆን አይገባም፡፡ ይህን ማድረግ ሕግ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለዉን
የሕግ መርህ የሚጥስ ከመሆኑም በላይ የሕግ የባላይነት እንዳይረጋገጥ ወይም እንዲሸረሸር ምክንያት
ይሆናል፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት ባለመብት አቶ አሊ ፈለቀ የሞቱት በ2003ዓ/ም መሆኑ
በግራ ቀኙ የታመነ ነዉ፡፡ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ጉዳይ የገጠር መሬትን ወራሽነት መብትን የሚመለከት
ሲሆን የወራሽነት መብት የሚተላለፍላቸዉን ሰዎች ማንነትና ቅደምተከተል አስመልክቶ በክልሉ የገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ከተመለከተዉ ዉጭ ከዉርስ ጋር በተያያዘ በፍትሐ ብሔር ሕጉ ላይ
የተመለከቱ ደንቦች እና መርሆዎች ከገጠር መሬት ወራሽነት ጋር በተያያዘም እንደየአግባብነታቸዉ
ተፈፃሚነት አላቸዉ፡፡ ዉርስ የሚከፈትበትን ሁኔታ አስመልክቶ በፍትሐ ብሔር ሕጉ አንቀጽ 826/1 ስር
እንደተደነገገዉ ዉርስ የሚከፈተዉ አዉራሹ በሞተበት ጊዜ እና ቦታ ነዉ፡፡ስለሆነም አንድ ሰዉ የሟች ወራሽ
መሆን ያለመሆኑ የሚረጋገጠዉ ሟች በሞተበት ጊዜ በሥራ ላይ ያለዉን ሕግ መሠረት በማድረግ ይሆናል፡፡
የወራሽነት ማረጋገጫ ከስሙም መገንዘብ እንደሚቻለዉ በሕግ የተገኘን መብት ለማረጋገጥ የሚሰጥ እንጂ
በእራሱ መብት የሚሰጥ ስላልሆነ ዉርሱ ተከፈተ የሚባለዉ የወራሽነት ማረጋገጫ የተወሰደበት ጊዜ
እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡በዚህ መሰረት የአከራካሪዉ መሬት ባለመብት የሞቱት በ2003 ዓ/ም
በመሆኑ በዚህ ጊዜ ተፈጻሚ ሲሆን የነበረዉ ከቀን 21/09/1998ዓ/ም ጀምሮ ተፈጻሚ መሆን የጀመረዉ
የተሻሻለዉ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና
ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም ከቀን 21/12/1998ዓ/ም ጀምሮ ተፈጻሚ የሆነዉ ደንብ ቁጥር 51/1999 ናቸዉ
እንጂ ከሐምሌ 2009ዓ/ም ጀምሮ ተፈጻሚ መሆን የጀመረዉ የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 252/2009 አይደለም፡፡ በዚህ አዋጅ ቁጥር 252/2009 በመሸጋገሪያ ድንጋጌ በአንቀጽ
57 ላይ በሌሎች ሕጎች የተቋቋሙ መብቶች እና ግዴታዎች ከዚህ አዋጅ ጋር እስካልተጋጩ ድረስ
ተፈፃሚነታቸዉ እንደሚቀጥል እንዲሁም አዋጁ ከመዉጣቱ በፊት በመታየት ላይ ያሉ ጉዳዮች በተጀመሩበት
አግባብ እልባት ያገኛሉ በሚል መደንገጉ ከዉርስ ጋር በተያያዘ ለሚነሳ ክርክር ይህ አዋጅ ወደ ኋላ ተመልሶ
ተፈጻሚ እንዲሆን ተደንግጓል የሚያስብል አይደለም፡፡ ስለሆነም ጉዳዩን በየደረጃዉ ያዩት የክልሉ ፍርድ
ቤቶች ለጉዳዩ ተፈጻሚነት ያለዉ አዋጅ ቁጥር 252/2009 ነዉ በማለት ይህንን አዋጅ መሰረት አድርገዉ
መወሰናቸዉ ሕግ ወደኋላ ተመልሶ አይሰራም በሚል የሚታወቀዉን ተቀባይነት ያለዉን የሕግ መርህ
የሚጥስ በመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በዚህ መሰረት በአዋጅ ቁጥር 133/1998 አንቀጽ 7(1/ለ) ስር እንደተደነገገዉ ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም
በወጣዉ ደንብ ላይ በሚወሰነዉ መሰረት በክልሉ ዉስጥ ነዋሪ የሆነና በግብርና ሥራ የሚተዳደር ወይም
በዚሁ ሥራ ለመተዳደር የሚፈልግ ማንኛዉም ሰዉ የመሬት ይዞታ መብት በዉርስ የማግኘት መብት
አለዉ፡፡በዚሁ ሕግ በአንቀጽ 16/5 ላይ አንድ የመሬት ባለይዞታና የመጠቀም መብቱን በተመለከተ ሳይናዘዝ
የሞተ ሰዉ መብቱ በግብርና ሥራ ለሚተዳደር ወይም በዚሁ ሥራ መተዳደር ለሚፈልግ የሟቹ ልጅ ወይም
ቤተሰብ አባል ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ በሚደነገገዉ ቅደም ተከተል መሰረት እንደሚተላለፍ
ተደንግጓል፡፡ ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በወጣዉ ደንብ ቁጥር 51/1999
አንቀጽ 11/7 ስር ማንኛዉም የገጠር መሬት ባለይዞታ ሳይናዘዝ የሞተ እንደሆነ ወይም ኑዛዜዉ በሕግ ፊት
የማይጸና የሆነ እንደሆነ የመሬት ይዞታዉ ለሟቹ የቅርብ ዘመዶች በዉርስ የሚተላለፍበት ቅደም ተከተል
ተደንግጓል፡፡በዚህ ቅደም ተከተል መሰረት በአንቀጽ 11(7/ሀ) ላይ እንደተደነገገዉ በቀዳሚነት የመዉረስ
መብት የተሰጣቸዉ ለአካለ መጠን ያልደረሱ የሟቹ ልጆች፣ልጅ ከሌለዉ የቤተሰብ አባላቱ እንደሆኑ
ተደንግጓል፡፡ከእነዚህ ሕግጋት አንጻር የክልሉ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን መርምረዉ አከራካሪዉ መሬት ተጠሪ
ሊለቁ የሚገባ መሆን አልመሆኑን በተመለከተ ዉሳኔ አለመስጠታቸዉ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሆነ
የክርክር አመራር ጉድለት ነዉ፡፡በተጨማሪም ክሱን የመሰረቱት የስር ከሳሽ አመልካች መሬቱን
እንዲለቁላቸዉ ያቀረቡት ዳኝነት ጥያቄ ዉድቅ ከተደረገና የአሁኑን ተጠሪዎች ጨምሮ የስር ጣልቃ ገቦች
በክርክሩ ተሳታፊ የሆኑት በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 41 መሰረት በመሆኑ ከሥነ ሥርዓት ሕጉ አንጻር የክርክሩ
ዉጤት ምን ሊሆን ይገባል የሚለዉም ተገናዝቦ ታይቶ ዉሳኔ ሊሰጥበት የሚገባ የሥነ ሥርዓት ጥያቄ
ነዉ፡፡በመሆኑም በእነዚህ ጭብጦች ላይ የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ስላልሰጡበት ከላይ ከተመለከተዉ አንጻር
ተገቢዉን ሕግ ተግባራዊ ካለማድረግ እና ከክርክር አመራር አንጻር የተፈጸመዉ የሕግ ስህተት ታርሞ
የሚከተለዉ ተወስኗል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. የወግድ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 28616 ላይ በቀን 12/05/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ ፣የደቡብ
ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 45606 ላይ በቀን 18/05/2012ዓ/ም የሰጠዉ ብይን እና
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 03-28591 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ
በቀን 07/04/2013ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል፡፡

2. የወግድ ወረዳ ፍርድ ቤት መዝገቡን በማንቀሳቀስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የሟች አቶ አሊ ፈለቀ መሬት
በቤተሰብ አባልነት አመልካች ይዘዉ ሊቀጥሉ የሚገባ ነዉ ወይስ ለወራሶች ሊተላለፍ ይገባል የሚለዉን
ከአዋጅ ቁጥር 133/1998 እና ከደንብ ቁጥር 51/1999 አንቀጽ 11/7 መስፈርቶችና ቅደም ተከተል
አንጻር በመመርመርና እነዚህ ሕግጋት ካስቀመጡት መስፈርቶች ጋር በተያያዘ በማስረጃ ሊረጋገጥ
የሚገባ ፍሬ ነገር ካለም በማስረጃ በማጣራት ከላይ በፍርዱ ሀተታ ላይ የተጠቀሰዉን የሥነ ሥርዓት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጥያቄ ከግምት በማስገባት ተገቢዉን ዉሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 343/1 መሰረት
መልሰንለታል፡፡

3. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ተወስኗል፡፡

ት እ ዛ ዝ

1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር የወረዳ ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡


2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል፡፡ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 200564

ቀን ፡- ሕዳር 30 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች ፡- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን - ነ/ፈጅ ጥበበ መኮንን - ቀረቡ

ተጠሪ ፡- 1. ወ/ሮ የጆቴወርቅ ኪዳኔ

2. አቶ ሚሊዮን ቅጣው

3. አልማዝ ቅጣው

4. ወርቅነሽ ቅጣው

5. መንበረ ቅጣው

6. ሔለን ቅጣው

7. ዮዲት ቅጣው

8. ምሥራቅ ቅጣው

ይሕ መዝገብ ከሰበር መዝገብ ቁጥር 204121 ጋር ተጣምሮ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 1 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍርድ

ጉዳዩ የውል አለመፈጸምና የኪሣራ አከፋፈልን የተመለከተ ክርክር ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው
አመልካች ከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ግንቦት 04 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ የክስ
ማመልከቻ ያቀረበው ክስ የ1ኛ ተጠሪ ባለቤትና ከ2ኛ-8ኛ ተጠሪዎች አባት የሆኑት አቶ ቅጣው መሸሻ
ከአመልካች ጋር በተደረገ የንግድ ቤት ኪራይ ውል በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 05 ቀበሌ 12 የቤት
ቁጥሩ 1165 የሆነ የንግድ ቤት በወር ብር 212.50 እየከፈሉ ከ1969 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2004
ዓ/ም ድረስ እየከፈሉ ሲጠቀሙበት ቆይተው የተከራዩትን ቤት ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከአከራዩ ዕውቅና
ውጪ ለሦስተኛ ወገን አከራይተው የማይገባ ጥቅም በማግኘታቸው ምክንያት አመልካች የኪራይ ተመኑን
በማስተካከል በወር ብር 31,479.00 እንዲከፍሉ አድርጓል፡፡ አቶ ቅጣው ቅሬታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት
አላገኘም፡፡ በዚህ መካከል አቶ ቅጣው መሸሻ ውል ሳያድሱ ሕዳር 13 ቀን 2005 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት
ተለይተዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ውል ያላደስነው ባለቤቴ ሕመም ላይ ስለቆየና ሞግዚትነትና ወራሽነት
እስከምናረጋገጥ ድረስ ስለሆነ ጊዜ እንዲሰጠን በማለት በጽሁፍ አመልክተዋል፤ ውዝፍ ዕዳውን በተመለከተ
የአንድ ዓመት የመክፈያ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ከአመልካች ጋር የውል ሥምምነት አድርገዋል፡፡
በሥምምነቱ መሠረት ዕዳውን መክፈል ጀምረው ያቋረጡ ሲሆን እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስም
ሲገለገሉበት ቆይተዋል፡፡ ስለሆነም የኪራይ ገንዘብ ብር 2,311,503.59 ተጠሪዎች ከወለድ ጋር እንዲከፍሉ
ሲል ዳኝነት ጠይቋል፡፡

1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ በፍ/ሕ/ቁ. 2024(መ) መሠረት ከሁለት ዓመት በላይ የተጠራቀመ የቤት
ኪራይ ክፍያዎችን አመልካች የመጠየቅ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው፣ በንግድ ቤት ያለኝ መብትና
ግዴታ በሌላ የፍርድ ቤት ክርክር የተወሰነ በመሆኑ ጉዳዩ በፍርድ ያለቀ ነው፣ የንግድ ድርጅቱ
የባለቤቴ የግል ሀብት ነው ስለተባለ 1ኛ ተጠሪ ክፍያው አይመለከተኝም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ በፍሬ ነገሩም የኪራይ ዋጋ ብር 31,479.00 እንዲሆን የተደረገ ሥምምነት
የለም፡፡ መክፈል ካለብኝ እንኳን በብር 212.50 ሂሳብ ነው፡፡ ሟች ባለቤቱ ሳይዋዋል ነው የሞተው፤
ባለቤት ከሞተ በኋላ ሟች ትክክለኛ ኪራይ ለማስከፈል የጀመረውን ክርክር ለማስቀጠል
በ10/05/2005 ዓ/ም እና በ08/08/2005 ዓ/ም ለአመልካች ጥያቄ አቅርቤያለሁ፡፡ ከአመልካች ጋር
በ09/08/2005 ዓ/ም ያደረግሁት ሥምምነት ንግዱ ወደኪሣራ እንዳይገባ በማሰብ አለ የተባለው ብር
547,287.13 ዕዳ በከፊል ከፍዬ ቀሪው ደግሞ ንግዱን እያንቀሳቀስኩኝ ለመክፈል የታለመ ነው፡፡
በውሉ መሠረት ብር 200,000.00 ከከፈልኩኝ በኋላ ቀሪዎቹ ተጠሪዎች ባለመፍቀዳቸው ንግድ ቤቱ
አስተዳዳሪ ተመድቦለት አስረክቤያለሁ፡፡ ከዚህ በኋላም ከንግዱ ምንም ዓይነት ጥቅም አላገኘሁም፡፡
በውሉ መሠረት የቅጣት ክፍያ 10% ሊያስከፍል የሚችለው ኪራይ የዘገየባቸውን የመጀመሪያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 2 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስድስት ወራት ብቻ ነው፤ በውሉ አንቀጽ 3(3) መሠረት ከስድስት ወር በላይ ክፍያ ቢዘገይ ውሉን
የመሠረዝ መበት አመልካች አለው፡፡ ከስድስት ወራት በላይ ላለው ጊዜ ቅጣት ልከፍል አይገባም ብለዋል፡፡

ከ2ኛ-8ኛ ያሉት ተጠሪዎች በበኩላቸው ሟች አባታችን ከሕግ ውጭ አከራይቷል መባሉ በማስረጃ


ያልተረጋገጠ ነው፤ የኪራይ ጭማሪ ተደርጓል የተባለውም የተጋነነ እና እኛን የማያስገደድ ነው፡፡
ከተገደድንም በውሉ መሠረት ብር 212.50 ወርሃዊ ሂሳብ ብቻ ነው፡፡ ሟች ከሞተ አንስቶ በንግድ ቤቱ
ፈቃድ በማሳደስ ሲጠቀሙበት እና ሲሰሩበት የነበሩት 1ኛ ተጠሪ እንጂ ከ2ኛ-8ኛ ያለነው ተጠሪዎች
ባለመሆናችን ለዕዳው ኃላፊነት የለብንም፡፡ ውል ሳንገባ ወራሽ በመሆናችን ብቻ ለዕዳው ልንጠየቅ አይገባም፡፡
አመልካች ጻፍኩት ያለው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች ለእኛ አልደረሰም፡፡ አመልካች የንግድ ቤቱን ተረከብን
በማለት በጽሁፍ አሳውቀነዋል፡፡ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ውድቅ ካደረገ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ
ከ2ኛ - 8ኛ ያሉት ተጠሪዎች በንግድ ቤቱ ላይ ወራሽነት ቢያረጋግጡም በንግድ ቤቱ ባለመጠቀማቸው
ኃላፊነት የለባቸውም፡፡ 1ኛ ተጠሪ በአዲስ ክፍያ ለመክፈል ተስማምተው መክፈልም ጀምረዋል፡፡ ስለሆነም
ቀሪውን ዕዳም የመክፈል ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ከሚያዚያ 01 ቀን 2004 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 17 ቀን
2009 ዓ/ም ድረስ ያለውን የ57 ወራት ብር 1,780,137.93 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች ይክፈሉ፤ የውል ቅጣትን
በተመለከተ አመልካች ከስድስት ወር በኋላ ውል መሠረዝ እየቻለ ያልሰረዘ በመሆኑ ከስድስት ወራት በላይ
ላለው ቅጣት 1ኛ ተጠሪ ሊከፍሉ ስለማይገባ የስድስት ወር ቅጣት ብር 18,887.40 ብቻ የመክፈል ኃላፊነት
አለባቸው፤ በአጠቃላይ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር ብር 2,066,045.33 1ኛ ተጠሪ እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካች ሆነ 1ኛ ተጠሪ በተለያዩ መዝገቦች ያቀረቡትን
ይግባኝ ባለመቀበል ሠርዟል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የኪራይ ውሉ
ያልተቋረጠው 1ኛ ተጠሪ በተለያዬ ጊዜ ውሉ እንዳይቋረጥ እና ዕዳውን ለመክፈል ጊዜ እንዲሰጣቸው
በመጠየቀቻውና መክፈልም በመጀመራቸው ነው፡፡ ቅጣት ብር 264,344.97 ሊከፈል ይገባል፡፡ ከ2ኛ - 8ኛ
ተጠሪዎች በንግድ ቤቱ መጠቀም አለመጠቀማቸው ሳይሆን የሟች አባታቸውን ዕዳና መብት ስለሚወርሱ
ነው ክሱ የቀረበው፤ በግልጽ ውርሱ ተጣርቶ አንወርስም አላሉም፤ ወራሽ በመሆናቸው ለዕዳው ኃላፊ ናቸው
ሊባል ይገባል የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ ከ2ኛ - 8ኛ ድረስ ያሉት ተጠሪዎች
በፍርድ ቤት ክርክር የንግድ ቤቱ ወራሽ መሆናቸው በተገለጸበት ሁኔታ ለዕዳው ኃላፊነት የለባቸውም መባሉ
ሕጋዊነቱን ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዲያቀርብ በማዘዙ 1ኛ ተጠሪ በውሉ ኪራይ ካልተከፈለና
ከስድስት ወራት በኋላ ውሉን የመሠረዝ መበት እንዳለው ተመልክቷል፤ ባለመሰረዙ ምክንያት ከስድስት
ወራት በኋላ ያለውን ቅጣት ሊጠይቅ አይችልም ብለዋል፡፡ ከ2ኛ - 8ኛ ያሉት ተጠሪዎች በበኩላቸው
የአባታችን ወራሽ በመሆናችን ብቻ ልንጠየቅ አይገባም፤ የኪራይ ውል አልተዋዋልንም፣ የንግድ ቤቱን
እንድንረከብ ሆነ እንድንጠቀም አልተደረገም፣ ስለሆነም ለዕዳው ተጠያቂነት የለብንም በማለት ተከራክረዋል፡፡
አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሠበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 3 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

1ኛ ተጠሪ በሰበር መዝገብ ቁጥር 204121 አመልካች ላይ ያቀረቡት የሠበር አቤቱታ ይዘት ደግሞ በፍ/ሕ/ቁ.
2024(መ) መሠረት ከሁለት ዓመት በላይ የተጠራቀመ የቤት ኪራይ ክፍያዎችን አመልካች የመጠየቅ መብቱ
በይርጋ የታገደ ነው፣ በንግድ ቤት ያለኝ መብትና ግዴታ በሌላ የፍርድ ቤት ክርክር የተወሰነ በመሆኑ ጉዳዩ
በፍርድ ያለቀ ነው፣ የንግድ ድርጅቱ የባለቤቴ የግል ሀብት ነው ስለተባለ ክፍያው አይመለከተኝም፤ የንግድ
ቤቱን ውርስ አጣሪ እያስተዳደረው ስለመሆኑና በንግድ ቤቱ ላይ መብት እንደሌለኝ የሚያስረዱ መዝገቦችን
የሥር ፍርድ ቤት በማስረጃነት አስቅርቦ አለመመርሩ ስህተት ያለበት ነው፡፡ የተሻሻለ የኪራይ ውል ሆነ
የኪራይ ዋጋ የለም የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን መርምሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የንግድ
ቤት የሟች የግል ሀብት ነው ተብሎ በተወሰነበት ሁኔታ 1ኛ ተጠሪ የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ የተወሰነበት
አግባብነትን ለማጣራት አመልካች መልስ እንዲያቀርብ የታዘዘ ሲሆን አመልካች ያቀረበው መልስ ይዘት 1ኛ
ተጠሪ ዕዳው መኖሩን አምነው በአዲስ የኪራይ ዋጋ ለመክፈል የውል ሥምምነት ከማድረጋቸውም ባሻገር
ክፍያ የጀመሩ በመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 2024(መ) መሠረት በይርጋ ሊታገድ አይችልም፡፡ በ1ኛ ተጠሪ እና ከ2ኛ-
8ኛ ድረስ ባሉት ተጠሪዎች መካከል የውርስ ሀብት ክርክር ተደርጎ መወሰኑ አመልካች ካቀረበው ክስ ጋር
የሚገናኝ ባለመሆኑ አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ሊባል አይገባውም፡፡ 1ኛ ተጠሪ ሟች ባለቤት
በመሆናቸውና በንግድ ቤቱም በጋራ ሲጠቀሙ የነበረ፣ ባለቤታቸው ከሞቱ በኋላም መጠቀም የቀጠሉ ስለሆነ
ዕዳው ለትዳር ጥቅም የዋለ በመሆኑ ኃላፊ መባላቸው ተገቢ ነው፡፡ የንግድ ቤቱ የግል ሀብት ነው ተብሎ
የተወሰነው ታህሳስ 25 ቀን 2009 ዓ/ም ሲሆን አመልካች እንዲከፈለው የጠየቀው ዕዳ ከሚያዚያ 01 ቀን
2004 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስ ስለሆነ ክፍያውን የማይከፍሉበት ሕጋዊ ምክንያት
የለም፡፡ አመልካች ተቋም እንደመሆኑ መጠን የኪራይ ተመን ሲያሻሻል ከተከራይ ጋር ሥምምነት ማድረግ
እንደማይጠበቅበት ሕጉ ይደነግጋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በገቡት የውል ግዴታ መሠረት የተወሰነ በመሆኑ የሥር
ፍርድ ቤት ተጨማሪ ማስረጃ አስቀርቦ የሚመረምርበት አግባብ የለም በማለት ተከራክሯል፡፡ 1ኛ ተጠሪ
የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘውን
ጭብጥ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካች ግንቦት 04 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ የክስ ማመልከቻ ያቀረበው ክስ የ1ኛ ተጠሪ
ባለቤትና ከ2ኛ-8ኛ ተጠሪዎች አባት የሆኑት አቶ ቅጣው መሸሻ ከአመልካች ጋር በተደረገ የንግድ ቤት
ኪራይ ውል በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 05 ቀበሌ 12 የቤት ቁጥሩ 1165 የሆነ የንግድ ቤት
የተከራዩ ሲሆን ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከአከራዩ ዕውቅና ውጪ ለሦስተኛ ወገን አከራይተው የማይገባ
ጥቅም በማግኘታቸው ምክንያት አመልካች የኪራይ ተመኑን በማስተካከል በወር ብር 31,479.00 እንዲከፍሉ
አድርጓል፡፡ አቶ ቅጣው ቅሬታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በዚህ መካከል አቶ ቅጣው መሸሻ ውል
ሳያድሱ ሕዳር 13 ቀን 2005 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ስለሆነም የሟች ባለቤት የሆኑት 1ኛ
ተጠሪ በገቡት የውል ሥምምነት መሠረት እና ከ2ኛ-8ኛ ያሉት ተጠሪዎች ወራሽ በመሆናቸው ከሚያዚያ
01 ቀን 2004 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስ ያለውን የኪራይ ገንዘብ ከነቅጣቱ ብር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 4 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2,311,503.59 እንዲከፍሉ የሚል ሲሆን ተጠሪዎች በፍ/ሕ/ቁ. 2024(መ) መሠረት ከሁለት ዓመት በላይ
የተጠራቀመ የቤት ኪራይ ክፍያዎችን አመልካች የመጠየቅ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው፣ 1ኛ ተጠሪ በንግድ
ቤት ያለኝ መብትና ግዴታ በሌላ የፍርድ ቤት ክርክር የተወሰነ በመሆኑ ጉዳዩ በፍርድ ያለቀ ነው የሚል
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በሥረ-ነገሩም ለኪራይ ገንዘቡ ኃላፊ አይደለንም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪዎች የፍ/ሕ/ቁ. 2024(መ) መሠረት በማድረግ ከሁለት ዓመት በላይ የተጠራቀመ የቤት ኪራይ
ክፍያዎችን አመልካች የመጠየቅ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው በሚል ያቀረቡትን መቃወሚያ ስንመርምር
ድንጋጌው መብትን አስመልክቶ ክስ የማቅረቢያ ጊዜን ቀሪ የሚያደርግ የይርጋ ጽንሰ ሃሳብ ያለው አይደለም፡፡
በክርክር ሂደት ፍሬ ነገሮችን ማረጋገጥ የሚቻልባቸው ዘዴዎች ማስረጃ፣ በፍርድ ቤት በሚሠጥ የእምነት
ቃል፣ ፍርድ ቤት በራሱ ግንዛቤ ሊወስድባቸው የሚችሉ ጉዳዮች /Judicial notice/፣ የሕግ ግምት
(presumption of fact) እና የመሓላ ቃል ሲሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 2024(መ) የተመለከተም ፍሬ ነገር ከማረጋገጫ
ዘዴዎች ከሆኑት አንዱ መካከል ስለሕግ ግምት የተደነገገ ነው፡፡ የኪራይ ገንዘብን አስመልክቶ አልተከፈለኝም
በሚል አከራይ ለሚያቀርበው ክርክር ተከሳሽ የሆነው ወገን ከፍያለሁ የሚል ክርክር የሚያቀርብ ከሆነ እና
ያልተከፈለው ኪራይ ገንዘብ ሁለት ዓመት ጊዜ ያለፈው መሆኑ ሲረጋገጥ ፍርደ ቤቱ ኪራይ ገንዘቡ
እንደተከፈለ ግምት የሚወስድበት ነው፡፡ ስለሆነም ጉዳዩ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሆኖ የሚቀርብ
ሳይሆን በፍሬ ነገሩ ክርክር ሂደት በክሱ የተመለከቱ ጉዳዮች በፍሬ ነገር ማረጋገጫ ዘዴዎች የተረጋገጠ
መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ ተጠሪዎች የሚከራከሩት ኪራይ ገንዘቡን ከፍለናል
የሚል ሳይሆን ገንዘቡን የመክፈል በውል ሆነ በውርስ ሕግ አንገደድም የሚል በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ኪራዩ
እንደተከፈለ የሕግ ግምት የሚወስድበት አግባብ የለም፡፡

በሀሉተኛ ደረጃ በ1ኛ ተጠሪ የቀረበው መቃወሚያ ጉዳዩ በፍርድ ያለቀ ነው የሚል ነው፡፡ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
5(1) መሠረት በሕግ ሥልጣን የተሠጠው ማናቸውም ፍርድ ቤት ክርክሩን ተቀብሎ የመጨረሻ ፍርድ
ከሠጠ በኋላ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ሥረ-ነገርና የተያዘው ጭብጥ አንድ ዓይነት ከሆነ፤ በክርክሩ
ላይ የነበሩት ወይም ከተከራካሪዎቹ መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች በዚያው ነገር ሁለተኛ ክስ ማቅረብ
አይችሉም፡፡ በድንጋጌው መሠረት ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ አልቋል ለማለት የተዘረዘሩት አራት መስፈርቶች
በአንድነት መሟላት አለባቸው፡፡ የመጀመሪያው መስፈርት ጉዳዩን የተመለከተው በሕግ ሥልጣን የተሠጠው
(ሠረዝ የተጨመረ) ማናቸውም ፍርድ ቤት መሆኑ ነው፡፡ በሕግ ሥልጣን የተሰጠው የሚለው ትርጉም
የሚያስፈልገው መስፈርት ነው፡፡ በፍርድ ቤት የሥረ-ነገር ሥልጣን ሳይኖረው የተሠጠ ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 212 እንደተመለከተው በይግባኝ እስካልተለወጠ ድረስ የጸና በመሆኑ ጉዳዩን አስቀድሞ
ፍርድ እንደተሠጠበት የሚያስቆጥር ነው፡፡ ስለሆነም በሕግ ሥልጣን የተሠጠው የሚለው የሥረ-ነገርና
አካባቢያዊ ሥልጣንን የሚመለከት ሳይሆን አስቀድሞ ጉዳዩ የታዬው በሕግ ዳኝነት ለመስጠት ሥልጣን
ያለው ፍርድ ቤት ወይም ዳኝነት ነክ አካል መሆኑን ለማመላከት ነው፡፡ ይህም በፍርድ ቤት ሥልጣን
ሳይኖረው ፍርድ መስጠት እንደ አስገዳጅ ውሳኔ የሚቆጠርና የሚፈጸም መሆኑን የሚያሳይ እና በኢትዮጵያ
እንዳልተሰጠ የሚቆጠር ፍርድ (void judgment) እንደሌለ ያስረዳል፡፡ ዳኝነት ለመስጠት በሕግ ሥልጣን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 5 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ያልተሠጣቸው አካላት ጉዳዩ ላይ አስቀድመው በአስተዳደር ማየታቸው ሆነ ውሳኔ መስጠታቸው ጉዳዩን


በፍርድ እንዳለቀ የማያስቆጥር እና ክርክር ከማድረግ የሚከለክል አይሆንም፡፡ ይህም በኢፌዲሪ ሕገ-
መንግሥት አንቀጽ 37 እና አንቀጽ 79(1) እንደተመለከተው የመዳኘት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች እና የዳኝነት
ነክ አካል ብቻ መሆኑን የሚያሳይ እና በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 50(2) የመንግሥት አካላትን
የሥልጣን ክፍፍል መርህን (principle of separation of powers) የተከተለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ሁለተኛው መስፈርት አስቀድሞ በፍርድ ቤት የተሠጠው የመጨረሻ ፍርድ መሆን አለበት የሚለው ነው፡፡
ፍርድ ቤቱ ክርክሩን አይቶ ጉዳዩ ላይ የመጨረሻ እልባት ወይም ውጤት የሠጠበት መሆን እንዳለበት
የሚያስረዳ መስፈርት ነው፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ ደረጃ በመሰማት ላይ እያለ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 73 መሠረት
ሆነ በይግባኝ ደረጃ ላይ እያለ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 69(2)፣ አንቀጽ 70(መ) እና አንቀጽ 73 በተመለከተው
አግባብ መዝገቡ ከተዘጋም፤ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 74(1) እንደተመለከተው በተቋረጠው ጉዳይ አዲስ ክስ
ማቅረብ መከልከሉ ጉዳዩ በፍርድ አልቋል የሚለውን መርህ የሚከተል ነው፡፡ በሌላ በኩል በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
231(1) የተመለከተው በክስ አቤቱታው የተገለጸው የማያስከስስ መሆን ወይም የሥረ-ነገር ሥልጣን
አለመኖር ምክንያት ተደርጎ ክሱ መቋረጡ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ያልተሠጠበት ስለሆነ በፍርድ
እንዳለቀ የሚያስቆጥር አይሆንም፡፡ የክስ ምክንያት ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ግዴታ መኖሩን፣
የተጠየቀው ዳኝነት በፍርድ ቤት የሚዳኝ መሆን አለመሆኑን እና በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተመለከቱት ጉዳዮች
ቢረጋገጡ የተጠየቀውን ዳኝነት ለከሳሽ ለመወሰን ህግ የሚፈቅድ መሆን አለመሆኑን መመርመርን የሚጠይቅ
ነው፡፡ ይህም የክስ ምክንያት የሌለው ጉዳይ የሚለው በዋነኛነት ዳኝነቱን ለመጠየቅ ከህግ የመነጨ ግንኙነት
እያለው ግን በፍርድ ቤት ሊዳኙ የማይችሉ ጉዳችን (non-justiciable matters) የጉዳዩ ባሕሪ በፍርድ ቤት
ሥልጣን ሥር ሊወድቁ የማይችሉ፣ አከራክሮ ሊፈጸም የሚችል ውሳኔ ሊሰጥባቸው የማይችሉ
በመሆናቸውና ከሳሽ ወገን ክሱን ሲያቀርብ የጠቀሰው ወይም የገለጸው የክሱ መሰረት የሆነው ምክንያት በህግ
የክስ መሰረት ሊሆን የማይችል ከሆነ የማያስከስስ ነው ተብሎ ክሱ ውደቅ የሚደረግበት ሥርዓት ነው፡፡
ጉዳዩም በሥረ-ነገሩ ታይቶ ውሳኔ ያላረፈበት በመሆኑ እንደ መጨረሻ ፍርድ የሚቆጠር አይደለም፡፡ የሥረ-
ነገር ሥልጣን ባለመኖር ክሱ ውድቅ መደረጉም ሥልጣን ባለው ሌላ የዳኝነት አካል ጉዳዩ ቀርቦ ሊወሰን
የሚችል በመሆኑና በሥረ-ነገሩ ጉዳዩ ላይ ውሳኔ ያልተሠጠበት በመሆኑ በፍርድ እንዳለቀ ጉዳይ ተቆጥሮ
መቃወሚያ ሊቀርብበት የሚችል አይደለም፡፡ ስለሆነም የመጨረሻ ፍርድ የሚለው በሥረ-ነገሩ መታየትን
መሠረት ያደረገ ቅድመ ሁኔታ መኖር እንዳለበት የሚያስገነዝብ ነው፡፡

ሦስተኛው መስፈርት አስቀድሞ ፍርድ ያረፈበት ጉዳይ ሥረ-ነገሩና ጭብጡ አሁን ከተያዘው ጉዳይ ጋር
አንድ ዓይነት መሆን አለበት የሚለው ነው፡፡ የክርክሩ መነሻ ጉዳይ አንድ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤቱ
በጭብጥነት የመረመረው ጉዳይ አሁን በተያዘው ክርክርም በጭብጥነት ተይዞ የሚመረመር ከሆነ ውጤቱ
አስቀድሞ ፍርድ ያረፈበት ይሆናል፡፡ ሥረ-ነገሩ ተመሳሳይ ሆኖ ነገር ግን የሚያዘው ወይም የተያዘው
ጭብጥ የተለያዬ ከሆነ በተያዘው ጭብጥ ላይ የቀደመ ፍርድ ባለመኖሩ ጉዳዩ በፍርድ እንዳለቀ ሳይቆጠር
ክርክሩ ቀጥሎ ፍርድ ሊያርፍበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ በሕጉ ላይ የተቀመጠው አራተኛው መስፈርት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 6 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተከራካሪዎች ወይም ከተከራካሪዎች መብት ያገኙ ሦስተኛ ወገኖች ተመሳሳይ መሆን እና በእነርሱ መካከል
ያለ ክርክር መሆኑ ነው፡፡ የዚህ መስፈርት መነሻ ፍርድ የአስገዳጅነት ሀይል ሆነ ውጤት የሚኖረው
በተከራካሪዎች መካከል ብቻ ነው የሚል ነው፡፡ ከተከራካሪዎች ውጭ ፍርዱን በመያዝ መብት ማቋቋም ሆነ
ማስፈጸም አይቻልም፡፡ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የሚመረምረው ሆነ ፍርድ የሚሠጠው ከተከራካሪዎች መካከል
የተሻለ መብት ያለው ማን ነው ከሚለው ነጥብ አኳያ ብቻ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ ያላቸው መብት በፍርድ ቤቱ
ሳይመረመር እና የመደመጥ ሆነ የመከላከል መብታቸው ሳይከበር ተከራካሪ ያልሆኑ ወገኖች ላይ ፍርዱ
አስገዳጅነት አለው ሊባል አይችልም፡፡ የተከራካሪዎች ተመሳሳይነት የሚለው ከተከራካሪዎች በሕግ ሆነ በውል
መብት የተላለፈላቸውን ሦስተኛ ወገኖች የመብታቸው ምንጭ የቀድሞው ክርክር ላይ ተከራካሪ በሆኑት
ወገኖች ልክ በመሆኑ በእነዚህ ወገኖች ላይም ጉዳዩ አስቀድሞ በፍርድ እንዳለቀ የሚያስቆጥር ነው፡፡

በተያዘው ጉዳይ መቃወሚያው የቀረበው 1ኛ ተጠሪ እና ከ2ኛ - 8ኛ ድረስ ያሉት ተጠሪዎች መካከል የንግድ
ቤቱን አስመልክቶ ያደረጉት ክርክርና በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 180343 ታህሳስ 25
ቀን 2009 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የንግድ ቤቱ የሟች ቅጣው መሸሻ የግል ሀብት ነው ተብሎ መወሰኑን
መሠረት በማድረግ ነው፡፡ በዚህ ክርክር ውርስ ማጣራት ሂደትን ተከትሎ አመልካች የኪራይ ገንዘብ
የጠየቀበት የንግድ ድርጅቱ የውርስ ሃብት መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ጭብጥ ሲሆን አሁን በሰበር
ችሎት ደረጃ የተያዘው ጉዳይ ደግሞ የኪራይ ገንዘብ አከፋፈልን የሚመለከት በመሆኑ የጭብጥ ልዩነት
ያለው ነው፡፡ በውርስ ክርክሩ አመልካች ባለመሳተፉና ሊሳተፍም የማይችል በመሆኑ የተከራካሪዎች
ተመሳሳይነትም የለም፡፡ ሥለሆነም ጉዳዩ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5(1) መሠረት በፍርድ ያለቀ ባለመሆኑ በዚህ
ረገድ 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም፡፡

በሥረ ነገሩ አመልካች የኪራይ ገንዘብ እንዲከፈለው የጠየቀ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 05
ቀበሌ 12 የቤት ቁጥሩ 1165 የሆነ የንግድ ቤት ላይ አመልካች እና ሟች ቅጣው መሸሻ ባደረጉት የኪራይ
ውል መነሻ የሚጠቀሙበት ሲሆን አመልካች የኪራይ ተመን ለማሻሻል በሕግ ባለው ሥልጣን መሠረት
ከጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ/ም በኋላ ላለው ጊዜ በወር ብር 31,479.00 እንዲከፍሉ አድርጓል፡፡ በማሻሻያው
ላይ ቅሬታ ቀርቦም ተቀባይነት ያጣ በመሆኑ የውል ማሻሻያው ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በሕግ አግባብ የተደረገ
ውል በተዋዋዮች መካከል በፍ/ሕ/ቁ. 1731(1) እንደተመለከተው እንደ ሕግ የሚቆጠር መሆኑ እና በፍ/ሕ/ቁ.
1785(2) መሠረት በውል ዓይነተኛ መጣስ ከሌለ በስተቀር መፈጸም እንዳለበት የተደነገገ መሆኑ ሲታይ
በተቻለ መጠን ተዋዋዮች ባስተላለፉት መብትና ግዴታ ልክ ውሉን የመፈጸም ግዴታ አለባቸው፡፡

ተከራይ የሆኑት አቶ ቅጣው መሸሻ ሕዳር 13 ቀን 2005 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ በመሆናቸው
ከሚያዚያ 01 ቀን 2004 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስ ያለውን የኪራይ ገንዘብ ከነቅጣቱ
ብር 2,311,503.59 ተጠሪዎች እንዲከፍሉ አመልካች ዳኝነት ጠይቋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ክፍያው አይመለከተኝም
የሚሉት የውል ግዴታ አልገባሁም፣ የንግድ ቤቱ በፍርድ ቤት ክርክር የሟች የግል ሀብት ተብሏል፣ ውርስ
አጣሪው ንብረቱን ተረክቦ እያስተዳደረው ነው በሚል ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ የሟች ቅጣው መሸሻ ባለቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 7 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመሆናቸው ከባለቤታቸው ጋር የነበራቸው ጋብቻ በሞት እስኪፈርስ ድረስ በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑ
አልተካደም፤ ንብረቱ የባለቤታቸው የግል ቢሆን እንኳን የተሻሻለው የፌዴራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 62(1)
መሠረት ገቢው የጋራ ስለሚሆን በጋራ ለሚጠቀሙበት ንግድ ሥራ ወጪውንም በጋራ የመክፈል ኃላፊነት
ይኖርባቸዋል፡፡ ጋብቻው በሞት ከፈረሰ በኋላም በሥር ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መካከል 1ኛ
ተጠሪ በ10/05/2005 ዓ/ም እና በ08/08/2005 ዓ/ም ለአመልካች ያቀረቡት ጥያቄ ሆነ ከአመልካች ጋር
በ09/08/2005 ዓ/ም ብር 547,287.13 ዕዳ ለመክፈል ያደረጉት ሥምምነት እና በውሉ መሠረት ብር
200,000.00 መክፈል መጀመራቸው በንግድ ቤቱ መጠቀማቸውን መቀጠላቸውን የሚያስገነዝብ ነው፡፡
አመልካች የኪራይ ገንዘብ እስከጠየቀበት ታህሳስ 17 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስ 1ኛ ተጠሪ በንግድ ቤቱ ላይ
ከ2ኛ-8ኛ ድረስ ካሉት ተጠሪዎች ጋር የውርስ ክርክር በማድረግ መቀጠላቸው መረጋገጡ ሆነ አመልካች
ንብረቱን እንዲረከባቸው ኃላፊነትን ስለማውረድ ክስ ባላቀረበቡት ሁኔታ ንብረቱን ለውርስ አጣሪ
አስረክቤያለሁ በሚል ለኪራይ ገንዘቡ ኃላፊ ልሆን አይገባም የሚለው ክርክር ተቀባይነት የለውም፡፡ ስለሆነም
በሥር ፍርድ ቤቶች 1ኛ ተጠሪ ለኪራይ ገንዘብ ኃላፊ ናቸው ተብሎ መወሰኑ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡

ከ2ኛ-8ኛ ድረስ ያሉት ተጠሪዎች የሟች ቅጣው ወራሾች በመሆናቸው የአባታቸውን ዕዳ እንዲከፍሉ የቀረበ
ዳኝነት ነው፡፡ የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከ2ኛ - 8ኛ ያሉት ተጠሪዎች በንግድ ቤቱ ላይ ወራሽነት
ቢያረጋግጡም በንግድ ቤቱ ባለመጠቀማቸው ኃላፊነት የለባቸውም ብሏል፡፡ ከ2ኛ-8ኛ ድረስ ያሉት ተጠሪዎች
የሟች አባታቸው ወራሽ ሲሆኑ አመልካች የኪራይ ገንዘብ የጠየቀበትን የንግድ ቤት ጨምሮ የውርስ ሀበት
መውረሳቸውን ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 180343 የተሰጠው ውሳኔ
ያስገነዝባል፡፡ በፍ/ሕ/ቁ. 826(1) መሠረት ሟች ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ ውርሱ የሚከፈት ሲሆን በንዑስ ቁጥር
ሦስት እንደተመለከተው የሟች መብቶችና ግዴታዎች ወደወራሾች ይተላለፋሉ፡፡ ሟች አባታቸው የንግድ
ቤት ከአመልካች በመከራየታቸው ምክንያት የሚመጣ ዕዳን ከ2ኛ-8ኛ ድረስ ያሉት ተጠሪዎች ወራሾች
በመሆናቸው ብቻ ለዕዳው ኃላፊ ናቸው፡፡ በንግድ ቤቱ መጠቀም አለመጠቀማቸው በጭብጥነት የሚመረመር
አይደለም፡፡ የሥር ፍርድ ቤት ወራሾች መሆናቸውን አረጋግጦ እያለ በንግድ ቤት አልተጠቀሙም በሚል
ለክሱ ኃላፊ አይደሉም በሚል የደረሰበት መደምደሚያ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡

አመልካች ክፍያው ሳይፈጸም በመዘግየቱ ቅጣት እንዲከፈለው ጠይቋል፡፡ በፍ/ሕ/ቁ. 1790 እና 1791
እንደተመለከተው ውል ያልተፈጸመው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ውል ያልፈጸመው
ወገን የደረሰውን የጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡ የሚከፈለው ኪሣራ ተዋዋዮች በፍ/ሕ/ቁ. 1889 መሠረት
አስቀድመው የወሰኑት ከሆነ በውሉ የተመለከተውን መጠን ሲሆን ተዋዋዮች አስቀድመው ኪሣራውን
ካልወሰኑ በክርክር ሂደት ፍርድ ቤት ኪሣራውን በማስረጃ አጣርቶ የሚወስነው ይሆናል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት
እስከ ስድስት ወራት ድረስ ያለውን የቅጣት ክፍያ 10% እንዲከፈል የወሰነ ሲሆን ቀሪ ቅጣት ክፍያውን
ውድቅ ያደረገው በውሉ አንቀጽ 3(3) መሠረት ከስድስት ወር በላይ ክፍያ ቢዘገይ ውሉን የመሠረዝ መብት
አመልካች እያለው መብቱን ሳይጠቀም ለተጠራቀመው ቅጣት ክፍያ እንዲከፈለው መጠየቅ አይችልም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 8 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በማለት ነው፡፡ በፍ/ሕ/ቁ. 1784 እና ከ1786-1789 መሠረት ውል በፍርድ ቤት ወይም በተናጠል በተዋዋይ
ወገን ሊሠረዝ ይችላል፡፡ በውሉ የተመለከቱ ሁኔታዎች ሲሟሉ ተዋዋይ ወገን ውሉን በተናጠል የመሠረዝ
መብት የሚኖረው ሲሆን ወሉን የመሰረዝ መብቱን አለመጠቀሙ እንደውል እንዲፈጸም ከመጠየቅ ወይም
ውሉ ባለመፈጸሙ ምክንያት ጉዳት ሲደርስ ጉዳት ኪሣራ እንዳይጠይቅ የሚያደርግ አይደለም፡፡

አመልካች ውሉን የመሠረዝ መብት ባለመጠቀሙ የውል አፈጻጸም የቀጠለ እስከሆነ ድረስ እና ተጠሪዎች
ክፍያ ሳይከፍሉ ለቆዩበት ጊዜ በውሉ የተመለከተው የጉዳት ኪሣራ/ቅጣት እንዲከፍሉ መጠየቁ ሕግን
መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በፍ/ሕ/ቁ. 1893 እንደተመለከተው ዳኞች መቀጫ መቀነስ የሚችሉት ውሉ በከፊል
ከተፈጸመ ብቻ ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ የኪራይ ውል ክፍያው በየወሩ የሚከፈል በመሆኑ እና ተጠሪዎች
ከሚያዚያ 01 ቀን 2004 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2009 ዓ/ም ድረስ ላሉት 57 ወራት ክፍያ
ባለመክፈላቸው በየወሩ ለዘገየው ክፍያ በውሉ የተመለከተውን ቅጣት የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህ
ረገድ የሥር ፍርድ ቤት ቅጣት ክፍያው በከፊል ብቻ ነው ሊከፈል የሚገባው ሲል የደረሰበት መደምደሚያ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 194706 በጥቅምት 16 ቀን 2013
ዓ/ም እና በመዝገብ ቁጥር 195936 ታህሳስ 08 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
በመዝገብ ቁጥር 191209 ግንቦት 04 ቀን 2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት
ተሻሽሏል፡፡

2. 1ኛ ተጠሪ እና ከ2ኛ - 8ኛ ድረስ ያሉት ተጠሪዎች ብር 2,311,503.59 በጋራ ለአመልካች እንዲከፍሉ


ተወስኗል፡፡

3. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት


በውሳኔው መሠረት እንዲያስፈጽም አዘናል፡፡ ይጻፍ
 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ካለ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 9 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 10 / 10
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-200687

ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር- ጠበቃ


ንጉሴ እሰየው ቀረቡ

ተጠሪ፡ አቶ ኢብራሒም አይዶግዱ- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው ኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ
ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ
አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ከመዝገብ እንደሚታዉ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት
ውስጥ የምግብ ባለሙያ ሁኜ በቀን 28/04/2000 ዓ.ም በወር 2500 ዶላር ደመወዝ ተቀጥሬ
እየሰራሁ እያለ በቀን 22/08/2011 ዓ.ም ያለጥፋት ከህግ ውጪ ውልህን ጨርሰሀል በማለት
ከስራዬ አሰናብቶኛል፣ስለዚህ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ ተብሎ የአገልግሎት ክፍያ፣የካሳ ክፍያ፣
የማስጠንቀቂያ ጊዜ፣ ክፍያ የዘገየበት እና ለአውሮፕላን ቲኬት በአጠቃላይ 41,264.33 ዶላር
ወይም በኢትዮጵያ ብር 1,190,477.44 ከ10% የጠበቃ አበል ጋር እንዲከፈልኝ እንዲወሰንልኝ
በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡አመልካች በበኩሉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የስራ ስምምነት ለተወሰነ ጊዜ ለአንድ አመት የሚቆይ ሆኖ ውሉ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ


ሊቋረጥ እንደሚችል ተስማምተናል፣ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራበት የቆየው የስራ መደብ ላይ
የኢትዮጵያ ዜጋ በብቃት ሊሰሩ የሚችሉት ነው፡፡ለአንድ የውጪ ዜጋ ደግሞ ፈቃድ የሚሰጠው
የሀገር ውስጥ ሰራተኞች ግንዛቤ እና ልምድ እስከሚያገኙ ብቻ ነው፡፡ስለዚህ የሀገር ውስጥ
ዜጎች መስራት እየቻሉ የውጭ ዜጋ መስራት የለበትም፡፡ውላችን ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ሲሆን
የውጭ ዜጋ ሆኖ ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ መስራቱ ከህግ ውጪ በመሆኑ ውሉ የተቋረጠው በህግ
አግባብ በመሆኑ የተጠየቀው ክፍያ ሊከፈለው አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች እና ተጠሪ የተፈራረሙት የስራ


ውል ከ23/04/2010 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን የሚያሳይ ቢሆንም
በአዋጅ ቁ/377/96 አንቀጽ 10 ስር ከተገለጹት ምክንያቶች ውስጥ በየትኛው ምክንያት ለተወሰነ
ጊዜ እንደተደረገ የተገለጸ ነገር የለም፡፡ውሉ ለተወሰነ ጊዜ ስለተባለ ብቻ የህጉን መስፈርት
አሟልቷል የሚያስብል አይደለም፣ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ስራ ሲሰራ እንደቆየ የሚያሳይ
ማስረጃ አመልካች አላቀረበም፡፡ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራበት የቆየው ስራ ደግሞ በባህሪው
በቀጣይነት የሚሰራ ስራ በመሆኑ እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.43160 ላይ
በሰጠው ዉሳኔ በአንቀጽ 10 ስር ተዘርዝረው ካሉት ስራዎች ውጭ ከሆነ ይህ ውል የተወሰነ
ጊዜ ነው ቢባል እንኳን የተወሰነ ጊዜ ዉል ሊሆን አይችልም በማለት አስገዳጅ ውሳኔ
ሰጥቷል፡፡የውጭ ሀገር ዜጋ ስለሆነ ውሉ የተወሰነ ጊዜ ነው የሚል ህግ የለም፣ስለዚህ የስራ ውሉ
ላልተወሰነ ጊዜ ነው፣አመልካች የውሉ ጊዜ ስለተጠናቀቀ በማለት ውሉን ማቋረጡ የህግ መሰረት
የለውም፣ስንብቱ ከህግ ውጭ ነው በማለት የተጠየቁ ክፍያዎች ለተጠሪ እንዲከፈል በማለት
ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ጉዳዩ አያስቀርብም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙን
ሰርዟል፡፡አመልካች ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ችሎቱም
ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኝ ክርክር ሰምቶ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የለዉም በማለት አጽንቷል፡፡ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ፡፡

አመልካች ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤ዉሉ ለተወሰነ ጊዜ ከውጭ ሀገር ዜጋ ጋር የተደረገ


የቅጥር ውል የሚል ሲሆን ይህንን የሚያረጋግጥ በስር ፍ/ቤት ሰነዱ ቀርቦ እያለ እና በቅጥር
ውሉ አንቀጽ 11(ሐ) መሰረት ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንዱ ወገን ውሉን በማንኛውም ጊዜ
መቋረጥ እንደሚቻል ተመልክቷል፣በኢንቨስትመንት ደንብ ቁጥር 474/2012 አንቀጽ 19(1)
መሰረት የውጭ ሀገር ዜጎችን የሚቀጥር ባለሀብት ለኢትዮጵያዊያን አስፈላጊውን የስራ ላይ
ስልጠና እንዲሰጥ እና እውቀት እንዲተላለፍ በማድረግ የውጭ ዜጋ ተቀጣሪዎች
በኢትዮጵያዊያን እንዲተኩ የማድረግ ግዴታ ያለበት ሲሆን በዚሁ መሰረት አመልካች የተጠሪ
የስራ ውል በውላቸው መሰረት እንዲቋረጥ ማድረጉ ህጋዊ ስንብት ነው፡፡ተጠሪ በአመልካች
ድርጅት ውስጥ ለ11 ዓመት የሰራው በጊዜያዊነት የስራ ቅጥር ውሉ እየታደሰ እና የስራ
ፍቃዱም እንዲታደስ በማድረግ ነው፡፡ተጠሪ በቋሚነት መቀጠሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
አላቀረበም፡፡ስለዚህ ለዜጎች ቅድሚያ የሥራ ዕድል ለመስጠት ሲባል በህጋዊ መንገድ የተቋረጠ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉል ላይ ብር 1,190,477.44 እንዲከፈል የተወሰነው መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ውሳኔው


እንዲሻር በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ ቅጥሩ ለተወሰነ ጊዜ
መሆኑን የቅጥር ውሉ ላይ ከመመልከቱ አንፃር የስር ፍ/ቤት ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የስራ
ውል ነው በሚል መነሻ ስንብቱ ህገወጥ ነው ማለቱን አግባብነት ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ
ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ታዟል፡፡

ተጠሪ ባቀረበው መልስ በውላችን መሰረት አመልካች በቅድሚያ የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ


ሳይሰጥ እንዲሁም የውሉ ቀን ሳይጠናቀቅ ውሉን ማቋረጡ ስንብቱን ህገ ወጥ ያደርጋል፡፡
በተጠሪ ድርጅት ላልተወሰነ ጊዜ ተቀጥሬ ለ11 ዓመታት ሲሰራ መቆየቴ በስር ፍ/ቤት
ተረጋግጧል፡፡አንድ ሰራተኛ ለተወሰነ ወይስ ላልተወሰነ ጊዜ ነው የተቀጠረው ለማለት
የሚቻለው ሰራተኛው የተቀጠረበት ስራ ባህሪይ እንጂ በውሉ ላይ ለጊዚያዊ ስራ ተቀጥረዋል
ስለተባለ ብቻ እንደማይሆን ሰበር ችሎቱ በመ/ቁ.43160 ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቷል፤
አመልካች ስራው እንዳልተጠናቀቀ እና በተጠሪ ስራ ቦታ ሌላ ሰው መቅጠሩ ተጠሪ ላልተወሰነ
ስራ እንደተቀጠረ ያረጋግጣል፡፡ስለዚህ በድርጅቱ ለተከታታይ ለ11 ዓመት አገልግዬ
ያለአገልግሎት ክፍያ፣ ያለማስጠንቀቂያ፣ የቲኬት ክፍያ እና ያለምንም ክፍያ ያሰናበተኝ ስለሆነ
የስር ፍ/ቤቶች ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በማለት የሰጡት ውሳኔ ስህተት የሌለበት በመሆኑ
እንዲፀና በማለት ተከራክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እና ክርክሩን
አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን
እንደተገነዘብነዉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ የስራ ዉል የተቋረጠዉ
በአመልካች አነሳሽነት መሆኑ አላከራከረም፡፡አመልካች አጥብቆ የምከራከረዉ ተጠሪ የዉጭ
ሀገር ዜጋ በመሆኑና ዉሉም ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ስለሆነ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ ሊባል
አይገባም በማለት ነዉ፡፡

በመሰረቱ የስራ ዉል እንደማናቸዉም ዉል የግራቀኙን መብትና ግዴታ በሚመለከት በአሰሪዉ


እና በሰራተኛዉ ነጻ ፈቃድና ስምምነት የሚደረግ ዉል ቢሆንም በህግ የተጠበቁ ዝቅተኛ
የሥራ ሁኔታዎችን የሚቀንስ ወይም የሚቃረን ሊሆን አይችልም፡፡የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ
ቁጥር1156/2011 አንቀጽ4 ድንጋጌ ስር የተመለከቱት ሁኔታዎች ይህንኑ ያስገነዝባሉ፡፡የስራ
ዉል አይነት በተመለከለተ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ ሊደረግ
እንደሚችል የአዋጁ አንቀጽ 4/1/ ድንጋጌ ይዘት ያሣያል፡፡ከዚህም የምንገዘነበዉ የስራ ዉሉ
ቆይታ በጊዜ ወይም እንደስራዉ ባህርይ በተዋዋዮች ሊወሰን የሚችል ስለመሆኑ ነዉ፡፡ይሁን
እንጂ የሰራተኛዉን የስራ ዋስትና እና የመደራደር አቅም ዉስንነት ከግምት በማስግባት የስራ
ዉሉን ቆይታ ጊዜ ወይም ባህርይ ለመወሰን የሚረዱ ሁኔታዎች በህግ ተደንግጎ
እናገኛለን፡፡በዚህ ረገድ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 9 እና 10 ድንጋጌዎች እንደሚያሣዩን
በመርህ ደረጃ የስራ ዉል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የሚገመት ሲሆን በተወሰኑ ሁኔታዎች
እና ምክንያቶች ብቻ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ ተብሎ የሥራ ዉል ሊደረግ የሚችል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሆኑን ነዉ፡፡ስለዚህም አሰሪዉ እና ሰራተኛዉ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ በሚል


መስማማት የሚችሉ ቢሆንም ጉዳዩ አከራካሪ ሆኖ ከቀረበ ዉሉ ከህጉ ጋር የሚጣጣም መሆን
አለመሆኑ ሊመመርመር ይገባል፡፡በዚህ ረገድ ይህ ሰበር ችሎት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ
ክርክር ዉሳኔ የሰጠባቸዉ ጉዳዮች ላይ እንዳመለካተዉ የሥራ ዉሉ ቆይታ ጊዜ አስመልከቶ
ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ በሚል መዋዋላቸዉ ብቻ ሳይሆን ዉሉ ከስራዉ ባህርይ ጋር
ተገናዘቦ መታየት እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡ሰበር መ/ቁ11924፣መ/ቁ/ 25765፣መ/ቁ.43160 እና
ሌሎች መሰል መዝገቦችን ማየት ይቻላል፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ በግራቀኙ መካከል የተደረገዉ ዉል ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ መሆኑን እና


በየጊዜዉ እየታደሰ መቆየቱንና ለመጨረሻ ጊዜም በ23/04/2010ዓ.ም ለአንድ ዓመት የተራዘመ
መሆኑን ዉሉ የተቋረጠዉ በ22/08/2011ዓ.ም ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት አረጋግጧል፡፡ፍርድ
ቤቱም ዉሉ ለተወሰነ ጊዜ ነዉ ቢባልም የስራዉ ባሕርይ ሲታይ የድርጅቱ ቋሚ ወይም
ቀጣይነት ያለዉ ስራ ነዉ በሚል ምክንያት ሰበር ችሎቱ በመ/ቁ/43160 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ
ድጋፍ በማድረግ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል በማለት ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ የሚል
ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ከክርክሩ እንደሚታየዉ ተጠሪ ለ11ዓመት በቋሚነት አገልግያለዉ
በሚል ምክንያት የሥራ ዉሉ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቆጠራል በማለት የሚከራከር
ቢሆንም ዉሉ በየጊዜዉ እየታደሰ የቆየ መሆኑ በተጠሪም አልተካደም፡፡በእርግጥ የስራ ዉል
ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ስራ የተደረገ ነዉ የሚያሠኘዉ የዉሉ ይዘት ብቻ ሳይሆን
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 10 ስር የተዘረዘሩት ምክንያቶች ወይም ሁኔታዎች መኖራቸዉ
መረጋገጥ እንዳለበት የህጉ አገላለጽ እና ይህ ሰበር ችሎት በመ/ቁ 43160 እና ሌሎች መሰል
መዝገቦች ላይ የሰጠዉ ዉሳኔ ያስገነዝባል፡፡ይሁንና የሰበር ችሎቱ ዉሳኔ በዚህ መዝገብ
ከቀረበዉ ክርክር አኳያ ተፈጻሚነት አለዉ ወይ የሚለዉ ከጉዳዩ ባህርይ አንጻር መመርመር
አለበት፡፡

ከመዝገቡ እንደሚታየዉ ተጠሪ የተቀጠረበት የሥራ መደብ የድርጅቱ ቋሚ ወይም ቀጣይነት


ያለዉ ስራ አይደለም የሚል ክርክር የለዉም፡፡የአመልካች ዋነኛ መከራከሪያ ነጥብ ተጠሪ
ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠረዉ እና ዉሉ እየታደሰ የቆየዉ የዉጭ ሀገር ዜጋ በመሆኑ በቋሚነት
ሊቀጠር አይችልም የሚል ነዉ፡፡ተጠሪ የዉጭ ሀገር ዜጋ መሆኑ አከራካሪ እስካልሆነ ድረስ
የሥራ ዉሉን ዓይነት በመወሰን ረገድ የሚኖረዉ ዉጤት ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ እና ሌሎች
አግባብነት ካላቸዉ ህጎች ጋር ተገናዝቦ መታየት አለበት፡፡

የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የዉጭ አገር ሠራተኞች የሚቀጠሩበትን ሁኔታ
የሚደነግግ ሲሆን በዚህም መሠረት የዉጭ አገር ዜጋ በማናቸዉም የስራ መስክ ተቀጥሮ
ለመስራት የሚችለዉ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ወይም ክልል ሲሆን የክልል
ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የሚሰጠዉን የስራ ፍቃድ ሲያገኝ እና የስራ ፍቃድ
የሚሰጠዉም በአንድ የስራ መስክ ለማገልገል እስከ ሦስት ዓመት ሲሆን በየዓመቱ መታደስ
ያለበት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 174 ላይ ከተመለከተዉ ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡በዚህ
ረገድ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ መሆኑን ልብ ይለዋል፡፡የአዋጁን
አንቀጽ 171/1/ሠ እና 176 መመልከት ይቻላል፡፡የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻልን አንዱ
ዓላማዉ ያደረገዉ (መግቢያዉን መመልከት ይቻላል) የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

769/2004 በአንቀጽ 37(2)፣ በዚህ አዋጅ የተተካዉ የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 280/94
አንቀጽ 36(2) እንዲሁም አሁን በስራ ላይ ያለዉ የእንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180/2012
አንቀጽ 22(4) የዉጭ ዜጎችን የሚቀጥር ባለሀብት ለኢትዮጵያዉያን አስፈላጊዉ ስልጠና
እንዲዘጋጅ እና እንዲሰጥ በማድረግ በተወሰነ ጊዜ ዉስጥ የዉጭ አገር ዜጋ ሠራተኞችን
እንዲተኩ ማድረግ እንዳለበት ይደነግጋሉ፡፡ ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበሩት ሁለቱ
የእንቨስትመንት አዋጆችም ሆነ አሁን በስራ ላይ ያለዉ የእንቨስትመንት አዋጅ ዓላማዎች
ናቸዉ ተብለዉ ከተዘረዘሩት ዉስጥ አንዱ ለኢትዮጵያዉያን ሰፊ እና ጥራት ያለዉ የስራ
ዕድል መፍጠር እና ለአገሪቱ ዕድገት የሚያስፈልገዉን የዕዉቀት፣ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ
ሽግግር ማሳለጥ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 280/94 አንቀጽ 4(6)፣ በአዋጅ ቁጥር 769/2004 እና
አዋጅ ቁጥር 1180/2012 አንቀጽ 5 ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ
ሁሉ መገንዘብ የሚቻለዉ በአገራችን የግል እንቨስትመንትን ማስፋፋት አስፈላጊ ከሆነባቸዉ
ምክንያቶች ዉስጥ አንዱ መንግስት ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በአገሪቱ ዉስጥ በማንኛዉም
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራት እና ለመተዳደሪያ የመስራት መብት ለመተግበር በተለይም
ሰፊ የሥራ እድል ለመፍጠር የሚያስችል ፖሊሲ መከተል እንዳለበት በኢፌዲሪ ህገ መንግስት
አንቀጽ 41 /1/ እና 4) በተጣለበት ግዴታ መሠረት ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለዜጎች
የስራ ዋስትና ማረጋገጥ መሆኑን ነዉ፡፡አንድ ዓላማ ያላቸዉ የተለያዩ ህጎች በሚኖርበት ጊዜ
በተለያዩ የህግ ክፍሎች በሚገኙ ድንጋጌዎች ተደጋጋፊ ሆነዉ የጋራ ዓላማ የሚያሳኩበትን የህግ
ትርጉም መሻት የህግ ባለሙያዎች ሊመርጡት የሚገባ የህግ አተረጓጓም ዘይቤን መከተል በህግ
አተረጓጎም ዕዉቅና ከተሰጣቸዉ መርሆዎች አንዱ ሲሆን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎትም
በሰ/መ/ቁጥር 21448 ላይ በሰጠዉ የህግ ትርጉም ለዚህ መርህ ዕዉቅና ሰጥቶታል፡፡

ከዉጭ አገር ዜጎች የቅጥር ሁኔታ ጋር በተያያዘ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 174 ላይ
የተመለከተዉ ድንጋጌ ዓላማዉ ምን እንደሆነ በግልጽ የሚያመላክት ድንጋጌ ባይኖርም ከላይ
ከተመለከቱት የእንቨስትመንት ህጎች ድንጋጌዎች እንዲሁም በኢፌዲሪ ህገ መንግስት መሠረት
መንግስት ለእራሱ ዜጎች የስራ ዕድል ለማመቻቸት ካለበት ግዴታ አንፃር ሲታይ በአዋጁ
አንቀጽ 174 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ አጠቃላይ ዓላማ የግል ድርጅቶች የዉጭ አገር
ዜጎችን የሚቀጥሩት ለስራ ዕድል ፈጠራ ዓላማ ሳይሆን ለድርጅቱ ስራ አስፈላጊነታቸዉ
ከታመነበት ብቻ መሆኑን ነዉ፡፡ከዚህም በተጨማሪ የዉጭ ሀገር ዜጋ በሀገር ዉስጥ ስራ
እንዲቀጠር የሚፈለገዉ በዘርፉ በቂ ባለሙያ በሀገር ዉስጥ ሳይኖር ወይም የእዉቀትና
ቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ ዓላማ በመያዝ ስለመሆኑ የኢንቨስትመንት አዋጅ እና አዋጁን
ተከትሎ የወጣዉ ደንብ የሚያስገነዝቡን ጉዳይ ነዉ፡፡ደንብ ቁጥር 474/2012 አንቀጽ
19/1/ይመለከታል፡፡በሌላ በኩል ከላይ እንደተገለጸዉ፣ የስራ ቅጥር ዉል ጊዜ ጋር በተያያዘ
በአዋጁ አንቀጽ 9 እና 10 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ የዜጎችን የስራ ዋስትና የማረጋገጥ ዓላማ
ያለዉ ነዉ፡፡የስራ ዋስትና ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ የሚታይ በመሆኑም በዚህ መብት
ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እድል ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል፡፡

በመሆኑም የስራ ቅጥሩ በሚመለከተዉ አካል ይሁንታ የሚፈጸም መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ


አንድ አሠሪ ከዉጭ አገር ሠራተኛ ጋር በሚያደርገዉ ዉል ዉሉ ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜ
በተመለከተ ተስማምተዉ የሚያስቀጡት የጊዜ ገደብ ህጋዊ ዉጤት ያለዉ በመሆኑ አሠሪዉ
የዉሉ ጊዜ ሲያበቃ ዉሉን አቋርጦ ሠራተኛዉን የማሰናበት መብት ይኖረዋል፡፡በዚህ ረገድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በተመሳሳይ ክርክር ይህ ሰበር ችሎት በመ/ቁ/194630 ላይ (ያልታተመ) የሰጠዉ ዉሳኔም


ተመሳሳይ አቋም የተወሰደበት መሆኑን ያሣያል፡፡

በመሆኑም በተያዘዉ ጉዳይ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገዉ የስራ ዉል በጊዜያዊ


ቅጥር ላይ የተመሠረተ ሆኖ በየጊዜዉ እየታደሰ ተጠሪ ለአስራ አንድ ዓመታት በአመልካች
ዘንድ ሲሰራ የቆየ መሆኑ ያላከራከረ ሲሆን፣ አመልካች ዉሉ ከተጠሪ ጋር እንዲቀጥል
ተስማምቶ ዉሉ ታድሶ በመካከላቸዉ ግንኙነቱ እንዲቀጥል ለማድረግ የስራ ፈቃድ እንዲታደስ
ያስፈልጋል፡፡ዉጪ ሀገር ዜጋ የስራ ፈቃድ የሚታደሰዉ በአሰሪዉ ጥያቄ መነሻ መሆኑን አዋጁ
ያሳያል፡፡በአዋጁ አንቀጽ 174(2-4) ላይ በተመለከተዉ ድንጋጌ መሠረት የስራ እና ማህበራዊ
ጉዳይ ሚኒስቴር (በክልል ሲሆን ቢሮ) የሚሰጠዉ የስራ ፍቃድ እና አድሳት ማንኛዉም የግል
ድርጅት ያለሚኒስቴሩ (ቢሮዉ) ዕዉቅና እና ይሁንታ የዉጭ አገር ዜጎችን እንዳይቀጥር
ለመከላከል ታስቦ የተቀረጸ ስለመሆኑ ከድንጋጌዉ መገንዘብ ይቻላል፡፡በመሆኑም አሠሪዉ
ድርጅት ከዉጭ አገር ዜጋ ጋር በጊዜያዊነት ያደረገዉ የስራ ቅጥር ዉል ግንኙነት እንዲቀጥል
የስራ ፈቃድ አስፈላጊ በመሆኑ ለሠራተኛዉ የስራ ፍቃድ በሚመለከተዉ አካል አለመታደሱም
አመልካች የቅጥር ዉሉ እንዲያራዝም የሚያስፈልግበት ምክንያት አለመኖሩን የሚያሣይ
ነዉ፡፡

በአጠቃላይ በየደረጃዉ ያሉት ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ከፍ ሲል በዝርዝር ከተመለከተዉ አንፃር


በማየት ስንበቱ ህጋዊ ነዉ ማለት ሲገባቸዉ በአዋጁ አንቀጽ 9 እና 10 ላይ የተመለከቱት
ድንጋጌዎች ለዉጭ አገር ዜጋ ሠራተኛም ጭምር ተፈፃሚ እንደሚሆኑ በመዉሰድ በግራ ቀኝ
መካከል ለተወሰነ ጊዜ የተደረገን የስራ ዉል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይገመታል በሚል
ሃሳብ አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበዉን ክርክር ዉድቅ በማድረግ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ
በማለት የሰጡት ዉሳኔ ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸዉን ድንጋጌዎቹ ዓይነተኛ ዓላማ እና ተጠሪ
የዉጭ ሀገር ዜጋ ከመሆኑ አኳያ በህጉ የተፈቀደለትን መሰረት በማድረግ ለተወሰነ ጊዜ ወይም
ስራ ለመስራት ግራቀኙ ያደረጉት ስምምነት ተገዥ ሊሆኑ ይገባል የሚለዉን የዉል አጠቃላይ
መርህ ያላገናዘበ በመሆኑ መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ስንበቱ ህጋዊ ነዉ ከተባለ ለተጠሪ የሚከፈል ክፍያ አለ ወይ የሚለዉንም መርመርናል፡፡በዚህ


ረገድ ከስር መዝገብ እንደሚታዉ ተጠሪ ስንበቱ ህገ ወጥ ነዉ በሚል ምክንያት
የስንብት፣ካሳ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ እና ክፍያ የዘገየበት የሚል የጠየቃቸዉ ክፍያዎች ሲሆኑ
በተጨማሪም ወደ ሀገር ቤት የሚመለስበት የትኬት ክፍያ ብር 431.053(አራት መቶ ሰላሳ
አንድ ከዜሮ ሃምሳ ሶስት ሳንቲም ዶላር) አመልካቹ እንድከፍል ጠይቋል፡፡የሥር ፍርድ ቤትም
ይህንኑ በመቀበል ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡ከላይ እንደተመለከተዉ በዚህ ሰበር ችሎት ዉሳኔ መሰረት
ስንበቱ ህጋዊ ነዉ ስለተባለ ህገ ወጥ ስንብት ነዉ ተብሎ በስር ፍርድ ቤት የተወሰኑት
ክፍያዎች ተገቢነት የላቸዉም፡፡ይሁንና ዉሉ ሲቋረጥ ተጠሪ ወደ ሀገሩ የሚመለስበት የትኬት
ወጪ በአመልካች እንደሚሸፈን የግራቀኙ ዉል አንቀጽ 9/d/ ላይ ተመላክቷል፡፡አመልካችም
ይህን በሚመለከት በመካድ ያቀረበዉ ክርክር የለም፡፡ ስለዚህም የሥራ ውሉ ሲቋረጥ
የመመለሻ ትኬት ወጪ በአመልካች የሚሸፈን ስለመሆኑ በስምምንቱ የተመለከተ በመሆኑ
ይህንኑ በተጠሪ የዳኝነት ጥያቄ መሰረት አመልካች ሊከፍል ይገባል ብለናል፡፡ስለሆነም ተከታዩ
ተወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉሳኔ

1ኛ/የሰበታ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 11361 በቀን 19/06/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት፣
የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 39465 በቀን 29/07/2012
ዓ.ም በዋለዉ ችሎት እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁ.333832 በቀን 06/04/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ህ/ቁ. 348(1) መሠረት
ተሻሽሏል፡፡

2ኛ/ አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገዉን የስራ ዉል ማቋረጡ በህጋዊ መንገድ በመሆኑ


ለተጠሪ ሊከፍል የሚገባዉ ክፍያ ወደ ሀገሩ የመመለሻ ትኬት ወጪ ብቻ ነዉ ተብሏል፡፡በዚሁ
መሰረት 431.053(አራት መቶ ሰላሳ አንድ ከዜሮ ሃምሳ ሶስት ሳንቲም ዶላር)በወቅቱ የባንክ
ምንዛሪ ተለዉጦ አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍል ብለናል፡፡በዚሁ ልክ የጠበቃ አበል 10%
ጨምሮ ይክፈል ብለናል፡፡የስር ፍርድ ቤትም ይህንኑ አዉቆ እንዲያስፈጽም የዉሳኔ ግልባጭ
ይተላለፍለት፡፡ይጻፍ

3ኛ/የሰበር አጣሪ ችሎት በቀን 04/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ እግድ
ተነስቷል፡፡

4ኛ/በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን


ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ8/8
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰ/መ/ቁ፡-200816

ዳኞች፡-እትመት አሰፋ
ፀሐይ መንክር
ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ልማት ፋና የደን ማሕበር

ተጠሪ፡- የአቶ አበበ ወልደየስ ሚስትና ወራሾች

1) ወ/ሮ ብዙዬ ደጀኔ


2) ወ/ሮ አረጋሽ አበበ
3) ወ/ሮ ፀሐይ አበበ
4) አቶ ተመስጌን አበበ
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ የተጠሪዎች አባት የተከሉትን ባሕር ዛፍ ከሕግ ውጪ ቆርጦ ወስዶል የተባለወን አመልካች የባህር
ዛፉን ግምት ለማስከፈል የቀረበ የንብረት ክርክርን የሚመለከት ሆኖ አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው ክርክር የአሁን ተጠሪዎች ከሣሽ አመልካች ደግሞ ተከሣሽ
ነበሩ፡፡

ተጠሪዎች ሰኔ 6ቀን 2008ዓ/ም በተፃፈ ክሳቸው በደሴ ከተማ ቧንቧ ውሐ ክፍለ ከተማ ሟች አባታቸው
በሊዝ የመሬት ስሪት ስርዓት ይዘው ለከተማ ግብርና ከሚጠቀሙበት 1035 ካሬ ሜትር ስፋት ካለው
ይዞታቸው አዋሣኝ የሆነው መሬት ላይ ወደ ደሴ ከተማ የሚገባውን ናዳ ለመከላከል በአካባቢው ማሕበረሰብ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተሣትፎ ባሕር ዛፍ እንዲተከልበት ከደሴ ከተማ አስተዳደር ከተወሰነ በኋላ ማህበረሰቡ ለመትክል ፈቃደኛ
ባመለመሆኑ የተጠሪዎች አውራሽ እንዲተክሉበት ተፈቅዶላቸው ብቻቸውን ተክለው ያሣደጉትንና በማህበራዊ
ፍርድ ቤትም የተረጋጠላቸውን ባሕር ዛፍ አመልካች ምንም መብት ሣይኖረው 500 አውራጅ፣ 800 ማገር
350 ቋሚ 3000 ጠርዝ በአጠቃለይ ግምቱ 94,000.00 የሚያወጣውን ባሕር ዛፍ ሰኔ 1ቀን 2001ዓ/ም
ቆርጦ የተጠቀመበት መሆኑን በመዘርዘር ግምቱን ከልዩ ልዩ ወጪ ጋር እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል፡፡

አመልካች መሬቱ የመንግስት በመሆኑ ተጠሪዎች ክስ የማቅረብ መብት የሌላቸው መሆኑን፤ በአመልካችና
በተጠሪ መካከል ያለው ግንኙነት ከውል ውጪ በመሆኑ ክስ የማቅረቢያ ጊዜው ማለፍንና ግምቱም የተጋነነ
መሆኑን፣ ጉዳዩ አስተዳደራዊ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ክሱን በቀጥታ የማዬት ስልጣን የሌለው መሆኑን
በመዘርዘር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና አመልካች ማሕበር በመሆኑ ከከተማ አስተዳሩ 34,000 ካሬ
ሜትር መሬት ለከተማ ግብርናና ለደን ልማት ተሰጥቶት ከ1994ዓ/ም ጀምሮ ባሕር ዛፍ አልምቶ
እየተጠቀመ የሚገኝ እንጅ የተጠሪን ባሕር ዛፍ ቆርጦ አለመውሰዱን በከተማው እና በተጠሪ ይዞታ ላይ
ይደርስ የነበረውን ናዳ እየተከላከለ ያለው ባሕር ዛፍ አመልካች የተከለው መሆኑን ለተጠሪም ባሕር ዛፍ
እንዲተክሉ ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆኑን በመዘርዘር የተጠሪ ክስ ውድቅ እንዲሆንለት ተከራክሯል፡፡

የስር ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን ውድቅ ካደረገ በኋላ የተጠሪዎች አውራሽ በመንግሰት
ቦታ ላይ ባሕር ዛፍ እንዲያለሙ ተፈቅዶላቸው አልምተው ነበር ወይስ አልነበረም? አልምተው ነበር ከተባለስ
አመልካች ቆጥሮ ወስዷል ወይስ አልወሰደም? የሚሉትን ነጥቦች በጭብጥነት ይዞ የግራቀኙ ያቀረቧቸውን
ማስረጃዎች እና ጉዳዩ የሚመለከተው የክፍለ ከተማው የመንግስት አካል ስለጉዳዩ አጣርቶ እንዲቀርብ
በሰጠው ትዕዛዝ የቀረበለትን ማስረጃ መርምሮ የተጠሪዎች አውራሽ ባህር ዛፍ ተክየበታለሁ የሚሉት መሬት
የመንግስት መሆኑንና እንዲተክሉበት ፈቃድ የተሰጣቸው ስለመሆኑ አላረጋጡም ሲል ክሱን ውድቅ
አድርጓል፡፡

በዚህ ውሣኔ ቅር የተሰኙት ተጠሪ የይግባኝ አቤቱታቸው ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ይግባኝ ሰሚ
ችሎቱም ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ባህር ዛፍ የተጠሪዎች አውራሽ መትከላቸው በተረጋጠበት ባሕር ዛፉን
እንዲተክሉ ፈቃድ አልተሰጣቸውም በሚል ያቀረቡት ክስ ውድቅ የመደረጉን ተገቢነት በጭብጥነት ይዞ የግራ
ቀኙን ክርክርና ተጨማሪ ማስረጃ እንዲቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ የቀረበለትን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ
የከተማው ምክር ቤት ለተጠሪዎች አባት ፈቅዶላቸው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ባሕር ዛፍ መትከላቸውን
አመልካችም የራሱን ባሕር ዛፍ ሲቆርጥ የተጠሪዎች አባት የተከሉትን ባሕር ዛፍ ደርቦ መቁረጡ
አረጋግጫለሁ በሚል የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሽሮ በባለሙያ የተገመተውን 27,977.60 ብር አመልካች
ለተጠሪ እንዲከፍል ወስኗል፡፡ ይህ ውሣኔም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መሰረታዊ የሕግ
ስህተት የተፈፀመበት አይደለም ተብሎ ፀንቷል፡፡

ይህ ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚለው አመልካች ጥር 4ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ
የሰበር አቤቱታው በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ፣ የተጠሪዎች አውራሽ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከሚመለከተው የመንግስት አካል ተፈቅዶላቸው ባህር ዛፍ መትከላቸውና ባሕር ዛፉን አመልካች


የቆረጠባቸው ስለመሆኑ ሣይረጋገጥ የባህር ዛፍ ግምትና ወጪና ኪሣራ እንዲከፍል መወሰኑ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት ነው ተበሎ እንዲታረም ጠይቋል፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ ከመሰረታዊ የማስረጃ ምዘና
መርህ አንፃር እንዲመረመር ተጠሪዎችም የመልስ ክርክር እንዲያቀርቡ በታዘዙት መሰረት የመልስ
ክርክራቸውን አቅርበዋል፡፡ተጠሪዎች በበኩላቸው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነው ውሣኔ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም የሚሉበትን ምክንያት በመዘርዘር ውሣኔው እንዲፀናላቸው
ተከራክረዋል፡፡ አመልካችም የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር መልስ መልስ አቅርበው የግራ ቀኙ ክርክር
ተጠናቋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው
የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ተመርምሯል፡፡ እንደተመረመረው ለክርክሩ መነሻ የሆነው የተጠሪዎች
አውራሽ ጉዳዩ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ባገኙት ፈቃድ መሰረት በመንግስት ይዞታ ላይ ተክለው
ተንከባክበው ያሣደጉትን ባሕር ዛፍ አዋሣኝ የሆነው ተጠሪ የራሱን ባሕር ዛፍ ሲቆርጥ የእነሱን ጨምሮ
የቆረጠባቸው መሆኑን በመዘርዘር ግምቱን እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ተጠሪ በመንግስት ፈቃድ
ባሕር ዛፍ አለመትከላቸውን እሱም ቆርጦ አለመውሰዱን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሯል፡፡

የተካደ ፍሬ ነገርን በማስረጃ የማጣራት የዳኝነት ስልጣን የተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች በመንግስት ይዞታ
ላይ ባሕር ዛፍ እንዲተክል የፈቀደለት የክፍለ ከተማው ሕዝብ ለመትከል ፈቃደኛ ሣይሆን ሲቀር የተጠሪዎች
አውራሽ እንዲተክሉበት የተፈቀደላቸውና ተክለው ሲንከባከቡ የነበረ ስለመሆኑ፣ ካደገ በኋላም ለመቁረጥ
እንዲፈቀድላቸው ጉዳዩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ጥያቄ አቅርበው ለጊዜው ለመቁረጥ ያልደረሰ
መሆኑን የተገለፀላቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ ተረጋግጧል፡፡ አመልካችም
የተጠሪዎች አባት የተከሉትን ባሕር ዛፍ ጨምሮ በመቁረጥ የወሰደ ስለመሆኑ በምስክሮች ተረጋግጧል፡፡
አመልካችም ከተሰጠው ይዞታ በላይ መያዙ በቦታው ከአመልካች በፊት የተጠሪዎች አባት ባህር ዛፍ ተክለው
ሲንከባከቡ እንደነበር ተረጋግጧል፡፡ ይህን ማስረጃ የመዘነው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባህር ዛፉን
በባለሙያ እንዲገመት ተደርጎ የባህር ዛፉን ግምትና ወጪና ኪሣራ እንዲከፍል ወስኗል፡፡

እንዲሚታወቀው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3) እንደሚደነግገው የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት


ሰበር ሰሚ ችሎት የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የመጨረሻ ውሣኔ በተሰጣባቸው ጉዳዮች የተፈፀመ መሰረታዊ
የሕግ ስህተትን ማረም መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡ በዚህ መሰረት በያዝነው ጉዳይ እንዲጣራ
የተፈለገው የማስረጃ ምዘና መርህን ሚመለከት ጉዳይ በመሆኑ በስር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ
የቀረቡት ማስረጃዎች ካረጋገጡት ፍሬ ነገር አንፃር በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ
ስህተት ያልተገኘ በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሣኔ

1) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት 0104428 በሆነው
ጥቅምት 24ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-30550 ታሕሳስ 9ቀን 2013ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2) ይህ የሰበር ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የዬራሣቸውን ይቻሉ፡፡

ትዕዛዝ
1. ይህ ችሎት የካቲት 5ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡
መዝገቡ እልባት ያገኘ በመሆኑ ተዘግቷል፣

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ገጽ 1
የመ.ቁ.200835
መስከረም 28/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ቤቶች ልማት ጽ/ቤት-ዐ/ህግ

ይታያል ደምሴ ቀረቡ

ተጠሪዎች፡ 1ኛ. አሳሳሽኝ ሃብተ ማርያም ጠበቃ አቶ በላይ ኃ/ስላሴ

2ኛ. መላከ ምህረት ተክለወልድ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል

ፍርድ

ጉዳዩ ለዚህ ችሎት የቀረበው ለክርክር ምክንያት የሆኑት ቤቶች ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ
በመንግስት እጅ የቆዩ ለመሆኑ ተረጋግጦ ባለበት ለተጠሪዎች እንዲመለሱ በስር ፍርድ ቤቶች
የተወሰነበትን አግባብነት በዚሁ ችሎት በመ/ቁ/119591 ላይ ከተሰጠው ውሳኔ አኳያ መርምሮ
ለመወሰን ነው፡፡

የክርክሩ ሥረ ነገር አመጣጥ እንዲህ ነው፡፡ የአሁን ተጠሪዎች በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች እና በሌሎች አራት ግለሰቦች ላይ ባቀረቡት ክስ በካርታ ቁጥር
16/30549 ተመዝግበው የሚታወቁት የቤት ቁጥር 677፣ 678፣ 679 እና 680 የሆኑት
ከአውራሻቸው ግራዝማች ሀብተማርያም ካብትይመር በውርስ የተላፈላቸው ሲሆኑ ቤቶቹን
የአሁን አመልካች ይዞ እያከራየ በመሆኑ ለቆ እንዲያስረክባቸው በተለያየ ጊዜ ሲጠይቁ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቆይተው ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ የቤት ቁር 678 እና 679 ያስረከባቸው ቢሆንም ቀሪዎቹን
የቤት ቁጥ 677 እና 680 በስር ፍርድ ቤት ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተጠቀሱት ግለሰቦች እያከራየ ያለ
መሆኑን በመግልፅ በፍርድ ኃይል ተገዶ ተከራዮቹን አስወጥቶ እንዲያስረክባቸው ጠይቀዋል፡፡

በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት አመልካች ቀርቦ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ
መቃወሚያ እና አማራጫ የስረ ነገር ክርክር አቅርቧል፡፡ የመቃወሚያው ይዘትም ክስ
የቀረበባቸው ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 47/67 ከተጠሪዎች አውራሽ እጅ በትርፍነት ተወርሰው
መንግስት እጅ የገቡ በመሆኑ በቤቶቹ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም
የላቸውም፤ ቤቶቹ በአዋጅ አልተወረሱም የሚባል ከሆኑም ጉዳዩን አይቶ የመወሰን የስረ ነገር
ስልጣኑ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ለመስማት የስረ ነገር
ስልጣን የለውም የሚል ነው፡፡ በአማራጭ የስረ ነገር ክርክር ደግሞ ቤቶቹ በመንግስት
ተወርሰው ከ40 ዓመት በላይ መንግስት እያከራየ ይዞ የቆየ በመሆኑ ሊመለሱ አይገባም በማለት
ተከራክሯል፡፡

ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም በመቃወሚያው ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ጉዳዩን
የማየት የስረ ነገር ሥልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን ዘግቷል፡፡ ይኸው ጉዳይ እስከዚህ ሰበር
ሰሚ ችሎት ድረስ ክርክር ተደርጎበት በሰ/መ/ቁ/119591 ላይ ግንቦት 21/2009 ዓ.ም በዋለው
ችሎት “መጣራት አለባቸው” የተባሉት ነጥቦች ተለይተው ፍሬ ነገሮቹ በተገቢው ማስረጃ
ከተጣሩ በኋላ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን
ያለው መሆን አለመሆኑ ላይ እንዲወስን ተመልሶለታል፡፡ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ
በድጋሚ ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን የዘጋ ቢሆንም ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይኑን በመሻር በክሱ ስረ ነገር ክርክር ላይ ግራ ቀኙን
አከራክሮ እንዲወስን መልሶለታል፡፡

በዚህ መልኩ ጉዳዩ የተመለሰለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን በመስማት
እንዲሁም ለጉዳዩ አወሳሰን ይረዳኛል ያለውን ማጣራት ካደረገ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ለክርክር
ምክንያት የሆኑት ቤቶች ከሌሎች ቤቶች ጋር በ1968 ዓ.ም በመንግስት ተወረሰው የነበረ
ቢሆንም በ1972 ዓ.ም የህብረተሰባዊ ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት የከተማ ልማት
እና ቤቶች ሚኒስቴር የግራዝማች ሀ/ማርያም ወራሾች ለሆኑት በአሁን ተጠሪዎች ስም ክስ
የቀረበባቸውን ቤቶች ጨምሮ በካርታ ቁጥር 16/30549 የተመዘገበ የባለሃብትነት ማረጋገጫ
ምስክር ወረቀት የተሰጠ መሆኑን፤ የአሁን አመልካች እነዚህን ቤቶች ለአሁን ተጠሪዎች
እንዲያስረክብ በ1984 ዓ.ም ውስጥ ከተለያዩ የመንግስት አስተዳደር አካላት በደብዳቤ ሲጠየቅ
የነበረ እና በቤቶቹ ላይም የቤትና የቦታ ግብር በተጠሪዎች ስም ሲከፈል የነበረ ስለመሆኑ
ማረጋገጡን ጠቅሶ ለተጠሪዎች የተሰጠው ካርታ ባልተሻረበት አመልካች ቤቱን አልለቅም
የሚልበት ምክንያት የለም በማለት ቤቶቹን ለቆ ለተጠሪዎች እንዲያስረክብ ወስኗል፡፡
አመልካች ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ቢሆንም
ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ዘግቷል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን በመቃወም ነው፡፡ አመልካች ጥር 04/2013 ዓ.ም
በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት
ጠቅሶ በዚህ ችሎት እንዲታረምለት ጠይቋል፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ከላይ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በዚህ ፍርድ መግቢያ ላይ የተጠቀሰውን ነጥብ ለማጣራት ሲባል ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር


እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም
የግራ ቀኙን ክርክር ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ነጥብ አኳያ አግባብነት ካለው ህግ
ጋር በማገናዘብ መርምሯል፡፡

እንግዲህ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ የስር ፍርድ ቤቶች
የደረሱበት ድምዳሜ በዚሁ ችሎት ቀደም ሲል በመ/ቁ/119591 ላይ ከተሰጠው ውሳኔ አንፃር
ይመርምር የሚል ነው፡፡ የተጠቀሰው የሰበር መዝገበ ቁጥር ግራ ቀኙ በክስ መቃወሚያው
ጉዳይ ላይ ክርክር አድርገው ውሳኔ የተሰጠበት ነው፡፡ የውሳኔው ይዘትም በአሁን አመልካች
በኩል የፍርድ ቤቱን ዳኝነት ስልጣን አስምልክቶ ያቀረበው መቃወሚያ በማስረጃ ተጣርቶ
ፍርድ ቤቱ ስልጣን ያለው መሆኑን ያለመሆኑ ላይ እንዲወስን የሚል ነው፡፡ በዚሁ አግባብ
ፍርድ ቤቱ አጣርቶ የዳኝነት ስልጣን የለኝም ያለ ቢሆንም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተሽሮ
በፍሬ ነገር ላይ ክርክር ተሰምቶ እንዲወሰን ተደርጓል፡፡

በክሱ ስረ ነገር ክርክር ሂደት በማስረጃ የተረጋገጠው ደግሞ ክስ የቀረበባቸው ቤቶች ቀደም
ሲል ለአሁን ተጠሪዎች ከተመለሱት ቤቶች ጋር ተወርሰው የነበረ ቢሆንም በ1972 ዓም
በቤቶቹ ላይ ሥልጣን ባለው አካል በተጠሪዎች ስም የባለሀብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
የተሰጠ መሆኑን፤ ከዚህ በኋላም ቢሆን አመልካች ቤቱቹን ለተጠሪዎች እንዲያስረክብ ከተለያዩ
የመንግስት አስተዳደር አካላት በፅሁፍ ሲጠየቅ የነበረ መሆኑን ነው፡፡ እነዚህ ፍሬ ነገሮች
የሚያሳዩት ተጠሪዎች ክስ በቀረበባቸው ቤቶች ላይ አግባብ ባለው አስተዳደር አካል በተሰጠ
የባለሀብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተረጋገጠ መብት ያላቸው መሆኑን እና ክሱም
በፍርድ ኃይል ይህንኑ መብት ለማስከበር የቀረበ የባለሃብትነት ክርክር መሆኑን ነው፡፡

እንግዲህ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል የባለሃብትነት


ምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው የዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት እንደሆነ
የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195(1) ይደነግጋል፡፡ በእርግጥ በዚህ መልኩ
የተሰጠ ምስክር ወረቀት በራሱ ፍፁም ሳይሆን ሊስተባበል የሚችል ማስረጃ ነው፡፡ ሊስተባበል
የሚችለውም የባለሀብትነት ምስክር ወረቀቱ የተሰጠው ከደንብ ውጭ በሆነ አሰራር ወይም
ማስረጃውን ለመስጠት ሥልጣን በሌለው አስተዳደር ክፍል መሆኑን፤ ወይም ማስረጃው
የተሰጠው በማይረጋ ፅሁፍ መሰረት ወይም ለከሳሹ መቃወሚያ ሊሆን በማይችል ፅሁፍ
መሰረት መሆኑን፤ ወይም ማስረጃው የተሰጠበት ንብረት የተገኘው የምስክር ወረቀቱ ከተሰጠ
በኋላ ስለመሆኑ በማስረዳት እንደሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1196 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የዚህ
ድንጋጌ አጠቃላይ መንፈስ የሚያስገነዝበው በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1195(1) የባለሃብትነት ማስረጃን
በመያዝ ብቻ የተወሰደውን የህግ ግምት ማስተባባል የሚቻለው ማስረጃው የተገኘው ከህግ
አግባብ ውጭ በሆነ ሁኔታ መሆኑን በማስረዳት እንደሆነ ነው፡፡

ከዚህ አኳያ አመልካች ቤቶቹ ተወርሰው ለረጅም ጊዜ በመንግስት እጅ የቆዩ ናቸው የሚል
መከራከሪያ ከማቅረቡ ውጭ ከተወረሱ በኋላ በቤቶቹ ላይ በአሁን ተጠሪዎች ስም የተሰጠው
የባለሃብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ ሁኔታ የተሰጠ መሆኑን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በማስረዳት ያስተባበለው ነገር የለም፡፡ ይህ ባልተረጋገጠብት የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት


ድምዳሜ የቀረበውን ክስ ጭብጥ እና በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ያደረገ ነው
ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም፡፡ በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ
ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/257712 ላይ ታህሳስ 13/2013 ዓ.ም በዋለው


ችሎት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1)
መሰረት ፀንቷል፡፡

ትዕዛዝ

1. የዚህን ሰበር ችሎት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡


2. በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠ እግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል፡፡ ይፃፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-200871

ቀን፡-27/01/2014ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ


ፀሐይ መንክር
ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ አባይነህ አለባቸው ፡- ጠበቃ የሽበር መልኬ ቀርበዋል

ተጠሪ፡- አቶ ሙሉጌታ አዳነ -ተወካይ ላንቺስል አዳነ ቀርበዋል

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ጎንደር ዞን ከፍኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው ቤትና ይዞታን
ለማስለቀቅ የቀረበውን ክርክር ተጠሪ ከሳሽ አመልካች 1ኛ ተከሣሽ በዚህ ክርክር ያልተጠሩት እማሆይ
ታከለች ረታ 2ኛ ተከሣሽ እነ ወ/ሮ ነገሱ አለባቸው 4 ሰዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የከተማ ቤትና ይዞታን በሚመለከት የቀረበ የመፋለም ክርክር የሚመለከት ሲሆን ተጠሪ ሰኔ
12ቀን2006ዓ/ም በተፃፈ ክሳቸው በወረታ ከተማ ቀበሌ 02 የቤት ቁጥር 042 የሆነውንና አዋሣኙ
የተጠቀሰውን ቤት የተጠሪ እናትና አባት ቤት ቢሆንም ወላጁቹ ከሞቱ በኋላ ለአመልካቹ በአደራ ተሰጥቶት
እየተጠቀመበት መሆኑን እንዲያስረክበው ቢጠይቀውም ሁለተኛ ተከሣሽ የነበረችዋ እማሆይ ታከለች ረታ
መሬት ነው በሚል ምክንያት ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆኑን በመዘርዘር ቤቱን እንዲለቅለት እንዲወሰንለት
ጠይቋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች ቀርቦ ቤቱ የተጠሪ እናትና አባት ሐብት ስላልሆነ ክስ ማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም
የለውም ሲል የመጀመሪያ መቃወሚያና ተጠሪው ማስረጃ አለማቅረቡን የተጠሪ አባት የደም ችግር
ስለነበረበት ለደህንነቱ ሲባል ከሚኖርበት ቤት የተሻለ መሆኑ ታምኖበትና ከእናታቸው ከእማሆይ ታከለች
ረታ ጋር ተማክረው እንዲኖርበት በመደረጉ እንጅ የቤቱ ባለሃብት አለመሆኑን፣ የመብራትና ውሃ ደረሰኝ
የቤት ባለሃብትነትን የማያረጋግጥ መሆኑን በመዘርዘር ቤቱ የአመልካች አባትና የእማሆይ ታከለች ረታ
ሃብት ነው ሲል ተከራክሯል፡፡ የእማሆይ ስላልቀረቡ መልስ የመስጠት መብታቸው የታለፈ ቢሆንም በኋላ
መሞታቸው ስለተረጋጠ ተተኪዎች ቀርበው መልስ ሰጥተዋል፡፡

ክርክሩ በዚህ ደረጃ ላይ እያለ ጣልቃ ገቦች ቀርበው ቤቱ የሁለተኛ ተከሣሽና የባለቤታቸው (የጣልቃ ገቦች
አያት) መሆኑን እነርሱ ተሣታፊ ሣይሆኑ በወንድ አያታቸውን ድርሻ ላይ የሚደረገው ክርክር መብታቸውን
እንደሚጎዳ በመዘርዘር መብታቸው እንዲከበርላቸው በመጠየቅ አመልካች ካቀረበው ክርክር ጋር
ተመሣሣይነት ያለው ክርክር አቅርበዋል፡፡ ተጠሪ በበኩሉ ጣልቃ ገቦች የሚያቀርቡት አቤቱታ በይርጋ የታገደ
ነው በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል መብትና ጥቅም የላቸውም እንዲሁም ክርክራቸው አመልካች
ከሚያቀርበው ክርክር ጋር ተመሣሣይ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግለት ተከራክሯል፡፡ እማሆይ ታከለች ረታ
በመሞታቸው አመልካችና ጣልቃ ገብ በክርክሩ ተተኪ ሆነው መልስ መስጠት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀው
ተፈቅዶላቸው መልስ ሰጥተዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክሩን ውድቅ ካደረገ በኋላ ግራ ቀኙ ያቀረቧቸው ማስረጃዎች
ያረጋገጡትን ፍሬ ነገር እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የተለያዩ የከተማው የመንግስት አካላት አጣርተው
መግልጫ እንዲያቀርቡለት ትዕዛዝ ሰጥቶ የቀረበለትን መግለጫ አከራካሪው ቤትና ይዞታ የተጠሪ አባትና
እናት ሃብት ነው ወይስ የአመልካች አባት የአቶ አለባቸው አድገህና የእማሆይ ታከለች ረታ የሚለውን
ጭብጥ ይዞ መርምሯል፡፡ በዚህም መሰረት የአመልካች አባት ከ1953 ዓ/ም አከራካሪውን ይዞታ ገዝተው ቤት
ለመስራት በ1963ዓ/ም ፈቀድ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም በ1976ዓ/ም በማዘጋጃ ቤቱ በተደረገ ምሪት
ይዞታውን የተጠሪው አባት የተመራው መሆኑ፣ የአመልካች አባት ከ1976ዓ/ም ጀምሮ ግብር ከፍለውበት
የማያውቁ መሆኑን፣ ለአጎራባች ባለይዞታዎች በተሰጣቸው ካርታ ላይ የተጠሪ አባት መመዝገቡ መረጋገጡን
የአመልካች አባት ከሞቱ በኋላ ሀሰተኛ የፍርድ ቤት ውሣኔ ተዘጋጅቶ ቤቱ በአመልካች እናት በሟች
እማሆይ ታከለች ረታ ስም መመዝገቡንና የተጠሪ አባት ማሕደር ከማዘጋጃ ቤት እንዲጠፋ መደረጉን
እንዲሁም የአመልካች ባለቤት ወረታ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የምትሰራ ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል
አመልካች ይዞታውን ለቆ ለተጠሪ እንዲያስረክብ ወስኗል፡፡ ይህ ውሣኔ በየደረጃው በሚገኙት የክልሉ ፍርድ
ቤቶች ስለፀና አመልካች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲታረምለት ይህን የሰበር
አቤቱታ አቅርቧል፡፡

አመልካች ታሕሣስ 14ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታው ለክርክሩ መንስዔ የሆነው ይዞታ በአመልካች
አባት የተገዛና ቤት የሰራበት ስለመሆኑ ሟች ከሞቱም በኋላ በእናታቸው ስም የተመዘገበ ስለመሆኑ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በማስረጃ ተረጋግጦ ሣለ በአጎራባች ይዞታ ላይና ውሃና መብራት ደረሰኝ ላይ የተጠሪ አባት መመዝገቡ
የተመዘገበበት ሁኔታ ግምት ውስጥ ሣይገባ እንደ ባለሃብት መቆጠሩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተበሎ
እንዲታረምለት ጠይቋል፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በስር ፍርድ ቤት አመልካች አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ እንዲያስረክብ
የተወሰነበት አግባብነት ከማስረጃ ምዘና መርህ አንፃር ተጣርቶ እንዲወሰን ታዞ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን
በፅኁፍ ተለዋውጠዋል፡፡

ተጠሪ በበኩሉ ሚያዚያ 6ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ መልሱ ማስረጃ የመመዘን ስልጣኑ የፌዴራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አለመሆኑንና በጥቅሉ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የማስረጃ ምዘና
ስህተት የተፈፀመበት አይደለም የሚልበትን ምክንያት በመዘርዘር የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ
እንዲደረግለት ተከራክሯል፡፡ አመልካችም የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር መልስ መልስ አቅርቦ ክርክሩ
ተጠናቋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት በሰጠውና በየደረጃው በሚገኙት
የክልሉ ፍርድ ቤቶች በፀናው ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ ማስረጃ ምዘና ስህተት መኖር አለመኖሩ ላይ
መልስ ለመስጠት የግራቀኑኝ ክርክር ለጉዳዩ አግባብት ካላቸው የህግ ድንጋዎች ጋር በማገናዘበብ
እንደሚከተለው ተመርምሯል፡፡

እንደተመረመረው ተጠሪ ባቀረበው ክስ በወረታ ከተማ የሚገኘውና ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ከአባቱ
በውርስ የተላፈለት ቢሆንም ተጠሪው የሁለተኛ ተከሳሽ እማሆይ ታከለች ረታ ነው በሚል የያዘበት መሆኑን
በመዘርዘር እንዲለቅለት ጠይቋል፡፡ አመልካች በበኩሉ ተጠሪ አባቱን ተክቶ የውርስ ድርሻውን ከሚካፈል
በስተቀር ቤቱ የተጠሪ አባት ሳይሆን የተጠሪ አያት የአመልካች አባትና የእማሆይ ታከለች ረታ በመሆኑ ክሱ
ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሯል፡፡ ጣልቃ ገቦችም ቀርበው ከአመልካች ጋር ተመሣሣይነት ያለው ክርክር
አቅርበዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት አከራካሪው ቤትና ይዞታ ባለሃብት ማን ነው የሚለውን ጭብጥ ይዞ በግራቀኙንና ራሱ


በሰጠው ትዕዛዝ ተጣርቶ የቀረበለትን ማስረጃ መዝኗል፡፡ በዚህም መሰረት የቀረቡት የግራ ቀኙ ምስክሮች
በጥቅሉ እንደሚያቀርቡት ክርክር ያስረዱ ቢሆንም የወረታ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አጣርቶ ባቀረበው ከመልስ
በተጨማሪ ገለልተኛ የሆነው የዞኑ ስራና ከተማ ልማት መምሪያ ስጉዳዩ አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ
ተሰጥቶ ከአጎራባች ይዞታዎች ሰነድ እና የአካባቢውን ሕዝብ ጠይቆ ባቀረበው መልስ ይዞታውን የአመልካች
አባት የተጠሪ አያት በ1953ዓ/ም ገዝተው በ1963ዓ/ም ቤት ለመገንባት ፈቃድ የጠየቁበት ቢሆንም
በ1976ዓ/ም ይዞታው ወደ ሽንሻኖ ገብቶ ለተጠሪ አባት ተመርቶ ቤት የተሰራበትና ወደ ባህር ዳር
እስከሚሔድ ድረስም የተጠሪ አባት በቤቱ ውስጥ ይኖር እንደነበር ማረጋገጡን በሌላ በኩል የአመልካች አባት
ከሞቱ በኋላ ሐሰተኛ የፍርድ ቤት ሰነድ(ውሣኔ) ተዘጋጅቶ ግልፅ ባልሆነ መንገድ ይዞታው ወደ አመልካች
እናት የተዛወረ መሆኑን በአንፃሩ የተጠሪ አባት ሰነድ ከማዘጋጃ ቤቱ እንዲጠፋ የተደረገ ስለመሆኑ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስለተረጋጠ አመልካች ይዞታውን እንዲለቅ ተወስኗል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
ጉዳዩን በድጋሚ አጣርቶና ተጨማሪ ማስረጃ አስቀርቦ ከመረመረ በኋላ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፅንቷል፡፡

ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት መደምደሚያና የሰጡት ፍርድ ተገቢነት በማስረጃ ከተረጋገጠው ፍሬ
ነገር አንፃር ሲመዘን መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርሆዎችን መሰረት ያላደረግ ነው የሚያስብል ምክንያት
ስላላገኘን ተከታዩን ውሣኔ ወስነናል፡፡

ውሣኔ

1) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር
97966 ጥቅምት 17ቀን 2013ዓ/ም በጉዳዩ ላይ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም ሲል የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1)
መሰረት ፀንቷል፡፡
2) ይህ ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዝግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


ሄ/መ የማይነበብ የአምስት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁጥር 200919

ጥቅምት 01 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ አቶ በቀለ ድሪብሳ- ጠበቃ ዘነበ ጥላሁን ጋር ቀረቡ

ተጠሪ ፡ አቶ የምክር በሪሁን- ጠበቃ ግሩም አየለ ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን የአፈጻጸም ክርክሩ በተጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
አመልካች የፍርድ ባለእዳ ተጠሪ ደግሞ የፍርድ ባለመብት በመሆን ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩን አመጣጥ ስንመለከት ተጠሪ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 15170
አመልካችን ጨምሮ በ5 ሰዎች ላይ በቀድሞ ወረዳ 17 ቀበሌ 21 የሚገኝ የቤት ቁጥር 552 እንዲያስረክቡኝ
እና ስመሀብት እንዲያዛውሩልኝ ይወሰንልኝ የሚል ክስ አቅርበው መስከረም 26 ቀን 1999 ዓ.ም.
አመልካችን ጨምሮ 4 ተከሳሾች ቤቱን ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ተወስኗል፡፡ ተጠሪም ይህንን ውሳኔ መሰረት
በማድረግ በአፈጻጸም መዝገብ ቁጥር 109064 የአፈጻጸም አቤቱታ አቅርበው ቤቱን ከተረከቡ በኋላ አመልካች
እና 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት ወ/ሮ ደስታ ከፈኔ ተጠሪ ቤቱን እንዲረከቡ በተሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ
አቅርበው ውሳኔውን አሽረዋል፡፡ የውሳኔውን መሻር ተከትሎ አመልካች እና ባለቤታቸው ተጠሪ በአፈጻጸም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተረከቡትን ቤት መልሰው እንዲያስረክቧቸው አቤቱታ አቅርበው ተጠሪ ቤቱን ለአመልካች እና ለባለቤታቸው


ወ/ሮ ደስታ ከፈኔ አስረክበው አፈጻጸሙ በመጠናቀቁ የአፈጻጸም መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ተጠሪ
አጠቃላይ ይዞታዬ 391 ካ.ሜ. የነበረ ሲሆን ከዚህ ላይ ለአመልካች እና ባለቤታቸው ቤቱን ከ200 ካ.ሜ.
ይዞታ ጋር ሳስረክብ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ይቀረኛል፡፡ ስለዚህ በቀሪው 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ
መሬት ልማት ማኔጅመንት የይዞታ ምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ እንዲሰጠኝ ይታዘዝልኝ በማለት በተዘጋው
የአፈጻጸም መዝገብ ላይ አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም በተጠሪ አቤቱታ መሰረት የምስክር ወረቀት

ተዘጋጅቶ ለተጠሪ እንዲሰጥ አዟል፡፡ አመልካች በዚህ ትእዛዝ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ
ቤት አቅርበው ቅሬታው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

አመልካች በ06/05/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረቡት በስር ፍርድ ቤት በተሰጠው የአፈጻጸም
ትእዛዝ ተፈጽሟል ያሉትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ለማሳረም ሲሆን የቅሬታው ይዘት በ191 ካ.ሜ. ይዞታ
ላይ ለተጠሪ ካርታ እንዲሰጥ ፍርድ አልተሰጠም፡፡ የአፈጻጸም ትእዛዙ ሲሰጥም አመልካች አስተያየት
እንድሰጥ አልተደረገም፡፡ ይዞታው ለ15 ዓመት ግብር የገበርኩበት ስለሆነ ለተጠሪ ካርታ ተሰርቶ ይሰጥ
መባሉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ የተሰጠው የአፈጻጸም ትእዛዝ ፍርዱን የተከተለ
ነው አይደለም? የሚለውን ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተጠሪም በ01/07/2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ የአፈጻጸም ትእዛዙ የተሰጠው በፌደራል መጀመሪያ
ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 15170 መስከረም 26 ቀን 1999 ዓ.ም. በተሰጠ ፍርድ መሰረት ነው፡፡
በዚህ ውሳኔ ቤት እንድረከብ የተወሰነ ቢሆንም አመልካች እና ወ/ሮ ደስታ ከፈኔ በውሳኔው ላይ የይግባኝ
ቅሬታ አቅርበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 25551 ቤት እንድረከብ የተሰጠውን ውሳኔ
ክፍል በመሻሩ ከአመልካች እና ከባለቤታቸው በአፈጻጸም የተረከብኩትን ቤት ከ200 ካ.ሜ. ቦታ ጋር መልሼ
አስረክቤአለሁ፡፡ አመልካች በውሳኔው መሰረት ሳይረከቡ የቀረ ነገር የለም፡፡ በተጨማሪም የይዞታ የምስክር
ወረቀት ተሰርቶ እንዲሰጠኝ የታዘዘው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ ፌደራል ሰበር
ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 02371፣ 04076፣ 04952፣ 34520 እንዲሁም በፌደራል ፍርድ ቤት መዝገብ
ቁጥር 09161 እና 38575 የተሰጡ ውሳኔዎች ታይተው በመሆኑ በተሰጠው የአፈጻጸም ትእዛዝ የተፈጸመ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካችም በ16/07/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታቸውን አጠናክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ
አንጻር ለቅሬታ መነሻ ከሆነው ትእዛዝ እና ከተገቢው የህግ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ለቅሬታ መነሻ የሆነው የአፈጻጸም ትእዛዝ ለተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የሚመለከተው
የአስተዳደር አካል የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ሰርቶ ይስጥ የሚል ነው፡፡ አመልካች ይህንን ትእዛዝ
የሚቃወሙት ተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰራላቸው የተሰጠ ውሳኔ የለም
በሚል ነው፡፡ ተጠሪ በበኩላቸው በመዝገብ ቁጥር 15170 እና በሌሎች መዝገቦች ላይ በተሰጠ ውሳኔ መሰረት
የአፈጻጸም ትእዛዙ የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ ትእዛዙ ተገቢ መሆኑን ተከራክረዋል፡፡ በመሆኑም የዚህን
ችሎት ምላሽ የሚያሻው ለተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ተሰርቶ እንዲሰጣቸው
የተሰጠ ፍርድ አለ ወይስ የለም? የሚለው ይሆናል፡፡

በፍርድ አፈጻጸም ጊዜ ፍርድ ቤቶች ሊያስፈጽሙ የሚገባው በተሰጠው ፍርድ መሰረት መሆን እንዳለበት
የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡ በነዚህ ድንጋጌዎች አግባብ ከተዘረጋው ስርአት
ውጪ የአፈጻጸም ችሎት የፍርዱን ይዘት በሚቀይር መልኩ ወይም ፍርድ ያልተሰጠበትን ነገር ማስፈፈጸም
አይችልም፡፡ የፍርድ አፈጻጸም ስርአት አንድ ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በራሱ አማካኝነት በህጉ
የተዘረጋውን የአፈጻጸም ስርአት በመከተል ወደውጤት የሚቀይርበት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አፈጻጸሙ ፍርዱን
የተከተለ መሆኑን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፡፡

በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታን በተመለከተ ፍርድ ተሰጥቶበታል የሚሉት አንድም በመዝገብ
ቁጥር 15170 በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመስከረም 26 ቀን 1999 ዓ.ም. የተሰጠውን ፍርድ
በመጥቀስ ሲሆን እኛም የዚህን ፍርድ ይዘት ተመልክተናል፡፡ የፍርዱ ይዘት ተጠሪ አመልካችን ጨምሮ
በአራት ሰዎች እና በአዲስ አበባ መስተዳድር የስራ ከተማ ልማት ቢሮ ላይ በቀድሞ ወረዳ 17 ቀበሌ 21
በካርታ ቁጥር 17910 የተመዘገበውን የቤት ቁጥር 552 የሆነውን ቤት ለመረከብ እና ስመ ሀብት
እንዲዛወርላቸው ክስ አቅርበው አራቱ ተከሳሾች የተጠቀሰውን ቤት ለተጠሪ እንዲያስረክቡ የተወሰነ መሆኑን
ያሳያል፡፡ በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች እና 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት የአመልካች ባለቤት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ
ቤት በመዝገብ ቁጥር 25551 የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው ተጠሪ ቤት እንዲረከቡ የተሰጠው ውሳኔ መሻሩን
የፍርዱ ግልባጭ የሚያመለክት ሲሆን በተጠሪም የታመነ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ማለት ተጠሪ በፌደራል
መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 15170 በግልጽ ቤት ይረከቡ በሚል የተፈረደላቸው ፍርድ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 25551 በሰጠው ውሳኔ የተሻረ በመሆኑ በመዝገብ ቁጥር
15170 በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በተሰጠ ውሳኔ መሰረት ለተጠሪ ሊፈጸምላቸው የሚችል ነገር
የለም ማለት ነው፡፡ የስር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ትእዛዙን ሲሰጥ በምክንያትነት
የጠቀሰው የተጠሪ አጠቃላይ ይዞታ 391 ካ.ሜ. ሲሆን ከዚህ ይዞታ ላይ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 349 መሰረት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

200 ካ.ሜ. ቦታ ተቀንሶ አመልካች እና ባለቤታቸው ሲረከቡ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ለተጠሪ ይቀራል በሚል
ነው፡፡ ነገር ግን ተጠሪ ክስ ያቀረቡበት የመዝገብ ቁጥር 15170 ላይ ተጠሪ ቤት እንዲረከቡ የተሰጠው ውሳኔ
በተሻረበት ሁኔታ ለተጠሪ ምን ያክል ይዞታ እንደሚቀር እና በሚቀረው ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ
እንዲሰራ በአፈጻጸም ችሎት ሊታዘዝ የሚችልበት የህግ አግባብ የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ተጠሪ ከፍርድ ቤት
የአፈጻጸም ትእዛዝ ውጪ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው መጠየቅ
አይችሉም ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ ተጠሪ ይዞታው ላይ በሚመለከተው የመንግስት አካል የይዞታ
ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጣቸው ከሚጠይቁ እና ይህ አካል በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ካላቸው በተገቢው
የህግ አግባብ አለኝ የሚሉትን መብት ክስ በማቅረብ ከሚያስከብሩ በስተቀር ተጠሪ በጠቀሱት በፌደራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 15170 ላይ የተሰጠው ውሳኔ የተሻረ በመሆኑ ለተጠሪ
የይዞታ የምስክር ወረቀት እንዲሰጣቸው በማድረግ የሚፈጸም ፍርድ የለም፡፡

ሌላው ተጠሪ ከአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እስከ ፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ
ቁጥር 02371፣ 04076፣ 04952፣ 34520 እንዲሁም በፌደራል ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 09161 እና

38575 የተሰጡ ውሳኔዎች ታይተው ነው የአፈጻጸም ትእዛዝ የተሰጠው በማለት የሚያነሱትን ክርክር
ስንመለከት በነዚህ በውሳኔዎች ላይም ቢሆን አመልካች የቤት ቁጥር 552 ን በተመለከተ ሁከት ይወገድልኝ
ክስ አቅርበው ውድቅ የተደረገበት እንጂ ተጠሪ የሚገባቸው ይዞታ ምንያክል እንደሆነ ተረጋግጦ ፍርድ
ያረፈበት አይደለም፡፡

ሲጠቃለል የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ
ተሰርቶ እንዲሰጥ በማለት የአፈጻጸም ትእዛዝ የሰጠው ተጠሪ መብት አግኝቻለሁ የሚሉበት ቤት እንዲረከቡ
የተሰጠው ውሳኔ በተሻረበት እና ተጠሪ 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ መብት ያላቸው መሆኑ ተረጋግጦ የተሰጠ
ፍርድ በሌለበት በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህ/ህጉ የተዘረጋውን የአፈጻጸም ስርአት የሚቃረን እና ከአፈጻጸም ችሎት
ስልጣን ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡ ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም
ይህንን ስህተት ሳያርም መቅረቱ መሰረታዊ ህግ ስህተት በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1ኛ. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር109006 በ10/03/2012 ዓ.ም. እና የፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 247114 በ22/04/2013 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል፡፡

2ኛ. ተጠሪ ቤት እንዲረከቡ የተሰጠው ውሳኔ በተሻረበት እና 191 ካ.ሜ. ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ
ተሰርቶ እንዲሰጣቸው የተሰጠ ፍርድ በሌለበት የአፈጻጸም ትእዛዝ መሰጠቱ ተገቢ አይደለም ብለናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

3ኛ. ይህ ውሳኔ ተጠሪ ለሚመለከተው የመንግስት አካል የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ጥያቄ እንዳያቀርቡ
የሚያግድ አይደለም፡፡

4ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገ ክርክር ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-200929

ቀን፤-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ሕዳሴ ቴሌኮም አ/ማ

ተጠሪ ፡- 1. አቶ ገዛኸኝ ለማ

2. አቶ ሕዝቂያስ ታፈሰ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ
እንደተረዳነው አመልካች የስር ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ተከሳሾች ሆነው ተከራክረዋል፡፡ አመልካች ያቀረበው ክስ
1ኛ ተጠሪ የአመልካች የሽያጭ ሠራተኛ ሆነው ሲሰሩ በውስጥ ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ብር 204,250.00
በጉድለት ስለተገኘ ገንዘቡን እንዲከፍሉ፤ 2ኛ ተጠሪም የ1ኛ ተጠሪ ዋስና ተያዥ በመሆናቸው እስከ
100,000.00 በአንድነትና ነጠላ ኃላፊነት እንዲከፍሉ የሚል ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ የሠጡት መልስ ገቢና
ወጪውን ያልለየ፣ ከመቼ እስከመቼ የተደረገ ኦዲት ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም፡፡ በውጭ ኦዲተር ኦዲት
ይደረግልኝ ብለዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ጉድለት የለም፣ ዋስ የሆንኩት 1ኛ ተጠሪ የመስመር ሠራተኛ
እያለ ነው፤ ልጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 58351 ግራቀኙን አከራክሮና በተፈቀደለት የሂሳብ
ባለሙያ ድጋሜ ኦዲቱ እንዲሰራ በማድረግ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ 1ኛ ተጠሪ እንዲከፍሉና 2ኛ ተጠሪ እስከ
ብር 100,000.00 ድረስ በአንድነት እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡ ተጠሪዎች ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ያቀረቡትን ይግባኝ ተቀብሎ በድጋሜ ኦዲቱ እንዲሰራ ካዘዘ በኋላ 1ኛ ተጠሪ ብር 204,250.00 ገንዘብ
ማጉደላቸውን የቀረበው ማስረጃ ያሳያል፡፡ ነገር ግን ይህንኑ ገንዘብ 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት GSM Mobile
Prepaid Card certificate ገቢ ስለመሆኑ ማስረጃ ያቀረቡ ቢሆንም በትክክል ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ
የሚረጋገጠው ቅጽ 7 (ውስጣዊ ደረሰኝ) ያላቀረቡ መሆኑን በመግለጽ ኦዲት የሰራው ተቋም ገልጿል፡፡ 1ኛ
ተጠሪ ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ ቅጽ 7 ደረሰኝ ከአመልካች ተቋም ማግኘታቸውን በመግለጽ በተጨማሪ
ማስረጃነት እንዲያያዝላቸው የጠየቁ ሲሆን አመልካች አዲስ ማስረጃ ሊያያዝ አይገባም፤ ይያያዝ ቢባል
እንኳን የሽያጭ ገንዘቡ ወደባንክ ገቢ ከሆነው ስሊፕ ጋር ያልቀረበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱን ለማሳሳት የቀረበ
ነው ሲል አስተያየቱን አቅርቧል፡፡ የቀረበው ማስረጃ የአመልካች ማሕተም ያረፈበት፣ የአመልካች ሠነድ
አለመሆኑ ያልተካደ በመሆኑና ማስረጃው ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚያግዝ በመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
345 መሠረት ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ በማያያዝ በጉድለት ተገኘ የተባለው ብር 204,250.00 ለአመልካች በቅጽ
7 (የውስጥ ደረሰኝ) ገቢ የተደረገ ስለመሆኑ ስለተረጋገጠ 1ኛ ተጠሪ ያጎደሉት ገንዘብ የለም በማለት የሥር
ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ክሱን ውድቅ አድርጓል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
የአመልካችን የይግባኝ አቤቱታ ባለመቀበል ሠርዟል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የገንዘብ ጉድለቱ
በኦዲት ምርመራ ተረጋግጧል፡፡ ከሥነ-ሥዓት ውጭ አዲስ ማስረጃ መቀበሉ ተገቢ አይደለም፡፡ ማስረጃው
የገቢ ሠነድ ማስረጃ አይደለም፡፡ የውስጥ ደረሰኝ አይደለም፤ ቢሆን እንኳን ከባንክ ስሊፕ ጋር ያልቀረበ
ስለሆነ ውጤት ሊኖረው አይችልም የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ ማስረጃው
የተያያዘበት አግባብነትና ማስረጃው ገንዘብ ገቢ ማድረጋቸውን የሚያሳይ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር
ተጠሪዎች መልስ እንዲያቀርብ በማዘዙ ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ የቅጽ 7 ሰነድ ከሥራ ተሰናብቼ ስለነበር
ማግኘት ባለመቻሌ ያልቀረበ ሲሆን በኋላ ግን 1ኛ ተጠሪ የአመልካች ኃላፊን አስፈቅዶ ሠነዶችን ፈትሾ
ያገኘው ነው፡፡ ሠነዱ የገቢ ደረሰኝ ሲሆን የገቢ ደረሰኝ አለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ያልተካደ ነው፡፡
ማስረጃው ተመዝኖ የተሰጠው ውሳኔ ሊፀና ይገባል ብለዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ይግበኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የክርክር አመራር ተገቢ
መሆን አለመሆኑን እና የማስረጃ ምዘና መርህን መሠረት አድርጎ መወሰን አለመወሰኑን? በጭብጥነት
በመያዝ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካች ያቀረበው ክስ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች የሽያጭ ሠራተኛ ሆነው ሲሰሩ በውስጥ
ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ብር 204,250.00 በጉድለት ስለተገኘ ገንዘቡን እንዲከፍሉ፤ 2ኛ ተጠሪም የ1ኛ
ተጠሪ ዋስና ተያዥ በመሆናቸው እስከ 100,000.00 በአንድነትና ነጠላ ኃላፊነት እንዲከፍሉ የሚል ሲሆን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪዎች በበኩላቸው ገንዘቡ አልጎደለም፤ የኦዲት አሰራሩ ተገቢነት የለውም፣ ድጋሜ ኦዲት ይደረግልን
ለክሱ ልንጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የፍትሐ ብሔር ክርክር ጉዳዩን
ለማስረዳት በሕግ ተቀባይነት ባለውና ለጉዳዩ አግባብነት ባለው ማስረጃ በማረጋገጥ ማን የተሻለ እንዳስረዳ
የመወሰን ኃላፊነት አለበት፡፡ ክርክርን ለማስረዳት ማስረጃ የሚቀርብበት ሥርዓት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 223
መሠረት የሰው ማስረጃ ዝርዝር እና በዕጁ የሚገኝ የፅሁፍ ማስረጃን የሚቀርብበት ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.
145 መሰረት ደግሞ በተከራካሪ ዕጅ የሌሉ ወይም ለማቅረብ ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቁ ማስረጃዎች በፍርድ
ቤት እገዛ የሚቀርቡበት ነው፡፡ የሠነድ ማስረጃ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 137 መሠረት ክሱ እስከሚሰማበት ጊዜ
ድረስ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን በእነዚህ ሂደቶች ማስረጃው ያልቀረበው ተከራካሪው ባለማወቁ ወይም አዲስ
የተገኘ ማስረጃ ከሆነ ደግሞ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 256 አግባብ ማስረጃው እንዲቀርብ ለፍርድ ቤት ጥያቄ
ሊቀርብ ይችላል፡፡ በዚህ አግባብ ማስረጃ እንዲቀርብ የሚጠየቀው ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ሊሆን ይገባል፡፡
ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በይግባኝ ደረጃ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 327(3) እና 345 መሠረት በልዩ ሁኔታ ማስረጃ
የሚስተናገድበት ሥርዓትም ተዘርግቷል፡፡

ተጠሪ ክሱን ለማስረዳት የኦዲት ውጤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤት የማስረጃውን ትክክለኛነት ማጣራት
ከፈለገ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 በተሠጠው ስልጣንና ኃላፊነት ድጋሜ ኦዲት እንዲሰራ በማዘዝ ክርክሩን
መወሰን ይችላል፡፡ በዚህም አግባብ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የኦዲት ሥራው በድጋሜ እንዲከናወን አዟል፡፡
የቀረበው የኦዲት ውጤት 1ኛ ተጠሪ የገንዘብ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ያሳያል፡፡ ነገር ግን ይህንኑ ገንዘብ
1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት GSM Mobile Prepaid Card certificate ገቢ ስለመሆኑ ማስረጃ ያቀረቡ ቢሆንም
በትክክል ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ የሚረጋገጠው ቅጽ 7 (ውስጣዊ ደረሰኝ) ያላቀረቡ መሆኑን ኦዲት የሰራው
ተቋም መግለጹ ተከትሎ 1ኛ ተጠሪ ገንዘቡ ገቢ ስለመሆኑ ቅጽ 7 ደረሰኝ ከአመልካች ተቋም ማግኘታቸውን
በመጥቀስ በተጨማሪ ማስረጃነት እንዲያያዝላቸው የጠየቁ ሲሆን ፍርድ ቤቱ አመልካች ክርክር
እንዲያቀርብበት ካደረገ በኋላ የቀረበው ማስረጃ የአመልካች ማሕተም ያረፈበት፣ የአመልካች ሠነድ
አለመሆኑ ያልተካደ በመሆኑና ማስረጃው ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚያግዝ በመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
345 መሠረት ተቀብሎ በማያያዝ በጉድለት ተገኘ የተባለው ብር 204,250.00 ለአመልካች በቅጽ 7 (የውስጥ
ደረሰኝ) ገቢ የተደረገ ስለመሆኑ ስለተረጋገጠ 1ኛ ተጠሪ ያጎደሉት ገንዘብ የለም ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡
የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 345(1)(ለ) እና 327(3) ላይ ይግባኝ ሰሚ ፍር ቤት ትክክለኛ ፍትሕ ለመስጠት የሚረዳ
ተጨማሪ ማስረጃ ማያያዝ የሚችል ስለመሆኑ የተመለከተ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤትም በዚህ ድንጋጌ
ማዕቀፍ ማስረጃውን በመቀበሉ የፈጸመው የሥነ-ሥርዓት ሕግ ጥሰት የለም ብለናል፡፡

ለቀረበው ክስ የግራቀኙን ማስረጃ ፍርድ ቤቱ ከተቀበለ በኋላ በፍትሐ ብሔር ክርክር የምንከተለው
የማስረዳት ደረጃ ከሁለቱ ወገን የተሻለ ያስረዳው ማን ነው (preponderance of evidence) የሚለውን
በመመርመር እና የማስረጃ ተገቢነት፣ የማስረጃው ተቀባይነትን ደንቦችን መከተል እና ለማስረጃው
የሚሰጠውን ክብደት (weight of evidence) በመለየት የመወሰን ኃላፊነት ማስረጃ ለመስማትና ለመመዘን
ኃላፊነት ያለባቸው ፍርድ ቤቶች ዋና ተግባር ነው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 80(3) በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ
ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሠበትን የፍሬ ነገር ድምዳሜ ላይ እንዲመለከት ሥልጣን አልተሠጠውም፡፡ የሥር
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራቀኙ ያቀረቡትን ማስረጃ መዝኖ 1ኛ ተጠሪ ገንዘብ ስለማጉደላቸው አልተረጋገጠም
በሚል የደረሰበት የፍሬ ነገር ድምዳሜና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የጸናው ውሳኔ
ላይ የተፈጸመ የማስረጃ ምዘና መርሕ ስህተት ያልተገኘበት ስለሆነ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት
የለም ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 193074 ጥቅምት 16 ቀን 2013
ዓ/ም እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 14397 ጥቅምት 14 ቀን 2012 የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰ/መ/ቁ፡-200948

ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ መ/ር ሲራጅ መሀመድ

ተጠሪ፡ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል::

ፍርድ

ጉዳዩ ከውል ውጭ ኃላፊነትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ


ደረጃ ፍ/ቤት ነዉ፡፡የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑን አመልካች ጨምሮ ሌሎች 4 ሰዎች
ላይ ባቀረበው ክስ ንብረትነቱ ከተከሳሾች የአንዳቸው ወይም የሁሉም የሆነ የሠ/ቁ.1-06754
አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ በ25/04/2006ዓ.ም በኮልፈ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ አከባቢ
ተጠሪ የመድን ሽፋን የሰጠውን የሰ/ቁ.4-01850ኢ.ት የሆነውን ተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት
አድርሷል፡፡ተጠሪ ከደንበኛው ጋር ባለው ውል ስምምነት ለደረሰው ጉዳት ብር 19,250.00
ለደንበኛው ከፍሏል፣ስለሆነም ተከሳሾች ገንዘቡን እንዲተኩ በማለት ዳኝነት
ጠይቋል፡፡አመልካች በበኩሉ አደጋ አድራሹን ተሽከርካሪ በ2005 ዓ.ም ለአቶ ጉግሳ ይልማ
በመሸጥ መኪናውን ያስረከብኩት ስለሆነ ደረሰ ስለተባለው ጉዳትም የማውቀው ነገር የለም፣በእኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ላይ የቀረበው ክስ አለአግባብ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡ሌሎች ተከሳሾች መልስ


አላቀረቡም ቀርበውም አልተከራከሩም ተብሎ የታለፈ መሆኑን መዝገቡ ያሣያል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የባለቤት ስም ዝውውር ባልተከናወነበት ጊዜ


ሁሉ በባለቤትነት የሚታወቀው ሰው ንብረቱ በስሙ በመገኘቱ ብቻ ኃላፊ የሚሆን ስለመሆኑ
ሰበር ችሎቱ መ/ቁ.24643 አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቷል፡፡የቀረበው ማስረጃ ጉዳት ያደረሰው
መኪና ለመሸጥ በሂደት ላይ ያለና አመልካች ለአቶ ጉግሳ ይልማ ለተባለው ሰው በማስተላለፍ
ሂደት ላይ ያለ መሆኑን እንጂ ስመ ሀብቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ገዥ መተላለፉን
አያስረዳም፣ስለዚህ ለደረሰው ጉዳት አመልካችን ጨምሮ የስር ተከሳሾች ኃላፊ ናቸዉ በማለት
የተጠየቀውን ብር 19,250.00 በአንድነትና በነጣላ ለተጠሪ እንዲከፍል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ መኪናው ጉዳት
ባደረሰበት ጊዜ አመልካችን ጨምሮ በስር ተከሳሾች ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በመሆኑ በፍ/ህ/ቁ
2081 መሰረት ባለሞተር ተሽከርካሪው ባለቤት የጉዳት ካሳ የመክፈል ኃላፊነት አለበት በማለት
የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ አጽንቷል፡፡ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ ቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ፡፡

የአመልካች አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሲታይ፤ አደጋው የደረሰው በ25/04/2006 ዓ.ም ሲሆን ክሱ
የቀረበዉ ታህሳስ 22/2011 ዓ.ም ሲሆን ክሱ የቀረበው ጉዳቱ ከደረሰ ከ5 ዓመት ከ2 ወር በኋላ
በመሆኑ ክሱ በይርጋ መታገድ ሲገባ መታለፉ የህግ ስህተት ነው፡፡ጉዳት አደረሰ የተባለው
ተሽከርካሪ ለአቶ ጉግሳ ይልማ በቀን 21/04/2006 ዓ.ም በተፈፀመ የሽያጭ ውል ያስተላለፍኩ
መሆኑን እና የተሸከርካሪዉ ባለቤት አቶ ጉግሳ ይልማ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ቀርቦ እያለ
የሥር ፍ/ቤት ሽያጩ በሚመለከት አካል አልተመዘገበም፣አልፀደቀም በማለት ውድቅ ማድረጉ
አግባብ አይደለም፣የሽያጭ ውሉ ባልተካደበት የጉዳት ካሳ እንዲከፍል መወሰኑ የህግ ስህተት
ነዉ፤ተሽከርካሪውን የገዛዉ ሰዉ ወደ ክርክሩ እንዲገባ ጠይቄ የስር ፍ/ቤት አለመቀበሉ አግባብ
አይደለም፣ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀበት በመሆኑ እንዲሻር
በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ አመልካች መኪናውን መቼ እንደሸጠ


መኪናውን የያዘው ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ የስር ፍ/ቤት አጣርተው የይርጋን ጉዳይ ባለየበት
ይህንን አልፎ ስመ ሀብቱ ሙሉ በሙሉ አልዞረም በማለት አመልካችን ተጠያቂ ያደረገበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አግባብነት ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት
ታዟል፡፡

ተጠሪ ባቀረበው መልስ ጉዳት ያደረሰው መኪና በአደጋው ቀን ስመ ሀብቱ በአመልካች ስም


እንደነበር ከመንገድ ትራንፖርት ባለስልጣን ለስር ፍርድ ቤት የቀረበው ማስረጃ ያረጋግጣል፣
ምዝገባው ያስፈለገው ዋናው ዓላማ አንዱ እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት በቀላሉ ለመለየት ሲሆን
በውል ተሸጠ የሚለው ከአደጋ ቀን በኋላ መሆኑን ደጋፊ ሰነዶች ያረጋግጣሉ፣ስለዚህ ስመ ሀብቱ
ሳይተላለፍ በአመልካች ስም ተመዝግቦ ስላለ በሰበር መ/ቁ.24643 ከተሰጠው ውሳኔ አንፃር
አመልካች በፍ/ህ/ቁ 2081(1) መሰረት ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት አለበት ተብሎ መወሰኑ
ስህተት የለበትም፡፡ይርጋን በተመለከተ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2143(2) መሰረት ጥፋቱ የመነጨው
ከወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ ሲሆን ሾፈሩ በንብረት ላይ ላደረሰው ጥፋት በደንብ መተላለፍ
ወንጀል የተቀጣ በመሆኑ ይርጋው 2 ዓመት ሳይሆን 5 ዓመት ይሆናል፡፡ተጠሪ ክስ ያቀረበው
ከ5 ዓመት በፊት መሆኑ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጦ የአመልካች መቃወሚያ በብይን ውድቅ
በመደረጉ የተፈፀመ ስህተት የለም፡፡አመልካች የመንደር ውል ምክንያት በማድረግ ገዢ ጣልቃ
እንዲገባ መጠየቁ አግባብ ስላልሆነ መታለፉ ትክክል ነው፡፡ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የሚነቀፍ
አይደለም በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ
አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ በተጠሪ
ደንበኛ ተሸከርካሪ ላይ ጉዳት አደርሷል የተባለዉ የሰሌዳ ቁጥር የሠ/ቁ.1-06754 የሆነዉ
ተሸርካሪ ጉዳት በደረሰበት ጊዜ በአመልካች ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት
ጉዳዩ ከሚመለከተዉ አካል አጣርቶ ያረጋገጠዉ ፍሬነገር ጉዳይ ነዉ፡፡ባለሞተር ተሸከርካሪ
ግዙፍነት ያለዉ ልዩ ተንቀሳቃሽ ንብረት በመሆኑ ባለቤትነት የሚረጋገጠዉ በምዝገባ ስርዓት
ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 681/20002 አንቀጽ 4 ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡መብቱን
የማስተላለፍ ዉልም ይህንኑ ስርዓት ተከትሎ መፈጸም ያለበት ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀጽ 6/3/
እና ከፍ/ብ ህግ አንቀጽ 1186/2/ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡የምዝገባ ስርዓት
አስፈላጊነቱ በአንድ በኩል ባለሞተር ተሸከርካሪ ካለዉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አኳያ
ለባለንብረቱ ጥበቃ ለማድረግ ሲሆን በሌላም በኩል የሶስተኛ ወገን መብትና ጥቅም ከማስከበር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አንጻር ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንደሆነ ይታመናል፡፡የተሸከርካሪ መለያ፣መመርመሪያና


መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 681/2002 ዓላማ እና ይዘትም ይህንኑ የሚያስገነዘብ ነዉ፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ የአመልካች መከራከሪያ ነጥብ በሁለት ተከፍሎ ሊታይ የሚችል


ነዉ፡፡አንደኛዉ ክሱ በይርጋ ሊታገድ ይገባል የሚል ሲሆን ሌላኛዉ ተሸከርካሪዉ ጉዳት ባደረሰ
ጊዜ ለሶስተኛ ወገን በሽያጭ ተልለፏል በሚል ምክንያት በሃለፊነት ሊጠየቅ አይገባም የሚለዉ
ነዉ፡፡በእኛም በኩል በቅድሚያ መታየት የሚገበዉ የይርጋ መቃወሚያ የታለፈበት ምክንያት
ተገቢ መሆን አለመሆኑ ላይ ነዉ፡፡

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 244 እና 245 እንደተደነገገዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የቀረበ


እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ወደ ስረ ነገር ክርክር ከመግባቱ በፊት እልባት ሊሰጠዉ ይገባል፡፡
በተያዘዉ ጉዳይ ክሱ በሁለት ዓመት ይርጋ ጊዜ ይታገዳል በማለት አመልካች ያቀረበዉን
መቃወሚያ አስመልክቶ ሥር ፍርድ ቤት በብይን ዉድቅ ማድረጉን የስር መዝገብ አስቀርበን
ተመልክተናል፡፡ከመዝገቡ እንደሚታዉ ፍርድ ቤቱ በ30/08/2011ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ
ብይን ይዘት ሲታይ አደጋዉ የደረሰዉ በ25/04/2006ዓ.ም መሆኑን እና ክሱ የቀረበዉ
በ22/04/2011ዓ.ም ሆኖ በዚህ መካከል ያለዉ ጊዜ 2ዓመት ያለፈዉ ቢሆንም ይርጋዉ ጊዜ
መታሰብ ያለበት በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2143/1/ ላይ የተመለከተዉ ሁለት ዓመት ጊዜ ሳይሆን
በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ሁለት መሰረት በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ በወንጀል
ህጉ አንቀጽ 572 እና 217/1/ሠ አግባብ መሆኑን በማመላከት ክሱ እስከ አምስት ሊቀርብ
እንደሚችል እና የአምስት ዓመት ጊዜዉ ያላለፈበት መሆኑን በማረጋገጥ የአመልካችን ይርጋ
ክርክር ዉድቅ ማድረጉን ያሣያል፡፡

በእኛም በኩል ከክርክሩ እንደተገነዘብነዉ ጉዳት አድራሹ ተሽከርካሪ አሽከርካሪ በቸልተኛነት


የተጠሪ ደንበኛ ተሽከርካሪ በመግጨት በንብረት ላይ ጉዳት በማድረሱ የትራፊክ በደንብ
መተላለፍ የተቀጣ መሆኑ አላከራከረም፡፡ለፍትሓብሔር ክስ የይርጋዉ ጊዜ የሚታሰበዉ
በፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 2143/1/ የተመለከተዉ የሁለት ዓመት ጊዜ ገደብ ሳይሆን በፍ/ብ/ህጉ
አንቀጽ 2143/2/ መሰረት ድርጊቱ በወንጀል የሚያሥጠይቅ መሆኑን ተክተሎ በወንጀል ሕጉ
የተመለከተዉ ይርጋ ጊዜ ተፈጻሚነት እንዲኖረዉ መደረጉ አግባብነት ያለዉ ነዉ፡፡በተመሳሳይ
ጉዳይ ይህ ይህ ሰበር ችሎት በመ/ቁ/58920 ላይ የሰጠዉ ዉሳኔም ይህንኑ የምያስገነዘብ
ነዉ፡፡ነገር ግን የወንጀል ይርጋ እንደወንጀሉ ክብደት የሚለያይ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ
ተፈጻሚነት ያለዉ የትኛዉ ነዉ የሚለዉ ከድርጊቱ አንጻር መታየት አለበት፡፡ከዚህ አኳያ
ጉዳቱ የደረሰዉ ተሽከርካሪ ከተሽከርካሪ ግጭት በመሆኑ ተፈጻሚነት ያለዉን የይርጋ ጊዜ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለመለየት የሚቻለዉ በድርጊቱ ጥፋተኛ የሆነዉ ሰዉ የሚቀጣዉ በትራፊክ ደንብ መተላለፍ


ብቻ ነዉ ወይስ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 572 ወይም ሌላ ከፍ ያለቅጣት በሚደነግገዉ የወንጀል
ህጉ አንቀጽ ነዉ የሚለዉ ምላሽ ማግኘት አለበት፡፡

በዚህ ረገድ ይህ በሰር ችሎት በመ/ቁ/194880 ላይ የወንጀል ህግ ቁጥር 572 ተፈጻሚነት ወሰን
አስመልከቶ ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡ከዉሳኔዉ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572
አነጋገር መሰረት አንድ አሽከርካሪ ወይም እግረኛ በቸልተኛነት የትራፊክ ደንብ በመጣስ በፈጸመዉ
ድርጊት ሌላዉ አሽከርካሪ ወይም እግረኛ የሌላዉን ሰዉ ሕይወት፣አካል፣ጤና ወይም ንብረት ለአደጋ
ሲያጋልጥ (ሲጎዳ) የመጀመሪያዉ አሽከርካሪ ወይም እግረኛ የትራፊክ ደንብን በመጣስ ሌላዉን ሰዉ
ለአደጋ በማጋለጡ የሚጠየቅበት ድንጋጌ እንጂ በተያዘዉ ጉዳይ የተከሰተዉን አንደኛዉ አሽከርካሪ
የትራፊክ ደንብ በቸልተኛነት በመጣሱ ምክንያት በሁለት ተሽከርካሪዎች መካከል ግጭት በመፈጠሩ
በሁለተኛዉ ተሽከርካሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዳት ጉዳት አድራሹን አሽከርካሪ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ
የተደነገገ ድንጋጌ አይደለም፡፡

በወንጀል ሕጋችን በአንቀጽ 677(1/ለ እና 2) ስር በተደነገገዉ መሰረት ማንም ሰዉ በመንግስት


ወይም በሕዝብ ንብረት ላይ በቸልተኛነት በድንጋጌዎቹ በተገለጸዉ አነጋገር ጉዳት በማድረሱ ሊጠየቅ
ከሚችል በስተቀር በንብረት መብቶች ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች ስድስተኛ መጽሐፍ ርእስ አንድ
ስር በተደነገጉ ድንጋጌዎች መሰረት በመንግስት ወይም በሕዝብ ወይም በግለሰብ ንብረት ላይ
በቸልተኛነት ጉዳት ማድረስ እንደ መደበኛ ወንጀል ተቆጥሮ የሚያስጠይቅ አይደለም፡፡ እንዲሁም
ምንም እንኳን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 559/2 መሰረት በቸልተኛነት የትራፊክ ደንብ በመጣስ በሰዉ
አካል ላይ ጉዳት ማድረስ በወንጀል የሚያስጠይቅ ቢሆንም ከላይ እንደተመለከተዉ በተለይም አንድ
አሽከርካሪ በቸልተኛነት የትራፊክ ደንብ በመጣስ በሚያሽከረክረዉ ተሽከርካሪ ራሱ ሌላ ተሽከርካሪ
ወይም ንብረት በመግጨት በሌላ ተሽከርካሪ ወይም በሌላ ንብረት ላይ ጉዳት ቢያደርስ በወንጀል
ተጠያቂ እንደሚሆን በወንጀል ሕጉ አልተደነገገም፡፡ይህም የሆነበት ምክንያት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ
662 ስር በተደነገገዉ መርህ ላይ እንደተመለከተዉ በሌላ ሰዉ ንብረትና የኢኮኖሚ መብት ወይም
በገንዘብ ሊተመኑ በሚችሉ መብቶች ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ከፍተኛነት ደረጃ ታይቶ በሕጉ
ስድስተኛ መጽሐፍ ስር እንደወንጀል ድርጊት ተቆጥሮ በግልጽ አስቀጪነታቸዉ ካልተደነገገ በስተቀር
እንደአነስተኛ ድርጊት ተቆጥሮ አጥፊዎች በደንብ መተላለፍ እንዲቀጡ ማድረግ የሕግ አዉጭዉ
ፍላጎት በመሆኑ ነዉ፡፡ከዚህም በመነሳት ተጠሪ በደንበኛዉ እግር በመተካት ከጉዳት አድራሹ ካሳ
ለመጠየቅ መሰረት ያደረገዉ ድርጊት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 572 የሚገዛ ባለመሆኑ ከዚህ አንጻር
ታይቶ የይርጋ ጊዜዉ 5ዓመት ነዉ ተብሎ መወሰኑ ስህተት ነዉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይልቁንም የጉዳት አድራሹ ድርጊት የትራፊክ ደንብ መተላለፍ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 856 ስር
የሚያስቀጣ በመሆኑ የይርጋ ጊዜም በወንጀል ህጉ አንቀጽ 773 ስር የተደነገገዉ የአንድ ዓመት ጊዜ
ነዉ፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ በወንጀል ህጉ የተመለከተዉ የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 2143/1/ስር
ከተመለከተዉ ጊዜ ያነሰ በመሆኑ እና ክሱ የቀረበዉ የፍትሓብሔር ሃላፊነትን የሚመለከት
እንደመሆኑ ተፈጻሚነት ያለዉ በፍ/ብ/ህጉ አንቀጽ 2143/1/ የተመለከተዉ የሁለት ዓመት ጊዜ
ገደብ ነዉ ብለናል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ ክሱን ያቀረበዉ በ22/04/2011ዓ.ም ሲሆን ጉዳቱ
ከደረሰበት 25/04/2006ዓ.ም ጀምሮ ወይም ለደንበኛዉ መኪና ማስጠገኛ ወጪ ከከፈለበት
ከ21/12/2006ዓ.ም ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ያለዉ ጊዜ ሲታሰብ ሁለት ዓመት ጊዜ
አልፎበታል፡፡ይህም በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2143/1/ የተደነገገዉ ሁለት ዓመት ጊዜ
ገደብ ካለፈ በኋላ የቀረበ መሆኑን ስለሚያሣይ ክሱ በይርጋ መታገድ ሲገባዉ ታልፎ በፍሬነገሩ
ላይ ዉሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ብለናል፡፡በዚሁ አግባብ
ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡
ዉሳኔ
1ኛ/በዚህ ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/271073 ላይ በቀን
30/08/2011ዓ.ም የሰተዉ ብይን እና በቀን በ11/02/2012ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህንኑ
በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መ/ቁ/247111 ላይ በ28/03/2013ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሸሯል፡፡
2ኛ/በዚህ ጉዳይ የተጠሪ ክስ በይርጋ ታግዷል ብለናል፡፡
3ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ
ብለናል፡፡

የስር ፍርድ ቤት መ/ቁ/271073 በመጣበት ሁኔታ ይመለስ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኖች ፊርማ አለበት፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ.200968

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡….1. ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

2. ቀነዓ ቂጣታ

3. ፈይሳ ወርቁ

4. ደጀኔ አያንሳ

5. ብርቅነሽ እሱባለዉ

አመልካች፡…….አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም- ቀርበዋል

ተጠሪ፡………….አቶ ነጋሽ ያደቴ- ተወካይ አባይነህ ነጋሽ ቀርበዋል

ይህ መዝገብ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍርድ

ይህ የእርሻ መሬት የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን


አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት
ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251106 ጥቅምት 26
ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ
በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል
ዉስጥ ግብር እየገበርኩበት ያለዉን ሁለት ቀርጥ (አዋሳኝ በመጥቀስ) የእርሻ መሬት ይዞታዬን
የካቲት ወር 1989 ዓ.ም ባደረግነዉ ዉል ለጊዜያዊ ችግሬ መዋያ ብር 7000 (ሰባት ሺህ)
ከተከሳሽ ተቀብዬ መሬቱን ለተከሳሽ የሰጠሁ፣ ገንዘቡን ስመልስለት ደግሞ መሬቱን
ሊመልስልኝ የተስማመን ሲሆን፣ ተከሳሽ ገንዘቡን ተቀብሎኝ መሬቱን እንዲያስረክበኝ ፈቃደኛ
ስላልሆነ፣ ተከሳሽ ገንዘቡን ተቀብሎኝ የእርሻ መሬቱን እንዲያስረክበኝ በማለት ዳኝነት
ጠይቋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተከሳሽ በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ ክርክር ከሳሽ በዚህ መሬት መብትና ጥቅም የለዉም፤ ተከሳሽ
ይህን መሬት በዉል አልተቀብኩም፤ መሬቱን በዉል ተቀብለአል የሚባል ከሆነ ዉሉ ተደርጓል
ከተባለ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ከ21 ዓመታት በላይ በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት
ተከራክሯል፡፡

ከዚህ በኋላ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር በመመርር ባሳለፈዉ
ዉሳኔ ከሳሽ የግብር ደረሳኝ ያቀረበ በመሆኑ በመሬቱ ላይ መብትና ጥቅም አለዉ፤ ከሳሽ
ባቀረበዉ ክስ ተከሳሽ መሬቱን ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ መያዙን ገልጸዉ የተከራከሩ በመሆኑ ይህ
ጊዜ ሲሰላ ከ10 ዓመት በላይ በመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠዉ
አስገዳጅ የህግ ትርጉም ዉሳኔ አንጻር በ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ገደብ ሊታገድ ይገባል በማለት
ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበለትን ይግባኝ በትዕዛዝ
በመሰረዝ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል፡፡ የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ
ዉሳኔና ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ፡፡

የአሁን አመልካች ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ፡ አመልካች ግብር


የሚገብርበትን አከራከሪዉን የእርሻ መሬት ይዞታዬን ከተጠሪ ገንዘብ ወስጀ የሰጠሁት በመሆኑ
አመልካች ከተጠሪ የወሰድኩትን ገንዘብ ስመልስለት ይዞታዉን ሊመልስልኝ ተስማመን ስለሆነ
ክሱ በይርጋ የሚታገድ አይደለም፤ አመልካች መሬቱን ለተጠሪ የሰጠሁት በወለድ አግድ ዉል
መልስ በመሆኑ የባለይዞታዉ መብት በይርጋ ሊቋረጥ የማይችል እና አመልካች ያቀረበዉ
አቤቱታ የመፋለም ክርክር ስለሆነ ጉዳዩ በይርጋ ዉድቅ ሊሆን አይገባም ተብሎ የሥር ፍ/ቤት
ብይን ተሽሮ ወደ ፍሬ ጉዳይ ክርክር ገብተን እንዲንከራከር እንዲወሰንልኝ በማለት በዝርዝር
አመልክቷል፡፡

ይህ ችሎት የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲሰጥ ባዘዘዉ መሰረት
በ249/2013 ዓ.ም በተጻፈ መልስ፡ ተጠሪ ከአመልካች ጋር ምንም ዓይነት የመያዣ ዉል
አልፈጸምኩም፣ የመያዣ ዉል አለ ቢባል እንኳን ክስ የቀረበዉ ከ21 ዓመት በላይ የሆነዉ
ስለሆነ ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ነዉ መባሉ የሚነቀፍበት አግባብ የለም፤ አመልካች
ያቀረበዉ ክስ ዉልን የሚመለከት እንጂ የመፋለም አይደለም በማለት ተከራክሯል፡፡ የአሁን
አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከፍ ሲል የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት


ካላቸዉ የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል፡፡ እንደመረመርነዉ በዚህ ጉዳይ
ምላሽ ማግኘት ያለበት ፣በዚህ ጉዳይ ተገቢ የሆነ የፍሬ ነገር ጭብጥ በመያዝ ዉሳኔ የተሰጠ
መሆን አለመሆኑን? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰዉ
አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረግነዉ ዉል ለክርክር መነሻ የሆነዉን ይዞታ ለተጠሪ የሰጡት
ከተጠሪ ገንዘብ ተቀብዬ ሲሆን ገንዘቡን ስመልስለት ተጠሪ ደግሞ መሬቱን ሊመልስኝ
ተስማምተን ስለሆነ አሁን ገንዘቡን ወስዶ መሬቱን እንዲያስረክበኝ የሚል ነዉ፡፡ ስለሆነም
አመልካች አከራከሪዉን መሬት ለተጠሪ ሰጠሁት የሚለዉ በዉል ምክንያት መሆኑን ነዉ፡፡
ተጠሪ በበኩሉ ባቀረበዉ ክርክር ከአመልካች ጋር ምንም ዓይነት ዉል አላደረግኩኝም፤ ዉሉ
አለ ቢባል እንኳን ከ21 ዓመት በላይ በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተከራክሯል፡፡ ስለሆነም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በይርጋ መቃወሚያ ትክክለኛ ዉሳኔ
ለመስጠት ተገቢዉን ጭብጥ በመለየት በመያዝ በማጣራት አግባብነት ካለዉ ሕግ አንጻር
መርምሮ መወሰንን ይጠይቃል፡፡

እንደሚታወቀዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244 (1) መሰረት ማስረጃ ተቀብሎ ከመመርመሩ ወይም


ምስክሮችን ከመስማቱ አስቀድሞ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ደረጃ ለቀረበለትና ማናቸዉም
ተከራካሪ ወገን ላቀረበዉ መቃወሚያ ዉሳኔ መስጠት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ እንዲሁም
ፍ/ቤቱም በቀረበዉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችን ተቀብሎ ሌላዉ ተከራካሪ ወገን በጉዳዩ
ላይ የሚያቀርበዉን ክርክር ከሰማ በኋላ ዉሳኔ ለመስጠት ተገቢ መስሎ የሚገምተዉ ማስረጃ
እንዲቀርብለት ትዕዛዝ ይሰጣል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.245 (1) ሥር ተመልክቷል፡፡
በመሆኑም ከዚህ የህግ ደንጋጌዎች መረዳት እንደሚቻለዉ በቀረበዉ የመጀመሪያ መቃወሚያ
ላይ አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ፍ/ቤት ማስረጃ በመስማት በመጣራት ዉሳኔ መስጠት እንደሚገባዉ
ያስገነዝባል፡፡

በዚህ መሰረት አሁን ወደ ተያዘዉ ጉዳይ ስንመለስ አመልካች ባቀረበዉ ክርክር አከራካሪዉን
መሬት ለተጠሪ በዉል ሰጥቻለሁኝ ያለዉ ሲሆን፤ ተጠሪ በበኩሉ ደግሞ ከአመልካች ጋር
ምንም ዓይነት ዉል አላደረግንም፣ ዉል አለ ቢባል እንኳን በይርጋ የሚታገድ ነዉ በማለት
ክዳዉ ተከራክሯል፡፡ አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገነዉ ዉል መሬቱን ሰጥቻለሁ ያለዉን፣
በተጠሪ በኩል የተካደ ስለሆነ፣ በግራ ቀኙ መካከል አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ተጣርቶ ነጥሮ
መዉጣት ያለበት ጭብጥ አመልካች ለክርክር መነሻ የሆነዉን መሬት በዉል ለተጠሪ ሰጥቷል
ወይስ አልሰጠም? አመልካች መሬቱን በዉል ለተጠሪ ሰጥቷል የሚባል ከሆነ የአመልካች ክስ
በይርጋ የሚታገድ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለዉ ነጥብ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በመሆኑም
የሥር ፍ/ቤቶች ግራ ቀኙን ካከራከረዉ ከዉል አንጻር ጭብጥ መስርቶ አግባብነት ባለዉ
ማስረጃ በማጣራት በሕጉ አግባብ ተገቢ ነዉ ያሉትን ዉሳኔ ማሳለፍ ይገባቸዉ ነበር፡፡ የሥር
ፍ/ቤቶች የግራ ቀኙን ክርክር አስመልክቶ ከዉል አንጻር ሳይመርምሩ ክሱን ዉድቅ
ማድረጋቸዉ የህግ ድጋፍ የለዉም ብለናል፡፡

ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የግራ ቀኙን ክርክር መሰረት በማድረግ ከዉል አንጻር ጭብጥ
በመመስረት አጣርቶ አለመወሰናቸዉ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ
ተከታዩን ወስነናል፡፡

ዉሳኔ

1. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.97708 በ15/4/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ብይን


እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251106 በ26/2/2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ
መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 (1) መሰረት
ተሽሯል፡፡
2. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተዘጋዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ በፍርድ
ሐተታዉ በተመለከተዉ አግባብ አመልካች ለክርክር መነሻ የሆነዉን የመሬት ይዞታ
በክሱ በተጠቀሰዉ አግባብ በዉል ለተጠሪ ሰጥቷል ወይስ አልሰጠም? አመልካች
መሬቱን በዉል ለተጠሪ ሰጥቷል የሚባል ከሆነ የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ ነዉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ወይስ አይደለም? የሚለዉን ከግራ ቀኙ የሚቀርብ ማስረጃ ካለ በመመርመር፣


አግባብነት ባለዉ ማስረጃም በማጣራት ተገቢ ነዉ ያለዉን ብይን እንዲሰጥበት
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 (1) መሰረት ተመልሶለታል፡፡
3. የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ፡፡
4. ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻሉ፡፡
5. ይህ ዉሳኔ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ተነቧል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት

የሰ.መ.ቁ.200968

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም

ስሜ በተራ ቁጥር 3ኛ ላይ የምገኘው ዳኛ የልዩነት ሀሳቤን እንደምከተለው አስቀምጫለሁ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ሲሆን የአሁን አመልካች ባቀረበው ክስ ለአሁን ተጠሪ የእርሻ መሬት ይዞታዬን ገንዘብ ተቀብዬው
መሬቱን እንዲጠቀምበት ያስረከብኩትና ገንዘቡን ስመልስለት መሬቱን እንዲመልስልኝ (ወለድ አግድ)
ተስማምተን በ1989 ዓ/ም የእርሻ መሬቴን የሰጠሁት ሲሆን አሁን ገንዘቡን ወስዶ መሬቴን
እንዲመልስልኝ ብጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆኑ መሬቴን እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን የአሁን
ተጠሪም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክሱ በይርጋ ውድቅ እንዲሆንለት ጠይቆ በፍሬ ነገሩ ላይም
መልስ ሰጥቷል፡፡ የስር ፍ/ቤቶችም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 69302
ላይ በሰጠው ውሳኔ አንድ የእርሻ መሬት ባለይዞታ በመሬት የመጠቀም መብት ለማስከበር በ10
ዓመት ውስጥ ክስ ካላቀረበ ክሱ ይርጋ ቀሪ እንደሚሆን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በሰጠው መሰረት
የአሁን አመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ነው ሲል ክሱን ውድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡ የአሁን አመልካችም
ይህን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ አቤቱታ ነው፡፡ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ የቀረበውን ዳኝነትና የእርሻ
መሬት ይዞታን በተመለከተ ከህገ መንግስቱ ጀምሮ ያሉትን ህጎች እና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት የሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም አንዲሁም የኢፌዴሪ ፌደሬሽን ም/ቤት የሰጠውን
ውሳኔ ካለመገንዘብ የደረሱበት ድምዳሜ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ይሄውም ማንኛውም በእርሻ
መሬት ላይ የሚደረጉ ውሎችን እንደማንኛውም የግል ንብረት ላይ የሚደረጉ ውሎች በፍ/ብ/ህግ የውል
ድንጋጌዎች ሲዳኙ ይታያል፡፡ በፍ/ብ/ህጋችን ላይ ስለመሬት የተደነገጉት ድንጋጌዎች መሬትን በግል
ንብረትነት እይታ መነሻነት ተወስዶ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ሲሆኑ የፍ/ብ/ህግ 1173፣ 1178፣ 1179
እና ሌሎቹም ድንጋጌዎች ይህንኑ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ይሁንና ከደርግ መንግስት ጀምሮ በመሬት
ላይ ያለው የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ የተለወጠና መሬት የህዝብና የመንግስት ሆኖ ባለይዞታው
ከመሬት ባለቤትነት ያነሰ መብት ያለው መሆኑ ማንኛውም ሰው ግንዛቤ የለውም ለማለት የሚቻል
አይደለም፡፡ የኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 40(3) የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት
ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው ሲል ደንግጎ ይገኛል፡፡ ይህ ሆኖ ባለበት የእርሻ
መሬት ላይ የሚደረጉ ክርክሮችን በተመለከተ ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ የወጡ ህጎች እያሉ
የኢፌዴሪ ፌደሬሽን ም/ቤት ውሳኔዎች እያሉ በፍ/ብ/ህጉ ድንጋጌዎች እይታ መዳኘት ተገቢነት
የሌለውና የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ይሆናል፡፡ የኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 40(4)

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነጻ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ
ነው፡፡ አፈጻጸሙን በተመለከተ ዝርዝር ሕግ ይወጣል ሲል ደንግጎ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የእርሻ
መሬት የሚተላለፈው ባለይዞታ ለቤተሰቡ አባላት በውርስና በስጦታ ልያስተላልፍ የሚችል ሲሆን
ከባለይዞታው የቤተሰብ አባለት ውጪ የሚደረጉ የእርሻ መሬት ማስተላለፍ ጉዳይ የእርሻ መሬት
ባለይዞታውን ከይዞታው የሚያፈናቅለው በመሆኑ ህገ መንግስቱን የሚጻረር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት በተለያዩ የእርሻ መሬት ክርክሮች ላይ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን የኢፌዴሪ
የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ መጋቢት 3 ቀን 2008
ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ፣ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት 4ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ
ስብሰባ ሰኔ 18 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔና ሌሎቹንም መመልከት ይቻላል፡፡ እነዚህ ውሳኔዎች
የእርሻ መሬት በተመለከተ በሚነሱ ክርክሮች የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ጨምሮ
የሚሰጡት ውሳኔዎች ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጻረሩ በመሆኑ ህገ መንግስቱን በመተርጎም የኢፌዴሪ
የፌዴሬሽን ም/ቤት የሰጣቸው ውሳኔዎች ናቸው፡፡ ከእርሻ መሬት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች
ይርጋን በተመለከተ የእርሻ መሬት ይዞታ በህገ ወጥ መንገድ ተላልፎ የተገኛ እንደሆነ ክሱ በይርጋ
የማይታገድ መሆኑን የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ
ስብሰባ መጋቢት 3 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ፣ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት 4ኛ የፓርላማ
ዘመን፣ 5ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ሰኔ 18 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና ሌሎችም ውሳኔዎች
በቂና አስገዳጅ ማሳያዎች ናቸው፡፡ መሬት በህጋዊ መንገድ የተላለፈ ስለመሆን አለመሆኑና በህገ ወጥ
መንገድ የተላለፈ ስለመሆኑ የኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 40(4) ባስቀመጠው ድንጋጌ መሰረት
የየክልሎቹ የገጠር መሬትን ለማስተዳደር የወጡት አዋጆች በግልጽ ደንግገው የሚገኙ ሲሆን የእርሻ
መሬት በህጋዊ መንገድ የሚገኘው ከመንግስት በምሬት ስገኝ፣ ከመሬት ባለይዞታው በውርስ ወይም
በስጦታ ለቤተሰቡ ሲተላለፍ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚደረጉ የእርሻ መሬት ማስተላለፍ ሁሉ ህገ ወጥ
የሚሆኑ ናቸው፡፡ የቤተሰብ አባል ማለት ምን እንደሆነ እነዚሁ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም
አዋጆች ደንግገው ይገኛሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር
179827 ላይ በሰጠው ውሳኔ እንድ ሰው የገጠር መሬት በህጋዊ መንገድ የያዘ ስለመሆኑ
እስካልተረጋገጠ ጊዜ ድረስ መሬቱን የያዘው በህገ ወጥ መንገድ መሆኑ ግምት የሚወሰድበት በመሆኑ
የይርጋ መቃወሚያን በስነ ስረዓት መቃወሚያነት ሊያነሳ የማይችል ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም
ሰጥቶበት ይገኛል፡፡ የፌደራል እና የየክልሎቹን የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጆችንም ማየት
ይቻላል፡፡ ሌላው የኢፌዴሪ ፌደሬሽን ም/ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ
መጋቢት 3 ቀን 2008 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔም ይርጋን በተመለከተ ተጠሪ ከአመልካች ላይ ለ50
ዓመት የእርሻ መሬት ተከራይቻለሁ በማለት ያቀረበው ክርክር የክልሉን የገጠር መሬት አስተዳደርና
አጠቃቀም አዋጅ ድንጋጌን የሚቃረን ከአዋጁ ውጪ የባለይዞታነት ማረጋገጫ ደብተር
አውጥቼበታለሁ በማለቱ ብቻ ባለይዞታው ይዞታውን እንዲያጣ እና ከይዞታው እንዲፈናቀል
የሚያደርገው በመሆኑና የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 40(4) የሚቃረን ስለሆነ ተፈጻሚነት የለውም
ሲል ውሳኔ ሰጥቶበት ይገኛል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በመ/ቁጥር 79394
ላይ በሰጠው ውሳኔ በህግ እንዲደረግ ያልተፈቀደ ወይም የህግ ክልከላ ባለበት ጉዳይ ላይ የተደረገ
ውል ህገ ወጥ ውል በመሆኑ ከመነሻውም ውጤት የሌለውና ፈራሽ መሆኑን፣ የውሉ መሰረታዊ ዓላማ
በህግ ያልተፈቀደና የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ ዳኞች ህገ ወጥ የሆነው ውል በቀረበላቸው ማንኛውም ጊዜ
ህጋዊ ውጤትና ተፈጻሚነት የለውም በማለት ለመወሰን የሚችሉና ህገ ወጥ የሆነውን ውል ውድቅ
ለማድረግ በህጉ የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ መቃወሚያ ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ
ትርጉም ሰጥቶበት ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት በዚህ ጉዳይ 1. ክሱ የአሁን አመልካች በወለድ አግድ
ውል የእርሻ መሬቴን ለተጠሪ ሰጥቼዋለሁ ሲል ያቀረበውን ዳኝነት ወለድ አግድ ህገ ወጥ የሆነ በእርሻ
መሬት ላይ የተደረገ ውል መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ እየታወቀ ክሱን በይርጋ ውድቅ ማድረጋቸው
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡ 2. የኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 40(3 እና 4)
መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የህዝብና የመንግስት ሀብት መሆኑንና ባለይዞታው ከይዞታው ያለመነቀል
መብት ያላቸው ስለመሆኑ ተደንግጎ እያለ በህገ ወጥ መንገድ የሚተላለፉ የእርሻ መሬቶች ሁሉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በይርጋ የማይታገዱ ስለመሆኑ የፌደሬሽን ም/ቤት እና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
ውሳኔ ሰጥተውበት እያለ ይህ ሁሉ ታልፎ የአሁን አመልካች ክስ በይርጋ ይታገዳል ተብሎ የተሰጠው
ውሳኔ መሰረታዊ ይህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው እላለሁ፡፡ በመሆኑም
የስር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካችን ክስ በይርጋ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት
የተፈጸመበት በመሆኑ ተሽሮ የአሁን ተጠሪ ክስ የቀረበበትን የመሬት ይዞታ ከአሁን አመልካች
አልተቀበልኩትም የሚል ክርክር ያለው በመሆኑ በፍሬ ጉዳዩ ላይ አከራክሮ እንዲወስን መመለስ ሲገባ
ህገ ወጥ በሆነ የወለድ አገድ ውል ላይ በመመስረት ክሱ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆን አለመሆኑ
ተጣርቶ እንዲወሰን ተብሎ መመለሱ ህጉን ያልተከተለና ካለአግባብ ተከራካሪ ወገኖችን ላልተፈለገ
ወጪና የጊዜ ብክነት የሚዳርግ በመሆኑ ተገቢ አይደለም እላለሁ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መዝገብ ቁጥር201100


ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)


ቀነዓ ቂጣታ
ፈይሳ ወርቁ
ደጀኔ አያንሳ
ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካቾች፡- 1ኛ. አቶ ዳንኤል ታደሰ

2ኛ. ወ/ሪት ኤልሳ ታደሰ የቀረበ የለም

3ኛ. ወ/ሪት ለምለም ታደሰ

4ኛ. ወ/ሪት ዘይድ ኦፔላ

5ኛ. ወ/ሪት ዘውዲቱ ታደሰ

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዘውዲ መንግስተአብ- ቀርበዋል

ለምርምራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል

ፍርድ

አመልካቾች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 259177 ጥር 7 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው
ችሎት ያቀረቡትን ይግባኝ መሰረዙ እንዲሁም ሟች አቶ ታደሰ ወልደጊዮርጊስ ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ/ም
አደረጉት የተባለው ኑዛዜ እንዲሰረዝ ያቀረቡትን መቃወሚያ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመዝገብ ቁጥር 266705 መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ
ስህተት ፈጽመዋል በማለት በሰበር ለማሳረም ጥር 12 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል
በመባሉ መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል፡፡

ጉዳዩ የሟች አቶ ታደሰ ወልደጊርጊስ ውርስ እንዲጣራ አመልካቾች ባቀረቡት አቤቱታ የውረስ አጣሪ ተሹሞ
ተጠሪ ሟች ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ/ም ኑዛዜ አትርፈዋል በማለት ለውርስ አጣሪ ያቀረቡት ኑዛዜ ላይ
የቀረበ መቃወሚያን የሚመለከት ሆኖ የክሱ ይዘትም፡- ሟች ለረጅም ጊዜ በእርጅና እንዲሁም የመርሳት
የአእምሮ በሽታ ፣ ኮልስትሮል ፣ ስኳር ደምግፍት እና የሌሎች በሽታዎች መድኀንት ይወስዱ የነበረና ኑዛዜ
አድርገዋል በተባለ ጊዜ የአእምሮ ሁኔታቸው ምርመራ እንዳይደረግ ተጠሪ ፓስፖርት በመከልከል የአእምሮ
ጤንነት ሁኔታቸውን ለማድበስበስ የሞከሩ ሲሆን ኑዛዜውም በተናዛዡ እና አራት ምስክሮች ፊት መነበቡ
በኑዛዜው ላይ ስላልተገፀ እና ኑዛዜውም ለተጠሪ ልጆች የሚያደላ አመልካቾችንም ከ1/4ኛ በላይ የሚጎዳ
በመሆኑ ሊፈርስ ይገባዋል በማለት አመልክተዋል፡፡ ተጠሪም ለክሱ በሰጡት መልስ ያቀረቡትን የመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ በብይን ያለፈው ሲሆን በፍሬ ነገር መልሳቸውም ሟች ኑዛዜውን ባደረጉበት
ወቅት የአእምሮ ህመም የነበራቸው ለመሆኑ የህክምና ማስረጃ አለመቅረቡ እና የተባሉት ህመሞች ሟች
ኑዛዜ እንዳያደርጉ የማያግዱ በመሆኑና ሟች ኑዛዜውን በኮምፒዩተር አፅፈው በማምጣት ለምስክሮቹ
አንብበው አይተው መፈረማቸው በኑዛዜው ላይ የሰፈረ በመሆኑ አጠራጣሪ ካለመሆኑም በላይ ኑዛዜው
ከተጠሪ ለተወለዱት ልጆች የሚያደላ አይደለም እንጂ የሚያደላ እንኳን ቢሆን ከልካይ የሕግ ድንጋጌ
ባለመኖሩ እና ሟች ተጠሪ ግማሽ ባለድርሻ የሆኑበትን ንብረት ያለተጠሪ ፈቃድ በኑዛዜ ለአመልካቾች
ያስተላለፋ በመሆኑ ተጠሪ በኑዛዜው ተጎጂ እንጂ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን በመግለፅ የአንድ ወራሽ ድርሻ
ከ1/4ኛ በታች መሆንም የክፍፍል ደንብ እንጂ የኑዛዜ ማፍረሻ ምክንያት ባለመሆኑ ክሱ እንዲሰረዝ
ጠይቀዋል፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ኑዛዜ በሟች የተደረገ መሆን አለመሆኑ
፣ ሟች ኑዛዜውን አድርገዋል በተባለ ጊዜ የአእምሮ ሁኔታቸው እንዴት እንደነበረ እንድጣራ እንዲሁም
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ኑዛዜ በሟች የተፈረመ መሆን አለመሆኑ እንዲጣራ እንዲሁም በኑዛዜው ላይ
የተዘረዘሩት ምስክሮች ቀርበው የመስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ትዕዛዝ ሰጥቶ የአማኑል የአእምሮ
እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሟች ስም በኮምፒተራቸው ውስጥ የሌለ በመሆኑ ካርድ ካለ ከመዝገብ የሚፈልግ
መሆኑን የገለፀ ሲሆን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንስክ ምርመራ ዳይሬክቶሬትም ለምርምራው የሚረዱ
ሟች የፈረሙባቸው የፊርማ ናሙናዎች እና ተመርማሪው ሰነድ እንዲቀርብለት ጠይቆ የአመልካቾች ጠበቃ
የተጠቀሱ ሰደነዶችን ለማቅረብ ደንበኞቻቸው በቅርበት እንደሌሉ በመግለፅ ለማቅረብ ጊዜ እንዲሰጣቸው
ጠይቀው ተደጋጋሚ ቀጠሮ ብሰጣቸውም ስላላቀረቡ መታለፉን እንዲሁም በኑዛዜው ላይ ስማቸው
የተጠቀሱት ምስክሮችን አድራሻ አመልካቾች ስለማያውቁ በተጠሪ በኩል እዲቀርብላቸው ጠይቀው መታለፋን
ግልፆ ፤ በኑዛዜው ላይ ምስክር ያልነበሩ የ1ኛ ፣ 5ኛ አመልካቾችን እና የሌላ ሶስተኛ ምስክር ቃል ሰምቶ
መዝገቡ እንደመረመረው፡- በአእምሮ ጉድልት ምክንያት ኑዛዜን ለመሻር ሟቹ በፍትሐ ብሔር ሕጉ ቁጥር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

863 መሰረት ተናዛዡ የታወቀ እብድ መሆኑ መረጋገጥ ያለበት ሲሆን በአመልካቾች የቀረቡት የሕክምና
ሰነዶች የሚያስረዱት ሟቹ ከልብ ህመም ጋር የተያያዘ የጤና ችግር የነበረባቸው መሆኑን እንጂ ሟች
የአእምሮ መጉደል ወይም የታወቀ እብድ መሆቻውን የማያሳይ ከመሆኑም በላይ 1ኛ እና 5ኛ አመልካቾች
ሟቹ በደም ግፍት ምክንያት ጤንነታቸው ተናግቶ የማስታውስ ችግር ገጥሟቸው እንደነበረ ያሳረዱ ቢሆንም
ኑዛዜው ሲደረግ ስላልነበሩ ሟቹ ኑዛዜውን ስያደርጉ የጤንነት ሁኔታቸው ፈቃዳቸውን ለመስጠት
የማያስችላቸው እንደነበረ ስላላስረዱ እና ኑዛዜው በተናዛዡ እና በአራት ምስክሮች ፊት ተነቦ መፈረሙን
የሚገልፅ በመሆኑና ተጠሪ በማስረጃነት ካቀረቡት ከሰንሻይን ኮንስትራክሽን ግንቦት 25 ቀን 2000 ዓ/ም
ከተፃፍ ሰነድ መረዳት እንደሚቻለው ሟች ከኑዛዜው አስቀድሞ ሌሎች ንብረቶችን ለአመልካቾች በስጦታ
ያስተላለፉ መሆኑ ሲታይ ሟች ንብረቶቻቸውን ለተወላጆች ከፍፍል ደረጉ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን
በተደረገው ከፍፍልም አመልካቾች ከሩብ የበለጠ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ስለማያሳይ ኑዛዜው ለተጠሪ
እና ለጆቻቸው ማድላቱን የማያመለክት በመሆኑ ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ/ም የተደረገው ኑዛዜ ሊፈርስ
አይገባም በማለት ወስኗል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመቃወም
ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ በመሰረዙ አመልካቾች ቀጣዩን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ታህሳስ 20 ቀን
2005 ዓ/ም ተደረገ የተባለው ኑዛዜ ተጠሪ እንድያቀርቡ ማድረግ ሲገባው ይህንን አለማድረጉ የሥነ ሥርዓት
ግድፈት ከመሆኑም በላይ ፍትህን የሚጎዳ ሆኖእያለ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ወሳኝ የሆነውን ኑዛዜ እና
በኑዛዜው ላይ የተቆጠሩ ምስክሮች ቀርበው ባለመሰማታቸው በኑዛዜው ላይ ያለው ፍርማ የሟች መሆኑ ፣
ኑዛዜው በሟች መደረጉ ፣ ኑዛዜው ሲደረግ ነበሩ የተባሉ ሰዎች በእርግጥም መኖራቸው ፣ ኑዛዜው
ምስክሮች በተገኙበት የተነበበ መሆኑ ለውሳኔ አሰጣጥ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ፍሬ ነገሮች ሳይጣሩ እና ሟች
የአእምሮ ህመም እንዳለባቸው ለማስረዳት የቀረበው በርካታ የሕክምና ማሰረጃ እና ተጠሪዋ ሟቹን አማኑኤል
ሆስፒታል እንዳሳከሟቸው የተናገሩ ለመሆኑ የተነገረው የምሰክርነት ቃል ተመርምሮ ተደርጓል የተባለው
ኑዛዜ መደረጉ ፤ ተደርጓል ከተባለም በነፃ ፈቃድ እና በትክክለኛ አእምሮ መደረጉ ሳይጣራ ያቀረቡት
መቃወሚያ ውድቅ መሆኑ እንዲሁም ሟቹ በኑዛዜ ያስተላለፉት ጠቅላላ ንብረት ግምት ተጣርቶ
የአመልካቾችን የውርስ ደርሻ ከሩብ የበለጠ መጉዳት አለመጉዳቱ ሳይረጋገጥ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት በሰበር ችሎቱ እንዲታረም ጠይቀዋል፡፡

የአመልካቾችን የሰበር ቅሬታ የመረመረው የሰበር አጣሪ ችሎቱ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ኑዛዜ በሟች
የተፈረም ባለመሆኑ እንድመረመርላቸው ፣ በኑዛዜው ላይ የተመለከቱት ምስክሮች እንዲሰሙላቸው
እንዲሁም ኑዛዜው ከ1/4ኛ በታች የውርስ ድርሻቸውን የሚጎዳ ነው በሚል አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት
ያቀረቡት ክርክር በአግባቡ ሳይጣራ የተወሰነበትን አግባብ ከመሰረታዊ የክርክር አመራር እና ማስረጃ ምዘና
መርህ ጋር አገናዝቦ ለመመርምር መዝገቡ ያስቀርባ በማለቱ ተጠሪ በሰጡት መልስ፡- ሟች የአእምሮ በሽታ
የነበረባቸው ለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ማስረጃ አለመቅረቡ ፣ አማኑኡል ሆስፒታልም ሟች ከሆስፒታሉ
የህክምና ፋይል የሌላቸው መሆኑንና ስታከሙ እንዳልነበረ በፅሁፍ ገልፆ ፣ ሟችም በሆስፒታሉ ስታከሙ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዳልነበረ በአመልካቾች ምስክር ባለመመስከሩ በአጠቃላይ ሟች ኑዛዜውን ባደረጉበት ወቅት የጤና ጉድለት
የነበረባቸው መሆኑ በማስረጃ ባለመረጋገጡ እና የፎረንስክ ምርመራ ውጤት እንድቀርብ በተደጋጋሚ ፍርድ
ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም አመልካቾች ለማቅረብ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ማስረጃ የማቅረብ መብታቸው እንዲሁም
አመልካቾች ለምስክርነት የቆጠሩትን በኑዛዜው ላይ ያሉ ሰዎችን ለአራት የፍርድ ቤት ቀጠሮዎች ለማቅረብ
ፈቃደኛ ስላልሆኑና ምስክሮቻቸውን የማቅረብ ግዴታቸውን ስላልተወጡ የታለፈ ሆኖእያለ ተጠሪ ምስክሮቹ
እንዳይቀርቡ እንዳገዷቸው ቅሬታ መቅረቡ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ኑዛዜውን ከነበረበት
የሟች ብቻ ንሰሓ አባት ከሆኑት አባ ዘርአብሩክ እጅ የአመልካቾች ጠበቃ ጠይቀው ኮፒውን ወስዶ እንድሰረዝ
ክስ ያቀረቡ ሲሆን ዋናውም ለውርስ አጣሪዋ ተሰጥቶ እያለ ተጠሪ ለማቅረብ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ እና
ኑዛዜው በሕጉ አግባብ በምስክሮች ፊት ተነቦ አለመፈረሙ በምሰክር ሳይረጋገጥ የቀረበው አቤቱታ
ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ/ም ሟች ያደረጉሩት ኑዛዜ በአራቱም ምስክሮች ፊት
ተነቦ የተፈረመ በሟች ነፃ ፈቃድ የተሰጠ ሆኖ አመልካቾች የህጉን ፍርማሊት ያላሟላ መሆኑን ስላላስረዱ
ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ መሆኑ ተገቢ ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡ ሟች ታህሳስ 20 ቀን 2005
ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜም ከሩብ በላይ ጉዳት መድረሱን የማሳይ ሲሆን ኑዛዜውም ሲታይ ተናዛዡ የውርስ
ሃብቱን ለተወላጆቹ መስጠቱ የኑዛዜ ስጦታ ማድረግ ሲሆን ፣ የሰበር ሰሚ ችሎቱም በሰበር መዝገብ ቁጥር
50901 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሟች በኑዛዜ የንብረት ድልድል ማድረግ እንደሚችል እና
በንብረት ድልድል አፈፃፀሙ ተወላጅ የሆነ ወራሽ መብቱ ከሩብ የበለጠ ጉዳት የደረሰበት ከሆነ ከውርስ
ማጣራ በኋላ ጉዳቱ በገንዘብ ወይንም በዓይነት የማስተካከል የክፍፍል ደንብ እንጅ የኑዛዜ ማፍረሻ ምክንያት
ባለመሆኑ ኑዛዜውን በተናዛዡ ሃሳብ እና ፈቃድ መሰረት ማስፈፀም እንደሚገባ የወሰነ ሲሆን ግንቦት 25
ቀን 2000 ዓ/ም በተፃፈ ሰነድ ሳንሻይን አፓርትመንት ላይ የሚገኝ መኖሪያ ቤት ለ1ኛ ፣ 2ኛ እና 3ኛ
አመልካቾች ፤ ለ1ኛ አመልካችም በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍል ከተማ የሚገኝ ባለአንድ ወለል መኖሪያ ቤት
ሰጥተው እና ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በእንግሊዝ ሀገር ያስተማሩ ሲሆን 4ኛ እና 5ኛ አመልካቾችንም
ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ሠርግ በመደገስ ድረው እያለ ኑዛዜው ከተጠሪ ለተወለዱ ልጆች አድልቷል
በማለት የሚቀርበው አቤቱታ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ የአመልካቾች አቤቱታ የሕግ መሰረት የሌለው እና
በማስረጃ ያልተደገፈ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት እንዲወሰንላቸው ጠይቀዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና ግራቀኙ በዚህ ችሎት ያደረጉት የጽሁፍ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን ለሰበር
ቅሬታው መነሻ የሆነው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑ መዝገቡ ያስቀርባል
ሲባል የተያዘው ጭብጥ አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ አንፃር ችሎቱ እንደሚከተለው መርምሯታል፡፡ ተጠሪ
ሟች ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ/ም ኑዛዜ አትርፈዋል በማለት ለውርስ አጣሪዋ ያቀረቡትን ሰነድ አመልካቾች
ሟች ለረጅም ጊዜ በእርጅና እንዲሁም የመርሳት የአእምሮ በሽታ ፣ ኮልስትሮል ፣ ስኳር ደምግፍት እና
የሌሎች በሽታዎች መድኀንት ይወስዱ የነበረ በመሆኑ ፤ ኑዛዜ ለማድረግ ችሎታ የላቸውም በማለት
ያቀረቡትን መቃወሚ ፣ ተጠሪ ሟች ኑዛዜውን ባደረጉበት ወቅት የአእምሮ ህመም የነበራቸው ለመሆኑ
የህክምና ማስረጃ አለመቅረቡ እና የተባሉት ህመሞች ሟች ኑዛዜ እንዳያደርጉ የሚያግዱ አይደሉም በማለት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተቃውመዋል፡፡ እንደማንኛውም የፀና ሕጋዊ ተግባር ኑዛዜ ማድረግም ችሎታን ይጠይቃል፡፡ በሕግ በሌላ
አግባብ ካልተወሰነ በቀር ማንኛውም ሰው ማንኛውንም ሕጋዊ ተግባር ለመፈፀም ችሎታ ያለው መሆኑን
የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 192 ይደነግጋል፡፡ ግልጽ የታወቀ የአእምሮ ጉድለት ያለበት ሰው በፍትሐ ብሔር
ሕግ ቁጥር 341 እና 342 ሥር የተገለፁ ሁኔታዎችን የሚያሟላ ከሆነ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ተናዛዡ
ኑዛዜውን በሚያደርግበት ጊዜ የታወቀ እብድ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር የአእምሮ ጉድለት ነበረበት በማለት
ብቻ ኑዛዜ ሊሻር የማይችል መሆኑን የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 863 ያስረዳል፡፡ አመልካቾች ተናዛዡ
የመርሳት የአእምሮ በሽታ ፣ ኮልስትሮል ፣ ስኳር ደምግፍት እና የሌሎች በሽታዎች የነበሩባቸው መሆኑን
ቢከራከሩም የተጠቃሾቹ በሽታዎች ተጠቂ ለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ ካለመኖሩም በላይ የተባሉት
በሽታዎች ተጠቂ እንደነበሩ ብረጋገጥ እንኳን በእነዚህ በሽታዎች መጠቃት የታወቀ እብድ የሚያሰኝ
ባለመሆኑ ፤ የሥር ፍርድ ቤት አመልካቾች ያቀረቡት የሕክምና ሰነዶች ሟች ከልብ ህመም ጋር የተያያዘ
የጤና ችግር የነበረባቸው መሆኑን እንጂ የአእምሮ መጉደል ወይም የታወቀ እብድ መሆቻውን አያሳይም
በማለት ከዚህ አንፃር አመልካቾች ያቀረቡትን መቃወሚያ የሥር ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉ በሕጉ አግባብ
ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡

በኑዛዜ የሚከናወኑት ተግባሮች ስጦታ(legacy) ወንም የክፍያ ደንብ (Rule of partition) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በመርህ ደረጃ አንድ ሰው ከውርስ ሀብቱ መካከል አንድን ንብረት ለወራሾቹ መስጠቱ የኑዛዜ ስጦታ
የማያሰኘው ሲሆን ፣ ይልቁንም ይህ ዓይነቱን ኑዛዜ ሕጉ የሚቀበለው እንደ አንድ የክፍያ ደንብ በመሆኑ
አንድ አውራሻ ለወራሹ አንድን ንብረት ቢናዘዝለት የኑዛዜ አፈፃፀም ስጦታ(legacy) አፈፃፀምን መከተል
ሳይሆን የክፍያ ደንብ (Rule of partition) በመከተል የሚከናወን ይሆናል፡፡ ሆኖም በኑዛዜው ላይ
የሚሰጠው የክፍያ መጠን በመገለፁ ብቻ ሁል ጊዜ የክፍያ ደንብ ሊባል የሚችል ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም የተሰጠው የንብረት መጠን ከሟቹ የውርስ ንብረት ጋር ታይቶ ውጤቱም በዚሁ ረገድ መታየት
አለበት፡፡ በተያዘው ጉዳይ ኑዛዜው ከተጠሪ ለሚወለዱት ልጆች ሚያዳላ እና ከ1/4ኛ በላይ የሚጎዳቸው
መሆኑን በመግለፅ ሊፈርስ ይገባዋል በማለት አመልካቾች ያቀረቡትን ክርክር ኑዛዜው ለተጠሪ ለተወለዱት
ልጆች የሚያደላ አይደለም እንጂ የሚያደላ እንኳን ቢሆን ከልካይ ሕግ ባለመኖሩ እና ሟች ተጠሪ ግማሽ
ባለድርሻ የሆኑበትን ንብረት ያለተጠሪ ፈቃድ በኑዛዜ ለአመልካቾች ያስተላለፋ በመሆኑ ተጠሪ በኑዛዜው
ተጎጂ እንጂ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ፤ እንዲሁም የአንድ ወራሽ ድርሻ ከ1/4ኛ በታች መሆንም የክፍፍል
ደንብ እንጂ የኑዛዜ ማፍረሻ ምክንያት ባለመሆኑ ኑዛዜው ሊሰረዝ አይገባም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ፤
ተጠሪ ለሰበር አቤቱታው በሰጡት መልስም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ኑዛዜ ከመደረጉ በፊት ለ1ኛ ፣ 2ኛ
እና 3ኛ አመልካቾች ግንቦት 25 ቀን 2000 ዓ/ም ስጦታ ተደርጎላቸዋል በማትለት ያቀረቡት ክርክር
በአመልካቾች ካለመስተባበሉም በላይ ፤ ሟች ለአመልካቾች በስጦታ ያስተላለፉት ንብረት መኖሩን ከሰንሻይን
ኮንስትራክሽን ግንቦት 25 ቀን 2000 ዓ/ም የተፃፈ ሰነድ በተጠሪ በማስረጃነት መቅረቡን ከመዝገቡ መረዳት
ተችሏል፡፡ ኑዛዜ ወደታች የሚቆጠር ተወላጅ ላይ ከሩብ የበለጠ ጉዳት ማድረሱ ለኑዛዜው መፍረስ ምክንያት
ሊሆን እንደሚችል የሰበር ሰሚ ችሎቱ ለፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1123 በሰበር መዝገብ ቁጥር 55648

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ለተያዘው ጉዳይም ተፈፃሚነት ያለው በመሆኑ ፤ ተጠሪ ኑዛዜው ከ1/4ኛ
በላይ ጉዳት ማድረሱ ቢረጋገጥም ጉዳዩ የክፍያ ደንብ በመሆኑ ከልካይ ሕግ የለም በማለት ያቀረቡት ክርከር
በሥር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ማግኘቱ ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም፡፡ ኑዛዜው በአመልካቾች ላይ ከ1/4ኛ
በላይ ጉዳት ማድረስ አለማድረሱ አስቀድሞ ግንቦት 25 ቀን 2000 ዓ/ም ለአመልካቾች የተላለፈው ንብረት
እና ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ኑዛዜ ለግራቀኙ የደረሰው ንብረት ግምት መታወቅ አለበት፡፡ የሥር ፍርድ
ቤት ግንቦት 25 ቀን 2000 ዓ/ም ለአመልካቾች የተላለፈው ንብረት እና የንብረቱ ግምት እንዲሁም
ለቅሬታው ምክንያት በሆነው ኑዛዜ ለአመልካቾች የደረሰው ንብረት ግምቱ ተለይቶ ሳይታወቅ ሟች
ለተወላጆች ያደረጉት የንብረት ክፍፍል ከሩብ የበለጠ በአመልካቾች ላይ ጉዳት ማድረሱን አያሳይም ማለቱ
ግልጽ የህግ ድንጋጌን የሚቃረን ነው፡፡

አመልካቾች ሟች ኑዛዜ አላተረፉም ፣ በሰነዱ ላይ ያለው ፊርማም የሟች አይደለም ፣ ኑዛዜውም አራት
ምሰክሮች ባሉበት አልተነበበም በማለት ያቀረቡትን ክርክር ማስረዳት አልቻሉም በማለት የመታለፉ
አግባብነት ሲታይ፡- የኑዛዜ መኖርን ማስረዳት ሸክም ያለበት የኑዛዜው ተጠቃሚ ነኝ የሚል ሰው መሆኑንና
ማስረዳት የሚቻለውም የኑዛዜ ሰነዱ በማቅረብ መሆኑን ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር
49831 እና 53279 አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠ ሲሆን የፍትሐ ብሔር ህጉ ቁጥር 896 እና 897
ድንጋጌም ይህንኑ የሚያስረዳ ነው፡፡ አመልካቾች የሟች ወላጅ አባታቸው አቶ ታደሰ ወልደጊርጊስ ውርስ
እንዲጣራ ያቀረቡትን አቤቱታ ተጠሪ ሟች ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ/ም ኑዛዜ አትርፈዋል በማለት ለክርክሩ
ምክንያት የሆነውን ሰነድ የሟች ውርስ እንዲጣራ አመልካቾች አቤቱታ ባቀረቡበት መዝገብ ላይ ያቀረቡ
ሲሆን ፤ አመልካቾች ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ/ም ተደርጓል በማለት ተጠሪ ያቀረቡትን የኑዛዜ ወራሽነት
ሰነድ ላይ ያላቸውን መቃወሚያ በመዘርዘር ኑዛዜው ሊፈርሰ ይገባም በማለት የመቃወሚያ አቤቱታ ለሰበር
ቅሬታው መነሻ በሆነው መዝገብ ላይ አቅርበው ፤ ተጠሪም ኑዛዜው ሊፈርስ አይገባም የሚሉበትን ዝርዝር
ክርክር አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም አከራካሪው ኑዛዜ በሟች የተደረገ መሆኑን አለመሆኑን ለማጣራት
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶረት ሟች አድርገዋል የተባለውን ኑዛዜ የሟች
መሆን አለመሆኑን አጣርቶ እንዲያቀርብ እና በኑዛዜው ላይ የተዘረዘሩ እማኞችም ቀርበው የምስክርነት
ቃላቸውን እንዲሰጡ ትእዛዝ ሰጥቶ ፤ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶረት የሟች
ፊርማ ናሙና እና ተመርማሪው ሰነድ እድቀርብለት ጠይቆ በአመልካች ባለመቅረቡ እንዲሁም በኑዛዜው ላይ
ስማቸው የተጠቀሱ እማኞች አመልካቾች አድራሻቸውን የማያውቁ በመሆኑ በተጠሪ በኩል እንድቀርቡላቸው
ጠይቀዋል በማለት አልፎታል፡፡ የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2007(2) ወራሾች የአውራሻቸው ጽሑፍ ፊርማ
አለመሆኑን ብቻ መካድ በቂ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ጽሑፉ ወይንም ፊርማው በተካደ ጊዜ እንዲመረመር
ዳኞች ሊያዙ እንደሚችሉ ከፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2008 ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡ የሥር ፍርድ ቤትም
ጽሕፈቱንና ፍርማውን ለማስመርመር ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ተመርማሪው ሰነድ በማን እጅ እንዳለ ሳይለይ
እና የፊርማ ናሙናዎቹም የሚገኙበትን ቦታ ተለይቶ እንድቀርብ ግልፅ ትዕዛዝ መስጠት ሲገባው ፤
አመልካቾች መኖሩን በውርስ ማጣራት ሂደት የሰሙትን ሰነድ ለምርመራ አላቀረቡ በማለት ፤ እንዲሁም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኑዛዜው ላይ ያለው ፍርማ ስለተካደ ፊርማው የሟች መሆን አለመሆኑ ኑዛዜው ሲደረግ በነበሩ ምስክሮች
ማረጋገጥ ሲገባው ፤ አመልካቾች በኑዛዜው ላይ ስማቸው የተጠቀሱ እማኞችን አድራሻ አናውቅም
በማለታቸው ብቻ የእማኞቹን አድራሻ ማወቅ አለማወቃቸው ሳይጣራ በአመልካቾች ጉድለት ትዕዛዙ
እዳልተፈፀመ ተወስዶ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 199(1) ታልፎ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው
ኑዛዜ በሟች የተደረገ መሆን አለመሆኑ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 255 ,257 እና 273
በማስረጃ ሳይጣራ ፤ እንዲሁም ፍርድ ቤቶች ለክርክሩ ፍትሓዊነት ተገቢ ነው ብለው ሲያምኑ ማንኛውንም
ዓይነት ማስረጃ አስቀርቦ መመርመር እንዳለባቸው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት
በሰበር መዝገብ ቁጥር 29861 ላይ የሰጠው በጉዳዩ ላይ ተፈፃሚነት ያለውን አስገዳጅ ውሳኔ በመተላለፍ ፤
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ሆኖእያለ በይግባኝ ሰሚው የፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አለመታረሙ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 259177 ጥር 7 ቀን ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው


ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 266705
መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1)
መሰረት ተሸሯል፡፡
2. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተዘጋውን የመዝገብ ቁጥር 266705 በማንቀሳቀስ በፍርድ
ሀተታው ውስጥ በተገለፀው መሰረት ለክርክሩ መነሻ የሆነው ኑዛዜ በሟች መደረግ አለመደረጉ ፣
ተደርጓል ከተባለ የፎርማሊት ችግር ያለበት መሆን አለመሆኑ ፣ በሕግ ፊት የፀና ኑዛዜ አለ ከተባለ
በአመልካቾች ላይ ከሩብ በላይ ጉዳት ማድረስ አለማደረሱ ፤ ጉዳት አደርሶ ከሆነ ውጤቱ ምን መሆን
እንዳለበት አጣርቶ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ እንዲሰጥበት መዝገቡን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1)
መሰረት ተመልሶለታል፡፡
3. በዚህ መዘገብ ላይ ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡
4. በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ውጪ እና ኪሳራ ግራቀኙ የግላቸውን ይቻሉ፡፡
መዝገቡ ውሳኔ አግኝቶ ሰለተዘጋ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
.

ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 201128

ጥቅምት 03 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች- ወ/ሮ መሠረት ኃይሉ- ጠበቃ ሰለሞን ረዳ

ተጠሪ- ወ/ሮ ቢቂልቱ በየነ- ቀርበዋል

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ የፍርድ አፈፃፀምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በቡራዩ ከተማ ወረዳ
ፍርድ ቤት ተጠሪ የፍርድ ባለመብት በመሆን የፍርድ ባለዕዳ በሆኑት በአመልካች እና ሌሎች
ሁለት ግለሰቦች ላይ ባቀረቡት አቤቱታ የቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 64593 ላይ በቀን
10/08/2009 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በሰጠዉ ውሳኔ መሠረት እንዲፈፀምላቸው የጠየቁትን ዳኝነት
መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡

የአፈፃፀም አቤቱታዉ የቀረበለት ፍርድ ቤት አከራካሪው ይዞታ በገፈርሳ ቡራዩ ቀበሌ


አስተዳደር አማካኝነት ተለክቶ እንዲቀርብለት ካደረገ በኋላ ስፋቱ 842.8 ካ.ሜ እንደሆነ፤ ተጠሪ
ደግሞ በክሳቸው ላይ የጠቀሱት የይዞታ መጠን 660 ካ.ሜ ስለመሆኑ መገንዘቡን ጠቅሶ የፍርድ
ባለእዳዎች በዚሁ መጠን ለአመልካች እንዲያስረክቡ፣ ከዚህ ውጪ የሚተርፍ ይዞታ ካለና
ባለመብት ካልተገኘ የከተማው አስተዳደር ወደ መሬት ባንክ እንዲያስገባ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ
ቤቱም የግራ ቀኙን የይግባኝ አቤቱታ በማጣመር ከመረመረ በኋላ ትርፍ ነው የተባለውን መሬት
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ይዉሰድ መባሉ ስህተት ነው፤

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ በአራቱም አቅጣጫ አዋሳኝ ጠቅሰው ያቀረቡትን ክስ መጠኑ በባለሞያ እንዲጣራ ከማዘዝ
ውጪ ትክክለኛውን መጠን አልጠቀሱም ሊባል አይገባም በማለት የወረዳ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን
ውሳኔ ሽሮታል፡፡ አመልካች በበኩላቸው በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ እና የሰበር
አቤቱታቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እና ሰበር ሰሚ ችሎቶች በቅደም ተከተል
ቢያቀርቡም ተቀባይት አላገኘም፡፡ ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ
በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡

አመልካች በቀን 12/05/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት 03 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ
ቤቶች ተፈጽመዋል ያሏቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችሎት እንዲታረሙላቸው ጠይቀዋል፡፡
የአቤቱታቸው ይዘትም በአጭሩ ክርክር ያስነሳውና ተጠሪ እንዲረከቡት የተወሰነላቸው ይዞታ መጠን
660 ካ.ሜ ሆኖ እያለ ከዚህ መጠን በላይ አመልካች በውርስ ያገኘሁትን ይዞታ በማጠቃለል
በአፈፃፀም እንዲረከቡ መወሰኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ
የሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ያላገናዘበ እና መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ
ሊታረም ይገባዋል የሚል ነው፡፡

ጉዳዩም በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ የአከራካሪው ይዞታ አፈፃፀም ፍርዱን የተከተለ
ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ከፍትሐብሔር ስነ-ስርዓት ህግ አንፃር መጣራት ያለበት
መሆኑ ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ችሎት ቀርቧል፡፡ በዚሁም መሠረት ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት
ተደርጎ በቀን 22/06/2013 ዓ.ም በተፃፈ መልሳቸው የቡራዩ ከተማ ወረዳ ፍርድ ለአፈፃፀሙ
ምክንያት የሆነውን ውሳኔ ሲሰጥ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን መሬት ስፋት ያላጣራ ሲሆን
በደፈናው የተጠሪ ይዞታ ላይ የተፈጠረው ሁከት ተወግዶ የፍርድ ባለእዳዎች የሰሩትን አጥር
አፍርሰው ይዞታውን እንዲለቁ ወሰነ እንጂ የይዞታውን መጠን አልገለፀም፤ በስር ፍርድ ቤት ክስ
ያቀረብቡኩበት ይዞታ መጠኑ 1300 ካ.ሜ የነበረ ሲሆን መንግስት በይዞታው ላይ መንገድ
በማውጣቱ መጠኑ ቀንሷል፤ አመልካች በዚህ አካባቢ ምንም አይነት መሬት የላቸውም፤ የስር
ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዋሳኙ የተጠቀሰውን መሬት በአፈፃፀም እንድረከብ ትዕዛዝ መስጠቱ ስህተት
ስለሌለው ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክራለች፡፡ አመልችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር
የመልስ መልስ ሰጥተው ተከራክረዋል፡፡

ከስር ጀምሮ የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ
ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችሎትም የአመልካችን የሠበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ
ከተያዘው ጭብጥ፣ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር
በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡ እንደመረመረዉም ለአፈፃፀሙ ምክንያት ለሆነዉ
ዉሳኔ መነሻ የሆነዉን ክስ ተጠሪ ሲያቀርቡ አዋሳኛቹንም በአራት አቅጣጫ በመጥቀስ ሲሆን
ለአፈፃፀሙ ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔ ይዘትም አዋሳኙ ከተጠቀሰዉ ይዞታ ዉስጥ የሚገኘዉ ይዞታ
የተጠሪ በመሆኑ አመልካችን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ሁከት አስወግዶ በቦታዉ ላይ ያጠሩትን
አጥር ያፍርሱ የሚል ስለመሆኑ በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሰጠዉ
የፍርድ ሃተታ መገንዘብ ይቻላል፡፡ አመልካች ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ ወይም ለአፈፃፀሙ መነሻ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሆነዉ ፍርድ ካረፈበት ይዞታ አጠገብ አዋሳኝ ይዞታ ያላቸዉ ስለመሆኑ የቀረበ ክርክር የለም፡፡
ለፍርድ አፈፃፀም ምክንያት የሆነዉ ዉሳኔም ይሄዉ ነዉ፡፡

ፍርድ እንዲያስፈጽም አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት እንደ ፍርዱ፣ ማለትም በፍርዱ ላይ


በተመለከተዉ ላይ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ፣ የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት፡፡ በፍርድ ቤት
የሚሰጥ ዳኝነት ያላግባብ የተወሰደ ንብረት ወይም ሀብት እንዲመለስ ወይም ገንዘብ እንዲከፈል
ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ መልኩ በሚሰጥ ዉሳኔ የፍርድ ባለመብት ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለዉ
በተሰጠ ፍርድ መሠረት የተፈጸመለት እንደሆነ ነዉ፡፡ እያንዳንዱ ጉዳይ የሚፈጀዉ ጊዜ እንደ
የጉዳዩ ዓይነትና ባህርይ ሊለያይ የሚችል ቢሆንም፣ ክስ ከቀረበበት ጀምሮ እስከ ዉሳኔ ድረስ ያለዉ
ሂደት የተወሰነ ጊዜ መዉሰዱ አይቀሬ ነዉ፡፡ በዚህም ሂደት የፍርድ ቤት ብሎም የተከራካሪ ወገኖች
ጊዜ ይባክናል፤ ወጪና ድካም ይኖራል፡፡ ስለሆነም ፍርድን እንደ ፍርዱ ማስፈጸም ይህን ሂደት
በማለፍ የተሰጠ ፍርድ ፍሬ አልባ እንዳይሆን የማድረግ ዉጤት ሊያስከትል የሚችል ከመሆኑም
በላይ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ፍርድ ተፈፃሚነቱ ተገማች እንዲሆን ያስችላል፡፡ የፍት/ብ/ሥነ
ሥርዓት ህጋችን ሰባተኛ መጽሐፍ ከአንቀጽ 371 ጀምሮ ባሉት ድንጋጌዎቹ የፍርድ አፈፃፀም
የሚመራበትን ሥነ-ሥርዓት ይደነግጋል፡፡ የፍርድ አፈፃፀም የቀረበለት ፍርድ ቤትም በዚህ
የመጽሐፉ ክፍል የተዘረጋዉን ስርዓት በመከተል ድንጋጌዎቹን እንደየአግባብነታቸዉ ተግባራዊ
በማድረግ አፈፃፀሙን በመምራት እንደ ፍርዱ የማስፈጸም ግዴታ አለበት፡፡

ከዚህ አንፃር የተያዘዉን ጉዳይ ስንመለከት ለአፈፃፀሙ መነሻ ለሆነዉ ዉሳኔ ምክንያት
በሆነዉ ክስ ተጠሪ የጠቀሱት የይዞታ መጠን 660 ካ/ሜትር የሚል ቢሆንም የተሰጠዉ ዉሳኔ በክሱ
ላይ አዋሳኞቹ የተጠቀሰዉ ይዞታ የተጠሪ መሆኑን የሚያሳይ ከሆነ በአዋሳኙ የተመለከተዉ የይዞታ
መጠን ከ660 ካ/ሜትር በላይ 842.8 ካ/ሜትር መሆኑ ቀሪዉ ይዞታ ማለትም 182 ካ/ሜትር ፍርድ
ያላላረፈበት ነዉ ለማለት የሚያስችል አይደለም፡፡ በመሆኑም የወረዳዉ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ከዚህ
አንፃር ማየት ሲገባዉ ይዞታዉ ተለክቶ በታወቀዉ መጠን እና በተጠሪ ክስ ላይ በተጠቀሰዉ መጠን
መካከል ልዩነት በመፈጠሩ ብቻ 182 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ፍርድ አላረፈም በማለት መቀነሱ የፍርዱን
ትክክለኛ ይዘት ያላገናዘበ ሲሆን፣ በአንፃሩ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንኑ በማረም በፍርዱ ላይ
አዋሳኙ የተጠቀሰዉ ይዞታ ለተጠሪ እንዲፈጸም በማለት ዉሳኔ መስጠቱ እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችሎቶች ይህንኑ ዉሳኔ በማጽናት የሰጡት ትዕዛዝ የፍርድ
አፈፃፀም ሥርዓት መሠረታዊ መርህን ለአፈፃፀሙ ምክንያት ከሆነዉ ዉሳኔ ጋር በማገናዘብ የተሰጠ
እና በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችሎት ሊታረም የሚችል መሠረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም፡፡ ስለሆነም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡
ዉሳኔ
1. በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 39788 በቀን
16/04/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ፣ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 325009 በቀን 27/04/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት
እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 334648 በቀን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

03/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ


348(1) መሠረት ጸንተዋል፡፡
2. የሰበር አጣሪ ችሎት በመ/ቁጥር 201128 በቀን 25/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት
የሰጠዉ እግድ ተነስቷል፡፡
3. በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን
ይቻሉ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ

ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መዝገብ ቁጥር 201142

ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)


ቀነዓ ቂጣታ
ፈይሳ ወርቁ
ደጀኔ አያንሳ
ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች፡- ወ/ሮ ፀሐይ ድሪባ- ጠበቃ አቶ መርጋ ታከለ - ቀርቧል

ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ ፅጌ ድሪባ- አቶ ተስፋዬ ድርባ ተወካይ ቀርቧል

2ኛ. ቢፍቱ የወተት አምራቾች ማህበር- ተወካይ አቶ ጎj ዋቅቶላ ቀርቧል

ለምርምራ ተቀጥሮ የነበረው መዝገብ ተመርምሮ ቀጣዩ ፍርድ ተሰጥቷል

ፍርድ

አመልካች የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 27389 ህዳር 3 ቀን
2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 77957 ሰኔ 17 ቀን 2011 ዓ/ም
በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ያቀረቡትን ይግባኝ የክልሉ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 331767 የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት
መሰረዙ እንዲሁም የሰበር አጣሪ ችሎቱም በመዝገብ ቁጥር 336213 ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው
ችሎት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ሰህተት የተፈፀመበት አይደለም
ማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽመዋል በማለት በሰበር ለማሳረም ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ/ም ያቀረቡት
የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል በመባሉ መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ የገጠር መሬት ይዞታ የውርስ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ የተጀመረው በወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት
ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ ፤አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ 1ኛ ተጠሪ በሥር ክሳቸው ወላጅ
አበታቸው አቶ ድሪባ ጎበና በ1998 ዓ/ም ፣ ወላጅ እናታቸው ወ/ሮ በሬዱ ሆርዶፋ በ2006 ዓ/ም ከዚህ ዓለም
በሞት መለየታቸውን ገልፀው ከወላጅ አባታቸው ሞት በኋላ መገኛው ፣ አዋሳኞቹ እና መጠኑ በክሱ ላይ
የተገለፀው ሟች እናታቸው በፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኙትን የመሬት ይዞታ የሥር ተከሳሾች ይዘው ስለሚገኙ
እንዲለቁላቸው ጠይቀዋል፡፡

አመልካችም በመልሳቸው አከራካሪውን ይዞታ ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ በእጃቸው ገብቶ ሲጠቀሙበት የቆዩ
በመሆኑ ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ ውድቅ እንዲሆንና በፍሬ ነገር ክርክራቸውም ለክርክሩ መነሻ የሆነው
መሬት የ1ኛ ተጠሪ እናት የባለይዞታነት መብት የሌላቸው አመልካች የግል ይዞታቸው መሆኑን ሲከራከሩ
2ኛ ተጠሪም በመልሳቸው ጉዳዩ የመጨረሻ እልባት ያገኘ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን
በማስቀደም በእጃቸው ይገኛል የተባለው የመሬት ይዞታ የ1ኛ ተጠሪ ወላጅ እናት ከዚህ ዓለም በሞት
ከመለየታቸው በፊት መሬቱ በሌላ ሰው ያልተያዘ መሆኑ ተረጋግጦ በማህበር ተደራጅቶ በሀገር ሽማግሌዎች
እና በኮሚቴ ተሰጥቷቸው የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና ካርታ ወስደው ለ8(ስምንት) ዓመት
የተጠቀሙበት በመሆኑ ልንጠየቅ አይገባም በማለት አማራጭ ክርክር አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያው ላይ የግራቀኙን ክርክር እና ማሰረጃ ሰምቶ አመልካች በእጇ አለ የተባለውን የመሬት
ይዞታ በ1998 ዓ/ም ይዛ የምትጠቀምበት እና በሰሟ ተመዝግቦ መኖሩ ቢረጋገጥም ለጉዳዩ አግባብነት ያለው
ይርጋ በደንብ ቁጥር 151/2005 ቁጥር 32 ላይ የተመለከተው 12 ዓመት በመሆኑ በክሱ በ1ኛ ተራቁጥር
ሥር የተመለከተው የመሬት ይዞታ በይርጋ ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡ የፍሬ ነገር
ክርክሩ 2ኛ ተጠሪ በሌለበት የቀጠለ ሲሆን የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪን ክርክር ሰምቶ በክሱ በ2ኛ, 3ኛ እና
4ኛ ተራቀጥር የተጠቀሱ የመሬት ይዞታዎችን በተመለከተ ሊጣራ ይገባል ያለውን ጭብጥ ይዞ ማስረጃ
ሰምቶ ፣ ኮሚቴዎችን አዋቅሮ ጉዳዩን በማጣራት ባደረገው ምርመራ በክሱ በ2ኛ እና 3ኛ ተራቁጥር
የተጠቀሱት የመሬት ይዞታዎች ለ1ኛ ተጠሪ እናት ተወስኖ ትታው የሞተች የውርስ ይዞታ መሆኑ
የተረጋገጠ ሲሆን አመልካች እንደ ክርክሯ ስላላስረዳች በክሱ በ2ኛ እና 3ኛ ተራቁጥር የተጠቀሱትን የመሬት
ይዞታዎች ለ1ኛ ተጠሪ እንድትለቅ የወሰነ ሲሆን በክሱ በ4ኛ ተራቁጥር ሥር የተጠቀሰው መሬት ለ2ኛ
ተጠሪ የተሰጠ መሆኑ መረጋገጡን ገልፆ ከተሰጠው ይዞታ ውጪ 0.75 ሄከታር ድንበር አልፎ የያዘውን
የአመልካች ይዞታ እንዲለቅ አስቀድሞ የተሰጠ ውሳኔ ያለ በመሆኑ እና 1ኛ ተጠሪም ይዞታው የራሷ
መሆኑን አላስረዳችም በማለት ወስኗል፡፡

አመልካች የወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመቃወም የይግባኝ አቤቱታቸውን ለፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ
ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን አከራክሮ በሰጠው ውሳኔ፡- በአመልካች እና
1ኛ ተጠሪ እናት መካከል ክፍፍል የተደረገው በ1999 ዓ.ም ሲሆን 1ኛተጠሪ በ2011 ዓ/ም የጠየቀችው
በ2006 ዓ/ም የሞተችውን እናቷን ውርስ በመሆኑ ፣ እናቷ በሕይወት እያለች ድርሻዋን ይዛ መገኘቷን
የሚያረጋግጥ ማሰረጃ ያልቀረበ ቢሆንም ይርጋው የሚቆጠረው የ1ኛ ተጠሪ እናት ከሞተችበት ከ2006 ዓ/ም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጀምሮ በመሆኑ እና ክርክሩም ወራሽ እና ወራሽ ባልሆኑ ተከራካሪዎች መካከል የተደረገ የውርስ ክርክር
በመሆኑ አግባብነት ያለው ይርጋ በውርስ ሕጉ የተመለከተው 10 ዓመት ስለሆነ 1ኛ ተጠሪ እናቷ ከሞተች
በአምስት ዓመት በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ የሚታገድ ባለመሆኑ አከራካሪው ይዞታ በአመልካች እና 1ኛ
ተጠሪ እናት መካከል በተደረግ ክፍፍል የ1ኛ ተጠሪ እናት የሚስትነት ድርሻ ስለሆነ አመልካች የ1ኛ ተጠሪ
እናት የሚስትነት ድርሻ የሆነውን ይዞታ የያዘችበት ሁኔታ ህጋዊ መሆኑንና በአከራካሪው ይዞታ ላይ ከ1ኛ
ተጠሪ እናት የተሻለ መብት ያላት መሆኑን አላረጋገጠችም በማለት የወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔን
ያፀና ሲሆን አመልካች ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበችው የይግባኝ እና ሰበር አቤቱታ ተቀባይነት
አላገኘም፡፡

አመልካች የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለት በሰበር ለማሳረም
ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት፡- የወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የ12 ዓመት ይርጋ ነው
በማለት የደረሰበት መደምደሚያ እንዲሁም ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን
ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግባብነት ያለው ይርጋ 10 ዓመት ነው ማለቱ አግባብ ቢሆንም ይርጋው መቆጠር
የነበረበት አከራካሪው መሬት በአመልካች ከተያዘበት ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ መሆን ሲገባው 1ኛ ተጠሪ
እንዳለችው መሬቱ በ1999 ዓ/ም ተይዟል ቢባል እንኳን 12 ዓመት ሞልቶት እያለ በወረዳ ፍርድ ቤት
ያላከራከረ እና በተከራካሪዎች ያልተነሳን መከራከሪያን መሰረት በማድረግ ይርጋው ሊቆጠር የሚገባው
ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ነው በማለት የአመልካችን የይርጋ ክርክር ውድቅ ማድረጉ ፤ የ1ኛ ተጠሪ እናት
አከራካሪውን ይዞታ ሳትጠቀም እና በአመልካች ላይ ጥያቄ ሳታቀርብ በ2006 ዓ/ም እንደሞተች የተረጋገጠ
በመሆኑ በመሬቱ ላይ መብት ቢኖራት እንኳን መብቷን አጥታ የሞተች በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች እናቷ
አጥታ የሞተችው መብት ለ1ኛ ተጠሪ ይተላለፋል ማለታቸው እንዲሁም አመልካች 2ኛ ተጠሪን በተመለከተ
ያቀረበችው መከራከሪያን ውድቅ በማድረግ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈፀመበት ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎቱ የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቡትን የይርጋ መቃወሚያን ያለፉበትን አግባብነት
ከፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1677(1) እና 1845 እንዲሁም ከክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር እና
አጠቃቀም አዋጅ አንፃር ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ይቅረብ በማለት አዟል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በመልሳቸው
አከራካሪው መሬት በሟች የ1ኛ ተጠሪ እናት ስም ተመዝግቦ እስከ 2006 ዓ/ም ድረስ ግብር እየተከፈለበት
በቁጥጥሯ ሥር አድርጋ ከዚህ ዓለም በሞት እስከተለየችበት ጊዜ ድረስ ስትጠቀምበት የቆየች በመሆኑ
አመልካች መሬቱን በ1999 ዓ/ም ነው የያዝኩት በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ሀሰት ስለሆነ የሥር ፍርድ
ቤት ወ/ሮ በሬዱ ሆርዶፋ ህዳር 28 ቀን 2006 ዓ/ም መሞቷን አረጋግጦ በክልሉ የመሬት አስተዳደር እና
አጠቃቀም ደንብ ቁጥር 151/2005 መሰረት ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት የሌለበት በመሆኑ ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪም በወልመራ ወረዳ ፍርድ
ቤት ከአመልካች ጋር ተከሳሾች ሆኖእያለ በሁለቱ መካከል ክርክር ሳይኖር እንዲሁም ግራቀኙ የተከራከሩበት
ይዞታ ለአመልካች ተወስኖ እያለ በ2ኛ ተጠሪ እጅ ያለ በማስመሰል በአመልካች የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የለውም በማለት ውድቅ እንዲሆንላቸው ጠይቀዋል፡፡ አመልካችም ዋናውን አቤቱታቸውን በማጠናከር


የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

የግራቀኙ ክርክር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎቱ ያስቀርባ ሲባል
የተያዘውን ጭብጥ አግባብነት ካለው የሕጉ ድንጋጌ አንፃር እንደሚከተለው ተመርምሯል፡፡ 1ኛ ተጠሪ
በ2006 ዓ/ም የሞተችው ወላጅ እናቷ ወ/ሮ በሬዱ ሆርዶፋ በ1998 ዓ/ም በክፍፍል ያገኘችው የሚስትነት
ድርሻዋ የሆነውን የመሬት ይዞታ አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ይዘው ስለሚገኙ አንዲለቁላት በ2011 ዓ/ም
ላቀረበችው ክስ አመልካች በሰጠችው መልስ ፤ አከራካሪው ይዞታ ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ በእጃዋ ገብቶ
ስትጠቀምበት የቆየች በመሆኑ ክሱ በ10 ዓመት ይርጋ ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ አቅርባለች፡፡ የወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች አከራካሪውን የመሬት ይዞታ በ1998 ዓ/ም
ይዛ የምትጠቀምበት መሆኑን ቢያረጋግጥም ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ይርጋ በደንብ ቁጥር 151/2005 ቁጥር
32 ላይ የተመለከተው 12 ዓመት ነው በማለት የይርጋ መቃወሚያውን ውድቅ ያደረገ ሲሆን ጉዳዩን
በይግባኝ ያየው በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፤ በአመልካች እና 1ኛ ተጠሪ እናት
መካከል የመሬት ክፍፍል የተደረገው በ1999 ዓ/ም ሲሆን ሟች ወ/ሮ በሬዱ ሆርዶፋ ድርሻዋን ይዛ
መገኘቷን የሚያረጋግጥ ማሰረጃ ባይቀርብም የስር ከሳሽ የሆነችው 1ኛተጠሪ ክስ ያቀረበችው በ2006 ዓ/ም
የሞተችውን እናቷን ውርስ ለመጠየቅ በመሆኑ አግባብነት ያለው ይርጋ በውርስ ሕጉ የተመለከተው 10
ዓመት ስለሆነ ፤ 1ኛ ተጠሪ እናቷ ከሞተች አምስት ዓመት በኋላ ያቀረበችው ክስ በይርጋ የሚታገድ
አይደለም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ክርክሩ የውርስ ይዞታን የሚመከለት በመሆኑ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው
በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1000(2) ስር የተመለከተው 10 ዓመት ነው መባሉ በአግባቡ ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ
ሟች እናቷ አከራካሪውን መሬት ከዚህ ዓለም በሞት እስከተለየችበት ጊዜ ድረስ ስትጠቀምበት የቆየች
በመሆኑ አመልካች መሬቱን በ1999 ዓ/ም ነው የያዝኩት በማለት የምታቀርበው ክርክር ሀሰት ነው በማለት
የምትከራከር ቢሆንም ክፍፍል ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ አከራካሪው መሬት በሟች የ1ኛ ተጠሪ እናት እጅ
ያልገባ እና በአመልካች ተይዞ መቆየቱን ከመዝገቡ መረዳት ተችሏል፡፡

አከራካሪውን መሬት በክፍፍል ለ1ኛ አመልካች እናት የደረሰ ቢሆንም ከአመልካች እጅ አለመውጣቱ
ከተረጋገጠ ይርጋው መቆጠር የነበረበት አከራካሪው መሬት በአመልካች ከተያዘበት ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ ነው
ወይስ የ1ኛ ተጠሪ እናት ከሞተችበት ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ነው የሚለው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ማግኘት
አለበት፡፡ 1ኛ ተጠሪ የምትጠይቀው መብት ከሟች እናቷ በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 826(2)
የሚተላለፍላትን መብት እና ግዴታ ነው፡፡ ጥያቀው የሚቀርበው የውርስ ንብረቶቹ መያዛቸው ከታወቀበት
ጊዜ አንስቶ እስከ አስር ዓመት ድረስ መሆኑን ከፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 1000 ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡
የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው በመብቱ መስራት ከሚቻልበት ጊዜ አንስቶ መሆኑን ከፍትሐ ብሔር ህግ
ቁጥር 1846 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተያዘው ጉዳይ የ1ኛ ተጠሪ እናት በክፍፍሉ የደረሳት መሬት
ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ አመልካች እንድትለቅላት የመጠየቅ መብት ያላት ቢሆንም ይህንን መበቷን
ሳትጠቀምበት ሞታለች፡፡ ምንም እንኳን 1ኛ ተጠሪ እናቷ በሕይወት እያለች አመልካች አከራካሪውን የመሬት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይዞታ እንድትለቅላት ለመጠየቅ መብት የሌላት ቢሆንም ፤ የምትጠይቀው ሟች እናቷ በሕይወት እያለች
የነበራት መብት በእናቷ እግር ተተክታ በመሆኑ አመልካች በ1ኛ ተጠሪ እናት ላይ ልታነሳ የሚትችለውን
መከራከሪያ በ1ኛ ተጠሪ ላይም የማንሳት መብት ያላት በመሆኑ ፤ የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚገባው
አመልካች አከራካሪውን መሬት ከያዘችበት 1999 ዓ/ም መሆን ሲገባው የ1ኛ ተጠሪ እናት ከሞተችበት
ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ነው በማለት አመልካች ያቀረበችው የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ ሆኖ አመልካች ከ10
ዓመት በላይ በእጇ የቆየውን አከራካሪውን የመሬት ይዞታ ለተጠሪ አንድትለቅ የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ
በመሆኑ ቀጣዩ ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1. የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር አጣሪ ችሎት በመዝገብ ቁጥር
336213 ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ ፣ ይግባኝ ሰሚው የክልሉ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 321767 የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው
ትዕዛዝ እንዲሁም በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 27389
ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና ትዕዛዝ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት
ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሏል፡፡
2. በክሱ በተራቁጥር 1 ሥር የተመለከተውን የመሬት ይዞታ አስመልክቶ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል
ፀንቷል፡፡
3. 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ ስለሆነ በክሱ በ2ኛ እና 3ኛ ተራቁጥር ሥር
የተመለከቱትን የመሬት ይዞታዎች አመልካች ለተጠሪ ሊለቁ አይገባም በማለት ተወስኗል፡፡
4. በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰ/መ/ቁጥር 201201


ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሀምሌ 30 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡-እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

ተጠሪ ፡- አቶ ጥላሁን ይስማ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርምራ ሲሆን በዚህ አግባብም ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ይዞታን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው
የሲያ/ዋዩ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች ለአከራካሪው ቤትና ይዞታ በተጠሪ ስም የባለቤትነት ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት ሰርቶ ሊሰጠው ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ስላመለከተ
ነው፡፡አመልካች በሲያ/ዋዩ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪ ህዳር 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፈው በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም አቶ ማናዜ መኮንን እና ወ/ሮ
እትሞላሽ ደመቀ የነበራቸውን ጋብቻ በፍርድ ቤት አፍርሰው የጋራ ንብረታቸው የሆነውን በደነባ 01

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቀበሌ ሐ ዞን የሚገኘውን ቤትና ቦታቸውን ከተካፈሉ በኋላ ለአቶ ማናዜ የደረሳቸውን 187 ካሜ ቤትና
ቦታ በ27/10/2006 ዓም በተደረገ ውል ገዝቼ አመልካችም ውል አዋውሎን፤ውሉን አፅድቆ በስሜ
በማዞር የግንባታ ፈቃድ ሰጥቶኝ የነበረውን ቤት አፍርሼ ቤት የሰራሁበት ሲሆን ለይዞታዬ ካርታ
እንዲሰጠኝ ስጠይቀው የቀበሌ ቤት አብሮ ስለተሸጠልህ አልሰጥህም ያለ ሲሆን ያሉትን አስተዳደራዊ
መንገዶች ሁሉ ተጠቅሜ ጥያቄን ባቀርብም ምላሽ ያላገኘሁ በመሆኑ ለቤትና ለቦታው የባለቤትነት
ማስረጃ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዲሰጡ በታዘዘው መሰረት አመልካች በሰጠው መልስም የንብረቱ ክፍፍል
ሲፈፀም ያላካፈልኩ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ባልና ሚስቱ የያዙት ቦታ 542.58 ካሜ ሆኖ በሰነድ
አልባ አጣሪ0 ኮሚቴ ተጣርቶ ህጋዊ ይዞታቸው 432 ካሜ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ቀሪው 110 ካሬ ወደ
መሬት ባንክ እንዲገባ የተወሰነ ሲሆን ባልና ሚስቱ ሲካፈል ለተጠሪ ሻጭ 216 ካሜ ይደርሳቸው የነበረ
ቢሆንም የሻጭ የቀድሞ ሚስት 364.5 ካሜ የያዙ በመሆኑ በፕላን 64.18 ካሜ ተነስቶ 300.32 ካሜ
የያዙ ሲሆን በሰነድ አልባ አጣሪ ኮሚቴው ተጣርቶ ተጠሪ ከያዘው 187 ካሜ ቦታ 110.58 ካሜ የቀበሌ
መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ በቀበሌ ቦታ ላይ ለሰራው ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ሊሰጠው አይገባም ተብሎ
ይወሰንልን በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካች ባቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስም ተጠሪ የያዘውን
የቀበሌ ቦታ የሆነውን 110.58 ካሜ ይዞታ የሰራውን ቤት አፍርሶ እንዲያስረክብ ይወሰንልን በማለት
አመልክቷል፡፡

ተጠሪ ለቀረበባቸው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስም ቦታው የቀበሌው ቦታ ስላልሆነና ስለመሆኑም ያልተረጋገጠ
ስለሆነ፤ቦታውን በሽያጭ ውል አግኝቼው በስሜ የምገብርበት በመሆኑና ሽያጩ ህጋዊ መሆኑን
አመልካች አረጋግጦልኝ የያዝኩት በመሆኑ አመልካች ክሱን ለማስረዳት ያቀረበው ማስረጃ ስርዝ ድልዝ
ያለው በመሆኑና በሰነድ አልባ ኮሚቴ ተጣርቶ የቀረበው ማስረጃም ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ የቀረበው
42.58 ካሜ ሆኖ እያለ በአመልካች 110.58 ካሜ መጠየቁ አግባብ ባለመሆኑ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ
ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔም አከራካሪው ቤትና
ቦታ ለተጠሪ በሽያጭ ሲተላለፍ በባለሙያ ተለክቶና ታይቶ ውሉ በማዘጋጃ ቤቱ ተደርጎ የፀደቀ
መሆኑን፤ቤትና ቦታው በተጠሪ ስም ተመዝግቦ ግብር የሚገብሩበት ፤ግንባታ በተጠሪ ሲፈፀምም
በአመልካች ተፈቅዶለት መሆኑን የቀረቡት ማስረጃዎች የሚያሳዩ መሆኑን፤አመልካች የቀበሌው ይዞታ
ምን ያህል እንደሆነ ምን ያህሉ በተጠሪ ተቀንሶ እንደተያዘ ይዞታውም በቀበሌው መመዝገቡን የሚያሳይ
ማስረጃ በአመልካች አለመቅረቡ አመልካች በደፈናው 110.58 ካሜ ተጠሪ ወደ ቀበሌው ገብቶ ያዘ
በማለት መጠየቃቸውን የሚያሳይ መሆኑን ፤የሰነድ አልባ መሬት አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ከምስክሮቹ
ቃል ጋር የማይጣጣም ስርዝ ድልዝ ያለበት እምነት የማይጣልበት መሆኑን በመጥቀስ የአመልካችን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውድቅ አድርጎ አመልካች ለአከራካሪው ቤትና ቦታ ለተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት ሊሰጥ ይገባል በማለት ወስኗል ፡፡ይህ ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ፀንቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ ጥር 04 ቀን 2013 ዓም በተፃፈ ባቀረበው የሰበር አቤቱታም ተጠሪ
ቤትና ቦታውን ከአቶ ማናዜ መኮንን የገዛው መሆኑና አመልካችም የሽያጭ ውሉን መዝግቦ የግንባታ
ፈቃድ የሰጠው ቢሆንም ይህንን ቤትና ቦታ ለተጠሪ የሸጠለት ግለሰብ ቦታው ነባር ይዞታ በመሆኑ
ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የሌለውና የተሟላ ሰነድ የሌለው መሆኑን ሻጩ በስር ፍርድ ቤት ምስክር ሆኖ
ያስረዳ በመሆኑ የክልሉ እንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ ባወጣው የከተማ ቤትና ስመ ንብረት
ዝውውር አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 4/2006 አንቀፅ 5(1) መሰረት የባለቤትነት ማስረጃ የሌለው ይዞታ
እና ቤት ስመ ንብረት ዝውውር ሊፈፀምበት እንደማይገባ የሚደነግግ ሆኖ እያለ በወቅቱ የነበረው
የማዘጋጃ ቤቱ ባለሙያ መመሪያውን በግልፅ በመተላለፍ ህጋዊ ሰነድ የሌለውን ይዞታና ቤት ሽያጭ
ውል መመዝገቡና ለተጠሪ የግንባታ ፈቃድ መስጠቱ ተገቢነት የሌለው ህገወጥ ተግባር በመሆኑ ፤

ለይዞታው ካርታ ተሰጥቶ ቢሆን እንኳ የአስተዳደር አካሉ ካርታውን ለማምከን የሚችል መሆኑ
በሰ/መ/ቁ.57044 አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቶ እያለ የሽያጭ ውሉ ስለተመዘገበና የግንባታ ፍቃድ
ስለተሰጠው ብቻ ፤የሰነድ አልባ አጣሪ ኮሚቴው አቶ መኮንን ለተጠሪ በሽያጭ 110.58 ካሜ የሆነ
የቀበሌውን ይዞታ በማጠቃለል ያስተላለፉ መሆኑን አረጋግጦ እያለ ተጠሪ ይህ ይዞታ የቀበሌው
አለመሆኑን ባላስረዱበት በየይዞታ ማረጋገጫ ለተጠሪ እንዲሰጥ መወሰኑ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች
መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሸሮ አመልካች
ለተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርቶ ሊሰጥ አይገባም ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡

ህጋዊ ይዞታው 432 ካሜ ሆኖ ተጠሪ የገዛው ሲጣራ 542 ካሜ በመሆኑ የመንግስት ይዞታ 110 ካሜ
ስለያዘ የባለቤትነት ማረጋገጫ ልሰጥ አይገባም በማለት አመልካች እየተከራከረ የባለቤትነት ማረጋገጫ
ለተጠሪ እንዲሰጥ የተወሰነበትን አግባብ ለማጣራት ለዚህ ሰበር ችሎት ቀርቦ እንዲታይ በመታዘዙ ግራ
ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ ተጠሪ የገዛሁት 187 ካሜ ብቻ ሆኖ እያለ
አመልካችም ተጠሪ የገዛው 542 ካሜ ነው ብሎ ባልተከራከረበት የማስቀረቢያ ጭብጥ በማድረግ 542
ካሜ እንደገዛው ተደርጎ ጭብጥ መያዙ አግባብ አይደለም፤ተጠሪ ለአቶ ማናዜ የደረሳቸውን 187 ካሜ
ቤትና ቦታ በ27/10/2006 ዓም በተደረገ ውል ገዝቼ አመልካችም ውል አዋውሎን፤ውሉን አፅድቆ በስሜ
በማዞር የግንባታ ፈቃድ ሰጥቶኝ የነበረውን ቤት አፍርሼ ቤት የሰራሁበት ለአመታትም በስሜ ግብር
የገበርኩበት በመሆኑ፤የአቶ ማናዜ መኮንን እና ወ/ሮ እትሞላሽ ደመቀ ጋብቻ ፈርሶ ንብረት ክፍፍልን
በተመለከተ ያደረጉት ስምምነት በፍርድ ቤት ፀድቆ አመልካች በፀደቀው የግልግል ውል መሰረት
ቦታውን ለክቶ አካፍሎ ድርሻቸውን በየስማቸው መዝግቦ ግብር በድርሻቸው ልክ እንዲገብሩ ያደረገ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሆኑን በስር ፍርድ ቤት ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ ያስረዳው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ
ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም
ከሰበር ቅሬታው አኳያ እና ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ይዘት አንፃር አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ
ተመርምሯል፡፡በመሰረቱ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ ለተጠሪ የይዞታ
ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰርቶ ሊሰጥ ይገባል በማለት ለግራ ቀኙ ክርክር እልባት የሰጠው ማስረጃን
የመስማት፤የመመርመርና የመመዘን ስልጣኑን ተጠቅሞ በደረሰው መደምደሚያ በአመልካች የሰበር
አቤቱታው ላይ ጭምር ከታመነው ተጠሪ ቤትና ቦታውን ከአቶ ማናዜ መኮንን ሲገዙ አመልካችም
የሽያጭ ውሉን መዝግቦ የግንባታ ፈቃድ ከመስጠቱ በተጨማሪ ቤትና ቦታው በተጠሪ ስም ተመዝግቦ
ግብር የሚገብሩበት መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባትና በዋነኝነትም አመልካች የቀበሌው ይዞታ ምን
ያህል እንደሆነ ምን ያህሉ በተጠሪ ተቀንሶ እንደተያዘ በግልፅ በክሱና ማስረጃው አለማሳየቱን
ይዞታውም በቀበሌው መመዝገቡን የሚያሳይ ማስረጃ በአመልካች አለመቅረቡን እንዲሁም ይዞታውን
በተመለከተ የቀረበው የሰነድ አልባ ይዞታ አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ከምስክሮቹ ቃል ጋር የማይጣጣም እና
ስርዝ ድልዝ ያለበት በዚህም ምክንያት እምነት የማይጣልበት መሆኑን በመጥቀስ መሆኑን የስር ፍርድ
ቤት ውሳኔ ያሳያል፡፡

የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን የመስማት፤የመመዘንና የመመርመር ስልጣናቸውን በመጠቀም በፍሬ ነገር
ጉዳይ ላይ የሚደርሱበት መደምደሚያ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10(1) እና በህገ
መንግስታችን አንቀፅ 80(3)(ሀ) መሰረት በስር ፍርድ ቤቶች የተፈፀመን መሰረታዊ የህግ ስህተት
የማረም ስልጣን ብቻ በተሰጠው በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የሚታረሙ ሆነው ስላልተገኙ የሚከተለው
ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

1.የሲያ/ዋዩ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.0114877 የካቲት 26 ቀን 2012 ዓም የሰጠው ፍርድ እና ይህንን


ፍርድ በማፅናት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.0133422 መስከረም 27 ቀን 2013 ዓም
እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.03-11887 ህዳር 17 ቀን 2013 ዓም
የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ፀንተዋል፡፡

2.ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ክርክሩ ተገቢውን እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 201235

ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

ቀነአ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች፡- አብዲ አሚን አሊሾ

ተጠሪዎች፡- 1ኛ. አቶ ሙሳ ኡስማን ዑመር

2ኛ. ወ/ሮ ደሃቦ አብደላ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍ ር ድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 06/05/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል
መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 75621 በቀን 14/12/2011 ዓ.ም እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ
ፍ/ቤት በመ/ቁ 16162 በቀን 08/04/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የጀመረው በፌደራል መጀመሪያ
ደረጃ ፍ/ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት የአሁን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት አቤቱታ ነው፡፡

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው አመልካች በቀን 03/11/2011 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ


በድሬዳዋ አስተዳደር ጀሎ በሊና ገጠር ቀበሌ ልዩ ስፍራው ኢጃነኒ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ
የሚገኝ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰ 1000 ካ/ሜ በግምብ አጥር የታጠረ ይዞታና ግምቱ 50,000.00
ብር የሆነ መኖሪያ ቤት ያለኝ ሲሆን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በእውነት በእጄ አድርጌ እያዘዝኩበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እገኛለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ተከሳሾች ምንም አይነት መብት ሳይኖራቸው ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ
በይዞታው ላይ በሃይል የተደገፈ ሁከት እየፈጠሩብኝ ይገኛሉ፡፡ በተደጋጋሚ ሁከቱን እንዲያቆሙ
በግልም ይሁን በሽማግሌ ባስጠይቃቸውም ሁከቱን ሊያቆሙ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የፈጠሩትን
ሁከት እንዲወገድ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪዎች በሰጡት መልስ ክርክር የተነሳበት ይዞታ ተከሳሾችና ቤተሰቦቻችን ለ17 አመት
የምንገለገልበት የግል ይዞታችን እንጂ የከሳሽ ይዞታ አይደለም፡፡ አከራካሪው ይዞታ በእኛ እጅ
የሚገኝ ራሳችን የምናስተዳድረው ነው፤ ከሳሽ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 መሰረት ይዞታውን በእጁ አድርጎ
የማያስተዳድረው በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149 መሰረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሊያቀርብ
አይችልም፡፡ ከሳሽ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን በቀርሳ ወረዳ ወተር ከተማ ነዋሪ ሆኖ
አከራካሪው ይዞታ የሚገኝበት በድሬዳዋ አስተዳደር ጀሎ በሊና በቀበሌ ያለውን ይዞታ ከ2005 ዓ.ም
ጀምሮ በእጁ አድርጎ የሚይዝበት ምክንያት የለም፡፡ ከሳሽ ከህግም ይሁን ከውል የመነጨ መብት
የለውም፡፡ በመሆኑም የከሳሽ ክስ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ከቀረቡት የከሳሽና
ተከሳሾች ምስክሮች እንዲሁም ከጀሎ በሊና ገጠር ቀበሌ የመጣው የሰነድ ማስረጃ አንጻር ሲመዘን
የእርሻ መሬቱ አመጣጥ የ1ኛ ተከሳሽ የነበረ መሆኑ በኋላ ላይ ግን 1ኛ ተከሳሽ ለከሳሽ በብር
100,000.00 ባዶ መሬት የሸጠለት መሆኑ፤ በዚህም መነሻነት ከሳሽ በግምት 1000 ካ/ሜ
የሚሆነውን ከ1ኛ ተከሳሽ የገዛውን ባዶ መሬት በግንብ ያጠረው መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከሳሽ
ይህን ከ1ኛ ተከሳሽ የገዛውን ባዶ መሬት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በግንብ አጥሮ በይዞታው ስር አድርጎ
የሚጠቀምበት መሆኑም ተረጋግጧል፡፡ ከሳሽ አከራካሪውን ይዞታ በሽያጭ ውል ከ1ኛ ተከሳሽ
ያገኘው መሆኑን ከከሳሽ ምስክሮች የተረጋገጠ በመሆኑ የከሳሽ ይዞታ መብት ከውል የመነጨ
መሆኑ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡ ከሳሽ ከ1ኛ ተከሳሽ የገዛው መሬት ባዶ መሬት በመሆኑ ህገ መንግስቱን
አንቀጽ 40(3) እና የፍ/ብ/ህ/ቁ 1678(ለ) የጣሰ ነው፤ በመሆኑም ውሉ እንዲፈርስ ከተዋዋዬች አንዱ
ወይም ማንኛውም ጥቅም ያለው ሰው መጠየቅ እንደሚችል የፍ/ብ/ህ/ቁ 1808(2) አስቀምጧል፡፡
በመሆኑም ውሉ ፈራሽ ነው፡፡ ከሳሽ አከራካሪውን ይዞታ ያገኘው ህገወጥ ውል መሰረት በማድረግ
ስለሆነ ውሉ ከመጀመሪያውኑ እንዳልተደረገ የሚቆጠር ነው፡፡ ህገወጥ በሆነ ውል አማካኝነት
የተቀባበሉትን በፍ/ብ/ህ/ቁ 1815(1) መሰረት ከውሉ በፊት ወደ ነበሩበት ሊመለሱ ይገባል፡፡ ከሳሽ
በውሉ አማካኝነት ለ1ኛ ተከሳሽ የከፈለው ገንዘብ ብር 100,000.00 ከ1ኛ ተከሳሽ ሊመለስለት
ይገባል፣ በምላሽ የተረከበውን መሬት በነበረበት ሁኔታ ለ1ኛ ተከሳሽ ሊመልስ ይገባል፡፡ ስለሆነም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተከሳሾች በህገ ወጥ ውል ወይም በፈራሽ ውል ያስተላለፉትን መሬት መልሰው መያዛቸው የሁከት


ተግባር አይደለም፡፡ ሊወገድ የሚገባው ሁከት የለም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ከሳሽ ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም ለክርክር
መነሻ የሆነውን ይዞታ በተመለከተ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 መሰረት በእውነት የሚያዝበት የይ/ባይ ይዞታ
ነው? ይ/ባይ በዚህ ይዞታ ላይ የህውከት ይወገድልኝ አቤቱታ ሊያቀርብበት የሚችል ነው? የስር
ፍርድ ቤት ግራቀኙ ወደነበሩበት እንዲመለሱ በማለት የሰጠው ውሳኔ ከቀረበው ክስ እና ከግራቀኙ
ክርክር አንፃር ተገቢ ነው? የሚሉ ጭብጦችን በመያዝ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በሰጠው ውሳኔ ቀበሌው
በጉዳዩ ላይ በጻፈው ማስረጃ ይ/ባይ እና 1ኛ መ/ሰጪ በነበራቸው የሽያጭ ውል መሰረት ይ/ባይ
ይህን ይዞታ የያዘው መሆኑን ከመግለፅ ውጪ አከራካሪው ይዞታ የይ/ባይ መሆኑን አላረጋገጡም፤
ይ/ባይም በምን አግባብ ይህን ይዞታ የያዘ ስለመሆኑ አላረጋገጠም፤ ቦታው የገጠር መሬት
እንደመሆኑም የገጠር መሬት ሊገኝባቸው በሚገኝባቸው መንገዶች ስለመገኘቱም የቀረበ ማስረጃ
የለም፤ ቦታው ወደ ከተማ የተከለለ ነው የሚባል ከሆነም አሁንም ይህንኑ ሊያረጋግጥ የሚችል
ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረበም፡፡ የስር ፍርድ ቤት ይዞታው በሽያጭ የተገኘ ስለመሆኑ ቢገልፅም
ህጋዊ የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልቀረበም፡፡ በአጠቃላይ ይ/ባይ በእውነት
ሊያዝበት የሚችል የራሱ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባለመቅረቡ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 እና 1149
መሰረት ሁከት ይወገድልኝ በማለት አቤቱታውን ሊያቀርብ የሚችልበት የህግ መሰረት የለም፡፡
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት የለውም፡፡ ግራቀኙ ወደ ነበሩበት ይመለሱ
በማለት የሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ይ/ባይ በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ሁከት ይወገድልኝ
የሚል ሲሆን በመ/ሰጪ በኩልም የቤት ሽያጭ ውል ወይንም የመሬት ሽያጭ ውልን በተመለከተ
የቀረበ ክርክር የለም፡፡ በመሆኑም በሁለቱም በኩል ውልን በተመለከተ የቀረበ ክርክር ባለመኖሩና
በፍ/ብ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 182(2) አንጻር ውሳኔ ሊሰጥ የሚገባው ከተጠየቀው ዳኝነት አንጻር በመሆኑ
የስር ፍርድ ቤት ይህን በማለፍ ግራ ቀኙ ወደ ነበሩበት ይመለሱ በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢነት
የለውም፡፡ በሌላም በኩል የህገወጥ መሬት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ በአግባቡ በጭብጥነት ተይዞ
በማስረጃ አጣርቶ ክርክር ሳይደረግበት ወደ ነበሩበት ይመለሱ በማለት የተሰጠው ውሳኔና
የተደረሰበት ድምዳሜ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 182(2) ያላገናዘበ ነው፡፡ በአጠቃላይ የስር ፍርድ ቤት
ውሳኔ ተሻሽሏል፤ ይ/ባይ ህውከት ፈጠሩብኝ በማለት ያቀረቡት የህውከት ይወገድልኝ አቤቱታ
ውድቅ ተደርጓል፤ የስር ፍ/ቤት ግራ ቀኙ ወደ ነበሩበት ይመለሱ በማለት የሰጠው ውሳኔ አቤቱታ
ባልቀረበበት ጉዳይ እና የክርክሩ ጭብጥ ባልሆነበት ጉዳይ የተሰጠ በመሆኑ ተሽሯል በማለት
ወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች በቀን 06/05/2013 ዓ/ም ባቀረቡት
ማመልከቻ ተፈፀመ የሚሉትን ስህተት ዘርዝረው የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሽሮ ተጠሪዎች እየፈጠሩ
ያለውን ሁከት ያቁሙ ተብሎ እንዲወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡ ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ እንዲቀርብ
ተደርጎ ግራቀኙ የስር ክርክራቸውን በማጠናከር መልስና የመልስ መልስ ተለዋውጠዋል፡፡

ከፍ ሲል ባጭሩ የገለፅነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ያቀረቡትን ክርክር፤


ቅሬታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የስር ፍርድ ቤቶች
ባሳለፉት ውሳኔ የተፈፀመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል፡፡

ከክርክሩ መረዳት እንደሚቻለው አመልካች ባቀረቡት ክስ ተጠሪዎች ምንም አይነት


መብት ሳይኖራቸው ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በይዞታየ ላይ በሃይል የተደገፈ ሁከት እየፈጠሩብኝ
ስለሆነ የፈጠሩት ሁከት እንዲወገድ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪዎች በበኩላቸው
አከራካሪው ይዞታ በእኛ እጅ የሚገኝ ራሳችን የምናስተዳድረው ነው፤ አመልካች ይዞታውን በእጁ
አድርጎ የሚያስተዳድረው አይደለም፤ በይዞታው ላይ ከህግም ይሁን ከውል የመነጨ መብት
የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት ከፍ ሲል እንደተገለፀው አመልካች ይዞታውን በሽያጭ ውል ከ1ኛ


ተጠሪ ያገኙ መሆኑ በአመልካች ምስክሮች ተረጋግጧል፤ ውሉም ህገወጥ በመሆኑ ፈራሽ ነው፤
ህገወጥ በሆነ ውል አማካኝነት የተቀባበሉትን በፍ/ብ/ህ/ቁ 1815(1) መሰረት በመመላለስ ከውሉ
በፊት ወደ ነበሩበት ሁኔታ ሊመለሱ ይገባል፤ ተጠሪዎች በህገ ወጥ ውል ያስተላለፉትን መሬት
መያዛቸው የሁከት ተግባር አይደለም በማለት ወስኗል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ችሎት በበኩሉ ውሳኔውን
አሻሽሎ አመልካች በእውነት ሊያዝበት የሚችል የራሱ ይዞታ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
ባለመቅረቡ ሁከት ይወገድልኝ በማለት አቤቱታውን ሊያቀርቡ አይችልም፤ ህውከት ፈጠሩብኝ
በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ሊደረግ ይገባል፤ ነገር ግን የስር ፍ/ቤት ባልተጠየቀ ዳኝነትና
ከክርክሩ ውጪ የውሉን ጉዳይ ተመልክቶ ግራ ቀኙ ወደ ነበሩበት ይመለሱ በማለት የሰጠው ውሳኔ
ተሽሯል በማለት ወስኗል፡፡

በመሰረቱ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሊቀርብ የሚችለው በይዞታው በእውን


በሚያዘው ሰው ሰላማዊ የይዞታ አጠቃቀም ላይ ችግር ወይም መሰናክል ሲፈጠር ስለመሆኑ
ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1140 እና 1149 ድንጋጌዎች ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡ በዚህ መልኩ ለቀረበው ክስ
የሚሰጠው ዳኝነትም የተነሳው ህውከት እንዲወገድ እንዲሁም ስለደረሰ ጉዳት ኪሳራ እንዲከፈል
ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ተከሳሽ አድራጎቱን የሚፈቅድ መብት እንዳለው በፍጥነትና በማይታበል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዓይነት ካላስረዳ በቀር ህውከቱ እንዲወገድ እንደሚታዘዝ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1149(3) ሥር ተመልክቷል፡፡


በአንፃሩም ሁከቱን ፈጠረ ከተባለው ሰው ጋር የተደረገ በውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ካለ
ግንኙነቱ የሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ ተለይቶ ራሱን ችሎ ዳኝነት ሊሰጥበት ይገባል፡፡

በተያዘው ጉዳይ በአከራካሪው ይዞታ አመልካች በእውነት ሊያዝበት የሚችል የራሱ


ይዞታ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያልቀረበ ስለመሆኑ ፍሬ ነገርን ለማጣራት እና ማስረጃ
ለመመዘን በህግ ስልጣን በተሰጣቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም ህውከት ይወገድልኝ
ተብሎ የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲሆን መወሰኑ ከፍ ሲል የተመለከተውን የህጉን ይዘትና መንፈስ
የተከተለ በመሆኑ የህውከት ይወገድልኝ ክሱን ውድቅ በማድረግ ረገድ የተላለፈው ውሳኔ የህግ
ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚሰኝ ሆኖ አላገኘንውም፡፡

በሌላ በኩል አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር አድርገውታል የተባለው የሽያጭም ሆነ ሌላ


ውል ህጋዊነት እንዲሁም ውል ፈርሶ ግራቀኙ ከውሉ በፊት ወደነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ በስር
ፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን ከህውከት ክሱ ጋር ተያይዞ ዳኝነት እንዲሰጥበት የቀረበ አቤቱታ
ባለመኖሩና በውል ላይ የተመሰረተው ግንኙነት ይኸው በሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ እራሱን
ችሎ ሲጠየቅ ዳኝነት ሊሰጥበት የሚገባ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ከተጠየቀው ዳኝነት በማለፍ
ያሳለፈው ውሳኔ ክርክሩ የሚመራበትን ስርዓት እና ከላይ የተጠቀሱትን የህጉን ድንጋጌዎች ይዘትና
መንፈስ የተከተለ ባለመሆኑ ውሳኔው በዚህ ረገድ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ በይግባኝ
ሰሚው ፍርድ ቤት መታረሙ በአግባቡ ነው፡፡

በአጠቃላይ ይግባኝ ሰሚው የፌ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈው ውሳኔ የህግ ስህተት


የተፈፀመበት አይደለም ብለናል፡፡ ተከታዩንም ወስነናል፡፡

ው ሳ ኔ

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 16162 በቀን 08/04/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔውሳኔ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348/1/ መሠረት ፀንቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2. አመልካች ህውከት ይወገድ በሚል ያቀረቡት ክስ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው፡፡

3. በአንፃሩ አመልካችና 1ኛ ተጠሪ አደረጉ የተባለውን ውል በተመለከተ አቤቱታ ሲቀርብ የውል


ግንኙነቱ ከሚገዛበት የውልና የህግ አግባብ አንፃር ታይቶ ዳኝነት ሊሰጥበት ከሚገባ በቀር
አመልካች ካቀረቡት የሁከት ይወገድልኝ የዳኝነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በስር ፍርድ ቤት
ውሳኔ መሰጠቱ የተጠየቀውን ዳኝነት እና ህጉን የተከተለ አይደለም ብለናል፡፡

4. በዚህ ችሎት ስለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሰ/መ/ቁጥር 201235
ቀን 28/3/2014 ዓ/ም

ስሜ በተራ ቁጥር 3ኛ ላይ የምገኘው ዳኛ የልዩነት ሀሳቤን እንደምከተለው አስቀምጫለሁ


ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና
የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጡት ውሳኔ ላይ የአሁን አመልካች ቅሬታ በማቅረቡ ሲሆን በስር ፍ/ቤት
በነበረው ክርክር የአሁን አመልካች በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ የአሁን ተጠሪ
በመሬት ይዞታዬ ላይ ሁከት ስለፈጠረብኝ ሁከት ያቁምልኝ ሲል ጠይቋል፡፡ የአሁን ተጠሪም የፈጠርኩት
ሁከት የለም ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም
አከራክሮ የአሁን አመልካች ክስ ያቀረበበት የመሬት ይዞታ ከተጠሪ በሽያጭ ውል አግኝቻለሁ የሚል
በመሆኑ የአሁን አመልካች በህገ መንግስቱ የተከለከለውን የመሬት የሽያጭ ውል መሰረት አድርጎ
አግኝቻለሁ በሚለው የመሬት ይዞታ ላይ ሁከት ተፈጥሮብኛል ሲል የሁከት ክስ ሊያቀርብበት የማይችል
ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 36645 በሰጠው አስገዳጅ የህግ
ትርጉም መሰረት በህገ ወጥ መንገድ ያዝኩ በሚለው መሬት የሁከት ክስ ሊያቀርብበት አትችልም፡፡
እንዲሁም ህገ ወጥ ውል በክርክርነት የቀረበ እንደሆነ ሌላ ክስ ማቅረብ ሳያስፈልግ በተያዘው የሁከት ክስ
መዝገብ ላይ ተቀባይነት እንደሌለው መወሰን እንደሚቻል የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁጥር 79394 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የአሁን አመልካች በሽያጭ ውል ይዣለሁ ሲል
ያቀረበው የሁከት ክስ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ክሱ ውድቅ ነው ሲል ወስኗል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ
ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔን እንደተገነዘብኩት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው አስገዳጅ
የህግ ትርጉምን መሰረት በማድረግ የአሁን አመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ ክፍል ተገቢ
ሆኖ፣ ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ሲል የሰጠው ውሳኔ ክፍል ግን ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው እላለሁ፡፡
ምክንያቱም የመሬት ሽያጭ ውል በህገ መንግሰቱ የተከለከለ ህገ ወጥ ውል ነው፡፡ የመሬት ሽያጭ ውል
ከመጀመሪያውኑ እንደውል የማይቆጠር ፈራሽ ውል በመሆኑ በቀረበው የሁከት ክስ ክርክር ውሉ
ተቀባይነት እንደሌለው ውሳኔ ሲሰጥ በህገ ወጥ ውሉ ካለ አግባብ ብልጽጓል የሚል ወገን ካለ በዚሁ አግባብ
ከመጠየቅ በቀር ህገ ወጥ የመሬት ሽያጭ ውል በፍርድ ቤት ውሳኔ ፈራሽ እንደተደረገ ተወስዶ ወደ
ነበሩበት እንዲመለሱ በሚል ውሳኔ መስጠቱ ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም፡፡ ሌላው የአሁን አመልካች
ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም አከራክሮ በሰጠው ውሳኔ
የአሁን አመልካች ላቀረበው የሁከት ክስ ይዞታው በእጁ የነበረ ስለመሆኑ አላስረዳም፡፡ የፌደራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባልተጠየቀ ዳኝነት ስለ ውል ጉዳይ አንስቶ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ ባለመሆኑ
ሊታረም ይገባል ብሎ በውጤት ደረጃ የፌደራል የመጀሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል፡፡
የአሁን አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስረጃ የመስማትና
የመመዘን በተሰጠው ሥልጣን አንጻር የአሁን አመልካች ክስ ያቀረበበት የመሬት ይዞታ በእጁ ያልነበረ
መሆኑን አረጋግጦ ሁከት የለም ብሎ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን
አመልካች ክስ ያቀረበበትን የመሬት ይዞታ ከአሁን ተጠሪ ላይ በሽያጭ ውል የገዛው ስለመሆኑ በማስረጃ
ያረጋገጠ በመሆኑና የመሬት ሽያጭ ውል በህገ መንግስቱ የተከለከ ስለሆነ ከመጀመሪያውኑ ፈራሽ በመሆኑ
የውል ይፍረስልኝ ክስ ማቅረብ ሳያስፈልግ በተያዘው መዝገብ ላይ ሕገ ወጥ ውሉን ውድቅ ማድረግ
እንደሚቻል የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 79394 ላይ በሰጠው አስገዳጅ የህግ
ትርጉም መሰረት የአሁን አመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ ስሀተት ያልተፈጸመበት ሆኖ
እያለ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የህገ ወጥ የመሬት ሽያጭ ውል ከክርክራቸው ውጪ ነው ሲል የሰጠው
እርማት ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም መጀመሪያውኑ የአሁን አመልካች ክስ ማቅረብ መቻል የሚገባውና
ይህን ባላሟላበት ይዞታው በማን እጅ ነበር ወደ ሚለው ጉዳይ ማለፍ አስፈላጊም ስለማይሆን ነው፡፡ ይህም
ሆኖ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ከላይ በተገለጸው መሰረት እርማት በማድረግ በውጤት ደረጃ ክሱ ውድቅ
መደረጉን ማጽናት ሲገባ የመሬት ሽያጭ ውል መጀመሪያ በፍርድ ቤት ውሳኔ ፈራሽ መደረግ ነበረበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚል ምክንያታዊ እርማት ውሳኔ መስጠቱ እንደ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ህገ ወጥ
የመሬት ሽያጭ ውል እንዲፈርስ ክስ ሊቀርብ ይገባል ብሎ ውሳኔ መስጠት የመሬት ሽያጭ ውል
ከመጀመሪያውኑ ፈረሽ መሆኑ እየታወቀ ካለአግባብ እንደገና ግራ ቀኙን ለሌላ ያልተገባ ክርክር የሚጋብዝ፣
ላልተገባ ወጪ እና ተጨማሪ ጊዜ ብክነት የሚዳረግ፣ ህገ ወጥ የመሬት ሽያጭ ውልን እውቅና የሚሰጥ፣
የራሱን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 79394 ላይ የሰጠውን አስገዳጅ ትርጉም
የሚጻረር፣ የውል መሰረታዊ መርሆን የሚጻረር እና የፌደራል ህገ መንግስትን የሚጻረር ውሳኔ ስለሚሆን
ተገቢነት ያለው ውሳኔ አይደለም እላለሁ፡፡

የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁጥር 201252
መስከረም 28 ቀን 2014ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ


ፀሐይ መንክር
ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ፶ አለቃ ሰቦቃ መገርሳ - ቀርበዋል

ተጠሪ፡- ወ/ሮ እቴነሽ ወንድሙ - አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 333318 ሕዳር
1ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው
ስለጠየቁ ነው።

ክርክሩ በተጀመረበት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፊንፊኔ ዙሪያ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች
አሻሽለው ባቀረቡት ክስ ሆሎታ ከተማ ጎሮ ቄረንሳ ቀበሌ አዋሣኙ በክሱ ላይ የተዘረዘረውንና በ250 ካሬ ቦታ
ላይ በእንጨት እና በጭቃ የተሰራውን 3 ክፍል የግል ቤታቸውን ተጠሪ የወንድማቸው ሚስት ስለሆኑ
የራሳቸውን ቤት እስከሚሰሩ ድረስ በነፃ እንዲኖሩበት ሰጥተዋቸው ሲኖሩበት ቆይተው እንዲለቁላቸው ከ2003
ዓ/ም ጀምሮ ሲጠየቁ ፍቃደኛ ስላልሆኑ በፍርድ ሀይል እንዲለቁ እንዲወሰንላቸው ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች በዚህ ጉዳይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 214887
ክስ አቅርቦባቸው የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ ስለሆነ በድጋሚ ክስ ሊቀርብበት የማይገባ መሆኑንና የቤቱ
ግምትም በባለሙያ የተገመተ አለመሆኑን በመጀመሪያ መቃወሚያነትና ይዞታዉ በአመልካች ስም የተመዘገበ
ቢሆንም አመልካች የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ስለነበሩ ሰራዊቱ ሲበተን ስራ በማጣታቸው በ1984
ዓ.ም የስራ መፈለጊያ እንዲሆናቸው መሬቱን ለተጠሪና ለባለቤታቸው መሬቱን ትተው ገንዘብ ተቀብለው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ድሬዳዋ መሔዳቸውን በዚህ መሰረት በመጀመሪያ በ6 ቆርቆሮ ቤት ሰርተው ቆይተው ይህን ቤት በ1991ዓ.ም
አፍርሰው ሌላ ሁለት 2 ክፍል ቤት ስርተው ለ22ዓመታት ያለ ተቃውሞ እየኖሩበት ሣለ በ1994 ዓ.ም
ባለቤታቸው ስለሞቱ አመልካች ለለቀሶ ሲመጣ የቤቱን ካርታ ላስተካክለው በሚል ከልጃቸው አታለው
ከተቀበሉ በኋላ በስማቸው ግብር መክፈል ጀመሩ እንጅ ለ22 ዓመታት ስጠቀምበት ቆየሁ የሚለው
የአመልካች ክስ እውነት አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የስር ፍርድ ቤት የተጢሪን የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ ውድቅ አድርጎ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ቤት አመልካች ሰርቶ በነፃ እንዲኖሩበት ሰጥቷቸው
አለቅም ብለዋል ወይስ ተጠሪ ራሳው ሰርተው የሚኖሩበት ቤት ነዉ? በማን መቼ ተሰራ? የሚለዉን
የክርክር ጭብጥ ይዞ የግራ ቀኝ ምስክሮች እና የሰነድ ማስረጀዎች መርምሯል፡፡

በቀረበዉ የሰነድ ማስረጃ የቤቱ ካርታ በአመልካች የተሰጠና ግብርም በአመልካች ስም የሚከፈል መሆኑ
ቢረጋገጥም አመልካች ለክርክሩ ምንስዔ የሆነውን ቤት ራሱ እንደሰራ ቢከራከርም በቀረቡት የግራ ቀኙ
ምስክሮች ቤቱን ተጠሪ ሰርተው እየኖሩበት ስለመሆኑ በመረጋጡና አመልካች ተጠሪ ቤቱን ሲሰሩ
እንደተቃወመ ያልተከራከረ በመሆኑ በፍትሐ ሕግ ቁጥር 1179/1/ ድንጋጌ መሰረት የቤቱ ባለቤት ተጠሪ
ናቸው ሲል የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጓል፡፡ በዚህ ውሣኔ ቅር የተሰኙት አመልካች የይግባኝ እና የሰበር
አቤቱታቸውን በየደረጃው ለሚገኙት የክልሉ ፍርድ ቤቶች አቅርበው ተጠሪም ጥሪ ተደርጎላቸው ከተከራካሩ
በኋላ የስር ፍርድ ቤቱ ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል የሚለው አመልካች ይህን የሰበር
አቤቱታ አቅርቧል፡፡

አመልካች ጥር 13 ቀን 2013 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40(7)
የተደነገገውን የባለይዞታ መብት በሚፃረር መልኩ የስር ፍርድ ቤቶች የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1179ን ድንጋጌ
መሰረት በማድረግ መወሰናቸው፣ ተጠሪም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነበራቸው ክርክር እና
በዚህ መዝገብ ላይ የተለያየ ክርክር እያቀረቡ መሆኑ ቤቱንም በሕገወጥ መንገድ ስለመያዟ በተረጋገጠበት
ቀደም ሲል ተጠሪ በሌለችበት በተደረገ ክርክር ለክርክሩ መንስዔ የሆነው ቤት የአመልካች ስለመሆኑ
በተረጋገጠበትና በአመልካች በኩል የተለየ ማስረጃ ሣይቀርብ ክሱ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት
ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በአመልካች የተሰራና በስማቸውም
ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑ በቀረቡት የሰነድ ማስረጃ እና በሰው ማስረጃ አስረድተው ባለበት የተጠሪ ተጨማሪ
ክፍል ቤት ሰርተዋል በማለት አመልካች የቤቱ ባላቤት አይደሉም በሚል የተወሰነበት አግባብነት ከፍ/ብ/ሕግ
ቁጥር 1195 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች አንፃር ተጣርቶ እንዲወሰን ተጠሪም የመልስ ክርክር እንዲያቀርቡ
ታዞ የፅኁፍ ክርክሩ ተጠናቋል፡፡

ተጠሪ በበኩላቸው የካቲት 17 ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ መልሣቸው አመልካቹ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበውን
የክርክር ይዘት ሆነ ብሎ ለሰበር ሰሚ ችሎቱ መደበቁን፣ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች
በ1983 ዓ/ም ባዶ መሬት ትቶ ከተጠሪና ባለቤታቸው ገንዘብ ተቀብሎ ወደ ድሬዳዋ ከሄደ በኋላ ተጠሪና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ባለቤታቸው ቤቱን ሰርተው መኖራቸውን አከራካሪውን ቤት አመልካች አለመስራቱንና ቤቱ ለአንድ ቀንም


በአመልካች እጅ ገብቶ የማያውቅ መሆኑ በምስክሮች ስለተረጋገጠ ካርታ መያዙ ብቻውን የቤቱ ባለቤት ነው
የሚያሰኘው ባለመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት
ፈፅመዋል የሚያሰኛቸው ባለመሆኑ ውሣኔው እንዲፃና ተከራክረዋል፡፡ አመልካችም የሰበር አቤቱታውን
የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርቦ የግራ ቀኙ ክርክር ተጠናቋል፡፡

ከፍ ሲል የተመለከትነው የጉዳዩን አመጣጥና የግራ ቀኙን ክርክር ሲሆን አከራካሪው ቤት የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር
1179 በሚደነግገው መሰረት የተጠሪ ነው ተብሎ በመወሰኑ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር
አለመኖሩን በተመለከተ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር
በማገናዘብ እንደሚከተው ተምርምሯል፡፡ እንደተመረመረው አመልካች ባቀረቡት ክስ ለክርክሩ ምክንያት
የሆነው የግል ቤታቸው መሆኑን ከ1996ዓ/ም ጀምሮ ተጠሪ የራሣቸውን ቤት እስከሚሰሩ ድረስ በነፃ
እንዲኖሩ ፈቅደውላቸው በ2003ዓ/ም ጀምሮ ግን እንዲለቁላቸው ሲጠይቁ ፈቃደኛ ስላልሆኑ በፍርድ ሐይል
ተገደው እንዲለቁላቸው እንዲወሰንባቸው ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ በበኩላቸው ቤቱ የተሰራበት ይዞታ በአመልካች
ስም የእርሣቸው ባለቤት በ1983ዓ/ም ተመርተው አመልካች ከስራ ሲፈናቀሉ በተጠሪዎች ሲረዱ ቆይተው
በ1984ዓ/ም ለስራ መፈለጊያ ከተጠሪና ከባለቤታቸው ገንዘብ ተቀብለው ወደ ድሬዳዋ ከሄዱ በኋላ ተጠሪና
ባለቤታቸው በይዞታው ላይ በስድስት ቆርቆሮ ቤት ሰርተውበት ከቆዩ በኋላ ይህን ቤት በ1991 ዓ/ም
አፍርሰው ሁለት ክፍል ቤት በአዲስ መልክ ሰርተው በመኖር ላይ ሣሉ በ1994ዓ/ም ባለቤታቸው ሲሞቱ
አመልካች ለለቅሶ መጥቶ ከዚህ በኋላ ግብር መክፈል አትችሉም በሚል ማስረጃውን ከልጃቸው መቀበላቸውን
በአሀኑ ጊዜ በ54 ቆርቆሮ ዋና ቤት በ21ቆርቆሮ ሰርቪስ ቤት ሰርተው ለ22ዓመታት ያለ ተቃውሞ የኖሩበት
ቤታቸውን ይዞታው በአመልካች ስም በመመዝገቡ ብቻ እንዲለቁ መጠየቁ ተገቢነት የለውም ሲሉ
ይከራከራሉ፡፡፡ በቃል ክርክር ወቅት አመልካች ሶስቱን ከፍል ቤት በ1983ዓ/ም ራሣቸው የሰሩ መሆኑን
ሌላውን ቤት ተጠሪ የሰሩ ቢሆን እንኳ የግምቱን አንድ አራተኛ ከሚጠይቁ በስተቀር ቤቱን አንዳትለቅ
የሚያበቃ ህጋዊ ምክንያት አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

በስር ፍርድ ቤት ቀርበው የተደመጡት የአመልካች 1ኛ እና 2ኛ ምስከሮች በጥቅሉ አመልካች በ1983ዓ/ም


ሁለት ክፍል ቤት ሰርቷል ሲሉ የመሰከሩ ቢሆንም ቀሪ ምስክሮች አመልካች በይዞታው ላይ ቤት
ስለመስራታቸው አልመሰከሩም፡፡ በሌላ በኩል ሁሉም የአመልካች ምስክሮች አመልካች እንደሚያቀርቡት
ክርክር በአከራካሪው ቤት ውስጥ ገብተው መኖር የጀመሩት ባለቤታቸው(የአመልካቹ ወንድም) ከሞቱ በኋላ
ከ1996ዓ/ም ጀምሮ የራሣቸውን ቤት እስኪሰሩ ድረስ በአመልካች መልካም ፈቃድ ስለመሆኑ አላረጋገጡም፡፡
ይልቁንም የአመልካች ምስክሮች አከራካሪው ቤት ውስጥ ተጠሪ መኖር የጀመሩት ባለቤታቸው ከሞሞታቸው
በፊት መሆኑን፣ የአመልካች ወንድም ከመሞታቸው በፊትም በይዞታው ላይ በራሳቸው ወጪ ተጨማሪ ቤት
ሰርተው እየኖሩ እያለ እዚሁ ቤት ውስጥ መሞታቸውን መስክረዋል፡፡ በአንፃሩ በተጠሪ በኩል የቀረቡት
ሁሉም ምስክሮች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት እንዲሁም አጥር አመልካች ሣይቃወሙ ተጠሪና
ባለቤታቸው ሰርተው ከ1991ዓ/ም ሲኖሩበት እንደነበርና አመልካች ቤቱ የኔነው ማለት የጀመሩት የተጠሪ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ልጅ አረብ ሐገር ሄዳ ሰርታ ባገኘችው ገንዘብ ለእናቷ (ተጠሪ) ሌላ ቤት ከሰራችላቸው በኋላ መሆኑን
አረጋግጠዋል፡፡

አንድ ሰው በተለያዬ መንገድ የግል ሀብት ሊያገኝ እንደሚችል የፍትሐ ብሔር ሕጋችን ሶስተኛ መፅሐፍ
አንቀፅ ሰባት የሚደነግግ በመሆኑ ከእነዚህ መንገዶች መካከል ደግሞ በሌላ ሰው ይዞታ ላይ ባለይዞታው
ሣይቃወመው ህንፃ የሰራ እንደሆነ የሕንፃው ባለቤት ሕንፃውን የሰራው ሰው እንደሆነ የፍ/ብ/ሕግ ቁጥር
1179(1) ይደነግጋል፡፡ ባለይዞታው ወይም ባለርስቱ ሣይቃወም በይዞታው ላይ በሌላ ሰው ሕንፃ የተሰራ
እንደሆነ የሕንፃው ባለቤት ህንፃውን የሰራው ሰው ነው ቢባልም እንኳ ግምቱን በመክፈል ሕንፃውን
የማስለቀቅ የባለይዞታው መብት መሆኑን ወይም ባለሕንፃው ከፈለገ ሕንፃውን በራሱ ወጪ አፍርሶ መሬቱን
ለባለይዞታው መልቀቅ አማራጩ ለባለሕንፃው የተሰጠው መሆኑን የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1179(2)
ወይም 1180 ይደነግጋሉ፡፡ ይህ ድንጋጌ የተደነገገው መሬት የባለይዞታው ወይም የባለርስቱ የግል ሀብት
በነበረበት የመሬት ስርዓትን ታሣቢ በማድረግና በባለይዞታው ሣይቃወም በመሬቱ ላይ የተሰራው ህንፃ
የመሬቱ ተቀጥላ ወይም ተጨማሪ ነገር ሆኖ ይቆጠር በነበረበት የሕግ ፖሊሲ ማዕቀፍ ውስጥ መሆኑ ልብ
ሊባል ይገባል፡፡ ሆኖም አሁን በስራ ላይ ባለው የመሬት ስሪት ስርዓት የገጠርም ይሁን የከተማ መሬት
ባለሃብቶች ህዝብና መንግስት እንጅ ግለሰቦች አይደሉም፡፡ በመሆኑም ይህ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 105125
እንደሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1178፣ 1197(2)ና 1180 ድንጋጌዎች
በአሁኑ ጊዜ ሲተረጉሙም ይሁን በተግባር ሲውሉ አሁን ያለውን የመሬት ስሪት ስርዓት ወይም መሬት
የሕዝብና የመንግስተ መሆኑን ተሣቢ በማድረግ ሊሆን ይገባል፡፡

ከዚህ በመነሣት አመልካች በቃል ክርክር ወቅት ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት ራሱ እንደሰራው የተከራከረና
ካቀረባቸው ምስከሮች መካከል ሁለቱ ብቻ ከ1983ዓ/ም በፊት አመልካች ሁለት ክፍል ቤት የሰራ መሆኑን
የመሰከሩ ቢሆንም ይዞታው በአመልካች ስም ከተመራበት ጊዜ ጀምሮ በይዞታው ላይ ተስርቶ የነበረውንም
ይሁን በአዲስ መልክ የተሰራውን ዋና ቤት ኩሽናና አጥር ተጠሪና ባለቤተቻው ሰርተው ከ1991ዓ/ም ጀምሮ
እንደሚኖሩበት በተጠሪ በኩል የቀረቡት ምስክሮች በተሻለ አስረድተዋል የሚል መደምደሚያ መደረሱ
ተገቢነት ያለው ምዘና ነው ብለናል፡፡ ይህ ከሆነ አመልካች ቤቱን ሰርተው ተጠሪ ቤት እስከሚሰሩ ድረስ
እንዲኖሩበት ስለመስጠታቸው ብቻ እንጅ ቤቱ በይዞታቸው ላይ የተሰራው እየተቃወሙ መሆኑን ወይም
መቃወም በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው መሆኑን በመዘርዘር ህጉን መሰረት ያደረገ ግልፅ ክርክር
ባላቀረበቡት የፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 1179(1) በሚደነግገው መሰረት የቤቱ ባለቤት ተጠሪ ናቸው ተበሎ
መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ውሣኔ ነው የሚያሰኝ ምክንያት ባለማግኘታችን ተከታዩ
ውሣኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሣኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

1) የአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር
333318 ሕዳር 1ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሣኔ በጉዳዩ ላይ የስር ፍርድ ቤቶች
የሰጡትን ውሣኔ በማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ
ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
2) ይህ የሰበር ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡

ትዕዛዝ
1) ይህ ችሎት ጥር 25ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡
2) መዝገቡ እልባት ያገኘ በመሆኑ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ.201365

ቀን፡-27/01/2013ዓ/ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ዐቃቤ ህግ ዓ/ህግ- አቶ ማዘንጊያ ደምሴ

ተጠሪ፡ ደሳለኝ ቸኮል

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ ያለደረሰኝ እና የጭያሽ መመዝገቢያ ማሽን ግብይት መፈፀም
ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው አመልካች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪን ጨምሮ በሁለት ሰዎች ላይ ባቀረበው ክስ ነው፡፡
በቀረበው ክስ ላይ ተጠሪ ሁለተኛ ተከሳሽ ነበር፡፡ የቀረበው ክስ ጭብጥም ተከሳሾቹ የፌዴራል ታክስ
አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120(1) እና 128 ድንጋጌን በመተላለፍ የስር 1ኛ ተከሳሽ
የድርጅቱ ባለቤት ሆኖ የአሁን ተጠሪ ደግሞ በድርጅቱ ውስጥ የመስተንግዶ ሰራተኛ ሆኖ እየሰራ እያለ
ታህሳስ 16/2012 ዓ.ም ከቀኑ 6፡50 ሰዓት አካባቢ ሁለቱ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች እያንዳንዳቸው
ለተጠቀሙት ሁለት ሁለት ቢራ ደረሰኝ ሳይሰጣቸው የአሁን ተጠሪ ሂሳብ የተቀበላቸው በመሆኑ
ያለደረሰኝ ግብይት ፈፅመዋል፤ በዚህም ውስጥም የአሁን ተጠሪ አስተናጋጅ ሆኖ ዳረሰኝ ሳይሰጥ ሂሳብ
በመቀበል ወንጀሉ እንዲፈፀም የስር 1ኛ ተከሳሽን ረድቷል የሚል ነው፡፡

ተጠሪ እና የስር 1ኛ ተከሳሽ ቀርበው ድርጊቱን እና ጥፋተኝነቱን ክደው ተከራክረዋል፡፡ በዚሁ


ምክንያት ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የዐቃቤ ህግን ምስክሮችን አስቀርቦ ከሰማ በኋላ የስር 1ኛ
ተከሳሽ ክሱን እንዲከላከል ሲያዝ የአሁን ተጠሪን በተመለከተ በድርጅቱ ውስጥ በአስተናጋጅነት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መስራቱ እንጂ በቀረበው ክስ አግባብ 1ኛ ተከሳሽ ስለመርዳቱ አልተረጋገጠም በሚል ክሱን መከላከል
ሳያስፈልገው በነፃ አሰናብቷል፡፡ በዚሁ ብይን ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(1) መሰረት ይግባኙን ሰርዟል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን በመቃወም ነው፡፡ አመልካች ጥር 07/2013 ዓ.ም በተጻፈ
የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ብይንና ትዕዛዝ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት
ጠቅሶ በዚህ ችሎት እንዲታረምለት ጠይቋል፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ የክርክር
መነሻ የሆነው ደረሰኝ እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ሳይጠቀሙ ግብይት በመፈፀም ሂደት ውስጥ
ተሳትፎ የነበራቸው ስለመሆኑ በተገለፀበት በማስረጃ አልተረጋገጠም በሚል በነጻ እንዲሰናበት
የተወሰነበት አግባብነት ለዚህ ችሎት ቀርቦ እንዲመረመር በመደረጉ ተጠሪ የፅሁፍ መልስ እንዲሰጥበት
ታዟል፡፡ ሆኖም ተጠሪ በተደረገለት የጋዜጣ ጥሪ ቀርቦ መልስ ያልሰጠ በመሆኑ ክርክሩ በሌለበት
እንዲታይ ታዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም
የአመልክችን የሰበር ቅሬታ ለአቤቱታው መሰረት ከሆነው የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይዘት ጋር
በማገናዘብ በሰር ፍርድ ቤቶች ብያኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመኖሩ መርምሯል፡፡

አመልካች በስር ፍርድ ቤት ካቀረበው የክስ ይዘት መረዳት እንደሚቻለው የአሁን ተጠሪ የወንጀል
ተሳትፎ ተብሎ የተጠቀሰው በወንጀሉ አፈጻፀም ሂደት የስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረውን ረድቷል በሚል
ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ የወንጀል ድርጊቱ ተካፋይ ስለመሆኑ እና በዚያው ውስጥም የነበረው የተሳትፎ
መጠን አግባብነት ባለው ማስረጃ መረጋገጥ ያለበት የፍሬ ነገር ጉዳይ ነው፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ
የአመልካችን ማስረጃ የመረመረው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ በወንጀል ህግ ቁጥር 37 አግባብ
የስር 1ኛ ተከሳሽን በወንጀል ድርጊቱ የረዳው ስለመሆኑ በዐቃቤ ህግ ማስረጃ አልተረጋገጠም ብሏል፡፡
እንግዲህ የቀረበው ማስረጃ የክሱ ፍሬ ነገር አረጋግጧል ወይስ አላረጋገጠም የሚለው የማስረጃ ምዘና
ጉዳይ ነው፡፡ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀፅ 80(3) እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ
ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10 መሰረት ለዚህ ሰበር ችሎት የተሰጠው የዳኝነት ስልጣን በማናቸውም
የመጨረሻ ውሳኔው ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ካለ ማረም እንጂ ማስረጃን የመመርመር
አና የመመዘን አይደለም፡፡ ከዚህ አኳያ ማስረጃን የመመርማር እና የመመዘን የዳኝነት ስልጣን ያላቸው
ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዳሜ በሰበር ሰሚ ችሎት ሊነቀፍ የሚችለው ፍርድ ቤቶቹ ማስረጃን
ከመመዘን አኳያ የተላለፉት መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህ ሲኖር አልያም የተወሰደው አቋም
በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ያላደረገ እንደሆነ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በሰበር ሰሚ ችሎት
ደረጃ ማስረጃ በድጋሚ የሚመረመርበትም ሆነ የሚመዘንበት ህጋዊ መሰረት የለም፡፡

ከዚህ አንፃር አመልካች ያቀረበው የሰበር ቅሬታም ሆነ በአጣሪ ችሎቱ የተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ በስር
ፍርድ ቤት ቀርበው የተሰሙት የአመልካች ማስረጃዎች በድጋሚ እንዲመረመሩ እና እንዲመዘኑ
የሚጋብዝ እንጂ በማስረጃ ምዘና ሂደት የተጣሰ መርህ መኖሩን የሚያሳይ አይደለም፡፡ ይህ ከሌላ ደግሞ
የአመልካች ማስረጃ በዚህ ችሎት በድጋሚ የሚመዘንበት ምክንያት የለም፡፡ በመሆኑም በስር ፍርድ
ቤቶች ብይን እና ትዕዛዝ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ለማለት የሚያስችል ምክንያት
ባለመኖሩ የአመልካች የሰበር ቅሬታ ውድቅ ተደርጎ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

1. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት


በመ/ቁ/02-23435 ላይ ታህሳስ 01/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን
በማፅናት የሰጠው ትዕዛዝ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ሀ)) መሰረት
ፀንቷል፡፡

2. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ፡-201746

ቀን፡-28/03/2014ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት -ዓ/ህግ ማዘንጊያ ደምሴ ቀረቡ

ተጠሪ፡- አዋድ ኢብራሂም - አልቀረቡም

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 03-29655 ሕዳር 06
ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት
አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የቀረበን የመቃወም አቤቱታን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ
የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡
በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች የመቃወም አመልካች፤ የአሁን ተጠሪ እና በዚህ የሰበር
ክርክር የሌለ ሆጤ ክፍለከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ደግሞ የመቃወም ተጠሪዎች በመሆን
ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው የመቃወም አቤቱታ ይዘት በአጭሩ፡- የአከራካሪው
የንግድ እና መኖሪያ ቤት ካርታ በቅይጥ የተሰራ ቢሆንም ሽያጭ በተከናወነበት ጊዜ የንግድ እንቅስቃሴው
ያልቆመ እና የንግድ ፈቃዱም ያልተመለሰ በመሆኑ የሽያጭ ውሉን መሠረት በማድረግ በመኖሪያ ቤት ስም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዲዛወርላቸው የተሰጠው ውሳኔ የመንግስትን መብት እና ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባል የሚል
ነው፡፡

የአሁን ተጠሪ በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው በብይን ውድቅ ተደርጓል፤ በፍሬነገሩ
ላይ ደግሞ አመልካች ክርክሩን ከዚህ በፊት አያውቅም ተብሎ አይገመትም፤ አመልካች አስቀድሞ ሲደረግ
የነበረውን ክርክር እያወቀ ውጤቱን ጠብቆ ያቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት የለውም፤ የሆጤ ክፍለከተማ
አስተዳደር ኮንስትራክሽን ልማት ጽ/ቤት የመኖሪያ ቤት ግብር እንዲከፈልበት አሳውቋል፤ የካፒታል ዕድገት
ታክስ ተጠሪን አይመለከትም፤ ለስመ ንብረት ዝውውር ሲባል በንግድ ድርጅት ግብር ልንከፍል አይገባም፤
የስመ ንብረት ዝውውር በጠየቅንበት ወቅት ንብረቱ ሲሰጥ የነበረው አገልግሎት ቅይጥ አገልግሎት ነው፤
የስም ዝውውርን በሚመለከት ተፈጻሚነት ያለው ሕግ መመሪያ ቁጥር 4/2006 ብቻ ነው፤ ስለሆነም
አመልካች ያቀረበው መቃወሚያ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት ምስክሮችን ከሰማ በኋላ አመልካች አስቀድሞ የነበረውን ክርክር ያውቅ ነበር
የሚያስብል የሚያስብል ማስረጃ አልቀረበም፤ የሽያጭ ውሉ የተደረገው ለመኖሪያ እና ለንግድ ቅይጥ
አገልግሎት በሚል ነው፤ በቅይጥ አገልግሎት ግብር የተገበረ ቢሆንም በመመሪያ ቁጥር 4/2006 አንቀጽ
14/6 ላይ ለቅይጥ አገልግሎት የተሰጠ ቦታ ይዞታው እየሰጠ ባለው አገልግሎት መሠረት ተገቢውን የስመ
ንብረት ዝውውር ክፍያ እንደሚፈጸም የሚደነግግ በመሆኑ በዚሁ አግባብ የስመ ንብረት ዝውውር ክፍያው
ሊፈጸም ይገባል በማለት አስቀድሞ የሰጠውን ውሳኔ ሰርዟል፡፡

ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ አመልካች በጉዳዩ ላይ አስቀድሞ ክርክር
ሲደረግበት ያውቅ እንደነበር መገንዘብ ተችሏል፤ የስር ፍርድ ቤት በተጠሪ በኩል የቀረበውን መቃወምያ
ተቀብሎ እንደ አዲስ አከራክሮ እና ማስረጃዎች ሰምቶ ውሳኔ መስጠት ሲገባው የቀደመ ውሳኔውን በቀጥታ
መሻሩ አግባብ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሯል፡፡

አመልካች በበኩሉ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ
አቅርቧል፡፡ አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ አመልካች የመቃወም አቤቱታ
ያቀረበው የሽያጭ ውል የተፈጸመበት ቤት የእኔ ነው በሚል ሳይሆን አመልካችን ሳያሳውቁ በመኖሪያ
አገልግሎት ስመ ንብረቱ ቢዛወር በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚከፈለው ክፍያ ስለሚቀንስ የመንግስት
ጥቅም ይነካል በሚል ነው፤ አመልካች ስመንብረት እንዲዛወር በተጠየቀው ዳኝነት ላይ በቀጥታ
ስለማይመለከተው ከጅምሩ የክርክሩ ተካፋይ ሊሆን የሚገባው አልነበረም፤ ሆኖም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት
ስመ ንብረቱ በመኖሪያነት ተዛውሮ ሽያጩ ሊፈጸም ይገባል በማለት የወሰነ በመሆኑ በውጤት ደረጃ
ተቀብለነዋል በማለት ወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን
ይዘቱም፡- በስር ፍርድ ቤት የተሰጠው የስመ ንብረት ዝውውር ውሳኔ መብት እና ጥቅማችንን የሚነካ
በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት ውሳኔውን ለሰጠው ለስር ፍርድ ቤት አቅርበን ማስወሰናችን
ተገቢ ሆኖ ሳለ የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን መሻራቸው አግባብ አይደለም የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪው ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የስር ፍርድ ቤት አመልካች
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት ጣልቃ ለመግባት ያቀረበውን አቤቱታ ያልተቀበለበትን አግባብነት
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 37502 ከሰጠው የሕግ ትርጉም እና ከክልሉ
አዋጅ ቁጥር 168/2002 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ
እንዲሰጡበት ተደርጎ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ቀርቧል፡፡

ተጠሪዎች የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች አስቀድሞ ሲካሄድ
የነበረውን ክርክር ያውቅ ነበር፤ አመልካች ይህን እያወቀ ከውሳኔ በኋላ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ በማድረግ
በስር ይግባኝ ሰሚ ፍርደ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡ አመልካችም
የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ
ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር
አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምሮታል፡፡

ከክርክሩ ሒደት መገንዘብ የቻልነው በአሁን ተጠሪ እና በስር ተከሳሽ መካከል የተደረገው ክርክር የስም
ሐብት ዝውውርነ የሚመለከት መሆኑን፤ አመልካች በበኩሉ በተጠሪ እና በስር ተከሳሹ መካከል በተደረገው
ክርክር የሽያጭ ውሉን መሠረት በማድረግ የአከራካሪው ቤት ስመ ሐብት በመኖሪያ ቤት ስም እንዲተላለፍ
በማለት የተሰጠው ውሳኔ የመንግስትን ገቢ የሚጎዳ መሆኑን በመግለጽ የክርክሩ ተካፋይ ሳይሆን የተሰጠው
ውሳኔ እንዲሰረዝለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ ያቀረበ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም
በዚህ ችሎት ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው የክርክሩ መሠረታዊ ጭብጥ ከመነሻውም ቢሆን አመልካች የቤቱ ስመ
ሐብት በመኖሪያ ቤት ሊተላለፍ አይገባም በማለት የሚያቀርበው ጥያቄ ሊስተናገድ የሚገባው
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት በሚቀርብ የመቃወም አቤቱታ መነሻነት ነው? ወይስ ራሱን ችሎ
በሚቀርብ ክስ ነው? የሚለው ነው፡፡

በመሠረቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ ማቅረብ የሚቻለዉ በክርክሩ ዉስጥ
ተካፋይ መሆን የሚገባዉ ወይም በክርክሩ ዉስጥ ለመግባት የሚችልና ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠዉ
ፍርድ መብቱን የሚነካበት ሰዉ ነዉ፡፡ ከድንጋጌው ይዘት መገንዘብ የሚቻለው መቃወሚያ የሚያቀርበው
ሰው በሙግቱ በቀጥታ ጥቅም ያለው እውነተኛ ወገን ሊሆን እንደሚገባ፤ በተሰጠው ፍርድ በእርግጥም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጥቅሙ የተነካበት እና በሌላ አግባብ መብቱን ለማስከበር የማይችል ሰው ስለመሆኑ በቅድሚያ ሊረጋገጥ
የሚገባ መሆኑን ነው፡፡

በያዝነው ጉዳይ በአሁን ተጠሪ እና የስር ተከሳሽ በነበረው የሆጤ ክፍለከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት
ጽ/ቤት መካከል በተደረገው ክርክር የአከራካሪው ቤት ስም ሐብት በመኖሪያ ቤት እንዲተላለፍ በሚል ዉሳኔ
ተሰጥቶበታል፡፡ አመልካች ይህ ውሳኔ ሊሰረዝ ይገባል በማለት አቤቱታ ያቀረበው ደግሞ ተካፋይ
ባልሆንኩበት ክርክር የተሰጠው ውሳኔ የመንግስትን ገቢ ይጎዳል በሚል ነው፡፡ ስለሆነም አመልካች በሕጉ
በተቀመጠው ሥርዓት መሠረት ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ላይ አዲስ ክስ በማቅረብ መብቱን
ከሚያስከብር በቀር የአከራካሪው ቤት ስመ ሐብት በመኖሪያ ቤት እንዲተላለፍ በማለት የተሰጠው ዉሳኔ
መብቴን ይጎዳል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት ያቀረበው መቃወሚያ ተገቢነት የለዉም፡፡
በመሆኑም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይህንኑ መሠረት በማድረግ የሰጠው ውሳኔ
በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም፡፡ በዚህም ምክንያት
ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 03-29655
ሕዳር 06 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

?? /? /? ? ? 201771
? ? 28/3/2014 ? /?

ዳኞች ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች - 1. ወ/ሮ ማስተዋል ዓለሙ 2. ህጻን ታጫውት አለማየሁ 3. ህጻን እያለ


አለማየሁ - የቀረበ የለም
ተጠሪ - አቶ ደሳለው ታደሰ - የቀረበ የለም

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ጥር 21 ቀን 2013
ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 92061 ጥቅምት 24
ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ፣ የአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
በመ/ቁጥር 52061 ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የምዕራብ
ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 0174616 ግንቦት 6 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት
የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን
በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች
የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል
የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት መሬቱ የኔ የ1ኛ አመልካችና የባለቤቴ ሲሆን
2ኛ እና 3ኛ ከሳሾች የአባታቸው ወራሾች ናቸው፡፡ የአሁን ተጠሪ ከ1ኛ አመልካች ጋር
የተስማማነው 12 ክፍል ቤት ሰርቶ ሊያካፍለኝ ሲሆን 12 ክፍል ቤት ሰርቶ ለግሉ ይዞታል፡፡ 3

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ክፍል ቤት ደግሞ በ2ኛ እና 3ኛ ከሳሾች የመሬት ድርሻ ላይ የሰራ በመሆኑ ሊያነሳላቸው የሚገባ
ሲሆን የወረዳ ፍ/ቤት አጣርቶ የሰጠውን ውሳኔ የከፍተኛውና የሰበር ሰሚው ችሎት መሻራቸው
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡

በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከአዲስ ዓለም ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ
የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ 1ኛ ከሳሽና ተከሳሽ በ24/4/2008 ዓ/ም በቃል ባደረግነው
ስምምነት በገጠር መሬት ላይ ተከሳሽ 12 ከፍል ቤት ሰርቶ ሊያከፍለኝ ተዋውለን በውሉ መሰረት
12 ክፍል ቤት ሰርቶ ያላካፈለኝ በመሆኑ፣ 2ኛ እና 3ኛ ከሳሾች በውርስ ባገኙት መሬት ላይ
ካለፈቃዳቸው ሶስት ክፍል ቤት የሰራበት በመሆኑ እንዲለቅላቸው ለ1ኛ ከሳሽ ደግሞ 12 ክፍል
ቤት እንዲያካፍለኝ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ተከሳሽም የአሁን ተጠሪ 1ኛ ከሳሽና እኔ ተከሳሽ
በተስማማነው መሰረት 3 ክፍል ቤት ሰርቼ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔ ደግሞ 12 ክፍል ቤት ሰርቻለሁ፡፡
2ኛ እና 3ኛ ከሳሾች መሬቱ የነሱ ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ የለም፡፡ ቤቱን ስሰራ
ያልተቃወሙኝ በመሆኑ ክሳቸው ውድቅ ይሁንልኝ በሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ ዓለም ንዑስ
ወረዳ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ቁጥር 015883 መጋቢት 17 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት
በሰጠው ውሳኔ በተዋዋዮች መሀከል የሚደረግ ውል በመሀላቸው እንደ ህግ የሚቆጠር ነው፡፡ አንድ
ውል በተለየ ፎርም እንዲደረግ ካልተደነገገ በቀር በፈለጉት መንገድ ሊዋዋሉ ይችላሉ፡፡ 1ኛ ከሳሽ
ከተከሳሽ ጋር ያደረጉት ስምምነት 12 ክፍል ቤት በተከሳሽ ተሰርቶ ሊካፈሉት ሲሆን የተሰሙት
ምስክሮችም በማረጋገጣቸው ተከሳሽ 12 ክፍል ቤቱን ግማሹን ለ1ኛ ከሳሽ ያካፍላት፡፡ 2ኛ እና
3ኛ ከሳሾች የአባታቸው ወራሾች ቢሆኑም፣ ይዞታው ተመዝግቦ ያለው በ1ኛ ከሳሽ ስም በመሆኑ፣
እና ተከሳሽ የ1ኛ ከሳሽ መሬት ነው በሚል አምኖ የተስማማ በመሆኑ፣ 2ኛ እና 3ኛ ከሳሾች
የሚከራከሩትም በ1ኛ ከሳሽ በኩል ሲሆን፣ ቤቱ ውስጥም ለ8 ወራት የኖሩበት በመሆኑ 3 ክፍል
ቤቱ በሚገባ ተጠናቆ ተከሳሽ ለከሳሾች ያስረክብ ሲል ወስኗል፡፡ ተከሳሽ ለምዕራብ ጎጃም ዞን
ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ በመ/ቁጥር 0174616 ግንቦት 6 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው
ችሎት በሰጠው ውሳኔ ክርክሩ የሚያስረዳው ስምምነቱ ተከሳሽ ለ1ኛ ከሳሽ 3 ክፍል ቤት ሰርቶላት
ለራሱ ደግሞ 12 ክፍል ቤት ለመስራት ሲሆን ጉዳዩን በእርቅ ያዩት ሽማግሌዎችም ከሳሽ
ያቀረበችው ቅሬታ ለራሱ በደንብ ሰርቶ ለኛ ያላለቀ ቤት ነው የሰጠን የሚል መሆኑን የመሰከሩ
በመሆኑ 12 ክፍል ቤት የተሰራው ለተከሳሽ ነው ሲል የወረዳ ፍ/ቤት ውሳኔን በማሻሻል ወስኗል፡፡
ከሳሾች ለአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው በመ/ቁጥር
52061 ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ
ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት
አያስቀርብም ሲል ይግባኛቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ ከሳሾች ለአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት አቤቱታ አቅርበው አከራክሮ በመ/ቁጥር 92061 ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም
በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትእዛዝና የከፍተኛ ፍ/ቤት
ውሳኔን በማጽናት ወስኗል፡፡

የአሁን አመልካቾችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል፡፡ መዝገቡም ተመርምሮ በዚህ


ጉዳይ አከራካሪው ይዞታ የ2ኛ እና 3ኛ የሰበር አመልካቾች አባት ጭምር መሆኑ ከመረጋገጡ
አንጻር 1ኛ የሰበር አመልካች አድርገዋለች ለተባለው ውል መነሻነት 2ኛ እና 3ኛ የአሁን
አመልካቾች መብት ጨምሮ የውሉ አካል ነበር ማለት ይቻላል ወይ? የምለውን ነጥብ
ለመመርመር ሲባል ቀርቧል፡፡ ተጠሪ መልስ ባለማቅረቡ ታልፏል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ የስር ፍርድ
ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ
በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል፡፡
እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ የአሁን
1ኛ አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገችው የቃል ስምምነት በአሁን አመልካች የገጠር መሬት ላይ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ 12 ክፍል ቤት ሰርቶ እኩል አንዲያካፍላት የተስማሙና የአሁን ተጠሪ 12 ክፍል ቤት


ሰርቶ ያላካፈላት መሆኑን እንዲሁም 3 ክፍል ቤት የሰራው በአሁን 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች
የመሬት ይዞታ ላይ በመሆኑ ያንሳልን የሚል ሲሆን የአሁን ተጠሪም በሰጠው መልስ ለአሁን 1ኛ
አመልካች 3 ክፍል ቤት ሰርቶ ያስረከባትና ለራሱ ደግሞ 12 ክፍል ቤት የሰራ መሆኑን፣
በውላቸውም መሰረት የተፈጸመ መሆኑን ተከራክሯል፡፡ በዚሁ መሰረት በስር ፍ/ቤት በተደረገው
ክርክር ይዞታው የአሁን 1ኛ አመልካችና የባለቤቷ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች አባት የሟች
አቶ አለማየሁ የጋራ ንብረት አንደሆነ፣ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾችም የአባታቸው የሟች
አቶ አለማየሁ ወራሽ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ቤት የተሰራበት የመሬት ይዞታ የአሁን 1ኛ
አመልካችና የአሁን 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የጋራ ይዞታ መሆኑም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡
በግራ ቀኙ ከቀረበው ክርክር የምንረዳው ቤት ተሰርቶ ለመከፋፈል የተስማሙት የአሁን 1ኛ
አመልካችና የአሁን ተጠሪ ብቻ ስለመሆናቸው ግራ ቀኙ የሚስማሙበት ጉዳይ ሲሆን የቀረበው
ክስና መልስ ይህንኑ የሚያስረዳ ነው፡፡ በመሆኑም የግራ ቀኙ ስምምነት የአሁን 2ኛ እና 3ኛ
አመልካቾችን የመሬት ይዞታ ድርሻ የሚመለከት አይደለም፡፡ የአሁን 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾችን
መብት የሚነካ የቤት ግንባታ ስምምነትም ከፍቃዳቸው ውጪ ስለሚሆን ተፈጻሚነት የሚኖረው
አይደለም፡፡ በገጠር መሬት ላይ የሚደረጉ ውሎች ህጋዊነት በተመለከተ በአሁን 1ኛ አመልካችና
ተጠሪ መካከል በገጠር መሬት ላይ ቤት ሰርቶ ለመካፈል የተደረገው ስምምነት ከክልሉ የገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ አንጻር ህጋዊነት ያለው አይሆንም፡፡ ይሁንና የአሁን 1ኛ
አመልካች ውሉን መሰረት አድርጋ ላቀረበችው ክስ የአዲስ ዓለም ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት የሰጠው
ውሳኔ የአሁን አመልካች የይግባኝ ቅሬታ ያላቀረበችበትና ይግባኝ ባልተባለበት ጉዳይ በዚህ ሰበር
ሰሚ ችሎት አንስቶ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የስነ ሥረዓት ህጉ የማይፈቅድ ሆኖ በመገኘቱ ሊታለፍ
ችሏል፡፡ በአሁን 1ኛ አመልካችና በአሁን ተጠሪ መካከል የተደረገው የቤት ግንባታ ስምምነትን
በተመለከተ የአሁን 1ኛ አመልካች ክርክር ተጠሪ 12 ክፍል ቤት ገንብቶ ግማሹን ሊያካፍለኝ
በቃል ተስማምተናል የሚል ሲሆን የአሁን ተጠሪ ደግሞ ስምምነቱ ከአሁን 1ኛ አመልካች ጋር
ብቻ የተደረገ መሆኑን ተቀብሎ ለአመልካች 3 ክፍል ቤት ሰርቶላት ለራሱ 12 ክፍል ቤት
ለመስራት የተስማማ መሆኑን ተከራክሯል፡፡ በስር ፍ/ቤት በተደረገው ማጣራት ደግሞ 12 ክፍል
ቤት በአንድ ቦታ ሶስት ክፍል ቤት በአንድ ቦታ የተሰራ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን የአሁን 1ኛ
አመልካች ግራ ቀኙ ያደረጉት የቃል ስምምነት 12 ክፍል ቤት ተሰርቶ ለመካፈል የተስምሙ
መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን የአሁን ተጠሪ ምስክሮች ደግሞ ጉዳዩን በሽምግልና ያዩትና በሽምግልና
ጊዜ የሰሙትን የሰጡት ቃል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የአዲስ ዓለም ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት የቀረበውን
ክርክር በማስረጃ አጣርቶ አሁን ተጠሪ በአሁን 1ኛ አመልካች የመሬት ይዞታ ላይ 12 ክፍል ቤት
ሰርቶ ለመካፈል የተስማሙ መሆኑን የደረሰበት ድምዳሜ ተገቢ ሆኖ እያለ የምዕራብ ጎጃም ዞን
ከፍተኛ ፍ/ቤት ካለ በቂ ምክንያት የወረዳ ፍ/ቤት ውሳኔን ማሻሻሉ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 38844 ላይ በሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ሰሚ
ፍ/ቤቶች የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በአግባቡ ሳይመረምሩ እና ለውሳኔያቸው በቂ ምክንያት
ሳይሰጡ መሻር የማይችሉ ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበት ይገኛል፡፡ በመሆኑም
የአዲስ ዓለም ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት በማስረጃ አጣርቶ በህጉ መሰረት የሰጠውን ውሳኔ ካለበቂ
ምክንያት የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በማሻሻል የሰጠው ውሳኔና የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ
ሰሚ ችሎትና ሰበር ሰሚ ችሎት ሳያርሙት ማለፋቸው መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው ብለናል፡፡

ውሳኔ
1. የአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 92061 ጥቅምት 24 ቀን 2013
ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ፣ የአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር
52061 ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የምዕራብ ጎጃም ዞን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር -174616 ግንቦት 6 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡ የአዲስ ዓለም ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አከራክሮ
በመ/ቁጥር 015883 መጋቢት 17 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል፡፡
2. በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል፡፡
4. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ፡-201929

ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡አቶ ሆርዶፋ ዴቲ

ተጠሪዎች ፡1ኛ/ ወ/ሮ ፀሐይ ሽፈራው

2ኛ/ አዋሽ ባንክ አ.ማ

3ኛ/ ዳሸን ባንክ አ.ማ

ይህ መዝገብ ከመ/ቁ/ 201929 ጋር ተጣምሮ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የፍርድ አፈፃፀም ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን
ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን 1ኛ ተጠሪ የአፈጻጸም ከሳሽ፤የአሁኑ አመልካች በአፈጻጸም ተከሳሽ፤የአሁኑ
2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ
አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ከተወሰነ በኋላ 200 ሄክታር የቡና ልማት
የኢንቨስትመንት ይዞታ የጋራ ንብረት ነዉ ተብሎ እኩል እንዲካፈሉ ተወስኖ የፌዴራል ፍ/ቤቶች
የአፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ንብረቱ ያለበት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በውክልና ውሳኔውን
እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ የአፈፃፀም መዝገብ ቁ/42899 ተከፍቶ በሂደት ላይ እያለ
2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በየበኩላቸዉ ባልና ሚስቱ ከባንኩ ተበድረዉ ያልከፈሉት እዳ መኖሩን
በተለያየ መዝገብ ያሰጡትን ፍርድ በማቅረብ ንብረቱ በባልና ሚስት መካከል ክፍፍል ከመደረጉ
በፊት እዳዉ እንዲከፈላቸዉ አቤቱታ በማቅረብ የክርክሩ ተካፋይ መሆናቸዉን መዝገቡ
ያሣያል፡፡አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸዉ በሰጡት መልስ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ከዚህ ቀደም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአፈጻጸም ክስ አቅርቦ የ2010ዓ.ም እና 2011 ዓ.ም የምርት ዘመን የቡናዉን ፍሬ አስለቅሞ


እዳዉን እንዲሰበስብ ትእዛዝ የተሰጠለት መሆኑን ጠቅሰዉ በባልና ሚስት መካከል በሚደረግዉ
የአፈጻጸም ክርክር ላይ አቤቱታ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት የተከራከሩ ሲሆን ፍርድ ቤቱ
ጉዳዩን መርምሮ እና ከሚመለከተዉ አካል አጣርቶ ለባንኩ እንደፍርዱ አለመፈጸሙን እና ንብረቱም
ከፍርድ ባለእዳ እጅ አለመዉጣቱን አረጋግጦ ክርክራቸዉን ዉድቅ በማድረግ ንብረቱ በሃራጅ
እንዲሸጥ እና ለባልና ሚስቱ ከመከፋፈሉ በፊት የባንኮቹ እዳ እንዲከፈል በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የአሁኑ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 224389 ላይ
ይግባኝ ቢያቀርብም ፍ/ቤቱ ይግባኙን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ/337 መሰረት ሰርዟል፡፡1ኛ ተጠሪ በበኩሏ
ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/224547 ላይ ያቀረበችዉ ይግባኝ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ለዚህ
ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት በቀን 17/05/2013ዓ.ም
ጽፎ ያቀረበዉ አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ሲታይ፣2ኛ ተጠሪ(አዋሽ ባንክ) በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.428(2) መሰረት
የሁለት ዓመት የቡና ምርት በብር 14,150,360.00 ግምት እንዲረከብ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት
በመ/ቁ.214298 በቀን 30/09/2010ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እስከ ፌዴራል ጠቅላይ
ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ቀርቦ ጸድቋል፤ነገር ግን ባንኩ ይህንን ትዕዛዝ አልቀበልም በማለት ለሁለት
አመት የቡና ምርት እንድበሰብስ በማድረግ ያደረሰውን ጉዳት ወደ ጎን በመተው በዚህ አፈፃፀም
መዝገብ እንደገና ጣልቃ ገብቶ ከኢንቨስትመነት መብታችን ጋር እንዲከፈል ያቀረበው አቤቱታ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.418(1) መሰረት ተቀብሎ ባለመብት ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት
ስለሆነ እንዲታረም፤ግምቱን በተመለከተ የቀረበው ግምት ፍትሃዊ እንዳልሆነ ግልፅ ሆኖ እያለ
ፍ/ቤቱ እንደ ትክክለኛ ውሳኔ በመውሰድ የሰጠው ብይን ስህተት ነው፡፡ለኢንቨስትመንት ከወሰድኩት
መሬት ስፋት 200 ሄክታር ውስጥ የቡና ተክል 78 ሄክታር ብቻ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የስር
ፍ/ቤት 122 ሄክታር ባዶ መሬት ጨምሮ እንዲሸጥ መወሰኑ ሰርቼ የመኖር መብቴን የሚነካ
በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ለ2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እዳ መጠን በተመለከተ
ተሽጦ ገቢ የተደረገውን እና ቀሪውን ሂሳቡ በባለሙያ እና በማስረጃ እንዲጣራ የሰጠውን ትእዛዝ
የስር ፍ/ቤት ሳያጣራ ማለፉ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የተሰጠው ብይን እንዲሻር በማለት
አመልክተዋል፡፡

1ኛ ተጠሪ በበኩሏ ተመሳሳይ ይዘት ያለዉ አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን ዝርዝር ይዘቱን ከሰበር መዝገብ
ቁ.201929 የሚቻል ሆኖ ባጭሩ ሲታይ፤2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጉዳያቸው በሌላ መዝገብ እልባት
አግኝቶ ተፈጽሞ እያለ በድጋሚ በባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል መዝገብ ላይ ጣልቃ ገብቶ በድጋሚ
ንብረቱ በሀራጅ እንዲሸጥ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ በሚል የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ
እንዲታረም ጠይቃለች፡፡

የአመልካቹ አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ቀደም ሲል ከአመልካች
ጋር በነበረው የአፈጻጸም ክርክር በጨረታ ገዥ ስላጣ ምርቱን እንዲረከብ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት
በመ/ቁ.214298 በ30/09/2010 ዓ.ም ውሳኔ ተሰጥቶ በፌዴራል ሰበር ችሎት የፀና ሲሆን በባልና
ሚስት ክርክር ላይ ባንኩ ጣልቃ እንዲገባ አድርጎ በጨረታ ተሽጦ ቅድሚያ ለባንኩ ይከፈል በማለት
የሥር ፍርድ ቤት የወሰነበት አግባብነት ለማጣራት በሚል እንዲሁም የ1ኛ ተጠሪ አቤቱታም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተመሳሳይና አንድ በመሆኑ ከዚህ መዝገብ ጋር ተጣምረው እንዲታይ በማለት ተጠሪዎች መልስ
እንዲሰጡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የተጠሪዎች መልስ ይዘት በቅደም ተከተል ስንመለከት 1ኛ ተጠሪ የአመልካች አቤቱታ በሚያጠናክር
መልኩ መልስ አቅርባለች፡፡2ኛ ተጠሪ ባቀረበው መልስ አንድ ፍርድ በውሳኔው መሰረት ተፈጽሟል
ሊባል የሚቻለው ፍርዱ ያረፈበት ገንዘብ ሲከፈል ወይም የተቻቻለ ነገር ያለ ሲሆን ነው፡፡ነገር ግን
አመልካች ክፍያ የፈፀመበትን ደረሰኝ ወይም ለሽያጭ የተዘጋጀ ምርት በሌለበት የቡና እርሻን
ለመረከብ አልገደድም እንጂ መረከበን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሳይቀርብ እና የ2010 ምርት ይረከብ
በተባለ ጊዜም በአካል የሌለና የ2011 ዓ.ም በይግባኝ ላይ ቆይተን ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም
የመጨረሻ ውሳኔ ሲሰጥ አመልካች ምርቱን ሰብስቦ የጨረሰ ሲሆን ሊፈፀም ወይም ተግባራዊ
የማይሆን ውሳኔ መሰረት በማድረግ አመልካች የ2ኛ ተጠሪ እዳ ተከፍሏል በማለት ያቀረበው ቅሬታ
ተቀባይነት የለውም፤የ2ኛ ተጠሪ እዳ በውሳኔው መሰረት ሳይፈፀም አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የባልና
ሚስት ንብረት ነው በማለት የ2ኛ ተጠሪ መያዣ ንብረት ለመከፋፈል በአፈፃፀም መዝገብ ክርክር
እያደረጉ ስለሆነ 2ኛ ተጠሪ ቀዳሚ መብት ያለው በመሆኑ ጣልቃ ገብ ሆኖ አቤቱታ ማቅረቡ
በአግባቡ ነው፤የጅማ ዞን ከፍተኛ የ2010 ዓ.ም እና የ2011 ዓ.ም ምርት ተጠሪ መረከብ
አለመረከቡን ለማረጋገጥ ፍ/ቤቱ በመ/ቁ 42899 ላይ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚመለከተው
አካል በሰጠው ትእዛዝ መሰረት በመስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ አከራካሪው የቡና
እርሻ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በአመልካች እጅ የሚገኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን
ርክክብ ያልተደረገና ተረከብ የተባለ የቡና ምርት የሌለ በመሆኑ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ
ከመከፋፈላቸዉ በፊት የ2ኛ ተጠሪ እዳ ይከፈል ማለቱ ትክክል በመሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት
የለውም፡፡ግምቱን በተመለከተ ምርቱ ከማሳ ተሰብስቦ ለገበያ እስኪቀርብ ድረስ ያሉት ወጪዎች እና
ሊያጋጥሙ የሚችሉ ብክነቶች ታሳቢ ያደረገ ሲሆን የባለሙያ ግምት የሚነቀፍ አይደለም፤ስለዚህ
የቀረበው ቅሬታ ውድቅ ሆኖ ወጪና ኪሳራ የማቅረብ መብት እንዲጠበቅልን በማለት መልስ
ሰጥቷል፡፡

3ኛ ተጠሪ በበኩሉ በአመልካች ላይ ያለው ብድር እዳ ብር 1,521,349.81 እንዲከፍል የተሰጠዉ


ውሳኔ እልባት ሳያገኝ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረት ክፍፍል ለማድረግ የአፈፃፀም
መዝገብ ስለከፈቱ የቡና ማሳ ሳይሸጥ በክርክሩ ጣልቃ ለመግባት ችለናል፡፡አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ
ይህንን ገንዘብ ሳይከፍሉ የቡናውን እርሻ ሊካፈሉ የሚችሉበት አግባብ የለም፡፡ስለዚህ የስር ፍ/ቤት
የባልና ሚስት ንብረት ሳይከፋፈል ንብረቱ በሀራጅ ተሸጦ ፍርድ ያረፈበት እዳ እንዲከፈለን የሰጠው
ብይን የሚነቀፍበት የህግ ምክንያት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡የ1ኛ ተጠሪን አቤቱታ
በተመለከተም ከላይ ከተገለጸዉ ጋር ተመሳሳይ የሆነ መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዳዩ
ለሰበር ያስቀርባል የተባለበትን ጭብጥ መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት
ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ ለአፈጻጸም
ክርክር መነሻ የሆነዉ ፍርድ በአንድ በኩል የባልና ሚስት ንብረት ክፍፍል የሚመለከት ሲሆን በሌላ
በኩል የአበዳሪ ባንኮችን ማለትም 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እዳ በሚመለከት የተሰጠ ዉሳኔ
ነዉ፡፡ፍርዱ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ መዝገቦች የተሰጠ ሲሆን ለአሁኑ አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ
የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነዉ የተባለዉ በጅማ ዞን የሚገኝ የቡና ኢንቨስትመንት ይዞታ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በአመልካችና በ1ኛ ተጠሪ ክፍፍል እንዲደረግ ባቀረቡት የአፈጻጸም መዝገብ ላይ 2ኛ እና 3ኛ


ተጠሪዎች እዳ በቅድሚያ እንዲከፈል ትእዛዝ እንዲሰጥላቸዉ ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ
ተቀብሎ ትእዛዝ መስጠቱን ተገንዝበናል፡፡አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ አሁንም አጥብቀዉ
የሚከራከሩት ከተጠሪዎች እዳ አከፋፈል ጋር በተያያዘ በተለይም 2ኛ ተጠሪ አዋሽ ባንክ አስቀድሞ
የቡና ፍሬ ለቅሞ እዳዉን እንዲሰበስብ የተሰጠዉን ትእዛዝ ሳያስፈጽም ቆይቶ አሁን እንደአዲስ
አቤቱታ ማቅረቡና ፍርድ ቤቱም መቀበሉ ስህተት ነዉ በማለት ነዉ፡፡የዚህ ሰበር ችሎት ምለሽ
የሚሻዉ አቢይ ነጥብ የስር ፍርድ ቤት የባለእዳዎቹን ክርክር ዉድቅ በማድረግ የ2ኛ እና 3ኛ
ተጠሪዎች እዳ በቅድሚያ እንዲከፈል በሰጠዉ የአፈጻጸም ትእዛዝ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት
መፈጸም አለመፈጸሙን የሚመለከት ነዉ፡፡

በመሠረቱ ፍርድ ማስፈጸም ማለት ፍርድ ቤቶች ወይም ሌላ የዳኝነት ስልጣን በህግ
የተሰጣቸዉ አካላት የሚሰጡትን ፍርድ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ወይም ዉጤት እንዲያገኝ
የሚደረግበበት ሥርዓት ሲሆን ሂደቱ የሚመራዉ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ ሰባተኛ መጽሓፍ
ስለፍርድ አፈጻጸም በስነስርዓት ህጉ አንቀጽ 371 እና ተከታዮቹ ላይ ከተመለከቱት
ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበዉ ነዉ፡፡ፍርዱን የማስፈጽም ስልጣን ፍርዱን የሰጠዉ ፍርድ
ቤት ወይም እንደ ፍርዱ እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ የተሰጠዉ ፍርድ ቤት ስለመሆኑም በህጉ
አንቀጽ 371(1) ላይ የተደነገገ ሲሆን፣ ፍርዱን የሰጠዉ ወይም እንደ ፍርዱ እንዲያስፈጽም
የታዘዘዉ ፍርድ ቤትም ፍርዱ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ወይም በፍርዱ መሠረት ለማስፈጸም
ባለበት ኃላፊነት መሠረት የተለያዩ እርምጃዎችን መዉሰድ እንደሚችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር
386 እና 392 ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባሉ፡፡ፍርድ እንዲያስፈጽም አቤቱታ የቀረበለት
ፍርድ ቤት አስቀድሞ እንዲመረምር የሚጠበቅበት መሰረታዊ ጉዳይ የሚፈጸም ፍርድ
ስለመኖሩ፤የሚፈጸመዉ ነገር ምንነት፤ፍርዱን እንዲፈጽም የሚገደደዉ ሰዉ ማነዉ? የሚሉ እና
መሰል ጉዳዮች ሲሆኑ ይህንኑ ፍርዱንና ተከራካሪ ወገኖችን በመመርምር ማረጋገጥ
ይኖርበታል፡፡የአፈጻጸም ክርክሩን የሚመራዉ ፍርድ ቤት የፍርድ ባለእዳዉን ጠርቶ
ከመረመረ በኋላ እንደፍርዱ የማይፈጸምበት ምክንያት ያለመኖሩን ሲያረጋግጥ ለአፈጻጸሙ
ተስማሚ በሆነ መንገድ ፍርዱ እንዲፈጸም ትእዛዝ እንደሚሰጥ ተደንግጓል፡፡የፍ/ብ/ስ/ስ/ህጉ
አንቀጽ 386 እና 392/1/ይመለከታል፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ወደ አፈጻጸም ክርክር የገቡት በየበኩላቸዉ በአመልካች ላይ


ክስ አቅርበዉ በፍርድ ያገኙትን መብት ለማስፈጸም ነዉ፡፡ለአፈጻጸም ክርክር መነሻ የሆነዉ
አመልካቹ ከ2ኛ ተጠሪ ተበድሮ ያልከፈለዉ ቀሪ እዳ ለማስከፈል ባቀረበዉ ክስ እስከ ፌዴራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ተደርጎ በሰበር መ/ቁ/ 98218 ላይ መስከረም 30 ቀን
2009ዓ.ም የተሰጠ ፍርድ መሆኑን፤ 3ኛ ተጠሪን በተመለከተ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
በመ/ቁ/ 175214 ላይ በጥቅምት 9 ቀን 2011ዓ.ም የተሰጠ ፍርድ እንዲሁም በአመልካች እና በ1ኛ
ተጠሪ መካከል የንብረት የባልና ሚስት ክፍፍል ላይ በመ/ቁ/ 33998 ላይ የተሰጠ ፍርድ ስለመሆኑ
ከክርክሩ መገንዘብ ተችሏል፡፡ይህ ፍርድ በስምምነት ወይም በሌላ አግባብ ስለመፈጸሙ በአመልካች
በኩል የቀረበ መከራከሪያ የለም፡፡

የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ ዋነኛ መከራከሪያ ነጥብ 2ኛ ተጠሪ አስቀድሞ ባስከፈተዉ የአፈጻጸም
መ/ቁ/31745 ላይ በተሰጠዉ ትእዛዝ መሰረት የፍርድ ባለእዳ ንብረት የሆነዉን ቡና ተረክቦ የ2010

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እና 2011ዓ.ም ምርት ፍሬዉን በመልቀም ማስፈጸም ሲገባዉ አሁን 1ኛ ተጠሪ ባስከፈተችዉ


የአፈጻጸም መዝገብ በጣልቃ ገብነት አቤቱታ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ
በወቅቱ በተሰጠዉ ትእዛዝ ባለመስማማት ለበላይ ፍርድ ቤቶች አቤቱታ መቅረቡንና በሂደቱም
ጊዜዉ ማለፋን እንዲሁም ለመረከብ የማይገደድ ስለመሆኑና መረከቡንም የሚያስረዳ ማስረጃ
ባልቀረበበት ሁኔታ እንደፍርድ አለመፈጸሙን ጠቅሶ ተከራክሯል፡፡ከክርክሩ እንደተገነዘብነዉ
በአመልካች እና 2ኛ ተጠሪ መካከል በአፈጻጸም መ/ቁ/ 31745 መዝገብ ላይ ክርክር ተደርጎ
ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የለማዉ ቡና ላይ ፍርዱ እንዲፈጸም ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡ይሁንና በግምቱ ላይ
አለመግባባት ተፈጥሮ ከአንድም ሁለት ጊዜ በተለያዩ ባለሙያዎች እንዲገመት ተደርጎ በመጨረሻም
ሁለት ጊዜ ጨረታ ወጥቶ ገዥ ባለመገኘቱ 2ኛ ተጠሪ ተረክቦ የ2010 እና የ2011ዓ.ም ምርት
የቡናዉን ፍሬ ለቅሞ በመሸጥ እዳዉን እንዲሰበስ የሚል ትእዛዝ የተሰጠ ቢሆንም ተጠሪ እስከ
ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ አቅርቦ ሰበር ችሎት በመ/ቁ/167078 ላይ በቀን 15/05/2011
ዓ.ም የሥር ፍርድ ቤት ማጽናቱን መዝገቡ ያሣያል፡፡ከዚህም መገንዘብ የሚቻለዉ ጉዳዩ በክርክር
ሂደት ላይ እያለ የስር ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሳይፈጸም የምርት ዘመኑ ያለፈ መሆኑን ነዉ፡፡ ከዚህም
ሌላ ለስር ፍርድ ቤት በቀን 29/01/3013ዓ.ም የቀረበዉ ሪፖርት ይህንኑ የሚያስረዳ ከመሆኑም
በተጨማሪ አመልካች ለባንኩ በተለያዩ ጊዜያት የጻፋቸዉ አቤቱታዎች ይህንኑ የሚያረጋግጡ
ናቸዉ፡፡በዚህ ረገድ አመልካቹ ለባንኩ አስተዳደር አካላት በቀን 12/03/2011ዓ.ም ባቀረበዉ አቤቱታ
ባንኩ ቡናዉን እንድረከበዉና የቡናዉ ፍሬ ሳይበላሽ እንድለቅም መጠየቁ ንብረቱ ከእጁ
አለመዉጣቱን የሚያሣይ ነዉ፡፡በተጨማሪም በመ/ቁ/31745 ላይ የተሰጠዉ ትእዛዝ በፌዴራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር መ/ቁ/167078 ላይ በ15/05/2011ዓ.ም አያስቀርብም ተብሎ እስከተዘጋበት
ጊዜ ድረስም ሆነ ከዚያም በኋላ 2ኛ ተጠሪ ንብረቱንም ሳይረከብ እንደፍርዱም ሳይፈጸም መዝገቡ
በእንጥልጥል ላይ የቆየ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡2ኛ ተጠሪም አጥብቆ የሚከራከረዉ ንብረቱ
ከመገመቱ ዉጪ በወቅቱ አለመረከቡን እንዲሁም ለመረከብ የሚያስገድደዉ ህግ አለመኖሩን
ነዉ፡፡በዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባዉ ጉዳይ በሁለተኛ ጨረታ ገዥ ያልቀረበ እንደሆነ የፍርድ
ባለገንዘቡ ንብረቱን እንዲረከብ ሊታዘዝ ይችላል የሚለዉ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 428/2/ ድንጋጌ
በራሱ ሲታይ ፈቃጅ እንጂ አስገዳጅ አይደለም፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰበር ችሎቱ በሰጠዉ ዉሳኔ
እንዳመለካተዉ ንብረቱን ለመረከብ የባለገንዘቡ ፈቃደኛ መሆን አስፈላጊ እንደሆነ ያሣያል፡፡መ/ቁ
128776 ቅጽ 21 መመልከት ይቻላል፡፡ስለሆነም 2ኛ ተጠሪ በአፈጻጸም መ/ቁ/ በመ/ቁ/31745 ላይ
ንብረቱን መረከቡ ወይም እንደፍርዱ የተፈጸመለት መሆኑ ካልተረጋገጠ ወይም መብቱ በይርጋ ቀሪ
ነዉ ካልተባለ በስተቀር በማናቸዉም ጊዜ አቤቱታ በማቅረብ የአፈጻጸም መዝገቡን በማንቀሳቀስ
እንደፍርዱ እንደፈጸምለት መጠይቅ የሚከለክለዉ የህግ ምክንያት የለም፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ ባልና ሚስቱ ንብረታቸዉን ለመከፋፈል ባስከፈቱት የአፈጻጸም መዝገብ ላይ 2ኛ


ተጠሪ ያቀረበዉ አቤቱታ የተስተናገደበት አግባብ ማየቱ ተገቢ ነዉ፡፡ከአንድ የፍርድ ባለእዳ ላይ
መብት የሚጠይቁ ብዙ የፍርድ ባለመብቶች ሲቀርቡ ፍርድ ቤቱ በፍርዱ መሰረት ያለመፈጸሙን
ካረጋገጠ በኋላ ተገቢዉን ትእዛዝ መስጠት እንደሚችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 403 ድንጋጌ ይዘት
ያመላክታል፡፡ከዚህ አኳያ ተጠሪዎች በየፊናቸዉ የአፈጻጸም መዝገብ ያስከፈቱ ሲሆን ፍርዱ
ማስፈጸምያ እንዲሆን የተባለዉ ንብረት አንድ የቡና ኢንቨስትመንት ይዞታ ነዉ፡፡ፍርድ ቤቱም በሌላ
አግባብ ለባለመብቶቹ እንደፍርድ አለመፈጸሙን ካረጋገጠ በኋላ የፍርድ ባለመብቶች አቤቱታ
ተቀብሎ አፈጻጸም ክርክሩን በአንድ መዝገብ መምራቱ ከስነስርዓት ዉጪ ነዉ የሚባልበት ምክንያት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የለም፡፡ምክንያቱም የፍርድ ባለእዳ ንብረት ሳይከፋፈል ወይም በሌላ ማናቸዉም ሁኔታ ለሶስተኛ
ወገን ከመተላለፉ በፊት የሁሉንም የፍርድ ባለገንዘብ እዳ መከፈል የሚያስችል ሁኔታ በስነስርዓት
ህጉ የተዘረጋዉን ስርዓት ተከትሎ ማስፈጸም የፍርድ ቤቱም ሃላፊነት ነዉና፡፡በሌላ በኩል 2ኛ
ተጠሪ በመብቱ ሳይሰራ የቀረዉ እና ምርቱ ሳይሰበሰብ ለብክንት የተዳረገዉ በባንኩ ችግር ነዉ
በማለት አመልካቹ ያቀረበዉን ክርክር እና ህጋዊ ዉጤቱ ምንድነዉ የሚለዉን ስንመለከት
በእርግጥም ፍሬዉ ሳይለቀም የቀረዉ በማን ጥፋት ነዉ የሚለዉን መመርመር ያስፈልጋል፡፡በዚህ
ረገድ አመልካች የሚከራከረዉ በወቅቱ 2ኛ ተጠሪ እንዲረከብ የተሰጠዉ ትእዛዝ ሳይፈጸም የቀረዉ
በተጠሪ ጥፋት ነዉ ቢልም 29/01/2013ዓ.ም የቀረበዉ ሪፖርት የሚያሣየዉ በአንድ በኩል የቡና
ልማቱ ከአመልካች እጅ አለመዉጣቱን ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ 2010 እና 2011ዓ.ም ምርት
ወድቆ መጥፋቱን ያሣያል፡፡ሆኖም ግን 2ኛ ተጠሪ ተረክቦ ነበር የሚል ማረጋጫ ካለመቅረቡም በላይ
ፍሬዉ ሳይለቀም የጠፋዉ በእርግጥም በ2ኛ ተጠሪ ጥፋት ነዉ ወይስ አይደለም የሚለዉ ተጨማሪ
ማጣራት የሚፈልግ ጉዳይ ነዉ፡፡ይህ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካቹ የሚኖረዉ መብት ቀደም
ሲል ለባንኩ ሃላፊዎች በጻፈዉ ማሳሰቢያ ላይ እንደገለጸዉ ለጉዳቱ ኪሳራ የመጠየቅ መብት
ከሚሰጠዉ በስተቀር እንደፍርዱ ተፈጽሟል ወይም ባለእዳዉ ግዴታዉን ተወጥቷል ብሎ
ለመደምደም የ2ኛ ተጠሪን አፈጻጸም ጥያቄ ላለመቀበል የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ሆኖ
አላገኘንም፡፡

3ኛ ተጠሪን በተመለከተ ከመዝገቡ እንደተረዳነዉ ለአፈጻጸሙ መሰረት የሆነዉ ፍርድ በፌዴራል


ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/175214 ላይ በ09/02/2011ዓ.ም የተሰጠ ፍርድ ስለመሆኑ ግራቀኙን
አላከራከረም፡፡በዚሁ ፍርድ መሰረት እንዲያስፈጽምለት ባንኩ በመ/ቁ/224096 ላይ የአፈጻጸም
አቤቱታ ለፌዴራል ከፍተኛ ካቀረበ በኋላ የፍርድ ባለእዳ ንብረት ላይ እንዲፈጸም መጠየቁን
ተከትሎ ንብረቱ የሚገኝበት የጅማ ዞን ፍርድ ቤት በዉክልና እንዲያስፈጽም ትእዛዝ በመሰጠቱ
የመ/ቁ/51721 ተከፍቶ 1ኛ ተጠሪ ካስከፈተችዉ የአፈጻጸም መዝገብ ቁጥር 42899 ጋር ተጣምሮ
ትእዛዝ የተሰጠበት መሆኑን የክርክሩ አመጣጥ ያሣያል፡፡በዚህ ላይ የአመልካች ቅሬታ ነጥብ
በጨረታ መሸጥ የሚገባዉ ለኢንቨስትመንት የወሰደዉ 200 ሄክታር በሙሉ ሳይሆን የለማ ቡና
ያለበት 78 ሄክታር ብቻ ተለይቶ መሆን አለበት በማለት ነዉ፡፡ሆኖም በዚህ ረገድ ለስር ፍርድ ቤት
የቀረበ ክርክር ዉድቅ የተደረገዉ የኢንቨስትመንት ይዞታዉ በባልና ሚስቱ መካከል ከመከፋፈሉ
በፊት የሌሎቹ ባለገንዘቦች እዳ እንዲከፈል በሚል ምክንያት በመሆኑና በኢንቨስትመንት የተያዘዉ
ይዞታ ተከፋፍሎ ወይም ተሸንሽኖ የሚሸጥበት አግባብ ባለመኖሩ ክርክሩ ተቀባይነት አለማግኘቱ
ስህተት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም፡፡

ሲጠቃለል ለፍርድ ባለገንዘቦች እንደፍርዱ አለመፈጸሙን በማረጋገጥ የፍርድ ባለእዳ ንብረት


በሃራጅ ተሽጦ ለፍርድ ባለገንዘቦች እንዲከፋፈል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠዉ ትእዛዝ ስለፍርድ
አፈጻጸም በፍ/ብ/ስ/ስ/ ህጉ የተዘረጋዉን ስርዓት ይዘት ዓላማ ያገናዘበ ነዉ ከሚባል በስተቀር
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም፡፡በዚሁ አግባብ
ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉሳኔ

1ኛ/በዚህ ጉዳይ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 42899 ላይ የሰጠዉን ትእዛዝ በማጽናት
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 224389 እና በመ/ቁ/224547 ላይ
የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ጸንቷል፡፡

2ኛ/በዚህ ችሎት በዚህ መዝገብ ላይ በ28/05/2013ዓ.ም እና በመ/ቁ/201929 ላይ


በ28/05/2013ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትእዛዝ ተስቷል፡፡ይጻፍ፡፡

3ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ግራቀኙ የየራሳቸዉን ወጪ ይቻሉ ብለናል፡፡

መዝገቡ በአዳሪ ተሰርቶ በቀን 15/03/2014ዓ.ም በችሎት ተነቧል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሠ/መ/ቁጥር 201974

ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ/ም


ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ ታደሰ ንጉሴ

ተጠሪ ፡- አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
ጉዳዩ የሥራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከተጠሪ ጋር በ1989 ዓ/ም በፈፀሙት የስራ ውል በባላንስ ሠራተኛነት የስራ
መደብ ላይ በወር 13,034.00 እየተከፈላቸዉ እንዲሰሩ ተቀጥረዉ ሲሰሩ መቆየታቸዉን፤ነገር ግን ያለምንም
ምክንያት በቀን 07/09/2011ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ የትራንዛክሽን ሥራ በመስራት በማሳለፍ ብድር በመዝጋት
ባንኩ ማግኘት ያለበትን በማሳጣት ጥፋት ፈጽመሀል በማለት ሥራዬ ትራንዛክሽን ማሳለፍ ባለመሆኑ
የሰራሁት ጥፋት ሳይኖር ከሕግ-ዉጭ ከሥራ አሰናብቶኛል፡፡ስለሆነም ወደ ሥራ እንዲመልሰኝ
እንዲወሰንልኝ፡፡ይህ የሚታለፍ ከሆነ የስንብት ክፍያ ብር 95,582.67 ፣የ15 ቀን ደመወዝ ብር 6,517.00
፣ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ ብር 39,102.00 ፣ካሳ የ6 ወር ደመወዝ ብር
78,204.00፣የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ብር 63,550.29፣ተጠሪ ባንክ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ከ20
ዓመት በላይ ላገለገለ ሰራተኛ 21 ካራት ወርቅ ስለሚሰጥ የዚህ ዋጋ የአንድ ካራት ዋጋ ብር 1,700.00 ብር
35,700.00፣የቦነስ ክፍያ የ2011 ዓ/ም ብር 39,102.00፣ከ2009-2011ዓ/ም ድረስ ያልተጠቀምኩበትን የሶስት
ዓመት የአመት እረፍት ወደገንዘብ ቀይሮ እንዲከፍለኝ በአቃላይ ብር 370,991.29 (ሶስት መቶ ሰባ ሺህ
ዘጠኝ መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም) እንዲከፈላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ለክሱ በሰጠዉ መልስ አመልካች በተጠሪ መስሪያ ቤት በካሼርነት የስራ መደብ ተቀጥረዉ በሚሰሩበት
ወቅት የባንኩ ደንበኛ የሆኑት መሀመድ ተካ ብድር ወስደው የነበረውን ገንዘብ መመለስ ስላልቻሉ በዋስትና
የተያዘውን ንብረት ለመሸጥ የወጣው የጨረታ ማስታወቂያ አንድ ቀን ሲቀር በቀን 18/07/2018 እ.እ.አ
ከቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ ጋር በመሆን ባለእዳው በቼክ 700,000.00(ሰባት መቶ ሺህ ብር) ገቢ እንዳደረጉ
አስመስለዉ የሀሰት ሂሳብ አሳልፈዉ ለጨረታው እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ በአመልካች ድርጊት ተጠሪ ብር
4,794.52 አጥቷል፡፡ አመልካች በቀን 11/11/2010 ዓ/ም በሀሰት ገቢ የሆነውን ብር ቆጥሬ ተቀብያለሁ
በማለት አፊሰር ይህንን ገንዘብ ገቢ እንዲያደርግ አድርገዋል፡፡ነገር ግን ገንዘቡ ገቢ የሆነበት ቀን ሲታይ ብር
350,000.00 በቀን 23/11/2011ዓ/ም ገቢ የሆነ ሲሆን ሌላዉ ብር 350,000.00 ገቢ የሆነዉ በቀን
350,000.00 ነዉ፡፡አመልካች ገንዘቡ ገቢ የሆነባቸዉን ኦርጅናል ሰነዶች እንዲጠፉ አድርገዋል፡፡አመልካች
የፈጸሟቸዉ ድርጊቶች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27(1/ሐ) እና በባንኩ የሠራተኞች የሥራ ሂደት
ፖሊሲ ቁጥር 1/ለ አንቀጽ 1/1 መሰረት በከባድ ማታለል ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያስናበት ጥፋት
በመሆኑ አመልካችን በማሰናበት የተወሰደዉ እርምጃ ሕጋዊ ነዉ፡፡ስለሆነም አመልካች ወደሥራ ሊመለስ
አይገባም እንዲሁም ሕገ-ወጥ ስንብት ተፈጽሟል በሚል የጠየቋቸዉ ክፍያዎችም ሊከፈላቸዉ
አይገባም፡፡በባንኩ አሰራር መሰረት ደመወዝ የሚከፈለዉ በአዉሮፓ አቆጣጠር ወር በገባ በ20ኛ ቀን ላይ
ጀምሮ በመሆኑ እስከ ቀን 20/06/2011ዓ/ም ድረስ ያለዉ የግንቦት ወር ደመወዝ ስለተከፈላቸዉ ያልተከፈለ
ደመወዝ የለም፡፡ያልተከፈለ ደመወዝ መኖሩን በመግልጽ ለተጠሪ ያመለከቱት ነገር ባለመኖሩ ክፍያ ዘግይቷል
በሚል የጠየቁት ሊከፈላቸዉ የሚገባ አይደለም፡፡ዉሉ የተቋረጠዉ የቦነስ ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት በቀን
07/09/2011ዓ/ም ስለሆነ ቦነስ ሊከፈላቸዉ አይገባም፡፡ አመልካች ብድር ስላለባቸዉና በብድር ዉሉ መሰረት
ሠራተኛዉ ስራ ሲለቁ ከማንኛዉም ተከፋይ ክፍያ(ከፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ) ላይ ጭምር ተቀንሶ
እንደሚከፈል ስለተመለከተ የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያቸዉ ለእዳቸዉ ገቢ ሆኗል፡፡አመልካች የ60.5 ቀን
የአመት እረፍት እንዳላቸዉ ባይካድም ሊከፈላቸዉ የሚገባዉ የባንኩን አሰራር በመከተል ያለባቸዉን እዳ ብር
294,429.66 ከፍለዉ ክሊራንስ ሲያቀርቡ ነዉ፡፡ያቀረቡት የወርቅ ሽልማት ጥያቄ የሕግ መሰረት የለዉም
በማለት መልሳቸዉን በመስጠት ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 09416 ላይ የግራ ቀኙን ክርክር በመስማትና ማስረጃዎችን በመመርመር በቀን
06/05/2012 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገዉ የሥራ ዉል ለማቋረጥ ምክንያት የሆነዉ
የባንኩ ባለዕዳ እዳዉን መክፈል ባለመቻሉ ባንኩ በመያዣነት የተያዘዉን ንብረት ለመሸጥ ጨረታ አዉጥቶ
እያለ አመልካች ባለዕዳዉ ብር 700,000.00 ገቢ እንዳደረገ በማስመሰል ትራንዛክሽን በማስተላለፍ ባንኩ
የወጣዉ ጨረታ ሂደት እንዲቋረጥ በማድረግ ጥፋት መፈጸሙ በኦዲት ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ነው፡፡
ይሁን እንጂ አመልካች የትራንዛክሽን መደብ ሠራተኛ ሳይሆኑ ገንዘብ ያዥ እንደሆኑ ተጠሪም አልካደም፡፡
ስለዚህ አመልካች ይህን ሂሳብ መዝጋታቸዉን የሚያሳይ ማስረጃ የለም፡፡ አመልካች ሲሰሩ በነበሩበት የሥራ
መደብ ላይ የፈፀሙት ጥፋት የለም፡፡ የገንዘብ ማስተላለፍም ሆነ ጨረታን መዝጋት ሥራ የአመልካች ድርሻ
መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም፡፡ ለሥራ ውል መቋረጥ ምክንያት የሆነው ገንዘብ ለተጠሪ መስሪያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቤት ገቢ መሆኑንም ተጠሪ አምኗል፡፡ በመሆኑም የሥራ ውሉ የተቋረጠው በሕገ-ወጥ መንገድ በመሆኑ


በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 43 መሰረት ተጠሪ አመልካችን ወደ መደበኛ ሥራቸዉ እንዲመልሳቸዉና
ከሐምሌ እስከ ጥር 2012 ዓ/ም ድረስ ያለዉን ደመወዛቸዉን እንዲከፍላቸው ወስኗል፡፡

ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ፍርድ ቤቱም
በመ/ቁጥር 41159 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 26/08/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ውሳኔ የስር ፍርድ ቤትን
ውሳኔ በማፅናት ወስኗል፡፡

በመቀጠል ተጠሪ የሰበር አቤቱታውን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አቅርበው ችሎቱም
በመ/ቁጥር 336132 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 15/03/2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠዉ ዉሳኔ በስር
የቀረበው የኦዲት ውጤት ማስረጃ ተጠሪ የስራ ድርሻዬ የእዳ ገንዘብ ማስከፈል አይደለም ይበሉ እንጂ ደረቅ
ቼክ በመውሰድ ባለእዳው እዳውን እንደከፈለ በማስመሰል ጨረታው እንዲሰረዝ ማድረጋቸዉንና ደንበኛው
ያለበትን እዳ ካዘጋ በኋላ ደንበኛው ያለበትን ብድር 2ኛ ዙር ክፍያ እዳ መክፈሉን የኦዲት ሪፖርቱ
ያረጋግጣል፡፡ዋናው እዳ ቢከፈልም ተጠሪ ሊያገኝ የሚገባውን በማጣቱ የኢኮኖሚ ጉዳት ደርሶበታል፡፡የሥር
ፍርድ ቤት ጨረታዉ እንዲሻር ያደረገዉ የባንኩ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን እንጂ አመልካች ጥፋት
መፈጸሙን የኦዲት ሪፖርቱ አያሳይም ያለ ቢሆንም ከተጠሪዉ ቅርንጫፍ ሥራ አሲኪያጅ ጋር በመሆን
ደረቅ ቼክ በመቀበል እዳ ካዘጋ በኋላ ደንበኛዉ ያለበትን ብድር የ2ኛ ዙር ክፍያ መክፈሉ ቢረጋገጥም
አመልካች በተጠሪ ላይ የብር 4,794.52 የኢኮኖሚ ጉዳት እንዲደርስበት አድርገዋል፡፡ስለሆነም አመልካች
በተጠሪ ላይ የኢኮኖም ጉዳት በማድረሳቸዉ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 27(1/ሸ) መሰረት
ያለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብታቸዉን ጥፋት ፈጽመዋል፡፡በተጨማሪም አመልካች ደረቅ ቼክ በመቀበል በአዋጅ
ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1/ሐ) መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብታቸዉን የማታለል ድርጊት
ፈመዋል፡፡ስለሆነም ተጠሪ አመልካችን ያሰናበተዉ በሕግ አግባብ ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ
በመሻር ወስኗል፡፡ አመልካች በቀን 27/05/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት በዚህ መልኩ
በተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታቸዉ ይዘት በአጭሩ የሚከተለዉ
ነዉ፡፡

አመልካች የተቀጠርኩበት የሥራ መደብ የካሼር የሥራ መደብ ሲሆን የሥራ ድርሻዬ ደግሞ ገንዘብ በካዝና
ቆጥሮ ማስቀመጥ፣ካሽ ከሲስተም ጋር በማገናዘብ ወጪና ገቢ ሚዛናዊ(ባላንስ) መሆኑን ማረጋገጥ መሆኑን
የሥራ ዉሌ የሚያሳይ ሲሆን ተጠሪም ከሥር ጀምሮ ይህንን አልካደም፡፡አመልካች ገንዘብ ትራንዛክት
የማድረግም ሆነ ብድር የመዝጋት ሥልጣን የለኝም፡፡በጨረታዉ ላይም አልተሳተፍኩም፡፡ተጠሪ ያሰናበተኝ
ትራንዛክሽን በማሳለፍ እና ብድር በመዝጋት ባንኩ ማግኘት የሚገባዉን ብር 4794.52 አሳጥቷል በማለት
ቢሆንም ያሰናበተኝ የሥራ ድርሻዬን ወደ ጎን በመተዉ በመሆኑ በሰ/መ/ቁጥር 92466 ላይ የተሰጠዉት
የሕግ ትርጉም የሚቃረን በመሆኑ ስንብቱ ከሕግ ዉጭ ነዉ፡፡ገንዘብ ትራንዛክሽን የሚደረገዉ የሚስጥር
ቁጥር ባለዉ የትራንዛክሽን ሠራተኛ ሲሆን ብድር የሚዘጉትም ይህ የሥራ መደብ የሚመለከታቸዉን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ኃላፊዎች እንደሆነ የተረጋገጠ ሲሆን በማንኛዉም የባንኪንግ አገልግሎት የሚሰራበት አሰራር ነዉ፡፡ቼኩንና
የተለያዩ ሰነዶችን ደብቋል የተባልኩትም በማስረጃ ካለመረጋገጡም በላይ የሥራ ድርሻዬን የሚመለከት
አይደለም፡፡የሻሸመነ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ከተበዳሪዉ የተከፈለዉን ብር 700,000.00 በራሳቸዉ ፊርማ
ገቢ አድርገዋል፡፡ተጠሪ ከሥራ ያሰናበተኝ ድርጊቱ ተፈጸመ ከተባለ ከአንድ አመት በኋላ በመሆኑ በአዋጅ
ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 ስር በተደነገገዉ መሰረት በ30 ቀን በኋላ የተወሰደ እርምጃ በመሆኑ
በይርጋ የታገደ ሆኖ እያለ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ስንብቱ በሕግ አግባብ የተፈጸመ ነዉ በማለት የስራ
መደቤንና የሥራ ድርሻዬን ወደ ጎን በመተዉ የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ
በማለት አቤቱታቸዉን አቅርበዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ጥፋት አጥፍቷል የተባለበት የስራ መደብና እሳቸው
የሚሰሩት የስራ መደብ ቦታ ተዛማጅነት ያለው መሆን አለመሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የሥራ ስንብቱ ሕጋዊ
ነዉ ተብሎ የተወሰነበትን አግባብነት ተጠሪ ባሉበት እንዲመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን
15/08/2013ዓ/ም የተጻፈ በአጭሩ የሚከተለዉን መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡

አንድ የባንኩ ተበዳሪ እዳዉን ባለመክፈሉ ምክንያት ባንኩ በመያዣነት የያዘዉን ንብረት በጨረታ ለመሸጥ
የጨረታ ማስታወቂያ አዉጥቶ ጨረታ ሊደረግ አንድ ቀን ቀርቶ እያለ አመልካች ከተበዳሪዉ ለምን ደረቅ
ቼክ ተቀብለን ብድሩን አንከፍልለትም በማለት በወቅቱ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ለነበሩት የማጭበርበር
ሀሳብ በማቅረብና በመስማማት በተበዳሪዉ ሂሳብ ዉስጥ ገንዘብ ሳይኖር ደረቅ ቼክ በመቀበል ለዚህ ሀሰተኛ
ትራንዛክሽን እንዲመች ወደሂሳቡ ጥሬ ገንዘብ ገቢ ማድረጊያ ቅጽ በመሙላት ብር 700,000.00 ከተበዳሪዉ
ሂሳብ ገቢ እንደሆነ በማስመሰል የደንበኞች ኦፊሰር አስፈርመዉ ትራንዛክሽኑ ፖስት እንዲደረግ ማድረጋቸዉ
ተረጋግጧል፡፡አመልካች አሁን ላይ የሲስተም መጠቀሚያ ፓስወርድ የለኝም የሚሉት ካጠፉት ጥፋት ጋር
የሚገናኝ አይደለም፡፡ስንቅ የሌለዉ ቼክ እንዲጻፍ ሀሳብ ከማቅረብ ጀምሮ ስለተሳተፉ የሲስተም ፓስወርድ
እንዲጠቀሙ የሚያስገድዳቸዉ ሁኔታ ባለመኖሩና በእለቱ የእለት ቲኬቶች ጠቅለለዉ ሲይዙ የነበሩትም
አመልካች ስለነበሩ ጉዳዩ ከእሳቸዉ ሥራ ጋር እንደማይገናኝ በመግለጽ ያቀረቡት ክርክር ዉድቅ ሊሆን
ይገባል፡፡የአመልካች ስራ ካሽ በካዝና ቆጥሮ ማስቀመጥና ከኮምፒዉተር ሲስተም ጋር ማገናዘብ እና ሚዛናዊ
መሆኑን ማረጋገጥ እንደሆነ ቢገልጹም በካዝና ዉስጥ ያለ ገንዘብ አረጋግጦ ማስቀመት ቀርቶ ገቢ ያልሆነን
ገንዘብ ደረቅ ቼክ በመቀበል ገቢ እንደሆነ በማስመሰል የማይጠበቅባቸዉን ተግባር ፈጽመዋል፡፡የእለቱ ሂሳብም
ባላንስ አለመሆኑን ለስር ፍርድ ቤት አስረድተናል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
ጉዳዩ ከዚህ አንጻር ተመርምሮ ጥፋቱ የአሁን አመልካች መሆኑ ተረጋግጦ ስንብቱ ሕጋዊ ነዉ ተብሎ
በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም፡፡አመልካች ይርጋን አስመልክቶ ያነሱት መከራከሪያ በስር ፍርድ ቤት
ያልተነሳ አዲስ ክርክር በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ሰ/ሕግ ቁጥር 329/1 መሰረት ተቀባይነት ሊኖረዉ
አይገባም፡፡አመልካችም በቀን 26/08/2013ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከዚህ በላይ የተመዘገበዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት ሲሆን እኛም
የሰበር አጣሪ ችሎት የየዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች በተሰጠ ዉሳኔ የተፈጸመ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ
መርምረናል፡፡

እንደመረመርነዉም አመልካች ተቀጥረዉ ሲሰሩ የነበረዉ የሥራ መደብ የካሼር መደብ(የገንዘብ ያዥነት
የሥራ መደብ) እንደሆነ ተጠሪ አልካደም፡፡ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዳኝነት ሥልጣን የተመለከተዉ ፍርድ
ቤት እና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተዉ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃዎችን
መርምረዉና መዝነዉ አመልካች ገንዘብ ያዥ(ካሼር) እንጂ የትራንዛክሽን መደብ ሠራተኛ እንዳልሆኑ፤
የገንዘብ ማስተላለፍም ሆነ ጨረታን መዝጋት ሥራ የአመልካች ድርሻ አለመሆኑንና ከዚህ ጋር በተያያዘ
ተጠሪ አመልካችን ሲያሰናብት አመልካች የፈጸሙት ጥፋት ነዉ የተባለዉን ድርጊት አመልካች የፈጸሙ
ስለመሆኑ ተጠሪ ባቀረቡት ማስረጃ አላስረዱም በሚል ተጠሪ አመልካችን ከሕግ-ዉጭ አሰናብቷል የሚል
ድምዳሜ ላይ በመድረስ ተጠሪ ዉዝፍ ደመወዝ በመክፈል አመልካችን ወደ ሥራ ገበታቸዉ እንዲመልስ
ወስነዋል፡፡

ዋናዉን ክርክር ከመመርመራችን በፊት አመልካች በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ
27/3 ስር የተደነገገዉን ይርጋ አስመልክቶ ያነሱትን ክርክር ተመልክተናል፡፡በዚህ ድንጋጌ ላይ አንድ አሠሪ
ዉሉን ለማቋረጥ የሚያስችል በአዋጁ አንቀጽ 27/1 ስር የተመለከተ ምክንያት መከሰቱት ካወቀብ ቀን ጀምሮ
ባለዉ 30 ቀን ዉስጥ ዉል የማቋረጥ እርምጃ ካልወሰደ መብቱ በይርጋ እንደሚታገድ ተደንግጓል፡፡ይህ ይርጋ
የተጠሪን ዉል የማቋረጥ መብት የሚያሳጣ በመሆኑ አመልካች ምክንያቱ የተከሰተበትን ቀን እና ተጠሪ
ምክንያቱ የተከሰተበትን ቀን መቼ እንዳወቀ በማሳየት ለስር ፍርድ ቤት በሥነ ሥርዓት ሕጉ አግባብ በግለጽ
ክርክር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ሆኖም በዚህ መልኩ ለስር ፍርድ ቤት ክርክር ማቅረባቸዉን የሥር ፍርድ
ቤት ዉሳኔ ግልባጭ አያሳይም፡፡ይህንን መከራከሪያ ለስር ፍርድ ቤት አቅርቤያለሁ በማለት በመልስ
መልሳቸዉ ላይ ያነሱ መከራከሪያም የለም፡፡በመሆኑም በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ደረጃ በስር ፍርድ ቤት
ያልተነሳ መሰረታዊ ሕግ ላይ ያለን የይርጋ መቃወሚያ በማንሳት ለመከራከር ስለማይቻል ከዚህ አኳያ
ያቀረቡትን አቤቱታ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 329/1 መሰረት አልተቀበልንም፡፡

በሌላ በኩል እንደሚታወቀዉ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች
አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 እና በተሻሻለዉ የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 64(2/ሐ) ስር
እንደተመለከተዉ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎትም ሆነ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የተሰጠዉ ሥልጣን መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ዉሳኔ እንዲያርሙ ነዉ፡፡ ሰበር
ችሎት የማስረጃ አቀራረብን፣ አግባብነትንና ተቀባይነትን (Production,relevancy and admissibility of
evidence)እንዲሁም የማስረጃ ምዘናን (weight of evidence) የሚመለከቱ መሰረታዊ መርሆዎች ተጥሶ
በግልጽ ተጥሶ የተሰጠ የመጨረሻ ዉሳኔ መኖሩን አረጋግጦ ስህተቱ እንዲታረም ሊወስኑ ከሚችሉ በስተቀር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተከራካሪ ወገኖች ማስረጃ ለመቀበል፣ለመስማትና ለመመዘን ሥልጣን ለተሰጣቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች
አቅርበዉ ተመርምረዉ የተመዘኑትን ማስረጃዎች በድጋሚ የመመዘን ተግባር ዉስጥ በመግባት ማስረጃዎችን
በመመርመርና በመመዘን አከራካሪ የሆነዉ ፍሬ ነገር መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጣን
የላቸዉም፡፡በመሆኑም ሰበር ሰሚ ችሎት ማስረጃዎችን የመመርመርና የመመዘን ሥልጣን የተሰጣቸዉ
የሥር ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸዉን ማስረጃዎች መርምረዉና መዝነዉ ያረጋገጡትን ፍሬ ነገር ወደ ጎን
በመተዉ ማስረጃ በመመርምርና በመመዘን በፍሬ ነገር ድምዳሜ ላይ በመድረስ የሚሰጠዉ ዉሳኔ በሕግ
ከተሰጠዉ ሥልጣን ዉጭ በመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ፡፡

በያዝነዉ ጉዳይ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ዳኝነት ሥልጣን የተመለከተዉ የወረዳ ፍርድ ቤት እና ጉዳዩን
በይግባኝ ያየዉ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና የቀረቡትን ማስረጃዎች በመመርመርና
በመመዘን የአመልካች የሥራ መደብ ገንዘብ ያዥነት እንደሆነ፣አመልካች ገንዘብ የማስተላለፍ (የትራንዛክሽን)
የሥራ መደብ ሠራተኛ እንዳልሆኑና ገንዘብ የማስተላለፍ ተግባር የሥራ ድርሻቸዉ እንዳልሆነ፣ከብድር
ገንዘብ አከፋፈልም ሆነ የተበዳሪዉን ንብረት በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ጨረታ እንዲቋረጥ ከማድረግ ጋር
በተያያዘ አመልካች የሥራ ድርሻቸዉ ስላልሆነ ሚና እንዳልነበራቸዉና ፈጸሙ የተባለዉን ጥፋት
ስለመፈጸማቸዉ ተጠሪ ባቀረባቸዉ ማስረጃዎች አለማስረዳቱን በማረጋገጥ ተጠሪ አመልካችን በሕገ-ወጥ
መንገድ አሰናብቷል በማለት የሰጡት ዉሳኔ ከማስረጃ ምዘና መርህ አተገባበር አንጻር ጉድለት አለበት ሊባል
የሚችል አይደለም፡፡በሌላ በኩል የክልሉ ሰበር ችሎት በተጠቀሰዉ መሰረት በሕግ ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን
የተሰጣቸዉ የሥር ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡትን ፍሬ ነገር ወደ ጎን በመተዉ በራሱ ማስረጃዎችን
በመመርመርና በመመዘን አመልካች በተጠሪ የኢኮኖሚ ጥቅም ላይ ጉዳት ማድረሳቸዉና የማታለል ድርጊት
መፈጸማቸዉ ተረጋግጧል የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ ተጠሪ አመልካችን ያሰናበተዉ በአዋጅ ቁጥር
377/1996 አንቀጽ 27(1/ሐ እና ሸ) መሰረት በመሆኑ ስንብቱ ሕጋዊ ነዉ ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ከማስረጃ
ምዘና መርህ አተገባበር አንጻር በስር ፍርድ ቤቶች የተፈጸመ ስህተት መኖሩን የማያሳይና በሕግ ከተሰጠዉ
ሥልጣን ዉጭ ማስረጃ የመመዘን ተግባር ዉስጥ በመግባት የሰጠዉ ዉሳኔ በመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ፡፡ ስለሆነም ተከታዩን ወስነናል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. የሻሸመኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 09416 ላይ በቀን 06/05/2012 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እና
የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 41159 ላይ በቀን 26/08/2012 ዓ/ም የሰጠዉ
ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል፡፡

2. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 336132 ላይ በቀን 15/03/2013
ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል፡፡

3. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ተወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ት እ ዛ ዝ

1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ ግራ ቀኙ ሲጠይቁም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡


2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ እግድ ካለ ተነስቷል፡፡ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት


ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ7/7
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 201980

ቀን ፡- ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ መሠለ ማሚቶ - አልቀረቡም

ተጠሪ ፡- አቶ እሸቱ መኮንን - ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ
መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ
ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች በአጭር ሥነ-ሥርዓት
ያቀረቡት ክስ ተጠሪ ላጋጠመው ችግር እንዲያውለው ለሠጠኋቸው ገንዘብ የቼክ ቁጥሩ 01960861 የሆነ
ብር 120,000.00 የተጻፈበት ቼክ ፈርመው ሠጥተው ባንክ ለክፍያ ስሄድ ሂሳቡ በቂ ስንቅ የለውም ተብሎ
የተመለሰ በመሆኑ ገንዘቡ እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ የመከላከያ ማስፈቀጃ ምክንያታቸው
ተቀባይነት በማግኘቱ ያቀረቡት መልስ ለአመልካች የምመለሰው ገንዘብ የለም፣ ለአመልካችም የሰጠሁት ቼክ
የለም፡፡ በክሱ የቀረበው ቼክ አመልካች ቤት ለሚጣለው ዕቁብ እኔ አባል በመሆኔ እጣ ወጥቶልኝ ብር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

450,000.00 ገንዘብ ስወስድ ቀንና የገንዘብ መጠን የሌለው ቼክ ለእቁቡ ዳኛና ፀሀፊ በዋስትና የሰጠሁ ሲሆን
አመልካች ራሱ ቼኩ ላይ ጽፎ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡

የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ ተጠሪ ላይ በቼኩ ምክንያት የወንጀል ክስ ቀርቦበት
ቼኩን ለአመልካች አለመስጠቱንና ለዕቁብ ለዋስትና የተሰጠ ቼክ መሆኑ ተረጋግጦ ከክሱ በነጻ ተሰናብቷል፡፡
ቼኩ ለዕቁብ ዋስትና እንጂ ለአመልካች ያልተሰጠ መሆኑ ስለተረጋገጠ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት
ወስኗል፡፡ የአሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ግራቀኙን አከራክሮ የሥር ፍርድ ቤት
ውሳኔን አጽንቷል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ለቀረበው ክስ ቼኩና
የባንክ ማረጋገጫ ቀርቧል፡፡ ለጉዳዩ የሰው ማስረጃ ሊሰማ አይገባም፡፡ የሰው ማስረጃ ከተሰማም የአመልካች
ማስረጃም ሊሰማ ሲገባ በተጠሪ ምስክሮች ብቻ መወሰኑ ስህተት ያለበት ነው የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ
ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ ቼክን መሠረት ያደረገው ክስ ውድቅ መደረጉ ከንግድ ሕግ አንቀጽ 717 እና
ተከታይ ድንጋጌዎች አንጻር ለማየት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ በማዘዙ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ አመልካች
የሠው ማስረጃ ባለመዘርዘሩ አልተሰማለትም፡፡ ቼኩ ለዕቁብ ዋስትና የተሰጠ ነው፡፡ ለቼክ ክርክር የሠው
ማስረጃ እንዳይቀርብ የሚከልክል ሕግ የለም፡፡ ተረጋግጦ የተወሰነ ነው ውሳኔው ሊፀና ይገባል በማለት
ተከራክረዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርከር፣ የሠበር አጣሪ ችሎት የያዘው
ጭብጥን በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካች በአጭር ሥነ-ሥርዓት ያቀረቡት ክስ ተጠሪ ላጋጠመው ችግር እንዲያውለው


ለሠጠኋቸው ገንዘብ የቼክ ቁጥሩ 01960861 የሆነ ብር 120,000.00 የተጻፈበት ቼክ ፈርመው ሠጥተው
ባንክ ለክፍያ ስሄድ ሂሳቡ በቂ ስንቅ የለውም ተብሎ የተመለሰ በመሆኑ ገንዘቡ እንዲከፈላቸው ዳኝነት
የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ የመከላከያ ማስፈቀጃ ምክንያታቸው ተቀባይነት በማግኘቱ ያቀረቡት መልስ ለአመልካች
የምመለሰው ገንዘብ የለም፣ ለአመልካችም የሰጠሁት ቼክ የለም፡፡ በክሱ የቀረበው ቼክ አመልካች ቤት
ለሚጣለው ዕቁብ እኔ አባል በመሆኔ እጣ ወጥቶልኝ ብር 450,000.00 ገንዘብ ስወስድ ቀንና የገንዘብ መጠን
የሌለው ቼክ ለእቁቡ ዳኛና ፀሀፊ በዋስትና የሰጠሁ ሲሆን አመልካች ራሱ ቼኩ ላይ ጽፎ ያቀረበው ክስ
ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክረዋል፡፡

በመሠረቱ ቼክ የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሀተታ የሌለበት ትዕዛዝ የያዘና ቼኩም እንደቀረበ የሚከፈል
መሆኑ በንግድ ሕግ ቁጥር 827/ሀ/ እና 854 ሥር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ቼኩ የታዘዘለት ሰው ቼኩን
ይዞ እንደቀረበ ቼኩ ሊከፈል ይገባዋል፡፡ ቼክ አውጪውም ሆነ የጀርባ ፈራሚዎቹ ለቼኩ አከፋፈል በንግድ
ሕግ ቁጥር 840 እና 868(ሐ) መሠረት ኃላፊዎች በመሆናቸው ቼክ ባልተከፈለ ጊዜ ተጠያቂዎች ይሆናሉ፡፡
በተያዘው ጉዳይ አመልካች በአጭር ሥነ-ሥርዓት ክሱን ያቀረቡ ቢሆንም ተጠሪ ክሱን ለመከላከል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ፍ/ቤቱ የተቀበለው በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 291 አግባብ ክርክሩ
በመደበኛው ሥርዓት የሚመራ ነው፡፡

ተጠሪ ቼኩ ቀንና የገንዘብ መጠን የሌለው መሆኑን ገልጸው የተከራከሩ ሲሆን በቼክ ላይ የሚጻፉ አስፈላጊ
መግለጫዎች ናቸዉ ተብለዉ በንግድ ሕግ አንቀጽ 827 ከፊደል ሀ እስከ ሠ ባሉት ንኡሳን አናቅጽ የተጠቀሱ
መግለጫዎች(Contents)፡- ሀ) የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ሐተታ የሌለበት ትእዛዝ፤ ለ) መክፈል የሚገባዉ
ከፋይ ስም፤ ሐ) የሚከፈልበት ቦታ፤ መ) ቼኩ የወጣበት ቦታና ጊዜ እና ሠ) ቼኩን ያወጣዉ ሰዉ ፊርማ
የሚሉ ናቸዉ፡፡በዚሁ ሕግ አንቀጽ 828 ስር ባለዉ የመግቢያ ዐረፍተ ነገር ላይ እንደተመለከተዉ ከእነዚህ
መግለጫዎች አንዱ እንኳን የሌለበት ሰነድ እንደ ቼክ እንደማይቆጠር ተመልክቷል፡፡በዚህ ድንጋጌ ላይ
“ከእነዚህ መግለጫዎች አንዱ እንኳን የሌለበት ሰነድ እንደ ቼክ አይቆጠርም” የሚለዉ አገላለጽ ላይ ላዩን
ሲታይ ግልጽ ቢመስልም አገላለጹ የሚያገለግለዉ መግለጫዎቹ ያልተሟላ ቼክ በቼክ አዉጪዉ ተፈርሞ
ለአምጪዉ በሚሰጥበት ጊዜ ነዉ ወይስ ቼኩ ለክፍያ ሲቀርብ ነዉ የሚለውን በመመልከት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመዝገብ ቁጥር 193270 ቼኩ በተሰጠ ጊዜ ከንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 አንጻር ቀንና የገንዘብ መጠኑ
ባለመጻፉ የተሟላ ባለመሆኑ እንደ Blank Cheque የሚቆጠር ቢሆንም ቀንና የገንዘብ መጠን ተሞልቶ
ለከፋዩ ባንክ በቀረበ ጊዜ ተሟልቶ ከቀረበ የንግድ ሕጉ አንቀጽ 827 እና 828 ያስቀመጣቸዉን አንድን ሰነድ
ቼክ የሚያሰኙ መገለጫዎችን የሚያሟላ ወይም እንደ ቼክ የሚቆጠር እና ሕጋዊ ዉጤት ያለው ነው
በማለት አስገዳጅ ትርጉም የሠጠበት በመሆኑ እና አመልካች ለክፍያ ባንክ ያቀረቡት ቼክ በቂ ስንቅ የለውም
መባሉ በቼኩ ላይ ያሉ መግለጫዎች ተሟልተው ለባንኩ መቅረቡን ስለሚያስገነዝብ ክስ የቀረበበት ቼኩ
ሕጋዊ ውጤት ያለው ሠነድ ነው ብለናል፡፡

ተጠሪ በሁለተኛ ደረጃ የሚከራከሩት እና የሥር ፍርድ ቤት የተቀበለው ቼኩ ለዕቁብ ዓላማ ለዋስትና የተሰጠ
ነው የሚል ነው፡፡ ቼክ ተላላፊ የገንዘብ ሠነድ በመሆኑና በዋስትናነት አይሰጥም በሚል በሕግ የተደነገገ
ክልከላ ባለመኖሩ በመርህ ደረጃ ቼክ ለዋስትና ሊሰጥ ይችላል፡፡ ሆኖም በሰበር መዝገብ ቁጥር 166392 ላይ
በቀን 26/08/2012 ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ ላይ በመርህ ደረጃ አግባብነት ያለዉ የፍ/ብ/ህጉና የንግድ ህጉ ለቼክ
የሰጡት ዋና ዓላማ ለመያዣነት እንዲያገለግል ነዉ ባይባልም እንደማንኛዉም ሊተላለፉ እንደሚችሉ ሰነዶች
በመያዣነት ወይም በዋስትና ሊሰጥ እንደሚችልና ይህ በሚሆንበት ጊዜ ግን በንግድ ህጉና በፍ/ብ/ህጉ ላይ
በተቀመጡት ግልፅ ድንጋጌዎች መመራት ይኖርበታል (የን/ህ/ቁ 950 ና ፍ/ብ/ህ/ቁ. 2866)። በተለይ
የመያዣ ዉል ስምምነት በሚደረግ ጊዜ ዉሉ መከተል ስላለበት ፎርም በተመለከተም በግልፅ የተደነገገ
ስለመሆኑ ከን/ህጉ ቁ. 952 እና የፍ/ብ/ህጉ ቁ. 2828 መመልከት ይቻላል። የመያዣ ወይም የዋስትና ዉል
ህጉ በፅሑፍ በሰነድ ካልተደረጉ በህግ ፊት ዋጋ የላቸዉም (ፈራሽ ናቸዉ) በማለት ከደነገጋቸዉ ጥቂት የዉል
ዓይነተች ዉስጥ አንዱ ስለመሆኑ ግልፅ ነዉ (የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1725(ሀ)፤ 1922(1-3)፣ 2828(1-2))። ሌላዉ
ደግሞ የመያዣዉ ስምምነት ለምን ግዴታ እንደተደረገ፣ የግዴታዉ መጠን (ከፍተኛ የገንዘብ ወሰን)
በጥንቃቄ ግልፅ መደረግ እንዳለበትና ስምምነቱ የተደረገበት ቀን በግልፅ ልቀመጥ እንደሚገባ ህጉ የግድ
ይላል (የፍ/ብ/ህ/አንቀጽ 2828 (1-2)፣ 2864-2866ና የን/ህ/ቁ. 952)። እነዚህ የህጉ አስገዳጅ ድንጋጌዎች

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ካልተሟሉ የመያዣ ስምምነት ዉል አለ ማለት አይቻልም። ስለሆነም ቼኩ የተሰጠዉ ለዋስትና ዓላማ


እንደሆነ ተገልጾ በጽሁፍ የዋስትና ዉል ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር ቼክ ለዋስትና አላማ ተሰጥቷል
በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይነት እንደሌለዉ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡

ተጠሪ ቼኩን የሠጡት የዕቁብ ዕጣ ሲወጣላቸው ለዋስትና ዓላማ ከሆነ ይሕ ስለመሆኑ በጸሁፍ የተደረገ
የመያዣ ውል (pledge) በማቅረብ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሥር ፍርድ ቤትም ቼክ ቁጥሩ ተገልጾ
ለታወቀ ዕዳ መያዣ ስለመሆን አለመሆኑ በግራቀኙ ማስረጃ ሆነ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 መሰረት
ተከራካሪዎች ካቀረቧቸው ማስረጃዎች በተጨማሪ ለክርክሩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆነ የዕቁብ ዋስትና ውል
ወይም መያዣ ውል ስለመኖር አለመኖሩ ጉዳዩን በማጣራት በሥነ-ሥርዓት ሕጉ የተመለከተውን አንጻራዊ
እውነትን የመፈለግ ኃላፊነቱን ሳይወጣ መወሰኑ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

1. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 338113 ጥር 18 ቀን 2013
ዓ/ም እና የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 32991 መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ/ም
የሠጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ቼኩን የሠጡት ለዕቁብ ዕጣ ሲወጣላቸው ለዋስተና ወይም
ለመያዣ መሆን አለመሆኑን በማስረጃ በማጣራት የመሠለውን እንዲወስን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1)
መሠረት ጉዳዩን መልሠናል፡፡

3. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡ የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሳኔው
መሠረት እንዲፈጽም አዘናል፡፡ ይጻፍ
 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-201990

ቀን፡-01/02/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ማክሼቭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - አልቀረቡም

ተጠሪ ፡- ወጋገን ባንክ አክሲዮን ማህበር- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የብድር ውል ይፍረስልኝ በሚል የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል
ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካች ታህሳስ 18 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ ክስ ከተጠሪ ጋር ሚያዝያ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተደረገ
የብድር ውል ስምምነት ብር 2,631,246.08 መበደሩን፣ አከፋፈሉም ውሉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በየሶስት
ወሩ ሁኖ ወለድና የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ ብር 349,124.00 መሆኑንና በ8 ጊዜ ክፍያ በ2 ዓመት
ውስጥ እስከ ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ መስማማታቸውን ነግር ግን ተጠሪ
ክፍያው በ7 ጊዜ እንዲጠናቀቅ ማድረጉን፤ ይህም የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ላይ ችግር መፍጠሩን፤ የወለድ
መጠኑ ላይም ከፍተኛ ልዩነት በማምጣት የተስተካከለ የኦዲት ሪፖርት እንዳይኖር እክል መፍጠሩን፤

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በዚህም ምክንያት አመልካች የ2012 ዓ.ም የግብር ክሊራንስ አግኝቶ የንግድ ፍቃዱን ለማሳደስ አለመቻሉን
እና ተጠሪም ይህን ለማስተካከል ፍቃደኛ አለመሆኑን ጠቅሶ የብድር ውሉ እንዲፈርስ ዳኝነት ጠይቋል፡፡

ተጠሪ የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የብድር ስምምነቱ የተደረገው አመልካች ከመሰቦ ሲሚንቶ
ፋብሪካ ጋር ባደረገው የማሽነሪ አቅርቦት ውል መሰረት ግዴታውን ባለመወጣቱ ተጠሪ በሰጠው መጠኑ ብር
2,631,246.08 የሆነ የቅድመ ክፍያ እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና መሰረት ለመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ
ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ.ም ክፍያ በመፈፀሙና ይህ የአመልካች እዳ ወደ ብድር ውል እንዲዞር በመስማማታችን
ነው፡፡ እዳው በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ በየ3 ወሩ በ8 ጊዜ ተከፍሎ የሚያልቅ ሲሆን በዚህ ላይ ምንም አይነት
ልዩነት አልተደረገም፡፡ በውሉ በተገለጸው እና በታሰበው ሒሳብ ላይ ልዩነት የመጣው ተጠሪ እዳውን ለመሰቦ
ሲምንቶ ፋብሪካ ከከፈለበት ጊዜ አንስቶ የብድር ውሉ እስከተደረገበት ሚያዝያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ
የታሰበ ወለድ ነው፡፡ በመሆኑም ውሉ ሊፈርስ አይገባም በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ተጠሪ ክፍያውን በ7 ጊዜ እንዳጠናቅቅ አስገድዶኛል በሚል
አመልካች ለውሉ መፍረስ በምክንያትነት የጠቀሰው ከውሉ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ አይደለም፡፡ ውሉን
ተከትሎ ባለ አፈፃፀም ተጠሪ በፃፈው ደብዳቤ ላይ የተፈጠረ እክል በመሆኑ ደብዳቤው እንዲሰረዝ ወይም
በውሉ መሰረት እንዲፈፀም አመልካች መጠየቅ እየቻለ በፍ/ሕ/ቁ 1784 እና 1785 መሰረት አይነተኛ የውል
መጣስ በሌለበት ውሉ እንዲፈርስ መጠየቁ ተገቢ አይደለም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል፡፡

አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ ቅሬታውን ያቀረበ
ሲሆን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት በመሰረዙ ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ ሰበር አቤቱታውን
አቅርቧል፡፡

የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ በስር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር ብድሩ በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ በየ3 ወሩ ለ8 ጊዜ
ተከፍሎ እንዲያልቅ ስምምነት የተደረገበት መሆኑን ነገር ግን በአፈፃፀም ሒደት በ7 ጊዜ እንዲከፈል
መደረጉን ተጠሪ ባልካደበት የፍ/ሕ/ቁጥር 1784 እና 1785 ድንጋጌዎች እንደማያሟላ ተደርጎ የውል
ይፍረስልኝ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም፡፡ ውሉ ሊፈርስ አይገባም ቢባል እንኳ በአማራጭ
በተጠየቀው ዳኝነት መሰረት ቀሪውን የብድር እዳ በሚመለከት አመልካች እና ተጠሪ መጀመሪያ በተደረገው
ስምምነት መሰረት ውላቸውን ሊያሻሽሉ ይገባል ተብሎ መወሰን ነበረበት፡፡ እንዲሁም በግራ ቀኙ የተጠቀሱ
ምስክሮች ሳይሰሙ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አቤቱታው በአጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ የአመልካችን የዳኝነት ጥያቄ የስር ፍ/ቤት ውድቅ ያደረገበትን
አግባብ ግራ ቀኙ ሚያዝያ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ካደረጉት የገንዘብ ብድር ውል አንቀፅ 2 እና ከፍ/ሕ/ቁጥር
1784ና 1785 ጋር በማገናዘብ ለመመርምር ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪ መልሱን እንዲያቀርብ ትዕዛዝ
ተሰጥቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው የብድር
ውል ስምምነት አንቀፅ 2.1. በተገለፀው የአከፋፈል ሁኔታ ክፍያው በ8 ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው
ስምምነት በተቃራኒ ተጠሪ በ7 ጊዜ ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ አለማድረጌን በስር ፍ/ቤት በግልፅ ክርክር
አቅርቤአለሁ፡፡ አመልካችም ክፍያው ከ8 ዙር ወደ 7 ዙር ስለመቀየሩ ምንም አይነት ማስረጃ ያላቀረበ ሲሆን
የአመልካች የዳኝነት ጥያቄ በሰነድ ማስረጃ የሚረጋገጥ በመሆኑ የሰው ምስክር ሳይሰማ ክሱ ውድቅ መደረጉ
ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡

አመልካች ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልሱን ያቀረበ ሲሆን የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር
ተከራክሯል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም በግራ ቀኙ መካከል ሚያዝያ 11 ቀን 2011 ዓ.ም
የተደረገው የብድር ውል ሊፈርስ አይገባም ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት በስር ፍ/ቤት ከተደረጉ ክርክሮችና
ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዲሁም ለጉዳዩ ተገቢነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ
እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡

እንደመረመርነው በግራ ቀኙ መካከል ሚያዝያ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል ስምምነት


አመልካች ብር 2,631,246.08 መበደሩን፣ አከፋፈሉም ውሉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በየሶስት ወሩ ሁኖ
ወለድና የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ ብር 349,124.00 መሆኑንና በ8 ጊዜ ክፍያ በ2 ዓመት ውስጥ እስከ
ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተከፍሎ የሚጠናቀቅ መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም፡፡ አመልካች ከዚህ
ስምምነት በተቃራኒ በአፈጻም ሒደት ተጠሪው ክፍያው በ7 ጊዜ እንዲፈፅም አድርጓል፤ ይህንንም ክዶ
አልተከራከረም በሚል ያቀረበውን ቅሬታ ስንመለከት አመልካች ድርጊቱን አለመፈፀሙን በግልጽ ክዶ
ስለመከራከሩ በስር ፍ/ቤት ፍርድ ላይ ሰፍሯል፡፡ ተጠሪ ይህንን ፍሬ ነገር ማለትም የክፍያው ጊዜ ወደ ሰባት
ዙር መቀየሩን ክዶ እስከተከራከረ ድረስ አመልካች ክፍያው ከ8 ዙር ወደ 7 ዙር መቀየሩን የሚያሳይ ማስረጃ
በማቅረብ በፍ/ህ/ቁጥር 2001/1 እና በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 223 ክርክሩን በማስረጃ ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡ ይሁን
እንጂ አመልካች ተጠሪ ክዶ አልተከራከረም ከሚል በስተቀር ይህንን ፍሬ ነገር ለማስረዳት ማስረጃ
ስለማቅረቡ ወይም አቅርቦ አላግባብ ውድቅ የተደረገበት ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክር የለም፡፡ በመሆኑም
ተጠሪ የክፍያ ጊዜ ለውጥ አለማድረጉን ክዶ የተከራከረ እና በአመልካች በኩል የክፍያ ጊዜ ለውጥ በተጠሪ
ለመደረጉ የቀረበ ማስረጃ በሌለበት ተጠሪ በአመልካች ለውል ማፍረሻ ተደርጎ የቀረበውን የክፍያ ጊዜ ለውጥ
አድርጓል ለማለት አይቻልም፡፡

ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት አመልካች ከውል ስምምነቱ ውጪ ተጠሪ ክፍያው በ7 ጊዜ
ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ ቢጠይቅ እንኳ ውሉን ለማፍረስ በቂ ምክንያት ይሆናል? ወይስ አይሆንም? የሚለው
ይሆናል፡፡ ከተዋዋዮቹ አንዱ እንደ ውሉ ያልፈፀመ እንደሆነ ሌላኛው ተዋዋይ እንደ ውሉ እንዲፈፀምለት
ወይም ውሉ እንዲሰረዝ እና ለደረሰበት ጉዳት ካሳ መጠየቅ የሚችል መሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 1771 ላይ
ተገልጿል፡፡ ውል እንዲረዝ ሲጠየቅ ዳኞች ጥያቅውን ተቀብለው ውሉ እንዲሰረዝ የሚወስኑት በውል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ግዴታው በተገለፀው አግባብ በሙሉ ወይም በከፊል ባለመፈፀሙ ብቻ ሳይሆን በውሉ ላይ አይነተኛ የውል
መጣስ ሲከሰት (Fundamental breach of contract) እና የውሉ መሰረዝ ለተዋዋዮቹ ጥቅምና ለቅን ልቦና
አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ ስለመሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 1784 እና 1785 ላይ ተመላክቷል፡፡ አመልካች ውሉ እንዲሰረዝ
በምክንያትነት የሚያነሳው ተጠሪው አከፋፈሉን በሚመለከት ከብድር ስምምነቱ በተቃራኒ በ7 ጊዜ ውስጥ
እንድከፍል አድርጎኛል ይህም በሒሳብ አያያዝ እና በንግድ ፈቃድ እድሳት ላይ እክል ፈጥሮብኛል በማለት
ነው፡፡ ተጠሪው ክፍያው በ7 ጊዜ እንዲጠናቀቅ ቢያደርግ እንኳ ይህ ድርጊት አመልካች በውሉ ከተገለፀው
ጠቅላላ የብድር መጠን በላይ እንዲከፍል በማድረግ መሰረታዊ የውል መጣስን የሚያስከትል አይደለም፡፡
በተጨማሪም አመልካች ውሉን መሰረት አድርጎ በውሉ በተገለፀው አግባብ ክፍያውን በ8 ዙር ከፍሎ
ከማጠናቀቅ የሚከለክለው ነገር ስለሌለ የሂሳብ አያያዙን በዚህ አግባብ በማስተካከል የንግድ ፍቃድ እድሳቱን
ማስተካከል የሚችል ሲሆን የሂሳብ አያያዙም ሆነ የንግድ ፍቃድ እድሳቱ ለውሉ መሰረታዊ ጉዳይ
አይደለም፡፡ ይህም የግራ ቀኙን ጥቅም የማያስጠብቅ ለቅን ልቦናም ተቃራኒ በመሆኑ አመልካች ውሉ
እንዲሰረዝ የጠየቀው ዳኝነት የፍ/ሕ/ቁጥር 1784 እና 1785 ድንጋጌዎች መመዘኛን አያሟልም ተብሎ
መወሰኑ ተገቢ ነው፡፡

በመቀጠልም አመልካች በአማራጭ በተጠየኩት ዳኝነት ቀሪውን የብድር እዳ በሚመለከት መጀመሪያ


በተደረገው ስምምነት መሰረት ውላችንን እንድናሻሽል አለመወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት የሚያነሳውን
መከራከሪያ ስንመለከት የስር ፍ/ቤት የክርክር ሒደት አመልካች ይህን የአማራጭ ዳኝነት ስለመጠየቁ
አያመላክትም፡፡ በተጨማሪም ፍርድ ቤቶች በውል መሰረት እንዲፈጸም ወይም ውሎች እንዲፈርሱ ወይም
እንዲሰረዙ ወይም በውሎቹ መሰረዝ ወይም ዘግይቶ በመፈም ምክንያት የደረሰ ጉዳት ካለ ካሳ እንዲከፈል
ከሚያደርጉ በቀር የህጉን መመዘኛ አሟልቶ የተደረገ ውል እንዲሻሻል ውሳኔ የሚያስተላልፉበት የሕግ
አግባብ የለም፡፡

በመጨረሻም አመልካች በጉዳዩ የሰው ምስክር አለመሰማቱን ጠቅሶ የሚከራከር ቢሆንም በፍትሐብሔር
ክርክር ማስረጃ የሚሰማው እና ፍሬ ነገሩ በማስረጃ እንዲነጥር የሚደረገው የግድ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ
ብቻ ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ በአመልካች በኩል ውሉ እንዲፈርስ ለማስወሰን የተጠቀሰውን ምክንያት ውሉን
ለማፍረስ በቂ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በራሱ ከሕጉ ጋር በማገናዘብ ድምዳሜ ላይ መድረስ
የሚቻል በመሆኑ በጉዳዩ ላይ የሰው ምስክር መስማቱ የግድ አስፈላጊ አይደለም፡፡ በመሆኑም አመልካች
በዚህ ረገድ ያቀረበው ቅሬታ ተገቢነት የለውም፡፡

ሲጠቃለል አመልካች ከተጠሪ ጋር ያደረገው የብድር ውል እንዲፈርስ ያቀረበው ምክንያት ተጠሪ የብድሩ
መክፍያ ጊዜ ከ8 ወደ 7 ዙር ተቀይሯል በሚል ሲሆን ይህንን ተጠሪ ስለማድረጉ በማስረጃ የተረጋገጠ
አለመሆኑ የአመልካችን የውል ይፍረስልኝ ክርክር ውድቅ ለማድረግ በቂ ከመሆኑም በላይ የተጠቀሰው የውል
ማፍረሻ ምክንያት በህጉ አነጋገር አይነተኛ የውል መጣስ በተጠሪ ተፈጽሟል የሚያስብል አይደለም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመሆኑም በስር ፍ/ቤቶች ውሉ ሊፈርስ አይገባም መባሉ ህጉን የተከተለ ነው ከሚባል በስተቀር የተፈጸመ
መሰረታዊ ሕግ ስህተት የለም በማለት ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁጥር 242750 ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም የፌደራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በይ/መ/ቁጥር 201347 ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው
ችሎት የሠጠው ትዕዛዝ በፍ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መ/ቁ/202092

ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ ግርማ ለገሠ ተምትሜ፡- ቀረቡ

ተጠሪ፡ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት፡- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የአሰሪና ሠራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል


የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ ፤የአሁኑ ተጠሪ (ተከሳሽ) በመሆን
ተከራክረዋል፡፡አመልካች በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በሾፈር
ስራ መደብ ላይ እየሰራሁ እያለሁ ተጠሪ ድርጅት የጡረታ መውጫ ጊዜህ ከሐምሌ 1 ቀን
2011 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን በቁጥር ፐ/ሰ/ድ/386/2011 በቀን 18/11/2011 ዓ.ም ስራዬን
እንዳቆም በደብዳቤ በገለጸልኝ መሰረት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልቼ ስራዬን ከለቀቅኩኝ
በኋላ ጡረታ ሚኒስቴር በመመላለስ የጡረታ አበል ለመቀበል እንዲችል በምጠይቅበት ጊዜ
የጡረታ መውጫ ጊዜዬ ሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ሳይሆን ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም
መሆኑን ገልጸውልኝ ወደ ስራዬ እንዲመለስ ጡረታ ሚኒስቴር ለተጠሪ ሲጽፍ ተጠሪ ድርጅት
ወደ ስራ እንዲመለስ እና ደመወዝ እንዲከፈለኝ ሲጠይቅ ፍቃደኛ ባለመሆኑ የጡረታ መውጫ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጊዜዬ እስኪደርስ ወደ መደበኛ ስራዬ እንዲመልሰኝ እና የተቋረጠብኝ ደመወዝ እና ጥቅማ


ጥቅም እንዲከፈለኝ እንዲወሰንልኝ የሚል ዳኝነት ያቀረበ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ የሰጠው መልስ
የአመልካች ሥራ የተቋረጠው በተጠሪ ጥፋት ሳይሆን አመልካች ሲቀጠር የሕይወት ታርክ ቅጽ
ሲሞላ የተወለደበት ቀን ራሱ የሞላው መሰረት ተድረጎ ስህተት የተፈጠረው አመልካች በሌላ
ድርጅት ሲቀጠር የሞላው የትውልድ ዘመን እና በተጠሪ ድርጅት ሲቀጠር የሞላው የትውልድ
ዘመን ሲጣራ የጡረታ እድሜ ያልደረሰ መሆኑን የጡረታ ሚኒስቴር ያረጋገጠ ሲሆን ተጠሪ
ድርጅትም ከመስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም ስራ እንዲጀምር ቢጠየቁም ውዝፍ ደመወዝ
ካልተከፈለኝ በማለት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ስለዚህ ወደ ስራ ቢመለስ ተቃውሞ የለንም፤
ላልሰራበት ጊዜ ደመወዝ እንዲከፈለው የጠየቀው ውድቅ እንዲሆን በማለት መከራከሩን
መዝገቡ ያሣያል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ወደ ስራው እንዲመለስ የተባለው ተጠሪም


ተቃውሞ የሌለው በመሆኑ ተጠሪ ድርጅት አመልካችን ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመልሱ
በማለት ሲወስን ውዝፍ ደመወዝ በተመለከተ የአመልካች የጡረታ መውጫ ጊዜ ላይ ስህተት
የተፈጠረው አመልካች በሞሉት የሕይውት ታሪክ ስለመሆኑ እና ወደ ስራ እንዲመለሱ
በተደጋጋሚ ጥሪ ተደርጎላቸውም ፍቃደኛ አለመሆናቸውን አስረድተዋል፣ ስለዚህ የአሰሪና
ሰራተኛ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 54(1) ደመወዝ የሚከፈለው ለተሰራ ስራ ብቻ እንደሆነ
የሚደነግግ ሲሆን አመልካች በራሳቸው ጉድለት ላልሰሩበት ጊዜ ያለውን ደመወዝ ይከፈለኝ
በማለት ያቀረቡት መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበው ሲሆን
ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ የተሰጠው ውሳኔ የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ግድፈት አልተገኘበትም
በማለት ይግባኙን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞበታል፡፡

አመልካች በውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽመዋል በማለት ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት
ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤ተጠሪ የጡረታ መውጫ ጊዜዬን ከሀምሌ 01 ቀን 2011 ዓ.ም
ጀምሮ መሆኑን ሀምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም በደብዳቤ ሲያሳውቀኝ ከጡረታ ሚኒስቴር
ሳያረጋግጥ ነው፣ አንድ ሰራተኛ ለጡረታ ሲዘጋጅ አሰሪው ከ3 እና 4 ወራት አስቀድሞ
ለማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ አመልክቶ ኤጀንሲውም ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጦ የጡረታ
መለያ ቁጥር አስቀድሞ ተሰጥቶት በደብዳቤ የሚያሳውቅ ሲሆን ተጠሪ ይህንን ሳያደርግ ከስራ
ማስወጣቱ አግባብ የሌለው ሲሆን የጡረታ ሚኒስቴር መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ተጠሪን
በደብዳቤ ያሳወቀው ሲሆን ይህንን ካወቀ በኋላም ወደ ስራ ለመመለስ ፍቃደኛ ባለመሆኑ በስር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍ/ቤት ገልፀን እያለ ይህንን ሳይመረምር ደመወዝ አይከፈልም ማለቱ ስህተት ነው፡፡ ስለዚህ
ተጠሪ የጡታ መውጫ ጊዜ እርግጠኛ ሳይሆን ጡረታ ውጣ ብሎኝ ለከፍተኛ እንግልት እና
ችግር ዳርጎኝ ያለደመወዝ ወደ ስራ እንዲመለስ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
በመሆኑ ከሐምሌ 01 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ስራ እስከ ጀመርኩበት ድረስ ያልተከፈለኝ
ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም እንዲከፈለኝ እንድወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ የሰበር አመልካች የጡረታ ጊዜወ ሳይደርስ
መውጣቱ ከመረጋገጡ አኳያ የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪው ውዝፍ ደመወዝ የመክፈል ሀላፊነት
የለበትም የመባሉን አግባብነት ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ
መልስ እንዲሰጥ ታዟል፡፡

ተጠሪ ያቀረበው መልስ ባጭሩ አመልካች በተጠሪ ድርጅት ሲቀጠር የተወለደበት ቀን በአግባቡ
መሙላት ሲገባው በቀድሞ መ/ቤት የሞላውን የትውልድ ቀን የተለየ የትውልድ ዘመን
በመሙላቱ በራሱ ችግር የተፈጠረ ስህተት ነው፡፡ ተጠሪም አመልካች በሞላው የትውልድ
ዘመን መሰረት የጡረታ መውጫ ጊዜ ስለደረሰ ለአመልካች እና ለጡረታ ሚኒስቴር በማሳወቅ
ሰነዶቹን አደራጅቶ የላከው ሲሆን አመልካች በራሱ በሞላው ታሪክ የጡረታ ጊዜ ስለደረሰ የስራ
ውል የተቋረጠ እንጂ ተጠሪ የፈፀመው ስህተት የለም፣ የጡረታ ማህበራዊ ኤጀንሲ ባደረገው
ማጣራት በሌላ መ/ቤት በሞላው የትውልድ ዘመን የአመልካች የጡረታ መውጫ ጊዜ ሐምሌ
2013 ዓ.ም እንደሆነ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም በደብዳቤ ባሳወቀን መሰረት አመልካች
ወደ ስራ እንዲመለስ ሲጠየቅ የሀምሌ፣ ነሐሴ እና መስከረም ወር ደመወዝ ካልተከፈልኝ
በማለት ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ በስር ፍ/ቤት በሰነድ እና በሰው ምስክሮች ተረጋግጦ የውዝፍ
ደመወዝ ጥያቄ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለውም፣ ስለዚህ አመልካች በራሱ
ምክንያት ስራ አልሰራም በማለት ላልሰራው ስራ ደመወዝ እንዲከፈለው የጠየቀው የስር
ፍ/ቤቶች ውድቅ ማድረጋቸው የህግ ስህተት የለዉም ተብሎ እንዲፀና
ተከራክረዋል፡፡አመልካቾች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ
ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ አመልካች
ለስር ፍርድ ቤት ያቀረበዉ የዳኝነት ጥያቄ ሁለት ናቸዉ፡፡አንደኛዉ የጡረታ መዉጫ ጊዜ
አልደረሰም ስለተባለ ወደ ስራ እንዲመለስ የሚል ሲሆን ሁለተኛዉ ያልተከፈለዉ ደመወዝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዲከፈል እንዲወሰን የሚል ነዉ፡፡የስር ፍርድ ቤትም ጉዳዩን አጣርቶ ተጠሪ አመልካችን
ወደ ስራ እንዲመልስ የወሰነ ሲሆን ክፍያን በተመለከተ ግን ስህተቱ የተፈጠረዉ አመልካች
የቅጥር ዉል ላይ የሞላዉ የትዉልድ ቀንና ዘመን ስህተት መሆኑ ስለተረጋገጠ ነዉ በሚል እና
የጡረታና ማህበራዊ ኤጀንሲ ከወሰነ በኋላ በራሱ ጉድለት ወደ ስራ ባለመመለሱ ያልሰራበት
ደመወዝ አይከፈለዉም የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን መዝገቡ ያሣያል፡፡አመልካች አሁንም
አጥብቆ የሚከራከረዉ የጡረታ ጊዜ ሳይደርስ ያሠናበተኝ ተጠሪ ስለሆነ የተቋረጠዉን ደመወዝ
ሊከፈለኝ ይገባል በማለት ነዉ፡፡

በህግ በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር ደመወዝ የሚከፈለዉ ለተሰራ ስራ ብቻ መሆኑን ነገር
ግን ሰራተኛዉ ለስራ ዝግጁ ሆኖ ሳለ ለስራ አስፈላጊ የሆነዉ መሳሪያ ወይም ጥሬ እቃ
ሳይቀርብ በመቅረቱ ወይም በሰራተኛዉ ጉድለት ባልሆነ ምክንያት ሳይሰራ ቢዉል ደመወዙን
የማግኘት መብት እንዳለዉ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 54ላይ
ተደንግጓል፡፡ከዚህም የምንገነዘበዉ አስሪ ደመወዝ ለመከፍል የሚገደደዉ አንድም ሰራተኛዉ
ስራ የመስራት ግዴታዉን የተወጣ ከሆነ ሲሆን በሌላ በኩል ሰራተኛዉ ለስራ ዝግጁ ሆኖ
በአሰሪዉ ጉድለት ሳይሰራ ከቀረ ስለመሆኑ ነዉ፡፡በተያዘዉ ጉዳይ ያከራከረዉ ለጡረታ
ደርሰሃል ተብሎ ከተጠሪ መ/ቤት ከተሰናበትበት ሐምሌ ወር 2011ዓ.ም ጀምሮ ጉዳዩ
በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዉሳኔ እስከተሰጠበት ጊዜ ያለዉ ደመወዝ ክፍያ
የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች በዚህ ጊዜ ዉስጥ ስራ ላይ እንዳልነበር አላከራከረም፡፡ስራ ላይ
ያልተገኘዉ ተጠሪ በፈጸመዉ ጥፋት ወይም ስህተት ነዉ በማለት ሲሆን ፍሬነገር የማረጋገጥ
እና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን የተሰጠዉ የሥር ፍርድ ቤት የጡረታ መዉጫ የቀን አቆጣጠር
ስህተት የተፈጠረዉ አመልካች ለተጠሪ ባቀረበዉ መረጃ ላይ የተፈጠረ ስህተት ስለመሆኑ
ተጠሪ በተሻለ ሁኔታ ማስረዳቱን አረጋግጧል፡፡ስለዚህም አመልካች ስራ ላይ ያልተገኘዉ
ተጠሪ ሆነ ብሎ በፈጸመዉ ድርጊት ወይም ስህተት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ ከሐምሌ
እስከ መስከረም ወር ሰራተኛዉ ላልሰራበት ጊዜ ደመወዝ የመክፈል ሃላፊነት የሚወስድበት
ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡በሌላ በኩል ጉዳዩ በማህበራዊ ዋስትና አጄንሲ በኩል ተጣርቶ ወደ
ስራ እንዲመለስ ከተባለበት መስከረም 26 ቀን 2011ዓ.ም በኋላ ላለዉ ጊዜ ተጠሪ ወደ ስራ
እንዲመለስ ጥሪ ተደርጎለት ከሐምሌ እስከ መስከረም ያለዉ ደመወዝ ካልተከፈለኝ በሚል
ከተጠሪ ጋር በተፈጠረ አለመግባባበት ስራ ሳይጀምር እንደቆየ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ
ፍሬነገር ጉዳይ ነዉ፡፡አመልካች ወደ ስራ እንዲመለስ ከተባለበት ቀን አንስቶ ስራዉን እየሰራ
ሌላዉን የመብት ጥያቄ በህግ አግባብ መጠየቅ ሲገባዉ የበኩሉን ግዴታ እንዳልተወጣ እና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይህንን ሁሉ ጊዜ ያልሰራበት ደመወዝ እንዲከፈል መጠየቁ ምክንያታዊነት የሌለዉ መሆኑን


ያሣያል፡፡

ሲጠቃለል አመልካች የጡረታ ጊዜ ሳይደርስ ጡረታ እንዲወጣ የተደረገዉ ራሱ በሰጠዉ መረጃ


ስህተት መነሻ መሆኑ ከመረጋገጡም ባሻገር ጉዳዩ ተጣርቶ ወደ ስራ እንዲመለስ ሲጠየቅም
በጊዜዉ ስራ ሳይጀምር በራሱ ጉድለት ስራዉን ሳይሰራ ለቀረበት ጊዜ ተጠሪ ደመወዝ
እንዲከፍል የሚገደድበት ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን በማረጋገጥ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት
ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አልተገኘም፡፡በዚሁ
አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ዉሳኔ

1ኛ/የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/75623 ላይ በ14/08/2012ዓ.ም የሰጠዉ


ፍርድ እና ይህንኑ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ./ቁ/250131 ላይ
በ13/04/2013ዓ.ም የሰጠዉ ብይን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል፡፡ 2ኛ/በዚህ
ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ. 202114

ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካቾች- 1. ሀድሌ ኢብራሂን

2. ኡመር ኢብራሂን

3. መሀሙድ አደን

4. ኡመር መታን

5. መሀመድ አህመድ አብዲ

6. መታን መሀሙድ

7. መሀመድ አረብ

ተጠሪዎች- 1. ጠይብ አብዲላሂ

2. አህመድ ጣሂር አብዲላሂ ሽዴ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ እርሻ መሬትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረውም በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ፋፈን ዞን ጅግጅጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር
አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በተጠሪዎች ላይ
ባቀረቡተ ክስ በሰሀሊቲ ቀበሌ ኮጃርታ ሼህ ጣሂር ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በሰሜን ሀጂ መሀመድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እና የጎሳ ቦታ፣ በምዕራብ ሙሳ አውሌ፣ በደቡብ ተጠሪዎች፣ በምስራቅ የአመልካቾች መሬት


የሚያዋስኑትን ስፋቱ 4 ጋሻ፣ ርዝመቱ ደግሞ 7.5 ጋሻ ጠቅላላ መጠኑ 30 ጋሻ የሆነ የእርሻ
መሬት ያለአግባብ ይዘውብናል፤ እንዲለቁልን ብንጠይቃቸው ፍቃደኛ ስላልሆኑ ለቀው
እንዲያስረክቡን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀው ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ የያዝነው የአመልካቾች መሬት የለም፤ አመልካቾች


ከክሳቸው ጋር ያቀረቡት የባለቤትነት ማስረጃ የለም፤ ክስ የቀረበበትን መሬት ከአባታችን በውርስ
ያገኘነው የተጠሪዎች ይዞታ ነው፤ ከበፊት ጀምሮ ስናርሰው የነበርነውም እኛ ነን፤ በዚህ ጊዜ
ውስጥም አመልካቾች መሬቱ ይገባናል የሚል ጥያቄ አላቀረቡም፤ አመልካቾች መሬቱን እንዴት እና
መቼ እንዳገኙት፤ መቼስ ከይዞታቸው እንደወጣ አልገለጹም፤ አመልካቾች ወደ አካባቢው የገቡት
መሬት ገዝተው ሲሆን የገዙትን መሬት የነካባቸው ሰው የለም በማለት ክሱ ውድቅ እንዲደረግላቸው
ጠይቀዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት የወረዳ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ካደመጠና ከመረመረ
በኋላ የአመልካቾችን ክስ ውድቅ በማድረግ ተጠሪዎች መሬቱን ሊለቁ አይገባም በማለት ወስኗል፡፡
አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በወረዳ ፍርድ ቤቱ የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል፡፡
አመልካቾች አሁንም በውሳኔው ባለመስማማት ለክልሉ ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ
ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካቾች
የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡

አመልካቾች በቀን 01/06/2013 ዓ.ም በተፃፈ 02 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች
ተፈፅመዋል ያሏቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችሎት እንዲታረሙላቸው ጠይቀዋል፡፡
የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ አከራካሪው መሬት የገጠር እርሻ መሬትን የሚመለከት ሲሆን
የሚገዛውም በክልሉ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 128/05 ነው፤ በአዋጁ መሠረት ደግሞ ጉዳዩ ወደ
መደበኛ ፍርድ ቤት ከመሄዱ አስቀድሞ በአካባቢው በሚገኝ ገበሬ ማህበር ጽ/ቤት፣ ማህበራዊ ፍርድ
ቤት፣ በአካባቢ ሽማግሌዎች እና በጎሳ መሪዎቸ መታየት እንዳለበት ቢደነግግም የስር ፍርድ ቤቶች
የአዋጁን መኖር ዘንግተው ጉዳዩ በዚህ መንገድ እንዲያልፍ አለማድረጋቸው ወይም ትዕዛዝ
አለመስጠታቸው፤ ክሱን ያቀረብነውና ዳኝነት የጠየቅነው አመልካቾች ሆነን እያለ የስር ፍርድ ቤቶች
ባልተጠየቀ ዳኝነት ላይ መሬቱ የተጠሪዎች ነው በማለት መወሰናቸው፤ እንዲሁም አመልካቾች ክስ
ያቀረብንበት መሬት ስፋት 4 ጋሻ በ7.5 ጋሻ ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ግን ከተጠየቀው ዳኝነት
በመውጣት ስፋቱ 16 ጋሻ በ5 ጋሻ የሆነ መሬት ላይ ውሳኔ መስጠቱ መሠረታዊ ስህተት ስለሆነ
ሊታረም ይገባዋል የሚል ነው፡፡ ጉዳዩም በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ ያስቀርባል ከመባሉ
ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት ጥሪ የተደረገላቸዉ ቢሆንም ባለመቅረባቸዉ በሌሉበት ክርክሩ
እንዲቀጥል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ከስር ጀምሮ የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ
የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችሎትም ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉን ዉሳኔ ከግራ ቀኝ ክርክር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ


መርምሮታል፡፡ እንደመረመረዉም አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ
ለጠየቁት ዳኝነት መሠረት ያደረጉት ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት የእራሳቸዉ መሆኑን በመግለጽ
ሲሆን፣ ተጠሪዎች በበኩላቸዉ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ከአባታቸዉ አብዱላሂ ሺዴ
የወረሱት የእራሳቸዉ እንጂ የአመልካቾች አለመሆኑን ገልጸዉ ተከራክረዋል፡፡ የግራ ቀኝ ክርክር
ይህ ከሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 246(1) መሠረት መያዝ የሚገባዉ ትክክለኛ ጭብጥ
ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት የአመልካቾች ነዉ ወይስ ተጠሪዎች ከአባታቸዉ በዉርስ ያገኙት
ነዉ? የሚል ነዉ፡፡ ጉዳዩ በመጀመሪያ የቀረበለት የወረዳዉ ፍርድ ቤትም በዚሁ መሠረት የግራ ቀኝ
ምስክሮችን በመስማት እንዲሁም መሬቱ ከሚገኝበት ቦታ በአካል በመሄድ አጣርቶ ይህንኑ ከግራ
ቀኝ ምስክሮች ቃል አንፃር በመመርመር እና በመመዘን ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት በተጠሪዎች
እጅ ያለ እና አመልካቾች መሬቱን ይዘዉት እንደማያዉቁ እና በመሬቱም ላይ መብት እንደሌላቸዉ
በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋግጧል፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ስልጣን
መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸዉን ዉሳኔዎች በማረም ላይ የተገደበ ስለመሆኑ በኢፌዲሪ
ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ላይ ከተመለከቱት
ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከማስረጃ አቀራረብ እና የምዘና መርህ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ
ስህተት ካለ እንደመሠረታዊ የህግ ስህተት ታይቶ በዚህ ችሎት ሊታረም የሚችል ቢሆንም
በተያዘዉ ጉዳይ ከማስረጃ አቀራረብ እና የምዘና መርህ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ ግድፈት ስለመኖሩ
የስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ አያሳይም፡፡ በመሆኑም አመልካቾች ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ መሬት ላይ
መብት የላቸዉም በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ዉሳኔ በዚህ ችሎት ሊታረም የሚችል
መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም፡፡

በሌላ በኩል ለክርክሩ መነሻ በሆነዉ መሬት ላይ መብት እንዳላቸዉ እና በተጠሪዎች በህገ
ወጥ መንገድ የተያዘባቸዉ ስለመሆኑ አመልካቾች በክሳቸዉ መሠረት የማስረዳት ሸክም ያለባቸዉ
ሲሆን ይህን ግዴታቸዉን አልተወጡም፤ በአንፃሩ መሬቱ ከተጠሪዎች እጅ ወጥቶ በእጃቸዉ
(በአመልካቾች) ገብቶ እንደማያዉቅ የተጠሪዎች ምስክሮች ያስረዱ ቢሆንም ይህ መሆኑ
የአመልካቾችን ክስ ዉድቅ የማድረግ ዉጤት ከሚያስከትል በስተቀር ፍርድ ቤቱ መሬቱ የተጠሪዎች
ነዉ በሚል እንዲወስን ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾች
ከመሬቱ መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ እና በተጠሪዎች ያላግባብ የተያዘ ስለመሆኑ በክሳቸዉ መሠረት
ማስረዳት ካልቻሉ እና/ወይም ይህ ክርክራቸዉ በተጠሪዎች ምስክሮች መስተባበሉን ከተረዱ
የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ መቆም ሲገባቸዉ ከዚህ በላይ በመሄድ መሬቱ የተጠሪዎች
እንዲሆን “ወስኘላቸዋለሁ” በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ የሥነ ሥርዓት ግድፈት፣ በተለይም የፍርድ
ቤቶች ዉሳኔ በተጠየቀዉ ዳኝነት ላይ የተገደበ ሊሆን እንደሚገባ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ
182 ላይ የተመለከተዉን ድንጋጌ የሚቃረን፣ በመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ተከታዩም ተወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉሳኔ

1. የጅጅጋ ደቡብ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1411/2011 በቀን 10/10/2011 ዓ.ም


በዋለዉ ችሎት፣ የፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 052-34/11/12 በቀን
12/05/2012 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጡት ዉሳኔ የሱማሌ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 05-1-201/12 በቀን 02/03/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት
የሰጠዉ ትዕዛዝ ተሻሽለዋል፡፡

2. አመልካቾች ከመሬቱ መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት


የዳኝነት ጥያቄያቸዉን ዉድቅ በማድረግ የተሰጠ የዉሳኔ ክፍል ጸንቷል፤ መሬቱ
የተጠሪዎች ነዉ በሚል የተሰጠ ዳኝነት ተሽሯል፡፡

3. በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን


ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 202486

ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- አቶ አዲሱ ዓለሙ- አልቀረቡም

ተጠሪ ፡- ወ/ሮ መስከረም ንጉሴ- ጠበቃ ዳጨው ዳመና- ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር መዝገቡ የቀረበው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ
ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ የአመልካች
ሚኒባስ መኪና በሆነ ተሳፍረን በምንጓዝበት ጊዜ ከቆመ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በቀኝ እግሬ የታፋ
አጥንት እና በግራ እግሬ ከጉልበት በታች አጥንት ስብራት በመድረሱ 28% ቋሚ አካል ጉዳት ደርሶብኛል፡፡
የጉዳት ካሣ ብር 406,230.00፣ የሕክምና ወጪ ብር 90,770.00፣ የአልሚ ምግብ ወጪ ብር 2,000.00
እና የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 በድምሩ ብር 500,00.00 አመልካች እንዲከፍሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡
አመልካች የሠጡት መልስ በንግድ ሕጉ መሠረት በውል ስትጓዝ ነው ጉዳቱ የደረሰው፣ የቀረበው የጉዳት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መጠን የተጋነነ የሚል ሲሆን ለመኪናው የመድን ሽፋን የሠጠው መድን ድርጅት ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር
ጠይቀዋል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ የጉዳት ካሣ ብር 350,844.00፣


የሕክምና ወጪ ብር 90,770.00፣ የምግብ ብር 2,000.00 እና የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 አመልካች
እንዲከፍል እና የመድን ሽፋን የሠጠው ድርጅት ብር 40,000.00 እንዲከፍል ወስኗል፡፡ ጉዳዩ እስከ ፌዴራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ በመዝገብ ቁጥር 180599 የተሰጠው ውሳኔ ጉዳቱ የደረሰው
ተጠሪ ተሳፍረው በሚጓ ዙበት ጊዜ ስለሆነ በንግድ ሕግ ሊገዛ ይገባል፤ የአመልካች ኃላፊነት የሚወድቀው
በንግድ ሕጉ አንቀጽ 597(1) ስር ነው ወይስ በአንቀጽ 599 የሚለውንና የጉዳት ካሣውን በርትዕ እንዲወስን
ጉዳዩን ለሥር ፍርድ ቤት መልሷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ከተመለሰለት በኋላ ጉዳቱ የደረሰው በአጓዡ ጥፋቱ
ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ጭብጥ ግራቀኙ ማስረጃ መስማት ሳያስፈልግ የትራፊክ ሪፖርት እንዲቀርብ
ባሳሰቡት መሠረት ማስረጃውን በማስቀረብ መዝኖ ጉዳቱ የደረሰው በአጓዡ ጥፋት መሆኑ ስለተረጋገጠ
የአመልካች ኃላፊነት በንግድ ሕጉ ቁጥር 599 መሠረት የሚወድቅ ስለሆነ ተጠሪ በጉዳቱ ምክንያት
በቤታቸው የሠራተኛ ወጪ የሚያስከትልባቸው በመሆኑና ወደሥራ ሲሄዱ የሚያስፈልገውን የትራንስፖርት
ወጪ በቀሪ ዕድሜያቸው ጊዜ በማስላት የጉዳት ካሣ ብር 228,000.00፣ የሕክምና ወጪ ብር 90,770.00፣
የምግብ ብር 2,000.00 እና የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 ለተጠሪ እንዲከፍልና መድን ድርጅት ከሚከፍለው
ብር 40,000.00 ውጭ ያለውን ካሣ አመልካች እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡ በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች
የአመልካችን ይግባኝ እና የሠበር አቤቱታ ባለመቀበል ሰርዘዋል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የሥር ፍርድ ቤት
በ21/12/2012 ዓ/ም ተጨማሪ ማስረጃው ሊያያዝ አይገባም በማለት ብይን ከሰጠ በኋላ ብይኑን በራሱ ሽሮ
የትራፊክ ሪፖርቱን በመቀበል መወሰኑ ስህተት ነው፡፡ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ ከተመለሰ በኋላ አዲስና
ተጨማሪ ማስረጃ ሊቀበል አይገባም፡፡ ቋሚ የአካል ጉዳቱ 28% ሆኖ እያለ በ100% ጉዳት ካሣው መሰላቱ
ተገቢ አይደለም የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ ተመልክቶ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው መመሪያ
መሰረት መወሰን አለመወሰኑን ለማጣራት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ በማዘዙ ተጠሪ የሠጡት መልስ
ግራቀኛችን የሠው ማስረጃ አናሰማም በትራፊክ ሪፖርት መሠረት ይወሰን በማለት ባሳሰብነው መሠረት
ማስረጃው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቀርቦ ተመዛዝኖ መወሰኑ ተገቢ ነው፡፡ ለተያዘው ጭብጥ አስፈላጊ ማስረጃ
ተቀብሎ ካሣውን በርትዕ አመዛዝኖ ተገቢ ነው ተብሎ ሊጸና ይገባል ብለዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራኙን ክርክር፣ የሠበር አጣሪ ችሎት የያዘውን
ጭብጥ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪ ያቀረቡት ክስ የአመልካች ሚኒባስ መኪና በሆነ ተሳፍረን በምንጓዝበት ጊዜ ከቆመ
ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በቀኝ እግሬ የታፋ አጥንት እና በግራ እግሬ ከጉልበት በታች አጥንት ስብራት
በመድረሱ 28% ቋሚ አካል ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ የጉዳት ካሣ ብር 406,230.00፣ የሕክምና ወጪ ብር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

90,770.00፣ የአልሚ ምግብ ወጪ ብር 2,000.00 እና የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 በድምሩ ብር


500,00.00 አመልካች እንዲከፍሉ የሚል ሲሆን አመልካች በበኩሉ በንግድ ሕጉ መሠረት በውል ስትጓዝ
ነው ጉዳቱ የደረሰው፣ የቀረበው የጉዳት መጠን የተጋነነ በማለት ተከራክሯል፡፡ ጉዳዩ ቀደም ሲል እስከ
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ በመዝገብ ቁጥር 180599 ሚያዚያ 29 ቀን 2012
ዓ/ም በሠጠው ውሳኔ ጉዳዩ በንግድ ሕጉ እንዲገዛ እና አጓዡ ጥፋት ያለበት መሆን አለመሆኑ በጭብጥነት
ተመርመሮ እንዲወሰን ለሥር ፍርድ ቤት መልሷል፡፡ የተመለሰለት ፍርድ ቤት ግራቀኙ ማስረጃዎቻቸውን
ለማሰማት ባለመፈለጋቸውና የአጓዡ ጥፋት መኖር አለመኖር በትራፊክ ሪፖርት ተመስርቶ እንዲወሰን
ማስረጃው እንዲቀርብ ባሳሰቡት መሠረት ማስረጃውን አስቀርቦ አጓዡ ጥፋት ያለበት ስለሆነ የአመልካች
ኃላፊነት የሚወሰነው በንግድ ሕጉ አንቀጽ 599 መሠረት ነው ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

አመልካች በሰበር አቤቱታቸው የሥር ፍርድ ቤት በ21/12/2012 ዓ/ም ተጨማሪ ማስረጃው ሊያያዝ
አይገባም በማለት ብይን ከሰጠ በኋላ ብይኑን በራሱ ሽሮ የትራፊክ ሪፖርቱን በመቀበል መወሰኑ እና ጉዳዩ
እንደገና እንዲታይ ከተመለሰ በኋላ አዲስና ተጨማሪ ማስረጃ መቀበሉ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን የተከተለ
አይደለም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ክርክሩን በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና
መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፊነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች
የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ
ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰሉትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል፡፡ ሰበር
ሰሚ ችሎት ጉዳዩን የመለሰው አጓዡ ጥፋት ያለበት መሆን አለመሆኑ በጭብጥነት ተይዞ እንዲወሰን ሲሆን
የተመሰረተው የፍሬ ነገርን ጭብጥ ያካተተ በመሆኑ ጉዳዩ በማስረጃ ሊረጋገጥ የሚገባው ነው፡፡ አመልካችና
ተጠሪ በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዘረዘሯቸውን ማስረጃ ማሰማት እንዳልፈለጉና የፍሬ ነገር ጭብጡ
በትራፊክ ሪፖርት መሠረት እንዲወሰን ማስረጃው እንዲቀርብ እንዲታዘዝ ያመለከቱ ስለመሆኑ ከውሳኔው
ግልባጭ ይዘት ተገንዝበናል፡፡ ፍርድ ቤት የማስረጃው መቅረብ አምኖበት ከአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
ማስረጃው እንዲያቀርብ ማዘዙም ጉዳዩ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 መሠረት መመራቱን ያመላክታል፡፡
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 264 መሰረት ተከራካሪዎች ካቀረቧቸው የሠው ሆነ የሠነድ ማስረጃዎች በተጨማሪ
ለክርክሩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆነ ማስረጃ ፍርድ ቤቱ የማስቀረብ ስልጣን እና ኃላፊነት እንዳለበት
ያስገነዝባል፡፡ ሕጉ ኮመን ሎው እና ኮንቲኔንታል ሎው የሕግ ሥርዓት የሚከተሉ ሀገሮችን አጣምሮ የያዘ
እና ከኮመን ሎው የህግ ሥርዓት ከሚከተሉ ሀገሮች በተለየ ለዳኛው ጉዳዩንና ግራቀኙ የሚያቀርቡትን
ማስረጃ ከማዳመጥ ያለፈ ተግባር እንደሰጠው ያሳያል፡፡ ድንጋጌው እውነትን የመፈለግ ዓላማ የሥነ-ሥርዓት
ሕጉ እንዳለው የሚያሳይ እና ዓላማው እንዲሳካ የማድረግም ኃላፊነት የዳኛውም እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ወደሥር ፍርድ ቤት ጉዳዩ የተመለሰው በፍሬ ነገር ጭብጥ ተመስርቶ ከመሆኑ አኳያ ፍርድ ቤት ጉዳዩ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሠረት ከተመለለሰት በኋላ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግና ፍትሐዊነትን
ሊያሳካ በሚችል መልኩ ማስረጃውን እንዲቀርብ ከማድረግ ሕጉ የመከልከል ሀሳብ አለው ሊባል አይችልም፡፡
ተጠሪ የሕክምና ማስረጃና የትራፊክ ሪፖርት በተጨማሪ ማስረጃነት እንዲቀርብላቸው ጠይቀው የሥር ፍርድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቤት በ21/12/2012 ዓ/ም የሕክምና ማስረጃ ሊያያዝ የማይገባው ስለመሆኑ ብይን የሠጠ ቢሆንም አሁን
አከራካሪ ሆኖ የቀረበው የትራፊክ ሪፖርት በተመለከተ የሠጠው ትዕዛዝ ባለመኖሩ በክርክሩ ሂደት
ማስረጃውን አስቀርቦ መዝኖ መወሰኑ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የማስረጃ አቀባበል ሆነ የክርክር
አመራር ግድፈት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘውም፡፡

የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ተሳፍረውበት የነበረው ሚኒባስ በፍጥነት ሲሽከረከር መንገዱን ለቆ ከቆመ ከባድ
ሎቬድ ተሽከርካሪ ጋር መጋጨቱ የተረጋገጠ ነው በሚል በንግድ ሕጉ አንጽ 599 መሠረት ጉዳቱ የደረሰው
በአጓዡ ጥፋት ስለመሆኑ ድምዳሜ ላይ መድረሱን ይሕ ሰበር ሰሚ ችሎትም የሚቀበለው ነው፡፡ ተጠሪ
ዘለቄታዊ የአካል ጉዳቱ 28% መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላም መደበኛ ሥራቸው
የቀጠሉ በመሆኑ በቀጥታ የገቢ መቋረጥ ያላስከተለ ቢሆንም በተጠሪ እግር ላይ የደረሠው ጉዳት ዘላቂ
በመሆኑ አሁን የሚሠሩትን የሥራ ዓይነት ማከናወን ቢችሉም እንኳን ለወደፊት ማንኛውንም ዓይነት
የሥራ ተግባር ማከናወን ላይ እክል እንደሚሆንባቸውና አጠቃላይ የመሥራት አቅማቸውን እንደሚቀነስ
ይገመታል፡፡ የጉዳት ካሣ ሲወሰን ግምት ውስጥ መግባት ከሚኖርበት ጉዳይ አንዱ በአጠቃላይ በተጎጂው ላይ
ጉዳት በመድረሱ ምክንያት እንደሰው በአጠቃላይ የመሥራት ኃይል ቅነሳ /General utility/ እንደሆነ በሰበር
ችሎቱ በመዝገብ ቁጥር 19338 አስገዳጅ ትርጉም የተሠጠበት ነው፡፡ በአጠቃላይ የመሥራት ኃይል መቀነሱ
ለወደፊት የሚደርስ ጉዳት (future damage) እንደሚያስከትል የሚታወቅ ሲሆን ትክክለኛ ጉዳቱ ግን
ለማወቅና ለመለየት ስለሚያስቸግር በፍ/ሕ/ቁ. 2102 እንደተመለከተው ጉዳት መድረሱ ተረጋግጦ ነገር ግን
የጉዳት መጠኑን ማወቅ ካልተቻለ ካሣውን በርትዕ መወሰን ይችላል፡፡ የሥር ፍርድ ቤት በርትዕ ካሣውን
ለማስላት ተጠሪ በጉዳቱ ምክንያት ከሚያጡት ገቢ አንጻር ሳይሆን ጉዳቱ ከሚያስከትለው ተጨማሪ ወጪ
በመነሳት በቤታቸው የሠራተኛ ወጪ የሚያስከትልባቸው በመሆኑና ወደሥራ ሲሄዱ የሚያስፈልገውን
የትራንስፖርት ወጪ በቀሪ ዕድሜያቸው ጊዜ በማስላት የጉዳት ካሣ ብር 228,000.00 መወሰኑ ተጠሪ ሙሉ
ገቢያቸውን እንዳጡ አድርጎ እንዳሰላው ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡ ፍርድ ቤቱ ምክንያታዊ የሆኑ
ጉዳዮችን በመያዝ ካሣውን በርትዕ መወሰኑ ሆነ የሕክምና ወጪ ብር 90,770.00፣ ለምግብ ብር 2,000.00
እና የሞራል ካሣ ብር 1,000.00 አመልካችና በሥር ፍርድ ቤት ለተሽከርካሪው የመድን ሽፋን የሠጠው
ጣልቃ ገብ በየድርሻቸው እንዲከፍሉ ውሳኔ መስጠቱ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም
ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 11078 ጥር 20 ቀን 2013
ዓ/ም፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 11058 ጥር
05 ቀን 2013 ዓ/ም እና የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 12050 ታህሳስ 08 ቀን 2013
ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 202581

ቀን፡- 26/02/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- ወ/ሮ ረሂማ አብዱላሂ

ተጠሪዎች ፡-1.ከዲር ዮሱፍ በከር

2. ሰይዳ ረመዳን

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
ጉዳዩ የጋራ የሆነ የእርሻ መሬት በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገ ነዉ የተባለዉ ዉል ቀሪ እንዲደረግና
ይዞታዉን ለማስለቀቅ እንዲሁም አላባ ለማስከፈል የቀረበ ክስ የመዳኝት ሥልጣን የሚመለከት ነዉ፡፡
አመልካች በተጠሪዎችና በስር 1ኛ ተከሳሽ አቶ ሙስጠፋ ዩሱፍ ላይ በሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
በመሰረቱት ክስ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ለ30 ዓመታት በትዳር ተሳስረን አብረን ስንኖር በሐረር ክልል በድሬ
ጠያራ ወረዳ በአቦከር ሙጢ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ዉስጥ ያለንን አንድ ጥማድ ከግማሽ የሆነ አዋሳኙ በክሱ
የተጠቀሰዉን የእርሻ መሬት ያለእኔ ፈቃድ በሕገ-ወጥ መንገድ ለአሁን ተጠሪዎች በሽያጭ አስተላልፈዋል፡፡
በዚህ ምክንያት በአመት 20 ኩንታል ማሽላ በማምረት ማግኘት የምንችለዉን በኩንታል በብር 1200.00
ሂሳብ ብር 24,000.00 አሳጥዉኛል፡፡እየተቃወምኩ በመሬቱ ላይ ተጠሪዎች ቤት ሰርተዉበታል፡፡ስለሆነም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉሉ ሕገ-ወጥ ስለሆነ እንዲፈርስና የገነቡትን ቤት አፍርሰዉ ይዞታዬን እንዲለቁ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት
ጠይቀዋል፡፡

የስር 1ኛ ተከሳሽ ለክሱ በሰጡት መልስ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉን መሬት ከአመልካች ጋር በጋራ የያዙት
መሬት እንደሆነና ያለአመልካች ፈቃድ በማንኛዉም ሁኔታ ማስተላለፍ እንደሌለብኝ ባለማወቅ ለተጠሪዎች
በማስተላለፌ ተጠሪዎች በእርሻ መሬታችን ላይ ቤት ሊሰሩበት ስለቻሉ በአመልካች ጥያቄ መሰረት ቢወሰን
አልቃወምም የሚል ይዘት ያለዉ መልስ ሰጥተዋል፡፡2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በሰጡት መልስ መኖሪያ ቤት
ለመግዛት እየፈለጉ ባሉበት የስር 1ኛ ተከሳሽ በመሬቱ የመጠቀም መብታቸዉን ለማስተላለፍ ፈልገዉ
የመጠቀም መብታቸዉን ብር 100,100.00 ሽጠዉልናል፡፡ የመሬት ባለቤትነት ለመዉሰድ በሂደት ላይ
እንገኛለን፡፡መሬቱ በዚህ አግባብ እንደተላለፈልንና ቤት ስንሰራም አመልካች እያወቁ አልተቃወሙንም በማለት
ክሱ ዉድቅ እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 17912 ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ምስክሮች ሰምቶና መርምሮ በቀን 26/01/2012
ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ የስር 1ኛ ተከሳሽ ያለተጠሪ ፈቃድ ባልና ሚስት ሆነዉ ከአመልካች ጋር በጋራ
ባለይዞታ የሆኑበትን የመሬት ይዞታ ለተጠሪዎች በሽያጭ በማስተላለፍ ያደረጉት ዉል የፌዴራል ቤተሰብ
ሕግ አንቀጽ 68ን የሚቃረን በመሆኑ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 69 መሰረት ዉሉ ፈርሶ ተጠሪዎች የገነቡትን
ግንባታ በራሳቸዉ ወጪ አፍርሰዉ መሬቱን ለቀዉ እንዲወጡና ወደነበሩበት እንዲመለሱ ሲል ወስኗል፡፡

ተጠሪዎች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ
በመ/ቁጥር 04953 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ በቀን 22/10/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካች ክስ
የመሰረቱት ፍርድ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት ጉዳዩን ለመዳኘት ሥልጣን አለዉ በማለት ቢሆንም
ግራ ቀኝ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች በመሆናቸዉ፣ዉሉ የተደረገበት የመሬት ይዞታ የሚገኘዉ በሐረሪ ክልል
ዉስጥ የሚገኝ በመሆኑ ጉዳዩን የፌዴራል ጉዳይ የሚያደርግ ምክንያት በሌለበት እንደፌዴራል ጉዳይ
ተቀብሎ መዳኘቱ ስህተት ነዉ፡፡እንዲሁም አመልካች ክስ ሲመሰርቱ በግምት ብር 24,000.00 ምርት
የሚገኝበት መሬት እንደሆነ ጠቅሰዉ ያቀረቡት ክስ ስለሆነ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህ ልክ የሚገመት
ክስ በመጀመሪያ ደረጃ ዳኝነት ሥልጣን ተቀብሎ ለመዳኘት የሚያስችል ስልጣን ሳይኖረዉ የሰጠዉ ዉሳኔ
ነዉ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ሽሯል፡፡በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች የሰበር አቤቱታቸዉን
ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም በመ/ቁጥር 00124 ላይ በቀን 24/03/2013ዓ/ም
በሰጠዉ ትእዛዝ አቤቱታቸዉን ሰርዞባቸዋል፡፡

አመልካች በቀን 07/10/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ግራ ቀኝ በተለያዩ ክልሎች ነዋሪ
መሆናችን ስለተረጋገጠ የስር የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እንደፌዴራል ጉዳይ በመቁጠር ዉሳኔ
መስጠቱ ተገቢ ሆኖ ሳለ ተጠሪዎችም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የመዳኘት ስልጣን እንደሌለዉ ገልጸዉ ያቀረቡት
መቃወሚያ ሳይኖር ዉሳኔዉ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሻሩ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5/2 ስር
የተደነገገዉንና በሰ/በ/ቁጥር 144613 ላይ የተሰጠዉን ዉሳኔ የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተፈጸመበት ነዉ፡፡እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረብኩትን የሰበር አቤቱታ ምርምሮ ለሰበር
እንዲቀርብ አዞ ግራ ቀኝ የጽሁፍ ክርክር አቅርበን ለዉሳኔ በተቀጠረበት ቀን ጉዳዩ ለሰበር አያስቀርብም
በማለት ዉሳኔ የሰጠበት አግባብ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337 እና ከቁጥር 339-348 ስር ስለዉሳኔ አሰጣጥ
የተደነገገዉን ሥነ ሥርዓት የተከተለ ባለመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነዉ በማለት
አቤቱታቸዉን አቅርበዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ለማጣራት ያስቀርባል ብሎ
ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ወደኋላ ተመልሶ አያስቀርብም በማለት ዉሳኔ የሰጠበት አግባብ ተጠሪዎች ባሉበት
እንዲመረመር ትዕዛዝ በመስጠቱ ተጠሪዎች በቀን 05/11/2013 ዓ/ም የተፃፈ መልስ በማቅረብ ግራ ቀኝ
በአንድ ክልል ዉስጥ ነዋሪ ስለሆንና ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬትም በሐረሪ ክልል የሐረሪ ከተማ አካል
ሆኖ የሚገኝ በመሆኑ ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣን ያለዉ የከተማ ነክ ፍርድ ቤት በመሆኑ የስር የክልሉ
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በፌዴራል ዳኝነት ሥልጣን ተቀብሎ መዳኘቱ ስህተት ነዉ ተብሎ በመሻሩ
የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት መልሳቸዉን ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ በላይ አጠር ባለ መልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች
ይዘት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ያስቀርባል ሲል ከያዘዉ ጭብጥ በተጨማሪ
የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እንደፌዴራል ጉዳይ ቆጥሮ በዉክልና ሥልጣን አከራክሮ መወሰኑ ተገቢ
አይደለም ተብሎ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉሳኔዉ በመሻሩ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር
አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነውም አመልካችና ተጠሪዎች ነዋሪነታቸዉ በአንድ ክልል ዉስጥ እንደሆነ ጉዳዩን በይግባኝ
ያየዉ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያረጋገጠዉ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡የክሱ ስረ ነገር እና በአመልካች
የተጠየቀዉ ዳኝነት አመልካች ያለፈቃደ የጋራ ባለይዞታ የሆንኩበትን የእርሻ መሬት ባለቤቴ ለተጠሪዎች
በሽያጭ ለማስተላለፍ የተደረገዉ ዉል ቀሪ ሆኖ ተጠሪዎች እየተቃወምኩ የሰራሁትን ቤት አፍርሰዉ
መሬቱን እንዲለቁ ይወሰንልኝ የሚል እንደሆነ ከክርክሩ ተገንዝበናል፡፡እንዲሁም ለክሱ መሰረት የሆነዉ
ዉልም የተደረገዉም ሆነ ተሸጠ የተባለዉ መሬት የሚገኘዉ በሐረሪ ክልል ዉስጥ መሆኑ አከራካሪ
አይደለም፡፡የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዘንድ ክሱ ሲቀርብ በሥራ ላይ በነበረዉ በፌዴራል ፍርድ
ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5/2 መሰረት መደበኛ ነዋሪነታቸዉ በተለያዩ ክልሎች ዉስጥ በሆኑ
ሰዎች መካከል የሚነሱ ክርክሮችን የመዳኘት ሥልጣን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እንደሆነ በተደነገገዉ
መሰረት የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ መደበኛ የመኖሪያ አድራሻ በተለያዩ ክልሎች ዉስጥ
መሆኑ ከተረጋገጠና ክርክር ያስነሳዉ ንብረት ግምት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ሥልጣን ሥር
የሚወድቅ መሆኑ ካረጋገጠ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/4 መሰረት በዉክልና ጉዳዩን ተቀብሎ
የመዳኘት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ሆኖም በተያዘዉ ጉዳይ የግራ ቀኙ መደበኛ አድራሻ በአንድ ክልል ዉስጥ
መሆኑ ከመረጋገጡም በላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ ዉል የተደረገዉና እንዲፈጸም የታቀደዉ መሬቱ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በሚገኝበት ሐረሪ ክልል ዉስጥ በመሆኑ ጉዳዩን የፌዴራል ጉዳይ የሚያደርግ ምክንያት የለም፡፡ስለሆነም
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እንደፌዴራል ጉዳይ በመቁጠር
በመጀመሪያ ደረጃ ዳኝነት ሥልጣን አከራክሮ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት መሻሩና ጉዳዩ የክልል ጉዳይ
ነዉ ሲል የሰጠዉ ዉሳኔ ሕግን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችሎት ደረጃ ሊታረም የሚችል
ስህተት የተፈጸመበት አይደለም፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከላይ በተመለከተዉ መሰረት በሰጠዉ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት
አመልካች ያቀረረቡትን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ተጠሪዎችን ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ
እንዲሰጡ ካደረገ በኋላ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 337ን በመጥቀስ የክልሉ ሰበር የአመልካችን የሰበር አቤቱታ
መሰረዙን ከቀረበዉ ክርክር ተገንዝበናል፡፡ እስካሁን የሰበር ችሎት ክርክሮችን የሚመራበት የተለየ ሥነ
ሥርዓት ሕግ ባለመኖሩ በሥነ ሥርዓት ሕጎች ለመደበኛ ክስና ለይግባኝ ክርክሮች አመራር የተቀመጡ
ድንጋጌዎችን ለሰበር በሚሆን መልኩ አመሳስሎ ተግባራዊ የማድረግ የዳበረ የሰበር ችሎቶች አሰራር መኖሩ
ግልጽ ነዉ፡፡በዚህ አግባብ የክልልም ሆነ የፌዴራል የሰበር ሰሚ ችሎቶች የሥነ ሥርዓት ሕጉን ድንጋጌዎች
ሲጠቀሙ በሥነ ሥርዓት ሕጎች የተዘረጋዉን የክርክር ሂደቶች አፈጻጸም ቅደም ተከተል በተቻለ መጠን
በጥንቃቄ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ለፍትሐ ብሔር ይግባኝ ክርክር አመራር በፍትሐ ብሔር ሥነ
ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 እና 338/1 መሰረት የይግባኝ ማመልከቻዉንና የመጀመሪያዉ ደረጃ ፍርድ ቤት
ፍርድ የሰጠበትን መዝገብ ግልባጭ በመመርምርና ይግባኝ ባይን በመስማት መልስ ሰጭ ቀርቦ እንዲከራከር
ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ከሰጠ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ እንዲሁም ሕግን መርምሮ እንደነገሩ
ሁኔታ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 341፣343/1 እና 348/1 መሰረት ዉሳኔ ሊሰጥ ይገባል እንጂ ወደኋላ ተመልሶ
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337ን በመጥቀስ የይግባኝ ማመልከቻዉ በመሰረዝ መወሰን የሚችልበት ሥነ
ሥርዓት አግባብ የለም፡፡በተመሳሳይ ለይግባኝ ክርክር አመራር የተቀመጠዉን ሥነ ሥርዓት በመጠቀም
የሰበር ክርክር ሲመራም የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ የሆነ ወገን መልስ አቅርቦ እንዲከራከር ከተደረገ
በኋላ በስር ፍርድ ቤት የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩ
ተመርምሮ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ከተባለ እንዲታረም ካልሆነም የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ
እንዲጸና ከሚወሰን በስተቀር ሂደቱን ወደኋላ በመመለስ የፍ/ብሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 ተጠቅሶ በሰበር ችሎት
እንዲመረመር የሚያስችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም ተብሎ የሰበር አቤቱታዉ የሚሰረዝበት አግባብ
የለም፡፡

በያዝነዉ ጉዳይ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩ በሰበር ችሎት እንዲመረመር ትእዛዝ ሰጥቶ
ተጠሪዎች መልስ ሰጥተዉ ከተከራከሩ በኋላ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337ን በመጥቀስ የአመልካችን የሰበር
አቤቱታ በመሰረዝ ትእዛዝ የሰጠበት መንገድ ሊታረም የሚገባዉ የክርክር አመራር ጉድለት ነዉ፡፡ሆኖም
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት የይግባኝ ማመልከቻም ሆነ የሰበር አቤቱታን በመሰረዝ የሚሰጠዉ
ዉሳኔ ከዉጤት አንጻር ሲታይ የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ የማጽናት ያክል ሕጋዊ ዉጤት ያለዉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ነዉ፡፡በመሆኑም ከመነሻዉም ክርክሩ የፌዴራል ጉዳይ ባልሆነበት እንደፌዴራል ጉዳይ ተቆጥሮ የተወሰነበት
የክርክር አመራር ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑና ጉዳዩ የክልል ጉዳይ ስለሆነ እንደአዲስ ክስ ቀርቦበት
ሥልጣን ባለዉ በሐረሪ ክልል ፍርድ ቤት ታይቶ ሊወሰን የሚገባ ከመሆኑ አንጻር በማየት ከዚህ አኳያ
በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ዘንድ የተፈጠረዉን የክርክር አመራር ጉድለት አልፈነዋል፡፡ስለሆነም ተከታዩን
ወስነናል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. የሐረሪ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 17912 ላይ በቀን 26/01/2012 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 04953 ላይ በቀን 22/10/2012ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ
በመሻር የወሰነዉና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ቁጥር 00124 ላይ በቀን
24/03/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል፡፡

2. ይህ ዉሳኔ አመልካች ሥልጣን ባለዉ የክልሉ ፍርድ ቤት ክስ ከማቅረብ አያግዳቸዉም፡፡

3. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 202681
ቀን ፡- ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- 1. ወ/ሮ ከበቡሽ ቡሎ 6. ወ/ሪት አስናቁ ዓለሙ

2. ወ/ሮ አስቴር አበበ 7. ወ/ሮ እየሩሳሌም ገለቱ

3. ወ/ሮ ወርቅነሽ አሰፋ ቀረቡ 8. ወ/ሮ አጸደ አረሩ ቀረቡ

4. ወ/ሮ ወይንሸት ተክሌ 9. ወ/ሮ ተረፉ አረሩ

5. ወ/ሮ ቆንጂት ዘውዴ 10. ወ/ሮ ጠጅነሽ ቴኒ

ተጠሪ ፡- አቶ መንግሥቱ ባለህ፡- ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው
አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በተጠሪ የንግድ ሥራ
በልብስ ስፌት፣ በልብስ እጅ ሥራና ዝምዘማ የሥራ መደብ ተቀጥረን ስንሰራ ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓ/ም
ከሕግ ውጭ በቃል ከሥራ አሰናብቶናል፡፡ የሥራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ስለሆነ የአገልግሎት ክፍያ፣ ካሣ፣
የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የዓመት ዕረፍት፣ ትርፍ ሰዓት የተሰራበት ክፍያ እንዲሁም ክፍያው ለዘገየበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቅጣት እንዲከፈላቸው እና የሥራ ልምድ እንዲሰጣቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት መልስ
በሕመም ምክንያት የተወሰኑ ወራትን አልነበርኩም፤ በዚህ ጊዜ በአደራ ሥራውን ሲያስተዳድሩ የነበሩት
ባለቤቴና ልጄ ናቸው፡፡ የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት በመግጠሙ ጥሬ ዕቃ በገበያው ላይ ማግኘት አልተቻለም፡፡
በዚህ ለአመልካቾች ስራ ሳይሰሩ የሰኔ እና ሀምሌ ወር 2011 ዓ/ም ደመወዝ ተከፍሏል፡፡ እጥረቱ ሊቀረፍ
ስላልቻለ ሠራተኞች ሳይሰሩ ከሚመላለሱ ተብሎ ብር 5,000.00 በመክፈል በመስከረም ወር እንዲመለሱ
ገልጸን የተለያየን ቢሆንም በመስከረም ወር ስራ ለመጀመር መቅረብ ሲገባቸው ከሥራም ሳይሰናበቱ ክስ
አቅርበዋል፡፡ አሁንም ወደሥራቸው ቢመለሱ ተቃውሞ የለኝም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 107631 የግራቀኙን ማስረጃ በመስማት
ከቀረበው ማስረጃ በተሻለ የተረጋገጠው አመልካቾች በመስረም ወር 2012 ዓ/ም ወደሥራ ተመልሰው የነበሩ
ቢሆንም ሥራ የለም ተብለው የተሰናበቱ መሆኑ ነው፡፡ በጥሬ ዕቃ ዕጥረት የተሰናበቱ ቢሆንም በአሠሪና
ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 28 መሠረት የሚደረግ ስንብት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሊከናወን
የሚገባ ሲሆን ተጠሪ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጡ አመልካቾችን ከሥራ ማሰናበታቸው ከሕግ ውጭ የሥራ ውሉ
እንደተቋረጠ ያረጋግጣል፡፡ ሥለሆነም የሥራ ሥንብቱ ሕገ-ወጥ ነው፡፡ ካሣ፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣
የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ክፍያ ለዘገየበት ቅጣት፣ የዓመት ዕረፍት ክፍያ ተጠሪ ለአመልካቾች ሊከፍሉ
ይገባል፤ የሥራ ልምድም ይሰጣቸው በማለት ሲወስን ትርፍ ሰዓት ሥራ መሰራቱ አልተረጋገጠም በማለት
ዳኝነቱን ውደቅ አድርጓል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡትን ይግባኝ የተቀበለው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግራቀኙን
አከራክሮ አመልካቾች በክሳቸው የሥራ ውሉ ተቋረጠ በተባለበት ቀን ከሥራ የተሰናበቱ ስለመሆኑ
ምስክሮቻቸው አላስረዱም፡፡ የተጠሪን ባለቤትና ልጅ እንደቀጣሪ በመቁጠር እንዲሁም የተጠሪ ምስክሮች
መስከረም ወር ላይ እንዲመለሱ ተነግሯቸዋል በማለት መመስከራቸው፣ 2ኛ ምስክርም ከዚህ በኋላ
እንዳትመጡ አላልኩም በማለት ያስረዳው ጋር ተገናዝቦ ሲታይ ተጠሪ አመልካቾችን ከሥራ ማሰናበታቸውን
አላስረዱም፡፡ የሥር ፍርድ ቤት በግራቀኙ ያልተነሳን መከራከሪያ በማንሳት በጥሬ ዕቃ ዕጥረት ነው
የተሰናበቱት ማለቱ ተገቢ አይደለም፡፡ ማስጠንቀቂያ አለመስጠትም የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ከሚያስከፍል
በስተቀር ስንብቱን ሕገ-ወጥ አያደርገውም፡፡ ተጠሪ አምነው ያልከፈሉት ክፍያ ስለመኖሩ የቀረበ ክርክርና
ማስረጃ ሳይኖር ክፍያ ለዘገየበት ቅጣት እንዲከፈል መወሰኑ ስህተት ያለበት ነው፡፡ ስለሆነም የሥራ ስንብቱ
ሕገ-ወጥ ነው በሚል ካሣ፣ የሥራ ስንብት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና ክፍያ ለዘገየበት ቅጣት ተጠሪ
እንዲከፍሉ የተሠጠውን የውሳኔ ክፍል ሽሯል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የሥራ ውላችን
ከሕግ ውጭ መቋረጡ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ የተጠሪ ባለቤትና ልጅ ሥራውን በአደራ ያስረከቧቸው
ስለመሆኑ ተጠሪም አምነዋል፡፡ ውሳኔው ሕግን የተከተለ አይደለም የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን
ተመልክቶ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ የማስረጃ ምዘና መርሕን የተከተለ ስለመሆን አለመሆኑ
ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ የታዘዙ ሲሆን ያቀረቡት መልስ አመልካች ከሥራ መሰናበታቸውን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አላስረዱም፡፡ ማስረጃው ተመዝኖ የተወሰነ ስለሆነ ውሳኔው ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም
ብለዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የአመልካቾች የሥራ ውል የተቋረጠው በአሠሪው
አነሳሽነት ወይስ በሠራተኛው አነሳሽነት? የሚለውን በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በተጠሪ የንግድ ሥራ በልብስ ስፌት፣ በልብስ እጅ ሥራና


ዝምዘማ የሥራ መደብ ተቀጥረን ስንሰራ ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓ/ም ከሕግ ውጭ በቃል ከሥራ
አሰናብቶናል፡፡ የሥራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ስለሆነ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸው እና የሥራ ልምድ
እንዲሰጣቸው ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት በመግጠሙ ጥሬ ዕቃ
በገበያው ላይ ማግኘት አልተቻለም፡፡ በዚህ ለአመልካቾች ስራ ሳይሰሩ የሰኔ እና ሀምሌ ወር 2011 ዓ/ም
ደመወዝ ተከፍሏል፡፡ እጥረቱ ሊቀረፍ ስላልቻለ ሠራተኞች ሳይሰሩ ከሚመላለሱ ተብሎ ብር 5,000.00
በመክፈል በመስከረም ወር 2012 ዓ/ም እንዲመለሱ ገልጸን የተለያየን ቢሆንም በመስከረም ወር ስራ
ለመጀመር መቅረብ ሲገባቸው ከሥራም ሳይሰናበቱ ክስ አቅርበዋል፡፡ አሁንም ወደሥራቸው ቢመለሱ
ተቃውሞ የለኝም በማለት ተከራክረዋል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት የሥራ ውል የሚቋረጠው አንደኛው በሕግ ወይም
በሥምምነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተዋዋይ ወገኖች አነሳሽነት ነው፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር
377/1996 አንቀጽ 24 በሕግ መሠረት ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ተዘርዝረዋል፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 25
ደግሞ በሥምምነት ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ይገልጻል፡፡ በአሠሪው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበት
ሁኔታ በአዋጁ ከአንቀጽ 26-30 በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ
31 እና 32 ደግሞ በሠራተኛው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበትን ሁኔታ ደንግጓል፡፡ የአዋጁ ድንጋጌ
አንቀጽ 31 በአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ለአሠሪው በመስጠት ሠራተኛው ውሉን ማቋረጥ እንደሚችል
የሚገልጽ ነው፡፡ ሌላው በሠራተኛው አነሳሽነት የሚፈጸም የሥራ ውል ማቋረጥ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ
ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 32(1)(ሀ እስከ ሐ) የተመለከተ ሲሆን በሕጉ የተዘረዘሩት ምክንያቶች አሠሪው
የሠራተኛውን ሠብዓዊ ክብርና ሞራል መንካቱ፣ በወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር በሠራተኛው ላይ መፈጸም፣
ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት አደጋ ሊያደርስ የሚችል ምክንያት እያለ አሠሪው ተገቢውን እርምጃ
ካልወሰደ ወይም ሌላ አሠሪው ለሠራተኛው መፈጸም ያለበትን ግዴታ በመደጋገም ካልፈጸመ ሠራተኛው
ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውሉን ማቋረጥ የሚችልበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡

በተያዘው ጉዳይ እያከራከረ ያለው የአመልካቾች የሥራ ውል በተጠሪ አነሳሽነት የተቋረጠ ነው ወይስ
በአመልካቾች በራሳቸው ሥራውን በመተዋቸው የሚል ነው፡፡ አመልካቾች የሥራ ውላችን በተጠሪ የተቋረጠ
ነው ያሉ በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁ. 2001(1) እና በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 259 እና 260 መሠረት የአንድን ፍሬ ነገር
መኖር ጠቅሶ የሚከራከር ወገን ፍሬ ነገሩ ስለመኖሩ የማስረዳት ግዴታ ስላለበት ውሉ በተጠሪ መቋረጡን
ማስረዳ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ማስረጃዎች ሰምቶ አመልካቾች

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በተጠሪ ስለመሰናበታቸው ተረጋግጧል በማለት የወሰነ ቢሆን ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ማስረጃው
በአግባቡ አልተመዘነም በሚል አመልካቾች በክሳቸው የሥራ ውሉ ተቋረጠ በተባለበት ቀን ከሥራ የተሰናበቱ
ስለመሆኑ ምስክሮቻቸው አላስረዱም፡፡ የተጠሪን ባለቤትና ልጅ እንደቀጣሪ በመቁጠር እንዲሁም የተጠሪ
ምስክሮች መስከረም ወር 2012 ዓ/ም ላይ እንዲመለሱ ተነግሯቸዋል በማለት መመስከራቸው፣ 2ኛ
ምስክርም ከዚህ በኋላ እንዳትመጡ አላልኩም በማለት ያስረዳው ጋር ተገናዝቦ ሲታይ ተጠሪ አመልካቾችን
ከሥራ ማሰናበታቸው በሚገባ አላስረዱም ሲል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ሆነ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988
አንቀጽ 10 ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ ማስረጃው ተመዝኖ
የተደረሠበትን የፍሬ ነገር ድምዳሜ ላይ እንዲመለከት ሥልጣን አልተሠጠውም፡፡ በሥር ፍርድ ቤት
የማስረጃ ምዘና ሂደት የተፈጸመ የማስረጃ ሕግና ማስረጃ ምዘና መርሕ ጥሰት መኖሩን የክርክሩ ሂደት
አያሳይም፡፡ ስለሆነም አመልካቾች በተጠሪ የሥራ ውላቸው መቋረጡን ያላስረዱ በመሆኑ ካሣ፣ የሥራ
ስንብት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና ክፍያ ለዘገየበት ቅጣት ተጠሪ የሚከፍሉበት ሕጋዊ ምክንያት የለም
ተብሎ የተሠጠው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 249944 ጥር 27 ቀን 2013 ዓ/ም የሠጠው ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ፡-202693

ቀን፡-28/03/2014ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ወ/ሮ ከድራ ጂብሪል አበዲድ -አልቀረቡም

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሀዲዮ ኬይሬ-አልቀረቡም

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች በቀን 26/05/2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል
ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 00181 በ19/05/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ
መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልጸው በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረቡት
ማመልከቻ መነሻነት ሲሆን አመልካች እና በዚህ የሰበር ክርክር በተከራካሪነት ያልተመዘገቡት
ኢስማሃን ጅብሪል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የፍርድ ባለዕዳዎች የነበሩ ሲሆን
ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ነበሩ፡፡

የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች እና በስር 2ኛ የፍርድ ባለዕዳ ላይ ባቀረቡት
የአፈፃፀም ክስ ባቀረብኩት የወራሽነት አቤቱታ መሰረት ጉዳዪ በአጣሪዎች ከተጣራ በኋላ የውርስ ሀብት
ነው ተብሎ በተወሰነልኝ መሰረት ይዞታው የውርስ ሀብቴ መሆኑ በተረጋገጠው መሰረት እንዲፈፀምልኝ
በማለት አመልክተዋል፡፡አመልካች በሰጡት መልስም በሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

188/92 አንቀጽ 4(2) መሰረት በፍርድ ቤት ቀርበን ለመዳኘት አንፈልግም በማለት ያመለከትን
በመሆኑ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ ማሰናበት ሲችል ጉዳዪን ማየት የለበትም፡፡ጉዳዩን ስልጣን ባለው
ፍርድ ቤት አቅርበን ታይቶ የመጨረሻ እልባት ያገኘ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ዘግቶ
ሊያሰናብተኝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ
በሰጠው ብይንም አመልካች እና የስር 2ኛ የፍርድ ባለዕዳ ስለውርስ ማጣራቱ ሂደት ማወቅ
አለማወቃቸውን አስመልክቶ ወጥነት ያለው ክርክር አለማቅረባቸውን፤ተጠሪ የውርስ ሀብቱ ተጣርቶ
የውርስ ድርሻቸውን ለመውረስ ያቀረቡት አቤቱታ ከህጉ አንፃር ክርክር የሚያስነሳ አለመሆኑን እና
በሸሪአ ፍርድ ቤቱ የተያዘው የውርስ ማጣራት ሂደት አስቀድሞ የተጀመረ ሆኖ እያለ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት
በድጋሚ ተከፍቶ መታየቱ አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ የአሁን ተጠሪ ያቀረቡት የአፈፃፀም ክስ
ሊቀጥል ይገባል በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡አመልካች እና የስር 2ኛ የፍርድ ባለዕዳ በዚህ ብይን ቅር
በመሰኘት ይግባኝ ለድሬደዋ ፌደራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኙ ውድቅ
ተደርጎባቸዋል፡፡

አመልካች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጭሩ፡- የሸሪዓ ፍርድ ቤት የውርስ ሀብትን በተመለከተ
አከራካሪ ሲሆን ጉዳዪን ለመዳኘት ስልጣን የሚኖረው በአዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀጽ 4(2) ስር
እንደተገለፀው በተከራካሪዎች ፈቃድና ስምምነት መሰረት እንደሆነ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም
አንድ ተከራካሪ ወገን በሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዳኘት አልፈልግም ያለ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የአስገዳጅነት
ባህሪ ያለው የዳኝነት ስልጣን ሊኖረው አይችልም ፡፡

ይሁን እንጂ የፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ለመዳኘት ፈቃደኛ አለመሆናችንን
መግለፃችንን እያወቀ ወዲያው መዝገቡን መዝጋት ሲገባው በአስገዳጅነት መዳኘቱ አግባብ አይደለም፤
አንድ ሰው የፍርድ ባለዕዳ ሊባል የሚችለው በፍርድ ቤት ተከሶ የተፈረደበት ሲሆን ብቻ ሆኖ እያለ
የአሁን አመልካች እና እህቴ ላይ እስካሁን ድረስ በተጠሪ አማካይነት የቀረበብን ክስም ሆነ ያስፈረደብን
ፍርድና ውሳኔ በሌለበት እኛ ወራሾች ሳንፈቅድ በሸሪዓ ፍርድ ቤት የፀደቀ የውርስ ሀብት ማጣሪያ
ሪፖርት ቢኖር እንኳንም እኛ ተወላጆች ያልተሳተፍንበት ከመሆኑም በላይ ሪፖርት እንደ አንድ ማስረጃ
የሚያገለግል በሌላ ማስረጃ ሊስተባበል የሚችል እንጂ እንደ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተቆጥሮ አፈፃፀም
የሚደረግበት ባልሆነበት፤ የሟች ወላጅ አባቴ አቶ ጂቢሪል አበዲድ እና ሟች ወላጅ እናቴ ወ/ሮ አዌያ
ዋወራህ የውርስ ሀብት መደበኛ በሆነው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.72370
ተጣርቶ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የፀደቀ ከመሆኑም በተጨማሪ በአሁን ተጠሪ ላይ በመ/ቁ.76758 ክስ
መስርተንባቸው ወራሽ እንዳልሆኑ ተረጋግጦ ተፈርዶባቸው በአፈፃፀም መ/ቁ.78088 ተስተናግዶ
የአፈፃፀም ሂደቱም ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ እያለ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ታይቶ ፍፃሜ
ያገኘውን ጉዳይ ወደ ጎን በመተው ውሳኔውን ለመቀልበስ ስለተፈለገ ብቻ ጉዳዪን እንደገና በፌደራል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መጀመሪያ ደረጀ ሸሪዓ ፍርድ ቤት መደኘት መሰረታዊ የሕግ ስሕተት በመሆኑ አመልካች
ባቀረብኳቸው ቅሬታዎች መሰረት ጉዳዪ ታይቶ የስር የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ይሻርልኝ
በማለት አመልክተዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ አመልካች ጉዳዪ ታይቶ በመደበኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኘና አፈፃፀሙም በዛው ፍርድ
ቤት ይደረግልኝ በማለት ያቀረበውን የመቃወሚያ ክርክር የሸሪዓ ፍርድ ቤቱ ወደ ጎን ትተው አፈፃፀሙ
ይቀጥል ያለበትን አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ
ግራ ቀኙ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ በሰጡት መልስም የአሁን ተጠሪ ከአመልካች ቀድሜ በድሬደዋ ፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት
በመ/ቁ 05388 ላይ ለክርክር መነሻ የሆነው ንብረት ላይ የሚስትነት ድርሻ ያለኝ ስለሆነ ንብረቱ
እንዲጣራልኝ አቤቱታ አቅርቤ እየተጣራ ባለበት የአሁን አመልካች የሟች ባለቤቴ ልጆች ነን በማለት
ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተው ተከራክረው በንብረቱ ላይ ተጠሪ የሚስትነት ግማሽ ድርሻ ያለኝ ስለመሆኑ
አመልካችና ሌሎች የሟች ባለቤቴ ልጆች ደግሞ በቀሪው ድርሻ ላይ የውርስ መብት ያለቸው ስለመሆኑ
ተወስኗል፡፡አመልካች ለክርክሩ መነሻ በሆነው ንብረት ላይ ተጠሪዋ የሚስትነት ድርሻ ያላቸው
ስለመሆኑ አስቀድሞ ተከራካሪ በሆኑበት ጉዳይ ላይ የተሰጠ ፍርድ መኖሩን እያወቁ ተጠሪን በቤቱ ላይ
ምንም መብት እንደሌለኝና 50 ዓመት የኖሩኩበትን ቤት በሕገ ወጥ መንገድ ነው የያዘችው ብለው ክስ
አቅርበው መጥሪያ ሳይደርሰኝ ለመቀበል እምቢተኛ እንደሆንኩ አድርገው ቃለ መሃለ አቅርበው ጉዳዪ
በሌለሁበት እንዲታይ በማድረጋቸው ይህንን በመቃወም አቤቱታ አቅርቤ በክርክር ላይ እንገኛለን፡፡

ተጠሪ በሸሪዓ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረብኩት የአሁን አመልካችን መልስ ሰጭ አድርጌ ባለመሆኑ
የእኔን አቤቱታ በመረጥኩት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት አቅርቤ የመዳኘት መብቴ ሕግ መንግስታዊ
ነው፡፡የአሁን አመልካችን በአቤቱታዬ ላይ መልስ ሰጭ አድርጊያት ቢሆን ኖሮ በፍርድ ቤቱ ለመዳኘት
ፈቃደኛ አይደለሁም በሚል የምታቀርበው ክርክር ተቀባይነት ይኖረው ነበር፡፡ነገር ግን ተጠሪ
አመልካችን መልስ ሰጭ አድርጌ ባለቀረብኩበት አቤቱታ ጣልቃ ለመግባት አመልክታ በፍርድ ቤት
ለመዳኘት ፈቃደኛ አይደለሁም በሚል የምታቀርበው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ሲሆን በሸሪዓ ፍርድ
ቤት በሚደረግ ክርክር ላይ ጣልቃ ገብቶ መከራከር በፍርድ ቤቱ ለመዳኘት ስምምነትን እንደመስጠት
የሚያስቆጠር ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰመ/ቁ 45806 በቅጽ 10
ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

ስለሆነም ተጠሪ በሸሪዓ ፍርድ ቤት ከአመልካች በፊት ንብረት እንዲጣራልኝ አቤቱታ ሳቀርብ ወደ
ክርክሩ ጣልቃ ለመግባት አመልክተውና ተከራክረው የተወሰነውን በውሳኔውም ቅሬታ አድሮባቸው
ይግባኝ ጠይቀው የፀናባቸውን ጉዳይ ለዚህ ፍርድ ቤት የክርክሩን ይዘት ለውጠው በሸሪዓ ፍርድ ቤት
ለመዳኘት ፈቃደኛ ሳንሆን ተወስኖብናል ሲሉ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ስላልሆነ ፍርድ ቤቱ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሊቀበለው አይገባም፡፡ስለሆነም የተከበረው ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ


እንዲያሰናብተኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ከመነሻውም የአፈፃፀም አቤቱታ
ሊቀርብበት የሚችል በስር ፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ አለን? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን
የሰበር ክርክር ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡ ተጠሪ
የውርስ ሀብት ይጣራልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ በተያዘው የውርስ መዝገብ
ላይ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 188/92 አንቀፅ 4(2) መሰረት በፍርድ ቤቱ ለመዳኘት አንፈልግም
በማለት ያመለከቱ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተመለከተ ሲሆን አመልካች ይህ
መቃወሚያቸው ታልፎ በፍርድ ቤቱ ለመዳኘት ፈቃዳቸውን ባልሰጡበት ለአፈፃፀም ክሱ መነሻ የሆነው
ውሳኔ መሰጠቱ አግባብ አለመሆኑን በመግለፅ የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

በመሰረቱ ከላይ እንደተመለከተው ተጠሪ ለስር ፍርድ ቤት አቤቱታቸውን ያቀረቡት የውርስ ሀብቱ
ተጣርቶ የውርስ ድርሻቸውን እንዲለይ በመሆኑ ይህ ደግሞ በመሰረታዊነት መብት አለን ባዮችን ወይም
ወራሾችን መወሰን፤የሟች ኑዛዜ ካለ መፈለግ፤በዚህ ኑዛዜ መሰረት ተጠቃሚዎችን መወሰን፤ውርሱን
ማስተዳደር፤የውርሱን ተከፋይ ገንዘብ መሰብሰብና እዳዎችን መክፈል፤የሟቹን ንብረት ማጣራትና
ማፈላለግ፤የኑዛዜ ስጦታዎችን መክፈልና የመሳሰሉት ተግባራት የሚከናወኑበት ሆኖ በመጨረሻም የሟች
ወራሽ መሆኑን የሚገልፅ አልያም ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ ጭምር የሚያመለክት የወራሽነት
ማስረጃ የሚሰጥበት በመርህ ደረጃ በአንድ ወገን አመልካችነት የሚቀርብ ከህጉ አንፃር ክርክር
የሌለበት ከመሆኑ አንፃር አመልካችና የስር 2ኛ የፍርድ ባለዕዳ በፍርድ ቤቱ ለመዳኘት ባይፈቅዱም
በተጠሪ ፈቃደኝነት የቀረበውን አቤቱታ መሰረት አድርጎ የስር ፍርድ ቤት የወራሽነት የምስክር ወረቀት
መስጠቱ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡

ነገር ግን ለተጠሪ የውርስ ሀብቱ ተጣርቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው በመሆኑ ይህንን
የምስክር ወረቀት መሰረት በማድረግ ተጠሪ ከወራሾች ጋር በስምምነት መከፋፈል ካልቻሉ በድርሻቸው
መጠን ዳኝነት ከፍለው ይሄው መብታቸው በፍርድ እንዲረጋገጥ ዳኝነት ባልጠየቁበት፤የወራሽነት
የምስክር ወረቀት ተጠሪ የዳኝነት በድርሻቸው መጠን ከፍለው መብታቸው በፍርድ እንዲረጋገጥ ክስ
ለማቅረብ መብት ወይም ጥቅም የሚሰጣቸው ብቻ ሆኖ እያለ፤በዚህ አግባብም የወራሽነት የምስክር
ወረቀት በራሱ ፍርድ ስላልሆነ አፈፃፀም ሊጠየቅበት እንደማይችል በሰበር መዝገብ ቁጥር 18576
አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶ እያለ የስር ፍርድ ቤት የወራሽነት የምስክር ወረቀቱን መሰረት አድርጎ
የቀረበውን የአፈፃፀም አቤቱታ ተቀብሎ አፈፃፀሙ እንዲቀጥል ብይን መስጠቱና ጉዳዩን በይግባኝ
የተመለከተው ከፍተኛ ሸሪአ ፍርድ ቤት ይህንኑ የስር ፍርድ ቤት የፈፀመውን ስነስርዐታዊ ግድፈት
ሊያርም ሲገባ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ወስነናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ

1. በድሬደዋ ፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ሸሪዓ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 07901 በቀን 22/04/2013 ዓ.ም
በዋለው ችሎት አፈፃፀሙ ይቀጥል በማለት የሰጠው ብይን እና የፌደራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍርድ
ቤት በመ/ቁ 00181 በቀን 19/05/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ይህንን ብይን በማፅናት የሰጠው
ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸሯል፡፡
2. በተጠሪ አቤቱታ መሰረት ውርስ ተጣርቶ የተሰጠው የወራሽነት የምስክር ወረቀት ተጠሪ
በድርሻቸው መጠን ዳኝነት ከፍለው መብታቸው በፍርድ እንዲረጋገጥ ክስ ለማቅረብ መብት
ወይም ጥቅም የሚፈጥር እንጂ አፈፃፀም ሊጠየቅበት የሚችል ፍርድ አይደለም ብለናል፡፡
3. በሰበር ሰሚው ችሎት ተለዋጭ እስኪደርሰው ድረስ በድሬደዋ ፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ሸሪዓ
ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 07901 የተጀመረው የአፈፃፀም መዝገብ ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ
በቀን 30/06/2012 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ይጻፍ፡፡
4. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰ/መ/ቁ፡-202737

ቀን፡-29/03/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ አቶ ረጋሳ ጉርሙ ጠበቃ ጋዲሳ ቡታ ቀረቡ

ተጠሪ፡ ወ/ሮ ዘነበች ገ/መንፈስ- ጠበቆች ዘበነ ፍቅሬ እና አዲሱ አየነው


ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በተወዉ ጉዳይ ላይ የቀረበዉ ክስ


ተቀባይነት የለዉም ተብሎ የተሰጠዉን ብይን ለማስለወጥ ነዉ፡፡የክርክሩ መነሻ የቤት ሽያጭ
ውል የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ላይ የአሁኑ
አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ተጠሪ ከሟች ባለቤታቸው አቶ
ተሾመ አፈወርቅ ጋር በመሆን በቀን 06/12/1996 ዓ.ም በአ/አ/ከ/ቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት
ቁጥር 047 የካርታ ቁጥር ሴ.ኬ.አሲ/02/31/1229/001040/01 የሚታወቅ መኖሪያ ቤት
ለአመልካችና ለአቶ ፀጋዬ ገ/መንፈስ ሽጠዋል፣ቤቱን እንዲለቁ ሲጠየቁ ፈቃደኛ
ባለመሆናቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/153563 ቤትን አንዲለቁልኝ ክስ አቅርቤ
ፍ/ቤቱን አስፈቅጄ ያነሳሁት ቢሆንም ተጠሪ ቤቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ተጠሪ ቤቱን
ለቀው እንዲወጡና እንዲያስረክቡኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋዋል፡፡ተጠሪ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በበኩላቸዉ በቀን 12/05/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረበውት መልስ አመልካች በመ/ቁ.153563


ላይ ቤቱን ከተጠሪ ለመረከብ ተመሳሳይ ክስ አቅርቦ አመልካቹ በውሉ በተመለከተው ጊዜ
የሽያጭ ገንዘቡን ባለመክፈሉ የውል ግዴታውን ስላልተወጣ የባለቤትነት መብት ስለሌው
ለቀን ልናስረክብ እንደማይገባ መከራከሪያ አቅርበን እያለ አመልካች በቀን 10/04/2011ዓ.ም
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.278 መሰረት በፈቃዱ ክሱን ለመተው ማመልከቻ አቅርቦ ፍ/ቤቱም
በ11/04/2011ዓ/ም ከሻስ ክስ በማቋረጡ ለተጠሪ ወጪና ኪሳራ እንዲከፍል በማለት መዝገቡን
ዘግቷል፣ስለሆነም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በተወዉ ጉዳይ አዲስ ክስ ማቅረቡ ተገቢ
አይደለም፣በተጨማሪም የቤት ሽያጭ ውሉ ተፈጽሟል የተባለዉ ከ16 እና ከ17 ዓመታት
በፊት ስለሆነ በፍ/ህ/ቁ/1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ይታገዳል፣እንዲሁም በፍ/ህ/ቁ.
2892(3) መሰረት ሻጩ ውሉን እንደ ውሉ ቃል ከመፈፀም መዘግየቱን ከተረዳበት ጊዜ
ጀምሮ እስከ 1(አንድ) ዓመት ድረስ ውሉ እንዲፈፀምለት ካልጠየቀ በቀር ገዢው ውሉ
በግዴታ እንዲፈፀም የማድረግ መብቱን ያጣል፣ስለዚህ በ1 (አንድ) ዓመት ውስጥ ስላልጠየቀ
በይርጋ ውድቅ ይደረጋል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና በፍሬነገር ረገድ
አማራጭ ክርክር ማቅረባቸዉን መዝገቡ ያሣያል፡፡

ፍ/ቤቱም በተጠሪ በኩል የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ የግራ ቀኝ ክርክር


ሰምቶና መርምሮ በመጀመሪያዉ ክስ አመልካች ክሱ እንዲቋረጥ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ
ሌላ ጊዜ ክስ ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቀድላቸው የጠየቁ ሳይሆን ክርክሩ እየገፋ
በመምጣቱ ውጣ ውረዶች ስለበዛባቸው ክሱን ማቋረጥ እንደፈለጉ የሚያሳይ ነው፡፡ፍ/ቤቱም
ከሳሽ(የአሁኑ አመልካች) ያቀረቡትን አቤቱታ በመቀበል ከሳሽ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278 /2/
መሰረት በማየት ጉዳዩን በተመለከተ አዲስ ክስ እንዲያቀርቡ አልፈቀደም፡፡እንዲህ ከሆነ
አመልካች ክሱን የተውት ከፍ/ቤት ፈቃድ ውጭ እንደሆነና አመልካች አስፈላጊውን ኪሳራ
ለተጠሪ ከፍለው መዝገቡ መዘጋቱን እንዲሁም አመልካችም ጉዳዩን በተመለከተ አዲስ ክስ
ማቅረብ እንደማይችል በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.279(1) ስር ተደንግጓል፣ስለዚህ አመልካች አሁን አዲስ
ክስ ማቅረባቸው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(2) እና 279(1) መሰረት አግባብነት የለውም በማለት
ክሱን ውደቅ አድርጓል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም


ፍ/ቤቱ ይግባኙ አያስቀርብም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰት መዝገቡን ዘግቷል፡፡የሰበር
አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ
ይዘት ባጭሩ፤ቤቱን እንዲለቁልኝ ሲጠይቅ ተጠሪ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በከፍተኛ ፍ/ቤት
በመ/ቁ.153563 ላይ ክስ መስርቼ ስንከራከር ከቆየን በኋላ ፍ/ቤቱን አስፈቅጄ ክስ
ያቋረጥኩበት ምክንያት ተጠሪ የባለቤቴ እህት በመሆናቸው እና ተጠሪ የሽያጭ ውል
ይፍረስልኝ ጥያቄም ውሉ ህጋዊ ነው ተብሎ ስለተወሰነ ከዚህ በኋላ ተጠሪ አለቅም የሚሉበት
ምንም ህጋዊ ምክንያት የለም በፈለኩ ጊዜ ይለቁልኛል በሚል እሳቤ ፍ/ቤት አስፈቅጄ ክሱ
ተቋርጧል፡፡ ፍ/ቤት ሳላስፈቅድ በራሴ ፈቃድ ለመተው ቢፈልግ ኖሮ ፈቃድ ለመጠየቅ
አቤቱታ ለፍ/ቤት ባላቀረብኩ ነበር፡፡የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 279(1) የሚመለከተው በራሱ ፈቃድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍ/ቤትን ሳያስፈቅድ ክሱን የተወ ወይም ያቋረጠ ከሳሽን ሲሆን እኔ ግን ለፍ/ቤት አመልክቼ
ፍ/ቤቱም ክሴን እንዲተው የፈቀደልኝ መሆኑን የቀረበው ማስረጃ ያረጋግጣል፡፡ስለዚህ አዲስ
ክስ ማቅረብ አትችልም በማለት የተሰጠው ብይን የንብረት ባለቤት የመሆን መብቴን
የሚቃረን ስለሆነ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ብይን ነው በማለት ብይኑ
እንዲታረም አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ ለክርክር ምክንያት በሆነው ቤት ላይ


ግራ ቀኙ ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ሊፈርስ አይገባም በሚል የተሰጠ ውሳኔ ጸንቶ ባለበት
ሁኔታ ተጠሪ ቤቱን እንዲለቁ አመልካች በስር ፍ/ቤት ተጠሪ ላይ ያቀረቡትን የክስ አቤቱታ
ቀደም ሲል ተጠሪ ቤቱን ይልቀቁልኝ ብለው ክስ አቅርበው በራስዎ ፈቃድ አመለክተው
እንዲቋረጥ አድርጓል በማለት አቤቱታቸው ውድቅ የተደረገበትን አግባብነት ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ
278 እና 279 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ጉዳዩ ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ መልስ
እንዲሰጡበት ታዟል፡፡

ተጠሪ በበኩላቸዉ በቀን 30/11/2013ዓ.ም ጽፎ ባቀረቡት መልስ በስር ፍርድ ቤት


እየተከራከርን እያለ አመልካች ክሱን መተዋቸውን ለፍ/ቤት አመልክተዋል፣ነገር ግን ወደ
ፊት በሙሉ ወይም በከፊል አዲስ ክስ የማቅረብ መብት
አልጠየቁም፣አላስጠበቁም፤የጀመርኩት ክስ በሙሉ ፍቃድ ማቋረጠን አረጋግጣለሁ የሚል
እንጂ አዲስ ክስ ለማቅረብ አይደለም፣የፍ/ቤቱም ትእዛዝ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(1) መሰረት ክስ
መቋረጡ ያረጋግጣል፡፡በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(1) መሰረት ክስ ሲቋረጥ ወደፊት ክስ ለማቅረብ
ያልተፈቀደለት መሆኑን በፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.116869 እና 158314 ላይ
አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቷል፣አዲስ ክስ ማቅረብ የሚቻለው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(2) መሰረት
በፍ/ቤት ፈቃድ ሲቋረጥ ነው፡፡ይርጋን በተመለከተ አመልካች ያቀረበው የመፋለም ክስ
ሳይሆን በሽያጭ ውል መነሻ ተገደው ቤቱን እንዲያስረክቡኝ የሚል ስለሆነ እና በስር ፍ/ቤት
ያልተነሳና በዚህ ረገድም የህግ ስህተት እንዳልተፈፀመ ስለተረጋገጠ አቤቱታው ውድቅ ሆኖ
የስር ፍ/ቤት ውሰኔ እንዲፀና በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር
የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት
ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡ መርምረን እንደተገነዘብነዉ
የአመልካች የዳኝነት ጥያቄ ተጠሪ የሸጡላቸዉን ቤት ለቀዉ እንዲያስረክቧቸዉ እንዲወሰን
የሚል ሲሆን ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የዳኝነት ጥያቄ በመ/ቁ.153563 ላይ አቅርበዉ
አመልካቹ ክሱን ለመተዉ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት መዝገቡ የተዘጋ መሆኑ
አላከራከረም፡፡ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካች ክሱን ሲያቋርጡ አዲስ ክስ
እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ አልፈቀደላቸዉም በማለት ነዉ፡፡አመልካች አጥብቀዉ የምከራከሩት
ክሱን ያቋረጥኩት ፍርድ ቤቱን አስፈቅጄ ስለሆነ አዲስ ክስ ከማቅረብ አያግደኝም በማለት
ነዉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በህግ በሌላ አኳኋን ካልተደነገገ በስተቀር የፍትሓብሔር ክርክር የሚመራዉ በፍትሓብሔር


ስነስርዓት ህግ በተደነገገዉ አግባብ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 1 ድንጋጌ ይዘት
የምንገዘበዉ ጉዳይ ነዉ፡፡የፍትሓብሔር ስነስርዓት ህግ ዓይነተኛ ኣላማ የፍትሓብሔር ክርክር
የሚመራበትን ስርዓት በመደንገግ የፍርድ ሂደት በፍትሃዊነት እንዲመራ በማድረግ
የተከራከሪ ወገኖችንም ሆነ የፍርድ ቤቱን ሀብት እና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ክርክሩ
እልባት እንዲያገኝ ማስቻል ነዉ፡፡ይህንኑ ዓላማ ለማስካት ያስችላሉ ተብለዉ ከተዘረጉት
ስርዓቶች አንዱ ከሳሽ ወገን በአንድ ጉዳይ ላይ ተደጋጋሚ ክስ እንዳያቀርብ ለመከላከል
የተዘረጋዉ ስርዓት የሚመለከት ነዉ፡፡በዚህ መዝገብ ለተያዘዉ ጉዳይ አግባብነት ያለዉ ከሳሽ
ወገን ክሱን ለመተዉ መቻሉና ዉጤቱን የሚመለከተዉ ድንጋጌ ነዉ፡፡

አንድ ክስ ከቀረበ በኋላ በማናቸዉም ጊዜ ከሳሹ ያቀረበዉን ክስ በማንሳት ከተከሳሾቹ አንዱን


ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ከክሱ ዉጭ ለማድረግ ወይም ያቀረበዉን ክስ በሙሉ ወይም
በከፊል ለመተዉ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/1/ ስር የተመለከተ ሲሆን
ፍርድ ቤቱ አቤቱታዉን ተቀብሎ ትእዛዝ በሚሰጥበት ጊዜ ከሳሽ ወገን ክሱን ለማንሳት
ወይም ለማቋረጥ የጠየቀበትን ምክንያት መርምሮ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘዉ ከሳሹ አዲስ ክስ
ለማቅረብ የሚችልበትን መብት መጠበቅ የሚችል ስለመሆኑ በዚሁ ድንጋጌ ንኡስ አንቀጽ
(2) ስር ተመልክቷል፡፡ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ በአንድ በኩል ከሳሹ
በግል ጉዳዩ ላይ የመወሰን መብቱን ተጠቅሞ ክሱን ለመተዉ የሚችል መሆኑን በሌላ በኩል
ከሳሹ በፈቃዱ በተወዉ ነገር ላይ አዲስ ክስ ለማቅረብ የሚችለዉ ፍርድ ቤት መብቱን
የተጠበቀለት ሲሆን ብቻ መሆኑን ነዉ፡፡በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/2/ ስር እንደተመለተዉ
ከሳሹ በሌላ ጊዜ አዲስ ክስ እንዲያቀርብ ሊፈቅድለት የሚችለዉም በክሱ አቀራረብ ስርዓት
ጉድለት ያለበት ሲሆን ወይም አዲስ ክስ ለማቅረብ ሊያስፈቅድለት የሚችል በቂ ምክንያት
ሲኖር እና ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ተቀብሎ መብቱን የጠበቀለት እንደሆነ ነዉ፡፡በሌላ
አገላለጽ በቁጥር 278/2/ የተነገረዉን ባለመጠበቅ ከሳሹ ከፍርድ ቤት ፈቃድ ሳይቀበል ክሱን
በሙሉ ወይም በከፊል የተወ እንደሆነ አዲስ ክስ ለማቅረብ እንደማይችል በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ
ቁጥር 289/1/ በግልጽ ተደንግጓል፡፡ስለዚህም የቀረበዉ አዲስ ክስ ተገቢነት ያለዉ መሆን
አለመሆኑ የሚወሰነዉ ክሱ በፍርድ ቤት ፈቃድ ወይም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ የተቋረጠ
ወይም የተተወ መሆን አለመሆኑ በመመርመር እንደሆነ ያስገነዝበናል፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይዘት መገንዘብ እንደተቻለዉ አመልካች ቀደም
ሲል በዚሁ ጉዳይ በመ/ቁ/ 153563 ላይ ያቀረበዉን ክስ ለመተዉ መፈለጉን ገልጾ ለፍርድ
ቤቱ ባቀረበዉ ማመልከቻ መሰረት መዝገቡ የተዘጋ ስለመሆኑና መዝገቡም የተዘጋዉ
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ 278/1/ መሰረት መሆኑን ያመላክታል፡፡የስር ፍርድ ቤትም ይህንኑ መርምሮ
አመልካች ክሱን የተወዉ ሌላ ጊዜ አዲስ ክስ ለማቅረብ ከፍርድ ቤቱ ፈቃድ አግኝቶ
አለመሆኑንና ያቀረበዉም ማመልካቻ ፈቃድ ለመጠየቅ ሳይሆን ክሱን መቋረጡን ፍርድ ቤቱ
እንዲያዉቀዉ ለማድረግ የቀረበ ስለመሆኑ ይዘቱን ጭምር በመመርመር ያረጋገጠዉ ጉዳይ
ነዉ፡፡አመልካች አሁንም የሚከራከረዉ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ማመልካቻ ፍርድ ቤቱን
ለማሳወቅ ተደርጎ መወሰዱ ስህተት ነዉ የሚል ነዉ፡፡ይሁንና መዝገቡ እንደሚሳየን
አመልካች በቀን 10/04/2011ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ ያቀረበዉ ማመልከቻ ይዘት ‹‹…ክርክሩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እየገፋ በመምጣቱ ከሳሽ አላስፈላጊ ዉጣ ዉረዶችን በመተዉ የጀመርኩትን ክስ ክርክር


በሙሉ ፈቃድ ክሴን ለማቋረጥ …›› በሚል በቃለ መኃላ ተደግፎ የቀረበ አቤቱታ መሆኑን
የሚገልጽ እንጂ በጉዳዩ ላይ ሌላ ጊዜ አዲስ ክስ ለማቀርብ የፍርድ ቤቱን ፈቃድ የጠየቀ
መሆኑን የሚያሣይ አይደለም፡፡ክሱን ለማቋረጥ ያቀረበዉም ምክንያትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ
ቁጥር 278/2/ ስር ከተደነገጉት ምክንያቶች አንዱም ስለመኖሩ የማያሳይ ነዉ፡፡ፍርድ ቤቱ
ማመልከቻዉን መርምሮ የሰጠዉ ትእዛዝ ይዘትም ክሱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/1
መቋረጡን የሚገልጽ እንጂ አዲስ ክስ ለማቅረብ መብት የተጠበቀለት መሆኑን
አያሣይም፡፡የመዝገቡ ይዘት ይህንን የሚያሳይ ሆኖ እያለ አመልካች ፍርድ ቤት ፈቃድ
አግኝቻለዉ በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ መሰረት ያለዉ ሆኖ አላገኝም፡፡ከዚህ አኳያ በተጠሪ
በኩል የቀረበዉን መቃወሚያ መነሻ በማድረግ የስር ፍርድ ቤትም መ/ቁ/153563 ላይ
የተጀመረዉ ክርክሩ የተቋረጠበትን አግባብ መርምሮ ከሳሹ ክሱን በራሱ ፈቃድ የተወዉ
መሆኑን እንጂ በፍርድ ቤት ፈቃድ የተወዉ መሆኑን የሚያሣይ አይደለም የሚል ድምዳሜ
ላይ መድረሱ ስህተት ነዉ የሚባልበት ምክንያት የለም፡፡እንዲህ በሆነ ጊዜ ደግሞ ከሳሽ ወገን
በዚያዉ ጉዳይ ላይ አዲስ ክስ ማቅረብ እንደማይችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 289/1 በግልጽ
ደንግጓል፡፡የስር ፍርድ ብይን መሰረቱም ይኸዉ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡በመሰል ክርክሮች
ላይ ይህ በሰር ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔም ይህንኑ የሚያጠናክር ነዉ፡፡ሰበር መ/ቁ/116869
፣158314 እና ሌሎች መመልከት ይቻላል፡፡

ሲጠቃለል በዚህ ጉዳይ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ትእዛዝ ይህንኑ የሥነስርዓት ህግ ድንጋጌ
እና በተመሳሳይ ክርክሮች ላይ ሰበር ችሎቱ የሰጠዉን ዉሳኔ ያገናዘበ ነዉ ከሚባል በስተቀር
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አልተገኘም፡፡በዚሁ አግባብ
ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ዉሳኔ

1ኛ/የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/236492 ላይ በቀን 29/09/2012ዓ.ም የሰጠዉ


ብይን እና ይህንኑ በማጽናት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
በመ/ቁ/194704 ላይ በቀን 30/04/2013ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/
መሰረት ጽንቷል፡፡ 2ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ
የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

?? /? /? ? ? 202810
? ? 27/3/2014 ? /?

-ዳኞች ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች - ወ/ሮ ደቡብ ገ/ጊዮርጊስ -ቀረቡ


ተጠሪ - አቶ ታደሰ ወልዴ - ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች የካቲት 9 ቀን
2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 247029 ታህሳስ 2 ቀን 2013
ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር180038
ሐምሌ 10 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታዋን በማቅረቧ ነው፡፡ ቅሬታዋም አቤት
የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የምትቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው
ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የምትለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት የመንግስት
ቤት ከጋብቻ በፊት እንደተገኘ የግል ንብረቶች ተቆጥሮ ልትካፈል አይገባም ተብሎ መወሰኑ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡

በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ
የአሁን አመልካች ባቀረበችው ክስ ከተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ጋር የነበረን ጋብቻ በ30/4/2011 ዓ/ም
ፈርሷል፡፡ ከተከሳሽ ጋር በጋብቻ ውስጥ በጋራ ያፈራናቸው ንብረቶች ከ1 እስከ 59 ድረስ የቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እቃዎች ዘርዝራ የጋራ ንብረታችን በመሆኑ ያካፍለኝ 2. መኪና የሰ/ቁጥር 2-42143 የሆነች የጋራ
ንብረታችን በመሆኗ ያካፍለኝ 3. የመንግስት ቤት በሁለታችን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በመሆኑ
ያካፍለኝ ስትል ጠይቃለች፡፡ ተከሳሽም ከሳሽ የጠየቀችው የቤት እቃዎች ከጋብቻ በፊት
ያፈራኋቸው ያለውን ዘርዝሮ የግሌ ነው አለ፡፡ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ውስጥ ያለው የቤት
ቁጥር 603 የሆነው ከሳሽ ከሌሎች ወራሾች ጋር በውርስ ያገኘችው ሲሆን በጋብቻ ውስጥ እያለን
ወጪ አውጥተን እድሳት ያደረግንበት በመሆኑ የወጪውን ግማሽ 25,000 ትክፈለኝ፣ መኪና
የሰ/ቁጥር 2-42143 ከጋብቻ በፊት ያፈራሁት ንብረት ስለሆነ የግሌ ነው፡፡ የመንግስት ቤት
የሆነው የቤት ቁጥር 326 ከጋብቻ በፊት የነበረኝን የቤት ቁጥር 402 በሆነው ምትክ በቅያሪ
የተሰጠኝ በመሆኑ ልትካፈል አይገባም በሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ
ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ቁጥር 180038 ሐምሌ 10 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ
ከሳሽና ተከሳሽ የተማመኑባቸውን የቤት ውስጥ እቃዎች ይካፈሉ፡፡ ቴሌቪዥን፣ ትሪ፣ ውሃ
ማፍያ፣ የቅቤ እቃ፣ ብርድ ልብስ የተከሳሽ የግል ንብረቶች ናቸው፡፡ መኪና የሰ/ቁጥር 2-42143
በተመለከተ የተሰሙት የሰው ምስክሮች ተከሳሽ ከጋብቻ በፊት በስጦታ ያገኘ መሆኑ ቢመሰከርም
ያስመዘገበበትን ቀን ለማወቅ ሊብሬ ያላቀረበ በመሆኑ የተመዘገበው በትዳር ውስጥ መሆኑን
የሚያመለክት በመሆኑ የጋራ ንብረት ነው፡፡ ተከሳሽ ከሳሽ በውርስ ያገኘችው ቤት ላይ ወጪ
አድርጌያለሁ ያለውን በተመለከተ የተሰሙት ምስክሮች የከሳሽ ወንድም ከውጪ ብር ልኮላት
ከሳሽ ያሳደሰችው መሆኑን በተሻለ ሁኔታ ያስረዳች በመሆኑ ለተከሳሽ የምትከፍለው ገንዘብ
የለም፡፡ የመንግስት ቤት በተመለከተ ተከሳሽ ከጋብቻ በፊት የነበረውን የመንግስት ቤት በጋብቻ
ውስጥ የተቀየረለት መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ለከሳሽ ሊያካፍላት አይገባም፡፡ ቀበሌው በቤቱ ላይ
የመወሰን ሥልጣኑን ይህ ውሳኔ አይከለክለውም ሲል ወስኗል፡፡ ከሳሽ ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት
የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ በመ/ቁጥር 247029 ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው
ትእዛዝ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት የተፈጸመበት አይደለም
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኝዋን ውድቅ አድርጎታል፡፡

የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል፡፡ መዝገቡም ተመርምሮ ግራ ቀኙ


በስር ፍ/ቤት በመካከላቸው የነበረው ጋብቻ መፍረስን ተከትሎ በነበረ የንብረት ክፍፍል ለክርክር
ምክንያት የሆነው የመንግስት የቤት ቁጥር 326 በጋብቻ እያሉ ከመንግስት የተከራዩት መሆኑ
በስር ፍ/ቤት በተረጋገጠበት ሁኔታ ቤቱን ተጠሪ ከጋብቻ በፊት ከመንግስት ተከራይቶ በነበረው
የቤት ቁጥር 402 ትክ ነው በሚል እና አመልካች በውርስ ያገኘችው ቤት አለ በሚል ለተጠሪ
እንዲሆን የተወሰነበትን አግባብነት ከቤተሰብ ህጉ ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ቀርቧል፡፡
መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል፡፡ ተጠሪ ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር
ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዳልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል
ተከራክሯል፡፡ አመልካችም ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታዋን
በማጠናከር ተከራክራለች፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና


የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን
የሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ
ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም አሁን ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት
ክርክር ምክንያት የሆነው የመንግስት ቤት የሆነ የቤት ቁጥር 326 በተመለከተ ሲሆን የአሁን
ተጠሪ ይህ ቤት ቀድሞ ከጋብቻ በፊት የቤት ቁጥር 402 ከመንግስት ተከራይቼ በነበረው ትክ
የተቀየረልኝ በመሆኑ በጋብቻ ውስጥ የተከራየሁት ባለመሆኑ የአሁን አመልካች ልትካፈል
አይገባም የሚል ክርክር ያቀረበ ሲሆን የአሁን አመልካች ደግሞ ቤቱ የመንግስት ቤት በመሆኑ
እና ይህ የቤት ቁጥር 326 በጋብቻ ውስጥ እየለን ከመንግስት የተከራየን በመሆኑ እንደ የግል
ንብረት ከጋብቻ በፊት የተከራየሁት ነው በሚል ልትካፈል አይገባም መባሉ ተገቢ አይደለም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚል ክርክር አላት፡፡ የመንግስት ቤት በተመለከተ የመኖሪያ ቤት ችግር ያለባቸው ሰዎች


በኪራይ የሚሰጥ ሲሆን አሁን አመልካችንና ተጠሪን ያከራከረው የመንግስት ቤት በትዳር አብረው
በቆዩበት ጊዜ በጋራ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡ የአሁን አመልካችም ሆነ ተጠሪ የራሳቸው የሆነ
መኖሪያ ቤት የሌላቸው ነው፡፡ ግራ ቀኙን ያከራከረው ቤት የመንግስት ቤት እንደመሆኑ
ተከራዮች በቤቱ በኪራይ የመጠቀም መብት ነው ያላቸው፡፡ የአሁን አመልካችና ተጠሪ ከተጋቡ
በኋላ በኪራይ አብረው ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡ በዚህ የመንግስት ቤት ሁለቱም የቤት ችግር
ያለባቸው እና የራሳቸው ቤት የሌላቸው አብረው ሲጠቀሙበት የቆዩትን ቤት እንደ ግል ንብረት
ታይቶ ከጋብቻ በፊት ተከራይቶ የነበረው ቤት በትዳር ውስጥ ተለውጦለት ነው በሚል አንዱን
ወገን ከቤቱ በማስወጣት የሚሰጥ ውሳኔ ፍትሐዊ ውሳኔ ሆኖ አይገኝም፡፡ የአሁን ተጠሪም ቢሆን
የመንግስት ቤቱን ተከራይ የሆነና የቤት ስለነበረበት በኪራይ የሚኖርበት ሲሆንየአሁን
አመልካችም በተመሳሳይ የቤት ችግር ያለባት በመሆኑ ሁለቱም በቤቱ ተጠቃሚነታቸው በተጠበቀ
ሁኔታ በቤቱ መጠቀም እንዲችሉ ሊካፈላቸው ሲገባ የአሁን አመልካች ከቤቱ አንዳትካፈል
መወሰኑ ካለአግባብ የተሰጠ ውሳኔ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ የኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ 41(3)
የኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ በመንግስት ገንዘብ በሚካሄዱ ማህበራዊ አግልግሎቶች በእኩልነት
የመጠቀም መብት እንዳላቸው ተደንግጎ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የኢፌዴሪ ህግ መንግስት አንቀጽ
35(2) ሴቶች በዚህ ሕገ መንግስት በተደነገገው መሰረት በጋብቻ ከወንዶች ጋር እኩል መብት
አላቸው ሲል ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ግራ ቀኙን ያከራከረውን የመንግስት ቤት የአሁን
አመልካችና ተጠሪ ተመሳሳይ የቤት ችግር ያላቸው ሆኖ እያለና በዚህ ቤት ሁለቱም በጋራ
ለረጅም ጊዜ ሲጠቀሙበት የቆዩ መሆኑ እየታወቀ የሁለቱንም መብት በሚጠቅም መልኩ
አንዲካፈሉ መወሰን ሲገባ አመልካች ቤቱን ለቃ አንዲትወጣ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 247029 ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት
የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር180038 ሐምሌ 10 ቀን
2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሏል፡፡
2. የመንግስት ቤት የሆነው የቤት ቁጥር 326 አመልካችና ተጠሪ ተካፍሎላቸው በኪራይ
አንዲኖሩበት ብለናል፡፡
3. በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
4. የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል፡፡
5. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁጥር 202839

ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ አቶ ሰለሞን አሰፋ- አልቀረቡም

ተጠሪዎች ፡ ቡና ኢንሹራንስ አክስዮን ማህበር -ነ/ፈጅ ቁምነገር ካሣሁን -ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የስራ ውል ከተቋረጠ በኋላ የተወሰነ የቦነስ ክፍያ ይከፈለኝ በሚል የቀረበ የአሰሪ እና ሰራተኛ ክርክርን
የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ
ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካች ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በስራ አስፈጻሚነት ስሰራ
ቆይቼ የ2010 በጀት አመት ከተጠናቀቀ በኋላ የስራ ውሌን አቋርጫለሁ፡፡ ተጠሪ የ2009 እና የ2010 ዓ.ም.

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቦነስ የሁለት ወር ደመወዝ ለሰራተኞቹ ከፍሏል፡፡ እኔም ለተገኘው ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስለነበረኝ
የሁለት ወር ደመወዜን ብር 38,992 ተጠሪ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪም መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ ነሐሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ተጠሪ የሰራተኞች
ቦነስ እና አመታዊ የደመወዝ ጭማሪ አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል፡፡ በዚህ መመሪያ ላይ የቦነስ ክፍያ
የሚፈጸመው በስራ ላይ የሚገኙ ሰራተኞችን ይዞ ለማቆየት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የተጠሪ ቦርድም ነሐሴ
21 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ቦነስ ከስራ ለለቀቀ ሰራተኛ እንደማይከፈል በቃለ ጉባኤ ወስኗል፡፡
በመሆኑም አመልካች የቦነስ ክፍያው በሚፈጸምበት ጊዜ ከስራ የለቀቁ በመሆኑ የቦነስ ክፍያው አይገባቸውም
በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ተጠሪ ቦነስን በተመለከተ አለ
የሚለው መመሪያ በዳይሬክተሮች ቦርድ የጸደቀ ባለመሆኑ ተፈጻሚነት የለውም፡፡ በቦርድ አባላት በቃለ ጉባኤ
የተወሰነውም ከስራ የለቀቁ ሰራተኞች ቦነስ እንደማይከፈላቸው በግልጽ የሚያመለክት አይደለም፡፡
በመሆኑም ለአመልካች ቦነስ እንዳይከፈል በግልጽ የሚከለክል ህግ ስለሌለ ለአመልካች ብር 38,992 ከወለድ፣
ወጪ እና ኪሳራ ጋር ይከፈላቸው በማለት ወስኗል፡፡ ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የተጠሪ ቦርድ የስራ ውሉ የተቋረጠ ሰራተኛ ቦነስ
እንደማይከፈለው ወስኗል፡፡ የስር ፍርድ ቤት አጠቃላይ የቃለ ጉባኤውን ይዘት ሳይመለከት ቃለ ጉባኤው
ለአመልካች ተፈጻሚ አይሆንም ማለቱ ተገቢ አይደለም፡፡ በመሆኑም የአመልካች የስራ ውል ቦነስ ከመከፈሉ
በፊት ስለተቋረጠ የተጠሪ ቦርድ በቃለ ጉባኤ በወሰነው መሰረት የቦነስ ክፍያ አይገባቸውም በማለት የስር
ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሯል፡፡

አመልካች በየካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረቡት ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ሲሆን ይዘቱም የተጠሪ ቦርድ ከስራ ለለቀቀ ሰራተኛ ቦነስ ሊከፈለው
አይገባም በሚል የውሳኔ ሀሳብ ቀርቦለት የተወያየ ቢሆንም በቃለ ጉባኤው የውሳኔ ኃሳቡን አላጸደቀውም፡፡
ስለዚህ ቃለ ጉባኤው እንዳይከፈለኝ ስለማይከለክል የይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይታረምልኝ
የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ አመልካች ስራ የለቀቁት ቦነስ ከመከፈሉ በፊት
ነው በሚል ሊከፈላቸው አይገባም የተባለበትን አግባብ የዳይሬክተሮች ቦርድ በነሀሴ 12 ቀን 2010 ዓ.ም.
በቃለ ጉባኤ ከወሰነው አንጻር ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተጠሪ በሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ የተጠሪ ቦርድ ነሐሴ 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በቃለ
ጉባኤ ከስራ የለቀቀ ሰራተኛ ቦነስ እንደማይከፈለው ወስኗል፡፡ አመልካች በራሳቸው ፍቃድ ከስራ ለቀው እያለ
ቦነስ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸው ከቦነስ ክፍያ አላማ እና መንፈስ ውጪ ነው፡፡ ስለዚህ በይግባኝ ሰሚው
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካችም በጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታቸውን
አጠናክረዋል፡፡

የክርከሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ
አንጻር በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ተገቢነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምረናል፡፡

አመልካች የጠየቁትን የቦነስ ክፍያ ተጠሪ ልከፍል አይገባም በማለት የሚከራከረው የተጠሪ ቦርድ ነሐሴ 12
ቀን 2010 ዓ.ም. በቃለ ጉባኤ ከስራ የለቀቀ ሰራተኛ ቦነስ እንደማይከፈለው ወስኗል፡፡ አመልካችም የቦነስ
ክፍያ ተወስኖ ከመፈጸሙ በፊት ከስራ ለቀዋል በሚል ነው፡፡ አመልካችም የቦነስ ክፍያው እንዲከፈል በተጠሪ
የተወሰነው የስራ ውላቸው ከተቋረጠ በኋላ መሆኑን ክደው ያልተከራከሩ ሲሆን አጥብቀው የሚከራከሩት
ተጠሪ የሚጠቅሰው ቃለ ጉባኤ ቦነስ እንዳይከፈለኝ የሚከለክል አይደለም በሚል ነው፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ
የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ የተገለጸው ቃለ ጉባኤ የስራ ውሉ ለተቋረጠ
ሰራተኛ ለሰራበት ጊዜ የተከፈለ ቦነስ እንዳይከፈል የሚከለክል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡፡
በተቃራኒው ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተጠቀሰው ቃለ ጉባኤ አጠቃላይ
ይዘት ሲታይ ከስራ የለቀቀ ሰራተኛ ቦነስ እንደማይከፈለው መወሰኑን ያመለክታል የሚል መደምደሚያ ላይ
ደርሷል፡፡ ስለዚህ ዋናው በዚህ ሰበር ችሎት እልባት ማግኘት ያለበት ጉዳይ ነሐሴ 12 ቀን 2010 ዓ.ም.
የተጠሪ ቦርድ በቃለ ጉባኤ ከስራ የለቀቀ ሰራተኛ ቦነስ እንደማይከፈለው ወስኗል ወይስ አልወሰነም? የሚለው
ነው፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት የተጠቀሰውን ቃለ ጉባኤ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ያደረገ በመሆኑ እኛም ቃለ
ጉባኤውን ተመልክተናል፡፡ እንደተመለከትነው በቃለ ጉባኤው 3ኛ ገጽ ውሳኔ ከሚለው አርእስት ከፍ ብሎ
እስከ በጀት አመቱ መጨረሻ ያገለገሉ ሰራተኞች ቦነስ ለምን ይከለከላሉ የሚል ሀሳብ ተነስቶ የቦነስ አላማ
በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞችን ለማበረታታት ስለሆነ በስራ ላይ ለሌሉ ሰራተኞች ቦነስ መክፈል ጥቅም የለውም
በሚል ቦነሱ እስከሚከፈልበት ድረስ ከስራ የለቀቁ ሰራተኞች ቦነስ እንደማይከፈላቸው መወሰኑን
ተገንዝበናል፡፡ በእርግጥ በቃለ ጉባኤው ውሳኔ በሚል አርእስት ስር ከተጠቀሱ ውሳኔዎች ውስጥ ቦነስን
የሚመለከት ውሳኔ የለም፡፡ ይህ ማለት ግን ውሳኔ ተብሎ አርእስት ባይሰጠውም ወይም ውሳኔ ከሚለው
አርእስት በላይ ባለው የቃለ ጉባኤው ክፍል ቦነስን የሚመለከት ውሳኔ ከተቀመጠ ተፈጻሚነት አይኖረውም
ወይም እንደተወሰነ ሊቆጠር አይገባም ማለት አይቻልም፡፡ በመሆኑም የቃለ ጉባኤው አጠቃላይ ይዘት ሲታይ
በስራ ላይ ለሌለ ሰራተኛ ቦነስ እንደማይከፈለው የተወሰነ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ በመሆኑ ይግባኝ
ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ቃለ ጉባኤው የቦነስ ክፍያን አይመለከትም በሚል የደረሰበትን
መደምደሚያ ማረሙ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ቦነስ ከአሠሪዉ ለሠራተኛዉ በጉርሻ መልክ የሚከፈል ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ
53(2/ሐ) ላይ ተመልክቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ አከፋፈሉ የሚመራዉ በአሠሪዉ በሚዘረጋዉ ሥርዓትና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ደንብ ሲሆን አሠሪዉ ለዚህ ዓላማ በሚያወጣዉ ደንብ/መመሪያ የቦነስ ክፍያ የሚፈጸምበትን ቅድመ ሁኔታ
እንዲሁም የክፍያዉ አፈፃፀም በሠራተኛዉ ላይ የሚያስከትለዉን ልዩ ግዴታ ጭምር ያካተተ ሊሆን
ይችላል፡፡ በህብረት ስምምነት በሌላ አኳኋን ካልተመለከተ በስተቀር የቦነስ ክፍያ በአሠሪዉ መልካም ፊቃድ
የሚፈጸም እንጂ በአሠሪዉ ላይ በህግ የተጣለ የክፍያ ግዴታ ባለመሆኑ የክፍያዉን አፈፃፀም እንዲሁም
የሚያስከትለዉንም ህጋዊ ዉጤት አስመልክቶ በዚህ መልኩ አሠሪዉ የሚያወጣዉ ደንብ/መመሪያ/የቃለ
ጉባኤ ውሳኔ ወይም ከሠራተኛዉ ጋር የሚደረግ ስምምነት ካለ ህጋዊ ዉጤት ተሰጥቶት እንደየአግባብነቱ
ተግባራዊ ሊደረግ የሚገባዉ እንጂ እንደ ሌሎች የሠራተኞች መሠረታዊ መብቶች በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ
ላይ ከተመለከቱት ዝቅተኛ መስፈርቶች (minimum standards) አንፃር ታይቶ ዉጤት እንዲኖረው ሊደረግ
የሚችልበት አግባብ የለም፡፡

ሲጠቃለል አመልካች የቦነስ ክፍያ የጠየቁት በስራ ላይ ለነበሩበት ጊዜ የተከፈለውን ቢሆንም የቦነስ ክፍያው
በተጠሪ ተወስኖ ተፈጻሚ የተደረገው አመልካች ከስራ ከለቀቁ በኋላ በመሆኑ እና ከስራ የለቀቀ ሰራተኞ ቦነስ
እንደማይከፈለው የተጠሪ ቦርድ በቃለ ጉባኤ የወሰነ በመሆኑ ለአመልካች የቦነስ ክፍያው ሊከፈላቸው
አይችልም፡፡ በመሆኑም ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት ለአመልካች እንዲከፈል
የወሰነውን የቦነስ ክፍያ በመሻሩ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሌለ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1ኛ. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 243556 በህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል፡፡

2ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

ማ/አ

የማይነበብ የአምስት ደኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰ/መ/ቁ፡-202872

ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ- ነ/ፈ እሸቱ ወርቅነህ ቀረቡ

ተጠሪ ፡ ወ/ሮ ሰብለ ሙሉነህ- ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል አዳማ
ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን
ተከራክረዋል፡፡

ከመዝገቡ እንደሚታየዉ የተጠሪ ክስ የሚለዉ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ


አገልግሎት ሀላፊ ሆኜ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 15,304 እየተከፈለኝ እየሰራሁ እያለ
በህገ ወጥ መንገድ በቀን 15/11/2011 ዓ.ም ከስራ ያሰናበተኝ ስለሆነ ወደ ስራዬን እንዲመልሰኝ
ወይም በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት ክፍያዎች እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀች
ሲሆን አመልካች በበኩሉ ተጠሪ ደንበኞች ያላመጡትን ሂሳብ እንዳመጡ በማድረግ የሌላቸውን
የሂሳብ ሚዛን ወይም ቀሪ ሂሳብ በመፃፍ የማይገባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ
አድርጋለች፣እንዲሁም ይህንን የድርጅት ሰነድ አስመስላ በመስራት የወንጀል ድርጊት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፈጽማለች፣በአጠቃላይ ወደ ባንኩ የመጣ ገንዘብ እና ከባንኩ የወጣ ገንዘብ በሌለበት በአየር ላይ


የገቢና የወጪ ገንዘብ እንዳላቸው በማስመሰል ጽፋላቸዋለች፡፡ስለዚህ ባንኩ ማግኘት ያለበት
ጥቅም ለሶስተኛ ወገን ጥቅም እንዲውል አድርጋለች፣ይህ ደግሞ በአዋጅ ቁ/1156/2011 አንቀጽ
27/1/መ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል እንዲቋረጥ የሚያደርግ ጥፋት በመሆኑ ተጠሪ
የተሰናበተችዉ በህጋዊ መንገድ በመሆኑ የካሳ፣ የአገልግሎት፣ የማስጠንቀቂያ እና ሌሎች
ክፍያዎች አይከፈላትም፣ ሌሎች በአንቀጽ 36 እና 38 የተጠየቀው ክፍያ ክሊራንስ ካጠናቀቀች
በኋላ የሚከፈል ክፍያ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ ገንዘብ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው


በሂሳብ ቁጥር እና በጥሬ ገንዘብ ስታስተላልፍ በባንኩ ውስጥ ያለው ገንዘብ እንዳልጎደለ
ኦዲተሩ ገልፅዋል፣የግራ ቀኝ ማስረጃም አረጋግጧል፣ገንዘብ ወዲህ ወዲያ በመተላለፉ ምክንያት
ሃላፊው ለግለሰብ ደብዳቤ ጽፏል ለተባለው ተጠሪ ደብዳቤ ለመፃፍ ስልጣን እንደሌላት
ተረጋግጧል፡፡ስለዚህ አመልካች ያለጥፋት ተጠሪን ከስራ በህገ ወጥ መንገድ አሰናብቷል
በማለት ወደ ስራዋ እንዲመልሳት ወይም ወደ ስራ የማይመልሳት ከሆነ ደግሞ ውዝፍ
ደመወዝ፣የአገልግሎት ክፍያ፣የ2011ዓ.ም ቦነስ፣ የ33 ቀናት የዓመት እረፍት፣ የማስጠንቀቂያ
ጊዜ ክፍያ፣ የካሳ ክፍያ፣ክፍያ ለዘገየበት እና ካዝና መጠባበቂያ ገንዘብ በድምሩ ብር
461,346.09 እንዲከፈላት በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለአዳማ ከተማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ
ሲሆን ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ አመልካች ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች
ኦዲት አድርገው ያገኙት ውጤት ተጠሪ ገቢ ያልሆነ ገንዘብ በአየር ላይ ገቢ እንደሆነ ጽፋ
በደንበኛ ሂሳብ ላይ እንዲታይ ካደረገች በኋላ ወደ ሌላ ደንበኛ ስም እንዲዛወር ያደረገች
መሆኑና ተጠሪ ይህንንም ያደረገችዉ በሃላፊዋ በተመራው መሰረት መሆኑ የተገለጸ ቢሆንም
ከድርጅቱ ደንብና መመሪያ ዉጪ በመሆኑ ሃላፊነት የሚያስከትል መሆኑን፤የአመልካች ስራ
የንግድ ስራ ከመሆኑ አንፃር ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግና መልካም ስም ለማትረፍ በደንበኞች
ዘንድ ታማኝ ሆኖ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ትልቁ አላማ ሆኖ እያለ ተጠሪ የአሰሪና ሰራተኛ
ህግና የመ/ቤቱ ደንብ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የፈፀመች መሆኑ ስለተረጋገጠ በአዋጅ
ቁ/1156/2011 አንቀጽ 27(1)መ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለመሰናበት በቂ ምክንያት
ነው፣ ስለዚህ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር ሌሎች ከፍያዎች ውድቅ
በማድረግ የተጠራቀመ ፕሮቪደንት ብር 130,000.00 የመጠባበቂያ ገንዘብ ብር 36,507.47፣
ያልተጠቀመችበት የአመት እረፍት የ13.36 ቀን ብር 6,815.38 በአጠቃላይ ብር 173,322.85

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለተጠሪ እንዲከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡አመልካች በክፍያ ረገድ ዉሳኔዉ መሰረታዊ የህግ
ስህተት አለበት በማለት ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበው አቤቱታ
ተቀባይነት አላገኘም፡፡ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ፡፡

የአመልካች አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤የተጠራቀመው ጠቅላላ የፕሮቪደንት ፈንድ ድምር ብር


121,203.35 ሆኖ እያለ ተጠሪዋ የጠየቀችውን ብር 130,000.00 እንዲከፈል መወሰኑ ስህተት
በመሆኑ ሊስተካከል ይገባል፣በተጨማሪም ሰበር ችሎት በመ/ቁ102994 በሆነ ፋይል ላይ
እንደወሰነዉ በስነ-ምግባር ምክንያት ከስራ ለተሰናበተ ሰራተኛ የሚከፈል ፕሮቪደንት ፈንድ
ክፍያ ሰራተኛዉ ራሱ ያዋጣው ገንዘብ ብቻ በመሆኑ የተጠሪ መዋጮ ብር 30,300.84 ሲሆን
ይህ ገንዘብ ደግሞ ስለተከፈላት በዚህ ረገድ የሚከፈላት ክፍያ የለም ተብሎ
እንዲስተካከል፣የአመት እረፍት በተመለከተ የ33.36 ቀናት ክፍያ የተከፈላትና በፍ/ቤት ትዕዛዝ
የቀረበው ማስረጃ 20 ቀናት የአመት እረፍት በብልጫ እንደወሰደች ተረጋግጦ እያለ የ20
ቀናት ብቻ እንደተከፈለ በማየት ልዩነቱ የ13.36 ቀናት እንደገና እንዲከፈል የሰጠው ውሳኔ
ስህተት በመሆኑ እንዲታረምልን፣የተከፈለው ብር 30,300.84 የፕሮቪደንት ፈንድ እንጂ የቦነስ
ክፍያ አይደለም፣ተጠሪ ባጠፋችው ጥፋት ከተሰናበተች በኋላ ስለተፈቀደው ቦነስ ሊከፈላት
አይገባም ተብሎ እንዲታረም በማለት አመልክቷል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ አመልካች የአመት ዕረፍት ክፍያ
የተከፈላት ስለሆነ በድጋሚ ሊከፈላት አይገባም እያለ ይህ ሳያጣራ በድጋሚ ይከፈል ተብሎ
የተወሰነበት አግባብነት ለማጣራት ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት
ታዟል፡፡

ተጠሪ ባቀረቡት መልስ የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ በተመለከተ የሚጠራቀመው ለሰራተኛ


ጥቅም ሲሆን መከፈል ያለበት መሆኑ በስር ፍ/ቤት በማስረጃ ተረጋግጦ የተወሰነ መሆኑን፣ሰበር
ችሎቱ የህግ ስህተት ማረም እንጂ የማስረጃ ምዘና ስልጣን እንደሌለዉ፣የአመት እረፍት
በተመለከተ ያልተከፈለኝ የ33 ቀን ነው ብዬ ክስ ያቀረብኩ ሲሆን ፍ/ቤቱ ከማህደር ጭምር
በማጣራት ቀሪ የ13.36 ቀን ያልተጠቀምኩበት የአመት እረፍት እንዳለኝ አጣርቶ እና
አረጋግጦ ውሳኔ የሰጠበት ጭብጥ በመሆኑ የተፈፀመ ስህተት የለም፤ቦነስ ክፍያም ለሁሉም
ሰራተኞች ተከፍሎ ለእኔ የሚከለከልበት ምክንያት የለም፤አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ በማለት
ተከራክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
የቀረበዉን አቤቱታ መሰረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች
ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ የስራ ዉሉ የተቋረጠዉ
በተጠሪ ጥፋት ስለመሆኑ ይግባኝ ሰሚ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ በይግባኝ የተለወጠ
ስለመሆኑ የቀረበ ክርክር የለም፡፡ስለዚሀም ስንብቱ ህጋዊ ነዉ የተባለዉ ተጠሪ በስራ ላይ
የፈጸመችዉን ጥፋት መሰረት በማድረግ መሆኑን መዝገቡ ያሣያል፡አሁን እያከራከረ ያለዉ
ስንብቱ ህጋዊ ነዉ መባሉን ተከትሎ የተወሰነዉ ክፍያ አግባብነት ያለዉ መሆን አለመሆኑ ላይ
ነዉ፡፡

የስራ ዉል ሲቋረጥ ለሰራተኛዉ የሚከፈሉት ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንደነገሩ ሁኔታ ማለትም


የስራ ዉሉ እንደተቋረጠበት ምክንያት የሚለያይ መሆኑን ከአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ
ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡በመሰረታዊነት የሚታየዉ ዉሉ የተቋረጠበት አግባብና
ህጋዊ ዉጤቱን በመመርመር ነዉ፡፡የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ
36፣39፣42 እና 43 ድንጋጌዎች እንደሚያስገነዝቡን የስራ ዉሉ ሲቋረጥ ለሰራተኛዉ
የሚከፈለዉ ክፍያ ዓይነት እና መጠን የሚወሰነዉ በዋነኛነት በአዋጁ በተመለከቱት ሁኔታዎች
ሲሆን በተጨማሪነት በህብረት ስምምነት ወይም በድርጅቱ የሥራ ደንብ እንደሁም የስራ ዉሉ
የሚያስገኝለትን መብትና ጥቅም ካለ ይህንኑ በማገናዘብ ነዉ፡፡በተያዘዉ ጉዳይ በስር ፍርድ
ቤት እንደተረጋገጠዉ የስራ ዉል የተቋረጠዉ ተጠሪ በስራ ላይ በፈጸመችዉ ጥፋት በመሆኑ
ስንብቱ ህጋዊ ነዉ ስለተባለ ዉጤቱም ከዚህ አኳያ የሚወሰን ነዉ፡፡እንዲህ በሆነ ጊዜ
ለሰራተኛዉ የሚከፈል ክፍያ እንደነገሩ ሁኔታ ስራ ላይ እያለ ያልተከፈለ
ደመወዝ፣ያልተጠቀመበት የዓመት እረፍት እና በድርጅቱ ህብረት ስምምነት ወይም የስራ
ደንብ ወይም የሥራ ዉል የተፈቀዱ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች መኖራቸዉ ሲረጋገጥ በዚሁ
አግባብ የሚፈጸም ስለመሆኑ ከአዋጁ አንቀጽ 4/5/፣ 36፣ 77/4/ እና 135 ድንጋጌዎች ይዘት
መገንዘብ ይቻላል፡፡በዚህም ጉዳይ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ለተጠሪ የወሰነዉ ክፍያ
ያልተጠቀመችበት የዓመት እረፍት የ13.36 ቀን፣ የተጠራቀመ ፕሮቪደንት ፈንድ እና የካዝና
መጠባበቂያ የሚሉት ናቸዉ፡፡ቦነስን በሚመለከት የ2011ዓ.ም ብር 30,300.84 የተከፈላት
መሆኑ ተረጋግጧል በሚል የሥር ፍርድ ቤት ዉሳኔ መሻሩን የዉሳኔዉ ይዘት
ያሣያል፡፡አመልካች አሁንም እነዚህ ክፍያዎች በዓይነትም በመጠንምተገቢ አይደሉም በማለት
ተከራክሯል፡፡በዋናነት የዓመት እረፍት፣የፕሮቭደንት ፈንድ እና የቦነስ ክፍያ ላይ ያቀረበዉን
አቤቱታ በቅደም ተከተል መርምረናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመጀመሪያዉ የዓመት እረፍት ክፍያ የሚመለከት ነዉ፡፡በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ/1156/11


አንቀጽ 77/5/ እንደተደነገገዉ የሥራ ዉሉ በሚቋረጥበት ጊዜ ሰራተኛዉ ያልተቀመበት
የኣመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተለዉጦ እንደሚከፈለዉ ተመልክቷል፡፡ተጠሪም
ያልተጠቀመችበት 33.36 ቀናት የዓመት ወደ ገንዘብ ተለዉጦ እንዲከፈላት ዳኝነት መጠየቋን
መዝገቡ ያሣያል፡፡ በዚህ ረገድ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የ13.36 ቀናት ብቻ የወሰነላት
ቢሆንም አመልካች ይህ ገንዘብ ከደመወዝ ጋር የተከፋላት መሆኑንና የ20 ቀናት በእላፊ
መዉሰዷን አስመልከቶ ያቀረበዉ ክርክር ሳይመረመር የ13.36 ቀናት እንዲንከፍል መወሰኑ
ስህተት ነዉ የሚል አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ተጠሪ በበኩሏ ፍርድ ቤቱ በማስረጃ አጣርቶ ዉሳኔ
መስጠቱን ገልጻ ተከራክራለች፡፡ከክርክሩ እንደሚታየዉ ተጠሪ ያልተጠቀመችበት የኣመት
እረፍት ምን ያህል ነዉ? ለዚህ የተከፈለ ገንዘብ አለ ወይስ የለም? የሚለዉ የፍሬነገር ክርክር
ጉዳይ ነዉ፡፡ከዚህ አኳያ ፍሬነገር የመመርመርና በማስረጃ የማጣራትና የመመዘን ስልጣን
ያለዉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የተጠሪን ማህደር ጭምር በማስቀረብ ያልተጠቀመችበት
የዓመት እረፍት 13.36 ቀን ብቻ መሆኑን አረጋግጧል፡፡በዚህም ልክ ወደ ገንዘብ ተለዉጦ ብር
6,815.38 እንዲከፈላት መወሰኑን ተገንዝበናል፡፡ይህንን ፍሬነገር ክርክር ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት
አጣርቶ ዉሳኔ የሰጠበት መሆኑን ዉሳኔዉ ይዘት በግልጽ ያሣያል፡፡ሰበር ችሎቱ የማስረጃ
ምዘና ጉዳይ የመመርመር ስልጣን የለዉም፡፡በእርግጥ በማስረጃ አቀባበል እና ምዘና ረገድ
ቅቡልነት ያላቸዉ መርሆዎች ጥሰት ሲኖር ይህንኑ የማረም ጉዳይ ይመለከቷል፡፡በዚህ ጉዳይ
ግን የስር ፍርድ ቤት የተጠሪን የግል ማህደር ጭምር በማስቀረብ ያልተጠቀመችበት 13.36
ቀን የዓመት እረፍት እንዳላት ከድምዳሜ የደረሰ መሆኑን ስለተገነዝብን በዉሳኔዉ ላይ
የማስረጃ አቀባበል ወይም ምዘና መርህ ጥሰት ተፈጽሞበታል የሚባልበት ምክንያት
አላገኘንም፡፡

ቀጥሎ መታየት ያለበት ጉዳይ የፕሮቪደንት ፈንድ ክፍያ ነዉ፡፡ለተጠሪ የፕሮቭደንት ፈንድ
ክፍያ መብት አመልካች ለሰራተኞች ያደረገዉ የጥቅማ ጥቅም ባኬጅ የዘረጋዉ ስርዓት
ስለመሆኑ በአመልካችም የታመነ ጉዳይ ነዉ፡፡ይሁንና የስራ ዉሉ የተቋረጠዉ በተጠሪ ጥፋት
ስለሆነ ሊከፈል የሚገባዉ ሰራተኛዉ ያጠራቀመዉ ፕሮቭደንት ገንዘብ መጠን ብቻ ነዉ
በማለት የጥቅማ ጥቅም ፓኬጁን እና ሰበር ችሎቱ በመ/ቁ/102994 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ ድጋፍ
በማድረግ ተከራክሯል፡፡በመሰረቱ የሥራ ዉሉ በሰራተኛዉ ጥፋት ሲቋረጥ አሰሪዉ የሚከፍለዉ
የፕሮቪደንት ፈንድ መጠን አመልካች እንደሚለዉ ሰራተኛዉ ያጠራቀመዉ ብቻ ነዉ ወይሥ
ከሁለቱም ወገን የተሰበሰበዉ ነዉ?የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ የጥቅማ ጥቅም ፓኬጁን ይዘት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመመርመር ነዉ፡፡በዚህ ረገድ የክፍያዉ መጠን አስመልከቶ የቀረበዉን ክርክር ፍርድ ቤቱ


ከጥቅማ ጥቅም ፓኬጁ ይዘት አንጻር ስለመመርመሩ መዝገቡ አያሣይም፡፡ስለዚህም የሥራ
ዉሉ በተጠሪ ጥፋት መቋረጡ ከግምት ዉስጥ ገብቶ በፕሮቭደንት ፈንድ ክፍያ መጠን ላይ
የሚኖረዉ ዉጤት ምንድነዉ? የሚለዉ ጭብጥ መጣራት ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡በዚህ ረገድ
የቀረበዉ ክርክር ተገቢነት ያለዉ መሆን አለመሆኑ ሳይጣራ መታለፉ የክርክር አመራር
ጉድለት ያለበት መሆኑን ያሣያል፡፡ይህ ጉዳይ ሳይጣራ ደግሞ ድምዳሜዉ ተገቢ ነዉ ወይም
አይደለም ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘንም፡፡ስለዚህም ፕሮቭደንት ፈንድ ክፍያን በተመለከተ
ለተጠሪ ሊከፈል የሚገባዉ የገንዘብ መጠን ከሁለቱም ወገን የተሰበሰበዉ ገንዘብ ባጠቃላይ ነዉ
ወይስ ከተጠሪ ደመወዝ ተቀንሶ የተጠራቀመዉ ብቻ ነዉ? መጠኑስ ምን ያህል ነዉ? የሚለዉ
በስር ፍርድ ቤት ክርክር ተደርጎ በማስረጃ ተጣርቶ ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡

የመጨረሻዉ የቦነስ ክፍያ የሚመለከት ነዉ፡፡ከክርክሩ እንደተገነዘብነዉ ተጠሪ ሥራ ላይ


በነበረችበት 2011.ዓ.ም ድርጅቱ ሌሎች ሰራተኞች ቦነስ ስለከፈለ ድርሻዋ እንዲከፈላት
የጠየቀች ሲሆን የሥር ፍርድ ቤትም ቦነስ እንዲከፈላት ወስኗል፡፡በዚህ ላይ በአመልካች በኩል
የቀረበዉ ክርክር ቦነስ እንዲከፈል የተደረገዉ ባንኩ ባለዉ የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ
መሰረት ስለመሆኑና በባንኩ ቦርድ ዉሳኔ መሰረት ቦነስ ከመከፈሉ በፊት ስራ የለቀቀ ሰራተኛ
ቦነስ የማግኘት መብት የለዉም የሚለዉን የስር ፍርድ ቤት አልመረመረም የሚል
ነዉ፡፡በእርግጥ ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ቦነስ አይገባትም ወይም ይገባታል የሚል ጭብጥ
ሳይመረምር ቦነስ ብር 30, 30,300.84 ለተጠሪ ተከፍሏል በሚል የወሰነ ቢሆንም የአመልካች
አቤቱታ እንደሚያሣን ይህ ገንዘብ ቦነስ ሳይሆን ተጠሪ ያጠራቀመችዉ የፕሮቭደንት ፈንድ
ነዉ ይላል፡፡በዚህ ረገድ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ስርዓቱን ጠብቆ የሚታረም መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆነ ቦነስ ለተጠሪ ሊከፈል ይገባል ወይስ አይገባም የሚለዉ ነጥብ ከጥቅማ ጥቅም
ከፓኬጁ አንጻር መታየት አለበት፡፡

ከላይ እንደተገለጸዉ የቦነስ ክፍያ መሰረቱ በድርጅቱ የጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ ለሰራተኛዉ
የተፈቀደ ጥቅም ስለሆነ አከፋፈሉን በሚመለከት በፓኬጁ የተመለከተ ሁኔታ ካለ ክርክሩ ከዚህ
አኳያ ተመርምሮ ዉሳኔ ሊሰጥበት ይገባል ማለት ነዉ፡፡ይህ ሰበር ችሎት ከዚህ ቀደም
በተመሳሳይ ጉዳዮች በሰጠዉ ዉሳኔ እንዳመለካተዉ የቦነስ ክፍያ ዓላማ ሰራተኛዉን ይበልጥ
ለማትጋትና ምርታማነቱን ለማሳደግ በመሆኑ ቦነስ ክፍያ ሳይቀበል ስራ የለቀቀ ሰራተኛ
የመብቱ ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ አከራካሪ ከሆነ ከዉሉ አንጻር መታየት የሚገባዉ
እንደሆነ ያስገነዝባል፡፡ስለሆነም ለተጠሪ የ2011ዓ.ም የቦነስ ክፍያ የሚገባት መሆን አለመሆኑን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለመወሰን የድርጅቱን የጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ እና የቦርዱን ዉሳኔ ይዘት መመርመር


ነበረበት፡፡ፍርድ ቤቱ ክርክሩን ከዚህ አንጻር ሳይመረምር ማለፉ ስነስርዓታዊ ባለመሆኑ
ሊታረም ይገባል ብለናል፡

ሲጠቃለል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ክርክሩን መርምሮ የስራ ዉሉ የተቋረጠዉ በተጠሪ ጥፋት


ነዉ በሚል ስንብቱ ህጋዊ ነዉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ ከፍል ላይ ቅሬታ የቀረበበት
አይደለም፡፡ሆኖም ክፍያን አስመልክቶ የፕሮቭደንት ፈንድ አከፋፈልና መጠኑን እንዲሁም
የቦነስ ክፍያ አይገባትም በማለት አመልካች ያቀረባቸዉ መከራከሪያ ነጥቦች በአግባቡ
ሳይመረመር እና ሳይጣራ ዉሳኔ መስጠቱን ስለሚያሣይ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የክርክር
አመራር ጉድለት ያለበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብለናል፡፡ሌላዉ ተጠሪ ያልተጠቀመችበት
የዓመት እረፍት በገንዘብ ተለዉጦ ብር 6,815.38 እና የካዝና መጠባበቂያ ብር 36,507.47
አመልካች ለተጠሪ እንዲከፈል የተወሰነዉ ማስረጃን እና ህጉን መሰረት ያደረገ ነዉ ከሚባል
በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አልተገኘም፡፡በዚሁ
አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ዉሳኔ

1ኛ/በዚህ ጉዳይ የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/35516 ላይ በ14/05/2013ዓ.ም


የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህንኑ በማጽናት የኦሮሚያ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁ/335005 ላይ በ21/05/2013ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1 መሰረት
ተሻሽሏል፡፡

2ኛ/ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት የዓመት እረፍት እና የካዝና መጠባበቂያ ለተጠሪ እንዲከፈል


የሰጠዉ ዉሳኔ ክፍል ጸንቷል፡፡

3ኛ/የፕሮቭደንት እና ቦነስ ክፍያን በተመለከተ ከላይ በፍርድ ሀተታ ላይ በተገለጸዉ አግባብ


ግራቀኙን በማከራከርና በማስረጃ በማጣራት ተገቢዉን ዉሳኔ እንዲሰጥበት ጉዳዩን
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 343/1/ መሰረት ለአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሰናል፡፡

4ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡ ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 202879

ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች- ወ/ሮ ዲዮን ማክፋርላን፡- ጠበቃ ለገሠ ቀርበዋል

ተጠሪ- ላየን ኸርት አካዳሚ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፡- ነፈጅ ሹሜ አለሙ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ
በመሆን የተከራከሩ ሲሆን አመልካች በቀን 07/01/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ተጠሪ እኔ
ባለሁበት የስራ መደብ ላይ በተመሳሳይ ለሚሰሩ ሰራተኞች የሐምሌ እና የነሐሴ ደሞዝ ሲከፍል
ለእኔ ግን የሚገባኝ ክፍያ ባለመክፈል በፈፀመው ህገ-ወጥ ተግባር ሞራሌ የተነካ በመሆኑ
ያልተከፈለኝን የሁለት ወር ደሞዝ፣ የስራ ስንብት ክፍያ ፣ ካሳ፣ ክፍያ በተገቢው ጊዜ ውስጥ
ባለመክፈሉ ቅጣት እና የዓመት እረፍት ክፍያ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው
ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ በበኩሉ በቀን 02/02/2012 ዓ.ም ጽፎ በሰጠው መልስ አመልካች በቀን 26/12/2011
ዓ.ም እና በቀን 04/13/2011 ዓ.ም በፃፉት ኢሜል በራሳቸው ፍቃድ ስራቸውን የለቀቁ ስለመሆኑ
ማስጠንቀቂያ በመስጠት ከቀን 27/12/2011 ዓ.ም በኋላ ስራቸው ላይ ያልተገኙ በመሆኑ ስንብቱ
ህገ-ወጥ አይደለም፤ በዚህም ምክንያት አመልካች የጠየቁትን ክፍያ ለመክፈል አንገደድም፤ ደሞዝን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በሚመለከት የገንዘብ እጥረት የገጠመን በመሆኑ ምክንያት ሐምሌ ወር በሁለት ጊዜ ክፍያ


ከፍለናል፤ የነሐሴ ወርን በሚመለከት አመልካች ያለማስጠንቀቂያ ስራቸውን የለቀቁ በመሆኑ ለእኛ
የሚከፈል ነው፤ ይከፈል ቢባል እንኳን በይርጋ ይታገዳል በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተጠሪ
ለአመልካች በተደጋጋሚ ጊዜ ደሞዝ ባለመክፈል ግዴታውን ያልተወጣ በመሆኑ አመልካች የስራ
ውላቸውን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጣቸው ህጋዊ ነው፤ የስራ ውሉን መቋረጥ ተከትሎ ያለውን
ውጤት በሚመለከት ተጠሪ የስራ ስንብት ክፍያ፣ ካሳ፣ የ14 ቀን የዓመት እረፍት ክፍያ፣ ክፍያ
ለዘገየበት ቅጣት የግማሽ ወር ደሞዝ እና የአንድ ወር ከ15 ቀን ያልተከፈለ ደሞዝ በድምሩ ብር
170,228.50 ይክፈል በማለት ወስኗል፡፡ አመልካች የስር ፍርድ ቤት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውሉን
ማቋረጡ የህግ መሠረት ያለው መሆኑን አረጋግጦ እያለ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43
መሠረት ካሳ እንዲከፈለኝ አለመወሰኑ ስህተት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት ይግባኛቸውን ለፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት በሌላ
መዝገብ ይግባኝ አቅርቧል፡፡ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ሁለቱን መዝገቦቹ አጣምሮ ከመረመረ በኋላ
አመልከች ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውላቸውን ማቋረጣቸው ተገቢ ነው ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ፣ ካሳ
እና የስራ ስንብት ክፍያ እንዲከፈላቸው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል ሽሮ
የዓመት እረፍት ክፍያ፣ ያልተከፈለ ደሞዝ እንዲከፈል እና ክፍያ በመዘግየቱ ምክንያት ቅጣት
እንዲከፈል የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል፡፡ ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች
የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ላማስለወጥ ነው፡፡

አመልካች በቀን 16/06/2013 ዓ.ም በተፃፈ 03 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች
ተፈፅመዋል ያሏቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችሎት እንዲታረሙላቸው ጠይቀዋል፡፡
የአቤቱታው ይዘትም በአጭሩ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ተጠሪ የሀምሌ እና ነሀሴ ወር 2011
ዓ.ም ደሞዝ ባለመክፈሉ ምክንያት አመልካች የስራ ውሉን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጤ ተገቢ
መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 43 መሠረት ካሳ እንዲከፈለኝ አለመወሰኑ
እና የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ውሳኔውን ማጽናቱ፤ እንዲሁም ተጠሪ ለሁለት ወር ደሞዝ ያልከፈለ
ስለመሆኑ ተረጋግጦ እያለ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ ከሁለት ጊዜ በላይ አልተፈፀመም በማለት
ለህጉ የተሳሳተ ትርጉም ሰጥቶ ከህገ-ወጥ ስንብቱ ጋር በተያያዘ ያሉ ክፍያዎች ሊከፈሉ አይገባም
በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ መሻሩ መሠረታዊ የህግ ስህተት
የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል የሚል ነው፡፡

ጉዳዩም በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ ተጠሪ የወሰደው የስራ ስንብት እርምጃ ህጋዊ ነው
የመባሉን አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 32(1)(ሐ) አንጻር መጣራት ያለበት መሆኑ
ስለታመነበት ለዚህ ሰበር ችሎት ቀርቧል፡፡ በዚሁም መሠረት ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ጥሪ
ተደርጎለት በቀን 11/08/2013 ዓ.ም ጽፎ በሰጠው መልስ ደሞዝ በተደጋጋሚ አለመክፈልን
በተመለከተ ለአመልካች ያልተከፈላቸው የሐምሌ ወር ደሞዝ ሲሆን ስራቸውን የለቀቁት ደግሞ
የነሐሴ ወር ደሞዝ ከመከፈሉ አምስት ቀናት አስቀድመው በመሆኑ ደሞዝ በተደጋጋሚ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አልተከፈላቸውም አያስብልም፤ ድርጊቱ የተደጋገመ ካልሆነ ደግሞ አመልካች የስራ ውላቸውን


ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጣቸው ህገ-ወጥ በመሆኑ ሊከፈላቸው የሚገባ ካሳም ሆነ የስንብት ክፍያ
የለም፤ በዚህ ረገድ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢነት ያለው በመሆኑ ሊፀና ይገባል
በማለት ተከራክሯል፡፡ አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተው
ተከራክረዋል፡፡

ከስር ጀምሮ የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኝ ክርክር ይዘት አጠር ባለ መልኩ ሲታይ ከላይ
የተገለፀውን ሲመስል ይህ ችሎትም የአመልካቾችን የሠበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ከተያዘው
ጭብጥ እና ለጉዳዩ እግባብነት ካላቸዉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ
መርምሮታል፡፡ እንደመረመረዉም አመልካች አጥብቀዉ የሚከራከሩት የስራ ዉሉ የተቋረጠዉ
ተጠሪ በተደጋጋሚ ለአመልካች ደመወዝ ባለመክፈሉ ምክንያት በመሆኑ እና ይህ መሆኑ ደግሞ
የስራ ዉሉ በህገ ወጥ የተቋረጠ ነዉ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በአዋጁ አንቀጽ
43 መሠረት ለተጠሪ ካሳ እንዲከፈል አለመወሰኑ መሠረታዊ የህግ ስህተት ነዉ በማለት ነዉ፡፡
በሌላ በኩል በግራ ቀኝ መካከል የነበረዉ የስራ ዉል ግንኙነት የተቋረጠዉ በአመልካች አነሳሽነት
እንጂ በተጠሪ አለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ አመልካችም ይህን ክደዉ
አይከራከሩም፡፡ ስለሆነም የስራ ዉሉ የተቋረጠዉ በተጠሪ ሳይሆን በአመልካች በሆነበት ሁኔታ የስራ
ዉሉ በህገ ወጥ መንገድ የተቋረጠ ነዉ በሚል የስራ ዉሉ በአሠሪዉ በህገ ወጥ መንገድ ሲቋረጥ
ብቻ ተፈፃሚ የሚሆነዉን የአዋጅ ቁጥር 377/96 (ለክርክሩ መነሻ የሆነ ጉዳይ የተፈጠረዉ አዋጅ
ቁጥር 377/96 ተሽሮ በሌላ አዋጅ ከተተካ በኋላ በመሆኑ ተፈፃሚነት ያለዉ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 ነዉ) አንቀጽ 43 ድንጋጌ በመጥቀስ አመልካች የሚያቀርቡት ክርክር ዉሉ
የተቋረጠበትን ምክንያት እና ህጋዊ ዉጤቱን ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ
አልተገኘም፡፡

ይልቁንም ከተያዘዉ ጉዳይ ተፈጥሮ አንፃር መታየት ያለበት ነጥብ በሠራተኛዉ አነሳሽነት
የስራ ዉል የሚቋረጥበትን ሁኔታ እና ህጋዊ ዉጤቱ ነዉ፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 የተመለከተዉን መሠረት በማድረግ ማየቱ ተገቢ ነዉ፡፡ ሠራተኛዉ ለአሠሪዉ የ30 ቀን
የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የስራ ዉል ማቋረጥ የሚችል በመርህ ደረጃ በአዋጁ የተመለከተ
ሲሆን (አንቀጽ 31 ይመለከቷል) ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ ሠራተኛዉ የስራ ዉሉን
ማቋረጥ የሚችልባቸዉንም ሁኔታዎች በአዋጁ በዝርዝር ተመልክተዋል (አንቀጽ 32/1)፡፡
ዉጤቱንም ስንመለከት ማስጠንቀቂያ መስጠት አስፈላጊ ከማይሆንባቸዉ ምክንያቶች ዉጪ በሆነ
ሁኔታ ሠራተኛዉ ለአሰሪዉ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የስራ ዉሉን ያቋረጠ እንደሆነ ከአንድ
ወር ያልበለጠ ደመወዙን ለአሠሪዉ ካሳ የመክፈል ሃላፊነት ያለበት ሲሆን፣ በአንፃሩ ማስጠንቀቂያ
መስጠት አስፈላጊ የማይሆኑ ሁኔታዎች ናቸዉ ብሎ አዋጁ ከዘረዘራቸዉ ሁኔታዎች ዉስጥ ቢያንስ
አንዱ በመፈጠሩ ምክንያት ሠራተኛዉ የስራ ዉሉን ያቋረጠ እንደሆነ አሠሪዉ ለሠራተኛዉ የሦስት
ወር ደመወዝ የመክፈል ሃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 41(2) እና 45 ላይ
ከተመለከቱት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተያዘዉ ጉዳይ አመልካች የሚከራከሩት ተጠሪ
የሐምሌ እና የነሐሴ ወር ደመወዝ ባለመክፈሉ ስራቸዉን የለቀቁ መሆኑን ነዉ፡፡ የስር ከፍተኛ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍርድ ፍርድ ቤት ተጠሪ በዚህ ምክንያት ካሳ የመክፈል ሃላፊነት የለበትም በሚል ድምዳሜ ላይ
የደረሰዉ ተጠሪ የሐምሌ እና ነሐሴ ደመወዝ አለመክፈሉ በአዋጁ አንቀጽ 32(1/ሐ) መሠረት
በተደጋጋሚ ግዴታዉን አልተወጣም የሚያሰኝ አለመሆኑን በመግለጽ ነዉ፡፡ ከላይ እንደተገለጸዉ
ሠራተኛ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ግዴታ ሳይኖርበት የስራ ዉሉን ማቋረጥ ከሚችልባቸዉ
ሁኔታዎች እና በዚህም ምክንያት አሠሪዉ ለሠራተኛዉ ካሳ የመክፈል ሃላፊነት እንዲኖርበት
ምክንያት ከሚሆኑት ምክንያቶች ዉስጥ አንዱ አሠሪዉ ግዴታዉን በተደጋጋሚ አለመወጣቱ አንዱ
ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 32(1/መ) የተመለከተዉ ድንጋጌ ያስገነዝባል፡፡ ይሁንና በተያዘዉ ጉዳይ
ለአመልካች ያልተከፈለዉ ደመወዝ የሁለት ወር ሳይሆን የአንድ ወር ተኩል መሆኑ በከፍተኛ
ፍርድ ቤቱ ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም ከአዋጁ አንቀጽ 32(1/መ) አንፃር አመልካች ለተጠሪ ደመወዝ
የመክፈል በአዋጁ የተጣለበትን ግዴታ በተደጋጋሚ ጊዜ አልተወጣም ለማለት የሚያስችል ህጋዊ
ምክንያት የለም፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በዚህ ረገድ
ያቀረቡትን ክርክር ዉድቅ በማድረግ የሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ ችሎት
ሊታረም የሚችል መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም፡፡ ስለሆነም ተከታዩ
ተወስኗል፡፡

ዉሳኔ

1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 257553 በቀን 17/05/2013 ዓ.ም በዋለዉ


ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሠረት ጸንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን


ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ.መ.ቁ 203198
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ወ/ሮ መህቡባ ቢላል- አልቀረቡም ከተባለ በኋላ ጠበቃ አሊ አወል ቀረቡ

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ነጃት ቢላል- አልቀረቡም

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 107958 ጥቅምት 09 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 260898 ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው
ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው
ነው፡፡

ጉዳዩ የሁከት ይወገድልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሸ፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ
በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አዋሳኙ በክሱ
የተገለጸው እና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ውስጥ የሚገኝ በግምት 200 ካ.ሜ የሚሆን ቤት እና
ይዞታ ከአቶ አወል ባሌ ጥር 05 ቀን 1994 ዓ.ም በተደረገ የቤት ሽያጭ ውል የገዙ መሆኑን፤ በስማቸውም
መብረት እና ውሃ አስገብተው የሚጠቀሙበት መሆኑን፤ ተጠሪ እህታቸው ስለሆኑ በ 2007 ዓ.ም ከውጪ
ሐገር ሲመጡ በግቢው ውስጥ በሚገኙ ሁለት ክፍል ቤቶች ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ እንዲያርፉበት
የፈቀዱላቸው መሆኑን፤ ሆኖም ተጠሪ ቤቱን እንዲለቁ ሲጠየቁ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እና ይባስ
ብለው ሁከት ፈጥራብኛለች በማለት ክስ የመሰረቱባቸው መሆኑን በመግለጽ ቤቱን ለቀው እንዲወጡ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ተጠሪ ለክሱ መልስ እንዲሰጡ መጥሪያ
ተልኮላቸው ስላልቀረቡ ጉዳያቸው በሌሉበት የታየ መሆኑን መዝገቡ ያመለክታል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤትም የአመልካችን ክስ እና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ሁለት ክፍል ቤቶች ለቀው
እንዲያስረክቧቸው የጠዩት ተጠሪ ወደ ቤቱ የገቡት በአመልካች ፈቃድ ለተወሰነ ጊዜ ነው በማለት ነው፤
ሆኖም በመዝገቡ ተከሳሽ የሆኑት ተጠሪ በዚሁ ችሎት በአመልካች ላይ በመ.ቁ 104651 ባቀረቡት ክስ
በተሰጠው ውሳኔ ተጠሪ ለክሱ ምክንያት ወደ ሆነው ቤት የገቡት የካቲት 10 ቀን 1996 ዓ.ም በተደረገ
የሽያጭ ውል ከአመልካች ላይ ገዝተው መሆኑ ስለተረጋገጠ እና ይህ የሽያጭ ውል ያልፈረሰ በመሆኑ ተጠሪ
ቤቱን ለቀው የሚያስረክቡበት የሕግ አግባብ የለም በማለት ወስኗል፡፡

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ
ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሠረት አቤቱታቸው በትዕዛዝ ውድቅ ተደርጓል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70/ሀ መሠረት በሌለበት ጉዳዩ የሚታይን ሰው ከሳሽ ካቀረባቸው ማስረጃዎች
በቀር ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን የሚጠቅሙ ማናቸውንም ማስረጃዎች አያይም፤ ከመዝገቡ ጋር ያልተያያዙ
ማስረጃዎች ተከሳሹ እንዳቀረባቸው ተደርጎ የተከሳሽን መብት በሚጠብቅ መልኩ ውሳኔ ሊሰጥ አይገባም፤
የስር ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው አመልካች ያቀረብኳቸውን ምስክሮች ሳይሰማ እና የሰነድ
ማስረጃዎችንም ሳይተች ነው፤ ስለሆነም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ
ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ ለክሱ መልስ ሳይሰጡ እና የግራቀኙ ማስረጃ ሳይሰማ ተጠሪ
ቤቱን ለአመልካች ሊያስረክቡ አይገባም ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት ከማስረጃ ምዘና መርህ አንጻር
ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ አመልካች የፍርድ ቤቱ መጥሪያ ተልኮላቸው
ለመቀበል ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ስለተረጋገጠ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፏል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

በዚህ ችሎት ትዕዛዝ መሠረት ከቀረቡት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመዝገብ ቁጥራቸው
107958 እና 104651 ከሆኑት መዝገቦች ይዘት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካች ክስ የቀረበብኝ
መሆኑን ያወቅኩት በመ.ቁ 104651 ባለን ክርክር በቀረብኩ ጊዜ ነው በማለት በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ
የተሰጠው ትዕዛዝ እንደነሳላቸው አቤቱታ አቅርበው አቤቱታቸው ውድቅ የተደረገባቸው መሆኑን፤ ክሱ
በተሰማበት እለትም አመልካች ተጠሪዋ ቤቱ የራሴ ነው በሚል በዚያው ችሎት በመ.ቁ 104651 ክስ
የመሰረቱባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ያሳወቁ መሆኑን፤ በሁለቱም መዝገቦች የቀረበው ጉዳይ በአንድ ዳኛ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የታየ እና በተመሳሳይ እለት ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑን፤ ተጠሪ ከሳሽ በሆኑበት እና አመልካችም ቀርበው
ክርክር በተደረገበት የመ.ቁ 104651 በሆነው መዝገብ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ አከራካሪውን ቤት
የያዙት ከአመልካች ላይ ገዝተውት ስለመሆኑ የካቲት 10 ቀን 1996 ዓ.ም የተደረገ የሽያጭ ውል
አቅርበዋል፤ የሽያጭ ውሉ በግራቀኙ መካከል የተደረገ እና በአመልካችም የተፈረመ ስለመሆኑ በሽያጭ ውሉ
ላይ በእማኝነት የተጠቀሱት ምስክሮች ያስረዱ በመሆኑ አመልካች ተጠሪዋ ቤቱን እንዲለቁ በማለት
የፈጠሩት ሁከት እንዲወገድ ሲል የወሰነ መሆኑን እና ይህንኑ መሠረት በማድረግ ለዚህ የሰበር አቤቱታ
መነሻ በሆነው የመ.ቁ 107958 በሆነው መዝገብ ተጠሪ በቤቱ የገቡት አመልካች እንደሚሉት ለጊዜው
ፈቅደውላቸው ሳይሆን የካቲት 10 ቀን 1996 ዓ.ም ከአመልካች ጋር በተደረገ የሽያጭ ውል በመሆኑ ቤቱን
ሊለቁ አይገባም በማለት የወሰነ መሆኑን ነው፡፡
በመሠረቱ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ነገር አንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይነት ያለወ ሆኖ ምላሽ
የሚያስፈልገውም የስረ ነገር ጭብጥ እና ተከራከሪ ወገኖችም ተመሳሳይ ሆነው ጉዳዩ ስልጣን ላለው ፍርድ
ቤት ቀርቦ በመሰማት ላይ እያለ ሌላው ፍ/ቤት ይህንኑ አንድ የሆነውን ጉዳይ ተቀብሎ ለመከራከር
አይችልም በማለት ተመሳሳይ የሆነው ጉዳይ በአንድ ፍ/ቤትም ሆነ በሌላ ፍ/ቤት በቀረበ ጊዜ ክርክሩ ሊቀጥል
እንደማይገባ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 8(1) ይደነግጋል፡፡ ይኸው ሥርዓት ሳይፈፀም ቀርቶ ተመሳሳይ የሆነውና
በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች የተነሳው ጉዳይ በተለያየ ክስ አማካኝነት በተለያየ ፍ/ቤት ቀርቦ በመሰማት ላይ
የሚገኝ መሆኑ ከታወቀም የክርክሩ ተነጣጥሎ መታየት ለዳኝነት ሥራ አመራር ወይም ለትክክለኛ ውሳኔ
አሰጣጥ የማይመች ወይም የማይገባ ሆኖ ስለሚገኝ ተጣምሮ መታየት ያለበት ስለመሆኑ የዚሁ ሕግ ቁጥር
11 ድንጋጌ ይዘት ያስገነዝበናል፡፡ ይህም ክርክሮችን ሥርዓት ባለው መንገድ በመምራት በአፋጣኝ እንዲታዩ
ለማድረግ እና ተለያይተው በሚቀርቡ ክሶች ላይ የተጣረሰ እና ውሳኔ እንዳይሰጥ ለማድረግ ስለመሆኑ
ከድንጋጌ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
በያዝነው ጉዳይ አመልካች እና ተጠሪ በየፊናቸው ያቀረቡት ክስ በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የቀረበ በመሆኑ
በሁለቱም መዝገቦች የቀረበው ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 11 መሠረት ተጣምሮ መወሰን ነበረበት፡፡ ሆኖም
የስር ፍርድ ቤት ምንም እንኳን በዚሁ መሠረት ሁለቱንም መዝገቦች አጣምሮ ያልወሰነ ቢሆንም
ውሳኔዎቹን በተመሳሳይ ቀን የሰጠ እና በአንደኛው መዝገብ የሰጠውን ውሳኔ በሌላው መዝገብ ላይም
በምክንያትነት የተጠቀመበት በመሆኑ በሁለቱም መዝገቦች ላይ የሰጣቸው ውሳኔዎች ተመሳሳይ ውጤት
ያላቸው ናቸው፡፡
በሌላ በኩል አመልካች ለዚች ችሎት ባቀረቡት ክርክር የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ
የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ነው በማለት የሚከራከሩት ተጠሪ ጉዳያቸው በሌሉበት የታየ ሆኖ ሳለ የስር
ፍርድ ቤቱ የአመልካችን ማስረጃዎች መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት ሲገባው ከመዝገቡ ጋር
ያልተያያዙ ማስረጃዎችን ተጠሪ እንዳቀረቧቸው በማድረግ የተጠሪን መብት በሚጠብቅ መልኩ ውሳኔ
መስጠቱ አግባብ አይደለም በሚል ነው፡፡ ተጠሪ በዚህ አግባብ የሚከራከሩ ቢሆንም አንድ ፍርድ ቤት
በቀረበለት ጉዳይ ላይ ውሳኔ የሚሰጠው ከሳሽ የሆነው ተከራከሪ ወገን ያቀረበውን ማስረጃ መሠረት በማድረግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሳይሆን ተከሳሹ ቀርቦ በተከራከረ ጊዜ ተከሳሹ ያቀረበውን ማስረጃ ጭምር በመመልከት እንዲሁም ለጉዳዩ
አወሳሰን ጠቃሚ መስሎ ሲታየው በክርከሩ ሒደት የተረዳውን እውነታ መሠረት በማድረግ ነው፡፡

በያዝነው ጉዳይ ምንም እንኳን ተጠሪ ጉዳያቸው በሌሉበት የታየ ቢሆንም አመልካች ክሱ በተሰማበት እለት
ተጠሪዋ በዚያው ችሎት የመ.ቁ 104651 በሆነው መዝገብ ሁከት ተፈጥሮብኛል በማለት ክስ ያቀረቡባቸው
መሆኑን ለችሎቱ የገለጹ በመሆኑ እና ተጠሪ አቅርበውታል የተባለው ክስም በዚያው ችሎት የቀረበ በመሆኑ
የስር ፍርድ ቤቱ የመ.ቁ 104651 በሆነው መዝገብ ተጠሪ በቤቱ የገቡት አመልካች እንደሚሉት ለጊዜው
ፈቅደውላቸው ሳይሆን የካቲት 10 ቀን 1996 ዓ.ም ከአመልካች ጋር በተደረገ የሽያጭ ውል መሠረት
ስለመሆኑ የተረጋገጠ እና ይህ የሽያጭ ውል ያልፈረሰ በመሆኑ ተጠሪ ቤቱን ለቀው ሊያስረክቡ አይገባም
በማለት መወሰኑ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም፡፡
ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 107958 ጥቅምት 09 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 260898 ጥር 24 ቀን
2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝበፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
ትዕዛዝ
- የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የመዝገብ ቁጥራቸው 107958 እና 104651 የሆኑት
መዝገቦች ወደ መጡበት ይመለሱ፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁጥር 203206
ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡-አቶ ወንድወሰን ፍልፍል -- አልቀረቡም

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ወይንሸት ወ/ገብርኤል- አልቀረቡም

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
በግራ ቀኙ መሃል ያለውን የአፈፃፀም ክርክር አስመልክቶ የሰጠው ትዕዛዝ ጉዳዩን በይግባኝ
በተመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው
ስሕተት እንዲታረምልኝ በማለት አመልካች ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻነት ሲሆን አመልካች በስር
ፍርድ ቤት የፍርድ ባለዕዳ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት ነበሩ፡፡

በግራ ቀኙ መሃል ባለው የሰሌዳ ቁጥር 2-38101 አአ መኪናን አስመልክቶ አመልካች ህዳር 09 ቀን
2013 ዓም በተፃፈ አቤቱታ አከራካሪው መኪና አቶ ደጀኔ ዘውዴ ለተባሉ አድራሻቸው ግንደበረት
ከተማ ቀበሌ 02 የቤት ቁጥር 238 ነዋሪ ለሆኑት የተሸጠ መሆኑን ገልፀው የፌደራል ፖሊስ በዚህ
አድራሻ ፈልጎ እንዲያመጣ እንዲታዘዝላቸው የጠየቁ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ትዕዛዝም አመልካች መግለፅ ያለባቸው አሁን መኪናው ያለበትን መሆኑን፤መኪናው ስለመሸጡ ፍርድ
ቤቱ በዋናው ውሳኔ ላይም ያልገለፀ መሆኑን፤መኪናው ተንቀሳቃሽ ከመሆኑ አንፃር አመልካች መኪናው
ያለበትን የመግለፅ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን መነሻ በማድረግ አመልካች መኪናውን የያዘውን ግለሰብና
አሁን ያለበትን ለፌደራል ፖሊስ እንዲያሳዩና ፌደራል ፖሊስም ተሸከርካሪውን በተገኘበት በመያዝ
እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ያቀረቡ ቢሆንም
ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት ሰርዞታል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም መኪናውን ከ7 አመት ከ1 ወር


በፊት በ06/05/2006 ዓም በተፈረመ ውል ለአቶ ደጀኔ ዘውዴ ጫላ በሽያጭ አስተላልፌ አስረክቤ እያለ
፤ውሳኔው ሲሰጥም መኪናው በእኔ እጅ ባልነበረበት ፤ገዢው መኪናውን ገዝተው ከተረከቡ በኋላ የት
እንደወሰዱት የማውቀው ነገር በሌለበት ፤መኪናውን ማቅረብና ውሳኔውን መፈፀም አለብህ በማለት
የተሰጠው ትዕዛዝ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.392(1) እና (2) እንዲሁም በሰበር መዝገብ ቁጥሮች 69471 እና
29344 የተሰጠውን አስገዳጅ ውሳኔ የሚፃረር በመሆኑ ሊሻር ይገባል በማለት አመልክተዋል፡፡

አመልካች መኪናውን የሸጡ መሆኑንና የሸጡለትንም ግለሰብ አድራሻ ለፍርድ ቤቱ አስረድተው በፖሊስ
እንዲቀርብለት እየጠየቁ አመልካች መኪናውን ካለበት እንዲያቀርቡ የታዘዘበትን አግባብ ለማጣራት
የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ በሰጡት መልስም የፍቺ ክርክሩን በያዘው ፍርድ ቤት መኪናው እንዳይሸጥ ታግዶ ስለነበረ በዚህ
ምክንያትም ስም ለማዛወር ስለማይችሉ ሆነ ብለው ቀኑን ወደ ኋላ በማድረግ በጋብቻ ውስጥ እንደተሸጠ
በማድረግ ያቀረቡት እንጂ መኪናው ጋብቻ ውስጥ እያለን ያልተሸጠ በመሆኑ፤የመኪናው መሸጥ በዋናው
ክርክር ጊዜ ያልተነሳ በመሆኑ አሁን እንደ አዲስ ሊነሳ ስለማይችል፤መኪናው የተሸጠ ከሆነ የጋራ ሀብት
ተብሎ ሲወሰን በይግባኝ ያላሻረው ስለሆነ ፤መኪና ተሸጠ የሚባለውም ስመሀብቱ ሲዘዋወር በመሆኑና
የመኪናው ስም ያልተዛወረ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ሊፀና ይገባል በማለት
ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡ፍርዱን
የሚያስፈፅመው ፍርድ ቤት ፍርዱን ለማስፈፀም ተስማሚ ነው ብሎ የሚገምተውን ትዕዛዝ የመስጠት
ስልጣን ያለው መሆኑን የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.392(1) ያመለክታል፡፡አከራከሪው መኪና መሸጡን ጠቅሰው
የገዢውን አድራሻ ጭምር በማመልከት መኪናው በፖሊስ ተፈልጎ እንዲቀርብ ህዳር 09 ቀን 2013 ዓም
በተፃፈ አቤቱታ ያመለከቱት አመልካች መሆናቸውን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል፡፡አመልካች
በዚህ አግባብ አፈፃፀሙ በአከራካሪው መኪና ላይ እንዲቀጥል ካመለከቱ በኋላ መኪናው ያለበትን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አሁናዊ አድራሻ ለፖሊስ እንዲያሳዩ በችሎቱ ሲታዘዙ አመልካች ሀሳባቸውን በመቀየር በመኪናው ላይ
ፍርዱ ሊፈፀም አይችልም በማለት የተከራከሩበትን በቂና አሳማኝ ምክንያት በክርክራቸው ላይ
አላመለከቱም፡፡

በገዛሁት መኪና ላይ አፈፃፀሙ ሊቀጥል አይገባም በማለት የመከራከሩ ድርሻ መኪናውን በእርግጥም
ገዝተው መብታቸውን አረጋግጠው ከሆነ የገዢው ድርሻ ሆኖ እያለ አመልካች መኪናውን ገዝተዋል
የሚሏቸውን ሰው አላግባብ በመወከል መኪናው ላይ አፈፃፀሙ ሊቀጥል አይገባም ሊፈፀም የሚችል
ፍርድ የለም በማለት ህዳ 09 ቀን 2013 ዓም ካቀረቡት አቤቱታ በተቃራኒ መከራከራቸው አሳማኝ ሆኖ
ስላላገኘነው በዚህ አግባብም በአከራካሪው መኪና ላይ አፈፃፀሙ እንዲቀጥል የስር የፌደራል መጀመሪያ
ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች መኪናው የሚገኝበትን አሁናዊ አድራሻ ለፖሊስ እንዲያመለክቱ ማዘዙና
ይህ ትዕዛዝ ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መፅናቱ የሚነቀፍ ሆኖ
ስላልተገኘ የሚከተለውን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌ/መ/ደ/ፍርድ ቤት በመ/ቁ.86371 በቀን 08/03/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው


የአፈጻፀም ትዕዛዝና ይህንን ትዕዛዝ በማፅናት የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.257832 ጥር 20 ቀን 2013
ዓም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ፀንተዋል፡፡
2. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡
ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰበር መ/ቁ/ 203210

ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም


ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ አቶ ገመቹ ቤኩማ፡- ጠበቅ ፍቅሬ ሞያ ቀረቡ

ተጠሪ፡ ሔና ፋርም ኃ/የተ/የግ/ማህበር፡- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ አመልካች ያቀረበዉ ጊዜ ያለፈበት ይግባኝ ማስፈቀጃ ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ
የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ በተጠሪ ሆቴል ውስጥ
ተቀጥሬ እየሰራሁ እያለ ያለጥፋት የስራ ውል ስለአቋረጠብኝ የስራ ስንብት ክፍያዎች
እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በሰጠዉ መልስ አመልካችን አላሰናበትንም
ይልቁንም አመልካች ካለበት ዕዳ ለመሸሽ ሲል ስራውን ለቆ በመሄዱ ተጠሪ ላይ ጉዳት ደርሷል
በማለት ተከራክረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ የስራ ውሉ በአሰሪዉ ስለመቋረጡ ያላስረዳ በመሆኑ


ተጠሪ የስራ ውሉ ያላግባብ አቋርጧል ለማለት አልተቻለም በማለት የክፍያ ጥያቄ ውድቅ
በማድረግ ያልተከፈል ደመወዝ እና የዓመት እረፍት እንዲከፈለው ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም
በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ከፍተኛ ያቀረበዉ ይግባኝ ጊዜ አልፎበታል


ስለተባለ የይግባኝ ጊዜ ያለፈበት ምክንያት በመግለጽ መስከረም 08 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ
የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ አቅርቦ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ይግባኙን በወቅቱ ለይግባኝ
ሰሚው ፍ/ቤት ማቅረብ ያልቻለው የአመልካች ጠበቃ አጋጠመኝ ባሉት እክል ምክንያት
በፍቃድ መጠየቂያው ማመልከቻ ላይ የተገለፀው ምክንያት ይግባኙን በጊዜው ለማቅረብ
ያልቻለው በአመልካች ጠበቃ ወይም ነገረ ፈጅ ወይም በወኪሉ ያለመቅረብና በነዚሁ ጉድለት
መሆኑ የታወቀ እንደሆነ ምክንያቱ እንደበቂ ምክንያት እንደማይወሰድ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 326(2)
በህጉ የተመለከተ በመሆኑ ይግባኙ በጊዜ ያልቀረበው በበቂ ምክንያት አይደለም በማለት
የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታውን ውድቅ አድርገዋል፡፡

ለዚህ ሰበር ችሎት የቀረበዉ አቤቱታ ይዘት ባጭሩ በሕግ የተፈቀደው የ30 ቀን ጊዜው ሳያልፍ
በ26/12/2012 ዓ.ም ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ሬጅስትራር የይግባኝ አቤቱታዬን አቅርቤ የስር
መዝገብ ግልባጭ እንዲላክ በማህተም አድርጎ ለሥር ፍ/ቤት ተመርቶ፣በዚሁ መሰረት ለስር
ፍ/ቤት አቅርቤ በዚሁ ቀን በ26/12/2012 ዓ.ም የመዝገብ ግልባጭ ተሰጥቶኝ በቦርሳዬ አድርጌ
ለከፍተኛ ፍ/ቤት ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እያለሁ ከቦርሳዬ ጋር ጠፍቷል፡፡በመሆኑም የይግባኝ
አቤቱታዬን አቅርቤ የይግባኝ ፋይል ቁጥር አሰጥቼ የይርጋ ጊዜ አቋርጫለሁ፣በጊዜ ማቅረብ
ያልቻኩት የመዝገብ ግልባጩን ነው፣ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት የይግባኝ ጊዜው ሳያልፍ ጊዜው
አልፏል፣በቂ ምክንያት አልቀረበም በማለት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ
ውሳኔው ተሽሮ ይግባኙን ለማቅረብ እንዲፈቀድልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ ዋና ፍርድ የተሰጠው
ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ሲሆን ይግባኝ አቤቱታ ያቀረበው ደግሞ ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም
ከመሆኑ አኳያ በወቅቱ ይግባኙ አልቀረበም ሊባል የሚችልበት አግባብ አለው ወይ የሚለው
ነጥብ ለማጣራት ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት
ታዟል፡፡ተጠሪ መጥሪያ ድርሶት መልስ ባለማቅረቡ የጽሁፍ መልስ የመስጠት መብቱ
ታልፏል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል
ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር
በማገናዘብ መርምረናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደመረመርነዉ ክሱ የስራ ዉል መቋረጥ በመቃወም የቀረበ የግል የሥራ ክርክር ሲሆን


የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ይግባኙ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሊቀርብ የሚገባዉ በሰላሳ ቀን ዉስጥ መሆን እንዳለበት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀጽ 139/3/ይደነግጋል፡፡በተያዘዉም ጉዳይ በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
ዉሳኔ የተሰጠዉ በሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ሲሆን ይግባኝ አቤቱታ ለይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ
ቤት ያቀረበው ነሐሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ስለመሆኑ አላከራከረም፡፡ነገር ግን ለይግባኝ ሰሚ
ፍርድ ቤት የቀረበዉ የሥር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልበጭ እና የይግባኝ ቅሬታ ብቻ በመሆኑ
የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ ግልባጭ እንዲቀርብ በሬጅስትራር ጽ/ቤት በመታዘዙ ይህ ተሟልቶ
እስኪቀርብ በዚህ ሂደት ጊዜ ያለፈበት ስለመሆኑ መዝገቡ ያሣያል፡፡ከዚህ እንደምንገነዘበዉ
አመልካች የይግባኝ ቅሬታዉንና የሥር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልባጭ ይግባኝ ማቅረቢያ በህጉ
የተመለከተዉ ሰላሳ ቀን ሳያልፍ ለይግባኝ ሰሚዉ ችሎት ማቅረቡን ያሣያል፡፡ይሁን እንጂ
የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ ግልባጭ ተያይዞ ባለመቅረቡ መዝገቡ ተከፍቶ ለችሎት ሳይቀርብ
ጊዜዉ እንዳለፈበት አከራካሪ ባይሆንም የአመልካች ጉድለት ነዉ ተብሎ መወሰዱ ተገቢ
መሆን አለመሆኑን ማየት አስፈላጊ ነዉ፡፡

የፍትሃብሔር ስነ ስርዓት ስለይግባኝ ማመልካቻ ይዘትና አቀራረብ የሚደነግግዉ ክፍል ላይ


እንደተመለከተዉ ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ የሰጠዉ ፍርድ ቤት የመዝገብና የፍርድ ግልባጭ
ትክክል ግልባጭ ለመሆኑ ታትሞበትና ተፈርሞበት ከይግባኙ ማመልከቻ ጋር ተያይዞ ለይግባኝ
ሰሚ ቤት መቅረብ እንዳለበት የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 327/2/ ላይ ተደንግጓል፡፡ከዚህ ድንጋጌ
ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለዉ በስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ቅር የተሰኘ ተከራካሪ ወገን ይግባኝ
ማቅረብ እንደሚፈለግ ለፍርድ ቤቱ አሳዉቆ የይግባኝ ቅሬታዉን አዘጋጅቶ ካቀረበ የፍርዱን
እና የመዝገቡን ትክክለኛ ግልባጭ አሟልቶ መስጠት የፍርድ ቤቱ ሃላፊነት መሆኑን
ነዉ፡፡ከዚህ አኳያ በፍርድ ቤት ያለዉ አሁናዊ አሰራር ሲታይ የመዝገብ ግልባጭ ወይም
መዝገቡ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት የሚቀርበዉ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ሲጠየቅ ወይም በችሎት
ሲታዘዝ መሆኑን ያሣያል፡፡ይህ አሰራር በአንድ በኩል ከህጉ ጋር የሚጣጣም አለመሆኑን በሌላ
በኩል ደግሞ በፍርድ ቤቶች ካለዉ የሥራ ጫና አኳያ የመዝገብ ግልባጭ እስከሚዘጋጅ
የይግባኝ ጊዜ እንዳያልፍበት ታስቦ የተዘረጋ አሰራር ከመሆኑ አንጻር ሲታይ በዚህ ሂደት
የሚፈጀዉ ጊዜ በተከራካሪ ወገን ጉድለት ነዉ ተብሎ ሊወሰድ የሚገባ አለመሆኑን መገንዘብ
ይቻላል፡፡ጉዳዩም በዋናነት መታየት የሚገባዉ የይግባኝ መብት በማያጣብብ ሁኔታ መሆኑን
ልብ ይለዋል፡፡ይሁንና የመዝገቡ ግልባጭ ተሟልቶ ለባለጉዳዩ ከተሰጠ ሳይዘገይ ለይግባኝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሰሚዉ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡በተያዘዉም ጉዳይ አመልካች የይግባኝ


ቅሬታዉንና የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ግልባጭ የይግባኝ ማቅረቢያ ሰላሳ ቀን ሳያልፍበት
ለይግባኝ ሰሚዉ ችሎት ማቅረቡ አከራካሪ አይደለም፡፡ነገር ግን የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ
ግልባጭ ለመጠባበቅ ተብሎ በዚህ ሂደት ጊዜ ያለፈበት በመሆኑ ለዚህ ዋነኛ ምክንያት
የአመልካች ጠበቃ ወይም የባለጉዳዩ ጉድለት ነዉ ሊባል አይገባም፡፡በሌላ በኩል በይግባኝ
ሰሚዉ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር ጽ/ቤት ትእዛዝ መሰረት የሥር መዝገብ ግልበጭ ለአመልካች
ጠበቃ ከተሰጠ በኋላ ይህ ሰነድ ለይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ እንደጠፋባቸዉ
የአመልካች ጠበቃ ያቀረቡትን ምክንያት ተገቢነትና አሳማኝነት ሳይመረምር የጠበቃዉ
ጉድለት ነዉ የሚለዉ የሥር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ሊከሰት የሚችል እዉነታን ያላገናዘበ በመሆኑ
ተገቢ ምክንያት ሆኖ አላገኘንም፡፡

ሲጠቃለል አመልካች የይግባኝ ጊዜ ሳያልፍ የይግባኝ ቅሬታ እና የሥር ፍርድ ቤት ዉሳኔ


ግልባጭ ለይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት አቅርበዉ እያለ በፍርድ ቤቱ አሰራር ምክንያት የስር
መዝገብ ግልባጭ ተያይዞ ባለመቅረቡ ለተፈጠረዉ መዘግየት ምክንያቱ የአመልካች ወይም
የጠበቃዉ ቸልተኝነትና ጉድለት ነዉ በማለት የሥር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዳሜ ህጉን
እና በፍርድ ቤቱ ያለዉ አሰራር ያስከተለዉን ሁኔታ ያላገናዘበ ስለሆነ ሊታረም ይገባል
ብለናል፡፡በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡
ዉሳኔ
1ኛ/የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/256736 ላይ በ09/04/2013ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ተሸሯል፡፡
2ኛ/ ይህ ዉሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ አስር የስራ ቀን ዉስጥ ይግባኙን ለፌዴራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ብለናል፡፡ይጻፍ
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

?? /? /? ? ? 203214
? ? 29/3/2014 ? /?

ዳኞች ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች - የጉምሩክ ኮምሽን - የቀረበ የለም

ተጠሪ - አቶ ተስፋ ዮሀንስ - ጠበቃ ካላአዩ አያለው ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች የካቲት 19 ቀን
2013 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 195827
ጥር 18 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት
በመ/ቁጥር 243070 ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ
ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች
የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 15 ተገቢ ያልሆነ ትርጉም
በመስጠት የተሰረዘ ዲክላራሲዮን ጸንቶ ያለ ነው በማለት ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ አይደለም፡፡
የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 15 የእቃ ዲክላራሲዮን ከተመዘገበበት ወይም የክፍያ
ማስታወቂያ ከተዘጋጀበት ቀን አንስቶ እስከ 5 የሥራ ቀን ድረስ የጉምሩክ ሥነ ሥረዓት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ካልጀመረ ዲክላራሲዮኑ ሊሰረዝ ይችላል እያለና በተጨማሪም የደንብ ቁጥር 118/08 አንቀጽ
20(1) ሊሰረዝ እንደሚችል ደንግጎ እያለ ላይሰረዝ ይችላል የሚል ትርጉም መስጠቱ ካለአግባብ
ሲሆን ግመሎቹ ከህጋዊ መስመር ውጪ ወደ ሱዳን ለመግባት ሲሉ መያዛቸው እየታወቀ ጊዜ
ባለፈበት ዲክላራሲዮን ህጋዊ አንደሆኑ ተወስዶ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡

በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከኢፌዴሪ ታክስ ይግባኝ ኮምሽን ሲሆን ይግባኝ
ባይ የአሁን ተጠሪ ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ የአሁን ተጠሪ የቁም እንሰሳት ወደ ውጪ የመላክ
ንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ነው፡፡ 43 ግመሎች ወደ ውጪ ለመላክ በ7/12/2008 ዓ/ም እና
በ13/12/2007 ዓ/ም ህጋዊ ዲክላራሲዮን የተመታለት እና በቀን 22/11/1007 ዓ/ም እቃ ወደ ውጪ
መላኪያ የባንክ ፈቃድ ተሰጥቶኛል፡፡ በወቅቱ በሱዳን መንግስት የቁም አንሰሳት ወደ ሀገር
እንዳይገባ በመከልከሉ የዘገዩና በፌደራል ፖሊስ ጥበቃ ስር ከቆዩ በኋላ በራሴ ጠባቅዎች
እያስጠበኩ ባለሁበት ሁኔታ 5 ቀን ያለፈበት ዲክላራሲዮን ነው በሚል እግራቸው ታስሮ ተኝተው
እያሉ ግመሎቹ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ሊሻገሩ ነው በሚል መውረሱ ተገቢ ባለመሆኑ
ይለቀቅልኝ ሲል አመልክቷል፡፡ የአሁን አመልካችም ግመሎቹ የይግባኝ ባይ አለመሆናቸው
ለዚህም ደግሞ በወቅቱ መቅረጫ ጣቢያው ዲክላራሲዮኑ ሲሰረዝ በባለሥልጣኑ ቁጥጥር ሥር
ከሚገኙ ግመሎች መካከል የይግባኝ ባይ ግመሎች የሚገኙ እንደሆኑ ለማጣራት በአካል ቀርቦ
እንዲለያቸው ቢጠየቅ በማፈግፈግ መብቱን አልተጠቀመም፡፡ በተደረገው የመስክ ምልከታም
የይግባኝ ባይ ግመሎች እንዳልተገኙ አረጋግጠናል፡፡ በተጨማሪም ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ 5
የስራ ቀናት ያለፈበትና ቀጣዩ የጉምሩክ ሥነ ሥረዓት ያልተጀመረበት በመሆኑ ይግባኝ ባይ
ህጋዊ ዲክላራሲዮን አለው ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡ በመሆኑም ውሳኔው ይጽናልኝ በሚል
መልስ ሰጥቷል፡፡ የኢፌዴሪ ታክስ ይግባኝ ኮምሽን አከራክሮ በመ/ቁጥር ታይኮ ከተ-1642 ሴኔ 3
ቀን 2011 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 15 መሰረት ዲክላራሲዮን
አቅራቢው ዲክላራሲዮን ከተመዘገበበት ወይም የክፍያ ማሳወቂያ ከተዘጋጀበት ቀን አንስቶ እስከ
5 የስራ ቀናት ድረስ ቀጣይ የጉምሩክ ሥነ ሥረዓት ካልተጀመረ ዲክላራሲዮኑ እንዲሰረዝ ሊደረግ
ይችላል ሲል ይደነግጋል፡፡ በመመሪያ ቁጥር 118/08 አንቀጽ 20(4 እና 5) እቃ ወደ ሀገር
እንዲገባ ወይም እንዲወጣ ከተፈቀደ ቀን ጀምሮ በተለያየ ምክንያት ሳይፈጸም ከቀረ በ10 ቀናት
ውስጥ ሲያሳውቅ ሊሰረዝ እንደሚችል ይገልጻል፡፡ እንዲሁም ከዚህ በላይ ከቆየ በበቂ ምክንያት
እስከ 1 ዓመት በሆነ ጊዜ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶ ዲክላራሲዮኑ እንደሚሰረዝ ይገልጻል፡፡
ይሁንና ቀርቦ ያላሰረዘ እንደሆነ መብቱ የሚቀር ይሆናል፡፡ በመሆኑም ግመሎቹ ዲክላራሲዮን
ተሰጥቶበት ወደ ውጪ ሳይወጡ የቀሩና መልስ ሰጪም የሚያውቅ መሆኑን ያስረዳል፡፡
ዲክላራሲዮን መሰረዝ የመ/ሰጪ መብት ሲሆን እያወቀ መቆየቱ ተገቢ አይደለም፡፡ በሌላ በኩል
ይ/ባይ ግመሎቹ ወደ ውጪ መውጣት የማይችሉ ከሆነ ዲክላራሲዮን አሰርዞ ከጉምሩክ ክልሉ
ማውጣት ሲኖርበት መ/ሰጪም ከጉምሩክ ክልሉ እንዲወጡ ማስገንዘብ ሲገባ በዝምታ መታለፉ
ተገቢ አይደለም፡፡ በመሆኑም ይ/ባይ ጊዜ ያለፈበት ዲክላራሲዮንና ግመሎቹ ወደ ውጪ መውጣት
የማይችሉ መሆኑን እያወቀ ዲክላራሲዮን ማሰረዝ ስገባው በጉምሩክ ክልል ውስጥ ማቆየቱ ተገቢ
ባለመሆኑ መወረሱ ስህተት አይደለም ሲል የመ/ሰጪን ውሳኔ በማጽናት ወስኗል፡፡ ይግባኝ ባይ
ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ አከራክሮ በመ/ቁጥር 243070 ሐምሌ 3 ቀን
2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ ይግባኝ ባይ በህጋዊ መንገድ 43 ግመሎች ወደ ውጪ
ለመላክ በመ/ሰጪ ፈቃድ በድንበር ላይ የተገኘ መሆኑ የተረጋገጠና ባልተወቀ ሁኔታ ወደ ውጪ
ሳይላኩ የቆዩና የይግባኝ ባይ ዲክላራሲዮን 5 ቀን ያለፈበት መሆኑ ታውቋል፡፡ አዋጅ ቁጥር
859/06 አንቀጽ 15(1) እቃ ወደ ወጪ ሳይላክ የቀረና በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ቀጣይ የጉምሩክ
ሥነ ሥረዓት ካልጀመረ ዲክላራሲዮኑ ሊሰረዝ እንደሚችል ይገልጻል፡፡ ካልተሰረዘ ግን ምን
እንደሚሆን የሚገልጽ ባለመሆኑ ካልተሰረዘ ጸንቶ እንዳለ የሚያመለክት በመሆኑ መ/ሰጪ
የይ/ባይን ግመሎች ካለአግባብ የወረሰ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ መ/ሰጪ የግመሎቹን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በወቅቱ ዋጋ መሰረት ለይ/ባይ ይከፈል ሲል ወስኗል፡፡ መ/ሰጪ የአሁን አመልካች ለፌደራል


ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ በመ/ቁጥር 195827 ጥር 18 ቀን
2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ስህተት
የተፈጸመበት አይደለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኙን
ውድቅ አድርጎታል፡፡

የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል፡፡ መዝገቡም ተመርምሮ በስር


ፍ/ቤት ዲክላራሲዮን ጸንቶ ባለበትና ባልተሰረዘበት ሁኔታ ግመሎቹ ሊወረሱ አይገባም ሲል
የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 15 እና ከመመሪያ ቁጥር
118/2008 አንቀጽ 20 አኳያ ለመመርመር ሲባል ቀርቧል፡፡ መልስና የመልስ መልስም
ተሰጥቶበታል፡፡ ተጠሪ መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ
መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዳልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል፡፡ አመልካችም
ሚያዝያ 12 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና


የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን
የሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ
ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም በስር
ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ 43 ግመሎች ወደ ውጪ ለመላክ ህጋዊ መስፈርቶቹን
አሟልቶ በአሁን አመልካች ፈቃድ ዲክላራሲኖን ተሰጥቷቸው በጉምሩክ ክልል የገቡና ወደ ውጪ
ሳይላኩ የቆዩና ግመሎቹን ወደ ውጪ መላኪያ ጊዜ 5 የስራ ቀን ያለፈበትና ግመሎቹ በጉምሩክ
ክልል ውስጥ የተገኙ መሆኑ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ በህጋዊ መንገድ ወደ ውጪ የሚላኩ
እቃውች በተፈቀደው ቀን ሳይላኩ በቀሩበት ጊዜ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 15
ዲክላራሲዮን አቅራቢው ዲክላራሲዮኑ ከተመዘገበበት ወይም የክፍያ ማሳወቂያ ከተዘጋጀበት ቀን
አንስቶ እስከ 5 የስራ ቀናት ድረስ ቀጣይ የጉምሩክ ሥነ ሥረዓት ካልተጀመረ ዲክላራሲዮኑ
እንዲሰረዝ ሊደረግ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ የመመሪያ ቁጥር 118/08 አንቀጽ 20(4 እና 5)
ደግሞ እቃ ወደ ሀገር እንዲገባ ወይም እንዲወጣ ከተፈቀደ ጀምሮ በተለያየ ምክንያት ሳይፈጸም
ከቀረ በ10 ቀናት ውስጥ ሲያሳውቅ ሊሰረዝ ይችላል ሲል ደንግገው ይገኛሉ፡፡ የአሁን ተጠሪ
ግመሎቹን በተፈቀደለት ጊዜ ውስጥ ወደ ውጪ ሳይልካቸው 5 የስራ ቀን አልፎበታል፡፡ እንዲህ
በሆነ ጊዜ ዲክላራሲዮኑን አሰርዞ ግመሎቹን ከጉምሩክ ክልል ማስወጣት የሚገባው ሲሆን
ዲክላራሲዮኑ ካልተሰረዘ በዲክላራሲዮኑ መጠቀም ይችላል የሚል ትርጉም የሚሰጠው ሳይሆን
ዲክላራሲዮኑን በማሰረዝ ሊያገኝ የነበረውን መብት የሚያጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ማለት
ዲክላራሲዮኑ የመላኪያ ጊዜ ካለፈበት ግመሎቹን ከጉምሩክ ክልል አውጥቶ እንደገና ወደ ውጪ
መላኪያ ማስፈቀጃ ዲክላራሲዮን የሚያወጣ አንጂ ጊዜ ባለፈበት ዲክላራሲዮን ወደ ውጪ መላክ
የሚችል አይደለም፡፡ እንዲሁም የዚህ የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/06 አንቀጽ 15 ድንጋጌ በህጋዊ
መንገድ በጉምሩክ ክልል ውስጥ የገቡ ወደ ውጪ የሚላኩ እቃዎች በተለያዩ ምክንያቶች ወደ
ውጪ ሳይላኩ የመላኪያ ጊዜው ያለፈበት አንደሆነ ላኪው ዲክላራሲዮኑን በማሰረዝ የሚሰጡትን
መብቶች መጠቀም የሚችል ሲሆን ዲክላራሲዮኑን ካላሰረዘ ግን ውደ ውጪ ሊልካቸው በጉምሩክ
ክልል ውስጥ የገቡት እቃዎች ህግ ወጥ ሆነው እንደ ኮንትሮባንድ እቃ ይወረሳሉ የሚል ትርጉም
የሚያሰጠውም አይደለም፡፡ እቃ ወደ ውጪ ለመላክ በህጋዊ መንገድ በጉምሩክ ክልል የገባ እቃ
የመላኪያ ጊዜው ካለፈበት ከጉምሩክ ክልል በማስወጣት ወደ መደበኛው ሁኔታ እንዲመለስ
ከሚደረግ በቀር በህጋዊ መንገድ በጉምሩክ ክልል የገባ እቃ የመላኪያ ጊዜ ስላለፈበት ብቻ በህገ
ወጥ መንገድ ወደ ወጪ ለማስወጣት የጉምሩክ ክልል ውስጥ እንደ ገባ እቃ እንደ ኮንትሮባንድ
ተቆጥሮ የሚወረስ ስለመሆኑ የጉምሩክ አዋጁ አያመለክትም፡፡ በመሆኑም የፌደራል ከፍተኛ
ፍ/ቤትም ከዚሁ አንጻር አይቶ አሁን አመልካች ካለ አግባብ የወረሰውን የተጠሪ ግመሎች ለአሁን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ በወቅቱ በነበራቸው ዋጋ አንዲመለስ ሲል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት


የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 195827 ጥር 18 ቀን 2013


ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 243070 ሐምሌ
3 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት
ጸንቷል፡፡
2. በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የፌደራል ከፍተኛ
ፍ/ቤት የመ/ቁጥር 289667 ላይ የተሰጠው የአፈጻጸም እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ፡፡
4. የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል፡፡
5. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

?? /? /? ? ? 203381
? ? 30/3/2014 ? /?

ዳኞች ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች - 1. አቶ ጌታቸው ዳንደና 2. ወ/ሮ ቅዲስት ቢያዝን


ከጠበቃ- ካሌብ አለባቸው ጋር ቀርበዋል
ተጠሪ - አቶ አልዓዛር ዳዊት
ከጠበቃ ደሳለኝ ደምሴ ጋር ቀርበዋል
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካቾች የካቲት 25 ቀን
2013 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 758936 የካቲት 17 ቀን 2013
ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 48597
መጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ማብራሪያ ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡
ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች
የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣
የስር ፍ/ቤቶች ሟች ከተናዘዘችው ኑዛዜ ውጪ የውርስ ንብረት ለተጠሪ እንዲሰጥ መወሰኑ ተገቢ
አይደለም፡፡ መጀመሪያ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ እርማት በሚል አዲስ ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡

በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ
የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ሟች ወ/ሮ ዓለም ፀሀይ እያሱ በ29/6/1992 ዓ/ም ኑዛዜ አድርጋለች፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከሳሽና ተከሳሾች ካርታ በጋራ ለማውጣት ስንስማማ አብላጫ ድርሻዬን ለመልቀቅ


አልተስማማሁም፡፡ በመሆኑም በኑዛዜው መሰረት ክፍፍል እንዲደረግልኝ ሲል ጠይቋል፡፡
ተከሳሾችም ሟች ለከሳሽና ተከሳሾች ኑዛዜ አድርጋለች፡፡ ይሁንና ከሳሽና ተከሳሾች በ7/7/1997
ዓ/ም ባደረግነው የውል ስምምነት ለከሳሽ የአብላጫ ድርሻ የተደረገለት ቢሆንም ሁላችንም እኩል
አንድንካፈል የተስማማን በመሆኑ እኩል አንድንካፈል በሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ የፌደራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ቁጥር 48597 ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት
በሰጠው ውሳኔ ሟች ወ/ሮ አለም ፀሀይ ኑዛዜ ያደረገች መሆኑ አልተካደም፡፡ በ7/7/1997 ዓ/ም
በከሳሽና ተከሳሾች መካከል ተደረገ የሚባለው ውል ቤቱን በስማቸው በሶስቱም ስም ለማስመዝገብ
የተስማሙና በውሉ ላይ “የቤቱ አብላጫ የኔ ቢሆንም…” የሚል ቃል ሲታይ ድርሻውን ትቷል
የሚል ሀሳብ የሚያመለክት ባለመሆኑ ከሳሽና ተከሳሾች በኑዛዜው መሰረት ይካፈሉ ሲል
የክፍፍሉን ዓይነት ዘርዝሮ ወስኗል፡፡ ከዚህ በኋላ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዚሁ
መዝገብ መጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት ከአፈጻጸም ችሎት ማብራሪያ ተጠይቄያለሁ
በሚል የማብራሪያ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዚሁ
መዝገብ መጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው የማብራሪያ ትእዛዝ ላይ ለፌደራል
ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርበው በመ/ቁጥር 758936 የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ/ም
በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ስህተት
የተፈጸመበት ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኛቸውን
ውድቅ አድርጎታል፡፡

የአሁን አመልካቾችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርበዋል፡፡ መዝገቡም ተመርምሮ


በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 48597 ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ/ም በተሰጠው
ውሳኔ “በተደረገው ኑዛዜ መሰረት ንብረቶቹ ላይ ለውጥ የተደረገበት ቢሆንም አሁን ባለበት ሁኔታ
ተለይቶ እና ተለክቶ ለአመልካቾች ተከፍሎ ይሰጥ“ የሚል ሲሆን ውሳኔውም በተጠሪ
አመልካችነት እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ፀንቶ ባለበት በተጠቀሰው
መዝገብ ላይ በመጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በተሰጠው የማብራሪያ ትእዛዝ ለአመልካቾች ከተሰጡ
ቤቶች ውጪ ያሉ በቤት ቁጥር 068 ሥር የሚጠቃለሉ ናቸው በሚል የተወሰነበትን አግባብነት
ለመመርመር ሲባል ቀርቧል፡፡ መልስና የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል፡፡ ተጠሪ ሚያዝያ 12
ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
እንዳልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል ተከራክሯል፡፡ አመልካቾችም ግንቦት 4 ቀን 2013
ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና


የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን
የሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ
ስህተት መኖር አለመኖሩን ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም በስር
ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ሟች ወ/ሮ ዓለም ፀሀይ እያሱ
በ29/6/1992 ዓ/ም ባደረገችው ኑዛዜ መሰረት የውርስ ንብረቱ ክፍፍል ይደረግልን ሲል ጠይቆ
የአሁን አመልካቾችም መልስ ሰጥተውበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራክሮ
በመ/ቁጥር 48597 ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ የሟች የውርስ
ንብረቶች ሟች በ29/6/1992 ዓ/ም ባደረገችው ኑዛዜ መሰረት እንዲፈጸም ይሄውም 1. በአዲስ
አበባ ከተማ ወረዳ 08 ቀበሌ25 የቤት ቁጥር 068 ከሆነው ቤት ጋር ተጠቃሎ የሚገኘውን እና
አሁን ደግሞ በእነ አላዛር ዳዊት ስም በተዘጋጀው በቤት ካርታ ውስጥ የሚገኘውን በኑዛዜ አገላለጽ
በወቅቱ የእቃ መሸጫ ሱቅ ተብሎ የተለየውን ቤት ከኑዛዜ በኋላ በዚህ ቤት ላይ ለውጥ
የተደረገበትም ቢሆንም አሁን ባለበት ሁኔታ ተለክቶ ለወ/ሮ ቅድስት ቢያዝን ተከፍሎ እንዲሰጥ፡፡
2. በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 08 ቀበሌ 25 የቤት ቁጥር 068 ከሆነው ቤት ጋር ተጠቃሎ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚገኘውን እና አሁን ደግሞ በእነ አላዛር ዳዊት ስም በተዘጋጀው በቤት ካርታ ውስጥ ተጠቃሎ
የሚገኘውን በኑዛዜ አገላለጽ በወቅቱ አቶ ጌታቸው ዳንደና ምግብ ቤት አድርጎ ይነግድበት
የነበረውን ምግብ ቤት ተብሎ የተለየውን ቤት ከኑዛዜው በኋላ በዚህ ምግብ ቤት በነበረው ቤት
ላይ የተደረገ ለውጥ ቢኖርም አሁን ባለበት ሁኔታ ተለይቶ እና ተለክቶ ለአቶ ጌታቸው ዳንደና
ተከፍሎ አንዲሰጥ፡፡ 3. ከዚህ በላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ ለወ/ሮ ቅድስት ቢያዝን እና ለአቶ
ጌታቸው ዳንደና የተወሰነላቸው ሱቅና ምግብ ቤት ለተጠሪዎች ከተሰጠ በኋላ የሚቀረውን
በአ/አበባ ከተማ ወረዳ 8 ቀበሌ 25 የቤት ቁጥር 068 የሆነው ቤት እና በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በእነ
አላዛር ዳዊት ስም በተዘጋጀው ካርታ የሚታወቀው ዋና መኖሪያ ቤት ከነ ከፍት ይዞታዎቹ
ከሌሎቹ ወራሾች በአብላጫነት ተከፍሎ ለአቶ አላዛር ዳዊት አንዲሰጥ ሲል ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ
በግልጽ እንደሚያመለክተው ለአሁን 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች የውርስ ንብረት ክፍፍሉ ለወ/ሮ
ቅድስት ቢያዝን የእቃ መሸጫ ሱቅ የነበረው ከኑዛዜ በኋላ በዚህ ቤት ላይ ለውጥ የተደረገበትም
ቢሆንም አሁን ባለበት ሁኔታ እንዲሰጣት የሚልና ለአቶ ጌታቸው ዳንደና ምግብ ቤት የነበረው
ከኑዛዜው በኋላ በዚህ ምግብ ቤት ላይ የተደረገ ለውጥ ቢኖርም አሁን ባለበት ሁኔታ እንዲሰጠው
የሚል ነው፡፡ በመሆኑም የፍርድ አፈጻጸም ችሎቱ ለአሁን አመልካቾች እንዲሰጣቸው የተባሉት
ቤቶች ላይ ከኑዛዜ በኋላም በነዚህ ቤቶች ላይ የተደረገ ለውጥ ቢኖር አሁን ባለበት ሁኔታ
የተወሰነላቸው በመሆኑ ከዚሁ ውሳኔ አንጻር አይቶ ማስፈጸም ሲቻል ማብራሪያ በሚል ምክንያት
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቤቶቹን ኑዛዜውን መሰረት በማድረግ በካሬ ሜትር ለይቶ
የሰጠው አዲስ ውሳኔ ከሥነ ሥረዓት ህጉ ውጪ የራሱን ውሳኔ በመለወጥ የተሰጠ ውሳኔ የሚሆን
ነው፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 373 (2) እንደ ፍርድ እንዲያስፈጽም ትእዛዝ የተላለፈለት ፍርድ
ቤት የተላለፈለትን ጽሁፎች በአንድ መዝገብ ውስጥ ይዞ ስለ ፍርዱ ትክክለኛነት ወይም
በግልባጮቸ ላይ ስለ ሰፈረው ነገር ሌላ መግለጫና ማብራሪያ ሳይጠይቅ በተሰጠው ትእዛዝ
መሰረት ማስፈጸም አለበት፡፡ ስለሆነም የፍርዱን ወይም የትእዛዙን ወይም የግልባጩን
ትክክለኛነት የሚያጠራጥር ልዩና በቂ ምክንያት ያጋጠመው እንደሆነ ይህንኑ መዝግቦ ማረጋገጫ
የሚሆን ማስረጃ አንዲላክለት ለመጠየቅ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ
ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ቁጥር 48597 ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ
ቅሬታ ያለው፣ በኑዛዜው መሰረት ውሳኔ አልተሰጠኝም የሚል ወገን ወይም ውሳኔው ግልጽ
ያልሆነና የማይፈጸም ነው የሚል ወገን ካለ ቅሬታውን በይግባኝ ለሚያየው ፍ/ቤት አቅርቦ
ማሳረም እንጂ በማብራሪያ መክንያት መጀመሪያ ከተሰጠው ውሳኔ የተለየ ውሳኔ መስጠት የሥነ
ሥረዓት ህጉ የማይፈቅድና ህጋዊ መሰረትም የሌለው ነው፡፡ በሌላ በኩል በዚህ ጉዳይ የፌደራል
መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ቁጥር 48597 ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት
በሰጠው ውሳኔ የአሁን አመልካቾችና የአሁን ተጠሪ ቅሬታ አቅርበውበት እስከ ፌደራል ጠቅላይ
ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ውሳኔ ያገኘ ጉዳይም ነው፡፡ የአሁን ተጠሪም በዚሁ ማብራሪያ
ተብሎ ውሳኔ በተሰጠበት ጉዳይ የማብራሪያ ትእዛዝ ሳይሰጥበት በፊት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦበት
እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ውሳኔ ያገኘ ሲሆን ውሳኔ ባገኘ ጉዳይ
እንደገና በማብራሪያ ምክንያት አዲስ ውሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 758936 የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት
የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 48597 መጋቢት 2 ቀን
2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ማብራሪያ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት
ተሽረዋል፡፡
2. በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

3. በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የፌደራል


የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ኮ/ቀ/ም/ችሎት የመ/ቁጥር 76038 ላይ የተሰጠው የአፈጻጸም እግድ
ተነስቷል፡፡ ይጻፍ፡፡
4. የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል፡፡
5. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 203538

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

ቀነአ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች፡- አቶ ሳቢት አባ ዲንካ- ቀረቡ

ተጠሪ፡- አቶ ጣሂር አባ ዲንካ- ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 26/06/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የሲግሞ

ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 34088 በቀን 20/06/2013 ዓ.ም፣ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 54191

በቀን 25/03/2013 ዓ.ም፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 224595 በቀን 22/04/2013 ዓ.ም

እንዲሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 334929 በቀን 20/05/2013 ዓ.ም

የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ

ነው። ክርክሩ የውረስ ይዞታ መሬትን የተመለከተ ሲሆን የጀመረው በወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች

ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በቀን 25/03/2012 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ እናቴ ወ/ሮ አቶሜ አባፎጊ በቀን

20/02/1991 ዓ.ም በሞት ተለይታለች፤ የሟች ወራሽ የሆነው ልጆች ከሳሽና ተከሳሽ ብቻ ነን፤ እናችን

ትታው ያለፈችው በሁለት ቦታ የሚገኝ ይዞታ ሲሆን በ1ኛው ቦታ ስፋቱ 20 በ 80 የሆነ አዋሳኙ በክሱ

የተገለፀው እና በግምት 2000.00 ብር የሚያወጣ ባህር ዛፍ፤ እንዲሁም 2ኛው ቦታ ስፋቱ 20 በ 30

የሆነ አዋሳኙ በክሱ የተገለፀው የሚገኝ ሲሆን ተከሳሽ የውርስ ድርሻየን ከህግ ውጪ ይዞ ስለከለከለኝ

ድርሻየን ግማሹን እንዲያካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪ በሰጡት መልስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት እናታችን ከሞተች 20 አመት ስለሆነ

ክሱ በይርጋ ቀሪ ሊሆን ይገባል ካሉ በኋላ በፍሬ ነገር መልሳቸው ደግሞ 1ኛው ቦታ 20 በ 80 የሆነውና

ባህርዛፍ እንዲሁም 2ኛው ቦታ 20 በ30 የሆነው ይዞታ የውርስ መሬት ሳይሆን የግል ይዞታዬ ነው፤

አባቴ በህይወት በነበረ ጊዜ የሰጠኝ ነው፤ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በይዞታው እየተጠቀምኩበት ስለሆነ

ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ክርክሩንና ማስረጃ ከሰማ በኋላ በ1ኛ ቦታ ያለው መሬት በሚመለከት ክሱ

በይርጋ ቀሪ ነው፤ በ2ኛ ቦታ ላይ ያለው መሬት በተመለከተ የግራ ቀኙ ምስክሮች በተመሳሳይ ቃል

የመሬት ይዞታው የውርስ መሆኑን አረጋግጠዋል፤ ተከሳሽ ይህ መሬት ይዞታ አባቴ በህይወት በነበረ ግዜ

በስጦታ የሰጠኝ ነው ከማለት ውጭ በሚያሳምን ሁኔታ ተቀባይነት ባለው መልኩ አባቱ መስጠቱን

የሚያሳይ እንዲሁም የግሉ መሆኑን የሚያስረዳ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር፣ የግብር ደረሰኝ

ወይም መሬቱ በስሙ መኖሩን እና መጠቀሙን የሚያሳይ ማስረጃ አልተገኘም፤ አከራካሪውን ይዞታ

ሲጠቀሙበት የነበሩበት ስለሆነ ወራሾች ለመውረስ መብት ያላቸው በመሆኑ 2ተኛውን የመሬት ይዞታ

እኩል እንዲካፈሉ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት እና ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት

ይግባኝ ሰሚ እንዲሁም የሰበር አቤቱታ ለክልሉ ሰበር ሰሚ ቢያቀርቡም ቀባይነት አላገኙም፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ነው። አመልካች ባቀረቡት ማመልከቻ የስር ወረዳ ፍ/ቤት

ከአከራካሪው 2ኛ ቦታ 20 በ30 በእኩል እንድንካፈል ወስኖልኝ 1ኛው ቦታ 20 በ 80 የሆነውን ተጠሪ

ያለአንዳች ምክንያት ከነድርሻዬ ጭምር ይዞ እያለ ተጠሪ በ3 አመት ይርጋ ክሱ ቀሪ ይሆናል ስላለ ብቻ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍ/ቤቱ በአግባቡ ሳያጣራ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው ምክንያቱም ይዞታውን እስከ 2011

ዓ.ም ከተጠሪ ጋር አብረን ስንጠቀም ስለቆየን ከይርጋ ጋር አይገናኝም፤ ተጠሪ ታናሼ በመሆኑ ቤተሰቦቼ

ለእኔ ትተው በመሞታቸው አብረን እስከ 2011 ዓ.ም ስንጠቀም ቆይተን በ2011 ዓ.ም ሁከት

ፈጥሮብኝ ተጋጭተን ከዛ በኋላ መሬቱን ፈቅደን ወደን ለመከፋፈል አሰብን እንጂ የተጠሪ የግል ይዞታ

አይደለም፡፡ አባቴ አከራካሪውን 20 በ 80 የሆነ ይዞታ በስጦታ ለተጠሪ አልሰጠም እንጂ ቢሰጥም ህጋዊ

የስጦታ ፎርማሊቲ ያላሟላ እና በገጠር መሬት አዋጅ 133/98 አንቀጽ 23/4 መሰረት እና ሰበር በመ/ቁ

115399 በሰጠው ትርጉም መሰረት አግባብ ባለው አካል ያልተመዘገበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፡፡

ተጠሪ አባቱ በህይወት እያለ በስጦታ መሰጠቱን እያመነ እና ምስክሮችም በስጦታ ከአባቱ እንደተላለፈ

እየመሰከሩለት በ1ኛው ቦታ ድርሻውን ተካፍሎ በ2ኛው ቦታ 20 በ 80 የሆነውን ከ20 አመት በፊት

ተላፎልኛል የሚለው ሚዛናዊነት የሌለው በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ተሽሮ ሁሉንም ቦታ በጋራ

እንድንካፈል ይወሰንልኝ በማለት ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ የክርክር መነሻ የሆነውና ተጠቅሶ የቀረበው 20 በ80

ሜትር ይዞታ በግራ ቀኙ መካከል ሳይካፈል የታለፈበት አግባብነት ለማጣራት በሚል ጉዳዩ ለዚህ ሰበር

ችሎት እንዲቀርብና ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡

ተጠሪ ባቀረቡት መልስ የስር ፍ/ቤቶች የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረጉበት መነሻ ተጠሪ

ያቀረብኩትን የመጀመሪያ ደረጃ የይርጋ መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ሲሆን መቃወሚያውም

የውርስ ጥያቄው እናታችን ከሞተች 20 አመት ካለፈው በኋላ የቀረበ በመሆኑ እና አከራካሪውን

ንብረት አመልካች በተጠሪ መያዙን ካወቀ ከ3 አመት በላይ ካለፈ በኋላ የቀረበ በመሆኑ ነው፡፡

አመልካች እናታችን በቀን 20/02/1991 ዓ.ም እንደሞተች በግልጽ ያስቀመጠው ሲሆን አቤቱታውን

ያቀረበው ደግሞ በቀን 25/03/12 ዓ.ም ነው፡፡ በሌላ በኩል ተጠሪ ይዞታውን በእጄ አድርጌ ከ1987

ዓ.ም ጀምሮ ስገለገልበት 25 አመት ያለፈኝ መሆኑን ያቀረብኳቸው ምስክሮች በሚገባ ያስረዱ

ከመሆኑም በተጨማሪ የአመልካች ምስክሮችም ይዞታውን አመልካች የውርስ ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት

ለረጅም ግዜ ስገለገልበት የነበርኩ መሆኑን መስክረዋል፡፡ አመልካች በአቤቱታው ይዞታውን እስከ 2011

ዓ.ም አብረን ስንጠቀም ነበር በሚል ያቀረበው ከእውነት የራቀ ሲሆን ተጠሪ ለብቻዬ ስገለገልበት የቆየ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሆኑን በስር ፍ/ቤት በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ አቤቱታው እናታችን ከሞቱ 20 አመት በኋላ

የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000 መሰረት የቀረበው የውርስ ጥያቄ በማንኛውም አስተያየት

ተቀባይነት የለውም፡፡ አመልካች በመብቱ ተጠቅሞ የውርስ ጥያቄ እንዳያቀርብ በህግ ፊት ተቀባይነት

ያለው ምክንያት የነበረው ስለመሆኑ ማስረዳትም አልቻለም፤ እንዲሁም ይርጋው ከመቆጠር መቋረጥ

የሚያስችል ምክንያት የነበረ ስለመሆኑም በስር ፍ/ቤት የቀረበ መከራከሪያ የለም፡፡ በመሆኑም የስር

ፍ/ቤት በአመልካች የቀረበው የውርስ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት የሰጠው ውሳኔ ምንም

አይነት የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት በመሆኑ ውሳኔው እንዲጸና በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካችም

በመልስ መልሳቸው አቤቱታቸውን በማጠናከር አቅርበዋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን የግራ ቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት

ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የተፈጸመ የህግ ስህተት መኖር አለመኖሩን

መርምረናል፡፡

እንደሚታወቀው ከውርስ ሃብት ጋር በተያያዘ ወራሽ ነኝ የሚል ወገን መብቱንና የውርስ

ንብረቶቹ በሌላ ወራሽ መያዛቸውን ካወቀ ከሶስት ዓመት በኃላ የሚያቀርበው የወራሽነት ክስ

ተቀባይነት እንደማይኖረው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000(1) ስር ተመልክቷል፡፡ ይህን የይርጋ ድንጋጌ አስመልክቶ

ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 26422 እና 20295 እንዲሁም በሌሎች በርካታ መዛግብት አስገዳጅ

ትርጉም ሰጥቷል፡፡ በሌላም በኩል በመጀመሪያው ፍርድ ቤት ያልተነሳውን ክርክና ያልቀረበውን አዲስ

ነገር ይግባኝ ሰሚው (የበላይ) ፍርድ ቤት ለመቀበል አይችልም፡፡

በተያዘው ጉዳይ አመልካች በስር ፍርድ ቤት እናታቸው ወ/ሮ አቶሜ አባፎጊ በቀን

20/02/1991 ዓ.ም መሞታቸውን ገልፀው ለወራሾች ሊተላለፍ የሚገባውን ሁለት ቦታ ላይ ያለ

ይዞታና ባህር ዛፍ ድርሻቸውን ተጠሪ እንዲያካፍላቸው የጠየቁት በቀን 25/03/2012 ዓ.ም ባቀረቡት

ክስ ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው በግልፅ ክሱ በይርጋ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት መቃወሚያ

አቅርበዋል፡፡ ስለሆነም ክርክሩ በወራሾች መካከል በመሆኑና ክሱ የቀረበው አውራሽ ከሞቱ ከ 20

ዓመት በኃላ በመሆኑ ይርጋ መቆጠር የሚቋረጥበት ምክንያት ስለመኖሩ ክርክርና ማስረጃ እስካልቀረበ

ድረስ ክሱ ከፍሲል በተጠቀሰው የህግ አግባብ በይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በውርስ ይዞታው እስከ 2011 ዓ.ም ከተጠሪ ጋር አብረን ስንጠቀም ቆይተናል

በማለት በዚህ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ቢገልፁም ይህን ክርክራቸውን በስር ፍርድ ቤት

ማቅረባቸውን መዝገቡ አያሳይም፡፡ በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳው ክርክር በዚህ ፍርድ ቤት

የሚቀርብበትና ተቀባይነት የሚያገኝነት የህግ አግባብ አግባብ የለም፡፡

ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት በ1ኛው ቦታ ያለውን መሬት በሚመለከት ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው

ብሎ 2ተኛውን የመሬት ይዞታ እኩል እንዲካፈሉ በማለት ውሳኔ መስጠቱ አመልካችን የጠቀመ ነው

ከሚባል በቀር ከአመልካች አንጻር ውሳኔው የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ ተከታዩንም ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የሲግሞ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 34088 በቀን 20/06/2013 ዓ.ም፣ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

በመ/ቁ 54191 በቀን 25/03/2013 ዓ.ም፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 224595 በቀን

22/04/2013 ዓ.ም እንዲሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 334929

በቀን 20/05/2013 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔና ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. እግድ ካለ ተነስቷል፡፡

3. የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ.መ.ቁ. 203654
ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1. ቤተልሄም ጌቱ አለሙ

2. እንግዳ ወርቅ አይናለም

3. አዜብ ጌታሁን

4. ህይወት ጌታቸው ታደሰ አልቀረቡም

5. ሩሚያ ጁሀር ኑሬ

ተጠሪ፡- የፌ/ጠ/ ዐቃቤ ህግ

መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር
አቤቱታ በሐረሪ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መ.ቁ. 05450
የካቲት 01 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠውን ብይን፤ በማጽናት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
መ.ቁ. 00159 የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በሐረሪ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት
በአጭሩ፡- የሙስና ወንጀል አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31(1) እና (2) በመተላለፍ አመልካቾች
የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው፡፡ የአሁን አመልካቾች ክሱን በሚመለከት ያቀረቡት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መቃወሚያ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 78(2)፤ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማደራጀ አዋጅ
ቁጥር 322/96 አንቀጽ 2 እና በአዋጅ ቁጥር 434/97 መሰረት ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም፤
አመልካቾች እምነት አጉድለዋል የተባለበት የግል የጤና አገልግሎት ከሚሰጥ ድርጀት ጋር በተያያዘ እንጂ
የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የመንግስት የልማት ድርጅት ባለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 ስር ክስ
ሊቀርብ አይገባም በማለት ከክሱ በነፃ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(2) በክልል መንግስት ስር የሚወድቁ የሙስና
ወንጀሎች በሚመለከት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ
በዚህ ረገድ የቀረበው መቃወሚያ ውድቅ አድርጎታል፤ ሆኖም ግን የግል ተበዳይ ሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል
ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በህክምና ባለሙያዎች በግል በራሳቸው ሀብት እና ንብረት የተቋቋመ የግል
ኩባንያ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 2(4) አንቀጸ 5፣6 እና 7 መሰረት በህዝባዊ ድርጅት
ውስጥ የሚካተት ኩባንያ አይደለም፤ በመሆኑም አመልካቾች የግል ተበዳይ ሐረር ሆስፒታል ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ማህበር ሰራተኞች ሆነው ለተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ክስ አዋጅ ቁጥር 881/2007
ተፈጻሚነት የለውም በማለት በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

ተጠሪ ይህን ብይን በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
አቅርቧል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤትም በአዋጅ ቁጥር 2(4) ስር “ህዝባዊ ድርጅት” ለሚለው ከተሰጠው
ትርጓሜ አግባብነት ያለው “ኩባንያ” የሚለው አገላለጽ አንቀጽ 2 (6) “በህዝባዊ ድርጅት የተቋቋሙ ኃላፊነቱ
የተወሰነ የግል ኩባንያ ሲሆን የሽርክና ማህበር ያጠቃልላል” በማለት የቃሉን ትርጉም ተሰጥቶበታል
በመሆኑም ከአዋጁ አጠቃላይ መንፈስ ህዝባዊ ድርጅት አግባብነት ያለው ኩባንያ እና የህዝባዊ ድርጅት
ሰራተኞ አገላለጾች በህጉ የተሰጣቸው ትርጉም አዋጅ ለትርፍ የተቋቋሙ የግል ተቋማት ላይ ተፈጻሚነት
እንዳለው በግልጽ የተመለከተ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩ በአዋጁ አይታይም በማለት የሰጠውን ብይን
ሽሮ በአመልካቾች ላይ የቀረበው ክስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ የሚመለከት ጉዳይ ስለሆነ
የስር ፍርድ ቤት ጉዩን እንዲያየው በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡ ይህንኑ ብይን በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ከአዋጅ ቁጥር 881/2007 ይዘት እና አላማ ውጪ አዋጁ የግል
ድርጅት ሰራተኞችም ላይ ተፈጻሚነት አለው በማለት የሰጠው ብይን አንቀጽ 2(4) ስር የተሰጠውን የህግ
ትርጉም የሳተ መሆኑን እንዲሁም ለጭብጡ እና ለብይኑ ዝርዝር ምክንያት ያደረገውን የህግ ትንታኔ በምን
ምክንያት ውድቅ እንዳደረገው ሳይገለጽ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን ብይን መሻሩ ይህም በክልሉ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መጽናቱ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር
ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአሁን አመልካቾች የሚሰሩበት ሆስፒታል ህዝባዊ ድርጅት ነው
በሚል በአዋጅ ቁጥር 881/07 አንቀጽ 31 በሙስና ወንጀል ሊከሰሱ ይገበል ተብሎ የተወሰነበትን አግባብ
ከዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2 ንዑስ ፣ 4 እና ተያይዞ ካሉት ድንጋጌዎች መሰረት መጣራት ያለበት መሆኑ
ስለታመነበት ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ
ተደርጓል፡፡

የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የግል ተበዳይ የሆነው የሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
የገንዘብ ምንጩ ከአባላት በተሰበበሰበ በአክሲዮን ግዥ በተገኘ ገንዘብ ከሚሰጠው የህክምና አገልግሎ ባፈራው
ገንዘብ፣ ንብረት እና ሀብቶች የሚስተዳደር የግል ዘርፍ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32/2
ስር የሚወድቅ ሲሆን አመልካቾች በዚሁ ህዝባዊ ድርጅት ሰራተኞች በመሆናቸው በዚሁ አዋጅ አንቀጽ
32(2) መሰረት ሊጠየቁ ይገባቸዋል፤ የአዋጁ ተፈጻሚነት በመንግስት ሰራተኞች ላይ ብቻ ተደርጎ መወሰዱ
ከአዋጁ ይዘት እና አላማ ጋር የሚፃረር ነው፤ በመሆኑም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

እንደመረመርነውም በተያዘው ጉዳይ አመልካቾች የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽማችኋል በሚል የሙስና
አዋጅን ጠቅሶ ተጠሪ ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን የሙስና ወንጀሉ ተፈፀመ የተባለውም አመልካቾች
ሲሰሩበት የነበረው የግል ተበዳይ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡
ከማስቀረቢያ ነጥቡ አኳያ ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው የግል ተበዳይ ድርጅት ህዝባዊ ድርጅት ሊባል
የሚገባው ነው ወይንስ አይደለም? የሚለው በመሆኑ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በጭብጥነት ተይዞ ሊመረመር
የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የግል ተበዳይ የሆነው የሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የገንዘብ ምንጩ ከአባላት በተሰበበሰበ
በአክሲዮን ግዥ በተገኘ ገንዘብ ከሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ባፈራው ገንዘብ፣ ንብረት እና ሀብቶች
የሚስተዳደር ነው፡፡
በአዋጅ ቁጥር 881/2007 አስቀድሞ የነበረውን የሙስና አዋጅ ያሻሻለበት ዋና አላማን በመግቢያው
ሲያብራራ ፡- “--------- የሙስና ወንጀሎቹ ማካተት የነበረባቸውን ተመሳሳይ ተግባራት በተለይም ከህዝብ
የተሰባሰበ ወይም ለህዝብ ተብሎ የተሰባሰበ ሀብት በሚያስተዳድሩ የግል ዘርፍ አካላት የሚፈፀሙ ተመሳሳይ
ተግባራትን በአግባቡ ያላካተቱ በመሆናቸው እነዚህኑ ማካተት በማስፈለጉ፣----"
በሚል ዓላማውን ይዘረዝራል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 2/4 ስርጓሜ ስር፡- “ ህዝባዊ ድርጅት ማለት በማንኛውም አግባብ ከአባላት ወይም
ከህዝብ የተሰበሰበ ወይም ለህዝባዊ አገልግሎት ታስቦ የተሰበሰበ ገንዘብ፣ ንብረት ወይም ሌላ ሃብትን
የሚያስተዳድር አካልና አግባብ ያለው ኩባንያን የሚያካትት የግል ዘርፍ ሲሆን፣ የሚከተሉትን አያካትትም፡-
ሀ. የሀይማኖት ድርጅትን፣
ለ/ የፖለቲካ ድርጅትን/ፖርቲን/፣
ሐ/የዓለም አቀፍ ድርጅትን፣ እና
መ/ ዕድርንና ተመሳሳይ ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ማህበርን፡፡ “
በሚል ይደነግጋል፡፡

እንዲሁም በአንቀጽ 2/6 ስር ፡- “ አግባብነት ያለው ኩባንያ ማለት በሕዝባዊ ድርጅት የተቋቋመ ኃላፊነቱ
የተወሰነ ኩባንያ ሲሆን እንደዚህ ዓይነት ኩባንያ ከሌሎች ጋር የሚቋቋመውን የሽርክና ማህበርን
ያጠቃልላል፣” በሚል ይደነግጋል፡፡

ወደ ያዝነው ጉዳይ ስንመለስ አመልካቾች የሚሰሩበት የግል ተበዳይ የሆነው የሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል
ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የገንዘብ ምንጩ ከአባላት በተሰበበሰበ በአክሲዮን ነው፡፡ አክስዬን ማህበር ደግሞ ኩባንያ
እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ከላይ እንደተመለከትነው የቀድሞው የሙስና አዋጅ በአዲስ እንዲሻሻል የተፈለገበት
ዓላማ የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣የዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ዕድሮች እንዲሁም እነዚህን
የመሳሰሉ የሃይማኖት እና የባህላዊ ማህበራት እስካልሆኑ ድረስ የሙስና ወንጀል በህዝባዊ ድርጅቶች እና
በኩባንያዎች ውስጥ በሚፈፀመ ጊዜ በአዋጁ የማይሸፈን በመሆኑ በአዋጁ እንዲጠቃለል የተደረገ መሆኑን
ነው፡፡
የግል ተበዳይ ኩባንያ ምንም እንኳን በግለሰቦች የተመሠረተ ቢሆንም ነገር ግን በአዋጁ ድንጋጌ መሠረት
በኩባንያ ውስጥ የሙስና ወንጀል በተፈፀመ ጊዜ በሙስና አዋጅ ክስ የሚመሰረት መሆኑን የሚያስገነዝብ
በመሆኑ በአመልካቾች ላይ የሙስና አዋጅን በመጥቀስ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል በሚል
የቀረበውን ክስ የስር ፍ/ቤት ተገቢ ነው ሲል የደረሰበት መደምደሚያም ሆነ የበላይ ፍ/ቤት መቀበሉ
መሠረታዊ የህግ ስህተት ፈጽማል ለማለት የማይቻል ስለሆነ ሊፀና የሚገባው ነው ብለን ተከታዩን
ወስነናል፡፡

ውሳኔ
1) የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ ዐዐ159 በ25/ዐ6/2ዐ12
ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ፣የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰማ
ችሎት በመ/ቁ/ዐ545ዐ በ1/6/2ዐ13ዓ.ም. በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ፣
፣የሀረራ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/ 2ዐ95ዐ ጥር ዐ5 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም.
በዋለው ችሎት የሰጠው ብይን በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 195/1/ መሠረት ፀንቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2) የውሣኔው ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረስ፡፡


መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

የሃሳብ ልዩነት
እኔ ስሜ በተራ ቁጥር 3 የተመለከተው ዳኛ በያዝነው ጉዳይ የግል ተበዳይ ሆኖ የቀረበው
የሐረር ጠቅላላ ሆስፒታል ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዋጁ መሠረት ህዝባዊ ድርጀት በመሆኑ አዋጅ
ቁጥር 881/2ዐዐ7 ን መሠረት በማድረግ በአመልካቾች ላይ ክሱ መቅረቡ አዋጁን መሠረት
ያደረገ ነው በማለት በአብላጫ ድምፅ የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማፅናት በተሰጠው ውሳኔ
የማልስማማ በመሆኑ የልዩነት ሀሳቤን እንደሚከተለው አስፍሬያለሁ፡፡
የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ ተሻሽሎ የወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2ዐዐ7 ወደ
ኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ የመጣው የቀደሙት የሙስና ህጎች በወንጀል ድርጊትነት
መካተት የነበረባቸውን በተለይም ከህዝብ የተሰበሰበ ወይም ለህዝብ ተብሎ የተሰበሰበ
ሀብት በሚያስተዳድሩ የግል ዘርፍ አካላት የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራትን አካትተው
ያልተቀረፁ በመሆናቸው እነዚህን ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መሆኑ በአዋጁ
መግቢያ ላይ በግልፅ ተመልክቷል፡፡ ህጉ ከላይ እንደተመለከተው በመግቢያው ላይ የግል
ዘርፍ / private sector / የሚለውን ሀረግ የተጠቀመ ቢሆንም በህጉ የትርጉም ክፍል
አንቀፅ 2/4/ እና 2/5/ እንዲሁም በዝርዝር የወንጀል ድንጋጌዎቹ ላይ በተደጋጋሚ
የተጠቀመው ህዝባዊ ድርጅት /public organization/ የሚለውን ከማካተት አንፃር
ጠበብ ብሎ የተቀረፀውን ሀረግ ነው፡፡ በህጉ አንቀፅ 2/4/ የተመለከተው ህዝባዊ ድርጅት
ለሚለው ሀረግ የተሰጠው ትርጉም ሰፋ ብሎ የተመለከተ መሆኑን በማስመልከት በሥራ
ባልደረቦቼ የተሰጠውን ገለፃ የምስማማበት ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ አንድ ድርጅት ህዝባዊ
ድርጅት ለመባል በሁለት መስፈርቶች ማለትም በምንጭ መስፈርት እና /ወይም በግብ
መስፈርት / The source-purpose test/ ሊሰፈር የሚገባ መሆኑን ያመለክታል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እነዚህ መስፈርቶች በአንድነት ማሟላት አለባቸው ወይስ የለባቸውም በሚለው ነጥብ


ላይ የዘርፉ ፀሀፍት የተለያየ አቋም የሚያንፀባርቁ ቢሆንም አንድ ድርጅት ህዝባዊ
ድርጅት ነው ለማለት መስፈርቶቹ በአንድ ላይ / cumulatively / መሟላት አለባቸው
ብዬ አላምንም፡፡
ስለዚህ የገንዘብ ምንጭ ህዝባዊ መሆኑ አልያም ለህዝባዊ አግልግሎት የተሰበሰበ ሀብት
ድርጀቱ ማንቀሳቀሱ ድርጅቱን ህዝባዊ ድርጅት ለማለት በቂ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እዚህ
ጋር በህጉ አንቀፅ 2/4/ የገንዘቡን ምንጭ አስመልክቶ በማንኛውም አግባብ ከአባላት
ወይም ከህዝቡ የተሰበሰበ ሀብት በማለት ህጉ ምንጩን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ትርጉምን
የተከተለ ቢሆንም ኩባንያን አስመልክቶ ግን የተለየ ትርጉምን የተከለ መሆኑን
በሚያሳይ መልኩ አግባብነት ያለውን ኩባንያን የሚያካትት መሆኑን በሚያመለክት
መልኩ የተቀረፀ ሲሆን አግባብነት ያለው ኩባንያ ማለት ምን ማለት እንደሆን ደግሞ
በአንቀፅ 2/6/ በግልፅ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ትርጉም መሠረት አግባብነት ያለው ኩባንያ
ማለት … any Private limited company which is established through the
contribution of shares…በማለት መመልከቱ ህጉ አግባብነት ያለው ኩባንያ ከሚለው
ሀረግ ትርጉም አንፃር ጠበብ ያለ ትርጉም መከተሉን ያሳያል ፡፡ ይህ ትርጉም አክሲዮንን
ለህዝብ በመሸጥ የተቋቋሙትን ኩባንያዎች( companes established by share
subscription by the public at large) ብቻ የሚያጠቃልል በመሆኑ መስራቾች
(Founders ) ብቻ ተደራጅተው ያቋቋሟቸው ኩባንያዎች (አክሲዩን ለህዝቡ በመሸጥ
ካፒታላቸውን በማሳደግ ህዝባዊ ድርጅትነትን ካልተጎናፀፉ በስተቀር) እንዲሁም ሁለት
ግለሰቦች ገንዘብ ወይም ንብረት አዋጥተው ያቋቋሙት ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ አሁን
ባለው ነባራዊ ሁኔታም የቤተሰብ አባላት የሚያቋቁሙት ከህዝባዊነት ይልቅ ግለሰባዊነት
የሚንፀባረቅበት ተቋም በመሆኑ የፀረ ሙስና ህጉ ተሻሽሎ የወጣው እንደዚህ አይነት
ምንም አይነት ህዝባዊነት የማይታይባቸውን ድርጅቶች ለመጠበቅ በዚህ አግባብም
ታላላቅ የሆኑ የሙሰና ወንጀሎችን ከመዋጋት ይልቅ ተቋሙ ጥቃቅን በሆኑ ህዝባዊ
ድርጅት ባልሆኑ ድርጀቶች ጊዜውንና ገንዘቡን እንዲሁም የሰው ሀይሉን ለማባከን ነው
ብዬ አላምንም፡፡
ስለሆነም ማንኛውም ሀላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ህዝባዊ ድርጅት ነው በሚል በጥቅል
የሚወሰድ ትርጉም የአዋጁን ግብ መሠረት ያደረገ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ከዚህ ይልቅ
የድርጅት ህዝባዊ መሆን እንደ ጉዳዩ አግባብ / case by case / ሊታይና ሊመረመር
ይገባል፡፡ መሠረታዊ መስፈርቱም ድርጅቱ አክሲዩንን ለህዝብ በመሸጥ የተቋቋመ ኩባንያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

(companies established by share subscripition by the public at large ) ነው


ወይስ አይደለም የሚለው ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ ትርጉምም ህጎችን
ወይም በህጎች ውስጥ የሚገኙ ድንጋጌዎችን ሀረጎችን እና ቃላቶችን ከአላማቸው አንፃር
አይቶ ትርጓሜ የመስጠት አስተሳሰብን የተከለ ዓላማዊነት (purposivism) ፅንሰ ሀሳብን
የተከተለ ነው፡፡ አሁን በያዝነው ጉዳይ የሐረር ጠቅላለ ሆስፒታል ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ህዝባዊ ድርጅት መሆን አለመሆን በዚህ አግባብ ተመርምሮ በሥር ፍርድ ቤቶች ለጉዳዩ
እልባት ያልተሰጠው በመሆኑ በዚህ አግባብ ተጣርቶ እንዲወሰን ጉዳዩ ለክልሉ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሊመለስለት ይገባ ነበር በማለት ከሥራ ባልደረቦቼ በሀሳብ ተለይቼያለሁ፡፡
የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ.203747
መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1. አንዳርጌ ከበደ ጠበቃ ክንፈ ዋለ ቀረቡ

2. ትዕግስት ከበደ

ተጠሪ፡- ሀብታሙ ላቀው- አልቀረቡም

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር
አቤቱታ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 142024 ጥር 21 ቀን 2012 ዓ.ም ተጠሪ
አከራካሪውን ቤት ሕዳር 05 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ገዝቶ የያዘ በመሆኑ ቤቱን ለቆ
ሊያስረክብ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 251737 ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ወሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡
በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን
ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ
09 ቀበሌ 07 ክልል ውስጥ በካርታ ቁጥር የካ/164566/03 የሚታወቅ ስፋቱ 150 ካ.ሜ የሆነ በአባታቸው
ስም የተመዘገበ ቤት ያላቸው መሆኑን፤ ተጠሪ በዚሁ ይዞታ ውስጥ የሚገኙትን ሰርቪስ ቤቶች አላግባብ
የያዘ እና ቤቱን እንዲለቅ ሲጠየቅ ከእናታችሁ ገዝቻለሁ በማለት ለመልቀቅ ፍቃደኛ አለመሆኑን፤ ሆኖም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ቤቱን የገዛ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ በቤቱ ማሕደር ላይም ሆነ በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የሌለ
መሆኑን በመግለጽ ተጠሪ ቤቱን ለቆ አንዲያስረክባቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ
ነው፡፡

የአሁን ተጠሪ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ ደግሞ
አከራካሪውን ቤት የአመልካቾች እናት ወ/ሮ ብርቱካን ጋሻውብዛ አመልካቾችን በመወከል እና በራሳቸውም
ስም ከወ/ሮ ጽጌ ከበደ እና ወ/ሮ ህብስተመና ከበደ ጋር በመሆን ሕዳር 05 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ
ውል በብር 17,000 የሸጡለት መሆኑን፤ አመልካቾች በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሆነው 1ኛ አመልካች በቀን
15/06/1997 ዓ.ም፤ 2ኛ አመልካች በቀን 21/06/1997 ዓ.ም እንዲሁም አመልካቾች በጋራ በመሆን በቀን
13/11/1997 ዓ.ም ለወላጅ እናታቸው ውክልና ሰጥተዋል፤ ውክልናውም ቤቱን እንዲሸጡ እና እንዲለውጡ
ስልጣን የሚሰጣቸው በመሆኑ በዚሁ ውክልና መሠረት ቤቱ ከተሸጠ በኋላ አላግባብ የቀረበው ክስ ወድቅ
ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ እና ከሚመለከተው አካል ስለጉዳዩ ተጣርቶ
እንዲቀርብለት ካደረገ በኋላ አመልካቾች ለእናታቸው ወ/ሮ ብርቱካን ጋሻውበዛ በሰጡት ውክልና መሠረት
እናታቸው ከወ/ሮ ጽጌ ከበደ እና ወ/ሮ ሕብስተመና ከበደ ጋር በመሆን አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ የሸጡለት
መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ቀርቧል ምስክሮችም ይህንኑ አስረድተዋል፤ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ
ጽ/ቤት አመልካቾች በማረሚያ ቤት ውስጥ ሆነው ለእናታቸው ውክልና ሰጥተው በቀን 18/11/1997 በጽ/ቤቱ
የተመዘገበ መሆኑን በማረጋገጥ ምላሽ ሰጥቷል፤ ውክልናው አመልካቾች በውርስ የሚያገኙትን ንብረት
የመሸጥ ስልጣን የሚሰጥ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ተጠሪ ቤቱን የገዛው አመልካቾች ለእናታቸው ውክልና
ከመስጠታቸው በፊት ህዳር 5 ቀን 1997 ዓ.ም ቢሆንም አመልካቾች የጠየቁት ዳኝነት አላግባብ ተጠሪ
የያዘውን ይዞታ ለቆ እንዲያሰረክባቸው ነው፤ አመልካቾች ቤቱ እንዲሸጥ ውክልና ከመስጠታቸው በፊት
ተጠሪ ቤቱን የገዛ ቢሆንም ውሉ የፈረሰ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተጠሪ ቤቱን አላግባብ ይዟል
ማለት ስለማይቻል ተጠሪ ቤቱን ለአመልካቾች ሊያስረክብ አይገባም፤ አመልካቾች ሕዳር 5 ቀን 1997 ዓ.ም
የተደረገው ውል ሊፈርስ ይገባል የሚሉበት ምክንያት ካላቸው ክስ የማቅረብ መብታቸው ተጠብቋል በማለት
ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል
ሲሆን ይዘቱም፡- የአከራካሪውን ይዞታ ስፋት 150 ካ.ሜ ሆኖ ሳለ ተጠሪ 220 ካ.ሜ ይዞታ በምን አግባብ
እንደገዛ አልተጣራም፤ ተጠሪ ገዛሁ በሚለው በ220 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ግብር ስለመክፈሉ ያቀረበው ማስረጃ
የለም፤ የአመልካቾች እናት የቤቱ ባለቤት ስለመሆኗ አልተረጋገጠም፤ የሽያጭ ውሉ አመልካቾች ለእናታቸው
ውክልና ከመስጣቸው በፊት መደረጉ በተረጋገጠበት ሁኔታ በሕግ አግባብ እንደተደረገ ውል ተቆጥሮ ተጠሪ
ቤቱን ሊያስረክብ አይገባም በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ
በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአሁን አመልካች ለእናታቸው ሰጡ የተባለው ውክልና ከቤቱ ሽያጭ
በኋላ የተደረገ ሆኖ ሳለ የጸና የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካቾች የውል ይፍረስ
ክስ ማቅረብ ነበረባቸው ተብሎ ክሳቸውን ውድቅ በማድረግ የመወሰኑን አግባብነት ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር
1723 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም
ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የአመልካቾች እናት የሽያጭ ውሉን ለመዋዋል የማይችሉ ስለመሆኑ
የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም፤ ቤቱን የሸጡልኝ የአመልካቾች እናት በፍርድ እስካልተከለከሉ ድረስ ውል
ለመዋዋል ይችላሉ፤ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን 220 ካ.ሜ ይዞታ ላይ የተሰራ ሁለት ክፍል ሰርቪስ
ቤት የገዛሁት በሟች አቶ ከበደ ወልደኪዳን ስም ተመዝግቦ ከሚገኘው 457.43 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ተቀንሶ
ነው፤ የሽያጭ ውሉ የተፈጸመው በአመልካቾች እውቅና እና ፍቃድ ስለመሆኑ ለእናታቸው የሰጡት ውክልና
ያሳያል፤ የሽያጭ ውሉ ጸንቶ ባለበት ሁኔታ ተጠሪ ከአሥራ አምሥት ዓመት በፊት በግዥ የያዝኩትን ቤት
ለአመልካቾች የማስረክብበት ሕጋዊ ምክንያት ስለሌለ ውሳኔው ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

አመልካቾች በማረሚያ ቤት ሆነው ለእናታቸው ወ/ሮ ብርቱካን ጋሻውበዛ ሰጥተውታል የተባለው ውክልና
በቀን 18/11/1997 ዓ.ም በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ቤት የተመዘገበ መሆኑ የተረጋጠ ፍርነገር ነው፡፡
ሆኖም ተጠሪ ቤቱን የገዛው አመልካቾች ለእናታቸው ውክልና ሰጥተውበታል ከተባለበት ከቀን 18/11/1997
ዓ.ም በፊት ሕዳር 5 ቀን 1997 ዓ.ም መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት መረጋገጡ በውክልናው ሕጋዊነት ላይ
ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ቤቱን ሸጠዋል የተባሉት የአመልካቾች እናት ወ/ሮ ብርቱካን
ጋሻውበዛ፤ ወ/ሮ ጽጌ ከበደ እና ወ/ሮ ሕብስተመና ከበደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 40/2 መሠረት በክርክሩ ተከፋይ
መሆን የሚገባቸው ናቸው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 43226 በሰጠው ውሳኔ በሕግ ያልተፈቀደና
የተከለከለ ሆኖ ሲገኝ ዳኞች ውሉ በቀረበላቸው ማንኛውም ጊዜ ሕጋዊ ውጤትና ተፈፃሚነት የለውም
በማለት ለመወሰን እንደሚችሉ በመግለጽ በየትኛውም እርከን ላይ ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች አስገዳጅ የሕግ
ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ከዚህ አንጻር ጉዳዩ ሲታይ አመልካቾች በውርስ የሚደርሳቸውን ድርሻ
እንዲሸጡላቸው ለእናታቸው ውክልና ከመስጠታቸው በፊት ተጠሪ ቤቱን መግዛቱ እስከተረጋገጠ ድረስ
የሽያጭ ውሉ ሕጋዊ መሆን አለመሆኑ ተመርምሮ የውሉ ሕጋዊ ዉጤቱ ምን እንደሆነ በቅድሚያ ምላሽ
ሊሰጠው ይገባል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩን በዚህ አግባብ በማየት በቅድሚያ በውሉ ሕጋዊ ውጤት ላይ ምላሽ
መስጠት ሲገባው የሽያጭ ውሉ ጸንቶ ባለበት ሁኔታ ተጠሪ ቤቱን ለቆ ሊያስረክባቸው አይገባም፤ አመልካቾች
ውሉ ሊፈርስ ይገባል የሚሉበት ምክንያት ካላቸው ክስ የማቅረብ መብታቸው ተጠብቋል በማለት የሰጠው
ውሳኔ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 43336 የሰጠውን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም የሚጥስ እና
አመልካቾችን ለተጨማሪ ክርክር የሚጋብዝ፤ ክርክሮች በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጪ እንዲቋጩ
ለማድረግ ታስቦ የወጣውን የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ዓይነተኛ ዓላማ ያላገናዘበ መሠረታዊ የሆነ
የክርክር አመራር ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ስለሆነም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ለእናታቸው ወ/ሮ ብርቱካን ጋሻውበዛ በቀን
18/11/1997 ዓ.ም የውክልና ሥልጣን ከመስጠታቸው በፊት ሕዳር 5 ቀን 1997 ዓ.ም ተደርጓል የተባለው
የቤት ሽያጭ ውል ሕጋዊ መሆን አለመሆኑን ቤቱን ለተጠሪ ሸጠዋል የተባሉትን የአመልካቾች እናት ወ/ሮ
ብርቱካን ጋሻውበዛ፤ ወ/ሮ ጽጌ ከበደ እና ወ/ሮ ሕብስተመና ከበደ ወደ ክርክሩ በማስገባት አግባብነት ያለውን
ትዕዛዝ በመስጠት ጉዳዩን አጣርቶ እና መርምሮ ውሳኔ እንዲሰጥበት ማድረግ ሥነ-ሥርዓታዊ ሆኖ
አግኝተነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 142024 በቀን 21/05/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 251737 ጥር
28 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ተሽሯል፡፡
2. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በውሳኔ የዘጋውን መዝገብ እንደገና በማንቀሳቀስ ከላይ
በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው መንገድ ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢውን እንዲወስን በማለት
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1 መሠረት ጉዳዩ ተመልሶለታል፡፡
3. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ

ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 203809

ቀን፡-26/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- 1. ወ/ሮ የብርጓል በላይነህ አልቀረቡም

2. አቶ ተክሌ ዝብሉ

ተጠሪ ፡- 1. ወ/ሮ እቴነሽ መብራት ወኪል ሙላቱ ባንቲጌ ቀረቡ

2. ወ/ሮ አስረሳች መብራት

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የይግባኝ ማስፈቃጃ አቤቱታን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል
ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የአዊ ብሔረሰብ
ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 01-18421 ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ/ም በሠጠው ውሳኔ ይግባኙን
ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የ60 ቀናት ጊዜው ያለፈባቸው በመሆኑ ጥር 20 ቀን 2013 ዓ/ም
በተጻፈ ማመልከቻ የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ በማቅረብ ጊዘው ያለፈው የኮሮና ወረሽኝ በሽታ በመኖሩ፣
በሚኖሩበት አካባቢ የጸጥታ ችግርና የትራንስፖርት ችግር ያጋጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ከአቅም በላይ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሆኑ ምክንያቶች መሆናቸውን በማንሳት ይግባኙን ማቅረብ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡ የአማራ ክልል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በአቤቱታው ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ካደረገ በኋላ ይግባኝ የሚባልበት
ፍርድ የተሰጠው ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ/ም ሲሆን የኮሮና ወረሽኝ የተከሰተው ደግሞ ከየካቲት ወር 2012
ዓ/ም በኋላ ነው፡፡ ፍርድ ቤቶች በኮሮና ወረሽኝ ምክንያት በከፊል ተዘግተው የነበረ ቢሆንም በሙሉ ሥራ
ከጀመሩ በኋላ አቤቱታው የቀረበው ዘግይቶ ከአምስት ወር በኋላ ነው፡፡ የአገሪቱ የጸጥታ ችግርም አልፎ
አልፎ የሚከሰት በመሆኑ አመልካቾች ይግባኝ ለማቅረብ ከወሰዱት የአንድ ዓመት ከሁለት ወር ጊዜ አኳያ
እንደበቂ ምክንያት የሚታይ አይደለም፤ በአመልካቾች ቸልተኝነት ጊዜው ያለፈ ስለመሆኑ ይግባኙን
እንዲያቀርቡ ሊፈቀድ አይገባም በማለት የቀረበው የማስፈቀጃ አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡

የሠበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካቾች የሠበር አቤቱታ ይዘትም አመልካቾች
ከምንኖርበት ሻኪሶ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ችግር፣ መንገድ መዘጋት፣ ኔትወርክ መቋረጥ እንደነበር
ማስረጃ አቅርበናል፡፡ በሽብር ኃይሎች የአመልካቾች ወኪል ታፍኖና ተደብድቦ ነበር፡፡ ውሳኔው የተሰጠበት
ፍርድ ቤት ከአመልካቾች አድራሻ አንጻር ሩቅ ነው፤ ከአቅም በላይ የሆኑ ምክንያቶች ስላጋጠመን ይግባኙን
እንድናቀርብ ሊፈቀድ ይገባል የሚል ሲሆን የሠበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ አመልካቾች በሚኖሩበት
አካባቢ የጸጥታ ችግር መኖሩ ማስረጃ በቀረበበት ሁኔታ ይግባኙ ጊዜው ያለፈው በአመልካቾች ቸልተኝነት
ነው መባሉ ተገቢነቱን ለማጣራት ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል በማለት ተጠሪዎች መልስ እንዲያቀርቡ
አዟል፡፡ ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ ይግባኙ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ጊዜ ያለፈበት ነው፤ አመልቾች በቂ
ምክያት ያላቀረቡ በመሆኑ ውሳኔው ሊጸና ይገባል ብለዋል፡፡ አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ የሠበር
አቤቱታቸውን አጠናክረው ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም አመልካቾች ያቀረቡት ይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ
ውድቅ መደረጉ ሕጋዊነቱን እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 323(2) መሠረት ይግባኝ የሚቀርበው ውሳኔው በተሰጠ በ60 ቀናት
ወስጥ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ የይግባኝ ማመልከቻው ጊዜ ያለፈበትና የማይመረመር ነው፡፡
አመልካቾች ይግባኝ ያቀረበቡትን ውሳኔ የሠጠው በአማራ ክልል የአዊ ብሔረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ/ም ነው፡፡ አመልካቾች ይግባኝ ግልባጭ እንዲሰጣቸው የጠየቁት አመት ከሁለት ወር
ጊዜ በኋላ ጥር 19 ቀን 2013 ዓ/ም ነው፡፡ ይሕም 60 ቀናት ጊዜው ያለፈ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ በዚህም
ምክንያት ይግባኝ ለሚቀበለው ፍርድ ቤት ጥር 20 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ ይግባኝ ማስፈቀጃ
አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ የፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ክርክር ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ወጭና ጊዜ ቆጣቢ
እንዲሁም ፍትሐዊ በሆነ ሁኔታ እንዲመራ ዓላማ አድርጎ የተቀረጸ ነው፡፡ አቤቱታዎች ሆኑ ክርክሮች
ሲቀርቡ ሕጉ ሊያሳካው ከፈለገው ግብ ጋር ተመዛዝኖ መወሰን አለበት፡፡ በውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ይግባኝ
በማቅረብ አቤቱታው እንዲመረመርለት ይግባኝ የማቅረብ መብት ያለው ቢሆንም መብቱ ለማስከበር ደግሞ
ጥንቃቄ የታከለበት ትጋት እንዲኖረው ሕጉ ይጠበቅበታል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካቾች የሚከራከሩት ጊዘው ያለፈው ከአቅም በላይ የሆኑ ምክንያቶች የኮሮና ወረርሽኝ በሽታ መከሰት፣
በሚኖሩበት አካባቢ የጸጥታ ችግርና የትራንስፖርት ችግር ያጋጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 326(1) እንደተመለከተው ፍርድ ቤቱ የቀረበው ምክንያት በቂ ስለመሆኑ ካመነበት
ይግባኙን እንዲያቀርቡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ ውሳኔ የተሰጠው ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ/ም ሲሆን በኢትዮጵያ
የኮሮና በሽታ በወረሽኝ መልክ የታወጀው ይግባኝ ማቅረቢያ 60 ቀናት ካለፈበት ጊዜ በኋላ በመሆኑ የኮሮና
ወረሽኝ በሽታ ይግባኙን በጊዜው ላለማቅረብ በቂ ምክንያት አይደለም፡፡ አመልካቾች በሚኖሩበት አካባቢ
የጸጥታ ችግርና የትራንስፖርት ችግር በመኖሩ ነው ይግባኙን በጊዜው ያላቀረብነው የሚለውን ምክንያት
በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት ችግሩ የሚያጋጥም መሆኑን ተቀብሏል፡፡ ነገር ግን አቤቱታውን ውድቅ
ያደረገው አመልካቾች የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ያለፈባቸው ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር ጊዜ መሆኑ ጋር
ተገናዝቦ ሲታይ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለዚህን ያሕል ጊዜ ይግባኝ እንዳያቀርቡ የሚከለክል ስለመሆኑ
አሳማኝ አይደለም በማለት ነው፡፡ ስለሆነም ይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤት በአመልካቾች
የቀረቡትን ምክንያቶች አመዛዝኖ ባለው ፍቅድ ሥልጣን አግባብ የወሰነው በመሆኑ በዚህ ችሎት ደረጃ
የሚመረመር መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አላገኘንበትም፡፡

ውሳኔ

1. የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 55100 የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ/ም የሠጠው ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሠረት ፀንቷል፡፡

2. ግራቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 ውሳኔው ለሥር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡


 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ 203882
መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1. አቶ ብርሃኑ ሻይ

2. ወ/ሮ ምህረት ሻይ አልቀረቡም ከተባለ በኋላ ጠበቃ ነብያት ግርማ ቀረቡ

3. ሲ/ር እየሩሳሌም ሻይ

4. ወ/ት አለምጸሐይ ሻይ

ተጠሪዎች፡-1. የአዲስ ከተማ ክፍለከተማ የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ አገልግሎት ፕሮጀክት ጽ/ቤት

2. የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ቤቶች አስተዳደር - ዐ/ህግ ለታ ባይሳ ቀረቡ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 03 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር
አቤቱታ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 276300 መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 254780 በቀን
01/03/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል
በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የከተማ ቤት ሁከት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካቾች ከሳሾች፤ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- በቀድሞ
አጠራር ወረዳ 05 ቀበሌ 15 በአሁኑ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ ቁጥሩ 1141 የሆነ ቤት
ከወላጆቻቸው በውርስ የተላለፈላቸው እና በቀን 24/05/2008 ዓ.ም በስማቸው ካርታ የተሰጣቸው መሆኑን፤
በዚሁ ቤት ግቢ ውስጥ አውራሾቻቸው በሕይወት እያሉ የዋናው ቤት አካል ሆኖ የሚጠቀሙበትን ማድቤት
እና መጸዳኛ ቤት ያለ መሆኑን፤ ወላጆቻቸው በሕይወት እያሉ ማድቤቱን በችግር ላይ ለነበረች ሴት ለጊዜው
ሰጥተዋት የነበሩ መሆኑን፤ ሆኖም አዋጁ ሲታወጅ የሴትየዋ ልጅ በወቅቱ ቀበሌ ይሰራ ስለነበር ስልጣኑን
ተጠቅሞ ቤቱን እንደተከራየ አድርጎ ቁጥር 1140 የሚል ቁጥር ያሰጠው መሆኑን፤ ግለሰቧም ቤቱን ለቃ
ለአውራሻቸው ሳታስረክብ የሄደች መሆኑን፤ አመልካቾች በይዞታቸው ስር አድርገው ሲጠቀሙበት የነበረ
መሆኑን፤ ሆኖም 1ኛው ተጠሪ በሰጣቸው ካርታ ላይ ይህንኑ ማድቤት እና መጸዳኛ ቤት የመንግስት ብሎ
በመስራት፤ 2ኛ ተጠሪም ቤቱ የራሴ ነው በማለት ሁከት እየፈጠሩባቸው የሚገኙ መሆኑን በመግለጽ
ተጠሪዎች የፈጠሩት ሁከት እንዲወገድ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን ተጠሪዎች በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ በሰጡት
መልስ የአመልካቾች አውራሾች ክስ የቀረበበትን ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 አስረክበዋል፤ 2ኛ ተጠሪ ቀደም
ሲል ቤቱን ለአቶ ወርጃ አበዙ አከራይቶ ኪራይ ሲሰበስብበት የቆየ ነው፤ ተከራይ ቤቱን በምን አግባብ
እንደለቀቀ ሳይታወቅ አመልካቾች ክስ የቀረበበትን ቤት ቀላቅለው ይዘዋል፤ ስለሆነም ክሱ ውድቅ ሊደረግ
ይገባል የሚል ነው፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ፤ ቁጥራቸው 1140 እና 1141 የሆኑትን ቤቶች
ማሕደሮች አስቀርቦ ከተመለከተ እና ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ስለጉዳዩ ተጣርቶ እንዲላክለት ካደረገ
በኋላ ጉዳዩን መርምሮ አመልካቾች ካርታ ያቀረቡ ቢሆንም አከራካሪው መጸዳጃ ቤት እና ማዕድ ቤት በይዞታ
ማረጋገጫ ካርታው ውስጥ የማይካተት መሆኑ ተረጋግጧል፤ የሚመለከተው የአስተዳደር አካል በሰጠው
መልስ ቁጥሩ 1140 የሆነው ቤት መጸዳኛ ቤት እንደሆነ እና አመልካቾች የያዙት ቢሆንም በሲአይኤስ ላይ
የቀበሌ ቤት በሚል የተፈለጸ ነው የሚል ምላሽ ልኳል፤ 2ኛ ተጠሪ የመንግስት ነው የሚለው ቤት
አመልካቾች ለመጸዳጃ ቤት የሚገለገሉበት እና 2ኛ ተጠሪም ይህን ቤት እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ ሲያከራየው
የነበረ ነው፤ 2ኛ ተጠሪ ቤቱ በምን አግባብ ከእጁ ሊወጣ እንደቻለ አላስረዳም፤ የአመልካቾች ምስክሮች
አመልካቾች ቤቱን ሲገለገሉበት እንደነበረ ያስረዱ ቢሆንም ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ስለሌለ አከራካሪው ቤት
የአመልካቾች አይደለም በማለት ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም
ጸንቷል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል
ሲሆን ይዘቱም፡- የስር ፍርድ ቤት ከቀረበለት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ጭብጥ ወጥቶ የባለቤትነት ፍርድ
መስጠቱ አግባብ አይደለም፤ ሁከት እንዲወገድ በሚል በሚቀርብ ክስ ላይ ተከሳሽ የሚያነሳው ባለቤትነትን
የተመለከተ ክርክር አግባብነትት የለውም፤ አመልካቾች ወደፊት ለክርክሩ መነሻ በሆነው መኖሪያ ቤት ላይ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የምናነሳውን የባለይዞታነት ክርክር በሚገድብ መልኩ የተሰጠው ፍርድ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ሁከት ይወገድ የሚል ክስ አቅርበው ሳለ
አከራካሪው ቤት የአመልካቾች የግል ሀብት አይደለም በማለት የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል
ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የተጠሪዎች መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች የአመልካቾች መሆን አለመሆናቸው
ጭብጥ ተይዞ ውሳኔ የተሰጠው አመልካቾች የቤቱ ባለቤት መሆናቸውን በመግለጽ የሁከት ይወገድልኝ ክስ
ስላቀረቡ ነው፤ የስር ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አስፈላጊ የሆነውን ጭብጥ በመያዝ እና አስፈላጊ የሆኑ
ማስረጃዎችን በማስቀረብ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ ውሳኔው ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

ከክርክሩ ሒደት መገንዘብ የቻልነው አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዳኝነት 1ኛው
ተጠሪ በሰጣቸው ካርታ ላይ አከራካሪ የሆነውን ማድቤት እና መጸዳኛ ቤት የመንግስት ብሎ በመስራት፤ 2ኛ
ተጠሪም ይህንኑ ቤት የራሴ ነው በማለት ሁከት የፈጠሩብን በመሆኑ ሁከቱ እንዲወገድልን የሚል ነው፡፡
ሆኖም የአመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ ሁከት ይወገድልን የሚል ቢሆንም ይህንኑ ዳኝነት ሊጠይቁ የቻሉት
አከራካሪ የሆነው ማድቤት እና መጸዳጃ ቤት ከአውራሾቻቸው የወረሱት ቤት አካል መሆኑን በመግለጽ ነው፡፡
ይህም አመልካቾች የአከራካሪው ማዕድ ቤት እና መጸዳጃ ቤት ባለቤት መሆናቸውን በመግለጽ በዚሁ ቤት
ላይ ተፈጠረ የሚሉት ሁከት እንዲወገድ ክስ ያቀረቡ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች አከረካሪ የሆነው ማዕድ
ቤት እና መጸዳጃ ቤት የቀበሌ ቤት መሆኑ እና 2ኛ ተጠሪም እስከ 1994 ዓ.ም ድረስ ሲያከራየው የነበረ
መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር
1234/2013 አንቀጽ 10/1 መሠረት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው ስልጣን
መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና
ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የለውም፡፡
በያዝነው ጉዳይ አመልካቾች ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዳኝነት በአከራካሪው ማዕድ ቤት እና መጸዳጃ ቤት ላይ
በተጠሪዎች ተፈጥሯል የሚሉት ሁከት እንዲወገድ የሚል ቢሆንም ይህንኑ ዳኝነት ሊጠይቁ የቻሉት
አከራካሪ የሆነው ማድቤት እና መጸዳጃ ቤት ከአውራሾቻቸው የወረሱት ቤት አካል መሆኑን እና የቤቱ
ባለቤት መሆናቸውን በመግለጽ በመሆኑ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የስር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍርድ ቤት ጉዳዩን አጣርቶ አመልካቾች የአከራካሪው ማዕድ ቤት እና መጸዳጃ ቤት የአመልካቾች የግል


ሐብት አይደለም በማለት የሰጠው ውሳኔ አመልካቾች ለጠየቁት ዳኝነት ምላሽ የሰጠ እና በአግባቡ ነው
ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም፡፡ ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ
ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 276300 መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ
254780 በቀን 01/03/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. ሚያዝያ 05 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 203886

ቀን ፡- ሕዳር 27 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- 1. ሀብታም ንጉሴ 14. አልያስ ትኩዬ

2. ዳንኤል ተሾመ 15. ኤልያስ ለሪሶ

3. አበበች ነገደ 16. እየሩስ ስብሀት

4. ወይንሸት ፍሬው 17. ደጀኔ ገመቹ

5. ሮቤል ገመቹ 18. ወንድምአገኘሁ አስፋው

6. ጣሂር አማን 19. ታረቀኝ አማኑ

7. ትዕግስት ገ/ክርስቶስ 20. ብርሃኑ ኃይሉ

8. ሕይወት ገዛኸኝ 21. ቤተልሔም ፀጋዬ

9. ፍቅሩ ቢረጋ 22. ሚኪያስ ሙሉዓለም

10. ዓለምፀሐይ ከተማ 23. ፋኖስ ጨንገሬ

11. ሽብር ደምሴ 24. ሐዊ ወሀበይ

12. ሐይማኖት አጌና

13. ሐያት አብዱ - የአመልካቾች ጠበቃ አንድነት በየነ -ቀረቡ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ይዞታ መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ ዐ/ህግ ሰለሞን ብርሃኑ -
ቀረቡ

ይሕ መዝገብ ከሰበር መዝገብ ቁጥር 203885 ጋር ተጣምሮ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ
እንደተረዳነው አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ
መሥሪያ ቤት ጋር በተለያዩ የሥራ መደቦችና ኃላፊነቶች ላይ ስንሰራ ቆይተናል፡፡ የሥራ ቅጥር ውላችንን
ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ የሚቋረጥ መሆኑን ስላሳወቀን ቋሚ ሠራተኞች መሆናችን እንዲታወቅና
ቅጥሩ እንዲቋረጥ የሠጠው ትዕዛዝ እንዲሰረዝ ሆኖ ወደሥራችን እንድንመለስ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት
ጠይቀዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረበው መልስ አመልካቾች በጊዜያዊነት የተቀጠሩት ለመሬት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ
ነው፡፡ በጊዜያዊ ቅጥር ውሉ መሠረት ሥራው ሲቀነስ ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሥራ ውሉን ማቋረጥ
ይቻላል፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ተጠሪነቱ ለተጠሪ መሥሪያ ቤት ሆኖ በመደራጀቱ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በመታጠፉ
ምክንያት እንዲሰናበቱ መደረጉ በሕግ አግባብ የተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት ቢሮ አስተዳደር ፍርድ ቤት ባደረገው
የቃል ክርክር አመልካቾች የሚከራከሩት የተቀጠርነው በጊዜያዊነት ቢሆንም እየሰራንበት ያለው የሥራ
መደብ ቀጣይነት ያለው፣ ሥራውን ለመስራት በማሰብ ይዞታ ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት በማቋቋም ሠራተኞችን
እየቀጠረ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ከ2006 - 2009 ዓ/ም ብቻ ሕልውና የነበረው ሲሆን ፕሮጀክቱ ካለቀም በኋላ
የሥራ መደቡን ይዘን ቆይተናል፤ ይሕም ግንኙነታችን ቀጣይነት ያለው መሆኑን ያሳያል ያሉ ሲሆን ተጠሪ
በበኩሉ የተቀጠሩበት ፕሮጀክት ታጥፏል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲታጠፍ መረጃ የመሰብሰብ ሥራው በተጠሪ መሥሪያ
ቤት ተካቶ ሥራው እየተሰራ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ያለቀው በ2011 ዓ/ም እንጂ በ2009 ዓ/ም አይደለም ብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ አመልካቾች የተቀጠሩት ለፕሮጀክት ጽ/ቤት ስለመሆኑ የተካካዱበት ነጥብ
አይደለም፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከፈረሰ በኋላም ሥራችን ቀጥለናል በማለት አመልካቾች የተከራከሩ ቢሆንም
አዲስ የፈጸሙት ውል ሆነ የነበራቸው ያደሱበት አግባብ በሌለበት ሁኔታ ቋሚ ሠራተኞች መሆናችን
ተረጋግጦ ወደሥራ ተመልሰን ያልተከፈለን ደመወዝ እንዲከፈለን በማለት ያቀረቡት ዳኝነት ተቀባይነት
የለውም በማለት ወስኗል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ ውሳኔውን
አጽንቷል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የአመልካቾችን የሠበር አቤቱታ ባለመቀበል ሠርዟል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ከነሀሴ ወር 2006
ዓ/ም ጀምሮ ዘላቂነት ባላቸው የሥራ መደቦች ላይ ተቀጥረን ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ስንሰራቸው የነበሩ
ሥራዎች አሁንም በተጠሪ መሥሪያ ቤት ሥር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት በማቋቋም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እየሰራበት ይገኛል፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከ2009 ዓ/ም በኋላ ሕልውና አልነበረውም፤ ከ2009 ዓ/ም በኋላ
የሥራ ቅጥር ውሉን ውጤቶች ስንፈጽም የነበረው በቀጥታ ከተጠሪ ጋር ነው፡፡ በቋሚነት ስንሰራ ስለነበር
ወደሥራችን ልንመለስ ይገባል የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ ውሉ መታደስ የነበረበት
በ2009 ዓ/ም ሆኖ እያለ አመልካቾች እስከ 2011 ዓ/ም መስራታቸው ባልተካደበት ሁኔታ የሥር ፍርድ ቤት
የታደሰ ውል አላቀረባችሁም በማለት የወሰነበት አግባብነትን ለመመርመር ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ያዘዘ
ሲሆን ተጠሪ ያቀረበው መልስ አመልካች ለፕሮጀክት ሥራ በጊዜያዊ ቅጥር ውል የተቀጠሩ ናቸው፡፡
በጊዜያዊ ቅጥር ውሉ ሆነ በአዋጅ ቁጥር 56/2010 መሠረት የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት የተቋረጠ
ስለሆነ ስንብቱ ሕጋዊ ነው፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ሕልውናውን ያጣው በ2011 ዓ/ም ነው፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ
ተጠሪነቱ ለተጠሪ መሥሪያ ቤት ሆኖ ቆየ እንጂ አመልካቾች ቀጥታ ከተጠሪ ጋር የሥራ ግንኙነት
አልነበራቸውም፡፡ ውሳኔው ተገቢ ስለሆነ ሊጸና ይገባል ብሏል፡፡ አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር
አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ የሠበር አጣሪ ችሎት የያዘውን
ጭብጥ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካቾች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ መሥሪያ ቤት ጋር በተለያዩ የሥራ መደቦችና


ኃላፊነቶች ላይ ስንሰራ ቆይተናል፡፡ የሥራ ቅጥር ውላችንን ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ የሚቋረጥ
መሆኑን ስላሳወቀን ቋሚ ሠራተኞች መሆናችን እንዲታወቅና ቅጥሩ እንዲቋረጥ የሠጠው ትዕዛዝ እንዲሰረዝ
ሆኖ ወደሥራችን እንድንመለስ ይወሰንልን በማለት ላቀረቡት ዳኝነት ተጠሪ የሚከራከረው አመልካቾች
በጊዜያዊነት የተቀጠሩት ለመሬት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሥራ ነው፡፡ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ተጠሪነቱ ለተጠሪ
መሥሪያ ቤት ሆኖ በመደራጀቱ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በ2011 ዓ/ም በመታጠፉ ምክንያት እንዲሰናበቱ መደረጉ
በሕግ አግባብ የተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ክርክሩን በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፊነት ሲሆን
በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣
ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰሉትን
ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን መብት ይነካል፡፡ ክርክር የሚወሰነው በተጠየቀው ዳኝነት አግባብ
እንደሆነ የፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 182(2) ላይ ተመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም ከቀረበው ዳኝነት አኳያ ከግራቀኙ
ክርክር በመነሳት በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 246 እና ተከታዮቹ መሠረት በተነሱት ጉዳዮች ጭብጥ መስርቶ ውሳኔ
የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡ አመልካቾች የሚከራከሩት የተቀጠርነው በጊዜያዊነት ቢሆንም እየሰራንበት
ያለው የሥራ መደብ ቀጣይነት ያለው፣ ሥራውን ለመስራት በማሰብ ይዞታ ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት
በማቋቋም ሠራተኞችን እየቀጠረ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ከ2006 - 2009 ዓ/ም ብቻ ሕልውና የነበረው ሲሆን
ፕሮጀክቱ ካለቀም በኋላ የሥራ መደቡን ይዘን ቆይተናል፤ ይሕም ግንኙነታችን ቀጣይነት ያለው መሆኑን
ያሳያል በሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ የተቀጠሩበት ፕሮጀክት ታጥፏል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲታጠፍ መረጃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመሰብሰብ ሥራው በተጠሪ መሥሪያ ቤት ተካቶ ሥራው እየተሰራ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ያለቀው በ2011 ዓ/ም
እንጂ በ2009 ዓ/ም አይደለም ብሏል፡፡ ስለሆነም ክርክራቸውን ለመወሰን ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ መቼ ነው
ሕልውናውን ያጣውና የተቋረጠው፡- በ2009 ዓ/ም ወይስ በ2011 ዓ/ም? አመልካቾች በቋሚነት የሥራ
መደብ ላይ ሲሰሩ ነበር ወይስ አልነበረም? የሚለው በጭብጥነት በመያዝ ግራቀኙ ባቀረቡት ሆነ ፍርድ ቤቱ
ተገቢ ነው ባለው ሌሎች ማስረጃዎች በማጣራት ፍሬ ነገሩን ካረጋገጠ በኋላ ሕጋዊ ውጤቱስ ምንድን ነው
የሚለውን መወሰን ሲገባ ተገቢውን ጭብጥ ሳይያዝ የአመልካቾች ውል አልታደሰም በማለት ክሱ ውደቅ
መደረጉ መሠረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ግድፈት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

1. የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥሮች 32586 እና 32587 ሕዳር 25 ቀን 2013
ዓ/ም፣ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥሮች 31640 እና 31639 ሚያዚያ 05
ቀን 2012 ዓ/ም እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት ቢሮ አስተዳደር
ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥሮች 1282/2011 እና 1314/2011 ሕዳር 04 ቀን 2012 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት ቢሮ አስተዳደር ፍርድ ቤት
ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ መቼ ነው ሕልውናውን ያጣውና የተቋረጠው፡- በ2009 ዓ/ም ወይስ በ2011 ዓ/ም?
አመልካቾች በቋሚነት የሥራ መደብ ላይ ሲሰሩ ነበር ወይስ አልነበረም? ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ፈርሶ አመልካቾች
ሥራቸውን ከቀጠሉ ሕጋዊ ውጤቱ ምንድን ነው? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ እና ፍሬ ነገሮችን በማስረጃ
በማጣራት የመሠለውን እንዲወስን በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሠረት ጉዳዩን መልሠናል፡፡

3. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና
የሠው ሀብት ልማት ቢሮ አስተዳደር ፍርድ ቤት በውሳኔው መሠረት እንዲፈጽም አዘናል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ማ/አ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

?? /? /? ? ? 203890
? ? 27/3/2014 ? /?

ዳኞች ተፈሪ ገብሩ(ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች - አቶ ደመላሽ ሙልጌታ


የቀረበ
ተጠሪ - የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ቁጠባ ጽ/ቤት የህብረት ሥራ ማህበር
ነ/ፈ - ሀብታሙ ውበቱ -ቀረቡ
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መጋቢት 3 ቀን
2013 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 254081 ታህሳስ 20 ቀን 2013
ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር
176095 ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡
ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና
በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት
ብር 59,879 እንድከፍል ሲወስን የግራ ቀኙን የሰው ምስክር ሳያዳምጥ ሳይጣራና ትክክለኛ
የኦዲት ሪፖርት ሳይቀርብ የተሰጠብኝ ውሳኔ በመሆኑ፣ ለጉዳዩ መነሻ በሆኑት ቼኮች ሁላችንም
ፈርመንበት እያለ ይህም የሶስታችን ፊርማ ለመሆኑ በፎረንሲክ ተረጋግጦ እያለ የጋራ ተጠቂዎች
መሆን ሲገባ አመልካች ብቻ ኃላፊ ነው ተብሎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በስር ፍ/ቤት የነበረው ክርክር የጀመረው ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ
የአሁን ተጠሪ ባቀረበው ክስ ተከሳሾች 1. የአሁን አመልካች 2. አቶ ፍቃዱ በቀለ 3. ወ/ሮ ዘነበች
ለማ ከመጋቢት 2003 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 2008 ዓ/ም ድረስ የከሳሽ ማህበር ሂሳብ ሹም፣
ሊቀመንበር እና ገንዘብ ያዥ ሆነው ሲሰሩ 1ኛ ተከሳሽ የአሁን አመልካች ሂሳብ ሹም ሆኖ ሲሰራ
በእጁ በስራ ምክንያት የገባውን የማህበሩን ቼክ ከፊት ለፊቱ ቁጥር በመጨመር በማበላለጥ ብር
29,499 በህገ ወጥ መንገድ የወሰደ በመሆኑ፣ ተከሳሾች የማህበሩ አመራር እና ቼክ ላይ ፈራሚ
በመሆናቸው በእጃቸው የሚገኘውን ቼክ እና የወጪ ደረሰኝ በመጠቀም የማህበሩ አባል ላልሆነ
ሰው ለአቶ ሙላቱ ደፋር ብር 10,199 እንዲከፈል ያደረጉ በመሆኑ እንዲሁም በተለያዩ ቼኮች
በ1ኛ ተከሳሽ ስም ብር 54,380.80 በአጠቃላይ ብር 83,879,80 ለግል ጥቅሙ ያዋለ በመሆኑ
ከወለድ ጋር ይክፈሉኝ ሲል ጠይቋል፡፡ ተከሳሾችም 1ኛ ተከሳሽ በሰጠው መልስ 2ኛ ተከሳሽ
የማህበሩ ሊቀመንበር የሆነው በ10/12/2004 ዓም ጽፎ በሰጠኝ ክሊራንስ ከሳሽ ከእዳ ነጻ መሆኔን
አረጋግጦ አሰናብቶኛል፡፡ በመሆኑም ያጎደልኩት ገንዘብ ሳይኖር ከ6 ዓመት በኋላ ያለምንም
ኦዲት ሪፖርት ሊከሰኝ አይገባም፡፡ በተጠቀሱት ቼኮች ብቻ፣ ቼክ የገንዘብ እንቅስቃሴን የሚያሳይ
ሆኖ እያለ ካለ ኦዲት ሪፖርት ልከሰስ አይገባም፡፡ ካሁን በፊት በወንጀልም ተከስቼ በነጻ
የተሰናበትኩ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይሁንልኝ ብሏል፡፡ የ2ኛ እና የ3ኛ ተከሳሾች ደግሞ ከ1ኛ
ተከሳሽ ጋር ሆነን ባገለገልንበት ጊዜያት 1ኛ ተከሳሽ ያለውን እውቀት በመጠቀም በተለያየ ቀን
በተዘጋጀ ቼክ ለአባላቱ የአጭር ጊዜ ብድር ተብሎ በእያንዳንዱ ቼክ 800 ብር ተዘጋጅቶ ለ1ኛ
ተከሳሽ ሲሰጠው ከ2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች እውቅና ውጪ ከፊት ለፊቱ ቁጥር 9 በመጨመር
በድምሩ ብረ 29,499 ለግል ጥቅሙ አውሏል፡፡ የማህበር አባል ላልሆነ ሰውም የ10,199 ብር ቼክ
አዘጋጅቶ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሽን አስፈርሞ በቼኩ ጀርባ ላይ በራሱ ስም በመፈረም ለግል ጥቅም
አውሎታል፡፡ በሌሎች ቼኮችም በተመሳሳይ መልኩ በአጠቃላይ ብር 82,100 ለግል ጥቅሙ
አውሏል፡፡ በዚሁ መሰረት ይህን ደርሰንበት ለፖሊስ አሳውቀን በስሙ መውሰዱ ስለተረጋገጠ
ቅድሚያ 15,000 ብር ከፍሎ በየወሩ 1,000 ብር እየከፈለ ለመጨረስ ተስማምቶ በ9 ወር 9,000
ብር ከፍሏል፡፡ እስከ 2007 ዓ/ም ኦዲት ተደርጎ በ1ኛ ተከሳሽ ላይ ብር 82,180 ተገኝቶበታል፡፡
በመሆኑም 1ኛ ተከሳሽ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በነጻ እንሰናበት
ብለዋል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አከራክሮ በመ/ቁጥር 176095 ታህሳስ 22 ቀን
2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ የከሳሽ ማህበር ብር 83,879 ስለመጉደሉ በኦዲት
የተረጋገጠ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ እኔ በሌለሁበት የተደረገ የኦዲት ሪፖርት ነው ቢልም ሌላ ኦዲት
ለማዘዝ በቂ ምክንያት የሚሆን ያቀረበው ምክንያትና ማስረጃ የለም፡፡ ለአቶ ሙላቱ ደፋር
ለወጣው ገንዘብ 1ኛ ተከሳሽ በራሱ ስም የተጻፈ ቼክ በመሆኑ እንዲሁም በቼኮቹ ላይ ቁጥር
ስለመጨመሩ በኦዲት የተረጋገጠ ሲሆን ስላለመጨመሩ ያላስረዳ በመሆኑ በኦዲት ሪፖርቱ
መሰረት ብር 83,879 ሊሰበሰብ የሚገባው ከ1ኛ ተከሳሽ እንደሆነ ስለሚያስረዳ እንዲሁም 1ኛ
ተከሳሽ የደረሰውን ጉድለት ተቀብሎ ለመክፈል ተስማምቶ መክፈል የጀመረ በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ
ኃላፊነት አለበት፡፡ ከብር 83,879.80 ውስጥ ብር 81,000 1ኛ ተከሳሽ ለመክፈል ስለተስማማ እና
ከዚህ ውስጥ 24,000 ብር በመክፈሉ ቀሪውን ብር 59,879 ለከሳሽ ሊከፍል ይገባል፡፡ 2ኛ እና 3ኛ
ተከሳሾች ብር 10,199 ላይ የፈረሙ ቢሆንም 1ኛ ተከሳሽ የማህበር አባል ላልሆነ ሰው እንዲከፈል
ቼክ ላይ የፈረሙት ለፊርማ ሊቀርብላቸው የማይገባውን አቅርቦላቸው ያስፈረማቸው እና ለራሱ
ጥቅም ያዋለ መሆኑ በኦዲት በመረጋገጡ 2ኛ እኛ 3ኛ ተከሳሾች ሊጠየቁ አይገባም፡፡ ክሱም 2ኛ
እና 3ኛ ተከሳሾች ጥፋታቸው ምን እንደሆነ በማስረጃ ተደግፎ ስላልቀረበና ያደረሱት ጉዳት
ስላልተረጋገጠ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር ሊጠየቁ አይገባም፡፡ 1ኛ ተከሳሽ ብር 59,879 ውሳኔ ከተሰጠበት
ቀን ጀምሮ እስኪ ጠናቀቅ ድርስ ከ9% ወለድ ጋር ለከሳሽ ይክፈል ሲል ወስኗል፡፡ 1ኛ ተከሳሽ
ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ በመ/ቁጥር 254081 ታህሳስ 20 ቀን 2013
ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ስህተት
የተፈጸመበት አይደለም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት አያስቀርብም ሲል ይግባኙን
ውድቅ አድርጎታል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአሁን አመልካችም ይህን ውሳኔ በመቃወም ቀርቧል፡፡ መዝገቡም ተመርምሮ ለክርክሩ


መነሻ የሆነው ቼክ የሰር ከ1-3 ያሉት ተከሳሾች መፈረማቸው ባልተካደበት ሁኔታ 1ኛ ተከሳሽ
የአሁን አመልካች ብቻ ክፈል የተባለበትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ቀርቧል፡፡ መልስና
የመልስ መልስም ተሰጥቶበታል፡፡ ተጠሪ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ መልስ የስር ፍ/ቤት
የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዳልተፈጸመበት በማንሳት ይጽናልኝ ሲል
ተከራክሯል፡፡ አመልካችም ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ የመልስ መልስ አቤቱታውን
በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል፣ እኛም የቀረበውን አቤቱታ፣ መልስ እና


የመልስ መልሱን እንዲሁም የስር ፍርድ ቤት ውሣኔዎችን እና ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸውን
የሕግ ድንጋጌዎችን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ
ስህተት መኖር አለመኖሩን መርምረናል፡፡ እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በነበረው ክርክር
የአሁን አመልካች የአሁን ተጠሪ ማህበር ሂሳብ ሹም ሆኖ ሲያገለግል በስራ አጋጣሚ በእጁ
የገባውን የማህበሩን ቼክ አብረው የተከሰሱትን 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች አሁን በክርክሩ ውስጥ
የሌሉትን ካስፈረመ በኋላ በቼኩ ላይ ከተሞላው ገንዘብ መጠን ኋላ ቁጥር በመጨመር ከባንክ
ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚልና ገንዘብ ሊከፈለው ለማይገባ ሰው ቼክ እንዲታዘዝ
ካደረገ በኋላ በቼኩ ጀርባ ለራሱ አንዲከፈል በማድረግ ለግል ጥቅሙ አውሏል ተብሎ ክስ
የቀረበበት ሲሆን የአሁን አመልካች በቼኩ ላይ የፈረምነው ሶስት ሆነን እያለ እኔ ብቻ ኃላፊ
ልሆን አይገባም የሚልና በማስረጃነት የቀረበው የኦዲት ሪፖርት እኔ በሌለሁበት የተሰራ ኦዲት
በመሆኑ በማስረጃነት ሊቀርብብኝ አይገባም የሚል ክርክር አቅርቧል፡፡ የፌደራል የመጀመሪያ
ደረጃ ፍ/ቤትም አከራክሮ ግራ ቀኙን ያከራከረው የማህበር ገንዘብ የመጉደል ጉዳይ በሰነድ
ማስረጃ የሚጣራ ሆኖ በማስረጃነት የቀረበውን የኦዲት ሪፖርት የአሁን አመልካች የቀረበበትን ክስ
የፈጸመ ስለመሆኑ ያረጋገጠበት በመሆኑ ለጎደለው ገንዘብ ኃላፊ መሆኑን ወስኖ የአሁን አመልካች
ቀደም ሲል የማህበሩን ገንዘብ ያጎደለ መሆኑን አምኖ ክፍያ የፈጸመው ተቀንሶለት አንዲከፍል
ተወስኖበታል፡፡ የአሁን አመልካች ቅሬታ ሶስት ሆነን በቼኩ ላይ ፈርመን እያለ እኔ ብቻ ኋላፊ
ሊሆን አይገባም የሚል ሲሆን ገንዘቡ የጎደለበት ሁኔታ በቼኩ ላይ ሶስቱም ከፈረሙበት በኋላ
ሌሎቹ ሁለቱ ሳያውቁ የአሁን አመልካች በቼኩ ላይ ከተጻፈው ቁጥር ከኋላ በመጨመርና ከቼኩ
ጀርባ ለራሱ አንዲከፈል በመፈረም ለግል ጥቅሙ ያዋለው ስለመሆኑ በቀረበው የሰነድ ማስረጃ
የተረጋገጠበት በመሆኑ ድርጊቱን የግሉ የሚያደረገው ነው፡፡ ሌላው የኦዲት ሪፖርት እንከን
ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ የቀረበ እንደሆነ በድጋሚ ኦዲት አንዲደረግ ሊታዘዝ የሚችል
ወይም የኦዲት ሪፖርቱ ውድቅ ሊደረግ የሚችል ሲሆን የኦዲት ሪፖርቱ ማስረጃ አይሆንብም
የሚል ቅሬታ ስለቀረበበት ብቻ ውድቅ የሚሆንበት አግባብ የለም፡፡ በመሆኑም ማስረጃ
የመስማትና የመመዘን ሥልጣን የተሰጣቸው የስር ፍ/ቤቶች ግራ ቀኙን አከራክረው በቀረቡው
ማስራጀ አጣርተው የሰጡት ውሳኔ ጉድለት የተፈተመበት ሆኖ አላገኘነውም፡፡ የፌደራል ጠቅላይ
ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 41526 ላይ በሰጠው ውሳኔ አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ
ከማስረጃ ምዘና ጋር የተያያዘና የፍሬ ነገር ክርክር ላይ ያተኮረ አንደሆነ በሰበር ችሎት
ሊስተናገድ የማይቸል ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበት ይገናል፡፡ የአሁን አመልካች
የቀረበብኝ ክስ በማስረጃ አልተረጋገጠብኝም የሚል የማስረጃ ምዘናን ጉዳይ ያቀረበው ቅሬታ
ለሰበር ሰሚው ችሎት ሊቀርብ የሚችል ቅሬታ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም፡፡

ውሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 254081 ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት
የሰጠው ትእዛዝ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 176095 ታህሳስ 22 ቀን
2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ መዝገብ ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ግልባጭ ለስር ፍ/ቤት ይድረሳቸው ብለናል፡፡
4. መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መ/ቤት ተመልሷል፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 204021

ቀን፡-05/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማሕበር - አልቀረቡም

ተጠሪ ፡- 1. አቶ ነገራ ለታ 9. አቶ ዘነባ ተስፋዬ

2. አቶ አዱኛ ለገሰ 10. ወ/ሮ አያንቱ ተስፋዬ

3. አቶ ጌቱ ሙሉጌታ 11. አቶ ደበበ ተስፋዬ

4. አቶ ታምሩ ጉታ 12. አቶ መገርሳ ኩሹሌ

5. አቶ ያዴሳ እጅጉ 13. አቶ አበበ ኢዶ

6. ወ/ሮ አበባ ድሪባ 14. ወ/ሮ ሕይወት መኮንን

7. አቶ ዳምጠው ገለጠ 15. አቶ አበራ ካባ

8. አቶ ተፈራ ፈይሳ የ15ቱ ተጠሪዎች ጠበቃ ገዳ ቡታ- ቀረቡ

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ
ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ከሳሾች ነበሩ፡፡ ተጠሪዎች የካቲት 30 ቀን
2012 ዓ/ም ባቀረቡት የተሻሻለ ክስ ከአመልካች ጋር በጥበቃ ሥራ ውል በኮንትራት ጊዜያዊ ውል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አድርገናል፤ እስከ ነሀሴ 25 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ውላችን ተራዝሟል፡፡ የ15 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት
የሥራ ቅጥር ውል ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ አላግባብ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሥራ
አሰናበቶናል፡፡ ስለሆነም የተለያዩ ክፍያዎች አመልካች ሊከፍለን ይገባል በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡
አመልካች ያቀረበው መልስ ከተጠሪዎች ጋር ባደረግነው የሥራ ውል ላይ ውሉን ማቋረጥ የፈለገ ወገን የ15
ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ማቋረጥ ይፈቅዳል፡፡ ከኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ጋር ሠራተኛ ለማቅረብ
የነበረን ውል በመቋረጡ ምክንያት ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር ያላቸው ውል ተቋርጧል፡፡ የሥራ ውሉ
መቋረጡ ሕጋዊ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የኢሉ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 29252 ጉዳዩን መርምሮ
አመልካች የሠው ኃይል አቅራቢ እንጂ ለራሱ ሥራ ተጠሪዎችን የቀጠረ አይደለም፡፡ የኦሮሚያ ሕብረት
ሥራ ባንክ የሠው ኃይል አቅርቦት ውሉን በ20/11/2011 ዓ/ም በማቋረጡ የአመልካች ሥራም በዚሁ
ምክንያት ቆሟል፡፡ በመሆኑም በውላቸውና በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 28(3)(ሀ)
መሠረት የሥራ ውሉ መቋረጡ ስንብቱ ሕጋዊ ነው፡፡ ደመወዝ ተከፍሏል፣ የዓመት ዕረፍት ያልተወሰደ
ስለመኖሩ አልተረጋገጠም፣ የጡረታ መዋጮ ክፍያ የሥራ ውል ሲቋረጥ በአሠሪው ተመላሽ የሚደረግ ክፍያ
አይደለም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን ይግባኝ
በመቀበል አከራክሮ ለኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ የአገልግሎት አቅርቦት ዋጋ እና ሁኔታዎችን ለማደስና
ለማመቻቸት ካልተስማማችሁ የሰው ኃይል አቅርቦት ውሉ ከ01/12/2011 ዓ/ም ጀምሮ የሚቋረጥ ስለመሆኑ
ማስጠንቀቂያ በ20/11/2011 ዓ/ም የጻፈው አመልካች ነው፡፡ ባንኩም በሠጠው ምላሽ ያቀረባችሁትን የሥራ
ማቋረጥ ውሳኔ እንቀበላለን ብሏል፡፡ ይሕም አመልካች በራሱ ተነሳሽነት ያደረገው መሆኑን ያሳያል፡፡
በተጨማሪም አመልካች ለተጠሪዎች ማስጠንቀቂያ የጻፈው ለባንኩ ከመጻፉ በፊት በ12/11/2011 ዓ/ም ነው፡፡
የ15 ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥቻለሁ ያለውም ከአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ ውጭ ነው፡፡ ሥራውን የሚያስቆም
አስገዳጅ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ሁኔታዎች አመቻችቶ የሥራ ውላቸው ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ማቋረጡ
የሥራ ውሉን እና የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 28(3)(ሀ) መሠረት ያላደረገ ስለሆነ
ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው በማለት የሥራ ስንብት ክፍያ፣ ካሣ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ የሁለት ወር ደመወዝ፣
ክፍያ ለዘገየበት ቅጣት ለእያንዳንዳቸው ብር 24,149.00 አመልካች ከወጭና ኪሣራ ጋር እንዲከፍል
ወስኗል፡፡ የዓመት ዕረፍትና የጡረታ መዋጮ ክፍያ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤትን
ውሳኔ አሻሽሏል፡፡ የክልሉ ሰበር ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ሠርዟል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ተጠሪዎች
የተቀጠሩበት ባንክ ከአመልካች ጋር ያለውን የአንድ ዓመት ውል አቋርጦ ከሌላ ኤጀንሲ ጋር ውል
በመፈጸሙ ምክንያት በውላችን አግባብ የ15 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጣችን ተገቢ ነው፡፡
ከባንኩ ጋር የገባነው ውል ተጠናቋል፡፡ ተጠሪዎች ከሌላ ኤጀንሲ ጋር በባንኩ ሥራቸውን ቀጥለዋል፡፡
በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 28(3)(ሀ) መሠረት የሥራ ውል ለማቋረጥ በቂ
ምክንያት ያለ በመሆኑ የሥራ ስንብቱ ሕጋዊ ነው፡፡ የሥራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ነው ነው ተብሎ መወሰኑ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሕግን የተከተለ አይደለም የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ
ባንክ ውሉን ማቋረጡን ከማሳወቁ እና ግራቀኙ ካደረጉት ውል አንጻር ሕገ-ወጥ ስንብት ነው መባሉ
ሕጋዊነቱን ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዲያቀርቡ ያዘዘ ሲሆን ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ ከባንኩ
ጋር ያለውን ውል ለማቋረጥ ማስጠንቀቂያ በመጀመሪያ የጻፈው አመልካች ነው፡፡ ለተጠሪዎች ማስጠንቀቂያ
የሠጠው ባንኩ ደብዳቤ ከመጻፉ በፊት ነው፡፡ የሥራ ውላችን ተቋርጦ ለችግር ተጋልጠን ከብዙ ወራት በኋላ
በሌላ ኤጀንሲ የተቀጠርነው፤ በሥርም የቀረበ ክርክር አይደለም፡፡ ውሳኔው ሊጸና ይገባል ብለዋል፡፡ አመልካች
የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የሥራ ውሉ የተቋረጠው በሕግ አግባብ ስለመሆን
አለመሆኑ ለጉዳዩ ተፈጻሚነት ያለውን ሕግና በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች አንጻር መዝገቡን
መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪዎች የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ/ም ባቀረቡት የተሻሻለ ክስ በሕገ-ወጥ መንገድ


አመልካች ከሥራ አሰናብቶናል በማለት የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸው ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን አመልካች
በበኩሉ የሥራ ውላቸው የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡ ግራቀኙ የአሠሪና ሠራተኛ
አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት በማድረግ የተከራከሩ ሲሆን የሥር ፍርድ ቤቶችም አዋጅ ቁጥር
1156/2011ን ለጉዳዩ ተፈጻሚ አድርገዋል፡፡ ተጠሪዎች ከሥራ የተሰናበቱት የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር
377/1996 በሥራ ላይ ባለበት ጊዜ ሀምሌ 30 ቀን 2011 ዓ/ም ነው፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀጽ 190(5) ላይ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ያለው ሲሆን በዳኝነት አካል ላይ በመታየት ላይ ያሉ
ጉዳዮች በተጀመሩበት ጊዜ በነበረው ሕግ መሠረት ፍጻሜ እንደሚያገኙ አስቀምጧል፡፡ በመርሕ ደረጃ
መሠረታዊ ሕግ ተፈጻሚ መሆን ያለበት በሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በተከሰቱ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ክሱ
የቀረበው አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ በ2012 ዓ/ም ቢሆንም ለተጠሪዎች የሥራ ውል
መቋረጥ ምክንያት የሆነው ድርጊት የተከሰተው አዋጅ ቁጥር 377/1996 በሥራ ላይ ባለበት ጊዜ ስለሆነ
የተግባሩ ሕጋዊነትም መመርመር ያለበት ይሕንኑ ሕግ መሠረት በማድረግ ሊሆን ይገባል፡፡ ስለሆነም የሥራ
ውል መቋረጥ ተግባር ሕጋዊ መሆን አለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት ሊመረመር የሚገባው
ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 መሠረት የሥራ ውል የሚቋረጠው አንደኛው በሕግ ወይም
በሥምምነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተዋዋይ ወገኖች አነሳሽነት ነው፡፡ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር
377/1996 አንቀጽ 24 በሕግ መሠረት ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ተዘርዝረዋል፡፡ የአዋጁ አንቀጽ 25
ደግሞ በሥምምነት ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ ይገልጻል፡፡ በአሠሪው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበት
ሁኔታ በአዋጁ ከአንቀጽ 26-30 በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ
31 እና 32 ደግሞ በሠራተኛው አነሳሽነት የሥራ ውል የሚቋረጥበትን ሁኔታ ደንግጓል፡፡ የአዋጁ ድንጋጌ
አንቀጽ 31 በአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ለአሠሪው በመስጠት ሠራተኛው ውሉን ማቋረጥ እንደሚችል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚገልጽ ነው፡፡ ሌላው በሠራተኛው አነሳሽነት የሚፈጸም የሥራ ውል ማቋረጥ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ
ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 32(1)(ሀ እስከ ሐ) የተመለከተ ሲሆን በሕጉ የተዘረዘሩት ምክንያቶች አሠሪው
የሠራተኛውን ሠብዓዊ ክብርና ሞራል መንካቱ፣ በወንጀል የሚያስቀጣ ተግባር በሠራተኛው ላይ መፈጸም፣
ለሠራተኛው ደኅንነት ወይም ጤንነት አደጋ ሊያደርስ የሚችል ምክንያት እያለ አሠሪው ተገቢውን እርምጃ
ካልወሰደ ወይም ሌላ አሠሪው ለሠራተኛው መፈጸም ያለበትን ግዴታ በመደጋገም ካልፈጸመ ሠራተኛው
ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውሉን ማቋረጥ የሚችልበትን ሁኔታ አስቀምጧል፡፡ ከእነዚህ ማዕቀፎች ውጭ
አሠሪው ሠራተኛን ከሥራ ሲያሰናብት ሕገ-ወጥ የሥራ ስንብት ይሆናል፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ አሠሪው በፈለገ ጊዜ የሠራተኛን የሥራ ውል ማቋረጥ እንዳይችልና የሠራተኛው


የሥራ ዋስትና መረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ሲሆን በሌላ በኩል የኢንዱስትሪው ምርትና ምርታማነት
ለመጨመርና አሰሪው ላይ ያልተገባ ጫና እንዳይፈጠርበት ሁለቱን ተወዳዳሪ ጥቅሞች/ፍላጎቶች የማስታረቅ
ግብ ይዟል፡፡ አመልካች በቅጥር ውሉ ላይ የሥራ ውሉን ማቋረጥ የፈለገ ወገን የ15 ቀን ማስጠንቀቂያ
በመስጠት ማቋረጥ እንደሚችል ስለተመለከተ በዚህ መሠረት የሥራ ውሉ መቋረጡ ሕጋዊ ነው በማለት
ተከራክሯል፡፡ አሠሪ በሥራ ውል ወይም ደንብ ወይም በሕብረት ሥምምነት መሠረት በሕጉ ከተመለከተው
ያነሰ መብት ሊዋዋል የማይችል መሆኑ እና ቢዋዋልም ሕጋዊ ውጤት የሌለው ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር
377/1996 አንቀጽ 4(5) እና 133(1) ላይ ተመልክቷል፡፡ በሕጉ ሥራው ሳያልቅ ለአሠሪው የ15 ቀን
ማስጠንቀቂያ በመስጠት የሠራተኛውን የሥራ ውል እንዲያቋርጥ መብት አልሠጠውም፡፡ ስለሆነም በዚህ
ረገድ የአመልካች ክርክር ሕጋዊ መሠረት ያለው አይደለም፡፡

በሌላ በኩል አመልካች ሥራዎችን ከሦስተኛው ወገን በውል እየወሰደ የሚሰራ አሠሪ መሆኑን ከክርክሩ
ተገንዝበናል፡፡ ተጠሪዎችም የተቀጠሩት የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ የጥበቃ ሥራን ለሦስተኛ ወገን
(outsource) በማድረጉና ሥራውን አመልካች በውል ለመሥራት በመውሰድ ተጠሪዎችን በመቅጠሩ ነው፡፡
ሥራውን ለአመልካች የሠጠው ባንክም ውሉን ከሀምሌ 20 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ ያቋረጠ ስለመሆኑ
አመልካች ያቀረበውን ክርክር ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተመለከተው ወረዳ ፍርድ ቤት
ተቀብሎታል፡፡ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ ለኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ የአገልግሎት አቅርቦት ዋጋ
እና ሁኔታዎችን ለማደስና ለማመቻቸት ካልተስማማችሁ የሰው ኃይል አቅርቦት ውሉ ከ01/12/2011 ዓ/ም
ጀምሮ የሚቋረጥ ስለመሆኑ ማስጠንቀቂያ በ20/11/2011 ዓ/ም የጻፈው አመልካች ስለመሆኑ፣ ባንኩም
በሠጠው ምላሽ ያቀረባችሁትን የሥራ ማቋረጥ ውሳኔ እንቀበላለን ማለቱ፣ አመልካች ለተጠሪዎች
ማስጠንቀቂያ የጻፈው ለባንኩ ከመጻፉ በፊት በ12/11/2011 ዓ/ም መሆኑ ሲታይ ሥራውን የሚያስቆም
አስገዳጅ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ሁኔታዎች አመቻችቶ የሥራ ውላቸው ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት
አመልካች ማቋረጡን በፍሬ ነገር ደረጃ አረጋግጧል፡፡ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ማስረጃን የመመዘን እና ፍሬ
ነገርን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለው በመሆኑ እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በኢፌዲሪ
ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) ላይ በመጨረሻ ውሳኔ ላይ በተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት እንጂ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስረጃው ተመዝኖ የተደረሠበትን የፍሬ ነገር ድምዳሜ ላይ እንዲመለከት ሥልጣን ያልተሰጠው በመሆኑ
በፍሬ ነገር ደረጃ የተደረሰበትን ድምዳሜ ተቀብለነዋል፡፡

ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አመልካች በራሱ አነሳሽነት የውሉ ሁኔታ እንዲለወጥ በማድረግ የሥራ ውሉን
ማቋረጡ ተገቢ ነው በሏል፡፡ አመልካች እንደ ድርጅት የንግድ ሥራውን በምን አግባብ መምራት እንዳለበት
የመወሰን ሥልጣን እና ነጻነት ሊኖረው ይገባል፡፡ አመልካች ከኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ጋር የገባው ውል
ባይጠናቀቅ እንኳን የንግድ ሁኔታ ለውጦች ካሉ እና ለአሠሪውም ሕልውና ችግር ውስጥ የሚከት ጉዳይ
ከተፈጠረ የውሉ ሁኔታ እንደሊወጥ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ጉዳዩ የሦስተኛ ወገን ጥቅም ያለበት
ማለትም የሠራተኞች የሥራ ዋስትና ጋርም የተያያዘ በመሆኑ አሠሪው ሲወሰን ይሕንንም የውሳኔ ሂደቱ
ላይ ማስገባት አለበት፡፡ ፍርድ ቤት የንግድ ሁኔታዎችን መዝኖ ለመወሰን ሥልጣን እና ሙያው ባይኖረውም
አመልካች ለሠራተኞች ውል መቋረጥ ምክንያት የሆነ ከኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ጋር የገባውን ውል
ሁኔታዎች እንዲለወጡ የጠየቀበት አመላካች ምክንያቶችን አቅርቦ ሊከራከር ይገባል፡፡ አመልካች የውል
ሁኔታዎች ለመለወጥ ማሳያ ምክንያቶችን ባላሳየበት ሁኔታ ለተጠሪዎች የሥራ ወል መቋረጥ የሆነው
ምክንያት በራሱ አነሳሽነት መውሰዱና ውሉን ማቋረጡ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ
28(2)(ሀ) የተመለከተውን ለውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ መከሰት የሚለውን የሚያሟላ ባለመሆኑ
የሥራ ሥንብቱ ሕገ-ወጥ ነው፡፡ ተጠሪዎች በሚሰሩበት ባንክ በሌላ ኤጀንሲ ሥራ ቀጥለዋል የሚለው
የአመልካች ክርክር በሥር ያልቀረበና አዲስ ክርክር በመሆኑ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 329(1) መሠረት ተቀባይነት
የሌለው ከመሆኑም በላይ ተጠሪዎች ሥራ ማግኘትና መቀጠል የአመልካችን የሥንብት እርምጃ ሕጋዊ
አያደርገውም፡፡ በአጠቃላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ የክልሉ ሰበር ችሎት የተጠሪዎች የሥራ ውል
የተቋረጠው ከሕግ ውጭ ነው በማለት የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸው የሠጡት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም ብለናል፡፡

ውሳኔ

1. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 335812 የካቲት 30 ቀን 2013
ዓ/ም እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 54351 የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ/ም
የሠጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-204074

ቀን፡-29/03/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ኑረዲን ከድር

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- በደሴ ከተማ የሆጤ ክፍለ ከተማ አስተዳደር - አልቀረቡም

ተጠሪዎች ፡- 1ኛ. የወ/ሮ ማሚቴ ሁሴን ወራሾች - አልቀረቡም

1ኛ. አያል አብርሃ

2ኛ. መዓዛ አብርሃ

3ኛ. ገነት አብርሃ

4ኛ. ዳኛቸው አብርሃ

5ኛ. ቴዎድሮስ አብርሃ

6ኛ. ዋሲሁን አብርሃ

2ኛ. አቶ ሽፈራው ሰይድ- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ክርክሩ የመንግስት የንግድ ቤትን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት 1ኛ
ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ተከሳሽ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

1ኛ ተጠሪ ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡተ ክስ 2ኛ ተጠሪ በሆጤ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኝ
የቤት ቁጥሩ 200 የሆነን የንግድ ቤት ከአመልካች ተከራይቶ ሲጠቀምበት ቆይቶ በእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ
በመውደሙ ምክንያት ከአመልካች ፍቃድ ተሰጥቶት ብር 500,000 ከራሱ ወጪ በማድረግ ምድር ቤት እና
18 መኝታ ቤት (አልቤርጎ) ያለው ፎቅ ገንብቶ እስከ 2008 ዓ.ም ሲገለገልበት ቆይቷል፡፡ 2ኛ ተጠሪ የንግድ
ቤቱን የግል ንብረቱ በማስመሰል የቤት ቁጥሩ 196 ከሆነ ሌላ የግል ንብረቱ ጋር አጠቃሎ በብር 1.8
ሚሊዮን ሽጦልኛል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ግዢውን በቅን ልቦና ያከናወንኩ ሲሆን 2ኛ ተጠሪ የንግድ ቤቱን ስመ
ሀብት እንዲያዞርልኝ ክስ መስርቼ የከተማው ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 12269 ውሳኔ ከሰጠ በኋላ
አመልካች የፍርድ መቃወሚያ በማቅረቡ የንግድ ቤቱ የአመልካች ነው ተብሎ ተወስኗል፡፡ በሌላ በኩል 2ኛ
ተጠሪ ለንግድ ቤቱ ግንባታ ያወጣው ወጪ በኪራይ እንዲካካስለት በደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች የመጀመሪያ
ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 105/2009 አመልካች ላይ ክስ መስርቶ በኪራይ ውል የይካካስልኝ ጥያቄ
የማቅረብ መብት እንዳለው የተረጋገጠ ሲሆን የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም በመዝገብ ቁጥር 26087 2ኛ
ተጠሪ የንግድ ቤቱን በኪራይ ይዞ መገልገል እንደሚችል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ 1ኛ ተጠሪ የንግድ ቤቱን በቅን
ልቦና የገዛው ስለሆነ 2ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ የሚኖሩትን መብቶች በእሱ እግር በመተካት የመጠየቅ መብት
አለኝ፡፡ የንግድ ቤቱ በአሁን ሰዓት የ1ኛ ተጠሪ ከሆነው የቤት ቁጥሩ 196 ጋር የተያያዘ፣ የራሱ መውጪና
መግቢያ በር የሌለው፣ የቤት ቁጥሩ 196 የሆነው ቤት ኩሽና እና ሽንት ቤት ከንግድ ቤቱ ጋር ተቀጣጥለው
የተሰሩ በመሆኑ አመልካች የንግድ ቤቱን ለሌላ ሰው ማከራየት አይችልም፡፡ በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ የንግድ
ቤቱን በኪራይ ይዤ እንድቀጥል፤ ይህ የሚታለፍ ከሆነም የግንባታ ወጪውን ብር 500,000 እንዲከፍለኝ፤
ይህ በበቂ ምክንያት የሚታለፍ ከሆነና የንግድ ቤቱ አሮጌ በመሆኑ ለመልሶ ማልማት የሚውል ከሆነ
ቅድሚያ እንዲሰጠኝ፣ ወጪና ኪሳራን ጨምሮ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

አመልካች ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ.ም ባቀረበው መልስ 1ኛ ተጠሪ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም የሚል
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬ ጉዳይ ላይ በሰጠው መልስ 2ኛ ተጠሪ በደሴ ከተማ ነክ
ጉዳዮች ፍርድ ቤት በንግድ ቤቱ ላይ ካርታ በስሙ ተሰርቶ እንዲሰጠው አመልካች ላይ ክስ መስርቶ እስከ
ክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 26087 ክርክር ተደርጎ የንግድ ቤቱ በ2ኛ ተጠሪ ወጪ የተሰራ
ቢሆንም ንብረትነቱ የመንግስት ነው ተብሎ ተወስኗል፡፡ ቤቱን በኪራይ ይዞ እንዲቀጥል የተሰጠ ውሳኔ
የለም፡፡ ለቤቱ ግንባታ ያወጣውን ወጪ ስልጣል ላለው አካል አቅርቦ ማስወሰን ይችላል ተብሎ መወሰኑ ክስ
የማቅረብ መብቱን ለ1ኛ ተጠሪ ለማስተላለፍ አያስችልም፡፡ ቤቱን የሚያስተዳድረው አመልካች ለ3ኛ ወገን
የሚያከራይበት አግባብ በመመሪያ ቁጥር 1/2009 የሚወሰን እንጂ ለማን ያከራይ የሚለው በፍርድ የሚወሰን
አይደለም፡፡ ይህም በቅፅ 12 በታተመው በመዝገብ ቁጥር 42150 አስገዳጅ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡ የከተማ
ይዞታ ለመልሶ ማልማት የሚውልበትን አግባብ የመወሰን ስልጣንም የከተማ አስተዳደሩ ነው፡፡ ይዞታው
የራሱ መግቢያ እና መውጪያ አለው፡፡ የለውም ቢባል እንኳ በህግ አግባብ መንገድ መጠየቅ ስለሚቻል ክሱ
ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ በመቃወሚያው ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ 2ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዲገቡ ትዕዛዝ የሰጠ
ሲሆን የ1ኛ ተጠሪን ክስ በማጠናከር እንደ ክሱ ሊወሰንላቸው ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡ ችሎቱም
በጣልቃ ገብ መልስ ላይ ግራ ቀኙ መልስ እንዲሰጡበት ካደረገ በኋላ መቃወሚያውን በብይን ውድቅ አድርጎ
በፍሬ ነገር ላይ የግራ ቀኙን የሰው ምስክር፣ የሰነድ ማስረጃ፤ በደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች ፍርድ ቤት በመዝገብ
ቁጥር 105/2009፣ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 26087፣ በደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
በመዝገብ ቁጥር 12269 የተሰጠውን ውሳኔ እንዲሁም ከደቡብ ወሎ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን
መምሪያ የቀረበውን ውጤት አብሮ መርምሯል፡፡ የ1ኛ ተጠሪ ምስክር የሆኑት 2ኛ ተጠሪ የንግድ ቤቱ
መግቢያ የቤት ቀጥሩ 196 የሆነው ሳሎን ቤት መሆኑን፤ የመብራት እና የውሃ ቆጣሪው ከቤት ቀጥሩ 196
ጋር የተያያዘ መሆኑን እና የቤት ቁጥሩ 196 የሆነው ቤት የራሱ ሽንት ቤት የሌለው መሆኑን ገልፀው
መስክረዋል፡፡ ከደቡብ ወሎ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በቁጥር ታህሳስ 16 ቀን 2011 ዓ.ም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተላከው ማስረጃ ቤቱ እራሱን ችሎ ለሌላ ለ3ኛ ወገን መተላለፍ የማይችል፣ የራሱ መግቢያ መውጪያ፣
መብራትና ውሃ የሌለውና ከቤት ቁጥር 196 ጋር በጋራ የሚጠቀም፣ በኮንክሪት መወጣጫ የተያያዘ መሆኑ
እንዲሁም የግንባታ ወጪው ብር 481,425.49 መሆኑን ገጸው መልስ የሠጡ ስለሆነ በኪራይ ለሌላ 3ኛ
ወገን ሊተላለፍ አይችልም፡፡ የንግድ ቤቱን ግንባታ ያከናወነው 2ኛ ተጠሪ መሆኑን ግራ ቀኙ ስላልተካካዱና
ግንባታውን ማዘጋጃ ቤቱ እና ቀበሌው ፈቅደውለት ያከናወነ ሲሆን ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ አስተላልፏል፡፡
በፍ/ሕ/ቁጥር 1161(1) መሰረት ሌላ ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ ንብረቱን በእጁ ያደረገው ሰው በቅን
ልቦና እንደገዛ የሚገመት በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ ያወጣውን ወጪ ሊቀበሉ የሚገባው 1ኛ ተጠሪ ስለሆኑ 2ኛ
ተጠሪ ይከፍሉት በነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ 1ኛ ተጠሪ ቤቱን ይዘው ሊገለገሉ ይገባል፡፡ አመልካች በዚህ
የማይስማማ ከሆነ የቤቱ የግንባታ ወጪ ብር 481,425.81 በኪራይ እንዲታሰብ ወይም ይህን ገንዘብ
እንዲከፍል እንዲሁም 1ኛ ተጠሪ የሊዝ ወይም የቅድሚያ መግዛት መብት እንዲጠበቅላቸው ሲል ወስኗል፡፡

አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኙን ለደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን


በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት በመሰረዙ ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታውን ቢያቀርብም
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 መሰረት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አፅንቶታል፡፡

አመልካች የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው ይህን የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ
በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡ የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ በደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር
12269 በነበረው ክርክር በተጠሪዎች መካከል የተደረገው የሽያጭ ውል ከቅን ልቦና ውጪ የተደረገ መሆኑ
ተረጋግጦ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በተጠሪዎች መካከል ያለው
ግንኙነት ስለተቋረጠ 2ኛ ተጠሪም ለ1ኛ ተጠሪ የሚያስተላልፈው መብት ስለሌለ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች ላይ
ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም፡፡ ክሱም እድሳቱ ከተደረገ ከ15 ዓመት በኋላ የቀረበ ነው በማለት አመልካች
ያነሳነው መቃወሚያ መታለፉ ተገቢ አይደለም፡፡ 2ኛ ተጠሪ የቤቱን ግንባታ በ1990 ዓ.ም በማከናወን
እንያንዳንዱን አልጋ በቀን ብር 50 ከ18ቱ ክፍሎ በቀን ብር 900 በወር ብር 27,000 በዓመት ብር 324,000

በ15 ዓመት ውስጥ 4.860,000 ገቢ በማግኘት ተካክሷል፡፡ አመልካች መክፈል ካለበትም የግንባታው ወጪ
ብር 47,506.81 ብቻ ነው በማለት ተከራክሮ እያለ ቤቱ በታደሰበት ጊዜ በነበረው ዋጋ በገለልተኛ አካል
እንዲጣራ ሳይደረግ መወሰኑ፣ አመልካች ለ3ኛ ወገን የሚያስተላልፍበት አግባብም በመመሪያ ቁጥር 1/2009
መሰረት የሚወሰን በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ በኪራይ ይዘው እንዲቀጥሉ እንዲሁም የከተማ ቦታን የማስተዳደር
እና የማስተላለፍ ስልጣን የከተማ አስተዳደሩ ሁኖ እያለ 1ኛ ተጠሪ በሊዝ ቅድሚያ የመግዛት መብት
ሊከበርላቸው ይገባል መባሉ፤ አከራካሪው የቀበሌ ቤት የራሱ መውጪያ እና መግቢያ ያለው ሲሆን የለውም
ቢባል እንኳ በህግ አግባብ መንገድ እንዲከፈትለት መጠየቅ የሚቻል መሆኑን በሚቃን ሁኔታ የተሰጠው
ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚል ነው፡፡

አቤቱታው በአጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት የመንግስት መሆኑ ያልተካደ በመሆኑ፤
ያለአመልካች ፍቃድ ተጠሪዎች ይዘው ኪራይ እየከፈሉ እንዲጠቀሙ የተሰጠውን ውሳኔ ከአመልካች
የመዋዋል ነፃነት አንፃር ለመመርመር ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪዎች መልሳቸውን እንዲያቀርቡ ታዟል፡፡

የ1ኛ ተጠሪ ጉዳዩ በክርክር ላይ እያሉ ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ወራሾቻቸው ሐምሌ 19 ቀን 2013
ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት መልስ 2ኛ ተጠሪ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ምክንያት በአመልካች ፍቃድ
በ1990 ዓ.ም አከራካሪውን ቤት የሰራ መሆኑ፣ 1ኛ ተጠሪም በ2003 ዓ.ም ይህን ቤት በቅን ልቦና
መግዛታቸው፣ እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 26087 2ኛ ተጠሪ ከማንም ተከራይ
የበለጠ እና ቤቱን የመጠቀም መብት እንዳለው መወሰኑ ተረጋግጧል፡፡ 2ኛ ተጠሪ የኪራይ እና የመጠቀም
መብት ያለው፣ ቤቱን በሽያጭ ሲያስተላልፍ የመጠቀም መብቱ ያልተቋረጠ እንዲሁም ከማይንቀሳቀስ ንብረት
ጋር የተገናኙ መብቶች በሽያጭ የሚተላለፉ በመሆኑ አመልካች ያልነበረ የኪራይ ውልን ተገዶ እንዲዋዋልና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመዋዋል ነጻቱን በመጋፋት የተሰጠ ውሳኔ አስመስሎ ያቀረበው መከራከሪያ ተገቢነት የለውም፡፡ አከራካሪው
የንግድ ቤት ከ1ኛ ተጠሪ ህጋዊ ቤት ጋር የተያያዘ፣ ለብቻው መጠቀም የማይቻል፣ በማናቸውም መንገድ
ራሱን ችሎ ለ3ኛ ወገን መተላለፍ የማይችል በመሆኑ 1ኛ ተጠሪ በተከራይነት ይዤው ካልቀጠልኩ የንብረት
መብት፤ የህጋዊ ቤትን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚጎዳ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦ የቀዳሚነት የመልሶ
ማልማት መብት ተጠብቆ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ በተከራይነት
እንድትቀጥል የተሰጠው ውሳኔ በአማራጭ የተሰጠ፣ አመልካች ከፈለገ የግንበታ ወጪውን ብር 481,425.91
በካሳ መልክ እንዲከፍል እና ቦታው በሊዝ ለ3ኛ ወገን የሚተላለፍ ከሆነም ለ1ኛ ተጠሪ እንዲቻቻል የሚል
ሁኖ እያለ እንደ ብቸኛ አማራጭ ተደርጎ የቀረበው መከራከሪያ አግባብ አይደለም፡፡ አከራካሪው ቤት
የተገነባው የፕላን ፈቃድ ለማግኘት በቀረበው ግምት ልክ ካለመሆኑም በላይ የግምቱ ክፍያ በወቅቱ የገበያ
ዋጋ ተሰልቶ ሊከፈል የሚገባው ክርክር ሲደረግ በነበረው የገበያ ዋጋ ብር 481,425.91 መሆኑ ተረጋግጦ
የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪም የ1ኛ ተጠሪ ወራሾች የሠጡትን መልስ
በማጠናከር መልሳቸውን አቅርበዋል፡፡

አመልካች በበኩሉ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልሱን ያቀረበ ሲሆን የሰበር አቤቱታውን
በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

ባጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን አመልካች 1ኛ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል
መብት የላቸውም፣ ክሱም በይርጋ ይታገዳል በማለት ያነሳው መቃወሚያ መታለፉ አግባብ ነው? ወይስ
አይደለም? መቃወሚያው መታለፉ አግባብ ነው ከተባለ 1ኛ ተጠሪ የንግድ ቤቱን በኪራይ ይዘው እንዲቀጥሉ
ወይም የንግድ ቤቱን ግምት ብር 481,425.91 አመልካች እንዲከፍል እና ቤቱ ለልማት የሚፈለግ ከሆነ
ቅድሚያ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲያመቻች የመወሰኑን አግባብነት በስር ፍ/ቤት ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ
ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዲሁም ለጉዳዩ ተገቢነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎችጋር በማገናዘብ
እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡

በቅድሚያ ምላሽ ማግኘት ያለበት 1ኛ ተጠሪ አመልካች ላይ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም በማለት
አመልካች ያቀረበው መቃወሚያ በስር ፍ/ቤቶች የመታለፉ አግባብት ነው፡፡ ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም
ሀብት ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ማንኛውም ሰው ክስ የማቅረብ መብት
የሌለው መሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33(2) ላይ ተመላክቷል፡፡ አከራካሪ የሆነውን የንግድ ቤት 2ኛ ተጠሪ
ከአመልካች ጋር በተደረገ የኪራይ ውል ስምምነት የያዘው መሆኑ፤ ይህ የንግድ ቤት በደረሰበት የእሳት
አደጋ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ በመውደሙ 2ኛ ተጠሪ በራሱ ወጪ ግንባታውን እንዲያካሒድ አመልካች
በሰጠው ፍቃድ መነሻነት 2ኛ ተጠሪ በ1990 ዓ.ም 18 ክፍል የመኝታ ክፍል (አልቤርጎ) ያለው ባለ አንድ
ፎቅ ሕንጻ ገንብቶ ሲገለገልበት መቆየቱ፤ ከዚህ የንግድ ቤት አጠገብም የቤት ቁጥሩ 196 የሆነ የግል ቤት
እንደነበረው፤ ይህን ከአመልካች በኪራይ ይዞ ሲገለግልበት የነበረውን የንግድ ቤት ከአጠገቡ ከሚገኘው የግል
ቤቱ ጭምር በ2003 ዓ.ም በ1.8 ሚሊየን ብር ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ማስተላለፉ፣ በዚህም መነሻነት 1ኛ
ተጠሪ 2ኛ ተጠሪ የንግድ ቤቱን ስመ ሀብት እንዲያዞርላቸው በደሴ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር
12269 ክስ መስርተው ስመ ሀብቱን እንዲያዞርላቸው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር
358 መሰረት የፍርድ መቃወሚያ በማቅረቡ በንግድ ቤቱ ላይ የተደረገው የሽያጭ ውል እንዲፈርስ እና
ቤቱም የአመልካች ነው ተብሎ መወሰኑ፤ ይህንንም ተከትሎ 2ኛ ተጠሪ በደሴ ከተማ ነክ ጉዳዮች ፍርድ ቤት
በመዝገብ ቁጥር 105/2009 ክስ መስርቶ የንግድ ቤቱን የግንባታ ወጪ ከሶ የመጠየቅ መብቱ ተጠብቆ ውሳኔ
የተሰጠ መሆኑ ግራ ቀኙን አላከራከረም፡፡

1ኛ ተጠሪ ከስር ጀምሮ የሚከራከሩት የንግድ ቤቱን አጠገቡ ከሚገኘወ የ2ኛ ተጠሪ የግል ንብረት ከነበረው
ቤት ጋር በቅን ልቦና የገዙት መሆኑን በመግለፅ እንዲሁም በከተማ ነክ ፍርድ ቤቱ በነበረው ክርክር 2ኛ
ተጠሪ የግንባታ ወጪውን ከሶ የመጠየቅ መብት ስለተጠበቀለት 2ኛ ተጠሪ በተጠበቀለት መብት በመተካት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዳኝነት መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን በመግለፅ ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ አከራካሪውን የንግድ ቤት በ2003 ዓ.ም
ከገዙት በኋላ የቤቱ ትክክለኛ ባለቤት አመልካች መሆኑ ተረጋግጦ የንግድ ቤት የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ
ተወስኗል፡፡ በተጠሪዎች መካከል ያለው ግንኙነት መነሻም ይህ በ2003 ዓ.ም የተደረገው የሽያጭ ውል
በመሆኑ ውሉ እንዲፈርስ ሲወሰን በንግድ ቤቱ ላይ በተጠሪዎች መካከል የነበረው ግንኙነት ተቋርጧል፡፡
ውሉ በመፍረሱም 1ኛ ተጠሪ ከንግድ ቤቱ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት መብት የላቸውም፡፡ በከተማ ነክ
ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር 2ኛ ተጠሪ የግንባታ ወጪውን በሚመለከት ክስ የማቅረብ መብቱ መጠበቁም
የአመልካችን እና የ2ኛ ተጠሪን ግንኙነት የሚወሰን እንጂ የሽያጭ ውሉ ከፈረሰ እና የተጠሪዎች ግንኙነት
ከተቋረጠ በኋላ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ እግር በመተካት ክስ ለማቅረብ የሚችሉበትን መብት የሚፈጥርበት
አግባብ የለም፡፡ የግንባታ ወጪን በተመለከተ አመልካች ላይ ክስ እንዲያቀርብ መብት የተጠበቀለት 2ኛ ተጠሪ
ነው፡፡ 2ኛ ተጠሪም ይህን መብቱን በፍ/ሕ/ቁጥር 1962 በተደነገገው አግባብ ለ1ኛ ተጠሪ ያደረገው ትክክለኛ
የመብት ማስተላለፍ ስለመኖሩ የቀረበ ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም፡፡

በፍ/ሕ/ቁጥር 33(2) መሰረት ክስ የማቅረብ መብት እና ጥቅም የሚመነጨው ከውል ወይም ከህግ ወይም
ከሁለቱም ነው፡፡ የዚህ ድንጋጌ አላማም በአንድ ጉዳይ የተለያዩ ሰዎች በአንድ ሰው ላይ በተለያየ ጊዜ
ወይም በተመሳሳይ ጊዜ ክስ እንዳያቀርቡ በማድረግ ትክክለኛው ባለመብት ብቻ ክስ እንዲመሰርት በማስቻል
ባለጉዳዮችንም ሆነ የፍርድ ቤትን ጊዜና ወጪ በመቆጠብ የባለጉዳዮችን እንግልት ማስቀረት እና ክርክሮች
ባጠረ ጊዜ እልባት እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ በንግድ ቤቱ ላይ መብት አግኝቼበታለሁ የሚሉበት
የሽያጭ ውል እንዲፈርስ ከተደረገ አመልካች የንግድ ቤቱን በተመለከተ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል ምንም
አይነት መብት የላቸውም ማለት ነው፡፡ የሽያጭ ውሉ እንኳን አልፈረሰም ቢባል ውሉ የተደረገው
በተጠሪዎች መካከል በመሆኑ የንግድ ቤቱ ባለቤት በሆነው አመልካች ላይ ውሉ ለ1ኛ ተጠሪ ክስ የማቅረብ
መብት አይሰጣቸውም፡፡ በመሆኑም ከዚህ አንፃር የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች 1ኛ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ
የሚያስችል መብት የላቸውም በማለት ያነሳውን መቃወሚያ ተቀብለው ክሱን ውድቅ አለማድረጋቸው
መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈመበት በመሆኑ ቀሪዎቹን ነጥቦች መመርመር ሳያስፈልግ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 21528 መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም የሠጠው ውሳኔ፣
የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 42361 ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ
እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 03-91593 ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው
ችሎት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡
2. 1ኛ ተጠሪ አመልካች ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላቸውም በማለት
ወስነናል፡፡
3. በዚህ ችሎት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ 204140
መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ ዘላለም አማረ - ከጠበቃ አሸናፊ ጌታቸው ጋር ቀረቡ

ተጠሪዎች፡- 1. ወ/ሮ አዜብ ወዳጅ

2. አቶ ግርማ አያሌው አልቀረቡም

3. አቶ ፋሲካ ባራኪ

4. ወ/ሮ አስቴር ወዳጅ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር
አቤቱታ፡- የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 64514 ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 261539 መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም
የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ
በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡
በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን
ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ሟች እናታቸው ወ/ሮ
እልፍነሽ በቀለ በቀድሞ አጠራር ከፍተኛ 21 ቀበሌ 19 አካባቢ በመንግስት ቦታ ላይ በግላቸው የገነቡት ቤት
በልማት ምክንያት ሲፈርስ በአሁኑ አጠራር ቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 06 ቤ.ቁ የሌለውን 4 በ 3 የሆነ ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በ 1999 ዓ.ም የሰሩ መሆኑን፤ እናታቸው በመታመማቸው ምክንያት ወደ 1ኛ ተጠሪ ቤት ሲመጡ በብር
600 ቤቱን ለአመልካች ያከራዩት መሆኑን፤ አመልካችም የቤቱን ኪራይ በ1ኛ ተጠሪ ስም በተከፈተ የነባክ
ሂሳብ እስከ መጋቢት ወር 2010 ዓ.ም ድረስ ሲከፍል ቆይቶ ከሚያዝያ ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ ኪራዩን
መክፈል ያቆመ መሆኑን በመግለጽ ያልከፈለውን ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከፍል፤ ቤቱን ሲከራይ በቤቱ
ውስጥ የነበረውን ቁምሳጥን እና ምንጣፍ በአይነት እንዲመልስ ወይም ግምቱን እንዲከፍል እና ቤቱን
እንዲያስረክባቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን አመልካች በሰጡት መልስ የተጠሪዎች እናት ቤቱን አልሰሩም፤ አመልካች የወረዳው የቀድሞ
አመራሮች ፈቅደውልኝ ቆሻሻውን አጽድቼ በመንግስት ባዶ ቦታ ላይ የሰራሁት ቤት ነው፤ ቤቱን በ1999
ዓ.ም ሰርቼ የተጠሪዎችን እናት በሰብአዊነት አስጠግቻቸዋለሁ፤ በልማት ምክንያት ቤት ሲፈር የሚሰጠው
የኮንዶሚንየም ቤት ወይም የቀበሌ ቤት ነው፤ የተጠሪዎች እናት ለአመልካች የሰጡት ቁምሳጥን እና
ምንጣፍ የለም፤ እናታቸው በሕይወት በነበሩ ጊዜ ያፈሩት ገንዘብ እንዳይጠፋ እና እንዳይሰረቅ በአደራ በእኔ
እጅ እንዲቀመጥላቸወ ብር 12,000 ሰጥተውኛል፤ እናታቸው ባስፈለጋቸው ጊዜ ብሩን ሲሰጣቸወ ነበር፤
እናታቸው ሲታመሙ ተጠሪዎቸ አንድም ቀን ሳይጠይቋቸው ወደ 1ኛ ተጠሪ ቤት ስለወሰዷቸው በ1ኛ ተጠሪ
ስም በተከፈተ ሂሳብ በየጊዜው የራሳቸውን ገንዘብ ስልክላቸው ነበር፤ ከወረዳው ተገኘ የተባለው የግንባታ
ፈቃድ ሀሰተኛ ነው፤ ስለሆነም ክስ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ እና ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ስለጉዳዩ ተጣርቶ
እንዲቀርብለት ካደረገ በኋላ ቤቱ የተሰራው ያለግንባታ ፈቃድ መሆኑ መረዳት ተችሏል፤ የተጠሪዎች
ምስክሮች የአፍሪካ ሕብረት የማስፋፊያ ስራ ሲሰራ የተጠሪዎቸ እናት ቤት እና የሌሎቹም ቤት እንዲፈርስ
ሲደረግ ሕጋዊ ሰነድ ያላቸውን መንግስት ምትክ ቦታ እና ካሳ ሲሰጣቸው በቀበሌ ቤት የሚኖሩትን ደግሞ
ሌላ የቀበሌ ቤት ተሰጥቷቸዋል፤ እንደ ተጠረዎች እናት ያሉትን ሕጋዊ ማስረጃ የሌላቸውን ደግሞ
በቡልጋሪያ አካባቢ ወንዝ ዳርቻ ቆሻሻ አጽድተው እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸው የተጠሪዎች እናት በ1999 ዓ.ም
ይህን ቤት እንደሰሩ፤ እናታቸው ሲታመሙ 1ኛ ተጠሪ እንደወሰዷቸው እና ቤቱን ለአመልካች እንዳከራዩት፤
ኪራዩንም ቤት እየመጣ ሲከፍል ቆይቶ በኋላ ላይ በ1ኛ ተጠሪ ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ሲያስገባ
እንደነበር የተጠሪዎች ምስክሮች አስረድተዋል፤ በማስረጃነት የቀረበው የባንክ ደብተርም አመልካች በየወሩ
ብር 600 አልፎ አልፎ ብር 1200 ሲከፍል እንደነበር ያሳያል፤ የተጠሪዎች እናት ልጆቻቸው እያሉ በስጋም
ሆነ በጋብቻ ለማይዛመዳቸው አመልካች ገንዘቡን በአደራ ይሰጣሉ ተብሎ ስለማይገመት አመልካች ይህንኑ
ለማስረዳት ያቀረባቸው ምስክሮች ቃል እምነት የሚጣልበት አይደለም፤ ስለሆነም አመልካች ያልከፈለውን
የቤት ኪራይ ከሚያዝያ 2010 ጀምሮ እስከ ጥር 2011 ድረስ ያለውን ብር 6000 / ስድስት ሺህ / ከፍሎ
ቤቱን ለቆ ለተጠሪዎች እንዲያስረክብ በማለት የወሰነ ሲሆን ምንጣፉን እና ቁምሳጥኑን በሚመለከት
የቀረበውን ጥያቄ ተጠሪዎች አላስረዱም በማለት ውድቅ አድርጎታል፡፡ ይህ ውሳኔ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ጸንቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል
ሲሆን ይዘቱም፡- አመልካች ያቀረብኩት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም፤
ተጠሪዎች ቤቱን በሚመለከት ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ የለም፤ የግራቀኛችን ክርክር እና ማስረጃ በአግባቡ
አልተመዘነም፤ ከወሳኝ ኩነት መጣ የተባለው ሰነድ ሀሰተኛ ነው፤ ቤቱን በሚመለከት የቀረበ በቂ የሆነ የሰነድ
ማስረጃ እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበት በማድረግ ሊወሰን ይገባው ነበር፤
ስለሆነም ይህ ታልፎ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ
በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የአሁን ተጠሪዎች ስለመሆኑ
ከሚመለከተው አካል የተመዘገበበ የሰነድ ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ አመልካች አከራካሪውን ቤት
ለተጠሪዎች እንዲያስረክብ የመወሰኑን አግባብነት ከመሠረታዊ የማስረጃ ምዘና መርሆዎች ጋር በማገናዘብ
ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ
እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የተጠሪዎች መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው መቃወሚያዎች መታለፋቸው
ተገቢ ነው፤ የስር ፍርድ ቤት በጉደዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው የግራቀቀኛችንን ክርክር እና ማስረጃ በአግባብ
መርምሮ እና መዝኖ በመሆኑ ውሳኔው ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሊታረም ይገባል በማለት የሚከራከሩት አመልካች የወረዳው
የቀድሞ አመራሮች ፈቅደውልኝ ቆሻሻውን አጽድቼ በመንግስት ባዶ ቦታ ላይ የሰራሁት ቤት ነው፤
የተጠሪዎችን እናት በሰብአዊነት ያስጠጋኋቸው እንጂ ቤቱን አልሰሩም ለአመልካችም አላከራዩም፤
ተጠሪዎችም ቤቱ በእናታቸው የተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረቡም በሚል ነው፡፡ አመልካች በዚህ
አግባብ የሚከራከሩ ቢሆንም ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ
ቤቶች በልማት ምክንያት የተጠሪዎቸ እናት ቤት እና ሌሎችም በአካባቢው ያሉት ቤቶች ሲፈርሱ በወቅቱ
ሕጋዊ ማስረጃ ለነበራቸው ምትክ ቤት የተሰጠ መሆኑን፤ እንደ ተጠረዎች እናት ያሉ ሕጋዊ ማስረጃ
የሌላቸው ደግሞ በቡልጋሪያ አካባቢ ያለውን የወንዝ ዳርቻ አጽድተው እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸው የተጠሪዎች
እናት በ1999 ዓ.ም ይህን ቤት እንደሰሩ ቤቱን የሰሩ መሆኑን፤ የተጠሪዎች እናት ሲታመሙም ወደ 1ኛ
ተጠሪ ቤት የተወሰዱ እና ለአመልካች በብር 600 / ስድስት መቶ / ቤቱን ያከራዩት መሆኑን እና ኪራዩን
በእጅ እና በባንክ ሒሳብ ሲከፍል የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ
10/1 መሠረት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው ስልጣን መሠረታዊ የሆነ የሕግ
ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን
ስልጣን የለውም፡፡

የተጠሪዎች እናት አከራካሪ የሆነውን ቤት ሰርተው በሕመም ምክንያት ልጃቸው ወደ ሆኑት 1ኛ ተጠሪ ቤት
ሲሄዱ ለአመልካች በብር 600 / ስድስት መቶ ብር / የተከራየ ስለመሆኑ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን
የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ በመሆኑ እና ይህ ችሎትም መሠረታዊ የሆነ
የሕግ ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን
ስልጣን የሌለው በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠውን ፍሬነገር መሠረት በማድረግ አመልካች
ያልከፈሉትን ውዝፍ የቤት ኪራይ ከፍለው አከራካሪውን ቤት ለተጠሪዎች ሊያስረክቡት ይገባል በማለት
የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት አላገኘንበትም፡፡
ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 64514 ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 261539 መጋቢት 02 ቀን 2013
ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁጥር 204264

ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (ኮርፖሬሽን) -አልቀረቡም

ተጠሪ ፡- ወ/ሮ ተሚማ ፋጂ- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ክርክሩ በገጠር መሬት ይዞታ የመጠቀም መብት ላይ ለደረሰ ጉዳት ካሳ ለማስከፈል የቀረበ ክስን መነሻ ያደረገ
ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የቡኖ በደሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ተከሳሽ፣
የኢፌድሪ ውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ታህሳሰ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ በቡኖ በደሌ ዞን ጋቺ ወረዳ ዲዴሳ ቀበሌ ውስጥ
የሚገኝ በስሜ የተመዘገበ ስፋቱ 2.5 ሄክታር የሆነ ለውዝ እየዘራው የምጠቀምበትን ይዞታ አመልካች
ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በመቆፈር የጠጠር ድንጋይ በማውጣት ይዞታው ለየትኛውም
አገልግሎት እንዳይውል አድርጎብኛል፡፡ ተጠሪ ከይዞታው በየአመቱ 50 ኩንታል ምርት የማገኝ ሲሆን የአንዱ
ኩንታል ዋጋ ብር 1,200 ሁኖ የተለያዩ ወጪዎች ተቀናሽ ተደርጎ የተጣራ አመታዊ ትርፍ ብር 50,000

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አገኛለው፡፡ አመልካች ይህን ጥቅም ስላሳጣኝ እና በዘላቂነት ስላፈናቀለኝ የ10 ዓመት ካሳ ብር 500,000
ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የፕሮጀክቱ ባለቤት የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ስለሆነ
ልከሰስ አይገባም፤ ጉዳዩም ከውል ውጪ ግንኙነትን መሰረት ያደረገ ስለሆነ በፍ/ሕ/ቁጥር 2143 መሰረት
በይርጋ ይታገዳል፤ የፕሮጀክቱ ባለቤትም ወደ ክሱ ጣልቃ እንዲገባ ይታዘዝልኝ በማለት ተከራክሯል፡፡ በፍሬ
ጉዳይ ላይ በሰጠው መልስ አመልካች ከፕሮጀክቱ ባለቤት ጋር ጥር 31 ቀን 2011 እ.አ.አ. ባደረገው የአርጆ
ዲዴሳ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ውል አንቀፅ 11(ኤ-1) መሰረት በፕሮጀክቱ አካባቢ ባሉ ባለይዞታዎች ላይ
ለሚደርስ ጉዳት አስፈላጊውን ክፍያ ለመፈፀምም ሆነ የስራ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ኃላፊነት ያለበት
የፕሮጀክቱ ባለበት ነው፤ ይዞታው ከመጀመሪያው በፕሮጀክቱ ክልል ውስጥ የሚገኝ ጥራት ላለው ድንጋይና
ገረጋንቲ ምርት ተለይቶ በአማካሪ መሀንዲሱ የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት የተፈቀደ
ነው፡፡ በክሱ እና በይዞታ ማረጋገጫው ላይ የተጠቀሰው የይዞታው ስፋት ልዩነት አለው፡፡ ይዞታውም ለእርሻ
የማይውል ድንጋያማ እና ተራራማ ነው፡፡ ለምርት ይውላል ቢባል እንኳ በየአመቱ አንድ አይነት የለውዝ
ምርት ብቻ ሊመረትበት አይችልም፡፡ ለምርታማነት የሚያስፈልጉ የምርት ግብዓት ወጪዎች በባለሞያ
ሊጣራ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴርም ወደ ክርክሩ ጣልቃ እንዲገባ ታዞ በሰጠው መልስ በፕሮጀክቱ ክልል
ውስጥ ለተካተቱ ይዞታዎች ተገቢውን የካሳ ክፍያ መፈጸሙን፤ አከራካሪው ይዞታ ከፕሮጀክቱ ክልል ውጪ
የሚገኝ፤ አመልካች በፕሮጀክቱ ባለቤት እና አማካሪ ድርጅት ከተሰጠው ዲዛይን ውጪ በመውጣት
አከራካሪውን ይዞታ ቆፍሮ ድንጋይ እና ገረጋንቲ በማውጣት ጥፋት የፈጸመ በመሆኑ ለክሱ ኃላፊነት
የለብኝም በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር
59979 ቅፅ 11 ላይ እንደታተመው በዚህ መዝገብ ከተያዘው ተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የሚቀርብ ክስ በ2 ዓመት
ይርጋ የማይታገድ መሆኑን ገልጾ ውሳኔ ስለሠጠ ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት መቃወሚያውን
አልፎታል፡፡ በፍሬ ጉዳይ ላይ የግራ ቀኙን የሰነድ ማስረጃ፣ የሰው ምስክር እንዲሁም ከተለያዩ የመንግስት
መስሪያ ቤቶች በተውጣጣ ኮሚቴ ጉዳዩ ተጣርቶ እንዲቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የቀረበውን ማስረጃ
መዝኖ የተጠሪ ምስክሮች በይዞታው ላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑን አስረድተዋል፤ የአመልካች ምስክሮችም
የተለያዩ ምክንያቶችን ይስጡ እንጂ በተጠሪ ይዞታ ላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑን አልደበቁም፡፡ የጋቺ ወረዳ
አስተዳደር ፅ/ቤትም ከተለያዩ መስሪያ ቤት ተወካዮች ጋር በመሆን ጉዳዩን አጣርቶ ከይዞታው ላይ
የሚገኘውን የምርት መጠን ግምት እንዲሁም ይዞታውን ወደ ፊት ለምርት አገልግሎት እንዲውል ለማስቻል
የተከመረውን አሸዋ ለማስተካከል የሚያስፈልገውን ወጪ ገልጾ ሚያዝያ 30 ቀን 2011 በቁጥር ቲ-
33/862/2011 ዓ.ም የፃፈው ደብዳቤ በተጠሪ ይዞታ ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል፡፡ በመሆኑም
አመልካች በፍ/ሕ/ቁጥር 2027(2) እና 2028 መሰረት ኃላፊነት ያለበት ሲሆን አመልካች በፕሮጀክቱ ባለቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከተሰጠው የፕሮጀክቱ ክልል ውጪ በመውጣት ካሳ ባልተከፈለበት ይዞታ ላይ ጉዳት ያደረሰ ስለሆነ ጣልገብ
ለክሱ ኃላፊነት የለበትም በማለት ወስኗል፡፡ የካሳ መጠኑን በሚመለከትም የተለያዩ የሚመለከታቸው
የመንግስት መስሪያ ቤቶች የላኩትን ማስረጃ መነሻ በማድረግ በደንብ ቁጥር 135/1999 አንቀፅ 16(2,3)
ተጠሪ ባለፉት 5 ዓመታት በአመት በአማካይ የሚያገኙት ብር 39,390 በ10 ተባዝቶ በድምሩ ብር
393,390፣ ውሳኔ ባረፈበት የገንዘብ መጠን ከሚሰላ ከ10 በመቶ የጠበቃ አበል እንዲሁም የዳኝነት ክፍያ ጋር
አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል፡፡

አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ችሎቱም ተጠሪ
በይዞታቸው ላይ በ2006 ዓ.ም ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ገልፀው ክሱን ያቀረቡት ታህሳስ 12 ቀን 2012
ዓ.ም 2 ዓመት ካለፈ በኋላ ስለሆነ በፍ/ሕ/ቁጥር 2143 እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት በቅፅ 20 በታተመው መዝገብ ቁጥር 119563 በሰጠው ውሳኔ መሰረት ክሱ በይርጋ ይታገዳል
በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሮታል፡፡

ተጠሪ በበኩላቸው ይህን ውሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት አቅርበዋል፡፡ ችሎቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ተጠሪ ክሱን ያቀረቡት አመልካች ከ2006 ጀምሮ
ይዞታቸውን ቆፍሮ ድንጋይ በማውጣት ይዞታው አገልግሎት እንዳይሰጥ በማድረግ ያፈናቀላቸው መሆኑን
በመግለፅ ስለሆነ ለጉዳዩ ተፈጻሚነት ያለው ከውል ውጪ ድንጋጌ ሳይሆን የህገ መንግስቱ አንቀፅ 40(8)
ሁኖ ተመጣጣኝ ካሳ ሊከፈል የሚገባ ስለመሆኑ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅፅ 11
በታተመው በመ/ቁጥር 59979 ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ በፍሬ ጉዳይ ላይ የቀረበውን
አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ይስጥ በማለት በነጥብ መልሶታል፡፡

አመልካች መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን ያቀረበው ይህን የክልሉን የሰበር ሰሚ
ችሎት ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ ጉዳዩን በመጀመሪያ በተመለከተው የቡኖ በደሌ
ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢፌድሪ ውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚስቴር በጣልቃ ገብነት የተከራካረ በመሆኑ
የክልሉ ፍርድ ቤት ጉዳን የተመለከተው በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80(3) መሰረት በውክልና ስልጣኑ ስለሆነ
የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን መመልከቱ ተገቢ አይደለም፤ ይዞታውም ለህዝብ አገልግሎት የዋለ
ስላልሆነ ለጉዳዩ ተፈጻሚነት ያለውን የፍ/ሕ/ቁጥር 2143 በመተው ተፈጻሚነት የሌለውን ውሳኔ መነሻ
በማድረግ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የይርጋ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚል ነው፡፡

የሰበር አቤቱታው በአጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በጉዳዩ ላይ አከራክሮ ውሳኔ
የመስጠት ስልጣን ያለው መሆን? አለመሆኑን? ለማጣራት ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪ መልሳቸውን
እንዲያቀርቡ ታዟል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪም ግንቦት 23 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈ መልሳቸውን አቅርበዋል፡፡ የመልሱ ይዘት ባጭሩ በስር ፍርድ
ቤት ተጠሪ ክስ ያቀረብኩት በአመልካች ላይ ነው፤ በአመልካች ጠያቂነት ወደ ክርክሩ የገባው የስር ጣልቃ
ገብ ከሃላፊነት ነፃ የተባለ በመሆኑና አመልካችም ጣልቃ ገቡ ነፃ መባሉን በመቃወም ይግባኝ ስላልጠየቀ
የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ ይዞታውንም ለህዝብ ጥቅም ሲባል አመልካች
ለም አፈሩን ቆፍሮ በማውጣት በቋሚነት ያፈናቀለኝ ስለሆነ የአዋጅ ቁጥር 455/97፣ የህገ መንግስቱን አንቀፅ
40(8) እና ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 59979 በሰጠው አስገዳጅ ትርጉም መሰረት የይርጋው
መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካችም ሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልሱን ያቀረበ ሲሆን የሠበር አቤቱታውን በማጠናከር
ተከራክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን የመመልከቱን
እንዲሁም ክሱ በይርጋ አይታገድም የመባሉን አግባብነት በስር ፍ/ቤት ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ
ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዲሁም ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ
እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡

እንደመረመርነውም አመልካች በዋናነት የሚከራከረው የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በሰበር አይቶ
የመወሰን ስልጣን የለውም፤ ለክርክሩ ተፈጻሚነት ያለው ድንጋጌም የፍ/ሕ/ቁጥር 2143 ሁኖ እያለ ክሱ
በይርጋ አይታገድም ተብሎ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት ነው፡፡ ተጠሪ በበኩላቸው በስር ፍርድ ቤት
ክርክር ጣልቃ ገብ የነበረው ተከራካሪ ኃላፊነት የለበትም ተብሎ ስለተወሰነና አመልካች ይህን በመቃወም
ያቀረበው ይግባኝ ስለሌለ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በሰበር መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ አመልካች
ከይዞታው በቋሚነት ያፈናቀለኝ በመሆኑ ክሱ በይርጋ አይታገድም ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ሊፀና ይገባል
በማለት ተከራክረዋል፡፡

በመጀመሪያ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በሰበር የመመልከቱን ተገቢነት መመርመሩ አስፈላጊ ነው፡፡
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በሰበር ተመልክቶ ውሳኔ በሰጠበት ታህሳስ 13 ቀን
2013 ዓ.ም ስራ ላይ በነበረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 5(1) መሰረት የፌደራል
መንግስት አካል ተከራካሪ የሚሆንባቸውን ጉዳዮች የመመልከት የፍትሐ ብሔር የዳኝነት ስልጣን የፌደራል
ፍርድ ቤቶች መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ በተመለከተው የቡኖ በደሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ተጠሪ ክስ ያቀረቡት በአመልካች ላይ ብቻ በመሆኑ ጉዳዩ ከመነሻው የክልል ጉዳይ ነበር፡፡ ነገር ግን
በአመልካች ጠያቂነት የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በክርክሩ ጣልቃ እንዲገባ ታዞ የክርክሩ
ተሳታፊ መሆኑ ጉዳዩን በፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ስር እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡ በክርክሩ
መጨረሻ ጣልቃ ገብ ለክሱ ኃላፊነት የለበትም ተብሎ ተወስኗል፡፡ አመልካች በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ
ላይ ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሲያቀርብ 2ኛ መልስ ሰጪ ተደርጎ የነበረ
ቢሆንም ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቅሬታ ሲቀርብ ግን ጣልቃ ገብ የነበረው የፌደራል ተቋም በተከራካሪነት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሳይሰየም ቀርቷል፡፡ ጉዳዩን በፌደራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር እንዲወድቅ አድርጎት የነበረው ምክንያት
ማለትም የፌደራል መንግስት ተቋም የነበረው የስር ጣልቃ ገብ ከክርክሩ ውጪ መሆኑ ጉዳዩ የፌደራል
መንግስት እንዲሆን ያደረገው ምክንያት ቀሪ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህም ጉዳዩ የክልል ጉዳይ እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 16
በታተመው በመዝገብ ቁጥር 95033 ላይ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ በመሆኑም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
የፌደራል መንግስት ተቋም ተከራካሪ ሳይደረግ በተጠሪ በቀረበለት የሰበር አቤቱታ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ
መወሰኑ በሌለው ስልጣን ነው የሚያስብል ሁኖ አላገኘነውም፡፡

በሁለተኛ ደረጃ መፍትሔ ማግኘት ያለበት ጉዳይ በተጠሪ የቀረበው ክስ በይርጋ አይታገድም የመባሉ
አግባብነት ነው፡፡ ተጠሪ ጉዳዩን በመጀመሪያ በተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሳቸውን የመሰረቱት
አመልካች ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ስፋቱ 1.5 ሄክታር የሆነ ለውዝ እያመረቱ የሚገለገሉበትን ይዞታ ቆፍሮ
ጠጠር እና ገረጋንቲ በማውጣት ለማንኛውም አገልግሎት እንዳይውል አድርጓል በሚል ነው፡፡ ተጠሪ
በክሳቸው ላይ ይዞታው በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ውሃ መስኖና እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤትነት ለሚገነባው የአርጆ
ዲዴሳ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እንዲውል ይዞታው ሙሉ ለሙሉ ተወስዶብኛል በማለት ያቀረቡት
መከራከሪያ የለም፡፡ ክሳቸው በአመልካቹ ድርጊት ይዞታው ለሌላ አገልግሎት እንዳይውል ስለተደረገ አመልካቹ
ካሳ ሊከፈለኝ ይገባል የሚል ነው፡፡ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካቹ በፕሮጀክቱ ባለቤት እንዲሁም
አማካሪው የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት ከተሰጠው ዲዛይን ውጪ በመውጣት
የተጠሪን ይዞታ በመቆፈር ጠጠር እና ገረጋንቲ በማውጣት ጉዳት ያደረሰ መሆኑ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ
በጉዳዩ ላይ ትክክለኛ ውሳኔ መስጠት እንዲቻል ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት በተውጣጡ ባለሞያዎች
ጉዳዩ ተጣርቶ እንዲቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በቀረበው ማስረጃ በይዞታው ላይ የተከመረውን አሸዋ
በማሽን በመደልደል ለማስተካከል 7 ሰዓት እንደሚፈጅ እና ለአንድ ሰዓት ብር 3,000 ክፍያ የሚጠይቅ
መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይህም የተጠሪ ይዞታ በፕሮጀክቱ ባለቤት ለመስኖ ግድብ ግንባታው የተወሰደባቸው
አለመሆኑን እንዲሁም በአመልካች በተፈጸመው ጥፋት በይዞታው ላይ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም በግንባታ
ማሽኖች ይዞታውን በ7 ሰአታት ውስጥ እንዲስተካከል በማድረግ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ማድረግ
የሚቻል መሆኑን የሚያስገነዝብ በመሆኑ ተጠሪ ለሕዝብ አገልግሎት ሲባል ከይዞታቸው በቋሚነት
አለመፈናቀላቸውን የሚያመላክት ነው፡፡ በመሆኑም ተጠሪ በፕሮጀክቱ ምክንያት ከይዞታቸው ለዘለቄታው
ተፈናቅለዋል ሊባል አይችልም፡፡

ጉዳዩ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል ያለን ግንኙነት መሰረት በማድረግ አመልካች ከፕሮጀክቱ ክልል
ውጪ በመሔድ በይዞታቸው ላይ ያደረሰውን ጉዳት የሚመለከት ከውል ውጪ የሆነን ኃላፊነት የሚያስከትል
ስለሆነ ይርጋን በተመለከተ ለክርክሩ ተገቢነት ያለው ድንጋጌ የፍ/ሕ/ቁጥር 2143 ነው፡፡ በድንጋጌው ንዑስ
ቁጥር 1 ስር ተበዳዩ ክስ ማቀረብ ያለበት ካሳ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ በ2 ዓመት ውስጥ
መሆን እንዳለበት ተመላክቷል፡፡ ተጠሪ አመልካቹ ይዞታቸውን በመቆፈር ጠጠር እና ገረጋንቲ ማውጣት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የጀመረው 2006 ዓ.ም መሆኑን በክሳቸው የገለጹ ሲሆን ክሱን ያቀረቡት ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም
ድርጊቱ መፈጸሙ ከታወቀ ከ2 ዓመት በኋላ ነው፡፡

ስለዚህ በፍ/ህ/ቁጥር 2143/1 እና በተመሳሳይ ጉዳይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ
20 በታተመው በሰበር መዝገብ ቁጥር 119563 በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት የተጠሪ የጉዳት ካሳ ክስ
በሁለት አመት ውስጥ ባለመቅረቡ በይርጋ የሚታገድ በመሆኑ ውድቅ መደረግ እያለበት ከዚህ በተቃራኒ
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በቅፅ 11 የታተመውን የሰ/መ/ቁጥር 59979 በልማት ምክንያት ከይዞታቸው በቋሚነት እንዲፈናቀሉ
የተደረጉ አርሶ አደሮች የሚያቀርቡት የካሳ ይከፈለኝ ክስ ላይ ተግባራዊ መደረግ ያለበትን የይርጋ ጊዜ
በሚመለከት የሰጠውን የሕግ ትርጉም በዚህ መዝገብ ለተያዘው ጉዳይ ተፈጸሚ በማድረግ ክሱ በ 2 ዓመት
ይርጋ አይታገድም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በአብጫ ድምፅ
ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የቡኖ በደሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 03498 ሰኔ 20 ቀን 2011 ዓ.ም እና የኦሮሚያ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 333952 ታህሳስ 13 ቀን 2012 ዓ.ም
በዋለው ችሎት የሠጡት ውሳኔ ተሽሯል፡፡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
በመዝገብ ቁጥር 220314 ጥር 28 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የልዩነት ሃሳብ

ሥሜ በተራ ቁጥር ሦስት ላይ የተሰየምኩት ዳኛ ከአብላጫው ሃሳብ የተለየሁበትን ምክንያት እንደሚከተለው


አስፍሬያለሁ፡፡

ኢትዮጵያ የፌደራል የመንግሥት አወቃቀር ሥርዓትን በ1987 ዓ/ም በወጣው የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት
መከተሏን ተከትሎ ሥልጣን በክልሎችና በፌደራል መንግሥት የተከፋፈለ ስለመሆኑ በሕገ-መንግሥቱ
ከአንቀጽ 50-52 ላይ ተመልክቷል፡፡ በዚህም ክልሎች በሥልጣናቸው ሥር ባሉ ጉዳዮች ሉዓላዊ ሥልጣን
አላቸው፡፡ ክልሎች እንደ ፌደራል መንግሥት ሕግ-አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና የዳኝነት አካል ያደራጃሉ፡፡
በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78 መሠረት የዳኝነት አካሉ በፌደራል እና በክልል መንግሥት ደረጃ
መቋቋሙ እና በአንቀጽ 80(1)(2) ላይ በፌደራል ጉዳዮች የፌደራል ፍርድ ቤት፤ በክልላዊ ጉዳዮች የክልል
ፍርድ ቤት የመጨረሻ ሥልጣን ያለው መሆኑ መመልከቱ በፌደራልና በክልል መንግሥታት መካከል
የፍርድ ቤት የሥልጣን ክፍፍል እንዳለ ያሳያል፡፡ የፌደራል ወይም የክልል ጉዳዮች የሚለው በጉዳይ ዓይነት
የተከፋፈለ ሥልጣን ስለሆነ የፍርድ ቤቶች ሥልጣን የተለየው የሥረ-ነገር ሥልጣንን መሠረት ያደረገ
ቢመስልም ጉዳዩ ከሉዓላዊ ሥልጣን እና ክልላዊ ጉዳይ በፌደራል ፍርድ ቤት ቢታይ ከጣልቃገብነት ጋር
የተያያዘ በመሆኑ ጉዳዩ የብሔራዊ ዳኝነት ሥልጣንን የሚያስነሳ ነው፡፡ በፌደራል መዋቅር የብሔራዊ
የዳኝነት ሥልጣን መሠረቱ ዓለምአቀፍ ሕግ ሳይሆን ሕገ-መንግሥት ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ የፌደራልን ሆነ
የክልልን ፍርድ ቤቶች ያቋቋመና አክብረው ለማስከበርም ግዴታ የጣለ ነው፡፡ ውጤቱም እንደ ሀገር
የሚመረመረው የብሔራዊ የዳኝነት ሥልጣን ከሌላ ሀገር ዜጋ ጋር በተያያዘ እና ሌሎች ሀገሮች ጋር
የዲፕሎማቲክ ቅራኔንም ሊፈጥር የሚችል ሲሆን በፌደራልና በክልል መንግሥታት መካከል ያለው ግን
በአንድ ሀገር ያሉና በሕገ-መንግሥቱ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማሕብረሰብ
ለመፍጠር በሚሠሩ ተቋማትና ዜጎች ላይ፣ የተለያየ ሥልጣን ቢሆንም የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ደግሞ ባላቸው
ተቋማት መካከል የሚነሳ ስለሆነ የተለየ ያደርገዋል፡፡ በፌደራል መዋቅር የፌደራል መንግሥት ሉዓላዊነቱ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመላው የኢትዮጵያ ግዛት ነው፡፡ ነገር ግን በግዛቱ ሥር ሁሉንም በፈቃዱ መወሰንና መፈጸም የሚችል
ሳይሆን በግልጽ በሕግ በተዘረጋው ሥርዓት ሥልጣኑን የሚጠቀም መሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ ለክልል
ፍርድ ቤት ሥልጣን መሠረቱ ግን በግዛት ክልል ሥር ያለ ሠውና ንብረት መሆን አለመሆኑን መሠረት
ያደረገ (limited sovereignty) ነው፡፡

በሕገ-መንግሥቱ የሥልጣን ክፍፍሉም የክልል ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የፌደራል ጉዳዮችን በውክልና
ማየት የሚችሉ ሲሆን ክልላዊ ጉዳዮች በክልሎች ሉዓላዊ ሥልጣን ክልል ውስጥ (exclusive jurisdiction
of state courts) ያለ በመሆኑ፤ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 80(3)(ሀ) ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር
ሰሚ ችሎት የተሠጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማየት አይችሉም፡፡ ይሕም
ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የመዳኘት ሥልጣን (judicial jurisdiction) የሌላቸው መሆኑን
ሲያሳይ በውክልና እና በጣምራ ሥልጣናቸው ከሚመለከቱት በሥተቀር የክልል ፍርድ ቤቶች የፌደራል
ጉዳዮችን ማየት አይችሉም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ መመርመር ያለበት በሕገ-መንግሥቱ የተመለከተው የፍርድ
ቤቶች የጣምራነት ሥልጣን (concurrent jurisdiction) እና የፌደራል ጉዳዮች የሚወሰኑበት ሥርዓት ነው፡፡
የፌደራል ጉዳዩች ምን እንደሆኑ በሕገ-መንግሥቱ ያልተወሰነ ቢሆንም በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር
25/1988 አንቀጽ 3 መሠረት የፌደራል ጉዳዮች ሕገ-መንግሥቱን፣ የፌደራል መንግሥት ሕጎችንና ዓለም
አቀፍ ሥምምነቶችን መሠረት ያደረጉ ጉዳዮች (based on laws)፤ በፌደራል ሕግ ተገልጸው በተወሰኑ
ባለጉዳዮች (parties) እና በሕግ በተገለጹ ቦታዎች (places) ላይ የሚነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በፌደራል ፍርድ
ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 4 እና 5 መሠረት የተዘረዘሩት የፌደራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት
ሥልጣኑ የሚመለከታቸው ሕግንና ባለጉዳዮችን መሠረት አድርጎ የተለዩ የፌደራል ጉዳዮች ሲሆን በሌሎች
ሕጎች በግልፅ ለፌደራል ፍርድ ቤት የተሠጡ ጉዳዮችን ይጨምራል፡፡ የአዋጁን አንቀጽ 11 እና ተከታዮችን
ሥንመለከት ደግሞ ቦታን መሠረት በማድረግ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች ላይ የሚነሡ ጉዳዮች የፌደራል
ፍርድ ቤት የሚመለከታቸው የፌደራል ጉዳዮች ስለመሆናቸው ተደንግጓል፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 3 መሠረት ሕግን መሠረት አድርጎ የተለዩት
የፌደራል ጉዳዮች ውስጥ የፌደራል መንግሥት ሕጎችን መሠረት ያደረጉ ጉዳዮች ያሉበት በመሆኑና በአዋጁ
የትርጉም ክፍል አንቀጽ 2(3) ላይ የፌደራል መንግሥት ሕጎች ማለት በሕግ በተሠጠው ሥልጣኑ ክልል
ሥር ያሉ ነባር ሕጎችን የሚጨመር መሆኑ ሲታይ በሕግ በግልጽ የፌደራል ፍርድ ቤት ሥልጣን ሥር
ከተመለከቱት ሕግን መሠረት ያደረጉ ጉዳዮች እና በፌደራል ሥልጣን ሥር እንዲታዩ ከተወሰኑት ባለጉዳዮች
ውጭ ያሉ የፌደራል ሕግን መሠረት ያደረጉ ጉዳዮች የፌደራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በጣምራ
ሥልጣናቸው የሚመለከቷቸው ናቸው፡፡ ሥለሆነም የፌደራል ሕግን መሠረት ያደረጉ ሌሎች ጉዳዮች
እንደተነሱበት ቦታ የፌደራል ፍርድ ቤት ወይም የክልል ፍርድ ቤት በክልላዊ ሥልጣኑ ሊመለከተው
ይችላል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓት መሠረት አድርጎ የተዋቀረው የዳኝነት ሥልጣን የፌደራል እና የክልል ፍርድ
ቤቶች ካላቸው የጣምራነት ሥልጣን ባለፈ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 78(2) እና 80(4-6) የፌደራል ፍርድ
ቤት በብቸኝነት ሥልጣኑ የሚመለከታቸውን ጉዳዮች የክልል ጠቅላይና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በውክልና
እንዲመለከቱ ሥልጣን ሰጥቷል፡፡ ይህም ሕገ-መንግሥቱ የክልል ፍርድ ቤቶችን ማብቃትን
(empowerment)፣ የክልሎችን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ዓላማ ያለውና ተቋሞቻቸው ላይ አመኔታ ያለው
መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በሕገ-መንግሥቱ የዳኝነት አካል በፌደራልና በክልል ደረጃ በየእርከኑ መዋቀሩ ሲታይ
አደረጃጀቱ በተዋረድ ያለ የትይዩ አቀራረጽ (dual system) ያለው ቢሆንም የፌደራልና የክልል ጉዳይን
የክልል ፍርድ ቤቶች መመልከታቸው የተደባለቀ (integrated system) እንደሚከተልም ያሳያል፡፡

የክልል ፍርድ ቤቶች በጣምራ ሥልጣናቸው በክልል ግዛታቸው የተነሱ ጉዳዮች የመመልከት ሥልጣን
ያላቸው በመሆኑ የፌደራል ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ሥልጣን አይኖረውም፡፡ ጉዳዩ በክልል ፍርድ ቤት
የሚታየው ጉዳዩ የተነሳበትን ቦታና ተከራካሪውን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ የጣምራነት ሥልጣን መሠረቱ
የፌደራል መንግሥት ሕግን መሠረት ያደረገ የፌደራል ጉዳይ በመሆኑ የፌደራል ፍርድ ቤት በፌደራል
ጉዳይ ላይ ብሔራዊ የመዳኘት ሥልጣን የለውም ሊባል አይችልም፡፡ ነገር ግን በፌደራል ፍርድ ቤት አዋጅ
ቁጥር 25/1988 አቀራረጽ መሠረት ከተለዩት ውስን የፌደራል ፍርድ ቤት ሥልጣኖች ውጭ ያሉ በክልል
ግዛት የሚነሱ ጉዳዮችን የክልል ፍርድ ቤቶች እንዲመለከቷቸው የተተወ በመሆኑ ጉዳዩ የሥረ-ነገር
ሥልጣን ጥያቄ የሚያስነሳ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ የክልል ፍርድ ቤቶች በፌደራል ፍርድ ቤት በብቸኝነት
እንዲታዩ የተለዩ ጉዳዮችን (exclusive jurisdiction) በግዛታቸው በተከሠቱ ጉዳዮች፣ ባሉ ሠዎቸ ወይም
ንብረቶች ጋር የሚነሱ ሲሆን በውክልና (delegation) እንዲመለከቱ በሕገ-መንግሥት ሥልጣን
ተሰጥቷቸዋል፡፡ የክልል ፍርድ ቤቶች በግዛታቸው ባሉ ሠዎቸ ወይም ንብረቶች ጋር የሚነሳ የፌደራል
ጉዳይን ውክልናቸው እስካልተነሳ ድረስ የመመልከት ሥልጣን አላቸው፡፡

በዚህም መሠረት በተያዘው ጉዳይ በግራቀኙ ክርክር በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሰሚ ችሎት የኢፌዴሪ ውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በክርክሩ በጣልቃገብነትና በመልስ
ሰጭነት ተከራክሯል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የፌደራል መንግሥት አካል በመሆኑ በፌደራል ፍርድ
ቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5(1) መሠረት ክርክሩ የፌደራል ጉዳይ ሆኗል፡፡ የሥር ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ክርክሩን የተመለከተውም የፌደራል ጉዳይን በውክልና የማየት ሥልጣን ያለው በመሆኑ ነው፡፡
የአመልካች ይግባኝ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከታየ በኋላ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
ጉዳዩን ሊመከተው አይችልም፡፡ የክልል ሠበር ሰሚ ችሎቶች በክልላዊ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻ የዳኝነት
ሥልጣን ያላቸው ስለመሆኑ በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 80(3)(ለ) ላይ ተመልክቷል፡፡ የክልል ፍርድ
ቤቶች በውክልና የሚመለከቷቸው ጉዳዮች የፌደራል ጉዳዮች በመሆናቸው የክልል ሠበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን
ለማየት ሥልጣን አይኖረውም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩን የፌደራል ያደረገው ተከራካሪ በክርክሩ አለመሳተፉ ጉዳዩን መልሶ ክልላዊ ጉዳይ አያደርገውም፡፡ ጉዳዩ
የፌደራል የሆነው በጉዳዩ ዓይነት ወይም በተከራካሪዎች አድራሻ ወይም በተከራካሪዎች ማንነት ቢሆንም
ጉዳዩ አንዴ የፌደራል ጉዳይ ከሆነ እስከመጨረሻው በፌደራል ፍርድ ቤት ወይም የፌደራል ጉዳይን
በውክልና ለመመልከት ሥልጣን ባላቸው የክልል ፍርድ ቤቶች ሊታይ የሚችል የፌደራል ጉዳይ እንጂ
የውክልና ሥልጣን በሌለው ፍርድ ቤት ወይም ችሎት ሊታይ የሚችል ክልላዊ ጉዳይ ሊሆን አይችልም፡፡
ጉዳዩ የፌደራል ወይም ክልላዊ ጉዳይ መሆን አለመሆን በሕገ-መንግሥቱ ከተቀረጸው የፌደራል አወቃቀርና
ከፌደራል መንግስት ሆነ ከክልሎች ሥልጣን ጋር ግንኙነት ያለው በመሆኑ አንድ ጉዳይ በፌደራል
መንግሥቱ ሥልጣን ሥር ካረፈ በኋላ ተመልሶ ጉዳዩ የክልል መንግሥት ሥልጣን የሚሆንበት ሥርዓት
ሊፈጠር አይችልም፡፡ ሥለሆነም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በተጠሪ የቀረበው
የሠበር አቤቱታን ለመመልከት ሥልጣን የለኝም በማለት መወሰን ሲገባው የሰበር አቤቱታውን መመልከቱ
መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡

ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሥር ከፍተኛ ፍርድ
ቤትን ውሳኔ በመሻሩ ተጠሪ ጉዳዩ ላይ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 321(2) መሠረት በሁለተኛ ይግባኝ ለፌዴራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የማቅረብ መብት ያላቸው በመሆኑና ጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ
ያልተሰጠበት ስለሆነ በሥረ-ነገሩ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ሊመረመር አይገባም በማለት በሃሳብ ተለይቻለሁ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ /መ/ቁ፡- 204300

ቀን፡- መስከረም 28 ቀን 2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን - ነ/ፈ አሰፋ እሸቱ ቀረቡ

ተጠሪዎች፡- 1. ዶ/ር በድሩ ሁሴን

2. ወ/ሮ አዜብ አመልማል ጠበቃ ማርሻል ፍቅረማርቆስ ቀረቡ

3. አቶ ኪሮስ መሐሪ

4. አቶ ሽፈራው በየነ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 268995 በቀን 22/12/2012 ዓ.ም አመልካች በመንገድ ሥራ
ምክንያት የፈጠረው የሁከት ተግባር እንዲወገድ ሲል የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 259606 በቀን 19/06/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ
መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ ሁከት ይወገድልኝ በሚል የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል
መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች፤ የአሁን
አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት
በአጭሩ፡- በማዕድን እና ኢነርጂ የመኖሪያ ቤት ሥራ ማሕበር በ 1981 ዓ.ም በተሰጠን የማሕበር ይዞታ
በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 14 ክልል ውስጥ ቤት ሰርተን ሕጋዊ ካርታ ተሰጥቶን የምንገለገልበት ይዞታ አለን፤
በመሠራት ላይ ያለው እና በይዞታችን ፊት ለፊት የሚያልፈው መንገድ ፕላን 20 ሜትር ነው፤

አመልካች መንገዱን አሻሽዬ እሰራለሁ በማለት 9ኛ እና 10ኛውን ማስተር ፕላን በሚጻረር ሁኔታ የመንገድ
ግንባታውን በማከናወን ከመንገዱ አጋማሽ ጀምሮ የተጠሪዎች ይዞታ በሚገኝበት በመንገዱ ቀኝ በኩል
አምስት ሜትር እና በላይ የሚያፈርስ ድርጊት በማከናወን ሁከት የፈጠረ በመሆኑ የፈጠረው ሁከት
እንዲወገድ ይወሰንልን የሚል ነው፡፡

የአሁን አመልካች በሰጠው መልስ ክሱ በድጋሚ የቀረበ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ
ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ ደግሞ ከከተማው መሪ ፕላን ውጪ የሠራው ሥራ እንደሌለ በመግለጽ የተጠሪዎች
ክስ ወድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን በመስማት እና አግባብነት ያለውን ትዕዛዝ በመስጠት ጉዳዩን ካጣራ በኋላ
አመልካች እያናከናወነ ባለው የመንገድ ሥራ ምክንያት የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ሲል ወስኗል፡፡
አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታ ያቀረበ
ቢሆንም አቤቱታው በትዕዛዝ ውድቅ ተደርጓል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል
ሲሆን ይዘቱም፡- ጉዳዩ በድጋሚ የቀረበ ክስ ነው በማለት የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚ ውድቅ
የተደረገው አላግባብ ነው፤ በፕላኑ ላይ የቀረበ ቅሬታ ሳይኖር የመንገድ ግንባታው ሕጋዊ ነው? ወይስ
አይደለም? በማለት የተያዘው ጭብጥ ተገቢ አይደለም፤ የጸደቀ መሪ ፕላን እያለ የሰው ምስክሮችን
በመስማት የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም
ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ኮሚኒኬሽን
መንገዱ እየተሰራ ያለው በጸደቀው የመንገድ ዲዛይን መሠረት መሆኑን መግለጫ ሰጥቶ ባለበት ሁኔታ
አመልካች በመንገድ ሥራው ምክንያት የፈጠረው የሁከት ተግባር እንዲወገድ በማለት የመወሰኑን አግባብነት
ከ9ኛው እና 10ኛው ማስተር ፕላን እንዲሁም ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይት ፕላን ጋር በማገናዘብ
ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ
እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተጠሪዎች መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የአመልካች የሰበር አቤቱታ የፍሬነገር እና ማስረጃ ምዘናን የሚመለከት
እንጂ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት መመዘኛን አያሟላም፤ የስር ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው
በአግባቡ አጣርቶ በመሆኑ ውሳኔው ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም የግራቀኙን ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው
መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ የስር ፍርድ ቤት አስቀድሞም
ቢሆን በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው ጉዳዩን ለማየት የሚያስችል የስረ ነገር ስልጣን ኖሮት ነው? ወይስ
አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

የአሁን ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ አመልካች 9ኛ እና 10ኛውን ማስተር ፕላን በሚጻረር
ሁኔታ የመንገድ ግንባታ በማከናወን በተጠሪዎች ይዞታ ላይ የፈጠረው የሁከት ተግባር እንዲወገድ የሚል
ሲሆን የአመልካች መከራከሪያ ደግሞ የመንገድ ግንባታው በከተማው ማስተር ፕላን መሠረት የሚሠራ
በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም የሚል ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41/1/ሀ የከተማውን መሪ ኘላን
አፈፃፀም የሚመለከት የይዞታ ባለመብትነት፣ የፈቃድ አሠጣጥ ወይም የቦታ አጠቃቀምን በተመለከተ
በሚነሡ ጉዳዮች ላይ የሚቀርበው ክርክር የከተማው አስተዳደር ፍ/ቤቶች ሥልጣን መሆኑን ይደነግጋል፡፡

በያዝነው ጉዳይ ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ 9ኛ እና 10ኛውን ማስተር ፕላን በሚጻረር ሁኔታ የመንገድ
ግንባታ በማከናወን በተጠሪዎች ይዞታ ላይ የፈጠረው የሁከት ተግባር እንዲወገድ የሚል በመሆኑ እና
አመልካችም በከተማው ማስተር ፕላን መሠረት መንገዱን በመገንባት ላይ ያለ መሆኑን በመግለጽ
የሚከራከር በመሆኑ የግራቀኙ ክርክር የከተማውን መሪ ኘላን አፈፃፀምን የሚመለከት ነው፡፡ በመንገድ
ምክንያት ይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ሰው ደግሞ እርምጃው ከሕግ ውጪ ነው የሚል ከሆነ
የከተማውን መሪ ፕላን መሠረት ተደርጎ ምላሽ የሚያገኝ እንጂ የይዞታ ባለመብትነትን ብቻ መሰረት
በማድረግ በሚቀርብ የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚወሰን ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህንኑ አስመልክቶም የፌዴራል
ጠቅለይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 18552፤ 56273፤100554 እና በሌሎችም መዛግብት
አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

ስለሆነም ጉዳዩ የቀረበለት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ከመንገድ ሥራ
ጋር በተገናኘ የከተማውን መሪ ፕላን አፈጻጸም የሚመለከት ሆኖ ሳለ ጉዳዩን የማየት የሥረ-ነገር ስልጣን
የለኝም በማለት መመለስ ሲገባው አከራክሮ ውሳኔ መስጠቱ፤ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የሥር ይግባኝ
ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ ሳያርም መቅረቱ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ
አግኝተነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ
1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 268995 በቀን 22/12/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 259606 በቀን
19/06/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ተሽሯል፡፡
2. የስር ፍርድ ቤት በዋናው ጉዳይ ላይ የሰጠው ፍርድ የሥረ ነገር ስልጣን ሳይኖረው የተሰጠ ነው
በማለት ወስነናል፡፡
3. ተጠሪዎች ያቀረቡትን የሁከት ይወገድልኝ ክስ ሥልጣኑ ለሚፈቅደው ፍርድ ቤት አቅርበው
ተገቢውን ዳኝነት የመጠየቅ መብታቸውን ይህ ውሳኔ አያግዳቸውም፡፡
4. መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 204608

ቀን፡-29/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡-እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር
ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1) ታጁዲን እንድሪስ

2) የተሁለደሬ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ፅ/ቤት

ተጠሪዎች፡- 1)እንድሪስ ሰይድ የቀረበ የለም፡፡

2) ዘሙየ የሱፍ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ለዚህ ውሣኔ ምክንያት የሆነው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-30456 ጥር 3ቀን 2013ዓ/ም በዋለው
ችሎት ቀደም ሲል በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተጣርቶ የቀረበለትን ጉዳይ በመለወጥ እንደገና ተጣርቶ
እንዲወሰን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስር ፍርድ ቤቱ መመለሱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ
እንዲወሰንላቸው አመልካቾች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ክርክሩ በተጀመረበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተሁለደሬ ወረዳ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪዎች
ከሣሽ የአሁን 1ኛ አመልካች ተከሳሽ እንዲሁም ሁለተኛ አመልካች ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡
ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ በይዞታ ማረጋጫ ደብተራቸው ተራቁጥር 2 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን 0.48
ሔክታር ስፋት ካለው ይዞታቸው ላይ 1ኛ አመልካች የመስጊዱ ተወካይ ነኝ በሚል በወርድ 25 ሜትር
በቁመት 60 ሜትር በመግፋት ይዞታቸውን የወሰዱባቸው መሆኑን ይህን መሬት ቢያካራዩት ያገኙት
የነበረውን 20 ሽኅ ብር ከፍሎ ይዞታውን እንዲመልስላቸው እንዲወሰንበት ክስ አቅርበዋል፡፡ አመልካቾች
በበኩላቸው የተጠሪዎችን መሬት ገፍተን አልያዝንም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከመረመረና በማስረጃ ካጣራ በኋላ አመልካቾች የተጠሪዎችን ይዞታ
ገፍተው መያዛቸው አልተረጋጠም ሲል የተጠሪዎችን ክስ ውድቅ ያደረገ ቢሆንም የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ
ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካቾች ከተጠሪዎች ይዞታ በጥቅሉ 48 ካሬ ሜትር
ስፋት ያለው መሬት ገፍተው መያዛቸው ተረጋግጧል በሚል እንዲለቁ ወስኗል፡፡ ይህን ውሣኔ እስከ ክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ተደርጎበት ሰበር ሰሚ ችሎቱ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሣኔ በመሻር የተጠሪዎች
ይዞታ በሰሜን በኩል የሚያዋስነው መንገድ ነው ወይስ የሁለተኛ አመልካች ይዞታ ነው የሚለው ተጣርቶ
እንደወሰን በነጥብ መልሶለታል፡፡ በዚህ መሰረት የወረዳው ፍርድ ቤት የደቡብ ወሎ ዞን የገጠር መሬት
አስተዳር መምሪያ በቦታው በመገኘት አጣርቶ እንዲያቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የቀረበለትን ማስረጃ
የመሬት ደልዳዮች ከሰጡት ምስክርነት ቃል ጋር በማገናዘብ የተጠሪዎችን ይዞታ በሰሜን በኩል የሚያዋስነው
የመስጊዱ ይዞታ መሆኑን ሆኖም ከጠቅላላ ይዞታቸው ላይ አመልካች በደቡብ(ከራሱ ይዞታ) በኩል 70 ሣንቲ
ሜትር ወርድ ያለው ይዞታ ግፍቶ ያላዘባቸው ስለመሆኑ ተረጋግጧል ሲል ይህን መሬት አመላከቾች
እንዲለቁ ወስኗል፡፡ በዚህ ውሣኔ ቅር የተሰኙት ተጠሪዎች ክርክራቸውን እስከ ክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
ድረስ አቅርበው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን መርምሮ በመዝብ ቁጥር 03-30456
ጥር 3ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት አመልካቾች የተጠሪዎችን መሬት ገፍተው ስለመያዛቸውና
አወሣኛቸውም መስጅድ ሣይሆን መንገድ ስለመሆኑ ቀደም ሲል የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር
03-19494 ውሣኔ የሰጠበት መሆኑን፤ የስር ፍርድ ቤቱ እንዲያጣራ የታዘዘው መጠኑን እንጅ አመልካቾች
ተጠሪዎችን ይዞታ ገፍተው መያዝ አለመያዛቸውን አለመሆኑን ከዘረዘረ በኋላ በዚህ መሰረት እስከ መንገድ
ያለውን ስፋት ያለውን መሬት ካስለከና በሚቀርብለት ውጤት መሰረት አመልካቾች እንዲለቁ መወሰን
ሲገባው የተጠሪዎችን ይዞታ ብቻ ለክተው መያዝ ከሚገባቸው 70 ሣንቲ ሜትር ባነሰ ይዘዋል በሚል ስሌት
70 ሣንቲ ሜትር ብቻ እንዲለቀቅቸው መወሰኑ መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህን ያልተከተለ ነው ሲል
ሽሮ የተጠሪዎች ይዞታ በሰሜን በኩል እስከ መንገዱ ድረስ ተለክቶ መጠኑ ላይ ውሣኔ እንዲሰጥ በድጋሚ
በነጥብ መልሶታል፡፡ አመልካቾች ይህ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሣኔ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚሉበትን ምክንያት በመዘርዘር እንዲታረምላቸው ይህን የሰበር አቤቱታ
አቅርበዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካቾች መጋቢት 15ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ ዘጠኝ ገፅ የሰበር አቤቱታቸው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት በሕግ ከተሰጠው የዳኝነት ስልጣን ውጪ ማስረጃ መዝኖ ውሣኔ መስጠቱ፣ በቀረበለት
የሰበር አቤቱታ ዳኝነት እንዲሰጥበት ባልተጠየቀ ጉዳይ ጭብጥ ይዞ መወሰኑ፣ የዞኑ መሬት አስተዳደር
የሰጠውን ማስረጃ የማይገባውን የማስረጃ ዋጋ በመስጠት ውሣኔ መስጠቱ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በሰጠው ውሣኔ የተጠሪዎች ይዞታ አዋሳኝ መንገድ ነው ወይስ መስጅድ ነው
የሚለው ነጥብ በማስረጃ ተጣርቶ እንዲወሰን የሰጠውን ውሣኔ ከሕግና ከአመንክዮ ውጪ ሽሮ መጠኑ ብቻ
እንዲጣራ ነው የተወሰነው የሚል አቋም በመያዝና በስር ፍርድ ቤት የቀረቡትን ማስረጃዎች ያረጋገጡትን
ፍሬ ነገር መሰረት ያላደረገ መደምደሚያ በመያዝ መጠኑ ብቻ እንደገና ተጣርቶ እንደወሰን መወሰኑ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተበሎ እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡

የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል ጉዳዩ
ተመልክቶ ተጠሪዎች ይዞታ በሰሜን በኩል እስከ መንገድ ድረስ የሚዋሰን መሆን አለመሆኑ ተጣርቶ
እንዲወሰን በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተጣርቶ የተወሰነው ውሣኔ ሲቀርብለት እንደገና እስከመንገዱ ድረስ
በማስለካት አመልካቾች እንዲለቁ እንዲወሰን ሲል ጉዳዩን ወደ ስር ፍርድ ቤት የመመለሱ ተገቢነት ላይ ግራ
ቀኙ ክርክር አድርገውበት እንዲወሰን በመታዘዙ የግራቀኙ የፅሁፍ ክርክር ተጠናቋል፡፡

ተጠሪዎች በበኩላቸው ሰኔ 10ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ በሰባት ገፅ የመልስ ክርክራቸውን አቅርበዋል፡፡ በጥቅሉ
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሣኔ ተገቢውን የክርክር አመራር ስነ-ስርዓት
የተከተለ መሆኑን ፣ አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት የተጠሪዎች አዋሣኝ መንገድ ነው የሚለው ትንሽ መንገድ
መሆኑን ለማመልከት እንጅ ዋናውን መንገድ የሚመለከት አይደለም ሲሉ የሚያቀርቡት ክርክር በስር ፍርድ
ቤት ያልተነሣ መሆኑን፣ በጠቅሉ አመልካቾች በዚህ ችሎት ከሚያቀርቡት ክርክር አንፃር የስር ፍርድ ቤቱ
ውሣኔ የሚነቀፍ አይደለም የሚሉበትን ምክንያት በመዘርዘር የአመልካቾች የሰበር ክርክር ውድቅ
እንዲደረግላቸው ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾቾም የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው
የግራቀኙ ክርክር ተጠናቋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዳዩን አመጣጥና የግራ ቀኙን ክርክር ሲሆን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አመልካቾች የተጠሪዎችን ይዞታ መግፋታቸው በመዝገብ ቁጥር 03-19494 በሆነው
ውሣኔ ያገኘ ጉዳይ ነው መጠኑን በሚመለከት እስከ መንገድ ድረስ ያለው ተለክቶ በሚገኘው ውጤት መሰረት
አመልካቾች እንዲለቁ እንዲወሰን ሲል ወደ ስር ፍርድ ቤት ጉዳዩን በመመለሡ የፈፀመው መሰረታዊ የሕግ
ስህተት መኖር አለመኖሩን በጨብጥነት ይዘን የግራ ቀኙን ክርክር ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው የክርክሩ መነሻ ተጠሪዎች በይዞታ ማረጋገጫ ደብተራቸው ላይ በተራቁጥር 2


ከተመዘገበው ይዞታቸው ላይ አመልካቾች ተገፍቶ ተይዞብናል የሚሉትን ይዞታ ለማስመለስ በቀረበ ክስ ነው፡፡
በዚህ ክስም የሁለተኛ አመልካች አመራር የሆነው አንደኛ አመልካች በወርድ 25 ሜትር በቁመት 60ሜትር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይዞታቸውን የወሰደባቸው መሆኑንና ይህ ይዞታ ቢከራይ ኖሮ ያስገኝ የነበረውን 20 ሽኅ ብር በመክፈል


ይዞታቸውን እንዲለቅላቸው እንዲወሰንበት ጠይቀው በጣልቃገብነት ወደ ክርክሩ የገባው ሁለተኛ አመልካችና
1ኛ አመልካች የተጠሪዎችን ይዞታ ገፍተው አለመያዛቸውን ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩን የመረመሩት የስር ፍርድ
ቤቶች በሰጡት ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል በሚል በተጠሪዎች የቀረበውን አቤቱታ
የመረመረው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር03-19494 በሰጠው ውሣኔ ጉዳዩ እንደገና
እንዲጣራ ወስኗል፡፡

በዚህ ችሎት አከራካሪ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመዘገብ ቁጥር 03-19494 የሰጠው ውሣኔ ይዘትን የሚመለከት ነው፡፡ ይህም ውሣኔው የተጠሪዎች ይዞታ
በሰሜን በኩል የሚዋሰነው ከመንገድ ጋር መሆኑ እና አመልካቾች የተጠሪዎችን ይዞታ መግፋታቸው
መደምደሚያ የተደረሰበትና መጣራት የማየስፈልገው መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ
ነጥብ ላይ መልስ ለመስጠት የክርክሩን አመጣጥ መርምረናል፡፡ እንደመረመርነው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-30456 በሰጠው ፍርድ የትንተና ክፍል ላይ የክልሉ ሰበር ሰሚ
ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-19494 በሰጠው ውሣኔ አመልካቾች የተጠሪዎችን ይዞታ መግፋታቸው እና
የተጠሪዎች የሰሜን አዋሳኝ መስጅድ ሣይሆን መንገድ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ቀደም ሲል ፍርድ የተሰጠበት
ጉዳይ መሆኑን ይዘረዝራል፡፡ ሆኖም ይኸው ችሎት እንደገና ተጣርቶ እንዲወሰን ከታዘዘ በኋላ በስር ፍርድ
ቤት የቀረቡትን ማስረጃዎች መርምሮ የስር ፍርድ ቤት መደምደሚያ ተገቢነት የለውም ሲል አቋም መያዙን
ራሱ የሰጠው ፍርድ ያስገነዝባል፡፡ አንድ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በተሰጠ ውሣኔ መደምደሚያ የተደረሰበት
ጉዳይ ነው ካለ ይህንኑ ጉዳይ በማስረጃ የሚያጣራበት ሂደት አለመኖሩ የሚያከራክር አይሆንም፡፡ የክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በሰጠው ውሣኔ አመልካቾች የተጠሪዎችን ይዞታ መግፋታቸው እና
የተጠሪዎችም ይዞታ እስከ መንገድ ድረስ መሆኑ ፍርድ የተሰጠበት ነው ካለ የስር ፍርድ ቤቱ የማስረጃ
ምዘን ሂደት ተገቢነት ሊመረምር ባለተገባው ነበር፡፡

ሆኖም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በሰጠው ውሣኔ በተሰጠው ትዕዛዝ
መሰረት እንደገና በማስረጃ ተጣርቶ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር የተደረሰበት መደምደሚያ ተገቢነት የሌለው
ነው ካላቸው መካከል አንዱ የተጠሪዎች አዋሳኝ መስጅድ መሆኑ ተረጋግጧል የተባለው መደምደሚያ
ነው፡፡ በመሆኑም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-19494 በሰጠው
ውሣኔ የተጠሪዎች ይዞታ አዋሳኝ መስጅድ ሣይሆን መንገድ መሆኑ መደምደሚያ የተደረሰበት ካለ የስር
ፍርድ ቤት እንደገና በማስረጃ አጣርቶ የያዘው አቋም ከቀረበት ማስረጃ አንፃር ተገቢነትን መምርመሩ ቀደም
ሲል በተሰጠው ፍርድ የተጠሪዎች ይዞታ በሰሜን በኩል የሚዋሰነው ከመንገድ ጋር ነው ወይስ ከመስጅድ
ይዞታ ጋር የሚለው ነጥብ እንዲጣራ ትዕዛዝ የተሰጠበትን ስለመሆኑ የሚያረጋግት ሆኖ ሣለ የክልሉ ሰበር
ሰሚ ችሎት ለሰጠው ፍርድ መደምደሚያ ላይ የደረሰው ተቃርኖ ያላቸውን መንደርደሪያ ሐሳቦች ምክንያቶች
በመጠቀም መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከዚህ በተጨማሪም የወረዳው ፍርድ ቤትና ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤት በፍርድ ሐተታቸው
ላይ እንዳሰፈሩት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-19494 በሰጠው
ትዕዛዝ መሰረት የተጠሪዎች ይዞታ በሰሜን በኩል የሚዋሰነው ከመንገድ ጋር ነው ወይስ ከመስጅድ ይዞታ
ጋር ነው የሚለው ነጥብ እንዲጣራ ትዕዛዝ መስጠቱንና በዚሁ መሰረት ያጣሩ መሆናቸውን እንዲሁም
ተጠሪዎች የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከሰጣቸው ትዕዛዝ በመውጣት አጣርተዋል የሚል
ክርክር አለማቅረባቸው ተጠቃሎ ሲታይ ቀደም ሲል በተሰጠው ውሣኔ የተጠሪዎች አወሣኝ መንግድ
ስለመሆኑ መደምደሚያ የተደረሰበ

ት ሣይሆን በማስረጃ የሚጣራ ጉዳይ የነበረ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

በሌላ በኩል የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝብ ቁጥር 03-19494 የሰጠው ውሣኔ አከራካሪ ቢሆንም እንኳ
ክርክሩ በነጥብ ከተመለሰ በኋላ የተጠሪዎች ይዞታ በሰሜን በኩል የሚዋሰነው ከመጅድ ይዞታ ጋር ነው
ወይስ ከዋና መንገድ ጋር ነው የሚለው ነጥብ የተጣራበትን ሁኔታና የተደረሰበትን መደምደሚያ ተገቢነት
ከሙግት አመራር እና ከማስረጃ ምዘና መርህ አንፃር መመርምሩ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩ እንደገና ከተመለሰለት በኋላ የተጠሪዎች ይዞታ በአመልካቾች ተገፍቶ መያዝ
አለመያዙን ለማጣራት እንዲሁም አወሣኙስ ተጠሪዎች እንደሚያቀርቡት መንገድ ነው ወይስ የመስጅዱ
ይዞታ የሚለው ነጥብ ላይ ማስረጃዎችን መርምሯል፡፡ በዚህ መሰረት በተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ላይ
በተራ ቁጥር ሁለት የተመዘገበው መሬታቸው በሰሜን በኩል ከመንገድ ጋር እንደሚዋሰን የተገለፀ ቢሆንም
የዞኑ መሬት አስተዳደር በቦታው ተገኝቶ ባደረገው ማጣራትና የመሬት ደልዳዮች እንዲሁም ሌሎች ምስክሮች
በሰጡት ቃል በጥቅሉ ከተጠሪዎች ይዞታና ከዋናው መንገድ መካከል ተጠሪዎች ይዘውት የማያውቁ
የመንግስት ይዞታ የነበረ መሆኑን ይህ ይዞታ ቀደም ሲል ለኳስ መጫዎቻነት አገልግሎት ይሰጥ የነበረ
መሆኑን በኋላም ለኢንቨስትመንት ተሰጥቶ አልሚው በተሰጠው ፈቃድ መሰረት ስላልሰራበት ከእርሱ ተነስቶ
ለመስጊዱ የተሰጠ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በአንፃሩ ተጠሪዎች በይዞታ
ማረጋገጫ ደብተራቸው ላይ ይዞታቸው በሰሜን በኩል መንገድ የሚያዋስናቸው መሆኑን ተመዝግቦልናል
ከሚል ክርክራቸው ውጪ ይዞታውን ይዘው ሲጠቀሙበት የነበረ ይዞታቸው የነበረ ስለመሆኑና በአመልካቾች
የተወሰደባቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ የተሻለ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ በመሆኑም ለአንድ ባለይዞታ የተሰጠ
የይዞታ ምስክር ወረቀት ላይ አዋሣኙ መንገድ መሆኑ መጠቀሱ ብቻውን ገለልተኛ በሆኑት የመሬት
አስተዳደር አካላት በቦታው ተገኝተው ይዞታውን በመለካት እንዲሁም ተቀባይነት ባላቸው የማጣራት ሂደት
ተከትለው ከሚሰጡት ማስረጃ ሁል ጊዜ የተሻለ ክብደት ሊሰጠው የሚገባና የማይስተባል ነው በሚል
የሚቀርበው የተጠሪዎች ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም፡፡

በመሆኑም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል በመዝገብ ቁጥር 03-19494 በሰጠው
ውሣኔ ፍፁማዊ አቋም ያልያዘበትን ጉዳይ ማለትም የተጠሪዎች ይዞታ በስተሰሜን በኩል በአመልካቾች
ስለመገፋቱና የሚዋሰኑትም ከመንገድ ጋር ስለመሆኑ እንደተረጋገጠ በመገንዘብ ይልቁንም ጉዳዩ በነጥብ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከተመለሰ በኋል የስር ፍርድ ቤት ባከናወነው የማጣራት ሂደት የተጠሪዎች ይዞታ በሰሜን በኩል
የሚዋሰነው ከመንገድ ጋር ሣይሆን ቀደም ሲል ከመንግስት ይዞታ ጋር አሁን ደግሞ ከመስጂድ ይዞታ ጋር
ስለመሆኑ በተረጋገጠበት የተጠሪዎች ይዞታ እስከመንገድ የሚዘልቅ ነው በሚል በማስረጃ ያልተረጋገጠ
መደምደሚያ እስከመንገዱ ድረስ ተለክቶ የሚገኘውን ውጤት አመልካቾች እንዲለቁ እንዲወሰን ክርክሩን
መመለሱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343(1) ድንጋጌንና የማስረጃ ምዘና መርህን ያልተከተለ መሰረታዊ የሕግ
ስህተት

የተፈፀመበት ውሣኔ ሆኖ ስላገኘው ተከታዩን ውሣኔ ወስነናል፡፡

ውሣኔ

1. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 03-
30456 ጥር 3ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት
በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡
2. የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዘገብ ቁጥር 46898
በሆነው ህዳር 10ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የስር የተሁለዴ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር
15117 በሆነው የካቲት 20ቀን 2012ዓ/ም የሰጠውን ውሣኔ በማፅናት የሰጠው ውሣኔ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
3. ይህ የሰበር ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ6/6
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁጥር 204746

መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡-1ኛ. የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 10 ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት አልቀረቡም

2ኛ. የቂ/ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት

ተጠሪ፡- አቶ አበበ ደምሴ ካሳ - ቀረቡ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች በቀን 15/07/2013 ዓ.ም በተፃፈ
አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 243668 በቀን 26/05/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት
የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልጸው በሰበር ታይቶ ይታረምልን
በማለት ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻነት ሲሆን አመልካቾች በፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት
ተከሳሾች የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ ባቀረቡት ክስ በቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የቤት


ቁጥር 142/11 አውራሼ ወ/ሮ አሰለፈች ካሳ በግል ጥረትና ገንዘባቸው ያፈሩት ንብረት ሲሆን የካቲት
24 ቀን 1984 ዓም በደብተር ቁጥር 21/09097 በስማቸው ተመዝግቦ ተሰጥቷቸው በአውራሼ ስም ግብር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እየተገበረ ይገኛል፡፡ሆኖም አመልካቾች ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱን ያለአግባብ በመያዝ አከራይተው
ሊመልሱልኝ አልቻሉም፡፡ስለሆነም በወረዳው ተሸንሽኖ የቤት ቁጥር 140፣ 141 እና 142 የሆነውን ቤት
እንዲያስረክቡኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡

አመልካቾች በሰጡት መልስም ተጠሪ ክስ ያቀረበባቸውን ቤቶች መንግስት በአዋጅ ቁጥር 47/67
መሰረት ወርሶ እያስተዳደራቸው ያሉ የመንግስት ቤቶች ናቸው፡፡ተጠሪ ቤቶቹ እንዲመለስላቸው
ለወቅቱ የአስተዳደር አካል አመልክተው እንዲመለስላቸው ያስወሰኑበትን ማስረጃ
አላቀረቡም፡፡ባለመብት መሆናቸውን የተረጋገጠበትን ውሳኔም አላቀረቡም፤ ደብተሩ እና ግብር
የተከፈለበት ደረሰኝ የሚያስረዳው ስለቤት ቁጥር 142/11 እንጂ ክርክር ስለተነሳባቸው ቤቶች
አይደለም፡፡ቤቶቹ ያለ አግባብ ከአዋጅ ውጪ ተወርሶብናል የሚል ክስም ለኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን
ኤጀንሲ አቅርበው ማስወሰን ይችሉ ነበር፡፡የተጠሪ ጥያቄ በተገቢው ማስረጃ የተረጋገጠ ስላልሆነ ክሱ
ውድቅ እንዲደረግልን በማለት ተከራክረዋል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ከሰማ በኋላ የቀረበውን የሰነድ
ማስረጃ መርምሮ ለተጠሪ አውራሽ የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር ባለቤትነታቸውን በመቀበል አፅድቆ
የሰጣቸውን የባለቤትነት ደብተር በማቅረብ ቤቱ የተፈቀደላቸው መሆኑን ስላስረዱ አመልካቾች
በቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የቤት ቁጥር 140፣141 እና 142 ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት
ወስኗል፡፡

አመልካቾች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ


አቤቱታቸውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ከፍተኛ
ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚነቀፍበት የሕግ ምክንያት
ስላልተገኘ ውሳኔው ተገቢ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አጽንቷል፡፡

አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም በአጭሩ የስር ፍርድ ቤቶች
ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች ለተጠሪ ሊመለሱ ይገባል በሚል ለሰጡት ውሳኔ መነሻ ያደረጉት
በተጠሪ በኩል የቀረበውን ደብተር እንደ በቂ ማስረጃ በመቁጠር ሲሆን ደብተር ብቻውን የይዞታ
ማረጋገጫ መሆን የማይችል መሆኑን በተመለከተ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁ. 170592
በሰጠው ውሳኔ ላይ ደብተር እንደማስረጃ ለመውሰድ ሌሎች ተገቢ ማስረጃዎችን በአንድነት ማገናዘብ
እንደሚገባ አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆኑት ቤቶች የአውራሻቸው
ስለመሆናቸው አግባብ ካለው አካል የተፈቀደላቸው ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ በሌለበት ለረዥም ጊዜ
መንግስት ተረክቦ ሲያስተዳድረው የነበረ ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተፈቀደላቸው ስለመሆኑ
(በቅፅ 004 ተመላሽ የሆነበት አግባብ በሌለበት) ወይም ከአዋጅ ውጭ ተወስዶብኝል በሚልም ከሆነ
በአዋጅ ቁጥር 110/87 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 572/2000 መሰረት ለቀድሞ የፕራይቬታይዜሽንና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ አቤቱታ አቅርበው ውሳኔ አግኝተው ባለመብት
መሆናቸውን አላረጋገጡም፡፡

በተጨማሪም አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤቶች በተመለከተ ለረዥም
ጊዜ እያስተዳደርን ስለመሆኑ በማስረጃ አስደግፈን አረጋግጠን አቅርበን እያለ የስር ፍርድ ቤት ይህን
አልፎ የሰጠው ውሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 14094፣45161፣33924
እና 36320 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ከተሰጠበት ውሳኔ ጋር ተገናዝቦ ያልተወሰነ እና በበቂ የሕግ
ምክንያት ያልተደገፈ በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልክተዋል፡፡

ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት መንግስት በአዋጅ ቁጥር 47/67 በመያዝ እያስተዳደረ ባለበት ሁኔታ
በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ተጣርቶ ለተጠሪ የተወሰነ ስለመሆኑ ማስረጃ ባልቀረበበት አመልካች ቤቱን
ለተጠሪ እንዲያስረክብ የተወሰነበት አግባብነት ከአዋጅ ቁጥር 47/67፣ 572/2000 እና የፌደራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 33924 እና ሌሎች አግባብነት ካላቸው የሕግ ትርጉሞች ጋር
በማገናዘብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ለተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው
መልሳቸው በፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

ተጠሪ በሰጡት መልስም በ1984 ዓ.ም ለክርክር ምክንያት የሆነው ቤት እንዲመለስ ተወስኖ ለማስረከብ
የተለያዪ አቤቱታ አውራሻችን እያቀረቡ ሳይረከቡ ቆይተዋል፤ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት
የተወረሰበት ሁኔታ አግባብ ያለመሆኑ በስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር በሚገባ ታይቶ እንዲመለስልን
ውሳኔ አግኝቶ በውሳኔው መሰረት ደብተር ተሰጥቶን በስማችን እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ግብር እየገበርን
ቆይተናል፡፡በዚሁ መሰረት ከተጠቀሰው አዋጅ ውጭ የግለሰብ ቤት የሚወረስበት ሕግ
አልነበረም፡፡ስለሆነም የፌደራል መጀመሪያ ደረጀ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ
የሕግ ስሕተት አልተፈፀመበትም በማለት ውሳኔው እንዲፀናልኝ እና የአመልካቾች አቤቱታው ውድቅ
እንዲደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካቾች የመልስ መልሳቸውን አላቀረቡም፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡ለረዢም ጊዜ
በመንግስት እጅ ሆነው እየተዳደሩ የሚገኙ ቤቶችን በተመለከተ ቤቱ ይለቀቅልኝ የሚለው ወገን
ጥያቄውን በቀጥታ ለፍርድ ቤት ሊያቀርብ የሚችለው ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀፅ 12(2) መሰረት
በተገቢው አካል የተፈቀደለት መሆኑን በማስረዳት አልያም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል ከሆነም
ለሚመለከተው አካል ጥያቄውን አቅርቦ ውሳኔ አግኝቶ ባለመበትነቱን ያረጋገጠበትን ማስረጃ በማቅረብ
ሊሆን እንደሚገባ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥሮች 14094፤45161 እና በሌሎች
ተመሳሳይ መዝገቦች አስገዳጅ ውሳኔ ሰጥቶበታል፡፡አከራካሪው ቤት(በኋላ በአደረጃጀት ምክንያት ሶስት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የቤት ቁጥሮችን የያዘው) ለረዢም ጊዜ በመንግስት እጅ ሆኖ ሲተዳደር የነበረ መሆኑ ግራ ቀኙ


ያልተካካዱበት ነጥብ ሲሆን ተጠሪ ቤቱ ተለቅቆ ልረከብ ይገባል የሚሉት ለአውራሻቸው በተገቢው
አካል የተፈቀደላቸው መሆኑን መነሻ በማድረግ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል፡፡

ከአዋጅ ቁጥር 47/67 መውጣት በኋላ የሚያዙ ቤቶችን በተመለከተ በህጉ አግባብ መያዛቸው በወቅቱ
በነበረው አደረጃጀት በስራና ቤቶች ሚኒስቴር ተጣርቶ ካልፀደቀላቸው አያያዙ የማይፀና መሆኑን
የአዋጁ አንቀፅ 12(2) እና 2(16) የጋራ ንባብ ያሳያል፡፡አሁን በያዝነው ጉዳይ ለአከራካሪዎቹ ቤቶች
በተጠሪ አውራሽ ስም የኢትዮጲያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር
በ24/06/1980 ዓም የሰጠው ደብተር በተጠሪ የቀረበ መሆኑ ማስረጃን የመስማት፤የመመርመርና
የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች መረጋገጡ ተጠሪ ቤቶቹ እንዲመለሱላቸው የጠየቁት
በተገቢው አካል የተፈቀደላቸው መሆኑን በማስረዳት መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ይህ ከሆነ ደግሞ
አከራካሪዎቹን ቤቶች አመልካቾች በመልቀቅ ለተጠሪ እንዲያስረክቡ የስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መወሰኑና
ይህ ውሳኔም በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ መፅናቱ ለጉዳዩ አግባብነት ያለውን ህግና አስገዳጅ የሰበር
ውሳኔዎችን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ
ስላላገኘነው የሚከተለው ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 65683 በቀን 29/11/2011 ዓ.ም በዋለው
ችሎት የሰጠው ፍርድ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 243668 በቀን
26/05/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤትን ፍርድ በማፅናት የሰጠው ፍርድ
በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
2. በዚህ መዝገብ በቀን 21/07/2013 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ይጻፍ፡፡
3. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 204813እና206556

ቀን፡-30/11/2013ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡-1. ኮ/ል ተክለብርሃን ገ/መድህን

2. ኮ/ል አሰፋ አየለ ይመር

ተጠሪ፡- የደ/ዕዝ ወታደራዊ ዓ/ህግ

በዚህ መዝገብና በሰ/መ/ቁ.206556 የቀረቡት የሰበር አቤቱታዎች በስር ፍርድ በመ/ቁ.24/2013


ከተሰጠው ውሳኔ የተነሱ ክርክሮች በመሆናቸው መዝገቦቹ ተጣምረው ተመርምረው ተከታዩ ፍርድ
ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የወታደራዊ አገልግሎት ተግባሮችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን
አስመልክቶ ለበላይ አለመታዘዝ እንዲሁም ጠቅላላ የአገልግሎት ደንቦችን መጣስ ወንጀልን የሚመለከት
ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው በኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ይግባኝ ሰሚ
ወታደራዊ ፍ/ቤት በመ/ቁ 074/2013 የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር የቀዳሚ
ወታደራዊ ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናት የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 1 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም በአመልካቾች ላይ በኢፌዲሪ


የቀዳሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ባቀረበው የመጀመሪያ ክስ አመልካቾች የመከላከያ ሰራዊት ማቋቋሚያ
አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀጽ 2 (12)፣ የኮቪድ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በወጣው አስቸኳይ አዋጅ
ቁጥር 3/2012 በወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 298/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ ሰኔ 23 ቀን
2012 በግምት ከምሽቱ 3፡30 ሲሆን የተደራጁ ህገወጥ ቡድኖች ገጀራ ፣ፌሮ ብረትና ዱላ በመያዝ
በሻሸመኔ ከተማ የህብረተሰቡን ንብረት እያቃጠሉ እያወደሙና እየዘረፉ በመሆኑ በክፍሉ አመራር ሜ/ር
ጀኔራል ሹማ አብዴታ በስልክ ይህንን ህገወጥ ተግባር ተመጣጣኝ እርምጃ በመውሰድ እንዲቆጣጠሩ እና
ህብረተሰቡን እንዲታደጉ የሰጣቸውን ትዕዛዝ በመጣስ ትዕዛዙን ሳይፈጽሙ ቀርተዋል በማለት የከሰሰ
ሲሆን፤በሁለተኛው ክስም አመልካቾች የመከላከያ ሰራዊት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀት
2/12፣ የኮቪድ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በወጣው አስቸኳይ አዋጅ ቂጥር 3/2012 እና በኢፌዲሪ ወንጀል
ህግ ቁጥር 32/1/ሀ እና 293/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በ1999 ዓ.ም የወጣውን የመከላከያ ሰራዊት
ቋሚ የግዳጅ አፈጻጸም ደንብ ቁጥር መከ-002/1999 ተ.ቁ 6.3 እና 7.5 መሰረት ሰራዊቱ ማናቸውም
ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲደርሱ አደጋውን ለማስቆም ተመጣጣኝ እርምጅ በመውሰድ ህዝቡን
ከአደጋ መታደግ እንዳለበት በግልጽ ተደንግጎ እያለ በተደራጁ ህገወጥ ቡድኖች የህብረተሰቡ ህይወት
አደጋ ላይ ሲወድቅ ንብረት በከፍተኛ ሁኔታ ሲዘረፍ ሲቃጠል የስር አመልካቾች ግዳጅ ላይ እያሉ
በመከላከያ ሀይሎች የአገልግሎት ደንብ መሰረት ተመጣጣኝ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ከአደጋ
ባለመታደጋቸው ጉዳት ሊደርስ ችሏል በማለት ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

አመልካቾች ባቀረቡት መቃወሚያም ሰራዊቱ ከኮቪድ ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ የመቆጣጠር ትዕዛዝ


ስላልተሰጠን በጦርነት ጊዜ የተፈፀመ ወንጀል ነው በሚል መቅረቡ አግባብነት የለውም፤ ሁለቱ ክሶች
በአንድ የወንጀል ማድረግ ሀሳብ የተፈጸሙ በመሆናቸው በወ/ህ/ቁ.61(1) መሰረት ተጠቃልለው በአንድ
ክስ ስር ሊቀርቡ ይገባል፤ አመልካቾች በአንድ መዝገብ መከሰሳቸው መብታቸውን ለይተው ለመከራከር
የማያስችላቸው መሆኑን ጠቅሰው ክሳቸው ተለይቶ እንዲከሰሱ ጠቅሰው ተከራክረዋል፡፡

የኢፌዲሪ የቀዳሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት በቀረቡት መቃወሚያዎች ላይ በሰጠው ብይን መቃወሚያዎቹን


ውድቅ አድርጎ አመልካቾች እምነት ክህደት ሲጠየቁም ክደው የተከራከሩ በመሆኑ ታህሳስ 16 ቀን
2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የዓ/ህግ ምስክሮችን አስቀርቦ የሰማ ሲሆን 1ኛ የዓ/ህግ ምስክር በሰጠው
የምስክርነት ቃልም ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በከተማው እንዳንድ አካባቢዎች የግርግር
ምልክት በመኖሩ ወደ 1ኛ አመልካች ሲደውሉ ስላላነሱ ኮ/ል ሰለሞን ለ1ኛ አመልካች ሄዶ ሲነግረው
1ኛ አመልካች መልሶ ሲደውልለት የሁከት ምልክቶች ስላሉ የነገው ስብሰባ ቀርቶ ሰራዊቱ ለግዳጅ
ይዘጋጅ ብለው ትዕዛዝ የሰጡት መሆኑን ፤በማግስቱ ጠዋት 12፡30 1ኛ አመልካች ደውሎለት ሜ/ጄ
ሰለሞን ደውሎ ነበር ከተማ ውስጥ ቃጠሎዎች ስላሉ ፈጠን ብላችሁ ድረሱ ብሎኛል ታውቃለህ ወይ
ሲላቸው ከታዘዛችሁ ግቡ ያላቸው መሆኑን ወደ ሜ/ጄ ሰለሞን ደውሎ ትዕዛዙ የተሰጠ መሆኑን
እንዳረጋገጡ፤

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 2 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለ1ኛ አመልካች ያለህን መኪና ሰብስበህ በፍጥነት ድረስ ባሉት መሰረት 1ኛ አመልካች ሰራዊቱን
በመያዝ ከጧቱ 2፡15 አካባቢ ጥቁር ውሃን ያለፈ መሆኑን በዚህ ጊዜም ለ1ኛ አመልካች ደውለው
ምንም ንብረት መቃጠል የለበትም ማስቆም አለባችሁ አመፀኛው የታጠቀ ሀይል አይደለም በዱላ
የሚበተን ነው ያሉ መሆኑን አልፎ አልፎ ከ2ኛ አመልካች ጋር ሲገናኙ እንደነበረ፤1ኛ አመልካች
ከሽማግሌዎች ጋር እየተነጋገርን ነው በማለት ሲነግራቸው የነበረ ቢሆንም ህብረተሰቡ ስለቃጠሎው
መቀጠል ደውሎ ይነግራቸው የነበረ በመሆኑ 1ኛ አመልካችን በስልክ ደውለው አናግረው ድጋሚ ትዕዛዝ
የሰጡ ቢሆንም አመራሮቹ ግዴታቸውን ስላልተወጡ ቃጠሎው የቀጠለ መሆኑን፤2ኛ አመልካችን አልፎ
አልፎ ቃጠሎ ሲበዛ ይጨቀጭቁት የነበረ መሆኑን እርምጃ ውሰድ ሲሉት ሰው ብዛት አለው ምን
ላድርግ ሲላቸው በዱላ የሚበትን ሀይል ነው ያሉት መሆኑን ትዕዛዝ አልቀበልም ግን ያላላቸው
መሆኑን፤ በከተማው ውስጥ ጉዳቱ የደረሰው በሰው እጥረት ሳይሆን ቃጠሎውን አመራሮቹ
ባለማስቆማቸው መሆኑን ፤በከተማው ውስጥ አስቀድሞ የተጀመረ ቃጠሎ ቢኖርም አብዛኛው ውድመት
የደረሰው ሰራዊቱ ከገባ በኋላ መሆኑን፤አመልካቾች 3 ሻለቃ ከ500 የማያንስ ሰው የሚመሩ ሆኖ ከዚህ
ውስጥ አንድ ሻምበል ብቻ ግዳጅ ላይ ከመሆኗ ውጪ ሌላው ለግዳጁ የወጣ መሆኑን ቃጠሎውን
ያላስቆሙት በሰው እጥረት ሳይሆን መስራት ስላልቻሉ መሆኑን፤1ኛ አመልካች ትዕዛዝ ሲሰጡት
ያልተቃወመ ቢሆንም በትዕዛዙ መሰረት ባለመስራቱ ግን ጉዳቱ የደረሰ መሆኑን ፤2ኛ አመልካች
በግምገማ ወቀት እርምጃ መውሰድ ጀምረው ያስቆማቸው 1ኛ አመልካች መሆኑን የኦራል ጠባቂ ሆነን
ቀረን በማለት የነገራቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

2ኛ ምስክር የደቡብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜ/ር ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ሲሆኑ በሰጡት የምስክርነት
ቃልም በእለቱ ከጠዋቱ 12፡10 ሰዓት ሲሆን ለስር 1ኛ ተከሳሽ ደውሎ ችግር መኖሩን ገልጾ በሰው
ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ሀይል አሰማርተው እንዲያስቆሙት ግዳጅ የሰጣቸው
መሆኑን፣1ኛ አመልካች የተሸከርካሪ እጥረት ያለበት መሆኑን ሲገልፅላቸው 5 ፓትሮል የላኩለት
መሆኑን፤ከዚያ በኋላ ሂደቱን 1ኛ ምስክር እየተከታተለው ነበር በማለት አስረድተዋል፡፡

3ኛ ምስክር የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪና የኢትዮቴሌኮም ሴኩሪቲ ሱፐርቫይዘር መሆኑን ገልጾ አርቲስት
ሀጫሉ ሁንዴሳ በመገደሉ ችግር ይፈጠራል በሚል ደቡብ ሪጅን ለሚገኘው አለቃው ደውሎ ያሳወቀ
መሆኑን ከለሊቱ 10፡00 ጀምሮ ቃጠሎ እንደጀመረ እና እየሰፋ በመምጣቱ ድጋሚ 1፡00 ሲሆን
ለአለቃው እንደደወለለት፣ አለቃው ትንሽ ቆይቶ እንደደወለና ከቶጋ መከላከያ እየመጣ እንደሆነ 1ኛ
አመልካች ይመጣልሃል ይህን ስልክ ያዝና ደውልለት እንዳለው፣ ሲደውልም እየመጣን ነው ያሉት
መሆኑን መከላከያ ገብቶ ወደ አቦስቶ አልፎ የሄደ መሆኑን ቴሌ አካባቢ ያሉ ቤቶች መቃጠል ሲጀምሩ
ለ1ኛ አመልካች ሲደውሉለት እየመጣሁ ነው ይለው የነበረ መሆኑን ቴሌ ማማ ላይ ወጥተው ሲመለከቱ
ገጀራ፤ዱላ የያዙት ቤት ሲያቃጥሉ ተዉ የሚላቸው ያልነበረ መሆኑን ንብረቱ ተቃጥሎ ሲያልቅ ሰራዊቱ
በርቀት ቆሞ ተመለስ ሲል የነበረ መሆኑን ሰራዊቱ ከጠዋቱ 3፡00 አካባቢ ገብቶ አብዛኛው ንብረት
የተቃጠለውም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውሥጥ መሆኑን ፤ ለ1ኛ አመልካች ድጋሚ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 3 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሲደውልም እየመጣሁ ነው ከተማ ውስጥ ነኝ በሚል ሲያናግረው እንደነበር፣ እሰከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት
ድረስ እየደወለለት እነደነበር ከዛ በኋላ ተስፋ በመቁረጥ መደወል እንዳቆመ፣ ሰራዊቱ ጧት 3፡ 00
ጀምሮ እንደገባ ግን ምንም እርምጃ ያልወሰዱ መሆኑን፣ ማታ ሁሉም ነገር ከጠፋ በኋላ ዱላ በመያዝ
ማባረር እንደጀመሩ አስረድቷል፡፡

4ኛ ምስክር ሌ/ኮ/ጌታቸው ለማ በቀን 22/10/2012 ዓ.ም ሌሊት 9፡00 ለ1ኛ የስር ተከሳሽ ትዕዛዝ
መሰጠቱን ተከትሎ ከስር የሚመራቸውን ሰራዊቶች ዝግጅት እንዲያደርጉ በማድረግ ጠዋት ወደ
ከተማው የሄዱ መሆኑን፣ ገጀራና ዱላ የያዘ ሰው እየበዛ ሲሄድ ምስክሩ ለ1ኛ አመልካች እንበትን
ሲለው ተው ራሳቸው ይበተናሉ እንዳለው፣እዛው ቆመው ቃጠሎው እየባሰ የሄደ መሆኑን ሰራዊቱ
የአመልካቾችን ትዕዛዝ እየተጠባበቀ እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ደረስ ቆመው እንደቆዩ 5፡30 ሲሆን
አመልካቾች ከአሁን በኋላ መበተን ትችላላችሁ እንዳሉት፣ ከተማ ሲገቡ እየነደዱ የነበሩ ፎቆችና
ሆቴሎች እንዲሁም ነደው ያለቁ ህንፃዎች ቢኖሩም እዚያው እያሉ የተቃጠሉም መኖራቸውን
ለማሳያነትም የፀጋዬ ህንፃ ከስር ጭስ የነበረው ቢሆንም ተቃጥሎ ያለቀው እዚያው እያሉ መሆኑን፤
2ኛ አመልካች ግዳጅ መቀበል ያለበት ከ1ኛ አመልካች መሆኑን ገልጾ መስክሯል፡፡

5ኛ ምስክር ደግሞ በጦር ሰፈር የነበረውን ከግዳጅ መልስ ባደረጉት ግምገማ አመልካቾች ግዳጅ
ከመፈጸም ይልቅ ከነውጠኛ ጋር ሽምግልና በመያዝ መደራደረ የአመልካቾች ችግር እንደሆነ
መገምገሙን መስክሯል፡፡ 6ኛ ምስክር የራሱን አለቃ ሌ/ኮ ጌታቸውን ለምን አንበትናቸውም ሲለው ወደ
አመልካቾች ሄዶ አነጋግሮ ሲመለስ ተረጋጉ ትዕዛዝ አየጠበቅን ነው ያለው መሆኑን፣ ነውጠኛው
እየጨመረ እና ወደ ምስክሩ ሲቀርቡ ወደ ኋላ ተመለሱ ትዕዛዝ እየጠበቅን ነው በማለት
እንደገለጸላቸውና ወደ ኋላ ያፈገፈጉ መሆኑን፣ ከዛም ነውጠኞቹን እንዳሳለፏቸው እነዚህ ያሳለፏቸው
አለፍ ብሎ ያለውን ፎቅ ያቃጠሉ መሆኑን ፣ እርምጃ መውሰድ የተጀመረው ከቀኑ 5፡30 በኋላ እንደሆነ
አስረድቷል፡፡ ፍ/ቤቱም የዓ/ህግ ምስክሮችን መርምሮ ምስክሮቹና ማስረጃው የዓ/ህግን ክስ ያስረዱ
በመሆኑ አመልካቾች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡

የአመልካቾች 1ኛ ምስክር በመሆን 2ኛ አመልካች ቀርቦ በሰጠው የምስክርነት ቃልም ኮ/ል ከማል
በ22/10/2012 ዓም ሌሊት 8፡00-9፡00 ባለው ደውሎ ያንተ ኮሚቴ 1ኛ አመልካች ስልክ አያነሳም ኮ/ል
ሹማ ይፈልግሃል ብለህ ንገረው እንዳለው፣ በሰዓቱ ሄዶ ኮ/ል ሹማ እንደሚፈልገው ለ1ኛ አመልካች
እንደነገረው የተነጋገሩትን ባያውቅም ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ተዘጋጁ ስለተባሉ የስራ ክፍፍል
አድርገው አድረው ከጠዋቱ 1፡30 ሰራዊት ይዞ መንገድ እያስከፈቱ ሻሸመኔ መግቢያ ላይ ከጠዋቱ 3፡00
የደረሱ መሆኑን 1ኛ አመልካችም የቀረውን ሀይል ይዞ የመጣ መሆኑን፤ እንደደረሱ ንብረት
እየተቃጠለና እየወደመ እንደነበር ለኮ/ል ሹማ ሲደውሉ ከተማው ተቃጥሎ አልቋል ለምንድነው
የመጣነው አሁን ያሉት ሰዎች ፖስተር ይዘው የሚያለቅሱ ናቸው ምን እናድርግ ሲለው ጠብቁ
እደውላለው ያላቸው ሲሆን እና በተደጋጋሚ ከ1ኛ ስር ተከሳሽ ጋር እንደሚደዋወሉ፣ በኋላ 5፡00 አካባቢ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 4 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ደውሎ ተመጣጣኝ እርምጅ እንዲወስዱ ደውሎ ለስር 1ኛ ተከሳሽ እንደነገረውና አመልካችም ወደ


ተግባር እንደገባ ፣አሳልፈዋቸው ያቃጠሉ ግለሰቦች አለመኖራቸውን አመፅ ከተነሳ ምን ማድረግ
እንዳለባቸው ያልተነገራቸው መሆኑን ከታዘዙ በኋላ ግን ግዳጃቸውን የፈፀሙ መሆኑን ወደ ከተማ ከገቡ
በኋላ አዲስ የተቃጠለ ነገር ያልተመለከቱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

2ኛ የመ/ምስክር 1ኛ አመልካች ሲሆን በ22/10/2012 ዓም ሌሊት 2ኛ አመልካች ኮ/ል ሹማ


ይፈልግሃል ሲለው ደውሎ ሲያናግረው የተያዘው ስብሰባ ይቅርና አርቲስት ሀጫሉ ስለሞተ ዝግጁ ሁኑ
የሚል ትዕዛዝ የተሰጠው መሆኑን፣ ጠዋት 3፡30 ሲሆን የደረሱና ወደ 4፡00 ገደማ ኮ/ል ሲደወልለት
ሰላማዊ በሆነ መንገድ ፍቱ ያለው መሆኑን፣ ከቀኑ 5፤00 ሰዓት ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ
የተሰጠው መሆኑን፣ መጀመሪያ ላይ ቀላል የነበርና በቀላሉ መፍትሔ ይገኝ እነደነበር በኋላ ግን ነውጠኛ
እየበዛ በመሄዱ አስቸግሯቸው እንደነበር፣በእርምጃ ደረጃ ከታየ የነበረው ያልታጠቀ ስለሆነ ከታጠቀው
ሰራዊት አንፃር እርምጃ ለመውሰድ ከአቅም በላይ አለመሆኑን ነገር ግን ሜ/ጀ ሹማ በተቻለ መጠን
ህይወት ሳይጠፋ ፍቱ ያላቸው መሆኑን፤እርምጃ እንዲወስዱ ከታዘዙ በኋላ ግን ለ2ኛ አመልካችና
ለሻለቃና ሻምበል አመራሮች ትዕዛዝ ሰጥቶ ተግባራዊ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

የአመልካቾች 3ኛ የመከላከያ ምስክር በሰጠው የምስክርነት ቃልም በእለቱ ወደ ከተማው ሲደርሱ


ከፍተኛ እሳት ስለነበረ እንምታቸው ሲሉ 2ኛ አመልካች ቆዩ ያላቸው መሆኑን፤ከጠዋቱ 3፡20 እስከ
5፡20 ድረስ ቆመው ቆይተው እርምጃ እንድንወስድ ታዘናል ሲሉ ወደ እርምጃ የገቡ መሆኑን
ከሰልፈኛው ጋር ከመነጋገር ይልቅ በትነው ማለፍ የነበረባቸው መሆኑን በየደረሱበት ሱቆች እየተቃጠሉ
ከመሆኑ ውጪ አዲስ ቃጠሎ አለመኖሩን ያስረዱ ሲሆን ፤4ኛ የመ/ምስክር በበኩላቸው በስፍራው
እንደደረሱ ጦሩ ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ቆዩ የተባሉ መሆኑን፤ከደረሱ በኋላ የተቃጠለ
ቤት አለመኖሩን፤ለአመልካቾች ከላይ የወረደ ትዕዛዝ ይኑር አይኑር የማያውቅ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የግራቀኙን ምስክሮች የሠጡትን የምስክርነት ቃል የሰነድ ማስረጃዎችንና የድምፅ
ማስረጃዎችን መርምሮ በሰጠው ውሳኔም ተጠሪ ባቀረባቸው ምስክሮች አመልካቾች ገና ከጦር ሰፈራቸው
ሲነሱ በሻሸመኔ ከተማ ቃጠሎ የተጀመረ መሆኑ ተነግሯቸው ይህንኑ ቃጠሎና ውድመት እንዲያስቆሙ
በሜ/ጀ ሹማ የታዘዙ መሆኑን ትዕዛዙ ለ1ኛ አመልካች በተደጋጋሚ የተሰጠ ቢሆንም 2ኛ አመልካችም
የታዘዙ መሆኑን ፤3ኛ ምስክርም እየደረሰ ያለውን ጥፋት መሰረት በማድረግ እንዲደርሱላቸው
ቢማፀኑም የንብረት ማቃጠልና የሰው ህይወት ማጥፋት ድርጊቱ የቀጠለ ቢሆንም ሰላማዊ ሰልፍ ነው
በማለት የራሳቸውን ትርጉም በመስጠት ትእዛዙን ሳይቃወሙ ግን ትዕዛዙ ወደ ተግባር ተለውጦ የሀገር
ሀብት የማዳን ስራ እንዳይሰራ ማድረጋቸውን ማስረዳቱን፤የመከላከያ ምስክሮቹ መጀመሪያም በዱላ
በመበተን የሰው ህይወትና ንብረት አድኑ በማለት ከተሰጠው ትዕዛዘ የተለየ ትዕዛዝ መኖሩን ሳያስረዱ
ከታዘዝን በኋላ በዱላ እየበተንን የሚቃጠለውን እያስጠፋን ስራችንን ቀጠልን ማለታቸው የተጠሪን
ማስረጃ የሚያጠናክር መሆኑን፤ከአመልካቾች ሀላፊነት አንፃር የበላይ አመራር ተመጣጣኝ እርምጃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 5 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እየወሰዳችሁ የህዝብ ንብረት አድኑ ቃጠሎ አስቁሙ ብሎ ማዘዝ ይቅርና በራሳቸውም የስራ ሀላፊነት
ከሰራዊቱ የቋሚ ግዳጅ አፈፃፀም ደንብ አንፃር መውሰድ የሚገባቸው መሆኑን፤

1ኛ አመልካች ያቀረበው የስልክ ልውውጥ ድምፅ ቅጂ ከጠዋቱ 4፡14 ከገጠር የመጡት እያቃጠሉ
እንደነበረ ለበላይ ሲናገር የነበረ መሆኑን ማስረዳቱ እኛ ከደረስን በኋላ ቃጠሎ አልነበረም በማለት
ከገለፁት ጋር የሚቃረን የተጠሪን ማስረጃ የሚያጠናክር መሆኑን፤የድምፅ ቅጂው 4፡14 መጀመሩም
አስቀድሞ የተደረገውን ያልያዘ ሆነ ተብሎ የተዘጋጀበትን የሚያሳይ መሆኑን ከረፋዱ 5፡02 እስከ 5፡24
የተቀረፀው ከበላይ አዛዦች ጋር ያለውን የስልክ ልውውጥ ሳይሆን ሆነ ተብሎ ክፍት ተደርጎ
የተቀረፀውን መሆኑን ሆነ ብሎ አስቀድሞ በመዘጋጀት የተቀረጣን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ
በአጠቃላይ አመልካቾች በተጠሪ የቀረበባቸውን ክስና ማስረጃ አለማስተባበላቸውን በመጥቀስ
በቀረበባቸው የወንጀል ህግ አንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ በማድረግ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት
ተቀብሎ በመመርመር 1ኛ አመልካች በዘጠኝ አመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት፤2ኛ አመልካች በ6
ዓመት ከ 6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሙሉ ድምጽ የወሰነ ሲሆን ይህ ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው
ወታደራዊ ፍ/ቤትም ፀንቷል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡1ኛ አመልካች በሰ/መ/ቁ.204813
መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓም በተፃፈ ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም አመልካች የተከሰሱት ከአስቸኳይ
ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በተሰጣቸው ግዳጅ አለመሆኑን ከኮቪድ ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ የተሰጣቸው
የበላይ አመራር ትዕዛዝ እና ጠቅላላ የአገልግሎት ደንብ አለመኖሩን በሰበር መዝገብ ቁጥር 193054
ከተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማያያዝ ያቀረብነው
መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም፤አመልካች የተሰጣቸውን ትዕዛዝ መጣሳቸው
ባልተመሰከረበት፤ሁለቱ ክሶች አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ሆነው እያለ አመልካቾች የበላይ አመራር
ትዕዛዝ አልፈፀሙም ተብሎ ክስ ቀርቦባቸው እያለ እንደገና በ2ኛው ክስ በራሳቸው ተነሳሽነት እርምጃ
መውስድ ነበረባቸው ተብሎ ክስ መቅረቡ አግባብ ባለመሆኑ ምስክር ከተሰማ በኋላም ቢሆን
በወ/ህ/ቁ.61(1) መሰረት ተጠቃልሎ በአንደኛ ክስ ስር ሳይቀርብ በሁለቱም ክሶች ጥፋተኛ መባላችን
መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፤

የመከላከያ ምስክሮቻችን በቦታው ሲደርሱ ሆቴሎች፤ፎቆችና ሱቆች ተቃጥለው ያለቁና በመቃጠልም


ላይ የነበሩ መሆኑን፤እኛ ከደረስን በኋላ እንደ አዲስ ያቃጠሉት አለመኖሩን ሰልፈኞቹ እርማችን
ለማውጣት ስለሆነ አሳልፉን ብለው በጠየቁት መሰረት ያለፉ ያደረሱትም ጉዳት አለመኖሩን ትዕዛዝ
ከተሰጠን በኋላ እርምጃ በመውሰድ ሰልፉን የበተንን መሆኑን አስረድተው እያለ የቀደመ ትዕዛዝ
አለመኖሩን አረጋግጠው መስክረው እያለ ክሱንና ማስረጃውን አላስተባበሉም በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ
መሰጠቱ ቅጣትን አስመልክቶም ሁለቱ ክሶች ወደ ንዑስ 1 ቀይረው ቢያከራክሩ ኖሮ ቅጣቱ ከብዶ
የማይወሰን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅጣቱ ሲሰላም ለረዢም ጊዜ ሀገራችንን በቁርጠኝነት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 6 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማገልገላችንና በዚህ አገልግሎትም 1ኛ አመልካች ሶስት ጊዜ መቁሰሌ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ቅጣቱ
መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ካቀረብነው መቃወሚያ
አንፃር የተሰጠው ብይን እንዲታረምልኝ፤በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮ በነፃ እንደሰናበት
ይወሰንልኝ ፤ይህ ቢታለፍ ቅጣቱ ከላይ በተመለከቱት ማቅለያዎች አግባብ ቀልሎ ይወሰንልኝ በማለት
አመልክተዋል፡፡

ለአመልካቾች ከበላይ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ግልፅ ስለመሆኑና፤የወንጀል ድርጊቶቹን ስለመፈፀማቸው


የተረጋገጠበትን አግባብ እንዲሁም ትዕዛዙ እንደ ጦር ሜዳ ግዳጅ ተወስዶ በሁለት ድንጋጌዎች ስር
ጥፋተኛ የተባሉበትን አግባብ አግባብነት ካላቸው ህጎች አንፃር ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል
ከተባለ በኋላ ለተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓም የተፃፈ መልሱን አቅርቧል፡፡

ተጠሪ በዚህ መልሱም በሁለቱም ክሶች የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ራሳቸውን ችለው የሚቋቋሙ እና
ግዙፋዊ ውጤትን የሚያስከትሉ በመሆናቸው ሁለቱም ክሶች ተነጣጥለው መቅረባቸው በአግባቡ
ነው፤አንድ የሰራዊት አባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ለፀጥታ አካላት የሚሰጠውን ግዳጅ
በላቀ ውጤት የመፈፀም ግዴታ ያለበት በመሆኑ የተከሰሱባቸው ሁለቱም ወንጀሎች በጦርነት ወቅት
እንደተፈፀሙ የሚቆጠሩ በመሆናቸው በወንጀል ህግ አንቀፅ 298(2) እና 293(2) መከሰሱ በአግባቡ
ነው፤በወቅቱ በተፈጠረው ህገወጥ ተግባር ምክንያት በሻሸመኔ ከተማ ውስጥ 287 አባወራዎች
የተፈናቀሉ፤26 ፎቆችና 179 ቤቶች የተሰባበሩ፤21 ፎቆች 52 መኪናዎች 26 ባጃጆች 40 ሞተር
ሳይክሎች 38 ሆቴሎች 23 ሱቆች፤9 ወፍጮ ቤቶችና 196 ቤቶች የተቃጠሉ በመሆኑ ለጉዳዩ አግባብነት
ያለውን ድንጋጌ በመጥቀስ ክሱን ያቀረብን በመሆኑ አመልካች በዚህ ወቅት ከበላይ የተሰጠውን ትዕዛዝ
አለመፈፀሙን ያስረዳን በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት አግባብነት ያላቸው ማቅለያዎች ተይዘውለት ቅጣቱ
የተሰላ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

2ኛ አመልካች ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔና ትዕዛዝ ላይ
ተፈፅሟል ያሉትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍሬ
ቃሉም በአንድ ወንጀል ማድረግ ሃሳብ እንደተፈፀሙ የሚቆጠሩ የተቀላቀሉ ድርጊቶችን ነጣጥሎ ሁለት
ተደራራቢ ወንጀሎች ክስ ማቅረብ በዚሁ የጥፋተኝነት ፍርድ በአመልካች ላይ ማስተላለፉ መሰረታዊ
የህግ ስህተት መሆኑን፣ የወንጀል ድንጋጌዎችን የሚያከብድ ድንጋጌ ስር ለማቅረብ የሚያበቃ ህጋዊ
ምክንያት በሌለበት ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የሰራዊቱን ማቋቋሚያ አዋጅ እና ከኮቪድ
ወረረሽኝ ጋር በተያያዘ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት በማድረግ ክስ መቅረቡ መሰረታዊ
የህግ ስህተት መሆኑን፣ በአመልካች ላይ የቀረበው ክስ በስር ፍ/ቤት አብረው ከተከሰሱት የቅርብ
አዛዣቸው ክስ ተነጥሎ ያለመቅረቡ መሰረታዊ የህግ ስሀተት መሆኑን፣ ተጠሪ በአመልካች ላይ
የቀረበውን ክስ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ ባላስረዳበት እና አመልካች ባቀረባቸው ማስረጃ
በተስተባበለበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ስህተት መሆኑን፣ የቅጣት ውሳኔው በፌ/ጠ/ፍ/ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 7 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የወጣውን የቅጣት መመሪያ ቁጥር 2/2006 ተከትሎ ያልተሰጠ መሆኑን በመግለጽ በነጻ እንዲሰናበት
ካልሆነ ቅጣቱ እንዲታይላቸው በማመልከታቸው ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአሁን አመልካች አግባብነት ካለው የበላይ አዛዥ ትዕዛዝ
የተሰጣቸው ለመሆኑና የቀረበባቸውን የወንጀል ድርጊት ስለመፈጸማቸው የተረጋገጠበት ትዕዙዙም እንደ
ጦር ሜዳ ግዳጅ ተወስዶ በወንጀል ህግ አንቀጽ 298/2/ እና 293/2/ ስር በሁለት ህግ ድንጋጌ
የጥፋተኝነት እና ቅጣት ውሳኔ የተሰጠበት አግባብነት ከመከላከያ ሰራዊት ማቋቋሚያ አዋጅ 1100/2011
አንቀጽ 2/12/ ፣ የኮቪድ 19 ወረረሽኝ ስርጭት ለመቆጣጠር የወጣው አስቸኳይ አዋጅ ቁጥር 3/2012፣
የወንጀል ህግ ቁጥር 61፣ የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ቋሚ የግዳጅ አፈጻጸም ደንብ ቁጥር መከ-
002/1999 ቁጥር 6.3፣7.5 አንጻር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ለመመርመር ለዚህ ሰበር ችሎት
ቀርቦ እንዲታይ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ በቀን ሰኔ 8/2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች የተከሰሰባቸው ወንጀሎች ተደራራቢ
መሆናቸውን፣ አመልካች ወንጀሉን በሚያከብድ አንቀጽ መከሰሱ ተገቢ መሆኑን፣ አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ባለበት ሁኔታ የጸጥታ ሁኔታ በላቀ ሁኔታ ነቅቶ መጠበቅ ሲገባው ግዳጅ ተሰጥቶትም በግዳጁ መሰረት
አለመፈጸሙ፣ የተፈጸሙት ሁለቱም ወንጀሎች ጦርነት ባለበት ወቅት እንደተፈጸሙ የሚቆጠሩ
መሆኑን፣ አንደኛው ክስ የበላይ አለቃን ትዕዛዝ አለማክበር ራሱን የቻለ ወንጀል ሲሆን 2ኛው ደግሞ
የህዝብ ንብረት እየወደመ፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት የመከላከል ግዴታ እያለበት
ግዴታውን ባለመወጣቱ የተከሰሰው ክስ ራሱን የቻለ ወንጀል መሆኑን፣ ክሱ በሁለቱም በአንድ ላይ
የቀረበው ግዳጁ በጋራ የተሰጠና የተከሰሱበት ወንጀል ህግም ተመሳሳይ በመሆኑ መሆኑን፣ ተጠሪ
ሁለቱንም ክሶች በበቂ ሁኔታ ያስረዱ መሆናቸውንና አመልካች በማስረጃው ያላስተባበለ መሆኑን፣
የቅጣት ውሳኔ መመሪያውን መጠቀም ነበረባቸው ለሚለው በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት መ/ቁ 118227
መመሪያውን የመከተል ግዴታ እንደደለሌበት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠ መሆኑን፣ በመሆኑም
ወንጀሉ በባህሪው ለየት ያለ እና የቅጣት ደረጃ ያልወጣላቸው መሆኑን፣ ጠቅሰው የስር ፍ/ቤት
የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በአግባቡ በመሆኑ እንዲፀናላቸው ተከራክረዋል፡፡

አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም ከሰበር
ቅሬታው አኳያ እና ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ይዘት አንፃር የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር አግባብነት ካለው
ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡በመሰረቱ በስር ፍርድ ቤት ቀርበው የተሰሙት
የተጠሪ ምስክሮች በዋነኝነትም 1ኛ ምስክር ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በከተማው እንዳንድ
አካባቢዎች የግርግር ምልክት በመኖሩ በመነሻነት ማታውን በማግስቱ የነበረው ስብሰባ ቀርቶ ሰራዊቱ
ለግዳጅ ይዘጋጅ ብለው ማታውን ትዕዛዝ ለ1ኛ አመልካች የሰጡት መሆኑን፤ጠዋቱን አመልካቾች
በስራቸው ያለውን ሀይል ይዘው ከካምፓቸው ሲነሱ በሻሸመኔ ከተማ ቃጠሎ የተጀመረ መሆኑ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 8 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተነግሯቸው ይህንኑ ቃጠሎና ውድመት እንዲያስቆሙ በሜ/ጀ ሹማ የታዘዙ መሆኑን ትዕዛዙ ለ1ኛ
አመልካች በተደጋጋሚ የተሰጠ ቢሆንም 2ኛ አመልካችም የታዘዙ መሆኑን፤

አመልካቾች ሀይላቸውን ይዘው ወደ ከተማው ሲገቡ ቃጠሎ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም አብዛኛው ቃጠሎ
የደረሰው አመልካቾች የሚመሩት ሀይል ወደ ከተማ ከገባ በኋላ መሆኑን፤በከተማው ውስጥ ጉዳቱ
የደረሰው በሰራዊቱ ባለው የሰው ሀይል እጥረት ሳይሆን ቃጠሎውን አመራሮቹ ባለማስቆማቸው መሆኑን
ምስክሮቹ ያስረዱ ሲሆን 1ኛ ምስክር ከዚህ በተጨማሪ አመልካቾች ሰራዊቱን እየመሩ ከጠዋቱ 2፡15
ወደ ከተማ ሲገቡ ጀምረው ለ1ኛ አመልካች ደውለው ምንም ንብረት መቃጠል የለበትም ማስቆም
አለባችሁ አመፀኛው የታጠቀ ሀይል አይደለም በዱላ የሚበተን ነው ብለው መንገራቸውን ቃጠሎው
ሲበዛም 2ኛ አመልካችን ይጨቀጭቁት የነበረ መሆኑን በማስረዳት ከመነሻውም አመልካቾች ወደ
ከተማው ሲገቡ በግልፅ የተፈጠረውን ሁከት እንዲያስወግዱ የታዘዙ መሆኑን አመልካቾች ግን
ምክንያት እያቀረቡ ትዕዛዙን ሳይፈፅሙ የቀሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አመልካቾች ከራሳቸው ውጪ ለጉዳዩ ገለልተኛ የሆኑ ሁለት የመከላከያ ምስክሮችን ያቀረቡ ሲሆን
ከመነሻውም ለአመልካቾች ከበላይ የተሰጠ ትዕዛዝ መኖር አለመኖሩን አለማወቃቸውን አስረዱ እንጂ
የበላይ ትዕዛዝ አለመኖሩን በማረጋገጥ የሰጡት የምስክርነት ቃል የለም፡፡3ኛ እና 4ኛ የመ/ምስክሮች
ቃጠሎውን ሲመለከቱ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ሲጀምሩ ቆይ መባላቸውን ከማስረዳት ውጪ
ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰዱ አስፈላጊ የነበረ ከማረጋገጥ ባለፈ አመልካቾች ቆይ ያሏቸው የበላይ
ትዕዛዝ ባለመኖሩ መሆኑን አላስረዱም፡፡እኝ ምስክሮች ሰራዊቱ ወደ ከተማ ከገባ በኋላ አዲስ ቃጠሎ
አለመኖሩን ያስረዱ ቢሆንም ይህንን የምስክርነት ቃል 1ኛ አመልካች ካስቀረቡት የስልክ ልውውጥ
ድምፅ ቅጂ ጋር ስንመረምረው 3ኛ የመ/ምስክር ከጠዋቱ 3፡20 ወደ ከተማው የገቡ መሆኑን አስረድተው
እያለ የድምፅ ቅጂው ከጠዋቱ 4፡14 ከገጠር የመጡት እያቃጠሉ እንደነበረ 1ኛ አመልካች ለበላይ
ሲናገሩ የነበረ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑ የምስክሮቹ ቃል በመከላከያ ማስረጃነት በቀረበው የድምፅ ቅጂ
እንደተስተባበለ ማስረጃን የመስማት፤የመመርምርና የመመዘን ስልጣን ባለው በስር ፍርድ ቤት
የተረጋገጠ መሆኑን ያሳያል ፡፡

በአጠቃላይ አመልካቾች በእለቱ ሰራዊቱን ይዘው ወደ ከተማ ሲገቡ የተፈጠረውን ሁከት እንዲያሰወግዱ
በግልፅ ከበላይ ትዕዛዝ የተሰጣቸው መሆኑን ትዕዛዙን ላለመፈፀም የሰው ሀይል ማነስን በምክንያትነት
ያስቀመጡ ቢሆንም በከተማው ውስጥ ጉዳቱ የደረሰው በሰራዊቱ ባለው የሰው ሀይል እጥረት ሳይሆን
በተሰጣቸው ትዕዛዝ አግባብ ሰርተው ቃጠሎውን አመራሮቹ ባለማስቆማቸው መሆኑን ተጠሪ
ባልተስተባበለ መልኩ ማስረዳቱ ማስረጃን የመስማት፤የመመዘንና የመመርመር ስልጣን ባላቸው የስር
ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ነጥብ ነው፡፡

ይህ ፍሬ ነገር በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ከሆነ ደግሞ በቀጣይ ሊመረመር የሚገባው ለጉዳዩ
አግባብነት ያለው ድንጋጌ የትኛው ነው የሚለው ይሆናል፡፡በዚህ አግባብም ማንኛውም የመከላከያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 9 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሰራዊት አባል አስቦ ከበላይ አዛዡ ተግባሩን በሚመለከት በቃል፤በፅሁፍ፤በምልክት ወይም በማናቸውም
ሌላ መንገድ በቀጥታ ለራሱ ወይም እርሱ ለሚገኝበት የጦር ክፍል የተሰጠውን ማናቸውንም ትዕዛዝ
ሳይፈፅም የቀረ ወይም ለመፈፀም እንቢተኛ ከሆነ ለበላይ ባለመታዘዝ የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ
ተብሎ ተገቢው የቅጣት ውሳኔ የሚተላለፍበት መሆኑን የወ/ህ/አ.298 (1) ይደነግጋል፡፡በወ/ህ/አ.298(2)
ቅጣቱ ከብዶ ሊወሰን የሚችለው ድርጊቱ የተፈፀመው የጦር አደጋ ምልክት በተሰጠበት፤የጦር ክተት
በታወጀበት ወይም በጦርነት ጊዜ ከሆነና እንቢተኛነቱም ቁርጠኛ ከሆነ እንደሆነ ድንጋጌው በግልፅ
ያሣያል፡፡

በመሰረቱ በህጉ መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚከናወን የመከለከያ ሰራዊት ግዳጅ የጦር ሜዳ
ግዳጅ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 በአንቀፅ 2(12)
የሚደነግግ ሲሆን አሁን በያዝነው ጉዳይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደርጎ የቀረበው የኮቪድ ወረርሺኝን
ለመቆጣጠር የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 መሆኑን የተጠሪ ክስ ያሳያል፡፡በነዚህ
ድንጋጌዎች አግባብ አመልካቾች በወ/ህ/አ.298(2) አግባብ በጦር ሜዳ ግዳጅ ላይ ሆነው ለበላይ
አለመታዘዝ የወንጀል ድርጊት ፈፅመዋል ሊባል የሚችለው ከኮቪድ ወረረሽኝ ጋር በቀጥታ በተያያዘ
መልኩ አዋጁን ለማስፈፀም አመልካቾች የሚመሩት ሰራዊት በራሱ ብቻውን ወይም ከሌሎች የሀገሪቱ
የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ጋር ተደራጅቶ በስምሪት ላይ ሆኖ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመፈፀም ላይ
የነበረ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡አሁን በያዝነው ጉዳይ ለክሱ ምክንያት የሆነው ለበላይ አለመታዘዝ
የወንጀል ድርጊት በአመልካቾች የተፈፀመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመፈፀም ላይ እያሉ ስለመሆኑ
ክሱም ሆነ ማስረጃው አያሳይም፡፡

ከኮቪድ ወረርሺኝ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ለአመልካቾች በግልፅ ትዕዛዝ የተሰጠ
ለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ለክሱ መነሻ የሆነው ሁከት የተፈጠረው የኮቪድ ወረርሺኝ አስቸኳይ ጊዜ
አዋጅ በሀገሪቱ ታውጆ ባለበት ጊዜ ውስጥ ስለሆነ ብቻ አመልካቾች በጦር ሜዳ ግዳጅ ላይ ነበሩ ሊባሉ
የሚችሉበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ ከዚህም በተጨማሪ የወ/ህ/አ.298(2) የህጉ መስፈርት ማለትም
እንቢተኛነቱ ቁርጠኛ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ከዚህ ይልቅ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች አመልካቾች
እንቢተኛ አለመሆናቸውን፤ ሆኖም አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት በማቅረብ ትዕዛዙን አለመፈፀማቸውን
እያስረዱ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾችን በወ/ህ/አ.298(2) ስር ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ውሳኔ
መስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው አመልካቾች ጥፋተኝ ሊባሉ
የሚገባው በወ/ህ/አ.298(1) ስር ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ሁለተኛውን ክስ በተመለከተም አመልካቾች በወ/ህ/አ.293 ስር ጥፋተኛ ተብለው የቅጣት ውሳኔ


ሊተላለፍባቸው የሚችለው በግልፅ የተሰጠ የበላይ ትዕዛዝ ባይኖርም ከመከላከያ ሰራዊት ቋሚ የግዳጅ
አፈፃፀም ደንብ አንፃር በወቅቱ የተፈጠረውን በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለውን
ሁከት በራሳቸው በሚወስዱት እርምጃ ሊያስቆሙ ሲገባ ይህንን ባለማድረጋቸው የደረሰ ጉዳት መኖሩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 10 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሲረጋገጥ ሲሆን አሁን በያዝነው ጉዳይ ከበላይ አዛዦች በግልፅ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለመኖሩ በተረጋገጠበት
በትእዛዙ መሰረት ባለመፈፀማቸውም ከላይ በተመለከተው አግባብ በ1ኛው ክስ ጥፋተኛ በተባሉበት
ትዕዛዝ ተሰጥቷችሁ ባለመስራታችሁ የወንጀል ሀላፊነት አለባችሁ እየተባሉ ባትታዘዙም ከመከላከያ
ሰራዊት ቋሚ የግዳጅ አፈፃፀም ደንብ አንፃር የወንጀል ሃላፊነት አለባችሁ ተብለው በሁለተኛው ክስ
ጥፋተኛ ሊባሉ የሚገባበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ የስር ፍርድ ቤቶች እነዚህን ነጥቦች ከግምት ውስጥ
ሳያስገቡ የሰጡትን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህሀት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው በመሻር አመልካቾች
ከሁለተኛው ክስ በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል በማለት ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ቅጣትን አስመልክቶ አመልካቾች ጥፋተኛ የተባሉበት የወንጀል ድርጊት ከአምስት አመት በማይበልጥ
ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን ቅጣቱን ለማክበድ የሚያስችል በቂ ምክንያ ያልቀረበ ቢሆንም
አመልካቾች በግልፅ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ባለመፈፀማቸው በሰው ህይወትና አካል ላይ እንዲሁም
በንብረቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ፤ትዕዛዙ በቀጥታ በተደጋጋሚ ሲሰጥ
የነበረው ለ1ኛ አመልካች መሆኑን እንደሁም ከትዕዛዙ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ያላቸውን የቀደመ
ሀላፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሌላ በኩል ደግሞ አመልካቾች የተያዘባቸው የቀደመ ሪከርድ
አለመኖሩ ያላቸውን መልካም ፀባይ የሚያሳይ መሆኑን፤የቤተሰብ አስተዳዳሪነታቸውን፤ረዥም
የውትድርና አገልግሎታቸውንና በዚህ ጊዜም የደረሰባቸውን አካላዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት
በዚህ ጉዳይ የታሰሩበት ጊዜ ታስቦ 1ኛ አመልካች በሶስት አመት ፅኑ እስራት ፤2ኛ አመልካች በሁለት
አመት ከስድስት ወር ፅኑ አስራት እንዲቀጡ የስር ፍርድ ቤትን የቅጣት ውሳኔ ማሻሻል ፍርድ
ሰጥተናል፡፡ስለሆነም የሚከተለው ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1.የቀዳሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የደቡብ ዕዝ ችሎት በመ/ቁ.24/2013 በ16/04/2013 ዓም የሰጠውና


ይግባኝ ሰሚችሎቱ በመ/ቁ.074/2013 በ19/06/2013 ዓም በሰጠው ፍርድ ያፀናው የቅጣትና የጥፋተኝነት
ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.195 (2)(ለ)(2) መሰረት ተሻሽሏል፡፡

2.አመልካቾች በወ/ህ/አ.298 (1) ስር ለበላይ ባለመታዘዝ የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ ናቸው


ብለናል፡፡ስለሆነም አመልካቾች በዚህ ጉዳይ የታሰሩበት ጊዜ ታስቦ 1ኛ አመልካች በሶስት አመት ፅኑ
እስራት ፤2ኛ አመልካች በሁለት አመት ከስድስት ወር ፅኑ አስራት ሊቀጡ ይገባል ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

1.ማረሚያ ቤቱ በተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዲያስፈፅም የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ይድረሰው፡፡

2.በዚህ መዝገብ የተሰጠው ውሳኔ ከመዝገብ ቁጥር 206556 ጋር እንዲያያዝ ታዟል፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 11 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሄ/መ

የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

የልዩነት ሃሳብ

እኔ ስሜ በተራ ቁጥር 2 ሰር የተሰየምኩት የችሎቱ ዳኛ ከሌሎች ባልደረቦቼ በሚከተለው ምክንያት በሃሳብ


ተለይቻለሁ፡፡

1. አመልካቾች እየተከራከሩያሉት አገር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ብትሆንም የጦርሜዳ ግዳጅ ሊባል


አይገባም በሚል በመሆኑ ሰራዊቱ ለግዳጁ እንዲዘጋጅ የግዳጅ አፈፃፀም ካርድ ወጥቶ የነበረ ስለመሆነ
በግልጽ በስር ፍ/ቤት ተረጋገጦ ያለ በመሆኑ ይህ የግዳጅ አፈፃፀም ካርድ አልወጣም ግዳጁም
ለሰራዊቱ አልወረደም በሚል አመልካቾች የተከራከሩም ሆነ ማስረጃ ባለማቅረባቸውም ከአጠቃላይ
ክርክሩ ያላየሁ በመሆኑ፣
ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የግዳጅ አፈፃፀም ካርድ በሰራዊቱ የተዘጋጀ ስለመሆኑ በክህደት
ያልተከራከሩበትና ውድቅ የተደረገ ክርክር ባለመሆኑ ግዳጅ ለሰሪዊቱ እንደተሰጠ የምቆጥረው
በመሆኑ፣በጊዜው የኮቪድ 19 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወጥቆ የነበረው ሰዎች እንዳይቀራረቡ እና
በሽታው እንዳይዛመት ከመሆኑ አንፃር በጊዜው የተፈፀመው ነገር ግን ሰዎች በህብረት ሆነው
እየዘፈኑ እና እየፎከሩ የነበረ እና በቀጣይም በህብረት ንብረት የማውደምና በሰዎች ህይወት ላይ
ጉዳይ እያደረሱ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ የጦር ሜዳ ግዳጅ አይደለም የሚል
ክርክር በአመልካዋች የተነሳ ቢሆንም በዚህ አስቸኳይ አዋጅ ከወጣበት አላማ አንፃር አንፃር ስናየው
ራሱ አዋጁን የጣሰ ድርጊት የተፈፀመ በመሆኑ፣

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወጣው ለጦርሜዳ አይደለም እንኳን ቢባል ሁለቱም አመልካቾች ግዳጅ ከበላይ
ኃላፊያቸው የተቀበሉ መሆኑ ባልተካደበት ይልቁንም ኮ/ል ተክለብርሃን ገ/መድህን በቀጥታ ግዳጁን
የተቀበለ መሆኑ፣ በስሩ የሚገኝ ኮ/ል አሰፋ አየለ ግዳጁን ከበላይ ኃላፊው የሰማ እና የቅርብ
አለቃውን ኮ/ል ተክለብርሃንን ግዳጁ እንዲፈፀም ሲጠይቀው እንደነበረ፣ ሌሎች የሰራዊቱ አባላትም
ለምን እርምጃ አንወስድም እያሉ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ የነበረ ቢሆንም ከበላይ ኃላፊያቸው ኮ/ል
ተክለብርሃን በቀጥታ እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ባለመውረዱ ብቻ ወታደራዊ የትዕዛዝ አቀባበል
ስርዓቱን ሲጠብቁ በጊዜው ከፍተኛ ጉዳይ የደረሰ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊት
የግዳጃ አፈፃፀም ጉድለት የተፈፀመ እና በሰውና በንብረት ላይ ጉዳይ የደረሰ መሆኑ የተረጋገጠ
በመሆኑ ለበላይ ያለመታዘዝ ወንጀል ነው የተፈፀመው ለማለት የማይቻልና ኮ/ል ተክለብርሃን
ግዳጁን ተቀብሎ ነገር ግን እንደግዳጁ ያለመፈፀም እና በስሩ ያሉትንም ግዳጁን አውረዶ አደጋውን
እንዲታደጉ ያለማድረጉ ግልጽ በመሆኑ በስር ወታደራዊ ፍ/ቤት በኮ/ል ተክለብርሃን ገ/መድሀን ላይ
የተላለፈው የጥፋተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ሊሻሻል የሚገባው እና የተጠቀሰውም የህግ ድንጋጌ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 12 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስለማይገባ የጥፋተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔው ሊፀና የሚገባው ነበር በሚል ከአብላጫው ድምጽ
በሀሳብ ተለይቻለሁ፡፡
2. ኮ/ል አስፋ አየለን አስመልክቶ ግን ምንም አንኳን ግዳጁ ከበላይ ኃላፊያቸው መሰጠቱን ቢያውቅም
እንደወታደራዊ የግዳጅ አፈፃፀም ምንም እንኳን ግዳጁ በበላይ ኃላፊ መሰጠቱን ቢስማም ከቅርብ
አለቃው ደግሞ በቀጥታ ግዳጁን መቀበል እና ማስማራት ያለበት ከመሆኑ አንፃር በተደጋጋሚም
የቅርብ ኃላፊነውን ግዳጁ ሊፈፀም ይገባል በማለት ቢጠይቀም ያልወረደለት በመሆኑ የግዳጁ
አወራረዱ ደግሞ የስልጣን ተዋረድን የሚጠይቅ በመሆኑ በቀጥታግዳጁን ተቀብለህ አልፈፀምክም
ሊባል የማይገባው በመሆኑ፣ ኮ/ል አሰፋ አየለ ሊጠየቅ የሚገባው ከሆነ ሁሉም በቦታው የነበሩ
የሰራዊት አባላት አደጋውን በጊዜው ያላስቆሙት የበላይ ትዕዛዝን እየጠበቁ በመሆኑ ትዕዛዝ መጠበቅ
አልነበረባችሁም ተብሎ ሊጠየቁ የሚገባው የነበረ በመሆኑ ከአጠቃላይ በቦታው ላይ ከነበሩ የሰራዊት
አባላት ኮ/ል አሰፋ የሚለየው እሱ ከዋናው አዛዥ ግዳጅ መውረዱን በስልክ ስለሰማና ለቅርብ አለቃው
አሳውቅ የተባለ በመሆኑ እንጂ እንደማንኛውም ሰላምና ደህንነትን ለመጠበቅ ሰራዊቱን የተቀላቀለ
ሁሉ አገር በችግር ውስጥ እየገባች ባለችበትና የህዘብ እና የአካባቢ ሰላም እየደፈረሰ እያየ ዝም ሊል
የማይገባው ከመሆኑ አኳያ ከታየ ሁሉም ሊጠየቁ የሚችሉ እንጂ በተለየ ከቅርብ አለቃው ግዳጅ
ሳይወርድለት ስላልፈፀመ ጥፋተኛ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ ባለመኖሩ ከቀረበበት ክስ ነፃ ሊወጣ
የሚገባው እንጂ ጥፋተኛ ተብሎ ቅጥት ሊወሰንበት አይገባም ነበር በማለት በስር ወታደራዊ ፍ/ቤት
የሰጠውንም ይሁን አብላጫው ድምጽ ያሻሻለው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተገቢ አይደለም ብዬ
በሃሳብ ተለይቻለሁ፡፡

የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 13 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 204829

ቀን፡-01/02/2014ዓ/ም
ዳኞች- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ፍቅር አብራክ የእናቶችና የሕፃናት ስፔሻላይዝድ የሕክምና ማዕከል -ወኪል ንጉስ አወቀ
ቀረቡ

ተጠሪ ፡- ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ- አልቀረቡም

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ
የስር ከሳሽ፤ አመልካች ተከሳሽ ሆኖ ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ አመልካች ከሕግ ውጭ የሥራ
ውሌን ስላቋረጠ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈል እንዲወሰንልኝ የሚል ነው፡፡ አመልካች ባቀረበው የመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያ ተጠሪ የሥራ መሪ በመሆናቸው ጉዳዩ በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ በሥራ ክርክር ችሎት
ሊታይ አይገባም በማለት ተከራክሯል፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 92429
አመልካች ያቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩን ክሱን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
አመልካች ባቀረበው ይግባኝ መሠረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ ውሳኔውን
አጽንቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ተጠሪ የሥራ መሪ
ሆነው እያለ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ
ችሎትም በዚሁ ነጥብ ላይ ለሰበር ሰሚ ችሎት ተጠሪን ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ
በማዘዙ ተጠሪ የሥራ መሪ አይደለሁም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ሲደረግ ዋናው
ክርክር ሳይጠናቀቅ ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን
መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪ ባቀረቡት የሥራ ክርክር ላይ አመልካች የሥራ መሪ ናቸው፣ ጉዳዩ በሥራ ክርክር
ችሎትና በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ መሠረት ሊታይ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ
ቢሆንም ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት መቃወሚያውን ባለመቀበል በፍሬ ነገሩ ጉዳዩን
ለመስማት ትእዛዝ ሰጥቷል፤ ሥረ-ነገሩ ላይ ውሳኔ አልሰጠበትም፡፡ አመልካች ይግባኝ ያቀረበው
መቃወሚያው ውደቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም በሚል ነው፡፡ ክርክሩን በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ
መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፊነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት
ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን
ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰሉትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን
መብት ይነካል፡፡

በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320(3) መሰረት ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ከሥረ ነገሩ ፍርድ በፊት የሚሰጥ ትዕዛዝ
እና የጉዳዩ የመጨረሻ ውጤቱ ሲታወቅ አብሮ ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ ላይ ይግባኝ ማቅረብ
እንደማይቻል ተመልክቷል፡፡ ድንጋጌው በክርክር ሂደት በሚሰጥ ትዕዛዝ ሁሉ ይግባኝ ከቀረበ የተከራካሪዎችን
ወጪና ጊዜ የሚያባክን፣ የፍርድ ቤትን ጊዜ የሚወስድ ከመሆኑም በላይ በአንድ ጉዳይ ብዙ ፋይል እንዲኖር
የሚያደርግና የሥራ ጫና የሚፈጥር እንዲሁም በይግባኝ ክርክር ምክያንት የሥር ክርክሩ ከታገደም ክርክርን
ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት እንዳይቻል የሚያደርግ በመሆኑ ይሕን ለማስቀረት
የተቀረጸ ነው፡፡ ጉዳዩ የመጨረሻ ዕልባት ሲያገኝ አብሮ ይግባኝ በማቅረብ ለተከራካሪዎች መብታቸውን
ማስከበር የሚችሉበት ሥርዓት ስለሚፈጥር ይግባኝ የማቅረብ መብታቸው ላይ ገደብ እንዳደረገ የሚወሰድ
አይደለም፡፡ አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውደቅ በመደረጉ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ
ሲያቀርብ ፍርደ ቤት ዋናው ክርክር ከመጠናቀቁ በፊት ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት ይግባኙን
ውደቅ ማድረግ ሲገባው የቀረበውን ክርክር ተቀብሎና አከራክሮ ውሳኔውን ማጽናቱ ክርክሩን በሥነ-ሥርዓት
ሕጉ አግባብ የመምራትና የመቆጣጠር ኃላፊነቱን አለመወጣቱን የሚያሳይና መሠረታዊ የሆነ የክርክር
አመራር ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 241335 የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ/ም የሠጠው ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሠረት ተሽሯል፡፡

2. አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በመደረጉ ያቀረበው ከሥረ-ነገሩ ውሳኔ በፊት ይግባኝ
ሊባልበት የሚችል ጉዳይ አይደለም በማለት ወስነናል፡፡

3. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 የሥር መዝገብ ይመለስ፡፡
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁጥር 204833

ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል፡- ነ/ፈጅ አመኑ ለሜሳ

ተጠሪ ፡ አቶ ፀጋዬ መለሰ፡- ከጠበቃ ፈለቀ ዋጎ ጋር ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የስራ ክርክር ሲሆን በተጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ
በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ በ08/11/2011 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች ሆቴል ውስጥ በዋና ምግብ አዘጋጅነት የስራ
መደብ በወር ብር 85,554 እየተከፈለኝ ስሰራ ቆይቼ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ በግንቦት 14
ቀን 2011 ዓ.ም. በነበረው የሙስሊሞች ጾም አፍጥር ዝግጅት ላይ ጉድለት አሳይተሀል በሚል ከግንቦት 15
ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የስራ ውሌን አቋርጧል፡፡ ነገር ግን የፈጸምኩት ጉድለት የለም፡፡ ጉድለት አለ ቢባል
እንኳን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብት ባለመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው ተብሎ አመልካች የማስጠንቀቂያ
ጊዜ፤ የካሳ እና የስንብት ክፍያ እንዲሁም የአንድ ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 705,820 እንዲከፍል ይወሰንልኝ
በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በ03/12/2011 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ ተጠሪ ዋና የምግብ አዘጋጅ እና የስራ መሪ ስለሆኑ
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም፡፡ ተጠሪ በቂ ምግብ ባለማዘጋጀታቸው እንግዶች ተሻምተው
እንዲበሉ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ተጠሪ በስራቸው የሚገኙ ሼፎችን አስተባብረው ባለመስራታቸው የተፈጠረ ችግር
ነው፡፡ በዚህም የሆቴሉ መልካም ስም ጎድፏል፡፡ ተጠሪ በተደጋጋሚ ጥፋት በመፈጸማቸው ማስጠንቀቂያ
ተሰጥቷቸው ሊታረሙ አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ
በሚሊኒየም አዳራሽ ለ750 ሰዎች ለተዘጋጀው የአፍጥር ስነስረአት ተጠሪ 15 በመቶ ተጨማሪ ምግብ
ማዘጋጀታቸው በተጠሪ ምስክር ተረጋግጧል፡፡ ተጠሪ በቂ ምግብ ስለማዘጋጀት አለማዘጋጀታቸው የእራት ሰአት
ከመድረሱ በፊት በአመልካች ቆጠራ አልተደረገም፡፡ ችግሩ ሊፈጠር የቻለው ተጠሪ በቂ ምግብ
ባለማዘጋጀታቸው ሳይሆን አመልካች እንግዶቹን እየተቆጣጣረ የሚያስገባበት ሁኔታ ስላልነበር መሆኑን የተጠሪ
ምስክሮች በተሻለ ሁኔታ ስላስረዱ በተጠሪ የተፈጸመ ጥፋት የለም፡፡ በመሆኑም ስንብቱ ህገወጥ ስለሆነ
የስንብት፣ የካሳ፣ የማስጠንቀቂያ ክፍያ በድምሩ ብር 655,914 እና የጠበቃ አበል ብር 25,000 አመልካች
እንዲከፈል ወስኗል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት በመሰረዙ የሚከተለውን የሰበር ቅሬታ አቅርቧል፡፡

አመልካች በ15/07/2013 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው የሰበር ቅሬታ ተጠሪ በተደጋጋሚ ለፈጸሙት ጥፋት
በ02/08/2011 ዓ.ም. እና በ19/08/2011 ዓ.ም. የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ሊታረም ባለመቻሉ ከስራ
እንዲሰናበቱ መደረጉ ተገቢ ነው፡፡ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ አቅርቤ፤ ተጠሪም ለሁለት ጊዜ ማስጠንቀቂያ
የተሰጣቸው መሆኑን ሳይክዱ ተጠሪ ጥፋተኛ አይደሉም መባላቸው ተገቢ አይደለም፡፡ ተጠሪ የስራ መሪ ናቸው
ብለን ያቀረብነው ክርክርም ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ የተጠሪ ስንብት ህገወጥ ነው የመባሉን አግባብነት
ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1(ሀ-ተ) አላማ እና አተገባበር አንጻር ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ
መልስ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተጠሪ በ26/08/2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች ቅሬታ ያቀረበው በፍሬ ነገር ክርክር ላይ ነው፡፡
የፍሬ ነገር ክርክሩ በማስረጃ ተጣርቶ የተወሰነ በመሆኑ የተፈጸመ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካችም በ13/09/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታውን አጠናክሯል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ከላይ ተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ
አንጻር ለቅሬታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ለተጠሪ ስንብት ምክንያት የሆነው ድርጊቱ ተፈጽሟል በተባለ እለት በእንግዶች ቁጥር ልክ
ምግብ ሳያዘጋጁ በመቅረታቸው እንግዶች ተገቢውን መስተንግዶ ሳያገኙ በመቅረታቸው የአመልካች መልካም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስም ጎድፏል በሚል ነው፡፡ ይህ ጥፋት በተጠሪ ተፈጽሞ ከሆነ የአመልካችን መልካም ስም በማጥፋት ደንበኛ
እንዲቀንስ በማድረግ በአመልካች ገቢ ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሸ
መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያበቃ ጥፋት ነው፡፡ ነገር ግን ተጠሪ ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለ
እለት ለእንግዶች የተዘጋጀው ምግብ ማነሱን ሳይክዱ ጥፋቱ የእኔ አይደለም በማለት የሚከራከሩ በመሆኑ
ስንብቱ ህጋዊ ነው አይደለም የሚለውን እልባት ለመስጠት በእለቱ ተጠሪ እንዲያዘጋጁ በአመልካች በታዘዙት
መጠን ልክ ባለማዘጋጀት ጥፋቱን መፈጸም አለመፈጸማቸው በማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ
የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዚህ ነጥብ ላይ የግራ ቀኙን ምስክር የሰማ ሲሆን
የተጠሪ ምስክሮች ተጠሪ ከእንግዶች ቁጥር በላይ 15 በመቶ ትርፍ ምግብ አዘጋጅተው የነበረ መሆኑን፤
እንግዶቹ በሚስተናገዱበት ሚሊኒያም አዳራሽ ሌላ ዝግጅት የነበረ በመሆኑ እና አመልካች ኩፖን አዘጋጅቶ
እንግዶችን እየተቆጣጠረ የሚያስገባ ሰራተኛ ባለመመደቡ ለሌላ ዝግጅት የተጠሩ ሰዎች ገብተው በመመገባቸው
የተዘጋጀው ምግብ ሊያልቅ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በአንጻሩ በአመልካች በኩል ሁለት ምስክሮች የቀረቡ
ቢሆንም አንደኛው ምስክር አመልካች እንግዶችን እየተቆጣጠረ የሚያስገባ ሰራተኛ መመደቡን ሌላኛው
የአመልካች ምስክር ደግሞ አመልካች ተቆጣጣሪ አለመመደቡን የመሰከሩ እና የአመልካች ምስክሮች ቃል
የተለያየ በመሆኑ ይልቁንም የአመልካች 2ኛ ምስክር ቃል የተጠሪን ምስክሮች ቃል የሚያጠናክር መሆኑን
የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ በማስፈር ለእንግዶች የምግብ እጥረት ሊፈጠር የቻለው ተጠሪ በቂ ምግብ
ባለማዘጋጀታቸው ሳይሆን አመልካች እንግዶቹን እየተቆጣጠረ ባለማስገባቱ ነው በሚል ስንብቱ ህገወጥ ነው
የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ
80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ላይ የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመባቸውን የመጨረሻ ውሳኔዎች ማረም ነው፡፡ በማስረጃ ተጣርቶ ድምዳሜ ላይ የተደረሰባቸውን የፍሬ
ነገር ክርክሮች ይህ ችሎት እንደገና የመመዘን ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ አመልካች ለተጠሪ በተደጋጋሚ
ማስጠንቀቂያ መስጠቱን በመግለጽ የሚያነሳው ክርክር በተመለከተ ተጠሪ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን
ባይክዱም እንኳን ለስንብት ምክንያት የሆነውን ጥፋት አለመፈጸማቸው እስከተረጋገጠ ድረስ አስቀድሞ በሌላ
ጥፋት ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ስንብቱን ህጋዊ ሊያደርገው አይችልም፡፡ በመሆኑም ተጠሪ ፈጽመዋል
የተባለውን ድርጊት አለመፈጸማቸውን ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች እስከተረጋገጠ
ድረስ ስንብቱ ህገወጥ ነው መባሉን ይህ ችሎት እንዳለ የሚቀበለው በመሆኑ እና በዚህ ችሎት ሊታረም
የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሌለ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1ኛ. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 70737 በ23/03/2013 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ
እና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 250280 በ02/07/2013 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል፡፡

2ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ትእዛዝ

በዚህ መዝገብ በ30/07/2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በአፈጻጸም መዝገብ ቁጥር 80332 ላይ የተሰጠው የእግድ
ትእዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-204866

ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የካ ክ/ከተማ ዐቃቤ ህግ ፅ/ቤት- ዮሴፍ ዲኖ ቀረቡ

ተጠሪዎች፡-1.አቶ ብሩክ ወንድሙ 2ኛ ተጠሪ ቀረቡ

2.ወ/ሮ ሚስጥረ ወንድሙ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም
በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358
የቀረበን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከውጤት አንፃር
ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን
አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን አመልካች በስር ፍርድ ቤት የመ/አመልካች የነበረ ሲሆን ተጠሪዎች
የመ/ተጠሪዎች ነበሩ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት ባቀረበው አቤቱታም አመልካች በአዋጅ


ቁጥር 64/2011 መሰረት የአስተዳደሩን እና የነዋሪዎችን መብት እና ጥቅም በማስከበር በማናቸውም
የዳኝነት አካል ዘንድ የመቃወም አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳለው በመግለፅ በመቃወም ተጠሪዎች
እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፅ/ቤት መካከል በተደረገው ክርክር ላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው
ውሳኔ መብቴን የሚነካ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባል በማለት አመልክቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም ተጠሪዎች በጉዳዩ ላይ መጥሪያ ደርሷቸው መልስ ከመስጠታቸው በፊት መዝገቡን
መርምሮ በሰጠው ውሳኔም ተጠሪዎች የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፅ/ቤትን ከሰው ክርክር ላይ
በነበሩበት ወቅት አመልካች ተከሳሹን ወክለው መልስ በመስጠት ከተከራከሩ በኋላ ውሳኔ የተሰጠ
መሆኑን፤በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ የሚችለው በክርክሩ ተካፋይ ባልነበረ ወገን
ሊሆን እንደሚገባ በግልፅ የሚያመለክት መሆኑን በመጥቀስ አመልካች ራሱ ተወካይ ሆኖ ተከራክሮ
የተሰጠውን ውሳኔ ቅሬታ ካለው ይግባኝ በማቅረብ እንዲስተካከል ከማድረግ ባለፈ በድጋሚ ተቃዋሚ
ሆኖ የሚቀርብበት አግባብ የለም በማለት የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ውድቅ ያደረገው ሲሆን
ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ብይኑን ከውጤት አንፃር አፅንቶታል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ ባቀረበው የሰበር አቤቱታም በመጀመሪያው ክስ እና በመቃወም


አቤቱታው ላይ ዐቃቤ ህግ ፅ/ቤት የወከላቸው የተለያዩ ተቋማት ሆነው እያለ ፍርድ ቤቱ ይህንን
ሳይገነዘብ፤በአዋጅ ቁጥር 64/2011 ለአመልካች የተሰጠውን የመቃወም አቤቱታ የማቅረብ ስልጣንና
ተግባር ሳይመረምር ፍርድ ቤቱ የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት
በመሆኑ፤የአስተዳር አካሉ ጣልቃ ለመግባት አቤቱታ አቅርብልኝ ብሎ ጉዳዩን ሲልክልኝ ብቻ ጉዳዩን
በመመርምር በጉዳዩ ላይ የጣልቃ ገብ አቤቱታ ሊቀርብበት እንደሚገባ ሲያምን አቤቱታ ከማቅረብ
ውጪ ዐቃቤ ህግ በራሱ ተነስቶ ጣልቃ ገብቶ ሊከራከር የሚችልበት አግባብ በሌለበት ከፍተኛ ፍርድ
ቤቱ የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ
ተሸሮ አመልካች የአስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ
በመቃወም አመልካችነት አቤቱታውን ተብሎ እንዲያከራክረን ይወሰንልን በማለት አመልክቷል፡፡

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በቀድሞ ክስ የወከለው የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳር ፅ/ቤትን ሆኖ እያለ
አሁን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት መብቴ ተነካ በማለት መቃወሚያ ያቀረበው የመሬት ባንክና ልማት
ማኔጅመንት ፅ/ቤትን በመሆኑ አመልካች የወከለው ሁለት የተለያዩ ተቋማትን ከመሆኑ አንፃር ጉዳዩን
ያውቃል በሚል አቤቱታው ውድቅ የተደረገበትን አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል
ከተባለ በኋላ ለተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸው መልሳቸውን አቅርበዋል፡፡

ተጠሪዎች በሰጡት መልስም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 6 በዝርዝር ከተሰጠው
ስልጣን አንጻር በተቋማት የምታዘዝ ስማ በለው ነኝ ማለቱ ተገቢነት የሌለው ሙግት ነው፤አመልካች
የቀደመው ክርክር መኖሩን እያወቀ ውጤቱን ጠብቆ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ የተሰጠው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ በሰበር መዝገብ ቁጥር 56795 የተሰጠውን አስገዳጅ ውሳኔ መሰረት ያደረገ በመሆኑ፤አመልካች
መብቱ ተነክቷል የሚለው የክፍለ ከተማው የይዞታ አስተዳር ፅ/ቤት በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ
የቤት ቁጥር 389 እና 390 መዝገብ ውስጥ ያሉትን ሰነዶች በመፈተሸ በሰጠው ምላሽ ይዞታው
በተጠሪዎች እጅ ያለ መሆኑን አረጋግጦ በሰጠው ምላሽ መሰረት በአፈፃፀም በተሰጠ ትዕዛዝ በሁከት
ተግባር የፈረሰውን ቤትና አጥር ባለበት ሁኔታ ተጠሪዎች የተረከብን በመሆኑ የሰበር አቤቱታው
ተቀባይነት የለውም ተብሎ ውሳኔ ይሰጥልን በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ
ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና
ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡በመሰረቱ የስር
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የአመልካችን የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የመቃወም አቤቱታ ውድቅ ያደረገው በመነሻነት
አመልካች በቀደመው ክርክር የየካ ክ/ከ/ወረዳ 07 አስተዳደር ፅ/ቤትን ወክሎ መከራከሩን በመጥቀስ
በዚህም የክርክሩ አካል ሳይሆን ወኪል መሆኑን በመጥቀስ ቢሆንም በመጨረሻ መደምደሚያው ላይ
በውሳኔው ቅር ከተሰኘ ስልጣን ላለው አካል ቅሬታውን በማቅረብ ማስተካከል እንደሚችል በውሳኔው ላይ
ማመልከቱ አመልካችን የክርክሩ አካል አድርጎ የወሰደ መሆኑን ያሳያል፡፡ጉዳዩን በይግባኝ
የተመለከተው ፍርድ ቤት የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ውድቅ ያደረገው ደግሞ ስለቀደመው
ዋናው ክርክር አመልካች የሚያውቅ ሆኖ እያለ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የመቃወም አቤቱታ ማቅረቡ
የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መቃወሚያ ማቅረቡን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡

አሁን በያዝነው ጉዳይ ለመቃወም አቤቱታው መነሻ የሆነው ክርክር ይዞታን የሚመለከት የሁከት
ይወገድልኝ ክርክር መሆኑ ግራ ቀኙ ያልተካካዱበት ነጥብ ሲሆን ተጠሪዎች ይዞታን በሚመለከት ክሱን
ያቀረቡት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፅ/ቤት ላይ ሲሆን በዚሁ ፅ/ቤት ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ
በክሱ ሊካተቱ የሚገባቸው ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ስልጣን ያላቸውና አስገዳጅ ውሳኔ
ቢሰጥም ለማስፈፀም አግባብነት ያላቸው አካላት ወደ ክርክሩ ገብተው መከራከራቸውን የስር ፍርድ ቤት
መዝገብ አያሳይም፡፡

አመልካች የመቃወም አቤቱታ ያቀረበው ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ስልጣን ያለውንና አስገዳጅ
ውሳኔ ቢሰጥም ለማስፈፀም አግባብነት ያለውን የየካ ክ/ከተማ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤትን
በመወከል መሆኑን በመጥቀስ በአዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 18(8)(9) በተሰጠው ስልጣን እና
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ.መ.ቁ 37502 በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም መሠረት
የመንግስትን እና የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል የሚያቀርበው የመቃወም አቤቱታ ሆኖ እያለ
ስለቀደመው ክርክር ማወቅ አለማወቁ ሊጣራና ሊመረመር የሚገባው ከመሬት አስተዳደር ጋር
በተያያዘ ስልጣን ያለውና አስገዳጅ ውሳኔ ቢሰጥም ለማስፈፀም አግባብነት ያለው የየካ ክ/ከተማ የመሬት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤት እንጂ ይህንን ፅ/ቤት ወክሎ የሚከራካረው አመልካች ባልሆነበት የክፍለ
ከተማው የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤት ስለቀደመው ክርክር እውቀቱ እያለው የክርክሩን ውጤት
ጠብቆ መቅረቡ ባልተረጋገጠበት የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ውድቅ
ማድረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.214399 ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓም የሰጠው


ብይን እና ይህንን ብይን በማፅናት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.261514 ሰኔ 09 ቀን
2013 ዓም የሰጠው ፍርድ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸረዋል፡፡
2. የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉዳዩን መዝገብ በማንቀሳቀስ የአመልካችን
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የቀረበ አቤቱታ ተቀብሎ ግራ ቀኙን አከራክሮ አስፈላጊ ከሆነም
ማስረጃዎችን ሰምቶ እና ተገቢውን ማጣራት አድርጎ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.360(2) መሰረት
የመሰለውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343(1) መሰረት መልሰንለታል፡፡
3. ሀምሌ 12 ቀን 2013 ዓም በዋለው ችሎት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
በመ/ቁ.261839 በተያዘው አፈፃፀም ላይ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ይጻፍ፡፡
4. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የ/ሰ/መ/ቁ. 204919

ቀን፡-27/01/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤሕግ-
ዓ/ህግ ሄኖክ ተስፋየ ቀረቡ

ተጠሪዎች፡- 1. አስረስ አዕሮ

2. ታምራት አዕሮ አልቀረቡም

3. አብይ አበራ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ብይን
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ
12027 በቀን 04/05/2013 ዓ.ም አመልካች ያቀረበውን ክስ ፍርድ ቤቱ በቀጥታ ተቀብሎ የማየት ስልጣን
የለውም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ፤ ይህንኑ ትዕዛዝ በማጽናት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ
ችሎት በመ.ቁ 08913 በቀን 27/05/2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ፤ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለ ጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአሁን አመልካች ተጠሪዎች የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 3
ድንጋጌን በመተላለፍ ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ያቀረበን ክስ የተመለከተው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች
እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበው ክስ በቀጥታ
በፍርድ ቤቱ የሚታይ ሳይሆን በይግባኝ የሚታይ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በቀጥታ ተቀብሎ ለማየት
የሚያስችል ሥልጣን የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል፡፡ አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ ያቀረበ ቢሆንም አቤቱታው በትዕዛዝ ውድቅ
ተደርጓል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 በመተላለፍ የሚቀርቡ ክሶች
ለፌዴራል ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሆነው ሳለ ክሱ የቀረበለት የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረበውን ክስ
በቀጥታ ለማየት የሚያስችል ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን ክስ በቀጥታ ለማየት
የሚያስችል ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ትዕዛዘስ አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት
እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ጉዳዩ የስረ ነገር የዳኝነት ስልጣን የሚመለከት በመሆኑ ፍርድ ቤቱ
የቀረበለትን አቤቱታ መርምሮ ጉዳዩን አከራክሮ መወሰን ያለበትን ፍርድ ቤት በመለየት ተገቢውን ፍርድ
ቢሰጥ አንቃወምም የሚል ነው፡፡ አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም የግራቀኙን ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው
መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ የሰበር አቤቱታው አቀራረብ
አግባብ መሆን አለመሆኑን በቅድሚያ መርምረናል፡፡

ከክርክሩ ሒደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ተጠሪዎች የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር
813/2006 አንቀጽ 3 ድንጋጌን በመተላለፍ ወንጀል ፈጽመዋል በማለት በቀጥታ የዳኝነት ስልጣኑ
እንዲመለከተው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሸካ ዞን ከፍተኛ
ፍርድ ቤት ክሱን ያቀረበ ቢሆንም ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ጉዳዩን በይግባኝ እንጂ በቀጥታ ለማየት
የሚያስችል ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን የዘጋው መሆኑን ነው፡፡

በመሠረቱ የክልል ሰበር ሰሚ ችሎቶች መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈፀመባቸውን የክልል ፍርድ
ቤቶች የመጨረሻ ውሳኔዎችን በሰበር አይተው የማረም ሥልጣን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ
80/3(ለ) የተሰጣቸው ሲሆን በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ሥልጣናቸውን መሠረት አድርገው
መስራት አለመስራታቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የክልል ሰበር ሰሚ ችሎቶች በሥራቸው ያሉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለ ጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የክልል ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን ጉዳይ አይተው ውሳኔ የሰጡት በሕግ በተሰጣቸው ስልጣን መሠረት
መሆን አለመሆኑን አይቶ የማረም ሥልጣን ያላቸው ለመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሰበር መዝገብ ቁጥር
78640፤ 82288፤ 106383 እና በሌሎችም መዛግብት አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ከዚህ
አንፃር የአሁን አመልካች አቤቱታውን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርቦ የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን
በቀጥታ ለማየት የሚያስችል ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ትዕዛዝ አግባብ መሆን አለመሆኑን ውሳኔ
ማሰጠት ሲገባው የሰበር ሥነ ሥርዓቱንና በመተላለፍ በቀጥታ ጉዳዩን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት ማቅረቡ ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. አመልካች ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ የመጨረሻ ውሳኔ
ያላገኘ በመሆኑ ተገቢውን ደረጃ ጠብቆ የቀረበ አይደለም በማለት ውድቅ አድርገናል፡፡

2. ይህ ውሳኔ መብቱን የሚጠይቅ ወገን በህጉ መሰረት አቤቱታውን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ከማቅረብ
የሚያግደው አይደለም ብለናል፡፡

- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለ ጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-205033

ቀን፡-27/01/2014ዓ/ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1ኛ ወ/ሪት የአብስራ ጥላሁን ጠበቃ ፋሲል ቀረቡ

2ኛ ህፃን ሚኪያስ ጥላሁን

ተጠሪ፡- አቶ ክፍለዪሀንስ ደረጀ - ከጠበቃ ደሳለኝ ደመቀ ጋር ቀረቡ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ይህ የሰበር ክርክር ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች በቀን 20/07/2013 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ የፌደራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 193736 በቀን 28/05/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ
መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልጸው በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት
ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻነት ሲሆን አመልካቾች በፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ከሳሾች
የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ የሟች አባታችን አቶ ጥላሁን በለጠ ልጆች
እና ሕጋዊ ወራሾች ስንሆን አባታችን በህይወት በነበሩ ጊዜ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር
አዲስ የሆነ በስማቸው ተመዝግቦ የሚገኝ መኖርያ ቤት የነበራቸው ሲሆን ለዚህ ቤት ተጠሪ ካርታ
አወጣለሁ በሚል ከሟች አባታችን ውክልና የተሰጠው ሲሆን አባታችን ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዪ በኋላ
ተጠሪ ይህንን ውክልና በመጠቀም በዚህ ቤት ላይ በአባታችን ስም በካርታ ቁጥር.20/41/17075/00
በቀን 30/12/99 ዓ.ም የይዞታ ማረጋጋጫ ካርታ ያወጣበት ሲሆን ሟች አባታችን ሕጋዊ ወራሽ
እንደሌለው በማስመሰል እና አባታችንን እንዲጠፋ በማድረግ በማናውቀው ሁኔታ ቤቱን በእጁ
በማድረግ እየተጠቀመ የሚገኝ በመሆኑ ተጠሪ በኃይል የያዘውን ቤት ከነይዞታ ማረጋገጫ
እንዲያስረክበን ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪ በሰጡት መልስም ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቤት ከሟች አቶ ጥላሁን በለጠ መጋቢት 29 ቀን
1994 ዓም ባደረግነው የመንደር ሽያጭ ውል በብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ገዝቼው ሚያዚያ 1 ቀን
1994 ዓ.ም ቤቱን ተረክቤ እስካሁን ድረስ እየኖርኩበት እገኛለሁ በይዞታው ላይ የነበረውን ቤት
አፍርሼ ሌላ ቤት ሰርቼለሁ ለ16 ዓመታት ለቤቱ ግብር ገብሬያለሁ ስለሆነም ቤቱን በኃይል ሳይሆን
በሽያጭ ውል የያዝኩት እና ሟችም ከመሞቱ በፊት መብቱን ሕግ በሚፈቅደው መሰረት በውል
ያስተላለፈልኝ በመሆኑ ለአመልካቾች ቤቱን የማስረክብበት ሕጋዊ ምክንያት የለም፤ ነገር ግን ቤቱን
ማስረከብ አለብህ ከተባልኩ ለቤቱ ያወጣሁትን ልዪ ልዪ ወጪዎችን ከአመልካቾች የመጠየቅ መብቴ
ይጠበቅልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ውሉ ሲደረግ ነበሩ የተባሉ ምስክርን አስቀርቦ በመስማትና
የሰነድ ማስረጃዎችን በመመርምር በሰጠው ውሳኔም ተጠሪ አከራካሪውን ቤት 1994 ዓም በተደረገ
የሽያጭ ውል ከአመልካቾች አባትና እናት በመግዛት ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ በእጃቸው በማድረግ
እየተጠቀሙበት መሆኑን የሚገኙ መሆኑን ያስረዱ ስለሆነ ተጠሪ አከራካሪውን ቤትና ሰነዶቹን
ለአመልካቾች ሊያስረክቡ አይገባም በማለት ወስኗል፡፡

ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በተጠሪ እና በአመልካቾች አውራሽ


መካካል የተደረገው ውል በፅሁፍ የተደረገ ሆኖ ሊመዘገብ ሲገባው ያልተመዘገበ በመሆኑ የህጉን
ፎርማሊቲ አሟልቷል ሊባል ስለማይችል ውሉ እንደ ረቂቅ የሚቆጠር እንጂ ህጋዊ ውጤት እንዳለው
የቤት ሽያጭ ውል ሊቆጠር ስለማይችል ተጠሪ በዚህ ውል አማካኝነት የቤቱ ባለቤት ተደርገው ሊወሰዱ
አይችሉም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር ተጠሪ በይዞታው ላይ ያፈሩት ንብረት ካለ ከስሶ
የመጠየቅ መብትን በመጠበቅ ወስኗል፡፡

የአሁን ተጠሪ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሰኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፌደራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የስር
የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም የስር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ የሽያጭ ውሉን ክደን እንደተከራከርን ባረጋገጠበት ደረጀና ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2003 ድንጋጌ በተቃረነ መልኩ አንድ ምስክር በመስማት በተካደ ውልና አግባብ ባለው ውል አዋዋይ
ፊት ያልተረጋገጠን ረቂቅ ውል መሰረት አድርጎ ለአሁን ተጠሪ የባለቤትነት መብት ማጎናፀፉ
ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.1723፣ 2878 እና ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ.21448 እና
በርካታ ከጉዳዪ ጋር የተያያዙ የሕግ ትርጎሞች አንፃር መሰረታ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ
ሊሽርበት የሚገባውን በቂ ምክንያት ሳያስቀምጥ የውሉን መኖር ክደን ተከራክረን እያለ በደፈናው
ያቀረብነውን ክርክር ወደጎን በማለት የስር የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማፅናቱ መሰረታዊ
የሕግ ስሕተት ነው፡፡ስለሆነም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሰጠውን ውሳኔ
በመሻር ጉዳዪ እንደገና እንዲታይልን ወይም አሁን ያቀረብነው ቅሬታ በሰ/መ/ቁ.195021 ላይ የስር
ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ተጠሪ ቤቱንና ሰነዶችን እንዲያስረክበን ፍርድ ሳይሰጥ በማለፉ
ቅሬታ አቅርበን ጉዳዪ ያስቀርባል ተብሎ ለምርመራ የተቀጠረ በመሆኑ ቅሬታው አንድ ላይ ተጣምሮ
ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲሰጥልን በማለት አመልክተዋል፡፡

ለክርክር መነሻ የሆነው ቤት ቋሚ /የማይንቀሳቀስ/ ንብረት ከመሆኑ አንፃር አለ የተባለው የሽያጭ ውል


በሚመለከተው አካል ቀርቦ ባልተመዘገበበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ከአመልካቾች አባት
ጋር የሽያጭ ውል ፈፅሟል በማለት ተጠሪ ቤቱን ሊለቅ አይገባም በማለት የወሰነበትን አግባብ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 21448 ከሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ እና
ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.1723፣ 2878 ጋር በማገናዘብ ለመመርመር የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ
ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው መልስ አቅርበዋል፡፡

ተጠሪ በዚህ መልሳቸውም በስር መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር ተጠሪ ውሉን
ሲያቀርብ አመልካቾችን በጉዳዪ ላይ ጥቅም አለን ካሉ በአባታችንና ተጠሪ መካካል ውል
አልተደረገም፣ወይም የአባታችን ፊርማ አይደለም፣ አባታችን የሽያጭ ገንዘብ አልተቀበለም፣ ውሉ ሀሰት
ነው፣ እናታችን በሕይወት ያለች ስለሆነ መሸጥ አለመሸጧን ችሎት ቀርባ ታረጋግጥ ወዘተ ማለት
ሲገባቸው ውሉ ረቂቅ ነው ይባልልን በማለት በክስ ላይ ያልጠቀሱትን ሀሳብ በይግባኝ ክርክር ወቅት
አቅርበዋል፡፡

አመልካቾች ውል መኖሩን በሚገባ ያውቃሉ፡፡አመልካቾችና እናታቸው ቤቱ መሸጡን ባያውቁ ኖሮ


ቢያንስ አባታቸው በሞተበት 1997 ዓ.ም እና ክስ ባቀረቡት 2010 ዓ.ም መካካል ባሉት አስራ ሶስት
ዓመታት ውስጥ በግለሰብ ኪራይ ቤት እየኖሩ ቤታቸውን ሌላ ሰው እንዲኖርበት ሊፈቅዱ
አይችሉም፡፡ስለዚህ አመልካቾች ውል መኖሩን በሚገባ እያወቁና ውሉ እንዲፈርስ ግልጽ ዳኝነት
ባልጠየቁበትና ክርክር ባልተደረገበት ሁኔታ የክርክር አቅጣጫ በሂደት እንዲቀየር በማድረግ በአቋራጭ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ለዓመታት የለፋሁበትንና ከፍተኛ ወጭ ያወጣሁበትን ቤት ለመረከብ ያቀረቡት አቤቱታ


ተቀባይነት የለውም ተብሎ አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግልኝ እና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት የለውም ተብሎ እንዲፀናልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካቾች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡በመሰረቱ አንድ
ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አወሳስን የጠራ ፍሬ ነገር የሌለ መሆኑን ከተገነዘበ ይኸው ፍሬ ነገር እንዲጣራ
ተገቢ ነው ያለውን ማጣራት ሁሉ ማድረግ እንደሚችል ከፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.136፤137፤272 እና 345
ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻል ሲሆን ለጉዳዩ አወሳሰን መሰረት የሚሆንን ፍሬ ነገር በማስረጃ ሳያጣሩ
መወሰን አግባብ ባለመሆኑ በክርክሩ የቀረቡት ማስረጃዎች በቂ ባልሆኑበት ጊዜ እና እነዚህን
ማስረጃዎች ብቻ መሰረት አድርጎ መወሰን ፍትህን የሚያዛባ ከሆነ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት ተጨማሪ
ማስረጃ ወይም ምስክር እንዲቀርብ መታዘዝ አለበት፡፡(በሰበር መዝገብ ቁጥር 72980 ፤ 22603፤180331
እና በተመሳሳይ ጉዳይ የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎችን ይመለከቷል፡፡)

አሁን በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ ውሉ አለመደረጉን በመካድ አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት አልተከራከሩም
በዚህ አግባብ የቀረበው ክርክር አዲስ ክርክር ነው በማለት የተከራከሩ ቢሆንም የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት
በሰጠው ውሳኔ ላይ «…አመልካቾች ውሉ ሀሰተኛ ነው፤ሚስትም አልፈረመችበትም፤የሽያጭ ውልም
አልተደረገም…»በማለት መከራከራቸውን ማመልከቱ አመልካቾች ከውሉ አለመኖር ጋር በተያያዘ
ያቀረቡት ክርክር በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዲስ ክርክር አለመሆኑን ያሳያል፡፡የውሉን መደረግ
አለመደረግ ለማጣራት አንድ ምስክር በማስቅረብ የሰማ መሆኑ በውሳኔው ላይ የተመለከተ ቢሆንም
የስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ካቀረቡት ክርክር አንፃር የውሉ ተዋዋይ መሆናቸው ተገልፆ በተጠሪ
ክርክር የቀረበባቸው ወ/ሮ አየሉ ሹሙ ወደ ክርክሩ እንዲገቡ በማድረግ ግለሰቧ በውሉ ላይ የፈረሙ
መሆን አለመሆኑን በማጣራት ከፈረሙም አመልካቾች የሽያጭ ውል አልተደረገም በማለት የተከራከሩ
በመሆኑ በህጉ አግባብ የተደረገ ውል መኖር አለመኖሩን በማጣራት የሰጠው ውሳኔ ስለመኖሩ የስር
ፍርድ ቤት ውሳኔ አያሣይም፡፡

ይህንን ውሳኔ በይግባኝ ተመልክቶ ያፀናው ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም አመልካቾች አከራካሪውን
ቤት አስመልክቶ በአውራሻቸውና እናታቸው ወ/ሮ አየሉ ሹሙ የተደረገ ውል የለም በማለት በግልፅ
ክርክር ማቅረባቸውን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እያሳየ አመልካቾች«…አባታቸው የተባለውን ውል
ከይግባኝ ባይ ጋር እንዳልፈፀመ ወይም አባታችን ውሉን አላደረገም በማለት በግልፅ ክደው
እንዳልተካራከሩ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ውስጥ መረዳት ይቻላል፡፡» በማለት ከውሉ የህጉን
መስፈርት ማሟላት አለማሟላት ጋር በተያያዝ የቀረበውን ክርክር ሳይመረምር የስር ፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት
የሰጠውን ውሳኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለው ተወስኗል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ

1.የፌደራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ 65262 በቀን 14/02/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት
የሰጠውን ፍርድ በማፅናት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በይ/መ/ቁ 193736 ጥር
28 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ፍርድ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸሯል፡፡

2.የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉዳዩን መዝገብ በማንቀሳቀስ ወ/ሮ አየሉ ሹሙን ወደ
ክርከሩ በማስገባት ውሉ በአመልካቾች አውራሽና ወ/ሮ አየሉ ሹሙ የተፈረመ ነው ወይስ አይደለም
የሚለውን ፊርማውን እንዲመረመር በማድረግ ውጤቱን በችሎቱ ቀርበው ከተሰሙት ምስክር ቃል ጋር
በመመርመር ውሉ በነዚህ ተዋዋይ ወገኖች (አቶ ጥላሁን በለጠን ጨምሮ) የተፈረመ ከሆነም ውሉ
የህጉን ፎርማሊቲ በማሟላት የተደረገ መሆን አለመሆኑን በመመርመር በህጉ አግባብ የመሰለውን ውሳኔ
እንዲሰጥ ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343(1) መሰረት መልሰንለታል፡፡

3.ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁጥር 205048

ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ ዮናስ ሰለሞን- ቀረቡ

ተጠሪዎች ፡ ሸገር ብዙሀን ትራንስፖርት ድርጅት- ነ/ፈ አየለ ወርቁ ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ በዲሲሊን ክስ ቀርቦ ሰራተኛው ከስራ እንዲሰናበት ከተወሰነ አሰሪው ሰረተኛው ከስራ የሚያሰናብተውን
ጥፋት መፈጸሙን አውቋል ሊባል የሚችለው መቼ ነው? የሚለውን የአሰሪ እና ሰራተኛ ክርክር የሚመለከት
ነው፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ
ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካች ሐምሌ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ ስራ ሳይጠናቀቅ ባስ አቁመህ ሄደሀል በማለት
ተጠሪ በሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ከስራ አግዶኛል፡፡ እንደዚሁም የስምሪት ኦፊሰር ላይ ድብደባ
ፈጽመሀል በማለት ከ30 ቀን በላይ ታግጄ ከቆየሁ በኋላ ተጠሪ ከስራ አሰናብቶኛል፡፡ በመሆኑም ስንብቱ
ህገወጥ ስለሆነ የተለያዩ ክፍያዎች ይከፈሉኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪም በሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካች ከስራ በመቅረታቸው ምክንያት
በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ቢሆንም ባለመታረማቸው በሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ከስራ
ታግደዋል፡፡ ሚያዝያ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰራተኛ ላይ ድብደባ በመፈጸማቸው የዲሲፕሊን ኮሚቴ አጣርቶ
አመልካች ከስራ እንዲሰናበቱ የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ በ30 ቀን ይርጋ አይታገድም በማለት
ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክር ሰምቶ
በአዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀጽ 27/3 አሰሪው ውል የሚያቋርጥበት ምክንያት መኖሩን ካወቀ ከ30 ቀናት
በኋላ የማሰናበት መብቱ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ይገልጻል፡፡ አመልካች ጥፋት ፈጸሙ ከተባለበት
ከሚያዝያ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ እስከፈረመበት ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ
ያለው ቀን ሲቆጠር 61 ቀን በመሆኑ እና የመስሪያ ቤቱ ሃላፊ የፈረመውም የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ከሰጠ
የ30 ቀን ካለፈ በኋላ በመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው፡፡ በመሆኑም ተጠሪ ለአመልካች ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎ
ወደስራ ይመልሳቸው በማለት ወስኗል፡፡

ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ላይ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ
የሰራተኛው ጥፋት በዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚጣራ ከሆነ አሰሪው ጥፋት መፈጸሙን አውቋል ሊባል የሚችለው
በዲሲፕሊን ኮሚቴው ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ ጊዜ ጀምሮ መሆን እንዳለበት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ሰበር አሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 53358 የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል፡፡ በድርጅቱ የህብረት ስምምነት
መሰረት ጥፋተኝነት የሚረጋገጠው በዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የመስሪያ ቤቱ የበላይ ሃላፊ
ሊያጸድቅ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ ስለዚህ የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ ከጸደቀ
ጀምሮ ሲቆጠር የ30 ቀን አልፏል ማለት ስለማይቻል ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ
ሽሯል፡፡

አመልካች በመጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረቡት ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ
ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለማሳረም ነው፡፡ የቅሬታው ይዘት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 53358 የህግ ትርጉም የተሰጠው የማጣራት ሂደት የሚያስፈልገው ጥፋት
ሲፈጸም ነው፡፡ አመልካች ፈጽመሀል የተባልኩት ጥፋት በእለቱ በአሰሪ የሚታወቅ በመሆኑ ማጣራት
የሚያስፈልገው አይደለም፡፡ ስለዚህ የይርጋ ጊዜ ሊቆጠር የሚገባው ጥፋቱ ተፈጸመ ከተባለ ጊዜ ጀምሮ ሊሆን
ይገባል፡፡ ይርጋው መቆጠር ያለበት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ከወሰነ በኋላ ነው ቢባል እንኳን የበላይ ሀላፊው
ውሳኔውን እስኪያጸድቀው ሊጠበቅ አይገባም፡፡ በመሆኑም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ ይርጋው መቆጠር የሚጀምረው ኮሚቴው ውሳኔ
ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ነው ወይስ የኮሚቴ ውሳኔ በኃላፊው ከጸናበት ጊዜ ጀምሮ ነው? የሚለውን ነጥብ
ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ በሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ በድርጅቱ የህብረት ስምምነት መሰረት አመልካች
ጥፋተኛ መሆኑ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ተረጋግጦ በበላይ ሃላፊ ውሳኔው ከጸደቀበት ጀምሮ የ30 ቀን የይርጋ
ጊዜ ሊቆጠር ይገባል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ
ቁጥር 53358 የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል በማለት ተከራክሯል፡፡

አመልካች በሐምሌ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታቸውን አጠናክረዋል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ
አንጻር በስር ፍርድ ቤት ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር እና ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካች ፈጽመዋል የተባለውን የሰራተኛ ድብደባ አለመፈጸማቸውን ክደው የሚያቀርቡት


መከራከሪያ የለም፡፡ የስራ ውል ከመቋረጡ በፊት በድርጅቱ ህብረት ስምምነት መሰረት መጀመሪያ ጥፋቱ
በዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጣርቶ ውሳኔ መሰጠት እንዳለበት እና የዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ በሀላፊ ሊጸድቅ
እንደሚገባ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ድርጊቱ በተፈጸመ
እለት ከስራ እንደሚያሰናብት የሚታወቅ ግልጽ ጥፋት በመሆኑ ከስራ ለማሰናበት በዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ
እስኪሰጥ እና የዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ በኃላፊ እስኪጸድቅ ሊጠበቅ አይገባም፡፡ በመሆኑም የስንብት
ደብዳቤ የተሰጠኝ በህጉ የተመለከተው የ30 ቀን ካለፈ በኋላ በመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው በሚል ነው፡፡
ተጠሪ በበኩሉ አመልካች የተሰናበቱት ለስንብት ምክንያት የሆነውን ድርጊት ከፈጸሙ ከ30 ቀን በኋላ
መሆኑን ሳይክድ የስንብት ኮሚቴ ውሳኔ እስኪሰጥ እና የኮሚቴው ውሳኔ በተጠሪ ኃላፊ እስኪጸድቅ መጠበቁ
ተገቢ መሆኑን ገልጾ ተከራክሯል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 አንድ አሰሪ ሰራተኛው በአዋጁ አንቀጽ 27/1 ላይ የተዘረዘሩትን
ከስራ የሚያሰናብተው ድርጊት መፈጸሙን ካወቀ ከ30 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ከስራ የማሰናበት
መብቱን እንደተወ እንደሚቆጠር ያመለክታል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው የ30 ቀኑ የጊዜ ገደብ
የበአላት እና የእረፍት ቀናትን ሳይጨምር የስራ ቀን ብቻ እንደሚቆጠር እና ይህ 30 የስራ ቀን መቆጠር
የሚጀምረው አሰሪው ድርጊቱ መፈጸሙን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ
አመልካች ድብደባውን በፈጸመ እለት አላውቅም ነበር በሚል ያቀረበው ክርክር ካለመኖሩም በላይ በአመልካች
ላይ የዲሲፕሊን ክስ ያቀረበው ተጠሪ በመሆኑ ድርጊቱ በተፈጸመ ቀን አመልካች መፈጸሙን ያቅ እንደነበር
አመላካች ነው፡፡ ይሁን እንጂ በድርጅቱ የህብረት ስምምነት ጥፋተኝነት በዲሲፕሊን ኮሚቴ ተወስኖ በበላይ
ሃላፊ መጽደቅ እንዳለበት ከተመለከተ አሰሪው ይህንን ሂደት ሳይከተል ድርጊቱ መፈጸሙን እንዳወቀ
ሰራተኛውን ቢያሰናብት ስንብቱን ህገወጥ ያደርገዋል፡፡ አሰሪው ያለው አማራጭ ድርጊቱ መፈጸሙን ድርጊቱ
በተፈጸመ እለት ቢያቅ እንኳን በጉዳዩ ላይ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ እስኪሰጥ መጠበቅ ነው፡፡ አሰሪው
ሰራተኛው በህብረት ስምምነት ያለውን መብት ለማክበር ጉዳዩ በዲሲፕሊን ታይቶ እስኪወሰን በመጠበቁ
ሰራተኛውን ከስራ ሳያሰናብት የ30 ቀን የጊዜ ገደብ ቢያልፍ አሰሪው የማሰናበት መብቱን እንደተወው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መቁጠር የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/3 ድንጋጌ አላማ ነው ተብሎም አይገመትም፡፡ በእርግጥ
የዲሲፕሊን ኮሚቴ አጣርቶ ከወሰነ በኋላ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በወሰነ በ30 ቀን ውስጥ
የዲሲፕሊን ኮሚቴውን ውሳኔ በማጽናት ወይም በመሻር ወይም በማሻሻል ሊወስን ይገባል፡፡ ምክንያቱም
የዲሲፕሊን ኮሚቴ አጣርቶ ከወሰነ በኋላ እንደገና የሀላፊውም ውሳኔ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ እንዲወስድ
ከተፈቀደ በአዋጁ አንቀጽ 27/3 የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ አላማ የሚቃረን ይሆናል፡፡በመሆኑም ጥፋቱ
በዲሲፕሊን ኮሚቴ መጣራት እንዳለበት በህብረት ስምምነት ወይም በሌላ ሁኔታ ከተመለከተ በአዋጅ ቁጥር
1156/2011 አንቀጽ 27/3 የተመለከተው የ30 ቀን የጊዜ ገደብ መቆጠር መጀመር ያለበት የዲሲፕሊን ኮሚቴ
ውሳኔ በሀላፊ ከጸደቀበት ሳይሆን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ሊሆን ይገባል፡፡ ከዚህ ጋር
በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 53358 የህግ ትርጉም
ሰጥቶበታል፡፡

ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ የአመልካች ጥፋተኝነት በዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጣርቶ ተፈርሞ የተጠናቀቀው
በግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው፡፡ በተጠሪ የበላይ ኃላፊ የተፈረመው ደግሞ በሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም.
ነው፡፡ ከግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በተከታታይ ሲቆጠር 35
ቀን የሚሆን ቢሆንም በመካከል ቢያንስ 8 ቅዳሜ እና እሁድ የእረፍት ቀን የሚኖር በመሆኑ የስራ ቀን ብቻ
ሲቆጠር ሃላፊው የዲሲፕሊን ኮሚቴውን ውሳኔ በማጽናት የወሰነው የ30 ቀን የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ ነው
ማለት አይቻልም፡፡

ሲጠቃለል አመልካች በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/1/ረ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ
ሊያሰናብታቸው የሚችል ድርጊት መፈጸማቸውን ተጠሪ ድርጊቱ በተፈጸመ እለት ቢያውቅ እንኳን በድርጅቱ
የህብረት ስምምነት ጥፋተኝነት የሚወሰነው በዲሲፕሊን ኮሚቴ ከተጣራና ከተወሰነ በኋላ መሆኑን
እስከተመለከተ ድረስ በአዋጁ አንቀጽ 27/3 የተመለከተው የ30 ቀን የጊዜ ገደብ መቆጠር መጀመር ያለበት
የዲሲፕሊን ኮሚቴ ከወሰነ ቀን ጀምሮ ሊሆን ሲገባ የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ30 ቀኑ መቆጠር መጀመር
ያለበት የዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ በኃላፊ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ነው ማለቱ ተገቢ ባይሆንም የተጠሪ ኃላፊ
ውሳኔውን ያጸናው የ30 ቀን የጊዜ ገደብ ሳያልፍ በመሆኑ ከውጤት አንጻር የሚያመጣው ለውጥ ስለሌለ
የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1ኛ. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 257967 በመጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም. የሰጠው
ውሳኔ ጸንቷል፡፡

2ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይ


መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ፡-205297
ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ፡- ዓ/ህግ ቴዎድሮስ ቀረቡ

ተጠሪ፡- እያሱ ያየህ ባየህ - አልቀረቡም

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 197256 ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም የስር
ከፍተኛው ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ያስተላለፈውን የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በመሻር ተጠሪን በነጻ
በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት
አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን አመልካች
በአሁን ተጠሪ ላይ በስር ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ
543/2 ድንጋጌን በመተላለፍ በቀን 24/09/2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡45 ሰዓት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-01771
ኢት የሆነ ተሸከርካሪ ይዞ ከሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ወደ ጃክሮስ አቅጣጫ በሚያሽከረክርበት ወቅት
ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲን አካባቢ ሲደርስ የመንገዱን እና የእግረኞቹን ሁኔታ በማየት ጥንቃቄ አድርጎ
ማሽከርከረ ሲገባው ይህን ባለማድረግ መንገዱን ከግራ ወደ ቀኝ ሲያቋርጥ የነበረውን ሟች ማቴዎስ ሀናቆ
የተባለውን ግለሰብ በተሸከርካሪው የፊት ለፊት የግራ አካል በመግጨት ጥሎት ሟችም በግጭቱ ምክንያት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በጭንቅላቱ ላይ በደረሰ ጉዳት ሕይወቱ ያለፈ በመሆኑ በፈጸመው በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል
ተከሷል የሚል ነው፡፡

ክሱ ለተጠሪ ተነቦለት እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ድርጊቱን መፈጸሙን ሆኖም ጥፋተኛ አለመሆኑን
በመግለጽ ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም የዓቃቤሕግን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ዓቃቤሕግ ባቀረበው ማስረጃ
ተጠሪ የተከሰሰበትን ወንጀል ስለመፈጸሙ በበቂ እና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ አስረድቷል በማለት ተጠሪ ክሱን
እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል፡፡ ተጠሪም መከላከያ ምስክሮቹን አስቀርቦ አሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም የግራቀኙን
ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ ባቀረበው መከላከያ ማስረጃ የቀረበበትን ክስ አልተከላከለም በማለት
ጥፋተኛ ብሎ በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ቀላል እስራት እና በብር 1,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ
የወሰነ ሲሆን ቅጣት እንዲገደብ የቀረበውን ጥያቄ በሚመለከት ደግሞ የትራፊክ አደጋ እንደሐገር እያደረሰ
ካለው ጉዳት አንጻር ተቀባይነት አላገኝም በማለት ውድቅ አድርጎታል፡፡

ተጠሪ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
አቅርቧል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ሟች በተጠሪ መኪና ከመገጨቱ በፊት
ተጠሪ ሟችን አይቶት ከሁለት ጊዜ በላይ ክላክስ ያደረገለት መሆኑ፤ መኪናውም ፍጥነት ያልነበረው
ይልቁንም በመቆም እና በእንቅስቃሴ መካከል የነበረ ስለመሆኑ እንዲሁም ሟች ፊቱን ከመኪናው ወደ
ተቃራኒ ኣጣጫ በማዞር ወደ ኋላ ወደ መኪናው መጥቶ መጋጨቱ መመስከሩ ሲታይ ተጠሪ
በሚያሽከረክረው መኪና ሟችን ሊገጨው እንደሚችል እያወቀ ይህ ክስተት አይደርስም በሚል ግምት ወይም
ባለማመዛዘን በሟች ላይ ጉዳት ደርሷል ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም፤ በተመሳሳይ ሟች
እንደሚገጨው ማወቅ እያለበት ወይም እየቻለ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ ሟች ላይ ጉዳት ደርሷል
ለማለት የሚያስችልም አይደለም፤ ይልቁንም መኪናው ፍጥነት አለመኖሩ እና ክላክስም ማድረጉ የደረሰውን
አደጋ ለማስቀረት ሙያው በሚፈቅደው መሠረት ጥረት ማድረጉን የሚስገነዝብ ነው፤ በመሆኑም በማስረጃ
የተረጋገጠው ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2፤ 24፤ 59/1፤ 543/2 የተመለከቱትን በሚያሟላ መልኩ
የተፈጸመ የቸልተኝነት የወንጀል ድርጊት ነው ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም በማለት በስር
ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በመሻር ተጠሪን በነጻ በማሰናበት
በአብላጫ ድምጽ ወስኗል፡፡

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን
ይዘቱም ፤ ሟች ሳያይ ወደ መኪናው መግባቱ ለአደጋው አስተዋጽኦ አለው ሊባል ከሚችል በቀር ሌሎች
ማስረጃዎችን በተለይም የተጠሪን ቸልተኝነት መኪናውን ፍሬን ይዞ አለማቆሙ መሆኑን የሚያሳየውን
የባለሙያ ምስክርነት ወደ ጎን በመተው የዓቃቤሕግ ምስክሮች ሟች መጥቶ ተጋጨ ብለዋል በሚል ለብቻው
መዝኖ ክላክስ በማድረጉ ብቻ ሟችን ለማዳን ጥረት ስላደረገ ቸልተኝነት የለም መባሉ አግባብ አይደለም፤
ዓቃቤሕግ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ እንደክስ አመሰራረቱ ያስረዳ እና ተጠሪም ይህንን በማስረጃዎቹ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ያላስተባበለ በመሆኑ ተጠሪን በነጻ በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪው ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪን ከቀረበበት ክስ በነጻ
የማሰናበቱን አግባብነት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 89676 ከሰጠው የማስረጃ
ምዘና መሠረታዊ መርህ አንጻር ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ
እንዲሰጡበት ተደርጎ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ቀርቧል፡፡

ተጠሪ ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የዓቃቤሕግ ሁለት ምስክሮች ተጠሪ
መኪናውን ከቆመበት አስነስቶ በዝቅተኛ ፍጥነት እየነዳ ሳለ ሟች በመኪናው በስተግራ ወደ ኋላው ዙሮ
እያወራ ዘሎ ሲገባበት ተጠሪ የመኪና ክላክስ እያደረገ መኪናውን ለማቆም በመታገል ላይ እያለ ሟች
ከመኪናው ጋር በመጋጨት እንደወደቀ መስክረዋል፤ 3ኛው የዓቃቤሕግ ምስክር አደጋው ሲፈጠር በቦታው
ላይ ያልነበረ እና የሙያ ምስክር እንደሆነ በመግለጽ ተጠሪ ሟችን በሆነ መንገድ ሊያተርፈው ይችል ነበር
ከማለት በቀር በዚህ ርቀት ተጠሪ ሟችን ሊያተርፍ የሚችልበትን መንገድ አላሳየም፤ የተጠሪ መከላከያ
ምስክሮች ክላክስ እያሰማሁ መኪናውን በማቆም ላይ እያለሁ ሟች ከመኪናው ፊት ለፊት በግራ በኩል
ተጋጭቶ መውደቁን መስክረዋል፤ ተጠሪ ማንበብ ስለማልችል በአደጋ ፕላኑ ላይ መፈረሜ ድርጊቱን
መፈጸሜን የማያሳይ በመሆኑ በስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪን በነጻ በማሰናበት የተሰጠው
ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ
ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር
አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምሮታል፡፡

አመልካች በስር ፍርድ ቤት ተጠሪን በነጻ በማሰናበት የተሰጠው ውሳኔ ሊታረም ይገባል በማለት
የሚከራከረው ተጠሪ ክላክስ ማድረጉ ብቻ ሟችን ለማዳን ጥረት አድርጓል አያስብልም፤ ተጠሪ ሌላ እርምጃ
በመውሰድ ሟችን ከሞት ለመታደግ ሲችል ተገቢውን ጥረት ያላደረገ በመሆኑ በወቅቱ ቸልተኝነት የነበረው
መሆኑን የሚያሳይ ነው በማለት ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ በዝቅተኛ ፍጥነት እየነዳሁ ሳለ ሟች በመኪናው
በስተግራ ወደ ኋላው ዙሮ እያወራ ዘሎ የገባብኝ እና ክላክስ በማድረግ መኪናውን ለማቆም በመታገል ላይ
የነበርኩ በመሆኑ ጥፋተኛ ልባል አይገባም በማለት የሚከራከር ነው፡፡ ስለሆነም ተጠሪ ሊወስደው ይገባው
የነበረውን እርምጃ ሳይወስድ በመቅረቱ ምክንያት የሟችን ሕይወት እንዲያልፍ አድርጓል? ወይስ አላደረገም?
የሚለው በዚህ ችሎት ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው የክርክሩ መሠረታዊ ጭብጥ ነው፡፡

የወንጀል ሕጉ ጠቅላላ ክፍል አንቀጽ 57 ለድርጊቱ ኃላፊ ሊሆን የሚገባው ሰው አስቦ ወይም በቸልተኝነት
አንድ ወንጀል ካላደረገ በቀር በወንጀል ጥፋተኛ አይሆንም በማለት ይደነግጋል፡፡ በዚሁ ሕግ አንቀጽ 59

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማንም ሰው በቸልተኝነት የወንጀል ተግባር አድርጓል የሚባለው ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት
ሊያስከትል እንደሚችል እያወቀ አይደርስም የሚል ግምት ወይም ባለማመዛዘን ወይም ድርጊቱ በወንጀል
የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም እየቻለ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ
ድርጊቱን የፈጸመ እንደሆነ ነው በማለት ተመልክቷል፡፡ ከድንጋጌዎቹ ይዘት መገንዘብ የሚቻለው በአንድ
ድርጊት ምክንያት አንድን ሰው በወንጀል ጥፋተኛ ነው ለማለት ከሳሽ የሆነው ዓቃቤ ሕግ ድርጊቱ
የተፈፀመው ሆነ ተብሎ ወይም በቸልተኝነት መሆኑን ማስረዳት የሚጠበቅበት መሆኑን ነው፡፡

በሌላ በኩል ተጠሪ የተከሰሰበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 543 ድንጋጌ በቸልተኝነት ሰውን ስለመግደል
የሚመለከት ሲሆን የዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር (2) የሌላ ሰውን ሕይወት፤ ጤንነት ወይም ደህንነት
የመጠበቅ የሙያ ወይም ሌላ ግዴታ ያለበት እንደ ሕክምና ባለሙያ ወይም አሽከርካሪ ያለ ሰው በቸልተኛነት
ሰውን የገደለ እንደሆነ በድንጋጌው የተመለከተውን ቅጣት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡

ስለሆነም በእርግጥም አመልካች እንደሚለው ተጠሪ ቸልተኝነት የነበረው መሆን አለመሆኑን ለመለየት
ተጠሪ በቸልተኝነት ወንጀል ፈጽሟል በማለት በተከሰሰበት በሕጉ ልዩ ክፍል ላይ የተቀመጡትን ሁኔታዎች
ከአድራጊው የግል ሁኔታ፤ በተለይም ዕድሜው፤ ያለው የኑሮ ልምድ፤ የትምሕርት ደረጃው፤ ሥራውን እና
የማሕበራዊ ኑሮ ደረጃው ጋር ሲመዘን በጉዳዩ ሁኔታዎች ሊደረጉ ይገባል ተብሎ በአግባቡ የሚጠበቁበትን
ጥንቃቄዎች ያላደረገ እንደሆነ ነው በሚል በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 59/1(ለ) ላይ ከተቀመጡት መስፈርቶች
ጋር በጥንቃቄ ታይቶ እና ተገናዝቦ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል፡፡

በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ አሽከርካሪነት ሙያው በመሆኑ የሌላውን ሰው ሕይወት እና ደህንነት የመጠበቅ
ግዴታ አለበት፤ ይህንኑ ግዴታውን ለመወጣትም ሙያው የሚፈቅደውን አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ሊያደርግ
ይገባል፡፡ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የሥር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት መኪናው ፍጥነት
አልነበረውም፤ ተጠሪ ክላክስ ማድረጉ የደረሰውን አደጋ ለማስቀረት ጥረት ማድረጉን ያስገነዝባል በማለት
ተጠሪን ከተከሰሰበት ክስ በነጻ ያሰናበተ ቢሆንም ተጠሪ በወቅቱ የመኪናውን ፍሬን በመያዝ ወይም መሪ
በማዞር የሟችን ሕይወት ለመታደግ ጥረት ያደረገ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር የለም፡፡
ይህም ተጠሪ ሙያው የሚፈቅድለትን አስፈላጊ የሆነውን ጥረት በማድረግ ሟችን ማትረፍ ሲችል አድራጎቱ
በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል እያወቀ አይደርስም የሚል ግምት ወይም
ባለማመዛዘን ወይም ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም
እየቻለ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ ድርጊቱን የፈጸመ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ይኸው የተጠሪ
አድርጎትም የቅዱስ ጳውሎሰ ሆስፒታል በሰጠው የሕክምና ማስረጃ ላይ እንደተገለጸው በሟች ሁለቱም የራስ
ቅል ውስጥ ደም መፍሰስ እና የራስ ቅሉ የቀኝ ጎን መካከለኛ እና ኋለኛው አጥንት መሰንጠቅ እና መሰበር
እንዲሁም አንጎሉ ውስጥ ደም መፍሰስ አስከትሎ የሟች ሕይወት እንዲያልፍ አድርጓል፡፡

ስለሆነም ተጠሪ በቸልተኝነት ለፈጸመው ድርጊት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 543/2 መሠረት ጥፋተኛ መባል
ሲገባው ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪን ከተከሰሰቡት ክስ በነጻ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በማሰናበት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በሌላ በኩል ተጠሪ
በፈጸመው በቸልተኝነት ሰውን መግደል ወንጀል ጥፋተኛ ሊባል ይገባል ካልን ዘንዳ የስር ከፍተኛው ፍርድ
ቤት ተጠሪ ያቀረበውን የቅጣት ይገደብልኝ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን
ቀጥለን እንመልከት፡፡

በመሠረቱ ቅጣት ሊገደብ የሚችለው ጥፋተኛ የተባለን ሰው ለጥፋቱ መነሻ የሆኑትን ምክንያቶችን
በጠቅላላው በመመልከት በጥፋተኛው ላይ የተወሰነውን ቅጣት ለጊዜው በገደብ እንዲታገድ በማድረግ
የወንጀለኛውን ጠባይ ለማረምና ለማሻሻል እንዲሁም ወደ መደበኛ ማህበራዊ ኑሮው ለመመለስ ጠቃሚ
መሆኑ በታመነ ጊዜ ስለመሆኑ የቅጣት ገደብን አስመልክቶ ከተደነገጉት የወንጀል ሕጉ ድንጋጌዎች
መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህንንም ተፈጻሚ ለማድረግ ፍ/ቤቶች ቅጣትን ለመገደብ የሚያስችሉ የተለያዩ
ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ማስባት እንዳለባቸው፤ እነዚህም ሁኔታዎች ወንጀለኛው ቀድሞ ያልተቀጣ ሆኖ
ጠባዩም አደገኛነት እንደሌለው የሚታመንበት እንደሆነ፤ጥፋቱ በመቀጮ፤ በግዴታ ስራ ወይም ከሶስት አመት
የማይበልጥ ቀላል እስራት የሚያስቀጣ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ ለወደፊት ጠባዩን
ለማረም እንደሚችል እምነት ሊጣልበት የሚችል መሆኑና በዚህ ውሳኔ ብቻ እስከ መጨረሻው ሊሻሻል
የሚችል መሆኑን ‘ያመነበት’ እንደሆነ፤ እንዲሁም ጥፋተኛው አስቀድሞ የተፈረደበት ቢሆንም ባይሆንም
የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈፀሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት
ከማድረግም የሚታገድ መሆኑና ስለጠባዩም መሻሻል አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ የሚበቃ መሆኑ ፍርድ
ቤቱ ያመነበት እንደሆነ ቅጣቱ ከአፈፃፀም ታግዶ እንዲቆይ ሊያዝ የሚችል ስለመሆኑ ከወንጀል ሕግ አንቀጽ
192 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡

በሌላ በኩል በጥፋተኛው ላይ የተወሰነው ቅጣት እንዳይገደብ ሊያደርጉ የሚችሉ በሕጉ የተቀመጡ ሁኔታዊች
ያሉ ሲሆን እነኚህም ሁኔታዎች ጥፋተኛው ከዚህ በፊት የጽኑ እሥራት ቅጣት ወይም ከሦስት ዓመት
የሚበልጥ ቀላል እሥራት ቅጣት ተፈርዶበት እንደሆነ እና እንደገናም በተከሰሰበት ወንጀል ከእነዚህ ቅጣቶች
አንዱ የሚወሰንበት እንደሆነ ወይም ጥፋተኛው ከዚህ ቀደም ያልተቀጣ ሆኖ በተከሰሰበት ወንጀል ከአምስት
አመት የበለጠ የጽኑ እሥራት ቅጣት የሚፈረድበት እንደሆነ ነው በማለት የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 194
ድንጋጌ ላይ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡ በሕጉ ከተመለከቱት ከእነኚህ ሁኔታዎች ውጪ ቅጣት እንዳይገደብ
ለማድረግ የሚያስችሉ ሌሎች ሁኔታዎች ስለመኖራቸው በሕጉ ላይ አልተመለከተም፡፡ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ
196/2 የወንጀሉ ከባድነት / the gravity of the crime /፤ በወንጀል ድርጊት መደጋገም ሊያደርስ
የሚችለውን ጉዳት እና በጥፋተኛው ላይ ሊጣልበት የሚችለው እምነት ከግምት ውስጥ መግባት አለበት
በማለት የተቀመጠውም ቢሆን ፍ/ቤቱ ቅጣቱ እንዲገደብ አቋም ከያዘ በኋላ ቅጣቱ ተገድቦ የሚቆይበትን
የፈተና ጊዜ ለመወሰን / ….. to fix the probation period ….. / እንጂ ቅጣቱን ለመገደብ ሊሟላ ይገባል
ተብሎ የተቀመጠ ቅድመ-ሁኔታ አይደለም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በሌላ በኩል በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197 የተመለከቱት ቅድመ-ሁኔታዎች ፈተና የሚሰጥባቸውን ሁኔታዎች
እንደሆኑ ከድንጋጌው ርዕስ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን እነኚህ ሁኔታዎች መሟላት አለመሟላታቸው
ሊረጋገጥ የሚችለው ፍ/ቤቱ ከተከሳሹ የቀድሞ ታሪክ፤ የጠባዩ እና የዓመሉ አካሄድ በመነሳት ቅጣቱን
መገደብ እንዳለበት ሲያምን እና ጥፋተኛው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197 ላይ የተመለከቱትን ቅድመ-
ሁኔታዎች እንደሚያሟላ ማረጋገጫ እንዲሰጥ በማድረግ እንደሆነ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 192፤196/1 እና
197 ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ፍ/ቤቱ በጥፋተኛው ላይ የሚጣለውን ቅጣት ለጊዜው ማገድ ለወደፊቱ ጥፋቱን ለማረም እንደሚችል ሊያምን
ወይም ላያምን የሚችለው የጥፋተኛውን የቀድሞ ታሪኩ፤ የጠባዩ እና የዓመሉ አካሄድ አስመልክቶ በችሎቱ
የተረጋገጡትን እውነታዎች መነሻ በማድረግ ሲሆን ፍ/ቤቶች በሕግ እና በተገቢ ምክንያት የተደገፈ ውሳኔ
መስጠት ያለባቸው በመሆኑ አመልካች ቅጣቱን ለማስገደብ ያቀረባቸው ምክንያቶች ፍ/ቤቱን የሚያሳምኑ
ናቸው ወይም አይደለም ለማለት ሕግን መሠረት በማድረግ እና አግባብነት ያለውን ምክንያት በመስጠት
ሊሆን ይገባል፡፡

በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ በፈጸመው ድርጊት ምክንያት ተጸጽቶ ለፍትሕ አካል እጁን የሰጠ መሆኑን፤ ሟችን
በተጎዳ ሰዓት ያሳከመ እና ከሟች ቤተሰብ ጋርም የታረቀ መሆኑን፤ የቤተሰብ አስተዳዳሪ እና የቀድሞ
ታሪኩም መልካም መሆኑን፤ በልማት እና በበጎ አድራጎት ስራ የሚሳተፍ እና የጤና ችግርም ያለበት መሆኑ
በስር ይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የልዩነት ሐሳብ ላይ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ይህም ተጠሪ በወንጀል
ሕጉ በተገለጸው አግባብ ቅጣትን ለማስገደብ የሚያስችሉ ቅድመ-ሁኔታዎችን ያሟላ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
በመሆኑም የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ ያስተላለፈውን ቅጣት መገደብ ሲገባው የትራፊክ አደጋ
እንደ ሐገር እያደረሰ ካለው ጉዳት አንጻር ቅጣቱ ሊገደብ አይገባም ሲል የደረሰበት ድምዳሜ ተገቢነት ያለው
ሆኖ አልተገኘም፡፡ ስለሆነም የቅጣት ገደብን አስመልክቶ በሕጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ
በማስገባት ይህ ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ተጠሪ ያፈጸመው ቀሪ የእስራት ቅጣት በሁለት ዓመት የጊዜ
ገደብ ሊገደብለት ይገባል በማለት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 197256 ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም


በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/2/ለ/2 መሠረት ተሽሯል፡፡
2. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 221450 ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው የጥፋተኝነት
ውሳኔ እና ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ጸንቷል፡፡
3. ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት ተጠሪ በስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት በተሰጠው
የቅጣት ውሳኔ መሠረት ያልፈጸመው ቀሪ ቅጣት በሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ ሊገደብለት ይገባል
በማለት ወስነናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ትዕዛዝ
- ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 197 መሠረት የብር 3000 / ሶስት ሺህ ብር / መተማመኛ ዋስትና
እንዲያስይዝ ታዟል፡፡
- የሚመለከተው ማረሚያ ቤት ተጠሪን እንዲረከብ እና ተጠሪ ለመተማመኛ ዋስትና ማስያዙ እና
በስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተላለፈበትን የብር 1000 / አንድ ሺህ / የገንዘብ መቀጮ መክፈሉ
በተረጋገጠ ጊዜ ተጠሪን እንዲለቅ ታዟል፡፡

- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
ሰ/መ/ቁ፡-205362

ቀን፡- 30/02/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ወ/ሮ ዓለሜ ቦጋለ - ጠበቃ አቶ አለማየሁ ሻረው

ተጠሪዎች፡ 1ኛ. አቶ ታዬ(ብስራት) ቦጋለ

2ኛ. አቶ ሰለሞን ቦጋለ

3ኛ. ወ/ሮ ብርሃኔ ቦጋለ

4ኛ. ወ/ሮ ወሰኔ(ማህደር) ቦጋለ የቀረበ የለም

5ኛ. ካሳሁን ቦጋለ

6ኛ. ወ/ሪት እታገኝ ቦጋለ

7ኛ. ህፃን ማክቤል መሰረት

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ በሁከት ይወገድልኝ ክስ መነሻነት የተጀመረ ክርክርን የሚመለከት
ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/08853 ላይ ታህሳስ 16/2013 ዓ.ም በዋለው
ችሎት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት የሰጠውን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን አመልካች በአሁን ከ1ኛ እስከ 4ኛ በተጠቀሱት ተጠሪዎች ላይ በቤንች ሸካ
ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ የክሱም ጭብጥ ከወላጅ አባቴ በተደረገልኝ እና በዞኑ
ፍትህ መምሪያ በተመዘገበ የስጦታ ውል በተላለፈልኝ ንብረት ላይ ሁከት የፈጠሩብኝ በመሆኑ ሁከቱ
ተወግዶ ንብረቱን ለቀው ሊያስረክቡኝ ይገባል የሚል ነው፡፡

በዚሁ ክስ ላይ መልስ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉ ተጠሪዎችም መልስ እና


ከመልሳቸው ጋርም የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል፡፡ የመልሳቸው ይዘት ሁከት ተፈጠረበት
የተባለው ንብረት የግራ ቀኛችን ወላጅ አባት የውርስ ሀብት እንጂ የአመልካችዋ ባለመሆኑ በንብረቱ
ላይ የፈጠርነው ሁከት የለም፤ አመልካች ተደረገልኝ የምትለውንም የስጠታ ውል አናውቅም፤ የስጦታ
ውሉ ተደረገ በተባለበት ጊዜም ወላጅ አባታችን በተስተካከለ የአእምሮ ሁኔታ ላይ ያልነበሩ በመሆኑ
ውሉ ፈራሽ ነው የሚል ነው፡፡

የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ይዘት ደግሞ በዞኑ ፍትህ መምሪያ ፀድቋል የተባለው የስጦታ ውል ከአመልካች
ውጭ ያሉትን ስድስት የሟች ወደታች የሚቆጠሩ ወራሾችን ከውርስ የሚነቅል በመሆኑ እና የስጦታ
ውሉም በተደረገበት ጊዜ ስጦታ አድራጊው በትክክለኛ የአእምሮ ሁኔታ ላይ ያልነበሩ በመሆኑ ውሉ
ፈራሽ ነው ሊባል ይገባል የሚል እና የሟች ሌላ የውርስ ሀብት ጠቅሶ በፍርድ ቤት ውሳኔ ለመካፈል
የሚጠይቅ ነው፡፡ ከዚሁ ክስ ጋርም የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን አስመልክቶ ከ5ኛ እስከ 7ኛ ያሉት
ተጠሪዎች በክርክሩ እንዲጨመሩላቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከ5ኛ እስከ 7ኛ ያለት ተጠሪዎች
በጣልቃ ገብነት የክርክሩ አካል ተደርገው ከ1ኛ እስከ 4ኛ ከተጠቀሱት ተጠሪዎች ጋር ተመሳሳይ ይዘት
ያለው መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ ግራ
ቀኙን ጨምሮ የሟች ወራሾች ስምንት ልጆች መሆናቸውን፤ ሁከት ተፈጠረበት ተብሎ የተጠቀሰው
ንብረትም ለአሁን አመልካች በስጦታ የተላለፈ መሆኑን፤ ለአመልካች የተደረገው ስጦታ አጠቃላይ
ካለው የውርስ ሀብት ጋር ሲነፃፀር ቀሪ ወደታች የሚቆጠሩ የሟች ወራሾችን ከውርስ የሚነቅል መሆኑን፤
ሟች ከአመልካች ውጭ ያሉትን ቀሪ ወራሾችን ከውርስ ለመንቀል የጠቀሱት ምክንያት “አልጠየቁኝም፤
አላሳከሙኝም፤ ከባለቤቴ ጋር አለያይተዉኛል” የሚል መሆኑን፤ በተናዛዡ የተጠቀሰው ምክንያት
የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾችን ከውርስ ለመንቀል በቂ ምክንያት እንዳልሆነ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/57836 እና 55648 ላይ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠ መሆኑን ጠቅሶ
የስጦታ ውሉ ፈራሽ ነው፤ ውሉ ፈራሽ ከሆነ ደግሞ ሁከት ተፈጠረበት የተባለው ንብረት የግራ ቀኙ
ያልተከፋፈለ የውርስ ሀብት በመሆኑ ሁከት ተፈጥሮበታል ሊባል አይቻልም፤ ግራ ቀኙ ሊከፋፈሉት
የሚገባ ሌላ የውርስ ሀብት ስለመኖሩ አልተረጋገጠም በማለት የሁከት ክሱን ውድቅ አድርጎ ግራ ቀኙ
ንብረቱን እኩል እንዲካፈሉ ወስኗል፡፡ አመልካች ይህንኑ ውሳኔን በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች መጋቢት 28/2013 ዓ.ም
በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያሉትን መሰረታዊ የህግ ስህተት
ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ
አመልካች ያቀረቡት የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ ውድቅ የተደረገበት፣ በስጦታ የተሰጣቸው
ንብረቶችም ከውርስ የነቀለ ነው በሚል የስጦታ ውል እንዲፈርስ የተወሰነበት አግባብነትና የሰ/መ/ቁ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

57836 እና 55648 ለጉዳዩ ያለው ተፈፃሚነት ለዚህ ሰበር ችሎት ቀርቦ እንዲመረመር በመታዘዙ ግራ
ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም በሰበር አጣሪው
ችሎት ሊጣራ ይገበዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው
የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል፡፡

እንደተመረመረውም አመልካች ክስ ያቀረቡት በስጦታ በተላለፈልኝ የግል ንብረቴ ላይ ሁከት ተፈጥሯ


በሚል ነው፡፡ በዚሁ ጉዳይ ተከሳሽ የነበሩት አካልት ደግሞ ንብረቱ ላይ የተደረገ ስጦታ አለመኖሩ እና
ንብረቱም የወራሾች የጋራ ሀብት መሆኑን ገልፀው የተፈጠረ ሁከት የለም ብለዋል፡፡ ከዚሁ ጋርም
በንብረቱ ላይ ተደርጓል የተባለው የስጦታ ውል ህጋዊ አይደለም የሚሉበትን ምክንያት ጠቅሰው
እንዲሻርላቸው የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ክርክር መነሻነት ጉዳዩን በመጀመሪያ የዳኝነት ስልጣኑ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ክስ
በቀረበበት ንብረት ላይ የተፈጠረ ሁከት አለ ወይስ የለም? ሁከት ተፈጠረበት የተባለው ንብረትስ
የአመልካች ነው ወይስ የግራ ቀኙ የውርስ ሃብት ነው? በንብረቱ ላይ ተደረገ የተባለው የስጦታ ውል
ሊፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? ግራ ቀኙ ሊካፈሉት የሚገባ ሌላ የውርስ ሀብት አለ ወይስ የለም?
የሚሉትን ጭብጦች መስርቶ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን መርምሯል፡፡ በውጤቱም ለክሱ
ምክንያት በሆነው ንብረት ላይ ተደርጓል የተባለው የስጦታ ውል ከተቀረው የሟች የውርስ ሀብት ጋር
ሲነፃፀር ሌሎች ወራሾችን ከውርስ የሚነቅል መሆኑን፤ በዚህ መልኩ ወደታች የሚቆጠሩ ወራሾችን
ከውርስ ለመንቀል በስጦታ አድራጊ የተጠቀሰው ምክንያትም ከህግ አንፃር ሲመረመር በቂ የሚባል
አይደለም ተብሎ ውድቅ ተደርጎ ንብረቱ የግራ ቀኙ የጋራ የውርስ ሀብት ነው ተብሏል፡፡ በዚሁ
መነሻነትም ሁከት ተፈጠረ የተባለው የጋራ በሆነ የውርስ ሀብት ላይ ነው በሚል የአመልካች የሁከት
ይወገድልኝ ክስ ውድቅ ተደርጎ ግራ ቀኙ ንብረቱን በጋራ እንዲካፈሉ ተወስኗል፡፡

እንግዲህ ከስር ፍርድ ቤት የፍርድ ትችት በግልፅ መረዳት እንደሚቻለው የአመልካች የሁከት
ይወገድልኝ ክስ ውድቅ የተደረገው ክስ የቀረበበት ንብረት የግል ይዞታቸው ሳይሆን የግራ ቀኙ የውርስ
ሀብት ነው በሚል መነሻነት ነው፡፡ ይህ ሊባል የተቻለው ደግሞ በንብረቱ ላይ ተደርጓል የተባለው
የስጦታ ውል ውድቅ ተደርጎ ነው፡፡ የስጦታ ውሉ ውድቅ የተደረገውም ከኑዛዜ አድራጊው ቀሪ ሀብት
ጋር ሲነፃር በስጦታ የተላለፈው ንብረት ሌሎች ተወላጆችን ከውርስ የሚነቅል መሆኑ ተረጋግጧል
በሚል ነው፡፡

በእርግጥ አንድ አውራሽ/ተናዛዥ/ በውርስ ሀብት ላይ ባደረገው የኑዛዜ ስጦታ ሌላኛው ወራሽ በውርስ
ሊደርሰው ከሚገባው ድርሻ ከሩብ በላይ ጉዳት እንዲደርስበት ካደረገ በውጤት ደረጃ ስጦታ
ያለተደረገለትን ሌላኛውን ወራሽ ከውርስ መንቀል መሆኑን፤ ወደታች የሚቆጠር ተወላጅን ከውርስ
ለመንቀል ተናዛዡ የሰጠው ምክንያት በቂ መሆን ያለመሆኑ በዳኞች ሊመረመር የሚችል መሆኑን፤
በዚሁ መሰረት “ታምሜ አልራዳኝም፣ አላስታመመኝም ወይም አልጠየቀኝም” በሚል በተናዛዡ
የሚጠቀስ ምክንያት ተወላጅን በኑዛዜ ከውርስ ለመንቀል የሚያስችል በቂ ምክንያት እንዳልሆነ
ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 912፣ 915፣ 938፣ 939፣ 1047 እና 1123 ድንጋዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶም በማስቀረቢያ ነጥቡ ውስጥ በተጠቀሱ የመዝገብ ቁጥሮች እና በሌላች
በርካታ መዝገቡት ላይ ይኸው ችሎ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

አሁን በቀረበው ጉዳይ ለክሱ ምክንያት በሆነው ንብረት ላይ በግራ ቀኙ አውራሽ ለአሁን አመልካች
ተደርጓል የተባለው የኑዛዜ ስጦታ ከተቀረው የውርስ ሀብት ጋር ሲነፃፀር ሌሎች ወደታች የሚቆጠሩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተወላጆችን ከውርስ የሚነቅል ስለመሆኑ ማስረጃን ፍሬ ነገርን የመመርመር እና የመመዘን የዳኝነት


ስልጣን በተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል፡፡ ይህ ከተረጋገጠ ለክሱ መነሻ
በሆነው ንብረት ላይ የተደረገው ስጦታ ውድቅ የሚደረግ በመሆኑ ንብረቱ የግራ ቀኙ የጋራ የውርስ
ሀብት ይሆናል፡፡ ንብረቱ የግራ ቀኙ የጋራ የውርስ ሃብት ከሆነ ደግሞ የጋራ ባለሀብቶች አንዱ
በሌላኛው ላይ ንብረቱን በተመለከተ ሁከት ፈጥሯል የሚባል አይደለም፡፡
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት ድምዳሜ ህግን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር
የሚነቀፍበት መሰረታ የህግ ስህተት ባለመኖሩ የአመልካች መከራከሪያ ውድቅ ተደርጎ ተከታዩ ውሳኔ
ተሰጥቷል፡፡
ውሳኔ

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ


ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/08853 ላይ ታህሳስ 16/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር
ፍርድ ቤት ውሳኔን በማፅናት የሰጠውን የመጨረሻ ውሰኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 348(1)
መሰረት ፀንቷል፡፡

ትዕዛዝ

1. የዚህን ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡


2. በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል፡፡ ይፃፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-205889

ቀን፡-29/03/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካቾች ፡- 1ኛ. አቶ ሰይድ እንድሪስ አልቀረቡም

2ኛ. አቶ መሀመድ እንድሪስ

ተጠሪ ፡- የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት- አልቀረበም

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
ጉዳዩ የውርስ ሀብት ነዉ የተባለዉን የመሬት ይዞታ አስለቅቆ ለመረከብ በቀረበ ክስ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በአማራ
ክልል በሰሜን ሸዋ ሮቢት ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ሟች አባታችን
እንድሪስ አደም ከባለቤቱ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አሊያ አህመድ ጋር በባልና ሚስት በነበሩበት ጊዜ ከ1966
ዓ/ም ጀምሮ ይዘዉ በኋላም በ1989 ዓ/ም በነበረው የመሬት ሽግሽግ በሕጋዊ መንገድ ተደልድሎ የተሰጣቸዉ
እና ከ1978 ዓ/ም ጀምሮ ግብር የሚገብሩበት በሸዋ ሮቢት ከተማ 05 ቀበሌ ውስጥ አዋሳኞቻቸዉ በክሱ
የተጠቀሰ ልዩ ቦታዉ እስላም ቀብር ተብሎ በሚታወቅበት አካባቢ 2 ጥማድ መሬት፣ልዩ ቦታዉ ንብ እርባታ
ተብሎ በሚታወቅበት አካበቢ 1 ጥማድ መሬት እንዲሁም እንስርቱ ዉሃ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እሩብ ጥማድ መሬት 1ኛ ተከሳሽ ለብቻቸዉ ይዘዉ እየተጠቀሙ ሊያካፍሉን ፈቃደኛ ስላልሆኑ ድርሻችንን
እንዲያካፍሉን ይወሰንልን፡፡ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ አለአግባብ ስለያዘብኝ ለቆ እንዲያስረክበን ይወሰንልን
በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

የስር 1ኛ ተከሳሽ ለክሱ በሰጡት መልስ ለአመልካቾች የአባታቸውን ድርሻ ለማካፈል ፈቃደኛ ነኝ በማለት
መልስ ሰጥተዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም በፍሬ ነገር ደረጃ ለክሱ በሰጠዉ
መልስ ለከተማው ነዋሪ በ2008 ዓ/ም መኖሪያ ቤት ለመስራት ካሳ ለ1ኛ ተጠሪ በመክፈል 2 ጥማድ መሬት
ተረክበናል፡፡ስለሆነም ክስ የተመሰረተበት መሬት በሕግ አግባብ ለሕዝብ ጥቅም የተወሰደ በመሆኑ ልንጠየቅ
ስለማይገባ ክሱ ዉድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 17364 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 30/08/2012 ዓ/ም
በሰጠው ውሳኔ 2ኛ ተጠሪ ከ1ኛ ተጠሪ ተገቢዉን ካሳ ከፍሎ በሕግ አግባብ ለህዝብ ጥቅም የወሰደው እና
ለህዝብ ጥቅም የዋለ መሆኑ ስለተረጋገጠ ከ2ኛ ተጠሪ አመልካቾች የሚጠይቁት መብት የለም በማለት 2ኛ
ተጠሪ ላይ የቀረበዉን ክስ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡ በሌላ በኩል የስር 1ኛ ተከሳሽ ከያዙት መሬት ላይ
የአመልካቾችን አባት ድርሻ ለአመልካቾች ይልቀቁ ሲል ወስኗል፡፡ አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት
ይግባኝ ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ በመ/ቁ 0133438 ላይ በቀን
03/03/2013 ዓ/ም በሰጠው ትዕዛዝ ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞባቸዋል፡፡ በመቀጠል
አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸዉን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም ችሎቱ በመ/ቁጥር 03-12059 ላይ
በቀን 14/05/2013 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ አቤቱታቸዉን ሰርዞባቸዋል፡፡

አመልካቾች በቀን 07/08/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ ዉሳኔ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡-

አከራካሪው የእርሻ መሬት የአመልካች ወላጅ አባት እና የባለቤቱ የ1ኛ ተጠሪ እንደሆነ የሥር ወረዳ ፍርድ
ቤት አረጋግጧል፡፡ይህንን ካረጋገጠ በኋላ ከአመልካቾች እጅ ላይ ቢሆንም እንኳን መሬቱን ይወስድ ነበር ሲል
የሠጠዉ ዉሳኔ የአንድ አርሶ አደር ይዞታ መሬት ለህዝብ ጥቅም ተብሎ የሚወሰድበትን በአዋጅ ቁጥር
252/2009 እና ከመመሪያ ቁጥር 7/2010 ስር የተደነገገዉን የሕግ አግባብነት ያላገናዘበ ነዉ፡፡ 2ኛ ተጠሪ
የያዘውን የአመልካቾችን የውርስ የእርሻ ይዞታ ለከተማ ቦታ ለመኖሪያ ቤት መስሪያ አገልግሎት እንዲውል
ሲወስን ይዞታው ከማንኛውም የይገባኛል ጥያቄ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለበትና ትክክለኛዉን ባለይዞታ
ከመለየት አንጻር ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት በወቅቱ የነበረው የካሳ አወሳሰን መመሪያ ቁጥር
7/2012 በግልፅ ደንግጓል፡፡በመሆኑም ይዞታዉ የአመልካቾች የዉርስ ድርሻ ጭምር ያለበት ሆኖ እያለ የገጠር
መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጁን በመጣስ ከእዉቅናችን ዉጭ መሬቱን ለህዝብ ጥቅም በማለት
መዉሰዱ ሕግን የሚቃረን ሆኖ እያለ ይስር ፍርድ ቤቶች 2ኛ ተጠሪ መሬቱን ሊለቅ አይገባም በማለት
መወሰናቸዉ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ይታረመልን በማለት አቤቱታቸዉን
አቅርበዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ አመልካቾች የሟች አባታቸውን ድርሻ መሬት የካሳ ክፍያ
አይገባቸውም ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ ተጠሪዎች ባሉበት እንዲመረመር ትእዛዝ በመስጠቱት ተጠሪ በቀን
27/01/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልሱን ያቀረበ ሲሆን ይዘቱ በአጭሩ፡-

ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ የእርሻ መሬት ባለይዞታ ማን እንደሆነ ለመለየት ተገቢዉ ማጣራት ሲደረግ በወቅቱ
ተመዝግቦ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ወጥቶለት የነረዉ 1ኛ ተከሳሽ ስም ስለነበር 1ኛ ተከሳሽ የመሬቱ ብቸኛ
ባለይዞታ ስለነበሩ መሬቱ ለሕዝብ ጥቅም ተፈልጎ ለመዉሰድ ሲወሰን ለባለይዞታዋ በሕጉ አግባብ ተገቢዉ ካሳ
ተከፍሏቸዋል፡፡የስር 1ኛ ተከሳሽም የመሬቱ ብቸኛ ባለይዞታ መሆናቸዉን አረጋግጠዉ ካሳ
ተቀብለዋል፡፡አመልካቾች የስር 1ኛ ተከሳሽ ከተቀበሉት ካሳ ላይ ድርሻቸዉን ጠይቀዉ ሊወስዱ ከሚችሉ
በስተቀር ተጠሪ ለሕዝብ ጥቅም ያዋለዉን መሬት እንዲለቅ የሚጠይቁበት የሕግ አግባብ የለም፡፡ ስለሆነም
የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾች በተጠሪ ላይ ያቀረቡትን ክስ ዉድቅ በማድረግ በመወሰናቸዉ የተፈጸመ
ስህተት ስለሌለ አቤቱታቸዉ ዉድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡ አመልካቾችም በቀን 09/02/2014
ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በላይ በአጭሩ የተመለከተዉ የግራ ቀኑን ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት
የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘዉን ማስቀረቢያ ጭብጥ በማሻሻል ተጠሪ ለክሱ መነሻ
የሆነዉን መሬት ሊለቅ አይገባም ተብሎ በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን
አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነዉም አመልካቾች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተቱ በክሱ ላይ የተመለከተዉን ከወላጅ አባታቸዉ


በዉርስ የሚተላለፍላቸዉ ድርሻ ያለበትን የእርሻ መሬት ተጠሪ አለአግባብ እንደያዘባቸዉ በመግለጽ
እንዲለቅላቸዉ እንዲወሰን ዳኝነት በመጠየቅ ነዉ፡፡ከዚህ ዉጭ ተጠሪ አከራካሪዉን መሬት ለሕዝብ ጥቅም
ብሎ ከመዉሰዱ በፊት በሕግ አግባብ የሚገባንን ካሳ ስላልከፈልን እንዲከፍለን ይወሰንልን በማለት በግልጽ
የጠየቁት ዳኝነት የለም፡፡ ምንም እንኳን የወረዳዉ ፍርድ ቤት ተጠሪ ለሕዝብ ጥቅም በሚል የወሰደዉ
አከራካሪዉ መሬት የአመልካቾች አዉራሽ ድርሻ ጭምር ያለበት እንደሆነ ወይም የአመልካቾች አባትና የስር
1ኛ ተጠሪ በጋራ ባለይዞታ የሆኑበት መሬት እንደሆነ ማረጋገጡን በዉሳኔዉ ላይ ቢገልጽም ተጠሪ መሬቱን
ለሕዝብ ጥቅም ለማዋል ፈልጎ ከስር 1ኛ ተጠሪ በተረከበበት ጊዜ መሬቱ በስር 1ኛ ተከሳሽ ስም በይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር ተመዝግቦ የሚገኝ መሬት እንደሆነ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነዉ፡፡እንዲሁም ተጠሪ መሬቱን
ከማስለቀቁ በፊት በሕግ አግባብ ተገቢዉን ካሳ ለስር 1ኛ ተጠሪ እንደከፈለም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር
ነዉ፡፡ተጠሪ አንድን መሬት ለሕዝብ ጥቅም ብሎ ሲያስለቅቅ እንዲፈጽም የሚጠበቅበት መሬቱ በማን ስም
ተመዝግቦ እንደሚገኝ በማረጋገጥ መሬቱን ለሕዝብ ጥቅም ከማዋሉ በፊት በሕግ አግባብ ለባለይዞታዉ
ተገቢዉን ካሳ መክፈል ነዉ፡፡ ተጠሪ በዚህ አግባብ መፈጸሙ ከተረጋገጠ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረጉንና የሕግ
ግዴታዉን እንደተወጣ ስለሚያስቆጥር ለሕዝብ ጥቅም ለማዋል የተረከበዉን መሬት የሚለቅበት ምክንያት
አይኖርም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በያዝነዉ ጉዳይ ተጠሪ መሬቱን ለሕዝብ ጥቅም ብሎ ሲያስለቅቅ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መሬት በስር 2ኛ
ተጠሪ ሥም በይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን አረጋግጧል፡፡አመልካቾችም ይህንን
አይክዱም፡፡እንዲሁም ተጠሪ ለስር 1ኛ ተከሳሽ በሕግ አግባብ ካሳ መክፈሉም የተረጋገጠ ፍሬ ነገር
ነዉ፡፡ተጠሪ ይህንን ካደረገ በመሬቱ ላይ ሌላ ባለድርሻ አለበት ወይስ የለበትም የሚለዉን ከቀረበለት የይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር ዉጭ በመዉጣት እንዲያረጋግጥ የሕግ ግዴታ አልተጣለበትም፡፡አመልካቾች የስር 1ኛ
ተከሳሽ ካሳ ለብቻቸዉ መቀበላቸዉ ተገቢ አይደለም የሚሉ ከሆነ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ድርሻቸዉን ሊጠይቁ
ከሚችሉ በስተቀር ተጠሪ መሬቱን ለሕዝብ ጥቅም ለማዋል የተረከበዉ በሕግ አግባብ በመሆኑ ይሄዉ
ተረጋግጦ አመልካቾች መሬቱን ለማስለቀቅ ያቀረቡት ክስ ዉድቅ ተደርጎ በክልሉ ፍርድ ቤቶች በመወሰኑ
በዚህ ችሎት ደረጃ ሊታረም የሚችል የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም፡፡ በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. የሸዋ ሮቢት ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 17364 ላይ በቀን 30/08/2012 ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ፣
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 0133438 ላይ በቀን 03/03/2013 ዓ/ም የሰጠዉ
ትእዛዝ እና የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 03-12059 ላይ በቀን
14/05/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ፀንተዋል፡፡

2. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ፡፡ ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ. 206060
ሕዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ወ/ሮ ፍቅርተ አያሌው በየነ

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ስንታየሁ ኃይሌ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነው፡፡ በመሆኑ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፋ ባቀረበችው የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል የመጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 148570 ሕዳር 21 ቀን 2013 ለፍርድ ማስፈጸሚያነት
የሚውለው ቤት የአመልካች ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በማለት አመልካች በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 418 መሰረት
ያቀረበችውን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ
ቤት በመ.ቁ. 267515 የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቧ ነው፡፡

ጉዳዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡
በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች የአፈጻጸም መቃወም አመልካች፤ የአሁን ተጠሪ
የፍርድ ባለመብት ፤ በዚህ የሰበር ክርክር ተካፋይ ያልሆኑት አቶ ዮሐንስ ሲሳይ ደግሞ የፍርድ ባለእዳ
በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የመቃወም አቤቱታ ይዘት በአጭሩ፡- በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ
ለተጠሪ ላልተከፈለ የብድር ገንዘብ ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺ/ ማስፈጸሚያ እንዲውል የተጠቀሰው ቤት
የአመልካች ነው፤ አመልካች እና ፍርድ ባለእዳ በ15/08/2011 ዓ.ም በሚመለከተው አካል ዘንድ ቀርበን
የሽያጭ ውል አድርገናል፤ አመልካች በስሜ ለማዘዋወር ሂደቶችን ጨርሼ ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ
ከተማ ስሄድ መስከረም 28 ቀን 2011 ዓ.ም በፍርድ ቤት የዕግድ ትዕዛዝ ያለበት መሆኑን ላውቅ ችያለሁ፤
ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 992/2008 መሰረት የሽያጭ ውሉን ከማዋዋሉ በፊት
እግድ መኖሩን የማጣራት ግዴታውን ሳይወጣ በመቅረቱ አመልካች በእምነት የግዥ ውል ፈጽሜአለሁ፤
አመልካች ቤቱን ስገዛ ቤቱ ላይ ማንኛውም ዓይነት የፍርድ ቤት እግድ የሌለበት መሆኑ ተረጋግጦ ውሉን
መፈጸም ችያለው፤ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 12 መ.ቁ. 616337 መሰረት
ተጠሪ ከሚመለከተው አካል ከመጠየቅ ውጪ የሽያጭ ውሉ ተፈጻሚ ሊሆን እንደሚገባ በመግለጽ ቤቱን
ለመሸጥ የተጀመረው ሀራጅ እንዲቋረጥ ይወሰንልኝ ስትል ዳኝነት መጠየቋን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን ተጠሪ በሰጠችው መልስ በአመልካች ማስረጃ ዝርዝር ተ.ቁ. 2 ላይ ያቀረበችው ቤቱ የፍርድ ባለእዳ
መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፤ ከሽያጭ ውሉ ቀደም ብሎ በመስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም በፍርድ ቤት
የእግድ ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል፤ ተጠሪ የቀዳሚነት መብት አለኝ፤ አመልካች በሚመለከተው አካል ፊት ቀርባ
መዋዋሏ የባለቤትነት መብት አይሰጣትም፤ ስመ ሀብቱ ወደ አመልካች ባልዞረበት፣ መብት እና ጥቅም
ባልተረጋገጠበት እና ንብረቱን ባልተረከበችበት መጠየቅ አትችልም፤ አመልካች እና የፍርድ ባለእዳ
ተመሳጥረው ያቀረቡት ክስ ነው፤ አመልካች የጠቀሰችው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
ቅጽ 12 መ.ቁ. 61637 የተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለጉዳዩ አግባብነት የሌለው መሆኑን በመግለጽ
የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯለች፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የአመልካች የሰው ምስክሮች ለጉዳዩ አግባብነት
የለውም፤ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲም ግዴታ እግድ ስለመኖር አለመኖሩ አስቀድሞ
የማረጋገጥ ግዴታ ቢኖርበትም አመልካች በራሷ እግድ ስለመኖር አለመኖሩ አግባብነት ካለው አካል ሳታጣራ
ከቅን ልቦና ውጪ የፍርድ ባለእዳ የክርክሩ ቤት ከፍርድ ባለመብት ጋር በነበረ ክርክር ታግዶ ፍርድ
ከተሰጠም በኋላ በአፈጻጸም ችሎት የእግድ ትዕዛዝ ተሰጥቶበት በሐራጅ እንዲሸጥ ትዕዛዝ እንደተሰጠበት
እያወቁ ለፍርድ ማስፈጸሚያነት እንዳይውል የሽያጭ ውል ያደረጉ በመሆናቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 12 መ.ቁ. 61637 ለዚህ ጉዳይ አግባብነት የለውም፤ ቤቱ ከእዳና እገዳ ነፃ
ስላለመሆኑ በሚመለከተው ተቋም አልተረጋገጠም፤ ለፍርድ ማስፈጸሚያ የሚውለው ንብረት በፍርድ ባለእዳ
ስም መመዝገቡ የፍርድ ባለመበትን መብት የሚያጠናክር ነው፤ ስለሆነም የተጀመረው የሀራጅ ማስታወቂያ
ሊቋረጥ አይገባም በሚል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡ይህንኑ ውሳኔ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት አጽንቶታል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች ይህን ትዕዛዝ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን ይዘቱም፡- ለፍርዱ ማፈጻሚያነት
የሚውለው ንብረት በ15/08/2011 ዓ.ም በሽያጭ ውል የተላለፈልኝ በመሆኑ ቤቱ የአመልካች ነው፤ የሰነዶች
ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በቤቱ ላይ እግድ አለመኖሩን አረጋግጦ አመልካች የሽያጭ ውል
ፈጽሜአለሁ፤ አመልካች እግድ መኖሩን ያወኩት ውሉን ከፈጸመች በኋላ በስሜ ለማዞር ሂደቶችን ጨርሼ
ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስሄድ ነው፤ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት ቅጽ 12 መ.ቁ. 61637 መሰረት የሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ግዴታውን ባለመወጣቱ
የተጠሪ መብት ተጎድቶ ከሆነ ኤጀንሲውን ከመጠየቅ ውጪ የሽያጭ ውሉ ሊፈርስ አይገባም፤ በመሆኑም
በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የአፈጻጸም ውሳኔ እና ትዕዛዝ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪው ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የአሁን አመልካች በአከራካሪው ቤት ላይ
የሽያጭ ውል የፈፀሙት በህጋዊ መንገድ ለማማዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርበው መሆኑ
ባልተስተባባለበት ሁኔታ፤ የስር ፍርድ ቤት በቤቱ ላይ አፈጻጸም ይቀጥል ያለበት አግባብ የፌዴራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 61637 ከተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ አንጻር ለማጣራት ሲባል ጉዳዩ
በዚህ ችሎት እንዲታይ ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የአሁን ተጠሪ የሰጠችው መልስ ይዘት በአጭሩ፡- ለፍርድ ማስፈጸሚያነት የተጠቀሰውን ቤት ከሽያጭ ውሉ
በፊት በ22/1/2011 ዓ.ም ታግዶ ይገኛል፤ በአመልካች ንብረት ላይ የወጣ ሀራጅ የለም፤ አመልካች ሀራጅ
ከታዘዘ በኋላ ከፍርድ ባለእዳ ላይ አመልካች ቤቱን መግዛቷ ተረጋግጧል፤ ንብረቱ በፍርድ ባለእዳ ስም
የተመዘገበ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ቤቱ በአመልካች ስም ያልዞረ እና በእጇ የማይገኝ ያልተረከበችው ነው፤
ከእዳና እገዳ ነፃ የሚል ሰነድ አላቀረበችም፤ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 153059 ላይ
አመልካች የፍርድ ባለእዳ ቤቱን እንዲያስረክባት ባቀረበችው ክስ ፍርድ ቤቱ አመልካች የገዛችው ቤት የታገደ
ስለመሆኑ አረጋግጦ ውሉ ሊፈጸም አይችልም በማለት የፍርድ ባለእዳ ገንዘቡን ለአመልካች ሊመልስ ይገባል
የሚል ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ አመልካች ሊፈጸምላቸው የሚችል ውል ካለመኖሩም በተጨማሪ አመልካች
በሰበር አቤቱታዋ የጠቀሰችው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 12 መ.ቁ. 61637
አስገዳጅ የህግ ትርጉም ለግራ ቀኛችን ጉዳይ አግባብነት የለውም፤ በመሆኑም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው
የአፈጻጸም ትዕዛዝ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ
ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር
አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምሮታል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደመረመርነውም በስር ፍ/ቤት በተከፈተ የአፈፃፀም መዝገብ ላይ የአሁን አመልካች ለሀራጅ ጨረታ
የወጣው ቤት ላይ መብት ያለኝ በመሆኑ ሃራጁ እንዲቆም በሚል አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን፣ ተጠሪ
በበኩላቸው ንብረቱ ላይ ከፍርድ ባለዕዳ ጋር በነበረን ክርክር ምክንያት የፍርድ ቤት እግድ አሰጥቼ
ተወስኖልኝ ለፍርድ ማስፈፀሚያ እንዲውል ትዕዛዝ የተሰጠበት ንብረት በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ
ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ውድቅ ይሁንልኝ በማለት የተከራከሩ ሲሆን በግራ ቀኙ መካከል
የሚከያከራክረው ንብረት በፍርድ ባለዕዳ ስም የሚገኝ እና ለፍርድ ማስፈፀሚያ በሚል አፈፃፀም ተከፍቶበት
ሀራጅ የወጣበት መሆኑን፣ እንዲሁም የፍርድ ቤት እግድ በማህደሩ ላይ ተያይዞ የሚገኝ መሆኑ በፍሬ ነገር
ደረጃ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል፡፡

በአንድ ንብረት ላይ ንብረቱ በማንኛውም መልኩ ወደ ሌላ ሰው እንዳይተላለፍ የእግድ ትዕዛዝ በፍርድ ቤት


የሚሰጠው በክርክር ሂደት ረቺ የሚሆነው ወገን ለፍርድ አፈፃፀም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲያስችለው
ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 154 እና ተከታታይ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚህ አግባብ በፍርድ ቤት
የሚሰጠው የዕግድ ትዕዛዝም በየትኛውም አካል ሊከበር ይገባል፡፡ በሌላ በኩል ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት
የተሰጠ ፍርድ ሊፈፀም የሚችለው በፍርድ ባለዕዳውና በሕግ አግባብ እንዳይያዙ ከሚጠቀሱት ንብረቶች
ውጪ ባሉት ንብረቶች/መብቶች ላይ ስለመሆኑ በቁጥር 378 እና ተከታዩቹ የፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ድንጋጌዎች
የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው በሕግ አግባብ ለሌላ ሰው ሊያስተላልፍ የሚችለው መብትም በህግ
አግባብ ገደብ ያልተደረገበትንና ያለውን ንብረት ወይም መብት ስለመሆኑ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም፡፡

በአጣሪ ችሎቱ የተጠቀሰው አስቀድሞ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ተሰጥቶ የነበረው የህግ ትርጉም በፍርድ ቤት
መነሳቱ ያልተረጋገጠ፤ ነገርግን እግድ ነገር ግን እግድ የተነሳ መሆኑን የሚያሳይ እና ከፍርድ ቤቱ የወጣ
መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ በቤቱ ማህደር ተያይዞ በመገኘቱ መሆኑን ከፍርዱ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን
አሁን በተያዘው ጉዳይ ግን በፍርድ ቤት በሚያከራክረው ንብረት ላይ እግድ መኖሩ በቤቱ ማህደር ላይ
ተያይዞ ያለ በመሆኑ አስቀድሞ ከተሰጠው የህግ ትርጉም ጋር የሚገናኝ እና ተመሳሳይነት ያለው ባለመሆኑ
ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ሆኖ አላገኘነው፡፡ ይልቁንም አመልካች ንብረቱን ልረከብ ብለው በሌላ መዝገብ
አቅርበውት በነበረው ክርክርም ንብረቱን አስመልክቶ በሌላ መዝገብ በሚደረግ ክርክር የእግድ ትዕዛዝ
ተሰጥቶበታል በማለት ክርክራቸው ውድቅ ተደርጓል፡፡
በሌላ በኩል የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ጽ/ኔት ከፍርድ ቤት የተሰጠ የዕግድ ትዕዛዝ እያለ በተዋዋይ
ወገኖች የተፈጸመውን የሽያጭ ውል ከመነሻውም ቢሆን ውጤት አልባ የሆነውን ውል የመዘገበ በመሆኑ
ውልን መሠረት በማድረግ የሚጠይቅ መብት ተፈጸሚ ሊሆን አይችልም፡፡
ሲጠቃለል አመልካች አከራካሪውን ቤት የገዙት በፍርድ ቤት አስቀድሞ የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ያለበት
መሆኑን እያወቁ ወይም ማረጋገጥ ሲገባቸው ሳያረጋግጡ በሌላ ዕዳ ምክንያት ፍርድ አርፎበት ሐራጅ
እንዲወጣ ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ በቀን 15/8/2ዐ11 ዓ.ም. በመሆኑ እና እስካሁንም ድረስ ንብረቱ በፍርድ
ባለዕዳው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ በመሆኑ በስማቸው ባላዛወሩት ንብረት ላይ የተጀመረው አፈፃፀም እንዲቆም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም፡፡ ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች ይህን መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሳኔ
በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የሚተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንበትም፡፡ በዚህም ምክንያት
ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ 14857ዐ ህዳር 21 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 267515
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ፀንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. የካቲት 13 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. በመዝገቡ የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፤ ይጻፍ
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፤-206283

ቀን፤- 01/02/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ አቶ ጌታቸው ሀይሉ- ቀረቡ

ተጠሪ ፡ የኢትዮጵያ የባህር ትራንፖርትና ሎጅስትክስ አገልግሎት ድርጅት- ነ/ፈጂ


ቤተልሄም ግርማ ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የዲስፕሊን ዉሳኔ በመቃወም የቀረበ ክስ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ
ነዉ፡፡የክሱ ይዘት ባጭሩ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከታህሳስ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በከባድ
መኪና ሹፌር የስራ መደብ ተቀጥሬ በማገልገል ላይ ሳለሁ ነሐሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ከጅቡቲ ወደ
ኢትዮጵያ እያሽከረከርኩ እያለ በጅቡቲ ውስጥ አርታ(ዊያ) በተባለ ቦታ የመልከዓ ምድሩ አቀማመጥ
አስቸጋሪ ቁልቁለትና መታጠፊያ በሆነበት ቦታ ሌላ መኪና ደርቦ የእኔን መስመር ይዞ በመምጣቱ
አደጋውን ለመከላከል በድንገት ፍሬን ሲያዝ አደጋ ያጋጠመ ሲሆን አደጋው ከአቅም በላይ በሆነ
ምክንያት የደረሰ ስለመሆኑ ከጅቡቲ ሪፐብሊክ የመንገድ ደህንነት የሰጠው የምርመራ ሪፖርት
የሚያረጋግጥ ቢሆንም የተጠሪ ድርጅት የዲስፕሊን ኮሚቴ ከባለሙያ ሪፖርት ውጭ እና አመልካች
ሃሳብ ባልሰጠሁበት ሁኔታ በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ ግምት ዋጋ ብር 2,820,778.92 መሆኑን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የዚህን ግምት ዋጋ 3% ሂሳብ ከአመልካች ደመወዙ በየወሩ 1/3ኛ እየተቀነሰ እንዲከፍል ውሳኔ
አስተላልፎ ከሀምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተቆረጠ ይገኛል፣ በመሆኑም በተጠሪ ንብረት ላይ
የደረሰው ጉዳት በመድን ፖሊሲው ሽፋን መሰረት ንብረቱ ተጠግኖ እያለ ያለአግባብ የአደጋ
ተጠያቂና ጥፋተኛ በማድረግ የተወሰነብኝ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲነሳልኝ እና የአደጋው ግምት
3% እንዲከፍል የተወሰነብኝ ከህግ ውጭ ነው ተብሎ የተቆረጠውም እንዲመለስልኝ በማለት ዳኝነት
ጠይቆ ተጠሪ በበኩሉ የፖሊስ ማስረጃ አመልካች አደጋውን ማስቀረት ወይም መቀነስ በሚችልበት
ሁኔታ አደጋው የተከሰተ በመሆኑ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነዉ በማለት ያቀረበው ክርክር
ተቀባይነት እንደሌለዉ፣አመልካች ለዲስፕሊን ክስ የጽሁፍ መልስ፣ ከፖሊስ ሪፖርት ጋር እንዲሁም
ከህብረት ስምምነት ድንጋጌ ጋር በማጣራት የፈፀመው ጥፋት ከስራ የሚያሰናብተው ቢሆንም ያለፈ
መልካም አገልግሎት ግምት ውስጥ በማስገባት አመልካች ላይ የተወሰደው አስተዳደራዊ የቅጣት
እርምጃ ተገቢ እና ህጋዊ በመሆኑ ሊነሳ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ስራቸው ሹፌር እንደመሆኑ ከስራቸው
ጋር በተያያዘ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚገባቸው ነገሮች አንዱ መኪናው የሚያሽከረከሩበትን አግባብ
ከአከባቢው አየር ሁኔታ እና ከመልከዓ ምድሩ ጋር ባገናዘበ መልኩ መሆን ያለበት መሆኑን እና
በጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ በዝግታና በጥንቃቄ ማሽከርከር የሚጠበቅበት ሙያዊ
ግዴታ ነው፣ ስለዚህ በጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ ላይ መነዳት ያለበት በ2ኛ እና በ3ኛ
ማርሽ እንደሆነ በዚህ ማርሽ ከተነዳ ከፊት ለፊት አደጋ ቢመጣበትም የእጅ ፍሬን በመያዝ
መኪናውን አደጋ ሳይደርስ በቀላሉ ማቆም እንደሚችል አመልካችም ተጠሪም ያቀረባቸው ምስክሮች
ያስረዱ ሲሆን አመልካች ከጅቡቲ ፖሊስ የመንገድ ደህንነት የተፃፈው ሪፖርትም ከሳሽ
ሲያሽከረከሩት የነበረው መኪና ወደ ቀኝ መውደቁን ከመግለጽ ባለፈ አደጋው የተከሰተበትን
ምክንያት የሚያመላክት ባለመሆኑ እና አመልካች በቸልተኝነት ጉዳት አለማድረሳቸውን
የሚያስተባብል ያቀረቡት ማስረጃ ባለመኖሩ ተጠሪ ድርጅት ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በአመልካች
ቸልተኝነት ነው በማለት፣ ቅጣቱን በተመለከተ በድርጅቱ ህብረት ስምምነት መሰረት በአመልካች
ጥፋት በድርጅቱ ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከስራ የሚያሰናብት ቢሆንም የቅጣት ማቅለያ
በማድረግ 3% እንዲቀጡ መወሰኑ የሰራተኛውን ጥቅም ያስጠበቀ በመሆኑ ቅጣቱ የተወሰነው
የህብረት ስምምነት አንቀጽ 31 (3) በሚፈቅደው መንገድ በመሆኑ ህጋዊ ነው በማለት ውሳኔ
ሰጥቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበዉን ይግባኝ ፍ/ቤቱም የስር
ፍ/ቤት ውሳኔ የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ግድፈት የለበትም በማለት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 337 መሰረት
ይግባኙን ሰርዞበታል፡፡

አመልካች ይህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ያቀረበዉ አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤
በድርጅቱ ህብረት ስምምነት መሰረት ጥፋቱ ከ250,000ብር በላይ መሆኑ ከስራ ማሰናበት እንጂ
በገንዘብ እንዲቀጣ ማድረጉ የህግ ስህተት ነው፣ ተጠሪ ይህንን ያደረገው ለአመልካች በማሰብ
ሳይሆን አደጋው መድረሱ ካወቀበት ከ06/12/2010 ዓ.ም እርምጀ እስከወሰደበት 28/09/2011 ዓ.ም
ድረስ ከ30 ቀናት በላይ በመሆኑ ነው፣በተጨማሪም የጥገና ወጪው ብር 353,162.81 ሆኖ እያለ
በተሽከርካሪው ላይ ያልደረሰውን ግምት ጨምሮ ገንዘብ ለማስከፈል የወሰነው ቅጣት ህግና የህብረት
ስምምነት ተቃራኒ በመሆኑ የህግ ስህተት ተፈጽሟል፡፡በህብረት ስምምነቱ የተፈቀደውን በመቃረን
በሰዓት 40 ኪ/ሜ ስለማሽከርከረ ማስረጃ ሳይቀርብ ማስረጃ እንደቀረበ ተደርጎ በተሽከርካሪው ላይ
ለደረሰው ጥገና ግምት እያለ እንዳልቀረበ ተደርጎ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
በመሆኑ እንዲታረምልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ
የማስረጃ ምዘና መርህንና ተገቢውን የስራና ሰራተኛ ጥቅም ያገናዘበ መሆን አለመሆኑ ተጠሪ
ባለበት ለማጣራት ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ታዟል፡፡

ተጠሪ ያቀረበው መልስ ባጭሩ የተጠሪ ንብረት የሆነው ከባድ ተሽከርካሪ በአመልካች ቸልተኝነት
በመገልበጡ ምክንያት የደረሰው ጉዳት መጠን ለመጀመሪያ ጊዜ የማስጠገኛ ግምት ከቀረበ በኋላ
ፕርፎርማ ሲሰበሰብ ግን አስቀድሞ በቀረበው የዋጋ ግምት ተሽከርካሪው ለማስጠገን የማይቻል
መሆኑን ተሽከርካሪውን ለማስጠገን በወቅቱ ዋጋ ብር 2,820,778.92 መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን
ይህም በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተጣርቶ ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ በአመልካች በኩል ግምቱ
ከዚህ በታች ስለመሆኑ ያቀረበው ምንም ማስረጃ ባለመኖሩ የአመልካች ቅሬታ ተቀባይነት
የለውም፡፡በስር ፍ/ቤት የግራ ቀኛችን ምስክሮች ሲሰሙ በተጠሪ በኩል የቀረቡ ምስክሮች አመልካች
አደጋው ባደረሱበት ወቅት በሰዓት 40 ኪ/ሜ ፍጥነት ሲያሽከረክሩ የነበሩ ስለመሆኑ አመልካች
ራሳቸው ሞልተው የፈረሙት ወደ ኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተላከ ቅጽ በችሎቱ ቀርቦ
ተረጋግጧል፡፡የቀረቡ ምስክሮችም አደጋው የደረሰበት ቦታ ላይ ፍጥነት በሰዓት ከ30 ኪ/ሜ በታች
በማድረግ በከባድ ማርሽ ተጠቅሞ ቢያሽከረክር ማንኛውም አደጋ ቢፈጠር ያለምንም ችግር
ተሽከርካሪ ማቆም እንደሚቻል እና በፍጥነት ላይ ከሆነ በድንገት ፍሬን ሲያዝ የመንሸራተት ወይም
የመገልበጥ አደጋ ሊደርስ እንዲሚችል እና አደጋው የደረሰው በአመልካች ጥንቃቄ ጉድለትና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቸልተኝነት መሆኑን አስረድቷል፡፡አመልካች አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት


መሆኑን ያስረዳ ነገር የለም፣ ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በሰ/መ/ቁ.111839 ላይ የሰጠው ትርጉም የተከተለ በመሆኑ የህግም ሆነ የፍሬ ነገር ስህተት
የለዉም፡፡የዲስፕሊን የቅጣት እርምጃ በተመለከተ ጥፋቱ ከስራ የሚያሰናብት ቢሆንም ከዚህ በፊት
የነበረው ፀባይ፣ የአግልግሎት ጊዜና የቤተሰብ አስተዳዳሪነት ከግምት በማስገባት ቅጣቱን በመቀነስ
የአደጋዉ ግምት ዋጋ 3% በየወሩ 1/3ኛ እየተቆረጠ እንዲከፍል ማድረጉ የሚነቀፍበት የህግ
ምክንያት የለም ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካች አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ
መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል
ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብ ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ
መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘበንዉ አመልካቹ የዲስፒሊን ዉሳኔዉ በመቃወም
ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ያቀረበዉ የተፈጸመዉ ጥፋት ከባድ ነዉ ከተባለ ከስራ ማናበት እንጂ ይህንን
ያህል ገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገቢ አይደለም በሚል
ዉሳኔዉ በፍርድ ቤት እንዲታረም ነዉ፡፡ተጠሪም በበኩሉ በአመልካች ቸልተኝነት የደረሰዉ ጉዳት
ከባድ በመሆኑና ጥፋቱ ከስራ የሚያሰናብት መሆኑን ነገር ግን አመልካች የሰጠዉ የረጅም ጊዜ
አገልግሎት እና የነበረዉ መልካም ባህርይ ከግምት በማስገባት ከስራ ከማሰናበት በመልስ ያለዉ
ቅጣት እንደተወሰነበት እና ይህም ለአመልካች ጥቅም ተብሎ የተደረገ ስለመሆኑ ተከራክሯል፡፡

በመሠረቱ አንድ ሠራተኛ ለስራው የተሰጡትን መሣሪያዎችና እቃዎች ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ


ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 1156/11 አንቀጽ 13/3/ ስር የተመለከተ ሲሆን በአሠሪው
ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብሎ
ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ ሠራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት
የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 27/1/ሸ/ ድንጋጌ ያሣያል፡፡ሆኖም ከባድ
ቸልተኝነት የሚለውን ቃል መለኪያ በተመለከተ ህጉ በግልጽ አያሣይም፡፡ይሁን እንጂ ቸልተኝነት
የጥንቃቄ ጉድለት እንደመሆኑ መጠን የጥንቃቄ ዓይነትና ደረጃ እንደየድርጊቱና አድራጊው የስራ
ድርሻ አኳያ በመመልከት ምላሽ ማግኘት እንደሚገባ ይህ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 41115 አስገዳጅ
የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡በተያዘዉ ጉዳይ ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ ላይ
በተመጣጣነ ማርሽ አስሮ ባለማሽከርከሩ አደጋው መድረሱ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ
አመልካች ማስተባበያ ማስረጃ ያላቀረበበት ጉዳይ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል፡፡ ፍሬ
ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶችም ጉዳቱ ሊደረስ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የቻለዉ በአመልካች ቸልተኝነት ስለመሆኑ አረጋግጠዋል፡፡በመሆኑም የአመልካች የጥፋት ደረጃ


"ከባድ ቸልተኝነትን" ሊያቋቁም የሚችል መሆን አለመሆኑን ከስራው ባህርይ አንፃር መመልከት እና
የቀረበዉን ማስረጃ በማመዛዘን በቁልልቁለት መንገድ ላይ በከባድ ማረሽ ማሽከርከር እየተገባዉ
በቀላል ማርሽ በሰዓት በ40 ኪ.ሜ ፍጥነት በማሽከርከር ጉዳት እንዲረስ ስለማድረጉ በክርክሩ ሂደት
የተረጋገጠ ፍሬነገር ጉዳይ በመሆኑ ይህንኑ ከመቀበል አልፎ ይህ ሰበር ችሎት የፍሬነገር ጉዳይ
የመመርመር ሃላፊነት የለበትም፡፡በዚህም ምክንያት የድርጅቱ ንብረት ላይ የደረሰዉን ጉዳት
ለማስጠገን ብር 2,820,778.92 የተገመተ ስለመሆኑ ከመድን ድርጅት የቀረበዉን ማስረጃ መሰረት
በማድረግ አመልካች አስተዳደራዊ ዉሳኔ መስጠቱን ከክርክሩ ተገንዝበናል፡፡በሌላ በኩል የጉዳቱን
ለማስተካካል ወይም ለማስጠገን መጀመሪያ የቀረበዉ ግምት ብር 353,162.81 ስለመሆኑ አመልካች
ያቀረበዉ ክርክር በስር ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያላገኘ ቢሆንም በህብረት ስምምነት ከተመለከተዉ
ጣሪያ በላይ በመሆኑ የመጠን ጉዳይ መመርመር አስፈላጊ አይደለም፡፡ስራ ላይ ባለዉ የድርጅቱ
የህብረት ስምምነት አንቀጽ 33/1/ ተራቁጥር 24 ላይ በተደነገገዉ መሰረት የከባድ መኪና አሽከርካሪ
በራሱ ጥፋት በድርጅቱ ንብረት ላይ ከብር 250,000/ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ/ በላይ ጉዳት ማድረሱ
በዲስፕሊን ኮሚቴ ከተረጋገጠ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ የሚሰናበት ስለመሆኑ ግራቀኙ
ያልተካካዱት ከመሆኑም በተጨማሪ በስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ የተገለጸ ጉዳይ ነዉ፡፡ይህ ከሆነ
ደግሞ የአመልካች ጥፋት በቀጥታ ከስራ ለማስናበት የሚያበቃ መሆኑ አከራካሪ
አይደለም፡፡አመልካችም አጥብቆ የሚከራከረዉ ጥፋቱ ለስንበት የሚያበቃ ነዉ ከተባለ ተጠሪ ከስራ
ሊያሰናብተኝ ሲገባዉ በገንዘብ መቅጣቱ ህገ ወጥ ነዉ በማለት ነዉ፡፡
በዚህ ረገድ የዲስፕሊን ኮሜቲ የቅጣት ዉሳኔ መሰረት ያደረገዉ የድርጅቱን የህብረት ስምምነት
አንቀጽ 33.3 ተራቁጥር 33.3.6 ሲሆን በዚህም መሰረት የከባድ መኪና ሾፈር ከብር 100,001 እስከ
200,000 ድረስ ለሚደርስ አደጋ ለመጀመሪያ ጥፋት ሲሆን ሰራተኛዉ የጉዳቱን ግምት ዋጋ 3%
በየወሩ 1/3ኛ ከደመወዙ እንዲከፍል የሚደነግግ መሆኑን መሰረት በማድረግ የአመልካችን የቀደመ
መልካም በህርይና አገልግሎት ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም የድርጊቱን ከባቢያዊ ሁኔታ ከግምት
በማስገባት ቅጣቱ ቀሎ እንዲወሰን የተደረገ ስለመሆኑ መዝገቡ ያሣያል፡፡ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ
ምንም እንኳን አመልካች ያደረሰዉ ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ተጠቅመዉ
ለአነስተኛ ጉዳት ተብሎ በተገመተዉ ወሰን ዉስጥ ቅጣት መወሰኑ ሲታይ በአንድ በኩል
ሰራተኛዉን በስራ ላይ በማቆየት የሥራ ዋስትናዉን ማስከበር በሌላ በኩል ለደረሰዉ ጉዳት ደግሞ
በህብረት ስምምነት የተቀመጠዉን ገንዘብ እንዲከፍል በማድረግ የሁለቱንም ወገን ጥቅም
ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡በዚህ አግባብ ቅጣቱ ቀሎ መወሰኑ ከቅጣት ዓላማ
አንጻር ሲታይ ስህተት ነዉ የሚያሰኝ ባይሆንም የገንዘብ መጠኑ ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ አመልካች

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ ከደመወዙ እንዲቆረጥ የሚያደርግ ዉሳኔ ከመሆኑ አኳያ
ሲታይ ግን በኑሮዉ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚፈጠር መሆኑን መገምት አዳጋች አይሆንም፡፡ከላይ
የተጠቀሰዉ የድርጅቱ የህብረት ስምምነት ድንጋጌ የገንዘብ መጠኑን እስከ ብር 200,000 ድረስ
ሲገድብ ታሳቢ ያደረገዉም የደረሰዉ ጉዳት መጠን ከዚያ በላይ ሲሆን ጥፋቱ ከባድ ስለሚሆን
ሰራተኛዉን ከስራ በማሰናበት ለደረሰዉ ጉዳት ግን በህግ አግባብ መጠየቅ የሚቻልበትን ሁኔታ
መኖሩን ከግምት ያስገባ ነዉ፡፡
ይሁንና የዲስፕሊን ኮሚቴ ዉሳኔ የሁለቱንም ወገን ጥቅም በማመዛን የተወሰነ ነዉ የሚባል ከሆነ
አመልካች ከደመወዙ እየተቀነሰ ሊከፍል የሚገባዉ በህብረት ስምምነት አንቀጽ 33.3.6 መሰረት
እስከ ብር 200,000 ድረስ ያለዉን ጉዳት እንጂ ከተቀመጠዉ ጣሪያ በላይ ሊሆን አይገባም፡፡ከዚህ
በላይ ለሆነዉ ገንዘብ ሊጠየቅ የሚገባዉ ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት የፍትሓብሄር ክስ ቀርቦ ግራ
ቀኙ በሚያቀርቡት ክርክርና በማስረጃ ተጣርቶ ሲወስንበት ብቻ ይሆናል፡፡ጉዳዩ ከዚህ አኳያ ሲታይ
አስተዳደራዊ ዉሳኔዉ አስቀድሞ በህብረት ስምምነት ያልተደነነገዉን ሁኔታ እና በሰራተኛዉ ላይ
ከፍተኛ ጫና በሚፈጥር አግባብ ይልቁንም ተጠሪን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዉሳኔ በመሆኑ የህግ
መሰረት የሌለዉና ፍትሃዊነትም የጎደለዉ ሆኖ አግኝተናል፡፡
በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች የዲስፕሊን ኮሚቴ ዉሳኔ ተገቢነትና ፍትሃዊነት ሲመረምሩ ቅጣቱ
ቀሎ መወሰኑ በመርህ ደረጃ ለሰራተኛዉ ጥቅም ነዉ የሚለዉን መሰረት በማድረግ ዉሳኔዉን
ማጽናታቸዉ ተገቢ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ በህብረት ስምምነት ከተመለከተዉ ጣሪያ ወሰን ማለፍ
አለማለፉን ሳያረጋገጡና ጉዳቱንም ሳያመዛዝኑ ስራ ላይ ያለዉን የህብረት ስምምነታቸዉን ዓላማ
እና ይዘት ያገናዘበ ባለመሆኑ ሊታረም ይገባል ብለናል፡፡በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡
ዉሳኔ
1ኛ/በዚህ ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተላቸው
በመ/ቁ/75575 እና 250187 ላይ የሰጡት ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር 348/1/መሰረት ተሻሽሏል፡፡
2ኛ/የተጠሪ መ/ቤት በአመልካች ላይ ያስተላለፈዉ አስተዳደራዊ ዉሳኔ ተሻሽሎ ተከታዩ ተወስኗል፡፡
ሀ/አመልካች በከባድ ቸልተኝነት በተጠሪ ንብረት ላይ ላደረሰዉ ጉዳት ጥፋተኛ መባሉ ተገቢ ነዉ
ብለናል፡፡
ለ/በአመልካች ጥፋት ምክንያት በተጠሪ ንብረት ላይ ለደረሰዉ ጉዳት ማስጠገኛ የወጣዉን ወጪ ብር
2,820,778.92 ዉስጥ 3% በየወሩ 1/3ኛ ከደመወዙ አመልካች እንዲከፍል በዲስፕሊን ኮሚቴ
የተሰጠዉ ዉሳኔ በድርጅቱ የህብረት ስምምነት አንቀጽ 33.3 ተራቁጥር 33.3.6 መሰረት ተሻሽሎ
ብር 200,000 ድረስ ያለዉን ብቻ 3% በየወሩ 1/3ኛ ከደመወዙ እንዲከፍል በማለት ወስነናል፡፡
ሐ/ለአመልካች የተሰጠዉ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ላይ ስህተት ባለመኖሩ ጸንቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መ/አመልካች ያደረሰዉ ጉዳት መጠን (ግምት) በፊደል ለ ላይ ከተጠቀሰዉ መጠን በላይ ነዉ


የሚል ከሆነ ተጠሪ ስልጣን ባለዉ ፍርድ ቤት ክስ የማቅረብ መብቱን ይህ ዉሳኔ የሚገድብ
አይደለም ብለናል፡፡
3ኛ/በዚሁ ዉሳኔ መሰረት እንዲፈጸም ለሚመለከተዉ ክፍል ይተላለፍ፡፡ይጻፍ፡፡
4ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡
ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፤

ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ሰራተኛዉን ጥፋቱ ከበድ ተብሎ ይደረጋል የሚል ስለሆነ ቅጣቱ
በማቅለል በዚህ መወሰኑ ተገቢ ነዉ የሚል ነዉ፡፡መደረግ እየከፈለ ስራዉን የሚቀጥልበት
ሁኔታ ስለመኖሩ ፋትይሁንና አመልካች
የጉዳት ስለመድረሱ ፡፡ ከክርክሩ ሂዯት መገንዘብ የተቻሇው ተጠሪ በአመሌካች ዴርጅት

በሹፋርነት ተቀጥረው እየሠሩ ባሇበት ወቅት ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ.ም መንገዯኛ በነበረው

ሰው ሊይ ጉዲት አዴርሰዋሌ፣ሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ.ም ዯግሞ የአመሌካች ዴርጅት ሰራተኞችን

ከዯሴ ወዯ መቐላ ሇስራ ይዞ በመሄዴ ሊይ እያሇ መንገደ ጠመዝማዛና የአየሩ ሁኔታም

ዝናብማ ሁኖ እያሇ ከጥንቃቄ ጉዴሇት መኪናውን እንዱወዴቅ በማዴረግ በመኪናው ሊይ

ጉዲት አዴርሷሌ፣በሰራተኞች ሊይም ቀሊሌ የመቁሰሌ አዯጋ አዴርሷሌ ተብል ስንብቱ

የተከናወነ መሆኑንና የስር ፌርዴ ቤቶች ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ.ም ተፇጸመ የተባሇው ጥፊት
በሰሊሳ ቀን የይርጋ ጊዜ መታገደን፣የሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ.ም ጥፊት ግን በወቅቱ ዝናባማ
የአየር ሁኔታ በነበረበትና መንገደ እርጥበታማና ቁሌቁሇታማ በሆነበት አካባቢ የተፇፀመ

ቢሆንም በተጠሪ በኩሌ ቸሌተኝነት ነበር ከሚባሌ በስተቀር በአዋጁ በተመሇከተው አግባብ

ከባዴ ቸሌተኝነት ነበር ሉባሌ የሚችሌ አይዯሇም በሚሌ ምክንያት የበታች ፌርዴ ቤቶች

የወሰኑ መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም የዚህን ችልት ምሊሽ የሚያስፇሌገው አቢይ ነጥብ የተጠሪ

አዴራጎት በከባዴ ቸሌተኝነት ስር ሉወዴቅ ይችሊሌን? የሚሇው ነው፡፡


ተጠሪ ስራቸው ሹፋር ሲሆኑ ከስራቸው በተያያዘ ሁኔታ ጥንቃቄ ማዴረግ ከሚገባቸው ነገሮች
አንደ መኪናውን የሚያሽከረክሩበትን አግባብ ከአከባቢው አየር ሁኔታ እና ከመሌክዓ ምዴሩ
ጋር በአገናዘበ መሌኩ መሆን ያሇበት መሆኑን የሚመሇከት ነው፡፡በመሆኑም በዝናባማ የአየር

ሁኔታና ጠመዝማዛና ቁሌቁሇታማ በሆነ መንገዴ በዝግታና በጥንቃቄ ተሽከርካሪን ማሽከርከር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከአንዴ አሽከርካሪ የሚጠበቅ ሙያዊ ግዳታ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ
መኪናውን ዝናባማ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ
ተጠሪ መኪናውን ሲያሽከረክሩ የነበረበት ሁኔታ ከሊይ የተገሇጸው ነው ከተባሇ ዯግሞ

ትክክሇኛ አእምሮ ባሇው ሰውና በተጠሪ የግሌ ሁኔታ መመዘኛ መሠረት ከባዴ ቸሌተኝነትን

ሉያሣይ የሚችሌ አይዯሇም ሉባሌ የሚችሌበትን አግባብ አሊገኘንም፡፤፡፡ በመሆኑም የበታች

ፌርዴ ቤቶች የተጠሪ ጥፊት ከባዴ ቸሌተኝነት አይዯሇም ማሇታቸው መሰረታዊ የህግ

ስህተት ሁኖ ስሇተገኘ የሚከተሇውን ወስነናሌ፡፡


ው ሣ ኔ
1. በዯሴ ከተማ ወረዲ ፌርዴ ቤት በመ/ቁ.10762 ታህሳስ 06 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ

በዯቡብ ወል መስተዲዯር ዞን ከፌተኛ ፌርዴ ቤት በመ/ቁ.19554 የካቲት 19/ 2007 ዓ.ም፣


በክሌለ ጠቅሊይ ፌርዴ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 03-10681 መጋቢት 18 ቀን
2ዏዏ7 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፌ/ብ/ሥ/ሥ/ሔ/ቁ. 348/1/ መሠረት ተሽሯሌ፡፡
2. አመሌካች

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 206511
ቀን ፡- ሕዳር 27 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ሴኪዩሪኮር ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግል ማሕበር፡- ጠበቃ ተከተል ዲያ ቀረበ

ተጠሪ ፡- 1. አቶ አበራ ተሾመ 14. አቶ ለገሰ በዳኔ

2. አቶ የኔዓለም ታደሰ 15. አቶ በላይ ገሠሠ

3. አቶ አማረ ተመቸ 16. አቶ ዓለማየሁ ገመቹ

4. አቶ ሀዋስ አብዱ 17. ሻምበል ገናናው ደግፌ

5. አቶ ጥበቡ ሺበሺ 18. አቶ ሙሉነህ ገዛኸኝ

6. አቶ ስሜነህ መኮንን 19. አቶ ብሩክ ገዛኸኝ

7. አቶ ተረፈ ቱምሳ 20. አቶ ለማ ቃበታ

8. አቶ ሻምበል በሻውረድ ነጋሽ 21. ፲ አለቃ ቶሎሳ መርጋ

9. ፻ አለቃ ተስፋዬ ደሳለኝ 22. አቶ መስፍን ለገሰ

10. አቶ ጌታቸው ግዛው 23. አቶ መለሰ መርከብ

11. አቶ በለጠ አደፍርስ 24. አቶ ንጋቱ አሸናፊ

12. አቶ አሰግድ ብዙነህ 25. አቶ ቾንቤ ሁሴን

13. አቶ አምደብርሃን ጋሹ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ
ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ከሳሾች ነበሩ፡፡ ተጠሪዎች ሠኔ 12 ቀን
2012 ዓ/ም ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ከአመልካች ጋር የዓለም ምግብ ፕሮግራምን እንድንጠበቅ የጥበቃ
ሥራ ውል ከግንቦት 23 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ እየሰራን እንገኛለን፡፡ የግል አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ
ኤጀንሲን አስመልክቶ በ2012 ዓ/ም በወጣው መመሪያ መሠረት አመልካች ከሚያገኘው ጠቅላላ ክፍያ ውስጥ
ለሠራተኛው የሚከፍለው ደመወዝ ከ80% በታች መሆን እንደሌለበት ተመልክቷል፡፡ አመልካች ለአንድ
ሠራተኛ ከሚያገኘው ብር 4,800.00 ውስጥ ብር 3,840.00 መክፈል ሲገባው ብር 1,574.00 እየከፈለን
በመሆኑ ከመስከረም 01 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ታስቦ ገንዘቡ ይከፈለን፤ እንዲሁም የበዓላት ክፍያ እና
ክፍያው ለዘገየበት ቅጣት ሊከፍለን ይገባል በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ያቀረበው መልስ ክሱ
በስድስት ወር ውስጥ ያልቀረበ ስለሆነ በይርጋ የታገደ ነው፡፡ የበዓላት ቀናት አላሰራንም፡፡ ብር 4,800.00
በሚል የቀረበው የገንዘብ መጠን የሕግ መሰረት የለውም፡፡ ክፍያው ከጥቅማጥቅም ጋር ብር 3,579.19
ሲሆን መደበኛ ደመወዝ ግብርና ጡረታ ተቆርጦ ብር 1,850.00 እንዲሁም የትራንስፖርት ክፍያ ብር
462.00 ለተጠሪዎች እየተከፈላቸው ይገኛል፡፡ መመሪያው የወጣው በታህሳስ 2012 ዓ/ም ሲሆን አንቀጽ
50(2) ላይ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ውል እንድናድስ ጊዜ የሠጠ
ሲሆን በዚህ መካከል የኮሮና ወረሽኝ ስለገባ ከሠራተኛ ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በነበረ ውይይት
የመመሪያው ተፈጻሚነት ለተጨማሪ ሦስት ወር ጊዜ እስከ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ተራዝሟል፡፡
የዘገየ ልፍያ የለም፤ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዳማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ መመሪያው
በሥራ ያሉ ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ውላቸውን በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያድሱ ጊዜ የሠጠ
ሲሆን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለተጨማሪ ሦስት ወር እስከ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ መመሪያው
የሚፈጸምበትን ጊዜ ስለማራዘሙ ከጻፈው ደብዳቤ መረዳት ተችሏል፡፡ አመልካች ከዓለም የምግብ ፕሮግራም
ጋር የገባውን ዋና ውል አመልካች ሆነ WFP(World Food Program) ለፍርድ ቤቱ ሊያቀርቡ አልቻሉም፣
ስለሆነም ውሉ ለአንድ ሠራተኛ የተገባው ክፍያ ብር 4,800.00 ነው የሚለውን ወስደናል፡፡ አመልካች ከሰኔ
22 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በወር ያልከፈለውን ብር 1,793.50 ለእያንዳንዳቸው ተጠሪዎች ይክፈል፤
ውሳኔው ከተሰጠበት ጥር 13 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በወር ብር 3,840.00 ይክፈል፡፡ የበዓላት ቀናት ክፍያና
ክፍያ ለዘገየበት የቀረበውን ዳኝነት ውደቅ አድርጓል፡፡ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን ይግባኝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ባለመቀበል ሠርዟል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ግራቀኙን አከራክሮ መመሪያው
አመልካች ውል የሚያድስበትን ጊዜ የሠጠ ቢሆንም ሥለሠራተኞች ክፍያ አከፋፈል ሥርዓት በዝምታ
የሚያልፈው በመሆኑና ሠራተኞች ሥራ እስከሰሩ ድረስ ክፍያ ሊከፈላቸው ስለሚገባ መመሪያ ከወጣበት
ታህስሳስ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ለተጠሪዎች ሊከፈላቸው የሚገባውን የተጣራ ክፍያ ብር 1,990.00
አመልካች እንዲከፍል፤ መመሪያው ከክፍያው ከ80% በታች መሆን የለበትም የሚለው የተጠሪዎችን
ደመወዝ በመሆኑ የትራንስፖርት አበል ሳይታሰብበት በወር ብር 3,840.00 ደመወዝ እንዲከፍል በማለት
የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም የተዋዋልነው በወር
ብር 4,880.00 ስለመሆኑ የማስረዳት ግዴታ ያለባቸው ተጠሪዎች ሆነው እያለ ማስረጃ ሳያቀርቡ በክሱ
የጠቀሱትን ክፍያ ፍርድ ቤቱ መውሰዱ ተገቢ አይደለም፡፡ ለተጠሪዎች እንዲከፈል የተወሰነው የክፍያ መጠን
ስህተት ያለበት ነው፡፡ የመመሪያው ተፈጻሚነት በድንጋጌው በተመለከተውና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ
በጻፈው ደብዳቤ መሠረት ተራዝሞ እያለ ክፍያው ከ80% በታች መሆን የለበትም የሚለው የመመሪያ
ድንጋጌ መመሪያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተፈጻሚ መደረጉ ተገቢ አይደለም፡፡ አመልካች ይግባኝ አቅርቦ
በመሰረዙ ለሰበር ሰሚ ችሎቱ ያቀረብውን መስቀለኛ ተቃውሞ ፍርድ ቤቱ ሳይመረምር በዝምታ ማለፉ
የክርክር አመራር ግድፈት ያለበት ነው፡፡ ወጭና ኪሣራ አወሳሰኑም ተገቢ አይደለም የሚል ነው፡፡ የሰበር
አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ ውሳኔው ተገቢው የክርክር አመራር እና የማስረጃ ምዘና ሥርዓት የተከተለና
ለጉዳዩ የወጣውን መመሪያ ያደረገ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪዎች መልስ እንዲያቀርቡ ያዘዘ
ሲሆን ተጠሪዎች ያቀረቡት መልስ የአመልካች መስቀለኛ ተቃውሞ አያስቀርብም ተብሎ አስቀድሞ
ተሰርዟል፡፡ አመልካች ዋናውን ውል በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተደረገውን እንዲያቀርብ ታዞ ማቅረብ አልቻለም፡፡
ሰበር ሰሚ ችሎቱ መመሪያውን በአግባቡ ተግባራዊ አድርጎ የሠጠው ውሳኔ ነው፡፡ ውሳኔው ሊጸና ይገባል
ብለዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የግራቀኙን ክርክር፣ የሠበር አጣሪ ችሎት የያዘውን
ጭብጥ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪዎች ሠኔ 12 ቀን 2012 ዓ/ም ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ከአመልካች ጋር የዓለም


ምግብ ፕሮግራምን እንድንጠበቅ የጥበቃ ሥራ ውል ከግንቦት 23 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ እየሰራን
እንገኛለን፡፡ የግል አሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲን አስመልክቶ በ2012 ዓ/ም በወጣው መመሪያ መሠረት
አመልካች ከሚያገኘው ጠቅላላ ክፍያ ውስጥ ለሠራተኛው የሚከፍለው ደመወዝ ከ80% በታች መሆን
እንደሌለበት ተመልክቷል፡፡ አመልካች ለአንድ ሠራተኛ ከሚያገኘው ብር 4,800.00 ውስጥ ብር 3,840.00
መክፈል ሲገባው ብር 1,574.00 እየከፈለን በመሆኑ ከመስከረም 01 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ታስቦ ገንዘቡ
ይከፈለን በማለት ዳኝነት የጠየቁ አመልካች በበኩሉ የደመወዝ መጠኑ ላይ ክርክር ከማቅረቡም በላይ
መመሪያው የወጣው በታህሳስ 2012 ዓ/ም ሲሆን አንቀጽ 50(2) ላይ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ እስከ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ውል እንድናድስ ጊዜ የሠጠ ሲሆን በዚህ መካከል የኮሮና ወረሽኝ ስለገባ
ከሠራተኛ ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በነበረ ውይይት የመመሪያው ተፈጻሚነት ለተጨማሪ ሦስት ወር
ጊዜ እስከ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡ ተጠሪዎች
ባቀረቡት ክስ ላይ የሥር ወረዳ ፍርድ ቤት አከራክሮ ውሳኔ ሲሰጥ ሁለቱም ወገን በውሳኔው ባለመስማማት
ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ተጠሪዎች ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሠበር አቤቱታ አቅርበው
አመልካችን ያስቀርባል ተብሎ ለክርክር በመጠራቱ አመልካች መስቀለኛ ተቃውሞ ማቅረቡን ከክርክሩ
ተገንዝበናል፡፡ አመልካች መስቀለኛ የሠበር አቤቱታው አልተመረመረልኝም ያለ ቢሆንም ተጠሪዎች ሰበር
ሰሚ ችሎቱ ውሳኔ ከመስጠቱ አስቀድሞ የአመልካችን የመስቀለኛ ተቃውሞ አያስቀርብም በሚል ውድቅ
መድረጉን ገልጸው ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በመልስ መልሱ ላይ ይህ ስላለመሆኑ ያቀረበው ክርክር
ባለመኖሩ የአመልካች መስቀለኛ የሠበር አቤቱታ ውድቅ የተደረገ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ አስገብተንና ሰበር
ሰሚ ችሎቱ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ አመልካች በተጠሪዎች የሠበር አቤቱታ ሆነ በመስቀለኛ ተቃውሞ
ማመልከቻው ያቀረበውን ክርክር አጠቃሎ ለዚህ ችሎት ያቀረበውን ተመልክተናል፡፡

ግራቀኙን እያከራከረ ያለው እና ለሥር ፍርድ ቤቶች ለውሳኔ አሠጣጥ ምክንያት የሆነው በሠራተኛና
ማሕበራዊ ሚኒስቴር በኩል በታህሳስ 2012 ዓ/ም የወጣው መመሪያ አፈጻጸም ነው፡፡ ተጠሪዎች ለክሱ
መሠረት ያደረጉት የመመሪያውን አንቀጽ 33 ሲሆን ድንጋጌው ከጠቅላላ አገልግሎት ክፍያ ውስጥ አመልካች
ከ80% በታች ደመወዝ መክፈል እንደማይገባው የሚያዝ ነው፡፡ የመመሪያውን አፈጻጸም በተመለከተ በአንቀጽ
50(2) ላይ መመሪያው በሥራ ላይ ከዋለበት ከታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በሦስት ወር ውስጥ
የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሆነው የተመዘገቡ ድርጅቶች አዲስ ፈቃድ ማውጣት ይጠበቅበቸዋል፡፡
በዚህ ጊዜ አዲስ ፈቃድ ማውጣት ያልቻለ ድርጅት ቀድሞ ተሰጥቶት የነበረው ፈቃድ ጥቅም አልባ
እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የመመሪያው አቀራረጽ ለሠራተኞች ክፍያን
አስመልክቶ ምንም ስለማይልና ለሰሩበት ሥራ ክፍያ እንዳያገኙ ሊከለከሉ ስለማይገባ መመሪያው ከወጣት
ጊዜ ጀምሮ ከጠቅላላ ክፍያው ከ80% በታች ሊከፈላቸው አይገባም ብሏል፡፡ መመሪያው የሚመለከታቸው
ድርጅቶች ላይ አዲሱ መመሪያ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ ሠራተኞች ሥራውን እስከሰሩ ድረስ ለሠሩበት
ክፍያ ማግኘት መብት ያላቸው በመሆኑ ለሠራተኞች ደመወዝ ሊከፈላቸው ይገባል መባሉ ተገቢ ነው፡፡

ነገር ግን ክፍያው ታሳቢ የሚያደርገው የሥራ ውላቸውን ነው ወይስ በመመሪያ አንቀጽ 33 መሠረት
አመልካች ከሚያገኘው ከጠቅላላ ክፍያው ከ80% በታች ሊሆን አይገባም ተብሎ በተመለከተው መጠን
መሠረት የሚለው ሊመረመር የሚገባው ነው፡፡ መመሪያው ይዞት ከመጣው አዲስ ነገር አንዱ አመልካች
ከሚያገኘው ጠቅላላ ክፍያ ለሠራተኞች ከ80% በታች ሊከፍል እንደማይገባ በአስገዳጅነት መደንገጉ ነው፡፡
መመሪያው የመሸጋገሪያ ጊዜ መስጠት የፈለገው ድርጅቶች በአዲሱ መመሪያ ባለባቸው ኃላፊነት መሠረት
እንዲሰሩ ለማስቻል አስተዳደራዊ መዋቅራቸውን ሆነ አስተዳደራዊ ወጪያቸውን በማስተካከል ከጠቅላላ
ክፍያው በሚያገኙት 20% ሥራውን ማስቀጠል የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠርና ይሕን ማድረግ ካልቻሉ
ከሥራው የሚወጡበትን ሂደት የያዘ ነው፡፡ ስለሆነም ሠራተኞች በሥራ ውላቸውና ቀድሞ ሲያገኙት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የነበረው ክፍያ መፈጸሙ እንደቀጠለ ሆኖ በመመሪያ አንቀጽ 33 የተመለከተው ክፍያ መሠረት አድርጎ
ለመጠየቅ ግን የመመሪያው አፈጻጸምን አስመልክቶ በአንቀጽ 50(2) የተሰጠውን ጊዜ ማክበርና መጠበቅ
ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የደረሰበት መደምደሚያ የመመሪያውን ዓላማ
ያላገናዘበና ስህተት ያለበት ነው፡፡ በተጨማሪም ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሥራና ሠራተኞች አገልግሎት አዋጅ
ቁጥር 632/2001 በውሳኔው መጥቀሱ ሕጉ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 192(1) የተሻረ በመሆኑ
ሊታረም የሚገባው ነው፡፡ ስለሆነም መመሪያው በአንቀጽ 50(2) ከሰጠው የሦስት ወር ጊዜ በተጨማሪ በሥር
ወረዳ ፍርድ ቤት እንደተረጋገጠው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ
22 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ የመመሪያውን አፈጻጸም ያዘገየ በመሆኑ ተጠሪዎች ተጨማሪ ክፍያውን እስከ ሰኔ
22 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ ሊጠይቁ አይገባም በማለት የሥር ወረዳ ፍርድ ቤት የሠጠው ውሳኔ ተገቢ ሆኖ
አግኝተነዋል፡፡

አመልካች ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ በመመሪያው አንቀጽ 33 በተመለከተው መሠረት ከጠቅላላ
ክፍያው ለሠራተኞች ደመወዝ ከ80% በታች መሆን የለበትም ተብሎ በተደነገገው መሠረት መፈጸም
ይኖርበታል፡፡ ከዚህ ላይ አከራካሪ የሆነው የክፍያው መጠን ነው፤ ተጠሪዎች የብር 4,800.00 ብር 80%
ደመወዝ እንዲከፈላቸው የጠየቁ ሲሆን አመልካች ይሕንን የክፍያ መጠን ክዶ ተከራክሯል፡፡ በመመሪያው
መሠረት ክፍያው የሚሰላው አመልካች ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በገባው ውል መሠረት ከሚከፈለው
የጠቅላላ ክፍያ አንጻር ነው፡፡ ውሉ የሚገኘው ከአመልካች ዕጅ እና ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ጋር ነው፡፡
በሥር ወረዳ ፍርድ ቤት እንደተረጋገጠው አመልካች ሆነ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋናውን ውል
እንዲያቀረቡ ተጠይቀው ሊያቀርቡ አልቻሉም፡፡ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዓለምአቀፍ ሕግን በመጥቀስ
ማስረጃውን ለማቅረብ አልገደድም ማለቱና አመልካች ማስረጃውን ለማቅረብ አለመፈለጉ በሥር ፍርድ ቤት
ውሳኔ ላይ ተገልጿል፡፡ አመልካች በዚህ ችሎት በሚያደርገው ክርክር የሥር ፍርድ ቤት አመልካችን አስገድዶ
ማስረጃውን ሊያስቀርብ ይገባ ነበር የሚል ነው፡፡ የሥር ፍርድ ቤት ማስረጃውን ለማስቀረብ ተገቢውን ጥረት
ያደረገ ሲሆን አመልካች ተከራካሪ ወገን እንደመሆኑ መጠን በዕጁ የሚገኘውን ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ
ማስረጃው ቢቀርብ ኖሮ ሊያረጋግጠው የሚችለውን ፍሬ ነገር መኖሩን ተቀብሎ ክርክሩን መምራቱ ላይ
የተፈጸመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አላገኘንበትም፡፡ ስለሆነም በመመሪያው አንቀጽ 33 በተመለከተው
መሠረት ከጠቅላላ ክፍያው ለሠራተኞች ደመወዝ ከ80% በታች መሆን የለበትም ተብሎ በተመለከተው
መሠረት አመልካች ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ አመልካች በሥራ ውሉ መሠረት ከሚከፍለው
የትራንስፖርት አበል ውጭ ያልተጣራ ደመወዝ ብር 3,840.00 ሊከፍል ይገባል መባሉ ተገቢ ነው ብለናል፡፡
በተጨማሪም ወጭና ኪሣራ አወሳሰን ላይ የተፈጸመ ሥህተት ባለመኖሩ በዚህ ሰበር ችሎት ደረጃ
የሚመረመር ሆኖ አላገኘነውም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ

1. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 374110 ሚያዚያ 05 ቀን
2013 ዓ/ም፣ የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥሮች 36347 እና 36329 እንዲሁም
የአዳማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 27502 ጥር 13 ቀን 2013 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሏል፡፡

2. አመልካች ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ለእያንዳንዳቸው ተጠሪዎች ያልተጣራ ደመወዝ ብር


3,840.00 ሊከፍል ይገባል ተብሎ ተወስኗል፡፡

3. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡ የአዳማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በውሳኔው
መሠረት እንዲፈጽም አዘናል፡፡ ይጻፍ
 አፈጻጸሙ ላይ የተሠጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-206636

ቀን፡-29/03/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የጎንደር ከተማ ቂርቆስ ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት

ተጠሪዎች፡- 1. ወ/ሮ ስመኝ አለሙ

2. ወ/ሮ ትዕግስት አለሙ

3. ሻለቃ ብርሃኔ አለሙ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 01-40457 የካቲት 05
ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት
አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን
ጎንደር መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪዎች ከሳሾች፤
የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪዎች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ
ይዘት በአጭሩ፡- በጎንደር ከተማ ጭርቆስ ክፍለከተማ አካባቢ 07 ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ እና አዋሳኙ በክሱ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተገለጸ 30.50 ካ.ሜ የሆነ ቤት እና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሠረት ያልተወረሰ እና የሟች አባታቸው
የምርጫ ቤት መሆኑን፤ ከዚሁ ይዞታ ውስጥ 6.5 ካ.ሜ ላይ ያረፈውን ቤት አመልካች ያለአግባብ የያዘባቸው
መሆኑን በመግለጽ ለቆ እንዲያስረክባቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን አመልካች በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ በሰጠው
መልስ ደግሞ ክስ የቀረበበት ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰ የመንግስት ቤት እንጂ የተጠሪዎች አባት
የምርጫ ቤት አለመሆኑን በመግለጽ የተጠሪዎች ክስ ወድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም መቃወሚውን በብይን ውድቅ ያደረገ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ ደግሞ የግራቀኙን
ምስክሮች ከሰማ በኋላ አመልከች አከራካሪው ቤት የተወረሰ እና ኪራይ የሰበሰበበት መሆኑን አላስረዳም፤
አከራካሪው ቤት የተጠሪዎች አባት የምርጫ ቤት እንደሆነ እና አበል የተበላበት እንዳልሆነ ከቀረቡት
ማስረጃዎች መረዳት ተችሏል፤ የተጠሪዎች አባት በ 30.50 ካ.ሜ ቤት እና ቦታ ላይ እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ
ግብር እንደከፈሉ የተረጋገጠ በመሆኑ ቤት እና ቦታው የተጠሪዎች የውርስ ሐብት ነው፤ ተጠሪዎች
ባቀረቡት ማስረጃዎች አመልካች ክስ የቀረበበትን ቤት እና ቦታ ገብቶ እንደያዘባቸው አስተድተዋል፤ መጠኑን
በተመለከተ ተጠሪዎች በአሁኑ ሰዓት የያዙት ይዞታ 27.72 እንደሆነ ክፍለ ከተማው አሳውቋል፤ በመሆኑም
ተጠሪዎች በውርስ ከያዙበት ቤት እና ቦታ ላይ አመልካች በቤት ቁጥር 191 በኩል 3 ካ.ሜ አካባቢ
የያዘባቸው በመሆኑ በአዋሰኝ የተገለጸውን 30.50 ካ.ሜ ቦታ እና ቤት ለተጠሪዎች እንዲያስረክብ ሲል
ወስኗል፡፡

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
አቅርቧል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን አለው የሚለውን
ጭብጥ በመያዝ ተጠሪዎችን አስቀርቦ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪዎች ከሚመለከታቸው አስፈጻሚ
አካላት የባለቤትነት ማስረጃ ባላቀረቡበት ሀኔታ የስር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት የስረነገር ስልጣን የለውም
በማለት ወስኗል፡፡

ተጠሪዎች በበኩላቸው ይህን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ቸሎት በሰ.መ.ቁ
131437 አቤቱታ አቅርበው ችሎቱ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ታሕሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት
በሰጠው ፍርድ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን
የለውም በማለት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ ፍሬነገሩን በሚመለከት አከራክሮ ተገቢውን እንዲወስን በማለት
ጉዳዩን መልሶለታል፡፡

ጉዳዩ የተመለሰለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም አስቀድሞ መዝገቡ ያስቀርባል ተብሎ
የነበረው የስር ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለውን ለመመልከት ነበር
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የስር ፍርድ ቤት ፍሬጉዳዩን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በሚመለከት የሰጠው ውሳኔ እንደመረመርነው ተጠሪዎችን መጥራት አላስፈለገም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ


337 መሠረት የአመልካችን አቤቱታ ሰርዞታል፡፡

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን
ይዘቱም፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው ውሳኔ መሠረት የስር ፍርድ ቤቱ
ፍሬጉዳዩን በሚመለከት ግራቀኛችንን አከራክሮ መወሰን ሲገባው ይህን ሳያደርግ መዝገቡን በትዕዛዝ መዝጋቱ
ተገቢ አይደለም፤ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ከጭብጥ ውጪ በመውጣት ባልተጠየቀ ዳኝነት
የተሰጠ ውሳኔ ነው፤ ቤቱ አልተወረሰም በማለት ክስ የሚያቀርብ ወገን ከሚመለከተው አካል የተፈቀደለት
ስለመሆኑ ማስረዳት ይጠበቅበታል፤ ስለሆነም ይህ ሳይረጋገጥ የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ
ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪው ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት ከ
30.50 ካ.ሜ ቤትና ቦታ ውስጥ 6.5 ካ.ሜ ላይ ያረፈ ቤት አመልካች አላግባብ ይዞብናል የሚል ሆኖ ሳለ
የስር ፍርድ ቤት አመልካች 30.50 ካ.ሜ ቤትና ቦታ እንዲለቅ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር የሚል
ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት ተደርጎ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ቀርቧል፡፡

ተጠሪዎች ጥቅምት 04 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- በስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩ
በአግባብ የተጣራ በመሆኑ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህንኑ መሠረት በማድረግ የአመልካችን አቤቱታ
በትዕዛዝ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው፤ የተጠሪዎች ጥያቄ በይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ከተረጋገጠልን 30.5
ካ..ሜ ውስጥ አመልካች አንድ ክፍል ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/47 ያልተወረሰ በባለሙያ ተለክቶ ይሰጠን
የሚል ነው፤ ቦታው በባለሙያ እንዲለካ ተደርጎ 27.72 ካ.ሜ መሆኑ እና ግብር ሰንከፍል የነበረው ግን በ
30.5 ካ.ሜ መሆኑ ተረጋግጧል፤ ቤቱ ተወርሷል አልተወረሰም የሚለውም በጭብጥነት ተይዞ ተረጋግጧል፤
ተጠሪዎች በአመልካች የተያዘብን ቤት እና ቦታ 6.5 ካ.ሜ ነው ብለን ከሰን የነበረ ቢሆንም በባለሙያ
ሲረጋገጥ 3 ካ.ሜ በመሆኑ ይኸው እንዲለቀቅ መወሰኑ በተጠየቀው ዳኝነት መሠረት ነው፤ ስለሆነም
ውሳኔው ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ
ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር
አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምሮታል፡፡

በመሠረቱ ፍ/ቤቶች በተከራካሪ ወገኖች የሚቀርብላቸውን ክርክር መርምረው ውሳኔ መስጠት የሚችሉት
ተከራካሪ ወገኖች በግልጽ በጠየቁት ዳኝነት ላይ ስለመሆኑ እና ከተጠየቀው ዳኝነት ውጪ በመውጣት ፍርድ
መስጠት እንደማይቻል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 182/2 ድንጋጌ ያስገነዝበናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በያዝነው ጉዳይ የአሁን ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ የጠየቁት ዳኝነት ከይዞታችን ውስጥ
ገፍቶ የያዘውን 6.5 ካ.ሜ ይዞታ እንዲለቅ ይወሰንልን የሚል ነው፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት አመልካች ገፍቶ
ይዞታል የተባለው የይዞታ መጠን እንዲጣራ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት አመልካች ገፍቶ የያዘው ይዞታ 3
ካ.ሜ አካባቢ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት አመልካች በቤት ቁጥር 191 በኩል 3 ካ.ሜ
አካባቢ የያዘባቸው በመሆኑ በአዋሰኝ የተገለጸውን 30.50 ካ.ሜ ቦታ እና ቤት ለተጠሪዎች እንዲያስረክብ
በማለት የሰጠው ውሳኔ የተጠየቀውን ዳኝነት እና የተረጋገጠውን ፍሬነገር ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የሰጠው ውሳኔ ሊሻሻል የሚገባው ሆኖ ስለተገኝ ተከታዩን ውሳኔ
ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 01-40457
የካቲት 05 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ተሻሽሏል፡፡
2. አመልካች ለተጠሪዎች ሊለቅ የሚገባው በባለሙያ የተረጋገጠውን ገፍቶ የያዘውን የይዞታ መጠን 3
ካ.ሜ አካባቢ ነው በማለት ወስነናል፡፡
3. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 206661

ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካቾች ፡ 1ኛ. መንግስቱ ከፋለ አልቀረቡም

2ኛ. አቶ ሳምሶን ሃይሌ

ተጠሪ ፡ ጃርኮ ኮንሰልቲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር- ጠበቃ ጥበቡ ምህረቴ -ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የስራ ውል መቋረጥን ተከትሎ የቀረበ የአሰሪ እና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ ክርክሩ
በተጀመረበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካቾች ከሳሾች ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ
በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካቾች ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ 1ኛ አመልካች
በእስታክትሲሺያን ሙያ 2ኛ አመልካች በሎጅስቲክስ ኦፊሰር የስራ መደብ ስናገለግል ቆይተን ተጠሪ የድርጅቱ
ስራ ስለቀዘቀዘ የስራ መደባችሁን ለመሰረዝ ተገደናል በሚል ከስራ አሰናብቶናል፡፡ በመሆኑም ተጠሪ የስራ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውላችንን ያቋረጠው በህገወጥ መንገድ ስለሆነ ተገቢ ክፍያዎችን እንዲከፍል ይወሰንልን በማለት ዳኝነት
ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪ ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካቾች ከስራ የተሰናበቱት የድርጅቱ የስራ
እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ እና ትርፍ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ አንዳንድ የስራ መደቦችን መሰረዝ አስፈላጊ ሆኖ
ተገኝቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የአመልካቾች የስራ መደብ የተሰረዘ ሲሆን ወደሌላ የስራ መደብም አዛውረን
ማሰራት ባለመቻላችን የስራ ውላቸውን ለማቋረጥ ተገደናል፡፡ በመሆኑም አመልካቾች በህጉ መሰረት
የተሰናበቱ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክርክሩን መርምሮ ማስጠንቀቂያ
መሰጠቱን፣ የስራ ስንብት እና የአመት እረፍት ክፍያ መከፈሉን ክሱ ሲሰማ ግራ ቀኙ ተማምነዋል፡፡ የተጠሪ
ገቢ እና ትርፍ እየቀነሰ መምጣቱን ተጠረ ካቀረበው የ2009 እና 2010 በጀት አመት ትርፍ መረዳት
ተችሏል፡፡ ይህም የስራ መደብን ለመሰረዝ በቂ ምክንያት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28/1/መ
መሰረት ስንብቱ ህጋዊ ነው፡፡ ነገር ግን በአዋጁ አንቀጽ 40/3 መሰረት አመልካቾች ተጨማሪ የስንብት ክፍያ
ሊከፈላቸው ይገባል በማለት ወስኗል፡፡

ተጠሪ ለአመልካቾች ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈል ይገባል በመባሉ ቅር በመሰኘት ለፌደራል ከፍተኛ
ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ
28/1/መ መሰረት የተሰናበተ ሰራተኛ በአዋጁ አንቀጽ 40/3 መሰረት ተጨማሪ የስንብት ክፍያ
እንደሚከፈለው አልተደነገገም፡፡ በመሆኑም አመልካቾች ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈላቸው አይገባም
በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ አሻሽሏል፡፡

አመልካቾች በሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጻፈ የሰበር ቅሬታ ያቀረቡት ስንብቱ ህጋዊ ነው እንዲሁም
ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈላቸው አይገባም መባሉን በመቃወም ለማሳረም ነው፡፡ የቅሬታው ይዘት ተጠሪ
የስራ ወሉን ያቋረጠበት ምክንያት ትርፍ ቀንሷል በሚል ነው፡፡ ትርፍ ቀንሷል ወይስ አልቀነሰም የሚለው
ፍሬ ነገር የተመዘነበት እና ህጉ የተተረጎመበት መንገድ መሰረታዊ ህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው፡፡ ስንብቱ
በስር ፍርድ ቤት ህጋዊ ነው በመባሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መስቀለኛ ይግባኝ አቅርበን በዝምታ
ታልፎብናል፡፡ የስራው መሰረዝ ምክንያት በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28/3/ለ ላይ
የተጠቀሰው ምክንያት በመሆኑ ቅነሳው የሚከናወነው በአዋጁ አንቀጽ 29 መሰረት ነው፡፡ በአንቀጽ 29
መሰረት የተፈጸመ ስንብት ከሆነ ደግሞ በአንቀጽ 40/3 መሰረት ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈል ይገባል፡፡
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ይታረምልን የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት የአመልካቾችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ አመልካቾች ክፍያ አይገባቸውም የመባሉን
አግባብነት ከአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጁ አንቀጽ 24፣28፣29 እና 40/3 አንጻር ለማጣራት ያስቀርባል በማለት
ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ትዝዛዝ ሰጥቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ በመስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ የድርጅቱ ትርፍ ቀንሷል ወይስ አልቀነሰም
የሚለው የፍሬ ነገር ክርክር እና በማስረጃ የሚጣራ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን መዝነው ትርፍ
መቀነሱን አረጋግጠዋል፡፡ ስለዚህ ስንብቱ ህጋዊ ነው በመባሉ የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም፡፡
አመልካቾች የማስጠንቀቂያ፣ የስንብት እና የአመት እረፍት ክፍያ የተከፈላቸው መሆኑ አልተካደም፡፡
በመሆኑም ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈል አይገባም መባሉ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡

አመልካቾችም የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታቸውን አጠናክረዋል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር የአመልካቾች የስራ ስንብት ህጉን
የተከተለ ነው ወይስ አይደለም? እና አመልካቾች ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈላቸው ይገባል ወይስ
አይገባም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ በስር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እና ከተገቢው ህግ ጋር
በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

በመጀመሪያም የአመልካቾች ስንብት ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ስንመለከት


ለአመልካቾች የስራ ስንብት ምክንያት የሆነው የተጠሪ ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የአመልካቾች የስራ መደብ
ተሰርዟል በሚል ነው፡፡ አመልካቾች በበኩላቸው ተጠሪ የስራ መደባቸውን መሰረዙን ክደው ያልተከራከሩ
ከመሆኑም በላይ የስር ፍርድ ቤት በምስክሮች ያረጋገጠው ፍሬ ነገር መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል፡፡
እንዲሁም አመልካቾች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው እና የስንብት ክፍያ የተከፈላቸው መሆኑም ተረጋግጧል፡፡
አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት የተጠሪ ስራ እየቀዘቀዘ ትርፍም የቀነሰ ሄዷል የሚለው በአግባቡ
አልተረጋገጠም በሚል ነው፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
ተጠሪ ያቀረበው የ2009 እና የ2010 በጀት አመት ትርፍ መጠን የተጠሪ ስራ እየተቀዛቀዘ እና ትርፍ
እየቀነሰ መሄዱን ያሳያል፡፡ ይህ ደግሞ የስራ መደብ ለመሰረዝ በቂ ምክንያት ስለሆነ የአመልካቾች ስንብት
ህጋዊ ነው የሚል መደምደሚያ ደርሷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አመልካቾች ያቀረቡት አንዱ ቅሬታ ስንብቱ
ህጋዊ ነው መባሉን በመቃወም ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ላይ
መስቀለኛ ይግባኝ አቅርበን በዝምታ ታልፎብናል የሚል ነው፡፡ እኛም የአመልካቾች መስቀለኛ ይግባኝ
በይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዝምታ ታልፏል አልታለፈም? የሚለውን ለማጣራት የፌደራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመዝገብ ቁጥር 250120ን አስቀርበን ተመልክተናል፡፡ መዝገቡን ተመልክተን የተረዳነው
አመልካቾች እንዳሉት መስቀለኛ ይግባኝ ማቅረባቸውን፤ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም የአመልካቾችን መስቀለኛ
ይግባኝ መስማቱን እና በጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት 2ኛ ተጠሪ በተገኙበት መስቀለኛ
ይግባኙን ባለመቀበል ብይን መሰጠቱን ነው፡፡ በመሆኑም አመልካቾች መስቀለኛ ይግባኝ አቅርበን በዝምታ
ታልፎብናል በማለት ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የለውም፡፡

እንደሚታወቀው የስራ ውል በህግ ወይም በስምምነት በአሰሪው ወይም በሰራተኛው አነሳሽነት እንደሚቋረጥ
በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 23 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ተመልክቷል፡፡
በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስጠንቀቂያ በአሰሪው አነሳሽነት የስራ ውል ሲቋረጥ የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አዋጁ ያስቀመጠውን የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያት ብቻ መሰረት በማድረግ ከሆነ ስንብቱ ህጋዊ ይሆናል፡፡
በተቃራኒው አሰሪው ሰራተኛውን በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውልን ለማቋረጥ የሚያስችሉ
ምክንያቶች መኖራችን ሳያረጋግጥ የስራ ውል የሚያቋርጥ ከሆነ ስንብቱ ህገወጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ
የአመልካቾች ስንብት ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም? የሚል መደምደሚያ ላይ ለመድረስ የስንብቱ ምክንያት
በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጁ የተመለከተ ስንብት ምክንያት መሆኑን መመርመር ተገቢ ነው፡፡

ከላይ እንደተገለጸው ተጠሪ አመልካቾችን ከስራ ያሰናበተው የስራ መደባቸው ተሰርዟል፤ በሌላ የስራ መደብ
ላይም መመደብ አልቻልኩም በማለት ነው፡፡ የስራ መደቡን የሰረዘበት ምክንያት ደግሞ የድርጅቱ ስራ እና
ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ መሆኑን ገልጾ ተከራክሯል፡፡ በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96
አንቀጽ 28/1/መ ላይ ሰራተኛው የያዘው የስራ መደብ በበቂ ምክንያት ከተሰረዘና ሰራተኛውን ወደሌላ የስራ
መደብ ማዛወር ካልተቻለ አሰሪው ማስጠንቀቂያ በመስጠት የስራ ውል ሊያቋርጥ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡
ከዚህ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለው የስራ መደብ መሰረዙ ብቻውን ሰራተኛውን ከስራ ለማሰናበት በቂ ምክንያት
አለመሆኑን ነው፡፡ የስራ መደቡ መሰረዝ ሰራተኛን ለማሰናበት በቂ ምክንያት ሊሆን የሚችለው የስራ መደቡ
በበቂ ምክንያት መሰረዙ እና አሰሪው ሰራተኛውን በሌላ የስራ መደብ ላይ መድቦ ለማሰራት ጥረት አድርጎ
መመደብ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ይህም ማለት አሰሪው በዘፈቀደ ያለበቂ ምክንያት የሰራተኛውን
የስራ መደብ በመሰረዝ እና በሌላ የስራ መደብ ላይ ለመመደብ ጥረት ሳያደርግ ሰራተኛውን ማሰናበት
አይችልም ማለት ነው፡፡

በተያዘው ጉዳይ ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የስር ፍርድ ቤቶች የተጠሪ ስራ እየቀዘቀዘ ትርፍም
እየቀነሰ መሄዱን በማስረጃ ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ነው፡፡ እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት
በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ መሰረት የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመባቸውን ውሳኔዎች ማረም ነው፡፡ ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ማስረጃን
መዝነው የደረሱበትን የፍሬ ነገር ድምዳሜ ይህ ችሎት እንዲመለከት ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ በመሆኑም
የተጠሪ ስራ ተቀዛቅዟል ወይስ አልተቀዛቀዘም እንዲሁም ትረፉ ቀንሷል ወይስ አልቀነሰም የሚለው በማስረጃ
የሚጣራ የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን መዝነው የተጠሪ ትርፍ ቀንሷል በሚል
የደረሰበት መደምደሚያ ይህ ችሎት እንዳለ የሚቀበለው ነው፡፡

በመቀጠል የተጠሪ ትርፍ መቀነሱ እንዲሁም ስራው መቀዝቀዙ በማስረጃ ከተረጋገጠ የስራ መደብን
ለመሰረዝ በቂ ምክንያት ይሆናል ወይ? የሚለውን ስንመለከት ይህ ምክንያት ሰራተኛን ለመቀነስ በቂ
ምክንያት መሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 28/3/ለ ላይ ተመልክቷል፡፡ ነገር ግን የስራ መደብን ለመሰረዝ በቂ
ምክንያት ስለመሆኑ በግልጽ አልተመለከተም፡፡ ከስራ መደብ መሰረዝ ጋር በተያያዘ በአዋጁ አንቀጽ 28/1/መ
ላይ በቂ ምክንያት ያስፈልጋል በሚል የተገለጸ በመሆኑ በቂ ምክንያት ምንድነው የሚለውን መመዘን
ለፍርድቤቶች የተሰጠ ስልጣን ነው፡፡ በአንድ የስራ መደብ ላይ አንድ ሰራተኛ ብቻ የሚሰራ ከሆነ እና አሰሪው
ትርፉ እየቀነሰ ስራው እየቀሰቀዘ ሲሄድ ድርጅቱን ውጤታማ ለማድረግ በአንድ ሰራተኛ የተያዘን የስራ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መደብ ቢሰርዝ የሰረዘበት ምክንያት በቂ ምክንያት ነው ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ይሆናል፡፡ በመሆኑም ተጠሪ
ስራው እየቀዘቀዘ መሄዱን እና ትርፉ መቀነሱን በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህ ምክንያትም የስራ
መደብን ለመሰረዝ በቂ ምክንያት ነው፡፡ እንዲሁም ተጠሪ አመልካቾችን በሌላ የስራ መደብ መድቦ ለማሰራት
የማይችል መሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች ስለተረጋገጠ ስንብቱ በአዋጁ አንቀጽ 28/1/መ መሰረት ህጋዊ ነው
በመባሉ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ስንብቱ ህጋዊ ነው ከተባለ ለአመልካቾች ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈል ይገባል ወይስ አይገባም?
የሚለውን ነጥብ ስንመለከት በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጁ አንቀጽ 40/3 ላይ የስራ ውል በአዋጁ አንቀጽ
24/4 እና በአንቀጽ 29 መሰረት ሲቋረጥ ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ሊከፈል እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ ይህም
ማለት በመክሰር ወይም በሌላ ምክንያት ድርጅቱ ለዘለቄታው ሲዘጋ እና ህጉ ባስቀመጠው ምክንያት የሰራተኛ
ቅነሳ ሲደረግ ተጨማሪ የስንብት ክፍያ ይፈጸማል፡፡ ከነዚህ ምክንያቶች ውጪ የስራ ውል ሲቋረጥ ግን
ተጨማሪ የስንብት ክፍያ እንደሚከፈል በአዋጁ አንቀጽ 40/3 ላይ አልተመለከተም፡፡ ስለዚህ የፌደራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካቾች የስራ ስንብት በአዋጁ አንቀጽ 28/1/መ መሰረት ህጋዊ ነው ካለ
በኋላ ተጠሪ ተጨማሪ የስንብት ክፍያ እንዲከፍል መወሰኑ የአዋጁን አንቀጽ 40/3 ድንጋጌ የሚቃረን
መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን
ስህተት ማረሙ ተገቢ ነው ከሚባል በስተቀር በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተፈጸመ መሰረታዊ የህግ
ስህተት ባለመኖሩ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1ኛ. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 250120 በጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ሰጠው ውሳኔ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል፡፡

2ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

ትእዛዝ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 250120 በመጣበት አኳኋን ተመላሽ ይደረግ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 206729
ህዳር 28 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ ኦቶሪኖ ከአንገት በላይ ሕክምና ማዕከል ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ ፍክርተ ጥበቡ

-ቀረቡ

ተጠሪ፡ ነርስ ሚካኤል ዳንኤል- ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ አግባብነት የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረበው
ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከሐምሌ 16 ቀን 2010ዓ.ም ጀምሮ በፕሮፌሽናል ነርስ የስራ
መደብ በወር ብር 11,200 ደመወዝ እየሰራሁ እያለ የዲስፕሊን ጥፋት ፈጽመሃል በማለት
በ08/01/2013 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ ከስራ አሰናበተኝ በማለት ስንብቱ ህገወጥ ነዉ ተብሎ
የህገወጥ ስንብት ክፍያዎች እንዲከፈለው ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካች በበኩሉ ባቀረበው
መልስ ተጠሪ በቀን 08/01/2013ዓ.ም በነበረው ስብሰባ ላይ ሁከትና አምባጓሮ በመፍጠርና
ለድብድብ በመጋበዝ በስራ ቦታ ረብሻና ሁከት በማድረጉ በአዋጅ ቁ/1156/2011 አንቀጽ
27(1)ረ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብት የስነምግባር ጉድለት መፈጸሙን፤በኦፕራሲዮን
ክፍል ውስጥ ዋና ሀኪም የሚናገረውን ንግግር በሹፈት በመድገም የታካሚ ስነልቦና እንዲታወክ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ያደረገ በመሆኑ ባህሪውን እንዲያስተካክል በቅርብ አለቃው በቀን 30/07/2020 የቃል


ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ቢሆንም ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም ንግግሩን በመድገም የታካሚ
ስነልቦና የሚጎዳ ንግግር በመናገሩ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ በፈፀመዉ ጥፋት
ያለማስጠንቀቂያ የተሰናበተ መሆኑን፤የዓመት እረፍት እና ያልተከፈለ ደመወዝ እንዲወስድ
ቢጠየቅም ፈቃደኛ ስላልሆነ የሚከፈል ክፍያ ባለመኖሩ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት
መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ በወቅቱ ስብሰባ ላይ የነበሩ ሰዎች ምንም
ፀብና አምባጓሮ እንዳልነበረ እና ተጠሪ በስራ አካባቢ ያለው ግንኙነትም መልካም መሆኑን
የገለጹ ስለሆነ በድርጅቱ ባለቤቶች በግነት የተገለጸዉ ማስረጃዉ ተጠሪን የማይገልጽ መሆኑን
ችሎቱ አምኗል፣ስለዚህ ተጠሪን ለማሰናበት የሚያስችል ጥፋት ያልፈመ እና ፀብ እና አምባጓሮ
እንዲሁም የታካሚን ስነልቦና መጉዳት የተባለው በማስረጃ የተረጋገጠ ባለመሆኑ የተጠሪ
ስንብት ህገወጥ ነው በማለት የተጠየቃቸዉ ልዩ ልዩ ክፍያዎችን አመልካች እንዲከፈል
በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር መርምሮ የአመልካች ምስክሮች ቃል በዘፈቀደ ውድቅ ተደርጓል
የተባለው የመከላከያ ምስክሮች ቃል ተመዝኖ ውድቅ የተደረገ በመሆኑ በዘፈቀደ ውድቅ
ተደርጓል ሊባል አይቻልም፣በቀን 08/01/2013ዓ.ም በስራ ቦታ /በቢሮ/ ውስጥ ፀብ እና አምባጓሮ
ፈጥሯል የተባለው በእለቱ ከቢሮ እስከወጡ ድረስ የተፈጠረ ፀብ አለመኖሩ በግራ ቀኝ
ምስክሮች ተረጋግጧል፣ስለዚህ በቢሮ ውስጥ የተፈጸመ ፀብና አምባጓሮ ሳይኖር ለጥያቄ ምላሽ
ባለመስጠቱ ወይም ዝም በማለቱ ብቻ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውል መቋረጡ ስንብቱን ህገወጥ
የሚያደርግ ነው በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል፡፡

ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል
በሚል እንዲታረም ሲሆን አቤቱታዉ ይዘት ባጭሩ ሲታይ፤ ተጠሪ በማኔጅመንት አባላት
ስብሰባ ላይ እንዲገኝ የተደረገው ከድርጅቱ ሰራተኛ ጋር ያለውን የግል ጠብ አስወግደው
የቡድን ስራውን በብቃት እንዲወጣ ለማስቻል ሲሆን ተጠሪ በስርዓት መልስ መስጠት ሲገባው
እየጮኸና እጁን እያወናጨፈ በመደጋገም ስትፈልግ አባረኝ እያለ ለጠብ አጫሪነት የሚጋብዝ
ሐይለ ቃል የተሞላበት የንቀት ንግግር መናገሩ ቀጥሎም ዋና ዳይሬክተሩን ለመደብደብ
መጋበዙና የፋይናንስ ኃላፊው ላይ መዛቱ በአዋጁ አንቀጽ 27(1(ረ)) መሰረት የስራ ውልን
ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ይህ አምባጓሮ ሊሆን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አይችልም፣ሞራል የሚነካ ንግግር ሊሆን አይችልም፣ከዚህ በፊት በኮሊደር ላይ ለጠብ


የሚጋብዝና መዛት አምባጓሮ ፈጽሟል የተባለው በቃል የስራ ውሉን አቋርጣችሁ በኋላ ወደ
ስራ መልሳችሁ እንደገና በዚህ ምክንያት የስራ ውሉን ሊታቋርጡ አትችሉም በማለት የሰጠው
ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡ተጠሪ በስራ ቦታ ፀብና አምባጓሮ መፍጠሩን፣ለድብድብ
መጋበዙን እና ዶ/ር ላይ በማሾፍ የቡድን ሥራውን የበደለ እና የታካሚ ሥነ ልቦና የጎዳ
ንግግር መናገሩን ባጠቃላይ ድርጊቱ የአዋጁን አንቀጽ 27(1(ረ)) ስር የተመለከተውን ጥፋት
የሚያሟላ መሆኑ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት የምስክርነት ቃል ሳይተችና ሳይመዘን ሙሉ
በሙሉ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡በተጨማሪም በስብሰባ ላይ የተገኙ
የማኔጅመንት አባላት የዲሲፕሊን ጥፋት ስለመፈፀሙ በስብሰባ ቃለ-ጉባኤ ላይ የፈረሙትን
ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተሽሮ
ወጪና ኪሳራ እንዲወሰንልን በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ የስር ፍርድ ቤት አመልካች
ያቀረባቸውን የሰውና የሰነድ ማሰረጃዎችን ውድቅ በማድረግ ተጠሪ በሥራ ቦታ አምባጓሮ እና
ፀብ አጫሪነት ተግባር መፈፀሙን መመስከሩን ከተቀበለ በኋላ ውድቅ በማድረግ ስንብቱ
ህገወጥ ነው ያለበትን ከአዋጁ አንቀጽ 27/1/ረ/ አንፃር ለማጣራት ጉዳዩ ያስቀርባል ተብሎ
ተጠሪ መልስ እንዲያቀርብ ታዟል፡፡

ተጠሪ በቀን 15/10/2013ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ ተጠሪ የዲሲፕሊን ጥፋት ፈፀመ የተባለው
በቀን 08/01/2013 ዓ.ም ሲሆን በማኔጅመንት ስብሰባ ወይም ለስራ በተደረገ ስብሰባ ላይ
ሳይሆን ሲ/ር አሰፋ ሙሉነህ እና አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ የተባሉ ሰራተኞችን ለማስታረቅ
በተደረገ ስብሰባ ላይ ተጠሪም ከአቶ አብዱላዚዝ ጋር አይነጋገሩም እርሱም ይጠራና
እናስታርቃቸው ተብሎ ከተጠራሁ በኋላ ወ/ሮ ቲማጅ እኔንም ዘግቶኛል ብለው ሲናገሩ ካንቺ
ጋር ደግሞ ምን ያገናኘናል ብሎ ተጠሪ በሚጠይቅበት ወቅት ዶ/ር ኢሳቅ በድሪ አለቃህ ናት
በስነ ስርዓት አናግራት ሲለው ተጠሪ ምላሽ ሳይሰጥ ዝም ያለ ሲሆን እንዳውም ከስራ
አባርራሃለው ሲለው ተጠሪ ከፈለክ አባርረኝ በማለቱ እንደጥፋት ተቆጥሮ ወዲያውኑ በቃል
ከስራ በማሰናበት በጥበቃ ከግቢ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ተጠሪ በሌላ ቀን ለክፍያ ጥያቄ በሄደበት
ወቅት በትዕቢትና በንቀት አለቆችን በማነጋገርና በመሳደብ፣ለጥል በመጋበዝና በመዛት የሚል
የስንብት ደብዳቤ ተሰጥቶኛል፡፡የቀረቡት የአመልካች ምስክሮች ጭምር እና ገለልተኛ
ምስክሮች ተጠሪ በቢሮ ውስጥም ሆነ ከቢሮ ውጭ የፈፀመው ፀብና አምባጓሮ እንደሌለ
አረጋግጧል፡፡ስለዚህ የስር ፍ/ቤት ተጠሪ የዲሲፕሊን ጥፋት መፈፀሙ አልተረጋገጠም በማለት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በማለት የሰጠዉ ውሳኔ የህግ ስህተት የለውም፡፡የሰነድ ማስረጃን


በተመለከተ አመልካች ያቀረበዉ ቃለ ጉባኤ ተጠሪ በቃል ከስራ ከተሰበተ በኋላ እና በምን
ምክንያት ውይይት እንደተደረገ፣ በምን ላይ እንደተስማሙ የማይገልፅ እንዲሁም
የተሰበሰቡትም የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሳይሆን ዶ/ር ይስሀቅ የሰበሰባቸዉ ሰዎች በስብሰባ ላይ
የተገኙ የሚል እንጂ ድርጊቱ ስለመፈፀሙ ምስክር ወይም ውሳኔ ሰጪ ነን በማለት የፈረሙት
አይደለም፣ስለዚህ ፍ/ቤቱ ይህንን አመዛዝኖ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው፤የስር ፍ/ቤት የሰውና
የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ተጠሪ ፀብና አምባጓሮ ስለመፈፀሙ አመልካች ያላስረዳ መሆኑን
በማረጋገጥ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት የህግ ምክንያት
ባለመኖሩ አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክሯል፡፡አመልካች አቤቱታውን
የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘበነዉ በአመልካች
እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ አሰሪና ሰራተኛ የስራ ዉል የተቋረጠዉ በአመልካች አነሳሽነት
መሆኑ አልተካደም፡፡ለዚህም በምክንያትነት የተገለጸዉ ተጠሪ በስራ ቦታ ጸብና አምጓሮ
በመፈጸም ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ስንብቱ ህጋዊ ነዉ የሚል መከራከሪያ አቅርቧል፡፡የአሰሪና
ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/1/ረ ላይ እንደተደነገገዉ እንደጥፋቱ ክብደት
በስራ ቦታ ላይ በአምባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ተጠያቂ መሆኑ የተረጋገጠ ሰራተኛ የስራ
ዉሉ በአሰሪዉ አነሳሽነት ሊቋረጥ ይችላል፡፡

አመልካች የተጠሪን የሥራ ዉል ያቋረጠዉ ተጠሪ በስራ ላይ በፈጸመዉ ጥፋት ነዉ በማለት


የተከራከረ በመሆኑ ይህንኑ የማስረዳት ሸክም የአመልካች ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 258-
259 እና የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2001 ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝል፡፡በተያዘዉ ጉዳይ ለስንብቱ
ምክንያት ነዉ የተባለዉ ተጠሪ በስራ ቦታ አምጓሮና ጠብ ፈጥሯል፤እንዲሁም የታካሚ ስነልቦና
የሚጎዳ ንግግር በማድረግ ጥፋት ፈጽሟል የሚል ሲሆን ይህንኑ በማጣራት ረገድ ማስረጃ
የመመርመርና የመመዘን ስልጣን ያላቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች በግራ ቀኙ በኩል የቀረበዉን
ማስረጃ አመዛዝነዉ ተጠሪ የተባለዉን ድርጊት ስለመፈጸሙ አልተረጋገጠም የሚል ድምዳሜ
ላይ ደርሷል፡፡አመልካች አሁንም አጥብቆ የሚከራከረዉ የስር ፍርድ ቤቶች የማስረጃ ምዘና
ስህተት ፈጽመዋል በማለት ነዉ፡፡በሰበር አጣሪ ችሎት የተያዘዉ ጭብጥም የምስክሮች ቃል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ድርጊቱ ስለመፈጸሙ አስረድተዉ እያለ ዉድቅ መደረጉን አግባብነት ለመመርመር የሚል


ነዉ፡፡

በመሰረቱ የሰበር ችሎቱ ስልጣንና ሃላፊነት የመጨረሻ ዉሳኔ በተሰጠባቸዉ ጉዳዮች ላይ


መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ ይህንኑ የማረም እንጂ ፍሬነገር የማጣራት፤ማስረጃ
የመመርመር እና የመመዘን ጉዳይ የሚመለከት አለመሆኑን ከሰበር ስርዓት መሰረታዊ ዓላማ
የምንገነዘበዉ ጉዳይ ነዉ፡፡የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ ይዘትና መንፈስ ይህንኑ
የሚያመለከት ሲሆን ህገ መንግስቱን ተከትሎ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 የሰበር
ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት ማረም የሚመለከት እንደሆነ በጥቅሉ የሚደነግግ ሲሆን
ይህንኑ እና ማሻሻያ አዋጆች የሻረዉ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በሰበር ሊታረም የሚገባ
መሰረታዊ የህግ ስህተት የሚያሰኙት ሁኔታዎች ምንድናቸዉ ለሚለዉ ትርጉም
ሰጥቷል፡፡የአዋጁን አንቀጽ 2/4/ እና 10 ይመለከቷል፡፡አዋጁ በዚህ መልኩ መቀረጹ በዋናነት
ሰበር ሰሚ ችሎት የተቋቋመበትን ዓላማ፤ አንድ ወጥ የህግ አተረጓጎም እንዲኖር እና
የዉሳኔዎችን ተገማችነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችና ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ ጉዳዮች ላይ
ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ የተዘረጋ ስርዓት መሆኑን ነዉ፡፡ስለዚህም ሰበር ችሎቱ ማስረጃ
የመመርመር ስልጣን የሌለዉ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

በሌላ በኩል ሰበር ችሎቱ የማስረጃ ምዘና ጉዳይ የመመርመር ስልጣን የለዉም ሲባል የስር
ፍርድ ቤቶች በክርክር አመራር ረገድ፤በማስረጃ አቀባበል እና ምዘና የሚመለከቱ መሰረታዊ
መርሆዎች አተገባበር ጋር በተያያዘ የፈጸሙትን ስህተት የማረም ሃላፊነትን የሚያስቀር ሊሆን
እንደማይገባ እንገነዘባለን፡፡በፍርዱ ላይ የማስረጃ አቀባበልና ምዘና ስህተት ተፈጽሟል ለማለት
የሚቻለዉ በተከራካሪ ወገኖች የተቆጠረ ማስረጃ ያለበቂ ምክንያት ሳይሰማ ሲታለፍ፣በማስረጃ
አቀባበል ረገድ የተከራካሪ ወገኖች እኩል የመደመጥ መብት አለማከበር፣የማስረዳት ሸክም
የማነዉ የሚለዉን አለመለየት ወይም የማስረጃ ተገቢነት፣ተቀባይነትና ምዘና ረገድ አግባብነት
ያለዉን መርህ ባለመከተል እንዲሁም በመሰረታዊ ህግ ወይም በስነስርዓት እና የማስረጃ ደንብ
ቅቡልነት ያላቸዉን የማስረጃ ህግ መርሆዎችን ባለመጠበቅ የሚሰጡ ዉሳኔዎችን የሚያጠቃልል
ስለመሆኑ ይህ ሰበር ችሎት ከዚህ ቀደም በተለያዩ መዝገቦች ላይ ከሰጠዉ ፍርድ ይዘት
መገንዘብ ይቻላል፡፡በዚህ ረገድ በሰበር መ/ቁ/37105፣29861፣47551፣49660 እና ሌሎች
ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ መመልከት ይቻላል፡፡

የአመልካች አቤቱታ ከዚህ አኳያ ሲታይ በተለይም የድርጅቱ ባለአክስዮን የሆኑት ባልና ሚስት
የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዘት ግነት ይታይበታል መባሉ የፍርድ ቤቱን የማስረጃ ምዘና

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስህተት ያሣያል በማለት ያቀረበዉን ቅሬታ አጽንኦት በመስጠት መርምረናል፡፡ ከማስረጃ


ምዘና ጋር በተያያዘ አንዱ መሰረታዊ መርህ የማስረጃዉ የማስረዳት ብቃት ወይም ክብደት
የመመርመር ጉዳይ ነዉ፡፡አንድን አከራካሪ ፍሬነገር መኖር/አለመኖሩ ወይም
መፈጸም/አለመፈጸሙ የሚረጋገጠዉ የቀረበዉን ማስረጃ ይዘትና ክብደት/weight of evidence/
በማመዛዘን ስለመሆኑ የማስረጃ ደንብ የምያስገነዝበን ጉዳይ ነዉ፡፡የአንድ የማስረጃ ክብደት
ከሚመዘንባቸዉ ሁኔታዎች አንዱ የማስረጃ ሰጪዉ አካል ወይም የምስክሩ ገለልተኝነት እና
ተአማንነት ወይም የማሳመን አቅሙን መመርመር ይጠይቃል፡፡የገለልተኝነት መርህ
የሚያወሳዉ ማስረጃ ሰጪዉ ወገን በአከራካሪዉ ጉዳይ ወይም ዉጤቱ ላይ ያለዉ ፍላጎት
ወይም ጥቅም መኖር/አለመኖር ጋር ተገናዝቦ መመዘን ያለበት ስለመሆኑ ነዉ፡፡የማስረጃ
ተአማንነትም የሚመዘነዉ ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር ያለዉ አንድነት እና ልዩነት እንዲሁም
ከተፈጸመዉ ሁኔታ ወይም ድርጊት ጋር ተነጻጽሮ ነዉ፡፡ከዚህ ሁሉ መገንዘብ የሚቻለዉ
ለማስረጃዉ የሚሰጠዉ ክብደት የሚወሰነዉ ከእነዚህ መመዘኛዎች ድምር ዉጤት አንጻር
ነዉ፡፡በመጨረሻም በፍትሓብሔር ጉዳይ አከራካሪዉ ፍሬነገር መኖር/አለመኖሩ ወይም
መፈጸም/አለመፈጸሙን በሚመለከት ከድምዳሜ የሚደረሰዉ ከተከራካሪዎቹ ጉዳዩን በተሻለ
ደረጃ ``preponderance of evidence``በማስረጃ የትኛዉ ወገን አስረድቷል የሚለዉን
መርምሮና አመዛዝኖ መሆን አለበት፡፡በዚህም ጉዳይ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በስራ ቦታ
አምባጓሮ እና ጠብ ፈጽሟል ወይ? የሚለዉ ጭብጥ ላይ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመመርመር
ሂደት አመልካች ካቀረባቸዉ ምስክሮች ዉስጥ ሁለቱ የድርጅቱ ባለአክስዮን የሆኑት ባልና
ሚስት መሆናቸዉን እና ምስከሮቹ የሰጡት ቃል ከሌሎች ምስክሮች ቃል ጋር በማነጻጸር
ሲመዘን ግነት ይታይበታል ብሎ ከመግለጽ ዉጪ ማስረጃዉ አግባብነት /relevancey/ ወይም
/inadmissibille/ ተቀባይነት የለዉም የሚል አቋም አልወሰደም፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ ፍርድ ቤቱ
ማስረጃ ሲመዝን የምስክሮቹ ቃል ግነት ይታይበታል ማለቱ ብቻዉን የማስረጃ ምዘና መርህ
ጥሰት ፈጽሟል የሚያሰኝ አይደለም፡፡

ሌላዉ የአመልካች የቅሬታ ነጥብ በአመልካች በኩል የቀረበዉ ቃለ ጉባዔ ዋጋ አልተሰጠዉም


የሚል ሲሆን ከዉሳኔዉ እንደተገነዘብነዉ ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ስልጣን ያለዉ
ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ሰነዱን መርምሮ ሰነዱ የተዘጋጀበት ሁኔታ አስተዳደራዊ ዉሳኔ
የተሰጠበት የሚመስል እንጂ የዲስፕሊን ክስ ቀርቦ ተጠሪ ባለበት ተሰምቶና ተጣርቶ ዉሳኔ
የተሰጠበት አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ያረጋገጠዉ ፍሬነገር ጉዳይ ነዉ፡ይህ ከሆነ ደግሞ
ማስረጃዉ ዋጋ አልተሰጠዉም ወይም አልተመረመረም የሚባል ዓይነት አይደለም፡፡ከዚህ ሁሉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መገንዘብ የሚቻለዉ በማስረጃ አቀባበልም ሆነ ምዘና ረገድ በስር ፍርድ ቤቶች ዉሳኔ ላይ
የተፈጸመ ስህተት አለመኖሩን ነዉ፡፡

ሲጠቃለል ተጠሪን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል ጥፋት መፈጸም


አለመፈጸሙን ከማረጋገጥ አኳያ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመመርመርና በማመዛዘን ለስንብት
የሚያበቃ ጥፋት መፈጸሙ አልተረጋገጠም በማለት የስራ ዉሉ የተቋረጠዉ ከህግ ዉጪ ነዉ
በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የደረሰቡት ድምዳሜ ላይ በማስረጃዉ አቀባበል እና ምዘና ረገድ
ቅቡልነት ያላቸዉን መርሆዎች ተከትሎ የተወሰነ ነዉ ከሚባል በስተቀር በኢፌዲሪ ህገ
መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/ 2013 አንቀጽ
2/4/ እና 10 ድንጋጌ መሰረት ለሰበር ችሎቱ ከተሰጠዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም
ስልጣን አንጻር በዉሳኔዉ ሊታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ
የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም፡፡በዚሁ አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ዉሳኔ

1ኛ/በዚህ ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/165191 በቀን


26/04/2013ዓ.ም የሰጠዉን ዉሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት በመ/ቁ/
258122 ላይ በቀን 13/08/2013ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ ጸንቷል፡፡

2ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡

3ኛ/በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 23/09/2013ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትእዛዝ


ተነስቷል፡፡ይጻፍ

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-206765

ቀን፡-30/03/2014ዓ/ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ተጠሪዎች ፡1ኛ/ ገልገሎ ቀጀላ 6ኛ/ ግስላው ይገባዋል

2ኛ/ አዱኛ አድባሩ 7ኛ/ ለገሰ ሰይፉ

3ኛ/ አንተነህ ነገሰ 8ኛ/ ንጉስ ሰይፉ

4ኛ/ በሪሁን ጌታቸው 9ኛ/ ታምር ሲሳይ

5ኛ/ ገብሬ ሰለሞን

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም ክፍያ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል
በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ
አመልካች ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ፡፡ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አመልካች ከአዋሽ-

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ ድረስ በሚያከናውነው የባቡር መንገድ ስራ ጊራና ሳይት ላይ ተቀጥረን


ሲንሰራ የቆየን ሲሆን ያልተከፈለን የትርፍ ሰዓት፣ የሳምንት እረፍት፣ የህዝብ በዓላት ቀን ክፍያ
እና የአልጋ አበል እንዲከፈለን ይወሰንልን የሚል ሲሆን አመልካች በበኩሉ የክፍያ ጥያቄ
በይርጋ ይታገዳል፣ተጠሪዎች እነዚህ ክፍያዎች የሚገባቸው መሆኑን በማስረጃ
አላረጋገጡም፣ትርፍ ሰዓት ስራ እንዲሰሩ አሰሪው ግልፅ ትዕዛዝ አልሰጠም፣የትርፍ ሰዓት
መስራታቸዉ አልተመዘገበም፣ 9ኛው ተጠሪ የድርጅቱ ሰራተኛ አይደለም፣ የአልጋ አበል
ለመክፈል አመልካች የገባው የውል ግዴታ የለም፣ለመክፈል አይገደድም በማለት ክሱ ውድቅ
እንዲደረግ መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክርና የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ሁሉም ተጠሪዎች የአመልካች


ድርጅት ሰራተኞች ናቸው በማለት አመልካች ለሰራተኞቹ የደህንነት መጠበቂያ የሆኑ ሄልሜት
እና አንፀባራቂ ጃኬት እና ሌሎች ከስራ ጋር የተያያዙ የደህንነት መጠበቂያዎች ለተጠሪዎች
እንዲያሟላ እና የተጠየቀው የትርፍ ሰዓት፣የሳምንት እረፍት፣የህዝብ በዓል እና የአልጋ አበል
ክፍያ በአጠቃላይ ብር 521,845 እና 10% የጠበቃ አበል ጋር ለተጠሪዎች ሊከፍል ይገባል
በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን
ፍ/ቤቱም ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት መዝገቡን መርምሮ የተጠየቁ ክፍያዎች መክፈል ይገባል
የተባለው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በማጽናት የክፍያውን መጠን በተመለከተ የአልጋ አበል
ለእያንዳንዳቸው ብር 18,000 ይክፈላቸው፤የትርፍ ሰዓት፣የሳምንት እረፍት፣የህዝብ በዓል እና
የአልጋ አበል ክፍያ በአጠቃላይ ብር 303,449.21 እና የጠበቃ አበል 4% ብር 12,137.96
ይከፈል ሲል የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በማሻሻል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ
ያቀረበ ሲሆን ችሎቱ የግራ ቀኝ ክርክር እና መዝገቡን መርምሮ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ
የህግ ስህተት የለበትም በማለት አጽንቷል፡፡

ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ፡፡የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘት
ባጭሩ ሲታይ፤8ኛ ተጠሪ ንጉሰ ሰይፉ የሚባል የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ ያልሆነ በፔሮል
ላይም ነገሰ ሰይፉ እንጂ ንጉሰ ሰይፉ የሚባል እንደሌለ፣የጠበቃ ውል ላይም ንጉሰ ሰይፉ
የሚባል ውክልና እንዳልሰጠ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጦ እያለ የስር ፍ/ቤት የድርጅቱ ሰራተኛ ነው
በማለት ክፍያ እንዲፈፀምለት መወሰኑ ስህተት ነው፡፡የአልጋ አበል በተመለከተ የቅጥር ውል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሲፈፀም የአልጋ አበል ለመክፈል አመልካች ግዴታ ባልገባበት ሁኔታ እና ተጠሪዎችም


በምስክሮች የአልጋ አበል ለመክፈል አመልካች ግዴታ መግባቱን ያላስረዱ እና የአመልካች
ምስክሮችም የአልጋ አበል ለመክፈል እንዳልተስማሙ፤ በሌሎች ሳይትም ቢሆን ከ2009 ዓ.ም
ጀምሮ የአልጋ አበል ተከፍሎ እንደማያውቅ አረጋግጠው እያለ የስር ፍ/ቤቶች ድርጅቱ
በሌሎች ሳይት ላይ ለሌሎች ሰራተኞት ይከፍል ከነበረ ተጠሪዎች የሚሰሩበት ሳይት ላይም
የማይከፍልበት ምክንያት የለም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡የትርፍ
ሰዓት ክፍያ፣ የሳምንት እረፍት፣የበዓል ቀናት እንዲከፈል የተወሰነው አግባብ አይደለም
ምክንያቱም ስራዎች እንዲሰሩ አመልካች ግልጽ ትዕዛዝ ያልሰጠ እና ስለመሰራቱ በአመልካች
ያልተመዘገበ በመሆኑ ክፍያዎቹ ሊከፈል አይገባም ተብሎ እንዲወሰን በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ የአልጋ አበልን በተመለከተ የክልሉ
ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ.0329295 እና 0326934 አይከፈልም ብሎ ከወሰነ በኋላ በዚህ መዝገብ
ላይ እንዲከፈል መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ከሰበር መ/ቁ.200544 ጋር ለማጣራት ጉዳዩ
ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት ታዟል፡፡

ተጠሪዎች ባቀረቡት መልስ እነዚህ የተለያዩ ናቸው የተባሉ ውሳኔዎች የተወሰኑት በተለያየ
ችሎት ከመሆኑም በላይ በተመሳሳይ ጉዳዮች በሌሎች ችሎቶች የተወሰኑ በመሆኑ ጉዳዩ አንድ
ሆኖ ባልተጣመረበት ሁኔታ ጠቅላይ ፍ/ቤት ስህተት ፈፅሟል የሚያስብል አይደለም፡፡ሌላው
ቀርቶ በአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 0326934 ላይ የሳምንት እና የህዝብ በዓላት ክፍያ
መወሰኑን ተከትሎ ለፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ቀርቦ አያስቀርብም ተብሎ ብይን
ሲሰጥ፣የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት መ/ቁ.0329295 ላይ የሰጠዉን ዉሳኔ የፌዴራል ሰበር ሰሚ
ችሎት የትርፍ ሰዓት ብቻ አጽድቆ የሳምንት ዕረፍት እና የህዝብ በዓላት ክፍያን ውድቅ
አድርጓል፡፡ስለዚህ ጉዳዩ እልባት ያገኘው በተለያየ ዳኞች እና በተለያየ ችሎቶች ከመሆኑም
በላይ ሰራተኞች ከተቀጠሩባቸው ውሎች አኳያ ልዩነት ያላቸውና በተናጠል መታየት ያለባቸው
እንጂ በአንድ መዝገብ ላይ የተሰጠ ውሳኔ አንድ መሆን አለመሆኑ ሳይረጋገጥ ልዩነት በመኖሩ
ብቻ የህግ ስህተት ተፈጽሟል አያስብልም በማለት የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ስህተት የለበትም
የሚል ክርክር አቅርበዋል፡፡አመልካች አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርቦ
ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ ጉዳዩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሰራተኞች የጠየቁት ልዩ ልዩ ከፍያ ይገባቸዋል ተብሎ የተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ


ስህተት ተፈጽሟል የሚያሰኝ ምክንያት መኖር አለመኖሩ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ነዉ፡፡

ከክርከሩ እንደሚያሳዉ ተጠሪዎች የጠየቁት ክፍያ የትርፍ ሰዓት፣የበዓላትና የሳምንት የእረፍት


ቀናት የሰሩበት በተጨማሪነትም የአልጋ አበል ታስቦ እንዲከፈላቸዉ ነዉ፡፡አመልካች አጥብቆ
የሚከራከረዉ እነዚህ ከፍያዎች ለመክፈል የሚያስችል የሥራ ትእዛዝ አልሰጠሁም፤የዉል
ግዴታም የለም በማለት ነዉ፡፡በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ እንደተመለከተዉ የትርፍ
ሰዓት፤የሳምንት የእረፍት ቀናት እና የበዓል ቀናት ስራ ለመስራት ሰራተኛዉ የሚገደደዉ በህግ
በተመለከቱ ዉስን ምክንያቶች ስለመሆኑና በአሰሪዉ ትእዛዝ መሰጠቱ መረጋገጥ እንዳለበት
ህጉ ያስገነዝባል፡፡አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 66-72ያሉት ድንጋጌዎች
ይመለከታል፡፡ከዚህ መገንዘብ እንደሚቻለዉ ሰራተኛዉም እነዚህን ክፍያዎች ሊጠይቅ
የሚችለዉ እና አሰሪዉም ከፍያዉን ለመክፈል የሚገደደዉ ስራዉ በአሰሪዉ እዉቅና እና
በተሰጠዉ የስራ ትእዛዝ መሰረት መስራቱን ሰራተኛዉ ማስረዳት ከቻለ ነዉ፡፡የትርፍ
ሰኣት፣የበዓል ቀናትና የሳምንት እረፍት ጊዜ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች በባህርያቸዉ ሰራተኛዉ
እንደመብት የሚጠይቀዉ ሳይሆን ለስራዉ መልካም አካሄድ አስፈላጊ መሆኑ በአሰሪዉ
ታምኖበት ትእዛዝ ሲሰጥ እና ሰራተኛዉም ተስማምቶ በተሰጠዉ ትእዛዝ መሰረት መስራቱ
ሲረጋገጥ የሚፈጸም መሆኑ ነዉ፡፡በተያዘዉ ጉዳይ እነዚህን ክፍያዎች አመልካች ሊከፍል
ይገደዳል ወይ የሚለዉን ጭብጥ የመረመሩት የስር ፍርድ ቤቶች የግራ ቀኙን ክርክርና
ማስረጃ መርምረዉ ተጠሪዎች የትርፍ ሰዓት፣የበዓል ቀናት እና የሳምንት የእረፍት ቀናት
ጨምረዉ መስራታቸዉንና ይህም የሆነዉ አሰሪዉ በቅርብ አለቃቸዉ በተሰጣቸዉ ትእዛዝ
መሰረት መሆኑን በማረጋገጥ ነዉ፡፡ይህ የማስረጃ ምዘና ዉጤት የሆነዉን የፍሬ ነገር ጉዳይ
ይህ ችሎት የማይቀበልበት ምክንያት የለዉም፡፡ሌላዉ አከራካሪ ጉዳይ የአልጋ አበል
የሚመለከት ሲሆን በዚህም ረገድ የስር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ሰምቶና አመዛዝኖ
የአልጋ አበል ለመክፍል በቃል ስምምነት ስለመደረጉ እና በተመሳሳይ ሳይት በተለይም
የካምፕ ፋሲሊቲ በሌለባቸዉ ሳይቶች ላይ የአልጋ አበል ሲከፈላቸዉ እንደነበር በማረጋገጥ
ክፍያዉ እንደሚገባቸዉ ከድምዳሜ ደርሷል፡፡አመልካች አሁንም አጥብቆ የሚከራከረዉ የስር
ፍርድ ቤቶች የማስረጃ ምዝና ስህተት ፈጽመዋል በማለት ቢሆንም ሰበር ችሎቱ የማስረጃ
ምዘና ጉዳይ ለመመርመር የሚያስችል የህግ መሰረት የለዉም፡፡ይልቁንም በስር ፍርድ ቤቶች
ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን ብቻ በመመርመር እና በማረም ላይ የተገደበ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስለመሆኑ ከኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና ከአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ


2/4/ እና 10 ይዘት የምንገነዘበዉ ጉዳይ ነዉ፡፡

ይሁንና ሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀረበዉ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት
በተመሳሳይ ክርክር በሌሎች መዝገቦች ላይ ክፍያዎቹ ለሰራተኞች እንዳማይከፈል ከሰጠዉ
ዉሳኔ ጋር እንዲሁም በዚህ ችሎት ቀጠሮ ላይ ካለዉ ሰበር መ/ቁ/200544 ጋር ለማየትና
ለማገናዘብ በሚል ሲሆን ከላይ እንደተጠቀሰዉ እነዚህ ክፍያዎች ለሰራተኛዉ ሊከፈል ይገባል
ወይስ አይገባም የሚለዉ የሚወሰነዉ እንደክርክሩ አቀራረብ እና ክርክሩን ለማስረዳት የቀረበዉ
ማስረጃ ተመርምሮና ተመዝኖ የሚወሰን የፍሬነገር ጉዳይ እንጂ የህግ ትርጉም ጉዳይ ባለመሆኑ
በአንድ መዝገብ ላይ የተሰጠዉ ዉሳኔ በሌላ መዝገብ ላይም ተፈጻሚነት አለዉ ተብሎ
በአስገዳጅነት የሚወሰድ ሊሆን አይችልም፡፡በሌላ አገላለጽ የትርፍ ሰዓት፣የእረፍት እና የበዓል
ቀናት የሚከፈለዉ ስራዉ መሰራቱ ሲረጋገጥ እንደመሆኑ ስራ ተሰርቷል ወይስ አልተሰራም
የሚለዉ የፍሬነገር ጭብጥ እንጂ የህግ ጭብጥ ባለመሆኑ ክርክሩ የሚወሰነዉ በመዝገቡ ላይ
የቀረበዉን ማስረጃ ብቃትና ክብደት ተመዝኖ እንጂ ቀድሞ በሌላ የሥራ ክርክር ተደርጎ
የተሰጠዉን ዉሳኔ በመከተል አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ይህንን የፍሬነገር ጉዳይ
ከማረጋገጥ አንጻር ማስረጃ የመመርመርና የመመዘን ስልጣን በህግ የተሰጣቸዉ የሥር ፍርድ
ዉሳኔ ላይ የተፈጸመ የማስረጃ አቀባበልም ሆነ ምዘና መርህ ጥሰት አልተገኘም፡፡

ሲጠቃለል ተጠሪዎች ትርፍ ሰዓት፣በበዓል ቀንና በሳምንት የእረፍት ቀናት ስራ እንዲሰሩ


ታዘዋል ወይስ አልታዘዙም? ስራ ሰርተዋል ወይስ አልሰሩም ሰርተዋል ከተባለ ምን ያህል
የሚለዉንና የክፍያ መጠን እንዲሁም የአልጋ አበል ሊከፈላቸዉ ይገባል ወይ የሚሉትን
የፍሬነገር ጭብጦች መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤቶቹ የቀረበላቸዉን ማስረጃ አመዛዝነዉ ዉሳኔ
የሰጡበት መሆኑን ተገንዝበናል፡፡በመሆኑም በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/4/ እና 10 ድንጋጌ መሰረት
ለሰበር ችሎቱ ከተሰጠዉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን አንጻር በዉሳኔዉ ሊታረም
የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ የሚባልበት ምክንያት አላገኘንም፡፡በዚሁ
አግባብ ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ዉሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

1ኛ/የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን ዉሳኔ
በማጽናት በመ/ቁ/0328396 ላይ በቀን 27/05/2013ዓ.ም የሰጠዉ ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ
ቁ.348/1/መሰረት ጸንቷል፡፡

2ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡

3ኛ/በዚህ መዝገብ ላይ በቀን 13/09/2013ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትእዛዝ


ተነስቷል፡፡ይጻፍ

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-206828

ቀን፡-27/03/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ ሰለሞን አረዳ

እትመት አሰፋ

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡ ወ/ሮ ሀለዊያ አብዱጀባር-ጠበቃ አቶ አውግቸው መኮንን ቀርበዋል

ተጠሪዎች፡ 1. ሂላል አበዱጀባር የቀረበ የለም

2. ካሊድ አበዱጀባር

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የአፈፃፀም ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/01-21392 ላይ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም
በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ያፀናበትን የመጨረሻ ትዕዛዝ በመቃወም ነው፡፡

ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ የአሁን አመልካች ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የአፈፃፀም
አቤቱታ ቀደም ሲል ከአሁን ተጠሪዎች ጋር በዚያው ፍርድ ቤት በነበራቸው ክርክር ለክሱ ምክንያት
ከሆነው ቤትና ይዞታ ላይ ለአሁን ተጠሪዎች እናት በፍርድ ቤቱ በፀደቀው ስምምነት ላይ ከተጠቀሰው
ውጭ ባለው ቤት እና ይዞታ ላይ በስማቸው ካርታ እና ፕላን እንዲሰራላቸው ለክፍሉ ይዞታ አስተዳደር
ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ይህንኑ የአፈፃፀም አቤቱታ አስመልክቶ በአሁን ተጠሪዎች በኩል
ምን መከራከሪያ እንደቀረበ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡ በሌላ በኩል በዚህ የሰበር ሰሚ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ችሎት ክርክር ተካፋይ ያልሆኑት አቶ አህመድ መሃመድ የተባሉት ግለሰብ የአፈፃፀም አቤቱታ
የቀረበበት ቤት እና ይዞታ የአሁን ተጠሪዎች እና የራሳቸው አውራሽ የጋራ የውርስ ሀብት መሆኑን
ጠቅሰው የአፈፃፀም አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህግ ቁጥር 418 መሰረት አፈፃፀሙን
በመቃወም ይቀርባሉ፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የአፈፃፀም አቤቱታው የቀረበው ፍርድ ባረፈበት ንብረት ላይ ነው?
ወይስ አይደለም?፤ የአፈፃፀም መቃወሚያውስ የቀረበው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚሉትን
ነጥቦች በመያዝ ጉዳዩን መርምሯል፡፡ በውጤቱም በአሁን አመልካች እና ተጠሪዎች መካከል ቀደም
ሲል የነበረው ክርክር በግራ ቀኙ ስምምነት ሲቋጭ ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ በፀደቀው ስምምነት ላይ ክሰ
ከቀረበበት ይዞታ ውስጥ ከይዞታው መግቢያ በር በስተቀኝ በኩል ካለው በምዕራብ ጌቱ ዮሐንስ፣ በሰሜን
ዋና መንገድ፣ በደቡብ አፈወርቅ፣ በምስራቅ ሀወሊያ አብዱጀባር የሚዋሰነውን በአጠቃላይ በ689 ካሬ
ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ የቤት ቁጥር 400.02፣ 4 ክፍል ሰርቪስ ቤት እና በፊት ለፊት ያለውን አንድ
ትልቅ መጋዘን በውስጡ ስምንት ክፍል ያሉትን ጨምሮ የአሁን ተጠሪዎች እናት ለሆኑት ወ/ሮ ዘምዘም
መሃመድ ለተባሉት ሰጥቻለሁ ከማለት ባለፈ የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበበት ቤት እና ይዞታ የአመልካች
ስለመሆኑ የእርቅ ስምምነቱም ሆነ ስምምነቱ የፀደቀበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አያሳይም፤ በእርቅ
ስምምነቱ ወይም ስምምነቱ በፀደቀበት የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ ያልተመለከተ ንብረት ፍርድ ቤት
በአፈፃፀም ሊያስገድድ የሚችልበት አግባብ ባለመኖሩ የአፈፃፀም አቤቱታው ውሳኔ ባላረፈበት ንብረት
ላይ የቀረበ ነው፤ ለአፈፃፀም ተብሎ የታገደ/የተያዘ/ ንብረት በሌለበት የአፈፃፀም መቃወሚያ መቅረቡም
አግባብ አይደለም በማለት የሁለቱንም አቤቱታዎች ውድቅ አድርጓል፡፡ በዚሁ ውሳኔ ላይ ይግባኝ
የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 337 መሰረት ይግባኙን ዘግቷል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች ሚያዝያ 28/2013 ዓ.ም
በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ ላይ ተፈፅሟል ያሉትን መሰረታዊ የህግ ስህተት
ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በስር
ፍርድ ቤት የተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/0121227 ላይ
ህዳር 16/2009 ዓ.ም የመዘገበውን የግልግል ስምምነት ያገናዘበ መሆን አለመሆኑን ለዚህ ችሎት ቀርቦ
እንዲመረመር በመደረጉ ተጠሪዎች የፅሁፍ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት ተጠሪዎች ሰኔ 30/2013 ዓ.ም የተፃፈ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል፡፡
ፍሬ ቃሉም ቀደም ሲል ከአመልካች ጋር በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/0121227 ላይ የነበራቸው
ክርክር በግራ ቀኙ መካከል ህዳር 16/2009 ዓ.ም በተደረገ ስምምነት መሰረት ስምምነቱ በፍርድ ቤቱ
ፀድቆ መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ የአሁን አመልካች አሁን የአፈፃፀም አቤቱታ ባቀረቡበት ንብረት ላይ
የካቲት 05/2011 ዓ.ም ክስ አቅርበው ክሳቸው ውድቅ ተደርጎ እስከ ፌዴራል ጠቅላፍ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት ድረስ ክርክር ተደርጎበት በመ/ቁ/170628 ላይ መስከረም 28/2012 ዓ.ም የፀና በመሆኑ ክሱ
ድጋሚ የቀረበ ነው፤ የአፈፃፀም አቤቱታውም በፍርድ ቤት ውሳኔ ያጡትን መብት በእቅር ስምምነት
ሽፋን በአቋራጭ ለመጎናፀፍ የቀረበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤ የአፈፃፀም አቤቱታ በቀረበበት
ንብረት ላይም በፍርድ ቤት የተሰጠ ግልፅ ውሳኔ ባለመኖሩ አቤቱታቸው ውድቅ መደረጉ በአግባቡ ነው
የሚል ነው፡፡ አመልካች በዚሁ ላይ የሚያቀርቡት የመልስ መልስ ካለ እንዲያቀርቡ እድል ቢሰጣቸውም
በተያዘላቸው ቀነ ቀጠሮ ያላቀረቡ በመሆኑ ይኸው መብታቸው ታልፏል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና መሰረታዊ የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም የግራ
ቀኙን ክርክር ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አኳያ አግባብነት ካለው ህግ ጋር
በማገናዘብ መርምሯል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመሰረቱ በፍርድ በተረጋገጠ መብት መሰረት የአፈፃፀም አቤቱታ የሚቀርበውም ሆነ በአቤቱታው


መሰረት እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሚሰጠው ለአፈፃፀም አቤቱታው መሰረት በሆነው ፍርድ ላይ በግልፅ
ፍርድ ባረፈበት ጉዳይ ላይ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 378 ይደነግጋል፡፡ አሁን በቀረበው
ጉዳይ ለአመልካች የአፈፃፀም አቤቱታ መሰረት የሆነው በግራ ቀኙ መካል ህዳር 16/2009 ዓ.ም ተደርጎ
በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/121227 ላይ የፀደቀው የእቅር ስምምነት ነው፡፡ ለእርቅ
ስምምነቱ ምክንያት በሆነው የፍርድ ቤት ክርክር ላይ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ እና
የአሁን አመልካች ደግሞ ጣልቃ ገብ የነበሩ መሆኑን፤ የእርቅ ስምምነቱም ክስ ቀረቦበት ከነበረው
ይዞታ ላይ የአሁን አመልካች ከይዞታው መግቢያ በር ወደ ቀኝ ያለውን በአጠቃላይ 689 ካሬ ሜትር
ይዞታ በላዩ ላይ ካለው ቤት ጋር ለአሁን ተጠሪዎች ወላጅ እናት ለሆኑት ወ/ሮ ዘምዘም መሃመድ
የሰጧቸው መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ይዘት እና አጣሪ ችሎት አስቀርቦ ከመዝገብ ካያያዘው
የእርቅ ስምምነት ሰነዱ ይዘት ለመረዳት ተችሏል፡፡ ስምምነቱ በዚህ መልኩ ለተጠሪዎች እናት
የተሰጠውን ይዞታ እና ቤት ከመግለፅ ባለፈ ክስ ከቀረበበት ይዞታ ላይ በስምምነቱ ውስጥ ሳይጠቀስ
ስለቀረው ይዞታ እና ቤት የሚገልፀው ነገር የለም፡፡ በሌላ አገላለፅ ከስምምነቱ ውጭ ያለው ይዞታ እና
ቤት የአሁን አመልካች ነው በሚል የተደረገ ስምምነትም ሆነ በፍርድ ቤት የተሰጠ ውሳኔ የለም፡፡

በሌላ በኩል ይኸው ችሎት ተጠሪዎች በመልሳቸው ውስጥ የጠቀሱትንና በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁ/170628 ላይ ተሰጥቷል የተባለውን መዝገብ አስቀርቦ ተመልክቷል፡፡ በመዝገቡ ላይ አመልካች
የነበሩት የአሁን አመልካች እራሳችው ናቸው፡፡ ተጠሪዎች ደግሞ የአሁን ሁለቱ ተጠሪዎች እና ሌላ
አቶ አህመድ መሃመድ የተባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ በመዝገቡ ላይ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ
የነበረው ክርክር የተጀመረው የአሁን አመልካች በአሁን በተጠሪዎች ላይ በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ
ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ነው፡፡ የክሱም ጭብጥ በፍርድ ቤት ቀርቦ ከፀደቀው የእርቅ ስምምነት ውጭ
ያለውን ይዞታ እና ቤት እንዲያስተዳድርላቸው ለአሁን 1ኛ ተጠሪ ውክልና ሰጥተው የውክልና ስልጣኑን
ከሻሩት በኋላ ተጠሪው ይዞታ እና ቤቱን ሊያስረክባቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን ጠቅሶ በፍርድ ኃይል
ተገዶ እንዲያስረክባቸው ዳኝነት የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህ መልኩ በቀረበው ክስ ላይ የግራ ቀኙ ክርክር
እና ማስረጃ ከተሰማ በኋላ የአሁን አመልካች ክስ ካቀረቡበት ይዞታ እና ቤት ላይ መብት የላቸውም
በሚል ክሱ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ይኸው ውሳኔ በየደረጃው ባሉት የበታች ፍርድ ቤቶች ክርክር
ሲደረግበት ቆይቶ በዚሁ ችሎት በመ/ቁ/170628 ላይ መስከረም 28/2012 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ
ፀድቋል፡፡

የአሁን አመልካች ለአሁኑ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነው የአፈፃፀም አቤቱታ ያቀረቡት ከዚሁ በኋላ
ነው፡፡ የአፈፃፀም አቤቱታው መነሻም ከእርቅ ስምምነቱ ውጭ ባለው ቤት እና ይዞታ ላይ በስማቸው
ካርታ እና ፕላን እንዲሰራላቸው ለክፍሉ አስተዳደር ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ዳኝነት የሚጠይቅ ነው፡፡
ሆኖም የአፈፃፀም አቤቱታ የቀረበበት ይዞታ እና ቤት የአመልካች ነው በሚል በእቅር ስምምነቱም ሆነ
ስምምነቱ በፀደቀበት የፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ የተገለፀ ነገር የለም፡፡ እንዲያውም አመልካች የአፈፃፀም
አቤቱታ ባቀረቡበት ንብረት ላይ የይገባኛል ክስ አቅርበው ከይዞታ እና ቤቱ ላይ መብት የላቸውም
በሚል በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ጭምር ተወስኗል፡፡ ጉዳዩ ይህ ሆኖ እያለ አመልካች በግልፅ ፍርድ
ያላረፈበትን ብቻ ሳይሆን በፍርድ ቤት ውሳኔ ጭምር አይገባቸውም ተብሎ ውሳኔ በተሰጠበት ንብረት
ላይ የአፈፃፀም አቤቱታ ማቅረባቸው ከህግ አግባብ ውጭ ነው፡፡ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ
በየደረጃው ያሉት ፍርድ ቤቶችም የአፈፃፀም አቤቱታው የቀረበው ፍርድ ባላረፈበት ንብረት ላይ ነው
በሚል ውድቅ ማድረጋቸው በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም፡፡
በመሆኑም የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/0121227 ላይ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም


ተሰጥቶ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ/01-21392 ላይ ሚያዝያ 07/2013
በተሰጠ ትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

ትዕዛዝ

1. የዚህን ሰበር ሰሚ ችሎት ክርክር ወጪ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡


2. በዚህ መዝገብ ላይ የተሰጠ የእግድ ትዕዛዝ ካለ ተነስቷል፡፡ ይፃፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-206988
ቀን፡-29/03/2014ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ


ፀሐይ መንክር
ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ወ/ሮ ዱሬቲ ረያድ -አልቀረቡም

ተጠሪ፡- አቶ መሐመድ ቱኬ- ቀርበዋል

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመዝገብ ቁጥር 335988 መጋቢት 6ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት ጉዳዩን በየደረጃው የተመረመሩት
የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔና ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈፀመበትም ሲል የሰጠው
ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው አመልካች በመጠየቃቸው
ነው፡፡ በምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጀመረው የአፈፃፀም ክርክር የአሁን አመልካች የወ/ሮ
ትግስት ግርማ ወራሾች ሞግዚት ሆነው የአፈፃፀም ክርክር ጣልቃ ገብ፣ የአሁን ተጠሪ የፍርድ ባለመብት፣
አቶ ሪያድ መሐመድ (የአመልካች አባት) የፍርድ ባለዕዳ፣ ሀዋስ ሀጅ ሁሴን(የአቶ ሪያድ መሀመድ ባለቤት)
ደግሞ ሁለተኛ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

የፍርድ ባለመብት የሆኑት ተጠሪ የፍርድ ባለዕዳው 1,785,000.00ብር እንዲከፍለው የተወሰነበትን ፍርድ
ለማስፈፀም በሻሸመኔ ከተማ የሚገኙ ሁለት ቤቶች የፍርድ ባለዕዳው ንብረት ናቸው ተብለው ቤቶችን
ለመሸጥ ጨረታ ሲወጣ ከእነዚህ ቤቶች መካከል በ350 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ቤት የሟች እናታቸው
የወ/ሮ ትዕግስት ግርማ ድርሻ ያለበት እና የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት አባታቸው ድርሻቸውን ለእነሱ
ያስተላለፈላቸው መሆኑን በመዘርዘር ጨረታው እንዲሰረዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 418 መሰረት አመልካች
መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ ሁለተኛ ጣልቃ ገብ ደግሞ በዚሁ ከተማ በ180 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራው ቤት
ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዲውል ለመሸጥ ጨረታ መውጣቱን በመቃወም አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

ተጠሪ በበኩሉ አመልካች መቃወሚያ ባቀረበቡት ንብረት ላይ የፍርድ ባለዕዳው በሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት
ድርሻውን ካስከበረ በኋላ ድርሻውን ለልጆቸ ሰጥቻለሁ ሲል መቅረቡ ሆን ብሎ የፍርድ ባለመብቱን ጥቅም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለመጉዳት አስቦ መሆኑንና ድርሻ ማስተላለፉም እውነትነት የሌለው የሕጉን ስርዓት ያልተከተለ መሆኑን
በመዘርዘር በአንፃሩ አመልካቾች በውርስ ያገኑትን ድርሻ በፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዲውል አልጠየቅሁም
ሲል ተከራካሯል፡፡

የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር የፍርድ ባለዕዳው በ350 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ በተሰራው ቤት ላይ
የባለቤትነት መብት አለው ወይስ የለውም? ድርሻውንስ ለወ/ሮ ትግስት ግርማ ወራሾች አስተላልፏል ወይስ
አላስተላለፈም? የሚለውን ጭብጥ ይዞ ከመረመረ በኋላ አመልካች ለፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዲውል
ጨረታ በወጣበት በ350 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ የተሰራውን ቤት የፍርድ ባለዕዳውና የአመልካቾች አውራሽ
በጋራ ያፈሩት መሆኑን፣ አመልካች የፍርድ ባለዕዳው ሌላ ቤት ወስዶ ለክርክሩ ምክንያት ከሆነው ቤት ላይ
ያለውን ድርሻ ሰጥቶናል ቢሉም በሕጉ መስፈርት መሰረት ስጦታ ወይም ኑዛዜ የተደረገ ስለመሆኑ
የሚያረጋግጥ ማሰረጃ አለማቅረባቸውን ይልቁንም የፍርድ ባለዕዳው ከፍርድ ባለመብቱ ገንዘብ ከወሰደ በኋላ
ንብረቱን ለማሸሽ የተጠቀመበት መላ ነው ሲል በውርስ ያገኙትን የ50% ድርሻ አስጠብቄ የፍርድ ባለዕዳው
ድርሻም ከፍርድ ማስፈፀሚያነት እንዲወጣላቸው አመልካቾች ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡ ይህ
ብይን በየደረጃው በሚገኙት የክልሉ ፍርድ ቤቶች ስለፀና ይህን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

አመልካች ግንቦት 9ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታው በጥቅሉ የፍርድ ባለዕዳ የሆኑት አቶ ሪያድ
መሀመድ ለክርክሩ ምክንያት ከሆነውን ቤት ላይ ያላቸውን ድርሻ ጥቅምት 18ቀን 2012ዓ/ም ለአመልካቾች
ማስተላለፋቸው በመዝብ ቁጥር 10639 የተሰጠው ውሣኔ ቀርቦ በተረጋገጠበትና ይህ ውሳኔ ባልተሸረበት
የስጦታ መስፈርቱ የሕጉን መስፈርት አላሟላም ተበሎ የአመልካቾች አቤቱታ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ
የሕግ ስህተት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው ተከራክረዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ለፍርድ ማስፈፀሚያነት የተከበረው ቤት ከክርክሩ በፊት ድርሻዬ ተላፎልኛል
ውድቅ የመደረጉን አግባብነት እንዲመረምር ታዞ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፅሁፍ ተለዋውጠዋል፡፡

ተጠሪ በበኩላቸው ጥቅምት 10ቀን 2014ዓ/ም በተፃፈ መልሣቸው የሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት መዝገብ
ቁጥር 19639 አመልካች የሟች እናታቸው ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የወሰዱበት እንጅ
የንብረት ስጦታ የተላለፈበት መዝገብ አለመሆኑን ለፍርድ አፈፃፀም ክርክሩ መቅረብ ምክንያት የሆነውን ቼክ
የተፃፈበት ቀን የአፃፃፍ ስህተት መሆኑን በቤቱ ላይ ያለው ድርሻ ተላልፏል የተባለበት አኳኋን የሕግ
መስፈርቱን የማያሟላ ውሉም ያለቀረበ መሆኑን በመዘርዘር አቤቱታው ውድቅ እንዲደረግ ተከራካሯል፡፡
አመልካች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ክርክሩ ተጠናቋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዳዩን አመጣጥና የግራ ቀኙን ክርክር ሲሆን የስር ፍርድ ቤት
የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ በማድረጉ የፈፀመው መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን በሚመለከት

ለመወሰን የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው አመልካች ለፍርዱ ማስፈፀሚያነት ከተጠቆሙት ቤቶች መካከል በ350 ካሬ ሜትር ላይ


የተሰራው ቤት ግማሽ ድርሻ ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ግማሹን ደግሞ አባታቸው በመዝገብ ቁጥር
10639 ላይ አስመዝግቦ ያስተላለፈላቸው በመሆኑ በጥቅሉ ቤቱ የፍርድ ባለዕዳው ሣይሆን የአመልካቾች
በመሆኑ እንዲሸጥ የወጣው ጨረታ እንዲሰረዝላቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁጥር 418 መሰረት አመልከተዋል፡፡
የአሁን ተጠሪ በበኩላቸው የፍርድ ባለዕዳው ፍርዱን ላለመፈፀም ንብረት እያሸሸ መሆኑን ይልቁንም የፍርድ
ባለዕዳው በሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት ሚያዚያ 18ቀን 2001ዓ/ም በቤቱ ላይ ግማሽ ድርሻ እንዳለው ካስወሰነ
በኋላ እንዲሁም የፍርድ ባለመብቱ በፍርድ ባለዕዳው ላይ የባለዕዳነት ውሳኔ ካሰጠበት በኋላ ለልጀቸ
አስተላለፊያሉ ማለቱ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተካደ ፍሬ ነገርን በማስረጃ አጣርቶ እንዲወስን የዳኝኘት ስልጣን የተሰጠው የስር ከፍተኛው ፍርድ ቤት
አመልካቾች የፍርድ ባለዕዳው ድርሻውን በጥቅምት 18ቀን 2013ዓ/ም አስተላልፎልናል ከሚሉ በስተቀር
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 881 እና 2443 ድንጋጌ በግልፅ ኑዛዜ ወይም በስጦታ ባለሃብትነቱ ተልልፎ ስልጣን ባለው
የመንግስት አካል ፊት መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላቀረቡም ሲል ውድቅ አድርጓል፡፡ አመልካች
አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት የሆነ ሰው የባለሀብትነት መብቱን በሚያስተላልፍበት ጊዜ ሊያሟላ
የሚገበው የሕጉን መስፈርት በማሟላት (በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2443 እና 1723) የተላፈላቸው ስለመሆኑ
የሚቀርቡት ክርክር የለም፡፡

በሌላ በኩል የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በኢ.ፌ.ደ.ሪ ሕግ መንግስት አንቀፅ 80(3)
የተሰጠው የዳኝነት ስልጣን የመጨረሻ ውሣኔ ባገኙ ጉዳዮች የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተትን ማረም
እንጅ የተካደ ፍሬ ነገርን በማስረጃ እንዲያጣራና እንዲወስን አይደለም፡፡ በመሆኑም አመልካች በስር ፍርድ
ቤቶች የተጠቀሰውን ማስረጃ ስለማቅረባቸው በማይከራከሩበት ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የተሰጣቸው
የክልሉ ፍርድ ቤቶች አመልካች የሕጉን መስፈርት የሚያሟላ ማስረጃ አላቀረቡም በሚል አቤቱታውን
ውድቅ በማድረጋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈፅመዋል የሚስብል ምክንያት ባለማግኘታችን ተከታዩን
ውሣኔ ሰጥተናል፡፡

ውሣኔ
1) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር
335988 መጋቢት 6ቀን 2013ዓ/ም በስር ፍርድ ቤቶች የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም
ሲል የአመልካችን የሰበር አቤቱታ በመሰረዝ የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል፡፡
2) ይህ ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መ/ቁ/206996

ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች፡ ቢዲኤፍሲ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ድርጅት ኃ/የተ/የግ/ማህበር -ምንታይ

መኮንን ቀርበዋል

ተጠሪ፡ አቶ በላቸው ጉተማ- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የሰራተኛ ደመወዝ ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል
ጅማ ዞን ጅማ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ላይ
ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በቀን 01/07/2000 ዓ.ም ተቀጥሮ በ5000 ሄክታር
መሬት ላይ የሚለማ የቡና እርሻ ስራ አስኪያጅ፣ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የድርጅቱ አማካሪ
በመሆን እየሰራሁ እያለ በአሁኑ ሰዓት በኮቪድ በሽታ ምክንያት በችግር ውስጥ መሆኔ
እየታወቀ እኔ እስከአሁን መስሪያ ቤት ተገኝቼ ስራ እየሰራሁ እያለ ከታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም
ጀምሮ ደመወዝ እየተከፈኝ ስላልሆነ የወር ደመወዝ ብር 10,000.00 ጥቅማ ጥቅም ብር 1,500
እስከ ግንቦት ወር 2012 ዓ.ም ያልተከፈለኝ ብር 69,000 የጠበቃ አበል ብር 15% እና
ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡አመልካች ባቀረበው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መልስ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው የስራ ውል በደብዳቤ ቁ.


ቢዲኤፍሲ/0034/2012 በቀን 28/03/2012 ዓ.ም ተቋርጧል፣ ተጠሪ ስራ አስኪያጅ ሆኖ እያለ
የተጠራቀመ ደመወዝ ጥያቄ ህጋዊነት የለውም፣ውሉ ተቋርጧል እንጂ ባይቋረጥ እንኳን
ላልተሰራ ስራ የሚከፈል ደመወዝ የለም፣ተጠሪ ያለማው 352 ሄክታር መሬት ብቻ ነው፣ የተጠሪ
ክስ ውድቅ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡

የወረዳዉ ፍ/ቤት የግራ ቀኝ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ የአመልካች ምስክሮች የስራ ስንብት
ደብዳቤ ለተጠሪ ስለመድረሱ ወይም አለመድረሱ እንደማያውቁና በምስክርነት ሲመጡ በጠበቃ
እጅ ያዩ መሆኑን የመሰከሩ በመሆኑ ውሉ መቋረጡና ተጠሪን መድረሱ ሳይረጋገጥ ውሉ
ተቋርጧል ማለት አይቻልም፤የተጠሪ ምስክሮ ተጠሪ ጅማ ጽ/ቤት ተመድቦ እየሰራ መሆኑ
ሲገልጹ የአመልካች ምስክሮች ግን በጅማ ከተማ ከተዛወሩ በኋላ ስራ ላይ መሆናቸው
አለመሆናቸው ያላወቁ ስለሆነ ተጠሪ ስራ ላይ የሉም ማለት አይቻልም በማለት ከህዳር 2012
ዓ.ም እስከ ግንቦት 2012 ዓ.ም ያለውን የ6ወር ደመወዝ ብር 69,000 እና 15% የጠበቃ አበል
1000 ወጪና ኪሳራ ጋር ለተጠሪ እንዲከፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን
ፍ/ቤቱም ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት የግራ ቀኝ ክርክር ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጋር መርምሮ ተጠሪ
ከስራ ስለመሰናበቱ በማስረጃ ስላልተረጋጠ ተጠሪ የአመልካች ቋሚ ሰራተኛ ነው፤ ተጠሪ ከህዳር
ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ ስለመቆየቱ የተጠሪ ምስክሮች እራሱ ተጠሪ ስራ ላይ
እንደነበረ የነገራቸው መሆኑ እንጂ እራሳቸው እንዳማያውቁ፣እንዲሁም የአመልካች ምስክሮች
ቃል ተጠሪ ከህዳር ወር ጀምሮ ስራ ላይ እንዳልነበረ ያስረዳል፣ ስለዚህ ተጠሪ ከህዳር ወር
2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ይገባ እንደነበር እስካልተረጋገጠ ድረስ ላልሰራ ስራ የደመወዝ ክፍያ
መጠየቁ የህግ መሰረት የለውም በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር አመልካች ለመክፈል
አይገደድም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ተጠሪ ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ችሎቱም ጉዳዩ ያስቀርባል በማለት መዝገቡን መርምሮ ተጠሪ
በህጉ መሰረት ከስራ የተሰናበቱ እና ስራ ላይ ያልነበሩ መሆኑ አመልካች በማስረጃ ለማረጋገጥ
አሰሪ የህግ አስገዳጅነት ያለው ቢሆንም ይህንን ግዴታ አመልካች ያልተወጣ መሆኑ፣ከፍተኛ
ፍ/ቤት ባንድ በኩል በህጉ መሰረት ከስራ አላተሰናበተም በሌላ በኩል ስራ ላይ መሆኑ
አልተረጋገጠም ሳይሰራ ደመወዝ አይከፈልም በማለት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉ የህግ አካሄድ
የጠበቀ አይደለም፣ስለዚህ ተጠሪ በህጉ መሰረት ከስራ የተሰናበተ መሆኑን እና ከታህሳስ ወር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት ወር 2012 ዓ.ም ስራ ላይ ያልነበረ መሆኑን አመልካች
በማስረጃ ሳያረጋግጥ ጥያቄው ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት
የከፍተኛ ፍ/ቤት ዉሳኔ በመሻር የወረዳው ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል፡፡

ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ ቀረበዉ በዚህ ላይ ነዉ፡፡በዚህ ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በማለት አመልካች ያቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፡ተጠሪ የድርጅቱ
ስራ አስኪያጅ በኋላ ደግሞ የድርጅቱ ከፍተኛ አማካሪ በመሆን በማገልገል ላይ እያለ የስራ
ውሉ በ28/03/2012 ዓ.ም ተቋርጧል፣ተጠሪ የስራ መሪ ነው በማለት በስር ፍ/ቤት እየተከራከርን
እንዲሁም አመልካች የፌዴራል ተመዝጋቢ ድርጅት ስለሆነ የወረዳ ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት
ስልጣን የለውም በማለት እየተቃወምን ያለምንም በቂ ምክንያት ክርክሩን አልፈው በአሰሪና
ሰራተኛ አዋጅ እንዲዳኝ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ እንዲሻርልን፤ የተጠሪ
የሥራ ውል የተቋረጠው በ28/03/2012 ዓ.ም ሲሆን ተጠሪ ክስ ያቀረበው በ08/11/2012 ዓ.ም
በመሆኑ 6 ወር ካለፈ በኋላ በመሆኑ በይርጋ ይታገዳል የሚለው ክርክር መታለፉ ስህተት ነው፤
የስራ ውል ስለመቋረጡና ደብዳቤውም በወ/ሮ ደራርቱ በላይ አማካኝነት በእጃቸው ተሰጥቷቸው
ካነበቡ በኋላ አልቀበልም በማለት መልሰው እያለ ይህም በስር ፍ/ቤት በምስክሮች ተረጋግጦ
እያለ የስራ ውሉ መቋረጡ አልተጋገጠም በማለት የተሰጠ ውሳኔ ስህተት ነው፤የተጠሪ የስራ
ውል ከተቋጠ በኋላ ተጠሪ ስራ ሰርቶ እንደማያውቁ በምስክሮች ተረጋግጦ እያለ ያልተሰራ ስራ
ደመወዝ እንዲከፈል መወሰኑ ስህተት በመሆኑ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት እና የወረዳ ፍ/ቤት
ውሳኔ ተሽሮ የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲፀናልን በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ ድርጅቱ በፌዴራል ተመዝጋቢ ከመሆኑ አንፃር
ወረዳ ፍ/ቤት አከራክሮ የወሰነበት አግባብ እንዲሁም ተጠሪ ሥራ አስኪያጅ ነው ተብሎ ባለበት
ሁኔታ የስር ፍ/ቤት ይህንን አልፎ ሰራተኛ ነው ተብሎ የተወሰነበት አግባብነት ለማጣራት
ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ታዟል፡፡

ተጠሪ በቀን 01/10/2013ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ ተጠሪ የስራ መሪ ሳይሆን ከ2000 ዓ.ም
እስከ ግንቦት 30/2011 ዓ.ም የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ መሆኑ የሚካድ አይደለም፣ ነገር ግን
በቀን 01/10/2011 ዓ.ም በደብዳቤ BDFC/0024/2011 ድርጅቱ በፃፈው ደብዳቤ የስራ
አስኪያጅነት ስራ መስራት ባለመቻሌ ከሰኔ 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ በጅማ ከተማ ባለው የድርጅቱ
ጽ/ቤት የነበረው ደመወዝ እየተከፈለኝ የድርጅቱ አማካሪ በመሆን እንዲሰራ
ተመድበያለሁ፣የስራ መሪ ሳልሆን የስራ መሪነት ስራ የማልሰራ አመልካች እራሱ ከስልጣን
አንስቶኝ የስራ መሪ ነው ማለቱ ክርክሩ መሰረተ ብስ ነው፤አመልካች የፌዴራል ተመዝጋቢ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቢሆንም ጉዳዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 139(1) መሰረት የክልል
ወረዳ ፍ/ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው፤የተጠሪ ስራ ውል ተቋርጧል የሚለው ክርክር
ከተጀመረ በኋላ እንደ ማስረጃ የቀረበ እንጂ የደረሰኝ ነገር የለም፤ተጠሪ እስካሁን የድርጅቱ
ስራ በመስራት ላይ እገኛለሁ፣ ከጅርጅቱ እንዳልተሰናበትኩ እና በጅማ ከተማ እየሰራሁ እንዳለ
በስር ፍ/ቤት በምስክሮች ተረጋግጧል፡፡ይርጋን በተመለከተ በCOVID 19 ወረሽን ምክንያት
ፍ/ቤት ዝግ ስለነበረ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም፡፡ ስለሆነም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት ውሳኔ ትክክል በመሆኑ እንዲፀና በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካች አቤቱታቸውን
የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ ተጠሪ
የዳኝነት ጥያቄ ያልተከፈለ የ6ወር ደመወዝ እንዲከፈል እንዲወስንለት ሲሆን አመልካች
በበኩሉ የስራ ዉል አስቀድሞ በህዳር 28 ቀን 2012ዓ.ም ላይ መቋረጡን እንዲሁም ተጠሪ ስራ
ላይ እንዳልነበር በመግለጽ ክሱ ዉድቅ እንዲደረግ መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡ይሁንና
ማስረጃ የመመርመር እና ፍሬነገር የማረጋገጥ ስልጣን ያላቸዉ የስር ፍርድ ቤቶች የግራ
ቀኙን ማስረጃ አመዛዝነዉ አመልካች ተጠሪን ከስራ ስለማሰናበቱ አለማስረዳቱን
አረጋግጠዋል፡፡በተጨማሪ ተጠሪ ስራ ላይ አልነበረም የሚለዉ የአመልካች ክርክር ተቀባይነት
ባለማግኘቱ ተጠሪ የጠየቀዉ የ6ወር ደመወዝ እንዲከፈል መወሰኑን ተገንዝበናል፡፡በእኛም
በኩል በዚህ ዉሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ መሆን አለመሆኑን በሰበር አጣሪ
ችሎት የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ መርምረናል፡፡

በሰበር አጣሪ ችሎት የተያዘዉ የመጀመሪያዉ ነጥብ አመልካች በፌዴራል መንግስት


የተመዘገበ ድርጅት ከመሆኑ አንጻር በወረዳ ፍርድ ቤት መወሰኑ አግባብነት የሚመለከት
ነዉ፡፡በዚህ ረገድ የስር ፍርድ ቤት ላይ አመልካች ይህንን ምክንያት በመግለጽ ጉዳዩ በወረዳ
ፍርድ ቤት መታየት እንደሌለበት ያቀረበዉ ክርክር ስለመኖሩ መዝገቡ አያሣይም፡፡የሆነ ሆኖ
ክርክሩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ የሚመለከት በመሆኑና ጉዳዩም የተወሰነዉ የአሰሪና ሰራተኛ
ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት ተደርጎ በመሆኑ ስራ ክርክር በክልል ፍርድ ቤቶች
በወረዳ ፍርድ ቤት የሚታይ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 139 የተደነገገ ከመሆኑ አኳያ በወረዳ
ፍርድ ቤት መታየቱ ስህተት ነዉ የሚባልበት ምክንያት የለም፡፡ሁለተኛዉ ነጥብ ተጠሪ ስራ
አስክያጅ ነዉ እየተባለ መታለፉ ተገቢ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነዉ፡፡ከዚህም አኳያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ እንደተመለከተዉ ተጠሪ ቀደም ሲል በስራ አስክያጅነት ሲሰራ


እንደቆየ ነገር ግን ከሰኔ 1 ቀን 2011ዓ.ም ጀምሮ በአማካሪነት እንዲያገለግል መመደቡን ተጠሪ
የተመደበበትን ደብዳቤ ጭምር በማቅረብ ያስረዳ መሆኑን፤ በአመልካች በኩልም ማስተባበያ
ክርክር ያልቀረበበት እንደሆነ ተገንዝበናል፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ የአመልካች የደመወዝ ክፍያ
ጥያቄ በስራ ክርክር ችሎት መታየቱ ስህተት ነዉ የሚያሰኝ ምክንያት የለም፡፡

ሌላዉ የአመልካች አቤቱታ ነጥብ ተጠሪ አስቀድሞ ከስራ ተሰናብቷል እናም ክሱ የ6 ወር


ይርጋ ጊዜ አልፎበታል፤አልተሰናበተም ከተባለም ስራ ላይ አልነበረም የሚለዉ ክርክር
በአግባቡ አልተመረመረም የሚል ነዉ፡፡በመሰረቱ አንድ ፍሬነገር መኖርን ወይም አለመኖርን
በመግለጽ የተከራከረ ወገን ይህንኑ የማስረዳት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር
258-259 እንዲሁም የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 2001 ድንጋጌ ይዘት ያስገነዝባል፡፡አመልካች ተጠሪን
ህዳር 28 ቀን 2012ዓ.ም ከስራ ማሰናበቱ ገልጾ የተከራከረ ቢሆንም አመልካቹ ያቀረባቸዉ
ማስረጃዎች በስር ፍርድ ቤት ተመዝኖ የስንብት ድብዳቤ ለተጠሪ አለመድረሱ
ተረጋግጧል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በተጠቀሱት ጊዜ ዉስጥ ተጠሪ ስራ ላይ ነበር ወይስ
አልነበረም የሚለዉም የፍሬ ነገር ጉዳይ እንደመሆኑ የግራ ቀኙ ማስረጃ ተመዛዝኖ ተጠሪ ስራ
ላይ እንደነበር በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ጉዳይ በመሆኑ ይህንን የፍሬነገር ድምዳሜ ይህ
ሰበር ችሎት የማይቀበልበት ምክንያት የለም፡፡

እንደሚታወቀዉ ሰበር ችሎቱ የፍሬነገር ክርክር የማጣራት ፣ ማስረጃ የመመርመር እና


የመመዘን ስልጣን በህግ አልተሰጠዉም፡፡ይልቁንም የመጨረሻ ዉሳኔ በተሰጠባቸዉ ጉዳዮች
ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ ይህንኑ በማረም ላይ የተገደበ መሆኑን ከሰበር
ስርዓት መሰረታዊ ዓላማ የምንገነዘበዉ ጉዳይ ነዉ፡፡የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ
ይዘትና መንፈስ ይህንኑ የሚያመለከት ሲሆን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር
1234/2013 በሰበር ሊታረም የሚገባ መሰረታዊ የህግ ስህተት የሚያሰኙት ሁኔታዎች
ምንድናቸዉ ለሚለዉ ትርጉም መሰጠቱ (አንቀጽ 2/4/ እና10 ይመለከታል) ስር መመልከቱ
ሰበር ሰሚ ችሎት የተቋቋመበትን ዓላማ ማለትም ወጥ የህግ አተረጓጎም እንዲኖር እና
የዉሳኔዎችን ተገማችነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ
የተዘረጋ ስርዓት መሆኑን የሚያሣይ ነዉ፡፡

በተለይም በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠ ዉሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን ሲሆን


የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታዉን ተቀብሎ በሰበር የማየት ስልጣን
የሚኖረዉ ዉሳኔዉ/ትዕዛዙ/ብይኑ የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎትን አስገዳጅ ዉሳኔ የሚቃረን ሲሆን እንዲሁም አግባብነት የሌለዉን ህግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመጥቀስ ወይም ህግን ያላግባብ በመተርጎም የተሰጠ ዉሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን ሆኖ ጉዳዩም አገራዊ


ፋይዳን የሚመለከት ሲሆን ብቻ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 10 (1/ሐ/ እና /መ) ድንጋጌዎች
ያስገነዝባሉ፡፡ከዚህም የምንረዳዉ የሰበር አቤቱታ የቀረበበት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር
ሰሚ ችሎት ዉሳኔ ከእነዚህ ሦስቱ ሁኔታዎች ዉጪ ባሉት ሁኔታዎች፣ መሠረታዊ የህግ
ስህተትን መስፈርት አስመልክቶ በአዋጁ አንቀጽ 2(4) ላይ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ዉስጥ
አንዱን የሚያሟላ ሆኖ ቢገኝ እንኳን፣የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን
በሰበር የማረም ስልጣን የሌለዉ መሆኑን ነዉ፡፡ስለሆነም ይህ የፌዴራል ጠቅላይ ሰበር ሰሚ
ችሎት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን ዉሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን በመቃወም
የቀረበለት አቤቱታ አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ከሆነ ዉሳኔዉ/ትዕዛዙ/ብይኑ
መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን ያለመሆኑን በመወሰን ረገድ እነዚህኑ ልዩ
ሁኔታዎች ማለትም በአዋጁ አንቀጽ 10(1/ሐ) ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ከግምት ዉስጥ
የማስገባት ኃላፊነት ይኖርበታል፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ ከፍ ሲል እንደተመለከተዉ ለሰበር አቤቱታዉ ምክንያት የሆነዉ የስራ ክርክር


ጉዳይ ላይ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠ ዉሳኔ ሲሆን
አቤቱታዉ የቀረበዉም፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ስራ ላይ ከዋለበት
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም (አንቀጽ 58 ይመለከቷል)፣ በቀን 02/09/2013 ዓ.ም በመሆኑ ለጉዳዩ
ተፈፃሚነት የሚኖረዉ ይሄዉ አዋጅ ነዉ፡፡ በመሆኑም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት ዉሳኔ ይዘት በአዋጁ አንቀጽ 10 (1/ሐ/ እና /መ) ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች አንፃር
ሲታይ በዚህ ችሎት ሊታረም የሚችል መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
አልተገኘም፡፡ስለሆነም ተከታዩ ተወስኗል፡፡

ዉሳኔ

1ኛ/የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 374196 ላይ በቀን


05/08/2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1)
መሠረት ጸንቷል፡፡

2ኛ/በዚህ ችሎት የተደረገ ክርክር ያስከተለዉን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን


ይቻሉ፡፡

3ኛ/በዚህ መዝገብ ላይ በ11/09/2013ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል፡፡ይጻፍ


መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-207003

ቀን፡- 28/01/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር
ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ ተመስገን ተሻገር - ጠበቃ ቀርበዋል

ተጠሪ፡- አቶ ሞላ ታረቀኝ- አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር
267605 ሚያዚያ 15 ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት
ነው ተበሎ እንዲታረምለት አመልካች ስለጠየቁ ነው።

ክርክሩ በተጀመረበት የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች አንደኛ ተከሣሽ በዚህ
ሰበር ክርክር ያልተጠሩት ወ/ሮ ፅጌ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ጥር 23 ቀን 2011ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አደስ ተበሎ የሚታወቀው ቤትና ይዞታቸውን አመልካች በሰሜን አቅጣጫ 60
ሣ.ሜትር ሁለተኛ ተከሣሽ የነበሩት በደቡብ አቅጣጫ 30 ሣ.ሜትር ገፍተው አጥረው የያዘቡባቸው
ከመሆናቸውም በላይ የአጥርና የፍሣሽ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ለመስራት የግንበታ ፈቃድ ለማውጣት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመጣው ባለሙያን ይዞታውን አላስለካም ያሉ መሆኑን በመዘርዘር እያንዳንዳቸው ገፍተው የያዙትን ይዞታ
እንዲለቁላቸው እንዲወሰንባቸው ጠይቀው አመልካች ይዞታቸውን ከ1983ዓ/ም ጀምረው አጥረው ይዘው
ከሚገለገሉ በስተቀር የተጠሪን ይዞታ አለማጠራቸውን ተከራክረዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት አመልካች ወደ ተጠሪ ይዞታ ውስጥ ገፍተው በመግባት አጥር አጥረው ይዘዋል ወይስ
አልያዙም ይዘዋል ከተባለስ አጥሩን አፍርሰው ሊለቁ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ ይዞ የግራ
ቀኙን ማስረጃ እንዲሁም የክፍለ ከተማው የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ አገልግሎት ፕሮጀክት ፅ/ቤት
የክፍለከተማ መሃንዲስና ግራቀኙ በተገኙበት በአመልካች ተገፍቶ የተያዘ የተጠሪ መሬት ካለ አጣርቶ
እንዲቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የቀረበለትን መልስ ከመረመረ በኋላ አመልካች 22ካሬ ሜትር የሚሆን
መሬትን ከተጠሪ ይዞታ ገፍተው አጥረው መያዛቸው ተረጋግጧል ሲል አጥሩን አፍርሰው ይሕን ይዞታ
እንዲለቁ ወስኗል፡፡ አመልካች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ ተጠሪ ሣይጠሩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ
ቁጥር 337 መሰረት ስለተሰረዘባቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚሉበትን ምክንያት
በመዘርዘር አቤቱታውን ለዚህ ችሎት አቅርበዋል፡፡

አመልካች ግንቦት 2ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በጥቅሉ 60 ሣ፣ሜትር መሬት ከተጠሪ ይዞታ
ገፍቶ መያዙን የሚያረጋግጥ አንድም ማስረጃ ሳይቀርብ ከ1983ዓ/ም ጀምሮ አጥሮ የሚጠቀምበትን የራሱን
ይዞታ ተጠሪ ከጠየቀው በላይ 22 ካሬ ሜትር መሬት እንዲለቅ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት
የተፈፀመበት ነው ተበሎ እንዲታረም ጠይቋል፡፡ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ የመረመረው አጣሪ ችሎት
በኃላ ተጠሪ ባቀረቡት ክስ አመልካች ገፍቶ የያዘባቸው 60 ሳ.ሜ እንዲለቀቅላቸው ጠይቀው ሣለ 22 ካሬ
ሜትር እንዲለቀቅ የመወሰኑን አግባብነት ላይ የግራ ቀኙ ክርክር ተመርምሮ እንዲወሰን ትዕዛዝ ስለሰጠ
ክርክራቸውን በፅሁፍ ተለዋውጠዋል፡፡

ተጠሪ በበኩሉ አጣሪ ችሎቱ የለየው የክርክር ጭብጥ የፍሬ ጉዳይ እንጂ የሕግ አለመሆኑን በስር ፍርድ ቤት
በተደረገው ማጣራት አመልካች በካርታ የተሰጣቸው 248 ካሬ ሜትር ቢሆንም በተደረገው ልኬት 340 ካሬ
ሜትር መሬት መያዛቸው መረጋጡን ተጠሪ በሣንቲ ሜትር የጠየቁት ወደ ካሬ ሜትር ሲቀየር 22 ካሬ
ሜትር በላይ ስለሚሆን ፍርድ ቤቱ ከተጠየቀው ዳኝነት በላይ ወስኗል ሊባል የማይችል መሆኑን በመዘርዘር
የአመልካች አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ ተከራክረዋል፡፡ አመልካች የሰበር አቤቱታውን የሚያጠናክር የመልስ
መልስ አቅርቦ ክርክሩ ተጠናቋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የተገለፀው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን የስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ ግራ ቀኙ
ያቀረቡትን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋዎች
በማገናዘብ ተመርምሯል፡፡

ተጠሪ ለስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ከይዞታቸው ጋር በሰሜን በኩል የሚዋሰነው አመልካች ይዞታቸውን
በ60ሣ.ሜትር በመግፋት ማጠሩን በመግለፅ አጥሩን አፍርሶ ይዞታቸውን እንዲለቅላቸው ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ክስ አቀራረብ 60 ሣንቲ ሜትር አመልካችና ተጠሪ በሚዋሰኑበት ቦታ ላይ በአንድ ቀጥታ መስመር በምን
ያህል ስፋት እንደተገፉ የሚያሣይ እንጅ ጠቅላላ ተገፍቶ የተያዘውን መሬት አጠቃላይ ስፋት( total area)
ለመግለፅ ታስቦ አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ አመልካች በጥቅሉ የተጠሪን ይዞታ ገፍቸ አልያዝኩም ሲሉ
ተከራክረዋል፡፡ የተካደን ፍሬ ነገር በማስረጃ አጣርቶ እንዲወስን በሕግ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው የስር
ፍርድ ቤት ስለጉዳዩ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች የተደራጀና ይዞታን በሚመለከት ባለይዞታዎችን ከነይዘታ
መጠናቸው መዝግቦ የመያዝ እንዲሁም ይዞታን በሚመለከት አስተዳራዊ ውሣኔ እንዲሰጥ በሕግ ስልጣን
የተሰጠው የመንግስት አስተዳደር አካል አመልካች ወደ ተጠሪ ሕጋዊ ይዞታን ገፍተው መያዝ አለመያዛቸውን
ይዘው ከሆነም መጠኑን አጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ የተሰጠው የክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር
የግራቀኙን የይዞታ ማረጋጫ ምስክር ወረቀት መሰረት አድር ለክቶ እንዳጣራው በጥቅሉ አመልካች 22ካሬ
ሜትር የተጠሪን ይዞታ ገፍተው መያዛቸውን አረጋግጧል፡፡ የስር ፍርድ ቤት የግራቀኙንና በትዕዛዝ
የቀረበለትን ማስረጃ መዝኖ አመልካች 22 ካሬ ሜትር መሬት እንዲለቁ ወስኗል፡፡

በመሰረቱ በፍትሐ ብሔር ጉዳይ የክስ አቤቱታ ያቀረበ ከሳሽ ፍርድ ቤቱ በተለይ ወይም በምትክ ወይም
በተለዋጭ እንዲወስንለት የሚፈልገውን ነጥብ መግለፅ የሚጠበቅበት መሆኑንና ፍርድ ቤቶችም የተጠየቁትን
ዳኝነት መሰረት አድርገው ውሳኔ መስጠት የሚገባቸው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 224(1) እና
182(2) ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ፍርድ ቤቶች ተከራካሪ ወገኖች ያላነሱትን ወይም ዳኝነት
እንዲሰጡበት በግልፅ ያልጠየቁትን ጉዳይ መሰረት በማድረግ የሚሰጡት ውሣኔ አግባብነት የማይኖረው
መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 33945 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም
ሰጥቶበታል፡፡

በያዝነው ጉዳይ መልስ የሚያሻው ጉዳይ ተጠሪ ባቀረቡት ክስ አመልካች 60 ሣንቲ ሜትር መሬት የገፏቸው
በመሆኑ የገፉትን መሬት እንዲለቁ እንዲወሰንላቸው በጠየቁት መሰረት ጉዳዩ ሲጣራ የተጠሪን 22 ካሬ
ሜትር መሬት ገፍተው ስለመያዛቸው በመረጋገጡ ይህን መሬት እንዲለቁ መወሰኑ ከተጠየቀው ዳኝነት
ውጪ የተሰጠ ውሳኔ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ ነው፡፡

በዚህ መዝገብ ላይ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው መሬት በከተማ አስተዳደር ስር የሚገኝ መሬት በመሆኑ
የእያንዳንዱ ሰው ይዞታ ወርዱ እና ቁመቱ በሜትር እንዲሁም አጠቃላይ ስፋቱ ደግሞ በካሬ ሜትር
በሚመለከተው የከተማ አስተዳር የመንግሳት አካል የሚታወቅ መሆኑ ግምት የሚወሰድበት ነው፡፡
በተለመደው አሰራር መሰረት በከተማው ውስጥ የሚገኝን የይዞታው አጠቃላይ ስፋት የሚታወቀው የመሬቱን
ርዝመት (ቁመት) እና ወርድን(ስፋት) በሜትር በመለካት የተገኘውን ውጤት ርስ በርሱ በማባዛት የሚገኘው
ውጤት የመሬቱ ካሬ ሜትር ስፋት መሆኑ የሚያከራክር አይሆንም፡፡ በዚህ እሳቤ መሰረት ተጠሪ የጠየቁት
ዳኝነት 60 ሣንቲ ሜትር መሬት ተገፍብኛል የሚል ነው፡፡ ከላይ በተገለፀው አጠቃላይ የዳኝነት ጥያቄ መርህ
እና ከተማ ይዞታ አለካክ በመነሣት የተጠሪ ዋና የዳኝነት ጥያቄ የተገፋባቸውን ይዞታ ፍርድ ቤቱ አጣርቶ
እንዲያስመልስላቸው በመጠየቅ ላይ ያተኮረ ሆኖ የተገፋውን መሬት ወርድ ብቻ የሚያመለክት ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍርድ ቤቱም በተጠሪ የቀረበውን የዳኝነት ጥያቄና በአመልክች የተሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ
አመልካች የተጠሪን ይዞታ ገፍተው አጥር አጥረው መያዝ አለመያዛቸውንና መጠኑን ጭምር ለማጣራት
ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባለሙያ በቦታው ተገኝቶ ለክቶ እንዲቀርብለት ትዕዛዝ ሰጥቶ በዚሁ
መሰረት ውጤቱ ስቀርብለት 22ካሬ ሜትር መሆኑ ተገልጾለታል፡፡ አመልካች በዚህ ችሎትም ይሁን በስር
ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር በሕጋዊ መንግድ እንዲጠቀሙበት ከተሠጣቸው ይዞታ በላይ ስለመያዛቸው
የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር የሚያስተባብል ማለትም የያዙት በሚመለከተው አስተዳደር አካል የተፈቀደላቸውን
ብቻ ስለመሆኑ ወይም የተጠሪን ይዞታ አለመግፋታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ በጥቅሉ የስር
ፍርድ ቤት ከተጠየቀው ዳኝነት በላይ ውሣኔ ሰጠ በሚል ከሚያቀርቡት ክርክር ውጪ ሲሰላ 22ካሬ ሜትር
የማይሆን መሆኑን የሚያሣምን ክርክር አያቀርቡም፡፡

በመሆኑም ተጠሪ በሚመለከተው የከተማ አስተዳደር የመንግስት አካል አንዲጠቀሙበት በሕጋዊ መንግድ
ከተሰጣቸው ይዞታ ላይ አመልካች በወርድ 60ሣንቲ ሜትር መሬት በመግፋት አጥር አጥረው የያዙባቸው
በመሆኑ አጥሩ ፈርሶ መሬቱ እንዲመለስላቸው ዳኝነት ጠይቀው ፍርድ ቤቱ የተጠሪ መሬት በአመልካች
መገፋት አለመገፋቱን በጭብጥነት ይዞ ሲያጣራ የተጠየቀው በወርድ 60 ሣንቲ ሜትር በቁመት ሲባዛ 22ካሬ
ሜትር የሚሰጥ ስለመሆኑ ግንዛቤ ተወስዶበት አመልካች በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተሰጣቸው
ይዞታ ባልይ 22ካሬ ሜትር የተጠሪን መሬት ገፍተው ስለመያዛቸው በተረጋገጠበት የመስፈሪያ ልዩነቱን
መሰረት በማድረግ ብቻ ባልተጠየቀ ዳኝነት ውሣኔ እንደተሰጠና መሰረታዊ የሕግ ስህተት እንደተፈፀ በማመን
በአመልካች በኩል የሚቀርበው ክርክር የሚያሣምን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚያሰኝ
ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩ ውሣኔ ተወስኗል፡፡

ውሣኔ

1) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 267605 ሚያዚያ 15 ቀን


2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠዉ ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈፀመበት በመሆኑ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
2) ይህ የሰበር ክርክር የስከተለው ወጪና ከሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

ትዕዛዝ
1) ይህ ችሎት ጥር 12ቀን 2013ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል፡፡
2) መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ

የማይነበብ የአምስት ዳኖች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 207081

ቀን፡-28/03/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካቾች ፡- 1ኛ አቶ ግርማ ገብራይ ተወካይ አቶ ሽመልስ ገብራይ

2ኛ አይናለም ገብራይ

3ኛ ሽመልስ ገብራይ- ቀረቡ

4ኛ ግዛቸው ገብራይ

ተጠሪ ፡- ወ/ሮ ወሰኔ ገብራይ- ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
ጉዳዩ ከገጠር መሬት ጋር የተያያዘ የውርስ ክርክርን የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ
ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ተጠሪ የእናታችንን እና የአባታችንን የውርስ ይዞታ
አዋሳኞቾቻቸዉ በክሱ ይዘት የተጠቀሱትን በአራት ቦታ የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን እንዲሁም በሻሸመኔ
ከተማ ዉስጥ በ2000 ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰ መኖሪያ ቤት በጋራ እያስተዳደሩ
ቆይተዉ ተጠሪ ድርሻችንን ሊያካፍሏቸዉ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ ድርሻቸዉ አንዲያካፍሏቸዉ
እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ አመልካቾች የዉርስ ሀብት ነዉ የሚሉት መሬቶች ከ1980 ዓ/ም ጀምሮ
በግላቸዉ ይዘዉ የሚጠቀሙበት እንደሆነ መኖሪያ ቤቱንም በግላቸዉ የሰሩት እንደሆነ በመግለጽ ክሱ ዉድቅ
እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ ተከራክረዋል፡፡እንዲሁም የዉርስ ንብረት በአመልካቾች እጅ እንደሚገኝ በመግለጽ
አመልካቾች እንዲያካፍሏቸዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡

የሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በይርጋ የታገደ ነዉ በሚል ክሱን ዉድቅ በማድረግ
ዉሳኔ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም አመልካቾች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ ዉሳኔዉ ተሸሮ የዉርስ ሀብት ናቸዉ
የተባሉትን ንብረቶች ግራ ቀኝ አብረዉ ሲጠቀሙ የነበረ መሆን አለመሆኑን በማስረጃ አጣርቶ በይርጋ
መቃወሚያዉ ላይ ዉሳኔ እንዲሰጥ ለወረዳዉ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መልሶለታል፡፡የወረዳዉ ፍርድ ቤት
በመ/ቁጥር 59200 የሆነዉን መዝገብ በማንቀሳቀስ የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቶ በቀን 09/07/2011ዓ/ም
በሰጠዉ ብይን የእርሻ መሬቶችን በተመለከተ በጋራ ሲጠቀሙ እንደነበር ተረጋግጧል በማለት የይርጋ
መቃወሚያዉን ዉድቅ በማድረግ መኖሪያ ቤቱን በተመለከተ ግን ተጠሪ ብቻቸዉን ሲጠቀሙ እንደነበር
ተረጋግጧል በማለት በተጠሪ የቀረበዉን የይርጋ መቃወሚያ ተቀብሎ ከመኖሪያ ቤቱ አንጻር የቀረበዉ ክስ
በይርጋ ታግዷል ሲል ወስኖ ከእርሻ መሬቶች አንጻር መዝገቡን መርምሮ ተገቢዉን ትእዛዝ ለመስጠት ቀጠሮ
ሰጥቷል፡፡በመቀጠልም የእርሻ መሬቶቹ የተጠሪ የግል ይዞታዎች ሳይሆኑ ለግራ ቀኙ በዉርስ የሚተላለፈዉ
የወርስ ሀብቶች ናቸዉ በማለት ተጠሪ እንዲያካፍሏቸዉ በማለት በቀን 06/10/2011ዓ/ም ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካቾች መኖሪያ ቤቱን በተመለከተ በተሰጠዉ ብይን ላይ ይግባኝ ለምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ያቀረቡት በቀን 11/11/2011ዓ/ም ሲሆን ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 40491 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ
በቀን 05/05/2012 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ተጠሪ አመልካች ይግባኝ ያቀረቡት ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ
በኋላ ነዉ በሚል ያቀረቡትን ክርክር አመልካቾች ይግባኝ ማቅረብ የሚችሉት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር
320/3 መሰረት የስር ፍርድ ቤት በጉዳየ ላይ የመጨረሻ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ በመሆኑ የአመልካቾች ይግባኝ
ማቅረቢያ ጊዜ አላለፈም በማለት ዉድቅ ካደረገ በኋላ የአመልካቾች ዳኝነት ጥያቄ የዉርስ ሀብት ክፍፍልን
የሚመለከት በመሆኑ በሰ.መ.ቁጥር 44025 ላይ በተሰጠ ዉሳኔ መሰረት አመልካቾች የመኖሪያ ቤቱን ተጠሪ
እንዲያካፍሏቸዉ ያቀረቡት ክስ በይርጋ አልታገደም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ በመሻር ፍሬ ነገሩ ላይ
አከራክሮ እንዲወስን ጉዳዩን ለስር ፍርድ ቤት መልሶለታል፡፡

በመቀጠል ተጠሪ ይግባኝ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበዉ ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 325451
ላይ በቀን 22/04/2013 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ አመልካቾች መኖሪያ ቤቱን በተመለከተ በቀን 09/07/2011ዓ/ም
በተሰጠዉ ዉሳኔ ላይ የእርሻ መሬቶችን በተመለከተ ዉሳኔ እስከሚሰጥ ድርስ በጠበቅ ሳያስፈልግ ይግባኝ
ማቅረብ ሲገባቸዉ ጊዜዉ ያለፈበትን ይግባኝ አቅርበዋል፤ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካቾች ማስፈቀጃ
አቅርበዉ ሳይፈቀድላቸዉ ጊዜዉ ያለፈበትን ይግባኝ አለአግባብ የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 320/3ን በመጥቀስ
አከራክሮ መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት አመልካቾች ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረቡት ይግባኝ
ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነዉ በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ ሽሯል፡፡አመልካቾች በዚህ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ ችሎቱ በመ/ቁጥር 335862 ላይ
በቀን 19/06/2013ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ ሰርዞባቸዋል፡፡

አመልካቾች በቀን 03/09/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም ከላይ በተገለጸዉ መሰረት በተሰጠ
ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የአቤቱታዉ ይዘት በአጭሩ፡-መኖሪያ ቤቱን
በተመለከተ የቀረበዉ ዳኝነት ጥያቄ በይርጋ ይታገዳል በማለት በተሰጠዉ ብይን ላይ ይግባኝ ማቅረብ
የምንችለዉ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 320/3 በተደነገገዉ መሰረት እና በሰ.መ.ቁጥር 116209 እና 89893 ላይ
በተሰጠዉ ትርጉም ላይ በቀሪ ጉዳዮች ላይ ፍርድ ቤቱ እያከራከረ ጉዳዩ በቀጠሮ ላይ እያለ ሳይሆን ፍርድ
ቤቱ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ ሆኖ እያለ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካቾች ለዞኑ
ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጊዜዉ ያለፈበትን ይግባኝ እንዳቀረብን አድርጎ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ
በመሻር ዉሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ይታረምልን በማለት አቤቱታቸዉን
አቅርበዋል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ አመልካቾች ወራሽነታቸውን አረጋግጠው ንብረቱንም በውርስ
እየተጠቀሙበት ባለበት ሁኔታ ጉዳዩ በይርጋ ቀሪ ነው ተብሎ የተወሰበነት አግባብ ተጠሪ ባሉበት
እንዲመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን 10/02/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልሳቸዉን ያቀረቡ ሲሆን
ይዘቱም በአጭሩ፡- የክልሉ ሰበር በቀን 19/06/2013ዓ/ም ዉሳኔ ሰጥቶ አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት
በቀን 30/09/2013ዓ/ም በ101ኛ ቀን ላይ በመሆኑ የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ አልፎባቸዋል፡፡የኦሮሚያ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዉሳኔ የሰጠዉ አመልካቾች ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ካለፈ በኋላ
ያቀረቡት ይግባኝ ታይቶ መወሰኑ ስህተት ነዉ በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከመሻሩ ዉጭ በዋናዉ
ጉዳይ ላይ በቀረበ የይርጋ መከራከሪያ ላይ ዉሳኔ ባልተሰጠበት ሰበር አጣሪ ችሎት ከይርጋ አንጻር በሰበር
ችሎት እንዲመረመር ጭብጥ መያዙ ስህተት ነዉ፡፡አመልካቾች መኖሪያ ቤቱን በተመለከተ በቀን
09/07/2011ዓ/ም በተሰጠ ብይን ላይ ከሶስት ወር በኋላ በቀን 11/11/2011ዓ/ም ይግባኝ ማቅረባቸዉን
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አረጋግጦ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጊዜዉ ያለፈበትን
ይግባኝ ተቀብሎ አከራክሮ መወሰኑ ስህተት ነዉ በማለት በመሻር በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 320(2-4) ስር
የተደነገገዉ መሰረት ያደረገ በመሆኑ የተፈጸመ ስህተት የለም በማለት መልሳቸዉን ሰጥተዋል፡፡አመልካቾችም
በቀን 01/03/2014ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በላይ በአጭሩ የተመለከተዉ የግራ ቀኝ ክርክርና በክልሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች ይዘት
የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘዉን ማስቀረቢያ ጭብጥ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 251
መሰረት በመለወጥ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካቾች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ያቀረቡት ይግባኝ ጊዜዉ ያለፈበት ነዉ በማለት ሽሮ በመወሰኑ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር
አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ መርምረናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንደመረመርነዉም አመልካቾች በተጠሪ ላይ በወረዳ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ የወርስ ሀብት የሆኑትን


በ2000ካሬ ሜትር ላይ የሚገኝ መኖሪያ ቤትና በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን ከተጠሪ ጋር
አብረዉ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ በመግለጽ ተጠሪ ድርሻቸዉን ሊያካፍሏቸዉ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ
ተጠሪ እንዲያካፍሏቸዉ እንዲወሰን ዳኝነት በመጤቅ ነዉ፡፡ተጠሪ ክሱ በይርጋ የታገደ ነዉ የሚል
መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር በማስረጃ
ከመረመረ በኋላ በቀን 09/07/2011ዓ/ም በሰጠዉ ብይን አመልካቾች የመኖሪያ ቤቱን ከተጠሪ ጋር በጋራ
መጠቀማቸዉን አላስረዱም በማለት መኖሪያ ቤቱን በተመለከተ የተጠየቀዉ ዳኝነት በይርጋ ታግዷል በማለት
ዉድቅ በማድረግ የእርሻ መሬቶቹን በተመለከተ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶና መርምሮ በቀን
06/10/2011ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ የዉርስ ሀብት ስለሆኑ ግራ ቀኙ ይከፈሉ በማለት የወሰነ ሲሆን
አመልካቾች መኖሪያ ቤቱን በተመለከተ በተሰጠ ብይን ላይ ይግባኝ ያቀረቡት ይህንን ዉሳኔ ተከትለዉ በቀን
11/11/2011ዓ/ም በተጻፈ ይግባኝ ነዉ፡፡ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለዉ በመቃወሚያዉ ላይ ብይን ከተሰጠበት
ቀን ጀምሮ ከታይ ይግባኝ የቀረበዉ ከ4 ወር በኋላ ሲሆን በፍርድ ቤቱ በመዝገቡ ላይ የመጨረሻ ዉሳኔ
ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከተቆጠረ ደግሞ ሁለት ወር ሳይሞላ አመልካቾች ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ
ማቅረባቸዉን ነዉ፡፡ የዚህን ችሎት ምላሽ የሚሻዉ ነጥብ አመልካቾች ይግባኝ ማቅረብ ያለባቸዉ
በመቃወሚያዉ ላይ ብይን ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 60 ቀን ወስጥ ነዉ ወይስ በመዝገቡ ላይ
የመጨረሻ የፍርድ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ ባሉት 60 ቀናት ዉስጥ ነዉ?የሚል ነዉ፡፡

እንደሚታወቀዉ በልዩ ሕግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር የፍትሐ ብሔር ክርክር መመራትና እና
እልባት ማግኘት ያለበት በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በተዘረጋዉ ሥርዓት መሰረት ነዉ፡፡ይህም
ሥርዓት የተዘረጋበት ምክንያት ክርክር ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ወጭና ጊዜ ቆጣቢ እንዲሁም ክርክሮች
ተለይተዉ በሚታወቅ ሥነ ሥርዓት አግባብ ተመርተዉ ወጥነት ያላቸዉና እርስ በእርሳቸዉ የማይጣረሱ
ፍተሐዊ እልባት እንዲያገኙ ለማድረግ በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ ለማሳካት የታቀደዉ ዓላማ ከግብ
እንዲደርስ ነዉ፡፡የይግባኝ አቀራረብ እና ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ነዉ ተብሎ በሕጉ የተደነገገዉ ሥነ
ሥርዓትም ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት በመሆኑ የሕጉን ዓላማ በሚያሳካ መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ
ይገባል፡፡በዚህ መሰረት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 320(3 እና 4) ጣምራ ንባብ መሰረት ከሥረ ነገሩ ፍርድ
በፊት በእጁ ያለዉን ንብረት ለሌላዉ ወገን እንዲያዘዉር የተሰጠ ዉሳኔ ካልሆነ በስተቀር በመጀመሪያ ደረጃ
በሚቀርብ መቃወሚያ ላይ በተሰጠ ጊዜ በሥረ ነገሩ ላይ የመጨረሻ የፍርድ ዉሳኔ ከመሰጠቱ በፊት
በመቃወሚያዉ ላይ ብቻ በተሰጠ ብይን ላይ ይግባኝ ማቅረብ እንደማይቻል ተደንግጓል፡፡ በተያዘዉ ጉዳይ
የክርክሩ ሥረ ነገር የዉርስ ሀብት ክፍያን መነሻ ያደረገ በመሆኑ የዉርስ ሀብት ከተባሉት ንብረቶች መካከል
መኖሪያ ቤት በሚመለከት የተጠየቀዉ ዳኝነት በይርጋ ይታገዳል ተብሎ አስቀድሞ ብይን የተሰጠ ቢሆንም
የዉርስ ሀብት ናቸዉ ተብሎ በዚያዉ አንድ ክስ ላይ ዳኝነት በተጠየቀባቸዉ ሌሎች ንብረቶች ላይ ይህ ብይን
በተሰጠበት ጊዜ የመጨረሻ የፍርድ ዉሳኔ ባለመሰጠቱ ጉዳዩ በቀጠሮ ላይ የነበረ መሆኑ ግራ ኙን ያከራከረ
ጉዳይ ካለመሆኑም በተጨማሪ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ግልባጭም ይህንኑ ያሳያል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስለሆነም አመልካቾች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ የተሰጠዉን ብይን በቀሪዎቹ የዉርስ ሀብት በተባሉ
ንብረቶች(ሥረ ነገሩ) ላይ የመጨረሻ የፍርድ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ
ማቅረባቸዉ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ ክርክሮች ተጠቃለው ቀልጣፋ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ
እንዲመሩና ከአንድ ሥረ ነገር ለሚመነጭ ጉዳይ የተለያየ መዝገብ እንዳይከፈት ለመከላከል በሚያስችል
መልኩ ክርክሮች እንዲመሩ የታቀደዉን ዓላማ ከግብ የሚያደርስ የይግባኝ አቀራረብ በመሆኑ ሥነ ሥርዓት
ሕጉ የዘረጋዉን ሥርዓት የተከተለ ነዉ፡፡በመሆኑም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካቾች ጊዜ
ያለፈበትን ይግባኝ እንዳቀረቡ ገልጾ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር የወሰነዉ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 320(3እና 4) ስር የተደነገገዉንና በዚህም ለማሳካት የታቀደዉን ዓላማ ከግምት
ያላስገባ እና በሰ.መ.ቁጥር 116209፣ 185154 እና በተማሳሳይ በሌሎች መዛግብት ላይ የተሰጠዉን አስገዳጅ
ትርጉም ያላገናዘበ በመሆኑ ሊታረም የሚገባዉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ዉ ሳ ኔ

1. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁጥር 325451 ላይ በቀን


22/04/2013ዓ/ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁጥር 335862 ላይ በቀን 19/06/2013ዓ/ም የሰጠዉ ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1
መሰረት ተሽረዋል፡፡

2. የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ.ቁጥር 325451 የሚታወቀዉን መዝገብ አንቀሳቅሶ ይግባኝ
የቀረበበትን ጉዳይ መርምሮ ሕግን መሰረት ያደረገ ዉሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር
341/1 መሰረት ተመልሶለታል፡፡

3. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ
1. በዚህ ዉሳኔ መሰረት እንዲፈጸም የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ
ችሎት ይተላለፍ፡፡ ለግራ ቀኙም ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ፤-208603
ቀን፡-29/03/2014ዓ/ም

ዳኞች፡-እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር
ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1) የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስ/ፅ/ቤት

2) አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ቤቶች አስ/ፅ/ቤት ዐ/ህግ ቀርበዋል፡፡


ቀርበዋል፡፡

3) አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ቤቶች አስ/ፅ/ቤት

ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ወዳጆ ተወካይ አቶ ዮናስ ሰለሞን ፡፡

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 261471 ግንቦት 17ቀን 2013
ዓ/ም የአመልካቾችን ይግባኝ አቤቱታ ከመረመረ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት መሰረዙ
መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብሎ እንዲታረምላቸው አመልካቾች በመጠየቃቸው ነው፡፡
ጉዳዩ የመፋለም ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ በተጀመረበት የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
1ኛ አመልካች 1ኛ ተከሣሽ፣ ወ/ሮ አሰገደች ዝናቡ 2ኛ ተከሣሽ፣ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ጣልቃ ገቦች ተጠሪ
ደግሞ ከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ጥቅምት 28 ቀን 2011 ዓ/ም በተፃፈ የተሻሻለ ክሱ በመምህርነት ሲያገለግል ከነበረበት ወለጋ ሲመልስ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር 889 የሆነና በደብተር ቁጥር 5/25444 የተመዘገበውን
ቤቱን የያዘበትን 1ኛ አመልካች ቤቱን እንዲያስረክበው ሲጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆኑ አቤቱታውን ለጠቅላይ
ዐ/ሕጉ አቅርቦ አንደኛ አመልካች ሰኔ 12ቀን 1982ዓ/ም በተፃፈ ለጠቅላይ ዐ/ሕግ በሰጠው መልሱ ቤቱን
ለተጠሪ ለማስረከብ ከ50 በላይ ጠያቂዎች በመኖራቸው እንዲሁም ሁለተኛ ተከሣሽ በቤቱ ከ14 ቤተሰቦች
በላይ የሚያስዳድሩበት መሆኑን በመግለፅ በቅደም ተከተል እንደሚያስተናግደው ከገለፀ በኋላ እስካሁን ድረስ
ቤቱን ያልመለሰለት መሆኑን በመዘርዘር ምንም መብት ሣይኖራቸው የያዙበትን ቤት ለቀው እንዲያስረክቡት
የተሰበሰበው ኪራይና ክሱ ከቀረበበት ጊዜጀምሮ 2ኛ ተከሣሽ ኪራይ እንዲከፍሉት እንዲወሰንባቸው ጠይቋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአሁን 1ኛ አመልካች የመጀመሪ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቦ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብትና ጥቅም
የለውም በሚል ብይን የተሰጠ በቢሆንም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተሽሯል፡፡ አንደኛ አመልካች ለክርክሩ
ምክንያት የሆነውን ቤት ይዞ ለ2ኛ ተከሣሽ በማከራዬት እያስተዳደረው መሆኑና ተጠሪ አስተዳድሮት
የማያውቅ መሆኑን፣ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ አለማቅረቡን፣
ያቀረበው ደብተርም ባለቤትነትን እንደማያረጋግጥ በመዘርዘር ክሱ ውድቅ እንዲደረግለት፤ ሁለተኛ ተከሣሽ
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተወረሰና ከ1ኛ አመልካች ተከራይተው
በሚኖሩበት ቤት ተከሣሽ መሆናቸው ተገቢ አለመሆኑን፣ የባለቤትነት ደብተር አሰራር በካርታ በተቀየረበት
ደብተር ማቅረቡ የቤቱ ባለቤት አለመሆኑን የሚያሣይ መሆኑን፣ በአዋጁ የተፈቀደለትመሆኑን
የሚያጋግጥና የውርስ አጣሪ ሪፖርት ባልቀረበበት ቤቱን እንዲድትቅ ኪራይም እንድትከፍል ክስ መቅረቡ
ተገቢ አለመሆኑን በመዘርዘር በጠቅሉ የተጠሪ ክስ ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በክርክሩ ጣልቃ እንዲገቡ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ቀርበው ለክርክሩ
ምክንያት የሆነው ቤት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ወርሰው አከራይተው የሚያስተዳድሩት መሆኑን
በአንፃሩ ተጠሪ ይህን ቤት አስተዳድሮት የማያውቅና በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት የተፈቀደለት መሆኑን
ወይም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል ከሆነም እንዲመለስለት የተወሰነለት መሆኑን የሚያረጋግጥ
ማስረጃ ሣያቀርብ ክስ ማቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን ቤቱ እንዲመለስ ትዕዛዝ ሰጥቷል የተባለው ጠቅላይ
ዐ/ሕግም ይህን የመወሰን ስልጣን የሌለው መሆኑን በመዘርዘር ክሱ ውድቅ እንዲደረግላቸው ተከራክረዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቤቱን አመጣጥና ሁኔታ በሚመለከት የአዲስ ከተማ የመሬት አስተዳደር ፅ/ቤት፣ የአዲስ ከተማ
ወረዳ 01 ቤቶች አስተዳርና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መንግስት ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት አጣርተው
መልስ እንዲሰጡ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሬት አስተዳደር ፅ/ቤቱ የቤቱ ማሕደር የሌለው መሆኑ የገለፀ
ቢሆንም ሌሎች ተቋማት ግን ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለሁለተኛ ተከሣሽ አከራይተው
የሚያስተዳድሩት መሆኑን በመግለፅ የቤቱ ማህደር የላኩለት መሆኑን የጉዳዩ አመጣጥ ያስገነዝባል፡፡

የስር ፍርድ ቤት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተጠሪ የግል ቤት ነው ወይስ በአዋጅ ቁጥር 47/67
መሰረት ተወርሶ ጣልቃ ገቦች የሚያስተዳድሩት? ቤቱን ለተጠሪ ሊያስረክቡት ይገባል ወይስ አይገባም?
የሚለውን ጭብጥ ይዞ የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ተጠሪ በማስጃነት ያቀረበው ቁጥሩ 5/25444
የሆነው ደብተር አዋጅ ቁጥር 47/67 ከፀና በኋላ ሰኔ 21 ቀን 1981ዓ/ም የተሰጠው በመሆኑ በአዋጁ መሰረት
የተሻረ ነው ማለት የማይቻል መሆኑን እንዲሁም በአመልካቾች በኩል ይህ ደብተር የተሻረ ስለመሆኑ
የሚያጋግጥ ማስረጃ አለመቅረቡን በደብተሩ ላይ ተጠሪ ቤቱን በ1978 ዓ/ም በውርስ ማግኘቱን የሚረያጋግጥ
ነው በማለት ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አመልካቾች ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ኪራይን በሚመለከት ግን
ሊከፍሉ አይገባም ሲል ወስኗል፡፡ አመልካቾች በውሣኔው ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታቸውን አቅርበው
ስለተሰረዘባቸው ይህን የሰበር

አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

አመልካቾች ግንቦት 30ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታቸው ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 110/97ና አዋጅ
ቁጥር 572/2000 መሰረት ለቋቋመው የመንግስት ተቋም ቤቱ እንዲመለስት አቤቱታውን አቅርቦ ሣያስወስን
ወይም በአዋጅ ቁጥር 47/67 ድንጋጌ መሰረት የተፈቀደት መሆኑን ማረጋገጫ ሣይቀርብ ክስ ማቅረቡና
ፍርድ ቤቱም መቀበሉን በሚመለከት በአመልካቾች የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ፤
የስር ፍርድ ቤት የደብተርና የካርታን ልዩነት በአግባቡ ሣይረዳ ደብተር የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ
እንደሆነ መገንዘቡ፤ ደብተሩም ለተጠሪ የተሰጠው ስለመሆኑና ስለትክክለኛነቱ ሣይረጋገጥ በመመሪያ ቁጥር
17/2006 እና 18/2006 ለደብተር ያልተሰጠውን ዋጋ ፍርድ ቤቱ መስጠቱ፤ ጠ/ዐ/ሕግ በአዋጅ ቁጥር
47/67 የተወረሰን ቤት እንዲመለስ የመወሰን ስልጣን ሣይኖረው እንደወሰነ በማስመሰልና በወቅቱ ስራ ላይ
የነበረው የቀበሌ አስተዳደር ለጠ/ሕግ የሰጠውን መልስ የቤቱ ባለቤት ተጠሪው ነው ሲል አምኗል በሚል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በተሣሣተ ግንዛቤ የመንግስት የሆነውን ቤት ለተጠሪ እንዲመለስ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው
ተብሎ እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡

የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት አመልካቾች ተረክበው


ሲያስተዳድሩት የነበሩ ስለመሆናቸው አስረድተው ሣለ ቤቱ ለተጠሪ እንዲመለስ ከሚመለከተው አካል ውሣኔ
ባልተሰጠበት ቤቱን ለተጠሪ እንዲያስረክቡ የመወሰኑ አግባብነት እንዲመረመር ተጠሪም የመልስ ክርክር
እንዲያቀርብ ታዞ የፅሁፍ ክርክራቸው ተጠናቋል፡፡

ተጠሪው በበኩሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚው ላይ የተሰጠው ብይን በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ በመሻሩ
ክርክሩ መቀጠሉንና አንደኛ አመልካች ቤቱን ለተጠሪ ለማስረከብ በቤቱ ውስጥ ለነበረው ሰው ቤት ፈልጎ
እስከሚያገኝ ድረስ ጊዜ እንዲሰጠው መጠየቁ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ቤቱ ለተጠሪ እንዲሆን
የተወሰነለት መሆኑን ስለሚያሣይ በፕራይቬታይዜሽን አጄንሲ ማስወሰን የማይስፈልግ መሆኑን፤ የስር ፍርድ
ቤት ውሣኔ የሰጠው በተጠሪ የቀረበውን የደብተር ካርታን ማስረጃ ብቻ መሰረት አድርጎ ሣይሆን ለጠቅላይ
ዐ/ህጉ የተሰጠውን መልስ በመመዘን ጭምር መሆኑን፣ የደብተር ካርታው ትክክለኛ መሆኑን በሚመለከት
የስር ፍርድ ቤት ከቤቱ ማሕደር ማረጋገጡን፣ በወቅቱ ለጠቅላይ ዐ/ሕግ የቀረበው አቤቱታ ቤቱ እንዲመለስ
እንዲወስን ሣይሆን በአዋጅ ቁጥር 47/67 ድንጋጌ መሰረት ለተጠሪ እንዲሆን የተወሰነውን ቤት በሕገወጥ
መንገድ የያዘው አንደኛ ተጠሪ አልቅም ማለቱን በተመለከተ እንደሆነና እንዲህ አይነት ጉዳይ ለዐ/ሕጉ
እንዲቀርብ መንግስት አዝዞ ስለነበር መሆኑን በስር ፍርድ ቤትም እንዲህ አይነት ክርክር አለመነሣቱን
በመዘርዘር የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈመበትም ተብሎ እንዲፀናለት
ተከራክሯል፡፡ አመልካቾች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታቸውን የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ክርክሩ
ተጠናቋል፡፡

ከፍ ሲል በአጭሩ የተመለከትነው የጉዳዩን አመጣጥና የግራ ቀኙን ክርክር ሲሆን የስር ፍርድ ቤት ለክርክሩ

ምክንያት የሆነውን ቤት ለተጠሪ እንዲያስረክቡ በሰጠው ውሣኔ የፈፀመው መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር
አለመኖሩን በሚመለከት ውሣኔ ለመስጠት የስር ፍርድ ቤትን መዝገብ በማስቀረብ ጉዳዩን አግባብነት ካላቸው
የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡ እንደመረመርነው ተጠሪ ከአያቱ በውርስ ያገኘውን ቤት
አንደኛ አመልካች በሕገወጥ መንገድ ይዞ ለሁለተኛ ተከሣሽ አውራሽ እያከራዬ መሆኑንና እንዲመልስለት
ሲጠይቀው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ቤቱን እንዲቁለት የሰበሰበውን ኪራይ እንዲከፍለው ሁለተኛ ተከሣሽም ኪራይ
እንዲከፍሉ እንዲወሰንለት ጠይቋል፡፡ አመልካቾች በጥቅሉ ተጠሪው በቤቱ ላይ መብትና ጥቅም የሌለው
መሆኑን፣ ቤቱም በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሰና አስተዳደሩ ይዞ የሚያስተዳድረው መሆኑን፣ በአዋጅ
ቁጥር 47/67 ቤቱ ለተጠሪ የተፈቀዳለት ወይም ከአዋጁ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል ከሆነም ቤቱ
እንዲመለስለት ስለመወሰኑ ማስረጃ አለማቅረቡን፣ ቤቱ እንዲመለስ የመወሰን ስልጣን ለጠ/ህግ
አለመሰጠቱን፣ ደብተር ባለቤትነትን የማያረጋግጥ መሆኑንና ጉዳዩ ከሚመለከተው አስተዳደር አካልም
የተሰጠ አለመሆኑን በመዘርዘር ተከራክረዋል፡፡

የስር ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ፍርድ ከመስጠቱ በፊት የካቲት 21ቀን 2011ዓ/ም በዋለው ችሎት አመልካቾች
ከ1976ዓ/ም ጀምሮ ቤቱን ይዘው እያከራዩ ለረጅም ጊዜ ሲያስተዳድሩት የነበረ ስለመሆኑ በተረጋገጠው ቤት
ተጠሪው ክስ ለማቅረብ የሚያስችለውን በጊዜና በተቋም የተገደበውን መብቱን የሚያሟላ መሆኑን
አላረጋገጠም ሲል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት በብይን ውድቅ ያደረገ ቢሆንም ከፍተኛው
ፍርድ ቤት ሽሮታል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ብይን የሻረው አዋጅ ቁጥር 572/2000
አንቀፅ 3እና 4 ድንጋጌ ቤት ይመለስልኝ አቤቱታ ለኤጀንሲው የሚቀርብበትን የሚወስን እንጅ የመፋለም
ክስን በይርጋ ለማቋረጥና የመፋለም ክስ በቀጥታ ለፍርድ ቤት እንዳይቀርብ ለመከልከል ታስቦ ባለመሆኑ
የተጠሪን ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 33(2) መሰረት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም በሚል ምክንያት
ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳዩ በዚህ መልክ የተመለሰለት የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካቾች ቤቱን
ለተጠሪ እንዲመልሱለት ውሣኔ ሰጥቷል፡፡ የስር ፍርድ ቤት ለሰጠው ውሣኔ መሰረት ያደረገው ተጠሪ
በማስረጃነት ያቀረበው ደብተር አዋጅ ቁጥር 47/67 ከተደነገገ በኋላ የተሰጠው በመሆኑ አዋጁ ሽሮታል
ማለት የማይቻል መሆኑን፣ ደብተሩ ራሱ ከከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር የተሰጠ እና ተጠሪ ቤቱን
በውርስ ያገኘው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ መሆኑን፣ የቀበሌ 23 ፅ/ቤት ሰኔ 12ቀን 1982 ዓ/ም የፃፈው
ደብዳቤም ቤቱ የተጠሪ መሆኑን የሚያጠናክር ማስረጃ መሆኑን በምክንያትነት በመዘርዘር መሆኑን ውሣኔው
ያስገነዝባል፡፡ ሆኖም አመልካቾች በማስረጃነት የቀረበውን ደብተር ጉዳዩ በሚመለከተው አካል የተሰጠ
ባለመሆኑ ባለቤትነትን የሚያረጋጥ አይደለም የሚል ክርክር ቢያቀርቡም ደብተሩ በሚኒስቴሩ ወይም በሌላ
በሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ ስለመሆኑ አለማረጋገጡን ተገንዝበናል፡፡

በሌላ በኩል አጣሪ ችሎቱ በዚህ ችሎት እንዲመረመር የያዘው ነጥብ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት

አመልካቾች ተረክበው ሲያስተዳድሩት የነበረ በመሆኑ ጉዳዩ በሚመለከተው አካል ቤቱ እንዲመለስ ውሣኔ

አለመሰጠቱን በሚመለከት ነው፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ የስር ፍርድ ቤት ቤቱ ለተጠሪ እንዲሆን ተወስኗል የሚል
መደምደሚያ እንዲይዝ ካስቻሉት ማስረጃዎች መካከል አንዱ ከላይ የተገለፀው የቀበሌ አስተዳደር ለጠ/ዐ/ሕግ
ፃፈው የተባለው ደብዳቤ መሆኑን የጉዳዩ አመጣጥ ያስገነዝባል፡፡ በደብዳቤው ይዘትና የአስረጅነት ደረጃ
አመልካቾች ከሚያነሱት ክርክር አኳያ መመዘኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ክሱ የቀረበው ደብዳቤው ተፃፈበት
ከተባለው ጊዜ 29ዓመት በኋላ በመሆኑ የደብዳቤው ትክክለኛነትም ደብዳቤውን ሰጥቷል በተባለው መስሪያ
ቤት ወይም ከወራሹ መረጋገጡ እውነተኛ ፍትህ ለመድረስ የሚረዳ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

በመሆኑም ፍርድ ቤቶች በግልፅ በቀረበላቸው ክርክር ውሣኔ ሊሰጡ የሚገባው በተቆጠረ ማስረጃ ወይም
አግባብነት ባለው መንገድ እንዲጣራ በማድረግ ሲሆን ይህ ሣያደርጉ የሚሰጡት ውሣኔ ተገቢነት የሌለው
ከመሆኑም በላይ የፍርድ ቤቶችን ዋና ግብ የሆነውን እውነትን የማፈላለግ ሃላፊነታቸው የሚጎዳ ነው፡፡
ሲጠቃለል የስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሚያቀርቡት ክርክር በመነሣት ተጠሪ ያቀረበው ደብተር ከከተማ
ልማትና ቤት ሚኒስቴር የተሰጠ መሆን አለመሆኑን፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ቀበሌ 23 ሰኔ12 ቀን
1982ዓ/ም ለጠቅላይ ዐ/ሕግ ፃፈው የተባለው ደብዳቤ በቀበሌው የተሰጠ መሆን አለመሆኑን በጥቅሉ ሁለቱም
የሰነድና የፅኁፍ ማስረጃዎች ከምንጫቸው መሰጠታቸውን ሳያረጋግጥ በተጠሪ ስለቀረቡ ብቻ አመልካቾች
ከ1976ዓ/ም ጀምረው ይዘው እያከራዩ ሲያስተዳድሩት የነበረውን ቤት ለተጠሪ እንዲመለሱ ውሣኔ መሰጠቱ
ተገቢውን የማጣራት ሂደት ያልተከተለ ሊታረም የሚገባው የሙግት አመራር ስህተት ሆኖ ስላገኘነው
ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል፡፡

ውሣኔ

1) የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 75761 ጥር 5ቀን 2013ዓ/ም የሰጠው
ውሳኔ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በመዝገብ ቁጥር 261471 ግንቦት 19ቀን 2013ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡
2) የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ በውሣኔ የዘጋውን መዝገብ ቁጥር 75761 እንደገና በማንቀሳቀስ
ከላይ በፍርዱ ሀተታ ላይ የተጠቀሱትን ሁለት የሰነድ ማስረጃዎች ከሚመለከታቸው የመንግስት
መስሪያ ቤቶች እና አካላት የተሰጡ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ በማድረግ እንዲሁም አስፈላጊ ነው
ብሎ ያመነበትን ጉዳይ ካጣራ በኋላ ግራቀኙን ከሚያቀርቡት ክርክር አንፃርተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ
እንዲሰጥበት ክርክሩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት ይመለስለት ብለናል፡፡
3) ይህ የሰበር ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የዬራሳቸውን ይቻሉ፡፡
ትዕዛዝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መዝገብ ቁጥር 75761 በጥንቃቄ ለስር ፍርድ ቤት ይመለስለት፤መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት


ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ5/5
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 204813እና206556

ቀን፡-30/11/2013ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡-1. ኮ/ል ተክለብርሃን ገ/መድህን

2. ኮ/ል አሰፋ አየለ ይመር

ተጠሪ፡- የደ/ዕዝ ወታደራዊ ዓ/ህግ

በዚህ መዝገብና በሰ/መ/ቁ.206556 የቀረቡት የሰበር አቤቱታዎች በስር ፍርድ በመ/ቁ.24/2013


ከተሰጠው ውሳኔ የተነሱ ክርክሮች በመሆናቸው መዝገቦቹ ተጣምረው ተመርምረው ተከታዩ ፍርድ
ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የወታደራዊ አገልግሎት ተግባሮችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን
አስመልክቶ ለበላይ አለመታዘዝ እንዲሁም ጠቅላላ የአገልግሎት ደንቦችን መጣስ ወንጀልን የሚመለከት
ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው በኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ይግባኝ ሰሚ
ወታደራዊ ፍ/ቤት በመ/ቁ 074/2013 የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር የቀዳሚ
ወታደራዊ ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናት የሰጠውን ፍርድ በመቃወም ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 1 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም በአመልካቾች ላይ በኢፌዲሪ


የቀዳሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት ባቀረበው የመጀመሪያ ክስ አመልካቾች የመከላከያ ሰራዊት ማቋቋሚያ
አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀጽ 2 (12)፣ የኮቪድ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በወጣው አስቸኳይ አዋጅ
ቁጥር 3/2012 በወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 298/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ ሰኔ 23 ቀን
2012 በግምት ከምሽቱ 3፡30 ሲሆን የተደራጁ ህገወጥ ቡድኖች ገጀራ ፣ፌሮ ብረትና ዱላ በመያዝ
በሻሸመኔ ከተማ የህብረተሰቡን ንብረት እያቃጠሉ እያወደሙና እየዘረፉ በመሆኑ በክፍሉ አመራር ሜ/ር
ጀኔራል ሹማ አብዴታ በስልክ ይህንን ህገወጥ ተግባር ተመጣጣኝ እርምጃ በመውሰድ እንዲቆጣጠሩ እና
ህብረተሰቡን እንዲታደጉ የሰጣቸውን ትዕዛዝ በመጣስ ትዕዛዙን ሳይፈጽሙ ቀርተዋል በማለት የከሰሰ
ሲሆን፤በሁለተኛው ክስም አመልካቾች የመከላከያ ሰራዊት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀት
2/12፣ የኮቪድ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር በወጣው አስቸኳይ አዋጅ ቂጥር 3/2012 እና በኢፌዲሪ ወንጀል
ህግ ቁጥር 32/1/ሀ እና 293/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በ1999 ዓ.ም የወጣውን የመከላከያ ሰራዊት
ቋሚ የግዳጅ አፈጻጸም ደንብ ቁጥር መከ-002/1999 ተ.ቁ 6.3 እና 7.5 መሰረት ሰራዊቱ ማናቸውም
ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲደርሱ አደጋውን ለማስቆም ተመጣጣኝ እርምጅ በመውሰድ ህዝቡን
ከአደጋ መታደግ እንዳለበት በግልጽ ተደንግጎ እያለ በተደራጁ ህገወጥ ቡድኖች የህብረተሰቡ ህይወት
አደጋ ላይ ሲወድቅ ንብረት በከፍተኛ ሁኔታ ሲዘረፍ ሲቃጠል የስር አመልካቾች ግዳጅ ላይ እያሉ
በመከላከያ ሀይሎች የአገልግሎት ደንብ መሰረት ተመጣጣኝ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ከአደጋ
ባለመታደጋቸው ጉዳት ሊደርስ ችሏል በማለት ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

አመልካቾች ባቀረቡት መቃወሚያም ሰራዊቱ ከኮቪድ ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ የመቆጣጠር ትዕዛዝ


ስላልተሰጠን በጦርነት ጊዜ የተፈፀመ ወንጀል ነው በሚል መቅረቡ አግባብነት የለውም፤ ሁለቱ ክሶች
በአንድ የወንጀል ማድረግ ሀሳብ የተፈጸሙ በመሆናቸው በወ/ህ/ቁ.61(1) መሰረት ተጠቃልለው በአንድ
ክስ ስር ሊቀርቡ ይገባል፤ አመልካቾች በአንድ መዝገብ መከሰሳቸው መብታቸውን ለይተው ለመከራከር
የማያስችላቸው መሆኑን ጠቅሰው ክሳቸው ተለይቶ እንዲከሰሱ ጠቅሰው ተከራክረዋል፡፡

የኢፌዲሪ የቀዳሚ ወታደራዊ ፍ/ቤት በቀረቡት መቃወሚያዎች ላይ በሰጠው ብይን መቃወሚያዎቹን


ውድቅ አድርጎ አመልካቾች እምነት ክህደት ሲጠየቁም ክደው የተከራከሩ በመሆኑ ታህሳስ 16 ቀን
2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የዓ/ህግ ምስክሮችን አስቀርቦ የሰማ ሲሆን 1ኛ የዓ/ህግ ምስክር በሰጠው
የምስክርነት ቃልም ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በከተማው እንዳንድ አካባቢዎች የግርግር
ምልክት በመኖሩ ወደ 1ኛ አመልካች ሲደውሉ ስላላነሱ ኮ/ል ሰለሞን ለ1ኛ አመልካች ሄዶ ሲነግረው
1ኛ አመልካች መልሶ ሲደውልለት የሁከት ምልክቶች ስላሉ የነገው ስብሰባ ቀርቶ ሰራዊቱ ለግዳጅ
ይዘጋጅ ብለው ትዕዛዝ የሰጡት መሆኑን ፤በማግስቱ ጠዋት 12፡30 1ኛ አመልካች ደውሎለት ሜ/ጄ
ሰለሞን ደውሎ ነበር ከተማ ውስጥ ቃጠሎዎች ስላሉ ፈጠን ብላችሁ ድረሱ ብሎኛል ታውቃለህ ወይ
ሲላቸው ከታዘዛችሁ ግቡ ያላቸው መሆኑን ወደ ሜ/ጄ ሰለሞን ደውሎ ትዕዛዙ የተሰጠ መሆኑን
እንዳረጋገጡ፤

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 2 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለ1ኛ አመልካች ያለህን መኪና ሰብስበህ በፍጥነት ድረስ ባሉት መሰረት 1ኛ አመልካች ሰራዊቱን
በመያዝ ከጧቱ 2፡15 አካባቢ ጥቁር ውሃን ያለፈ መሆኑን በዚህ ጊዜም ለ1ኛ አመልካች ደውለው
ምንም ንብረት መቃጠል የለበትም ማስቆም አለባችሁ አመፀኛው የታጠቀ ሀይል አይደለም በዱላ
የሚበተን ነው ያሉ መሆኑን አልፎ አልፎ ከ2ኛ አመልካች ጋር ሲገናኙ እንደነበረ፤1ኛ አመልካች
ከሽማግሌዎች ጋር እየተነጋገርን ነው በማለት ሲነግራቸው የነበረ ቢሆንም ህብረተሰቡ ስለቃጠሎው
መቀጠል ደውሎ ይነግራቸው የነበረ በመሆኑ 1ኛ አመልካችን በስልክ ደውለው አናግረው ድጋሚ ትዕዛዝ
የሰጡ ቢሆንም አመራሮቹ ግዴታቸውን ስላልተወጡ ቃጠሎው የቀጠለ መሆኑን፤2ኛ አመልካችን አልፎ
አልፎ ቃጠሎ ሲበዛ ይጨቀጭቁት የነበረ መሆኑን እርምጃ ውሰድ ሲሉት ሰው ብዛት አለው ምን
ላድርግ ሲላቸው በዱላ የሚበትን ሀይል ነው ያሉት መሆኑን ትዕዛዝ አልቀበልም ግን ያላላቸው
መሆኑን፤ በከተማው ውስጥ ጉዳቱ የደረሰው በሰው እጥረት ሳይሆን ቃጠሎውን አመራሮቹ
ባለማስቆማቸው መሆኑን ፤በከተማው ውስጥ አስቀድሞ የተጀመረ ቃጠሎ ቢኖርም አብዛኛው ውድመት
የደረሰው ሰራዊቱ ከገባ በኋላ መሆኑን፤አመልካቾች 3 ሻለቃ ከ500 የማያንስ ሰው የሚመሩ ሆኖ ከዚህ
ውስጥ አንድ ሻምበል ብቻ ግዳጅ ላይ ከመሆኗ ውጪ ሌላው ለግዳጁ የወጣ መሆኑን ቃጠሎውን
ያላስቆሙት በሰው እጥረት ሳይሆን መስራት ስላልቻሉ መሆኑን፤1ኛ አመልካች ትዕዛዝ ሲሰጡት
ያልተቃወመ ቢሆንም በትዕዛዙ መሰረት ባለመስራቱ ግን ጉዳቱ የደረሰ መሆኑን ፤2ኛ አመልካች
በግምገማ ወቀት እርምጃ መውሰድ ጀምረው ያስቆማቸው 1ኛ አመልካች መሆኑን የኦራል ጠባቂ ሆነን
ቀረን በማለት የነገራቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

2ኛ ምስክር የደቡብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜ/ር ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ሲሆኑ በሰጡት የምስክርነት
ቃልም በእለቱ ከጠዋቱ 12፡10 ሰዓት ሲሆን ለስር 1ኛ ተከሳሽ ደውሎ ችግር መኖሩን ገልጾ በሰው
ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ሀይል አሰማርተው እንዲያስቆሙት ግዳጅ የሰጣቸው
መሆኑን፣1ኛ አመልካች የተሸከርካሪ እጥረት ያለበት መሆኑን ሲገልፅላቸው 5 ፓትሮል የላኩለት
መሆኑን፤ከዚያ በኋላ ሂደቱን 1ኛ ምስክር እየተከታተለው ነበር በማለት አስረድተዋል፡፡

3ኛ ምስክር የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪና የኢትዮቴሌኮም ሴኩሪቲ ሱፐርቫይዘር መሆኑን ገልጾ አርቲስት
ሀጫሉ ሁንዴሳ በመገደሉ ችግር ይፈጠራል በሚል ደቡብ ሪጅን ለሚገኘው አለቃው ደውሎ ያሳወቀ
መሆኑን ከለሊቱ 10፡00 ጀምሮ ቃጠሎ እንደጀመረ እና እየሰፋ በመምጣቱ ድጋሚ 1፡00 ሲሆን
ለአለቃው እንደደወለለት፣ አለቃው ትንሽ ቆይቶ እንደደወለና ከቶጋ መከላከያ እየመጣ እንደሆነ 1ኛ
አመልካች ይመጣልሃል ይህን ስልክ ያዝና ደውልለት እንዳለው፣ ሲደውልም እየመጣን ነው ያሉት
መሆኑን መከላከያ ገብቶ ወደ አቦስቶ አልፎ የሄደ መሆኑን ቴሌ አካባቢ ያሉ ቤቶች መቃጠል ሲጀምሩ
ለ1ኛ አመልካች ሲደውሉለት እየመጣሁ ነው ይለው የነበረ መሆኑን ቴሌ ማማ ላይ ወጥተው ሲመለከቱ
ገጀራ፤ዱላ የያዙት ቤት ሲያቃጥሉ ተዉ የሚላቸው ያልነበረ መሆኑን ንብረቱ ተቃጥሎ ሲያልቅ ሰራዊቱ
በርቀት ቆሞ ተመለስ ሲል የነበረ መሆኑን ሰራዊቱ ከጠዋቱ 3፡00 አካባቢ ገብቶ አብዛኛው ንብረት
የተቃጠለውም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውሥጥ መሆኑን ፤ ለ1ኛ አመልካች ድጋሚ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 3 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሲደውልም እየመጣሁ ነው ከተማ ውስጥ ነኝ በሚል ሲያናግረው እንደነበር፣ እሰከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት
ድረስ እየደወለለት እነደነበር ከዛ በኋላ ተስፋ በመቁረጥ መደወል እንዳቆመ፣ ሰራዊቱ ጧት 3፡ 00
ጀምሮ እንደገባ ግን ምንም እርምጃ ያልወሰዱ መሆኑን፣ ማታ ሁሉም ነገር ከጠፋ በኋላ ዱላ በመያዝ
ማባረር እንደጀመሩ አስረድቷል፡፡

4ኛ ምስክር ሌ/ኮ/ጌታቸው ለማ በቀን 22/10/2012 ዓ.ም ሌሊት 9፡00 ለ1ኛ የስር ተከሳሽ ትዕዛዝ
መሰጠቱን ተከትሎ ከስር የሚመራቸውን ሰራዊቶች ዝግጅት እንዲያደርጉ በማድረግ ጠዋት ወደ
ከተማው የሄዱ መሆኑን፣ ገጀራና ዱላ የያዘ ሰው እየበዛ ሲሄድ ምስክሩ ለ1ኛ አመልካች እንበትን
ሲለው ተው ራሳቸው ይበተናሉ እንዳለው፣እዛው ቆመው ቃጠሎው እየባሰ የሄደ መሆኑን ሰራዊቱ
የአመልካቾችን ትዕዛዝ እየተጠባበቀ እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ደረስ ቆመው እንደቆዩ 5፡30 ሲሆን
አመልካቾች ከአሁን በኋላ መበተን ትችላላችሁ እንዳሉት፣ ከተማ ሲገቡ እየነደዱ የነበሩ ፎቆችና
ሆቴሎች እንዲሁም ነደው ያለቁ ህንፃዎች ቢኖሩም እዚያው እያሉ የተቃጠሉም መኖራቸውን
ለማሳያነትም የፀጋዬ ህንፃ ከስር ጭስ የነበረው ቢሆንም ተቃጥሎ ያለቀው እዚያው እያሉ መሆኑን፤
2ኛ አመልካች ግዳጅ መቀበል ያለበት ከ1ኛ አመልካች መሆኑን ገልጾ መስክሯል፡፡

5ኛ ምስክር ደግሞ በጦር ሰፈር የነበረውን ከግዳጅ መልስ ባደረጉት ግምገማ አመልካቾች ግዳጅ
ከመፈጸም ይልቅ ከነውጠኛ ጋር ሽምግልና በመያዝ መደራደረ የአመልካቾች ችግር እንደሆነ
መገምገሙን መስክሯል፡፡ 6ኛ ምስክር የራሱን አለቃ ሌ/ኮ ጌታቸውን ለምን አንበትናቸውም ሲለው ወደ
አመልካቾች ሄዶ አነጋግሮ ሲመለስ ተረጋጉ ትዕዛዝ አየጠበቅን ነው ያለው መሆኑን፣ ነውጠኛው
እየጨመረ እና ወደ ምስክሩ ሲቀርቡ ወደ ኋላ ተመለሱ ትዕዛዝ እየጠበቅን ነው በማለት
እንደገለጸላቸውና ወደ ኋላ ያፈገፈጉ መሆኑን፣ ከዛም ነውጠኞቹን እንዳሳለፏቸው እነዚህ ያሳለፏቸው
አለፍ ብሎ ያለውን ፎቅ ያቃጠሉ መሆኑን ፣ እርምጃ መውሰድ የተጀመረው ከቀኑ 5፡30 በኋላ እንደሆነ
አስረድቷል፡፡ ፍ/ቤቱም የዓ/ህግ ምስክሮችን መርምሮ ምስክሮቹና ማስረጃው የዓ/ህግን ክስ ያስረዱ
በመሆኑ አመልካቾች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡

የአመልካቾች 1ኛ ምስክር በመሆን 2ኛ አመልካች ቀርቦ በሰጠው የምስክርነት ቃልም ኮ/ል ከማል
በ22/10/2012 ዓም ሌሊት 8፡00-9፡00 ባለው ደውሎ ያንተ ኮሚቴ 1ኛ አመልካች ስልክ አያነሳም ኮ/ል
ሹማ ይፈልግሃል ብለህ ንገረው እንዳለው፣ በሰዓቱ ሄዶ ኮ/ል ሹማ እንደሚፈልገው ለ1ኛ አመልካች
እንደነገረው የተነጋገሩትን ባያውቅም ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ተዘጋጁ ስለተባሉ የስራ ክፍፍል
አድርገው አድረው ከጠዋቱ 1፡30 ሰራዊት ይዞ መንገድ እያስከፈቱ ሻሸመኔ መግቢያ ላይ ከጠዋቱ 3፡00
የደረሱ መሆኑን 1ኛ አመልካችም የቀረውን ሀይል ይዞ የመጣ መሆኑን፤ እንደደረሱ ንብረት
እየተቃጠለና እየወደመ እንደነበር ለኮ/ል ሹማ ሲደውሉ ከተማው ተቃጥሎ አልቋል ለምንድነው
የመጣነው አሁን ያሉት ሰዎች ፖስተር ይዘው የሚያለቅሱ ናቸው ምን እናድርግ ሲለው ጠብቁ
እደውላለው ያላቸው ሲሆን እና በተደጋጋሚ ከ1ኛ ስር ተከሳሽ ጋር እንደሚደዋወሉ፣ በኋላ 5፡00 አካባቢ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 4 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ደውሎ ተመጣጣኝ እርምጅ እንዲወስዱ ደውሎ ለስር 1ኛ ተከሳሽ እንደነገረውና አመልካችም ወደ


ተግባር እንደገባ ፣አሳልፈዋቸው ያቃጠሉ ግለሰቦች አለመኖራቸውን አመፅ ከተነሳ ምን ማድረግ
እንዳለባቸው ያልተነገራቸው መሆኑን ከታዘዙ በኋላ ግን ግዳጃቸውን የፈፀሙ መሆኑን ወደ ከተማ ከገቡ
በኋላ አዲስ የተቃጠለ ነገር ያልተመለከቱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

2ኛ የመ/ምስክር 1ኛ አመልካች ሲሆን በ22/10/2012 ዓም ሌሊት 2ኛ አመልካች ኮ/ል ሹማ


ይፈልግሃል ሲለው ደውሎ ሲያናግረው የተያዘው ስብሰባ ይቅርና አርቲስት ሀጫሉ ስለሞተ ዝግጁ ሁኑ
የሚል ትዕዛዝ የተሰጠው መሆኑን፣ ጠዋት 3፡30 ሲሆን የደረሱና ወደ 4፡00 ገደማ ኮ/ል ሲደወልለት
ሰላማዊ በሆነ መንገድ ፍቱ ያለው መሆኑን፣ ከቀኑ 5፤00 ሰዓት ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ
የተሰጠው መሆኑን፣ መጀመሪያ ላይ ቀላል የነበርና በቀላሉ መፍትሔ ይገኝ እነደነበር በኋላ ግን ነውጠኛ
እየበዛ በመሄዱ አስቸግሯቸው እንደነበር፣በእርምጃ ደረጃ ከታየ የነበረው ያልታጠቀ ስለሆነ ከታጠቀው
ሰራዊት አንፃር እርምጃ ለመውሰድ ከአቅም በላይ አለመሆኑን ነገር ግን ሜ/ጀ ሹማ በተቻለ መጠን
ህይወት ሳይጠፋ ፍቱ ያላቸው መሆኑን፤እርምጃ እንዲወስዱ ከታዘዙ በኋላ ግን ለ2ኛ አመልካችና
ለሻለቃና ሻምበል አመራሮች ትዕዛዝ ሰጥቶ ተግባራዊ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

የአመልካቾች 3ኛ የመከላከያ ምስክር በሰጠው የምስክርነት ቃልም በእለቱ ወደ ከተማው ሲደርሱ


ከፍተኛ እሳት ስለነበረ እንምታቸው ሲሉ 2ኛ አመልካች ቆዩ ያላቸው መሆኑን፤ከጠዋቱ 3፡20 እስከ
5፡20 ድረስ ቆመው ቆይተው እርምጃ እንድንወስድ ታዘናል ሲሉ ወደ እርምጃ የገቡ መሆኑን
ከሰልፈኛው ጋር ከመነጋገር ይልቅ በትነው ማለፍ የነበረባቸው መሆኑን በየደረሱበት ሱቆች እየተቃጠሉ
ከመሆኑ ውጪ አዲስ ቃጠሎ አለመኖሩን ያስረዱ ሲሆን ፤4ኛ የመ/ምስክር በበኩላቸው በስፍራው
እንደደረሱ ጦሩ ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ቆዩ የተባሉ መሆኑን፤ከደረሱ በኋላ የተቃጠለ
ቤት አለመኖሩን፤ለአመልካቾች ከላይ የወረደ ትዕዛዝ ይኑር አይኑር የማያውቅ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የግራቀኙን ምስክሮች የሠጡትን የምስክርነት ቃል የሰነድ ማስረጃዎችንና የድምፅ
ማስረጃዎችን መርምሮ በሰጠው ውሳኔም ተጠሪ ባቀረባቸው ምስክሮች አመልካቾች ገና ከጦር ሰፈራቸው
ሲነሱ በሻሸመኔ ከተማ ቃጠሎ የተጀመረ መሆኑ ተነግሯቸው ይህንኑ ቃጠሎና ውድመት እንዲያስቆሙ
በሜ/ጀ ሹማ የታዘዙ መሆኑን ትዕዛዙ ለ1ኛ አመልካች በተደጋጋሚ የተሰጠ ቢሆንም 2ኛ አመልካችም
የታዘዙ መሆኑን ፤3ኛ ምስክርም እየደረሰ ያለውን ጥፋት መሰረት በማድረግ እንዲደርሱላቸው
ቢማፀኑም የንብረት ማቃጠልና የሰው ህይወት ማጥፋት ድርጊቱ የቀጠለ ቢሆንም ሰላማዊ ሰልፍ ነው
በማለት የራሳቸውን ትርጉም በመስጠት ትእዛዙን ሳይቃወሙ ግን ትዕዛዙ ወደ ተግባር ተለውጦ የሀገር
ሀብት የማዳን ስራ እንዳይሰራ ማድረጋቸውን ማስረዳቱን፤የመከላከያ ምስክሮቹ መጀመሪያም በዱላ
በመበተን የሰው ህይወትና ንብረት አድኑ በማለት ከተሰጠው ትዕዛዘ የተለየ ትዕዛዝ መኖሩን ሳያስረዱ
ከታዘዝን በኋላ በዱላ እየበተንን የሚቃጠለውን እያስጠፋን ስራችንን ቀጠልን ማለታቸው የተጠሪን
ማስረጃ የሚያጠናክር መሆኑን፤ከአመልካቾች ሀላፊነት አንፃር የበላይ አመራር ተመጣጣኝ እርምጃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 5 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እየወሰዳችሁ የህዝብ ንብረት አድኑ ቃጠሎ አስቁሙ ብሎ ማዘዝ ይቅርና በራሳቸውም የስራ ሀላፊነት
ከሰራዊቱ የቋሚ ግዳጅ አፈፃፀም ደንብ አንፃር መውሰድ የሚገባቸው መሆኑን፤

1ኛ አመልካች ያቀረበው የስልክ ልውውጥ ድምፅ ቅጂ ከጠዋቱ 4፡14 ከገጠር የመጡት እያቃጠሉ
እንደነበረ ለበላይ ሲናገር የነበረ መሆኑን ማስረዳቱ እኛ ከደረስን በኋላ ቃጠሎ አልነበረም በማለት
ከገለፁት ጋር የሚቃረን የተጠሪን ማስረጃ የሚያጠናክር መሆኑን፤የድምፅ ቅጂው 4፡14 መጀመሩም
አስቀድሞ የተደረገውን ያልያዘ ሆነ ተብሎ የተዘጋጀበትን የሚያሳይ መሆኑን ከረፋዱ 5፡02 እስከ 5፡24
የተቀረፀው ከበላይ አዛዦች ጋር ያለውን የስልክ ልውውጥ ሳይሆን ሆነ ተብሎ ክፍት ተደርጎ
የተቀረፀውን መሆኑን ሆነ ብሎ አስቀድሞ በመዘጋጀት የተቀረጣን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ
በአጠቃላይ አመልካቾች በተጠሪ የቀረበባቸውን ክስና ማስረጃ አለማስተባበላቸውን በመጥቀስ
በቀረበባቸው የወንጀል ህግ አንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ በማድረግ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት
ተቀብሎ በመመርመር 1ኛ አመልካች በዘጠኝ አመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት፤2ኛ አመልካች በ6
ዓመት ከ 6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሙሉ ድምጽ የወሰነ ሲሆን ይህ ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው
ወታደራዊ ፍ/ቤትም ፀንቷል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡1ኛ አመልካች በሰ/መ/ቁ.204813
መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓም በተፃፈ ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም አመልካች የተከሰሱት ከአስቸኳይ
ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በተሰጣቸው ግዳጅ አለመሆኑን ከኮቪድ ወረርሺኝ ጋር በተያያዘ የተሰጣቸው
የበላይ አመራር ትዕዛዝ እና ጠቅላላ የአገልግሎት ደንብ አለመኖሩን በሰበር መዝገብ ቁጥር 193054
ከተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማያያዝ ያቀረብነው
መቃወሚያ ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም፤አመልካች የተሰጣቸውን ትዕዛዝ መጣሳቸው
ባልተመሰከረበት፤ሁለቱ ክሶች አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ሆነው እያለ አመልካቾች የበላይ አመራር
ትዕዛዝ አልፈፀሙም ተብሎ ክስ ቀርቦባቸው እያለ እንደገና በ2ኛው ክስ በራሳቸው ተነሳሽነት እርምጃ
መውስድ ነበረባቸው ተብሎ ክስ መቅረቡ አግባብ ባለመሆኑ ምስክር ከተሰማ በኋላም ቢሆን
በወ/ህ/ቁ.61(1) መሰረት ተጠቃልሎ በአንደኛ ክስ ስር ሳይቀርብ በሁለቱም ክሶች ጥፋተኛ መባላችን
መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፤

የመከላከያ ምስክሮቻችን በቦታው ሲደርሱ ሆቴሎች፤ፎቆችና ሱቆች ተቃጥለው ያለቁና በመቃጠልም


ላይ የነበሩ መሆኑን፤እኛ ከደረስን በኋላ እንደ አዲስ ያቃጠሉት አለመኖሩን ሰልፈኞቹ እርማችን
ለማውጣት ስለሆነ አሳልፉን ብለው በጠየቁት መሰረት ያለፉ ያደረሱትም ጉዳት አለመኖሩን ትዕዛዝ
ከተሰጠን በኋላ እርምጃ በመውሰድ ሰልፉን የበተንን መሆኑን አስረድተው እያለ የቀደመ ትዕዛዝ
አለመኖሩን አረጋግጠው መስክረው እያለ ክሱንና ማስረጃውን አላስተባበሉም በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ
መሰጠቱ ቅጣትን አስመልክቶም ሁለቱ ክሶች ወደ ንዑስ 1 ቀይረው ቢያከራክሩ ኖሮ ቅጣቱ ከብዶ
የማይወሰን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅጣቱ ሲሰላም ለረዢም ጊዜ ሀገራችንን በቁርጠኝነት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 6 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማገልገላችንና በዚህ አገልግሎትም 1ኛ አመልካች ሶስት ጊዜ መቁሰሌ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ቅጣቱ
መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት ካቀረብነው መቃወሚያ
አንፃር የተሰጠው ብይን እንዲታረምልኝ፤በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ተሽሮ በነፃ እንደሰናበት
ይወሰንልኝ ፤ይህ ቢታለፍ ቅጣቱ ከላይ በተመለከቱት ማቅለያዎች አግባብ ቀልሎ ይወሰንልኝ በማለት
አመልክተዋል፡፡

ለአመልካቾች ከበላይ የተሰጣቸው ትዕዛዝ ግልፅ ስለመሆኑና፤የወንጀል ድርጊቶቹን ስለመፈፀማቸው


የተረጋገጠበትን አግባብ እንዲሁም ትዕዛዙ እንደ ጦር ሜዳ ግዳጅ ተወስዶ በሁለት ድንጋጌዎች ስር
ጥፋተኛ የተባሉበትን አግባብ አግባብነት ካላቸው ህጎች አንፃር ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል
ከተባለ በኋላ ለተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓም የተፃፈ መልሱን አቅርቧል፡፡

ተጠሪ በዚህ መልሱም በሁለቱም ክሶች የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ራሳቸውን ችለው የሚቋቋሙ እና
ግዙፋዊ ውጤትን የሚያስከትሉ በመሆናቸው ሁለቱም ክሶች ተነጣጥለው መቅረባቸው በአግባቡ
ነው፤አንድ የሰራዊት አባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ፀንቶ ባለበት ጊዜ ለፀጥታ አካላት የሚሰጠውን ግዳጅ
በላቀ ውጤት የመፈፀም ግዴታ ያለበት በመሆኑ የተከሰሱባቸው ሁለቱም ወንጀሎች በጦርነት ወቅት
እንደተፈፀሙ የሚቆጠሩ በመሆናቸው በወንጀል ህግ አንቀፅ 298(2) እና 293(2) መከሰሱ በአግባቡ
ነው፤በወቅቱ በተፈጠረው ህገወጥ ተግባር ምክንያት በሻሸመኔ ከተማ ውስጥ 287 አባወራዎች
የተፈናቀሉ፤26 ፎቆችና 179 ቤቶች የተሰባበሩ፤21 ፎቆች 52 መኪናዎች 26 ባጃጆች 40 ሞተር
ሳይክሎች 38 ሆቴሎች 23 ሱቆች፤9 ወፍጮ ቤቶችና 196 ቤቶች የተቃጠሉ በመሆኑ ለጉዳዩ አግባብነት
ያለውን ድንጋጌ በመጥቀስ ክሱን ያቀረብን በመሆኑ አመልካች በዚህ ወቅት ከበላይ የተሰጠውን ትዕዛዝ
አለመፈፀሙን ያስረዳን በመሆኑ በስር ፍርድ ቤት አግባብነት ያላቸው ማቅለያዎች ተይዘውለት ቅጣቱ
የተሰላ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

2ኛ አመልካች ሚያዚያ 19/2013 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔና ትዕዛዝ ላይ
ተፈፅሟል ያሉትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍሬ
ቃሉም በአንድ ወንጀል ማድረግ ሃሳብ እንደተፈፀሙ የሚቆጠሩ የተቀላቀሉ ድርጊቶችን ነጣጥሎ ሁለት
ተደራራቢ ወንጀሎች ክስ ማቅረብ በዚሁ የጥፋተኝነት ፍርድ በአመልካች ላይ ማስተላለፉ መሰረታዊ
የህግ ስህተት መሆኑን፣ የወንጀል ድንጋጌዎችን የሚያከብድ ድንጋጌ ስር ለማቅረብ የሚያበቃ ህጋዊ
ምክንያት በሌለበት ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን የሰራዊቱን ማቋቋሚያ አዋጅ እና ከኮቪድ
ወረረሽኝ ጋር በተያያዘ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሰረት በማድረግ ክስ መቅረቡ መሰረታዊ
የህግ ስህተት መሆኑን፣ በአመልካች ላይ የቀረበው ክስ በስር ፍ/ቤት አብረው ከተከሰሱት የቅርብ
አዛዣቸው ክስ ተነጥሎ ያለመቅረቡ መሰረታዊ የህግ ስሀተት መሆኑን፣ ተጠሪ በአመልካች ላይ
የቀረበውን ክስ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ ባላስረዳበት እና አመልካች ባቀረባቸው ማስረጃ
በተስተባበለበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ስህተት መሆኑን፣ የቅጣት ውሳኔው በፌ/ጠ/ፍ/ቤት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 7 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የወጣውን የቅጣት መመሪያ ቁጥር 2/2006 ተከትሎ ያልተሰጠ መሆኑን በመግለጽ በነጻ እንዲሰናበት
ካልሆነ ቅጣቱ እንዲታይላቸው በማመልከታቸው ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የአሁን አመልካች አግባብነት ካለው የበላይ አዛዥ ትዕዛዝ
የተሰጣቸው ለመሆኑና የቀረበባቸውን የወንጀል ድርጊት ስለመፈጸማቸው የተረጋገጠበት ትዕዙዙም እንደ
ጦር ሜዳ ግዳጅ ተወስዶ በወንጀል ህግ አንቀጽ 298/2/ እና 293/2/ ስር በሁለት ህግ ድንጋጌ
የጥፋተኝነት እና ቅጣት ውሳኔ የተሰጠበት አግባብነት ከመከላከያ ሰራዊት ማቋቋሚያ አዋጅ 1100/2011
አንቀጽ 2/12/ ፣ የኮቪድ 19 ወረረሽኝ ስርጭት ለመቆጣጠር የወጣው አስቸኳይ አዋጅ ቁጥር 3/2012፣
የወንጀል ህግ ቁጥር 61፣ የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት ቋሚ የግዳጅ አፈጻጸም ደንብ ቁጥር መከ-
002/1999 ቁጥር 6.3፣7.5 አንጻር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ለመመርመር ለዚህ ሰበር ችሎት
ቀርቦ እንዲታይ በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

ተጠሪ በቀን ሰኔ 8/2013 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች የተከሰሰባቸው ወንጀሎች ተደራራቢ
መሆናቸውን፣ አመልካች ወንጀሉን በሚያከብድ አንቀጽ መከሰሱ ተገቢ መሆኑን፣ አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ባለበት ሁኔታ የጸጥታ ሁኔታ በላቀ ሁኔታ ነቅቶ መጠበቅ ሲገባው ግዳጅ ተሰጥቶትም በግዳጁ መሰረት
አለመፈጸሙ፣ የተፈጸሙት ሁለቱም ወንጀሎች ጦርነት ባለበት ወቅት እንደተፈጸሙ የሚቆጠሩ
መሆኑን፣ አንደኛው ክስ የበላይ አለቃን ትዕዛዝ አለማክበር ራሱን የቻለ ወንጀል ሲሆን 2ኛው ደግሞ
የህዝብ ንብረት እየወደመ፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት የመከላከል ግዴታ እያለበት
ግዴታውን ባለመወጣቱ የተከሰሰው ክስ ራሱን የቻለ ወንጀል መሆኑን፣ ክሱ በሁለቱም በአንድ ላይ
የቀረበው ግዳጁ በጋራ የተሰጠና የተከሰሱበት ወንጀል ህግም ተመሳሳይ በመሆኑ መሆኑን፣ ተጠሪ
ሁለቱንም ክሶች በበቂ ሁኔታ ያስረዱ መሆናቸውንና አመልካች በማስረጃው ያላስተባበለ መሆኑን፣
የቅጣት ውሳኔ መመሪያውን መጠቀም ነበረባቸው ለሚለው በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት መ/ቁ 118227
መመሪያውን የመከተል ግዴታ እንደደለሌበት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የተሰጠ መሆኑን፣ በመሆኑም
ወንጀሉ በባህሪው ለየት ያለ እና የቅጣት ደረጃ ያልወጣላቸው መሆኑን፣ ጠቅሰው የስር ፍ/ቤት
የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በአግባቡ በመሆኑ እንዲፀናላቸው ተከራክረዋል፡፡

አመልካቾች የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክር ይዘት ጠቅለል ባለ መልኩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም ከሰበር
ቅሬታው አኳያ እና ከስር ፍ/ቤት መዝገብ ይዘት አንፃር የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር አግባብነት ካለው
ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡በመሰረቱ በስር ፍርድ ቤት ቀርበው የተሰሙት
የተጠሪ ምስክሮች በዋነኝነትም 1ኛ ምስክር ከአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በከተማው እንዳንድ
አካባቢዎች የግርግር ምልክት በመኖሩ በመነሻነት ማታውን በማግስቱ የነበረው ስብሰባ ቀርቶ ሰራዊቱ
ለግዳጅ ይዘጋጅ ብለው ማታውን ትዕዛዝ ለ1ኛ አመልካች የሰጡት መሆኑን፤ጠዋቱን አመልካቾች
በስራቸው ያለውን ሀይል ይዘው ከካምፓቸው ሲነሱ በሻሸመኔ ከተማ ቃጠሎ የተጀመረ መሆኑ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 8 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተነግሯቸው ይህንኑ ቃጠሎና ውድመት እንዲያስቆሙ በሜ/ጀ ሹማ የታዘዙ መሆኑን ትዕዛዙ ለ1ኛ
አመልካች በተደጋጋሚ የተሰጠ ቢሆንም 2ኛ አመልካችም የታዘዙ መሆኑን፤

አመልካቾች ሀይላቸውን ይዘው ወደ ከተማው ሲገቡ ቃጠሎ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም አብዛኛው ቃጠሎ
የደረሰው አመልካቾች የሚመሩት ሀይል ወደ ከተማ ከገባ በኋላ መሆኑን፤በከተማው ውስጥ ጉዳቱ
የደረሰው በሰራዊቱ ባለው የሰው ሀይል እጥረት ሳይሆን ቃጠሎውን አመራሮቹ ባለማስቆማቸው መሆኑን
ምስክሮቹ ያስረዱ ሲሆን 1ኛ ምስክር ከዚህ በተጨማሪ አመልካቾች ሰራዊቱን እየመሩ ከጠዋቱ 2፡15
ወደ ከተማ ሲገቡ ጀምረው ለ1ኛ አመልካች ደውለው ምንም ንብረት መቃጠል የለበትም ማስቆም
አለባችሁ አመፀኛው የታጠቀ ሀይል አይደለም በዱላ የሚበተን ነው ብለው መንገራቸውን ቃጠሎው
ሲበዛም 2ኛ አመልካችን ይጨቀጭቁት የነበረ መሆኑን በማስረዳት ከመነሻውም አመልካቾች ወደ
ከተማው ሲገቡ በግልፅ የተፈጠረውን ሁከት እንዲያስወግዱ የታዘዙ መሆኑን አመልካቾች ግን
ምክንያት እያቀረቡ ትዕዛዙን ሳይፈፅሙ የቀሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አመልካቾች ከራሳቸው ውጪ ለጉዳዩ ገለልተኛ የሆኑ ሁለት የመከላከያ ምስክሮችን ያቀረቡ ሲሆን
ከመነሻውም ለአመልካቾች ከበላይ የተሰጠ ትዕዛዝ መኖር አለመኖሩን አለማወቃቸውን አስረዱ እንጂ
የበላይ ትዕዛዝ አለመኖሩን በማረጋገጥ የሰጡት የምስክርነት ቃል የለም፡፡3ኛ እና 4ኛ የመ/ምስክሮች
ቃጠሎውን ሲመለከቱ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ሲጀምሩ ቆይ መባላቸውን ከማስረዳት ውጪ
ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰዱ አስፈላጊ የነበረ ከማረጋገጥ ባለፈ አመልካቾች ቆይ ያሏቸው የበላይ
ትዕዛዝ ባለመኖሩ መሆኑን አላስረዱም፡፡እኝ ምስክሮች ሰራዊቱ ወደ ከተማ ከገባ በኋላ አዲስ ቃጠሎ
አለመኖሩን ያስረዱ ቢሆንም ይህንን የምስክርነት ቃል 1ኛ አመልካች ካስቀረቡት የስልክ ልውውጥ
ድምፅ ቅጂ ጋር ስንመረምረው 3ኛ የመ/ምስክር ከጠዋቱ 3፡20 ወደ ከተማው የገቡ መሆኑን አስረድተው
እያለ የድምፅ ቅጂው ከጠዋቱ 4፡14 ከገጠር የመጡት እያቃጠሉ እንደነበረ 1ኛ አመልካች ለበላይ
ሲናገሩ የነበረ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑ የምስክሮቹ ቃል በመከላከያ ማስረጃነት በቀረበው የድምፅ ቅጂ
እንደተስተባበለ ማስረጃን የመስማት፤የመመርምርና የመመዘን ስልጣን ባለው በስር ፍርድ ቤት
የተረጋገጠ መሆኑን ያሳያል ፡፡

በአጠቃላይ አመልካቾች በእለቱ ሰራዊቱን ይዘው ወደ ከተማ ሲገቡ የተፈጠረውን ሁከት እንዲያሰወግዱ
በግልፅ ከበላይ ትዕዛዝ የተሰጣቸው መሆኑን ትዕዛዙን ላለመፈፀም የሰው ሀይል ማነስን በምክንያትነት
ያስቀመጡ ቢሆንም በከተማው ውስጥ ጉዳቱ የደረሰው በሰራዊቱ ባለው የሰው ሀይል እጥረት ሳይሆን
በተሰጣቸው ትዕዛዝ አግባብ ሰርተው ቃጠሎውን አመራሮቹ ባለማስቆማቸው መሆኑን ተጠሪ
ባልተስተባበለ መልኩ ማስረዳቱ ማስረጃን የመስማት፤የመመዘንና የመመርመር ስልጣን ባላቸው የስር
ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ነጥብ ነው፡፡

ይህ ፍሬ ነገር በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ከሆነ ደግሞ በቀጣይ ሊመረመር የሚገባው ለጉዳዩ
አግባብነት ያለው ድንጋጌ የትኛው ነው የሚለው ይሆናል፡፡በዚህ አግባብም ማንኛውም የመከላከያ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገ ጽ 9 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሰራዊት አባል አስቦ ከበላይ አዛዡ ተግባሩን በሚመለከት በቃል፤በፅሁፍ፤በምልክት ወይም በማናቸውም
ሌላ መንገድ በቀጥታ ለራሱ ወይም እርሱ ለሚገኝበት የጦር ክፍል የተሰጠውን ማናቸውንም ትዕዛዝ
ሳይፈፅም የቀረ ወይም ለመፈፀም እንቢተኛ ከሆነ ለበላይ ባለመታዘዝ የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ
ተብሎ ተገቢው የቅጣት ውሳኔ የሚተላለፍበት መሆኑን የወ/ህ/አ.298 (1) ይደነግጋል፡፡በወ/ህ/አ.298(2)
ቅጣቱ ከብዶ ሊወሰን የሚችለው ድርጊቱ የተፈፀመው የጦር አደጋ ምልክት በተሰጠበት፤የጦር ክተት
በታወጀበት ወይም በጦርነት ጊዜ ከሆነና እንቢተኛነቱም ቁርጠኛ ከሆነ እንደሆነ ድንጋጌው በግልፅ
ያሣያል፡፡

በመሰረቱ በህጉ መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚከናወን የመከለከያ ሰራዊት ግዳጅ የጦር ሜዳ
ግዳጅ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አዋጅ ቁጥር 1100/2011 በአንቀፅ 2(12)
የሚደነግግ ሲሆን አሁን በያዝነው ጉዳይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደርጎ የቀረበው የኮቪድ ወረርሺኝን
ለመቆጣጠር የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 መሆኑን የተጠሪ ክስ ያሳያል፡፡በነዚህ
ድንጋጌዎች አግባብ አመልካቾች በወ/ህ/አ.298(2) አግባብ በጦር ሜዳ ግዳጅ ላይ ሆነው ለበላይ
አለመታዘዝ የወንጀል ድርጊት ፈፅመዋል ሊባል የሚችለው ከኮቪድ ወረረሽኝ ጋር በቀጥታ በተያያዘ
መልኩ አዋጁን ለማስፈፀም አመልካቾች የሚመሩት ሰራዊት በራሱ ብቻውን ወይም ከሌሎች የሀገሪቱ
የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ጋር ተደራጅቶ በስምሪት ላይ ሆኖ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመፈፀም ላይ
የነበረ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡አሁን በያዝነው ጉዳይ ለክሱ ምክንያት የሆነው ለበላይ አለመታዘዝ
የወንጀል ድርጊት በአመልካቾች የተፈፀመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመፈፀም ላይ እያሉ ስለመሆኑ
ክሱም ሆነ ማስረጃው አያሳይም፡፡

ከኮቪድ ወረርሺኝ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ለአመልካቾች በግልፅ ትዕዛዝ የተሰጠ
ለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ለክሱ መነሻ የሆነው ሁከት የተፈጠረው የኮቪድ ወረርሺኝ አስቸኳይ ጊዜ
አዋጅ በሀገሪቱ ታውጆ ባለበት ጊዜ ውስጥ ስለሆነ ብቻ አመልካቾች በጦር ሜዳ ግዳጅ ላይ ነበሩ ሊባሉ
የሚችሉበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ ከዚህም በተጨማሪ የወ/ህ/አ.298(2) የህጉ መስፈርት ማለትም
እንቢተኛነቱ ቁርጠኛ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ከዚህ ይልቅ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች አመልካቾች
እንቢተኛ አለመሆናቸውን፤ ሆኖም አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት በማቅረብ ትዕዛዙን አለመፈፀማቸውን
እያስረዱ የስር ፍርድ ቤቶች አመልካቾችን በወ/ህ/አ.298(2) ስር ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ውሳኔ
መስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው አመልካቾች ጥፋተኝ ሊባሉ
የሚገባው በወ/ህ/አ.298(1) ስር ነው በማለት ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ሁለተኛውን ክስ በተመለከተም አመልካቾች በወ/ህ/አ.293 ስር ጥፋተኛ ተብለው የቅጣት ውሳኔ


ሊተላለፍባቸው የሚችለው በግልፅ የተሰጠ የበላይ ትዕዛዝ ባይኖርም ከመከላከያ ሰራዊት ቋሚ የግዳጅ
አፈፃፀም ደንብ አንፃር በወቅቱ የተፈጠረውን በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለውን
ሁከት በራሳቸው በሚወስዱት እርምጃ ሊያስቆሙ ሲገባ ይህንን ባለማድረጋቸው የደረሰ ጉዳት መኖሩ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 10 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሲረጋገጥ ሲሆን አሁን በያዝነው ጉዳይ ከበላይ አዛዦች በግልፅ የተሰጠ ትዕዛዝ ስለመኖሩ በተረጋገጠበት
በትእዛዙ መሰረት ባለመፈፀማቸውም ከላይ በተመለከተው አግባብ በ1ኛው ክስ ጥፋተኛ በተባሉበት
ትዕዛዝ ተሰጥቷችሁ ባለመስራታችሁ የወንጀል ሀላፊነት አለባችሁ እየተባሉ ባትታዘዙም ከመከላከያ
ሰራዊት ቋሚ የግዳጅ አፈፃፀም ደንብ አንፃር የወንጀል ሃላፊነት አለባችሁ ተብለው በሁለተኛው ክስ
ጥፋተኛ ሊባሉ የሚገባበት የህግ አግባብ ባለመኖሩ የስር ፍርድ ቤቶች እነዚህን ነጥቦች ከግምት ውስጥ
ሳያስገቡ የሰጡትን ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህሀት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው በመሻር አመልካቾች
ከሁለተኛው ክስ በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል በማለት ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ቅጣትን አስመልክቶ አመልካቾች ጥፋተኛ የተባሉበት የወንጀል ድርጊት ከአምስት አመት በማይበልጥ
ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ ሲሆን ቅጣቱን ለማክበድ የሚያስችል በቂ ምክንያ ያልቀረበ ቢሆንም
አመልካቾች በግልፅ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ባለመፈፀማቸው በሰው ህይወትና አካል ላይ እንዲሁም
በንብረቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ፤ትዕዛዙ በቀጥታ በተደጋጋሚ ሲሰጥ
የነበረው ለ1ኛ አመልካች መሆኑን እንደሁም ከትዕዛዙ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ያላቸውን የቀደመ
ሀላፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሌላ በኩል ደግሞ አመልካቾች የተያዘባቸው የቀደመ ሪከርድ
አለመኖሩ ያላቸውን መልካም ፀባይ የሚያሳይ መሆኑን፤የቤተሰብ አስተዳዳሪነታቸውን፤ረዥም
የውትድርና አገልግሎታቸውንና በዚህ ጊዜም የደረሰባቸውን አካላዊ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት
በዚህ ጉዳይ የታሰሩበት ጊዜ ታስቦ 1ኛ አመልካች በሶስት አመት ፅኑ እስራት ፤2ኛ አመልካች በሁለት
አመት ከስድስት ወር ፅኑ አስራት እንዲቀጡ የስር ፍርድ ቤትን የቅጣት ውሳኔ ማሻሻል ፍርድ
ሰጥተናል፡፡ስለሆነም የሚከተለው ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1.የቀዳሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የደቡብ ዕዝ ችሎት በመ/ቁ.24/2013 በ16/04/2013 ዓም የሰጠውና


ይግባኝ ሰሚችሎቱ በመ/ቁ.074/2013 በ19/06/2013 ዓም በሰጠው ፍርድ ያፀናው የቅጣትና የጥፋተኝነት
ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ.195 (2)(ለ)(2) መሰረት ተሻሽሏል፡፡

2.አመልካቾች በወ/ህ/አ.298 (1) ስር ለበላይ ባለመታዘዝ የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ ናቸው


ብለናል፡፡ስለሆነም አመልካቾች በዚህ ጉዳይ የታሰሩበት ጊዜ ታስቦ 1ኛ አመልካች በሶስት አመት ፅኑ
እስራት ፤2ኛ አመልካች በሁለት አመት ከስድስት ወር ፅኑ አስራት ሊቀጡ ይገባል ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

1.ማረሚያ ቤቱ በተሻሻለው የቅጣት ውሳኔ መሰረት እንዲያስፈፅም የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ይድረሰው፡፡

2.በዚህ መዝገብ የተሰጠው ውሳኔ ከመዝገብ ቁጥር 206556 ጋር እንዲያያዝ ታዟል፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 11 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሄ/መ

የማይነበብ የአራት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

የልዩነት ሃሳብ

እኔ ስሜ በተራ ቁጥር 2 ሰር የተሰየምኩት የችሎቱ ዳኛ ከሌሎች ባልደረቦቼ በሚከተለው ምክንያት በሃሳብ


ተለይቻለሁ፡፡

1. አመልካቾች እየተከራከሩያሉት አገር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ብትሆንም የጦርሜዳ ግዳጅ ሊባል


አይገባም በሚል በመሆኑ ሰራዊቱ ለግዳጁ እንዲዘጋጅ የግዳጅ አፈፃፀም ካርድ ወጥቶ የነበረ ስለመሆነ
በግልጽ በስር ፍ/ቤት ተረጋገጦ ያለ በመሆኑ ይህ የግዳጅ አፈፃፀም ካርድ አልወጣም ግዳጁም
ለሰራዊቱ አልወረደም በሚል አመልካቾች የተከራከሩም ሆነ ማስረጃ ባለማቅረባቸውም ከአጠቃላይ
ክርክሩ ያላየሁ በመሆኑ፣
ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የግዳጅ አፈፃፀም ካርድ በሰራዊቱ የተዘጋጀ ስለመሆኑ በክህደት
ያልተከራከሩበትና ውድቅ የተደረገ ክርክር ባለመሆኑ ግዳጅ ለሰሪዊቱ እንደተሰጠ የምቆጥረው
በመሆኑ፣በጊዜው የኮቪድ 19 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወጥቆ የነበረው ሰዎች እንዳይቀራረቡ እና
በሽታው እንዳይዛመት ከመሆኑ አንፃር በጊዜው የተፈፀመው ነገር ግን ሰዎች በህብረት ሆነው
እየዘፈኑ እና እየፎከሩ የነበረ እና በቀጣይም በህብረት ንብረት የማውደምና በሰዎች ህይወት ላይ
ጉዳይ እያደረሱ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ የጦር ሜዳ ግዳጅ አይደለም የሚል
ክርክር በአመልካዋች የተነሳ ቢሆንም በዚህ አስቸኳይ አዋጅ ከወጣበት አላማ አንፃር አንፃር ስናየው
ራሱ አዋጁን የጣሰ ድርጊት የተፈፀመ በመሆኑ፣

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወጣው ለጦርሜዳ አይደለም እንኳን ቢባል ሁለቱም አመልካቾች ግዳጅ ከበላይ
ኃላፊያቸው የተቀበሉ መሆኑ ባልተካደበት ይልቁንም ኮ/ል ተክለብርሃን ገ/መድህን በቀጥታ ግዳጁን
የተቀበለ መሆኑ፣ በስሩ የሚገኝ ኮ/ል አሰፋ አየለ ግዳጁን ከበላይ ኃላፊው የሰማ እና የቅርብ
አለቃውን ኮ/ል ተክለብርሃንን ግዳጁ እንዲፈፀም ሲጠይቀው እንደነበረ፣ ሌሎች የሰራዊቱ አባላትም
ለምን እርምጃ አንወስድም እያሉ በተደጋጋሚ ሲጠይቁ የነበረ ቢሆንም ከበላይ ኃላፊያቸው ኮ/ል
ተክለብርሃን በቀጥታ እርምጃ እንዲወስዱ ትዕዛዝ ባለመውረዱ ብቻ ወታደራዊ የትዕዛዝ አቀባበል
ስርዓቱን ሲጠብቁ በጊዜው ከፍተኛ ጉዳይ የደረሰ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ የመከላከያ ሰራዊት
የግዳጃ አፈፃፀም ጉድለት የተፈፀመ እና በሰውና በንብረት ላይ ጉዳይ የደረሰ መሆኑ የተረጋገጠ
በመሆኑ ለበላይ ያለመታዘዝ ወንጀል ነው የተፈፀመው ለማለት የማይቻልና ኮ/ል ተክለብርሃን
ግዳጁን ተቀብሎ ነገር ግን እንደግዳጁ ያለመፈፀም እና በስሩ ያሉትንም ግዳጁን አውረዶ አደጋውን
እንዲታደጉ ያለማድረጉ ግልጽ በመሆኑ በስር ወታደራዊ ፍ/ቤት በኮ/ል ተክለብርሃን ገ/መድሀን ላይ
የተላለፈው የጥፋተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ሊሻሻል የሚገባው እና የተጠቀሰውም የህግ ድንጋጌ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 12 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስለማይገባ የጥፋተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔው ሊፀና የሚገባው ነበር በሚል ከአብላጫው ድምጽ
በሀሳብ ተለይቻለሁ፡፡
2. ኮ/ል አስፋ አየለን አስመልክቶ ግን ምንም አንኳን ግዳጁ ከበላይ ኃላፊያቸው መሰጠቱን ቢያውቅም
እንደወታደራዊ የግዳጅ አፈፃፀም ምንም እንኳን ግዳጁ በበላይ ኃላፊ መሰጠቱን ቢስማም ከቅርብ
አለቃው ደግሞ በቀጥታ ግዳጁን መቀበል እና ማስማራት ያለበት ከመሆኑ አንፃር በተደጋጋሚም
የቅርብ ኃላፊነውን ግዳጁ ሊፈፀም ይገባል በማለት ቢጠይቀም ያልወረደለት በመሆኑ የግዳጁ
አወራረዱ ደግሞ የስልጣን ተዋረድን የሚጠይቅ በመሆኑ በቀጥታግዳጁን ተቀብለህ አልፈፀምክም
ሊባል የማይገባው በመሆኑ፣ ኮ/ል አሰፋ አየለ ሊጠየቅ የሚገባው ከሆነ ሁሉም በቦታው የነበሩ
የሰራዊት አባላት አደጋውን በጊዜው ያላስቆሙት የበላይ ትዕዛዝን እየጠበቁ በመሆኑ ትዕዛዝ መጠበቅ
አልነበረባችሁም ተብሎ ሊጠየቁ የሚገባው የነበረ በመሆኑ ከአጠቃላይ በቦታው ላይ ከነበሩ የሰራዊት
አባላት ኮ/ል አሰፋ የሚለየው እሱ ከዋናው አዛዥ ግዳጅ መውረዱን በስልክ ስለሰማና ለቅርብ አለቃው
አሳውቅ የተባለ በመሆኑ እንጂ እንደማንኛውም ሰላምና ደህንነትን ለመጠበቅ ሰራዊቱን የተቀላቀለ
ሁሉ አገር በችግር ውስጥ እየገባች ባለችበትና የህዘብ እና የአካባቢ ሰላም እየደፈረሰ እያየ ዝም ሊል
የማይገባው ከመሆኑ አኳያ ከታየ ሁሉም ሊጠየቁ የሚችሉ እንጂ በተለየ ከቅርብ አለቃው ግዳጅ
ሳይወርድለት ስላልፈፀመ ጥፋተኛ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ ባለመኖሩ ከቀረበበት ክስ ነፃ ሊወጣ
የሚገባው እንጂ ጥፋተኛ ተብሎ ቅጥት ሊወሰንበት አይገባም ነበር በማለት በስር ወታደራዊ ፍ/ቤት
የሰጠውንም ይሁን አብላጫው ድምጽ ያሻሻለው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተገቢ አይደለም ብዬ
በሃሳብ ተለይቻለሁ፡፡

የማይነበብ የአንድ ዳኛ ፊርማ አለበት


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እገንጂ


ጽ 13 / 13
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 204829

ቀን፡-01/02/2014ዓ/ም
ዳኞች- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ፍቅር አብራክ የእናቶችና የሕፃናት ስፔሻላይዝድ የሕክምና ማዕከል -ወኪል ንጉስ አወቀ
ቀረቡ

ተጠሪ ፡- ዶ/ር ልንገርህ ተፈራ- አልቀረቡም

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ
የስር ከሳሽ፤ አመልካች ተከሳሽ ሆኖ ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ አመልካች ከሕግ ውጭ የሥራ
ውሌን ስላቋረጠ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈል እንዲወሰንልኝ የሚል ነው፡፡ አመልካች ባቀረበው የመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያ ተጠሪ የሥራ መሪ በመሆናቸው ጉዳዩ በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ በሥራ ክርክር ችሎት
ሊታይ አይገባም በማለት ተከራክሯል፡፡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 92429
አመልካች ያቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩን ክሱን ለመስማት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
አመልካች ባቀረበው ይግባኝ መሠረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ ውሳኔውን
አጽንቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ተጠሪ የሥራ መሪ
ሆነው እያለ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያው ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ሲሆን የሰበር አጣሪ
ችሎትም በዚሁ ነጥብ ላይ ለሰበር ሰሚ ችሎት ተጠሪን ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ
በማዘዙ ተጠሪ የሥራ መሪ አይደለሁም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ ሲደረግ ዋናው
ክርክር ሳይጠናቀቅ ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ መሆን አለመሆኑን? በጭብጥነት በመያዝ መዝገቡን
መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪ ባቀረቡት የሥራ ክርክር ላይ አመልካች የሥራ መሪ ናቸው፣ ጉዳዩ በሥራ ክርክር
ችሎትና በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ መሠረት ሊታይ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ
ቢሆንም ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት መቃወሚያውን ባለመቀበል በፍሬ ነገሩ ጉዳዩን
ለመስማት ትእዛዝ ሰጥቷል፤ ሥረ-ነገሩ ላይ ውሳኔ አልሰጠበትም፡፡ አመልካች ይግባኝ ያቀረበው
መቃወሚያው ውደቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም በሚል ነው፡፡ ክርክሩን በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ
መሰረት መምራት እና መቆጣጠር የፍርድ ቤቱ ኃላፊነት ሲሆን በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሥነ-ሥርዓት
ሕጉን ዓላማዎች የሆኑትን እንደ አንጻራዊ እውነትን የመፈለግ፣ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትህ፣ ክርክርን
ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት የመሳሰሉትን ማሳካት ስለማይቻል የተከራካሪዎችን
መብት ይነካል፡፡

በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 320(3) መሰረት ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ከሥረ ነገሩ ፍርድ በፊት የሚሰጥ ትዕዛዝ
እና የጉዳዩ የመጨረሻ ውጤቱ ሲታወቅ አብሮ ይግባኝ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ ላይ ይግባኝ ማቅረብ
እንደማይቻል ተመልክቷል፡፡ ድንጋጌው በክርክር ሂደት በሚሰጥ ትዕዛዝ ሁሉ ይግባኝ ከቀረበ የተከራካሪዎችን
ወጪና ጊዜ የሚያባክን፣ የፍርድ ቤትን ጊዜ የሚወስድ ከመሆኑም በላይ በአንድ ጉዳይ ብዙ ፋይል እንዲኖር
የሚያደርግና የሥራ ጫና የሚፈጥር እንዲሁም በይግባኝ ክርክር ምክያንት የሥር ክርክሩ ከታገደም ክርክርን
ውጤታማ፣ ወጭና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አግባብ መምራት እንዳይቻል የሚያደርግ በመሆኑ ይሕን ለማስቀረት
የተቀረጸ ነው፡፡ ጉዳዩ የመጨረሻ ዕልባት ሲያገኝ አብሮ ይግባኝ በማቅረብ ለተከራካሪዎች መብታቸውን
ማስከበር የሚችሉበት ሥርዓት ስለሚፈጥር ይግባኝ የማቅረብ መብታቸው ላይ ገደብ እንዳደረገ የሚወሰድ
አይደለም፡፡ አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውደቅ በመደረጉ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ
ሲያቀርብ ፍርደ ቤት ዋናው ክርክር ከመጠናቀቁ በፊት ይግባኝ የሚባልበት አይደለም በማለት ይግባኙን
ውደቅ ማድረግ ሲገባው የቀረበውን ክርክር ተቀብሎና አከራክሮ ውሳኔውን ማጽናቱ ክርክሩን በሥነ-ሥርዓት
ሕጉ አግባብ የመምራትና የመቆጣጠር ኃላፊነቱን አለመወጣቱን የሚያሳይና መሠረታዊ የሆነ የክርክር
አመራር ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ውሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 241335 የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ/ም የሠጠው ውሳኔ
በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሠረት ተሽሯል፡፡

2. አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ በመደረጉ ያቀረበው ከሥረ-ነገሩ ውሳኔ በፊት ይግባኝ
ሊባልበት የሚችል ጉዳይ አይደለም በማለት ወስነናል፡፡

3. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 የሥር መዝገብ ይመለስ፡፡
 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
ሄ/መ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁጥር 204833

ሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡ ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል፡- ነ/ፈጅ አመኑ ለሜሳ

ተጠሪ ፡ አቶ ፀጋዬ መለሰ፡- ከጠበቃ ፈለቀ ዋጎ ጋር ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የስራ ክርክር ሲሆን በተጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ
በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ በ08/11/2011 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች ሆቴል ውስጥ በዋና ምግብ አዘጋጅነት የስራ
መደብ በወር ብር 85,554 እየተከፈለኝ ስሰራ ቆይቼ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ በግንቦት 14
ቀን 2011 ዓ.ም. በነበረው የሙስሊሞች ጾም አፍጥር ዝግጅት ላይ ጉድለት አሳይተሀል በሚል ከግንቦት 15
ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የስራ ውሌን አቋርጧል፡፡ ነገር ግን የፈጸምኩት ጉድለት የለም፡፡ ጉድለት አለ ቢባል
እንኳን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብት ባለመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው ተብሎ አመልካች የማስጠንቀቂያ
ጊዜ፤ የካሳ እና የስንብት ክፍያ እንዲሁም የአንድ ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 705,820 እንዲከፍል ይወሰንልኝ
በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በ03/12/2011 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው መልስ ተጠሪ ዋና የምግብ አዘጋጅ እና የስራ መሪ ስለሆኑ
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም፡፡ ተጠሪ በቂ ምግብ ባለማዘጋጀታቸው እንግዶች ተሻምተው
እንዲበሉ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ተጠሪ በስራቸው የሚገኙ ሼፎችን አስተባብረው ባለመስራታቸው የተፈጠረ ችግር
ነው፡፡ በዚህም የሆቴሉ መልካም ስም ጎድፏል፡፡ ተጠሪ በተደጋጋሚ ጥፋት በመፈጸማቸው ማስጠንቀቂያ
ተሰጥቷቸው ሊታረሙ አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ
በሚሊኒየም አዳራሽ ለ750 ሰዎች ለተዘጋጀው የአፍጥር ስነስረአት ተጠሪ 15 በመቶ ተጨማሪ ምግብ
ማዘጋጀታቸው በተጠሪ ምስክር ተረጋግጧል፡፡ ተጠሪ በቂ ምግብ ስለማዘጋጀት አለማዘጋጀታቸው የእራት ሰአት
ከመድረሱ በፊት በአመልካች ቆጠራ አልተደረገም፡፡ ችግሩ ሊፈጠር የቻለው ተጠሪ በቂ ምግብ
ባለማዘጋጀታቸው ሳይሆን አመልካች እንግዶቹን እየተቆጣጣረ የሚያስገባበት ሁኔታ ስላልነበር መሆኑን የተጠሪ
ምስክሮች በተሻለ ሁኔታ ስላስረዱ በተጠሪ የተፈጸመ ጥፋት የለም፡፡ በመሆኑም ስንብቱ ህገወጥ ስለሆነ
የስንብት፣ የካሳ፣ የማስጠንቀቂያ ክፍያ በድምሩ ብር 655,914 እና የጠበቃ አበል ብር 25,000 አመልካች
እንዲከፈል ወስኗል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 337 መሰረት በመሰረዙ የሚከተለውን የሰበር ቅሬታ አቅርቧል፡፡

አመልካች በ15/07/2013 ዓ.ም. ጽፎ ባቀረበው የሰበር ቅሬታ ተጠሪ በተደጋጋሚ ለፈጸሙት ጥፋት
በ02/08/2011 ዓ.ም. እና በ19/08/2011 ዓ.ም. የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ሊታረም ባለመቻሉ ከስራ
እንዲሰናበቱ መደረጉ ተገቢ ነው፡፡ የሰው እና የሰነድ ማስረጃ አቅርቤ፤ ተጠሪም ለሁለት ጊዜ ማስጠንቀቂያ
የተሰጣቸው መሆኑን ሳይክዱ ተጠሪ ጥፋተኛ አይደሉም መባላቸው ተገቢ አይደለም፡፡ ተጠሪ የስራ መሪ ናቸው
ብለን ያቀረብነው ክርክርም ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎትም የአመልካችን የሰበር ቅሬታ መርምሮ የተጠሪ ስንብት ህገወጥ ነው የመባሉን አግባብነት
ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1(ሀ-ተ) አላማ እና አተገባበር አንጻር ለማጣራት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ
መልስ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተጠሪ በ26/08/2013 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት መልስ አመልካች ቅሬታ ያቀረበው በፍሬ ነገር ክርክር ላይ ነው፡፡
የፍሬ ነገር ክርክሩ በማስረጃ ተጣርቶ የተወሰነ በመሆኑ የተፈጸመ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካችም በ13/09/2013 ዓ.ም. የተጻፈ የመልስ መልስ በማቅረብ የሰበር ቅሬታውን አጠናክሯል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ከላይ ተመለከተው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር ያስቀርባል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ
አንጻር ለቅሬታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው ህግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ለተጠሪ ስንብት ምክንያት የሆነው ድርጊቱ ተፈጽሟል በተባለ እለት በእንግዶች ቁጥር ልክ
ምግብ ሳያዘጋጁ በመቅረታቸው እንግዶች ተገቢውን መስተንግዶ ሳያገኙ በመቅረታቸው የአመልካች መልካም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስም ጎድፏል በሚል ነው፡፡ ይህ ጥፋት በተጠሪ ተፈጽሞ ከሆነ የአመልካችን መልካም ስም በማጥፋት ደንበኛ
እንዲቀንስ በማድረግ በአመልካች ገቢ ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሸ
መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያበቃ ጥፋት ነው፡፡ ነገር ግን ተጠሪ ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለ
እለት ለእንግዶች የተዘጋጀው ምግብ ማነሱን ሳይክዱ ጥፋቱ የእኔ አይደለም በማለት የሚከራከሩ በመሆኑ
ስንብቱ ህጋዊ ነው አይደለም የሚለውን እልባት ለመስጠት በእለቱ ተጠሪ እንዲያዘጋጁ በአመልካች በታዘዙት
መጠን ልክ ባለማዘጋጀት ጥፋቱን መፈጸም አለመፈጸማቸው በማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ
የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዚህ ነጥብ ላይ የግራ ቀኙን ምስክር የሰማ ሲሆን
የተጠሪ ምስክሮች ተጠሪ ከእንግዶች ቁጥር በላይ 15 በመቶ ትርፍ ምግብ አዘጋጅተው የነበረ መሆኑን፤
እንግዶቹ በሚስተናገዱበት ሚሊኒያም አዳራሽ ሌላ ዝግጅት የነበረ በመሆኑ እና አመልካች ኩፖን አዘጋጅቶ
እንግዶችን እየተቆጣጠረ የሚያስገባ ሰራተኛ ባለመመደቡ ለሌላ ዝግጅት የተጠሩ ሰዎች ገብተው በመመገባቸው
የተዘጋጀው ምግብ ሊያልቅ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በአንጻሩ በአመልካች በኩል ሁለት ምስክሮች የቀረቡ
ቢሆንም አንደኛው ምስክር አመልካች እንግዶችን እየተቆጣጠረ የሚያስገባ ሰራተኛ መመደቡን ሌላኛው
የአመልካች ምስክር ደግሞ አመልካች ተቆጣጣሪ አለመመደቡን የመሰከሩ እና የአመልካች ምስክሮች ቃል
የተለያየ በመሆኑ ይልቁንም የአመልካች 2ኛ ምስክር ቃል የተጠሪን ምስክሮች ቃል የሚያጠናክር መሆኑን
የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው ላይ በማስፈር ለእንግዶች የምግብ እጥረት ሊፈጠር የቻለው ተጠሪ በቂ ምግብ
ባለማዘጋጀታቸው ሳይሆን አመልካች እንግዶቹን እየተቆጣጠረ ባለማስገባቱ ነው በሚል ስንብቱ ህገወጥ ነው
የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ
80/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 ላይ የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመባቸውን የመጨረሻ ውሳኔዎች ማረም ነው፡፡ በማስረጃ ተጣርቶ ድምዳሜ ላይ የተደረሰባቸውን የፍሬ
ነገር ክርክሮች ይህ ችሎት እንደገና የመመዘን ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ አመልካች ለተጠሪ በተደጋጋሚ
ማስጠንቀቂያ መስጠቱን በመግለጽ የሚያነሳው ክርክር በተመለከተ ተጠሪ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑን
ባይክዱም እንኳን ለስንብት ምክንያት የሆነውን ጥፋት አለመፈጸማቸው እስከተረጋገጠ ድረስ አስቀድሞ በሌላ
ጥፋት ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ስንብቱን ህጋዊ ሊያደርገው አይችልም፡፡ በመሆኑም ተጠሪ ፈጽመዋል
የተባለውን ድርጊት አለመፈጸማቸውን ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች እስከተረጋገጠ
ድረስ ስንብቱ ህገወጥ ነው መባሉን ይህ ችሎት እንዳለ የሚቀበለው በመሆኑ እና በዚህ ችሎት ሊታረም
የሚችል መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሌለ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1ኛ. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 70737 በ23/03/2013 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ
እና የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 250280 በ02/07/2013 ዓ.ም. የሰጠው ትእዛዝ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር 348/1 መሰረት ጸንቷል፡፡

2ኛ. በዚህ ፍርድ ቤት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ትእዛዝ

በዚህ መዝገብ በ30/07/2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በአፈጻጸም መዝገብ ቁጥር 80332 ላይ የተሰጠው የእግድ
ትእዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-204866

ቀን፡-30/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የካ ክ/ከተማ ዐቃቤ ህግ ፅ/ቤት- ዮሴፍ ዲኖ ቀረቡ

ተጠሪዎች፡-1.አቶ ብሩክ ወንድሙ 2ኛ ተጠሪ ቀረቡ

2.ወ/ሮ ሚስጥረ ወንድሙ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 20 ቀን 2013 ዓ.ም
በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358
የቀረበን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከውጤት አንፃር
ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን
አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን አመልካች በስር ፍርድ ቤት የመ/አመልካች የነበረ ሲሆን ተጠሪዎች
የመ/ተጠሪዎች ነበሩ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት ባቀረበው አቤቱታም አመልካች በአዋጅ


ቁጥር 64/2011 መሰረት የአስተዳደሩን እና የነዋሪዎችን መብት እና ጥቅም በማስከበር በማናቸውም
የዳኝነት አካል ዘንድ የመቃወም አቤቱታ የማቅረብ መብት እንዳለው በመግለፅ በመቃወም ተጠሪዎች
እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፅ/ቤት መካከል በተደረገው ክርክር ላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው
ውሳኔ መብቴን የሚነካ በመሆኑ ሊሰረዝ ይገባል በማለት አመልክቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም ተጠሪዎች በጉዳዩ ላይ መጥሪያ ደርሷቸው መልስ ከመስጠታቸው በፊት መዝገቡን
መርምሮ በሰጠው ውሳኔም ተጠሪዎች የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፅ/ቤትን ከሰው ክርክር ላይ
በነበሩበት ወቅት አመልካች ተከሳሹን ወክለው መልስ በመስጠት ከተከራከሩ በኋላ ውሳኔ የተሰጠ
መሆኑን፤በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ የሚችለው በክርክሩ ተካፋይ ባልነበረ ወገን
ሊሆን እንደሚገባ በግልፅ የሚያመለክት መሆኑን በመጥቀስ አመልካች ራሱ ተወካይ ሆኖ ተከራክሮ
የተሰጠውን ውሳኔ ቅሬታ ካለው ይግባኝ በማቅረብ እንዲስተካከል ከማድረግ ባለፈ በድጋሚ ተቃዋሚ
ሆኖ የሚቀርብበት አግባብ የለም በማለት የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ውድቅ ያደረገው ሲሆን
ከፍተኛ ፍርድ ቤቱም ብይኑን ከውጤት አንፃር አፅንቶታል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝቶ ባቀረበው የሰበር አቤቱታም በመጀመሪያው ክስ እና በመቃወም


አቤቱታው ላይ ዐቃቤ ህግ ፅ/ቤት የወከላቸው የተለያዩ ተቋማት ሆነው እያለ ፍርድ ቤቱ ይህንን
ሳይገነዘብ፤በአዋጅ ቁጥር 64/2011 ለአመልካች የተሰጠውን የመቃወም አቤቱታ የማቅረብ ስልጣንና
ተግባር ሳይመረምር ፍርድ ቤቱ የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት
በመሆኑ፤የአስተዳር አካሉ ጣልቃ ለመግባት አቤቱታ አቅርብልኝ ብሎ ጉዳዩን ሲልክልኝ ብቻ ጉዳዩን
በመመርምር በጉዳዩ ላይ የጣልቃ ገብ አቤቱታ ሊቀርብበት እንደሚገባ ሲያምን አቤቱታ ከማቅረብ
ውጪ ዐቃቤ ህግ በራሱ ተነስቶ ጣልቃ ገብቶ ሊከራከር የሚችልበት አግባብ በሌለበት ከፍተኛ ፍርድ
ቤቱ የደረሰበት መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ
ተሸሮ አመልካች የአስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ
በመቃወም አመልካችነት አቤቱታውን ተብሎ እንዲያከራክረን ይወሰንልን በማለት አመልክቷል፡፡

አመልካች በስር ፍርድ ቤት በቀድሞ ክስ የወከለው የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 አስተዳር ፅ/ቤትን ሆኖ እያለ
አሁን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት መብቴ ተነካ በማለት መቃወሚያ ያቀረበው የመሬት ባንክና ልማት
ማኔጅመንት ፅ/ቤትን በመሆኑ አመልካች የወከለው ሁለት የተለያዩ ተቋማትን ከመሆኑ አንፃር ጉዳዩን
ያውቃል በሚል አቤቱታው ውድቅ የተደረገበትን አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል
ከተባለ በኋላ ለተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸው መልሳቸውን አቅርበዋል፡፡

ተጠሪዎች በሰጡት መልስም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀፅ 6 በዝርዝር ከተሰጠው
ስልጣን አንጻር በተቋማት የምታዘዝ ስማ በለው ነኝ ማለቱ ተገቢነት የሌለው ሙግት ነው፤አመልካች
የቀደመው ክርክር መኖሩን እያወቀ ውጤቱን ጠብቆ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑን በመጥቀስ የተሰጠው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ በሰበር መዝገብ ቁጥር 56795 የተሰጠውን አስገዳጅ ውሳኔ መሰረት ያደረገ በመሆኑ፤አመልካች
መብቱ ተነክቷል የሚለው የክፍለ ከተማው የይዞታ አስተዳር ፅ/ቤት በስር ፍርድ ቤት በተሰጠ ትዕዛዝ
የቤት ቁጥር 389 እና 390 መዝገብ ውስጥ ያሉትን ሰነዶች በመፈተሸ በሰጠው ምላሽ ይዞታው
በተጠሪዎች እጅ ያለ መሆኑን አረጋግጦ በሰጠው ምላሽ መሰረት በአፈፃፀም በተሰጠ ትዕዛዝ በሁከት
ተግባር የፈረሰውን ቤትና አጥር ባለበት ሁኔታ ተጠሪዎች የተረከብን በመሆኑ የሰበር አቤቱታው
ተቀባይነት የለውም ተብሎ ውሳኔ ይሰጥልን በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ
ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና
ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡በመሰረቱ የስር
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የአመልካችን የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የመቃወም አቤቱታ ውድቅ ያደረገው በመነሻነት
አመልካች በቀደመው ክርክር የየካ ክ/ከ/ወረዳ 07 አስተዳደር ፅ/ቤትን ወክሎ መከራከሩን በመጥቀስ
በዚህም የክርክሩ አካል ሳይሆን ወኪል መሆኑን በመጥቀስ ቢሆንም በመጨረሻ መደምደሚያው ላይ
በውሳኔው ቅር ከተሰኘ ስልጣን ላለው አካል ቅሬታውን በማቅረብ ማስተካከል እንደሚችል በውሳኔው ላይ
ማመልከቱ አመልካችን የክርክሩ አካል አድርጎ የወሰደ መሆኑን ያሳያል፡፡ጉዳዩን በይግባኝ
የተመለከተው ፍርድ ቤት የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ውድቅ ያደረገው ደግሞ ስለቀደመው
ዋናው ክርክር አመልካች የሚያውቅ ሆኖ እያለ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የመቃወም አቤቱታ ማቅረቡ
የክርክሩን ውጤት ጠብቆ መቃወሚያ ማቅረቡን የሚያሳይ መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡

አሁን በያዝነው ጉዳይ ለመቃወም አቤቱታው መነሻ የሆነው ክርክር ይዞታን የሚመለከት የሁከት
ይወገድልኝ ክርክር መሆኑ ግራ ቀኙ ያልተካካዱበት ነጥብ ሲሆን ተጠሪዎች ይዞታን በሚመለከት ክሱን
ያቀረቡት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፅ/ቤት ላይ ሲሆን በዚሁ ፅ/ቤት ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ
በክሱ ሊካተቱ የሚገባቸው ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ስልጣን ያላቸውና አስገዳጅ ውሳኔ
ቢሰጥም ለማስፈፀም አግባብነት ያላቸው አካላት ወደ ክርክሩ ገብተው መከራከራቸውን የስር ፍርድ ቤት
መዝገብ አያሳይም፡፡

አመልካች የመቃወም አቤቱታ ያቀረበው ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ስልጣን ያለውንና አስገዳጅ
ውሳኔ ቢሰጥም ለማስፈፀም አግባብነት ያለውን የየካ ክ/ከተማ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤትን
በመወከል መሆኑን በመጥቀስ በአዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 18(8)(9) በተሰጠው ስልጣን እና
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ.መ.ቁ 37502 በሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም መሠረት
የመንግስትን እና የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል የሚያቀርበው የመቃወም አቤቱታ ሆኖ እያለ
ስለቀደመው ክርክር ማወቅ አለማወቁ ሊጣራና ሊመረመር የሚገባው ከመሬት አስተዳደር ጋር
በተያያዘ ስልጣን ያለውና አስገዳጅ ውሳኔ ቢሰጥም ለማስፈፀም አግባብነት ያለው የየካ ክ/ከተማ የመሬት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ3/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤት እንጂ ይህንን ፅ/ቤት ወክሎ የሚከራካረው አመልካች ባልሆነበት የክፍለ
ከተማው የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ፅ/ቤት ስለቀደመው ክርክር እውቀቱ እያለው የክርክሩን ውጤት
ጠብቆ መቅረቡ ባልተረጋገጠበት የስር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የመቃወም አቤቱታ ውድቅ
ማድረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.214399 ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓም የሰጠው


ብይን እና ይህንን ብይን በማፅናት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.261514 ሰኔ 09 ቀን
2013 ዓም የሰጠው ፍርድ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸረዋል፡፡
2. የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉዳዩን መዝገብ በማንቀሳቀስ የአመልካችን
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 የቀረበ አቤቱታ ተቀብሎ ግራ ቀኙን አከራክሮ አስፈላጊ ከሆነም
ማስረጃዎችን ሰምቶ እና ተገቢውን ማጣራት አድርጎ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.360(2) መሰረት
የመሰለውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343(1) መሰረት መልሰንለታል፡፡
3. ሀምሌ 12 ቀን 2013 ዓም በዋለው ችሎት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
በመ/ቁ.261839 በተያዘው አፈፃፀም ላይ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ይጻፍ፡፡
4. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ አምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ4/4
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡209319

ቀን፡28/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ አብደላ ከሊል - አልቀረቡም

ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ - ኤጀታ ሓተኡ- ቀረቡ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ
የሰበር አቤቱታ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ
ቤት የሰጠውን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በማፅናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት
የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ ያደረገ ሲሆን
አመልካች በፊንፊኔ ዙርያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ
ነበር፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) እና አዋጅ ቁጥር
609/2001 አንቀፅ 2(10) ፤22(10) እና 50(ለ)(1) ን በመጥቀስ ባቀረበው ክስ ጥር 05 ቀን 2013 ዓም
ከቀኑ 3፡00 በሰበታ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 08 ውስጥ በሚገኘው ለተጨማሪ እሴት ታክስ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በተመሰገበው የህንፃ መሳሪያ መሸጫ ድርጅት ባለቤትና አስተናጋጅ ሆነው ሲሰሩ ብረት የሚታሰርበት
ፒንሳ በብር 130.00 ለዐቃቤ ህግ ምስክሮች ሲሸጡ ወዲያውኑ ደረሰኝ ሊሰጡ ሲገባ ያለደረሰኝ ግብይት
ፈፅመዋል በማለት ከሷል፡፡

አመልካች ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ክሱን ክደው ስለተከራከሩ የዐቃቤ ህግ
ምስክሮች ቀርበው የተሰሙ ሲሆን ምሰክሮቹም በክሱ ላይ በተመለከተው ጊዜና ቦታ ንብረትነቱ
የአመልካች በሆነ የህንፃ መሳሪያ መሸጫ ሱቅ ውስጥ አመልካች አስተናጋጅ ሆነው እየሰሩ ፒንሳ በብር
130.00 ገዝተው ገንዘቡን ከፍለው እቃውን የተረከቡ ቢሆንም አመልካች የተጨማሪ እሴት ታክስ
ደረሰኝ ያልሰጧቸው መሆኑን ስላስረዱ ፤ይህንን የምስክርነት ቃል ከሰነድ ማስረጃዎቹ ጋር መርምሮ
አመልካች እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቶ አመልካች ሁለት ምስክሮችን አቅርበው በእለቱ ሽያጩ ተከናወነ
በተባለበት ስፍራ ያልነበሩ መሆኑን ከዚህ ይልቅ ጀሞ ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ከዚያም ወደ
ቃሊቲ በመሄድ እስከ 6፡30 ድረስ የዋሉ መሆኑን ያስረዱ ቢሆንም 1ኛ የመ/ምስክር አመልካች ከነሱ
ጋር የነበረው ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ነው ሲል 2ኛ የመ/ምስክር ከ2፡40 ጀምሮ ነው ማለቱ መሰረታዊ
ልዩነት ያለው በመሆኑ የምስክርነት ቃሉ እምነት የማይጣልበት መሆኑን ፤አመልካች በስራ
አስኪያጅነት ጭምር የተከሰሱ በመሆኑ በስፍራው አለመኖራቸውን ማስረዳታቸውም ቢሆን ከወንጀል
ሀላፊነት ሊያስመልጣቸው የማይችል መሆኑን በመጥቀስ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ በማለት በአንድ
አመት ቀላል እስራትና በብር 3,000.00 እንዲቀጡ የወሰነ ሲሆን ይህ ውሳኔም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ፀንቷል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም በክሱ ላይ ተጠቅሶ የወነጀል ክስ
የቀረበብኝ ድንጋጌ በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 138 መሰረት ተፈፃሚነቱ ያበቃ ሆኖ እያለ በተሻረ
ህግ የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰጠቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው፤አዋጅ ቁጥር
609/2001 አዋጅ ቁጥር 285/1994 ን ያሻሻለ ሆኖ ሶስት አንቀፆችን ብቻ የያዘ ሆኖ እያለ አንቀፅ 22
እና 50 እንዳለው በመውሰድ በሌለ ድንጋጌ የስር ፍርድ ቤት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መስጠቱ
አግባብ አይደለም፤የስር ፍርድ ቤት ስራ አስኪያጅ ሳልሆን ከአዋጅ ቁ.983/2008 አንቀፅ 2(19) ትርጉም
በመውጣት ስራ አስኪያጅ ነህ በማለት የሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት ያለበት ነው፤የዐቃቤ ህግ ምስክሮች
ያደሩበትን ቦታ፤አመልካች የተያዝኩበትን ጊዜ አስመልክቶ ልዩነት ያለው የምስክርነት ቃል ሰጥተው
እያለ ፤ምስክሮቹ ሽያጩ ተከናወነ ያሉት በ05/05/2013 ዓም ሆኖ እያለ ቃሌን ለፖሊስ የሰጠሁት
ደግሞ በ04/05/2013 ዓም ሽጠሃል ተብዬ ሆኖ እያለ በአጠራጣሪ ማስረጃ ይህንን አጠራጣ ማስረጃም
የመከላከያ ምስክሮቼ ባስተባበለ መልኩ አስረድተው እያለ የጥፋኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰጠቱ
አግባብ አይደለም፤

የስር ፍርድ ቤት ውሳኔውን የሰጠው ማስረጃዎቼን በአግባቡ ሳያስቀርብ የመከላከል መብቴን በማጣበብ
በሰ/መ/ቁ.139107 እና 95921 የተሰጡትን አስገዳጅ ውሳኔዎች ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ከላይ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በተመለከተው አግባብ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት
የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ሊሻር እና በነፃ ልሰናበት ይገባል፤ይህ ቢታለፍብኝ በመኪና አደጋ
ምክንያት ያለብኝ የዲስክ እና የነርቭ በሽታ ከግምት ውስጥ ገብቶ ቅጣቱ ሊገደብልኝ ሲገባ የስር ፍርድ
ቤት ይህንን በማለፍ የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ተሸሮ የእስራት ቅጣቱ ሊገደብልኝ ይገባል በማለት
አመልክተዋል፡፡

አመልካች የጤና ችግር ያለባቸው ስለመሆኑ ከሆስፒታሎች ማስረጀ ቀርቦ እያለ የስር ፍርድ ቤቶች
ቅጣቱን ሳይገድቡ ያለፉበትን አግባብ በሰ/መ/ቁ.48956 እና85596 ከተሰጡት አስገዳጅ ውሳኔዎች አንፃር
ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ለተጠሪ መጥሪያ ደርሶት መልሱን አቅርቧል፡፡

ተጠሪ በሰጠው መልስም አመልካች ያለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑን በመጥቀስ
ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን አዋጅ ቁጥር 285/94 እና 609/2001 በመጥቀስ ክሱ መቅረቡ በአግባቡ
ስለሆነ አዋጅ ቁጥር 983/2008 የታክስ አስተዳደርን የሚመለከት አጠቃላይ አዋጅ በመሆኑ ይህ
አዋጅም ክስ የቀረበባቸውን አዋጆች በግልፅ ያልሻረ በመሆኑ አመልካች በዚህ አግባብ ያቀረቡት ክርክር
ውድቅ ሊደረግ ይገባል፤ማስረጃ ምዘናን በተመለከተ የስር ፍርድ ቤት የቀረበለትን ማስረጃ ያገናዘበው
በሰ/መ/ቁ.89676 በተሰጠው አስገዳጅ ውሳኔ አግባብ በመሆኑ ገደብን አስመልክቶም አመልካች
በጠቀሷቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች አግባብ እልባት የተሰጠ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊፀና ይገባል
በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልሳቸውን አላቀረቡም፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ
ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና
ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡በመሰረቱ የስር ፍርድ
ቤቶች ማስረጃን ሰምተው በመመርመርና በመመዘን የሚደርሱበት መደምደሚያ በስር ፍርድ ቤቶች
የተሰጠን መሰረታዊ የህግ ስህተት የማረም ስልጣን ብቻ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10(1) እና
በህገ መንግስታችን አንቀፅ 80(3)(ሀ) በተሰጠው በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የሚታረም አይደለም፡፡አሁን
በያዝነው ጉዳይም የስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ የሰጠው የተጠሪ ምሰክሮች
ንብረትነቱ የአመልካች በሆነ የህንፃ መሳሪያ መሸጫ ሱቅ ውስጥ አመልካች አስተናጋጅ ሆነው እየሰሩ
ፒንሳ በብር 130.00 ገዝተው ገንዘቡን ከፍለው እቃውን የተረከቡ ቢሆንም አመልካች የተጨማሪ እሴት
ታክስ ደረሰኝ ያልሰጧቸው መሆኑን ሲያስረዱ የአመልካች መከለከያ ምስክሮች አመልካች ሽያጭ
ተከነወነ በተበለበት ወቅት በስፍራው አለመኖራቸውን በሚያሳምንና ልዩነት በሌለው መልኩ
አለማስረዳታቸውን በመጥቀስ ነው፡፡የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን በመስማት በመመርመርና በመመዘን
በፍሬ ነገሮች ላይ የደረሱበት ድምዳሜ በስር ፍርድ ቤቶች የተፈፀመን መሰረታዊ የህግ ስህተት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማረም ስልጣን ብቻ በተሰጠው በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የሚታረም ሆኖ ስላላገኘነው አመልካች በፍሬ
ነገር ጉዳይ ክርክር ላይ ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም፡፡

ለጉዳዩ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ በተመለከተም አመልካች ጥፋተኛ የተባሉበትን የወንጀል ድርጊት
የፈፀሙት ጥር 05 ቀን 2013 ዓም ሆኖ እያለ ተጠሪ ድርጊቱ ተፈፀመ ከተባለበት ጊዜ አንፃር ተግባራዊ
አፈፃፀም ያለውን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 131(1)(ለ) በመጥቀስ ክሱን
ሊያቀርብ ሲገባ የአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) እና አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀፅ
2(10)፤22(10) እና 50(ለ)(1) ን በመጥቀስ ክሱን ማቅረቡና የስር ፍርድ ቤቶችም ይህንን ስህተት
በማረም ለግራ ቀኙ ክርክር እልባት ሊሰጡ ሲገባ አመልካችን አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀፅ 56(1) እና
አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀፅ 2(10)፤22(10) እና 50(ለ)(1) ን በመጥቀስ ጥፋተኛ ማለታቸውና
የቅጣት ውሳኔውንም በዚሁ ድንጋጌ ስር መስጠታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ
ስላገኘነው በአመልካች ላይ ከሚጣለው የእስራት ቅጣት አንፃር በሁለቱ ድንጋጌዎች መሃል ልዩነት
ባለመኖሩ አመልካች ጥፋተኛ ሊባሉ የሚገባው በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ
131(1)(ለ) ስር ሊሆን ይገባል ብለናል፡፡

የገንዘብ መቀጮን በተመለከተ አመልካች ጥፋተኛ በተባሉበት የአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ
131(1)(ለ) የገንዘብ መቀጮ ከእስራት ቅጣቱ በተጨማሪ ያልተመለከተ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች
ይህንን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ አመልካች ብር 3,000.00 እንዲቀጡ የሰጡት የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ
የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ገደብን አስመልክቶ አመልካች ለገደብ ጥያቄያቸው መሰረት ያደረጉት የህክምና ማስረጃ የዲስክ
መንሸራተት ህመም ያለባቸው መሆኑን ከሚያሳይ በስተቀር አመልካች ባለባቸው ከፍተኛ የጤና ችግር
ምክንያት በማረሚያ ቤት ሊቆዩ የሚችሉበት አግባብ ሁኔታ የሌለ መሆኑን የሚያሳይ ባለመሆኑ ከዚህ
የተለየ እና የእስራት ቅጣቱን ለመገደብ የሚያስችል በቂና አሳማኝ ምክንያት ከተገቢው ማስረጃ ጋር
ማቅረባቸውን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ስለማያሳይ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ
ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. በፊንፊኔ ዙርያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.72079 ሚያዝያ 14 ቀን 2013


ዓም የሰጠው የጥፋተኝነት እና ሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓም የሰጠው የቅጣት ውሳኔ እና ይህንን
ውሳኔ በማፅናት የኦ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.350497 ግንቦት 12 ቀን 2013 ዓም
የሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.195(2)(ለ)(2) መሰረት ተሻሽለዋል፡፡አመልካች ጥፋተኛ ሊባሉ
የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 131(1)(ለ) ስር ሊሆን ይገባል፤ በዚህ አግባብም ብር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

3,000.00 እንዲቀጡ በስር ፍርድ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ክፍል ተሸሯል፡፡ከዚህ
ውጪ ያለው የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት መደምደሚያ ፀንቷል፡፡
2. ጉዳዩ ውሳኔ እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-209647

ቀን፡-28/03/2014ኣ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ አምሳሉ ቶሮ-አልቀረቡም

ተጠሪ፡- የብርብር ከተማ አንድነት ንግድ ማሕበር - ተወካይ አሜጫ አይጎት ቀረቡ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሠኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ
በደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ
ችሎት በመ.ቁ 33612 ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የክልሉ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 35627 ሠኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ
የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የከተማን ይዞታ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ሕዝቦች
ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ዐባያ ወረዳ ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን
ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት
ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አዋሳኙ በክሱ የተገለጸ እና በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ ቀጠና 1

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውስጥ የሚገኝ አጠቃላይ ስፋቱ 1234 ካ.ሜ የሆነ የድርጅት ይዞታ ያለው መሆኑን፤ አመልካቹ በጥቅምት
ወር 2011 ዓ.ም 9.6 x 1.1 = 10.56 ካ.ሜ ድንበር አልፎ የያዘበት መሆኑን፤ አመልካች አላግባብ የያዘውን
ይዞታ እንዲለቅ በተደጋጋሚ ተጠይቆ ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጽ አልፎ የያዘውን ይዞታ እንዲለቅ እና
ወጪ ኪሳራ የማቅረብ መብቱ እንዲጠበቅ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን አመልካች በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው ውድቅ የተደረገ ሲሆን በፍሬነገሩ
ላይ በሰጡት መልስ ደግሞ አመልካች ይዞታውን የተመራሁት በ1989 ዓ.ም ነው፤ በ1992 ዓ.ም በድንበር
ክርክር ተነስቶ በቀበሌ አስተዳደር ኮሚቴ ታይቶ አመልካች 1200 ካ.ሜ የቀድሞ ምሪት እንዳለኝ ካርኒ
አቅርቤ ተጠሪ ደግሞ የቀድሞ ምሪቱ 250 ካ.ሜ መሆኑ ታይቶ በትርፍነት የያዘው 522 ካ.ሜ እንዲመልስ
ተወስኖበታል፤ አመልካች በወቅቱ በስተሰሜን በኩል ድንበር ያላለፍኩ መሆኑም በማሕበራዊ ፍርድ ቤት
ተወስኖልኛል፤ ተጠሪ ያቀረበው ማስረጃ በማጭበርበር የተገኘ ነው፤ ስለሆነም ክሱ ወድቅ ሊደረግ ይገባል
በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ እና የሚመለከተው የአስተዳደር አካል ቦታው ድረስ
በመሄድ አጣርቶ ምላሽ እንዲልክለት ካደረገ በኋላ ከተጠሪ ምስክሮች ቃል እና የሚመለከተው አካል
ከሰጠው ምላሽ አመልካች የተጠሪን ድንበር ማለፉን መገንዘብ ተችሏል፤ አመልካች ባቀረባቸው ምስክሮችም
ሆነ በሰነድ ማስረጃ ድንበር አለማለፉን አላስረዳም፤ የማሕበራዊው ፍርድ ቤት ውሳኔ የራስጌ ማሕተም
የሌለበት እና ዳኞቹ እነማን እንደሆኑ የማይገልጽ ሲሆን በ1992 ዓ.ም ማሕበራዊ ፍርድ ቤቱ ያልተቋቋም
በመሆኑ ተቀባይነት ያለው አይደለም፤ አመልካች ከይዞታው ውጪ አልፎ የያዘው 9 ሜ x 0.5 ሜ= 4.5
ካ.ሜ ሲሆን ወደ ተጠሪ ይዞታ አልፎ የያዘውን 0.5 ሜትር የሆነ ይዞታ ለተጠሪ ሊለቅ ይገባል፤ አመልካች
በተደጋጋሚ ይዞታውን እንዲለቅ ተጠይቆ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተጠሪ በማስረጃ ያላረጋገጠ በመሆኑ ይህን
አስመልክቶ ያቀረበው የወጪ ኪሣራ ጥያቄ ተቀባይን የለውም ሲል ወስኗል፡፡

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ለጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤተቱታ አቅርበዋል፡፡ ተጠሪም
የስር ፍርድ ቤቱ ወጪ ኪሳራን አስመልክቶ የሰጠውን ውሰኔ በተመለከተ መስቀለኛ ይግባኝ አቅርቧል፡፡
ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ተጠሪ ወጪ ኪሳራን በሚመለከት ያቀረበውን መስቀለኛ ይግባኝ ውድቅ
አድርጎ ዋናውን ጉዳይ በሚመለከተ ደግሞ የጋሞ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ስለጉዳዩ
አጣርቶ ሙያዊ አስተያየት እንዲልክለት ካደረገ በኋላ አመልካች በይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃው ላይ 220.05
ካ.ሜ ይዞታ እንዳላቸወ የተገለጸ ሲሆን በመሬት ላይ ደግሞ 227.05 ካ.ሜ ሆኖ በብልጫነት 6.55 ካ.ሜ
ይዘዋል፤ የተጠሪ ይዞታ 1240 ካ.ሜ መሆን ሲገባው 4 ካ.ሜ በስህተት ተደምሮ 1243 ካ.ሜ ሆኗል፤
የቀረበው ሪፖርት ተጠሪ ካለው ይዞታ የተቀነሰበት ይዞታ እንደሌለ የሚያስረዳ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቱ
አመልካች አልፎ የያዘውን የተጠሪ ይዞታ እንዲለቅ ሲል የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሮታል፡፡

ተጠሪ በበኩሉ ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
አቅርቧል፡፡ ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ከተለያዩ አካላት የተውጣጡ ባለሙያዎች ስለጉዳዩ አጣርተው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዲያቀርቡለት እና አስቀድሞ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት መግለጫ የሰጡ ሁለት ባለሙያዎች ማብራሪያ


እንዲሰጡት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተጣራው ውጤት አመልካች አልፎ
ይዞታል የተባለውን የይዞታ መጠን በሚመለከት የተለያየ ቢሆንም አመልካች የተጠሪን ይዞታ አልፎ መያዙ
ተረጋግጧል፤ ስለሆነም የስር ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ገፍቶ የያዘው የተጠሪ ይዞታ
የለም በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ሽሮ አመልካች በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ
ቀጠና 01 ውስጥ ከተጠሪ ድርጅት አልፎ የያዘውን 1.1 ሜ x 9.55 ሜ =10.505 ካ.ሜ ይዞታ እንዲለቅ
ሲል ወስኗል፡፡

አመልካች በተራቸው ይህን ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ
ያቀረቡ ቢሆንም ውሳኔው ሳይለወጥ ቀርቷል፡፡

አመልካች ሠኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ይህን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ሲሆን
ይዘቱም፡- ተጠሪ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የጠየቀው ዳኝነት በወረዳው ፍርድ ቤት
የተሰጠው ውሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነው፤ ስለሆነም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
አመልካች 10.505 ካ.ሜ ይዞታ ለተጠሪ እንድለቅ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪው ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የስር ወረዳው ፍርድ ቤት አመልካች 0.5
ሜትር አልፎ የያዘውን የተጠሪ ይዞታ እንዲለቅ በማለት የሰጠውን ውሳኔ ለማስለወጠ አመልካች ይግባኝ
ብለው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የወረዳውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻረበት ሁኔታ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካች 10.505 ካ.ሜ የሆነ ይዞታ ለተጠሪ እንዲለቅ የመወሰኑን አግባብነት
ከመሠረታዊ የክርክር አመራር ሥነ ሥርዓት ጋር በማገናዘብ ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ
በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጎ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ቀርቧል፡፡

ተጠሪ መስከረም 25 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጠው መልስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች 10.56 ካ.ሜ ከተጠሪ
ይዞታ ላይ አልፎ የያዘውን ይዞታ እንዲለቅ ክስ ቀርቦበት የወረዳው ፍርድ ቤት 0.5 ሜትር አልፎ የያዘውን
ይልቀቅ ብሎ ወስኗል፤ አመልካች ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ
የወረዳው ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር መስቀለኛ ይግባኙን ሲሰርዝ ተጠሪ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ይግባኝ አቅርቤአለሁ፤ ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ተጨማሪ ማጣራት አድርጎ በስር ወረዳው ፍርድ
ቤት በጠየቅኩት ዳኝነት መሠረት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡ አመልካችም
የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ
ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምሮታል፡፡

ከክርክሩ ሒደት መገንዘብ እንደተቻለው አመልካች የተጠሪን ይዞታ አልፎ የያዘበት ስለመሆኑ ፍሬነገርን
የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ባላቸው የወረዳው ፍርድ ቤት እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተረጋግጧል፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች
አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10/1 መሠረት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የተሰጠው ስልጣን መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም እንጂ ፍሬነገርን
የማጣራት እና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን የሌለው በመሆኑ አመልካች የተጠሪን ይዞታ አልፈው ይዘዋል?
ወይስ አልያዙም? የሚለው በዚህ ችሎት የሚጣራ አይደለም፡፡

በሌላ በኩል በሰበር አጣሪው ችሎት ከተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አንጻር የወረዳው ፍርድ ቤት አመልካች
ለተጠሪ ሊለቁት የሚገባውን የይዞታ መጠን 0.5 ሜትር ነው በማለት በሰጠው ውሳኔ ላይ ተጠሪ ስርዓቱን
ጠብቆ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ በሌለበት ሁኔታ የወረዳው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ
በከፍተኛው ፍርድ ቤት መሻሩን ተከትሎ ተጠሪ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበው ይግባኝ መነሻነት
አመልካች ከተጠሪ ድርጅት አልፎ የያዘውን 1.1 ሜ x 9.55 ሜ =10.505 ካ.ሜ ይዞታ እንዲለቅ በማለት
በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ የይግባኝ ክርክሮች
የሚመሩበትን ሥርዓት ያላገናዘበ እና መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ስለሆነም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ
1. በደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ
ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 33612 ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 35627 ሠኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ተሻሽሏል፡፡
2. አመልካቸ ለተጠሪ ሊለቁት የሚገባው የይዞታ መጠን በወረዳው ፍርድ ቤት ላይ የተገለጸውን የይዞታ
መጠን ነው በማለት ወስነናል፡፡
3. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
4. ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
- ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የመ.ቁ.209733

ህዳር 27/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡ 1. ዳዊት መንገሻ የቀረበ የለም

2. አበራሽ በዳኔ

ተጠሪ፡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ- የቀረበ የለም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የእምነት ማጉደል ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም
የተጀመረው የአሁን ተጠሪ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ አንቀፅ 675(1) ድንጋጌን ጠቅሶ በአሁን
አመልካቾች ላይ በባሌ ዞን ጋሰራ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ ነው፡፡ የክሱም ይዘት
አመልካቾች የማይገባቸውን ብልፅግና ለራሳቸው ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስበው በወንጀል
ተጠርጥሮ በክፍሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው በአጠቃላይ 656 ቁምጣ የዳንጎቴ ሲሚንቶ
በወቅቱ በወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ንብረቱን ለማስቀመጥ የሚያስችል ቦታ ባለመኖሩ በአሁን አመልካቾች
መጋዘን እንዲራገፍ ተጠይቀው ፈቃደኛ በመሆናቸው ንብረቱ በህገ ሲፈለግ ለማቅረብ ተስማምተው 1ኛ
አመልካች 310 ቁምጣ፤ 2ኛ አመልካች ደግሞ 346 ቁምጣ ሲሚንቶ ከወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ
ፈርመው በአደራ ከተቀበሉ በኋላ ሲሚንቶውን እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ ለማቅረብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው
የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው፡፡

አንደኛ አመልካች ለዚሁ ክስ በሰጠው መልስ በክሱ ውስጥ የተጠቀሰው ንብረት በህጋዊ መንገድ
የገዛሁት የራሴ ንብረት ነው፤ ሲሚንቶውን ሳራግፍ ህገ ወጥ ነው የሚል ጥያቄ ተነስቶ እስኪጣራ ድረስ
እንዳራግፍ ተፈቅዶ በዚሁ መሰረት ያራገፍኩት እንጂ በአደራ የተቀበልኩት አይደለም፤ ንብረቱም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኤግዚቢትነት ያልተመዘገበ በመሆኑ ልከሰስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡ ሁለተኛ አመልካች


በበኩላቸው ንብረቱ የአንደኛ አመልካች ነው፤ በመጋዘኔ እንዳስቀምጥላቸው ጠይቀዉኝ ያስቀምጥኩት
እንጂ በክሱ ውስጥ በተገለፀው አግባብ በአደራ የተቀበልኩት አይደለም በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃን ከሰማ በኋላ አመልካቾች ለወንጀል
ክሱ ምክንያት የሆነውን ንብረት በክሱ ዝርዝር በተገለፀው አግባብ በአደራ ተቀብለው እንዲያቀርቡ
ሲጠየቁ ያላቀረቡ ስለመሆኑ በዐቃቤ ህግ የሰው እና አመልካቾች ንብረቱን በአደራ ስለመቀበላቸው
በፈረሙት የአደራ ሰነድ የተረጋገጠ መሆኑን፤ በአንፃሩ አመልካቾች ንብረቱን በአደራ የተቀበልነው
ሳይሆን የአንደኛ አመልካች ነው በሚል የተከራከሩ ቢሆንም አቅርበው ባሰሟቸው የሰው ምስክሮች
የዐቃቤ ህግ ክስ እና ማስረጃን አላስተባበሉም በሚል ክስ በቀረበበት አንቀፅ ስር ጥፋተኛ ብሎ
እያንዳንዳቸውን በ6(ስድስት) ወር ቀላል እስራ እንዲቀጡ ወስኗል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በይግባኝ የተመለከተው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በበኩሉ የግራ ቀኙን የይግባኝ ክርክር
ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ አመልካቾች ለወንጀል ክሱ ምክንያት የሆነውን ሲሚንቶ የተረከቡት በውል
ስምምነት በመሆኑ የውል ግዴታቸውን ካልፈፀሙ በፍትሓ ብሄር ከሚጠየቁ በቀር በወንጀል
የሚያስጠይቃቸው ነገር የለም በማለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/65054
ላይ የሰጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም በዋቢነት ጠቅሶ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ውድቅ በማድረግ
አመልካቾን ከቀረበባቸው ክስ በነፃ አሰናብቷቸዋል፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በበኩሉ አመልካቾች በአደራ ለማስቀመጥ


የተረከቡትን ንብረት ሲጠየቁ ማቅረብ እንዳልቻሉ ተረጋግጦ እያለ እና ይህንን ሊያስተባብል የሚችል
መከላከያ ማስረጃ ባልቀረበበት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾችን በነፃ ማሰናበቱ አግባብ
አለመሆኑን በመተቸት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ውድቅ አድርጎ የወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔን
አፅንቷል፡፡ ይኸው ውሳኔ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው፡፡ አመልካቾች ሰኔ 22/2013 ዓ.ም በተፃፈ
የሰበር አቤቱታ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል
ያሉትን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጠቅሰው በዚህ ችሎት እንዲታረምላቸው ጠይቅዋል፡፡ የአመልካቾች
የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካቾች በአደራ የተሰጣቸውን 656 ቁምጣ ሲሚንቶ እንዲያቀርቡ
ሲጠየቁ ባለማቅረባቸው የወንጀል ህግ አንቀፅ 675(1) በመተላለፍ የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈፅመዋል
በሚል የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የተሰጠበት አግባብነት በዚህ ችሎት ቀርቦ እንዲመረመር በሰበር
አጣሪ ችሎት በመታዘዙ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡ ግራ ቀኙ በፅሁፍ
ባቀረቡት መከራከሪያም ከሞላ ጎደል በስር ፍርድ ቤት የቀረቡትን መከራከሪያዎች በመድገም
ሞግተዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ይህንን ሲመስል ችሎቱም የግራ ቀኙን ክርክር ጉዳዩ
ለዚህ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አኳያ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ
መርምሯል፡፡

እንግዲህ አመልካቾች የተከሰሱት በእምነት ማጉደል ወንጀል ነው፡፡ የእምነት ማጉደል ወንጀል ምን
ማለት እንደሆነ እና የወንጀሉ ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች በወንጀል ህጉ አንቀፅ 675 ስር ተመልክቷል፡፡
በዚሁ አግባብ አንድ ሰው የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ በወንጀል የሚቀጣው ተገቢ
ያልሆነ ብልፅግናን ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰው የሆነውን እና ለአንድ
ለተወሰነ አገልግሎት ወይም በአደራ የተሰጠውን ዋጋ ያለውን ነገር ወይም ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወይም
በከፊል ለራሱ ያደረገ፣ የወሰደ፣ ያስወሰደ፣ የሰወረ፣ ወይም ይህንን የመሳሰለውን ማናቸውንም አድራጎት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የፈፀመ እንደሆነ እና ይህንኑ በእምነት ወይም በአደራ የተቀበለውን ንብረት ወይም ጥሬ ገንዘብ
እንዲመልስ ወይም እንዲከፍል ሲጠየቅ ንብረቱ ያለበትን ሁኔታ ለማሳየት ወይም ለተገቢው አገልግሎት
ያዋለው ለመሆኑ ማስረዳት ያልቻለ ስለመሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆን ከዚሁ ድንጋጌ ንዑስ አንቀፅ 1 እና 3
ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ የእምነት ማጉደል ወንጀል ማቋቋሚያ
መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ውስጥ አንዱ በአደራ የተቀበሉትን ንብረት እንዲመልስ ሲጠየቅ አለመመለስ
እንደሆነ በዚሁ ድንጋጌ ስር በግልፅ ተመልክቷል፡፡

አሁን በቀረበው ጉዳይ አመልካቾች የእምነት ማጉደት ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉት በህገ ወጥነት
ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር የዋለውን ንብረት በአደራ እንዲያስቀምጡ የተሰጣቸውን ንብረት ሲጠየቁ
አላቀረቡም በሚል ነው፡፡ አመልካቾች ንብረቱን በተመለከተ የባለቤትነት መከራከሪያ ያቀረቡ ቢሆንም
ማስረጃን የመስማት እና የመመርመር ስልጣን በተሰጣቸው የስር ፍርድ ቤቶች ለወንጀል ክሱ መሰረት
የሆነው ንብረት አመልካቾች በአደራ ለማስቀመጥ ፈርመው ከህግ አካል የተቀበሉት ስለመሆኑ በፍሬ
ነገር ደረጃ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን ከስር ፍርድ ቤቶች የመዝገብ ይዘት መረዳት
ይቻላል፡፡ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም አመልካቾችን ከወንጀል ክሱ በነፃ ሲያሰናብት በምክንያትነት
የጠቀሰው ጉዳዩ ወንጀል ሳይሆን የውል ግዴታን አለመፈፀምን የሚመለከት ፍትሓ ብሄራዊ ኃላፊነት
ነው በሚል እንጂ ንብረቱ የአመልካቾች ስለመሆኑ አስረድተዋል በሚል አይደለም፡፡ በእርግጥ
አመልካቾች ንብረቱን በአደራ ፈርመው መቀበላቸው በግራ ቀኙ መካከል ያለው ግኑኝነት የውል
የሚያስመስለው ነው፡፡ ሆኖም የውሉ ጉዳይ በአደራ የተቀበሉትን ንብረት በአደራ ሰጪው ሲጠየቁ
ለመመለስ እንጂ ለሌላ ዓላማ ባለመሆኑ በዚህ መልኩ አምነዉበት የተቀበሉትን ንብረት እንዲመልሱ
ሲጠየቁ አለመመለስ ተራ የውል ግኑኝነትን የሚመለከት ሳይሆን የእምነት ማጉደል ወንጀል
የሚመለከት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ያዩበት እና የደረሱበት ድምዳሜ
በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር እና ክስ የቀረበበትን የወንጀል ህግ ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት
መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር ሊነቀፍ የሚችልበት መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም፡፡ በመሆኑም
የአመልካቾች አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

1. የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት


የአመልካቾችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በመ/ቁ/374852 ላይ ግንቦት 10/2013 ዓ.ም
የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ለ(2))) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ.209757

ቀን፡-30/03/2014ዓ.ም

ዳኞች፡ ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካቾች ፡1ኛ/ አቶ ከበደ ደሴ ጠበቃ ይልማ አቻሜ

2ኛ/ አቶ ደግፍ ባረዳ

ተጠሪዎች ፡1ኛ/ ወ/ሮ እልፍነሽ አብደላ ጠበቃ ሰለሞን ታደሰ ቀረቡ

2ኛ/ ወ/ሪት ትዝታ ፈቀደ

መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ
ጉዳዩ የሽያጭ ውል የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን በአመልካቾች ላይ በሁለት የተለያዩ መዝገቦች
ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካቾች በደራጀማ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ ስድስት
አክሲዮኖችን ከአንድ ሱቅ ጋር እንሸጥላችኋለን በማለት በ2004 ዓ.ም በተደረገው ውል ለ1ኛ
ተጠሪ በብር 450,000.00 እንዲሁም ለ2ኛ ተጠሪ በብር 480,000.00 የሸጡልን ቢሆንም ውሉ
ከህግ ውጪ የተደረገ በመሆኑ አመልካቾች በሽያጭ ውሉ መሰረት የወሰዱት ገንዘብ
እንዲመልሱልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡አመልካቾች በበኩላቸዉ ውሉ የተደረገው በቃል
መሆኑንና አንደኛው ተዋዋይ በውሉ ጥቅም አለማግኘቱ የውል ማፍረሻ ምክንያት
አይሆንም፣የተሸጠው በሱቅ የመጠቀም መብት እንጂ የሱቅ ባለሀብት እንዲሁም የአክሲዮን
ድርሻ ላይ አይደለም፣ተጠሪዎች ሱቁን በመረከብ ሲጠቀሙበት ቆይቷል፤ይህም በሱቁ ላይ
ጥቅም ሲያገኙ እንደነበር የሚያሳይ ነው፣ተጠሪዎች የከፈሉት ገንዘብ የሚመለስበት የህግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አግባብ የለም፣ማህበሩ የሚሰራበት ቤት ከቤቶች ኮርፖሬሽን በመከራየት ነዉ፤በመሆኑም


ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር እና የቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ደራጀማ ሆቴል


ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚሰራበት ቤት ንብረትነቱ የመንግስት ሆኖ አመልካቾች የመጠቀም
መብታችን ነው የሸጥንላቸው የሚሏቸው ሱቆች በምን አግባብ አግኝተው የመጠቀም
መብታቸውን እንደሸጡ አላስረዱም፤አመልካቾች ለክርክሩ ምክንያት የሆኑ ሱቆች ላይ ምንም
አይነት በህግ የተረጋገጠ መብት ሳይኖራቸው ሱቆቹ የእኛ ናቸው በማለት ለተጠሪዎች
የሸጡላቸው መሆኑ ስለተረጋገጠ የሽያጭ ውሉ ፈርሶ ግራ ቀኙ ወደ ነበሩበት ሊመለሱ ይገባል
በማለት የሽያጭ ገንዘቡን ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ከ9% ወለድ ጋር ለተጠሪዎች
እንዲመለሱላቸው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዉ


ፍ/ቤቱም የግራ ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋላ መዝገቡን መርምሮ ውሉ ፈርሶ ገንዘቡ ለተጠሪዎች
እንዲመለስ የተባለዉን በማጽናት ወለዱ መታሰብ ያለበት ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን እንደሆን
በማለት አሻሽሎ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ላይ ነዉ፡፡ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት
ተፈጽሞበታል በማለት አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት ባጭሩ፤1ኛ አመልካች እና 1ኛ
ተጠሪ ጉዳዩን በሽማግልና በዕርቅ ጨርሰን የእርቅ ስምምነቱን ለፍ/ቤቱ አቅርበን ክርክሩ
እንዲቋረጥ አመልክተን ፍ/ቤቱም መጋቢት 1 ቀን 2013ዓ.ም በዋለው ችሎት ክርክሩ
በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(1) መሰረት ተቋርጧል ብሎ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ሚያዝያ 18 ቀን 2013
ዓ.ም ውሳኔ ሲሰጥ ብር 450,000.00 ለ1ኛ ተጠሪ ይክፈል በማለት የሰጠው ውሳኔ ስህተት
ነው፤የስር ፍ/ቤት ሁለቱም አመልካቾች ባልተነጣጠለ ኃላፊነት ብር 480,000.00 ለ2ኛ ተጠሪ
እንዲከፍሉ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግን 2ኛ አመልካች ብቻውን እንዲከፍል
በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡ የስር ፍ/ቤት ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮቹ ወደ
ነበሩበት እንዲመለሱ በማለት ገንዘቡ ለተጠሪዎች እንዲመለስ ሲወስን ሱቆቹ ደግሞ
ለአመልካቾች እንዲመለስ መወሰን ሲገባ ይህንን በዝምታ ማለፉ ስህተት በመሆኑ ውሳኔው
እንዲታረምልን በማለት አመልክተዋል፡፡

የአመልካቾች አቤቱታ በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ ፍ/ቤቱ በ1ኛ አመልካች እና 1ኛ


ተጠሪ መካከል የነበረው ክርክር በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 278(1) መሰረት ተቋርጧል በማለት ክርክሩ
በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ መካከል እንዲቀጥል ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ 1ኛ አመልካች ለ1ኛ
ተጠሪ ብር450,000.00 እንዲከፈል እንዲሁም 2ኛ አመልካች ለ2ኛ ተጠሪ ብር 480,000.00
እንዲከፍሉ የወሰነበት አግባብ ለማጣራት ጉዳዩ ያስቀርባል ተብሎ ተጠሪዎች መልስ
እንዲያቀርቡ ታዟል፡፡

ተጠሪዎች ባቀረቡት መልስ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የእርቅ ስምምነቱን መዝግቦ እያለ 1ኛ
አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ብር 450,000.00 እንዲከፍሉ የሰጠው ውሳኔ ባለማስተዋል የተፈፀመ
ስህተት ስለሆነ ሊታረም ይገባል፤ክርክሩ ሊቀጥል አይገባም፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ብር
480,000.00 እስከነወለዱ አመልካቾች ለ2ኛ ተጠሪ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት የሰጠዉን ውሳኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከፍተኛ ፍ/ቤት ያፀና ቢሆንም በውሳኔው ላይ 2ኛ አመልካች ብቻ ፍርድ ያረፈበት ገንዘብ


ለ2ኛ ተጠሪ ሊከፍል ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ ስህተት በመሆኑ ሊታረም እንደሚገባ
እናምናለን ነገር ግን መሰረታዊ የህግ ስህተት አይደለም፤ሱቆቹ በተጠሪዎች እጅ የሌሉ እና
ንብረትነቱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስለሆነ ለአመልካቾች ሊናስረክብ አንችልም፣በዚህ
ረገድ የቀረበው ቅሬታ ውድቅ እንዲሆን በማለት ተከራክረዋል፡፡አመልካቾች አቤቱታቸውን
የሚያጠናክር የመልስ መልስ አቅርበው ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከትነው ሲሆን
ጉዳዩ ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥ አንጻር የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አግባብነት ካላቸው
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡መዝገቡን መርምረን እንደተገነዘብነዉ
በአመልካቾች እና ተጠሪዎች መካከል የተደረገዉ የሽያጭ ዉል እንዲፈርስ የተወሰነዉ
አመልካቾች ሊተላለፍ የሚችል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ አላስረዱም ተብሎ ነዉ፡፡በዚህ ረገድ
የቀረበ ቅሬታ የለም፡፡ይህንኑ ተከትሎ አመልካቾች በዉሉ መነሻ የተረከቡትን ገንዘብ
ለተጠሪዎች እንዲመልሱ የተወሰነ ሲሆን የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነዉ የገንዘቡን አመላለስ
በተመለከተ ይግባኝ ሰሚዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈጸመዉ ስህተት እንዲታረም በማለት
ነዉ፡፡ተጠሪዎችም ቢሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ስህተት እንዳለበት አምነዉ ነገር ግን
በዚያዉ ፍርድ ቤት ሊታረም ይችላል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡እኛም በሰበር አጣሪ ችሎት
የተያዘዉን ጭብጥ መሰረት በማድረግ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ዉሳኔ አግባብነት በቅደም
ተከተል መርመረናል፡፡

የመጀመሪያዉ በ1ኛ አመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉ ዉል የሚመለከት


ነዉ፡፡ከክርክሩ እንደተገነዘበነዉ በሁለቱ መካከል የተደረገዉ ዉል መፍረሱንና ዉጤቱን
በሚመለከት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዉሳኔ ላይ አመልካች ቅር ተሰኝተዉ በይግባኝ
ሰሚ ፍርድ ቤት በክርክር ሂደት ላይ እያሉ ጉዳዩን በስምምነት በሽምግልና መጨረሳቸዉን
ገልጸዉ ማመልከቻ በማቅረባቸዉ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 278/1/
መሰረት ክርክሩ እንዲቋረጥ በቀን 01/07/2013ዓ.ም ትእዛዝ ስለመስጠቱ መዝገቡ ያሣያል፡፡ግራ
ቀኙም አልተካካዱም፡፡በፍትሓብሔር ስነስርዓት ህጉ እንደተመለከተዉ በፍርድ ቤት በክርክር
ላይ ያሉ ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸዉን ከፍርድ ቤት ዉጪ በስምምነት ለመጨረስ የተስማሙ
ከሆነ እና ይህንኑ ለፍርድ ቤቱ ሲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ የእርቅ ስምምነቱ ለሞራል እና ለህግ
ተቃራኒ አለመሆኑን ካረጋገጠ በኋላ እርቁን ተቀብሎ በማጽደቅ መዝገቡን እንደሚዘጋ በሌላ
በኩል ደግሞ ተከራካሪ ወገን ክሱን ወይም ክርክሩን ለማቋረጥ ሲፈልግ ይህንኑ ለፍርድ ቤቱ
ካሳወቀ ክርክሩ እንዲቋረጥ ትእዛዝ የሚሰጥበት ሁኔታ ተመልክቷል፡፡(የፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር
277 እና 278 ድንጋጌዎችን ይመለከታል)፡፡ በሁለቱ ድንጋጌዎች መካከል የምክንያት እና
የዉጤት ልዩነት መኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ እንዲህ በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቱ በስረነገሩ ወይም
አከራካሪዉ ጉዳይ ላይ ፍርድ እንዲሰጥ አይጠበቅበትም፡፡ይልቁንም እንደ ተከራካሪ ወገኖች
ጥያቄ ስምምነቱ የሚፈጸምበትን አግባብ ወይም ሌላ ተገቢ መስሎ የታየዉን ትእዛዝ መስጠት
እንዲችል ስነስርዓት ህጉ ይፈቅድለታል፡፡ፍርድ ቤቱም ይህንኑ ስነስርዓታዊ ጉዳይ ላይ
እንዲወሰን ይጠበቃል፡፡ በተያዘዉ ጉዳይ በ1ኛ አመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል በተደረገዉ
ዉል የተቀባበሉትን ብር 450,000 አመላለስ አስመልከቶ ስምምነት ማድረጋቸዉ ስለገለጹ
ክርክሩ በፍ/ብ/ስ/ስ ህግ ቁጥር 278/1/ መሰረት እንዲቋረጥ ከተደረገ በኋላ በዚህ ጉዳይ ፍርድ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቤቱ ዉሳኔ መስጠቱ ስነስርዓታዊ መሰረት የለዉም፡፡ስለዚህም 1ኛ አመልካች ለ1ኛ ተጠሪ ብር


450,000 እንዲከፍሉ በማለት የሰጠዉ ዉሳኔ በግራቀኙ ጠያቂነት ክርክሩ እንዲቋረጥ የሰጠዉን
ትእዛዝ ከግምት ያላስገባ እና የክርክር አመራር ስርዓት ግድፈት የተፈጸመበት ከመሆኑም
በተጨማሪ ስምምነታቸዉንም ዋጋ የሚያሳጣ ስለሆነ ሊታረም ይገባል፡፡

ሁለተኛዉ የቅሬታ ነጥብ በሁለተኛ ዉል መሰረት ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ የ2ኛ አመልካች
ብቻ እንደሆነ ተደርጎ መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነዉ፡፡ከክርክሩ
እንደሚታየዉ ሁለተኛዉ ዉል የተደረገዉ በ2ኛ ተጠሪ እና በአመልካቾች መካከል ስለመሆኑ
አላከራከረም፡፡ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተዉ ፍርድ ቤትም በሁለተኛዉ ዉል
መሰረት አመልካቾች ከ2ኛ ተጠሪ የተቀበሉትን ብር 480,000 በአንድነትና በነጠላ ለ2ኛ
ተጠሪ እንዲመልሱ ወስኗል፡፡ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ይህንን የአንድነትና የነጠላ ሃላፊነት
የለወጠበት ምክንያት ስለመኖሩ በዉሳኔዉ ላይ አላተመላከተም፡፡ከመሰረቱም ገንዘቡን
የመመለስ ሃላፊነት የአንደኛዉ ወገን ብቻ ነዉ የሚል ክርክር በአመልካቾች በኩል
አልቀረበም፡፡ይህ ከሆነ ደግሞ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የክርክሩን ይዘት ባለማገናዘብ
የተፈጸመ ስህተት ነዉ ከሚባል በስተቀር ሌላ አሳማኝ ምክንያት የለዉም፡፡ስለሆነም
በሁለተኛዉ ዉል መሰረት ከ2ኛ ተጠሪ የተቀበሉትን ብር 480,000 አመልካቾች በአንድነትና
በነጠላ ለ2ኛ ተጠሪ እንዲመልሱ በማለት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዉሳኔ
ተገቢ ሆኖ እያለ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት 2ኛ አመልካች ብቻ እንዲከፍሉ መወሰኑ ስህተት
ስለሆነ ሊታረም ይገባል ብለናል፡፡

የመጨረሻዉ ነጥብ ዉሉ መፍረሱን ተከትሎ ተጠሪዎች ሱቁን እንዲመልሱ ዉሳኔ አለመስጠቱ


ስህተት ነዉ የሚል ሲሆን በተጠሪዎች በኩል የቀረበዉ ክርክር ከጅምሩም ቢሆን ሱቅ የተባለዉ
የመንግስት ቤት ስለመሆኑና በእጃቸዉ የሌለ መሆኑን በመግለጽ የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ
ስህተት የለዉም በሚል ተከራክረዋል፡፡አንድ ዉል ሲሰረዝ ወይም ሲፈርስ ተዋዋይ ወገኖች
በተቻለ መጠን ከዉሉ ከመደረጉ በፊት እንደ ነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚገባ
የፍ/ብ/ህግ አንቀጽ 1815 ድንጋጌ ያስገነዝባል፡፡በተያዘዉ ጉዳይ የስር ፍርድ ቤት የሽያጭ
ዉል ሊፈርስ ይገባል በማለት አመልካቾች የወሰዱትን ገንዘብ ለተጠሪዎች እንዲመልሱ ሲወስን
የዉሉ ጉዳይ ሱቅ በሚመለከት በግልጽ ያለዉ ነገር የለም፡፡ይሁንና አመልካቾች ለተጠሪዎች
ሽጠናል የሚሉት ሱቅ ወይም በሱቁ የመጠቀም መብት ያላቸዉ መሆኑን አላስረዱም የሚለዉ
የፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ምክንያት የሚያሣየዉ አመልካቾች ሱቅ ለተጠሪዎች አላስረከቡም የሚል
ግንዛቤ በመዉሰድ እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ፡፡በእርግጥ አመልካቾች ቤቱን (ሱቁን) ለተጠሪዎች
አስረክበዉ ከነበረ የርክብክብ ማስረጃዉን በመያዝ እንዲመልሱላቸዉ መጠየቅ የሚከላክላቸዉ
ምክንያት ስለመኖሩ በፍርዱ ላይ አልተገለጸም፡፡ከጅምሩም ቢሆን ዉሉ እንዲፈርስ የተደረገዉ
አመልካቾች በሽያጭ ለማስተላላፍ ዉል የገቡበት ንብረት ላይ መብት የሌላቸዉ እና ሊፈጸም
የማይቻል ዉል መሆኑን በማረጋጋጥ ስለሆነ በዚህ ረገድ አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ
ተቀባይነት አላገኘም፡፡

ሲጠቃለል የገንዘቡን አመላለስ በተመለከተ ብቻ ከላይ በዝርዝር በተገለጸዉ ምክንያት


የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዉሳኔ የስነስርዓት ግድፌት የተፈጸመበት መሆኑን በመገንዘብ
እና ይህንኑ በማረም ተከታዩን ዉሳኔ ሰጥተናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ዉሳኔ

1ኛ/የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/247093 ላይ በቀን 18/09/2013ዓ.ም ላይ የስር


ፍርድ ቤት ዉሳኔ በማሻሻል የሰጠዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሏል፡፡

2ኛ/በ1ኛ አመልካች እና በ1ኛ ተጠሪ መካከል የተደረገዉን ዉል በሚመለከት ብር 450,000


አመላለስ ላይ ከፍርድ ቤት ዉጭ መስማማታቸዉን ገልጸዉ ባቀረቡት አቤቱተ መሰረት
ክርክሩ በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር 278/1/ መሰረት እንዲቋረጥ ከተደረገ በኋላ ገንዘቡን እንዲመላለሱ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠዉ ዉሳኔ ክፍል ተሽሯል፡፡

3ኛ/በሁለተኛዉ ዉል መሰረት ከ2ኛ ተጠሪ የተቀበሉትን ብር480,000 አመልካቾች


በአንድነትና በነጠላ ለ2ኛ ተጠሪ እንዲለመሱ በሚል ተሻሽሏል፡፡

4ኛ/ወለድን እና ወጪ ኪሳራ የሰጠዉ ዉሳኔ ክፍል ጸንቷል፡፡

4ኛ/በዚህ ፍርድ ቤት ለተደረገዉ ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸዉን ይቻሉ ብለናል፡፡

3ኛ/በዚህ መዝገብ ላይ በ30/10/2013ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረዉ የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል፡፡ይጻፍ

መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰ/መ/ቁ፡-209840

ቀን፡-29/02/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት - አልቀረቡም

ተጠሪ፡- ጣና ፕላስቲክ ፋብሪካ ሀላፊነቱ የተወሰነ አክሲዮን ማሕበር - ጠበቃ ታፋ ይርጋ- ቀረቡ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሠኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 113862 ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ ይህንኑ
ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 270023 ሠኔ 10 ቀን 2013
ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ
በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩ የሁከት ይወገድልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍ/ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች እና የአዲስ አበባ
እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ደግሞ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት
ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም በተደረገ የሊዝ ማሻሻያ ውል 2,293 ካ.ሜ የሆነ
ይዞታ ከከተማው አስተዳደር በቀን 22/09/2010 ዓ.ም ተረክቦ የግንባታ ፈቃድ ያወጣ መሆኑን፤ በይዞታው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ላይ አጥር ሊያጥ ሲል በአመልካች ስር የሚተዳደረው ኑር መስጊድ ተወካዮች አናሳጥርም በማለት ሁከት


የፈጠሩበት መሆኑን፤ ጉዳዩን ለስር 2ኛ ተከሳሽ ያሳወቀ ቢሆንም ምላሽ ያላገኘ መሆኑን በመግለጽ
የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድ እና የደረሰበትን ጉዳት አስልቶ ክስ የማቅረብ መብቱ እንዲጠበቅለት
ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን አመልካች በሰጠው መልስ ክሱ ግልጽ አይደለም፤ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም፤
ተጠሪ ክሱን ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የለውም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
ያቀረበ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ በሰጠው መልስ ይዞታው በተጠሪ እጅ አልገባም፤ ቦታው በ2ኛ ተከሳሽ ስር
የሚገኝ በመሆኑ የአመልካች ሰራተኞች መከልከላቸው ተገቢ ነው፤ ተጠሪ የተቋረጠ ጥቅም የለውም፤
ስለሆነም የቀረበው ክስ ወድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

የስር 2ኛ ተከሳሽ በሰጠው መልስ አመልካች ካቀረበው መቃወሚያ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው መቃወሚያ
ያቀረበ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ በሰጠው መልስ ተጠሪ ክስ የቀረበበትን ይዞታ በእጁ ሳያደርግ ሁከት
ተፈጥሮብኛል በማለት ክስ ማቅረብ አይችልም፤ ይዞታው የተጠሪ ሳይሆን 2ኛ ተከሳሽ በእጁ አድርጎ
የሚያዝበት ነው፤ ተጠሪ ካርታ ወስጀበታል በሚለው ይዞታ ላይ 2ኛ ተከሳሽ የፈጠረው ሁከት የለም፤
ስለሆነም ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል የሚል ነው፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የግራቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ በማስረጃነት ከቀረቡት ሰነዶች
መገንዘብ የሚቻለው ተጠሪ ይዞታው ላይ የባለቤትነት መብት አግኝቶ የአጥር ስራ ፈቃድ የተሰጠው
መሆኑን፤ የአመልካች እና የስር 2ኛ ተከሳሽ የማስፋፊያ ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግ በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ
መሠረት ተጠሪ በአፋጣኝ ይዞታውን እንዲያለማ የተሰጠው ማሳሰቢያ መኖሩን እና አመልካችም ይዞታው
ላይ ጥያቄ ስላቀረብን የወሰን ምልክት አይደረግም በማለት መከልከሉን ነው፤ በአመልካች በኩል ከስራ እና
ቤት ሚኒስቴር በ 1968 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ የኑር መስጊድ ካለው የቦታ ጥበት የተነሳ ሁኔታዎች
ተጠብቀው ቦታው ቢሰጠው ተቃውሞ የሌላው መሆኑ የገለጸበት ሰነድ፤ ግምቱን እንዲከፍሉ የተጻፈ
ደብዳቤ፤ ግምቱን የከፈሉ በመሆኑ ቦታውን ለመረከብ በተደጋጋሚ የቀረበ ጥያቄ እና የፌዴራል መጀመሪያ
ደረጀ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 492/90 ሐምሌ 23 ቀን 1994 ዓ.ም የአፈጻጸም ትዕዛዝ የቀረበ ቢሆንም ይዞታውን
እንዲረከቡ ውሳኔ ተሰጥቶ ይዞታውን ስለመረከባቸው የሚያሳይ ሰነድ አልቀረበም፤ ስለሆነም የተፈጠረው
ሁከት ሊወገድ ይገባል ሲልወስኗል፡፡ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ውሳኔውን አጽንቷል፡፡

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን
ይዘቱም፡- የስር ፍርድ ቤት በሀይማኖት ተቋሙ ላይ የቀረበውን ክስ ተቀብሎ ለማየት ስልጣን የለውም፤
የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረብ የሚችለው ይዞታውን በእጁ አድርጎ የሚያዝበት ሰው ነው፤ ቦታውን ተረክቦ
ድንበሩን ያላወቀ ሰው የሁከት ይወገድልኝ ክስ ማቅረብ አይችልም፤ አከራካሪው ይዞታ ለመስጊድ ማስፋፊያ
የተሰጠ ቦታ ነው፤ ስለሆነም አመልካች ይዞታውን እንዲለቅ የተሰጠው መሠረታዊ የሕግ ስሕተት
የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሰበር አጣሪው ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው መሬት ላይ
ሁከት ተፈጠረ በተባለበት ወቅት ተጠሪ ይዞታውን ይዞ የነበረ መሆኑ ስለመረጋገጡ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ
ባልተመለከተበት ሁኔታ ሁከት እንዲወገድ የመወሰኑን አግባብነት ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1149 ጋር
በማገናዘብ ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጎ ጉዳዩ ለዚህ
ችሎት ቀርቧል፡፡

ተጠሪ ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው መልስ ይዘት በአጭሩ፡- መንግስት ሁከት የተፈጠረበትን ቦታ
ለተጠሪ በሊዝ ሸጦለት ከቦታው ላይ ለተነሱ ሰዎች ካሳ አስከፍሎት ካርታ ተሰጥቶት ቦታውን በሰነድ ተረክቦ
ጥበቃ ቀጥሮ እያስተዳደረው ይገኛል፤ ተጠሪ ቦታውን ተረክቦት በይዞታው ስር ካደረገ በኋላ ግንባታ
ለመጀመር አጥር ለማጠር ሲል አመልካች እና የስር 2ኛ ተከሳሽ ሰዎችን አስተባብረው ሁከት ፈጥረዋል፤
ስለሆነም ይህንኑ መሠረት በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ስለሆነ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካች በሰጠው የመልስ መልስ አከራካሪው ይዞታ ለመስጊድ ማስፋፊያ እንዲውል ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ
ከተለያዩ የመንግስት አካላት ደብዳቤዎች ተጽፈውልናል፤ የሊዝ አዋጁ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለወደፊት
አገልግሎት ከሚሰጥ በቀር አመልካች በ1968 ዓ.ም በሕጋው መንገድ ለኑር መስጊድ ማስፋፊ በተሰጠው ቦታ
ላይ ተፈጻሚነት የለውም፤ ተጠሪ ቦታው በእጁ እንዳለ በማስመሰል ያቀረበው ክስ በማስረጃ የተደገፈ
አይደለም፤ ቦታው ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በኑር መስጊድ አስተዳዳሪ እጅ የሚገኝ ነው በማለት
የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል፡፡

የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ
ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር
አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምሮታል፡፡

በመሠረቱ የአንድ ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው ይዞታውን ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለመፍጠር
የሚፈፀምን ማናቸውም ድርጊት እንዲቆም ወይም ተገቢው መብት እንዲመለስለት ሕጉ ከዘረጋቸው
መንገድች አንዱ የይዞታ ክስ ስለመሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1149/1 ድንጋጌ የሚያስገነዝብ ሲሆን
በዚህ ድንጋጌ መሠረት የሁከት ይወገድልኝ ክስ ለማቅረብ የሚቻለው አቤቱታ አቅራቢው ለክርክሩ መነሻ
በሆነው ንብረት ላይ በቀጥታ ወይም በጠባቂ ይዞታ ሲኖረውና ይህንኑ በሀይል ሲነጠቅ ወይም በይዞታዉ ስር
ባለ ንብረት ላይ የመጠቀም መብቱን የሚያዉክ ተግባር ሲፈጸም ሲሆን ማረጋገጥ ያለበትም ንብረቱ በሕግ
አግባብ በይዞታው ሥር የነበረና የሁከት ድርጊት ፈፃሚው የሀይል ተግባር በመጠቀም ወይም በሚስጥር
ንብረቱን የወሰደበት መሆኑን ነው፡፡

በያዝነው ጉዳይ የአሁን ተጠሪ አከራካሪ የሆነው ይዞታ ከከተማው አስተዳደር ጋር በተፈጸመ የሊዝ ውል
ማሻሻያ መሠረት የተረከበው እና ግንባታ ለማከናወን ሲል አመልካች እና የስር 2ኛ ተከሳሽ ሁከት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የፈጠሩበት መሆኑን በመግለጽ የሚከራከር መሆኑን፤ የአሁን አመልካች እና የስር 2ኛው ተከሳሽ ደግሞ
ይዞታው ለመስጊድ ማስፋፊያነት እንዲሰጣቸው ጠይቀው በጊዜው ከነበረው ሥራ እና ከተማ ልማት
ሚኒስቴት በ1968 ዓ.ም ቦታው ቢሰጣቸው ተቃውሞ እንደሌለ ተገልጾ ደብዳቤ የተጻፈላቸው መሆኑን፤ ጉዳዩ
ከሚመለከታቸው የአስተዳደር አካላት ግምቱን እንዲከፍሉ ደብዳቤ የተጻፈላቸው እና ግምቱን የከፈሉ
መሆኑን በመግለጽ ቦታውን እንዲረከቡ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ መሆኑን እና ቦታውም
በቁጥጥራቸው ስር የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ የሚከራከሩ ስለመሆኑ ከግራቀኙ ክርክር እና ከስር ፍርድ
ቤት ውሳኔ ይዘት ሒደት መገንዘብ ችለናል፡፡ ይህም በሕጉ በተመለከተው ሁኔታ አመልካች እና የስር 2ኛ
ተከሳሽ የተጠሪን ይዞታ በሀይል በመንጠቅ ተጠሪ በይዞታው ላይ የመጠቀም መብቱን የሚያዉክ ተግባር
መፈጸማቸውን የሚያሳይ ሳይሆን ቦታው በይዞታቸው ስር ቆይቶ ለመስጊድ ማስፋፊያ እንዲሆን
እንዲሰጣቸው ጠይቀው ቦታው እንዲሰጣቸው የተጀመረ ሒደት መኖሩን የሚያሳይ ነው፡፡ ስለሆነም፡-

1. አመልካች እና የስር 2ኛ ተከሳሽ ቦታው በይዞታቸው ስር ቆይቶ ለመስጊድ


ማስፋፊያ እንዲሆን እንዲሰጣቸው ጠይቀው ቦታው እንዲሰጣቸው የተጀመረ ሒደት እና የተጻፉ
የተለያዩ የድጋፍ ደብዳቤዎች እያሉ በምን አግባብ ይዞታው ለተጠሪ ሊሰጥ እንደቻለ ?
2. አከራካሪ የሆነው ይዞታ በተጨባጭ በማን ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ?
3. አመልካች እና የስር 2ኛ ተከሳሽ ለቦታው የከፈሉት ካሣ ካለ ሕጋዊ ውጤቱ ምን
እንደሆነ ? የሚሉ እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ነጥቦች ምላሽ ሊሰጣቸው የሚገባ የክርክሩ
መሠረታዊ ጭብጦች ናቸው፡፡

በመሆኑም በጉዳዩ ላይ ተገቢው ጭብጥ ሳይያዝ እና በአግባቡ ሳይጣራ የተሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሔር
ሥነ ሥርዓት ሕጉ ስለጭብጥ አመሰራረት የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ያልተከተለ እና መሠረታዊ የሆነ
የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከላይ
የተዘረዘሩትን መሠረታዊ ጭብጦች በመያዝ ለጉዳዩ አወሳሰን ይረዳኛል የሚለውን አግባብነት ያለውን
ትዕዛዝ በመስጠት እና ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ተጣርቶ እንዲቀርብለት በማድረግ በመዝገቡ
አስቀድሞ ከተሰሙት ማስረጃዎች ጋር በማገናዘብ እንዲሁም ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስፈላጊ መስሎ
የታየውን ምስክር በመስማት ወይም ማስረጃ በማስቀረብ ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር
በማገናዘብ መርምሮ እና መዝኖ ተገቢውን እንዲወስን ማድረግ ሥነ-ሥርዓታዊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 113862 ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 270023 ሠኔ
10 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ተሽሯል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው ምክንያት ጉዳዩን
አጣርቶ ተገቢውን እንዲወስን በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1 መሠረት ጉዳዩ ተመልሶለታል፡፡
3. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
4. ሠኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡


ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 209987

ቀን፡-30/03/2014ዓ.ም

ዳኞች ፡-ብርሃኑ አመነዉ

ተሾመ ሽፈራዉ

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግሥቱ

ነጻነት ተገኝ

አመልካች ፡- ፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን-ነ/ፈጂ ተስፋዬ በቀለ ቀረቡ

ተጠሪ ፡- ወ/ሮ ፍሬህይወት ተረፈ-ቀረቡ

መዝገቡ ተመርምሮ ከዚህ የሚከተለዉ የፍርድ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
ጉዳዩ ተጠሪ በአመልካች ኮሚሽን አለአግባብ ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ ተደርጌያለሁ በማለት ለፌዴራል ሲቪል
ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት
የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ተጠሪ በአመልካች ላይ በአስተዳደር
ፍርድ ቤት ዘንድ ባቀረቡት ይግባኝ ከንብረት አወጋገድ፣ከሂሳብ አዘጋግ፣ በኦዲት ግኝት ለይ የተሰጠዉን
ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ ከማድረግ እና ሥራዎቼን በወቅቱ ከመፈጸም አንጻር የፈጸምኩት ጥፋት ሳይኖር
አለአግባብ ከነበርኩበት ሥራ መደብ አንድ ደረጃ ዝቅ አድርጎ መድቦኛል፡፡ በመሆኑም አመልካች የሰጠኝ
የዲሲፕሊን ውሳኔ አግባብ አይደለም ተብሎ ወደ ቀድሞ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክተር ደረጃ -15 ስራ መደብ ላይ እንዲመልሰኝ እንዲሁም በእግድ ምክንያት ያልተከፈለኝን የሐምሌ እና
የነሐሴ ወር 2012 ዓ/ም ደመወዝ ብር 20,300.00 አመልካች እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት
ጠይቀዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካች በሰጠው መልስ ተጠሪ በኃላፊነት በኮሚሽኑ የተሰጣቸውን ሥራ በተገቢው አልሰሩም፡፡ አገልግሎት
የማይሰጡ ንብረቶችን በተገቢው ጊዜ እንዲያስወግዱ የተጣለባቸዉን ኃላፊነታቸውን በአግባብ
አልተወጡም፡፡የኮሚሽኑ የ2012 በጀት ዓመት ሂሳብ እንዲዘጋ በተሰጠው መመሪያ መሰረት በተሰጠው ጊዜ
አልተጠናቀቀም፡፡ እንዲሁም የ2013 ዓመታዊ የግዥ ጨረታ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ/ም ድረስ
ተጠናቆ ከሐምሌ 01 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷቸዉ የነበረ ቢሆንም
ተግባራዊ አላደረጉም፡፡ ይህንን በማስረጃ በማረጋገጥ በፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ከ2008ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በጸደቀዉና በተሻሻለዉ የኮሚሽኑ ሠራተኞችና
የሥራ መሪዎች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 1/2008 አንቀፅ 75(2/5 እና 31) መሰረት ተጠሪ በሥራ መሪነት
እንዲቀጥሉ የሚያስችል እምነት አመልካች በተጠሪ ላይ ስለሌለዉ ወደ ሥራ መደቤ ልመለስ ይገባል በማለት
ተጠሪ ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት ሊሰጠዉ አይገባም በማለት ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ በይ/መ/ቁ 110/13 ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮና ማስረጃዎችን መርምሮ በቀን 12/04/2013 ዓ/ም
በሰጠው ውሳኔ የዲሲፕሊን ቅጣት ዓላማ የመንግስት ሠራተኛው በፈፀመው የዲሲፕሊን ጉድለት ተፀፅቶ
በአመለካከቱና በሥነ ምግባሩ እንዲታረምና ብቁ ሠራተኛ እንዲሆን ለማስቻል ወይም የማይታረም ሆኖ ሲገኝ
ለማሰናበት ነዉ፡፡ ተጠሪ በአመልካች ተቋም ውስጥ በቆዩባቸው ጊዜያት የፈፀሙት የዲሲፕሊን ግድፈት
እንደሌለ የዲሲፕሊን ኮሚቴው የተረጋገጠ በመሆኑ ይህንን እንደማቅለያ ምክንያት በመቀበል የስር
የዲሲፕሊን ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ በፌዴራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀፅ 81/3
መሰረት በማሻሻል ተጠሪ በአዋጁ አንቀጽ 69(1/መ) መሰረት በአንድ ወር ደመወዝ ተቀጥተዉ የሐምሌ እና
የነሐሴ ወራት 2012 ዓ/ም ደመወዝ ክፍሏቸዉ ወደ ቀድሞ የሥራ መደብ እንዲመልሳቸዉ ወስኗል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
ቢያቀርብም ችሎቱ በመ/ቁጥር 202851 ላይ በቀን 11/10/2013 ዓ/ም በሰጠዉ ትእዛዝ በጉዳዩ ላይ አመልካች
የሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ ሆኖ እያለ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በይግባኝ ተቀብሎ ለማየት ስልጣን
ሳይኖረው ተመልክቶ መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ከሆነ ይሄንኑ ቅሬታውን በቀጥታ ለሰበር ሰሚ ችሎት
አቅርቦ በዚህ አግባብ ስህተቱ እንዲታረም ሊያደርግ ከሚችል በቀር ይህ መደበኛ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት
ጉዳዩን በይግባኝ ተቀብሎ ለማየት ሥልጣን የለውም በሚል ምክንያት የይግባኙን ተጠሪን ሳይጠራ
ሠርዞበታል፡፡

አመልካች በቀን 21/10/2013 ዓ/ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረበዉ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን
ለመዳኘት ሥልጣን ሳይኖረዉ የሰጠዉ ዉሳኔ ነዉ፡፡ አመልካች ኮሚሽን ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው
በፌዴረላ መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 መሰረት ሳይሆን የኮሚሽኑን ማቋቋሚያ አዋጅ
ቁጥር 433/1997 አንቀጽ 15ን ተከትሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 1/2008 መሰረት ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር
1064/2010 አንቀጽ 2(1/ሠ) መሰረት አዋጁ በኮሚሽኑ ሠራተኞች ላይ ተፈጻሚነት የለዉም፡፡በዚህ ደንብ
በአንቀጽ 82/3 በማናቸውም ስራ ክርክር የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው ኮሚሽነሩ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ስለዚህ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 1064/2010 መሰረት ጉዳዩን ተመልክቶ ያለሥልጣኑ
የሰጠዉን ዉሳኔ ይግባኝ ሰሚዉ ችሎት እንዲያርም ያቀረብነዉን ይግባኝ በሰበር ሰሚ ችሎት የሚታይ ነዉ
በሚል ስለሰረዘብን ችሎቱ ተመልክቶ የአስተዳደር ፍርድ ቤት የሠጠዉን ዉሳኔ እንዲሽርልን በማለት
አቤቱታዉን አቅርቧል፡፡

የሰበር አጣሪ ችሎት አቤቱታውን መርምሮ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት ጉዳዩን
የማየት ስልጣን ያለዉ መሆን አለመሆኑ ተጠሪ ባሉበት እንዲመረመር ትእዛዝ በመስጠቱ ተጠሪ በቀን
03/02/2014 ዓ/ም የተፃፈ መልስ በማቅረብ የሥር የአስተዳደር ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመዳኘት የሚያስችል
ሥልጣን በሕግ ስለተሰጠዉ የአመልካች አቤቱታ ዉድቅ ሊሆን ይገባል የሚልና ሥረ ነገሩን የሚመለከት
መልስ በመስጠት ተከራክረዋል፡፡አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል፡፡

ከዚህ በላይ አጠር ባለመልኩ የተመለከተዉ የግራ ቀኙ ክርክርና በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡ ዉሳኔዎች
ይዘት የሚመለከት ሲሆን እኛም የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘዉን ማስቀረቢያ ጭብጥ መሰረት በማድረግ
የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖር አለመኖሩን አግባብነት ካለዉ ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለዉ
መርምረናል፡፡

እንደመረመርነዉም አከራካሪ የሆነው የአመልካች ኮሚሽነር በዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ የሚሰጠውን ውሳኔ


የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት በይግባኝ ሊታይ ይችላል ነዉ ወይስ አይችልም?
የሚለው ነው፡፡ በአመልካች ኮሚሽነር የተሰጠዉ ዉሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ በተጠሪ ላይ በተሰጠው ውሳኔ
ላይ ይግባኝ ለአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ሊቀርብ አይችልም በማለት አመልካች የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን
የማየት ስልጣን እንደሌለው ገልጾ የተከራከረ ስለመሆኑ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ግልባጭ አያሳይም፡፡
ሆኖም የዐስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በይግባኝ ተቀብሎ ለመዳኘት የፌዴራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ
ቁጥር1064/2010 መሰረት ሥልጣን እንዳለዉ በመቁጠር በዋናው ጉዳይ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ውሳኔ
እንደሰጠ ከዉሳኔዉ መገንዘብ ችለናል፡፡ አመልካች ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
ይግባኝ ያቀረበው የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመዳኘት ስልጣን የለውም በሚል ነው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም የስር አስተዳደር ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመዳኘት ስልጣን የለውም ከተባለ
እኔም ስልጣን የለኝም በማለት የአመልካችን ይግባኝ ሠርዞበታል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 81 ላይ እንደተደነገገዉ በአስተዳደር ፍርድ
ቤት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ የሕግ ስህተት ካለ መርምሮ ስህተቱን ማረም እንዲችል ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡
ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ስልጣን ባለው ጉዳይ ላይም ይሁን ስልጣን
በሌለው ጉዳይ ላይ የሚሰጠውን ውሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ የመመልከት ስልጣን
እንደተሰጠው ነው፡፡ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ የመዳኘት ስልጣን የተሰጠውን ጉዳይ ብቻ መርምሮ መወሰን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዳለበት ከፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 መገንዘብ ይቻላል፡፡ ነገር ግን
የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ በአዋጁ ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ወይም በሌላ ሕግ ለሌላ የዳኝነት ነክ አካል
የተሰጠን ጉዳይ ተቀብሎ የሚወስን ከሆነ አስተዳደር ፍርድ ቤቱ ከስልጣኑ ውጪ የሰጠውን ውሳኔ ማረም
የሚችለው የአስተዳደር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በይግባኝ አይቶ ስህተቱን ለማረም ስልጣን የተሰጠው የፌደራል
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
የአስተዳደር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሲመረምር አስቀድሞ ሊመረምር የሚገባው ጉዳይም ቅሬታ ባይቀርብበት
እንኳን አስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለውን ሊሆን ይገባል፡፡
ምክንያቱም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ቅሬታ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት በሌለው ስልጣን የሰጠው ውሳኔ
ከሆነ የስር ፍርድ ቤቱ ስልጣን እንደሌለው የሚደነግገውን ሕግ እና የፍ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 9 እና 231/1/ለን
በመጣስ የሚሰጥ ዉሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ውሳኔ ስለሚሆን ነዉ፡፡ ስለሆነም የፌደራል ጠቅላይ
ፍርድ ቤት የስር አስተዳደር ፍርድ ቤት በሚሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት ካለ በይግባኝ የማረም ስልጣን
እስከተሰጠው ድረስ የአመልካችን የይግባኝ ቅሬታ ተቀብሎ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመዳኘት
የሚያስችል ስልጣን አለው ወይስ የለውም የሚለውን መመርመር ነበረበት፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በይግባኝ ለማየት ስልጣን የለኝም ያለበት
ምክንያት አመልካች የኮሚሽኑ ውሳኔ የመጨረሻ ነው በሚል ያቀረበውን ክርክር መሰረት በማድረግ ነው፡፡
በእርግጥ የኮሚሽኑ ውሳኔ የመጨረሻ ነው አይደለም? የመጨረሻ ነው ተብሎ ተደንግጎ ከሆነም ይህ ማለት
የይግባኝ ሊቀርብበት አይችልም ለማለት የተደነገገ ነዉ ወይስ አይደለም? የሚለው አግባብነት ካለው ሕግ
ጋር ተገናዝቦ መመርመር የሚገባዉ የሕግ ጭብጥ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ላይ
የአስተዳደር ፍርድ ቤት ከስልጣኑ ውጪ በይግባኝ አይቶ ከሆነ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ በሌለው ስልጣን
ውሳኔ መስጠቱ የሕግ ስህተት ስለሚሆን ይህ ስህተት መታረም ያለበት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው፡፡ እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ
80(3/ሀ) ላይ የተሰጠው ስልጣን መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጸመበትን የመጨረሻ ውሳኔ ማረም ነው፡፡
የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመዳኘት ስልጣን አለው ወይም የለውም የሚለው በይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ
ፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እስካልሰጠበት ድረስ የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ
ስለማይሆን አመልካች በአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ በቀጥታ የሰበር አቤቱታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡

ሲጠቃለል የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት በሚሰጠው ማናቸውም
ውሳኔ ላይ የሕግ ስህተት ካለ በይግባኝ የማረም ስልጣን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
ሆኖ እያለ የስር አስተዳደር ፍርድ ቤት በአመልካች ኮሚሽነር የተሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ የማየት ሥልጣን
የለዉም በሚል የቀረበለትን ይግባኝ ይግባኝ ሰሚዉ ችሎት በይግባኝ የማየት ሥልጣን የለኝም ማለቱ በአዋጅ
ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 81 ስር የተደነገገዉን የሚቃረን በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነዉ
ብለናል፡፡በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ው ሳ ኔ

1. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 202851 ላይ በቀን


11/10/2013ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 348/1 መሰረት ተሽሯል፡፡

2. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን በይግባኝ የመዳኘት ስልጣን አለው
ብለናል፡፡

3. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መዝገቡን አንቀሳቅሶ የስር አስተዳደር ፍርድ ቤት
በአመልካች ኮሚሽነር የተሰጠውን ውሳኔ በይግባኝ ለማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም? የሚለውን
መርምሮ ያስቀርባል የሚል ከሆነ ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ አድርጎ ተገቢውን እንዲወስን ጉዳዩ
በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 341/1 መሰረት ተመልሶለታል፡፡

4. ግራ ቀኝ በዚህ ችሎት ደረጃ ያወጡትን ወጭ የየራሳቸዉን እንዲችሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ
1. የዉሳኔዉ ግልባጭ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይተላለፍ፡፡ ለግራ ቀኙም
ግልባጩ ይሰጣቸዉ፡፡
2. በመዝገቡ ላይ የተሰጠ የዕግድ ትእዛዝ ካለ ተነስቷል፤ይጻፍ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡
ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

ሰመ/ቁ፡-210020

ቀን፡-08/03/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ወ/ሮ ትዕግስት ታደሰ- ቀረቡ

ተጠሪ፡- ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከባድ አካል ጉዳት ማድረስ የወንጀል ክስን የሚመለከት
ነው፡፡የሰበር አቤቱታ የቀረበው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአመልካች
ላይ የሰጠው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው ፌ/ከፍተኛ ፍርድ ቤት
መፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ስለሆነ ይህ ውሳኔ እንዲታረምልኝ በማለት አመልካች
ስላመለከቱ ነው፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የወንጀል ህግ አንቀፅ 555(ለ) ን በመጥቀስ ባቀረበው ክስ


በክሱ ላይ በተመለከተው ጊዜና ቦታ የግል ተበዳይ አስቴር ደገፉን በቦክስ ሰንዝራ ፊቷ ላይ በመምታት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የላይኛው የፊት ለፊት በቀኝ በኩል ያለው አንድ ጥርስ እና የፊት ለፊት በግራ በኩል ያለው ጥርሶቿ
በከፍተኛ ደረጃ እንዲነቃነቁ አድርጋለች በዚህም ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ፈፅማለች
በማለት ከሷል፡፡

ተከሳሽ ክሱ ተነቦላት እንድትረዳው ከተደረገ በኋላ መቃወሚያ የለኝም ድርጊቱን አልፈፀምኩም


ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ክዳ ስለተከራከረች የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው የተሰሙ ሲሆን 1ኛ
የዐቃቤ ህግ ምስክር በክሱ ላይ በተመለከተው ጊዜና ቦታ ከአመልካች በተፈጠረው አለመግባባት
ምክንያት አመልካች በቦክስ አፏን በመምታት አፏ እንዲደማና የላይኛው በቀኝ እና በግራ በኩል ያሉት
ሁለት ጥርሶቿ እንደተነቃነቁ ስላስረዳች 2ኛ እና 3ኛ ምስክሮች አመልካችና የግል ተበዳይ ተጣልተው
ያገላገሏቸው መሆኑን በወቅቱ የግል ተበዳይ አፍ ይደማ የነበረ መሆኑን ስላስረዱ ይህንን የምስክርነት
ቃል ከህክምና የምስክር ወረቀቱ ጋር በመመርመር አመልካች እንዲከላከሉ ብይን ቢሰጥም አመልካች
የመከላከያ ማስረጃ የሌላቸው መሆኑን ስለገለፁ በቀረበባቸው ክስ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቶ የግራ ቀኙን
የቅጣት አስተያየት ከግምት ውስጥ በማስገባት አመልካች በሁለት አመት ከስድስት ወር ቀላል እስራት
እንዲቀጡ ወስኗል፡፡

ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌ/ከ/ፍ/ቤት በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ያፀናው
ሲሆን ቅጣትን በተመለከተ በአመልካች የቀረቡት ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች አላግባብ በስር
ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጋቸውን በመጥቀስ እነዚህን የቅጣት ማቅለያ ምክንያች ከግምት ውስጥ
በማስገባት የስር ፍርድ ቤትን የቅጣት ውሳኔ በማሻሻል አመልካች በሁለት አመት ቀላል እስራት
እንድትቀጣ ወስኗል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ባቀረበቸው የሰበር አቤቱታም በወ/ህ/ቁ.555(ለ) አንድ ሰው


ጥፋተኛ ሊባል የሚችለው የሌላውን ሰው አካል ወይም አስፈላጊ ከሆኑ ብልቶች አንዱን
ያጎደለ፤እንዳያገለግሉት ያደረገ ወይም በሚያሰቅቅና ጉልህ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ መልኩን ያበላሸ ሲሆን
በግል ተበዳይ ላይ ደረሰ የተባለው ጉዳት የጥርስ መነቃነቅ በመሆኑ የአካል ጉዳት ተደርጎ የሚወሰድ
ባለመሆኑ ፤የግል ተበዳይም ችሎት ቀርባ የተነቃነቀው ጥርስ የዳነ መሆኑን የገለፀች በመሆኑ
የጥፋተኝነት ውሳኔ ሊሰጥ የሚገባው በወ/ህ/አ.556(1) ስር ሆኖ ቅጣቱም በዚሁ አግባብ ሊወስን ሲገባ
የስር ፍርድ ቤት በወ/ህ/አ.555(ለ) ስር የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መስጠቱ መሰረታዊ የህግ
ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ውሳኔ ይሻርልኝ፤የእስራ ቅጣቱ እንዲገደብላት ጠይቃ ፍርድ ቤቱ ውድቅ
ማድረጉ አላግባብ ስለሆነ ውሳኔው ይሻርልኝ በማለት አመልክታለች፡፡

በግል ተበዳይ ላይ የደረሰው ጉዳት የጥርስ መነቃነቅ መሆኑ በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ
በተመለከተበት በከባድ የአካል ጉዳት አመልካች ጥፋተኛ የተባሉበትን አግባብ ከወ/ህ/አ.23(2) እና
555(ለ) አንፃር ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ለተጠሪ መጥሪያ ደርሶት
መልሱን አቅርቧል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ በዚህ መልሱም በግል ተበዳይ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ደረጃ የጥርስ መነቃነቅ በመሆኑና
እነዚህ ጥርሶችም በሽቦ ታስረው ወደ ቦታው መመለስ ስለማይችሉ ተነቅለው በሰው ጥርስ መተካት
ያለባቸው ስለመሆኑ በህክምና ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አግባብነት ያለውን
ድንጋጌ በመጥቀስ የሰጠው ውሳኔ ሊፀና ይገባል፤ገደብን አስመልክቶም የስር ፍርድ ቤት በአመልካች
ላይ የተወሰነው የእስራት ቅጣት ቢገደብ አመልካች ወንጀል ከማድረግ የሚታገዱ አለመሆኑን
ስለፀባያቸው መሻሻልም አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ በቂ መሆኑን ባለማመኑ የተነሳ የገደብ ጥያቄውን
ውድቅ ያደረገው በህጉ አግባብ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

አመልካቾች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡አመልካች በስር
ፍርድ ቤቶች ከተሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ አንፃር የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡት ከመነሻውም የጥርስ
መነቃነቅ አካል ጉዳት አለመሆኑን፤የግል ተበዳይ ጥርስ የዳነ መሆኑን የግል ተበዳይ የገለፁ በመሆኑ
የደረሰ የአካል ጉዳት ባለመኖሩ በወ/ህ/አ.555(ለ) ስር ጥፋተኛ ልባል አይገባም በማለት ነው፡፡በመሰረቱ
የሌላን ሰው አካል ማጉደል ወይም እንደያገለግሉት ማድረግ ታስቦ በሚፈፀም ከባድ የአካል ጉዳት
ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ለማለት በቂ መሆኑን የወ/ህ/አ.555(ለ) በግልፅ ያመለክታል፡፡

አሁን በያዝነው ጉዳይ አመልካች በቦክስ በመምታት እንዲነቃነቁ ካደረጓቸው የግል ተባዳይ ጥርሶች
መሃል የቀኝ መንጋጋ የፊት ለፊት የቀኝ በኩል አንድ ጥርስ በከፍተኛ ሁኔታ መነቃነቁን በግራ በኩል
ያሉት ጥርሶች ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ የሚነቃነቁ መሆኑን፤ጥርሶቹ በሽቦ ታስረው ወደ ቦታቸው
ሊመለሱ ስለማይችሉም መነቀል ያለባቸው መሆኑን በስር ፍርድ ቤት የቀረበው የሕክምና ወረቀት
የሚያሳይ ሲሆን አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ የግል ተበዳይ ጥርሳቸው የዳነ መሆኑን
መግለፃቸውን በማመልከት የሰበር አቤቱታቸውን ያቀረቡ ቢሆንም የግል ተበዳይ በዚህ አግባብ
ማስመዝገባቸውን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡ከዚህ ይልቅ የህክምና የምስክር ወረቀቱ
በአመልካች ቦክስ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የግል ተበዳይ የሰውነት አካል የሆኑት ጥርሶች መነቀል
ያለባቸው መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ በወ/ህ/አ.555(ለ) ስር ታስቦ
በሚፈፀም ከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ማለቱ የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡

ገደብን አስመልክቶ አመልካች በስር ፍርድ ቤት የካቲት 24 ቀን 2013 ዓም በተፃፈ ባቀረቡት የቅጣት
ማቅለያ አስተያየት የገደብ ጥያቄ ያላቀረቡ በመሆኑ በዚህ አግባብም የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ገደብን
አስመልክቶ የሰጠው ብይን የሌለ ሲሆን አመልካች የይግባኝ አቤቱታቸውን ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ሲያቀርቡ
የገደብ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ቅጣቱን ለመገደብ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ተሟልተው
አለመገኘታቸውን፤ቅጣቱን ለመገደብ የሚያስችል በቂ ምክንያት አለመቅረቡን በመጥቀስ ፍርድ ቤት
የገደብ ጥያቀውን ውድቅ ማድረጉን የስር ፍርድ ቤት መዝገብ ያሳያል፡፡በመሰረቱ ጥፋተኛው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተፈረደበትን ቅጣት ከመፈፀሙ በፊት ለተወሰነ ጊዜ ቅጣቱ ታግዶለት አመሉ ቢፈተን ሁለተኛ ጥፋት
ከማድረግ የሚታገድ መሆኑንና ስለጠባዩም መሻሻል አንድ ፅኑ ማስጠንቀቂያ ብቻ የሚበቃ መሆኑ
ፍርድ ቤቱ ያመነበት እንደሆነ ቅጣቱን ከወሰነ በኋላ የተወሰነ የፈተና ጊዜ በመስጠት የቅጣቱ አፈፃፀም
ታግዶ እንዲቆይ ለማዘዝ የሚችል መሆኑን የወ/ህ/አ.192 ይደነግጋል፡፡

አሁን በያዝነው ጉዳይ አመልካች በግል ተበዳይ ላይ ለወንጀል ክሱና የጥፋተኝነት ውሳኔ መሰረት
የሆነውን ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሱት በቂም በቀል ሳይሆን በዕለታዊ ግጭት መሆኑን መሆኑን የግል
ተበዳይ በስር ፍርድ ቤት ከሰጡት የምስክርነት ቃል እና ግራ ቀኙ ጥር 26 ቀን 2012 ዓም ካደረጉት
የእርቅ ስምምነት ለመረዳት የሚቻል ሲሆን፤አመልካች በግል ተበዳይ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ካደረሱ
በኋላ ከግል ተበዳይ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት በእርቅ መፍታታቸው በድርጊታቸው
መፀፀታቸውንና ከዚህ በኋላም በተመሳሳይ ድርጊት ከመሰማራት የሚታቀቡ ለመሆኑ ያሳዩትን ጥረት
የሚያሳይ በመሆኑ እንዲሁም የአራዳ ክ/ከ/ወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ጥር 09 ቀን 20123 ዓም
በሰጠው መግለጫ አመልካች አባት የሌላቸውን ልጆች ብቻቸውን የሚያሳድጉ መሆኑን መግለፁ
አመልካች ያለባቸውን ተደራራቢ ሀላፊነት የሚያሳይ ሆኖ እያለ እነዚህ ዝርዝር ሁኔታዎች የእስራት
ቅጣቱ ከሚፈፀም ይልቅ ቢገደብ መልካም ውጤት የሚያመጣ መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ እያለ ይግባኝ
ሰሚ ፍርድ ቤቱ የአመልካችን የገደብ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት
ሆኖ ስላገኘነው የስር ፍርድ ቤቱ ይህንን በተመለከተ የሰጠውን የውሳኔ ክፍል ብቻ በመሻር በአመልካች
ላይ የተጣለው የእስራት ቅጣት በሁለት አመት የፈተና ጊዜ ሊገደብ ይገባል ብለናል፡፡ስለሆነም
የሚከተለው ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ይግባኝ ችሎት በመ/ቁ.006623 በ12/09/2013


ዓ.ም በዋለው ችሎት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.191068 የካቲት 25 ቀን
2013 ዓም በዋለው ችሎት በአመልካች ላይ የሠጠውን የጥፋተኝነት ውሳኔ በማፅናት የቅጣት
ውሳኔውን በማሻሻል የሰጠው የውሳኔ ክፍል በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.195(2)(ለ)(2) መሰረት
ፀንቷል፡፡ገደብን አስመልክቶ የሠጠው የውሳኔ ክፍል ተሸሯል፡፡

ትዕዛዝ

1.አመልካች ለገደብ ስርዓቱ አፈፃፀም በፈተናው ጊዜ ውስጥ በወንጀል ድርጊት ላለመሰማራት


ግዴታ ገብተው እንዲፈርሙና ዋስትና ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር) እንዲያሲዙ ታዟል፡፡

2.አመልካች የእስራት ቅጣቱ ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለገደብ ዋስትና
አፈፃፀም ተመጣጣኝ ስለሆነ በዚሁ አግባብ ተቀይሮ በዋስትናነት እንዲቆይ ታዟል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

3.የስር ፍርድ ቤት መዝገብ በመጣበት አኳኃን ይመለስ፡፡

ጉዳዩ እልባት ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡210525

ቀን፡-30/03/2014ዓ/ም

ዳኞች፡-ሰለሞን አረዳ

እትመት አሰፋ

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ዶ/ር ሙሉጌታ በካሎ

ተጠሪዎች፡-1ኛ. አቶ አማኑኤል ዮካሞ

2ኛ. ወ/ሮ ወሰን ጋዲዮ

3ኛ. ወ/ሮ መሰለች ዳንባራ

4ኛ.አቶ አየለ ጋዲዮ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሀምሌ 05 ቀን 2013 ዓ.ም
በተፃፈ አቤቱታ የግራ ቀኙን የአፈጻጸም ክርክር አስመልክቶ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ
መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፀው በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረቡት
ማመልከቻ መነሻነት ሲሆን አመልካች በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአፈፃፀም ከሳሽ የነበሩ ሲሆን
1ኛ ተጠሪ የአፈፃፀም ተከሳሽ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በመቃወም አመልካቾች ነበሩ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የጉዳዩ አመጣጥ እንዲህ ነው፡-አመልካችና 1ኛ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት እያደረጉ ያሉትን የአፈፃፀም
ክርክር አስመልክቶ አመልካች ለፍርዱ ማስፈፀሚያ እንዲሆን የ1ኛ ተጠሪ ንብረት እንደሆነ በመግለፅ
ያቀረቡትን በአለታ ጩኮ ወረዳ 01 ቀበሌ የሚገኘውን በ1ኛ ተጠሪ ስም የሚታወቀውን ቤት ማዘጋጃ
ቤቱ የቤቱን ግምት አውጥቶ እንዲልክ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ ግምቱን ልኮ ግራ ቀኙ
አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በዚህ እለትም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.418 አቤቱታ 3ኛ ተጠሪ የሟች ጋዲሶ
ቃቂዮ ሚስት 4ኛ ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ገልፀው አከራካሪውን ቤት
ግንቦት 07 ቀን 1985 ዓም በተደረገ ውል ከአቶ አማሎ ሄክሶ እና ወ/ሮ አስቴር አረፋይኔ ገዝተው ቤቱን
እየኖሩ እንዲጠብቁ ለ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ሰጥተዋቸው እያለ በድብቅ ስም ለማዞር ሙከራ እያደረጉ
መሆኑንና በስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለአፈጻጸም ሂደቱ መገመቱን እንደሰሙ ማዘጋጃ ቤቱን ጨምሮ
በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ላይ ክስ አቅርበው በክርክር ላይ መሆናቸውን ገልፀው በቤቱ ላይ የወጣው
የሃራጅ ሽያጭ ሂደት እንዲታገድ ብፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.418(4) እንዲሁም በቤቱ ላይ የተሰጠው የመያዢያ
ትዕዛዝ እንዲነሳ ጠይቀዋል፡፡

አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ለዚህ አቤቱታ ምላሻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ክርክሩ በሂደት ላይ እያለ በቤቱ
ላይ የነበረው የይገባኛል ክርክር ውሳኔ ማግኘቱን ገልፀው 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ስላመለከቱ ውሳኔው
ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ በማድረግ ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ውሳኔ ከግራ ቀኙ ክርክር ጋር
በመመርመር በሰጠው ብይንም 3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎችን ጨምሮ በሶስት
ተከሳሾች ላይ በአለታ ጩኮ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 00942 ያቀረቡት
ክስ ተመርምሮ ህዳር 04 ቀን 2013 ዓም በተሰጠው ውሳኔ አከራካሪው ቤት የ1ኛ ተጠሪ ሳይሆን የ3ኛ
እና 4ኛ ተጠሪዎች መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑን ይህ ውሳኔ ተጠሪዎች በመመሳጠር ያሰጡት ነው በማለት
አመልካች የተከራከሩ ቢሆንም ውሳኔውን በይግባኝ ያላሻሩት ፀንቶ ያለ ውሳኔ መሆኑን በመጥቀስ በቤቱ
ላይ ተላልፎ የነበረው እግድ እንዲነሳ ብይን ሰጥቷል፡፡

አመልካች በዚህ ብይን ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለሲዳማ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው


የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አከራክሮ በሰጠው ውሳኔም የስር ፍርድ ቤትን ብይን ያፀና
ሲሆን የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም አመልካች የውጪ ሀገር ዜጋ
በመሆናቸው አከራካሪውን የአፈፃፀም ክርክር ከፍተኛ ፍርድ ቤቱና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ያዩት ባላቸው
የውክልና ስልጣን መሆኑን በመጥቀስ በፌደራል ጉዳይ ላይ ጉዳዩን በሰበር የማየት ስልጣን የለኝም
በማለት ሰርዞታል፡፡

አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም በዋናው ክርክር ወቅት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በስማቸው


ተመዝግቦ የሚገኘውን ቤት ለማሸሽ እና ስም ለማዛወር ሲንቀሳቀሱ አመልክቼ የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ
ፍርድ ቤት ቤቱ በ1ኛ ተጠሪ ስም የተመዘገበና የሚገበርበት መሆኑን አረጋግጦ አግዶ ካቆየ በኋላ
ተጠሪዎች ያላቸውን ዝምድና በመጠቀም ንብረት ለማሸሽ ሀሰተኛ የመንደር ውል በማቅረብ ያቀረቡትን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ክስ ተቀብሎ የተሰጠውን ኢ-ፍትሀዊ ውሳኔ በመቀበል ቤቱ የ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ለመሆኑ አንዳችም


ማስረጃ ሳይቀርብለት ፤የግዢ ውል ነው የተባለው የመንደር ውል በፍ/ብ/ህ/ቁ.1723 ያልፀደቀ ሆኖ እያለ
የመንደር ውልን በመቀበል የተሰጡትን ውሳኔዎች በመቀበል የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት
መደምደሚያ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተሽሮ ቤቱ ተሽጦ ለፍርድ ማስፈፀሚያ
እንዲውል ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡

ፍርድ ባረፈበት ቤት ላይ የስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎችን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.418 አስገብቶ ለተጠሪዎች


የወሰነበትን አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ተጠሪዎች በህጉ አግባብ
ተጠርተው ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች በሰጡት መልስም 2ኛ ተጠሪ በዋናው ክርክርም ሆነ በአፈፃፀም ክርክሩ


ሳልካተት በሰበር ክርክሩ በ2ኛ ተጠሪነት ተካትቼ መቅረቤ አግባብ ባለመሆኑ ከሰበር ክርክሩ ውጪ
እንድሆን ይወሰንልኝ፤አከራካሪው ቤት ቤተሰቦቻችን በአደራ እንድንጠብቅላቸው የሰጡን የቤተሰቦቻችን
ቤት በመሆኑ፤በቤቱ ውስጥ በጠባቂነት መኖራችን ብቻ ባለቤት የሚያደርገን ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ
ስህተት ያልተፈፀመበት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በሰጡት መልስም የሰበር አቤቱታው የቀረበው በስር ፍርድ ቤት በመ/ቁ.76684


ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓም ከተሰጠ ከ6 ወር ከ20 ቀን በኋላ ሀምሌ 05 ቀን 2013 ዓም በመሆኑ በህጉ
የተመለከተው የ90 ቀናት የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ የቀረበው የሰበር አቤቱታ
ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ከሰበር አቤቱታው አቀራረብ ጋር በተያያዘ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን
በፍሬ ጉዳዩ ላይ በሰጡት መልስም አከራካሪው ቤት ላይ ፍርድ እንዳረፈበት ተደርጎ የማስቀረቢያ
ጭብጥ መያዙ አግባብ አይደለም፤3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች በመ/ቁ.00942 በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እና
በማዘጋጃ ቤቱ ላይ ባቀረብነው ክስ አከራካሪው ቤት ላይ በአሻጥር የሚያደርጉት ክርክር እንዲቆምና
ቤቱ በ3ኛ ተጠሪ ስም እንዲዞርና 4ኛ ተጠሪ የወራሽነት ድርሻቸውን እንዲያገኙ የተወሰነ በመሆኑ እና
ውሳኔው ጸንቶ ያለ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ይህንን ውሳኔ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሰጡት ውሳኔ
ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አከራካሪው ቤት ለ1ኛ ተጠሪ የፍርድ
እዳ ሊውል የሚችል የ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች ንብረት ነው? ወይስ የ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች ንብረት?
ውጤቱስ ምን ሊሆን ይገባል? የሚሉትን ጭብጦች በመመስረት የግራ ቀኙን የሰበር ክርክር ከተገቢው
ሕግና ከስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክር አንፃር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡በኢፌዲሪ
ህግ መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ) እና በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10(1)
እንደተመለከተው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው የዳኝነት ስልጣን በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ውስጥ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞ ሲገኝ በሰበር አይቶ የማረም ነው፡፡በዚህ አግባብም ይህ ሰበር ሰሚ
ችሎት የሰበር ሰሚነት ስልጣኑን ተግባራዊ ሲያደርግ ፍሬ ነገርን በተመለከተ በዋነኝነት መነሻ
የሚያደርገው ስልጣን ባላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ነው፡፡

አሁን በያዝነው ጉዳይ የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን በአከራካሪው ቤት ላይ አፈፃፀሙ
ይቀጥልልኝ ክርክር ውድቅ በማድረግ በአከራካሪው ቤት ላይ ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ እንዲነሳ
ብይን የሠጠውና ይህ ውሳኔ ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው የሲዳማ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ
ችሎት የፀናው ማስረጃን የመስማት የመመርመርና የመመዘን ስልጣናቸውን ተጠቅመው የቀረቡትን
ማስረጃዎች በመመርመርና በመመዘን በዋነኝነትም በአለታ ጩኮ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
በመ/ቁ.00942 ህዳር 04 ቀን 2013 ዓም በተሰጠው ውሳኔ በአለታ ጩኮ ከተማ ቀበሌ 01 ውስጥ
የሚገኘውን አከራካሪውን ቤት አቶ ጋዲዮ ቃቂሶ በውል ገዝተው ያገኙት ሆኖ እያለ በስር ፍርድ ቤት
የፍርድ ባለዕዳ የነበሩት 1ኛ ተጠሪና በመ/ቁ.00942 2ኛ ተከሳሽ የነበሩት 2ኛ ተጠሪ አላግባብ ስሙን
ማዛወራቸውን በማረጋገጥ አከራካሪውን ቤት ለ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች እንዲመልሱላቸው መወሰኑንና
ይህ ውሳኔ ፀንቶ የሚገኝ መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡ይህ በ3ኛ እና 4ኛ ተጠሪዎች አመልካችነት ክርክር
ተደርጎበት የተሰጠው ውሳኔ አመልካች አፈፃፀሙ ሊቀጥልበት ይገባል በማለት የሚጠቀሱት ቤት የ1ኛ
ተጠሪ አለመሆኑ በፍርድ የተረጋገጠ መሆኑን ያሳያል፡፡

ይህ የስር ፍርድ ቤቶች ማስረጃን የመስማት፤የመመርመርና የመመዘን ስልጣናቸውን ተጠቅመው


የደረሱበት ድምዳሜ በዚህ ችሎት ሊለወጥ የሚችለው የስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ምዘና ረገድ
የፈፀሙት ስህተት ከተገኘ ብቻ ሲሆን ይህ ችሎት ባደረገው ምርመራ በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመ
የማስረጃ ምዘና መርህ ጥሰት አልተገኘም ፤ በዚህ አግባብም በስር የሀዋሳ ከተማ ከ/ፍ/ቤት እና የሲዳማ
ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በሰጡት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት የማይቻል በመሆኑ
የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 26825 በቀን 20/05/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት
የሰጠው ብይንና እና ይህንን ብይን በማፅናት የሲዳማ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ. 76684
ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት
ፀንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ሀምሌ 06 ቀን 2013 ዓም የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ይፃፍ፡፡
3. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሄ/መ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ.መ.ቁ 210711
ሕዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ ተስፋዬ አዱኛ

ተጠሪዎች፡- 1. ወ/ሮ አየሉ ታደሰ

2. ታሪኩ ታደሰ

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች በቀን 23/10/ 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 80590 በቀን 16/03/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፤ ይህንኑ
ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 258188 ሚያዝያ 06 ቀን
2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት
አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የከተማን ይዞታ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡
በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን
ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ቁጥሩ 123(ሐ) የሆነው ቤት
ባለይዞታ መሆናቸውን፤ 2ኛው ተጠሪ ይህንኑ ቤት አስመልክቶ በመ.ቁ 71430 አቅርበውት የነበረው ክስ
ውድቅ ሆኖባቸው ሳለ በሌላ መዝገብ ባስወሰኑት ውሳኔ መነሻነት አፈጻጸም ከፍተው የሚመለከታቸውን
አካለት በማሳሳት ቤቱን በአፈጻጸም የተረከቡት መሆኑን በመግለጽ ክስ የቀረበበትን ቤት መልሰው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንዲያስረክቡአቸው እና ለ10 ወራት ቤቱን አከራይተው ያገኙትን ብር 17,500 / አስራ ሰባት ሺህ አምስት
መቶ / እንዲከፍሏቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን ነው፡፡

የአሁን ተጠሪዎች በሰጡት መልስ ክሱ በድጋሚ የቀረበ በመሆኑ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት የመጀመሪያ
ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲሆን በፍሬነገሩ ላይ በሰጡት መልስ ደግሞ አመልካች ከአውራሻችን አንድ ክፍል
ቤት ተከራይተው ኪራይ ሲከፍሉ ቆይተው አውራሻችን በሞት ሲለዩ በወቅቱ የመብራት ለመክፈል ከአቅም
በላይ ሆኖብን ሲቆረጥ በስማቸው መብራት አስገብተዋል፤ አከራካሪው ቤት የአባታችን የውርስ ሀብት ነው፤
አመልካች ቤቱ ይገባኛል ከማለት በቀር በምን አግባብ ቤቱን እንዳገኙት ለማሳየት ያቀረቡት ማስረጃ የለም፤
አመልካች በአፈጻጸም መዝገብ አቤቱታ አቅርበው ውደቅ ተደርጎባቸዋል፤ ተጠሪዎች ቤቱን የተረከብነው
አስፈጻሚ አካላትን አታለን ሳይሆን በውሳኔው መሠረት እንዲፈጸም በመ.ቁ 123407 በተሰጠ ትዕዛዝ
መሠረት ነው፤ የሚመለከተው የአስተዳደር አካል በሰጠው ምላሽ በግቢው ውስጥ የመንግስት ቤት እንደሌለ
እና በአጎራባች ቁጥር ውስጥ አመልካች የጠቀሱት የቤት ቁጥር እንደሌለ ተረጋግጧል፤ ተጠሪዎች
የአመልካችን ቤት አላከራየንም፤ ስለሆነም ክሱ ወድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍ/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በብይን ውድቅ አድርጓል፤ በፍሬነገሩ ላይ ደግሞ
ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ስለጉዳዩ ተጣርቶ እንዲቀርብለት ካደረገ እና የመ.ቁ 123407 የሆነው
መዝገብ በትዕዛዝ አስቀርቦ ከተመለከተ በኋላ የቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት በቀን
06/02/2011 ዓ.ም ለቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ አገልግሎት ፕሮጀክት
ጽ/ቤት በጻፈው ደብዳቤ በተጠሪዎች አባት ይዞታ ውስጥ የምናስተዳድረው የቀበሌ ቤት ውስጥ የለም በማለት
ገልጾአል፤ ተጠሪዎች በመ.ቁ 101280 በቀን 11/4/2009 ዓ.ም በተሰጠ ፍርድ በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 05
የቤት ቁጥር 123 የሆነው ቤት የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ስለሆነ እኩል እንዲካፈሉ በማለት ተወስኗል፤
አመልካች የመ.ቁ 123407 በሆነው የአፈጻጸም መዝገብ አቤቱታ አቅርበው አመልካች የቤቱ ባለቤት
መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ያላቀረቡ እና ፍርዱ ተፈጽሞ የተጠናቀቀ በመሆኑ በቤቱ ላይ መብት አለኝ
የሚሉ ከሆነ ክስ አቅርበው ከሚጠይቁ በቀር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ ተደርጎባቸዋል፤
በመ.ቁ 71430 ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ በማስረጃ አልተደገፈም ተብሎ ውድቅ ከመደረጉ በቀር ለአመልካች
መብት አልፈጠረም፤ ተጠቃሹ ቤት የመንግስት ቤት ካልሆነ አመልካች የግላቸው ስለመሆኑ ማስረዳት
ይጠበቅባቸዋል፤ አመልካች ቤቱ የግላቸው ስለመሆኑ ያላስረዱ በመሆኑ ቤቱ ይመለስልኝ በማለት ያቀረቡት
ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል፡፡ አመልካች ያቀረቡትን የይግባኝ አቤቱታ የተመለከተው
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሠረት የይግባኝ
አቤቱታውን ሰርዞታል፡፡

አመልካች ይህን ውሳኔ በመቃወም በቀን 23/10/2013 ዓ.ም የተጻፈ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን
ይዘቱም፡- 2ኛ ተጠሪ በመ.ቁ 71430 አስቀድመው አቅርበውት የነበረው ክስ ውድቅ ተደርጎባቸዋል፤
በመጀመሪያው ክስ በወረዳው ውስጥ ኗሪ መሆኔ እና ካርታ ለማውጣት በዝግጅት ላይ የነበርኩ መሆኔ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በተገለጸበት ሁኔታ ተጠሪዎች ለቤት ቁጥር 123 በከፈቱት የአፈጻጸም መዝገብ አሳስተው የተረከቡትን ቤት
ለመረከብ ያቀረብኩትን ክስ ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት
በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የሰበር አጣሪው ችሎት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ መርምሮ የአሁን 2ኛ ተጠሪ በመ.ቁ 71430 አመልካችን
ተከሳሽ በማድረግ በመሰረተው ክስ አስተዳደሩ አመልካች በራሱ ይዞታ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጾ 2ኛ ተጠሪ
ያቀረበው ክስ በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት ተወስኖ ሳለ 2ኛ ተጠሪ ይህን ውሳኔ ሳያሽር በአፈጻጸም
የቤቱ ባለመብት የሆነበት አግባብ ለመመርመር የሚል ማስቀረቢያ ጭብጥ በመያዝ ተጠሪዎች መልስ
እንዲሰጡበት ተደርጎ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ቀርቧል፡፡

ተጠሪዎች ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም የሰጡት መልስ ይዘት በአጭሩ፡- 2ኛ ተጠሪ ቤቱን የተረከብኩት
በመ.ቁ 84805 የ1ኛ ተጠሪ ወላጅ እናት የሆኑት የሟች ወ/ሮ አቻሜ ጨንገሬ የውርስ ሐብት ተጣርቶ
ክርክር የተነሳበት ቤት እና ይዞታ የ2ኛ ተጠሪ ወላጅ አባት እና ባለቤታቸው የነበሩት ወ/ሮ አቻሜ ጨንገሬ
መሆኑ ተረጋግጧል፤ በዚሁ መሠረት ክፍፍል እንዲደረግ በመ.ቁ 101280 ክስ ቀርቦ ተጠሪዎች ቤቱን
እንድንካፈል ተወስኗል፤ ይህን ተከትሎም የአፈጻጸም ትዕዛዝ ተሰጥቶ ቤቱ እኩል ታከፍሎ ተረክቤአለሁ፤
የቤት ቁጥር 123/ሐ በሚል የተደለደለ ቤት የለም፤ አመልካች ቤት ቁጥር 123/ሐ ማለት የጀመሩት ከጊዜ
በኋላ ነው፤ ስለሆነም በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡ አመልካችም የሰበር
አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል፡፡

የግራቀኙ ክርክር እና በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ
ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር
አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው
መርምሮታል፡፡

በመሠረቱ ከሣሽ የሆነው ተከራካሪ ወገን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 222 መሠረት አዘጋጅቶ ከሚያቀረበው የክስ
ማመልከቻ ጋር ለጉዳዩ ማስረጃ ይሆኑኛል የሚላቸውን የሠውም ሆነ የጽሁፍ ማስረጃዎችን ዝርዝርና
ዋናውን ወይም ትክክለኛ ግልባጮቻቸውን ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 223 እና 234
ድንጋጌዎች ስር የተደነገገ ሲሆን የግራ ቀኙ ክርክር በቃል ተሰምቶና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 246፣ 247፣ 248
እና 249 ድንጋጌዎች አግባብ ተገቢው ጭብጥ ተይዞ ለጉዳዩ በሕጉ አግባብ የቀረቡት የተከራካሪ ወገኖች
ማስረጃዎች ተሰምተውና አስፈላጊ ሲሆንም በሕጉ አግባብ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንዲቀርቡ
በማድረግ ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 138፣ 257፣ 258
እና 259፤ 181 እና 182 ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝቡናል፡፡

በያዝነው ጉዳይ አመልካች የአከራካሪው ቤት ባለይዞታ ነኝ፤ ተጠሪዎች መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው
ቤቱን ይዘውብኛል በማለት ከመከራከር በቀር በእርግጥም ይህን ክርክራቸውን የሚደግፍላቸውን ማስረጃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ያቀረቡ ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አያመለክትም፤ ይልቁንም ፍሬነገርን የማጣራት እና ማስረጃን
የመመዘን ስልጣን ባላቸው የስር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩ ከሚመለከተው የአስተዳደር አካል ተጣርቶ እንዲቀርብ
በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ከቀረበው ምላሽ እና በተለያዩ መዝገቦች ከተሰጠው ውሳኔ ይዘት የተረጋገጠው
ፍሬነገር አከራካሪ የሆነው ቤት በሚገኝበት ይዞታ ውስጥ ቀበሌው የሚያስተዳደረው ቤት የሌለ መሆኑን፤
ተጠሪዎች ቤቱን የተረከቡት የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ስለሆነ እኩል እንዲካፈሉ በማለት የተሰጠውን ውሳኔ
ለማስፈጸም በተከፈተ የአፈጻጸም መዝገብ በተሰጠው የአፈጻጸም ትዕዛዝ መሠረት መሆኑን፤ ተጠሪዎች
አስቀድሞ በመ.ቁ 71430 አቅርበውት የነበረው ክስ በማስረጃ አልተደገፈም ተብሎ ውድቅ ከመደረጉ በቀር
ለአመልካች የፈጠረው መብት የሌለ መሆኑን እና አመልካች የቤቱ ባለቤት መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ
ያላቀረቡ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ይህንኑ የተረጋገጠ ፍሬረገር መሠረት በማድረግ
አመልካች የቤቱ ባለቤት መሆናቸውን ስላላስረዱ ቤቱን ለመረከብ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት
የሰጡት ውሳኔ በሕግ አግባብ የተሰጠ ነው ከሚባል በቀር የተፈጸመ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት
አላገኘንበትም፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 80590 በቀን 16/03/2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፤
ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 258188
ሚያዝያ 06 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ጸንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
3. ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም በመዝገቡ የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
ማ/አ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ.210727

ቀን፡-28/03/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሃኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ - ዐቃቤ ሕግ ማዘንጊያ

ደምሴ ቀረቡ

ተጠሪ ፡- አቶ አዕምሮ ዘሪሁን

መዝገቡ ተምርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሠጠ፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ
እንደተረዳነው ተጠሪ በባሕር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የታክስ ኦዲትና የሕግ ማስከበር የሥራ ሂደት
አስተባባሪነት ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው ከደረጃ 9 ወደ ደረጀ 8 ዝቅ ብለው በሽያጭ መመዝገቢያ
ኤክስፐርት ሆነው እንዲሰሩ በመመደባቸው ቅሬታ አቅርበው ተቀባይት በማጣቱ ለአማራ ክልል ሲቪል
ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ጥፋት ሳይኖረብኝና የዲሲፕሊን ክስ ሳይቀርበብኝ
ከሥራ መደቡ መነሳቴ ሆነ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ መደረጌ አግባብ አይደለም የሚል ሲሆን አመልካች
ባቀረበው መልስ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 9(4) መሠረት ማንኛውም የሥራ ሂደት አስተባባሪ
በአሳማኝ ምክንያት ከኃላፊነት ሲነሳ ከያዘው መደብ ዝቅ ብሎ እንደሚመደብ ስለሚገልጽ በዚህ አግባብ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተከናወነ ነው ብሏል፡፡ አስተዳደር ፍርድ ቤቱ ግራቀኙን አከራክሮ ተጠሪ ከደረጃ 9 ወደ ደረጃ 8 ዝቅ ብለው
እንዲሰሩና ደመወዛቸው እንዲቀነስ የተደረገው ጥፋት ያለባቸው ስለመሆኑ ወይም የሥነ-ምግባር ጥሰት
መፈጸማቸው የዲሲፕሊን ክስ ቀርቦ ሳይረጋገጥ በጥርጣሬ ብቻ መሆኑ ፍትሕ የማግኘት መብታቸውን
የሚጥስ ነው በማለት የተጠሪ መሥሪያ ቤት ውሳኔን ሽሯል፡፡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝና
ሰበር ሰሚ ችሎቶች የአመልካችን የይግባኝና የሠበር አቤቱታ ባለመቀበል ሠርዘዋል፡፡

ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ነው፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ይዘትም ተጠሪ የዕውቀትና
ክህሎት ክፍተት ያለባቸው እና የሥነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ በመሆኑ ከሥራ መደባቸው መነሳታቸው
ተገቢ ነው፡፡ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 9(4) መሠረት የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ የሥራ ሂደት ባለቤቶችን
ያለዲሲፕሊን ክስ ሂደት ምደባ ማስተካከል ይችላል፡፡ ቅሬታ ቀርቦ አመልካች በሚሰጠው ውሳኔ ላይ
አስተዳደር ፍርድ ቤቱ የማየት ሥልጣን የለውም የሚል ነው፡፡ የሰበር አጣሪ ችሎት ጉዳዩን ተመልክቶ
አስተዳደር ፍርድ ቤቱ ፍሬ ነገሩን አከራክሮ የመወሰን ሥልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ለሰበር
ችሎት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተጠሪ የሠጡት መልስ አስተዳደር
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት በሕግ ሥልጣን ያለው አካል ነው፡፡ አመልካች ያለዲሲፕሊን ክስ ከሥራ መደብና
ከደረጃ የማንሳት ሥልጣን በሕግ አልተሰጠውም፤ ውሳኔው ተገቢ ስለሆነ ሊጸና ይገባል ብለዋል፡፡ አመልካች
የመልስ መልስ በማቀረብ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር ተከራክሯል፡፡

የክርክሩ ሂደት በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ግራቀኙን ክርክር፣ የሰበር አጣሪ ችሎት የያዘውን
ጭብጥ በሥር ፍርድ ቤት ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መዝገቡን መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው ተጠሪ በባሕር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የታክስ ኦዲትና የሕግ ማስከበር የሥራ ሂደት
አስተባባሪነት ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው ከደረጃ 9 ወደ ደረጀ 8 ዝቅ ብለው በሽያጭ መመዝገቢያ
ኤክስፐርት ሆነው እንዲሰሩ በመመደባቸው ጥፋት ሳይኖረብኝና የዲሲፕሊን ክስ ሳይቀርበብኝ ከሥራ መደቡ
መነሳቴ ሆነ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ መደረጌ አግባብ አይደለም የሚል ክርክር አቅርበው በየደረጃው የሚገኙ
ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ከደረጃ 9 ወደ ደረጃ 8 ዝቅ ብለው እንዲሰሩና ደመወዛቸው እንዲቀነስ የተደረገው ጥፋት
ያለባቸው ስለመሆኑ ወይም የሥነ-ምግባር ጥሰት መፈጸማቸው የዲሲፕሊን ክስ ቀርቦ ሳይረጋገጥ በጥርጣሬ
ብቻ መሆኑ ፍትሕ የማግኘት መብታቸውን የሚጥስ ነው በማለት የተጠሪ መሥሪያ ቤት ውሳኔን
በመሻራቸው የቀረበ የሠበር አቤቱታ ነው፡፡

የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም በሚል ጭብጥ በሰበር አጣሪ ችሎት
የተያዘ ሲሆን በአማራ ክልል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 253/2010 አንቀጽ 4 ላይ
እንደተመለከተው የሕጉ የተፈጻሚነት ወሰን በመንግስት መሥሪያ ቤትና በመንግስት ሠራተኞች ላይ ነው፡፡
የአስተዳደር ፍርድ ቤቱም ከሥራና ከሠራተኞች ጋር በሚሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ ጉዳዩን
የመመልከት ሥልጣን በአዋጁ ተሰጥቶታል፡፡ በመርሕ ደረጃ ማንኛውም የክልሉ የመንግስተ ሠራተኛ
የሚተዳደረው በዚሁ ሕግ መሠረት ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ሕግ አውጪው ሲፈቅድና በተለየ ሕግ ሲደነገግ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞቻቸውን በተለየ ሕግ ሊያስተዳድሩ ይችላሉ፡፡ የአማራ ክልል የገቢዎች
ባለስልጣን ተግባራትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 168/2002 አንቀጽ 14 እና 8(1) መሠረት
መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞቹን በአዋጁና አዋጁን ለማስፈጸም በሚወጣው ደንብ መሠረት እንደሚያስተዳድር
ተመልክቷል፡፡ ይህን ተከትሎም ደንብ ቁጥር 79/2003 የተደነገገ ሲሆን ሠራተኞቹን የሚተዳደሩበትን
ዝርዝር ድንጋጌዎች ይዟል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ መሥሪያ ቤት ሠራተኞችን የሚያስተዳድረው በተለየ ሕግ
ስለመሆኑ ተገንዝበናል፡፡ በደንቡ አንቀጽ 44(1) ላይ የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ተፈጻሚነቱ በደንቡ
ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ በደንብ ቁጥር 79/2003 ላይ የገቢዎች ባለስልጣን ሠራተኞች
የሥራ ክርክርን የሚመለከት የዳኝነት ሥልጣን ያለው አካል አልተመለከተም፡፡ ስለሆነም በደንቡ የሥራ
ክርክርን የሚመለከት አካል ማን እንደሆነ ያልተሸፈነ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 253/2010 መሠረት
የተቋቋመው የአስተዳደር ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለመዳኘት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ አስተዳደር ፍርድ ቤቱ በአዋጅ
ቁጥር 253/2010 አንቀጽ 80 ከተሰጠው ሥልጣን መካከል የደመወዝ መቀነስ አንዱ በመሆኑ ተጠሪ ከሥራ
ደረጃና መደብ ዝቅ ተደርገው የተቀነሰው ደመወዛቸው ላይ ይግባኝ ለአስተዳደር ፍርድ ቤቱ አቅርበው
መታየቱ ተገቢ በመሆኑ አስተዳደር ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመዳኘት ሥልጣን ያለው ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

በሌላ በኩል አመልካች በሰበር አቤቱታው ተጠሪ የዕውቀትና ክህሎት ክፍተት ያለባቸው እና የሥነ-ምግባር
ጥሰት የፈጸሙ በመሆኑ ከሥራ መደባቸው መነሳታቸው ተገቢ ነው፡፡ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 9(4)
መሠረት የመሥሪያ ቤቱ ኃላፊ የሥራ ሂደት ባለቤቶችን ያለዲሲፕሊን ክስ ሂደት ምደባ ማስተካከል ይችላል
በሚል ያቀረበው ክርክር በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2(4)(ሀ) እና (ሸ)
እንዲሁም አንቀጽ 10(1)(ሐ) እና (መ) መሠረት የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሕገ-መንገስቱን የሚቃረን
ባለመሆኑ፣ ግልጽ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔንና የሕግ ትርጉምን ያልተቃረነ
ስለሆነና ጉዳዩም ከተከራካሪዎች ባለፈ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ባለመሆኑ በዚህ ችሎት ደረጃ ቀርቦ
የሚመረመር ሆኖ አላገኘነውም፡፡

ውሳኔ

1. የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 105612 ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ/ም፣
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 55215 ግንቦት 12 ቀን 2015
ዓ/ም እና የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዳደር ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 10251/2013
ሚያዚያ 18 ቀን 2013 ዓ/ም የሠጡት ውሳኔ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. በዚህ ችሎት ለወጣ ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

ትዕዛዝ

 የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ፡፡


 አፈጻጸሙ ላይ የተሰጠው እግድ ተነስቷል፡፡ ይጻፍ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

 መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለ ፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ.መ.ቁ. 210876

ሕዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች፡- ሰለሞን አረዳ

እትመት አሠፋ

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- ቻላቸው ክንዴ- ቀረቡ

ተጠሪ፡- ወ/ሮ ነኢማ ከማል

መዝገቡ ለምርመራ የተቀጠረ ነው፡፡ በመሆኑም መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሐምሌ 03 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረበው የሰበር አቤቱታ
በጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 01006/2013
ሠኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል
በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ የቤት ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጋምቤላ
ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ
ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች 1ኛ ተከሳሽ፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌሉ አቶ ደረጀ ተፈራ የተባሉ ግለሰብ ደግሞ
2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ከስር
2ኛ ተከሳሽ ባል እና ሚስት መሆናቸውን እና በጋምቤላ ከተማ 03 ቀበሌ ውስጥ በአመልካች ስም ተመዝግቦ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በሚገኘው 208 ካ.ሜ ላይ ያረፈውን ቤት በጋራ ያፈሩ መሆኑን፤ በሕመም ምክንያት ወደ ጅማ በሄዱበት
ወቅት አመልካች ከእውቅናቸው ውጪ በቤቱ ውስጥ የገባ መሆኑን በመግለጽ በቤቱ ውስጥ በምን ምክንያት
እንደገባ ተጠይቆ ቤቱን ለቆ እንዲያስረክባቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁን አመልካች በሰጡት መልስ የተጠሪ ጥያቄ ግዙፍ የሆነውን የባለቤትነት መብት የሚመለከት በመሆኑ
የንብረቱ ባለቤት መሆንዋን የሚያሳይ የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ ልታቀርብ ይገባል፤ ተጠሪ ይህን ማስረጃ
ያላቀረበች በመሆኑ ክሱን ለማቅረብ የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላትም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ አቅርቧል፡፡ በሌላ በኩል የስር 2ኛ ተከሳሽ መልስ የመስጠት መብቱ የታለፈ መሆኑን ከመዝገቡ
ጋር ተያይዞ የቀረበልን የውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ መብት እና ጥቅም ያላቸው
ስለመሆኑ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1723 አግባብ የቤት ባለቤትነት ካርታ ወይም የአፈር ግብር በሰነድ
ማስረጃነት ያላቀረቡ በመሆኑ አመልካች ያቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተገቢ ነው በማለት ክሱን
በብይን ውድቅ አድርጎታል፡፡

ተጠሪ ይህን ብይን በመቃወም ለጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የይግባኝ አቤቱታ
ያቀረቡ ሲሆን ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት ግራቀኙን አከራክሮ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን
አጽንቷል፡፡

ተጠሪ በመቀጠል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ አቤቱታው
የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተጠሪ እና ባለቤታቸው
የሆኑት የስር 2ኛ ተከሳሽ የጋራ ንብረት በመሆኑ ቢሸጥም ባልና ሚስቱ እኩል የመካፈል መብት ያላቸው
በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪ መብት እንደሌላት የሰጡት ውሳኔ አግባብ አይደለም በማለት ሽሮ
የመኖሪያ ቤቱ የሽያጭ ውል ፈራሽ ነው ሲል ወስኗል፡፡

የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም መሠረታዊ የሕግ ስሕተት ተፈጽሞበታል በሚል ሲሆን
ይዘቱም፡- የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳን አዲስ ጭብጥ በመያዝ ውሳኔ ሰጥቷል፤
የሽያጭ ውሉ በማስረጃነት ባልቀረበበት ሁኔታ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ለስር
ፍርድ ቤት መመለስ ሲገባው የሽያጭ ውል ሊፈርስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ
ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል የሚል ነው፡፡

የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበችው አቤቱታ የተያዘብኝ ቤት
ይለቀቅልኝ የሚል ሆኖ ሳለ የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ የመወሰኑን አግባብነት
ከመሠረታዊ የክርክር አመራር ስነ ስርዓት ጋር በማገናዘብ ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ በዚህ ችሎት እንዲታይ
ተደርጓል፡፡ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የተጠሪ መልስ ይዘት በአጭሩ፡- የስር ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ማጣራት ሳያደርግ በብይን መዝጋቱ ተገቢነት
የለውም፤ የስር 2ኛ ተከሳሽ የራሱን ድርሻ ከመሸጥ ውጪ የተጠሪን ድርሻ ከእኔ እውቅና ውጪ መሸጥ
አይችልም፤ ስለሆነም ይህንኑ መሠረት በማድረግ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው
ውሳኔው ሊጸና ይገባል የሚል ነው፡፡

አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ይህ ችሎትም በሰበር አጣሪው ችሎት ሊጣራ ይገባዋል
ተብሎ የተያዘውን ነጥብ ከግራቀኙ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት
ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምሮታል፡፡

ከክርክሩ ሒደት መገንዘብ የቻልነው የአሁን ተጠሪ አላግባብ የተያዘባቸው ቤት እንዲለቀቅላቸው ሲጠይቁ
የአሁን አመልካች በሰጡት መልስ ተጠሪ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ ያላቀረቡ በመሆኑ ክሱን ለማቅረብ
የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላትም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረቡ መሆኑን፤ ጉዳዩ
የቀረበለት ፍርድ ቤትም ይህንኑ መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ወደ ፍሬነገሩ ሳይገባ የተጠሪን ክስ በብይን
ውድቅ ያደረገው መሆኑን፤ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ደግሞ የስር ፍርድ ቤት
በመቃወሚያው ላይ የሰጠውን ብይን ምንም ሳይል አልፎ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የተጠሪ እና
ባለቤታቸው የሆኑት የስር 2ኛ ተከሳሽ የጋራ ንብረት በመሆኑ የመኖሪያ ቤቱ የሽያጭ ውል ፈራሽ ነው
በማለት የወሰነ መሆኑን ነው፡፡

በመሠረቱ አንድ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ወገኖች በተለያዩበት የፍሬነገር ጉዳይ ላይ ጭብጥ መስርቶ ውሳኔ
መስጠት የሚችለው በቅድሚያ በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ ተገቢውን ብይን ከሰጠ በኋላ
ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 246 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ በሐገራችን የሰበር
ክርክሮች የሚመሩበት የተለየ ስርዓት የሌለ በመሆኑም አንድን የፍትሐብሔር ጉዳይ በሰበር የሚያይ ፍርድ
ቤትም በተመሳሳይ የፍትሐብሔር ክርክሮች የሚመሩበትን የሥነ ሥርዓት ሕግ ሊከተል ግድ ይለዋል፡፡

በያዝነው ጉዳይ የጋምቤላ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪን ክስ ውድቅ ያደረገው አመልካች
ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሠረት በማድረግ በብይን ነው፤ ከዚህ ውጪ ግራቀኙ
በተከራከሩበት የፍሬነገር ክርክር ላይ ተገቢውን ጭብጥ በመያዝ አጣርቶ የሰጠው ውሳኔ የለም፤ ይህ ብይን
ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው የጋምቤላ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እስካልተቀየረ ድረስ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ፍሬ ጉዳዩን ከመመርመሩ በፊት በቅድሚያ የስር ፍርድ ቤቶች የቀረበላቸውን
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሠረት በማድረግ የሰጡት ብይን ተገቢ መሆን አለመሆኑን መርምሮ ውሳኔ
ሊሰጥበት ይገባል፡፡ ስለሆነም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን ስነ ስርዓታዊ የክርክር
አመራር ሒደት ሳይከተል በፍሬነገሩ ላይ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ስሕተት
የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ውሳኔ
1. በጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.
01006/2013 ሠኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም በስሩ ያሉት ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ትዕዛዝ በመሻር
የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሠረት ተሽሯል፡፡
2. በጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በአመልካች
በኩል የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሠረት በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት
ብይን ተገቢ መሆነ አለመሆኑን በቅድሚያ መርምሮ ውሳኔ መስጠት ሲገባው ይህን ሳያደርግ
በፍሬነገሩ ላይ የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የክርክር አመራር ስሕተት የተፈጸመበት ነው
በማለት ወስነናል፡፡
3. በጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በውሳኔ
የዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተገለጸው መሠረት በስሩ ያሉት ፍርድ
ቤቶች አመልካች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሠረት በማድረግ የሰጡት ብይን ተገቢ
መሆን አለመሆኑን መርምሮ ውሳኔ እንዲሰጥበት፤ በሚሰጠው ውሳኔ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ
የሚለወጥ ከሆነ በፍሬ ጉዳዩ ላይ አከራክረው እንዲወስኑ ለስር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን
እንዲመልስላቸው በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341/1 መሠረት ጉዳዩ ተመልሶለታል፡፡
4. በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርከር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡፡
- መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል፡፡ ይመለስ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ፡-210953

29/03/2014ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካቾች፡- 1ኛ. አቶ አርአያ ዮሴፍ -ቀረቡ

2ኛ. አቶ ፈቀደ ዮሴፍ - -አልቀረቡም

ተጠሪዎች፡- 1ኛ. ወ/ሮ አስናቀች መንግስቴ - አልቀረቡም

2ኛ. ወ/ሮ ብዙ ደበሌ - ቀረቡ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች በቀን 09/11/2013 ዓ.ም በተፃፈ
ማመልከቻ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ.376953 በቀን 8/11/2013 ዓ.ም
በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ሰሚው ችሎት
እንዲታረምልን በማለት ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን አመልካቾች በአለልቱ ወረዳ
ፍርድ ቤት ተከሳሾች የነበሩ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡

የአሁን 1ኛ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካቾች ላይ አሻሽለው ባቀረቡት ክስ አመልካቾች በጋራ


በመሆን በ2009 ዓ.ም ምንም መብት ሳይኖርቸው ከሚበቃ ከተማ ቀበሌ 01 ፍትሕ ጽ/ቤት አካባቢ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኘውን 600 ካ.ሜ የሆነ 39 ቅጠል ቆርቆሮ በላዪ ላይ ያለውን ግምቱ ብር
200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ሊያወጣ የሚችል እና አወሳኙ በክስ ዝርዝር የተገለፀው በ1984 ዓ.ም
እናቴ ወ/ሮ መንግስቴ ደስታ የምትባል የተናዘዘችልኝ ይዞታ በዚሁ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.12873 በቀን
06/05/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዚህ ይዞታ ላይ ወራሽነትን አረጋግጬ ወንድሞቼ የሆኑትን ጣልቃ
ገቦችን ውስጥ ትቼ በስራ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ከሄድኩ በኋላ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ በስራ
ምክንያት ወደ አረብ ሀገር በመሄዷ ምክንያት በሕገ ወጥ መንገድ ይዘውብኝ ቤት ሰርተውበት
እየነገዱበት ስለሆነ በራሳቸው ወጪ የሰሩትን ቤት አፍርሰው ይዞታውን እንዲለቁልኝ ይወሰንልኝ
በማለት አመልክተዋል፡፡

የአሁን አመልካቾች በሰጡት መልስም የአሁን 1ኛ ተጠሪ ተደረገልኝ የምትለው ኑዛዜ ላይ የቤት ቁጥር
የቤት ቁጥር የለውም፣ ካሬ ሜትርም የለውም፣ አዋሳኝም የለውም፣ ቤቱ ስንት ቅጠል ቆርቆሮ እንደሆነም
አይገልጽም፣ ስለሆነም የአሁን 1ኛ ተጠሪ ጠቅሳ ያቀረበችው ቤት የቀበሌ ሆኖ ለጊዜው እንዲያርፉበት
የተደረገ ነው ስለሆነም 1ኛ ተጠሪ በዚህ ይዞታ ላይ የባለይዞታነት ማስረጃ ስለሌላት ልትጠይቀን
አትችልም፡፡እኛ በማይክሮ እና በጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ ተደራጅተን መኖሪያ
ቤታችንን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚያወጣ የሰራንበት እና በብሎኬት ምርት እና
ስራ ደብሊዪ/ኬ/ቲ/አይ/ቲ በቀን 23/04/2007 ማስረጃ አውጥተንበት እየሰራንበት ስለሆነ የአሁን 1ኛ
ተጠሪ ክስ ውድቅ እንዲሆንልን በማለት ተከራክረዋል፡፡

የአለልቱ ወረደ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶና ተገቢውን ማጣራት አድርጎ በሰጠው ውሳኔም
ተጠሪዎች ለይዞታው ማስረጃ የሌላቸው መሆኑንና ግብርም ያልገበሩበት በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት
የለውም በማለት ውድቅ አድርጎት ይህ ውሳኔ ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ
ፍርድ ቤት የፀና ቢሆንም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር የቤት ቁጥር
39 የሆነው ቤት በማን ስም እንዳለ በማጣራት ከሰው ምስክሮቹ ቃልና ከኮሚቴ ሪፖርቱ ጋር በመመዘን
ተገቢውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን መልሶታል፡፡

በዚህ አግባብም የአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ባደረገው ማጣራት የሚቃዋ ፊቼ ገሊላ ከተማ አስተዳደር
ቤቱ በማን ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ ማስረጃ የሌለው መሆኑን መግለፁን፤ከዚህ ባለፈ የሽማግሌዎችን
ቃል በመቀበል ያቀረበው ሪፖርት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፤የግራ ቀኙ ምስክሮች የሰጡት ቃል
ተመጣጣኝ መሆኑን፤የወራሽነት ማስረጃን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ መብት ከሌላቸው ውድቅ ሊደረግና
ዋጋ ሊያጣ የሚችል መሆኑን፤ኑዛዜው ስለይዞታው ምንም የማይል ቤቱ የት እንደሚገኝና አዋሳኙ
እነማን እንደሆኑ የማያመለክት መሆኑን፤አመልካቾች ያቀረቡት ህዳር 19 ቀን 1983 ዓም የተፃፈው
ውል አዋሳኙ ሙሉ ለሙሉ ባይመሳሰልም ግንኙነት ያለው መሆኑን፤በይዞታው ላይ ማንም ግብር
የማይከፍልበት መሆኑን፤ተጠሪዎች ያቀረቧቸው ምስክሮች የባለይዞታ የምስክር ወረቀትን ለመደገፍ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የሚረዱ እንጂ በራሳቸው ባለቤትነትን ለማሳየት በቂ አለመሆኑን በመጥቀስ የቀረበው ክስ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.


33(2) እና (3) መሰረት ውድቅ ነው በማለት ወስኗል፡፡

የአሁን ተጠሪዎች የአለልቱ ወረደ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኛ አቤቱታ ለሰሜን
ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል፡፡ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔም የተጠሪዎች ምስክሮች በአከራካሪው
ቦታ ላይ ያለው አሮጌ ቤት የ1ኛ ተጠሪ እናት መሆኑን፤ይህንን ቤትም 1ኛ ተጠሪ በውርስ ያገኙ
መሆኑን በቦታው ላይ አሁን የተሰራው ቤት ሁለት አመት የማይሞላው መሆኑን ያስረዱ
መሆኑን፤የተለያዩ አካላት የአካባቢውን ሽማግሌዎች በመያዝ ባደረጉት ማጣራት ይዞታው የወ/ሮ
መንግስቴ ደስታ መሆኑን ፤አመልካቾች በሽያጭ አስተላልፎልናል የሚሉት ሀምሳ አለቃ ገ/ማሪያም
ጉደታ በይዞታው ላይ መብት የሌለው መሆኑን ማረጋገጣቸውን በመጥቀስ በማስረጃ ምዘና ረገድ
ተጠሪዎች በይዞታው ላይ የተሻለ መብት ያላቸው መሆኑን ማስረዳታቸውን በመጥቀስ አመልካቾች
መብት በሌላቸው መሬት ላይ ያከናወኑት ግንባታ በራሳቸው ወጪ በማፍረስ ይዞታውን ለአሁን
ተጠሪዎች እንዲለቁ በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ሽሯል፡፡

የአሁን አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኙን በፍ/ስ/ስ/ ሕግ ቁጥር.337 መሰረት የሰረዘው ሲሆን ሰበር ሰሚ ችሎቱም በስር
ፍርድ ቤቶች የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም በማለት አመልካቾች ያቀረቡትን የሰበር
አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል፡፡

አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም በአጭሩ የአለልቱ ወረዳ ፍርድ
ቤት ከዚህ በፊት ለክርክር መነሻ የሆነውን ቤት የማን እንደሆነ፤ በማን ስም ተመዝግቦ እንዳለ
እንዲሁም ማን ግብር እንደሚገብርበት ተጣርቶ እንዲቀርብ በታዘዘው መሰረት በዚህ አከራካሪ በሆነው
እና ክርክር ባስነሳው ቦታ ላይ ማንም መብት እንደሌለው፤ እንዲሁም ማንም ግብር የገበረበት
እንደሌለ፤ የሚቃዋ ፍቼ ገሊላ ከተማ አስተዳደር በደብዳቤ ቁጥር G/9/B/M/M/F/G 1113/64 በቀን
03/10/2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ለወረዳው ፍርድ ቤት ገልጿል፡፡ይህም ተጠሪዎች ከመነሻውም
አመልካቾች ላይ መብት በሌላቸው ጉዳይ ላይ ክስ ማቅረባቸውን ፤ክስ ባቀረቡበት ጉዳይም የመክሰስ
መብት የሌላቸው መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ እያለ በዚህ አግባብም የወረዳው ፍርድ ቤት ሕጉን በተከተለ
መልኩ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በይዞታው ላይ ምንም መብት የላትም ብሎ ክሱን ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ
ሆኖ እያለ በየደረጃው ያሉት የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የአሁን ተጠሪዎች ባለመብት ናቸው
ብለው መወሰናቸው አግባብነት የለውም፡፡የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የተፈፀመውን የሕግ ስሕተት ሊያርም ሲገባው የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ማጽናቱ አግባብነት
የለውም፡፡ስለሆነም የስር የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተሸሮልን
ተገቢው ፍርድ እንዲሰጥልን በማለት አመልክተዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ለክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታና ቤት የተጠሪዎች አውራሽ ይዞታ ስለመሆኑ የሰነድ ማስረጃ ባላቀረቡበት
እና የሚመለከተው የአስተዳደር አካል ተጠይቆ ቤትና ይዞታው የተጠሪዎች አውራሽ አለመሆኑን ምላሽ
በቀረበበት የስር ፍርድ ቤት አመልካቾች የሰሩትን ቤት አፍርሰው ይልቀቁ በማለት የወሰነበትን
አግባብነት ከፍ/ስ/ስ/ ሕግ ቁጥር 33(2)(3) አኳያ ለመመርመር የሰበር አቤቱታው ያስቀርባል ከተባለ
በኋላ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

ተጠሪዎች በሰጡት መልስም የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.81912 ላይ ግንቦት 17 ቀን


2013 ዓ.ም ለወሰነው ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 344570 ላይ
ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ለሰጠው ትዕዛዝ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
በመ/ቁ.376953 ላይ ሐምሌ 08 ቀን 2013 ዓ.ም ለሰጠው ትዕዛዝ መሰረቱ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 321496 ላይ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ
ነው፡፡ይዞታው የማነው የሚለውን በተመለከተ በግራ ቀኝ የቀረበ የሰነድ ማስረጃ ያልቀረበ ስለሆነ
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታ የማነው የሚለውን ጭብጥ የምስክሮችን ቃል እና ከከተማ አስተዳደሩ
የቀረበውን ቃለ ጉባኤ በመመዘን ውሳኔ እንዲሰጥ ትዕዛዝ የሰጠው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ነው፡፡የሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት
ውሳኔ መሰረት በማድረግ ማስረጃን ለመመዘን ባለው ስልጣን የምስክሮችን ቃል እና የቃለ ጉባኤውን
ይዘት በመመዘን ለክርክር መነሻ የሆነው ይዞታ የአሁን ተጠሪዎች አውራሽ የሆኑት የሟች ወ/ሮ
መንግስቴ ደስታ መሆኑን አረጋግጦ መወሰኑ እንዲሁም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በይግባኝ ሰሚ
እና ሰበር ሰሚ ችሎት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በማጽናት መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ
ስሕተት የለውም፡፡

አመልካቾች በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 321496 ላይ የካቲት 17 ቀን


2012 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው ውሳኔ አግባብ አልነበረም የሚሉ ከሆነ በወቅቱ ስልጣን ላለው የበላይ
ፍርድ ቤት ተፈጥሯል የሚሉትን መሰረታዊ የሕግ ስሕተት በመጥቀስ አቤቱታ ማቅረብ ነበረባቸው
እንጂ አሁን በዚህ ደረጃ በስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ተወስኖ እያለ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት
ተፈጽሟል ማለታቸው ራሱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት ነው፡፡ስለሆነም የተፈጠረ መሰረታዊ የሕግ
ስሕተት የሌለ በመሆኑ የስር ከፍተኛ፣ ጠቅላይ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የለውም ተብሎ እንዲወሰንልን በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካቾችም የመልስ መልሳቸውን በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡በኢፌዲሪ ህግ
መንግስት አንቀፅ 80(3)(ሀ) እና በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10(1)
እንደተመለከተው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው የዳኝነት ስልጣን በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ውስጥ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞ ሲገኝ በሰበር አይቶ የማረም ነው፡፡በዚህ አግባብም ይህ ሰበር ሰሚ
ችሎት የሰበር ሰሚነት ስልጣኑን ተግባራዊ ሲያደርግ ፍሬ ነገርን በተመለከተ በዋነኝነት መነሻ
የሚያደርገው ስልጣን ባላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ነው፡፡

አሁን በያዝነው ጉዳይ የስር የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ
የሻረው አመልካቾች በ1993 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል አከራካሪውን ቤት በመግዛት ቀድሞ የነበረውን
ቤት በማፍረስ አዲስ ቤት መስራታቸውን ካስረዱት የአመልካቾች ምስክሮች ቃል ይልቅ በፍርድ ቤቱ
ትዕዛዝ የተደረገው ማጣራት ስለጉዳዩ በጥልቀት የሚያውቁትን የአካባቢውን ሽማግሌዎች በመያዝ
የተደረገ ሆኖ ይዞታው የወ/ሮ መንግስቴ ደስታ መሆኑን ፤አመልካቾች በሽያጭ አስተላልፎልናል
የሚሉት ሀምሳ አለቃ ገ/ማሪያም ጉደታ በይዞታው ላይ መብት የሌለው መሆኑን
ማረጋገጣቸውን፤የተጠሪዎች ምስክሮች በአከራካሪው ቦታ ላይ ያለው አሮጌ ቤት የ1ኛ ተጠሪ እናት
መሆኑን፤ይህንን ቤትም 1ኛ ተጠሪ በውርስ ያገኙ መሆኑን በቦታው ላይ አሁን የተሰራው ቤት ሁለት
አመት የማይሞላው መሆኑን ያስረዱ መሆኑን፤በዚህም ከማስረጃ ምዘና አንፃር ተጠሪዎች በይዞታው ላይ
የተሻለ መብት ያላቸው መሆኑን ማስረዳታቸውን በመጥቀስ ነው፡፡ይህ የስር ፍርድ ቤቶች የደረሱበት
ድምዳሜ በዚህ ችሎት ሊለወጥ የሚችለው የስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ምዘና ረገድ የፈፀሙት ስህተት
ከተገኘ ብቻ ሲሆን ይህ ችሎት ባደረገው ምርመራ በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመ የማስረጃ ምዘና መርህ
ጥሰት ያልተገኘ በመሆኑ የአመልካቾችን መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 81912 ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው


ችሎት የሰጠው ፍርድ እና ይህንን ፍርድ በማፅናት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ
ችሎት በመ/ቁ. 344570 ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት እንዲሁም የኦሮሚያ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.376953 ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው
ችሎት የሰጡት ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር.348(1) መሰረት ፀንተዋል፡፡
2. በሰበር ሰሚው ችሎት ተለዋጭ ትዕዛዝ እስኪደርሰው ድረስ በአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት አፈፃፀም
ምድብ ችሎት በመ/ቁ. 17076 የተጀመረው የአፈፃፀም መዝገብ ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ በቀን
15/11/2013 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡ይጻፍ፡፡
3. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ. 211260

ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች- የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ-ክርስቲያን ኮሚሽን

ተጠሪ- አቶ መስፍን አዱኛ- ቀርበዋል

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ
ጉዳዩ የግል የስራ ቅጥር ዉልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በጀመረበት በፌደራል መጀመሪያ
ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በቀን 30/06/2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ
ከጥር 23 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በፕሮጀክት ኦፊሰርነት በወር ብር 10,095.00 እየተከፈለኝ
ሳገለግል የቆየሁ ቢሆንም አመልካች ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ፣ በማላውቀው እና በቂ
ባልሆነ ምክንያት ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም የስራ ውሌን ያቋረጠው በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ
ነው ተብሎ ወደ ስራዬ እንድመለስ፤ ወደ ስራ የማልመለስ ከሆነ ደግሞ ያልተጠቀምኩበት የ58 ቀን
የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ፣ ካሳ፣ የሶስት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ክፍያ
ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ ቅጣት እንዲከፍል እና የስራ ልምድ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት
የጠየቀዉን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡

አመልካች በበኩሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያን በማስቀደም ፍሬ ነገሩን አስመልክቶ


ባቀረበው መልስ ተጠሪ የተቀጠረው በአዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ-ክርስቲያን የእርዳታ
እና ልማት ዘርፍ ውስጥ ኦ ቪ ሲ በሚባል ፕሮጀክት ስራ ሲሆን ስራዉም ለተወሰነ ጊዜ የሚሰራ
መሆኑን፤ ከዚህ ባለፈ ግሬስ ኢምፓወርመንት በሚባል ሌላ ፕሮጀክት ላይ እንዲሳተፍ ተደርጎ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለ ጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ እንዲሰናበት የተደረገ በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው፡፡ የዓመት እረፍት ክፍያን
በሚመለከት ተጠሪ የነበረው የእረፍት ጊዜ 25 ቀናት ሲሆን ከዚህ ውስጥም 8 ቀናት ተጠቅሟል፤
ለቀረው የ17 ቀን እረፍት የስራ ውሉ እንደተቋረጠ ወደ ገንዘብ ተለውጦ የተከፈለው በመሆኑ ክሱ
ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ
አመልካች ድርጅት የሚሰራው ስራ የገንዘብ ችግር ያለባቸው እና የኤች አይ ቪ ታማሚዎችን
በየጊዜው ድጋፍ እና ስልጠና በመስጠት ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን ግለሰቦቹ ስልጠናውን
አጠናቀው የጨረሱበትን ጊዜ እንደ አንድ የፕሮጀክቱ ፌዝ በመቁጠር ቀጣይ ተጠቃሚዎች ሲመጡ
ደግሞ እንደ ሌላ ፌዝ በመቁጠር ቀጣይነት ባለው መልኩ ሰራተኞችን ሲያሰራ እንጂ እየበተነ
ያልነበረ በመሆኑ ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ ስራ የተቀጠረ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ስለሆነም የተጠሪ
ስንብተ ህገ-ወጥ ነው በማለት አመልካች ለተጠሪ የሶስት ወር ማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና ካሳ
በጠቅላላው ብር 90,855.00 ይክፈለው በማለት ወስኗል፡፡ በዚህ ውሳኔ ቅር የተሰኘው አመልካች
ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ይግባኙ ተሠርዞበታል፡፡ ለዚህ ፍርድ መነሻ
የሆነው የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህን በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡

አመልካች በቀን 15/11/2013 ዓ.ም በተፃፈ 03 ገጽ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች
ተፈጽመዋል ያላቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችሎት እንዲታረሙለት ጠይቀዋል፡፡ የአቤቱታው
ይዘትም በአጭሩ የተጠሪ የስራ ውል ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቋረጥ ማስጠንቀቂያ
ከተሰጠ በኋላ የደመወዝ ጭማሪ መደረጉ ስራው የቀጠለ መሆኑን ያረጋግጣል በሚል ከተጠሪ በኩል
የቀረበ ክርክር ሳይኖር ውሳኔ መሰጠቱ፤ ፕሮጀክቱ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የተጠሪን የስራ
መደብ መሠረዙ በማስረጃ ተረጋግጦ ሳለ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው መባሉ፤ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ
ባለመዘጋቱ ብቻ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው መባሉ፤ እንዲሁም አመልካች ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እያለ
የማስጠንቀቂያ ክፍያ እንድንከፍል መወሰኑ መሠረታዊ የህግና የማስረጃ ምዘና ስህተት የተፈፀመበት
በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል የሚል ነው፡፡

ጉዳዩም በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ አመልካች ተጠሪን ለፕሮጀክት ስራ የቀጠረው እና


ፕሮጀክቱ በበጀት እጥረት ምክንያት በመቋረጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ተጠሪን የተቀጠረበትን የስራ
መደብ ከሠረዘ በኋላ በሌላ መደብ ላይ ደመወዝ በመክፈሉ ማስጠንቀቂያውን ትቷል እና ስንብቱ
ህገ-ወጥ ነው ተብሎ የተወሰነበት አግባብነት ተጠሪ ባለበት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት
ለዚህ ሰበር ችሎት እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ በዚሁም መሠረት ተጠሪ መልስ እንዲሰጥት ተደርጎ
በቀን 04/02/2014 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካች በቀን 10/06/2000 ዓ.ም እና በቀን
20/02/2013 ዓ.ም በተፃፉ ደብዳቤዎች ስራውን በቋሚነት ተቀጥሬ ላልተወሰነ ጊዜ እንድሰራ
የሚገልጹ ሲሆኑ አመልካች ስራው ለተወሰነ ጊዜ የሚሰራ እንደሆነ በመግለጽ ያቀረበው ክርክር
ተቀባይነት የለውም፤ አመልካች በቀን 20/02/2013 ዓ.ም በሰጠኝ ደብዳቤ ደመወዝ የተጨመረው
በአዲስ የስራ መደብ ላይ ሳይሆን ባለው ህግ እና ደንብ መሠረት ሀብት አግኝቶ በቀጣይ በመልካም
አፈፃፀም እንድሰራ በማበረታታት በማሰብ ነው፤ ፕሮጀክቱ ተሠርዟል በሚል የቀረበውም ክርክርም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለ ጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሀሰተኛ በመሆኑ የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ተደርጎ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊፀና ይገባል
በማለት ተከራክሯል፡፡ አመልካችም የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቶ ከመዝገቡ
ጋር ተያይዟል፡፡

ከስር ጀምሮ የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ
ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችሎትም የአመልካችን የሠበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ
ችሎት ከተያዘው ጭብጥ፣ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸዉ
ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መዝገቡን እንደሚከተለዉ መርምሮታል፡፡ እንደመረመረዉም ተጠሪ
በስር ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ ለጠየቀዉ ዳኝነት መሰረት ያደረገዉ አመልካች የስራ ዉሉን ከህግ
ዉጪ ማቋረጡን ሲሆን፣ አመልካች በበኩሉ ዉሉ የተቋረጠዉ ተጠሪ የተቀጠረበት የፕሮጀክት ስራ
በመጠናቀቁ ምክንያት መሆኑን ጠቅሶ ስንብቱ ህጋዊ ነዉ በማለት ተከራክሯል፡፡ ስለሆነም ለክርክሩ
እልባት ለመስጠት በፍት/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 246(1) መሠረት መያዝ የሚገባዉ ትክክለኛ
ጭብጥ የስራ ዉሉ የተቋረጠዉ ተጠሪ የተቀጠረበት የፕሮጀክት ስራ በመጠናቀቁ ነዉ ወይ? የሚል
ነዉ፡፡ አመልካች የስራ ዉሉን ማቋረጡን ሳይክድ ያቋረጠዉ ተጠሪ የተቀጠረበት የፕሮጀክት ስራ
በመጠናቀቁ ምክንያት ጠቅሶ የተከራከረ በመሆኑ ይህን በቅድሚያ የማስረዳቱ ሸክም የአመልካች
ይሆናል፡፡ የስር የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ይህንኑ በጭብጥነት በመያዝ የግራ ቀኝ
ማስረጃዎችን ሰምቶ እና መርምሮ አመልካች ለተጠሪ በፃፈዉ ደብዳቤ የስራ ዉሉ ከጥቅምት 20
ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቋረጥ ተጠሪን ካሳወቀዉ በኋላ ዉሉ ይቋረጣል የተባለበት ጊዜ ካበቃ
በኋላ ተጠሪ ደመወዝ ተጨምሮለት በስራዉ እንዲቀጥል በሌላ ደብዳቤ የገለጸለት መሆኑንና ይህ
ከሆነ በኋላ የተከሰተ የስራ ዉሉን ሊቋርጥ የሚችል ሌላ ምክንያት ስለመኖሩ የቀረበ ማስረጃ
ያለመኖሩን፣ ምንም እንኳ አመልካች በለጋሾች የሚደገፍ ቢሆንም ሰራተኞችን እየቀጠረ ሰፊ እና
ቀጣይነት ያለዉ ነገር ግን በፌዝ በፌዝ እየተከፋፈለ ስራዉም እየተሰራ የሚገኝ እንጂ አለመሰረዙን
ከድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3/ሀ) እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች
አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 10 መሠረት የዚህ ችሎት ስልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት
የተፈጸመባቸዉን ዉሳኔዎች በማረም ላይ የተገደበ በመሆኑ ማስረጃን መዝኖ ፍሬ ነገርን የማረጋገጥ
ስልጣን የለዉም፡፡ የስር የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከላይ በተመለከተዉ መልኩ
የደረሰበት የፍሬ ነገር ድምዳሜ በአዋጁ ስለ መሠረታዊ የህግ ስህተት ትርጓሜ በሚሰጠዉ የአዋጁ
አንቀጽ 2(4) ላይ ከተመለከተዉ አንፃር ሲታይ የተፈጸመ የህግ ስህተት የለም፡፡ ስለሆነም የስር
ፍርድ ቤቶች ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ በማለት የደረሱበት ድምዳሜ በዚህ ችሎት ሊታረም የሚችል
መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም፡፡ ስለሆነም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ዉሳኔ

1. የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 171736 ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም


በዋለዉ ችሎትየሰጠዉ ዉሳኔ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 267883
ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ
አንቀጽ 348(1) መሰረት ጸንተዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለ ጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2. የሰበር አጣሪ ችሎት ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ እግድ
ተነስቷል፡፡

3. በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን


ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለ ጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 211693

ቀን፡- 3ዐ/11/2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ሸምሱ ሲርጋጋ

ዓለማየሁ ሹናራ

ዋዚሞ ዋሲራ

አመልካች/ቾች/፡- ወ/ሮ ፀሐይነሽ ወርቁ ጠበቃ ራሄል ከፍያለው ቀረቡ

ተጠሪ ፡- እነ አቶ አርአያ በዛብህ

መዝገቡ ከቀጠሮ በፊት ሊቀርብልን የቻለው አመልካች/ቾች 23/11ቀን 2ዐ13 ዓ.ም የሰበር
አቤቱታው ታይቶ ውሳኔ እስኪሚያገኝ ጊዜ ድረስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ችሎት በመ/ቁ
268732 በ15/11/2ዐ13 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ አፈፃፀሙ ታግዶ እንዲቆይ ይታዘዝልን የሚል
አቤቱታ በቃለ መሃላ አስደግፈው ስላቀረቡ ነው፡፡

አንድ ጉዳይ ለሰበር ችሎት ሊቀርብ የሚችለው ቅሬታ የቀረበበት ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት
የተገኘበት እንደሆነ ብቻ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 25/88 ዓንቀፅ 22/1/ ይደነግጋል፡፡ ፍርድ እንዲታይ
ትእዛዝ የሚሰጠውም ተከራካሪ ወገኖች በክርከር ባሉበት ጊዜ ነገሩ እስከሚሰማ ድረስ መሆኑን
በወንጀልና በፍትሐብሔር ስነ ሰርዓት ህጎች ተደንግጓል፡፡

በዚህ መሠረት የቀረበውን የእግድ ጥያቄና የሰበር አቤቱታው መነሻ በማድረግ መሠረታዊ
የህግ ስህተት ተፈጽሞባቸዋል የተባሉትን ውሳኔዎች አግባብ ካለው ሕግ ጋር ማገናዘብ
መርምረናል፡፡ አመልካችንም አነጋግረን ተከታዩን ትዕዛዝ ሰጥተናል፡፡

ት እ ዛ ዝ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔዎች መሰረታዊ የህግ ስህተት ተሰርቷል ለማለት ባለመቻሉ የቀረበውን ዕግድ
ጥያቄ አልተቀበልነውም፡፡ ጉዳዩም ለሰበር ችሎት አያስቀርብም ብለናል፡፡ ይፃፍ መዝገቡ ተዘግቷል
ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የሦስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡- 212313

ቀን፡-30/03/2014ዓ/ም

ዳኞች፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- አቶ ሁሴን ሙክታር

ተጠሪዎች፡-1. ወ/ሮ ብዙነሽ ፋፋ

2.ወ/ሪት ውብዓለም ታረቀኝ

መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን በዚሁ አግባብ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ሊቀርብ የቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
በይ/መ/ቁ.275565 በቀን 28/11/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች በምዕራብ
በኩል 1 ሜትር ወደ ተጠሪዎች ይዞታ በመግባት በመያዝ የፈጠረው ሁከት ሊወገድ ይገባል በማለት
የሰጠውን ውሳኔ በማፅናት ብይን መስጠቱ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይኸው
ስህተት እንዲታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን
አመልካች በፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት 2ኛ ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪዎች ከሳሾች
ነበሩ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪዎች በስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ላይ ባቀረቡት ክስም በን/ስ/ላ/ክፍለ


ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር ኮድ 44 የሆነ በ180 ካሜ ላይ ያረፈ የመኖሪያ ቤት ከሟች ባለቤቴ አቶ
ታረቀኝ አላምረው ጋር በመሆን ነሀሴ 04 ቀን 1991 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ከአቶ አረብሳ ማሞ
እና ወ/ሮ መስታወት ሀይሌ በመግዛት ተረክበን ስንኖር አመልካች በስተምዕራብ በኩል ወደ ይዞታችን
ጥሶ በመግባት ህገወጥ ግንባታ የፈፀመ እና በጥር ወር 2011 ዓም አጥር በማፍረስ ሁከት የፈጠረብን
በመሆኑ ይዞታችንን ለቅቆ እንዲያረክበን ይወሰንልን በማለት አመልክተዋል፡፡

አመልካች በሰጡት መልስም ተጠሪዎች ይዞታውን ስለመግዛታቸው እና ስለመረከባቸው የሚያስረዳ


ማስረጃም ሆነ በይዞታው ላይ ስለመገበራቸው ያቀረቡት ማስረጃ ስለሌለ ክሱ ውድቅ ሊደረግ
ይገባል፤አመልካች ከተጠሪዎች 10 አመት አስቀድሜ ክርክር የተነሳበትን ይዞታ በእጄ አድርጌ ቤቶች
ሰርቼ እየኖርኩ እያለ 1ኛ ተጠሪ የዛሬ 17 ዓመት ወደ ይዞታው የመጣችና በድንበሯ ላይ ጨርሳ ቤት
ሰርታ የሰራችና ፍሳሽ ወደ አመልካች በማድረጓ በሽምግልና ታይቶ ፍሳሹን ወደምትኖርበት ይዞታ
እንድታደርግ ጉዳዩ ሲታይ የነበረ በመሆኑና አመልካች ወደ ተጠሪዎች ይዞታ ያልገባሁ በመሆኑና ምን
ያህል ካሜ እንኳ እንደያዝኩ ክሱ ተብራርቶ ያልቀረበ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት
ተከራክረዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው የሚለውን ማጣራት አድርጎ የግራ ቀኙን ምሰክሮች ሰምቶ በሰጠው
ውሳኔም የክፍለ ከተማውና የከተማው የይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤቶች በተለያየ ጊዜ አጣርተው በሰጡት
ምላሾች ትክክለኛውን የተጠሪዎችን ይዞታ ስፋት ማወቅ ያልተቻለ መሆኑን ነገር ግን የተጠሪዎች ይዞታ
በግራም በቀኝም በኩል እየጠበበ መምጣቱን በእስኬች አስደግፎ መግለፁን፤የተጠሪዎች ምስክሮች
በምዕራብ በኩል 1 ሜትር የሚያክል ይዞታ አመልካች መያዛቸውን ሲያስረዱ የአመልካች ምስክሮች
የአመልካች ይዞታ ምን ያህል እንደሆነ እንደማያውቁ ወደ ተጠሪዎች ይዞታ ስለማለፋቸው የማያውቁ
መሆኑን ማስረዳታቸውን በመጥቀስ አመልካች በምዕራብ በኩል 1 ሜትር ወደ ተጠሪዎች ይዞታ
በመግባት በመያዝ የፈጠሩት ሁከት ሊወገድ ይገባል ፤አመልካች ወደ ተጠሪዎች ይዞታ 1 ሜትር
በመግባት ያከናወኑትን ግንባታ በማፍረስ ለተጠሪዎች ሊያስረክቡ ይገባል በማለት ወስኗል፡፡አመልካች
በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ይግባኛቸውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኙን
በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.337 መሰረት ሰርዞታል፡፡

አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታም በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በተደረገው
ማጣራት 3 ምላሾች የቀረቡ ሆኖ ባለሙያውም በችሎቱ ቀርቦ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተደርጎ በቀረበው
አጠቃላይ ውጤት በ1997 ዓም ሆነ በ2003 ዓም በተነሳው የአየር ካርታ የግራ ቀኛችን ይዞታ በአንድ
ጊቢ ውስጥ የሚታይና ስንት ካሬ ሜትር እንደሆነ ለማወቅ የማይቻል መሆኑን፤ተጠሪዎች በአመልካች
ይዞታ ውስጥ ይዞታ አለኝ ቢሉም በእጃቸው ያልያዙት መሆኑን ፤በግራ ቀኛችን መሃል የድንበር
መገፋፋት አለ ለማለት የሚያስችል ማስረጃ እንደሌለ የሚገልፅ ሆኖ እያለ፤የስር ፍርድ ቤት ይህንን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መግለጫ ወደ ጎን በመተው የሰጠው ውሳኔ በሰበር መዝገብ ቁጥሮች 97132፤48608 የተሰጡትን


አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች መሰረት ያላደረገ የባለሙያን ማብራሪያ ባለመቀበል የሰው ምስክርን ቃል
በመቀበል የተሰጠ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሊሻር
ይገባል በማለት አመልክተዋል፡፡

አመልካች የተጠሪዎችን ይዞታ ገፍተው አለመያዛቸው በክፍለ ከተማው የይዞታ አስተዳደር በተገለፀበት
ባለሙያ ያልሆኑ ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል መሰረት በማድረግ አመልካች 1ሜትር ላይ
የገነቡትን ግንባታ አፍርሰው ለተጠሪዎች እንዲለቁ የተወሰነበትን አግባብ ለማጣራት የሰበር አቤቱታው
ያስቀርባል ከተባለ በኋላ ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

ተጠሪዎች በሰጡት መልስም መልሳችንን ስናቀርብ ከሰው ምስክሮች በተጨማሪ ከ1988 ዓም ጀምሮ
የግብር ማህደር ያለን ለመሆኑ፤በ1993 ዓም ካዳስተር ቢል ላይ የተጠሪዎች ይዞታ የቦታ ስፋት 155
ካሜ የነበረ ስለመሆኑና በ2009 ዓም የቦታው ስፋት 83 ካሜ ብቻ እንደቀረ የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09
ያረጋገጠበትን የሰነድ ማስረጃ ያቀረብን ስሆን የክፍለ ከተማው ይዞታ አስተዳደር ለፍርድ ቤቱ በሰጠው
ምላሽም የ1988፤1997 እና 2003 ዓም የአየር ላይ ካርታ ምልከታ ስኬች በመላክ በሶስቱም የአየር
ካርታ ላይ የተጠሪዎች ይዞታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየውን ልዩነት ያሳየ በመሆኑ አመልካች የተጠሪዎችን
ይዞታ ጥሶ በመግባት ይዞታችንን በሀይል እና በህገወጥ መንገድ ስለመያዙ የሰነድ የባለሙያ እና የሰው
ማስረጃዎችን ያቀረብን በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክራቸውን አጠናክረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር ክርክሩን ያስቀርባል ከተባለበት
ነጥብ፣ከተገቢው ሕግና ከስር ፍርድ ቤት ክርክር አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል፡፡በመሰረቱ አንድ
ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አወሳስን የጠራ ፍሬ ነገር የሌለ መሆኑን ከተገነዘበ ይኸው ፍሬ ነገር እንዲጣራ
ተገቢ ነው ያለውን ማጣራት ሁሉ ማድረግ እንደሚችል ከፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.136፤137፤272 እና 345
ድንጋጌዎች ለመረዳት የሚቻል ሲሆን ለጉዳዩ አወሳሰን መሰረት የሚሆንን ፍሬ ነገር በማስረጃ ሳያጣሩ
መወሰን አግባብ ባለመሆኑ በክርክሩ የቀረቡት ማስረጃዎች በቂ ባልሆኑበት ጊዜ እና እነዚህን
ማስረጃዎች ብቻ መሰረት አድርጎ መወሰን ፍትህን የሚያዛባ ከሆነ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት ተጨማሪ
ማስረጃ ወይም ምስክር እንዲቀርብ መታዘዝ ያለበት ስለመሆኑ በሰበር መዝገብ ቁጥሮች 72980፤22603
እና በሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡

ተጠሪዎች በአመልካች ላይ በስር ፍርድ ቤት ክሳቸውን ያቀረቡት ከይዞታቸው በስተምዕራብ በኩል


ጥሰው በመግባት ግንባታ የፈፀሙ መሆኑንና በጥር ወር 2011 ዓም አጥር በማፍረስ ሁከት የፈጠሩ
መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን አመልካች ወደ ተጠሪዎች ይዞታ በመግባት የፈጠሩት ሁከት የሌለ መሆኑን
በመጥቀስ መከራከራቸውን የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ክርክር ያሳያል፡፡በመሰረቱ የግራ ቀኙ ይዞታ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሰነድ አልባ መሆኑ ግራ ቀኙ የተማመኑበት ነጥብ ሲሆን የአስተዳደር አካላቱ ምላሽም ይህንኑ
የሚያረጋግጥ ነው፡፡የአስተዳደር አካላቱ ይህንን መነሻ በማድረግ በሰጡት ምላሽ የግራ ቀኙን ይዞታ
ትክክለኛ ስፋት ማወቅ እንዳልቻሉ የገለፁ ሲሆን ከዚህ ምላሽ ጋር አያይዘው በሰጡት መግለጫ
የተጠሪዎቸ ይዞታ በግራ እና በቀኝ በኩል እየጠበበ መሆኑን እንደገለፁ የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው
ላይ ያመለከተ ሲሆን ይህ ምላሽ በእስኬች የተደገፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ላይ ገልጿል፡፡ይህ
ምላሽ በግራ ቀኝ በኩል የተጠሪዎች ይዞታ እየጠበበ መምጣቱን ቢያመለክትም መሰረታዊ በሆነ
የአቅጣጫ ማመልከቻ ጠበበ ያለውን ይዞታ በማመልከት፤ክስ ከቀረበበት ከተጠሪዎች ይዞታ ምዕራብ
አቅጣጫ አንፃር ይህ የይዞታ መጥበብ መኖር አለመኖሩን አያመለክትም፡፡

የግራ ቀኙን ይዞታ ስፋት ልክ ማወቅ ያልቻለ ከሆነ የይዞታውን በሂደት መጥበብ በምን
እንደተገነዘበ፤ይህ የይዞታ በየጊዜው መጥበብ ከመቼ ጀምሮ እንደመጣ (አመልካቾች በጊዢ አገኘን ካሉ
በኋላ ይሁን በፊት) ፤አመልካች በተጠሪዎች ይዞታ መጥበብ ላይ ድርሻ ያላቸው መሆን አለመሆኑን
በማብራራት የሠጠው ምላሽ ስለመኖሩ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያሳይም፡፡

በተለያዩ ጊዜያት በተነሱት የአየር/መስመር ካርታዎች የተጠሪዎች ወይም ለተጠሪዎች መብቱን


ያስተላለፉት አቶ አረብሳ ማሞ እና ወ/ሮ መስታወት ሀይሌ በይዞታው ላይ ያከናወኑት ግንባታ ልክ እና
ይህንን መሰረት በማድረግ የሚታወቀው የይዞታ ልክ እና/ወይም በተቃራኒው የአመልካች በይዞታው ላይ
ያከናወኑት ግንባታ ልክ እና ይህንን መሰረት በማድረግ የሚታወቀው የይዞታ ልክ ምን ያህል እንደሆነ፤
ከዚህ በማለፍ በተጠሪዎች ይዞታ በምዕራብ በኩል አመልካች የያዙት የተጠሪዎች ይዞታ መኖር
አለመኖሩ፤ካለም ምን ያህል እንደሆነ ከተገቢው የአስተዳደር አካል መጣራቱን የስር ፍርድ ቤት
አያሣይም፡፡ይህ ባልሆነበት የስር ፍርድ ቤት ለግራ ቀኙ አዋሳኝ የሆኑትን አስቀርቦ ሳይሰማ
የተጠሪዎች ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል ብቻ መሰረት በማድረግ የደረሰበት መደምደሚያ እና
ይህንን መሰረታዊ የህግ ስህተት ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ሊያርም ሲገባ
ማፅናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለው ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.279049 በ06/0122012 ዓ.ም በዋለው ችሎት


የሰጠው ፍርድ እና ይህንን ፍርድ በማፅናት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.259509
በ21/07/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ብይን በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ተሸሯል፡፡
2. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት የጉዳዩን መዝገብ በማንቀሳቀስ ከተገቢው የአስተዳደር
አካል በተለያዩ ጊዜያት በተነሱት የአየር/መስመር ካርታዎች የተጠሪዎች ወይም ለተጠሪዎች
መብቱን ያስተላለፉት አቶ አረብሳ ማሞ እና ወ/ሮ መስታወት ሀይሌ በይዞታው ላይ ያከናወኑት
ግንባታ ልክ እና ይህንን መሰረት በማድረግ የሚታወቀው የይዞታ ልክ እና/ወይም በተቃራኒው

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአመልካች በይዞታው ላይ ያከናወኑት ግንባታ ልክ እና ይህንን መሰረት በማድረግ የሚታወቀው


የይዞታ ልክ ምን ያህል እንደሆነ፤ ከዚህ በማለፍ በተጠሪዎች ይዞታ በምዕራብ በኩል አመልካች
የያዙት የተጠሪዎች ይዞታ መኖር አለመኖሩ፤ካለም ምን ያህል እንደሆነ እና መቼ እንደያዙት
በማጣራት እንዲሁም ስለጉዳዩ በጥልቀት ሊያውቁ የሚችሉትን የግራ ቀኙን አዋሳኞች አስቀርቦ
በመስማት በዚህ አግባብ የሚቀርበውን ምላሽ ከግራ ቀኙ ምስክሮች ቃል ጋር በመመዘን በህጉ
አግባብ የመሰለውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.343(1) መሰረት መልሰንለታል፡፡
3. በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በአፈፃፀም መዝገብ ቁጥር 294015 በተያዘው አፈፃፀም ላይ ነሀሴ 05 ቀን
2013 ዓም የተሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል፡፡
4. ግራ ቀኙ በሰበር ክርክሩ ምክንያት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ፡፡

ጉዳዩ ውሳኔ ስላገኘ መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ሄ/መ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መ.ቁ 212620

ቀን፡- 18/4/2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ከድር አልይ

ሱልጣን አባተማም

ዋዚሞ ዋሲራ

አመልካች፡ቾች- እነ አበበ ጨዶ /26 ሰዎች/ ጠበቃ ሲሳይ ገመቹ ቀረቡ

ተጠሪ፡/ዎች- እነ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ አስ/ፅ/ቤት /3 ሰዎች/

መዝገቡ ለዚህ ችሎት 10/12/2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ
ችሎት በመ/ቁ 35305 በ ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ
ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረበው ማመልከቻ
መነሻነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ትአዛዝ ሰጥተናል፡፡

ትዕዛዝ

ለክርክሩ ምክንያት የሆኑ ይዞታዎችን አመልካቾች 1987 ዓ.ም ጀምሮ በመያዝ ከ 26 ዓመት
በላይ ያለው መሆናቸው ተጣርቶ ከሚመለከተው አካላት መግለጫዎች ቀርቦ እያለ ከይዞታቸውና
ከንብረቶቻቸው በሚያፈናቅል ሁኔታ እንድለቁ የተወሰነበትን አግባብ
የፌ/ጠ/ፍ/ቤትሰበርሰሚችሎት በመ/ቁ 37391፣ 47252፣107217፣77983፣37184፣33945
ከሰጠው የሕግ ትርጎሞች እና መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርሆች እንዲሁም ከክልሉ የገጠር
መሬት አዋጅ ጋር በማገናዘብ

መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ ብለናል፡፡

1.መጥሪያ ለተጠሪ/ዎች/ ይድረስ ብለናል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/2
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2. ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክራቸውን በሬጅስትራር ፅ/ቤት በኩል ይቀባበሉ፡፡

3. ቀጠሮ ለ 09/05/2014 ዓ.ም ተቀጥሮአል፡፡ 5፡00 ሰዓት

የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/2
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የመ/ቁ/212950
ህዳር 30/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ ሰለሞን አረዳ

እትመት አሰፋ

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡ አቶ ቶቼኖ ቶማ

ተጠሪ፡ የደቡብ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጠቷል፡፡

ፍርድ

ጉዳዩ የውንብድና ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በአመልካች ላይ
የወንጀል ህግ አንቀፅ 670 ድንጋጌን ጠቅሶ በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ
ነው፡፡ የክሱም ይዘት አመልካች የተጠቀሰውን የወንጀል ህግ ድንጋጌን በመተላለፍ የማይገባውን
ብልፅግና ለራሱ አልያም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በክሱ ዝርዝር ውስጥ በተገለፀው ቀን፣ ቦታ እና
ሰዓት የግል ተበዳይ ወደሆኑት ወ/ሮ አበበች ባደቦ የንግድ ቤት በመሄድ የተበዳይን ጉረሮ አንቆ
በመያዝ አንገታቸው ላይ የነበረ የዋጋ ግምቱ ብር 50,000(ሃምሳ ሸህ) የሚያወጣ 20 ግራም የወርቅ
ሀብል፤ እንዲሁም ባንኮኒ ውስጥ የነበረውን ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ወስዶ በጓሮ በኩል ያመለጠ በመሆኑ
የውንብድና ወንጀል ፈፅሟል የሚል ነው፡፡

አመልካች ለዚሁ ክስ በሰጠው መልስ ድርጊቱን እና ጥፋተኝነቱን ክዶ በመከራከሩ የዐቃቤ ህግ


ምስክሮች ቀርበው እንዲሰሙ ከተደረገ በኋላ እንደክሱ አቀራረብ አስረድተዋል በሚል አመልካች ክሱን
እንዲከላከል ታዟል፡፡ አመካችም አራት መከላከያ ምስክሮችን አሰምቷል፡፡ የመከላከያ ምስክሮቹም
አመልካች እና የግል ተበዳይ ባል አና ሚስት የነበሩ መሆኑን፤ ክስ የቀረበበት ድርጊት ተፈፀመ ከተባለ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኋላ በዚያው ጉዳይ ሁለቱን ለማሸማገል ሽምግልና ተቀምጠው የነበረ መሆኑን፤ በዚሁ ጊዜ የግል
ተበዳይን ስለድርጊቱ ሲጠይቋቸው አመልካች ንብረት ዘርፎኛል በሚል የከሰሷቸው ዘወትር ሰክሮ እየሄደ
ስለሚረብሻቸው እንጂ የተወሰደባቸው ንብረት እንደሌላ የነገሯቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩን
የያዘው ፍርድ ቤትም ለጉዳዩ አወሳሳን ይረዳኛል በማለት የሽማግሌዎቹ ሰብሳቢ የነበሩትን ፓስተር
ታደሰ ታንቱ የተባሉትን ግለሰብ አስቀርቦ ሰምቷል፡፡ ተጨማሪ ምስክሩም አመልካች እና የግል ተበዳይ
ባልና ሚስት መሆኑቻውን፤ ክስ የቀረበበት ጉዳይ ተፈፀመ ከተባለ በኋላ የሁለቱን ጉዳይ በሽምግልና
የተመለከቱ መሆኑን፤ በሽምግልናው ላይም የግል ተበዳይ በእርግጥም ዝርፊያ ተፈፅሞባቸው እንደሆን
በሚል የጠየቋቸው መሆኑን፤ ተበዳይም አመልካች ዘወትር ሰክሮ ንግድ ቦታቸው እየሄደ ስለሚረብሻቸው
ለመከላከል በሚል የከሰሷቸው እንጂ የተፈፀመባቸው ውንብድና እንደሌለለ የነገሯቸው መሆኑን
ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙ ክርክር መርምሮ እና የቀረቡትን ማስረጃዎች መዝኖ የዐቃቤ ህግ
ክስ እና ማስረጃ ተስተባብሏል በሚል አመልካችን ከቀረበባቸው ክስ በነፃ አሰናብቷል፡፡ ይህንኑ ውሳኔ
በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካች በመከላከያ
ማስረጃው ያስመሰከረውን ፍሬ ነገር አስምልክቶ በዋናው ክርክር ወቅት በመስቀልኛ ጥያቄ ያስተባበለው
ነገር የለም፤ ከተበዳይ ጋር ተደርጓል የተባለውን የእርቅ ስምምነት አስምልክቶም በጽሑፍ የቀረበ
የእርቅ ስምምነት የለም፤ የድርጊቱ አፈፃፀምም አመልካች ከግል ተበዳይ ጋር የነበረው ጋብቻ ከተቋረጠ
በኋላ ጉልበቱን በመጠቀም ለማስቀጠል ፍላጎት ያለው መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ድርጊቱ ከውንብድና
ወንጀል ይልቅ በማስገደድ መጠቀም ወንጀልን የሚያቋቁም ነው በማለት ክስ የቀረበበትን አንቀፅ ወደ
አንቀፅ 713 በመቀየር አመልካችን ጥፋተኛ ብሎት በ1 ዓመት ከ2 ወር ቀላል እስራት እና በብር
2,000(ሁለት ሺህ) የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ አመልካች ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለክልሉ
ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች ነሓሴ 14/2013 ዓ.ም በተፃፈ
የሰበር አቤቱታ በክልሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስሀተት
ጠቅሶ በዚህ ችሎት እንዲታረምለት ጠይቋል፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ያስቀርባል
በመባሉ ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዲከራሩ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ችሎቱም አመልካች
የዐቃቤ ሀግ ክስ እና ማስረጃን አላስተባበለም በሚል በወንጀል ህግ አንቀፅ 713 ስር ጥፋተኛ ተብሎ
የመቀጣቱን አግባብነት በወንጀል ጉዳት ተከሳሽ የሆነ ሰው በመከላከያ ማስረጃው ማስረዳት
ከሚጠበቅበት የማስረዳት ደረጃ አኳያ መርምሯል፡፡

በወንጀል ጉዳይ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ አስረድቷል የሚባለው ባቀረባቸው ማስረጃዎች ክሱን በቂ


እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ሲያስረዳ እንደሆነ የወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 141 ይደነግጋል፡፡
በወንጀል ክሱ ተከሳሽ የሆነው ሰውም የቀረበበትን ክስ አስምልክቶ ማስተባበያ ማስረጃ እንዲያቀርብ
የሚታዘዘው ይኸው ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ከወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 141 እና 142 ድንጋጌዎች
መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አንድ ሊነሳ እና መልስ ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ “በወንጀል
የተከሰሰ ሰው በመከላከያ ማስረጃው ማስረዳት/ማረጋገጥ/ የሚጠበቅበት የማስረዳት ደረጃ ምን ያክል
ነው?” የሚለው ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ በወንጀል ተከስሶ ክሱን እንድከላከል ከተነገረው ተከሳሽ
የሚጠበቀው ዐቃቤ ህግ ባስረዳው ልክ በመከላከያ ማስረጃው በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልሉ መረጋገጥ
ነው ወይስ የዐቃቤ ሀግ ማስረጃ ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ማድረግ ነው እንደማለት ነው፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

እንግዲህ ከላይ እንደተመለከተው በወንጀል የተከሰሰ ሰው መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ የሚታዘዘው


በዐቃቤ ህግ ማስረጃ የተረጋገጠበትን ክስ እና ማስረጃን እንዲያስተባብል ነው፡፡ ማስተባበል ማለት
ደግሞ የተከሳሹን የወንጀል ድርጊት እና ጥፋተኝነት አረጋግጠዋል በተባሉት ማስረጃዎች ላይ በአንድም
ይሁን በሌላ መንገድ ጥርጣሬ እንዲፈጠር በማድረግ በማስረጃዎቹ የማስረዳት አቅም ላይ መተማመን
እንዳይኖር ማድረግ ስለመሆኑ ከማስረጃ ህግ መሰረተ ሀሳብ እና በዚሁ ዙሪያ ከተደረጉ የምርምር
ፅሁፎች የምንረዳው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከተከሰሰው ሰው የሚጠበቀው በመከላከያ ማስረጃው በቂ
እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን የዐቃቤ ሀግ ማስረጃን አስመልክቶ ቀድሞ በተያዘው አቋም
ላይ ጥርጣሬን መፍጠር ብቻ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ ዐቃቤ ህግ ክሱን ለማረጋገጥ ያቀረበው የሰው ምስክር ብቻ ነው፡፡ ቀርበው
የተሰሙት የዐቃቤ ህግ ምስክሮችም እንደ ክሱ አቀራረብ አመልካች በግል ተበዳይ ላይ የውንብድና
ወንጀል ሲፈጽም መመልክታቸውን ተናገረዋል፡፡ ሆኖም አመልካች ከተከሰሰበት የወንጅል ድርጊት ጋር
በተያያዘ በአመልክች እን የግል ተበዳይ መካከል ሽምግልና ተቀምጠው የነበሩት የአመልካች መከላከያ
ምስክሮች እና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማጣሪያ ምስክርነት የተሰሙት ሽማግሌዎቹ ሰብሳቢ የግል
ተበዳይዋ በሽምግልናው ላይ አመልካችን በወንጀል የከሰሷችው ዘወትር ሰክሮ በመሄድ ስለሚረብሻቸው
እንጂ የፈፀመባቸው የወንብድና ድርጊት እንደሌለ የነገሯቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡ በእንዚህ
አሸማጋይ ሽማግሌዎች ይህ ሁኔታ መረጋገጡ ቀድሞ በተሰሙት የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የምስክርነት
ቃል ላይ ጥርጣሬ እንዲኖር የሚያደርግ ነው፡፡

ጉዳዩ ይህ ሆኖ እያለ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአመልካች እና የግል ተበዳይ መካከል ተደርጓል
የተባለው የእርቅ ስምምነት በፅሁፍ አልቀረበም፤ እንዲሁም አመልካች በመከላከያ ማስረጃው
ያረጋገጠውን ፍሬ ነገር በመስቀልኛ ጥያቄ አልጠየቀም በሚል ምክንያት የአመልካችን መከላከያ
ማስረጃ ውድቅ ማድረጉ የቀረበው ጉዳዩ የወንጀል ክርክር መሆኑን እና በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ
የሚጠበቅበትን የማስረዳት ደረጃ ያላገናዘበ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ
1. የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/34748 ላይ ግንቦት 04/2013 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ
እና ይህንኑ ውሳኔን በማፅናት የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/36060 ላይ ነሐሴ
04/2013 የሰጠው ትዕዛዝ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁር 195(2(ለ(2))) መሰረት
ተሽሯል፡፡

2. የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/46898 ላይ ታህሳስ 19/2013 ዓ.ም በዋለው


ችሎት አመልካችን ከተከሰሰበት ወንጀል ነፃ በመልቀቅ የሰጠው ውሳኔ በወንጀል ህግ
ሥነ ሥርዓት ቁጥር 195(2(ለ(2))) ፀንቷል፡፡
ትዕዛዝ

1. አመልካች በዚህ መዝገብ ላይ ከተከሰሰበት ወንጀል በነፃ የተሰናበተ በመሆኑ


በሌላ ወንጀል የማይፈለግ መሆኑን አረጋግጦ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀው
ለሚገኝበት ማረሚያ ቤት ይፃፍ፡፡

2. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበርመ.ቁ.-213330

ቀን፡- ታህሳስ 13/2014 ዓ/ም

ዳኞች፡- ሸምሱ ሲርጋጋ

አለማየሁ ሹናራ

ደረጀ አያና

አመልካች/ቾች/ ፡- እነ ወ/ሮ ማርታ በቀለ /2 ሰዎች/ ጠበቆች በሻዳ ገመቹ - አብርሃ አሽ / ቀረቡ

ተጠሪ/ዎች/፡- እነ አቶ ሚልኪያስ መንገሻ /2 ሰዎች/

መዝገቡ ተከፍቶ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው አመልካች /ቾች/ ነሐሴ 21 ቀን /2013 ዓ.ም በተፃፈ
ማመልከቻ በ ፌደራል ጠቅላይ /ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.199317 በ ግንቦት 25 ቀን 2013
ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት አለበት በመግለፅ በሰበር ታይቶ እንዲታረምላቸው በሚል የቀረበ
ነው፡፡ በመሆኑም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ት እ ዛ ዝ

1. የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ያቀረቡትን የወራሽነት ማስረጃ ውጫዊ ዜጋ ስለሆኑ በአ/ቁ
922/2008 አንቀፅ 6/1/ መሰረት ስልጣን ባለው የኢትዮጲያ ቆንስላ ፅ/ቤት ተረጋግጦ ያልቀረበ
መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ተጠሪዎች ወራሽ አለመሆናቸውን አመልካቾች አልካዱም በማለት ክስ
ለማቅረብ መብትና ጥቅም አላቸው ሲል የወሰነበት አግባብነት ከአ/ቁ 922/2008 አንቀፅ 6/1/ እና
ከፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር መ/ቁ 32282 አንፃር መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩለ ሰበር ሰሚ
ችሎት ይቅረብ ብለናል፡፡
2. የትዕዛዝ ግልባጭ ከመጥሪያ ጋር ለተጠሪዎች ደርሷቸው መልስ እና የመልስ መልስ በሬጅስትራር ፅ/ቤት
በኩል ይቀባበሉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ1/2
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መልስ ለመቀበል ለ 05/05/2014 ተቀጠረ፡፡ 9፡00

የማይነበብ የሦስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ገጽ2/2
ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 214108

ቀን፡- 15/4 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ተፈሪ ገብሩ/ዶ/ር

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሣ ወርቁ

ደጀኜ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካቾች፡- እነ ወ/ሮ ገነት ቶላ /2 ሰዎች/ አልቀረቡም

ተጠሪ/ዎች፡- እነ አቶ ብርሃኑ ቶላ /2 ሰዎች/ 2ኛ ተጠሪ ቀረቡ

መዝገቡ ለችሎት የቀረው 2ኛ ተጠሪ ወ/ሮ ኤልሳቤት አንበርብር ህዳር 27 ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ
አቤቱታ በዚህ ሰበር ችሎት በክርከር ላይ የምንገኘው በጋራዥ ቤቱ ላይ ሆኖ እያለ በመኖሪያ ቤት
ላይ ጨምሮ እግድ የተሰጠበት በመሆኑ ከመኖሪያ ቤቱ ላይ እግድ እንዲነሳልት ስትል
አመልክታለች፡፡ የአሁን አመልካቾችም መልስ እንዲሰጡበት ተደርጎ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም
በተፃፈ መልስ የአፈፃፀም እግድ የተሰጠው በሚያከራክረን ንብረት ላይ በመሆኑ እግዱ ሊነሳ
አይገባም ብለዋል በዚሁ መሰረት ተከታዩ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ትዕዛዝ

በዚህ መዝገብ መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአፈፃፀም
መዝገብ ቁጥር 162907 ላይ እግድ ተሰጥቷል፡፡ እግዱ የተሰጠው አሁን ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው በንፋስ
ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ አዋሳኙ በሰሜን አቶ መሀመድ፣ አቶ ገመቹ፣ አቶ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መለስ፣ በምዕራብና በምስራቅ መንገድ፣በደቡብ ከድር ሁሰኔን የሚያዋስኑት ጋራዥ ቤት ላይ ብቻ ሳይሆን


የአፈፃፀም መዝገቡ ላይ በመሆኑ በሌሎች ንብረቶች ላይ እየተደረገ ያለ አፈፃፀም ካለ አፈፃፀሙን የሚከለክል
መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በመሆኑም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአፈፃፀም መዝገብ ቁጥር 162907
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ አዋሳኙ በሰሜን አቶ መሀመድ፣ አቶ
ገመቹ፣ አቶ መለስ፣ በምዕራብና በምስራቅ መንገድ፣ በደቡብ ከድር ሁሰኔ የሚያዋስኑት ጋራዥ ቤት ላይ
የተሰጠው የአፈፃፀም እግድ እንዲቀጥል ብለናል፡፡ በሌሎች ንብረቶች ላይ እየተደረገ ያለ አፈፃፀም ካለ በዚህ
ችሎት መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ.ም የተሰጠው እግድ ተሻሽሎ ከሌሎቹ ንብረቶች ላይ የተሰጠው እግድ
ተነስቷል፡፡ ይፃፍ መደበኛ ቀጠሮ አልተለወጠም፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የሰ/መ/ቁ. 214192

ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካቾች- 1. አቶ ግርማ አንቂቶ- ቀርበዋል

2. አቶ ዳንኤል ባልካቸው- ቀርበዋል

3. አቶ ኃይሉ ታደሰ- ቀርበዋል

4. አቶ እንዳካቸው መኮንን- ቀርበዋል

ተጠሪ- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ- ፅጌ ካሳ -
ቀርበዋል

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ ር ድ

ጉዳዩ በአስተዳደር አካል የወጣ መመሪያ አግባብነት በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ
ቁጥር 1183/2013 መሠረት እንዲከለስ የቀረበ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

የአመልካቾች ክስ ይዘትም በአጭሩ በታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በፌደራል ደረጃ ባወጣው


የመምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ስፐርቫይዘሮች የስራ መደብ ድልድል አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር
2/2012 መሠረት በተደረገ ጂ.ኤ.ጂ ጥናት አንቀጽ 9 መሠረት ከነበርንበት ደረጃ ያለ ውድድር
ከሐምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተመድበን በመስራት ላይ እያለን የመመሪያውን አንቀጽ 17
ድንጋጌ በሚቃረን መልኩ በነሐሴ 2012 ዓ.ም በወጣ አዲስ መመሪያ በተመደብንበት የስራ መደብ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ላይ አዲስ ውድድር ተደርጎ ሌሎች ሰዎች እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡ በጂ.ኤ.ጂ ምደባ የተሰጣቸው
ርዕሰ መምህራንን ከምደባቸው ላይ ለማንሳት የሚያስችል የተደረገ ጥናት በሌለበት የተሰጠው አዲስ
ምደባ የህግ መሠረት የለውም፡፡ ህግ ወይም መመሪያ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለው መርህ
እንዳለ ሆኖ በጂ.ኤ.ጂ የተሰጠው ምደባ በአዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም መሠረት ተሠርዟል እንኳን
ቢባል አመልካቾች በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ተመሳሳይ ደረጃ ወዳለው የስራ መደብ ልንመደብ ሲገባ
ለምደባው ውድድር እንዲኖር መደረጉ የመመሪያ ጥሰት ነው፤ መስሪያ ቤቱ ያወጣው መመሪያም
በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ የተመለከቱትን የስነ-ስርዓት
ድንጋጌዎች ያልተከተለና ከበላዩ ካሉ ሌሎች ህጎች ጋር የሚቃረን ሲሆን በድልድል ስም የተደረገው
ውድድርም የኮሚሽኑን መመሪያ የሚጥስ በመሆኑ መመሪያ እና ውድድሩ ተሽሮ ከሐምሌ 1 ቀን
2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተመደብንበት የስራ መደብ እንድንመለስ እንዲሁም ካሳ በቁርጥ ይወሰንልን
በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተጠሪ በበኩሉ በሰጠው መልስ ፍርድ ቤቱ ክሱን ለማየት ስልጣን የለውም የሚል
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም በፍሬ ነገሩ ላይ በሰጠው መልስ ነሐሴ 2012 ዓ.ም
ባወጣነው መመሪያ በአዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 19 መሠረት የወጣ ስለሆነ ተገቢነት ያለው
ነው፤ የአመልካቾች ቅሬታ ሊፈታ የሚችለው በመመሪያው ውስጥ ባሉ የቅሬታ መፍቻ መንገዶች
እንጂ መመሪያውን በማሻሻል አይደለም፤ ድልድሉ የተካሄደው የከተማው ትምህርት ቢሮ
የትምህርት ቤት ተቋማዊ አደረጃጀት ጥናት በተጠሪ ሙያዊ ድጋፍ ሲካሔድ ቆይቶ ቢሮው ጥናቱ
እንዲፀድቅለት በቀን 22/03/2012 ዓ.ም ለተጠሪ ጥያቄ አቅርቦ የጥናቱ ሰነድ በቀን 25/03/2012
ዓ.ም ከፀደቀ በኋላ በመሆኑ መመሪያን የተከተለ ነው፤ መመሪያውም ሆነ ምደባው የህግ ጥሰት
የሌለባቸው ሲሆን አለባቸው እንኳን ቢባል የአመልካቾች ቅሬታ በቀን 08/12/2012 ዓ.ም በወጣው
መመሪያ ላይ የተመለከቱትን የቅሬታ አፈታት ስርዓቶች ተከትለው ሊያቀርቡ ይገባል እንጂ ክስ
ሊያቀርቡ አይገባም በማለት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ
በኋላ አመልካቾች ነሀሴ 2012 ዓ.ም የወጣው መመሪያ የበላይ ከሆኑ ህጎች ጋር ይቃረናል የሚሉት
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ያወጣውን መመሪያ ሲሆን ይህ መመሪያ በራሱ መመሪያ
ከመሆኑ አንፃር ነሐሴ 2012 ዓ.ም የወጣው መመሪያ በእርከን ከመመሪያ በላይ ከሆኑ ሌሎች ህጎች
ጋር አይቃረንም፤ ይህ መመሪያ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
ያልተመዘገበ እና በተጠሪ ተቋም ድህረ-ገጽ ላይ ያልተጫነ በመሆኑ በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት
አዋጅ ቁጥር 1183/12 አንቀጽ 18 መሰረት ተፈፃሚነት የሌለዉ አዲስ የመመሪያ አወጣጥ ስነ-
ስርዓትን ተከትሎ ተጠሪ መመሪያዉን እንደ አዲስ ሊያወጣ ይገባል ካለ በኋላ፣ አመልካቾች
ያቀረቡትን የካሳ እና የምደባ ይስተካከልልን ጥያቄን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል፡፡ አመልካቾች በዚህ
ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ውድቅ
ተደርጎባቸዋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

አመልካቾች በቀን 11/01/2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች
ተፈጽመዋል ያሏቸውን ስህተቶች በመዘርዘር በዚህ ችሎት እንዲታረሙላቸው ጠይቀዋል፡፡
የአቤቱታቸዉ ይዘትም በአጭሩ በታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም የወጣው የመምህራን፣ ርዕሰ መምህራን
እና ሱፐርቫይዘሮች የስራ መደብ ድልድል አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2012 መሠረት በተደረገ
የጂ.ኤ.ጂ ጥናት ያለውድድር ከሐምሌ 01 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ብንመደብም ተጠሪ መስሪያ ቤት
በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ያወጣው የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመሠረታዊ
የስራ ሂደት ለዉጥ ትግበራ የትምህርት ቤቶች አመራሮች የድልድል አፈፃፀም መመሪያ ያወጣ
ሰሲሆነ ይህም መመሪያ የከተማ አስተዳደሩን ቻርተር፣ የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 25 እና 37
‘ን’ የሚቃረን እና በፌደራል አሰተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ 1183/2012 ከአንቀጽ 12 እስከ 19 ላይ
የተቀመጠውን ስነ-ስርዓት ሳይከተል የወጣ ነው፤ የስር ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ ግንዛቤ በመውሰድ
መመሪያ ተፈፃሚነት እንዳይኖረው ቢያደርጉም ውጤቱን በሚመለከት መመሪያውን መሠረት
አድርጎ የተፈፀመው ውድድር እና ምደባ አንዲቀርና ወደ ቀደመው መደባችን እንድንመለስ
ያቀረብነውን ጥያቄ በዝምታ ማለፉቸው መሠረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል
የሚል ነው፡፡

ጉዳዩም በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ ህጋዊ ተፈፃሚነት የለውም በተባለ መመሪያ
የተሰጠ አስተዳደራዊ ውሳኔ ቀሪ ሊሆን አይገባም ተብሎ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ
አግባብነት አጣርቶ ለመወሰን ሲባል ያስቀርባል ተብሏል፡፡ በዚሁም መሠረት ተጠሪ መልስ
እንዲሰጥበት ተደርጎ በቀን 06/03/2014 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ በፌደራል አስተዳደር ስነ-
ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 57(1) መሠረት ፍርድ ቤት አንድን የአስተዳደር መመሪያ
ከመሻሩ በፊት በተሻረው መመሪያ መሰረት የተሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች እንደፀኑ እንደሚቆዩ
የሚደነግግ በመሆኑ አመልካቾች ውሳኔው ተሽሮ ወደ ስራችን እንድንመለስ ይወሰንልን በማለት
ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢነት የለውም፤ አመልካቾች በመመሪያው ይዘት ላይ ያላቸውን ቅሬታ
በሚመለከት በመመሪያው ከአንቀጽ 16 እስከ 21 ድረስ በተቀመጠው ስርዓት ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ
ማቅረብ ከሚችሉ በስተቀር ለፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ አይችሉም፤ የህገ-መንግስቱን አንቀጽ 25
በመጥቀስ የእኩልነት ጥያቄን ያነሱበት መከራከሪያ በስር ፍርድ ቤቶች ያልቀረበ በመሆኑ በዚህ
ደረጃ ሊቀርብና ሊስተናገድ አይችልም በማለት ተከራክሯል፡፡ አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን
በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

ከስር ጀምሮ የጉዳዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ሲታይ
ከፍ ሲል የተመለከተዉን ሲመስል ይህ ችሎትም የአመልካችን የሠበር አቤቱታ በሰበር አጣሪ
ከተያዘው ጭብጥ፣ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር
በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡ እንደመረመረዉም አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት
ባቀረቡት ክስ ለጠየቁት ዳኝነት መሠረት ያደረጉት ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 ላይ
በተመለከተዉ አግባብ ሥነ ሥርዓቱን ጠብቆ ያልወጣ እንዲሁም ከሌሎች አዋጆች እና በፌዴራል
ደረጃ የወጣዉን መመሪያ የሚቃረን ሌላ መመሪያ ስራ ላይ በማዋል ቀደም ሲል በነበረዉ መመሪያ
መሰረት ያለዉድድር ተመድበንበት የነበረዉን ቦታ አስለቅቆን ሌሎች ሠራተኞችን የመደበ መሆኑን

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ሲሆን፣ የጠየቁት ዳኝነትም ሥርዓቱን ሳይጠብቅ ተግባራዊ የተደረገዉ መመሪያ እንዲከለስ እና


መመሪያዉን መሠረት በማድረግ የተደረገዉ ምደባም እንዲሰረዝ የሚል ነዉ፡፡

የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣዉ አዋጅ ቁጥር 1183/2012


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞኪራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት እና ተጠሪነታቸዉ ለፌዴራል መንግስት
የሆነዉ አስፈፃሚ አካላት የሚያወጧቸዉ መመሪያዎች መከተል ያለባቸዉን መርሆዎች እና
ሥርዓቶች፣ አንድ መመሪያ ተገቢዉን ሥርዓት ተከትሎ አልወጣም የሚል ማንኛዉም ጉዳዩ
የሚመለከተዉ ሰዉ መመሪያዉ እንዲከለስ ዳኝነት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ
እንደሚችል እና የዳኝነት ጥያቄዉ የቀረበለት ፍርድ ቤት የሚሰጠዉ ዉሳኔ ወሰኑ እስከምን ድረስ
አንደሆነ ይደነግጋል፡፡ አዋጁ እነዚህንና መሰል ድንጋጌዎችን እንዲያካትት የተደረገበት ምክንያትም
የሚመለከተዉ የአስፈፃሚ አካል የሚያወጣዉ መመሪያ ግልጽ የሆኑ ሥነ ሥርዓቶችን ተከትሎ
እንዲወጣ እና ይህን ሥርዓት ተከትሎ ያልወጣ ከሆነ ከነግድፈቱ ተፈፃሚ ሆኖ እንዳይቀጥል
በማድረግ መንግስታዊ አሠራር ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲከናወን እና በመመሪያዎች
አወጣጥ መርሆዎች እና ሥነ ስርዓት ላይ ቅሬታ ያለዉ ሰዉ የመመሪያዎቹን ህጋዊነት በፍርድ
ቤት የሚያስመረምርበት ሥርዓትን በመደንገግ አስተዳደራዊ ፍትሕ ማስፈን ነዉ የሚለዉን
የአዋጁን አንዱ ዓላማ ገቢራዊ ለማድረግ እንዲቻል ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ አመልካቾች
መመሪያዉ እንዲከለስ ዳኝነት የጠየቁትም በዚሁ መነሻነት ሲሆን፣ ከፍ ሲል እንደተገለጸዉ ጉዳዩ
የቀረበለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካቾች ሥርዓቱን ሳይጠብቅ የወጣ ነዉ የሚሉት መመሪያ
እንዲከለስ የወሰነ ሲሆን መመሪያዉን መሠረት በማድረግ የተደረገ ምደባ ግን ሊሰረዝ አይገባም
በሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

በበኩላችንም እንደተመለከትነዉ ስለ ክለሳ ዉሳኔ አሰጣጥ እና አፈፃፀም የሚደነግገዉ የአዋጁ


ክፍል አራት ንዑስ ክፍል አራት የዉሳኔ አሰጣጥ በሚለዉ አንቀጽ 56 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 ላይ
የክለሳ አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት የሚመለከተዉ የአስተዳደር አካል ያወጣዉን መመሪያ ሊያጸና
ወይም በሙሉ ወይም በከፊል መሻር እንደሚችል እና መመሪያዉን በሙሉ ወይም በከፊል የሻረ
እንደሆነ የሚመለከተዉ የአስተዳደር አካል መመሪያዉን እንደገና እንዲያወጣ ወይም እንዲያሻሽል
ማዘዝ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ስለ ክለሳ ዉሳኔ አፈፃፀም በሚያወራዉ አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 3
ስር የክለሳ አቤቱታ የቀረበበት መመሪያ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲሻር ከተደረገ በዚያዉ ልክ
መመሪያዉ ህጋዊ ኃይል እንደማይኖረዉ በመርህ ደረጃ የሚደነግግ ሲሆን፣ የመመሪያዉ በከፊል
ወይም በሙሉ መሻር የአስተዳደር ተቋሙ መመሪያዉ ከመሻሩ በፊት በተሻረዉ መመሪያ መሰረት
የሰጣቸዉ አስተዳደራዊ ዉሳኔዎቹ እንደጸኑ እንደሚቀሩ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ በግልጽ
ተመልክቷል፡፡ ከዚህም የምንረዳዉ በአዋጁ ላይ የተመለከተዉን የመመሪያ አወጣጥ ሥርዓትን
ተከትሎ አልወጣም በሚል መብት ባለዉ ሰዉ የቀረበለትን የክለሳ አቤቱታ በመቀበል የፌዴራል
ከፍተኛ ፍርድ ቤት መመሪያዉ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲሻር በሚል የሚሰጠዉ ዉሳኔ ዉጤቱ
ዉሳኔዉ ከተሰጠ በኋላ የተሻረዉን መመሪያ መሠረት በማድረግ የአስተዳደር አካሉ የሚሰጠዉ
ዉሳኔ ዋጋ እንዳይኖረዉ የሚያደርግ ሲሆን፣ መመሪያዉ ከመሻሩ በፊት በሚመለከተዉ የአስተዳደር
አካል በተሻረዉ መመሪያ መሰረት የተሰጠዉን አስተዳደራዊ ዉሳኔ ዋጋ እንዲያጣ ወይም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተፈፃሚነት እንዳይኖረዉ የማድረግ ዉጤት የሌለዉ መሆኑን ነዉ፡፡ ይህም የሚያሳየዉ ማንኛዉም
ሰዉ ተገቢዉን ሥርዓት ተከትሎ አልወጣም የሚለዉ መመሪያ በፍርድ ቤት እንዲከለስ ዳኝነት
ለመጠየቅ መብት ያለዉ ቢሆንም (የአዋጁ አንቀጽ 46/1/ ይመለከቷል)፣ ይህ መብቱ አቤቱታ
በቀረበበት መመሪያ መሠረት በአስተዳደር አካሉ የተሰጠ ዉሳኔ እንዲሻር ጭምር መጠየቅን
የማያካትት መሆኑን ነዉ፡፡ ይልቁንም የአስተዳደር አካሉ መመሪያዉን መሠረት በማድረግ የሰጠዉ
ዉሳኔ መብቴን ይነካል የሚል ሰዉ መብቱን የሚያስከብረዉ እንደየጉዳዩ ዓይነት ለጉዳዩ አግባብነት
ባለዉ ህግ መሠረት የተዘረጋዉን የአቤቱታ አቀራረብ ሥርዓት መሠረት በማድረግ ቅሬታዉን
ስልጣን ላለዉ አካል በማቅረብ ሊሆን ይገባል፡፡ አዋጁ የመመሪያዉ መሻር ቀደም ሲል በመመሪያዉ
መሰረት የተሰጠዉን አስተዳደራዊ ዉሳኔ የመሻር ዉጤት እንደሌለዉ ከላይ በተመለከተዉ አንቀጽ
57(4) ላይ የደነገገበት አንዱ ምክንያት ሊሆን የሚችለዉም እንደየጉዳዩ ባህርይ አንድ የአስተዳደር
አካል በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ቅሬታ የሚቀርብበት አካል እና የአቀራረብ ሥርዓቱን በተመለከተ በሌሎች
ህጎች ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንዲከበሩ እና የአንድ አስተዳደር አካል ዉሳኔ ህጋዊነት
በሁለት የተለያዩ አካላት ሊታዩ የሚችሉበትን ሁኔታ እንዳይኖር ለማድረግም ጭምር እንደሆነ
ይታመናል፡፡

በተያዘዉ ጉዳይ አመልካቾች በዚህ ችሎት ባቀረቡት ቅሬታ አጥብቀዉ የሚከራከሩት


መመሪያዉ ከተሻረ መመሪያዉን መሠረት በማድረግ የተደረገ ምደባም መብቴን የሚጎዳ በመሆኑ
ተሰርዞ ቀደም ሲል ያለዉድድር ተመድቤበት ወደ ነበረዉ ቦታ ልመለስ ይገባል በማለት ነዉ፡፡
በመሠረቱ ከስራ ምደባና ደረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያለዉ የመንግስት ሠራተኛ ቅሬታዉን
የሚያቀርብበትን ሥርዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር
56/2010 ይደነግጋል፡፡ የቅሬታ አቀራረብ ሥርዓቱ በልዩ ሁኔታ እንዲደነግግ የተፈለገበት
ምክንያትም ለቅሬታዎች አፋጣን መፍትሔ ለመስጠት፣ ለቅሬታዎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ
ስህተቶችንና ድክመቶችን የማረም እና ሁሉንም የመንግስት ሠራተኞች በእኩልነት ለማስተናገድ
የሚያስችል እና ፍትሐዊ የሆነ አሠራር በማስፈን የሰመረ የስራ ግንኙነት እንዲኖር በማሰብ
ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 75 ይዘት ያስገነዝባል፡፡ በዚህም መሠረት ከስራ ምደባ ጋር በተያያዘ
ቅሬታ ያለዉ ሠራተኛ ቅሬታዉን በቅድሚያ ለመስሪያ ቤቱ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታዉን ማቅረብ
እንዳለበት፣ ቅሬታ ሰሚዉ ኮሚቴ በሰጠዉ ፍርድ ቤት ላይ ቅሬታ ካለዉ ይግባኙን ለአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችል እና የአስተዳደር ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ የህግ ስህተት
አለዉ የሚል ከሆነም ቅሬታዉን ለአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በማቅረብ መብቱን
ማስከበር የሚችል ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 77(4)፣ 77፣ 81(1/ሠ) እና 81(5) ላይ ከተመለከቱት
ድንጋዎች መገነዝብ ይቻላል፡፡ ቅሬታዉ በዚህ መልኩ የሚቀርብለት ፍርድ ቤት ህግን የመተርጎም
ስልጣን ያለዉ በመሆኑ የምደባዉን አግባብነት ሲመረምር ቅሬታ የቀረበበት ምደባ ለጉዳዩ አግባብነት
ያለዉን ህግ መሠረት ያደረገ መሆን ያለመሆኑን ብቻ ሳይሆን ለምደባዉ መሠረት የሆነዉ መመሪያ
ስልጣን ባለዉ አካል ተገቢዉን ሥርዓት ጠብቆ የወጣ እና ከሌሎች የበላይ ህጎች (superior laws)
ጋር የሚጋጭ መሆን ያለመሆኑን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በመመርመር እና ትርጉም በመስጠት
የመመሪያዉን ህጋዊ ዉጤት ጭምር በማየት የምደባዉን ህጋዊነት መወሰን ይችላሉ፡፡ በተያዘዉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ጉዳይም አመልካቾች ምደባዉ መብታችን ይነካል የሚሉ ከሆነ ከፍ ሲል በተመለከተዉ አግባብ


ለሲቪል ሰርቪስ ፍርድ ቤት ብሎም ለአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቤቱታ ቢያቀርቡ
ኖሮ ፍርድ ቤቶቹ የምደባዉን ህጋዊነት ሲመረምሩ ለምደባዉ መሰረት የሆነዉ መመሪያ በአዋጅ
ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 6 እና ተከታዮቹ ላይ የተመለከቱትን የመመሪያ አወጣጥ ሥርዓቶችን
ተከትሎ የወጣ መሆን ያለመሆኑን ጭምር መርምረዉ የመመሪያዉን ህጋዊ ዉጤት ወስነዉ ይህን
መሰረት በማድረግም በምደባዉ ህጋዊነት ላይ ተገቢዉን መወሰን ይችሉ ነበር፡፡ በመሆኑም
አመልካቾች ከምደባ ጋር በተያያዘ በህግ የተዘረጋዉን ሥርዓት ተከትሎ ቅሬታቸዉን አቅርበዉ
መብታቸዉን ማስከበር እየቻሉ፣ በመመሪያ ክለሳ ዳኝነት ሰበብ አስቀድሞ በመመሪያ መሠረት
በተጠሪ የተሰጠዉ ምደባ እንዲሰረዝ የሚያቀርቡት መከራከሪያ ተቀባይነት ያለዉ ሆኖ አልተገኘም፡፡

በአጠቃላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነዉ መመሪያ በአዋጁ የተመለከተዉን ሥርዓት የተከተለ


አለመሆኑን አረጋግጦ መመሪያዉ እንዲሻር በማለት፣ በሌላ በኩል መመሪያዉን መሰረት በማድረግ
በተጠሪ የተደረገዉ ምደባ ሊሰረዝ አይገባም በማለት በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠ ዉሳኔ
በአዋጁ አንቀጽ 57(4) ላይ የተመለከተዉን ግልጽ ድንጋጌ ያገናዘበ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዚህ
ችሎት ሊታረም የሚችል መሠረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ለማለት የሚያስችል ህጋዊ
ምክንያት የለም፡፡ ስለሆነም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ዉሳኔ

1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 261985 ሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓ.ም


በወለዉ ችሎት የሰጠዉ ዉሳኔ እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር
209483 ሐምሌ 06 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት የሰጠዉ ትዕዛዝ
በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 348(1) መሠረት ጸንተዋል፡፡

2. በዚህ ችሎት የተደረገዉ ክርክር ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኝ የየራሳቸዉን


ይቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ

ማ/አ የማይነበብ የአምሰት ዳኞች ፊርማ አለበ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት
የመ.ቁ.215452
ህዳር 30/2014 ዓ.ም

ዳኞች፡ ሰለሞን አረዳ

እትመት አሰፋ

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሳዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡ ወልዳይ ገ/ማርያም

ተጠሪ፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ ገደብ የተደረገበትን ወይም ቁጥጥር የሚደረግበትን የውጭ ሀገር
ገንዘብ ይዞ መገኘት ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው የአሁን ተጠሪ የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 591/2000 አንቀፅ 26(1(ሀ(1))) እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ
አንቀፅ 346 ድንጋጌን ጠቅሶ በአሁን አመልካች ላይ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረበው
የወንጀል ክስ ነው፡፡ የክሱም ይዘት አመልካች የተጠቀሰውን ድንጋጌ በመተላለፍ ገደብ የተደረገበት
ወይም ቁጥጥር የሚደረግበት የውጭ ሀገር ገንዘብ መሆኑን እያወቀ በዲኪላራሲዮን ያልተመዘገበ
5,000(አምስት ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ይዞ ህዳር 17/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ በመገናኛ
ባቡር ፌርማታ ባቡር ሊሳፈር ሲል በወቅቱ በነበሩት የፀጥታ ኃይሎች በተደረገ ፍተሻ የተያዘ በመሆኑ
የውጭ ሀገር ገንዘብ አከማችቶ ይዞ መገኘት ወንጀል ፈፅሟል የሚል ነው፡፡

አመልካች ለዚህ ክስ በሰጠው መልስ ድርጊቱን አምኖ በአፈፃፀም ረገድ ጥፋተኝነቱን ክዶ የተከራከረ
በመሆኑ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲቀርቡ ተደርጎ ሁለት ምስክሮች ተሰምተዋል፡፡ የቀረቡት
ምስክሮችም ድርጊቱ ተፈፀመ በተባለበት ቀን የፍተሻ ስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ ባልደረቦች መሆናቸውን
ገልፀው በክሱ ውስጥ የተጠቀሰውን መጠን የአሜሪካን ዶላር በአመልካች እጂ ማግኘታቸውን፤
ከ3,000(ሶስት ሺህ) በላይ የሆነ የአሜሪካን ዶላር ይዞ የሚንቀሳቀስ ሰው ካገኙ በቁጥጥር ስር እንዲያውሉ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከመስሪያ ቤታቸው በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት አመልካችን ከእነ ገንዘቡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ
የወሰዱት መሆኑን በመናገራቸው አመልካች ክሱን እንዲከላከል ተደርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት አመልካች ሁለት መከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል፡፡ የቀረቡት ምስክሮችም
በክሱ ውስጥ የተጠቀሰውን ገንዘብ ማህደር ትዕዛዙ የተባሉት ግለሰብ ከኩዌት ሀገር ለእናታቸው ህክምና
ወጪ እንዲውል ወ/ሮ አልማዝ ግደይ በተባሉት ግለሰብ በኩል ወደ ሀገር ቤት ልከው አመልካች
ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በቦሌ አየር ማረፊያ ገንዘቡን ከወ/ሮ አልማዝ የተቀበሉ መሆኑን እንደሚያውቁ
ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃን ከመረመረ በኋላ በሰጠው ውሳኔ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር FXD/49/2017 አንቀፅ 4.1(ለ) መሰረት
ከ3,000(ሶስት ሺህ) ዶላር በላይ ይዞ ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር የሚገባ ሰው ዶላሩን ዲኪሌር ማስደረግ
የሚገባው ስለመሆኑ የተደነገገ ቢሆንም ክስ የቀረበበት ገንዘብ ዲኪሌር ያልተደረገ መሆኑን
ተረጋግጧል፤ አመልካች ገንዘቡን በአደራ ከሌላ ግለሰብ የተቀበሉ ስለመሆኑ በመከላከያ ማስረጃቸው
ያስመሰከረ ቢሆንም ገንዘቡን ሲቀበሉ ዲክሌር ስለመደረጉ ያረጋገጠው ነገር ባለመኖሩ ህግን ያለማወቅ
ከህግ ተጠያቂነት የሚያስመልጥ አይደለም፤ ገንዘቡን ተቀብልኩ ያለውም ጥቅምት 30/2013 ሆኖ እያለ
በእጁ እስከተያዘበት ህዳር 17/2013 ዓ.ም ድረስ ይዞ መቆየቱ ገንዘቡን መደበቁን የሚያሳይ በመሆኑ
ይዞ መገኘቱ ብቻ ጥፋተኛ ያደርገዋል በሚል ምክንያት የአመልካችን መከራከሪያ ውድቅ አድርጎ ክስ
በቀረበበት አንቀፅ ስር ጥፋተኛ ብሎት በ3/ሶሰት/ ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 10,000(አስር ሺህ
ብር) የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኖ ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን አዟል፡፡ በዚሁ ውሳኔ ላይ
ይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት
ቁጥር 195(1) መሰረት ሰርዟል፡፡

የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ነው፡፡ አመልካች ጥቅምት 17/2014 ዓ.ም
በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ተፈፅሟል ያለውን መሰረታዊ የህግ ስህተት
ጠቅሶ በዚህ ችሎት እንዲታረምለት ጠይቋል፡፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ የስር ፍርድ
ቤት አመልካችን ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ውሳኔ የሰጠበት አግባብነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብር
እና የውጭ ምንዛሪ አያያዝን በተመለከተ ካወጣው መመሪያ ቁጥር 49/2017 አንቀፅ 3 አኳያ በዚህ
ችሎት እንዲመረመር በመታዘዙ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር እንዲለዋወጡ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት በአጭሩ ይህንን ሲመስል ችሎቱም የግራ ቀኙን ክርክር ጉዳዩ
ለዚህ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ማስቀረቢያ ነጥብ አኳያ አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ
መርምሯል፡፡

አመልካች የተከሰሰው ገደብ የተደረገበት ወይም ቁጥጥር የሚደረግበት የውጭ ሀገር ገንዘብ መሆኑን
እያወቀ በዲኪላራሲዮን ያልተመዘገበ 5,000(አምስት ሺህ) የአሜሪካን ዶላር ይዞ ተገኝቷል በሚል ነው፡፡
አመልካች የተጠቀሰውን ገንዘብ ይዞ መገኘቱን አይክድም፡፡ ከዚህ ይልቅ እየተከራከረ ያለው ገንዘቡን
ለሌላ ሰው በሚል ከውጭ ሀገር በእኔ በኩል በአደራ ተልኮ የተቀበልኩት ነው በሚል ነው፡፡ አመልካች
አቅርቦ ያሰማቸው የሰው ምስክሮችም ከሞላ ጎደል በዚሁ መልኩ የመሰከሩ ስለመሆኑ የስር ፍርድ
መዝገብ ያሳያል፡፡ ጉዳዩን የያዘው ፍርድ ቤትም የአመልካችን መከላካያ ምስክሮች ቃል መርምሮ
መከላከያውም ሆነ የተሰጠው የምስክርነት ቃል የዐቃቤ ህግ ክስ እና ማስረጃን የሚያስተባበል አይደለም
በማለት ውድቅ አድርጓል፡፡

እንግዲህ ማስረጃ የሚያስፈልገው አንድን ክርክር የቀረበበትን ፍሬ ነገር መኖር ወይም አለመኖር
ለማረጋገጥ ነው፡፡ የቀረበው ማስረጃ የተባለውን ፍሬ ነገር ስለመኖሩ ወይም ስላለመኖሩ አስረድቷል
ወይም አላስረዳም በሚለው ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የቀረበውን ማስረጃ መመርመር፣ ማገናዘብ፣

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

መተቸት በጥቅሉ መመዘን ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መልኩ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ማስረጃን
በመመርመር እና በመመዘን የተደረሰበት ድምዳሜ በዚህ ሰበር ችሎት ሊለወጥ የሚችለው ፍርድ ቤቱ
በማስረጃ ምዘና ረገድ የፈፀመው ስህተት ከተገኘ ብቻ ስለመሆኑ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ
አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 10 ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል፡፡

አሁን በቀረበው ጉዳይ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ጥፋተኝነቱን በመካድ፤ በዚህ የሰበር ክርክር ደግሞ
ድርጊቱ ወንጀል አይደለም የሚል መከራከሪያ ከማቅረብ ባለፈ የስር ፍርድ ቤት ከማስረጃ ምዘና አንፃር
የፈፀመው የምዘና መርህ ጥሰት ስለመኖሩ የቀረበው የአመልካች የሰበር አቤቱታ የሚገልፀው ነገር
የለም፡፡ ለአመልካች መከራከሪያ መሰረት የሆነው ማስረጃ ተመዝኖ ተቀባይነት እንደሌለው ተወስኖ
ባለበት ይኸው ማስረጃ መሰረት ተደርጎ ድርጊት ወንጀል አይደለም በሚል ክርክር ሊቀርብ የሚችልበት
አግባብ የለም፡፡ በመሆኑም በስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት
የማይቻል በመሆኑ የአመልካች መከራከሪያ ውድቅ ተደርጎ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

ውሳኔ

1. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ


በማድረግ በመ/ቁ/274377 ላይ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በወንጀል ህግ
ሥነ ሥርዓት ቁር 195(2(ለ(2))) መሰረት ፀንቷል፡፡

2. መዝገቡ ተዘግቷል፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መ.ቁ 216709

ቀን፡- 1/4/2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ሱልጣን አባተማም

ምፅላል ኃይለ

ዋዚሞ ዋሲራ

አመልካች፡ቾች- እነ ኦሜጋ የወርቅ ግብይት ማህበር ጠበቃ አክሊሉ ኤርሚያስ

ተጠሪ፡/ዎች- እነ አቦቦ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት

መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመልካች 30/3/2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ
አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡ ለዚህ ችሎት 16/3/2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የጋምቤላ ብ/ክ/መ/ጠ
ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 01080/2014 በ 16/3 /2014 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ
የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረበው
ማመልከቻ መነሻነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ትአዛዝ ሰጥተናል፡፡

ትዕዛዝ

ያሁኑ አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ይሁን የምንሰራውን
ፈቃዳችን ነጥቆ እንዳንሰራ አደረገን የሚል ሲሆን ፍ/ቤት ግራቀኝ በፍሬ ነገር ሣያከራክር
የመክሰስ መብት የላችሁም በማለት የወሰነበት አግባብነት

መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ ብለናል፡፡

1.መጥሪያ ለተጠሪ/ዎች/ ይድረስ ብለናል፡፡ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክራቸውን በሬጅስትራር ፅ/ቤት


በኩል ይቀባበሉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ቀጠሮ ለ 25/4/2014 ዓ.ም ተቀጥሮአል፡፡ 5፡20 ሰዓት

የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በ ኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 189155

ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ/ም

ዳኞች፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

ቀነአ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካቾች፡- 1ኛ. አቶ መርጋ ከበደ - ቀረቡ

2ኛ. አቶ ግርማ ከበደ

3ኛ. ወ/ሮ ሌሎ ከበደ አልቀረቡም

4ኛ. ወ/ሮ ኡርጌ ከበደ

ተጠሪ ፡- አቶ አበራ ከበደ - ጠ/ዮሴፍ አመንቴ - ቀረቡ

መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።

ፍ ር ድ

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ


48351 በቀን 01/09/2011 ዓ.ም የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 30573 በቀን 06/07/2011 ዓ.ም
የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠውን ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 313390 በቀን
29/01/2012 ዓ.ም እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 319820 በቀን 19/02/2012 ዓ.ም
በመሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በስር የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ ሲሆን ተጠሪ
ተከሳሽ ነበሩ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ን ገጂጽ 1 / 5


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላ ማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ከሳሾች በቀን 14/09/10 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ እናታችን
ወ/ሮ አዛለች አስፋው በ11/08/1980 ዓ.ም አባታችን አቶ ከበደ አዋስ ደግሞ በ10/12/1977 ዓ.ም
የሞቱ ሲሆን እናታችን በህይወት እያለች ያላት ይዞታ መሬት በጠቅላላው 14 ቀርጥ (አስራ አራት
ቀርጥ) እናታችን ከሞተች ግዜ ጀምሮ ተከሳሽ የሚመረተውን ምርት እያካፈለን አብረን
የምንጠቀምበት የኖርን ሲሆን ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ተከሳሽ መብት ሳይኖረው ስለከለከለን ንብረቱንና
ይዞታ መሬቱን እንዲለቅልን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ተከሳሽ በሰጡት መልስ የተጠቀሰው የይዞታ መሬት በ1980 ዓ.ም ከመንግስት በክፍፍል
አግኝቼ ለ30 አመት በግሌ በማረስ እየተጠቀምኩበት ነው፤ በ1999 ዓ.ም የባለቤትነት ደብተር
የተሰጠኝና ግብር እየገበርኩበት ቆይቻለሁ፤ መሬቱ 10 ቀርጥ መሬት ብቻ ነው፤ የመውረስ መብት
አላቸው ቢባል እንኳ ከ30 አመት በኃላ ሊጠይቁኝ አይችሉም፤ የግሌ በመሆኑና የሟች መሬት
ስላልሆነ ክሳቸው ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት የስር ፍርድ ቤት መዝገቡን መርምሮ የተጠቀሰው ይዞታ
መሬት የተከሳሾች እናት በ1980 ዓ.ም በአምራቾች በህይወት እያለች የተወሰደባት እና በ1982 ዓ.ም
እና 83 ዓ.ም ይዞታው ለባለይዞታው በሚመለስበት ጊዜ የከሳሾች እናት በህይወት ስላልነበረች
የተመለሰላት መሬት እንደሌለ ተረጋግጧል፤ በተከሳሽ እጅ የሚገኘው ይዞታ ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ
በግል ይዞ እየተጠቀመበት ያለ መሆኑም ተረጋግጧል፤ በመሆኑም ከሳሾች በውርስ
እንዲተላለፍላቸው የጠየቁት መሬት የከሳሾች እናት በህይወት እያለች ያልነበራትና በፍ/ብ/ህ/ቁጥር
826(2) መሰረት ምንም መብትና ግዴታ የማይተላለፍ ስለሆነ ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33(2) እና
(3) መሰረት ውድቅ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ከሳሾች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለደቡብ ምዕራብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


አቅርበው ፍ/ቤቱም የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ለክርክር ምክንያት የሆነው ይዞታ መሬት
ከድሮም የግራቀኙ ቤተሰብ ሆኖ ወላጆቻቸው ከሞቱ በኋላ አምራች ሲፈርስና መሬት ለባለይዞታዎች
ሲመለስ ከሳሾች ልጆች ስለነበሩ ተከሳሽ ቤተሰቡን እየመራ እንዲያሳድግበት የተሰጠው መሬት እንጂ
በግል ይዞታነት የተሰጠው እንዳልሆነ፤ እንዲሁም እስከ 2010 ዓ.ም ከሳሾችም ሲጠቀሙበት
ቆይተው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ተከሳሽ የከለከላቸው መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል፤ የተከሳሽ ምስክር
እንኳ ያረጋገጡት ይዞታው የተከራካሪዎቹ ቤተሰቦች መሆኑን እንጂ የተከሳሽ ይዞታ መሆኑን
አላረጋገጡም፤ በመሆኑም ክስ የቀረበበትን የውርስ ይዞታ መሬት ወራሾች እኩል ሊካፈሉት ይገባል
በማለት የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ሽሯል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ን ገጂጽ 2 / 5


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላ ማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በዚህ ውሳኔ ተከሳሽ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም
ጉዳዩን ከመረመረ በኃላ ክርክር ያስነሳው መሬት ቀደምትነቱ የእናታቸው መሬት የነበረ ሲሆን
በ1980 ዓ.ም በህይወት እያለች የገበሬዎች መሬት በሚወሰድበት ጊዜ የእርሷም የተወሰደባት
መሆኑና በዚያው ዘመን መሬቱ ከተወሰደ በኃላ አውራሽ የሞተች መሆኑ፤ በአምራቾች ተወስዶ
የነበረ ይዞታ መሬት በ1982 እና 1983 ዓ.ም አምራች ፈርሶ ይዞታው ለገበሬዎች ሲመለስ የከሳሾች
እናት በህይወት ስለሌለች ለእሷ ተብሎ የተመለሰ ይዞታ እንደሌለና ይዞታውን ተከሳሹ በግሉ ይዞ
ሲጠቀምበት የቆየ መሆኑን በመዝገቡ ያለው ማስረጃ በአብላጫ ያረጋግጣል በማለት የከፍተኛው
ፍርድ ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በመሻር የስር የወረዳው ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት ውሳኔ
ሰጥቷል፡፡ በዚህ ውሳኔ ከሳሾች ቅር በመሰኘት ለክልሉ ለሰበር ችሎት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም
ተቀባይነት አላገኙም፡፡

የሰበር አቤቱታው ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው በዚህ ነው። አመልካቾች ጥር 13/2012 ዓ.ም
ባቀረቡት ቅሬታ በውሳኔው ተፈፀመ የሚሉትን ስህተት ዘርዝረው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የከፍተኛ ፍ/ቤቱን ውሳኔ የሻረበት አግባብ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተሸሮ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ
ቤት ውሳኔ እንዲፀና ጠይቀዋል፡፡፡

ቅሬታው በሰበር አጣሪ ችሎት ተመርምሮ ተጠሪ አቅርቦት በነበረው የ3 አመት ይርጋ
ክርክር ላይ የከፍተኛው ፍ/ቤት አመልካቾች ለክርክር ምክንያት በሆነው መሬት ከተጠሪ ጋር እስከ
2010 ዓ.ም ድረስ ሲጠቀሙ የቆዩ መሆኑን መሰረት በማድረግ የስር ወረዳ ፍ/ቤትን ብይን በመሻር
በመለሰበት ሁኔታ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይዞታው የተጠሪ ነው በማለት የወረዳው ፍ/ቤትን ውሳኔ
በማጽናት የወሰነበትን አግባብ ከመሰረታዊ የክርክር አመራርና ማስረጃ ምዘና ጋር በማገናዘብ
ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ እና ተጠሪ መልስ እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡

ተጠሪ በቀን13/08/2012 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ የስር ክርክራቸውን አጠናክረው የወረዳው


ፍርድ ቤት እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቴ ይግባኝ ሰሚና ሰበር ችሎቶች የሰጡት ውሳኔ እንዲፀና
ጠይቀዋል፡፡ አመልካቾችም የመልስ መልስ አቅርበዋል፡፡

ከፍሲል በአጭሩ የገለጽነው የጉዳዩን አመጣጥ ሲሆን የግራቀኙን ክርክር ቅሬታ ከቀረበበት
ውሳኔ እና ከተገቢው የህጉ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል፡፡

እንደመረመርነው በስር ወረዳ ፍርድ ቤት የተሰጠውና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያፀናው


ውሳኔ አከራካሪው ይዞታ መሬት የአመልካቾች እናት በ1980 ዓ.ም በአምራቾች በህይወት እያለች
የተወሰደባት እና በ1982 ዓ.ም እና 83 ዓ.ም ይዞታው ለባለይዞታ አርሶ አደሮች በሚመለስበት ጊዜ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ን ገጂጽ 3 / 5


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላ ማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የአመልካቾ እናት በህይወት ስላልነበረች የተመለሰላት መሬት የለም፤ አመልካቾች በውርስ


እንዲተላለፍላቸው የጠየቁት መሬት አውራሻቸው በህይወት እያለች ያልነበራትና በፍ/ብ/ህ/ቁጥር
826(2) መሰረት መብትና ግዴታ የማይተላለፍበት ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33(2) እና (3)
መሰረት የአመልካቾች ክስ ውድቅ ነው የሚል ነው፡፡

በእርግጥ ለወራሾች የሚተላለፈው የሟች መብትና ግዴታዎች ስለመሆናቸው ከፍ/ብ/ህ/ቁ


826(2) ግልጽ ድንጋጌ እና ከውርስ ህጉ አጠቃላይ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ እንዲሁም ማንኛውም
ሰው ክስ ማቅረብ የሚፈቀድለት ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ክሱ በተመሰረተበት ሀብት ላይ
ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33 ድንጋጌ
መገንዘብ ይቻላል፡፡

በተያዘው ጉዳይ ከፍሲል እንደተገለፀው ለክርክር ምክንያት የሆነው ይዞታ መሬት ከድሮም
ጀምሮ የግራቀኙ ቤተሰብ ሆኖ ወላጆቻቸው ከሞቱ በኋላ አምራቾች ሲፈርስና መሬት ለባለይዞታዎች
ሲመለስ የአሁን አመልካቾች ልጆች (ህጻናት) ስለነበሩ ተጠሪ ቤተሰቡን እየመሩ እንዲያሳድጉበት
ለቤተሰቡ የተመለሰ መሬት እንጂ ለተጠሪ በግል ይዞታነት የተሰጣቸው ይዞታ እንዳልሆነ፤ በዚህም
ምክንያት እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር ሲጠቀሙበት ቆይተው ከዚህ ጊዜ
ጀምሮ ተጠሪ የከለከላቸው መሆኑ ፍሬ ነገር ለማጣራት እና ማስረጃ ለመመዘን ስልጣን ባላቸው
ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ የተጠሪ ማስረጃዎችም ቃል ይዞታው የተከራካሪዎቹ
ቤተሰቦች መሆኑን እንጂ የተጠሪ የግል ይዞታ መሆኑን የሚያስረዳ አለመሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ከፍሲል የተመለከተው ከሆነ ደግሞ አመልካቾች ይዞታውን
በተመለከተ የመከራከር መብት የላቸውም እንዲሁም ለአመልካቾች በውርስ የሚተላለፍ መብት
የለም ለማለት የሚቻልበት የህግ ምክንያት የለም፡፡

ስለሆነም አመልካቾች ክሱን ለማቅረብ መብት ወይም ጥቅም ያላቸው መሆኑን አሳይተው እያለ
እንዲሁም አከራካሪው ይዞታም በውርሰ የሚተላለፍላቸውና ሲጠቀሙበት የኖሩት ሆኖ እያለ
የወረዳው ፍርድ ቤት አመልካቾች በውርስ እንዲተላለፍላቸው የጠየቁት መሬት አውራሻቸው
በህይወት እያለች ያልነበራትና በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 826(2) መሰረት መብትና ግዴታ የማይተላለፍበት
ስለሆነ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33(2) እና (3) መሰረት የአመልካቾች ክስ ውድቅ ነው በማለት የደረሰበት
መደምደሚያ እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚና ሰበር ችሎቶችም ይህን በመቀበል
ያሳለፉት ውሳኔ የአመልካቾችን የዳኝነት ጥያቄውንና የተረጋገጠውን ፍሬነገር እንዲሁም

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ን ገጂጽ 4 / 5


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላ ማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.33(2) እና የፍ/ብ/ህ/ቁ 826(2) ይዘትና መንፈስ የተከተለ ባለመሆኑ የህግ


ስህተት ተፈፀመበት ነው ብለናል፡፡

ይልቁንም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለክርክር ምክንያት የሆነው ይዞታ መሬት የቤተሰቡ
መሆኑን፤ የግራቀኙ ወላጆች ከሞቱ በኋላ አምራቾች ሲፈርስ መሬቱ ለቤተሰቡ መመለሱን፤ በግዜው
አመልካቾች ልጆች (ህጻናት) ስለነበሩ ተጠሪ ቤተሰቡን እየመሩ እንዲያሳድጉበት መረከባቸውን፤
መሬቱ ለቤተሰቡ የተመለሰ እንጂ ለተጠሪ በግል ይዞታነት የተሰጣቸው ይዞታ እንዳልሆነ፤
ከተመለሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር ሲጠቀሙበት
መቆየታቸውንና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ የከለከላቸው መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ክስ
የቀረበበትን የውርስ ይዞታ መሬት ወራሾች እኩል ሊካፈሉት ይገባል በማለት የደረሰበት
መደምደሚያና ያሳለፈው ውሳኔ ህጉንና በማሰረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ያደረገ ነው
ከሚባል በቀር የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘነውም ፡፡ ስለሆነም ተከታዩነ ወስነናል፡፡

ው ሣ ኔ

1. የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 30573 በቀን 06/07/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፤ የኦሮሚያ
ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 313390 በቀን 29/01/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፤ እንዲሁም
የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 319820 በቀን 19/02/2012 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል፡፡

2. የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 48351 በቀን 01/09/2011 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡

3. እግድ ካለ ተነስቷል፡፡ ይፃፍ፡፡

4. በዚህ ፍርድ ቤት ስለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ

ሰ/ጥ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይምለግን ዛ ቤ እ ን ገጂጽ 5 / 5


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ምዓላ ማአ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ.መ.ቁ 204992
ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም

ዳኞች፡- እትመት አሠፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱዓለም

አመልካች፡- የጉለሌ ክ/ከ/ወረዳ 2 የመ/ቤቶች ጽ/ቤት ፡-ቀረቡ

ተጠሪ፡- ወ/ሪት ፍቅርተ ከተማ ፡- አልቀረቡም

መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል፡፡

ፍርድ
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 22 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. በተፃፈ የሰበር አቤቱታው
የሚያከራክረው የመንግሥት ቤትን አስመልክቶ የስር ፍ/ቤት ተጠሪ መብት አላት ብሎ መወሰኑ እና የበላይ
ፍ/ቤቶችም የስር ፍ/ቤት በውሣኔው የፈፀመውን ስህተት ሳያርሙ ማለፋቸው መሠረታዊ የሕግ ስሕተት
በመሆኑ በሰበር ታይቶ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ላየው የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ አቅርባው የነበረው ክስ
ከሚያከራክረው ቤት ተከራይ ከነበሩት አቶ አስፋው ቢራቱ ጋር በቤት ቁጥር 167 ውስጥ እንደልጅ ማደጓን፣
በቤቱ ውስጥ ያደገችው ከህፃንነቷ ጀምሮ መሆኑን እና እናቷም በህይወት የሌለች መሆኑን፣ ነገር ግን
አመልካች ከቤቱ በህገወጥ መንገድ ስላስወጣት በቤቱ የመኖር መብት አላት ተብሎ እንዲወሰንላት ዳኝነት
ጠይቃለች፡፡

አመልካችም ክሱ ደረሶት በሰጠው ምላሽ በሚያከራክረው ቤት ውስጥ ስሟ የሌለ መሆኑን፣ በቤቱ ውስጥ
እንደልጅ አለማደጓን፣ ከከሣሽ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላት በመሆኑ ቃለ ጉባዔ አስፈርመን ቤቱን
አስለቅቀናል፡፡ በመሆኑም ክሱ ውድቅ ይደረግልን ሲል ጠይቋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሲሰማ የስር ከሣሽ ቃለጉባዔ የተባለውን ያስፈረሙኝከቤት ካስወጡኝ
በኋላ ነው በሚል ስታስረዳ ተከሣሽ በበኩሉ በከሣሽ ላይ ምንም ዓይነት የመንፈስ ጫና ሳያሳድር
ቃለጉባዔውን መፈረሟን አስረድቷል፡፡ ፍ/ቤቱም ጭብጥ መስርቶ በግራ ቀኙ የቀረቡ ምስክሮችን ከሰማ በኋላ
ተጠሪ በቤቱ ውስጥ እንደልጅ ማደጓን የቀረበው ቃለጉባዔም ቤቱን ለመልቀቅ መስማማቷን የሚያሳይ
አለመሆኑን ፣ መመሪያ ቁጥር 5/2ዐዐ11 አንቀጽ 16 ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሟች እስከሞተበት
ቀን ድረስ በቤቱ ከወላጆቻቸው ተለይተው እንደልጅ ከኖሩ መብቱ የሚተላለፍላቸው መሆኑን የሚደነግግ
በመሆኑ ተጠሪ በቤቱ የመከራየትና የመኖር መብት አላት ሲል ወስኗል፡፡

አመልካች ይግባኝ ቢያቀርብም ለከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ቢያቀርብም የስር ፍ/ቤት ውሣኔ
ሳይለወጥ ቀርቷል፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡

አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መብት አለኝ በማለት የሚከራከር ወገን መብቱ ያለው መሆኑን
የማስረዳት ሸክም እንዳለበት አስቀድሞ በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቶ ባለበት፣
ተጠሪ በቤቱ ውስጥ የነበሩ ሰራተኛ የወንድም ልጅ ሆኖ እያለ አቶ አስፋው ቢራቱ አምጥተው ያላሳደጓት
በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ከማስረጃ ምዘና አንፃር የፈፀሙት ስህተት ሊታረም ይገባል ሲል ሰፊ የሰበር አቤቱታ
አቅርቧል፡፡ አቤቱታው በአጣሪ ተመርምሮ ጭብጥ በመያዙ ተጠሪም መልሷን አቅርባለች፡፡ ይዘቱም በአጭሩ፡-
ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በአዋጅ የተሰጠው ሥልጣን የህግ ስህተትን ማረም እንጂ የማስረጃ ምዘና ባለመሆኑ
አቤቱታው ውድቅ ሊሆን የሚገባው መሆኑን፣ ይህ ከታለፈም ከዋናው ተከራይ ጋር ከ3 ዓመቷ ጀምሮ
እንደልጅ የኖረች በመሆኑ ዋናው ተከራይም ልጃቸው አድርገው አስፈላጊውን እያሟሉ ያሳደጓት በመሆኑ
በስር ፍ/ቤት ይህ ተረጋግጦ የተወሰነ በመሆኑ ሊፀናልኝ ይገባል ብላለች፡፡ አመልካችም የመልስ መልስ
አቅርቦ የግራ ቀኙ የጽሁፍ ልውውጥ በዚህ ተጠናቋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል እኛም የቀረበውን አቤቱታ መልስ እና የመልስ
መልስ ከስር ፍ/ቤቶች ውሣኔ እና አጠቃላይ ከማስቀረቢያ ነጥቡ አንፃር አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች
ጋር በማረናዘብ እንደሚከተለው መርምረናል፡፡

እንደመረመርነውም ተጠሪ በቤት ቁጥር 167 ውስጥ እንደልጅ ኖሬ ዋናው ተከራይ ሲሞቱ ከቤት እንድወጣ
የተደረገ በመሆኑ በቤቱ የመኖር መብቴ ይከበርልኝ በማለት ክስ ያቀረበች ሲሆን አመልካች ደግሞ በቤቱ
ውስጥ እንደልጅ አልኖረችም በቅጽ ውስጥም አልተመዘገበችም ለመልቀቅ ቃለጉባዔ ፈርማለች በሚል
ተከራክሯል፡፡

ከአጠቃላይ ክርክሩ ተጠሪ በሚያከራክረው ቤት ውስጥ እንደልጅ ስለመኖር አለመኖሯ በማስረጃ ሳይረጋገጥ
እና መመሪያ ቁጥር 5/2ዐ11 አንቀጽ 16 ከሚያዘው ውጪ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ አለ ወይንስ የለም
የሚለውን በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በጭበጥነት ተይዞ ሊመረመር የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የመንግሥት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ
ቁጥር 5/2ዐ11 ዓ.ም. አንቀጽ 16 የቀበሌ ቤት ለ3ኛ ወገኖች የሚተላለፍበትን ሁኔታ በንዑስ አንድ ስር
ዋናው ተከራይ በሞት ሲለይ ወይም ከአካባቢው በተለያዩ ምክንያት ሲርቅ ቤቱን ለቢሮው እንዲመልስ
ስለመደረጉ የሚደነግግ ሆኖ ነገር ግን በሟች ቤት ውስጥ ለሚኖሩ የኪራይ ውሉ የሚተላለፍበትን ሁኔታ
በዚሁ ንዑስ ቁ. ከሀ-መ ድረስ እነማን እንደሆኑ ዘርዝሯል፡፡

ከዚህም ውስጥ ዋናው የቤቱ ተከራይ በሞት በተለየ ጊዜ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ እና
ከወላጆቻቸው ተለይተው በቤቱ ውስጥ እንደልጅ ይኖሩ የነበሩ ልጆች መብት የሚያገኙ መሆኑን ይደነግጋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በዚህ መሠረት ተጠሪ በሚያከራክረው ቤት ውስጥ ከእናቷ ጋር ትኖር የነበረ እና እናቷ ስትሞትባትም የቤቱ
ዋና ተከራይ አቶ አስፋው ቢራቱ እኔ አሳድጋታለሁ ብለው እያኖሯትና እያሳደጓት የነበረ መሆኑ በፍሬ ጉዳይ
ደረጃ በስር ፍ/ቤት ተረጋግጧል፡፡ አመልካች ከቤት ውስጥ ተጠሪን ለማስወጣት ያስፈረማት ቃለጉባዔም
ቢሆን ስምምነቷን የገለፀችበት አለመሆኑ የስር ፍ/ቤት በውሣኔው ገልጿል፡፡

ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 8ዐ/3/ሀ እና በአዋጅ ቁጥር 1234/2ዐ13 አንቀጽ 1ዐ/1/
መሠረት የተሰጠው ሥልጣን በማናቸውም ደረጃ ባሉ ፍ/ቤቱች የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ ጉዳዩች ላይ
መሠረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞ ሲገኝ ማረም እንጂ ማስረጃ አያጣራም ፍሬ ነገርንም አይመረምርም፡፡

ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች በማስረጃ አጣርተውና ፍሬ ነገርን መርምረው ተጠሪ በሚያከራክረው ቤት ውስጥ
ተከራይታ የመኖር መብት አላት ሲሉ የደረሱበት መደምደሚያ ተገቢ እንጂ መሠረታዊ የህግ ስህተት
የተፈፀመበት ሆኖ ባለመገኘቱ ሊፀና ይገባል ብለን ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሣኔ

1) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/ 32929 የካቲት 26


ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የስር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ ተቀብሎ በማጽናት የሰጠው ውሣኔ
በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ/ 348/1/ መሠረት ፀንቷል፡፡
2) በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በግራ ቀኙ የወጣ ወጪ ካለ የየራሳቸውን ይቻሉ
ብለናል፡፡
3) የውሣኔ ትክክል ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ፡፡
4) በዚህ ፍ/ቤት በ13/8/2ዐ13 ዓ.ም በዋለው ችሎት በመ/ቁ 2ዐ295 በሆነው ላይ
የተሠጠው እግድ ተነስቷል

መዝገቡ ውሣኔ ስላገኘ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለሰ፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ሠ/ኃ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግንዛ ቤ እ ንጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 217149

ቀን፡- ታህሳስ 14 ቀን 2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- እትመት አሰፋ

ፀሐይ መንክር

ኑረዲን ከድር

መላኩ ካሣዬ

እስቲበል አንዱአለም

አመልካቾች፡- አቶ ናሆም ተወልደ

ተጠሪ/ዎች፡- እነ ወ/ሮ ንግስቲ ገዛኽኝ /8 ሰዎች

መዝገቡ ዛሬ በችሎት የቀረበው 6ኛ ፣7ኛ 8ኛ ተጠሪዎች በግልና በጋራ ባቀረቡት የተሰጠ የዕግድ
ይነሣልንና ወደ አከራካሪው ቤት እንድገባ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ አቤቱታ የሚመለከታቸው አካላት
ደርሷቸው አስተያየት እንዲያቀርቡ በዚህ ችሎት መታዘዙን ተከትሎ፤ 7ኛ እና 8ኛ ተጠሪዎች
አመልካችን ማግኘት አለመቻላቸውን በመግለፅ ትአዛዙ ለአመልካች የሚደርስበት አማራጭ
በመዘርዘር ባቀረቡት አቤቱታና 6ኛ ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተዳደሩ አስተያየት መስጠቱን
ተከትሎ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት በማስፈለጉ ነው፡፡

በዚህ መሰረት ጉዳዩን መርምረን ተከታዩን ትዕዛዝ ሰጥተናል

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ትዕዛዝ

1. 7ኛ እና 8ኛ ተጠሪዎች ያቀረቡት የእግድ ይነሳልን አቤቱታ ቅጅና የችሎቱ ትእዛዝ


አመልካች በዋናው የሰበር ክርከር መልስ በሚያቀርቡበት ታህሳስ 25 ቀን/2014 ዓ.ም
በሬጅስትራር በኩል ደርሷቸው አስያየታቸውን ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም 3፡30 ያቅርቡ
2. 6ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ አስተዳደሩ የሰጠውን አስተያየት
መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት እና 7ኛ እና 8ኛ ተጠሪዎች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አመልካች
የሚያቀርቡትን አስተያየት መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት መዝገቡ ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም
ለችሎት ይቅረብ
3. መልስ ለመቀበል ለታህሳስ 25 ቀን 2014 የተያዘው ቀጠሮ አልተለወጠም፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ 217272

ቀን፡- 5/04/2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ገበየሁ ፈለቀ

ሌሊሴ ደሣለኝ

ሰናይት አድነው

አመልካች፡ቾች- እነ ሲሳይ ጥላሁን 8 ሰዎች -ጠበቃ ሙሉጌታ ማረጉ -ቀረቡ

ተጠሪ፡/ዎች- ወሰኔ ጥላሁን -አልተጠሩም

መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመለካች 01/04/2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ
አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡ ለዚህ ችሎት 28/03/ቀን 2014 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ ፌደራል ጠቅላይ
ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 193860 በ 23/02 ቀን 2014 የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ
የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ/ን/ በማለት ባቀረቡት
ማመልከቻ መነሻነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ትዕዛዝ

ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ተጠሪ በጋብቻ ውላቸው አከራካሪ የሆነው ቤት ካርታው በተጠሪ ስም
የተመዘገበ ቢሆንም የእርሱ አለመሆኑን ጠቅሶ ባለበት ንብረቱ የውረስ ነው ሲል የደረሰበት
ድምዳሜ ህግን የተከተለ መሆን

መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሠበር ችሎት ይቅረብ ብለናል፡፡


1. መጥሪያ ለተጠሪዎች ይድረስ፡፡ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክራቸውን በሬጅስትራር ፅ/ቤት በኩል
ይቀባበሉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2. በሰበር ሰሚ ችሎት ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪደርስ ድረስ ባህር ዳር ከተማ ግሽአባይ ክፍለ
ከተማ በተጠሪ ስም በካርታ ቁጥር 28984/04 የተመዘገበው ቤት ለሶስተኛ ወገን
እንዳይተላለፍ እንዳይሸጥ በፍ/ብሥ/ሥ/ 154 መሰረት ታግዷል ይፃፍ
3. ቀጠሮ ለ 28/4/2014 ተቀጥሮአል፡፡ 4፡ዐ0 ሰዓት
የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰ/መ/ቁ፡-197008

ቀን፡- 05/02/2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ብርሀኑ አመነው

ተሾመ ሽፈራው

ሀብታሙ እርቅይሁን

ብርሀኑ መንግስቱ

ነፃነት ተገኝ

አመልካች ፡- ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን - ጠበቃ መኮንን ይማም ቀረቡ

ተጠሪ ፡- ፀጋ ረታ አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር - አልቀረቡም

መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ

ክርክሩ የሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው
ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ
ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት እቃዎቹ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም
ኬብሎቹን እንዲያቀርብ ወይም በወቅቱ የገበያ ዋጋ የእቃዎቹን ግምት ብር 182,900 ወጪና ኪሳራን
ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች እቃዎቹ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ካወቀበት
ጊዜ ጀምሮ በ1 አመት ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
አቅርቧል፡፡

ፍርድ ቤቱም በመቃወሚያው ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ግንኙነታቸው የሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ ስለሆነ
ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለው ስለውሎች በጠቅላላው የተደነገገው የፍ/ሕ/ቁጥር 1845 ሳይሆን የሽያጭ ውልን
የሚመለከተው የፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) ነው፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረትም በሻጩ አጭበርባሪነት ካልሆነ በቀር
ገዢው ጉድለቱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ ማቅረብ አለበት፡፡ አመልካች የተጠሪ
አጭበርባሪነት ያለበት ስለመሆኑ በክሱ ያልገለፀ ሲሆን ተጠሪው የእቃዎቹን ጉድለት እንዲያስተካክል
ያሳወቀው ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲሁም ለተረከባቸው እቃዎች ክፍያ የፈጸመው ጥቅምት 25 ቀን
2009 ዓ.ም በመሆኑ ክሱ የቀረበው ሁለት ኣመት ካለፈው በኋላ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ነው፡፡ የተጠሪ
ሰራተኛ ሰኔ 10 ቀን 2009 ዓ.ም UPS 5kg ለቼክአፕ መውሰዱ ጉድለቱን በግልፅ አምኗል አያስብልም፡፡
አምኗል ቢባል እንኳ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በ1 ዓመት ውስጥ ክሱ ስላልቀረበ በይርጋ ይተጋዳል በማለት ብይን
ሰጥቷል፡፡

አመልካች ውሳኔውን በመቃወም ይግባኙን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ውሳኔን
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት በማፅናቱ ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታውን
አቅርቧል፡፡ የአቤቱታው ይዘት ባጭሩ አመልካች በክሱ ላይ ፍሬ ነገርን ከመግለፅ በዘለለ ተጠሪው መቃወሚያ
ሊያቀርብ ይችላል ብሎ በማሰብ በክስ መስማት ወቅት ሊያቀርብ የሚችለውን መከራከሪያ አስቀድሞ ማቅረብ
ግዴታ በሌለበት ተጠሪው የማታለል እና የማጭበርበር ተግባር ስለመፈፀሙ አመልካች በክሱ አልገለፀም
መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ ተጠሪ እቃዎቹን አስተካክላለው ብሎ መውሰዱን አልካደም፡፡ የወሰደውም እቃውን
ባስረከበ በአንድ ዓመት ውስጥ ሲሆን እቃውን በእምነት በመውሰድ በተግባር የማታለል እና የማጭበርበር
ተግባር የፈፀመ ሲሆን እቃዎቹን አስተካክሎ የሚያቀርብበት ጊዜም ስላልተወሰነ እና እቃዎቹን አስተካክሎ
እንዲያስረክብ በተደጋጋሚ በአመልካች ሲጠየቅ ከዛሬ ነገር አስተካክዬ እመልሳለው ማለቱ ስላልተካደ አስፈላጊ
ከሆነም ምስክሮቻችንን በመስማት ሊጣራ ሲገባ ክሱ በይርጋ ይታገዳል መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ ውሉ
የሽያጭ ብቻ ሳይሆን የጥገና ማደስና መለዋወጫ ማቅረብ መሆኑ በሰነድ ተረጋግጦ እያለ ሽያጭ ብቻ ነው
ተብሎ የሽያጭ ሕግ የይርጋ ድንጋጌ ተግባራዊ መደረጉ እንዲሁም እቃው በተጠሪ እጅ ያለ በመሆኑ
አመልካች በማንኛውም ጊዜ ንብረቱን መጠየቅ የሚችል ሁኖ እያ ክሱ በይርጋ ይታገዳል መባሉ የፍ/ሕ/ቁጥር
1206 እና የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 63600 ቅፅ 10 የሰጠውን ውሳኔ
የሚቃረን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚል ነው፡፡

አቤቱታው በአጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ ተጠሪ የእቃውን ጉድለት አምኖ መልሶ መቀበሉን ለክሱ በሰጠው
መልስ አምኖ እያለ ክሱ በአንድ አመት ይርጋ ይታገዳል ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት ከፍ/ሕ/ቁጥር

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2298(1) እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝቦ ለመመርመር ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪ
መልሱን እንዲያቀርብ ታዟል፡፡

ተጠሪም ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል፡፡ የመልሱ ይዘት ባጭሩ ተጠሪ ለክሱ በአማራጭ
በሰጠው መልስ አመልካች የመለሳቸውን እቃዎች አስመልክቶ ክትትል አላደረገም በሚል መቀመጡ
አማራጭ ክርክር ከሚሆን በቀር በፍ/ሕ/ቁጥር 1851(ሀ) መሰረት እዳውን አምኗል አያስብልም፡፡ እቃው
ጉድለት አለበት በሚል ማሳወቅም ሆነ ጉድለት አለ በሚል እቃ መመለሱ መታመኑ በውጤት ደረጃ አንድ
ስለሆነ በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) መሰረት አመልካች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ
ይታገዳል መባሉ ተገቢ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡

አመልካች የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልሱን ያቀረበ ሲሆን የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር
ተከራክሯል፡፡

የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የአመልካች ክስ በይርጋ ይታገዳል ተብሎ የመወሰኑን
አግባብነት በስር ፍ/ቤት ከተደረጉ ክርክሮች፣ በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዲሁም ለጉዳዩ ተገቢነት
ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርምረነዋል፡፡

እንደመረመርነውም አመልካች በዋናነት የሚከራከረው ተጠሪው ክርክር ያስነሳውን እቃ መልሶ መረከቡ እና


በተለያዩ ጊዜያትም ከዛሬ ነገ አስተካክዬ አስረክባለው እያለ እንደነበር ባልተካደበት አስፈላጊ ከሆነም ምስክር
ሊሰማ ሲገባ እንዲሁም ውሉ ሽያጭ ብቻ ሳይሆን የጥገና እና የመለዋወጫ እቃ አቅርቦት ጭምር ሆኖ እያለ
ክሱ በአንድ አመት ይርጋ ይታገዳል መባሉ ተገቢ አይደለም በማለት ነው፡፡ ተጠሪ በበኩሉ እቃውን መልሶ
መቀበሉን በአማራጭ ክርክር ማቅረቡ እዳውን አምኗል የማያስብል እና አመልካች ጉድለት አለበት በሚል
ማሳወቁም ሆነ እቃውን መመለሱ በውጤት ደረጃ ልዩነት ስለሌለው ክሱ በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) መሰረት
በይርጋ ይታገዳል ተብሎ መወሰኑ ተገቢ መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል፡፡

ገዢው ክስ ማቅረቡን የከለከለው የሻጩ አጭበርባሪነት ካልሆነ በቀር እቃው እንደ ውሉ ትክክል አለመሆኑን
ወይም ጉድለት ያለበት መሆኑን ካስታወቀበት ቀን አንስቶ እስከ አንድ አመት ውስጥ ክስ ያላቀረበ እንደሆነ
እቃው ጉድለት አለበት ወይም እንደ ውሉ የቀረበ አይደለም በማለት ክስ ማቅረብ የማይችል መሆኑ
በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) ላይ ተመላክቷል፡፡ ይህም ማለት አንድ ገዢ የገዛው እቃ ላይ ጉድለት ያለበት ከሆነ
ጉድለቱ ለሻጩ ባሳወቀ በአንድ አመት ውስጥ ጉድለቱ እንዲስተካከልለት ክስ ካላቀረበ ክሱ በይርጋ
ይታገዳል፡፡ ነገር ግን ገዢው በዚህ አንድ አመት ውስጥ ክስ እንዳያቀርብ የሻጩ አጭበርባሪነት ከልክሎት
ከሆነ ገዢው ጉድለት መኖሩን ካሳወቀ ከአንድ አመት በኋላም ቢሆን ጉድለቱ እንዲስተካከልለት ክስ ማቅረብ
ይችላል፡፡ በሌላ አባባል የሻጩ የማጭበርበር ድርጊት የአንድ አመቱን የይርጋ ጊዜ ገደብ የሚያቋርጥ
ምክንያት ይሆናል፡፡ የዚህ ድንጋጌ አላማ ሻጩ በፈጸመው የማጭበርበር ተግባር የወንጀል ድርጊት በመሆኑ
በአንድ አመት ውስጥ ክስ አልቀረበም በሚል በወንጀል ድርጊቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን ለመከላከል ነው፡፡ ይህ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

ማለት ግን የማጭበርበር ድርጊት ከተፈጸመ ምንም አይነት የክስ ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ አይኖረውም ማለት
አይደለም፡፡ የማጭበርበር ድርጊቱ እንደ ይርጋ ማቋረጫ ጊዜ ተወስዶ የአንድ አመቱ የይርጋ ጊዜ
የማጭበርበር ድርጊቱ ከተፈጸመ ጊዜ ጀምሮ እንደአዲስ መቁጠር የሚጀምር ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
ሌላው መታየት ያለበት የሻጩ አጭበርባሪነት የሚለው አገላለጽ ምን አይነት እና መቼ የሚፈጸም የሻጩን
ድርጊት የሚያመለክት ነው? የሚለው ሊሆን ይገባል፡፡ በፍ/ህ/ቁጥር 2297 ሻጩ የሸጠውን ነገር ጉድለቶች
ያሉበት መሆኑን ገዢው እንዳያውቃቸው በተንኮል ደብቋቸው ከሆነ ሻጩን ከሀላፊነት የሚያድኑ የውል
ቃሎች ቢኖሩ ሻጩ ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችል ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት ሻጩ ለገዢ በሸጣቸው
ነገሮች ላይ ጉድለት መኖሩን እያወቀ በተንኮል በሽያጭ ወቅት ምንም አይነት ጉድለት እንደሌለባቸው
አስመስሎ ከሸጠ ወይም ከሽያጭ በኋላም ቢሆን ጉድለቱ እንዳይታወቅ ለማድረግ ሻጩ የማጭበርበር ድርጊት
የፈጸመ በመሆኑ ተጠያቂ የማያደርገው የውል ቃል እንኳን ቢኖር ውሉ ተፈጻሚ እንደማይሆን እና ሻጩ
በኃላፊነት እንደሚጠየቅ የሚያመለክት ነው፡፡ የፍ/ህ/ቁጥር 2298/1 የፍ/ሕ/ቁጥር 2297 ተከታይ እንደመሆኑ
ተጣምረው ሲነበቡ ሻጩ እቃውን ወይም የሚሸጠውን ነገር ለገዢ በሚሸጥበት ወይም በሚያስረክብበት
ወቅት እቃው ጉድለት ያለበት መሆኑን እያወቀ ጉድለት እንደሌለ አድርጎ ወይም ጉድለቱ እንዳይታወቅ
አድርጎ በማጭበርበር ለገዢ መሸጡ ወይም ማስረከቡ ከተረጋገጠ ክስ የማቅረቢያ ጊዜው በአንድ አመት
ይርጋ የማይገደብ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በተቃራኒው ሻጩ በሽያጭ ወይም በርክክብ ወቅት
የፈጸመው የማጭበርበር ድርጊት ከሌለ ጉድለቱን ገዢው ለሻጭ ባሳወቀ በአንድ አመት ውስጥ ክስ ካላቀረበ
ክሱ በይርጋ ይታገዳል ማለት ነው፡፡

በተያዘው ጉደይ አመልካች ተጠሪው ከዛሬ ነገ እቃውን እጠግናለው በማለት የማጭበርበር ተግባር ስለፈጸመ
ክሱ በይርጋ ተቋርጧል መባሉ ተገቢ አይደለም በማለት የሚከራከር ቢሆንም ከላይ እንደተገለጸው
በፍ/ሕ/ቁጥር 2298(1) የተገለፀው የማጭበርበር ተግባር እቃውን ከሚመለከት ዝርዝር መግለጫ ወይም
በግብይቱ ጊዜ እቃው ጉድለት ያለበት መሆኑ እየታወቀ ይህን በመደበቅ ከተፈጸመ ተግባር ጋር የሚገናኝ
ነው፡፡ ተጠሪ ከዛሬ ነገ እቃውን አስተካክላለሁ እያለ ቆይቶ ቢሆን እንኳን ተጠሪ የዋቢነት ሃላፊነቱን
አለመወጣቱን የሚያሳይ እንጂ በግዢ ወቅት በእቃው ላይ ያለው ጉድለት በአመልካች እንዳይታወቅ
የማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙን የሚያመለክት አይደለም፡፡ ከግብይቱ በኋላ የተጠሪ ሰራተኛ ሰኔ 10 ቀን
2009 ዓ.ም UPS 5kg ለቼክአፕ መውሰዱ ጉድለቱን በግልፅ አምኗል የሚያስብል ካለመሆኑም በላይ ተጠሪ
ጉድለቱን ለማስተካከል እቃውን ተቀብሏል ቢባል እንኳ በዚህ አግባብ ባለማስተካከሉ አመልካች ተጠሪ
እቃውን ለማስተካከል ከተቀበለበት ጊዜ ጀምሮ በሕግ በተገለፀው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ክስ በመመስረት
ዳኝነት ሊጠይቅ ይገባ ነበር፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አመልካች ተጠሪው ከዛሬ ነገ እቃውን አስተካክላለው በማለት
ያጭበረበረኝ ስለመሆኑ ምስክሮቼ መሰማት ነበረባቸው በማለት የሚከራከር ቢሆንም በፍትሐብሄር ክርክር
ማስረጃ የሚሰማው እና ፍሬ ነገር እንዲነጥር የሚደረገው ለጉዳዩ አወሳሰን የግድ አስፈላጊ ሲሆን ብቻ
ስለመሆኑ ከፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለሆነም አመልካች ምስክሮቼ ሊሰሙ ይገባ ነበር
በማለት የሚያቀርበው ቅሬታ ተገቢነት የለውም፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በመጨረሻም አመልካች ለክሱ መነሻ ያደረገው የገዛዋቸው እቃዎች በውሉ መሰረት ተሟልተው የቀረቡ
ባለመሆኑ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም የሚል ሁኖ እያለ እና ውላችን የጥገና እና
የመለዋወጫ አቅርቦትን ስለሚጨምር የፍ/ሕ/ቁጥር 2298 ለጉዳዩ ተፈጻሚነት የለውም በማለት የሚያነሳው
መከራከሪያ ተገቢነት ስንመለከት አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ተጠሪው ጥገና እንዲያደርግልኝ
ይወሰንልኝ የሚል ግልጽ ዳኝነት አልጠየቀም፡፡ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከመለዋወጫ እና ጥገና ውል ጋር
የተያያዘ ክስ ባላቀረበበት የተጠቀሰው የይርጋ ድንጋጌ ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም በሚል የሚያቀርበው
መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው አይደለም፡፡ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበው የሽያጭ ውልን መሰረት
አድርጎ በተሸጠው እቃላይ አለ የሚለው ጉድለት በገንዘብ ወይንም በአይነት እንዲስተካከልለት በመሆኑ
ለጉዳዩ የፍ/ሕ/ቁጥር 2298/1 ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

በመሆኑም አመልካች ተጠሪ እቃውን እንዲያስተካክል ያሳወቀው ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም መሆኑ እና
ክሱ የቀረበው የካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም መሆኑ ተረጋግጦ በይርጋ ይታገዳል ተብሎ በስር ፍ/ቤቶች
በተሰጠው ብይን ላይ እና ብይኑን በማጽናት በተሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለም
በማለት ተከታዩን ወስነናል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁጥር 65181 ግንቦት 16 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠው
ብይን እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 239590 ሐምሌ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው
ችሎት ሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል፡፡
2. በዚህ ችሎት የተደረገው ክርክር ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የራሳቸውን ይቻሉ፡፡
3. አመልካች ለተጠሪ እንዲስተካከል ሰጥቻለሁ የሚለውን እቃ በተመለከተ ባለበት ሁኔታ ለማስመለስ
ክስ ከማቅረብ ይህ ውሳኔ አያግደውም፡፡

መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ፡፡


ሄ/መ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

በኢትዮጵያ ፌዴራላ ዊ ዲሞክራሲያዊ ሪ ፐብሊክ


የ ፌዴራል ጠቅላ ይ ፍር ድ ቤት
ሰበር ሰሚችሎት

የሰበር መ.ቁ 217691

ቀን፡- 15/4/2014 ዓ.ም

ዳኞች ፡- ገበየሁ ፈለቀ

ሸምሱ ሲርጋጋ

ምፅላል ሀይለ

አመልካች፡ቾች- የሟች ወ/ሮ ዋጋዬ ወ/ማርያም ወራሾች ጠበቃ አይሌ አየለ

ተጠሪ፡/ዎች- ወ/ሮ የሺሐረግ ከበደ

መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመልካች 15/4/ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ
ስላቀረቡ ነው፡፡ ለዚህ ችሎት 7/4/2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ
ችሎት በመ/ቁ 279892 በ 27/3 /2014 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት
የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረበው ማመልከቻ መነሻነት
ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ትአዛዝ ሰጥተናል፡፡

ትዕዛዝ

ክርክሩ ፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት ደርሶ በመደበኛ ፍ/ቤት የመክሰስ መብታቸው ተጠብቆ
በውሳኔው መሰረት የቀረበ ክስ ሲሆን የስር ፍ/ቤት በ 3 ወር ይርጋ የታገደው በማለት
የወሰነበት አግባብነት

መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ይቅረብ ብለናል፡፡

1.መጥሪያ ለተጠሪ/ዎች/ ይድረስ ብለናል፡፡ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክራቸውን በሬጅስትራር ፅ/ቤት


በኩል ይቀባበሉ፡፡

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም
DANIEL FIKADU LAW
http://wordpress.com/home/lawethiopiacomment.wordpress.com
OFFICE

2. በሰበር ሰሚ ችሎት ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪደርስ ድረስ በ ፌ/መ/ደ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር
173758 የተጀመረው አፈፃፀም ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ ታዟል ይፃፍ፡፡

3. ቀጠሮ ለ 09/05/2014 ዓ.ም ተቀጥሮአል፡፡ 4፡45 ሰዓት

የማይነበብ የሶስት ዳኞች ፊርማ አለበት

ማ/አ

ማስታወሻ፡ - ይህ የ ሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነ ድ ለጥና ትና ምር ምር ሥራ ወይም ለግን ዛ ቤ እ ን ጂ


ለፍር ድ አ ፈጻ ጸ ም ዓላማ አ ያገ ለግልም

You might also like