Professional Documents
Culture Documents
አዲስ አበባ
1|Page
ምልክቶች
መልመጃ
∆
ፍቺ/ማብራሪያ(Definition)
ምሳሌ
ማጠቃለያ
ማውጫ ገጽ
አጠቃላይ ዓላማ................................................................................................................................................2
I|Page
ዝርዝር ዓላማ...............................................................................................................................................2
ክፍል አንድ........................................................................................................................................................3
የአመራርነት ንድፈ ሀሳቦች (Leadership Theories)............................................................................................3
1.1 በመሪው ማንነት ላይ የተመሰረተ ንድፈ ሀሳብ (Trait Theories)............................................................3
3) አለቃ ያዝዛል፤ መሪ በትህትና ነገሮች እንዲሰራለት ይጠይቃል /A boss commands. A leader ask./........26
4.4 የስነ-አመራር አስፈላጊነት /IMPORTANCE OF LEADERSHIP/..........................................................28
ክፍል አምስት..................................................................................................................................................31
5. የአመራር ክህሎት....................................................................................................................................31
5.1 ንድፈሃሳባዊ ችሎታ/conceptual skill/...................................................................................................32
II | P a g e
5.2 ግለሰባዊ/ሰዋዊ ችሎታዎች.....................................................................................................................35
5.3 ውሳኔ አሰጣጥ እና የችግር አፈታት ክህሎት..............................................................................................36
III | P a g e
መግቢያ
ሥነ-አመራር እና መሪ የሚሉት ቃላት በጣም ጥንታዊ ናቸው። ስቶግዲል (1950) "ስነ-አመራር" እና "መሪ" የሚሉት
ቃላት በ 1300 ዎቹ እና 1800 ዎቹ ውስጥ ወሳኝ ጉዳይ እንደነበረ ይገልፃል በጊዜ ሂደት በተለያዩ መንገዶች ሲገለፁ
የነበሩ ሲሆን በተመሳሳይ አንዳንድ የመሪ ባህሪያት በአንድ ወቅት ተገቢ ሆነው ይታዩ የነበሩ ነገርግን በሌላ ጊዜ ተገቢ
አይደሉም ሲባል ይስተዋላል። በተመሳሳይ እንደ (MALIK, 2019) አገላለፅ የአንድ መሪ ባህሪ እና መገለጫ ከቦታ ቦታ
ሊለያይ ይችላል፡፡
የሃያኛው ክፍለ ዘመን የስነ-አመራር አረዳድ እና ትርጓሜን ስንመለከት በመሰረታዊነት የሚተረጎምበት አጠቃላይ
እንድምታዎች ከስነ ባህሪ፣ ከተፅህኖ ፈጣሪነት፣ ከመስተጋብር ንድፈ ሃሳብ፣ ከግንኙነት ሚና እና ከአስተዳደር ኃላፊነት
አንፃር ሲቃኙት ይስተዋላል (Yukl, 2013)፡፡ በአንድ አንድ ድርሳናት ላይ ስነ-አመራርን እና ስራ-አመራርን ተመሳሳይ
ትርጓሜ እንዳላቸው አድርጎ በመውስድ ፀሃፊያን ሲጠቀሙት ይስተዋላል፡፡ ይህም ሁኔታ በሁለቱ ሰፊ እና የረጅም ጊዜ
የሰው ልጅ ተሞክሮ በሆኑት ፅንሰ ሐሳቦች ላይ ያለውን ግልፅ አለመረዳት ያመላክታል ምክንያቱም የሁለቱን ትርጓሜ
በግልፅ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን ባለንበት ዘምን የምርት እና የአገልግሎት ተቋሞቻችን ለውድቀታቸው ተጠያቂ
ለስኬታቸው ተሞጋሽነት የሚሆኑት ባላቸው የስራ አመራር እና የስነ- አመራር ክህሎት እንደሆነ ይስተዋላል፡፡
ስለሆነም በዚህ የስልጠና ማንዋል መሰረታዊ በሆኑ የሥነ-አመራር ፅንሰ ሐሳቦች ዙርያ እና በተለይም ወቅቱ
በሚጠይቀው የአመራር ሚና ዙርያ በግልፅ የሚያብራራ እና በተለያዩ ድርሳናት ላይ የአመራር ክህሎቶች ተብለው
የሚለዩ ጉዳዬች በዓይነት እና በይዘት የሚለያዩ ቢሆንም ይህ ማንዋል በፐብሊክ ሰርቪሱ የአመራር ሂደት ውስጥ
ይህ የስልጠና ማንዋል አምስት ክፍሎችን የሚይዝ ሲሆን በክፍል አንድ የስነ-አመራር ስርዓተ ትምህርት ዝግመታዊ
ለውጥን የሚያትት ሲሆን በክፍል ሁለት ላይ የአመራርነት ፅንሰ ሃሳብ ትርጓሜን ሲይዝ በክፍል ሶስት የዓመራር
ዘይቤዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን በስፋት ይዳስሳል በክፍል አራት ላይ በስነ-ዓመራርና ስራ አመራር መካከል ያሉ
አንድነቶች እና ልዩነቶች በጥልቀት የሚዳስ ሲሆን በመጨረሻው ክፍል አምስት ላይ በጣም ወሳኝ የሆኑ የአመራር
1|Page
አጠቃላይ ዓላማ
የዚህ የስልጠና ሰነድ ዓላማ ሰልጣኞችን ከመሰረታዊ የአመራር ፅንሰ ሀሳቦች እና የአመራር ክህሎቶች ጋር ማስተዋወቅ ነው፡፡
ዝርዝር ዓላማ
በስልጠናው መጨረሻ ሰልጣኞች :
የአመራር ምንነትና ዘይቤዎች በተመለከተ ግንዛቤ ይጨብጣሉ፡፡
በስነ-አመራር እና ስራ-አመራር መካከል ያለውን አንድነት እና ልዩነት ይረዳሉ፡፡
የስነ አመራር ጠቀሜታን በተቋም ደረጃ እንዲረዱ ያስችላል፡፡
በስነ አመራር ክህሎቶችን በመለየት በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማስቻል፤
2|Page
ክፍል አንድ
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የረጅም ጊዜ ተሞክሮ እንደመሆኑ መጠን የስራ-አመራር መሰረትን እና ታሪካዊ ዝግመታዊ
ለውጡን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን በዘርፉ የተሰማሩ ሊቃውንቶች በአመራር ንድፈ ሃሳቦች እና መላምቶች
ላይ አከራካሪ ጉዳዮች የሚያነሱ ቢሆንም ሁሉም የክርክር ነጥባቸው ትኩረት የሚያደርጉት እንዴት አንድ መሪ የተሻለ
እና ውጤታማ መሪ ይሆናል የሚለው መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ነበር፡፡ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ንድፈ ሃሳቦች
የአመራርን ምንነት ለማስረዳት የሞከሩ ቢሆንም ሁልም ንድፈ ሐሳቦት በጊዜው የነበረው የአመራር ትርጓሜን
ለማስረዳት የሞከሩ ናቸው፡፡ በተለያየ ወቅት በርካታ ንድፈ ሐሳቦች የአመራር ምንነትን ለማስረዳት እንዲያስችሉ
ተደርገው የተነደፉ ቢኖሩም ዋንኞቹ እና በስነ- አመራር መስክ ውስጥ በሰፊው የተዋወቁት የሚከተሉት ናቸው፡-
ይህ ንድፈ ሐሳብ በዋናነት መሰረት የሚያደርግበት ሕሳቤ መሪ ይወለዳል እንጂ አይሰራም የሚል ሲሆን የመሪነትን
እጣፈንታ ከውልደት ጋር የሚያያዝ እንጂ ከጥረት እና ከትምህርት ጋር አለመሆኑን ያሳያል፡፡ የንድፈ ሀሳቡ ዋና ትኩረት
የመሪ መለያ መስፈርቶችን ማውጣት ላይ ሲሆን እንደ መሪ መለያ ነጥብ ትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች፡ ጾታ፣ ቁመት፣
ግርማሞገስ፣ በራስ መተማመን፣ ቅንነት፣ ዕውቀት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ነገር ግን እንደተለያዩ አጥኚዎች እይታ
ከመሪው የግል ባህሪና ማንነት ባለፈ ለመሪ ውጤታማነት አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ሌሎች ጉዳዮች ያሉ በመሆኑ Trait
በ 1939 ኩርት ሌዊን እና ረዳቶቹ በመሪ ማንነት ንድፈ ሀሳብ እና ህሳቤዎቹ ዙርያ ያካሄዱትን ጥናት መሰረት
በማድረግ በማንነት ላይ የተመሰረተውን ንድፈ ሃሳብን ተቀባይነት በማሳጣት መሪነት በትምህርት እና በልምድ
ሂደት ውስት ሊመጣ የሚችል ማንነት እንጂ በተፈጥሮ አይደለም በማለት ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል (IGNOU,
2017)፡፡ በመሆኑም ንድፈ ሀሳቡ በዋነኛነት መሪ ከተመሪዎች ጋር በሚኖረው መስተጋብር በተለያዩ ሁኔታዎች
3|Page
እንዴት አይነት ባህሪ ሊያሳይ ይገባዋል የሚለውን የሚመልስ ሲሆን የተለያዩ መሪ ሊያሳያቸው ይገባሉ የሚባሉ
• በዋነኛነት ለስራ ትኩረት መስጠት (Concern for task)- በዚህ የአመራር ዘይቤ መሰረት የመሪዎች ዋና
ትኩረት ያስቀመጣቸውን ግቦች ማሳካት ላይ ሲሆን ይሄን ለማሳካትም ከፍተኛ የሆነ ምርታማነት
ስለማምጣት እና ግቦች በተሻለ መልኩ ለማሳካት የሚያስችል የሰዎች አደረጃጀትና የስራ ስምሪት መፍጠር
ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡
ለሰው ትኩረት መስጠት(Concern for people)- በዚህ የአመራር ዘይቤ መሰረት የመሪዎች ዋና ትኩረት
አሳታፊ ያልሆነ አመራር (Directive leadership) - በዚህ የአመራር ዘይቤ መሰረት መሪዎች ውሳኔዎችን
ብቻ ይሆናል፡፡
አሳታፊ የሆነ አመራር (Participative leadership) - በዚህ የአመራር ዘይቤ መሰረት መሪዎች ተመሪዎች
በሁለንተናዊ ለውጥ አመራር ዕሳቤ ውስጥ የለውጥን የማያቆርጥ ሂደትን የሚረዳና አሁን ያለው አሰራር
የሚጠይቅ እና የሚፈትሽ መሆን አለበት፡፡ በዚህ የመሪ ተግባር ውስጥ እንደ መሪ የለውጥ ሐሳብ ማመንጨት፣
አዳዲስ አሰራሮችን መቃኘት እና ተከታዮች አዳዲስ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ የማገዝ እና የማበረታታት
ስራዎችን መስራት ይጨምራል፡፡
መሪ የዕለት ትናንሽ ስራዎች ላይ ሳይሆን በስራዎች ድምር ውጤት ሊመጣ የሚችውን ትልቁን ስኬት ማሰብ
እና የተቋሙን ራዕይ የሚቀርፅ መሆን መቻል ይኖርበታል፡፡ በዚህ የአመራር ተግባር ላይ መሪ ራዕይ ከማስረፅ
ባለፈ ተከታዮቹ ራዕዩን በባለቤትነት ስሜት እንዲቀበሉት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
መ. ተምሳሌት መሆን
አመራሮች ተምስላሌታዊ መሪ ከመሆን አንፃር ወጥነት ያለው ስብዕናን መላበስን የሚጠበቅባቸው ሲሆን
በዚህም ተግባር መሪዎች ለተቀመጡ የግብ መለኪያዎች፣ የአፈፃፀም መለኪያዎች፣ ለሚተገበሩ ህጎችና
አሰራሮች እና ተቋማዊ እሴቶችን ቅድሚያ መስጠት እና ተገዥ መሆን ከራሳቸው የሚጀምር መሆኑን
መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡
ሠ. የተመሪዎችን ልብ ማግኘት
ይህ ተግባር የመሪን አቅም እና ብስለትን የሚጠይ ሲሆን በርካታ መሪዎች የተከታዮቻቸውን ልብ ማግኘት ላይ
በተግባር ሲፈተኙ ይስተዋላል፡፡ ልብ የማግኘት ጉዳይ ለአንድ መሪ
5|Page
የተከታዩን በአካል መገኘትና የነሱን ጊዜ እንደማግኘት ቀላል የሚሆን ተግባር አይደለም፡፡ ተመሪዎች ልባቸውን
ለመስጠት የሚፈልጓቸው ነገሮትን ስንመለከት በመሪው ዘንድ ብዙ አቅምና ኢንቨስትመንት የሚጠይቁ
እንደ አጠቃላይ የቀድሞ የስነ-አመራር ንድፈ ሐሳቦች ትኩረት ያደርጉ የነበረው ስብዕና እና ባህሪያቸው ላይ
ሲሆን የቅርብ ጊዜ ንድፈ ሐሳቦች ደግሞ የአመራር ተግባራት ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ናቸው፡፡
ክፍል ሁለት
2. የአመራርነት ፍቺ/ትርጓሜ
አጠቃላይ ዓላማ
የዚህ የስልጠና ሰነድ ክፍል ሁለት ዋና አላማ አጠቃላይ በስነ-አመራር ትርጓሜ ከተለያዩ የዘርፉ ተመራማሪዎች አንፃር እና
አጠቃላይ የዕይታ ሁኔታዊችን ለሰልጣኞች ማስገንዘብ፡፡
ዝርዝር ዓላማ
በስልጠናው መጨረሻ ሰልጣኞች :
የአመራር ምንነት በተመለከተ ግንዛቤ ይጨብጣሉ፡፡
በስነ-አመራር ትርጓሜ ውስጥ መሰረታዊ ጉዳዮችን እንዲለዩ ማስቻል፡፡
6|Page
የመወያያ ነጥብ
የውይይቱ ዓላማ
በሥነ ጽሑፍ መስክ መሪነት በብዙ ፈላስፎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና መሪዎች በራሳቸው በተለያየ
መንገድ ይገለጻሉ። በተለያዩ ገጽታዎች ላይ በማተኮር የአመራር ብዙ ትርጓሜዎች አሉት። ስቶግዲል (1974)
“ጽንሰ-ሐሳቡን ለመግለጽ የሞከሩ ሰዎች እንዳሉ ያህል የመሪነት ትርጓሜዎች አሉ ማለት ይቻላል” ብለዋል።
አመራር ምን እንደሆነ ለመወሰን ሙከራ ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ነገር ግን ከተለያዩ ባህሎች እና አውድ
እይታዎች በቂ ጥናት አልተደረገም፡፡ በዚህ የጽሁፉ ክፍል የተለያዩ የአመራር ቁልፍ ፍቺዎች ተተንትነዋል።
Hicks and Gullet መሪ ማለት አስቀድሞ ያስቀመጠውን ግብና ኢላማ ለማሳካት አቅጣጫ ማሳየት
(1975) በሚያስችል መልኩ መቆጣጠርና አቅጣጫ የማሳየት ተግባር ነው፡፡ ግብን ማሳካት
Cuban (1988) መሪዎች ማለት የተከታዮቻቸውን ተግባር የሚቆጣጠሩ፣ ተነሳሽነት
ግቦታቸውን የሚያመላክቱ እና ተነሳሽነታቸውን የሚጨምሩ ናቸው አቅጣጫ ማሳየት
Erickson and Harvey መሪዎች ሙሉ ለሙሉ ለተቋም ለውጥና ውጤት ብቻ ሳይሆን የሰው ሃብት
(2011) ትኩረት የሚሰጡት በተከታዮቻቸው ለሚመዘገቡ ውጤትና እውቅና
ለተቋሙ አባላት ጭምር እንጂ፡፡
Silva (2016) መሪነት በተወሰነ አውድ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች አንድን ሰው እንደ ተፅእኖ
7|Page
ነው”
እንደ አጠቃላይ በስነ-አመራር ትርጓሜ ላይ ወጥ የሆነ አንድ ትርጓሜ ባይኖርም በአብኛው ፅሁፎች ይህ ትርጓሜን
ሲጋሩት ይስተማላል
የአመራርነት ትርጓሜ
ስነ-አመራር ተከታዮቹ የጋራ ዓላማ ሊያሳኩበት የሚችሉበት እና ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚግባቡበትና
የሚስማሙበት ለዚህም ውጤታማነት ግለሰቦችንና ቡድኖችን የምናስተባብርበት ሂደት ነው፡፡
ክፍል ሦስት
ዝርዝር ዓላማ
በስልጠናው መጨረሻ ሰልጣኞች :
እያንዳንዱን የአመራር ዘይቤ ምንነትን በተመለከተ ግንዛቤ ይጨብጣሉ፡፡
የአመራር ዘይቤዎችን መለያ ባህሪያቶችን እንዲለዩ ማስቻል፡፡
የእያንዳንዱን የአመራር ዘይቤዎች በምን ሁኔታና መቼ እንደምንጠቀማቸው እንዲለዩ ማስቻል፡፡
የአመራር ዘይቤዎች ጥንካሬና ደካማ ጎኖችን እንዲለዩ ማስቻል፡፡
1. የአመራር ዘይቤዎች/Leadership Styles
8|Page
የመወያያ ነጥብ
የውይይቱ ዓላማ
የመሪ የመምራት ችሎታ በእራሱ የስብዕና ሁኔታ እና በቡድን ውስጥ ባሉ የአባላት ባህሪ ተጽዕኖ ይደረግበታል። ስራን
ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስራት በጣም ጥሩ በሆነ የአመራር ዘይቤ መከተል የሚያስፈልግበት ጊዜዎች እንዳሉ ከግምት
ውስጥ ማስገባት ተገቢ ሲሆን በቡድን አባላት ባህሪ ጋር በተሻለ ሁኔታ ለመስራት ሲፈልጉ ተገቢውን ዘይቤ መከተል
ያስፈልጋል። በአጠቃላይ ቡድኑን ወደ ስኬት ለመምራት የሚከተሉትን የአመራር ዘይቤ ማወቅ ብቻ ሳይሆን
የሚከተሉትን ዘይቤ መቼ መለወጥ እንዳለቦ መረዳት ያስፈልጋል ፡፡ ልክ እንደ መሪው ስብዕና የአመራር ዘይቤዎችን
ለመከፋፈል ብዙ መንገዶች ሲኖሩን የተለያዩ ማዕቀፎችን መተግበር የሚያስፈልጓቸውን ሁኔታዎች እንደሚከተለው
ቀርቧል፡-
መቼ ጥቅም ላይ ይውላል?
9|Page
ከፍተኛ የሠራተኞች ፍልሰት በሚኖርበት ጊዜ ተቋማዊ እውቀትን በመሪው ውስጥ ብቻ ማቆየት አስፈላጊ
ሲሆን
አምባገነናዊ/ፈላጭ ቆራጭ የአመራር ዘይቤ ጥቅሞች እና ጉዳቶች
10 | P a g e
3.3 የቢሮ ስርዓት አመራር ዘይቤ/ the Bureaucratic Leadership Style
የቢሮ ስርዓት የአመራር አደረጃጀት ውስጥ የመሪው ትኩረት ሰራተኞች ደንቦቹን ወጥነት ባለው መልኩ እንዲከተሉ
ማድረግ ነው። ይህ ዘይቤ የኢንዱስትሪው ዘመን በጀመረበት ጊዜ በጣም ተወዳጅ ነበር። ምክንያቱም የፋብሪካ ሥራ
ጥራትን፣ የሰራተኞችን ጤና እና ደህንነት ለመጠበቅ የተወሰኑ ህጎችን እና ሂደቶችን ያስጠብቃል። በዚህ የአመራር ሁኔታ
መሪው ከሌሎች ምክንያቶች ይልቅ ከስልጣኑ የበለጠ የስራ ውጤት ያገኛል ተብሎ ይታመናል።
ሰራተኞች ባላቸው የፈጠራ ወይም አእምሮ አቅም ሳይሆን ህጎቹን መከተል በመቻላቸውና በምርታማነታቸው
ይሸለማሉ። በዚህ ዘይቤ በመሪዎቹ እና በሰራተኞቻቸው መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት ያለ ሲሆን በተለምዶ በነባርና
ትልልቅ ድርጅቶች ወይም በሆነ ምክንያት ድርጅታዊ መዋቅራቸውን ባላደጉ ድርጅቶች ውስጥ ይገኛል።
3.3.2 መቼ ጥቅም ላይ ይውላል
የመሪው ፍላጎት የቁጥጥር ምስልን መፍጠር ከሆነ የቢሮ ስርዓት የአመራር ዘይቤ ጥሩ ምርጫ ነው። እንዲሁም በጤና
እና ደህንነት እርምጃዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ለሚያስፈልጋቸው ተቋማት ተፈጥሯዊ ምርጫ ነው።
3.3.3 ቢሮ ስርዓት አመራር ዘይቤ ጥቅሞችና ጉዳቶች
11 | P a g e
3.4 የካሪዝማቲክ የአመራር ዘይቤ/ the Charismatic Leadership Style
3.4.1 ባህሪያት/ Characteristics
የዚህ ዘይቤ ዋናው ባህሪው መሰረት የሚያደርገው መሪው ሌሎችን የማነሳሳበት መንገድ ሲሆን በቁርጠኝነት ይህን
የሚያደርጉት ከቡድናቸው ጋር ያጋሩትን ተቋማዊ ራዕይ ለማሳካት ነው። መሪው ራዕዩን መፍጠርና አዳዲስ ሃሳቦችን
የማመንጨት ምናልባትም አደገኛ ሃሳቦች በማምጣት በተቋሙ ላይ የደስተኝነትን ሰሜት መፍጠር መቻልን ይጠይቃል።
የካሪዝማቲክ መሪ ለመሆን ትልቅ ጉልበት ይጠይቃል ምክንያቱም ቡድኑን በድርጅቱ ራዕይ እና ተልዕኮ ለማሳካት ያለውን
አጋጣሚ ሁሉ መጠቀምን ስለሚጠይቅ ነው። አንዳንድ የቡድኑ አባላት ለመነሳሳት ቀላል ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ቀስ
ብለው ወይም በሚያሳዝን ሁኔታ በጭራሽ ተነሳሽ ላይሆኑ ይችላሉ። ይህ ዘይቤ መሪው የግል ታማኝነትን በማሳየት
ከቡድን አባላት ጋር መተማመንን ለመፍጠር ባለው ችሎታ ላይ የተመሰረተ ነው።
12 | P a g e
3.5 ሌዝስፌር/ልቅ የአመራር ዘይቤ/ Laissez-Faire Leadership
ሌዝስፌር አመራር የውክልና አመራር በመባልም የሚታወቅ ሲሆን የመሪዎች ሚና ሳይኖርበት የቡድን አባላት
ውሳኔዎችን እንዲወስኑ የሚያስችል የአመራር ዘይቤ ነው። ይህ በቡድን አባላት መካከል ዝቅተኛ ምርታማነት
እንዲኖር የሚያደርግ የአመራር ዘይቤ መሆኑን ተመራማሪዎች ይናገራሉ (Anbazhagan, 2014)፡፡ ሌስፌር
አመራርን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ መሪዎች የስራ አፈፃፀሙን ማረጋገጥ እና መደበኛ ግብረ-መልስ
መስጠት አለባቸ (Amanchukwu R. N., 2015)። ይህ ዘይቤ እንደ እነሱ በሚያውቁት የቡድን አባላት ጋር
መቼ በተሻለ ሁኔታ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት መሪዎች እንዲገነዘቡም ይረዳል (Anbazhagan, 2014)።
በሌዝስፌር መሪዎች ውስጥ በደንብ የሚሰሩ የተወሰኑ አይነት ሰራተኞች ሲኖሩ እና እነዚህም ሰራተኞች
ብዙውን ጊዜ የፈጠራ ችሎታ ይዘው ሲገኙ፣ በተቋሙ ወይም በኢንዱስትሪው ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆዩ
ሰራተኞች ሲኖሩን፣ የሙያዊ ብቃት ያላቸው ሰራተኞች የሚያደርጉትን በትክክል ስለሚረዱ ነገሮችን በደንብ
ለመስራት ብዙ አቅጣጫ ሰለማያስፈልጋቸው እና መሪዎች ብዙውን ጊዜ እምነት የሚጣልባቸው ሰራተኞች
13 | P a g e
ሲኖራቸውና የተረጋገጠ የስኬት መረጃዎች በመያዝ የበለጠ የስራ ነፃነት እንዲሰጣቸው ስለሚያስችላቸው
በየጊዜውየላቀ ብቃት የሚያሳይ የስራ ሃይል ሲፈጠር ይህ ዘይቤ ተገቢ ሆኖ ይገኛል።
14 | P a g e
3.6.1 የልውውጥ ተኮር መሪዎች ባህሪያት
የልውውጥ ተኮር አመራር ሰራተኞቹን ውጤት እንዲያመጡ ለማነሳሳት የተነደፈ ሲሆን ሽልማቶችን እና ቅጣትን
መሰረት ያደረገ አሰራር ነው። ግትር የሆነ አስቀድሞ የተገለጸ ሂደትን የሚከተል ጥብቅ ስርዓት ነው። ሰራተኞች
የሚጠበቅባቸውን ካሳኩ ይሸለማሉ ካላሳኩ ይቀጣሉ ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን ባህሪ ያሳያሉ፡- (Ward, 2010)
የይዘት ሽልማት/ Contingent reward:- የልውውጥ ተኮር አመራር ዘይቤ ሽልማቶችን እና እውቅና
ሰራተኞችን ለማነሳሳት እንደ አንድ መንገድ ይጠቀማል። በዚህ ስርዓት መሪዎቹ የሰራተኞችን አፈፃፀም
በቋሚነት ይቆጣጠራሉ ግባቸውን ሲያሳኩ ይሸልሟቸዋል።
በተለየ ሁኔታ ንቁ ስራ-አመራር/ Active management by exception:- በተለየ ሁኔታ ንቁ የአመራር
ዘይቤ አስተዳዳሪዎች የሰራተኛውን የስራ አፈጻጸም የሚቆጣጠሩ ሲሆን ስህተቶች ያሉባቸውን ቦታዎችን፣
በትክክል ያልተሰሩ ስራዎችን እና የአፈጻጸም ደረጃዎችን ያላሟሉ ቦታዎችን ለመለየት ጥረት ያደርጋሉ ችግር
እንዳዩ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል።
በተለየ ሁኔታ ንቁ ያልሆነ አስተዳደር/ Passive management by exception ፡- በተለየ ሁኔታ ንቁ ያልሆነ
አስተዳደር መሪዎቹ የሰራተኛውን የስራ አፈጻጸም በየጊዜው የሚቆጣጠሩ ቢሆንም ነገር ግን ሌላ አማራጭ
እስኪያመጡ ድረስ ችግሮችን እና ስህተቶችን ለማስተካከል እርምጃ ከመውሰድ የሚቆጠቡበት ሌዝስፌር ባህሪ
ነው።
የፍትሃዊነት ስሜት ይፈጥራል/ Creates a sense of fairness፡- ግንኙነቶችን በመገንባት ላይ ትኩረት ማጣት/ Lack of focus on
በልውውጥ ተኮር አመራር የሚሰጡ ግብረ-መልሶች ከአስተዳዳሪው building relationships፡-
አስተያየት ወይም ስሜት ይልቅ ፍትሃዊ እና በመለኪያዎች ላይ የልውውጥ ተኮር አመራር መሪዎች ሰራተኞችን ለማነሳሳት እና እርካታን
የተመሰረተ ነው። በዚህ አቀራረብ ሁሉም ሰራተኞች በተመሳሳይ ለማሳደግ ሽልማቶችን በመጠቀም ላይ ያተኩራሉ። የሰራተኞችን ተሳትፎን
መንገድ ይለካሉ ይሸለማሉ። እና እርካታን ለማሳደግ አነሳሽ የሆነውን ሰራተኞች ከመሪዎቻቸው ጋር
ያላቸውን የግንኙነት ሁኔታ ላይ ትኩረት አያደርጉም።
ለመረዳት ቀላል ስርዓት/ Easy-to-understand system፡- ሁሉንም ሰራተኞች የሚያነሳሱ ሽልማቶችን ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑ/
የሽልማት እና የቅጣት ስርዓቱን ለመረዳት ቀላል እና ሌላ አሻሚ Difficult to find rewards that motivate all employees፡-
ትርጉም ለመስጠት የማይመች ነው። ሰራተኞቻቸው ምን ማሳካት ሁላችንም ተመሳሳይ በሆኑ ምክንያቶች አንነሳሳም። አንዳንዶቻችን
ተጨማሪ ገንዘብን እንደ ሽልማት ነው የምናየው፣ ሌሎች ደግሞ የእረፍት
እንዳለባቸው፣ ምን እንደሚሸለሙ እና ግባቸውን ካላሳኩ ደግሞ
ጊዜን እናደንቃለን እና ሌሎች እንደ ፕሪሚየም የጤና ኢንሹራንስ ወይም
ውጤቱ ምን እንደሆነ ያውቃሉ። ተለዋዋጭ የስራ መዋቅር ያሉ ጥቅማጥቅሞችን እንፈልጋለን።
ሰራተኞች በተቋሙ ላይ ያላቸውን ተፅእኖ ማየት ያስችላል/ ፈጠራን ያዳክማል/ Discourages creativity፡-
Employees can see their impact on the business፡- በአንድ ተቋም የሥራ ፈጠራን እና እድገት እንዲኖር ከተፈለገ ሰራተኞች
ሰራተኞች ግባቸውን ካሳኩ ወይም የበለጠ ከሰሩ ተቋማቸው የበለጠ እና መሪዎች ስለ ውጤቶቹ ሳይጨነቁ ስህተት መስራት እና ውደቀትን
ማስተናገድ አለባቸው።
ቀልጣፋ ስራዎችን እንዲያከናውን ፣ አዲስ የምርት መስመር
እንዲፈጥር እና ገቢን እንደሚያሳድግ ያውቃሉ።
15 | P a g e
የረጅም ጊዜ ራዕይ የለውም/ No long-term vision፡-
የልውውጥ ተኮር አመራር በአጭር ጊዜ ግቦች እና እቅድ ላይ በማተኮር
የወደፊቱን ትልቅ ምስል ወይም ራዕይ ይጥላል።
በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ይፋ የወጡ የድርጅት የስነምግባር ቅሌቶች ተከስቷል። በ 2000
እና 2003 መካከል; የኢንሮን፣ ወርልድኮም፣ አርተር አንደርሰን ኤልኤልፒ፣ Qwest Communications
International Inc. እና Global Crossing Ltd. የመሳሰሉ ተቋማት የኮርፖሬት የስነ-ምግባር ቅሌቶች ሲናወጡ
ተስተውሏል። በባለሀብቶች ዘንድ በኮርፖሬሽኖች እና በመሪዎች ላይ ያላቸው እምነት ፣የሥነ ምግባር አመራር
አስፈላጊነት እና የባለድርሻ አካላትን የረጅም ጊዜ ጥቅሞች ግምት ውስጥ ማስገባት የበለጠ ተቀባይነት እያገኘ
መጥቷል።
አገልጋይ አመራር የመሪውን ሚና የሌሎችን ፍላጎት ማገልገል እንደሆነ የሚገልጽ የአመራር ዘይቤ ነው። በዚህ ዘይቤ
መሰረት የመሪው ተቀዳሚ ተልእኮ ሰራተኞችን ማፍራት እና ግባቸው ላይ እንዲደርሱ መርዳት ነው። አገልጋይ መሪዎች
ሰራተኞቻቸውን የሚያስቀድሙ፣ የግል ፍላጎቶቻቸውን እና ምርጫዎቻቸውን የሚገነዘቡ፣ የሚያበረታቱ እና
በሙያቸው እንዲያድጉ ሌሎቹን የሚረዱ ናቸው። ከዋናው የአስተዳደር አካሄዶች በተለየ በአገልጋይ አመራር ውስጥ
ዋነኛው አላማ ሰራተኞችን ለድርጅታዊ ግቦች አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ይልቁንም የአገልጋይ
መሪዎች ለሠራተኞቻቸው፣ ለደንበኞቻቸው እና ለውጭው ማህበረሰብ ግዴታ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። በዚህ
የአመራር ዘይቤ ውስጥ የሰራተኞች ደስታ በራሱ እንደ አንድ ስኬት የሚታይ ሲሆን አንዳንድ ጊዜም ሰራተኞቻቸውን
ስኬታማ ለማድረግ የራሳቸውን ደህንነት ይሠዋሉ። የሞራል ኮምፓስ እንዲኖረን ከሚደረግ ግልጽ ትኩረት በተጨማሪ
አገልጋይ መሪዎች ማህበረሰቡን የማገልገል ፍላጎት አላቸው። በሌላ አነጋገር ሌሎችን ለመርዳት የሚያደርጉት ጥረት
በተቋሙ ውስጥ ብቻ የተገደበ ሳይሆን በድርጅታቸው ዙሪያ ስላለው ሰፊው ማህበረሰብ ከልብ ያሳስባቸዋል እንጂ
(ግሪንሊፍ፣ 1977፣ ሊደን እና ሌሎች፣ 2008)። የታሪክ ምሁሩ ዶሪስ ኬርንስ ጉድዊን እንዳሉት “አብርሃም ሊንከን
በማህበራዊ ህሊና ሚዛኑ፣ ርህራሄ እና ልግስና ምክንያት አገልጋይ መሪ ነበር (ጉድዊን፣ 2005)።”
ምንም እንኳን የአገልጋይ አመራር ከሌሎች የአመራር አካሄዶች ጋር መደራረብ ቢኖረውም እንደ የለውጥ
(ትራንስፎርሜሽናል) አመራር ካሉ በሥነ ምግባር፣ በማኅበረሰብ ልማት እና ራስን መስዋዕትነት ላይ ያለው ግልጽ
ትኩረት የዚህ የአመራር ዘይቤ ልዩ መገለጫዎች ናቸው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት አገልጋይ አመራር በሰራተኛ
ቁርጠኝነት፣ የሰራተኛ በጎ ፈቃደኝነት እና የስራ አፈጻጸም ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ( Liden et al., 2008)።
የአገልጋይ አመራር አካሄድን የሚከተሉ መሪዎች በየክፍላቸው ውስጥ የፍትሃዊነት ሁኔታን ይፈጥራሉ፤ ይህም ወደ
ከፍተኛ የእርስ በርስ የመረዳዳት ባህሪ ይመራል ( Ehrhart , 2004)።
የአገልጋይ አመራር የራሳቸውን ፍላጎት እንዲያስቀድሙ፣ በስኬት እንዲመሩ እና ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው
እንዲነግሩ ለሚፈልጉ ብዙ አስተዳዳሪዎች ከባድ ሽግግር ነው። ብዙዎቹ የዛሬዎቹ የተቋማት መሪዎች በትህትና
አይታወቁም! ይሁን እንጂ ይህን አካሄድ የተከተሉ መሪዎች ውጤታማነቱን ይመሰክራሉ። በኒው ጀርሲ የሚገኘው
አክሽን ፋስት ፕሪንት ባለቤት ዴቪድ ቮልስኬል የ 24 ዓመት ልጅ እያለ የሕትመት ድርጅቱን አቋቋመ። ሰራተኞቹን ምን
16 | P a g e
ሊሰራላቸው እንደሚችል መጠየቅ የጀመረበትን ቀን የተቋሙ አዲስ ባህል እንደጀመረ ይናገራል። በሚቀጥሉት 2
ዓመታት ውስጥ የእሱ ኩባንያ ምርታማነቱን በ 30% ጨምሯል (ቡቻናን, 2007).
17 | P a g e
ክፍል አራት
ዝርዝር ዓላማ
በስልጠናው መጨረሻ ሰልጣኞች :
በስነ-አመራር/ Leadership እና ስራ-አመራር/ Management መካከል ያለውን አንድነት እንዲለዩ ማስቻል፡፡
በስነ-አመራር/ Leadership እና ስራ-አመራር/ Management መካከል ያለውን ልዩነት እንዲለዩ እና የተናጠል
ሚናቸውን ማስገንአብ፡፡
በመሪ እና አለቃ መካከል ያለውን መሰረታዊ ስድስት ልዩነቶች ላይ ግንዛቤ መፍጠር፡፡
2. ስራ-አመራርና ስነ-አመራር
የመወያያ ነጥብ
የውይይቱ ዓላማ
ስለ ስራ-አመራር ያላቸውን አስተሳሰብ እንዲፈትሹ ለማድረግ
በአመራር እና ስራ-አመራር መካከል ያለውን አንድነት እና ልዩነት እንዲገነዘብ
ማስቻል፡፡
በዓለቃ እና በመሪ መካከል ያሉት ልዩነቶችን እንዲረዱ ማስቻል፡፡
ለውይይት የተሰጠ ጊዜ: 5 ደቂቃ
የመወያያ ጥያቄ:
የስራ-አመራር ማለት ምን ማለት ነው?
የስነ-አመራር እና ስራ-አመራር መካከል ያለው አንድነት እና ልዩነት ያብራሩ?
መአለቃና በመሪ መካከል ያለው ልዩነት ያብራሩ?
ስነ-አመራር እና ስራ አመራር ተመሳሳይና አንድ ተግባር እደሆኑ የሚቆጥሩ እና በሌላ መልኩ የተለያዩና
የማይገኛኙ አድርገው የሚያስቡም አሉ፡፡ይሁን እጅ ሁለቱ በርካታ ተመሳሳይነት እዳላቸው ሁል ልዩነትም
አላቸው ፡፡ የመሪነትና የስራ አመራርን ልዩነት መመልከት የአስፈላጊነተታቸውን ደረጃ ለማውጣት እና አንዱ
18 | P a g e
ካንዱ የበለጠ ወይም ያነሰ ጥቅም አለው ለማለት ሳይሆን አንድነትም ልየዩነትም እዳላቸው አውቆ የተናጠል
እና የጋራ ጠቀሜታቸውን ለመረዳት ማስቻል ነው፡፡ ስለሆነም ርዕሰ ጉዳዩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ የመሪነትና
የማናጅመንት ሁኔታ በንስር አሞራ ሁለት ክንፎች መመሰል እችላላን፡፡ ንስር አሞራ ለመብረር ሁለቱም
ክንፎች ያስፈልጉታል በአንድ ክንፍ ብቻ ወይም ያለክንፍ ሊበር አይችልም ፡፡
አሁን በደረስንበት 21 ኛው ክፍለ ዘመን የተለመደው የማኔጅመት አሰራር ብቻውን በመተግበር እያደገ ያለውን
እና በማያቋርጥ ለውጥ ውስጥ እየሄደ ያለውን የቢዝነስ አሰራር መልስ መስጠት ስላልቻለ ስነ- አመራር
አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህም ሁለቱን በቅንጅት በመተግበር ተቋማዊ ስኬትን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
በተለይ ጠንካራ ተቋም /ድርጀት/ ለመፍጠር፣ የድርቱ አላማና ግቦች በተሟላ ማሳካት ይቻል ዘንድ ፣ ጠንካራ
አመራርና ስራ አስኪያጅ መኖር የግድ ይላል ከሁለቱ በአንዱ ላይ ድክመት ካለ አንዱ ሌላውን አይተካም
ድርጅቱም ደካማ መሆኑ አይቀሪ ነው፡፡ በተግባር እደሚታየው አንደኛው በተጎደለበት ቦታ የድርጅቱ እድገት
የማይታሰብ ይሆናል፡፡ የመሪነትና የስራ አመራር ተሰጥኦ በአንድ ሰው ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በዚህ
የማንዋል ክፍል የስነ-አመራር እና ስራ-አመራር አንድነታቸውና ልዩነታቸው እንደሚከተመው ቀርቧል፡-
ጥቅሞች/Advantage ጉዳቶች/Disadvantages
ራዕይ ይወልዳል ለሰዎች ያስተላልፋል የሰዎችን አቅም ይገነባል ግቦችን ያደራጃል ሂደቱን ይመራል ፣ይቆጣጠራል አስፈላጊውንም ሲሆን
19 | P a g e
የእርምት እርምጃ ይወሰስዳል
ስልጣኑ የሚመነጨው በውሥጡ ካለው ሰዎችን የማስተካከል ሃይለወ ነው፡፡ የስራ አመራር ስልጣን የሚመነጨው ቦታዎን ከሰጠው ተቋም ነው
በለውጥና በላውጥ እቅስቃሴ ላይ ያተኩራል በድርግት ወየይም ተቋም ውሥጥ መረጋጋት እዲፈጠር ጥረት ያደርጋል
ሰዎች በራይና ተልኮ ላይ ትኩረት እዲያደርጉ ያነሳሳል ህግ ተኮር በሆኑ አስፍላጊ ሽልማትና ቅጠጣት በመፈጸም ይቆጣጣራል
አንድ ወጥ ምንገድ አይከተልም ለአዳዴስና ሃሳቦችና ልዩነቶች ክፍት ነው በጥኝቃቂ በማቀድና በመቆጣጠር ግብ ለመምታት ይጥራል
ሰዎቸች ላይ ትኩረት ያደርጋል /Focusing people ሂደትና አሰራር ላይ ትኩረት ያደርጋል /Focusing system and
stractures
ስኬታማ በመሆን በመሆን ላይ ያተኩራል ትክክለኛውን ነገር ማድረግ የተሳለ ስራዎች በተገቢው መንገድ መከናዎናቸውን ነገርሮች በትክክል መከናን
በረጅም ጊዜ እቅዶች ላይ ያተኩራሉ አርቆ አሳቢና የሩቁን አይተው በአጫጭር ጉዳዮች ቅድሚያ ይሠጣሉ በድርጅቱ /በተቋሙ /የስልጣን
ሠራተኞቻቸው መሪ እንዲሆኑ የሚያነሳሱ እና የሚደግፉ ሲሆን፡፡ አለቆች ግን ሰውን መጥቀምና ተከታዮቹን መደገፍ
20 | P a g e
2. አለቆች ፍርሃት ያጭራል፤ መሪዎች በራስ የመተማመን ስሜት ያሳድራል /Bosses Cause
Nervousness. Leaders Inspire Confidence./
በአለቃ እና በመሪ መካከል ያለው ልዩነት ስሜትን የሚነኩበት መንገድ ነው። ሠራተኞች ሐሳባቸውን መግለጽ
በሚችሉበት በመንፈስ አነሳሽነት ከተሰማራ የሥራ ቦታ የበለጠ አለቃን ደስ የሚያሰኘው ነገር የለም።
አብዛኛውን ጊዜ አለቆች እነዚህን ባህሪያት ተስፋ የሚያስቆርጥ የፍርሃት መንፈስ ይፈጥራሉ፤ በዚያም
ማድረግ ያለብህ ነገር ቢኖር ለእነሱ አክብሮት ማሳየትና ሽልማት መስጠት ብቻ ነው ። ለዚህም ነው ትልቅ
21 | P a g e
3) አለቃ ያዝዛል፤ መሪ በትህትና ነገሮች እንዲሰራለት ይጠይቃል /A boss commands. A leader
ask./
ሁላችንም የምናውቀው አለቃዎች ቀጥታ ትዕዛዝ በመስጠት እናጂ እራሱን የስራው አካል በማድረግ በትህትና
አይጠየቁም ይህ ማለት ትዕዛዝ ይሰጣሉ እንጂ ፈጽሞ አይሰሙም!፡፡ ይሁን እንጂ መሪዎች ሁልጊዜ የሥራ
የዘርፉ መሪዎች እንደሚሉት ታላላቅ መሪዎች ሰርተው የሚያሳዩ እንዲ ተናግረው የሚያሰሩ አይደሉም፡፡ አለቆችን
ስንመለከት ስራዎችን በንድፈ ሃሳብ የሚያውቁ እና የሚናገሩ እንጂ ሰርተው የሚያሳዩ አይደሉም፡፡
አለቆች በጋራና በቡድን ጥረት በሚመጡ ስኬቶች የራሳቸው እና የግል ጥረታቸው እንደሆነና እራሳቸው ብቻ
እንዲሞገሱ የሚፈልጉ ሲሆን መሪዎች ደግሞ ለሚገኝ ስኬት በጋራ አድናቆች እና እውቅናን የሚሰጡ ሲሆን በሁለቱ
መካከል ያለው ልዩነት "እኔ" እና "እኛ" ነው፡፡
22 | P a g e
6) አለቃ ትልቅ ውጤት ይጠብቃል፤ መሪ ምስጋና ለጋስ ነው /A boss expects big results. A leader is
generous with praise./
23 | P a g e
4.4 የስነ-አመራር አስፈላጊነት /IMPORTANCE OF LEADERSHIP/
የመወያያ ነጥብ
የውይይቱ ዓላማ
አመራር ውጤታማነትን ከፍ ለማድረግ እና ተቋማዊ ግብን ለማሳካት የሚረዳ ጠቃሚ መሳሪያ ነው። ከዚህ
አኳያ በማንኛውም ደረጃ የሚገኝ አንድ መሪ አፉን ሞልቶ የተቀመጠውን ግብ በተሟላ መንገድ አሳክቻለሁ
ማለት የሚችለው ስኬታማነትን እና ውጤታማነትን አጣምሮ ማሳካት ሲችል ነው፡፡ ይህም እንዴት
እንደሚገለጽ በሚከተለው የማትሪክስ ሰንጠረዥ አማካኝነት በቀላሉ መረዳት ይቻላል (Nursalim, 2022)፡፡
ከፍተኛ
ውጤታማነት
ዝቅተኛ
ዝቅተኛ ከፍተኛ
ስኬታማነት
ከላይ ከተገለጹት የውጤታማነት እና ስኬታማነት መለኪያዎች አንዱ እንኳን ባልተሟላበት ሁኔታ ግቤን
አሳክቻለሁ የሚል መሪ ሊኖር አይገባም፤ ምክንያቱም ከሁለቱ አንዱ የጎደለው የታለ ተብሎ መጠየቅ መቻል
ይኖርበታል፡፡ ውጤት የተባለው ስራ፤ ምናልባት ኪሳራም ሊሆን ይችላልና፤ ከፍተኛ የሪሶርስ አጠቃቀም
የሚለው አገላለጽ ሪሶርስን ሳያባክኑ በከፍተኛ ብቃትና ቁጠባ የተጠቀመ መሪ መሆኑን ያመለክታል፡፡
24 | P a g e
ይህን መነሻ በማድረግ ከላይ ከተመለከትናቸው አራት የድርጅት ስራ መሪዎች መካከል ስኬታማው ስራ መሪ በ
"ለ" ሳጥን ውስጥ የተመለከተው ከፍተኛ የግብ አፈፃፀምና ከፍተኛ የሪሶርስ አጠቃቀም ያስመዘገበው ሲሆን፤
መሸለምም ሆነ መመስገን ካለበት እርሱ መሆን አለበት፡፡ የተቀሩት ሦስቱ ማለትም "ሀ"፣ "ሐ" እና "መ" ግን
ተቋሙን ለኪሳራ የሚዳርጉ ስራ መሪዎች በመሆናቸው አንድ ሊባሉ ወይም ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡
1. ሰራተኞችን ለማነሳሳት፡- ስራን በተሻለ ሁኔታ ለማሰራት ከሚያስችሉ መንገዶች ውስጥ አንዱ የመሪዎች
የማበረታቻ እና የማንቂያ ስርአትን መከተል ነው፡፡ መሪዎች ሰራተኞቻቸው ለተቋማቸው ያላቸውን
አቅም አሟጠው እንዲጠቀሙ ያደርጋሉ (Alam, 2016)፡፡
2. ተቋምን ከለውጥ ጋር እንዲላመድ ለማስቻል፡- መሪዎች በማደግ ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን፣ የገበያ አዝማሚያዎችን
እና ተግዳሮቶችን የሚዳስሱና በአስቸጋሪ ጊዜ ተከታዮቻቸው ሊያሳኩ የሚፈልገው ግብ ላይ እንዲያተኩሩ እና
በተገቢው መንገድ እንዲጓዙ ብቃት እንዲኖረው ይጠበቃል።
3. በተከታዮቹ ዘንድ በራስ መተማመንን ይፈጥራል፡- በራስ መተማመን ወሳኝ ነገር ሲሆን ይህም የስራ
ጥረትን ለተከታዮች በመግለጽ ማግኘት ይቻላል።
4. ጥሩ የስራ ሁኔታን ይፈጥራል/ይሰጣል፡- መሪ ግለሰቦች ወደ አላማዎች በደስታ የሚገቡበትን ጤናማ የስራ
ሁኔታን ይሰጣል። እሱ ለሰራተኞች ምናባዊ፣ አርቆ አስተዋይነት፣ ጉጉት እና ተነሳሽነት ይሰጣል እና
የፍላጎት፣ የአመለካከት እና የድርጊት መለያ እንዲኖራቸው ያስገድዳቸዋል።
5. ኃላፊነትን በመውሰድ ይጀምራል፡- መሪ ማለት ስራው በትክክል ከተጀመረበት ቦታ ሆነው ፖሊሲዎችን
እና እቅዶችን ለተከታዮቹ በማስተላለፍ ስራውን የሚጀምር እና በተግባሩም ውስጥ መላውን ቡድን
የሚመራው ነው።
6. በሰራተኞች ዘንድ ተነሳሽነትን ለመጨመር፡- መሪ በተቋም ውስጥ የማበረታቻ ስርዓትን በመተግበር
ተከታዮቹ ለሚያስመዘግቡት ኢኮኖሚያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ማበረታቻዊችን በመስጠት
የተከታዮቹን ተነሳሽነት እንዲኖር የመስራት ስራ እንዲስራ ያስችለዋል፡፡
7. ሞራልን ለመገንባት፡- ሞራሌ ማለት ሰራተኞቹ በስራቸው ላይ ያላቸውን የፈቃደኝነት ትብብር፣ በራስ
መተማመን እና እምነትን ማሳደር ያመለክታል። አንድ መሪ ሙሉ ትብብርን በማግኘት የሞራል
ማበረታቻ ሊሆን ይችላል ይህም ግቦችን ለማሳካት በሚሰሩበት ጊዜ አቅማቸውን በተሻለ ሁኔታ
እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል።
8. ጥሩ የስራ አከባቢ ለመፍጠር ያስችላል፡- በአንድ ተቋም ውስጥ በመሪና ተከታዮቹ መካከል መልካም
የሚባል የግል ግንኙነት ሊኖረው እና ችግሮቻቸውን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት እያዳመጠ የሚፈታበት
ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ያስችለዋል፡፡ እንደ አጠቃላይ ሰራተኞችን በሰብአዊነት አያያዝ እንዲኖር
ያስችላል፡፡
25 | P a g e
9. ተቋማዊ ምርታማነትን/ ስኬታማነትን ያሻሽላል፡- የአንድ ቡድን ምርታማነት በአመራር ውጤታማነት
ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ደካማ መሪ በበኩሉ ሰራተኞችን ከስራ ውጪ እንዲሆኑ እና ለሥራቸው ፍላጎት
የሌላቸው እንዲሆኑ ያደርጋል በሌላ በኩል ደግሞ እጅግ በጣም ጥሩ የአመራር ዘይቤ የቡድኑን አፈፃፀም፣
ውጤታማነት እና አጠቃላይ ስኬት ይጨምራል፡፡
10. ጠንካራ የተቋም ራዕይ እና አቅጣጫ እንዲኖር ያስችላል፡- ጥሩ መሪ የጠራ ራዕይ መኖር ያለውን
ጠቀሜታ እና አንድን ቡድን ወደ ብልጽግና ለመምራት የሚያስችሉ መንገዶችን እንዴት ማዳበር
እንዳለበት ያውቃል። ጥሩ ሀሳብ የድርጅቱን አቅጣጫ እና ግቦች የተለየ ግንዛቤ መያዝን ያካትታል።
ክፍል አምስት
5. የአመራር ክህሎት
አጠቃላይ ዓላማ
የዚህ የስልጠና ሰነድ ክፍል አምስት በስነ-አመራር/ Leadership ክህሎቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ
እንዲፈጥሩ ማስቻል፡፡
ዝርዝር ዓላማ
በስልጠናው መጨረሻ ሰልጣኞች :
የስነ-አመራር/ Leadership ክህሎቶችን እንዲለዩ ማስቻል፡፡
በስነ-አመራር/ Leadership ክህሎትች ምንነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ማስቻል፡፡
26 | P a g e
የመወያያ ነጥብ
የውይይቱ ዓላማ
የአመራር ክህሎት አንድ መሪ በተሳካ ሁኔታ ግቦችን እና ዓላማዎችን ለማሳካት ሊኖሩት የሚገባ እና ሊጠቀምባቸው
የሚገቡ ብቃቶች እና እውቀቶች ናቸው። ካትዝ የሚባለው የዘርፉ ተመራማሪ ውጤታማ አመራር በሶስት ዓይነት የግል
ክህሎቶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጿል። እነሱም፡- ቴክኒካል ክህሎቶች (የቡድን ግንባታ፣የጊዜ አመራር፣የውሳኔ
አሰጣጥና ችግር አፈታት ክህሎቶች)፣ ግለሰባዊ/ ሰዋዊ እና ፅንሰ-ሐሳባዊ ክህሎቶች ናቸው። እነዚህ ክህሎቶች
ከመሪዎች ግላዊ ባህሪያት በእጅጉ የሚለዩ ናቸው። ባህሪያት መሪዎቹ እነማን እንደሆኑ ሲገልጹ፣ ክህሎቶች መሪዎቹ
ምን ማከናወን እንደሚችሉ የሚወስኑ ናቸው (Katz, 2009)።
ችሎታዎች ናቸው። የእለት ተእለት ስራዎችን ከመመልከት፣ የፅንሰ-ሃሳብ ችሎታዎች መሪዎች የተቋማትን
ትላልቅ ግቦች እንዲመለከቱ እና ለእነሱ የሚሰሩባቸውን መንገዶች እንዲያቅዱ ይረዳሉ። እነዚህ ችሎታዎች
የፅንሰ-ሀሳብ ችሎታዎች ትርጓሜ በተቋም ውስጥ ትልቅ ምስልን የማየት ችሎታ ሲሆን ለምሳሌ ትልወቁ
ፕሮጀክት ወደተግባር አፈፃፀም ከመግባቱ በፊት በቅድሚያ ፕሮጀክቱን ለምን እደሚሰራ መረዳት
የሚገነዘብብት መሰረታዊ አስተሳሰሳብ ሲሆን የፅንሰ-ሀሳብ ችሎታ ያለው ሰው ለምን አንድ ነገር እየተሰራ
እንደሆነ ሊረዳ የሚያስችልና የተቋሙን ግቦች ማሳካት ላይ ያተኮሩ በመሆኑ እነዚህ ችሎታ የአመራር
27 | P a g e
ሀ. የትንተና/analysis/፡- የተቋሙ ሰራተኞች ግቦች ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል ሁኔታን መተንተን መቻል እና
መሪዎች ለስኬት መለኪያዎችን እንዲፈጥሩ እና ተቋሙ ወደፊት እንዴት እንደሚሰራ የሚቀርፅ መረጃ
እንዲሰበስብ ያግዛል። ትንተና ለተቋሙ ስኬት ወሳኝ በሆኑ ጽንሰ ሃሳብ ፣ ሂደቶችና እና ሃሳቦች መካከል
ለመፍታት የትንታኔ፣ ችግር ፈቺ፣ ቅንጀት እና የተግባቦት ችሎታዎችን ማሰባሰብ ይጠይቃል። ፈጠራ
የማሰብ ችሎታን የሚያሰፋ በመሆኑ ሰዎች አንድን ሁኔታ በልዩ እይታ መገምገም ያስችላል (Indeed carer
ኪዚህ በፊት የሚታወቀውን መፍትሄ ከግምት ውስጥ ማስገባት /Consider the obvious solution or
process/
ተጨማሪ የመፍትሄ ሃሳቦችን መዘርዘር /Brainstorm additional solutions/
ትኩረት መስጠት ከተቋሙ አጠቃላይ ግቦች ጋር ጥሩ ውሳኔዎችን ለማድሰሳለፍ አስፈላጊ ነው፡፡ 7 ወሳኝ
የጥልቅ አስተሳሰብ ስልቶች ከፍተኛ አፈጻጸም ያላቸው መሪዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለማድረግ
28 | P a g e
የጥልቀት አስተሳሰብ በመሪዎች ውስጥ በተለይም በዚህ ዘመን አዲስ በመሆኑ መዳበር ያለበት ክህሎት ነው።
ከፍተኛ አፈፃፀም ያላቸው መሪዎች ሁኔታዎችን በጥልቀት ማሰብ እና ያለፉትን ልምዶች መሳል
እንዳለባቸው አስፈላጊ ቢሆንም ውሳኔ ለማሳለፍ ያለፉ ተሞክሮ ብቸኛ አማራጨጭ እንዲሆኑ አለመፍቀድ
በጣም አስፈላጊ ነው። ልምድ ያካበቱ መሪዎች ከባለፈው አፈፃፀማቸው ጠቃሚ መረጃዎችን እና
ምልከታዎችን ከተሰራው እና ከዚህ በፊት ካልተሰራው ነገር መውሰድ እዳለባቸው ያውቃሉ ፡፡ መሪዎች
መንገድ ለማስተዳደር እና አዳዲስ መፍትሄዎችን ለመፍጠር አዲስ ቴክኖሎጂ ማከተት እዳለባቸወ ማወቅ
ተገቢ ነው ።
አንድ መሪ በሚመሩት ሰራተኛ መሀል ሄዶ በተግባር ሊያያቸው የሚገባ ሲሆን ከቡድን አባላት ጋር በተናጠል
ስለሚችሉት ነገሮች ጠቃሚ መረጃ ያገኛሉ ። ሰራተኞች መሪው ትኩረት እዲሰጠው የሚፈልጉትን
ከልምድ ጋር እንደሚያዋህዱት ማየት ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ እርምጃ ሲወሰድ፣ ሊጠየቁ የሚገባቸው ሁለቱ
29 | P a g e
ጥያቄዎች፡- የምወስደው እርምጃ የምፈልገውን ውጤት ከማግኘት ጋር የተጣጣመ ነው ወይ? እና የወሰድኩት
እርምጃ የሚጠበቀውን ውጤት አግኝቷል? ካልሆነ ለምን? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ቀጣዩ
አዳዲስ እውቀቶች እና ልምዶች ሲዋሃዱ ይህ አዲስ መረጃ እንዴት እንደሚተገበር እና እንዴት እንደሚዋሃዱ
አስፈላጊ በመሆኑ ሰዎች የሚያውቁት ነገር በመለየት ውሳኔው ምንም ቢሆን የሚደግፉትን እና የማይደግፉ
ሰዎችን ታገኛለህ፡፡
ተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎች ስላላቸው ልምድ ቃለ መጠይቅ ማድረግ በየጉዳይ ጥናት ወይም ሁኔታ ትንተና
እንደ አዲስ መሪ ሰዎች በሃሳባቸው እና በድርጊታቸው እንዲስማሙ ማድረጉ የመሪውን ሁኔታ ማረጋገጫ
ሊሆን ይችላል። ምንም እንኳን የድሮው አባባል ራስህን ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር እንድትከበብ
30 | P a g e
5.2 ግለሰባዊ/ሰዋዊ ችሎታዎች
ቴክኒካል ክህሎቶች ከነገሮች ጋር መሥራትን የሚያካትቱ ሲሆኑ፣ ግለሰባዊ ወይም ሰዋዊ ክህሎቶች ግን ከሰዎች ጋር
መስራትን የሚያንጸባርቁ ናቸው። መሪዎች ስለ ሰው ባህሪ እና የቡድን ግንባታ ሂደት እውቀት ሊኖራቸው ይገባል
እንዲሁም የተከታዮቻቸውን ስሜት፣ አመለካከት እና ዓላማ መረዳት መቻል አለባቸው። ግለሰባዊ ክህሎት መሪዎች
ከተከታዮቻቸው፣ እኩዮቻቸው፣የበላይ አለቆች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰሩ ያስችላቸዋል።
ከግለሰባዊ ክህሎት ወሳኝ ክፍል አንዱ የሌሎች ሰዎች እሴቶችን፣ አላማዎችን እና ስሜቶችን የመረዳት ችሎታ ነው።
በተጨማሪም በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ ተቀባይነት ያላቸውን ባህሪያቶች ለማወቅ የሚያስችል ማህበራዊ ግንዛቤን
ያካትታል።
እንደ መሪ ተገቢውን የተፅዕኖ መፍጠሪያ ስትራቴጂ የመምረጥ ችሎታ የሚወሰነው ተከታዮች ምን እንደሚፈልጉ እና
አንድን ሁኔታ እንዴት እንደሚገነዘቡ በማወቅ ላይ ነው። እራሳቸውን ቀጣይነት ባለው መንገድ የሚከታተሉ መሪዎች
የራሳቸውን ባህሪ እና በተከታዮቻቸው ላይ የሚኖረውን ተፅእኖ በተሻለ ሁኔታ ይገነዘባሉ። እንደነዚህ ያሉት መሪዎች
ራሳቸውን ከሁኔታዎች ጋር እንዲያላምዱ ባህሪያቸውን ማስተካከል ይችላሉ። በአመራር ተፅእኖ ሂደት ውስጥ ጠቃሚ
የሆኑ ሌሎች ግለሰባዊ/ሰዋዊ ክህሎቶች የቃል ተግባቦት እና የማሳመን ችሎታ ያካትታል።
ውጤታማ አመራር ሰጪነት መሪው ባለው ብቃት ላይ የተመሰረተ ነው። ጠንካራ የግለሰባዊ/ሰዋዊ ክህሎት ያላቸው
መሪዎች የቡድን ትብብርን ያሳድጋሉ፣ የጋራ ግቦችን ለማሳካት ይደግፋሉ፣ እንዲሁም በተፅእኖ እና በአስተምህሮ
የአመራር ዘዴዎች ስኬታማ ይሆናሉ። ካትዝ እንዲህ ብሏል:- “ከሌሎች ጋር የመሥራት እውነተኛ ክህሎት በውሳኔ
አሰጣጥ ወቅት ብቻ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ የዕለት ተዕለት ባህሪ ውስጥም ስሜታዊነትን ስለሚጨምር ከሌሎች ጋር
የመሥራት ችሎታ ተፈጥሯዊና ቀጣይነት ያለው ተግባር መሆን አለበት። አንድ መሪ የሚናገረው እና የሚያደርገው ሁሉ
በባልደረቦቹ ላይ ተጽእኖ ስላለው እውነተኛው ማንነቱ በጊዜ ሂደት ይታያል ይላል። ስለዚህ ውጤታማ ለመሆን ይህ
ክህሎት በተፈጥሮ የዳበረ እና በተከታታይ በግለሰቡ እያንዳንዱ ድርጊት ውስጥ መገለጥ አለበት። ከሱፐርቫይዘሮች እና
ከመካከለኛ አመራር ጀምሮ እስከ የድርጅቱ ከፍተኛ የአመራር ቦታዎች ድረስ እንደዚህ ያሉ ክህሎቶች በሁሉም
ደረጃዎች አስፈላጊ ናቸው። (James W. Holsinger, 2018)
ተግባሮች ውሳኔዎችን በመወሰን የሚከናወን ሂደት ነው፡፡ ታድያ አንድ መሪ ውሳኔ በመስጠት እና ባለ መስጠት
፣ውሳኔን በመተግበርና ባለመተግበር እንዲሁም ለውሳኔ በመገዛትና ባለመገዛት ሊመጣ የሚችል ውድቀት እና
ስኬት እንዳለ መረዳት ይኖርበታል፡፡ በማንኛውም የስራ ደረጃ ያለ መሪ ብቃት ከሚረጋገጥባቸው አበይት
ጉዳዮ ውስጥ አንዱ በሚሰጠው የውሳኔ ትክክለኛነት እና ወቅታዊነት ነው ፡፡ ውሳኔ አሰጣጥ ሆንብልን
የምናከናውነው ተግባር ሲሆን በእያንዳንዱ የችግር አፈታት ሂደት ላይ የተሻለውን የመፍትሔ መንገድ
31 | P a g e
ለመምረጥ የሚያስችል ዘዴ ነው። ይህም ችግሩን ለመፍታት ከሚወሰዱ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ
አንድ መሪ ውሳኔ ከመስጠቱና ውሳኔውን ከመተግበሩ በፊት የችግርን ምንነት እና ተያያዥ ጉዳዮችን መረዳት
ይኖርበታል፡፡ ችግር ማለት የተወሳሰበና ምላሽ ያላገኘ ጥያቄ ነው፡ የግራ መጋባት፣ የጭንቀት ወይም የብስጭት
ምንጭ ሲሆን ይስተዋላል እሱም የሚያመለክተው አንድ ሰው አሁን ባለበት እና መድረስ በሚፈልግበት
መካከል ክፍተት መኖሩን ነው፡፡ ስለሆነም ችግር አፍታት ሁኔታን በዘዴ ለመመርመር እና መፍትሄዎችን
ለመፍጠር፣ ለመተግበር እና ለመገምገም ያለሙ ተግባራትን ማከናወን ነው። ይህም በአንድ ተቋም ውስጥ
ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ መፈለግን ያካትታል። የችግር አፈታት ሂደት ጥልቅ እውቅና እና ችግሮች
ለመፍታት የተወሰኑ ውሳኔዎችን ወደ መግባባት መቀየር የሚያስችል ቁርጠኝነት ይፈልጋል። ችግሮች በተቻለ
መጠን በጥናት ላይ የተመሰረተ መፍትሔን የሚፈልጉ ሰለሚሆኑ አመራሮች በችግር አፈታት ሂደት ላይ
የተሻለ አረዳድ ለመፍጠር ስለችግሩና ተያያዥ ጉዳዮች በቀላሉ ለመረጃት የሚከተሉትን ነጥቦች ላይ ትኩረት
ሊደረግባቸው ይገባል፡-
ራሱ ችግሩ/ Problem
ስለሆነም መሪ ችግሩ ይህ ነው ከማለቱ በፊት በርጋታ እነዚህን ጉዳዮች ማየት እና የእርስ በእርስ
ሃምሳ በመቶ እንደማግኘት ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን የሃሳቡ ትክክለኛነት የሚረጋገጠው ችግሩን ከተረዳን በኃላ
በዝርዝር የተጠኑ አማራጮች ቀርበውለት ወደ ተሻለ የመፍትሔ ውሳኔ መድረስ ስንችል ነው፡፡
ውሳኔ ስንል ከአንድ ችግር ተነስተን መፍትሔ ይሁናል ብልን የምናስበው እርምጃና ድምዳሜ ነው፡፡ ውሳኔ
ለችግሩ መፍትሄ ስትራቴጂያዊ አተገባበር ነው፡፡ ውሳኔዎች በአምስት ዋና ዋና ዓይነቶች ሊከፈሉ ይችላሉ
እነዚህም ፡-
32 | P a g e
የግል ውሳኔዎች ለሌሎች ሊተላለፉ የማይችሉ ውሳኔዎች ናቸው። እነዚህ ውሳኔዎች የግል ግቦችን ለማሳካት ብቻ
የታሰቡ ሲሆኑ ድርጅታዊ ውሳኔዎች ደግሞ ድርጅታዊ ግቦችን ለማሳካት የሚወሰዱ ውሳኔዎች ናቸው።
መደበኛ ውሳኔዎች በባህሪያቸው በዕለት ተዕለት ተግባር የተቋማትና ግላዊ ህይወት እንቅስቃሴ ውሰጥ
የሚወሰኑ የውሳኔ ዓይነቶች ናቸው። በሌላ በኩል 'ስልታዊ' ውሳኔዎች ከመደበኛ ውሳኔዎች በተለየ መልኩ
የደመወዝ ሚዛን ማስተካከል ወይም አዲስ የስርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ ማዘጋጀት ሊሆን ይችላል።
የአተገባበር ውሳኔዎች የፖሊሲውን አፈፃፀም ሂደት የሚዘረዝሩ እና ከፖሊሲ የተቀዱ ውሳኔዎች ናቸው።
በዕቅድ ያልተያዙ ውሳኔዎች ያልተደራጁ እና አስቀድመው በመርሃ ግብር ያልተያዙ ውሳኔዎች ናቸው። በሌላ
በኩል በዕቅድ የተያዙ ውሳኔዎች አስቀድመው በመርሃ ግብር የተያዙ እና የተደራጁ የውሳኔ አይነቶች ናቸው፡፡
የግል ውሳኔ ማለት በቡድን ውስጥ ያሉ አባላትን ሳያሳትፉ በግል ደረጃ የሚወሰን ውሳኔ ተብሎ የሚታወቅ
ሲሆን አውቶክራሲያዊ የአሠራር ዘይቤ የሚያሳይ ነው። የቡድን ውሳኔ ማለት ሁለት እና ከዛበላይ ያሉ የቡድን
አባላትን በማሳተፍ የሚወሰን የውሳኔ ዓይነት ነው ይህም ዲሞክሪያሳዊ የአሰራር ዘይቤን የሚከተል ነው፡፡
ችግሮችን ውጤታማና ትክክለኛ በሆነ መንገድ የመፍታት ጉዳይ ሲሆን መሪ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ
33 | P a g e
የሚከተሉትን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን/ደረጃዎችን መከተልና የችግር አፈታት ሂደት ላይ የምንወስነውን
1. ችግርን መለየት
8. እና የችግሩ አፈታት አርኪ መሆኑን እና አለመሆኑን መመዘንና መከታተል ሲሆኑ በዝርዝር ለማስረዳት
I need to buy
Identification
of a a new car.
Problem
Price/
Comfort
identification Durability
of Decision Repair
Record
Criteria
Performance
Price 10
Allocation Comfort 8
of Weights Durability 6
Repair Record 4
to Criteria
Performance 2
Development
of
Alternatives Dodge Audi Isuzu Chevy
34 | P a g e
Analysis
of Price
Alternatives Comfort
Durability
Repair Record
Performance
Selection
of an The Toyota
Alternative is the best
1. የእውቀት መነስ
2. በቂ ጊዜ አለመኖር
3. በስራ አለመተማመን
/intangible asset/ ሃብት ነው፡፡ ጊዜ አንዲ ካመለጠ የማይመለስ ባክኖ የሚጠፋ ነው፡፡የሚያሳዝነው ጊዜን
ሳንሰራበት ባግባቡ ሳንጠቀምበት ስንቀር ምሳሌ የያዝነውን ስራ በወቅቱ መስራት ሲገባን ነገ እሰራዋለሁ
በሚል ዕሳቤ /procrastination/ ስራን አስተላለፍን ማለት ከህይወታችን ላይ ያለአግባብ ጊዜን ማባከናችንን
35 | P a g e
ያረጋግጣል፡፡ አንድ መሪ ከሚመዘንባቸው ነገሮች አንዱ ጊዜውን ጠብቆ የሚሰራበት ሁኔታ፣ ጊዜውን እንዲት
2022)፡፡ እንደ ማንኛውም ተግባራት የጊዜ አመራር ክሎት በሙያ ውስጥ መለማማድ ጠቃሚ ሲሆን ሁሉም
ነገር የሚሆነው በጊዜ ውስጥ መሆኑን የሚረዳ መሪ መሆን እና ጊዜ ስኬትና ውድቀት የሚመዝን አንዱ
ጊዜ የለኝም የሚባል ሰበብ የደካሞችና የፍሬ ቢሶች ማምለጫ ሲሆን ስራ የሚበዛባቸው ሰዎች ጊዜ አጥተው
አያውቁም፡፡ ችግሩ ያለንን ጊዜ ባግባቡ መጠቀሙ አለመጠቀሙ ላይ ነው እንጂ ጊዜ ማጣት ጉዳይ አይደለም ፡፡
ሊሎች የጠፉብን ቁሳዊ ሀብቶችን እደገና ማግኘት፣ ማስተካካል እና መልሶ መጠቀም ሲቻል ጊዜ ግን አንዴ
ከባከነ ወደኃላ መመለስ፣ መጠገን እና መልሶ መቀጠም አይቻልም ፡፡ ምክነያቱም እንጠቀምበታለን እንጅ እደ
እንደ መሪ የጊዜ አመራር ምንነት እና ትርጓሜን በጥልቀት መረዳት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ የጊዜ አመራር
ጉዳይ ራሱን ጊዜን ከመምራት ያለፈ ትርጓሜ ያለው ጉዳይ ሲሆን ይህም ማለት የጊዜ አመራር ራሱን ጊዜን
መምራት ሳይሆን ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ነው። የጊዜ አመራር ቅድሚያ መስጠት ለሚገባን ቅድሚያ
በመስጠት፣ ጊዜን በተገቢው መጠቀም እና አባካኝ የሆኑ ልማድና አሰራሮችን መቀየር የሚጨምር ነው።
የጊዜ አመራር ጊዜን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል ስሌቶችና ልማዶችን ለመቀበል
ፈቃደኛ መሆንን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ለጊዜ ዋጋ ስጥቶ ጊዜን ለመምራት ከሚጠቅሙ በርካታ ነገሮች
ጊዜን በትክክል የት እንደሚያሳልፉ በመገምገም መጀመር በስራ፣ በትምህርት ቤት፣ በቤት ውስጥ እና የቤት
ሰአታት ምስላዊ ካርታ በመፍጠር ከዚያ ያለፈውን ሳምንትዎን በቀናት ከዚያም በሰዓታት በመከፋፈል
ማቀድ ለእያንዳንዱ ተግባራት /ግብ/ የድርጌት መርሃግበር ማዘጋጀት አስፈላጌ በመሆኑ እለታዊ እቅድን
መላመድ ናቸው፡፡
36 | P a g e
በጊዜ አያያዝ ዘዴዎች ዋና ዋናዎቹ ግንዛቤ፣ የዝግጅት እና የመላመድ ችሎታዎች ናቸው ። ይህ ማለት ጊዜ
business machine/ የክህሎት ክፍተት ዳሰሳ ውስጥ “የጊዜ አስተዳደር ችሎታ እና ቅድሚያ የመስጠት
የአይዘንሃወር ማትሪክስ አስፈላጊ፣ አስፈላጊ ያልሆኑ፣ አስቸኳይ እና አስቸኳይ ያልሆኑ ተግባራትን ለመለየት
የሚረዳህ ታዋቂ ሞዲል ነው።ቅድሚ መሰጠት ያለበትን እና ቅድሚያ መስጠት የሌለበትን እዲሁም
እንዲሁም ከ 4 ዲ/ D’s of execution: do, defer, delegate, and delete./ አፈጻጸም ጋር ይዛመዳሉ ፡፡
ሣጥን 1 ፡፡- አስፈላጊ እና አጣዳፊ። በመጀመሪያ እነዚህን ተግባራት ያከናውኑ ከግቦችዎ ጋር በጣም
አስፈላጊ የሆኑት እነዚህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ናቸው።
ሣጥን 2 ፡፡- አስፈላጊ ግን አጣዳፊ ያልሆነ። በጊዜ ሳጥን ውስን አስፈላጌ ሆኑ ነገርግን አጣዳፊ/ አስቸኳይ
ባለመሆኑ ወደኋላ ማቆየት እና ማቀድ ያስፈልጋል።
37 | P a g e
ሣጥን 4 ፡- አስቸኳይ ነገር ግን አስፈላጊ አይደለም። ከተቻለ እነዚህን ለሌሎች አሳልፈው መስጠት ፣
በተለይም ለረጅም ጊዜ ግቦችዎ ላይ አስተዋፅዖ ካላደረጉ።
በቀላል አቀራረብ የተግባር ዝርዝር በመፃፍ እና እያንዳንዱን ሳጥን እንደ አጣዳፊነቱ ወይም አስፈላጊነቱ
ምልክት ማድረግ አስፈላጌ ሲሆን ብዙ ጊዜ አስፈላጊ ከሆኑ ተግባራት ይልቅ አስቸኳይ ስራዎችን
እናስቀድማለን እንደ ፈጠራ ፣ ጠቃሚ እና የተሟላ ነገር ግን የመጨረሻ ቀን የሌላቸው ተግባራትን መለየት
እና መለያ መስጠት የግል እና ሙያዊ ግቦችዎን ለማሳካት አጋዥ እርምጃ ሊሆን ይችላል።
ለአብዛኞቻችን ብዙ ስራዎችን መስራት በአንድ ጊዜ በአንድ ተግባር ላይ ከማተኮር ያነሰ ቅልጥፍና አለው።
እንዲያውም አንድ ጥናት እንደሚያሳየው 2.5 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ብዙ ተግባራትን በብቃት
ሲሆን ይህም በሰራ ህይወት ላይ ውጤታማ እንዳንሆን ወይም እርካታ እንዳይኖር ያደርጋል.፡፡ ሌላ ሥራ
ከመጀመር በፊት አንድ ሥራ መጨረስ እና ጊዜን ማደራጀት በራስ የመተማመን ስሜትን እዲጨምር
ያደርጋል።
38 | P a g e
ጥሩ የጊዜ አያያዝ ልማዶችን ለማስቀጠል ሽልማቶች ትልቅ የማበረታቻ ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
ለሚያከናውኗቸው እያንዳንዱ አስፈላጊ ተግባራት ለእራስዎ ትንሽ ማትጊያ መስጠት ጥሩነው፡፡ ከመጠን
ያለፈ ወይም ውድ መሆን አያስፈልገውም እራስን ለማነሳሳት አንዳንድ ቀላል መንገች መከተል አስሀፈላጊ
ነው፡፡ ለምሳሌ በሚወዱት ጨዋታ ለመደሰት ቢሞክሩ፣ ለአጭር ጊዜ የእግር ጉዞማድረግ ቢያደርጉ፣ ከጓደኞች
አስደሳች ሽልማቶች በተለይ ከባድ በሆነ ፕሮጀክት ወይም የስራ ጊዜ ውስጥ አሸናፊ ሆነው እንዲያጠናቅቁ
ያግዝዎታል።
ጥሩ ጊዜን ማስተዳደር ወደ ጤናማ እና ሚዛናዊ የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይር ሲሆን የሚከተሉትን ጥቅሞችን
መስጠት፣ባነሰ ጊዜ ውስጥ የበለጠ ማሳካት ፣ መዘግየትን መቀነስ እና በራስ መተማመንን መጨመር ናቸው
(coursera, 2023)
39 | P a g e
ማስገባት የተለያዩ ማህበራዊና ሙያዊ ዳራ ያላቸው ሰዎች ለተመሳሳይ ዓላማዎች ማሰባሰብ ለተቋሙ
ውጤታማነት እና ስኬታማነት አስፈላጊነት የማይካድ ነው Khan, Z. (2022, 10 31).፡፡
የአንድ ተቋም መሪ በየዕለት ተዕለት ስራ ሂደት ውስጥ ውጤታማ ከሚሆንባቸው አንዱና ወሳኝ የሆነው ጉዳይ
የተግባባት ክህሎቱ ነው፡፡ ውጤታማ የተግባቦት ክህሎት ያለው መሪ በተከታዮቹ፣ በበላይ አመራሮቹ እና
በተገልጋዮቹ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሪ ነው፡፡ ምክንያቱም በየደረጃው የሚያደርገው ተግባቦት ከፍተኛ የሆነ
የስራ ውጤታማነትንና መልካም ግንኙነትን የሚፈጥርለት ስለሚሆን ከታች የምናየው የግራፍ ማስረጃ በጥናት
የተደገፈና አንድ መሪ በየደረጃው ካሉ የስራ ሃይሎች ጋር የሚያደርገው ተግባቦት በመቶኛ ለማሳየት
14
ከዳይሬክተሮች ጋር
% 17
ከውስጥ ባለጉዳዮች ጋር
46% %
ከውጭ ባለጉዳዮች ጋር
የበታች ሰራተኞች ጋር
23%
ይሞክራል፡
አንድ መሪ የተግባቦት ክህሎት ፍሰት ግራፍ ማሳያ እንደሚያመላክተው በስራ ቦታ የሚኖር የተግባቦት ሂደት
በጣም ከፍተኛ እንደሆነ እና መሪ በየደረጃ ካሉ አካላት ጋር የሚያደርገው ተግባቦት በጣም አስፈላጊ መሆኑን
ያመላክታል፡፡ ስለሆነም አንድ መሪ መርህን የተከተለ የተግባቦት ሂደትን በመተግበር የመሪነት ድርሻውን ከፍ
ማድረግ የሚችል ሲሆን መሪ ባለ ሰባት "C" የተግባቦት መርሆችን መከተል ይኖርበታል እነሱም የሚከተሉት
ናቸው፡-
40 | P a g e
4. ተጨባጭ Concreteness/፡- በላኪና ተቀብዩ መካከል ውጤታማ የሆነ ተግባቦት እንዲኖር ተጨባጭነት
5. ግልጽነት/ Clarity/፡- መሪ ነሚኖረው ተግባቦት ላይ ግልጽ ለመሆን ከሚያስችሉ ጉዳዮች ቀላል ቋንቋ
መጠቀም እና በሚተላለፈው መልእክት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ማተኮር እንዲሁም ማንኛውንም
ውዥንብር እና ግራ መጋባትን ለመከላከል ፈሊጣዊ ንግግሮችን አለመጠቀም ይመከራል።
6. ትህትና /Courtesy፡- ትህትና ጨዋነት የተሞላበት ባህሪ ሲሆን በማንኛውም የተግባቦት ጊዜ ለሌሎች
አክብሮትን ማሳየት ማለት ነው። እንደ መሪ ሰዎችን ማክበር ተግባቦትን ያሳድጋል፣ ግንኙነቶችን
ያጠናከራል እንዲሁም በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ትብብርን ይፈጥራል (Dr. D. Y. Patil Law
College, 2015)።
7. ትክክለኛነት/ Correctness/፡- ተግባቦትን የተሻለ የሚያደርጉት ሶስት ባህሪይ ትክክለኛውን የቋንቋ ደረጃ
መጠቀም፣የአሃዞችን፣እውነታዎችንና ቃላትን ትክክለኛነት ማረጋገጥና እና ተቀባይነት ያለው የአጻጻፍ
ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
41 | P a g e
Bibliography
Al-Malki, M. &. (2018). Impact of laissez-faire leadership on role ambiguity and role conflict:
Implications for job performance. International Journal of Innovation and Economic
Development, 29-43.
Amanchukwu, R. N. ( 2015). A review of leadership theories, principles and styles and their relevance to
educational management. Management.
Buchanan, L. (2007). In praise of selflessness: Why the best leaders are servants. Inc. Magazine, 29(5),
33-35.
change ledership. (2022, March 24). Retrieved November 3, 2023, from change ledership.
coursera. (2023, jul 18). Retrieved novenber 2, 2023, from sstrategies to better manages your time.
David R.Kolzow. (2014). LEADING FROM WITHIN: Building Organizational Leadership. San
fransisco: Jossy Bass.
Debrezit/busheftu. (2022). the role of leadership. In m. nursalim, the role of leadership (p. 153).
kuweenof sheba.
Indeed carer guide. (2022, july 21). Retrieved November 3, 2023, from Indeed carer guide.
Vullinghs, J. T. (2020). Ethical and passive leadership and their joint relationships with burnout via role
clarity and role overload. Journal of Business Ethics,, 165, 719-733.
Walton, S. (2023). custemr service represntative. Retrieved November 2, 2023, from Conceptual skills
definition and examples.
42 | P a g e
Ward, K. M. (2010). Back to the future: visionary, entrepreneurial, missional Anglican leadership for
today’s church. In K. M. Ward, Anglican Theological Review, (pp. 92(1), 167-173.). Chicago.
43 | P a g e