You are on page 1of 515

የፍትሐብሔር ሕግ

የፍትሐብሔር ሕግ ማውጫ
የፍትሐ ብሔር ሕግ መግቢያ
የፍትሐ ብሔር ሕግ ዐዋጅ
አንደኛ መጽሐፍ፡፡
ስለ ሰዎች፡፡
አንቀጽ 1፡፡
ስለ ሰዎች፡፡
ምዕራፍ 1፡፡ ስለ ሰውና ስለ መብቶቹ፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ሰው መብት አሰጣጥ፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ሰው መብቶች፡፡
ምዕራፍ 2፡፡ ስለ ስም፡፡
ምዕራፍ 3፡፡ ስለ ክብር መዝገብ ማስረጃነት፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ክብር መዝገብ ሹማምቶች፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ የክብር መዝገብ ሹማምት ሥልጣን አሰጣጥ፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የክብር መዝገብ ሹም ተግባር፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ሕዝብ የክብር መዝገቦች፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ክብር መዝገብ ጽሑፎች፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ በጠቅላላው፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የመወለድ ጽሑፎች፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ የመሞት ጽሑፎች፡፡
ንኡስ ክፍል 4፤ የጋብቻ ጽሑፎች፡፡
ክፍል 4፤ የክብር መዝገብ ጽሑፎችን ስለማቃናት፡፡
ክፍል 5፤ የክብር መዝገብ ጽሑፎች ግልባጮችና ቅጂዎች
ክፍል 6፤ የክብር መዝገብ ጽሑፍን ደንብ አለመፈጸም የሚያስከትለው ቅጣት፡፡
ክፍል 7፤ ስለ ታወቁ ሰነዶች፡፡
ምዕራፍ 4፡፡ ስለ መጥፋት
ክፍል 1፤ የመጥፋት መገለጫ፡፡
ክፍል 2፤ የመጥፋቱ ማስታወቂያ የሚያስከትለው ውጤት፡፡
ክፍል 3፤ ጠፋ መባሉ የሚቀርበት ጊዜ፡፡
ምዕራፍ 5፡፡ ስለ መኖሪያ ቦታና ስለመደበኛ ቦታ፡፡
ክፍል 1፤ ስለ መኖሪያ ቦታ፡፡
ክፍል 2፤ መደበኛ ቦታ፡፡
አንቀጽ 2፡፡
ስለ ሰዎች ችሎታ፡፡
ምዕራፍ 1፡፡ ጠቅላላ የሆኑ መሠረታውያን ደንቦች፡፡
ምዕራፍ 2፡፡ አካለመጠን ስላላደረሱ ሰዎች፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ክፍል 2፤ አካለ መጠን ያላደረሰውን ሰው ስለሚጠብቁ ክፍሎች ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ስለ አሳዳሪና ስለ ሞግዚት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ስለ ቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር አባሎችና ስለ ተጠባባቂ ሞግዚት፡፡
ክፍል 3፡፡ የአሳዳሪውና የሞግዚቱ ሥልጣን፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ሰውነት አጠባበቅ፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ አካለመጠን ያላደረሰን ልጅ ሀብቶች ስለ ማስተዳደር፡፡
ክፍል 4፤ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ለመጠበቅ የተመለከቱትን ደንቦች መጣስ የሚያስከትለው ቅጣት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ አካመጠን ያላደረሰ ልጅ ሥራዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የሞግዚቱ ሥራዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ ሊደርሱ የሚችሉ ኀላፊነቶች፡፡
ክፍል 5፤ አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ችሎታ ማጣት ስለ መቅረቱ
ንኡስ ክፍል 1፤ ከሞግዚት አስተዳደር ነጻ ስለ መውጣት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የሞግዚትነት ሥራ ሒሳቦች፡፡
ምዕራፍ 3፡፡ አእምሮዋቸው ስለ ጐደለ ሰዎችና ስለ ድውዮች፡፡
ክፍል 1፤ ችሎታ ስላልተከለከሉት የአእምሮ ጐደሎዎችና ድውዮች፡፡
ክፍል 2፤ በፍርድ ስለሚደረግ ክልከላ
ምዕራፍ 4፤ በሕግ ስለ፤ ተከለከሉ ሰዎች፡፡
ምዕራፍ 5፤ ስለ ውጭ አገር ሰዎች፡፡
አንቀጽ 3፡፡
በሕግ የሰው መብት ስለ ተሰጣቸው ማኅበሮችና ለልዩ አገልግሎት ስለ ተመደቡ ንብረቶች፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ አስተዳደር ክፍል ድርጅቶችና ስለ ቤተ ክርስቲያን፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ ማኅበሮች፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፎችና ስለ ውስጥ ደንቦች፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ማኅበረተኞች፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ሥራው አመራር፡፡
ክፍል 4፤ ስለ ጠቅላላ ጉባኤ፡፡
ክፍል 5፤ የማኅበሩ መብቶችና ግዴታዎች፡፡
ክፍል 6፤ ስለ ማኅበሩ መፍረስና ሒሳብ መጣራት፡፡
ክፍል 7፤ ማኅበሮችን ስለ መቈጣጠር፡፡
ምዕራፍ 3፤ ለልዩ አገልግሎት ስለ ተመደቡ ንብረቶች፡፡
ክፍል 1፤ የበጎ አድራጎት ድርጅት፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ኮሚቴዎች፡፡
ክፍል 3፤ ለልዩ በጎ አድራጎት የሚወጡ የአደራ ንብረቶች፡፡
ምዕራፍ 4፤ በሕግ የሰው መብት ስለ ተሰጣቸው የውጭ አገር ዜጋ ማኅበሮችና ለልዩ አገልግሎት ስለ ተመደቡ የውጭ አገር ዜጋ
ንብረቶች፡፡
ሁለተኛ መጽሐፍ፡፡
ስለ ቤተ ዘመድና ስለ ውርስ (አወራረስ)
አንቀጽ 4፡፡
ስለ ሥጋ ዝምድናና ስለ ጋብቻ ዝምድና፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ዝምድናና ስለ ጋብቻ በጠቅላላው፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ መተጫጨት፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ ጋብቻ አፈጻጸም፡፡
ክፍል 1፤ ለማንኛዎቹም ዐይነቶች ጋብቻዎች የሚሆኑ አጠቃላይ ሁኔታዎች፡፡
ክፍል 2፤ ብሔራዊ ጋብቻ፡፡
ክፍል 3፤ ሌሎች ዐይነቶች ጋብቻዎች፡፡
ምዕራፍ 4፤ የጋብቻ ሁኔታዎች ባለመጠበቃቸው ምክንያት የሚወሰን ቅጣት፡፡
ክፍል 1፤ ለጋብቻ ሥርዐቶች ሁሉ የሚሆን የወል ሁኔታ
ክፍል 2፤ ብሔራዊ ጋብቻ
ክፍል 3፤ ሌሎች ጋብቻዎች
ምዕራፍ 5፤ የጋብቻ ውጤት፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ክፍል 2፤ በሰዎች ላይ ጋብቻው ያለው ውጤት፡፡
ክፍል 3፤ ጋብቻው በገንዘብ በኩል ያለው ውጤት፡፡
ምዕራፍ 6፤ ስለ ጋብቻ መፍረስ፡፡
ክፍል 1፤ ጋብቻ የሚፈርስበት ምክንያት፡፡
ክፍል 2፤ በተጋቢዎቹ መካከል ያለውን የገንዘብ ግንኙነት ጒዳይ ስለማጣራት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ከባልና ከሚስት የአንዱ መሞት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የመፋታት ሁኔታ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ ሌላ የጋብቻ መፍረስ፡፡
ምዕራፍ 7፤ የጋብቻ ማስረጃ፡፡
ምዕራፍ 8፤ ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ስለ መኖር፡፡
ምዕራፍ 9፤ በጋብቻና በፍቺ፤ ከጋብቻው ውጭ በሆነ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጒዳይ ስለሚነሡ ክርክሮች፡፡
ምዕራፍ 10፤ ስለመወለድ፡፡
ክፍል 1፤ አባትና እናትን ስለ ማወቅ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ አባት ነው ስለሚያሰኝ ግምት፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ አባትነትን ስለ ማወቅ፡፡
ንኡስ ክፍል 4፤ በፍርድ ስለሚደረግ የአባትነት ማወቅ፡፡
ክፍል 2፤ በአባትነት ምክንያት ስለሚነሣ ክርክር፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ልጅነት ማስረጃ፡፡
ክፍል 4፤ በሁኔታው ላይ ስለሚነሣው ክርክርና ስለመካድ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ በሁኔታው ላይ ስለሚደረግ ክርክር፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ስለ መካድ፡፡
ምዕራፍ 11፤ ስለ ጉዲፈቻ (የማር) ልጅ፡፡
ምዕራፍ 12፤ ስለ ቀለብ መስጠት ግዴታ፡፡
አንቀጽ 5፡፡
ስለ ውርስ (ስለ አወራረስ)፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ውርስ አስተላለፍ፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ስለ ውርስ አከፋፈትና በውስጡ ስለሚገኝበት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ወራሽ ለመሆን የሚያስፈልግ ችሎታ፡፡
ክፍል 2፤ ሳይናዘዝ የሞተ ሰው ውርስ፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ኑዛዜ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ የኑዛዜ ዋጋ መኖር ሁኔታዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ በኑዛዜዎቹ የሰፈረ ቃልና የኑዛዜ ትርጓሜ፡፡
ምዕራፍ 2፤ ወራሽነትን ስለ ማጣራት፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ውርሱ አጣሪ፡፡
ክፍል 2፤ መብት አለኝ ባዮችን ቁርጥ በሆነ አኳኋን ስለመወሰን፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ የወራሾቹን ሁኔታ ለጊዜው ስለ መወሰን፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ወራሾችና ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች ስለሚያደርጉት ምርጫ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ ለወራሹ ስለሚሰጡ የምስክር ወረቀቶችና የወራሽነት ጥያቄ፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ውርስ አስተዳደር፡፡
ክፍል 4፤ የውርሱን ዕዳ ስለ መክፈል፡፡
ክፍል 5፤ ከውርሱ ላይ ስለሚጠየቀው የቀለብ ገንዘብ፡፡
ክፍል 6፤ የኑዛዜ ስጦታዎችን ስለ መክፈል፡፡
ክፍል 7፤ ስለ ውርሱ መዘጋት፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ ውርስ ክፍያ፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ውርሱ አለመነጣጠልና ለውርስ ክፍያ ስለ ሚቀርብ ጥያቄ፡፡
ክፍል 2፤ የጋራ ወራሾች ስለሚመልሱት ንብረቶች፡፡
ክፍል 3፤ የመከፋፈሉ አሠራር፡፡
ክፍል 4፤ መከፋፈሉ ከተፈጸመ በኋላ በወራሾቹ መካከል ስላለው ግንኙነት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ የጋራ ተካፋዮች ሊሰጡ ስለሚገባቸው ዋስትና፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ክፍያውን ስለ ማፍረስ፡፡
ክፍል 5፤ የውርሱ ሀብት ከተከፋፈለ በኋላ ገንዘብ ጠያቄዎች ያላቸው መብት፡፡
ምዕራፍ 4፤ ውርስን ስለሚመለከቱ ስምምነቶች፡፡
ክፍል 1፤ ወደፊት በሚገኝ ውርስ ላይ ስለሚደረግ የውል ስምምነት፡፡
ክፍል 2፤ የተከፋፈሉ ስጦታዎች፡፡
ክፍል 3፤ የውርስ መብቶችን ስለ ማስተላለፍ፡፡
ሦስተኛ መጽሐፍ፡፡
ስለ ንብረቶች፡፡
አንቀጽ 6፡፡
ስለ ንብረት በጠቅላላውና ስለ ይዞታ፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ንብረት በጠቅላላው፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ ይዞታ፡፡
አንቀጽ 7፡፡
ስለ ግል ሀብት፡፡
ምዕራፍ 1፤ ሀብት ስለሚገኝበት ሁኔታ፤ ሀብትን ስለ ማስተላለፍ፤ ሀብት ስለሚቀርበትና ስለ ባለሀብትነት ማስረጃ፡፡
ክፍል 1፤ ሀብት ስለሚገኝበት ሁኔታ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ስለመያዝ፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የቅን ልቡና ባለይዞታነት፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ ስለ ይዞታ፡፡
ንኡስ ክፍል 4፤ የዋና ተጨማሪ ነገር፡፡
ክፍል 2፤ ባለሀብትነትን ስለ ማስተላለፍ፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ሀብትነት መቅረት፡፡
ክፍል 4፤ ስለ ሀብትነት ማስረጃ፡፡
ምዕራፍ 2፤ የባለሀብቱ መብቶችና ግዴታዎች፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ክፍል 2፤ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ የተለዩ ደንቦች፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ውሃዎች ባለሀብትነትና በውሃዎች ስለ መገልገል፡፡
አንቀጽ 8፡፡
የጋራ ባለሀብትነት፤ በአላባ ስለ መጠቀምና ስለ ሌሎች ግዙፍ መብቶች፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ጋራ ባለ ሀብትነት፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ክፍል 2፤ ልዩ ሁኔታዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ የአማካይ ወሰን አጥሮች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ያንድ ቤት ፎቅ ወይም ለመኖሪያ የተመደቡ ክፍሎች ባለሀብትነት፡፡
ምዕራፍ 2፤ በአላባ ብቻ ስለ መጠቀም መብት፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ግዙፍ ተንቀሳቃሽ ሀብቶች የሚጸና (የሚፈጸም) ልዩ ደንብ፡፡
ክፍል 3፤ የገንዘብና ሌሎች ግዙፎች ያልሆኑ ነገሮች በአላባ የመጠቀም መብት ልዩ ደንቦች፡፡
ክፍል 4፤ በቤት ውስጥ የመኖር መብት፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ ንብረት አገልግሎት፡፡
ምዕራፍ 4፤ በቀዳሚነት ግዢ ይገባኛል የማለት መብት፡፡
ምዕራፍ 5፤ ባለሀብቱ አንዳንዶቹን ንብረቶች እንደ ፈቀደው እንዳያደርግ መብቱን ስለ ማጥበብ፡፡
ክፍል 1፤ የግዢን ወይም በቀደምትነት የመግዛትን መብት ስለሚመለከት የውል ስምምነት፡፡
ክፍል 2፤ ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይያዝ የማድረግ ስምምነት
አንቀጽ 9፡፡
በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በኅብረት ስለ መጠቀም፡፡
ምዕራፍ 1፤ የመንግሥት ንብረት (የሕዝብ አገልግሎት ንብረት እና) ንብረትን ስለ ማስለቀቅ፡፡
ክፍል 1፤ የሕዝብ አገልግሎት የሚጠቅሙትን ሀብቶች ስለ ማስለቀቅ
ምዕራፍ 2፤ የኅብረት ስለሆኑ የእርሻ መሬቶች፡፡
ምዕራፍ 3፤ በመንግሥት የታወቁ የመሬት ባለሀብቶች ማኅበር፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ማኅበሮቹ መቋቋም፡፡
ክፍል 2፤ ለአመዘጋገብ የሚያገለግሉ ፎርሙሎች፡፡
ክፍል 3፤ የተመዘገቡትን ጽሑፎች ስለ ማቃናትና ስለ መሠረዝ፡፡
ምዕራፍ 4፤ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ማስመዝገብ የሚያስከትለው ውጤት፡፡
አንቀጽ 11፡፡
ስለ ድርሰትና ስለ ኪነ ጥበብ ባለሀብትነት፡፡
4 ኛ፤ መጽሐፍ፡፡
ስለ ግዴታዎች፡፡
አንቀጽ 12፤
ስለ ውሎች በጠቅላላው፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ውል አመሠራረት፡፡
ክፍል 1፤ ፈቅዶ ስለ መዋዋል፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ውለታን የመቀበል አቋሞች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የተዋዋዮቹ ፈቃድ ጕድለት፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ውለታው ጕዳይ፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ውል አጻጻፍ (ፎርም)፡፡
ምዕራፍ 2፤ የውሎች ውጤት፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ውል ትርጕም፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ውሎች አፈጻጸም፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ውል መሻሻል፡፡
ክፍል 4፤ ውልን ስላለመፈጸም፡፡
ምዕራፍ 3፤ የግዴታዎች መቅረት፡፡
ክፍል 1፤ ውሎችን ስለመሠረዝና ስለ ማፍረስ፡፡
ክፍል 2፤ ውልን ስለ ማስቀረትና ዕዳን ስለ መተው፡፡
ክፍል 3፤ ስለ መተካት፤ (ኖባሲዩን)፡፡
ክፍል 4፤ ስለ ማቻቻል፡፡
ክፍል 5፤ ስለ መብት መቀላቀል፡፡
ክፍል 6፤ ስለ ይርጋ፡፡
ምዕራፍ 4፤ የአንዳንድ ግዴታዎች ወይም የአንዳንድ ውሎች አኳኋን፡፡
ክፍል 1፤ ጊዜ፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ሁኔታ፡፡
ክፍል 3፤ ማማረጫ ያለው ግዴታ፡፡
ክፍል 4፤ ቃብድ፡፡
ክፍል 5፤ ስለ ኀላፊነት የተጻፈ የውጭ ቃል፡፡
ምዕራፍ 5፤ ስለ ብዙዎች ባለዕዳዎች ወይም ባለገንዘቦች፡፡
ክፍል 1፤ በባለዕዳዎች መካከል ስላለው የማይከፋፈል አንድነት፡፡
ክፍል 2፤ በባለገንዘቦቹ መካከል ስላለው አንድነት፡፡
ክፍል 3፤ ስለማይከፋፈሉ ግዴታዎች፡፡
ክፍል 4፤ ዋስትና፡፡
ምዕራፍ 6፤ ከውሉ ጋራ ግንኙነት ስላላቸው ሦስተኛ ወገኖች፡፡
ክፍል 1፤ ስለሌላ ሰው ሆኖ የሚሰጥ ተስፋና የሚደረግ ውል፡፡
ክፍል 2፤ የገንዘብ መብትን ስለ ማስተላለፍና ስለመዳረግ (ዳረጎት፡፡)
ክፍል 3፤ የምትክ ውክልናና የዕዳ ማስተላለፍ፡፡
ክፍል 4፤ ስለ ተዋዋዮቹ ወገኖች ወራሾች (የወገኖቹ ወራሾች)፡፡
ክፍል 5፤ ከተዋዋዮቹ ወገኖች ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች፡፡
ምዕራፍ 7፤ የውልን ጕዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ፡፡
ክፍል 1፤ የማስረጃ ማቅረብ ግዴታና አቀባበሉ፡፡
ክፍል 2፤ የጽሑፍ ማስረጃ፡፡
ክፍል 3፤ ገንዘቡ እንደ ተከፈለ የሚያስቈጥሩ የሕሊና ግምቶች፡፡
አንቀጽ 13፡፡
ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነትና ያላገባብ ስለ መበልጸግ
ምዕራፍ 1፤ ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት፡፡
ክፍል 1፤ በጥፋት ላይ ስለ ተመሠረተ አላፊነት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ልዩ ሁኔታዎች፡፡
ክፍል 2፤ አጥፊ ሳይሆን አላፊ ስለ መሆን፡፡
ክፍል 3፤ የካሣ አከፋፈልና ልክ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ስለ ጉዳት ኪሣራ፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ በሌላ አኳኋን ስለ መካስ፡፡
ክፍል 4፤ ለሌላ ሰው ተግባር አላፊ ስለ መሆን፡.፡
ክፍል 5፤ ካሣ ስለሚጠየቅበት ክስ፡፡
ምዕራፍ 2፤ ያላግባብ ስለ መበልጸግ፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ክፍል 2፤ የማይገባውን ስለ መክፈል፡፡
ክፍል 3፤ስለ ወጪ ገንዘብ፡፡
አንቀጽ 14፡፡
ስለ እንደራሴነት፡፡
ምዕራፍ 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ ወኪልነት፡፡
ክፍል 1፤ የወኪልነት ሥልጣን አቋቋምና የሥራው ግብ፡፡
ክፍል 2፤ የተወካዩ ግዴታዎች፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ወካዩ ግዴታዎች፡፡
ክፍል 4፤ ስለ ውክልና መቅረት፡፡
ክፍል 5፤ ለሦስተኛ ወገኖች የውክልናው ሥልጣን የሚያስ ከትለው ውጤት፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ ኮሚሲዮን፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ግዢ ወይም ስለ ሽያጭ ኮሚሲዮን፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ማመላለሻ ኮሚሲዮን፡፡
ምዕራፍ 4፤ ዳኞች ስለሚሰጡት ውክልና፡፡
ምዕራፍ 5፤ ስለ ሥራ አመራር፡፡
5 ኛ መጽሐፍ፡፡
ስለ ልዩ ውሎች፡፡
አንቀጽ 15፡፡
መብቶች ማስተላለፍን ስለሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ሽያጭ፡፡
ክፍል 1፤ የውሉ አደራረግ፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ውሉ መፈጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የግዢው ግዴታዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ በሻጩና በገዢው ላይ ያሉ አጠቃላይ ድንጋጌዎች፡፡
ክፍል 3፤ ውልን ስላለመፈጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ውልን በግድ ስለ ማስፈጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የውል መፍረስ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ የጉዳት ኪሣራ፡፡
ክፍል 4፤ ልዩ ልዩ የሽያጭ አሠራር፡፡
ንኡስ ክፍል 4፤ ዋጋው በየጊዜው ስለ ሚከፈልበት ሽያጭ፡፡
ንኡስ ክፍል 5፤ ባለሀብትነቱን ለራሱ በማስጠበቅ የሚደረግ ሽያጭ፡፡
ንኡስ ክፍል 6፤ የተሸጠውን መልሶ ስለ መግዛት የሚደረግ ውል
ንኡስ ክፍል 7፤ ዕቃውን ከመላክ ግዴታ ጋራ የሚደረግ ሽያጭ
ምዕራፍ 2፤ የመሸጥ ውል መሰልነት ያላቸው ልዩ ልዩ ውሎች፡፡
ክፍል 1፤ የለውጥ ውል፡፡
ክፍል 2፤ የባለሀብትነትን መብት ሳይሆን ሌሎችን መብቶች፡፡ ስለ ማስተላለፍ፡፡
ክፍል 3፤ ስለ ኪራይ ሽያጭ፡፡
ክፍል 4፤ የዕቃ ማቅረብ ውል፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ ስጦታ፡፡
ምዕራፍ 4፤ የሚያልቅ ነገር ብድር፡፡
ምዕራፍ 5፤ መጦሪያን ስለ ማቋቋም፡፡
ክፍል 1፤ ለዘለዓለም ስለሚኖር መጦሪያ፡፡
ክፍል 2፤ እስከ ዕድሜ ልክ ስለሚቈይ መጦሪያ፡፡
አንቀጽ 16፡፡
የሥራዎች አገልግሎት መስጠትን የሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ሥራ ውል በጠቅላላው፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ውሉ አፈጻጸም፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ሠራተኛው ሥራ፡፡
ክፍል 3፤ ለሠራተኛው ስለሚገባው ደሞዝ፡፡
ክፍል 4፤ ስለ አሠሪው የጸጥታ አጠባበቅ ግዴታ፡፡
ክፍል 5፤ ለሠራተኞች የሚገባ የዕረፍት ጊዜ፡፡
ክፍል 6፤ ውልን ስለ ማቋረጥ፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ አንዳንድ ልዩ ልዩ የሥራዎች ውሎች፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ሞያ ሥራ መልመጃ ውል፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ሥራ ሙከራ ውል፡፡
ክፍል 3፤ በቤተሰብ አስተዳደር ውስጥ ስለሚኖር አሽከር የሥራ ውል፡፡
ክፍል 4፤ ስለ እርሻ ሥራ ውል፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ስለ እርሻ ውል፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ ሥራ ውል፡፡
ምዕራፍ 4፤ ስለ ዕውቀት ሥራ ማከራየት ውል፡፡
ምዕራፍ 5፤ ስለ ሕክምና ወይም ስለ ሆስፒታል ውል፡፡
ምዕራፍ 6፤ ስለ ሆቴል ሥራ ውል፡፡
ምዕራፍ 7፤ አትሞ የማውጣት (ፒብሊሽንግ) ውል፡፡
አንቀጽ 17፡፡
የዕቃ ጥበቃን በዕቃ መገልገልን ወይም በዕቃ መጠቀሙን የሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ ዕቃ ማከራየት፡፡
ክፍል 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ክፍል 2፤ እንስሳን ስለ መከራየት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ በአንድ የእርሻ መሬት ሥራ ኪራይ ውስጥ ከብትን ጭምር ስለ ማከራየት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የከብቶቹ ኪራይ ዋና በሆነ ጊዜ፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ መገልገያ ብድር ወይም ትውስት፡፡
ምዕራፍ 4፤ አደራ፡፡
ክፍል 1፤ ስለ አደራ በጠቅላላው፡፡
ክፍል 2፤ በትእዛዝ የተቀመጠ አደራ፡፡
ክፍል 3፤ አስፈላጊ የሆነ አደራ፡፡
ክፍል 4፤ ባለቤቱ ሳያውቅ የተገኙ ዕቃዎች ወይም ከሌላ ሰው ዘንድ የተቀመጡ ዕቃዎች፡፡
ምዕራፍ 5፤ የዕቃ ማከማቻ ቦታ፡፡
ምዕራፍ 6፤ ስለ መያዣ ውል፡፡
ክፍል 1፤ ስለ መያዝ ውል በጠቅላላው፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ የሚጸናባቸው ሁኔታዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የመያዣ ሰጪው መብትና ግዴታ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ ዕቃውን የያዘው ባለገንዘብ መብቶችና ግዴታዎች፡፡
ንኡስ ክፍል 4፤ የመያዣ ውል የሚቀርበት፡፡
ንኡስ ክፍል 5፤ የመያዣ ውል አፈጻጸም፡፡
ክፍል 2፤ የገንዘብ መጠየቂያ ሰነዶችን ወይም ግዙፍ ያልሆኑ ሌሎች ሀብቶችን መብት ስለ ማስያዝ፡፡
አንቀጽ 18፡፡
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለ ሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ ኪራይ፡፡
ክፍል 1፤ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይ በጠቅላላው፡፡
ክፍል 2፤ የቤትን ኪራይ ስለሚመለከቱ ልዩ ደንቦች፡፡
ክፍል 3 ስለ መሬት የተሰጡ ልዩ ደንቦች፡፡
ምዕራፍ 3፤ ስለ ማይንቀሳቀስ ንብረት የሥራ ውል፡፡
ምዕራፍ 4፤ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣና ስለ ወለድ አግድ፡፡
ክፍል 1፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ አቋቋም፡፡
ክፍል 2፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውጤቶች፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ ቀደምትነት የብልጫ መብት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የመከታተል መብት፡፡
ክፍል 3፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ስለ መቅረት፡፡
ክፍል 4፤ ስለ ወለድ አግድ (አንቲክሬዝ)፡፡
አንቀጽ 19፡፡
የአስተዳደር ክፍል መሥሪያ ቤቶች (አድሚኒስትራሲዮኖች) የሚያደርጓቸው ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ውሎች ሥርዐት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ፈቃድን ስለ መስጠት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ የጨረታ ሥነ ሥርዐት፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ የውል ምክንያት፡፡
ክፍል 2፤ ውል ስለሚያስከትለው ውጤት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ስለ ውሎች ደንበኛ አፈጻጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ስለ ውሎች ምርመራ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ ስለ ውሎች ያለመፈጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 4፤ ውሎችን ለሌላ ሰው ስለ መልቀቅና፡፡ ከዋናው ተቋራጭ ስለ ተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ ሕዝብ አገልግሎት ሥራ ኮንሲሲዮን፡፡
ምዕራፍ 3፤ የመንግሥት ሥራዎች የመቋረጥ ውል፡፡
ክፍል 1፤ ውልን ስለ ማዘጋጀት፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ውል ደንበኛ የሆነ አፈጻጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 1፤ ስለ ሥራዎች የበላይ ተጠባባቂነት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፤ ስለ ዋጋ አከፋፈል፡፡
ንኡስ ክፍል 3፤ ስለ ሥራዎች ርክክብ፡፡
ክፍል 3፤ ውልን ስለ ማሻሻል፡፡
ክፍል 4፤ ስለ ውል አለመፈጸም፡፡
ክፍል 5፤ ውልን ስለ ዋስትና መያዣነት ስለማስተላለፍ፡፡
ምዕራፍ 4፤ ስለ ዕቃዎች ማቅረብ ውል፡፡
አንቀጽ 20፡፡
ስለ ግልግልና ስለ ስምምነት የሚደረግ ውል፡፡
ምዕራፍ 1፤ ስለ ግልግል፡፡
ክፍል 1፤ ስለ ግልግል በጠቅላላው፡፡
ክፍል 2፤ ስለ ዕርቅ፡፡
ምዕራፍ 2፤ በዘመድ ዳኛ የመጨረስ ስምምነት፡፡
ስድስተኛ መጽሐፍ፡፡
አንቀጽ 21፡፡
በቀድሞው ሕግና በዚህ በአሁኑ ሕግ መካከል ስላለው ግንኙነት
ምዕራፍ 1፤ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ምዕራፍ 2፤ ልዩ ድንጋጌ፡፡
አንቀጽ 22፡፡
መሸጋገሪያ ሕግ፡፡
ምዕራፍ 1፤ ሰዎችንና ውርስን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ፡፡
ምዕራፍ 2፤ ስለ ንብረትና የማይንቀሳቀሰውን ንብረት መያዣ ማድረግን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች፡፡

የፍትሐ ብሔር ሕግ መግቢያ


መ ቅ ድ ም፡፡
ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፡፡
ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የሥልጣኔ ደረጃ በዛሬው ጊዜ ከሚለዋወጠው የዓለም ሁኔታ ጋር እኩል ለማራመድ የንጉሠ ነገሥት ግዛታችንን
ማኅበራዊ አቋም የሚመለከተውን ሕግ በዘመናዊ አኳኋን ማሻሻል አስፈላጊ ስለሆነ ይህን የፍትሐ ብሔር ሕግ አወጅን፡፡ እስካሁን
የተደረገውን እርምጃ ለማጠንከርና ወደፊትም የበለጠ መስፋፋትንና እድገትን ለማግኘት እያንዳንዱን ሰው ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው
አገራችንን በሙሉ የሚያጋጥሙትን ጉዳዮች ለማከናወን እንዲቻል ትክክለኛና ዝርዝር የሆኑ ደንቦች ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ሕግ
ውስጥ የሚገኙት ድንጋጌዎች ከጥንት ዘመናት ከወረስናቸው በጽኑ ከተመሠረቱት ከንጉሠ ነገሥት መንግሥታችን የሕግ ልምዶችና
በ 25 ኛው የዘውድ በዓላችን በሰጠነው ሕገ መንግሥት ውስጥ ከሚገኙት መሠረታውያን ሐሳቦች ጋር የሚስማሙ ናቸው፤ እንደዚሁም
ደግሞ በዓለም ላይ ከሁሉ ተሽለው የሚገኙት ሕጎች ተጠንተዋል፡፡
ማናቸውም ሕግ የሰዎችን መብትና ግዴታ ለመግለጽ እንዲሁም በመካከላቸው ያሉት ግንኙነቶች የሚተዳደሩበትን መሠረታውያን ሐሳቦች
ለመግለጽ የወጣ ሲሆን ሕጉ ከወጣላቸው ሰዎች ልብ የሚደርስ ፍላጎታቸውን ልምዳቸውን ወይም የተፈጥሮ ፍትሕን የሚጠብቅ ካልሆነ
በቀር ዋጋ ሊኖረው አይችልም፡፡
እኛ ያቋቋምነው የፍትሐ ነገሥት ኮሚሲዮን ይህን የፍትሐ ብሔር ሕግ ሲያዘጋጅ በተከበረውና በጥንቱ ፍትሐ ነገሥት መጽሐፍና ፍርድ
በመዝገብ መጻፍ ከተጀመረ ወዲህ የተገለጹትን ጥንታዊ የሆኑትን የንጉሠ ነገሥት መንግሥታችንን ታላቅ የሕግ ልምዶችና አቋሞች
በመመልከትና በተለይም ለንጉሠ ነገሥት መንግሥታችንና ለተወደደው ሕዝባችን የሚያስፈልጉትን በማሰብ ነው፡፡
በንጉሠ ነገሥት መንግሥታችን ማናቸውም ሰው ለኑሮው አስፈላጊ የሆኑትን መብቶቹንና ግዴታዎቹን ሁሉ ያለ ችግር እንዲገባው
ለማድረግ ዐቅደን በዚህ ሕግ ውስጥ የሚገኙት ቃላቶች ግልጽ ሆነው እንዲዘጋጁ አድርገናል፡፡
እንደዚሁም ልዩ ልዩ ጒዳዮችን የሚመለከትና የሚጠቀልል ሕግ ሁሉ አንድነትን ያለውና የተሟላ እንዲሆን አስፈላጊ ስለሆነ ይህ ዛሬ
በዐዋጅ የምናወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ በዚሁ መሠረት ተዘጋጅቶ ይገኛል፡፡
የፍትሐ ነገሥት ኮሚሲዮን ይህን ሕግ በጥንቃቄ ያዘጋጀውና ፓርላሜንታችንም ከፍ ባለ ትጋት እንደገና ያየው በመሆኑ የታቀደበትን ዓላማ
እንደሚያስገኝ የሚያሳምን ነው፡፡
የፍርድ ምንጭ የጥበብና የሀብት ማግኛ በሆነ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አሠሪነት ይህ ሕግ ላሁኑ ሕዝባችንና ለመጭው ትውልድ
ለሰላሙና ለደኅንነቱ እንደሚሆን እናምናለን፡፡
በነገሥን በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዛሬ ሚያዝያ ሀያ ሰባት ቀን ዐሥራ ዘጠኝ መቶ አምሣ ሁለት ዓመተ ምሕረት አዲስ አበባ በገነተ ልዑል
ቤተ መንግሥታችን ተጻፈ፡፡
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ንጉሠ ነገሥት፡፡
የፍትሐብሔር ሕግ ዐዋጅ
ቊጥር 185 1952 ዓ.ም. የፍትሐብሔር ሕግ ዐ ዋ ጅ
ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ፡፡
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
ሥዩመ እግዚአብሔር ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
የንጉሠ ነገሥት ግዛታችን የሕግ አቋም በሚገባ እንዲስፋፋ ለማድረግ አዲስ የፍትሐ ብሔር ሕግ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ስለ አገኘነው፤
ይህ የፍትሐ ብሔር ሕግ በኛ መሪነት እንዲዘጋጅ አድርገን የሕግ መወሰኛና የሕግ መምሪያ ምክር ቤቶቻችን ስለ ተቀበሉት፤
በተሻሻለው ሕገ መንግሥታችን በ 34 ተኛውና በ 86 ተኛው አንቀጽ የተጻፈውን ተመልክተን፤
የሕግ መወሰኛና የሕግ መምሪያ ምክር ቤቶቻችን የመከሩበትን አይተን ቀጥሎ ያለውን አውጀናል፡፡
1. ይህ አዋጅ የ 1952 ዓ.ም. የፍትሐ ብሔር ሕግ አዋጅ ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል፡፡

2. ይህ የ 1952 ዓ.ም. የፍትሐ ብሔር ሕግ ዐዋጅ በተለይ በቊጥር 2 1953 ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ሚያዝያ 27 ቀን 1952 ዓ.ም.፡፡


ጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የጽሕፈት ሚኒስትር፡፡
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የፍትሐ ብሔር ሕግ፡፡
አንደኛ መጽሐፍ ስለ ሰዎች፡፡
አንቀጽ 1፡፡
ስለ ሰዎች፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ስለ ሰውና ስለ ሰው መብቶች፡፡
ክፍል 1፡፡
የሰው መብት አሰጣጥ፡፡
ቊ 1፡፡ መሠረቱ፡፡

ሰው ከተወለደበት ቀን አንሥቶ እስከ ሞተበት ቀን ድረስ የሕግ መብት አለው፡፡


ቊ 2፡፡ የተፀነሱ ልጆች፡፡

የተፀነሰ ልጅ በሕይወት ከተወለደና የሚኖር ከሆነ የራሱ ጥቅም በሚያሻበት ጊዜ ሁሉ እንደ ተወለደ ይገመታል፡፡

ቊ 3፡፡ የተፀነሰበት ጊዜ፡፡

(1) የልጅ መፀነስ ጊዜ የሚቈጠረው ልጁ ከተወለደበት በፊት ካለው ከሦስት መቶኛው ቀን ወዲህ ነው፡፡

(2) ይህንንም ግምት መቃወሚያ የሚሆን ማንኛውንም ማስረጃ ለማቅረብ አይቻልም፡፡

(3) የልጁ አባት ማን እንደሆነ መወሰንን የሚመለከት ነገር በሆነ ጊዜ ልጁ የተፀነሰበትን ቀን መሠረት አድርጎ ስለ መያዝ የተነገሩት
ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 4፡፡ የሚኖር ወይም የማይኖር ልጅ፡፡

(1) ይህን ተቃዋሚ የሚሆን ማናቸውም ማስረጃ ቢቀርብም እንኳ አንድ ልጅ ተወልዶ 48 ሰዓት በሕይወት ከቈየ በሕይወት እንደ ኖረ ሆኖ
ይቈጠራል፡፡
(2) አንድ ልጅ ተወልዶ በሕይወት የቈየው ከ 48 ሰዓት ያነሰ ጊዜ የሆነ እንደ ሆነ በሕይወት እንዳልኖረ ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(3) የልጁን መሞት ያስከተለው፤ በተፈጥሮው ጒድለት ምክንያት ያልሆነ ሌላ ሁኔታ መሆኑን ለማስረዳት የተቻለ እንደሆነ ከዚህ በላይ
ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተውን አገማመት ቀሪ ለማድረግ ይቻላል፡፡

ቊ 5፡፡ አንድ ሰው በሕይወት መኖሩን ወይም መሞቱን ስለ ማስረዳት፡፡

(1) ማስረጃ ማቅረብ የሚገባው ወገን፡፡

(1) አንድ ሰው፡፡ ባንድ በተወሰነ ጊዜ በሕይወቱ አለ ወይም በዚህ ጊዜ በሕይወቱ ነበረ፤ ወይም በእንደዚህ ያለ ጊዜ ሞቷል ብሎ ማስረዳት
የሚገባው በዚህ ምክንያት አንድ መብት ኖሮት ሊጠቀምበት የሚጠይቀው ወገን ነው፡፡

(2) አንድ ሰው በሕይወት አለ ወይም በሕይወት ነበረ ተብሎ ለማስረዳት የሚቻለው ይህንኑ በሕይወት አለ ወይም ነበረ የተባለውን ሰው
ራሱን በማቅረብ፤ ወይም በቂ ምስክሮችን አቅርቦ በማስመስከር ወይም በቂ ማስረጃ አቅርቦ በማስረዳት ነው፡፡

(3) ያንድ ሰውን መሞት ጒዳይ በማስረጃ ማረጋገጥ የሚቻለውም በዚሁ አንቀጽ በምዕራፍ 3 ቊጥር 47 በተጻፈው ድንጋጌ መሠረት
ነው፡፡

ቊ 6፡፡ (2) አብሮ ሟቾች፡፡


ብዙ ሰዎች አብረው በሞቱ ጊዜና ከነዚሁ ማንኛው በኋላ እንደ ሞተ ለማስረዳት የማይቻል ሲሆን የተባሉት ሰዎች ሁሉ ባንድ ጊዜ እንደ
ሞቱ ይቈጠራል፡፡

ቊ 7፡፡ የመለያ ማስረጃ፡፡

(1) አንድ ሰው ማን እንደሆነ የሚታወቀው የመታወቂያ ሰነድ ለመስጠት የተቋቋመው መሥሪያ ቤት የሰጠውን ሰነድ በማቅረብ ነው፡፡

(2) ይህም ሰነድ የሌለ እንደሆነ በቂ ምስክሮች አቅርቦ በማስመስከር ነው፡፡

(3) ምስክሮቹም የሰጡት መግለጫ ትክክለኛ ባለመሆኑ ምክንያት በሌሎች ሰዎች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት አላፊዎች ይሆናሉ፡፡

ክፍል 2፡፡
ስለ ሰው መብቶች፡፡
ቊ 8፡፡ ሰው መሆን የሚያስገኘው ውጤት፡-

(1) ማንኛውም ሰው በሰው ልጆች መብት የመጠቀም መብትና በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሕገ መንግሥት የተመለከተው የሰው ልጅ ነፃነት
የተረጋገጠለት ይሆናል፡፡

(2) በዚህም አስተያየት ረገድ የዘርንም ልዩነት ሆነ ወይም የቀለምን የሃይማኖትንም ሆነ የፆታን ልዩነት መከተል አይቻልም፡፡

ቊ 9፡፡ የዚህ ውጤት ወሰን፡፡

(1) የሰው ልጆች መብትና በንጉሠ ነገሥቱ ሕገ መንግሥት የተረጋገጡት የሰው ልጆች ነፃነቶች አይነገድባቸውም፡፡

(2) ይህን መብቱን በሥራ ላይ ለማዋል በራስ ፈቃድ የተደረገ የመቀነስ አወሳሰን ጒዳይ ሁሉ ተገቢ ለሆነ ለማኅበራዊ ኑሮ ጥቅም መሆኑ
ካልተረጋገጠ በቀር ዋጋ የሌለው (የማይጸና) ነው፡፡

ቊ 10፡፡ ሕገ ወጥ የሆነ አሠራርን ስለ ማስቀረት፡፡

በሰውነቱ ላይ ሕገ ወጥ የሆነ አሠራር የደረሰበት ሰው በአድራጊው ላይ ሊደርስ የሚችለው የአላፊነት ጒዳይ ሳይቀር ተበዳዩ በደሉ
እንዲቀርለት የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ቊ 11፡፡ በነፃነት ላይ ስለሚደረግ መሰናክልና ስለ መበርበር፡፡

በሕግ በተመለከተው መሠረት ካልሆነ በቀር ማንም ሰው የግል ነፃነቱን ማጣትም ሆነ ያላግባብ መበርበር ሊደርስበት አይገባም፡፡
ቊ 12፡፡ የመኖሪያ ስፍራን የመምረጥ ነፃነት፡፡

(1) ማንኛውም ሰው የመኖሪያ ስፍራውን በሚስማማው ቦታ የመወሰንና እንደ ፈለገም ይህን መኖሪያ ስፍራውን የመለወጥ ነጻነት አለው፡፡

(2) ማንኛውም ሰው የመኖሪያ ስፍራውን ባንድ በተወሰነ ቦታ አደርጋለሁ ብሎ የሚገባው ግዴታ በፍትሐ ብሔር ሕግ አስተያየት በኩል
አንዳችም ዋጋ የሌለው ነው፡፡

(3) ማንኛውም ሰው ባንድ ስፍራ አልኖርም ወይም በአንድ በተወሰነ ስፍራ አልደርስም ብሎ የሚገባው ግዴታ ተገቢ ለሆነ ጥቅም
ምክንያት መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር አይጸናበትም፡፡

ቊ 13፡፡ የመኖሪያ ቤት አለመደፈር፡፡

(1) ያንድ ሰው ማናቸውም መደበኛ መኖሪያ ቤት የማይደፈር ነው፡፡

(2) በሕግ በተመለከተው መሠረት ካልሆነ በቀር ባለቤቱ ሲቃወም ማንኛውም ሰው ከሌላ ሰው መኖሪያ ቤት ለመግባት፤ የሌላውን ሰው
መኖሪያ ቤት ለመበርበር አይችልም፡፡

ቊ 14፡፡ የማሰብ ነፃነት፡፡

(1) ማንኛውም ሰው የማሰብና አሳቡን የመግለጽ ነፃነት አለው፡፡

(2) ይህንንም ነጻነቱን ሊቀንሱበት የሚችሉት የሌሎችን መብቶች የማክበር ግዴታዎች መልካም ባህልንና ሕጎችን አክብሮ የመጠበቅ
ግዴታዎች ናቸው፡፡

ቊ 15፡፡ ስለ ሃይማኖት፡፡

የሕዝብን መልካም ጠባይ ወይም ጸጥታን ወይም በፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ግዛት የሚኖሩ ሰዎች
የሃይማኖታቸውን ሥርዐት አክብረው በነፃ ከመፈጸም አይከለከሉም፡፡

ቊ 16፡፡ የመሥራት ነፃነት፡፡

(1) ማንም ሰው ሁሉ የሞያ ሥራውን ወይም የዕረፍት ጊዜዎቹን በሚመለከተው ረገድ መልካም ነው ብሎ በገዛ አሳቡ የመረጠውን ሥራ
ለማካሄድ ነፃነት አለው፡፡

(2) ይህንን ነፃነቱን ሊቀንሱበት የሚችሉት ምክንያቶች የሌላውን ሰው መብት መልካም ባህልንና ሕጎችን የማክበር ግዴታዎች ብቻ
ናቸው፡፡
(3) ማንኛውም ሰው ሁሉ ይህን የመሥራት ነፃነቱን በመቀነስ አንድ የተወሰነ ሥራ ብቻ ለማካሄድ ወይም አንድ ሥራ ላለመሥራት የገባው
የውል ግዴታ ሁሉ ተገቢ ጥቅም መኖሩን ካላረጋገጠ በቀር ሊጸናበት አይችልም፡፡

ቊ 17፡፡ ስለ ማግባትና ስለ መፍታት፡፡

(1) ማንኛውም ሰው ሚስት እንዳያገባ ወይም እንደ ገና እንዳያገባ ያደረገው የውል ግዴታ ሁሉ በፍትሐ ብሔር ሕግ አስተያየት ረገድ ዋጋ
የሌለው ነው፡፡

(2) እንዲሁም ማንም ሰው እፈታለሁ ወይም አልፈታም ብሎ የሚገባው ግዴታ ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 18፡፡ የሰው አካል የማይደፈር ስለ መሆኑ፡፡

(1) ማንኛውም ሰው ቢሆን አካሉን በሙሉ ወይም በከፊል አሳልፎ ለመስጠት የሚያደርገው የውል ስምምነት ግዴታ ሁሉ፤ ይህ ጒዳይ
የሚፈጸመው አካሉን አሳልፎ የሚሰጠው ሰው ከመሞቱ በፊት የሆነ እንደ ሆነና በአካሉ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ ስምምነቱ
በፍትሐ ብሔር በኩል ዋጋ የሌለው ነው፡፡

(2) የሆነ ሆኖ አካሉን አሳልፎ የመስጠቱ ጒዳይ በሕክምና ጥበብ በኩል ጉዳት የማያደርስ መሆኑ ከተረጋገጠ የዚህ ደንብ አፈጻጸም
አይጸናበትም፡፡

ቊ 19፡፡ ይህንን ጒዳይ የሚመለከቱት ውሎች ተለዋጭ ስለ መሆናቸው፡፡

(1) ማንኛውም ሰው በሕይወት ሳለሁ ወይም ከሞትሁ በኋላ አካሌን በመላውም ሆነ በከፊሉ ሰጥቻለሁ ብሎ የገባበትን ግዴታ
በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ሊሽረው ይችላል፡፡

(2) የሆነ ሆኖ በዚህ አሠራር ሊጠቀም የነበረው ሰው በተሰጠው ተስፋ መሠረት ላደረገው ወጪ ሁሉ ኪሣራ መቀበል አለበት፡፡

ቊ 20፡፡ የሐኪሞች ምርመራና ሕክምና (1) መሠረቱ፡፡

(1) ማንኛውም ሰው የሐኪም ወይም የተቀዳጀ ሐኪም ምርመራ ወይም ሕክምና እንዳይደረግለት በማንኛውም ጊዜ ሁሉ እንቢ ለማለት
ይችላል፡፡
(2) ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ሰዎች የጤንነት ምርመራ እንዲያደርጉ ወይም የግዴታ ክትባት እንዲፈጽሙ ወይም ይህን ስለ መሳሰለው የጤና
አጠባበቅ ጥንቃቄ ጒዳይ የወጡት የሕግ ክፍል ማስታወቂያዎችና ሕጋውያን ዐዋጆች እንደ ተጠበቁ ናቸው፡፡

(3) እንዲሁም አንድ ችሎታ ለሌለው ወይም በሕግ ለተከለከለው ሰው አሳዳሪ የሆነው ሰው፤ በሥልጣኑ የሚተዳደረው ችሎታ የሌለው
ሰው ጤንነቱ እንዲጠበቅ የሐኪም ምርመራ የሚያደርግበትና የሚያሳክምበት ሥልጣኑ የተጠበቀ ነው፡፡
ቊ 21፡፡ (2) አወሳሰን፡፡

ቢሆንም አንድ ሰው በሐኪም እንዲመረመር ወይም እንዲታከም የሚጠይቅበት ምርመራ ማንኛውንም ያለመጠን የሆነ ጉዳትን
የማያስከትል ሲሆን፤ ሰውዬውም ይህንን የሐኪም ምርመራና ሕክምና ለማድረግ እንቢ ያለ እንደሆነ፤ ይህ ሕክምናና ምርመራ
ሊያግድለት፣ ሊያስቀርለት ወይም ሊያሽለው ይችል በነበረው ሕመም ወይም ደዌ ክርክር ሊያቀርብ አይችልም፡፡

ቊ 22፡፡ የሐኪም ምርመራ፡፡

አንድ ሰው በሰውነት ላይ አንዳችም እርግጠኛ አደጋ ሊያስከትል በማይችል በሐኪም ምርመራ ለመመርመር እንቢ ያለ እንደሆነ ዳኞች
ተመርምሮ ሊገኝበት ይችላል ተብሎ የተገመተው ነገር እንዳለበት ያህል ሊቈጥሩት ይችላሉ፡፡

ቊ 23፡፡ የዝምታ መብት፡፡

የሰውን አካል በመድፈር (በሰውነት ላይ ጉዳት በማድረስ) የተገኘ ማንኛውም የእምነት ቃል ወይም የአሳብ መግለጫ ሁሉ ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 24፡፡ የሞያ ሥራ ምስጢር፡፡

(1) አንድ ሰው፤ ሌላው ሰው በእርሱ ላይ ያለውን እምነት የሚያጐድል ወይም ለማጒደል የሚችል መስሎ ሲታየው በሞያ ሥራው
ምክንያት ያወቃቸውን ሁኔታዎች እንዲገልጽ ለመገደድ አይችልም፡፡

(2) እነዚህን ሁኔታዎች ለባለአደራው የገለጸ ወይም እንዲያውቃቸው ያደረገ ሰው እነዚህ ሁኔታዎች በባለአደራው አንደበት
እንዳይገለጹበት የመከልከል መብት አለው፡፡

(3) በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ውስጥ በመንግሥት ላይ፤ በሀገርና በእንቴርናሲዮናል ጥቅሞች ላይ ስለሚሠሩ ወንጀሎች የተወሰኑት
ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 25፡፡ ስለ መቃብር ሥርዐት፡፡ (1) የሟቹ ፈቃድ፡፡

(1) ማንኛውም ለመናዘዝ ችሎታ ያለው ሰው ሁሉ የመቃብሩን ሥርዐት አስቀድሞ ለማደራጀት ይችላል፡፡

(2) የዚህንም ድርጅት አፈጻጸም እንዲጠብቁለት አንድ ወይም ብዙ ሰዎች ለማዘዝ ይችላል፡፡

(3) እነዚህም የሟቹን የመጨረሻ ፈቃድ ለማስፈጸም አደራ የተቀበሉት ሰዎች እንደሌሉም፤ የግዙፍ ወይም የሕሊና (የሞራል) ጥቅም
ያለው ማንኛውም ሰው፤ ሰውዬው ለሞተበት ቦታ ባለሥልጣን የሆኑት ዳኞች የታሰበውን ድርጅት እንዲያስፈጽሙ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 26፡፡ (2) ያልተገለጸ አሳብ (ፈቃድ)፡፡


(1) ሟቹ ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር ድንጋጌ መሠረት አሳቡን (ፈቃዱን) ሳይገልጽ ቀርቶ እንደሆነ የመቃብሩን ሥርዐት ድርጅት
የሚያከናውኑት የሟቹ ባለቤት ወይም የቅርብ ዘመዶቹ ናቸው፡፡

(2) በሞተ ጊዜ ባለቤት የሌለው እንደሆነ ወይም የቅርብ ዘመዶቹ ባቅራቢያው ያልተገኙ እንደሆነ ወይም ያልታወቁ እንደሆነ በራሳቸው
ፈቃድ ሥርዐቱን ለማስፈጸም በጀመሩት ሰዎች አማካይነት ይከናወናል፡፡

(3) በአፈጻጸሙም በኩል ክርክር የተነሣ እንደሆነ ጒዳዩን በቅርብ በሚከታተሉት ሰዎች አማካይነት ሰውዬው በሞተበት ቦታ ያሉት ዳኞች
ጒዳዩን እንዲወስኑ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡

ቊ 27፡፡ የሰው ሥዕል፡፡ (1) (መሠረቱ)፡፡

ባለ ፎቶግራፉ ወይም ባለሥዕሉ ካልፈቀደ በቀር የማንም ሰው ፎቶግራፍ ወይም ሥዕል በሕዝብ አደባባይ ሊለጠፍም ሆነ ሊባዛ ወይም
ሊሸጥ አይችልም፡፡

ቊ 28፡፡ (2) ልዩ አስተያየት፡፡

የፎቶግራፉ ወይም የሥዕሉ መባዛት ምክንያት የሆነው ባለፎቶግራፉ የታወቀ ሰው በመሆኑ ወይም በሚያከናውነው ሕዝባዊ ሥራ
ምክንያት፤ ወይም በፍርድና በፖሊስ መሥሪያ ቤቶች በኩል አስፈላጊነቱ የተረጋገጠ ምክንያት ያለው በመሆኑ ወይም ለኪነ ጥበብ (ሲያንስ)
ለሥልጣኔ አስተዳደግ ወይም ለትምህርት መስጫ ጥቅም በመሆኑ፤ ወይም ደግሞ የፎቶግራፉ መባዛት የተፈጸመው በክብረ በዓል ወይም
በሕዝብ ስብሰባ ላይ ከተፈጸመ ሥርዐት ጋራ ግንኙነት ባለው ምክንያት ሲሆን የባለፎቶግራፉ ፈቃድ አስፈላጊ አይደለም፡፡

ቊ 29፡፡ (3) ክልከላ፡፡

(1) ባለሥዕሉ ሳይፈቅድ ያንድ ሰው ሥዕል ከዚህ በላይ ከተመለከተው ቊጥር ድንጋጌ ውጭ በሆነ ሁኔታ በአደባባይ የተለጠፈ ወይም
ለሽያጭ የቀረበ (የተዘጋጀ) እንደሆነ ባለሥዕሉ ይህ አድራጎት እንዲወገድ ለመጠየቅ (ለማስገደድ) መብት አለው፡፡

(2) በርትዕ አስፈላጊ ሆኖ ሲታይ ሥዕሉን በአደባባይ በለጠፍና በመሸጥ የተጠቀመው ሰው በዚሁ ምክንያት ያገኘው ሀብት ተመዛዛኝ
በሚሆንበት መጠን ዳኞች ካሣ እንዲከፍል ሊወስኑበት ይችላሉ፡፡

(3) የሥዕሉ በአደባባይ መለጠፍና መሸጥ እንዲቋረጥ እንዲታገድ እንደተጠየቀ ወዲያውኑ ጥያቄው ሳይፈጸም የቀረ እንደሆነ በስም
ማጥፋት ጊዜ እንደሚፈጽመው ዳኞች የሞራል ጉዳት ካሣ ሊያሰጡት ይችላሉ፡፡

ቊ 30፡፡ (4) የቤተ ዘመድ መብት፡፡


(1) ሥዕሉ በአደባባይ የወጣበት ወይም የተሸጠበት ሰው ሞቶ እንደሆነ ወይም ፈቃዱን ለመግለጽ የማይችል ሆኖ የሚገኝ እንደሆነ፤
የሥዕሉ በአደባባይ መገለጽ ወይም መሸጥ የሟቹን ክብር የሚነካ ወይም ግምቱን የሚያጐድልበት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ
በተጻፈው ቊጥር ውስጥ የተመለከቱት መብቶች የሟቹ ቤተ ዘመዶች ይሆናሉ፡፡

(2) በዚህም ቊጥር ለተጻፈው አፈጻጸም ለቤተ ዘመድ እንደራሴ ለመሆን የሚችለው የሟቹ ባለቤት፤ ይህም ባይኖር የቅርብ ተወላጅ (ልጅ
የልጅ ልጅ) ወይም ተወላጁ የሌለ ሲሆን ወደ ላይ የሚቈጠር የሟቹ የቅርብ ወላጅ ብቻ ነው፡፡

(3) የዝምድናው ደረጃ እኩል በሆነ ጊዜ ለቤተ ዘመዱ እንደራሴ ለመሆን የሚችለው ከተወላጆቹ በዕድሜ የሚበልጠው ወይም ወደ ላይ
ከሚቈጠሩት ወላጆቹ በዕድሜ ከፍ ያለው ብቻ ነው፡፡

ቊ 31፡፡ ደብዳቤ የማይደፈር ስለ መሆኑ፡፡

(1) ለራሱ ብቻ የተጻፈለትን ደብዳቤ ተቀባይ የሆነው ሰው ይህ በዚህ ደብዳቤ የተጻፈውን ላኪው ካልፈቀደለት በቀር ለሌላ ሰው ለመግለጽ
አይችልም፡፡
(2) ስለሆነም ተገቢ ጥቅም ያለው ለመሆኑ ማስረዳት የቻለ እንደሆነ በፍርድ በኩል ለሚያጋጥመው ጒዳይ ለፍርድ ችሎት ለማቅረብ
ይችላል፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
ስለ ስም፡፡
ቊ 32፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) እያንዳንዱ ሰው አንድ የቤተ ዘመድ ስምና አንድ ወይም ብዙ የግል ስሞችና የአባት ስም ይኖረዋል፡፡

(2) በአስተዳደር ክፍል (በአድሚኒስትራሲዮን) ጽሑፎች፤ የግል ስሞቹንና የአባቱን ስም በሚያሰከትል በቤተ ዘመድ ስም ይመለከታል፡፡

ቊ 33፡፡ የስም አሰጣጥ፡፡

(1) የልጁ የቤተ ዘመድ ስም የአባቱ የቤተ ዘመድ ስም ነው፡፡

(2) የልጅ አባት ያልታወቀ በሆነ ጊዜ ወይም ልጁ ተክዶ እንደሆነ የልጁ የቤተ ዘመድ ስም የእናቱ የቤተ ዘመድ ስም ነው፡፡

(3) እንዲሁም በእናቲቱ መጠለፍ ወይም መደፈር ምክንያት የልጁ አባት በፍርድ ውሳኔ ተረጋግጦ እንደሆነም አፈጻጸሙ በዚህ ዐይነት
ነው፡፡

ቊ 34፡፡ የግል ስም ምርጫ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የአንድ ልጅን የግል ስም የሚመርጠው አባቱ፤ ወይም አባቱ በሌለ ጊዜ የእናቱ ቤተ ዘመድ ነው፡፡
(2) ለልጁ ሁለተኛ የግል ስም እናቱ ወይም እርስዋ እንደሌለች የእናቱ ቤተ ዘመዶች መርጠው ሊያወጡለት ይችላሉ፡፡

(3) የልጁ አባት ያልታወቀ በሆነ ጊዜ፤ ወይም ልጁ የአባቱ ወገን የሆኑ ቤተ ዘመዶች የሌሉት የሆነ እንደሆነ የልጁ እናት ወይም እርስዋ
ባትኖር የእናቱ ቤተ ዘመዶች ለልጁ ሁለት የግል ስም ሊሰጡት ይችላሉ፡፡

ቊ 35፡፡ (2) የቤተ ዘመድ እንደራሴ፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተመለከተው ቊጥር ያለው ደንብ በሥራ በሚውልበት ረገድ የቤተ ዘመድ እንደራሴ ለመሆን የሚችለው በጣም ቅርብ
የሆነ ወደ ላይ የሚቈጠር ወላጅ፤ ወይም ይህ በታጣ ጊዜ በጣም ቅርብ የሆነው የጐን ዝምድና ያለው ሰው ነው፡፡

(2) የዝምድናውም ደረጃ እኩል በሆነ ጊዜ የልጁን የግል ስም የሚመርጠው በዕድሜ ከፍ ያለው ወደ ላይ የሚቈጠር ወላጅ ወይም የጐን
ዝምድና ያለው ሊሆን ይችላል፡፡

ቊ 36፡፡ የአባት ስም፡፡

(1) ለልጁ ያባት ስም የሚሆነው የአባቱ የግል ስም ነው፡፡

(2) አባቱ ባልታወቀ ጊዜ ሰውዬው ያባቱ ስም አይኖረውም፡፡

(3) በአስተዳደር ክፍል (በአድሚኒስትራሲዮን) ጽሑፎች ውስጥ ያባት ስም ከቤተ ዘመድ ስም ጋራ አንድ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ያባት ስም
አይጻፍም፡፡

ቊ 37፡፡ ለክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት የሚሰጥ መግለጫ፡፡

ልጁ በተወለደበት ቀበሌ (አጥቢያ) ለሚገኘው የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሹም የልጁን መወለድ መግለጫ ሊሰጥ የሚገባው ሰው፤ ልጁ
ከተወለደበት ቀን አንሥቶ ባለው በተከታዩ ዘጠና ቀን ውስጥ ለተወለደው ልጅ የተሰጠውን የግል ስም ማቅረብ አለበት፡፡

ቊ 38፡፡ የተከለከለ የግል ስም፡፡

(1) ማንኛውም ልጅ፤ ያባቱ ወይም የናቱ ወይም ደግሞ በሕይወት ካሉት እኅቶቹና ወንድሞቹ ያንደኛው የግል ስም ብቻ ሊሰጠው
አይቻልም፡፡
(2) እንዲህ ያለ ነገርም ባጋጠመ ጊዜ ከነዚህ ሰዎች የሚለየው አንድ ሌላ የግል ስም ሊኖረው ይገባል፡፡

ቊ 39፡፡ ወላጆቹ ያልታወቀ ልጅ፡፡


(1) አባቱን ወይም እናቱን ለማወቅ ያልተቻለ ልጅ በመወለዱ የምስክር ወረቀት ውስጥ የክብር መዝገብ ሹም የሚሰጠው የቤተ ዘመድ
ስምና ሁለት የግል ስሞች ይኖሩታል፡፡

(2) የቤተ ዘመድ ስምና የግል ስሞቹም የሚመረጡለት በተወለደበት አውራጃ ውስጥ ከሚገኘው ልማዳዊ የቤተ ዘመድ ስምና የግል ስሞች
መካከል ነው፡፡

(3) የግዙፍ ወይም የሕሊና (የሞራል) ጥቅም ያለው መሆኑን የሚያስረዳ ማንኛውም ሰው የተባለው ልጅ አምስት ዓመት እስኪሞላው
ድረስ የተሰጠው ስምና የግል ስም እንዲለወጥለት ዳኞችን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 40፡፡ ያገባች ሴት ስም፡፡


(1) ያገባች ሴት የራስዋ የሆነውን የቤተ ዘመድ ስም እንደ ያዘች ትቈያለች፡፡

(2) ስለሆነ ግን ጋብቻዋ ጸንቶ እስከሚቈይበት ጊዜ ድረስ በባልዋ ስም ልትጠራ ወይም ራስዋ እንድትጠራ ለማድረግ ይቻላል፡፡

(3) ጋብቻው የቀረው በመፋታቷ ወይም እንደ ገና ሌላ ባል በማግባቷ ምክንያት ካልሆነ በቀር ከዚህ በላይ የተጻፈው የስም መጠራት
መብት ቢጠቅማትም ቢጐዳትም ከጋብቻው በኋላ እንደ ጸና ይቀራል፡፡
ቊ 41፡፡ የጉዲፈቻ ልጅ የቤተ ዘመድ ስምና የግል ስም፡፡
(1) የጉዲፈቻ ልጅ የጉዲፈቻ አድራጊው የቤተ ዘመድ ስም ይኖረዋል፡፡

(2) በጉዲፈቻው ውል መሠረት አንድ አዲስ የግል ስም ሊሰጠውና የጉዲፈቻ አድራጊውም መደበኛ የግል ስም እንደ አባት ስም ሊሆነው
ይችላል፡፡
ቊ 42፡፡ የቤተ ዘመድ ስም መለወጥ፡፡
(1) በቂ ምክንያት የተገኘ እንደሆነ በሰውዬው ጠያቂነት የዚህ ሰው የቤተ ዘመድ ስም እንዲለወጥ ዳኞች ለመፍቀድ ይችላሉ፡፡

(2) ዳኞቹም የቀረበላቸውን ጥያቄ ሲመረምሩ የስሙ መለወጥ ጒዳይ በሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ አንዳችም ጉዳት እንዳያስከትል ጥንቃቄ
ያደርጋሉ፡፡
ቊ 43፡፡ የግል ስም መለወጥ፡፡
ከግል ስሞቹ አንዱ ወይም ብዙዎቹ እንዲሠረዙ ወይም ሌላ የግል ስም እንዲጨመርለት ባለጥቅሙ ጥያቄ ባቀረበ ጊዜ ሊፈቀድለት
ይቻላል፡፡
ቊ 44፡፡ ስምን የሚመለከቱት ውሎች፡፡
(1) ስለ ስም የሚደረግ ማንኛውም ውል ሁሉ በፍትሐ ብሔር ሕግ ረገድ ዋጋ የሌለው ነው፡፡

(2) የንግድ ስምን የሚመለከቱ ደንቦች የተጠበቁ ናቸው፡፡


ቊ 45፡፡ በራስ ስም ያለ አግባብ ስለ መጠቀም፡፡
(1) አንድ ሰው የሞያ ሥራውን በሚያከናውንበት ሁኔታ ውስጥ በገዛ ስሙ የመገልገል ጒዳይ በይመስላል ከሚደርሰው መዘባረቅ የተነሣ
በሌላው ሰው ክብርና ገናናነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ ግብ ወይም ውጤት የሚያስከትል ነገር ሊኖረው አይገባም፡፡

(2) አስፈላጊ መሆኑም በተገመተ ጊዜ፤ በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ጒዳይ ያለ አግባብ የመወዳደርና የስም ማጥፋት ደንቦች ተፈጻሚዎች
ይሆናሉ፡፡
ቊ 46፡፡ በሌላው ስም ያለ አግባብ ስለ መገልገል፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ስም ያለው ሰው በዚሁ በመሰል ስሙ ምክንያት ሌላ ሰው ያላግባብ በመገልገሉ ግዙፍና የሕሊና (የሞራል) ጉዳት
የሚያደርስበት ሁኔታ የሚያጋጥመው የሆነ እንደሆነ ይህን የቤተ ዘመድ ስሙን ሌላ ሰው ያለ አግባብ እንዳይገለገልበት ለመቃወም
ይችላል፡፡

(2) ባለ ስሙ ከሞተ በኋላ፤ ወይም ፈቃዱን ለመግለጽ ችሎታ ባጣ ጊዜ ይህ ስም የማይጠራበት ቢሆንም እንኳ የሟቹ ሚስት ወይም ባልና
ተወላጆቹ ይህ የመቃወም መብት ይኖራቸዋል፡፡

(3) ይህ በስም ያላግባብ የመገልገል ጒዳይ እንዲታገድ ተጠይቆ ወዲያውኑ ሳይታገድ የቀረ እንደሆነ እንደ ስም ማጥፋት ተቈጥሮ የሕሊና
(የሞራል) ጉዳት ካሣ ሊወሰን ይቻላል፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ክብር መዝገብ አስረጅነት፡፡
ቊ 47፡፡ የአስረጅነቱ ዐይነት፡፡
(1) ልደት፤ ሞትና ጋብቻ ያጠራጠሩ እንደሆነ፤ ወይም ክርክር የተነሣባቸው እንደሆነ የሚረጋገጡት በክብር መዝገብ ጽሑፍ አስረጅነት
ነው፡፡
(2) እንዲሁም ሕግ በሚፈቅድበት ጊዜ በታወቀ ሰነድ አስረጅ አማካይነት ወይም በሁኔታ መኖር ሊረጋገጡ ይችላሉ፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ ክብር መዝገብ ሹማምቶች፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
የክብር መዝገብ ሹማምት ሥልጣን አሰጣጥ፡፡
ቊ 48፡፡ በአገረ ገዢው ስለ መሾም፡፡
(1) ጠቅላይ አገረ ገዥ በግዛቱ ውስጥ ለሚገኘው የከተማና የባላገር ቀበሌ (አጥቢያ) የክብር መዝገብ ሹም የሚሆነውን ሰው ይሾማል፡፡

(2) እንዲሁም በያንዳንዱ ቀበሌ (አጥቢያ) ለእነዚህ ሹማምቶች ምትክ ሆነው የሚሠሩ አንድ ወይም ብዙ ሠራተኞችን ይሾማል፡፡
ቊ 49፡፡ ሰፈር ወይም የቀበሌ ክፍል፡፡
(1) አንድ የከተማ ቀበሌ በብዙ ሰፈሮች የተከፈለ እንደሆነ ለያንዳንዱ ልዩ ሰፈር አንዳንድ የተለየ የክብር መዝገብ ሹምን ጠቅላይ ገዢው
ሊሾም ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ያንድ የባላገር ቀበሌ ክፍል ለብቻው የሆነ ወይም ከዋናው ቀበሌ የተራራቀ የሆነ እንደሆነ አገረ ገዢው ለዚሁ የተለየ የክብር
መዝገብ ሹምን ለመሾም ይችላል፡፡

(3) እንዲህም በሆነ ጊዜ ለያንዳንዱ የክብር መዝገብ ሹም አንድ ወይም ብዙ ምትክ ይሾምላቸዋል፡፡
ቊ 50፡፡ የክብር መዝገብ ሹም ምትክ፡፡
(1) ዋናው የክብር መዝገብ ሹም ሥራውን ለማከናወን የሚያውከው በራሱ በኩል የደረሰ እክል ባጋጠመ ጊዜ ምትኮቹ ተተክተው
ይሠራሉ፡፡

(2) ምትክ የሆኑት ሰዎች ሥራቸውን እንዲያከናውኑ በሚጠሩበት ጊዜ የቅደም ተከተል ተራቸውን የክብር መዝገቡ ሹም አልወሰነላቸው
እንደሆነ በቀዳሚነት የሚተካው በዕድሜ ከፍተኛ የሆነው ነው፡፡

(3) ከምትኮች አንደኛው ያደራጀው ሰነድ የክብር መዝገቡ ሹም ልክ እንደሠራው ያህል የሚቈጠርና ዋጋ ያለው አስረጅ ነው፡፡
ቊ 51፡፡ የሥራቸው አጀማመር፡፡
(1) የክብር መዝገብ ሹሙ ሥራ የሚጀመረው፤ ሥራውን ከተቀበለና፤ ፊርማውም በጠቅላይ ግዛቱ ጽሕፈት ቤት ወይም በክብር መዝገቡ
ደብተር ላይ ከገባ በኋላ ነው፡፡

(2) እንደዚሁም የክብር መዝገብ ሹም ሥራዎች የሚጀመሩት አገረ ገዢው የሾመው ሰው አንድ ሰነድ በማደራጀት፤ ወይም ይኸው ሰነድ
ሲደራጅ በክብር መዝገብ ሹም ስም ተካፋይ በመሆን፤ የዚሁኑ አሠራር በተግባሩ አከናውኖ እንደሆነ ነው፡፡ ወይም የዚሁኑ የሥራውን
ጒዳይ የሚመለከት ሁኔታ መዝገብ በጀመረ ጊዜ ነው፡፡

(3) ከዚህ በላይ ባሉት ኀይለ ቃሎች የተመለከቱት ድንጋጌዎችም የክብር መዝገብ ሹሙን ምትኮች በሚመለከተው ጒዳይም ተፈጻሚዎች
ይሆናሉ፡፡
ቊ 52፡፡ ሥራው የሚቀርበት ጊዜ፡፡
(1) የክብር መዝገብ ሹም ሥራ ቀሪ የሚሆነው ሲሞት ወይም ከሥራው ሲነሣ፤ ወይም ሲሻር ወይም ስንብት ጠይቆ ይህንኑ አገረ ገዢው
ሲቀበለው ነው፡፡

(2) የክብር መዝገብ ሹሙ ምትኮች ሥራ የሚቀረው በዚሁ ዐይነት ነው፡፡


ቊ 53፡፡ የክብር መዝገብ ሹም ወይም ምትኮች ሠራተኞች መሞትና ብዙ ጊዜ የሚቈይ እክል፡፡
(1) የክብር መዝገብ ሹም ከምትኮቹ ያንዱን ሞት ወይም ለዘወትር ከሥራ የሚለያቸው እክል የገጠማቸው መሆኑን ያለ መዘግየት ለግዛቱ
አገረ ገዢ ያስታውቃል፡፡

(2) እንዲሁም የክብር መዝገብ ሹም ምትኮች የሆኑት የክብር መዝገቡ ሹም መሞቱን ወይም ሥራውን እንዳያከናውን ለዘወትር የሚቈይ
እክል የደረሰበት መሆኑን ማንኛውንም ይህን የመሳሰለ ሁኔታ ለግዛቱ አገረ ገዢ ሳይዘገይ ያስታውቃል፡፡

ቊ 54፡፡ የቀበሌ (የአጥቢያ) ሹም፡፡

(1) አገረ ገዢው የሾመው ሰው ወይም ለዚሁ ምትክ የሆኑት ሰዎች ሥራቸውን ለማከናወን በማይችሉበት ሁኔታ በሚገኙበት ጊዜ የቀበሌው
ሹም በሕግ መሠረት በዚሁ ቀበሌ የክብር መዝገብ ሹም ይሆናል፡፡

(2) እንደዚህ ያለ ነገርም ባጋጠመ ጊዜ ለክብር መዝገብ ሹምነት ሥራው፤ በራሱ ኅላፊነት በአንድ ወይም በብዙ ረዳቶች እየተተካ ወይም
እየተረዳ ለመሥራት ይችላል፡፡
ቊ 55፡፡ የጠቅላይ ግዛት ጽሕፈት ቤት፡፡
(1) ጠቅላይ አገረ ገዢው በጠቅላይ ግዛቱ ውስጥ ለሚገኘው ለያንዳንዱ አውራጃ ግዛት ከተማ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ሠራተኞችን መርጦ
ያቋቁማል፡፡

(2) እነዚህም ሠራተኞች በሥራው አቋቋምና አመራር በኩል አላፊ ከሚሆን የሥራ አስኪያጅ (ዲሬክተር) በቀር የጽሕፈት ቤቱን
(የቢሮውን) ሥራ ለማካሄድ በቂ የሆኑ፤ ቍጥራቸው እንደ መጠኑ የተወሰነ ሠራተኞች ይኖሩበታል፡፡
ቊ 56፡፡ የንጉሠ ነገሥቱን ቤተ ዘመድ የሚመለከት የክብር መዝገብ፡፡
(1) ግርማዊ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትንና ንጉሠ ነገሥታዊ ቤተ ዘመድን በሚመለከተው የክብር አመዘጋገብ ጒዳይ የክብር መዝገብ
ሹምነትን ሥራ የሚፈጽመው የጽሕፈት ሚኒስትሩ ነው፡፡

(2) በዚህ ቍጥር ላይ የተመለከተው ቃል በሥራ ላይ በሚውልበት ረገድ የንጉሠ ነገሥቱ ቤተ ዘመዶች የሚባሉት በሕገ መንግሥቱ
በአንቀጽ 06 እንደተመለከተው ነው፡፡
ቊ 57፡፡ የኢትዮጵያ ቆንሲሎች፡፡
የኢትዮጵያ ቆንሲሎች በተሾሙበት አገር ውስጥ ያሉትን የኢትዮጵያ ዜጎች በሚመለከተው ረገድ የክብር መዝገብ ሹማምቶች ናቸው፡፡
ቊ 58፡፡ የመርከብ አዛዦች፡፡
የኢትዮጵያ መርከብ አዛዦች በመርከባቸው ውስጥ በሚደርሰው ልደት ሞትና ጋብቻ ረገድ የክብር መዝገብ ሹሞች ናቸው፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
የክብር መዝገብ ሹም ተግባር፡፡
ቊ 59፡፡ መሠረቱ፡፡
የክብር መዝገብ ሹም ተግባር በራሱ ክፍል ውስጥ የሚደርሰው ልደት ሞት፤ ጋብቻ በክብር መዝገብ ውስጥ እንዲጻፍ መቈጣጠርና
መጠባበቅ ነው፡፡

ሀ) የከተማ ቀበሌ፡፡
ቊ 60፡፡ የመዝገቦች አያያዝና አቀማመጥ፡፡
(1) ጠቅላይ አገረ ገዢው ይህን ግዴታ እንዲያከናውን በግልጽ ያዘዘው የክብር መዝገብ ሹም በዚሁ ቀበሌ የክብር መዝገቦችን ራሱ መያዝ
አለበት፡፡

(2) የዚህንም መዝገብ ጥበቃና አቀማመጥ ራሱ አረጋግጦ ባለጒዳዮቹም በጠየቁት ጊዜ የዚህን መዝገብ ጽሑፍ ቅጅ ወይም ትክክለኛ
ግልባጭ ለባለጥቅሞቹ ይሰጣል፡፡
ቊ 61፡፡ የመዝገቦች አያያዝና አቀማመጥ፡፡
(1) የክብር መዝገብ ላይ የሚጻፉትን ማስረጃዎች፤ የክብር መዝገብ ሹም አስፈላጊ የሆኑት ጒዳዮች በእጁ እንደገቡለት፤ በራሱ አሳቢነት
መመዝገብ አለበት፡፡

(2) የክብር መዝገቡ ሹም አስፈላጊ መስሎ የታየው እንደሆነ የሚያስፈልጉትን ማስረጃዎች በመዝገቡ ላይ አሟልቶ ለመጻፍ እንዲችል
ለባለጒዳዮቹ ጥሪ ያደርግላቸዋል፡፡
ቊ 62፡፡ የጊዜ ውሳኔ፡፡
የሕዝብ የክብር መዝገብ ጽሑፎች በሚከተሉት ጊዜዎች ውስጥ መመዝገብ አለባቸው፡፡
ሀ/ ስለ ልደት ጽሑፎች ሦስት ወር፡፡

ለ/ ስለ ሞት ጽሑፎች አንድ ወር፡፡

ሐ/ ስለ ጋብቻ ጽሑፎች አንድ ወር፡፡


ቊ 63፡፡ የጊዜው ውሳኔ አለመፈጸም፡፡
(1) የተወሰነው ሕጋዊ ጊዜ ካለፈ በኋላ የሚጻፉ የሕዝብ የክብር መዝገብ ጽሑፎች ዋጋቸው እንደ ተራ ማስታወቂያዎች አስረጂ ብቻ
የሚቈጠሩ ናቸው፡፡

(2) ስለሆነም በመዝገቡ ላይ የተመዘገቡት በአንድ ፍርድ መሠረት እንደሆነ ከዚህ በላይ የተጻፈው አይጸናም፡፡

(3) ይህ ሲሆን ጽሑፉ ፍርዱን የሚጠቅስ ቃል በላዩ ላይ ይኖርበታል፡፡

ለ) የገጠር ቀበሌዎች፡፡
ቊ 64፡፡ ማስታወቂያዎች፡፡
(1) ይህን ግዴታ እንዲፈጽም የክብር መዝገብ ሹሙ በአገረ ገዢው በግልጽ ባልታዘዘበት የገጠር ቀበሌዎች፤ የክብር መዝገብ ሹሙ ራሱ
መዝገቦችን እንዲይዝ አይገደድም፡፡

(2) በቀበሌው ውስጥ የደረሱትን ልደት መሞትና ጋብቻ የሚመለከቱትን የክብር መዝገብ ጽሑፎች ለመመዝገብ አስፈላጊ የሆኑትን
መረጃዎች የክብር መዝገብ ሹሙ ለጠቅላይ ግዛት የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ማስታወቅ ብቻ አለበት፡፡
(3) እነዚህን መረጃዎች እምነት በማድረግ የጠቅላይ ግዛት የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች የክብር መዝገብ ጽሑፎችን ወዲያውኑ
ይመዘግባሉ፡፡
ቊ 65፡፡ የአፈጻጸሙ ደንብ፡፡
(1) እያንዳንዱን ቀበሌ ስለሚመለከተው እነዚህ መረጃዎች በምን ሁኔታ መሰብሰብ እንዳለባቸው ከአገረ ገዢው የሚሰጡት ትእዛዞች
ይወስናሉ፡፡
(2) በተለይም እነዚህ ትእዛዞች በምን ስፍራና በምን ጊዜ መረጃዎቹ መሰጠት እንዳለባቸው ይወስናሉ፡፡
ቊ 66፡፡ መረጃዎቹ የሚቀርቡበት ስፍራ፡፡
(1) ትእዛዞቹም የሕዝብ የክብር መዝገብ የሚመለከቱትን መረጃዎች ለመስጠት ወደ ጠቅላይ ግዛቱ ዋና ከተማ ወይም ለቀበሌው ቀረብ
ባለው ባንድ ሌላ ቦታ እንዲሄድ የክብር መዝገቡን ሹም ለማስገደድ ይችላሉ፡፡

(2) እንደዚሁም ትእዛዞቹ መዝገቦችን ማቋቋም ከሚያስፈልግበት ቀበሌ ውስጥ የጠቅላይ ግዛት የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች
እነዚህን መረጃዎች መሰብሰብ እንዳለባቸው አስቀድሞ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

(3) ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል እንደተመለከተው መዝገቦቹ በቀበሌው ወይም በጠቅላይ ግዛቱ በክብር መዝገብ ክፍል ጽሕፈት ቤት
ውስጥ የሚኖሩ ለመሆናቸው ትእዛዝን ለይተው ይወስናሉ፡፡
ቊ 67፡፡ መረጃዎቹ የሚቀርቡበት ጊዜ፡፡
(1) የሕዝብ የክብር መዝገብን የሚመለከቱ መረጃዎች ለያንዳንዱ ቀበሌ ቢያንስ በዓመት 1 ጊዜ መሰብሰብ አለባቸው፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው ቍጥር በ 1 ኛ ኀይለ ቃል ስለተመለከተው በጠቅላይ ግዛቱ ዋና ከተማ ወይም በሌላ ስፍራ የሕዝብ የክብር መዝገቡ
ሹም ከ 3 ወር ባነሰ ጊዜ የመሄድ ግዴታ የለበትም፡፡
ቊ 68፡፡ አማካይ በሆነ ጊዜ ውስጥ መግለጫዎችን ማቅረብ ስለመቻሉ፡፡
(1) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም በማናቸውም ጊዜ አገረ ገዢው ከወሰነው ጊዜ ውጭ በሚገኝበት ቀበሌ ያሉትን ሰዎች የክብር መዝገብ
የሚመለከቱ መረጃዎችን ለጠቅላይ ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) ቀበሌውን የሚመለከቱ መዝገቦች በዚሁ ጽሕፈት ቤት ተቀምጠው የሚገኙ እንደሆነ እነዚህ መረጃዎች ወዲያውኑ በጠቅላይ ግዛቱ
የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት መመዝገብ አለባቸው፡፡
ቊ 69፡፡ የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም የጽሑፎች አሠራር፡፡
(1) ትእዛዞቹ፤ የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹሙን ራሱ የክብር መዝገብ ጽሑፎችን እንዲጽፍ ሊፈቅዱለት ይችላሉ፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ በእንደዚህ ያለ አኳኋን የተጻፉትን ጽሑፎች የያንዳንዱን ጽሑፍ የጠቅላይ ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት
እንዲያጸድቃቸው ያስፈልጋል፡፡

(3) ይህም ማጽደቅ በጽሑፉ ላይ የሚመለከት ይሆናል፡፡


ቊ 70፡፡ የዘገዩ ማስታወቂያዎች፡፡
(1) ምክንያት የሆናቸው ነገር ከደረሰ ከሁለት ዓመት በኋላ የተጻፉ ወይም የጸደቁ ጽሑፎች ዋጋቸው እንደ ተራ ማስታወቂያዎች አስረጂ
ብቻ የሚቈጠሩ ናቸው፡፡

(2) ስለሆነም በአንድ ፍርድ መሠረት በሕዝብ የክብር መዝገቦች ላይ የተጻፉ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተነገረው አይጸናም፡፡

(3) ይህም ሲሆን ጽሑፉ ፍርዱን የሚጠቅስ ቃል በላዩ ይኖርበታል፡፡

ሐ) ልዩ ሁኔታዎች፡፡
ቊ 71፡፡ የጽሕፈት ሚኒስትር፡፡
(1) ግርማዊ ንጉሠ ነገሥትንና ንጉሣዊ ቤተ ዘመድን የሚመለከቱ የክብር መዝገቦችን የሚይዘው ራሱ የጽሕፈት ሚኒስትሩ ነው፡፡

(2) ሚኒስትሩም አጠባበቃቸውንና አቀማመጣቸውን ያረጋግጣል፡፡ የነዚህንም መዝገቦች ግልባጭ ይሰጣል፡፡


ቊ 72፡፡ ቆንሲሎች፡፡
(1) በውጭ አገር ያሉ የኢትዮጵያ ቆንሲሎች በባለጒዳዮቹ ጥያቄ ካልሆነ በቀር ጽሑፎችን አይመዘግቡም፡፡

(2) ቆንሲሎቹ ራሳቸው የሕዝብ የክብር መዝገቦችን ይይዛሉ፡፡

(3) ቆንሲሎቹ አጠባበቃቸውንና አቀማመጣቸውን ያረጋግጣል፡፡ የነዚህንም መዝገቦች ግልባጭ ይሰጣል፡፡


ቊ 73፡፡ የመርከብ አዛዦች፡፡
የኢትዮጵያ መርከብ አዛዦች በሕዝብ የክብር መዝገብ ጽሑፍ ሊጻፉ የሚገባቸውን በመርከባቸው ላይ የደረሱባቸውን ሁኔታዎች
በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ወደብ ወይም የኢትዮጵያ ቆንሲል በሚኖርበት የመጀመሪያ ወደብ ወዲያውኑ ያስታውቃሉ፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ሕዝብ የክብር መዝገቦች፡፡
ቊ 74፡፡ የመዝገቦቹ ዝርዝር፡፡
በያንዳንዱ ቀበሌና በያንዳንዱ ቆንሲላ የልደት አንድ መዝገብ፤ የሞት አንድ መዝገብና የጋብቻ አንድ መዝገብ ይኖራል፡፡
ቊ 75፡፡ የመዝገቦቹ አሰጣጥ፡፡
(1) ጠቅላይ ገዢው መዝገቦችን ከአገር ግዛት ሚኒስቴር ተቀብሎ ለሕዝብ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤቶች በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡

(2) መዝገቦችን እንዲይዙ የተደረጉት ሰዎች መዝገቡ ያልቃል ተብሎ ከሚገመተው ከ 6 ወር በፊት አንድ አዲስ መዝገብ እንዲሰጣቸው
መጠየቅ አለባቸው፡፡

(3) የጠቅላይ ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ይህ ትእዛዝ እንዲከበር ያደርጋል፡፡


ቊ 76፡፡ የመዝገቦቹን ከቦታቸው መዘዋወር ስለ መከልከል፡፡
ከተቋቋሙበት ስፍራ ወደሌላ የማዛወሩ ጒዳይ በሕጉ ላይ ተገልጾ ካልተመለከተ ወይም ካልተፈቀደ በቀር መዝገቦቹ በማንኛውም ምክንያት
ካሉበት ስፍራ መዘዋወር የለባቸውም፡፡

ቊ 77፡፡ የግድ የሚያስፈልጉ ጽሑፎች (1) የቀበሌው መዝገቦች፡፡

(1) እያንዳንዱ መዝገብ ቀበሌውንና ያለም እንደሆነ ሰፈሩን ወይም የሚመለከተውን የቀበሌውን ክፍል እንዲሁም ይህ ቀበሌ የሚገኝበትን
ጠቅላይ ግዛት ያመለክታል፡፡

(2) እንደዚሁም መዝገቡ የማስረጃ ቍጥር ያለው ይሆናል፡፡

(3) እነዚህ ማመልከቻዎች በመዝገቡ ልባስና ክፈፍ ላይ የሚገኙ ሆነው በያንዳንዱ የመዝገቡ ቅጠል ላይ ይጻፋሉ፡፡

ቊ 78፡፡ (2) ሌሎች መዝገቦች፡፡

(1) ንጉሣዊ ቤተሰብን የሚመለከቱ መዝገቦች ከዚህ በላይ ባለው ቍጥር በ 1 ኛ ኀይለ ቃል እንደተመለከተው ጽሑፍ ሳይሆን የንጉሣዊ ቤተ
ዘመድ መዝገቦች የሚል ጽሑፍ የያዙ ይሆናሉ፡፡

(2) በቆንሲላዎች ውስጥ የሚገኙ መዝገቦች በተቋቋሙበት ውስጥ ያለውን የቆንሲላ ምልክት የያዙ ይሆናሉ፡፡

ቊ 79፡፡ የመዝገቦቹ ዐይነት (ፎርም)፡፡


(1) መዝገቦቹ በብዙ ገጾች የሚጀምሩ ሆነው እነዚህን መዝገቦች እንዲይዙ የተፈቀደላቸው ሰዎች ስም እንዲጻፍባቸውና በስማቸው
አቅጣጫ የነዚሁ ሰዎች ፊርማ ያሉባቸው ይሆናሉ፡፡

(2) ቀጥሎም መዝገቦቹ ተራ ቍጥር ያላቸው፤ ብዙ ቅጠሎች የያዙና እያንዳንዱም ቅጠል ለአንዳንድ የክብር መዝገብ ጽሑፍ የሚያገለግል
መሆን አለበት፡፡

(3) እንዲሁም የመዝገቦቹ ጽሑፎች የሚመለከቱዋቸውን ሰዎች በፊደል ተራ ማውጫ ለመመዝገብ የተመደቡ ገጾች በመጨረሻው ገጽ ላይ
ይኖራቸዋል፡፡
ቊ 80፡፡ የመዝገቦቹ ቅጠሎች፡፡
(1) የሕዝብ የክብር መዝገቦች ቅጠሎች ከተያያዙበት ቀሪ ጋራ ትክክል የሆኑ ጽሑፎችን የያዙ በራሪዎች ያሉባቸው ናቸው፡፡

(2) የመወለድና የጋብቻ መዝገቦች ሦስት በራሪዎች፤ የሙታን መዝገቦች ግን ሁለት በራሪዎች ብቻ ያሏቸው ናቸው፡፡

(3) የቅጠሎቹ ጀርባ በእጅ እንዲጻፉ በሕግ ለተመለከቱት የእጅ ጽሑፎች የተጠበቀ ነው፡፡
ቊ 81፡፡ ሦስተኛ ቍጥር በራሪ፡፡
(1) ከቀሪው በጣም የራቀው ሦስተኛ ቍጥር ተብሎ የሚጠራው በራሪ ጽሑፍ እንደተዘጋጀ ወዲያውኑ ከቀሪው የሚለያይ ይሆናል፡፡

(2) ይህ በራሪ ስለመወለድ ጽሑፍ የሆነ እንደሆነ ለልጁ አሳዳሪ ስለ ጋብቻ ጽሑፍ የሆነ እንደሆነ ለባል በሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም
አማካይነት ይሰጣል፡፡

(3) ባለጒዳዩም በራሪውን ያኖራል፡፡


ቊ 82፡፡ ሁለተኛ ቍጥር በራሪ፡፡
(1) መዝገቡ በአለቀ ጊዜ ሁለተኛ ቍጥር ተብለው የሚጠሩ በራሪዎች ከቀሪው ተለይተው ተሰብስበው አንድነት ተያይዘው በጠቅላይ ግዛቱ
ዋና ከተማ ባለው የፍርድ መዝገብ ቤት ወይም በደንብ በተወሰነው፤ መጀመሪያዎቹ በራሪዎች ከተቀመጡበት ልዩ በሆነ ሌላ ስፍራ
ይቀመጣሉ፡፡

(2) በጽሕፈት ሚኒስትርና በቆንሲሎቹ የሚገኘው መዝገብ ሁለተኛ ቍጥር የሆኑት በራሪዎች ተቀማጭ እንዲሆኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት
የውጭ ጒዳይ ሚኒስቴር ይላካሉ፡፡

(3) ሁለተኛ ቍጥር የሆኑት በራሪዎች እንደ ደረሱ እንዲያስቀምጥ በተመደበው ሰው አማካይነት እንዲጠረዙ ይደረጋል፡፡
ቊ 83፡፡ አንደኛ ቍጥር በራሪ፡፡
ከቀሪው ጋራ የተያያዙ አንደኛ ቍጥር በራሪዎች ከመዝገቡ ቀሪ ጋራ ተያይዘው መዝገቦቹ በነበሩበት ቦታ ወይም በደንብ በተወሰነው ሌላ
ስፍራ ይኖራሉ፡፡
ቊ 84፡፡ ያልተሠራባቸው ቅጠሎች አለመኖር፡፡
(1) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም አንድ ጽሑፍ ከማዘጋጀቱ በፊት በዚህ መዝገብ ላይ በመጨረሻ ተጽፎ የሚገኝበትን ቅጠል ተራ ቍጥር
መመርመር አለበት፡፡

(2) ይህ የመጨረሻ ጽሑፍ ከተደረገበት ቅጠል ቀጥሎ ባለው ቁጥር ላይ ጽሑፍን ይመዘግባል፡፡

(3) በማንኛውም ሁኔታ በመዝገቡ ውስጥ ያልተሠራበትን ቅጠል እንዲተው አልተፈቀደለትም፡፡


ቊ 85፡፡ በስሕተት ያልተሠራበት ቅጠል፡፡
(1) ከአንድ ስሕተት የተነሣ አንዱ ቅጠል ሳይሠራበት የቀረ እንደሆነ የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ይህን ስሕተት እንደተመለከተ
የተባለውን ቅጠል ይሠርዘዋል፡፡
(2) ባልተሠራበትም በራሪ ወረቀት ላይ መስቀልኛ የሆነ ሁለት መሥመር አድርጎ በበራሪው ላይ ሳይሠራበት በስሕተት የቀረ የሚል ቃል
ይጽፍበታል፡፡

(3) ያልተሠራበት ቅጠል በምንም አኳኋን ለክብር መዝገብ ጽሑፍ አገልጋይ ለመሆን አይችልም፡፡
ቊ 86፡፡ ማውጫ፡፡
(1) አንድ መዝገብ በአለቀ ጊዜ የክብር መዝገብ ሹም በመዝገቡ ማለቂያ ገጾች ውስጥ የመዝገቡ ጽሑፍ የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁሉ
በቤተ ዘመድ ስም መሠረት በፊደል ተራ (ሊስት) ይመዘግባል፡፡

(2) ሁለተኛ ቍጥር በራሪዎችን አንድነት አያይዞ አስሮ እርሱ ካሰናዳው የማውጫ ቅጂ ጋራ አድርጎ በደንቦቹ ወደተመለከተው ስፍራ ይህን
የተያያዘ እስር ይልካል፡፡
ቊ 87፡፡ ስለ መዝገቦች መጥፋት፡፡
(1) በአንድ ቀበሌ የተቀመጠ መዝገብ የጠፋ ወይም የወደመ እንደሆነ የቀበሌው የክብር መዝገብ ሹም በሚያመለክተው በመዝገቡ ሁለተኛ
ቍጥር በራሪዎች ረዳትነት ወዲያውኑ እንደገና ይቋቋማል፡፡

(2) የአንድ መዝገብ ሁለተኛ ቍጥር በራሪዎች የጠፉ ወይም የወደሙ እንደሆነ የጠፉት ወይም የወደሙት በራሪዎች አስቀማጭ የሆነው
ሰው በሚያመለክተው በቀበሌው በተቀመጡት በራሪዎች ረዳትነት ወዲያውኑ እንደገና ይቋቋማሉ፡፡

(3) የጠፉት መዝገቦች በአንድ ቀበሌ ያሉት ሳይሆን በሌላ ስፍራ ያሉት የሆኑ እንደሆነ ከዚህ በላይ ያሉት ኀይለ ቃላት ውሳኔዎች
በተመሳሳይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 88፡፡ የሚሠራባቸው መዝገቦች ስለ መጥፋታቸው፡፡
(1) ሁለተኛ ቍጥር በራሪዎች የሆኑት ሳይቈረጡ የሚሠራበት አንድ መዝገብ የጠፋ ወይም የወደመ እንደሆነ የክብር መዝገብ ሹም
ወዲያውኑ ለጠቅላይ ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ያስታውቃል፡፡

(2) የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤትም መዝገቡን እንደገና ለማቋቋም አስፈላጊውን ያደርጋል፡፡

(3) የአንድ መዝገብ አንደኛና ሁለተኛ ቍጥር በራሪዎች በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ሁለቱም ቢጠፉ ወይም ቢወድሙ እንደዚሁ
ይደረጋል፡፡
ቊ 89፡፡ የመዝገቡን አያያዝ ስለ መቈጣጠር፡፡
(1) የጠቅላይ ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት በቀበሌዎቹ ውስጥ የክብር መዝገቦችን መልካም አያያዝ ይቈጣጠራል፡፡

(2) የምርመራውን ሥራ አደራጅቶ ባገኛቸው በወንጀል ሥራዎች ለማስቀጣት ራሱ ይከታተላል፡፡

(3) የበቆንሲላዎቹ ውስጥ ለሚገኙ መዝገቦችም እነዚሁኑ የመሰሉ ተግባሮች የሚፈጽመው የውጭ ጒዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ ክብር መዝገብ ጽሑፎች
ንኡስ ክፍል 1 በጠቅላላው፡፡
ቊ 90፡፡ የሚጻፉ ቃሎች፡፡
(1) የክብር መዝገብ ጽሑፎች በመዝገቦቹ ውስጥ የቀሩትን ባዶ ቦታዎች በመሙላት ይጻፋሉ፡፡

(2) በማናቸውም ጊዜ የተጻፉበት ቀን፤ ወርና ዓመት፤ የተቀበላቸው የክብር መዝገብ ሹም ፊርማ ይኖርባቸዋል፡፡
ቊ 91፡፡ የሚጻፉ ቃሎች፡፡
በሕጉ ከተመለከቱት ጽሑፎች በቀር ማናቸውንም ሌላ ጽሑፍ በመዝገቦቹ ውስጥ መጻፍ አይገባም፡፡
ቊ 92፡፡ ያልታወቁ ወይም ያልተረጋገጡ መረጃዎች፡፡
(1) በአንድ የክብር መዝገብ ውስጥ የቀረው ባዶው ቦታ እርግጠኛ በቂ የሆነ መረጃ ባለማግኘት መዝገቦችን የሚይዘው ሰው ሊሞላ
ያልተቻለ እንደሆነ ይኸው ሰው ‹‹ያልታወቀ፤›› የል ሌላ ጽሑፍ በማግባት ባዶውን ቦታ ይሞላል፡፡

(2) የክብር መዝገቡ ሹም የሚሰጠውን መልስ ያወቀ እንደሆነ፤ ይህን ጽሑፍ በተገባው ቦታ ‹‹ምናልባት›› የሚል ቃል በመጨመር
ይጽፋል፡፡
ቊ 93፡፡ የቃሎች ማሳጠር አለመኖር፡፡
በጽሑፎች ውስጥ የሚጠየቁት ማመልከቻዎች ግልጽ በሆነ አኳኋንና ምንም ማሳጠር ሳይደግ የሚጻፉ ይሆናሉ፡፡
ቊ 94፡፡ ሥርዝና እመጫት አለመኖር፡፡
የክብር መዝገብ ጽሑፎች ምንም ስርዝ ወይም እመጫት፤ ወይም ተጨማሪ ቃል ሊጻፍባቸው አይገባም፡፡
ቊ 95፡፡ ፊርማ፡፡
በጽሑፉ ላይ እንዲፈርሙ ከተጠየቁት ሰዎች ውስጥ አንዱ ለመፈረም ያልቻለ ወይም ያላወቀ እንደሆነ በጽሑፉ ላይ በፊርማው ፈንታ
የጣቱን አሻራ ምልክት ያደርጋል፡፡
ቊ 96፡፡ ያልተሠራባቸው ቅጠሎች፡፡
(1) በሥርዝ ምክንያት ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት አንድ ጽሑፍ እንደገና መሠራት ያለበት እንደሆነ እያንዳንዱ ያልተሠራበት በራሪ
ቅጠል በመዝገቦቹ ውስጥ መስቀልኛ የሆኑ ሁለት ሥርዞች ይደረጉበታል፡፡

(2) በያንዳንዱ የጽሑፍ በራሪ ላይም ያልተሠራበት ቅጠል የሚል ጽሑፍ ያደርግበታል፡፡

(3) የቅጠሉ ሦስተኛ ቍጥር በራሪ ወዲያውኑ ይቀደዳል፡፡


ቊ 97፡፡ የጽሑፎች አስረጂነት ኀይል፡፡
(1) ለያዙአቸው ማስታወቂያዎች ተቃራኒ ማስረጃ ከሌለ በቀር በመዝገቦቹ ውስጥ ደንበኛ ሆነው የተመዘገቡ የክብር መዝገብ ጽሑፎች
የሚታመኑ ናቸው፡፡

(2) ተቃራኒ የሆነውን ማስረጃ ለማቅረብ የዳኞችን ፈቃድ ያስፈልጋል፡፡

(3) እንዲህ በሆነ ጊዜ በማናቸውም ዐይነት ለማስረዳት ይቻላል፡፡


ቊ 98፡፡ በመዝገቦቹ ውስጥ ያልተጻፉ ጽሑፎች፡፡
(1) በመዝገቦቹ ውስጥ ያልተመዘገቡ ጽሑፎች፤ በመዝገቦቹ ውስጥ እንደተጻፉት ጽሑፎች ያለ አስረጂነት የላቸውም፡፡

(2) እንደ ተራ ማስረጃዎች ብቻ ይቈጠራሉ፡፡


ንኡስ ክፍል 1፡፡
የመወለድ ጽሑፎች፡፡
ቊ 99፡፡ የጽሑፉ ቃል፡፡
የመወለድ ጽሑፍ የሚያመለክተው፡፡
(ሀ) የተወለደበትን ቀን ወርና ዓመት፡፡

(ለ) የልጅን ፆታ፡፡

(ሐ) የተሰጡትን የግል ስሞች፡፡


(መ) የአባቱንና የእናቱን የቤተ ዘመድ ስም፤ የግል ስም፤ የተወለዱበትን ቀንና ቦታ፤

(ሠ) ያለም እንደሆነ ያመልካቹን የቤተ ዘመድ ስም፤ የግል ስም፤ የተወለደበትን ቀንና ቦታ ነው፡፡

ቊ 100፡፡ የጽሑፍ አስፈላጊነት፡፡


ልጁ አርባ ስምንት ሰዓት ከኖረና፤ የመወለድ ጽሑፍን ለማስመዝገብ ከተመለከተው ጊዜ ማለቅ በፊት ቢሞትም እንኳ፤ መወለዱን
ማስታወቅና የመወለዱን ጽሑፍ ማዘጋጀት አስፈላጊዎች ናቸው፡፡

ቊ 101፡፡ መወለድን ስለ ማስታወቅ፡፡

(1) የልጅ መወለድ በማናቸውም ሰው ለክብር መዝገብ ሹም መገለጽ አለበት፡፡

(2) ይህም መግለጫ የልጁ አባት፤ አባቱ የሌለ ሲሆን የልጁ እናት ወይም የልጁ አሳዳጊ (ሞግዚት) እነዚህም ባይኖሩ ልጁን አግኝቶ ያነሣው
ሰው ሊገልጽ ይገባዋል፡፡

(3) የክብር መዝገብ ሹሙ የልጁን መወለድ ካወቀ በራሱ ሥልጣን የልጁን መወለድ ለመመዝገብ ይችላል፡፡

ቊ 102፡፡ የልጁ የግል ስም፡፡

(1) የክብር መዝገብ ሹም መወለዱን በክብር መዝገብ ከመመዝገቡ በፊት ለልጁ የሚሰጠውን የግል ስም ወይም ስሞች ዘመዶቹን፤
ዘመዶችም የሌሉ እንደሆነ የልጁን አሳዳሪ ይጠይቃል፡፡

(2) መልስ ያልተሰጠው እንደሆነ ወይም የቀረቡት የግል ስሞች በሕግ መሠረት ሊቀበሏቸው ያልተቻለ እንደሆነ የክብር መዝገቡ ሹም ራሱ
የልጁን የግል ስም ወይም ስሞች ይመርጣል፡፡

ቊ 103፡፡ ወድቀው ስለሚገኙ ልጆች፡፡

(1) ወድቆ ለሚገኝ ማን መሆኑ ላልታወቀ ለአራስ ልጅ ሁሉ የመወለዱ ጽሑፍ መደራጀት አለበት፡፡

(2) ልጁ የተገኘበትን ቀንና ስፍራ ይኖረዋል የሚባለውን ዕድሜ ፆታውን፤ የተሰጡትን የቤተ ዘመድ ስምና የግል ስሞች በዝርዝር የሚያሳይ
ፕሮሴቬርባል ይደራጃል፡፡

(3) ስለ ልጁ መወለድ በተጻፈው ጽሑፍ ላይ ወደ ፕሮሴቬርባሉ የሚመራ ምልክት ይጠቀሳል፡፡


ንኡስ ክፍል 3፡፡
የመሞት ጽሑፎች፡፡
ቊ 104፡፡ የጽሑፉ ቃል፡፡
የመሞት ጽሑፍ የሚያመለክተው፡፡
(ሀ) የሞተበትን ቀን ወርና ዓመት፡፡

(ለ) የሞተውን ሰው የቤተ ዘመድ ስም የግል ስም፤ የተወለደበትን ቀንና ቦታ፡፡

(ሐ) የአባቱን፤ የእናቱን፤ የቤተ ዘመድና የግል ስም የተወለደበትን አገርና ቀን፡፡

(መ) በሕይወት ያለ እንደሆነ የሞተውን ሰው ባል ወይም ሚስት፤ የቤተ ዘመድ ስምና የግል ስም፤ የተወለደበትን ቀንና ቦታ፤ ጋብቻው
የተደረገበትን ቀን፡፡

(ሠ) ያለም እንደሆነ የሞተውን ያስታወቀውን ሰው የቤተ ዘመድና ስም የግል ስም፤ የተወለደበትን ቀንና ቦታ ነው፡፡

ቊ 105፡፡ የጽሑፍ አስፈላጊነት፡፡


የሞተው ሰው የመወለድ ጽሑፍ ሊጻፍለት ይገባው የነበረ ሲሆን መሞቱን ማስታወቅና የመሞቱንም ጽሑፍ ማደራጀት አስፈላጊ ነው፡፡
ቊ 106፡፡ የሞተውን ሰው ስለ ማስታወቅ ግዴታ፡፡

(1) አንድ ሰው የሞተ እንደሆነ መሞቱን የማስታወቁ ግዴታ ያለባቸው ከእርሱ ጋራ የሚኖሩት ሰዎች ናቸው፡፡

(2) እነዚህ ሰዎች የሌሉ እንደሆነ፤ የማስታወቁ ግዴታ ያለባቸው በአንድ ቀበሌ ይኖሩ እንደሆነ የሥጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶቹ እነዚህ
የሌሉ እንደሆነ የቅርብ ጎረቤቶቹ ናቸው፡፡

ቊ 107፡፡ በሌላ ሰው ቤት ስለ መሞት፡፡


ሟቹ ከመኖሪያ ስፍራው ውጭ የሞተ እንደሆነ የማስታወቁ ግዴታ ያለበት ሰውዬው የሞተበት ቤት ባለቤት ነው፡፡

ቊ 108፡፡ ሆስፒታሎች ትምህርት ቤቶች፤ ሆቴሎችና ወህኒ ቤቶች፡፡

(1) የሞተው በአንድ ሆስፒታል፤ ትምህርት ቤት፤ ወይም ወህኒ ቤት የሆነ እንደሆነ መሞቱን መግለጽ ያለበት ከዚህ በላይ የተባለው የሥራ
ቦታ መሪ የሆነው ሰው ነው፡፡

(2) በሠሩት የወንጀል ቅጣት መሠረት የተገደሉትን ሰዎች ማስታወቅ ያለበት የተፈረደበት ሰው በሚገደልበት ጊዜ የታሰረበት የወህኒ ቤት
ዲሬክተር ነው፡፡

ቊ 109፡፡ በሥራ አገልግሎት ላይ ያሉ ወታደሮች፡፡


ወታደሩ ከቤተሰቡ ጋራ የሚኖር ሆኖ ወይም ለዕረፍት በተፈቀደለት የስንብት ጊዜ ወይም ክፍለ ጦሩ ከሰፈረበት ውጭ የሞተ ካልሆነ በቀር
በሥራ አገልግሎት ላይ ያሉ ወታደሮችን መሞት መግለጽ ያለበት ክፍሉን የሚያዘው ሹም ነው፡፡

ቊ 110፡፡ ሬሳ ስለ ማግኘት፡፡

(1) የአንድ ሰው ሬሳ ከአንድ መኖሪያ ቤት ውጭ የተገኘ እንደሆነ የዚህን ሰው መሞት ማስታወቅ ያለበት ሬሳውን ያገኘው ሰው ነው፡፡

(2) የሞተው ሰው ማን እንደሆነ ያልታወቀ እንደሆነ ሬሳው የተገኘበትን ቀንና ቦታ፤ ሟቹ ሊኖረው የሚችለውን ዕድሜ ፆታውንና በግምት
የሞተበትን ቀን የማዘረዝር ፕሮሴርቬባል ይደራጃል፡፡

(3) ስለ መሞቱ የሚደረገው ጽሑፍ ወደ ፕሮሴቬርባሉ የሚመራ ምልክት ይደረግበታል፡፡

ቊ 111፡፡ ያልተገኘ ሬሳ (1) መሞቱን የሚያስታውቅ ፍርድ፡፡

(1) አንድ ሰው የመጥፋቱ ምክንያት መሞቱን የሚያረጋግጥ ሆኖ ሬሳው ያልተገኘ ቢሆንም እንኳ ማናቸውም ባለጒዳይ የዚህን ሰው ሞት
የሚያስታውቅ ፍርድ እንዲሰጥ ዳኞችን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) መሞቱን የሚያስታውቀው ፍርድ እንደመሞት ጽሑፍ ይቈጠራል፡፡

ቊ 112፡፡ (2) ሥልጣን ያላቸው ዳኞች፡፡

(1) ባለሥልጣን የሚሆኑት ዳኞች፤ መሞቱ እንዲረጋገጥለት ጠያቂው የጠየቀለት የሟች ዋና መኖሪያ በሚገኝበት ስፍራ የሚገኙት ናቸው፡፡

(2) እነዚህም ዳኞች ሞትን ባስከተለው አጋጣሚ ቦታ ላሉ ዳኞች ወይም በሌላ ቦታ ላሉ ዳኞች መብት ሥልጣናቸውን መተው ይችላሉ፡፡

(3) እንደዚሁ የሆነው የሥልጣን ማስተላለፍ፤ መብቱ የተላለፈላቸውን ዳኞች ያስገድዳል፡፡

ቊ 113፡፡ አደጋዎች፡፡ (1) የኅብረት ፍርድ፡፡

(1) መሞቱ ባንድ አደጋ ነገር፤ እንደ መስጠም፤ እንደ አየር አደጋ እንደ መሬት መናወጥ እንደ መሬት መንሸራተት ሆኖ በዚሁ ሁኔታ ብዙ
ሰዎች የሞቱ መሆናቸውን የሚያሳምን የሆነ እንደሆነ የነዚህን ሰዎች መሞት የኅብረት ፍርድ ለመገለጽ ይችላል፡፡
(2) በዚህ ጊዜ ሥልጣን ያላቸው ዳኞች አደጋው በደረሰበት ቦታ ያሉት ናቸው፡፡

(3) ስለሆነም አንድ መርከብ ወይም አንድ በራሪ ሲጠፋ ሥልጣን ያላቸው ዳኞች መርከቡ ወይም በራሪው በሚነሣበትና በሚያርፍበት
መደበኛ ቦታ ያሉት ናቸው፡፡

ቊ 114፡፡ (2) እያንዳንዶቹ ቅጂዎች፡፡

(1) ከኅብረቱ ፍርድ የያንዳንዶቹን ቅጂዎች ባለጒዳዮቹ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡

(2) መሞቱን የሚያስታውቀው ፍርድ እንደ መሞት ጽሑፍ ይቈጠራል፡፡

ቊ 115፡፡ የሞተበት ቀን፡፡

(1) መሞቱን የሚያስታውቀውን ፍርድ ሲሰጡ ዳኞች ምክንያቱን በመከታተል ያደረጉትን ግምት በመመልከት በፍርዳቸው ውስጥ
የሞተበትን ወይም የሞቱበትን ቀን በግምት የወሰኑትን ቀን ይገልጻሉ፡፡

(2) የተሰጠው ውሳኔ በተንኰል መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር እንደዚህ የተወሰነው ቀን ሊለወጥ አይቻልም፡፡

(3) ለማስለወጥም የቀረበው ጥያቄ ፍርዱ ከተሰጠበት ቀን ሁለት ዓመት ያለፈ እንደሆነ ተቀባይነት ማግኘቱ ይቀራል፡፡

h ቊ 116፡፡ መሞትን የሚያስታውቀው ፍርድ መሻር መሠረዝ፡፡


መሞቱ በፍርድ የተገለጸው ሰው፤ ፍርዱ ከተሰጠ በኋላ የመጣ እንደሆነ በራሱ ወይም በዐቃቤ ሕግ ጠያቂነት ፍርዱን የሰጡት ዳኞች
ፍርዱን ይሽራሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 4፡፡
የጋብቻ ጽሑፍ፡፡
ቊ 117፡፡ የጋብቻው ጽሑፍ ቃል፡፡
የጋብቻው ጽሑፍ የሚያመለክተው፡፡
(ሀ) የባልና የሚስትን የቤተ ዘመድ ስም የግል ስም የተወለዱበትን ቀንና ቦታ፤

(ለ) የባልና የሚስትን ምስክሮች የቤተ ዘመድ ስም፤ የግል ስም የተወለዱበትን ቀንና ቦታ፤

(ሐ) በሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ሳይሆን በሌላ ባለሥልጣን ፊት ጋብቻው የተከበረ ሆኖ እንደሆነ ጋብቻው የተከበረበትን ቀን ነው፡፡

ቊ 118፡፡ የጽሑፉ አስፈላጊነት፡፡


ጋብቻው የተከበረው በምንም ዐይነት ፎርም ቢሆን አንድ የጋብቻ ማስታወቂያና የጋብቻውን ጽሑፍ ማደራጀት አስፈላጊ ነው፡፡
ቊ 119፡፡ ጋብቻውን ስለ ማስታወቅ ግዴታ፡፡

(1) ጋብቻውን የማስታወቁ ግዴታ ያለበት ጋብቻውን ያከበረው ባለ ሥልጣን ነው፡፡

(2) እንዲሁም ተጋቢዎቹ ይኸው ግዴታ አለባቸው፡፡

ቊ 120፡፡ በሥልጣን ብቻ ጽሑፍን ስለ ማደራጀት፡፡

(1) የክብር መዝገብ ሹም ጋብቻ መደረጉን ከዐወቀ፤ የጋብቻውን ጽሑፍ በሥልጣኑ ብቻ ያደራጃል፡፡

(2) ይህ ሲሆን የጋብቻውን ጽሑፍ ለማስፈረም ባለጒዳዮቹን ይጠራል፡፡


ክፍል 4፡፡
የክብር መዝገብን ጽሑፎች ስለ ማቃናት፡፡
ቊ 121፡፡ በሥልጣን ብቻ ጽሑፍን ስለ ማደራጀት፡፡
ዳኞች በሚሰጡት ትእዛዝ ወይም ፍርድ መሠረት ካልሆነ በቀር የክብር መዝገብ ጽሑፎችን ለማቃናት አይቻልም፡፡
ቊ 122፡፡ ስለ ማቃናት ጥያቄ፡፡
የክብር መዝገብን ጽሑፍ የማቃናት ጥያቄን ዐቃቤ ሕግ ወይም የጠቅላይ ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት፤ ወይም ማንኛውም
ባለጒዳይ ለዳኞች ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ቊ 123፡፡ አንድ ተጨማሪ የግል ስም ስለ ማግባት፡፡


አንድ ሰው ጋብቻን በሚያደርግበት ጊዜ ወይም ይህንኑ ጋብቻ በሚከተለው ስድስት ወር ውስጥ አንድ ተጨማሪ የግል ስም ለመጨመር
የጠየቀ እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት የትእዛዝ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

ቊ 124፡፡ ስለ አጻጻፍ ስሕተት፡፡


ጥያቄው በክብር መዝገብ አጻጻፍ ውስጥ የተደረገን ስሕተት ለማቃናት ብቻ የሆነ እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት በዚሁ ጥያቄ ላይ
የትእዛዝ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

ቊ 125፡፡ ሌሎች ሁኔታዎች፡፡

(1) በማንኛውም ሌላ አኳኋን ጊዜ በጥያቄው ላይ ዳኞች የሚሰጡት ውሳኔ የፍርድ ውሳኔ ይሆናል፡፡

(2) ዳኞች ከመደንገጋቸው በፊት ጽሑፉ የሚመለከታቸው ሰዎች ወይም ሰው ባለጒዳዮች ሁሉ እንዲናገሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡

ቊ 126፡፡ ጽሑፉ የሚቃናበት ዐይነት፡፡

(1) እንዲቃኑ ትእዛዝ የተሰጠባቸው ቃሎች እንደሚነበቡ ሆነው በጽሑፉ ውስጥ ይሠረዛሉ፡፡

(2) በተሠረዙት ምትክ የሚገቡ ወይም ተጨማሪ ሆነው የሚገቡ ቃሎች፤ ጽሑፉ እንዲቃና የተሰጠውን ትእዛዝ ወይም ያዘዘውን ፍርድ
ከሚጠቅስ ማስገንዘቢያ ጋራ በጽሑፉ ላይ ይጻፋሉ፡፡

(3) እነዚህም መለዋወጫዎች በተቻለ መጠን፤ በተቃናው ጽሑፍ በራሪ ወረቀቶች ሁሉ ላይ ይደረጋሉ፡፡

ቊ 127፡፡ አዲስ ጽሑፍ ስለ መጻፍ፡፡

(1) የሚቃናው ጽሑፍ እንዲሠረዝ የሚል ውሳኔ መስጠት የሚገባ መስሎ የታያቸው እንደሆነ ዳኞች ጽሑፉ እንዲሠረዝና በተባለው ጽሑፍ
ፈንታ አዲስ ጽሑፍ እንዲደራጅ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

(2) በዚህ ጊዜ እያንዳንዱ የፊተኛው ጽሑፍ በራሪ ወረቀት በመስቀልኛ ቅርጽ ሆነው ከላይኛው ማዕዘን ወደ ታችኛው ማዕዘን መሓል
ለመሓል በሚሸጋገሩት ሁለት መሥመሮች በመዝገቦቹ መካከል ተሰርዞ በቀድሞው ጽሑፍ ምትክ በገባው በአዲሱ ጽሑፍ በያንዳንዱ በራሪ
ወረቀት ላይም የመምሪያ ጽሑፍ ይደረግበታል፡፡

(3) በአዲስ ጽሑፍ ላይ እንዲጻፍ ወደ አደረገው ፍርድ የሚመራ ምልክት ይደረግበታል፡፡

ቊ 128፡፡ የፍርድ ውሳኔ ሥልጣን፡፡


የክብር መዝገብ ጽሑፍ እንዲቃና ትእዛዝን የሚሰጠው የፍርድ ውሳኔ በፍርዱ ውሳኔ የተቃናው የጽሑፍ ሥራ በነበረው ሁኔታ
በማንኛውም ላይ መቃወሚያ ሊሆን ይችላል፡፡
ክፍል 5፡፡
የክብር መዝገብ ጽሑፎች ግልባጮችና ቅጂዎች፡፡
ቊ 129፡፡ የመወለድ ጽሑፍ፡፡
(1) በቀበሌዎች ወይም በቆንሲላዎች የክብር መዝገብ አስቀማጮች የሆኑ ሠራተኞች ስለ ሕፃኑ መወለድ ከተደረገው ጽሑፍ የሚመነጩትን
የክብሩ መዝገብ የተዘጋጀበትን ጊዜ፤ ሕፃኑ የተወለደበትን ቦታና ጊዜ፤ የተወለደው ልጅ ወንድ ወይም ሴት መሆኑን፤ የሕፃኑን አባት የቤተ
ዘመድና የግል ስም ለሚጠይቅ ለማንኛውም ሰው ሌላ ሐተታ ሳይጨምሩ ቅጂዎቹን ለመስጠት ይገደዳሉ፡፡

(2) ለልጁ ወራሾች ወይም ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ወይም ዳኞች ለፈቀዱለት ካልሆነ በቀር የመወለዱ ጽሑፍ ግልባጮች ሊሰጡ
አይችሉም፡፡
ቊ 130፡፡ የመሞት ጽሑፍ፡፡
በቀበሌዎች ወይም በቆንሲላዎች የክብር መዝገብ አስቀማጭ የሆኑ ሠራተኞች፤ የመሞትን ጽሑፍ ግልባጭ ለሚጠይቅ ለማናቸውም ሰው
ለመስጠት ይገደዳሉ፡፡

ቊ 131፡፡ የጋብቻ ጽሑፍ፡፡


እንደዚሁም፤ የጋብቻን ጽሑፍ ግልባጭ ለሚጠይቅ ለማናቸውም ሰው፤ ግልባጩን ለመስጠት ይገደዳሉ፡፡
ቊ 132፡፡ ንጉሣዊ ቤተ ዘመድን ስለሚመለከቱት የክብር መዝገብ ጽሑፎች፡፡
ዳኞች ሲጠይቁት ንጉሣዊ ቤተ ዘመድን በሚመለከቱ መዝገቦች ውስጥ ያሉትን የክብር መዝገብ ጽሑፎችን ግልባጭ የጽሕፈት ሚኒስትሩ
መስጠት አለበት፡፡

ቊ 133፡፡ የሁለተኛ ቊጥር በራሪ ወረቀቶች አስቀማጮች፡፡


ከዚህ የሚከተሉት ሁኔታዎች ባጋጠሙ ጊዜ የሁለተኛ ቊጥር በራሪ ወረቀቶች አስቀማጮች ከዚህ በታች በተነገሩት ግዴታዎች ዐይነት
ይገደዳሉ፡፡

(ሀ) የክብር መዝገብ ጽሑፍን የያዘ የቀበሌው የክብር መዝገብ የወደመ ወይም የጠፋ እንደሆነ፡፡

(ለ) ለመዝገቡ በቀበሌው ተጠብቆ የተቀመጠ ሆኖ ሳለ በዚህ በተባለው መዝገብ ውስጥ የሁለተኛ ቊጥር በራሪ ወረቀቶች በተያያዙበት
ውስጥ የተጠቀሰው አንድ የክብር መዝገብ ጽሑፍ የጐደለ እንደሆነ፤

(ሐ) በቀበሌው ተጠብቆ በተቀመጠው መዝገብ ውስጥ ያለው ጽሑፍ በሁለተኛው ቊጥር በራሪ ወረቀቶች ከተያያዙት ጋራ ትክክል ሆኖ
ያልተገኘ እንደሆነ፤

(መ) ጽሑፉ የተደራጀው በውጭ አገር ባለው በኢትዮጵያ ቆንስላ የሆነ እንደሆነ፤

(ሠ) ይህ የተባለው ግዴታ ልዩ በሆነ ምክንያት፤ በዳኞች የታዘዘ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 134፡፡ የተቃና የክብር መዝገብ ጽሑፍ፡፡

(1) በሕግ መሠረት፤ አንድ የክብር መዝገብ ጽሑፍ የተቃና እንደሆነ፤ ለባለጒዳዮቹ የሚሰጠው ቅጂ ወይም ግልባጭ ይህንኑ መቃናት
በመከተል ነው፡፡

(2) በቅጂው ወይም በግልባጩ ላይ የተጻፈው ቃል ከጽሑፉ መቃናት የተነሣ መሆኑን ማመልከት የለበትም፡፡

(3) ጽሑፉን እንዳለ የሚያሳዩና በጽሑፉ ሊደረግለት የተቻለውን መቃናት የሚገልጹ ትክክል የሆኑ ግልባጮች የሚሰጡት፤ ዳኞቹ
ራሳቸው በጠየቁ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ቊ 135፡፡ ፎርሙና ወጪው ገንዘብ፡፡

(1) የክብር መዝገብ ጽሑፎች ቅጂዎች ወይም ግልባጮች ታትመው በጠቅላይ ገዢው አማካይነት ለቀበሌው የክብር መዝገብ ሹም
በተሰጡት ሞዴሎች ላይ በተቻለ መጠን ይዘጋጃሉ፡፡

(2) እነዚህን ቅጂዎች ወይም ግልባጮች እነርሱን መስጠት ያለበት የክብር መዝገብ ሹም ፈርሞባቸው እርሱ የሚሠራበት መሥሪያ ቤት
ማኅተም ይታተምባቸዋል፡፡
(3) ቅጂዎቹ ሲሰጡ፤ ተቀባዮቻቸው አንድ የኢትዮጵያ ብርና፤ እንዲሁም ኮፒው ወይም ቅጂው በፖስታ የሚላክ ሲሆን የፖስታውን ዋጋ
ይከፍላሉ፡፡
ቊ 136፡፡ የጽሑፎች አስረጂነት ኀይል፡፡
የክብርን መዝገብ ጽሑፎች አስቀማጮች የሚሰጧቸው ቅጂዎች ወይም ግልባጮች በመዝገቦቹ ውስጥ ያሉት ጽሑፎች የሚያስረዱትን
ያህል ያስረጂነት ኀይል አላቸው፡፡

ቊ 137፡፡ መስታያየት፡፡

(1) ጠቃሚ መስሎ የታያቸው እንደሆነ፤ ዳኞች ቅጂዎቹ ወይም ግልባጮቹ ከዋናው ጋራ እንዲተያዩ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

(2) እንደዚሁም፤ የክብር መዝገብ ጽሑፍ ፎቶግራፍ እንዲሰጣቸው ለማዘዝ ይችላሉ፡፡


ክፍል 6፡፡
የክብር መዝገብ ጽሑፍን ደንብ አለመፈጸም የሚያስከትለው ኪሣራ፡፡
ቊ 138፡፡ በሠራተኞቹ በፍትሐ ብሔር በኩል ያለባቸው ኀላፊነት፡፡
በዚህ ምዕራፍ በተነገሩት ድንጋጌዎች ወይም ስለ ደንቦቹ አፈጻጸም በተመለከቱት ድንጋጌዎች ስለ መዝገቦች አያያዝ ወይም ስለ
አጠባበቃቸው በታዘዙት ሠራተኞች በኩል የተደረገ የደንብ መተላለፍ ሲኖር በዚህ በተባለው የደንብ መተላለፍ ምክንያት ጉዳት
ለደረሰባቸው ሰዎች ሁሉ ኀላፊነትን ያመጣባቸዋል፡፡

ቊ 139፡፡ ጽሑፍን ለመጻፍ እንቢ ማለት፡፡

(1) የክብር መዝገብ ሹም ወይም መዝገቦቹን ለመያዝ የተሾመው ሠራተኛ በክብር መዝገብ የሚገባውን በተሰጠው ማስታወቂያ መሠረት
በእንቢተኛነት አላገባም ያለ እንደሆነ፤ ባለጒዳዮቹ እንቢ አለን ሲሉ ለዳኞች ክስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

(2) እንደዚሁም የክብር መዝገብ ሹም በክብር መዝገብ ላይ እንዲጻፍ የሚያደርገውን ምክንያት የሚመለከቱትን ማስታወቂያዎች ለክብር
መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሳይሰጥ የቀረ እንደሆነ ባለጒዳዮቹ ክስ ሊያቀርቡበት ይችላሉ፡፡

(3) እንደዚሁም ደግሞ የመዝገቦቹ አስቀማጭ (መዝገብ ያዥ) የመዝገቦቹን ጽሑፍ ቅጂ ወይም ግልባጭ አልሰጥም ያለ እንደሆነ ሊከሰስ
ይችላል፡፡
ቊ 140፡፡ የምስክሮቹና ያመልካቾቹ ኀላፊነት፡፡

(1) በክብር መዝገብ ጽሑፍ ነገር፤ አመልካቾቹና ምስክሮቹ ለሚያረጋግጡዋቸውና ለሚደግፉዋቸው ነገሮች እርግጠኛነት ኀላፊዎች
ናቸው፡፡

(2) ያስታወቁት ወይም ምስክር የሆኑበት ነገር ትክክለኛ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት ጉዳት ለሚደርስባቸው ሦስተኛ ወገኖች በኀላፊነት
ይጠየቃሉ፡፡
ቊ 141፡፡ የወንጀል ኀላፊነት፡፡ (1) በጽሑፍ ስላለማግባት፡፡
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የተመለከቱት ቅጣቶች የሚያገኙዋቸው ሰዎች ከዚህ ቀጥለው ያሉት ናቸው፡፡
(ሀ) የክብር መዝገብ ጽሑፍን እንዲያዘጋጅ ግዴታ እያለበት በሕግ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሳያዘጋጅ የቀረ የክብር መዝገብ ሹም፤

(ለ) በክብር መዝገብ መሥሪያ ቤት ጽሕፈት ቤት የሆነውን አንድ ነገር ለማስታወቅ ግዴታ እያለበት በሕግ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ
ሳያስታውቅ የቀረ የክብር መዝገብ ሹም፤

(ሐ) ጽሕፈቱን እንዲያገባ የተላለፉለት ማስታወቂያዎች በደረሱለት ጊዜ፤ ወዲያውኑ በፍጥነት ጽሑፉን ያላዘጋጀ የጠቅላይ ግዛቱ የክብር
መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሠራተኛ፤

ቊ 142፡፡ (2) ያለ ማስታወቅ፡፡


በወንጀለኛ መቅጫ የተመለከቱት ቅጣቶች የሚወድቁባቸው ሰዎች ከዚህ ቀጥለው ያሉት ናቸው፡፡
(ሀ) ለክብር መዝገብ ሹም የሆነውን አንድ ነገር ማስታወቅ ግዴታ እያለባቸው በሕግ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ያላስታወቁና ይህ
አለማስታወቃቸው የክብር መዝገብ ጽሑፍ መዝገብ እንዳይገባ መሆንን ያስከተለ እንደሆነ፤ እነዚህ ሳያስታውቁ የቀሩ ሰዎች፤

(ለ) የክብር መዝገብ ጽሑፍን መዝገብ ስለ ማግባት ማስታወቂያ እንዲሰጡ፤ የክብር መዝገብ ሹም ጠይቋቸው እነሱን የሚመለከቱትን
ማስታወቂያዎች ሳይሰጡ የቀሩ ሰዎች፡፡

ቊ 143፡፡ (3) ትክክል ያልሆኑ ማስታወቂያዎች፡፡

(1) በክብር መዝገብ ጽሑፍ መዝገብ ለማስገባት፤ ለክብር መዝገብ ሹም ወይም ለጠቅላይ ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች
ትክክል አለመሆናቸውን እያወቁ ትክክል ያልሆኑትን ማስታወቂያዎች የሚሰጡ ሰዎች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተደነገጉት ቅጣቶች
ይቀጣሉ፡፡

(2) እንደዚሁም ሐሰት መሆናቸውን እያወቁ፤ እነዚህን ማስታወቂያዎች በሚደግፉ ምስክሮች ላይ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የተመለከቱት
ቅጣቶች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

(3) እንደዚሁም ደግመ ያልተረጋገጡ መሆናቸውን ዐውቆ ሳለ፤ እነዚህን ማስታወቂያዎች እንዲታመኑ አድርጎ የክብር መዝገብን ጽሑፍ
መዝገብ በሚያደራጅ ወይም ከዋናው ጋራ ትክክል ያልሆነውን ቅጂ ወይም ግልባጭ በሚሰጥ የክብር መዝገብ ሹም፤ ወይም የጠቅላይ
ግዛቱ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሠራተኛ ላይ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የተመለከቱት ቅጣቶች ይፈጸሙበታል፡፡

ቊ 144፡፡ (4) የመዝገብ መጥፋት ወይም መበላሸት፡፡


የክብር መዝገብን የሚያጠፉ ወይም የሚያበላሽ ሰው፤ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የተመለከቱት ቅጣቶች ይፈጸሙበታል፡፡
ቊ 145፡፡ (5) በተበላሸው ጽሑፍ ስለ መገልገል፡፡
በተንኰል በተበላሸው፤ በክብር መዝገብ ጽሑፍ ግልባጭ ወይም በጽሑፉ ቅጂ ዐውቆ የተገለገለ ሰው፤ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ
የተመለከቱት ቅጣቶች ይፈጸሙበታል፡፡
ክፍል 7
ስለ ታወቁ ሰነዶች፡፡
ቊ 146፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) የታወቁ ሰነዶችን የሚያዘጋጁ የክብር መዝገብ ጽሕፈት ቤት ሹማምቶች ወይም በሕግ ውል እንዲያፈራርሙ የተፈቀደላቸው ሰዎች
ናቸው፡፡
(2) እነዚህንም ጽሑፎች ዳኞች እንዲፈቅዱዋቸውና እንዲያጸድቋቸው ያስፈልጋል፡፡

ቊ 147፡፡ መፍቀድ፡፡
የታወቁ ጽሑፎችን ማስረጃ እንዲሆኑ የሚፈቅዱ ዳኞች ብቻ ናቸው፡፡ ይኸውም የሚሆነው፤
(ሀ) መዝገቦቹ በደንብ የተያዙ ላለመሆናቸው ወይም ጒድለት ያለባቸው ለመሆናቸው አስረጂ የተገኘ እንደሆነ፤

(ለ) እነዚህ መዝገቦች የጠፉ የተቀደዱ ለመሆናቸው አስረጂ የተገኘ እንደሆነ፤

(ሐ) የነዚህን መዝገቦች የጽሑፍ ግልባጭ ለማግኘት የማይቻል ወይም ለማግኘት እጅግ አስቸጋሪ የሆነ እንደሆነ፤

(መ) ጽሑፉን የሚጠይቀው ሰው፤ ጽሑፉ የተፈጸመበትን ቦታ የማያውቅ እንደሆነና ላለማወቁም ይቅርታ ሊደረግለት የሚቻል እንደሆነ፤

(ሠ) በሌላም በሕግ በታወቁ ሁኔታዎች ነው፡፡

ቊ 148፡፡ ጽሑፉን የሚያዘጋጀው፡፡


(1) የታወቀ ጽሑፍ ማስረጃ እንዲሆን ዳኞች በፈቀዱ ጊዜ ይህ የታወቀ ጽሑፍ የሚደረጅበትን ቦታ ይወስናሉ፡፡

(2) ዳኞቹ፤ ለሚጠይቁት የክብር መዝገብ ሹም፤ ወይም ውል እንዲያዋውል በሕግ ለተፈቀደለት ሰው ተቃዋሚዎችን ለመቀስቀስና፤
የጽሑፉን እውነተኛነት ለማረጋገጥ የሚረዱትን ትእዛዞች ሁሉ ይሰጣሉ፡፡

ቊ 149፡፡ የጽሑፉ ቃሎች፡፡


ባልተገኙት የክብር መዝገብ ጽሑፎች ወይም የነዚሁን ጒድለት እንዲያቃኑ ሲባል የተደራጁት የታወቁ ጽሑፎች በእነዚያ ላይ ሊገኝባቸው
ይገባ የነበረው ቃል ይኖርባቸዋል፡፡

ቊ 150፡፡ የተያያዘ ራፖር፡፡

(1) የታወቀውን ጽሑፍ ያደራጀው የክብር መዝገብ ሹም ወይም ውል እንዲያፈራርም በሕግ የተፈቀደለት ሰው የታዘዘውነ ተግባር
የፈጸመባቸውን ሁኔታዎች የሚያስረዳ ራፖር ከጽሑፉ ጋራ አያይዞ ለዳኞቹ ያቀርባል፡፡

(2) በተለይም የታወቀው ጽሑፍ አስቀድሞ መዝገብ ከገባው ከአንድ የክብር መዝገብ ጽሑፍ ጋራ ወይም ከሌላ ከአንድ ከታወቀ ጽሑፍ
ጋራ ተቃዋሚነት ያለበት መሆኑን ያመለክታል (ያስታውቃል)፡፡

ቊ 151፡፡ የጽሑፉ አስረጅነት ኀይል፡፡ (1) ከመጽደቁ በፊት፡፡

(1) የተዘጋጁበትን ጊዜና የተሰናዱበትን ሁኔታዎች በመገመት የታወቁት ጽሑፎች የሚኖራቸውን የአስረጅነት ዋጋ እንደመሰላቸው ዳኞች
ይወስናሉ፡፡
(2) ዳኞቹ የጽሑፉን ቃል ለመመርመር፤ የሚገባ መስለው የሚታዩዋቸውን አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

ቊ 152፡፡ (2) ከመጽደቁ በኋላ፡፡


የታወቀውን ጽሑፍ ዳኞቹ ባጸደቁት ጊዜ፤ እንደ ክብር መዝገብ ጽሑፍ ልክ የአስረጅነት ኀይል አለው፡፡
ቊ 153፡፡ የምስክሮቹ ኀላፊነት፡፡

(1) አንድ ሰው በምስክርነት ሌላውን ሰው እገሌ ነው ብሎ ወይም የዚህኑ ሰው የክብር መዝገብን ሁኔታ ወይም ይህንኑ ሰው ወይም የክብር
መዝገቡን ሁኔታ የሚመለከተውን ጒዳይ አረጋግጦ የሰጠው መግለጫ ትክክለኛ ባልሆነ ጊዜ በፍትሐ ብሔር ኀላፊ ይሆናል፡፡

(2) ሰውዬው በቅን ልቡና ሠርቶ እንደሆነ እርሱን ባሳሳተው ሰው ላይ ክስ የማቅረብ መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
ስለ መጥፋት፡፡
ክፍል 1፡፡
የመጥፋት መግለጫ
ቊ 154፡፡ ጥያቄ፡፡

(1) አንድ ሰው የጠፋና ከሁለት ዓመት ወዲህ ወሬውን ያልሰጠ እንደሆነ ማናቸውም ባለጒዳይ ቢሆን የሰውዬው መጥፋት በዳኞች
እንዲነገር ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ለዚህ ነገር ባለሥልጣኖች የሚሆኑት ዳኞች፤ የጠፋው ሰው ዋና መኖሪያ አድርጎ ይቀመጥበት በነበረው ቦታ የሚገኙት ናቸው፡፡

ቊ 155፡፡ የጥያቄው በማስታወቂያ መውጣት፡፡


ጥያቄው በማስታወቂያ የሚወጣው ዳኞች በሚወስኑት ሁኔታና የጠፋው ሰው በመጨረሻ ዋና መኖሪያው በነበረበት ቦታና እንዲሁም
ማስታወቂያው ይጠቅማል ብለው በገመቱት ቦታ ነው፡፡
ቊ 156፡፡ ምርመራ፡፡
የሰውዬውን መጥፋት ለመረዳት፤ ዳኞቹ፤ ከዐቃቤ ሕግ ጋራ ተቃራኒ በመሆን ጠቃሚ በሚመስላቸው በማናቸውም ቦታ ሁሉ ይልቁንም
የጠፋው ሰው በመጨረሻ ዋና መኖሪያ አድርጎት በነበረው ቦታና፤ በመጨረሻ ጊዜ መኖሩ በታየበት ቦታ ስለጠፋው ሰው ምርመራ
እንዲደረግ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

ቊ 157፡፡ የውሳኔ መሠረት፡፡

(1) ዳኞቹ የጠፋው ሰው መሞት የሚመስል ሆኖ የታያቸው እንደሆነ፤ ጠፍቷል ሲሉ ያስታውቃሉ፡፡

(2) በዚህ ረገድ፤ ዳኞቹ የነገሩን አካባቢ ሁኔታ ጠባይ፤ መሠረት አድርገው ይይዛሉ፡፡ በተለይም ይህ በመጥፋት የተገመተው ሰው ንብረቱን
የሚያስተዳድርለት ወኪል ማድረጉንና አለማድረጉን፤

(3) ወሬውን ለማስታወቅ ሊከለከሉ የቻሉትን ምክንያቶች መመርመር አለባቸው፡፡

ቊ 158፡፡ ነገሩን ለመወሰን የሚሰጠው የቀጠሮ ቀን፡፡


ዳኞቹ፤ ስለ ሰውዬው መጥፋት የሚሰጡትን ፍርድ እስከ አንድ ዓመት ለማቈየት፤ ወይም ስለ መጥፋቱ የሰጡት የማስታወቂያ ፍርድ
ከተሰጠ ከአንድ ዓመት በኋላ ካልሆነ በቀር ውጤት እንዳይኖረው ለመወሰን ይችላሉ፡፡

ቊ 159፡፡ መጥፋቱን የማስታወቅ ግዴታ፡፡

ጠያቂው ከአቀረበ ከአንድ ዓመት በኋላና ጥያቄውም በቀረበበት ቀን ሰውዬው ከጠፋ 5 ዓመት አልፎት እንደሆነና ጥያቄውም
በማስታወቂያ እንዲወጣ ዳኞች ከወሰኑ በኋላ ወሬውን ያልሰጠ እንደሆነ መጥፋቱን የማስታወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

ቊ 160፡፡ የመጨረሻዎቹ ወሬዎች የደረሱበት ቀን፡፡


ዳኞቹ በሚሰጡት ፍርድ ውስጥ፤ የጠፋው ሰው የመጨረሻ ወሬዎች የደረሱበትን ቀን ለመወሰን ይችላሉ፡፡
ቊ 161፡፡ የሞት ማስታወቂያ ፍርድ፡፡
ዳኞቹ ያገኙዋቸው አስረጂዎች፤ የጠፋው ሰው፤ የሞተ ለመሆኑ እንደ እርግጠኛ ዐይነት ሆኖ ሊቈጠር የሚቻል መሆኑን የሚያረጋግጡ
እንደሆነ፤ ለመጥፋቱ ውሳኔ እንዲሰጡ ጥያቄ የቀረበላቸው ዳኞች የጠፋውን ሰው የሞት ማስታወቂያ ፍርድ ይሰጣሉ፡፡

ቊ 162፡፡ የሥነ ሥርዐት ወጪ፡፡

(1) የተደረገው ሥነ ሥርዐት የሰውዬውን መጥፋት ማስታወቂያ ያስከተለ እንደሆነ ለሥነ ሥርዐቱ የተደረጉት ወጪዎች በጠፋው ሰው ላይ
ይታሰባሉ፡፡
(2) እንደተባለው ያልሆነ እንደሆነ ግን፤ በጠያቂው ላይ ይታሰባል፡፡
ክፍል 2 ፡፡
የመጥፋቱ ማስታወቂያ የሚያስከትለው ውጤት፡፡
ቊ 163፡፡ ጋብቻ፡፡

(1) የጠፋ ሰው ጋብቻ የመጥፋቱ ማስታወቅ ፍርድ የመጨረሻ በሆነበት ቀን ይፈርሳል፡፡

(2) የመጨረሻዎቹ ወሬዎች ከተሰሙበት በኋላ የተፈጸመውን የወንዱን ወይም የሴቲቱን ጋብቻ ጠፋ የተባለው ሰው ካልሆነ በቀር፤
ሊቃወመው የሚችል የለም፡፡

(3) ነገር ግን ክሱ በተጀመረበት ቀን የጠፋው ሰው በሕይወቱ ያለ መሆኑን በማያከራክር አኳኋን ዐቃቤ ሕግ ያረጋገጠ እንደሆነ ጋብቻውን
ሊቃወመው ይችላል፡፡

ቊ 164፡፡ ጠፋ ለተባለው ሰው የሚሰጡት ውርሶች፡፡


(1) የመጨረሻዎቹ ወሬዎች ከደረሱ በኋላ፤ ጠፋ የተባለው ሰው በሕይወቱ ቢገኝ ኖሮ እርሱ ወራሽ ለመሆን የሚችልበት ያወራረስ ሥርዐት
የተጀመረ እንደሆነ፤ ለእርሱ ሊደርስ የሚችለው ድርሻ በግምት ውስጥ ሳይገባ ሥርዐቱ ይፈጸማል፡፡

(2) የወራሽነት ንብረቶች ይዞታ የተሰጣቸውን ሰዎች፤ ጠፋ ለተባለው ሰው መብቶች መድን የሚሆን ዋስ እንዲጠሩ ወይም ሌላ ማረጋገጫ
እንዲሰጡ ዳኞች ሊያስገድዷቸው ይችላሉ፡፡

ቊ 165፡፡ በጠፋው ሰው መሞት የሚገኙ መብቶች፡፡

(1) በጠፋው ሰው ሞት የሚገኙት መብቶች ያሏቸው ሰዎች መጥፋቱን የሚወስነው ፍርድ የመጨረሻ ከሆነ በኋላ የጠፋው ሰው እንደሞተ
ተቈጥሮ፤ በመብቶቻቸው ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ፡፡

(2) ስለሆነም እነዚህ ሰዎች ባገኙዋቸው መብቶች ከጠቀማቸው በፊት ሊመለሱ ስለሚችሉ ነገሮች አስቀድመው ዋስ እንዲጠሩ ወይም ሌላ
ማረጋገጫ እንዲሰጡ ዳኞች ሊያስገድዷቸው ይችላሉ፡፡

ቊ 166፡፡ በጠፋው ሰው መኖር የሚሰጡ ግዴታዎች፡፡

(1) ጠፋ ከተባለው ሰው መኖር የተነሣ ግዴታዎች ያሉባቸው ሰዎች እነዚህን ግዴታዎች መፈጸም ይቀርላቸዋል፡፡

(2) ስለሆነም እነዚህ ሰዎች፤ የጠፋው ሰው ገና በሕይወት ያለ እንደሆነ በማለት ዋስ እንዲጠሩ ወይም ተመሳሳይ የሆነውን ማረጋገጫ
እንዲሰጡ በዳኞቹ በኩል ሊገደዱ ይችላሉ፡፡

ቊ 167፡፡ የጠፋው ሰው ንብረቶች፡፡ (1) ይዞታን ስለመስጠት

(1) የጠፋው ሰው፤ ኑዛዜ ያለው እንደሆነ ባለጒዳዮቹ በሚያቀርቡዋቸው ጥያቄዎች መሠረት ኑዛዜው ይፈሳል (ይነገራል)፡፡

(2) የጠፋው ሰው የመጨረሻ ወሬዎቹ በተሰሙበት ቀን የሞተ ቢሆን ኖሮ ንብረቶቹን ለመውረስ የሚችሉ ሰዎች፤ የንብረቱ ይዞታ
እንዲሰጣቸውና ንብረቶቹን እንዲካፈሉ ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቊ 168፡፡ (2) ወራሽነቱ የሚያስከትላቸው ግዴታዎች፡፡

(1) ንብረቶቹን እጅ ያደረገ ሰው፤ በንብረቶቹ ሲጠቀም፤ እንደ መልካም የቤተ ዘመድ አባት እንዲሆን ይገደዳል፡፡

(2) የጠፋው ሰው የመጨረሻ ወሬዎቹ በተሰሙበት ቀን የሞተ ቢሆን ኖሮ ንብረቶቹን ለመውረስ የሚችሉ ሰዎች፤ የንብረቱ ይዞታ
እንዲሰጣቸውና ንብረቶቹን እንዲካፈሉ ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቊ 169፡፡ (3) ባለይዞታ እንዲሆን የተፈቀደለትን ሰው ሥልጣን ስለ ማጥበብ፤ (ስለ መቀነስ)፡፡

(1) ገንዘቦቹን በተቀበለ በሦስት ወር ውስጥ የተቀበላቸውን ገንዘቦች በሥራ ላይ ለማዋል ይገደዳል፡፡

(2) የጠፋውን ሰው፤ ልጆች ለማቋቋም ካልሆነ በቀር፤ ንብረቶቹን በስጦታ ስም ለማስተላለፍ አይችልም፡፡
ክፍል 3፡፡
ጠፋ መባሉ የሚቀርበት ጊዜ፡፡
ቊ 170፡፡ ምክንያቶች (1) መሠረቱ፡፡
ጠፍቷል የማለት ማስታወቅ ውጤት መሰጠቱ የሚቀረው፡፡
(ሀ) ጠፋ የተባለው የመጣ እንደሆነ፤

(ለ) ጠፍቷል የሚለው የፍርድ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ በሕይወት ለመኖሩ አስረጂ የተገኘ እንደሆነ፤

(ሐ) የመጨረሻ ወሬዎቹ የተሰሙበት ተብሎ ከተወሰነው ጊዜ በሌላ ጊዜ ለመሞቱ አስረጂ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 171፡፡ (2) ጠፋ የተባለው ሰው መመለስ፡፡


(1) ጠፋ የተባለው ሰው በተመለሰ ጊዜ ንብረቶቹን በሚገኙበት አኳኋን እንዲሁም የተሸጡትን ንብረቶች ዋጋና እነዚህንም ዋና ገንዘቦች
በሥራ ላይ በማዋል የተገኙትን ንብረቶች ሁሉ መልሶ ይወስዳል፡፡

(2) ጠፋ ከተባለው ሰው ንብረቶች የተገኙት ገቢዎች ንብረቶቹን በይዞታ ተሰጥቷቸው እነዚህን ገቢዎች ላገኙ ሰዎች ገቢ እንደሆኑ
ይቀራሉ፡፡

(3) ንብረቶቹን እጅ ለማድረግ የተላኩት ሰዎች በተንኮል ወይም በመጥፎ አስተዳደር ላጠፉት ነገር፤ ጠፋ የተባለው ሰው ኪሣራ የመጠየቅ
መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 172፡፡ ስለ ሞቱ የሚሰጥ ግምት (1) ሁኔታዎች፡፡


መጥፋቱን በሚወስነው ፍርድ ውስጥ ከተወሰነው፤ የመጨረሻ ወሬዎች ከተሰሙበት ጊዜ ወዲህ ዐሥር ዓመት ያለፈ እንደሆነ፤ መሞቱ
የመጨረሻ ወሬዎቹ በተሰሙበት ሳይሆን በሌላ ቀን ለመሆኑ ማስረጃ ለማቅረብ የሚችለው ጠፋ የተባለው ሰው ራሱ ወይም ስለ መጥፋቱ
የተሰጠው የፍርድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በኋላ ልዩ የሆነው ወኪል ብቻ ነው፡፡

ቊ 173፡፡ (2) ውጤቶች፡፡

(1) የጠፋውን ሰው ንብረቶች እጅ ለማድረግ የተላኩት ሰዎች ከዚህ በላይ ከተነገረው ቀን አንሥተው ለይዞታው ማስረጃ እንዳቀረበው ሰው
ባለመብት ሆነው ይሠራሉ፡፡

(2) ጠፋ የተባለው ሰው የተመለሰ እንደሆነ ተብሎ የተሰጡት ዋሶች ወይም ማረጋገጫዎች ነፃ ይሆናሉ፡፡
ምዕራፍ 5፡፡
ስለ መኖሪያ ቦታና ስለ መደበኛ ቦታ፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ መኖሪያ ቦታ
ቊ 174፡፡ ትርጓሜ፡፡
የአንድ ሰው መኖሪያ ቦታ የሚባለው ለጊዜው የሚኖርበት ስፍራ ነው፡፡
ቊ 175፡፡ ድንገተኛ የመሰንበቻ ቦታ፡፡

(1) አንድ ሰው፤ ለጊዜው በአንድ ቦታ ቢሰነብት ይህ የተባለው ቦታ መኖሪያ ቦታው ነው ለማሰኘት አይበቃም፡፡

(2) ስለሆነም መሰንበቱ የሚቀጥል የሆነ እንደሆነ ወይም ከሦስት ወር በላይ ቈይቶ እንደሆነ የመኖሪያ ቦታው ነው ይባላል፡፡

ቊ 176፡፡ የመኖሪያ ቦታ አለመኖር፡፡


አንድ ሰው የመኖሪያ ቦታው ከሌላ ዘንድ ለመሆኑ አስረጂ ካልተገኘ ይህ ሰው የሚገኝበት ቦታ የመኖሪያ ቦታው እንደሆነ ይገመታል፡፡
ቊ 177፡፡ ብዙ የመኖሪያ ቦታዎች፡፡

(1) አንድ ሰው ብዙ የመኖሪያ ቦታ ሊኖረው ይችላል፡፡

(2) በዚህ ጊዜ በነዚህ የመኖሪያ ቦታዎች አንዱ ደንበኛ መኖሪያ ቦታ ሌሎቹ ተጨማሪ የመኖሪያ ቦታዎች ለመሆን ይችላሉ፡፡

ቊ 178፡፡ ያገቡ ሴቶችና አካለመጠን ያላደረሱ ልጆች፡፡

(1) ያገቡት ሴቶች የራሳቸው የመኖሪያ ቦታ ሊኖራቸው ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም አካለመጠን ያላደረሱት ልጆችና፤ ችሎታ የተከለከሉ ሰዎች የራሳቸው የመኖሪያ ቦታ ሊኖራቸው ይችላሉ፡፡

ቊ 179፡፡ የመንግሥት ሠራተኞች፡፡


የመንግሥት ሠራተኞች ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ቦታ አንድ የመኖሪያ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
ቊ 180፡፡ ነጋዴዎች፡፡
አንድ ሰው የንግድ ሥራውን የሚሠራበት ቦታ እንደ አንደኛ መኖሪያ ቦታው ይገመታል፡፡
ቊ 181፡፡ በውል ቃል ውስጥ የሚጠቀስ የመኖሪያ ቦታ (1) መሠረቱ፡፡
አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋራ ባለው ግንኙነት ውስጥ፤ ወይም አንዱን ጒዳይ ወይም አንድ የተወሰነውን የሥራ ክንውን ስለሚመለከት ነገር፤
አንድ የተወሰነ ቦታ እንደ መኖሪያ ቦታው ሆኖ እንዲቈጠር በሚጸና አኳኋን የውል ቃል ለማግባት ይችላል፡፡

ቊ 182፡፡ (2) ውጤቶች፡፡

(1) ግልጽ በሆነ ዐይነት የተነገረ ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት ከሌለ በቀር ይህ የውል ቃል ለእርሱ ጥቅም ሲባል የተደረገለት ሰው፤ በዚህ
የመኖሪያ ቦታ አይገደድም፡፡

(2) ይህ የውል ጥቅም የተደረገለት ሰው እርሱ እንደመረጠ፤ የተዋዋዩን እውነተኛ የመኖሪያ ቦታ፤ ወይም በውሉ የተጠቀሰውን የመኖሪያ
ቦታ ከሁለቱ አንዱን የተዋዋዩ የመኖሪያ ቦታ አድርጎ ለመቍጠር ይችላል፡፡
ክፍል 2፡፡
መደበኛ ቦታ፡፡
ቊ 183፡፡ ትርጓሜ፡፡
የአንድ ሰው መደበኛ ቦታ ማለይ፤ ይህ ሰው በነዋሪነት ዐይነት እዚያው ቦታ በመኖር አሳብ የጒዳዮቹና የጥቅሞቹ ዋና ስፍራ ያደረገው ቦታ
ነው፡፡
ቊ 184፡፡ የሐሳብ ግምት፡፡

(1) የአንድ ሰው ደንበኛ የመኖሪያ ስፍራው አንድ በሆነ ጊዜ፤ በዚሁ ስፍራ በነዋሪ አኳኋን ለመኖር አሳብ እንዳለው ይገመታል፡፡

(2) ይህ የተባለው ሰው የገለጸው ተቃራኒ አሳብ ቢኖር፤ አሳቡ በቂ በሆነ አነጋገር የተለየ ካልሆነና ውጤትም የሚኖረው እንደ ነገሩ ደንበኛ
ሁኔታ ወደፊት ለመድረስ የሚችል አንድ ሁኔታ ከደረሰ በኋላ የሚሆን ካልሆነ በቀር በደንበኛው የነገሮቹ መንገድ ወደ ፍጻሜ ደርሶ
መታየት ያለበት ተቃራኒው አሳብ ከቁም ነገር አይቈጠርም፡፡

ቊ 185፡፡ የሞያ ሥራ መኖሪያና የቤተ ዘመድ መኖሪያ ቦታ፡፡


አንድ ሰው የሚሠራቸው የሞያ ሥራዎች በአንድ ቦታ ውስጥ ሆኖ የቤተ ዘመድ ወይም የማኅበራዊ መኖሪያ ቦታው በሌላ ቦታ የሆነ
እንደሆነ፤ ጥርጣሬ በሚያጋጥምበት ጊዜ መደበኛ መኖሪያ ቦታው የቤተዘመድ ወይም የማኅበራዊ መኖሪያ ቦታው እንደሆነ ይገመታል፡፡

ቊ 186፡፡ መደበኛ ቦታው አንድ ስለ መሆኑ፡፡


ማንኛውም ሰው በአንድ ጊዜ ብዙ መደበኛ ቦታ ሊኖረው አይችልም፡፡
ቊ 187፡፡ መደበኛ ቦታን ስለ መለወጥ፡፡
አንድ ሰው መደበኛ ቦታውን በሌላ ቦታ እስካደረገ ድረስ መደበኛ አድርጎ የተቀመጠበትን ቦታ ይዞ ይቈያል፡፡
ቊ 188፡፡ ያልታወቀ መደበኛ ቦታ፡፡

(1) የአንድ ሰው የመጨረሻ መደበኛ ቦታው የት እንደሆነ ወይም የት እንደነበረ ለማረጋገጥ ያልተቻለ እንደሆነ በደንብ የሚቀመጥበት ቦታ
መደበኛ ቦታው እንደሆነ ይቈጠራል፡፡

(2) በደንብ የሚቀመጥበት ቦታ የሌለ እንደሆነ፤ በጣም ራቅ ካለ ጊዜ ጀምሮ ምክትል መኖሪያ ቦታ ያደረገው፤ እንደ መደበኛ ቦታ
ይቈጠራል፡፡
(3) መኖሪያ ቦታ የሌለው ሲሆን ባለጒዳዩ የሚገኝበት ቦታ እንደ መደበኛ ቦታ ይቈጠራል፡፡

ቊ 189፡፡ ያገቡ ሰዎች፡፡

(1) ያገባች ሴት ጋብቻው እስከ ቈየበት ጊዜ ድረስ መደበኛ ቦታዋ የባልዋ መደበኛ ቦታ ነው፡፡

(2) ጋብቻው የፈረሰ ወይም ባልዋ በፍርድ ወይም በሕግ የተከለከለ እንደሆነ ሴቲቱ የራሱዋ የሆነ መደበኛ ቦታ ለማቋቋም ትችላለች፡፡

ቊ 190፡፡ ከሞግዚት አስተዳደር ነፃ ያልወጣ ልጅ መደበኛ ቦታ፡፡


ከሞግዚት አስተዳደር ነፃ ያልወጣ ልጅ መደበኛ ቦታ የአሳዳሪው መደበኛ ቦታ ነው፡፡
ቊ 191፡፡ ችሎታ የተከለከለ ሰው፡፡
ችሎታ የተከለከለው ሰው በተከለከለ ጊዜ የነበረበትን መደበኛ ቦታ እንደያዘ ይቈያል፡፡

አንቀጽ ሁለት፡፡
ስለ ሰዎች ችሎታ፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ጠቅላላ የሆኑ መሠረታውያን ደንቦች፡፡
ቊ 192፡፡ የችሎታ ደንብ፡፡

ማንኛውም ሰው ሁሉ ችሎታ የሌለው መሆኑ በሕግ ተወስኖ ካልተገለጸ በቀር ማንኛውንም ዐይነት የማኅበራዊ ኑሮውን ተግባር ለመፈጸም
ችሎታ አለው፡፡

ቊ 193፡፡ ጠቅላላ ችሎታ ማጣት፡፡

ጠቅላላ የችሎታ ማጣትን ሁኔታ የሚያስከትሉ ምክንያቶች ዕድሜ ወይም የሰው አእምሮ ሁኔታ ወይም በዚሁ ሰው ላይ የደረሰው የፍርድ
ቅጣት ናቸው፡፡

ቊ 194፡፡ የተለየ ችሎታ ማጣት፡፡

(1) የተለየ ችሎታ ማጣትን ለመወሰን በግምት ውስጥ ለማግባት የሚቻለው የሰውዬውን ዜግነት በመመልከት ወይም የሚያከናውነውን
ሥራ መሠረት አድርጎ በመያዝ ነው፡፡

(2) ይኸውም በዚህ አንቀጽ በምዕራፍ 5 ከ 389 እስከ 393 ቍጥር በተነገረው ሕግና በልዩ ሕጎች ላይ ይደነገጋል፡፡

ቊ 195፡፡ በፈቃድ ስለ መወሰን፡፡


(1) ማንኛውም ሰው የሕዝባዊ መብቶቹን አልጠቀምባቸውም ወይም አልሠራባቸውም ብሎ በከፊልም ቢሆን እንኳ ለመተው አይችልም፡፡

(2) ስለ ማኅበራዊ ጥቅም ሕጋዊ ተገቢነት ያለው መሆኑ ካልተገለጸ በቀር እነዚህን መብቶች አልሠራባቸውም ወይም አልጠቀምባቸውም
ብሎ በፈቃዱ የሚወሰንበት ስምምነት ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 196፡፡ ችሎታን የማጣት አስረጂ፡፡

(1) ሰው ሁሉ ችሎታ እንዳለው ይገመታል፡፡

(2) ይህ ሰው ችሎታ የሌለው ነው ብሎ ማስረዳት የሚገባው፤ ሰውዬው ችሎታ የለውም ብሎ የሚከራከረው ወገን ነው፡፡

ቊ 197፡፡ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶችና ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ ንብረቶች፡፡

የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶችና ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ ንብረቶች ችሎታ ያላቸው መሆኑ የሚረጋገጠው እንደ ዐይነታቸው
ለነዚሁ የሰውነት መብት በሚሰጧቸው ድንጋጌዎች መሠረት ነው፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
አካለመጠን ስላላደረሱ ሰዎች፡፡
ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች
ቊ 198፡፡ ትርጓሜ፡፡

አካለመጠን ያላደረሰ ማለት፤ በሁለቱም ፆታ (ወንድ ወይም ሴት) ዕድሜው ገና ዐሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ሰው ነው፡፡

ቊ 199፡፡ አካለመጠን ያላደረሰ ሰው ችሎታ ማጣት፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰ ሰው ስለ ሰውነቱ አስተዳደር በአንድ አሳዳሪ ሥልጣን ሥር እየተጠበቀ በመኖር ለዚህም ላሳዳሪው ሊታዘዝ
የሚገባው ሰው ነው፡፡

(2) የገንዘብ ጥቅሞቹን በሚመለከተው ጒዳይና ስለ ንብረቱም አስተዳደር ሞግዚቱ እንደራሴው ነው፡፡

(3) በሕግ በተመለከቱት ጒዳዮች ካልሆነ በቀር አካለ መጠን ያላደረሰው ሰው የሕግ ተግባሮችን ለመፈጸም አይችልም፡፡

ቊ 200፡፡ የዕድሜ ማስረጃ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


(1) የአንድ ሰው ዕድሜ ስንት እንደሆነ ሊረጋገጥ የሚቻለው በተወለደበት ቀን በተጻፈው መዝገብ አስረጅነት ነው፡፡

(2) የመወለድ ጽሑፍ የሌለ እንደሆነ የአንድ ሰው ዕድሜ ስንት እንደሆነ የሚረጋገጠው በቂ ምስክሮች በፈረሙበት በተረጋገጠ ጽሑፍ
አማካይነት ሊሆን ይችላል፡፡

ቊ 201፡፡ (2) የመወለድን ጽሑፍ ተቃዋሚ ስለሚሆን ማስረጃ፡፡

(1) የማስረጃውን አቀራረብና የአስረጅነቱን ዝርዝር የሚያጠራጥር ከባድ ሁኔታ ያጋጠማቸው እንደሆነ ዳኞች የአንድ ሰው ዕድሜ ስንት
እንደሆነ ለማስረዳት የመወለድን ጽሑፍ ተቃዋሚ የሆነ ማስረጃ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

(2) አንድ ሰው የተወለደበትን ዘመን ለማረጋገጥ በመወለድ ጽሑፍ ዝርዝር ላይ ተቃራኒ ማስረጃ እንዳይቀርብ የሚከለክለው የዳኞች ውሳኔ
ማንኛውም ዐይነት ይግባኝ ሊቀርብበት ይችላል፡፡

(3) በማናቸውም አጋጣሚ ሁኔታ ሁሉ የታወቀውን ጽሑፍ በቂ ምስክሮች በማቅረብ ለመቃወም ይቻላል፡፡

ቊ 202፡፡ (3) በፍርድ ውሳኔ ስለሚሰጥ ማስረጃ፡፡

(1) አንድ የታወቀ የዕድሜ ማረጋገጫ ጽሑፍ መቃወሚያ የቀረበበት እንደሆነ ወይም በመወለዱ ጽሑፍ ዝርዝር ላይ ተቃራኒ ማስረጃ
እንዲቀርብ የተፈቀደ ሲሆን ዳኞቹ፤ የቀረበላቸውን ችግር ለማቃናት እንዲችሉ የሰውዬውን ዕድሜ ልክ ይወስናሉ፡፡

(2) ስለዚሁም ጒዳይ ለመረጃ የሚሆናቸውን ውሳኔ ሁሉ ያዛሉ፡፡

ቊ 203፡፡ (4) ስለ ይግባኝ፡፡

(1) በመጀመሪያ ደረጃ ችሎት ያደረጉት ዳኞች፤ አንድ የምርመራ ጒዳይ ተደርጎ ነገሩ እንዲጣራ ወይም እንዳይጣራ የሰጡት የፍርድ ውሳኔ
ማናቸውንም ዐይነት ይግባኝ ያስከትላል፡፡

(2) የሰውዬውንም የዕድሜ መጠን ስለሚወስኑትም ዳኞች ፍርድ፤ አፈጻጸሙ በዚሁ ዐይነት ነው፡፡
ክፍል 2፡፡
አካለመጠን ያላደረሰውን ሰው ስለሚጠብቁ ክፍሎች፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ስለ አሳዳሪና ስለ ሞግዚት፡፡
ቊ 204፡፡ የወላጆች ሥልጣን፡፡
አባትና እናት ጋብቻቸው ጸንቶ አብረው በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ አካለ መጠን ላላደረሱት ልጆቻቸው አሳዳሪነትና ሞግዚትነት በአንድነት
ሥልጣን አላቸው፡፡
ቊ 205፡፡ ከወላጆች የአንዱ አለመገኘት፡፡
(1) ከወላጆቹ አንዱ የሞተ እንደሆነ ችሎታ ያጣ እንደሆነ፤ የተገቢነት መብት ያጣ እንደሆነ፤ ወይም ከቤተዘመድ አስተዳዳሪነት መብቱ
የታገደ እንደሆነ የአስተዳዳሪነቱን ሥልጣን ይዞ የሚቈየው አንደኛው ወገን ብቻ ነው፡፡

(2) እንዲሁም የልጁ አባት ያልታወቀ በሆነ ጊዜ የዚህን ሥልጣን ሥራ የምትፈጽም እናት ብቻ ናት፡፡
ቊ 206፡፡ የልጆቹ አባትና እናት መፋታት፡፡
(1) አባትና እናት በተፋቱ ጊዜ ለልጁ ሞግዚትና አሳዳሪ የሚመርጡ የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ናቸው፡፡

(2) ከተፋቱትም ባልና ሚስት አንደኛው የሞተ እንደሆነ በዚሁ ምክንያት ብቻ በሕይወቱ ያለው አባት ወይም እናት ይህን ሥልጣን
ለመያዝ መብት አይኖረውም፡፡
ቊ 207፡፡ በኑዛዜ ቃል የተመረጠ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በሕይወት ያለው አባት ወይም እናት ከጊዜ ሞቱ በኋላ ልጁን የሚያስተዳድር ወይም ለልጁ ሞግዚት
የሚሆነውን ሰው በመጨረሻ የኑዛዜ ቃል ለመምረጥ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም የአሳዳሪውን ወይም የሞግዚቱን ሥልጣኖች ለመወሰንና ወይም የአሳዳጊነቱን ሥራ አመራር ሥልጣን በተወሰነ ሁኔታ ብቻ
ለመስጠት ይችላል፡፡

(3) እንዲሁም ደግሞ አንድ ወይም ቊጥራቸው የተወሰነ ሰዎች ለልጁ አሳዳሪ ወይ ሞግዚት ሊሆኑ አይችሉም ብሎ ቃሉን የመስጠት
መብት አለው፡፡

ቊ 208፡፡ (2) አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ለመሾም የሚፈጸም ግዴታ፡፡


አባት ወይም እናት በሕይወቱ ሳለ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጁን አሳዳሪነት ወይም ሞግዚትነት ሥራ ያካሂድ የነበረ ካልሆነና በዚሁም
ጊዜ በገዛ ፈቃዱ ሥልጣኑን ዐውቆ የተወ ካልሆነ በቀር ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር ለአባት ወይም ለእናት የተሰጠው መብት አይኖረውም፡፡

ቊ 209፡፡ (3) ወደ ዳኞች አቤቱታን ስለ ማቅረብ፡፡


አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ጥቅም የሚያስገድድ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ ስለ አሳዳሪው ወይም ስለ ሞግዚቱ አባቱ ወይም እናቱ
ያደረጓቸውን አወሳሰኖች ወይም ሁኔታዎች ዳኞች ሊያስቀሩት ወይም ሊለዋውጡት ይችላሉ፡፡

ቊ 210፡፡ የልጅን አሳዳሪነት ወይም የሞግዚትነት ሥልጣን ሊይዙ የሚገባቸው ዘመዶች (1) ሊከተሉት የሚገባው ተራ፡፡
አንድ ልጅ አባትና እናት የሌለው እንደሆነና ከሁለቱ በመጨረሻ የሞተው ወላጁ በሚገባ ሁኔታ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ሳያደርግለት ቀርቶ
እንደሆነ በልጁ አሳዳሪነት ወይም ሞግዚትነት በሕጉ መሠረት የሚመረጡና ይህ ሥልጣን የሚሰጣቸው ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ሰዎች
ነው፡፡

(ሀ) የልጁ የአባት ወገን አያት ወይም ይህ እንደሌለ የእናቱ ወገን ሴት አያት፡፡

(ለ) የልጁ የእናት ወገን ወንድ አያት ይህ እንደሌለ የእናቱ ወገን ሴት አያት፡፡

(ሐ) እነዚህ በሌሉ ጊዜ በዕድሜ ታላቅ የሆኑት የልጁ አባት ወገን አጎት ወይም የአባት ወገን አክስት፤

(መ) እነዚህም የሌሉ እንደሆነ በዕድሜ ታላቅ የሆኑት የልጁ የእናት ወገን አጎት ወይም የእናት ወገን አክስት፡፡

(ሠ) እነዚህም የሌሉ ሲሆን በዕድሜ ታናሽ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ አጎት ወይም አክስት፡፡

ቊ 211፡፡ (2) ይህ ተራ ሊለወጥ የሚችልበት መንገድ፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር እንደተመለከተው፤ ሥልጣን በሚሰጠው ሰው ፈንታ ለልጁ የሥጋ ዝምድና ወይም የጋብቻ ዝምድና
ያለው ማንኛውም ሰው ሆነ የአሳዳሪነቱ ወይም የሞግዚትነቱ ሥልጣን ይሰጠኝ ሲል ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል፡፡

(2) ይህም ጥያቄ መቅረብ የሚገባው ባለጥቅሞቹ የተስማሙ እንደሆነ ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ፤ ወይም ባለጒዳዮቹ ሳይስማሙ ሲቀሩ
ለዳኞቹ ነው፡፡ ለጠያቄውመ ማቅረቢያ የተወሰነው ጊዜ አሳዳሪው ወይም ሕጋዊ ሞግዚቱ የዚህን ሥልጣን መያዙ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ
እስከ ሁለት ወር ድረስ ነው፡፡

(3) የባለጒዳዮቹ አሳብ ከተመረመረ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር አሳብ ከተጠየቀ በኋላ ስለ እንደዚህ ያለው ጒዳይ
የቀረበውን ጥያቄ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚገባው የልጁን ጥቅም ብቻ በመገመት ነው፡፡
ቊ 212፡፡ በሕግ የሚመረጡ ዘመዶች መታጣት፡፡
(1) ከዚህ በላይ የተጻፉት ቊጥሮች የተመለከቱት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ለልጁ አንድ አሳዳሪ፤ ሞግዚት ለማግኘት ያልተቻለ እንደሆነ ይህ
ሥራና ሥልጣን ዳኞች ለመረጡት ሰው ሊሰጥ ይችላል፡፡
(2) ዳኞቹም ይህን ጒዳይ ለመፈጸም በራሳቸው ሥልጣን ብቻ ወይም የልጁ ዘመድ በሆነ ወይም ባልሆነ ባለጒዳይ ጥያቄ አቅራቢነት
ሊሠሩ ይችላሉ፡፡

(3) በሕጉ መሠረትም ይህን ጒዳይ በሚመለከተው ባለሥልጣን ጥያቄ ጒዳዩ ሊቀርብላቸው ይገባል፡፡

ቊ 213፡፡ የዳኞች ምርጫ፡፡ (1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ የሥጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች፡፡
ዳኞች ለልጁ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት እንዲሆን የሚመርጡትና ይህን ሥልጣን የሚሰጡት የልጁ የቅርብ የሥጋ ዘመድ ወይም የጋብቻ
ዝምድና ያለውንና በተቻለም መጠን ይህን ሥራ ለማከናወን ችሎታና ፈቃደኛነት ያለውን ሰው ነው፡፡

ቊ 214፡፡ (2) የበጎ አድራጎት ድርጅት፡፡

(1) የአሳዳሪነትን ወይም የሞግዚትነት ሥልጣን አስፈላጊ ሆኖ ሲታይ ዳኞች ላንድ ለበጎ አድራጎት ድርጅት ሊሰጡት ይችላሉ፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ የበጎ አድራጎት ድርጅት ያስተዳደር ክፍል ከአባሎቹ አንዱ ይህን ሥራ እንዲያከናውን ለመወከል ይችላል፡፡
ቊ 215፡፡ ተመሳሳይ ሁኔታዎች፡፡
(1) ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች የተመለከቱትን ድንጋጌዎች እንዲፈጸሙ ለማድረግ አንድ ሰው እንደሞተ የሚቈጠረው ከሕጋዊ
ምክንያት ወይም ከሁኔታ የተነሣ የልጁ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ሆነው ሥራውን ለማከናወን ባልቻሉ ጊዜ ነው፡፡

(2) ሕፃኑም ለማደጎ (ለጉዲፈቻ) ተሰጥቶ እንደሆነ የልጁ የሥጋ ዘመዶች በግምት ውስጥ አይገቡም፡፡
ቊ 216፡፡ የአሳዳሪው ወይም የሞግዚቱ መታወቂያ፡፡
(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አሳዳሪ እንዲሆን ሥልጣን ተሰጥቶት የልጁን ባለአደራነት የተቀበለው ሰው በጠቅላላው ደንብ ሞግዚትም
ነው፡፡
(2) ከነገሩ አካባቢ ሁኔታ የተነሣ ተቃራኒ የሆነ ነገር ካልተገኘ በሕይወት ያለው አባት ወይም እናት ወይም ዳኞች ለልጁ የሚሾሙት
ሞግዚት ወይም አሳዳሪ ሁለቱንም ሥልጣን እንደያዘ ይቈጠራል፡፡
ቊ 217፡፡ ለአባትና ለእናት የተሰጠ መብት፡፡
አባት ወይም እናት ጒዳዩ ጠቃሚ መስሎ የታያቸው እንደሆነ የልጃቸውን አሳዳሪነት ሥልጣን ራሳቸው ይዘው አንድ ሞግዚት ለመሾም
ይችላሉ፡፡
ቊ 218፡፡ ለዳኞቹ የተሰጠ መብት፡፡
ዳኞች የልጁን አሳዳሪና ሞግዚት የመሾም ሥልጣን የራሳቸው በሆነ ጊዜና ይህን ለማድረግ በቂ ምክንያት ያለ እንደሆነ ከአሳዳሪው ሌላ
ለልጁ ሌላ ሞግዚት ለመሾም ይችላሉ፡፡
ቊ 219፡፡ ተጨማሪ ሞግዚት፡፡
(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ስለ እያንዳንዱ ሀብት አስተዳደር ጒዳይ ዳኞች ለመረጡት ለአንድ ተጨማሪ ሞግዚት ሊሰጥ ይችላል፡፡

(2) አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ በስጦታ ወይም በኑዛዜ ሀብቶች ተሰጥተውት እንደሆነ ሀብት ተቀባዩ ወይም በኑዛዜ ተጠቃሚው ልጅ
አካለመጠን እስኪያደርስ ድረስ ንብረቱን የሚጠብቅለት ተጨማሪ ሞግዚት ሀብት ሰጪው ወይም ተናዛዡ መርጦ ሊሾምለት ይችላል፡፡

(3) የልጁ አባት ወይም እናት ወይም ሌሎች ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች ትተውት ከሚሞቱት የውርስ ገንዘብ አካለመጠን ላላደረሰው
ለጅ ለሚደርሰው ንብረትም በዚሁ መብት ሊሠሩበት ይችላሉ፡፡

ቊ 220፡፡ ምትክ ሞግዚት፡፡ (1) በሞግዚትና አካለመጠን ባላደረሰ ልጅ ጥቅም መካከል ስለሚነሣ ግጭት፡፡

(1) በሞግዚቱና አካለመጠን ባላደረሰ ልጅ ጥቅም መካከል ግጭት የተነሣ (ተቃዋሚ የሆነ ጥቅም ያለ) እንደሆነ ዳኞቹ አካለመጠን
ላላደረሰው ልጅ ምትክ ሞግዚት ይሾሙለታል፡፡
(2) ምትክ ሞግዚት የሚመረጠው በሞግዚቱ ወይም የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር አባል ከሆኑት በአንደኛው ጥያቄ አቅራቢነት ነው፡፡

(3) ተጠባባቂ ሞግዚት አስቀድሞ ተሾሞም እንደሆነ ለዚሁ ተጠባባቂ ሞግዚት በሕጉ መሠረት የምትክ ሞግዚትነት ሥልጣንና ሥራ
ይኖረዋል፡፡
ቊ 221፡፡ (2) አካለመጠን ባላደረሱ በብዙ ሕፃናት ጥቅም መካከል ስለሚነሣ ግጭት፡፡

(1) አካለመጠን ባላደረሱ በብዙ ሕፃናት ጥቅም መካከል ግጭት (ተቃዋሚ ጥቅም) የተነሣ እንደሆነና የነዚህም ተጠሪ ወኪል አንድ
የኅብረት የጋራ ሞግዚት ብቻ በሆነ ጊዜ ከሆነ በላይ በተመለከተው ቊጥር ውስጥ የተሰጠው ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

(2) ግጭት የተነሣበት (ተቃዋሚ የሆነው) ጥቅም የሚተካከለውም በሞግዚቱና በምትክ ሞግዚቱ መካከል በሚደረግ ስምምነት ነው፡፡
ቊ 222፡፡ የሥራው አጀማመር፡፡
(1) የአሳዳሪነቱ ወይም የሞግዚትነቱ ሥራ የሚጀመረው አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ በሕጉ መሠረት ወይም በዳኞች ትእዛዝ ተመርጠው
እንደተሾሙ ወዲያውኑ ነው፡፡

(2) ቢሆንም የአሳዳሪነት ወይም የሞግዚትነት ሥራ የተሰጠው መሆኑን ከማወቁ በፊት አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ ይህን ሥራውን
ሳይጀምር ለደረሰው ነገር ሁሉ ማንኛውም ዐይነት አላፊነት ሊደርስበት አይችልም፡፡
ቊ 223፡፡ ሥራው የግዴታ ስለ መሆኑ፡፡
የአሳዳሪነትን ወይም የሞግዚትነትን ሥራዎች እንዲያከናውን ተመርጦ የተሾመው ሰው ሥራውን እንዲያከናውን ግዴታ አለበት፡፡
ቊ 224፡፡ ሥራው እንዲቀርለት የሚቀርብ ጥያቄ፡፡
(1) አንድ ሰው ለአንድ ሕፃን ሞግዚት ወይም አሳዳሪ ቢሆን፤ የዚህ ሥራ አፈጻጸም በግል ጒዳዩ ላይ ችግር የሚያስከትል ወይም
የማይስማማ ነገር የሚያደርስበት የሆነ እንደሆነ ሥራ እንዲቀርለት ዳኞችን ሊጠይቅ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም አንድ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ከተሰጣቸው የአሳዳሪነትና የሞግዚትነት ሥራቸው እንዲሻሩ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
ቊ 225፡፡ በሕግ አግባብ የሚሰጥ ልዩ አስተያየት፡፡
እራሳቸው ጥያቄ ካቀረቡና ለራሳቸው ልጆች ካልሆነ በቀር፤ የአሳዳሪነት ወይም የሞግዚትነት ሥራ እንዳይዙ በሕግ የሚፈቀድላቸው፡፡
(ሀ) ሴቶች፤

(ለ) ዕድሜው ስድሳ ዐምስት ዓመት የሞላው ሰው፤

(ሐ) አካለመጠን ያላደረሱ አራት ልጆች ያሉት ሰው፤

(መ) በሥራ ላይ ያሉ ወታደሮች፤

(ሠ) በውጭ አገር እንዲኖሩ ሥራቸው የሚያስገድዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው፡፡


ቊ 226፡፡ ለጊዜው ሥራውን የማከናወን ግዴታ፡፡
(1) የልጅ አሳዳሪነት ወይም የሞግዚትነት ሥራ ችግር ያደርስብኛል ብሎ ምክንያት በማቅረብ ይህ አላፊነት እንዲወገድለት የሚጠይቅ
አሳዳሪ ወይም ሞግዚት በዚህ ሥራ ሌላ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ተተክቶ ሥልጣኑን እስኪረከበው ድረስ የተሰጠውን ሥራ ለጊዜው
የማከናወን ግዴታ አለበት፡፡

(2) እንዲሁም የአሳዳሪነቱ ወይም የሞግዚትነቱ ሥራ በሹመት የተሰጠው አሳዳሪና ሞግዚትም የዚሁ ዐይነት ግዴታ ይኖርበታል፡፡
ቊ 227፡፡ ስለ ሥራው መቅረት፡፡
(1) የአሳዳሪው ወይም የሞግዚቱ ሥራ ቀሪ የሚሆነው የሚጠበቀው ልጅ የሞተ እንደሆነ ወይም አካለመጠን ባደረሰ ጊዜ ወይም ከሞግዚት
ጥበቃ ነፃ በወጣ ጊዜ ነው፡፡
(2) እንዲሁም አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ ሲሞት ወይም ችሎታ ሲያጣ ወይም ተገቢ ያለመሆኑ ሲገለጽ ወይም ከሥራው ሲሻር ቀሪ
ይሆናል፡፡
(3) በመጨረሻውም አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ አሳዳሪነት ወይም ሞግዚትነት አንድ አዲስ ሰው በተሾመ ጊዜ የቀድሞው ሞግዚት
ሥራውን ይተዋል፡፡

ቊ 228፡፡ ችሎታ ማጣት፡፡ (1) አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ፡፡


የራሱን ልጆች በሚመለከት ጒዳይ ካልሆነ በቀር አካለመጠን ያላደረሰ ሰው የአሳዳሪነት ወይም የሞግዚትነት ሥራን ለማካሄድ ችሎታ
የለውም፡፡
ቊ 229፡፡ (2) በፍርድ ውሳኔ የተከለከሉ ሰዎች፡፡

(1) ችሎታ የሌለው መሆኑ ታውቆ በፍርድ ውሳኔ የተከለከለ ማንኛውም ሰው የአሳዳሪነት ወይም የሞግዚትነት ሥራን ለማከናወን
አይችልም፡፡

(2) ይህን ሥራ ያከናውን የነበረ አንድ ሰው፤ ችሎታ ያጣ መሆኑ በፍርድ ውሳኔ የተገለጸ እንደሆነ፤ በፍርድ ውሳኔ ችሎታ የተከለከለውን
ሰው ሥራ ተረክቦ በምትክነት ለማካሄድ በሕግ መሠረት ለሚገባው ሰው ሞግዚቱ ወዲያውኑ ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) እንዲህ ያለ ሰው የሌለም እንደሆነ በፍርድ ውሳኔ የታገደው ሰው ምትክ እንዲደረግለት ሞግዚቱ ለዳኞች ጥያቄ ማቅረብ አለበት፡፡
ቊ 230፡፡ ተገቢ ስላለመሆን፡፡
(1) አንድ ሰው የአሳዳሪነት ወይም የሞግዚትነት ሥራን ለማካሄድ ተገቢ አይደለም ብለው ደኞች ለመወሰን የሚችሉት የወንጀል ተግባር
በመፈጸሙ ከግል ነፃነት የሚከለከል የእስራት ቅጣት ወይም የሞት ፍርድ ቅጣት የተፈረደበት ኖሮ እንደሆነ ነው፡፡

(2) ዳኞች የዚህን ዐይነት ቅጣት በአንድ ሰው ላይ በሚወስኑበት ጊዜ ነገሩ ተገቢ መሆኑን የገመቱ እንደሆነ የተፈረደበት ሰው ለዚህ ሥራ
ተገቢ አለመሆኑን ጭምር ለመበየን ይችላሉ፡፡

ቊ 231፡፡ (1) የአሳዳሪው መሻር፡፡

(1) አካለመጠን ላላደረሰ ሰው አሳዳሪ እንዲሆን የተሾመ ሰው ልጁ ለኑሮው አስፈላጊ የሆነውን ጥበቃ ሳያገኝ ወይም ከግብረ ገብነት ጋራ
የተመሳሰለ የአእምሮ አስተዳደግ ወይም ከችሎታው ጋራ ተመዛዛኝ የሆነ ትምህርት እንዲያገኝ ሳያደርግለት የቀረ እንደሆነ ይህ አሳዳሪው
እንዲሻር ዳኞች ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(2) ይህንንም ውሳኔ ለማድረግ፤ አሳዳሪው የሚኖርበትን አካባቢ የስፍራ ሁኔታና የጊዜውንም አጋጣሚ ሁኔታ መገመትና መሠረት ማድረግ
አስፈላጊ ነው፡፡

(3) በተለይም ዳኞች አሳዳሪውን ለመሻር የሚችሉት አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ወንጀል መሥራቱ የተረጋገጠ ሲሆንና ይህም ቅጣት
የደረሰበት በመጥፎ አስተዳደግ ወይም በአሳዳሪው ጒድለት ተገቢውን የግብረ ገብነት ሥልጣኔ ለማግኘት ካለመቻሉ የተነሣ የሆነ እንደሆነ
ነው፡፡
ቊ 232፡፡ (2) የሞግዚቱ መሻር፡፡
አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ ሞግዚት የሆነ ሰው እንዲሻር ዳኞች የሚወስኑት ሞግዚቱ የሕፃኑን ንብረትና ሀብት በመጥፎ ሁኔታ ያስተዳደረና
አጠባበቁም በቂ ያልሆነ እንደሆነ ወይም የልጁ አባትና እናት ወይም የቤተ ዘመድ ጉባኤ አማካሪዎች በሚገባ የሰጡትን ደንብና የንብረት
አስተዳደር ሥርዐት ሳይጠብቅና ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ ወይም ዕዳ ለመክፈል ያለመቻሉ በፍርድ ውሳኔ የተረጋገጠ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 233፡፡ (3) የወላጆች መሻር፡፡

(1) ዳኞች ጥብቅ በሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተጠብቀው ካላደረጉ በቀር የልጁ አባት ወይም እናት ወይም ሌሎቹ ወላጆች ከልጃቸው አሳዳሪነት
ወይም ሞግዚትነት ሥራቸው እንዲሻሩ የፍርድ ውሳኔ አይሰጡም፡፡
(2) ዳኞች ስለዚህ ጒዳይ ያደረጉት የፍርድ ውሳኔ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን በተሻረው ወገን ጠያቂነት እንደገና ሊመረመር ይችላል፡፡

ቊ 234፡፡ (4) ሥነ ሥርዐት፡፡

(1) አንድ አሳዳሪ ወይም አንድ ሞግዚት እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ በአንድ የልጁ የሥጋ ዘመድ ወይም የጋብቻ ዝምድና ግንኙነት በአለው
ወይም በሕግ አስከባሪው በኩል ሊደረግ ይችላል፡፡

(2) ዳኞች የአሳዳሪውን ወይም የሞግዚቱን መሻር በፍርድ ከመወሰናቸው በፊት አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ሰውነት ላይ ወይም በሀብቱ
ላይ ከባድ ጉዳት እንዳይደርስ አድርገው አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ የሚያመለክተውን ነገር ሊሰሙት ይገባል፡፡

(3) ዳኞች አንድ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት እንዲሻር ውሳኔ በሰጡት ጊዜ በማንኛውም ጊዜ ሌላ ምትክ እንዲኖር አስፈላጊውን መፈጸም
አለባቸው፡፡
ቊ 235፡፡ የዳኞች ሥልጣንና ግዴታ፡፡
(1) ዳኞች አንዱን ሰው አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ አሳዳሪነት ወይም ሞግዚትነት ለመሾም ሲመርጡ ወይም የተሾመውን ከሥራው
ሲለውጡ (ሲሽሩ) ይህን ውሳኔ ከመስጠታቸው በፊት በተቻለ መጠን ከልጁ የቤተ ዘመድ ጉባኤ አማካሪ ጋራ መመካከር ይገባቸዋል፡፡

(2) እንዲሁም አስፈላጊነቱን የገመቱ እንደሆነ ባለጒዳይ የሆነውን አካለመጠን ያላደረሰውን ሰው አሳብ ይሰማሉ፡፡

(3) ዳኞች ይህን ውሳኔ ሲሰጡ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ጥቅም የማይጓደልበትን ነገር ብቻ መከተል እንጂ በመመርመር ያገኙትን አሳብ
የመቀበል ግዴታ የለባቸውም፡፡
ቊ 236፡፡ ሥራው ያለ ዋጋ ወይም በዋጋ የሚከናወን ስለ መሆኑ፡፡
(1) የአሳዳሪነትና የሞግዚትነት ሥራ የሚከናወነው ማናቸውም ዋጋ ሳይከፈልበት በነፃ ነው፡፡

(2) ቢሆንም፤ አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ ይህን ሥራ ለማከናወን ረጅም ጊዜ የሚጠይቀው የሆነ እንደሆነና፤ አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ
አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ የሥጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና የሌለው የሆነ እንደሆነ አንድ የተወሰነ የዓመት አበል ሊቈረጥለት ይቻላል፡፡

(3) ይህም የዓመት አበል አካለመጠን ካላደረሰው ልጅ የሀብት ገቢ ላይ ካልሆነ በቀር ከሌላ ሀብት ሊወስድ አይችልም፡፡ የአበሉም ልክ
ከጠቅላላው የሀብት ገቢ ከሦስት አንድ እጅ ሊያልፍ አይችልም፡፡
ቊ 237፡፡ የሥራው አካሄድ የግል ስለ መሆኑ፡፡
(1) የአሳዳሪነቱ ወይም የሞግዚትነቱ ሥራ የግል ጠባይ የያዘ ስለሆነ ሥራውን የሚያከናውነው ያው ራሱ እንጂ ለአሳዳሪው ወይም
ለሞግዚቱ ወራሾች ለመተላለፍ አይችልም፡፡

(2) ወራሾቹ ግን በአላፊነት የሚጠየቁት አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ በፈጸመው የሥራ አካሄድ ጒድለት ብቻ ነው፡፡ ይኸውም በዚህ ሕግ
በውርስ አንቀጽ በተመለከተው መሠረት ነው፡፡
ቊ 238፡፡ የወራሾች ግዴታ፡፡
(1) የአንድ አሳዳሪ ወይም ያንድ ሞግዚት ወራሾች አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ እንደ ሞተ ወዲያውኑ፤ በቊጥር 2 ፲ በተመለከተው በሕጉ
መሠረት ለሟቹ ምትክ ሊሆን ለሚገባው ሰው ማስታወቅ ግዴታ ነው፡፡ የዚህ ዐይነት ሰው የሌለም እንደሆነ በሟቹ ምትክ የሚመረጠውን
ሰው እንዲያዝዙ ለዳኞች ማስታወቅ አለባቸው፡፡

(3) የአሳዳሪው ወይም የሞግዚቱ ወራሾች ይህን ከዚህ በላይ በ 1 እና በ 2 ንኡስ ቊጥር የተጻፈውን ግዴታቸውን እስከሚፈጽሙበት ጊዜ
ድረስ አካለመጠን ላላደረሰውም ሰው ሆነ ለሌላ ሦስተኛ ወገኖች አላፊዎች ሆነው ይቈያሉ፡፡
ቊ 239፡፡ የሞግዚትነት ማስረጃ፡፡
(1) አስፈላጊ በሆነ ጊዜ አሳዳሪነቱን ወይም ሞግዚትነቱን የሚያስረዳለት ጽሑፍ ዳኞች እንዲሰጡት አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱ ዳኞችን
ለመጠየቅ ይችላል፡፡
(2) የውል ቤት ሹም ባለበት ቦታ ይህንኑ ጽሑፍ የውል ቤቱ ሹም ለሞግዚቱ ወይም ለአሳዳሪው ሊሰጥ ይችላል፡፡
ቊ 240፡፡ ከሞግዚትነት ጋራ የሚመሳሰል ሁኔታ፡፡
ሞግዚትነትን የሚመለከተው የዚህ አንቀጽ ድንጋጌ በተጨማሪ ሞግዚትና በምትክ ሞግዚትም ጒዳይ ሊፈጸም ይችላል፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
ስለ ቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር አባሎችና
ስለ ተጠባባቂ ሞግዚት፡፡
(ሀ) ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የሚሆን አቋቋም፡፡
ቊ 241፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር ቤት አባሎች የሚሆኑት የልጁ ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆችና አካለመጠን
ያደረሱ ወንድሞችና እኅቶች ናቸው፡፡

(2) አካለመጠን ያላደረሰው ሰው የጉዲፈቻ (የማደጎ) ልጅነት ውል ያለው የሆነ እንደሆነ የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር አባሎች የሚሆኑት
የጉዲፈቻ አድራጊው ቤተ ዘመዶች ናቸው፡፡
ቊ 242፡፡ የወላጆች አለመኖር፡፡
አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በአንድ የዝምድና መሥመር ውስጥ ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች የሌሉት እንደሆነ የቤተ ዘመድ አማካሪ
አባሎች እንዲሆኑ የሚጠሩ ከአጎቶቹ ወይም ከአክስቶቹ በዕድሜ ታላቅ የሆነው እነዚህም ባይኖሩ ከዚሁ የዝምድና መሥመር
ከተመራጮቹ እንደ ዕድሜያቸው ቅደም ተከተል የሆኑት ናቸው፡፡
ቊ 243፡፡ እናትና አባት በተፋቱ ጊዜ ስለሚደረግ ሁኔታ፡፡
አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ እናትና አባት ተፋትተው እንደሆነ የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር ቤት አባሎች የሚሆኑት ከዚህ በላይ ባሉት
ቊጥሮች ውስጥ ከተጠቀሱት ዘመዶቹም በላይ የመፋታቱን ጒዳይ የወሰኑትም ሽማግሌዎች ጭምር ናቸው፡፡
ቊ 244፡፡ የአማካሪ አባሎች ተጨማሪነት፡፡
(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አባት በመጨረሻ ኑዛዜው ላይ አንድ ወይም ሁለት ሰዎች የምክር አባሎች ሆነው በተጨማሪነት እንዲሠሩ
ቃሉን ለመስጠት ይችላሉ፡፡

(2) እናትም የዚሁ ዐይነት መብት አላት፡፡


ቊ 245፡፡ አባሎቹ ከምክር ውጭ ስለሚሆኑበት ጒዳይ፡፡
አባት ወይም እናት ከልጆቻቸው አንዱ ወይም ብዙዎቹ አካለመጠን ላላደረሱት ወንድሞቻቸው ወይም እኅቶቻቸው የቤተ ዘመድ ምክር
ጉባኤ አባል እንዳይሆኑ በመጨረሻ የኑዛዜ ቃላቸው ለመወሰን ይችላሉ፡፡
ቊ 246፡፡ ተጨማሪ አባሎችን ስለ መምረጥ፡፡
(1) ከዚህ በላይ በተመለከተው ቊጥር ድንጋጌ መሠረት የተቋቋመው የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር ቤት አራት አባሎች ሳይኖሩት የቀረ
እንደሆነ አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ ጥቅም ከሚያስቡት ሰዎች መካከል ዘመዶች ወይም ባዕዶች ከሆኑት ውስጥ ተጨማሪ አባሎች
ይመረጣሉ፡፡
(2) የቤተ ዘመድ ጉባኤ አማካሪዎች ብዛታቸው ከሁለት ያላነሰ ከሆነ ተጨማሪ አባሎችን ይመርጣሉ፡፡

(3) ከሁለት ያነሱ እንደሆነ ወይም የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር ቤት አባሎች በአንድ ቃል ሳይስማሙ የቀሩ እንደሆነ ተጨማሪ አባሎችን
የሚመርጠው አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በሚኖርበት ቀበሌ ያለው የክፍል ሹም ነው፤ ይኸውም ቢሆን ጒዳዩ ይመለከተናል የሚሉ
ወገኖች ለዳኞች አቤቱታ የማቅረብ መብታቸው እንደተጠበቀ ነው፡፡
ለ) የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር አባሎች ስብሰባ፡፡
ቊ 247 ፡፡ በሕጉ መሠረት የሚደረግ ስብሰባ፡፡
የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር ቤት አባሎች ስብሰባ የሚደረገው፤ በሕጉ መሠረት ከተወሰነው ቀን አስቀድመው ካልተሰበሰቡ በቀር አካለመጠን
ካላደረሰው ልጅ አባትና እናት በመጨረሻ ከሞተበት ቀን አንሥቶ በአርባኛው ቀን ነው፡፡
ቊ 248፡፡ የአማካሪዎቹ ጥሪ፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር ቤት አባሎች፤ ስብሰባ የሚያደርጉት አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ወይም ዳኞች ጥሪ
ባደረጉላቸው ቊጥር ነው፡፡

(2) እንዲሁም በተጨማሪው ሞግዚት ጠያቂነት ጥሪ ሊደረግላቸው ይቻላል፡፡

(3) ተጨማሪ ሞግዚት አልተሾመ እንደሆነም ማንኛውም የቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር አባል በሚያደርገው ጥያቄና ጥሪ አባሎቹ ሊሰበሰቡ
ይችላሉ፡፡
ቊ 249፡፡ የጊዜ ውሳኔ፡፡
የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ለመሰብሰብ እንዲችሉ በአእምሮ ግምት በቂ ነው ተብሎ የሚገመት ለስብሰባው አንድ ቀጠሮ የተወሰነ ጊዜ ሊሰጥ
ይገባል፡፡
ቊ 250፡፡ ጉባኤው የሚነጋገርበት ጒዳይ፡፡
(1) ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ከሚላከው መጥሪያ ጋሪ የሚመከርበትና ድምፅ የሚሰጥበት ጒዳይ ይላክላቸዋል፡፡

(2) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አባት ወይም እናት ከሞተበት ቀን በኋላ የሚሰበሰበው የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ በጠቅላላው አደራረግ
አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ሁኔታ መርምሮና በሚከተሉትም ቊጥሮች መሠረት ተገቢዎች መስለው የሚታዩትን ጥንቃቄዎች በሥልጣኑ
ይወስናል፡፡
ቊ 251፡፡ የስብሰባው ቦታ፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ስብሰባ የሚደረገው፤ አባት ወይም እናት በሞተ ጊዜ፤ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በሚገኝበት መኖሪያ ቤት
ነው፡፡

(2) ዳኞች አካለመጠን ባላደረሰ ልጅ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ጥያቄ፤ አንድ ከባድ ምክንያት ያገኙ እንደሆነ የቤተ ዘመድ ጉባኤ ስብሰባ
ባንድ ሌላ ቦታ እንዲሆን ለመፍቀድ ይችላሉ፡፡
ቊ 252፡፡ ወጪ፡፡
ለጥሪውና ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የሚደረጉት ወጪዎች በነዚሁ የምክር አባሎች ኪሣራ ይሆናል፡፡
ቊ 253፡፡ በጽሑፍ ስለ መመካከር፡፡
ይህ ሥነ ሥርዐት የሚገባ መስሎ የታየው እንደሆነ ሞግዚቱ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ስብሰባ ሳያደርግ ልዩ በሆነ አንድ ጒዳይ የዚሁኑ
ምክር አባሎች የየአንዳንዱን ሐሳብ መጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 254፡፡ ስለ አባሎች በስብሰባው መገኘት አለመቻል፤ ወይም ወኪል ስለ ማድረግ፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ምክር ስብሰባ አባሎች ባንድ ስብሰባ ለመገኘት ያልቻሉ እንደሆነ ሐሳባቸውን ወይም የድምፃቸውን ብልጫ በጽሑፍ
መግለጽ ይችላሉ፡፡

(2) በምክሩም ስብሰባ ሌላ ወኪል ለማድረግ አይችሉም፡፡


ቊ 255፡፡ አስፈላጊው የድምፅ ብልጫ ብዛት፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ውሳኔ በስብሰባው ያሉት ወይም የሌሉት የጉባኤው አባሎች ድምፅ ፍጹም በሆነ ብልጫ ተቈጥሮ ነው፡፡
(2) ውሳኔዎቹም በአንድ ፕሮሴቬርባል ውስጥ ተጽፈው የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አባሎች ይፈርሙባቸዋል፡፡

(3) አንድ ውሳኔ ዋጋ ያለው እንዲሆን ውሳኔውን ባጸደቁት በአብዛኛዎቹ አባሎች መፈረም አለበት፡፡
ቊ 256፡፡ የአሳዳሪውና የሞግዚቱ ሁኔታ፡፡
(1) አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ አሳዳሪና ሞግዚት ምንም አባሎች ባይሆኑም በቤተ ዘመድ ምክር ክርክር ውስጥ የሚገኙ ይሆናሉ፡፡

(2) አባሎች ባልሆኑም ጊዜ በምክሩ ክርክር ውስጥ ምክር ከመስጠት በቀር የውሳኔ ድምፅ የመስጠት መብት አይኖራቸውም፡፡
ቊ 257፡፡ አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ሁኔታ፡፡
የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ተቃራኒ ውሳኔ ካልሰጠ በቀር አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ክርክር ውስጥ አይገኝም፡፡
ቊ 258፡፡ በምክር አባሎች ፈንታ፤ ዳኞችን ስለ መተካት፡፡ (1) የድምፅ ብልጫ ብዛት ስላለመኖሩ፡፡

(1) በአባሎቹ አለመኖር ወይም አለመስማማት ምክንያት አንድም የድምፅ ብልጫ ብዛት በምክሩ ስብሰባ ሊሰጥ ያልቻለ እንደሆነ፤ የምክሩ
ስብሰባ ሊፈጽመው ያልቻለውን ውሳኔ ዳኞች ይወስናሉ፡፡

(2) አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ አሳዳሪ ወይም ሞግዚት ለዳኞች ነገሩን ለማቅረብ ይችላሉ፡፡

(3) እንዲሁም ተጨማሪ ሞግዚት፤ ወይም ተጨማሪ ሞግዚት በሌለ ጊዜ ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አባል የሆነ ማንኛውም ሰው ጒዳዩን
ለዳኞች ለማቅረብ ይችላል፡፡

ቊ 259፡፡ (2) አስቸኳይነት፡፡


የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤን ለመሰብሰብ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜና አንድ ውሳኔ ለማድረግ አስቸኳይ የሆነ እንደሆነ በነዚሁ ሰዎች ጥያቄ በቤተ
ዘመድ ጉባኤ ፈንታ ዳኞቹ ተተክተው ውሳኔ ለመስጠት ይችላሉ፡፡
ቊ 260፡፡ አቤቱታ፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ በሰጠው ውሳኔ ላይ ከተሰጠበት ቀን አንሥቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለዳኞች አቤቱታ ሊቀርብ ይቻላል፡፡

(2) አቤቱታውንም የልጁ ሞግዚት ወይም ተጨማሪ ሞግዚቱ ወይም ማናቸውም የቤተ ዘመድ ምክር አባል የሆነ አንድ ሰው ሊያቀርበው
ይችላል፡፡
(ሐ) ስለ ተጨማሪ ሞግዚት፡፡
ቊ 261፡፡ ምርጫ፡፡
የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የተጨማሪ ሞግዚትን ሥራ የሚሠራ ሰው ከአባሎቹ አንዱን ወይም አንድ ሌላ ሰው ለመምረጥ ይችላል፡፡
ቊ 262፡፡ የሞግዚቱ ተጠባባቂነት፡፡
(1) ተጨማሪውም ሞግዚት በቤተ ዘመድ ጉባኤ ፈንታ የሞግዚቱን ሒሳቦች ይቀበላል፡፡

(2) በቤተ ዘመድ ጉባኤ በተዘረዘሩት ተግባሮች አፈጻጸም ውስጥ ሞግዚቱን ይረዳል፡፡

(3) ጠቃሚ መሆኑንም የገመተ እንደሆነ የቤተ ዘመድ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ጥሪ ያደርጋል፡፡
ቊ 263፡፡ ሞግዚትን ስለ መተካት ወይም ስለ መርዳት፡፡
(1) ሞግዚቱ በአንድ ጒዳይ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ጥቅሞች ተቃዋሚ የሚሆኑ ጥቅሞች ያሉት እንደሆነ በሞግዚቱ ጥያቄ
ተጨማሪው ሞግዚት ምትኩ ይሆናል፡፡

(2) አካለመጠን ባላደረሱ በብዙ ሰዎች ጥቅም መካከል ተቃራኒ ጥቅም ባለ ጊዜና ሞግዚቱም የእነዚሁ የኅብረት (የጋራ) እንደራሴ እንደሆነ
በዚሁ ጠያቂነት ተጨማሪው ሞግዚት ዋናውን ሞግዚት ይረዳዋል፡፡
(መ) የወል ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 264፡፡ የሥራዎቹ አካሄድ፡፡
(1) ስለ ሞግዚት የሚሰጡት አስተያየቶች ለእነዚህም እንደተጠበቁ ሆነው የቤተ ዘመድ አባልና የተጨማሪ ሞግዚት ሥራዎች ግዴታ
ያለባቸው ናቸው፡፡

(2) እንዲሁም ያለ ዋጋ የሚፈጸሙ ናቸው፡፡

(3) ለሞግዚትነት አለመቻልንና አለመገባትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በቤተ ዘመድ ምክር አባሎችና በተጨማሪ ሞግዚት ላይ የሚፈጸሙ
ይሆናሉ፡፡
ክፍል 3፡፡
የአሳዳሪውና የሞግዚቱ ሥልጣን፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ሰውነት አጠባበቅ፡፡
ቊ 265፡፡ አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ መኖሪያ፡፡
(1) አሳዳሪው አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ የሚኖርበትን ቦታ ይወስናል፡፡

(2) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ያላሳዳሪው ፈቃድ ይህን ቦታ ለመተው አይችልም፡፡

(3) ያለፈቃድ የራቀ እንደሆነ አሳዳሪው እንዲመለስ ሊያስገድደው ይችላል፡፡


ቊ 266፡፡ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ጤና፡፡
(1) አሳዳሪው አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ጤና ይጠብቃል፡፡

(2) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ የታመመ እንደሆነ እንዲድን አስፈላጊዎችን ጥንቃቄዎች ያደርግለታል፡፡


ቊ 267፡፡ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አስተዳደግ፡፡
(1) አሳዳሪው አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ አስተዳደግ ይመራል፡፡

(2) ያደረጋቸውን ጥፋቶች በማመዛዘንና አስተዳደጉንም በመጠበቅ አስተያየት፤ ቀላል የሰውነት ቅጣቶችን አካለመጠን ባላደረሰ ልጅ ላይ
ለመፈጸም ይችላል፡፡
ቊ 268፡፡ ግንኙነትና ደብዳቤ መጻጻፍ፡፡
(1) አሳዳሪው አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ግንኙነቶች ይጠብቃል፡፡

(2) አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ የሚላከውን ደብዳቤ ለመቀበል ይችላል፡፡

(3) የሆነ ሆኖ አሳዳሪው ከባድ ምክንያት ሳይኖር አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ወላጆቹን እንዳያይ ወይም ከነርሱ ጋራ እንዳይጻጻፍ
መከልከል አይችልም፡፡
ቊ 269፡፡ ጠቅላላ ትምህርትና የሞያ ትምህርት፡፡
(1) አሳዳሪው አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በተቻለ መጠን ከችሎታው ጋራ ተመሳሳይና ሙሉ የሆነ ጠቅላላ ትምህርትና የሞያ ትምህርትን
እንዲያገኝ መትጋት አለበት፡፡

(2) አሳዳሪውም ለዚሁ ትምህርት አስፈላጊ የሆኑትን ውሎች ጨርሶ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ የሞያ ትምህርትን እንዲያከናውን
ይፈቅዳል፡፡
ቊ 270፡፡ አካለመጠን ስላላደረሱ ልጆች ገቢ ገንዘብ (1) ጠቅላላ ሁኔታ፡፡

(1) አሳዳሪው አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ ገቢ የሚሆነውን የግሉን ገንዘብ ተቀብሎ ለዚሁ ልጅ ጥቅም ያውለዋል፡፡

(2) አሳዳሪውም ገንዘቡን ለምን አገልግሎት እንዳዋለው ለልጁ ማስታወቅ የለበትም፡፡

ቊ 271፡፡ (1) ገቢ ስለሚሆን ብዙ ገንዘብ፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ገቢ ገንዘብ ብዙ የሆነ እንደሆነ አሳዳሪውም አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አባት ወይም እናት ያልሆነ
እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ በቊጥር 2 ፸ በንኡስ ቁጥር 1 የተወሰነው ደንብ በቤተ ዘመድ ጉባኤ ምክር ቀሪ እንዲሆን ሊደረግ ይቻላል፡፡

(2) ይህ ሲሆን የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አካለመጠን ካላደረሰው ልጅ ገቢዎች ላይ ለአጠባበቁና ለትምህርቱ ደንበኛ የሆነ ወጪ በየ ዓመቱ
ለአሳዳሪው የሚሰጥ አንድ የተቈረጠ ገንዘብ ይወስናል፡፡

(3) አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ የገቢ ትርፎቹን ለዚሁ ልጅ ጥቅም ሞግዚቱ ተቀማጭ ያደርጋቸዋል፡፡

ቊ 272፡፡ (3) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ሥራ፡፡


ለአካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ዐሥራ አምስት ዓመት ከሞላው በኋላ በሥራው ያገኛቸውን ገቢዎች ራሱ ይቀበላል፡፡ ለራሱ አስተዳደር
የሚያስፈልገውን ካደረገ በኋላ በነዚህ ገቢዎች ለማዘዝ ነፃነት አለው፡፡

ቊ 273፡፡ (4) በስጦታ ወይም በኑዛዜ የተሰጡ ሀብቶች፡፡

(1) አካለ መጠን ላላደረሰ ልጅ ሀብቶችን በስጦታ ወይም በኑዛዜ የሚሰጥ ወይም የሚተው ሰው፤ ልጁ አካለመጠን አደረሰ ድረስ የነዚሁ
ገቢዎች ሀብቶች የማይነኩ ናቸው ብሎ ለአሳዳሪው ማስጠንቀቅ ይቻላል፡፡

(2) በስጦታ ወይም በኑዛዜ ውል እነዚህን የሀብት ገቢዎች ስለ ማስተዳደር በሥራ ላይ ስለ ማዋል የተጻፉት ትእዛዞች ተፈጻሚ መሆን
አለባቸው፡፡
ቊ 274፡፡ (5) ገቢዎቹን ስለ ማስተላለፍ ወይም ስለ መያዝ፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ የሀብት ገቢዎች አሳዳሪው ለሌላ ሰው ሊያስተላልፍ ወይም አስቀድሞ ውል ሊገባባቸው አይችልም፡፡

(2) ከአሳዳሪውም ሌላ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ሊይዙት አይችሉም፡፡


ቊ 275፡፡ አባትነትን ስለ ማወቅ፡፡
(1) ዲቃላ ልጅን ለማወቅ ለመቀበል አካለ መጠን ያላደረሰው ልጅ ፈቃድ አስፈላጊ ነው፡፡

(2) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በአሳዳሪው ፈቃድ ያደረገው ካልሆነ በቀር ችሎታ ማጣቱ እስከ ቈየበትና ችሎታ ማጣቱ በቀረበት
በተከታዩ ዓመት ውስጥ ይህን የዲቃላ ማወቅ ቃል ለመሻር ይችላል፡፡

(3) ይህ የመሻር መብት የግሉ ስለሆነ እንደራሴዎቹ ወይም ወራሾቹ ሊፈጽሙት አይችሉም፡፡

ቊ 276፡፡ የአባትና የእናት ሥልጣን ሥራ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የልጅ አባትና እናት የአሳዳሪነት ሥልጣን ሁለቱም በተሰጣቸው ጊዜ፤ ሥራውን የሚያከናውነው አባት ብቻ ነው፡፡

(2) አባትዬው በመራቁ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ሐሳቡን ለመግለጽ በማይችልበት ሁኔታ በሚገኝበት ጊዜ በእሱ ምትክ
ሥራውን የምታከናውነው የልጁ እናት ናት፡፡

ቊ 277፡፡ (2) ክርክር፡፡

(1) የልጁን ሰውነት አጠባበቅ በሚነካ ጒዳይ በአባትና በእናት መካከል ክርክር የተነሣ እንደሆነ የልጁ እናት ለቤተ ዘመድ ዳኞች አቤቱታ
ለማቅረብ ትችላለች፡፡
(2) እናት ካልሆነች በቀር ይህን ክርክር ማናቸውም ሌላ ሰው ለቤተ ዘመድ ዳኞች ለማቅረብ አይችልም፡፡

ቊ 278፡፡ ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አቤቱታ ስለ ማቅረብ (1) መሠረቱ፡፡


የልጁ አባት ወይም እናት አሳዳሪ ሆኖ በሚያደርገው ውሳኔ ተቃዋሚ በመሆን አንዳችም አቤቱታ ሊቀርብበት አይችልም፤ አቤቱታ ሊቀርብ
የሚችለው ግን፡-

(ሀ) የልጁ አባትና እናት የተፋቱ እንደሆነ፤

(ለ) በልጁ ላይ ሥልጣን ያላቸው አባትና እናት እንደገና ሌላ ያገቡ ወይም ከጋብቻ ውጭ በሆነ ግንኙነት አብረው የኖሩ እንደሆነ ነው፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
አካለ መጠን ያላደረሰን ልጅ ሀብቶች ስለ ማስተዳደር፡፡
ቊ 280፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) ሞግዚቱ በብሔራዊ ኑሮው ሥራዎች ሁሉ አካለ መጠንን ላላደረሰ ልጅ እንደራሴ ነው፡፡

(2) ሞግዚቱ አካለመጠን ያላደረሰን ልጅ የገንዘብ ጥቅሞችንና ሀብቶቹን እንደ ቤተ ዘመድ መልካም አባት በመሆን ሀብቶቹን
ያስተዳድራል፡፡

ቊ 281፡፡ የሀብት ዝርዝርና የዋጋ ግምት መግለጫ መዝገብ (እንቫንቴር)፡፡

(1) ሞግዚቱ ሥራ ከጀመረ በኋላ ስለሚሆን ነገር፡፡

(1) ሥራ ከጀመረበት ቀን ቀጥለው በአሉት አርባ ቀኖች ውስጥ ሞግዚቱ ቢቻል ከቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ መካከል የተመረጡ በቂ
ምስክሮች በአሉበት አካለመጠን ያላደረሰን ልጅ የሀብት ዝርዝርና የዋጋ ግምት መግለጫ መዝገብ ያዘጋጃል፡፡

(2) ሞግዚቱ አካለመጠን ካላደረሰው ልጅ ላይ የሚገባው ነገር እንዳለው በሀብቱ ዝርዝር መዝገብ ውስጥ እንዲገለጽ ካላደረገ
ይቀርበታል፡፡
ቊ 282፡፡ (2) አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ የደረሰ ውርስ (አወራረስ)፡፡

(1) አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ የደረሰውን ውርስ ሞግዚቱ አካለመጠን ስላላደረሰው ልጅ ሆኖ ውርሱን ከመቀበሉ በፊት ቢቻል ከቤተ
ዘመድ ምክር አባሎች መካከል የሆኑ በቂ ምስክሮች ባሉበት የሚወርሰውን የሀብት ዝርዝርና የዋጋ ግምት መግለጫ (እንቫንቴር) መዝገብ
አስቀድሞ ያዘጋጃል፡፡

(2) ሞግዚቱ የመጠየቅ ሥልጣን መሻር እንዳይደርስበት ከዚህ ውርስ ውስጥ የሚገባው ነገር እንዳለው ሀብቱ በተቈጠረበት መዝገብ
ውስጥ እንዲገለጽ ካላደረገ ይቀርበታል፡፡

(3) የሀብቱ ዝርዝር ቊጥር መዝገብ ጒድለት ተገኝቶበት አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ላይ ሊያደርስበት ለሚችለው ጉዳት ሞግዚቱ አላፊ
ነው፡፡
ቊ 283፡፡ የሞግዚቱና አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ሀብቶች ስለ መደባለቅ፡፡
(1) ሞግዚቱ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ሀብቶች ከራሱ የግል ሀብቶች ጋራ እንዳይደባለቁ አስፈላጊ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ሁሉ ማድረግ
አለበት፡፡
(2) በተለይም አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ገንዘብ ሞግዚቱ በራሱ በግል ሒሳብ እባንክ ማግባት ወይም እንዲገባ ማድረግ የተከለከለ
ነው፡፡
ቊ 284፡፡ እርግጠኛ በሆነ በታመነ ቦታ ሰነዶችንና ዋጋ ያላቸውን ዕቃዎች ስለ ማስቀመጥ፡፡
አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ ሀብቶች አስተዳደር ችግር የማያመጣ ከሆነ ሞግዚቱ የገንዘብ ሰነዶችን፤ ዋጋ ያላቸው ዕቃዎችን፤ ዋና ዋና
ጽሑፎችን፤ እነዚህንም የሚመሳስሉ ሌሎች ነገሮችን እርግጠኛ በሆነ በታመነ ቦታ ያስቀምጣል፡፡
ቊ 285፡፡ ስለ ቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ጥሪ፡፡
(1) አባት ወይም እናት ካልሆነ በቀር ሞግዚቱ ሥራውን ሲጀምር ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ጥሪ አድርጎ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ
ሀብት ሁኔታ ያመለክታቸዋል፡፡

(2) እስከዚያ ድረስ ሞግዚቱ የአስቸኳይነት ጠባይ ያላቸውን የአሳዳሪነት ሥራዎቹን ብቻ በመሥራት ተወስኖ ይቈያል፡፡
ቊ 286፡፡ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የሚሰጠው ትእዛዝ፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ከአባት ወይም ከእናት በቀር አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ሀብት አስተዳደር የሚመለከቱ ትእዛዞች
ለሞግዚቱ መስጠት ይችላል፡፡

(2) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ሞግዚቱ አንዳንድ ነገሮችን እንዳያደርግ አንዳንዶችንም ነገሮች የሚፈጽመው በዚህ ሁኔታ ወይም አስፈቅዶ
ነው ብሎ ሊከለክለው ይችላል፡፡
ቊ 287፡፡ አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ በስጦታ በኑዛዜ ወይም በውርስ ክፍያ የሚደርሱት ሀብቶች፡፡
(1) አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ በስጦታ ወይም በኑዛዜ ሀብቶችን የሚሰጥ ሰው፤ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በውርስ ከእርሱ ለሚያገኘው
ገንዘብ እነዚሁኑ ሀብቶች ሲያስተዳድር ሞግዚቱ በአንዳንድ ደንቦች ተመርቶ እንዲሠራ የሚል ቃል ሊጽፍ ይችላል፡፡

(2) እነዚህን ደንቦች ተከትሎ መሠራት የማይቻል ወይም አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ላይ ጉዳት የሚያመጣ መስሎ የታየ እንደሆነ፤ ዳኞቹ
እንዲያሻሽሏቸው ሞግዚቱ መጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 288፡፡ የንግድ ወይም ሌሎች ሥራዎች፡፡
(1) በልጁ አባት ወይም እናት ላይ ካልሆነ በቀር አካለመጠን ካላደረሰው ልጅ ሀብት ክፍል ውስጥ የንግድ የኢንዱስትሪ ወይም ሌሎች
ሥራዎች የተገኙ እንደሆነ፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ለሞግዚቱ የእነዚህን ሥራዎች ሒሳብ የሚያጣራ ወይም ሥራውን የሚቀጥል
ለመሆኑ ትእዛዝ ይሰጣል፡፡

(2) ስለዚሁ ጒዳይ ሞግዚትነቱ የሚቈይበትን ጊዜና የሞግዚቱን ችሎታዎችና ለማድረግ የሚቻለውን እንዲሁም አካለመጠን ያላደረሰውን
ልጅ ጥቅሞች በሚገባ ይመለከታል፡፡
ቊ 289፡፡ ስለ አንዳንድ ሀብቶች ሽያጭ፡፡
(1) ሞግዚቱ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ የሆኑትን ግዙፍ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ሰነድ መሸጥ ይችላል፡፡

(2) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ በልጁ አባት ወይም እናት ላይ ካልሆነ በቀር፤ ይኸንኑ የሽያጭ አሠራር፤ ትእዛዝ ለመስጠት ወይም
እንዲያውም ሽያጩን ለመከልከል ይችላል፡፡
ቊ 290፡፡ ለአምጪው የሚል ሰነድ፡፡
(1) በልጁ አባት ወይም እናት ላይ ካልሆነ በቀር አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ ገንዘብ ከሆኑ በኋላ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ለአምጪው
የሚሉ ሰነዶችን መሸጥ ወይም ስም በተጻፈባቸው ሰነዶች እንዲለወጡ ማድረግ አለበት፡፡

(2) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ከዚህ ግዴታ ነፃ ሊያደርገው ይችላል፡፡


ቊ 291፡፡ ዕዳዎችና ገቢ ገንዘቦች፡፡
(1) ሞግዚቱ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ዕዳዎች ይከፍላል፡፡

(2) አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ የሚገቡትን ካፒታሎችና ሌሎች ገቢዎችን ተቀብሎ ለሚከፍለው ሰው የደረሰኝ ይሰጣል፡፡

ቊ 292፡፡ ዋናውን (ካፒታሉን) ገንዘብ በሥራ ላይ ስለ ማዋል፡፡ (1) የሞግዚቱ ግዴታ፡፡፡


(1) ዋናዎቹ ገንዘቦች (ካፒታሎቹ) ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የበለጡ እንደሆነ፤ ሞግዚቱ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ካፒታሎች
በሥራ ላይ ሊያውላቸው ይገባል፡፡

(2) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተውን ለማሻሻል ይችላል፡፡

ቊ 293፡፡ (2) የተወሰነ ጊዜ፡፡

(1) ካፒታሎቹ በሞግዚቱ እጅ ከገቡበት ጀምሮ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ አለበት፡፡

(2) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ይህን ጊዜ ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

ቊ 294፡፡ (3) የሚገዙ ሀብቶች ዐይነት፡፡


የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ በልጁ አባት ወይም እናት ላይ ካልሆነ በቀር አካለ መጠን ላላደረሰ ልጅ ሞግዚቱ የሚገዛውን ሀብቶች ዐይነት
አስቀድሞ ለመወሰን ይችላል፡፡

ቊ 295፡፡ (4) ቅጣት፡፡

(1) ሞግዚቱ በሥራ ላይ ሳያውል የተዋቸውን ገንዘቦች ደንበኛ ወለድ አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ መክፈል አለበት፡፡

(2) አስፈላጊም ሲሆን ተጨማሪ የጉዳት ኪሣራ እንዲከፍል ሊፈረድበት ይቻላል፡፡


ቊ 296፡፡ ገቢዎች፡፡
(1) ለአጠባበቁና ለአስተዳደጉ አገልግሎት እንዲውል አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ገቢዎች ሞግዚቱ ላሳዳሪው ይሰጠዋል፡፡

(2) ይህ የሚሰጠውም በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ በተወሰኑት ሁኔታዎችና ጊዜዎች መሠረት ነው፡፡

(3) ይህን የመሰለ ውሳኔ የሌለ እንደሆነ በየስድስቱ ወር በአሳዳሪው ዋና መኖሪያ ቤት መሆን አለበት፡፡
ቊ 297፡፡ የኪራይ ውሎች፡፡
በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ተፈቅደው የተፈጸሙ ካልሆኑ በቀር ሞግዚቱ ያደረጋቸው የኪራይ ውሎች፤ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ
አካለመጠን ካደረሰ በኋላ ለሦስት ዓመት ጊዜ ካልሆነ በቀር አያስገድዱትም፡፡
ቊ 298፡፡ ውርስ፡፡
(1) ሞግዚቱ አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ በውርስ የደረሱትን ሀብቶች በዝርዝር መዝገብ አስገብቶ ስለ ልጁ ሆኖ ይቀበላል፡፡

(2) ይህ ውርስ በታወቀ አኳኋን ለአውራሹ ዕዳ የሚበቃ ካልሆነ በቀር አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ በውርስ የደረሰውን ሀብት የቤተ
ዘመድ ምክር ጉባኤ ካልተፈቀደለት ሞግዚት ለመተው አይችልም፡፡
ቊ 299፡፡ ስጦታ፡፡
(1) ሞግዚቱ አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ የተሰጠውን ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር በላይ የሆነውን ስጦታ በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ
ካልተፈቀደለት አልቀበልም ለማለት አይችልም፡፡

(2) ልማድ ለማስገደድ ከሚችለው አነስተኛ ከሆኑ ስጦታዎች በቀር ሞግዚቱ አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ስም ምንም ስጦታ ለማድረግ
አይችልም፡፡
ቊ 300፡፡ የዋስትና ውለታ፡፡
ሞግዚቱ በማናቸውም አኳኋን አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ስም ለሌላ ሰው ዕዳ ዋስ መሆን አይችልም፡፡
ቊ 301፡፡ ግልግል፡፡
ሞግዚቱ ክርክር የሚደረግበት ጥቅም ከሦስት መቶ የኢትዮጵያ ብር ያነሰ ካልሆነ በቀር አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ጥቅሞች
በሚመለከት ነገር ከቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ካልተፈቀደለት ምንም ግልግል ለመፈጸም አይችልም፡፡
ቊ 302፡፡ ሞግዚቱ አካለመጠን ካላደረሰው ልጅ ጋራ የሚያደርጋቸው ውሎች፡፡
(1) ሞግዚቱ ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ካልተፈቀደለት በቀር፤ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ሀብቶች ለመግዛት፤ በኪራይ ውል ለመውሰድ
ወይም አካለመጠን ካደረሰው ልጅ ጋራ ሌላ ውል ለመዋዋልም አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም ሞግዚቱ በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ካልተፈቀደለት በቀር አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ላይ ማናቸውንም መብት ወይም
ገንዘብ የሚጠይቅበትን መብት ለመቀበል አይችልም፡፡
ቊ 303፡፡ ብድር፡፡
ሞግዚቱ በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ካልተፈቀደለት በቀር አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ስም የብድርን ውጭ ለመዋዋል አይችልም፡፡
ቊ 304፡፡ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ስለ ማማከር፡፡
(1) ጥፋትንና ልማትን ለይቶ ለማወቅ የቻለና ቢያንስ ዐሥራ አምስት ዓመት ዕድሜ የለው የሆነ እንደሆነ እርሱን በሚመለከቱት ዋና ዋና
ሥራዎች ሁሉ አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ በተቻለ መጠን ማማከር ያስፈልጋል፡፡

(2) አካለመጠን ካላደረሰው ልጅ ፈቃድ መቀበል ሞግዚቱን ከኀላፊነት ነፃ አያደርገውም፡፡

ቊ 305፡፡ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ እንዲሠራ የተሰጠው ፈቃድ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ዕድሜና የሀብቱን ልክ ተመልክቶ ለዕለት ጒዳይ በሚሆን ነገር ላይ ልጁ ብቻውን ውሎችን እንዲያደርግ
ሞግዚቱ ሊፈቅድለት ይችላል፡፡

(2) ይኸውም ፈቃድ በዝምታም መሆን ይችላል፡፡

ቊ 306፡፡ (2) የዕለት ጒዳይ ሥራዎች፡፡

(1) አንድ ሥራ በማናቸውም አኳኋን በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ እንዲታይ ሕግ ሲያዝ የዕለት ጒዳይ ሥራ ሆኖ ሊታይ አይቻልም፡፡

(2) አንድ ሥራ ምንጊዜም ቢሆን፤ ዋጋው ከመቶ የኢትዮጵያ ብር የሚበልጥ ወጪን ወይም ግዴታዎችን እንዲያደርግ አካለመጠን
ያላደረሰውን ልጅ የሚያስገድደው ሲሆን የዕለት ጒዳይ ሥራ ሆኖ ሊታይ አይቻልም፡፡

ቊ 307፡፡ (3) በሞግዚቱ ላይ የሚደርሰው ውጤት፡፡


የሞግዚቱ ፈቃድ፤ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ላደረጋቸው የግዴታ ውሎች ሞግዚቱ ሦስተኞች ወገኖች ሰዎች ለሚጠይቁት ዋስ ነው፡፡
ቊ 308፡፡ ኑዛዜ፡፡
(1) ሞግዚቱ አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ስም ኑዛዜ ሊያደርግ አይችልም፡፡

(2) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ዐሥራ አምስት ዓመት ከሞላው፤ ኑዛዜ ሊያደርግ ይችላል፡፡

(3) አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ዐሥራ አምስት ዓመት ሳይሞላው ያደረገው ኑዛዜ ቢኖር ዐሥራ አምስት ዓመት ከሞላው በኋላ ኑዛዜውን
ባይሽረውም እንኳ ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 309፤ አካለ መጠን ያላደረሱ ሰዎች ጋብቻ፡፡
(1) አካለ መጠን ያላደረሰው ልጅ በጋብቻው ሲስማማ በዚህ ሕግ በጋብቻ አንቀጽ ቊ 562 የተመለከተው ሰው አብሮ መስማማት (ፈቃድ
መስጠት) ይገባዋል፡፡

(2) ለጋብቻ ፈቃድ የሚሰጠው ሰው በእንደራሴ አማካይነት ለመስጠት ይችላል፡፡


(3) አካለ መጠን በዚህ ሕግ በጋብቻ አንቀጽ በቊጥር 562 ከተመለከቱት ሰዎች አንዱ የሆነ እንደሆነ የእንደራሴነት ሥልጣን ያለው
ስለመሆኑ አንዳችም ማስረጃ እንዲያቀርብ አይገደድም፡፡
ቊ 310፤ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች፡፡
ሞግዚቱ አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ ጥቅሞች ለሥራ ማካሄጃ ወጪ ያደረገው ገንዘብ እንዲከፈለው መብት አለው፡፡
ቊ 311፡፡ የሥራው አካሄድ ማስረጃዎች፡፡
(1) ሞግዚቱ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ በወሰነው ሁኔታዎችና ጊዜዎች ውስጥ በሞግዚትነቱ የሠራውን ማስረጃና ሒሳብ ማቅረብ አለበት፡፡

(2) አካለ መጠን ያላደረሰው ልጅ አባት ወይም እናት የሞግዚትነትን ሥራዎች የሠሩ እንደሆነ ከዚህ ግዴታ ነፃ ናቸው፡፡

(3) እነርሱም የመረጡትን ሞግዚት ነፃ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡


ቊ 312፡፡ የሥራው መምራት፡፡
በዚህ ሕግ ከቊጥር 277 እስከ 2 ፹ ያሉት ድንጋጌዎች በሞግዚትነትና በሞግዚቱ ውሳኔዎች በሚደረገው አቤቱታ ላይ ተፈጻሚዎች
ይሆናሉ፡፡
ክፍል 4፡፡
አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ለመጠበቅ የተመለከቱትን ደንቦች መጣስ የሚያስከትለው ቅጣት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ሥራዎች፡፡
ቊ 313፡፡ መሠረቱ፡፡
አካለ መጠን ያላደረሰው ልጅ ከሥልጣኑ በላይ የሚፈጽማቸው ሥራዎች ሁሉ ፈራሽ ይሆናሉ፡፡
ቊ 314፡፡ እንዲፈርስ ስለ መጠየቅ፡፡
(1) እኒህ ተግባሮች እንዲፈርሱ ለመጠየቅ የሚችሉት አካለ መጠን ያላደረሰው ልጅ ወይም ወራሾቹ ወይም እንደራሴዎቹ ናቸው፡፡

(2) በሚከተሉት ድንጋጌዎች መሠረት ከሚሻሻሉት በቀር፤ በስሕተት ስለተሰጠ ፈቃድ ውል ፈራሽነት የተመለከቱት ደንቦች ለዚህም ጒዳይ
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 315፡፡ የተዋዋዩ ቅን ልቡና፡፡
አካለመጠን ካላደረሰው ልጅ ጋራ የተዋዋለ ሰው አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ይህን እንዲያደርግ ፈቃድ የተቀበለ መሆኑን በቅን ልቡና
አምኖ እንደሆነና አካለመጠን ያላደረሰውም ልጅ የልማድ ዕውቀት ስለሌለው ተዋዋዩ የልጁን ጥቅም በማስቀረት ያልተጠቀመበት ከሆነ
አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ያደረጋቸው ውሎች ዋጋ ያላቸው ናቸው፡፡
ቊ 316፡፡ መክፈል፡፡
(1) አካለ መጠን ያላደረሰውን ልጅ የጠቀሙት ለመሆናቸው ማስረጃ የቀረበ እንደሆነና ሥራው እንዲፈርስ ክስ እስከቀረበበት ቀን ድረስ
አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ጥቅም ውስጥ በሚገኘው ብልጽግና መጠን አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ የሚደረጉ የገንዘብ መክፈሎች ዋጋ
ያላቸው ናቸው፡፡

(2) ከዚህ ሁኔታ ውጭ አካለ መጠን ያላደረሰው ልጅ መመለስ የለበትም፡፡

ቊ 317፡፡ ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነትና ያላግባብ ስለ መበልጸግ (1) መሠረቱ፡፡


በዚህ ሕግ ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነትና ያላግባብ ስለ መበልጸግ በተመለከተው አንቀጽ ድንጋጌዎች ላይ በተነገረው መሠረት ሕገ
ወጥ በሆኑ ሥራዎች ወይም ተገቢ ያልሆነ ብልጽግናን በመመልከት የተጠቀመ ሲሆን አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ኀላፊነት አለበት፡፡
ቊ 318፡፡ (2) አካለመጠን ሳያደርስ አድርሻለሁ ማለት፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አካለመጠን አድርሻለሁ ብሎ ቢናገርም እንኳ ይህ መናገሩ አካለመጠን ባለማድረሱ የሚጠቀምበትን
መብት አያሳጣውም፡፡

(2) እንዲሁም ከውል ውጭ የሆነ ኀላፊነትን የሚያመጣ ጥፋት ሆኖ አይቈጠርበትም፡፡


ንኡስ ክፍል 2፡፡ የሞግዚቱ ሥራዎች
ቊ 319፡፡ በደንብ የተፈጸሙ ሥራዎች፡፡
(1) ሥልጣኑ እስከሚፈቅድለት ወይም ፈቃድ ተቀብሎ ሞግዚቱ የፈጸማቸው ሥራዎች አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ የተሠሩ ናቸው በማለት
ሊጣሱ አይቻልም፡፡

(2) አካለመጠን ላላደረሰው ልጅ ሞግዚቱ የሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ልጁ አካለመጠን በአደረሰ ጊዜ እንደሠራቸው ሥራዎች ተቈጥረው
በኀላፊነት ያስጠይቁታል፡፡

(3) ሞግዚቱ በተገለጸ አኳኋን በኀላፊነት እጠየቅበታለሁ ሲል ተስፋ የሰጠበትና ወይም በሕጉ መሠረት ልጁ አካለመጠን ከአደረሰ በኋላም
ሞግዚቱን ያስጠይቁታል ተብሎ የተደነገገ ካልሆነ በቀር ሞግዚቱን ኀላፊ አያደርገውም፡፡
ቊ 320፡፡ ሕጋውያን ድንጋጌዎችን ስለ መተላለፍ፡፡
(1) የሕግ ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ሞግዚት የሚፈጽማቸው ሥራዎች፤ እንደራሴ የሆነ ሰው ከተሰጠው ሥልጣን በላይ አልፎ በሚሠራበት
ጊዜ፤ በዚህ ሕግ ስለ እንደራሴነት በሚል አንቀጽ የተጻፉት ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) እንደዚሁም፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ፈቃድን መቀበል በሕግ ግዴታ ሆኖ ሲገኝ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ሳይፈቅድ ሞግዚቱ
የሚፈጽማቸው ሥራዎች ከዚህ በላይ እንደተነገረው ይሆናሉ፡፡

(3) እንደዚሁም ደግሞ፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ከደንብ ውጭ በሆነ ስብሰባ ወይም ከደንብ ውጭ በሆነ ዐይነት በሰጠው ውሳኔ
ሞግዚቱ የሚፈጽማቸው ሥራዎች ከዚህ በላይ እንደተነገረው ይሆናል፡፡
ቊ 321፡፡ ሕጋውያን ያልሆኑትን ትእዛዞች ስለ መተላለፍ፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ለሞግዚቱ የሰጠውን ሥልጣን ወሰን፤ ሦስተኛ ወገኖች ባስፈላጊው ጊዜ ካላወቁት ወይም ማወቅ ይገባቸው
ካልነበረ በቀር፤ ሞግዚቱ፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፍ የሠራው ነገር በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ
ሊሆንባቸው አይችልም፡፡

(2) አካለመጠን ላላደረሰ ልጅ ንብረቶቹን የሰጠ የተናዘዘ ወይም የተወ ሰው ለሞግዚቱ ሥልጣን ወሰን ባደረገለትም ጊዜ እንደዚሁ ነው፡፡

(3) ሞግዚቱ ያደረገው ሥራ እንዲፈርስ የሚጠይቅ ሰው ሦስተኛ ወገን በክፉ ልቡና የሠራው መሆኑን ማስረዳት አለበት፡፡
ቊ 322፡፡ ስለ ተጨማሪ ሞግዚትና ስለ ምትክ ሞግዚት፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከቱት ደንቦች በተጨማሪ ሞግዚትና በምትክ ሞግዚትም ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
ሊያሲዙ የሚችሉ ኀላፊነቶች፡፡
ቊ 323፡፡ ስለ ሞግዚት፡፡
(1) ሞግዚቱ፤ በሠራው መጥፎ አመራር በመጽናቱ ምክንያት ወይም የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ለሰጠው ትእዛዝ ባለመታዘዙ ምክንያት
ወይም የእርሱ ጥቅም አካለመጠን ካላደረሰ ልጅ ጥቅም ጋራ የሚጋጭ ሲሆን በመሥራቱ አካለመጠን ባላደረሰው ልጅ ለደረሱት ጉዳቶች
ሁሉ በኀላፊነት ይጠየቃል፡፡

(2) ሞግዚቱ በቤተ ዘመድ ጉባኤ በተሰጡት ትእዛዞች መሠረት የሠራ እንደሆነ፤ ተንኰል ካልተገኘበት በቀር በኀላፊነት አይጠየቅም፡፡
(3) ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተነገሩት ድንጋጌዎች በተጨማሪ ሞግዚትና በምትኩ ሞግዚትም ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 324፡፡ ስለ ተጠባባቂ ሞግዚት፡፡
ተጠባባቂው ሞግዚት፤ አንዳች ጥፋት አለመሥራቱን ካላስረዳ በቀር፤ በሞግዚቱ ላይ ስለሚፈረደው ነገር፤ በአንድነት ኀላፊነት ዋስ ነው፡፡
ቊ 325፡፡ የሁኔታ ሞግዚት፡፡
(1) ሞግዚት ሳይሆን፤ የሞግዚትነትን ሥራ የሚፈጽም ሰው፤ በሥራ አካሄድ ደንቦች መሠረት፤ ስለሚያካሂደው ሥራ በኀላፊነት
ይጠየቃል፡-

(2) ሞግዚት ሳይሆን በሠራው ሰው በሚፈረደው ፍርድ ሞግዚቱ ባንድነት ኀላፊ ነው፡፡
ቊ 326፡፡ ስለ ሞግዚቲቱ ባል፡፡
ሞግዚቱ ሆና፤ ከሞግዚትነቷ ጋራ በተያያዘ ሥራ የተደረገውም ተጋብተው በነበረበት ጊዜ የሆነ እንደሆነ፤ የሞግዚቲቱ ባል በእርስዋ ላይ
በሚፈረደው ፍርድ ባንድነት ኀላፊነት ዋስ ነው፡፡
ቊ 327፡፡ ስለ ቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አባሎች፡፡
(1) የማታለል ነገር ካልተገኘባቸው በቀር፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አባሎች በሚሠሩዋቸው ሥራዎች አንዳች ኀላፊነት የለባቸውም፡፡

(2) ነገር ግን፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ፤ ቃለ ጉባኤውን (ፕሮሴቬርባልን) ሲፈርሙ፤ አባሎቹ፤ በሕጉ መሠረት የተጠሩ ለመሆኑና
ውሳኔውንም በሕጉ መሠረት የሰጡ መሆናቸውን በኀላፊነት ያረጋግጣሉ፡፡
ክፍል 5፡፡
አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ችሎታ ማጣት ስለ መቅረቱ፡፡
ቊ 328፡፡ ምክንያቶች፡፡
አካለመጠንን ያላደረሰ ልጅ አካለመጠን ሲያደርስ ወይም ከሞግዚት አስተዳደር ነፄ ይውጣ ሲባል፤ ችሎታ የለውም መባሉ ይቀራል፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ከሞግዚት አስተዳደር ነፃ ስለመውጣት፡፡
ቊ 329፡፡ ጋብቻ፡፡
አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ በጋብቻው ምክንያት ብቻ በሞግዚት ከመተዳደር ነፃ ይወጣል፡፡
ቊ 330፡፡ በተለይ በሞግዚት ከመተዳደር ነፃ ማውጣት (1) ምክንያቶች፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ ዐሥራ አምስት ዓመት ሲሞላው ከሞግዚት አስተዳዳሪነት ሥልጣን ነፃ ለማውጣት ይቻላል፡፡

(2) ለዚሁም፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ውሳኔ ሊሰጥበት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
ቊ 331፡፡ ጥያቄ፡፡
ከሞግዚት አስተዳደር ሥልጣን ለመውጣት ይችላል ብሎ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ውሳኔ የሚሰጠው አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ እርሱ
ራሱ ወይም ከወላጆቹ አንዱ፤ ወይም አሳዳሪው፤ ወይም ሞግዚቱ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ነው፡፡
ቊ 332፡፡ ጥያቄውን ስላለመቀበል፡፡
አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ አባትና እናት ያሉት እንደሆነና ከነርሱ አንዱ፤ ልጁ ከሞግዚት አስተዳደር ሥልጣን ለመውጣት በቅቷል ብሎ
ፈቃዱ መሆኑን በግልጽ ካልተናገረ በቀር፤ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ልጁ ከሞግዚት አስተዳደር ሥልጣን ይውጣ ሲል ለመወሰን
አይችልም፡፡
ቊ 333፡፡ ውጤቶች፡፡
ከሞግዚት አስተዳደር ሥልጣን ይውጣ ተብሎ የተበየነለት ልጅ ሰውነቱን ለማስተዳደርና ገንዘቡን የሚመለከቱትን ጥቅሞች ለማስተዳደር
ስለሚመለከተው ስለማናቸውም ነገር ሁሉ፤ በሕግ አካለመጠን እንዳደረሰ ሆኖ ይቈጠራል፡፡
ቊ 334፡፡ የማይሻር ስለ መሆኑ፡፡
(1) ከሞግዚት አስተዳደር ሥልጣን ይውጣ ተብሎ የተበየነው ሊሻር አይቻልም፡፡

(2) ከጋብቻ ምክንያት የተገኘው ከሞግዚት አስተዳደር ሥልጣን መውጣት ጋብቻው ቢፈርስም እንኳ፤ ውጤቱን እንደጠበቀ ይቀራል፡፡

(3) ነገር ግን፤ ከተጋቡት ባልና ሚስት አንዱ ለጋብቻ የተወሰነው ሕጋዊ ዕድሜ ባለመድረሱ ምክንያት፤ ዳኞች ጋብቻው ይፈርሳል ሲሉ
የፈረዱ እንደሆነ፤ ለተባለው ነገር ተቃራኒ የሆነውን ውሳኔ ለመስጠት ይችላሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
የሞግዚትነት ሥራ ሒሳቦች፡፡
ቊ 335፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) የሞግዚትነቱ ሥራ ሲፈጸም፤ ሞግዚት ሆኖ ለአስተዳደረው ልጅ ወይም ለወራሾቹ የአስተዳደረበትን የሥራ ሒሳብ ማስረጃዎች ሞግዚቱ
ማቅረብ አለበት፡፡

(2) የልጁን ንብረት ሁሉ ይመልስለታል፡፡ ሞግዚት የሆነበትን የልጁን መብትና ሁኔታ የሚገደድባቸውንም ዕዳዎች ያስታውቀዋል፡፡
ቊ 336፡፡ የንብረቶች መዝገብ አለመግባት፡፡
(1) ሞግዚቱ፤ ሥራዎቹን በያዘ ጊዜ ወይም አካመጠን ላላደረሰው ልጅ በውርስ ሀብት በተሰጠው ጊዜ የንብረቶቹን ዝርዝር መዝገብ
ከማግባት ቸል ያለ እንደሆነ፤ የልጁን ንብረት ወይም ልጁ በውርስ ያገኘውን ሀብት በማናቸውም አደራረግ ለማስረዳት ይቻላል፡፡

(2) ተቃራኒ የሚሆን አስረጂ ካልተገኘ በቀር በቂ ምስክሮች በሚያረጋግጡት ቃል አንድ ንብረት አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ገንዘብ
በመሆን ይቈጠራል፡፡
ቊ 337፡፡ ሒሳቦችን ስለ መጽደቅ፡፡
(1) በሞግዚት የሚተዳደረው ልጅ የሞግዚትነቱን ሥራ ሒሳቦች ያጸደቀ እንደሆነ ሒሳቦቹን ካጸደቀ በኋላ እስከ አንድ ዓመት ድረስ፤
አትድቆት የነበረውን ሒሳብ ራሱ ሊያፈርሰው ይችላል፤ ይህም ሊሆን የሚቻለው ልጁ ዐሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ሆኖ በሚገኝበት
ጊዜ ሁሉ ነው፡፡

(2) በሞግዚት የሚተዳደረው ልጅ ሒሳብ እንዳይቀርብ ለሞግዚት ፈቃድ ቢሰጠውም ከዚህ በላይ የተጻፈው ኀይለ ቃል ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡
(3) አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ አካለመጠን ያደረሱት ሲወርሱት፤ እነዚህ አካለመጠን ያደረሱት ወራሾች የልጁ ሞግዚት ያደረገውን
ሒሳብ ያጸደቁት እንደሆነ ወይም ሞግዚቱን ከመተሳሰብ ነፃ አውጥተው እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ በሁለቱ ኀይለ ቃሎች የተነገሩት ድንጋጌዎች
ለመጠቀስ አይችሉም፡፡
ቊ 338፡፡ ስለ ይርጋ፡፡
(1) አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ፤ ወኪሎቹ ወይም ወራሾቹ በሞግዚትነቱ ሥራ ምክንያት በሞግዚቱ ላይ ስለ ኀላፊነት የሚያቀርቧቸው
ማንኛዎችም ክሶች፤ ሞግዚቱ የሞግዚትነቱን ሥራ ከተወበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አምስት ዓመት ሳያቀርቡ የቀሩ እንደሆነ በይርጋ ይታገዳሉ፡፡

(2) ስለሆነም የተባለው ጊዜ ካለፈ በኋላ አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ንብረቶች እንዲመለሱለት የመጠየቅ፤ ወይም በማይገባ በተደረገው
(በተገኘው) ብልጽግና ላይ የሚሆነው ክስ የማቅረብ መብቱ አይከለከልበትም፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
አእምሮዋቸው ስለ ጐደለ ሰዎችና ስለ ድውዮች፡፡
ቊ 339፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) አእምሮው ጐድሎ ነው የሚባለው በተፈጥሮ ዕውቀቱ ያልተስተካከለ በመሆኑ፤ ወይም በአእምሮ መናወጥ ወይም በእርጅና ምክንያት
የሚሠራው ሥራ የሚያደርሰውን ለማወቅ የማይችል ነው፡፡

(2) የአእምሮ ደካሞች ሰካራም ወይም በመጠጥ፤ አፍዛዥ በሆኑ ነገሮች ልማድ የተመረዙና ገንዘብን ያለ አግባብ የሚያባክኑ ሰዎች የተገኙ
እንደሆነ፤ አእምሮዋቸው እንደጐደለ ሰዎች ይቈጠራሉ፡፡
ቊ 340፡፡ ድውዮች፡፡
ድዳ፤ ደንቆሮ፤ ዕውር፤ የሆኑና ነዋሪ በሆነ ደዌ ምክንያት፤ ራሳቸውን ችለው ለመተዳደር ወይም ንብረታቸውን ለማስተዳደር ችሎታ
ለሌላቸው ሰዎች፤ ስለ አእምሮ ጐደሎዎች የተነገሩትን እርዳታዎች ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡
ክፍል 1፡፡
ችሎታ ስላልተከለከሉት የአእምሮ ጐደሎዎችና ድውዮች፡፡
ቊ 341፡፡ በግልጽ ስለ ታወቀ የአእምሮ ጒድለት፤ (1) የተዘጋበት ዕብድ፡፡
ዕብደቱ በግልጽ እንደታወቀ ሆኖ ሕግ የሚቈጥረው ይህ የተባለው ሰው በሆስፒታል ውስጥ ወይም በአንድ የዕብዶች መኖሪያ ቦታ ውስጥ
ወይም በአእምሮ ሁኔታ ምክንያት በአንድ የጤና ጥበቃ ቤት ውስጥ ተዘግቶበት፤ በዚህ በተዘጋበት ቦታ እስከሚቈይበት ጊዜ ነው፡፡

ቊ 342፡፡ (2) ስለ ገጠር የቀበሌ ግዛቶች፡፡


እንዲሁም ከሁለት ሺህ የማያንሱ ነዋሪዎች በሚገኙባቸው የቀበሌ ግዛቶች ውስጥ አንድ ሰው በቤተ ዘመድ ወይም አብሮዋቸው በሚኖር
ሰዎች በኩል፤ በአእምሮው ሁኔታ ምክንያት የግድ የሚያስፈልግ ተጠባባቂነት የሚደረግለት ሆኖ ሲገኝና ከእርሱ ጋራ የሚኖሩት ሰዎች
በተባለው ሁኔታው ምክንያት ለመዛወሩ ፈቃድ ወሰን ሰጥተውት ሲገኙ ይህ ሰው ዕብደቱ በግልጽ እንደታወቀ ሆኖ የሚቈጠር ነው፡፡

ቊ 343፡፡ በግልጽ የታወቀ ዕብድ ስለሚሠራቸው ሥራዎች፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ዕብደቱ ግልጽ በሆነበት ጊዜና ቦታ ላይ የሠራቸውን ሥራዎች እርሱ ወይም ወኪሎቹ ወይም ወራሾቹ ሊቃወሟቸው ይችላሉ፡፡

(2) እንደዚሁም አንድ ሰው ራሱን ችሎ ለመተዳደር ወይም ንብረቶቹን ለማስተዳደር ችሎታ የሚያሳጣው ድውይነቱ ግልጽ በሆነ ጊዜ
ስለሠራቸው ሥራዎች ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተጻፈው ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 344፡፡ (2) በሥራ ላይ ስለ ማዋል፡፡

(1) ተቃራኒ የሚሆን አስረጂ ከሌለ በቀር የነዚህ ሰዎች ሥራና ፈቃድ የውለታን ፈራሽነት የሚያስከትል ጒድለት ያለበት ነው ተብሎ
የሚገመት ነው፡፡

(2) በስሕተት መገኘት ምክንያት የሥራዎችንና የውሎችን መፍረስ የሚመለከቱት የዚህ ሕግ ደንቦች በዚህ አስተያየት ላይ ተፈጻሚዎች
ይሆናሉ፡፡
ቊ 345፡፡ ስለሚመጣው ኀላፊነት፡፡ (1) የሥረ ነገሩ ደንቦች፡፡
ዕብድ የሆነ ሰው ከእርሱ ጋራ የተደረጉት ውሎች በመፍረሳቸው ምክንያት፤ በቅን ልቡና በተዋዋዮች ሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው
ጉዳት ኀላፊ ይሆናል፡፡

ቊ 346፡፡ (2) ስለ ማስረጃ፡፡

(1) ተቃራኒ የሚሆን ማስረጃ ከሌለ በቀር የሦስተኛ ወገኖች ቅን ልቡና አለ በመባል ይገመታል፡፡

(2) ስለሆነም ሦስተኛ ወገኖች ማናቸውንም ተቃራኒ ማስረጃ ቢያቀርቡም እንኳ ዕብድ የሆነው ሰው ባለበት አንድ ቀበሌ ውስጥ፤ ወይም
በዚሁ ቀበሌ አዋሳኝ ውስጥ የሚኖሩ ለመሆናቸው የተገለጸ እንደሆነ፤ በዚህ አንቀጽ በቊጥር 342 የተመለከተው ነገር ሲያጋጥም፤ በክፉ
ልቡና ያደረጉት ለመሆናቸው በቂ ማስረጃ ነው፡፡
ቊ 347፡፡ ዕብደቱ በግልጽ ስላልታወቀ ሰው፡፡
(1) የዕብደቱ ሁኔታ፤ በግልጽ ያልታወቀ ሰው የፈጸማቸው የሕግ ሥራዎች ውሎች በዚሁ ሰው የአእምሮ ጒድለት ምክንያት ሊሻሩ
አይችሉም፡፡
(2) ዕብድ የሆነው ሰው፤ እነዚህን ውሎች በፈጸመበት ጊዜ ጒድለት የሌለበትን ፈቃድ ለመስጠት በማይችልበት ሁኔታ እንደነበረ
ለማስረዳት ከቻለ ውሎቹን ለማስፈረስ ይቻላል፡፡

ቊ 348፡፡ ስለ ወራሾችና ስለባለገንዘቦች፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


ዕብደቱ በግልጽ ያልታወቀው ሰው ወራሾች ወይም ባለገንዘቦች፤ ይህ ሰው ለፈጸመው ውል ጒድለት የሌለበት ፈቃድ ቃል አልሰጠበትምና፤
ውሉ ሊፈርስ ይገባዋል ሲሉ ዕብደቱን ምክንያት በማድረግ፤ የውሉን መፍረስ ለመጠየቅ አይችሉም፡፡

ቊ 349፡፡ (2) ልዩነት፡፡

(1) ስለሆነም፤ የዚህ የውል አድራጊው የአእምሮ ጒድለት ከተደረገው የውል ቃል የተነሣ የሚታወቅ እንደሆነ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር
የተነገረው ደንብ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

(2) እንዲሁም ውል አድራጊው ውል እንዳይፈጽም የክልከላ ጥያቆ ቀርባበት እንደሆነ ጥያቄው የቀረበው፤ የተባለው ውል ከተደረገ በኋላ
ቢሆንም እንኳ፤ ዳኞቹ ስለ ክልከላው በቀረበው ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ከመቻላቸው በፊት ውል እንዳያደርግ ይከልከል ተብሎ ጥያቄ
የቀረበበት ሰው ቀድሞ ካልሞተ በቀር የተባለው ደንብ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
ቊ 350፡፡ ከውል ውጭ ስለ ሆነ ኀላፊነት፡፡
(1) ዕብደቱ በግልጽ ለታወቀው ሰው ያለበት ከውል ውጭ የሆነ ኀላፊነት ለጤናማ ሰው እንዳለው ኀላፊነት ነው፡፡

(2) እንዲሁም ይህ ዕብድ ያለ አግባብ ካገኘው ብልጽግና የተነሣ ላሉት ግዴታዎች ጤናማ ለሆነ ሰው ያሉበት ግዴታዎች ይኖሩበታል፡፡
ክፍል 2፡፡
በፍርድ ስለሚደረግ ክልከላ፡፡
ቊ 351፡፡ ስለ ክልከላ የሚሰጠው ፍርድ፡፡
(1) መከልከሉ ለጤናውና ለጥቅሙ የሚያስፈልግ ሆኖ ሲገኝ ዕብድ ሰው እንዲከለከል (እንዲጠበቅ) ዳኞች ፍርድ ለመስጠት ይችላሉ፡፡

(2) እንደዚሁም፤ ስለ ዕብዱ ሰው ወራሾች ጥቅም ዳኞች የዕብዱን መከልከል ለመፍረድ ይችላሉ፡፡

(3) እንደዚሁም ደግሞ፤ በዚሁ አንቀጽ በቊጥር 3 ፵ በተመለከቱት ሰዎችም ላይ የመከልከል ፍርድ ሊሰጥ ይቻላል፡፡
ቊ 352፡፡ ግልጽ የሆነ የዕብድነትን ስለ ማስታወቅ፡፡
(1) ዳኞቹ ስለ አንዳንድ ሰው መከልከል ፍርዳቸውን ሲሰጡ፤ በሚሰጡት ውሳኔ ውስጥ ጊዜውን በመወሰን የተባለው ሰው ዕብደት
የጀመረው ከእንደዚህ ያለው ጊዜ ጀምሮ ነው ሲሉ ለማስታወቅ ይችላሉ፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተው ውሳኔ ስለ ክልከላው ከተሰጠው ፍርድ በኋላ ሊፈጸም ይችላል፡፡

(3) በተሰጠው ውሳኔ ውስጥ የተቈረጠው ቀን ስለ ክልከላው ከቀረበው ጥያቄ በፊት ከሁለት ዓመት የበለጠ ጊዜ ሊኖረው አይችልም፡፡
ቊ 353፡፡ ለክልከላው ስለሚቀርብ ጥያቄ፡፡
(1) ስለ ክልከላው ውሳኔ እንዲሰጥ፤ ዕብድ የሆነው ወይም ድውዩ እርሱ ራሱ፤ ወይም ከባልና ሚስት አንዱ ወይም ከሥጋ ወይም ከጋብቻ
ዘመዶች አንዱ ወይም ዐቃቤ ሕጉ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

(2) የክልከላው ፍርድ የሚከለክለው ሰው አካለ መጠን ከማድረሱ በፊት ሊሰጥ ይቻላል፡፡

(3) ስለሆነም እንዲከለከል ጥያቄ የቀረበበት ሰው ከሞተ በኋላ የክልከላ ፍርድ አይሰጥም፡፡
ቊ 354፡፡ ስለ ክልከላው አደራረግ ሥነ ሥርዐት፡፡
(1) ዳኞቹ የአንዱን ሰው መከልከል ከመፍረዳቸው በፊት፤ ይህን ክልከላ ለማድረግ የግድ አስፈላጊ መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡

(2) እንዲከለከል ጥያቄ የቀረበበትን ሰው እነርሱ ራሳቸው ሳያዩት እንዲከለከል አስቀድመው ለመፍረድ አይችሉም፡፡

(3) ይከልከል የሚባለው ሰው እርሱ ራሱ ለመቅረብ የማይቻለው እንደሆነ፤ ዳኞቹ ከነርሱ መካከል አንዱን በመላክ፤ ወይም አንዱን ልዩ
ዕውቀት ያለውን ሰው በመላክ ነገሩን ይመራመራሉ፡፡
ቊ 355፡፡ አቤቱታ፡፡
አእምሮው ጐደሎ ወይም ድውይ የሆነው ሰው እርሱ ራሱ፤ ከባልና ሚስት ደኅነኛው፤ ከሥጋ ወይም ከጋብቻ ዘመዶቹ አንዱ፤ ወይም
ዐቃቤ ሕግ፤ ዳኞቹ ስለ ክልከላ በሰጡት ፍርድ ላይ አቤቱታ ለማቅረብ ይችላሉ፡፡
ቊ 356፡፡ በፍርድ የተከለከሉ ሰዎች መዝገብ፡፡
(1) በፍርድ ቤቱ ሥልጣን ውስጥ ሆነው የክልከላ ፍርድ የተፈረደባቸውን ሰዎች ሁሉ የስም ዝርዝር የያዘ ልዩ የሆነ መዝገብ፤ በያንዳንዱ
ጠቅላይ ግዛት የፍርድ ቤት መዝገብ ቤት መኖር አለበት፡፡

(2) መዝገቡም ሰዎቹ የሚለዩባቸውን ማስታወቂያዎችና ክልከላውን ስለሚመለከት ጒዳይ የተሰጠውን ፍርድ ወይም የተሰጡትን ፍርዶች
የሚገልጹ ማስታወቂያዎች ብቻ ይጻፉበታል፡፡
ቊ 357፡፡ ፍርዱን ስለ ማስታወቅ፡፡
(1) የተከለከለው ሰው በሚኖርበት ጠቅላይ ግዛት ቦታ ወይም በሚኖርባቸው ጠቅላይ ግዛቶች፤ ወይም ተቀማጭ ሆኖ እንዲኖርበት
በተጠራበት ስፍራ ለሚገኘው ፍርድ ቤት መዝገብ ቤት፤ አሳሳቢ በመሆን የሚሰጠውን ፍርድ የሚያስታውቅ፤ የተከለከለው ሰው አሳዳሪ
ነው፡፡

(2) ደግሞ የክልከላውን ውጤቶች ስለ መለዋወጥ የሚሰጠውን ማናቸውንም ፍርድ ከዚህ በላይ እንደተነገረው የሚያስታውቅ አሳዳሪው
ነው፡፡
ቊ 358፡፡ ለተከለከለው ሰው ስለሚደረገው ጥበቃ፡፡
ከዚህ ቀጥለው ያሉት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ ለተከለከለው ሰው የሚደረገው ጥበቃ አካለመጠን ስላላደረሰው ልጅ ሰውነትና
ንብረቶች አጠባበቅ በተሰጠው ደንብ ዐይነት ነው፡፡
ቊ 359፡፡ ስለ አሳዳሪና ስለ ሞግዚት፡፡
(1) ለተከለከለው ሰው አሳዳሪና ሞግዚት የሚሆኑትን በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን የሚሾሟቸው ዳኞች ናቸው፡፡

(2) ከባል ወይም ከሚስት ወደ ላይ ከሚቈጠሩ ወላጆቹ ወይም ከተወላጆቹ ልጆች በቀር ማንኛውም ቢሆን የዕብዱን ሰው የአሳዳሪነትን
ወይም የሞግዚትነትን ሥራ ከአምስት ዓመት የበለጠ ይዞ ለመኖር አይገደድም፡፡

ቊ 360፡፡ ስለ ቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ፡፡ (1) ስለ አቋቋሙ፡፡

(1) አካለመጠን ያላደረሰውን ልጅ የቤተ ዘመድን ምክር ጉባኤ ስለሚመለከት ጒዳይ፤ በዚህ አንቀጽ የተሰጡት ድንጋጌዎች ስለ ተከለከለው
ሰው ተፈጻሚዎች አይሆኑም፡፡

(2) በተከለከለው ሰው ምክር ጉባኤ የሚገኙት ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆቹ አካለመጠን ያደረሱ ወንድሞቹና እኅቶቹ፤ ባል ወይም ሚስትና
አካለመጠን ያደረሱት ተወላጆቹ ናቸው፡፡

(3) በዚህ አኳኋን የተቋቋመው የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አራት አባሎች ያልተገኙበት እንደሆነ፤ ዳኞቹ ለዚህ ለተከለከለው ሰው ዕድል
አሳቢ ከሆኑት ከዘመዶቹ ወይም ዘመዶቹ ካልሆኑት ሰዎች ጠርተው የጐደለውን የአባሎቹን ቊጥር ይሞላሉ፡፡

ቊ 361፡፡ (2) የስብሰባው ቦታ፡፡


(1) የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ መሰብሰቢያ፤ ዳኞቹ በወሰኑት ቦታ ላይ ነው፡፡

(2) እንደዚህ ያለው ቦታ የሌለ ሲሆን ቤተ ዘመድ ለምክር የሚሰበሰብበት፤ የተከለከለው ሰው የክልከላው ፍርድ በተሰጠበት ቀን
በሚገኝበት ሕጋዊ መኖሪያ ቦታው ላይ ነው፡፡
ቊ 362፡፡ የተከለከለው ሰው መኖሪያ ቦታ፡፡
(1) የተከለከለው ሰው አሳዳሪ፤ ይህ የተከለከለ ሰው፤ ችሎታ የሌለው ለመሆኑ በሕግ መሠረት ማስታወቂያ በወጣበት ቦታ ተቀማጭ ሆኖ
እንዲኖር መጠባበቅ አለበት፡፡

(2) የተከለከለው ሰው መኖሪያ ቦታውን የለወጠ እንደሆነ፤ አሳዳሪው፤ እንዲደረግ የሚጠይቀው ማስታወቂያ በአዲሱ መኖሪያ ቦታው
እንዲነገር ያደርጋል፡፡
ቊ 363፡፡ ስለ ተከለከለው ሰው ገቢ ገንዘብ፡፡
(1) የተከለከለው ሰው ገቢ ገንዘብ፤ የአሳዳሪው ሀብት አይሆንም፡፡

(2) የተከለከለው ሰው መኖሪያ ቦታውን የለወጠ እንደሆነ፤ አሳዳሪው፤ እንዲደረግ የሚጠይቀው ማስታወቂያ በአዲሱ መኖሪያ ቦታው
እንዲነገር ያደርጋል፡፡
ቊ 364፡፡ አሳዳሪው ባደረጋቸው ውሳኔዎች ላይ አቤቱታ ስለ ማቅረብ፡፡
በማናቸውም ሁኔታ የተከለከለው ሰው አሳዳሪ ባደረጋቸው ውሳኔዎች ላይ ማናቸውም የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ አባል ለቤተ ዘመድ ምክር
ጉባኤ አቤቱታ ሊያቀርብላቸው ይችላል፡፡
ቊ 365፡፡ የተከለከለው ሰው አባት ወይም እናት፡፡
አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ሞግዚት፤ አባቱ ወይም እናቱ ሲሆኑ ስለእነሱ ልዩ አስተያየት የሚሰጡት ድንጋጌዎች ለተከለከለው ሰው
ሞግዚት ተፈጻሚዎች አይሆኑም፡፡
ቊ 366፡፡ የኪራይ ውል፡፡
ሞግዚት ያደረጋቸው የኪራይ ውሎች፤ በቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ ፈቃድ ካልተደረጉ በቀር፤ የተከለከለው ሰው የችሎታ ማጣቱ ሁኔታ
ከቀረ በኋላ የሚያስገድዱት እስከ 3 ዓመት ብቻ ነው፡፡
ቊ 367፡፡ ስጦታዎች፡፡
(1) የተከለከለው ሰው ሞግዚት፤ በዚህ በተከለከለው ሰው ስም፤ ለተከለከለው ሰው ተወላጆች ልጆች ስጦታ ለማድረግ ይችላል፡፡

(2) እነዚህ ስጦታዎች በተከለከለው ሰው ቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የተፈቀዱ ካልሆኑ በቀር ፈራሾች ናቸው፡፡
ቊ 368፡፡ ኑዛዜ፡፡
(1) የተከለከለ ሰው ክልከላው በፍርድ ከተነገረ በኋላ ኑዛዜ ለማድረግ አይችልም፡፡

(2) ከተከለከለበት ቀን በፊት የተናዘዘው ኑዛዜ ይጸናል፡፡

(3) ነገር ግን የኑዛዜው ድንጋጌዎች ለርትዕ ነገር ተቃራኒ መስለው ለዳኞቹ የታዩዋቸው እንደሆነና የናዘዘውም የጤናው ሁኔታ ያስደረገው
መስሎ የታያቸው እንደሆነ ዳኞቹ ኑዛዜውን በሙሉ ወይም በከፊል ፈራሽ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
ቊ 369፡፡ ጋብቻ፡፡
(1) በፍርድ የተከለከለ ሰው ዳኞች ካልፈቀዱለት በቀር የጋብቻ ውል መዋዋል አይችልም፡፡

(2) ስለዚህ ጒዳይ የሚቀርበውን ጥያቄ የተከለከለው ሰው ራሱ ወይም አሳዳሪው ሊያደርግ ይችላል፡፡

(3) ማንኛውም ባለጥቅም ሁሉ የተከለከለው ሰው ከዳኞች ሳያስፈቅድ ያደረገው የጋብቻ ውል እንዲፈርስ ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል፡፡
ቊ 370፡፡ ስለ ፍችና ልጅን ስለ መካድ፡፡
(1) ፍቺ ወይም ከሕግ ውጭ የሚደረገው የገብረ ሥጋ ግንኙነት እንዲቀር ጥያቄ ለማቅረብ፤ የተከለከለው ሰው ፈቃድ የግድ አስፈላጊ
እንደሆነ ያሳዳሪውም ፈቃድ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡

(2) የተከለከለ ሰው ልጅን የሚክድበት ሁኔታ በዚህ ሕግ ስለ ሥጋ ዝምድናና ስለ ጋብቻ ዝምድና በተነገረው አንቀጽ ውስጥ ተገልጾ
ተመልክቷል፡፡
ቊ 371፡፡ የክልከላን ውጤቶች ስለ ማጥበብ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ዳኞች የክልከላን ፍርድ ሲሰጡ፤ ወይም ይህን ውሳኔ ከሰጡ በኋላ የክልከላውን ውጤቶች ለማጥበብ ይችላሉ፡፡

(2) ለተከለከለው ሰው እርሱ ራሱ አንዳንዶቹን ውሎች እንዲያደርግ ሊፈቅዱለት ይችላሉ፡፡

(3) እንደዚሁም ከተከለከለው ሰው ጋራ አንድነት ካልሆነ በቀር አንዳንዶችን ውሎች ሞግዚቱ ለብቻው ለመፈጸም አይችልም ሲሉ ዳኞቹ
ለመከልከል ይችላሉ፡፡

ቊ 372፡፡ (2) የማጥበቡ ውጤቶች፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር መሠረት ለተከለከለው ሰው ሞግዚት የተደረገው የሥልጣን ማጥበብ ከሞግዚቱ ጋራ በቅን ልቡና
ለተዋዋሉ ለሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ለመሆን አይችልም፡፡

(2) ተቃራኒ የሚሆን አስረጂ ካልተገኘ በቀር ሦስተኛ ወገኖች በቅን ልቡና እንደተዋዋሉ ይገመታል፡፡
ቊ 373፡፡ የተከለከለው ሰው ስላደረጋቸው ውሎች ፈራሽነት፡፡
(1) የተከለከለው ሰው የፈጸማቸውንና ከሥልጣኑ በላይ የሆኑትን ሥራዎች አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ያደረጋቸውን ሥራዎች
ለመቃወም በሚቻልበት አኳኋን ለመቃወም ይቻላል፡፡

(2) አእምሮው የጐደለ ሰው አእምሮው መለስ ባለለት ጊዜ የፈጸማቸው ውሎች ናቸው፡፡ በማለት፤ ዳኞቹ የእነዚህን ውሎች ውጤት
ለማጽደቅ አይችሉም፡፡

ቊ 374፡፡ የተከለከለው ሰው ሞግዚት ስላለበት ኀላፊነት (1) መሠረቱ፡፡


የተከለከለው ሰው፤ ችሎታ የሌለው መሆኑን ከማያውቅ ቅን ልቡና ካለው ሰው ጋራ ውል ያደረገ እንደሆነ ውሉ በመፍረሱ ምክንያት በዚህ
በቅን ልቡና በተዋዋለው ሰው ላይ ስለሚደርሰው ጉዳት የተከለከለው ሰው አሳዳሪ በኀላፊነት ይጠየቃል፡፡

ቊ 375፡፡ (2) ቅን ልቡና፡፡


ከተከለከለው ሰው ጋራ ያደረገው ውል በሕጉ መሠረት ክልከላው በተገለጸበት ጠቅላይ ግዛት ውስጥ የሆነ እንደሆነ ውሉን የሚፈርመው
ሰው በማናቸውም አኳኋን በቅን ልቡና እንዳደረገው አይቈጠርም፡፡
ቊ 376፡፡ ስለ መዝገብ ቤት ሹም ኀላፊነት፡፡
(1) የፍርድ ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹም ስለ ክልከላ የተሰጠውን የፍርድ ማስታወቂያ ከተቀበለ በኋላ የተከለከለውን ሰው ስም በተለይ ስለዚሁ
ጒዳይ በተዘጋጀው መዝገብ ውስጥ ሳያገባ የቀረ እንደሆነ የዚህ ኀላፊነት የተከለከለው ሰው አሳዳሪ መሆኑ ቀርቶ የመዝገብ ቤቱ ሹም
ይሆናል፡፡

(2) ከተከለከለው ሰው ጋራ የተዋዋለውን ሦስተኛ ወገን መዝገብን እንዳያይ የከለከለ እንደሆነም እንደዚሁ ኀላፊ ይሆናል፡፡

ቊ 377፡፡ ስለ ክልከላው መቅረት (መነሣት)፡፡ (1) ስለሚቀርበው ጥያቄ

(1) ስለ ክልከላ የተሰጠው ፍርድ ሲሻር የችሎታ ማጣት ፍጻሜ ይሆናል፡፡


(2) አእምሮው ከጐደለው ሰው በቀር ስለ ክልከላው ፍርድ እንዲሰጥ ለመጠየቅ የሚችሉ ሰዎች በማናቸውም ጊዜ የክልከላው ውሳኔ
እንዲቀር ለዳኞች ጥያቄ ለማቅረብ ይችላሉ፡፡

(3) እንደዚሁም የተከለከለው ሰው አሳዳሪ ወይም ሞግዚት የክልከላው ውሳኔ እንዲቀር ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቊ 378፡፡ (2) ውሳኔ፡፡


ክልከላው እንዲወሰን ያስደረጉት ምክንያቶች በቀሩ ጊዜና የተከለከለውም ሰው ንብረቱን ለመምራትና ለማስተዳደር የሚችል የሆነ እንደሆነ
ዳኞች የክልከላውን ውሳኔ ማስቀረት ማንሣት አለባቸው፡፡

ቊ 379፡፡ (3) ውጤቶች፡፡


የክልከላው ውሳኔ መቅረት አካለመጠን ያላደረሰው ልጅ ከሞግዚት አስተዳደር መውጣት ያለው ውጤት ይኖረዋል፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
በሕግ ስለ ተከለከሉ ሰዎች፡፡
ቊ 380፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) በሕግ የተከለከለ ሰው ማለት አንድ የተቀጣ ሰው በመቀጣቱ ምክንያት ንብረቶቹን እንዳያስተዳድር ሕግ የከለከለው ነው፡፡

(2) አንድ ሰው በሕግ እንደተከለከለ ሆኖ የሚቈጠርባቸው ሁኔታዎች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ተወስነዋል፡፡


ቊ 381፡፡ በሕግ ስለሚወሰነው ክልከላ አስተዳደር፡፡
ከዚህ ቀጥለው ባሉት ድንጋጌዎች ከተወሰኑት መለያየቶች በቀር በሕግ የሚደረገው የክልከላ አስተዳደር በፍርድ ከሚሰጠው የክልከላ
አስተዳደር ጋራ አንድ ዐይነት ነው፡፡
ቊ 382፡፡ አሳዳሪ ስላለመኖሩ፡፡
በሕግ ለተከለከለው ሰው አሳዳሪ የለውም፡፡
ቊ 383፡፡ ስለ ሞግዚት፡፡ (1) ስለ መመረጡ፡፡

(1) በሕግ የተከለከለው ሰው የንብረቶቹ አስተዳደር ዳኞች ለመረጡት ሞግዚት ይሰጣል፡፡

(2) ዳኞች የመረጡት ሞግዚት ወይም ከባልና ሚስት አንዱ ወይም ከተከለከለው ሰው ዘመዶች አንዱ ወይም ዐቃቤ ሕግ በሚያቀርቡት
ጥያቄ መሠረት በሞግዚቱ ምትክ ሌላ ሞግዚት ሊደረግ ይቻላል፡፡
ቊ 384፡፡ ሥራዎቹን መቀበል በፈቃድ ስለ መሆኑ፡፡
(1) በሕግ የተከለከለውን ሰው የሞግዚትነት ሥራዎች መቀበል የፈቃድ ነው፡፡

(2) እነዚህን ሥራዎች ፈቅዶ የተቀበለው ሰው፤ ዳኞቹ በሚያመዛዝኑት ትክክለኛ ምክንያት ካልሆነ በቀር፤ በእርሱ ምትክ ሌላ ሞግዚት
እንዲተካለት ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(3) ሥራዎቹን አምስት ዓመት ወይም ከዚህ የበለጠ አካሂዶ እንደሆነ ሞግዚቱ የሚያቀርበውን ጥያቄ መቀበል ያስፈልጋል፡፡
ቊ 385፡፡ የቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ፡፡
በፍርድ ክልከላ በተደረገ ጊዜ ለቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የተሰጠው ሥልጣን በሕግ ሲደረግ ዳኞች ይሠሩበታል፡፡
ቊ 386፡፡ በቤተ ዘመድ ሕግ ረገድ ስላሉት ሥራዎች፡፡
(1) በሕግ ክልከላ የተከለከለው ሰው ጋብቻን ለማድረግ፤ ወይም አንድ ዲቃላ ልጅን የኔ ነው ሲል ለማወቅ ይችላል፡፡

(2) እንደዚሁም ፍቺን ለመጠየቅ ወይም ልጅን ለመካድ በሚመለከት ጒዳይ፤ ክስን ለማቅረብ ይችላል፡፡
(3) ሞግዚቱ በሕግ በተከለከለው ሰው ስም እነዚህን ሥራዎች ለመፈጸም አይችልም፡፡
ቊ 387፡፡ የተከለከለው ሰው ሥራዎች ፈራሾች ስለ መሆናቸው፡፡
(1) በሕግ የተከለከለው ሰው ያደረጋቸው ሥራዎች ውሎች ከሥልጣኑ በላይ የሆኑ እንደሆነ፤ ፈራሾች ናቸው፡፡

(2) እነዚህ ሥራዎች እንዲፈርሱ ሥራው ከሕግ ውጭ በሆነ ጊዜ በሚደረገው አኳኋን በሕግ የተከለከለው ሰው፤ ከእርሱ ጋራ የተዋዋለው
ወይም ዐቃቤ ሕግ ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 388፡፡ ስለ ክልከላው ፍጻሜ፡፡
በሕግ የተከለከለው ሰው ችሎታ ማጣትን ያስከተለበትን ቅጣት በፈጸመ ጊዜ በሕግ የተወሰነበት ክልከላ ቀሪ ይሆንለታል፡፡
ምዕራፍ 5፡፡
ስለ ውጭ አገር ሰዎች፡፡
ቊ 389፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ስለ መቈጠር፡፡
(1) በፍትሐ ብሔር መብቶች የመሥራትንና የመጠቀም ችሎታን በሚመለከት ረገድ የውጭ አገር ዜጋ እንደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(2) እንደ ፍትሐ ብሔር መብቶች የሚቈጠሩትም ከመንግሥቱ ወይም ከአገሩ የአስተዳደር ሥራ ጋራ ተካፋይ መሆንን የማይመለከቱ
ማናቸውም መብቶች ናቸው፡፡

(3) የውጭ አገር ሰው በኢትዮጵያ ሥራ እንዲሠራ ፈቃድ መስጠት ሕጎች ወይም ደንቦች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 390፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ባለሀብትነትን ስለሚመለከቱ የተጠበቁ ሁኔታዎች (1) መሠረቱ፡፡


ማንኛውም የውጭ አገር ሰው ከንጉሠ ነገሥቱ በሚሰጥ ትእዛዝ መሠረት ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት ሊሆን
አይችልም፡፡
ቊ 391፡፡ (2) እንዲሸጥ ስለ ማስገደድ፡፡
ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በቊጥር 3 ፺ በተመለከተው፤ ከንጉሠ ነገሥቱ በሚሰጥ ትእዛዝ ውጭ በሆነ አኳኋን በቅን ልቡና
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ አግባብ ያላቸው ባለሥልጣኖች በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ ርስቱን ለኢትዮጵያዊ
እንዲያስተላልፍ ሊያስገድዱ ይችላሉ፡፡

ቊ 392፡፡ (3) ቅጣት፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተወሰነው 6 ወር ጊዜ ውስጥ የውጭ አገሩ ዜጋ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሳያስተላልፍ የቀረ
እንደሆነ ንብረቱ በመንግሥት ባለሥልጣኖች ጠያቂነት ተይዞ ይሸጣል፡፡

(2) ስለማይንቀሳቀሰው ንብረት መሸጫ ለተደረገው ወጪና ደንብን በመተላለፍ ለተደረገው ሥራ መቀጫ የሚሆን ከመቶ ሓያ ተቀንሶ
የማይንቀሳቀሰው ንብረት የሽያጭ ዋጋ ለውጭ አገሩ ሰው ይመለስለታል፡፡

(3) የውጭ አገሩ ሰው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት ያገኘው በወራሽነት ምክንያት በሆነ ጊዜ ተቀናሹ በመቶ ዐሥር ብቻ ነው፡፡
ቊ 393፡፡ ከባለሀብትነት ጋራ ተመሳሳይ የሆኑ መብቶች፡፡
አንድ የውጭ አገር ሰው በኢትዮጵያ የሚገኝ አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከኀምሳ ዓመት ለበለጠ ጊዜ ወይም አንድ የተወሰነ ሰው በዕድሜ
እሰከሚቈይበት ዘመን ድረስ በዚህ በማይንቀሳቀስ ሀብት ላይ የመገልገል ወይም የመጠቀም መብት የሚያገኝባቸው ውሎች ሁሉ
የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለሀብትነት እንደሚያስተላልፉ ወሎች ይቈጠራሉ፡፡

አንቀጽ ሦስት፡፡
በሕግ የሰው መብት ስለ ተሰጣቸው ማኅበሮችና ለልዩ አገልግሎት ስለ ተመደቡ ንብረቶች፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ አስተዳደር ክፍል ድርጅቶችና ስለ ቤተ ክርስቲያን፡፡
ቊ 394፡፡ መንግሥት፡፡

(1) መንግሥት በሕግ በኩል እንደ አንድ ሰው የሚቈጠር ነው፡፡

(2) እንዲህ እንደ መሆኑ መንግሥቱ በመሥሪያ ቤቶቹ አማካይነት ከተፈጥሮው ጋራ የሚስማሙትን መብቶች ሁሉ ሊያገኝና ሊሠራባቸው
ይችላል፡፡

ቊ 395፡፡ የመንግሥቱ ግዛት ክፍሎች፡፡

(1) ጠቅላይ ግዛቶች፤ አውራጃዎች፤ ወረዳዎች፤ ምክትል ወረዳዎች የከተማና የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁ በሕግ ግዴታ ያለባቸውና መብት
ያላቸው ናቸው፡፡

(2) እንዲህ እንደ መሆናቸው በመሥሪያ ቤቶቻቸው አማካይነት በአስተዳደር ሕጎች የተፈቀዱትን መብቶች ሁሉ ሊያገኙና ሊሠሩባቸው
ይችላሉ፡፡

ቊ 396፡፡ ሚኒስቴሮች፡፡

(1) የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሚኒስቴሮች በሕግ ግዴታ ያለባቸውና መብት ያላቸው ናቸው፡፡

(2) እንዲህ እንደ መሆናቸው በመሥሪያ ቤቶቻቸው አማካይነት በአስተዳደር ሕጎች የተፈቀዱትን መብቶች ሁሉ ሊያገኙና ሊሠሩባቸው
ይችላሉ፡፡

ቊ 397፡፡ የሕዝብ አስተዳደር ክፍሎችና መሥሪያ ቤቶች፡፡

እንዲሁም ማንኛዎቹም የሕዝብ አስተዳደር ክፍሎች ወይም የሕዝብ መሥሪያ ቤቶች ወይም ድርጅቶች በአስተዳደር ወይም በሕግ
የሰውነት መብት በተለይ የተሰጣቸው ሁሉ በሕግ ግዴታ ያለባቸውና መብት ያላቸው ናቸው፡፡

ቊ 398፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን፡፡

(1) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሕግ በኩል እንደ አንድ ሰው የምትቈጠር ናት፡፡

(2) እንዲህ እንደ መሆኗ በመሥሪያ ቤቶቿ አማካይነት በአስተዳደር ሕጎች የተፈቀዱትን መብቶች ሁሉ ልታገኝና ልትሠራባቸው
ትችላለች፡፡
ቊ 399፡፡ የጳጳስ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት፡፡
በአስተዳደር ሕጎች ሁኔታዎችና ወሰኖች በተሰጡ ውሳኔዎች መሠረት የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክፍል የሆኑ የጳጳስ ሀገረ
ስብከት፤ አድባራትና ገዳማት በሕግ በኩል ግዴታ ያለባቸውና መብት ያላቸው ናቸው፡፡
ቊ 400፡፡ የሥራውና የመሥሪያ ቤቶቹ ተግባር ሥልጣን የሚደርስበት፡፡
(1) የአስተዳደር ሕጎች፤ ከዚህ በፊት ባሉት ቊጥሮች የተመለከቱትን የሰውነት መብት የተሰጧቸውን ድርጅቶች የያንዳንዱ ተግባር ሥልጣን
የሚደርስበትን፤ እንዲሁም ከነዚሁ ድርጅቶች እንደራሴ ለመሆን የተመረጡትን መሥሪያ ቤቶች ይወስናሉ፡፡

(2) ሕጎቹም አንዳንድ ሥራዎችን ለማስፈጸም እነዚህም መሥሪያ ቤቶች፤ የሁኔታዎችን ወይም የተወሰኑትን ፎርሞች አፈጻጸም ለማስገደድ
ይችላሉ፡፡
ቊ 401፡፡ ሕጋዊ ትእዛዞችን ስላለመፈጸም፡፡
(1) በሕግ የታወቀላቸው የተግባር ሥልጣን ከሚዘረጋበት ውጭ ወይም በሕጉ የተገደዱትን ሁኔታዎች ወይም ፎርም ባለመፈጸም በዚህ
ምዕራፍ የተመለከቱት የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች የሚፈጽሟቸው ሥራዎች ፈራሾች ናቸው፡፡

(2) እንደዚሁ ሕጉ በነዚህ ምክንያቶች ሥራዎቹ ፈራሾች ናቸው ብሎ በግልጽ ባይናገርም ከዚህ በላይ እንደተነገረው ይሆናል፡፡

ቊ 402፡፡ ፈራሽነት፡፡
(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተውን ፈራሽነት ማንኛውም ባለ ጒዳይ ሁሉ ሊጠይቀው ይችላል፡፡

(2) ሥራው ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ዐሥር ዓመት ያለፈ እንደሆነ፤ ፈራሽነቱ ሊጠየቅ አይችልም፡፡
ቊ 403፡፡ ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት፡፡
(1) በዚህ ምዕራፍ የተጠቀሱት ድርጅቶች በዚህ ሕግ ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነትና ያላገባብ ስለ መበልጸግ በተነገረው አንቀጽ
በተወሰኑት ሕጋውያን ደንቦች መሠረት፤ በመሥሪያ ቤቶቻቸው ወይም በሠራተኞቻቸው ጥፋት ወይም ተግባር፤ በሌላው ሰው ላይ
ለሚደርሰው ጉዳት አላፊዎች ናቸው፡፡

(2) እንደዚሁ ድርጅቶቹ በተባለው አንቀጽ ሕጋውያን ደንቦች መሠረት ያላግባብ ያገኙትን ብልጽግና መመለስ አለባቸው፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
ስለ ማኀበሮች፡፡
ቊ 404፡፡ ትርጓሜ፡፡
ማኀበር ማለት ትርፎችን ለማግኘት ወይም ለመከፋፈል ሳይሆን፤ አንድ ውጤት ለማግኘት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል
የሚቋቋም ስብሰባ ነው፡፡
ቊ 405፡፡ የንግድ ማኀበሮች፡፡
(1) ትርፎችን ለማግኘት ወይም ለመካፈል የተቋቋሙ ስብሰባዎች፤ በንግድ ሕግ የንግድ ማኀበሮችን በሚመለከቱ ውሳኔዎች የሚመሩ
ናቸው፡፡

(2) የአባሎቻቸውን የገንዘብ ጥቅም ለማበርከት ቁጠባ (ኤኰኖሚ) እንዲያደርጉ በመፍቀድ በመተባበር አብሮ መሥራት ወይም ሌሎች
ስብሰባዎች በግልጽ ማኀበር ደንቦች ይመራሉ፡፡

ቊ 406፡፡ የሞያ ሥራ ማኀበር (ሰንዲካ)፡፡


(1) የአባሎቻቸውን የገንዘብ ጥቅም ለመከላከል ወይም ላንድ ለተወሰነ የሞያ ሥራ እንደራሴ ለመሆን የተቋቋሙ ስብሰባዎች፤ የሞያ ሥራ
ማኀበሮችን (ሰንዲኮችን) በሚመለከቱ ልዩ ሕጎች የሚመሩ ናቸው፡፡

(2) እነርሱን የሚመለከቱ ልዩ ሕጎች ባይኖሩም እነዚህ ስብሰባዎች እንደ ተራ ማኀበሮች ተገምተው በዚህ ምዕራፍ ሕጋውያን ደንቦች
የሚመሩ ይሆናሉ፡፡
ቊ 407፡፡ ሃይማኖታዊ ጠባይ ያላቸው ስብሰባዎች፡፡
(1) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በቀር ሌሎች አብያተ ክርስቲያኖች፤ ሃይማኖቶችና ማኀበሮች የሚተዳደሩት እነዚሁኑ
በሚመለከቱ ልዩ ሕጎች ነው፡፡

(2) እነርሱን የሚመለከቱ ልዩ ሕጎች እንደሌሉ እነዚህ ስብሰባዎች እንደ ተራ ማኀበሮች ተገምተው በዚህ ምዕራፍ ድንጋጌዎች የሚመሩ
ይሆናሉ፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ ማኀበሩ መመሥረቻ ጽሑፎችና ስለ ውስጥ ደንቦች፡፡
ቊ 408፡፡ የመመሥረቻው ጽሑፍ፡፡
(1) ማኀበሩ በመሥራቾቹ መካከል በሚደረገው ስምምነት በአንድ የመመሥረቻ ጽሑፍ የሚመራ ነው፡፡

(2) የመመሥረቻው ጽሑፍ የማያመለክት ወይም ከደንቦቹ አንዱ በሕግ የተከለከለ የሆነ እንደሆነ፤ የዚህ የመመሥረቻው ጽሑፍ ደንቦች
በዚህ ምዕራፍ ውሳኔዎች የሚሟሉ ወይም የሚተኩ ይሆናሉ፡፡
ቊ 409፡፡ የውስጥ ደንብ እንዲኖር የመስማማት ግዴታ፡፡
(1) ከማኀበርተኞቹ አንዱ ጥያቄ ያደረገ እንደሆነ፤ ማናቸውም ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ቢኖርም እንኳ ማኀበሩ የውስጥ ደንቦች
እንዲኖሩት ያስፈልጋል፡፡

(2) እንዲሁም ማኀበሩ የውስጥ ደንብ ይኑረው ተብሎ የሚቀርበውን ጥያቄ፤ ማኀበሩ ሥራውን በሚያካሂድበት ጠቅላይ ግዛት የማኀበሮቹ
ጽሕፈት ቤት ሊያቀርበው ይቻላል፡፡

(3) ጥያቄው ከተደረገ በኋላ በሦስት ወር ውስጥ ማኀበሩ የውስጥ ደንቦችን ሳያዘጋጅ የቀረ እንደሆነ፤ የማኀበሮች ጽሕፈት ቤት ፈርሷል
ብሎ ለማስታወቅ ይቻላል፡፡
ቊ 410፡፡ የውስጡ ደንብ መኖር ውጤት
(1) ማኀበሩ የውስጥ ደንብ ሲኖረው የመመሥረቻው ጽሑፍ ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) ከዚያም በኋላ ማኀበሩ የሚመራው በውስጡ ደንብ ይሆናል፡፡

(3) የመመሥረቻው ጽሑፍ የማያመለክት ወይም ከደንቦቹ አንዱ በሕግ የተከለከለ የሆነ እንደሆነ የውስጥ ደንቡ በዚህ ምዕራፍ ውሳኔዎች
የሚሟላ ወይም የሚተካ ይሆናል፡፡
ቊ 411፡፡ የደንቦቹ ፎርምና የሚጻፉባቸው ነገሮች፡፡
(1) የማኀበሩ የውስጥ ደንብ ፈራሽነትን እንዳያስከትል፤ የማኀበሩን ስም ዓላማውን የማኀበሩ ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኝበትን ቦታና
የተቋቋመበትን ቀን ማመልከት አለበት፡፡

(2) የማኀበሩ መሥራቾች ተብለው የተመረጡ እጅግ ቢያንስ አምስት ማኀበርተኞች ይፈርሙበታል፡፡
ቊ 412፡፡ ዐይነተኛ የሆኑትን የውስጥ ደንቦች ስለ መቀበል፡፡
(1) የውስጥ ደንቦቹ በአገር ግዛት ሚኒስቴር የተፈቀደውን የውስጥ ደንብ ዐይነት የሆነ እንደሆነ በማኀበሩ የውስጥ ደንብ ላይ መፈረሙ
አስፈላጊ አይደለም፡፡
(2) በዚህ ጊዜ እነዚህን ደንቦች በመጥቀስና ሁለት ማኀበርተኞች የፈረሙበት ልዩ ጽሑፍ ካለ በቂ ነው፡፡

(3) ይህ ጽሑፍ ፈራሽነትን እንዳያስከትል፤ የማኀበሩን ስም፤ ዓላማውን የማኀበሩ ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኝበትን ቦታና የተቋቋመበትን ቀን
ማመልከት አለበት፡፡
ቊ 413፡፡ የውስጡን ደንብ ስለ ማስቀመጥ፡፡
የማኀበሩ የውስጥ ደንብ ወይም ይህንኑ የሚጠቅሰው ልዩ ጽሑፍ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የማኀበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት
በጠቅላይ ግዛቱ የማኀበሮች ጽሕፈት ቤት መቀመጥ አለበት፡፡
ቊ 414፡፡ የውስጥ ደንቦችን ስለ ማስተላለፍ፡፡
(1) ለማኀበሩ ፕሬዚዳንት ጥያቄ በማቅረብ የማኀበሩ የውስጥ ደንቦች ለባለጒዳዩ ሁሉ ሳይዘገዩ እንዲተላለፉ መደረግ አለባቸው፡፡

(2) የውስጥ ደንቦቹ የተላለፉበት ቀን በተላለፈው ግልባጭ ላይ ይጻፋል፡፡

(3) አስፈላጊ ከሆነ የውስጥ ደንቦቹን በፖስታ ለመላክ ስለሚደርሰው ወጪ በተወሰነው ታሪፍ መሠረት ማኀበሩ ለማስከፈል ይችላል፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ማኀበረተኞች፡፡
ቊ 415፡፡ ማኀበረተኛነት፡፡
ማኀበሩ መሥራቾቹና በዚሁ ማኀበር የገቡ አባሎች ያሉበት ይሆናል፡፡
ቊ 416፡፡ አዲስ አባሎች፡፡
ተቃራኒ ደንብ ከሌለ በቀር ማኀበሩ አዲስ አባሎች ለማስገባት ይችላል፡፡
ቊ 417፡፡ ለመግባት ተስፋ መስጠት፡፡
በአንድ ማኀበር ለመግባት ተስፋ መስጠት በሕግ በኩል ዋጋ የሌለው ነው፡፡
ቊ 418፡፡ የማኀበረተኞቹ ትክክለኛነት፡፡
የማኀበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦቹ ተቃራኒ ውሳኔዎች ከሌሉ በቀር ማኀበረተኞቹ ሁሉ ትክክለኛ መብት አላቸው፡፡
ቊ 419፡፡ ማኀበረተኛነቱ የግል ስለ መሆኑ፡፡
(1) ማኀበረተኛነት ተላልፎ የማይሰጥ ነው፡፡

(2) ለማኀበረተኛውም ወራሾች አያልፍም፡፡

(3) የመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም የውስጥ ደንቦቹ እነዚህን ውሳኔዎች ሊያፈርሱ አይችሉም፡፡

ቊ 420፡፡ በማኀበረተኛነት መብቶች ስለ መሥራት፡፡ (1) ስለ መወከል፡፡


የመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም የውስጥ ደንቦቹ ተቃራኒ ውሳኔ ከሌላቸው በቀር አንድ ማኀበረተኛ የማኀበረተኛነቱን መብቶች ባንድ
ሦስተኛ ሰው አማካይነት ሊሠራባቸው አይችልም፡፡

ቊ 421፡፡ (1) የመዋጮ አከፋፈል፤ ማኀበረተኞቹ በየጊዜው ስለሚከፍሉት ድርሻ፡፡


ማኀበርተኛው አስቀድሞ ለመክፈል የሚገባውን መዋጮ ለማኀበሩ ካልከፈለ በቀር ማናቸውንም የማኀበረተኛነቱን መብት ሊሠራበት
አይችልም፡፡
ቊ 422፡፡ (3) አከፋፈል፡፡

(1) ተቃራኒ ውሳኔ ከሌለ በቀር የሚከፈለው ድርሻ በየዓመቱ መጀመሪያ ሦስት ወር ውስጥ የሚከፈል መሆን አለበት፡፡
(2) ስለ ድርሻው ገንዘብ አከፋፈል ስላለፈው ዓመትና ስላለበት ዓመት ካልሆነ በቀር ባንድ ማኀበረተኛ ላይ ማናቸውም ክስ ሊቀርብበት
አይቻልም፡፡
ቊ 423፡፡ ከማኀበረተኛነት የመውጣት መብት፡፡
(1) ማናቸውም ማኀበረተኛ በማናቸውም ጊዜ ማኀበሩ ለአንድ ለተወሰነ ጊዜም የተቋቋመና ማናቸውም ተቃራኒ የውል ቃል ቢኖርም እንኳ
በነፃ ለመውጣት ይችላል፡፡

(2) ከማኀበሩ የሚወጣው ማኀበረተኛ ሊከፍል የሚገባውን ያለፉትን መዋጮዎችና ያለበትንም ዓመት ድርሻ ለመክፈል ይገደዳል፡፡
ቊ 424፡፡ ማኀበረተኛውን ስለ ማስወጣት፡፡
(1) ማኀበረተኛው በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም የውስጥ ደንቦች በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት ከማኀበሩ ሊወገድ ይችላል፡፡

(2) ከነዚሁ ሁኔታዎች ውጭ ለማስወገድ ትልቅ ምክንያት ያለ እንደሆነ ማኀበረተኛውን ዋናው ጉባኤ ከማኀበሩ ሊያስወግደው ይችላል፡፡

(3) የተወገደው ማኀበረተኛ መወገዱ ከተነገረው በኋላ በሦስት ወር ውስጥ መወገዱ ትክክለኛ ያልሆነ እንደሆነ፤ በዚህ ውሳኔ ላይ ለዳኞች
አቤቱታ ለማቅረብ ይችላል፡፡
ቊ 425፡፡ ማኀበረተኞቹ በማኀበሩ ሊወከሉ ስላለመቻሉ፡፡
ማኀበሩ ስላከናወናቸው ነገሮች ማኀበረተኞቹ በሦስተኞች ወገኖች ዘንድ አንድም የግዴታ ኀላፊነት አያገኛቸውም፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ ሥራው አመራር፡፡
ቊ 426፡፡ ዲሬክተሮችን ስለ መሾም፡፡
(1) ማኀበሩ በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በተቋቋመበት ደንብ መሠረት በተሾሙ በአንድ ወይም በብዙ ዲሬክተሮች ይመራል፡፡

(2) ተቃራኒ ውሳኔ የሌለ እንደሆነ ዲሬክተሮችን የሚሾማቸው ጠቅላላው ጉባኤ ነው፡፡
ቊ 427፡፡ አባልነት፡፡
ተቃራኒ ውሳኔ ከሌለ በቀር ዲሬክተሮች የሚመረጡት ከማኅበሩ አባሎች ውስጥ ነው፡፡
ቊ 428፡፡ የሥራ አመራር ምክር ቤት፡፡
(1) ብዙ ዲሬክተሮች ያሉ እንደሆነ ማኅበሩ አንድ የሥራ አመራር ምክር ቤት ይኖረዋል፡፡

(2) ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር በሚገኙት በአሉት ወይም በተወከሉት አባሎች ድምፅ ብልጫ ማኅበሩን የሚመለከቱትን ውሳኔዎች
የሚወስነው ይህ የሥራ አመራር ምክር ቤት ነው፡፡

(3) በድምፅ ብልጫ በተደረገው ውሳኔ በማይስማሙት ማኅበረተኞች አለመስማማታቸውን በአንድ ፕሮሴቬርባል ውስጥ ለማጻፍ መብት
አላቸው፡፡
ቊ 429፡፡ የዲሬክተሮቹ ሥልጣን፡፡ (1) ሕግ፡፡

(1) የማኅበሩ ዲሬክተሮች ለማኅበሩ አመራር አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች ሁሉ ይፈጽማሉ፡፡

(2) ዲሬክተሮቹ ከፍርድ ሥራ ጋራ ባለው ግንኙነትም ሆነ ወይም ከፍርድ ሥራ ውጭ የማኅበሩ እንደራሴዎች ናቸው፡፡

ቊ 430፡፡ (2) የውስጥ ደንቦች፡፡

(1) የውስጥ ደንቦቹ የዲሬክተሮችን ሥልጣኖች ለመወሰን ወይም እነዚህ ሥልጣኖች እንዴት እንደሚሠራባቸው ለመወሰን ይችላሉ፡፡
(2) ደንቦቹ በማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ተቀምጠው እንደሆነ ወይም ሦስተኛ ወገኖች እነዚህን ደንቦች ያወቁ መሆናቸው የተረጋገጠ እንደሆነ
ደንቦቻቸው ለሦስተኞች ወገኖች መከራከሪያ ሊሆኑባቸው ይችላሉ፡፡

ቊ 431፡፡ (3) የመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ጠቅላላ ጉባኤ፡፡

(1) የማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የዲሬክተሮችን ሥልጣን የሚወስኑባቸው ወይም እነዚህ ሥልጣኖች
እንዴት እንደሚሠራባቸው ሁኔታውን የሚቈርጡባቸው ድንጋጌዎች ሦስተኛ ወገኖች ያወቁ መሆናቸው የተረጋገጠ ካልሆነ በቀር ለሦስተኛ
ወገኖች መቃወሚያ ሊሆኑባቸው አይችሉም፡፡

(2) ደንቦቹን መተላለፍ፤ የሚያስከትለው ቅጣት ለማኅበሩ የዲሬክተሩን ወይም የዲሬክተሮቹን ኀላፊነት ነው፡፡
ቊ 432፡፡ ለጊዜው የሚሠራ ዲሬክተር፡፡
ለማኅበሩ እንዲሠሩ የተፈቀደላቸው ሰዎች የሌሉ ወይም መሰናክል ያገኛቸው እንደሆነ ማንኛውም ባለጒዳይ በሚያቀርበው ጥያቄ ለጊዜው
የሚሠራ አንድ ዲሬክተር ዳኞች ይመርጣሉ፡፡
ቊ 433፡፡ ችሎታን ስለ ማረጋገጥ፡፡
(1) በማኅበሩ ስም እንዲህ ያለ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ችሎታቸውንና ሥልጣናቸውን የሚያረጋግጥ ጽሑፍ ከማኀበሮች ጽሕፈት ቤት
እንዲሰጣቸው ለማድረግ ይችላሉ፡፡

(2) ይህም ጽሑፍ አስፈላጊ ሲሆን ተግባሮቹ ለስንት ጊዜ እንዲቈዩ እንደተሰጣቸው ለይቶ ያመለክታል፡፡
ቊ 434፡፡ የዲሬክተሮች ኀላፊነት፡፡
የማኅበሩ ዲሬክተሮች በውክልና ደንቦች መሠረት በዚህ ማኅበር በኩል አላፊዎች ናቸው፡፡
ቊ 435፡፡ የድምፅ መስጠት መብትን ስለ ማስወገድ፡፡
ተቃራኒ የውል ቃል ቢኖርም እንኳ ሐሳባቸውን ለማጽደቅ ወይም በዲሬክተሮች ኀላፊነት የተደረገውን ለመደንገግ በሚደረገው ጠቅላላ
ጉባኤ ዲሬክተሮች በዚሁ ጉባኤ የድምፅ መስጠት መብቶቻቸውን ሊሠሩባቸው አይችሉም፡፡
ክፍል 4፡፡
ስለ ጠቅላላው ጉባኤ፡፡
ቊ 436፡፡ የመጨረሻ ባለሥልጣን ስለ መሆኑ፡፡
(1) የማኀበረተኞቹ ጠቅላላ ጉባኤ ለማኅበሩ የበላይ የመጨረሻ ባለሥልጣን ነው፡፡

(2) በሌላው ክፍል ሥልጣን ውስጥ ያልሆኑትን የማኀበሩን ነገሮች ሁሉ ጠቅላላው ጉባኤ ይወስናል፡፡
ቊ 437፡፡ ዲሬክተሮችን ስለ መሾምና ስለ መቈጣጠር፡፡
(1) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር ጠቅላላው ጉባኤ ዲሬክተሮችን ይሾማል፤ ሥራቸውን ይቈጣጠራል፤ ሒሳባቸውንም ያጸድቃል፡፡

(2) ስለ ማኅበሩም አመራር የሚመለከቱትን ትእዛዞች ሊሰጣቸው ይችላል፡፡


ቊ 438፡፡ ዲሬክተሮችን ስለ መሻር፡፡
(1) እንደ ስምምነቱ፤ የሥራ ድካም ዋጋ መብታቸው የተጠበቀ ሆኖ ጠቅላላው ጉባኤ በማናቸውም ጊዜ ዲሬክተሮችን ለመሻር ይችላል፡፡

(2) ዲሬክተሮች ግዴታዎቻቸውን ከባድ በሆነ ሕገ ወጥነት እንደ ማፍረስ ወይም የማኅበሩን ነገሮች በደንበኛው ለመምራት ችሎታ
እንደማጣት የሆኑ ከባድ ምክንያቶች ያሉት እንደሆነ ይህን የመሻር መብት ለማስወገድም ሆነ ለመቀነስ አይፈቀድም፡፡
ቊ 439፡፡ አባሎችን ስለ ማስገባትና ስለ ማስወገድ፡፡
(1) ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ አባሎችን ስለ ማስገባት ወይም የማኅበሩን አባሎች ስለ ማስወገድ ይወስናል፡፡
(2) አባሎችን የማስገባት ወይም የማስወገድ ሥልጣን በጠቅላላው ጉባኤ መጽደቁ የተጠበቀ ካልሆነ በቀር ለሥራ መምሪያ ክፍሎች ሊሰጥ
አይቻልም፡፡
ቊ 440፡፡ የውስጥ ደንቦቹን ስለ መለዋወጥ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ጠቅላላው ጉባኤ የመመሥረቻውን ጽሑፍ ወይም የማኅበሩን የውስጥ ደንቦች ለመለዋወጥ ይችላል፡፡

(2) የመመሥረቻውን ጽሑፍ ወይም የውስጥ ደንቦች የመለዋወጡ ሥልጣን ለማንም ሌላ ሰው ወይም ክፍል ሊፈቀድ አይቻልም፡፡

ቊ 441፡፡ (2) ወሰን፡፡

(1) የሚደረገው ውሳኔ የማኅበሩን ዓላማ ለመለዋወጥ ወይም ለማኅበረተኞቹ ትክክል ያልሆኑ መብቶችን ለመፍቀድ የሆነ እንደሆነ
የማኅበረተኞቹ ሁሉ ፈቃድ አስፈላጊ ነው፡፡

(2) ማኅበረተኞቹ ካልፈቀዱ በቀር ለማኅበረተኞቹ የተሰጡት እነዚህ ልዩ መብቶች ሊወሰዱባቸው አይቻልም፡፡

ቊ 442፡፡ ስለ ጥሪ (1) መሠረቱ፡፡


በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም የውስጥ ደንቦች እንደ ተመለከቱትና አስቸኳይ ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜና የማኅበሩ ጥቅም አስፈላጊነቱን
በሚያስገኝበት ጊዜ ሁሉ ዲሬክተሮች ለጠቅላላው ጉባኤ ጥሪ እንዲላክለት ያደርጋሉ፡፡

ቊ 443፡፡ (2) የማኅበረተኞቹ መብት፡፡

(1) በውስጡ ደንብ የተወሰነው የማኅበረተኞች ብዛት ጥሪ እንዲደረግ የጠየቀ እንደሆነ ጠቅላላው ጉባኤ ጥሪ ሊደረግለት ይገባል፡፡

(2) ስለዚህ ጒዳይ ደንቦቹ ምንም የማያመለክቱ የሆነ እንደሆነ ማኅበረተኞች የሚነጋገሩባቸውን ነገሮች በማመልከት በጽሑፍ ጥያቄ
ያደረጉ እንደሆነ ከማኅበረተኞቹ አንድ አምስተኛው ለጠቅላላው ጉባኤ ጥሪው እንዲደረግ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

ቊ 444፡፡ (3) ዳኞች የሚያደርጉት ጥሪ፡፡

(1) ጥሪ እንዲያደርግ በሚገደድበት ጊዜ የሥራው አመራር ምክር ቤት ለጠቅላላው ጉባኤ ጥሪ ያላደረገ እንደሆነ፤ በአንድ ወይም በብዙ
ማኅበረተኞች ጥያቄ ጠቅላላው ጉባኤ እንዲሰበሰብ ዳኞች ጥሪ ይልኩለታል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ዳኞች ስለ ጉባኤው ፕሬዚዳንትነት የሚመለከቱትን ውሳኔዎች ያደርጋሉ፡፡

ቊ 445፡፡ (4) አደራረግና የተወሰነ ጊዜ፡፡

(1) የጠቅላላው ጉባኤ ጥሪ አደራረግና ጊዜው በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦቹ የተወሰኑ ናቸው፡፡

(2) ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ለሕሊና ተስማሚ በሆነ ሁኔታ ዲሬክተሮች ይወስኗቸዋል፡፡
ቊ 446፡፡ በጉባኤው የሚደረግ የድምፅ አሰጣጥ፡፡
(1) የጠቅላላው ጉባኤ የሚያደርጋቸው ውሳኔዎች በሚገኙት ወይም በተወከሉት አባሎች ድምፅ ብልጫ የሚሆን ነው፡፡

(2) ሊነጋገሩበት ከቀረበው በቀር በሌላ ጒዳይ ላይ የሚደረግ ውሳኔ ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 447፡፡ ትክክልነት፡፡
ማኅበረተኞቹ ሁሉ በጽሑፍ የተቀበሉት ሐሳብ እንደ ዋናው ጉባኤ ውሳኔ የሚተካከል ነው፡፡
ቊ 448፡፡ የጠቅላላው ጉባኤ ውሳኔዎች ፈራሽነት፡፡ (1) ክስ፡፡

(1) ማንኛውም ማኅበረተኛ ምንም ተቃራኒ የውል ቃል ቢኖርም እንኳ እርሱ ባልተቀበላቸውና የሕጉን ውሳኔዎች ወይም የማኅበሩን
መመሥረቻ ጽሑፍ የውስጥ ደንቦቹን በሚጥሱት በጠቅላላው ጉባኤ ውሳኔዎች ላይ ለዳኞች ክስ፤ ለማቅረብ ይችላል፡፡
(2) ይህን ክስ፤ ውሳኔ መደረጉን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በያዘው ወር ውስጥ ካላቀረበ ተቀባይነትን አያገኝም፡፡

(3) በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦቹ ወይም በሕጉ እንደተመለከተው ዐይነት ዋናው ጉባኤ ተንኰል ሳይኖርበት ጥሪ
የተደረገለት የሆነ እንደሆነ፤ በጠቅላላው ጉባኤ የተደረጉትን ውሳኔዎች ማኅበረተኛው እንዳወቃቸው ይገመታሉ፡፡

ቊ 449፡፡ (2) የፍርዱ ሥልጣን፡፡


የጠቅላላውን ጉባኤ ውሳኔ ለመሻር የሚነገረው ፍርድ በሁሉ ላይ ሥልጣን አለው፡፡
ቊ 450፡፡ ውሳኔዎች እንዳይፈጸሙ ስለ ማቋረጥ፤ (ስለ ማገድ)፡፡
ከማኅበሩ ዲሬክተሮች በአንዱ ወይም በማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ማቅረብ ፍርድ ቤቱ ፈራሽነቱ የተጠየቀውን ውሳኔ አፈጻጸም
ለመከልከል (ለማገድ) ይችላል፡፡
ክፍል 5፡፡
የማኅበሩ መብቶችና ግዴታዎች፡፡
ቊ 451፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) ማኅበሩ በውስጡ ከአሉት ሰዎች ልዩነት ያለው ነው፡፡

(2) የማኅበሩ መብቶችና ግዴታዎች የአባሎቹ ግዴታዎችና መብቶች አይደሉም፡፡

(3) እንዲሁም የማኅበሩ አባሎች መብቶችና ግዴታዎች የማኅበሩ መብቶችና ግዴታዎች አይደሉም፡፡
ቊ 452፡፡ ስም፡፡
(1) የማኅበሩ ስም እንደ ሰዎች ስም ዐይነት ልክ የሚጠበቅ ነው፡፡

(2) የሆነ ሆኖ ይህ ጥበቃ በሕግ የሚደረገው የማኅበሩ የውስጥ ደንቦች በማኅበሮች ጽሕፈት ቤት የተቀመጡ ሲሆኑ ወይም በማኅበሩ
መብቶች ላይ ጉዳት ያደረገው ሰው ጒዳዩን በማወቅና በመጥፎ ልቡና የሆነ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 453፡፡ መኖሪያ ቦታ፡፡
(1) የማኅበሩ ዋና መኖሪያ ቦታ የሚባለው በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም የውስጥ ደንቦች መሠረት ዋና መሥሪያ ቤቱ በተቋቋመበት ቦታ
ያለው ነው፡፡

(2) ማኅበሩ በኑዋሪ አኳኋን ያሉት የያዛቸው ሌሎች ቦታዎች ሁሉ ምክትል መኖሪያ ቦታዎች ይባላሉ፡፡

ቊ 454፡፡ ችሎታ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ማኅበሩ ከዐይነቱ ጋራ የሚስማሙትን የብሔራዊ ኑሮ ተግባሮችን ሁሉ መፈጸም ይችላል፡፡

(2) ማኅበሩም እነዚህን ተግባሮች በሥራ መምሪያ መሥሪያ ቤቶቹ አማካይነት ይፈጽማል፡፡

ቊ 455፡፡ (2) የፍርድ ጒዳዮች፡፡

(1) ማኅበሩ በጠያቂነት ወይም በተከላካይነት በዳኝነት ፊት ለመቆም ይችላል፡፡

(2) በዚህ ነገር ማኅበሩ በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦቹ ሥልጣን በተሰጣቸው ሰዎች የሚወከል ይሆናል፡፡

(3) የመልእክትን ደብዳቤ ወይም አንድ ጽሑፍን ለማድረስ የሚላከውን ማስታወቂያ በማኅበሩ ስም ሆኖ ሊቀበል የሚችለው አባል
የትኛው እንደሆነ ለይቶ መግለጽ አስፈላጊ ሳይሆን በማኅበሩ ወይም በዲሬክተሩ አድራሻ ለማኅበሩ ቢላክለት የተላከው ደብዳቤ ወይም
አንድ ጽሑፍን ለማድረስ የተጻፈው ማስታወቂያ በሚገባ የተላከ ሆኖ ይቈጠራል፡፡

ቊ 456፡፡ (3) ስጦታዎችና ውርስ፡፡


(1) አንድ ማኅበር በስጦታ ወይም በውርስ ያገኛቸው ሀብቶች ከአንድ ከተወሰነ ገንዘብ በላይ የሚያልፉ ሲሆኑ የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት
እነዚህ በቁም ስጦታ ወይም በውርስ ለአንድ ማኅበር የተሰጡ ሀብቶች እንዲገለጹለት ማኅበሮችን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ጊዜ ተጠቃሚው ማኅበር የቁም ስጦታዎችን ወይም የውርሶችን ሀብቶች ከተቀበለበት ቀን አንሥቶ እስከ
ስድስት ወር ድረስ የተቀበለውን የቁም ስጦታ ወይም ያገኘውን ውርስ ለማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ማስታወቅ አለበት፡፡ ሳያስታውቅ ቢቀር
ግን በወንጀለኛ መቅጫ በ 4)!8 ቊጥር መሠረት ቅጣት ያገኘዋል፡፡
ቊ 457፡፡ ከውል ውጭ ስለሚደርስ የማኅበሩ ኀላፊነት፡፡
(1) ዲሬክተሮቹና ሠራተኞቹ ሳይፈጽሟቸው የቀሩትና የሠሯቸው ተግባሮች ግዴታ ባለባቸውና አላፊነትን የሚያመጡ ተግባሮችን
በሚፈጸሙበት ጊዜ የተደረጉ እንደሆነና ኀላፊነትን የሚያስከትሉ ሲሆን ማኅበሩ ዲሬክተሮቹና ሠራተኞቹ ሳይፈጽሟቸው በቀሩት
በሠሯቸው በአላፊነት ይጠየቃል፡፡

(2) እንዲሁም ማኅበሩ በማይገባ የበለጸገ እንደሆነ በአላፊነት ይጠየቃል፡፡

(3) ለዚህ ነገር ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነትና ያላገባብ ስለ መበልጸግ በሚለው አንቀጽ የተነገሩት ውሳኔዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 458፡፡ ስለ ማኅበሩ ዕዳዎች ዋስትና፡፡


በማኅበሩ ስም የሠራው ዲሬክተር፤ በማኅበሮች ጽሕፈት ቤት በተቀመጡት በውስጥ ደንቦች መሠረት ማኅበሩ ያልተከናወነ እንደሆነ፤
ለማኅበሩ በሕጉ መሠረት የአንድነት ዋስ ነው፡፡
ክፍል 6፡፡
ስለ ማኅበሩ መፍረስና ሒሳብ ማጣራት፡፡
ቊ 459፡፡ መፍረስ፡፡ (1) የውስጥ ደንቦች፡፡
ማኅበሩ የሚፈርሰው በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቡ በተመለከተው መሠረት ነው፡፡
ቊ 460፡፡ (2) ጠቅላላ ጉባኤ፡፡
ተቃራኒ ውሳኔ ቢኖርም እንኳ በማናቸውም ጊዜ ጠቅላላው ጉባኤ የማኅበሩን መፍረስ ለመወሰን ይችላል፡፡
ቊ 461፡፡ (3) ዳኞች፡፡
በሥራ መምሪያ ምክር ቤት ወይም በማኅበረተኞቹ በአንድ አምስተኛ ወይም በማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ዳኞች ማኅበሩ እንዲፈርስ
የሚወስኑት፤
(ሀ) በማኅበረተኞቹ ብዛት ማነስ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦች መሠረት የሥራ
መምሪያ ምክር ቤትን አባሎች ለመምረጥ ወይም ማኅበሩን ለማካሄድ ያልተቻለ ሲሆን፤

(ለ) የማኅበሩ ዓላማ የተደረሰበት ሲሆን ወይም ሊደረስበት ያልተቻለ ሲሆን ወይም ረጅም በሆነ ጊዜ ባለመከናወኑ ማኅበሩ ይህን ዓላማ
መከተል ያቋረጠ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤

(ሐ) በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦች ከተወሰነው የተለየ ዓላማ ማኅበሩ የሚከተል ሲሆን፤

(መ) ማኅበሩ ዕዳውን የመክፈል ችሎታ የሌለው ሲሆን ነው፡፡

ቊ 462፡፡ (4) የአስተዳደር ውሳኔ፡፡

(1) ዓላማውና ክንውኑ ሕገ ወጥ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆኑ እንደሆነ የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት የማኅበሩን መፍረስ ይናገራል
(ይወስናል)፡፡
(2) ከማኅበሩ ዲሬክተሮች አንዱ፤ ውሳኔው ለማኅበሩ ከተነገረ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ፤ በዚሁ ውሳኔ ላይ ለአገር ግዛት ሚኒስቴር
የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ ይችላል፡፡

(3) ፍርድ ቤቱ በዚህ አቤቱታ ላይ ውሳኔ እስኪሰጥ ማኅበሩን የሚሽረው ውሳኔ አፈጻጸሙ እንዲዘገይ ለማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 463፡፡ የሒሳብ ማጣራት ሁኔታ፡፡
(1) ማኅበሩ በሒሳብ ማጣራት ሁኔታ ላይ የሚገኘው በሕጉ መሠረት የፈረሰ እንደሆነ ነው፡፡

(2) ማኅበሩም ለዚህ የሒሳብ ማጣራት አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች እስከ መጨረሻው የሰውነት መብት እንዳለው ይቈጠራል፡፡

ቊ 464፡፡ ሒሳብ አጣሪዎች፡፡ (1) ምርጫ፡፡

(1) በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦቹ ተቃራኒ ነገር ከሌለ፤ ወይም ዳኞች ካልወሰኑ በቀር ማኅበሩን ይመሩ በነበሩ ሰዎች
የማኅበሩ ሒሳብ ይጣራል፡፡

(2) እነዚህ ሰዎች የሌሉ እንደሆነ፤ ዳኞች የመረጧቸው አንድ ወይም ብዙ ሒሳብ አጣሪዎች የማኅበሩን ሒሳብ ያጣራሉ፡፡

ቊ 465፡፡ (2) ሥልጣን፡፡

(1) ሒሳብ አጣሪው ለሥራ መምሪያ ምክር ቤት የነበረው ሥልጣን አለው፡፡

(2) ለሒሳብ ማጣራት አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ካልሆነ በቀር ባለው መብቱ ሊሠራበት አይችልም፡፡

(3) አዲስ ሌላ ሥራ ሊጀምር አይችልም፡፡

ቊ 466፡፡ (3) ኀላፊነት፡፡

(1) ሒሳብ አጣሪው በማኅበሩ ላይና ከማኅበሩ ገንዘብ ጠያቂዎች በሆኑት ላይ ሥራዎችን በማከናወን በሚያደርገው ጥፋት ጉዳት
ያደረሰባቸው እንደሆነ ኀላፊ ነው፡፡

(2) ከክሱ መቅረብ በፊት አምስት ዓመት ጊዜ በማኅበሩ የዲሬክተርነትን ሥራዎች የሠራ ማናቸውም ከማኅበረተኞቹ አንድ ሰው፤ በማኅበሩ
በኩል የሒሳብ አጣሪውን በአላፊነት ሊያስጠይቀው ይችላል፡፡
ቊ 467፡፡ የፈረሰው ማኅበር ንብረት፡፡
(1) የፈረሰው ማኅበር ንብረት በማናቸውም ሁኔታ በማኅበረተኞቹ መካከል ሊከፋፈል አይቻልም፡፡

(2) በመመሥረቻው ጽሑፍ ወይም በውስጥ ደንቦቹ ውስጥ ውሳኔ የሌለ ሆኖና ጠቅላላው ጉባኤም በሚገባ ለሌላ ሥራ ያላዋላቸው
እንደሆነ እነዚህ ሀብቶች የመንግሥት ንብረት ይሆናሉ፡፡

(3) ማኅበሩን ያፈረሰው የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት የሆነ እንደሆነ፤ ጠቅላላው ጉባኤ ሀብቶችን በሌላ ሥራ ላይ ለማዋል ለመወሰን
አይችልም፡፡
ክፍል 7፡፡
ማኅበሮችን ስለ መቈጣጠር፡፡
ቊ 468፡፡ የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት፡፡
(1) በያንዳንዱ የጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ ከጠቅላይ ግዛቱ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋራ የተያያዘ (የተሳሰረ) አንድ ጽሕፈት ቤት
ይኖራል፡፡

(2) የተባለውም ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ግዛቱ ውስጥ የሚገኙትን ማኅበሮች ይቈጣጠራል፡፡


ቊ 469፡፡ የማኅበር የውስጥ ደንቦችን ማስቀመጥ፡፡
የሚያስፈልግ ሲሆን፤ የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት የማኅበሩን የውስጥ ደንቦች እንዲያዘጋጁና እነዚህኑም በመሥሪያ ቤቱ እንዲያስቀምጡ
መሥራቾቹን ወይም መሪዎቹን ያስጠነቅቃቸዋል፡፡
ቊ 470፡፡ የታወቁ ማኅበሮች መዝገብ፡፡
(1) የማኀበሮች ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ግዛቱ ውስጥ ያሉትንና አሉ ተብለው የተነገሩትን ማኅበሮች መዝገብ፤ በፊደል ተራ ይይዛል
(ያስቀምጣል)፡፡

(2) የአንድ ማኅበር ዲሬክተሮች፤ በመዝገብ እንዳይጻፍ የማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት በተቃወመበት እንቢታ ላይ ለዳኞች አቤቱታ ለማቅረብ
ይችላሉ፡፡
ቊ 471፡፡ የተራ ቊጥር፡፡
(1) በመዝገብ የተጻፈው እያንዳንዱ ማኅበር ጽሕፈት ቤቱ ስለ ማኅበሩ ያዘጋጀውን ዶሴ ቊጥር የሚያመለክት አንድ ተራ ቊጥር
ይቀበላል፡፡
(2) ይህ የተባለው ተራ ቊጥር በማኅበሮቹ የውስጥ ደንቦች ውስጥና ማኅበሮቹን ከሦስተኛ ወገኖች ጋራ በሚያገናኙት የደብዳቤ ጽሑፎች
ላይ መግባት አለበት፡፡
ቊ 472፡፡ የማኅበሩ ዶሴ፡፡
በመዝገብ የተጻፈው የያንዳንዱ ማኅበር ዶሴ የሚያመለክተው፡፡
(ሀ) የማኅበሩን ስም ከነተራ ቊጥሩ፤

(ለ) የማኅበሩን የውስጥ ደንቦችና በነዚህ የውስጥ ደንቦች ላይ የተደረጉትን መለዋወጥ እነዚህ የውስጥ ደንቦች ወይም መለዋወጦች
የተደረጉበትን ጊዜ ጭምር፤

(ሐ) የማኅበሩ ዲሬክተሮችን፤ ወይም ለማኅበሩ ወኪልነት ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች ስም፣

(መ) ለማኅበሩ ሊኖሩት የሚችሉትን የሁለተኛ ደረጃ የተቀማጭነትን ቦታዎች መግለጫ፤

(ሠ) ስለ ማኅበሩ መፍረስ የተሰጠውን ውሳኔና አስፈላጊም ሲሆን የመጨረሻ አስተሳሳቢዎቹን ሰዎች ስም ነው፡፡

ቊ 473፡፡ ጠቅላላ ስብሰባዎች፡፡ (1) የስብሰባ ጥሪ፡፡

(1) ጠቅላላ የሆነው ስብሰባ በሚቀመጥበት ጊዜ ሁሉ ለማኅበሩ ጽሕፈት ቤት በአስፈላጊው ጊዜ ማስታወቂያ ይላክለታል፡፡

(2) ጽሕፈት ቤቱ በነዚህ ጠቅላላ ስብሰባዎች ውስጥ አንድ ታዛቢ ወኪል ለማድረግ ይችላል፡፡

(3) በተለይ የስብሰባውን ጥሪ አደራረግና የጥሪውን ጊዜ፤ ስብሰባው የሚነጋገርበትን ጒዳይና የስብሰባውን አያያዝ ስለሚመለከተው ነገር፤
የጠቅላላውን ስብሰባ የሥራውን መልካም አፈጻጸም ለማረጋገጥ ጠቃሚዎች የሚመስሉትን ጥንቃቄዎች ለማዘዝ ይችላል፡፡

ቊ 474፡፡ (2) ውሳኔዎች፡፡


በማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ጠቅላላ ስብሰባ የተደረገበትን ቀን በሚከተለው ወር ውስጥ ጽሕፈት ቤቱ በሚይዘው መዝገብ ዶሴ ውስጥ
መጻፍ ያለባቸው፤ በተባለው ስብሰባ የተሰጡት ውሳኔዎች ሁሉ በማስታወቂያ ይላኩለታል፡፡

ቊ 475፡፡ (3) የውሳኔዎቹ ፈራሽነት፡፡

(1) የማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ጠቅላላው ስብሰባ የሰጣቸውን የሕግ ወይም የማኅበር የውስጥ ደንቦች ተቃራኒ የሆኑትን ውሳኔዎች በዳኞች
ፊት ለመቃወም ይችላል፡፡

(2) ክሱም እንዳይፈርስ፤ የተደረገው የውሳኔው ግልባጭ ከተላከለት ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ወር መቅረብ አለበት፡፡
ቊ 476፡፡ የማኅበር የውስጥ ደንቦች መለዋወጥ፡፡
(1) በማኅበሮቹ የውስጥ ደንቦች ላይ መለዋወጥ የተደረገ እንደሆነ፤ ጠቅላላው ስብሰባ መለዋወጡን የተቀበለበትን ቀን በሚከተለው ወር
ውስጥ የተባለውን መለዋወጥ የያዘው አንድ አዲስ የደንቦቹ ግልባጭ ጽሑፍ ለማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ይሰጣል፡፡

(2) ይኸው ግልባጭ በገበሩ ላይ በ-----------ቀን የተሻሻለ ጽሑፍ የሚል ጽሕፈት ይኖረዋል፡፡

(3) ሦስተኛ ወገኖች የማኅበሩ የውስጥ ደንቦች መለዋወጣቸውን ማወቃቸው ካልተረጋገጠ በቀር ለማኅበሮቹ የውስጥ ደንቦች የተደረጉት
መለዋወጦች በማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት እስከ ተነገረ ድረስ በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሊሆኑባቸው አይችሉም፡፡
ቊ 477፡፡ የማኅበር ዲሬክተሮች፡፡
(1) የሥራው አመራር (ዲሬክሲዮን) ምክር ቤት አባሎች ስም እንዲሁም ለማኅበሩ ወኪል የመሆን ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ስም እነዚህ
ሰዎች ከተመረጡበት ቀን በሚከተለው ወር ውስጥ ለማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ይነገራል፡፡

(2) እንደዚሁም የነዚህ ሰዎች ስም ለተጻፈበት ሊስት የተደረገውም ማናቸውም መለዋወጥ በዚሁ ጊዜ ውስጥ ይነገራል፡፡
ቊ 478፡፡ የሒሳብ ሚዛን፡፡
(1) ማኅበሩ በያመቱ ጠቅላላው ስብሰባ ያጸደቀውን የሒሳብ ሚዛን ለማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ያስታውቃል፡፡

(2) ያገር ግዛት ሚኒስቴር የዚህን የሒሳብ ሚዛን መልካም አቀራረብና እውነተኛነትን ለማረጋገጥ የሚስማሙ መስለው የሚታዩትን ደንቦች
ለማዘዝ ይችላል፡፡
ቊ 479፡፡ የአገር ግዛት ሚኒስቴር፡፡
(1) ያገር ግዛት ሚኒስቴር፤ የማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤቶች በማኅበሮች ላይ እርግጠኛ የሆነውን የመቈጣጠር ሥራ እንዲሠሩ ለማድረግ
ሌሎችንም ጠቃሚነት ያላቸውን ጥንቃቄዎች ሁሉ በሚገኙት ሕጎች መሠረት ለማዘዝ ይችላል፡፡

(2) እነዚህ ጥንቃቄዎች እንደ ማኅበሩ ልብ ትልቅነትና እንደሚቈይበት ጊዜ ልዩ ልዩ ለመሆን ይችላሉ፡፡

(3) እንደዚሁም ዋና መሥሪያ ቤታቸው በውጭ አገር ለሆኑ ማኅበሮች ወይም በውጭ አገር ለሆኑ ማኅበሮች ወይም በውጭ አገር
የማኅበርን ሥራ ክንውን ለያዙ ወይም አብዛኞቹ አባሎቹ የውጭ አገር ዜጎች ለሆኑ ወይም በሥራ አመራሩ (ዲሬክሲዮን) ምክር ቤት
ውስጥ አንድ ወይም ብዙዎች የውጭ አገር ሰዎች ለሚገኙባቸው ማኅበሮች ልዩ የሆኑት ጥንቃቄዎች ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡

ቊ 480፡፡ የወንጀል ቅጣቶች (1) ለጽሕፈት ቤት የሚደረጉ ማስታወቂያዎች፡፡


በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች የሚቀጡት፤
(ሀ) የማኅበርን የውስጥ ደንቦች በሕግ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ለማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት ያልሰጡት የማኅበር መሥራቾች፡፡

(ለ) ለማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ስለሚደረጉት ማስታወቂያዎች ወይም ስለ ሚሰጡት ጽሑፎች በዚህ ምዕራፍ የተመለከቱትን ውሳኔዎች
የተላለፉ የማኅበሩ መሪዎች ናቸው፡፡

ቊ 481፡፡ (2) የልዩ ልዩ ሕጋውያን ትእዛዞች መጣስ፡፡


በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች የሚቀጡት፡፡
(ሀ) ተራ ቊጥሩን በማኅበር ደንቦች ወይም ከሦስተኛ ወገኖች ጋራ በሚያደርገው በደብዳቤ ጽሑፎች ላይ ያላመለከተ ማኅበር፤

(ለ) ባለጒዳዩ ባቀረበው ጥያቄ የማኅበሩን የውስጥ ደንቦች ለተባለው ባለጒዳይ በሕጉ መሠረት ያላስታወቀ ማኅበር ነው፡፡

ቊ 482፡፡ (3) ሕገ ወጥ ነው የተባለ ማኅበር፡፡

(1) የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ለአፈረሰው ማኅበር በሥራ አስኪያጅነት የአንድ የሥራ ክንውን የቀጠሉ ሥራ አስኪያጆች በወንጀለኛ መቅጫ
ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣሉ፡፡
(2) እንደዚሁም የማኅበሩን ሕገ ወጥነት እያወቁ የሥራውን መካሄድ ተካፋዮች በመሆን የቀጠሉ የተባለው ማኅበር አባሎች በወንጀለኛ
መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣሉ፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ልዩ አገልግሎት የተመደበ ንብረት፡፡
ክፍል 1፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅት፡፡
ቊ 483፡፡ ትርጓሜ፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅት ተግባር ማለት አንድ ሰው አንድ ሀብት ወይም ብዙ ሀብቶች ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን በማይመለስ አኳኋንና
ለዘለዓለም አንድ የተወሰነ የጠቅላላ ጥቅም ግብ ላለው የሚያውልበት ሥራ ነው፡፡
ቊ 484፡፡ ፎርሞች፡፡
(1) የበጎ አድራጎት ድርጅት በቁም ስጦታ ወይም በኑዛዜ ስጦታ ሊቋቋም ይችላል፡፡

(2) የዚህም ነገር መቋቋም በዐይነቱና በሥረ ነገሩ ስጦታዎችን ወይም ኑዛዜዎችን በሚመለከቱ ደንቦች የሚመራ ይሆናል፡፡
ቊ 485፡፡ የአስተዳደር ክፍል ነገሩን ማጽደቅ አስፈላጊ ስለ መሆኑ፡፡
(1) የበጎ አድራጎት ድርጅትን ተግባር ያገር ግዛት ሚኒስቴር ካላጸደቀው በቀር አይቋቋምም፡፡

(2) የአገር ግዛት ሚኒስቴር ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት አስፈላጊ ሲሆን ይህ የበጎ አድራጎት ድርጅት የሚመለከታቸውን የሌሎች ሚኒስቴሮችን
ሐሳብ ይጠይቃል፡፡

ቊ 486፡፡ ነገሩ እንዲጸድቅ ለማድረግ የሚቀርበው ጥያቄ፡፡ (1) የበጎ አድራጎት ድርጅት መሥራቹ በሕይወቱ ሳለ፡፡
የበጎ አድራጎቱ ድርጅት ተግባር እንዲጸድቅ ለማድረግ የሚቀርበውን ጥያቄ መሥራቹ በሕይወት ካለ መሥራቹ ራሱ ወይም ወኪሉ ካልሆነ
በቀር ሌላ ሰው ጥያቄ ለማቅረብ አይችልም፡፡

ቊ 487፡፡ (2) የበጎ አድራጎት ድርጅት መሥራቹ ከሞተ በኋላ፡፡

(1) መሥራቹ ከሞተ በኋላ የተባለውን ጥያቄ፤ መሥራቹ፤ ሥራውን ሰጥቶት እሺ ብሎ የተቀበለው ሰው ሊጠይቅ ይገባል፡፡

(2) እንደተባለው ጠያቂ የሌለ ሲሆን የበጎ አድራጎትን ድርጅት ጽሑፍ ያዘጋጁ ሰዎች፤ ወይም ለዚህ ነገር ምስክር የሆኑት ወይም የዚህን
ተግባር አደራ ያስቀመጡት ሰዎች ሊጠይቁ ይገባል፡፡

(3) የዚህን ተግባር ፈቃድ የመጠየቅ ግዴታ የሚወድቅባቸው ሰዎች ፈቃዱን ሳይጠይቁ የቀሩ እንደሆነ የተባለውን የበጎ አድራጎት ድርጅት
ጽሑፍ እንዲጸድቅ የሚቀርበውን ጥያቄ መሥራቹ ከሞተ በኋላ በሦስት ወሩ ዐቃቤ ሕግ ወይም ማናቸውም ባለጒዳይ ሊያቀርበው
ይችላል፡፡
ቊ 488፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅትን ተግባር ስለ መሻር፡፡
(1) የበጎ አድራጎት ድርጅትን ተግባር መሥራች ይህን ተግባሩን እንዲያጸድቅለት ለአገር ግዛት ሚኒስቴር ያቀረበውን ጥያቄ ሚኒስቴሩ
ከመፍቀዱ በፊት ያቆመውን በጎ አድራጎት በነፃ ለመሻር ይችላል፡፡

(2) የመሥራቹ ወራሾች በዚህ በመሻር መብታቸው ሊሠሩ የሚችሉት የበጎ አድራጎቱን ሥራ ፈቃድ የመቀበል ግብ ያለው ጥያቄ ለአገር
ግዛት ሚኒስቴር ከቀረበ በኋላ በሁለት ዓመት ውስጥ የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ተግባር ሚኒስቴሩ ሳያጸድቀው የቀረ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 489፡፡ የማጽደቁ ተግባር ወደ ኋላ ስለ መሥራቱ፡፡
(1) የበጎ አድራጎት ድርጅት ፈቃድ ጥያቄ የቀረበው በመሥራቹ እንደሆነ፤ ድርጅቱን የሚያጸድቀው የአስተዳደር ውሳኔ የፈቃዱ ጥያቄ
ከቀረበበት ቀን አንሥቶ የሚጸና ይሆናል፡፡
(2) የፈቃድ ጥያቄ የቀረበው፤ መሥራቹ ከሞተ በኋላ እንደሆነ፤ ውሳኔው መሥራቹ ከሞተበት ቀን አንሥቶ የሚጸና ይሆናል፡፡

(3) ስለሆነም ይህ ወደ ኋላ ተመልሶ መሥራት የበጎ አድራጎት ድርጅት ከመፈቀዱ በፊት በበጎ አድራጎት ድርጅት ንብረቶች ላይ በቅን ልቡና
ባለመብቶች በሆኑት ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያመጣ አይችልም፡፡
ቊ 490፡፡ ለበጎ አድራጎት ድርጅት የሚደረገው ጥበቃና ተጠባባቂነት፡፡
(1) የበጎ አድራጎት ድርጅት ተግባር የተፈቀደበት ጽሑፍ ለበጎ አድራጎት ድርጅቱ ተግባር የሚደረገውን ጥበቃና ተጠባባቂነት የታዘዘውን
መሥሪያ ቤት ለይቶ ያስታውቃል፡፡

(2) በተባለው ጽሑፍ ውስጥ ለዚሁ ሥራ ማናቸውም መሥሪያ ቤት ያልተመረጠበት እንደሆነ ለበጎ አድራጎት ተግባር የሚደረገውን
ጥበቃና ተጠባባቂነት የሚያከናውነው የበጎ አድራጎቱ ድርጅት ተግባር ባለበት ጠቅላይ ግዛት በሚገኘው የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ነው፡፡

ቊ 491፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅት የውስጥ ደንቦች፤ (1) ግብ፡፡


የበጎ አድራጎት ድርጅት በተቋቋመባቸውና በሚተዳደርባቸው የውስጥ ደንቦች የሚመራ ይሆናል፡፡
ቊ 492፡፡ (2) በውስጥ ደንቦቹ ውስጥ የሚጻፈው፡፡
የውስጥ ደንቦቹ በተለይ የበጎ አድራጎት ድርጅቱን ስም ግቡንና ያለበትን ቦታ ያመለክታሉ፡፡
ቊ 493፡፡ የውስጥ ደንቦቹን የሚያሰናዳው፡፡
(1) የበጎ አድራጎት ድርጅትን የውስጥ ደንቦች የበጎው አድራጎት ድርጅት መሥራች ሊያሰናዳቸው ይችላል፡፡

(2) እርሱ ያላሰናዳቸው እንደሆነ በአገር ግዛት ሚኒስቴር ወይም ለጠባቂነትና ለተጠባባቂነት በአገር ግዛት ሚኒስቴር በተሰጠው መሥሪያ
ቤት ይደራጃሉ፡፡

(3) የውስጥ ደንቦቹ ለበጎ ተግባር ድርጅት ተቃራኒዎች ሆነው የተገኙ እንደሆነ ማናቸውም ባለጒዳይ የተባሉትን ደንቦች ለዋውጡልን ሲል
በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለዳኞች ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል፡፡
ቊ 494፡፡ አመራሩ፡፡
(1) የበጎ አድራጎቱ ድርጅት የሚመራው በውስጥ ደንቦቹ መሠረት በአንድ ወይም በብዙ ዲሬክተሮች ነው፡፡

(2) የማኅበሮችን ዲሬክተሮች የሚመለከቱት የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች ለድርጅት ዲሬክተሮችም ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡
ቊ 495፡፡ የአስተዳደሩ ምክር ቤት፡፡
(1) የበጎ አድራጎት ድርጅት የውስጥ ደንቦች መሠረት የተቋቋመው የአስተዳደሩ ምክር ቤት የበጎ አድራጎት ድርጅት የመጨረሻው ባለ
ሥልጣን ነው፡፡

(2) ለበጎው አድራጎት ድርጅት የተደረገው የጠባቂነትና የተጠባባቂነት መሥሪያ ቤት በአስተዳደሩ ምክር ቤት ውስጥ ወኪል ይኖረዋል፡፡
ቊ 496፡፡ የአስተዳደሩ ምክር ቤት ሥራ፡፡
(1) የአስተዳደሩ ምክር ቤት የሌላው ክፍል ሥልጣን ባልሆኑት በበጎ አድራጎት ድርጅት ጒዳዮች ሁሉ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

(2) ምክር ቤቱ በተለይ ዲሬክተሮቹን ይሾማል፤ ይሽራል፤ የሥራቸውን መካሄድ ይቈጣጠራል፤ ሒሳባቸውንም ያጸድቃል፡፡

ቊ 497፡፡ የውስጥ ደንቦቹን ስለ መለዋወጥ (1) መሠረቱ፡፡


የአስተዳደር ምክር ቤቱ የወሰነው የበጎ አድራጎት ድርጅት የውስጥ ደንቦች መለዋወጥ፤ የድርጅቱ ጠባቂና ተጠባባቂው መሥሪያ ቤት
ካላጸደቀው በቀር ውጤት የለውም፡፡

ቊ 498፡፡ (2) የበጎ አድራጎት ድርጅቱ መሥራች የሚያደርገው ክልከላ፡፡


(1) የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ሥራ መሥራች አንዳንዶቹ የበጎ አድራጎት ድርጅት ደንቦች እንዳይለዋወጡ ግልጽ በሆነ ውሳኔ ለመከልከል
ይችላል፡፡
(2) የበጎው አድራጎት ድርጅት መሥራች እንዲህ አድርጎ የገለጸውን ፈቃድ ተቃራኒ በመሆን የውስጥ ደንቦቹ የተለዋወጡ እንደሆነ፤
መሥራቹ የመረጠው ሰው፤ ወይም የመሥራቹ ወራሾች የበጎ አድራጎቱ ድርጅት ተግባር ፈርሷል ብለው እንዲያስታውቁላቸው ለዳኞች
ጥያቄ ለማቅረብ ይችላሉ፡፡

(3) የውስጥ ደንቦቹ መለዋወጥ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ሦስት ዓመት ወይም መሥራቹ ከሞተ ሠላሳ ዓመት ካለፈ በኋላ፤ ከዚህ በላይ
ባለው ኀይለ ቃል የተነገረው መብት ቀሪ ይሆናል፡፡
ቊ 499፡፡ የምክር ቤቱ ስብሰባ፡፡
(1) የአስተዳደሩ ምክር ቤት በውስጥ ደንቦቹ በተወሰነው ጊዜ ይሰበሰባል፡፡

(2) በሚያስቸኵል ጊዜ፤ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ በሚያሳይበት ጊዜ ሁሉ ዲሬክተሮቹ ስብሰባው እንዲደረግ ጥሪውን
ያደርጋሉ፡፡
ቊ 500፡፡ የምክር ቤቱ ውሳኔዎች፡፡
(1) የአስተዳደሩ ምክር ቤት ውሳኔዎች የሚፈጸሙት ፍጹም የሆነ የድምፅ ብልጫ ሲኖር ነው፡፡

(2) ለበጎ አድራጎት ድርጅት የተደረገው የጠባቂነትና የተጠባባቂነት መሥሪያ ቤት፤ የውሳኔዎቹን ፈራሽነት ወይም እንዳይፈጸሙ
መታገዳቸውን እንዲያስታውቁለት ለዳኞች ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል፡፡
ቊ 501፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅት መብቶችና ግዴታዎች፡፡
(1) የማኅበሮችን ስም፤ የመኖሪያ ስፍራንና ችሎታን የሚመለከቱት የዚህ አንቀጽ ውሳኔዎች በድርጅቶችም ላይ ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡

(2) ድርጅቱ የጠባቂውንና የተጠባባቂውን መሥሪያ ቤት አስፈቅዶ የቁም ስጦታዎችንና የኑዛዜ ስጦታዎችን መቀበል ይችላል፡፡
ቊ 502፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተጠቃሚዎች መብቶች፡፡
(1) ለጥቅማቸው ተብሎ የበጎው አድራጎት ድርጅት የተቋቋመላቸው ሰዎች መብታቸው እንዲከበርላቸው ሲሉ በበጎው አድራጎት ድርጅት
ላይ ክስ ለማቅረብ ይችላሉ፡፡

(2) ተጠቃሚዎቹ በደንቦቹ በሚበቃ (በሚገባ) ተለይተው ያልታወቁ እንደሆነ የበጎው አድራጎት ድርጅት ዲሬክተሮች ተገቢ መስሎ
በሚታያቸው ግምት ይወስኗቸዋል፡፡

ቊ 503፡፡ የበጎው አድራጎት ድርጅት መቅረት፡፡ (1) የውስጥ ደንቦቹ፡፡


የበጎ አድራጎት ድርጅት በውስጥ ደንቦቹ በተወሰኑት ምክንያቶች ቀሪ ይሆናል፡፡
ቊ 504፡፡ (2) ሌሎች ሁኔታዎች (ምክንያቶች)፡፡
የበጎ አድራጎት ድርጅት ለጠባቂነት በተደረገለት መሥሪያ ቤት ወይም በዐቃቤ ሕግ በኩል በሚቀርበው ጥያቄ ዳኞች የበጎው አድራጎት
ድርጅት ቀሪ ሁኗል ብለው የሚወስኑት፡-

(ሀ) ግቡ (ዓላማው) የተፈጸመ እንደሆነ፤ ወይም ወደ ግቡ ለመድረስ የማይችል እንደሆነ፤

(ለ) የተባለው ግብ ሕገ ወጥ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ እንደሆነ፤

(ሐ) የበጎው አድራጎት ድርጅት በደንቦቹ ከተመለከተው ግብ ሌላ የተከተለ እንደሆነ፤

(መ) የበጎው አድራጎት ድርጅት ዕዳውን ለመክፈል ችሎታ ያጣ እንደሆነ ነው፡፡


ቊ 505፡፡ የብዙዎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መቀላቀል፡፡
(1) የሁለት ወይም የብዙዎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መቀላቀል ለጠቅላላ ጥቅም ተፈላጊ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ የነዚህን የበጎ አድራጎት
ድርጅት የሥራ መካሄድ መከናወን አንድነት ለማያያዝ በአገር ግዛት ሚኒስቴር ጥያቄ ዳኞቹ የነዚህኑ መቀላቀል ለመፍቀድ ይችላሉ፡፡

(2) ለጠባቂነትና ለተጠባባቂነት የተደረገው መሥሪያ ቤት ባለጒዳዮቹ ለሆኑት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የጋራቸው ከሆነ እንደሆነ፤
ስለተባለው ጒዳይ የሚቀርበውን ጥያቄ የተባለው መሥሪያ ቤት ሊያቀርበው ይችላል፡፡

(3) በዚህ ዐይነት ለተቋቋመው ድርጅት አዲስ የውስጥ ደንቦች ይኖሩታል፡፡


ቊ 506፡፡ የሒሳብ መጣራትና መቈጣጠር፡፡
(1) ስለ ማኅበሮች ሒሳብ ማጣራት የተነገሩት የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች በበጎ አድራጎት ድርጅት ሒሳብ ማጣራትም ላይ ተፈጻሚዎች
ይሆናሉ፡፡

(2) ስለ ማኅበሮች የሒሳብ መቈጣጠር የተነገሩት የዚህ አንቀጽ ውሳኔዎች ስለ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የሒሳብ መቈጣጠር ነገር
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(3) ለድርጅቶች ጠባቂነትና ተጠባባቂነት የተቋቋመ መሥሪያ ቤት ያለ እንደሆነ ለማኅበሮቹ ጽሕፈት ቤት የተሰጠው ሥራ ለድርጅቶች
ጠባቂና ተጠባባቂ መሥሪያ ቤት ይሰጣል፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ኮሚቴዎች፡፡
ቊ 507፡፡ ፈቃድን የማግኘት ግዴታ፡፡
(1) ስለ አንድ የተወሰነ ሥራ ጥቅም፤ ስለ ሰው ፍቅር ወይም ስለ ጠቅላላ ጥቅም በይፋ በሚደረጉት ልመናዎች በታላላቅ የሕዝብ በዓላት
ቀኖች፤ ወይም በዚህ ተራ ውስጥ በሚገኙት አደራረጎች ረዳትነት፤ ገንዘብን ወይም ሌሎችን ንብረቶች የመሰብሰብ ዓላማ ያላቸው
ኮሚቴዎች የተቋቋሙትና የሚሠሩት በመንግሥቱ ጠቅላላ ግዛት ውስጥ ሲሆን በአገር ግዛት ሚኒስቴር ውሳኔ፤ በአንድ አገር ክፍል ወይም
በአንድ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሲሆን ደግሞ ክፍሉን በሚመለከተው ጠቅላይ ገዢ ካልተፈቀደላቸው በቀር ይህን ሥራቸውን ለማከናወን
አይችሉም፡፡

(2) ሳይፈቀድላቸው በይፋ የሚደረገውን ልመና የሚያደራጁ ወይም ከሕዝብ ስጦታዎችን ወይም ገንዘብን የሚለምኑ ኮሚቴዎች ለዚሁ
ነገር በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ውሳኔዎች ይቀጣሉ፡፡
ቊ 508፡፡ የኮሚቴዎች ድርጅት፡፡
(1) ውሳኔው በኮሚቴ የሚሰበሰቡትን ሰዎች ያስታውቃል፡፡

(2) የተባለው የጊዜ ውሳኔ የኮሚቴውን ሥራና ዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም ሥራውን ሊፈጽምበት የሚገባውን ጊዜ ለይቶ ያስታውቃል፡፡

(3) አስፈላጊ ሲሆን የኮሚቴው ሥራ ሊፈጸም የሚቻልበትን የአደራረጉን ዐይነት ይወስናል፤ በኮሚቴው የተሰበሰበውን መላውን ገንዘብና
በሥራ ላይ የመዋሉን ለመቈጣጠርም አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን ያዛል፡፡
ቊ 509፡፡ ስጦታዎችን የእንሰጣለን ባዮች ፊርማ፡፡
(1) ኮሚቴው ስጦታዎችንና የእንሰጣለን ባዮችን ፊርማ ለመቀበል ይችላል፡፡

(2) የኮሚቴው ፕሬዚዳንት፤ ፈራሚዎች የሰጡትን ቃል ለማስፈጸም በፈራሚዎቹ ላይ ክስ ለማቅረብ ሥልጣን አለው፡፡
ቊ 510፡፡ የአባሎቹ ኀላፊነት፡፡
(1) የኮሚቴው አባሎች ስለ ሥራው መካሄድና ስለ አስተዳደሩ በየራሳቸውና በአንድነት ኀላፊዎች ናቸው፡፡

(2) ማናቸውም ሰጪ ወይም እሰጣለሁ ብሎ የፈረመ ሰው ወይም ዐቃቤ ሕግ የኮሚቴውን አባሎች ባለባቸው ኀላፊነት ሊጠይቃቸው
ይችላል፡፡
ቊ 511፡፡ የኮሚቴው መቅረት፡፡
ኮሚቴው የተወሰነው ጊዜ ሲያልቅ ወይም ሥራውን በፈጸመ ጊዜ ቀሪ ይሆናል፡፡
ቊ 512፡፡ የኮሚቴው መፍረስ፡፡
ኮሚቴው በአገር አገዛዝ ትእዛዝ ብቻ ለመፍረስ የሚቻለው፡-

(ሀ) ከዓላማው የተለየ እንደሆነ፤

(ለ) የዓላማው አፈጻጸም የማይቻል እንደሆነ ወይም በማናቸውም ዐይነት የተተወ መሆኑ ግልጽ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 513፡፡ የሒሳብ ማጣራት (1) ንብረቱ የማይበቃ ሲሆን፡፡

(1) በኮሚቴው የተጠራቀሙት ንብረቶች ኮሚቴው ያሰበውን ሥራ ለመፈጸም በቂ ሆነው ያልተገኙ እንደሆነ ወይም የተባለው ሥራ
የማይቻል መሆኑ የተገለጸ እንደሆነ ለኮሚቴው ፈቃድ በሰጠው ውሳኔ፤ ለተመለከተው ዓላማ ይውላሉ፡፡

(2) ስለዚህ ነገር በውሳኔው የተነገረ ቃል የሌለ እንደሆነ፤ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት እንዲያዝባቸው ተደርጎ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት
ለአንድ የበጎ አድራጎት ሥራ ያውላቸዋል፡፡

(3) ለኮሚቴው ንብረትን የሰጡ ሰዎች፤ መልሰው የመውሰድን መብት በውል በግልጽ አግብተው ካልተገኙ በቀር መልሰው ለመውሰድ
አይችሉም፡፡
ቊ 514፡፡ (2) ቀሪ ንብረት፡፡

(1) ኮሚቴው የተሰበሰበው ንብረት ለተወሰነው ሥራ አስፈላጊ ከሆነው በላይ ትርፍ የተገኘ እንደሆነ በተወሰነው ሒሳብ ላይ ትርፍ ሆኖ
የተገኘው ገንዘብ ኮሚቴው በፈቀደው ውሳኔ ለተመለከተው ዓላማ ይውላል፡፡

(2) ስለዚህ ነገር በውል የተነገረ ቃል የሌለ እንደሆነ ገንዘቡ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት እንዲያዝበት ተደርጎ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት
ለአንድ የበጎ አድራጎት ሥራ ያውለዋል፡፡

(3) ለኮሚቴው ገንዘብ የሰጡት ሰዎች ገንዘቡን መልሰው ለመውሰድ አይችሉም፡፡


ቊ 515፡፡ ወደ በጎ አድራጎት ድርጅት መለወጥ፡፡
(1) ኮሚቴው የሰበሰበው ንብረት በውስጥ ደንቦቹ መሠረት ቀዋሚ እንዲሆን ለተወሰነ ዓላማ እንዲውል የታሰበ እንደሆነ በኋላ ወደ
ተባለው ዓላማ ለመድረስ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ማቋቋም ይገባል፡፡

(2) የበጎ አድራጎት ድርጅትን የሚመለከቱ ደንቦች በዚህ ጊዜ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡


ክፍል 3፡፡
ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውሉ የአደራ ንብረቶች (ፊዴይኮሚስ)፡፡
ቊ 516፡፡ ትርጓሜ፡፡
ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውል የአደራ ንብረት ማለት፡- የአደራ ንብረት አቋቋሚው በሰጠው መሪ ትእዛዝ መሠረት የአደራ ጠባቂ
የሚያስተዳድራቸው አንድ ወይም ብዙ ንብረቶች ራሳቸውን ችለው የተቋቋሙበት ድርጅት (ስሪት) ነው፡፡

ቊ 517፡፡ አቋቋሙ (ፎርሙ)፡፡

(1) ይህ ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውል የአደራ ንብረት በሕይወት ባሉ ሰዎች መካከል በሚደረግ ስጦታ ወይም በኑዛዜ ሊቋቋም ይችላል፡፡

(2) የዚህ የአደራ ንብረት መቋቋም ስለ አቋቋሙም ሆነ ስለ ሥረ ነገሩ ስጦታዎችን ወይም ኑዛዜዎችን በሚመለከቱ ደንቦች ይመራል፡፡
(3) አንድ ለልዩ በጎ አድራጎት የሆነውን የአደራ ንብረት ለማቋቋም በስጦታው ወይም በኑዛዜው ረገድ አንድ ግልጽ የሆነ የውል ቃል መጻፍ
የግድ አስፈላጊ ነው፡፡
ቊ 518፡፡ በልዩ በጎ አድራጎት ንብረት ተጠቃሚ፡፡
በልዩ በጎ አድራጎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚችለው በሕይወት ያለ ወይም ባይሆን እንኳን ይህ የአደራ ንብረት በተቋቋመበት ጊዜ የተፀነሰ
ሰው ብቻ ነው፡፡
ቊ 519፡፡ የአደራ ንብረት አስተዳዳሪዎች ብዛት፡፡
(1) የልዩ በጎ አድራጎት ንብረት አስተዳዳሪዎች ቊጥር ከአራት በላይ ሊሆን ሳይችል፤ ባንድ ብቻ ወይም በብዙ አስተዳዳሪዎች ለመተዳደር
ይችላል፡፡

(2) ቊጥራቸው ከአራት በላይ የሆነ አስተዳዳሪዎች ተመርጠው እንደሆነ በመጀመሪያ የተመረጡት 4 ቱ ብቻ ይህን ሥራ ያካሂዳሉ፡፡

(3) የተመረጡት የአደራ ንብረት አስተዳዳሪዎች ሥራውን አንቀበልም ያሉ፤ የሞቱ ወይም ችሎታ ያጡ እንደሆነ ሌሎች የተመረጡት ሰዎች
በምርጫቸው ተራ ገብተው በፊተኞቹ እግር ይተካሉ፡፡
ቊ 520፡፡ የአደራ ንብረት አስተዳዳሪዎች ብዛት፡፡
(1) የአደራ ንብረት አስተዳዳሪን የሚመርጠው፤ ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለውን የአደራ ንብረት ያቋቋመው ሰው ወይም እርሱ የመረጠው
ሰው፤ እርሱ የመረጠው ባይኖር ዳኞች ናቸው፡፡

(2) በእንደዚህ ያለ የተመረጠው አስተዳዳሪ የተሰጡትን ሥራዎች አልቀበልም ያለ ወይም የሞተ ወይም ችሎታ ያጣ እንደሆነ፤ የአደራውን
ንብረት ያቋቋመው ሰው ለዚህ ነገር የመምረጥን ሥልጣን የሰጠው ወይም የተባለው ሰው ያልተገኘ እንደሆነ ዳኞቹ አንድ አዲስ አስተዳዳሪ
ይመርጣሉ፡፡
ቊ 521፡፡ የአስተዳዳሪዎቹ ሥራ መልቀቅ፡፡
(1) አስተዳዳሪው (ፊዴይኮሚሴሩ) የሚገባ ምክንያት ያለው ሲሆን ወይም የተሰጡትን ሥራዎች ዐሥር ዓመት ሙሉ አካሂዶ እንደሆነ፤
ሥራውን ለመተው ይችላል፡፡

(2) የአስተዳዳሪነቱ ኀላፊነት እርሱ የሥራ መልቀቂያ ስንብቱን ከመስጠቱ በፊት ወይም ከሰጠ በኋላ በተመረጠው ሌላ የአደራ ንብረት
አስተዳዳሪ ላይ እስኪወድቅ ድረስ፤ የተባለው የአስተዳዳሪነት ኀላፊነት በሱው ላይ እንደሆነ ይቈያል፡፡
ቊ 522፡፡ የአዲሱ አስተዳዳሪ መሻር፡፡
የሚገባ ምክንያት ሲኖር ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለውን የአደራ ንብረት ያቋቋመው ወይም እርሱ የመረጠው ሰው ወይም
ከአስተዳዳሪዎቹ አንዱ ወይም በአደራው ንብረት ተጠቃሚ ከሆኑት አንዱ ሰው ባቀረበው ጥያቄ ዳኞች ያንድ አስተዳዳሪ ሥልጣን
እንዲቀር አድርገው በርሱ ቦታ እነርሱ የመረጡትን አዲስ አስተዳዳሪ ለማድረግ ይችላሉ፡፡
ቊ 523፡፡ የአደራ አስተዳዳሪ ሹመት ማስረጃ፡፡
(1) አስተዳዳሪው የአስተዳዳሪነቱንና የሥልጣኑን ማስረጃ ዳኞች እንዲሰጡት ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) ይህ ማስረጃ አስፈላጊ ሲሆን የተሰጠው ሥልጣን የሚቈይበትን ጊዜ ለይቶ ያስታውቃል፡፡


ቊ 524፡፡ ስለ ብዙ የአደራ ንብረት አስተዳዳሪዎች፡፡
(1) ብዙዎች አስተዳዳሪዎች ያሉ እንደሆነ ተቃራኒ የሚሆን ውሳኔ ከሌለ በቀር አስተዳዳሪዎቹ በመካከላቸው በሚደረገው ስምምነት የአደራ
ንብረት አስተዳደርን የሚመለከቱትን ውሳኔዎች ይሰጣሉ፡፡

(2) ሳይስማሙ በሚቀሩበት ጊዜ፤ በድምፅ ብልጫ ይወሰናል፡፡


(3) በድምፅ ብልጫ የተሰጠውን ውሳኔ ያልተቀበሉ ሰዎች በውሳኔው ያለ መስማማታቸውን በፕሮሴቬርባል ውስጥ እንዲጻፍላቸው
ለመጠየቅ መብት አላቸው፡፡
ቊ 525፡፡ ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለው የአደራ ንብረት አስተዳደር፡፡
(1) አስተዳዳሪው (ፊዴይኮሚሴሩ) ጠንቃቃና እንደ አስተዋይ የሥራ ሰው ሁኖ ይህን የተባለውን የአደራ ንብረት ያስተዳድራል፡፡

(2) ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውሉት እነዚህ የአደራ ንብረቶች የሚባሉትና የራሱ ንብረቶች እንዳይቀላቀሉ ይጠነቀቃል፡፡

(3) ለዚሁ ነገር አስፈላጊ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ሁሉ እንዲያደርግ ይገደዳል፡፡


ቊ 526፡፡ በፍርድ በኩል የንብረቱ ወኪል፡፡
(1) አስተዳዳሪው በፍርድ ረገድ ለተባለው የአደራ ንብረት እንደራሴ ነው፡፡

(2) በአስተዳዳሪነቱም በተቋቋሙ የአደራ ንብረቶች ተጠቃሚዎች ነን የሚሉት ሰዎች በፍርድ ቤት ሊከሱት ይችላሉ፡፡
ቊ 527፡፡ የአደራ ንብረት አስተዳዳሪ ሥልጣን፡፡
(1) የአደራ በሚባሉት ንብረቶች ላይ ያለው የአስተዳዳሪው ሥልጣን የአንድ ባለሀብት ሥልጣን ነው፡፡

(2) ስለሆነም ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለው የአደራው ንብረት በተቋቋመበት የመመሥረቻ ጽሑፍ ተቃራኒ የሚሆን ውሳኔ ከሌለ በቀር
አስተዳዳሪው የማይንቀሳቀሱትን ንብረቶች ዳኞች ካልፈቀዱለት በቀር ለመሸጥ ለመለወጥ አይችልም፡፡

(3) በማናቸውም ሁኔታ አስተዳዳሪው ንብረቶቹን ያለ ዋጋ ለመልቀቅ አይችልም፡፡

ቊ 528፡፡ የአቋቋሚው መሪ ትእዛዞች (1) መሠረቱ፡፡

(1) የአደራ ንብረት አስተዳዳሪው ንብረቶቹን ካቋቋመው ሰው የተቀበላቸውን ግልጽ የሆኑ መሪ ትእዛዞች መከተል አለበት፡፡

(2) ስለሆነም በንብረቱ ተጠቃሚ ለሆነው ሰው ጥቅም የሚያስፈልግ ሆኖ የታየ እንደሆነ ከተባሉት መሪ ትእዛዞች ውጭ እንዲሠራ ከዳኞች
ማስፈቀድ አለበት፡፡

ቊ 529፡፡ (2) ቅጣት፡፡

(1) ለአደራ ንብረት አስተዳዳሪው ሥልጣን ወሰን የሚሰጥባቸው ወይም በሥልጣኑ የሚሠራበትን ዐይነት የሚደነባባቸው የአደራው
ንብረት የተቋቋመበት ወል ውሳኔዎች መኖራቸውን የሦስተኛ ወገኖች ማወቃቸው ወይም ማወቅ እንደ ነበረባቸው ካልተረጋገጠ በቀር
ውሳኔዎቹ ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ለመሆን አይችሉም፡፡

(2) እነዚህን ውሳኔዎች አለመከተል የሚያስከትለው ቅጣት አስተዳዳሪውን በኀላፊነት ተጠያቂ ማድረግ ብቻ ነው፡፡

(3) የአደራ ንብረት አስተዳዳሪው ለልዩ በጎ አድራጎት ለሚውለው የአደራ ንብረት ጥቅም ሲል በቅን ልቡና የሠራው ወይም በቅን ልቡና
የሠራ መስሎት ያደረገው ወይም ይህን መልካም አሳቡን እውነተኛ ለመሆኑ አእምሮ የሚቀበለው መስሎ የታያቸው እንደሆነ ዳኞች
ለአስተዳዳሪው ከሙሉ ኀላፊነት ወይም በከፊል ነፃ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
ቊ 530፡፡ የንብረት መተካት፡፡
የአደራ አስተዳዳሪው ባደረገው መሸጥ መለወጥ በተተኩት ንብረቶች የተገኙት ወይም ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውሉት የአደራ ንብረቶች
ያፈሩዋቸው ገቢዎች በተባሉት የአደራ ንብረቶች ላይ ተጨማሪ ይሆናሉ፡፡
ቊ 531፡፡ የግል ጥቅም ያለ መኖር፡፡
የአደራ ንብረት አስተዳዳሪው ለልዩ የበጎ አድራጎት የሚውለው የአደራ ንብረት በተቋቋመበት ውል ውስጥ በግልጽ ተነግረው ከተፈቀዱለት
ጥቅሞች በቀር ከተባለው የአደራ ንብረት ላይ አንዳች የግል ጥቅም መውሰድ አይገባውም፡፡
ቊ 532፡፡ የጉዳት ካሣ፡፡
የአደራ ንብረት አስተዳዳሪው በተባለው የአደራ ንብረት አስተዳደር ምክንያት ስላደረገው ወጪ ገንዘብና፤ ስለ ደረሱበት ግዴታዎች
የጉዳትን ካሣ የማግኘት መብት አለው፡፡
ቊ 533፡፡ የአስተዳዳሪው ኀላፊነት፡፡
የአደራ ንብረት አስተዳዳሪው ውክልናን በሚመለከቱት ውሳኔዎች መሠረት በልዩ አድራጎት በአደራው ንብረቶች በሚጠቀሙት ሰዎች
ዘንድና የተባለው የአደራ ንብረት በሚቋረጥበት ጊዜ ንብረቶችን መቀበል ለሚገባቸው ሰዎች ለአደራ ንብረቱ መልካም አስተዳደር ኀላፊ
ይሆናል፡፡
ቊ 534፡፡ ሒሳቦቹን ማቅረብ፡፡ (1) ለማን እንደሚደረግ፡፡

(1) አስተዳዳሪው አስተዳደሩን የሚመለከቱትን ሒሳቦችና የአደራውን ንብረት ሁኔታ የሚመለከተውን መግለጫ በአደራው ንብረት
መመሥረቻ ጽሑፍ ውስጥ ለተመረጠው ሰው ማቅረብ አለበት፡፡

(2) የተመረጠ ሰው የሌለ እንደሆነ በአደራው ንብረት የመመሥረቻ ጽሑፍ መሠረት ጥቅም ላለው ለማናቸውም ሰው ወይም በአስተዳደሩ
ሥራ ምትክ ለሆነው ሰው ማቅረብ አለበት፡፡

ቊ 535፡፡ (2) በምን ጊዜ እንደሚቀርብ፡፡

(1) የልዩ በጎ አድራጎት መመሥረቻ ጽሑፍ ሒሳብ የሚቀርብበትን ሌላ ጊዜ ያልወሰነ እንደሆነ፤ የተባለው ሒሳብ በዓመት በዓመት
አስተዳዳሪው አስተዳደሩን ሲጀምር በተወሰነው ወር ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡

(2) ለአእምሮ ተገቢ መስሎ የሚታይ አንድ ምክንያት ሲኖር አንድ ባለ ጕዳይ ባቀረበው ጥያቄ ዳኞች ሒሳቦቹ በመካከል ባለው ጊዜ ውስጥ
እንዲቀርቡ ለመፍቀድ ወይም አስተዳዳሪው ሒሳቦቹን ስለ ማቅረብ የተወሰነውን ጊዜ እንዲያዘገይ ወይም እንዲለወጥ ለመፍቀድ
ይችላሉ፡፡
ቊ 536፡፡ ከአስተዳዳሪው ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች፡፡
ከአስተዳዳሪው ላይ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች የአደራ ንብረት በሆኑት ሀብቶች ላይ አንዳች መብት የላቸውም፡፡
ቊ 537፡፡ ከአደራ ንብረት ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች፡፡
(1) አስተዳዳሪው በአደራው ንብረት ረገድ የተቋቋሙትን ሀብቶች በሚመለከት ውል የተዋዋላቸው ሰዎች የአደራው ንብረት በሆኑት
ሀብቶች ሁሉ መብታቸውን ሊሠሩበት ይችላሉ፡፡

(2) የአደራ ንብረት አስተዳዳሪው በግልጽ ራሱ የገባበት ግዴታ ከሌለ ወይም ስለ እንደራሴነት በሚለው አንቀጽ በተሰጡት ውሳኔዎች
መሠረት ካልሆነ በቀር ከአደራው ንብረት ላይ ገንዘብ ላላቸው ሰዎች የአደራ ንብረት አስተዳዳሪው ራሱ አላፊ ሆኖ አይያዝም፡፡

ቊ 538፡፡ የባለጥቅሞቹ መብቶች፡፡ (1) በአስተዳዳሪው ዘንድ፡፡

(1) የአደራው ንብረት ባለጥቅም፤ በአደራው ንብረት መመሥረቻ ጽሑፍ መሠረት ለእርሱ የሚገባው ትርፍ እንዲሰጠው የአደራ ንብረት
አስተዳዳሪውን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) ባለጥቅሙ መብቶቹ በሚያሠጋ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን አስተዳዳሪው እንዲሻር ወይም የተገቡ ተያዦችን እንዲሰጥ ለዳኞች ጥያቄ
ማቅረብ ይችላል፡፡

ቊ 539፡፡ (2) በአደራ ንብረቶች ላይ፡፡

(1) የአደራ ንብረቶች ባለጥቅም የአደራ ንበረት በሚባሉት ሀብቶች ላይ የማዘዝ ወይም የአስተዳደር አንዳች መብት የለውም፡፡

(2) ነገር ግን እነዚህን ንብረቶች በሚመለከተው ነገር የይርጋ ዘመን እንዲቋረጥ ማድረግን በመሳሰለው ሥራ መብቶቹን የመጠበቅ
ተግባሮችን ለመፈጸም ይችላል፡፡

(3) እንደዚሁም ደግሞ ለሦስተኞች ወገኖች ወይም ለአንዳንድ ሦስተኞች ወገኖች አንዳንዶቹ ንብረቶች የአደራው ንብረት (ሀብቶች)፤
ንብረቶች መሆናቸውን በማስታወቂያ ለመግለጽ አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን ለመፈጸም ይችላል፡፡
ቊ 540፡፡ ከተጠቃሚው ገንዘብ ጠያቂዎች፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለውን የአደራ ንብረት ያቋቋመው ሰው፤ የዚህን የአደራውን ንብረት ገቢ ከአስተዳዳሪው እጅ ላይ፤ በአደራው
ንብረት ተጠቃሚ ከሆነው ሰው ላይ ገንዘብ ጠያቂ የሆኑ ሰዎች ሊያዙት አይችሉም ብሎ ለመወሰን ይችላል፡፡

(2) ገቢዎቹ የማይያዙ ናቸው ተብሎ በዚህ በተባለው ዐይነት በውሉ ቃል ተነግሮ እንደሆነ ዋጋ ባለው ሁኔታ የንብረቱ ተጠቃሚ
ሊያስተላልፋቸው ወይም በዕዳ ውስጥ ሊያገባቸው አይቻልም፡፡

ቊ 541፡፡ (2) የዳኞች ሥልጣን፡፡


ስለሆነም ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር የተነገረው ሁኔታ ሲያጋጥምና በአደራው ንብረት ተጠቃሚ ሆኖ ሲገኝ ወይም የተጠየቀው ገንዘብ
የአደራው ንብረት ተጠቃሚ ከሠራው ወንጀል ወይም አታላይነት ጋራ ግንኙነት ያለው ሲሆን የአደራው ንብረት ባለጥቅም ወይም ከገንዘብ
ጠያቂዎች አንዱ በሚያቀርበው ጥያቄ የአደራው ንብረት ገቢ ገንዘቦች እንዲያዙ ወይም እንዲተላለፉ ለመፍቀድ ይችላሉ፡፡

ቊ 542፡፡ ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለውን የአደራውን ንብረት የሚያቋቁመው ውለታ መቅረት፡፡ (1) መደበኛ ሁኔታ፡፡

ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለው የአደራ ንብረት ውል የአደራውን ንብረት ያቋቋመው ሰው የወሰነው ጊዜ ሲያልቅ ቀሪ ይሆናል፡፡
ቊ 543፡፡ (2) የዳኞች ሥልጣን፡፡

(1) ዳኞች የአደራው ንብረት ባለጥቅም፤ ለሚያቀርበው ጥያቄ የሚሰጠው ውሳኔ በነገሩ አካባቢ ሁኔታ የሚገባ መስሎ የታያቸው እንደሆነ፤
በቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት በማናቸውም ጊዜ ቢሆን የተባለው የአደራው ንብረት ውል እንዲቀር ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(2) የአደራው አስተዳዳሪ በዳኝነቱ ሥነ ሥርዐት ጊዜ መሰማት አለበት፡፡

(3) ለልዩ በጎ አድራጎት የሚውለውን ንብረት ያቋቋመው ሰው፤ ግልጽ በሆነ የውል ቃል በዚህ በተባለው መብት ዳኞች እንዳይሠሩበት
ለመወሰን ይችላል፡፡
ቊ 544፡፡ የአደራው ንብረት የሒሳብ መጣራት፡፡
የአደራው ንብረት ውል ቀሪ በሚሆንበት ጊዜ አስተዳዳሪው የነዚህን ንብረቶች ባለሀብትነትና የአስተዳዳሪውን ሥራ ለማስረዳት
ጠቃሚዎች ከሆኑት ጽሑፎች ጋራ በንብረቱ መመሥረቻ ጽሑፍ መሠረት መብት ላላቸው ሰዎች የተባሉትን ንብረቶች ማስረከብ አለበት፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
በሕግ የሰው መብት ስለ ተሰጣቸው የውጭ አገር ዜጋ ማኅበሮችና ለልዩ አገልግሎት ስለ ተመደቡ የውጭ አገር ዜጋ ንብረቶች፡፡
ቊ 545፡፡ የሰው መብት ስለ ተሰጣቸው ማኅበሮች፡፡
(1) የማኅበሩ ዋና መኖሪያ ስፍራ በውጭ አገር ሆኖ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሥራ ለማካሄድ የሚፈቅድ የውጭ አገር ዜጋ ማኅበር አዲስ
አበባ ለሚገኘው ለማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ማመልከቻውን ማቅረብ አለበት፤ ከማመልከቻውም ጋራ የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ ተያይዞ
መቅረብ አለበት፡፡

(2) ለማቋቋም የተጠየቀው ሥራ ሕገ ወጥ ወይም ከመልካም ባህል ጋራ የማይስማማ የሆነ እንደሆነ የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት
የተጠየቀውን ፈቃድ ለመከልከል ይችላል፤ የማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ለነገሩ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት እንዲቋቋሙ በተጠየቁት ማኅበሮች
ጕዳይ የሚያገባቸውን ሚኒስቴሮች አሳብ መጠየቅ አለበት፡፡

(3) አንድ የውጭ አገር ዜጋ የሆነ በሕግ የሰው መብት የተሰጠው ማኅበር ይህን ፈቃድ ከማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ከማግኘቱ በፊት
በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ለመጀመርም ሆነ አባሎችን ለመሰብሰብ አይችልም፡፡
ቊ 546፡፡ ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ የውጭ አገር ዜጋ ንብረቶች፡፡
(1) በውጭ አገር የተቋቋሙ ለልዩ አገልግሎት የተመደበ ንብረት ድርጅቶች ይህ ሥራ እንዲፈቀድላቸው ለአገር ግዛት ሚኒስቴር
ማመልከቻቸውን ካላቀረቡ በቀር በኢትዮጵያ ውስጥ ሥራቸውን ለመጀመር አይችሉም፡፡

(2) ይህ ሥራ ሕገ ወጥ ዓላማ ያለው ወይም ለመልካም ባህል ተቃራኒ የሆነ እንደሆነ የአገር ግዛት ሚኒስቴር ፈቃድን ለመከልከል ይችላል፡፡
የአገር ግዛት ሚኒስቴርም በጕዳዩ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት በዚህ ጕዳይ የሚያገባቸውን ሚኒስቴሮች አሳብ መጠየቅ አለበት፡፡
ቊ 547፡፡ ፈቃዱን ወይም ጥያቄውን የመቀበሉ ውጤት፡፡
(1) በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው የውጭ አገር ማኅበሮች ወይም ለልዩ አገልግሎት የተመደበ የውጭ አገር ዜጋ ንብረት ድርጅቶችን
ይህን በቊጥር 547 የተመለከተውን ፈቃድ ወይም በቊጥር 546 የተመለከተውን የማጽደቅ ፈቃድ እንዳገኙ ወዲያውኑ በፍትሐ ብሔር
መብታቸው በሚጠቀሙበትና በሚሠሩበት ረገድ ልክ በኢትዮጵያ እንደ ተቋቋሙ በሕግ የሰው መብት እንደ ተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን
ማኅበሮችና ለልዩ አገልግሎት እንደ ተመደቡ እንደ ኢትዮጵያ ንብረቶች የሚቈጠሩ ይሆናሉ፡፡

(2) እንዲሁም በተቋቋሙበት አገር የታወቀላቸው ዜግነት በኢትዮጵያም የታወቀላቸው ይሆናል፡፡


ቊ 548፡፡ የተጠበቁ ሁኔታዎች፡፡
(1) በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው የውጭ አገር ዜጋ ማኅበሮች ወይም ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ ንብረቶች ድርጅቶች ወይም አንዳንድ
ልዩ ክፍል የሆኑት በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ማኅበሮችና ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ ንብረቶች የሚያካሂዱትና የሚያከናውኑት
ሥራ ሁሉ በአገር ግዛት ሚኒስቴር ልዩ ውሳኔ ሊከለከል ወይም ሊፈቀድ ይችላል፡፡

(2) የውጭ አገር ዜጋ የሆኑ በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች ወይም ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ የውጭ አገር ንብረቶች
ድርጅቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት የመሆን ችሎታቸው የሚቀነስባቸው፤ ስለዚሁ ጕዳይ ለውጭ አገር ሰው
በተሠራው ሕግ መሠረት ነው፡፡
ቊ 549፡፡ የፈቃዱን ወይም የማጽደቅ ፈቃዱን ጥያቄ ስለ መሻር፡፡
(1) በቊጥር 545 በተመለከተው መሠረት የተሰጠው ፈቃድና በቊጥር 546 መሠረት የማጽደቅ ፈቃድ ያገኘው ጥያቄ እንደ ነገሩ አጋጣሚ
ሁኔታ በማኅበሮች ጽሕፈት ቤት ወይም በአገር ግዛት ሚኒስቴር ሊሻር ይቻላል፡፡

(2) ይህም የፈቃድ መሻር ውሳኔ ለማኅበሩ ወይም ለንብረቱ ድርጅት በተገለጸበት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሕግ የሰው መብት የተሰጠው
ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ወይም ዲሬክተር ወይም ለልዩ አገልግሎት የተመደበው ንብረት አስተዳዳሪ ለዳኞች የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ
ይችላል፡፡
(3) ፍርድ ቤቱም፤ ይህ የተሰጠው ፈቃድ ወይም የማጽደቅ ፈቃድ ማመልከቻ የሚሻር ወይም የማይሻር መሆኑን እስኪወስን ድረስ
የፈቃዱን መሻር ውሳኔ አግዶ ለማቈየት ይችላል፡፡

ሁለተኛ መጽሐፍ፡፡
ስለ ቤተ ዘመድና ስለ ውርስ (አወራረስ)
አንቀጽ 4፡፡
ስለ ሥጋ ዝምድናና ስለ ጋብቻ ዝምድና፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ስለ ዝምድናና ስለ ጋብቻ
በጠቅላላው፡፡
ቊ 550፡፡ የሥጋ ዝምድና፡፡
(1) በዝምድና መተሳሰር የሚገኘው ከሥጋ ዝምድና ነው፡፡

(2) በወላጆችና በተወላጆች (ተወላድያን) መካከል በቀጥታ መሥመር የሚቈጠር የዝምድና መተሳሰር አለ፡፡

(3) ካንድ አባት እናት በተወለደ ወይም በአንድ ወላጅ ብቻ በሚገናኙ ሰዎች መካከል ወደ ጐን የሚቈጠር የትውልድ መሥመር አለ፡፡

ቊ 551፡፡ የሥጋ ዝምድና ደረጃ፡፡

(1) የሥጋ ዝምድና አቈጣጠር የጋራ ከሆነው የግንድ ወላጅ የዝምድና ደረጃ ጀምሮ ግራና ቀኝ ካለው ትውልድ መሥመር እስከ ሰባት
ትውልድ ድረስ ነው፡፡

(2) የሥጋ ዝምድና ከሰባተኛው የትውልድ ደረጃ ወዲያ ምንም ውጤት አይሰጥም፡፡

ቊ 552፡፡ ጋብቻ፡፡

(1) የጋብቻ ዝምድና ከጋብቻ ይገኛል፡፡

(2) ባል ከሚስት ወደ ላይ ከሚቈጠሩ ወላጆች ወይም ወደ ታች የሚቈጠሩ ተወላጆች ጋራ፤ ሚስት ከባሏ ወደ ላይ ከሚቈጠሩ ወላጆች
ወይም ወደ ታች ከሚቈጠሩ ተወላጆች (ተወላድያን) ጋራ ቀጥታ የሆነ የጋብቻ ዝምድና አላቸው፡፡

(3) ባል ከሚስቱ የጐን ዘመዶች ሚስት ከባሏ የጐን ዘመዶች ጋራ ወደ ጐን የሚቈጠር የጋብቻ ዝምድና አላቸው፡፡

ቊ 553፡፡ የጋብቻ ዝምድናን በ 3 ኛ ደረጃ ስለ መወሰን፡፡

የጋብቻ ዝምድና ወደ ጐን የሚቈጠር ዝምድና ላይ ከሦስተኛ የዝምድና ደረጃ ወዲያ ምንም ውጤት የለውም፡፡

ቊ 554፡፡ በሁለት በኩል ያለ የጋብቻ ዝምድና፡፡

(1) ባል ከሚስቱ ወንድም ሚስት፤ ወይም ከሚስቱ አኅት ባል፤ ሚስት ከባሏ ወንድም ሚስት ወይም ከባሏ እኅት ባል ጋራ ዕጥፍ የሆነ
የጋብቻ ዝምድና አላቸው፡፡

(2) ይኸው ዕጥፍ የሆነ የጋብቻ ዝምድና ተራ እንደሆነው የጋብቻ ዝምድና ውጤቶች አሉት፡፡

ቊ 555፡፡ የጋብቻ ዝምድና መጨረሻ፡፡

ዝምድናውን ያስገኘው ጋብቻ ቢፈርስም በጋብቻ የተገኘው የቀጥታ ዝምድናና የጐን ዝምድና መተሳሰር እንደ ጸና ይኖራል፡፡
ቊ 556፡፡ የጉዲፈቻ ዝምድና (1) መሠረቱ፡፡

በአንድ የጉዲፈቻ ውል የሥጋ ዝምድናና የጋብቻ ዝምድና በዚህ አንቀጽ በምዕራፍ ፲ በተጻፈው ድንጋጌ መሠረት ሊቋቋም ይችላል፡፡

ቊ 557፡፡ (2) ውጤት፡፡

በቊጥር 558 የተነገረው ድንጋጌ እንደ ተጠበቀ ሆኖ በማናቸውም አስተያየት የጉዲፈቻ እንደ ጉዲፈቻ አድራጊው ልጅ ይቈጠራል፡፡

ቊ 558፡፡ (3) የተጠበቀ ሁኔታ፡፡

(1) የጉዲፈቻ አድራጊው ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች ወይም ወደ ጐን የሚቈጠሩ ዘመዶች ጉዲፈቻውን በግልጽ የሚቃወሙ መሆናቸውን
ካስታወቁ ጉዲፈቻው በነርሱ በኩል አንዳችም ውጤት አያስከትልም፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል እንደ ተነገረው የጉዲፈቻ አድራጊው ዘመዶች መቃወሚያ የጉዲፈቻው ውል ከጸደቀበት ቀን አንሥቶ
እስከ አንድ ዓመት በአንድ ውል አዋዋይ መዝገብ ወይም በአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ካልተመዘገበ በቀር ፈራሽ ነው (አይጸናም)፡፡

(3) ጉዲፈቻ በጉዲፈቻ አድራጊው ባል ወይም ሚስት በተወላጆቹም ላይ ውጤት አለው (ይጸናል)፡፡

ቊ 559፡፡ የጉዲፈቻው ልጅ የጥንት ቤተ ዘመዶች፡፡

(1) የጉዲፈቻው ልጅ ከጥንት ቤተ ዘመዶቹ ጋራ ያለውን የዝምድና መተሳሰር እንደ ያዘ ይኖራል፡፡

(2) እንደዚሁም የጉዲፈቻ ልጅ በሆነው ሰው ባል ወይም ሚስትና ተወላጆች ላይ የዝምድናው መተሳሰር ይጸናል፡፡

(3) በማንኛዎቹም ሁኔታዎች፤ ከጉዲፈቻው ቤተ ዘመድና ከጥንት ቤተ ዘመድ መካከል ምርጫ ማድረግ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ
የጉዲፈቻው ቤተ ዘመድ ቅድሚያ ያገኛል፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
ስለ መተጫጨት፡፡
ቊ 560፡፡ ትርጓሜ፡፡

(1) መተጫጨት ማለት የእጮኛውና የእጮኛ À ቱ ቤተ ዘመዶች በልጆቻቸው መካከል ጋብቻ ይኖራል ብለው የእነዚሁ የሁለቱ ቤተ
ዘመድ አባሎች የሚያደርጉት ውል ነው፡፡

(2) ወደፊት ተጋቢዎች የሆኑት የእጮኛዎቹ የየአንዳንዳቸው ቤተ ዘመዶች ፈቃድ ካልሰጡ በቀር መተጫጨት ሕጋዊ ውጤት
አይኖረውም፡፡
ቊ 561፡፡ ለማግባት የተስፋ ቃል መስጠት፡፡

(1) በሁለት ሰዎች መካከል የማግባት የተስፋ ቃል መለዋወጥ መተጫጨት አይደለም፡፡

(2) ይህ የተስፋ ቃል በጥፋት ምክንያት ቢፈርስ በዚህ ሕግ በአንቀጽ 03 ከውል ውጭ ስለሚደርስ ኀላፊነትና ያላገባብ ስለ መበልጸግ
በተነገረው መሠረት ስለ ደረሰው ጕዳት ኪሣራ ማስከፈልን ያስከትላል፡፡

ቊ 562፡፡ የቤተ ዘመድ እንደራሴ፡፡ (1) የመጀመሪያው ጋብቻ እንደራሴ፡፡

የመጀመሪያ ጋብቻ ለሚያደርገው ዕጮኛ የቤተ ዘመድ እንደራሴ ሆኖ የሚቈጠረው፡-

(ሀ) የዚሁ የአግቢው አባት፤

(ለ) አባት የሌለ ወይም ፈቃዱን ለመስጠት የማይችል የሆነ እንደሆነ፤ እናት፤

(ሐ) እናት የሌለች፤ ወይም ፈቃድዋን ለመስጠት የማትችል የሆነች እንደሆነ፤ ከአያቶቹ ወይም ከቅድም አያቶቹ አንዱ፡፡

(መ) ወላጆች የሌሉ፤ ወይም ከነዚሁ ማናቸውም ፈቃዱን ለመስጠት የማይችል የሆነ እንደሆነ፤ ታላቅ ወንድም ወይም ያባት ወይም የእናት
ወንድም፡፡

ቊ 563፡፡ (2) ተከታይ ጋብቻ፡፡

ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር ከተጠቀሱት ማንኛዎቹም ሰዎች አንዱ፤ አስቀድሞ አግብቶ ለነበረ ሰው መተጫጨቱ የሚደረግ እንደሆነ የቤተ
ዘመድ እንደራሴ ሆኖ መተጫጨቱን ለመፍቀድ ይችላል፡፡

ቊ 564፡፡ (3) ሕጋዊ እንደራሴ ስለ ማጣት፡፡

(1) ወደፊት ከሚጋቡት አንዱ የቤተ ዘመድ እንደራሴ የሚሆነው ወላጅ ወይም ታላቅ ወንድም ወይም ታላቅ እኅት፤ ያባት ወይም የናት
ወንድም የሌለው እንደሆነ ለመተጫጨቱ የቤተ ዘመድ እንደራሴ የሚሆነውን ሰው በነጻ ይመርጣል፡፡

(2) ወደፊት ከሚጋቡት አንዱ ዕጮኛ፤ ዕድሜው ከሠላሳ ዓመት በላይ የሆነ እንደሆነ ወይም ዕጮኛ À ቱ ዕድሜዋ ሓያ አምስት ዓመት የሆነ
እንደሆነ ለመተጫጨቱ የቤተ ዘመድ እንደራሴ የሚሆነውን ሰው በነፃ ይመርጣል፡፡
ቊ 565፡፡ የዕጮኛዎቹ ፈቃድ፡፡
ዕጮኛውና ዕጮኛ À ቱ ፈቃዳቸውን ካልሰጡ በቀር መተጫጨቱ ሕጋዊ ውጤት የለውም፡፡
ቊ 566፡፡ ጋብቻን የሚከለክል ምክንያት፡፡
(1) የዕጮኛዎቹን ጋብቻ የሚከለክል ሕጋዊ ምክንያት ያለ እንደሆነ መተጫጨቱ ሕጋዊ ውጤት የለውም፡፡

(2) በተለይም ዕጮኛው ወይም ዕጮኛ À ቱ ለጋብቻ በሕግ የሚጠየቀውን ዕድሜ ካላደረሰ መተጫጨቱ ውጤት የለውም፡፡
ቊ 567፡፡ የመተጫጨቱ ሥርዐት (ፎርም)፡፡
የመተጫጨት ሥርዐት መተጫጨቱ በሚደረግበት ቦታ ልማድ መሠረት ይፈጸማል፡፡
ቊ 568፡፡ ምስክሮች፡፡
(1) የሆነ ሆኖ በማናቸውም አኳኋን ለተጋቢዎቹ ሁለት ሁለት ምስክሮች ከሌሏቸው የመተጫጨቱ ውል ፈራሽ ይሆናል፡፡

(2) ከባል ምስክሮች አንዱ፤ ከሚስቱ ምስክሮች አንዱ፤ የመጀመሪያ ምስክሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ቊ 569፡፡ የመተጫጨት ማስረጃ፡፡
(1) መተጫጨት በማናቸውም በሕዝብ ቊጥር መዝገቦች (የክብር መዝገብ) መጻፍ የለበትም፡፡

(2) መተጫጨትን በማናቸውም ማስረጃ ለማስረዳት ይቻላል፡፡


ቊ 570፡፡ መተጫጨቱ የሚቈይበት ጊዜ፡፡
መተጫጨቱ ሲደረግ የሠርጉን በዓል ለማድረግ የተወሰነ ጊዜ ያልተደረገ እንደሆነ፤ ዕጮኛው ወይም ዕጮኛ À ቱ ወይም ከቤተ ዘመዳቸው
የተፈቀደለት እንደራሴ የሰርጉ በዓል እንዲደረግ ፈቃድን ከገለጸበት ቀን አንሥቶ በስድስት ወር ውስጥ መፈጸም አለበት፡፡
ቊ 571፡፡ የመተጫጨት መፍረስ፡፡
(1) ዕጮኛው ወይም ዕጮኛይቱ ወይም ለመተጫጨቱ ፈቃድ የሰጠው ሌላው ሰው መዘግየታቸውን ወይም እንቢተኛነታቸውን
የሚያስረዳ ሕጋዊ ትክክለኛ ምክንያት ሳይኖር ጋብቻውን እንቢ ያሉ እንደሆነ መተጫጨት ፈራሽ ይሆናል፡፡

(2) እንዲሁም ዕጮኛው ወይም ዕጮኛ À ቱ ወይም ለመተጫጨቱ ፈቃድ የሰጠው ሰው በሁኔታ ወይም በጠባይ (በሞራል) ጋብቻው
እንዳይፈጸም የሚያደርግ ሁኔታ ያሳየ እንደሆነ መተጫጨቱ ፈራሽ ይሆናል፡፡

ቊ 572፡፡ የመተጫጨት መፍረስ የሚያስከትለው ውጤት፡፡ (1) ወጪና የተቀበሉትን ማጫ ስለ መመለስ፡፡

(1) ለመተጫጨቱ መፍረስ አላፊ የሆነው ሰው በመተጫጨት ምክንያት የተደረጉትን ወጪዎች ሁሉ ለመክፈል ይገደዳል፡፡

(2) በመተጫጨት ምክንያት የተቀበለውን ስጦታ ለመተጫጨቱ መፍረስ አላፊ የሆነው ሰውና እንዲሁም የቤተ ዘመዱ ወገኖች መመለስ
አለባቸው፡፡
ቊ 573፡፡ (2) የሕሊና ጉዳት፡፡

(1) የመተጫጨቱ መፍረስ ስለሚያስከትለው የሕሊና ጉዳት፤ ለመፍረሱ አላፊ ላልሆነው ዕጮኛ ወይም ለዕጮኛይቱ ወይም ለቤተ ዘመዱ
በሕሊና ግምት ተገቢ የሆነ ካሣ ሊሰጥ ይቻላል፡፡

(2) የዚህን ካሣ ልክ ለመወሰንና ካሣውንም ለመጠየቅ የሚችለውን ባለመብት ዳኞች የአገሩን ልማድ መሠረት አድርገው ይከተላሉ፡፡

(3) ስለ ሕሊና ጉዳት እንዲከፈል የሚደረገው ኪሣራ ከአንድ ሺሕ የኢትዮጵያ ብር የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡

ቊ 574፡፡ (3) የመቀጫ የውል ቃል፡፡

(1) በመተጫጨት ውል ውስጥ አንድ የመቀጫ ውል ቃል ተጽፎበት እንደሆነ መተጫጨቱ እንዲፈርስ ያደረገው ሰው፤ በውሉ
የተጠቀሰውን ገንዘብ መክፈል አለበት፡፡

(2) ሁኔታው የሚያስከትላቸውን ሁሉ በመገመት በውሉ የተጠቀሰውን ገንዘብ ዳኞች ሊቀንሱት ይቻላል፡፡

(3) ገንዘቡ ከመጠን በላይ መሆኑ የተገለጸ እንደሆነ መቀነስ አለበት፡፡


ቊ 575፡፡ የወላጅ መቃወም፡፡
(1) በግልጽ ፈቃዱን ያልሰጠ ከዕጮኛዎቹ ያንደኛው ወላጅ ለጋብቻው ተቃዋሚነቱን የገለጸ እንደሆነ የመተጫጨቱ መፍረስ ምንም
አላፊነትን አያስከትልም፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ሁለቱም ወገኖች የተቀበሏቸውን ስጦታዎች ብቻ መመለስ አለባቸው፡፡


ቊ 576፡፡ ይርጋ፡፡
በመተጫጨት መፍረስ ላይ ተመሥርተው የሚቀርቡት ክሶች ሁሉ መተጫጨቱ ከፈረሰበት ቀን አንሥቶ በአንድ ዓመት ውስጥ ካልቀረቡ
በይርጋ የሚታገዱ ይሆናሉ፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ጋብቻ አፈጻጸም፡፡
ቊ 577፡፡ ልዩ ልዩ ዐይነት ጋብቻ፡፡
(1) ጋብቻ ባንድ የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ፊት ሊደረግ ይቻላል፡፡

(2) እንደዚሁም ሕጉ በሁለቱ ወገኖች ሃይማኖት ወይም ባገር ልማድ መሠረት የሚደረጉትን ጋብቻዎች ያውቃል (ይቀበላል)፡፡
ቊ 578፡፡ ብሔራዊ ጋብቻ፡፡
ጋብቻ ለማድረግ አንድ ወንድና አንዲት ሴት በክብር መዝገብ ሹም ፊት ሲቀርቡና የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹምም ፈቃዳቸውን ሲቀበለው
ጋብቻ ተፈጸመ ይባላል፡፡
ቊ 579፡፡ የሃይማኖት ጋብቻ፡፡
አንድ ወንድና አንዲት ሴት ውሳኔዎችን ወይም ሥርዐቶችን እንደ ሃይማኖታቸው ወይም ከነርሱ ባንደኛው ሃይማኖት ሲፈጽሙ ዋጋ ያለው
የሚጸና ጋብቻ እንዳቋቋሙ ይቈጠራል፡፡
ቊ 580፡፡ የልማድ ጋብቻ፡፡
አንድ ወንድና አንዲት ሴት በጐሣቸው ልማድ ወይም ከነርሱ በአንደኛው ጐሣ ልማድ ከሁለቱ መካከል ነዋሪ የሆነውን ግንኙነት
የሚያስከትል ሥነ ሥርዐትን ፈጽመዋል የሚያሰኘውን ካደረጉ በመካከላቸው ጋብቻ አለ ይባላል፡፡
ክፍል 1፡፡
ለማንኛዎቹም ዐይነቶች ጋብቻዎች የሚሆኑ አጠቃላይ ሁኔታዎች፡፡
ቊ 581፡፡ ዕድሜ፡፡
(1) ወንድ አሥራ ስምንት ዓመት፤ ሴቲቱ ዐሥራ አምስት ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ ለማድረግ አይችሉም፡፡

(2) ስለ ከባድ ምክንያት በከፍተኛ ግምት ሁለት ዓመት ዕድሜ ለመቀነስ እንዲቻል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ወይም ንጉሠ ነገሥቱ ለዚሁ
ጕዳይ በተለይ የሚሾሙት ሰው ለመፍቀድ ይችላል፡፡
ቊ 582፡፡ የሥጋ ዝምድና፡፡
ጋብቻ የሥጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የተከለከለ ነው፡፡
ቊ 583፡፡ የጋብቻ ዝምድና፡፡
ጋብቻ የጋብቻ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል የተከለከለ ነው፡፡
ቊ 584፡፡ በሕግ ያልተረጋገጠ ልጅነት፡፡
የዲቃላ ልጅነት ተወላጅነቱ በሕግ የታወቀለት ባይሆንም እንኳ ከዚህ በላይ ባሉት ሁለት ቊጥሮች እንደተመለከተው ጋብቻን
ለማስከልከል በቂ ነው፡፡
ቊ 585፡፡ በጋብቻ ላይ ጋብቻ፡፡
አንድ ሰው አስቀድሞ በጋብቻ የተሳሰረ ከሆነ ጋብቻው እስካለ ድረስ ሁለተኛ ጋብቻ ለማድረግ አይችልም፡፡
ቊ 586፡፡ ጋብቻን በእንደራሴ ለመፈጸም የማይቻል ስለ መሆኑ፡፡
(1) እያንዳንዳቸው ተጋቢዎች፤ ጋብቻ በሚፈጸምበት ጊዜ ራሳቸው መፍቀድ አለባቸው፡፡

(2) ስለ ከባድ ምክንያት የመንግሥቱ ዐቃቤ ሕግ ካልፈቀደ በቀር በእንደራሴነት ጋብቻን መፈጸም አይፈቀድም፡፡
ቊ 587፡፡ አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ ጋብቻ፡፡
አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ ጋብቻ ሊፈጸም የሚቻልበት ሁኔታ በዚህ ሕግ ስለ ሰዎች ችሎታ በተነገረው አንቀጽ ውስጥ ተመልክቷል፡፡
ቊ 588፡፡ በፍርድ የተከለከለ፡፡
(1) በፍርድ የተከለከለ ሰው ዳኞች ካልፈቀዱለት በቀር ጋብቻ ለማድረግ አይችልም፡፡

(2) ስለዚህ ጕዳይ ለዳኞቹ የሚደርሳቸውን ጥያቄ በፍርድ የተከለከለው ሰው ራሱ ወይም አሳዳሪው ለማቅረብ ይችላል፡፡

(3) በፍርድ የተከለከለ ሰው የጋብቻ ውል ሊፈጽም የሚችልበት ሁኔታ በዚህ ሕግ ስለ ሰዎች ችሎታ በተነገረው አንቀጽ ውስጥ
ተመልክቷል፡፡
ቊ 589፡፡ ኀይል፡፡
(1) መፍቀዱ የተደረገው በኀይል የሆነ እንደሆነ ዋጋ የለውም፡፡

(2) በኀይል ተደረገ የሚባለው ከባድ ከሆነ ጉዳትና ከቀረበ ዛቻ የተነሣ ፈቃዱን የሰጠውን ሰው ራሱን ወይም ከወላጆቹ አንዱን ወይም
ከተወላጆቹ አንዱን ለማዳን ሲል ያደረገ እንደሆነ ነው፡፡

(3) ፈቃዱን የሰጠው፤ አንዱን ወላጅ ወይም አንዱን ሌላ ሰው አክብሮ በመፍራት የሆነ እንደሆነ ሕገ ወጥ አይሆንም፡፡

ቊ 590፡፡ ዋና መሳሳት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


አንደኛው ተጋቢ በአንደኛው ሰውነት ላይ መሳሳት ያደረገ እንደሆነ ፈቃዱ የተጓደለ ነው ይባላል፡፡
ቊ 591፡፡ (2) የተወሰኑ ምክንያቶች፡፡

ማንኛውም መሳሳት የማይሆን ሆኖ፤ ዋና መሳሳት የሚባሉት፡-

(ሀ) በሚያገቡት ሰው ላይ መሳሳት፤ ይኸውም አገባዋለሁ ብሎ ያላሰበውን አግብቶ ሲገኝ፤

(ለ) በሚያገቡት ሰው ሃይማኖት መሳሳት፤ ይኸውም ያገባው ሰው ሃይማኖት የርሱን ሃይማኖት ያልመሰለ ሲሆን፤

(ሐ) በሚያገቡት ሰው ጤና ወይም ሰውነት መሳሳት ይኸውም ያገቡት ሰው ደዌ ሥጋ የያዘው ወይም የሩካቤ ሥጋ ግንኙነትን ለመፈጸም
የማይችል ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

ቊ 592፡፡ መቃወሚያ፡፡ (1) ማን ለማድረግ እንደሚችል፡፡

(1) ጋብቻውን ለመቃወም የሚቻለው በዚህ ሕግ በጋብቻ አንቀጽ በቊጥር 562 በተመለከተው መሠረት የቤተ ዘመዱ እንደራሴ የሚባለው
ወይም አካለ መጠን ያላደረሰው አግቢ አሳዳሪው ነው፡፡

(2) እንዲሁም በዓቃቤ ሕግ መቃወሚያ ለማቅረብ ይችላል፡፡

(3) ማናቸውም ሌላ ሰው መቃወሚያ ለማቅረብ አይችልም፡፡

ቊ 593፡፡ (2) የሚቀርብበት ጊዜና ዐይነት፡፡


(1) እጅግ ቢዘገይ መቃወሙ የጋብቻው በዓል በሚከበርበት ጊዜ መሆን አለበት፡፡

(2) ለመቃወሙ ማናቸውም ልዩ አሠራር አያስፈልገውም፡፡

ቊ 594፡፡ (3) መቃወምን ስለ ማስቀረት፡፡

(1) በጋብቻው ላይ የተደረገው መቃወም እንዲቀር ከተጋቢዎቹ አንዱ አካለመጠን ያላደረሰም ቢሆን ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል፡፡

(2) የሆነ ሆኖ የጋብቻው ጊዜ መቃወም የተደረገበት ሰው ዕድሜው ከሓያ ዓመት በታች የሆነ እንደሆነ ወደፊት ከሚጋቡት ዕጮኞች
ያንደኛው አባት ወይም እናት ባደረገው መቃወም ላይ ማንኛቸውንም አቤቱታ ሊያቀርብ አይችልም፡፡

ቊ 595፡፡ (4) ለመቃወም ስላለመቻሉ፡፡

(1) በጋብቻ ላይ የተደረገውን የመጀመሪያውን መቃወም ያልተቀበሉት እንደሆነ ለጋብቻው ሌላ መቃወሚያ ማቅረብ አይቻልም፡፡

(2) ዐቃቤ ሕግ ካልሆነ በቀር አስቀድሞ አግብቶ በነበረ ሰው ላይ ማናቸውንም መቃወሚያ ለማቅረብ አይቻልም፡፡
ቊ 596፡፡ በብቸኛነት ለመኖር የተወሰነ ጊዜ፡፡
(1) ሴቲቱ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ከቀረበት ጊዜ በኋላ መቶንያ ቀን ካላለፈ በቀር እንደገና ለማግባት አትችልም፡፡

(2) ሴቲቱ ይህ አብሮ መኖር ከተቋረጠ በኋላ ልጅ የወለደች እንደሆነ ከዚህ በላይ ያለው ኀይለ ቃል ውሳኔ የጸና አይሆንም፡፡

(3) በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነውን ጊዜ እንዳትጠብቅ ዳኞች ሊፈቅዱላት ይችላሉ፡፡


ክፍል 2፡፡
ብሔራዊ ጋብቻ፡፡
ቊ 597፡፡ ሥልጣን ያለው የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም፡፡
ከእጮኛዎቹ አንዱ ወይም ከዘመዶቹ ወይም ከወላጆቹ አንዱ ከጋብቻው ጊዜ ጀምሮ እጅግ ቢያንስ ስድስት ወር ሳያቋርጥ በሚኖርበት ቦታ
ጋብቻው በቀበሌው በሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ፊት ይፈጸማል፡፡

ቊ 598፡፡ ያለ ማግባት ግዴታዎች (ውለታዎች)፡፡

(1) አንድ ሰው አላገባም ብሎ ወይም ደግሞ እንደገና አላገባም ብሎ ቃሉን ቢሰጥ በፍትሐ ብሔር በኩል ውጤት የለውም፡፡

(2) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹምም ይህን ነገር አይመለከትም፡፡


ቊ 599፡፡ ጋብቻን ለማድረግ የሚቀርብ ጥያቄ፡፡
ወደ ፊት የሚጋቡት ዕጮኛዎች የጋብቻ ውል ለማድረግ ማሰባቸውን እጅግ ቢያንስ ካንድ ሳምንት አስቀድመው ለሕዝብ መዝገብ ሹም
ያስታውቃሉ፡፡
ቊ 600፡፡ ጋብቻው እንዳይፈጸም ስለ መከልከል፡፡
(1) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹምም የጋብቻው ሁኔታዎች ተከናውነው እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡

(2) ጋብቻውን የሚከለክል ነገር ቢኖር የተወሰነ ወይም እርግጠኛ ምክንያት መኖሩን የተረዳ እንደሆነ ጋብቻው እንዳይፈጸም ይከለክላል፡፡

(3) እንዲህ ሲሆን የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ወደ ፊት ለሚጋቡት ዕጮኛዎች የከለከለበትን ምክንያት ያስታውቃል፡፡
ቊ 601፡፡ በመከልከሉ ላይ አቤቱታ ስለ ማቅረብ፡፡
(1) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ባደረገው ክለከላ ላይ ከዕጮኛዎቹ አንዱ ለዳኞች አቤቱታ ሊያቀርብ ይችላል፤ ዳኞቹም ስለዚሁ ክልከላ
ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡
(2) ክልከላው ያላግባብ መሆኑን ዳኞቹ የበየኑ እንደሆነ በማናቸውም ምክንያት ጋብቻው እንዳይፈጸም የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም
ሊከለክል አይችልም፡፡
ቊ 602፡፡ የጋብቻን ቀን ስለ መወሰን፡፡
ጋብቻው የሚፈጸምበት (የሚከበርበት) ጊዜ ወደ ፊት የሚጋቡት ዕጮኛዎችና በሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም መካከል በስምምነት
ይወሰናል፡፡
ቊ 603፡፡ የጋብቻን ሥርዐት አፈጻጸም ስለ ማስታወቅ፡፡
(1) ጋብቻው ወደ ፊት የሚጋቡት ዕጮኛዎችና ለያንዳንዳቸው ዕጮኛዎች ሁለት ምስክሮች ባሉበት በግልጽ ይፈጸማል፡፡

(2) ምስክሮቹም የባልና የሚስቱ ዘመዶች ወይም ባዕዶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡


ቊ 604፡፡ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዐት፡፡
(1) ወደ ፊት የሚጋቡት ዕጮኛዎች ምስክሮች ጋብቻውን የሚከለክል ነገር መኖሩን አናውቅም ሲሉ በመሓላ ቃላቸውን ይሰጣሉ፡፡

(2) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ወደ ፊት ከሚጋቡት ዕጮኛዎች ከያንዳንዳቸው ተራ በተራ ባልና ሚስት ለመሆን የመፍቀዳቸውን ቃል
ይቀበላል፡፡

(3) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም በሥልጣኑ ውስጥ ለሆነ ጕዳይ በሕግ ስም በጋብቻ የተሳሰሩ መሆናቸውን አስታውቆ ወዲያውኑ
የጋብቻውን ጽሑፍ ያዘጋጃል፡፡
ክፍል 3፡፡
ሌሎች ዐይነቶች ጋብቻዎች
ቊ 605፡፡ የሃይማኖት ጋብቻ፡፡
(1) የሃይማኖት ጋብቻ ሊፈጸም የሚችልበት ሁኔታና የአፈጻጸሙ ዐይነት እንደ ሃይማኖቱ ይወሰናል፡፡

(2) በዚህ ሕግ ስለ ማንኛውም ዐይነት የጋብቻ ሥርዐት (ፎርም) የተመለከቱት ሁኔታዎች በማንኛውም አኳኋን መፈጸም አለባቸው፡፡

(3) በዚህ ሕግ ስለ ሰዎች በሚለው አንቀጽ በተመለከተው መሠረት አንድ የጋብቻ ውል መጻፍ ይገባዋል፡፡
ቊ 606፡፡ የልማድ ጋብቻ፡፡
(1) የልማድ ጋብቻ ሊፈጸም የሚቻልበት ሁኔታና የአፈጻጸሙ ዐይነት በአገሩ ልማድ ይወሰናል፡፡

(2) በዚህ ሕግ ስለ ማንኛውም ዐይነት የጋብቻ ሥርዐት የተመለከቱት ሁኔታዎች በማንኛውም አኳኋን መፈጸም አለባቸው፡፡

(3) በዚህ ሕግ ስለ ሰዎች በሚለው አንቀጽ በተመለከተው መሠረት አንድ የጋብቻ ውል መጻፍ ይገባዋል፡
ምዕራፍ 4፡፡
የጋብቻ ሁኔታዎች ባለመጠበቃቸው ምክንያት የሚወሰን ቅጣት፡፡
ክፍል 1፡፡
ለጋብቻ ሥርዐቶች ሁሉ የሚሆን የወል ሁኔታ፡፡
ቊ 607፡፡ የዕድሜ ሁኔታ፡፡ (1) የወንጀል ቅጣት፡፡

(1) ዕድሜው ከዐሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆነውን ሰው ወይም ዕድሜዋ ከዐሥራ አምስት ዓመት በታች የሆነችውን ሴት፤ እያወቀ
ወይም ይህን ሁኔታ ማወቅ ሲገባው የጋብቻን ሥነ ሥርዐት ያስፈጸመ የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ወይም ባለሥልጣን በወንጀለኛ
መቅጫ ሕግ በተጻፈው ቅጣት ይቀጣል፡፡
(2) ከሁለቱ ተጋቢዎች ዕድሜው ከዐሥራ ስምንት በላይ የሆነው ወንድ ከ 15 በታች የሆነችውን ሴት ወይም ከ 15 ዓመት በላይ የሆናት ሴት
ከ 16 ዓመት በታች የሆነውን ወንድ ያገባችና እንዲሁም ጋብቻቸውን የፈቀዱ ሰዎች፤ ለጋብቻው ሥነ ሥርዐት ምስክሮች የሆኑት በወንጀለኛ
መቅጫ ሕግ በተወሰነው ቅጣት ይቀጣሉ፡፡
ቊ 608፡፡ የጋብቻው መፍረስ፡፡
(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር ውስጥ በተመለከተው አኳኋን በማናቸውም ባለጕዳይ ወይም በሕግ አስከባሪው ጥያቄ ጋብቻው እንዲፈርስ
ይወሰናል፡፡

(2) በሕጉ በሚያስገድደው መሠረት ለጋብቻ የተወሰነው የዕድሜ ልክ ተሟልቶ የተገኘ እንደሆነ ጋብቻው እንዲፈርስ ጥያቄ ሊቀርብ
አይችልም፡፡
ቊ 609፡፡ የሥጋ ዝምድና ወይም የጋብቻ ዝምድና፤ (1) የጋብቻ መፍረስ፡፡
በሥጋ ወይም በጋብቻ ዝምድና ምክንያት ያለውን ክልከላ በመጣስ ጋብቻ ተደርጎ የተገኘ እንደሆነ ማንኛውም ባለጕዳይ ወይም ዐቃቤ ሕግ
በሚያቀርበው ጥያቄ ጋብቻው እንዲፈርስ ይደረጋል፡፡ (ይወሰናል)፡፡

ቊ 610፡፡ (2) የወንጀል ቅጣት፡፡

(1) በሥጋ ወይም በጋብቻ ዝምድና ምክንያት የሚከለከል ነገር መኖሩን እያወቀ ወይም ይህን ሁኔታ ማወቅ ሲገባው በሁለት ተጋቢዎች
መካከል ጋብቻን የሚያስፈጽም ባለሥልጣን ወይም የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የተመለከቱት ቅጣቶች
ይፈጸሙበታል፡፡
(2) እንዲሁም የዝምድና ወይም የጋብቻ መተሳሰር መኖሩን ወይም ማወቅ ሲገባው ጋብቻ እንዲደረግ የፈቀዱ ተጋቢዎች ራሳቸው
ጋብቻውን የፈቀዱና ለጋብቻው ሥነ ሥርዐት ምስክሮች የሆኑ ሰዎች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣሉ፡፡

(3) ከዚህ በላይ በተጻፉት ኀይለ ቃሎች የተጻፉት ቅጣቶች ተፈጻሚ የሚሆኑት ዳኞች የጋብቻውን መፍረስ የወሰኑ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 611፡፡ በጋብቻ ላይ ስለሚደረግ ጋብቻ፡፡ (1) የወንጀል ቅጣት፡፡

(1) ከዚህ በፊት በጋብቻ የተሳሰረ መሆኑን እያወቀ ወይም ይህን ሁኔታ ማወቅ ሲገባው የአንድ ሰውን ጋብቻ ያስፈጸመ ባለሥልጣን ወይም
የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣል፡፡

(2) እንዲሁም ይህን ሁኔታ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ጋብቻ እንዲደረግ የፈቀዱ ተጋቢዎቹ ራሳቸው ጋብቻውን የፈቀዱና ለጋብቻው
ሥነ ሥርዐት ምስክር የሆኑት ሰዎች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ይቀጣሉ፡፡

ቊ 612፡፡ (2) የጋብቻ መፍረስ፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር በተመለከተው አኳኋን በጋብቻ ላይ ጋብቻ ያደረገው ሰው (ባል ወይም ሚስት) አንደኛው ወይም ዐቃቤ ሕጉ
በሚያቀርበው ጥያቄ ጋብቻው ይፈርሳል፡፡

(2) ዳኞች ጋብቻው እንዲፈርስ የሚያደርጉት በማይጠረጠር አኳኋን በጋብቻ ላይ ጋብቻ ያደረገው ሰው ባለቤት ጋብቻው በተደረገበት ጊዜ
በሕይወት መኖሩ የተረጋገጠ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 613፡፡ (3) ስለ ማጽናት፡፡


የመጀመሪያዪቱ ሚስት ለመኖርዋ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት በጋብቻ ላይ ጋብቻ ተደርጓል የሚለው ወገን ነው፡፡
ቊ 614፡፡ ችሎታ የሌለው ሰው ጋብቻ፤ (1) የወንጀል ቅጣት፡፡

(1) በአእምሮው መናወጽ የተከለከለ ወይም አካለመጠን ያላደረሰ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው በአእምሮው መናወጽ
የተከለከለውን ወይም አካለመጠን ያላደረሰውን ሰው አስፈላጊ የሆነ ፈቃድ ሳይኖር ጋብቻውን ያስፈጸመው ባለሥልጣን ወይም የሕዝብ
የክብር መዝገብ ሹም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣል፡፡
(2) እንዲሁም አካለ መጠን ያላደረሰውን፤ ወይም በፍርድ የተከለከለውን ሰው ያጋባና ለዚሁ ጋብቻ ምስክሮች የነበሩት ሰዎች በወንጀለኛ
መቅጫ ሕግ የተመለከቱት ቅጣቶች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

ቊ 615፡፡ (2) የጋብቻው መፍረስ፡፡

(1) ጋብቻው እንዲፈርስ አካመጠን ያላደረሰው ሰው ወይም በአእምሮው መናወጽ ምክንያት የተከከለው ሰው ወይም አካለመጠን
ያላደረሰውን ሰው ጋብቻ መፍቀድ ይገባው የነበረው ሰው ወይም የተከለከለው ሰው አሳዳሪ ዳኞችን መጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ችሎታ ያጣው ሰው ጋብቻው እንዲፈርስ የሚያቀርበው ጥያቄ ችሎታ ማጣቱ ከቀረ ከ 6 ወር በኋላ ለመቅረብ አይችልም፡፡

(3) ለዚሁ ጒዳይ ሌሎች ሰዎች የሚያቀርቡት ጥያቄ ጋብቻው መኖሩን ካወቁ ከ 6 ወር በኋላ ደግሞ በሌላ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን
አካለ መጠን ያላደረሰው ወይም የተከለከለው ሰው ችሎታ ማጣት ከቀረ በኋላ ሊቀርብ አይችልም፡፡

ቊ 616፡፡ ከኀይል ሥራ የተነሣ የተደረገ ጒድለት፤ (1) የወንጀል ቅጣት፡፡

(1) በኀይል ጋብቻን እንዲፈቅድ ያደረጉት ሰዎችና ለዚሁ ጋብቻ ምስክሮች የሆኑት ሰዎች በወንጀል መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች
ይቀጣሉ፡፡

(2) እንዲሁም ይህን ሁኔታ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ይህን ጋብቻ ያሰፈጸመ ባለሥልጣን ወይም የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣል፡፡

ቊ 617፡፡ (2) የጋብቻ መፍረስ፡፡

(1) ማናቸውም ሰው በኀይል ጋብቻ ያደረገ እንደሆነ ጋብቻው እንዲፈርስ ዳኞችን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ስለዚሁ ጒዳይ የሚሆነው ጥያቄ፤ የኀይል ሥራው ከተቋረጠ ከስድስት ወር በኋላና በማናቸውም አኳኋን ጋብቻው ከተፈጸመ ከሁለት
ዓመት በኋላ ሊቀርብ አይችልም፡፡
ቊ 618፡፡ ስሕተት፡፡
(1) ማንም ሰው ከዋና ስሕተት የተነሣ ጋብቻ ያደረገ እንደሆነ ጋብቻው እንዲፈርስለት ዳኞችን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ስለዚሁ ጒዳይ የሚሆነው ጥያቄ ስሕተቱን ካወቀበት ቀን አንሥቶ በሚቀጥለው 6 ወር ውስጥና በማናቸውም አኳኋን ጋብቻው
ከተፈጸመበት በሚከተሉት 2 ዓመታት ውስጥ ካልቀረበ ፈራሽ ይሆናል፡፡
ቊ 619፡፡ መቃወም፡፡
(1) በጋብቻው ላይ የተደረገውን ተገቢ የሆነውን መቃወም በማቃለል፤ ጋብቻውን የሚያስፈጽም ባለሥልጣን ወይም የሕዝብ የክብር
መዝገብ ሹም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቅጣቶች ይቀጣል፡፡

(2) እንዲሁም ለጋብቻው ፈቃደኛ የሆኑ ዕድሜያቸው ከዐሥራ አምስት ዓመት በላይ የሆኑ ተጋቢዎች፤ ጋብቻውን የፈቀዱ ሰዎችና
ምስክሮች በወንጀለኛ መቅጫ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣሉ፡፡

(3) በጋብቻው ላይ ለቀረበው መቃወሚያ ዋጋ አልተሰጠውም በማለት ምክንያት ብቻ ጋብቻው እንዲፈርስ ሊወሰን አይቻልም፡፡
ቊ 620፡፡ በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነ ጊዜ፡፡
(1) በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነው ጊዜ ከማለቁ በፊት ያንዲቱን ሴት ጋብቻ የሚያስፈጽም ባለሥልጣን ወይም የሕዝብ የክብር መዝገብ
ሹም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣል፡፡

(2) እንዲሁም ለጋብቻው ፈቃደኛ የሆኑ ተጋቢዎች፤ ጋብቻውን የፈቀዱ ሰዎችና ምስክሮች በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተለከቱት ቅጣቶች
ይቀጣሉ፡፡

(3) በብቸኝነት ለመኖር የተወሰነው ጊዜ አልተከበረም በማለት ምክንያት ብቻ ጋብቻ እንዲፈርስ ሊታዘዝ አይችልም፡፡
ክፍል 2፡፡
ብሔራዊ ጋብቻ፡፡
ቊ 621፡፡ የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ሥልጣን አለመኖር፡፡
(1) ስለ መኖሪያ ሁኔታ በዚህ ሕግ የተደነገገውን ሳይፈጽም ዐውቆ ወይም ይህን ሁኔታ ማወቅ ሲገባው ጋብቻውን ያስፈጸመ የሕዝብ የክብር
መዝገብ ሹም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣል፡፡

(2) እንዲሁም ተጋቢዎቹና ለዚሁ ጋብቻ ምስክሮች የሆኑት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣሉ፡፡

(3) የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ሥልጣን የለውም ነበር በማለት ብቻ ጋብቻ እንዲፈርስ ሊወሰን አይቻልም፡፡
ቊ 622፡፡ ሥርዐቶችን አለመጠበቅ፡፡
(1) የጋብቻን አፈጻጸም የሚመለከቱትን ውሳኔዎች (ደንቦች) ያልጠበቀ የሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ
በተመለከቱት ቅጣቶች ይቀጣል፡፡

(2) በእንደዚህ ያሉት ምክንያቶች ጋብቻው እንዲፈርስ ሊወሰን አይቻልም፡፡


ክፍል 3፡፡
ሌሎች ጋብቻዎች
ቊ 623፡፡ ፈራሽነት፡፡
(1) በሃይማኖት ወይም በልማድ የሚያስፈልጉት ግዴታዎች ወይም ሥርዐቶች ባመፈጸማቸው ምክንያት ጋብቻውን ዳኞች ሊያፈርሱት
አይችሉም፡፡

(2) በሃይማኖት ባለሥልጣኖች የተነገረ የሃይማኖት ጋብቻ መሻር ለፍችው ዋና ምክንያት ይሆናል፡፡

(3) በልማድ ጋብቻ ባለሥልጣኖች የተነገረ የልማድ ጋብቻ መሻር በሕግ ፊት ተቀባይነትን አያገኝም፡፡
ቊ 624፡፡ የገንዘብ መቀጫና የጉዳት ካሣዎች፡፡
(1) የሃይማኖት ወይም ለልማድ ጋብቻ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎችና ሥርዐቶች፤ በሃይማኖት ወይም በተከተሉት ልማድ መሠረት ጉዳት
ለደረሰበት ወገን ጥቅም፤ የጉዳት ካሣ እንዲሰጥ እንዲከፍል ሊወሰን ይቻላል፡፡

(2) ይህን ተቃዋሚ ልማድ ወይም የውል ቃል ቢኖርም የተሰጡት የጉዳት ካሣዎች አለመጠን የበዛ መስሎ ከታያቸው ዳኞች መቀነስ
ይችላሉ፡፡

(3) እንዲሁም በዚህ ረገድ ለርትዕ ወይም ለመልካም ተግባር፤ አእምሮ የማይቀበለው ወይም ተቃራኒ መስሎ የታያቸው እንደሆነ፤ ልማዱ
ውጤት እንዳይኖረው ለመወሰን ይችላሉ፡፡
ምዕራፍ 5፡፡
የጋብቻ ውጤት፡፡
ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ቊ 625፡፡ የልዩ ልዩ ዐይነት ጋብቻ ትክክለኛነት፡፡
(1) በማናቸውም ዐይነት ሥርዐት መሠረት የተፈጸመ ቢሆን ጋብቻ በሕግ መሠረት ትክክል የሆኑ ውጤቶችን ይሰጣል፡፡

(2) በዚህ ረገድ ጋብቻ በሕዝብ የክብር መዝገብ ሹም ፊት ወይም በሃይማኖት ወይም በልማድ በታዘዙት ሥርዐቶች መሠረት የተፈጸመም
ቢሆን ልዩነት አይደረግለትም፡፡
ቊ 626፡፡ የሩካቤ ሥጋው ግንኙነት መፈጸም፡፡
ጋብቻው ለሚያስከትለው ውጤት የሩካቤ ሥጋው ግንኙነት በውነት መፈጸሙ ወይም በግምት ተፈጽሟል መባሉ አስፈላጊ አይደለም፡፡
ቊ 627፡፡ የጋብቻው ውል፡፡
(1) ተጋቢዎቹ በገንዘባቸው በኩል ጋብቻቸው ስለሚያስከትለው ውጤት ጋብቻቸውን ከማድረጋቸው በፊት በውል ሊስማሙ ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም በዚሁ ውል ውስጥ በመካከላቸው ስላለው ግንኙነት አንዱ ላንዱ ያሉበትን ግዴታዎችና ያሉትን መብቶች ሊያረጋግጡ
ይችላሉ፡፡

(3) ልዩነት እንዳይደረግባቸው ሕግ የማይፈቅዳቸው ድንጋጌዎች ሁሉ እንደ ተጠበቁ ናቸው፡፡


ቊ 628፡፡ ከባልና ሚስት የአንደኛው ችሎታ ማጣት፡፡
(1) አካለ መጠን ያላደረሰ ሰው የሚያደርገውን የጋብቻ ውል እርሱ ራሱ እንዲፈቅድ አስፈላጊ እንደመሆኑ የሞግዚቱም ፈቃድ አስፈላጊ
ነው፡፡

(2) በፍርድ የተከለከለ ሰው የሚያደርገውን የጋብቻ ውል እርሱው ራሱ ሊፈጽም ይገባዋል፡፡ ዳኞች ካላጸደቁት ግን ፈራሽ ነው፡፡

(3) በሕግ የተከለከለ ሰው የጋብቻ ውል መዋዋልን ስለሚያስከትል ጒዳይ የችሎታ ማጣት ደንብ አይጸናበትም፡፡

ቊ 629፡፡ የውሉ ሥርዐት (ፎርም)፡፡


የጋብቻው ውል በጽሑፍ ካልሆነና አራት ምስክሮች ሁለቱ በባልዮው ወገን ሁለቱ በሚስቲቱ ወገን የፈረሙበት ካልሆነ በቀር ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 630፡፡ የውሉ ጽሑፍ የሚቀመጥበት ቦታ፡፡
(1) የውሉ አንድ ግልባጭ በፍርድ ቤት መዝገብ ቤት ወይም ውል ለማፈራረም ሥልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

(2) ተጋቢዎቹ ለማየት ሲፈቅዱ እንዲሁም ዳኛው ወይም ተጋቢዎቹ የፈቀዱላቸው ሰዎች የውሉን ጽሑፍ ለማየት መብት አላቸው፡፡
ቊ 631፡፡ ውል ለመዋዋል ስላለው ነፃነት ወሰን፡፡
(1) የጋብቻ ውል በሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ ማንኛውም ግዴታ ሊያስከትል ወይም አዛዥነት ባላቸው በሌሎች የሕግ ድንጋጌዎች፡- ላይ
የመቃወምን ሁኔታ ለማምጣት አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም የጋብቻው ውል በቀጥታ ወይም ያለ ሐተታ በአገር ልማድ ተጋብተናል በማለት ብቻ ለመመራት አይችልም፡፡
ቊ 632፡፡ የጋብቻን ውል ስለ መለዋወጥ፡፡
(1) የጋብቻው ውል እንዲለዋወጥ ሁለቱ ባልና ሚስት በሚያቀርቡት ጥያቄ በቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኝነት ሊለዋወጥ ይችላል፡፡

(2) የቤተ ዘመድ ጥቅም የሚጠይቅ በሆነ ጊዜም ከሁለቱ ባንደኛው ጠያቂነት ውሉ ሊለዋወጥ ይችላል፡፡

(3) የውሉን መለዋወጥ የሚያመለክተው ጽሑፍ ግልባጭ በፍርድ ቤት መዝገብ ቤት ወይም ውል ለማፈራረም ሥልጣን በተሰጠው ሰው
ዘንድ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡
ቊ 633፡፡ በባልና ሚስት መካከል የሚደረግ ውል፡፡
(1) ባልና ሚስት ተጋብተው በሚኖሩበት ጊዜ በሁለቱ መካከል የሚደረገውን ውል የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ወይም የፍርድ ቤት
ዳኞች ካላጸደቁት በቀር በፍትሐ ብሔር ሕግ ዋጋ የሌለው ነው፡፡

(2) በዚህ ሕግ በግልጽ ተለይተው የተነገሩት ውሎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 634፡፡ ሕጋዊ አስተዳደር (ሥርዐት)፡፡


የጋብቻ ውል የሌለ እንደሆነ ወይም የጋብቻው ውል ስምምነት ወይም በባልና ሚስት መካከል የተደረገው ውል ሳይጸና የቀረ እንደሆነ
ከዚህ ቀጥሎ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ይሠራል፡፡
ክፍል 2፡፡
በሰዎች ላይ ጋብቻው ያለው ውጤት፡፡
ቊ 635፡፡ የቤተ ዘመድ ሹም፡፡
(1) ባል የቤተ ዘመድ ሹም ነው፡፡

(2) በዚህ ሕግ በቃራኒ የሆኑት ድንጋጌዎች እንደ ተጠበቁ ሆነው፤ እንዲሁም ባል ለሚያዛት ሕጋውያን ለሆኑ ነገሮች ሚስት መታዘዝ
አለባት፡፡
ቊ 636፡፡ መከባበር መረዳዳትና መተጋገዝ፡፡
(1) ባልና ሚስት እርስ በርሳቸው መረዳዳትና መተጋገዝ አለባቸው፡፡

(2) በጋብቻው ውል ውስጥ ለዚህ ተቃራኒ የሆነ ደንብ ሊጻፍበት አይቻልም፡፡

ቊ 637፡፡ የቤተ ዘመድ መሪነት (1) ጠቅላላ ሁኔታ፡፡

(1) በባልዮው መሪነት ለቤተ ዘመዶቻቸው ጥቅም ሲሉ፤ ባልና ሚስቲቱ የልጆቻቸውን የግብረ ገብነትና የተፈጥሮ እድገት ማረጋገጥና
እንዲሁም ወደፊት ልጆቻቸውን በመልካም ሁኔታ ለማሳደግና የኑሮዋቸውን ድርጅት ለማረጋገጥ መረዳዳት አለባቸው፡፡

(2) በጋብቻቸው ውል ውስጥ ባልና ሚስት ስለዚሁ ጒዳይ የገቡበት ግዴታ ተከብሮ መጠበቅ አለበት፡፡

ቊ 638፡፡ (2) ከባልና ሚስት የአንዱ መታወክ፡፡

(1) ከባልና ሚስት አንደኛው ችሎታ ማጣት የደረሰበት እንደሆነ ወይም በስፍራው የማይገኝ ወይም ቤተ ዘመዱን በመተው ምክንያት
የተፈረደበት እንደሆነ ከዚህ በላይ በተመለከተው ቊጥር ያለውን ሥልጣን አንደኛው ብቻውን ይፈጽማል፡፡

(2) ከሁለቱ አንዳቸው የአንድነት ኑሮውን በፈቃዱ ትቶ የሄደ እንደሆነ ወይም ከመኖሪያ ስፍራው በመራቁም ሆነ በማናቸውም ሌላ
ምክንያት የፈቃኛነት አሳቡን ለመግለጽ በማይችልበት ሁኔታ በሚገኝበት ጊዜም በዚሁ ዐይነት ይፈጸማል፡፡

(3) የጋብቻው ውል ከዚህ በላይ ያሉትን ሥርዐቶች አፍራሽ ሊሆን አይችልም፡፡


ቊ 639፡፡ ከጋብቻ በፊት ከሌላ ስለ ተወለደ ልጅ፡፡
(1) ከባልና ሚስቲቱ አንዱ ከጋብቻው በፊት ከሌላ ስለ ወለዳቸው ልጆች ማሳደግን በሚመለከተው ረገድ በራሱ አሳብና መሪነት
የፈቀደውን ውሳኔ ለማድረግ ሙሉ መብት ይኖረዋል፡፡

(2) ይህን ሥርዐት ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ሁሉ ፈራሽ ነው፡፡


ቊ 640፡፡ አብሮ መኖር፡፡
(1) ባልና ሚስት አብረው እንዲኖሩ ይገደዳሉ፡፡

(2) ይህ አድራጎት ጤንነታቸውን በብርቱ የሚቃወም ካልሆነ በቀር ከጋብቻቸው ውል በተገኘው ግዴታ መሠረት አንዱ ከአንዱ ጋራ
ደንበኛውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም አለባቸው፡፡

(3) ይህን ሥርዐት ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ሁሉ ፈራሽ ነው፡፡


ቊ 641፡፡ የመኖሪያ ስፍራን ስለ መወሰን፡፡
(1) አብረው የሚኖሩበትን ስፍራ የሚወስነው ባልዮው ነው፡፡
(2) የመኖሪያቸውን ቦታ ባልዮው የወሰነው ያለ አገባብ ወይም የጋብቻውን ውል ድንጋጌዎች በግልጽ ተቃራኒ ሆኖ ሲታይ ሚስቲቱ ለቤተ
ዘመድ ዳኞች አቤቱታ ለማቅረብ ትችላለች፡፡
ቊ 642፡፡ በስምምነት ስለ መለያየት፡፡
(1) ባልና ሚስት ላንድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተለያይተው ለመኖር ስምምነት ለማድረግ ይችላሉ፡፡

(2) ስለዚህ ጒዳይ የተደረገውንም ስምምነት የመለወጡ ጒዳይ የማይገባ ካልሆነ በቀር ከሁለቱ አንደኛው ወገን አስቦ ሊለውጠው
ይችላል፡፡
ቊ 643፡፡ የመተማመን ግዴታ፡፡
(1) ሚስት ለባሉዋ ታማኝ መሆን ይገባታል፡፡

(2) ምክንያት የሌለው የማይበድል ከመጠንም ያላለፈ ከሆነ ለኑሮዋቸውም መልካም ጥቅም ከሆነ፤ ባል፤ ሚስቱ የምታደርጋቸውን
ግንኙነቶች ለመቈጣጠርና የጠባይዋንም አመራር ለመጠበቅ ይችላል፡፡
ቊ 644፡፡ የባልዮው የጥበቃ ተግባር፡፡
(1) ባል ሚስቱን መጠበቅ አለበት፡፡

(2) ምክንያት የሌለው የማይበድል ከመጠንም ያላለፈ ከሆነ ለኑሮዋቸውም መልካም ጥቅም ከሆነ፤ ባል፤ ሚስቱ የምታደርጋቸውን
ግንኙነቶች ለመቈጣጠርና የጠባይዋንም አመራር ለመጠበቅ ይችላል፡፡
ቊ 645፡፡ የባልና የሚስት የሞያ ሥራ፡፡
(1) ከተጋቢዎቹ እያንዳንዱ የመረጠውን የሞያ ሥራ ወይም የጥበብ ሥራ ለማከናወን ይችላል፡፡

(2) ከሁለቱ አንደኛው ግን ለትዳራቸው ለቤተ ዘመዳቸው መልካም አኗኗር የማይጠቅም እንደሆነ ያንደኛውን የተወሰነ ሥራ ወይም ሞያ
ለመቃወም ይችላል፡፡
ቊ 646፡፡ የቤት አያያዝ፡፡
ባል አሽከር ለመቅጠር ችሎታ የሌለው እንደሆነ ሚስቲቱ የቤት አያያዝን ሥራ እንድታከናውን ግዴታ አለባት፡፡
ክፍል 3፡፡
ጋብቻው በገንዘብ በኩል ያለው ውጤት፡፡
ቊ 647፡፡ የባልና ሚስት የግል ሀብት (1) ያለገንዘብ የተገኙ ሀብቶች፡፡
የጋብቻቸው ጊዜ የነበሯቸው የባልና ሚስት ሀብቶች ወይም ከጋብቻቸው በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ ያገኙዋቸው ሀብቶች ለየራሳቸው
የግል ሀብቶቻቸው ሆነው ይኖራሉ፡፡

ቊ 648፡፡ (2) በገንዘብ የተገኙ ሀብቶች፡፡

(1) እንዲሁም ከተጋቡ በኋላ ከባልና ሚስት አንዱ በገንዘቡ የገዛቸው ሀብቶች የግል ሀብቶቹ ናቸው፤ ይኸውም የሚሆነው ሀብቱ የተገኘው
በግል ገንዘቡ የገዛው ሲሆንና ወይም የግል ገንዘቡ በሆነው ነገር ልውጫ ያገኘው ሲሆን ወይም በገዛ ገንዘቡ የገዛው ወይም ደግሞ በራሱ
ሀብት ልውጫ ያገኘው ሀብት የሆነ እንደሆነ ነው፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው በመጨረሻው ኀይለ ቃል የተመለከተው ድንጋጌ ግን፤ በዚህ ዐይነት የተገዛው የተገኘው ሀብት የግል ይሁንልኝ ብሎ
አንደኛው ያቀረበውን ጥያቄ የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኛ ካላጸደቀው በቀር ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም፡፡

ቊ 649፡፡ የግል ሀብትን ስለ ማስተዳደር (1) መሠረቱ፡፡

(1) ከተጋቢዎቹ አንዱ የግል ንብረቱን ለማስተዳደርና ገቢውንም ለመቀበል ይችላል፡፡


(2) የዚህን የሀብቱን ገቢ ራሱ ሊያዝዝበት ነፃነት አለው፡፡

ቊ 650፡፡ (2) የጋብቻ ውል፡፡

(1) በጋብቻው ውል ከተጋቢዎቹ አንደኛው የሀብቱ መሪና ሥራ አስኪያጅ ይሆናል፤ ወይም ከሀብታቸው ውስጥ የተወሰነውን ክፍል
ያስተዳድራል፤ እንዲያውም ይህን ሀብት ያዝዝበታል የሚል የስምምነት ቃል ሊኖርበት ይችላል፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ሁኔታ ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር የንብረቱ ሥራ አስኪያጅ ባልሆነው ወገን ጥያቄ በየዓመቱ አንድ
የሀብት ማስተዳደር መግለጫ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
ቊ 651፡፡ የእንደራሴነት ሥልጣን፡፡
ከባልና ከሚስት አንዱ ላንደኛው የንብረቱን አስተዳዳሪነት ወይም ከግል ሀብቱ ያንዱን ንብረት ጠባቂነትና አስተዳዳሪነት ሥልጣን
ለመስጠት ሙሉ ነፃነት አለው፡፡
ቊ 652፡፡ የጋራ ሀብት፡፡
(1) የባልና ሚስት ደመወዝና ገቢዎች የጋራ ሀብቶቻቸው ናቸው፡፡

(2) እንዲሁም ባልና ሚስቱ ከተጋቡ በኋላ በገንዘብ የገዟቸው ሀብቶችና በቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኝነት የአንዱ የግል ሀብት ይሁኑ
ያልተባሉት ነገሮች ሁሉ የሁለቱ የጋራ ሀብቶች ናቸው፡፡

(3) እንዲሁም በስጦታው ውል ወይም በኑዛዜው ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ለሁለቱ ተጋቢዎች በስጦታ ወይም በኑዛዜ የተሰጠጡት
ንብረቶች የጋራ ሀብቶች ናቸው፡፡
ቊ 653፡፡ የሕሊና ግምት፡፡
(1) ከባልና ሚስት አንዱ የግል ሀብቱ ነው ብሎ ካላስረዳ በቀር ማንኛውም ሀብታቸው ሁሉ እንደ ጋራ ንብረታቸው ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(2) የግል ሀብት መሆኑን ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች የሚያውቁት ወይም ሊያውቁት የሚገባው ካልነበረ በቀር ተጋቢዎቹ በሦስተኛው ወገን
ላይ መቃወሚያ ሊያደርጉበት አይችሉም፡፡

ቊ 654፡፡ ደመወዝና ገቢ (1) ደንበኛ አመራር፡፡

(1) ተጋቢዎቹ እያንዳንዱ ደመወዙንና ገቢውን ይቀበላል፡፡

(2) ባልና ሚስትም፤ ለየራሱ የሚያገኘውን ደመወዝና ገንዘብ እንዲሁም ከግል ንብረቱ የሚያገኘውን ለማስቀመጥ በራሱ ስም የባንክ
ሒሳብ ለመክፈት ይችላል፡፡

(3) ከሁለቱ በአንደኛው ጠያቂነት ከደመወዝና ከንብረት ገቢ ያገኘውን የገንዘብ ልክ መግለጽ አለበት፡፡

ቊ 655፡፡ (2) የባልና የሚስት መብት፡፡

(1) ከባልና ከሚስት አንዱ የሚገባውን ደመወዝ ገቢ አንደኛው እንዲቀበል ሥልጣን ለመስጠት ሙሉ ነፃነት አለው፡፡

(2) የዘመድ የሽምግልና ዳኞች ከባልና ከሚስቱ በአንደኛው ጠያቂነት ከሁለቱ የአንደኛውን ደመወዝ አንዱ እንዲቀበልና ለመቀበሉም
ደረሰኝ እንዲሰጥ በስምምነት ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(3) እንዲሁም የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ከባልና ሚስት ደመወዝ ወይም ገቢ ላይ አንደኛው እንዲይዝና በመላው ወይም በከፊል
ተቀባይ እንዲሆን ለመፍቀድ ይችላሉ፡፡
ቊ 656፡፡ የጋራ ሀብትን ስለ ማስተዳደር፡፡
(1) ሚስትዮዋ ከምታገኘው ጥቅም ደመወዝና ገቢ በቀር በሌላ ሁኔታ የተገኘውን የጋራ ሀብት የሚያስተዳድረው ባልዮው ነው፡፡

(2) በዚህ ሕግ በቊጥር 638 የተመለከቱት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡


(3) ከዚህም በቀር ሴቷ በምታቀርበው ጥያቄ መሠረት የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ለቤተ ዘመዱ ጥቅም ሲሆን የጋራ ሀብታቸውን
ወይም ከጋራ ሀብታቸው አንዳንዱን ሚስትዮዋ እንድታስተዳድር ሊፈቅዱ ይችላሉ፡፡
ቊ 657፡፡ የማስታወቅ ግዴታ፡፡
ከተጋቢዎቹ አንዱ በጋራ ሀብቶቹ ላይ ያስተዳደር ተግባር ሲፈጽም ባመዘግየት ለአንደኛው ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 658፡፡ የሥልጣኑ መቀነስ፡፡


የሁለቱን ተጋቢዎች ስምምነት የሚያስፈልገው፡፡
(ሀ) የጋራ የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ፡፡

(ለ) ዋጋው ከአምስት መቶ ብር በላይ የሆነውን የሚንቀሳቀስ ንብረት ወይም በባልዮውና በሚስቲቱ ስም የተጻፈውን የገንዘብ ሰነድ
ለመሸጥ፡፡

(ሐ) ከመቶ የኢትዮጵያ ብር በላይ ለመበደር፤

(መ) ከመቶ ብር በላይ የሆነ ስጦታ ለማድረግ፤ ወይም ከመቶ ብር በላይ ለሆነ ለሌላ ሰው ዕዳ ዋስ ለመሆን ሲሆን ነው፡፡
ቊ 659፡፡ የባልና የሚስት ዕዳ፡፡
(1) ከባልና ከሚስቱ ከአንደኛው የሚጠየቀው ዕዳ ከግል ሀብቱ ላይ ወይም ከጋራ ንብረታቸው ላይ ሊጠየቅ ይቻላል፡፡

(2) ዕዳው የመጣው ለጋራ ንብረታቸው ጥቅም በሆነ ጊዜ እንደ አንድነት ዕዳ ተቈጥሮ ከባልና ከሚስቱ በአንደኛው የግል ሀብት ላይ ወይም
በጋራ ሀብታቸው ላይ ሊጠየቅ የሚችል ይሆናል፡፡
ቊ 660፡፡ ለትዳር ጥቅም እንደተደረገ ስለሚቈጠር ዕዳ፡፡
ለትዳር ጥቅም እንደተደረገ የሚቈጠረው ዕዳ፡-

(ሀ) የባልና ሚስትን ወይም የልጆቻቸውን ምግብና መኖሪያ ለማዘጋጀት የተደረጉ ዕዳዎች፤

(ለ) ባልዮው ወይም ሚስትዮዋ ምግብ ለመስጠት ያለውን ግዴታ ለመክፈል የደረሱ ዕዳዎች፤

(ሐ) ከባልና ከሚስቱ በአንደኛው ወይም በገንዘብ ጠያቂው አመልካችነት ዕዳው የደረሰው ለትዳር ጥቅም መሆኑን የቤተ ዘመድ ሽምግልና
ዳኞች ዐውቀው የተቀበሉት ሌላ ዕዳ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 661፡፡ ለትዳራቸው ወጪ ባልና ሚስት ስለሚያደርጉት መረዳዳት፡፡
ባልና ሚስት የትዳራቸውን ወጪ ለማደራጀት እያንዳንዳቸው ባላቸው ችሎታና ዐቅም መጠን እርስ በርሳቸው መረዳዳት አለባቸው፡፡
ምዕራፍ 6፡፡
ስለጋብቻ መፍረስ፡፡
ቊ 662፡፡ ልዩ ልዩ የጋብቻ ሥርዐቶች ትክክል ስለ መሆናቸው፡፡
(1) የጋብቻው ሥርዐት የተፈጸመበት ሥርዐት ማንኛውም ዐይነት ቢሆን የጋብቻው መፍረስና ይህ የሚያስከትለው ውጤት አንድ ዐይነት
ነው፡፡

(2) ጋብቻው የተፈጸመው በአንድ የሕዝብ አገልግሎት መሥሪያ ቤት ባለ ሥልጣን ፊት ወይም በሃይማኖት ሥርዐት ወይም በአገር ልማድ
መሠረት ቢሆን በጋብቻ መፍረስ ረገድ ማናቸውም ልዩ አስተያየት አይደረግም፡፡
ክፍል 1፡፡
ጋብቻ የሚፈርስበት ምክንያት፡፡
ቊ 663፡፡ ልዩ ልዩ ምክንያቶች፡፡
(1) ጋብቻው ቀሪ የሚሆነው ከተጋቢዎቹ አንደኛው በሞተ ጊዜ፡-

(2) እንዲሁም ከጋብቻው ሕግ አንደኛው በመጣሱ ምክንያት ዳኞቹ ጋብቻው እንዲፈርስ የፍርድ ውሳኔ በሰጡ ጊዜ፤

(3) በጋብቻው ፍቺ ሲኖር ነው፡፡


ቊ 664፡፡ አልፈልግም ስለ ማለት፡፡
ሚስት ባሉዋን ወይም ባል ሚስቱን አልፈልግም ማለትን ሕግ አይፈቅድም፡፡
ቊ 665፡፡ በስምምነት የሚደረግ መፋታት፡፡
(1) በባልና በሚስት ስምምነት የሚደረግ መፋታት በሕጋዊ መንገድ ካልተፈጸመ በቀር አይፈቀድም፡፡

(2) በዚህ ሕግ ድንጋጌ ላይ ከተመለከተው ውጭ በሆነ አፈጻጸም መፋታትን ለመወሰን አይቻልም፡፡


ቊ 666፡፡ ለመፋታት የሚቀርብ ጥያቄ፡፡
(1) ለመፋታት የሚቀርበው ጥያቄ ከባልና ሚስት አንደኛው ወይም ሁለቱ አንድነት ሆነው ለቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች የመፋታቱን
ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡

(2) ሌላ ማናቸውም ሰው የመፋታትን ጥያቄ ሊያቀርብ አይችልም፡፡

(3) የመፋታቱ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ከባልና ከሚስቱ የአንደኛው መሞት ስለ መፋታት የቀረበውን አሠራር ያስቀረዋል፡፡
ቊ 667፡፡ ከባድ ምክንያቶችና ሌሎች ምክንያቶች፡፡
መፋታቱ የሚወሰንባቸው ሁኔታዎችና መፋታቱም የሚያስከትላቸው ውጤቶች፤ መፋታቱን የሚጠይቀው ተጋቢ ለእርሱ የሚጠቅመው
ከባድ ሁኔታ መኖሩን ለማስረዳት በሚችለው ወይም በማይችለው መጠን ልዩ የሚሆኑ ናቸው፡፡
ቊ 668፡፡ በከባድ ምክንያቶች የሚደረግ የመፋታት ውሳኔ፡፡
መፋታትን የሚጠይቀው ወገን የጋብቻውን መጽናት ሊያፈርስ የሚችል ከፍተኛ ምክንያት ካቀረበ፤ የመፋታቱ ጥያቄ የቀረበላቸው የቤተ
ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ጥያቄው ከቀረበላቸው ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ወር የመፋታትን ውሳኔ መስጠት አለባቸው፡፡

ቊ 669፡፡ መፋታትን ሊያስከትሉ የሚችሉ ከባድ ምክንያቶች፡፡ (1) ከባልና ሚስት የአንደኛው ጥፋት፡፡

(1) ከባልና ከሚስት በአንደኛው ጥፋት መፋታትን ለማስከተል የሚችሉ ከባድ ምክንያቶች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡፡

(ሀ) ባል ወይም ሚስት የዝሙት ተግባር የፈጸሙ እንደሆነ፤

(ለ) ከባልና ከሚስት ከሁለቱ አንደኛው ከሚኖሩበት ቤት ጠፍቶ ስለ ሄደ እጅግ ቢያንስ ከሁለት ዓመት ጊዜ ጀምሮ ያለበትን ስፍራ
አንደኛው ሳያውቅ የቈየ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 670፡፡ (2) ከባልና ከሚስት በአንዱ ጥፋት ያልሆነ መፋታትን የሚያስከትል ከባድ ምክንያት፡፡
እንዲሁም መፋታትን የሚያስከትል ከባድ ምክንያት አለ የሚያሰኘው
(ሀ) ከባልና ከሚስት አንዱ እጅግ ቢያንስ ለሁለት ዓመት ጊዜ አእምሮው የተናወጸና የዕብድ መጠበቂያ በሆነ ስፍራ ተዘግቶበት የቈየ
እንደሆነ፤
(ለ) ከባልና ከሚስት ያንደኛው ከአገር መጥፋት በፍርድ ውሳኔ ተገልጾ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 671፡፡ (3) የሃይማኖት ሥርዐት ጋብቻ የሚፈርስበት ሁኔታ፡፡


እንዲሁም በሃይማኖት ሥርዐት የተፈጸመ ጋብቻ በሃይማኖት ባለሥልጣኖች የማይጸና መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ የዚሁኑ ጋብቻ መፍረስ
የሚያስከትል ከባድ ምክንያት አለ ለማለት ይቻላል፡፡
ቊ 672፡፡ መፋታትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች የሚቀሩበት ሁኔታ፡፡
(1) መፋታትን ሊያስከትል የቻለው ከባልና ከሚስት በአንደኛው ላይ የሚመካኝ ጥፋት መታሰቡ የሚቀረው አንደኛው ይቅርታ ያደረገለት
እንደሆነ ነው፡፡

(2) ማናቸውም ተቃራኒ ማስረጃ ቢቀርብ ይቅርታ ተደርጓል ተብሎ የሚታሰበው ከሁለቱ አንደኛው በአጥፊነቱ ከተፈረደበት ወይም
የአጥፊነቱን ጠባይ ከተወበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ስድስት ወር ድረስ የመፋታት ጥያቄ ያልቀረበ እንደሆነ ነው፡፡

(3) በሃይማኖት ሥርዐት የተፈጸመ የጋብቻ መሠረዝ ጒዳይ መፋታትን የሚያስከትለው ከባድ ምክንያት ቀርቷል የሚያሰኘው የጋብቻውን
ሥርዐት መፍረስ የሚወስነው ብይን ከተሰጣቸው በኋላ ባልና ሚስቱ ሳይለያዩ አብረው መኖራቸውን ያላቋረጡ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 673፡፡ ሌሎች ምክንያቶች፡፡
(1) ከባልና ከሚስት በአንደኛው የተጠየቁት ሌሎቹ የመፋታት ምክንያቶች እንደ ከባድ የመፋታት ምክንያቶች አይቈጠሩም፡፡

(2) ስለሆነም ከዚህ በታች በሚከተሉት ቊጥሮች በተወሰኑት ሁኔታዎችና ጊዜዎች መሠረት መፋታቱ እንዲወሰን የሚያበቁ ምክንያቶች
ናቸው፡፡
ቊ 674፡፡ ለጊዜው የሚሰጡ ውሳኔዎች፡፡
(1) የሽምግልና ዳኞች የዚህ ዐይነት ጥያቄ እንደቀረበላቸው ወዲያውኑ በተለይም ባልና ሚስቱ ልጆቻቸውም የሚኖሩበትን መተዳደሪያ
ወይም የባልንና ወይም የሚስትን ወይም የጋራ ንብረትን አጠባብቅ ስለሚመለከተው ጒዳይ ሊይዝ የሚገባውን ያጠባበቅ ሥርዐት እንደ
ነገሩ አካባቢ ሁኔታ ለጊዜው የሚጸና ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡

(2) የባልዮውን ወይም የሚስቲቱን መኖሪያ ወይም እንዳይደርሱበት የሚያስፈልገውን ስፍራ ለይተው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
ቊ 675፡፡ የማሻሻል ችሎታ፡፡
የሽምግልና ዳኞች የሰጡትን ለጊዜው የተደረገውን ውሳኔ ከባለጥቅሞቹ በአንደኛው ጥያቄ ምን ጊዜም ቢሆን ሊለዋውጡትና እንዲያውም
በፍጹም ሊቀር ይችላል፡፡
ቊ 676፡፡ ስለ ማስታረቅ የሚደረግ ሙከራ፡፡
(1) መፋታትን የሚያስከትል ከባድ የሆነ ምክንያት ካልኖረ በቀር የቤተ ዘመድ ሽምግልና ዳኞች ባልና ሚስት እንዲታረቁና የመፋታት
አሳባቸውን እንዲተዉ መጣጣርና መድከም አለባቸው፡፡

(2) ስለዚሁም ጒዳይ መልካም መስሎ የሚታያቸውን ገደብ በባልና ሚስቱ ይወስኑባቸዋል፡፡
ቊ 677፡፡ በመፋታቱ ሁኔታ ላይ የሚደረግ ስምምነት፡፡
(1) የቤተ ዘመድ ሽምግልና ዳኞች ባልና ሚስቱ የመፋታት አሳባቸውን የማይለውጡ መሆናቸውን የተረዱ እንደሆነ በመፋታታቸው ሁኔታ
ላይ ስምምነት እንደሚያደርጉ መድከም አለባቸው፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ሁኔታ ስለ መፋታታቸው ባደረጉት ስምምነት መሠረት ውሳኔያቸውን ይሰጣሉ፡፡

ቊ 678፡፡ የመፋታታቸውን ብይን ለመስጠት የሚደረግ የጊዜ ውሳኔ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ተጋቢዎቹ ሳይሰማሙ የቀሩ እንደሆነ በቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች የመፋታቱ ጥያቄ ከቀረበላቸው በዓመት ውስጥ የመፋታትን
ብይን ይሰጣሉ፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተውን የአንድ ዓመት ጊዜ ጋብቻው ከመደረጉ በፊት ወይም ጋብቻው ከተደረገ በኋላ ሁለቱ
ወገኖች በሚያደርጉት ስምምነት እስከ 5 ዓመት ሊያረዝሙት ይችላሉ፡፡
ቊ 679፡፡ በመፋታቱ ብይን ላይ የሚጻፈው ቃል፡፡
(1) የመፋታቱን ብይን የሚወስነው የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ብይን የመፋታታቸውን ጒዳይ የሚያስከትለውንም ውጤት መግለጽ
አለበት፡፡
(2) ይህም ብይን በተለይ የሚገልጸው ከጋብቻው የተወለዱትን ሕፃናት አጠባበቅና አስተዳደግ ጒዳይ ሆኖ እንዲሁም ስለባልና ሚስቱ
ሀብት መከፈል ጒዳይ በሚመለከተው ረገድ አስፈላጊውን ትእዛዝ ይወስናል፡፡
ቊ 680፡፡ ተጨማሪ ብይን፡፡
(1) የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞቹ በመጀመሪያው ጊዜ የመፋታቱን ብይን ብቻ በመስጠት ይወስናሉ፤ ቀጥሎም የመፋታቱ ጒዳይ
የሚያስከትለውን ሌላ ክርክር ወይም ልዩ ክርክሮች በተጨማሪነት ለመበየን በቀጠሮ አውለው ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡

(2) የዚህም ተጨማሪ ብይን መስጠት የመፋታቱ ብይን ከተወሰነበት ከስድስት ወር በኋላ መሆን አለበት፡፡

ቊ 681፡፡ የሕፃናት አጠባበቅ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ከጋብቻው ስለ ተወለዱት ሕፃናት አጠባበቅና አያያዝ ጒዳይ የሚሰጠው ውሳኔ በተለይ ለሕፃናቶቹ ምቾትና ጥቅም የሚሆነውን ጒዳይ
በመመልከት ብቻ ነው፡፡

(2) ሌላ ውሳኔ የሚያሰጥ ምክንያት ከሌለ በቀር 5 ዓመት እስኪሞላቸው ድረስ ልጆቹ በናቲቱ እጅ እንዲቈዩ ይደረጋል፡፡

ቊ 682፡፡ (2) ለማሻሻል የሚቻልበት ዘዴ፡፡


ስለ ሕፃናቱ አጠባበቅና አስተዳደግ የተሰጠው ውሳኔ በአባት፤ በእናት ወይም ወደ ላይ በሚቈጠር ወላጅ በሆነው ጥያቄ አቅራቢነት
በማንኛውም ጊዜ ቢሆን የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ሊያሻሽሉት ይችላሉ፡፡
ክፍል 2፡፡
በተጋቢዎቹ መካከል ያለውን የገንዘብ ግንኙነት ጒዳይ ስለ ማጣራት፡፡
ንኡስ ክፍል 1
ከባልና ከሚስት የአንዱ መሞት፡፡
ቊ 683፡፡ የፈቃድ ነፃነት፡፡
(1) ከተጋቢዎቹ አንደኛው በሞተ ጊዜ የሀብታቸው ክፍያ ጒዳይ የሚጣራው በጋብቻቸው ውል ላይ በተመለከተው የስምምነት ቃል
መሠረት ወይም በተጋቢዎቹ መካከል በተደረገው ስምምነት ነው፡፡

(2) የዚህ ዐይነት ስምምነት የሌለ እንደሆነ ወይም ይህ ስምምነት በሚጸና አኳኋን ሳይደረግ ቀርቶ እንደሆነ የተጋቢዎቹ ሀብት ክፍያ
ሥርዐት የሚፈጸመው በዚሁ ክፍል ላይ በተደነገገው መሠረት ነው፡፡
ቊ 684፡፡ የግል ሀብቱን መልሶ ስለ መውሰድ፡፡
ከተጋቢዎቹ እያንዳንዱ የግል ሀብት መሆኑን አስረድቶ የራሱን የግል ድርሻ ሀብት በዐይነቱ መልሶ ለመውሰድ መብት አለው፡፡
ቊ 685፡፡ የጋራ ሀብቱን በየድርሻው ስለ መውሰድ፡፡
(1) ከተጋቢዎቹ አንዱ የግል ንብረቱ የነበረው ነገር ተሽጦ ዋጋው ወደ ጋራ ንብረት ውስጥ የተደባለቀ መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ከጋራ ሀብቱ
ውስጥ ለዚሁ የግል ገንዘቡ ተመዛዛኝ የሚሆነው መጠን ቀንሶ ዋጋውን ለራሰ ድርሻ ለመውሰድ ይችላሉ፡፡

(2) ሚስት የግል ሀብቷን ከባሏ አስቀድማ መውሰድ ይገባታል፡፡

ቊ 686፡፡ ስለ ካሣ (1) መሠረቱ፡፡


ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ወይም የሒሳብ ማስተካከል መተማመኛ ቢኖርም እንኳ፤ በሠራቸው ሥራዎችና የጋራ ሀብቶችን ወይም
ያንደኛውን የግል ሀብት በጎዱት ሥራዎች ምክንያት ከተጋቢዎች አንዱ ላንደኛው ኪሣራ እንዲከፍለው ለማድረግ የሚቻለው፡፡

(ሀ) ሥራውን የፈጸመው ይህንን ለማድረግ ሥልጣን ያልነበረው እንደሆነ፤

(ለ) የሀብት ጠባቂነቱ ተግባር መጥፎ ዐይነት አስተዳደር የሆነ እንደሆነ ወይም በከሳሹ ሀብት ላይ የማጭበርበርን ተግባር ፈጽሞ የተገኘ
እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 687፡፡ (2) ጥያቄን ስለ አለመቀበል፡፡


ጋብቻው ከመፍረሱ ከሦስት ዓመት በፊት በተሠሩት ሥራዎች ምክንያት ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር ላይ የተመሠረተው የኪሣራ ጥያቄ
ሊደረግ አይቻልም፡፡
ቊ 688፡፡ ያለ አገባብ ስለ መበልጸግ፡፡
ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ያንደኛው ወገን የግል ሀብት ባንደኛው የግል ሀብት ወይም የጋራ ሀብት ላይ ያለ አገባብ መብዛቱን ማረጋገጥ
ለሚችለው ወገን ኪሣራ እንዲከፈለው ይደረጋል፡፡
ቊ 689፡፡ የጋራ ሀብት ክፍያ፡፡
(1) ከዚህ በላይ ባለፉት ቊጥሮች የተለከቱት ድንጋጌዎችና በጋብቻቸው ውል ወይም ተጋቢዎቹ በሚጸና አኳኋን የተፈራረሙት ድንጋጌዎቹ
እንደተጠበቁ ሆነው የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ክፍያ የሚፈጸመው እኩል በእኩል ነው፡፡

(2) የክፍያን ሥርዐት፤ ክፍያ ከተደረገ በኋላ በጋራ ወራሾች መካከል ያለውን ግንኙነትና ክፍያ ከተደረገ በኋላ የገንዘብ ጠያቄዎችን መብት
ስለ መጠበቅ ጒዳይ በዚህ ሕግ በውርስ አንቀጽ በተነገረው ድንጋጌ የባልና የሚስትን የጋራ ንብረት በማካፈልም ጊዜ በተመሳሳይነት
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
የመፋታት ሁኔታ፡፡
ቊ 690፡፡ ጠቅላላ ደንብ፡፡
(1) ከዚህ ቀጥሎ በተመለከቱት ቊጥሮች ያሉት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ተጋቢዎቹ በተፋቱ ጊዜ የገንዘባቸው ግንኙነት የሚጣራው
ከሁለቱ አንዱ በሞተ ጊዜ ለሚደረገው የንብረት ክፍያ በተሰጠው ደንብ ዐይነት ነው፡፡

(2) በነዚህም ቊጥሮች ውስጥ የተመለከቱት ድንጋጌዎች በጋብቻም ውል ሆነ፤ የጋብቻቸውን ውል ከማፍረሳቸው በፊት ተጋቢዎቹ
በሚያደርጉት በሌላ ዐይነት ስምምነት እንዲቀር ለማድረግ አይቻልም፡፡
ቊ 691፡፡ ስጦታዎችና የጋብቻ ጥቅሞች፡፡
(1) ስጦታ የሰጡ ወይም ወራሾቻቸው በጠየቁ ጊዜና አስፈላጊ መሆኑም የተገመተ እንደሆነ የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ተጋቢዎቹ
የጋብቻቸውን ሥርዐት በፈጸሙ ጊዜ ወይም ጋብቻቸው በመኖሩ ምክንያት አንዱ ለአንዱ የሰጠውን ስጦታ፤ ወይም ከሁለቱ ወደ ላይ
ከሚቈጠሩ ወላጆች ወይም ከሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ያገኙትን ስጦታ እንዲመልሱ ያዛሉ፡፡

(2) በጋብቻው ጊዜ ወይም በጋብቻው ምክንያት ከተጋቢዎቹ ለአንደኛው ወይም ለሁለቱ ከሦስተኛ ወገን ተሰጥቶ የነበረውን ስጦታ ወይም
ተደርጎ የነበረውን የስጦታ ተስፋ ቃል ወይም ባልዮው ለሚስቱ ወይም ሚስት ለባልዋ የተሰጣጡትን ወይም ለመስጠት የገቡበትን የተስፋ
ቃል መሠረዝ አስፈላጊ መስሎ የታየ እንደሆነ፤ የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ሊያስቀሩት ይችላሉ፡፡
ቊ 692፡፡ ባልና ሚስቱን ስለ አለማስተካከል፡፡
(1) የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ከተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ውስጥ በርከት ያለውን ድርሻ ወይም ጠቅላላውን ላንደኛው ብቻ ደልድለው
ለመስጠት ይችላሉ፡፡
(2) እንዲሁም የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ከተጋቢዎቹ የአንደኛውን የግል ንብረት ለአንደኛው ድርሻ እንዲሆን ለመወሰን ይችላሉ፡፡
ይሁን እንጂ፤ ይህ ለአንደኛው እንዲሰጥ የሚወሰኑት የግል ንብረት ከባልዮው ወይም ከሚስትዮዋ ከሚወስደው ጠቅላላ ሀብት ሢሶ በላይ
መብለጥ አይገባውም፡፡

ቊ 693፡፡ የመፋታቱ አላፊነት (1) ከባድ ምክንያት፡፡

(1) መፋታቱ የተወሰነው አንደኛው ወገን ጥፋት በሆነ ከባድ ምክንያት የሆነ እንደሆነ ከዚህ በላይ በተጻፉት 2 ቊጥሮች የተመለከቱት
ቅጣቶች በተባለው ጥፋተኛ ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) አጥፊ ባልሆነው በአንደኛው ተጋቢ ላይ እነዚህ ቅጣቶች ተፈጻሚዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡

(3) መፋታቱ የተወሰነው የሁለቱም ወገኖች ጥፋት ባልሆነ ከባድ ምክንያት የሆነ እንደሆነ የተባሉት ቅጣቶች በሁለቱም ላይ
አይፈጸሙባቸውም፡፡
ቊ 694፡፡ (2) ከባድ ምክንያት ስላለመኖሩ፡፡

(1) መፋታቱ የተወሰነው ከባድ ባልሆነ ምክንያት የሆነ እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች የተመለከቱት ቅጣቶች ፍቺውን
በጠየቀው ተጋቢ ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) ፍቺውን ባልጠየቀው ተጋቢ ላይ እነዚህን ቅጣቶች እንዲፈጽሙ ለማድረግ አይቻልም፡፡


ቊ 695፡፡ መሪ የሆኑ ሐሳቦች፡፡
(1) በመሠረቱ የዘመድ ዳኞች የሚወስኗቸው ቅጣቶች ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች ውስጥ የተመለከቱትን ነው፡፡

(2) ስለሆነም በማናቸውም ጊዜ እነዚሁኑ ለመወሰን ወይም ላለመወሰን እንዲሁም ተፈጻሚ የሚሆኑበትን መጠን ለመወሰን ሙሉ
ሥልጣን አላቸው፡፡

(3) ለጒዳዩ ውሳኔ በሚሰጡበት ጊዜ ለጒዳዩ ምክንያት የሆነውን ነገር በተለይም መፋታትን ያስከተለውን የተጋቢዎቹን ጥፋት ከባድነትና
በሕሊናም በኩል (በሞራል) የፍቺው ጥያቄ የሚያስወቅስበትን መጠን መመርመር አለባቸው፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
ሌላ የጋብቻ መፍረስ፡፡
ቊ 696፡፡ መሪ ደንቦች፡፡
(1) የጋብቻን ሁኔታዎች ከማጓደል የተነሣ የጋብቻውን መፍረስ ዳኞች በሚወስኑበት ጊዜ መፍረሱ የሚያስከትለውን ውጤት በርትዕ
ይወስናሉ፡፡

(2) ፍቺ በሆነ ጊዜ በተጋቢዎቹ መካከል ያለውን የገንዘብ ግንኙነት ለማጣራት በተደነገጉት ደንቦች ዳኞቹ ይመራሉ፡፡

(3) በተለይም ዳኞቹ የሚመለከቱት የተጋቢዎቹን በቅን ወይም በመጥፎ ልቡና መሆን፤ ሩካቤ ሥጋ መፈጸሙን ወይም አለመፈጸሙን
ያሉም እንደሆነ ከፈረሰው ጋብቻ የተወለዱትን ልጆች ጥቅምና በቅን ልቡና የሆኑትን የሦስተኛ ወገኖችን ጥቅም ነው፡፡
ምዕራፍ 7፡፡
የጋብቻ ማስረጃ፡፡
ቊ 697፡፡ የሕጋዊ ማስረጃ አቋቋም ሥርዐት፡፡
ጋብቻ መኖሩን ለማስረዳት የሚቻለው በዚህ ምዕራፍ በተመለከቱት ማስረጃዎች ብቻ ነው፡፡
ቊ 698፡፡ የጋብቻ ጽሑፍ፡፡
ጋብቻ ለመኖሩ ማስረጃ የሚሆነው ጋብቻው በተፈጸመበት ጊዜ ወይም ጋብቻው ከተፈጸመ በኋላ በሕጉ መሠረት የተደረገውን በጽሑፍ
የተቋቋመውን የጋብቻ ጽሑፍ በማቅረብ ነው፡፡

ቊ 699፡፡ የባልና የሚስትነት ሁኔታ መኖር (1) ትርጓሜ፡፡

(1) የጋብቻ ጽሑፍ በሌለ ጊዜ ጋብቻ መኖሩን ለማስረዳት የሚቻለው የባልና ሚስትነት ሁኔታ መኖሩን በማስረዳት ነው፡፡

(2) ሁለት ሰዎች የባልና ሚስትነት ሁኔታ አላቸው የሚባለው፤ ባልና ሚስት ነን እየተባባሉ አብረው የሚኖሩ እንደሆነና ቤተ
ዘመዶቻቸውና ሌሎችም ሰዎች በዚሁ ሁኔታ መኖራቸውን ሲያረጋግጡላቸው ነው፡፡

ቊ 700፡፡ (2) ማስረጃና ክርክር፡፡

(1) የባልና ሚስትነት ሁኔታ መኖሩን ለማስረዳት የሚቻለው የተጋቢዎቹ ዘመዶች የሆኑ ወይም ያልሆኑ አራት ምስክሮችን በማስመስከር
ነው፡፡
(2) የባልና ሚስትነት ሁኔታ አለመኖሩን ለመከራከር የሚቻለው የተከራካሪዎቹ ዘመዶች የሆኑ ወይም ያልሆኑ አራት የመከላከያ
ምስክሮችን በማስመስከር ነው፡፡
ቊ 701፡፡ በግልጽ የታወቀ ጽሑፍ፡፡
የጋብቻ ሁኔታ መኖሩን የሚያስረዳ ነገር የሌለ እንደሆነ፤ ወይም ይህ ለመኖሩ የሚያከራክር የሆነ እንደሆነ ጋብቻ መኖሩን ለማስረዳት
የሚቻለው ዳኞች ባጸደቁት በግልጽ በታወቀ ጽሑፍ የተረጋገጠ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 702፡፡ ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ስለመሆኑ፡፡
(1) የዚህን ዐይነት ጽሑፍ ለማቅረብ ይቻላል ብለው ዳኞች ካልፈቀዱ በቀር ጋብቻ መኖሩ በዚህ በግልጽ በታወቀ ጽሑፍ ሊረጋገጥ
አይችልም፡፡

(2) ይህ ጒዳይ እንዲፈጸም የሚቀርበውን ማመልከቻ በማናቸውም ጊዜ ማናቸውም ባለጒዳይ ሊያቀርበው ይችላል፡፡

(3) ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል ካላጋጠመ በቀር የተጋቢዎቹ ወይም የወራሾቻቸው ቃል መሰማት አለበት፡፡
ቊ 703፡፡ ይህ አድራጎት ሊፈቀድ የሚችልበት ሁኔታ፡፡
ዳኞች በታወቀ ግልጽ በሆነ ጽሑፍ አማካይነት የጋብቻ ጒዳይ ለመኖሩ ማስረጃ እንዲሆን የሚፈቅዱት፡-

(ሀ) በዚህ ሕግ በቊጥር 145 በተመለከቱት ድንጋጌዎች አካባቢ ሁኔታ፤

(ለ) በሃይማኖት ባለሥልጣኖች የተሠራ የጋብቻ ውል በጠያቂው አቅራቢነት አስረጂ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ፤

(ሐ) አንድ የጋብቻ ውል በጠያቂው አማካይነት የቀረበ እንደሆነ፤

(መ) ተከሳሽ የሆነው ወገን ጋብቻ መኖሩን ያመነ እንደሆነ ወይም ጋብቻው አለ የሚያሰኝ ግምትና ምልክት የተገኘ ሲሆን፤ ይህም ግምትና
ምልክት ዳኞቹ ጒዳዩን ዐውቀው እንዲቀበሉት የሚያደርጋቸው ግልጽና ከፍ ያለ ሁኔታ ያጋጠመ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 704፡፡ በግልጽ የታወቀ ጽሑፍ እንዲዘጋጅ ሥልጣን የተሰጠው ሰው ግዴታዎች፡፡
(1) የጋብቻውን ሥነ ሥርዐት በክብር መዝገብ እንዲያገባና ጋብቻው በግልጽ እንዲታወቅ አስፈላጊውን ደንብ ይፈጽም ዘንድ ጥያቄ
የሚቀርብለት የጋብቻውን ሥነ ሥርዐት በግልጽ በታወቀ ጽሑፍ እንዲያዘጋጅ ሥልጣን የተሰጠው ሰው፤ ዳኞች በሰጡት ትእዛዝና ደንብ
መሠረት ለዚሁ ጒዳይ ሊደረግ የሚገባውን የማስታወቅ ሥርዐት ማረጋገጥ አለበት፡፡

(2) ይህ ማስታወቂያ ከተሰጠበት ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ወር ድረስ ጋብቻው እንዳይፈጸም የሚቃወሙ ሌሎች ወገኖች እንዳሉ
የመቃወሚያ ቃላቸውን እንዲያስመዘግቡ ያስታውቃል፡፡

ቊ 705፡፡ ውሉን የማጽናት ጒዳይና ሥርዐቱ (ፎርሙ)፡፡


(1) የጋብቻ ጒዳይ መኖሩን ስለ ማረጋገጥ የሚቀርበው በግልጽ የታወቀው ጽሑፍ በተቻለ መጠን ጋብቻው የተፈጸመበትን ቀንና ዓመተ
ምሕረት፤ አስፈላጊም ቢሆን ጋብቻው የቀረበበትን ቀንና ዓመተ ምሕረት ያመለክታል፡፡

(2) ይኸውም አራት ምስክሮች ካላረጋገጡለትና ዳኞች ካላጸደቁት ፈራሽ ይሆናል፡፡


ቊ 706፡፡ የማስረጃው ባለዋጋነት፡፡
(1) የጋብቻ ጽሑፍ ወይም ዳኞች ያጸደቁት በግልጽ የታወቀ የጋብቻ ጒዳይ መኖሩን የሚያረጋግጥ ሰነው በማንኛውም ዘንድ ዋጋ ያለ ነው፡፡

(2) የጋብቻው ሥርዐት አልተፈጸመም በማለት ወይም ጋብቻው የተፈጸመው በነዚህ ሰነዶች ላይ ከተጻፈው ቀን በሌላ ቀን ነው በማለትም
ቢሆን ማስረጃ ማቅረብ ያለበት የነዚህን ሰነዶች ትክክለኛ አለመሆን የሚከራከረው ወገን ነው፡፡
ቊ 707፡፡ የጋብቻው አለመጽናት ወይም መፍረስ
ጋብቻው አይጸናም ወይም ፈርሷል የሚለው ተከራካሪ ይህን ጒዳይ ማስረዳት አለበት፡፡
ምዕራፍ 8፡፡
ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ስለ መኖር፡፡
ቊ 708፡፡ ትርጓሜ፡፡
ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖር ማለት አንድ ሰውና አንዲት ሴት በሕግ በሚጸና አኳኋን ጋብቻ ሳያደርጉ እንደ ባልና ሚስት
ሆነው በመኖር አድርገውት የሚገኘው ሁኔታ ነው፡፡
ቊ 709፡፡ ማጠናቀቂያ፡፡
(1) ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አለ ለማለት ሰውዬውና ሴትዮዋ የሚያሳዩት ሁኔታ በደንብ እንደ ተጋቡ ሰዎች ዐይነት መሆኑ
አስፈላጊና በቂ ነው፡፡

(2) ለሦስተኛ ወገኖች እንደ ተጋቡ ሆነው መቅረብ አስፈላጊ አይደለም፡፡

(3) በታወቀ በተደጋገመ አኳኋን ቢሆንም እንኳ ከአንድ ሰውና ከአንዲት ሴት መካከል የግብር ሥጋ ግንኙነት ብቻ በሁለቱ መካከል
ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ይኖራሉ ለማለት በቂ ምክንያት አይደለም፡፡
ቊ 710፡፡ የጋብቻ ዝምድናን ስላለማስከተሉ፡፡
(1) ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖር በወንድዬውና በሴቲቱ የሥጋ ዘመዶች መካከል እንዲሁም በሴቲቱና በወንድዮው የሥጋ
ዘመዶች መካከል አንዳችም የጋብቻ ዝምድና ግንኙነትን አያስከትልም፡፡

(2) ስለሆነም የጋብቻ ዝምድና ባለ ጊዜ ጋብቻን የሚከለክሉ ድንጋጌዎች ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ባለም ጊዜ ተፈጻሚዎች
ይሆናሉ፡፡
ቊ 711፡፡ የጡረታ ግዴታን ስላለማስከተሉ፡፡
ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖር በዚህ አኳኋን በሚኖሩት ሴትና ወንድ መካከል አንዳችም የጡረታ ግዴታ አያስከትልም፡፡
ቊ 712፡፡ የጋራ ሀብት እንዲኖር ስላለመደረጉ፡፡
ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖር በዚህ አኳኋን በሚኖሩት ሴትና ወንድ መካከል የጋራ ሀብት እንዳላቸው አያስቈጥራቸውም፡፡
ቊ 713፡፡ የመውረስን መብት ስለአለማስከተሉ፡፡
ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖር በዚሁ አኳኋን በሚኖሩት ሴትና ወንድ መካከል ማንኛውንም የመውረስ መብትን
አያስከትልም፡፡
ቊ 714፡፡ ሴትዮዋ ለምትገባባቸው ዕዳዎች ወንድዮው ዋስ ስለ መሆኑ፡፡
ከጋብቻ ውጭ በግብር ሥጋ ግንኙነት ሁኔታ የሚኖር ሰው ለእርሱ ወይም ለርሱዋ ወይም ከግንኙነቱ ለተወለዱት ልጆች መኖሪያ ስትል
ሴቲቱ ለፈረመቻቸው አስፈላጊ ለሆኑት ውሎች ሁሉ በሕግ መሠረት በአንድነት ኀላፊ ነው፡፡
ቊ 715፡፡ የልጆች መወለድ፡፡
ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖር የተወለዱት ልጆች መወለዳቸው የሚጋገጠው ስለ መወለድ በተባለው ምዕራፍ ውስጥ
በተደነገጉት ደንቦች መሠረት ነው፡፡

ቊ 716፡፡ የግንኙነቱ ማለቅ፤ (1) እንዲያልቅ የምታደርገው ሴትዮዋ ስትሆን፡፡

(1) ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የምትኖር ሴት በማናቸውም ጊዜ ግንኙነትን እንዲያልቅ ለማድረግ ትችላለች፡፡

(2) እንዲህም በማድረጓ አንዳችም ኪሣራ እንድትከፍል ወይም የተሰጣትን እንድትመልስ አትገደድም፡፡

ቊ 717፡፡ (2) እንዲያልቅ የሚያደርገው ወንድዮው ሲሆን፡፡

(1) ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚኖር ሰው በማናቸውም ጊዜ ግንኙነቱን እንዲያልቅ ለማድረግ ይችላል፡፡

(2) እንዲህም በሆነ ጊዜ ርትዕ ሲያስገድድ እጅግ ቢበዛ ለሦስት ወር ለሴትዮዋ ኑሮ የሚበቃ ኪሣራ ዳኞች እንዲከፍላት ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

ቊ 718፡፡ የግንኙነት ማስረጃ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖሩን የግንኙነቱ ሁኔታ በመኖሩ ለማስረዳት ይችላል፡፡

(2) አንድ ወንድና አንዲት ሴት ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የመኖር ሁኔታ አላቸው የሚባለው ምንም እንኳ በደንብ የተጋቡ
ባይሆን፤ የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተ ዘመዶቻቸውና ጎረቤቶቻቸው እንደተጋቡ ሰዎች የሚኖሩ ናቸው ብለው ሲገምቷቸው ነው፡፡

ቊ 719፡፡ (2) ማስረጃና መከራከሪያ፡፡

(1) ከጋብቻ ውጭ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መኖሩን ለማስረዳት የሚቻለው በቂ ምስክሮችን በማስመስከር ነው፡፡

(2) እንዲሁም ይህ ግንኙነት ያለመኖሩን በመቃወም ለመከራከር የሚቻለው የባለጒዳዮቹ ዘመዶች የሆኑ ወይም ያልሆኑ በቂ ምስክሮችን
በማስመስከር ነው፡፡

ቊ 720፡፡ (3) በግልጽ የታወቀ ጽሑፍ፡፡

(1) ከጋብቻ ውጭ የግብር ሥጋ ግንኙነት መኖሩ የተካደ እንደሆነ ይህ ግንኙነት መኖሩን ለማስረዳት የሚቻለው ዳኞች ያጸደቁትን በግልጽ
የታወቀውን የጽሑፍ ማስረጃ በማቅረብ ነው፡፡

(2) ስለ ጋብቻ መኖር ማረጋገጫ ሰነድ ጒዳይ በዚህ አንቀጽ በቊጥር 72 እስከ 76 የተመለከቱት ውሳኔዎች ደንብ ከጋብቻ ውጭ የግብር
ሥጋ ግንኙነት መኖሩንም ስለ ማስረዳት ጒዳይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 721፡፡ ከጋብቻ ውጭ የሆኑ ሌሎች ግንኙነቶች፡፡
(1) ከጋብቻ ሥርዐት ወይም ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሆነ ዐይነት በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የተደረጉ ሌሎች
ግንኙነቶች በሕግ ፊት ምንም ውጤት የላቸውም፡፡

(2) ባለጒዳዩ ወይም ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች በእንደዚህ ያለው ጒዳይ በሕግ ፊት በማንኛውም ምክንያት መከራከሪያ ሊያደርጋቸው
አይችልም፡፡

(3) ከእንደዚህ ያለ ግንኙነት የተወለዱትም ልጆች ከእናታቸው ጋራ በቀር ከሌላ ጋራ ማናቸውም ዐይነት ሕጋዊ መተሳሰር የላቸውም
ስለሆነም በዚህ ሕግ የጉዲፈቻ ልጅ ለማድረግ ወይም ልጄ ነው ብሎ ለመቀበል የተወሰነው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ነው፡፡
ምዕራፍ 9፡፡
በጋብቻና በፍቺ ከጋብቻው ውጭ በሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ጒዳይ ስለሚነሡ ክርክሮች፡፡
ቊ 722፡፡ የሚጸና መተጫጨት ስለ መኖሩ፡፡
የመተጫጨት ሥነ ሥርዐት ተፈጽሟል ወይም አልተፈጸመም ለማለትና ይህ መተጫጨት ይጸናል ወይም አይጸናም ብሎ ውሳኔ ለመስጠት
ሥልጣን ያላቸው ዳኞች ብቻ ናቸው፡፡
ቊ 723፡፡ በመተጫጨት ጒዳይ ውስጥ የሚፈጠሩ ክርክሮች፡፡
(1) በመተጫጨት ጒዳይ ውስጥ ወይም በመተጫጨት ውል መፍረስ ላይ የሚነሡትን ክርክሮች መርምረው ውሳኔ የሚሰጡ በዚሁ
በመተጫጨቱ ሥርዐት ምስክሮች የነበሩት የቤተ ዘመድ የሽምግልና ዳኞች ናቸው፡፡

(2) እንደ መጀመሪያ ምስክሮች ሆነው የተመረጡ ሰዎች እንዳሉ ክርክሩ እንዲመረመር የሚቀርበው ለነዚሁ የሽምግልና ዳኞች ነው፡፡

(3) ባለጒዳዮቹ የመተጫጨታቸው ሥርዐት በተፈጸመ ጊዜ ወይም ከዚያ በኋላ ክርክራቸውን ሌሎች የሽምግልና ዳኞች እንዲመረምሩ
ለመምረጥ (ለመስማማት) ይችላሉ፡፡
ቊ 724፡፡ የሚጸና ጋብቻ ስለ መኖሩ፡፡
የጋብቻ ሥነ ሥርዐትና ውል የተፈጸመ ለመሆኑና ይህም ጋብቻ የሚጸና መሆኑን ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው ዳኞች ብቻ ናቸው፡፡
ቊ 725፡፡ ከጋብቻ ጒዳይ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች፡፡
(1) በጋብቻው ጊዜ በባልና ሚስት መካከል የሚነሡትን ችግሮች በሽምግልና ዳኝነት መርምረው ውሳኔ የሚሰጡት በጋብቻው ጊዜ
ምስክሮች የነበሩት ናቸው፡፡

(2) እንደ መጀመሪያ ምስክሮች ሆነው የተመረጡ ሰዎች እንዳሉ እንዲመረመር ክርክሩ የሚቀርበው ለነዚሁ የሽምግልና ዳኝነት ነው፡፡

(3) ባለጒዳዮቹ የጋብቻው ሥርዐት በሚፈጸምበት ጊዜ ወይም ከተፈጸመ በኋላ በመካከላቸው የተነሣውን ችግር ሌሎች የሽምግልና ዳኞች
እንዲመረምሩ ለመስማማት ይችላሉ፡፡
ቊ 726፡፡ በሞት ምክንያት የሚፈርስ ጋብቻ፡፡
የጋብቻውን መፍረስ ያስከተለው ምክንያት ከባልና ከሚስት የአንደኛው መሞት በሆነ ጊዜ የጋብቻው መፍረስ የሚያመጣው ክርክር
እንዲወሰን የሚቀርበው ለነዚሁ ሰዎች የሽምግልና ዳኝነት ነው፡፡
ቊ 727፡፡ የመፋታት ጥያቄ፡፡
ከባልና ከሚስት ወይም ከሁለቱ አንደኛው ወገን የሚያቀርበው የመፋታት ጥያቄ እንዲወሰን የሚቀርበው ለነዚሁ የሽምግልና ዳኞች ነው፡፡
ቊ 728፡፡ በመፋታት ምክንያት የሚፈጠሩ ክርክሮች፡፡
(1) ከመፋታት ጒዳይ ውስጥ የሚነሣው ክርክር ለምርመራ የሚቀርበው የመፋታቱን ውሳኔ ለሰጡት የሽምግልና ዳኞች ነው፡፡

(2) ባለጒዳዮቹ በሚፋቱበት ጊዜ ወይም ከተፋቱ በኋላ ክርክራቸውን ለሚመረምሩ ለሌሎች ሰዎች የሽምግልና ዳኝነት እንዲቀርብ
ለመስማማት ይችላሉ፡፡
ቊ 729፡፡ የመፋታት ጒዳይ ስለ መኖሩ፡፡
የመፋታት ውሳኔ የተሰጠ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ሥልጣን ያላቸው ዳኞች ብቻ ናቸው፡፡
ቊ 730፡፡ ከጋብቻ ውጭ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ስለ መኖሩ፡፡
(1) ከጋብቻ ውጭ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሁለት ሰዎች መካከል መኖር አለመኖሩን ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው ዳኞች ብቻ ናቸው፡፡

(2) እንዲሁም በዚህ ግንኙነት ምክንያት በሚነሡት ክርክሮች ላይ ውሳኔ ለመስጠት የሚችሉት ዳኞች ብቻ ናቸው፡፡
ቊ 731፡፡ ሽማግሌ ባልተመረጠበት ጊዜ የሚሆን አሠራር፡፡
ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች በተነገሩት ደንቦች መሠረት ለሽምግልና መቅረብ ያለበትን ክርክር የሚቈርጥ ምንም ሽማግለ ሳይመረጥ
ቀርቶ እንደሆነ፤ ተጋቢዎቹ እያንዳንዳቸው ሁለት ሽማግሌዎችን ይመርጣሉ፡፡
ቊ 732፡፡ ተጨማሪ ሽማግሌዎችን ስለ መምረጥ፡፡
ማናቸውም ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ቢኖርም እንኳ የቤተ ዘመድ ሽማግሎች ሽምግልናቸውን የተሟላ ለማድረግ በመካከላቸው
በሚሰጥ የድምፅ ብዛት አንድ ወይም ብዙዎች ተጨማሪ ሽማግሌዎችን ስለ መምረጥ ለመስማማት ይችላሉ፡፡

ቊ 733፡፡ ሽማግሌን ስለ መተካት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ውሳኔ እንዲሰጥ የተመረጠው ሽማግሌ የሞተ እንደሆነ ወይም የተነሣውን ክርክር ያለ መዘግየት ለመቊረጥ ያልቻለ እንደሆነ፤ በእርሱ
ምትክ እርሱ በተመረጠበት ዐይነት ሌላ ሽማግሌ ሊተካ ይቻላል፡፡

(2) ይኸው የተመረጠው ሰው የሽምግልናውን ሥራ ለመፈጸም እንቢ ያለ እንደሆነ፤ ወይም ዳኞቹ ያስወገዱት እንደሆነ ዳኞቹ ሌላ ሽማግሌ
ይመርጣሉ፡፡
ቊ 734፡፡ (2) ሽማግሌን በመምረጥ ስላለመስማማት፡፡
ሁለቱም ወገኖች በመስማማት አንድ ሽማግሌ መምረጥ ያለባቸው ሲሆንና በተባለው ምርጫ ያልተስማሙ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች
በሚያቀርቡት ጥያቄ ዳኞቹ ሽማግሌውን ይመርጣሉ፡፡

ቊ 735፡፡ (3) አንደኛው ወገን ሽማግሌን ስላለመምረጡ፡፡


ሽማግሌ መምረጥ ያለበት አንደኛው ወገን እንዲመርጥ ከታዘዘበት ቀን አንሥቶ በዐሥራ አምስት ቀን ውስጥ ሽማግሌውን ሳይመርጥ የቀረ
እንደሆነ፤ ወይም ሥራውን ለመፈጸም የማይፈቅደውን ሽማግሌ የመረጠ እንደሆነ፤ በማናቸውም ምክንያት ይህንኑ ሥራ ባለመዘግየት
ለመፈጸም የማይችለውን ሽማግሌ የመረጠ እንደሆነ፤ ሌላው ወገን በሚያቀርበው ጥያቄ ሽማግሌ እንዲመርጥ ስለታዘዘው ወገን ዳኞቹ
ሽማግሌውን ይመርጡለታል፡፡
ቊ 736፡፡ ሽማግሌዎች በቈረጡት ነገር ላይ ለፍርድ ቤት ስለሚቀርበው አቤቱታ፡፡
ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች መሠረት ሽማግሌዎች የሰጧቸው ውሳኔዎች ሽማግሌዎቹ በጉቦ መሥራታቸውን ወይም በሦስተኛ ሰዎች
ላይ ተንኰል በመሥራት የተደረጉ ወይም ለሕግ ተቃራኒ የሆነ ጠባይ ያላቸው መሆናቸውን ወይም የተሰጡት ውሳኔዎች በግልጽ ከአእምሮ
ሚዛን ውጭ መሆናቸውን በማስረዳት ካልሆነ በቀር በዳኞች ፊት ክስ ሊቀርብባቸው አይችሉም፡፡
ቊ 737፡፡ ሽማግሌ ነገሩን ሳይቈርጥ ስለ መቅረቱ፡፡
እንዲሁም ሽማግሌዎቹ በሕግ የተወሰነ ጊዜ የሌለ እንደሆነ በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ሳይሰጡ የቀሩ እንደሆነ አንደኛው
ወገን በሚያቀርበው ጥያቄ ዳኞቹ ነገሩን ሊመረምሩ ይችላሉ፡፡
ምዕራፍ 10፡፡
ስለ መወለድ፡፡
ክፍል 1፡፡
አባትንና እናትን ስለ ማወቅ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 738፡፡ በሕግ የተወሰኑት ደንቦች የማይጣሱ ስለ መሆናቸው፡፡
ሕጉ በግልጽ ስምምነቶችን ካልፈቀዳቸው በቀር አባትንና እናትን ስለ ማወቅ የተሰጡት ደንቦች በስምምነት ሊለወጡ አይቻልም፡፡
ቊ 739፡፡ እናትነትን ስለ ማስረዳት፡፡
በመወለድ ብቻ እናትነትን ለማስረዳት ይቻላል፡፡
ቊ 740፡፡ አባትነትን ስለ ማስረዳት፡፡
(1) ልጁ በተፀነሰበት ወይም በተወለደበት ጊዜ በእናትና በአንድ ሰው መካከል በሕግ የታወቀ ግንኙነት የኖረ እንደሆነ ከሴትዮዋ በመወለዱ
አባትነትን ለማስረዳት ይቻላል፡፡

(2) እንዲሁም አባት ልጄ ነው ሲል የተቀበለ እንደሆነ አባትነት ይገለጻል፡፡

(3) በመጨረሻም እናት በመጠለፍ ወይም በመደፈር ተገድዳ ስትገኝ ዳኛ ልጅህ ነው ሲል በሚሰጠው ፍርድ አባትነት ይገለጻል፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
አባት ነው ስለሚያሰኝ ግምት፡፡
ቊ 741፡፡ ባልዮው ወላጅ አባት ነው ስለሚያሰኝ ግምት፡፡
በጋብቻው ጊዜ የተፀነሰው ወይም የተወለደው ልጅ አባቱ ያው የእናቱ ባል ነው፡፡
ቊ 742፡፡ የዚህ ግምት ጠቅላላነት፡፡
(1) ከእናት የሚገኘው የልጁ ተወላጅነት በማናቸውም ዐይነት የተረጋገጠ ቢሆን ከዚህ በላይ ያለው ቊጥር ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

(2) እንዲህም የልጁ የመወለዱ የምስክር ጽሑፍ የእናቱ ባል የልጁ አባት መሆኑን ባያመለክት እንኳ ወይም የልጁ አባት ሌላ ወንድ መሆኑን
ቢያመለክትም ይህ ከዚህ በላይ የተጻፈው ቊጥር ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

(3) እንደዚህ ያለው ነገር በሚያጋጥምበት ጊዜ፤ የመወለድ ጽሑፍ ተቃንቶ በባልዮው ስም መጻፍ አለበት፡፡
ቊ 743፡፡ እርግዝናው ስለሚቈይበት ጊዜ፡፡
(1) ልጁ የጋብቻው ሥርዐት ከተፈጸመ በኋላ ከ 180 ቀን በላይና ከመፋታቱም በኋላ 300 ቀን ሳይሞላ የተወለደ እንደሆነ አባትና እናቱ
ተጋብተው በነበሩበት ጊዜ እንደ ተፀነሰ ሆኖ ይገመታል፡፡

(2) ለዚሁ ተቃራኒ የሚሆን ማስረጃ እንዲቀርብ አይፈቀድም፡፡


ቊ 744፡፡ የባል በአገር አለመኖር፡፡
የልጁ መወለድ ባልዮው በአገር የለም ተብሎ በፍርድ ከተነገረ በኋላ የሆነ እንደሆነ የተባለው ባል አባቱ አይደለም፡፡
ቊ 745፡፡ ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚኖረ ወንድ አባትነትን ስለመገመት፡፡
(1) ከጋብቻ ውጭ በሆነ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ የተፀነሰው ወይም የተወለደው ልጅ አባቱ እናቲቱን ይዞ የተቀመጠው ነው፡፡

(2) የሕሊና ግምትን ጠቅላላ ጒዳይና በርግዝና የመቈየትን የሕሊና ግምት የሚመለከቱት ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች የተጻፉት ደንቦች
ለዚሁ ግምት ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
አባትነትን ስለ ማወቅ፡፡
ቊ 746፡፡ መሠረቱ፡፡
ከዚህ በላይ የተጻፉትን ቊጥሮች ተፈጻሚ በማድረግ የልጁ አባት እገሌ ነው ተብሎ ያልታወቀ እንደሆነ ከአባት የሚገኘው የልጁ መወለድ፤
አባት የኔ ነው ሲል ከማወቁ የተነሣ የልጁ አባት መሆኑ ሊረጋገጥ ይቻላል፡፡
ቊ 747፡፡ የማወቁ ጽሑፍ የሚጻፍበት፡፡
(1) አባትነትን ማወቅ የተፀነሰው ወይም የተወለደው ለልጁ አባት እኔ ነኝ የሚል አንድ ሰው በሚሰጠው ቃል ይታወቃል፡፡

(2) ይህ የሚሰጠው ቃል አባትነትን ማወቅ የሚያስከትለው ውጤት እንዲኖረው ሲል የተናገረው መሆኑ አስፈላጊ አይደለም፡፡
ቊ 748፡፡ የማወቁ አሠራር ፎርምና ማስረጃ፡፡
(1) አባትነትን ማወቅ በጽሑፍ ካልሆነ ምንም ውጤት የለውም (አይጸናም)፡፡

(2) በዚህ ሕግ በ 146 ቊጥር ከተደነገጉት ሁኔታዎች ውጭ አባትነትን ለማወቁ በምስክር ለማረጋገጥ አይቻልም፡፡
ቊ 749፡፡ በውክልና ስለሚነገረው ቃል፡፡
(1) የኔ ልጅ ነው በማለት የሚሰጠውን ቃል የሚገልጸው አካለመጠን ያላደረሰም ቢሆን ራሱ የልጁ አባት ነው፡፡

(2) አባትነትን ለማስታወቅ የሚደረገው ወኪልነት፤ በጽሑፍ ሆኖ ዳኞቹ ባጸደቁት ልዩ ውክልና ብቻ የሚሰጥ ነው፡፡

(3) የመግለጫውንም ቃል በፍርድ የተከለከለው ወይም በእርሱ ስም አሳዳሪው በዳኞች ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ቊ 750፡፡ ስለ አባት መሞት፡፡
(1) የልጁ አባት የሞተ ወይም ፈቃዱን (ሐሳቡን) ለመግለጽ በማይችልበት ሁኔታ የተገኘ እንደሆነ፤ የአባትነቱን ማስታወቅ፤ በእርሱ ስም
ሆኖ በአባት በኩል ያለ ወንድ አያት ወይም ሴት አያት ሊፈጽም ይችላል፡፡

(2) እነዚህ ሲታጡ በአባት በኩል ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች ሊፈጽሙ ይቻላል፡፡


ቊ 751፡፡ ስለ እናቱ ማመን፡፡
(1) የአባት ልጁን መቀበል ውጤት የሚያገኘው የልጁ እናት ያረጋገጠችለት ሲሆን ነው፡፡

(2) የልጁ እናት የሞተች ወይም አሳቧን ለመግለጽ በማትችልበት ሁኔታ የተገኘች እንደሆነ፤ አባት የሚያደርገውን የልጅነቱን መቀበል
በእናት በኩል ያለ ወንድ አያት ወይም ሴት አያት እንዲፈቅዱ ያስፈልጋል፡፡

(3) በእናት በኩል ያሉ አያቶች ሲታጡ ወደ ላይ የሚቈጠሩ በእናት በኩል ያሉ ወላጆች ወይም ለተከለከለው አሳዳሪ የሆነው ሰው
እንዲፈቅዱ ያስፈልጋል፡፡
ቊ 752፡፡ ስለ ልጁ አካለመጠን ማድረስ፡፡
የአባት ልጁን መቀበል የተደረገው፤ ልጁ አካለመጠን ካደረሰ በኋላ የሆነ እንደሆነ ልጁን መቀበሉ ውጤት የሚያገኘው ልጁ ራሱ አባትነቱን
የተቀበለ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 753፡፡ የመቀበሉ ፎርም፡፡
የአባትነትን ማወቅ የሚቀበለው ሰው ይህንኑ ካወቀ በኋላ እስከ 1 ወር ክርክር ካላነሣ የአባትነትን ማወቅ እንደ ተቀበለ ይቈጠራል፡፡
ቊ 754፡፡ ስለ ልጁ መሞት፡፡
ልጅዮው ልጅ ወይም የልጅ ልጅ ተክቶ ካልሞተ በቀር በአባት በኩል የሚነገረው የልጁ መታወቅ ከልጁ መሞት በኋላ ሊሆን አይችልም፡፡
ቊ 755፡፡ ቃልን ስለመለወጥ (ስለማፍረስ)፡፡

(1) ልጄ ነው ሲል አባት የሰጠውን ቃል ለመለወጥ አይችልም፡፡

(2) ልጄ ነው ብሎ የተቀበለ አካለመጠን ያላደረሰ ሰው ይህን ቃሉን አካመጠን ባላደረሰበት ዘመን ለመሻር ይችላል፡፡ እንዲሁም አካለ
መጠንን ካደረሰ በኋላ አካለመጠን ባደረሰበት ዓመት ውስጥ ለመሻር ይችላል፡፡ ይህንንም ማድረግ የሚችለው፤ ልጄ ነው ብሎ በተቀበለ
ጊዜ የተቀበለው አሳዳሪው ፈቅዶለት ያልሆነ እንደሆነ ነው፡፡

(3) ልጄ ነው ብሎ የተቀበለበትን ቃሉን የሚሽረው ራሱ ብቻ ነው እንጂ ሕጋዊ እንደራሴዎቹ ወይም ወራሾቹ ይህ መብት የላቸውም፡፡
ቊ 756፡፡ ስለ መሠረዝ፡፡
(1) በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚል አንቀጽ በተሰጡት ደንቦች መሠረት የኀይል ሥራ የተገኘበት እንደሆነ ቢፈርስ ይቻላል፡፡
(2) በዚሁ አንቀጽ ደንቦች መሠረት ልጁ ልጄ ነው ብሎ ከተቀበለው ሰው አልተፀነሰም ተብሎ ግልጽ በሆነ ዐይነት ለማስረዳት ካልተቻለ
በቀር ልጄ ነው ሲል የሰጠውን ቃል በስሕተት ወይም በማታለል የተደረገ ነው ብሎ ለማፍረስ አይቻልም፡፡
ቊ 757፡፡ ለአንድ ልጅ የብዙ ሰውን አባትነት ማወቅ ስለ መከልከል፡፡
ስለ ልጁ ጥቅም አባት ነኝ ሲል አንድ ሰው አባትነቱን ካወቀለትና ይህንንም ማወቅ በሚገባ ከተቀበሉት በኋላ በመጀመሪያ የተሰጠው
የማወቅ ቃል ፈርሶ በሚገኝበት ጊዜ ካልሆነ በቀር ሌላ ሰው የሚያደርገውን የኔ ልጅ ነው ማለትን ሊቀበሉት አይቻልም፡፡
ንኡስ ክፍል 4፡፡
በፍርድ ስለሚደረግ የአባትነት ማወቅ፡፡
ቊ 758፡፡ ስለ መጥለፍና ወይም ስለ መድፈር ሥራ፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመፈጸም ልጁ አባት የሌለው ሲሆን ወይም ልጅነቱ የተካደ እንደሆነ፤ የልጁ እናት ልጁ
በተፀነሰበት ወራት የመጠለፍ ወይም የመደፈር ሥራ ደርሶባት እንደሆነ የአባትነት መታወቅ፤ በፍርድ ሊነገር ይቻላል፡፡
ቊ 759፡፡ በፍርድ ለመጠየቅ ስለሚያስፈልጉ ምክንያቶች፡፡
(1) አባትነቱ በፍርድ እንዲገለጽ የሚደረገው ክስ በልጁ እናት ብቻ ወይም እናቱ የሞተች እንደሆነ ወይም አሳቧን ለመግለጽ በማትችልበት
ሁኔታ የተገኘች እንደሆነ፤ በልጁ አሳዳሪ ሊቀርብ ይችላል፡፡

(2) ልጁ ከተወለደ ወይም መጠለፉን ወይም መደፈሩን በሚመለከተው ጒዳይ በወንጀል ውሳኔ ከተሰጠ ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ክስ
ለማቅረብ አይቻልም፡፡
ቊ 760፡፡ ስለ ክሱ መከናወን፡፡
በፍርድ (በዳኝነት) የሚደረገው የአባትነት ማወቅ እናቲቱን ከጠለፈው ወይም በኀይል ከተገናኘው ሰው ሥራ ልጁ ያልተፀነሰ ለመሆኑ
ማፍረሻ በማይገኝለት አኳኋን ማስረጃ ካልቀረበ በቀር፤ ለመጠለፉ ወይም ለመደፈሩ አቋም የሆኑት ነገሮች እንደ ተረጋገጡ ወዲያውኑ
በፍርድ የሚነገረው የአባትነት ማወቅ ወዲያውኑ መገለጽ አለበት፡፡
ቊ 761፡፡ የሌላ ሁኔታ ስላለመኖር፡፡
በፍርድ ስለሚደረገው የአባትነት ማወቅ በመጠለፍ ወይም በመደፈር ካልሆነ በማናቸውም ሌላ ሁኔታ ሊጠየቅ ወይም ሊወሰን
አይቻልም፡፡
ክፍል 2፡፡
በአባትነት ምክንያት ስለሚነሣው ክርክር፡፡
ቊ 762፡፡ አባትነትን ስለ መወሰን፡፡ (1) መሠረቱ፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከቱትን ቊጥሮች ተፈጻሚ በማድረግ አንድ ልጅ ብዙ አባቶች አሉት የተባለ ሲሆን፤ ለልጁ አባትነት በሕግ
በሚሰጣቸው አባቶች መካከል በሚደረግ ውል ሊወሰን ይችላል፡፡

ቊ 762፡፡ (2) ሥርዐት (ፎርም)፡፡

(1) የአባትነትን ውሳኔ የሚያሰጠውን ውል፤ አራት ምስክሮች ሊያረጋግጡትና ዳኞች ሊያጸድቁት ይገባል፡፡

(2) ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል ካልገጠመ በቀር የልጁን እናት ቃል መስማት ይገባል፡፡
ቊ 764፡፡ ስለ ሕጋዊ ግምት፡፡
ስለ አባትነት በሚደረገው ክርክር ስምምነት ያልተገኘ እንደሆነ አስፈላጊ ሲሆን ከዚህ ቀጥለው ያሉትን ሁለት ግምቶች በመከተል
ይፈጸማሉ፡፡
(ሀ) ከጋብቻ ውጭ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ከያዛት ሰው ይልቅ ባልዋ ይመረጣል፡፡
(ለ) እናቲቱ ልጁን በወለደችበት ጊዜ ላላት ባል ልጁ ነው ከማለት ይልቅ ልጁ በተፀነሰበት ጊዜ ለነበራት ባል ልጁ ነው ማለት ይገባል፡፡

ቊ 765፡፡ ያባትነትን ውል ስለ ማስተላለፍ (1) የተፈቀዱ ሁኔታዎች፡፡

(1) ልጁ የተወለደው ጋብቻው ከፈረሰ ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከቀረ በኋላ ከ 210 ቀን በላይ ቈይቶ የሆነ እንደሆነ ባልዮው ወይም
ከሴትዮዋ ጋራ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የነበረው ሰው የልጁ አባት እኔ ነኝ ለሚለው ለሌላው ሰው በውል ልጅነቱን ሊያውቅለት ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ልጁ ከጋብቻው መፈረስ ወይም የግብረ ሥጋው ግንኙነት መኖር ከቀረበት ቀን በኋላ ሁለት መቶ ዐሥር ቀኖችን አሳልፎ
ተወልዶ እንደሆነ ለባልዮው ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላለው ሰው ከዚህ በላይ የተነገረው መብት አለው፡፡

ቊ 766፡፡ (2) ሥርዐት፡፡ (ፎርም)፡፡

(1) በውል የሚደረግ የአባትነት ማስተላለፍ አራት ምስክሮች ያረጋገጡትና ዳኞች ያጸደቁት መሆን አለበት፡፡

(2) ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል ካልተከለከለች በቀር፤ የልጁ እናት ቃሏ መሰማት አለበት፡፡
ቊ 767፡፡ ስለ እንደራሴነት፡፡
(1) በዚህ ክፍል የተመለከቱትን ውሎች አካለ መጠን ያደረሱና በፍርድ ያልተከለከሉ ባለጒዳዮቹ ራሳቸው መጨረስ አለባቸው፡፡

(2) ውሎቹን ሕጋዊው እንደራሴ (ወኪል) በባለጒዳዮቹ ስም ሆኖ ሊጨርሳቸው አይችልም፡፡

(3) ውሎቹን የመጨረስ ወኪልነት፤ በጽሑፍ ተደርጎ፤ ይህንኑም ዳኞቹ አጽድቀውት በልዩ ውክልና ካልሆነ በቀር ሊሰጥ አይቻልም፡፡
ቊ 768፡፡ ቃልን ስለ ማፍረስና ስለ መለወጥ፡፡
(1) በዚህ ክፍል የተመለከቱት ውሎች ሊፈርሱ አይችሉም፡፡

(2) በዚህ ሕግ ‹‹ስለ ውሎች በጠቅላላው›› በሚል አንቀጽ የተሰጠውን ደንቦች መሠረት በማድረግ በኀይል በሚደረግ ሥራ ምክንያት
ሊፈርሱ ይችላሉ፡፡

(3) በዚሁ አንቀጽ ደንቦች መሠረት ልጁ ልጄ ነው ብሎ ከተቀበለው ሰው አልተፀነሰም ብሎ ግልጽ በሆነ ዐይነት ለማስረዳት ካልተቻለ
በቀር ልጄ ነው ሲል የሰጠውን ቃል በስሕተት ወይም በማታለል የተደረገ ነው ብሎ ለማፍረስ አይቻልም፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ ልጅነት ማስረጃ፡፡
ቊ 769፡፡ የመወለድ የምስክር ወረቀት፡፡
በአባትነት ወይም በእናትነት በኩል የአንድ ሰው ልጅነት የእገሌ ልጅ ነው በሚል በመወለድ የምስክር ወረቀት ይረጋገጣል፡፡
ቊ 770፡፡ የልጅነት ሁኔታ መኖር፡፡ (1) ትርጓሜ፡፡

(1) የመወለድ የምስክር ወረቀት የሌለ እንደሆነ የልጅነት ሁኔታ በመኖሩ ልጅነቱ የተረጋገጠ ይሆናል፡፡

(2) አንድ ሰው የልጅነት ሁኔታ አለው የሚባለው አንድ ሰው ወይም አንዲት ሴት ወይም ዘመዶቻቸው ወይም ሌሎች ሰዎች የዚያ ሰው
ወይም የዚያች ሴት ልጅ ነው እያሉ የሚገምቱት ሲሆን ነው፡፡

ቊ 771፡፡ (2) ስለ ማስረጃና ስለ ክርክር፡፡

(1) የልጅነት ሁኔታ መኖርን የባለጒዳዩ ዘመዶች ቢሆኑም ባይሆኑም አካለ መጠን ባደረሱ አራት ምስክሮች ለማስረዳት ይቻላል፡፡

(2) የባለጒዳዮቹ ዘመዶች ቢሆኑም ባይሆኑም አራት ምስክሮችን በማቅረብ የልጅነት ሁኔታ መኖርን የለውም በማለት ክርክር ለማድረግ
ይቻላል፡፡
ቊ 772፡፡ የልጅነት ሁኔታ መኖርን በመጠየቅ ስለሚቀርብ ክስ፡፡
የልጅነት ሁኔታ መኖር የሌለ እንደሆነ ወይም በዚሁ ሁኔታ ላይ ክርክር የተነሣበት እንደሆነ፤ ወይም የልጅነት ሁኔታ መኖር በመወለድ
የምስክር ወረቀት ላይ ከተዘረዘሩት ነገሮች ጋራ የማይስማማ እንደሆነ፤ የልጅነቱን ሁኔታ መኖር ለመጠየቅ በሚቀርበው ክስ መሠረት ግልጽ
ሆኖ በባለሥልጣን በተሰጠና ዳኞች ባጸደቁት ጽሑፍ ልጅነቱ ይወሰናል፡፡
ቊ 773፡፡ ክሱን ስለ መቀበል፡፡
(1) የልጅነት ሁኔታ መኖርን ለመጠየቅ የሚቀርበው ክስ ዳኞች ካልፈቀዱት በቀር ሊቀርብ አይቻልም፡፡

(2) የልጅነት ሁኔታ መኖርን ስለ መጠየቅ ክስን ለማቅረብ ፈቃድ የሚሰጠው ዳኞቹ ክሱን እንዲቀበሉ ከሚያደርጉ በቂ ከሆኑ ከባድነት
ካላቸው ተግባሮች የሚመነጩ ግምቶች ወይም ምልክቶች ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡
ቊ 774፡፡ ክስን ስላለመቀበል፡፡
ልጅነቱን ለማረጋገጥ የሚፈልገው ሰው ስለ መወለዱ ከተሰጠው የምስክር ወረቀት ጋራ የሚስማማ ሌላ የልጅነት ሁኔታ መኖር ያለው
እንደሆነ ለሌላ ሰው የልጅነት ሁኔታ መኖርን ለመጠየቅ ክስን ለማቅረብ አይፈቀድለትም፡፡
ቊ 775፡፡ ስለ ከሳሽ፡፡
(1) የልጅነት ሁኔታ መኖርን ለመጠየቅ ክስ ለማቅረብ የሚችሉት ልጁ ወይም አሳዳጊው ወይም ወራሾቹ ናቸው፡፡

(2) እንዲሁም የልጅ አባት ወይም እናት ነን የሚሉት ሰዎች ክስ ለማቅረብ ይችላሉ፡፡

(3) ክሱ የተከናወነ በሚሆንበት ጊዜ የልጁ አባት ነው ተብሎ አባት መሆን ሊደርስበት የሚችለው ሰው አባትነቱን ለመካድ ሲል ክስ
ለማቅረብ ይችላል፡፡
ቊ 776፡፡ ክስ ስለሚቀርበት ጊዜ፡፡
(1) ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ የልጅነት ሁኔታ መኖርን ለመጠየቅ ክስ ለማቅረብ ይችላል፡፡

(2) የልጁ አሳዳሪና በላይኛው ቊጥር በ 2 ኛውና በ 3 ኛው ኀይለ ቃል የተመለከቱት ሰዎች ልጁ አካለመጠን ባላደረሰበት ጊዜ ካልሆነ በቀር
ክስ ለማቅረብ አይችሉም፡፡

(3) ልጁ ሓያ ዓመት ሳይሞላው የሞተ እንደሆነ እርሱ ከሞተ በኋላ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልሆነ በቀር ወራሾቹ ክሱን ለማቅረብ
አይችሉም፡፡
ቊ 777፡፡ ስለ ተከሳሽ፡፡
(1) የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ለመጠየቅ ክስ ያቀረበችው እናት ነኝ የምትለዋ በሆነች ጊዜ ክሱ የሚቀርበው በልጁ ላይ ነው፡፡

(2) የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ለመጠየቅ ክሱን ያቀረበችው አናት ባልሆነች ጊዜ ክሱ የሚቀርበው እናት ነች በተባለችዋ ወይም በወራሾቿ
ላይ ነው፡፡

(3) የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ለመጠየቅ ክስ የቀረበው በማናቸውም ሲሆን ክሱ የተከናወነ በሚሆንበት ጊዜ፤ የልጁ እናት ነች የተባለችውና
ልጁ ያንተ ነው የተባለው ሰው በክሱ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ክፍል 4፡፡
በሁኔታው ላይ ስለሚነሣው ክርክርና ስለ መካድ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
በሁኔታው ላይ ስለሚደረግ ክርክር፡፡
ቊ 778፡፡ መሠረቱ፡፡
በእናት በኩል ያለው መወለድ (ልጅነት) በማናቸውም ባለጒዳይ በምን ጊዜም ሁሉ ክርክር ሊደረግበት ይቻላል፡፡
ቊ 779፡፡ ክስን ስለ መቀበል፡፡
(1) በሁኔታው ላይ ስለሚደረገው ክርክር የሚቀርበው ክስ ዳኞች ካልፈቀዱ በቀር ሊቀርብ አይችልም፡፡

(2) በሁኔታው ላይ ክርክር ለማድረግ ስለሚቀርበው ክስ ፈቃድ የሚሰጠው ዳኞቹ ክሱን እንዲቀበሉ ከሚያደርጉ እርግጠኛ ከሆኑና በቂ
ከባድነት ካላቸው ተግባሮች የሚመነጩ ግምቶች ወይም ምልክቶች ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡
ቊ 780፡፡ ክስን ስላለመቀበል፡፡
ከሳሹ እከራከርበታለሁ የሚለው ልጅነት ለባለጒዳዩ ካለው የመወለድ የምስክር ወረቀት የመነጨና ከዚህ ከመወለድ የምስክር ወረቀት ጋራ
ጸም ያልተቻለ እንደሆነ ምትክ ለሆነ ሰው እንዲያስተላልፍ የተሰጡት ንብረቶች በዋናው ወራሽ ለሆነው ሰው ወራሾች ይተላለፋሉ፡፡

ቊ 781፡፡ ስለ ተከሳሽ
1. በሁኔታው ላይ የሚቀርበው ክስ በልጅነቱ(በመወለዱ)ላይ ክርክር በተነሳበት ሰው ወይም
በወራሾቹ ላይ ይደረጋል፡፡
2. የልጁን እናት አስፈላጊም ሲሆን አባትዮውን በነገሩ ክርክር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ
ነው፡፡

ንዑስ ክፍል 2

ስለመካድ

ቊ 782፡፡ መሰረቱ
ከአባት የሚመጣው ለልጁ አባት እኔ አይደለሁም በማለት የሚቀርበው ክርክር የሚፈፀመው የመካድ
ክስ በማቅረብ ነው፡፡
ቊ 783፡፡ ከልጁ እናት ጋር ግንኙነት ስላለመኖር(1) መሰረቱ
የልጁ አባት ነህ ተብሎ በህግ አባትነት የሚሰጠው ሰው ልጁ ከመወለዱ በፊት በ 300 ኛውና
በ 180 ኛው ቀን መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ከልጁ እናት ጋር በግብረ ስጋ ላለመገናኘቱ ተቃራኒ
ማስረጃ በማይገኝበት አኳኋን ያስረዳ እንደሆነ የተባለውን ልጅ ልጄ አይደለም ለማለት ይችላል፡፡
ቊ 784፡፡ ስለ ህሊና ግምት
1. ከሁለቱ አንዱ ባቀረበው የመፋታት ጥያቄ መሰረት ወይም በሁለቱ መካከል በጽሑፍ በተደረገው
የመለያየት ስምምነት ምክንያት ባልና ሚስት በእውነት ተለያይተው በነበሩበት ጊዜ
በመካከላቸው የሥጋ ግብር ግንኙነት እንዳልተደረገ ይገመታል፡፡
2. ለዚህ ተቃራኒ ሆኖ የሚቀርበው ማስረጃ በማንኛዎቹም ምክንያት ቢሆን ይሰማል፤ይኸውም
ማስረጃ በተለየ ቀላሎች ከሆኑ ግምቶች ሊመነጭ(ሊገኝ)ይችላል፡፡
ቊ 785፡፡ አባት ነህ ለማለት ስላለመቻሉ፡፡(1) መሰረቱ
የልጁ አባት ነህ ተብሎ አባትነቱ በሕግ የሚሰጠው ሰው ልጁ ከዚህ ከተባለው ሰው ስራ ተወልዷል
ለማለት በዐይነቱ በጭራሽ የማይቻል መሆኑን ተቃራኒ ማስረጃ በማይገኝበት አኳኋንያስረዳ
እንደሆነ ልጁ የኔ አይደለም ለማለት ይችላል፡፡
ቊ 786፡፡ በፍርድ የተከለከለ ሰው
1. ዳኞችን አስፈቅዶ የልጅ መካድ ክስ ለማቅረብ ይችላል፡፡
2. እንዲሁም በፍርድ የተከለከለ ሰው አሳዳሪ ይህንኑ ፈቃድ ከተቀበለ በኋላ በፍርድ በተከለከለው
ሰው ስም ሆኖ ክስ ለማቅረብ ይችላ፡፡
ቊ 787፡፡ (2) ክስን ለማቀበል ስለ መቻል
1. ከዚህ በላይ በተፃፈው ቁጥር የተመለከተው በሚያጋጥምበት ጊዜ የእኔ ልጅ አይደለም ስል ማለት
የሚቀርበው የመካድ ክስ ዳኞቹ ካልፈቀዱ በቀር ሊቀርብ አይችልም፡፡
2. የእኔ ልጅ አይደለም ስለማለት ለሚቀርበው የመካድ ክስ ፈቃድ የሚሰጠው ዳኞቹ ክሱን
እንዲቀበሉ ከሚያደርጋቸው እርግጠኛ ከሆኑና በቂ ከባድነት ካላቸው ተግባሮች የመነጩ
ግምቶች ወይም ምልክቶች ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡
ቊ 788፡፡ (3) ስለ ህሊና ግምቶችና ስለ ከባድ ምልክቶች
1. የህሊና ግምቶችና ከባድ(ትልቅ) ምልክቶች የሚባሉት ልጅህ ነው ከተባለ ሰው አባትነት ጋር
የማይስማሙ (የማይገናኙ) ለመሆናቸው በሲያንስ ዕውቀት ተለይተው የሚታዩ ግዙፍ
ሁኔታዎች ለመሆን ይችላሉ፡፡
2. እንዲሁም እነዚህ ነገሮች ሴቲቱ በሰውዬው አባትነት ጥርጣሬ ለማግባት በሚችል አኳኋን የልጅን
መወለድ ወይም እንዲያውም እርግዝናዋን ለባልዋ ከደበቀችበት ምክንያት ሊመነጩ ይችላሉ፡፡
ቊ 789፡፡ (4) ስለ ሴሰኝነት(በባል ላይ ስለሚደረግ ዝሙት) ወይም ስለሴቲቱ ማመን
ሴቲቱ በባልዋ ላይ ያደረገችው የሴሰኝነት(የዝሙት) ሥራ ወይም ልጁ የሌላ ሰው ለመሆኑ
የምትሰጠው የእምነት ቃል እነዚህ ነገሮች ብቻ እንደ ከባድ ትልቅ ምክንያት ሊቆጠሩ አይችሉም፡፡
ቊ 790፡፡ የማይመስል አባትነት
የልጅነት ሁኔታው እንዲገለጽነት በመጠየቅ ልጁ ከእናቲቱ ለመወለዱ የተረጋገጠ እንደሆነ አባትነቱ
የተሰጠው ሰው የልጁ አባት ላለመሆኑ የሚያቀርባቸውን ምክንያቶች በማስረዳ የእኔ ልጅ አይደለም
ብሎ ለመካድ ይችላል፡፡
ቊ 791፡፡ ስለ ከሳሽ
የእኔ ልጅ አይደለም ብሎ የመካድ ክስ ለማቅረብ የሚችለው፡-
1. የልጁ አባት ነህ ተብሎ በሕጋውያን ደንቦች መሠረት የልጁ አባትነት የሚሰጠው ሰው ብቻ ነው፡፡
2. በዚዚህ ጉዳይ በተለይ እናቲቱ ወይም አባት ነኝ ባዩ ወይም ዐቃቤ ሕግ ወይም ልጁ ራሱ ክስ
ሊያቀርብ አይችልም፡፡
ቊ 792፡፡ ክስ የሚቀርብበት ጊዜ (1) መሠረት
1. የእኔ ልጅ አይደለም የሚል የመካድ ክስ ልጁ ከተወለደ በኋላ በሚከተሉት 180 ቀኖች ውስጥ
መቅረብ አለበት፡፡
2. የልጅነት ሁኔታ መኖሩ እንዲገለጽ ለመጠየቅ በቀረበው ክስ ምክንያት ልጁ ከእናቲቱ ለመወለዱ
የተረጋገጠ ሲሆን የእኔ ልጅ አይደለም የሚል የመካድ ክስ የሚቀርበው የልጅነት ሁኔታ መኖሩ
እንዲገለጽ ለመጠየቅ የቀረበውን ክስ የሚወስን የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ በ 180 ቀኖች
ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
ቊ 793፡፡ (2) ስለ ልዩ አጋጣሚ ምክንያ
1. ልጅህ ነው ተብሎ አባትነቱ በህግ የተሰጠው ሰው የሞተ እንደሆነ ወይም ልጄ አይደለም በማለት
ስለሚቀርበው ክስ በተወሰኑ ጊዜዎች ውስጥ ክሱን ለማቅረብ ችሎታ የሌለው ሆኖ የተገኘ
እንደሆነ በርሱ ፈንታ ልጄ አይደለም ብሎ የመካድን ክስ ወደታች ከሚቆጠሩ ተወላጆቹ አንዱ
ሊያቀርብ ይችላ፡፡
2. የተወላጆቹ(ተወላዲያን) የለሉ እንደሆነ አባቱና እናቱ እነዚህም የሌሎ እንደሆነ ወደ ላይ
ከሚቆጠሩ ከወላጆቹ አንዱ መብቱን ሊሠራበት ይችላል፡፡
3. ወደ ላይ ከሚቆጠሩ ወላጆች የሌሉ እንደሆነ የተባለውን መብት ማናቸውም ሌላው
ወራሽወይም እንደራሴ ቀሪ ሆኖ ከወንድሞቹ ወይም ከእኅቶቹ አንዱ ሊሠራበት ይችላል፡፡
ቊ 794፡፡ ክስን ስላለመቀበል
ባልዮው በጽሑፍ ፈቅዶ በጥበባዊ(በአርቲፊሲየል) መንገድ ልጁ የተፀነሰ ለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ
ልጄ አይደለም የማለትን የክስ ጥያቄ ሊቀበሉት አይችሉም፡፡
ቊ 795፡፡ ስለ ተከሳሽ
1. ልጄ አይደለም ብሎ የመካድ ክስ በልጁ ላይ እርሱም ሞቶ እንደሆነ በወራሾቹ ላይ ይቀርባል፡፡
2. የልጁን እናት በሚቀርበው ክስውስጥ እንድትገባ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
3. ልጁ አካለመጠን ያልደረሰ እንደሆነ ዳኞች በተለይ የመረጡት ተጠባባቂ ሞግዚት ወኪል ይሆናል፡፡
ምዕራፍ 11
ስለ ጉድፍቻ የማር ልጅ
ቊ 796፡፡ በጉድፍቻ ስለሚገኝ ልጅነት
1. በጉድፍቻ አባትና በጉድፍቻ ልጅ መካከል በሚደረገው ውል ምክንያት አንድ የሚያስተሳስር
የልጅነት ግንኙነት ሊፈጠር ይችላል፡፡
2. በጉድፍቻ ልጅና በጉድፍቻ አድራጊው ቤተ ዘመድ መካከል ከአሠራሩ የተነሳ የሚገኝ የስጋ
ዝምድናና የጋብቻ መተሳሰር በዚሁ አንቀጽ በመጀመሪያው ምዕራፍ ተገልጸዋል፡፡
ቊ 797፡፡ ስለጉዲፈቻ አድራጊው ዕድሜ
1. ማናቸውም ሰው አካለመጠን ካደረሰ የጉድፍቻ ልጅ ማድረግ ይችላል፡፡
2. ባልና ሚስት የጉድፊቻ ልጅ በሚወልዱበት ጊዜ ከባልና ሚስት አንዱ የአርባ ዓመት ዕድሜ ያለው
ከሂነ ይበቃ፡፡
ቊ 798፡፡ ያገባ ሰው ስለ ጉዲፈቻ ልጅ ስለማበጀቱ
1. ጉዲፊቻ አድራው ያገባ የሆነ እንደሆነ ባልና ሚስቱ ባንድነት ሆነው የጉዲፈቻውን ልጅ
ለመቀበል ውል ካላደረጉ የጉዲፈቻው ስርዓት ሊፈፀም አይችልም፡፡
2. ባል የሚስቱን ሚስት የባልዋን ልጅ የጉዲፈቻ ልጅ ያደረጉት እንደሆነ ከዚህ በላይ ባለው
ኀይለቃል የተመለከተው ድንጋይ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
3. እንዲሁም ከባልና ሚስት አንዱ አሳቡን ለመግለጽ በማይችልበት ሁኔታ ሲገኝ ድንጋው ተፈፃሚ
አይሆንም፡፡
ቊ 799፡፡ የተፀነሰውን ልጅ በጉዲፊቻ ስለመውለድ
1. የተፀነሰውን ልጅ የጉዲፈቻ ልጅ ለማድረግ ይቻላል፡፡
2. በዚህ ጊዜ የተደረገው የጉዲፈቻ ልጅነት ልጁ ከመወለዱ በፊት ወይም ልጁ ከተወለደ በኋላ
በሚከተሉት ሦስት ወሮች ውስጥ በእናት በኩል በሚደረገው ማስታወቅ ብቻ ሊቀር ይችላል፡፡
ቊ 800፡፡ ጉዲፈቻ አድራጊው ልጅ ያለው ስለመሆኑ
ጉዲፈቻ አድራጊው ልጅም ቢኖረው የጉዲፈቻ ልጅን መውለድ አይከለክልም፡፡
ቊ 801፡፡ ብዙ ሰዎች አንዱን ሰው የጉዲፈቻ ልጅ ማድረግ የማይገባቸው ስለ መሆኑ
1. ባልና ሚስት ካልሆኑ በቀር ማንም ሰው ለብዙ ሰዎች የጉዲፈቻ ልጅ ለመሆን አይችልም፡፡
2. ስለሆነም ጉዲፈቻ አድራጊው የሞቱ እንደሆነ እንደገና ለሌላ ሰው የጉዲፈቻ ልጅ ለመሆን
ይቻላል፡፡
3. የጉዲፈቻው ልጅ ባልና ሚስት በጉዲፈቻ የወለዱት ሲሆን ከባልና ሚስት አንዳቸው በሞት
የጉዲፈቻው ልጅ በሕይወት ካለው ጋራ የሚጋራው አዲስ ተጋቢ ጉዲፈቻ ሊያደርገው ይችላል፡፡
ቊ 802፡፡ ውሉን ስለሚያደርጉ ወገኖች
1. ስለ ጉዲፈቻ የሚደረገው ውል በጉዲፈቻ የሚወለደው ልጅ ዕድሜው ከአስራ አምስት ዓመት
በላይ የሆነ እንደሆነ በጉዲፈቻ አድራጊውና በጉዲፈቻው ልጅ መካከል ይፈፀማል፡፡
2. ጉዲፈቻ የሚደረገው ልጅ ዕድሜው ከ 15 ዓመት በታች የሆነ እንደሆነ ውሉን ጉዲፈቻ
አድራውና የጉዲፈቻው ልጅ አሳዳሪ ይፈጽሙታል፡፡
ቊ 803፡፡ የጉዲፈቻ ልጅ ወላጆች ፈቃድ
1. የጉዲፈቻው ልጅ አባትና እናት በሕይወት ያሉና የታወቁ ከሆኑ ሁለቱም ልጃቸው የጉዲፈቻ
ልጅ እንዲሆን እንዲፈቅዱ ያስፈልጋል፡፡
2. አባትና እናቱ ሞተው የሌሉ ወይም ፈቃዳቸውን ለመግለጽ የማይችሉ እንደሆነና የማይቻል
ሲሆን ጉዲፈቻውን ለመፍቀድ ወደላይ የሚቆጠሩ ወላጆቻቸው በእነርሱ ምትክ ይሆናሉ፡፡
3. ልጁ ጉዲፈቻ እንዲሆን ፈቃድ ለመስጠት የሚችል ወደላይ የሚቆጠር ወላጅ የለለው እንደሆነ
ፈቃድ የሚሰጠው የቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ነው፡፡
ቊ 804፡፡ ስለ ጉዲፈቻው ውል መጽናት
1. የጉዲፈቻው ውል ዳኞች ካላጸኑት በቀር ውጤት የለውም (አይጸናም)፡፡
2. ዳኞቹ ውሳኔ ከመሰጠታቸው በፊት ጉዲፈቻ የሚሆነው ልጅ ከአስር ዓመት በላይ የሆነ እንደሆነ
እርሱ የሚለውንና ይህን የጉዲፈቻውን ውል አስቀድሞ አሳዳጊው ያልፈቀደ እንደሆነም
የአሳዳጊውን ቃል መስማት አለባቸው፡፡
ቊ 805፡፡ የጉዲፈቻውን ውል ለማጽደቅ አስፈላጊ የሆኑ ምክንያቶች
የጉዲፈቻ ልጅ ለመሆን የሚያስፈልገው ትክክለኛ ምክንያት ሲኖርና ጉዲፈቻ ለሚሆነው ልጅ
ጥቅም ያለው ሆኖ ሲታይ ብቻ ነው፡፡
ቊ 806፡፡ የጉዲፈቻን ውል ስለ ማፍረስ
ጉዲፈቻ ውል ከተፈፀመ በኋላ በማናቸውም ምክንያት ቢሆንሲፈርስ አይችልም፡፡
ምዕራፍ 12
ስለ ቀለብ መስጠት ግዴታ
ቊ 807፡፡ ስለ ግዴታው ዓላማ
የቀለብ መስጠት ግዴታ ያለበት ሰው ለባለጉዳዮች ሁኔታና ለአገሩ ልምድ የሚስማሙትን በመከተል
እንደሚገባ ዐይነት ተጠዋሪው የሚመገባቸውን የሚኖርባቸውን የሚለብሳቸውንና ጤናውን
የሚጠብቅባቸውን አስፈላጊ ነገሮች መስጠት አለበት፡፡
ቊ 808፡፡ ግዴታው በእነማን መካከል ያለ ስለመሆኑ
1. የቀለብ መሰጠት ግዴታ ያለው በቀጥታ ወላጆችና ተወላጆች ወይም በቀጥታ የጋብቻዘመዶች
መካከል፡፡
2. እንዲሁም ከአንድ አባትና ከአንድ እናት በተወለዱት ወይም በአባት በኩል ወይም በእናት በኩል
ብቻ ወንድማማችና እትማማች በሆኑትም መካከል የቀለብ መስጠት ግዴታ አለ፡፡
ቊ 809፡፡ (1) ግዴታው የሚወገድበት አጋጣሚ ምክንያት
በጋብቻው ምክንያት የዝምድና መተሳሰር በመፈታት ምክንያት የቀረ እንደሆነ በጋብቻ ዘመድ
መካከል ያለው የቀለብ መስጠት ግዴታ ቀሪ ይሆናል፡፡
ቊ 810፡፡ (2) በዳኝነት በኩል ስለሚነገር አባትነት
ሴትዮዋ በተጠለፈችበት ወይም በተደፈረችበት ጊዜ ልጅህ ነው ተብሎ በዳኝነት ለተነገረበት ሰው
የቀለብ መስጠት ግዴታ አይገባቸውም ፡፡
ቊ 811፡፡ (3) ገንዘብ ጠያቂው ቀለብ ለመቀበል የማይገባው ስለመሆኑ
እንዲሁም ቀለብ ተቀባዩ በቀለብ ሰጪው ወይም በዚሁ ሰው ወደ ላይና ወደታች በሚቆጠሩ
ወላጆችና ተወላጆች ወይምባል ወይም ሚስት ህይወት ላይ አደጋ በመጣል ሙከራ ተፈርዶበት እንደ
ሆነ ቀለብ መቀበሉ ይቀርበታል፡፡
ቊ 812፡፡ ግዴታ እንዲኖር አስፈላጊ የሆኑ ሁኔታዎች
የቀለብ መስጠት ግዴታ የሚገባ ሆኖ የሚገኘው ግዴታው እንዲፈፀምለት የሚጠይቀው ሰው ሠርቶ
ለመብላት የማይችል ሲሆንና በችግር ላይ የወደቀ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
ቊ 813፡፡ ስለ ግዴታ አፈፃፀም ዐይነት
1. በመደቡ የቀለብ መስጠት ግዴታ የሚፈፀመው ጧሪው ለተጠዋሪው የቀለቡን ገንዘብ በመስጠት
ነው፡፡
2. የዚህ የጡረታ ጠቅላላ ገንዘብ የሚወሰነው (የሚቆጠረው) የጡረታውን ገንዘብ የሚጠይቀው
ሰው ያለበትን ችግርና የከፋዩን ሀብት በማመዛዘን ነው፡፡
ቊ 814፡፡ ሁኔታውን ለማሻሻል ስለ መቻል
ቀለብ ሰጪው ወይም ተቀባዩ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ለጡረታ ገንዘብ ልክ የተሰጠውን ውሳኔ
በማናቸውም ጊዜ ሁሉ ለማሻሻል ይችላል፡፡
ቊ 815፡፡ የጡረታ ገንዘብ የሚከፈልበት ቦታ
ዳኞቹ የሰጡት ተቃራኒ የሚሆን ውሳኔ ከሌለ በቀር የጡረታ ገንዘቦች የሚከፈሉት በተጠዋሪው
መኖሪያ ቦታ ነው፡፡
ቊ 816፡፡ የሚከፈል የጡረታ ገንዘብ (1) ሊተላለፍና ሊያዝ ሳላለመቻሉ
1. ለጡረታ የሚከፈል ገንዘብ ሊተላለፍና ሊያዝ አይችልም
2. እንዲሁም ስለ ተባለ ለጡረታ የሚከፈሉ ገንዘቦች የሚከፈልበት ጊዜ ከመድረሱ አስቀድሞ
እንኳን ቢሆን በጡረታው ምግብ የሚጠቀመው ሰው ላለበት ችግር አሳቢ ለሚሆኑ ስለእርዳታ
ለተቋቋሙ ድርጅቶች ሊተላለፉ ይችላል፡፡
3. እንዲሁም ውዝፎችን በጡረታው ለሚጠቀመው ሰው ለሕይወቱ አስፈላጊ የሆነውን የተጡት
ሰዎች ሊቀበሉት ይችላሉ፡፡
ቊ 817፡፡ (2) የሚጠራቀም ስላለመሆኑ
ቀለብ ተቀባዩ ውዝፉ ለኑሮው አስፈላጊ መሆኑን ካላረጋገጠ በቀር ማናቸውም ውዝፍ ቢሆን
ለመክፈሉ የተወሰነውን ጊዜ በሚከተሉ ሦስት ወሮች ውስጥ የተባለውን ገንዘብ ሳይቀበለው ወይም
ሳይጠይቀው የቀረ እንደሆነ ቀሪ ይሆንበታል፡፡
ቊ 818፡፡ ቀለብ ተቀባዩን ከቤት ለማኖር ስለ መቻል
1. ቀለብ ሰጪው ቀለብ ተቀባዩን መኖሪያ ቤቱ ተቀብሎ በማስቀመጥ ግዴታውን ልፈጽም ሲል
ጥያቄ ለማቅረብ ይችላል፡፡
2. ዳኞች ይህን የቀረበውን ጥያቄ የሚቀበሉት ወይም የማይቀበሉት ለመሆኑ አካባቢዎቹን ነግሮች
ሁሉ ተመልክተው ይወስናሉ፡፡
3. ቀለብ ሰጪው ቀለብ ተቀባዩን በመኖሪያ ቤት እንዲያስቀምጥ ምን ጊዜም ሰጪው ለመገደድ
አይችልም፡፡
ቊ 819፡፡ ስለ ቀለብ ሰጪዎች ብዛት (1) መሰረቱ
ለቀለብ ተቀባዩ ቀለብ ተቀባዩን በመኖሪያ ቤቱ እንዲያስቀምጥ ምን ጊዜም ቢሆን ለመገደድ
አይችልም፡፡
ቊ 820፡፡ (2) ስለ አቤቱታ
1. ቀለብ እንዲከፍሉ የተፈረደባቸው ሰዎች ሳይከፍሉ የቀሩትን ባለዕዳዎች ለመክሰስ ይችላሉ፡፡
2. ዳኞቹ ተከሳሾቹ ባለዕዳዎች ያላቸውን ሀብትና ከከሳሹ ጋራ ያላቸውን የስጋ ዝምድና ወይም
የጋቻ ዝምድና ደረጃ በማመዛዘን እነዚህ የተከሰሱት ባለዕዳዎች የቀለቡን ገንዘብ በሙሉ ወይም
በከፊል እንዲከፍሉ ሊፈረድባቸው ይችላሉ፡፡
ቊ 821፡፡ (3) ለቀለብ ሰጪዎች የሚሰጥ የከፋይኘት ተራ
ልዩ ልዩ የሆኑትም ቀለብ ሰጪዎች ባለባቸው ግዴታ ምክንያት በቁጥር የዚህን የቀለብ ሰጪነት ዕዳ
የሚችሉበት የከፋይነት ተራ
ሀ. በመጀመሪያ ደረጃ ባል ወይም ሚስት
ለ. በሁለተኛ ደረጃ ተወላጆቹ እንደየደረጃቸው
ሐ. በሦስተኛ ደረጃ ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆቹ እንደየደረጃቸው
መ. በአራተኛው ደረጃ ከአንድ አባትና ከአንድ እናት የተወለዱ ወንድማማችና እህትማማቾች
ሠ. በአምስተኛው ደረጃ ከአባት በኩል ወይም ከእናት በኩል ብቻ ወንድማማችና እህትማማች
ረ. በስድሰተኛው ደረጃ የጋብቻ ተወላጆቹ እንደየደረጃቸው
ሰ. በሰባተኛው ደረጃ የጋብቻ ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች እንደየደረጃቸው
ቊ 822፡፡ (4). በጋራ ቀለብ ሰጪዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት
1. የጋራ ቀለብ ሰጪዎች እርስ በእርሳቸው ስለአላቸው ግንኙነት ለጋራ ቀለብ ተቀባያቸው ከእነርሱ
መካከል አንዱ ቀለቡን እንዲሰጠው በማለት የሚጸና ስምምነት ለማድረግ ይችላሉ፡፡
2. ቀለብ ተቀባዩ ስምምነቱን ይሁን ሲል የተቀበለ እንደ ሆነ ይህን ስምምነት የማያከብርበት ከባድ
ምክንያት ካልተገኘለት በቀር ቀለቡን ለመቀበል ሌሎቹን ቀለብ ሰጪዎች መጠየቅ አይችልም፡፡
ቊ 823፡፡ ስለ ጉዲፈቻ ልጅነት ልዩ ሁኔታ
1. የጉዲፈቻ ልጅ ባል ወይም ሚስትና የቀጥታ መስመር ተወላጆቹ የጉዲፈቻ አድራጊው ቤተ
ዘመዶች ቀለቡን ለመስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ካልተገኙ በቀር የስር ወላጆቹን ቤተ ዘመዶች
ቀለብ ለመጠየቅ አይችሉም
2. የሥር ወላጆቹ ቀለብ ለማግኘት ሌላውን ከዝርያቸው አንዱን ለመጠየቅ የማይችሉ ካሆኑ በቀር
በጉዲፈቻ የሰጡትን ልጅ ቀለብ ሊጠይቁት አይችሉም፡፡
ቊ 824፡፡ ስለ ስርዓተ ቀብር ኪሳራ
1. የቀለብ መስጠት ግዴታ ያለበት ሰው ለዚህ ለተባለው ሰው ሥርዐተ ቀብር የወጣውንም ኪሳራ
ለመክፈል ተገዳጅ ይሆናል፡፡
2. የዚህን ኪሳራ ወጪ ያደረገው ሰው የሥራ አካሄድን በሚመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ገንዘቡን
እንዲያገባለት ቀለብ ሰጪውን ለመጠየቕ ይችላል፡፡
ቊ 825፡፡ ልዩ ስምምነቶች
ልዩ ስምምነቶችን በማድረግ በዚህ ምዕራፍ የተፃፉትን ድንጋጌዎች ለመለወጥ አይፈቀድም፡፡
አንቀጽ አምስት
ስለውርስ(ስለአወራረስ)
ምዕራፍ 1
ስለውርስ አስተላለፍ
ክፍል 1
ጠቅላላ ድንጋጌዎች
ንዑስ ክፍል 1 ስለ ውርስ አከፋፈልና በውስጡ ስለሚገኝበት
ቊ 826፡፡ ስለውርስ መክፈት
1. አንድ ሰው የሞተ እንደሂነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያው ስፍራ በሆነበት ቦታ የዚህ ሟች
ውርስ ይከፈታል፡፡
2. በሟቹ መሞት ምክንያት የሚቆጠሩ ካልሆኑ በዚህ አንቀጽ ደንቦች መሰረት በውርስ ውስጥ
የሚገኙት የሟች መብቶችና ግዴታዎች ለወራሾቹና በኑዛዜ ባለሱጠታዎች ይተላለፋል፡፡
ቊ 827፡፡ በውርስ ውስጥ የሚገኘው (1) ስለ ሕይወት የሚደረግ አሹራንስ
1. ሟቹ ተጠቃሚውን ያልወሰነ እንደሆነ ወይም አሹራንስ ለሟቹ ወራሾች ጥቅም የተደረገ
እንደሆነ ሟቹ በፈረመው ስለ ሕይወት አሹራንስ ውል አፈፃፀም የሚከፈሉ ገንዘቦች የውርስ
ንብረት ክፍል ይሆናሉ፡፡
2. ተቃራኒ ሁኔታ ሲኖር የውርስ ሀብት ክፍል አይሆኑም፡፡
ቊ 828፡፡ (2). ጡረታና ካሳ
በሞት ምክንያት ለሟቹ ዘመዶች ወይም ባል ወይ ሚስት የሚሰጡ ጡረታዎች ወይም ካሳዎች
የውርስ ሀብት ክፍል አይሆኑም
ቊ 829፡፡ ልዩ ልዩ ዐይነት ውርስ
1. የሟች ውርስ ያለ ኑዛዜ ወይም በኑዛዜ ሊሆን ይችላል፡፡
2. ውርሱም በከፊል ያለ ኑዛዜና በከፊል በኑዛዜ ሊሆን ይችላል
3. ሟቹ በኑዛዜ ያላደላደላቸው ሀብቶች ያለ ኑዛዜ ለሚወርሱት ይሰጣሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 2
ወራሽ ለመሆን የሚያስፈልግ ችሎታ
ቊ 830፡፡ ወራሽ ለመሆን የሚያስፈልጉ ምክንያቶች
ለሟቹ ሀብት ወራሽ መሆን ለመቻል በሕይወት ያለ መሆንና ለወራሽነት የማይገባ አለ መሆን
ነው፡፡
ቊ 831፡፡ የሟቹ ወራሾች በህይወት ስለመኖር
1. ሟቹ በሞተበት ቀን አንድ ሰው በሕይወቱ አለ የማለት ማስረጃ የሚደረገው ስለ ሰዎች በዚህ
ሕግ አንቀጽ በተመለከቱት ድንጋዎች መሠረት ነው፡፡
2. የዚሁ አንቀጽ ድንጋዎች ከአገር መጥፋት የሚያስከትሉትን ምክንያቶች ይወሰናሉ፡፡
3. ምትክ ሆኖ መውረስን የሚመለከቱ ደንቦች የተጠበቁ ናቸው፡፡
ቊ 832፡፡ ስለ አብሮ ሟቾች ሰዎች
ሁለት ወይም ብዙ ሰዎች የሞቱ ሲሆንና ከነዚሁ ሰዎች መካከል በኋላ የሞተው የትኛው እንደሆነ
ለማወቅ ያልተቻለ እንደሆነ ከአብሮ ሟቾች ሰዎች ሀብት ወራሽነት ምንም ሳያገኝ የነዚሁ ሰዎች
የያንዳንዳቸው ውርስ በመጨረሻ እንደሞተ ዐይነት ተቆጥሮ ይወሰናል፡፡
ቊ 833፡፡ ስለ ወራሹ መሞት
ለአንድ ውርስ ወራሽ የሆነ አንድ ሰው ውርስ ከተከፈተ በኋላ የሞተ እንደሆነ የወራሽነቱ መብቶች
ለርሱ ወራሾች ይተላለፋሉ፡፡
ቊ 834፡፡ ስለ ተፀነሰ ልጅ
የተፀነሰ ልጅ በዚህ ህግ ስለ ሶች በሚለው አንቀጽ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ወራሽ ሊሆን
ይችላል፡፡
ቊ 835፡፡ በሕግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች
በሕግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች በተለይ ለአንድ አገልግሎት የተመደቡ ንብረቶች
የኑዛዜን ስጦታ ለመቀበል ያላቸው ችሎታ በዚህ ሕግ በሕግ የሰውነት መብት ስለ ተሰጣቸው
ድርጅቶችና በተለይ ለአንድ አገልግሎት የተመደቡ ንብረቶች በሚለው አንቀጽ ተወስኗል፡፡
ቊ 836፡፡ ስለ ሕጋ ልግ ወይም ዲቃላ ወይም የጉዲፈቻ ልጅ
1. የሟቹ ወይም የወራሹ የሕግ ልጅ ወይም የዲቃላ ልጅ መሆን ወራሾችን ወይም
የያንዳንዳቸውንድርሻ ልክ ለመወሰን በሚመለከተው ምንም ዋጋ የለውም
2. እንዲሁም በዚህ ሕግ ስለ ስጋ ዝምድናና ስለ ጋብቻ ዝምድና በሚለው አንቀጽ በቁጥር 557
የተፃፉት ደንቦች እንደተጠበቁ ሆነው የጉዲፈቻ ልጆችም እንደ ሌሎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡
ቊ 837፡፡ ስለ ወራሾች ፆታ እድሜና ዜግነት
የወራሹ ፆታ ዕድሜና ዜግነት በወራሽነት መብቶቹ ውሳኔ ውስጥ ምንም ልዩነትን የሚያስከትሉ
አይደሉም፡፡
ቊ 838፡፡ ያልተገባ ስለ መሆን (1) ወንጀሎች ወይም ቅጣቶች
ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ የወራሽነትን መብት የሚያጣ
ሀ. ሟቹን ወይም የሟቹን ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጅ ወይም ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች
አንዱን ወይም የሟቹን ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል የተፈረደበት፡፡
ለ. ከነዚሁ ሰዎች መካከል አንደኛውን ለመግደል በመሞከር የተቀጣ
ሐ. በሐሰት በወንጀል ወይም በሐሰት ምስክርነት ይህ በሐሰት መወንጀል በሐሰት መመስከር ከነዚሁ
ሰዎች መካከል በአንደኛው ላይ የሞት ፍርድ ወይም ከዓስር ዓመት የበለጠ የጽኑ እስራት
ቅጣትን ለማስተካከል የሚያሰጋ ሁኖ የተቀጣ ማኛውም ሰው ነው፡፡
ቊ 839፡፡ (2) ስለ ማጣራት
ወራሽ የሆነው ሰው ወንጀሉን ወይም የወንጀሉን ሙከራ ያደረገው አውራሹ ከሞተ በኋላ ወደታች
በሚቆጠር ተወላጅ ወይም ወደ ላይ በሚቆጠር ወላጅ ወይም ባል ወይም ሚስት ላይ የሆነ እንደሆነ
በዚህ በላይ የተባለው የወራሽነት መብት ማጣት አይፈፀምበትም
ቊ 840፡፡ (3) ሌሎች ምክንያቶች
በተለይ ሟቹን ለመውረስ የማይገባ ነው ተብሎ
ሀ. የሟቹን ሰውነት ሁኔታ ምክንያት በማድረግ አውራሹ ከመሞቱ በፊት በአሉት በሦስት ወር
ውስጥ ኑዛዜ እንዲያደርግ እንዳይለውጥ ወይም እንዳይሽር የከለከለ
ለ. አስቦ ያለሟቹ ፈቃድ የሟቹን የመጨረሻ ኑዛዜ ያበላሸ እንይገኝ ያደረገ ያጠፋ ወይም ጉዳዩን
በማወቅ በሐሰት ኑዛዜ የተጠቀመ የወራሽነት መብት ያጣል፡፡
ቊ 841፡፡ (4) ይቅርታ
1. ከዚህ በፊት ባሉት ቁጥሮች የተመለከተው የመውረስ መብት ማጣት ሟቹ ግልጽ በሆነ ጽሑፍ
ወራሹን ይቅርታ ያደረገለት መሆኑን አስታውቆ እንደሆነ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
2. በኑዛዜ ስለሚደረግ ስጦታ ሲሆን ሟቹ በኑዛዜ ስጦታውን ያደረገው ወራሽ መሆን እዳይገባው
የሚያደርገው ነገር ከተፈፀመ በኋላና ጉዳዩንም ዐውቆት እንደሆነ እንዲሁ የመውረስ መብት
ማጣት አይኖርም፡፡
ክፍል ሁለት
ሳይናዘዝ የሞተ ሰው ውርስ
ቊ 842፡፡ የመጀመሪያ ዝምድና ደረጃ
1. የሟቹ ልጆች በመጀመሪያ ደረጃ የሟች ወራሾች ናቸው
2. ከውርስም እያንዳንዱ ትክክል ድርሻ ይቀበላሉ
3. የሟቹ ልጆች ወይም ከልጆቹ አንዱ ሞተው እንደ ሆነና ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ትተው
እንደሆነ በእነርሱ ምትክ ሆነው ይወርሳሉ፡፡
ቊ 843፡፡ ሁለተኛ የዝድና ደረጃ (1) መሠረቱ
ሟቹ ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ያልተወ እንደሆነ አባትና እናቱ ወራሾች ይሆናሉ
ቊ 844፡፡ (2) አፈፃፀሙ
1. የሟች አባትና እናት የውርሱን ንብረት እኩል በእኩል ይካፈላሉ፡፡
2. ከአባትና ከእናት አስቀድሞ የሞተ ቢኖር የሱን ፈንታ ልጆቹ ወይም ሌሎች ወደታች የሚቆጠሩ
ተወላጆቹ በሱ ተተክተው ይወርሳሉ፡፡
3. ከነዚህ መሥመሮች በአንዱ መሥመር ያለው ወራሽ ቢታጣ ውርሱ በሙሉ በሌላው መሥመር
ላው ወራሽ ይሰጣል፡፡
ቊ 845፡፡ ሦስተኛ ዝምድና ደረጃ (1) መሠረቱ
1. ሟቹ ወደ ታ የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም አባት ወይም እናት ወይም የነርሱ ወደታች
የሚቆጠሩ ተወላጆች የሌለው እንደሆነ አያቶች ወራሾች ይሆናሉ፡፡
2. የውርሱ እኩሌታው በአባት መስመር ላሉ አያቶች ወይም ወደ ታች ለሚቆጠሩ ተወላጆቻቸው
ይሆናል የቀረው የውርሱ እኩሌታ በእናት መሥመር ላሉ አያቶች ወይም ወደ ታች ለሚቆጠሩ
ተወላጆቻቸው ይሆናል፡፡
ቊ 846፡፡ (2). ለሌላ የዝምድና መሥመር ስለማስተላለፍ
1. በአባት ወይም በእናት የትውልድ መሥመር የዘር ተከታይ ሳይኖረው የሞተ አያት ድርሻው ለዚሁ
መሥመር ወራሾች ይተላለፋል፡፡
2. አንድ የትውልድ መስመር የዘር ተከታታይ ሳይኖራቸው የሞቱ አያቶች ማናቸውም የውርስ
ሀብት ሁሉ ለሌላው ወገን የዝምድና መስመር ወራሾች ይተላለፋል፡፡
ቊ 847፡፡ አራተኛ የዝምድና ደረጃ(1) መሠረቱ
የሦስተኛ ደረጃ ዘመድ ወራሾችየሌሎ እንደሆነ የሟቹ ቅድመአያቶች ወራሾች ይሆናሉ፡፡
ቊ 848፡፡ አፈፃፀም
1. የውርስ እኩሌታ የአባት መሥመር ለሆኑ ቅድመ አያቶች ወይም ለተወላጆቻው እኩሌታው
የእናት መሥመር ለሆኑ ቅድመ አያቶች ወይም ለተወላጆቻቸው ይሰጣል፡፡
2. በላይኛው ኀይለ ቃል የተነገረው ውሳኔ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሟቹ በኋላ በሕይወት የሚገኘው
የዚሁ ምትክ ለመሆን አግባ ያለው ቅድመ አያት ወይም የዚሁ ተወላጅ የውርሱን ሀብት እኩል
ይካፈላል፡፡
ቊ 849፡፡ የአባትን ለአባት ወገን የእናትን ለእናት ወገን መስጠት ደንብ ስለመሆኑ (1) መሠረቱ
1. ሟቹ ሳይናዘዝ በሞት ጊዜ ከዚህ በላይ ባሉት ቁጥሮች በተጻፈው ደንብ አፈፃፀም ለሟቹ
በውርስ ወይም በስጦታ ከአባቱ መስመር ወገን የመጣለትን የማይንቀሳቀስ ንብረት የእናት
መስመር ወገን ለሆኑ ወራሾች በርስትነት መስጠት አይቻልም፡፡
2. እንደዚሁም ለሟቹ በውርስ ወይም በስጦታ ከእናቱ መስመር ወገን የመጣለትን የማይንቀሳቀስ
ንብረት የአባት ወገን ለሆኑ ወራሾች በርስትነት መስጠት አይችልም፡፡
3. ከአባት ወገን አያት በስጦታ ወይም በውርስ የተገኘው የማይንቀሳቀስ ንብረት የእናት ወገን ለሆነ
ተወላጅ እንዳይተላለፍ እንዲሁም ከእናት ወገን አያት የተገኘ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለአባት
ወገን እንዳይተላለፍ ለማድረግ ከዚህ በላይ ባሉት ሁለት ኀይለ ቃሎች የተነገረው ደንብ
ለሁለተኛ ደረጃ ትውልድም ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ቊ 850፡፡ (2) አፈፃፀም
1. ከዚህ በላይ ባለው ቁጥር ደንብ ምክንያት በውርስ ለአንድ ወራሽ ከአንድ ውርስ የመጣለትን
ድርሻ ሊሰጠው የማይችል በሆነ ጊዜ በርስትነት ሊሰጠው ከማይቻለው የማይንቀሳቀስ ላይ
የሪም መብት ብቻ ይሰጠዋል፡፡
2. በዚህም የተነሳ ከመብቶቹ ለተቀነሱበት ወራሽ የሚከፈለው ምንም ኪሳራ የለም፡፡
ቊ 851፡፡ (3) ስለ መወሰን
በአባት መሥመር ወገን ወይም በእናት መሥመር ወገን ወራሾች ከሌሉ ከዚህ በላይ በተፃፉት በሁለቱ
ቁጥሮች የተነገሩት ድንጋዎች ተፈፃሚዎች አይሆኑም፡፡
ቊ 852፡፡ ለመንግስት ስለማስተላለፍ
ዘመዶች የሌሉ እንደሆነ የሟቹ ወራሽነት ለመንግስት ይተላለፋል፡፡
ቊ 853፡፡ ምትክነት(1) መሠረቱ
1. ምትክ ባለበት ጊዜ ክፍያ በትውልድ አወራረድ ይፈጸማል፡፡
2. ተተኪ የሆኑት ልጆች ምትክ በሆኑበት ሰው እግር ገብተው በወራሽነት መብት ይሰሩበታል፡፡
3. አነዚህም ሲሞቱ በዚሁ ሐሳብ መሠረት ልጆቻቸው ምትክ ሁነው ይገባሉ፡፡
ቊ 854፡፡ (2) ወራሽነትን የመተው ሁኔታ
1. ወራሽ ሁኖ ወራሽነትን አልፈልግም ያለ እንደ ሆነ የእርሱ ተተኪ ሊገባበት አይችልም፡፡
2. ነገር ግን ውርሱን አልፈልገውም በተባለው ሰው ምትክ ለመግባት ይችላል፡፡
ቊ 855፡፡ ለመውረስ የማይገባ ስለ መሆን
ሟችን መውረስ የማይገባው ሰው ልጆች ወይም ሌሎች ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች በእሱ
ተተኪ ሆነው የሟች ወራሽ መሆን አይችሉም፡፡
ቊ 856፡፡ ህጋዊ የሆነ የዝምድና መተሳሰር አስፈላጊነት
ምትክ ለመሆን የሚፈልገው ሰው በሕጉ መሠረት ከሟቹ ጋር የዝምድና መተሳሰርየሌለው እንደሆነ
ምትክ ለመሆን አይችልም፡፡
ክፍል 3
ስለ ኑዛዜ
ንዑስ ክፍል 1
የኑዛዜ ዋጋ መኖር ሁኔታዎች
(ሀ) የሥረ ነገር ሁኔታዎች
ቊ 857፡፡ ኑዛዜው ጥብቅ የሆነ የግል ጠባይ ያለው ስለመሆኑ
1. ኑዛዜው የሟቹ ጥብቅ የሆነ ራሱ የሚፈጽመው ሥራ ነው፡፡
2. አንድ ሰው ለሌላ ሰው በስሙ አንድ ኑዛዜ እንዲያደርግ እንዲለወጥ ወይም እንዲሻር ሥልጣን
ሊሰጠው አይችልም፡፡
3. አንድ ሰው ላንድ ሶስተኛ ሰው ወራሹን እንዴት እንደሚወስን ወይም ለማን እንደሚተላለፍ
እንዲፈጽም ሊያደርግ አይችልም፡፡
ቊ 858፡፡ የጋራ ኑዛዜ ስለ መከልከል
ብዙ ሰዎች አንድ ብቻ በሆነ ጽሁፍ የተናዘዙ እንደሆነ ኑዛዜው ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 859፡፡ ኑዛዜን ስለሚመለከት ቃል መግባት
1. ኑዛዜን ለማድረግ ለመለወጥ ወይም ለመሻር ባንዱ ሰው የተደረገ ቃል መግባት በሕግ በኩል
ውጤት የለውም፡፡
2. ተቃራኒ የሆነ ማናቸውም የውል ቃል ቢኖርም እንኳ ምን ጊዜም ቢሆን ተናዡ ኑዛዜውን
ሊለውጥ ወይም ሊሽር ይችላ፡፡
ቊ 860፡፡ ችሎታ (1) አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ ኑዛዜ
አካለ መጠን ስላላደረሰ ልጅ ኑዛዜ ጉዳይ በዚህ ሕግ ስለ ሰዎች ችሎታ በሚለው አንቀጽ ውስጥ
ተመልክቷል፡፡
ቊ 861፡፡ (2) በፍርድ የተከለከለ ሰው
በፍርድ የተከለከለ ሰው ኑዛዜ ለማድረግ የሚችልበት ሁኔታ በዚህ ሕግ ስለ ሰዎች ችሎታ በሚለው
አንቀጽ በ-- ቁጥር ተመልክቷል፡፡
ቊ 862፡፡ (3) የዳኞች ስልጣን
1. ስለሆነም ዳኞች ከእንደዚህ ያለው ኑዛዜ ውስጥ የተመለከቱትን የኑዛዜ ቃሎች ተናዛዡ በጤናው
ሁኔታ ምክንያት ያላደረጋቸው የመሰላቸው እንደ ሆነ በሙሉ ወይም በከፊል ውጤት
እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡
2. ነገር ግን ዋጋው ከአምስት ሺህ በኢትዮጵያ ብር በላይ የሆነውን የኑዛዜ ስጦታ በእንደዚህ ያለው
ሁኔታ ሊያጸድቁት አይችሉም፡፡
3. እንዲሁም ደግሞ በፍርድ የተከለከለው ሰው ያለ ኑዛዜ ወራሽ የሆኑት ሰዎች እጅግ ቢያንስ
ከውርሱ ሀብት ሦስቱን ሩብ ማግኘት አለባቸው፡፡
ቊ 863፡፡ (4) የአእምሮ መጉደል
ከዚህ እንደሚከተሉት ካልሆነ በቀር ተናዛዡ አእምሮ ጎደሎ ነበር በማለት ምክንያት ኑዛዜው ሊሻር
አይችልም፡፡ ይኸውም ተናዛዡ ኑዛዜውን ባደረገበት ጊዜ የታወቀ ዕብድ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 864፡፡ (5) በህግ የተከለከለ
በሕግ የተከለከለው ሰው ኑዛዜ ማድረግን ስለሚመለከት ጉዳይ ሙሉ ችሎታ አለው፡፡
ቊ 865፡፡ የማይቻል አፈፃፀም
1. አንድ የኑዛዜ ቃል በሚበቃ አኳኋን ተጠቃሚውን ወይም ጉዳዩን ካላመለከተ ፈራሽ ነው፡፡
2. አፈፃፀሙም የማይቻል እንደ ሆነ እንደዚሁ ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 866፡፡ ሕገ ወጥ የሆኑ የኑዛዜ ቃላት
አንድ የኑዛዜ ቃል ለሕግ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ እንደ ሆነ ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 867፡፡ ኀይል
1. በአንድ ኑዛዜ ውስጥ የተፃፈውን ቃል ሟቹ ያደረገው በተገዳጅ እንደሆነ ፈራሽ ነው፡፡
2. እንዲህ ሲሆን በኃይል የተደረጉ ውሎች የሚመለከቱ የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች በተመሳሳይነት
ተፈፃሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 868፡፡ የመንፈስ መጫን(1) መሠረቱ
በአንድ ኑዛዜ ውስጥ ያለ ቃል በዚህ የኑዛዜ ቃል ተጠቃሚ የሆነው ወይም ማናቸውም ሌላ ሰው
በተናዛዡ ላይ በአለው ከመጠን በላይ የሆነ የመንፈስ መጫንን ምክንያት በማድረግ ፈራሽ ሊሆን
አይችልም፡፡
ቊ 869፡፡ (2) ለአስተዳዳሪ ወይም ለሞግዚት ጥቅም የሚደረግ የኑዛዜ ቃል
1. ስለሆነም ለአስተዳዳሪው ወይም ለሞግዚቱ ጥቅም ሟቹ ያደረገውን የኑዛዜ ቃል ዳኞች
እንዲቀንሱ ወይም እንዲሽሩ ተፈቅዷል፡፡
2. ከዚህ በላይ ያው ኀይለ ቃል ደንብ ሟቹ ከሃያ ዓመት ዕድሜ በፊት የሞተ ካሆነ በቀር ተፈፃሚ
አይሆንም፡፡
3. በኑዛዜው ቃል ተጠቃሚ የሆነው ወደ ላይ የሚቆጠር የሟቹ ወላጅ የሆነ እንደሆነ ይህ ደንብ
ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
ቊ 870፡፡ (3) ሐኪሞች ወይም የቤተክርስቲያን ሰው
1. ዳኞች ሟቹ ከመሞቱ አስቀድሞ ባሉት ስድስት ወር ውስጥ ሕክምና ወይም ርዳታ ላደረጉለት
ሐኪም ቀዳጅ አስታማሚ በሽተኛ ጠባቂ ጥቅም ወይም በሞያ ሥራው የሕክምና ርዳታና
የመንፈስ ርዳታ ላደረገ ለሌላ ሰው ጥቅም ያደረገውን የኑዛዜ ቃል ለመቀነስ ወይም ለመሻር
ይችላሉ፡፡
2. ከዚህ በላይ ባለው ኀይለቃል ሐኮም ማለት ማናቸውም ሰው ሕገ ወጥ በሆነ ሁኔታም ሆነ ለሟቹ
አንድ የሕክምና ርዳታ ያደረገ ወይም ያዘዘ ማለት ነው፡፡
3. በኑዛዜው ቃል ተጠቃሚ የሆነው ሰው የሟቹ የሥጋ ዘመድ ወይም የጋብቻ ዘመድ ወይም ባል
ወይም ሚስት የሆኑ እንደ ሆነ የዚህ ቁጥር ደንብ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
ቊ 871፡፡ (4) ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ወይም የኑዛዜ ምስክሮች
ዳኞች ሟቹ ለኑዛዜው አደራረግ ተሳታፊ ለሆነ ለአንድ ለማዋዋል ሥልጣን ለተሰጠው ሰው ፍርድ
መዝገብ ቤት ሹም ለ 1 ምስክር ወይም አስተርጓሚ ያደረገውን የኑዛዜ ቃል ለመቀነስ ወይም ለመሻር
ይችላሉ፡፡
ቊ 872፡፡ (5) የተናዛዡ ባል ወይም ሚስት
ዳኞች ሟቹ በፊት ካደረገው ጋብቻ የተገኙ ተወላጆች ያሉት እንደሆነ ለኋለኛው ባል ወይም ሚስት
ጥቅም ያደረገውን የኑዛዜ ቃል ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ፡፡
ቊ 873፡፡ (6) ስለ ሰዎች ጣልጋ ገብነት
ከዚህ በፊት ባሉት ቁጥሮች ውስጥ ከተመለከቱት ሰዎች ለአንዱ ተወላጅ ወይም ወላጅ ወይም ባል
ወይም ሚስት ጥቅም የተደረገ የኑዛዜን ቃል ዳኞች ሊቀንሱት ወይም ሊሽሩት ይችላሉ፡፡
ቊ 874፡፡ (7) ለመቀነስ ወይም ለመሻር ስለሚደረግ ጥያቄ
1. የኑዛዜው ቃል ሟቹ ለባል ወይም ለሚስት ጥቅም ያደረገው የሆነ እንደሆነ የኑዛዜው ቃል
እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የማድረጉን ጥያቄ የሟቹ ተወላጆች ካልሆኑ በቀር ለዳኞች ሌሎች
ሊያቀርቡት አይቻልም፡፡
2. በሌላው ጊዜ ግን ከሌሎች ማናቸውም ወራሾች በቀር ወደ ላይ የሚቆጠሩ የሟቹ ወላጆች
ወይም ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት ለዳኞች ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
3. በኑዛዜው ቃል ተጠቃሚ የሆነው ሰው ኑዛዜው እንዲፈፀምለት ጥያቄውን ካቀረበበት ቀን
አንስቶ በ 3 ወር ውስጥ የኑዛዜው ቃል እንዲቀንስ ወይም እንዲሻር የሚለውን ጥያቄ ካላቀረበ
ተቀባይነት አያገኝም፡፡
ቊ 875፡፡ (8) ዳኞች ምክንያቱን ማስታወቅ ያለባቸው ስለ መሆኑ
ሟቹ የተናዘዘውን ቃል ማፍረስ ወይም መቀነስ ከልቡና ፍርድ ከርትዕ ጋር የተስማማ ነው
የሚልበትን ምክንያ ዳኞች በፍርዳቸው ውስጥ መግለጽ ይገባቸዋል፡፡
ቊ 876፡፡ ተንኮል
በአንድ ኑዛዜ ውስጥ ያሉ ቃላት ተናዛዡ በተንኮል ምክንያት ያደረጋቸው ናቸው በማለት ሊሻሩ
አይቻሉም፡፡
ቊ 877፡፡ ስሕተት
1. ስሕተት በሚገኝበት ጊዜ በስሕተት ምክንያት ውሎችን ስለ መሻር የተመለከቱት የዚህ ሕግ
ድንጋጌዎች በተመሳሳይነት ተፈፃሚዎች ይሆናሉ፡፡
2. ስለ ሆነም በአንድ ኑዛዜ ውስጥ ያለ ቃል በተናዛዡ ስሕተት የተደረገ ነው ተብሎ ሊሻር
የሚችለው ይህ የተናዛዡ ፈቃድ እንዲያዘነብል ያደረገው ስሕተት በኑዛዜው አነጋገር ወይም
ኑዛዜውን በሚመለከት በአንድ የተፃፈ ሰነድ ግልጽ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
ቊ 878፡፡ የአንድ የኑዛዜ መሻር የሚያስከትለው ነገር
በእርግጠኛ አኳኋን በተናዛዡ መንፈስ ውስጥ ፈራሽ በሚሆነው ቃል አፈፃፀምና በሌሎቹ ቃላት
አፈፃፀም መካከል አስፈላጊ የሚያስተሳስር ነገር ያለ መሆኑ የታወቀ ካልሆነ በቀር በአንድ ኑዛዜ
ውስጥ ያለ ቃል መሻር በዚሁ ያሉትን ሌሎች ቃላት መሻር አያስከትልም፡፡
ቊ 879፡፡ ዋጋ የሌላቸው የውለታ ቃላትና ግዴታዎች
1. ተናዛዡ አንድ የኑዛዜ ስጦታን በአንድ ውለታ የሰጠ ወይም ከአንድ ግዴታ ጋር የሰጠ እንደ ሆነ
ይህ ውለታ ወይም ይህ ግዴታ የማይቻል ወይም ለሕግ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ
እንደሆነ እንዳልተፃፈ ይቆጠራል፡፡
2. ይህ ሲሆን ምንም የውለታ ወይም የግዴታው መፈፀም ተናዛዡ ኑዛዜውን ያደረገበት ዋና
ምክንያት ቢሆንም እንኳ የኑዛዜው ስጦታ ፈራሽ አይሆንም፡፡
(ለ). የኑዛዜዎች ፎርምና ማስረጃ
ቊ 880፡፡ ልዩ ልዩ ዐይነት ኑዛዜዎች
ሦስት ዐይነት የኑዛዜ ፎርሞች አሉ እነዚሁም
ሀ. በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ
ለ. በተናዛዡ ጽሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ
ሐ. በቃል የሚደረግ ኑዛዜ
ቊ 881፡፡ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ(1) ፎርም
1. በግልጽ የሚደረገው ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ማናቸውም ሌላ ሰው ወይም ተናዛዡ ራሱ
የሚጽፈው ነው፡፡
2. ኑዛዜው(ፎርማሊቲ መፈፀሙን የተፃፈበትን ቀን የሚያመለክት ካልሆነ በቀር ፈራሽ ነው፡፡
3. ተናዛዡ ና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራ ጣት ምልክታቸውን
ካላደረጉበት በቀር ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 882፡፡ (2) የምስክሮቹ ብዛት
በግልጽ ለሚደረገው ኑዛዜ ከምስክሮቹ መካከል አንዱ ዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን
የተሰጠው ሰው ሆኖ ኑዛዜውም የተደረገው ይህ ዳኛ ወይም ይህ ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው
ሥራቸውን በሚያካሄዱበት ክፍል ውስጥ የሆነ እንደ ሆነ ለኑዛዜው ዋጋ ለማግኘት ሁለት ምስክሮች
ብቻ በቂ ናቸው፡፡
ቊ 883፡፡ (3) የምስክሮች ችሎት
1. በግልጽ የሚደረገው ኑዛዜ ምስክሮች አካለመጠንን ያደረሱና በፍርድ ወይም በሕግ ያልተከለከሉ
መሆን አለባቸው፡፡
2. ምስክሮቹ ኑዛዜው የተፃፈበትን ቋንቋ ለማወቅና የተፀፈውን ለመስማት ወይም ለማንበብ
ራሳቸው ችሎታ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3. እነዚህ ትእዛዞች ያልተፈጸሙ እንደ ሆነ ኑዛዜ ተናዛዡ ራሱ በሙሉ ካልጸፈው ፈራሽ ይሆናል፡፡
ቊ 884፡፡ በተናዛዡ ጽሑፍ የሚደረግ ኑዛዜ(1) ፎርም
1. በተናዛዡ ጽሁፍ የሚደረገው ኑዛዜ ተናዛዡ ራሱ በሙሉ ካልፃፈው ፈራሽ ይሆናል፡፡
2. ኑዛዜ መሆኑ በግልጽ ካተመለከተ በቀር ፈራሽ ይሆናል፡፡
3. ኑዛዜው የተደረገባቸው ወረቀቶች እያንዳንዳቸው ተናዛዡ ካልፈረመባቸውና ቀን ካጸፈባቸው
ፈራሾች ይሆናሉ፡፡
ቊ 885፡፡ (2) በመኪና የተፃፈ ኑዛዜ
ተናዛዡ ያደረገውን ኑዛዜ ራሱ በመኪና ጽፎት እንደ ሆነ በያንዳንዱ ቅጠል ላይ ይህን ሁኔታ በእጁ
ጽሕፈት ካላመለከተው በቀር ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 886፡፡ (3) የኑዛዜውን ጽሑፍ ለማወቅ ችሎታ የሌለው ተናዛዥ
በተናዛዡ የእጅ ጽሑፍ የሆነውን ኑዛዜ ተናዛዡ ያልተማረ መሐይምን በመሆኑ ወይም ኑዛዜው
የተፃፈበትን ቋንቋ ባለማወቁ ፍቺውን በማያውቃቸው ፊደሎች የጻፈ እንደሆነፈራሽ ይሆናል፡፡
ቊ 887፡፡ ኑዛዜው የተደረገበት ቀን
1. በግልጽ ወይም በተናዛዡ ጽሑፍ የሚደረገው ኑዛዜ ቀኑን ወሩንና ዓመተ ምሕረቱን ወይም ይህን
የመሳሰሉ መግለጫዎች ከሌሉበት ፈራሽ ይሆናል፡፡
2. ስለ ሆነም በሐሰት የተፃፈበት ምክንያት በዝንጋታ የተደረገ መሆኑና ኑዛዜው የተደረገበት
እውነተኛ ቀን በኑዛዜው ላይ በተመለከተው ጽሑፍ ወይም ከሟቹ በሚገኙት ሌሎች የጽሁፍ
ሰነዶች ረዳትነት በትክክል ሊረጋገጥ የተቻለ እንደ ሆነ በኑዛዜ ጽሑፍ ላይ የተመለከተው የቀን
መሳሳት የኑዛዜውን መፍረስ አያስከትልም፡፡
ቊ 888፡፡ ማስረጃ በመጥቀስ የሚደረግ ኑዛዜ
ግልጽ የሆነ ኑዛዜና በተናዛዡ ጽሁፍ የተደረገ ኑዛዜ የኑዛዜውን ቃል ለመረዳት ሟቹ ያልፃፈውን
ያልፈረመውን ሌላ ጽሑፍ መጥቀስ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 889፡፡ መፋቅ መሰረዝና መደለዝ
1. ግልጽ የሆነ ኑዛዜና በተናዛዡ ጽሑፍ የተደረገ ኑዛዜ የተናዛዡ ፈቃድ ለመለወጥ የሚችል ፍቀት
ስርዝ ወይም ድልዝ ያለባቸው ሲሆን ፈራሾች ናቸው፡፡
2. ስለሆነም የተናዛዡን ሃሳብና ማኛዎችንም ሌሎች አካባቢ ነገሮችን በመገመት ከቀረው የኑዛዜ
ቃል የተለየ ቃል ለመሆን የቻለ እንደሆነ ይህን ፍቀትስርዝ ወይም ድልዝ የያዘ የኑዛዜ ቃል ብቻ
ፈራሽ ይሆናል፡፡
3. በተናዛዥ ጽሑፍ የተደረገ ኑዛዜ ሲሆን ፍቀቱን ስርዙን ወይም ድልዙን ተናዛዡ ግልጽ በሆነ
ዐይነት በፊርማው ያጸደቃቸው መሆናቸው ከታወቀ እንዲሁም የግልጽ ኑዛዜ ሲሆን ምስክሮቹ
በፊርማቸው ያጸደቁት ከሆኑ ኑዛዜው ፈራሽነትን አያስከትልም፡፡
ቊ 890፡፡ ተጨማሪ ነገሮች
1. አንድ ግልጽ የሆነ ኑዛዜ በጽሑፍ ኀዳግ ላይ ወይም በመስመሮቹ መካከል ወይም ከምስክሮቹ
ፊርማ በኋላ ተጨማሪ ነገሮች ያሉበት ሲሆን ከዚህ በላይ ባለው ቁጥር የተመለከቱት ደንቦች
ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
2. በተናዛዡ ጽሑፍ የሆነ ኑዛዜ በእንደዚህ ያለ ተጨማሪ ነገሮች ፈራሽ አይሆንም፡፡
ቊ 891፡፡ ኑዛዜውን ስለ ማስቀመጥ
1. ግልጽ ወይም በተናዛዡ ጽሁፍ የተደረገ ኑዛዜ በአንድ ሰው ዘንድ በተለይም ለማዋዋል ሥልጣን
በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም በአንድ የፍርድ መዝገብ ቤት ዘንድ ሊቀመጥ ይችላል፡፡
2. ለማዋዋል ሥልጣን የተሰጠው ሰው ወይም የፍርድ መዝገብ ቤት ኑዛዜው የተቀመጠላቸውን
ሰዎች በየአንዳንዱ ሰው ስም በፊደል ተራ የያዘ መዝገብ ይኖራል፡፡
3. ይኸው መዝገብ ኑዛዜው የተሰጠበትን ቀን የሚያመለክት ይሆናል፡፡
ቊ 892፡፡ የቃል ኑዛዜ(1) ፎርም
1. የቃል ኑዛዜ ማት አንድ ሰው የሞቱ መቃብር ተሰምቶት የመጨረሻ ፈቃድ ቃሎቹን ለሁለት
ምስክሮች የሰጠበት ነው፡፡
2. የቃል ኑዛዜ ምስክሮች አካ መጠን ያደረሱና በፍርድ ወይም በሕግ ያልተከለከሉ መሆን
አለባቸው፡፡
ቊ 893፡፡ (2) በኑዛዜው ውስጥ የሚገኘው ቃል
ተናዛዡ በተለይ በአንድ የቃል ኑዛዜ፡-
ሀ. ለቀብሩ ስነ ስርዓት የሚመለከቱትን ትዕዛዞች ለመስጠት፣
ለ. እያንዳንዱ ውርስ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር ለመብለጥ የማይችል ግምት ያለው የኑዛዜ
ስጦታ ለማድረግ
ሐ. አካለመጠንን ላላደረሱ ልጆች አስተዳዳሪን ወይም ሞግዚትን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን
ለመስጠት ይችላል፡፡
ቊ 894፡፡ (3) ቅጣት
1. በቃል ኑዛዜ ውስጥ ማናቸውንም ሌላ የኑዛዜ ቃል ፈራሽ ነው፡፡
2. በአንድ የቃል ኑዛዜ ውስጥ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር በላይ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገ እን ሆነ
ከ 500 በላይ ያለው ስጦታ ተቀናሽ ይሆናል፡፡
895፡፡ ብዙ ኑዛዜዎች
1. የአንድ ሰው ያደረጋቸው የኑዛዜ ውሳኔዎች በአንድ ወይም በብዙ የኑዛዜ ጽሑፎች ውስጥ ሊኖር
ይችላሉ፡፡
2. አብሮ ተፈፃሚዎች ለመሆን በሚችሉበት መጠን ልዩ የሆኑ ኑዛዜዎች አብረው ተፈፃሚዎች
ይሆናሉ፡፡
3. የሁለት ኑዛዜዎችም ቃላት ሁለቱም ሊፈፀሙ ያልተቻለ እንደ ሆነ በኋላ በተደረገው ኑዛዜ
ውስጥ ላለው ቃል ምርጫ ይሰጠዋል፡፡
ቊ 896፡፡ የኑዛዜው አስረጂ(1) ማስረዳት ያለበት ሰው
በኑዛዜው የሰፈረውን ቃልና ኑዛዜው መኖሩን ማስረዳት ያለበት በዚሁ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚለው
ሰው ነው፡፡
ቊ 897፡፡ (2) የአስረጂው አይነት
1. በግልጽ ወይም በተናዛዡ ጽሑፍ የተደረገ የኑዛዜ መኖር የሚረጋገጠው የኑዛዜውን ጽሑፍ
ዋናውን በማቅረብ ወይም ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም በፍርድ መዝገብ
ቤት ሹም ትክክለኛ ሆኖ በተመሰከረ አንድ ግልባጭ በማቅረብ ነው፡፡
2. ኑዛዜዎቹን ለማስፈፀም በማናቸውም ሌላ መንገድ ለማስረዳት አይቻልም፡፡
3. በጥፋት ወይም በቸልተኝነት ኑዛዜው እንዲጠፋ ካደረገው ሰው የጉዳት ኪሳራ ለማግኘት ሲሆን
በማናቸውም ዐይነት መንገድ ኑዛዜዎቹን ለማስረዳት ይቻላል፡፡
(ሐ) ስለ ኑዛዜዎች መሻርና ውድቅ መሆን
ቊ 898፡፡ ግልጽ የሆነ መሻር
1. ተናዛዡ ኑዛዜዎቹ ዋጋ ያላቸው እንዲሆኑ በሚያስፈልገው ፎርም ዐይነት ግልጽ አድርጎ
በማስታወቅ ኑዛዜውን የሻረ እንደሆነ ኑዛዜው በጠቅላላው አኳኋን የሚሻር ይሆናል፡፡
2. ተናዛዡ እንዲሁ በሆነ ፎርም ከአንድ የኑዛዜ የውል ቃል ጋራአብሮ ሊፈጽም የማይቻል አንድ
ውሳኔ ያደረገ እንደሆነ ኑዛዜው በከፊል የሚሻር ይሆናል፡፡
ቊ 899፡፡ ማጥፋት ወይም መሰረዝ
1. እንደዚሁ ተናዛዡ ኑዛዜውን ለመሻር ወይም ለመለወጥ ያለውን ሐሳብ በቂ አድርጎ በመግለጽ
ዐይነት ኑዛዜውን ራሱን በማጥፋት ወይም በመቅደድ ወይም የኑዛዜውን አነጋገር በመሰረዝ
ኑዛዜውን ወይም በኑዛዜው ውስጥ የተመለከተውን አንድ ቃል ለመሻር ይችላል፡፡
2. ተቃራኒ አስረጂ ከሌለ በቀር ተናዛዡ ከዚህ በላይ ከተመለከቱት ተግባሮች አንዱን የፈፀመ እንደ
ሆነ ኑዛዜውን ለመሻር ፍላጎት ያለው መሆኑ ይገመታል፡፡
3. ተቃራኒ አስረጂ ከሌለ በቀር የኑዛዜው መጥፋት ወይም መሰረዝ የተናዛዡ ተግባር ነው ተብሎ
ይገመታል፡፡
ቊ 900፡፡ በኑዛዜ የተሰጠን ነገር ለሌላ ስለ ማስተላለፍ
1. በኑዛዜ የተሰጠን ነገር በሙሉ ወይም ከከፊል ተናዛዡ ፈቅዶ ለሌላ ማስተላለፍ የተደረገውን
የኑዛዜ ስጦታ ፈራሽ ያደርገዋል፡፡
2. ይህ የተላለፈው ነገር ተመልሶ ከባለቤቱ እጅ ቢገባም እንኳ ኑዛዜው በከፊል እንደ ተሻረ ይቀራል፡፡
ቊ 901፡፡ የመሻር ውጤት
1. ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር ያንዱ ኑዛዜ መሻር አስቀድሞ ተደርጎ የነበረውን የኑዛዜውን ቃል
አያጸድቀውም፡፡
2. በተሸሩበት የኑዛዜዎች ቃላት ምትክ የገቡት አዳዲስ ቃላት ኑዛዜ በተደረገለት ሰው ችሎታ
ማጣት ወይም የኑዛዜውን ስጦታ አልፈልግም በማለት ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት
ፍፃሜ ለማግኘት ባይችሉም እንኳ የተሸሩት የኑዛዜ ቃላትተፈፃሚነት ለማግኘት
አይገባቸውም፡፡
ቊ 902፡፡ በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ውድቅ መሆን
በቃል የተደረገ ኑዛዜ ከተደረገበት ከሦስት ወር በኋላ ተናዛዡ በዚህ ጊዜ በሕይወት ያለ ከሆነ ውድቅ
ነው፡፡
ቊ 903፡፡ በተናዛዡ የሚደረግ ኑዛዜ ውድቅ መሆን
በተናዛዡ ጽሑፍ የተደረገ ኑዛዜ ፈራሽ የሚሆነው ኑዛዜው በተደረገ በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ
ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ወይም እፍርድ መዝገብ ቤት ዘንድ ያልተቀመጠ እንደ ሆነ ነው፡፡
ቊ 904፡፡ ስለ ልጅ መወለድ (1)መሠረቱ
1. በአንድ ኑዛዜ ውስጥ የተመለከቱ ጠቅላላ ወይም ልዩ ስጦታዎች ምንም ተቃራኒ ቃል ቢኖር እንኳ
ከኑዛዜው በኋላ ተናዛዡ አንድ ልጅ ቢወልድና ይህ ልጅ ውርሱን ለመቀበል የፈቀደ እንደሆነ
ስጦታዎቹ ፈራሾች ይሆናሉ፡፡
2. ከኑዛዜው ቀን በኋላ የተናዛዡ ወደ ታች የሚቆጠር ተወላጅ የተወለደ ሆነ በምትክነት
ለወራሽነት ቀርቦ ይኸንኑ ውርስ የፈቀደ እንደሆነ ከዚህ በላይ እንደ ተፃፈው ዐይነት ይፈፀማል፡፡
ቊ 905፡፡ (2) ልዩ አስተያየት
1. ስለሆነም ከዚህ በፊት ባለው ቁጥር እንደ ተጠቀሰው ተናዛዡ ጉዳዩን ቢያውቅ ኑሮ ስጦታውን
አያስቀርም ነበር ተብሎ የሚገመት የሆነ እንደሆነ ዳኞች በኑዛዜ የተሰጡትን ኑዛዜ ስጦታዎች
በሙሉ ወይም በከፊል እንዳሉ እንዲጸኑ ለማድረግ ይችላሉ፡፡
2. እንዲሁም ተናዛዡ የወለደው ልጅ ወይም ወደ ታች የሚቆጠር ተወላጅ እጅግ ቢያንስ የውርሱ
ሀብት ሦስት እሩብ በማናቸውም ምክንያት ማግኘት አለበት፡፡
ቊ 906፡፡ ለባል ወይም ለሚስት ተብሎ የሚደረግ የኑዛዜ ስጦታ
ሟች ለባል ወይም ለሚስት ብሎ በኑዛዜው ውስጥ ያደረገው ቃል ውድቅ የሚሆነው ሟቹ ከባል
ወይም ከሚስት ጋር ያደረገው ጋብቻ በመሞት ሳይሆን በሌላ ምክንያት የፈረሰ የሆነ እንደ ሆነ ነው፡፡
ቊ 907፡፡ የኑዛዜ ስጦታ ውድቅ መሆን (1) መሰረቱ
ለአንድ ሰው የተደረገ የኑዛዜ ስጦታ ውድቅ የሚሆነው ኑዛዜ የተደረገለት ሰው ከተናዛዡ በፊት
የሞተ ወይም የተደረገለት የኑዛዜ ስጦታ ለመቀበል ያልቻለ ወይም ያልፈቀደ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 908፡፡ (2) ምትክነት
የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ከተናዛዡ በፊት የሞተ እንደሆነ ምትክ ሊኖረው የሚችለው
(ሀ) የኑዛዜው ስጦታ የሟቹን ጠቅላላ ሀብት የያዘ ሲሆን
(ለ) ልዩ ስጦታ በሆነ ጊዜ ተቀባዩ ባለመኖሩ ሀብቱ ለመንግስት የሚተላለፍ ሲሆን ነው፡፡
ንዑስ ክፍል 2
በኑዛዜዎች የሰፈረ ቃልና የኑዛዜ ትርጓሜ
ቊ 909፡፡ ልዩ ልዩ አይነት የኑዛዜ ቃላት
ተናዛዡ በኑዛዜው ውስጥ፡-
(ሀ) አንድ ወይም ብዙ የጠቅላላ ሀብት ወራሾች ማድረግ
(ለ) ልዩ የኑዛዜ ስጦታ ማድረግ
(ሐ) አንድ ወይም ብዙ የሆኑ ወራሾችን ከወራሽነት መንቀል ወይም አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት
ወይም የአደራ ንብረት ጠባቂ ድርጅት ማቆም
(መ) የቀብሩን ስነ ስርዓት የሚመለከቱ ትእዛዞችን መናገር መጻፍ
(ሠ) ከሞተ በኋላ ይህ ሕግ ወይም ልዩ የሆኑ ሕጎች ሕጋዊ ውጤት ይኖራቸዋል የሚለውን የሐሳቡን
ማስታወቂያዎች ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 910፡፡ ትርጓሜ
1. ጥርጣሬ በሚፈጥርበት ጊዜ በራሱ በኑዛዜው ውስጥ ወይም በሌሎች አካባቢ ነገሮች እንደ
ተመለከተው የተናዛዡ ፈቃድ ነው ተብሎ በተገመተበት መሠረት ኑዛዜው መተርም አለበት፡፡
2. ስለሆነም የኑዛዜው ቃላት ግልጽ የሆነ እንደሆነ የተናዛዡ እውነተኛ ትክክለኛ ፈቃድ የትኛው
ነው ብሎ ትርጓሜ በመስጠት ከኑዛዜው ቃል መራቅ አይፈቀድም፡፡
ቊ 911፡፡ የሕሊና ግምት
1. ተናዛዡ የኔ ወራሾች ወይም የኔ ሀብቶች ወይም የኔ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሚል ቃል አይነት
አገላለጽ ተናዞ እንደ ሆነ ለእነዚህ ቃላቶች ተናዛዡ በሞተበት ቀን የነበራቸውን ፍቺ በመመልከት
እንደ ተናገራቸው ይገመታል፡፡
2. ስለዚህ የህሊና ግምት ተቃራኒ የሆነ ማስረጃ ለማቅረብ ይቻላል፡፡
ቊ 912፡፡ ጠቅላላና ልዩ የኑዛዜ ስጦታ
1. ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ማለት ተናዛዡ ሀብቱን በጠቅላላ ወይም ከመላ ንብረቱ አንዱን ክፍል
በሙሉ ሀብትነት ወይም በሌጣ ርስትነት ለአንድ ወይም ለብዙ ሰዎች የሚያወርስበት የኑዛዜ ቃል
ነው፡፡
2. ማንኛውም ሌላ የኑዛዜ ቃል ሁሉ እንደ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ ይቆጠራል፡፡
ቊ 913፡፡ የኑዛዜ ስጦታና የክፍያ ደንብ
የኑዛዜው ቃል የተናዛዡን ተቃራኒ ሐሳብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሀብት አንድ ድርሻን
ወይም አንድ ንብረትን ሟቹ ለወራሾች መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ
ነው ተብሎ አይቆጠርም፡፡
ቊ 914፡፡ ስለ አንድ ጠቅላላ ሀብት ወራሽ መመረጥ(1)ፎርም
የአንድ የጠቅላላ ሀብትተቀባይን አመራረጥ ማንኛውንም ዐይነት ፎርም መከተል የለበትም፡፡
ቊ 915፡፡ (2) ውጤት
1. የኑዛዜው ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ቃል ከሌላ በቀር ጠቅላላ ሀብት በኑዛዜ ስጦታ ያገኘ ሰው ያለ ኑዛዜ
ወራሽ እንደ ሆነ ሰው ይቆጠራል፡፡
2. በኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሌሎች ሰዎችና ያለ ኑዛዜ ወራሾች የሌሉ እንደ ሆነ ጠቅላላውን
ውርስ ለመቀበል መብት አለው፡፡
3. ስለ ሆነም ተናዛዡ ግልጽ በሆነ ዐይነት ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጠው ሰው ከውርሱ አንድ
ክፍል በላይ አያገኝም ብሎ በኑዛዜው ውስጥ ለመግለጽ ይችላል፡፡
ቊ 916፡፡ ገደብ ያለበት የኑዛዜ ስጦታ (1) መሠረቱ
በጠቅላላው ወይም በተለይ የሚደረጉ የኑዛዜ ስጦታዎች አንድ ሁኔታ ሲደርስ የሚጸኑ ወይም አንድ
ሁኔታ ሲደርስ የሚቀሩ ሁነው ሊደረጉ ይችላል፡፡
ቊ 917፡፡ (2) የማግባት ወይም ያለ ማግባት ገደብ
1. የኑዛዜ ስጦታ የተሰጠው ሰው በተለይ አንድ ሰው ያግባ ወይም አያግባ ተብሎ የሚደረግ የኑዛዜ
ገደብ ዋጋ ያለው ነው፡፡
2. በጠቅላላው ሁኔታ ወራሹ እንዳያገባ ወይም እንደ ገና እንዳያገባ የሚያስገድደው የኑዛዜው ገደብ
ፈራሽ ነው፡፡
3. ስለ ሆነም ወራሹ እስከ አገባ ወይም እንደገና እስከ አገባ ድረስ የአንድ የተወሰነ ሀብትን ሪም
ወይም አንድ የተወሰነ ቀለብ በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ያገኛል ብሎ ተናዛዡ ለመወሰን
ይችላል፡፡
ቊ 918፡፡ (3) የሕሊና ግምት
1. የተናዛዡ ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው
የተወሰነውንአንድ ነገር እንዲያደርግ በማለት በውለታ የተሰጠ የኑዛዜ ስጦታውን በሚያስቀር
ገደብ ዐይነት እንደ ተደረገ ይቆጠራል፡፡
2. ወራሹ የተወሰነውን አንድ ነገር እንዲያደርግ በማለት በውለታ የተሰጠ የኑዛዜ ስጦታ ከዚህ በላይ
ባለው ኀይለ ቃል እንደተባለው ዐይነት ይቆጠራል፡፡
ቊ 919፡፡ (4) ማረጋገጫዎች
1. ሟቹ ያደረገው ኑዛዜ ስጦታ አንድ ሁኔታ ሲደርስ ስጦታው ይቀራል በሚል ገደብ አድርጎት እንደ
ሆነ ይህ ስጦታውን የሚያስቀረው ሁኔታ የደረሰ እንደ ሆነየተሰጠውን ሀብት ሊመልስ ማረጋገጫ
የሚሆን ዋስ ወይም ሌላ ዋስትና እንዲሰጥ ባለጥቅም የሆነ ሰው በሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት
ዳኞች በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለትን ሰው ሊያስገድዱት ይችላሉ፡፡
2. ሟቹ ያደረገው የኑዛዜ ስጦታ አንድ ሁኔታ ሲደርስ ስጦታው የሚጸና ይሆናል በሚል ገደብ
አድርጎት እንደሆነ ይህ ስጦታውን የሚያጸናው ሁኔታ የደረሰ እንደሆነ የኑዛዜውን ስጦታ ሀብት
በእጅ የሚያገኘው ሰው በኑዛዜ ስጦታ ለተደረገለት ሰውም ሊያስረክብ በዚሁ የኑዛዜ ስጦታ
በተደረገለት ሰው ጥያቄ ዋስ ወይም ሌላ ዋስትና እንዲሰጥ እንዲሁም ዳኞች ሊያስገድዱት
ይችላሉ፡፡
ቊ 920፡፡ ግዴታ(1) መሠረቱ
ተናዛዡ ወራሾቹን ወይም በኑዛዜ ስጦታ የተሰጣቸውን ሶች ከሚደርሳቸው ሀብት ላይ በተለየ ለአንድ
ወይም ለብዙ ሰዎች አንድ አገልግሎት እንዲሰጡ ግድ እንዲሆንባቸው በኑዛዜው ለመወሰን ይችላል፡፡
ቊ 922፡፡ (2) የግዴታው ወሰን
አንድ ግዴታ የተጣለበት ወራሽ ወይም በኑዛዜ ስጦታ የተሰጠው ሰው ስለዚሁ ግዴታ አፈፃፀም
በደረሰው ውርስ ወይም የኑዛዜ ስጦታ መጠን ካልሆነ በቀር ሊገደድ አይችልም፡፡
ቊ 923፡፡ (3) ስለ ግዴታው አፈፃፀም
1. በግዴታው ተጠቃሚ የሆነው ሰው የታዘዘለት እንዲፈጸምለት ለማስገደድ ይችላል፡፡
2. እንዲሁም በአካባቢው ነገሮች ምክንያት አስፈላጊ ሆኖ ሲታይ ስለ ግዴታው አፈፃፀም አንድ ዋስ
ወይም ሌላ ማረጋገጫ እንዲሰጠው ወራሹን ወይም በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለትን ሰው
ተጠቃሚው ለማስገደድ ይችላል፡፡
3. እንደዚሁም ተናዛዡ የመረጠው ሰው ወይም የተመረጠ ሰው ባይኖር ለያንዳንዱ የሟቹ ወራሾች
ወይም ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጣቸው ሶች የዚሁ ዓይነት መብት ይኖራቸዋል፡፡
ቊ 923፡፡ (4) ስለ ኑዛዜ ስጦታ መፍረስ
1. ተናዛዡ ይህንኑ በግልጽ ካላመለከተ በቀር በኑዛዜው የተወሰነውን ግዴታ አለመፈጸም የኑዛዜውን
ስጦታ አያፈርሰውም፡፡
2. በኑዛዜው የተሰጠውን ንብረት በቅን ልቦና ያገኙ ሰዎች መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ቊ 924፡፡ በኑዛዜው ስጦታ ተጠቃሚ የሆነውን ሰው ስለ መወሰን
1. በኑዛዜው ስጦታ ተጠቃሚው በሚቃ አኳኋን ተወስኗል የሚለው አንድ ክፍል ከሆኑ ሰዎች
ውስጥ ይህንኑ ሰው ወራሹን ወይም የጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጠውን ወይም ሌላ ሰው
እንዲመረጥ ኑዛዜው የሚስገድድ የሆነ እንደ ሆነ ነው
2. በጉዳዩ ጥቅም ባለው በማናቸውም ሰው ጥያቄ በኑዛዜው ስጦታ ተጠቃ የሆነውን
ለሚያስታቀው ሰው ምርጫውን የሚያከናውንበት ጊዜ ሊወስኑለት ይችላሉ፡፡
3. ይህን ማስታወቅ ሳያደርግ የቀረ እንደ ሆነ ወይም ለማስታወቅ እንቢ ያለ እንደ ሆነ ዳኞች
የተናዛዡ ፈቃድ በተሸለ መጠን የሚፈጸምበት ነው ብለው በሚገምቱበት መንገድ ተጠቃሚውን
በሚመርጥ ሌላ ሰው ያደርጋሉ፡፡
ቊ 925፡፡ ለድኾች የሚደረግ የኑዛዜ ስጦታ
1. ሌላ ዝርዝር ሳይኖርበት ለድኾች ጥቅም የተሰጠ የኑዛዜ ስጦታ ዋጋ ያለው ነው፡፡
2. የኑዛዜውም ስጦታ ተቃራኒ ማስረጃ ከሌለ በቀር ተናዛዡ በሞተ ጊዜ በነበረበት ዋና መኖሪያ
ስፍራ በሚገኘው ቦታ ላሉት ደኾች ጥቅም እንደተደረገ ይገመታል፡፡
3. በርሱ ጠባቂነት የተናዛዡን ፈቃድ ለማስፈጸም ይህን የኑዛዜውን ስጦታ ለመቀበል ችሎታ
ያለውን ባለስልጣን ያስተዳደር ደንቦች ይወስናሉ፡፡
ቊ 926፡፡ ለብዙ ሰዎች የሚደረግ የኑዛዜ ስጦታ

1. ተናዛዡ የያንዳንዱን ድርሻ ምን እንደሆነ ሳይለይ ለሁለት ወይም ለብዙ ሰዎች ጠቅላላ የኑዛዜ
ስጦታ አድርጎላቸው እንደ ሆነ ወይም አንዱን ሀብት ለሁለት ወይም ለብዙ ሰዎች የኑዛዜ ስጦታ
አድርጎ እንደ ሆነ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሰዎች በውርሱ ውስጥ ወይም በኑዛዜ ስጦታ
በተሰጠው ንብረት ውስጥ ትክክል የሆነ መብት አላቸው፡፡
2. ከነዚህ የኑዛዜ ስጦታ ከተደረገላቸው ሰዎች አንዱ ለርሱ የተደረገለትን የኑዛዜ ቃል ለመቀበል
ያልቻለ ወይምያልፈቀደ እንደ ሆነ ድርሻው ከርሱ ጋር አብሮ ለተሰጣቸው ሰዎች ይተላለፋል፡፡
ቊ 927፡፡ በኑዛዜ ስጦታ የተመለከተውን ንብረት ስለ መለየት

1. በኑዛዜ የተሰጠ ስጦታ በሚበቃ ተለይቷል የሚባለው ወራሹ ወይም በኑዛዜ ስጦታ የተሰጠው
ሰው ራሱ ወይም ማናቸውም ሌላ ሰው ከብዙ ዕቃዎች ውስጥ እንዲመርጥ ኑዛዜው የወሰነ እንደ
ሆነ ነው፡፡
2. የኑዛዜ ውርስ የተሰጠው ሰው ራሱ ምርጫ የሚያደርገው ሟቹ የሚመርጠውን ሰው ባልለየ ጊዜ
ወይም ምርጫውን እንዲያደርግ የተመረጠው ሰው የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው በወሰነለት
ተገቢ ጊዜ ውስጥ ያላደረገ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 928፡፡ ማናቸውንም ሰው ስለ መተካት

1. በጠቅላላ ወይም በልዩ ሀብት የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ባይኖር የኑዛዜውን ስጦታ ሌላ
አንድ ሰው ሊቀበል ይችላል ብሎ ተናዛዡ ለመወሰን ይችላል፡፡
2. ተቃራኒ የኑዛዜ ቃል ከሌለ በቀር በኑዛዜ ስጦታ ለተደረገለት ሰው የሚጠቅመው በማናቸውም
ሁኔታ የተመረጠው የኑዛዜ ስጦታ ቀዳሚ የተደረገለት የኑዛዜውን ስጦታ ለመቀበል ያልቻለ
ወይም ያልፈቀደ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 929፡፡ ለሌላ ሰው እንደሚተላለፍ አድርጎ መተካት(1) መሠረቱ

1. ተናዛዡ አንድ የተወሰነ ጊዜ አልፎ ወይም በሞተ ጊዜ ወይም አንድ የተወሰነ ሁኔታ የተፈፀመ
ሲሆን ወራሹ ወይም የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው የውርሱን ሀብቶች ወይም የተወሰኑትን
ሀብቶች በርሱ ምትክ ለሚሆኑት ለአንዱ ወይም ለብዙ ሰዎች ማስተላለፍ አለበት በሚል ኑዛዜ
ለማድረግ ይችላል፡፡
2. ሀብቱን በመጀመሪያ የሚቀበል ወራሽ ወይም የኑዛዜ ስጦታ ተቀባይ የሆነ ሰው ባለግዴታ
ይባላል፡፡
3. የምትክነቱ ሠራ በሚፈጸምበት ጊዜ ከወራሹ ወይም የኑዛዜ ስጦታ ከተደረገለት ሰው ላይ
ንብረቱን የሚያገኘው ሰው ዋና ወራሽ ነው፡፡
ቊ 930፡፡ (2) የሚተካው ሰው

1. ዋናው ወራሽ ሟቹ በሚሞትበት ቀን ለመቀበል ችሎታ ያለው መሆን አስፈላጊ አይደለም፡፡


2. ለውርስ መተካቱ ውጤት በሚያገኝበት ቀን ለመለየትና ለመቀበል ችሎታ ያለው ከሆነ በቂ ነው፡፡
3. ስለዚህ ወደ ታች ለሚቆጠሩ ተወላጆች ጥቅም ወይም ግዴታ ለተጣለበት ሰው ወራሾች ለሆኑት
ጥቅም የተደረገ የውርስ መካተት ዋጋ ያለው ነው፡፡
ቊ 931፡፡ (3) ውጤት

1. ከዚህ በላይ ባለው ቁጥር የተጠቀሰው የኑዛዜ ቃል በሚመለከተው ሀብት ንብረቱ እንዳይሸጥ
እንዳጥተላለፍ እንዳይያዝ ተብሎ የሚደረገው የውል ቃል ስምምነት ዐይነት ውጤት ይኖረዋል፡፡
2. ከዚህ የሚቀጥሉት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ሆነው የዚህን የኑዛዜ ቃል ውጤት ለመወሰን በዚህ ሕግ
ስለ የጋራ ሀብትነት ስለ ሪምና ስለ ሌሎች ግዙፍ መብቶች በሚመለከተው አንቀጽ የተፃፉት
ደንቦች ተፈፃሚዎች ይሆናል፡፡
ቊ 932፡፡ (4) የዳኞችን ሥልጣን ስለ መወሰን

ግዴታ በተጣለበት ሰው ወይም ከሱ ላይ ገንዘብ በሚጠይቁ ሰዎች ጥያቄ በሚገኘውም አኳኋን ቢሆን
ዳኞች የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲሸጥ እንዲተላለፍ ወይም እንዲያዝ ለማዘዝ አይችሉም፡፡
ቊ 933፡፡ (5) ጥያቄ ለማቅረብ የተወሰነ ጊዜ

1. ዋናው ተጠቃሚነት ወይም ወኪል ወይም ተናዛዡ የመተካቱን ሥረዐት ለማስፈፀም የመረጠው
ሰው በማይገባ የተደረገን መሸጥ ለመለወጥ ወይም መያዝ እንዲፈርስ በማናቸውም ጊዜ
ለመጠየቅ ይችላል፡፡
2. የመተካቱ ሥርዓት ከተደረገ በኋላ በሚከተለው ሁለት ዓመት ውስጥ ክሳቸውን ቢያቀርቡ በቂ
ይሆናል፡፡
ቊ 934፡፡ (6) በመተካት ጉዳይ በአንድ ደረጃ ላይ ስለ መወሰን

1. ተናዛዡ ዋና ወራሽ ለሆነው ሰው ሀብቶቹ ወይም መብቶቹ ከተላለፉ በኋላ የማይሸጡ


የማይተላለፉ ወይም የማይያዙ ናቸው ብሎ በኑዛዜው ውስጥ የሚያገባው ዋጋ የሌለው ነው፡፡
2. እንዲሁም ዋና ወራሽ ለሆነው ሰው ሀብቶቹ ወይም መብቶቹ ከተላለፉ በኋላ የነዚሁ ሀብቶች
ወይም መብቶች ሁኔታ የሚወስንበት ኑዛዜ ቃል ዋጋ የለውም፡፡
ቊ 935፡፡ (7)በኑዛዜ ግዴታ የተጣለበት ሰው እንቢታ

የኑዛዜው ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር የኑዛዜ ስጦታ ሲሰጠው ግዴታ የተጣለበት ሰው ስጦታውን
ለመቀበል ያልቻለ ወይም ያልፈለገ ሲሆን በሱ ምትክ የኑዛዜው ስጦታ የሚደርሰውን ሰው ወዲያውኑ
እንእንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
ቊ 936፡፡ (8) በምትክ እንዲቀርብ የተጠራው ሰው አለመቅረብ

1. ባለግዴታው ለሌላ ሰው እንዲተላለፍ ተደርጎ ይህ ግዴታ የሚጸናባቸውን ንብረቶችና መብቶች


በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ክሱ በምትክ የሚቀበለው ሰው የሞተ እንደሆነ በማናቸውም
ምክንያት በምትክነቱ ሥርዐት ሊፈፀም የማይችል መሆኑ የተረጋገጠ እንደ ሆነ በነዚሁ
ሀብቶችና መብቶች በኑዛዜው ስጦታ የተደረገለት ሰው እንደ ፈለገው ሊያዝባቸው ይችላል፡፡
2. የሚተካው ሰው በአለመቅረብ ወይም እንቢ በማለት ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት
ተናዛዡ አስቦበት የነበረው መተካት ሊፈጸም ያልቻለ እንደሆነ ምትክ ለሆነ ሰው
እንዲያስተላልፍ የተሰጡት ንብረቶች በዋናው ወራሽ ለሆነው ሰው ወራሾች ይተላለፋሉ
3. በኑዛዜው ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር የተናዛዡ ወራሾች በነዚህ ንብረቶች ላይ አንድም መብት
አይኖራቸውም፡፡

ቊ 937፡፡ ከወራሽነት መንቀል፡፡ (1) ግልጽ ኑዛዜ፡፡

(1) ተናዛዡ በኑዛዜው ውስጥ ጠቅላላ የውርስ ስጦታ የሚያደርግለትን ሳይጠቅስ ያለ ኑዛዜ የሚወርሱትን ወይም ከነዚሁ አንዱን ግልጽ
በሆነ ቃል ከወራሽነት ለመንቀል ይችላል፡፡

(2) ይህ ሲሆን የተነቀሉት ወራሽ ወይም ወራሾች ከተናዛዡ በፊት እንደ ሞቱ ተቈጥረው የውርሱ ሥርዐት ይፈጸማል፡፡

ቊ 938፡፡ (2) ወደ ታች ለሚቈጠሩ ተወላጆች ልዩ ድንጋጌ፡፡

(1) ተናዛዡ ከርስት ከውርስ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለጸ በቀር ልጁን ወይም ወደ ታች የሚቈጠር ተወላጁን
ከውርስ ቢነቅል አይጸናም፡፡

(2) ተናዛዡ ወራሹን ከውርስ ለመንቀል የሰጠው ምክንያት ትክክል (እውነት) እንደሆነ ተቈጥሮ ዳኞች ይህ ምክንያት ከውርስ (ከርስት)
ለመንቀል የሚያበቃ መሆን አለመሆኑን ይመረምራሉ፡፡

(3) ዳኞች ተናዛዡ በኑዛዜው ያስታወቀው ምክንያት ትክክል (እውነት) መሆን አለመሆኑን መመርመር አይችሉም፡፡

ቊ 939፡፡ (3) በዝምታ ከውርስ መንቀል፡፡

(1) ተቃራኒ የኑዛዜ ቃል ከሌለ በቀር ዘመዶቹ የሁለተኛ የ 3 ኛ ወይም የአራተኛ ደረጃ ዝምድና ያላቸው ሆነው ተቃራኒ የኑዛዜ ቃል ከሌለ
በቀር የጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ማድረግ የሟቹን ዘመዶች ወራሽነት መንቀሉን ያስከትላል፡፡

(2) ስለሆነም የሟቹን ወደ ታች የሚቈጠሩ የተወላጆች ከወራሽነት መንቀልን አያስከትልም፡፡

(3) ሟቹ ወደ ታች የሚቈጠሩ ተወላጆች ኖሮትና ከወራሽነት በግልጽ ያልነቀላቸው የሆነ እንደሆነ በኑዛዜ የጠቅላላ ስጦታ የተደረገለት ሰው
እንደ ሟቹ ልጅ ተቈጥሮ ከነዚሁ ከተባሉት ወደ ታች ከሚቈጠሩ ተወላጆች ጋራ በውርሱ ተካፋይ ይሆናል፡፡

ቊ 940፡፡ (4) አንዳንድ የውል ቃላትን ስለ መከልከል፡፡


የኑዛዜውን ወይም በኑዛዜው ውስጥ ያለውን የአንድ ቃል መጽደቅ የተቃወሙ እንደሆነ ወራሾቹን ወይም ከነርሱ መካከል አንዱን በሙሉ
ወይም በከፊል ከወራሽነት ነቅየዋለሁ ብሎ ተናዛዡ የሚያስታውቅበት የኑዛዜ ቃል ሁሉ ፈራሽ ይሆናል፡፡
ቊ 941፡፡ የግልግል ቃል፡፡
የውርስ ሀብት ስለ ማጣራት (ማስላት) ወይም ስለ ማካፈል በሚመለከት ጒዳይ ከወራሾቹ ወይም የኑዛዜ ስጦታ በተደረገላቸው ሰዎች
መካከል የሚደረገው ክርክር ሁሉ ኑዛዜው እንደ ዘመድ ዳኞች አድርጎ በሚመርጣቸው በአንድ ወይም በብዙ ሰዎች የሚወሰን ይሆናል
ብሎ ሟቹ በኑዛዜው ውስጥ ቃል ለማግባት ይችላል፡፡

አንቀጽ 5፡፡
ስለ ውርስ (ስለ አወራረስ)፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
ወራሽነትን ስለ ማጣራት፡፡
ቊ 942፡፡ መሪ ሐሳብ፡፡
ውርሱም እስከተጣራ ድረስ እንደተለየ ንብረት ሆኖ ይቈጠራል፡፡
ቊ 943፡፡ ለገንዘብ ጠያቂዎች የሚሆን መያዣ (ዋስትና)፡፡

(1) ከውርሱ ሀብት ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች ለገንዘባቸው ዋስትና መያዣ የሚሆናቸው በመጣራት ላይ ያለው በውርሱ
ውስጥ የሚገኘው ንብረት ነው፡፡

(2) ገንዘብ ጠያቂዎቹ በወራሾቹ የግል ሀብት ላይ አንዳችም መብት የላቸውም፡፡

(3) ከወራሾቹ ከራሳቸው ላይ ገንዘብ ጠያቂ የሆኑት ሰዎች የውርሱ ሀብት በሚጣራበት ጊዜ በውርሱ ሀብት ላይ አንዳችም መብት
የላቸውም፡፡
ቊ 944፡፡ በማጣራቱ ሥራ ስለሚፈጸመው፡፡
ውርሱን ማጣራት ማለት፡-

(ሀ) የውርሱን ተቀባይ እነማን እንደሆኑ መወሰን፡፡

(ለ) የውርሱ ሀብት ምን መሆኑን መወሰን፤

(ሐ) ለውርሱ የሚከፈለውን ገንዘብ መቀበል ለመክፈል አስገዳጅ የሆነውን ዕዳ መክፈል፤

(መ) ሟቹ በኑዛዜው ስጦታ ላደረገላቸው ሰዎች የሰጣቸውን መክፈል ነው፡፡


ቊ 945፡፡ የግልግል ቃል፡፡
ወራሾችና በኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሰዎች ስለ ውርሱ ማጣራት ወይም መካፈል ጒዳይ በመካከላቸው በሚደረገው (በሚሆነው)
ክርክር ሁሉ አንድ ወይም ብዙ የዘመድ አስታራቂ ዳኞች እንዲያዩት ስምምነት ለማድረግ ይችላሉ፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ ውርሱ አጣሪ፡፡
ቊ 946፡፡ መሠረቱ፡፡
ያለ ኑዛዜ ወይም በኑዛዜ የሆነ ውርስ ከዚህ ቀጥሎ አጣሪ ተብሎ በተመረጡ በአንድ ወይም በብዙ ሰዎች የሚጣራ ይሆናል፡፡
ቊ 947፡፡ በሕግ ስለ መመረጥ፡፡
ያለ ኑዛዜ ወራሾች የሆኑ ሰዎች ሰውዮው ከሞተበት ቀን አንሥቶ ያለ አንዳች ፎርማሊቴ የአጣሪነት መብት ይኖራቸዋል፡፡
ቊ 948፡፡ በኑዛዜ ስለ መመረጥ፡፡
(1) ሟቹ አንድ ኑዛዜ የተወ እንደሆነ ሟቹ በዚሁ ኑዛዜ ውስጥ የኑዛዜው አስፈጻሚ እንዲሆን የመረጠው ሰው የአጣሪነት መብት
ይኖረዋል፡፡
(2) አንድ ግልጽ የሆነ የኑዛዜ ቃል ከሌለ በጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ወይም ሰዎች ያላንዳች ፎርማሊቴ የአጣሪነት መብት
ይኖራቸዋል፡፡
(3) አንድ የኑዛዜ አስፈጻሚን የሚመርጥ ወይም በጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የሚደረግለትን ሰው የሚያመለክት ኑዛዜ መገኘት ያለ ኑዛዜ ወራሽ
የሆኑትን ሰዎች የአጣሪነት ሥራ የሚያስቀረው ይሆናል፡፡
ቊ 949፡፡ አካለመጠንን ያላደረሰ ወይም የተከለከለ አጣሪ፡፡
አንድ አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ወይም አንድ የተከለከለ ሰው ከዚህ በፊት ባሉት ቊጥሮች ቃላት መሠረት የውርሱ አጣሪ የሆነ እንደሆነ
ስለ ሥራው አካሄድ ሞግዚቱ ወኪሉ ይሆናል፡፡

ቊ 950፡፡ በፍርድ የሚጣራ ውርስ፡፡ (1) ይገባኛል ባይ የሌለው የውርስ ሀብት ወይም ጠያቂ የሌለው ውርስ፡፡

(1) ወራሾቹ የማይታወቁ የሆነ እንደሆነ ወይም ያለ ኑዛዜ ወራሽ የሚሆኑት ሰዎች ሁሉም ውርሱን ለማጣራት የማይፈቅዱ መሆናቸውን
ገልጸው ያስታወቁ እንደሆነ፤ ማናቸውም ባለጒዳይ በሚያቀርበው ጥያቄ ዳኞች አንድ አጣሪ ይሾማሉ፡፡

(2) እንዲሁም ተናዛዡ ወራሾቹ ያልተዉና ውርሱም ማንግሥት የሚወርሰው የሆነ እንደሆነ ዳኞች አንድ አጣሪ ይሾማሉ፡፡

(3) እንዲህ ሲሆን የአስተዳደር ሕጎች ወይም ደንቦች በዳኞች አጣሪ ሆኖ የሚመረጠውን ሰው ወይም መሥሪያ ቤት ማን እንደሆነ
ይወስናሉ፡፡
ቊ 951፡፡ (2) ሌሎች ሁኔታዎች፡፡
ዳኞች በማናቸውም ባለጒዳይ ጥያቄ ከዚህ በፊት ባሉት ቊጥሮች የተመለከተውን አጣሪ ለመተካት አንድ ውል ለመዋዋል ሥልጣን
የተሰጠው ሰው ወይም ማናቸውም ሌላ ሰው ለመምረጥ የሚችሉት፤

(ሀ) ሒሳብ አጣሪውን የመረጠው ኑዛዜ ዋጋ ያለው መሆኑ የሚያከራክር ሆኖ ወይም በሌላ ማናቸውም ምክንያት ሒሳብ አጣሪውን
በመለየት ላይ የሚያጠራጥር ነገር ሲኖር፤

(ለ) ብዙ ሒሳብ አጣሪዎች ኖረው ውርሱን ለማስተዳደርና ሒሳቡን ለማጣራት ያልተስማሙ እንደሆነ፤

(ሐ) በወራሾቹ መካከል አንዱ አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ወይም የተከለከለ ሰው ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ጥቅሙን ለመከላከል
የማይችል አንድ ሰው ያለ ሲሆን፤

(መ) የውርሱ አስተዳደር ወይም ማጣራቱ ልዩ የሆነ ችግር ያስነሣ እንደሆነ፤

(ሠ) አጣሪው ትጉህ ያልሆነ ወይም ሐቀኛ ያልሆነ ወይም ሥራውን በሚገባ ለመፈጸም ችሎታ የሌለው መሆኑ የታወቀ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 952፡፡ ዋስ፡፡
ዳኞች በማናቸውም ባለጒዳይ ጥያቄ በማናቸውም ጊዜ ስለ ሥራው መልካም አፈጻጸም አንድ ዋስ ወይም ማናቸውም ሌላ ማረጋገጫ
መያዣ እንዲሰጥ አጣሪውን ለማስገደድ ይችላሉ፡፡
ቊ 953፡፡ ሥራው የፈቃድ ሥራ ስለመሆኑ፡፡
ማንም ሰው የአጣሪነት ሥራዎችን እንዲቀበል አይገደድም፡፡
ቊ 954፡፡ ከሥራው ስንብት ስለ መጠየቅ፡፡
(1) አጣሪው ሥራውን እፍጻሜ ለማድረስ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ለመሥራት በግልጽ ግዴታ የገባ ካልሆነ በቀር በማናቸውም ጊዜ ሥራውን
ለመተው ይችላል፡፡

(2) የሥራው መተው በማይገባ ጊዜ የተደረገ እንደሆነ የአጣሪውን አላፊነት ያስከትላል፡፡

(3) በማናቸውም ሁኔታ ሌሎች አጣሪዎች ካልተነገረ ወይም አንድ አዲስ አጣሪ ካልተመረጠ የአጣሪው ሥራዬን ትቻለሁ ማለት ዋጋ
የለውም፡፡

ቊ 955፡ የሥራው መቅረት፡፡


(1) የአጣሪው ሥራ የሚቀረው አጣሪው በሕጉ ወይም በኑዛዜ ወይም በዳኞች ውሳኔ መሠረት በአንድ አዲስ አጣሪ የተተካ እንደሆነ ነው፡፡

(2) እንዲሁም የአጣሪው ሥራ የሚቀረው አጣሪው ሥራውን ፈጽሞ አሠራሩን የሚያመለክት ሒሳብ በሰጠ ጊዜ ነው፡፡
ቊ 956፡፡ የአጣሪው ሥራ፡፡
(ሀ) ሟቹ አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆኑ መፈለግና በመጨረሻው ውርሱ የሚደርሳቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑ ማረጋገጥ፡፡

(ለ) የውርሱን ሀብት ማስተዳደር፤

(ሐ) መከፈያቸው የደረሰውን የውርስ ዕዳዎች መክፈል፡፡

(መ) ሟቹ በኑዛዜ ያደረጋቸውን ስጦታዎች መክፈልና የኑዛዜውን፤ ቃል ለመፈጸም ማንኛቸውም ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ማድረግ
አለበት፡፡
ቊ 957፡፡ የሥልጣን ወሰን፡፡
(1) ሟቹ ወይም ዳኞች የአጣሪውን ሥልጣን ለመወሰን ወይም ሥራውን እንዴት እንደሚፈጽም ትእዛዝ ሊሰጡት ይችላሉ፡፡

(2) ዳኞች ልዩ ምክንያት ካገኙ ከዚህ በፊት ባለው ኀይለ ቃል የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ለመለወጥ ይችላሉ፡፡

(3) ማናቸውም የኑዛዜ ቃል ተቃራኒ ቢኖርም እንኳ ከዚህ በላይ የተባሉትን ውሳኔዎች አለመተላለፍ የሚያስከትለው የአጣሪውን ኀላፊነት
ብቻ ነው፡፡
ቊ 958፡፡ ብዙ አጣሪዎች፡፡
(1) ብዙ አጣሪዎች ያሉ እንደሆነ ከሟቹ ወይም ከዳኞች የተሰጠ ተቃራኒ ቃል ከሌለ ብዙ አጣሪዎች ያሉ እንደሆነ እነዚሁ በመተባበር
መሥራት አለባቸው፡፡

(2) አጣሪዎቹ በማጣራት ያሉትን ሥራዎች መከፋፈል ወይም ከነርሱ መካከል አንዱ በመወከል ይህን የሒሳብ ማጣራት እንዲሠራ
ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

(3) የነዚህ ዐይነት ቃላት ወይም የዚህ ዐይነት ውክልና የሌለ ሁኖ እንደ ሒሳብ አጣሪ ብቻውን የማጣራቱን አንዱን ሥራ ፈጽሞ እንደሆነ
ስለ ሥራ አካሄድ የተሰጡት ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 959፡፡ የአጣሪው የአገልግሎት ዋጋ፡፡
አጣሪው በሟቹ በተወሰኑት ሁኔታዎች (ውለታዎች) መሠረት ወይም በወራሾቹ ወይም በዳኞቹ መካከል በተደረገ ስምምነት የሚሠራው
ሥራ የሚያረጋግጥለት ከሆነ አንድ የአገልግሎት ዋጋ ለማግኘት መብት አለው፡፡
ቊ 960፡፡ የሥራውን ክንውን ጒዳይ የሚያመለክት ራፖር ፡፡
(1) ሒሳብ አጣሪው ሥራውን ሲጨርስ ወራሾች ለሆኑት የሥራውን ክንውን ጒዳይ የሚያመለክት ራፖር ማቅረብ አለበት፡፡
(2) እንዲሁም በማናቸውም ዐይነት ሟቹ ከሞተ ከስድስት ወር በኋላ ወይም ከዚህ ጊዜ በፊት ከወራሾቹ ጋራ በስምመነት በተወሰነው ቀን
ወይም ዳኞች በወሰኑት ቀን የሥራውን ክንውን በራፖር ማመልከት አለበት፡፡
ቊ 961፡፡ አላፊነት፡፡
(1) ሒሳብ አጣሪው በጥፋቱ ወይም በቸልተኝነቱ ለሚያደርጋቸው ጉዳዮች አላፊ ነው፡፡

(2) ማናቸውም ለሕጉ ድንጋጌዎች ወይም ለኑዛዜው ወይም በዳኞች ለሱ የተሰጡትን ትእዛዞች ተቃራኒ የሆነ ተግባር ሁሉ እንደ ጥፋት
ይቈጠራል፡፡

(3) ዳኞች አጣሪው ከወራሾቹና በኑዛዜ ስጦታ ከተሰጣቸው ሰዎች ጋራ ባለው ግንኙነት ውስጥ በሚደርስበት አላፊነት ሥራዎቹን
ለመፈጸም በማሰብ በቅን ልቡና ያደረገ መሆኑ የታወቀ እንደሆነ ከዚህ አላፊነት በሙሉ ወይም በከፊል ነጻ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
ክፍል 2፡፡
መብት አለኝ ባዮችን ቊርጥ በሆነ አኳኋን ስለ መወሰን፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
የወራሾቹን ሁኔታ ለጊዜው ስለ መወሰን፡፡
ቊ 962፡፡ ኑዛዜውን ስለ መፈለግ፡፡
(1) ሒሳብ አጣሪው ከሁሉ አስቀድሞ ሟቹ የኑዛዜ ቃል ትቶ እንደሆነ መፈለግ አለበት፡፡

(2) ሒሳብ አጣሪውም ይህን እፍጻሜ ለማድረስ የሟቹን ጽሑፎች ይመረምራል እንዲሁም ሟቹ በኖረበት ቦታ በሚገኙት በሕግ
ለማዋዋል ሥልጣን ከተሰጣቸው ዘንድና በፍርድ መዝገብ ቤቶች ውስጥ ተገቢ የሆኑ ፍለጋዎችን ያደርጋል፡፡
ቊ 963፡፡ ኑዛዜውን የማስታወቅ ግዴታ፡፡
(1) ሟቹ ያደረገውን አንድ ኑዛዜ በእጅ የያዘ ያገኘ ወይም ምስክር በመሆን ያወቀ ሰው ወዲያው የሟቹን መሞት እንዳወቀ ለሒሳብ
አጣሪው ማስታወቅ ግዴታ አለበት፡፡

(2) ኑዛዜውን የሚያፈርስ ነገር ያለበት መስሎ ቢታየውም የማስታወቅ ግዴታ አለበት፡፡
ቊ 964፡፡ ኑዛዜውን ስለ ማስቀመጥ፡፡
(1) በግልጽ ወይም በሟቹ ጽሑፍ የሆነ ኑዛዜ ሒሳብ አጣሪው ወይም ማናቸውም ሌላ ባለጒዳይ ጥያቄ ያደረገ እንደሆነ ኑዛዜው በተገኘበት
ወይም በኖረበት ቦታ ባለው በሕግ ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ዘንድ ወይም በፍርድ መዝገብ ቤት ወዲያውኑ መቀመጥ አለበት፡፡

(2) በቃል የሆነ ኑዛዜ ከዚህ በላይ ባለው ሁኔታ የኑዛዜ ምስክር በሆኑ ሰዎች ወዲያውኑ በጽሑፍ ሆኖ መሰጠት አለበት፡፡

ቊ 965፡፡ ስለ ኑዛዜ መከፈት (1) ቀን፡፡

(1) ሟቹ ከሞተ በኋላ በአርባው ቀን አጣሪው የሟቹን ኑዛዜ ይናገራል፡፡

(2) ከዚህ ጊዜ በኋላ ኑዛዜ የተገኘ እንደሆነ የተገኘበትን ቀን በሚከተለው ወር ውስጥ በሒሳብ አጣሪው በተወሰነው ቀን ይነበባል፡፡

(3) እንዲህ ሲሆን ከዚህ በፊት ባለው ቊጥር ድንጋጌ መሠረት አስቀድሞ ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ወይም በፍርድ መዝገብ ቤት
ይቀመጣል፡፡
ቊ 966፡፡ (2) አስቀድሞ የሚደረግ የኑዛዜ መከፈት፡፡

(1) ሟቹ ካዘዘ ወይም ለቀብሩ ሥነ ሥርዐት ዝግጅት ጒዳይ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ ወይም በሕግ መጀመሪያ ወራሾች የሆኑት ኑዛዜው
የሚነገርበትን ቀን አስቀድሞ ለማድረግ በድምፅ ብልጫ የተስማሙበት እንደሆነ ከዚህ በፊት ባለው ቊጥር በ 1 ኛው ኀይለ ቃል
ከተመለከተው ቀን ቀደም ሊል ይችላል፡፡
(2) መጀመሪያ ወራሾች ከሆኑት አንዱ ቀደም ብሎ የሚነገረው ኑዛዜ ለመገኘትና እንደራሴ ለማድረግ ያልቻለ እንደሆነ የኑዛዜው ጽሑፍ
አስቀድሞ ከመነገሩ በፊት በሚገኝበት ቦታ ባለው ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ዘንድ ወይም በፍርድ መዝገብ ቤት መቀመጥ አለበት፡፡

ቊ 967፡፡ (3) ቦታ፡፡

(1) ሟቹ በሕይወት ላለ ወይም ከሞተ በኋላ ኑዛዜው በተቀመጠበት ቦታ ባለው ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ወይም በፍርድ መዝገብ
ቤት ኑዛዜው ይከፈታል፡፡

(2) ይህ ማስቀመጥ አልተደረገ እንደሆነ ኑዛዜው የሚከፈተው ሟቹ በሞተ ጊዜ በነበረው ዋና መኖሪያ ቦታ ነው፡፡

ቊ 968፡፡ (4) ማስታወቂያ፡፡

(1) ስለ ሟቹ ውርስ ያለ ኑዛዜ ወራሽ የሆኑትና በመጀመሪያ ሕጉ የሟቹ ወራሾች የሚያደርጋቸው ኑዛዜው ሲነበብ እንዲገኙ ወይም
እንደራሴ እንዲልኩ ይጠራሉ፡፡

(2) በማናቸውም አኳኋን ኑዛዜው ሲፈስ እጅግ ቢያንስ አራት አካለመጠንን ያደረሱና ያልተከለከሉ ሰዎች መገኘት አለባቸው፡፡

ቊ 969፡፡ (5) የዕለት ሥራ ተግባር፡፡

(1) ኑዛዜው በሚፈስበት ጊዜ ሒሳብ አጣሪውና ቀርበው የሚገኙ ሰዎች ሁሉ የኑዛዜውን ፎርምና ዋጋ ያለው መሆኑን ይመረምራሉ፡፡

(2) የኑዛዜው ቃል ይነበባል፡፡

(3) ኑዛዜውን ለማስቀመጥ አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶች ይደረጋሉ፡፡

ቊ 970፡፡ (6) ብዙ ኑዛዜዎች፡፡


ሟቹ አንድ ኑዛዜ ወይም ብዙ ኑዛዜዎች ቢተውም ከዚህ በፊት ያሉት ቊጥሮች ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 971፡፡ የክፍያ ደንብ ስለ ማቋቋም፣ (1) የኑዛዜ ውርስ፡፡

(1) ሒሳብ አጣሪው በስብሰባው ላይ ወዲያውኑ የሟቹ ወራሾች ወይም በኑዛዜው ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑና
የያንዳንዱም የውርስ መብት ምን እንደሆነ ያስታውቃል፡፡

(2) ሒሳብ አጣሪውም ወዲያውኑ ውርሱ እንዴት እንደሚከፋፈል ለባለ ጒዳዮቹ ያስታውቃል፡፡

(3) ከዚህ በፊት ባለው ኀይለ ቃል ባለጒዳዮች ማለት፤ የሟቹን ሀብቶች እንዲቀበሉ የተጠሩ ሰዎችና የኑዛዜ ቃል ባይኖር ኑሮ ሀብቶችን
እንዲወስዱ ይጠሩ የነበሩት ሰዎች ማለት ነው፡፡

ቊ 972፡፡ (2) ሳይናዘዝ የሞተው ሰው ውርስ፡፡

(1) እንዲሁም ሟቹ የኑዛዜው ቃል አለመተው የተገለጸ እንደሆነ፤ ሒሳብ አጣሪው የውርሱ አደራረግ እንደ ምን መሆን እንዳለበት
ያቀደውን የአከፋፈል ዐይነት ለባለጒዳዮቹ ያስታውቃል፡፡

(2) ይህም ማስታወቂያ የሚነገረው የኑዛዜው አለመኖር እርግጥ መስሎ እንደታየ ወዲያውኑና እጅግ ቢዘገይ ሟቹ ካለፈ ከአርባ ቀን በኋላ
ነው፡፡

ቊ 973፡፡ ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል ክስ፤ (1) ኑዛዜው ሲነገር ያሉ ሰዎች፡፡

(1) ኑዛዜው ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከሉ ሰዎች ኑዛዜው አይጸናም ወይም አንዱ በኑዛዜው የተነገረ ቃል አይጸናም በማለት ክስ
ለማቅረብ ያላቸውን ሐሳብ መግለጫ ወይም ስለ ክፍያው በሒሳብ አጣሪው የቀረበውን የድልድልን አመዳደብ አሳብ ለመቃወም፤ ኑዛዜው
ከተነበበበት አንሥቶ የሚቈጠር የዐሥራ አምስት ቀን ጊዜ አላቸው፡፡
(2) ይህ መግለጫ በጽሑፍ ካልሆነና ለአጣሪው ወይም ለዳኞች ወይም በውርሱ ላይ የተነሣውን ነገር ለመጨረስ ለተመረጡት የሽምግልና
ዳኞች እንዲደርስ ካልተደረገ በቀር አይጸናም፡፡

(3) ይህ መግለጫ ከተሰጠበት ቀን አንሥቶ እስከ ሦስት ወር ጥያቄውን (ክሱን) ለዳኞች ወይም ለሽምግልና ዳኞች ካላቀረበ በቀር የመጠየቅ
መብቱን ያጣል፡፡

ቊ 974፡፡ (2) ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ሰዎች፡፡

(1) በኑዛዜው ንባብ ሥነ ሥርዐት ላልነበሩ ወይም በኑዛዜው ንባብ ሥነ ሥርዐት በወኪልነት ላልሰሙ ሰዎችና፤ እንዲሁም፤ ኑዛዜው
በሌሉበት ይህ የተባለው፡፡ ጊዜ የሚቈጠርበት መነሻ አጣሪው ስለ ክፍያው የድልድል አመዳደብ አሳቡን ከነገራቸው ቀን አንሥቶ ነው፡፡

(2) ኑዛዜ ከፈሰሰበት ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ፤ ወይም ኑዛዜ የሌለ እንደሆነ ሟቹ ከሞተ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለኑዛዜው መጽናትና
ስለ ክፍያው አመዳደብ አጣሪው ያቀረበው የድልድል አሳብ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን መቃወሚያ ሊቀርብበት አይችልም፡፡

ቊ 975፡፡ (3) ለጊዜው የሚደረጉ ጥንቃቄዎች፡፡


ዳኞቹ አንድ ባለጒዳይ ሲጠይቅና፤ በተቀዳሚዎቹ ቊጥሮች ለተመለከቱት ጥያቄዎች ፍርድ እስኪሰጣቸው ድረስ የወራሽነቱ ሥራ
አፈጻጸም እንዳይዘገይ አስፈላጊዎች መስለው የታዩዋቸውን ለጊዜው የሚሆኑ ጥንቃቄዎች ሁሉ ለማድረግ ይችላሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
ስለ ወራሾችና ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች ሰለሚያደርጉት ምርጫ፡፡
ቊ 976፡፡ የአስፈላጊዎቹ ወራሾች አለመኖር፡፡
ማናቸውም ወራሽ እንዲወርስ የተጠራበትን ውርስ ወይም የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለትን ለመቀበል አይገደድም፡፡
ቊ 977፡፡ ምርጫው የግል ስለ መሆኑ፡፡
(1) ወራሽነትን የመቀበል ወይም አልቀበልም የማለት ፈቃድ የወራሹ የራሱ መብት ብቻ ነው፡፡

(2) በዚህ በተባለው መብት ከወራሹ ላይ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ሊሠሩበት አይችሉም፡፡

(3) ከውርሱ ላይ ገንዘብ የሚጠይቁትን ሰዎች መብት ለማጭበርበር ወራሹ ውርሱን አልቀበልም በሚልበት ጊዜ የገንዘብ ጠያቂዎቹ መብተ
የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ቊ 978፡፡ ውርስን አልቀበልም ለማለት የተወሰነው ጊዜ፡፡
(1) ወራሹ ውርሱን አልቀበልም ብሎ ለማስታወቅ የተሰጠው ጊዜ ወራሽ መሆኑን አጣሪው ካስታወቀው ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ወር
ነው፡፡

(2) ዳኞቹ፤ ወራሹ ባቀረበው ጥያቄ ከዚህ በላይ ባለው ኃይለ ቃል፤ የተመለከተው ጊዜ እጅግ ቢበዛ እስከ ሦስት ወር ድረስ ሊያረዝሙት
ይችላሉ፡፡
ቊ 979፡፡ የአልቀበልም ባይነት አደራረግ፡፡
(1) በኑዛዜው አልስማማም ባይነት በጽሑፍ ወይም አራት ምስክሮች ባሉበት ካልተደረገ በቀር ፈራሽ ነው፡፡

(2) እንደዚሁም፤ አልቀበልም ባይነቱ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተወሰነው ጊዜ ከማለፉ በፊት ለአጣሪው ካልተነገረ በቀር ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 980፡፡ የመቀበሉ አደራረግ፡፡
ወራሽነትን መቀበል በግልጽ ወይም በዝምታ ለመሆን ይችላል፡፡
ቊ 981፡፡ በግልጽ የሚሆን ተቀባይነት፡፡
በወራሹ በኩል በግልጽ የሚሆን የወራሽነት መቀበል ወራሹ ወራሽነቱን በጽሑፍ ሰነድ ሲቀበል ነው፡፡
ቊ 982፡፡ በዝምታ የሚሆን ተቀባይነት፡፡
(1) በዝምታ ወራሽነትን ተቀብሏል የሚባለው ወራሹ በማያሻማ ዐይነት ወራሽነቱን የመቀበል አሳብ የሚገልጽ ተግባር የፈጸመ እንደሆነ
ነው፡፡
(2) እንዲሁም፤ ወራሹ በሕግ በተፈቀደለት ጊዜ ውስጥ ወራሽነቱን አልቀበልም ያላለ እንደሆነ፤ ውርሱን በዝምታ ተቀብሏል ይባላል፡፡
ቊ 983፡፡ ለሌላ ሰው ጥቅም ወራሽነቱን ስለ መልቀቅ፡፡
(1) ተለይተው ለተነገሩ ለአንድ ወይም ለብዙ ሰዎች ጥቅም ተብሎ ወራሽነቱን መልቀቅ ማለት የወራሽነትን መብት እንደመተው ሆኖ
ይቈጠራል፡፡

(2) በዚህ ዐይነት ወራሽነቱን ለሌላ ሰው ጥቅም የለቀቀ ወራሽ ወራሽነቱን እንደተቀበለ ይቈጠራል፡፡

(3) ወራሹ ለእገሌ ብሎ ሳይለይ ከርሱ ጋራ ወራሾች ለሆኑት ሰዎች ጥቅም ድርሻውን የለቀቀ እንደሆነና ለዚሁም መቻቻያ ገንዘብ
ያልተቀበለ እንደሆነ ውርሱን እንደተቀበለ አይቈጠርም፡፡
ቊ 984፡፡ የአጠባበቅ ወይም የአስተዳደር ተግባሮች፡፡
ወራሹ በውርሱ ውስጥ ስለሚገኙ ንብረቶች የፈጸማቸው እንደ ጥበቃ ወይም የዕቃ ዝርዝር መዝገብ ማደራጀትን የመሰሉ የአጠባበቅ
ተግባሮች እና አስቸኳዮች የሆኑ የአስተዳደር ተግባሮች ወራሹን ውርሱን በዝምታ እንደተቀበለ አያስቈጥሩትም፡፡
ቊ 985፡፡ በውርሱ ስለ መጠቀም ወይም ስለ መደበቅ፡፡
ወራሹ በውርሱ ውስጥ ባለ ንብረት መጠቀም ወይም ንብረቱን መደበቅ፤ ወራሽነትን እንደተቀበለ ያስቈጥረዋል፡፡
ቊ 986፡፡ ምርጫውን እያንዳንዱ ሰው የሚያደርገው ስለ መሆኑ፡፡
ወራሾቹ ብዙ በሆኑ ጊዜ ውርሱን፤ አንዳንዶቹ ሲቀበሉ ሌሎቹ አንቀበልም ሊሉ ይችላሉ፡፡
ቊ 987፡፡ ከመምረጡ በፊት የወራሽ መሞት፡፡
(1) ወራሽ የሆነው ሰው ወራሽነቱን ከመቀበሉ ወይም አልቀበልም ከማለቱ አስቀድሞ የሞተ እንደሆነ፤ ተቀባይነቱ ወይም የአልቀበልም
ባይነቱ መብት ለርሱ ወራሾች ይተላለፋል፡፡

(2) ከነዚሁም ወራሾች አንዳንዶቹ ወራሽነቱን እንዲቀበሉ ሌሎቹ ግን አንቀበልም እንዲሉ ይፈቀድላቸዋል፡፡

(3) የወራሹን ውርስ አንቀበልም ያሉት ሰዎች በዚህ አድራጎታቸው መጀመሪያ የሞተውን ሰው ውርስ አንቀበልም እንዳሉ ይቈጠራሉ፡፡
ቊ 988፡፡ ምርጫው ቊርጠኛ ቃል መሆን ስለሚገባው፡፡
(1) የውርሱን የመቀበል ወይም የአለመቀበል ቃል የተወሰነ ጊዜ ወይም ውለታ ሊኖርበት አይችልም፡፡

(2) ወራሹ ውርሱን መቀበሉን ወይም የአለመቀበሉን ቃል ሲሰጥ በዚህ ውስጥ የተወሰነ ጊዜ ወይም በውለታ ቃል ጨምሮበት እንደሆነ
ምርጫ እንዳላደረገ ይቈጠራል፡፡
ቊ 989፡፡ ወራሽነትን በከፊል መቀበል ወይም አልቀበልም ማለት፡፡
(1) ውርሱን በከፊል ለመቀበል ወይም አልቀበልም ለማለት አይቻልም፡፡

(2) ስለሆነም ውርሱን አልቀበልም ያለ፤ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ያለኑዛዜ የሞተው ሰው ወራሽ በመሆን ወራሽነቱን እንደገና
ለመቀበል ይችላል፡፡

(3) እንደዚሁም ልዩ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጠው ወራሽ ውርሱን አልቀበልም የኑዛዜውን ስጦታ እቀበላለሁ ወይም ውርሱን እቀበላለሁ
የኑዛዜውን ስጦታ አልቀበልም ብሎ ለማማረጥ ይፈቀድለታል፡፡
ቊ 990፡፡ መቀበል የማይሻር ስለ መሆኑ፡፡
(1) ወራሹ ውርሱን እቀበላለሁ ያለው ቃል ሊፈርስ አይችልም፡፡

(2) በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን የመቀበሉ ቃል ሊፈርስ አይቻልም፡፡

ቊ 991፡፡ ውርሱን ለቅቄአለሁ የማለት ቃል መሻር፤ (1) ምክንያት፡፡

(1) ውርሱን አልፈልግም ያለውን ቃል ወራሹ ተገድዶ አድርጎት እንደሆነ ሊሽረው ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ይህን ወራሽነቱን ለቅቄአለሁ የማለቱን ቃል፤ ለወራሽነት የተጠራ ሰው ወይም የዚህ ሰው ወደ ታች የሚቈጠር ተወላጅ
ወይም ወደ ላይ የሚቈጠር ወላጅ ወይም ወንድም ወይም እኅት ወይም ባል ወይም ሚስት በማታለል አድርጎት እንደሆነ ሊሽረው
ይችላል፡፡
(3) በሌላ ምክንያት ግን ውርሱን ለቅቄአለሁ ያለውን ቃል ሊሽር አይቻልም፡፡

ቊ 992፡፡ (2) አደራረጉና ውጤቶቹ፡፡

(1) ወራሽነቱን ለቅቄአለሁ ያለውን ቃል መሻር የሚፈልግ ወራሽ፤ ለቅቄአለሁ የማለት ቃሉን ለመስጠት ያስገደደው ኀይል ከቀረለት፤
ወይም የተታለለበት ተንኰል ከተገለጸ በኋላ በሁለት ዓመት ውስጥ ለፍርድ ቤት ክሱን ካላቀረበ በቀር ክሱ ዋጋ የሌለው ይሆናል፡፡

(2) በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ለቅቄአለሁ የማለት ቃል፤ ከተነገረ ከዐሥር ዓመት በኋላ ሊሻር አይቻልም፡፡

(3) ወራሽነቱን ለቀቅሁ የማለትን ውጤቶች፤ በዚህ ሕግ፤ ስለ ውሎች መሰረዝና መፍረስ በሚለው ክፍል ስለ ውሎች በጠቅላላው
በሚለው አንቀጽ የተጻፉትን መሠረቶች በመከተል ዳኞቹ ይወስናሉ፡፡
ቊ 993፡፡ በወራሹ ምትክ ሆኖ ስለ መክሰስ፡፡
(1) ውርሱን አልፈልግም መባሉ ጉዳት የሚያደርስባቸው የሆነ እንደሆነ ውርሱን አልፈልግም ካለው ሰው ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች የሆኑት
ሰዎች አልፈልግም የተባለው ቃል ከተነገረበት ቀን አንሥቶ በ 2 ዓመት ውስጥ ዳኞች አልፈልግም የተባለውን ቃል እንዲያፈርሱት ክስ
ለማቅረብ ይችላሉ፡፡

(2) ለገንዘብ ጠያቂዎች ጥቅም ሲባልና በሚጠይቁትም ገንዘብ ልክ ካልሆነ በቀር ዳኞቹ ውርሱን አልፈልግም የተባለውን ቃል ሊሽሩት
አይችሉም፡፡

(3) ወራሽነቱን ለቀቅሁ ብሎ ለተወው ወራሽ ጥቅም ሲባል ውርሱን አልፈልግም የተባለው ቃል አይሻርም፡፡
ቊ 994፡፡ የውርስ መቀበል ውጤት፡፡
ውርሱን መቀበል ሟቹ ከሞተበት ቀን አንሥቶ ውጤት ይኖረዋል፡፡
ቊ 995፡፡ ወራሽነቱን የመልቀቅ ውጤት፡፡
(1) ወራሽነቱን ትቻለሁ የሚል ወራሽ መቼውንም ወራሽ እንዳልሆነ ይገመታል፡፡

(2) ወራሹ አልፈልግም ሲል የተወውን ድርሻ ወራሽነቱን ለተቀበሉት ለአብሮ ወራሾች አስፈላጊም ሲሆን ለተከታይ ወራሾች
የሚተላለፍላቸው ይሆናል፡፡

(3) ከነሱ ጋራ አብሮ ወራሽ የሆነው ውርሱን አልፈልግም ብሎ መልቀቁን ከአስታወቃቸው ቀን ጀምሮ ወራሽነትን ከዚህ ቀደም
የተቀበሉትን ወራሾች እስከ አንድ ወር፤ አብሮ ወራሽ የሆነው ሰው የተወውን ውርስ እንቀበላለን ወይም አንቀበልም ለማለት ይችላሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
ለወራሹ ስለሚሰጡ የምስክር ወረቀቶችና የወራሽነት ጥያቄ፡፡
ቊ 996፡፡ ለወራሹ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት፡፡ (1) የምስክርነቱ ወረቀት መሰጠት፡፡
(1) ወራሽ የሆነው ሰው፤ ለሟቹ ወራሽ መሆኑና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጡት
ዳኞቹን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ዳኞቹም፤ እንደዚህ ያለውን ጥያቄ ያቀረበውን ወራሽ፤ ማስረጃዎቹን ሁሉ እንዲያቀርብና አስፈላጊ መስሎ የታያቸውን ማናቸውንም
የማረጋገጫ ዋስትና እንዲሰጣቸው ሊያስገድዱት ይችላሉ፡፡

ቊ 997፡፡ (2) ውጤቶቹ፡፡

(1) የምስክር ወረቀቱ እስከተሰረዘ ድረስ ወራሹ በተባለው የምስክር ወረቀት እንደተገለጠው ወራሽ እንደሆነ ይገመታል፡፡

(2) በወራሽነት ስም፤ በወራሹ የተፈጸሙ ተግባሮች ያሉ እንደሆነ፤ ተግባሮቹ በተፈጸሙበት ጊዜ፤ የተባለው ወራሽ የወራሽነት መብት
እንዳልነበረው በግልጽ ማወቁ ካልተረጋገጠ በቀር እነዚህን ተግባሮች ለመቃወም አይቻልም፡፡

ቊ 998፡፡ (3) ስለ መሰረዝ፡፡

(1) የወራሽነቱ ጥያቄ በቀረበላቸው ጊዜ ዳኞቹ፤ እነርሱ የሰጡትን የወራሽ የምስክር ወረቀት ለመሰረዝ ይችላሉ፡፡

(2) እንዲህ ሲሆን፤ ወራሹ የተሰጠውን የምስክር ወረቀት መመለስ አለበት፡፡

(3) ወራሹ፤ የምስክሩ ወረቀት ጠፍቶብኛል ሲል ያመካኘ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ወረቀቱን ለመመለስ ያልቻለ እንደሆነ፤
ለወደፊቱ በዚህ በተባለው የምስክር ወረቀት እንዳይገለገልበት፤ የሚያረጋግጥ ለዚሁ የሚገባውን ዋስትና እንዲሰጥ ይፈረድበታል፡፡

ቊ 999፡፡ የወራሽነት ጥያቄ (1) መሠረቱ፡፡


አንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው፤ ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ያደረገ እንደሆነ፤ እውነተኛው ወራሽ
ወራሽነቱ እንዲታወቅለትና፤ የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት፤ በዚህ ሰው ላይ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ሊያቀርብበት
ይችላል፡፡
ቊ 1000፡፡ (2) ጥያቄውን ለማቅረብ የተወሰነ ጊዜ፡፡

(1) ከሳሹ መብቱንና የውርሱ ንብረቶች በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀ ሦስት ዓመት ካለፈ በኋላ፤ ስለ ወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ
ተቀባይነት ለማግኘት አይችልም፡፡

(2) እንደዚሁም ሟቹ ከሞተበት ወይም ከሳሹ በመብቱ ለመሥራት ከቻለበት ቀን አንሥቶ ዐሥራ አምስት ዓመት ካለፈ በኋላ፤ ከዘር
የወረደ ርስት ካልሆነ በቀር የተባለው የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን ተቀባይነት አያገኝም፡፡

ቊ 1001፡፡ (3) ውጤቶች፡፡

(1) ከሳሹ ባቀረበው የወራሽነት ጥያቄ ተከሳሹ የተረታ እንደሆነ፤ እጅ ያደረጋቸውን የወራሽነትን ንብረቶች ሁሉ ለከሳሹ መመለስ አለበት፡፡

(2) በቅን ልቡና ባለሀብት ሁኛለሁ በማለት ምክንያት ሊከራከር አይችልም፡፡

(3) ለቀረው ጒዳይ ሁሉ በዚህ ሕግ የተጻፉት አላገባብ መበልጸግን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይፈጸማሉ፡፡

ቊ 1002፡፡ (4) ልዩ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሰዎች፡፡


ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች የተነገሩት ድንጋጌዎች ልዩ የኑዛዜ ስጣታ ለተደረገላቸው ሰዎችም ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ ውርስ አስተዳደር፡፡
ቊ 1003፡፡ መሠረቱ፡፡
አጣሪው ከተመረጠበት ቀን ጀምሮ የወራሽነት ባለመብቶች ድርሻቸውን ወይም የሚደርሱዋቸውን ንብረቶች እስከተቀበሉ ድረስ የሟቹን
ንብረት ማስተዳደር አለበት፡፡
ቊ 1004፡፡ እሽግ፡፡

(1) በውርስ ንብረት ላይ ወይም በአንዳንዱ የወራሽነት ንብረቶች ላይ በማናቸውም ባለጒዳይ ጥያቄ ዳኞች ሟቹ እንደሞተ ወዲያውኑ እሽግ
እንዲደረግ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

(2) የማሸጉና እሽጉን የማንሣት ኪሣራ የሚታሰበው፤ እንዲታሸግልኝ ሲል ጥያቄ ባቀረበው ሰው ላይ ነው፡፡

ቊ 1005፡፡ የዕቃው ዝርዝር መዝገብ (1) በውርሱ ውስጥ ስለሚገኘው ንብረት፡፡

(1) አጣሪው የሟቹን መሞት በሚከተሉ አርባ ቀኖች ውስጥ በውርሱ የሚገኙትን ንብረቶች በአንድ የዕቃ ዝርዝር መዝገብ ውስጥ መጻፍ
አለበት፡፡

(2) አስፈላጊም ከሆነ አዳዲስ ንብረቶች ከተገኙበት ቀን አንሥቶ በዐሥራ አምስት ቀን ውስጥ በተጨማሪ በዝርዝር መዝገብ ላይ ይጻፋሉ፡፡

ቊ 1006፡፡ (2) የንብረቶቹ ግምት፡፡

(1) በውርስ ንብረት ወይም ለውርስ ዕዳ ለሆኑት እያንዳንዱ ጒዳዮች ከዚህ በላይ ባሉት ጊዜዎች ውስጥ፤ አጣሪው ለጊዜው የዋጋ ግምት
ይሰጣቸዋል፡፡

(2) አስፈላጊም ሲሆን ግምቱ በልዩ ዐዋቂዎች ረዳትነት ይደረጋል፡፡

ቊ 1007፡፡ (3) ወራሾቹ ያለባቸው ግዴታዎች፡፡

(1) በሟቹ ሞት ምክንያት የሚጠፉት መብቶችና ግዴታዎች እንደተጠበቁ ሁነው ወራሾቹ በውርሱ ባላቸው ግንኙነት ውስጥ በዚህ በሟቹ
ላይ የነበራቸውን መብቶችና ግዴታዎች እንደያዙ ይቈያሉ፡፡

(2) እነዚህ ወራሾች ስለተባሉት መብቶችና ግዴታዎች በዕቃ ዝርዝሩ መዝገብ እንዲረጋገጥ ለማድረግ አስፈላጊዎች የሆኑትን አስረጂዎች
ለአጣሪው ማስታወቅ አለባቸው፡፡

ቊ 1008፡፡ (4) ለባለጒዳዮቹ የሚደረግ ማስታወቂያ፡፡

(1) ከውርሱ አንድ ድርሻ ለማግኘት መብት ያላቸው ሰዎች ሁሉ በኪሣራቸው የዕቃው መዝገብ ዝርዝር ግልባጭ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ
ይችላሉ፡፡
(2) ይህን የተባለውን መብት ከሟቹ ላይ ወይም ከውርሱ ላይ ገንዘብ ጠያቂ ለሆኑት ሰዎች ዳኞች ሊሰጧቸው ይችላሉ፡፡

ቊ 1009፡፡ (5) ግምቱን እንደገና ስለ ማየት፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከቱት ሰዎች የውርሱ ሀብት የመጨረሻ ክፍያ እስከሚደረግ ድረስ ለጊዜው አጣሪው ያደረገው
የንብረቶቹ ግምት እንደገና እንዲታይ ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

(2) ይህ ለጊዜው የተደረገው ግምት ትክክለኛ አለመሆኑ የታወቀ እንደሆነ፤ ለልዩ ዐዋቂዎች የሚደረገው ወጪ የሚታሰበው በውርሱ ሀብት
ላይ ነው፡፡

(3) እንደገና መታየቱን ወራሾቹ ያልጠየቁ እንደሆነ ግን ወጪውን የሚችለው ግምቱን እንደገና ይታይልኝ ያለው ሰው ነው፡፡

ቊ 1010፡፡ የአጣሪው ጠቅላላ ሥልጣን፡፡

(1) አጣሪው እንደ መልካም የቤተሰብ አባት ሆኖ የውርሱን ንብረቶች በጥንቃቄ በትጋት ያስተዳድራል፡፡

(2) ወራሾቹ በስምምነት፤ ወይም ዳኞች፤ ማንኛውም ባለጒዳይ በሚያቀርበው ጥያቄ ስለዚሁ ስለ አስተዳደሩ ጒዳይ ለአጣሪው መሪ
ትእዛዝ ሉሰጡት ይችላሉ፡፡

ቊ 1011፡፡ የጥበቃ ተግባሮች፡፡


አጣሪው በተለይ ከዚህ እንደሚከተለው ለማድረግ ይችላል፡፡
(ሀ) የውርሱን ንብረቶች ሁሉ ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑትን ማከናወንና ክሶችን ማቅረብ፡፡

(ለ) በውርስ ንብረቶች ላይ መብት አለን ሲሉ ሦስተኛ ወገኖች የሚያቀርቡትን ክስ መከላከል፡፡

ቊ 1012፡፡ የውርሱ የገንዘብ መብቶች፡፡

(1) አጣሪው የመከፈያቸው ጊዜ ደርሶ እንደሆነ የውርሱ የገንዘብ መብት የሆኑትን ገንዘቦች ሁሉ እንዲከፈሉ መጠየቅ አለበት፡፡

(2) እነዚህንም እየተቀበለ የደረሰኝ ወረቀት ለመስጠት ሥልጣን አለው፡፡

ቊ 1013፡፡ የውርሱን ንብረቶች ስለ መሸጥ፡፡

(1) በቶሎ የሚበላሹ ወይም በጥበቃቸው ወይም ለማስቀመጣቸው ከፍ ያለ ወጪ ገንዘብ ወይም ልዩ ጥንቃቄ የሚጠይቁትን በውርሱ
ውስጥ የሚገኙትን ፍሬዎች ሰብሎች እንዲሁም የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሁሉ ለመሸጥ ይችላል፡፡

(2) አጣሪው የውርሱን ዕዳ ለመክፈል የግድ አስፈላጊ በሚሆንበት መጠን ካልሆነ በቀር ሌሎቹን ተንቀሳቃሾች ንብረቶች ለመሸጥ
አይችልም፡፡

(3) በወራሾቹ ሁሉ ስምምነት ወይም በዳኞች ፈቃድ ካልሆነ በቀር የማይንቀሳቀሱትን ንብረቶች ለመሸጥ አይችልም፡፡
ክፍል 4፡፡
የውርሱን ዕዳ ስለ መክፈል፡፡
ቊ 1014፡፡ የአከፋፈሉ ቅደም ተከተል፡፡
የውርሱ ዕዳዎች እንደሚከተለው ቅደም ተከተል ተራ ይከፈላሉ፡፡
(ሀ) በመጀመሪያ የሚከፈለው ለሥርዐተ ቀብሩ ወጪ የሆነው ገንዘብ፤

(ለ) ቀጥሎ የሚከፈለው ስለ ውርሱ አስተዳደርና ውርሱን ለማጣራት የተደረገው ወጪ፤

(ሐ) ሦስተኛ የሟቹን ዕዳዎች፤

(መ) አራተኛ የጡረታን ዕዳ፤

(ሠ) አምስተኛ ሟቹ ያደረጋቸውን ልዩ የኑዛዜ ስጦታዎች፡፡

ቊ 1015፡፡ ለሥርዐተ ቀብር ወጪ የሆነ ገንዘብ፡፡

(1) ሟቹ ይዞት የነበረው ማኅበራዊ ኑሮ ተገቢ መስሎ በሚታየው መጠን ካልሆነ በቀር የሥርዐተ ቀብሩ ወጪ ከሌሎቹ ዕዳዎች ቀደምትነት
አይሰጠውም፡፡

(2) ለሟቹ መታሰቢያ የሚደረገው ወጪ የተስካር ወጪ ለሥርዐተ ቀብሩ በወጣው ገንዘብ ውስጥ አይታሰብም፡፡

(3) ለሟቹ መታሰቢያ ማድረግ ለሚስቱ ወይም ለባል ወይም ለዘመዶቹ ሕጋዊ ግዴታ አይሆንባቸውም፡፡

ቊ 1016፡፡ ለወራሽነቱ አስተዳደር የተደረገው ወጪ፡፡


ውርሱን ለማስተዳደር ለማጣራት የሚደረጉት ወጪ ገንዘቦች እነዚህ ናቸው፡፡
(ሀ) ለማሸግ፤ የዕቃ ዝርዝር ለመጻፍና፤ ስለ ማጣራቱ ሒሳብ የወጣው ገንዘብ፤

(ለ) ስለ ውርሱ ንብረቶች ደንበኛ ጥበቃ አጠባበቅ መልካም አያያዝና አስተዳደር አጣሪው ያደረገው ጠቃሚ የሆነ ወጪ ገንዘብ፤
(ሐ) ለክፍያ የተደረገው ወጪና የውርሱን ንብረቶች ለወራሾቹ ለማስተላለፍ የተደረገው ወጪ፤

(መ) ለመንግሥት የሚከፈለውን የውርስ ማዛወሪያ ገንዘብ፤

ቊ 1017፡፡ የሟቹ ዕዳዎች (1) ገንዘብ ጠያቂዎችን ስለ መፈለግ፡፡

(1) በውርሱ ላይ የገንዘብ መጠየቂያ መብቶች ያላቸው ሰዎች እንዳሉ ለማወቅ አጣሪው የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡

(2) ስለዚህም ነገር የሟቹን መዝገቦችና ወረቀቶት ይመረምራል፡፡ እንዲሁም ሟቹ በኖረባቸው ስፍራዎች በሚገኙት የመንግሥት
መዝገቦችና የሟቹም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለበት ቦታዎች በሚገኙት መዝገቦች አስፈላጊውን ፍለጋ ያደርጋል፡፡

ቊ 1018፡፡ (2) ማስታወቂያ፡፡

(1) እነዚህ ፍለጋዎች ያልገለጹዋቸው ከሟቹ ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች እንዳሉ የሚያስገምት ነገር የተገኘ እንደሆነ አጣሪው ጠቃሚ መስሎ
በሚታየው ቦታ ላይ ለገንዘብ ጠያቂዎቹ ባለዕዳቸው መሞቱን የሚገልጽ ተገቢ የሆነ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡

(2) እነዚህም ገንዘብ ጠያቂዎች፤ ለርሱ እንዲያመለክቱ ያስተውቋቸዋል፡፡ ስለዚህም ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንሥቶ የሦስት ወር ጊዜ
ይወሰንላቸዋል፡፡
ቊ 1019፡፡ የመከፈያቸው ጊዜ የደረሰ ዕዳዎች፡፡

(1) ዕዳው እንዳይከፈል መቃወሚያ ካልቀረበ ወይም የውርሱ ጠቅላላ ሀብት ለባለዕዳዎቹ ሁሉ ተከፍሎ ሊደርስ ያለመቻሉ በግልጽ
ካልታወቀ በቀር የውርስ ሒሳብ አጣሪው ከውርሱ ላይ የሚጠየቁትን የመከፈያቸው ጊዜ የደረሰ ዕዳዎች ሁሉ ይከፍላል፡፡

(2) እነዚህ ሁለቱ ሁኔታዎች ባጋጠሙ ጊዜ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ላይ የተመለከቱትን የባለዕዳዎች የመክፈል ችሎታ ማጣት
ደንቦች መጠበቅ አለበት፡፡

ቊ 1020፡፡ ተፈጻሚነት ያለው ሰነድ፡፡

(1) በሟቹ ላይ ተፈጻሚነት ያላቸው ሰነዶች በአጣሪው ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) አጣሪው የውርሱን የንብረት ዝርዝር መዝገብ እስከሚያዘጋጅበት ጊዜ ድረስ የነዚህን ዕዳዎች መክፈል ለማዘግየት ይችላል፡፡

(3) ውርሱ እነዚህን ዕዳዎች ለመክፈል የሚችል መሆኑ ግልጽ ሆኖ የታየ እንደሆነ ማናቸውም ባለጒዳይ በሚያቀርበው ጥያቄ ደኞች ከዚህ
በላይ የተጠቀሰው ጊዜ ከመድረሱ በፊት የውርሱን ዕዳዎች ወይም አንዳንዶቹን ዕዳዎች እንዲከፍል አጣሪውን ለማስገደድ ይችላሉ፡፡

ቊ 1021፡፡ የመከፈያቸው ጊዜ ያልደረሱ ዕዳዎች፡፡

(1) ከውርሱ ሀብት ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸውና የመክፈያው ጊዜ ያልደረሰ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች የገንዘቡ መከፈያ ጊዜ
ሲደርስ ይህ ገንዘብ ሊከፈላቸው እንዲችል የማረጋገጫ ዋስትና እንዲሰጣቸው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተው ድንጋጌ ከውርሱ ላይ የውለታ ቃል ያለበት የገንዘብ መጠየቅ መብት ላላቸው
ሰዎችም ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 1022፡፡ ለዕዳው መክፈያ የሆኑ ንብረቶች (1) ጥሬ ገንዘብ፡፡


አጣሪው፤ የውርሱን ዕዳ ለመክፈል አስቀድሞ በውርሱ ንብረት ውስጥ የሚገኘውን ጥሬ ገንዘብ ያወጣል፡፡
ቊ 1023፡፡ (2) በኑዛዜ ያልተሰጡ ንብረቶች፡፡

(1) ዕዳዎቹን ለመክፈል ንብረቶቹን ለመሸጥ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ እነዚህን ንብረቶች ለሌላ ሰው ከመሸጡ በፊት አጣሪው ወራሾቹ
ለመግዛት የሚፈልጉ እንደሆነ መጠየቅ አለበት፡፡
(2) አንዱ ወራሽ በገበያው ዋጋ ወይም በበለጠ ዋጋ እገዛለሁ ያለ እንደሆነ አጣሪው ለዚሁ ወራሽ ንብረቶቹን መሸጥ አለበት፡፡

ቊ 1024፡፡ (3) በኑዛዜ የተሰጡ ንብረቶች፡፡


ሌሎችን ንብረቶች በመሸጥ ዕዳዎቹን ለመክፈል የሚቻል የሆነ እንደሆነ ሟቹ በኑዛዜ የሰጣቸውን ንብረቶች ለመሸጥ አይቻልም፡፡
ክፍል 5፡፡
ከውርሱ ላይ ስለሚጠየቀው የቀለብ ገንዘብ፡፡
ቊ 1025፡፡ መሠረቱ፡፡
የውርሱ አጣሪ፤ በኑዛዜ የተሰጡትን ስጦታዎች ከመክፈሉ አስቀድሞ አንዳንድ ሰዎች ይገባናል ሲሉ ለማረጋገጥ የሚችሉትን የቀለብ ገንዘብ
መክፈል አለበት፡፡

ቊ 1026፡፡ የቀለብ ገንዘብ (ጡረታ) ጠያቂዎችን መወሰን፡፡

(1) ከዚህ በታች በሚከተሉት ቊጥሮች በተወሰኑት ሁኔታዎች የቀለብ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች፤ የሟቹ ባል ወይም ሚስት ወይም ወደ ታች
የሚቈጠሩ ተወላጆች ወይም ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች ወይም ወንድሞችና እኅቶች ናቸው፡፡

(2) የውርሱ ንብረት ለመንግሥት የሚገባ በሆነ ጊዜ ሟቹ በሞተበት ጊዜ፤ ከርሱ ጋራ ይኖሩ የነበሩ ወይም እርሱ ያኖራቸው የነበሩ ሰዎች
ከዚህ በታች በሚከተሉት ቊጥሮች በተወሰኑት ሁኔታዎች እንደዚሁ ቀለብ የመጠየቅ መብት አላቸው፡፡

ቊ 1027፡፡ ለቀለብ ገንዘብ የመጠየቅ መብት አለመኖር፡፡


እነዚህ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተነገሩት ሰዎች በችግር ላይ ካልተገኙና ሠርተው ኑሩዋቸውን ለማሸነፍ የማይችሉ ካልሆኑ በቀር፤
የጡረታ ቀለብ ለመጠየቅ አይችሉም፡፡

ቊ 1028፡፡ የጡረታ ቀለብ ጠያቂው ያለ ኑዛዜ ወራሽነት ያለው ስለ መሆኑ፡፡

(1) ለሟቹ ወደ ታች ለሚቈጠሩ ተወላጆች ወይም ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች ወይም ለወንድሞችና ለእኅቶች የጡረታ ቀለብ
የሚሰጣቸው የሟቹን ውርስ ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በሕግ መሠረት የሚወርሱ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

(2) እነዚህ ሰዎች ሟቹን ለመውረስ የማይገባቸው ናቸው ተብለው ከውርሱ ተከልክለው እንደሆነ የጡረታ ቀለብ የማግኘት መብት
አይኖራቸውም፡፡

(3) እንደዚሁም በሕግ መሠረት ከነሱ ቅድሚያ በሚያገኙ ወራሾች ምክንያት ወራሽ መሆናቸው ቀርቶ እንደሆነ የቀለብ ማግኘት መብት
አይኖራቸውም፡፡
ቊ 1029፡፡ ከፍተኛ የጡረታ ቀለብ፡፡

(1) ወደታች የሚቈጠሩ ተወላጆች ወይም ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች ወይም ወንድሞችና እኅቶች ያላቸው የጡረታ ቀለብ የመጠየቅ
መብት ሟቹ እነሱን የሚጎዳ የኑዛዜ ቃል ባያደርግ ኑሮ በሕግ መሠረት ከውርሱ ለማግኘት በሚችሉት ንብረት ዋጋ ልክ ለማግኘት
የመጠየቅ መብት ነው፡፡

(2) ሟቹ ከመሞቱ በፊት ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ ያደረጋቸው ችሮታዎች በኑዛዜ ቃል እንደተሰጡ ይቈጠራሉ፡፡

ቊ 1030፡፡ ለባልና ሚስቱ የሚከፈል የጡረታ ገንዘብ፡፡


በዚህ ሕግ ሰለ ሥጋ ዝምድናና ስለ ጋብቻ ዝምድና በተጻፈው አንቀጽ ውስጥ ቀለብ መኖ የመስጠት ግዴታ በሚለው ምዕራፍ በተሠራው
ደንብ መሠረት ከውርሱ ውስጥ ባል ወይም ሚስት ለቀብ የማግኘት መብት አላቸው፡፡

ቊ 1031፡፡ የቀለብ ገንዘብ ጠያቂው ስለሚያቀርበው ጥያቄ፡፡


(1) የቀለብ ገንዘብ ለማግኘት የሚደረገው ጥያቄ የውርሱ ሀብት ከመከፋፈሉ በፊት ለአጣሪው መቅረብ አለበት፡፡

(2) አስቸኳይ በሆነ ጊዜ አጣሪው ለባለጒዳዮቹ ለጊዜው የቀለብ ገንዘብ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡

(3) አጣሪው የቀለብ ገንዘብን ጥያቄ አልቀበልም ያለ እንደሆነ በዚህ ውሳኔው ወዲያውኑ ለዳኞች አቤቱታ ሊቀርብበት ይችላል፡፡

ቊ 1032፡፡ የቀለብ ገንዘብ አከፋፈል፡፡

(1) ቀለብ ተቀባይ የሟቹ ባል ወይም ሚስት የሆነ እንደሆነ፤ ወይም ተቀባዩ እጅግ ሲያንስ የስልሳ ዓመት ዕድሜ ያለው የሆነ እንደሆነ
የቀለቡ አከፋፈል እስከ ዕድሜው ልክ ድረስ ቀለብ በመስጠት ነው፡፡

(2) በሌሎች ሁኔታዎች ጊዜ ቀለብ መከፈሉ የሚፈጸመው ለቀለብ ተቀባዩ የተወሰነ ገንዘብ በመስጠት ነው፡፡

ቊ 1033፡፡ ጡረታ (1) የጡረታውን ገንዘብ መክፈልና ለዚሁ የሚሰጥ ዋስትና፡፡

(1) ጡረታ የተፈቀደ እንደሆነ ሟቹ ከሞተበት ቀን አንሥቶ የሚከፈል ይሆናል፡፡

(2) የጡረታውም ተከፋይ የሆነው ገንዘብ በተጠዋሪው መኖሪያ ቤት የሚከፈል ይሆናል፡፡

(3) አስፈላጊ ሲሆን ዳኞች ስለ ጡረታው መከፈል ከፋዩ ዋስትና እንዲሰጠው ያደርጋሉ፡፡

ቊ 1034፡፡ (2) ማሻሻል፡፡

(1) የጡረታው ገንዘብ ልክ የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ይቈረጣል፡፡

(2) በውርሱ ውስጥ ያለው ንብረት በተገመገመ ጊዜ በስሕተት የተደረገ ሆኖ ካልተገኘ በቀር የጡረታው ገንዘብ እንደገና ሊሻሻል
አይቻልም፡፡
(3) በሕይወት ላለው የሟቹ ባል ወይም ሚስት የተሰጠው የጡረታ ገንዘብ እንደገና ያገባ እንደሆነ ቀሪ ይሆናል፡፡

ቊ 1035፡፡ (3) ለጡረታ ተከፋይ የሆኑ ገንዘቦች፡፡

(1) ለጡረታ ተከፋይ የሆኑ ገንዘቦች የማይተላለፉና የማይያዙ ናቸው፡፡

(2) ይህም ስለተባለ፤ እነዚሁ ለጡረታ ተከፋይ የሆኑ ገንዘቦች የመከፈያቸው ጊዜ ከመድረሱ አስቀድሞ ቢሆንም እንኳ በጡረታው
ተጠቃሚዎች ለሆኑ ሰዎች ችግር አስፈላጊውን ለሚሰጡ የመረዳጃ ማኅበር ድርጅቶች እንዲተላለፉ ለማድረግ ይቻላል፡፡

(3) እንዲሁም በጡረታው ተጠቃሚ ለሆነው ሰው ለኑሮው አስፈላጊ የሆነውን የከፈሉት ሰዎች ለጡረታ ተከፋይ የሆኑትን ገንዘቦች
ለመያዝ ይችላሉ፡፡

ቊ 1036፡፡ የቀለብ ገንዘብ የሚመለከት ስምምነት፡፡

(1) ሟቹ በሕይወቱ ሳለ ከርሱ ውርስ ላይ ያገኛሉ ተብለው በታሰቡት የጡረታ ገንዘቦች ላይ የሚደረጉት ውሎች ወይም ጽሑፎች ፍርስ
ናቸው፡፡

(2) እንደዚሁም በዚህ ክፍል የተጻፉትን ደንቦች ለማስቀረት ወይም ለማሻሻል በማሰብ የተደረጉ የኑዛዜ ቃሎች ሁሉ አይጸኑም፡፡
ክፍል 7፡፡
የኑዛዜ ስጦታዎችን ስለ መክፈል፡፡
ቊ 1037፡፡ መሠረቱ፡፡
ሟቹ በኑዛዜ የሰጣቸውን ስጦታዎች በኑዛዜው ከወራሾቹ አንዱ እንዲከፍል ካላደረገ በቀር አጣሪው ሟቹ በኑዛዜው የሰጣቸውን ስጦታዎች
መክፈል አለበት፡፡
ቊ 1038፡፡ በኑዛዜው ስጦታ የተሰጠው ሰው ምርጫ፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ሁለት ቊጥሮች እንደተጠበቁ ሆነው ስለወራሾች ወይም ጠቅላላ የኑዛዜው ስጦታ ለተሰጣቸው ሰዎች ምርጫ ጒዳይ
በዚህ አንቀጽ የተጻፉ ውሳኔዎች ልዩ የኑዛዜውን ስጦታ የተደረገላቸው ሰዎች ይህንኑ ስጦታ ለመቀበል ወይም አልፈልግም ለማለትም
ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡

ቊ 1039፡፡ ብዙ የኑዛዜ ስጦታዎች፡፡


ለአንድ ሰው በኑዛዜ ልዩ ልዩ የሆነ ብዙ ስጦታ እንዲቀበል የታዘዘለት እንደሆነ ከነዚሁ ከኑዛዜ ስጦታዎች አንዱን ለመቀበል ሌላውን
አልፈልግም ለማለት ይችላል፡፡

ቊ 1040፡፡ የአልፈልግም የማለቱ ውጤቶች፡፡


የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ስጦታውን አልፈልግም ያለ እንደሆነ፤ በኑዛዜው የታዘዘውን ነገር እንዲያስፈጽም በአደራ የተቀበለ ሰው
ተጥሎበት ለነበረ ሰው ጥቅም ይሆናል፡፡

ቊ 1041፡፡ የመከፈያው ጊዜ፡፡


በኑዛዜው የተሰጡትን ስጦታዎች ውርሱ ለመክፈል በቂ ሆኖ እንደታየ የሚከፈል ይሆናል፡፡
ቊ 1042፡፡ በኑዛዜው የተሰጡትን ስጦታዎች መቀነስ፡፡

(1) ውርሱ በኑዛዜው የተሰጡትን ስጦታዎች ሁሉ ለመክፈል በቂ ያልሆነ እንደሆነ ለአከፋፈሉ ሟቹ በኑዛዜው ውስጥ የገለጸው ተራ
ይጠበቃል፡፡

(2) በኑዛዜው ወይም በግልጽ የተነገረ ቃል የሌለ እንደሆነ፤ በኑዛዜው ወይም ሟቹ በጻፈው ሌላ ጽሑፍ ውስጥ የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት
ሰው ላደረገው የአገልግሎት ዋጋ የተሰጡ ናቸው ተብሎ የተመለከቱት የኑዛዜ ስጦታዎች በቅድሚያ ይከፈላሉ፡፡

(3) ሌሎቹ በኑዛዜው የተደረጉ ስጦታዎች ባላቸው ግምት መጠን የሚቀነሱ ይሆናሉ፡፡

ቊ 1043፡፡ በኑዛዜ የተሰጠ የተለየ ነገር፡፡

(1) የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው የተሰጠውን ንብረት በሚገኝበት ሁኔታ እንዳለ የዚሁ ንብረት ተጨማሪ ከሆኑት ነገሮች ጋራ አጣሪው
ያስረክባል፡፡

(2) የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው በኑዛዜ የተሰጠው ነገር በመልካም ሁኔታ ሆኖ ይሰጠኝ ብሎ ለማስገደድ አይችልም፡፡

ቊ 1044፡፡ በዐይነት ብቻ የተነገረ የኑዛዜ ስጦታ፡፡

(1) ዐይነቱ ብቻ የተነገረ የኑዛዜ ስጦታ የሆነ እንደሆነ የተናዛዡ ገንዘብ ከሆኑት ያንኑ ዐይነት ንብረቶች ውስጥ በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት
ሰው የመረጠውን ለመውሰድ ይችላል፡፡

(2) የኑዛዜው ስጦታ የተነገረላቸው ብዙ ሰዎች አንድ ዐይነት ከሆኑ ነገሮች ውስጥ በኑዛዜ የታዘዘላቸውን ለመምረጥ የተጠሩ እንደሆነ
ስለሚያደርጉት የምርጫ ቀዳሚነት ዕጣ ይጣላል፡፡

(3) በውርሱ ውስጥ በኑዛዜ የተሰጠው ንብረት ዐይነት ያልተገኘ እንደሆነ ኑዛዜ የተነገረለት ሰው እንደፈቀደ፤ የኑዛዜ ሒሳብ አጣሪው
በዐይነት መካከለኛ የሆነውን ንብረት እንዲሰጠው ወይም የእንደዚህ ያለውን ንብረት ግምት እንዲከፍለው ኑዛዜ አስፈጻሚውን ለመጠየቅ
ይችላል፡፡

ቊ 1045፡፡ በመያዣ የተሰጠውን ነገር በኑዛዜ መስጠት፡፡

(1) በኑዛዜ የተሰጠው ንብረት ሟቹ በሚንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የአስያዘው ንብረተ የሆነ እንደሆነ
የዕዳው መከፈያ ጊዜ ሲደርስ የተሰጠውን ስጦታ እንዲያገኝ መድን የሚሆን ማረጋገጫ ይሰጠዋል፡፡
(2) በመያዣ ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ዋስትና የተሰጠበትን ዕዳ የመክፈያው ጊዜ ሲደርስ በኑዛዜ የተሰጠው ሰው የከፈለ
እንደሆነ፤ በተከፈለው ገንዘብ ጠያቂ ተተክቶ በሟቹ ወራሾች ላይ ገንዘብ ጠያቂ የነበረው መብት ይኖረዋል፡፡

ቊ 1046፡፡ የሌላ ሰው ገንዘብ በኑዛዜ ስለ መስጠት፤ (1) የዐይነት ነገሮች፡፡


ሟቹ በዐይነት የሚሰጥ ዕቃ ተናዞ በሞተበት ጊዜ የዚሁ ዕቃ ዐይነት በውርሱ ውስጥ ያልተገኘ እንደሆነ፤ አጣሪው የኑዛዜ ስጦታ
ለተደረገለት ሰው፤ ግምቱን መክፈል አለበት፡፡

ቊ 1047፡፡ (2) የተለያዩ ነገሮች፡፡

(1) በኑዛዜው የተደረገው ስጦታ በተለየ ነገር እንደሆነና ሟቹ በሞተበት ቀን በዚሁ ነገር ላይ አንዳችም መብት የሌለው እንደሆነ የኑዛዜው
ስጦታ ፍርስ ነው፡፡

(2) ስለሆነም፤ ሟቹ ይህን ሁኔታ እያወቀ በኑዛዜው ሰጥቶ እንደሆነ፤ ስጦታው ዋጋ ያለው ይሆናል፡፡

(3) እንደዚህ በሆነ ጊዜ፤ አጣሪው በኑዛዜ የተሰጠውን ዕቃ ዋጋ መስጠት አለበት፡፡

ቊ 1048፡፡ የገንዘብ መብትን በኑዛዜ ስጦታ ስለ ማድረግ፡፡

(1) የገንዘብ መብት በኑዛዜ ስጦታ የተደረገ እንደሆነ ሟቹ በሞተበት ቀን ባለው የገንዘብ መብት መጠን ስጦታው ውጤት ይኖረዋል፡፡

(2) አጣሪው በኑዛዜ የተነገረውን ግዴታ የኑዛዜው ስጦታ ለተደረገለት ሰው ስጦታው የሚገኝበትን የገንዘብ መብት ማስረጃ በመስጠት
ግዴታውን ይፈጽማል፡፡

(3) ውርሱ የገንዘቡ መብት ለመከፈሉ መድንነት የለበትም፡፡

ቊ 1049፡፡ በየጊዜው የሚከፈል በኑዛዜ የተደረገ ስጦታ (ጡረታ)፡፡


ሟቹ ካንድ ነገር የሚገኘውን ገንዘብ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ የሚከፈለው ገንዘብ የሚታሰበው ተናዛዡ ከሞተበት ቀን አንሥቶ ነው፡፡
ቊ 1050፡፡ ፍሬዎችና ወለዶች፡፡
(1) አንድ የተለየ ነገር በኑዛዜ የተሰጠ እንደሆነ የሚያፈራው ፍሬ የሚታሰበው ተናዛዡ ከሞተበት አንሥቶ ነው፡፡

(2) በኑዛዜ የተሰጠው ጥሬ ገንዘብ እንደሆነ፤ የዚህ የገንዘብ ወለድ በሕጋዊው ወለድ ልክ የሚታሰበው አጣሪው ይህን ገንዘብ እንዲከፍል
ማስጠንቀቂያ ከደረሰው ቀን አንሥቶ ነው፡፡

ቊ 1051፡፡ የማስረከቢያ ወጪ፡፡


በኑዛዜ የተሰጠውን ነገር ለማስረከብ የሚደረገው ወጪ ገንዘብ የሚታሰበው በውርሱ ላይ ነው፡፡
ክፍል 7፡፡
ስለ ውርሱ መዘጋት፡፡
ቊ 1052፡፡ የውርሱ መዝጊያ ጊዜ፡፡

(1) የውርሱ የሒሳብ ማጣራት ሥራ ሟቹ ከሞተ ከአንድ ዓመት በኋላ ይዘጋል፡፡

(2) የነገሩ አካባቢ ሁኔታ የሚያስገድድ በሆነ ጊዜ ሒሳብ አጣሪው ወይም ከባለጒዳዮቹ አንዱ ጥያቄ ሲያቀርብ ዳኞች ይህን የጊዜ ውሳኔ
ሊያራዝሙት ይችላሉ፡፡

ቊ 1053፡፡ የንብረቶች መቀላቀል፡፡

(1) የውርሱ ሒሳብ ማጣራት በተዘጋ ጊዜ ከውርሱ ውስጥ ሆኖ የሚገኘው ንብረት ከሌላው ከወራሹ ንብረት ጋራ ይቀላቀላል፡፡

(2 ) የጋራ ወራሾችም እንዳሉ የውርሱ ሆኖ የሚገኘው ንብረት የጋራ ወራሾች ንብረት ይሆናል፡፡
ቊ 1054፡፡ አዲስ ገንዘብ ጠያቂዎች ስለ መቅረባቸው፡፡

(1) የውርሱ ሒሳብ ማጣራት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ ከውርሱ ላይ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ገንዘባቸውን ወራሹ እንዲከፍላቸው መጠየቅ
ይችላሉ፡፡
(2) ስለሆነም ከውርሱ ላይ ገንዘብ የሚጠይቁት ሰዎች የወራሹ የራሱ ባለዕዳዎች ከሆኑት ሰዎች ጋራ ስላለው ግንኙነት ወራሹ ከውርሱ
ባገኘው ንብረት ላይ የቀደምትነት ልዩ መብት የላቸውም፡፡

(3) ወራሹ በውርስ ካገኘው ሀብት የበለጠ ገንዘብ ከውርሱ ላይ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ላላቸው ሰዎች እንዲከፍል አይገደድም፡፡

ቊ 1055፡፡ በግምት ውስጥ የሚገባ የድርሻ ዋጋ፡፡

(1) ገንዘብ ጠያቂዎች ተቃራኒ የሆነ ማስረጃ ካላቀረቡ በቀር በውርሱ ውስጥ የሚገኙት ሀብቶችና የነዚህም ሀብቶች ዋጋ በዕቃው ዝርዝር
መዝገብና በመከፋፈያው ጽሑፍ ውስጥ እንደተመለከተው ነው ተብሎ ይገመታል፡፡

(2) የዕቃ ዝርዝር መዝገብ አልተደረገ እንደሆነ ወይም ይህንኑ ጽሑፎች ለማቅረብ ያልተቻለ እንደሆነ የንብረቶቹን ብዛትና ግምት ገንዘብ
ጠያቂዎቹ በማናቸውም ማስረጃ ለማስረዳት ይችላሉ፡፡

ቊ 1056፡፡ የመደበቅ ሁኔታ፡፡

(1) የአንድ ንብረትን ግምት ስለሚመለከት ጒዳይ፤ ገንዘብ ጠያቂው ይህ ንብረት በውርሱ ውስጥ የነበረ ለመሆኑ በወራሾቹ ለማስረዳት
የቻለ እንደሆነ እርሱ የሚለው ግምት የታመነ ይሆናል፡፡

(2) ይህም በሆነ ጊዜ ገንዘብ ጠያቂው ያቀረበው ግምት በቅን ልቡና ለመሆኑ እንደሚል ወራሾቹ የጠየቁ እንደሆነ መማል አለበት፡፡

ቊ 1057፡፡ የዕቃው መጥፋት፡፡


የውርሱ መጣራት ከተዘጋ በኋላ ደርሷል በሚለው ምክንያቶች የደረሰው ንብረት ዋጋ ተቀንሷል ወይም ጠፍቷል በማለት ከግዴታው ነጻ
ሊሆን አይችልም፡፡

ቊ 1058፡፡ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች ግዴታ፡፡

(1) የውርሱ ሒሳብ ማጣራት ሥራ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ ከውርሱ ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች፤ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ
የተሰጣቸውን ሰዎች፤ ከውርሱ በስጦታ በደረሳቸው ንብረት መጠን ካልሆነ ዕዳ እንዲከፍሉ ሊጠይቋቸው አይችሉም፡፡

(2) ወራሹ የማይከፍል ካልሆነ በቀር የኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ከውርሱ ላይ ገንዘብ የመጠየቅ መብት ላለው ሰው መክፈል
የለበትም፡፡

(3) በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በተባለው አንቀጽ ውስጥ በተመለከተው መሠረት ዋስ የሆነ ሰው በሚከራከርባቸውም መብቶች
በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው የከሰሰውን ገንዘብ ጠያቂ ሊከራከርባቸው ይችላል፡፡

ቊ 1059፡፡ በኑዛዜ ስጦታ የተደረገለት ሰው ስለሚያቀርበው ክስ፡፡

(1) የውርሱን ዕዳ የከፈለ ልዩ ኑዛዜ ስጦታ ተቀባይ የሆነ ሰው ስለከፈለው ዕዳ በገንዘብ ጠያቂው መብት ተተክቶ ወራሾቹን ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
(2) ከሌሎቹ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ ተቀባዮች ላይ ግን ለመጠየቅ መብት የለውም፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ውርስ ክፍያ፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ ውርሱ አለመነጣጠልና ለውርስ ክፍያ ስለሚቀርብ ጥያቄ፡፡
ቊ 1060፡፡ ስለ ውርሱ አለመነጣጠል፡፡

(1) የውርሱ አከፋፈል እስኪፈጸም ድረስ በወራሾቹ መካከል ውርሱ ሳይነጣጠል ይቈያል፡፡

(2) የጋራ ወራሾች የሆኑ ሰዎች ባልተከፋፈሉት የውርስ ንብረቶች ላይ ያላቸው መብት በዚህ ሕግ ስለ የጋራ ባለሀብትነት ስለ ሪምና ስለ
ሌሎች ግዙፍ መብቶች የሚለው አንቀጽ በተነገሩት ድንጋጌዎች መሠረት ይወስናል፡፡

(3) የውርስ ሀብት አጣሪነትን የሚመለከቱ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተነገሩት ድንጋጌዎች እና ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ድንጋጌዎች
እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1061፡፡ የልዩ ንብረቶች መሸጥ ወይም ክፍያ፡፡


የማይነጣጠለው የጋራ ወራሾች ንብረት ክፍል የሆነውን ልዩ ንብረት በሐራጅ እንዲሸጥ ወይም እንዲከፋፈሉት ለማስገደድ አይችሉም፡፡
ቊ 1062፡፡ የክፍያው ጊዜ፡፡
ውርሱ በተጣራ ጊዜ፤ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን እያንዳንዱ የጋራ ወራሾች ውርሱን እንከፋፈል ብለው ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡
ቊ 1063፡፡ ውርሱን ለመከፋፈል የታዘዘ ጊዜ፡፡

(1) ውርሱን ለመከፋፈል የቀረበው ጥያቄ የተደረገው በማይስማማ ጊዜ እንደሆነ፤ ዳኞች ከሁለት ዓመት ሊበልጥ እስከማይችል ጊዜ ድረስ
ውርሱ ሳይነጣጠል እንዲቈይ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

(2) የውርሱ መከፋፈል የተፀነሰው ልጅ መወለድን ሁኔታ የሚጠብቅ የሆነ እንደሆነ ዳኞቹ ካልፈቀዱ በቀር ውርሱ ሳይነጣጠል መቈየት
አለበት፡፡

(3) እንዲህ ያለው ነገር ባጋጠመ ጊዜ፤ ዳኞቹ አስፈላጊ ሲሆን፤ የውርሱን ንብረቶች ሁሉ ወይም አንዳንድ ንብረቶችን የሚያስተዳድር አንድ
ሰው ይመርጣሉ፡፡

ቊ 1064፡፡ ውርሱን ስለ አለመነጣጠል የሚደረግ ስምምነት፡፡

(1) የውርሱ መከፋፈል እንዲፈጸም ለመጠየቅ የጋራ ወራሾች ያላቸው መብት ሟቹ በኑዛዜው ወይም የጋራ ወራሾቹ በመካከላቸው
በሚያደርጉት ውል ሊወገድ ይቻላል፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተው የውል ቃል ለአምስት ዓመት ወይም በተባለው የውል ቃል የተመለከተው አጭር ጊዜ
ካልሆነ በቀር ውጤት የለውም፡፡

(3) የኑዛዜው ወይም የውሉ ቃል የተወሰነውን ጊዜ ያላመለከተ እንደሆነ ወይም ከአምስት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ
በአምስቱ ዓመት መጨረሻ ወዳቂ ይሆናል፡፡
ክፍል 2፡፡
የጋራ ወራሾች ስለሚመልሱት ንብረቶች፡፡
ቊ 1065፡፡ የተመላሽነቱ መሠረት፡፡
ውርሱን የሚቀበለው የሟቹ ወደ ታች የሚቈጠር ተወላጅ የሆነ ሰው መመለስ የለብህም ተብሎ ከሟቹ ያገኘው ችሮታ ካለሆነ በቀር
ተቀብሎት የነበረውን ዋጋውን ከውርሱ ውስጥ መልሶ ማግባት አለበት፡፡

ቊ 1066፡፡ የሚመለሱትን ስጦታዎች መለየት፡፡

(1) በውርሱ ውስጥ ተመልሶ መግባት የሚገባው ነገር ከጋራ ወራሾቹ የአንዱን ለትዳሩ ማቋቋሚያ ወይም የዚህኑ የጋራ ወራሽ የሆነውን
ሰው ዕዳ መክፈያ እንዲሆነው የተሰጠው ነገር ነው፡፡

(2) ከጋራ ወራሾቹ ለአንዱ አስቀድሞ የተሰጠው የማጫ ገንዘብ ዋጋ መመለስ አለበት (ይቈጠርበታል)፡፡
(3) ከጋራ ወራሾቹ ለአንዱ ለመማሪያው ሟቹ ያደረገው ወጪ መመለስ የለበትም (አይቈጠርበትም)

ቊ 1067፡፡ ከመመለሱ ነጻ ስለ መሆን፡፡

(1) ሟቹ ለወራሽ ያደረገለት ችሮታዎች በእልቅናና ከሚደርሰው ውጭ በማድረግ ወይም የተቀበለውን እንዳይመልስ (እንዳይቈጠርበት) ነጻ
በማድረግ እንደሆነ የተባለው ወራሽ አስቀድሞ የወሰደውን ንብረት መመለስ የለበትም፡፡

(2) የቁም ስጦታ በሆነ ጊዜ ይህን፤ አሳብ ለማረጋገጥ አንድ ግልጽ የሆነ የውል ቃል አስፈላጊ ነው፡፡

(3) የኑዛዜ ስጦታ በሆነ ጊዜ ሟቹ ለወራሹ የሰጠውን ነገር እንዳይመልስ ነጻ በማድረግ ነው ብሎ ለማረጋገጥ በማናቸውም ዐይነት ማስረጃ
ለማስረዳት ይቻላል፡፡

ቊ 1068፡፡ ከአንድ ነገር የሚገኝ ጥቅም ወይም የአሱራንስ ገንዘብ፡፡

(1) ሟቹ ለወራሹ ካንድ ነገር ከሚያገኘው ገቢ ላይ ችሮታ ያደርገለት እንደሆነ፤ መመለስ የለበትም፡፡

(2) እንዲሁም ሟቹ ለወራሹ ጥቅም የከፈለውን የአሱራንስ ዋጋ መመለስ የለበትም፡፡

ቊ 1069፡፡ ቀጥታ ያልሆነ ጥቅም፡፡


ወራሹ ከሟቹ ጋራ ባደረጋቸው ስምምነቶች ወይም የማኅበረተኛነት ውል ያገኛቸውን ትርፎች ወደ ውርሱ መልሶ ማግባት የለበትም፡፡
ቊ 1070፡፡ ገንዘቡን መልሶ በውርሱ ውስጥ ማግባት ያለበት ሰው፡፡

(1) አስቀድሞ የተወሰደውን ንብረት ሊመልስ የሚገባው ወደ ታች የሚቈጠር የሟች ተወላጅ ብቻ ነው፡፡

(2) እንዲሁም ሌሎቹ ወራሾች የወሰዱትን እንዲመልሱ ሟቹ ግዴታ ሊያደርግባቸው ይችላል፡፡

ቊ 1071፡፡ ወራሽ የሆነው ሰው፡፡


ችሮታው በተደረገለት ቀን የሟቹ ወራሽ ነው ተብሎ የማይገመት የሆነ ቢሆንም እንኳ ወራሹ አስቀድሞ የወሰደውን መመለስ አለበት፡፡
ቊ 1072፡፡ ምትክነት፡፡

(1) ማንም ሰው ለሌላ ሰው ምትክ በመሆን ለወራሽነት የመጣ እንደሆነ፤ እርሱ ራሱ የተቀበላቸውን ስጦታዎች በውርሱ ውስጥ መመለስ
አለበት፡፡
(2) እንዲሁም ምትክ የሆነ ሰው የተተካለት ሰው አስቀድሞ ከሟቹ የተቀበላቸውን ችሮታዎች በውርሱ ውስጥ መመለስ አለበት፡፡

ቊ 1073፡፡ ወራሽነትን አልቀበልም ባይ፡፡


ውርሱን አልቀበልም ያለ ወራሽ ከሟቹ አስቀድሞ የወሰደውን ነገር በውርሱ ውስጥ መልሶ ማግባት የለበትም፡፡
ቊ 1074፡፡ መመለሱ ያለው ውጤት፡፡

(1) የጋራ ወራሾች የሚከፋፈሉትን ጠቅላላውን የሟቹን ንብረት ለመመደብ፤ ሟቹ በተዋቸው ንብረቶች ላይ፤ በውርሱ ውስጥ መመለስ
ያለባቸውን ሟቹ በቁም ወይም በኑዛዜ የሰጣቸው ንብረቶች ዋጋ የሚጨመር ይሆናል፡፡

(2) አንድ የጋራ ወራሽ አስቀድሞ የወሰደውን ንብረት መመለስ የለበት እንደሆነ፤ ሊመልሰው እስከሚገባው ድረስ ያለውን ግምት
አስቀድሞ ከድርሻው ላይ እንደተቀበለ ይቈጠራል፡፡

ቊ 1075፡፡ በጋራ ወራሾች መካከል የገንዘብ መመለስ ስላለው ወሰን፡፡

(1) አስቀድሞ የተወሰደውን ንብረት መመለስ፤ የወራሽነቱን ሀብት ክፍያና፤ ስለዚህም ጒዳይ በጋራ ወራሾቹ መካከል ያሉትን ግንኙነቶች
በሚመለከት ነገር ካልሆነ በቀር አንዳችም ውጤት የለውም፡፡
(2) ከውርሱ ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች ወይም የኑዛዜ ስጦታ የተነገረላቸው ሰዎች ወራሹ አስቀድሞ የተቀበለውን መመለስ አለበት ብለው
ሊከራከሩ አይችሉም፡፡

ቊ 1076፡፡ የገንዘብ መመለሱ አነስተኛ ገንዘብ በመውሰድ ስለሚፈጸም፡፡

(1) አስቀድሞ የተወሰደው ነገር በውርሱ ውስጥ የሚመለሰው ከድርሻው ላይ በመቀነስ ነው፡፡

(2) ወራሽ የሆነው ሰው፤ በውርሱ ውስጥ ከሚደርሰው ድርሻ ግምት በላይ በማናቸውም ጊዜ አስቀድሞ የወሰደውን ንብረት ለመመለስ
አይገደድም፡፡

(3) አስቀድሞ የተወሰዱት ንብረቶች በዐይነታቸው እንዲመለሱ ተብሎ ሟቹ ከመሞቱ በፊት የውል ቃል ለማግባት አይፈቀድም፡፡

ቊ 1077፡፡ የሚመለሰው ንብረት ግምት፡፡

(1) ሊመለስ የሚገባው አስቀድሞ የተወሰደው ንብረት ግምት፤ ሰነድ ላይ የተሰጠው ግምት ነው፡፡

(2) የዚህ ዐይነት ግምት አልተደረገ እንደሆነ ስጦታው በተደረገ ጊዜ በነበረው ግምት መሠረት መመለስ ያስፈልጋል፡፡

ቊ 1078፡፡ አስቀድሞ የተሰጠው ንብረት መጥፋት፡፡


ወራሹ አስቀድሞ የወሰዳቸው ንብረቶች ቢጠፉና በተደረገለትም ስጦታ መበልጸጉ ያቋረጠ ቢሆንም እንኳ ንብረቶቹን በውርሱ ውስጥ
መልሶ ማግባት አለበት፡፡
ክፍል 3፡፡
የመከፋፈሉ አሠራር፡፡
ቊ 1079፡፡ ክፍያው በማን እንደሚደረግ፡፡

(1) የክፍያው ሥራ የሚፈጸመው፤ በወራሾቹ መካከል በሚደረገው ስምምነት ነው፡፡

(2) ወራሾቹ ያልተስማሙ እንደሆነ ከነርሱ መካከል አንዱ ተግቶ ያሰናዳው የክፍያ ሐሳብ እንዲጸድቅ ለዳኞች ይቀርባል፡፡

ቊ 1080፡፡ ዳኞቹ የሚያደርጉት ማጽደቅ፡፡ (1) ለአንድ ወራሽ የሚደረገው ጥበቃ፡፡

(1) ከወራሾቹ አንዱ ሳይኖር የቀረ ወይም በሚገባ ወኪል ያላደረገ እንደሆነ፤ ክፍያውን ዳኞች ካላጸደቁት ፈራሽ ነው፡፡

(2) ስለሆነም እንዲህ በሆነ ጊዜ የክፍያውን ፈራሽነት ለመጠየቅ የሚችለው እርሱ ሳይኖር ክፍያው የተፈጸመበት ወራሽ ብቻ ነው፡፡

(3) ይኸውም የክፍያው ፈራሽነት፤ ጠያቂው ክፍያውን ካወቀ በኋላ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በማናቸውም አሳብ ሲሆን ሟቹ
ከሞተበት ቀን አንሥቶ በሚቈጠር በዐሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በቀር ጥያቄው ውድቅ ይሆናል፡፡

ቊ 1081፡፡ (2) ለገንዘብ ጠያቂዎች የሚደረግ ጥበቃ፡፡

(1) እንዲሁም፤ በጋራ ወራሾቹ መካከል የሚደረገው የውርሱ ሀብት ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት ከጋራ ወራሾቹ ከአንዱ ላይ ገንዘብ ጠያቂ የሆነ
ሰው የጠየቀ እንደሆነ፤ የውርሱን ክፍያ ዳኞቹ እንዲያጸድቁት ያስፈልጋል፡፡

(2) ይህን ጥያቄ የሚያቀርበው ገንዘብ ጠያቂ የክፍያው ሥነ ሥርዐት ማጽደቅ በሚከናወንበት ጊዜ የሚያመለክተው ነገር መሰማት
አለበት፡፡
(3) የጋራ ወራሾች ባደረጉት የማጭበርበር ሥራ ምክንያት ዳኞቹ ጥያቄውን አናጸድቅም ሲሉ እንቢ ካላሉ በቀር፤ ስለ ሥርዐት የሚወጣው
ገንዘብ የሚታሰበው ጥያቄውን ባቀረበው ገንዘብ ጠያቂው ላይ ነው፡፡

ቊ 1082፡፡ የመከፋፈሉ አፈጻጸም ደንብ፡፡

(1) ክፍያው የሚፈጸመው፤ ሟቹ በጻፈው የኑዛዜ ቃል መሠረት ነው፡፡


(2) ስለ ክፍያው አፈጻጸም የተጻፈ የኑዛዜ ቃል የሌለ እንደሆነ፤ ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ድንጋጌዎች መሠረት ይፈጸማል፡፡

ቊ 1083፡፡ የንብረቶቹ ግምት (1) መሠረቱ፡፡

(1) በወራሾቹ ድርሻ የተመደቡት ንብረቶች፤ ክፍያው በሚደረግበት ቀን ይገመታሉ፡፡

(2) የንብረቶቹን ግምት የሚያደርጉት ራሳቸው ወራሾቹ ናቸው፡፡

(3) ወራሾቹ በግምቱ ያልተስማሙ እንደሆነ ግምቱ እነሱ በመረጧቸው የሽምግልና ዳኞች ግምቱ ይደረጋል፡፡

ቊ 1084፡፡ (2) ልዩ ዐዋቂዎች የሚያደርጉት ግምት፡፡

(1) ስለ ማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ልዩ ዐዋቂዎች የሚያቀርቡት ቃለ ጉባኤ (ፕሮሴቬርባል) ግምቱ የተደረገበትን መሠረት የሚያሳይ መሆን
አለበት፡፡
(2) ፕሮሴቬርባሉ፤ የተገመተው ንብረት በሚመች አኳኋን ለመከፋፈል መቻሉንና የሚከፈልበትንም አኳኋን መግለጽ አለበት፡፡

(3) እንዲሁም ንብረቱ የሚከፋፈል ሲሆን፤ የሚደለደለውን የያንዳንዱን ድርሻና የድርሻውን ግምት መወሰን አለበት፡፡

ቊ 1085፡፡ ዕጣ ድልድል፡፡

(1) የክፍያዎቹን ድርሻ የሚያደላድለው፤ የጋራ ወራሾች በስምመነት የመረጡት ሰው ነው፡፡

(2) ወራሾቹ ያልተስማሙ እንደሆነ ዳኞች የመረጡት ልዩ ዐዋቂ ድልድሉን ያደርጋል፡፡

ቊ 1086፡፡ የውርሱ ንብረት በመሠረቱ በዐይነታው የሚከፋፈል ስለ መሆኑ፡፡

(1) ክፍያው በመሠረቱ የሚደረገው እያንዳንዱ ወራሽ ከውርሱ ውስጥ ንብረት እየተሰጠው በዐይነታው ነው፡፡

(2) በዐይነታው የተመደቡት ድርሻዎች ትክክል ያልሆኑ እንደሆነ ተጨማሪ ገንዘብ በመስጠት ይስተካከላሉ፡፡

ቊ 1087፡፡ የድርሻዎቹ አመዳደብ፡፡

(1) ከዚህ በታች የተጻፉት ደንቦች የተጠበቁ ሆነው ወራሾቹ በተቻለ መጠን፤ አንድ ዐይነት አመዳደብ ያላቸውን ድርሻ ይቀበላሉ፡፡

(2) በተቻለ መጠን ለያንዳንዱ ወራሽ በበለጠ የሚያገለግሉት ንብረቶች ይሰጡታል፡፡

ቊ 1088፡፡ የንብረቶቹ አመጣጥ፡፡


በክፍያው ውስጥ፤ ክፍያው እንደሚከተለው ይደለደላል፡፡
(ሀ) የአባት መሥመር ወራሽ ለሆኑት ለሟቹ የዚሁ መሥመር የሆኑ ሰዎች ያስተላለፉትን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፤

(ለ) የእናት መሥመር ወራሽ ለሆኑት፤ ለሟችቱ የዚሁ መሥመር የሆኑ ሰዎች ያስተላለፉትን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡

ቊ 1089፡፡ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ወራሾች፡፡


ከወራሾቹ መካከል አንዳንዶቹ የኢትዮጵያ ዜግነት ደግሞ አንዳንዶቹ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው የሆኑ እንደሆነ በኢትዮጵያ ያሉት
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የሚቻል ቢሆን ኢትዮጵያውያን ለሆኑት ወራሾች በቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡

ቊ 1090፡፡ የወራሾቹ ዕዳ፡፡


ከወራሾቹ አንዱ ለውርሱ የሚከፍለው ዕዳ ያለበት እንደሆነ፤ ዕዳው በድርሻው ውስጥ ይታሰባል፡፡
ቊ 1091፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠባቸው ዕዳዎች፡፡
ለአንድ ወራሽ ስለ ሟቹ ዕዳ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ወይም በመያዣ የተሰጡባቸው ንብረቶች የደረሱት እንደሆነ፤ ለዕዳዎቹ አላፊ
ይሆናሉ፡፡
ቊ 1092፡፡ በሚያስቸግር ሁኔታ የሚከፋፈሉ ሀብቶች (1) መሠረቱ፡፡
በውርሱ ሀብት ውስጥ ከፍ ያለ ጉዳት ሳይደርባቸው ሊከፈሉ የማይችሉ ንብረቶች ያሉ እንደሆነና ከወራሾቹ መካከል ይህን የማይከፈል
ሀብት ሊወስድ የሚገባው የትኛው እንደሆነ በስምምነት ለመወሰን ያልቻሉ እንደሆነ ይህ ንብረት ተሸጦ ገንዘቡ በወራሾቹ መካከል
ይከፋፈላል፡፡
ቊ 1093፡፡ (2) በሐራጅ ስለ መሸጥ፡፡

(1) ከወራሾቹ መካከል አንደኛው ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ሽያጩ የሚደረገው በሐራጅ ነው፡፡

(2) በወራሾቹ መካከል ስምምነት የታጣ እንደሆነ በሐራጅ ጨረታ ውስጥ ባዕድ ሰዎች እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

ቊ 1094፡፡ የቤተ ዘመድ መታሰቢያ ዕቃዎች፡፡

(1) የቤተ ዘመድ ጽሑፎችና የመታሰቢያ እምነት ያላቸው ዕቃዎች እንዳይሸጡ ከወራሾቹ አንዱ ለመቃወም ይችላል፡፡

(2) በወራሾቹ መካከል ስምምነት የታጣ እንደሆነ እነዚህ ዕቃዎች እንዲሸጡ ወይም ከወራሾቹ ለአንደኛው እንዲሰጡ የሚወስኑት ዳኞች
ናቸው፡፡
(3) እንደዚህ በሆነ ጊዜ ይህ የመታሰቢያ ዕቃ ከቤተ ዘመድ መካከል እንዳይወጣ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ አለባቸው፡፡

ቊ 1095፡፡ በክፍያ ውስጥ የሚገቡ መብቶች ዐይነት፡፡

(1) በውርሱ ውስጥ ለተገኙት ንብረቶች ሟች ባለሀብት ወይም ተከራዩ ወይም ተጋዥ ወይም በእነዚህ ንብረቶች ላይ ሌላ መብት ነበረው
ሳይባል ልዩነት ሳይደረግ የዚህ ክፍል ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) እነዚህን ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ለማድረግ በንብረቱ አከፋፈል ዐይነትና ሁኔታ የክፍያውን ሥርዐት ለመፈጸም የሚቻል መሆኑ ብቻ
ይበቃል፡፡
ቊ 1096፡፡ በብዙ የጋራ ወራሾች መካከል ንብረቱ ሳይከፋፈል ስለ ማቈየት፡፡

(1) ለአንድ ወራሽ ብቻ ብዙ መብቶች የሚሰጠውን የዚህን ክፍል ድንጋጌ ሌሎቹ ወራሾች በነዚህ መብቶች በአንድነት እንዲሠሩበት
ተስማምተውበት እንደሆነ በዚህ ከፍል ድንጋጌዎች እነሱም ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

(2) ብዙዎቹ ወራሾች አንዱን ሀብት አብረን እንወርሳለን ሲሉ ግልጽ የሆነ ስምምነት ካላደረጉ በቀር ይህ ሀብት ለብዙ ወራሾች በአንድነት
ሊሰጣቸው አይችልም፡፡
ክፍል 4፡፡
መከፋፈሉ ከተፈጸመ በኋላ በወራሾቹ መካከል ስላለው ግንኙነት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
የጋራ ተካፋዮች ሊሰጡ ስለሚገባቸው ዋስትና፡፡
ቊ 1097፡፡ ሕግን ስለ መጥቀስ፡፡

(1) በየድርሻቸው ውስጥ የተደለደለውን ግዙፍ ሀብት ስለሚመለከተው ጒዳይ፤ ሻጭ ለገዥ መድን በሚሆነው ዐይነት ወራሾችም አንዱ
ለአንዱ መድን ናቸው፡፡

(2) በየድርሻው ውስጥ የተመደቡትን መብቶችና የገንዘብ ጠያቂነት መብቶች በሚመለከተው ጒዳይም እንዲሁ በዋጋ የገንዘብ መብት
በሚተላለፈበት ጊዜ የሚሰጠውን መድን ዐይነት አንዱ ለአንዱ መስጠት አለበት፡፡

ቊ 1098፡፡ የኪሣራው ልክ፡፡


ሊከፈል የሚገባው የኪሣራ ልክ የሚወሰነው ክፍያው በተደረገበት ጊዜ ሀብቱ በነበረው ዋጋ መጠን ነው፡፡
ቊ 1099፡፡ ኪሣራውን የሚከፍለው ሰው፡፡

(1) እያንዳንዱ ወራሽ ኪሣራውን የሚከፍለው ከውርሱ በደረሰው ድርሻ ዋጋ መጠን ነው፡፡

(2) ከወራሾቹ መካከል አንደኛው ዕዳ ለመክፈል የማይችል በሆነ ጊዜ እያንዳንዱ ወራሽ ከደረሰው ዕጣ ጋራ ተመዛዛኝ በሚሆን መጠን
ዕዳው መድን በተሰጠው ወራሽና ዕዳ ሊከፍሉ በሚችሉት ወራሾች መካከል የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

ቊ 1100፡፡ የማረጋገጫ ዋስትና የማግኘት መብት፡፡


ከወራሾቹ አንደኛው፤ በብልጫ ድርሻ ምክንያት ሊከፈለው የሚገባ ሐሳብ እንዳለው ወይም በድርሻው ውስጥ የተደለደለው የገንዘብ
መጠየቂያ መብት መከፈሉ የሚያጠራጥር እንደሆነ መከፋፈሉ እንደተፈጸመ ይህ የጋራ ወራሽ መብቱን የሚያረጋግጡለት ዋስትና
እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1101፡፡ ዋስትና የማይሰጥበት ሁኔታ፡፡

(1) ውርሱን በጋራ ተካፋይ ከሆኑት አንደኛው የሚጠይቀው ዋስትና በራሱ ጥፋት በደረሰበት የመብት ማጣት ምክንያት ወይም በውርስ
የተገኘው ሀብት ከተከፋፈለ በኋላ ለደረሰ ነገር የሆነ እንደሆነ ዋስትና ሊሰጠው አይገባውም፡፡

(2) እንዲሁም የውርሱ መከፋፈል በተደረገበት ጊዜ ከተከፋዮቹ ላንደኛው ስለ ደረሰው ዕጣ ያለ መድን የተሰጠው መሆኑ በመከፋፈያው
ጽሑፍ ውስጥ ተገልጾ እንደሆነ ዋስትና አይሰጥም፡፡
ክፍል 2፡፡
ክፍያውን ስለ ማፍረስ፡፡
ቊ 1102፡፡ ክፍያው የሚፈርስበት ምክንያት፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ቊጥሮች ድንጋጌ፤ እንደተጠበቀ ሆኖ የክፍያው ጒዳይ ሌሎች ውሎች በሚፈርሱበት አኳኋን ሊፈርስ ይችላል፡፡
ቊ 1103፡፡ የተረሱ ንብረቶች፡፡

(1) ክፍያው ከተደረገ በኋላ በክፍያ ውስጥ ያልገቡ በውርሱ ንብረት ውስጥ ገብተው የሚቈጠሩ አዲስ ሀብቶች የተገኙ እንደሆነ በነዚሁ
አዲስ ንብረቶች መጠን አዲሰ የክፍያ ሥርዐት መፈጸም ያስፈልጋል፡፡

(2) አስቀድሞ የተደረገው መከፋፈል እንዳለ ይረጋል፡፡

ቊ 1104፡፡ ንብረት ስለ መደበቅ፡፡


ይህ በክፍያ ውስጥ ሳይገባ ቀርቶ የተገኘው አዲስ ንብረት ከወራሾቹ በአንዱ እጅ እንደነበረና ይህንኑ ደብቆት የነበረው በመጥፎ ልቡና ከሆነ
በዚህ ዐይነት ከደበቀው ንብረት የሚደርሰውን ድርሻ ያጣል፡፡

ቊ 1105፡፡ ክፍያውን ስለ ማቃናት፡፡ (1) ማቃናት ስለሚደረግበት ጊዜ፡፡

(1) የአንዳንድ ንብረቶች ዋጋ በተሳሳተ ሁኔታ በመገመቱ ምክንያት የክፍያው ተጠቃሚ ከሆነው ወራሽ አንዱ ሊደርሰው ከሚገባው ከሦስት
ሩብ በታች ደርሶት እንደሆነ በዚሁ ባለመብት በሆነው ወራሽ ጠያቂነት የክፍያውን ሥርዐት እንደገና እንዲቃና ያደርጋል፡፡

(2) እንዲሁም አስቀድሞ ተቀብሎት የነበረውን ስጦታ መልሶ በውርሱ ውስጥ ማግባት ያለበት ሆኖ ሳል ይህንኑ ሁኔታ ለሌሎች ወራሾች
ሳይገልጽ የቀረ እንደሆነ የተደረገው ክፍያ እንዲቃና ይደረጋል፡፡

ቊ 1106፡፡ (2) ጥያቄው የሚቀርብበት ጊዜ፡፡

ክፍያው እንዲቃና የሚቀርበው ጥያቄ ውርሱ በተከፋፈለ በ 3 ዓመት ውስጥ ያልቀረበ እንደሆነ ተቀባይነትን ያጣል፡፡

ቊ 1107፡፡ (3) የክፍያው መቃናት ውጤት፡፡


(1) ክፍያው እንዲቃና የሚለውን ጥያቄ ዳኞች የተቀበሉት እንደሆነ ለጠያቂው ሊከፈል የሚገባውን የኪሣራ ልክና ይህን ኪሣራ
የሚከፍለው ማን እንደሆነ፤ በምን ዐይነት ሁኔታ እንደሚከፈል ይወስናሉ፡፡

(2) ክፍያው አንዲቃና የተደረገው በውርሱ ውስጥ ተመልሶ የሚገባ ስጦታ ባለመነገሩ ምክንያት የሆነ እንደሆነ ይህንኑ ስጦታ የተቀበለው
የጋራ ወራሽ መልሶ ማግባት በነበረበት ዋጋ (ግምት) መጠን በተቃናው መከፋፈል ውስጥ ድርሻውን ያጣል፡፡

(3) ይህንኑ ንብረት በክፍያ ውስጥ ሳያገባ የቀረው በቅን ልቡና መሆኑን ወራሹ ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ ዳኞች ከዚህ በላይ
በተመለከተው ኀይለ ቃል ድንጋጌ ተፈጻሚ እንዳይሆነ ለማድረግ ይችላሉ፡፡

ቊ 1108፡፡ (4) የኪሣራው አከፋፈል፡፡

(1) ሊከፈል የሚገባው ኪሣራ የሚወሰነው በማናቸውም ጊዜ በጥሬ ገንዘብ ነው፡፡

(2) አከፋፈሉን ለመጠየቅ የሚቻለው የኪሣራ ጠያቂው አብሮ ወራሽ ከሆኑት ወይም ከወራሾቻቸው ወይም የኑዛዜ ስጦታ ከተሰጣቸው
ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡

ቊ 1109፡፡ የመካፈሉን ሥርዐት ስለ መቃወም፡፡


ከጋራ ወራሾቹ ባንደኛው ላይ የገንዘብ መጠየቂያ መብት ያላቸው ሰዎች ክፍያው የተደረገው በመብታችን ላይ ማጭበርበር ተደርጓል
ብለው ክፍያውን ለመቃወም የሚችሉት ያደረጉት መቃወሚያ ሳይሰማ እነሱ በሌሉበት መከፋፈሉ ተፈጽሞ እንደሆነ ነው፡፡
ክፍል 5፡፡
የውርሱ ሀብት ከተከፋፈለ በኋላ ገንዘብ ጠያቂዎች ያላቸው መብት፡፡
ቊ 1110፡፡ የክሶች መከፋፈል፡፡
(1) ገንዘብ ጠያቂው፤ የገንዘብ መጠየቂያ መብቱ የማይከፋፈል ካልሆነ በቀር በወራሾቹ ላይ የሚያቀርበውን ጥያቄ እያንዳንዱ ወራሽ
በደረሰው የውርስ ሀብት ግምት መጠን ጥያቄውንም አከፋፍሎ ማቅረብ አለበት፡፡

(2) ስለሆነም ወራሾቹ ውርሱን ሲከፋፈሉ ባደረጉት ስምምነት ዕዳውን በሞላው ወይም አብዛኛውን አንዱ ወራሽ ወይም ብዙ ወራሾች
እንዲከፍሉ ተስማምተው እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂው በዚህ ስምምነት ለመጠቀም ይችላል፡፡
ቊ 1111፡፡ ከወራሾቹ አንዱ ዕዳ ለመክፈል ስላለመቻሉ፡፡
ከወራሾቹ መካከል አንደኛው ዕዳ ለመክፈፀል የማይችል በሆነ ጊዜ ዕዳው በሌሎቹ ወራሾች መካከል በትክክል ይከፈላል፡፡
ቊ 1112፡፡ በኑዛዜ ስጦታ የተደረገላቸው ሰዎች እንደ ገንዘብ ጠያቂዎች ተመሳሳይ ስለ መሆናቸው፡፡
ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች ውስጥ የተነገሩት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች በሚሆኑበት ጒዳይ፤ የኑዛዜ ስጦታ የተሰጣቸው ሰዎች ከውርሱ ላይ
ገንዘብ ጠያቂ እንደሆኑት ሰዎች ተመሳሳይ ይሆናሉ፡፡
ቊ 1113፡፡ በወራሾች መካከል ላለው ግንኙነት፡፡
(1) ውርሱ ከተከፋፈለ በኋላ፤ መክፈል ከሚገባው የበለጠ የዕዳ ድርሻ የከፈለው ወራሽ በብልጫ የከለውን ሒሳብ እንዲያገቡለት ሌሎቹን
የጋራ ወራሾችን ሊጠይቃቸው ይችላል፡፡

(2) የዋስትናን አሰጣጥ በሚመለከተው ረገድ ይህ ደንብ ተፈጻሚ ስለሚሆንበት ጒዳይ ስለ ውል በጠቅላላው የሚለው የዚህ ሕግ ድንጋጌ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
ውርስን ስለሚመለከቱ ስምምነቶች፡፡
ክፍል 1፡፡
ወደፊት በሚገኝ ውርስ ላይ ስለሚደረግ የውል ስምምነት፡፡
ቊ 1114፡፡ ወደፊት በሚገኝ የውርስ ሀብት ላይ የውል ስምምነት ማድረግ የተከለከለ ስለ መሆኑ ፡፡
በሕግ ተገልጸው ከተፈቀዱት ሁኔታዎች ውጭ ገና በሕይወቱ ባለው ሰው ውርስ ላይ በአንድ በኩል የሚደረጉ ውሎችና ግዴታፖዋች ሁሉ
ፈራሾች ናቸው፡፡
ቊ 1115፡፡ ወደ ፊት የሚገኝን ውርስ ስለ መቀበል ወይም ስለ መንቀፍ፡፡
(1) ገና ለወደፊት ይሰጣል ተብሎ ተስፋ የሚደረግበትን የውርስ ሀብት መቀበል ወይም ያለመቀበል ወይም በዚህ ውርስ ውስጥ ያሉትን
መብቶች ማስተላለፍ አይቻልም፡፡

(2) ባለንብረት የሆነው ሰው የፈቀዳቸው ቢሆንም እንኳ ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከቱት የውል ስምምነቶች ፈራሾች ናቸው፡፡
ቊ 1116፡፡ ለማውረስ ውል ስለ መግባት፡፡
አንድ ሰው ውርሱን እሰጥሃለሁ ወይም በኑዛዜ ስጦታ አደርግልሃለሁ ብሎ ለተዋዋዩ ወይም ለሦስተኛ ወገን የውል ግዴታ ሊገባ
አይችልም፡፡
ክፍል 2፡፡
የተከፋፈሉ ስጦታዎች፡፡
ቊ 1117፡፡ መሠረቱ፡፡
አባትና እናት ሌሎች ወደ ላይ የሚቈጠሩ ወላጆች ለልጆቻቸውና ለሌሎች ወደ ታች የሚቈጠሩ ተወላጆቻቸው ሀብታቸውን ለመስጠትና
ለማከፋፈል ይችላሉ፡፡
ቊ 1118፡፡ የአፈጻጸሙ ፎርም፡፡
በቁም ስለሚደረጉ ስጦታዎች በሕግ በተደነገጉት ደንቦች መሠረት ይህ የስጦታ አከፋፈል መፈጸም አለበት፡፡
ቊ 1119፡፡ ግቡ፡፡
ይህ የስጦታ ማከፋፈል ጒዳይ በተፈጸመበት ጊዜ ወደ ላይ የሚቈጠረው ወላጅ ባሉት ሀብቶች ላይ ካልሆነ በቀር ሊፈጸም አይችልም፡፡
ቊ 1120፡፡ የተረሳ ንብረት፡፡
ወደ ላይ የሚቈጠረው ወላጅ በሞተበት ቀን ትቷቸው የሚሞተው ንብረቶች ሁሉ በስጦታ መከፋፈሉ ውስጥ ሳይገቡ ቀርተው እንደሆነ
ከስጦታ መከፋፈል ውስጥ ያልገቡት ንብረቶች በሕግ መሠረት ይከፋፈላሉ፡፡

ቊ 1121፡፡ የተረሳ ልጅ (1) ስጦታው ፈራሽ ስለ መሆኑ፡፡


ስጦታ አድራጊው የስጦታ ማከፋፈል ባደረገ ጊዜ ከልጆቹ አንዱን የረሳው እንደሆነ ወይም ስጦታው ከተደረገ በኋላ ልጅ የወለደ እንደሆነ
ሰጪው በሞተ ጊዜ የተተወው ልጅ ወይም እንደራሴዎቹ በስጦታ አከፋፈሉ እንዲፈርስ በመጠየቅ ይችላሉ፡፡
ቊ 1122፡፡ ልዩ አስተያየት፡፡
(1) ስለሆነም ሟቹ ይህን የተዘነጋውን ልጅ ከውርስ መንቀሉን የሚገልጽ የሚጸና ኑዛዜ ትቶ ሞቶ እንደሆነ የስጦታ ክፍያው እንዲፈርስ
መጠየቅ አይቻልም፡፡

(2) እንደዚህም በሆነ ጊዜ ከውርስ የተነቀለው ልጅ ወይም እንደራሴዎቹ በውርሱ ላይ ሊኖራቸው የሚችለው የገንዘብ መጠየቅ መብት
የተጠበቀ ነው፡፡

(3) እንዲሁም፤ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር እንደተመለከተው ሟቹ በስጦታ ማከፋፈል ውስጥ ከሰጣቸው ንብረቶች ለተረሳው ልጅ ድርሻ
በቂ የሚሆኑ ሌሎች ንብረቶች ያሉ እንደሆነ፤ የተደረገው ማከፋፈል ድልድል እንዲፈርስ መጠየቅ አይቻልም፡፡
ቊ 1123፡፡ ጉዳት፡፡
(1) በስጦታው አከፋፈል ውስጥ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር፤ ወደ ታች ከሚቈጠሩ ተወላጆች አንዱ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዳት
ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፋፈሉ እንዲቀር ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ጉዳት መኖሩ የሚገመተው የስጦታው ክፍያ በተደረገበት ቀን ንብረቱ የነበረውን ዋጋ በመመልከት ነው፡፡

(3) ይህ የስጦታ ክፍያ እንዲቀር የሚደረገው ክስ ወደ ላይ የሚቈጠረው ስጦታ አድራጊው ወላጅ በሞተ በሁለት ዓመት ውስጥና
የስጦታው መከፋፈል ከተደረገበት ቀን አንሥቶ በ 0 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በቀር ዋጋ የሌለው ይሆናል፡፡
ክፍል 3፡፡
የውርስ መብቶችን ስለ ማስተላለፍ፡፡
ቊ 1124፡፡ የወራሹ መብት፡፡
(1) ውርሱ ከተከፈተ በኋላ አንድ ወራሽ በውርስ የሚያገኘውን መብት በከፊል ወይም በሙሉ ለሌላ አሳልፎ ለመስጠት ይችላል፡፡

(2) ስለሆነም በውርሱ ውስጥ ካለው ንብረት በተለይ በአንድ ላይ ያሉትን መብቶች ይህ ንብረት በእርሱ ድርሻ ውስጥ ከመደረጉ በፊት
አሳልፎ ሊሰጥ አይችልም፡፡

ቊ 1125፡፡ አሳልፎ የተሰጠውን የውርስ ሀብት የማስቀረት (የማስመለስ) መብት፡፡

(1) መብቱ የተላለፈው ከወራሾቹ ላንዱ ካልሆነ በቀር የውርስ መብት ከተላለፈለት ሌላ ሰው ላይ ሌሎቹ የጋራ ወራሾች ግምቱን ከፍለው
ለማስቀረት በሕግ የቀደምትነት መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡

(2) ይህን የማስመለስን መብት በሚመለከተው ጒዳይ ስለ ጋራ ባለሀብትነት ስለ አላባ ጥቅም ተቀባይነት ስለ ሌሎቹ ግዙፍ መብቶች
በሚመለከተው አንቀጽ የተጻፉት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ስለ ንብረቶች፡፡
PrintEmail

наклейки

Joomla
ሦስተኛ መጽሐፍ
ስለ ንብረቶች፡፡
አንቀጽ ስድስት፡፡
ስለ ንብረት በጠቅላላውና ስለ ይዞታ፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ስለ ንብረቶች በጠቅላላው፡፡
ቊ 1126፡፡ ስለ ንብረቶች አከፋፈል፡

ግዙፍነት ያላቸው ንብረቶች ሁሉ ተንቀሳቃሽ የሆኑና ወይም የማይንቀሳቀሱ ናቸው፡፡

ቊ 1127፡፡ ግዙፍነት ስላላቸው ንብረቶች፤ (1) መሠረቱ፡፡


ግዙፍነት ያላቸው ንብረቶች ግዙፋዊ ሀልዎት ያላቸው ነገሮች ሆነው የማይለያይ ሁኔታቸውን ሳያጡ በራሳቸውም ሆነ በሰው ካንዱ ቦታ
ወደ ሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ የሚችሉ ናቸው፡፡

ቊ 1128፡፡ (2) ላምጪው የሚሰጡ ሰነዶች፡፡

ተቃራኒ የሚሆን የሕግ ድንጋጌ ከሌለ በቀር የገንዘብና ሌሎቹም ግዙፍነት የሌላቸው ነገሮች መብቶች ላምጪው በተሰጠው ሰነድ ውስጥ
ሲገኙ እንደ ተንቀሳቃሾች ነገሮች ሆነው ይቈጠራሉ፡፡

ቊ 1129፡፡ (3) ስለ ተፈጥሮ ኀይል፡፡

እንዲሁም እንደ ኤሌክትሪሲቴ ያሉት የኤኮኖሚ ዋጋ ያላቸው የተፈጥሮ ኀይል ነገሮች ተቃራኒ የሚሆን የሕግ ድንጋጌ ከሌለ በቀር በሰው
ገዢነት ውስጥ ያሉና ለሰው አገልግሎት ሥራ የተደረጉ ከሆኑ እንደ ተንቀሳቃሾች ነገሮች የሚቈጠሩ ናቸው፡፡

ቊ 1130፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የመሬት ርስቶችና ቤቶች ናቸው፡፡

ቊ 1131፡፡ ያንድ ነገር ሙሉ ክፍሎች፤ (1) መሠረቱ፡፡

ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር አንዱን ነገር የሚመለከቱት መብቶች ወይም ተግባሮች የዚህ የተባለው ነገር ሙሉ ክፍል
የሚሆነውን ሁሉ ይጠቀልላሉ፡፡

ቊ 1132፡፡ (2) ትርጓሜ፡፡

(1) የአንዱ ነገር ሙሉ ክፍል የሚባለው በልማድ እንደሚታየው ለዚሁ ነገር አንድ አቋም ሆኖ የሚቈጠረው ነው፡፡

(2) እንደዚሁም ከተባለው ነገር ጋራ በግዙፍነት የተያያዘ ሆኖ ይህ የተባለው ነገር ሳይጠፋና አጒል ሳይሆን ለመለያየት የማይችል ነገር
ሲኖር ይህ ነገር የዚያ ነገር ሙሉ ክፍል ይባላል፡፡

ቊ 1133፡፡ (3) ዛፎችና ሰብሎች፡፡


(1) ዛፎችና ሰብሎች ከመሬት ሳይለያዩ በሚቈዩበት ጊዜ ከመሬቱ ጋራ እንደ አካል ሆነው ይቈጠራሉ፡፡

(2) ስለሆነም ከመሬቱ ጋራ መለያየት ያለባቸው ወይም መለያየታቸውን በሚያስከትል ውል ውስጥ የሚገኙ ከሆነ፤ ራሱን የቻለ ግዙፍነት
ያለውና ተንቀሳቃሽ ንብረት እንደሆኑ ይቈጠራሉ፡፡

ቊ 1134፡፡ (4) የሦስተኛ ወገኖች መብት፡፡

(1) አንድ ነገር ያንድ ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት አካል ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ አንድ የተለየ ሀብት ነው መባሉ ይቀራል፡፡

(2) ከዚህም ጊዜ አስቀድሞ በዚሁ ነገር ላይ የሌላ የሦስተኛ ወገን መብቶች ናቸው ይባሉ የነበሩት ቀሪዎች ይሆናሉ፡፡

(3) በዚያን ጊዜ ከአላፊነት የተነሣ ወይም ሌላውን ሰው ያለአገባብ እንዲበለጽግ ከመደረጉ የተነሣ የተባሉት ሦስተኞች ወገኖች ያሏቸው
መብቶች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1135፡፡ ደባሎች ነገሮች፤ (1) መሠረቱ፡፡

የሚያጠራጥር ጒዳይ ያለ እንደሆነ አንድ ነገርን የሚመለከቱ መብቶች ወይም ተግባሮች ከዚሁ ነገር ጋራ ተያይዘው የሚገኙትን
ተጨማሪዎችን ነገሮች የሚጠቀልሉ ናቸው፡፡

ቊ 1136፡፡ (2) ትርጓሜ፡፡

የአንድ ነገር ተጨማሪ ነው የሚባለው ይህን ነገር በባለሀብትነት ወይም በባለአላባ ጥቅም ተቀባይነት ይዞ በሚጠቀምበት ባንድ ሰው አሳብ
ይህ ነገር ለሚያገለግልበት ጒዳይ በነዋሪ ዐይነት ከዚሁ ጋራ ተያይዞ የሚገኘው ነው፡፡

ቊ 1137፡፡ (3) ደባል (ተጨማሪ) የሆነው ነገር ለጊዜው ስለ መለያየቱ፡፡

ተጨማሪዎች ነገሮች ለጊዜው ብቻ ከዋናው ነገር የተለያዩ ሲሆኑ ተጨማሪ መሆናቸውን አያጡም፡፡

ቊ 1138፡፡ (4) የሦስተኛ ወገኖች መብት፡፡

(1) አንድ ተጨማሪ ነገር ከአንድ ከሚንቀሳቀስ ወይም ከማይንቀሳቀስ ሀብት ጋራ የመያያዙ ጒዳይ፤ ይህ ተጨማሪ ነገር ከመያያዙ በፊት
በዚህ ላይ የነበራቸውን የሦስተኛ ወገኖች ባለመብትነት አያስቀርባቸውም፡፡

(2) ቢሆንም ነገሩ ካንድ ንብረት ጋራ ከመያያዙ በፊት በጽሑፍ በተደረጉ ቀናቸው በተረጋገጠ ውሎች ላይ የተመለከተ ስምምነት ከሌለ
በቀር እነዚህን መብቶች በቅን ልቡና ባገኛቸው ሦስተኛ ወገን ላይ መቃወሚያ ሊሆኑበት አይችሉም፡፡
ቊ 1139፡፡ (5) የተጨማሪነት ሁኔታ የሚቀርበው ጊዜ፡፡

(1) ያንድ ነገር ባለሀብት ከዚሁ ጋራ የተያያዘውን ተጨማሪ ነገር ደባልነቱን ለማስቀረት ይችላል፡፡

(2) ተጨማሪው ነገር እንዲህ መሆኑን በማመን ከባለሀብቱ ጋራ በቅን ልቡና የተዋዋሉት የሦስተኛ ወገኖች መብቶች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
ስለ ንብረት በጠቅላላውና ስለ ይዞታ፡፡
ቊ 1140፡፡ ትርጓሜ፡፡

ይዞታ ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

ቊ 1141፡፡ በቀጥታ ወይም በጠባቂ የሆነ ይዞታ፡፡

በቀጥታ ወይም እንዲያው ነገሩን ይዞ ብቻ በሚቈይ በአንድ በሌላ ሰው አማካይነት ባለይዞታ ለመሆን ይቻላል፡፡

ቊ 1142፡፡ የሚያልፍ መሰናክል፡፡

በይዞታው መብት መገልገሉ በሚያልፉ ነገሮች የተከለከለ ወይም የተቋረጠ እንደሆነ፤ ይዞታው የሚቀር አይሆንም፡፡

ቊ 1143፡፡ ይዞታን ለሌላ ሰው ስለ ማስተላለፍ፡፡

በውል ምክንያት ይዞታን የማስተላለፍ ነገር የተደረገ እንደሆነ፤ ይዞታው የሚተላለፈው ነገሩን በሚያስረክብበት ጊዜ ነው፡፡

ቊ 1144፡፡ ነገሩን የሚያሳዩ አስረጂዎች፡፡

(1) የሚተላለፈውን ነገር አዲስ ባለይዞታ ለሚሆነው ሰው የሚያሳዩና ይዞታውን የሚፈቅዱ አስረጂዎችን በማስረከብ ይዞታን ማስተላለፍ
ይቻላል፡፡
(2) ሰነዶችን ባቀረበና እውነተኛ ይዞታ ባለው ሰው መካከል ክርክር የተነሣ እንደሆነ፤ ክፉ ልቡና (ተንኰል) እንዳለበት ካልተገለጸ በቀር
ለባለይዞታው ብልጫ ይሰጠዋል፡፡
ቊ 1145፡፡ የይዞታ ማስታወቂያ፡፡

(1) ዕቃዎቹ መኖራቸው የተረጋገጠና በዐይነት የሚሰጡ፤ በመለየት የታወቁ በሆኑ ጊዜ የዕቃው ይዞታ አዲስ ባለይዞታ ለሚሆነው ሰው
እንደተላለፈ የሚቈጠረው በዕቃው የሚያዝበት ሰው ዕቃውን ወደ ፊት አዲስ ይዞታ ለተሰጠው ሰው ነው የያዝሁት ብሎ ዋጋ ባለው
(በሚጸና) አኳኋን የገለጸ እንደሆነ ነው፡፡

(2) በዕቃው በእውነት የሚያዝዝበት ሰው የከሠረ እንደሆነ ከእርሱ ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች የሆኑት ሰዎች መብቶች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1146፡፡ በስውር ወይም በሚያሻማ አኳኋን የተደረገ ይዞታ፡፡

(1) በስውር ወይም በሚያሻማ አኳኋን የተደረገው ይዞታ ማናቸውንም መብት አይሰጥም፡፡

(2) በስውር የተደረገ ይዞታ የሚባለው ነገሩን በእጁ ይዞ የሚገኘው ሰው በያዘው ነገር ላይ አንዳች መብት እንደሌለው ለማሳሰብ በሚችል
አኳኋል ባለይዞታነቱን የደበቀ እንደሆነ ነው፡፡

(3) በሚያሻማ ዐይነት የተደረገ ይዞታ የሚባለው በነገሩ የሚጠቀመው ሰው የራሱ ገንዘብ ለመሆኑ በአካባቢዎቹ ነገሮች ሁኔታ
የሚያጠራጥር ሲሆን፤ ወይም ነገሩን በእጁ የያዘው ሰው ስለ ሌላ ሰው የያዘው ሲሆን ነው፡፡

ቊ 1147፡፡ የባለይዞታውን ስም ስለ መለወጥ፡፡

(1) ስለ ሌላ ሰው ሆኖ ባለይዞታ መሆንን የጀመረ ሰው ተቃራኒ የሚሆን ማስረጃ ከሌለ በቀር ምን ጊዜም በጠባቂነት እንደያዘ ሆኖ
ይገመታል፡፡
(2) ለዚህ ተቃራኒ የሚሆን ማስረጃ በማናቸውም መንገድ ሊቀርብ ይችላል፡፡

(3) ስለሆነም በጠባቂነት የያዘው ሰው አሳቡን በመለወጡ ብቻ ለይዞታው ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡

ቊ 1148፡፡ የይዞታ መድን (1) በኀይል መከላከል፡፡

(1) ባለይዞታ የሆነ ሰው እንዲሁም ለሌላ ሰው የያዘ ቢሆንም ይዞታውን ለመንጠቅ ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ለማንሳት የሚያደርገውን
ማንኛውንም ኀይል በመከላከል ለመመለስ መብት አለው፡፡

(2) እንዲሁም እጅ ያደረገው ነገር በንጥቂያ ወይም በስውር የተወሰደበት እንደሆነ ነጣቂውን በማስወጣት ወይም ነገሩን በግፍ ሲወስድ
ከተገኘው ወይም ይዞ ሲሸሽ ከተያዘው ነጣቂ ሰው ላይ ወዲያውኑ በጒልበት በማስለቀቅ የተወሰደበትን ነገር ለመመለስ ይችላል፡፡

(3) ስለሆነም የጊዜው አጋጣሚ ሁኔታ ካላስገደደ በቀር ከእጅ እልፊት መታገስ አለበት፡፡

ቊ 1149፡፡ (2) በዳኝነት የመጠየቅ ሥራ፡፡


(1) ይዞታው የተወሰደበት ወይም በይዞታው ላይ ሁከት የተነሣበት ሰው የተወሰደበት ነገር እንዲመለስለት ወይም የተነሣው ሁከት
እንዲወገድለት እንዲሁም ስለ ደረሰበት ጉዳት ኪሣራ እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) የያዘው ነገር ከተነጠቀበት ወይም በይዞታው ላይ ሁከት ከተነሣበት ቀን አንሥቶ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ በፍርድ ካልጠየቀ እጅ
ይዛወርልኝ የማለት ክስ መብቱ ይቀርበታል፡፡

(3) ተከሳሹ የሥራውን አደራረግ የሚፈቅድ ለርሱ የሚናገርለት መብት መኖሩን በፍጥነትና በማይታበል ዐይነት ካላስረዳ በቀር ዳኞቹ
የተወሰደው ነገር እንዲመለስ ወይም የተነሣው ሁከት እንዲወገድ ያዛሉ፡፡

ቊ 1150፡፡ የይዞታ መደረብ፡፡

(1) የራሱ ሀብት ለማድረግ የሚገባ የይዞታ መብት ያለው ሰው ከራሱ የይዞታ ጊዜ ላይ ንብረቱን ያስተላለፈለትን ሰው የይዞታ ጊዜ
ለመደረብ የሚችለው፤ የንብረቱን ይዞታ ያስተላለፈለት ሰው በይርጋ የራሱ ይዞታ ለማድረግ የሚፈቅድ መብት ኖሮት እንደሆነ ነው፡፡

(2) ባለዐፅመርስቱ፤ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የከፈለውን ግብር መከራከሪያ ሊያደርገው ይችላል፡፡

አንቀጽ 7፡፡
ስለ ግል ሀብት፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ሀብት ስለሚገኝበት ሁኔታ፤ ሀብትን ስለ ማስተላለፍ፡፡
ሀብት ስለሚቀርበትና ስለ ሀብትነት ማስረጃ፡፡
ክፍል 1፡፡
ሀብት ስለሚገኝበት ሁኔታ፡፡
ንኡስ ክፍል ፡፡
ስለ መያዝ፡፡
ቊ 1151፡፡ መሠረቱ፡፡

ባለቤት የሌለውን አንድ ግዙፍነት ያለውን ተንቀሳቃሽ ነገር ባለ ሀብት ለመሆን በማሰብ የያዘ ሰው ሀብትነቱን ያገኛል፡፡

ቊ 1152፡፡ እንስሳት፡፡

(1) ለማዳ የሆኑ ወይም የተያዙ እንስሶች ከባለሀብቱ ሰው ቢያመልጡና ቢጠፉ እርሱም በሚከተለው ወር ውስጥ ሳይፈልጋቸው የቀረ
እንደሆነ ወይም አንድ ወር ሙሉ መፈለጉን ቢተው ባለቤት የሌላቸው ይሆናሉ፡፡

(2) ስለሆነም ይህ ድንጋጌ ለቀንድ ከብቶች ለጋማ ከብቶች ለግመሎች ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
ቊ 1153፡፡ ንቦች፡፡

(1) ቀፎዋቸውን ትተው የሄዱ ንቦች ባለቤት እንደሌለው ሀብት ይቈጠራሉ፡፡

(2) በሌላ ቀፎ ውስጥ የገቡ እንደሆነ በቀፎው የገቡለት ሰው በአግኚ ባለመብትነት የንቦቹ ባለሀብት ይሆናል፡፡

(3) ስለሆነም የቀድሞው የንቦቹ ባለሀብት የሄዱበትን ሲከታተል ደርሶባቸው በሌላ ሰው ቀፎ ውስጥ በገቡ ጊዜ በስፍራው ላይ ከተገኘ
መልሶ ለመውሰድ ይችላል፡፡

ቊ 1154፡፡ ስለ ተገኙ ዕቃዎች፡፡ (1) የአግኚው ግዴታዎች፡፡

(1) ግዙፍነት ያለውን አንድ ተንቀሳቃሽ ነገር ያገኘና እጅ ያደረገ ሰው ያገኘውን ነገር እንዲያስታውቅ የሚያዝዘውን የአስተዳደር ደንብ
መፈጸም አለበት፡፡

(2) እንደዚህ ያለ ደንብ የሌለ እንደሆነ የተገኘው ነገር ግልጽ እንዲወጣ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ሁሉ መፈጸምና ያገኘውን ነገር ባለሀብት
ለሆነው ሰው ለማስታወቅ እንደነገሩ ሁናቴ የታዘዘውን ምርመራ ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡

ቊ 1155፡፡ (2) የተገኘውን ነገር እጅ ስለ ማድረግ፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር የተነገሩት ግዴታዎች ሁሉ የፈጸመ አግኚ ያገኛቸውን ነገሮች በእጁ አድርጎ ለማስቀመጥ መብት አለው፡፡

(2) በዚህ ጊዜ ለዕቃው አጠባበቅ በአእምሮ አስፈላጊ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለበት፡፡

ቊ 1156፡፡ (3) የተገኘውን ነገር ስለ መሸጥ፡፡

(1) የጠፋ ዕቃ ያገኘ ሰው ዕቃው በቶሎ የሚበላሽ ሆኖ ሲታይ ወይም ጥበቃው ብዙ ወጪ የሚያስፈልገው የሆነ እንደሆነ ያገኘውን ዕቃ
በአደባባይ በሐራጅ ለመሸጥ ይችላል፡፡

(2) በዚህ ጊዜ የሽያጩ ዋጋ የዕቃው ምትክ ይሆናል፡፡

ቊ 1157፡፡ (4) የተገኘውን ዕቃ ባለሀብቱ መልሶ ስለሚወስድበት ሁኔታ፡፡

(1) የዚህ ዕቃ የባለሀብትነቱ መብት እስከሚቀርበት ድረስ ባለሀብቱ ዕቃው እንዲመለስለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) በዚህ ጊዜ ዕቃውን ላገኙና እንዲጠበቅ ላደረጉ ሰዎች ኪሣራቸውን ሁሉ መክፈል አለበት፡፡
ቊ 1158፡፡ (5) ዕቃውን ላገኘ ሰው የሚሰጠው ኪሣራ፡፡

(1) አስፈላጊ ሲሆን ዳኞች የጠፋውን ዕቃ ላገኘ ሰው ካገኘው ዕቃ ግምት ከአራት አንድ ጉርሻ እንዲሰጠው ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

(2) ዳኞቹ ጒርሻ መስጠት አስፈላጊ መሆኑንና የገንዘቡንም ልክ የሚወስኑት የሁለቱን ባለጒዳዮች ሀብትና የጠፋበትን ነገር ባለሀብቱ እርሱ
ራሱ ለማግኘት የነበረውን ዕድል በመገመት ነው፡፡

(3) የጠፋውን ነገር ያገኘው ሰው ከመለሰበት ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ የሚገባውን ገንዘብ ያልጠየቀ እንደሆነ የመጠየቅ
መብቱ ይቀርበታል፡፡

ቊ 1159፡፡ የተቀበረ ገንዘብ፡፡

(1) ተቀብሮ የተገኘ ገንዘብ፤ ገንዘቡ የተገኘበት የማይንቀሳቀስ ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት ባለቤት ለሆነው ሰው ይሆናል፡፡

(2) የተባለውን ገንዘብ ያገኘ ሰው የተገኘውን ገንዘብ ግምት አጋማሽ በጒርሻ ለማግኘት መብት አለው፡፡

(3) የተቀበሩ ገንዘቦች ተብለው የሚቈጠሩት ማናቸውም ሰው ቢሆን የእኔ ናቸው ሲል የማይረታባቸውና ሲገኙም ከአምሳ ዓመት ከማያንስ
ዘመን አንሥቶ በእርግጥ ተቀብረው ወይም ተደብቀው የቈዩ መስለው የሚታዩ ናቸው፡፡

ቊ 1160፡፡ ጥንታዊ ዕቃ (አንቲካ)፡፡

የጥንታዊ ነገርን ምርመራ አርኬዎሎዢንና ጥንታዊ ዕቃዎችን አንቲካዎችን የነዚህም ዘርፍ የሆኑትን ነገሮች ስለሚመለከቱ ጒዳዮች የወጡት
የሕግ ድንጋጌዎች ወይም ልዩ ደንቦች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ንኡስ ክፍል 2፡፡


የቅን ልቡና ባለይዞታነት፡፡
ቊ 1161፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) ግዙፍነት ያለው የተንቀሳቃሽ ነገር ባለሀብት ለመሆን በቅን ልቡና ዋጋ ሰጥቶ ውል የተዋዋለ ሰው የተባለውን ተንቀሳቃሽ ነገር እጅ
ሲያደርግ በቅን ልቡናው ምክንያት የዚህ ንብረት ባለሀብት ይሆናል፡፡

(2) ከርሱ ጋራ የተዋዋለው ሰው በዕቃው ላይ መብት የሌለው ሰው ነው ተብሎ መቃወሚያ ሊሆንበት አይችልም፡፡

ቊ 1162፡፡ የቅን ልቡና ትርጓሜና ማስረጃ፡፡

(1) ግዙፍነት ያለውን ተንቀሳቃሽ ነገር የሚገዛ ሰው ይህን ንብረት እንዲያስተላልፍለት የተዋዋለውን ሰው ባለመብት ነው በማለት አምኖ
ከተዋዋለ፤ በቅን ልቡና ተዋውሏል ተብሎ ይገመታል፡፡
(2) ተቃራኒ ማስረጃ ከሌለ፤ የገዛው እጅ ያደረገው ሰው በቅን ልቡናው ነው ተብሎ ይገመታል፡፡

ቊ 1163፡፡ ቅን ልቡና ምን ጊዜ መኖር እንደሚገባው፡፡

(1) ቅን ልቡና ንብረቱ እጅ በሚደረግበት ጊዜ መኖር አለበት፡፡

(2) እጅ አድራጊው እጅ ያደረገውን ንብረት የሰጠው ሰው የዚህን ንብረት ባለመብትነት ለመስጠት መብት ያልነበረው መሆኑን ንብረቱን
እጅ ካደረገ በኋላ ቢያውቅ ይህ ማወቁ ጉዳት አያደርስበትም፡፡

ቊ 1164፡፡ ለመጠየቅ አለመቻል፡፡

(1) ግዙፍነት ያለውን ተንቀሳቃሽ ነገር በፈቃዱ ከእጁ ያውጣ ሰው በቅን ልቡናው እጅ በማድረግ ባለሀብት ከሆነው ሰው ላይ መልስልኝ
ለማለት አይችልም፡፡

(2) ዕቃውን ከእጁ ያወጣው ሰው ይህን ዕቃ በሌላ ሰው እጅ ቢያገኘውም እንኳ ቀድሞ የለቀቅሁለት ሰው ይህን ዕቃ ያስለቀቀኝ በማታለል
ነውና ዕቃዬን መልስልኝ ብሎ ዕቃው በእጁ የተገኘውን ሰው ሊጠይቅ አይችልም፡፡

ቊ 1165፡፡ የተሰረቀውን ነገር ለመጠየቅ ስለ መቻል፡፡

(1) አንድ ግዙፍነት ያለው ተንቀሳቃሽ ነገር የተሰረቀበት ሰው ይህን ዕቃ በቅን ልቡና ባለሀብት ከሆነው ሰው ላይ የኔ ነው ብሎ ለመጠየቅ
ክስ ለማቅረብ ይችላል፡፡

(2) ዕቃው ከተሰረቀበት አንሥቶ በአምስት ዓመት ውስጥ ክስ ካላቀረበ የኔ ነው ብሎ ለመጠየቅ ክስ የማቅረብ መብቱን ያጣል፡፡

ቊ 1166፡፡ በዚህ ጊዜ ለባለይዞታው ስለሚከፈለው ኪሣራ፡፡

(1) ፈለማ የተደረገበትን ዕቃ ተጠያቂው የገዛው ይህንኑ ዕቃ የመሳሰሉትን ነገሮች በሚሸጥ ነጋዴ ቤት ወይም በሕዝብ ገበያ ውስጥ

ወይም ዕቃ በሐራጅ በሚሸጥበት በአደባባይ ውስጥ የሆነ እንደሆነ የእኔ ነው ባዩ (ተፋላሚው) ባስያዘው ነገር፤ ገዢው፤ ለዚህ ነገር
ያወጣሁትን ገንዘብ አግባልኝ ብሎ ሻጩን ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) በዚህ ጊዜ የተባለውን ነገር ላገኙና በደንብ እንዲጠበቅ ላደረጉ ሰዎች ኪሣራቸው ሁሉ መከፈል አለበት፡፡

ቊ 1167፡፡ ጥሬ ገንዘብና ላምጪው የሚከፈል ሰነድ፡፡


(1) ጥሬ ገንዘብን ወይም ለአምጪው የሚከፈል ሰነድን በቅን ልቡና ካገኘ ሰው ላይ ሌላ ሰው የኔ ነው ብሎ ልቀቅልኝ ለማለት
በማገኛቸውም ሁኔታ ቢሆን አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም በቅን ልቡና እነዚሁኑ ነገሮች በገዛው በሌላው ሰው ላይ እንደዚህ ያለ መከራከሪያ ለማቅረብ አይቻልም፡፡

ንኡስ ክፍል ሦስት ስለ ይዞታ፡፡


ቊ 1168፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለእጅ (ባለይዞታ) የሆነ ሰው የዚሁኑ ንብረት ግብር ባለማቋረጥ 15 ዓመት በስሙ ከከፈለ የዚሁ ሀብት ባለቤት
ይሆናል፡፡ ስለሆነም የማይንቀሳቀሰው ንብረት፤ መሬት ሲሆንና በአገሩ ሥሪት መሠረት የመሬቱ ርስትነት የግል የአንድ ሰው ሳይሆን
ተወላጆች የሚካፈሉት በሆነበት ስፍራ ተወላጅ የሆነው ሰው የትውልድ ሐረጉን መዝዞ ርስቱ እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይህ የይርጋ ሕግ
አያግደውም፡፡
(2) በዚህ ሕግ በአንቀጽ ስድስት በምዕራፍ ሁለት የተደነገጉት ውሳኔዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1169፡፡ ስለ መምራት፡፡

(1) ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ ውስጥ ስለ ይርጋ መቋረጥ የተነገሩት ውሳኔዎች ስለ ይዞታም ነገር ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) እንዲሁም በይርጋ ሕግ ስለ መከራከርና በሥራ ላይ ስለ ማዋል በይርጋ መከራከርንም ስለ መተው የተነገሩት የዚሁ አንቀጽ ውሳኔዎች
የተጠበቁ ናቸው፡፡

ንኡስ ክፍል 4፡፡


የዋና ተጨማሪ ነገር፡፡
ቊ 1170፡፡ የንብረቱ ፍሬ፡፡

(1) ያንድ ነገር ባለሀብት የሆነ ሰው እንዲሁም ይህ ነገር የሚሰጠው የተፈጥሮ ፍሬ ባለሀብት ነው፡፡

(2) ፍሬ ሲባልም ሀብቱ በየጊዜው የሚሰጠው አበልና ነገሩም እንደተመደበበት ጒዳይ ከዚሁ ላይ ለመውሰድ ልማድ በሚፈቅደው
መሠረት የሚገኘው ሁሉ ነው፡፡

ቊ 1171፡፡ የእንስሳት ውላጆች፡፡

(1) የእንስሳትን ወላጅ ባለሀብትነት በሚመለከተው ረገድ ባለሀብትነቱ የሚከተለው እንስቲቱን (እናቲቱን) ነው፡፡

(2) ስለዚህም የእንስቲቱ ባለሀብት የወላጁ ባለሀብት ነው፡፡


ቊ 1172፡፡ ስለ ሰብል (1) ባለመሬቱ ሲቃወመው፡፡

(1) ባለመሬቱ ሲቃወመው በሌላ ሰው መሬት ላይ የዘራ ሰው የጀመረውን ሥራ ለመቀጠል ወይም የዘራውን ሰብል ለመሰብሰብ መብት
የለውም፡፡

(2) ሰብሉ ተሰብስቦ እንደሆነ በሙሉ የባለመሬቱ ይሆናል፡፡

(3) ከዚህ በላይ በሁለቱ ንኡስ ቊጥሮች የተጻፉት ውሳኔዎች በማንኛውም ምክንያት ባለመሬቱ መቃወሙን ለመግለጽ ባልቻለበትም ጊዜ
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 1173፡፡ (2) ባለመሬቱ ሳይቃወም፡፡

(1) ባለመሬት ሳይቃወመው በሌላ ሰው መሬት ላይ ዘር የዘራ ሰው ሰው የጀመረውን ሥራ ወደ ፍጻሜ ለማድረስና የዘራውን ሰብል
ለመሰበሰብ መብት አለው፡፡

(2) ዘሩን የዘራው መሬቱ የራሱ ሀብት መስሎት ወይም በመሬቱ ላይ ሊዘራ መብት ያለው መስሎት የሆነ እንደሆነ ከሰብሉ ከአራት እጅ
ሦስቱን እጅ ለባለመሬቱ ለቆና አንዱን እጅ ሰብል ወስዶ መሬቱንም ለቆ ይሄዳል፡፡

(3) ዘሩን የዘራው መሬቱ የራሱ አለመሆኑን ወይም በመሬቱ ላይ ሊዘራ መብት የሌለው መሆኑን እያወቀ የሆነ እንደሆነ ሰብሉን በሙሉ
ለባለመሬቱ ለቆ ይሄዳል፡፡

(4) ከዚህ በላይ ባሉት በሦስት ንኡስ ቊጥሮች የተጻፉት ውሳኔዎች ባለመሬቱ በመሬቱ ላይ መዝራቱን እያወቀ ባይቃወምም የጸኑ
ይሆናሉ፡፡

ቊ 1174፡፡ (3) ይህ መብት የሚሠራበት ሁኔታ

(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር ለባለመሬቱ የታወቀለትን መብት፤ መሬቱ ቀድሞ የታሰረ ወይም ያልታሰረ ቢሆንም ባለ መሬቱ ማግኘት
ይገባዋል፡፡

(2) ሰብሉ ተሸጦ ወይም ተሰጥቶ ወይም ተበልቶ አልቆ እንደሆነ ባለመሬቱ ለርሱ የሚገባውን ሰብል በጠየቀበት ጊዜ ያለውን ግምቱን
የማግኘት መብት አለው፡፡

(3) ባለመሬቱ ሰብሉ በተሰበሰበ በአንድ ዓመት ውስጥ መብቱን ለማግኘት የሚገባውን ሳያደርግ የቀረ እንደሆነ የመጠየቅ መብቱን ያጣል፡፡

ቊ 1175፡፡ ስለ አትክልቶች፤ (1) የባለመሬቱን ፈቃድ በመጣስ የተተከለ፡፡

(1) ባለመሬቱ ሳይፈቅድ በሌላ ሰው መሬት ላይ ዛፍ የተከለ ሰው ከተከላቸው ዛፎች ላይ አንዳችም መብት አይኖረውም፡፡

(2) አትክልቱ ለባለርስቱ ስላስገኘው የሀብት ጥቅም አንዳችም ኪሣራ ለመጠየቅ መብት አይኖረውም፡፡

(3) ዛፉ ከመሬቱ ላይ ይነሳልኝ ብሎ ባለርስቱ የጠየቀ እንደሆነ ለማንሻው የሚያስፈልገውን ወጪ የሚችለው ተካዩ ነው፡፡
ቊ 1176፡፡ (2) በባለመሬቱ ፈቃድ የተተከለ፡፡

(1) ዛፉን የተከለው ሰው፤ ባለርስቱ ፈቅዶለት የሆነ እንደሆነ ባላትክልቱን በማናቸውም ጊዜ ለማስለቀቅ ቢፈልግ፤ ሊከፍለው የሚገባው
ኪሣራ የሚወሰነው ሁለቱ ወገኖች ባደረጉት ስምምነት መሠረት ነው፡፡

(2) ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ለማድረግ ባይችሉ ግን ከዚህ ቀጥሎ ያለው ቊጥር ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 1177፡፡ (3) ስለ ኪሣራ፡፡

(1) በላይኛው ቊጥር የተመለከተው ኪሣራ የሚከፈለው የተተከሉት ዛፎች የሚሰጡት መደበኛ ጥቅም በሰብል አሰጣጥ የሆነ እንደሆነ
ዛፎቹ በዐሥር ዓመት ውስጥ ይሰጣሉ ተብሎ ከሚታሰበው ሰብል እኩሌታው ነው፡፡

(2) የተተከሉት ዛፎች የሚሰጡት መደበኛ ጥቅም በሰብል አሰጣጥ ያልሆነ እንደሆነ የኪሣራው አከፋፈል የሚታሰበው፤ ዛፎቹ በ 0 ዓመት
ከሚያወጡት የዋጋ ግምት እኩሌታው ነው፡፡

(3) በሁለቱም ሁኔታዎች ቢሆን የዐሥር ዓመቱ የጊዜ ውሳኔ መቈጠር የሚጀመረው ባለመሬቱ የዛፉ የጋራ ባለሀብትነት ፍጻሜ እንዲያገኝ
ሲል አሳቡን ከገለጸበት ቀን አንሥቶ ነው፡፡

ቊ 1178፡፡ በሌላው ሰው መሬት ላይ ሕንፃ ስለመሥራት 1/ባለመሬቱ ሲቃወም፡፡

(1) ባለመሬቱ በግልጽ እየተቃወመው ማንም ሰው በሌላ ሰው መሬት ላይ ሕንፃ የሠራ እንደሆነ በዚሁ ሕንፃ ላይ አንዳችም መብት
አይኖረውም፡፡
(2) ባለመሬቱ እንደመረጠ ሕንጻ የሠራውን ሰው ያለ ኪሣራ ለቆ እንዲሄድ ለማድረግ ወይም ባለሕንጻው በራሱ ኪሣራ አፍርሶ እንዲሄድ
ለማድረግ ይችላል፡፡

(3) ከዚህ በላይ ባሉት በሁለቱ ንኡስ ቊጥሮች የተጻፉት ውሳኔዎች በማናቸውም ምክንያት ባለመሬቱ መቃወሙን ባልቻለበትም ጊዜ
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 1179፡፡ 2/ ባለመሬቱ ሳይቃወም፡፡

(1) ባለመሬቱ ሳይቃወም በሌላ ሰው መሬት ሕንፃ የሠራ ሰው የዚሁ ሕንጻ ባለሀብት ነው፡፡

(2) ባለመሬቱ ከባለ ሕንጻው ጋራ የተስማሙበትን ግምት በመክፈል ወይም በግምቱ ያልተስማማ እንደሆነ ከዚህ በታች ባለው በቊጥር
ሺ)' በተመለከተው መሠረት የሕንፃውን ግምት በመክፈል ሕንፃውን ለማስለቀቅ ይችላል፡፡
ስለሆነም የሕንጻው ባለሀብት በማናቸውም ጊዜ በራሱ ኪሣራ ሕንጻውን አፍርሶ ለመሄድ መብት አለው፡፡
(3) ከዚህ በላይ ባሉት በሁለቱ ንኡስ ቊጥሮች የተጻፉት ውሳኔዎች ባለመሬቱ የሕንፃውን መሠራት እያወቀ ሳይቃወም በቀረበትም ጊዜ
የሚጸኑ ናቸው፡፡

ቊ 1180፡፡ ስለ ግምት አወሳሰን፡፡

(1) ከዚህ በላይ በቊጥር 1179 በተመለከተው መሠረት ለባለ ሕንጻው የሚከፍለው ግምት፤ በዚህ ፍትሐ ብሔር ሕግ ስለ ግልግልና ስለ
ስምምነት በሚለው በ!ኛው አንቀጽ መሠረት ይሆናል፡፡

(2) ሕንጻውን የሠራው ሰው መሬቱ የእርሱ አለመሆኑን አውቆ ወይም ማወቅ ሲገባው ወይም መብት የሌለው መሆኑን እያወቀ የሆነ
እንደሆነ ባለመሬቱም የሕንፃውን መሠራት እያወቀ ሳይቃወመው ሠርቶ እንደሆነ ሕንጻውን ባለመሬቱ በዋጋ እንዲያስቀረው የሚስማማ
ሲሆን ለሕንጻው ዋጋ ሊከፈል ከሚገባው ግምት ከአራት እጅ አንዱን እጅ ብቻ ባለመሬቱ ከፍሎ ሕንፃውን ያስቀረዋል፡፡

ቊ 1181፡፡ የሌላ ሰው በሆነ መሥሪያ (ማቴሪያል) ሕንፃ ስለ መሥራት፡፡

(1) የራሱ ባልሆኑ መሥሪያዎች ሕንጻ የሠራ፤ የአትክልት ድርጅቶችን ያቋቋመና ሌሎችንም ሥራዎች የፈጸመ ባለመሬት ለሠራባቸው
መሥሪያዎች ባለሀብት ይሆናል፡፡

(2) የዕቃዎቹን ዋጋ መክፈልና አስፈላጊም ሲሆን ኪሣራና ካሣ እንዲከፈል ሊፈረድበት ይቻላል፡፡

(3) የመሥሪያዎቹ ባለሀብት ዕቃውን ነቅሎ ለመውሰድ መብት የለውም፡፡

ቊ 1182፡፡ ዐይነቱን መስጠት፡፡

(1) አንድ ሰው የራሱ ገንዘብ ያልነበረውን ነገር ያበጀ ወይም የለወጠ እንደሆነና ከታደሰው ነገር ይልቅ የሥራው ግምት ብልጫ ያለው ሆኖ
የተገኘ እንደሆነ ይህ ነገር የሠራተኛው ሀብት ይሆናል፡፡

(2) በዕቃው ላይ ያዋለው የሥራ ዋጋ የበለጠ ቢሆንም እንኳ ሠራተኛው በቅን ልቡና ያላደረገው ሲሆን፤ ዳኞች የአዲሱ ዕቃ ባለሀብትነት
ለዕቃው ባለሀብት እንዲሰጥ ለመፍቀድ ይችላሉ፡፡

(3) ከውል ውጭ ስለሚደርሱ አላፊነቶችና ያላገባብ ስለ መበልጸግ የተነገሩት የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1183፡፡ ቅልቅል ወይም ተጨማሪ ነገር፡፡

(1) በጣም ሳይበላሹ ወይም በከባድ ሥራ ወይም በብዙ ኪሣራ ካልሆነ ሊለያዩ ወይም ሊላቀቁ የማይችሉ እስከ መሆን የተቀላቀሉ ወይም
የተጣበቁ የብዙዎች ሀብቶች የሆኑ የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ሲያጋጥሙ ባለጒዳዮቹ በነገሩ መቀላቀል ጊዜ የየራሳቸውን ገንዘብ በነበረው ግምት
ምክንያትና መጠን በመቀላቀል አዲስ ለሆነው ነገር የጋራ ባለሀብቶች ይሆናሉ፡፡

(2) ነገር ግን ሁለት የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ሲቀላቀሉ ወይም ሲዋሐዱ አንዱ የሌላው ተጨማሪ ነው ተብሎ ሊገመት የሚገባው ሲሆን
በመቀላቀል አዲስ የሆነውን ነገር የዋናው ነገር ባለሀብት ይወስደዋል፡፡
(3) ከውል ውጭ ስለሚደርሱ አላፊነቶችና ያላገባብ ስለ መበልጸግ የተነገሩት የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ክፍል 2፡፡
ባለሀብትነትን ስለ ማስተላለፍ፡፡
ቊ 1184፡፡ የማስተላለፉ ምክንያቶች፡፡

ባለሀብትነት የሚተላለፈው በሕግ ወይም የግል ባለጒዳዮች በሚያደርጉዋቸው ሕጋውያን ተግባሮች ይሆናል፡፡
ቊ 1185፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ባለሀብትነት (ባለርስትነት) በውል ወይም በኑዛዜ ለማስተላለፍ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ማስመዝገብ
አስፈላጊ ነው፡፡

ቊ 1186፡፡ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፡፡

(1) ግዙፍነት ያላቸው የተንቀሳቃሽ ንብረቶች ባለሀብነት ንብረቱን በመግዛት ወይም በሌላ አኳኋን ያገኘው ወይም በኑዛዜ የተሰጠው ሰው
ንብረቱን እጅ ባደረገው ጊዜ የተላለፈ ይሆናል፡፡

(2) ልዩ የሆኑ አንዳንድ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሚመለከቱት የሕጎች ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1187፡፡ ሀብትነትን ስለ መጠበቅ፡፡

የአንድ ንብረት ሀብትነቱ የሚተላለፍበት ለሌላ ጊዜ ይሁን በማለት የተደረጉ የውል ቃሎች በሕጉ መሠረት ባንድ የመንግሥት መዝገብ
የተጻፉ ሆነው ሦስተኛ ወገኖች በግልጽ የተቀበሏቸው ካልሆኑ በቀር ወይም በመንግሥት መዝገብ የተጻፉ ሆነው ሦስተኛ ወገኖች
እንዲያውቋቸው ካልተደረገ በቀር መቃወሚያ ሊሆኑባቸው አይቻልም፡፡

ክፍል 3፡፡
ስለ ሀብትነት መቅረት፡፡
ቊ 1188፡፡ ስለ ዕቃው መጥፋት፡፡

ሀብትነቱ የዋለበት ዕቃ የተበላሸ ወይም ሀልዎቱ (መኖሩ) የጠፋ እንደሆነ ሀብትነቱ ይቀራል፡፡

ቊ 1189፡፡ ሀብትነቱ የሌላ ሰው ስለ መሆኑ፡፡


እንደዚሁም ሀብትነቱ የሚቀረው በሕግ መሠረት ሀብትነቱ ለሌላ ሰው የሆነ ወይም የተላለፈ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1190፡፡ ከርስት መዝገብ ስለ መሰረዝ፡፡

በርስት መዝገብ የተመዘገቡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሀብትነት በርስትነት ከዚሁ መዝገብ ሲሰረዝ ሀብትነቱ (ርስትነቱ) ይቀራል፡፡

ቊ 1191፡፡ የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች መብትን ስለ መተው፡፡

ግዙፍነት ያላቸው የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ባለሀብትነት ባለሀብቱ በማያጠራጥር ሁኔታ መብቱን የመተውን ሐሳብ ካስታወቀ ቀሪ
ይሆናል፡፡

ቊ 1192፡፡ ሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን፡፡

ግዙፍነት ያለው ያንድ የሚንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት ሀብቱ የሚገኝበትን ቦታ ወይም ሀብቱ መሆኑን ባለማወቅ ዐሥር ዓመት
ያልተገለገለበት እንደሆነ መብቱን ያጣ ሆኖ ይቀራል፡፡

ክፍል 4፡፡
ስለ ሀብትነት ማስረጃ፡፡
ቊ 1193፡፡ የሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ሀብቶች፡፡

(1) የሚንቀሳቀስ ግዙፍ ነገር ባለይዞታ (ባለእጅ) የሆነ ሰው በራሱ ስም እንደያዘውና የዚሁ ነገር ባለሀብት (ባለቤት) እንደሆነ ይገመታል፡፡

(2) ይህ ግምት እንደነገሩ አካባቢ ሁኔታ ልክ አይደለም ብሎ የሚከራከረው ሰው ትክክል ግምት ላለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡

ቊ 1194፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፤ ጠፍ የሆኑና ባለቤት (ጌታ) የሌላቸው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ጠፍ የሆኑና ባለቤት የሌላቸው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች የመንግሥት ንብረቶች ናቸው፡፡

ቊ 1195፡፡ የባለሀብትነት የርስት ምስክር ወረቀት፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነትን በማወቅ በአስተዳደር ክፍል ለአንድ ሰው የተሰጠ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ይህ ማስረጃ
የተሰጠው ሰው የዚሁ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት እንደሆነ ያስቈጥረዋል፡፡
(2) የዚህ ዐይነት የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የሚሰጥበት ደንብና ሥርዐት እንዲሁም በምን ጊዜ ሊታደስ እንደሚገባው በአስተዳደር
ክፍል ደንብ ይወሰናል፡፡

(3) እንዲሁም የአስተዳደሩ ክፍል ያደረገውን ወጪ ለመተካትና በዚህም ምክንያት በአስተዳደሩ ክፍል ላይ ለሚደርሰው አላፊነት ዋስትና
ለማግኘት መጠባበቂያ እንዲሆን የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የመሰጠቱ ሥራ በሚሠራበት ጊዜ የሚከፈለው ታክስ ልክ በአስተዳደር
ክፍል ደንብ ይወሰናል፡፡

ቊ 1196፡፡ (1) ተቃራኒ ማስረጃ፡፡

ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነገሮች ለማስረዳት የተቻለ እንደሆነ፤


(ሀ) የባለርስትነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ከደንብ ውጭ በሆነ አሠራር ወይም ይህን ለመስጠት ሥልጣን በሌለው የአስተዳደር ክፍል
የሆነ እንደሆነ፤

(ለ) የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው በማይረጋ ጽሑፍ መሠረት የሆነ እንደሆነ ወይም ለከሳሹ መቃወሚያ ሊሆን በማይችል
ጽሑፍ መሠረት የሆነ እንደሆነ፤

(ሐ) ከሳሹ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘው፤ የገዛው የእርስት የምስክር ወረቀት ከተሰጠ በኋላ መሆኑን ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ከዚህ
በላይ የተነገረው የሕሊና ግምት ፈራሽ ይሆናል፡፡

ቊ 1197፡፡ (2) የአስተዳደር ክፍል ግዴታዎች፡፡

(1) አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለሚመለከት ነገር የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ከመሰጠቱ በፊት የአስተዳደሩ ክፍል፤ ለዚሁ
ለማይንቀሳቀሰው ንብረት ካሁን በፊት ለሌላ ሰው ሰጥቶ የነበረው የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት እንዲመለስለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) ይህ የርስት የምስክር ወረቀት ጠፍቷል የሚያሰኝ ምክንያት የቀረበለት እንደሆነ አንድ አዲስ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ይሰጠኝ
ብሎ የሚጠይቀው ሰው ይህ የቀድሞው ወረቀት ያለ መሰረዙ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለማስወገድ እንዲቻል
አዲስ የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ጠያቂው በቂ የሆነ ዋስትና እንዲሰጥ የአስተዳደሩ ክፍል ሊያስገድደው ይችላል፡፡

ቊ 1198፡፡ (3) የመንግሥት አላፊነት፡፡

(1) በአንድ ሰው፤ ለአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከደንብ ውጭ የተሰጠውን ወይም ይህን ለመስጠት ሥልጣን በሌለው መሥሪያ ቤት
የተሰጠውን የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት በማመን በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ የመያዣ መብት ካገኘ በኋላ የባለሀብትነት የምስክር
ወረቀት ትክክለኛ ባለመሆኑ ምክንያት ለሚደርስበት ጉዳት መንግሥት አላፊ ነው፡፡

(2) እንዲሁም የአስተዳደሩ ክፍል ሳይሰርዘው የቀረውን የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት በማመን በአንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ
አንድ መብት ያገኘ ሰው ለሚደርስበት ጉዳት አላፊው መንግሥት ነው፡፡

(3) በአስተዳደር ክፍል ሹማምቶችና በማናቸውም ምክንያት በአላፊነት በሚጠየቁት ሰዎች ላይ መንግሥት ኪሣራውን የሚጠይቅበት
መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ቊ 1199፡፡ የርስት ወሰን፡፡

(1) የመሬቱ ርስት ወሰን የሚታወቀው በርስት ክፍል ፕላንና በመሬቱ ላይ በሚደረግ የወሰን ምልክት ነው፡፡

(2) በፕላኑ ላይ ባለው ወሰንና በመሬቱ ላይ በተደረገው ወሰን መካከል ልዩነት የተገኘ እንደሆነ የፕላኑ ወሰን ትክክለኛ ነው ተብሎ
ይገመታል፡፡
ቊ 1200፡፡ ስለ ግንብ ሥራዎች፤ ስለ ተክሎችና ስለ ሌሎች ሥራዎች፡፡

(1) ባንድ ቦታ ላይ የሚደረጉ ማንኛዎቹም ሥራዎች ተክሎችና ሌሎች ሥራዎች ከዚህ የሚከተሉት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው በባለ
ሀብቱ (በባለርስቱ) ኪሣራ የተሠሩና የራሱ እንደሆኑ ይገመታሉ፡፡

(2) ተቃራኒ ማስረጃ የማቅረብ መብት የተጠበቀ ነው፡፡


ቊ 1201፡፡ ስለ አጥር፡፡

ሁለት ርስትን የሚለይ ማናቸውም አጥር የሁለቱ ርስት ባለሀብቶች የጋራ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ ይኸውም ተቃራኒ ማስረጃ ከሌለና
ከነዚሁ ሁለት ቦታዎች አንዱ ብቻ አጥር ያለው ካልሆነ በቀር ነው፡፡
ቊ 1202፡፡ ስለ ቦይ፡፡
(1) ስለ ቦይ የአፈሩ አወጣጥ ወይም አጣጣል ከቦዩ በአንደኛው ወገን ብቻ የሆነ እንደሆነ የጋራ አለመሆኑን ያመለክታል፡፡

(2) ቦዩ አፈሩ ወደተጣለበት ወገን ያለው ሰው ብቻ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡

(3) ተቃራኒ ማስረጃ የማቅረብ መብት የተጠበቀ ነው፡፡


ቊ 1203፡፡ ስለ ውሃ ቧንቧዎች ስለጋዝና ኤሌክትሪክ ማደያ መሥመሮች፡፡
(1) የውሃ ቧንቧዎች የጋዝና የኤሌክትሪክ ማደያ መሥመሮችና ሌሎችም እንደዚሁ ከተዘጋጁበት መሬት ውጭ ቢገኙም እንኳ የሚነሡበት
የዋናው ድርጅት ተጨማሪዎች ሆነው የሚገመቱና የዋናው ክፍል ባለቤት ንብረት ሆነው የሚቈጠሩ ናቸው፡፡

(2) ተቃራኒ ማስረጃ የማቅረብ መብት የተጠበቀ ነው፡፡


ምዕራፍ 2፡፡
የባለሀብቱ መብቶችና ግዴታዎች፡፡
ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 1204፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) ሀብትነት ማለት በአንዱ ግዙፍ ንብረት ላይ ከሁሉ የሰፋ መብትን የያዘ ማለት ነው፡፡

(2) ይህ መብት በሕግ በተመለከቱት ሥርዐቶች ካልሆነ በቀር ሊከፋፈል ወይም ሊቀነስ ወይም ሊወሰን አይችልም፡፡
ቊ 1205፡፡ በመብቱ ውስጥ ስላለው ነገር በንብረቱ ስለ መገልገልና ስለ መጠቀም፡፡
(1) በሕጎችና በደንቦች ከሚደረገው የመብት መቀነስ በቀር ባለሀብቱ በመሰለው መንገድ ሀብቱን ሊገለገልበትና ሊጠቀምበት ይችላል፡፡
(2) ባለሀብት የሆነው ሰው በሕይወት ሳለ ወይም በሚሞትበት ጊዜ ዋጋ ተቀብሎ ወይም ዋጋ ሳይቀበል በንብረቱ ሊያዝዝበት ይችላል፡፡
ቊ 1206፡፡ የመፋለም መብት፡፡
ባለሀብት የሆነው ሰው መብት ሳይኖረው እጁ ካደረገው ሰው ወይም ከያዘው ሰው ላይ ሀብቱ ይገባኛል ሲል ለመፋለምና ማናቸውንም
የኀይል ተግባር ለመቃወም ይችላል፡፡
ክፍል 2፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ የተለዩ ደንቦች፡፡
ቊ 1207፡፡ ቦታውን ስለ ማጠር፡፡
ባለሀብቱ ቦታውን ማጠር ይችላል፡፡
ቊ 1208፡፡ ወሰን፡፡
ወሰኖቹ የሚያጠራጥሩ የሆኑ እንደሆነ ጎረቤቱ በጠየቀው ጊዜ እያንዳንዱ ባለሀብት (ባለርስት) ወሰኖቹን ለማረጋገጥ ርዳታ ማድረግ
አለበት፡፡
ቊ 1209፡፡ የመሬት ውስጥ ሀብትነት፡፡
የመሬት ሀብትነት (የመሬት ርስትነት) ማለት መሬቱን ሥራ ለማስያዝ ጠቃሚ እስከሆነው ጥልቀት ድረስ ያለውን የውስጥ ሀብትነትን
ጭምር የያዘ ነው፡፡
ቊ 1210፡፡ የመሬት ውስጥ ቊፈራ ወይም ሥራ፡፡
በራሱ መሬት ውስጥ ሥራዎችን የሚያደራጅ ወይም የሚቈፍር ባለሀብት (ባለርስት) የጎረቤቶቹን መሬት ማናጋት አይገባውም፤
እንደዚሁም በመሬቱ ላይ የሚገኙትን የሥራዎቹን ጥንካሬ አደጋ ወይም ጉዳት እንዳያገኛቸው ማድረግ ይገባዋል፡፡
ቊ 1211፡፡ የመሬት በላይ ሀብትነት፡፡
የመሬት ሀብትነት ማለት መሬቱን ሥራ ለማስያዝ ጠቃሚ እስከሆነውም ጥልቀት ድረስ ያለውንና የወደ ላይ ሀብትነትን የያዘ ነው፡፡
ቊ 1212፡፡ ስለ ቅርንጫፎችና ስለ ዛፍ ሥሮች፡፡
(1) ማናቸውም ሰው ወደ መሬቱ ላይ ተዘርግተው የገቡትን የጎረቤቱን የዛፎች ቅርንጫፎች በአንድ ወር ውስጥ እንዲቈርጥ በዳኛ ማስገደድ
ይችላል፡፡

(2) ያንድ መሬት ባለሀብት የማስታወቅ ግዴታ ሳይኖርበት ከወሰኑ መሥመር አልፎ በመሬቱ ውስጥ ለውስጥ የሚሄዱትን ሥሮች
ሊቈርጣቸው ይችላል፡፡
ቊ 1213፡፡ ስለ መሥራትና ተክል ስለ ማቋቋም፡፡
ባለሀብቱ በመሬቱ ላይ ለርሱ መልካም መስለው የታዩትን ሥራዎችና ተክሎች ለመሥራትና ለማቋቋም ይችላል፡፡
ቊ 1214፡፡ በመሬቱ ላይ ያለ መብት (1) መሠረቱ፡፡

(1) ባንድ መሬት ላይ ወይም ውስጥ የተቋቋሙ ሥራዎችና ሌሎች የጥበብ ሥራዎች ወይም ከመሬቱ ጋራ ነዋሪነት ባለው ሁኔታ የተያያዙ
ሁሉ ሌላ ባለሀብት ሊኖራቸው ይችላሉ፡፡

(2) የዚህ ባለሀብት መብት ለሌላ ንብረት የአገልግሎት ግዴታ ባለቤቶች ንብረቶች ደንብ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 1215፡፡ (2) የተጠበቁ ሁኔታዎች፡፡

(1) ያንድ ቤት ፎቆችን ወይም ክፍሎችን የጋራ ሀብትነት የሚመለከቱት ደንቦች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡
(2) እንዲሁም በሌላ ሰው መሬት ስለ ተሠሩት ሕንጻዎች ጒዳይ የተነገረው በዚህ አንቀጽ ቊጥሮች የተመለከተው ደንብ ተፈጻሚነት
የተጠበቀ ነው፡፡
ቊ 1216፡፡ በመሬቱ ላይ መግባትን ስለ መከልከል፡፡
ባለሀብቱ በመሬቱ ላይ ማንም ሌላ ሰው እንዳይገባ ለመከልከል ይችላል፡፡
ቊ 1217፡፡ አስፈላጊ የሆነ መግባት፡፡ (1) ሊደርስ የሚችል ጉዳት ወይም አደጋ፡፡

(1) አንድ ሰው በሌላ ሰው መሬት ውስጥ ካልገባ በቀር ሊደርስ ከሚችል ጉዳት ወይም ከተቃረበ አደጋ ሌላውን ሰው ሊጠብቀው ወይም
ራሱን ለመጠበቅ ያልቻለ እንደሆነ የዚህ መሬት ባለሀብት እንደዚህ ባለ ሁኔታ የሚደረገውን እቦታው ላይ መግባት መቻል አለበት፤
(መፍቀድ አለበት)፡፡

(2) ከዚህም የተነሣ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ ባለሀብቱ ተገቢ የሆነ ካሣ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1218፡፡ (2) አጥር ወይም ቤት ስለ ማደስ፡፡

(1) በአንድ መሬት ላይ የተሠራውን አጥር ወይም ቤት ለማደስ በጎረቤት መሬት ላይ ማለፍ አስፈላጊ ሲሆን ጎረቤት የሆነው መሬት
ባለሀብት በመሬቱ ላይ መተላለፍን መፍቀድ አለበት፡፡

(2) በዚህ የተነሣ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ ባለሀብቱ ኪሣራ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1219፡፡ (3) የጠፉ ነገሮች ወይም እንስሶች፡፡

(1) በተፈጥሮ ኀይል ወይም በድንገተኛ ሁኔታ ማንኛዎቹም ዕቃዎች በሌላ ሦስተኛ ሰው መሬት ላይ የተገኙ እንደሆነ ወይም እንደ ከብቶች
እንደ ንብ መንጋ እንደ ዶሮ የመሰሉ እንስሶች ተላልፈው እንዲሁ የተገኙ እንደሆነ ባለመብት የሆኑት ሰዎች እንዲፈልጓቸውና
እንዲወስዷቸው የመሬቱ ባለሀብት በመሬቱ ውስጥ መግባትን መፍቀድ አለበት፡፡

(2) ከዚህም የተነሣ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ የመሬቱ ባለሀብት ከዚሁ ባለመብት ላይ ኪሣራ ለመጠየቅና ኪሣራው እስኪከፈለው ድረስ
ዕቃውን ወይም እንስሳውን የመያዝ መብት ሊኖረው ይችላል፡፡

(3) ባለመሬቱ ራሱ ወዲያውኑ ፈልጎ የጠፋውን ዕቃ ወይም እንስሳ ባለመብት ለሆነው ሰው የሰጠ እንደሆነ ሌላ ሰው በመሬቱ ላይ
እንዳይገባ ለመቃወም ይችላል፡፡
ቊ 1220፡፡ ስለ መተላለፊያ ቦዮችና ቧንቧዎች፡፡
(1) ባለርስቱ የሚደርስበትን ኪሣራ በሙሉና አስቀድሞ ካገኘ በራሱ መሬት ላይ ለሌሎች መሬቶች ጥቅም የሚሆኑ የውሃ ቧንቧዎች የጋዝ
መተላለፊያዎች የኤሌክትሪክ መሥመሮችና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎች ሥራዎች እንዲተላለፉ መፍቀድ አለበት፡፡

(2) አሠራሩም ሌላ መሬት የአገልግሎት ግዴታ ላለበት መሬት የበለጠ በሚመች አኳኋንና ከሁሉ ያነሰ ኪሣራ በሚያስከትል ዐይነት
መፈጸም አለበት፡፡

(3) የዚህም መሬት ባለቤት የተቋቋመው ሥራ በራሱ ኪሣራ ከመሬቱ ላይ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲዘዋወርና እንዲቋቋም በማናቸውም ጊዜ
ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 1221፡፡ የመተላለፍ መብት (1) መሠረቱ፡፡


መሬቱ የተዘጋበት ወይም በመሬቱ ለመጠቀም ለሕዝብ በሚያገለግለው መንገድ ላይ በቂ ያልሆነ መውጫ ያለው ባለሀብት ሊያደርስ
በሚችለው ጉዳት መጠን ግምቱን ከከፈለ አስፈላጊውን መተላለፊያ እንዲሰጠው ጎረቤቱን ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 1222፡፡ (2) በእጅ ያለ መሬት፡፡

(1) የመተላለፊያ መንገድ መብት የመተላለፊያ መንገድ እንዲወጣ በመሬቱ ተፈጥሮ ሁኔታ ምክንያት በጣም ሊጠየቅ በሚችለው ጎረቤት
ላይ ይፈጸማል፡፡
(2) ለዚህም ነገር የመሬቶቹና የመተላለፊያዎቹ ሁኔታ መተላለፊያ የታጠረበት (የተከለለው) ጠቃሚነትና መተላለፊያ እንዲወጣበት
የተጠየቀው መሬት በመተላለፊያው መንገድ ምክንያት የሚደርስበትን ጉዳት ማመዛዘን ያስፈልጋል፡፡

ቊ 1223፡፡ (3) የመሬት ክፍያ ሲሆን፡፡


መሬቱ መተላለፊያ ያጣበት ምክንያት መሬቱ ተከፍሎ በመሸጡ በልዋጭ በክፍያ ወይም በማናቸውም ውል ምክንያት የሆነ እንደሆነ
የመተላለፊያው መንገድ እነዚህ ውሎች በተፈጸሙባቸው መሬቶች ላይ ካልሆነ በቀር ይጠየቅ ዘንድ አይቻልም፡፡

ቊ 1224፡፡ (4) አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎች፡፡


የመተላለፊያ መብት ያለው ባለጥቅም በዚሁ መብቱ ቢገለገል መተላለፊያ መንገድ ለወጣበት መሬት የሚደርስበት ጉዳት አነስተኛ ይሆን
ዘንድ አስፈላጊዎች የሆኑትን እንዲሠራና እንዲጠብቅ ሊገደድ ይቻላል፡፡

ቊ 1225፡፡ በባለሀብትነት መብት አለመጠን ስለ መገልገል፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ባለሀብቱ በመብቱ በሚገለገልበት ጊዜ የጎረቤቱ ርስት ጥቅም የሚቀነስበትን ወይም የሚጎዳበትን ማናቸውንም ከመጠን ያለፈ ነገር
ከመሥራት መጠበቅ ይገባዋል፡፡

(2) በተለይም ጢስን ወይም ጠለሸትን ወይም በጉርብትና አኗኗር ሊታገሡት ከሚቻለው በላይ የሆኑትን ሽታዎች ጩኸቶች ወይም ንውጽ
ውጽታዎች ወደ ጎረቤት እንዲሄድ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

(3) እነዚህም የሚወሰኑት የአገሩን ልማድ በመከተልና እንዲሁም የመሬቱን አቀማመጥና የተፈጥሮውን ዐይነት በመመልከት ነው፡፡

ቊ 1226፡፡ (2) ስለ ቅጣት፡፡


አንድ ባለሀብት በመብቱ ከመጠን በላይ በመገልገሉ ምክንያት ማናቸውም ሰው ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፤ ወይም ጉዳት እንደሚደርስበት
የሚያሠጋው ሆኖ ሲገኝ በሚደርስበት ጉዳት የኪሣራ መጠየቁ መብት ሳይነካበት የተባለው ባለሀብት ጉዳት ያደረሰበትን ነገር እንደነበረ
እንዲያደርግ ወይም ጉዳት ያደርሳል ተብሎ የተሠጋበት ነገር እንዳይደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲፈጽም ሊከሰው ይችላል፡፡
ቊ 1227፡፡ በባለሀብትነት መብት ላይ የተሰጡት የመብት ወሰኖች የማይታለፉ ስለ መሆናቸው፡፡
(1) የባለሀብቶች ልዩ መብቶችን የሚቀንሱት ከዚህ በላይ በተመለከቱት ቊጥሮች የተነገሩት በርስት መዝገብ ባይጻፉም እንዳሉ የሚቈጠሩ
ናቸው፡፡
(2) በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስምምነት ሊሰረዙ ወይም ሊለዋወጡ ሊሻሻሉ አይቻልም፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ ውሃዎች ባለሀብትና በውሃዎች ስለ መገልገል፡፡
ቊ 1228፡፡ ለኅብረት ኑሮ ጥቅም በቀደምትነት አስፈላጊዎች ስለ መሆናቸው፡፡
(1) ፈሳሾችም ቢሆኑ ወይም ባይሆኑ ውሃዎች ለኅብረት ኑሮ ጥቅም ከሁሉ በፊት የተመደቡ ናቸው፡፡

(2) ለኅብረት ኑሮ ጥቅም አስፈላጊዎች እንደመሆናቸውም መጠን የሕዝብ ባለሥልጣኖች የሚጠባበቋቸውና የሚጠብቋቸው ናቸው፡፡
ቊ 1229፡፡ የውሃ ባለሀብት ስለ መሆን፡፡
ውሃ የግል ሀብት ተብሎ የሚገመተው በሰው እጅ በተሠራው በውሃ ማጠራቀሚያ በኩሬ ወይም ለውሃ በተበጀ ጒድጓድ ውስጥ ሁኖ
ዐውቆ የማይፈስ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 1230፡፡ የውሃ ሕጋዊ ሁኔታ፡፡
(1) ውሃው የወል የጋርዮሽ ሀብት እንዲሆን ወይም ለጥቅም እንዲውል የሚያደርጉ ሁኔታዎችና እንዲሁም የውሃው የንብረት ግዴታና
የመገልገል መብቶች በዚሁ አንቀጽ በተነገሩት ድንጋጌዎች የተወሰኑ ናቸው፡፡
(2) የውሃ መገደቢያ ወይም ማድረጊያ የሆኑትን የኅብረት ሀብቶችን ባለሀብትነት የሚመለከቱት የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ
ናቸው፡፡

(3) እንደዚሁም የልዩ ሕጎች ድንጋጌዎችና በጠቅላላ ወይም ለአንድ ክፍል በተሰጡት የአስተዳደር ደንቦች የሚገኙት ድንጋጌዎች
እንደተጠበቁ ናቸው፡፡
ቊ 1231፡፡ ስለ ዳኞች ሥልጣን፡፡
(1) ውሃው ሊጠቅማቸው በሚችል ሰዎች መካከል ክርክር የተነሣ እንደሆነ ዳኞች ፍርዳቸውን ሲሰጡ ለሀብትነት የሚገባውን ክብር
በመስጠት ልዩ ልዩ የሆኑት ጥቅሞች የሚስማሙበትን መንገድ መፈለግ አለባቸው፡፡

(2) ዳኞቹ በሚሰጡት ውሳኔ ምናልባት ከባለሀብትነት መብቶች ላይ የደረሱ ጒዳቶች ቢኖሩ በሕግ የተደነገገ ሌላ ነገር ከሌለ በቀር፤ የጉዳት
ኪሣራን የሚያሰጡ ናቸው፡፡

ቊ 1232፡፡ ውሃውን ለቤት ጒዳይ ስለ ማዋል፤ (1) የባለሀብቱ መብቶች፡፡


የአንድ መሬት ባለሀብት በመሬቱ ላይ ወይም በመሬቱ ውስጥ የሚገኘውን ውሃና በመሬቱ አቋርጦ የሚያልፈውን ወይም በመሬቱ ወሰን
የሚሄደውን ውሃ ለግል ጥቅሙ፤ ለቤቱ ሰዎች ጥቅም ለማዋልና መንጋውን ሊያጠጣበት ይችላል፡፡

ቊ 1233፡፡ (2) የጎረቤቶች መብት፡፡


ጎረቤቶች ከውሃው ዋጋ እጅግ የበዛ የሆነውን የማይመዛዘን ገንዘብ ካልከፈሉ በቀር ውሃ በሌላ ቦታ የማያገኙ በሆኑ ጊዜና የውሃው ባለ
ሀብትም በመሬቱ ላይ የሚገኘው የውሃው ብዛት ለራሱ ቤት አስፈላጊ ከመሆን አልፎ የሚተርፍ በሆነ ጊዜ ለጎረቤቶቹ አስፈላጊ የሆነውንና
ከብቶቻቸውን የሚያጠጡበትን የግድ አስፈላጊ የሆነውን ውሃ መስጠት አለበት፡፡

ቊ 1234፡፡ (3) በጎረቤቶቹ መብት ላይ ስለሚሰጠው ደንብ፡፡

(1) ጎረቤቶቹ በዚህ ባላቸው መብት የሚገለገሉበትን አኳኋን የሚያመለክት ደንብ ለአእምሮ ተስማሚ በሆነ ዐይነት ባለሀብቱ መወሰን
ይችላል፡፡
(2) ለጎረቤቶቹ በታወቀላቸው በዚህ መብት በመገልገላቸው ምክንያት የመሬት ባለሀብት በመሬቱ የሚገለገልበት ወይም የሚጠቀምበት
ነገር ከፍ ባለው ዐይነት የተቀነሰ ወይም የታወከ እንደሆነ፤ እነዚህ ጎረቤቶቹ የሚገባውን ኪሣራ እንዲሰጡት ለማስገደድ ይችላል፡፡
ቊ 1235፡፡ ስለ ተከለከሉ ሥራዎች፡፡
(1) በጒድጓድ ውሃ በምንጭ ውሃ ወይም በፈሳሽም ሆነ ወይም በማይፈስ በሌላ ውሃ የመገልገል መብት ያላቸው ሰዎች፤ ይህን
የሚገለገሉበትን ውሃ ለማበላሸት የሚችል በመሬት ውስጥ እንደሚደረግ የእድፍ ውሃ መሄጃ እንደ ሽንት ቤት ያለው ማናቸውም ሥራ
እንዳይሠራ ለመቃወም ይችላሉ፡፡

(2) ይህ የተጠቀሰው ሥራ የባለጥቅሞቹን መብት በመናቅ ተሠርቶ እንደሆነም፤ የተባሉት ባለጥቅሞች ሥራው እንዲፈርስ ለማስገደድ
ይችላሉ፡፡
ቊ 1236፡፡ ስለ መስኖ ውሃ (1) የባለሀብቱ መብት፡፡

(1) ማንም ሰው በመሬቱ ላይ አቋርጦ የሚያልፈውን ወይም በመሬቱ ወሰን ላይ የሚወርደውን ውሃ መሬቱን ለማጠጣት ሲገለገልበት
ይችላል፡፡

(2) ይህም ስለተባለ መብቱ ለቤት አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ወይም መንጋቸውን ለማጠጣት በመሬቱ ላይ በሚገኘው ወይም
መሬቱን አልፎ ከመሬቱ በታች በሚወርደው ውሃ የሚጠቀሙትን (የሚገለገሉትን) ሰዎች በሚጎዳ አኳኋን ሊሠራበት አይችልም፡፡

ቊ 1237፡፡ (2) ለቤት አገልግሎት የሚሆን ውሃ ቀደምትነት ያለው ስለ መሆኑ፡፡


(1) መሬትን በመስኖ በማጣጣት የሚደረገው የውሃ መገልገል፤ ይህንኑ ውሃ ለቤት አገልግሎት ሳይሆን በሌላ አኳኋን የሚገለገሉበትን
ሰዎች የሚጎዳ ወይም ይጎዳል ተብሎ የሚያሠጋ በሆነ ጊዜ እነዚሁ ሰዎች በውሃው ለመገልገል መብት አለን የሚሉበትን ለማስረዳት በቻሉ
ጊዜ የተባለውን አዲሱን የውሃ መገልገል ለመቃወም ይችላሉ፡፡

(2) በዚሁ መሬት ላይ በውሃው ለመጠቀሚያ የሚሆኑ ግልጽ የሆኑ የታወቁ ትልልቅ ሥራዎች ወይም የማቋቋም ሥራዎች ተፈጽመው
እንደሆነ ባለመብቶቹ ለቤት አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ውሃውን ለሌላ ጥቅም ለማዋል በውሃው ለመጠቀም ያገኙት መብት አላቸው
ይባላል፡፡
ቊ 1238፡፡ (3) ቅጣት፡፡
ዳኞች ከወደታች የሚገኙት ባለመሬቶች በውሃው ለመጠቀም ያገኙት መብት መኖሩን ያወቁ እንደሆነ ይህን ያገኙትን መብታቸውን
በሚጎዳው መጠን ከወደ ላይ ባለው መሬት ላይ የተጀመሩት ወይም የተፈጸሙት ሥራዎችና የተቋቋሙት ነገሮች እንዲቋረጡ ወይም
ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ ያዝዛሉ፡፡

ቊ 1239፡፡ (4) ለባለሀብቱ ስለሚገባው ኪሣራ፡፡


ከወደ ላይ ያለውን መሬት በላዩ አቋርጦ በሚያልፈው ወይም በወሰኑ ላይ በሚሄደው ውሃ እንዳይገለገል በሚወሰነው ክልከላ ምክንያት
መሬቱን ለማልማት የማይቻል ወይም በልማቱ ላይ ጉዳት የሚያደርስበት የሆነ እንደሆነ ከወደ ላይ ላለው መሬት ባለሀብት ኪሣራ
ይገባዋል፡፡
ቊ 1240፡፡ (5) የኪሣራው ልክ፡፡

(1) የዚህን የኪሣራውን ልክ ዳኞች በርትዕ መሠረት ይወስናሉ፡፡

(2) ዳኞች ስለ ኪሣራው ውሳኔ የሚሰጡት የነገሩን ሁኔታዎች ሁሉ በተለይም በውሃው እንዳይገለገል በመከልከሉ ምክንያት ወደ ላይ
ከሚገኘው መሬት ዋጋ የተቀነሰውን ወደ ታች ያሉት ሰዎችም በውሃው ከመገልገላቸው የተነሣ የሚያገኙትን ጥቅም በማመዛዘን ነው፡፡

(3) በማናቸውም ሁኔታ ኪሣራው፤ በቅን ልቡናና ከመሬቱ ወደ ታች ያሉት በውሃው የሚገለገሉት ሳይቃወሙዋቸው የተሠሩትንና ዳኞች
ከአገልግሎት ውጭ ያደረጉዋቸውን ሥራዎችና የተቋቋሙትን ነገሮች ዋጋ የሚጨምር ነው፡፡

ቊ 1241፡፡ (6) ባለሥልጣን ዳኞች፡፡


ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች የተመለከቱትን ክርክሮች ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው ዳኞች እነዚህ ከዚህ በላይ የተነገሩት ሥራዎች
በተደቀኑበት ወይም በተፈጸሙበት መሬት ላይ ያለውን ስፍራ የሚዳኙት ናቸው፡፡

ቊ 1242፡፡ ውሃውን ለእንዱስትሪ አገልግሎት ስለ ማዋል፡፡ (1) የባለሀብቱ መብት፡፡

(1) የመሬቱ ባለሀብት መሬቱን አቋርጦ በሚያልፈው ወይም በመሬቱ ወሰን ላይ በሚሄደው ውሃ ወፍጮን ለመትከል የልብስ ማጠቢያን
ወይም የሰው መታጠቢያን የመሳሰለ የእንዱስትሪን ወይም የንግድን ድርጅት በማቋቋም ሊገለገልበት ይችላል፡፡

(2) እርሱም ውሃው ከመሬቱ ወደ ውጭ በሚወጣበት ጊዜ ውሃውን ያልተበላሸና ውሃው ለሚሄድላቸው ሰዎች አገልግሎት ለመሆን
እንዲችል አድርጎ መልቀቅ አለበት፡፡

ቊ 1243፡፡ (2) የነዚህ መብቶች አወሳሰን፡፡

(1) ባለሀብቱ ውሃው ከመሬቱ ወደ ውጭ በሚወጣበት ጊዜ ውሃውን ያልለቀቀው እንደሆነ ወይም አበላሽቶ ወይም ለአንድ አገልግሎት
የማይሆን አድርጎ የለቀቀው እንደሆነ፤ ስለ መስኖ ውሃ አገልግሎት በሚናገሩት ከዚህ በላይ የተጻፉት ቊጥሮች የተመለከቱት ድንጋጌዎች
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) ይህም ስለ ተባለ ከወደ ላይ ለሚገኘው መሬት ባለሀብት በቅን ልቡና ከወደታች ያሉት ባለመብቶች ሳይቃወሙ ለተፈጸሙትና ዳኞች
ከአገልግሎት ውጭ ለአደረጓቸው ሥራዎች ወይም ለተቋቋሙት ድርጅቶች ዋጋ ካልሆነ በቀር አንዳች ኪሣራ አይከፈለውም፡፡
ቊ 1244፡፡ ከውሃ ስለሚገኝ ኀይል፡፡
የውሃውን ኀይል በማከፋፈል በማመላለስ ወይም በመሸጥ ወራጆች የሆኑትን ውሃዎች ለማከናወን የሚችሉት ከመንግሥት ባለሥልጣኖች
ኮንሴሲዮን የተሰጣቸው ድርጅቶች ብቻ ናቸው፡፡
ቊ 1245፡፡ ስለ ዝናም ውሃ፡፡
(1) የአንድ ቤት ባለሀብት (የቤት ጌታ) የጣራውን የዝናም ውሃ በራሱ መሬት ላይ እንዲወርድ ዐይነት እንጂ በጎረቤት መሬት ላይ
በማይወርድበት ዐይነት አድርጎ ለመሥራት ይገደዳል፡፡

(2) የሚያስፈልግ ሲሆን የዝናሙ ውሃ በመሬት ውስጥ ወደ ተበጀው የሕዝብ የውሃ መሄጃ በአሸንዳ ወይም በቧምቧ እንዲያመራ
አስፈላጊዎች የሆኑትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለበት፡፡
ቊ 1246፡፡ ከወደ ታች የሚገኘው መሬት ግዴታዎች፡፡
(1) ከወደ ታች የሚገኙ መሬቶች የሰው እጅ ሳያግዘው በተፈጥሮው ከወደላይ ከሚገኙት መሬቶች የሚወርደውን ውሃ በግድ የሚቀበሉ
ናቸው፡፡

(2) ከወደ ታች የሚገኘው የመሬት ባለሀብት እንደዚህ ባለ አኳኋን የሚፈሰውን ውሃ የሚያገድ ግድብ ለመሥራት አይችልም፡፡

(3) ከወደ ላይ የሚገኘው የመሬት ባለሀብት ከወደ ታች የሚገኘውን የመሬት ግዴታ የሚያከብድ አንዳች ነገር ለማድረግ አይችልም፡፡

ቊ 1247፡፡ የውሃ መውረጃውን የመጥረግ (የመሠንጠቅ) ሥራዎች፡፡

(1) ከወደ ላይ የሚገኘው የመሬት ባለሀብት በመሬቱ ላይ የውሃ መውረጃ የመጥረግ (የመሠንጠቅ) ሥራዎችን የፈጸመ እንደሆነ ከወደ ታች
የሚገኙት የመሬቶች ባለሀብቶች ከተባለው መጥረግ የተነሣ በመሬታቸው ላይ የሚወርደውን ውሃ ኪሣራ ሳይከፈላቸው መቀበል
አለባቸው፡፡
(2) ከወደ ታች የሚገኙት የመሬቶች ባለሀብቶች በዚህ ወደ እነርሱ በሚወርደው ውሃ ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት በተቻለ መጠን
አነስተኛ እንዲሆን ከወደ ላይ የሚገኘው የመሬት ባለሀብት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግና የሚገባውን ሥራ ሁሉ መፈጸም
አለበት፡፡

(3) ከወደታች የሚገኙት የመሬቶች ባለሀብቶች ወራጁ ውሃ ቤቶች ባሉበት ቦታ ላይ ወይም በቤቶች አጠገብ በሚገኝ ወለል ወይም
የአትክልት ቦታ ላይ አቋርጦ የሚያልፍ ሲሆን ውሃው በመሬት ውስጥ በሚደረግ ቦይ እንዲሄድ ሲሉ ከወደ ላይ ያሉትን የመሬቶች
ባለሀብቶች ማስገደድ ይችላል፡፡
ቊ 1248፡፡ ስለ አዳዲስ ምንጮች፡፡
መሬትን በመቈፈር ወይም የመሬት ውስጥ ሥራዎችን በመፈጸም ምክንያት አንድ የመሬት ባለሀብት ከመሬቱ ውስጥ ውሃ ያመነጨ
እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተነገረው ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 1249፡፡ ውሃን ስለ መውሰድ፤ (1) የባለሀብቱ መብት፡፡

(1) ባለሀብቱ መሬቱን በውሃ ለማጠጣት ወይም ለማናቸውም ሌላ አገልግሎት በመሬቱ ወሰን ላይ በሚሄደው ውሃ ለመጠቀም የፈለገ
እንደሆነ ውሃውን ለመውሰድ አስፈላጊዎች የሆኑትን ሥራዎች ጎረቤት በሆነው በሌላው ሰው መሬት ላይ ለማስደገፍ መብት አለው፡፡

(2) እነዚህን ሥራዎች ለመፈጸምና በመልካም ሁኔታ ለመያዝ በዚህ በጎረቤቱ መሬት ላይ ለማሳለፍ ይችላል፡፡
ቊ 1250፡፡ ስለሚገባው ኪሣራ፡፡
(1) ለዚህ ለውሃ መክተሪያ የተሠራው ግድብ ከጎረቤቱ መሬት አንዱን ክፍል ነዋሪነት ባለው ሁኔታ የሚያሳጣው የሆነ እንደሆነ ለጎረቤቱ
ኪሣራ የሚገባው ይሆናል፡፡

(2) እንዲሁም በግድቡ ሥራዎች ወይም ሥራዎቹን በመልካም ሁኔታ በመጠበቅ ምክንያት ወይም ሥራዎቹ ተሠርተው የሚቈዩበት ጊዜ
በመርዘሙ ምክንያት ወይም በሥራው ትልቅነት ምክንያት ጎረቤቱ በመሬቱ በሚያገኘው አገልግሎት ላይ የደረሰው ሁከት ከደንበኛው
የጉርብትና ሁከት ያለፈ እንደሆነ ኪሣራ የሚገባው ይሆናል፡፡
ቊ 1251፡፡ በግድቡ ስለ መጠቀም፡፡
(1) በመሬቱ ላይ ግድብን ለማስደገፍ የተጠየቀው አዋሳኙ ጎረቤት ለሥራውና ሥራውን በመልካም ሁኔታ ለመጠበቅ የሚወጣውን ኪሣራ
አጋማሽ ተካፋይ ሆኖ ግድቡ ለጋርዮሽ እንዲያገለግል በማናቸውም ጊዜ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ለጋርዮሹ እንዲያገለግል የተጠየቀው ሥራዎቹ ከተጀመሩ ወይም ከተፈጸሙ በኋላ እንደሆነ፤ ከወንዙ በሁለቱም ወገን ያሉትን መሬቶች
ለማጠጣት ሲባል የግድቡ የመለዋወጥ ሥራዎች የሚያስከትሉትን ትርፍ ወጪዎች ሁሉ ጠያቂው ብቻውን መቻል አለበት፡፡

ቊ 1252፡፡ ስለ መስኖ ቦይ (1) የመሬት ባለሀብቶች መብት፡፡


ለቤቱ አስፈላጊነት ወይም መሬቱን ለማጠጣት ወይም ለማናቸውም ለሌላ አገልግሎት በመሬቱ ወሰን ላይ በማይሄድ ወይም በመሬቱ ላይ
አቋርጦ በማያልፍ ውሃ ለመገልገል የፈለገ ባለሀብት ለባለርስት አስቀድሞ የሚከፈል ትክክለኛ ኪሣራ እንዲሰጥ ተደርጎ ይህን የተባለውን
ውሃ፤ አማካይነት ባላቸው መሬቶች ላይ ወደ መሬቱ ለማሳለፍ መብቱን ከዳኞች ለመቀበል ይችላል፡፡

ቊ 1253፡፡ (2) የቦዮች ሥራ የሚሄድበት መሥመር፡፡

(1) ቦዮቹ የሚከተሉት መሥመር አቋቋማቸውና ዐይነታቸው የሚወስነው ለጒዳዩ አካባቢ የሆኑትን ሁኔታዎች በማየት ነው፡፡

(2) የቦዮቹ ሥራ ቦዮቹ የሚያልፉባቸው መሬቶች ባለሀብቶች በሆኑት ሰዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከሁሉ አነስተኛ እንዲሆን በማድረግ
መፈጸም አለበት፡፡

(3) የቦዮችም አመራር በተቻለ መጠን ቤቶች በቆሙበት ቦታ እንዲሁም በቤቶች አጠገብ በሚገኘው ወለል ወይም የአትክልት ቦታ ላይ
እንዳይሄድ መሆን አለበት፡፡

ቊ 1254፡፡ (3) የሚከፈለው ኪሣራ፡፡

(1) ቦዩ በመሬታቸው ላይ ለሚያልፍባቸው ባለርስቶች አንድ ኪሣራ ይከፈላቸዋል፡፡

(2) የዚህንም የኪሣራ ልክ ለመወሰን ባለመሬቶቹ ለዘወትር እንዳይጠቀሙበት የተደረገው መሬት ዋጋ ይገመታል፡፡

(3) ከዚህም በቀር ቦዩን በመሥራት ሥራውን በመጠበቅ ምክንያት ባለመሬቶች ከመሬታቸው በሚያገኙት ጥቅም ላይ የደረሰው ሁውከት
በግምት ውስጥ ይገባል፡፡
ቊ 1255፡፡ በመሬት ውስጥ ስለሚገኝ ውሃ፡፡

(1) በመሬት ውስጥ የታፈነና ወንዝነት ያለው የመሬት ውስጥ ውሃ የመንግሥት (የሕዝብ) ንብረት ነው፡፡

(2) ማንም ሰው ያለ ፈቃድ በመሬቱ ላይ ከመቶ ሜትር አብልጦ ወደ ታች ጒድጓድ ለመቈፈር አይችልም፡፡
ቊ 1256፡፡ ስለ ዓሣ ማጥመድና በጀልባ ስለ መሄድ፡፡
(1) ዓሣን የማጥመድ መብቶች በልዩ ሕግ ድንጋጌዎች የተወሰኑ ናቸው፡፡

(2) በፈሳሽ ውሆችና በሐይቆች ላይ በጀልባ የመሄድ መብቶችም እንደዚሁ የተወሰኑ ናቸው፡፡

አንቀጽ 8፡፡
የጋራ ባለሀብትነት፤ በአላባ ስለ መጠቀምና ስለ ሌሎች ግዙፍ መብቶች፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
የጋራ ባለሀብትነት፡፡
ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ቊ 1257፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) የአንድ ንብረት ሀብትነት የብዙ ሰዎች ለመሆን ይችላል፤ እነዚህም የጋራ ባለሀብቶች ናቸው፡፡

(2) የእርሻ ኅብረቶችንና በዐዋጅ የታወቁትን የባለርስቶች ማኅበር ስለሚመለከተው ጒዳይ በንብረቶች በኅብረት ስለ መጠቀም በዚህ
አንቀጽ የተጻፉት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1258፡፡ የጋራ ሀብት ደንብ አመራር፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶች መብትና ግዴታዎች የሚወስኑት የጋራ ሀብቱ በተቋቋመበት ውል መሠረትና፤ የሕጉ ግልጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ
ሆነው በጋራ ባለሀብቶቹ መካከል በተደረገው የውል ስምምነት መሠረት ነው፡፡

(2) የዚህ ዐይነት ስምምነት ያልኖረ እንደሆነ ወይም ስምምነቶቹ ያልተሟሉና የማይበቁ በሆኑ ጊዜ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ድንጋጌዎች
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 1259፡፡ የእኩልነት አገማመት፡፡

የያንዳንዶቹ የጋራ ባለሀብቶች ድርሻ ሀብት እኩል እንደሆነ ይገመታል፡፡

ቊ 1260፡፡ በድርሻው ላይ ስላለው መብት፡፡

(1) እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት የራሱን ድርሻ ለመሸጥ ለማስተላለፍ ለማስያዝ ይችላል፡፡

(2) ከያንዳንዶቹ የጋራ ባለሀብቶች ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች የባለዕዳውን ድርሻ ለመያዝ ይችላሉ፡፡

ቊ 1261፡፡ ሕጋዊ የሆነ የቀዳሚነት መብት፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶች የሆኑ ሰዎች ያልተከፈለውን የጋራ ንብረት ከማንኛውም ሦስተኛ ወገን በፊት ቀዳሚ ሆነው በግዥ የማስቀረት ሕጋዊ
መብት አላቸው፡፡

(2) ይህ በቀዳሚነት የማስቀረት መብት በሥራ ላይ ስለሚውልበት አኳኋን በዚህ አንቀጽ በምዕራፍ 4 በተነገረው ድንጋጌ ውስጥ
የተመለከተው ደንብ ጸንቶ ይሠራበታል፡፡
ቊ 1262፡፡ ድርሻ ሀብትን ስለ መተው፡፡

(1) ከጋራ ባለንብረቶቹ አንዱ የአንድነት ከሆነው ሀብት ውስጥ ያለውን ድርሻ በፈቃዱ የለቀቀ መሆኑን የገለጸ እንደሆነ ይህ የተለቀቀው
ድርሻ የቀሩትን የጋራ ባለንብረቶች ድርሻ ያሳድጋል፡፡

(2) ድርሻውን የለቀቀው የጋራ ባለሀብት ሀብቱን ከመልቀቁ በፊት ስለነበረበት ዕዳ ኀላፊነት አይቀርለትም፡፡

ቊ 1263፡፡ የአንድነት በሆነው ንብረት ስለ መገልገል፡፡

እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት፤ ሀብቱ እንዲያገለግል በተመደበበት ነገር መሠረትና ከሌሎቹ የጋራ ባለሀብቶች ጋራ ተስማሚ በሚሆንበት
መንገድ የአንድነት በሆነው ንብረት ሊገለገል (ሊጠቀም) ይችላል፡፡

ቊ 1264፡፡ የንብረቱ ፍሬ፡፡

(1) ካልተከፈለው ንብረት ላይ የሚገኘው ፍሬ ጥቅም እንዲሁም ያልተከፋፈለ ነው፡፡

(2) ምን ጊዜም ቢሆን እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት ክፍያ እንዲደረግ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1265፡፡ የንብረቱ አስተዳደር፡፡ (1) በድምፅ ብልጫ ስለ መሠራቱ፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶቹ የሀብታቸውን አስተዳደር ሥራ አካሄድ የሚመሩት በአንድነት ነው፡፡

(2) የጋራ የሆነ ንብረትን ስለ ማስተዳደር በሚመለከተው ጒዳይ የጋራ ባለሀብቶቹ ውሳኔ የሚያደርጉት በድምፅ ብልጫ ነው፤ ይኸውም
የድምፅ ብልጫ ከሀብቱ አጋማሽ የበለጠ ቊጥር ድርሻ ያላቸው እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡

ቊ 1266፡፡ (2) የሁሉን ስምምነት የሚጠይቁ ጒዳዮች፡፡


የጋራ የሆነውን ንብረት ለመሸጥ፤ ለማስተላለፍ ወይም በዋስትና ለማስያዝ ወይም የተመደበበትን አገልግሎት ለመለወጥ ሲሆን የጋራ
ባለንብረቶቹ ሁሉ ስምምነት አስፈላጊ ነው፡፡

ቊ 1267፡፡ (3) ወጪ፡፡


ለንብረቱ ማስተዳደሪያ፤ ለግብርና ለሌሎችም ጒዳዮች የሚደረገውን ወጪ ወይም ከአንድነቱ ንብረት ላይ የሚጠየቀውን ወጪ ሁሉ
የሚችሉት እያንዳንዳቸው የጋራ ባለንብረቶች በየድርሻቸው መጠን ነው፡፡
ቊ 1268፡፡ ለንብረቱ መጠገኛ አስፈላጊ ወጪ፡፡
(1) ከጋራ ባለሀብቶቹ አንዱ ንብረቱ እንዳይበላሽ ወይም እንዳይጠፋ፤ ያለ ፈቃድ ወጪ ያደረገ እንደሆነ፤ ይህን ወጪ የጋራ ባለሀብቶቹ
ሁሉ እንዲከፍሉት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ስለሆነም ወጪው ለማይጠቅም ጒዳይ የወጣ መሆኑ ከተረጋገጠ ወይም ወጪ ማድረግ ያስፈለገው ገንዘቡን ያወጣው ሰው ወይም
ራሱ ምክንያት የሆነ እንደሆነ ማንኛውንም ኪሣራ ለመጠየቅ አይቻልም፡፡

(3) ማንኛውም የጋራ ባለሀብት ሁሉ በዚሁ ቊጥር በተመለከተው መሠረት የጋራ ሀብት ድርሻውን ለቀሩት የጋራ ባለሀብቶች በመልቀቅ
ለንብረቱ መጠገኛ ወጪ የሆነውን ገንዘብ አልከፍልም ለማለት ይችላል፡፡
ቊ 1269፡፡ ለንብረቱ መጠገኛ አስፈላጊ ያልሆነ ወጪ፡፡ (1) ጠቅላላ ደንብ፡፡

(1) ከጋራ ባለሀብቶቹ አንዱ ሳይፈቀድለት ለንብረቱ አስፈላጊ ያልሆኑትንና የንብረቱን ዋጋ ለማሳደግ ጠቃሚ ለማድረግ ወይም ለማሳመር
ወጪ ያደረገ እንደሆነ፤ በዚህ ምክንያት ማንኛውንም ወጪ የመጠየቅ መብት የለውም፡፡

(2) ከዚህ ንብረት ጋራ የተያያዘውን ነገር ብቻ ለይቶ ለመውሰድና ዋነኛውን ንብረት ቀድሞ በነበረበት ሁኔታ ለማድረግ ይችላል፡፡

ቊ 1270፡፡ (2) ፍሬዎችን ስለ ማራባት፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተነገረው ቊጥር የተመለከተው ድንጋጌ በንብረቱ ላይ ፍሬን ለማራባት ወይም የተገኘውን ፍሬ ወይም ሰብልን
ለመሰብሰብ ስለተደረጉ ወጪዎች ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

(2) ከጋራ ባለሀብቶቹ አንዱ ሳይፈቀድለትም ቢሆን እንኳ ንብረቱን ለማልማት ወይም ፍሬውንና ሰብሉን ለመሰብሰብ ወጪ አድርጎ
እንደሆነ ፍሬው ወይም ሰብሉ ከመከፋፈሉ አስቀድሞ ያወጣውን ገንዘብ ከዚሁ ከፍሬውና ከሰብሉ ላይ ለመከፈል ይችላል፡፡
ቊ 1271፡፡ ያልተከፈለ ተንቀሳቃሽ ንብረት በሐራጅ የሚሸጥበት ሁኔታ፡፡
(1) ይህን ተቃራኒ የሚሆን ስምምነትም ቢኖርም እንኳ ሀብቱ የሚንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት ምን ጊዜም ቢሆን
ያልተከፋፈለው ሀብት በግልጽ በሐራጅ እንዲሸጥ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ይህ ጥያቄ የቀረበው ተስማሚ ባልሆነ ጊዜ የሆነ እንደሆነ ዳኞች ንብረቱ ከስድስት ወር ለማያልፍ ጊዜ ሳይከፋፈል እንዲቈይ ለማዘዝ
ይችላሉ፡፡
ቊ 1272፡፡ ያልተከፋፈለ የማይንቀሳቀስ ንብረት ክፍያ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ሀብቱ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሆነ እንደሆነ እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት በማንኛውም ጊዜ ሀብቱ እንዲከፋፈል ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ክፍያው ለሀብቱ ተፈጥሮ ጠባይ ሁኔታ ወይም ለተመደበበት ጒዳይ ጉዳትን የሚያስከትል ተቃዋሚ ነገር ያለበት ሲሆን ወይም
የሀብቱን ባለዋጋነት በግልጽ የሚቀንሰው፤ ወይም የሀብቱን ፍሬ አሰጣጥ ከፍተኛ ግምት ባለው ሁኔታ የሚጎዳው ሆኖ ሲታይ ክፍያውን
ከማድረግ ይልቅ የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሐራጅ እንዲሸጥ ይታዘዛል፡፡

ቊ 1273፡፡ (2) የዳኞች ሥልጣን፡፡

(1) የሀብቱ ክፍያ ወይም በሐራጅ የመሸጡ ጥያቄ የቀረበው ተስማሚ ባልሆነ ጊዜ መሆኑን ዳኞች የተረዱት እንደሆነ ከሁለት ዓመት
ለማያልፍ ጊዜ ንብረቱ ሳይከፋፈል እንዲቈይ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ሁኔታ አስፈላጊ መሆኑ የተገመተ እንደሆነ በዚህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ለሀብቱ አስተዳዳሪ የሚሆን ሰው
ዳኞች ይመርጣሉ፡፡

ቊ 1274፡፡ (3) ንብረቱ እንዳይከፋፈል የማድረግ ስምምነት፡፡

(1) ከጋራ ባለሀብቶቹ አንዱ ንብረቱ ይከፋፈል ብሎ የሚጠይቅበት መብቱ፤ ይህ ንብረት አይከፋፈልም ተብሎ በተደረገው ስምምነት
መሠረት ወይም በባለሀብቶቹ ሁሉ ስምምነት መሠረት ሊወገድ ይችላል፡፡

(2) ቢሆንም ከዚህ በላይ በተጻፈው ኀይለ ቃል የተደረገው ስምምነት ለአምስት ዓመት ጊዜ ብቻ ወይም ከዚህ ላነሰ ጊዜ ብቻ እንጂ፡-
ከአምስት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ አይጸናም፡፡

(3) ስምምነቱ የተደረገው ላልተወሰነ ጊዜ ወይም ከአምስት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ እንደሆነ በአምስት ዓመት መጨረሻ ላይ የስምምነቱ
ጊዜ ያልቃል፡፡
ቊ 1275፡፡ የግልግል ስምምነት፡፡
(1) የጋራ ንብረቱ የተቋቋመበት ውል ወይም በጋራ ባለሀብቶቹ ስምምነት፤ በጋራ ባለንብረቶቹ መካከል የሚነሣው ክርክር ሁሉ በአንድ
ወይም በብዙ የሽምግልና ዳኞች ውሳኔ ሊቈረጥ ይችላል ተብሎ ለመዋዋል ይቻላል፡፡
(2) እንደዚህ ያለው አጋጣሚ ሁኔታም የሽምግልና ዳኝነቱ ሥራ የሚፈጸመው በዚህ ሕግ ስለ ግልግልና ስለ ስምምነት በተመለከተው
አንቀጽ ድንጋጌዎች መሠረት ነው፡፡

ቊ 1276፡፡ ንብረቱ ምን ጊዜም ቢሆን የማይከፋፈል ስለመሆኑ (1) ይህን ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ፡፡
ለሀብቱ የተፈጥሮ ሁኔታ ወይም ሀብቱ ለተመደበበት አገልግሎት አለመከፋፈሉ ተስማሚ የሆነ እንደሆነና የሀብቱ መሸጥ ወይም መከፋፈል
የማይቻል ወይም ለደኅና አእምሮ ተቃራኒ በሆነ ጊዜ፤ የሀብቱ ያለ መከፈል ጒዳይ እስከ ምን ጊዜም ቢሆን ጸንቶ እንዲኖር ለማድረግ
ይችላል፡፡
ቊ 1277፡፡ (2) ንብረቱ የማይከፋፈልበት ሥርዐት፡፡

(1) ሀብቱ ለመከፋፈል የማይችል በሆነ ጊዜ የያንዳንዱን የጋራ ባለን ብረት መብትና ግዴታ የሚወሰንና የአንድነት ሀብት የሆነው ነገር
የሚተዳደርበትን ሁኔታ የሚገልጽ አንድ ያለመከፋፈል ደንብ ይደራጃል፡፡

(2) ስለዚህ ጒዳይ የጋራ ባለሀብቶቹን ሁሉ ስምምነት ለማግኘት ያልተቻለ እንደሆነ ይህን ደንብ ለማቆም ወይም ለማሻሻል ዳኞች
ስምምነቱን ተቀብለው እንዲያጸድቁት አስፈላጊ ነው፡፡
ክፍል 2፡፡
ልዩ ሁኔታዎች
ንኡስ ክፍል 1፡፡
የአማካይ ወሰን አጥሮች፡፡
ቊ 1278፡፡ የባለሀብት ነፃነት፡፡
ማንም ሰው ቢሆን ጎረቤቱን አንድ የአማካይ ወሰን አጥር እንዲያጥር ወይም አጥሩን እንዲያድስ ሊያስገድድ አይችልም፡፡
ቊ 1279፡፡ የወሰን መሐል ግንብ አጥርን እንደገና ስለ መሥራት፡፡
(1) አንድ በአማካይ ወሰን ላይ ያለ አጥር ፈርሶ ከባለርስቶቹ አንደኛው እንደገና የመገንባትን ሥራ ለመፈጸም እንቢ ያለ እንደሆነ አንደኛው
ባለርስት ብቻ እንደገና ሊገነባው ይችላል፡፡

(2) ከግንቡ አንደኛው ክፍል በጎረቤቱ ርስት ላይ የተሠራም ቢሆን እንኳ በዚህ ዐይነት የተገነባው አጥር የሠሪው ንብረት ይሆናል፡፡

(3) ቢሆንም አጥሩን ያልሠራው ባለሀብት አጥሩን የሠራው ጎረቤቱ ያወጣውን ኪሣራ አጋማሽ መልሶ በመከፈል አጥሩን የጋራ የወሰን
አማካይነት አጥር ሊያደርገው ይችላል፡፡
ቊ 1280፡፡ በአማካይ ወሰን አጥር ላይ ስላለ መብት፡፡
ማንኛውም የጋራ ባለሀብት አንደኛው ወገን አዋሳኙ ሳይፈቅድለት የወሰን አማካይ የግንብ አጥር ከፍ ለማድረግም ሆነ ሌላ ሕንጻ አስገድፎ
ለመሥራት፤ በር ለመቅደድ በጠቅላላውም በአጥሩ ላይ የባለሀብትነት ተግባር ለመፈጸም አይችልም፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
የአንድ ቤት ፎቅ ወይም ለመኖሪያ የተመደቡ
ክፍሎች ባለሀብትነት፡፡
ቊ 1281፡፡ የአንድነት ሀብት እንደሆነ የሚቈጠር ክፍል፡፡
(1) ያንድ ቤት ልዩ ልዩ ፎቆች ወይም ለመኖሪያ የተመደቡ ክፍሎች (አፓርተማን) የልዩ ልዩ ባለሀብቶች ንብረት በሆኑ ጊዜ ተቃራኒ የሆነ
ሰነድ ከሌለ ከነዚህ ሀብቶች አንዱ ክፍል ለአንደኛው ባለንብረት የግል አገልግሎት የሚጠቅም እንዲሆን ከተደረገው በቀር፤ የመሬቱና
የሌላውም የቤቱ ክፍሎች የጋራ ንብረት እንደሆኑ ይቈጠራሉ፡፡
(2) የቤቱን ለመኖሪያ የተመደቡትን ሁለት ክፍሎች አፓርተማን የሚለያዩ ግድግዳዎች የነዚሁ የቤት ክፍሎች ባለሀብቶች የጋራ
ግድግዳዎች ናቸው፡፡
ቊ 1282፡፡ የጋራ ንብረት አስተዳደር ደንብ፡፡
(1) የያንዳንዱ የጋራ ባለንብረት መብቶችና ግዴታዎች እንዲሁም የማይንቀሳቀሰው የጋራ ንብረታቸው የአስተዳደር ሥርዐት፤
ስለማይንቀሳቀስ የጋራ ባለሀብትነት ጒዳይ በወጣው ደንብ መሠረት ይመራል፡፡

(2) ይህም ደንብ በማንቀሳቀሰው የጋራ ንብረት ላይ ለያንዳንዱ የጋራ ባለሀብቶች ያላቸውን ድርሻ ይወስናል፡፡
ቊ 1283፡፡ የደንቡ ፎርም፡፡
የጋራ ንብረት የሚመራበት ደንብ በጽሑፍ ካልሆነ በቀር ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 1284፡፡ ደንቡን ስለ ማስቀመጥ፡፡
(1) የጋራ ንብረት ማስተዳደሪያ የሆነው የጽሑፍ ደንብ አንዱ ግልባጭ የማይንቀሳቀሰው ሀብት በሚገኝበት አገር ባለ ባንድ ውል አዋዋይ
ዘንድ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ቤት ውስጥ ይቀመጣል፡፡

(2) ይህንንም ደንብ ባለጥቅም የሆኑት ወገኖች ሁሉ ሊመለከቱትና አንዳንድ ግልባጭም እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡
ቊ 1285፡፡ ደንቡ የሚቋቋምበት ሁኔታ፡፡
(1) የጋራ ባለሀብቶች ማስተዳደሪያ የሚሆነውን ደንብ የማይንቀሳቀሰው ሕንጻ ከመሠራቱም በፊት ቢሆን ለወደፊት የጋራ ባለሀብቶቹ
የሚሆኑት በሚያደርጉት ስምምነት መሠረት ወይም የጋራ ንብረት የሚሆነውን ሕንጻ ሥራ በወጠነው ሰው አማካይነት ሊዘጋጅ ይችላል፡፡

(2) እንዲህ ባልሆነ ጊዜ ከጋራ ባለሀብቶቹ አንዱ እንደጠየቀ ወዲያውኑ የጋራ ባለሀብቶቹ ሁሉም ተስማምተው ያዘጋጁታል፡፡

(3) በጋራ ንብረቱ አስተዳደር ደንብ ጒዳይ ደንቡን ስለማዘጋጀት ወይም ስለ ማሻሻል የጋራ ባለሀብቶቹ የሁሉም ስምምነት የማይገኝ በሆነ
ጊዜ ዳኞች ደንቡን እንዲያጸድቁት ወይም እንዲያሻሽሉት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ቊ 1286፡፡ ደንቡን መቃወሚያ ስለ ማድረግ፤ ደንቡን ስለ ማስቀመጥ፡፡
ለጋራ ንብረቱ ማስተዳደሪያ የሆነው ደንብ፤ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ መብት አለን የሚሉትን ማንኛዎቹንም ሰዎች መቃወሚያ
ሊሆንባቸው የሚችለው ይህን መብት ያገኙት፤ ደንቡ በሕጉ መሠረት ሕግ በሚያዝበት ስፍራ ተቀማጭ ከሆነ በኋላ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 1287፡፡ በመዝገብ ቤት ያልተቀመጠ ደንብ፡፡
(1) የጋራ ንብረት ማስተዳደሪያ ደንብ በሚገባ ተቀማጭ ያልሆነ ቢሆንም እንኳ የፈረሙትን የጋራ ባለሀብቶች ወይም ይህንኑ ደንብ
በሚመለከት ጽሑፍ ላይ የፈረሙትን ያስገድዳቸዋል፡፡

(2) እንዲሁም በዚሁ ሥርዐት መሠረት የነዚህን የጋራ ባለንብረቶችና ወራሾቻቸውን ከነዚሁ ላይ ልዩ መብትና መያዣ የሌላቸውን ገንዘብ
ጠያቂዎች ያስገድዳል፡፡
ቊ 1288፡፡ ያልተሟላ ወይም ዋጋ የሌለው ስምምነት፡፡
የጋራ ንብረት ማስተዳደሪያው ደንብ ምንም የማያመለክት ወይም ከመተዳደሪያው ደንብ አንዱ ክፍል በሕግ የተከለከለ ሲሆን እነዚህ የጋራ
ንብረት ማስተዳደሪያ ደንቦች በዚህ ምዕራፍ ባሉት ድንጋጌዎች በተመለከተው ይሟላሉ፤ ወይም የዚሁ ምዕራፍ ድንጋጌዎች በምትክ
ይገቡባቸዋል፡፡
ቊ 1289፡፡ የማይንቀሳቀሰው ንብረት የአንድነት ያልሆኑት ክፍሎች (1) መሠረቱ፡፡

(1) እያንዳንዱ የጋራ ባለንብረት የአንድነት ሀብት ባልሆነው ክፍል ንብረቱ ላይ ሕግ ለባለሀብት የሚሰጣቸው መብቶች ይኖሩታል፡፡

(2) በተለየም የግሉ የሆነውን ለመኖሪያ የተመደቡትን ክፍሎች (አፓርተማን) ወይም ፎቅ ለመሸጥ ለማስተላለፍ ለማከራየት ወይም
በዋስትና ለማስያዝ ይችላል፡፡
ቊ 1290፡፡ (2) የተጠበቀ ሁናቴ፡፡
ምን ጊዜም ቢሆን ግን የማይንቀሳቀሰው ንብረት የተመደበበትን አገልግሎት አክብሮ መጠበቅ ይገባዋል፤ እንዲሁም የተከፈለ ድርሻው
የሆነው ንብረት እንዲያገለግል የተደበበትን ጒዳይም ሆነ የመጠቀሚያውን ዐይነተኛ ነገር ሌሎቹን ባለሀብቶች የሚጎዳ ሁኔታ ለመለወጥ
አይችልም፡፡
ቊ 1291፡፡ የአንድነት የሆነው የማይንቀሳቀሰው ንብረት ክፍሎች፡፡ (1) አገልግሎት፡፡
እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት ተካፍሎ የራሱ ድርሻ የሆነውን የማይንቀሳቀሰውን የአንድነት ንብረት በተመደበበት አገልግሎት መሠረት
በሌሎች የጋራ ባለሀብቶች መብት ላይ አንዳችም መሰናክል በማያመጣ መንገድ በድርሻ ሀብቱ ለመጠቀም ሙሉ ነፃነት አለው፡፡

ቊ 1292፡፡ (2) ወጪ፡፡

(1) እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት የአንድነት ለሆነው ንብረት አያያዝ፤ አጠባበቅና አስተዳደር ወጪ የሚሆነውን ገንዘብ ከሌሎቹ ባለንብረቶች
ጋራ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡

(2) የአንድነት ለሆነው ንብረት ወጪ የሚሆነው ገንዘብ የሚደለደለው፤ ከማይንቀሳቀሰው ንብረት ክፍያ ድርሻ ጋራ ተመዛዛኝ በሚሆን
ዐይነት ነው፡፡

ቊ 1293፡፡ የጋራ ባለሀብቶች ማኅበር፡፡(1) ሥራው፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶቹ፤ ሁሉም የጋራ ንብረታቸውን ለመምራት ሕጋዊ እንደራሴ በመሆን በሕግ መሠረት በአንድ የጋራ ባለሀብቶች ማኅበር
ውስጥ የሚገቡ ናቸው፡፡

(2) የጋራ ባለሀብቶች ማኅበር የጋራ የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ስለ መጠበቅና ስለ ማስተዳደር ጒዳይ በጋራው ንብረት ማስተዳደሪያ
ደንብ መሠረት አስፈላጊ የሆነውን ጥንቃቄ ሁሉ ያደርጋል፡፡

ቊ 1294፡፡ (2) የሥራው አካሄድ፡፡

(1) እያንዳንዱ የጋራ ባለንብረት የአንድነት በሆነው ንብረት ላይ ካለው ድርሻ ጋራ ተመዛዛኝ በሆነ መጠን በሥራ መሪው ማኅበር ውስጥ
ቊጥሩ ተስተካካይ የሆነ ድምፅ የመስጠት መብት ይኖረዋል፡፡

(2) የጋራ ባለሀብቶች ማኅበር ለሚያደርገው ስብሰባና ድምፅ የመስጠት ጒዳይ ባለሀብቱ እንደራሴውን ለመላክ ይችላል፡፡

ቊ 1295፡፡ (3) ስብሰባ፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶች ማኅበር ስብሰባ የሚያደርገው በማኅበሩ ሥራ መሪ አሳሳቢነት የጋራ የሆነው የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚገኝበት
ቦታ ነው፡፡

(2) እጅግ ቢያንስ ከጋራ ባለሀብቶቹ አምስቱ ሥራ መምሪያ ማኅበሩ ስብሰባ እንዲያደርግ ከጠየቁ ማኅበሩ በግድ መሰብሰብ ይገባዋል፡፡

(3) የማኅበሩን ስብሰባ ሥርዐቱንና ጊዜውን የማኅበሩ ሥራ መሪ ለሕሊና በሚስማማ ዐይነት ይወስናል፡፡

ቊ 1296፡፡ (4) ውሳኔ፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶች ማኅበር ውሳኔዎች የሚጸኑት በማኅበረተኞቹ የድምፅ ብልጫ ነው፡፡

(2) በስብሰባው ላልተገኙትና ወኪሎቻቸውን ላልላኩት የጋራ ባለሀብቶች የማኅበሩ ውሳኔ የሚገለጽላቸው በሥራ መሪው አማካይነት
ነው፡፡
ቊ 1297፡፡ (5) ስለ አቤቱታ፡፡

(1) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ቢኖርም እንኳ ማንኛውም የጋራ ባለሀብት እርሱ በሌለበት ማኅበሩ የሰጠውን የጋራ ንብረት ሥራ መምሪያ
የሆነውን ደንብና ሕግን የሚጥሰውን ውሳኔ በዳኞች ፊት ሊቃወም ይችላል፡፡
(2) ይህም የመቃወም ክስ የማኅበሩ ውሳኔ ለባለጥቅሙ በተገለጸለት ባንድ ወር ውስጥ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ተቀባይነትን አያገኝም፡፡

(3) የጋራ ባለሀብቶቹ የማኅበሩ ውሳኔ ዋጋ የሌለው ነው ብሎ የሚወሰነው ፍርድ በሁሉም ላይ የሚጸና ነው፡፡

ቊ 1298፡፡ (1) ስለ ሥራ መሪው (ሰንዲክ)፡፡ (1) ሹመት፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶች የንብረት ሥራ የሚመራው የጋራ ባለሀብቶቹ ከመካከላቸው ወይም ከውጭ በመረጡት ባንድ የማኅበር ኅብረት ሥራ
ሹም (ሰንዲክ) ነው፡፡

(2) ሥራ መሪውም (ሰንዲኩም) የሚሾመው በጋራ ባለንብረቶች ማኅበር መራጭነት ነው፡፡

(3) አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ከጋራ ባለሀብቶቹ ባንደኛው ጥያቆ አቅራቢነት ለጊዜው የሚሆን አንድ ሥራ መሪ ዳኞች መርጠው ሊሾሙ
ይችላል፡፡
ቊ 1299፡፡ (2) የሥልጣኑ ማስረጃ፡፡

(1) የጋራ ንብረት ሥራ መሪው የሥልጣኑንና የችሎታውን ማስረጃ ሰነድ ከጋራ ንብረት ሥራ መምሪያ ማኅበርተኞች ላይ ጠይቆ ለመቀበል
ይችላል፡፡

(2) አስፈላጊ ሆኖም ሲገኝ ይህ የሥልጣን ማስረጃ ሥራው ለምን ያህል ጊዜ ተወስኖ እንደተሰጠው ይገልጻል፡፡

ቊ 1300፡፡ (3) የአገልግሎት ዋጋ፡፡

(1) በተለይ የተወሰነ ካልሆነ በቀር በመሠረቱ የንብረት ሥራ መሪው ማንኛውንም አበል የማግኘት መብት የለውም፡፡

(2) ሥራ መሪው ለማኅበሩ ሲል ወጪ ያደረገውን ሒሳብ ብቻ እንዲመለስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1301፡፡ (4) የሥራ መሪው መሻር (መለወጥ)፡፡

(1) የጋራ ባለሀብቶቹ የንብረት ሥራ መሪው ማኅበር (ሰንዲክ) በስምምነታቸው ላይ ሊገኝ የሚችለው ለሥራ መሪው የሚከፈለው የአበል
አከፋፈል ጒዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ የንብረት ሥራ መሪውን (ሰንዲክ) በማንኛውም ጊዜ ሊሽሩት ይችላሉ፡፡

(2) ሥራ መሪው የተጣለበትን አደራ በግልጽ እንደመጣስ ያለ ወይም የተሰጠውን የሥራ ተግባር በሚገባ ለመፈጸም ችሎታ እንደማጣት
ያለ ከፍተኛ የሆነ ምክንያት ሲገኝበት ይህን የሥራ መሪውን የመሻር መብት የሚወስን ወይም የሚያግድ ተግባር አይፈቀድም፡፡

ቊ 1302፡፡ (5) የሥራ መሪው ሥራዎች፡፡

(1) ሥራ መሪው የአንድነት የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረትን አያያዝ፤ የአጠባበቅና ንብረቴም በሚገባ ሁኔታ እንዲኖር፤ የማደስ ሥራዎችን
መፈጸም አለበት፡፡

(2) አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሥራ መሪው፤ የማኅበሩ አባሎች እንዲሰበሰቡና የሰጡት ውሳኔ ፍጻሜ እንዲያገኝ ይጠባበቃል፡፡

(3) በፍርድ በኩል ወይም ከፍርድ ውጭ ባለው ግንኙነት ሁሉ ሥራ መሪው የማኅበሩ ወኪል ሆኖ በማኅበሩ ስም ይሠራል፡፡

ቊ 1303፡፡ (6) የሥራ መሪው አላፊነት፡፡

(1) ሥራ መሪው በተሰጠው የእንደራሴነት ሥልጣኑ መሠረት ለማኅበሩ (ለሰንዲካው) አላፊ ነው፡፡

(2) የጋራ ንብረት ማኅበር፤ ሥራ መሪው ያቀረበውን ሒሳብ በማጽደቅ ወይም አላፊነት የሚያመጣበት ሥራ አድርጓል የሚል አንድ ውሳኔ
ቢያደርግ ይህን የሚቃወም ስምምነት ቢኖርም እንኳ ይህን ተግባር የፈጸመው በራሱ ድምፅ ብልጫ ወይም የእርሱ እንደራሴ በሆነው ሰው
አሳብ ከሆነ የሥራ መሪው ማኅበር የሰጠውን ውሳኔ በዳኞች ፊት ለመቃወም ይችላል፡፡
ቊ 1304፡፡ የማይንቀሳቀሰው ንብረት መጥፋት፡፡
የማይንቀሳቀጸው ንብረት በእሳት ቃጠሎ ወይም በሌላ ሁኔታ በሙሉ የጠፋ እንደሆነ እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት፤ ቦታውና ከጠፋው
ንብረት የተረፈው ዕቃ በግልጽ በሐራጅ እንዲሸጥ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1305፡፡ የማይንቀሳቀሰው ንብረት በከፊል መጥፋት፡፡ (1) የጋራ ንብረት ሥራ መሪ ማኅበር ሥልጣን፡፡
ንብረቱ በከፊል የፈረሰ እንደሆነ የጋራ ንብረቱ ማኅበር የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እንደገና መሥራት ወይም አለመሥራት ወይም ማደስ
የሚያስፈልገው ወይም የማያስፈልገው ስለ መሆኑ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

ቊ 1306፡፡ (2) እንደገና የመሥራት ውሳኔ፡፡

(1) የጋራ የሆነው ንብረት ማኅበር የሰጠው ውሳኔ ሕንፃው እንደገና እንዲሠራ ወይም እንዲታደስ የሆነ እንደሆነ ከሕንጻው ክፍል ውስጥ
እንደገና መሠራት ወይም መታደስ ለሚያስፈልገው ክፍል የሚሆነውን ወጪ እያንዳንዱ የጋራ ባለሀብት በሀብቱ ላይ ባለው ድርሻ መጠን
ማዋጣት አለበት፡፡

(2) የጋራ ሀብት የሆነው፤ ሕንጻ የፈረሰው ወይም ጉዳት የደረሰበት አንዳንዱ ክፍል ብቻ ነው እንጂ ሌላው አንዳንዱ ክፍል አልፈረሰም
የሚያሰኘው አጋጣሚ ሁኔታ መነሣት አይገባውም፡፡

(3) በሕንጻው ላይ ጉዳት የደረሰበት ከጋራ ባለሀብቶቹ አንዱ በአደረገው ጥፋት ነው ወይም ከነዚሁ የጋራ ባለሀብቶች ውስጥ የፍትሐ
ብሔር አላፊው በሆነው በአንድ ሰው ጥፋት ኪሣራው በእርሱ ላይ ሊጣል ይገባል የሚባል ጒዳይ ቢኖር ይህ የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 1307፡፡ (3) እንደገና እንዳይሠራ የሚደረግ ውሳኔ፡፡

(1) የጋራ ንብረቱ ማኅበር የሰጠው ውሳኔ በከፊል የፈረሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት እንደገና እንዳይሠራ ወይም እንዳይታደስ የሆነ እንደሆነ
ይህ ንብረት ያልፈረሰውም ክፍል ጭምር በግልጽ ሐራጅ ይሸጣል፡፡

(2) የኅብረት ንብረቱን የሽያጭ ዋጋም የጋራ ባለንብረቶቹ እንደየድርሻቸው ይከፋፈሉታል፡፡

(3) ከዚህ በላይ በአለው ቊጥር የተነገሩት የሁለተኛውና የሦስተኛው ኀይለ ቃል ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡
ቊ 1308፡፡ የንብረት ማኅበር ገንዘብ ጠያቂዎች መያዣ፡፡
የጋራ ባለንብረቶች ወይም የንብረት ሥራ መሪው የተበደሩትን ዕዳ አስፈላጊ ከሆነ ከሌላ ሀብታችን ጥቅም ላይ እንከፍላለን ብለው ግልጽ
የሆነ ስምምነት ካላደረጉ በቀር የጋራ ንብረት ሥራ መሪ ማኅበር አባሎች ባደረጉት ውሳኔ መሠረት ለተደረጉት የብድር ውሎች የዋስትና
መያዣ የሚሆነው የማይንቀሳቀሰው የጋራ ንብረትና የተከፋፈለውም ድርሻ ጭምር ነው፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
በአላባ ብቻ ስለ መጠቀም መብት፡፡
ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ቊ 1309፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) የአላባ መብት ማለት የሚጠቀሙበትን ነገር ከመጠበቅ ግዴታ ጋራ ከዚሁ ነገር ላይ በሚገኙት ነገሮች (ፍሬዎች) ወይም መብቶች
ለመጠቀምና ለመገልገል የሚሰጥ መብት ነው፡፡

(2) ይህም መብት በሚንቀሳቀሱና በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በመብቶች ወይም ባንድ ጠቅላላ ንብረት ላይ ሊሆን የሚችል ነው፡፡

ቊ 1310፡፡ ስለ መምራት (ስለ መጥቀስ)፡፡

(1) አላባ ማግኘትን ማስተላለፍን ማጣትን የሚመለከቱ ደንቦች፤ የአላባው መብት ግዙፍነት ባለው ተንቀሳቃሽ ዕቃ ላይ በሆነ ጊዜ ተቃራኒ
ድንጋጌ ከሌለ በቀር ስለ ግዙፍ ተንቀሳቃሽ ዕቃዎች ሀብትነት ማግኘት ማስተላለፍና ማጣት የተደነገጉት ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
(2) የአላባ ጥቅም ማግኘትን ማስተላለፍን ማጣትን የሚመለከቱ ደንቦች በገንዘብ ወይም ግዙፍነት በሌላቸው መብቶች ወይም ባንድ
ጠቅላላ ንብረት ላይ በሆነ ጊዜ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ስለ ገነዘብና ግዙፍነት ስለሌላቸው ሌሎች መብቶች ማግኘት፤ ማስተላለፍና
ማጣት የተደነገጉት ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 1311፡፡ የአላባ ለጥቅም ተቀባዩ መብቶች፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባነት የተሰጠውን ነገር ወይም መብት እጅ ለማድረግ፤ በዚሁም ለመገልገልና ንብረቱ በሚያስገኘው ፍሬም
ለመጠቀም መብት አለው፡፡

(2) የማስተዳደሩም መብት የእርሱ ነው፡፡


ቊ 1312፡፡ የንብረቱ አስተዳደር፡፡
የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በመብቱ በሚሠራበት ጊዜ የመልካም አስተዳደርን ሥርዐቶች አክብሮ መጠበቅ አለበት፡፡
ቊ 1313፡፡ የንብረቱ አያያዝ፡፡
የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ስለ ንብረቱ አያያዝና ከዚሁም ላይ ስለሚገኘው ጥቅም የሚደረገውን የወጪ ገንዘብ ኪሣራና እንዲሁም ከንብረቱ
ላይ የማይለየውን የዕዳ ወለድ መቻል አለበት፡፡
ቊ 1314፡፡ ደንበኛ ወጪ፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባነት በያዘው ንብረት ደንበኛ ከሆኑት ገቢዎች ላይ የሚጠየቁትን የዓመት ግብሮችና ሌሎቹንም ወጪዎች
ሁሉ የሚከፈሉበት ጊዜ ሲደርስ በባለርስቱ ስም መክፈል አለበት፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባነት በያዘው በማይንቀሳቀስ ንብረት ግብር በመክፈል ይረጋልኛል ወይም በዚሁ በማይንቀሳቀስ ንብረት
ላይ የመብት ማስረጃ ይሆነኛል ብሎ ርስቱን ሊከራከርበት አይችልም፡፡
ቊ 1315፡፡ የተለዩ ወጪዎች፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በዚህ ሀብት በሚጠቀምበት ጊዜ ከባለንብረቱ ላይ የሚጠየቁ አዲስ ልዩ ወጪዎች የተወሰኑ እንደሆነ ይህንን
ወጪ የሚከፍለው የአላባ ጥቅም ሰጪው ነው፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ሰጪው ይህን በተለይ እንዲከፍል የተጠየቀውን ገንዘብ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ያለ ወለድ እንዲያበድረው ጠይቆት ያለ
አበደረው እንደሆነ ይህ የተጠየቀው ልዩ ወጪ ከዚያው በአላባነት ከተሰጠው ሀብት ላይ አንድ አንድ ነገሮች በመሸጥ ለመከፈል ይቻላል፡፡
ቊ 1316፡፡ የዕቃው መዝገብ ዝርዝር፡፡
የአላባ ጥቅም ሰጪውና የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ምን ጊዜም ቢሆን በአላባው ውስጥ የሚገኙትን ንዋዮች ዝርዝራቸውን የሚናገር መዝገብ
በሁለቱም ኪሣራ እንዲደረግላቸው ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡
ቊ 1317፡፡ የዕቃው መመለስ፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ የመጠቀም ዘመን በተፈጸመ ጊዜ በአላባ የተሰጠውን ንብረት ለአላባ ሰጪው መልሶ ማስረከብ አለበት፡፡

(2) በዕቃው ላይ የደረሰው መጥፋትና መበላሸት ከዐቅሙና ከችሎታው በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑን ካላስረዳ በቀር ለዕቃው መጥፋት
ወይም መበላሸት የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ኀላፊ ይሆናል፡፡
ቊ 1318፡፡ ግዙፍ መብቶች፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የአላባነት በሚጠቀምበት ንብረት ላይ የአላባ ጥቅም ሰጪውን መብቶች ለመጉዳት የሚችል አንዳች ግዙፍ መብት
ሊያቋቁምበት (ሊያደርግበት) አይችልም፡፡

(2) በተለይም በአላባ ጥቅም ሰጪው መብት ላይ ጉዳት በሚያመጣ ዐይነት በአላባነት የተሰጠውን ንብረት ለዕዳ መያዣ አድርጎ መስጠት
አይችልም፡፡
(3) የአላባ ጥቅም ሰጪው ሳይፈቅድለት የአላባ ጥቅም ተቀባዩ እነዚህን ደንቦች ጥሶ የተገኘ እንደሆነ በአላባነት ስለ ተሰጠው መብቱ
መቅረት አንዳችም ኪሣራ ሳይሰጠው ወዲያውኑ ከአላባነት ጥቅሙ ይወገዳል፡፡
ቊ 1319፡፡ የዕቃው መጥፋት፡፡
(1) በአላባ የተሰጠው ነገር የጠፋ እንደሆነ የአላባው መብት ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) በአላባነት የተሰጠው ነገር ለጠቅላላ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ የተነቀለ ወይም የተወሰደ እንደሆነ በምትክነት በተሰጠው ነገር ጥቅም ላይ
የአላባው ጥቅም ይተላለፋል፡፡
ቊ 1320፡፡ ኢንሹራንስ፡፡
(1) በአላባ ጥቅም ሰጪውና የአላባ ጥቅም ተቀባዩ እያንዳንዳቸው መልካም መስሎ የታያቸው እንደሆነ እየራሳቸው መብታቸውን
የሚጠብቅ ኢንሹራንስ ይገባሉ፡፡

(2) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌላቸው በቀር የአላባ ጥቅም ሰጪው የገባው የኢንሹራንስ ወል፤ ለአላባ ጥቅም ተቀባዩ አይጠቅመውም፡፡

(3) እንዲሁም ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌላቸው በቀር የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የገባው የኢንሹራንስ ወል ለአላባ ጥቅም ሰጪው
አይጠቅመውም፡፡
ቊ 1321፡፡ የሀብቶቹ ግምት፡፡
(1) በዕቃ ዝርዝር መዝገብ ወይም በሌላ ሰነድ ላይ በአላባነት በተሰጡት ንዋዮች ላይ የሚደረግ ግምት ሁለቱ ተዋዋዮች የተስማሙበት
ተቃራኒ የሚሆን ነገር ከሌለ በቀር የንዋዮችን ሀብትነት ለአላባ ጥቅም ተቀባዩ አያስተላልፍም፡፡

(2) ስለዚህ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ የመጠቀሙ ዘመን ሲፈጸም ለአላባ ጥቅም ሰጪው የሚመልሰው ሀብቶቹ የተገመቱበትን ዋጋ
ሳይሆን ያንኑ በአላባነት ተሰጥተውት የነበሩትን ሀብቶች ነው፡፡
ቊ 1322፡፡ በአላባ የመጠቀም መብት መቅረት፡፡
(1) በአላባ ጥቅም ተቀባዩ ሲሞት ወይም ስለዚሁ ማለቂያ የተወሰነው ቀን ሲደርስ የአላባው መብት ይቀራል፡፡

(2) በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ማኅበሮች በአላባ ተጠቃሚነት ከሠላሳ ዓመት በላይ መቈየት አይችልም፡፡
ቊ 1323፡፡ የአላባ ሰጪው በአላባነት በተሰጠው ነገር የሚያዝበት ተግባር፡፡
(1) በአላባ ጥቅም ሰጪው በአላባ የሰጠውን ነገር ወይም አላባው በሚመለከተው መብት ላይ ትእዛዝ ቢያደርግ ከዚህ በላይ በተነገረው
በልዩ ግዴታም አጋጣሚ ሁኔታ ካልሆነ በቀር የአላባ ጥቅም ተቀባዩን መብት ሊለውጠው አይችልም፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ የተሰጠውን ሀብት ለመተው መፍቀዱን በግልጽ ካላረጋገጠ በቀር በአላባው መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡
ቊ 1324፡፡ ለአላባ ጥቅም ሰጪው የሚሰጥ ዋስትና፡፡
(1) የአላባ ጥቅም፤ ሰጪው መብቶቹ አደጋ (ጥፋት) የሚያገኛቸው መሆኑን ካስረዳ ለመብቱ ማረጋገጫ ዋስትና እንዲሰጠው የአላባ ጠቅም
ተቀባዩን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) የአላባ መብት የተሰጠው በሚያልቁ ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ የአላባ ጥቅም ሰጪው ዕቃዎቹን ከማስረከብ በፊትና ማስረጃም ሳይሰጥ
ዋስትና እንዲሰጠው የአላባ ጥቅም ተቀባዩን መጠየቅ ይችላል፡፡

(3) የአላባ ጥቅም ሰጩው በአእምሮ ግምት በቂ ነው ተብሎ በሚታሰብና በወሰነለት ቀን የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ማረጋገጫ ዋስትና ያልሰጠ
ጥቅም ተቀባዩ በያዘው ነገር ላይ ሕግ ያልፈቀደውን ሁኔታ በአላባ በተሰጠው ነገር መገልገሉን የቀጠለ እንደሆነ ዳኞች ይዞታውን
አስለቅቀው ለሌላ ጠባቂ ለመስጠት ይችላሉ፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ግዙፍ ተንቀሳቃሽ ሀብቶች የሚጸና
(የሚፈጸም ልዩ) ደንብ፡፡
ቊ 1325፡፡ የአላባ ጥቅም ሰጪው ግዴታ የሌለበት ስለ መሆኑ፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ የሚሰጠውን ነገር በአላባ በሚቀበልበት ጊዜ ባለው ሁኔታ መወሰድ አለበት፡፡

(2) ዕቃውን አድስልኝ በማለት የአላባ ጥቅም ሰጪውን ለማስገደድ አይችልም፡፡


ቊ 1326፡፡ በአላባ በተሰጠው ነገር ስለ መገልገል፡፡
(1) የግዙፍ ተንቀሳቃሽ ዕቃ በአላባ ተጠቃሚ የሆነ ሰው የተሰጠው ነገር ሊያገለግል በተመደበበት ጒዳይ መሠረት ሊገለገልበት መብት
አለው፡፡

(2) በአላባ በተሰጠው ሀብት በሚገለገልበት ጊዜ ዕቃው በደንበኛ አገልግሎቱ ምክንያት ዋጋው ቢቀነስ አላባ ተቀባዩ አንዳችም ኪሣራ
እንዲከፍል አይገደድም፡፡
ቊ 1327፡፡ የሚያልቁ ነገሮች፡፡
(1) አላባው በሚያልቁ ነገሮች ላይ ሆኖ እንዲያልቁ ሳይደረግ በአላባ በተሰጠው ነገር ለመገልገል የማይቻል በሆነ ጊዜ በአላባ ተጠቃሚው
የነዚህ የሚያልቁ ነገሮች ባለሀብት ይሆናል፡፡

(2) በአላባ ጥቅም ተቀባዩ የአላባ ጥቅም ተቀባይነቱ ሲቀር አላባው በተሰጠበት ጊዜ የሚያልቁት ነገሮች የነበራቸውን ግምት መመለስ
አለበት፡፡
ቊ 1328፡፡ በአላባ የተሰጠው ነገር አላባ፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በቅን ልቡና በነገሩ ዓላማና ነገሩ በሚሰጠው አገልግሎት መሠረት የተፈጥሮ ፍሬዎች ካፈሯቸው ነገሮች
በተለያየበት ጊዜ ከተገኙ፤ የፍሬዎቹ ባለሀብት ይሆናል፡፡

(2) ያለ አገባብ የተወሰዱ አላባዎች አላባ ጥቅም ሰጪው ይመለሳሉ፡፡


ቊ 1329፡፡ የተቀበረ ገንዘብ፡፡
የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ የተሰጠውን ነገር በያዘው ጊዜ ሁሉ ለሚገኘው የተቀበረ ገንዘብ አንድም መብት የለውም፡፡
ቊ 1330፡፡ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ መብቶች ወሰን፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በያዘው ነገር መገልገሉ ከመጠን በላይ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለበት፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ የተሰጠውን ነገር ዐይነተኛ በሆነ አኳኋን ለማሻሻል ወይም የሚገኝበትን ቦታ ለመለወጥ አይችልም፡፡

(3) የአላባ ጥቅም ሰጪው የአላባው ጊዜ እስከቈየበት ጊዜ ድረስ የተባሉት ግዴታዎቹ መፈጸማቸውን በሚገባ ሁኔታ ሊመረምር ይችላል፡፡
ቊ 1331፡፡ በአላባነት የተሰጠው ነገር ስለ ማከራየት፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባነት የሚጠቀምበትን ነገር ለማከራየት ይችላል፡፡

(2) በአከራየው ነገር በየቀኑ የሚገኘው ኪራይ የርሱ ሀብት ይሆናል፡፡


ቊ 1332፡፡ ስለ ኪራዩ መቅረት፡፡
(1) ያንድ የሚንቀሳቀስ ነገር ኪራይ የአላባ ጥቅም ተቀባይነቱ ሲቀር ይቀራል፡፡

(2) ላንድ ገበሬ ወይም ተከራይ ባንድ ርስት ወይም ቤት ላይ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የሰጣቸው ውሎች የአላባው ጊዜ ካለቀበት በኋላ እስከ
ሦስት ዓመት ድረስ የአላባ ጥቅም ሰጪውንና ሦስተኛ ወገኖችን የሚያስገድዷቸው ይሆናሉ፡፡
(3) የአላባ ጥቅም ሰጪው በአላባ ጥቅም ተቀባዩ በገበሬው ወይም በተከራዩ መካከል የተደረገው ውል በመብቶቹ ላይ በማይገባና
በተንኰል የተደረገ መሆኑን የስረዳ እንደሆነ፤ ለአላባ ጥቅም ሰጪው በአላባ የተሰጠው ነገር በሚቀርበት ጊዜ ወዲያውኑ ውሉን ለማቋረጥ
ይችላል፡፡
ቊ 1333፡፡ የሥራ ድርጅት ፕላን (1) መደራጀት የሚገባበት ጊዜ፡፡
የአላባ ጥቅም ሰጪው ወይም የአላባ፤ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ የተሰጠውን ንብረት የሚመለከት አንድ የሥራ ጥቅም ፕላን እንዲደራጅ
ለመጠየቅ የሚችሉት፡፡

(ሀ) በአላባ የተሰጠው ነገር እንደ ደን የመሰለ ሆኖ የሥራው ጥቅም በያመቱ ወይም ካንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ አላባዎችን የሚሰጥ
ያልሆነ እንደሆነ፤

(ለ) በአላባ የተሰጠው ነገር የድንጋይ መፍለጫ ቦታን የመሰለ ሀብትን የሚመለከት ሆኖ የሥራው ጥቅም ቀስ በቀስ ዋናውን ነገር
የሚጨርሰው የሆነ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1334፡፡ (2) የአቋቋሙ ዐይነት፡፡

(1) የሥራው ድርጅት ፕላን በባለጒዳዮቹ ስምምነት የሚቋቋም ይሆናል፡፡

(2) በባለጒዳዮቹ መካከል ስምምነት ያልተደረገ እንደሆነ፤ ዳኞች በመረጧቸው አንድ ወይም ብዙ ዐዋቂዎች የሥራው ድርጅት ፕላን
የሚሰናዳ ሆኖ ዳኞቹ የሚያጸድቁት ይሆናል፡፡

ቊ 1335፡፡ (3) መለዋወጥ፡፡


ልዩ የሆኑ ምክንያቶች የሥራውን ዐቅድ እንዳይፈጸም የከለከሉ እንደሆነ ወይም የኤኮኖሚ ረገድ መለዋወጡን መልካም አድርገው ያሳዩ
እንደሆነ፤ ከሁለቱ ወገኖች ባንዱ ጥያቄ ዐቅዱ ሊለወጥ ይችላል፡፡
ቊ 1336፡፡ በአላባ በተሰጠው ነገር ላይ የተደረገ መሻሻል፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ በተሰጠው ነገር ላይ ለሚያደርገው ማሻሻል አንድም ኪሣራ ለማግኘት መብት የለውም፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባ በተሰጠው ርስት ላይ እንደዚሁ ለሚሠራቸው ሥራዎች ሁሉ አንድም ኪሣራ ለማግኘት መብት
የለውም፡፡

(3) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የአላባው ጥቅም ጊዜ ሲያልቅ የተሠሩትን ሥራዎች አፍርሶና ሀብቱን በተረከበ ጊዜ እንደነበረ ለመመለስ ብቻ
ይችላል፡፡
ቊ 1337፡፡ ከፍ ያለ ማደስ (1) ትርጓሜ፡፡
ከፍ ያለ ማደስ የሚባለው በአላባ የተሰጠው ነገር ካንድ ዓመት መጠነኛ ከሆነ ገቢ ሀብት በላይ ወጪን የሚያስገድድ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 1338፡፡ (2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ግዴታዎች፡፡

(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በማንኛዎቹም ሁኔታዎች በአላባ የተሰጠውን ነገር ለመጠበቅ ከፍ ያለ ማደስ የሚያስፈልግ ሲሆን በአላባ ጥቅም
ሰጪው ማመልከት አለበት፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ይህን ከፍ ያለ ማደስ ለማድረግ የሚገደደው ይህ ከፍ ያለ ማደስ በራሱ ሥራ ምክንያት የሆነ እንደሆነና በተለይም
በአላባ የተሰጠው ጊዜ ከተጀመረ ወዲህ ባለማደስና ባለመጠገን የደረሰ ጒድለት ሲሆን ነው፡፡

ቊ 1339፡፡ (3) ከፍ ያለ ማደስ አፈጻጸም፡፡

(1) የአላባ ጥቅም ሰጪው በማናቸውም ሁኔታ በአላባ በተሰጠው ነገር ላይ ከፍ ያለ ማደስ ለማድረግ አይገደድም፡፡

(2) ባለሀብቱ ከፍ ያለ ማደስ ለማድረግ የፈቀደ እንደሆነ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በዚህ በመታደሻው ጊዜ የተነሣ የሚደርስበትን በአላባ ያለ
መጠቀምና አንድ፤ አንድ ጉዳትን መታገሥ አለበት፡፡
(3) የአላባ ጥቅም ሰጪው ለዚህ አስተያየት በሚያደርጋቸው ውሳኔዎች በተቻለ መጠን የአላባ ጥቅም ተቀባዩን ጥቅሞች መጠበቅ አለበት፡፡
ቊ 1340፡፡ በመያዣ የተሰጡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ዕዳ፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ባንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት በልዩ ስም በማያዣ የተሰጠውን ርስት ዕዳ ለመክፈል አይገደድም፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ እንዲከፍል የተገደደ እንደሆነ ገንዘቡ እንዲመለስለት የአላባ ጥቅም ሰጪውን ለማስገደድ ይችላል፡፡
ቊ 1341፡፡ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ክስ፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በአላባነት በተሰጠው ነገር ላይ መብት አለኝ ለማለት ይችላል፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ይህን ነገር በሚመለከቱ የይዞታ (የጅ ማድረግ) ክሶችን ለማቅረብ ይችላል፡፡
ቊ 1342፡፡ የአላባ ጥቅም ሰጪው ስለ ማስታወቅ፡፡
(1) አላባው የሚቈይበት ጊዜ አንድ ሦስተኛ ወገን የሆነ ከርስቱ ላይ አንዳንድ የንጥቂያ ተግባር ያደረገ ወይም የአላባ ጥቅም ሰጪውን
መብቶች ከጉዳት ላይ የጣለ እንደሆነ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ለአላባ ጥቅም ሰጪው ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ይህን ባያደርግ እርሱ ባደረገው ማበላሸት ኀላፊ እንደሚሆነው ሁሉ ለሚደርሰው ጉዳት ኀላፊ ይሆናል፡፡
ቊ 1343፡፡ በአላባ የተሰጠው ነገር መጥፋት፡፡
የአላባ ጥቅም ሰጪው ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በማርጀት የወደቀውን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የፈረሰውን ለማደስ አይገደድም፡፡
ቊ 1344፡፡ በከፊል ስለ መጥፋት፡፡
በአላባ የተሰጠው ነገር በከፊል ብቻ የጠፋ እንደሆነ የአላባው መብት በቀሪው ላይ እንደጸና ይቈያል፡፡
ቊ 1345፡፡ የከብት መንጋ በአላባነት፡፡
(1) በአላባ ጥቅም፤ ተቀባዩ ጥፋት ሳይሆን በአላባ የተሰጠው መንጋ በድንገተኛ አደጋ ወይም በበሽታ በሙሉ ያለቀ እንደሆነ የአላባ ጥቅም
ተቀባዩ ለአላባ ጥቅም ሰጪው ቆዳዎችን ለመመለስ ወይም የቆዳዎቹን ዋጋቸውን ለመስጠት ብቻ ይገደዳል፡፡

(2) መንጋው በሙሉ ያላለቀ እንደሆነ፤ የአላባ ጥቅም ተቀባዩ በተወለዱት ከብቶች መጠን ያለቁትን መተካት አለበት፡፡
ቊ 1346፡፡ ይርጋ፡፡
(1) በአላባ የተሰጠውን ነገር በመለወጥ ወይም ዋጋውን በመቀነስ ምክንያት የአላባ ጥቅም ሰጪው የመጠየቅ መብት በአላባ የተሰጠው ነገር
ከተመለሰበት ቀን አንሥቶ በአንድ ዓመት ይርጋ ይታገዳል፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ራሱ የሠራቸውን ሥራዎች ለማንሣት ያለው መብት እንደዚሁ በ 1 ዓመት ይርጋ ይታገዳል፡፡
ክፍል 3፡፡
የገንዘብና ሌሎች ግዙፎች ያልሆኑ ነገሮች የአላባ መብት ልዩ ደንቦች፡፡
ቊ 1347፡፡ ገቢ፡፡
የገንዘብ ወይም ግዙፍነት የሌለው ነገር የአላባ ጥቅም ተቀባይ የሆነ ሰው መብት ካገኘበት ነገር የሚገኙት ግዙፍ ወይም ድርሻ ገንዘቦች
የመከፈያ ቀናቸው በደረሰ ጊዜ እኒሁኑ ለመውሰድ ይችላል፡፡
ቊ 1348፡፡ ያልታሰቡ ልዩ ትርፎች፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የአላባ ጥቅም ተቀባይ ከሆነበት መብት ሊገኙ የሚችሉ ያልታሰቡ ልዩ ትርፎች ቢገኙ በነዚህ ትርፎች ባለሀብት
አይሆንም፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቀባይነት መብት በነዚህም ትርፎች ላይ ይሆናል፡፡


ቊ 1349፡፡ በአዲስ አክሲዮኖች ስለ መጻፍ፡፡
(1) በአላባነት ለተሰጠ አክሲዮን እንደገና ስለ ወጡት አዲስ አክሲዮኖች በቀደምትነት የመጻፍ መብት የተሰጠ እንደሆነ መርጦ የመጻፉ
መብት አክሲዮኑን በአላባነት ለሰጠው ባለሀብት ነው፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ተቃራኒ መብት የአላባ ጥቅም ሰጪው በገባባቸው አዲስ አክሲዮኖች ወይም የቀዳሚነት ፈራሚነትን መብት በመሸጥ
ባገኘው ዋና ገንዘብ ላይ ይሆናል፡፡

ቊ 1350፡፡ የገንዘብ፤ ወይም የመብቱ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡፡

(1) የአላባ ጥቅም ተቀባዩ መብት የተሰጠበት ገንዘብ ወይም መብት አላባው ጸንቶ በሚቈይበት ጊዜ ተከፍሎ ወይም ተተክቶ እንደሆነ
የአላባ ጥቅም ሰጪው በአከፋፈሉ ረገድ ተስማምቶበት ካልተገኘ በቀር ገንዘቡ ለአላባ ጥቅም ተቀባዩ መሰጠት የለበትም፡፡

(2) የአላባ ጥቅም ሰጪው የሚከፈለው ገንዘብ ለአላባ ጥቅም ተቀባዩ እንዲሰጥ ያልፈቀደ እንደሆነ ባለዕዳው ሊከፈል የሚገባውን ገንዘብ
ለሚገባው በማስረከብ ከዕዳው ነፃ ይሆናል፡፡

(3) የአላባ ጥቅም ሰጪው ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ዕዳው የሚከፈልበት ጊዜ ሲደርስ ገንዘቡን መረከብ በሚገባው ሰው እጅ
እንዲቀመጥ ለማስገደድ ይችላል፡፡
ቊ 1351፡፡ እስከ ዕድሜ ልክ የሚሰጠውን ጡረታ በአላባነት ስለ መስጠት፡፡
እስከ ዕድሜ ልክ በተሰጠ ጡረታ ላይ የሚሰጥ አላባ፤ አላባው ጸንቶ በሚቈይበት ጊዜ ሁሉ አንዳችም ነገር ለመመለስ ተገዳጅ ሳይሆን
የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የተባለውን ለጡረታ የሚከፈለውን ገንዘብ ለመቀበል መብት አለው፡፡
ቊ 1352፡፡ ልዩ የሆኑ ሰነዶችን ስለ መስጠት፡፡
(1) የአላባ ጥቅም ሰጪው ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባዩ ከባለዕዳው ወይም አላባው የተሰጠበትን ሰነድ ካወጣው መሥሪያ ቤት በሁለቱም
ባለጒዳዮች ኪሣራ አንዱ የአላባ ጥቅም ሰጭነት መብት አንደኛው የአላባ ጥቅም ተቀባይነት መብት የሚያረጋግጡ ሁለቱ ልዩ ሰነዶች
ይሰጡን ሲሉ ባለዕዳውን ወይም መሥሪያ ቤቱን ለማስገደድ ይችላሉ፡፡

(2) ይህ ድንጋጌ በባንክኖቶች (ወረቀቶች) ላይ አይፈጸምም፡፡


ክፍል 4፡፡
በቤት ውስጥ የመኖር መብት፡፡
ቊ 1353፡፡ ትርጓሜ፡፡
በቤት ውስጥ የመኖር መብት ማለት ባንድ ቤት ውስጥ የመቀመጥ ወይም አንዱን ክፍል የመያዝ መብት ነው፡፡
ቊ 1354፡፡ የመብቱ ባለጥቅሞች፡፡
በቤት ውስጥ የመኖር መብት ያለው ማናቸውም ሰው ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር በያዘው ቤት ከሚስቱ በቀጥታ መሥመር ዘመዶቹ
ከሆኑና ከቤተ ሰዎቹ ጋራ ለመኖር መብት አለው፡፡
ቊ 1355፡፡ ባንድ ቤት በከፊል ላይ ያለ መብት፡፡
ባንድ ቤት ከፊል ላይ ብቻ የመኖር መብት ያለው ሰው ለጋራ አገልግሎት በተቋቋሙት ነገሮች ለመጠቀም መብት አለው፡፡
ቊ 1356። የመጠገኛ ወጪ (ኪሣራ)፡፡

(1) ባለመብት የሆነው ቤቱን ወይም ክፍሉን ብቻውን የሚገለገልበት ከሆነ ለመጠገን ደንበኛ ወጪዎችን (ኪሣራ) መክፈል አለበት፡፡

(2) በቤቱ ውስጥ የመኖሩ መብት ከባለሀብቱ ጋራ አብሮ የሆነ እንደሆነ የመጠገኛውን ወጪዎች የሚከፍለው ባለሀብቱ ነው፡፡
ቊ 1357፡፡ የማይተላለፍ ስለ መሆኑ፡፡
ባንድ ቤት የመኖሩ መብት ለሌላ የማይተላለፍ ስለሆነ ለወራሾች የማይተላለፍ ነው፡፡
ቊ 1358፡፡ ወደ አላባ ደንቦች ስለ መምራት፡፡
ለሌሎቹ ጒዳዮች የአላባ ደንቦች ባንድ ቤት የመኖር መብት ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ንብረት አገልግሎት፡፡
ቊ 1359፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) የንብረት አገልግሎት ማለት ስለ ሌላው የማይንቀሳቀስ ንብረት ጥቅም በአንዱ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ግዴታ ነው፡፡

(2) ይህ ግዴታ አገልጋይ በሆነ ርስት ባለቤት ፈንታ አገልግሎት የሚቀበለው ርስት ባለቤት አንዳንድ የልማድ ተግባሮች እንዲሠራ ወይም
ከሀብቱ ጋራ የተያያዙትን አንዳንድ መብቶች ከማከናወን ራሱ እንዲታገድ ያስገድደዋል፡፡
ቊ 1360፡፡ የማድረግ ግዴታ፡፡
አንድ የማድረግ ግዴታ ከአንድ የንብረት አገልግሎት ጋራ በተጨማሪ የተያያዘ ካልሆነ በቀር ሊኖር አይችልም፡፡
ቊ 1361፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ሀብትነት ስለ መለወጥ፡፡
(1) የንብረት አገልግሎት የተቋቋመላቸው ወይም ግዴታ የነበራቸው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሀብትነት መለወጥ የንብረቱን አገልግሎት
የሚለዋውጠው አይደለም፡፡

(2) በሕግ የሚጠየቀው ማስታወቂያ ከተደረገለት የንብረቱ አገልግሎት እነዚህን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ወደ ማንም ሰው እጅ
በሚተላለፉበት ጊዜ የሚከተል ነው፡፡

ቊ 1362፡፡ ስለ ንብረት አገልግሎት መቋቋም (1) ውል ወይም ኑዛዜ፡፡

(1) የንብረት አገልግሎት አገልጋይ በሆነ ርስት ባለቤትና አገልግሎት በሚቀበለው ርስት ባለቤት መካከል ከሚደረገው ውል የመነጨ
ለመሆን ይችላል፡፡

(2) እንደዚሁም የንብረት አገልግሎትን ያንድ ርስት ባለቤት ይህን ርስት በሁለት ወይም በብዙ ወራሾች መካከል ከሚያከፋፍልበት ኑዛዜ
የመነጨ ለመሆን ይችላል፡፡

ቊ 1363፡፡ (2) የጽሑፍ አስፈላጊነት፡፡


አንድ የንብረት አገልግሎትን ለማቋቋም ዓላማ ያለው ተግባር፤ በጽሑፍ ካልተደረገ በቀር ዋጋ የለውም፡፡
ቊ 1364፡፡ (3) ሦስተኛ ወገኖችን ስለ መቃወም፡፡
አገልግሎት ለመስጠት ግዴታ ያለበት መሬት ይህ ግዴታ ያለበት ስለ መሆኑ ንብረቱ በሚገኝበት አገር ባለው በማይንቀሳቀስ ንብረት
መዝገብ ካልተጻፈ በቀር ለሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ አይሆንም፡፡
ቊ 1365፡፡ ለንብረት አገልግሎት ተቃዋሚ የሆነ ትርጓሜ መሠረት፡፡
ባንድ ውል ውስጥ የሚገኘው የውል ቃል የንብረት አገልግሎትን ለማቋቋም ወይም በንብረቱ ባለሀብት ላይ የግል ግዴታ ብቻ ለመወሰን
የተደረገ መሆኑ የሚያጠራጥር በሆነ ጊዜ ሁለቱ ተዋዋዮች ተራ (ሰነፍ) የሆነ ግዴታ ብቻ ለማቋቋም እንደተስማሙ ይገመታል፡፡

ቊ 1366፡፡ በቀን ብዛት ምክንያት ለመገልገል መብት ማግኘት፤ (1) የሚታይ የንብረት አገልግሎት፡፡

(1) ዐሥር ዓመት በመያዝ፤ የሚታይ (የታወቀ) የአገልግሎት መብት ይገኛል፡፡

(2) የንብረት አገልግሎት የሚተይ ነው የሚባለው መኖሩን የሚገልጽ አንድ የውጭ ምልክት ያለው እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1367፡፡ (2) የማይታይ የንብረት አገልግሎት፡፡


የማይታይ (ያልታወቀ) የንብረት አገልግሎት መብት በቀን ብዛት ምክንያት መብት ሊያስገኝ አይቻልም፡፡

ቊ 1368፡፡ (3) ሦስተኛ ወገኖችን ስለ መቃወም፡፡

(1) በቀን ብዛት በንብረት መገልገል ምክንያት የሚታይ የንብረት አገልግሎትን መብት ያገኘና ይህንንም አገልግሎት በማይንቀሳቀስ ንብረት
መዝገብ ያስመዘገበ ማናቸውም ሰው የንብረት አገልግሎትን መኖርና መሠረቱን የሚገልጽ ሰነድ እንዲሰናዳለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) በቀን ብዛት መገልገል ምክንያት የሚገኘው የንብረት አገልግሎት መብት፤ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ካልተጻፈ በቀር ለሦስተኛ
ወገኖች መቃወሚያ ሊሆን አይችልም፡፡
ቊ 1369፡፡ የፈቃድ ተግባር፡፡
(1) ባንድ መሬት ላይ ለመገልገል ወይም ለመጠቀም የተሰጠ ፈቃድ ለተፈቀደለት ሰው የንብረት አገልግሎትን ሊሰጠው አይችልም፡፡

(2) በማናቸውም ጊዜ ሁሉ ፈቃዱ ሊሻር ይችላል፡፡


ቊ 1370፡፡ የንብረቱ አገልግሎት መሠረት፡፡
(1) ከአገልግሎት የሚመነጩ መብቶችና ግዴታዎች በርስት መዝገብ በሚደረገው ጽሑፍ የሚደነገጉ ይሆናሉ፡፡

(2) የንብረቱ አገልግሎት ወሰን ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል በተደረገው ወሰን መሠረት በአመጣጡ ወይም በሰላምና በቅን ልቡና ብዙ
ጊዜ የንብረቱ አገልግሎት በተደረገበት ሁኔታ ሊጠናቀቅ ይችላል፡፡

(3) የሚያጠራጥር ሲሆን ከአገልግሎት የሚመነጩ መብቶችና ግዴታዎች በሚከተሉት በዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች መሠረት የሚወሰኑ
ይሆናሉ፡፡
ቊ 1371፡፡ የገጠር የመተላለፍ መብትና የንብረት አገልግሎት፡፡
(1) የመተላለፍ መብት በእግር ወይም ከከብት ጋራ ወይም ሰብል በሌለበት ወቅት ወይም በእርሻ መካከል ወይም ከደን ለመውጣት
መተላለፍን የመሰሉ ሁሉ፤ ልዩ ድንጋጌ ከሌለ በቀር የመተላለፉ መብት መጠን በቦታው ወሰን ላይ እንዳለው ያገር ልማድ ይሆናል፡፡

(2) ስለ ግጦሽ ወይም ደን ስለ መግባት ውሃ ስለ ማጣጣት ስለ መስኖ ስለ ሌሎች የገጠር የንብረት አገልግሎት መብት ከዚህ በላይ
እንዳለው ይደረጋል፡፡

ቊ 1372፡፡ ስለ ንብረት አገልግሎት አከናወን አስፈላጊ የሆኑ ዘዴዎች (ሁኔታዎች)፡፡

(1) የንብረት አገልግሎት መኖረ ለአከናወኑ አስፈላጊ ዘዴዎችን ያስከትላል፡፡

(2) እንደዚሁ ካንድ ምንጭ ውሃ የመቅዳት መብት ያለው ሰው እስከ ምንጩ ለመድረስ እንደዚሁ የመተላለፍ መብት ይኖረዋል፡፡

ቊ 1373፡፡ አስፈላጊ ሥራዎች (1) መሠረቱ፡፡

(1) የንብረት አገልግሎት መስጠት (መቀበል) የሚገባው መሬት ባለሀብት በንብረቱ አገልግሎት ለመጠቀምና አገልግሎቱን ለመጠበቅ
አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን ለማድረግና ሥራዎችን ሁሉ ለመሥራት ይችላል፡፡

(2) የንብረቱን አገልግሎት የሚያቋቁመው ሰነድ ተቃራኒ የሆነ ነገር ካልተናገረ በቀር የነዚህ ሥራዎች ወጪ በራሱ እንጂ የንብረቱን
አገልግሎት ሰጪ የሚሆነው ርስት ባለቤት ኪሣራ አይሆንም፡፡

ቊ 1374፡፡ (2) የመተው መብት፡፡


የንብረት አገልግሎት ሰጪ የሆነው ርስት ባለሀብት በአገልግሎቱ ለመጠቀም ወይም በደኅና ለመኖር በኪሣራው አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎችን
ለመሥራት፤ ሰነዱ የሚያስገድደው ቢሆንም በአገልግሎቱ ለሚጠቀመው ባለሀብት አገልግሎት የሚሰጠውን ርስት ወይም ለአገልግሎቱ
አከናወን በቂ የሆነ ድርሻውን በመተው ዘወትር ከግዴታው ነፃ ለመውጣት ይችላል፡፡
ቊ 1375፡፡ በአገልግሎቱ የሚጠቀመው መሬት ባለሀብት ግዴታ፡፡
(1) በአገልግሎቱ የሚጠቀመው መሬት ባለሀብት፤ አገልግሎት የሚሰጠው መሬት ባለሀብት በተቻለ መጠን ጉዳት እንዳያገኘው አድርጎ
በመብቱ ሊሠራበት ይገባዋል፡፡

(2) በአገልግሎቱ የሚጠቀመው መሬት ባለሀብት በአገልግሎት የሚጠቀመው መሬት ላይ ወይም አገልግሎት በሚሰጠው መሬት ላይ
አገልግሎት የሚሰጠውን መሬት ሁኔታ የሚያከብድ ማለዋወጥ ሳያደርግ (ለማድረግ ሳይችል) በሰነዱ መሠረት በንብረቱ አገልግሎት
ሊገለገልበት ይችላል፡፡
ቊ 1376፡፡ በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለሆነ መሬት የሚያስፈልጉ አዳዲስ ነገሮች፡፡
በንብረቱ አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆነው መሬት የሚያስፈልጉት አዳዲስ ነገሮች ምንም የአገልግሎትን ማክበድ አያስከትሉም፡፡
ቊ 1377፡፡ በንብረቱ አገልግሎት ስለሚጠቀመው መሬት መከፋፈል፡፡
(1) በንብረቱ አገልግሎት የሚጠቀመው መሬት የተከፋፈለ እንደሆነ አገልግሎት የሚሰጠው መሬት ሁኔታ የከበደ ሳይሆን፤ አገልግሎቱ
ለያንዳንዱ ድርሻ የተገባ ሆኖ ይቈያል፡፡

(2) እንዲሁም ለምሳሌ ሰለ መተላለፍ መብት የሆነ እንደሆነ ማንኛዎቹም የጋራ ባለሀብቶች ሁሉ በዚያው በተለመደው ቦታ ለመተላለፍ
የተገደዱ ይሆናሉ፡፡

(3) በንብረቱ አገልግሎት የሚጠቀመው ከድርሻዎች ውስጥ አንዱ ብቻ የሆነ እንደሆነ አገልግሎቱን የሚሰጠው መሬት ባለሀብት የሌሎቹ
የንብረት አገልግሎት መብት እንዲሠረዝ ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 1378፡፡ የንብረቱን አገልግሎት ስለሚሰጠው መሬት መከፋፈል፡፡
(1) ንብረቱን አገልግሎት የሚሰጠው መሬት የተከፋፈለ እንደሆነ እያንዳንዱ ክፍል እንደ ደንቡ አገልግሎቱን ይቀጥላል፡፡

(2) አገልግሎቱ ባንዳንድ ክፍሎች ላይ በርግጥ የማይከናወንና ለመከናወን ያልቻለ እንደሆነ የንዚሁ ክፍሎች ባለሀብት በክፍሎች ላይ
ያለው የንብረት አገልግሎት እንዲሰረዝ ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 1379፡፡ የንብረት አገልግሎት የሚሰጠው መሬት ባለሀብት ግዴታ፡፡
የንብረት አገልግሎትን የሚሰጠው መሬት ባለሀብት አገልግሎት የሚቀንስ ወይም የማይመች ዘዴ የማድረግ ዝንባሌን ለመሥራት
አይችልም፡፡
ቊ 1380፡፡ የንብረት አገልግሎትን ሥራ ዐይነት ስለ መለወጥ፡፡
የንብረት አገልግሎትን በሚሰጠው መሬት አንድ ክፍል ላይ ብቻ የሚደረግ እንደሆነ አገልግሎት ተቀባይ የሆነው መሬት ባለሀብት ጥቅም
ያለውና ወጩውን (ኪሣራውን) የሚችል ከሆነ፤ ሥራው በአገልግሎት ለሚጠቀመው መሬት ባለሀብት ምቹነትን ሳያሳጣ ሌላ ቦታ
እንዲዛወር ለማስገደድ ይችላል፡፡
ቊ 1381፡፡ የንብረቱ አገልግሎት መቅረት፡፡
(1) በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ላይ የተጻፈው የንብረት አገልግሎት በጽሑፉ መሠረዝ ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) በአገልግሎቱ የሚጠቀመው መሬት ባለሀብት ለማይንቀሳቀስ ንብረቱ የሚገባውን አገልግሎት ትቻለሁ ሲል በጽሑፍ በማረጋገጥ
አሳቡን በግልጽ የሰጠ እንደሆነ ስለ አገልግሎቱ በመዝገብ የተጻፈው ጽሑፍ እንዲሠረዝ ለመጠየቅ ይቻላል፡፡

(3) እንዲሁም የሚታይ አገልግሎት በሆነ ጊዜ ይህ አገልግሎት መኖሩን የሚገልጹት ሥራዎች በጠፉ ወይም ከዐሥር ዓመት ጀምሮ
የማያገለግሉ ሆነው በተገኙ ጊዜ ስለ ንብረቱ አገልግሎት በመዝገብ የገባው ጽሑፍ እንዲሠረዝ ለመጠየቅ ይቻላል፡፡
ቊ 1382፡፡ የንብረቱ አገልግሎት በከፊል መቅረት፡፡
የንብረቱ አገልግሎት ሁኔታ እንደ ንብረቱ አገልግሎት መኖርና እሱን በሚመለከተው ዐይነት በይርጋ ቀሪ ሊሆን ይችላል፡፡
ቊ 1383፡፡ የንብረት አገልግሎትን መልሶ ስለ መግዛት፡፡ (1) የሚቻልበት ሁኔታ፡፡
የንብረት አገልግሎትን መልሶ ለመግዛት የሚቻለው፡፡
(ሀ) ለአገር ኤኮኖሚ ጥቅም ወይም ለሌላ አንዳንድ የሕዝብ ጥቅም ተቃራኒ የሆነ እነደሆነ፤

(ለ) በአገልግሎት ለሚጠቀመው መሬት አገልግሎት የሚሰጠው ጥቅም አገልግሎትን በሚሰጠው መሬት ላይ የሚያስከትለው ማወክና
የዋጋ መቀነስ የማይመዛዘን ሲሆን ነው፡፡

ቊ 1384፡፡ (2) አሠራር፡፡

(1) በባለጒዳዮቹ መካከል ስምምነት የሌለ እንደሆነ አገልግሎትን በሚሰጠው መሬት ባለሀብት ጥያቄ የአገልግሎቱን መልሶ መገዛት ዳኞች
ያዝዛሉ፡፡

(2) የንብረቱን አገልግሎት መልሶ በመግዛት የሚደርሰውን ኪሣራ ዳኞች ይወስናሉ፡፡

(3) ዳኞች ይህን ኪሣራ ለመወሰን በአገልግሎት ለሚጠቀመው መሬት ጥቅም ወይም አገልግሎትን ለሚሰጠው መሬት ጉዳት አገልግሎቱ
ሊያስከትል የሚችለውን ማናቸውንም ምክንያትና በተለይም አገልግሎቱ የቈየበትን ጊዜ ያመዛዝናሉ (በግምት ውስጥ ያገባሉ)፡፡
ቊ 1385፡፡ መልሶ መግዛትን የሚያስቀር የውል ቃል፡፡
ባለጒዳዮቹ አገልግሎትን በሚያቋቁመው ጽሑፍ ወይም በኋላ በተጻፈ ውል ውስጥ ከዐሥር ዓመት ለመብለጥ በማይችል ጊዜ ውስጥ
አገልግሎትን መልሶ ለመግዛት ዳኞችን የመጠየቅ ሥልጣንን ለማስቀረት ይችላሉ፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት፡፡
ቊ 1386፡፡ ትርጓሜ፡፡
በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት ዋጋን በመክፈል የአንድ ንብረት ሀብትነት ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባይነትን ባንዳንድ
ምክንያቶች የሚገዛውን ሦስተኛ ወገን ለማስለቀቅ ላንዱ ሰው የተሰጠ መብት ነው፡፡
ቊ 1387፡፡ በአገልግሎት ብቻ ላይ የተመሠረተ መብትን ስለ ማስቀረት፡፡
በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት ማናቸውም መብት ለብዙ ዘመን በቈየ አገልግሎት ቢሆንም በአገልግሎቱ ብቻ ሊገኝ አይችልም፡፡
ቊ 1388፡፡ የጋራ ባለሀብቶች በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት፡፡
(1) በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት ከጋራው ንብረት ውስጥ ለሚሸጠው አንድ ክፍል ለጋራ ባለሀብቶቹ በሕግ መሠረት
አላቸው፡፡

(2) የጋራ ባለሀብቶች የሆኑት ባልተከፋፈለው ሀብት ላይ ባላቸው ድርሻ መጠን ባንድ ጊዜ በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት
መብታቸውን ይሠሩበታል፡፡

(3) ከመካከላቸው አንዱ ወይም ብዙዎቹ የተዉ እንደሆነ ሌሎቹ በተተዉ ንብረቶች ሁሉ በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት መብታቸው
ይሠሩበታል፡፡

ቊ 1389፡፡ የዘመዶች በቅድሚያ የመግዛት መብት (መሠረቱ)፡፡


አንድ ሰው ከዘመዶቹ ከአንደኛው በውርስ ያገኘውን ርስት የሸጠ እንደሆነ የሻጩ ዘመዶች በቅድሚያ የመግዛት መብት በሕግ መሠረት
አላቸው፡፡
ቊ 1390፡፡ (2) የዝምድናው ደረጃ አገማመት፡፡

(1) ሻጩ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘው በአባቱ የዝምድና መሥመር ከሆነው ከአንዱ ዘመዱ እንደሆነ በቀደምትነት ለመግዛት
በተሰጠው መብት ሊጠቀሙ የሚችሉት በሻጩ የአባት ወገን የዝምድና መሥመር ውስጥ የሚገኙት ዘመደቹ ብቻ ናቸው፡፡
(2) እንዲሁም ሻጩ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘው በእናቱ የዝምድና መሥመር ከሆነ ከአንዱ ዘመዱ እንደሆነ በቀደምትነት ለመግዛት
በተሰጠው መብት ሊጠቀሙ የሚችሉት በሻጩ የእናት መሥመር ውስጥ የሚገኙት ዘመዶቹ ብቻ ናቸው፡፡

ቊ 1391፡፡ (3) የቅደም ተከተል ተራ፡፡


የቤተ ዘመድ የይገባኛል ቀዳሚነት ተራ የሚወሰነው ኑዛዜ በሌለ ጊዜ የውርስ ንብረት የሚከፋፈልበትን አኳኋን በሚመለከተው በዚህ ሕግ
ስለ ውርስ በተጻፈው አንቀጽ መሠረት ነው፡፡

ቊ 1392፡፡ (4) ለአንዳንድ ሰዎች የሚሰጥ ምርጫ፡፡


በእነዚህ ድንጋጌዎች መሠረት በይገባኛል መብታቸው ሊጠቀሙ የሚችሉ ብዙ ሰዎች ያሉ እንደሆነ የቀዳሚነቱ ምርጫ የሚሰጠው
በሚሸጠው መሬት ላይ ለሚኖሩት ወይም ራሳቸው እየሠሩ በዚሁ መሬት ለሚጠቀሙት ቤተ ዘመዶች ነው፡፡
ቊ 1393፡ ስለ ብዙ ባለመብቶች፡፡
(1) በአንድ የተራ ደረጃ ውስጥ በቀዳሚነት ይገባናል በማለት እኩልነት ያላቸው ብዙዎች ሰዎች ያሉ እንደሆነ መብቱን በኅብረት
ይሠሩበታል በመሬቱም ትክክል በሆነ ድርሻ የጋራ ባለሀብቶች ይሆናሉ፡፡

(2) በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት የማይገለገሉ ሰዎች ድርሻ የዝምድና ተራ ውስጥ ያሉትን የሌሎቹን ዘመዶች ድርሻ የሚያበዛው ይሆናል፡፡
ቊ 1394፡፡ በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት አመዳደብ፡፡
በሕግ የተደነገገው በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብቶች በሚከተለው ተራ ተመድበዋል፡፡
(1) የጋራ ባለሀብት በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት፤

(2) የሥጋ ዘመዶች በቀዳሚነት ይገባናል የማለት መብት፤


ቊ 1395፡፡ የአንዳንዶች ሰዎችን በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብትን ስለ ማስቀረት፡፡
ዝቅተኛ ደረጃ ያለው ቢሆንም እንኳ በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት ያለውን ሰው በዚሁ መብት ሌላ ሰው ሊቃወመው አይችልም፡፡
ቊ 1396፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብትን ስለ ማስቀረት፡፡
የተሸጠው ርስት በከተማ ቀበሌ ውስጥ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ወይም የተሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት መኖሪያ ቤት ወይም ማናቸውም
ሌላ ሕንፃ የሆነ እንደሆነ ከዚህ አስቀድሞ ስለ ሥጋ ዘመዶች የተደነገገው በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት ሊሠራበት አይቻልም፡፡
ቊ 1397፡፡ በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት፤ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ ስለ መሆኑ፡፡
(1) በሕግ የተደነገገው በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት በሕግ፤ መብቱ ከተሰጣቸው ሰዎች ጋራ የተሳሰረ ነው፡፡

(2) መብቱንም ባለጥቅሞቹ ለሌላ ሰው ሊያስተላልፉ አይችሉም፡፡

(3) ከባለጥቅሞቹም ገንዘብ ጠያቂዎች የሆኑ ሰዎች በዚሁ መብት ተተክተው ሊሠሩበት አይቻልም፡፡
ቊ 1398፡፡ በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብትን እንዲሠሩበት ስለ ማድረግ፡፡
(1) በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት ባለጥቅም የሆነ ሰው ባለሀብቱ በፈቃዱ ሀብቱን ወይም የሀብቱን አላባ በዋጋ በሚሸጥበት
በማናቸውም ጊዜ ሁሉ በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት በመብቱ ሊሠራበት ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ከባለሀብቱ ላይ የዕዳ ገንዘብ ጠያቂው ባቀረበው ጥያቄ ሀብቱ በሚያዝበት ጊዜ በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት ያለው
ሰው በዚሁ በመብቱ ሊሠራበት ይችላል፡፡
ቊ 1399፡፡ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ስለ ማስለቀቅ፡፡
የማይንቀሳቀሰው ንብረት ለሕዝብ አገልግሎት በሚያስፈልግ ምክንያት እንዲለቀቅ በሚደረግበት ጊዜ በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት
ያለው ባለጥቅም በዚህ መብቱ ሊሠራበት አይችልም፡፡
ቊ 1400፡፡ በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት መብቱ እንዲገለገልበት ለመጠየቅ የተወሰነው ጊዜ (1) የማስተላለፍ ማስታወቅ፡፡
የማንም ሰው በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት መብት ሊገለገልበት የፈለገ እንደሆነ ንብረቱ በሀብትነት ወይም በአላባነት ለገዡ ወይም
በሐራጅ ለሚገዛው ሰው የተላለፈ መሆኑ ለይገባኛል ባዩ ከተነገረበት ቀን አንሥቶ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ በመብቱ ሊገለገልበት የፈለገ
መሆኑን ካላስታወቀ መብቱ ይቀርበታል፡፡

ቊ 1401፡፡ (2) ስላለማስታወቅ፡፡

(1) ይህ እንደዚህ ያለው ማስታወቂያ ሳይነገር የቀረ እንደሆነ የጋራ ባለሀብቶቹ በማያጠራጥር አኳኋን ንብረቱ ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑን
ካወቁበት ቀን አንሥቶ በሚቈጠር በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት መብታቸው ሊገለገሉበት የፈለጉ መሆናቸውን
ማስታወቅ አለባቸው፡፡

(2) የሥጋ ዘመዶች፤ አዲሱ ባለሀብት (ገዢው) ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እጅ ካደረገበት ቀን አንሥቶ
በሚቈጠር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በቀዳሚነት ይገባናል በማለት መብታቸው ሊገለገሉበት የፈለጉ መሆናቸውን ማስታወቅ አለባቸው፡፡
ቊ 1402፡፡ በቀደምትነት ይገባኛል የማለት መብት ለማን እንደሚነገር፡፡
በቀደምትነት ይገባኛል በማለት መብት ለመጠቀም የሚፈልገው ሰው ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች በተመለከቱት ጊዜዎች ውስጥ ይህ
መብት ለሚመለከተው ንብረት አዲስ ባለሀብት ለሆነው ሰው መግለጽ አለበት፡፡
ቊ 1403፡፡ ዋስትና የመስጠት ግዴታ፡፡
በቀደምትነት ይገባኛል በማለት መብት ለመገልገል እንደሚፈልግ የሚሰጠው መግለጫ የንብረቱን ሙሉ ዋጋ ለመክፈል የሚያርጋግጡና
ዳኞቹም በቂ አድርገው የሚቀበሏቸው አንድ ወይም ብዙ ሰዎች ወይም ሌሎች ማረጋገጫዎች ካላቀረበ በቀር መግለጫው ዋጋ የሌለው
ይሆናል፡፡
ቊ 1404፡፡ በተሰጠው መግለጫ የሚጠቀሙት፡፡
(1) ከባለመብቶቹ አንዱ የሚያደርገው መግለጫ የሚጠቅመው በተለይ ማስታወቂያውን ያደረገውን ሰው ብቻ ነው፡፡

(2) ይህም ስለ ተባለ ማስታወቂያው የቀድሞው ባለሀብት ዘመዶች ከሆኑት በዝምድና ስም ብቻ ሥራውን በሚፈጽም ባንድ ዘመደ ተደርጎ
እንደሆነና በዝምድናው መደብ እኩል የሆኑት ዘመዶች በማስታወቂያው ለመጠቀም አሳባቸውን የገለጹ እንደሆነ ሁሉም ሊጠቀሙበት
ይችላሉ፡፡

(3) ይህም አሳብ ማስታወቂያው ከተሰጠበት ቀን አንሥቶ በሚቈጠር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ካልተገለጸና ለዚህም በአመልካቹ ላይ
የሚታሰብ ከዋጋው ድርሻውን ለመክፈል የሚያረጋግጡ በቂዎች የሆኑ ዋሶችን በመጥራት ወይም ማረጋገጫዎችን በመስጠት ካልሆነ በቀር
ውጤት የለውም፡፡
ቊ 1405፡፡ በቀደምትነት ይገባኛል የማለት መብት ውጤት፡፡
(1) በቀደምትነት ይገባኛል የማለት መብት ያለው ሰው ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት በመብቱ ለመገልገል
መፈለጉን የገለጸ እንደሆነ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የገዛው ሰው በዚህ ንብረት ላይ ያለውን መብት ለይገባኛል ባዩ እንዲያስተላልፍለት
ይገደዳል፡፡

(2) የሚገባው ዋጋ እንደተከፈለው ይህን ግዴታውን ወዲያውኑ ራሱ መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 1406፡፡ ንብረቱን እንዲለቅ የተደረገው ሰው መብቶች፡፡ (1) ዋጋ፡፡

(1) ንብረቱን እንዲለቅ የተደረገው ሰው የከፈለው ዋጋ እንዲመለስለት መብት አለው፡፡

(2) ንብረቱን ገዝቶ የነበረው ሰው በሽያጩ ውል ላይ የተመለከተው ዋጋ በውነት ከከፈለው ዋጋ ዝቅተኛ መሆኑን ለማስረዳት
አይፈቀድለትም፡፡
(3) በቀደምትነት ይገባኛል በማለት መብት ለመጠየቅ የሚፈልገው ሰው ግን በሽያጩ ውል ላይ የተመለከተው ዋጋ በማስመሰል የተነገረ
ዋጋ ለመሆኑ በማናቸውም መንገድ ሁሉ ለማስረዳት ይችላል፡፡

ቊ 1407፡፡ (2) የማይንቀሳቀሰው ንብረት ግምት፡፡

(1) በቀደምትነት መግዛት ይገባኛል የማለትን መብት ያስከተለው የንብረት ማግኘት ያለ ዋጋ የተፈጸመ ሆኖ እንደሆነ ይህንኑ ንብረት
እንዲለቅ የተደረገው ሰው የማይንቀሳቀሰውን የንብረት ግምት የሚተካከል ዋጋ የመቀበል መብት አለው፡፡

(2) ክርክርም በተነሣበት ጊዜ ዋጋው የሚወሰነው በዚህ ሕግ ያለ አገባብ ስለ መበልጸግ በተመለከተው ምዕራፍ መሠረት ነው፡፡

ቊ 1408፡፡ (3) ስለ ተጨማሪ ገንዘብ፡፡

(1) ንብረቱን እንዲለቅ የተደረገው ሰው ከሚገባው ዋጋ በላይ በማናቸውም ሁኔታ ንብረቱ ሲተላለፍለት ያወጣቸውን የውልና የማዘዋወር
ወጪዎች እንዲከፈለው መብት አለው፡፡

(2) ከዚህም ሌላ የዚህን ንብረት ዋጋ ከከፈለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተመለሰለት ቀን ድረስ ለከፈለው ዋጋና ወጪዎች ሕጋዊ ወለድ
እንዲከፈለው መብት አለው፡፡

(3) በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት መብት ለመጠቀም የሚፈልገው ሰው ንብረቱን እጅ ካደረገበት ቀን አንሥቶ በሚቈጠር በአንድ ዓመት
ጊዜ ውስጥ የተባለው ንብረት ያፈራውን ሀብት ለባለይዞታው በመተው ወለዱን ከመክፈል ነፃ ለመሆን ይችላል፡፡

ቊ 1409፡፡ (4) ወጪ፡፡


ንብረቱን እንዲለቅ የተደረገው ሰው በለቀቀው ንብረት ላይ ያወጣውን ገንዘብና ንብረቱ በእጁ ሆኖ በቈየበት ጊዜ ውስጥ በተባለው ንብረት
ላይ የደረሰውን መበላሸት ስለሚመለከተው ነገር በዚህ የፍትሐ ብሔር ሕግ አለ አገባብ ስለ መበልጸግ በሚለው አንቀጽ የተመለከቱት
ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ምዕራፍ 5፡፡
ባለሀብቱ አንዳንዶቹን ንብረቶች እንደ ፈቀደው፡፡
እንዳያደርግ መብቱን ስለ ማጥበብ፡፡
ክፍል 1፡፡
የግዢን ወይም በቀደምትነት የመግዛትን
መብት ስለሚመለከት የውል ስምምነት፡፡
ቊ 1410፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) የሽያጭ ተስፋ መስጠት ማለት የአንድ ንብረት ባለሀብት የሆነ ሰው ይህንኑ ሀብቱን ለመግዛት ሌላው ሰው ወዲያው አሳቡን
እንደገለጸለት እሸጥልሃለሁ ሲል ለዚያው ሰው የሚገባለት የስምምነት ቃል ነው፡፡

(2) በቀደምትነት የመግዛት መብት ማለት የአንድ ንብረት ባለሀብት የሆነ ሰው ይህንኑ ሀብቱን ለመሸጥ በሚወስንበት ጊዜ አንድን ሰው
በመምረጥ ሀብቱን እሸጥልሃለሁ ሲል ለዚህ ለመረጠው ሰው ከሚገባለት የስምምነት ቃል የሚመነጭ መብት ማለት ነው፡፡
ቊ 1411፡፡ የዚህ ምዕራፍ ዓላማ ወሰን፡፡
(1) ለሽያጭ የተስፋ ቃል መስጠት ወይም በቀደምትነት ለመግዛት ለአንድ ሰው መብት የሚሰጠው ስምምነት የማይንቀሳቀስ ንብረትን
ወይም አንድ የተለየ የሚንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከት ካልሆነ በቀር ለተስፋ ሰጪው የባለሀብትነቱን መብት የሚያጠብና በነዚህም
ንብረቶች ላይ ለተስፋ ተቀባዩ መብትን የሚሰጥ አይደለም፡፡

(2) በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል ያሉት የግዴታዎች ግንኙነቶች በዚህ ሕግ በአራተኛውና በአምስተኛው አንቀጽ ተወስኗል፡፡

(3) ከዚህ በታች የሚከተሉት ድንጋጌዎች እነዚህ ስምምነቶች ከሚያስከትሉት ከእውነተኛው ውጤት በቀር ሌላ አያመለክቱም፡፡
ቊ 1412፡፡ ስምምነቱ የሚጸናበት ሁኔታ፡፡
ለሽያጭ የተስፋ ቃል መስጠት ወይም በቀደምትነት ለመግዛት ለአንድ ሰው መብት የሚሰጠው ስምምነት በጽሑፍ ካልተደረገና ባለጥቅሙ
የሚጠቀምበት ጊዜና ዋጋ ተለይቶ ካልታወቀ በቀር ዋጋ የላቸውም፡፡
ቊ 1413 ፡፡ ከፍተኛ ጊዜ፡፡
(1) ለሽያጭ የተስፋ ቃል መስጠት ወይመ በቀደምትነት ለመግዛት በውል የሚሰጠው መብት ከዐሥር ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ሊሰጥ
አይቻልም፡፡

(2) በውሉ ቃል ጊዜው ከዐሥር ዓመት በላይ እንዲቈይ ተነግሮ እንደሆነ ከዐሥር ዓመት በላይ የሆነው ጊዜ ተቀናሽ ይሆናል፡፡
ቊ 1414፡፡ ለሕዝብ ጥቅም ርስትን ስለ ማስለቀቅ፡፡
(1) ለሽያጭ የተስፋ ቃል መስጠትና ስለ ግዡ ቀደምትነት መብት መስጠት የሚደረጉት ስምምነቶች የሚመለከቱት፤ ንብረት ስለ ሕዝብ
ጥቅም የተወሰደ ወይም ለጊዜው የተያዘ እንደሆነ ፈራሾች ይሆናሉ፡፡

(2) በዚሁ ምክንያት የነዚህ መብቶች ባለጥቅሞች ለሆኑት ሰዎች አንዳች ኪሣራ አይሰጣቸውም፡፡
ቊ 1415፡፡ መብቶቹ የማይተላለፉ ስለ መሆናቸው፡፡
(1) ለሽያጭ የተስፋ ቃል መስጠትና በቀደምትነት ለመግዛት በውል የሚሰጠው መብት ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር የነዚህ
መብቶች ባለጥቅም ለሆነው ሰው ብቻ የተሰጡ ናቸው፡፡

(2) ባለጥቅሞቹ መብቶቻቸውን ሊያስተላልፏቸው አይችሉም፤ እንዲሁም ለወራሾቻቸው አያልፍም፡፡

(3) ከባለጥቅሙ ገንዘብ ጠያቂዎች በባለጥቅሙ ስም በሻጭነት ምርጫ ወይም በግዢ ቀደምትነትም መብት ለመሥራት አይችሉም፡፡

ቊ 1416፡፡ ለሽያጭ የተስፋ ቃል መስጠት (1) በንብረቱ ላይ ዋስትናን ስለ ማቋቋም፡፡

(1) ማንም ሰው በአንድ ንብረት ላይ ለመሸጥ የተስፋ ቃል የሰጠ እንደሆነ ባለጥቅሙ ለመግዛት መፈለጉን እንዲያስታውቅ የተወሰነው ጊዜ
እስኪያልፍ ድረስ ተስፋ ሰጪው ንብረቱን ለመሸጥ ለማስተላለፍ፤ ወይም በዚሁ ንብረት ላይ ማንኛውንም ዋስትና ሊያቋቁም አይችልም፡፡

(2) ስለሆነም ለመሸጥ የተስፋ ቃል በተሰጠው ውስጥ ከተጠቀሰው ዋጋ በላይ ላልሆነ ገንዘብ ዋስትና እንዲሆን በንብረቱ ላይ መያዣ
ለማቋቋም ወይም ንብረቱን በመያዣ ለመስጠት ይችላል፡፡

ቊ 1417፡፡ (2) ስለ ንብረቱ መያዝ፡፡

(1) ለሽያጭ የተስፋ ቃል የተሰጠበት ንብረት የተያዘ እንደሆነ ባለዕዳው የንብረቱን መያዝ ቃል ለተገባለት ባለጥቅም ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ባለጥቅሙም ውሉ እንዳይፈርስበት (እንዳይቀርበት) ይህ የተባለው ንብረት በፍርድ በሐራጅ ከመሸጡ በፊት ስለ ግዢ በተሰጠው
የምርጫ መብቱ መሥራት አለበት፡፡
ቊ 1418፡፡ በቀደምትነት የመግዛት መብት፤ በንብረት ላይ ዋስትናን ስለ ማቋቋም፡፡
(1) ለሌላ ሰው የግዥ ቀደምትነትን መብት የሰጠ ማንኛውም ሰው ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር የግዢ ቀደምትነት
በሚመለከተው ንብረት ላይ ዋስትናን ሊያቋቁምበት ይችላል፡፡

(2) ይህን የተባለውን ንብረት ለመሸጥ ለመለወጥ ያሰበ እንደሆነ ለዚህ መብት ባለጥቅም ማስታወቅ ብቻ አለበት፡፡

(3) እንደዚሁም የማይንቀሳቀሰው ንብረት የተያዘ እንደሆነ ለባለጥቅሙ ማስታወቅ አለበት፡፡


ቊ 1419፡፡ በግዢ ቀደምትነት መብት ለመሥራት የተወሰነው ጊዜ፡፡
(1) የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የመሸጥ የመለወጥ አሳብ መኖሩን የገዥ ቀደምትነት መብት ለተሰጠው ባለጥቅም ከተነገረበት ጊዜ አንሥቶ
በሚቈጠር በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ እንዲሠራበት ያስፈልጋል፡፡
(2) ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተመለከተው ጊዜ በውል እጅግ ቢበዛ ለአንድ ዓመት ሊደረግ ይቻላል፡፡

(3) ጊዜው ከአንድ ዓመት በላይ እንዲሆን ተወስኖ እንደሆነ ያለክርክር አንድ ዓመት ወደ መሆን እንዲወርድ ይደረጋል፡፡
ቊ 1420፡፡ በግዥ ቀደምትነት መብት ስላለመሥራት፡፡
(1) የግዥ ቀደምትነት መብት የተሰጠው ባለጥቅም በመብቱ ሳይጠቀምበት ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተውን ጊዜ ያሳለፈ እንደሆነ
መብቱ ይቀርበታል፡፡

(2) ባለሀብቱም የማይንቀሳቀሰውን ንብረቱን እንደ ፈቀደው በነፃ ለመሸጥ ለማስተላለፍ ይችላል፡፡

(3) እንደዚሁም ንብረቱን እንደያዘ ለማስቀረት ይችላል፡፡


ቊ 1421፡፡ የንብረት መያዝ፡፡
(1) ንብረት በሚያዝበት ጊዜ ንብረቱ በሐራጅ ከመሸጡ በፊት ስለ ግዢ ቀደምትነት የተሰጠው መብት ካልተሠራበት በቀር ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) ማናቸውም ለዚህ ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 1422፡፡ ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ስለ መሆኑ፤ (1) ሁኔታዎች፡፡


ለሽያጭ የተሰጠው የተስፋ ቃል ወይም በቀደምትነት ለመግዛት በውል የሚሰጠው መብት በማይንቀሳቀስ ርስት መዝገብ በሚገባ ካልተጻፈ
በቀር በሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ሊሆንባቸው አይችልም፡፡

ቊ 1423፡፡ (2) ስለ ሌሎች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡

(1) የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ጒዳይ በሚያጋጥምበት ጊዜ፤ እነዚህ ከዚህ በላይ የተባሉት መብቶች ይህ የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለበት
ቦታ ላይ በሚገኘው ፍርድ ቤት መዝገብ ካልተጻፈ በቀር በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሊሆንባቸው አይችልም፡፡

(2) የዚህ ዐይነት አመዘጋገብ የሌለ እንደሆነ ሦስተኞች ወገኖች መኖሩን ያወቁ ወይም ማወቅ የነበረባቸው ካልሆኑ በቀር ስለ ሽያጭ
የሚሰጠው የተስፋ ቃል ወይም ስለ ግዥ ቅድሚያነት የሚደረገው የስምምነት መብት በነዚህ በሦስተኛ ወገኖች ወቃወሚያ
አይሆንባቸውም፡፡

ቊ 1424፡፡ (3) ስለ ተንቀሳቃሾች ንብረቶች፡፡


ለሽያጭ የተሰጠው የተስፋ ቃል ወይም በቀደምትነት ለመግዛት በውል የተሰጠው መብት የሚመለከተው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የሆነ
እንደሆነ በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሊሆንባቸው የሚችለው 3 ኛ ወገኖች የመብቶቹን መኖር ዐውቀው እንደሆነ፤ ወይም ማወቅ
የነበረባቸው እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1425፡፡ (4) መቃወሙ ስለሚያስከትለው ውጤት፡፡

(1) ለሽያጭ የተሰጠው የተስፋ ቃል ወይም በቀደምትነት ለመግዛት የተሰጠው መብት በሦስተኛ ወገን ላይ መቃወሚያ ሊሆንበት
በሚችልበት ጊዜ ይህ ሦስተኛው ወገን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለራሱ ገንዘብ ያደረገው፤ መብታቸውን ባለማክበር በመጣስ የሆነ
እንደሆነ፤ ባለጥቅም የሆነው ሰው መብቱ በተቋቋመበት ጽሑፍ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት የተባለውን ሦስተኛ ወገን የንብረቱን
ሀብትነት እንዲለቅለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) ለሽያጭ የተስፋ ቃል የተሰጠው ወይም በቀደምትነት ለመግዛት መብት የተሰጠው ባለጥቅም የሆነ ሰው ማናቸውም ተቃራኒ የሚሆን
የውል ቃል ቢኖርም እንኳ የንብረቱ ባለይዞታ የሆነው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እጅ ካደረገበት ቀን አንሥቶ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ
በመብቱ ካልሠራበት መብቱ ቀሪ ይሆናል፡፡

(3) ሦስተኛው ወገን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት በሸጠለት ሰው ላይ ክስ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ክፍል 2፡፡
ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይያዝ የማድረግ ስምምነት፡፡
ቊ 1426፡፡ ተንቀሳቃሽ የሆነውን ንብረት የሚመለከት ስምምነት፡፡
(1) ግዙፍ የሆነ ተንቀሳቃሽ ንብረት የሠራ ያወጣ የሸጠ ወይም የዚህ ንብረት ባለሀብት የሆነ ሰው ስለ ንብረቱ መሸጥ ወይም መያዝ ወሰን
አደርጋለሁ ሲል የሚገባባቸው የውል ስምምነቶች በግልጽ በተቀበሏቸው ሰዎች ዘንድ ካልሆነ በቀር ዋጋ የላቸውም፡፡

(2) እነዚህ የውል ስምምነቶች በሕግ ግልጽ ሆነው ካልተፈቀዱ በቀር በሦስተኛ ወገኖች ላይ አይጸኑባቸውም፡፡
ቊ 1427፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት የሆነ ሰው በሕግ በግልጽ ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውጭ የተባለውን ንብረት የማይሸጥ ወይም የማይያዝ
ነው ብሎ ለማስታወቅ አይችልም፡፡
ቊ 1428፡፡ ተንቀሳቃሽ ያልሆነውን ንብረት የሚሸጥ የሚያስተላልፍ ሰው መብት፡፡
(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ሀብትነትን ለሌላ ሰው የሚያስተላልፍ ሰው ንብረቱ የተላለፈለትን ሰው ንብረቱን እንዳይሸጥ፡- እንዳያስተላልፍ
ለመከልከል ወይም ንብረቱን ለመሸጥ ለማስተላለፍ ያለውን ሥልጣን ለመቀነስ ይችላል፡፡

(2) እንደዚሁም የተባለው ንብረት ከተላለፈለት ሰው እጅ ንብረቱ የማይያዝ ነው ብሎ ለመስማማት ይችላል፡፡


ቊ 1429፡፡ የውል ቃሎችን ስለ መተርጐም፡፡
(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር እንደተመለከተው እንዳይሸጥ እንዳይያዝ ተብሎ የሚደረገው ስምምነት በማናቸውም ሁኔታ ሁሉ በማጥበብ
መተርጐም አለባቸው፡፡

(2) እንደዚሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይተላለፍ የሚነገረው የውል ቃል የማይንቀሳቀሰውን መሬት የማይያዝ
አያደርገውም፡፡

(3) ደግሞ ንብረቱ እንዳይሸጥ እንዳይያዝ የተነገሩት ስምምነቶች ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ድንጋጌዎች በሰጧቸው ሁኔታዎችና በወሰኑዋቸው
ወሰኖች ካልሆነ በቀር ዋጋ የላቸውም፡፡
ቊ 1430፡፡ ስለ ውሉ ቃል ፎርም፡፡
አንድ ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ወይም እንዳይያዝ የሚነገሩት ስምምነቶች ፈራሽነትን እንዳያስከትሉ በጽሑፍ መደረግና
የማይንቀሳቀሰው ንብረት የማይሸጥ የማይለወጥ ሆኖ የሚቈይበትን ጊዜ መለየት አለባቸው፡፡
ቊ 1431፡፡ ከፍተኛ ጊዜ፡፡
(1) የማይንቀሳቀሰው ንብረት እንዳይሸጥ እንደይለወጥ ወይም እንዳይያዝ የሚደረገው ስምምነቱ ከኻያ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ወይም
ንብረቱን ሀብቱ ካደረገው ሰው ዕድሜ በላይ ሊሆን አይችልም፡፡

(2) ስምምነት ከኻያ ዓመት በላይ የሆነ እንደሆነ የውሉ ስምምነት ውጤት የሚያገኘው እስከ ኻያ ዓመት ብቻ ነው፡፡

(3) ጊዜው የሚቈጠርበት መነሻ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ሀብትነት ለአገኘው ሰው ከተላለለፈበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
ቊ 1432፡፡ በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ለመሆን ስላለመቻሉ፡፡
(1) የውሉ ስምምነት የሚመለከተው የማይንቀሳቀሰው ንብረት በርስት መዝገብ ላይ ተጽፎ እንደሆነ ይህ ስምምነት በመዝገብ ተጽፎ
ካልተገኘ በቀር ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ሊሆንባቸው አይችልም፡፡

(2) የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በሆኑ ጊዜ ስምምነቱ የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ ባለው ፍርድ ቤት መዝገብ ተጽፎ
ካልተገኘ በቀር ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ ሊሆንባቸው አይችልም፡፡

ቊ 1433፡፡ ስለ ዳኞች ሥልጣን፡፡ (1) ንብረቱ እንዳይያዝ የሚደረግ ስምምነት፡፡

ማናቸውም ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት ቢኖርም እንኳ የማይንቀሳቀሰው ንብረት እንዲያዝ ለመፍቀድ የሚችሉት፡-
(ሀ) ንብረቱ እንዲያዝለት የሚጠይቀው ገንዘብ ጠያቂ ለማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት፤ ወይም ይህ የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት
የሆነው ሰው የቀለብ መስጠት ግዴታ ላለበት ሰው ላቀረበው ምግብ ዋጋ እንዲከፈለው ሲሆን፤

(ለ) ዕዳው የመነጨው ባለሀብቱ ከሠራው ወንጀል ሲሆን ነው፡፡

ቊ 1434፡፡ (2) ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የሚደረግ ስምምነት፡፡

(1) ዳኞች እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የተባለው የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት የሆነ ሰው ጥቅም እንዲሸጥ እንዲለወጥ ውሳኔ የሚያሰጥ
መስሎ የታያቸው እንደሆነ የተባለውን ንብረት እንዲሸጥ እንዲለወጥ ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(2) ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች የተለየ ስምምነት በማድረግ የተባለውን ሥልጣን ሊያስቀሩባቸው ይችላሉ፡፡

(3) እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የተባለውን የውሉን ቃል በመጣስ የማይንቀሳቀሰው ንብረት እንዲሸጥ እንዲለወጥ ተብሎ የሚሰጠው ፈቃድ
የዚህን የንብረት ባለሀብትነት ያስተላለፈው (ያዛወረው) ሰው በሕይዋት ያለ እንደሆነ እና እርሱም ፈቃድን ለመግለጽ በሚችልበት ሁኔታ
የሚገኝ እንደሆነ ሊሰጥ አይቻልም፡፡

ቊ 1435፡፡ ንብረት እንዳይያዝ የሚደረግ ስምምነት የሚሰጠው ውጤት፡፡ (1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት፡፡

(1) እንዳይያዝ ስምምነት የተነገረበት የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት የሆነ ሰው የተባለው ንብረት ተይዞ በፍርድ እስከተሸጠ ድረስ
ንብረቱ እንዳይያዝ የተነገረ ስምምነት አለኝ ሲል ለማመልከት ይችላል፡፡

(2) በዚህ ስምምነት አልጠቀምም በማለት አስቀድሞ የተነገረው የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

(3) ባለሀብቱ ለገንዘብ ጠያቂው ይህ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚያዝ አለመሆኑን በሚገባው ጊዜ ሳያስታውቀው ቀርቶ እንደሆነ በዚህ
ንበረት መያዝ ምክንያት ለሚወጣው ኪሣራ ኀላፊ ይሆናል፡፡

ቊ 1436፡፡ (2) ሌሎች ሰዎች፡፡

(1) ንብረቱ እንዳይያዝ የተነገረውን ስምምነት የውሉን ቃል የተናገረው ሰው ወይም ይህን የውል ቃል እንዲያስከብር እርሱ የላከው ሰው
ሊያመለክት ይችላል፡፡

(2) የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት የሆነ ሰው ንብረቱ እንዳይያዝ በተነገረው ስምምነት ሊጠቀምበት ያልፈለገ እንደሆነ የንብረቱ
መያዝ የውሉን ቃል እንዲያስከብር ለተባለው ሰው ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) ንብረቱን ለሚያስይዝው ገንዘብ ጠያቂም ይህ ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 1437፡፡ (3) የውሉን ቃል የማስታወቂያ ጊዜ፡፡

(1) የንብረቱ መያዝ ተነግሮት በውሉ ቃል ለመጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ንብረቱ በሐራጅ ለሌላ ከመሸጡ በፊት በዚህ የውል ቃል
ለመጠቀም መፈለጉን ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) የዚህ የማይንቀሳቀሰው ንብረት መያዝ ያልተነገረው እንደሆነ ንብረቱ ለሌላ ሰው በሐራጅ ከተሰጠበት አንሥቶ እስከ ሁለት ዓመት
ድረስ በውሉ ቃል ለመጠቀም መፈለጉን ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) የተባለው ንብረት እንዳይያዝ የተነገረው ስምምነት እነዚህን ጊዜዎች ለማስረዘም አይችልም፡፡

ቊ 1438፡፡ (4) ንብረቱን በሐራጅ ከሚሸጠው ሰው ጋራ ስላሉት ግንኙነቶች፡፡

(1) በውሉ ቃል ለመጠቀም የሚፈልገው ማንም ሰው በዚሁ የውል ቃል የተወሰነውን ዋጋ በማስከፈል ወይም ዋጋው ያልተወሰነ እንደሆነ
በሐራጅ የተላለፈለት ሰው የከፈለውን ዋጋ በመክፈል ንብረቱ የተላለፈለት ሰው ንብረቱን እንዲያስተላልፍለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) በንብረቱ ላይ ስለተደረጉት ወጪዎች ወይም በሐራጅ ንብረቱ የተላለፈለት ሰው በንብረቱ ላይ ስላደረሰው ጉዳት በዚህ ሕግ ያለ
አገባብ ስለ መበልጸግ በተነገረው ምዕራፍ የተጻፉት ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 1439፡፡ (5) በሐራጅ ካገኘው ሰው ላይ ንብረቱን የራሱ ካደረገ ሰው ጋራ ስላለ ግንኙነት፡፡

(1) የማይንቀሳቀሰውን ንብረት በሐራጅ ያገኘ ሰው ንብረቱን ለሌላ የሸጠ ያስተላለፈ እንደሆነ በአካባቢ ነገሮች ይህን ለማወቁ ማስረጃ
ካልቀረበ በቀር ወይም ንብረቱን ያለ ዋጋ ያገኘ ካልሆነ በቀር ንብረቱን የራሱ ያደረገውን የኋለኛውን (አዲሱን) ሰው ለመጉዳት አይቻልም፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ በውሉ ለመጠቀም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ንብረቱ በሐራጅ በተላለፈበት ሰው ላይ ያለው መብት ንብረቱን
ገንዘብ ባደረገው በኋለኛው (በአዲሱ) ሰው ላይ ይኖረዋል፡፡

(3) እንዲህ ባልሆነ ጊዜ የውል ቃል ውጤት መስጠቱ ይቀራል፡፡

ቊ 1440፡፡ ንብረቱ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የሚነገር የውል ቃል የሚሰጣቸው ውጤቶች፡፡ (1) የውሉን ቃል ለመጥቀስ ማን
እንደሚችል፡፡
(1) አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የተነገረውን የውል ቃለ በመጣስ ይህን የተባለውን ንብረት የሸጠ ባለሀብት
ንብረቱን በገዛው ሰው ላይ በዚህ የውል ቃል ሊጠቀምበት አይችልም፡፡

(2) አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የተነገረውን የውል ቃል ለመጥቀስ የሚችለው በውሉ ቃል የተስማማው ወይም
ይህን የውሉን ቃል ለማስከበር እርሱ የላከው ሰው ብቻ ነው፡፡

ቊ 1441፡፡ (2) ጊዜ፡፡


አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ በተነገረው የውል ቃል ለመጠቀም ሲባል የሚቀርበው ጥያቄ ይህ ንብረት
ከተሸጠበት ከተለወጠበት ቀን አንሥቶ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥና የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ
የተወሰነው ጊዜ ከማለቁ በፊት ካልቀረበ ፈራሽ ይሆናል፡፡
ቊ 1442፡፡ ንብረቱን የራሱ ካደረገው ሰው ጋራ ስላሉት ግንኙነቶች፡፡
(1) የማይንቀሳቀሰው ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ የውል ስምምነት ያደረገና ወይም ይህን ውል ለማድረግ መብት ያለው ሰው
የማይንቀሳቀሰው ንብረት እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ እንዳይያዝ በተደረገው ስምምነት መሠረት በስምምነቱ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ በዚሁ
በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ ያላቸውን የመግዛት ተቀዳሚነት መብታቸውን ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

(2) ንብረቱን እንዲለቅ የተደረገው ሰው ንብረቱን ሸጦለት በነበረው ሰው ላይ በዋስነቱ የሚያቀርብበት አቤቱታ እንደተጠበቀ ነው፡፡
ቊ 1443፡፡ ስለ አደራ ንብረት አስተዳዳሪ፡፡
የአደራ ንብረት አስተዳዳሪን ስለሚመለከተው ጒዳይ በዚህ ሕግ፤ በሕግ የሰውነት መብት ስለ ተሰጣቸው ማኅበሮችና ለልዩ አገልግሎት
ስለተመደቡ ሀብቶች የተነገሩት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ፡፡
በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በኅብረት ስለ መጠቀም፡፡
ምዕራፍ አንድ፡፡
የመንግሥት ንብረት (የሕዝብ አገልግሎት ንብረት) እና
ንብረትን ስለ ማስለቀቅ፡፡
ክፍል 1፡፡
የሕዝብ አገልግሎት ንብረት፡፡
ቊ 1444፡፡ የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ሁኔታ፡፡
(1) የመንግሥት ንብረት ወይም የሰውነት መብት የተሰጣቸው የአድሚኒስትራሲዮን ክፍል ንብረቶች በጠቅላላው የባለግል ንብረት ለሆኑት
ሀብቶች በተደነገጉት ሕጎች የሚተዳደሩ ናቸው፡፡

(2) ስለሆነም እነዚህ ንብረቶች ለጠቅላላ አገልግሎት ጥቅም የተመደቡ በሆኑ ጊዜ በዚህ ክፍል ድንጋጌዎች የሚተዳደሩ ይሆናሉ፡፡

ቊ 1445፡፡ የሕዝብ አገልግሎት ንብረት (1) መሠረቱ ፡፡

የመንግሥት ንብረቶች ወይም የሰውነት መብት የተሰጣቸው የአስተዳደር ክፍል ድርጅት ንብረቶች የሆኑ ሀብቶች ተብለው የሚቈጠሩት፤
(ሀ) ሕዝብ እንዲጠቀምባቸው ወይም በቀጥታ እንዲገለገልባቸው የተመደቡ ሲሆኑ፤

(ለ) ለአንድ የሕዝብ ጥቅም ለሚሆን የሥራ አገልግሎት ለተመደቡ ሲሆኑና በዐይነታቸው ወይም በልዩ ልዩ አሠራሮች ለዚሁ የአገልግሎት
ድርጅት ብቻ ወይም ለዚሁ ሥራ ይበልጥ እንዲያገለግሉ የተመደቡ ሲሆኙ ነው፡፡

ቊ 1446፡፡ (2) የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡

የመንግሥት ወይም የአስተዳደር ክፍል ድርጅት ንብረቶች የሆኑት የሕዝብ አገልግሎት ንብረቶች፡፡
(ሀ) ጎዳናዎችና መንገዶች የውሃ ቦዮችና የምድር ባቡሮች፤

(ለ) የባሕር ዳርቻዎች፤ በወደቡ ላይ የተቋቋሙ ነገሮችና የወደብ መብራቶች፡፡

(ሐ) በተለይ ለሕዝብ አገልግሎት የተቋቋሙ ሕንጻዎች እንደ ምሽግና እንደ ቤተ ክርስቲያን ያሉ ነገሮች ሁሉ፤ የሕዝብ አገልግሎት ንብረቶች
ናቸው፡፡

ቊ 1447፡፡ (3) ውሃዎች፡፡

(1) እንደዚሁም ወራጅ ውሃዎች ሐይቆችና በመሬት ውስጥ የሚገኙ የውሃ ንጣፎች በተለይ የሕዝብ አገልግሎት ንብረት ተብለው
ይቈጠራሉ፡፡

(2) የውሃዎችን ባለሀብትነትና አገልግሎት በሚመለከተው ጒዳይ ከዚህ በፊት የተጻፉት የዚህ ሕግ ውሳኔዎች ይፈጸማሉ፡፡

ቊ 1448፡፡ (4) ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፡፡

ከዚህም በቀር አቀማመጣቸው ወይም የተመደቡት ለሕዝብ አገልግሎት የሆኑና ለሕዝብ ትርእይት የተቀመጡ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች
የሕዝብ አገልግሎት ንብረቶች ሆነው ይቈጠራሉ፡፡

ቊ 1449፡፡ ለሕዝብ አገልግሎት ንብረት ወሰን ስለ መስጠት፡፡


(1) የአስተዳደር ክፍል ባለሥልጣኖች የወራጅ ውሃዎችንና የባሕር ጠረፎችን የተፈጥሮ ወሰን ክልል ይመድባሉ፡፡

(2) የአስተዳደር ክፍል የሰጠው ውሳኔ ያለ አገባብ መሆኑን ዳኞች የገመቱ እንደሆነ በነዚህ ውሳኔዎች የተጎዱት የግል ባለሀብቶች
ስለንብረት ማስለቀቅ በተደነገጉት ሕጎች መሠረት የጉዳት ኪሣራ እንዲያገኙ ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(3) በእንደዚህ ያለው ጒዳይ የአስተዳደር ክፍል የሰጠውን ውሳኔ ዳኞች ሊሽሩት አይችሉም፡፡

ቊ 1450፡፡ ንብረትን ስለ ማስለቀቅና መሥመር ስለ ማግባት፡፡

(1) የአስተዳደር ክፍል ባለሥልጣኖች ለሕዝብ አገልግሎት ንብረት ለማስለቀቅ በተሰጠው ሥርዐት መሠረት ለአውራ ጐዳናዎችና
ለመንገዶች አስፈላጊ የሆኑትን መሬቶች ከባለግሎች ላይ ለመውሰድ ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም መሥመር ስለ ማግባት በተደነገገው ሥርዐት መሠረት የሕዝብ ጐዳናዎችንና መንገዶችን ለማስፋትና ለማስተካከል
ይችላሉ፡፡

ቊ 1451፡፡ መሥመር ስለ ማግባት፡፡ (1) ሕንጻ ያልተሠራባቸው መሬቶች፡፡


በከተማው ፕላን አቀያየስ መሠረት በሕዝብ ጎዳናዎች ክልል ውስጥ የሚገኙት መሬቶች ሕንጻ ያልተሠራባቸው የሆኑ እንደሆነ ወዲያውኑ
በዚሁ በመንገድ ክልል ውስጥ ገብተው ይመደባሉ፡፡

ቊ 1452፡፡ (2) ሕንጻ የተሠራባቸው መሬቶች፡፡

(1) በከተማው ቅያስ መሠረት ለሕዝብ ጎዳና በተከለለ መሬት ላይ የሚገኙ ሕንጻዎች የማፈግፈግ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

(2) የነዚህ ሕንጻዎች ባለሀብት የነዚህን ሕንጻዎች ጥንካሬ የሚያሳድግ ወይም የሚቈዩበትን ጊዜ የሚያራዝም ሥራ ለመሥራት አይችልም፡፡

ቊ 1453፡፡ (3) ስለ ኪሣራ፡፡

የንብረቶቹ ባለቤቶች ወይም ሌላ ባለመብቶች ሀብታቸው በከተማው ቅያስ ፕላን መሠረት ስለ መወሰዱ ወይም ለዚህ ዐይነት አገልግሎት
በመመደቡ ለሚደርስባቸው ጉዳት የሚጠይቁት ኪሣራ የሚወሰነው በዚሁ አንቀጽ ለሕዝብ አገልግሎት ጥቅም ስለሚለቀቁ ሀብቶች ኪሣራ
አከፋፈል ጒዳይ በተደነገገው ሕግ መሠረት ነው፡፡

ቊ 1454፡፡ ለሕዝብ አገልግሎት የተመደቡ ሀብቶች የማይሸጡ የማይተላለፉ ስለ መሆናቸው፡፡

ለሕዝብ አገልግሎት የተመደቡ ሀብቶች ከዚሁ አገልግሎት ውጭ መሆናቸው ወይም ለዚሁ ጒዳይ መመደባቸው መቅረቱ በሚገባ
ካልተወሰነ በቀር ሊሸጡ ሊተላለፉ አይቻልም፡፡
ቊ 1455፡፡ በቅን ልቡና የተደረገ ይዞታና በንብረቱ በመጠቀም ስለሚገኙ ሀብቶች፡፡

በቅን ልቡና በሆነ ይዞታ ወይም በንብረቱ በመጠቀም ለሕዝብ አገልግሎት በተመደበው ንብረት ባለሀብት ለመሆን አይቻልም፡፡

ቊ 1456፡፡ ስለ ኪራይ፡፡

ውሎቹ ለሕዝብ አገልግሎት የተመደበውን ንብረት ለአገልግሎቱ እንዳይውል ለማድረግ ሲባል ካልተደረጉ በቀር ንብረቶቹን በኮንሴሲዮን
ለግል ሰዎች ለመስጠት ይቻላል፡፡

ቊ 1457፡፡ ለሕዝብ አገልግሎት በተመደበው ሀብት የመጠቀም ፈቃድ፡፡

(1) የአስተዳደር ክፍል ካልፈቀደ በቀር አንድ ሰው ለራሱ ጥቅም ለሕዝብ አገልግሎት ከተመደበው ንብረት አንዱን ክፍል በባለግልነት
ለመያዝ አይችልም፡፡

(2) ይህም የአስተዳደር ክፍል የሚሰጠው ፈቃድ የተፈቀደለት ባለጥቅም በዚህ በቦታ ላይ አንድ ሥራ ማቋቋም የሚችል መሆኑንና
የሚቋቋመውን ሥራ ዐይነት ለይቶ ይገልጻል፡፡

(3) ከዚህም በቀር ይህ ፈቃድ ለምን ያህል ጊዜ እንደተሰጠና ተጠቃሚውም ምን ያህል ዋጋ እንደሚከፍል ለይቶ ይገልጻል፡፡
ቊ 1458፡፡ ግዴታን ስላለመፈጸም፡፡
ፈቃድ የተሰጠው ሰው የገባባቸውን ግዴታዎች ያልፈጸመ እንደሆነ ያስተዳደር ክፍል የሰጠውን ኮንሴሲዮን ወይም በሕዝብ አገልግሎት
ንብረት ላይ የሰጠውን ፈቃድ ሊሰርዘው ወይም ሊሽረው ይችላል፡፡
ቊ 1459፡፡ የአስተዳደር ክፍል ስላለው የመሻር መብት፡፡
(1) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ቢኖርም እንኳ ለሕዝብ አገልግሎት የተመደበውን ንብረት አጠባበቅን የሚጎዳ ወይም የንብረቱን አገልግሎት
ግብ የሚቃወመውን ማናቸውንም ሥራ እንዲፈርስ ወይም ማናቸውም አሠራር እንዲቀር የአስተዳደሩ ክፍል በማናቸውም ጊዜ ለማዘዝ
ይችላል፡፡

(2) በዚሁ አኳኋን የአስተዳደሩ ክፍል የተስማማባቸውን ኮንሴሲዮኖች ወይም በሕዝብ አገልግሎት ንብረት ላይ የሰጣቸውን ፈቃዶች
ለመሻር ይችላል፡፡

(3) በዚህ ሕግ ስለ አስተዳደር ድርጅት ውሎች በተባለው አንቀጽ ላይ በተነገረው ሕግ መሠረት ባለኮንሴሲዮኑ ወይም ባለይዞታው
ያላቸው የኪሣራ መጠየቅ መብት እንደተጠበቀ ነው፡፡
ክፍል 2፡፡
ለሕዝብ አገልግሎት የሚጠቅሙትን ሀብቶች ስለ ማስለቀቅ፡፡
ቊ 1460፡፡ ትርጓሜ፡፡
ንብረት ማስለቀቅ ማለት የአስተዳደር ክፍል ለሕዝብ ጥቅም አገልግሎት የሚያስፈልገውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት ይህንኑ ንብረት
እንዲለቅ የሚያስገድድበት ሥርዐት ነው፡፡
ቊ 1461፡፡ ይህ ሥነ ሥርዐት በሥራ ላይ የሚውልበት ሁኔታ፡፡
(1) የንብረት ማስለቀቁ ሥነ ሥርዐት በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን የንብረት አገልግሎት ወይም የሪም ወይም ሌላ ግዙፍ መብት
ለማግኘት ወይም ለማስቀረት ተብሎ ሊሠራበት ይቻላል፡፡

(2) እንዲሁም የአስተዳደሩ ክፍል በወሰደው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የነበረው የኪራይ ውል ዘመኑ ከመፈጸሙ በፊት እንዲቋረጥ
በማድረግ የንብረት ማስለቀቁ ሥነ ሥርዐት ሊሠራበት ይቻላል፡፡
ቊ 1462፡፡ ባለኮንሴሲዮን፡፡
የሕዝብ አገልግሎት ሥራ በኮንሴሲዮን የተሰጠው ሰውና አድሚኒስትራሲዮን ኮንሴሲዮን የሰጣቸውን ሌሎች ሰዎች በኮንሴሲዮኑ ውል
ውስጥ መብት የተሰጣቸው ካልሆኑ በቀር የንብረት ማስለቀቅ መብት ሊኖራቸው አይችልም፡፡
ቊ 1463፡፡ ለሕዝብ አገልግሎት ጠቃሚ ስለመሆኑ የሚደረግ መግለጫ፡፡
አንድ ሀብት እንዲለቀቅ የታቀደ ሲሆን ሀብቱ ከመወሰዱ በፊት ተገቢ የሆኑት ባለሥልጣኖች አስቀድሞ ይህ ሀብት ለሕዝብ አገልግሎት
ጠቃሚ መሆኑን መወሰንና በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በቊጥር #4 በተደነገገው መሠረት ግልጽ ሁኖ እንዲወጣ መደረግ አለበት፡፡
ቊ 1464፡፡ ለሕዝብ አገልግሎት ጥቅም የሚሆን ሀብት፡፡
(1) የንብረት ማስለቀቅ ግቡ ገንዘብ ለማግኘት ብቻ የሆነ እንደሆነ ንብረትን ለማስለቀቅ አይቻልም፡፡

(2) ስለሆነም ለሕዝብ አገልግሎት በተሠሩት ሥራዎች ምክንያት መሬቶቹ ያገኙትን የዋጋ ብልጫ ለኅብረት ጥቅም እንዲሆን ለማድረግ
ከሆነ ንብረቱን ለማስለቀቅ የሚቻል ይሆናል፡፡
ቊ 1465፡፡ ምርመራ፡፡
(1) አንድ ንብረት ለሕዝብ አገልግሎት ይጠቅማል መባሉ ከመገለጹ በፊት ምርመራ ማድረግ በቂ ምክንያት ያለበት መስሎ ሲታይ
ምርመራው በግልጽ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

(2) ይህ የጥናት መርመራ በሚደረግበት ጊዜ ባለጒዳዮች የሆኑት ሰዎች ሁሉ በታቀደው ሥራ ላይ ያላቸውን ነቀፌታና አስተያየት ለማቅረብ
ይችላሉ፡፡
(3) ባለጒዳይ የሆነው የአስተዳደር ክፍል የምርመራውን አሠራርና ጊዜ በደንቦቹ መሠረት ይወስናል፡፡
ቊ 1465፡፡ የማስለቀቅ ትእዛዝ፡፡
(1) አንድ ዐቅድ ለሕዝብ አገልግሎት ጥቅም አስፈላጊ ነው ተብሎ በተወሰነ ጊዜ አግባብ ያላቸው ባለሥልጣኖች ይህንኑ ዐቅድ ለመፈጸም
እንዲለቀቁ ያስፈልጋል የተባሉትን የግል ሰዎች ሕንጻዎች ያመለክታሉ፡፡

(2) የነዚህ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ባለሀብቶች ሌጣ ባለርስቶችና ባለሪሞች የታቀደውን የኅብረት መልቀቅ ለያንዳንዳቸው በሚላክላቸው
ማስታወቂያ ይገለጽላቸዋል፡፡

(3) እንዲሁም የአስተዳደሩ ክፍል በአእምሮ በቂ ነው ብሎ በወሰነው ጊዜ ውስጥ ንብረታቸውን በሚለቁበት ጒዳይ ላይ ያላቸውን
አስተያየት እንዲያቀርቡ ጥያቄ ይደረግላቸዋል፡፡
ቊ 1467፡፡ የንብረት ማስለቀቅ ትእዛዝ፡፡
(1) የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች እንዲለቀቁ የሚደረገው በንብረት ማስለቀቂያ ትእዛዝ ነው፡፡

(2) ይህም የንብረት ማስለቂያ ትእዛዝ የሚለቀቀውን ንብረት ከማንኛውም መብት ነጻ አድርጎ ለአስተዳደሩ ክፍል እንዲተላለፍ የሚያደርግ
ነው፡፡
(3) ሦስተኛ ወገን የሆኑ ሰዎች ከአስተዳደሩ ክፍል ጋራ በቀጥታ ያሏቸው መብቶችና እንዲሁም የአስተዳደሩ ክፍል ንብረቱን እንዲለቅ
ለተደረገው ባለሀብት በሚከፍለው የኪሣራ ገንዘብ ያሏቸው መብቶች የተጠበቁ ናቸው፡፡
ቊ 1468፡፡ ትእዛዙን ስለ ማስታወቅ፡፡
(1) ንብረት የማስለቀቁ ትእዛዝ የተለቀቀው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለ ሀብት ለሆነው ሰውና በዚሁ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያላቸውን
መብቶች በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መዝገብ ላስመዘገቡት ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡

(2) እንዲሁም ባለሀብቱ በዚሁ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብት አላቸው ብሎ ለአስተዳደር ክፍል ላመለከተው ሰዎች ሁሉ ትእዛዙ
ይነገራቸዋል፡፡
ቊ 1469፡፡ አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በከፊል እንዲለቀቅ ስለ ማድረግ፡፡
(1) አንድ ሕንጻ በከፊል እንዲለቀቅ የተደረገ እንደሆነ ባለሀብቱ ይህን ሕንጻ በሙሉ አድሚኒስትራሲዮኑ እንዲወስደው ለማስገደድ
ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም አንድ መሬት በከፊል እንዲለቀቅ ሲደረግ ቀሪው የማይጠቅም የሆነ እንደሆነ የመሬቱ ባለሀብት አድሚኒስትራሲዮኑ በሙሉ
እንዲወሰድ ለማስገደድ ይችላል፡፡

(3) ከዚህ በላይ የተባሉት መብቶች እንዲለቀቅ በተደረገው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ካላቸው መብቶች ሌላ፤ ባለርስቱና የአላባ ጥቅም
ተቀባዩ ከዚህ በላይ ባሉት ኀይለ ቃሎች የተጻፉት መብቶች ይኖራቸዋል፡፡
ቊ 1470፡፡ የኪሣራ ግምት አወሳሰን፡፡
ለሕዝብ ጥቅም አገልግሎት የማይንቀሳቀስ ንብረት የተወሰደሳቸው ባለ ሀብቶች ወይም ሌጣ ባለርስቶች ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባዮችና
በዚሁ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የንብረት አገልግሎት ያላቸው ሰዎች የንብረቱን ማስለቀቂያ ትእዛዝ እንዲያውቁት ከተነገራቸው ቀን
አንሥቶ በሚከተለው ወር ውስጥ የሚጠይቁትን ኪሣራ ልክ ለአስተዳደር ክፍል ማስታወቅ አለባቸው፡፡
ቊ 1471፡፡ ግምቱ እንዳይከፈል ስለ መቃወም፡፡
ባለጒዳዮች የሆኑ ሌሎችም ሰዎች በተባለው ጊዜ ውስጥ ከአስተዳደሩ ክፍል የሚከፈለው የኪሣራ ዋጋ ከአንድ ከተወሰነ ዋጋ በታች
እንዳይሆን ወይም መብታቸውን በመጉዳት የኪሣራው ገንዘብ እንዳይከፈል ላስተዳደር ክፍል ለማስታወቅ ይችላሉ፡፡
ቊ 1472፡፡ በመብቱ አገማመት ላይ ስለሚነሣ ክርክር፡፡
ባለጒዳዩ የጠየቀውን ዋጋ የአስተዳደሩ ክፍል አልቀበልም ያለ እንደሆነ የመብቱን አገማመት ክርክር የሚወስነው የግምት የሽምግልና
ኮሚሲዮን ነው፡፡
ቊ 1473፡፡ የመገመት የሽምግልና ኮሚሲዮን፡፡
(1) የአገማመቱ የሽምግልና ኮሚሲዮን በተሰጡት ደንቦች መሠረት የሚቋቋም የሚሠራና የሚወሰን ይሆናል፡፡

(2) የኮሚሲዮኑ ሥራ የአስተዳደሩ ክፍል መክፈል ያለበትን የግምት ልክ መገመት ብቻ ነው፡፡

(3) ክርክር በተነሣባቸው መብቶች ሥረ ነገር ላይ ውሳኔ መስጠት አይችልም፡፡

ቊ 1474፡፡ የንብረቱ አገማመት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ስለ መሬት ማስለቀቅ የሚከፈለው ትክክል የሆነ ግምት ወይም መሰል ምትኩ መሬቱን ከማስለቀቁ የተነሣ በደረሰውና በተረጋገጠው
ጉዳት ልክ ይሆናል፡፡

(2) ይህ ትክክል የሆነ ግምቱ ወይም መሰል ምትኩ የሚገመተው የአገማመት የሽምግልና ኮሚሲዮን በገመተበት ቀን ባለው ዋጋ መሠረት
ነው፡፡
ቊ 1475፡፡ በግምት ውስጥ የሚገቡት ነገሮች፡፡
(1) ኮሚሲዮኑ በሚያደርገው ግምት ውስጥ ባለጒዳዮቹን በማስለቀቅ የአስተዳደር ክፍል ስለሚወስዳቸው ንብረቶች ወይም መብቶች
በሚመለከት ጒዳይ ባለጒዳዮች ከዚያ በፊት ለአስተዳደር ክፍል ያቀረቡዋቸውን መግለጫዎች በግምት ውስጥ ያገባል፡፡
(2) ከዚህም በቀር ለሕዝብ አገልግሎት በተሠሩት ሥራዎች ምክንያት እንዲለቀቅ ያልተደረገው የመሬቱ ክፍል ያገኘውን የዋጋ ብልጫ
እንዲሁም ኮሚሲዮኑ በግምት ውስጥ ያገባለ፡፡

ቊ 1476፡፡ (3) በግምት ውስጥ የማይገቡ ነገሮች፡፡

(1) የበለጠ ግምት ለማግኘት ሲባል በሚለቀቀው ንብረት ላይ የንብረት ማስለቀቂያ ትእዛዝ ከደረሰው በኋላ የተሠሩትን ሥራዎች ወይም
ማሻሻያዎች ኮሚሲዮኑ በግምት ውስጥ አያገባቸውም፡፡

(2) እንዲሁም የሕዝብ አገልግሎት ሥራዎች ሊፈጸሙ ነው በመባሉ ምክንያት የሚደርሰውን የዋጋ መነሣሣት በግምት ውስጥ አያገባም፡፡
ቊ 1477፡፡ ለዳኞች የሚቀርብ አቤቱታ፡፡
(1) የግምት ክፍል የሽምግልና የአገማመት ኮሚሲዮን በሰጣቸው ውሳኔዎች ላይ ለዳኞች አቤቱታ ለማቅረብ ይቻላል፡፡

(2) ይህም አቤቱታ የግምቱ ኮሚሲዮን ስለ ግምቱ ያደረገውን የመጨረሻ ውሳኔ ለባለጥቅሞቹ ካስታወቀበት ቀን አንሥቶ እስከ ሦስት ወር
ድረስ መቅረብ አለበት፡፡
ቊ 1478፡፡ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እጅ ስለማድረግ፡፡
(1) የአስተዳደር ክፍል የሚያስለቅቀውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል እጅ ለማድረግ አይችልም፡፡

(2) የግምት የሽምግልና ኮሚሲዮን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ዋጋ ከወሰነ በኋላ ግምት አነሰኝ ወደ ዳኛ እሄዳለሁ ብሎ የሚከራከረው ባለ
ሀብቱ የሆነ እንደሆነ የአስተዳደር ክፍል ወዲያው ዋጋውን ከፍሎ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እጅ ያደርጋል፡፡

(3) ስለተወሰደው መሬት የሚሰጠው ምትክ መሬት የሆነ እንደሆነ ኮሚሲዮኑ እንደወሰነ ወዲያውኑ ለተወሰደበት ሰው ይሰጠዋል ዳኞችም
የተሰጠው መሬት አይበቃም ብለው ቢወስኑ ትርፉን ገንዘብ የአስተዳደር ክፍል ይከፍለዋል፡፡

(4) ለሚወሰደው መሬት ዋጋውን የግምት የሽምግልና ኮሚሲዮን ከወሰነ በኋላ ግምት በዛብኝ ወደ ዳኛ እሄዳለሁ ብሎ የሚከራከረው
የአስተዳደሩ ክፍል የሆነ እንደሆነ ዳኞች ፍርዳቸውን እስኪሰጡ ባለመሬቱን መሬቱን ማስለቀቅ አትችልም፡፡ ክሱ ለዳኞች ከቀረበበት ቀን
አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት ዳኞቹ የሚከፍለውን ግምት ሳይወስኑ የቀሩ እንደሆነ የንብረት ማስለቀቂያው ትእዛዝ ቀሪ ሆኖ የባለርስቱ
መሬት እንደነበረ ይሆናል፡፡

(5) ለማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚከፈለው ገንዘብ ላይ ክርክር የተነሣበት ወይም አንድ ባለ ጥቅም የሆነ አይከፈል ብሎ የተቃወመ
እንደሆነ ክርክር የተነሣበትን ገንዘብ አስይዞ የአስተዳደር ክፍል የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እጅ ማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 1479፡፡ ዳኞች የሚያደርጉት የዋጋ ተጨማሪ፡፡
(1) በቊጥር 1478 በን ቊ 2 በተመለከተው መሠረት መሬት ለተወሰደበት ሰው የሚከፍለውን ገንዘብ ዳኞች የጨመሩለት እንደሆነ የዳኞቹ
ውሳኔ መጨረሻ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የአስተዳደሩ ክፍል የተጨመረውን ገንዘብ መክፈል አለበት፡፡

(2) የመሬቱ ምትክ ለተሰጠውም ሰው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፈለው ቢወሰን በዚሁ ዐይነት መፈጸም አለበት፡፡
ቊ 1480፡፡ በገደብ የሚደረግ የንብረት ማስለቀቅ፡፡
(1) የአስተዳደር ክፍል ያቀዳቸው ልዩ ልዩ ዐቅዶች የሚጠይቁትን የገንዘብ ወጪ ለማወቅ ሲል ለባለጒዳዮቹ መብታቸውን በውለታ
ሊያስለቅቃቸው መፈለጉን ሊያስታውቃቸው ይችላል፡፡

(2) እንደዚህም በሆነ ጊዜ ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች የተመለከተው የኪሣራ አገማመት ሥነ ሥርዐት ንብረቱ እንዲለቀቅ የሚያደርገው
ትእዛዝ ከመውጣቱ በፊት ተጀምሮ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ቊ 1481፡፡ ስለ አላፊነት፡፡ (1) ንብረት የማስለቀቅ ነገር ይደረጋል ስለማለት፡፡


ንብረት የማስለቀቅ ነገር ይደረጋል በመባሉ ብቻ ለሚደርስበት ጉዳት አንድ ሰው ከአስተዳደር ክፍል ኪሣራ መጠየቅ አይችልም፡፡
ቊ 1482፡፡(2) የኪሣራው አገማመት፡፡
(1) የአስተዳደሩ ክፍል የተቃወመው የአገማመቱ ኪሣራ ተገቢ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ የአገማመቱን ኪሣራ የሚችለው ይህ የአስተዳደሩ
ክፍል ነው፡፡

(2) ለመቃወሚያ የቀረበው ጥያቄ ያለ አገባብ ሆኖ በተገኘው መጠን ግን የአገማመቱን ኪሣራ የሚችለው ጥያቄ የአቀረበው ሰው ነው፡፡

ቊ 1483፡፡ የታሰበውን ዐቅድ ስለ መተው (1) መሠረቱ፡፡


ይሠራሉ ተብለው ለንብረት ማስለቀቂያ የሆኑት ሥራዎች ሳይፈጸሙ የቀሩ እንደሆነ የቀድሞዎቹ ባለሀብቶች የቀድሞ ሀብታቸውን መልሶ
ለመግዛት የቀዳሚነት መብት ይኖራቸዋል፡፡
ቊ 1484፡፡ የቀዳሚነት መብት፡፡
(1) ከዚህ በላይ የተጻፈው ቊጥር ውስጥ የተነገረው የቀዳሚነት መብት በመዝገብ ተራ ቊጥር የያዘ ወይም የተመዘገበ ባይሆንም እንኳ
ንብረቱን የአስተዳደሩ ክፍል መልሶ ከሸጠበት ወይም ከሥራው አፈጻጸም ጋራ የማይስማማ መብት በዚህ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ
ለሌላ ሦስተኛ ወገን ከሰጠበት ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ በሦስተኛ ሰዎች ላይ መቃወሚያ ሊሆን ይችላል፡፡

(2) ከዚህ በቀር የዚህ የተባለው መብት የሚሠራበት ሁኔታና የሚያስከትለው ውጤት በዚህ ሕግ በአንቀጽ 5 ስለ ጋራ ሀብት፤ ስለ አላባ
ጥቅምና ስለ ሌሎች ግዙፍ መብቶች በተጻፈው ሕግ ውስጥ በተነገረው መሠረት ተወስኗል፡፡

(3) የቀዳሚነት መብት ያለው ሰው በዚሁ በመብቱ መሠረት የቀድሞ ንብረቱን የሚገዛው ቀድሞ ንብረቱን በማስለቀቅ በተወሰደበት ጊዜ
ከአስተዳደር ክፍል በተቀበለው ዋጋ ልክ ነው፡፡

ቊ 1485፡፡ ቀጥተኛ ያልሆነ የንብረት ማስለቀቅ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


የአስተዳደር ክፍል በባለግል ባለቤቶች ንብረት ላይ የሚፈጽመው ሥራ በሀብቱ ጥቅም አሰጣጥ ላይ ከፍ ያለ መሰናክል የማያደርስበት
ከሆነና የንብረቱንም ጥቅም ከፍ ባለ አኳኋን የሚቀንስ ካልሆነ በቀር የንብረት ማስለቀቅ ሥነ ሥርዐትን ሳይከተል በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች
ላይ አንዳንድ ሥራዎች ለመፈጸም ወይም ቀዋሚ የሆኑ ድርጅቶች ለማቋቋም ይችላል፡፡

ቊ 1486፡፡ (2) አፈጻጸም፡፡


ቀጥተኛ ባልሆነ የንብረት ማስለቀቅ በተለይ ሊፈጸሙ የሚችሉም ሥራዎች፡፡
(ሀ) ተቋቁመው የሚቈዩበት ጊዜ ከአንድ ወር በታች የሆነና የማይንቀሳቀሰውን ሀብት ደንበኛ ፍሬ አሰጣጥ የማያሰናክሉ ሥራዎች ሁሉ፡-

(ለ) በመሬት ውስጥ ለውስጥ የሚያልፉ የውሃ መሥመሮች በአየር ላይ የሚያልፉ መሥመሮች የስልክ ወይም የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች
ናቸው፡፡
ቊ 1487፡፡ (3) የተጠበቀ መብት፡፡
ቀጥተኛ ያልሆነ የንብረት ማስለቀቅ አሠራር በመኖሪያ ቤቶች መብቶች ላይ ማናቸውንም የመብት መንካት የሚያደርስ ሊሆን አይገባም፡፡
ቊ 1488፡፡ (4) ኪሣራ፡፡

(1) የግል ባለንብረቶች ከዚህ በላይ በተነገረው ቊጥር በተሠራው ሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በደረሰባቸው ጉዳት መጠን
ብቻ ኪሣራ ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

(2) በኪሣራ አከፋፈሉ ረገድ ከአስተዳደር ክፍል ጎራ በሰላማዊ መንገድ ለመስማማት ያልተቻለ ሲሆን፤ በንብረታቸው ላይ ሥራዎቹ
ከተፈጸሙበት ቀን አንሥቶ በሚቈጠር በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለ ኪሣራቸው አከፋፈል ጒዳይ አቤቱታቸውን ካላቀረቡ ጥያቄያቸው
ተቀባይነት አያገኝም፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
የኅብረት ስለሆኑ የእርሻ መሬቶች፡፡
ቊ 1489፡፡ መሠረቱ፡፡
ሀብትነታቸው የኅብረት የሆኑ (የደሽ) እንደ የጐሣ ወይም የመንደር የሆኑ መሬቶች በኅብረት በመሠራታቸው የኅብረቱን ባህልና ልማድ
የተከተሉ መስሎ በታየ ጊዜ በኅብረት የሚሠሩ ይሆናሉ፡፡
ቊ 1490፡፡ ልማዶችን በጽሑፍ ስለ ማድረግ፡፡
ለእነዚህ ኅብረቶች ለያንዳንዱ እንደ የልማዶቻቸውና አስፈላጊም ሲሆን ልማዶቻቸውን የሚያሟላ በጽሑፍ የሆነ የመተዳደሪያ ደንብ
እንዲያገኙ ለማድረግ ያገር ግዛት ሚኒስቴር ያስብበታል፡፡
ቊ 1491፡፡ በመተዳደሪያው ጽሑፍ ላይ ስለሚጻፈው ቃል፡፡
የኅብረት መተዳደሪያው ደንብ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ጒዳዮች በተለይ መግለጽ አለበት፡፡
(ሀ) በኅብረቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ወይም ቤተ ዘመዶች፤

(ለ) የኅብረቱ መብት የሚዘረጋባቸው መሬቶች፤

(ሐ) ኅብረቱ የሚተዳደርበትን አኳኋንና ለኅብረቱም ወኪል ለመሆን ሥልጣን ያላቸውን ክፍሎች፤

(መ) የኅብረቱ መሬቶች ወይም ሌሎች ሀብቶች በምን አኳኋን እንደሚሠሩና እንደ ተከፋፈሉ፤

(ሠ) የኅብረቱ መተዳደሪያ ደንብ በመሻሻል የሚለዋወጥበትን አኳኋን፤


ቊ 1492፡፡ ልዩነት ማድረግ ክልክል ስለ መሆኑ፡፡
በኅብረቱ አባሎች መካከል በዘራቸው፤ በሃይማኖታቸው ወይም በማኅበራዊ ኑሮ ደረጃቸው ልዩነትን የሚያቋቁም ውሳኔ ወይም ልማድ
ሁሉ ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 1493፡፡ የኅብረቱ መሬቶች የማይሸጡ የማይተላለፉ ስለ መሆናቸው፡፡
(1) በባለይዞታነት ምክንያት የኅብረቱ የሆኑትን መሬቶች ሀብትነት ለማግኘት አይቻልም፡፡

(2) ማንኛውም ተቃራኒ ልማድ ቢኖር እንኳ የአገር ግዛት ሚኒስቴርን ካላስፈቀደ በቀር ኅብረቱ መሬቶቹን ለመሸጥ፤ ለማስተላለፍ፤
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ለማቋቋም ወይም በወለድ አግድ ለመስጠት አይችልም፡፡
ቊ 1494፡፡ የኅብረቱ ግዴታዎችና እንደራሴነት፡፡
(1) ኅብረቱ በድርጅቶቹ አማካይነት ውሎቹን ለመዋዋል ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም በዚሁ ዐይነት በፍርድ ቤት ለመክሰስ ወይም ለመከሰስ ይችላል፡፡

(3) ከውል ውጭ ስለሚደርሱ አላፊነቶችና ያላገባብ ስለ መበልጸግ የተመለከቱት የዚህ ሕግ ውሳኔዎች በሌሎቹ ማኅበሮች ላይ
ተፈጻሚዎች እንደሚሆኑ ሁሉ በእርሻ ኅብረቶችም ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 1495፡፡ የገንዘብ ጠያቂዎች መብት፡፡
(1) ከእርሻ ኅብረቱ ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች ለኅብረቱ መሬት የእርሻ ሥራ ወይም ለኅብረቱ አባሎች መተዳደሪያ ፍጹም
አስፈላጊ ያልሆኑትን የኅብረቱን የሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ለማስያዝ ይችላሉ፡፡

(2) የአገር ግዛት ሚኒስቴር ካልፈቀደ በቀር ሌሎቹን ንብረቶች፤ ለማስያዝ አይችሉም፡፡

(3) ከኅብረቱ አባሎች ላይ የገንዘብ መጠየቅ መብት ያላቸው ሰዎች በኅብረቱ ንብረት ላይ አንዳችም መብት የላቸውም፡፡

ቊ 1496፡፡ የመሬቶች ማልማት ሥራ፤ (1) መሠረቱ፡፡

የእርሻ ኅብረት መሬቶች የሚለሙበት አሠራር ሁኔታ በኅብረቱ መተዳደሪያ ደንብ (ቻርት) ይህም ባይኖር በልማድ መሠረት ይወሰናል፡፡
ቊ 1497፡፡ አፈጻጸም፡፡
(1) የኅብረቱ ሀብት የሆኑት መሬቶች ለአባሎቹ በድርሻ የሚደለደሉ ወይም በኅብረት ሥራ የሚውሉ መሆናቸው የሚወሰነው በልማድ
ነው፡፡
(2) በዚህም ውሳኔ መሠረት የኅብረቱና የኅብረቱ አባሎች በእነዚህ መሬቶች ላይ ያሉባቸው ግዴታዎችና ያሉዋቸው መብቶች ምን
እንደሆኑ በልማድ ይወሰናሉ፡፡

(3) እንዲሁም ቀድሞ የተደረጉትን የመሬት ክፍያ ድልድሎች እንደገና የማሻሻል ጒዳይ የሚፈጸምባቸው በምን ጊዜና በምን ሁኔታ እንደሆነ
ልማዶች ይወስናሉ፡፡
ቊ 1498፡፡ ልማዶችን ስለ ማሻሻል፡፡
(1) የአገር ግዛት ሚኒስቴር የኅብረቱን የኤኮኖሚ እድገት ለማሻሻል፤ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተመሠረተበትን የፍትሕንና የሞራልን
መሠረታዊ አሳቦች ለመከተል ከነገሩ አካባቢ ሁኔታ ጋራ ተስማሚ በሚሆንበት መጠን የኅብረቱ ልማዶች በየጊዜው እንዲሻሻሉ ለማድረግ
ያስብበታል፡፡
(2) ልማዶች ወይም ከነዚሁ አንዳንዶቹ እንዳይለዋወጡ ወይም የእነዚህን አለዋወጥ ለአእምሮ ግምት በማይስማማ አኳኋን እንዲሆን
የሚያደርግ ልማድ ወይም ውሳኔ ሁሉ ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 1499፡፡ ለዳኞች አቤቱታ ስለ ማቅረብ፡፡
(1) የኅብረቱ ድርጅቶች በሰጡት ውሳኔ ላይ ማናቸውም ባለጒዳይ ወይም ዐቃቤ ሕጉ ለዳኞች አቤቱታ ለማቅረብ የሚችለው፤

(2) ውሳኔዎቹ ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ወይም ሊታለፉ ከማይቻሉት ከዚህ ሕግ ወይም ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች ጋራ ተቃራኒ የሆኑ
እንደሆነ፤

(3) ድርጅቶቹ ውሳኔውን የሰጡት ከሥልጣናቸው በላይ ወይም የሥነ ሥርዐትንና የፍትሕን መሠረታዊ ነገር በመተላለፍ የሆነ እንደሆነ
ነው፡፡
ቊ 1500፡፡ ጸጥታን የሚመለከቱ ደንቦች፡፡
ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተውን ለዳኞች አቤቱታ የማቅረብን መብት የሚያስቀሩ ወይም ይህ መብት የሚሠራበትን አኳኋን
በአእምሮ ግምት የሚገባ ባልሆነ ግዴታ ውስጥ የሚያገባ ማናቸውም ገደብ ያለበት ልማድ ወይም ውሳኔ ፈራሽ ነው፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
በመንግሥት የታወቁ የመሬት ባለሀብቶች ማኅበር፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ ማኅበሮች መቋቋም፡፡

ቊ 1501፡፡ የኅብረት ሥራዎቹ የሚፈጸሙባቸው መንደሮች፡፡


ባንድ በተለየ መንደር ከፍ ያሉ ሥራዎች የሚሠሩ ሆነው በነዚህም ሥራዎች ምክንያት በዚሁ መንደር የሚገኙትን መሬቶች ዋጋ እጅግ
የሚለዋውጠው ሲሆን ይህን መንደር በኅብረት ሥራዎች የሚፈጸምበት መንደር ብሎ የንጉሠ ነገሥት ዐዋጅ ሊያስታውቅና በዚሁ መንደር
በሚገኙት መሬቶች ባለሀብቶች መካከል በመንግሥት የታወቀ የመሬት ባለሀብቶች ማኅበር እንዲቋቋም ለማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 1502፡፡ የግል ሙከራ፡፡
ባንድ መንደር ውስጥ የሚገኙት መሬቶች ባለሀብቶች በኅብረት ይህን መንደር ለመሥራት ወይም ለማሻሻል ወይም ዋጋ ያለው ለማድረግ
የጋራ ሥራዎችን ለመሥራት በፈቃዳቸው በመካከላቸው የባለሀብቶች ማኅበር ለማቋቋም ይችላሉ፡፡
ቊ 1503፡፡ መንግሥት እንዲያጸድቀው የሚቀርብ ጥያቄ፡፡
አንድ የባለሀብቶች ማኅበር እጅግ ቢያንስ ግማሽ የሚሆኑ ባለሀብቶች ያሉበት እንደሆነ፤ ይህ ማኅበር ዓላማውን እንዲፈቅድለትና
በመንግሥት የታወቀ ማኅበር እንዲሆን ፈቃድ እንዲሰጠው የርሻ ሚኒስቴርን ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 1504፡፡ ምርመራ፡፡
የርሻ ሚኒስቴር ባለጒዳይ በሆኑ ባለሀብቶች መካከል በኤኮኖሚና በማኅበራዊ ጥቅም ረገድ ከማኅበሩ ይገኛል የተባለው ጥቅም በሀብትነት
መብቶች ላይ ሊያስከትል ከሚችለው ጉዳት ይልቅ የበለጠ ጥቅም የሚሰጥ መሆኑን ምርመራ ያደርጋል፡፡

ቊ 1505፡፡ የመተዳደሪያ ደንብ ዐቅድ (ፕሮዤ)፡፡

(1) የርሻ ሚኒስቴር በሚያደርገው ምርመራ መንግሥት እንዲያውቀው ለማድረግ በሚደግፍ ሐሳብ ላይ የደረሰ እንደሆነ ለማኅበሩ የሚሆን
አንድ የደንብ ረቂቅ ያደራጃል፡፡

(2) ባለጒዳዮቹም በዚሁ የደንብ ረቂቅ ላይ ሐሳባቸውን እንዲያስታውቁ ይጠየቃሉ፡፡

(3) የመጀመሪያው ረቂቅ ለባለጒዳዮቹ እንዲገለጽ ወይም እንዲላክ ከተደረገበት ቀን አንሥቶ እጅግ ቢበዛ በ 6 ወር ውስጥ መጨረሻውን
የደንብ ረቂቅ የርሻ ሚኒስቴር ያደራጃል፡፡
ቊ 1506፡፡ የማኅበሩ መታወቂያ፡፡
ማኅበሩን በመንግሥት የታወቀ (ኦፊሲየል) የሚያደርገው መብቱ የሚፈቅድለት ሚኒስትር በነጋሪት ጋዜጣ በሚያወጣው ማስታወቂያ
ነው፡፡
ቊ 1507፡፡ አንድ ማኅበር ለማቋቋም ወይም ለመፍቀድ በነጋሪት ጋዜጣ በሚወጣው ማስታወቂያ የሚጻፈው፡፡
(1) በነጋሪት ጋዜጣ በሚወጣ ማስታወቂያ በመንግሥት የታወቀ የባለ ሀብቶች ማኅበር ከማቋቋሙ ወይም ከዚያም በፊት ያለውን ማኅበር
በመንግሥት እንዲታወቅ ከማድረጉም በላይ ማኅበሩ ሥራውን የሚያከናውንበትን አጥቢያ ትክክለኛ ክልል ይወስናል፡፡

(2) እንዲሁም የማኅበሩን ደንብ ያጸድቃል፡፡


ቊ 1508፡፡ ማኅበሩን ስለ መጠባበቅ፡፡
በመንግሥት የታወቀው የባለሀብቶች ማኅበር ሥራውን በተፈቀደለት ደንብ መሠረት መፈጸም አለመፈጸሙን መሬቶቹ ወይም አብዛኛዎቹ
መሬቶች በሚገኙበት መንግሥት በነጋሪት ጋዜጣ በሚያመጣው ማስታወቂያ በተከለለው አጥቢያ የሚገኙት የጠቅላይ ግዛቱ
ባለሥልጣኖች ይጠባበቁታል፡፡

አንቀጽ ዐሥራ አንድ፡፡


ስለ ድርሰትና ስለ ኪነ ጥበብ ባለሀብትነት፡፡
ቊ 1647፡፡ የመብቱ አሰጣጥ፡፡

(1) አንድ ሰው በአእምሮው አስቦ አንድ ቀዋሚ ነገር ፈጥሮ ያወጣ እንደሆነ ፈጥሮ በማውጣቱ ምክንያት ብቻ ለዚያ ፈጥሮ ላወጣው
ግዙፍነት የሌለውን የባለሀብትነትን መብት ያገኛል፡፡

(2) ሥራው ማናቸውም የአገላለጽ ዐይነት መልክ ፎርም ማንኛውም ምስጋና ወይም ግብ ቢኖረው ይህ መብት ይኖራል፡፡

(3) ሠሪው የሠራው ነገር በሥራ ወይም በሥራ ማከናወን ውል (በአንትሪፕሪዝ) ምክንያት እንኳን ቢሆን ለሠራው ሥራ ዐይነት ይህ
መብት አለው፡፡
ቊ 1648፡፡ በአእምሮ ታስቦ የሚወጣ ሥራ፡፡

የአእምሮ ሥራዎች ናቸው የሚባሉት ቀጥለው ያሉት ናቸው፡፡


(ሀ) እንደ መጻሕፍት በጥራዝ እየሆኑ እንደሚወጡት ጽሑፎች እንደ መጽሔት ጽሑፎች (ረቪዮ) ወይም እንደ ጋዜጦች በጉባኤ
እንደሚሰጡት ንግግሮች እንደ አጭር ንግግሮች እንደ ስብከቶች ወይም እንደ ቲያትሮችና ቲያትርን እንደ መሳሰሉ ሌሎች ሥራዎች ያሉት
የዕውቀት ድርሰቶች፤

(ለ) በቃል ወይም ያለ ቃል በሙዚቃ እንዲሰሙ የተዘጋጁ ሥራዎች በሙዚቃ እንዲሰሙ የተዘጋጁ የቲያትር ሥራዎች በራዲዮ ድምፅ
እንዲሰሙ ወይም በራዲዮቢዙየል እንዲታዩ የተዘጋጁ ሥራዎች ለቲያትር የተዘጋጁ የዳንስ ወይም የዜማ ስልቶች ሆነው አፈጻጸማቸውም
በጽሑፍ ወይም በሌላ አደራረግ የተወሰነ ሲሆን፤

(ሐ) እንደ ሥዕል፤ እንደ ንድፍ ሥዕል፤ እንደ ቅርጽ ወይም እንደ ድንጋይ ማነጥ ያሉ ሥራዎች፤ እንዲሁም እንደ ፎቶግራፍ ወይም እንደ
ሲኒማ ያሉት የሚታዩ ሥራዎች፤

(መ) የሥዕል መጽሔቶች የጂኦግራፊ ካርታዎች ፕላኖች የመጀመሪያ ንድፍ ሥራዎች ጂኦግራፊን የአገር መልክን (ቶፖግራፊ) የሕንጻ
አሠራርን ኦርሺቴክቱር ኪነ ጥበብን ወይም ሌላ ዕውቀትን ሁሉ የሚመለከቱ እንደ እጅ ጥበብ ማንሻ ያሉ የሥዕል ሥራዎች፤

(ሠ) በሠሪያቸው አእምሮ የተፈጠሩና የዚሁኑ አሠራር ልዩነት የሚያሳዩ ሌሎችም ሥራዎች ሁሉ ናቸው፡፡

ቊ 1649፡፡ ትርጒምና ማስማማት ፡፡

የመጀመሪያው አዲስ ሥራ አውጪ መብት ሳይነካ የመጽሐፉን ትርጒም የሥራውን ማስማማት (ማሻሻል) የሙዚቃ ማስማማቱን እና
የድርሰትን ወይም የኪነ ጥበብን ዐይነት መለወጥ እንደ መጀመሪያ ሥራ ሆነው ይጠበቃሉ፡፡

ቊ 1650፡፡ አንሲክሎፔዲና የቅኔ ጥርቅም፡፡

ነገሮቹን በማማረጥ ወይም በማዘጋጀት ከድርሰቶችና ከኪነ ጥበብ ሥራዎች ተለቅመው የአእምሮ ሥራ ፈጠራ እንደሚወጣቸው እንደ
አንሲክሎፔዲና እንደ ቅኔ ያሉት የጥርቅም አስተዋጽኦችም በነዚህ በተዋጽኦ ውስጥ የሚገኙ በያንዳንድ ሥራዎች ላይ ያላቸው የመጀመሪያ
አውጪዎች መብት ሳይነካ እንደ መጀመሪያ ሥራ ሆነው የሚጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1651፡፡ ግልጽ የሆኑ የመንግሥት ጽሑፎች፡፡

(1) የሕግ የአስተዳደር ወይም የዳኝነት ጠባይ ያላቸው ከመንግሥት ባለሥልጣኖች የሚነገሩት ጽሑፎች በዚህ ምዕራፍ የተነገረውን ጥበቃ
አያገኙም፡፡

(2) እንደ ተፈለገ በነጻ ሊባዙ ይቻላል፡፡

ቊ 1652፡፡ የወጣውን ሥራ የማስታወቅ መብት፡፡


(1) ያወጣውን ሥራ የማስታወቅ መብት ያለው ሥራ አውጪው ብቻ ነው፡፡

(2) እርሱ ከሞተ በኋላ በተባለው መብት የሚሠራ እርሱ የመረጠው ሰው ነው እርሱ የመረጠው የሌለ እንደሆነ የሥራው አውጪ ወራሾች
ናቸው፡፡

(3) የሥራ አውጪው ወራሾች ስለ ሥራው አወጣጥ ጊዜ ወይም ስለ ማስታወቁ ሁኔታዎች ያልተስማሙ እንደሆነ፤ ዳኞቹ ወራሾቹ
እያንዳንዳቸው ያቀረቡትን የጥያቄ ቃል ያመዛዝናሉ፡፡

ቊ 1653፡፡ የወጣውን ሥራ ስለ ማሳየትና ማባዛት፡፡

(1) ያወጣውን ሥራ በሕይወቱ ሳለ ለማሳየት መብት ያለው ሥራ አውጪው ብቻ ነው፡፡

(2) እንደዚሁም ያወጣውን ሥራ በሕይወቱ ሳለ ለማባዛት መብት ያለው ያው ሥራ አውጪው ብቻ ነው፡፡

ቊ 1654፡፡ ሥራውን ስለ ማስማማት፡፡

(1) ለቲያትር ለሲኒማ ለራዲዮ ቢዚዮን ወይም ለማንኛውም ዐይነት ሥራ የሠራው ሥራ እንዲስማማ ለመፍቀድ መብት ያለው ሥራ
አውጪው ብቻ ነው፡፡

(2) ለሌላ ሰው ሥራ ሆኖ አሠራሩን በማስማማት ወጣ የሚባለው አዲስ ሥራ የአሠራሩን ሁኔታዎች በማየት በፊት ከወጣው ሥራ ጋራ
ግልጽ የመነጨ ለመሆኑ በግልጽ ሲታይ ነው፡፡

(3) በሌላው ሰው ጽሑፍ ላይ ሐተታ መግለጽ ወይም በግጥም ላይ መግጠም ወይም በሚያሥቅ ዐይነት ሥዕሎችን ነድፎ የማውጣት
የመጀመሪያውን ሥራ አስማምቶ እንደ ማውጣት አይቈጠርም፡፡

ቊ 1655፡፡ ትርጒም፡፡

(1) ያውጣው ሥራ (መጽሐፍ) እንዳይተረጐም ደራሲው ለመቃወም አይችልም፡፡

(2) ያለደራሲው ፈቃድ የተደረገው ትርጒም፤ የዚህን ሁኔታ በተተረጐመው መጽሐፍ መጀመሪያ ላይ በግልጽ ማመልከት አለበት፡፡

(3) ይህን ሳይገልጽ የቀረ እንደሆነ የደራሲውን መብት እንደነካ ይቈጠራል፡፡

ቊ 1656፡፡ በግልና ያለ ዋጋ የሚደረግ ማሳየት፡፡

በተለይ በቤተ ዘመድ ክበብ ውስጥ ወይም በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ለብቻና ያለ ዋጋ የሚፈጽመውን የሥራውን ማሳየት ተግባር ሥራ
አውጪው ለመከልከል አይችልም፡፡
ቊ 1657፡፡ የዘመኑ ሁኔታ ጽሑፎችና ወሬዎች፡፡

(1) የዘመኑን ጠባይ የሚገልጹ ጋዜጣዎች ወይም በማኅተም መባዛታቸው በግልጽ ያልተጠበቀ እንደሆነ በማኅተም ወጥተው ወይም
በራዲዮ ተገልጸው ለመታየት ይችላሉ፡፡

(2) ቢሆንም የተገኙበት ምንጭ ሁል ጊዜ በግልጽ መነገር አለበት፡፡

(3) የተራ ነገር ጠባይ ያላቸው የዕለት ወሬዎችና ልዩ ልዩ ሥራዎች በነጻ ታትመው ለመውጣት ይችላሉ፡፡

ቊ 1658፡፡ በአደባባይ የተደረጉ ንግግሮች፡፡

በፖለቲካ ጉባኤ በሕዝብ ስብሰባ ወይም በመንግሥት ሥነ በዓል ምክንያት በተሰበሰበው ሕዝብ ውስጥ የተደረጉትን ንግግሮች ከተነገሩበት
ቀን አንሥቶ እስከ ዐሥራ አምስት ቀን ድረስ እየታተሙ ሊወጡና በራዲዮ ሊነገሩ ይችላሉ፡፡

ቊ 1659፡፡ የንግግሮቹ ወይም የጋዜጦቹ መድበል፡፡

የራሱን ንግግሮችና ጽሑፎች በመጽሐፍ ዐይነት አድርጎ ለማውጣትና በአንድ ለማጠቃለል መብት ያለው ራሱ ደራሲው ብቻ ነው፡፡

ቊ 1660፡፡ ሥራውን ሌላ ሰው እንዳያበዛ የመከልከል መብት ወሰን፡፡

(1) ጸሓፊው እርሱ ስለ ጻፈው ጒዳይ የሚደረገውን ማፍታታትና በጋዜጣ የሚወጡትን የመግለጫ (ጽሑፎች) ለመከልከል አይችልም፡፡

(2) እንደዚሁም ለግል አገልግሎት ብቻ የሚሆን ከመጽሐፉ አንድ ቅጂ ወይም ግልባጭ ብቻ ለመውሰድ ይፈቀዳል፡፡

ቊ 1661፡፡ ጥቅሶች፡፡

የሚጠቀሱ ነገሮች ከአንድ የቅኔ መጽሐፍ ሲሆን ከአርባ መሥመሮች ከሌላ ዐይነት መጽሐፍ ሲሆን ከዐሥር ሺሕ ፊደላት የማያልፉ
(ማይበልጡ) ከሆኑ ከወጣው መጽሐፍ ውስጥ እንዳይጠቀሱ ደራሲው ለመከልከል አይችልም፡፡

ቊ 1662፡፡ የፎቶግራፍ ሥራዎች፡፡

(1) የፎቶግራፍ ሥራዎች የሚጠበቁት በአንድ የፎቶግራፍ ማጠራቀሚያ ውስጥ ተያይዘው የሚገኙ ወይም በአንድ መጽሐፍ ውስጥ
ታትመው የወጡ ሲሆኑ ነው፡፡
(2) በሌላ ሁኔታዎች የፎቶግራፍ አንሺውን ወይም የወኪሉን ስምና አድራሻ የያዙ ካልሆኑ በቀር እንዳይባዙ የተጠበቁ አይሆኑም፡፡
ቊ 1663፡፡ የወጣውን ሥራ ስለ ማስተላለፍ፡፡
(1) አንድ ሰው አስቦ ያወጣውን (ግዙፍነት) የሌለው ሥራ ባለሀብትነት መጠበቅ ከሚገባው ከግዙፍ ዕቃ ባለሀብትነት የተለየ ነው፡፡

(2) ይህን ዕቃ በመግዛት እጅ ያደረገ ሰው ይህን ዕቃ እጅ በማድረጉ ምክንያት በዚህ ምዕራፍ ከተነገሩት መብቶች አንዱም አይሰጠውም፡፡

(3) ስለሆነም ሥራውን አስቦ ያወጣው ሰው በለቀቀው ዕቃ ላይ በመብቱ እንድሠራበት አድርግልኝ ሲል የተባለው ግዙፍ ዕቃ ባለቤት
የሆነውን ሰው ለማስገደድ አይችልም፡፡
ቊ 1664፡፡ አሳትሞ ለማስወጣት ወደ ተጻፈው የውል ደንብ ስለ መምራት፡፡
ድርሰትን ወይም ኪነ ጥበብን ያወጣው ሰው የዚህን ያወጣውን ሥራ መብት ለሌላ ሰው የሚለቅባቸው ሁኔታዎች የአሳትሞ ማስወጣት
ውል በሚል አንቀጽ ውስጥ በዚህ ሕግ ተወስነዋል፡፡
ቊ 1665፡፡ የወጣውን ሥራ ስለ መለዋወጥ፡፡
ማንኛቸውም ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ቢኖርም እንኳ ያወጣውን ሥራ ዐይነቱን ሌላ ሰው የለወጠበት እንደሆነ የተባለው ሥራ የዚያ
የለወጠው ሰው ነው በመባል እንዳይቀጥል ሥራ አውጪው ለመቃወም ይችላል፡፡
ቊ 1666፡፡ ሥራ አውጪው ማን መሆኑን ስለ መወሰን፡፡
(1) ተቃራኒ የሚሆን አስረጂ ከሌለ በቀር የሥራው አውጪ ነው የሚባለው ሥራው በስሙ መውጣቱ የታወቀለት ሰው ነው፡፡

(2) ሥራ አውጪው ያወጣው ሥራ የፈጠራ ስምን በመስጠት እንኳ ቢሆን ስለ ስሙ ትክክለኛነት አንዳች ጥርጥር ከሌለ በዚህ ምዕራፍ
በተወሰኑት መብቶች ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡
ቊ 1667፡፡ የአውጪው ስም የሌለባቸው ሥራዎች፡፡
የአውጪው (የደራሲው) ስም የሌለባቸው ሥራዎችና ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር ከተጠቀሱት በቀር በፈጠራ ስም የተጻፉ ሌሎች
ሥራዎች ሲገኙ በወጣው ሥራ ላይ ስሙ የተመለከተው አሳትሞ ጽሑፍ አውጪው ሌላ ማስረጃ ሳያስፈልግ የሥራ አውጪው ወኪል
እንደሆነ ይገመታል፡፡

ቊ 1668፡፡ በብዙ ሰዎች የወጣው ሥራ፤ (1) የጋራ ሥራዎች መብት፡፡

(1) በብዙ ሰዎች ሠሪነት ታስቦ የወጣው ሥራ የአውጪዎቹ የጋራ ሀብት ይሆናል፡፡

(2) የሥራው አውጪነት መብት በመካከላቸው በሚደረግ በጋራ ስምምነት ሊሠራበት ይገባል፡፡

(3) የጋራ ሠሪዎቹ የያንዳንዱ ድርሻ መሳተፍም የወጣበት ከልዩ ልዩ ዐይነት ነገር የሆነ እንደሆነ ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት ከሌለ በቀር
የጋራው ሥራ የሚሰጠው ጥቅም ሳይነካ እያንዳንዱ ለዚሁ ሥራ ባደረገው በራሱ ድርሻ ወጪ ገንዘብ ለብቻው መጠቀም ይችላል፡፡

ቊ 1669፡፡ (2) ሌሎች ሦስተኛ ወገኖችን ስለ መቃወም፡፡

(1) አንድ የወጣ ሥራ በአንዱ አውጪ ስም ብቻ የወጣ እንደሆነ ሌሎቹ ሦስተኛ ወገኖች ይህ በሥራው አውጪነት ስሙ የተጠራው ሰው
እርሱ ብቻ የሥራው አውጪ ነው ለማለት በቂ ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡

(2) የጋራ ሥራ አውጪዎቹ መብት እነዚህን ሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ሊሆን አይችልም፡፡

ቊ 1670፡፡ የሥራ አውጪው ወራሾች፤ (1) የገንዘብ መብት፡፡

(1) አስቦ ሥራ ያወጣው ሰው ያወጣውን ሥራ የማሳየት የማባዛት ወይም የሥራውን ማስማማት የመፍቀድ መብቱ እርሱ ከሞተ በኋላ
ወራሾቹ ሥራው በአደባባይ ወጥቶ ከታወቀበት አንሥቶ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ሊሠሩበት ይችላሉ፡፡

(2) ወራሾቹ በነገሩ ሳይስማሙ በሚቀሩበት ጊዜ ዳኞቹ እያንዳንዱ ወራሽ ስለዚህ ጒዳይ ያቀረበውን ጥያቄ ለማመዛዘን ይችላል፡፡
ቊ 1671፡፡ (2) የሕሊና መብት፡፡
የወጣውን ሥራ አንድ ሌላ 3 ኛ ወገን ዐይነቱን ሲለውጥ ይህ ዐይነቱ የተለወጠው ሥራ የአውጪው ነው ተብሎ እንዲቀጥል የማስደረጉ
መብት በሕይወት ሳሉ ከባልና ከሚስት አንዳቸው የሥራ አውጪው ወላጆች ልጆቹና የልጅ ልጆቹ በየራሳቸው ሊሠሩበት ይችላሉ፡፡
ቊ 1672፡፡ ከሞት በኋላ የሚታወቅ ሥራ፡፡
ሥራውን ያወጣ ሰው ከሞተ በኋላ በግልጽ የታወቀ ሥራ ከታወቀበት ቀን አንሥቶ አምሳ ዓመት ድረስ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ቊ 1673፡፡ የሕዝብ ባለሥልጣኖች መብት፡፡
(1) የወጣው ሥራ አውጪው ባለቤቱ ወይም ወራሾቹ በግልጽ አስታውቀውት ከታየ በኋላ ሠሪው ቢቃወምም ቅሉ ለጠቅላላ ጥቅም ከሆነ
ይህ አስቦ ያወጣው ሥራ እንዲታይ ወይም መሰሉ እንዲባዛ ወይም ዐይነቱ የተስማማ በመሆን እንዲሻሻል የሕዝብ ባለሥልጣኖች
ለመፍቀድ ይችላሉ፡፡

(2) የዚህ የአፈቃቀድ ምክንያቶችና ፎርሞች ለሥራ አውጪው የሚገባ ትክክለኛ ኪሣራ እንዲሰጠው በሚናገረው ልዩ ሕግ ይወሰናሉ፡፡

(3) የሕዝብ ባለሥልጣኖች በማናቸውም ምክንያት ቢሆን የሥራው ዐይነት እንዲለዋወጥ ለመፍቀድ አይችሉም፡፡
ቊ 1674፡፡ የድርሰት ወይም የኪነ ጥበብ ባለሀብትነት፡፡
(1) የድርሰት ወይም የኪነ ጥበብ ባለ ሀብትነት መብቱ የተነካበት ሥራ አውጪ የተባለው መነካት እንዲቆም እና ሕግን በመተላለፍ
(በመጣስ) የተደረጉት የሥራው ቅጂዎች ወይም የሥራው ማሻሻያዎች እንዲጠፉ ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) ከዚህም በላይ በሕሊናም ሆነ በግዙፉ ረገድ ስለ ደረሰበት ጉዳት የገንዘብ ኪሣራ እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) ይህን ለማድረግ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ከውል ውጭ ስለሚደርስ ኀላፊነት በሚል አንቀጽ በዚህ ሕግ ተወስነዋል፡፡

አራተኛ መጽሐፍ፡፡
ስለ ግዴታዎች፡፡
አንቀጽ 12፡፡
ስለ ውሎች በጠቅላላው፡፡
ቊ 1675፡፡ የውል ትርጓሜ፡፡

ውል ማለት ንብረታቸውን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት፤ ባላቸው ተወዳዳሪ ግንኙነት
በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡

ቊ 1676፡፡ ውሎች የሚመሩባቸው ደንቦች፡፡

(1) ውሎች ዐይነታቸው ምክንያታቸውም ማንኛውም ቢሆን በዚህ አንቀጽ በተጻፉት ጠቅላላ ደንቦች ይመራሉ፡፡

(2) እነዚህን ጠቅላላ ደንቦች የሚለውጡ ወይም የሚያሟሉ ስለ አንዳንድ ውሎች የተጻፉ ልዩ የሆኑ ደንቦች በዚህ ሕግ በ 5 ኛው
መጽሐፍና በንግድ ሕግ ውስጥ ተመልክተዋል፡፡
ቊ 1677፡፡ የዚህ አንቀጽ አፈጻጸም፡፡

(1) ግዴታዎቹ ከውል የተገኙ ባይሆኑም የዚህ አንቀጽ ደንቦች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

(2) የአንዳንድ ግዴታዎችን ከስር አመጣጣቸውን ወይም ዐይነታቸውን በመመልከት ከዚህ ደንብ የተለዩት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ምዕራፍ 1፡፡
ስለ ውል አመሠራረት፡፡
ቊ 1678፡፡ የውል አቋሞች፡፡

የሚጸና ውል ነው ለማለት ሦስት ሁኔታዎች ያስፈልጉታል፡፡


(ሀ) ውል ለመዋዋል ችሎታ ባላቸው ሰዎች መካከል ጒድለት የሌለው ስምምነት መኖር፤

(ለ) በቂ የሆነ እርግጠኛነት ያለው የሚቻልና ሕጋዊ የሆነ ጒዳይ፤

(ሐ) ይኸውም የውሉ አጻጻፍ ፎርም (ዐይነት) በሕግ የታዘዘ ሆኖ፤ እንደ ትእዛዙ ባይፈጸም ፈራሽነትን የሚያስከትል ሲሆን አንድ ልዩ
ፎርም፡፡

ክፍል 1፡፡
ፈቅዶ ስለ መዋዋል፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ውለታን የመቀበል አቋሞች፡፡
ቊ 1679፡፡ ውልን ፈቅዶ መዋዋል መሠረት ስለ መሆኑ፡፡

ውል ተዋዋዮቹ በገቡባቸው ግዴታዎችና እነዚሁም አስገዳች እንዲሆኑ የተስማሙበትን በሚገልጸው የፈቃድ መስጠት ላይ የተመሠረተ
ነው፡፡

ቊ 1680፡፡ የተዋዋዮቹ ስምምነት፡፡

(1) ውሉ ፍጹም ነው ለማለት የሚቻለው ተዋዋዮቹ በተስማማ አኳኋን መፍቀዳቸውን ገልጸው ሲገኙ ነው፡፡

(2) ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን ሳያውቀው ከውሉ ውስጥ የማስቀረትና የማገድ ቃላት ተጨምረውበት ቢገኙ፤ በአጻጻፉ በግልጽ ተነግሮ
የሚገኘው የመፍቀድን ዋናውን ሁኔታ ሊያቃውሱትና ሊቀንሱት አይችሉም፡፡

ቊ 1681፡፡ የውል አቀራረብና አቀባበል፡፡


(1) ፈቃድን በቃል ወይም በጽሑፍ ወይም በተለመዱ ጠቅላላ ምልክቶች ወይም ለውሉ መነሻ ከሆነው ምክንያት የተነሣ ግዴታ ለመግባት
መፍቀዱን በማያጠራጥር አሠራር ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) ቢሆንም ለውሉ አቀባበል አቅራቢው የተለየ አሠራር ለመወሰን ይችላል፡፡

ቊ 1682፡፡ ዝምታ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

የውል አቀራረብ ሲቀርብለት ዝም ማለት ብቻ የቀረበለትን የውል አሳብ እንደተቀበለ አያስቈጥርም፡፡

ቊ 1683፡፡ (2) የመቀበል ግዴታ፡፡

(1) በሕጉ መሠረት የአስተዳደር ክፍል መሥሪያ ቤት በሰጠው ውል (ኰንሰሲዮን) ምክንያት የተወሰነ የውል አፈጻጸም ሲኖርና አስቀድሞ
በተሠራው የውል ቃል የተለዩ ሰዎች የሚገደዱበት ሲሆን፤ የተባሉት ሰዎች ውሉን ስለ መቀበላቸው ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ አይገኝም፡፡

(2) እንዲሁም ሲሆን ውል ተቋቋመ (ተፈጸመ) የሚባለው የውሉን ድርድር አቀራረብ በተቀበለበት ጊዜ ነው፡፡

ቊ 1684፡፡ (3) አስቀድመው ስላሉ የውለታ ግንኙነቶች፡፡

(1) ቀድሞ የነበረውን የውል ዘመን ለማስረዘም ወይም ለማሻሻል ወይም ተጨማሪ ውል ለማድረግ ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን ያቀረበውን
ማስታወቂያ በዝምታ ብቻ ለመቀበል ይቻላል፡፡

(2) እንዲሁም በተለይ የሚሆነው ጽሑፍ ሆነ ብሎ በተሰናዳ አቀራረብ ድርድሩ ቀርቦ፤ በዚሁ ጽሑፍ ላይ በቂ ጊዜ ተቈርጦለት በተወሰነው
ጊዜ ውስጥ መልስ ሳይሰጥ ቢቀር የቀረበለትን ድርድር እንደተቀበለ ይቈጠራል፡፡

ቊ 1685፡፡ (4) ፋክቱር፡፡

ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን ብቻ በፋክቱር ላይ ሌላ ጽሑፍ ወይም የግዴታ ማስታወሻ ጽፎበት ቢገኝ በዚሁ ጽሑፍ ለመስማማቱ ሌላው
ወገን አስቀድሞ ከሰጠው ስምምነት ጋራ የሚገጣጠም ስምምነት ካልሆነ በቀር ወይም በተለይ ይህንኑ ግዴታ በግልጽ ካልተቀበለ
አያስገድደውም፡፡

ቊ 1686፡፡ (5) ጠቅላላ የሆኑ የሥራ አፈጻጸም ሁኔታዎች፡፡

ባለውል የፈጸማቸው ጠቅላላ የጒዳይ ሁኔታዎች ሌላውን ተዋዋይ ወገን ሊያስገድዱት የሚችሉት አንደኛው ወገን እነዚህን ጒዳዮች
አስቀድሞ ዐውቋቸውና ወዶ ተቀብሏቸው የተገኘ እንደሆነ፤ ወይም የሕዝብ ባለሥልጣኖች የደነገጓቸው ወይም ያጸኗቸው ሲሆኑ ነው፡፡
ቊ 1687፡፡ አሳብን ብቻ ስለ መግለጽ፡፡

(ሀ) ለተጠቃሚው ሳያስታውቅ አንድ ሰው፤ አንድ ነገር ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን፤ አንድ ጒዳይ የማድረግ ወይም ያለ ማድረግ አሳቡን
የገለጸ እንደሆነ፤

(ለ) እንዲሁም የንግድ ዕቃ ዋጋ ተመን (ታሪፍ) ወይም የዕለት ገበያ ዋጋ መግለጫ፤ ወይም የዕቃ ዝርዝር የሚያሳይ ጽሑፍ ለሌላ ሰው
የላከ፤ ወይም በአደባባይ በሚለጠፍ ማስታወቂያ የገለጸ ወይም የንግድ ዕቃዎችን ለሕዝብ ስለ መሸጥ ያሳየ የደረደረ እንደሆነ፤ ይህ ሁሉ
አድራጎት የውል ግዴታ እንደገባ አያስቈጥረውም፡፡

ቊ 1688፡፡ ለሕዝብ ስለሚደረግ ሐራጅ፡፡

(1) ማንም ሰው ሀብቱን በሐራጅ የሚሸጥ መሆኑን ሲያስታውቅ፤ አሳቡን መግለጹ ነው እንጂ፤ ውል እንዳቀረበ አይቈጠርም፡፡

(2) እንዲሁም በሆነ ጊዜ ውል ተፈጸመ ለማለት የሚቻለው በመጨረሻው ሐራጅ ለጨረታ፤ የቀረበው ሀብት ለዋጋ አቅራቢው በተሰጠ
ጊዜ ነው፡፡

ቊ 1689፡፡ ሽልማት ስለ መስጠት በግልጽ የተሰጠ የተስፋ ቃል፡፡

(1) የጠፋ ዕቃ ላገኘ ወይም ሌላ ነገር ለፈጸመ ሰው ሽልማት ይሰጠዋል ተብሎ በተለጠፈ ማስታወቂያ ወይም በአደባባይ ሊታወቅ በሚቻል
ሌላ ዐይነት ማስታወቂያ ወጥቶ ቃል ከተሰጠ በኋላ የጠፋውን ዕቃ አግኝቶ ቢያመጣ ወይም እንዲፈጸም የተባለውን ሥራ ፈጽሞ ቢገኝ
ይህን ያደረገው ሰው የወጣውን ማስታወቂያ ሳያውቅ ቢቀርም የተሰጠውን የተስፋ ቃል እንደተቀበለ ይቈጠራል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ቃል ሰጪውም በበኩሉ የሰጠውን የተስፋ ቃል የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 1690፡፡ ጊዜ ተወስኖ ስለሚቀርብ ውል፡፡

(1) የመቀበያውን ጊዜ ወስኖ አንድ ውል እንዲደረግ ለሌላ ሰው የሚያቀርብ ሁሉ ለዚሁ የወሰነው ጊዜ እስኪያልፍ ድረስ በዚሁ አቀራረብ
የሰጠው ቃል ይጸናበታል፡፡

(2) ከዚህ የውል ግዴታ ሊድን የሚችለው ጊዜው ከማለፉ በፊት ያቀረበውን ውል፤ የቀረበለት ሰው ያልተቀበለው እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1691፡፡ ጊዜ ሳይወሰን የሚቀርብ ውል፡፡

(1) ለቀረበው ውል የጊዜ ውሳኔ ሳይደረግለት ቢቀር ውሉን ያቀረበው ሰው በውሉ ቃል ተገዳጅ ሆኖ የሚገኘው የቀረበለት ሰው መቀበል
ያለ መቀበሉን መልስ ሊሰጥ ይችል የነበረበት ጊዜ በአእምሮ ግምት በቂ ይሆናል እስከሚባልበት ጊዜ ድረስ ነው፡፡
(2) መቀበሉን ዘግይቶ ቢያስታውቅና ውል አቅራቢው በዚህ ባቀረበው የውል ቃል መገደድ ባይፈልግ ወዲያውኑ ለተቀባዩ ማስታወቅ
አለበት፡፡

ቊ 1692፡፡ ተዋዋዮቹ ሳይገናኙ ስለሚደረግ ውለታ፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ሳይገናኙ የተደረገ ውለታ ተዋውለውበታል ተብሎ የሚታወቀው ውል ተቀባዩ መቀበሉን ያስታወቀበት ስፍራና የላከበት ጊዜ
ነው፡፡

(2) በቴሌፎን የሚደረግ ውል ተዋዋዩ በቴሌፎን በተጠራበት ስፍራ የተፈጸመ ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(3) ይህን ተቃራኒ የሆኑት የተዋዋዮቹ ወገኖች ስምምነቶች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1693፡፡ የውል ማቅረብን ወይም መቀበልን ስለ ማስቀረት፡፡

(1) ውል ተቀባዩ የውል ድርድር መኖሩን ከማወቁ በፊት ወይም ይህ መኖሩን እንዳወቀ ወዲያውኑ ድርድሩ መሻሩን ያወቀ እንደሆነ የውሉ
ድርድር እንዳልተደረገ ይቈጠራል፡፡

(2) ይኸው ደንብ የውሉን ድርድር ከተቀበለ በኋላ ትቻለሁ ለሚለውም ወገን ተፈጻሚ ነው፡፡

ቊ 1694፡፡ ፍጹም ያልሆነ የውል አቀባበል፡፡

የተጠበቀ ሁኔታ ያለበት ወይም ከቀረበው የውል ድርድር ቃል ጋራ በትክክል የማይስማማ የውል አቀባበል ድርድሩን እንደ አለመቀበልና
አዲስ ድርድር እንደማቅረብ ይቈጠራል፡፡

ቊ 1695፡፡ የውል ፍጹምነት፡፡

(1) ከውሉ ባንዱ ሁኔታ ላይ ጥቃቅን ነገሮች ቢሆኑም እንኳ ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን አለመስማማቱን የሚገልጽ ነገር ካለ ውሉ ተፈጸመ
ለማለት አይቻልም፡፡

(2) ተዋዋዮቹ በውላቸው የተስማሙ መሆናቸውን ከገለጹና ካመኑ ስምምነቱ ያልተሟላ ሆኖ ቢገኝም ውሉ እንዳለ ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(3) በዚህ ጊዜ በተዋዋዮቹ መካከል የጐደለው ስምምነት የሚሟላው በሕግ ተደንግጎ በሚገኘው ነው፡፡

ንኡስ ክፍል 2፡፡


የተዋዋዮቹ ፈቃድ ጒድለት፡፡
ቊ 1696፡፡ ውልን የሚፈርሱ ምክንያቶች፡፡
(1) ውል የሚፈርሰው ከተዋዋዮቹ የአንደኛው መፍቀድ፤ በስሕተት በድንገተኛ ተንኰል፤ ወይም በኀይል የተገኘ ሲሆን ነው፡፡

ቊ 1697፡፡ ውልን ከመቀበል ስለሚያደርስ ስሕተት፡፡

መሳሳቱ ይታወቅልኝ ሲል የሚከራከረው ወገን ስሕተቱ ለመዋዋል ያደረሰው መሆኑን ማስረዳት አለበት፤ እንዲህ መባሉ፤ እውነቱን ዐውቆ
ቢሆን ኖሮ ፈቅዶ የማይሠራው መሆኑ ሲታወቅ ነው፡፡

ቊ 1698፡፡ ለውል አስፈላጊ በሆነ አቋም ላይ ስለ መሳሳት፡፡

ለመዋዋል ያደረሰው ስሕተት ውል ማፍረሻ የሚሆነው፤ ተዋዋዮቹ አስፈላጊ አቋም ነው ሲሉ በሚቀበሉት አኳኋን ላይ የተደረገ ስሕተት
ሲሆንና ወይም፤ ውሉ ሲፈጸም በአኳኋኑና በቅን ልቡና አስፈላጊ አቋም በሆነው ላይ መሆኑ ሲገመት ነው፡፡

ቊ 1699፡፡ በውሉ ዐይነት ወይም ጒዳይ ላይ ስለሚሆን ስሕተት፡፡

ለመዋዋል ያደረሰው ስሕተት በተለይ ውሉን የሚያፈርሰው፤


(ሀ) በውሉ ዐይነት ላይ ስሕተቱ የደረሰ ሲሆን፤

(ለ) አንደኛው ተዋዋይ በሰጠው ቃል ስለ መሳሳቱ የሚያቀርበው መከራከሪያ ከፍ ያለ አስረጅነት የሚያገኝ ሲሆን፤ ወይም ውል ተቀባይ
የሰጠው መልስ በእውነት ከፈቀደው እጅግ ያነሰ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

ቊ 1700፡፡ በተዋዋዩ ስለ ማሳሳት፡፡

ተዋዋዩ ማን እንደሆነ ወይም ሥራው ሞያው ምን እንደሆነ በማሳሳት የሆነ ውል የሚቀረው በተለመደው የነገር አግባብ ወይም በነገሩ ልዩ
ሁኔታ ተዋዋዩን ወይም ሞያውን ማወቅ ለውሉ ዋና አስፈላጊ ጒዳይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ነው፡፡

ቊ 1701፡፡ በቂ ምክንያት የማይሆን ስሕተት፡፡

(1) ለመዋዋል ባደረሱት ምክንያቶች ላይ የተደረገ ስሕተት ውሉን አያስቀረውም፡፡

(2) በውሉ ላይ የተደረገ የሒሳብ ስሕተት ብቻ የተሳሳተው ሒሳብ እንዲተካከል ያደርገዋል እንጂ፤ ውሉን በሙሉ አያፈርሰውም፡፡

ቊ 1702፡፡ ለቅን ልቡና ደንብ ተቃራኒ የሆነ አሠራር፡፡


(1) በስሕተቱ ተጎጂ የሆነው ወገን የቅን ልቡና አሠራርን ተቃዋሚ በሆነ አኳኋን ይታይልኝ ሊል አይችልም፡፡

(2) ሌላው ወገን ተዋዋይ እንደ ውሉ እንዲፈጸምለት የሚፈቅድ መሆኑን ካረጋገጠ ተዋውሎበት በነበረው ውል መገደድ አለበት፡፡

ቊ 1703፡፡ ኪሣራ የመክፈል ግዴታ፡፡

ውሉ ከሚያደርስበት ግዴታ ለመዳን ሲል በስሕተቱ የሚያመካኘው አንደኛው ወገን ተዋዋይ፤ ሁለተኛው ወገን ይህን ስሕተቱን ካላወቀለት
ወይም ማወቅ እንደነበረበት ካልገለጸ በቀር በውሉ መፍረስ ምክንያት ለደረሰው ጉዳት ኪሣራ ይከፍላል፡፡

ቊ 1704፡፡ ተንኰል፡፡

(1) በተንኰል የተደረገ ውል ፈራሽ የሚሆነው ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን ውሉ እንዲደረግ ያደረገው በሁለተኛው ተዋዋይ ላይ ተንኰል
ባይደርስበት ኖሮ ውል የማያደርግ እንደነበረ ሲገለጽ ነው፡፡

(2) ከተዋዋዮቹ ውጭ በሆነ በሌላ ወገን ተንኰል ያለ ውዴታ ባደረገው ውል ጉዳት የደረሰበት ወገን፤ ሁለተኛው ተዋዋይ ይህ ተንኰል
የደረሰበት መሆኑን ካላወቀለት ወይም ማወቅ እንደነበረበት ካልተገለጸ ወይም ከውሉም ጥቅም ካገኘ በውሉ ተገዳጅ ይሆናል፡፡

ቊ 1705፡፡ እርግጠኛ ባልሆነ ጒዳይ ስለ መዋዋል፡፡

(1) በክፉ ልቡና ወይም በቸልተኛነት የተደረገ ሲሆን ይልቁንም በተዋዋዮቹ መካከል የተለየ የታወቀ መተማመን ያለ በመሆኑ
በግንኙነታቸውም አንዱ ላንዱ የተለየ ታማኝነት እንዲኖረው ሲገደድ፤ እርግጠኛ ባልሆነ ጒዳይ የሰጠው ውል ለማፍረስ የሚፈቅድ
ምክንያት ይሆናል፡፡

(2) እንዲሁም ዝም በማለት፤ የተዋዋለው ሌላውን ወገን ያልተካከለውን ነገር አሳምኖት እንደሆነ፤ ይኸው ሥርዐት ተፈጻሚ ነው፡፡

ቊ 1706፡፡ በመገደድ የተደረገ ውለታ፡፡

(1) የኀይል ሥራ ለውሉ ማፍረሻ ምክንያት የሚሆነው አንደኛውን ወገን እሱን ራሱን ወይም ወላጆቹን ወይም ተወላጆቹን ወይም ባልን
ወይም ሚስትን ከባድና የማይቀር አደጋ በሕይወቱ በአካሉ፤ በክብሩ ወይም በንብረቱ እንደሚመጣበት ያሳመነው ሲሆን ነው፡፡

(2) ይኸውም የኀይል ሥራ አእምሮው የተደላደለውን ሰው ለማሥጋት የሚችል መሆን አለበት፡፡

(3) እንዲህም ሲሆን የማስገደድ ሥራ የደረሰበትን ሰው ዕድሜውን ጾታውን አኳኋኑን ማመዛዘን ያስፈልጋል፡፡

ቊ 1707፡፡ ሦስተኛ ወገን ስለሚያደርገው የኀይል ሥራ፡፡


(1) በተዋዋለው ሰው ላይ የኀይል ሥራ ሲፈጸም የኀይል ሥራ ሠሪው በስምምነቱ ተጠቃሚ ያልሆነ ሌላ ሰው ቢሆንም እንኳ የውል
ማፍረሻ ምክንያት ይሆናል፡፡

(2) የኀይል ሥራውን የፈጸመው ሦስተኛ ወገን ሆኖ አንደኛው ወገን ያላወቀውና ሊያውቀውም የማይገባው ያልሆነ እንደሆነ፤ ከተዋዋዮቹ
አንዱ በመገደዱ ምክንያት ከውሉ አፈጻጸም እድናለሁ ባዩ፤ ውሉ ባለመፈጸሙ ሌላውን ወገን ላገኘው ጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 1708፡፡ በመብት ስለ ማስፈራራት፡፡

በመብት ማስፈራራት ውሉን ማፍረሻ የሚሆነው ከልክ ያለፈ ጥቅም ለማግኘት አገልግሎት ሲገኝ ነው፡፡

ቊ 1709፡፡ በአክብሮት ስለሚደረግ ውለታ፡፡

(1) ሳይገደድ ወላጅን ወይም የበላይን በማክበር ብቻ በሆነ ሥጋት የተፈጸመ ጒዳይ ውልን ለማፍረስ በቂ አይደለም፡፡

(2) ቢሆንም፤ ውሉን ያደረገው ከሚፈራውና ከሚያከብረው ሰው ጋራ ሆኖ ይኸውም ሰው በዚሁ ሰው ከልክ ያለፈ ጥቅም አግኝቶበት
እንደሆነ ውሉ የሚፈርስ ይሆናል፡፡

ቊ 1710፡፡ ስለ መጉዳት፡፡

(1) ላንደኛው ተዋዋይ ወገን የበለጠ ጥቅም የሚሰጥ ነው በማለት ብቻ ውሉን ለማፍረስ አይቻልም፡፡

(2) ቢሆንም የተጎጂው ፈቃድ የተገኘው፤ ችግሩን የመንፈሰ ቀላልነቱን መጃጀቱን በዕድሜ መግፋቱን ወይም በንግድ ግልጽ የሆነ የልማድ
ዕውቀት የሌለው መሆኑን በመደገፍ እንደሆነና በሕሊናም ግፍ መስሎ ሲታይ ውሉን ለማፍረስ ይቻላል፡፡

ክፍል 2፡፡
ስለ ውለታው ጒዳይ፡፡
ቊ 1711፡፡ የውል ጒዳይ አወሳሰን፡፡

ሕግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች በቀር ተዋዋዮች ሁሉ የሚዋዋሉበትን ጒዳይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት አላቸው፡፡

ቊ 1712፡፡ የመስጠት የማድረግ ወይም ያለ ማድረግ ግዴታዎች፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ለሚዋዋሉት ሰው፤ በአንድ ነገር ላይ ያላቸውን መብት ለመስጠት ወይም አንድ ነገር ለማድረግ ወይም ስላለማድረግ ሊዋዋሉ
ይችላሉ፡፡
(2) እናደርግልሃለን በማለት በተዋዋዩ ጊዜ ተዋዋዮቹ የተወሰነ አድራጎት ለመፈጸም ሊዋዋሉና ወይም የሚዋዋሉት ሰው ጥቅም እንዲያገኝ
የተቻላቸውን የሚያደርጉ መሆናቸውን ብቻ ሊዋዋሉ ይችላሉ፡፡

ቊ 1713፡፡ ለውለታው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች፡፡

ውሎች አስገዳጅነታቸው በውሉ በተነገረው ጒዳይ ብቻ ሳይሆን ልማድ፤ ፍትሕ፤ ቅን ልቡና የውለታው ዐይነት የሚያስከትሉዋቸውን
ነገሮች ጭምር ነው፡፡

ቊ 1714፡፡ በማይበቃ አወሳሰን የተመለከተ የውል ጒዳይ፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ወይም ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን የገቡት ግዴታዎች በትክክልና በሚበቃ ሁኔታ ካልተገለጹ በቀር ውሉ ፈራሽ ነው፡፡

(2) ውል መተርጒምን ሰበብ በማድረግ ለተዋዋዮቹ ወገኖች አንድ ውል ዳኞች ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡

ቊ 1715፡፡ የሚዋዋሉበት ጒዳይ ለመፈጸም የሚቻል ስለ መሆኑ፡፡

(1) የውል ጒዳይ ለመፈጸም የሚቻል መሆን ይገባዋል፡፡

(2) ተዋዋዮቹ ወይም አንዱ ወገን ተዋዋይ ሊፈጸም በማይቻል ነገር ላይ የተዋዋለ እንደሆነና የተዋዋሉበትም ነገር በፍጹም የማይቻልና
የማይሞከር ጠባይ ያለው ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ውሉ ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 1716፡፡ ሕገ ወጥ ወይም ለሕሊና ተቃራኒ የሆነ ጒዳይ፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ወይም አንዱ ወገን ተዋዋይ የገቡበት ግዴታ ሕግን ወይም መልካም ጠባይን ተቃራኒ የሆነ እንደሆነ ውሉ ፈራሽ ነው፡፡

(2) እንዲሁም ሌላው ወገን ለገባለት ግዴታ ሲል፤ አንዱ ወገን የገባበት ግዴታ ለሕግ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ መስሎ በታየ ጊዜ
ውሉ ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 1717፡፡ (ሀ) ምክንያት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን የውል ግዴታ የገባበት ምክንያት፤ ውሉ ሕገ ወጥ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ መሆኑን ለማመዛዘን
ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡

ቊ 1718፡፡ (ለ) (2) የተጠበቀ ሁኔታ፡፡


ስለሆነም ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ሁለት ምክንያቶች ባጋጠሙ ጊዜ ዳኞች ውሉ እንዲፈጸም የቀረበላቸውን ጥያቄ አንቀበልም ለማለት
ይችላሉ፡፡
(ሀ) ተዋዋዮቹ ወይም ከተዋዋዮቹ አንዱ የሚፈልጉት የውል ዓላማ ሕገ ወጥ የሆነ ወይም ግብረ ገብ ያልሆነ መሆኑ ከውሉ ቃል የታወቀ
እንደሆነ፤
(ለ) ይህ ዓላማ ውሉ እንዲፈጸም ከሚጠይቀው ተዋዋይ ጽሑፍ የተገኘ እንደሆነ፤

ክፍል 3፡፡
ስለ ውል አጻጻፍ (ፎርም)
ቊ 1719፡፡ ስለ ውል አጻጻፍ ነጻነት፡፡

(1) በጠቅላላው ሥርዐት በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች በማናቸውም ሁኔታ የተደረገ ስምምነት ውል ለማድረግ በቂ ነው፡፡

(2) ሕጉ በግልጽ የሚያስገድድ በሆነ ጊዜ ግን አንድ ልዩ የሆነ የሚጠበቅ አጻጻፍ (ፎርም) እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡

(3) እንዲሁም ተዋዋዮቹ የውላቸውን አፈጻጸም ልዩ በሆነ አጻጻፍ ሥርዐት ሊወስኑት ይችላሉ፡፡

ቊ 1720፡፡ ስለ ውል አጻጻፍ (ፎርም) የተሰጠ ደንብ አለመፈጸም የሚያስከትለው፡፡

(1) ሕግ የተለየ ጽሑፍ (ፎርም) እንዲኖር ባዘዘ ጊዜ ይህ አኳኋን እስኪፈጸም ድረስ ውሉ እንደ ረቂቅ ብቻ ሆኖ ይታያል፡፡

(2) እንደ ቴምብር መክፈል ወይም እንደ መመዝገብ ግዴታ ያሉት ስለ ውል ጒዳይ የተወሰኑት የቀረጥና የግብር ድንጋጌዎች አለመፈጸም
ውሉን ፈራሽ አያደርገውም፡፡

(3) እንዲሁም ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ስለ ውል ጒዳይ የተወሰኑ የማስታወቂያ ድንጋጌዎች አለመፈጸም ውሉን ፈራሽ አያደርገውም፡፡

ቊ 1721፡፡ ተቀዳሚ ውሎች፡፡

ተቀዳሚ ውሎች ለመጨረሻ ውል በተወሰነው አጻጻፍ (ፎርም) ዐይነት መሠራት አለባቸው፡፡

ቊ 1722፡፡ ውልን ስለ መለዋወጥ፡፡

ዋናውን ውል የመለወጥ ጒዳይ ለዚሁ ውል በተደነገገው አጻጻፍ (ፎርም) መሠራት አለበት፡፡

ቊ 1723፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች፡፡


(1) የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ባለቤትነት ወይም ባንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የአላባ ጥቅም መብት ወይም የመያዣ ወይም የሌላ
አገልግሎት መብት ለማቋቋም፤ ወይም ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውሎች ሁሉ በጽሑፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም
ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ፊት መሆን አለባቸው፡፡

(2) እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ የክፍያ ወይም የማዛወር ስምምነቶች ሁሉ በጽሑፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ ቤት
መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ፊት መሆን አለባቸው፡፡

ቊ 1724፡፡ ካስተዳደር መሥሪያ ቤት ጋራ የሚደረጉ ውሎች፡፡

መንግሥት ወይም ለሕዝብ አገልግሎት የቆሙ መሥሪያ ቤቶች ግዴታ የሚዋዋሉባቸው ውሎች ሁሉ በጽሑፍና በሚገባ አኳኋን በፍርድ
ቤት መዝገብ ወይም ባንድ ባስተዳደር ክፍል መሥሪያ ቤት መዝገብ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ፊት መሠራት
አለባቸው፡፡

ቊ 1725፡፡ ለብዙ ዘመን የሚቈዩ ውሎች፡፡

እንዲሁም፡-

(ሀ) የዋስትና ውሎች

(ለ) የኢንሹራንስ ውሎች፡-

(ሐ) ይህ አጻጻፍ (ፎርም) በሕግ ያስፈልጋቸዋል የተባሉት ሌሎች ውሎች ሁሉ፤ በጽሑፍ መሠራት አለባቸው፡፡

ቊ 1726፡፡ በስምምነት ስለሚሆን ያጻጻፍ ዐይነት (ፎርም)፡፡

ተዋዋዮዡ ለሚዋዋሉት ውል ሕግ የማያስገድደውን ልዩ አኳኋን (ፎርም) ለመፈጸም የተስማሙ እንደሆነ ለምሳሌ፤ ሕግ ሳያስገድድ
በጽሑፍ ለመዋዋል የተስማሙ ሲሆኑ ውሉ ፍጹም የሚሆነው የተስማሙበትን የውላቸውን አፈጻጸም ሞልተው በተዋዋሉ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ቊ 1727፡፡ የውል ጽሑፍ አኳኋን (ፎርም)፡፡

(1) ውል በጽሑፍ እንዲደረግ ግዴታ ሲኖር ልዩ በሆነ አሠራር ተገልጾ በውሉ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ መፈረም አለባቸው፡፡

(2) በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ አይጸናም፡፡

ቊ 1728፡፡ ፊርማ፡፡
(1) ፊርማ በውሉ ተገዳጅ በሆነው ሰው እጅ መጻፍ ይገባዋል፡፡

(2) ለመፈረም የማይችል ሰው በጽሕፈት ፊርማው ፋንታ የጣት ምልክት መተካት ይችላል፡፡

(3) የዕውራን ወይም የመሐይምናን ፊርማ የጣትምልክት ፊርማ የነሱ ፊርማ መሆኑን ውል አዋዋይ ሹም ወይም አንድ ፈርድ ጸሓፊ ወይም
አንድ ዳኛ በሥራቸው ላይ ሆነው ያረጋገጧቸው ካልሆነ አያስገድዳቸውም፡

ቊ 1729፡፡ ምስክሮች (1) ችሎታ፡፡

(1) በዚህ ሕግ ወይም ተዋዋዮች በተዋዋሉት ውል ምስክሮች እንዲኖሩ የተባለ ሲሆን ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ምስክሮቹ
አካለ መጠን ያደረሱና ያልተከለከሉ እንዲሆኑ አስፈላጊ ነው፡፡

(2) የሰዎቹ ጾታ ወይም ዜግነት ምስክር የመሆንን ችሎታ አያስቀርም፡፡

ቊ 1730፡፡ (2) የምስክሮቹ አግባብ፡፡

(1) የአንድ ውል ምስክሮች አስፈላጊ በሆነ ጊዜ እንዲመሰክሩ የሚፈለጉት ተዋዋዮቹ ውሉን ተስማምተው የፈጸሙ መሆናቸውንና የውሉ
ቃል ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡

(2) ከተዋዋዮቹ ለአንዱ ዋስ ነን ብለው ገልጸው ውል የገቡ ካልሆነ በቀር ምስክሮቹ ተዋዋዮቹ ግዴታቸውን እንዲፈጽሙ የዋስትና አላፊነት
የለባቸውም፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
የውሎች ውጤት፡፡
ቊ 1731፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) በሕጉ አግባብ የተቋቋሙ ውሎች ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ ናቸው፡፡

(2) በውል የማይለወጡና አዛዥ የሆኑ የሕግ ቃሎች እንደተጠበቁ ሆነው በውሉ ውስጥ የሚገባው ቃል ተዋዋዮቹ የተስማሙበት ነው፡፡

(3) ተዋዋዮቹ እንዳይፈጸምባቸው በማድረግ ያስቀሯቸው ባልሆነበት መጠን ወይም በውል እንዳይለወጥ የሚያዝ ሕግ ባለ ጊዜ የዚህ
አንቀጽ ድንጋጌዎች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

ክፍል 1፡፡
ስለ ውል ትርጒም፡፡
ቊ 1732፡፡ በቅን ልቡና ውሎችን ስለ መተርጐም፡፡
በተዋዋዮቹ መካከል ሊኖር የሚገባውን የቅንነትንና የመተማመንን ግንኙነት መሠረት በማድረግና በጒዳዮቹ ውስጥ ያለውን ልማዳዊ
ሥርዐት በመከተል ውሎች በቅን ልቡና ሊተረጐሙ ይገባል፡፡

ቊ 1733፡፡ የትርጒሙ ወሰን፡፡

ውለታዎች ግልጽ በሆኑ ጊዜ ግልጽ ሆኖ ከሚሰማው በመራቅ የተዋዋዮቹ ፈቃድ ምን እንደነበረ ዳኞች ለመተርጐም አይችሉም፡፡

ቊ 1734፡፡ የተዋዋዮቹ ሐሳብ አንድነት፡፡

(1) የውሉ ቃል የሚያሻማ በሆነ ጊዜ የተዋዋዮቹ ሐሳብ ምን እንደነበረ ለማወቅ መፈለግ ይገባል፡፡

(2) ስለዚህም ተዋዋዮቹ ውላቸውን ከመዋዋላቸው አስቀድሞ ወይም ከተዋዋሉ በኋላ የነበሩበትን ሁኔታ ማመዛዘን ያስፈልጋል፡፡

ቊ 1735፡፡ ጠቅላላ አነጋገር፡፡

በውሉ የተገለጠው አነጋገር ምንም ጠቅላላ አነጋገር ቢሆን ውሉ የሚጸናው ተዋዋዮቹ ሊዋዋሉበት የፈለጉ መስሎ በሚታየው ነገር ብቻ
ነው፡፡

ቊ 1736፡፡ የውል ቃሎችን እርስ በርሳቸው ስለ መተርጐም፡፡

(1) በውሉ መሠረት ለያንዳንዱ ክፍል የሚገባውን ትርጒም በመስጠት የውል ቃሎች ሁሉ አንደኛው ክፍል በአንደኛው አነጋገር
ይተረጐማሉ፡፡
(2) ሁለት ፍቺ ለሚያሳዩት ውለታዎች ትርጒም የሚሰጠው፤ ለውሉ ጒዳይ ይበልጥ በሚስማማው አኳኋን ነው፡፡

ቊ 1737፡፡ ውጤት ያለው ትርጒም፡፡

አንድ ስምምነት ሁለት ፍቺ የሚያመጣ ሲሆን መቀበል የሚገባው ፍሬ ነገር ሊሰጥ ከማይችለው አኳኋን ይልቅ ተጨባጭ ውጤት ሊሰጥ
በሚችለው አኳኋን ነው፡፡

ቊ 1738፡፡ ለባለዕዳው ምቹ የሆነ ትርጒም፡፡


(1) የውሉ አኳኋን የሚያጠራጥር ሲሆን የሚተረጐመው በውሉ አስገዳጅ የሆነው በሚጠቀምበት ሁኔታ ሳይሆን በውሉ ተገዳጅ ለሆነው
ሰው ምቹ በሚሆንበት አኳኋን ነው፡፡

(2) ቢሆንም በጠቅላላው ስምምነት፤ በውል ዐይነት፤ ወይም ለውል ፎርም ተመልክተው የሚገኙት ውለታዎች በአንደኛው ወገን ተዋዋይ
ብቻ የተሠሩ ሲሆኑ የሚተረጐሙት እንዲቀበልና እንዲፈቅድ ለተጠየቀው ለውል ተቀባዩ ጥቅም ምቹ በሚሆንበት አኳኋን ነው፡፡

ቊ 1739፡፡ ያለ ዋጋ ስለሚደረግ ውል፡፡


ተዋዋይ የተቀበለው ግዴታ በቀላል አኳኋን የሚተረጐምለት የተቀበለው ውል ጥቅም ለማግኘት ያልተደረገ መሆኑ ሲታወቅ ነው፡፡

ክፍል 2፡፡
ስለ ውሎች አፈጻጸም፡፡
ቊ 1740፡፡ የውሉን ግዴታ መፈጸም የሚገባው ማን እንደሆነ ስለ ማወቅ፡፡

(1) ከውሉ ዐይነት የተነሣ ለባለገንዘቡ ጥቅም፤ ግዴታውን ባለዕዳው እንዲፈጽመው የሆነ እንደሆነ፤ ወይም በዚህ ዐይነት እንዲደረግ ግልጽ
የሆነ ስምምነት እንዳለ፤ ባለዕዳው የዚህን ግዴታ እርሱ ራሱ መፈጸም አለበት፡፡

(2) በሌለው ጊዜ ሁሉ ግዴታውን እንዲፈጽምለት ከባለዕዳው ሥልጣን የተቀበለ ወይም ስለ ባለዕዳው ሆኖ ግዴታዎችን እንዲፈጽም
በፍርድ ወይም በሕግ የተፈቀደለት ሌላ ሦስተኛ ወገን የተባለውን ግዴታ ሊፈጽም ይችላል፡፡

ቊ 1741፡፡ የገንዘቡ መከፈል ለማን እንደሚገባው፡፡

የሚከፈለው ለባለገንዘቡ ወይም ከባለገንዘቡ ሥልጣን ለተቀበለ ወይም ስለ ርሱ ሆኖ እንዲቀበልለት በፍርድ ወይም በሕግ ለተፈቀደለት
ሰው መከፈል አለበት፡፡

ቊ 1742፡፡ ስለ ባለገንዘቡ ችሎታ ማጣት፡፡

ባለገንዘቡ ገንዘቡን ለመቀበል ችሎታ ያልነበረው ሆኖ ሲገኝ ባለዕዳው የከፈለው ገንዘብ፤ ለባለገንዘቡ ጥቅም መዋሉን ካላስረዳ የባለዕዳው
መክፈል ዋጋ የሌለው ይሆናል፡፡

ቊ 1743፡፡ የመቀበል መብት፤ ለሌለው ሰው ስለ መከፈል፡፡

(1) ስለ ባለገንዘቡ ሆኖ ለመቀበል ሥልጣን ለሌለው ሰው የተደረገ አከፋፈል የሚጸናው ባለገንዘቡ አከፋፈሉን ሲያጸድቀው ወይም የከፈሉ
ጥቅም ለባለገንዘቡ የዋለ ሲሆን ነው፡፡

(2) እንደዚሁም በማያጠራጥር አኳኋን ባለገንዘቡን መስሎ ለተገኘ ሰው በቅን ልቡና የሚጸና አከፋፈል ነው፡፡
ቊ 1744፡፡ ባለገንዘቡ መሆኑ አጠራጣሪ ሆኖ ሲገኝ፡፡

(1) ሊከፈለው የሚገባው ሰው ማን እንደሆነ ባጠራጠረ ጊዜ ባለዕዳው ለጠያቂው አልከፍልም በማለት የሚከፈለውን ሀብት ለፍርድ ቤት
በማስረከብ ከዕዳው ነጻ ለመውጣት ይችላል፡፡

(2) ያለውን ክርክር እያወቀ ባለገንዘቦች እኛ ነን ከሚሉት እርግጠኞች ካልሆኑ ላንደኛው ቢከፍል ግን አላፊነቱ የራሱ ነው፡፡

(3) የተጀመረ ሙግት ያለ እንደሆነና ገንዘቡም ሊጠየቅ የሚገባው ከሆነ፤ ከባለገንዘቦች ነን ከሚሉት አንደኛው ሊከፈል የሚገባውን ልክ
ባለዕዳው እንዲያስረክብ ሊያስገድደው ይችላል፡፡

ቊ 1745፡፡ የዕቃው ዐይነት አንድ ስለ መሆን፡፡

ባለገንዘቡ ሊሰጠው ከሚገባው ዕቃ በቀር የቀረበለትን ነገር ዋጋ ከሚቀበለው ዕቃ ዋጋ ጋራ እኩል ወይም የበለጠ ቢሆን እንኳ ያንኑ ካልሆነ
በቀር ሌላ እንዲቀበል አይገደድም፡፡

ቊ 1746፡፡ በከፊል ስለ መክፈል፡፡

(1) ዕዳው በሙሉና ባንድ ጊዜ የሚከፈል እንደሆነ ባለገንዘቡ በከፊል መከፈልን እንቢ ለማለት ይችላል፡፡

(2) አንድ ዕዳ በከፊል ክርክር በተነሣበት ጊዜ ባለገንዘቡ ባለዕዳው ያመነለትን ከዕዳው በከፊል መቀበልን የፈቀደ እንደሆነ ባለዕደው ይህንኑ
ያመነውን ሊከፍለው ይገባል፡፡

ቊ 1747፡፡ በዕዳው ዐይነት መገደድ (1) ተገቢውን ዐይነት መክፈል፡፡

(1) ዕዳው ከራሱ ተፈጥሮ ዐይነት በቀር ሌላ መጠሪያ የሌለው ሲሆን ተቃራኒ ውል ከሌለ በቀር የመመለሱ ምርጫ የሚሰጠው ለባለዕዳው
ነው፡፡
(2) ቢሆንም ባለዕዳው ተመሳሳይ ከሆነው ከመጠነኛው ዐይነት ዝቅተኛ የሆነውን ለማቅረብ አይችልም፡፡

ቊ 1748፡፡ (2) በቂ ያልሆነ ዐይነት ወይም ብዛት፡፡

(1) ግዴታው የሚመለከተው የዕቃውን ዐይነት እንደሆነ፤ ጥቅም ከሌለው ወይም ይኸው መብት እንዲጠበቅለት ካልተዋዋለ በቀር
ባለገንዘቡ የዕቃው ብዛት ወይም ዐይነቱ በውሉ ላይ እንደተመለከተው በፍጹም ትክክለኛ ተመሳሳይ ዐይነት አይደለም በማለት ሊከፈለው
የቀረበለትን አልቀበልም ብሎ እንቢ ለማለት አይችልም፡፡
(2) የተሰጠው ነገር በትክክል እንደ ውሉ ቃል ተመሳሳይ ያልሆነ እንደሆነ፤ የራሱን ፋንታ እንደመጠኑ (በሒሳቡ) ለመቀነስ ወይም
አስቀድሞ ይህንኑ ግዴታውን ፈጽሞ እንደሆነ ለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1749፡፡ የገንዘብ ዕዳ፡፡

(1) ገንዘብን የሚመለከት ዕዳ ሲሆን ዕዳው የሚከፈለው በአገሩ መገበያያ ገንዘብ ነው፡፡

(2) ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን ሊከፍል የሚገባው የገንዘብ ሒሳብ በውሉ ላይ ሊወሰን የሚችለው የዋነኛ ጠባያቱን ዋጋዎች የንግድ
ዕቃዎች ያገልግሎት ዋጋ፤ ወይም ዋጋው ሊወሰን የሚችል የማንኛውንም ሌላ ዐይነት ዕቃ ዋጋ በመመለከት ነው፡፡

ቊ 1750፡፡ ሕጋዊ መገበያያ ያልሆነ ገንዘብ፡፡

ዕዳው በሚከፈልበት ቦታ፤ ውሉ ሕጋዊ ዋጋ የሌለው ገንዘብ ጠቅሶ እንደሆነ ውሉ ቃል በቃል እውነተኛ ዋጋ ወይም ይህንኑ የመሰለ ቃል
ከሌለበት በቀር ዕዳው በሚከፈልበት ቀን ዋጋ ልክ በአገሩ ገንዘብ ሊከፈል ይቻላል፡፡

ቊ 1751፡፡ ሕጋዊ ወለድ፡፡

በውል ያልተወሰነ ወለድ (ጥቅም) ከፋይ የሆነ ሰው በዓመት በመቶ ዘጠኝ ሒሳብ ይከፍላል፡፡

ቊ 1752፡፡ ስለ ተከፈለ ገንዘብ አቀናነስ፡፡ (1) ወጪ ገንዘብ፤ ወለድ፤ ዋና ገንዘብ፡፡

አንድ ተበዳሪ ከዋናው ዕዳ በቀር ወጪና ወለድ እንዲከፍል የሚገባው ሲሆን በከፊል የሚከፍለው ገንዘብ የሚቀነሰው መጀመሪያ ከወጪ
ገንዘቡ፤ ቀጥሎ ከወለዱ፤ በመጨረሻ ከዋናው ገንዘብ ነው፡፡

ቊ 1753፡፡ (2) በሁለቱ ወገኖች የሚደረግ ምርጫ፡፡

(1) ለአንዱ ባለሀብት ብዙ ዐይነት ነገር የሚከፍል ባለዕዳ ዕዳውን በሚከፍልበት ጊዜ ከዕዳዎቹ ውስጥ የትኛውን አስቀድሞ ለመክፈል
እንደሚፈልግ የመግለጽ መብት አለው፡፡

(2) የትኛውን አስቀድሞ ለመክፈል መግለጫ ሳይሰጥ የቀረ እንደሆነ፤ ባለዕዳው ወዲያውኑ ያልተቃወመ ሲሆን ባለገንዘቡ ለየትኛው ዕዳ
ደረሰኝ ለመስጠት እንደሚፈቅድ ለማመልከት ይችላል፡፡

ቊ 1754፡፡ (3) ሕጋዊ የሆነ አቀናነስ፡፡


(1) በደረሰኙ ላይ ምንም ያልተመለከተበት እንደሆነ የተከፈለው ገንዘብ ከዕዳው የሚቀነሰው የመክፈያው ጊዜ ከደረሰው ዕዳ ላይ ነው፡፡
ወይም የመክፈያው ቀን ያልደረሰ ዕዳ እንዳለ የመክፈያው ጊዜ ይበልጥ የተቃረበ ከሆነው ዕዳ ላይ ነው፡፡

(2) የመክፈያው ጊዜ ውሳኔ ባለፈበት ዕዳ መካከል ወይም ጊዜው ለማለፍ በተቃረበ ዕዳ መካከል ክፍያው የሚታሰበው ባለዕዳው
አስቀድሞ ለመክፈል ይበልጥ ከሚጠቅመው ዕዳ ሒሳብ ላይ ነው፡፡

(3) ዕዳዎቹ አንድ ዐይነት የሆኑ እንደሆነ የሚከፈለው ገንዘብ እንደየመጠናቸው ይቀነሳል፡፡

ቊ 1755፡፡ የመክፈያ ስፍራ፡፡

(1) ክፍያው ሊደረግ የሚገባው በውሉ ላይ በተመለከተው ስፍራ ነው፡፡

(2) የመክፈያው ስፍራ በውሉ ላይ ያልተመለከተ ሲሆን ክፍያው የሚፈጸመው ውሉ በተደረገበት ጊዜ ባለዕዳው ይገኝበት በነበረው
በመደበኛ መኖሪያ ቤቱ ነው፡፡

(3) ቢሆንም የሚከፈለው ነገር የተረጋገጠ ግዙፍነት ወይም የተወሰነ አካል ያለው ሲሆን፤ በውሉ ላይ ተቃራኒ ነገር ካልተመለከተበት በቀር
ክፍያው የሚፈጸመው ውሉ በተፈጸመ ጊዜ ይህ በጒዳዩ የተመለከተው ዕቃ ይገኝ በነበረበት ስፍራ ነው፡፡

ቊ 1756፡፡ የመከፈያ ዘመን፡፡

(1) ክፍያው ሊደረግ የሚገባው በውሉ ላይ በተመለከተው ዘመን ነው፡፡

(2) የመክፈያው ዘመን ያልተመለከተ እንደሆነ ክፍያው ወዲያውኑ መፈጸም ይችላል፡፡

(3) ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን የውሉን ግዴታ እንዲፈጽም እንዳስገደደው ክፍያው ወዲያውኑ መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 1757፡፡ ተዋዋዮቹ ባንድነት ስለሚፈጽሙት ግዴታ፡፡

ተዋዋዩ የተዋዋለበትን ግዴታ በውሉ እንደተመለከተው እንዲፈጽምለት የሚጠይቀው ወገን ከውሉ ስምምነት የተነሣ ወይም በውሉ ትርፍ
ጊዜ ካልተሰጠው በቀር እሱም በበኩሉ ያለውን ግዴታ ወዲያውኑ መፈጸም ወይም ለመፈጸም የተዘጋጀ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡

ቊ 1758፡፡ የጉዳት አላፊነትን ስለ ማስተላለፍ፡፡

(1) አንድ ዕቃ የማስረከብ ግዴታ ያለበት ባለዕዳ በውላቸው መሠረት ለተዋዋለው ሰው ከአስረከበበት ቀን ድረስ በዚህ ዕቃ ላይ
የሚደርሰውን የመበላሸትን ወይም የመጥፋትን ጉዳት የሚችለው እሱ ነው፡፡

(2) ስለሆነም ዕቃውን እንዲረከብ ማስጠንቀቂያ ከተደረገለት ጊዜ አንሥቶ የሚደርሰውን ጉዳት የሚችለው ተዋዋዩ ነው፡፡
(3) አንድ ተዋዋይ በአንድ ውል ያለበትን ግዴታውን ሌላው ወገን ተዋዋይ በማያሻማ አኳኋን ውሉን አልፈጽምም ብሎ ያስታወቀው
እንደሆነ ወይም ይኸው ሌላው ወገን ተዋዋይ ዕዳ ለመከፈል የማይችል ሁኗል ብሎ ፍርድ ቤቱ የወሰነ እንደሆነ ተዋዋዩም በበኩሉ
ግዴታውን አልፈጽምም ለማለት ይችላል፡፡

ቊ 1759፡፡ የዚህ መብት ወሰን፡፡

አንደኛው ወገን ተዋዋይ በውሉ መሠረት ግዴታውን ለመፈጸም የተዘጋጀ መሆኑን በማረጋገጥ በቂ የሆነ ዋስትና እንደሰጠ ወዲያውኑ ከዚህ
በላይ ባለው ቊጥር እንደተመለከተው አሳብ ውሉ መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 1760፡፡ ስለ አከፋፈሉ የሚሆን ወጪ፡፡

ስለ ዕዳው አከፋፈል የሚደረገው ሌላ ወጪ የሚታሰበው በውሉ ላይ ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር በባለዕዳው ላይ ነው፡፡

ቊ 1761፡፡ ደረሰኝ፡፡

(1) ዕዳውን የሚከፍል ባለዕዳ ስለ መክፈሉ የደረሰኝ እንዲሰጠው ዕዳውም በሙሉ ተከፍሎ እንደሆን የውሉ ሰነድ እንዲመለስለት ወይም
እንዲሰረዝለት የመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) ክፍያው በሙሉ ያልሆነ እንደሆነ ወይም የውሉ ሰነድ ለባለ ሀብቱ ሌላ መብት የሚያስገኝለት ሲሆን ባለዕዳው አንድ ደረሰኝ
እንዲሰጠው ወይም የከፈለው ገንዘብ ልክ በሰነዱ ላይ እንዲጻፍለት የማስገደድ መብት አለው፡፡

ቊ 1762፡፡ ስለ ሰነድ ማጥፋት፡፡

ባለገንዘቡ ሰነዱ ጠፍቶብኛል ያለ እንደሆነ ሰነዱ ዋጋ የሌለው ስለ መሆኑና ዕዳውም ያለቀለት ስለመሆኑ ማስረጃ እንዲሰጠው ዕዳ ከፋዩ
የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ክፍል 3፡፡
ስለ ውል መሻሻል፡፡
ቊ 1763፡፡ ውሎች በዳኞች የማይሻሻሉ ስለ መሆናቸው፡፡

በሕጉ ላይ ተገልጾ የተመለከተ ካልሆነ በቀር ዳኞች ርትዕን ምክንያት በማድረግ ውሉን ለማሻሻልም ሆነ ለመለወጥ አይችሉም፡፡

ቊ 1764፡፡ የውሉ ሚዛናዊነት ስለ መቅረቱ፡፡


(1) የአፈጻጸሙ ሁኔታ ቢለወጥና ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን የገባበት ግዴታ አስቦት ከነበረው የበለጠ ከባድ ቢሆንበትም እንኳ ውሉ
እንዳለ ጸንቶ ይቈያል፡፡

(2) በመሠረታዊው ስምምነታቸው ወይም በአዲስ ስምምነት የዚህ ዐይነት አጋጣሚ ነገር የሚያስከትለውን ሁኔታ የማሻሻሉ ጒዳይ
የተዋዋዮቹ ወገኖች ነው እንጂ፤ የዳኞች ሥልጣን አይደለም፡፡

ቊ 1765፡፡ የዘመድ ዳኛ ስለ መምረጥ፡፡

የውሉ ስምምነት በሚደረግበት ጊዜ ወይም በኋላ የውሉን የዋጋ ሁኔታ የለወጠውን ነገር በስምምነት ለማሻሻል የሚቻልበትን መንገድ
ለመፈለግ ተዋዋዮቹ ወገኖች ነገራቸውን ወደ ዘመድ ዳኛ እንዲቀርብ ሊስማሙ ይችላሉ፡፡

ቊ 1766፡፡ በተዋዋዮቹ ወገኖች መካከል ያለ ልዩ የመተማመን ግንኙነት፡፡

በተዋዋዮቹ ወገኖች መካከል ስምምነት የታጣ እንደሆነ፤ ተዋዋዮቹ ወገኖች በሥጋ ዝምድና ወይም በጋብቻ ዝምድና የተሳሰረ ግንኙነት
ወይም በመካከላቸው አንድ የመተማመን ልዩ ግንኙነት ያላቸው ከመሆኑ የተነሣ ለተዋዋያቸው በተለይ በርትዕ አስተያየት እንዲያደርጉለት
በሚገደዱበት ጊዜ ዳኞች ውሉን ለማሻሻል ይችላሉ፡፡

ቊ 1767፡፡ ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋራ ስለሚደረግ ውል፡፡

(1) ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋራ የተደረጉ ውሎች ሊሻሻሉ የሚችሉት፤ የውሉ ስምምነቶች የተፈጸሙበት የዋነኛው ስምምነት ሁኔታ
በሕዝባዊ ባለሥልጣን የተለወጠ ሲሆንና ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋራ የተዋዋለው ሰው የውሉን ግዴታ ለመፈጸም የከበደ የገንዘብ
ጉዳት የሚያመጣበት ወይም ለመፈጸም የማይቻል ሲሆን ነው፡፡

(2) ስለ እንደዚህ ያለው ጒዳይ በአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ስለ ተፈጸሙ ውሎች ሁሉ በዚህ ሕግ ስለ አስተዳደር ክፍል መሥሪያ ቤት
ውሎች የተነገሩት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 1768፡፡ እንደ ውሉ ለመፈጸም በከፊል የሚያጋጥም ችግር፡፡

ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን የገባውን ግዴታ ለመፈጸም በከፊሉ የማይቻል ሲሆንበትና ቢሆንም የውሉ ስምምነት ውሳኔ እንዲቀር
ለመፍረድ በቂ ምክንያት ሆኖ ሳይታይ የቀረ እንደሆነ ዳኞች የሚፈጸመውን ግዴታ ለመቀነስ ይችላሉ፡፡

ቊ 1769፡፡ የውሉ ሚዛናዊነት፡፡


ከላይ የተመለከቱት የሁለቱ ቊጥሮች ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ዳኞች ውሳኔ ሲሰጡ የውሉ ሚዛናዊነት አፈጻጸም እንዳይጓደል ጥንቃቄ ማድረግ
አለባቸው፡፡

ቊ 1770፡፡ ስለ ችሮታ የሚሰጥ ጊዜ፡፡

(1) ዳኞች የባለዕዳውን ሁኔታና የነገሩን አግባብ በመረዳት (በመመልከት) ይህንንም ሥልጣናቸውን በሥራ ላይ ሲያውሉ ከፍ ያለ ጥንቃቄ
በማድረግ ለባለዕዳው ግዴታውን ለመፈጸሚያ አስፈላጊ ጊዜ የሚያሻው ሲሆን አንድ የችሮታ ጊዜ ሊሰጡት ይችላሉ፡፡

(2) ይህም ጊዜ በማንኛቸውም ምክንያት ቢሆን ከስድስት ወር የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡

(3) ተዋዋዮቹ ወገኖች ዳኞች የምሕረት ጊዜ ሊሰጡ አይችሉም የሚል ቃል በውላቸው ውስጥ ሊያገቡ ይችላሉ፡፡

ክፍል 4፡፡
ውልን ስላለመፈጸም፡፡
ቊ 1771፡፡ የውል አለመፈጸም ስለሚያስከትለው ነገር፡፡

(1) ከተዋዋዮቹ አንዱ የውሉን ግዴታ ያልፈጸመ እንደሆነ ሌላው ወገን እንደነገሩ አጋጣሚ ሁኔታ ውሉን እንዲፈጽምለት ሊጠይቅ ይችላል፤
ይህም ባይሆን የውሉን መፍረስ ራሱ ሊጠይቅ ወይም ሊገልጽ ይችላል፡፡

(2) በሌላ በኩል ደግሞ የውሉ አለመፈጸም ጒዳይ፤ ጉዳት ስላደረሰበት የጉዳት ኪሣራ እንዲከፈለው ለመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡

ቊ 1772፡፡ የማስጠንቀቅ አስፈላጊነት፡፡

እንደ ውሉ ሳይፈጸምልኝ ቀርቷል በማለት ክርክር ለማቅረብ የሚፈልገው አንደኛው ወገን ተዋዋይ፤ የተዋዋለው ሰው ግዴታውን
እንዲፈጽምለት ለማድረግ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው ያስፈልጋል፡፡

ቊ 1773፡፡ ማስጠንቀቂያ የሚደረግበት ሥርዐትና (ፎርም) ዘመን፡፡

(1) የማስጠንቀቂያ መስጠት ጒዳይ የሚደረገው ይህን እንድትፈጽም የሚል እንደ መጨረሻ ትእዛዝ በሆነ ማስታወቂያ ወይም በሌላ
አድራጎት የባለገንዘቡን አሳብ መግለጫ በሆነ ዐይነት የሚቀርብ የውሉን ፍጻሜ ለማግኘት የሚደረግ ተግባር ነው፡፡

(2) ይህን ለማድረግ የሚቻለው ግዴታው ተጠያቂ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡

ቊ 1774፡፡ ጊዜ ስለ መወሰን፡፡
(1) ባለ ገንዘቡ ለባለዕዳው ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ለግዴታው መፈጸሚያ የሚሆን አንድ የተወሰነ ጊዜ ሊወስንለት ይችላል፤ ይህ የተወሰነው
ጊዜ ካለፈ በኋላ ግን ውሉ በዐይነታው እንዲፈጸም የማይቀበለው መሆኑን ያስታውቃል፡፡

(2) ይህ ጊዜ ሊወሰን የሚገባው በጒዳዩ ዐይነትና በአካባቢው ሁኔታ በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ መጠን ነው፡፡

ቊ 1775፡፡ ማስጠንቀቂያ መስጠት ጠቃሚ የማይሆንበት ጒዳይ፡፡

ማስጠንቀቂያ መስጠት ጠቃሚ የማይሆነው፤


(ሀ) ያለ ማድረግ ግዴታ በሚያጋጥምበት ጊዜ፤

(ለ) ባለዕዳው በውሉ ላይ በተመለከተው መሠረት የውሉን ግዴታ የሚፈጽምበት ጊዜ በውሉ ላይ ተመልክቶ እንደሆነና ይህ የተወሰነው
የግዴታ መፈጸሚያ ዘመን ያለፈ እንደሆነ፤

(ሐ) ባለዕዳው ግዴታውን የማይፈጽም ስለ መሆኑ በጽሑፍ ያስታወቀ እንደሆነ፤

(መ) ማንኛውም ሌላ ተግባር ሳያስፈልግ በውሉ የተወሰነው ጊዜ እንዳለፈ ወዲያውኑ ለባለዕዳው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው
ይቈጠራል የሚል ቃል በስምምነቱ ላይ ተመልክቶበት እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1776፡፡ ውልን በግድ ስለ ማስፈጸም፡፡

(1) ውሉ በግዴታ እንዲፈጸም ሊታዘዝ የሚቻለው፤ እንደ ውሉ ይፈጸምልኝ ብሎ ለሚጠይቀው ተዋዋይ ወገን የተለየ ጥቅም የሚሰጠው
በሆነ ጊዜና አፈጻጸሙም በባለዕዳው ነጻነት ላይ ምንም መሰናከል ሳያደርስበት ሊፈጸም የሚቻል በሆነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ቊ 1777፡፡ የማድረግና ያለ ማድረግ ግዴታ፡፡

(1) ባለዕዳው ሊፈጽመው የሚገባውን የማድረግ ግዴታ፤ ባለገንዘቡ በባለዕዳው ኪሣራ እንዲፈጽም ወይም እንዲያስፈጽም ሊፈቅድለት
ይችላል፡፡
(2) እንዲሁም ባለዕዳው በውል ተገድዶበት የነበረውን ያለማድረግ ግዴታ ተላልፎ የሠራውን ሁሉ ባለገንዘቡ በባለዕዳው ኪሣራ ሊያፈርስ
ወይም ራሱ ሊያስፈርስ ሊፈቅድለት ይችላል፡፡

ቊ 1778፡፡ ዐይነቱ በታወቀ ነገር ስለ መዋዋል፡፡

በውሉ የተገባው ግዴታ ዐይነቱ በታወቀ ነገር ላይ የሆነ እንደሆነ ይህን ለመጠየቅ መብት ያለው ወገን ባለዕዳው እንዲያስረክበው
የተገደደበትን ዐይነቱ የታወቀውን ነገር ያለ አንዳች ችግርና ከፍተኛ ግምት ያለው ወጪ ለማድረግ ሳይገደድ በሌላ ዐይነት ዘዴ ለማግኘት
የሚችል ከሆነ ውሉ በግዴታ እንዲፈጸም ለማስገደድ አይችልም፡፡
ቊ 1779፡፡ የተሰጠውን ነገር አልቀበልም ስለ ማለት፡፡

ባለገንዘቡ ሊመለስለት የቀረበለትን ነገር ሕጋዊ ባልሆነ ምክንያት አልቀበልም ያለ እንደሆነ፤ ባለዕዳው ይህን ነገር በባለገንዘቡ ኪሣራ
ሕዝባዊ በሆነ የዕቃ ማስቀመጫ ቦታ ወይም በመንግሥት መሥሪያ ቤት ሣጥን ወይም ዕቃው ሊከፈልበት ይገባው በነበረበትና ዳኞች
ባዘዙበት በማንኛውም ስፍራ ለማስረከብ መብት አለው፡፡

ቊ 1780፡፡ ተገቢውን ነገር ለማድረግ ስላለመቻል፡፡

ባለገንዘቡ ማን እንደሆነ ለማወቅ ያልተቻለ እንደሆነ ወይም ራሱ ስለ መሆኑ የሚያጠራጥር ሲሆን፤ ወይም በባለገንዘቡ የግል ጒዳይ
ምክንያት ለባለገንዘቡ ተገቢ የሆነው ነገር ሊቀርብ (ሊሰጥ) የማይቻል ሲሆንም እንደዚሁ፤ ለባለዕዳው ከዚህ በላይ የተመለከተው መብት
አለው፡፡

ቊ 1781፡፡ ዕቃውን ስለ መሸጥ፡፡

(1) የተዋዋሉበት ነገር ዕቃ ለመበላሸት የሚችል ይበላሻል ተብሎ የሚያሠጋ ሲሆን ወይም ከራሱ ዋጋ ያልተመዛዘነ የጥበቃ ወይም
የማስቀመጫ ዋጋ የሚጠይቅ የሆነ እንደሆነ ባለዕዳው ፍርድ ቤትን አስፈቅዶ ይህን ዕቃ በሐራጅ ሊሸጠው ይችላል፡፡

(2) እንደዚሁም ዕቃው በዕለት ገበያ ተወስኖ የታወቀ ዋጋ ያለው ሲሆን ወይም በነዋሪ ዋጋ ተወስኖ እንደሆነ፤ ወይም ደግሞ በሐራጅ
ለመሸጥ ከሚጠየቀው ዋጋ የሚበልጥ ተመዛዛኝ ያልሆነ ወጪ የሚያስፈልገው ዝቅተኛ ዋጋ የሆነ እንደሆነ ባለዕዳው የፍርድ ቤትን ፈቃድ
ጠይቆ ዕቃውን አስማምቶ ለመሸጥ ይችላል፡፡

(3) እንዲህም ሲሆን የዕቃውን ሽያጭ ዋጋ ለመንግሥት መሥሪያ ቤተ ሣጥን ማስረከብ ይገባዋል፡፡

ቊ 1782፡፡ ማስረከብ የሚጸናበት፡፡

ያስረከበው ዕቃ ወይም ዋጋ ትክክለኛ መሆኑ በዳኞች ከተረጋገጠለትና ባለዕዳውም ይህንኑ በደንብ ካስረከበ ከግዴታ ነጻ ይሆናል፡፡

ቊ 1783፡፡ ያስረከበውን ዕቃ መልሶ ስለ መውሰድ፡፡

(1) ያስረከበውን ነገር ተገቢ ባለዋጋ መሆኑ ከታወቀለት በኋላም ቢሆን ይህን ያስረከበውን ነገር ባለገንዘቡ የሚቀበለው መሆኑን ካላስታወቀ
ባለዕዳው አስረክቦት የነበረውን ነገር ወይም ዋጋውን መልሶ ሊወስድ ይችላል፡፡

(2) ይህ በሆነ ጊዜ ዕዳው እንደገና በባለዕዳው ላይ ይመለስበታል፡፡

(3) ባለዕዳው አስረክቦት የነበረው ነገር ወይም ዋጋው ትክክል መሆኑ በዳኞች ከታወቀ በኋላ፤ ቀድሞ በዋስትና አላፊነት ውስጥ ገብተው
የነበሩትን ዋሶች አላፊነት እንደገና አያገኛቸውም፡፡
ቊ 1784፡፡ ውልን በፍርድ ስለ መሰረዝ፡፡

በተወሰነው ጊዜ ግዴታዎቹን ያልፈጸመ እንደሆነና ወይም የፈጸማቸው ሙሉ ወይም ፍጹም ባልሆነ አኳኋን እንደሆነ ዳኞቹ በአንደኛው
ወገን ጠያቂነት ውሉን ሊያስቀሩት ይችላሉ፡፡

ቊ 1785፡፡ ቅን ልቡና፡፡

(1) ዳኞቹ ውሳኔ ለመስጠት የተዋዋዮችን ጥቅምና ለቅን ልቡና የሚያስፈልገውን ነገር መሠረት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

(2) በውሉ ላይ ዐይነተኛ የሆነ ውል መጣስ ካልተደረገ በቀር ዳኞች ውሉ እንዲፈርስ አይበይኑም፡፡

(3) እንዲሁም የውሉ መሠረታዊ ነገሮች ካልተነኩና በዚሁም ምክንያት ጠያቂው ይህን የመሰለው ነገር ይሆናል ቢል ኖሮ ተዋዋዩ
ካለመፈጸሙ የተነሣ ውሉ በሚገኝበት ሁኔታ ውሉን የማይዋዋል መሆኑ በአእምሮ ግምት ሊገለጽ የሚቻል በሆነ ጊዜ አፈጻጸሙ በዚሁ
ዐይነት ነው፡፡

ቊ 1786፡፡ በአንድ ወገን ብቻ የሚደረግ የውል ማፍረስ፡፡ (1) የውል ማፍረሻ የሚሆኑ የውል ቃሎች፡፡

በአንድ ውል ውስጥ ውልን የሚያፈርሱ የስምምነቶች ቃል ተገልጾ ከተጻፈበትና የዚሁም ስምምነት አፈጻጸም ጒዳይ ተሟልቶ ከተገኘ
አንደኛው ተዋዋይ ውሉ ፈርሷል ሲል ለመግለጽ ይችላል፡፡

ቊ 1787፡፡ (2) ቊርጠኛ የሆነ የውል መፈጸሚያ ጊዜ፡፡

በውሉ ላይ አንድ ግዴታ መፈጸሚያ ሆኖ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ወይም ማስጠንቀቂያ በተሰጠበት ጊዜ በአእምሮ ግምት ይበቃል ተብሎ
በተሰጠው ቀን ወይም ደግሞ በዳኛ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ከተዋዋዩ አንደኛው ወገን የገባውን ግዴታ ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ፤
ውሉ ይፍረስልኝ የሚለው ወገን ይህ ከዚህ በላይ የተነገረው የማፍረስ መብት አለው፡፡

ቊ 1788፡፡ (3) መፈጸም ስላለመቻል፡፡

ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን የገባበትን ግዴታ ለመፈጸም የማይቻለው ሆኖ ከተገኘ ወይም የመፈጸሚያውን ጊዜ ካዘገየ በዚህም ምክንያት
የውሉ መሠረታዊ ስምምነት የተነካ ሆኖ ከተገኘ ያንደኛው ወገን የውል አፈጻጸም ግዴታ ጊዜ ከመድረሱም በፊት ቢሆን እንኳ ውሉ
ይፈጸምልኝ የሚለው ወገን ውሉ እንደፈረሰ ለማስታወቅ ይችላል፡፡

ቊ 1789፡፡ (4) መፈጸምን እንቢ ስለ ማለት፡፡


(1) እንዲሁም ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን ውሉን የማይፈጽም ስለመሆኑ ግልጽ በሆነ መንገድ ያስታወቀው እንደሆነ ከላይ የተመለከተው
የማፍረስ መብት አለው፡፡

(2) ይህ ሲሆን አስቀድሞ አንደኛውን ወገን ከማስጠንቀቅ በፊት የውሉን መሻር መብት ሊሠራበት አይችልም፤ ይህ መብት ተሠርቶበት
እንደሆነ በውሉ ተገዳጅ የሆነው ወገን ማስጠንቀቂያ ከደረሰለት በኋላ በ 05 ቀን ውስጥ በውሉ መሠረት ለመፈጸም ስለመቻሉ በቂ ዋስትና
ያቀረበ እንደሆነ ይህ የውል ማፍረስ መብት ይቀራል፡፡

(3) አንደኛው ወገን ግዴታውን የማይፈጽም መሆኑን በጽሑፍ ካስታወቀ፤ የማስጠንቀቂያ መስጠቱ ጒዳይ አስፈላጊ መሆኑ ይቀራል፡፡

ቊ 1790፡፡ ውልን ባለመፈጸም የተደረገ ጉዳት፡፡

(1) ተዋዋዩ ግዴታውን ባመፈጸሙ ውሉን በግዴታ እንዲፈጽም ወይም እንዲፈርስ ከማስደረጉም በቀር ከነዚሁ ማሻሻያዎች ጋራ አጣምሮ
አንዱ ወገን ለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ መጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ቀጥሎ የተጻፉት ቊጥሮች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ኪሣራውና ልኩ በዚህ ሕግ ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት በሚለው
ምዕራፍ በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት ይወሰናል፡፡

ቊ 1791፡፡ ኪሣራ የሚከፈልበት ጊዜ፡፡

(1) ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን ምንም ጥፋት ባያደርግ እንኳ ያለበትን ግዴታ ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ ይህን ግዴታውን ባለመፈጸሙ
ምክንያት ብቻ የጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(2) ተዋዋይ የውል ግዴታውን ያልፈጸመበትን በቂ ምክንያት ካላስረዳና፤ ይህም ምክንያት ከዐቅም በላይ መሆኑ ካልተረጋገጠለት፤ የውሉ
አለመፈጸም ከሚያመጣው አላፊነት ሊድን አይችልም፡፡

ቊ 1792፡፡ ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል፡፡

(1) ከዐቅም በላይ የሆነ ሊመልሱት የማይቻል ኀይል ደርሷል የሚባለው አንድ ባለዕዳ ባላሰበው ነገር ድንገት ደራሽ ሆኖበት ግዴታውን
እንዳይፈጽም ፍጹም መሰናክል በሆነ ዐይነት የሚያግደው ነገር ባጋጠመው ጊዜ ነው፡፡

(2) በአእምሮ ግምት ባለዕዳው ቀደም ብሎ ሊያስብበት የሚቻል መሆኑ የታወቀ አንድ ድንገተኛ ደራሽ ነገር ወይም ለውሉ አፈጻጸም ከባድ
የሆነ ወጪ በባለዕዳው ላይ የሚደርስበት ቢሆን ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል ነው ተብሎ አይገመትም፡፡

ቊ 1793፡፡ ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል ነው የሚያሰኙ ምክንያቶች፡፡

እንደ ነገሩ ሁኔታ ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል ነው ሊያሰኙ የሚችሉ ምክንያቶች፤
(ሀ) ባለዕዳው አላፊ የማይሆንበት፤ ያልታሰቡና በሌላ ሰው ላይ የሚመጡ ድንገት ደራሽ ነገሮች፤

(ለ) ውሉ እንዳይፈጸም በመንግሥት የሚደረግ ክልከላ፤


(ሐ) እንደ መሬት መናወጽ መብረቅ፤ ማዕበል ይህን የመሳሰለ ፍጥረታዊ መቅሠፍት፤

(መ) የጠላት የውጭ አገር ጦርነትና የአገር ውስጥ ጦርነት፤

(ሠ) የባለዕዳው መሞት ወይም ባልታሰበ ሁኔታ የሚደርስበት ከባድ አደጋ ወይም ጽኑ ሕመም ናቸው፡፡

ቊ 1794፡፡ ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል አለመኖር፡፡

ምን ጊዜም ቢሆን ግልጽ የሆነ ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር፤


(ሀ) በተዋዋዩ ፋብሪካ ቤት ወይም ሥራውን ከሚያከናውንበት ባንደኛው መሥሪያ ቤቱ ቅርንጫፍ ውስጥ የተደረገ የሠራተኞች አድማ
ወይም የመሥሪያ ቤቱ መዘጋት ጉዳት፤

(ለ) ለውሉ አፈጻጸም አስፈላጊ የሆነው ዋነኛ ጠባይ ያለው ዕቃ ዋጋ መወደድ ወይም መርከስ፤

(ሐ) ባለዕዳው ያለበትን የግዴታ አፈጻጸም ወጪ የሚያከብድበት የአዲስ ሕግ መውጣት፤


ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል ነው አያሰኝም፡፡

ቊ 1795፡፡ ጥፋት መደረጉን ስለ ማስረዳት፡፡

አንደኛው ወገን ሁለተኛውን ወገን ግዴታውን አልፈጸመልኝም ብሎ ኪሣራ ለማግኘት የሚችለውና የተዋዋዩን ጥፋት ለማረጋገጥ
የሚያስፈልገው፤
(ሀ) ባለዕዳው ለተዋዋዩ አንድ የተወሰነ ፍጻሜ ሊያስገኝለት ለዚህም እርግጠኛ ነኝ ሳይል የሚችለውን ያህል ብቻ ለማድረግ ውል የገባ
እንደሆነ፤
(ለ) ሕግ በአንድ በተወሰነ የውል ልዩነት ለይቶ ይህን ደንብ የጠቀሰ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1796፡፡ ከባድ ጥፋት፡፡

ውሉ ለአንደኛው ተዋዋይ ጥቅም ብቻ ተደርጎ እንደሆነ ውሉ ባልተፈጸመ ጊዜ ሁለተኛው ወገን ኪሣራ ለመክፈል የሚገባው ከባድ የሆነ
ጥፋት አድርጎ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 1797፡፡ ለተዋዋዩ ስለ ማስታወቅ፡፡

(1) ባለዕዳው ግዴታውን ለመፈጸም የሚከለክለውን ምክንያት ለተዋዋዩ ወዲያውኑ ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ተዋዋዩ በጊዜው ማስታወቂያ ደርሶት ኖሮ ቢሆን ጉዳት እንዳይደርስበት አስፈላጊውን ለማድረግ ይችል ስለነበረ፤ ግዴታውን
ባለመፈጸሙ በተዋዋዩ ላይ ለደረሰው ጉዳት ባለዕዳው ኀላፊ ይሆናል፡፡
ቊ 1798፡፡ የማስጠንቀቂያ ውጤት፡፡

ለባለዕዳው ማስጠንቀቂያ ከደረሰው፤ ውሉ ያልተፈጸመበት ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል ምክንያት ቢሆንም ኪሣራ መታሰቡ አይቀርም፡፡

ቊ 1799፡፡ ደንበኛው የኪሣራ አቈራረጥ፡፡

(1) የሚከፈለው ኪሣራ የሚታሰበው አእምሮ ያለው ሰው ውሉ ባለመፈጸሙ ይደርሳል ብሎ በሚገምተው አስተያየት ልክ ነው፡፡

(2) በዚህ አኳኋን የውሉ መሠረቶች ናቸው ተብለው የሚያዙት የውሉን ዐይነት መመልከት ብቻ ሳይሆን የተዋዋዮቹን የሞያ ሥራ ከዚህ
በፊት የነበራቸውን ግንኙነት፤ ባለዕዳው የሚያውቃቸውን ሁኔታዎችና ማንኛዎቹንም አጋጣሚ ሁኔታዎች ሁሉ በመመልከት ነው፡፡

ቊ 1800፡፡ ዝቅተኛ ጉዳት፡፡

ባለገንዘቡ ከጠየቀው ዝቅ ያለ ጉዳት ያገኘው መሆኑን ባለዕዳው ያስረዳ እንደሆነ ኀላፊነቱ በዚሁ ጉዳት ልክ ነው፡፡

ቊ 1801፡፡ ከፍተኛ ጉዳት፡፡

(1) ባለገንዘቡ ውል ሲያደርግ ጉዳቱን ይበልጥ የሚያከብዱትን ልዩ ልዩ ምክንያቶች ለባለዕዳው አስቀድሞ ያስታወቀ እንደሆነ ኪሣራው
ባለገንዘቡ በደረሰበት እርግጠኛ ጉዳት ልክ ይሆናል፡፡

(2) የአፈጻጸሙ ጒድለት ባለዕዳው ለመጉዳት ሲል ባደረገው ነገር ወይም ጒልህ በሆነ ቸልተኛነት ወይም ከባድ በሆነ ጥፋት ምክንያቶች
የሆነ እንደሆነ ለባለገንዘቡ የሚገባው ኪሣራ በደረሰበት እርግጠኛ ጉዳት ልክ ይሆናል፡፡

ቊ 1802፡፡ የጉዳት ኪሣራን የመቀነስ ግዴታ፡፡

(1) ውል አልተፈጸመልኝም የሚለው ወገን ውሉ ባለመፈጸሙ ምክንያት የሚደርሰው ኪሣራ ያነሰ እንዲሆን ተገቢ የሆነውን ጥንቃቄ ሁሉ
ማድረግ አለበት፤ ይኸውም ይህ የሚያደርገው ጥንቃቄ አስቸጋሪና ብዙ ወጪ እንዲያደርግ የማያስገድደው ሲሆን ነው፡፡

(2) ይህ ጥንቃቄ በቸልተኛነት ሳይደረግ ቢቀር ውሉን ያልፈጸመው ሰው የሌላውን ወገን ቸልታ መከራከሪያ አድርጎ ኪሣራው
እንዲቀነስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1803፡፡ የገንዘብ ዕዳ፡፡ (1) ጊዜ በማሳለፍ ስለሚከፈል ወለድ፡፡

(1) የገንዘብ ዕዳ፤ እንዲከፍል ማስጠንቀቂያ የደረሰው ባለዕዳ አነስተኛ ወለድ እንዲከፍል በስምምነቱ ቢወሰንም እንኳ በሕግ የተወሰነውን
ወለድ መክፈል አለበት፡፡
(2) በውለታው ውስጥ የበለጠ ወለድ የታሰበ እንደሆነ በዚሁ በከፍተኛው ወለድ መታሰቡ ይቀጥላል፡፡

(3) ባገንዘቡ ምንም ኪሣራ ባይደርስበትም ወለድ ይገባዋል፡፡

ቊ 1804፡፡ (2) የወለድ ወለድ፡፡

(1) ከባለዕዳው ላይ ያለው ገንዘብ በየጊዜው የሚከፈል ሆኖ ለባለገንዘቡ በየጊዜው የሚገኘው ገቢ የሆነ እንደሆነ ለምሳሌ ኪራይ፤ የርስት
አላባ፤ የዘወትር ጡረታ ወይም ለሕይወቱ የተወሰነ ጡረታ የአንድ ካፒታል ወለድ፤ ይህን የመሰለ ከሆነ ደንበኛው ወለድ የሚታሰበው ክስ
ለአንድ ፍርድ ቤት ከቀረበበት ቀን ጀምሮና ይኸውም ባለዕዳው የአንድ ዓመት ሙሉ ሒሳብ ያለበት እንደሆነ ነው፡፡

(2) ተመላላሽ ሒሳብን የሚመለከቱት ደንቦች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 1805፡፡ የጉዳት ኪሣራ ማቻቻያ፡፡

ባለገንዘቡን ያገኘው ጉዳት ጊዜ በማሳለፍ ምክንያት ከሚከፈለው ወለድ የበለጠ የሆነ እንደሆነ ውሉን በተዋዋሉ ጊዜ ባለዕዳው
ማስጠንቀቂያ ተደርጎለት እንደሆነ ወይም ውለታው ያልተፈጸመበት፤ ባለ ገንዘቡን ለመጉዳት በመፈለጉና በከባድ ቸልታና ወይም በከባድ
ጥፋት ሲሆን ኪሣራውን ባለዕዳው በሙሉ መክፈል አለበት፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
የግዴታዎች መቅረት፡፡

ቊ 1806፡፡ (ሀ) ግዴታን የሚያስቀሩ መደበኛ ምክንያቶች፡፡

ውለታው፤ በተደረገው ስምምነት መሠረት የተፈጸመ እንደሆነ ግዴታው ይቀራል፡፡

ቊ 1807፡፡ (ለ) ሌሎች ምክንያቶች፡፡

እንደዚሁም ግዴታው የሚቀረው፡፡


(ሀ) ግዴታው የተፈጸመበት ውል የተሰረዘ ወይም የፈረሰ እንደሆነ፤

(ለ) ተዋዋዮቹ ወይም አንዱ ወገን ውለታው እንደሚፈቀድለት እንዲያልቅ ያደረጉ እንደሆነ፤

(ሐ) ተዋዋዮቹ ያለውን ግዴታ በሌላ ግዴታ በመተካት ለማደስ (ኖባሲዮን) የተስማሙ እንደሆነ፤

(መ) ባለገንዘቡ ለባለዕዳው ያለበት ሌላ ግዴታና ዋናው ግዴታ የተቻቻሉ እንደሆነ፤

(ሠ) የባለገንዘቡና የባለዕዳው መብት የተቀላቀለ እንደሆነ፤

(ረ) የግዴታውን አፈጻጸም ሳይጠይቅ የተወሰነው ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ነው፡፡


ክፍል 2፡፡
ውሎችን ስለ መሰረዝና ስለ ማፍረስ፡፡
ቊ 1808፡፡ የውልን ማፍረስ ማን ስለሚጠየቅ፡፡

(1) ከውል ፈቃድ መስጠት ጒድለት ወይም ከተዋዋዮቹ ወገኖች በአንደኛው ችሎታ ማጣት የተነሣ ውሉ እንዲሰረዝ ለመጠየቅ የሚችለው
በስምምነት ጒድለት ምክንያት ውሉን ለመሰረዝ እንዲጠይቅ መብት የተሰጠው ወገን ብቻ ነው፡፡

(2) ውሉ የተደረገበት ጒዳይ ወይም ምክንያት ከሕግ ውጭ የሆነ ነው ወይም ለሕሊና ተቃራኒ ነው ወይም ለውሉ አጻጻፍ የተደነገገው
ፎርም አልተጠበቀም ብሎ ከተዋዋዮቹ አንዱ ወይም ማንኛውም ጥቅም ያለው ሰው ውሉ እንዲሰረዝ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 1809፡፡ ውልን ለመፈጸም እንቢ ማለት፡፡

ውሉን ለመፈጸም እንቢ ለማለት የሚፈልገው ወገን፤ ውሉ የማይረጋ መሆኑን በማናቸውም ጊዜ መቃወሚያ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ቊ 1810፡፡ የውል መሰረዝ ክስ፡፡

(1) ውል በማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ ጀምሮ ከሁለት ዓመት በኋላ የማሰረዝ ክስ ለማቅረብ አይቻልም፡፡ ጉዳቱ የደረሰበት አካለ
መጠን ያደረሰ ሰው እንደሆነ ውሉን የማሰረዝ ክስ መቅረብ የሚገባው ውሉ በተደረገ በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፡፡

ቊ 1811፡፡ ውልን ለማጽናት መቻል፡፡

(1) ስምምነቱ የጐደለበት ተዋዋይ፤ ፈቃዱ ሳይሆን የተዋዋለባቸው ሁኔታዎች ከቀሩ በኋላ ውሉን ለማሰረዝ እንዲጠይቅ የተሰጠውን
መብት ለመተው ይችላል፡፡

(2) የማጽናቱም አሠራር መፍረስ እንዲቀርለት የተባለው ውል ስለዚሁ ውል አሠራር ፎርም በተደነገገው አኳኋን መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 1812፡፡ ጥያቄን ስላለመቀበል፡፡

በጉዳት ምክንያት ውሉ እንዲሰረዝ የተጠየቀ እንደሆነ በውሉ የሚጠቀመው ተዋዋይ ጒድለቱን ለመሙያ በሚበቃ ያኽል ተጨማሪውን
ከፍሎ ውሉ እንዲሰረዝ የቀረበውን ጥያቄ ለማቆም ይችላል፡፡

ቊ 1813፡፡ (ሀ) ውለታን በከፊል ስለ ማፍረስ፡፡


ውሉ በመሠረቱ የማይረጋ ነው የሚያሰኝ ካልሆነ በቀር ውሉ የተሳሳተው በአንዳንድ ክፍል ቃላት ሆኖ ሲገኝ የሚሰረዙት እነዚህ የተሳሳቱት
ቃላት ብቻ ናቸው፡፡

ቊ 1814፡፡ (ለ) የማስታወቅ ግዴታ፡፡

(1) ውሉ እንዲቀር እንዲፈርስ ለመጠየቅ ወይም ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ መብት ያለው ሰው ውሉ ፈርሷል ወይም አልፈረሰም የሚል
መሆኑን ሌላው ወገን በጠየቀው ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገልጾ ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ይህኛውም ተዋዋይ በበኩሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልስ ሳይሰጠው የቀረ እንደሆነ ተቃራኒ ማስረጃ ቢኖርም ውሉ እንዲፈርስ መርጧል
ያሰኘዋል፡፡

ቊ 1815፡፡ የመሰረዙ ወይም የመፍረሱ ውጤት፡፡

(1) አንድ ውለታ ሲሰረዝ ወይም ሲፈርስ ተዋዋዮቹ በተቻለ መጠን ውለታ ከመደረጉ በፊት እንደነበሩት ሁኔታ እንዲመለሱ ማድረግ
ይገባቸዋል፡፡
(2) ውለታውን ለመፈጸም የተሠራ ሁሉ ቀሪ ሆኖ በማናቸውም አኳኋን ውጤት የሌለው ይሆናል፡፡

ቊ 1816፡፡ የ 3 ኛውን ወገን መብት ስለ መጠበቅ፡፡

በቅን ልቡና በሆነ ሦስተኛ ወገን የተሠራው ሥራ ውጤት ጠቃሚ ከሆነ እንደረጋ እንዲቀር ይደረጋል፡፡

ቊ 1817፡፡ እንደ ነበር ለማድረግ ስለ አለመቻል፡፡

(1) ውለታውን ለመፈጸም የተሠራውን ሥራ ለማፍረስ የማይቻል ሲሆን ወይም አስቸጋሪ ሆኖ ሲገኝ ወይም ከፍ ያለ መሰናክል የሚያመጣ
ሲሆን እነዚህ የተሠሩት ሥራዎች እንደረጉ እንዲቀሩ ይደረጋል፡፡

(2) እንዲሁም በሆነ ጊዜ ዳኞች ተገቢ መስሎ እንደታያቸው ኪሣራ በማስከፈል ወይም ሌላ ውሳኔ በማድረግ በተቻለ መጠን ተዋዋዮቹን
ውሉ ከመደረጉ በፊት እንደነበሩት ሁኔታ ለማድረግ ይችላሉ፡፡

ቊ 1818፡፡ ስለ ወጪ፡፡

ውሉ ከመፍረሱ ወይም ከመሰረዙ የተነሣ ንብረትን የመመለስ ግዴታ ያለበት ሰው፤ ንብረቱን ለውጦ ወይም በዚሁ ላይ ወጪ አድርጎ
እንደሆነ ከዚህ መለዋወጥ ወይም ወጪ የተነሣ ያሉት መብቶች ወይም ግዴታዎች በዚህ ሕግ ያላገባብ መበልጸግን በሚመለከተው ምዕራፍ
ውስጥ በተወሰኑት ድንጋጌዎች መሠረት ይመራሉ፡፡
ክፍል 2፡፡
ውለታን ስለ ማስቀረትና ዕዳን ስለ መተው፡፡
ቊ 1819፡፡ የሁለቱ ወገኖች መስማማት፡፡

(1) ውልን የተዋዋሉት ወገኖች ተስማምተው ሊያስቀሩት (ሊያፈርሱት) ይችላሉ፡፡

(2) ውሉ ቀሪ ሲሆን ወደፊት የውልን መፈጸም ግዴታ ያስቀራል፡፡

(3) የውሉ መፍረስ ያለፈውን ሁኔታ አይነካም፡፡

ቊ 1820፡፡ በአንድ ወገን በኩል ውልን ስለ ማስቀረት፡፡

(1) ሁለቱም ወገኖች ወይም አንደኛው በማስታወቅ ብቻ ውሉ እንዲቀር ለማድረግ ይፈቀዳል ብለው ለመዋዋል ይችላሉ፡፡

(2) ውሉ ከሁለት በበለጡ ሰዎች መካከል የተደረገ ሲሆን ከተዋዋዮቹ አንዱ ቢወጣ ውሉ እንደ ፊቱ በቀሩት ተዋዋዮች መካከል እንደ ረጋ
ይቀራል ብለው ለመዋዋል ይችላሉ፡፡

ቊ 1821፡፡ ጊዜ ያልተወሰነላቸው ውሎች፡፡

ውሉ የተደረገው ላልተወሰነ ጊዜ እንደሆነ በአንዱ ወገን ብቻ ማስታወቅ ውሉን የማስቀረት መብት ለሁለቱም ወገኖች ይኖራቸዋል፡፡

ቊ 1822፡፡ የሚከበር ጊዜ፡፡

(1) በማስታወቅ ብቻ ውሉን ለማስቀረት የሚፈልገው ወገን በሕግ ወይም በልማድ የተወሰነውን ጊዜ ማክበር አለበት፡፡

(2) ይህ የተወሰነ ጊዜ ባይኖር እንደ ሁኔታው በአእምሮ ግምት የሚበቃው ጊዜ መከበር አለበት፡፡

ቊ 1823፡፡ ልዩ የእምነት ግንኙነት፡፡

በተዋዋዮቹ መካከል ለውሉ አስፈላጊ የሆነው እምነት መረዳዳት አንድ ዐይነት አስተያየት ሲቀርና እንደገና ማገናኘት የማይቻል ሆኖ ሲታይ
አንዱ ወገን ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ዳኞች ውለታውን ለማፍረስ ይችላሉ፡፡

ቊ 1824፡፡ ያለ ጥቅም የተደረገ ውል፡፡


አንድ ውል ለአንድ ተዋዋይ ጥቅም ብቻ ተደርጎ ሌላው ተዋዋይ በቂ መሠረት ያለው ምክንያት አቅርቦ ውሉ እንዲፈርስ ጥያቄ ያቀረበ
እንደሆነ ዳኞች እንደዚሁ ውሉን ለማፍረስ ይችላሉ፡፡

ቊ 1825፡፡ ዕዳን ስለ መተው፡፡

ባለገንዘብ ለባለዕዳው የምፈልግብህ ነገር የለም ብሎ ባስታወቀው ጊዜ ባለዕዳ የሆነ ሰው ለባለገንዘቡ ወዲያውኑ ዕዳ እንዲቀርብልኝ
አልፈቅድም ብሎ ካላስታወቀ በቀር ዕዳው ይቀራል፡፡

ክፍል 3፡፡
ስለ መተካት (ኖባሲዮን)፡፡
ቊ 1826፡፡ መሠረቱ፡፡

ግዴታው ቀሪ የሚሆነው ሁለቱ ወገኖቹ ሌላ አዲስ ግዴታ በጒዳዩ ወይም በምክንያቱ በተለይ አዲስ ግዴታ ሊተኩበት የተስማሙ እንደሆነ
ነው፡፡

ቊ 1827፡፡ የመተካቱ ውጤት፡፡

(1) ከመጀመሪያው ግዴታ ጋራ የሚገኙት ዋስትናዎች፤ ቅድሚያዎች መያዣዎች እንዳሉ እንዲኖሩ ይሆን ዘንድ በግልጽ የተጠበቀ ካልሆነ
በቀር ምትክ ወደሚሆነው የገንዘብ መብት አይተላለፉም፡፡

(2) እንዲሁም በግልጽ እንዲጠበቁ የተደረገ ካልሆነ በቀር ግዴታን ከመተካቱ አስቀድመው የነበሩ ወለዶች ሊጠየቁ አይቻልም፡፡
ቊ 1828፡፡ ግዴታውን የማስቀረት ፍላጎት፡፡
አዲሱን ግዴታ ለመተካት እንዲቻል የመጀመሪያውን ግዴታ በማያጠራጥር አኳኋን የሚያስቀር ፈቃድ እንዲኖር አስፈላጊ ነው፡፡
ቊ 1829፡፡ የምትክ አለመኖር፡፡
ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር ምትክ ሊደረግ የማይቻለው፡፡
(ሀ) ዕዳውን የሚያረጋግጥ አዲስ ሰነድ የተደራጀ እንደሆነ፤

(ለ) ባለዕዳው ባለበት ዕዳ አንድ የሐዋላ ወረቀት ወይም ለመክፈል ቃል የተሰጠበት ወረቀት (ፕሮሚሶሪ ኖት) የፈረመ እንደሆነ፤

(ሐ) ግዴታውን ለመክፈል አዲስ ዋስትናዎች የተደረጉ እንደሆነ ነው፡፡


ቊ 1830፡፡ ተመላላሽ ሒሳብ፡፡
(1) በያይነቱ የሆኑትን ጒዳዮች በተለመደው ሒሳብ በማጻፍ ምትክ አይሆኑም፡፡

(2) ሆኖም ሒሳቡ ከቆመና ከታወቀ ምትክ ተደረገ ይባላል፡፡


(3) ከጉዳዮቹ አንዱ ልዩ ዋስትና ያለው እንደሆነ፤ ባለገንዘቡ ሒሳቡ ከቆመና ከታወቀ በኋላም ሌላ ስምምነት ካልተደረገ በቀር እነዚህን
ዋስትናዎች እንደያዘ ይቀራል፡፡
ክፍል 4፡፡
ስለ ማቻቻል፡፡
ቊ 1831፡፡ የማቻቻሉ መሠረት፡፡
ሁለት ሰዎች አንዱ ለአንዱ ባለዕዳ ሆኖ ሲገኝ፤ ከዚህ እንደሚቀጥለው ደንብ የሁለቱን ዕዳዎች የሚያስቀር ማቻቻል ይደረጋል፡፡
ቊ 1832፡፡ መቻቻያን የማያስደርጉ ሁኔታዎች፡፡
ማቻቻል የሚደረገው ለገንዘብ ዕዳዎች ወይም ተመሳሳይ በሆኑትና የመከፈያቸው ጊዜ በደረሰ ዕዳዎች መካከል ብቻ ነው፡፡
ቊ 1833፡፡ መቻቻያን የማያስደርጉ ሁኔታዎች፡፡
ቀጥሎ ከተዘረዘረው በቀር የዕዳው ምክንያት ማናቸውም ዐይነት ቢሆን ማቻቻያ ይደረጋል፡፡
(ሀ) የዕዳው ዐይነት ልዩ በመሆኑ ለባለገንዘቡ በእጅ የሚከፈል ሲሆን ይኸውም ለባለዕዳውና ለቤተሰቡ ከደመወዙና አስፈላጊውን ወይም
ለቀለቡ የሚሆነውን ዐይነት የመሳሰለ ሲሆን፤

(ለ) ለመንግሥትና ለመሥሪያ ቤቶች የሚከፈል ገንዘብ ሲሆን፤

(ሐ) ባለቤቱ በማይገባ የተወሰደበት እንዲመለስለት ጥያቄ ሲያቀርብ፤

(መ) በአደራ የሰጠውን ዕቃ እንዲመለስለት ሲጠይቅ መቻቻያ ሊደረግ አይቻልም፡፡


ቊ 1834፡፡ በችሮታ የሚሰጥ ጊዜ፡፡
በችሮታ የተሰጠ ተጨማሪ ጊዜ ለማቻቻያ ዕንቅፋት አይሆንም፡፡
ቊ 1835፡፡ የአከፋፈል አቀናነስ፡፡
በአንድ ሰው ላይ ብዙ የሚቻቻሉ ዕዳዎች ሲኖሩበት ስለ ማቻቻሉ አሠራር የአከፋፈል አቀናነስ በዚህ አንቀጽ በምዕራፍ 2 የተመለከተው
ደንብ ይጸናበታል፡፡
ቊ 1836፡፡ የማቻቻያው ውጤት፡፡
ሁለት ዕዳዎች በአንድ ጊዜ ሲኖሩ፤ በአንድነት የሚቻቻሉት ባነስተኛው ዕዳ ልክ ነው፡፡
ቊ 1837፡፡ የሦስተኛ ወገን መብት፡፡
ከዕዳዎች መካከል በአንዱ ላይ ያለውን የሦስተኛውን ወገን መብት በሚጎዳ አኳኋን ማቻቻል አይደረግም፡፡
ቊ 1838፡፡ መቻቻያ እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረብ አስፈላጊ ስለ መሆኑ፡፡
(1) ማቻቻያ የሚደረገው ባለዕዳው እንዲቻቻልለት መፈለጉን ለባለገንዘቡ ሲያስታውቅ ብቻ ነው፡፡

(2) ዳኛው የማቻቻሉን ጒዳይ በራሱ ሥልጣን ብቻ ሊያዝ አይችልም፡፡


ቊ 1839፡፡ መቻቻያን አልፈልግም ስለ ማለት፡፡
ባለዕዳ የሆነ ሰው አስቀድሞ መቻቻልን አልፈልግም ለማለት ይችላል፡፡
ቊ 1840፡፡ በውል የሚደረግ መቻቻል፡፡
(1) በሕግ ከተወሰነውም በቀር መቻቻል በሁለቱ ወገኖች ፈቃድ ሊደረግ ይቻላል፡፡

(2) ተዋዋዮቹ አስቀድመው መቻቻል በምን አኳኋን እንደሚፈጸም መወሰን ይችላሉ፡፡


ቊ 1841፡፡ በፍርድ ቤት ስለሚደረግ ማቻቻል፡፡
(1) አንደኛው ዕዳ የበሰለ ያልሆነ እንደሆነ ዳኞቹ ለጊዜው ክርክር በሌለበት ገንዘብ መጠን ዕዳው እምን ድረስ እንዲቻቻል ሊገልጹ
ይችላሉ፡፡
(2) አንደኛው ዕዳ የበሰለ ባይሆንም ነገር ግን በቅርብ ጊዜ ሊከፈል የማያስቸግር ከሆነ፤ ዳኞች የበሰለውን ገንዘብ ባለዕዳው እንዳይከፍል
አድርገው የአንደኛው ዕዳ የሚከፈልበት ቀን እስኪደርስ ከማስገደድ ሊያቈዩ ይችላሉ፡፡
ክፍል 5፡፡
ስለ መብት መቀላቀል፡፡
ቊ 1842፡፡ የመቀላቀል መሠረት፡፡

የባለዕዳውና የባለገንዘቡ መብት በአንድ ሰው ላይ ሲጠቀለሉ፤ በሕግ ሁለቱን ዕዳዎች የሚያስቀር መቀላቀል ይሆናል፡፡
ቊ 1843፡፡ የሦስተኛ ወገን መብት፡፡
ሦስተኛው ወገን ገንዘብ የሚጠይቅበትን መብቱን በመጉዳት፤ የዕዳ ማቀላቀል ሊደረግ አይቻልም፡፡
ቊ 1844፡፡ የዕዳ መቀላቀል መቅረት፡፡
የዕዳው መቀላቀል ሲቀር ግዴታው እንደገና ይጀመራል፡፡
ክፍል 6፡፡
ስለ ይርጋ፡፡
ቊ 1845፡፡ የይርጋ ጊዜ፡፡

ሕግ በሌለ አኳኋን ካልወሰነ በቀር ውሉ እንዲፈጸም ወይም ካለመፈጸሙ የተነሣ ስለሚደርስ ጉዳት ወይም ውሉ እንዲፈርስ የመጠየቅ
መብት በዐሥር ዓመት ይርጋ ይቀራል፡፡
ቊ 1846፡፡ የይርጋው መነሻ ጊዜ፡፡
የይርጋ ቀን መቈጠር የሚጀምረው ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው፤ ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሠራበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
ቊ 1847፡፡ በየጊዜው የሚሰጥ ገንዘብ፡፡
በየጊዜው የሚሰጥ ገንዘብን የመጠየቅ መብት ይርጋ መቈጠር የሚጀመረው፤ መከፈሉ ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
ቊ 1848፡፡ የጊዜው አቈጣጠር፡፡
(1) የይርጋው መጀመሪያ ቀን ከይርጋው ዘመን ሒሳብ ውስጥ ገብቶ አይታሰብም፡፡

(2) የይርጋው ቀን የሚሞላው ለይርጋው የተወሰነ መጨረሻ ቀን ካለፈ በኋላ ነው፡፡

(3) ምናልባት ይህ ቀን ገንዘቡ በሚከፈልበት ቦታ በሕግ የታወቀ የበዓል ቀን የሆነ እንደሆነ ይርጋው የሚሞላው ከበዓሉ ተከታይ በሆነው
በዓል ባልሆነው ቀን ነው፡፡
ቊ 1849፡፡ ተጨማሪ ገንዘብ፡፡
የዋነኛው ገንዘብ ይርጋ በወለዱና በሌሎቹም ተጨማሪ ገንዘቦች ይጸናል፡፡
ቊ 1850፡፡ መያዣ፡፡
ባለገንዘቡ ለገንዘቡ መያዣ በእጁ ያለው እንደሆነ፤ በይርጋ ገንዘቡ ቀርቷል ተብሎ መቃወሚያ ሳይሆንበት በመያዣው ላይ ያለው መብት
እንዲፈጸምለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 1851፡፡ ይርጋ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች፡፡
ይርጋ የሚቋረጠው፡-

(ሀ) ባለዕዳ ዕዳውን ሲያምን፤ ይልቁንም ወለድ ወይም ከዕዳው ላይ በከፊል ሰጥቶ ሲገኝ ወይም መያዣ ወይም ዋስ የሰጠ እንደሆነ፤

(ለ) ባለገንዘቡ መብቱ እንዲታወቅለት በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ለባለዕዳው አስታውቆ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 1852፡፡ የይርጋው ማቋረጥ ውጤት፡፡
(1) ይርጋው ከተቋረጠበት ጀምሮ እንደገና አዲስ የይርጋ ዘመን መቈጠር ይጀምራል፡፡

(2) ዕዳው በአንድ ማስረጃ ወይም በአንድ ፍርድ የተረጋገጠ እንደሆነ አዲሱ የይርጋ አቈጣጠር ዘመን ሁል ጊዜ ዐሥር ዓመት ነው፡፡
ቊ 1853፡፡ የመታዘዝ ወይም የቤተ ዘመድ ግንኙነት፡፡
(1) ፍርድ ቤቱ ይርጋን አልቀበልም ለማለት የሚችለው ባለገንዘቡ የሚፈልገውን ያልጠየቀበት ምክንያት ባለዕዳውን የመፍራትና የማክበር
ስሜት ኑሮት ለሱም የተቀራረበ ዝምድና ወይም ታዛዥነት ያለው ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡

(2) እንዲህ ሲሆንም ዕዳውን ለመክፈል ዋስ የሆኑት ሰዎች ከኀላፊነታቸው ነጻ ይሆናሉ፡፡


ቊ 1854፡፡ ክፉ ልቡና፡፡
ይርጋ እንዳይቈጠርበት ክፉ ልቡናን መቃወሚያ አድርጎ ለመከራከር አይቻልም፡፡
ቊ 1855፡፡ ተቃራኒ ስምምነቶች፡፡
ሕግ የወሰነው የይርጋ ዘመን እንዲቀር ወይም እንዲለወጥ አስቀድሞ ለመስማማት ወይም ለመዋዋል አይቻልም፡፡
ቊ 1856፡፡ የሞላውን ይርጋ ሰለ መተው፡፡
(1) በይርጋ ተጠቃሚ የሆነው ሰው የሞላውን ይርጋ ለመተው ይችላል፡፡

(2) ዳኞች በገዛ ሥልጣናቸው የይርጋውን ደንብ መከላከያ ለመጥቀስ አይችሉም፡፡


ምዕራፍ 4፡፡
የአንዳንድ ግዴታዎች ወይም የአንዳንድ ውሎች አኳኋን፡፡
ክፍል 1፡፡
ጊዜ፡፡
ቊ 1857፡፡ የተወሰነ ጊዜ፡፡
ውል ከተደረገ ጀምሮ ወይም ከሌላ ማናቸውም ጊዜ ጀምሮ አንድ ግዴታ ወይም አንድ በሕግ ፊት የሚረጋ ነገር መፈጸም ሲያስፈልግ
የጊዜው አወሳሰን ቀጥለው በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት ይወሰናል፡፡
ቊ 1858፡፡ በቀኖች የተወሰነ ጊዜ፡፡
ጊዜው በቀኖች የተወሰነ እንደሆነ ውል የተደረገበት ቀን ሳይታሰብ ዕዳ ለመክፈል የሚገባው በተወሰነው ጊዜ መጨረሻ ቀን ነው፡፡
ቊ 1859፡፡ በሳምንቶች የተወሰነ ጊዜ፡፡
ጊዜው በሳምንቶች የተወሰነ እንደሆነ ዕዳውን መክፈል የሚገባው ውል በተደረገበት ቀን ስም በመጨረሻ ሳምንት ውስጥ በዋለው ቀን
ነው፡፡
ቊ 1860፡፡ በወሮች የተወሰነ ጊዜ፡፡
(1) ጊዜው በወር ወይም በብዙ ወሮች የተወሰነ እንደሆነ ዕዳውን ለመክፈል የሚገባው ውሉ በተደረገበት ቀን በመጨረሻው ወር መጨረሻ
ቀን ነው፡፡

(2) ጊዜውም የተወሰነው እንደ ኤሮፓ አቈጣጠር ከሆነና በመጨረሻው ወር ውስጥ ይህ ቀን ሳይኖር ዕዳ ለመክፈል የሚገባው በተባለው
ወር መጨረሻ ቀን ነው፡፡

(3) ጳጉሜ እንደ ዐሥራ ሦስተኛ ወር አይቈጠርም፡፡


ቊ 1861፡፡ ለወሮች የተወሰነ ጊዜ፡፡
(1) ለመፈጸሚያ የተወሰነው ጊዜ በወሩ መጀመሪያ ወይም የወሩ መጨረሻ የሆነ እንደሆነ፤ በወሩ መጀመሪያ ወይም በወሩ መጨረሻ ቀን
ማለት ነው፡፡

(2) ጊዜው በወር መካከል ከሆነ የወሩ 15 ኛ ቀን ማለት ነው፡፡


ቊ 1862፡፡ የበዓላት ቀኖች፡፡
በሚከፈልበት ቦታ የመክፈያው ቀን ከአንድ የበዓል ቀን ጋራ የገጠመ እንደሆነ በዓል ባልሆነበት በማግሥቱ የዋለው ቀን በደንብ
ይተላለፋል፡፡
ቊ 1863፡፡ የተወሰነ ጊዜ፡፡
(1) አንድ ግዴታ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንዲፈጸም የተደረገ እንደሆነ ባለዕዳው የተወሰነው ጊዜ ሳያልቅ አስቀድሞ ግዴታውን መፈጸም
አለበት፡፡

(2) ግዴታው የሚፈጸምበትን ቀን ለመወሰን መብት የተሰጠው ለሌላው ወገን ተዋዋይ ለመሆኑ ሁኔታው የሚያስረዳ ካልሆነ በቀር
የግዴታውን መፈጸሚያ ቀን በዚሁ ጊዜ መካከል ባለዕዳው ይወስናል፡፡
ቊ 1864፡፡ የተወሰነን ጊዜ ስለ ማርዘም፡፡
ላፈጻጸሙ የተወሰነው ጊዜ እንዲረዝም የተደረገ እንደሆነ ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር አዲሱ ጊዜ የሚቈጠረው በመጀመሪያ
የተሰጠው ጊዜ ካለቀበት ከመጨረሻው ቀን አንሥቶ ነው፡፡
ቊ 1865፡፡ የጊዜው ጠቃሚነት፡፡
በስምምነቱ ወይም በልዩ ሁኔታው ለባለገንዘቡም እንዲጠቅም ተብሎ ካልተደረገ በቀር፤ የጊዜው መሰጠት ሁል ጊዜ ለባለዕዳው ጥቅም
እንደተደረገ ይቈጠራል፡፡
ቊ 1866፡፡ የተወሰነ ጊዜን መጠበቅ ስለ መተው፡፡
(1) በውሉ ውሳኔ ወይም በውሉ ዐይነት ወይም በነገሩ አኳኋን የተዋዋዮቹ ሐሳብ ተቃራኒ ሆኖ ካልተገኘ፤ ባለዕዳው የተዋዋለበት ቀን
ከመድረሱ በፊት ግዴታውን ለመፈጸም ይችላል፡፡

(2) ለዕዳ መክፈያ ከተወሰነው ጊዜ በፊት የተከፈለ ገንዘብ እንደገና አይመለስም፡፡


ቊ 1867፡፡ የባለገንዘቡ መብት፡፡
(1) ፍጻሜው ለራሱ ጥቅም ብቻ ካልተደረገ በቀር የተወሰነው ጊዜ ሳይደርስ ባለገንዘቡ ግዴታው እንዲፈጸም ለመጠየቅ መብት የለውም፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ለባለዕዳው ግዴታውን እንዲፈጽም በአእምሮ ግምት የሚበቃ ጊዜ ይሰጠዋል፡፡
ቊ 1868፡፡ የተወሰነውን ጊዜ የሚያስቀር ምክንያት፡፡
ባለዕዳ ለመክፈል ችሎታ ማጣቱ በፍርድ የተረጋገጠ እንደሆነ፤ ወይም ለባለገንዘቡ የሰጣቸውን ዋስትናዎች በእሱ ምክንያት ያጐደላቸው
እንደሆነ የተወሰነው የጊዜው ጥቅም ይቀርበታል፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ሁኔታ፡፡
ቊ 1869፡፡ የሁኔታ መሠረት፡፡
ለውሉ ጒዳይ የሆነው ግዴታ መኖር ካጠራጣሪ ሁኔታ ጋራ የተያያዘ ሲሆን ውሉ በሁኔታ የተሠራ ነው ይባላል፡፡
ቊ 1870፡፡ ቅን ልቡና፡፡
አንደኛው ወገን የቅን ልቡናን አሠራር በመጣስ ውሉ እንዳይፈጸም ያደረገ እንደሆነ ሁለተኛው ወገን ሁኔታው እንደ ተፈጸመ ለመቈጠር
ይችላል፡፡
ቊ 1871፡፡ ውሉን የማቈያ ሁኔታ፡፡
ተዋዋዮቹ ሌላ ተቃራኒ ሒሳብ ካልገለጹ ውሉ ውጤት ማግኘት የሚጀምረው ሁኔታው ከሚፈጸምበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡
ቊ 1872፡፡ የሚያስቀር ሁኔታ፡፡
(1) ውሉ የሚቀረው፤ ያልተረጋገጠ ነገር ወደ ፊት ሲፈጸም ብቻ ከሆነ የውሉ ውጤት ወዲያውኑ ይጀመራል፡፡

(2) ሁኔታው ሲፈጸም ግን ውሉ ውጤት መስጠቱ ይቀራል፡፡


ቊ 1873፡፡ ተዋዋዮች ስለሚከለከሉት ነገር፡፡
ውሉ በሚፈጸምበት ጊዜ ተዋዋዮቹ የውሉን ደንበኛ አፈጻጸም የሚከለክለውን ተግባር ሁሉ አለማድረግ አለባቸው፡፡
ቊ 1874፡፡ የማስተዳደር ሥራዎች፡፡
ሁኔታው ከመፈጸሙ በፊት ያስተዳደር መብት ያለው ሰው የሠራውን ሁሉ በክፉ ልቡና ሠርቶት እንደሆነ፤ ሁኔታው ከተፈጸመ በኋላ
ኪሣራ ይከፍላል እንጂ፤ በአስተዳዳሪነት መብት የሠራቸው ተግባሮች ጸንተው ይኖራሉ፡፡
ቊ 1875፡፡ የማዘዝ ሥራዎች፡፡
(1) ሁኔታ ያለበት ውል ሲኖር አንደኛው ወገን በማዘዝ ያስፈጸማቸው ሥራዎች በሁለተኛው ወገን ጥያቄ ይሰረዛሉ፡፡

(2) ባለጥቅሞቹ በሚበቃ ጊዜ ውስጥ የተሠራው ሥራ እንዲሰረዝ የሚፈልግ መሆኑን እንዲገልጽ ይህን ሁለተኛውን ወገን ሊጠይቁት
ይችላሉ፡፡

(3) የመሰረዙም ጒዳይ የሚያስከትለው ውጤት የሚወሰነው በዚህ አንቀጽ የውሎችን መሰረዝ ወይም መፍረስ በሚመለከተው ድንጋጌ
ላይ በተነገረው መሠረት ነው፡፡
ቊ 1876፡፡ ፍሬና ትርፍ፡፡
ሁኔታው ከመፈጸሙ በፊት መብት ያለው ሰው እስከዚያ ቀን ድረስ በቅን ልቡና ያገኘው ፍሬና ትርፍ ሁኔታው ከተፈጸመ በኋላም
ይረጋለታል፡፡
ቊ 1877፡፡ የመጠበቂያ እርምጃ፡፡
በሁኔታ የተሰጡት መብቶች አደጋ የሚደርስባቸው ሆኖ ለተዋዋዩ ሲታየው ለሌላ ያለሁኔታ ለተሰጡ መብቶች የሚደረገውን መጠበቂያ
ለእነዚህም ሊያደርግላቸው ይችላል፡፡
ቊ 1878፡፡ ሊፈጸም የማይቻል ከሕግ ውጭ የሆነ ወይም ለሕሊና ተቃራኒ የሆነ ሁኔታ፡፡
የውሉን መኖር የሚያረጋግጠው ሁኔታ የማይቻል ሕገ ወጥ ወይም ለሕሊና ተቃራኒ የሆነ እንደሆነ፤ ለውል ጒዳይ አለመቻል ለውል ጒዳይ
ሕገ ወጥ ስለ ውል ጒዳይ የሕሊና ተቃራኒነት ስለሚሆነው ጒዳይ የሚጸኑት ድንጋጌዎች ለዚህም በተመሳሳይነት ይፈጸማሉ፡፡
ቊ 1879፡፡ ብችል እሠራለሁ ስለ ማለት ሁኔታ፡፡
(1) የሚሠራው ግዴታ በባለዕዳው ፈቃድ ሁኔታ ብቻ እንዲፈጸም ተዋውለው ሲገኝ ግዴታው ፈራሽ ነው፡፡

(2) ውሉ የተደረገው ተገዳጁን ውሉ ባይፈጸምም ማናቸውም ኀላፊነት እንዳያገኘው ሆኖ ሲገኝ፤ ብችል እሠራለሁ ለማለት ሁኔታ
እንደተሠራ ውል ሆኖ ይቈጠራል፡፡
ክፍል 3፡፡
ማማረጫ ያለው ግዴታ፡፡
ቊ 1880፡፡ ማማረጫ ያለው ግዴታ መሠራት፡፡
ባለዕዳው በውለታው ከተመለከቱት ሁለት ዐይነቶች ግዴታዎች አንዱን የፈጸመ እንደሆነ ግዴታውን ፈጸመ ማለት ነው፡፡
ቊ 1881፡፡ ጒዳዩን መምረጥ፡፡
(1) የመምረጥ መብት ተገልጾ ለባለገንዘቡ ወይም ለአንድ ሌላ 3 ኛ ወገን ካልተሰጠ በቀር፤ መርጦ መፈጸም የባለዕዳው ነው፡፡

(2) አንደኛው ወገን ግዴታውን ለመምረጥ ውሉ ሲፈቅድለት ያልመረጠ እንደሆነ እንደ ውሉ እንዲመርጥ ማስጠንቀቂያ ደርሶት ሳይመርጥ
ቢቀር ወዲያውኑ የመምረጡ መብት ለ 2 ኛው ወገን ይሰጣል፡፡
ቊ 1882፡፡ መፈጸም ስላለመቻሉ፡፡
(1) በውለታ ከተመለከቱት ግዴታዎች አንዱን ለመፈጸም የማይቻል ሲሆን፤ ባለዕዳው ቀሪውን ግዴታ መፈጸም አለበት፡፡

(2) የግዴታው አፈጻጸም ያልተቻለው ምርጫ ባልተሰጠው ወገን ጥፋት እንደሆነ ኪሣራ ይከፍላል፡፡
ክፍል 4፡፡
ቃ ብ ድ፡፡
ቊ 1883፡፡ የቃብድ ትርጒም፡፡
አንዱ ወገን ለአንዱ ወገን ቃብድ መስጠቴ በሚያከራክር ሁኔታ ውል መደረጉን ያረጋግጣል፡፡
ቊ 1884፡፡ የውሉ አፈጻጸም፡፡
ቃብድ የተቀበለው ወገን ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር መመለስ ወይም ውሉ ሲፈጸም ከሚገባው ገንዘብ ላይ መታሰብ አለበት፡፡
ቊ 1885፡፡ የውል አለመፈጸም፡፡
(1) ሌላ ስምምነት ከሌለ በቀር ቃብድ የሰጠው ወገን የሰጠውን ቃብድ በመልቀቅ ውለታውን በራሱ ፈቃድ ለማፍረስ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ሌላ ስምምነት ከሌለ በቀር ቃብድ የተቀበለው ወገን የተቀበለውን ቃብድ አጠፌታ በመክፈል ውለታውን ለማፍረስ
ይችላል፡፡
ክፍል 5፡፡
ስለ ኀላፊነት የተጻፈ የውል ቃል፡፡
ቊ 1886፡፡ ኀላፊነትን ስለ ማስፋፋት፡፡
ተዋዋዮቹ በውላቸው ውስጥ ሁሉ ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል ሳይፈጸም ቢቀርም የውሉ አለመፈጸም ለሚያመጣው ጉዳት ኀላፊ እንሆናለን
ብለው አላፊነታቸውን አስፋፍተው ለመዋዋል ይችላሉ፡፡
ቊ 1887፡፡ አላፊነትን በጥፋት ጊዜ ብቻ ስለ መወሰን፡፡
ተዋዋዮቹ በውሉ የሚደርስባቸውን አላፊነት ለመቀነስና አላፊነታቸውም ጥፋት ባደረጉ ጊዜ ብቻ እንዲሆን አድርገው ለመዋዋል ይችላሉ፡፡
ቊ 1888፡፡ ስለ ሠራተኞች አድራጎት፡፡
(1) ውሉ በሠራተኞቻቸው ወይም በረዳቶቻቸው ጥፋት ያልተፈጸመ እንደሆነ ተዋዋዮቹ አላፊ አንሆንም ብለው ለመዋዋል ይችላሉ፡፡

(2) ስለሆነም ይህ ስምምነት የተደረገው፤ በአንደኛው ወገን ሥልጣን ሥራ ውስጥ የሚሠራው ሰው እንዲጎዳ የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 1889፡፡ ስለ መቀጫ ስምምነት (ስለ ገደብ)፡፡


አንደኛው ወገን ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ፤ የሚከፈለውን መቀጮ ተዋዋዮቹ
አስቀድመው ለመወሰን ይችላሉ፡፡
ቊ 1890፡፡ የባለገንዘቡ መብት፡፡
(1) (የገደብ) የመቀጫ ስምምነት በተደረገ ጊዜ ባለገንዘቡ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ የውሉ አፈጻጸም እንዲቀጥል ለማድረግ ይችላል፡፡

(2) ኪሣራው የተወሰነው ለሥራው አፈጻጸም መዘግየት ብቻ ወይም ለተጨማሪ ግዴታዎች አለመፈጸም ካልሆነ በቀር ባለገንዘቡ ውሉ
እንዲፈጸምና (ገደቡን) መቀጫውንም እንዲቀበል ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ለመጠየቅ አይችልም፡፡
ቊ 1891፡፡ የሚፈጸምበት ሁኔታ፡፡
ባለገንዘቡ መቀጫ (ገደብ) ሊቀበል የሚገባው ውሉ ባለመፈጸሙ ኪሣራ ለመጠየቅ በሚችልበት ጊዜ ሁሉ ነው፡፡
ቊ 1892፡፡ የተረጋገጠ ጉዳት፡፡
(1) ባለገንዘቡ ኪሣራ ባይደርስበትም የተዋዋለው መቀጫ (ገደብ) ሊከፈለው ይገባዋል፡፡

(2) ባለገንዘቡ ከተወሰነው መቀጫ (ገደብ) የበለጠ ኪሣራ ለመጠየቅ የሚችለው ውሉ ያልተፈጸመው ባለዕዳው ባለገንዘቡን ለመጉዳት
አስቦ፤ ጒልህ በሆነ ቸልተኛነት ወይም በከባድ ጥፋት እንዳይፈጸም ያደረገ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 1893፡፡ የተወሰነውን ስምምነት ስለ ማሻሻል፡፡
ግዴታው ባለመፈጸሙ እንዲከፈል የተወሰነውን መቀጫ (ገደብ) ዳኞች ለመቀነስ የሚችሉት ግዴታው በከፊል የተፈጸመ ሁኖ ሲገኝ ነው፡፡
ቊ 1894፡፡ የማፍረስ ውጤት፡፡
(1) የውለታ መፍረስ የመቀጫውን (የገደቡን) ስምምነት ያስቀረዋል፡፡

(2) የመቀጫው (የገደቡ) ስምምነት መፍረስ፤ ውሉን አያፈርሰውም፡፡


ቊ 1895፡፡ በውሉ የሚወሰን ቅጣት፡፡
አንድ ተዋዋይ የገባበትን ግዴታ ባጓደለ ጊዜ 2 ኛው ወገን የተለዩ ቅጣቶችን ያስፈጽምበታል ተብሎ በውሉ ስምምነት ተደርጎ እንደሆነ፤
ማናቸውም ተቃራኒ ስምምነት ቢኖር እንኳ የተባሉትን ቅጣቶች የሚያስከትሉ ነገሮች ተደርገው እንደሆነ ለማረጋገጥ የሚችሉት ዳኞች
ናቸው፡፡
ክፍል 1፡፡
በባለዕዳዎች መካከል ስላለው የማይከፋፈል አንድነት፡፡
ቊ 1896፡፡ አንድነት ስለሚገኝበት ጊዜ፡፡
ተቃራኒ የሆነ የውል ስምምነት ከሌለና በሕግም ላይ የተገለጹ ልዩ ድንጋጌዎች ከሌሉ በቀር የጋራ ባለዕዳዎች በማይከፋፈል አላፊነት
ዕዳውን እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡
ቊ 1897፡፡ ስለማይከፋፈል አላፊነት፡፡
(1) ባለገንዘቡ ስለ ግዴታው አፈጻጸም በሙሉ ወይም በከፊሉ እንደፈቀደው አላፊዎች የሆኑትን ሁሉ ወይም ከነዚህ አንዱን ለማስገደድ
ይችላል፡፡
(2) ዕዳው በሙሉ ተከፍሎ እስካለቀ ድረስ ባለዕዳዎች እያንዳንዳቸው ይገደዳሉ፡፡
ቊ 1898፡፡ ፍርድ ስለ ተሰጠው ነገር፡፡
ከባለዕዳዎቹ መካከል በአንዱ ላይ በፍርድ ቤት ያቀረበው የገንዘብ ክስ ነገር ጠያቂውን በቀሩት ላይ ክስን እንዳያቀርብ አያግደውም፡፡
ቊ 1899፡፡ ዕዳዎቹ እንዲከፈሉ ስለሚደረገው ማስጠንቀቂያ፡፡
ለአንዱ ባለዕዳ የተደረገው ማስጠንቀቂያ (ማስታወቂያ) በሌሎቹ ባለዕዳዎች ላይ ሁሉ ውጤት አለው፡፡
ቊ 1900፡፡ ስለማይረጋ ግዴታ፡፡
(1) ግዴታው በሕግ የተከለከለ ዓላማ ከመሆኑ የተነሣ እንዲሁም ግዴታውን የሚያፈርሱትን ልዩ ምክንያቶች በመጥቀስ ባለዕዳዎች ሁሉ
ባለገንዘቡን ለመቃወም ይችላሉ፡፡

(2) ስለሆነም የመስማማት ጒድለት ያለበት ነው፤ ወይም ችሎታ የሌለው ባለዕዳ የተዋዋለው ነው በማለት ግዴታን ለማፍረስ በሚደረገው
ክርክር ምክንያት ለመከራከር የሚችለው አንድነት ከተበደሩት ባለዕዳዎች በስምምነቱ ጒድለት ተደርጎብኛል የሚለው ወይም ችሎታ
የሌለው ባለዕዳ ብቻ ነው፡፡
ቊ 1901፡፡ ስለ መክፈልና ስለ ይርጋ፡፡
ባለዕዳ የሆኑት ሁሉ ዕዳው በሙሉ ወይም በከፊል ተከፍሏል ወይም በይርጋ ታግዶዋል በማለት ባለገንዘቡን ለመከራከር ይችላሉ፡፡
ቊ 1902፡፡ ዕዳን ስለ መማር፡፡
(1) ባለገንዘቡ የጋራ ባለዕዳዎች ከሆኑት መካከል አንዱን ዕዳውን የማረው እንደሆነ የጋራ ባለዕዳዎች ለሆኑት ሁሉ ለአንዱ የተደረገ
ምሕረት ጠቃሚ ይሆናቸዋል፡፡

(2) ቢሆንም ባለገንዘቡ ዕዳውን የማረው ከጋራ ባለዕዳዎቹ መካከል በተለይ አንዱን ብቻ መሆኑን ለመግለጽ ይችላል፡፡

(3) እንዲህም በሆነ ጊዜ ለሌሎች የጋራ ባለዕዳዎች የዕዳው መማር ጠቃሚ የሚሆናቸው ዕዳውን የተማረው ባለዕዳ በመጨረሻው
ይከፍለው በነበረው ገንዘብ ልክ ብቻ ነው፡፡
ቊ 1903፡፡ ስለ መተካት፡፡
(1) እንደዚሁም ባለገንዘቡ ከጋራ ባለዕዳዎቹ ከአንዱ ጋራ በፊተኛው ዕዳው ምትክ ሌላ አዲስ ዕዳ ለውጦ እንዲተካ የተስማማ እንደሆነ፤
ከዚህ በላይ የተደነገጉት ለዚህም ይጸናል፡፡

(2) ባለገንዘቡ በተለይ ከአንዱ ጋራ መዋዋሉን የገለጸ እንደሆነ የዕዳው መተካት የሚጸናው በዚሁ የጋራ ባለዕዳ ድርሻ ላይ ብቻ ነው፡፡
ቊ 1904፡፡ ስለ ማቻቻል፡፡
ከባለዕዳዎቹ አንዱ ከዋናው ባለገንዘብ ላይ ገንዘብ ጠያቂ ሆኖ ሲገኝ የጋራ ባለዕዳዎች ዕዳው ይቻቻልልናል ለማለት የሚችሉት ዕዳው
የሚቻቻልለት የጋራ ባለዕዳቸው በመጨረሻው ይከፍለው በነበረው ዕዳ ልክ ነው፡፡
ቊ 1905፡፡ መቀላቀል፡፡
ከጋራ ባለዕዳዎቹ መካከል አንዱ ገንዘብ ጠያቂ የሆነ እንደሆነ፤ ኀላፊ ለሆኑት ለሌሎች ባለዕዳዎች ዕዳው የሚቀርላቸው፤ ይህ ገንዘብ ጠያቂ
የሆነው የጋራ ባለዕዳ በመጨረሻው ዕዳውን የሚከፍል እንደሆነ በሚከፍለው ልክ ነው፡፡
ቊ 1906፡፡ ስለ አላፊነት፡፡
(1) የአንድነት ባለዕዳ ከሆኑት መካከል አንዱ በራሱ አድራጎት የሌሎችን ሁኔታ ለማክበድ አይችልም፡፡

(2) የአንድነት ባለዕዳ ለሆኑት ሁሉ መከራከሪያ የሚሆናቸውን ነገር ያልሠራበት እንደሆነ ለጋራ ተገዳጆቹ አላፊ ይሆናል፡፡
ቊ 1907፡፡ የመጨረሻ አከፋፈል፡፡
በውሉ ወይም በሕጉ ተቃራኒ ውሳኔ የሌለ እንደሆነ፤ በአንድነት ባለዕዳ የሆኑት ሰዎች የሚከፍሉትን ዕዳ እያንዳንዳቸው ትክክል
ድርሻቸውን መክፈል አለባቸው፡፡
ቊ 1908፡፡ ስለ ጥያቄ፡፡
(1) ሊከፍለው ከሚገባው በላይ አብልጦ የከፈለ የአንድነት ባለዕዳ፤ አብልጦ ስለከፈለው ገንዘብ ሌሎችን የያንዳንዳቸውን ድርሻ
እንዲከፍሉት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ከአንድነት ባለዕዳዎች መካከል አንዱ ዕዳውን መክፈል ያልቻለ እንደሆነ፤ ዕዳው በየአንዳንዳቸው ላይ ሊደርስባቸው በሚገባው ድርሻ
መጠን ይከፋፈላል፡፡

ቊ 1909፡፡ ስለ መዳረግ (ድርጎ)፡፡

(1) ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው የአንድነት ባለዕዳ የሆነው ሰው ለባለ ገንዘቡ በከፈለው ልክ በባለገንዘቡ መብት ተዳራጊ ይሆናል፡፡

(2) ገንዘቡን ለከፈለው የጋራ ባለዕዳ ማስረጃዎቹንና ወደፊትም ለሚያደርገው ጥያቄ የሚጠቅሙትን አሠራር ለመፈጸም እንዲችል
ባለገንዘቡ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡

(3) ከባለገንዘቡ ተግባር የተነሣ፤ በባለገንዘቡ ስም የአንድነት ባለዕዳው ለመዳረግ ያልቻለ እንደሆነ ባለገንዘቡ በዚሁ ሰው ላይ ለደረሰበት
ጉዳት አላፊ ይሆናል፡፡
ክፍል 2፡፡
በባለገንዘቦቹ መካከል ስላለው አንድነት፡፡
ቊ 1910፡፡ አንድነት ስለሚገኝበት ጊዜ፡፡
ለዚህ ጒዳይ በተለይ በግልጽ የተነገረ ስምምነት ከሌለና እንደዚሁም በሕጉ የተወሰነ ካለሆነ በቀር፤ በባለገንዘቦቹ መካከል አንድነት የለም፡፡
ቊ 1911፡፡ የአንድነት መሠረታዊ ሒሳብ፡፡
(1) አንድነት ካላቸው ባለገንዘቦች የአንዳንዱ ባለዕዳው ዕዳውን በሙሉ እንዲከፍለው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) አንድነት ካላቸው ባለገንዘቦች ለአንዱ የተከፈለ ዕዳ ባለዕዳውን ነጻ ያደርገዋል፡፡

(3) አንድነት ካላቸው ባለገንዘቦች መካከል ከአንዱ ማስጠንቀቂያ ካልደረሰው ባለዕዳው እንደፈቀደ ለአንዱ ወይም ለሌላው ለመክፈል
ምርጫ አለው፡፡
ቊ 1912፡፡ ስለ ይርጋ፡፡
አንድነት ካላቸው ባለገንዘቦች መካከል ለአንዱ የይርጋ ዘመን መቈጠሩን የሚያቋርጥ ተግባር፤ ለሌሎችም ባለገንዘቦች የይርጋውን ዘመን
ያቋርጥላቸዋል፡፡
ቊ 1913፡፡ ዕዳን ስለ መማር፡፡
አንድነት ካላቸው ባለገንዘቦች መካከል አንዱ ባለዕዳውን የማረው እንደሆነ፤ ይህ የተደረገው ምሕረት ባለዕዳውን ለዚሁ ባለገንዘብ
ከሚደርሰው ድርሻ እንጂ፤ ከሌሎቹ ዕዳ ነጻ አያወጣውም፡፡
ቊ 1914፡፡ ስለ መተካት፡፡
እንዲሁም በአንድ ባለገንዘብና በባለዕዳው መካከል ስለሚደረገው የመተካት ስምምነት ከዚህ በላይ የተደነገገው ይጸናል፡፡
ቊ 1915፡፡ ስለ ማቻቻል፡፡
ባለዕዳው አንድነት ካላቸው ባለገንዘቦች መካከል ከአንዱ ገንዘብ ጠያቂ የሆነ እንደሆነ፤ ለሌሎች አንድነት ለአላቸው ባለገንዘቦች
የተቻቻለውን ገንዘብ መከራከሪያ ማድረግ የሚችለው የተቻቻለው ገንዘብ በመጨረሻው ላቻቻለው ባለገንዘብ የሚጠቅም ሲሆንና፤
በዚያውም ልክ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 1916፡፡ የመጨረሻ አከፋፈል፡፡
(1) በውሉ ወይም በሕግ ውስጥ ተቃራኒ የሆነ ውሳኔ ከሌለ አንድነት ያላቸው ባለገንዘቦች ባለዕዳው ከከፈለው ገንዘብ እያንዳንዳቸው
ትክክል ድርሻ መቀበል አለባቸው፡፡

(2) ከድርሻው በላይ የወሰደ ባለገንዘብ በብልጫ ስለወሰደው ነገር ለሌሎቹ ባለገንዘቦች አላፊ ይሆናል፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለማይከፋፈሉ ግዴታዎች
ቊ 1917፡፡ (ሀ) አለመከፋፈል፡፡
አንድነት ለአላቸው ግዴታዎች የተወሰኑት ደንቦች ከጒዳዩ የተነሣ የማይከፋፈል በሆነው ግዴታ ላይም በተመሳሳይነት ተፈጻሚዎች
ናቸው፡፡
ቊ 1918፡፡ (ለ) የባለዕዳዎች ብዙ መሆን፡፡

(1) ግዴታዎቹ በሙሉ የአንድነት አላፊነት ያለባቸው ያልሆኑ እንደሆነና የማይከፋፈሉ ያልሆኑ እንደሆነ ግዴታው በዕዳው ተጠያቂ በሆኑ
ሰዎች መካከል ይከፋፈላል፡፡

(2) እያንዳንድ ባለዕዳዎች በሚደርስባቸው ልክና በውሉ ወይም በሕግ ለተወሰነባቸው ሌላ የዕዳ ድርሻ ይጠየቃሉ (ይያዛሉ)፡፡

(3) ከባለዕዳዎቹ አንደኛው ለዋናው ባለዕዳ አላፊ ሆኖ ለመክፈል ዋስ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ በዋስትናው የሚገደድበት ደንብ የተጠበቀ
ነው፡፡
ቊ 1919፡፡ (ሐ) የገንዘብ ጠያቂዎቹ ብዙ መሆን፡፡

(1) ግዴታው የአንድነት አላፊነት ያለበት ያልሆነና በዐይነቱም ሁኔታ የማይከፋፈል ያልሆነ እንደሆነ በገንዘብ ጠያቂዎች መካከል
ይከፋፈላል፡፡
(2) እያንዳንዱ ገንዘብ ጠያቂ የሚደርሰውን ገንዘብ ብቻና በውል ወይም በሕግ የተወሰነለትን ድርሻ ብቻ እንዲከፈለው ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
ክፍል 4፡፡ ዋስትና፡፡
ቊ 1920፡፡ የዋስትና መሠረት፡፡
ለግዴታው አፈጻጸም ዋስ የሚሆን ሰው ባለዕዳው ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ፤ ለባለገንዘቡ ይህን ግዴታ ሊፈጽም ይገደዳል፡፡
ቊ 1921፡፡ ስለ ባለዕዳው ፈቃድ፡፡
ባለዕዳው ሳይጠይቅ፤ ወይም ሳያውቅም እንኳ ቢሆን ለሱ ዋስ ለመሆን ይቻላል፡፡
ቊ 1922፡፡ ስለ ዋስትና ፎርም፡፡
(1) በሕሊና ግምት ብቻ ዋስትና እንዳለ አይቈጠርም፡፡

(2) ዋስትና ግልጽ መሆን አለበት፤ እንደዚሁም ከተደረገው ውል ወሰን ለማለፍ አይችልም፡፡

(3) ለግዴታው ዋስ የሆነበት የገንዘቡ ልክ በዋስትናው ውል ካልተገለጸ ዋስትናው ፈራሽ ነው፡፡


ቊ 1923፡፡ የዋናው ግዴታ ፈራሽ መሆን፡፡
(1) ዋስትና በማይጸና ግዴታ ላይ ሊኖር አይችልም፡፡

(2) በተዋዋዩ የፈቃድ ጒድለት ወይም ችሎታ የሌለው በመሆኑ ምክንያት በውሉ የመጣው ዕዳ ባለዕዳውን የማያስገድደው ቢሆንም ዋሱ
ባለዕዳው ውል ለመግባት የማይችልበትን ጒድለት እያወቀ ዋስ ሆኖ እንደሆነ፤ ዋስትናው ሊጸናበት ይችላል፡፡
ቊ 1924፡፡ የዋስትና ወሰን፡፡
(1) ዋስነት ባለዕዳው ሊከፍለው ከሚገባው ነገር በላይ ወይም የበለጠ ከባድ ወጪ በሚያመጣ ሁኔታ ሊሆን አይችልም፡፡

(2) ዋስነት ከዕዳው በከፊል ብቻና ያነሰ ወጪ በሚያመጣ ሁኔታ ለመስማማት ይቻላል፡፡

(3) ከዕዳው በላይ ወይም በበለጠ ከባድ ወጪ ሁኔታ የተደረገ ዋስነት፤ በዋናው ግዴታ መጠን ይቀነሳል እንጂ፤ ፈራሽ አይሆንም፡፡
ቊ 1925፡፡ ለወደፊት ስለሚሆን ወይም በአንድ ዐይነት ሁኔታ ስለሚመጣ ግዴታ፡፡
(1) ወደፊት ለሚሆን ግዴታ ወይም በአንድ ዐይነት ሁኔታ ለሚመጣ ግዴታ ዋስ ለመሆን ይቻላል፡፡

(2) ዋስነቱ ለስንት ጊዜ እንደሚረጋ በስምምነቱ ያልተወሰነ ሲሆን የዋናው ዕዳ ተጠያቂነት ካልደረሰ በዚህ ጊዜ ዋሱ ዋስትናውን ሊያስቀር
ይችላል፡፡
ቊ 1926፡፡ ስለ ዕዳ መቅረት፡፡
(1) ዋናው ዕዳ በማናቸውም ምክንያት ቀሪ የሆነ እንደሆነ፤ ዋሱ ነጻ ይሆናል፡፡

(2) ዋናው ባለዕዳ መቃወሚያ አያደርጋቸውም ነበር ለማለት ሳይቻል ባለዕዳው ባለገንዘቡን በሚቃወምባቸው ነገሮች ሁሉ ዋሱ
ሊከራከርባቸው ይችላል፡፡

(3) ነገሩን እያወቀ ውል የገባ ዋስ ዋናው ባለዕዳ ግዴታ የገባው የፈቃድ ጒድለት ወይም ችሎታ የሌለው በመሆኑ ምክንያት ነው በማለት
ውሉ ፍርስ ነው ብሎ መከራከር አይችልም፡፡
ቊ 1927፡፡ ዕዳን በተለዋጭ ስጦታ ስለ መክፈል፡፡
ባለገንዘቡ አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም ማናቸውንም ዕቃ ስለገንዘቡ ወዶ የተቀበለ እንደሆነ፤ የተቀበለው ዕቃ በክርክር
ቢወሰድበትም ዋሱ ነጻ እንደወጣ ይቀራል፡፡
ቊ 1927፡፡ በዋናው ባለዕዳ ግዴታ ላይ ስለሚደረግ መለዋወጥ፡፡
(1) ውሉ ከተደረገ በኋላ በባለገንዘቡና በባለዕዳው መካከል የሚደረግ ሌላ ውል የዋሱን ግዴታ ሊያስብበት አይችልም፡፡

(2) ለዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዝሞ የመስጠትን ጒዳይ በተለይ ዋሱን ሳያስፈቅድ ባለገንዘቡ ለባለዕዳው የመክፈያ ጊዜ አራዝሞ የሰጠ እነደሆነ፤
ዋሱ ነጻ ይሆናል፡፡
ቊ 1929፡፡ ስለ ይርጋ፡፡
በዋናው ባለዕዳ ላይ የተጀመሩ ክሶች ለዋሱ መቈጠር የተጀመረለትን የይርጋ ዘመን ያቋርጡበታል፡፡
ቊ 1930፡፡ ስለ ወለድ፡፡
ዕዳን ለመክፈል ዋስ የሆነ ሰው ዕዳው ወለድ የሚያስከፍል እንደሆነ፤ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር በዋስትናው ውል ውስጥ በተወሰነው
ገንዘብ ልክ ለወለዱም እንደተዋሰ ይቈጠራል፡፡
ቊ 1931፡፡ ስለ ዳኝነት ወጪ፡፡
በሚገባ ጊዜ ውስጥ ማስጠንቀቂያ ደርሶት ለባለገንዘቡ ዕዳውን ካልከፈለ፤ ዋሱ በዋስትናው ውል ውስጥ ከተወሰነው ገንዘብ በላይ በዋሱም
ላይ ለቀረበው ክስ የዳኝነት ወጪ ተገዳጅ ይሆናል፡፡
ቊ 1932፡፡ ዕዳ ስለሚከፈልበት ጊዜ፡፡
(1) ከባለዕዳው መክሠር የተነሣ፤ ዕዳው በቶሎ እንዲከፈል ቢጠየቅም እንኳ ዋናው ዕዳ እንዲከፈል ከተወሰነበት ጊዜ አስቀድሞ ዋሱን
ዕዳውን እንዲከፍል ማስገደድ አይቻልም፡፡
(2) የዋናው ዕዳ አከፋፈል በአንዱ በተቀዳሚ ማስታወቂያ መሠረት የሆነ እንደሆነ ይህ የተባለው ተቀዳሚ ማስታወቂያ ለዋሱም ሊሰጠው
ይገባዋል፡፡

(3) ዕዳው በሚከፈልበት ጊዜ የሚደረገው ማስታወቂያ በዋሱ ላይ መቈጠር የሚጀምረው ማስታወቂያው ከደረሰው ቀን ጀምሮ ነው፡፡
ቊ 1933፡፡ አንድነት ስለሆነ ዋስትና፡፡
(1) ዋሱ፤ አንድነት በሆነ ዋስትና የጋራ ባለዕዳ ወይም በሌላ በማናቸውም ተመሳሳይነት ስም በመሆን፤ ከዋናው ባለዕዳ ጋራ የሚገደድ
እንደሆነ፤ ባለገንዘቡ ለዋናው ባለዕዳ ከመናገሩ በፊት በዋሱ ላይ ክስ ማቅረብና በእጁ ያለውንም መያዣ ለመሸጥ ይችላል፡፡

(2) ከዚህም በቀር፤ በዚህ ምዕራፍ የተመለከቱ ድንጋጌዎች አንድነት በሆነ ዋስትና ላይ ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡
ቊ 1934፡፡ ስለ ተራ ዋስትና፡፡
(1) ከዚህ በላይ ከተመለከተው ቊጥር ውጭ ዋናው ባለዕዳ ግዴታውን የማይፈጽም ካልሆነ በቀር ዋሱ ለባለገንዘቡ እንዲከፍለው
አይገደድም፡፡
(2) ዋሱ፤ በዋስትና የገባበትን ግዴታ እንዲከፍል በባለገንዘቡ ከመገደዱ በፊት ባለገንዘቡ በዋናው ባለዕዳ ሀብቶች ላይ እንዲከራከርና
በተለይም ከባለዕዳው ሀብቶች በመያዣ የተቀበለውን ሽጥ ለማለት ይችላል፡፡
ቊ 1935፡፡ ከዋናው ባለዕዳ ተከራከር የማለት መብት፡፡
(1) ዋሱ እንደተከሰሰ ወዲያውኑ ባለገንዘቡን ከባለዕዳው ጋራ ተከራከር ካላለ በቀር ባለገንዘቡ ከዋናው ባለዕዳ ጋራ ለመከራከር ግዴታ
የለበትም፡፡
(2) የባለዕዳው የመክፈል ችሎታ ማጣት በፍርድ ቤት የተረጋገጠ ሲሆን ባለገንዘቡ ከባለዕዳው ጋራ እንዲከራከር ዋሱ ለመጠየቅ
አይችልም፡፡
ቊ 1936፡፡ መከራከር የሚቻልባቸው ንብረቶች፡፡
(1) ክርክሩን የሚጠይቀው ዋስ ለባለገንዘቡ የዋናውን ባለዕዳ ንብረቶች መምራትና ለዚሁም ክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ አስቀድሞ
ለባለገንዘቡ መስጠት አለበት፡፡

(2) እንዲህም ሲሆን ዋሱ ዕዳው ከሚከፈልበት አገር ውጭ ያሉትን፤ ወይም በክርክር ላይ የሚገኙትን ወይም በመያዣ ተሰጥተው በእጁ፤
የማይገኙትን የዋናውን ባለዕዳ ንብረቶች መምራት አይገባውም፡፡
ቊ 1937፡፡ ክስን ስላለማቅረብ፡፡
ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ቊጥር እንደተባለው የተፈቀዱትን ንብረቶች ዋሱ ካሳየና ለክርክሩም አስፈላጊውን ወጪ ከከፈለ ዋናው ባለ ዕዳ
ሳይከሰስ በመቈየቱ የመክፈል ችሎታ ያጣ እንደሆነ፤ ባለገንዘቡ በተመለከቱት ንብረቶች ዋጋ ልክ ለዋሱ አላፊ ነው፡፡
ቊ 1938፡፡ በባለዕዳው ላይ ስለሚቀርበው ክስ፡፡
(1) ዋናው ግዴታ ተጠያቂ ሲሆን፤ በባለገንዘቡ በስድስት ሳምንቶች ውስጥ ከባለዕዳው ላይ የመብቶቹን አፈጻጸም ይጠይቅ ዘንድ ክስ
እንዲያቀርብ ዋሱ ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) ዋሱ የነገረውን ባለገንዘቡ ያልፈጸመ እንደሆነና፤ ወይም ክሱን በሚገባ ትጋት ያልቀጠለ እንደሆነ፤ ዋሱ ነጻ ይሆናል፡፡
ቊ 1939፡፡ ዕዳን ልክፈል ስለ ማለት፡፡
(1) ዋናው ግዴታ ተጠያቂ ሲሆን፤ ዋሱ የሚከፍለውን ዕዳ እንዲቀበለው ባለገንዘቡን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) ባለገንዘቡ የሚከፍለውን አልቀበልም ያለ እንደሆነ፤ ወይም በዋስትና የተሰጡትን መያዣዎች አልመልስም ያለ እንደሆነ፤ ዋሱ ነጻ
ይሆናል፡፡
ቊ 1940፡፡ ዋሱ ስለሚያቀርበው ጥያቄ፡፡
(1) ባለዕዳው ዐውቆት ወይም ሳያውቀው በተደረገው ዋስትና፤ ዕዳን የከፈለ ዋስ በዋናው ባለዕዳ ላይ ክስን ለማቅረብ መብት አለው፡፡

(2) ይህ ክስ ስለ ዋናው ገንዘብ፤ ስለ ወለዱና ስለ ወጪውም ጭምር ሊቀርብ ይችላል፡፡

(3) ስለሆነም ዋሱ የቀረበበትን ክስ ለዋናው ባለዕዳ ካስታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ባለው ኪሣራ ብቻ ካልሆነ በቀር በሌላ ወጪ በባለዕዳው ላይ
አቤቱታ ለማቅረብ አይችልም፡፡
ቊ 1941፡፡ ስለ ኪሣራ፡፡
(1) ዋሱ ዕዳውን ለባለገንዘቡ የከፈለው በባለዕዳው ጥፋት ወይም፤ ቸልተኛነት፡፡ የሆነ እንደሆነ፤ ከባለዕዳው ላይ ኪሣራ ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
(2) የኪሣራውም ልክ የሚወሰነው በዚህ አንቀጽ በምዕራፍ 2 በተነገረው መሠረት ነው፡፡
ቊ 1942፡፡ የጥያቄ መብት ስለ ማጣት፡፡
(1) ከግዴታው ዐይነት የተነሣ እንዲቀሩ ካልሆነ በቀር ባለገንዘቡን መከራከሪያ እንዲሆኑት ለባለዕዳው የተሰጡት ሁሉ ዋሱ
እንዲሠራባቸው መብትና ግዴታ አለው፡፡

(2) እነዚህን መከራከሪያዎች ሳይሠራባቸው የቀረ ዋስ እንዳይከፍል ለማድረግ የሚችሉትን የተሰጡትን የጥያቄ መብቶች ያጣል፡፡

(3) ስለሆነም በርሱ በኩል ጥፋት ሳይኖር መከራከሪያዎች መኖራቸውን ላለማወቁ ማስረጃ ያቀረበ እንደሆነ ይህ መብት የማጣቱ ደንብ
አይጸናበትም፡፡
ቊ 1943፡፡ ሁለተኛ ስለ መክፈል፡፡
(1) ዋሱ መክፈሉን ሳይነግረው ቀርቶ ባለዕዳው ሁለተኛ የከፈለ እንደሆነ ዋሱ የከፈለውን ከባለዕዳው መጠየቅ አይችልም፡፡

(2) ባለገንዘቡን በማይገባ የተቀበለውን መልስ ብሎ ሊጠይቀው ይችላል፡፡

ቊ 1944፡፡ ስለ መዳረግ (ዳረጎት)፡፡

(1) ዋሱ በከፈለው ገንዘብ ልክ በባለገንዘቡ መብት ተዳራጊ ሆኖ ይገባል፡፡

(2) የዚህን ጥቅም መብት ለመተው አስቀድሞ መዋዋል አይፈቀድም፡፡


ቊ 1945፡፡ የባለገንዘቡ ግዴታዎች፡፡
ባለገንዘቡ የማስረጃ ሰነዶችን እንዲያስረክብ፤ እንደዚሁም አቤቱታን ለማቅረብ ሊረዱት የሚችሉትን ለፍርድ ቤቱ ሥርዐት አስፈላጊ
የሆኑትን ደንቦች እንዲሞላና ስለ ገንዘቡም የተያዙት መያዣዎች እንዲሸጡ ዕዳውን ለከፈለው ዋስ አስፈላጊውን እንዲደረግለት ይገደዳል፡፡
ቊ 1946፡፡ የማይቻል ዳረጎት፡፡
ከባለገንዘቡ ምክንያት የተነሣ ዋሱ በባለገንዘቡ መብቶች፤ መያዣዎች፤ ልዩ መብቶች በተዳራጊነት ሊገባ ያልቻለ እንደሆነ፤ በባለገንዘቡ
ዘንድ ካለበት ግዴታ ነጻ ይሆናል፡፡
ቊ 1947፡፡ የባለዕዳው መክሠር፡፡
(1) ባለዕዳው የከሠረ እንደሆነ ባለገንዘቡ የኪሣራውን ሥራ ለተቀበለው ሰው የገንዘቡን ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡

(2) እንዲሁም ባለገንዘቡ የባለዕዳውን መክሠር እንዳወቀ ይህንኑ ሁኔታ ለዋሱ ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) እነዚህ ድንጋጌዎች ሳይከበሩ ቢቀሩ ባለገንዘቡ የዚሁኑ አሠራር ካለመፈጸሙ የተነሣ ስለሚደርስበት ጉዳት በዋሱ ላይ ያሉትነን
መብቶች በደረሰው ጉዳት ልክ ያጣል፡፡
ቊ 1948፡፡ ለዋሱ ስለሚሰጥ ማረጋገጫ፡፡
ዋሱ ከመክፈሉ በፊት ቢሆንም፤ በባለዕዳው ላይ ክስን ለማቅረብና ከባለዕዳውም የማረጋገጫ ዋስትናዎችን ለመጠየቅ የሚችለው ከዚህ
ቀጥሎ ያሉት ሦስት ነገሮች ባጋጠሙት ጊዜ ነው፡፡

(ሀ) ባለዕዳው ዕዳውን እንዲከፍል ማስጠንቀቂያ ደርሶት እንደሆነ፤

(ለ) የባለዕዳው መክሠር የተገለጸ እንደሆነ፤

(ሐ) ባለዕዳው በደረሰበት ኪሣራ ወይም ከኪሣራው ጥፋት የተነሣ ዋሱ በዋስትና ከገባበት ጊዜ ይልቅ በጣም ከፍ ያለ ጉዳት የሚደርስበት
የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 1949፡፡ የጠለፋ ዋስ፡፡
ስለ ዋናው ዋስ የሚደረገው የጠለፋ ዋስ፤ በዋናው ባለዕዳ ላይ ስለሚቀርቡት አቤቱታዎች መልካም ውጤት አላፊ ነው፡፡
ቊ 1950፡፡ የዋስ አረጋጋጭ፡፡
(1) ለዋናው ባለዕዳ ብቻ ሳይሆን ለዋናው ባለዕዳ ዋስም ዋስ ለመሆን ይቻላል፡፡

(2) ለዋስ አረጋጋጩ ከዋሱ ጋራ ያለውን ግንኙነት፤ የተራው ዋስ ግንኙነት ከባለዕዳው ጋራ እንዳለው ግንኙነት ነው፡፡

(3) በዋናው ባለዕዳና በዋሱ መካከል የሚሆነው የመብት መቀላቀል ባለገንዘቡን ባረጋጋጭ ዋስ ላይ ያለውን የክስ መብት አያስቀርበትም፡፡
ቊ 1951፡፡ ብዙ ሰዎች ዋስ ስለ መሆናቸው፡፡
(1) ለአንድ ባለዕዳ ለአንድ ዕዳ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ዋስ የሆኑ እንደሆነ፤ ለየድርሻቸው እንደ ተራ ዋሶች ለሌሎቹ ዋሶች እንደ አረጋጋጭ
ዋስ ሆነው ይገደዳሉ፡፡

(2) ዋሶቹ ተከታታይ በሆኑ ስምምነቶች ዋስ ሆነው እንደሆነ፤ በሁለተኛው ጊዜ ዋስ የሆነው ሰው ከሱ አስቀድሞ ዋስ ለሆነው ሰው እንደ
አረጋጋጭ ዋስ ተቈጥሮ ይገደዳል፡፡

(3) ከዋና ባለዕዳ ጋራ በመሆንም ሆነ፤ እርስ በርሳቸው በመሆንም ሆነ፤ ዋሶቹ በአንድነት ዋስ የሆኑ እንደሆነ፤ ስለ ሌሎቹ ድርሻ የመጠየቁ
መብት ሳይነካ እያንዳንዳቸው ስለ መላው ዕዳ ተገዳጆች ይሆናሉ፡፡
ምዕራፍ 6፡፡
ከውሉ ጋራ ግንኙነት ስላላቸው ሦስተኛ ወገኖች፡፡
ቊ 1952፡፡ ውሎችን የሚመለከት ጒዳይ ስለሚያስከትለው ውጤት፡፡
(1) በዚህ ሕግ ተለይቶ የተመለከተ ካልሆነ በቀር ውሎች ውጤት ያላቸው በተዋዋሏቸው ወገኖች መካከል ነው፡፡

(2) ከውሉ ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት የተነገሩት የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

(3) እንደዚሁም ስለ እንደራሴነት የተነገሩት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡


ክፍል 1፡፡
ስለ ሌላ ሰው ሆኖ የሚሰጥ ተስፋና የሚደረግ ውል፡፡
ቊ 1953፡፡ የትእዛዝ ቃል አሰጣጥ፡፡
አንድ ውል በሚፈጸምበት ጊዜ ከተዋዋዮቹ አንደኛው ወገን፤ በራሱ ምትክ ሌላ ሰው ተተክቶ በውሉ ላይ የተመለከተውን መብት
እንዲሠራበት ከውሉም የሚመጣውን ግዴታ እንዲፈጽም የማድረግ ችሎታ እንዲኖረው ሊስማማ ይችላል፡፡
ቊ 1954፡፡ ውጤት፡፡
(1) በዚህ ዐይነት የታሰበው የሌላ ሰው በውሉ የመጠቀስ ጒዳይ በሦስት ቀን ውስጥ ተደርጎ እንደሆነ የውሉ ውጤት በእንደራሴነት
ሥልጣን እንደተፈጸመ ሆኖ ይቈጠራል፡፡
(2) ሰውዬውን በውሉ ላይ የመጥቀሱ ጒዳይ በተወሰነው ሦስት ቀን ውስጥ ሳይፈጸም የቀረ እንደሆነ ውሉ ውጤቱን የሚያገኘው በሁለቱ
ወገን ዋና ተዋዋዮች መካከል ነው፡፡

ቊ 1955፡፡ መጪውን እመልሳለሁ (አጠናለሁ) ስለ ማለት፡፡


ሦስተኛው ሰው ተግባሩን የሚፈጽም ለመሆኑ፤ መጪውን እመልሳለሁ ብሎ ግዴታ ለመግባት ይችላል፡፡
ቊ 1956፡፡ እመልሳለሁ ማለት የሚያስከትለው ነገር፡፡
(1) እመልሰዋለሁ የተባለው ሰው ስለ እርሱ የገባለትን ግዴታ ያጸደቀው እንደሆነ፤ እመልሳለሁ ባዩ ነጻ ይወጣል፡፡

(2) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር እመልሳለሁ ባዩ ስለ ውሉ መልካም አፈጻጸም ዋስ አይደለም፡፡

(3) እመልሰዋለሁ የተባለው ሰው ውሉን ያላጸደቀ እንደሆነ፤ የዚህ ውል አለመፈጸም ጒዳይ በአንደኛው ወገን ተዋዋይ ላይ ስለሚያደርሰው
ጒዳት ተጠያቂ የሚሆነው እመልሳለሁ ባዩ ነው፡፡
ቊ 1957፡፡ ለሌላ ሰው ስለ መዋዋል፡፡
በአንድ ውል ውስጥ ከተዋዋዮቹ ወገኖች አንደኛው ለሌላ ሰው ጥቅም ሲል አንድ የውል ግዴታ ልፈጽም እችላለሁ ብሎ ለመዋዋል
ይችላል፡፡
ቊ 1958፡፡ የተዋዋዩ መብት
(1) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ካልኖረ በቀር፤ ስለ ሌላ ሆኖ የተዋዋልው ሰው በውሉ ላይ ለተመለከቱት ውል ሦስተኛው ወገን የመምረጥ
መብት ያልተሰጠው ከሆነ ወይም ይኸው ሦስተኛው ወገን ከውሉ ውስጥ የሚገኘውን ጥቅም የማይፈልግ መሆኑን ካረጋገጠ፤ ከውሉ
የሚገኘውን ጥቅም ለራሱ ለማስቀረት ወይም የዚሁ ውል ስምምነት በሚያስገኘው ትርፍ የሚጠቀም ሌላ አዲስ ሰው ለማቅረብ ይችላል፡፡

(2) በውሉ ስምምነት ተጠቃሚ የሆነው ሰው ይህንን ጥቅም ፈቅዶ የተቀበለ እንደሆነ፤ ተስፋ ሰጪው የውሉን ግዴታ የማይፈጽም ሲሆን
ተዋዋዩ በውሉ አለመፈጸም ምክንያት ሊያገኝ የሚገባው ጥቅም እንዲከፈለው ክርክር የማቅረብ መብት ይኖረዋል፡፡
ቊ 1959፡፡ የባለጥቅሙ ምርጫ፡፡
ለራሱ ጥቅም በውል ስምምነት የተደረገለት ሰው በውሉ ስምምነት መሠረት የመራጭነት መብት የተሰጠው እንደሆነ፤ የዚህን ስምምነት
ጥቅም እንደፈለገው የመቀበል ወይም ያለመቀበል ምርጫ ለማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 1960፡፡ የተዋዋዩ ወራሾች፡፡
(1) ተስፋ ሰጪው፤ በውሉ የገባውን ግዴታ ሊፈጽም የሚገባው፤ ተዋዋዩ ከሞተ በኋላ የሆነ እንደሆነ፤ ተዋዋይ በውሉ እንዲጠቀም
ያመለከተው ሰው እንደ ውሉ ለመጠቀም መፍቀዱን ከገለጸ ተዋዋዩ በሞተበት ጊዜ የተሰጡት መብቶች በተስፋ ሰጪው ላይ ይኖሩታል፡፡

(2) የተዋዋይ ወራሾች ተዋዋዩ በውሉ ትርፍ ሊጠቀም ይችላል ሲል ሟቹ ተጠቃሚውን በማመልከት ቃል የሰጠለትን ሰው ለመለወጥ
አይችሉም፡፡
ቊ 1961፡፡ የተጠቃሚው መብቶች፡፡
(1) ተጠቃሚው የውሉን ስምምነት የተቀበለው ሲሆን፤ በተስፋ ሰጪው ላይ ውሉ የሚያስገኛቸውን መብቶች በማይመለስ አኳኋን
እንደያዘ ይቀራል፡፡

(2) ተስፋ ሰጪው በተዋዋዩ ላይ የሚያገኛቸውን በተለይ የራሱ የሆኑትን መከራከሪያዎች ሰበብ በማድረግ በተጠቃሚው ላይ መቃወሚያ
ሊያደርግበት አይችልም፡፡
ክፍል 2፡፡
የገንዘብ መብትን ስለ ማስተላለፍና ስለ መዳረግ (ዳረጎት)፡፡
ቊ 1962፡፡ የገንዘብን መብት ስለ ማስተላለፍ፡፡
የገንዘብ መብትን ማስተላለፍ በሕግ ወይም በውል ካልተከለከለ ወይም የጒዳዩ ተፈጥሮ ካላገደው በቀር፤ የባለዕዳው ፈቃጅነት አስፈላጊ
ሳይሆን ባለገንዘቡ መብቱን ለሌላ ሦስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ይችላል፡፡
ቊ 1963፡፡ የማስተላለፉ መጠን፡፡
ወደ ኋላ የቀሩ የወለድ ገንዘቦችም ከዋናው ገንዘብ ጋራ እንደተላለፉ ይቈጠራሉ፡፡
ቊ 1964፡፡ ዋቢነት፡፡
(1) የገንዘቡ መብት መተላለፍ የተደረገው በዋጋ የሆነ እንደሆነ፤ አስተላላፊው በሚያስተላልፍበት ጊዜ ስለገንዘቡ መኖር ዋቢ ይሆናል፡፡

(2) በግልጽ ግዴታ ካልገባ በቀር አስተላላፊው ለባለዕዳው መክፈል አላፊ አይሆንም፡፡

(3) የገንዘቡ መብት መተላለፍ ያለዋጋ ሲሆን አስተላላፊው ለገንዘቡ መኖር እንኳ ዋቢ አይሆንም፡፡
ቊ 1965፡፡ የዋቢነት ወሰን፡፡
(1) መብቱን አስተላላፊው በዋቢነት ተገዳጅ በሆነ ጊዜ በመብት ተቀባዩ በኩል የሚገደደው በተቀበለው በዋናው ገንዘብና በወለዱ ልክ
ነው፡፡
(2) ከዚህ በቀር የመብት ማስተላለፊያውን ወጪና በባለዕዳው ላይ ክስ ቀርቦ ምንም ፍሬ ሳያገኝ የቀረውን ለክሱ ኪሣራም መክፈል
አለበት፡፡
ቊ 1966፡፡ መቃወሚያ የሚሆኑ ልዩ ነገሮች፡፡
(1) ባለዕዳው፤ የገንዘቡ ማስከፈል መብት ለሌላ ሰው ተላልፎ መሰጠቱን ባወቀበት ጊዜ በነበረውና ሊያቀርባቸው በሚችለው የመቃወሚያ
ነገሮች መብት አስተላላፊውን ሊቃወም ይችል እንደነበረው ሁሉ መብት ተቀባዩን ሊቃወምባቸው ይችላል፡፡

(2) መብቱን ከሚያስተላልፈው ባለገንዘብ ላይ ባለዕዳው የመክፈያው ጊዜ ያልደረሰ ገንዘብ ያለው እንደሆነ፤ መብቱ ከተላለፈለት ሰው
እንዲቻቻልለት ለመጠየቅ የሚችለው የገንዘቡ መክፈያ ጊዜ መብቱ ከተላለፈ ወዲህ ያልሆነ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 1967፡፡ ባለዕዳው የሚያቀርበው መቃወሚያ፡፡
(1) የዕዳ ማስከፈሉን መብት ለሌላ ሰው የመተላለፉ ጒዳይ በመብት አስተላላፊው ወይም በመብት ተቀባዩ በኩል ለባለዕዳው ከመገለጹ
በፊት በቅን ልቡና ዕዳውን ለመብት ሰጪው አስቀድሞ ከፍሎ እንደሆነ ባለዕዳው በሚገባ ነጻ ይሆናል፡፡

(2) የዚያው የአንዱ ዐይነት ዕዳ ማስከፈል መብት ተከታትሎ ለብዙ መብት ተቀባዮች ተላልፎ የተሰጣቸው እንደሆነ መብቱ ተላልፎ
መሰጠቱን ለባለዕዳው መጀመሪያ ላስታወቁት ሰው ወይም የተረጋገጠ ቀን ባለበት ጽሑፍ እከፍላለሁ ብሎ ባለዕዳው ለተቀበለው ሰው
መክፈል አለበት፡፡

(3) ባለዕዳው መክፈል የሚገባው መብቱ የተላለፈለት ሰው መብቴ የተላለፈልኝ ከሁሉ ቀደምትነት ባለው ቀን ነው ብሎ ለሚከራከረው
ወገን ነው፡፡

ቊ 1968፡፡ ባለገንዘቡ ስለሚሰጠው ዳረጎት (ድርጎ)፡፡

(1) ሦስተኛ ወገን የከፈለውን ገንዘብ ባለገንዘቡ የተቀበለ እንደሆነ በራሱ መብቶች ተዳራጊ ሊያደርገው ይችላል፡፡

(2) የዳረጎቱ ጒዳይ ግልጽ መሆኑና የገንዘቡ መከፈል እንደተደረገ ወዲያውኑ መፈጸም ይገባዋል፡፡

ቊ 1969፡፡ ባለዕዳው የሚሰጠው ዳረጎት (ድርጎ)፡፡


ባለዕዳው፤ የተበደረውን ነገር ለመክፈል ሲል አንድ የተወሰነ ጥሬ ገንዘብ ወይም አንድ ሌላ አላቂ ነገር ተበድሮ እንደሆነ በመጀመሪያ አበዳሪ
የነበረው ባይፈቅድም እንኳ ለዚሁ ለመጀመሪያው አበዳሪ ሰጥቶት በነበረው መብት ይህን በመጨረሻ የተመለከተውን አበዳሪ ለመዳረግ
ይችላል፡፡
ቊ 1970፡፡ የዳረጎት ሁኔታ፡፡
(1) በባለዕዳው ፈቃጅነት የሚደረገው የዳረጎት ጒዳይ የሚጸናው የብድሩ ውል የተደረገበት ዘመን የተረጋገጠ ቀን ያለው ሲሆንና በብድር
የተወሰደው ገንዘብ ለምን እንደተመደበ የተመለከተ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ነው፡፡

(2) እንዲሁም የገንዘቡ ደረሰኝ የተረጋገጠ ቀን እንዲኖረውና የተከፈለውም በመጨረሻ ከተበደረው ገንዘብ ለመሆኑ ግልጽ የሆነ ቃል
ሊመለከትበት ይገባል፡፡

(3) ባለዕዳው ይህን ነገር እንዲጠቅስለት የመጀመሪያውን ባለገንዘብ ከጠየቀው፤ በሚሰጠው ደረሰኝ ላይ ይህን ጠቅሶ ለመጻፍ እንቢተኛ
ሊሆን አይችልም፡፡

ቊ 1971፡፡ ሕጋዊ መዳረግ (ዳረጎት)፡፡


በባለገንዘቡ መብቶች በተከፈለው ገንዘብ ልክ በሕግ የሚተላለፈው ድርጎ፡፡
(ሀ) ከሌሎች ጋራ ወይም ስለ ሌሎች ሆኖ አንድ ዕዳ እንዲከፍል በመገደድ ይህን ዕዳ ከፍሎ የጋራ ባለዕዳዎችን ድርሻ ለመጠየቅ መብት
ላለው ሰው የሆነ እንደሆነ፤

(ለ) የአንድ ንብረት ባለቤት በመሆኑ ወይም በዚህ ንብረት ላይ ልዩ መብት ወይም በቀዳሚነት ባለው መያዣ ወይም በመያዣ መብት
ያለው በመሆኑ ምክንያት በዚሁ ንብረት ላይ በልዩ መብት፤ ወይም በመያዣ መብት (ሞርጌጅ) ወይም መያዣ ላለዉ ባለገንዘብ የከፈለ
እንደሆነ፤
(ሐ) በሌላዎችም በሕግ በተወሰኑ ጒዳዮች የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 1972፡፡ በከፊል የሚደረግ ክፍያ፡፡
(1) ድርጎ መዳረግ ገንዘቡ በከፊል ብቻ የተመለሰለትን ባለገንዘብ ሊጎዳው አይችልም፡፡

(2) ባለገንዘቡ ከተዳራጊው የተቀበለው ገንዘብ በከፊል ከሆነ ላልተከፈለው ለቀሪው ገንዘብ ባለገንዘቡ በመብቶቹ ከተዳራጊው በቀዳሚነት
ሊሠራባቸው ይችላል፡፡
ቊ 1973፡፡ የማስተላለፍ ወይም የዳረጎት ውጤት፡፡
(1) የተዳረገው ባለገንዘብ ወይም የባለገንዘብነት መብት የተላለፈለት ሰው በዕዳው ላይ በተሰጡት ልዩ መብቶች በዋስትናዎች በሌሎችም
ተጨማሪ መብቶች ሊሠራባቸው ይችላል፡፡

(2) ስለሆነም መያዣውን ሰጭ የሆነው ሰው ካልፈቀደ በቀር ባለገንዘቡ በመያዣ ስም ተቀብሎት የነበረውን ሀብት የተዳረገው ሰው ከእጁ
ሊያገባው አይችልም፡፡
ቊ 1974፡፡ የዋነኛው ባለገንዘብ ግዴታዎች፡፡
(1) የዕዳ ማስከፈሉን መብት ለሌላ አሳልፎ የሰጠው ወይም የገንዘቡን ክፍያ ከሌላ ሰው ላይ የተቀበለ ባለገንዘብ የብድሩን ሰነድ
ለተላለፈለት ወይም ለተዳራጊው ሊያስረክበውና ያሉትንም የማስረጃ ሰነዶች ሊያቀርብለት እንዲሁም ደግሞ የሚጠይቃቸው መብቶቹ
በሕግ ፊት ዋጋ እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሚሆኑትን መረጃዎች ሁሉ እንዲሰጠው ይገደዳል፡፡

(2) የዕዳው ማስከፈል መብት የተላለፈው ወይም ገንዘቡ የተመለሰለት በከፊል ብቻ የሆነ እንደሆነ ይህ ዕዳ መኖሩን የሚያረጋጋጡትን
በሁለት ምስክሮች የተፈረሙ ሰነዶች ትክክለኛ ግልባጭ ሊሰጥ ይገባዋል፡፡
ቊ 1975፡፡ የማይነኩ ጒዳዮች፡፡
(1) አንዳንድ መብቶችን የማስተላለፍ ጒዳይ በሕግ በታዘዘው ዐይነት እንዲፈጸም ያስፈልጋል ተብሎ የተመለከተው ድንጋጌ እንደተጠበቀ
ነው፡፡
(2) እንዲሁም ተጠያቂው ሀብት በስሙ በትእዛዝ ወይም ላምጪው የሚከፈል ተብሎ በሚጠራ ሰነድ ውስጥ የገባ ሲሆን እንደዚህ ላለው
ጒዳይ የተሰጠው ድንጋጌም እንደተጠበቀ ነው፡፡
ክፍል 3፡፡
የምትክ ውክልናና የዕዳ ማስተላለፍ፡፡
ቊ 1976፡፡ የምትክ ውክልና፤ መሠረቱ፡፡
በሕጉ ወይም በልማዳዊ ሕግ እንደተመለከተው ሁኔታ በባለገንዘቡ ፈቃድ ወይም ያለ ፈቃዱ ባለዕዳው ራሱ ሊፈጽመው የሚገባውን
ግዴታ እንዲፈጽምለት ሌላ ሦስተኛ ወገን ሊወክል ይችላል፡፡
ቊ 1977፡፡ የባለገንዘቡ መፍቀድ እቀበላለሁ ማለት፡፡
(1) በምትክ የተወከለውን ፈቅዶ የተቀበለ ባለገንዘብ ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት በውሉ ላይ ካልተገለጸ በቀር በዋነኛው ባለዕዳ ላይ ያለውን
መብት እንደያዘ ይቈያል

(2) ስለሆነም የምትክ ውክልና ሥልጣን የተቀበለውን ሰው አስቀድሞ ከመጠየቁ በፊት ዋነኛውን ባለዕዳ ገንዘቡን እንዲከፍለው
ሊጠይቀው አይችልም፡፡

ቊ 1978፡፡ የተወካዩ መፍቀድ (እቀበላለሁ ማለት)፡፡


ለሚወክለው ሰው ባለዕዳም ቢሆን እንኳ የልማድ አሠራር እንደተጠበቀ ሆኖ ተወካዩ የወኪልነቱን ሥልጣን እንዲቀበል አይገደድም፡፡
ቊ 1979፡፡ የውክልናውን ሥልጣን ስለ መሻር፡፡
(1) በምትክ የተወከለው ሰው ለባለገንዘቡ የሚከፈለውን ገንዘብ ለመክፈል የምትክነቱን ሥልጣን ፈቅዶ ከተቀበለ ወይም ይህንኑ ዕዳ
ከከፈለ በኋላ ምትክ አድራጊው ከምትክነት ሥልጣኑ ሊሽረው አይችልም፡፡

(2) ምትክ አድራጊው ከሞተ ወይም ችሎታ ማጣቱ ከተረጋገጠ በኋላም ቢሆን ተተኪው የምትክ አድራጊውን ግዴታ ለመቀበል ወይም
የመክፈሉን ጒዳይ ለመፈጸም ይችላል፡፡
ቊ 1980፡፡ የተተኪው መብቶች፡፡
(1) ተተኪው ከምትክ አድራጊው ጋራ ባለው የግል ግንኙነት ምክንያት ወይም በባለገንዘቡንና በምትክ አድራጊው መካከል ባለው የግል
ግንኙነት ምክንያት የሚኖራቸውን ልዩነት ያላቸውን መከራከሪያዎች በመጥቀስ ባለገንዘቡን ሊከራከረው አይችልም፡፡

(2) ተተኪው በባለገንዘቡና በሱ መካከል ያለውን የግል ግንኙነት በሚመለከተው ጒዳይ ውስጥ ሊኖር በሚችለው መቃወሚያ ሊከራከር
ይችላል፡፡
ቊ 1981፡፡ የተተኪው የመክፈል ችሎታ ማጣት፡፡
(1) ባለዕዳው የዕዳውን መክፈል ሥልጣን ለተተኪው በማሳለፉ የተተኪውን መተካት ፈቅዶ ባለዕዳውን ነጻ ያወጣ ባለገንዘብ
በስምምነታቸው ላይ የተገለጸ ልዩ መብት ከሌለ በቀር ተተኪው የመክፈል ችሎታ ያጣ እንደሆነ ዋነኛውን ባለዕዳ ሊጠይቀው አይችልም፡፡

(2) ተተኪው የምትክነቱን ሥልጣን በተቀበለበት ጊዜ የመክፈል ችሎታ የሌለው መሆኑ በፍርድ ውሳኔ ተረጋግጦ እንደሆነ ግን ባለገንዘቡ
ዋነኛውን ባለዕዳ ሊጠይቅ የሚችልበት መብት እንደተጠበቀለት ይቈያል፡፡
ቊ 1982፡፡ ማረጋገጫዎች፡፡
ዋስ የሆኑና ለዕዳው ዋስትና እንዲሆን ንብረታቸውን አላፊ ያደረጉ ሦስተኛ ወገኖች የምትክነቱን ጒዳይ ፈቅደው የተቀበሉ ካልሆኑ በቀር
ለባለገንዘቡ ተገዳጆች አይሆኑም፡፡
ቊ 1983፡፡ ንብረትንና መብትን ስለ ማስተላለፍ፡፡
(1) አንድ ንብረት ወይም አንድ የሥራ ማከናወኛ መሥሪያ ቤት ካለው መብትና ከሚጠየቅበት ዕዳ ጋራ የገዛ ሰው ግዢውን ለገንዘብ
ጠያቂዎቹ እንዳስታወቀ ወይም በጋዜጣ እንደገለጸ ወዲያውኑ ለባለገንዘቦቹ አላፊ ይሆናል፡፡

(2) የቀድሞው ባለዕዳ ከአዲሱ ባለዕዳ ጋራ በአንድነት አላፊ ሆኖ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ይቈያል፡፡
(3) ይህም የጊዜ ውሳኔ መታሰቡን የሚጀምረው የመክፈያቸው ጊዜ ለደረሰ ዕዳዎች የግዢው መግለጫ ወይም ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን
አንሥቶ፤ ለሌሎች ዕዳዎች ደግሞ የመክፈያው ጊዜ ከደረሰበት አንሥቶ ነው፡፡
ቊ 1984፡፡ የሥራ ማከናወኛ መሥሪያ ቤቶች መቀላቀል፡፡
ሁለት የሥራ ማከናወኛ መሥሪያ ቤቶች (እንትረፕሪዞች) ያላቸውን መብትና የሚጠየቅባቸውን ዕዳ አንዱ ለአንደኛው በማስተላለፍ
ተደራርበው በአንድነት በተቀላቀሉ ጊዜ በያንዳንዳቸው ላይ ለሚጠየቀው ዕዳ አለፊ የሚሆነው አዲሱ የሥራ ማከናወኛ መሥሪያ ቤት
(እንትረፕሪዝ) ነው፡፡
ቊ 1985፡፡ የአንድ ማኅበር መቋቋም፡፡
(1) እንዲሁም አንድ የግል የነበረ የሥራ መከናወኛ መሥሪያ ቤት (እንትረፕሪዝ) ወደ አንድነት ማኅበር ወይም ኀላፊነቱ ወደ ተለየ ማኅበር
ስም በተለወጠ ጊዜ አፈጻጸሙ በላይኛው ዐይነት ነው፡፡

(2) አዲሱ ማኀበር፤ ወደ ራሱ አጠቃሎ ለደረሰው ማኀበር ዕዳ ተጠያቂ ይሆናል፡፡


ክፍል 4፡፡
ስለ ተዋዋዮቹ ወገኖች ወራሾች፤ (የወገኖቹ ወራሾች)
ቊ 1986፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ካልተደረገና ወይም የውሉ ተፈጥሮ ዐይነት የሚከለክል ካልሆነ በቀር የተዋዋዩ ወራሾች የሆኑት ሰዎች
በአውራሾቻቸው ስፍራ ከውሉ ውስጥ ይገባሉ፡፡
ቊ 1987፡፡ ስለ ሌላ ሆኖ መዋዋል፡፡
ስለ ሌላ ሰው የተደረገ ስምምነት በስምምነቱ ተጠቃሚው ሰው ውሉን ከተቀበለ በኋላና ከመፈጸሙ በፊት የሞተ እንደሆነ ወራሾቹ
ተተክተው ይህ ውል በሚሰጠው ትርፍ ይጠቀማሉ፡፡
ክፍል 5፡፡
ከተዋዋዮቹ ወገኖች ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች፡፡
ቊ 1988፡፡ መያዝ፡፡
(1) ለባለዕዳው ግዴታ አፈጻጸም ማረጋገጫ የሚሆነው፤ ሊያዝበት አይገባም ተብሎ በሕግ ከተደነገገው በቀር የሚገኘው ንብረቱ ሁሉ
ነው፡፡
(2) የመያዝን ጒዳይ የሚመለከቱ ይልቁንም የባለዕዳው ሀብት በዕዳ ማስከፈል ስም የመያዝን ጒዳይ የሚመለከተው ደንብ በፍትሐ ብሔር
ሥነ ሥርዐት ውስጥ ይገለጻል፡፡

ቊ 1989፡፡ ባለዕዳው ያደረገው የውል ስምምነት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አንድ ሰው የፈጸማቸው ውሎች ከርሱ ላይ ገንዘብ ያላቸውን ሰዎች መመለሻ ይሆናል፡፡

(2) አንድ ሰው በተወሰነ ሀብት ላይ የስምምነት ውል የፈጸመ እንደሆነ ውሉ የተረጋገጠ ቀን ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ ወይም ይህ ጽሑፍ
ለሕዝብ እንዲገለጽ ማድረግ የታዘዘ ሲሆን፤ ይህ ሥርዐት ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ከዚህ ሰው ንብረት ላይ ልዩ መብት የሚያገኙትን
ሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ይሆናል፡፡

ቊ 1990፡፡ (2) ልዩ መብት ስላለው ባለገንዘብ፡፡


በሕጉ ላይ ተለይቶ በተገለጸው መሠረትና በተለይም ለገንዘብ ጠያቂው ሕጉ ወይም የውሉ ስምምነት ልዩ መብት የሚሰጠው ሲሆን፤
ወይም ባለዕዳው የሀብቱን ሥራ የማካሄዱን ጒዳይ ራሱ እንዳያከናውን በፍርድ ውሳኔ የታገደ ሲሆን ከዚህ በላይ የተመለከቱት ደንቦች
የአፈጻጸም ልዩነት አላቸው፡፡
ቊ 1991፡፡ (3) መሰል፡፡

(1) እንዲሁም ውሉ የተደረገው ለይምሰል ሲሆን ከዚህ በላይ ለተደነገጉት ደንቦች ልዩ አፈጻጸም ይሰጣቸዋል፡፡

(2) ድብቅ የሆነ የስምምነት ጽሑፍ ዋጋ የሚያገኘው በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ነው፡፡

(3) ከተዋዋዮቹ ወገኖች ከአንደኛው ገንዘብ ጠያቂ የሆነው ሰው፤ ይህንኑ በማመን በተዋዋለበት ለይምሰል በተደረገው ውል ላይ መብቱን
ለማዋል ይችላል፡፡
ቊ 1992፡፡ የመጠበቅ ተግባሮች፡፡
አንድ ገንዘብ ጠያቂ የባለዕዳው መብቶች እንዳይጠፉ ሲል ማናቸውንም የመጠበቂያ ተግባሮች በባለዕዳው ስም ሆኖ ለማከናወን ይችላል፡፡
ቊ 1993፡፡ በባለዕዳው መብቶች ስለ መሥራት፡፡
(1) አንድ ገንዘብ ጠያቂ የባለዕዳው መደኽየት ገንዘቡን የማያስከፍል ምክንያት እንዳይሆንበት ሲል፤ ዳኞችን አስፈቅዶ እንደ ባለዕዳው
እንደራሴ ሆኖ የባለዕዳውን መብቶች ሊሠራባቸው ይችላል፡፡

(2) ገንዘብ ጠያቂው ክስ ለማቅረብ የሚጠይቅበት መብት በመብቱ ዐይነት ወይም በሕግ መሠረት ለባለዕዳው ብቻ የሚሆን መብት የሆነ
እንደሆነ ነገሩን በፍርድ ቤት ለመከታተል እንዲፈቀድለት የሚያቀርበው ጥያቄ ሊከለከል ይገባል፡፡

(3) እንዲሁም ዕዳ ለመክፈል የማይችል ሁኗል ተብሎ የሚያሠጋ ባለዕዳ ክስ ባለማቅረቡ የገንዘብ ጠያቂው መብቶቹ ጉዳት
የሚደርስባቸው ካልሆነ ገንዘብ ጠያቂው ለመክሰስ እንዲፈቅድለት የሚያቀርበው ጥያቄ ሊከለከል ይገባል፡፡
ቊ 1994፡፡ ስለ ማስመሰል፡፡
አንድ ገንዘብ ጠያቂ ባለዕዳው ያደረገው ውል የማስመሰል እንጂ፤ ተፈጻሚ እንዲሆን የተደረገ ያለመሆኑን በፍርድ እንዲታወቅለት
ለማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 1995፡፡ የባለዕዳው አጭበርባሪነት፡፡
ባለዕዳው በአጭበርባሪነት ተግባሩ መብቱን አሳልፎ የሰጠ ወይም አንድ ግዴታ የመፈጸም ስምምነት ያደረገ እንደሆነ ባለገንዘቡ እነዚህን
ተግባሮች በራሱ ስም ሆኖ ለመቃወም ይችላል፡፡
ቊ 1996፡፡ ስለ አጭበርባሪነት ሥራ፡፡
(1) አንድ ሥራ በገንዘብ ጠያቂው መብቶች ላይ በአጭበርባሪነት የተፈጸመ ነው ተብሎ የሚገመተው፤ ባለዕዳው የሚጠየቀውን ዕዳ
ለመክፈል እንዳይችል ወይም የመክፈል ችሎታው ይበልጥ እንዲቀነስ ሲል፤ እያወቀ ያደረገ እንደሆነ ነው፡፡

(2) የመክፈያ ጊዜያቸው ደርሶ የተከፈሉትን ዕዳዎች ሌሎች ባለገንዘቦች ሊቃወሙዋቸው አይችሉም፡፡
ቊ 1997፡፡ ቅን ልቡና ስላላቸው ሦስተኛ ወገኖች፡፡
ገንዘብ ጠያቂው የሚያቀርበው ክስ ጒዳይ የሚያመጣበት እንደሆነና ሦስተኛው ወገን የተቃወመው ሥራ ወይም መብቶቹን ያገኘባቸው
ሥራዎች በዋጋ እንደሆነ በቅን ልቡና መሠረት ክሱን አልቀበልም ሲል ሦስተኛው ወገን ለመቃወም ይችላል፡፡
ቊ 1998፡፡ የጊዜ ልክ፡፡
ገንዘብ ጠያቂዎች ክስ ለማቅረብ የሚችሉት፤ የተነቀፈው ሥራ ከተደረገበት ቀን አንሥቶ እስከ ሁለት ዓመት ነው፡፡
ቊ 1999፡፡ ውጤቱ፡፡
(1) ባለዕዳው የፈጸመው ሥራ በማጭበርበር መሆኑ ከተገለጸ ክስ ያቀረበውን ገንዘብ ጠያቂ መቃሚያ ሊሆን አይችልም፡፡

(2) በተዋዋዮቹ ወገኖች መካከል ባለው ግንኙነትና በሌሎቹ ገንዘብ ጠያቂዎች ዘንድ በሚኖረው ጒዳይ ግን ሥራው ይጸናል፡፡
ቊ 2000፡፡ መክሠር፡፡
ባለዕዳው በከሠረ ጊዜ ገንዘብ ጠያቂዎቹ የባለዕዳውን የሥራ መብት ማከናወን ወይም ባለዕዳው ባደረገው የማጭበርበር ተግባር የገንዘብ
ጠያቂዎቹ የክስ ማቅረብን መብት የሚመለከቱ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ይኖራሉ፡፡
ምዕራፍ 7፡፡
የውልን ጒዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ፡፡
ክፍል 1፡፡
የማስረጃ ማቅረብ ግዴታና አቀባበሉ፡፡
ቊ 2001፡፡ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ፡፡

(1) አንድ ግዴታ እንዲፈጸምለት የሚጠይቅ ሰው ለግዴታው መኖር ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡

(2) እንዲህም ግዴታው ፍርስ ነው ወይም ተለውጧል ወይም ቀርቷል የሚለው ወገን፤ ይኸንኑ ግዴታ ያፈረሰውን የለወጠውን ወይም
ያስቀረውን ተግባር ማስረዳት አለበት፡፡
ቊ 2002፡፡ የማስረጃ ዐይነቶች፡፡
በዚህ ምዕራፍ ላይ በተመለከቱት ደንቦች መሠረትና በፍትሐ ብሔር ሕግ ሥነ ሥርዐት ደንብ ላይ በተገለጸው ድንጋጌ ዐይነት፤ በጽሑፍ
በምስክር፤ በሕሊና ግምት በተከራካሪው ወገን እምነት፤ ወይም በመሓላ ማስረጃ ማቅረብ ይችላል፡፡

ቊ 2003፡፡ ጽሑፍ በሆነ ሥርዐት (ፎርም) ይደረጉ የተባሉ ውሎች፡፡


ውሉ በጽሑፍ እንዲሆን ሕግ ባዘዘ ጊዜ ይህ ጽሑፍ የተቀደደ የተሰረቀ የጠፋ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ውሉን በምስክሮች ወይም በሕሊና
ግምት ለማስረዳት አይቻልም፡፡
ቊ 2004፡፡ በማስረጃ አቀራረብ ጒዳይ ስለ መዋዋል፡፡
አንዳንድ ማስረጃዎችን የሚያስቀሩትን ወይም አቀራረቡን የሚቀንሱትን ደንቦች ጥሰው ተዋዋዮቹ እንዲዋዋሉ አይፈቀድላቸውም፡፡
ክፍል 2፡፡
የጽሑፍ ማስረጃ፡፡
ቊ 2005፡፡ የጽሑፍ ማስረጃ በቂነት፡፡
(1) የጽሑፍ ሰነድ፤ በላዩ ስለሚገኘው የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ ስለተጻፈው ቀን በተፈራራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት
የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው፡፡

(2) እንዲሁም በእንደራሴ በተፈጸመላቸው ሰዎች በኩልና የተዋዋዮቹ ወገኖች ወራሾች በሆኑት ዘንድም ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ
ማስረጃነት አለው፡፡
ቊ 2006፡፡ መቃወሚያ ማስረጃ፡፡
(1) በጽሑፍ ውስጥ ያሉትን ቃሎች ተዋዋዮቹ ለመቃወም የሚችሉት፤ ቃሉ ይኽው ነው የሚለውን ወገን በማስማል ብቻ ነው፡፡

(2) በውሉ ውስጥ ስለ ተጻፉት ቃላቶች፤ የሰው ምስክር ወይም የሕሊና ግምት ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ቊ 2007፡፡ ጽሕፈትን ለመካድ፡፡
(1) የግል በሆነ ጽሑፍ የተጻፈ ሰነድ የቀረበለት ሰው የኔ አይደለም ለማለት የፈለገ እንደሆነ፤ ጽሕፈቱን ወይም ፊርማውን ግልጥ አድርጎ
መካድ አለበት፡፡

(2) ወራሽ የሆኑ ሰዎች የአውራሾችን ፊርማ ወይም ጽሕፈት መሆኑን አናውቅም ማለት ብቻ ይበቃቸዋል፡፡
ቊ 2008፡፡ የጽሕፈት ምርመራ፡፡
አንዱ ወገን ተከራካሪ ፊርማውን ወይም ጽሕፈቱን በካደ ጊዜ ወራሾቹም ማን እንደፈረመውና እንደጻፈው አናውቅም ያሉ እንደሆነ፤
ፊርማው ወይም ጽሕፈቱ እንዲመረመር ዳኞች ሊያዙ ይችላሉ፡፡
ቊ 2009፡፡ ሦስተኛ ወገኖች፡፡
(1) ሰነዱን የጻፈው ወይም የተቀበለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን ካልሆነ በቀር በሰነዱ ውስጥ የተጻፉትን ቃሎች ሐሰተኛነት
በማንኛውም ዐይነት ሦስተኛ ወገኖች ለማስረዳት ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም በቀረበው ሰነድ ላይ የተጻፈው ቀን የተረጋገጠ ካልሆነ በቀር በተለይ ይህ የተጻፈው ቀን ሐሰተኛ መሆኑን በማንኛውም
ዐይነት ለማስረዳት ይችላሉ፡፡
ቊ 2010፡፡ በባለሥልጣን የተረጋገጠ ሰነድ፡፡
(1) ሰነዱን ያዘጋጀው ወይም የተቀበለው ይህንኑ ለማድረግ የሚችል የመንግሥት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን የሆነ እንደሆነ ባለሥልጣኑ
ራሱ ለመመርመር ያልቻላቸውን የውሉን ቃላት ሁሉ ሦስተኛ ወገኖች እንደፈቀዱ ሊቃወሟቸው ይችላሉ፡፡

(2) የመንግሥት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን ራሱ የመረመራቸውን የውል ቃላት ለመቃወም የሚቻለው ዳኞች ይህ እንዲፈጸም በተለይ
የፈቀዱ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

ቊ 2011፡፡ በባለሥልጣን የተረጋገጠ የሰነድ ግልባጭ፡፡

(1) በባለሥልጣን ከተረጋገጠ ዋነኛ ሰነድ ላይ የተቀዱ ግልባጮች ወይም ከዋናው ሰነድ ላይ የተነሡ ፎቶግራፍ ኮፒዎች ይህንኑ ጒዳይ
ለመሥራት በተመደበ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን በሆነ ሹም ትክክለኛ ግልባጭ መሆናቸው ከተመሰከረ የዚሁ ዐይነት ዋጋ
ያላቸው ሆነው ይቈጠራሉ፡፡

(2) ይኸውም ደንብ ከዋናው ሰነድ ላይ ለተነሡ ፎቶግራፍ ኮፒዎችም ይጸናል፡፡

ቊ 2012፡፡ የመንግሥት ቤተ መዛግብት፡፡


በመንግሥት ቤተ መዛግብት የሚቀመጡ የመንግሥት ወይም የግል ሰነዶች ከዋናው ሰነድ ላይ የተገለበጡት እንደ ደንቡ የመዝገብ ቤቱ
ባለሥልጣን በሆነው ሰነድ አስቀማጭ ሠራተኛ ከሆነ እንደ ዋናዎቹ ሰነዶች ተቈጥረው ይታመናሉ፡፡

ቊ 2013፡፡ ማስተያያ ሰነዶች ወይም ፎቶግራፎች፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ቊጥሮች የተመለከተው ነገር በሚያጋጥምበት ጊዜ ተከራካሪዎቹ ወገኖች ዋናው ሰነድ ይቅረብልን ብለው
ዳኞችን ለመጠየቅ አይችሉም፤ ነገር ግን የያዙት ግልባጭ ከዋናው ሰነድ ጋራ ይህም ባይኖር ከቤተ መዛግብቱ ከተቀመጠው ግልባጭ ጋራ
በራሳቸው ኪሣራ እንዲመሳከርላቸው ምን ጊዜም ቢሆን የመጠየቅ መብት አላቸው፡፡

(2) እንዲሁም ደግሞ ዋናው ሰነድ በራሳቸው ኪሣራ በፎቶግራፍ እንዲገለበጥላቸው ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቊ 2014፡፡ የዋናው ሰነድ መጥፋት፡፡

ዋናው ሰነድ፤ ወይም በቤተ መዛግብቱ የተቀመጠው ትክክል ግለባጭ በጠፋ (በሌለ) ጊዜ ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ቊጥሮች ድንጋጌ
መሠረት በሚገባ የተገለበጡት የሰነድ ቅጂዎች ስርዝም ሆነ የቃል መለወጥ ድልዝ ወይም ይህን የመሰለ ማናቸውም የሚያጠራጥር ነገር
የሌለባቸው ከሆነ የሚታመኑ ናቸው፡፡

ቊ 2015፡፡ የተረጋገጠ ቀን፡፡


ሰነዱ የተጻፈበት እርግጠኛ ቀን ነው የሚባለው፡፡
(ሀ) ሰነዱን የጻፈው ወይም የተቀበለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን ሲሆን የጻፈበት ወይም የተቀበለበት ቀን፤

(ለ) ሰነዱ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን በጻፈው ወይም በተቀበለው ሌላ ሰነድ ውስጥ ተጠቅሶ እንደሆነ ይህ ሌላው ሰነድ
የተጻፈበት ወይም ባለሥልጣኑ የተቀበለበት ቀን፤
(ሐ) ይህን ሰነድ ከፈረሙት ወገኖች አንደኛው የሞተ እንደሆነ ወይም ለመፈረም የአካል ችሎታ ያጣ እንደሆነ ሰውዬው የሞተበት ወይም
የመፈረም ዐቅም ያጣበት ቀን ነው፡፡

ቊ 2016፡፡ የነጋዴዎች መዝገብ፡፡

(1) የነጋዴዎች መዛግብት፤ ለጻፋቸው ሰው አስረጅ ሊሆኑት አይችሉም፡፡

(2) እነዚህ መዛግብት በጻፋቸው ሰው ላይ ማስረጃ ይሆኑበታል፡፡ ነገር ግን በነዚህ ለመጠቀም የሚፈልገው ወገን የሚጠቅመውን ቃል
ከሚቃወመው ጽሑፍ ውስጥ ለይቶ ጠቃሚውን ብቻ ያስረዳልኝ ለማለት አይችልም፡፡

ቊ 2017፡፡ የቤት መዛግብትና የቤት ደብዳቤዎች፡፡


የቤት መዛግብት የቤት ደብዳቤዎች ለጻፋቸው ሰው አስረጅ ሰነድ ሊሆኑት አይችሉም፡፡
ቊ 2018፡፡ በጻፉዋቸው ሰዎች ላይ አስረጅ ስለ መሆናቸው፡፡
የቤት መዛግብትና የቤት ደብዳቤዎች በጻፋቸው ላይ ተቃዋሚ ማስረጃ መሆናቸው የሚታመነው፡፡
(ሀ) አንድ ገንዘብ የተከፈለ መሆኑ በግልጽ ተመልክቶባቸው በተገኘ ጊዜ፤

(ለ) ግዴታው ለሚጠቅመው ሰው የሚያስረዳው ሰነድ የጠፋ እንደሆነና ለዚሁ ሰነድ ምትኩ እንዲሆን ተብሎ በግልጽ የተጻፈባቸው
እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2019፡፡ የምክንያቱ ማስረጃ፡፡

(1) አንድ ሰው አንድ ገንዘብ ለመክፈል ቃል የሰጠ እንደሆነ ወይም ባለዕዳ መሆኑን ያመነ እንደሆነ፤ እከፍልሃለሁ የተባለው ወይም ዕዳው
የታመነለት ሰው የነዚህን ምክንያት ማረጋገጥ የለበትም፡፡

(2) ተቃራኒ ማስረጃ ከሌለ በቀር በአእምሮ ግምት በሚገባ የተሰጠ ቃል እንዳለ ይቈጠራል፡፡

(3) የግዴታው ምክንያት ስለ መደበቁ ማስረጃ በሚቀርብበት ጊዜ ይህንኑ ማስረዳት ያለበት ለግዴታው ሌላ ሕጋዊ ምክንያት አለ የሚለው
ሰው ነው፡፡
ክፍል 3፡፡
ገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቈጥሩ የሕሊና ግምቶች፡፡
ቊ 2020፡፡ ዕዳው የተከፈለ ያህል የሚያስቈጥሩ የሕሊና ግምቶች፡፡
ሰነድ ለባለዕዳው መመለሱ ዕዳውን እንደተከፈለ ያስቈጥራል፡፡
ቊ 2021፡፡ የባለገንዘቡ ጽሕፈት፡፡
በእጁ ቈይቶ በሚገኘው በዕዳው ሰነድ ላይ ባለገንዘቡ በግርጌው፤ በጐኑ ወይም በጀርባው ጽፎበት የተገኘው ቃል የባለዕዳውን ነጻነት ወደ
ማረጋገጥ የሚያዘነብል ጽሑፍ ከሆነ፤ ሳይፈረምበት ወይም ቀን ሳይሞላበት ቢቀርም እንኳ እምነት ሊጣልበት የሚችል አስረጅ ይሆናል፡፡

ቊ 2022፡፡ ስለ ውዝፍ ዕዳ ወይም ባንድ ጊዜ ስለሚከፈል ገንዘብ፡፡

(1) የተከፈለው ዕዳ፤ ወለዶችን ወይም የተወሰነ ጊዜ የሚከፈሉትን ሌሎች የክፍያ ድርሻዎች የሚመለከት እንደሆነ፤ የተከፋዩን ዐይነት ለይቶ
ሳይገልጽ ለአንዱ የክፍያ ደረሰኝ የሰጠ ባለገንዘብ ያለፈውንም ድርሻ እንደተቀበለ ይቈጠራል፡፡

(2) ባለገንዘቡ ለዋናው ገንዘብ ደረሰኝ ከሰጠ ባለዕዳው ወለዱንም ጭምር እንደከፈለ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2023፡፡ በስድስት ወር የተወሰነ ጊዜ፡፡


ዕዳው እንዲከፈል መጠየቅ ከሚገባው ቀን አንሥቶ እስከ ስድስት ወር ድረስ ሳይከፈል የቈየ ገንዘብ እንደተከፈለ የሚቈጠረው፤
(ሀ) ለንግድ ቤት ወኪሎች ለቢሮ ሠራተኞች በቀን ሒሳብ ለተቀጠሩ አሽከሮችና የቀን ሒሳብ ለሚከፈሉ የዕለት ኩሊዎች፤ የሚከፈል
የደመወዝ ዕዳ እንደሆነ፤

(ለ) ለአስተማሪዎችና ለአሠልጣኞች ለሚሰጡት ትምህርት በየወሩ የሚከፈል ዕዳ እንደሆነ፤

(ሐ) ለባለሆቴሎች፤ ለመጋቢዎችና ለማደሪያ ሆቴል ቤት ሥራ አስኪያጆች ለሚሰጡት ምግብና ለመኝታ ቤቱ ኪራይ የሚከፈል ዕዳ
እንደሆነ፤
(መ) ለዕለት ምግብ ወይም ለዘወትር አገልግሎት ነጋዴዎች ለባለግል ሰዎች ለሸጡት ሀብት ወይም ለምግብ ዕቃ ዋጋ የሚከፈል ዕዳ የሆነ
እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2024፡፡ በሁለት ዓመት የተወሰነ ጊዜ፡፡


ዕዳው እንዲከፈል መጠየቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ የሚቈጠረው፤
(ሀ) ለሐኪሞች፤ ለቀዳጅ ሐኪሞች፤ ለጥርስ ሐኪሞች፤ ለአዋላጅ ሴቶች፤ ለመድኀኒት ተቀማሚዎችና ሻጮች፤ ለከብት ሐኪሞች፤ በልዩ
ሞያቸው ስላደረጉት አገልግሎት ወይም ስለሰጡት ሕክምና ዋጋ የሚከፈል ዕዳ፤

(ለ) ለጠበቆች፤ ለውል አዋዋዮች ለሌሎችም የሕግ አማካሪዎች በሞያ ሥራቸው ወይም በሹመት ሥራቸው ላደረጉት አገልግሎት የሚከፈል
ዕዳ፤
(ሐ) ለጥበበኞች ለአንጥረኞች በልዩ ሞያቸው ስለሠሩት ሥራ የሚከፈል ዕዳ፤

(መ) ለቤቶች ኪራይና ለእርሻ ሀብት ለሆነ የሚከፈል ዕዳ፤

(ሠ) ለመጦሪያ የሚከፈል ገንዘብ፤

(ረ) በብድር ለተሰጠ የገንዘብ ወለድና በጠቅላላውም የዓመት ጊዜ ተወስኖለት በየዓመቱ ወይም ከዚህ ባነሰ የጊዜ ውሳኔ ውስጥ ሊከፈል
የሚገባው ዕዳ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2025፡፡ ተቃራኒ ማስረጃ፡፡

(ሀ) ባለዕዳው በጽሑፍ ዕዳውን ያመነ እንደሆነ፤

(ለ) በሕግ የተደነገገው የጊዜ ውሳኔ ሳይደርስ ባለገንዘቡ ገንዘቡን እንዲከፍለው ባለዕዳውን ከፍርድ ቤት አስጠርቶ እንደሆነ ዕዳው
እንደተከፈለ መቈጠሩ ቀሪ ይሆናል፡፡

ቊ 2026፡፡ መሓላ፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች ላይ ለተገለጠው የሕሊና ግምት መቃወሚያ የሚሆን ማንኛውንም ዐይነት ማስረጃ ለመቀበል አይቻልም፡፡

(2) ምን ጊዜም ቢሆን ግን፤ ዕዳው በእርግጠኛ መከፈሉን ወይም ያለ መከፈሉን ለማስረዳት ባለገንዘቡ ለባለዕዳው ወይም ባለዕዳው
ለባለገንዘቡ የመሓላ ቃሉን ሊያወርድለት ይችላል፡፡

(3) የባለገንዘቡ ወይም የባለዕዳው ወራሾች ገንዘቡ የተከፈለ ወይም ያልተከፈለ መሆኑን ለማስረዳት የመሐላ ቃላቸውን ለመስጠት
ይችላሉ፡፡

አንቀጽ 13፡፡
ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነትና ያላገባብ ስለ መበልጸግ፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት፡፡
ቊ 2027፡፡ ከውል ውጭ የሆኑ የአላፊነት ምንጮች፡፡

(1) አንድ ሰው በራሱ በኩል ምንም የገባው ግዴታ ባይኖር በራሱ ጥፋት በሌላው ሰው ላይ ጉዳትን ካደረሰ አላፊ ነው፡፡

(2) እንዲሁም ደግሞ አንድ ሰው በሕጉ ላይ እንደተመለከተው በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ሥራ ከሠራ ወይም በእጁ የያዘው
ነገር በሌላው ሰው ላይ ጉዳት ካደረሰ አላፊ ይሆናል፡፡

(3) በመጨረሻውም በጥፋት ምክንያት ወይም በሕግ መሠረት አላፊነት ሲኖር ሌላ ሰው ለፈጸመው አድራጎት በሕጉ አላፊነት አለበት
የተባለው ሰው አላፊ ነው፡፡

ክፍል 1፡፡
በጥፋት ላይ ስለ ተመሠረተ አላፊነት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ደንቦች፡፡
ቊ 2028፡፡ ጠቅላላ መሠረት፡፡

ማንም ሰው ከራሱ ጥፋት የተነሣ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ካደረሰ ላደረገው ጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2029፡፡ የጥፋት ልዩ ልዩነት፡፡

(1) አስቦ ወይም በቸልተኛነት በሚሠራ ተግባር ጥፋት ሊደረግ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም አንድ ተግባርን መፈጸም ወይም ተግባርን አለመፈጸም፤ ጥፋት ሊሆን ይችላል፡፡

ቊ 2030፡፡ መልካም ጠባይ፡፡

(1) አንድ ሰው ሕሊናን ወይም መልካም ጠባይን ተቃዋሚ በሆነ ዐይነት የማይገባውን ሥራ የሠራ ወይም የሚገባውን ሳይሠራ የቀረ
እንደሆነ፤ ጥፋት ማድረጉ ነው፡፡

(2) እንደዚህ ስላለውም ጒዳይ ትክክለኛ አእምሮ ባለው ሰው አሠራር ዐይነት አስተያየት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

(3) በሕግ የተነገረ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ጥፋት ነው ተብሎ የሚገመተው የጥፋት አድራጊውን ዕድሜም ሆነ የአእምሮውን
ትክክለኛነት መሠረት አድርጎ ባለመያዝ ነው፡፡

ቊ 2031፡፡ በሞያ ሥራ ስለሚደረግ ጥፋት፡፡


(1) በልዩ ሞያው አንድ ሥራ የሚፈጽም ሰው ወይም በዚህ በሞያው የሥራ ተግባሩን የሚያካሂድ ሰው የዚሁ የሞያ ሥራው የሚመራበትን
ደንብ መጠበቅ ይገባዋል፡፡

(2) በሥነ ጥበብ ወይም ራሱ በሚሠራው ኪነ ጥበብ ደንቦች መሠረት ያሉበትን ግዴታዎች አለመከተሉ ሲገለጽ ባለመጠንቀቅ ወይም
በቸልተኛነት ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ አላፊ ይሆናል፡፡

ቊ 2032፡፡ የመጉዳት አሳብ፡፡

(1) አንድ ሰው የግል ጥቅሙን ለመፈለግ ሳይሆን በማናቸውም ሁኔታ ሌላውን ሰው ለመጉዳት በማሰብ በሠራው ሥራ ጥፋተኛ ነው፡፡

(2) እንዲሁም ከተደረገው ጉዳት ጋራ ግንኙነት የሌለውን የራሱን ጥቅም ሲፈልግ እያወቀ በሌላው ሰው ላይ ከፍ ያለ ጉዳትን ያደረሰ
እንደሆነ፤ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2033፡፡ በሥልጣን ያላገባብ ስለ መጠቀም፡፡

(1) አንድ ሰው ስለ ሌላ ሰው ጥቅም የተሰጠውን ሥልጣን ለግል ጥቅሙ የሠራበት እንደሆነ አጥፊ ነው፡፡

(2) የመንግሥት ሠራተኛ የሆነ ሰው ለጠቅላላው ጥቅም እንዲያገለግልበት በሥራው (በሹመቱ) ያገኘውን ሥልጣን ለግል ጥቅሙ ወይም
ለተለየ ሰው ጥቅም ያዋለው እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2034፡፡ ስለ መብቶች ግብ፡፡

ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች በተለከቱት ድንጋጌዎች ሳይነኩ፤ አንድ ሰው የተሰጠውን መብቱን በሥራ ላይ ያዋለበት ሁኔታ ከኤኮኖሚክና
(የቁጠባ ዘዴ) ከማኅበራዊ አስተዳደር ጋራ ተስማሚ አይደለም በማለት መንቀፍ አይቻልም፡፡

ቊ 2035፡፡ ሕግን ስለ መጣስ፡፡

(1) አንድ ሰው በሕግ ላይ በትክክል ተገልጾ የተመለከተውን ልዩ ድንጋጌ፤ ልዩ ደንብና ሥርዐት የጣሰ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

(2) ሕግን አለማወቅ ይቅርታ ሊያስገኝ አይችልም፡፡

ቊ 2036፡፡ የበላይ ትእዛዝ፡፡

(1) በበላይ ባለሥልጣን ትእዛዝ የተፈጸመ ተግባር፤ ትእዛዙ ምክንያት ሆኖ የሥራውን ጥፋትነት ግድ አያስቀረውም፡፡
(2) የተባለውን ሥራ ሠርቶ የተገኘ ሰው፤ የዚህን ሥራ ሕገ ወጥነት እያወቀ፤ በተለይም ትእዛዝ ሰጪው ሥልጣን (ችሎታ) እንደሌለውና
የሥራውን የዐመፅ ጠባይ፤ ወይም አስወቃሽነቱን እያወቀ ሠርቶት እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

(3) በነገሩ ሁኔታ ዐይነት፤ በተለይም አጥፊው ጥብቅ በሆነ በመንግሥታዊ ወይም በወታደራዊ ዲሲፕሊን ምክንያት፤ በተሰጠው ትእዛዝ
ለመከራከር ወይም ያንን የታዘዘውን እንጂ ሌላ ነገር ለማድረግ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ከመገኘት የተነሣ የተባለውን ሠርቶ እንደሆነ፤
ጥፋት የለበትም፡፡

ቊ 2037፡፡ የውል አለመፈጸም፡፡

(1) አንድ ሰው በአንድ ውል ምክንያት የመጣበትን ግዴታ ሳይፈጽም በቀረ ጊዜ ከውሉ ውጭ ለሆነ ነገር አላፊነትን የሚያስከትልበትን
ጥፋት እንደሠራ አያስቈጥረውም፡፡

(2) እንዲህም በሆነ ጊዜ የውል አለመፈጸም ደንብ ብቻ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ንኡስ ክፍል 2፡፡


ልዩ ሁኔታዎች፡፡
ቊ 2038፡፡ ሰውነትን ስለ መጉዳት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አንድ ሰው ሆነ ብሎ ሌላው ሰው ሳይፈቅድ በሚያደርገው መንካት በዚህ በመንካቱ ጥፋተኛ ነው፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ሰውዬውን በቀጥታም ሆነ ወይም በሌላ ሕይወት ባለው ወይም በሌለው ነገር አማካይነት ቢነካውም ጥፋተኛ ነው፡፡

(3) በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ለማድረግ የተደረገ የመዛት ሁኔታ ብቻ በጠቅላላው ጥፋት አይባልም፡፡

ቊ 2039፡፡ (2) በቂ ምክንያት፡፡

ተከሳሹ ጥፋተኛ ነው የማይባለው፤


(ሀ) ከሳሹ ሥራውን የሚቃወም መሆኑን ተከሳሹ በአእምሮው ግምት ሊያስበው የማይችል መሆኑ የታወቀ እንደሆነ፤

(ለ) ሥራው የተፈጸመው፤ በሚገባ አኳኋን ወይም ለሌላ ሰው ለመከላከል ወይም በደንብ በእጁ ያለውን ወይም የያዘውን ንብረት
ለመጠበቅ ሲል እንደሆነ፤

(ሐ) ሥራው የተፈጸመው ተከሳሹ ልጁን የአደራ ልጁን ተማሪውን ወይም አሽከሩን በሚገባ ለመቅጣት ሲል በሰውነቱ ላይ ተገቢ የሆነውን
አቀጣጥ ፈጽሞበት እንደሆነ፤

(መ) ከሳሹ አደገኛ እብድ በመሆኑ፤ ጉዳት እንዳያደርስ በሌላ አኳኋን ለመከልከል ስላልተቻለውና ተከሳሹ ሥራውን የፈጸመው በሚገባ
አኳኋን እንደሆነ፤

(ሠ) የተከሳሹ ሥራ አእምሮ ባለው ሰው ግምት የሚገባ ነው የሚያሰኝ ሌላ ማናቸውም ምክንያት በተገኘ ጊዜ ሁሉ ነው፡፡
ቊ 2040፡፡ የሌላውን ሰው ነፃነት ስለ መንካት (1) መሠረቱ፡፡

(1) አንድ ሰው ሕግ ሳይፈቅድለት ለተወሰነ ጊዜ ቢሆንም የሌላውን ሰው ነፃነት የነካና እንደተፈቀደለት መጠን ካንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ
እንዳይዘዋወር ሰውዬውን የከለከለ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ በከሳሹ ሰውነት ላይ ጉዳት ያላደረሰም ቢሆን እንኳ ጥፋቱ እንደተሠራ መቈጠሩ አይቀርም፡፡

(3) ከሳሹ አንድ ዐይነት የግዴታ ሥራ እንዲፈጽም በተከሳሹ ዛቻ ተገድዶ እንደሆነና ይህም ዛቻ ሊያስከትልበት የሚችለውን አደጋ
ለመገመት የሚችል መሆኑ ከታወቀ እንደ ጥፋት ለመቈጠር በቂ ነው፡፡

ቊ 2041፡፡ (2) ሕጋዊ ሥልጣን፡፡

ቢሆንም ተከሳሹ ይህን የማስገደድ ሥራ የፈጸመው በሚገባ አኳኋን፤ ሕግ በሚፈቅድለት ሥልጣኑ ምክንያት እንደሆነና በሥልጣኑ ሥር
በሚገኝ ሰው ላይ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ እንደ ጥፋት አይቈጠርበትም፡፡

ቊ 2042፡፡ (3) ወንጀል መሰል እልፊት፡፡

(1) የሌላውን ሰው ነጻነት የነካ ሰው፤ ይህን ነጻነቱ የተነካበትን ሰው አንድ ወንጀል ሠርቶዋል ብሎ ለማሰብ የሚያስችለው በቂ ምክንያት
ካገኘ ጥፋተኛ አያሰኘውም፡፡

(2) ቢሆንም አስገድዶ ነጻነቱን የነካበትን ሰው ወዲያውኑ ለክፍሉ ባለሥልጣን ወስዶ ካላስረከበው በቀር በዚሁ ምክንያት ብቻ የሰውን
ነጻነት በመንካት አላፊነት ያገኘዋል፡፡

ቊ 2043፡፡ (4) ዋስ፡፡

አንድ ሰው ባንድ በተወሰነ ቦታ እንዲኖር ለመንግሥት ባለሥልጣኖች በዋስትና አላፊነትና አላፊነትን የተቀበለ ሰው ይህ በአንድ ስፍራ
ታግዶ እንዲቀመጥ የተደረገው ሰው ከዚህ ለማምለጥ መሰናዳቱን የሚያሳምን በቂ ምክንያት ካለው የዚህን ሰው ነጻነት ቢነካበት ጥፋተኛ
አይደለም፡፡

ቊ 2044፡፡ ስምን ስለ ማጥፋት፤ (1) መሠረቱ፡፡

አንድ ሰው በንግግሮቹ በጽሑፎቹ ወይም በሌላ ዐይነት አድራጎቶቹ በሕይወት ያለውን የአንደኛውን ሰው ስም በማጥፋት ይህ ስሙ
የጠፋው ሰው እንዲጠላ፤ ወይም እንዲዋረድ ወይም እንዲሳቅበትና በእሱ ላይ ያለው እምነትና መልካም ዝናው ወይም የወደፊት ዕድሉ
እንዲበላሽ ያደረገ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡
ቊ 2045፡፡ (2) የመጉዳት አሳብ የሌለው አድራጎት፡፡

(1) ስም አጥፊ ለመባል የመጉዳት አሳብ መኖር አስፈላጊ አይደለም፡፡

(2) በስም ማጥፋት ነገር ስም ያጠፋል የተባለውን ነገር በንግግርና በጽሑፍ የሠራው ሰው በዚሁ ጽሑፍ ወይም በንግግሩ የማንንም ሰው
ስም በተለይ ካልገለጸ በቀር ስም እንደ ጠፋ አያስቈጥረውም፡፡

(3) በእንደዚህ ያለው ሁኔታ የስም ማጥፋትን አድራጎት በንግግር ወይም በጽሑፍ የገለጸው ሰው ይህ አድራጎቱ ሌላ ሰው እንደሚጎዳ
አስቀድሞ ለመረዳት መቻሉ ካልተገለጸ በቀር በዚሁ ጒዳይ አላፊነት አይኖርበትም፡፡

ቊ 2046፡፡ (3) የሕዝብን ጥቅም የሚነኩ ጒዳዮች፡፡

(1) አንድ ሰው ለሕዝብ ጥቅም በሚሆን ጒዳይ ላይ አሳቡን በመግለጽ ብቻ ከተወሰነ፤ ምንም እንኳ ይህ አሳቡ በሕዝብ ድምፅ ሌላውን ሰው
የሚያስወቅሰው ሆኖ ቢገኝ ጥፋተኛ አይደለም፡፡

(2) ተከሳሹ በከሳሹ ላይ የገለጸው አሳብ ሐሰት መሆኑን በእርግጥ ያወቀው ካልሆነ በቀር ስም እንዳጠፋ አያስቈጥረውም፡፡

ቊ 2047፡፡ (4) የተነገረው ጒዳይ እውነትነት፡፡

(1) ተከሳሹ ያወራው የስም ማጥፋት ጒዳይ እርግጠኛ ለመሆኑ ማስረጃ ካገኘ ስም አጠፋ አያሰኘውም፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው ሁኔታ፤ ያደረገው የስም ማጥፋት ጒዳይ በተለይ ሰውዬውን ለመጉዳት ብቻ ያደረገው መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር
በአላፊነት አይጠየቅም፡፡

ቊ 2048፡፡ (5) የማይደፈር መብት፡፡

(1) በምክር ቤት (በፓርላማ) ክርክር ወይም በፍርድ ቤት ክርክር ላይ በተደረገው ንግግር ተናጋሪው በአላፊነት አይጠየቅም፡፡

(2) የዚህን ዐይነት ንግግር በትክክለኛ እርግጥነቱን የገለጠው ሰው በአላፊነት የሚጠየቀው፤ ይህን ተግባር የፈጸመው ሰውዬውን ለመጉዳት
ብቻ ያደረገው መሆኑ በታወቀ ጊዜ ነው፡፡

ቊ 2049፡፡ (6) በቂ ምክንያት፡፡

(1) በጋዜጣ ታትሞ የተወራ የስም ማጥፋት ነገር ተደርጎ እንደሆነና ተከሳሹም በጋዜጣ አማካይነት የሰውን ስም ያጠፋው በተለይ አንዱን
ሰው ለመጉዳት አስቦ ሳይሆንና ከፍ ያለ ቸልተኛነትም ያላደረገ ሆኖ ሲገኝ በከሳሹም ጠያቂነት የስም ማጥፋቱን ጒዳይ እንደገና ቃሉን
መልሶ ይቅርታ ከጠየቀ አላፊነቱ ይወገድለታል፡፡
(2) የስም ማጥፋቱ ነገር የተደረገው ከአንድ ሳምንት በበለጠ ጊዜ በሚወጣ (በሚታተም) ጋዜጣ ላይ የሆነ እንደሆነ፤ የስም ማጥፋቱ ነገር
የሚለውጥበትን የይቅርታ መጠየቂያው ጽሑፍ ጠያቂው ራሱ በመረጠው ጋዜጣ ላይ በፍጥነት እንዲታተምለት ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

(3) የስም ማጥፋቱ ነገር የሚለወጥበትን ጋዜጣ፤ ጠያቂው ባልመረጠ ጊዜ፤ የስም ማጥፋቱ ነገርና የይቅርታ መጠየቁ ነገር የሚታተመው
በዚያው ቀድሞ በወጣው ጋዜጣ ዐይነት ነው፡፡

ቊ 2050፡፡ የባልና የሚስትን መብት ስለ መንካት፤ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አንድ ሰው፤ ሴትዮዋ ባለባል መሆኑዋን እያወቀ ያለባልዋ ፈቃድ ባልዋን ትታው እንድትሄድ ቊርጥ አሳብ እንዲኖራት ያደረገ እንደሆነ
ጥፋተኛ ነው፡፡

(2) አንድ ሰው ባለሚስት የሆነውን ሰው፤ ሚስት እንዳለችው እያወቀ ሚስቲቱ ሳትፈቅድ ትቷት እንዲሄድ ያደረገ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

(3) እንደዚሁም ባሉዋ ነገሩን እንደሚቃወም ሲያውቀው የሰው ሚስት ተቀብሎ እቤቱ ያስቀመጠ ወይም ያስተናገደ እንደሆነ ጥፋተኛ
ነው፡፡

ቊ 2051፡፡ (2) የሚበቃ ምክንያት፡፡

በላይኛው ቊጥር በ 3 ኛው ንኡስ ቊጥር እንደተመለተው ሁሉ እንደ ጥፋት የማይቈጥሩት፤


(ሀ) ባልና ሚስቱ ተለያይተው ለመኖር ተስማምተው እንደሆነ፤

(ለ) ባልዮው በሚስቱ ላይ የማሠቅየት ተግባር በመፈጸሙ ጥፋተኛ ሆኖ እንደሆነ ወይም ባልዮው በሚስቱ ላይ ግፍ መሥራቱን ተከሳሹ
በሕሊና መንገድ በእርግጥ በመገመቱ ሴትዮዋን ተቀብሎ ያኖራት ሰብዓዊ ርኅራኄን በሚመለከት አድራጎት የሆነ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2052፡፡ የማስተማርና የመጠበቅ ግዴታ፡፡

(1) አንድ ሰው በሕግ አገባብ ወይም በሕጉ መሠረት በራሱ አሳዳሪነት ወይም በራሱ ጠባቂነት ሥር እንዲተዳደር በአደራ የተሰጠውን
ሌላውን ሰው በአስተዳዳሪነቱ ምክንያት ሊፈጽምለት የሚገባውን በሕሊና አገማመት ከእርሱ ዘንድ የሚጠበቀውን ተግባር በጊዜው
አጋጣሚና በልማድ አሠራር ሁኔታ ባለው ምቾት መጠን በትምህርት የማሳደግንና በሚገባ የመጠበቅን ጒዳይ ሳይፈጽምለት የቀረ እንደሆነ
ጥፋተኛ ነው፡፡
በዚሁ ባደረገው ጒድለት ምክንያት በሥልጣኑ ሥር የሚተዳደረው ሰው አንድ ጒዳት የደረሰበት እንደሆነ አላፊ ነው፡፡
እንዲሁም ከዚህ ጒድለት የተነሣ በሥልጣኑ ውስጥ ሆኖ የሚጠብቀው ሰው በሌላ ሰው ላይ ባደረሰው ጒዳት ምክንያት አላፊ ነው፡፡

ቊ 2053፡፡ በሌላው ሰው ቤት ወይም መሬት ስለ መግባት፡፡

አንድ ሰው፤ በሕግ ሳይፈቀድለትና ቤቱን ወይም መሬቱን በደንብ ባለ እጅ የሆነው ወይም የያዘው ሳይፈቀድለትና የማይፈቅድ መሆኑንም
በግልጽ እየተናገረ፤ የሌላ ሰው ርስት በሆነ መሬት ወይም በሌላ ሰው ቤት የገባ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡
ቊ 2054፡፡ ንብረትን ስለ መድፈር፡፡

አንድ ሰው በሕግ ሳይፈቀድለት ባለንብረቱ ሳይፈቅድለትና አለመፍቀዱንም በመግለጽ ሲናገር በደንብ በእጁ የሆነውን የሌላውን ሰው
ንብረት የወሰደ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2055፡፡ ውል ከማድረግ በፊት የተደረገ ድርድር፡፡

አንድ ሰው፤ ሌሎች ሰዎች ከሱ ጋራ ውል እንዲያደርጉ አሳቡን ከገለጸላቸው በኋላና እነዚሁንም ሰዎች ወጪ እንዲያደርጉ አግባብቷቸው
እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2056፡፡ በውል የገባውን የግዴታ ቃል ስላማክበር (ስለ መጣስ)፡፡

(1) አንድ ሰው በሁለት ሰዎች መካከል ውል መኖሩን እያወቀ ውል ካደረጉት ሰዎች መካከል ካንደኛው ወገን ጋራ ሌላ ውል አድርጎ ቀድሞ
የነበረውን ውል ለመፈጸም እንደማይቻል ያደረገ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

(2) ቢሆንም የመጀመሪያው ውል ተጣሰብኝ ብሎ የክስ አቤቱታ የሚያቀርበው ሦስተኛ ወገን፤ ውሉ እንዲፈጸም አስፈላጊውን ጥንቃቄ
በቸልተኛነት ሳያደርግ ቀርቶ እንደሆነ፤ ይህ የኋለኛው ተዋዋይ በአላፊነት አይጠየቅም፡፡

ቊ 2057፡፡ የማይገባ ውድድር፡፡

አንድ ሰው፤ ሐሰተኛ በሆነ ማስታወቂያ ወይም ቅን ልቡናን ተቃራኒ በሆነ በማናቸውም ሌላ ዐይነት አድራጎት የአንዱን ፋብሪካ የሥራ ፍሬ
(ዕቃ) ወይም የአንድ የንግድ ቤት መልካም ስም የሚያጠፋ ስብከት ያደረገ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2058፡፡ የሌለውን አስመስሎ ማሳየት፡፡

አንድ ሰው፤ በሚሰጠው የማረጋገጫ ቃል፤ በጠባዩ፤ በአካሄዱ ወይም ባለማድረጉ የአንድ ያልተወሰነ ነገር ሁኔታ መኖሩን ሌሎች ሰዎች
ወይም አንዳንድ ባዕዶች ሰዎች እንዲያምኑ ያግባባቸው እንደሆነ የዚሁንም ነገር እርግጠኛውን ሀልዎት በተቃራኒ ሁኔታ እንዲያምኑ ቅን
ሕሊናን ተቃዋሚ በሆነ ዐይነት ሌሎቹን ሰዎች ያግባባ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2059፡፡ ያልተካከለ ወሬ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

ማንም ሰው ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኛነት ለሌላ ሰው ያልተካከለ ወሬ የማስተላለፍ ጥፋት እንዳደረገ የሚቈጠረው፡-


(ሀ) ከእርሱ ወሬውን የሰማው፤ ወይም ሌላው ሰው ይህን ወሬ በማመን በሚሠራው ሥራ ጉዳት የሚያገኘው መሆኑን ያወቀ ወይም ማወቅ
የሚገባው የሆነ እንደሆነ፤

(ለ) በልዩ ሞያ ሥራው ምክንያት ትክክለኛ ወሬ (መረጃ) እንዲሰጥ የሚገባው እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2060፡፡ (2) ልዩነት፡፡

(1) ይህን ያልተካከለ ወሬ የሰጠ ሰው፤ በሰጠው ወሬ ላይ ያስረዳው የአንዱን ሰው ሁኔታዎቹን፤ ዐመሉን ለመክፈል የሚችል መሆኑን፤
ችሎታውን በመናገር ለዚሁ ሰው አንድ ሥራ ወይም እምነት ወይም ገንዘብ ወይም የንግድ ዕቃ እንዲያገኝ በማሰብ አድርጎት እንደሆነ፤
አላፊነት የለበትም፡፡

(2) ይህንንም የመግለጫ ቃሉን በጽሑፍ አድርጎ ራሱ ካልፈረመ በቀር አላፊነት ሊመለከተው አይችልም፡፡

ቊ 2061፡፡ (3) ምስክሮች፡፡

(1) አንድ ነገር መፈጸሙን ወይም ያለ መፈጸሙን ወይም አንድ አድራጎት መኖሩን ወይም ያለመኖሩን የሚያረጋግጡ ምስክሮች የሰጡት
የምስክርነት ቃል እርግጠኛ ስለመሆኑ አላፊዎች ናቸው፡፡

(2) አላፊነታቸውም የአረጋገጡትን እውነት ያልሆነ ቃል እንደ እውነተኛ በማመን አንድ ነገር ለሠሩ ሰዎች ነው፡፡

(3) ምስክሮቹ ይህን ያደረጉት በቅን ልቡና የሆነ እንደሆነ፤ ስሕተት እንዲገቡ ባደረጓቸው ሰው ላይ ክስ የማቅረብ መብታቸው የተጠበቀ
ነው፡፡
ቊ 2062፡፡ ምክር ወይም የአደራ ቃል ስለ መስጠት፡፡

አንድ ሰው ለሌላው ሰው ምክር ቢሰጥ ወይም አደራ ቢለው ጥፋተኛ አይደለም፡፡


ቊ 2063፡፡ ስለ መያዝ፡፡
አንድ አበዳሪ ባለዕዳው ሊከፍለው የሚገባውን ዕዳ ለማስከፈል ሲል ሊቀበል ከሚገባው ገንዘብ ጋራ ተመዛዛኝ ያልሆነ ከፍ ያለ ነገር
አስፈላጊ ሳይሆን የያዘ እንደሆነ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2064፡፡ የፍርድን ትእዛዝ ስለ መፈጸም፡፡

(1) አንድ ፍርድ አስፈጻሚ፤ ዳኛው የሰጠው የፍርድ ውሳኔ ትክክለኛ አሠራሩን የያዘ (ፎርም) ከሆነ የተሰጠውን ትእዛዝ ቢፈጽም ጥፋተኛ
አይደለም፡፡
(2) ነገር ግን ትእዛዙ ከደንበኛው አሠራር ፎርም ውጭ የሆነ እንደሆነ ወይም ፍርድ አስፈጻሚው ከተሰጠው ትእዛዝ ያለፈ፤ ወይም
ትእዛዙን ሕግን ባለማክበር የፈጸመ እንደሆነ፤ ጥፋተኛ ነው፡፡

ቊ 2065፡፡ ስለ ይርጋ፡፡
አንድ ሰው በባለ ይዞታነቴ ወይም በይርጋ ደንብ መክሰስ ቀርቶልኛል ብሎ ቢከራከር ጥፋተኛ አይደለም፡፡
ክፍል 2፡፡
አጥፊ ሳይሆን አላፊ ስለ መሆን፡፡
ቊ 2066፡፡ አስፈላጊ ሁኔታ፡፡

(1) አንድ ሰው ራሱን ወይም ሌላውን ሀብቱን ወይም የሌላውን ሰው ሀብት በርግጥ ሊደርስበት ከሚችል አደጋ ለማዳን ሲከላከል በሌላው
ሰው ላይ ሆነ ብሎ ጉዳት ያደረሰበት እንደሆነ አላፊ ይሆናል፡፡

(2) ነገር ግን የደረሰው ጉዳት ጉዳቱ በደረሰበት ሰው ጥፋትና ምክንያት እንደሆነ አላፊነት አያመጣም፡፡

ቊ 2067፡፡ በሰው አካል ላይ ጉዳት ስለ ማድረስ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አንድ ሰው በሠራው ሥራ በሌላ ሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ አላፊ ነው፡፡

(2) ቢሆንም፤ ይህን ጉዳት ያደረሰው ሥራ በሕግ የተፈቀደ የታዘዘ እንደሆነ ወይም ሥራው የተፈጸመው ራስን ለማዳን በሚገባ ሲከላከል
እንደሆነ ወይም ደግሞ አደጋው ሊደርስ የቻለው በተበዳዩ ጥፋት ምክንያት ብቻ እንደሆነ በአድራጊው ላይ ማናቸውም አላፊነት
አይደርስበትም፡፡
ቊ 2068፡፡ (2) የስፖርት ሥራ፡፡ (ጨዋታ)፡፡
አንድ ሰው የስፖርት ሥራ በመሥራት ላይ ሳለ በዚሁ እስፖርት ተካፋይ የሆነውን ወይም ተመልካቹን ቢያቈስለው፤ በስፖርት ሥነ
ሥርዐት የሚመለከተውን ደንብ በግልጽ ካልጣሰ ወይም የተንኰል ሥራ ካልፈጸመ በቀር በአላፊነት አይጠየቅም፡፡

ቊ 2069፡፡ አደገኛ ሥራ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አንድ ሰው የሚፈነድ ወይም መርዝ የሚሆኑ ቅመማት በሥራ ላይ በማዋል ወይም በማከማቸት፤ ወይም ከፍተኛ ጒልበት ያለው
የኤሌክትሪክ መሥመር በመዘርጋት፤ ወይም የመሬትን የተፈጥሮ መልክ በለወጥ ወይም በተለይ አደገኛ የሆነ የእንዱስትሪ ሥራ በማካሄድ
ይህ ሥራው በሌላ ሰው ላይ አደጋ ያደረሰ እንደሆነ ለደረሰው ጉዳት አላፊ ይሆናል፡፡

(2) ይህን ከዚህ በላይ የተመለከተውን ጉዳት ያደረሰው መንግሥትም ቢሆን ወይም ይህ ሥራ በባለሥልጣን የተፈቀደለት መሥሪያ ቤት
ቢሆንም ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተው ደንብ ይጸናል፡፡

ቊ 2070፡፡ (2) ለመድረስ የሚችል አደጋ፡፡


ጥፋት ያለበት ካልሆነ በቀር ጎረቤት በሆኑት ንብረቶች ላይ በአደጋ ምክንያት የደረሰ መበላሸት አላፊነትን አያመጣም፡፡
ቊ 2071፡፡ እንስሳዎች ባደረጉት ጉዳት የሚመጣ አላፊነት (1) የእንስሳው ባለቤት፡፡
የአንድ እንስሳ ባለሀብት ከብቱ ጉዳቱን ያደረሰው በድንገት በማምለጥም ቢሆን ያደርጋል ተብሎ ያልታሰበውንም ጉዳት አድርሶ ቢገኝ፤ ይህ
እንስሳው ባደረሰው ጉዳት አላፊ ነው፡፡

ቊ 2072፡፡ (2) የእንስሳው ጠባቂ፡፡

(1) እንዲሁም አንድ ሰው ለግል ጥቅሙ እንዲያውለው በራሱ ጠባቂነት ውስጥ የሚገኘው የሌላ ሰው ከብት በእርሱ እጅ ባለበት ጊዜ
ላደረሰው ጉዳት አላፊ ነው፡፡

(2) እንዲሁም ደግሞ እንስሳውን በኪራይ ወይም በተውሶ ወይም ለመጠበቅ ወይም ለመቀለብ፤ ወይም ደግሞ በማናቸውም ሌላ ዐይነት
ሁኔታ የተረከበ፤ በራሱ ጠባቂነት ውስጥ ያለው እንስሳ ጉዳት ባደረሰ ጊዜ አላፊ የሚሆነው ይኸው እንስሳ በእጁ የሚገኘው ሰው ነው፡፡

(3) አንድ እንስሳ በታዛዥነት የተረከበ፤ ወይም ለባለከብቱ ወይም ለሌላው ሰው የሚሠራበት ሰው፤ እንስሳው ያደረሰው ጉዳት በርሱ
ጥፋት ካልሆነ በቀር አላፊ አይሆንም፡፡

ቊ 2073፡፡ (3) የአላፊነቶች ግንኙነት፡፡

(1) የእንስሳው ባለመብት እንስሳው ጉዳት ያደረሰበትን ተበዳይ ከካሰ በኋላ፤ የእንስሳው ጠባቂ የነበረውን ሰው ሊጠይቀው ይችላል፡፡
(2) እንስሳው ጉዳት ያደረሰው በባለሀብቱ ጥፋት ወይም በራሱ አላፊነት ውስጥ በሚተዳደረው በሌላው ሰው ጥፋት ካልሆነ በቀር፤ በዚህ
ምክንያት ያደረሰበትን ኪሣራ በሙሉ እንዲመልስለት ጠባቂ የነበረውን ሰው ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

ቊ 2074፡፡ (4) ጌታው የለቀቀው እንስሳ፡፡

(1) የሰው አገልጋይ የሆነ የቤት እንስሳ በሌላ ሰው ሀብት ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ፤ የዚህ እንስሳ ባለቤት የሆነው ሰው እንስሳውን ጉዳት
ላደረሰበት ሰው የለቀቀ እንደሆነ ከአላፊነቱ ለመዳን ይችላል፡፡

(2) ቢሆንም፤ እንስሳው ጉዳት ያደረሰው በራሱ ጥፋት ዋይም በሱ ሥልጣን ሥር በሚተዳደረው ሰው ጥፋት ከሆነ ግን ይህ መብት
አይኖረውም፡፡

(3) የቤት እንስሶችና የቤት አራዊት ተብለው የሚቈጠሩት ለመደሰት ወይም ከነሱ ጥቅምን ለማግኘት እንደተለመደው ሰው የሚያኖራቸው
ናቸው፡፡
ቊ 2075፡፡ (5) ጠባቂው የለቀቀው እንስሳ፡፡

(1) የእንስሳው ጠባቂ (እረኛ) የሚገደደው ጉዳቱ በደረሰበት ጊዜ፤ እንስሳው በነበረው ግምት ልክ ብቻ ነው፡፡

(2) ሆኖም የደረሰው ጉዳት በቤት እንስሳና በቤት አራዊት ያልሆነ እንደሆነ ወይም ጉዳቱ በራሱ ወይም በርሱ አላፊነት ሥር በሚገኘው
ሰው ጥፋት የተፈጸመ እንደሆነ፤ ለእንስሳው ጠባቂ ተገዳጅነት ወሰን የለውም፡፡

ቊ 2076፡፡ ለተበዳዩ ስለሚከፈለው ኪሣራ የሚሆን መያዣ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት የሌላ ሰው እንስሶች በማይንቀሳቀሰው ንብረት ገብተው ጉዳት ያደረሱበት እንደሆነ ስለ ደረሰበት ጉዳት
ሊከፈለው የሚገባውን ኪሣራ ከባለከብቱ ላይ እስኪቀበል ድረስ እንስሶችን መያዣ አድርጎ በእጁ ሊያቈይ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ከእንስሳው ግምት መጠን በላይ የሆነውን ጉዳት ለማስቀረት እንስሳውን ለመግደል አስፈላጊ ሲሆን፤ እንስሶቹን ለመግደል
መብት አለው፡፡

(3) በሁለቱ አጋጣሚ ሁኔታዎች ሳይዘገይ ለእንስሶቹ ባለቤት ማስታወቅ ይገባዋል፡፡ ባለቤቱንም ባያውቀው ለማግኘት የሚችልበትን
አስፈላጊውን ማድረግ አለበት፡፡

ቊ 2077፡፡ ሕንጻ (ቤት)፡፡(1) መሠረቱ፡፡

(1) ያንድ ሕንጻ ባለሀብት ወይም ባለይዞታ ሕንጻው ሊያደርስ ይችላል ተብሎ ያልታሰበ ድንገተኛ ነገር ቢያደርስም ይህ ሕንጻ
በሚያደርሰው ጉዳት አላፊ ነው፡፡

(2) ሕንጻውን የሠራውን፤ ወይም በዚህ ሕንጻ ውስጥ የሚገኘውን፤ ወይም ይህ ሕንጻ ባደረሰው ጉዳት አጥፊ የሆነውን ሰው፤ ለባለቤቱ
ያለው የመጠየቅ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2078፡፡ (2) ሕንጻን ስለ መልቀቅ፡፡

(1) የሕንጻው ባለቤት ይህን ቤቱን ጉዳት ለደረሰበት ሰው የለቀቀለት እንደሆነ ከአላፊነቱ ውጭ ለመሆን ይችላል፡፡

(2) ቢሆንም፤ ጉዳቱ የደረሰው እሱ ራሱ ባደረገው ጥፋት ወይም እርሱ በሥልጣኑ ሥር በሚያሳድረው ሰው ጥፋት ከሆነ ይህ መብት
አይኖረውም፡፡
ቊ 2079፡፡ (3) የሚያሠጋ ጉዳት፡፡
ከሌላ ሰው ቤት ላይ ጉዳት ይደርስብኛል ብሎ የሚሠጋ ሰው፤ የዚህ አሥጊ የሆነው ሕንጻ ባለቤት ይህ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ
አሥጊው ነገር እንዲወገድለት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሊጠይቅ መብት አለው፡፡

ቊ 2080፡፡ (4) ከሕንጻ ላይ የሚወድቁ ነገሮች፡፡


በአንድ ሕንጻ ውስጥ የሚኖር ሰው፤ ከዚህ ሕንጻ እየወደቁ በሌላው ላይ ጉዳት በሚያደርሱት ተንቀሳቃሽ ነገሮች አላፊ ነው፡፡
ቊ 2081፡፡ መኪናዎችና ባለሞተር ተሽከርካሪዎች፤ (1) ባለቤቱ፡፡

(1) የአንድ መኪና ወይም የአንድ ባለሞተር ተሽከርካሪ ባለቤት የሆነ ሰው አደጋውን ያደረሰው ይህን መኪና ወይም ይህን ባለሞተር
ተሽከርካሪ ለማንቀሳቀስ ወይም ለመንዳት ባልተፈቀደለትም ሰው ቢሆን እንኳ መኪናው ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው ባደረሰው ጉዳት
አላፊ የሚሆነው ባለሀብቱ ነው፡፡

(2) ቢሆንም አደጋው በደረሰ ጊዜ መኪናው ወይም ተሽከርካሪው የተሰረቀበት ለመሆኑ ማስረዳት የቻለ እንደሆነ ባለሀብቱ አላፊነት
የለበትም፡፡
ቊ 2082፡፡ (2) ጠባቂ ወይም ሠራተኛ፡፡

(1) እንዲሁም መኪናውን ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪውን ለግል ጥቅሙ ሊገለገልበትና ሊጠቀምበት የወሰደው ሰው፤ ይህ መኪና ወም
ባለሞተር ተሽከርካሪው በእጁ በሚገኙበት ጊዜ ላደረሰው ጉዳት አላፊ ነው፡፡

(2) ከመኪናው ወይም ከባለሞተር ተሽከርካሪው ጋራ ግንኙነት ያለው ታዛዥ ስለ ባለቤቱ ወይም ስለ ሌላ ሰው ሆኖ በመኪናው ወይም
በባለሞተር ተሽከርካሪው በሚሠራበት ጊዜ ይህ መኪና ወይም ባለሞተር ተሽከርካሪው ጉዳት ያደረሰው በራሱ ጥፋት ምክንያት ካልሆነ
በቀር ለደረሰው ጉዳት አላፊ አይሆንም፡፡

ቊ 2083፡፡ (3) የአላፊነቶች ግንኙነት፡፡

(1) የመኪናው የባለሞተር ተሽከርካሪው ባለቤት ተበዳዩን ተገድዶ ከካሠ በኋላ ጠባቂ የነበረውን ሰው በኪሣራው አከፋፈል ሊጠይቀው
ይችላል፡፡
(2) እሱ ራሱ ባደረሰው ጉዳት ጥፋት ካልሠራ ወይም ጒዳቱ የደረሰው እርሱ ሥልጣን ሥር በሚተዳደረው ሰው በተደረገ ጒድለት ካልሆነ
በቀር የከፈለው ኪሣራ በሙሉ እንዲመለስለት ጠባቂውን ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

ቊ 2084፡፡ የተሽከርካሪዎች መጋጨት፡፡

(1) ሁለት ባለሞተር ተሽከርካሪዎች ሲጋጩ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ በየራሱ አንዱ በአንዱ ላይ አደጋ እንዳደረሰ ይቈጠራል፡፡

(2) ለየአንዳንዱ ተሽከርካሪ ባለሀብት ወይም ለአደጋው አላፊ የሆነው ሰው በአደጋው ምክንያት ከደረሰው ጠቅላላ ጉዳት ገሚሱን መክፈል
አለበት፡፡
(3) ይህ አደጋ የደረሰው በተለይ ወይም በጠቅላላው በአንደኛው መኪና ነጂ ስሕተት መሆኑ በማስረጃ የተገለጸ እንደሆነ ግን ከዚህ በላይ
ያለው ደንብ አይጸናም፡፡

ቊ 2085፡፡ የተሠሩ ዕቃዎች፡፡

(1) ትርፍ ለማግኘት ሲል ዕቃዎችን የሚሠራና እነዚህኑ ዕቃዎች ለሕዝብ የሚያቀርብ ሰው በዕቃዎቹ በሚገባ ሲጠቀምባቸው በሌላ ሰው
ላይ ጉዳት ያደረጉ እንደሆነ አላፊ ነው፡፡

(2) ቢሆንም፤ ይህ ዕቃ በልማድ እንደሚደረገው ተመርምሮ ቢሆን ኖሮ፤ ጉዳቱን ያመጣው ጒድለት ተገልጾ ሊታወቅ የሚችል ከሆነ፤
ምንም አላፊነት የለበትም፡፡

ቊ 2086፡፡ ከአላፊነት ውጭ ስለ መሆን፡፡

(1) በእንስሳት፤ በሕንጻዎች፤ (በቤቶች) በመኪናዎች ወይም በባለሞተር ተሽከርካሪዎች ወይም በፋብሪካ ተሠርተው በወጡት ነገሮች
ምክንያት፤ አደጋ በሚፈጠርበት ወይም በሚደርስበት ጊዜ ሕጉ አላፊዎች የሚያደርጋቸው ሰዎች አንዳች ጥፋት ያላደረጉ መሆናቸውን
በማስረዳት ወም የጉዳቱ ምክንያት ሳይታወቅ በመቅረት፤ ወይም ሦስተኛ ወገን ጥፋት ነው ብሎ በማስረዳት ጉዳቱ በደረሰበት ሰው በኩል
ከአላፊነት ለማምለጥ አይችሉም፡፡

(2) ጉዳቱ የደረሰው በከፊል ወይም በሙሉ ከተበዳዩ ጥፋት የተነሣ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር፤ በከፊልም ሆነ በሙሉ ከአላፊነቱ ለመዳን
አይችሉም፡፡
ቊ 2087፡፡ ሌሎች ነገሮች፡፡
የአንድ ነገር ባለቤት ወይም ጠባቂ የሆነ ሰው ራሱ ጥፋት ካላደረገ ወይም በራሱ አላፊነት ውስጥ የሚተዳደር ሰው ካላጠፋ በቀር ከዚህ
በላይ ባሉት ቊጥሮች ከተመለከተው አስተያየት ውጭ በሆነ ጒዳይ በአላፊነት አይጠየቅም፡፡

ቊ 2088፡፡ የውል ግንኙነቶች፡፡

(1) ጉዳቱን ካደረሰው አደገኛ እንዱስትሪ፤ ወይም እንስሳ፤ ወይም ሕንጻ ወይም ሌላ ነገር ግንኙነት ያለውና በሕግ በኩልም ለነዚሁም አላፊ
ነው ከተባለው ሰው ጋራ ተዋውያለሁ የሚለው ሰው አሥጊ የሆኑ ነገሮችን በመፍጠር ወይም በእንስሳዎች ወይም በሕንጻዎች ወይም በሌላ
ነገሮች ለሚደርሱ ጉዳቶች የአላፊነትን ደንቦች በመጥቀስ ከአላፊነት ለመዳን አይችልም፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ጉዳቱ የሚያደርሰው ነገር የሚመራሉ በተደረገው የውል ደንብ መሠረት ነው፡፡

ቊ 2089 ፡፡ ጥቅም የሌለው ግንኙነት፡፡

(1) እንዲሁም ውል ባይኖርም እንኳ ጉዳቱ በተደረገ ጊዜ ባለሀብቱ ወይም ጠባቂው አንድ ጥቅም ሳያገኝ በእንስሳው በሕንጻው፤ ወይም
በሌላ ነገር ይገለገል የነበረው ሰው እንስሳው ሕንጻው፤ ወይም ሌላ ነገር ለሚያደርሰው ጉዳት የአላፊነትን ደንቦች ጠቅሶ ለመከራከር
አይችልም፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ጥፋት ካላደረጉ፤ ባለሀብቱ ወይም ጠባቂው አላፊነት የለባቸውም፡፡
ክፍል 3፡፡
የካሣ አከፋፈልና ልክ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ስለ ጉዳት ኪሣራ፡፡
(ሀ) ግልጽ የሆኑ ጉዳቶች፡፡

ቊ 2090፡፡ የኪሣራ አከፋፈል፡፡

(1) በመደቡ በጉዳቱ ምክንያት ተበዳዩ የሚካሠው ለጉዳቱ ተመዛዛኝ የሆነ ኪሣራ በመክፈል ነው፡፡

(2) የሰዎች ነጻነትና የሦስተኛ ወገን መብቶች እንደተጠበቁ ሆነው በጉዳቱ ኪሣራ ፋንታ ወይም ከኪሣራው በላይ ለጉዳቱ ኪሣራ እንዲሆን
ወይም ለጉዳቱ ወሰን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ዳኞች ለመበየን ይችላሉ፡፡

ቊ 2091፡፡ የኪሣራው ልክ፡፡


ለደረሰው ጉዳት አላፊ መሆኑ በሕግ የታወቀው ሰው የሚከፍለው የጉዳት ካሣ፤ አላፊነቱን ያመጣው ጒዳይ በተበዳዩ ላይ ከደረሰው ጉዳት
ጋራ እኩል ሆኖ መመዛዘን አለበት፡፡

ቊ 2092፡፡ ለወደፊት ሊደርስ ስለሚችል ጉዳት፡፡


ለወደፊት ሊደርስ ይችላል ተብሎ የሚገመተው ጉዳት የተረጋገጠ ሲሆን፤ እስኪፈጸም ድረስ ሳይጠበቅ ካሣ ሊከፈለው ይገባል፡፡
ቊ 2093፡፡ አሹራንስ የገባ ተበዳይ፡፡

(1) ተበዳዩ ለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ እንዲከፈለው አሹራንስ ቢገባም አሹራንስ እንዳልገባ ሰው ሁሉ ለደረሰበት ጉዳት ካሣ ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
(2) አሹራንስ አድራጊው እከፍላለሁ ብሎ በገባው የአሹራንሱ ውል መሠረት የከፈለውን የአሹራንስ ኪሣራ ይህን ጉዳት ካደረሰው ሰው
ላይ በራሱ ስም ሆኖ ማናቸውንም ኪሣራ ሊጠይቅ አይችልም፡፡
(3) ነገር ግን የአሹራንስ ውል አድራጊው ለደረሰው ጉዳት አላፊ ከሚሆነው ሰው ላይ በተበዳዩ ስም ተዳራጊ ሆኖ የተበዳዩን መብቶች
የመጠየቅ ሥልጣን እንዲኖረው አስቀድሞ ለመዋዋል ይችላል፡፡

ቊ 2094፡፡ ጉዳት የደረሰበት ጡረተኛ፡፡

(1) ተበዳዩ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት


መጦሪያ የሚቀበል እንደሆነ መጦሪያ እንደማይቀበል ሰው ሁሉ ለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ ለመጠየቅ ይችላል፡፡
(2) ጡረታ የሚከፍል ሰው በተጠዋሪ ላይ በደረሰው ጉዳት ምክንያት ለተጎጂው ጡረታ በመክፈሉ፤ ጡረታውን ለመክፈል ያደረሰውን
የጉዳት ሥራ የፈጸመውን ሰው ማናቸውንም ኪሣራ ይክፈለኝ ብሎ በራሱ ስም ሊጠይቀው አይችልም፡፡

(3) ከተበዳዩ ጋራ በሚያስተሳስረው ግንኙነት ምክንያት በተበዳዩ ስም ተዳራጊ ሆኖ የተበዳዩን መብት ሊጠይቅ ይችላል ተብሎ አስቀድሞ
ለመስማማት ይቻላል፡፡

ቊ 2095፡፡ ስለ ሞት አደጋ (1) አንዳንድ የቅርብ ዘመዶች ስለ አላቸው መብቶች፡፡

(1) የተጎጂው ባል ወይም ሚስት፤ ወይም ወላዶቹና ልጆቹ በተጎጂው ላይ ከደረሰው የሞት አደጋ የተነሣ በራሳቸው ስም ሆነው
በመተዳደሪያ ረገድ ለሚደርስባቸው ጉዳት ካሣ ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

(2) ስለዚህ ጉዳት የሚከፈለው ካሣ ምግብን (መተዳደርን) በመስጠት እንደሚደረገው ጡረታ፤ መልክና ዐይነት ይሆናል፡፡

(3) ከሳሾቹ ቀለብ እንዲሰጧቸው የሚጠይቋቸው ዘመዶች ቢኖሯቸው እንኳ፤ ይህ በምግብ ረገድ ለመጦሪያ የሚሰጣቸው ካሣ
ይገባቸዋል፡፡
ቊ 2096፡፡ ሌሎች ሰዎች፡፡
ሌሎች ሰዎች አደጋ የደረሰበት ሰው ይረዳቸው ወይም ያስተዳድራቸው እንደነበረ ቢያረጋግጡ እንኳ፤ በተበዳይ ላይ በደረሰው የሞት አደጋ
ምክንያት በገዛ ራሳቸው ስም ሆነው ማናቸውንም ኪሣራ ሊጠይቁ አይችሉም፡፡

ቊ 2097፡፡ ቅን ልቡና፡፡

(1) ለደረሰው ጉዳት የሚከፈለው ካሣ ለቅን ልቡና ተቃራኒ በሆነው አኳኋን ሊጠየቅ አይችልም፡፡

(2) ተበዳዩ በማስተዋል ቢሠራ ኖሮ የደረሰበትን ጉዳት ሊያግደው ወይም ሊያቀለው የሚችል ሲሆን፤ በደረሰበት ጉዳት መጠን በሙሉ ካሣ
ለመጠየቅ አይችልም፡፡

ቊ 2098፡፡ ስለ ተበዳዩ ጥፋት፡፡

(1) በተበዳዩ ላይ የደረሰው ጉዳት በከፊሉ በገዛ ራሱ ጥፋት እንደሆነ ለተበዳዩ የሚከፈለው የጉዳት ካሣ በከፊሉ ብቻ ነው፡፡

(2) የጉዳቱ ካሣ በእንዴት ያለ ሁኔታ መካሥ የሚገባው መሆኑ መጠኑን ለመወሰን የአካባቢዎችን ሁኔታዎች ሁሉ፤ በተለይም ጉዳት
እንዲደርስ ጥፋቶቹ የተባበሩበት መጠን እንደዚሁም የነዚህን ጥፋቶች የየአንዳንዳቸውን ከባድነት በመገመት ነው፡፡

ቊ 2099፡፡ በርትዕ የመወሰን ችሎታ፡፡ (1) ጥፋት መሆኑን ስላለማወቅ፡፡

(1) የሥራውን ጥፋት ለመገመት የማይችል ሰው፤ አላፊነትን የሚያስከትል ሥራ ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ በዚሁ ጒዳይ ላይ አስተያየት
እንዲደረግበት ርትዕ ሲያስገድድ ዳኞች ሊከፈል የሚገባውን የካሣውን ልክ መወሰን ይችላሉ፡፡

(2) ስለዚህ ዳኞች የነገረተኞችን ንብረት ሁኔታንም፤ እንደዚሁም በዳዩን ካሣ በመክፈሉ የሚደርስበትን ጉዳት ማመዛዘን አለባቸው፡፡

ቊ 2100፡፡ (2) የበላይ ትእዛዝ፡፡

(1) በዲሲፕሊን ወይም በታዛዥነት የተግባር ተገቢነት ስሜት ምክንያት ጥፋተኛው ጥፋቱን እንዲፈጽም አድርጎት በሚገኝበት ጊዜ በርትዕ
(በአገባብ) በኩል አስገዳጅ ሆኖ ሲገኝ ዳኞቹ የካሣውን ልክ፤ ለመወሰን ይችላሉ፡፡
(2) ለዚሁም ነገር ዳኞች የመታዘዙን ተገቢነት ማነስ ማደጉን መገመት አለባቸው፡፡

ቊ 2101፡፡ (3) ይደርሳል ተብሎ ሊታሰብ የማይችል ጉዳት፡፡

(1) ሊታሰቡ በማይቻሉ አጋጣሚ ሁኔታዎች ምክንያት የደረሰው ጒዳት እስከዚህ ከፍ ያለ ነገር ያስከትላል ተብሎ በአእምሮ ግምት ሊታሰብ
የማይችል እንደነበረ የታወቀ ሲሆን፤ የርትዕ ሁኔታ የሚያስገድድ በሆነ ጊዜ፤ ዳኞች ለዚህ ጉዳት አላፊ የሆነው ሰው ሊከፍል የሚገባውን
የካሣ ልክ አሻሽለው ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(2) አላፊነቱ የደረሰው ሆነ ብሎ ከተደረገ ጥፋት የመነጨ የሆነ እንደሆነ ግን በማናቸውም ምክንያት ቢሆን በዚህ ሥልጣናቸው ሊሠሩበት
አይችሉም፡፡
ቊ 2102፡፡ (4) ስለ ግምት አስቸጋሪነት፡፡

(1) ስለ ጉዳቱ ምን ያህል ኪሣራ እንደሚከፍል በትክክል ለመወሰን ያልተቻለ እንደሆነ፤ ዳኞቹ የነገሮቹን ተራ ሁኔታዎችንና ተጐጂውም
ያደረገውን ጥንቃቄ አመዛዝነው በመገመት የኪሣራውን ልክ በርትዕ ይወስናሉ፡፡

(2) ስለሆነም፤ የሚከፈለው ካሣ መጠን ብቻ ሳይሆን የጉዳቱም መፈጸም የሚያጠራጥር በሆነ ጊዜ ማንኛቸውንም የጉዳትካሣ እንዲከፈል
ለማድረግ አይቻልም፡፡

ቊ 2103፡፡ (5) አስፈላጊ ሁኔታ፡፡


ማንም ሰው ጥፋት ሳያደርግ ራሱን ለማዳን ወይም ሌሎችን ከጉዳት ወይም ከድንገተኛ አደጋ ለማዳን ሲል በሌላ ሰው ንብረቶች ላይ
ጉዳትን ያደረሰ አንደሆነ፤ ዳኞች አድራጊው የሚከፍለውን የካሣ ገንዘብ ልክ በርትዕ ይወስናሉ፡፡

ቊ 2104፡፡ ለደንቡ ብቻ ስለሚወሰኑት የጉዳት ኪሣራዎች፡፡


የከሳሹ መብት በመደፈሩ ምክንያት ወይም የመጣው አላፊነት በተከሳሹ ምክንያት መሆኑን ለማስረዳት ብቻ የክስ ተግባር በሚቀርብበት
ጊዜ ለደንቡ ብቻ የጉዳት ኪሣራዎች ሊወሰኑ ይችላሉ፡፡

(ለ) የሕሊና ጉዳት፡፡

ቊ 2105፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) ለደረሰው ጉዳት፤ ካሣ ለመክፈል ተመዛዛኝ በሆነ አድራጎት ሊፈጸም በሚቻልበት ጊዜ ሁሉ ጥፋተኛው በደሉ ለሚያስከትለው የሕሊና
ጉዳት ካሣን መክፈል ይገባዋል፡፡

(2) የሕሊና ጉዳት በሕጉ በግልጽ ካልተመለከተ በቀር ስለ ጉዳት ካሣ የገንዘብ ኪሣራ አያስከፍልም፡፡

ቊ 2106፡፡ ታስቦ ስለ ተደረገ ጥፋት፡፡


በከሳሹ ላይ ታስቦ የሕሊና ጉዳት በሚደረግበት ጊዜ ዳኞቹ በዚሁ በደል ካሣ ስም ተከሳሹ ለከሳሹ በርትዕ አንድ የሚገባ ካሣ እንዲከፍል
ወይም ከሳሹ ላመለከተው ለበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲከፈል ለመፍረድ ይችላሉ፡፡

ቊ 2107፡፡ በተበዳዩ ሰውነት ላይ ስለሚደርሰው ጉዳት፡፡


ተከሳሹ በከሳሹ ላይ አስቀያሚ ወይም የሚያስጠላ መጥፎ መንካት አድርጎ በተገኘ ጊዜ፤ ለከሳሹ ወይም ከሳሹ ላመለከተው በጎ ድርጅት
ለዚሁ በደል በካሣ ስም በርትዕ የሚገባ ካሣ እንዲከፍል ዳኞች ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

ቊ 2108፡፡ ያለ አገባብ ሰውን ስለ መያዝና ስለ ማገድ፡፡


እንዲሁም ተከሳሹ ሕግን ተቃራኒ በሆነ አኳኋን የከሳሹን ነፃነት አግዶ፤ በተገኘ ጊዜ፤ ለከሳሹ ወይም ከሳሹ ላመለከተው በጎ ድርጅት ለዚሁ
በደል ካሣ ስም በርትዕ የሚገባ ካሣ ሊቈረጥለት ይቻላል፡፡

ቊ 2109፡፡ ስምን ስለ ማጥፋት፡፡


ከሳሹ ተሰድቦ ወይም ስሙ ጠፍቶ በሚገኝበት ጊዜ ለከሳሹ ወይም ከሳሹ ላመለከተው በጎ ድርጅት ለዚሁ በደል በካሣ ስም በርትዕ የሚገባ
ካሣ እንዲከፍል ሊደረግ የሚችለው፡-

(ሀ) ከሳሹ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የሚያስቀጣ ወንጀል ሠርቷል በማለት ስሙን በማጥፋት የበደለው እንደሆነ፤

(ለ) የስም ማጥፋት ሥራዎች ከሳሹን በሞያ ሥራው ችሎታ የሌለው ወይም እውነተኛነት የሌለው መሆኑን ለማሳመን የተደረገ እንደሆነ፤

(ሐ) ነጋዴ ሆኖ ዕዳውን ለመክፈል አይችልም በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሆነ እንደሆነ፤

(መ) ተላላፊ በሽታ አድሮበታል በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ፤

(ረ) አስነዋሪ የሆነ ጠባይ አለው በማለት አስመስሎ ለማሳመን የሚጥር እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2110፡፡ የባልና ሚስትን መብት ስለ መድፈር፡፡


ተከሳሹ የባልነትን ወይም የሚስትነትን መብቶች ነክቶ በተገኘ ጊዜ ለከሳሹ ወይም ከሳሹ ላመለከተው በጎ ድርጅት ለዚሁ በደል በካሣ ስም
በርትዕ የሚገባ ካሣ ሊቈረጥ ይቻላል፡፡

ቊ 2111፡፡ ልጅን ነጥቆ ስለ መውሰድ፡፡


የልጁ ጠባቂነት፤ የከሳሹ ሆኖ ተከሳሹ ልጁን ነጥቆ በመውሰዱ ጥፋተኛ ሆኖ በወንጀል በሚቀጣበት ጊዜ ለከሳሹ ወይም እሱ ላመለከተው
በጎ ድርጅት ለዚሁ በደል በካሣ ስም በርትዕ የሚገባ ካሣ ሊቈረጥ ይቻላል፡፡

ቊ 2112፡፡ ንብረቶችን ስለ መድፈር፡፡


ከሳሹ እንዳይደርስበት በግልጽ ያስታወቀውን በመቃወም ተከሳሹ በደንብ በእጁ ወይም በይዞታው የሚገኘውን ንብረት የወሰደበት
እንደሆነ፤ ወይም በርስቱና በቤቱ የገባበት እንደሆነ፤ በከሳሹ ላይ ስለ ደረሰው ጉዳት ለዚሁ በደል ካሣ ሊወስን ይችላል፡፡

ቊ 2113፡፡ የአካል ጉዳት ወይም የሰው ሞት፡፡


አካሉ በመጒደል ለተበደለው ሰው፤ ወይም ሰውዬው የሞተ እንደሆነ ለዘመዱ የጉዳት ካሣ ዳኞች በአስተያየት ተገቢ ኪሣራ ሊቈርጡ
ይችላሉ፡፡
ቊ 2114፡፡ የንጽሕናን ክብር ስለ መድፈር፡፡

(1) ማንኛውም ሰው በመድፈር ሥራ ወይም ለክብረ ንጽሕና ተቃራኒ በሆነ ተግባር በወንጀል የተቀጣ እንደሆነ፤ ዳኞቹ ለተደፈረችው ሴት
በሕሊና በደል ካሣ ስም ተከሳሹ የሚሰጠውን በርትዕ የሚገባ ካሣ ለመቊረጥ ይችላሉ፡፡

(2) እንደዚሁም በሆነ ጊዜ ለሴቲቱ ባል ወይም በኀይል ለተገሠሠችው ልጃገረድ ቤተ ዘመዶች ካሣ ሊቈረጥ ይቻላል፡፡

ቊ 2115፡፡ በሚስት ላይ ስለ ደረሰ ጉዳት፡፡

(1) ማንም ሰው በሌላ ሰው ሚስት ላይ የአካል ጉዳት በማድረሱ በትዳር በኩል ለባሏ የምትሰጠው ጥቅም ወይም ደስታ እንዲቀነስ ያደረገ
እንደሆነ፤ ስለ በደል ካሣ ዳኞች በበዳዩ ላይ ለባለቤቷ በርትዕ ተገቢ የሆነ ኪሣራ ሊቈርጡለት ይችላሉ፡፡

(2) በዚህ ምክንያት በሚስቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት ባል የሚያቀርበው ክስ ሚስቱ ለደረሰባት ጉዳት ስለ ካሣ ጥቅም ከምታቀርበው ክስ
የተለየ ነው፡፡

ቊ 2116፡፡ ስለ አገር ልማድ፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተመለከቱት ቊጥሮች መሠረት የካሣውን ልክ ምን ያህል መሆኑን በርትዕ በአስተያየት ለመወሰንና እንዲሁም የቤተ
ዘመዱ እንደራሴ ሆኖ ለመነጋገር የሚችል ማን እንደሆነ ለማወቅ ዳኞች የአገር ልማድን መሠረት አድርገው ይይዛሉ፡፡

(2) ዳኞች እነዚህን የአገር ልማዶች ጊዜያቸው ያለፈና ከሕሊና፤ ከሰብዓዊ አእምሮ ተቃራንያን መሆናቸውን መዘንጋት አይገባቸውም፡፡

(3) የጉዳት ካሣውም በማናቸውም ምክንያት ከአንድ ሺሕ የኢት/ብር የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡
ቊ 2117፡፡ የቤተ ዘመድ እንደራሴ፡፡

(1) በሥራ ላይ የሚውሉ የአገር ልማዶች የሌሉ እንደሆነ፤ የቤተ ዘመድ እንደ ራሴነት ሥልጣን እንዳላቸው የሚቈጠሩት፡-

(ሀ) የተበደለው ሰው ባል ወይም ሚስት፤

(ለ) እነዚህ በሌሉበት ወይም ችሎታ የሌላቸው እንደሆነ፤ በዕድሜ ታላቅ የሆነና ለመሥራት ችሎታ ያለው ልጅ፤

(ሐ) ልጆቹ ባይኖሩ ወይም ችሎታ የሌላቸው እንደሆነ አባት፤

(መ) አባት ባይኖር ወይም ችሎታ የሌለው እንደሆነ እናት፤

(ሠ) እናት ባትኖር፤ ወይም ችሎታ የሌላት እንደሆነ፤ ከወንድሞቹ ወይም ከእኅቶቹ ታላቅ የሆነና ለመሥራት ችሎታ ያለው ብቻ ነው፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
በሌላ አኳኋን ስለ መካሥ፡፡
ቊ 2118፡፡ ዕቃዎችን ስለ መመለስ፡፡

(1) ዳኞች ከከሳሹ ያለ አገባብ የተወሰዱበት ዕቃዎችና እነዚሁም ዕቃዎች ከተወሰዱበት ጊዜ ጀምሮ ያፈሯቸውን ጥቅሞች ለከሳሹ
እንዲመለስለት ያዛሉ፡፡

(2) ዕቃዎቹ ጠፍተው እንደሆነ፤ ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል ቢሆን እንኳ ተከሳሹ ግምታቸውን መክፈል አለበት፡፡

(3) ተከሳሹ ሊመልሳቸው ለሚገባው ዕቃዎች ወጪ አድርጎ እንደሆነ፤ እንደዚህ በሆነ ጊዜ ያለ ምክንያት ስለ መክበር የተደነገጉት ውሳኔዎች
ይጸናሉ፡፡
ቊ 2119፡፡ በዐይነቱ ስለ መተካት፡፡

(1) የተበላሹ ወይም የተጎዱ ዕቃዎችን የማበላሸቱ ወይም የጉዳቱ አላፊ ከሆነው ሰው እንዲተኩ ወይም በዚሁ ሰው ኪሣራ እንዲሠሩ
(እንዲታደሱ) የሚስማማ ውጤት የሚሰጥ መስሎ የታያቸው እንደሆነ ዳኞች ተከሳሹ ዐይነቱን እንዲተካ ወይም በራሱ ኪሣራ እንዲሠራ
ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(2) እንደዚህም በሆነ ጊዜ ዳኞች ያተካኩን ወይም ያሠራሩን ዐይነት ይወስናሉ፡፡

(3) ስለሆነም እንዲከፍል የተወሰነው በመንግሥት ላይ የሆነ እንደሆነ ግምቱን ይከፍላል እንጂ ዐይነቱን ይተካ ተብሎ ሊወሰንበት
አይቻልም፡፡
ቊ 2120፡፡ ስለ ክብርና ስለ መልካም ዝና፡፡
በሰዎች ክብር ወይም በመልካም ዝና ላይ ተቃራኒ የሆኑ ሥራዎች የተፈጸሙ እንደሆነ፤ ዳኞች እነዚህ የነቀፌታ ተግባሮች ያደረሱትን
ውጤት ለመሻር በተከሳሹ ኪሣራ ተገቢ የሆነ የስም ማደሻ ማስታወቂያ እንዲገለጽና እንዲጻፍ ለማዘዝ ይችላሉ፡፡

ቊ 2121፡፡ ማስጠንቀቂያዎች፡፡

(1) ዳኞች ተከሳሹ በከሳሹ ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ነገር እንዳይሠራ በመሥራትም ላይ ቢገኝ እንዳይቀጥል ወይም እንደገና እንዳይጀምር
የሚያግድ ትእዛዝ ለመስጠት ይችላሉ፡፡

(2) የጉዳት ተግባር በከሳሹ ላይ ጉዳቱን የሚያመጣ መሆኑን ለማመን በቂ ምክንያቶች የሌለው እንደሆነ፤ እንደዚሁም ከሳሹን
የሚያስፈራው ጉዳት ኪሣራውን በመክፈል የማይካሥ ጠባይ ያለው ካልሆነ በቀር የማገጃ ትእዛዝ አይሰጥም፡፡

ቊ 2122፡፡ ተገቢ ያልሆነ ውድድር፡፡


ተከሳሹ ለቅን ልቡና ተቃራኒ በሆነ አኳኋን የሚያደርገውን የተንኰል ውድድር እንዲተው ዳኞች ትእዛዝ ለመስጠት ይችላሉ፡፡
ቊ 2123፡፡ በይመስላል ስለሚፈጸም ተግባር፡፡
ሦስተኛ ወገኖች በይመስላል እምነት አድርገው የፈጸሙት ተግባር በአድራጎቱ ወይም ባለመናገሩ ለዚሁ ሁኔታ አላፊ የሆነውን ሰው
መቃወሚያ ሊሆናቸው ይችላል፡፡
ክፍል 4፡፡
ለሌላ ሰው ተግባር አላፊ ስለ መሆን፡፡
ቊ 2124፡፡ ስለ አባት አላፊነት፡፡
አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ አላፊነትን የሚያስከትል ሥራ የሠራ እንደሆነ በፍትሐ ብሔር በኩል ለተሠራው ሥራ አላፊ የሚሆን አባት
ነው፡፡
ቊ 2125፡፡ የልጁ ሌሎች ጠባቂዎች፡፡
በአባት አላፊነት ምትክ ሆነው የሚጠየቁት፡፡
(ሀ) በልጅዋ ላይ ባባትነት ሥልጣን በምትሠራበት ጊዜ እናት፡፡

(ለ) አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ከአባቱ ቤት ውጭ ሲኖር በእምነት የተሰጠው የልጁ ጠባቂ፡፡

(ሐ) ልጅ እተማሪ ቤት ሳለ፤ ወይም የሞያ ሥራ በሚማርበት ጊዜ የቀለም ወይም የሞያ ሥራ አስተማሪው፤

(መ) ከዚህ በሚከተሉት ቊጥሮች መሠረት ለልጁ አላፊ ነው በሚባልበት ጊዜ አሠሪው ናቸው፡፡

ቊ 2126፡፡ ስለ መንግሥት አላፊነት (1) መሠረቱ፡፡

(1) የመንግሥት ሹም ወይም ሠራተኛ በራሱ ጥፋት በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ኪሣራውን
ለመክፈል ይገደዳል፡፡

(2) የተደረገው ጥፋት የመንግሥቱን ሥራ ሲሠራ የደረሰ የሥራ ጥፋት የሆነ እንደሆነ የተጎዳው ሰው ኪሣራ ከመንግሥት ላይ ለመጠየቅ
ይችላል፤ ሆኖም ስለከፈለው ገንዘብ መንግሥት የተባለውን ሠራተኛ ወይም ሹም መልሶ እንዲከፍለው ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

(3) ሠራተኛው ያደረገው ጥፋት የግል ጥፋቱ የሆነ እንደሆነ መንግሥት አላፊነት አይኖርበትም፡፡

ቊ 2127፡፡ (2) የሥራ ጥፋት፡፡

(1) ጥፋቱ እንደ ሥራ ጥፋት ሆኖ የሚቈጠረው ጥፋት አድራጊው በዚህ ጥፋት ላይ የወደቀው በቅን ልቡና በሥልጣኑና ለሥራው ክፍል
መልካም ያደረገ መስሎት የፈጸመው ሲሆን ነው፡፡

(2) ከዚህ ውጭ በሆነው በማናቸውም ሌላ ጒዳይ ግን እንደ ግል ጥፋት ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(3) በቅን ልቡና ያልተሠራ ለመሆኑ ተቃዋሚ ማስረጃ ያልቀረበ እንደሆነ፤ የሹሙ ወይም የሠራተኛው አሠራር በቅን ልቡና እንደተሠራ
ይገመታል፡፡
ቊ 2128፡፡ (3) ተመሳሳይነት ያላቸው ነገሮች፡፡
ከዚህ በላይ ባሉት ሁለት ቊጥሮች የተጻፈው ድንጋጌ በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ክፍለ አገሮችና ለሕዝብ አገልግሎት በተቋቋሙ በሕግ
የሰውነት መብት በተሰጣቸው ድርጅቶች ሠራተኞችም ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2129፡፡ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶች አላፊነት፡፡


የማኅበሩ እንደራሴዎች ወኪሎች ወይም ደመወዝተኞች የተሰጣቸውን ሥራ በሚያከናውኑበት ጊዜ አላፊነትን የሚያስከትል ሥራ የፈጸሙ
እንደሆነ በፍትሐ ብሔር በኩል በአላፊነት የሚጠየቁ በሕግ የሰው መብት የተሰጣቸው ማኅበሮች ወይም ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ
ንብረት ድርጅቶች ናቸው፡፡
ቊ 2130፡፡ ስለ አሠሪ አላፊነት፡፡
አንድ ሠራተኛ ሥራውን በሚሠራበት ጊዜ አላፊነትን የሚያስከትል ጥፋት የሠራ እንደሆነ በፍትሐ ብሔር በአላፊነት የሚጠየቀው አሠሪው
ነው፡፡
ቊ 2131፡፡ ሥራዎችን ስለ ማካሄድ፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባሉት ሁለት ቊጥሮች ለተመለከቱት ድንጋጌዎች አፈጻጸም አላፊነት የደረሰው ሥራውን በማከናወን ላይ ነው የሚባለው
በመሥራት ወይም ባለመሥራት የደረሰውን ጥፋት ሥራን በማከናወን ሐሳብ ተፈጽሞ እንደሆነ ነው፡፡

(2) በመሥራት ወይም ባለመሥራት የደረሰው ጥፋት ሥልጣንን በመተላለፍ ሆኖ ሠሪው እንዳይሠራ በግልጽ ተከልክሎ ቢገኝ እንኳ፤
ጉዳት የደረሰበት ሰው ምክንያቱን ካላወቀ ወይም ሊያውቀው ይገባው ነበር የሚል ካልሆነ በቀር በፍትሐ ብሔር ኀላፊነት የሚጠየቀውን
ክልከላው ምክንያት ሆኖ ከኀላፊነት አያድነውም፡፡

ቊ 2132፡፡ የሕሊና ግምት፡፡

(1) የሰውነት መብት የተሰጠው የማኅበር እንደራሴ ወይም ወኪል አንድ ደመወዘኛ እንደ ደንቡ በሚሠራበት ቦታና ጊዜ የስሕተት ተግባር
የፈጸመ እንደሆነ ጉዳቱን ሥራውን በማከናወን ላይ ሳለ እንደ ሠራው ይቈጠራል፡፡

(2) በዚህ ግምት ላይ ተቃዋሚ የሆነ ማስረጃ ለማቅረብ ይፈቀዳል፡፡

ቊ 2133፡፡ በሥልጣኑ ስላለመሥራት፡፡


የጥፋቱን ተግባር ለመፈጸም ወይም የሚገባውን ላለመፈጸም የተሰጠው ሥልጣን ምክንያት ብቻ ሆኖት እንደሆነ በሥልጣኑ ያከናወነው
ነው ሊባል አይቻልም፡፡

ቊ 2134፡፡ በራሱ ሥልጣን ስለሚሠራ ሠራተኛ፡፡


አንድ ሰው የተጠየቀውን ሥራ በሚሠራበት ጊዜ ለሠራው ጥፋት ጥፋተኛው በሥራ ሰጪው ሥልጣን ሥር ያልሆነ እንደሆነ ነጻነቱንም
እንደያዘ መሆኑ ከታወቀ አሠሪው በአላፊነት አይጠየቅም፡፡

ቊ 2135፡፡ ለምን ስለ ማጥፋት፡፡

የጋዜጣ መሪ፤ የአንድ ተባራሪ ማስታወቂያ ወይም (ፖንፍሌት) አሳታሚ መጽሐፍ አውጪ ደራሲው ለጻፈው የስም ማጥፋት በፍትሐ
ብሔር በኩል አላፊዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 2136፡፡ የአላፊነቶች መደራረብ፡፡

(1) አንድ ሰው ለአንድ ጉዳት በፍትሐ ብሔር በኩል አላፊ ነው ተብሎ በሕግ የተረጋገጠ መሆኑ፤ ጉዳት አድራጊው ላደረገው ጉዳት ካሣ
መክፈልን አያስቀርለትም፡፡

(2) ጉዳትን ያደረሰውና በፍትሐ ብሔር በኩል አላፊ የሆነው ለካሣው አከፋፈል የአንድነት ግዴታ አለባቸው፡፡

(3) በሕጉ አስተያየት ረገድ በፍትሐ ብሔር በኩል አላፊ ነው የተባለው ሰው በበኩሉ፤ ጉዳት ያደረሰውን ዋነኛውን አላፊ በቀረበበት ክስ
ውስጥ እንዲገባ ለማስገደድ ይችላል፡፡
ክፍል 5፡፡
ካሣ ስለሚጠየቅበት ክስ፡፡
ቊ 2137፡፡ የማይደፈሩ ሕጋዊ መብቶች (1) ነጋሢ፡፡
ጥፋትን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ምንም የኀላፊነት ክስ አይቀርብም፡፡
ቊ 2138፡፡ (2) ስለ ሚኒስትሮች፤ ስለ ፓርላማ አባሎችና ስለ ዳኞች፡፡
(ሀ) በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት አባሎች ላይ፤

(ለ) በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በፓርላማ አባሎች ላይ፤

(ሐ) በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳኞች ላይ፤


የሥራቸው ነክ በሆነው ተግባር የኀላፊነት ክስ ሊቀርብባቸው አይቻልም፡፡
ቊ 2139፡፡ ልዩነት፡፡
ከዚህ በላይ በተነገረው ቊጥር ደንብ የተከበሩት ሰዎች በሥራቸው ምክንያት ባደረጉት ተግባር፤ በወንጀል ተቀጥተዋል ብሎ ከሳሹ
ጠቅሶባቸው እንደሆነ ይህ ደንብ አይጸናላቸውም፡፡

ቊ 2140፡፡ የአስተዳደር ሕግ ስለሚወስናቸው ተግባሮች፡፡


መንግሥት በአላፊነት በሚጠየቅበት ጊዜ ክስ በማን ላይ መቅረብ የሚገባው ለመሆኑና እንደዚሁም የትኛው መሥሪያ ቤት ወይም ክፍል
በመጨረሻው ዐይነት አከፋፈል ወይም በእንዴት አኳኋን ዕዳውን መክፈል የሚገባው ለመሆኑ ያስተዳደር ደንቦች ይወስናሉ፡፡

ቊ 2141፡፡ አስረጅ ለማቅረብ ግዴታ ያለበት፡፡


የደረሰበትን ጉዳት ልክና እንዲሁም የአካባቢ ሁኔታዎች መሠረት በማድረግ ተከሳሹን ካሣ እንዲከፍለው ያለበትን ግዴታ ማስረዳት ያለበት
ጉዳት የደረሰበት ሰው ነው፡፡

ቊ 2142፡፡ ጉዳት አድራጊውን ለይቶ ስለ ማወቅ፡፡

(1) ከብዙ ሰዎች መካከል ጉዳቱን የፈጸመው ማን እንደሆነ በርግጥ ለማወቅ ባልተቻለ ጊዜ በርትዕ አስፈላጊ ሆኖ ሲታይ አድርጓል ለማለት
የሚቻለውን ስብሰባና በዚሁ መካከል አጥፊው በርግጥ እንደሚገኝ የታወቀውን ዳኞች ለጉዳቱ እንዲክስ ሊፈርዱበት ይችላሉ፡፡

(2) ይህን የመሰለ ነገር ባጋጠመ ጊዜ ዳኞቹ በፍትሐ ብሔር በኩል ለአድራጊው አላፊ የሆነው ሰው ለጉዳት እንዲክስ ለመፍረድ ይችላሉ፡፡

ቊ 2143፡፡ ክስ ስለሚቀርብበት ጊዜ፡፡

(1) ተበዳዩ ክስ ማቅረብ የሚችለው ካሣ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ነው፡፡

(2) ስለሆነም ጉዳቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ሆኖ የይርጋ ዘመኑ ርዝመት የበለጠ እንደሆነ፤ የካሣው ጒዳይ ክስ የይርጋ ዘመን ልክ በዚሁ
መሠረት ይሆናል፡፡

(3) ተበዳዩ የራሱ የሆኑትን ነገሮች የሚጠይቅበትና ያለ አገባብ ስለ መበልጸግ በተነገሩት ድንጋጌዎች መሠረት የሚከራከርበት መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2144፡፡ ስለ ተበዳዩ ወራሾች፡፡

(1) በተበዳዩ ላይ ለደረሰው የገንዘብ ጉዳት ወራሾች ካሣን ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በሕጉ ላይ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር፤

(2) የተበዳዩ ወራሾች በተበዳዩ ላይ ለደረሰው ለሕሊና ጉዳት ካሣ ለመጠየቅ የሚችሉት ተበዳዩ በሕይወቱ ሳለ ክስ ጀምሮ እንደሆነ ብቻ
ነው፡፡
(3) የጉዳቱ አላፊ የሆነ ሰው ወራሾች ልክ እንደ ኀላፊው ተቈጥረው ለደረሰው ጉዳት ካሣ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡

ቊ 2145፡፡ ከተበዳዩ ላይ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች፡፡

(1) ገንዘብ የሚጠይቁ ሰዎች ይህ ባለዕዳቸው ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ ጉዳቱም ሰውነቱን ሙሉ አካሉን ወይም ክብሩን የሚነካ እንደሆነ
በሱ ስም ሆነው ለደረሰበት ጉዳት ካሣ ሊጠይቁ አይችሉም፡፡

(2) ባለገንዘቦቹ ካበደሩበት ቀን በኋላ በባለዕዳው ላይ የገንዘብ ጥቅምን ብቻ የሚነካ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ የተባሉት ባለገንዘቦች በዚህ
ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ የተወሰኑትን ሁኔታዎች በመከተል የባለዕዳውን የክስ መብት ሊሠሩበት ይችላሉ፡፡
ቊ 2146፡፡ የገንዘብ መብት የማይተላለፍ ስለ መሆኑ፡፡

(1) ለተበዳዩ የሚከፈለው ካሣ መኖሩና፤ ልኩም በፍርድ እስኪታወቅና እስኪወሰን ድረስ ተበዳዩ ለጉዳቱ አላፊ በሚሆነው ሰው ላይ
ያለውን የገንዘብ መጠየቅ መብት ሊያስተላልፍ አይችልም፡፡

(2) በፍርድ ከታወቀለትና ልኩም ከተወሰነለት በኋላ በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ መሠረት ሊያስተላልፍ
ይችላል፡፡
ቊ 2147፡፡ አላፊ ስለ መሆን የሚደረግ የውል ስምምነት፡፡

(1) አንድ ሰው ራሱ የሠራው ጥፋት የሚያስከትለውን አላፊነት ለማስወረድ ለማስወገድ መዋዋል አይፈቀድለትም፡፡

(2) ሌላው ለሚሠራው ጥፋት በፍትሐ ብሔር በኩል በአላፊነት ሊጠየቅ የሚገባው ሰው ለሚሠራው ጥፋት አላፊ እንዳይሆን ለመዋዋል
ይችላል፡፡
(3) በዚህ አንቀጽ መሠረት ጥፋትም ባይኖር በሚደርሰው አደጋ ሁሉ ካሣ መክፈል የሚገባም ሆኖ ቢገኝ ጥፋት ካልተደረገ በቀር ካሣ
አይከፈልም የሚል ስምምነት ለመዋዋል ይቻላል፡፡

ቊ 2148፡፡ ግልግል፡፡
አንድ አደጋ ከተደረገ በኋላ ሁለቱ ወገኖች ለዚሁ አደጋ መሻሻያ ካሣ የማይከፈልበት መሆኑን ሊስማሙበት ወይም ይህ አደጋ በምን ዐይነት
እንደሚካሥ በስምምነት ሊገላገሉ ይችላሉ፡፡

ቊ 2149፡፡ የወንጀል ፍርድ ቤት በፍትሐ ብሔር ስላለው ሥልጣን፡፡


በፍትሐ ብሔር በኩል ጥፋት ተደርጓል ብሎ ለመወሰን በወንጀል ፍርድ ተከሳሹ ነፃ መለቀቁ ወይም በወንጀል አያስከስሰውም ተብሎ
መበየኑ፤ ዳኞቹን አያግዳቸውም፡፡

ቊ 2150፡፡ የኪሣራው መገመቻ ጊዜ፡፡

(1) ዳኞች በተበዳዩ ላይ የደረሰበትን ጉዳት ለማመዛዘን የፍርድ ውሳኔ የሚሰጡበትን ቀን መሠረት አድርገው መያዝ አለባቸው፡፡

(2) ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ፍርድ በሚወስንበት ጊዜ ለመገመት የማይቻል መስሎ የታያቸው እንደሆነ ለጊዜው ብቻ የሚጸና ትእዛዝ
ፍርድ ሰጥተው ይህ ፍርድ እንደገና እንዲታይ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል የሚል ፈቃድ መስጠት ይችላሉ፡፡

(3) ይህ ፍርድ እንደገና ይታይልን የማለት ጥያቄ ለጊዜው የተሰጠው ትእዛዝ ፍርድ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ከዘገየ
ለመቅረብ አይችልም፡፡

ቊ 2151፡፡ በፍርድ ያለቀ ነገር መጽናት፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር የተመለከተው ነገር ከሌለ በዳኞች የተደረገ የጉዳት ግምት የመጨረሻ ነው፡፡

(2) ጉዳት የደረሰበት ሰው የተባለው ጉዳት በአመጣጡ ምክንያት አስቀድሞ ካሣ ከጠየቀበት ጉዳት ጋራ ግንኙነት የሌለው ካልሆነ በቀር
ለዚሁ ለደረሰበት ጉዳት በአዲስ ክስ ካሣ ለመጠየቅ አይችልም፡፡

ቊ 2152፡፡ የይግባኝ አለመኖር፡፡


ስለ ኪሣራ ጥቅም አከፋፈል በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች የተወሰነ ፍርድ ለበላይ ፍርድ ቤት ለይግባኝ ለመቅረብ አይችልም፡፡
ቊ 2153፡፡ የተጠበቁ ሁኔታዎች፡፡
ቢሆንም ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተው ደንብ ልዩ አስተያየት የሚሰጠው፤
(ሀ) ዳኞች ሊገምቱት የሚገባቸውን የነገሩን አጋጣሚ ሁኔታ ያላገባብ በመያዝ ውሳኔ ሰጥተው እንደሆነ ወይም ሊገምቱ የሚገባቸውን
ትክክለኛውን መንገድ ትተው ያላገባብ የሆነውን ያገማመት መንገድ ይዘው የተገኙ እንደሆነ፤
(ለ) በዳኞች የተወሰነው የኪሣራ ገንዘብ ልክ በግልጽ ከአእምሮ ግምት ውጭ የሆነና የተወሰነውም በማድላት ወይም በዝንባሌ መሆኑ
እርግጥ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤

(ሐ) በዳኞቹ የተወሰነው የጉዳቱ ካሣ በሒሳብ ማሳሳት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2154፡፡ በየጊዜው ስለሚከፈል ገንዘብ፡፡

(1) የዚህ ዐይነት የኪሣራ ሒሳብ አከፋፈል እንደ ጊዜው አጋጣሚ ሁኔታ ተስማሚ መሆኑን የሚያሳስብ በቂ ምክንያት በተገኘ ጊዜ ዳኞች
የካሣው ሒሳብ በየጊዜው እንዲከፈል ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(2) ይህ ሲሆን ባለዕዳው ኪሣራውን በየጊዜው ሊከፍል የሚችል ስለ መሆኑ የሚያረጋግጥ በቂ ዋስትና መስጠት አለበት፡፡

ቊ 2155፡፡ ያንድነት ኀላፊነት፡፡

(1) ብዙዎች ሰዎች አንድ በሆነው ጒዳይ ለደረሰው ጉዳት ካሣን እንዲከፍሉ የተገደዱ እንዳሆነ፤ በአንድነት እያንዳንዳቸው ኀላፊ ይሆናሉ፡፡

(2) ለበደሉ ተግባር አነሣሽ በሆነውና በዋናው አድራጊ፤ በበደሉ ተግባር ተባባሪዎች፤ መካከል ልዩነት አይደረግም፡፡

(3) እንዲሁም የግዴታው መነሻ ለየአንዳንዶቹ ከውል ውስጥ ለየአንዳንዳቸው ከውል ውጭ የሆነ አላፊነት ነው ተብሎ ልዩነት ሳይደረግ
አንድ ለሆነ ጉዳት እንዲክሡ ግዴታ ባለባቸው ሰዎች መካከል ያለው አላፊነት የአንድነት አላፊነት ነው፡፡

ቊ 2156፡፡ የማይከፋፈል ጥፋት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


አላፊዎች ከሆኑ ሰዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ጥፋት የሠራ እንደሆነ፤ በመጨረሻው የተወሰነውን ዕዳ እርሱ ራሱ ብቻ መቻል አለበት፡፡
ቊ 2157፡፡ (2) በርትዕ ልዩነት ስለ ማድረግ፡፡

(1) የመንግሥት ሠራተኛ፤ የሰውነት መብት የተሰጠው የአንድ ማኅበር እንደራሴ ወይም ወኪል ወይም ደመወዘኛ ጥፋቱን የፈጸመው
ሥራውን በሚሠራበት ጊዜ እንደሆነ፤ በመጨረሻው ጊዜ ዕዳውን በሙሉ ወይም በከፊል መንግሥት ወይም ማኅበር ወይም አሠሪው
ይከፍላሉ ብለው ዳኞች ለመወሰን ይችላሉ፡፡

(2) ዳኞቹ ውሳኔያቸውን በሚሰጡበት ጊዜ፤ የተሠራውን ጥፋት ከባድነትና አድራጊው ጥፋቱን ሲሠራ የተሰጡትን ሥራዎች አብልጦ
ለመፈጸም ሲል የነበረውን ፈቃድ መገመት አለባቸው፡፡

ቊ 2158፡፡ ማመዛዘንን የሚያስፈልጉ ነገሮች፡፡

(1) ዳኞች ጥፋት አድራጊው ጥፋት በአደረገበት ጊዜ ፈቃዱ ሥራውን በመልካም ለማከናወን መሆኑንና ያደረገውንም ጥፋት ከባድነት
ያመዛዝናሉ፡፡
(2) ዳኞቹ ኀላፊ ናቸው የተባሉት ሰዎች ያላቸውን የየአንዳንዳቸውን ሀብት መሠረት አድርጎ መያዝ የለባቸውም፡፡

ቊ 2159፡፡ የዚህ ልዩነት ወሰን፡፡


በዳኞቹ በኩል አንዳች የኀላፊነት ክፍያ የማይፈቀደው፤
(ሀ) ኀላፊነቱን ያመጣው ሥራ ታስቦ ለመጉዳት የተደረገ እንደሆነ፤

(ለ) ወይም ይህ ተግባር ወንጀል ሆኖ አድራጊው ቅጣት ተፈርዶበት እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2160፡፡ የሚከፋፈል ጥፋት፡፡

(1) ብዙዎች ሰወች አንድ በሆነ ጒዳይ የጥፋት ተግባርን በመፈጸም ላይ የተባበሩ እንደሆነ፤ ዳኞች በመጨረሻ በየአንዳንዳቸው መካከል
ሊከፈል የሚገባውን ዕዳ በርትዕ ይወስኑባቸዋል፡፡
(2) ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ የነበሩትን ምክንያቶች ሁሉ በተለይም የየአንዳንዱን በደለኛ ጥፋት ያደረሰውን የጉዳት ተግባር መጠንና
የጥፋቱንም ከባድነት መገመት አለባቸው፡፡

ቊ 2161፡፡ ስለ መዳረግ፡፡

(1) አንድ ሰው ከሚወሰነው ዕዳ የክፍያውን ድርሻውን መክፈል የሚገባው ሲሆን፤ ዕዳውን በሙሉ የከፈለ እንደሆነ፤ ከእርሱ ጋራ ዕዳውን
እንዲከፍሉ ግዴታ ባለባቸው ሰዎች ላይ የመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) ጥያቄውን ለማቅረብ የተበደለው ሰው መብቶች እንደ ገባ የቈጠራል፡፡


ምዕራፍ 2፡፡
ያላገባብ ስለ መበልጸግ፡፡
ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች
ቊ 2162፡፡ ጠቅላላ መሠረት፡፡
በሌላ ሰው የሥራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው፤ አላገባብ ጥቅም ባገኘበት
መጠንና ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ይህ አድራጎት በደረሰበት ጉዳት መጠን ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው
ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2163፡፡ ያላገባብ የተገኘ መበልጸግ ስለ መቅረቱ፡፡

(1) መልስ በሚባልበት ጊዜ ተከሳሹ ላለመበልጸጉ ማስረጃ ባቀረበበት መጠን ኪሣራ መክፈል የለበትም፡፡

(2) ስለሆነም ተከሳሹ በክፉ ልቡና ዕቃውን ለሌላ ሰው አስተላልፎ እንደሆነ ወይም መመለስ እንዳለበት ማወቅ ሲገባው አስተላልፎ
እንደሆነ ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(3) ያለ አገባብ የበለጸገበትን ሀብት ያለ ዋጋ ለሦስተኛ ወገን ሰጥቶ እንደሆነ ይህ ሦስተኛ ወገን ያለ ዋጋ የወሰደውን እንዲመልስ ሊጠየቅ
ይቻላል፡፡
ክፍል 2፡፡
የማይገባውን ስለ መክፈል፡፡
ቊ 2164፡፡ የማይገባውን ስለ መክፈል፡፡

(1) ሊከፍል የማይገባውን ነገር የከፈለ ሰው እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) የሚከፈለው ነገር የተቀበለው እምነትን በሚያጐድል ሁኔታ እንደሆነ የማይገባውን ነገር የከፈለው ሰው ከከፈለበት ቀን አንሥቶ ይህ
የከፈለው ነገር የሰጠውን ፍሬ ወይም ሕጋዊውን ወለድ ጭምር እንዲመልስለት ለመጠየቅ ይችላል፡

ቊ 2165፡፡ ስሕተት ስላለመኖሩ፡፡


ሊከፍለው የማይገባው ዕዳ መሆኑን እያወቀና የሚያስከፍለውም ምክንያት ያለመኖሩን እየተረዳው በራሱ ፈቃድ የከፈለ ሰው ይመለስልኝ
ብሎ ለመጠየቅ አይችልም፡፡

ቊ 2166፡፡ በቂ ምክንያት፡፡

(1) የመክፈሉ ጒዳይ የተፈጸመው በይርጋ ለታገደ ዕዳ (ወይም) የሕሊና ግዴታ የበጎ አድራጎትን መንፈስ በመከተል ሁኔታ እንደሆነ ለከፋዩ
አይመለስለትም፡፡
(2) እንዲሁም በሆነ ጊዜ የከፈለው ሰው የሚከፍለውን ነገር ያለ ዋጋ የመስጠት ችሎታ ያልነበረው እንደሆነ ያላገባብ የከፈለው ሊመለስለት
ይችላል፡፡
ቊ 2167፡፡ የማይመለስ ዕዳ፡፡

(1) የማይገባውን ገንዘብ ያላገባብ የተቀበለ ሰው የተቀበለውን ገንዘብ ያላገባብ ለከፈለው ሰው የማይመልስለት ይህ ባለገንዘብ የብድሩ
ሒሳብ ስለተከፈለው በቅን ልቡና ያበደረበትን ሰነድ ቀዶ ወይም ሰርዞ እንደሆነ ወይም ዋሶቹን ከዕዳው ነፃ አውጥቶዋቸው እንደሆነ ወይም
ደግሞ ከእውነተኛው ባለዕዳው ላይ ሊቀበል የሚገባውን ገንዘብ በይርጋ አሳልፎ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡

(2) ይህ በሆነበት ጊዜ ያላግባብ የከፈለው ሰው ሒሳቡን ለመጠየቅ የሚችለው ከዋናው ባለዕዳ ላይ ብቻ ነው፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ ወጪ ገንዘብ፡፡
ቊ 2168፡፡ የዚህ ክፍሉ ተፈጻሚነት፡፡
አንድ ሰው ለተወሰነ ጊዜ በእጁ የቈየውን ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ እንደሆነ የሕግ ወይም የውል ተቃራኒ የሚሆን ድንጋጌ ከሌለ በቀር ይህ
ሰው የተባለውን ዕቃ ከመለዋወጥ የተነሣ ያሉት መብቶችና ግዴታዎች ከዚህ በታች በሚከተሉት ደንቦች መሠረት ይወሰናሉ፡፡

ቊ 2169፡፡ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ስለ ተደረገው ወጪ፡፡


የያዘውን ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው ዕቃው እንዳይጠፋ ወይም እንዳይበላሽ ያደረገው ወጪ ገንዘብ ለዚህ ጒዳይ ጠቃሚ ሳይሆን ከቀረ
ወይም የወጪው ግዴታ ዕቃውን ሊመልስ በተገደደው ሰው ወይም ተገዳጁ ኀላፊ በሚሆንበት ሰው ጥፋት ምክንያት ሆኖ ካልተገኘ በቀር
ተገዳጁ ለተባለው ጒዳይ ያወጣው ገንዘብ ሊመለስለት ይገባል፡፡

ቊ 2170፡፡ ስለ ዕቃው አጠባበቅ የተደረገ ወጪ፡፡


የያዘውን ዕቃ ለመመለስ የተገደደ ሰው ለዕቃው አጠባበቅ ስለተደረገው ወጪ ገንዘብ ወይም በይዞታው ምክንያት ስለ ከፈለው ግብር
አንዳች ኪሣራ ለመጠየቅ መብት የለውም፡፡

ቊ 2171፡፡ ዋጋ ከፍ ስላደረገው ወጪ፡፡

(1) እንደዚሁም ለዕቃው የተደረገው ወጪ የዕቃውን ዋጋ ግምት ከፍ አድርጎት እንደሆነ ዕቃውን ለመመለስ የተገደደው ሰው ስለዚሁ
ጒዳይ ያወጣው ገንዘብ ሊመለስለት ይገባል፡፡

(2) ቢሆንም ለዕቃው መጀመሪያ ከነበረው ዋጋ በላይ ብልጫ እንጂ፤ ዕቃውን በሚመልስበት ጊዜ ከሚገኘው የዕቃ ዋጋ ግምት በላይ
ባደረገው ወጪ ልክ ሊጠይቅ አይችልም፡፡

ቊ 2172፡፡ ክፉ ልቡና፡፡

(1) ወጪ ገንዘብ በተደረገበት ጊዜ ተከሳሹ ዕቃውን ለመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያውቅ እንደነበረ ወይም ማወቅ ይገባው እንደነበረ
ርትዕም ሲያስገድድ ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር የተመለከተውን ኪሣራ ዳኞች ለመቀነስ ወይም በጭራሽ ለማስቀረት ይችላሉ፡፡

(2) ደግሞ ርትዕ ሲያስገድድ ለከሳሹ ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር የተመለከተውን ኪሣራ የሚከፍልበት ቢበዛ የሁለት ዓመት ጊዜ
ለመስጠት ይችላሉ፡፡

ቊ 2173፡፡ የማለያየት መብት፡፡


የያዘውን ዕቃ ለመመለስ የተገደደው ሰው ዕቃውን ከመመለሱ በፊት በዕቃው ላይ አገጣጥሞት የቈየውን ነገር ከፍ ያለ ጉዳት በዕቃው ላይ
ሳይደርስ ለማላቀቅ የቻለ እንደሆነ ለይቶ ለመውሰድ መብት አለው፡፡

ቊ 2174፡፡ የመያዝ መብት፡፡


(1) የያዘውን ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች እንደተመለከተው ሊመለስለት የሚገባውን የኪሣራ ወጪ
ገንዘብ ከልተቀበለ እስኪቀበል ድረስ ወይም ኪሣራው በሚከፈልበት ቀን መከፈሉን የሚያረጋግጥለት በቂ ዋስትና ካልተቀበለ አልመልስም
ለማለት ይችላል፡፡

(2) ስለሆነም ዕቃውን የመያዝ መብት ለሌባ ወይም ዕቃውን እጅ ሲያደርግ በዕቃው ላይ ሕግም ሆነ ወይም የሚጸና ውል የሚሰጠው
አንዳች መብት እንደሌለው እያወቀ እጅ ባደረገ ሰው ላይ ይህ መብት አይጸናለትም፡፡

ቊ 2175፡፡ ስለ ዕቃው መበላሸት፡፡

(1) የያዘውን ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው ዕቃውን አበላሽቶ እንደሆነ፤ ለባለመብቱ ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(2) የዕቃው መበላሸት ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል የደረሰ እንኳን ቢሆን፤ ዕቃው የተበላሸበት ጊዜ በዕቃው ላይ ሕግም ሆነ ወይም የሚጸና
ውል የሚሰጠው አንዳች መብት እንደሌለው ያውቅ ኖሮ እንደሆነ በዕቃው ላይ ለደረሰው መበላሸት ኀላፊ ነው፡፡

ቊ 2176፡፡ ስለ ዕቃው መጥፋት፡፡

(1) ዕቃው በሙሉ ወይም በከፊል በሚጠፋበት ጊዜ ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ለባለመብቱ ዕቃው በዐይነቱ ሊከፈለው በማይቸልበት ጊዜ እነዚህ ድንጋጌዎቹ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 2177፡፡ የኪሣራው ልክ፡፡

(1) የሚከፈለው ኪሣራ ዕቃውን ለመመለስ ባልተቻለበት ቀን ከነበረው ዋጋ እኩል መሆን አለበት፡፡

(2) ስለሆነም የያዘውን ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው በዚያን ጊዜ በዕቃው ላይ ሕግ ወይም የሚጸና ውል የሚሰጠው አንዳች መብት
እንደሌለው ያውቅ ኖሮ እንደሆነ ተጨማሪ ሁኖ ስለ ጉዳት ኪሣራ እንዲከፍል ሊጠየቅ ይቻላል፡፡

(3) እንዲህም በሆነ ጊዜ ዕቃው እንዲመለስለት መብት ያለው ሰው በእጁ ይዞት እንደኖረ ሆኖ ኪሣራው ይታሰብለታል፡፡

ቊ 2178፡፡ ዕቃው ያስገኘው ፍሬ፡፡

(1) የያዘውን ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው የተቀበለው ዕቃ ያፈራውን ነገር ያስቀራል፡፡

(2) ዕቃውን እጅ ባደረገ ጊዜ በዕቃው ላይ ሕግ ወይም የሚጸና ውል የሚሰጠው አንዳች መብት እንደሌለው እያወቀ እጅ አድርጎት
እንደሆነ፤ ለከሳሹ ዕቃው ያፈራውን ግምት መክፈል አለበት፡፡

አንቀጽ 14፡፡
ስለ እንደራሴነት፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 2179፡፡ የእንደራሴነት ምንጭ፡፡

የሌላ ሰው እንደራሴ በመሆን ሥራዎችን የመፈጸም ሥልጣን የሚገኘው ከሕግ ወይም ከውል ነው፡፡

ቊ 2180፡፡ ስለ ሥልጣን ፎርም፡፡


ስለ ውሉ አፈጻጸም፤ ሕጉ አንድ ዐይነት ፎርም እንዲደረግ ያስገደደ እንደሆነ ውሉን የሚፈጽምበት ሥልጣን በዚሁ ዐይነት ፎርም ለወኪሉ
መስጠት አለበት፡፡

ቊ 2181፡፡ ስለ ሥልጣን ወሰን፡፡

(1) የእንደራሴነት ሥልጣን የተገኘው በውል መሠረት የሆነ እንደሆነ፤ ሥልጣኑ የሚወሰነው በተዋዋዮቹ ስምምነት ነው፡፡

(2) እንደራሴው የተሰጠውን ሥልጣን ሦስተኛ ወገን ለሆነ ሰው አስታውቆ እንደሆነ፤ በሦስተኛው ሰው ላይ ሥልጣኑ የሚጸናው፤
ባስታወቀው ማስታወቂያ መሠረት ነው፡፡

(3) የእንደራሴነት ሥልጣን የሚተረጐመው ሳይስፋፋ በጠባቡ ነው፡፡

ቊ 2182፡፡ ስለ ሥልጣኑ መቅረት፡፡

(1) ተቃራኒ የሆነ ውል ከሌለ በቀር፤ እንደራሴው ወይም ሿሚው መሞቱ ወይም የሌለ መሆኑ ወይም ችሎታ የሌለው መሆኑ ወይም ደግሞ
መክሠሩ የተገለጸ እንደሆነ ከአንድ ጽሑፍ የተገኘው ሥልጣን ይቀራል፡፡

(2) እንዲሁም የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት መኖሩ ሲቀር ይህ ሥልጣን ይቀራል፡፡

ቊ 2183፡፡ ሥልጣንን ስለ መውሰድ፡፡

(1) እንደራሴ ሿሚው በማንኛውም ጊዜ በእሱ ስም ሆኖ እንዲሠራ በሦስተኛ ወገን ሰዎች ፊት ለእንደራሴው የሰጠውን ሥልጣን
ሊቀንስበት ወይም ጨርሶ ሊያስቀርበት ይችላል፡፡

(2) ይህን መብት የሚያስቀር በውሉ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ጽሑፍ ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2184፡፡ እንደራሴነትን ስለ መመለስ፡፡

(1) ሥልጣኑን የሚያረጋግጥ ጽሑፍ የተሰጠው እንደራሴ በተሰጠው ሥልጣን የሚሠራበት ጊዜ ሲፈጸም፤ ይህን የተሰጠውን የሥልጣን
ጽሑፍ ለሿሚው መመለስ አለበት፡፡

(2) እንደራሴው ሒሳቡ ሳይጣራና የሚገባኝን ሿሚው ሳይሰጠኝ የተሰጠኝን ሥልጣን ይዤ እቈያለሁ ለማለት አይፈቀድለትም፡፡

ቊ 2185፡፡ የእንደራሴነቱ ጽሑፍ ስለ መጥፋት፡፡


እንደራሴው የሹመቱ ወረቀት መጥፋቱን ያስታወቀ እንደሆነ ሿሚው በእንደራሴው ኪሣራ ከፍርድ ቤቱ የእንደራሴነቱን መሰረዝ የሚገልጽ
ውሳኔ ለማግኘት ይችላል፡፡

ቊ 2186፡፡ ሥልጣንን ስለ ማረጋገጥ፡፡

ከአንድ እንደራሴ ጋራ ሕጋዊ ተግባር የፈጸመ የሦስተኛ ወገን ሁል ጊዜ እንደራሴው ሥልጣኑን እንዲያረጋግጥለት ሊያስገድድና
እንደዚሁም የእንደራሴነቱ ተግባር በጽሑፍ የተደረገ እንደሆነ፤ እንደራሴው ስለዚሁ ተግባር በሚገባ የፈረመበትን ግልባጭ እንዲሰጠው
ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 2187፡፡ ተቃዋሚ ጥቅሞች፡፡

(1) እንደራሴው በፈጸመው ውል ምክንያት የሿሚውና የእንደራሴው ጥቅሞች የሚቃወሙ የሆኑ እንደሆነ ይህን ውል የፈረመው 3 ኛ ወገን
ይህን ሁኔታ የወቀና ሊያውቀውም የሚገባ የሆነ እንደሆነ በሿሚው ጥያቄ መሠረት ይህ የተፈጸመው ውል ሊፈርስ ይችላል፡፡

(2) ሿሚው የዚሁኑ አካባቢ ሁኔታ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ውሉን ለማፍረስ አሳቡን ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) አንደኛው ወገን ተዋዋይ ይህን ማስታወቂያ ከተቀበለ ወዲህ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ውሉን የመቀጠል አሳቡን ያልገለጠ እንደሆነ ውሉ
ይፈርሳል፡፡

ቊ 2188፡፡ ከገዛ ራስ ጋራ ስለሚደረግ ውል፡፡

(1) እንደራሴው ለራሱ ጒዳይ በመሥራትም ሆነ ወይም በሌላ ሰው ስም ለሌላ ሰው ጒዳይ በመሥራት ውሉን ከራሱ ጋራ ባደረገ ጊዜ
ሿሚው ይህ ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር በ 2 ና በ 3 ንኡስ ቊጥሮች የተሰጡ ውሳኔዎች ለዚህም ተፈጻሚነት አላቸው፡፡

(3) ስለ ኮሚሲዮኔሮች የተሠሩ ልዩ ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡ (ቊ)

ቊ 2189፡፡ ፍጹም ስለሆነ እንደራሴነት፡፡

(1) እንደራሴው ከወኪልነቱ ሥልጣን ወሰን ሳያልፍ በሌላ ሰው ስም የመዋዋል ተግባሮችን የፈጸመ እንደሆነ፤ እነዚህ በርሱ የተፈጸሙት
ተግባሮች በቀጥታ በሿሚው እንደተፈጸሙ ሆነው ይቈጠራሉ፡፡

(2) ነገር ግን ውሉ በተደረገበት ጊዜ በእንደራሴው ፈቃድ ላይ የተፈጸሙትን ጒድለቶች ሿሚው ለራሱ ጥቅም ጠቅሶ ሊከራከርባቸው
ይችላል፡፡
(3) ከእንደራሴው ጋራ የውል ስምምነት ያደረገ ሰው እንደራሴው ባደረሰበት የማሳሳት ጉዳት ሿሚውን ሊከራከረው ይችላል፡፡
ቊ 2190፡፡ የሥልጣን ወሰን ስለ ማለፍ፤ ወይም ቀሪ ስለሆነ ሥልጣን፡፡

(1) እንደራሴው የሥልጣኑን ወሰን በመተላለፍ በሌላ ሰው ስም የሠራ እንደሆነ፤ በስሙ የተሠራለት ሰው ራሱ እንደ ፈቀደ እንደራሴው
የፈጸመውን ተግባር ለማጽደቅ ወይም ለማፍረስ ይችላል፡፡

(2) እንደዚሁም እንደራሴው ቀሪ በሆነው ሥልጣን መሠረት በሌላ ሰው ስም በሠራ ጊዜ በስሙ የተሠራለት ሰው እንደ ፈቀደ በስሙ
የተሠራውን ሥራ ለማጽደቅ ወይም ለመሻር ይችላል፡፡

ቊ 2191፡፡ ለሿሚ ስለ ተሰጠው ምርጫ፡፡

(1) ከእንደራሴው ጋራ የተዋዋሉ ሦስተኛ ወገኖች ሿሚው በስሙ የተሠራለትን ሥራ ለማጽደቅ ወይም ለማፍረስ የቈረጠውን ውሳኔ
በፍጥነት እንዲያስታውቃቸው ለማስገደድ ይችላሉ፡፡

(2) ሿሚው የመቀበሉን ውሳኔ በፍጥነት ሳያስታውቃቸው የቀረ እንደሆነ፤ እንደራሴው የሠራውን ሥራ እንዳልተቀበለው ይቈጠራል፡፡

ቊ 2192፡፡ የመቀበሉ ውጤት፡፡

ሿሚው እንደራሴው የፈጸመውን ተግባር ያጸደቀ እንደሆነ፤ እንደራሴው የፈጸመውን ተግባር ከውክልናው ሥልጣን ሳያልፍ እንደ
ፈጸመው ይቈጠራል፡፡

ቊ 2193፡፡ ያለመቀበል የሚያስከትለው ውጤት፡፡

(1) እንደራሴው የሠራውን ሥራ ሿሚው ባልተቀበለው ጊዜ በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ በተለከተው መሠረት
ስለ ውሎች መሰረዝና መፍረስ የተነገሩት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) ከእንደራሴው ጋራ የስምምነቱን ተግባር የፈጸመው ሦስተኛ ወገን የእንደራሴነትን ሥልጣን መኖሩን በቅን ልቡና በማመኑ ስለ ደረሰበት
ጉዳት ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ቊጥሮች ድንጋጌ መሠረት ካሣ እንዲከፈለው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2194፡፡ ስለሚደርሱት አላፊነቶች፡፡

(1) ስለ ደረሰው ጉዳት ኪሣራ እንዲከፍል መጠየቅ የሚገባው እንደራሴው ነው፡፡

(2) ስለሆነም፤ የእንደራሴነቱን ሥልጣን የሚያስቀረውን ምክንያት ባለማወቅ በቅን ልቡና ሠርቶት እንደሆነ፤ በአላፊነት አይጠየቅም፡፡

(3) እንደዚህም በሆነ ጊዜ ስለ ደረሰው ጉዳት ኪሣራ እንዲከፍል የሚጠየቀው ሿሚው ነው፡፡
ቊ 2195፡፡ (1) ስለ ሿሚው አላፊነት፡፡

በሌላው በኩል በሚደርሰው ጉዳት ሁሉ ሿሚው ከእንደራሴው ጋራ በሙሉ አላፊ የሚሆነው፤


(ሀ) ሿሚው ለሌላ ሦስተኛ ወገን የእንደራሴነቱን ሥልጣን አስታውቆ ሳለ፤ የሰጠውን የእንደራሴነት ሥልጣን በሙሉ ወይም በከፊሉ
መሰረዙን ለዚያው ለሦስተኛ ወገን ያላስታወቀ እንደሆነ፤

(ለ) ሿሚው ለእንደራሴው የሰውን የእንደራሴነት ሥልጣን ጽሑፍ እንዲመልስለት እንደራሴውን ከማስገደድ ችላ ያለ እንደሆነና እንዲሁም
ይህ ሿሚው የሰጠው የእንደራሴነት ሥልጣን ጽሑፍ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሰረዝ ያላደረገ እንደሆነ፤

(ሐ) በማናቸውም ሌላ አኳኋን ሿሚው በሚሰጣቸው መግለጫዎች ወይም በሥራው ወይም በአመራሩ ወይም ሊያደርግ የሚገባውን
ባማድረጉ ከእንደራሴው ጋራ ስምምነት የሚያደርጉት ሦስተኛ ወገኖች እንደራሴው ይህ ሥልጣን ያለው መስሎዋቸው ስሕተት
ያደረሰባቸው እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2196፡፡ ከአላፊነት ውጭ ስለ መሆን፡፡

(1) ከእንደራሴው ጋራ የተዋዋለው ሌላ ሦስተኛ ወገን ከመዋዋሉ በፊት የእንደራሴነቱን ሥልጣን ጽሑፍ ዐውቆ የተዋዋለ ከሆነ፤ በነገሩ
የማታለል ሥራ ከሌለበት በቀር ከሥልጣኑ አልፎ የሠራውን እንደራሴ ማንኛውንም ኪሣራ ሊጠይቀው አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም ሦስተኛው ወገን የሚዋዋለው ማንም ቢሆን ግድ የሌለው ከሆነና እንደራሴውም ለሌላ ሰው የተፈጸመውን ውል በራሱ ስም
ለማድረግ የተቀበለ እንደሆነ ሦስተኛው ወገን ማንኛውንም ኪሣራ ለመጠየቅ አይችልም፡፡

ቊ 2197፡፡ እንደራሴው በራሱ ስም ስለሚፈጽመው ተግባር፡፡

(1) እንደራሴው በራሱ ስም የተዋዋለ እንደሆነ፤ ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ከእንደራሴው ጋራ መዋዋላቸውን ቢያውቁትም እንኳ፤ ከነዚህ ጋራ
የፈጸማቸው ተግባሮች ለሚያስከትሉዋቸው ግዴታዎችና መብቶች እሱ ራሱ ባለቤት ይሆናል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ የተባሉ ሦስተኛ ወገኖች ከሿሚው ጋራ አንዳችም ቀጥታ ግንኙነት የላቸውም፤ ነገር ግን በእንደራሴው ስም ሆነው
የእንደራሴውን መብት ከሿሚው ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቊ 2198፡፡ ስለ ሿሚው መብቶች፡፡

(1) ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች በቅን ልቡና ያገኙዋቸው መብቶች እንደተጠበቁ ሆነው እንደራሴው ለሿሚው ሲል በራሱ ስም ያፈራቸውን
ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፤ ሿሚው ገንዘቦቼ ናቸው ብሎ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) እንደዚሁም እንደራሴው ለሿሚው ሲል ያገኛቸውን የገንዘብ መብቶች ሿሚው በእንደራሴው ተተክቶ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

(3) ስለሆነም፤ ሿሚው በበኩሉ በእንደራሴው ዘንድ ያሉበትን ግዴታዎች ፈጽሞ ካልተገኘ በቀር እነዚህን መብቶች ለመጠየቅ አይችልም፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
ስለ ወኪልነት፡፡
ቊ 2199፡፡ ትርጓሜ፡፡

ውክልና ማለት ተወካይ የተባለ አንድ ሰው ወካይ ለተባለው ሰው እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ሕጋዊ ሥራዎች በወካዩ ስም
ለማከናወን ግዴታ የሚገባበት ውል ማለት ነው፡፡

ክፍል 1፡፡
የወኪልነት ሥልጣን አቋቋምና የሥራው ግብ፡፡
ቊ 2200፡፡ የውክልና ፎርም፡፡

(1) ውክልና በግልጽ ወይም በዝምታ ሊሰጥ ይችላል፡፡

(2) ቢሆንም ተወካዩ ሊፈጽመው የሚገባው የሥራ ተግባር፤ ስለ አፈጻጸሙ በአንዳንድ ሕጋዊ ፎርም ውስጥ እንዲገባ የሚያስፈልገው
ሲሆን ውክልናው ለተወካዩ ሊሰጠው የሚገባው ይኸው ሕግ በሚያዝዘው ፎርም መሠረት ነው፡፡

ቊ 2201፡፡ ውክልናን ስለ መቀበል፡፡

(1) ውክልናን የመቀበል ጒዳይ በግልጽ ወይም በዝምታ ሊፈጸም ይችላል፡፡

(2) ተወካዩ ወኪል የሚሆንበት ነገር ከሚያካሂደው ሥራ ጋራ ግንኙነት ያለው ጒዳይ መሆኑ በግልጽ የታወቀ ከሆነ፤ ወይም ከሞያ ሥራው
አመራር ጋር የሚመሳሰል ጒዳይ ከሆነ፤ ወይም ይህንን የመሰለውን ጒዳይ ለመሥራት ፈቃደኛ ለመሆኑ በአደባባይ ገልጾ አሳብ በማቅረብ
አስታውቆ እንደሆኘ፤ ውክልናውን የማይቀበል ለመሆኑ ወዲያውኑ ካልገለጸ በቀር እንደተቀበለ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2202፡፡ የውክልናው ወሰን፡፡

(1) የውክልናው ወሰን በውሉ ላይ በግልጽ ተጠቅሶ ካልተመለከተ በቀር ለውክልናው የሚሰጠው ወሰን እንደ ጒዳዩ ዐይነት ነው፡፡

(2) ውክልናው ለአንድ ልዩ ጒዳይ ወይም ለየአንዳንዱ ጒዳዮች ወይም ለወካዩ ጒዳዮች ሁሉ ጠቅላላ ውክልና ሊሆን ይችላል፡፡

ቊ 2203፡፡ ጠቅላላ ውክልና፡፡

በጠቅላላ አነጋገር የተደረገ ውክልና ለተወካዩ የአስተዳደርን ሥራ እንዲፈጽም ከሚያደርገው በቀር ሌላ ሥልጣን አይሰጠውም፡፡
ቊ 2204፡፡ የአስተዳደር ሥራ፡

(1) የወካዩን ሀብት የማስቀመጥ የመጠበቅ ከሦስት ዓመት ለማያልፍ ዘመን የማከራየት፤ በብድር የተሰጠውን ሀብት የመሰብሰብ፤ ከሀብቱ
የሚመጣውን ገቢ ተቀብሎ የማስቀመጥና ለተከፈሉ ዕዳዎች ደረሰኝ የመስጠት ሥራዎች ሁሉ እንደ አስተዳደር ሥራ ይቈጠራሉ፡፡

(2) እንዲሁም የሰብልን መሸጥ፤ ለሽያጭ የተመደቡ የንግድ ዕቃዎችን ወይም ይበላሻሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮችን የመሸጥ ሥራ እንደ
አስተዳደር የሥራ አፈጻጸም የሚቈጠር ነው፡፡

ቊ 2205፡፡ ልዩ ውክልና፡፡

(1) ተወካዩ ከአስተዳደር ሥራ በቀር ሌላ ሥራ ለመሥራት የሚያስፈልግ ሲሆን ልዩ ውክልና እንዲኖረው አስፈላጊ ነው፡፡

(2) ተወካዩ ልዩ የውክልና ሥልጣን ከሌለው በቀር፤ ይልቁንም የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መሸጥ ወይም አሲዞ መበደር ካፒታሎችን
በአንድ ማኀበር ዘንድ ለማግባት የለውጥ ግዴታን ውል መፈራረም መታረቅ ለመታረቅ ውል መግባት ስጦታ ማድረግና በአንድ ጒዳይ
በፍርድ ቤት ቀርቦ መከራከር አይችልም፡፡

ቊ 2206፡፡ ልዩ ውክልና የተሰጠው ሰው ሥልጣን፡፡

(1) ልዩ ውክልናው በላዩ ተዘርዝረው የተመለከቱትን ጒዳዮችና የነዚሁ ተከታታይና ተመሳሳይ የሆነውን እንደ ጒዳዩ ዐይነትና እንደ ልማድ
አሠራር አስፈላጊ የሆነውን ከማከናወን በቀር ለተወካዩ ሌላ ሥልጣን አይሰጠውም፡፡

(2) ተወካዩ ከተሰጠው የውክልና ሥልጣን ውጭ አልፎ የፈጸመውን የሥራ ተግባር ወካዩ ካላጸደቀው ወይም በሥራ አመራር መሠረታዊ
ደንብ ካልሆነ በቀር ወካዩን አስገድደውም፡፡

ቊ 2207፡፡ የማጽደቅ ግዴታ፡፡

(1) ተወካዩ በውክልናው ከተሰጠው ሥልጣንና ወካዩ ከሰጠው ትእዛዝ ውጭ በማለፍ ሠርቶ የተገኘ እንደሆነ ተወካዩ የሠራው በቅን ልቡና
ሆኖ ሲገኝ ሥራውን ወካዩ እንዲያጸድቅለት ይገደዳል፡፡

(2) ወካዩ የሥራውን አረማመድና መልካም አካሄድ ሁኔታ ቢረዳው ኖሮ ለተወካዩ የሥራውን የሥልጣን ወሰን ማስፋት የሚያስፈልግ
መሆኑን መገመት ይችል ነበር ተብሎ በአእምሮ ግምት የሚታመን ሆኖ ሲገኝም አፈጻጸሙ በዚሁ ዐይነት ነው፡፡

(3) ተወካዩ ያልተፈቀደለትን ሥራ በገዛ አሳቡ ከመፈጸሙ አስቀድሞ የሥልጣኑን ወሰን እንዲያሰፋለት ወካዩን ለመጠየቅ የሚያስችለው
ምቹ መንገድ እያለው ፈቃድ ሳይጠይቅ ቸል ብሎ በራሱ አሳብ ሠርቶ እንደሆነ፤ ወይም አስፈላጊ ተግባሩን ከፈጸመ በኋላ ለወካዩ
ሳያስታውቀው ቀርቶ እንደሆነ ያለ ፈቃድ የፈጸምኩትን አጽናልኝ ብሎ ወካዩን የመጠየቅ መብት አይኖረውም፡፡

ክፍል 2፡፡
የተወካዩ ግዴታዎች፡፡
ቊ 2208፡፡ ጥብቅ የሆነ ቅን ልቡና፡፡

(1) ተወካዩ ከወካዩ ጋራ በሚያስተሳስረው ግንኙነት ውስጥ ጥብቅ የሆነ ቅን ልቡና ሊኖረው ይገባል፡፡

(2) የውክልናውን ሥልጣን የሚያስቀሩትን ምክንያቶችና ወይም የቃላቸውን አነጋገር ማሻሻል አስፈላጊ የሚሆንበትን ምክንያት ለወካዩ
አሳብ ማቅረብና ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2209፡፡ አፈጻጸሙ፡፡

(1) ተወካዩ ሥራውን የሚፈጽመው በተለይ ለወካዩ ጥቅም ሊሰጥ በሚችልበት መንገድ ብቻ ነው፤ ስለዚሁም በወኪልነቱ ምክንያት
በሚሠራው ሥራ ወካዩ ሳያውቅ አንዳችም ጥቅም ለግሉ መውሰድ አይችልም፡፡

(2) ተወካዩ በውክልናው ምክንያት ያገኛቸውን መረጃዎች፤ የወካዩን ጥቅም በሚጎዳ ሁኔታ ሊሠራባቸው አይችልም፡፡

ቊ 2210፡፡ የውክልናው ሒሳብ አያያዝ፡፡

(1) ተወካዩ በውክልና ሥራው ምክንያት ገቢ ላደረገው ገንዘብና በሥራውም ላገኘው ትርፍ ሁሉ ያገኘው ገንዘብ ሁሉ ለወካዩ የማይገባው
እንኳ ቢሆን ስለ ሒሳብ አያያዝ ሥራ ለወካዩ አላፊ ይሆናል፡፡

(2) ተወካዩ ለወካዩ ሊከፍል የሚገባውን ገንዘብ ለራሱ ጥቅም አውሎት እንደሆነ፤ ገንዘቡን ከወሰደበት ቀን አንሥቶ አንድም ማስጠንቀቂያ
ሳያስፈልግ እስከ ወለዱ ለወካዩ ሊከፍለው ይገባል፡፡

ቊ 2211፡፡ አስፈላጊ ትጋት፡፡

(1) ተወካዩ በውክልና ሥራው ላይ በሚገኝባቸው ጊዜዎች ሁሉ በውክልናው የተሰጠውን አደራ፤ አንድ መልካም የቤተሰብ አባት ቤተሰቡን
ለመጠበቅ እንደሚያደርገው ሁሉ በትጋትና በጥንቃቄ መጠበቅ አለበት፡፡

(2) በአላፊነት የሚጠየቀው የማታለል በሠራው ሥራ ብቻ ሳይሆን በሥራው አመራር በሚያደርጋቸው ጥፋቶችም ጭምር ነው፡፡

(3) የውክልናው ሥልጣን የተሰጠው በነፃ እንደሆነ የወካዩን ጒዳዮች እንደራሱ ጒዳይ አድርጎ ተጠንቅቆ ከሠራ በአላፊነት ሊያስጠይቀው
አይችልም፡፡

ቊ 2212፡፡ ዋቢነት የሌለው ጒዳይ፡፡

(1) በውላቸው ውስጥ ተቃዋሚ የሆነ ስምምነት የሚገኝበት ካልሆነ በቀር፤ ተወካዩ በራሱ ስም ሆኖ ቢሠራም ከሌላው ጋራ ላደረገው ውል
አፈጻጸም ጒዳይ በራሱ ስም አላፊነት ሊጠየቅ አይገባውም፡፡
(2) ውሉን በፈጸመበት ጊዜ የተዋዋለው ሰው እንደ ውሉ ቃል ለመፈጸም የማይችልና በገባበት ግዴታ መሠረት ገንዘቡን የማይከፍል
መሆኑን የሚያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው የሆነ እንደሆነ አፈጻጸሙ ከዚህ በላይ ከተጻፈው የተለየ ይሆናል፡፡

ቊ 2213፡፡ የሒሳብ ማቅረብ ግዴታ ፡፡

(1) ተወካዩ ወካዩ በጠየቀው ጊዜ የሥራውን አካሄድ መግለጫና ሒሳብ በየጊዜው የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

(2) የተሰጠውን የውክልና ሥራ መፈጸሙን ያለመዘግየት ለወካዩ ማስታወቅ ይገባል፡፡

ቊ 2214፡፡ የሥራውን አመራር ተግባር ስለ ማጽደቅ፡፡

(1) ተወካዩ ያቀረበው የሥራ አካሄድ መግለጫ ለወካዩ ደርሶት የጒዳዩ ዐይነትና ልማዳዊው ደንብ ለመልስ መስጫ የሚበቃ ጊዜ
እስከሚፈቅድለት ቀን ድረስ፤ (በቀረበለት መግለጫ መሠረት የሚፈቅድ ወይም የማይፈቅድ መሆኑን) መልስ ሳይሰጠው ከተወሰነው
የበለጠ ጊዜ በዝምታ ያሳለፈው እንደሆነ ተወካዩ የያዘውን የሥራ አካሄድ ዘዴ ወካዩ ፈቅዶ እንደተቀበለው ያስቈጥረዋል፡፡

(2) ተወካዩ ወካይ ከሰጠው ትእዛዝ አልፎ ሠርቶ እንደሆነና በውክልናው ከተሰጠው ሥልጣን በላይም ሠርቶ እንደሆነ፤ ለወካዩ ላቀረበው
መግለጫ ተቃዋሚ ወይም አጽዳቂ መልስ ካልተሰጠው አፈጻጸሙ ከላይ በተመለከተው ዐይነት ይሆናል፡፡

ቊ 2215፡፡ በተወካይ ስለ መተካት፡፡ (1) የሚቻልበት ሁኔታ፡፡

(1) ከውክልናው ሥልጣን ውጭ የሆነውን ሌላ ሰው በራሱ ምትክ አድርጎ እንዲያሠራ ወካዩ ካልፈቀደለት በቀር፤ ተወካዩ የተወከለበትን
ሥራ እሱ ራሱ መፈጸም አለበት፡፡

(2) የተወካዩ በሥራው ላይ መገኘት ወይም ሌላ ሰው መተካቱ እንደ ልማዳዊው ሕግ ለወካዩ እኩል ሆኖ የሚታየው ከሆነ ተወካዩ ሌላ
ሰው ተተክቶ ሥራውን እንዲያሠራ እንደ ተፈቀደለት ያህል ይቈጠራል፡፡

(3) ተወካዩ በውክልናው የተሰጠውን የሥራ ጒዳይ ራሱ እንዳያካሂደው ድንገተኛ መሰናክል የገጠመው እንደሆነና የወካዩም ሥራ
መልካም አመራር ጒዳይ የሚያስገድደው ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ ይህንንም ከማድረጉ በፊት ለወካዩ ለማስታወቅና ለማስፈቀድ ጊዜ
የሚያጥረው የሆነ እንደሆነ ሌላ ሰው ተክቶ ሥራውን ማሠራት አለበት፡፡

ቊ 2216፡፡ (2) የተወካዩ አላፊነት፡፡

(1) ተወካዩ በማይገባ በሥራው ላይ ተክቶ ያሠራው ሰው በሚያደርገው ሥራ ሁሉ፤ እሱ ራሱ እንደ ሠራው ያህል ተቈጥሮ በአላፊነት
ይጠየቃል፡፡
(2) በሥራው ላይ ሌላ ሰው እንዲተካና እንዲያሠራ በሚገባ ተፈቅዶለት እንደሆነ ግን፤ በአላፊነት የሚጠየቀው ተተኪውን በመምረጥ ላይ
ጥንቃቄ ባላደረገበት ጒዳይና ለተተኪውም የሰጠው የሥራ መሪ ትእዛዝ የሚያስከትለውን ጒድለት በሚመለከተው ነገር ብቻ ነው፡፡
ቊ 2217፡፡ (3) በወካዩና በተተኪው ተወካይ መካከል ያሉ ግንኙነቶች፡፡

(1) በወካዩና ተተኪው ተወካይ መካከል ያሉት ግንኙነቶች የሚወሰኑት ተተኪው ወኪል ዋናው ወኪል በሌላ ሦስተኛ ሰው ለመተካት
መብት ያለው እንደሆነ ያህል በሚገባ ያመነ ሲሆን ተተኪው ወኪል ይህን ሥልጣን ያገኘው በቀጥታ ከወካዩ ላይ እንደሆነ ያህል
በመቊጠር ነው፡፡

(2) እንዲህ ባልሆነ ጊዜ ግን ጒዳዩ የሚወሰነው ስለ ሥራ አመራር በተነገረው ድንጋጌ መሠረት ነው፡፡

ቊ 2218፡፡ ስለ ብዙ ወኪሎች፡፡

(1) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር፤ በአንድ ዐይነት ውል ላይ ብዙ ሰዎች ተወክለው እንደሆነ፤ ይህን የውክልና ሥልጣን ሁሉም
በአንድነት መቀበላቸው ካልተረጋገጠ በቀር ውክልናው እንደ ጸና አይቈጠርም፡፡

(2) እንዲሁም ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር በአንድ ውል ብዙ ሰዎች ተወክለው እንደሆነ፤ የሠሩዋቸው ሥራዎች ወካዩን
ሊያስገድዱት የሚችሉት ተወካዮቹ ሁሉ አብረው ሠርተው ሲገኙ ነው፡፡

ክፍል 3፡፡
ስለ ወካዩ ግዴታዎች
ቊ 2219፡፡ በውል ስምምነት መሠረት ስለሚከፈል የድካም ዋጋ፡፡

(1) ተወካዩ በውሉ ላይ ታስቦ የተመለከተውን የድካም ዋጋ የመቀበል መብት አለው፡፡

(2) በውሉ ላይ የተመለከተው የድካም ዋጋ ከመጠን ያለፈ ሆኖ ያገኙት እንደሆነና ተወካዩም ከሰጠው የአገልግሎት ፍሬ የበለጠ ሆኖ
የመገቱት እንደሆነ፤ ዳኞች በውሉ ላይ ከተመለከተው የድካም ዋጋ ላይ በመጠኑ ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡

ቊ 2220፡፡ በውል ያልተወሰነ የድካም ዋጋ፡፡

(1) ስለ ድካሙ ዋጋ ሊከፈለው የሚገባው ነገር በውል ላይ ያልተመለከተ እንደሆነ፤ የሥራውን ተግባር በውክልናው የፈጸመው በሞያ
ሥራው ውስጥ በተመለከተ በግል ሥራው ካልሆነና እንደ ልማዳዊው ሕግ የድካም ዋጋ ማግኘት የሚገባው ካልሆነ በቀር ወኪሉ ዋጋ
የመጠየቅ መብት አይኖረውም፡፡

(2) በተዋዋዮቹ መካከል ስምምነት የሌለ ሲሆንና በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ሁኔታ ለሞያ ሥራ ሊከፈል በሚገባው በታወቀው የሥራ ዋጋ
ልክ ማስታወቂያ ታሪፍና በልማዳዊው ሕግ መሠረት ለወኪሉ የሚከፈለውን የድካም ዋጋ ዳኞች ይወስናሉ፡፡

ቊ 2221፡፡ ተቀዳሚ ተከፋይና ወጪ፡፡


(1) ለተወካዩ ስለ ውክልናው ሥራ ማስኬጃና ማከናወኛ የሚሆን ተቀዳሚ ተከፋይ ወጪ ሊሰጠው ይገባል፡፡

(2) እንዲሁም ተወካዩ ስለ ውክልና ሥራው መልካም አካሄድ ያደረገውን ወጪ ሁሉ ወካዩ ሊከፍለው ይገባል፡፡

(3) የዚህም የተቀዳሚ ተከፋይና የወጪ ገንዘብ ወለድ ወጪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ አንዳችም ማስጠንቀቂያ ሳያስፈልግ መታሰብ አለበት፡፡

ቊ 2222፡፡ ግዴታና ኪሣራ፡፡

(1) ተወካዩ ለወካዩ ጥቅምና ለውክልናው ሥራ መልካም አካሄድ ሲል በወኪልነቱ ከገባው የውል ግዴታ ወካይ ነፃ ሊያወጣው ይገባል፡፡

(2) እንዲሁም ተወካዩ በራሱ ጥፋት ያመጣው ካልሆነ በቀር የውክልና ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ስለደረሰበት አደጋ ወካዩ ኪሣራ
ሊከፍለው ይገባዋል፡፡

ቊ 2223፡፡ ለመቃወም የሚቻልበት ነገር፡፡

(1) ወካዩ የሥራውን ጒዳይ መልካም ውጤት አላገኘም በማለት ምክንያት፤ ለወኪሉ ሊከፍለው የሚገባውን ገንዘብ አልከፍልም ለማለት
አይችልም፡፡

(2) ተወካዩ ሊከፍለው ከሚገባው በተለይም የውክልና ሥራውን ሲፈጽም ስላደረገው ጥፋት ከሚከፍለው ገንዘብ ጋራ ወካዩ ለተወካዩ
የሚከፍለውን ገንዘብ ለማቻቻል ይችላል፡፡

ቊ 2224፡፡ የመያዝ መብት፡፡

ወካዩ ሊከፍለው የሚገባውን ገንዘብ ጨርሶ እስኪከፍለው ድረስ ተወካዩ በውክልናው ሥልጣን መሠረት እንዲሠራበትና እንዲገለገልበት
ከተረከበው ዕቃ ውስጥ ሊከፈለው በሚገባው ገንዘብ መጠን በእጁ ለማቈየት ይችላል፡፡

ቊ 2225፡፡ ስለ ብዙ ወካዮች፡፡

ብዙ ወካዮች ሆነው ለአንድ ዐይነት የጋራ ጒዳይ የወከሉት እንደሆነ፤ ወካዮቹ ሁሉ ስለ ውክልናው ውል መልካም አፈጻጸም ጒዳይ
እየአንዳንዳቸው ለተወካዩ በሙሉ አላፊዎች ይሆናሉ፡፡

ክፍል 4፡፡
ስለ ውክልና መቅረት፡፡
ቊ 2226፡፡ ውክልናውን ስለ መሻር፡፡
(1) ወካዩ አስፈላጊ መስሎ በታየው ጊዜ የውክልናውን ሥልጣን ለመሻርና አስፈላጊ ሆኖም ቢገኝ በወካዩ የውክልና ሥልጣኑን
የተቀበለበትን የውል ጽሑፍ በፈቀደ ጊዜ እንዲመልስለት ሊያስገድደው ይችላል፡፡

(2) ይህንንም ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2227፡፡ የውክልናው ሥልጣን መሻር የሚያስከትለው ውጤት፡፡

(1) በውክልናው የተሰጠው የሥልጣን ጊዜ ከማለቁ በፊት ወካዩ ወኪሉን ከሥልጣኑ ሽሮት እንደሆነ፤ ወይም የሽረቱ ጒዳይ በተወካዩ ላይ
ጉዳት የሚያደርስበት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ ወካዩ ተወካዩን ከሥልጣኑ በሻረው ጊዜ በሚደርስበት ጉዳት ሁሉ ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(2) የውሉ መጽኛ ዘመን የተወሰነው ለራሱ ልዩ ጥቅም ብቻ እንደሆነና ወይም ተወካዩን ለመሻር በቂ የሆነ ምክንያት ካለው ወካዩ
ማናቸውም አላፊነት የለበትም፡፡

ቊ 2228፡፡ ስለ ብዙ ወካዮች፡፡

(1) ብዙ ወካዮች ሁነው ለጋራ ጒዳያቸው የወከሉትን ተወካይ አንዱ ብቻ ሊሽረው አይችልም፡፡

(2) ስለ ተወካዩ መሻር በቂ የሆነ ትክክለኛ ምክንያት ከሌለ በቀር ወካዮቹ በመላው ሳይስማሙበት አንዱ ወካይ ብቻውን ተወካዩን
ሊሽረው አይችልም፡፡

ቊ 2229፡፡ ወኪሉ የውክልና ሥልጣኑኑ ስለ መተው፡፡

(1) ተወካዩ የውክልናውን ሥራ የሚተው መሆኑን ለወካዩ አስታውቆ ውክልናውን ለመተው ይችላል፡፡

(2) ይህ የተወካዩ ሥራ መተው በወካዩ ላይ ጉዳት የሚያደርስበት ከሆነ፤ ተወካዩ በወካዩ ላይ የደረሰውን ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡ ሆኖም
ተወካዩ የውክልናውን ሥራ መቀጠሉ በራሱ ላይ ከፍ ያለ ግምት ያለው ጉዳት የሚያደርስበት መሆኑ ከታወቀና ሥራውንም ለመቀጠል
በፍጹም የማያስችለው ምክንያት መኖሩ ከተረጋገጠለት ማንኛውንም የጉዳት ኪሣራ ለመክፈል አይገደድም፡፡

ቊ 2230፡፡ የተወካዩ መሞት ወይም ሥራ ያለ መቻል፡፡

(1) ተወካዩ የሞተ እንደሆነ፤ በስፍራው ያለመኖሩ የተረጋገጠ እንደሆነ፤ ለመሥራት ችሎታ ያጣ እንደሆነ፤ ወይም ኪሣራ ደርሶበት በንግድ
ኪሣራ ላይ መውደቁ የተረጋገጠ እንደሆነ ስለዚህ ጒዳይ ታስቦ ተቃራኒ የሚሆን ውል ተመልክቶ ካልተገኘ በበር የውክልናው ሥልጣን
ወዲያውኑ ይቀራል፡፡

(2) የተወካዩ ወራሾች ወይም ሕጋዊ እንደራሴ የውክልና ሥልጣን መኖሩን ካወቁ፤ በተወካዩ ላይ ይህን የመሰለ ነገር እንደ ደረሰበት
ወዲያውኑ ለወካዩ ማስታወቅ አለባቸው፡፡
(3) እንዲሁም ዋናው ተወካይ ይህን የመሰለ ነገር ከደረሰበት በኋላ ወካዩ ነገሩን ዐውቆ አስፈላጊውን ድርጅት እስኪያደርግ ድረስ ለወካዩ
ጥቅም የሚሆነውን አስፈላጊ ነገር ሁሉ መፈጸም አለባቸው፡፡

ቊ 2231፡፡ ስለ ብዙ ተወካዮች፡፡

(1) ብዙዎች ተወካዮች አንድ ዐይነት ጒዳይ ለማከናወን ተወክለው እንደሆነና ከመካከላቸው አንደኛው በአንድ ምክንያት ሥራውን
ለመቀጠል የማያስችለው ነገር ገጥሞት የውክልናውን ሥራ ለማቋረጥ የተገደደ እንደሆነ፤ ስለ እንደዚህ ያለው ጒዳይ ተቃራኒ የሆነ ቃል
በውላቸው ውስጥ ተመልክቶ ካልተገኘ በቀር የአንዱ ሥራ ማቆም የሁሉንም ተወካዮች ሥራ ለማቆም ይችላል፡፡

(2) ሌሎቹ ተወካዮች የውክልና ሥልጣናቸው የቆመበትን ምክንያት እንዳወቁ ወዲያውኑ ለወካዩ ማስታወቅ አለባቸው፡፡ ወካዩም
አስፈላጊውን ነገር እስኪያዘጋጅ ድረስ የሥራው ሁኔታና የጊዜው አጋጣሚ የሚያስገድደውን ዋና ዋና ጒዳይ እያከናወኑ መቈየት
ይገባቸዋል፡፡

ቊ 2232፡፡ የወካዩ መሞት ወይም ሥራ ያለ መቻል፡፡

(1) ወካዩ የሞተ እንደሆነ፤ በስፍራው አለመኖሩ የተረጋገጠ እንደሆነ ለመሥራት ችሎታ ያጣ እንደሆነ ወይም በንግድ የመውደቅ ኪሣራ
የደረሰበት እንደሆነ ለጒዳዩ ተቃራኒ የሚሆን ውል ካልተገኘ በቀር የውክልናው ሥልጣን ወዲያውኑ ይቀራል፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ሁኔታ ተወካዩ ሥራውን ቢያቋርጥ በጒዳዩ ላይ አደጋ የሚደርስበት እንደሆነና በውክልናው ሥልጣንም
መሠረት ሥራውን ጀምሮ እንደሆነ የዋናው ወካይ ወራሾች ወይም ሕጋዊ እንደራሴዎች አስፈላጊውን ጒዳይ እስኪያደርጉና ራሳቸውም
ሊያስቡበት እስኪችሉ ድረስ ሥራውን መቀጠል አለበት፡፡

ክፍል 5፡፡
ለሦስተኛ ወገኖች የውክልናው ሥልጣን የሚያስከትለው ውጤት፡፡
ቊ 2233፡፡ ወደ እንደራሴነት ደንብ ስለ መምራት፡፡

በወካዩ በተወካዩና የሦስተኛ ወገን በሆኑ በሌሎች ሰዎች መካከል የሚደረገው የግንኙነት ጒዳይ በዚህ አንቀጽ በምዕራፍ 1 በተደነገገው
ደንብ ላይ በተመለከተው ሕግ መሠረት ይከናወናል፡፡

ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ኮሚሲዮን፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ ግዥ ወይም ስለ ሽያጭ ኮሚሲዮን፡፡
ቊ 2234፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) የግዥ ወይም የሽያጭ ኮሚሲዮን ሲባል ኮሚሲዮኔር ተብሎ የሚጠራው፤ ተወካይ ኮሚሲዮን ሰጭ ተብሎ ለሚጠራው ወካይ ተወካዩ
በራሱ ስም ሆኖ ነገር ግን ለወካዩ ጥቅም የንግድ ዕቃዎችን ዋጋ ያላቸው ወረቀቶችን፤ ወይም ይህን የመሳሰሉትን ሌላ ነገሮች፤ ለመግዛት
ወይም ለመሸጥ ግዴታ የሚገባበት ውክልና ማለት ነው፡፡

(2) በዚህ ክፍል ውስጥ ከተመለከተው ግልጽ ድንጋጌና የማሻሻል ደንብ በመሠረቱ ልዩነት ከሚኖረው በቀር የውክልና ደንብ ለእንደዚህ
ያለው ውል ጒዳይ ይጸናል፡፡

ቊ 2235፡፡ የአጠባበቅ ጥንቃቄዎች፡፡

(1) ኮሚሲዮኔሩ፤ በኮሚሲዮን ሰጪው ስም የተላኩለትን ዕቃዎች ለመጠበቅ የሚያስፈልገውን ጒዳይ ሁሉ መፈጸምና ዕቃዎችም የተበላሹ
መስለው የታዩ እንደሆነ፤ ወይም ከተወሰነው ጊዜ በመዘግየት ደርሰው እንደሆነ በዕቃ ጫኚው ዘንድ እንደ ባለንብረት ሆኖ የኮሚሲዮን
ሰጪውን መብት ይዞ መሥራት አለበት፡፡

(2) ስለ እንደዚህ ያለውም ጒዳይ ዕቃዎቹ እንዳልደረሱ ያህል በሚያስቈጥር አጋጣሚ ሁኔታ፤ ኮሚሲዮኔሩ ለኮሚሲዮን ሰጪው ወዲያውኑ
አሳቡን ማቅረብ ይገባዋል፡፡

(3) አንድ ሰው የኮሚሲዩኑን አደራ ያልተቀበለም ቢሆን እንኳ የኮሚሲዮኑ ሥራ ጒዳይ የዚህን ሰው የሞያና የግል ሥራውን የሚመለከት
ከሆነ ይህን የመሰሉ ግዴታዎችን መፈጸም ይገባዋል፡፡

ቊ 2236፡፡ የንግድ ዕቃዎች መሸጥ፡፡

በኮሚሲዮን የተላኩትን የንግድ ዕቃዎች በቶሎ ይበላሻሉ ተብሎ የሚያሠጋ ነገር የተገኘ እንደሆነ፤ ኮሚሲዮኔሩ የንግድ ዕቃዎች በሚገኙበት
አገር ባሉት ባለሥልጣኖች ፊት እንዲሸጣቸው መብት ይኖረዋል፤ እንዲያውም የኮሚሲዮን ሰጪው ጥቅም የሚያስገድደው ሆኖ ሲገኝ
ይህንኑ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 2237፡፡ አስቀድሞ ዋጋ ስለ መክፈል፡፡

ሻጭ ዕቃውን ከማስረከቡ በፊት ኮሚሲዮን ሰጪው ሳይፈቅድለት ኮሚሲዮኔሩ ላልተረከበው ዕቃ አስቀድሞ ዋጋ የከፈለ እንደሆነ
ለሚመጣው ኪሣራና ጥፋት አላፊ የሚሆነው ራሱ ነው፡፡

ቊ 2238፡፡ በዱቤ የመሸጥ ጒዳይ፡፡

(1) የሽያጩ ጒዳይ በሚፈጸምበት ስፍራ ያለው የንግድ ልማድ የዚሁ ዐይነት እንደሆነና ኮሚሲዮን ሰጪውም ተቃዋሚ የሆነ ትእዛዝ
ካልሰጠው በቀር ኮሚሲዮኔሩ ለዕቃ ገዢው ዕቃውን በዱቤ ሸጦ የዋጋውን መክፈያ ጊዜ ሊወስንለት ይችላል፡፡

(2) ለዕቃ ገዢው የመክፈያ ቀን የፈቀደለት ኮሚሲዮኔር ገዢው ማን መሆኑንና ለዋጋ መክፈያ የፈቀደለት ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ
ለኮሚሲዮን ሰጪው ማስታወቅ አለበት፡፡
(3) ኮሚሲዮኔሩ በራሱ ጥፋት ይህን ጒዳይ ለኮሚሲዮን ሰጪው ሳያስታውቅ የቀረ እንደሆነ፤ የዕቃው ዋጋ እጅ በእጅ እንደተከፈለ
ከመቈጠሩም ይልቅ ከዚህ ቀጥሎ ባለው ቊጥር ውስጥ የተመለከተው ድንጋጌ የጸና ይሆናል፡፡

ቊ 2239፡፡ ያለ ፈቃድ የተደረገ ዱቤ፡፡

(1) ኮሚሲዮኔሩ ኮሚሲዮን ሰጪው የሰጠውን ትእዛዝ በመቃምና የአገሩንም ልማድ ተቃራኒ በሆነ ዐይነት የንግድ ዕቃውን በዱቤ ሸጦ
ለዋጋው መክፈያ ጊዜ ሰጥቶ እንደሆነ፤ ባለንብረቱ የዕቃውን ዋጋ ወዲያውኑ እንዲከፍለው ኮሚሲዮኔሩን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው ጊዜ ኮሚሲዮኔሩ ለዕቃው ዋጋ አከፋፈል ጊዜ በመስጠት ያገኘውን ትርፍ ለግል ጥቅሙ ለማስቀረት ይችላል፡፡

ቊ 2240፡፡ ኮሚሲዮኔሩ መስጠት ስለሚገባው ዋቢነት፡፡

(1) ኮሚሲዮኔሩ፤ በኮሚሲዮን ሥራው የተሰጠው ሥልጣን ራሱ በሚያምነው ነገር ሁሉ እንዲሠራ እንደሆነ፤ በዚሁ ሥራው ከሌሎች ጋራ
ለተዋዋለው ግዴታ መልካም አፈጻጸምና ስለ ዕቃውም ዋጋ አከፋፈል ጒዳይ ሁሉ ለኮሚሲዮን ሰጪው አላፊ ነው፡፡

(2) ዋጋ ያላቸው ወረቀቶችን የመግዛትና የመሸጥ ኮሚሲዮን ሥልጣን የተሰጠው ኮሚሲዮኔር፤ ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር፤ በራሱ
እምነት ሊሠራ የሚችል ኮሚሲዮኔር ተብሎ የሚጠራ ነው፡፡

(3) የንግድ ዕቃዎችን ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ሥልጣን የተሰጠው ኮሚሲዮኔር፤ የኮሚሲዮኑ ውል በተደረገበት አገር ያለው የንግድ
ልማዳዊ ሕግ የዚሁ ዐይነት እንደሆነ ወይም ስለ ንግድ ለተዋዋላቸው ሰዎች አላፊ ዋስ ሆኗቸው እንደሆነ፤ በራሱ እምነት ሥልጣን የሚሠራ
ኮሚሲዮኔር ነው፡፡

ቊ 2241፡፡ በራሱ እምነት ስለሚሠራ ኮሚሲዮኔር፡፡

(1) በራሱ እምነት የሚሠራ ኮሚሲዮኔር በኮሚሲዮኑ ጒዳይ ለሚዋዋለው ሰው ሙሉ አላፊ የሆነ ዋስ ነው፡፡

(2) የውሉን ስምምነት ያለመፈጸም ጒዳይ ያስከተለው በኮሚሲዮን ሰጪው ጒድለት በተነሣ ምክንያት ካልሆነ በቀር ኮሚሲዮኔሩ
ላደረገው ውል አፈጻጸምና ለማናቸውም አጋጣሚ ነገር ሁሉ ለኮሚሲዮን ሰጪው አላፊ ነው፡፡

ቊ 2242፡፡ የአደጋ መጠባበቂያ ውል (ኢንሹራንስ)፡፡

ኮሚሲዮን ሰጪው ትእዛዝ ካልሰጠው በቀር ኮሚሲዮኔሩ የአደጋ መጠባበቂያ ውል (ኢንሹራንስ) እንዲያደርግ አይገደድም፡፡

ቊ 2243፡፡ ለኮሚሲዮኔሩ የሚከፈል የድካም ዋጋ፡፡


(1) ለኮሚሲዮኔሩ ሊከፈለው የሚገባው የድካም ዋጋ በውሉ ላይ ያልተወሰነ እንደሆነ፤ ኮሚሲዮኔሩ የኮሚሲዮኑን ውል በተዋዋለበት አገር
ባለው ልማድ መሠረት እንዲከፈለው ይደረጋል፡፡

(2) ልማድ የሌለ እንደሆነ፤ ኮሚሲዮኔሩ የፈጸመውን የሥራ ፍሬ መሠረት አድርጎ በመያዝና ሥራውንም ለማከናወን ያደገውን ወጪና
የደረሰበትን ኪሣራና ድካም በመገመት ዳኞች በትክክለኛ ፍትሐዊ መንገድ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

(3) ኮሚሲዮኔሩ በራሱ እምነት የሚሠራ እንደሆነ፤ በኮሚሲዮኑ ውል መሠረት የተወሰነለትን፤ በልማድ ወይም በትክክለኛ ሥርዐት
መሠረት ልዩ የሆነ የድካም ዋጋ የማግኘት መብት አለው፡፡

ቊ 2244፡፡ የድካሙ ዋጋ የሚከፈልበት ጊዜ፡፡

(1) ኮሚሲዮኔሩ እንዲፈጽም ለታዘዘው ሥራ የድካም ዋጋ የማግኘት መብት የሚኖረው የታዘዘውን ጒዳይ እግቡ በማድረስ፤ በሚገባ
በፈጸመ ጊዜ ወይም ይህ ሥራ ሳይፈጸም የቀረው በኮሚሲዮን ሰጪው ጒድለት የተነሣ የሆነ እንደሆነ አፈጻጸሙ እግቡ ሊደርስ ሲችል
በዚህ ምክንያት ተሰናክሎ በቀረ ጊዜ ነው፡፡

(2) ሥራውን በሚያካሂድበት ስፍራ ላይ ተቃራኒ የሚሆን ልማድ ካልኖረ በቀር እንዲፈጽም የተሰጠው የሥራ ጒዳይ እግቡ ደርሶ
ሳይፈጸም የቀረው በሌላ ምክንያት ከሆነ የድካም ዋጋ የመጠየቅ መብት አይኖረውም፡፡

ቊ 2245፡፡ የድካም ዋጋ የማግኘት መብት ስለ ማጣት፡፡

(1) ኮሚሲዮኔሩ በኮሚሲዮን ሰጪው ፊት እምነቱን በማጒደል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ ማንኛውንም የድካም ዋጋ ለመጠየቅ መብት
ይቀርበታል፡፡

(2) እንዲሁም የገዛውን ዕቃ በእርግጥ ከገዛበት ዋጋ አብልጦ የገዛው ያስመሰለ እንደሆነ ወይም የሚሸጠውን ከሸጠበት ከእውነተኛው ዋጋ
በታች አሳንሶ የሸጠ ያስመሰለ እንደሆነ የድካም ዋጋ መብት የማጣቱ ጒዳይ በዚሁ ዐይነት ይፈጸማል፡፡

ቊ 2246፡፡ ልዩ ልዩ ወጪና ተቀዳሚ ተከፋይ፡፡

(1) ኮሚሲዮኔሩ፤ ኮሚሲዮን ሰጪው ያዘዘውን የሥራ ጒዳይ ለማከናወን በቅን ልቡና ያደረገውን ወጪና በተቀዳሚነት የከፈለውን ሒሳብ
ሁሉ ከነወለዱ እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ወጪ ያደረገበት ጒዳይ ፍጻሜ ያላገኘም ቢሆን እንኳ ሥራውን ለማከናወኛ የከፈለው ወጪ
ሊመለስለት ይገባል፡፡

ቊ 2247፡፡ የመያዝ መብት፡፡

(1) ኮሚሲዮን ሰጪው ለኮሚሲዮኔሩ ሊከፍል የሚገባውን ገንዘብ እስኪከፍለው ድረስ ኮሚሲዮኔሩ አንድ ነገር በመያዣ ስም የማስቀረት
መብት አለው፡፡
(2) ይህንንም መብት ለኮሚሲዮን ሰጪው ሊገዛ ወይም ሊሸጥ ከመደባቸው ዕቃዎች ውስጥ በማናቸውም ዐይነት ዕቃ ላይ ሊፈጽም
ይችላል፡፡
(3) እንዲሁም በኮሚሲዮን ሰጪው ስም ከተቀበለው ከአንድ ዕቃ ዋጋ ላይ ይዞ ለማቈየት ይችላል፡፡

ቊ 2248፡፡ የኮሚሲዮኔሩ የመግዛት መብት፡፡

(1) እንዲገዛ ወይም እንዲሸጥ ትእዛዝ የተቀበለበት ዕቃ የንግድ ታሪፍ ተወስኖለት ወይም በገበያ ተወስኖ የታወቀ ዋጋ ያለው ሲሆን
ኮሚሲዮኔሩ እንደ ሌላ ሰው ሆኖ ከራሱ ጋራ የውል ስምምነት ለመፈጸም ይችላል፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው ጊዜ፤ በስምምነቱ መሠረት ወይም እንደ ልማድ ሊከፈለው የሚገባውን መብት አይከለክልበትም፡፡

(3) ከራሱ ጋራ የሚስማማበት ዋጋ፤ ኮሚሲዮን ሰጪው ከወሰነው ዋጋ በንግድ ታሪፍ ወይም በዕለት የገበያ ዋጋ ከተወሰነው በታች ሊሆን
አይገባውም፡፡

ቊ 2249፡፡ የይመስላል ግምት፡፡

ኮሚሲዮኔሩ ራሱ ገዥ ወይም ሻጭ ሆኖ በግዥው ወይም በሽያጩ ጒዳይ ከማን ጋራ እንደተዋዋለ ለኮሚሲዮን ሰጪው ሳይገልጽለት
በውክልናው ሥልጣን የተሰጠው አደራ የተፈጸመ መሆኑን ብቻ ለኮሚሲዮን ሰጪው ያስታወቀ እንደሆነ የገዥነቱን ወይም የሻጭነቱን
አላፊነት እሱ ራሱ እንደወሰደ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2250፡፡ ስለ ኮሚሲዮን መቅረት፡፡

ኮሚሲዮን ሰጪው፤ ወይም ኮሚሲዮኔሩ ቢሞቱ የመሥራት ችሎታ ቢያጡ፤ ወይም በአገር አለመኖራቸው ቢረጋገጥም እንኳ፤ የኮሚሲዮን
ሰጪው ወይም የኮሚሲዮኔሩ ወራሾች ወይም እንደራሴዎቻቸው የነዚሁ ምትክ ሆነው የንግድ ሥራውን በማካሄድ ከቀጠሉ የኮሚሲዮኑ
ሥራ እንደቀረ አይቈጠርም፡፡

ክፍል 2፡፡
ስለ ማመላለሻ ኮሚሲዮን፡፡
ቊ 2251፡፡ የማመላለሻ ኮሚሲዮን፡፡

(1) የማመላለሻ ኮሚሲዮን ሲባል ላኪ ኮሚሲዮኔር ወይም የትራንስፖር መልክተኛ ተብሎ የሚጠራ ተወካይ በራሱ ስም ሆኖ ነገር ግን
ኮሚሲዮን ሰጪ ተብሎ ለተጠራው ወካይ ጥቅም ሲል የንግድ ዕቃዎች የማመላለሻ ስምምነት ከትራንስፖር ኮሚሲዮኔሮች ጋራ የመዋዋል
ውክልና ማለት ነው፡፡

(2) የግዥው ወይም የሽያጭ ኮሚሲዮን ደንቦች ለእንደዚህ ያለው ውልም የሚጸኑ ናቸው፡፡
ቊ 2252፡፡ የአደጋ መጠባበቂያ ውልና ኢንሹራንስ የዚሁ ለውጥ መብት፡፡

(1) ዕቃ ላኪው ኮሚሲዮኔር ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር ለሚልካቸው የንግድ ዕቃዎች መጠባበቂያ ኢንሹራንስ እንዲያደርግ
አይገደድም፡፡
(2) የማመላለሱን (የትራንስፖርን) ጒዳይ እርሱ ራሱ ሊጠባበቀው ይችላል፡፡

(3) በእንደዚህ ያለው ጊዜ ዕቃ ጫኙ የሚገባውን መብት ያገኛል፡፡ የሚደርስበትንም ግዴታ ይፈጽማል፡፡

ምዕራፍ 4፡፡
ዳኞች ስለሚሰጡት ውክልና፡፡
ቊ 2253፡፡ መሠረቱ፡፡

አንድ የተወሰነ ሥራን ወይም የተመደቡ ሥራዎችን በሌላው ስም ሆኖ እንዲያከናውን ዳኞች ጠባቂ ባላደራ ለተባለው ለአንድ ሰው
ውክልና ለመስጠት ይችላሉ፡፡

ቊ 2254፡፡ እንዲሾም ስለ መጠየቅ፡፡

(1) እንደራሴ እንዲደረግበት ለሚያስፈልገው ሰው ባል ወይም ሚስት የሆኑ ወይም ዘመዶች የሆኑ ወኪል እንዲሾሙለት ለዳኞች ጥያቄ
ማቅረብ ይችላሉ፡፡

(2) ሌላ ሰው ግን ይህን ጥያቄ ማቅረብ አይችልም፡፡

ቊ 2255፡፡ የዳኞች ውሳኔ፡፡

(1) እንደራሴ ይደረግለት የተባለው ሰው በመራቅ ወይም በሕመም ወይም በሌላ ምክንያት ወኪል ከማጣት ሁኔታ ውጭ ካልሆነ በቀር
ዳኞች ወኪል እንዲሾሙለት የቀረበላቸውን ጥያቄ አይቀበሉትም፡፡

(2) እነርሱም የሚሾሙት ጠባቂ ባላደራ አስቸኳይ የሆኑትን ጒዳዮች ብቻ እንዲያከናውን ይፈቅዱለታል፡፡

(3) እንደራሴ የተደረገለት ሰው መብቶች በሙሉ የሚጠበቁበትንና እንደራሴ የተደረገለት ሰው ንብረት ጠባቂ ባላደራ በጥበቃ ሥራው
ምክንያት በአላፊነት የሚፈረድበት ፍርድ እንዲፈጸም አስፈላጊ የሆኑትን ትእዛዞች ሁሉ ያደርጋሉ፡፡

ቊ 2256፡፡ ውጤቶች፡፡
(1) ዳኞች የመረጡት ጠባቂ ባለአደራ እንደራሴው እንዲሆን ለተሾመለትሰው የርሱ ወኪል ሆኖ መሾሙን እንደተቻለ ወዲያው
ያስታውቀዋል፡፡

(2) ወኪልነቱን የሰጡት ዳኞች በሆኑ ጊዜ እንደራሴ የተደረገለት ሰውና የጠባቂው (ባለአደራው) የየራሳቸው መብቶችና ግዴታዎች በዚህ
አንቀጽ በሁለተኛው ምዕራፍ ድንጋጌዎች መሠረት ይወሰናሉ፡፡

ምዕራፍ 5፡፡
ስለ ሥራ አመራር፡፡
ቊ 2257፡፡ የአፈጻጸሙ ሥልጣን፡፡

አንድ ሰው የነገሩን ሁኔታ እየተገነዘበ ይህን እንዲፈጽም ሳይገደድ የወኪልነትም ሥልጣን ሳይሰጠው የሌላውን ሰው ጒዳይ በመምራት
ሥራ ውስጥ ገብቶ ጒዳዩን ያካሄደ እንደሆነ የሥራ ጒዳይ አመራር እንዳለ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2258፡፡ ባለቤቱ ያልፈቀደውን ሥራ ስለ መምራት፡፡

(1) አንድ ሰው የባለቤቱን ፈቃድ ተቃራኒ በሆነ መንገድ የሥራውን ጒዳይ መምራት ያከናወነ እንደሆነ ያላገባብ ስለመበልጸግ የተወሰነው
ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል፤ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ከውል ውጭ የሚመጣ አላፊነትን ስለሚመለከተው ጒዳይ
የተወሰነውን ድንጋጌ መፈጸም ይቻላል፡፡

(2) ባለንብረቱ የሥራ አስኪያጅን ተግባር ያጸደቀለት እንደሆነ ግን በዚሁ ምዕራፍ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት
አይኖራቸውም፡፡

ቊ 2259፡፡ ለባለንብረቱ ጥቅም በማይሰጥ ሁኔታ የተፈጸሙ የሥራ ጒዳይ አመራሮች፡፡

(1) የሥራው አመራር ጒዳይ የተወሰነው ለባለንብረቱ ጥቅም ሳይሆን ሥራ መሪው ለራሱ ጥቅም ሲል በሌላው ሰው ጒዳይ ውስጥ
ገብቶሥራውን ለመምራት ወጥኖ እንደሆነ፤ ያለአገባብ ስለ መበልጸግ ጒዳይ የተወሰነው ድንጋጌ ሊጸና ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ የተገመተ እንደሆነ ከውል ውጭ የሚመጣን አላፊነት ስለሚመለከተው ጒዳይ የተወሰነው ድንጋጌ የሚጸና
ይሆናል፡፡

(3) ይህ ሥራ መሪ ያካሄደው የሌላው ሰው ጒዳይ ከራሱ ሥራ ጋራ የተያያዘ ግንኙነት ያለው ሆኖ አንዱ ሥራ ካንደኛው ተለይቶ ብቻውን
ሊካሄድ የማይችል በመሆኑ ምክንያት የሌላውን ሰው ሥራ ከራሱ ሥራ ጋራ ደርቦ መርቶት እንደሆነም ምን ጊዜም ቢሆን በዚህ ምዕራፍ
ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች መጽናታቸው አይቀርም፡፡

ቊ 2260፡፡ የሥራ መሪው ግዴታዎች፡፡


(1) የሌላውን ሰው የሥራ ጒዳይ ለመምራት የወጠነው የሥራ መሪ፤ የወጠነውን የሥራ ጒዳይ በተቻለ መጠን ለባለንብረቱ የስታወቅ
ግዴታ አለበት፡፡

(2) የጉዳዩ ባለቤት የሥራውን ጒዳይ ራሱ ለማካሄድ እስኪችል ድረስ፤ ሥራ መሪው የወጠነውን የሌላውን ሰው ሥራ መቀጠል አለበት፡፡

(3) የሥራውን ሁኔታ መግለጫ ስለ መስጠት ጒዳይ አንድ ተወካይ ሊፈጽመው የሚገባውን ጒዳይ የመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 2261፡፡ ትጋትና አላፊነት፡፡

(1) ሥራ መሪው ለማከናወን የወጠነውን ሥራ፤ እንደ መልካም የቤተ ዘመድ አባት ለቤተ ዘመዱ እንደሚያስብና እንደሚጠነቀቅ ያህል
በጥንቃቄና በትጋት ማከናወን ይገባዋል፡፡

(2) ምን ጊዜም ቢሆን፤ ዳኞች ከሥራ መሪው ጥፋት የተነሣ ለሚደርሰው ካሣና ኪሣራ አከፋፈል ጒዳይ ውሳኔ ለመስጠት ሲያስቡ ሥራ
መሪው የሌላውን ሰው ሥራ ለማካሄድ ያነሳሱትን አጋጣሚ ምክንያቶች ገምቶ መሠረት በማድረግ የኪሣራውን ውሳኔ ከዚሁ ጋራ
ማመዛዘን ይችላሉ፡፡

ቊ 2262፡፡ የመሪው ችሎታ ማጣት፡፡

ሥራ መሪው ይህን ሥራ ለመምራት በውል ግዴታ ለመግባት የማይችል ሆኖ ሲገኝ በመራው ሥራ አላፊ የሚሆነው በጥቅሙ በከበረበት
መጠን ተመዛዛኝ ሊሆን በሚቻል ግምት ወይም በክፉ ልቡና በሥራው ካገኘው ትርፍ ባስቀረው ጥቅም ልክ ነው፡፡

ቊ 2263፡፡ ቅን ልቡና፡፡

(1) የሥራ መሪው፤ ከባለንብረቱ ጋራ በሚያደርገው የሥራ ግንኙነት ጒዳይ ሁሉ የቅን ልቡናን ደንብ መከተል አለበት፡፡

(2) እንደዚህ ላለው ነገር የውክልናን ሥልጣን ስለሚመለከቱት ጒዳዮች የተሰጠው ድንጋጌ ይጸናል፡፡

ቊ 2264፡፡ የባለንብረቱ ግዴታዎች፡፡

(1) የሥራው አመራር እንዲወጠንና በሥራ መሪው እንዲካሄድ የባለቤቱ ጥቅም የሚያስገድድ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ ሥራ መሪው በስሙ
የወጠነውን የሥራ ተግባር ባለንብረቱ ሊያጸድቅለት ይገባዋል፡፡

(2) ሥራ መሪውም ይህን ሥራ ስለ መራለት ሥራውን ለማካሄድ ያወጣውን ወጪ መክፈል ለድካሙም የሚገባውን ዋጋ መስጠትና
ለሥራውም መምራት ጒዳይ ያወጣውን ወጪ መተካት፤ በራሱ ጥፋት ሳይሆን በሥራው ጒዳይ ለደረሰበት አደጋ ኪሣራ መክፈል
አለበት፡፡

(3) ለሥራው ማካሄጃ በሥራ አስኪያጁ ሒሳብ ወጪ የሆነውን ገንዘብ አንዳችም ማስጠንቀቂያ አስፈላጊ ሳይሆን ወጪ ከሆነበት ቀን
አንሥቶ ወለድ ይታሰብለታል፡፡
ቊ 2265፡፡ የሥራውን ማጽደቅ ጒዳይ የሚያስከትለው ውጤት፡፡

በሕጉ መሠረት ወይም በሥራው የጒዳዩ ባለቤት የሥራውን አመራር ተግባር ለሥራ መሪው የሚያጸድቅለት በሆነ ጊዜ ስለ ውክልና ጒዳይ
የወጣው ደንብ ይጸናበታል፡፡

አምስተኛ መጽሐፍ
ስለ ልዩ ውሎች፡፡
አንቀጽ 15፡፡
መብቶች ማስተላለፍን ስለሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ስለ ሽያጭ፡፡
ቊ 2266፡፡ ትርጓሜ፡፡

ሽያጭ ማለት ሻጭ የሆነው አንዱ ወገን ገዥ ለሆነው ሌላ ወገን ዋጋው በገንዘብ የተወሰነውን አንድ ነገር ገዢው ሊከፍለው ግዴታ በገባበት
መሠረት ሊያስረክብና ሀብትነቱን ሊያስተላልፍ የሚገደድበት ውል ነው፡፡

ቊ 2267፡፡ የዚህ ምዕራፍ ተፈጻሚነት፡፡ (1) ግዙፍነት ያለው ተንቀሳቃሽ፡፡

(1) በዚህ ምዕራፍ የተወሰኑት ድንጋጌዎች ግዙፍነት ባላቸው ተንቀሳቃሾች ነገሮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

(2) ግዙፍነት ያላቸውን አንዳንድ ዐይነት ተንቀሳቃሾች የሆኑትን ነገሮች ስለሚመለከት የመሸጥ ውል፤ የተወሰኑ ልዩ ድንጋጌዎች የተጠበቁ
ናቸው፡፡

ቊ 2268፡፡ (2) ከማይንቀሳቀሱ ንብረት የማይለይ አካል የሆነ ክፍል፡፡

(1) ከማይንቀሳቀሱ ነገሮች ጋራ የተያያዙ ክፍሎች መሸጥ እነዚህ ክፍሎች በተደረገው ውል ምክንያት ከማይንቀሳቀሰው ነገር ተለይተው
ግዙፍነት እንዳላቸው ተንቀሳቃሾች በመሆን ለገዢው መተላለፍ የሚገባቸው ሲሆን የተንቀሳቃሽ ንብረት መሸጥ ይባላል፡፡

(2) ይልቁንም እንደዚህ የሚሆንበት፤ ሰብልን ወይም የሚፈርስ ሕንጻ የተሠራባቸው ነገሮችን ወይም ድንጋይን እብነ በረድን፤ እነዚህን
የመሳሰሉትን ከመሬት የሚወጡትን ነገሮች የመሸጥ ነገር ሲሆን ነው፡፡

ቊ 2269፡፡ የማስረከብ ስምምነት፡፡


ስለዚህ ምዕራፍ ተፈጻሚነት፤ የሚሠሩትን ወይም የሚወጡትን ግዙፍነት ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ነገሮች ስለ ማስረከብ የሚደረገው ውል
እነዚህን የተባሉትን ነገሮች ለማስረከብ ግዴታ የገባው ሰው ለሚሠራው ወይም ለሚወጣው ነገር አስፈላጊ የሆኑትን ዐይነተኞች ነገሮች
መስጠት ያለበት እንደሆነ ውሉ እንደ ሽያጭ ውል ይቈጠራል፡፡

ክፍል 1፡፡
የውሉ አደራረግ፡፡
ቊ 2270፡፡ የሚሸጠው ነገር፡፡

(1) የሚሸጠው ነገር፤ የሻጩ ገንዘብ ሆኖ ሀልዎት ያለው ነገር ለመሆን ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም የሽያጩ ጒዳይ ሻጩ ወደፊት ለገዢው የሚያስረክበውና ሠርቶ ለማውጣት ግዴታ የሚገባበት ነገር ለመሆን ይችላል፡፡

(3) እንዲሁም ደግሞ፤ የሌላ ገንዘብ በሆነ ነገር ላይ ለመዋዋል ይችላል፡፡

ቊ 2271፡፡ ዋጋውን ሌላ ሽማግሌ እንዲገምተው ስለ መተው፡፡

(1) ዋጋውን ሌላ ሽማግሌ እንዲገምተው ለመተው ይቻላል፡፡

(2) የተባለው ሌላ ሽማግሌ ዋጋውን ለመገመት ያልፈለገ ወይም ያልቻለ እንደሆነ ሽያጩ ይቀራል፡፡

ቊ 2272፡፡ የውሉ ዐይነት፡፡

(1) የሽያጩ ውል ያለአንዳች ሁኔታ ወይም ሁኔታ ያለበት መሆን ይችላል፡፡

(2) ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር፤ ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች የገቡባቸው ግዴታዎች የውሉን መኖር የሚነኩ ምክንያቶች ለመሆን
አይችሉም፡፡

ክፍል 2፡፡
ስለ ውሉ መፈጸም፡፡
ቊ 2273፡፡ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡

(1) ሻጩ፤ በውሉና በዚህ ሕግ እንደተለከቱት ሁኔታዎች የሸጠውን ነገር ማስረከብ ግዴታው ነው፡፡

(2) ሻጩ የሸጠውን ነገር ባለሀብትነት ለገዢው ለማዛወርና ለዚህም ለሸጠው አንዳንድ ጒድለቶች ዋቢ መሆን ግዴታው ነው፡፡
(3) ከዚህም በቀር በሽያጭ ውል የተጣሉበትን ሌሎች ግዴታዎች ለመፈጸም ይገደዳል፡፡

(ሀ) የማስረከብ ግዴታ

ቊ 2274፡፡ በግዴታው ውስጥ ያለው ነገር፡፡

ማስረከብ ማለት በውሉና በተጨማሪው ውስጥ የተመለከተውን ነገር ለገዢው በውሉ ልክ መስጠት ነው፡፡

ቊ 2275፡፡ በግምት የሚወሰን ብዛት፡፡

(1) ሻጩ፤ ብዛቱ በግልጽ የተወሰነ ነገር ለማስረከብ ግዴታ ገብቶ እንደሆነ፤ ለገዢው ጥቅም ሲባል ብቻ የተደረገ መሆኑን የሚገልጹ
ምክንያቶች ካልተገኙበት በቀር የሚሰጠውን ነገር የብዛት ልክ መወሰን የሻጩ ነው፡፡

(2) በተደረገው ውል ይህን ያህል ይሁን በተባለው የግምት ብዛትና በውነተኛው ባስረከበው ብዛት መካከል ያለው ልዩነት የተገዛው ነገር
የአንድ መርከብ ሙሉ ጭነት የንግድ ዕቃ ሲሆን ከመቶ ዐሥር በሌላ ጊዜ ግን ከመቶ አምስት በላይ መሆን የለበትም፡፡

ቊ 2276፡ የማስረከቢያው ጊዜ፡፡

የተሸጠውን ነገር የማስረከቢያው ጊዜ በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ቃል ያልተገለጸ ሲሆን፤ ገዢው አስረክበኝ ብሎ ሲጠይቅ ሻጩ የሸጠውን
ነገር ወዲያውኑ ማስረከብ አለበት፡፡

ቊ 2277፡፡ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚደረግ ማስረከብ፡፡

የተሸጠውን ነገር ማስረከብ የሚፈጸምበት በእንደዚህ ያለ ጊዜ ውስጥ ይሁን በመባባል ሁለት ወገን ተዋዋዮች የተስማሙ እንደሆነ፤ ገዥው
የሚረከብበትን ቀን የሚወስንበት ምክንያት ካልተገኘ በቀር፤ የሸጠውን ነገር የማስረከቢያውን ቀን መወሰን የሻጩ ነው፡፡

ቊ 2278፡፡ የማስረከቢያውና የዋጋው መክፈል አንድ ጊዜ ስለ መሆን፡፡

(1) በውሉ የተነገረ ተቃራኒ ነገር ከሌለ በቀር የተሸጠውን ማስረከብ ከዋጋው መክፈል ጋራ በአንድ ጊዜ መሆን አለበት፡፡

(2) በዚህ ጊዜ ሻጩ ዋጋው እስኪከፈለው ድረስ የሸጠውን ነገር በጁ ይዞ ለመቈየት መብት አለው፡፡

ቊ 2279፡፡ የማስረከቢያው ቦታ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


የተሸጠው ነገር መረከቢያ ቦታ በሁለት ወገን ተዋዋዮች ያልገለጹ እንደሆነ፤ ሻጩ የሸውን ነገር ማስረከብ ያለበት ውሉ በተደረገበት ጊዜ
በነበረው መሥሪያ ቤት ወይም መሥሪያ ቤት ባይኖረው ዘወትር በሚቀመጥበት መኖሪያ ቤቱ ነው፡፡

ቊ 2280፡፡ (2) ልዩነት፡፡

(1) የተሸጠው አንድ የተረጋገጠ ነገር ሲሆንና ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ውሉ በተደረገ ጊዜ የተባለው ነገር ያለበትን ቦታ ያወቁ እንደሆነ ሻጩ
የሸጠውን ነገር ማስረከብ ያለበት በዚሁ በተባለው ቦታ ላይ ነው፡፡

(2) እንዲሁም የተሸጡት ነገሮች አንድ ዐይነት ሆነው ከአንድ የንግድ ዕቃ ማከማቻ ውስጥ የመወሰዱ ወይም አንድ የተወሰነ ጠቅላላ ነገር
ሲሆኑ፤ ወይም ውሉ በተደረገበት ጊዜ በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች በታወቀ ቦታ ላይ የሚሠሩ ወይም የሚወጡ ሲሆኑም ከዚህ በላይ
እንደተነገረው ይሆናል፡፡

(ለ) ባለሀብትነቱን ለገዢው የማስተላለፍ ግዴታ፡፡

ቊ 2281፡፡ ባለሀብትነቱን ለገዢው ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆኑ ግዴታዎች፡፡

ሻጩ የሸጠውን ነገር የማያስነካ መብት ለገዢው ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች ለመፈጸም ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 2282፡፡ የኔ ነው ባይ ሲመጣ መድን ስለመሆን፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

በተሸጠው ነገር ላይ በውሉ ጊዜ ለሌላ ሰው በነበረው መብት ምክንያት ሻጩ የተሸጠውን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ይለቀቅልኝ
የሚለውን መጪ ለመመለሰ ለገዢው መድን ነው፡፡

ቊ 2283፡፡ (2) ስለ መድኑ የተሰጠ ሕጋዊ ወሰን፡፡

(1) ገዢው በገዛው ነገር ላይ ይለቀቅልኝ ባይ መኖሩን በውሉ ጊዜ ዐውቆ እንደሆነ፤ ሻጩ መጪውን ለመመለስ ቃሉን ሰጥቶ ካልተገኘ በቀር
መድንነት የለበትም፡፡

(2) ነገር ግን በእንደዚህ ያለ ጊዜም ቢሆን ይለቀቅልኝ ባይነቱ ሻጩ በሰጠው የዋስትና መያዣ ምክንያት የተፈጠረ እንደሆነ፤ ለሸጠው ነገር
መድንነቱ የርሱ ይሆናል፡፡

ቊ 2284፡፡ መድን ላለመሆን የሚደረግ ውለታ፡፡

(1) ይለቀቅልኝ ባይ (መጪን) ለመመለስ የሻጩን መድንነት የሚያስቀሩ ወይም የሚቀንሱ ውለታዎች በጠባቡ መተርጐም አለባቸው፡፡
(2) የተሸጠው ነገር ለይለቀቅልኝ ባይ በሚለቀቅበት ጊዜ በግልጽ የገባ ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር እነዚህ ውለታዎች
በሺያጩ ላይ የተቀበለውን ዋጋ በሙሉ ወይም በከፊል ለገዢው የመመለስ ግዴታ እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡

(3) ሻጩ፤ በሸጠው ነገር ላይ ለሌላ ሰው ያለውን የይለቀቅልኝ ባይነት መብት ሆነ ብሎ ሰውሮት ቢገኝ ወይም ይህ ይለቀቅልኝ ባይነት
ሻጩ በሠራው ሥራ ምክንያት የተፈጠረ ሲሆን፤ አላፊነትን የሚያስቀር ወይም የሚቀንስ ማንኛቸውም ውለታ ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2285፡፡ ሻጩን በዋቢነት ስለ ማሳለፍ፡፡

(1) የኔ ነው ባይ የተነሣበት ገዥ በርሱ ላይ ለተነሣው ሙግት ሻጩን በዋቢነት ማሳለፍ አለበት፡፡

(2) ሻጩ በሚገባ ጊዜ ለነገሩ እንዲያልፍ ሲጠየቅ፤ ይለቀቅልኝ ባይ የመጣው በገዢው በሚመካኝ ምክንያት መሆኑን ካላስረዳ በቀር፤ ዋቢ
የመሆን ግዴታ አለበት፡፡

(3) ሻጩ ጨነገሩ እንዲያልፍ ያልተጠየቀ እንደሆነ፤ በአስፈላጊው ጊዜ ለነገሩ ቢያልፍ ኖሮ ሙግቱ ለርሱ ይቀናው እንደነበረ
በሚያስረዳበት መጠን ለነገሩ ያለ ማለፉ ምክንያት ሳይነካው ከአላፊነት ግዴታ ነጻ ይሆናል፡፡

ቊ 2286፡፡ ግልግል፡፡

ግዥው በዳኛ ፊት ከሚደረገው ክርክር ውጭ ለሌላው ሦስተኛ ሰው መብቱን ዐውቆለት እንደሆነ፤ ወይም ከተባለው ሦስተኛ ሰው ጋራ
ወዶ ተገላግሎ እንደሆነ፤ ሻጩ የኔ ነውና ይልቀቅልኝ ባይ መጪን ለመመለስ የማይችል መሆኑን ካላስረዳ በቀር ገዢው ሻጩ
እንዲያልፍለት መድንነቱን ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(ሐ) በተሸጠው ነገር ላይ ለሚገኝ ጒድለት ዋቢ መሆን፡፡

ቊ 2287፡፡ መሠረቱ፡፡

ሻጩ ያስረከበው ነገር እንደ ውሉ ትክክል ለመሆኑና ጒድለትም የሌለበት ለመሆኑ ለገዢው መድን (አላፊ) ነው፡፡

ቊ 2288፡፡ እንደ ውሉ ትክክል ስለ መሆኑ፡፡

ዕቃው እንደ ውሉ ትክክል ሆኖ አልተገኘም የሚባለው፡-

(ሀ) ሻጩ ከተሸጠው ነገር አንዱን ክፈል ብቻ የሰጠ እንደሆነ ወይም ሻጩ ሊሰጥ በውል ቃል ከገባበት ልክ አብልጦ ወይም አሳንሶ የሰጠ
እንደሆነ፤
(ለ) በውሉ የተመለከተው ሳይሆን ሌላ ነገር ወይም ዐይነቱ ሌላ የሆነውን ነገር የሰጠ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2289፡፡ ዋቢ ያላቸው ጒድለቶች፡፡


ዋቢ ሊሰጥበት የሚገባው፡-

(ሀ) የሸጠው ነገር ለደንበኛው አገልግሎት ወይም በንግድ ረገድ ለመጠቀሚያ ጥሩነት የሌላቸው ሲሆን፤

(ለ) የሸጠው ነገር በውሉ ውስጥ በግልጽ ወይም በውስጣዊ አሳብ ለተነገረው ልዩ አገልግሎት የሚሆኑ አሰፈላጊ የሚሆኑት ጥሩነት የሌሉት
ሲሆን፤
(ሐ) ዕቃዎቹ በውሉ ቃል ውስጥ በግልጽ ወይም በዝምታ የተመለከተው ዐይነታቸው ወይም ልዩነታቸው የሌለ ሲሆን ነው፡፡

ቊ 2290፡፡ የማመዛዘን ግምት ስለሚደረግበት ጊዜ፡፡

(1) ዕቃው እንደ ውሉ ትክክል መሆኑ እንዲሁም ጒድለቶች የሌሉበት መሆኑ የሚወሰነው፤ የአደጋ አላፊነት በሚዛወርበት ጊዜ ዕቃው
በነበረው ሁኔታ መሠረት ነው፡፡

(2) ውሉ ፈርሷል ወይም ለጐደለው ነገር ምትክ ይሰጥ ብሎ መግለጫ በመስጠት ምክንያት የአደጋ ኪሣራ አላፊነት አልተዛወረ እንደሆነ፤
ዕቃው እንደ ውሉ ትክክል ኑሮ ቢሆን የአደጋ ኪሣራ ይዛወር ነበር የሚባልበትን ጊዜ መሠረት በማድረግ ነው፡፡

(3) በዕቃው ላይ የተገኘ ጒድለት ወይም የዕቃው ትክክል ያለመሆን የደረሰው ከዚህ በላይ ከተመለከተው ቀን በኋላ ቢሆንም ዕቃው እንደ
ውሉ ትክክል ያልሆነው ወይም ጒድለት የደረሰበት በሻጩ አድራጎት ወይም እሱ አላፊ በሆነው ሰው አድራጎት የሆነ እንደሆነ፤ ዕቃው እንደ
ውሉ ትክክል ሳይሆን ለመቅረቱ ወይም ጒድለት ያለበት ሆኖ ለመገኘቱ ሻጩ መድን መሆን ይገባዋል፡፡

ቊ 2291፡፡ ገዢው የሚያደርገው ምርመራ

(1) ገዢው የገዛውን ነገር ለመመርመር እንደተቻለው ወዲያው ባጭር ጊዜ ውስጥ ነገሩን መመርመር አለበት፡፡

(2) ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር የዚህ ምርመራ አሠራር ፎርም ምርመራው በሚፈጸምበት ስፍራ ባሉት ልማዶች መሠረት
ይፈጸማል፡፡

(3) ገዢው በምርመራው ውጤት እጠቀማለሁ የሚል እንደሆነ፤ ዕቃውን የጥፋት አደጋ የሚያገኘው ካልሆነ በቀር፤ ሻጩን ወይም ወኪሉን
በምርመራው ጊዜ ውስጥ መጥራት አለበት፡፡

ቊ 2292፡፡ ገዢው የሚያደርገው ማስታወቅ፡፡

(1) የተደረገው ምርመራ ዕቃው እንደ ውሉ ትክክል አለመሆኑን ወይም ጒድለት ያለው መሆኑን የገለጠ እንደሆነ፤ ገዢው ይህንኑ ባጭር
ጊዜ ውስጥ ለሻጩ ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ጒድለቱን ሲያስታውቅ ገዢው እንደ ልማድ አሠራርና በቅን ልቡና የጒድለቱን ዐይነት መለየት አለበት፡፡

ቊ 2293፡፡ አለማስታወቅ፡፡
(1) ገዢው የነገሩን ጒድለት ሳያስታውቅ የቀረ እንደሆነ ሻጩ ጒድለት መኖሩን ካላመነ በቀር፤ ገዢው ዕቃው ከውሉ ስምምነት ጋራ አንድ
ዐይነት አይደለም ወይም፡-

(2) ስለሆነም እንደ አሠራሩ ልማድ በተደረገው ምርመሪ ሊገለጽ ያልቻለው ጒድለት በኋላ የተገኘ እንደሆነ፤ የተባለው ጒድለት
እንደተገለጸ ገዢው ወዲያው በፍጥነት የተገለጸውን ጒድለት ለሻጩ ካስታወቀ ስለ ጒድለቱ ሻጩን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) አስቦ ገዢውን እንዲታለል ያግባባ ሻጭ ጒድለቱ እንደሚገባ በቂ ሆኖ አልተለየልኝም ወይም በአስፈላጊ ጊዜ አላስታወቅኸኝም በማለት
ከአላፊነት ሊያመልጥ አይችልም፡፡

ቊ 2294፡፡ የስምምነት አላፊነት፡፡

ሻጩ የገባበት አላፊነት፤ ለነገሩ አንዳንድ ዐይነት ወይም ለነገሩ መልካም አገልግሎት፤ እስከዚህ ቀን ድረስ ነው ሲል ጊዜ በመወሰን ዋቢ ሆኖ
እንደሆነ፤ ገዢው የነገሩን ጒድለት በዚያው በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ለሻጩ ማስታወቅ በቂው ነው፡፡

ቊ 2295፡፡ የተሸጠውን ነገር ጒድለቶች ገዢው ስለ ማወቁ፡፡

(1) ሻጩ የተሸጠውን ነገር ጒድለቶች ውሉ በተደረገ ጊዜ ገዢው ዐውቆዋቸው እንደነበረ ያስረዳ እንደሆነ በዋቢነት አይያዝም፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ሻጩ የገባበት አላፊነት ግልጽ ቢሆንም ዋጋ የሌለው ነው፡፡

ቊ 2296፡፡ የገዢው ከባድ ቸልተኛነት፡፡

(1) የተሸጠው ነገር ጒድለቶች ግልጽ ሆነው የሚታዩ እንደሆኑና ገዢው ያላወቃቸውም ከራሱ ከባድ ቸልተኛነት ብቻ የተነሣ ሲሆን ሻጩ
ለነዚሁ ጒድለቶች ዋቢ አይሆንም፡፡

(2) ነገር ግን በዚህም ጊዜ ቢሆን፤ ሻጩ ጨተሸጠው ነገር ጒድለት የለበትም ሲል በግልጽ አስታውቆ እንደሆነ ወይም ለዕቃው አንዳንድ
ዐይነት ዋቢ በመሆን ተዋውሎ ሲገኝ አላፊነት አለበት፡፡

ቊ 2297፡፡ ከዋቢነት የሚያድን የውል ቃል፡፡

የተሸጠውን ነገር ጒድለቶች ገዢው እንዳያውቃቸው ሻጩ በተንኰል ደብቋቸው እንደሆነ፤ አላፊነትን የሚሰርዙ ወይም የሚቀንሱ
ውለታዎች ወራሾች ናቸው፡፡

ቊ 2298፡፡ የዋቢነት ክስ የሚቀርብበት ጊዜ፡፡


(1) ክስ ማቅረቡን የከለከለው የሻጩ አጭበርባሪነት ካልሆነ በቀር ገዢው ዕቃው እንደ ውሉ ትክክል አለመሆኑን ወይም ጒድለት ያለበት
መሆኑን ካስታወቀበት ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት ክስ ያላቀረበ እንደሆነ፤ ዕቃው እንደ ውሉ ትክክል አይደለም ወይም ጒድለት
ያለበት ነው ብሎ የመክሰስ መብቱን ያጣል፡፡

(2) ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ይህን የተባለውን ጊዜ ለማሳጠር አይችሉም፡፡

(3) ስለ ተባለው ዐይነት ወይም ስለ ነገሩ መልካም አገልግሎት ሻጩ የሰጠው ዋቢነት ለተወሰነ ጊዜ እንደሆነ፤ ገዢው ክሱን ለማቅረብ
መነሻ የሚያደርገው የተባለው ጊዜ የተፈጸመበትን ቀን ነው፡፡

ቊ 2299፡፡ የተወሰነው ጊዜ ሲያልፍ የገዢው ሁኔታ፡፡

(1) ከዚህ በላይ በተመለከተው ቊጥር የተነገረው ጊዜ ካለፈ በኋላ ገዢው የገዛውን ነገር ከውሉ ጋራ ትክክል ያለመሆኑን ወይም ጒድለቱን
ለማንሣት አይችልም፡፡

(2) ነገር ግን ዋጋውን ያልከፈለ እንደሆነ፤ የነገሩን ከውሉ ጋራ ያለ መስማማት ወይም ጒድለት በቂ በሆነ ጊዜ አስታውቆ እንደሆነ፤ ገዢው
ስለ አከፋፈል ለሚደረግለት ጥያቄ የዋጋውን መቀነስ ወይም በተገኘው ጒድለት ምክንያት ስለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ መክፈልን መቃሚያ
ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡

ቊ 2300፡፡ ጒድለትን ለማደስ የሚችል ስለ መሆኑ፡፡

(1) ሽያጩ አንድ ዐይነት ባላቸው ነገሮች ላይ እንደሆነ፤ ሻጩ፤ በውሉ የተወሰኑት ጊዜዎች እስኪያልፉ ድረስ ጒድለት በተገኘባቸው ነገሮች
ፋንታ፤ አዲስ የሆኑትን ነገሮች ለማስረከብ መብት አለው፡፡

(2) ሽያጩ በገዢው ልዩ ትእዛዝ መሠረት ሻጩ በሚሠራቸው ወይም በሚያወጣቸው ነገሮች ሲሆን፤ የነዚህ ነገሮች የመረከባቸው
መዘግየት ለገዢው ችግር ወይም ኪሣራ የሚያመጣበት አይሁን እንጂ፤ ነገሮቹን ለማስረከብ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ በኋላም ቢሆን፤ በነገሮቹ
የተገኙትን ጒድለቶች በቂ በሆነ ጊዜ ለማደስ መብት ያለው ይሆናል፡፡

(3) ስለ ጉዳት የተወሰነው ኪሣራ መቀበል መብት ለገዢው እንደተጠበቀ ነው፡፡

(መ) የሻጩ ሌሎች ግዴታዎች፡፡

ቊ 2301፡፡ አስረጅ ጽሑፎችን ስለ ማስተላለፍ፡፡

(1) ሻጭ፤ የተሸጠውን ነገር የሚመለከቱ አስረጅ ጽሑፎችን ለገዢው እንዲያስተላልፍ ልማድ ያለ እንደሆነ፤ ሻጭ የሸጠውን ነገር
ከማስረከብ ሌላ የተባሉትን አስረጅ ጽሑፎችን ለገዢው መስጠት አለበት፡፡

(2) ይኸውም አስረጅ ጽሑፎቹ የመስጠት ሥራ በውሉ በተወሰነው ወይም ለልማድ ትክክል በሆነው ስፍራ በሙሉ ትጋትና በተቻለ
ፍጥነት መፈጸም አለበት፡፡

(3) አስረጅ ጽሑፎቹ ከውሉ ጋራ የተስማሙ ካልሆኑ በቀር ገዢው ሊቀበላቸው አይገደድም፡፡
ቊ 2302፡፡ ኢንሹራንስ፡፡

አካባቢ ሁኔታዎችን በመመልከት የማመላለስ ኢንሹራንስ ማድረግ ልማድ እንደሆነና ሻጩም ራሱ ኢንሹራንስ ለማድረግና ለመፈረም
ግዴታ የሌለበት እንደሆነ፤ ወይም ኢንሹራንስ እንዲያደርግ ገዢው ለሻጩ አላስታወቀው እንደሆነ፤ ወይም እንደዚህ ያለውን ኢንሹራንስ
ለመዋዋል ገዢው የጠየቀው እንደሆነ ሻጭ አስፈላጊዎች የሆኑትን መግለጫዎች ሁሉ ለገዢው ማስታወቅ ግዴታው ነው፡፡

ንኡስ ክፍል 2፡፡


የገዢው ግዴታዎች፡፡
ቊ 2303፡፡ ጠቅላላ ድንጋጌ፡፡

(1) ገዢው ዋጋ ለመክፈልና የገዛውን ነገር ለመረከብ ይገደዳል፡፡

(2) ከዚህም በቀር ገዢው በሽያጩ ውል የገባባቸውን ሌሎች ግዴታዎች ሁሉ መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 2304፡፡ ዋጋውን የመክፈል ግዴታ፡፡

(1) ዋጋን የመክፈል ግዴታ ዋጋውን ለመክፈል ስለ ማዘጋጀት ወይም በአላፊነት ስለ ማረጋገጥ በተደረገው ውል ወይም ስለዚህ ጒዳይ
ባለው ልማድ መሠረት አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ሁሉ የመፈጸምን ግዴታ ይጠቀልላል፡፡

(2) ገዢው እንደ ነገሩ ሁኔታዎች የሐዋላ ደብዳቤ እንዲሰጥ ወይም አንድ ገንዘብ የሚያስጥ ሰነድ (ክሬዲ ደኩማንቴር) እንዲከፍት ወይም
የባንክ ወይም ሌላ ዋስ እንዲሰጥ ሊገደድ ይቻላል፡፡

ቊ 2305፡፡ በክብደት የተወሰነ ዋጋ፡፡

ዋጋው የተወሰነው በዕቃው ክብደት መሠረት የሆነ እንደሆነ፤ ጥርጣሬ ባለ ጊዜ መገመት ያለበት የዕቃው የራሱ ብቻ ጥሩ ክብደቱ ነው፡፡

ቊ 2306፡፡ የታወቀ ዋጋ ያለው ዕቃ፡፡

የተሸጠው ዕቃ በገበያ የተወሰነ ወይም የታወቀ ዋጋ ያለው ሲሆን፤ ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለተሸጠው ነገር ሻጩ የሸጠውን
በሚያስረክብበት ቀንና ቦታ በሚገበይበት ዋጋ እንደተዋዋዩ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2307፡፡ ሻጭ ዘወትር የሚሸጣቸው ነገሮች፡፡


(1) ሽያጩ ዘወትር ሻጩ በሚሸጠው ነገር ሲሆን ሁለት ወገን ተዋዋዮች ሽያጩ ሻጩ የሸጠውን በሚያስረክብበት ቀንና ቦታ ዘወትር
በሚሸጥበት ዋጋ እንደተዋዋዩ ይቈጠራል፡፡

(2) ሻጩ ባቀረበው ፋክቱር ላይ የተጻፈው ዋጋ ከዚህ በላይ ከተጻፈው ዋጋ ጋሪ ትክክለኛ ዋጋ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡

ቊ 2308፡፡ የዕቃው ብዛት በውሉ ከተመለከተው ብዛት በላይ ስለ መሆኑ፡፡

(1) ሻጩ በውሉ ከተመለከተው ብዛት በላይ ዕቃ ለገዢው ያቀረበ እንደሆነ፤ ገዢው በውሉ ከተመለከተው ብዛት በላይ የሆነውን
ላለመቀበል ወይም ለመቀበል ይችላል፡፡

(2) ገዢው የቀረበለትን በሙሉ የተቀበለ እንደሆነ፤ በተጨመረው ዕቃ ብዛት መጠን ዋጋውን መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2309፡፡ ዋጋው የሚከፈልበት ቦታ፡፡

(1) ገዢው በውሉ በተወሰነው ቦታ ላይ ዋጋውን መክፈል አለበት፡፡

(2) የተወሰነ ቦታ የሌለ እንደሆነ ገዢው ዋጋውን መክፈል ያለበት በሻጩ ቤት ነው፡፡

(3) ውሉ የዋጋው መከፈል የተሸጠው ነገር ወይም ሰነዶቹ በገዢው እጅ ሲገቡ መሆን አለበት የሚል እንደሆነ፤ እንደ ውሉ ቃል ዋጋው
እነዚህ በሚሰጡበት ቦታ ዋጋው መከፈል አለበት፡፡

ቊ 2310፡፡ ዋጋው የሚከፈልበት ጊዜ፡፡ (1) የጅ በጅ ሽያጭ፡፡

የዋጋው መከፈል ገዢው የገዛውን ነገር በሚረከብበት ጊዜ ሲሆን ገዢው የገዛውን ነገር ሳይመረምር ዋጋውን ለመክፈል አይገደድም፡፡

ቊ 2311፡፡ (2) የዱቤ ሽያጭ፡፡

በዱቤ በተደረገው ሽያጭ ዋጋው የሚከፈልበት ጊዜ በውሉ ያልተወሰነ እንደሆነ፤ ገዢው የገዛውን ነገር ከተረከበ በኋላ ሻጩ እንደ ጠየቀው
ወዲያውኑ ዋጋውን መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2312፡፡ ከማስረከብ ጋራ የሚደረጉ ተግባሮች፡፡

ሻጩ የሸጠውን ነገር የማስረከብ ግዴታውን ለመፈጸም እንዲችል አስፈላጊ ሲሆን ገዢው በበኩሉ የሚደረጉትን አስፈላጊ ተግባሮች
መፈጸም አለበት፡፡
ቊ 2313፡፡ ዕቃውን መረከብ፡፡

ገዢው የገዛውን ነገር ከተረከበ በኋላ ዕቃውን እጅ ስለ ማድረግ አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች መፈጸም አለበት፡፡

ንኡስ ክፍል 3፡፡


በሻጩና በገዢው ላይ ያሉ አጠቃላይ ድንጋጌዎች፡፡
(ሀ) ወጪ፡፡

ቊ 2314፡፡ የውሉ ወጪ፡፡

ለሽያጩ ስለተደረገው ውል የሚደረገውን ወጪ የሚችል ገዢው ነው፡፡

ቊ 2315፡፡ ስለ መክፈል የሚደረገው ወጪ፡፡

(1) ለገዛው ነገር ዋጋውን ስለ መክፈል የሚደረገውን ወጪ የሚችለው ገዢው ነው፡፡

(2) ውሉ ከተደረገ በኋላ ሻጩ መሥሪያ ቤቱን ወይም መኖሪያውን በመለወጡ ምክንያት ወጪው በዝቶ የተገኘ እንደሆነ፤ ሻጩ ተጨማሪ
የሆነውን ወጪ መቻል አለበት፡፡

ቊ 2316፡፡ ስለ ማስረከብ የሚደረገው ወጪ፡፡

(1) የተሸጠውን ነገር ስለ ማስረከብ የሚደረገውን ወጪ የሚችል ሻጩ ነው፡፡

(2) ይኸውም ወጪ በተለይ የተሸጠውን ነገር ለመቊጠር ለመለካትና ለመመዘን የሚደረገውን ወጪ ያጠቃልላል፡፡

ቊ 2317፡፡ ከመረከብ በኋላ የሚደረገው ወጪ፡፡

የገዛውን ነገር ከተረከበ በኋላ የሚወጣውን ወጪ የሚችል ገዢው ነው፡፡

ቊ 2318፡፡ የማመላለስ (የትራንስፖርት) ወጪ፡፡

(1) የተሸጠው ነገር ወደ መረከቢያው ቦታ መላኩ ቀርቶ፤ ወደ ሌላ ቦታ የሚላክ ሲሆን፤ (የትራንስፖርቱን) የማመላለሱን ወጪ የሚችለው
ገዢው ነው፡፡
(2) ነገር ግን የተሸጠውን ነገር መረከብ ያለ ኪሣራ ይሆናል የሚል የውል ቃል ያለ እንደሆነ፤ የማመላለሱን (የትራንስፖርቱን) ወጪ
የሚችል ሻጩ ነው፡፡

(3) ከሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ማንኛቸውም አላፊ በማይሆኑበት ነገር ምክንያት (ትራንስፖርት) ለማመላለሻው የተቋረጠ እንደሆነ፤ ልዩ
የሆነውን የማመላለሻ (የትራንስፖርትን) ወጪ የሚችል ድንገተኛውን የሚችለው ወገን ነው፡፡

ቊ 2319፡፡ የጉምሩክ ቀረጥ፡፡

(1) ስለ ዕቃው ማምጣት የሚከፈለውን የጉምሩክ ቀረጥ ወይም የመጣውን ዕቃ ስለሚመለከት ጒዳይ የሚከፈለውን ሌላ ተከፋይ ገንዘብ
የሚችለው ሻጩ የሆነ እንደሆነና ውሉ ከተደረገ በኋላ በዚህ በሚከፈለው ቀረጥ ላይ ሌላ ተጨማሪ ተከፋይ ያለ እንደሆነ፤ ይህ ተጨማሪ
ሒሳብ ከዋጋው ጋራ ይደመራል፡፡

(2) ስለሆነም ይህን ቀረጥ የደረሰበትን ዕቃ ተቀባዩ ሳይረከብ የቈየው በሻጩ ወይም ሻጩ በአላፊነት በሚጠየቅበት ሰው አድራጎት የሆነ
እንደሆነ፤ ይህን ዕቃ በውሉ ላይ ወይም በሕግ በተወሰነው ጊዜ ገዢው ተረክቦ ቢሆን ኖሮ በዕቃው ላይ ሌላ ተጨማሪ ቀረጥ ወይም ሒሳብ
መክፈል ሊደርስ አይችልም ነበረ ብሎ ሻጩ ካላስረዳ በቀር ይህን በተጨማሪነት የሚጠየቀውን ሒሳብ የሚከፍል ሻጩ ነው፡፡

(3) በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን የጉምሩክ ቀረጥ በሚቀነስበት መጠን ዋጋም ይቀነሳል፡፡

(ለ) የተሸጠውን ነገር መጠበቅ፡፡

ቊ 2320፡፡ የሻጩ ግዴታ፡፡

(1) ገዢው የገዛውን ነገር ሳይረከብ ወይም ዋጋውን ሳይከፍል የዘገየ እንደሆነ፤ ሻጩ የተሸጠውን ነገር በገዢው ኪሣራ ማስጠበቅ አለበት፡፡

(2) ሻጩ የተሸጠውን ነገር በመጠበቅ ያወጣው ወጪ እስኪከፈለው ድረስ የተባለውን ነገር በጁ ለማቈየት መብት አለው፡፡

ቊ 2321፡፡ የገዢው ግዴታ፡፡

(1) ገዢው የተሸጠውን ገንዘብ የቀበለ ሲሆን፤ የማይፈልገው መሆኑን በሚያስብበት ጊዜ የተቀበለውን ነገር በሻጩ ኪሣራ ማስጠበቅ
አለበት፡፡

(2) የተቀበለውን ነገር አንዳች ምክንያት ሳይሰጥ እንዲያው ዝም ብሎ ወደ ሻጩ ለመመለስ መብት የለውም፡፡

(3) የተቀበለውን ነገር በመጠበቅ ያወጣው ወጪ እስኪከፈለው ድረስ ይህን የተቀበለውን ነገር በጁ ይዞ ለማቈየት መብት አለው፡፡

ቊ 2322፡፡ የተሸጠውን ነገር ማስረከብ ወይም መሸጥ፡፡

ሻጩ ወይም ገዢው ጠቅላላው ስለ ውሎች በሚል አንቀጽ በተሰጡት በዚህ ሕግ ውሳኔዎች መሠረት፤ ዕቃውን በማስረከብ ወይም በመሸጥ
ዕቃውን ከመጠበቅ ግዴታ ነፃ ለመውጣት ይችላል፡፡

(ሐ) ሊደርሱ የሚችሉትን አደጋዎች ስለ ማስተላለፍ፡፡


ቊ 2323፡፡ መሠረቱ፡፡
የአደጋ አላፊነት ለገዢው ተዛውሮ እንደሆነ፤ በዕቃው ላይ ጥፋት ቢደርስ ወይም ዋጋው ቢለዋወጥ እንኳ ገዢው ዋጋውን መክፈል
ይገባዋል፡፡
ቊ 2324፡፡ የተሸጠውን ዕቃ ስለ ማስረከብ፡፡

(1) በውሉና በዚህ ሕግ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት ዕቃው ለገዢው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ የአደጋ አላፊነትም ለገዢው ይዛወራል፡፡

(2) ለገዢው የተሰጠው እንደ ውሉ ትክክል ያልሆነ ዕቃ ቢሆንም፤ ገዢው ውሉ እንዲፈርስ ያላስታወቀ ወይም ያልጠየቀ፤ ወይም ዕቃው
እንዲለወጥና እንዲተካለት ያልጠየቀ ሲሆን ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተጻፈው ደንብ ይፈጸማል፡፡

ቊ 2325፡፡ የገዢው መዘግየት፡፡

(1) እንዲሁም ሊደርሱ የሚችሉ የአደጋ አላፊነቶች ገዢው የዕቃ ማስረከቢያ ዋጋውን ለመክፈል ከሚዘገይበት ቀን አንሥቶ ለገዢው
ይዛወራሉ፡፡
(2) ሽያጩ የተደረገው የተወሰነ ዐይነት በአላቸው ነገሮች ላይ የሆነ እንደሆነ፤ ሻጩ ስለ ውሉ አፈጻጸም በግልጽ የተጠበቁትን ነገሮች ለብቻ
አስቀድሞ ለይቶ ማኖሩን ለገዢው ካላስተወቀው ገዢው ሳይቀበል በመዘግየቱ በነዚህ ነገሮች ሊደርሱ የሚችሉት የአደጋ አላፊነቶች
ወደርሱ አይዛወሩበትም፡፡

(3) ዐይነታቸው ተለይቶ የታወቁት ነገሮች ከዐይነታቸው የተነሣ የማይለያዩ በመሆናቸው ምክንያት ገዢው እስኪረከባቸው ድረስ ሻጩ
ለይቶ ለማስቀመጥ የማይችል የሆነ እንደሆነ፤ ገዢው እነዚህን ዕቃዎች ሊረከብ የሚችልበትን ማናቸውንም የተቻለውን ነገር ሁሉ ቢያደርግ
በቂ ነው፡፡

ቊ 2326፡፡ በጒዞ ላይ ስላለ ነገር፡፡

(1) ሽያጩ የተፈጸመው በጒዞ ላይ ባለው ነገር ስሆን፤ የተሸጠው ነገር ለጫኙ በመሰጠቱ የማስረከቡ ነገር ስለተፈጸመ ሊደርሱ የሚችሉት
የአደጋዎች አላፊነቶች በገዢው ላይ ይሆናሉ፡፡

(2) ስለሆነም ውሉ በተደረገበት ጊዜ የተሸጠው ዕቃ ጠፍቶ ወይም ተበላሽቶ እንደነበረ ሻጩም የሚያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው የሆነ
እንደሆነ፤ ይህ ደንብ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

ቊ 2327፡፡ ወጪዎችን የሚመለከት የውል ቃል፡፡

(1) ስለ ወጪ የተደረገው የውል ስምምነት ይልቁንም ወጪውን የሚችለው ሻጩ እንዲሆን የተደረገ ቢሆንም ይህ ሁኔታ ሊደርሱ
የሚችሉትን የአደጋ አላፊነቶች ለማዛወር በቂ አይሆንም፡፡

ቊ 2328፡፡ በክፍል በክፍል ተደርገው በአንድነት የሚጫኑ ሸቀጦች፡፡


ሸቀጦቹ በክፍል በክፍል ተደርገው በአንድነት በተጫኑ ጊዜ ሻጩ ለገዢው ዕቃው የተጫነበትን ማስረጃ ወረቀት ወይም ዕቃው መጫኑን
የሚያስረዳ ሌላ ማስታወቂያ ከላከለት፤ ሻጩ ዕቃውን ለጫኙ በመስጠት የማስረከቡን ነገር ስለፈጸመ ሊደርስ የሚችለው አላፊነት
ለገዢዎች ለየአንዳንዱ በየድርሻቸው መጠን ይዛወራል፡፡
ክፍል 3፡፡
ውልን ስላለመፈጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ውልን በግድ ስለ ማስፈጸም፡፡
ቊ 2329፡፡ የመረካከብን ግዴታ ስላለመፈጸም፡፡ (1) መሠረቱ፡፡
ሻጩ የሸጠውን ነገር በደንብ ያላስረከበ እንደሆነ፤ የተዋዋለበት ውል በግድ ሲፈጸም ልዩ የሆነ ጥቅም የሚያስገኝለት ሆኖ ሲታየው ገዢው
ውሉ በግድ እንዲፈጸምለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 2330፡፡ (2) ምትክ ለመስጠት ስለ መቻሉ፡፡


የሽያጭ ስምምነት የተደረገበት ዕቃ በልማድ ምትክ ሊገዛበት የሚቻል እንደሆነ፤ ወይም የተባለው ምትክ በገዢው በኩል ያለ ችግርና ከፍ
ያለ ወጪ ሳይደረግበት ሊፈጸም የሚቻል እንደሆነ፤ ገዢው ውሉ በግድ እንዲፈጸምለት ለማስገደድ አይችልም፡፡

ቊ 2331፡፡ (3) የማስገደጃ ጊዜ፡፡

(1) ገዢው ውሉ ሳይፈጸም መዘግየቱን ከተመለከተ በኋላ በግዴታ እንዲፈጸምለት የማስገደድ አሳቡን ባጭር ጊዜ ለሻጩ ያልገለጸለት
እንደሆነ፤ ውሉ በግድ እንዲፈጸም ለማስገደድ የሚፈቀድለት መብቱን ያጣል፡፡

(2) የውሉ መፈጸሚያ ጊዜ በጥብቅ ተወስኖ እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ የተነገረው የማስታወቂያው ጊዜ ልዩ በሆነ ጥብቅ አኳኋን የተገመተ
መሆን አለበት፡፡

ቊ 2332፡፡ ዕቃው እንደ ውሉ ቃል ትክክል ስለ አለመሆኑ ወይም ጒድለት ያለበት ስለ መሆኑ፡፡

(1) ገዢው የተሸጠውን ዕቃ እንደ ውሉ ትክክል ያለመሆኑን ወይም ጒድለት ያለበት መሆኑን በሚገባ ያስታወቀው እንደሆነ፤ ውሉን
በግዴታ ለማስፈጸም በሚቻልበት ጊዜ ሻጩ አዲስ ዕቃዎች ወይም ከዕቃው የጐደለውን እንዲያስረክበው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) የሽያጩ ስምምነት በገዢው ልዩ ትእዛዝ መሠረት ሻጩ በሚሠራው ወይም ከአንድ ሥራ በሚያወጣው ነገር ላይ ሲሆንና የተሠራው፤
ወይም የወጣው ነገር ጒድለት ሲገኝበት ሻጩ ጒድለቱን በማጥፋት ሊያድሰው የሚችል እንደሆነ፤ በሚገባ ጊዜ እንዲያድስለት ገዢው
ሻጩን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2333፡፡ ዋጋን አለመክፈል፡፡


ገዢው ዋጋውን ያልከፈለ እንደሆነ፤ ለዕቃው የተደረገው የሽያጩ ስምምነት በንግድ ልማድ መሠረት ሁለቱን ባለጒዳዮች በሚያቻችል
ሽያጭ ለመሆን የሚችል ካልሆነ በቀር ሻጩ ዋጋው እንዲከፈለው ለማስገደድ መብት አለው፡፡

ቊ 2334፡፡ ዐይነቱ ወደፊት የሚገለጽ ሽያጭ፡፡

(1) የሻጩ መብት፡፡


በውሉ ውስጥ ገዢው ከስምምነቱ በኋላ የገዛውን ነገር ፎርም፤ መለካትን ወይም ለነገሩ ሌላውን ዐይነት ሁሉ ስለ መስጠት የመወሰን
መብት የርሱ እንዲሆን አድርጎ እንደሆነና የሚለየውን ዐይነት በተወሰነው ጊዜ ወይም ለርሱ በሚበቃ በተወሰነለት ጊዜ ውስጥ ሳይለይ የቀረ
እንደሆነ ሻጩ ራሱ ለገዢው አስፈላጊ የሚሆነውን በሚያውቀው መሠረት ዐይነቱን ሊለይለት ይችላል፡፡

ቊ 2335፡፡ (2) ለነገሩ አሠራር የተሰጠው ዐይነትና ውሳኔ፡፡

(1) ሻጩ ለነገሩ የሰጠው ዐይነት ሁኔታ ለይቶ እንደዚያው እንደተለየው ለገዢው ያስታውቃል፡፡ ደግሞ የተለየ አሠራር ዐይነት የሚፈልግ
እንደሆነ፤ የሚበቃ ጊዜ ይወሰንለታል፡፡

(2) ገዢው በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የሚፈልገውን የአሠራር ልዩነት ዐይነት ሳይለይ የቀረ እንደሆነ፤ ሻጩ የፈጸመው ዐይነት አስገዳጅ
ይሆናል፡፡ (ገዢውን እንዲቀበል ያስገድደዋል)፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
የውል መፍረስ፡፡
(ሀ) ገዢው ውሉን የሚያፈርስበት ምክንያት፡፡

ቊ 2336፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት ገዢው ውሉ ፈርሷል ብለው እንዲበይኑ
ለዳኞች ማመልከቻ ማቅረብ ወይም ውሉ ፈርሷል ብሎ ማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) በዚህ ምዕራፍ የተጻፉት ከዚህ ቀጥለው ያሉት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2337፡፡ ጥብቅ የሆነ የውሳኔ ጊዜ፡፡

(1) ዕቃዎች በገበያ ላይ ዋጋቸው የተወሰነ ሲሆንና ገዢውም እነዚህኑ በገበያ ላይ ሊያገኛቸው የሚችል ሲሆን ስለ ማስረከብ የሚወሰነው
ጊዜ ዘወትርም የጠበቀ ነው፡፡

(2) እንደዚህም በውሉ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ሻጩ ወይም ገዢው ቀኑን ለመወሰን የሚችሉ ሲሆን ይህ የተወሰነው ቀን በጥብቅ እንደተወሰነ
ይቈጠራል፡፡
ቊ 2338፡፡ ተጨማሪ ጊዜ፡፡ (1) ስለ መቻሉ፡፡

(1) የተሸጠውን ነገር ስለ ማስረከብ የተሰጠው ጊዜ በጥብቅ ያልተወሰነ ጊዜ ሲሆን ዳኞቹ ለሻጩ ግዴታውን የሚፈጽሙበት የችሮታ ጊዜ
ሊሰጡት ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም ገዢው ለሻጩ በቂ የሆነ ተጨማሪ ጊዜ ወስኖ ይህ ጊዜ ካለፈ ዕቃውን የማይቀበል መሆኑን ለሻጩ ሊያስታውቅ ይችላል፡፡

(3) ሻጩ የተወሰነው ተጨማሪ ጊዜ ሲደርስ የተሸጠውን ነገር ያላስረከበ እንደሆነ፤ ውሉ ያለ ክርክር ፈራሽ ይሆናል፡፡

ቊ 2339፡፡ የማይበቃ ጊዜ ስለ መስጠት፡፡

(1) ገዢው የወሰነው የመረከብ ጊዜ፤ በአእምሮ ግምት በቂ ያልሆነ ሲሆን፤ ሻጩ በአእምሮ ግምት በቂ ጊዜ ካለፈ በኋላ ካልሆነ የማረካከቡን
ተግባር እንደማይፈጽም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለገዢው ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) ሳያስታውቅ የቀረ እንደሆነ ግን፤ ገዢው የወሰነውን ጊዜ ሻጩ እንደተቀበለ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2340፡፡ የመረኪያ ስፍራ፡፡

(1) ሻጩ ሊየስረክብ ይገባው የነበረበትን ስፍራ ትቶ ዕቃውን በሌላ ስፍራ ያስረከበ እንደሆነ፤ ውሉ የተፈጸመበት መንገድ የውሉን
ስምምነት የመጣስ ዐይነተኛ ነገር ሆኖ ካልተገኘ በቀር ገዢው በሚያቀርበው ጥያቄ ዳኞች ውሉ እንዲፈርስ አይበይኑም፡፡

(2) እንዲሁም ከውሉ ግዴታ የጐደለውን ነገር ውሉ ወይም በሚፈቅደው ጊዜ ውስጥ ሻጩ ሊያሻሽል የማይችል ካልሆነ በቀር ዳኞች ውሉ
እንዲፈርስ አይፈርዱም፡፡

ቊ 2341፡፡ በሙሉ ለገዢው ያልተላለፈ ሀብትነት፡፡

(1) መብቱን በሚነካ ጒድለት ምክንያት ሻጩ የኔ ነው ከሚሉ ሦስተኛ ወገኖች መብት ሁሉ ነፃ የሆነ ነገር ለገዢው ሳያስረክብ የቀረ እንደሆነ
ውሉን ለማፍረስ ይቻላል፡፡

(2) ነገር ግን ገዢው ዕቃውን ሲገዛ ከዚህ በላይ የተነገረው የሌላ ሰው መብት ያለበት መሆኑን እያወቀ ገዝቶት እንደሆነ፤ ውሉ ፍርስ
ለመሆን አይችልም፡፡

(3) እንደዚሁም የሌላ ሰው መብት ያለበት ሆኖ የተገኘው የተሸጠው ዕቃ እጅግም የማያጎዳ የሆነ እንደሆነና ገዢው በዕቃው ላይ የተባለው
የሌላ ሰው መብት መኖሩን ቢያውቅም ኖሮ ሳይገዛው የማይቀር እንደነበረ መስሎ ሲታይ ውሉ ፍርስ ለመሆን አይችልም፡፡

ቊ 2342፡፡ እንዲለቅ ስለ መደረጉ፡፡

(1) ሻጩ የኔ ነው ባይ ተፋላሚ ሲመጣ ለገዢው መድን መሆን የሚገባው እንደሆነ፤ ገዢ የገዛውን ዕቃ በሙሉ ሲለቅ ውሉ ያለ ክርክር
ፈራሽ ይሆናል፡፡

(2) ገዢው ከገዛው ነገር በከፊል እንዲለቅ የተደረገ እንደሆነ ውሉ ሊፈርስ ይችላል፡፡
ቊ 2343፡፡ በከፊል ስለ ማስረከብ፡፡

(1) ሻጩ የሸጠውን ዕቃ አንዱን ክፍል ብቻ ያስረከበ እንደሆነ፤ ወይም ካስረከበው ዕቃ አንዱ ክፍል ብቻ እንደ ውሉ ቃል ትክክል ሆኖ
ያልተገኘ እንደሆነ፤ ገዢው ውሉ በዚህ አኳኋን የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦት ቢሆን ኖሮ ውሉን አያደርግም ነበር ተብሎ ካልተገመተ በቀር
ገዥ በሞላው ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(2) ገዢው የገዛውን ነገር በከፊል እንዲለቅ የተደረገ እንደሆነ፤ ውሉን ለማፍረስ ይችላል፡፡

(3) እንዲህም በሆነ ጊዜ ገዢው እንዲለቅ የተደረገው ዕቃ እጅግም የማያጎዳ የነገሩ ክፍል ሲሆንና፤ ገዢው የዚህን በጣም የማያጎዳ
ያልሆነውን ነገር መልቀቅ የሚደርስበት መሆኑን ዐውቆ ቢሆን ኖሮም ሳይገዛው የማይቀር እንደነበረ መስሎ ሲታይ ውሉን ለማፍረስ
አይቻልም፡፡
ቊ 2344፡፡ የተሸጠው ነገር ጒድለት፡፡

(1) የተሸጠው ነገር ሻጩ ለገዢው ዋቢ ሊሆንበት የሚገባው ጒድለት የተገኘበት እንደሆነ ውሉን ለማፍረስ ይቻላል፡፡

(2) እንዲህም በሆነ ጊዜ ጒድለቱ እጅግም የማያጎዳ እንደሆነና ገዢው ጒድለቱን ዐውቆ ኖሮም ቢሆን ጒድለት የተገኘበትን ነገር ሳይገዛው
የማይቀር እንደነበረ ሲታይ ውሉን ለማፍረስ አይቻልም፡፡

ቊ 2345፡፡ ከተሸጡት ነገሮች በአንዱ ክፍል ብቻ የሚገኝ ጒድለት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የተሸጡት ነገሮች ብዙዎች ሲሆኑ ወይም የአንድ ጠቅላላ ነገር ዕቃዎች ሲሆንና የተገኘው ጒድለት ከነገሮቹ መካከል በአንዳንዶቹ ላይ
ብቻ ሲሆን ውሉን ለማፍረስ የሚቻለው ጒድለት በተገኘባቸው ነገሮች ብቻ ነው፡፡

(2) እንዲህም በሆነ ጊዜ ገዢው ለሻጩ ጒድለት የሌለባቸው ሆነው ስለ ተረከባቸው ነገሮች እንደ ግምታቸው መጠን ዋጋቸውን
ይከፍላል፡፡
ቊ 2346፡፡ (2) ልዩነት፡፡

(1) ጒድለት የተገኘበት ነገር ወይም ዕቃው፤ በገዢው ወይም በሻጩ ላይ ጉዳት ሳያደርስ ጒድለት ከሌለባቸው ነገሮች ሊነጠል የማይቻል
የሆነ እንደሆነ ውሉን በሙሉ ለማፍረስ ይቻላል፡፡

(2) ተጨማሪ የሆኑት ነገሮች በልዩ ልዩ ዋጋ የተሸጡ እንኳ ቢሆን በዋናው ነገር የተደረገው የውል መፍረስ በተጨማሪዎቹም ላይ
ይደርሳል፡፡
(ለ) ሻጩ ውሉን የሚያፈርስበት ምክንያት፡፡

ቊ 2347፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ በተመለከቱት ሁኔታዎች መሠረት፤ ሻጩ ውሉ ፈርሷል ብለው እንዲፈርዱለት
ዳኞቹን ለመጠየቅ ወይም ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) ከዚህ ቀጥሎ የተጻፉት የዚህ ምዕራፍ ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2348፡፡ የዋጋ አለመክፈል፡፡

(1) ዋጋውን የመከፈል መብት በውሉ ግልጽ ሆኖ ለሻጩ የተሰጠው ሆኖ ሲገኝ ዋጋው ያልተከፈለው እንደሆነ፤ ሻጩ ወዲያውኑ ውሉ
ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) ሽያጩ የተደረገው ዋጋቸው በተወሰነ ወይም የዕለት ዋጋቸው በታወቀ ዕቃዎች ላይ የሆነ እንደሆነ፤ ወይም እንደዚህ ያለው መብት
በውሉ ላይ ለሻጩ በግልጽ ተሰጥቶ እንደሆነ፤ ሻጩ የሚበቃ ቀን ሰጥቶ በማስጠንቀቂያ ቃል ለገዢው የወሰነለት ጊዜ ሲያልፍ ሻጩ ውሉ
ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ ይችላል፡፡
(3) እንደዚሁም ዳኞች ለገዢው የችሮታ ጊዜ ሰጥተውት እንደሆነ፤ ይህ የተባለው ጊዜ ሲያልፍ ሻጩ ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ
ይችላል፡፡
ቊ 2349፡፡ ዕቃውን ስላለመረከብ፡፡
ገዢው የገዛውን ነገር በውሉ በተነገሩት ውለታዎች አደራረግ ያልተረከበ እንደሆነና ይህ ገዥ የገዛውን ነገር አለመረከብ ዋጋውን ሳይከፍል
ይቀራል ተብሎ የሚያሠጋ ሲሆን፤ ወይም የነገሩ ሁኔታዎች ንሰታዩ ከውሉ ዋነኛው አንዱ የውል ቃል ገዢው የገዛውን ነገር መረከብ
እንደሆነ ሻጩ ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ ይችላል፡፡

ቊ 2350፡፡ ለይቶ የማስታወቅ ጒድለት፡፡

በውሉ ውስጥ ገዢው ከስምምነቱ በኋላም ቢሆን የገዛውን ነገር ፎርም (ቅጡን) ለመለካት ወይም ለነገሩ ሌላውን ዐይነት ሁሉ ስለ መስጠት
የመወሰን መብት ለርሱ እንዲሆን አድርጎ እንደሆነና የሚለየውን ዐይነት በተወሰነው ጊዜ ወይም ለርሱ በሚበቃ ሻጩ በወሰነለት ጊዜ
ውስጥ ሳይለይ የቀረ እንደሆነ ሻጩ ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስተወቅ ይችላል፡፡

(ሐ) ሁለቱም ወገን ተዋዋዮች ውሉን የሚያፈርሱባቸው ምክንያቶች፡፡

ቊ 2351፡፡ የተሸጠውን ነገር በማከታተል ስለ ማስረከብ የተደረገ ውል፡፡

(1) በማከታተል ስለ ማስረከብ በተደረገው ውል ከሁለቱ ወገን ተዋዋዮች አንዱ ግዴታ የገባበትን ነገር ሳይፈጽም በመቅረቱ ወይም
የሚሰጠው ነገር የተበላሸ በመሆኑ ምክንያት ሌላው ወገን ወደፊት ሊፈጽሙ የሚገባቸውም የመስጠት ተግባሮች ሳይፈጸሙ ይቀራሉ
ወይም የተበላሹ ይሆናሉ ተብሎ የሚያሠጋ ምክንያት ያለው ሲሆን ይህ ሥጋት ያደረበት ወገን ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ከዚህም በቀር፤ ገዢው የሚረከባቸው ነገሮች ሳይፈጸሙለት ከቀሩት ወይም ከተበላሹ ነገሮች ጋራ የተያያዙ በመሆናቸው ምክንያት
ለርሱ ጠቃሚነት የሌላቸው መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ፤ ወደፊት ለሚረከባቸው ወይም አስቀድሞ ለተረከባቸው ወይም ለሁለቱም ውሉ
እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2352፡፡ ውልን ለመፈጸም የማይቻል ስለ መሆኑ፡፡


ለውሉ መፈጸም የተወሰነው ጊዜ ከመድረሱ በፊትም ቢሆን አንድ ወገን ተዋዋይ የተዋዋልውን ቃል ለመፈጸም የማይቻል ሲሆን ወይም
የውሉ መሠረት የሚነካ እስከ መሆን መፈጸሙ የሚዘገይ ሲሆን፤ ሌላው ወገን ተዋዋይ ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ ይችላል፡፡

ቊ 2353፡፡ አስቀድሞ የሚደረግ የውል ማፍረስ፡፡


ለውሉ መፈጸም የተወሰነው ጊዜ ከመድረሱ በፊት ከሁለቱ ወገን ተዋዋዮች አንዱ ውሉን የማይፈጽም መሆኑን ለሌላው ወገን ያስታወቀ
እንደሆነ ሌላው ወገን በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚል አንቀጽ በተጻፈው መሠረት ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ መብት
አለው፡፡
(መ) የውሉ መፍረስ ሁኔታዎችና የሚያስከትላቸው ውጤቶች፡፡

ቊ 2354፡፡ በመዘግየት ምክንያት የሚደረግ የሚገባ የውል መፍረስ፡፡


አንዱ ወገን ተዋዋይ ከውሉ አንዱን ዋነኛ የሆነውን ግዴታ ሳይፈጽም የዘገየ እንደሆነ፤ ሌላውን ወገን ውሉን እንዲፈጽምለት መፈለጉን
ከጠየቀ በኋላ ባጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ሳይሰጠው የቀረ እንደሆነ ውሉ በሚገባ ፈራሽ ይሆናል፡፡

ቊ 2355፡፡ የውሉ መፍረስ የሚያስከትላቸው ውጤቶች፡፡

(1) ውሉ በፈረሰ ጊዜ ተገቢ ለመሆን የሚችሉት ኪሣራዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ባደረጉት ውል ከገቡባቸው
ግዴታዎች ነጻ ይሆናሉ፡፡

(2) አንዱ ወገን የውሉን ቃል በሙሉ ወይም በከፊል ፈጽሞ እንደሆነ ስለ ጒዳዩ ያወጣውን ኪሣራ ጭምር የሰጠው ነገር እንዲመለስለት
ለመጠየቅ ይችላል፡፡
(3) ሁለቱም ወገኖች በየበኩላቸው የፈጸሙት ግዴታ እንዳለ የተቀበሉትን ነገር ስለ መመለስ በያንዳንዳቸው ላይ ስለሚወድቀው ግዴታ
አንዱ ወገን ለሌላው ያለበትን የመመለስ ግዴታ እስኪፈጽምለት ድረስ ሌላውም አልመልስም ለማለት ይችላል፡፡

ቊ 2356፡፡ የዋጋው ወለድና ሌላ ጥቅም፡፡

(1) ሻጩ የተቀበለውን ዋጋ በሚመለስበት ጊዜ ሁሉ ዋጋውን ከተቀበለበት ቀን አንሥቶ ከነወለዱ መክፈል አለበት፡፡

(2) ገዢውም፤ የገዛውን ነገር ሲመልስ፤ ከዚያው ነገር ያገኘውን ጥቅም ጭምር መመለስ አለበት፡፡

ቊ 2357፡፡ የተገዛውን ነገር እንዳለ ለመመለስ አለመቻል፡፡

(1) በርሱ ወይም እርሱ አላፊ በሚሆንለት ሰው ምክንያት ሳይሆን የገዛው ነገር በሙሉ ወይም አንዱ ክፍል ብቻ ጠፍቶ ወይም ተበላሽቶ
የተገኘ እንደሆነ፤ ገዢው ውሉ እንዲፈርስ የመጠየቅ ወይም የማስታወቅ ወይም ፈርሷል የተባለውን ውል የመጥቀስ መብቱን እንደያዘ
ይቈያል፡፡
(2) እንዲሁም በልማድ እንደሚደረገው የገዛውን ነገር ለምርመራ ሰጥቶት በምርመራው ምክንያት የተበላሸ እንደሆነ፤ ይህን የተባለውን
መብት እንደያዘ ይቈያል፡፡

(3) ነገር ግን ገዢው የገዛውን ነገር ስለሸጠው ወይም ስለ ለዋወጠው ወይም የተባለው ነገር በርሱ ምክንያት ስለ ጠፋ ወይም ስለ ተበላሸ
ለመመለስ የማይቻለው ሆኖ ሲገኝ ውሉ ሊፈርስ አይችልም፡፡

ቊ 2358፡፡ በተሸጠው ነገር ላይ ስለሚደርስ መለዋወጥ፡፡


የተሸጠው ነገር ዐይነት ተለዋውጦ በሚገኝበት ጊዜ ገዢው ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ወይም ለማስታወቅ ያለውን መብቱን እንደያዘ
የሚቈየው፡-

(ሀ) ውሉ እንዲፈርስለት የሚጠይቅበትን ወይም የሚያስታውቅበትን ጒድለት ለማግኘት ከመቻሉ በፊት ገዢው የገዛው ነገር ወይም
አንዱን ክፍል ከለዋወጠው በኋላም ቢሆን ጒድለቱ የተገለጸ እንደሆነ፤

(ለ) በነገሩ ላይ የደረሰው መለዋወጥ ግን የማይጎዳ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2359፡፡ ወጪ ገንዘብ፡፡

(1) ገዢው ስለ ገዛው ነገር ያደረገውን ወጪ ገንዘብ ስለሚመለከተው ጒዳይ ያለአገባብ ስለ መበልጸግ በሚል ምዕራፍ በተነገረው ሕግ
የተጻፉት ውሳኔዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) ገዢው የገዛውን ነገር እንዲለቅ በተደረገበት ጊዜ ከዚያው ከሚያስለቅቀው ሦስተኛ ወገን ኪሣራውን ለመቀበል የማይችል ካልሆነ በቀር
ለገዛው ነገር ያደረገውን ወጪ ከሻጩ ለመጠየቅ አይችልም፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
የጉዳት ኪሣራ፡፡
ቊ 2360፡፡ ጠቅላላ ውሳኔ፡፡

(1) አንዱ ወገን ተዋዋይ ለአንደኛው ወገን ከገባበት ግዴታዎች አንዱን ሳይፈጽምለት በመቅረቱ ምክንያት ጉዳት አድርሶበት ሲገኝ፤ ሻጩ
ወይም ገዢው ስለደረሰበት ጉዳት ኪሣራውን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ውሉ በትክክልና በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሳይፈጸም በቀረ ጊዜ ውሉ ቢፈርስም ጸንቶ ቢቀርም ኪሣራ ለመጠየቅ ይቻላል፡፡

(ሀ) ውሉ ባልፈረሰ ጊዜ ስለሚሰጥ ኪሣራ፡፡

ቊ 2361፡፡ የኪሣራው ልክ፡፡

(1) ውሉ ያልፈረሰ እንደሆነ የጉዳት ኪሣራው በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ መሠረት ይወሰናል፡፡
(2) ገዢው ዋጋውን ሳይከፍል በሚዘገይበት ጊዜ፤ በሕግ በተወሰነው ወለድ መሠረት የመዘግየት ወለድ መክፈል አለበት፡፡

(3) በገዢውና በሻጩ መካከል ሁለቱን የሚያገናኝ ተመላላሽ ሒሳብ ከሌለ በቀር በየዓመቱ በዋናው ገንዘብ ላይ የወለድ ወለድ
አይከፈልም፡፡
(ለ) ውሉ በፈረሰ ጊዜ ስለሚሰጥ ኪሣራ፡፡

ቊ 2362፡፡ ነገሩ የታወቀ ዋጋ ያለው ስለ መሆኑ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ውሉ በፈረሰ ጊዜ የተሸጠው ነገር የታወቀ ዋጋ ያለው ሲሆን፤ የጉዳቱ ኪሣራ የውሉን ፈራሽነት የማስታወቅ መብት ሊሠራበት
በተቻለበት ቀን ወይም ውሉ በዳኞች ፍርድ ወይም በሙሉ መብት ፈራሽ በሆነበት ቀን ማግሥት በነበረው ዋጋ መካከል ካለው የዋጋ
ልዩነት ጋራ እኩል ይሆናል፡፡

(2) ከዚህም ሌላ በምትክ በሚሆን ግዥ፤ ወይም በማቻቻያ በሚደረግ የሽያጭ ውል ምክንያት የሚደርሰውም ደንበኛ ወጪ አብሮ
ይታሰባል፡፡

(3) ለኪሣራው ማመዛዘኛ የሚሆነው ዋጋ፤ ገዢው ወይም ሻጩ የንግድ ሥራዎቻቸው በሚያከናውኑበት ደንበኛ ጊዜ በውሉ የተነገሩትን
ሸቀጦች ለመግዛት ወይም ለመሸጥ የሚሄዱበት ገበያ ዋጋ ነው፡፡

ቊ 2363፡፡ (2) በምትክ ስለሆነ ግዥ ወይም በመቻቻያ ስለተደረገ ሽያጭ፡፡

(1) ገዢው በምትክ የተደረገውን ግዥ ወይም ሻጩ የማቻቻያውን ሽያጭ በውነት ፈጽመው እንደሆነ የጉዳትን ኪሣራ ለማሰብ መሠረት
የሚደረገው፤ ስለ ግዥው የተከለው ዋጋ ወይም በሽያጩ የተገኘው ዋጋ ነው፡፡

(2) አንዱ ወገን ተዋዋይ በምትክ የሆነው ግዥ ወይም በመቻቻያ የተደረገው ሽያጭ በክፉ ልቡና ወይም ለንግድ አሠራር ደንበኛ ባልሆነ
አኳኋን መፈጸሙን ያስረዳ እንደሆነ፤ ኪሣራው ሊቀነስ ይችላል፡፡

ቊ 2364፡፡ የበለጠ ጉዳት፡፡

(1) ጉዳት የደረሰበት አንዱ ወገን ተዋዋይ ውሉ በተደረገ ጊዜ ከልዩ አካባቢዎች ምክንያቶች የተነሣ፤ የጉዳቱ ልክ የበለጠ ለመሆን
እንደሚችል ለሁለተኛው ወገን ማስጠንቀቁን ያስረዳ እንደሆነ የሚከፈለው ኪሣራ በውነት በደረሰበት ጉዳት ልክ ነው፡፡

(2) እንዲሁም አንድ ወገን ተዋዋይ ግዴታው ሳይፈጸም የቀረበት ተዋዋዩን በመጉዳት ፍላጎት በከባድ ቸልተኛነት ወይም ከባድ በሆነ ጥፋት
ምክንያት መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተጻፈው ይፈጸማል፡፡

ቊ 2365፡፡ ነገሩ የታወቀ ዋጋ የሌለው ስለ መሆኑ፡፡

(1) ዕቃው የታወቀ ዋጋ የሌለው ሲሆን የሚከፈለው የጉዳቱ ኪሣራ ዕውቀት ባለው ሰው ግምት የውሉ አለመፈጸም በባለገንዘቡ
ይደርስበታል ተብሎ በሚገመተው ጉዳት ልክ ነው፡፡

(2) ስለሆነም ባለፈው ቊጥር እንደተመለከተው አጋጣሚ ሁኔታ ሲሆን ስለ ኪሣራው የሚከፈለው የካሣ ልክ በእውነት ከደረሰው ጉዳት
ጋራ እኩልነት ያለው በሚሆን መጠን ነው፡፡

ቊ 2366፡፡ ከተወሰነው ጊዜ በፊት የውሉ መፍረስ፡፡

(1) ከተወሰነው ጊዜ በፊት ውሉ በሚፈርስበት ጊዜ ዕቃው የታወቀ ዋጋ ያለው ሲሆን ኪሣራ የሚገመተው፤ ስለ ግዴታው መፈጸም በውሉ
በተወሰነው ጊዜ ማለቂያ መጨረሻ ቀን ዕቃው ባለው ዋጋ መሠረት ነው፡፡

(2) በውሉ ማንኛውም ጊዜ ያልተወሰነ እንደሆነ ኪሣራው የሚገመተው የውሉን መፍረስ የማስታወቅ መብት ሊሠራበት በቻለ ቀን
የነበረውን የዕቃውን ዋጋ መሠረት በማድረግ ነው፡፡

(3) ስለሆነም የጉዳቱ ኪሣራ አስቀድሞ ለተሸጠው ዕቃ ምትክ በተገዛበት ጊዜ እርግጥ ከተከፈለው ገንዘብ በላይ፤ ወይም አስቀድሞ
ለተሸጠው ዕቃ የማቻቻያ ሽያጭ በተደረገበት ጊዜ እጅ በእጅ ከተከፈለው ዋጋ በላይ ለመሆን አይችልም፡፡
ቊ 2367፡፡ የገዛውን ዕቃ እንዲለቅ ስለ መደረጉ፡፡
ገዢው የገዛውን ነገር እንዲለቅ በተደረገበት ጊዜ፤ ሻጩ ሌላውን ኪሣራ መክፈሉ ሳይቀር ክስ የሚያቀርብ መሆኑን ለሻጭ ገዥ ነግሮት
ቢሆን ሊያስቀረው ይችል የነበረ ወጪ፤ ቀሪ ሆኖ ለዳኝነትና ከዳኝነት ውጭ ያወጣውን ገንዘብ መክፈል አለበት፡፡
ክፍል 4፡፡
ልዩ ልዩ የሽያጭ አሠራር፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ስለ ከብቶችና ሌሎች በሕይወት ስላሉ እንስሶች ሽያጭ፡፡
ቊ 2368፡፡ (1) መሠረቱ፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ቊጥሮች የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ስለ ከብቶችና ስለ ሌሎች በሕይወት ስላሉ እንስሶች ሽያጭ የተመለከተው
ደንብ ከዚህ በላይ በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት ተወስኖዋል፡፡

ቊ 2369፡፡ ተላላፊ በሽታዎች፤ መድን የመሆን ሕጋዊ ግዴታ፡፡


ሻጩ የሸጠውን እንስሳ በሚያስረክብበት ጊዜ እንስሳው ከዚህ ቀጥሎ ካሉት በሽታዎች በአንዱ ያልተያዘ ለመሆኑ መድን ነው፡፡ በሽታዎች
የተባሉትም፤ ከአበደ ውሻ በሽታ ከማናቸውም ዐይነት እንስሶች ሁሉ፤
ከደስታ በሽታ በቀንድ ከብቶችና እነሱንም ለመሳሰሉት ሁሉ፤
ከሳምባ በሽታ በቀንድ ከብቶች፤
ከዕባጭና ከንድፍት በጋማ ከብቶችና እነሱንም በመሳሰሉት ሁሉ፤
ከአባ ሠንጋና ልዩ ልዩ ዐይነት መዥገር አመጣሽ በሽታዎች በጋማ ከብት፤ በቀንድ ከብቶች፤ በፍየልና በበጎች ላይ፤
ከአፍታ (አፈማዝ) በቀንድ ከብቶች፤ በበግ፤ በፍየሎችና በላሞች እንዲሁም በአሳማና በግመል ላይ፤
ከአባ ጐርባና ነቀርሳ በሽታ በቀንድ ከብቶች ላይ፤
ከበጎች ፈንጣጣ በበጎችና በአሳሞች ላይ፤
ከልዩ ዐይነቶች የአሳሞች በሽታና ፈንጣጣ፤
ከእከክ (የቆዳ በሽታ) በጋማ ከብትና እነሱን በመሳሰሉት ሁሉ፤
ከአሳማ ነቀርሳ፡፡
ከንድፍት (ቲሪፓኖ ዞማዚስ) ከዝንብ የሚተላለፍ በሽታ በጋማ ከብቶችና በግመል ላይ፤

ከኤፕ ቶስፖይሮሲስ (የጉበት በሽታ) በጋማ ከብቶች ላይ፤

ከኩልኩልት ኦስፋ (ጐስቶ ማቶሲስ) (ትል በሽታ) በበጎች ላይ፤


ከውርጃ በሽታ በቀንድ ከብቶች በበግና በፍየሎች ላይ፤
ከመዥገር አመጣሽ በሽታ፤
ከተላላፊ የጋማ ከብት የመስክ በሽታ፤
ከልዩ ዐይነት የአዕዋፍ በሽታ፤
ተላላፊ ከሆነና የተጋብኦ ጠባይ ያለው ልዩ ዐይነት የቆዳ በሽታና ማናቸውም ዐይነት የንብ በሽታ ሁሉ፤
ቊ 2370፡፡ (2) ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል፡፡
ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር ለተነገሩት ድንጋጌዎች ተቃራኒ የሚሆን ማናቸውም ውል ፍርስ ነው፡፡ (አይረጋም)

ቊ 2371፡፡ ስለ ጒድለቶች (1) መድን የመሆን ሕጋዊ ግዴታ፡፡


የተሸጠው እንስሳ ለተፈጥሮው ወይም በውሉ ለተነገረው አገልግሎት እንዳይሆን የሚያደርገው ጒድለት ያደረገበት ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤
ሻጩ መድን መሆን አለበት፡፡

ቊ 2372፡፡ (2) በስምምነት የሚደረግ የውል ቃል፡፡

(1) ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ለእንስሳው አለበት የተባለውን ጒድለት ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር መሠረት፤ ግልጽ በሆነ የውል ቃል
ለማስወገድ ይችላሉ፡፡

(2) ደግሞ በሻጩ በኩል እንስሳው እንደዚህ ያለ ስጦታ አለው ስለሚባለው ነገር የመድንነቱን ወሰን ለማስፋትና ስለ ዋቢነቱም የውል ቃል
ለማድረግ ይችላሉ፡፡

ቊ 2373፡፡ የውሉ መፍረስ፡፡


እንደ ሕጉ ወይም እንደ ውሉ ስለ እንስሳው መድን መሆን የሚገባ ሲሆን ተላላፊ በሽታ የያዘው ወይም ጒድለት ያለበት ሆኖ የተገኘ
እንደሆነ፤ ገዢው፤ የሺያጩ ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2374፡፡ የእንስሳው መሞት፡፡


መድን መሆን ባለበት በሽታ ወይም ጒድለት ምክንያት ወይም በዚህ ጒድለት በደረሰው ድንገተኛ ነገር ምክንያት እንስሳው የሞተ እንደሆነ
የእንስሳው መሞት የሻጩ ኪሣራ ሆኖ ዋጋውን መመለስ አለበት፡፡

ቊ 2375፡፡ የጉዳት ኪሣራ፡፡


ከዚህም በቀር ሻጩ ከዚህ ቀጥሎ በተመለከቱት ሁለት ምክንያቶች በገዢው ላይ ለደረሰው ጒዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡
(ሀ) ለሽያጩ ውል መፍረስ ምክንያት የሆነው እንስሳ በሽታ ያልያዘው ወይም ጒድለት የሌለበት መሆኑን በግልጽ አረጋግጦ መድን ሆኖ
እንደሆነ፤
(ለ) ለሽያጩ ውል መፍረስ ምክንያት የሆነውን እንስሳ ሻጩ ባስረከበበት ጊዜ እንስሳው በሽታ ወይም ጒድለት ያለበት መሆኑን ሻጩ
ማወቁን ለማስረዳት የተቻለ እንደሆነ፤

ቊ 2376፡፡ የውሉ አለመፍረስ፡፡

(1) ገዢው የእንስሳውን በሽታ ወይም ጒድለት፤ በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል በጽሑፍ በተነገረው የውል ቃል በተወሰነው ጊዜ ውስጥ፤ በልዩ
ዐዋቂዎች አሳይቶ እንስሳው በሽታ ወይም ጒድለት ያለበት መሆኑን ለሻጩ ካላስታወቀው ገዢው በሻጩ ላይ ያለውን መብቱን ያጣል፡፡

(2) በውል የተወሰነ ጊዜ የሌለ እንደሆነ ሻጩ እንስሳውን ካስረከበበት ቀን ጀምሮ በሠላሳ ቀን ጊዜ ውስጥ የእንስሳውን በሽታ ወይም
ያለበትን ጒድለት በልዩ ዐዋቂዎች አሳይቶ ለሻጩ ካላስታወቀው እንደዚሁ ገዢው በሻጩ ላይ ያለውን መብቱን ያጣል፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
በዐይነት ስለሚደረግ ሽያጭ፡፡
ቊ 2377፡፡ ሻጩ ኀላፊ መድን የሚሆንባቸው ዐይነቶች፡፡

(1) ዐይነትን ወይም ሞዴልን (ናሙናን) በማሳየት የሚደረግ ሽያጭ የተባለው ነገር ዐይነት ልክ እንደታየው ዐይነት ወይም እንደታየው
ሞዴል መሆን አለበት፡፡

(2) በተሰጠው ዐይነትና (በናሙናው) በውሉ ውስጥ የዚሁ ዐይነት አጻጻፍ መካከል የሚያጣላ ነገር የተገኘ እንደሆነ፤ የተሰጠው ዐይነት
ብልጫ ይኖረዋል፡፡
(3) የሚያጣላ ነገር ሳይኖር፤ ልዩነት ብቻ የተገኘ እንደሆነ፤ የተባለው ዕቃ የዐይነቱንና (ናሙናውን) በውሉ ውስጥ የተጻፉትን ዐይነቶች
ሁለቱም እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡

ቊ 2378፡፡ የዕቃውን ዐይነት ስለ ማቅረብ፡፡


ዐይነቱ የተሰጠው ወገን ለማሳየት የሚያቀርበው ዐይነቱ አስቀድሞ ከተቀበለው ጋራ አንድ መሆኑን ማስረዳት አለበት፡፡
ቊ 2379፡፡ የነዚህ ውሳኔዎች ተፈጻሚነት፡፡

(1) ሽያጩ፤ (ናሙናውን) ዐይነቱን (ኤሻንቲዮውን) ወይም ሞዴሉን ለገዢው ለማሳየት ያህል ብቻ እንጂ፤ የዕቃውን ዐይነት ለመስጠት ያለ
አንዳች መገደድ መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ዐይነትን (ኤሻንቲዮን) ወይም ሞዴልን በማሳየት የተደረገ ሽያጭ አለ አይባልም፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
በፈተና የሚደረግ ሽያጭ፡፡
ቊ 2380፡፡ ወዶ ለመቀበል የሚሰጥ ጊዜ፡፡

(1) የሽያጩ ውል በፈተና የተደረገ እንደሆነ ገዢው በውሉ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ የተባለውን ነገር ወዶ መቀበሉን ወይም አለመቀበሉን
ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) በውሉ ማናቸውም ጊዜ ያልተወሰነ እንደሆነ፤ ገዢው ለመፈተን የወሰደውን ነገር ወዶ መቀበሉን አለመቀበሉን የሚያስታውቅበትን በቂ
ጊዜ ሻጩ ሊወስንለት ይችላል፡፡

ቊ 2381፡፡ የገዢው ዝምታ፡፡

(1) ገዢው የወሰደውን ነገር ወዶ መቀበሉን ወይም አለመቀበሉን ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ያላስታወቀ
እንደሆነ፤ የተባለውንም ነገር እንዲፈትን ተሰጥቶት እንደሆነ፤ የሽያጩ ውል ደንበኛ ይሆናል፡፡

(2) ከዚህ በላይ እንደተነገረው ያልሆነ እንደሆነ፤ ገዢው ዕቃውን እንዳልፈለገው ሆኖ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2382፡፡ የዝምታ መቀበል፡፡


እንደዚሁም ገዢው አንድ ነገር ሳይለይ ለወሰደው ነገር ዋጋውን በሙሉ ወይም በከፊል የሰጠ እንደሆነ፤ ወይም ለመፈተን አስፈላጊ
ከነበረው ሥራ አልፎ በወሰደው ነገር በሌላ ዐይነት አደራረግ የሠራበት እንደሆነ፤ ሽያጩ ደንበኛ ይሆናል፡፡

ቊ 2383፡፡ በነገሩ ሊደረስ የሚችል መበላሸት፡፡


የሚፈተነውን ነገር ገዢው የተረከበውም እንኳ ቢሆን፤ ገዢው ለመፈተን የወሰደውን ነገር መውደዱን ሳያውቅ በሚቈይበት ጊዜ በተባለው
ነገር ላይ ሊደርስ የሚችለው መበላሸት በሻጩ ላይ ይሆናል፡፡
ንኡስ ክፍል 4፡፡
ዋጋው በየጊዜው ስለሚከፈልለት ሽያጭ፡፡
ቊ 2384፡፡ ለሻጩ ያለው የመምረጥ መብት፡፡
በየጊዜው ዋጋው እንዲከፈል ውለታ በማድረግ፤ አንድ ነገር ተሸጦ፤ ለገዢው የተሰጠ እንደሆነና፤ ገዢው በየጊዜው እንዲከፍለው
ከተመደበው ገንዘብ አንዱን መደብ እንዲከፍለው ሻጩ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶት እንደሆነ፤ ያልተከፈለውን ገንዘብ እንዲያገባለት ገዢውን
ለመክሰስ ይችላል፤ ወይም የውሉን ፈራሽነት የማስታወቅ መብት የራሱ እንዲሆን አድርጎ እንደሆነ፤ ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ
ይችላል፡፡

ቊ 2385፡፡ የውሉ መፍረስ፡፡

(1) ውሉ በፈረሰ ጊዜ፤ ሻጩና ገዢው አንዱ ለአንዱ የተሰጣጡትን ነገር መመለስ አለባቸው፡፡
(2) ስለሆነም፤ ሻጩ በገዢው እጅ ስለቈየው ነገር አገልግሎት የሚገባ ኪራይና በማገልገሉ፤ ስለተበላሸበትም ኪሣራ እንዲከፈለው
ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) በገዢው ላይ በጣም ከባድ የሆኑትን ግዴታዎች ለመጣል የሚናገረው ማንኛውም የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2386፡፡ ቀሪው ዕዳ ስለሚከፈል የአስገዳጅነት ውል፡፡

(1) ዋጋው በየጊዜው እንዲሰጥ የተደረገው አከፋፈል በሚቀርበት ጊዜ ቀሪውን ዕዳ የማስከፈል አስገዳጅነት በውሉ ተነግሮ እንደሆነ፤
ባለዕዳው በማከታተል ሁለት ጊዜ ያልከፈለው ገንዘብ እጅግ ቢያንስ ከሽያጩ ዋጋ ዐሥረኛው እጅ ካልሆነ በቀር ሻጩ በተደረገው
ስምምነት ሊጠቀምበት አይችልም፡፡

(2) በገዢው ላይ የበለጠና ከፍ ያለ ወጪን የሚያስከትል ተቃራኒ ስምምነት ሁሉ አይጸናም፡፡


ንኡስ ክፍል 5፡፡
ባለሀብትነቱን ለራሱ በማስጠበቅ የሚደረግ ሽያጭ፡፡
ቊ 2387፡፡ በሌላ ሦስተኛ ወገን ላይ መቃወሚያ ስለሚሆን ውል፡፡

(1) ይዞታው ለገዥው ተላልፎ ባለሀብትነቱ ግን ዋጋው እስኪከፈልለት ድረስ የሻጩ ሆኖ እንዲቈይ የተደረገ የውል ቃል፤ ስለዚሁ ጒዳይ
በተዘጋጀ የሕዝብ መዝገብ ላይ በገዢው መኖሪያ ቤት ካልተጻፈ በቀር የተባለው የውል ቃል ነገሩን በገዙት በሦስተኛ ወገኖች ላይ
መቃወሚያ ሊሆንባቸው አይችልም፡፡

(2) በንግድ ሕግ በተወሰኑት ድንጋጌዎች መሠረት ካልሆነ በቀር ነገሩን የገዛው ሰው በከሠረ ጊዜ ይህ የውል ስምምነት ከገዢው ገንዘብ
በሚፈልጉት ሰዎች ላይ መቃወሚያ ሊሆን አይችልም፡፡

ቊ 2388፡፡ በዕቃው ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች፡፡


የማስረከቡ ተግባር ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ በዕቃው ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች የገዢው ናቸው፡፡
ቊ 2389፡፡ የሽያጭ መፍረስ፡፡

(1) ሽያጩ በሚፈርስበት ጊዜ ሻጩ በየጊዜው በተደረገው አከፋፈል የተቀበለውን ገንዘብ ለገዢው መመለስ አለበት፡፡

(2) ደግሞም በገዢው እጅ ስለቆየው ነገር አገልግሎት የሚገባ ኪራይና በማገልገሉ ስለ ተበላሹትም ኪሣራን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) በገዢው ላይ በጣም ከባድ የሆኑትን ግዴታዎች ለመጣል የሚናገረው ማንኛውም የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡
ንኡስ ክፍል 6፡፡
የተሸጠውን መልሶ ስለ መግዛት የሚደረግ ውል፡፡
ቊ 2390፡፡ መልሶ የመግዛት ችሎታ፡፡
ሻጩ የሸጠውን ነገር በተወሰነ ጊዜ ውስጥ መልሶ ከገዥው ለመግዛት የሚፈቅድለትን መብት አስጠብቆ ለመዋዋል ይችላል፡፡
ቊ 2391፡፡ የሚወሰነው ጊዜ፡፡

(1) ሻጩ የሸጠውን ነገር መልሶ ስለ መግዛት ባለው ችሎታ የሚሠራበት ጊዜ፤ ከሁለት ዓመት የበለጠ ሊሆን አይችልም፡፡

(2) ከዚህ ያነሰ ጊዜ በመወሰን ስምምነት አልተደረገ እንደሆነ በሁለት ዓመት የተወሰነ ይሆናል፡፡

ቊ 2392፡፡ ቅጣት (ኪሣራ)፡፡

(1) መልሶ በመግዛት ውል የተሸጠውን ነገር፤ ገዢው ለሌላ ሰው ሊሸጠው አይችልም፡፡


(2) ነገር ግን ሻጩ የሸጠውን ነገር መልሶ እንዲገዛ የሚፈቅደው ውል ስለዚህ ጒዳይ በተዘጋጀው የሕዝብ መዝገብ ላይ በገዢው መኖሪያ
ቦታ ካልተጻፈ በቀር፤ ይህ የተባለው ለሌላ ሰው ለመሸጥ አለመቻል ለሌሎች ሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ለመሆን አይችልም፡፡

ቊ 2393፡፡ (ሀ) የሻጩ ግዴታ፡፡

(1) የሸጠውን መልሶ ለመግዛት ችሎታ ያለው ሻጭ የተቀበለውን ዋጋ ለባለውሉ መመለስና ተዋዋዩ ስለ ሽያጩ ውል ያደረገውን ወጪ
መክፈል አለበት፡፡

(2) ገዢው ለገዛው ነገር ያደረገው ወጪ እንዳለም፤ ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር በዚህ ሕግ ያላገባብ ስለ መበልጸግ በሚለው
ምዕራፍ የተወሰኑት ድንጋጌዎች የሚፈጸሙ ይሆናሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 7፡፡
ዕቃውን ከመላክ ግዴታ ጋራ የሚደረግ ሽያጭ፡፡
ቊ 2394፡፡ ዕቃውን የማመላለስ ጥንቃቄ፡፡
ውሉ የተሸጠውን ነገር ሻጩ እንዲልክ የሚያስገድደው የሆነ እንደሆነ፤ የተሸጠው ዕቃ በሺያጩ ውል እስከተመለከተው ስፍራ ድረስ
እንዲደርስ ሻጩ በተለመዱት ዘዴዎች ለመላክ አስፈላጊዎችን የማመላለስ ውሎች ከዕቃ ጫኙ ጋራ መዋዋል አለበት፡፡

ቊ 2395፡፡ ማስረከብ፤ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የሽያጩ ውል የዕቃውን ማጓጓዝ ግዴታ የሚጨምር ሲሆን ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር የዕቃው ማስረከብ ጒዳይ የሚፈጸመው
ዕቃውን ለዕቃ አመላላሹ በመስጠት ነው፡፡

(2) ይህን የዕቃ ማመላለስ ሥራ የሚያከናውነው ሻጩ በራሱ የማመላለሻ ዘዴዎች ወይም በሻጩ ስም በሚሠሩና እሱ በቀጠራቸው ዕቃ
አመላላሾች አማካይነት በሆነ ጊዜ የዕቃው ማስረከብ ሥራ የሚፈጸመው በገዢው ስም የተደረገ የዕቃ ማመላለስ ውል ተሠርቶ ለዕቃ
አመላላሹ ዕቃው በተሰጠ ጊዜ ነው፡፡

(3) የዕቃው ማጓጓዝ ሥራ በብዙ ዕቃ አመላላሾችና በተከታታይ ሁኔታ የሚፈጸም የሆነ እንደሆነና የሽያጩም ውል ሻጩ ስለ ዕቃው
ማጓጓዝ አንድ ወይም ብዙ ውል በማድረግ ጠቅላላውን የዕቃ መጫን ውል ራሱ እንዲፈጽም የሚያስገድደው የሆነ እንደሆነ የዕቃው
ማስረከብ ጒዳይ የሚፈጸመው ዕቃውን ለመጀመሪያው ዕቃ አመላላሽ በመስጠት (በማስረከብ) ነው፡፡

ቊ 2396፡፡ (2) ውልን ለመፈጸም የተላከ መሆኑ ያልተገለጸበት ዕቃ፡፡


አድራሻ በማድረግ ወይም በሌላ አኳኋን ለጫኙ የተሰጠው ዕቃ የተላከው ውልን ለመፈጸም መሆኑን የሚገልጽ ነገር ያልተደረገበት
እንደሆነ ሻጩ ለገዢው ዕቃው መላኩን ማስታወቂያ አስፈላጊ በሆነ ጊዜም የዕቃውን ዝርዝር የሚያስታውቅ ወረቀት ካላከለት በቀር
የማስረከቡ ነገር እንደተፈጸመ ሆኖ አይቈጠርም፡፡

ቊ 2397፡፡ በውሃ ላይ የሚደረግ ማጓጓዝ፡፡

(1) ከዚህ በላይ እንደተነገሩት ድንጋጌዎች ዕቃውን እንዲጭን የሚሰጠው ዕቃ ጫኝነቱ በውሃ ላይ የማመላለስ ሥራ ለሚሠራ የሆነ እንደሆነ
የማስረከቡ ሥራ የሚፈጸመው እንደ ውሉ አኳኋን ዕቃውን በመርከቡ ላይ ወይም በመርከቡ አጠገብ በመስጠት ነው፡፡

(2) ሻጩ ለገዢው ዕቃው በመርከብ የተሳፈረበትን ደረሰኝ ወይም ማናቸውንም ይህን የመሰለ ሌላ ሰነድ እንደ ውሉ ቃል የማቅረብ መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2398፡፡ ሻጩ ዕቃውን ለመያዝ መብት ያለው ስለ መሆኑ፡፡

(1) ዕቃው የሚጫንበት ውል ሻጩ ዕቃው በጒዞ ላይ ባለበት ጊዜ ሊያዝበት መብት የሚሰጠው ካልሆነ በቀር ሻጩ ዋጋው እስኪከፈለው
ድረስ ዕቃ መላኩን ለመዘግየት ይችላል፡፡
(2) ስለሆነም ውላቸው ዕቃውን ሻጩ ለገዢው የሚያስረክበው በተላከበት ስፍራ የሆነ እንደሆነ ወይም ዋጋው የሚከፈለው ዕቃውን
ካስረከበ በኋላ የሆነ እንደሆነ ወይም ዋጋው የሚከፈለው ዕቃውን ካስረከበ በኋላ የሆነ እነደሆነ፡፡ ሻጩ ዕቃውን መያዝና ማቈየት
አይችልም፡፡

(3) ሻጩ ዕቃው በጒዞ ላይ ሳለ የሚያዝበት በመሆኑ ዕቃውን ልኮ እንደሆነ፤ ዕቃው በተላከበት ስፍራ ዋጋው ሳይከፈለው ለገዢው
አንዳይሰጥ መቃወም ይችላል፡፡

ቊ 2399፡፡ ጽሑፍ ከተቀበለ በኋላ ስለሚደረግ የዋጋ አከፋፈል፡፡

(1) ዕቃውን ለመቀበል የሚያስችል ዕቃው የተጫነበት ማስረጃ ወረቀት (ኮኔስማ) ወይም ሌላ ጽሑፍ ተደርጎለት እንደሆነ በዚሁም ዕቃ
ለማዘዝ ይህንኑ ጽሑፍ መያዝ የሚያስፈልግ ሲሆን በውሉ የተመለከቱት ወይም በልማድ የታወቁት ጽሑፎች ሳይሰጡ የዕቃውን ዋጋ
መጠየቅ አይቻልም፡፡

(2) ዕቃውን ለመቀበል የሚያስችለው ጽሑፍ ለገዢው ከተሰጠው ዕቃውን ለመመርመር አልቻልሁም በማለት ዋጋውን አልከፍልም
ለማለት መብት የለውም፡፡

(3) ጽሑፉ ዕቃው የተጫነበት ማስረጃ ወረቀት ወይም ሌላ ጽሑፍ ሲሆንና ዕቃውን ለመቀበል የሚያስችለው ይኸው ጽሑፍ ሲሆን ወይም
በዕቃው ለማዘዘ ይህንኑ ጽሑፍ መያዝ አስፈላጊ ሲሆን ጽሑፎቹን የመስጠት ግዴታ የውሉ ፍሬ ነገር ሆኖ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2400፡፡ ዕቃውን በመንገድ ላይ ስለ ማቆም፡፡

(1) ሻጩ ዕቃውን ከላከ በኋላ ገዢው መክፈል አለመቻሉን በፍርድ እንደተነገረ የሰማ እንደሆነ የተባለው ዕቃ የተጫነበትን የደረሰኝ
ማስታወቂያ ወይም የገዛውን እንዲረከብ የሚፈቅድለት ማንኛቸውም ሌላ ሰነድ በጁ ቢገኝም ለገዢው ዕቃው እንዳይሰጠው ሲል ሻጩ
ለመቃወም ይችላል፡፡

(2) ሻጩ ዕቃው የተጫነበት የማስታወቂያ ደረሰኝ ወይም ከዚህ በላይ የተመለከተውን ሰነድ በደንብ ይዞ የሚጠይቅ ሌላ ሦስተኛ አምጪ
ዕቃውን እንዳይረከብ ለመቃወም አይችልም፡፡

(3) በዚህ ጊዜ ዕቃው የተጫነበትን የማስታወቂያ ደረሰኝ ወይም ሰነዱ ዕቃዎቹን ስለ ማስተላለፍ በሚመለከተው ጒዳይ ልዩ ልዩ
ድንጋጌዎች ያሉበት ካልሆነ በቀር፤ ወይም የደረሰኙ ወይም የሰነዱ አምጪ ያመጣውን ደረሰኝ ወይም ሰነድ ለማግኘት ዐውቆ ሻጩን
ለመጉዳት ሲል ያደረገው መሆኑን ሻጩ ካላስረዳ በቀር ዕቃው እንዳይሰጥ የመቃወም መብት የለውም፡፡

ቊ 2401፡፡ የተገዛውን ነገር የመረከብ ግዴታ፡፡

(1) የተሸጠው ነገር ለገዢው ተልኮለት እንደሆነና በመረከቢያው ቦታ ዝግጁ ሆኖ ሲገኝለት ገዢው ዕቃውን ለመቀበል፤ የማይፈቅድ ሲሆን
ዋጋውን ሳይከፍልና ያለ ችግርም ሌላ ወጪ ሳያደርግ ለመቀበል ከቻለ የተላከውን ነገር በሻጩ ስም ሆኖ መቀበል አለበት፡፡

(2) ሻጩ በሸጠው ነገር መድረሻ ቦታ ላይ ሲገኝ ወይም በዚሁ ቦታ ላይ ስለ ርሱ ሆኖ የተላከውን ነገር አላፊ ሆኖ እንዲቀበልለት የተደረገ
ሰው ሲኖር፤ ከዚህ በላይ በተጻፈው መሥመር የተሰጠው ውሳኔ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

ቊ 2402፡፡ በነገሩ ላይ የተገኘው ጒድለት መታየት፡፡

(1) የተሸጠው ነገር በሚላክበት ጊዜ፤ ገዢው በተባለው ነገር መድረሻ ቦታ ላይ የተላከለትን ነገር መመርመር አለበት፡፡

(2) ገዢው የገዛውን ዕቃ መልሶ የላከው ከጭነቱ ሳይራገጀፍ የሆነ እንደሆነና ሻጩም ውሉ በተደረገበት ጊዜ ዕቃው ተመልሶ መላክ
የሚችል መሆኑን የሚያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው እንደሆነ የተሸጠው ዕቃ ምርመራ የሚደረገው ይህ ዕቃ ተመልሶ ወደ አዲሱ
መድረሻ ቦታው በደረሰ ጊዜ ነው፡፡
ንኡስ ክፍል 7፡፡
በሐራጅ ስለሚደረግ ሽያጭ፡፡
ቊ 2403፡፡ የውሉ አደራረግ፡፡
(1) በሐራጅ የሚደረግ ሽያጭ ተፈጸመ የሚባለው፤ ሻጩ ወይም ለሐራጁ አሻሽጥ ተመረጠው ሰው ዕቃውን ለገዢው የንተ ነው ባሉበት
ጊዜ ነው፡፡

(2) ሻጩ ተቃራኒ የሚሆን አሳቡን ካልገለጸ በስተቀር ሐራጁን የሚያካሂደው ዋጋ ላበለጠ ለመሸጥ መብት እንዳለው ይቈጠራል፡፡

ቊ 2404፡፡ በሐራጅ ገዥ የሆነ ሰው ግዴታ፡፡

(1) በሐራጅ ላይ እገዛለሁ ያለ ሰው ለሽያጩ ሁኔታ በተመለከቱት ቃሎች መሠረት በሚያደርገው የዋጋ አቀራረብ ይገደዳል፡፡

(2) ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል የሌለ እንደሆነ ከቀረበው ዋጋ በላይ ሌላ ዋጋ ካልተነገረ ወይም ያቀረበውን ዋጋ ከተለመደው ከሐራጅ
ድምፅ በኋላ ወዲያውኑ ካልተቀበሉት ከግዴታው ነጻ ይሆናል፡፡

ቊ 2405፡፡ እጅ በጅ ስለ መክፈል፡፡

(1) በሽያጩ ስምምነት ሁኔታ ውስጥ የተነገረ ተቃራኒ የሚሆን ነገር ከሌለ በሐራጅ ገዢው እጅ በጅ ዋጋውን ለመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

(2) ሻጩ ገንዘቡ እጅ በጅ ወይም በሽያጩ ስምምነት እንደተነገሩት ሁኔታዎች፤ ያልተከፈለው እንደሆነ ሻጩ ውሉ ፈርሷል ብሎ ወዲያው
ለማስታወቅ ይችላል፡፡

ቊ 2406፡፡ ሻጩ ዋቢ ስለ መሆኑ፡፡

(1) ሻጩ በተለመደው የሽያጭ ስምምነት ለሚሸጠው ነገር ዋቢ በመሆን እንደሚገደድ ሁሉ በአደባባይና በፈቃድ ለሚደረገው የሐራጅ
ስምምነት ዋቢ ነው፡፡

(2) እርሱ የተንኰል ሥራ የሠራ ካልሆነ በቀር ሻጩ በግድ ለሚደረግ ሐራጅ ዋቢ መሆን የለበትም፡፡

ቊ 2407፡፡ በሐራጅ ይሸጥልኝ ባዩ ዋቢ ስለ መሆኑ፡፡

(1) አንድ ሰው ባቀረበው ጥያቄ ምክንያት ሐራጅ ሲባል ጥያቄ አቅራቢው በሐራጅ ስለሚሸጠው ነገር ለሰጠው ዝርዝር ዋቢ ነው፡፡

(2) እንዲሁም በዚሁ ነገር ለሠራው አታላይነትም ተጠያቂ ይሆናል፡፡


ምዕራፍ 2፡፡
የመሸጥ ውል መሰልነት ያላቸው ልዩ ልዩ ውሎች፡፡
ክፍል 1፡፡
የለውጥ ውል፡፡
ቊ 2408፡፡ ከሽያጭ ውል ያለው ልዩነት፡፡

(1) እያንዳንዱ ለዋጭ ለመለዋወጥ የተነገሩትን ነገሮች ስለሚመለከት ጒዳይ፤ የአንድ ሻጭ መብቶችና ግዴታዎች አሉት፡፡

(2) በለውጡ ውል መሠረት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲከፍል ግዴታ ያለበት ለዋጭ ተጨማሪውን ገንዘብ ስለሚነካው ጒዳይ ገዥ የሆነ ሰው
በሚገደድበት ግዴታ ይገደዳል፡፡

(3) ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር ስለ ለውጥ ውል የሚደረገውን ወጪ ሁለቱ የለውጥ ተዋዋዮች እኪል በኩል ይችላሉ፡፡

ቊ 2409፡፡ ስለ ሽያጭ ውል ወደ ተሰጡት ደንቦች መምራት፡፡


የሽያጩን ስምምነት ውል የሚመለከቱት ደንቦች ስለ ለውጥ ውል ለቀረበውም ጒዳይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ክፍል 2፡፡
የባለሀብትነትን መብት ሳይሆን ሌሎችን መብቶች
ስለ ማስተላለፍ፡፡
ቊ 2410፡፡ ሪምን ስለ ማስተላለፍ፡፡

(1) አንድ ሰው በአንድ ንብረት ላይ ያለውን የሪም መብት ለሌላ ሰው በዋጋ ባስተላለፈ ጊዜ የሽያጭን ውል የሚመለከቱት ደንቦች ተፈጻሚ
ይሆናሉ፡፡
(2) የዕቃውን ሀብትነት ስለ ማስተላለፍ ሻጩ ግዴታ እንዳለበት እንዲሁም በዚህ ጊዜ ሪም ሰጪው ሪሙን የማስተላለፍ ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 2411፡፡ ግዙፍነት የሌላቸውን መብቶች ስለ ማስተላለፍ፡፡

(1) አንድ ሰው፤ ግዙፍነት የሌላቸውን መብቶች በዋጋ ለሌላ ሰው የሚያስተላልፍ ሲሆን ልዩ የሆኑት ሕጎች እንደተጠበቁ ሆነው በተቻለ
መጠን የሽያጭ ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

(2) ስለ ገንዘብ መብት ማስተላለፍ የተደነገጉት ደንቦች ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚል አንቀጽ ተገልጸው ይገኛሉ፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ ኪራይ ሽያጭ፡፡
ቊ 2412፡፡ ሽያጭን ስለ መምሰሉ፡፡
ተዋዋዮቹ የሚያደርጉት ውል የዕቃ ኪራይ ውል ነው፡፡ በየጊዜውም የተወሰነው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ተከራዩ ለተከራዩ የዕቃው ባለ
ሀብት ይሆናል ብለው የተዋዋዩ እንደሆነ ከዚህ የሚከተሉት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ስለ ሽያጭ የተወሰኑት ደግቦች ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡
ቊ 2413፡፡ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች፡፡
የተከራየው ነገር ከተሰጠው ጊዜ አንሥቶ በዕቃው ላይ ሊደርስ የሚችል አደጋ በተከራዩ ላይ የሚታሰብ ነው፡፡
ቊ 2 ሺ 414፡፡ ውልን ስላለመቀጠል የሚደረግ ማስታወቅ፡፡
ተከራይ የተከራየውን ነገር ለአከራዩ በመመለስ፤ በማንኛቸውም ጊዜ ቢሆን ውሉ እንዲቀር ለማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 2415፡፡ የውል መፍረስ፡፡

(1) ውሉ በፈረሰ ጊዜ፤ አከራዩ በኪራይ የተቀበለውን ገንዘብ ለተከራዩ መመለስ አለበት፡፡

(2) ነገር ግን አከራዩ የሚገባውን ኪራይና ተከራዩ የተከራየውን ነገር በመገልገል ስለ ጐዳበት ኪሣራን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) በተከራዩ ላይ ይበልጥ ከፍ ያለ ወጪን የሚያስከትል ተቃራኒ የሆነ ማንኛውም የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡
ክፍል 4፡፡
የዕቃ ማቅረብ ውል፡፡
ቊ 2416፡፡ ትርጓሜ፡፡
የዕቃዎች ማቅረብ ውል ማለት ከተዋዋዮቹ አንዱ ለሌላው ተዋዋይ አስፈላጊ የሆኑትን ዕቃዎች በየጊዜው ወይም ባለማቋረጥ በዋጋ
ለመስጠት ውለታ የሚገባበት ውል ነው፡፡

ቊ 2417፡፡ የውሉ ዓላማ፡፡

(1) የሚቀርበው ዕቃ ልክ ያልተወሰነ ሲሆን አቅራቢው ውሉ የተደረገበትን ጊዜ በማመዛዘን ለተዋዋዩ ደንበኛ አስፈላጊ ሆኖ የሚገኘውን
ያህል ለመስጠት ይገደዳል፡፡
(2) ተዋዋዮቹ የሚቀርበውን ዕቃ በጠቅላላው ወይም በየአንዳንድ ጊዜ የሚቀርበውን ከፍ ያለውን ወይም ያነሰውን ወሰን ብቻ ቈርጠው
የተዋዋሉ ሲሆኑ የአቅራቢው ተዋዋይ ሊቀበለው የሚገባውን ልክ፤ በነዚህ በተሰጡት ወሰኖች ውስጥ ለመወሰን መብት አለው፡፡

(3) ሊቀርብ የሚገባው ዕቃ ልክ ለተዋዋዩ አስፈላጊነት እንደሚበቃ ሆኖ እንዲሰጥ የተወሰነ ሲሆን የቀረበው ልክ አነስተኛ ተብሎ
ከተወሰነው ልክ በላይ ሆኖ ቢገኝ እንኳን ተቀባዩ አስፈላጊውን በሙሉ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡

ቊ 2418፡፡ ዋጋ፡፡
የሚቀርቡት ዕቃዎች በየተወሰነው ጊዜ የሚቀርቡ ሲሆኑ፤ በውሉ የተነገረ የውለታ ቃል ከሌለ የነዚህ ዕቃዎች የየአንዳንዱ ጊዜ ዋጋ በዚህ
አንቀጽ በምዕራፍ 1 በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት ይወሰናል፡፡

ቊ 2419፡፡ የዋጋው መከፈያ ጊዜ፡፡

(1) ዕቃዎቹ በየጊዜው የሚቀርቡ ሲሆኑ፤ ዋጋቸው በየቀረቡበት ጊዜ ተካፋይ ነው፡፡

(2 ) ባለማቋረጥ ሊቀርቡ የሚገባቸው ሲሆኑ፤ ዋጋው በልማድ በሚወሰነው ጊዜ ይከፈላል፡፡

ቊ 2420፡፡ የጊዜው ወሰን፡፡

(1) ለሚቀርቡት ዕቃዎች የተወሰነ ጊዜ ሲኖር የተባለው ጊዜ ስለ ሁለቱ ተዋዋዮች ጥቅም እንደተወሰነ ሆኖ ይገመታል፡፡

(2) በሚቀርቡት ዕቃዎች ላይ መብት ያለው ሰው ልዩ ልዩ ሆነው ስለሚቀርቡት ዕቃዎች ጊዜ ለመወሰን ሥልጣን ያለው እንደሆነ በአእምሮ
ግምት በቂ በሆነ ማስታወቂያ ለዕቃ አቅራቢው ጊዜውን ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2421፡፡ ውልን አለመፈጸም፡፡

(1) ከተዋዋዮቹ አንዱ ስለተነገረው የዕቃ ማቅረብ የገባባቸውን ግዴታዎች ያልፈጸመ እንደሆነና አለመፈጸሙም ከፍ ያለ ነገር ያሳየ
እንደሆነ፤ ይኸውም ነገር ለወደፊት በሚፈጸሙ ግዴታዎች የደንብ አፈጻጸም ውስጥ እምነት የሚያጠፉ ጠባይ ያለበት ሲሆን፤ ውሉ
ለመፍረስ ይችላል፡፡

(2) ዕቃ አቅራቢው ለተዋዋለው ሰው አስቀድሞ በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ ማስታወቂያ ካልሰጠ በቀር፤ ውሉን ለማፍረስ ወይም
አፈጻጸሙን ማቆም አይችልም፡፡

(3) ማንኛቸውም ስለዚሁ ጒዳይ የተነገረው ተቃራኒ የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2422፡፡ የምርጫ ስምምነት (1) የሚቈይበት ጊዜ፡፡

(1) አንድ ሰው የተለየ ዐይነት ያላቸው ዕቃዎች ባስፈለጉት ጊዜ በምርጫ ከአንድ ዕቃ አቅራቢ ብቻ ለመውሰድ ግዴታ የሚገባበት ውል
ከሦስት ዓመት የበለጠ ጊዜ ሊጸና አይችልም፡፡

(2) ይበልጥ እንዲቈይ ተደርጎም እንደሆነ፤ ከሦስት ዓመት የበለጠ ሊጸና አይችልም፡፡

ቊ 2423፡፡ (2) ተፈጻሚነት፡፡

(1) እንደዚህ ባለ ቃል ውል የሚገባ ተዋዋይ ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ያቀረቡለትን ውለታዎች ለዕቃ አቅራቢው ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ለምርጫ ባለው መብት እጠቀማለሁ ያለ እንደሆነ፤ ዕቃ አቅራቢው በውሉ በተወሰነው ወይም በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ፤
ማስታወቅ አለበት፡፡ ካላስታወቀ መብቱ ይቀርበታል፡፡

ቊ 2424፡፡ ከተመረጠው አቅራቢ ብቻ በደንበኛው ያለበት የመቀበል ግዴታ፡፡

(1) በውሉ ውስጥ አንድ ሰው አንዳንድ የዕቃ ዐይነት ከአንድ የታወቀ ዕቃ አቅራቢ ብቻ ለመውሰድ የተዋዋለ እንደሆነ፤ የተባለው ሰው
በውሉ የተነገረውን የዕቃ ዐይነት ከሌላ ሦስተኛ ወገን ለመውሰድ አይችልም፡፡
(2) እንዲሁም ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር፤ ይህ ሰው በውሉ የተነገሩትን ዕቃዎች ለመሥራት ወይም ለማውጣት
አይችልም፡፡
ቊ 2425፡፡ ለተመረጠው ደንበኛ ብቻ ለማቅረብ፤ በዕቃ አቅራቢው ያለበት ግዴታ፡፡

(1) ዕቃ አቅራቢው ለአንድ የታወቀ ሰው ብቻ ለማቅረብ የተዋዋለ እንደሆነ፤ ዕቃ አቅራቢው በውሉ በተነገረው ቀበሌ ውስጥና ውሉ
በሚቈይበት ጊዜ፤ በውሉ የተነገሩትን የዕቃ ዐይነቶች በቀጥታም ሆነ በጅ አዙር ለሌላ ሦስተኛ ወገኖች ጥቅም ለማቅረብ አይችልም፡፡

(2) ተዋዋዩ የግል ሆነው የተጠበቁለትን ነገሮች በመሸጥ በተወሰነለት ቀበሌ ውስጥ ለማስፋፋት ተዋውሎ ሳለ፤ ይህን ግዴታ ያልፈጸመ
እንደሆነ፤ በውሉ የተነገረውን አነስተኛውን መጠን ሸጦ ቢገኝ እንኳን ኀላፊ ይሆናል፡፡

ቊ 2426፡፡ ውሉን ስለ ማስቀረት፡፡


የዕቃው አቀራረብ የተወሰነ የውል ጊዜ፤ በውሉ አልተጻፈ እንደሆነ፤ አስቀድሞ ማስታወቂያ ስለ መስጠት በውሉ የተጻፈውን ጊዜ አስቀድሞ
በመስጠት ወይም አስቀድሞ ስለ ማስታወቅ የተጻፈ የውል ቃል የሌለ እንደሆነ፤ በአእምሮ ግምት በቂ ጊዜ በመስጠት ተዋዋዮቹ
እየአንዳንዳቸው ውሉ እንዲቀር ለማድረግ ይችላሉ፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ስጦታ፡፡
ቊ 2427፡፡ ትርጓሜ፡፡
ስጦታ ማለት አንድ ወገን ተዋዋይ ማለት ሰጪው ተቀባይ ተብሎ ለሚጠራው ለሌላ ሰው ችሮታ በማድረግ አሳብ ከንብረቶቹ አንዱን
የሚለቅበት ወይም ግዴታ የሚገባበት ውል ነው፡፡

ቊ 2428፡፡ በሞት ምክንያት የሚደረጉ ስጦታዎች፡፡


ሰጪው ሲሞት ይፈጸማሉ ተብለው በተወሰኑት ስጦታዎች ላይ ስለ ኑዛዜ የተነገሩትን ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡
ቊ 2429፡፡ ስለ ጋብቻ ርዳታ የሚደረጉ ስጦታዎች፡፡

(1) በጋብቻ ምክንያት በሚደረጉት ስጦታዎች ላይ ስለ ሌሎቹ ስጦታዎች የተወሰኑት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) እነዚህ ስጦታዎች በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን በዋጋ እንደተደረጉ ሆነው አይቈጠሩም፡፡

(3 ) ስለዚህ ስጦታዎች በተለይ የተነገሩት የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2430፡፡ ያለ ዋጋ የሚሆን አገልግሎት፡፡


ያለ ዋጋ የሚደረግ የአገልግሎት ሥራ፤ ወይም የራሱን ዕቃ ያለዋጋ ለሌላው ሰው ዝግጅ ማድረግ ስጦታ አይባልም፡፡
ቊ 2431፡፡ አለመቀበል፡፡
እንደዚሁም፤ ወራሽነትን አልፈልግም ብሎ መተው ወይም በኑዛዜ የተደረገለትን ስጦታ አልቀበልም ማለት ወይም አንድ መብትን
የሚያስገኘውን ወይም መብትን እንደ ያዙ ለመቅረት የሚያስፈልገውን ግዴታ ሳይፈጽሙ መቅረት ስጦታ ነው ተብሎ አይቈጠርም፡፡

ቊ 2432፡፡ የተፈጥሮ ግዴታ፡፡


መንፈሳዊ ተግባርን ለመፈጸም የሚደረገው የገንዘብ መክፈል ሥራ ስጦታ አይባልም፡፡
ቊ 2433፡፡ ስለ ሥራ ዋጋ የሚደረግ ስጦታ፡፡
እንደዚሁም፤ አንድ ሰው ለሰጪው ወይም ለቤተሰቡ ስላደረገው አገልግሎት በልማድ መሠረት ያደረገው የሥራ ዋጋ መከፈል ስጦታ
አይባልም፡፡
ቊ 2434፡፡ ስጦታ ማድረግ የሰጭ የራሱ ተግባር ስለ መሆኑ፡፡
(1) ስጦታ የሰጭ የራሱ የተለየ ተግባር ነው፡፡

(2) ስጦታ የሚደረገው በወኪሉ ሲሆን የሚሰጡት ንብረቶች እንዴት ያሉ እንደሆኑና ለማን እንደሚሰጡ ገልጾ ካላስታወቀ በቀር ፈራሽ
ነው፡፡

ቊ 2435፡፡ ስለ ስጦታ የተስፋ ቃል መስጠት፡፡

(1) ስጦታ አደርጋለሁ ብሎ የተስፋ ቃል መስጠት አንዳች ግዴታ አያስከትልም፡፡

(2) እንደዚህ ያለውን ቃል አለመፈጸም፤ ቃል የተሰጠው ወገን በዚህ በተሰጠው ቃል ምክንያት በቅን ልቡና ያወጣው ገንዘብ እንዲመለስ
ብቻ ያስገድዳል፡፡

ቊ 2436፡፡ ስጦታን ተቀባዩ እቀበላለሁ ማለት አስፈላጊ ስለ መሆኑ፡፡

(1) የስጦታ ውል ፍጹም የሚሆነው፤ ስጦታ ተቀባዩ ለእርሱ የተደረገውን ልግስና እቀበላለሁ ብሎ አሳቡን የገለጸ እነደሆነ ነው፡፡

(2) ሰጪው ከሞተ ወይም ችሎታ ከአጣ በኋላ ስጦታውን እቀበላለሁ የማለት ቃል ዋጋ የለውም፡፡

(3) ስጦታን የስጦታ ተቀባዩ ሕጋዊ እንደራሴ ስለሱ ሆኖ ሊቀበል ይችላል፡፡ የስጦታ ተቀባዩ ወራሾች ግን ስለሱ ሆነው መቀበል
አይችሉም፡፡
ቊ 2437፡፡ የሰጪው አእምሮ ትክክል አለመሆን፡፡

(1) ከዚህ ቀጥሎ ባሉት ሁኔታዎች ካልሆነ በቀር፤ የሰጪው አእምሮው ትክክል አልነበረም የማለት ምክንያት ስጦታን መያፈርስም፤
ስጦታው ፈራሽ የሚሆነው፤

(ሀ) ሰጪው ስጦታውን ባደረገበት ጊዜ ተከልክሎ የነበረ ሰው እንደሆነና ስጦታው በሞግዚቱ በኩል በደንብ ያልተደረገ እንደሆነ፤

(ለ) ሰጪው በፍርድ እንዲከለከል ጥያቆ የቀረበው በሕይወቱ ሳለ የሆነ እንደሆነና ዳኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ውሳኔ ለመስጠት
ከመቻላቸው በፊት ሰጪው የሞተ እንደሆነ፤

(ሐ) የሰጪው አእምሮ ትክክል አለመሆን ስለ ስጦታው በተደረገው የውል አጻጻፍ የሚታወቅ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 2 ሺ 438፡፡ ሕገ ወጥ የሆነ ምክንያት፡፡
(1) ስጦታው፤ የተደረገበት ምክንያት ግብረ ገብ ካልሆነ ወይም ሕገ ወጥ ከሆነ መንፈስ የሆነ እንደሆነ ፈራሽ ነው፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ግብረ ገብነት የሌለው ወይም ሕገ ወጥ ምክንያት ያለበት ስጦታ ከዚያው ከስጦታው አደራረግ ወይም ከሰጪው
የጽሑፍ አስረጅ ካልተገኘ በቀር፤ ስጦታው ፍርስ መሆኑን ለማስረዳት አይቻልም፡፡

ቊ 2439፡፡ የመንፈስ መጫን፡፡ (1) በውርስ አንቀጽ በተመለከተው ሁኔታ፡፡

(1) ዳኞች፤ የኑዛዜን ቃል ለመቀነስ ወይም ለመሻር ሕግ በሚፈቅድላቸው ሁኔታ፤ ስጦታን ለመቀነስ ወይም ለመሻር ይችላሉ፡፡

(2) ስጦታ ተቀባዩ የሰጪው ዘመድ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው ሰው ወይም ከተጋቢዎቹ አንዱ (ባል ወይም ሚስት) ቢሆንም ስጦታው
እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) ለአስተዳዳሪ (ላሳዳጊ) ወይም ለሞግዚት የተደረገ ስጦታ ሲሆን የሰጪውን ዕድሜ መገመት አያስፈልግም፡፡

ቊ 2440፡፡ (2) ክርክር ያለበት በመሆኑ ምክንያት ስለተደረገ ስጦታ፡፡


ስጦታው የተደረገው የሰጪውን ወይም ከባልና ሚስት ያንደኛውን ወይም የዘመዱን ጥቅም የሚጎዳ ክርክር በተነሣበት ሀብት ላይ ሆኖ
ስጦታ ተቀባዩ ወይም ማናቸውም ሌላ ሰው በዚሁ ንብረት ላይ የተነሣው ክርክር እንዲወገድ የመንፈስ መጫን መብቱን (የሥልጣን
መብቱን) በዚህ ላይ እንዲያውል ወይም እንዲረዳው ለማድረግ የሆነ እንደሆነ በዚህ ዐይነት የተደረገው ስጦታ እንዲፈርስ ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
ቊ 2441፡፡ (3) ስጦታን ለመቀነስ ወይም ለመሻር የሚቀርብ ጥያቄ፡፡

(1) ስጦታ እንዲቀነስ ወይም እንዲሻር የሚቀርበው ጥያቄ ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንሥቶ እስከ ሁለት ዓመት ለዳኞች ካልቀረበ በቀር
ዋጋ የሌለው ነው፡፡

(2) ሟች ያደረገውን ኑዛዜ በመጫን ምክንያት ነው በማለት ኑዛዜው እንዲፈርስ ለመጠየቅ ሕግ የሚፈቅድላቸው ሰዎች ካልሆኑ በቀር
ሰጭ፤ ከሞተ በኋላ በቁም ያደረገው ስጦታ እንዲፈርስ ለመጠየቅ አይቻልም፡፡

ቊ 2442፡፡ ስሕተት ወይም ተንኰል፡፡

(1) በመሳሳት የተደረገ የኑዛዜ ቃል እንዲሻር ሕግ በሚፈቅደው ምክንያት ካልሆነ በቀር የሰጭ ወራሾች በሰጭ ስሕተት ምክንያት ስጦታው
እንዲሻር ጥያቄ ለማቅረብ አይችሉም፡፡

(2) የሰጪው ወራሾች በተደረገው ስጦታ ተንኰል አለበት በማለት ስጦታው እንዲሻር ለመጠየቅ አይችሉም፡፡

(3) ስጦታው ስሕተት ወይም ተንኰል ያለበት ነው በማለት ሰጪው በሕይወቱ ሳለ ስጦታው እንዲሻር ክስ አቅርቦ እንደሆነ ግን ወራሾቹ
ክሱን ለመቀጠል ይችላሉ፡፡

ቊ 2443፡፡ የስጦታው ሥርዐት ፎርም (1) የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡


በማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ መብትን የሚሰጥ ስጦታ በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ አሠራር ዐይነት ካልተደረገ
ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2444፡፡ (2) የሚንቀሳቀሱ ግዙፎች ንብረቶችና ለአምጪው የሚከፈሉ፣ ሰነዶች፡፡

(1) ግዙፎች የሆኑ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችና፤ ለአምጪው የሚከፈሉ ሰነዶች፤ እጅ በጅ በሚደረግ ማስተላለፍ ብቻ ሊሰጡ ይቻላል፡፡

(2) ወይም ለማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ፤ አስፈላጊ የሆነውን ሥርዐት ሞልቶ ሊሰጡ ይቻላል፡፡

ቊ 2445፡፡ (3) ሌሎች መብቶችና የገንዘብ መጠየቂያ መብቶች፡፡

(1) ሌሎች መብቶችን ወይም የገንዘብ መጠየቂያ መብቶችን፤ በዋጋ ስለማስተላለፍ በታዘዘው ሥርዐት ፎርም መሠረት ሊሰጡ ይቻላል፡፡

(2) ተቀባዩ ያለበትን ዕዳ በመተው ስጦታ ሊደረግ ይቻላል፡፡

(3) ሰጭ ከሦስተኛ ወገን ጋራ ለሌላ ሰው ጥቅም እንዲሰጥ የተዋዋለበትን የውል ስምምነት ለስጦታ ተቀባይ በመስጠት ስጦታ ለማድረግ
ይቻላል፡፡
ቊ 2446፡፡ የተሰወረ ስጦታ፡፡

(1) ስጦታን ዋጋ የተቀበሉበት ዐይነት አድርጎ ለመስጠት ይቻላል፡፡

(2) ስለ ስጦታዎች የተወሰኑት መሠረታውያን ደንቦች በስውር በተደረጉ ስጦታዎች ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 2447፡፡ ማስረጃ፡፡

(1) ስጦታ አለ የሚለው ሰው ስጦታ መኖሩን ማስረዳት አለበት፡፡

(2) ግዙፍ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ወይም ለአምጪው የሚሰጡ ሰነዶችን ይዞ መገኘት የነዚህ ነገሮች ይዞታ የሚያሻማ ምክንያት
የሌለበት ካልሆነ በቀር ይዞታው ስጦታ መኖሩን አያረጋግጥም፡፡
ቊ 2448፡፡ በውለታ ቢስነት ምክንያት ስጦታን ስለ መሻር፡፡
1 ሰጪው የሚያቀርበው ክስ፡፡
(1) ስጦታ ተቀባዩ ሟችን ለመውረስ የማይገባ የሚያደርግ ወንጀል በሰጭ ላይ በመሥራት ውለታ ቢስ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ ማናቸውም
ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ቢኖርም እንኳ ስጦታው ሊሻር ይቻላል፡፡

(2) ተቀባዩ ያደረገውን ውለታ ቢስነት ሰጪም ምሕረት አድርጎለት እንደሆነ ስጦታውን ለመሻር አይቻልም፡፡

(3) ሰጪው ያደረገውን ስጦታ ለመሻር፤ የሚችልበትን ምክንያት ካወቀ በኋላ፤ ያደረገለትን ስጦታ የመሻር አሳቡን በአንድ ዓመት ጊዜ
ውስጥ ለተቀባዩ ያላስታወቀው እንደሆነ ማናቸውም ተቃራኒ የሚሆን አስረጅ ቢኖር እንኳ ይቅርታ እንደ አደረገለት ይገመታል፡፡

ቊ 2449፡፡ የስጦታ አድራጊው ወራሾች ስለሚያቀርቡት ክስ፡፡


የሰጪው ወራሾች፤ አውራሻቸው ያደረገውን ስጦታ እንዲሻር ለመጠየቅ የሚችሉት፤
(ሀ) ሰጪው በሕይወቱ ሳለ ለተቀባዩ ያደረገለትን ስጦታ የመሻር አሳቡን በማያሻማ አነጋገር አስታውቆት እንደሆነ፤

(ለ) ተቀባዩ ሰጪውን ሆነ ብሎ እንዲሞት አድርጎ እንደሆነ፤

(ሐ) የውለታ ቢስነት ሥራ፤ ሰጪው ከሞተ በኋላ ተሠርቶ እንደሆነ፤

(መ) ሰጪው በስጦታ መሻር መብቱ እንዳይሠራበት ስጦታ ተቀባዩ ከልክሎ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2450፡፡ የልጅ መወለድ፡፡


በተደረገው የስጦታ ውል ውስጥ ተቃራኒ የሚሆን ቃል ከሌለ በቀር፤ ስጦታ ከተደረገ በኋላ ልጅ በመወለዱ ምክንያት ስጦታውን ለመሻር
አይቻልም፡፡
ቊ 2451፡፡ የሚሰጠው ነገር፡፡

(1) ስጦታ የሚደረገው፤ ስጦታው በተደረገበት ቀን የሰጪው ገንዘብ ከሆነ ንብረት ላይ ብቻ ነው፡፡

(2) ስጦታው ገና ወደፊት የሚገኙትን ንብረቶች የሚመለከት በሚሆንበት መጠን ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 2452 ፡፡ ክርክር ያለበት ሀብት፡፡


ስጦታው በተደረገበት ጊዜ የተሰጠው ንብረት ክርክር ያለበት የሆነ እንደሆነ በእንደዚህ ያለው ሀብት ላይ የተደረገው ስጦታ ፍርስ ነው፡፡
ቊ 2453፡፡ አላባን ለራስ ጠብቆ ስለሚደረግ ስጦታ፡፡
ሰጪው የሰጣቸውን ንብረቶች አላባውን ለራሱ የተጠበቀ ለማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 2454፡፡ በየጊዜው ስለሚደረጉ ስጦታዎች፡፡
በግልጽ የተነገረ ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር፤ ስጦታ በየጊዜው የሚሰጥ ነገር የሆነ እንደሆነ፤ ሰጪው ሲሞት ይቋረጣል፡፡
ቊ 2455፡፡ ገደብ ወይም ግዴታ፡፡

(1) ስጦታው ገደብ ያለበት ወይም ግዴታ የተጣለበት ሊሆን ይችላል፡፡

(2) በኑዛዜ ለሚሰጡ ነገሮች ስለ ገደብ ወይም ስለ ግዴታ በውርስ አንቀጽ ውስጥ የተሠራው ደንብ በቁም ስጦታዎችም ላይ ለተደረገ ገደብ
ወይም ግዴታ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 2456፡፡ የማይቻል ወይም ሕገ ወጥ የሆነ ገደብ ወይም ግዴታ፡፡


(1) ሰጪው ስጦታውን ገደብ ወይም ግዴታ ያለበት አድርጎት እንደሆነና ገደቡ ወይም ግዴታው የማይቻል ወይም ለሕግ ወይም ለመልካም
ጠባይ ተቃራኒ የሆነ እንደሆነ እንደልተጻፈ ይቈጠራል፡፡

(2) ገደቡ ወይም ግዴታው እንዳልተጻፈ ሆኖ የሚቈጠር ሲሆን ስጦታውን ያደረገበት ዋና ምክንያት ገደቡ ወይም ግዴታው ቢሆንም እንኳ
ስጦታው አይፈርስም፡፡

ቊ 2457፡፡ በጋብቻ ምክንያት የሚደረጉ ስጦታዎች፡፡

(1) በጋብቻ ምክንያት ወደፊት ለሚጋቡ ዕጮኞች የሚደረጉ ስጦታዎች ጋብቻው እስቲፈጸም ድረስ ታግዶ የሚቈይ ውለታ ያሉባቸው
ስጦታዎች ሆነው የቈያሉ፡፡

(2) በጋብቻ ምክንያት ለዕጮኞቹ አባት ወይም እናት ወይም ለሌሎቹ ዘመዶቻቸው የተደረጉትም ስጦታዎች ጋብቻው እስቲፈጸም ድረስ
ታግዶ የሚቈይ ውለታ ያለባቸው ስጦታዎች ሆነው ይቈያሉ፡፡

(3) የጋብቻው መሰረዝ ወይም መፍረስ ውጤት ስጦታዎችን ስለሚመለከተው ጒዳይ በዚህ ሕግ ስለ ሥጋ ዝምድና ስለ ጋብቻ ስጦታዎችን
ስለሚመለከተው ጒዳይ (ዝምድና) በተነገረው አንቀጽ መሠረት ይወሰናል፡፡

ቊ 2458፡፡ ለሰጭ ቀለብ የመስጠት ግዴታ፡፡

(1) በግልጽ የተነገረ የውል ቃል ባይኖርም ሰጪው በድኅነት ላይ ወድቆ ሲገኝ ስጦታ ተቀባዩ ለሰጭ የቀለብ መስጠት ግዴታ አለበት፡፡

(2) ሰጭ እንደመረጠ ቀለቡን፤ እርሱ ስጦታ ካደረገለት ሰው ወይም ሕግ ለርሱ ቀለብ ለመስጠት ግዴታ አለባቸው ከሚላቸው ሰዎች ላይ
ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) ለሰጭ ቀለቡን የሰጡ ሰዎች የሰጡትን ቀለብ፤ ስጦታ የተደረገለት ሰው እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቊ 2459፡፡ ዕዳ የመክፈል ግዴታ፡፡


ስጦታ ተቀባይ የሰጪውን ዕዳ እንዲከፍል ውል ተደርጎ እንደሆነ ስጦታ ተቀባዩ ስለ ሰጭው መክፈል ያለበት የዕዳው ልክ ተወስኖ የታወቀ
ካልሆነ በቀር ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 2460፡፡ ስጦታው ለሰጭ እንዲመለስ ስለሚደረግ ውል፡፡

(1) ከሰጭ አስቀድሞ ስጦታ ተቀባይ የሞተ እንደሆነ ሰጭ የሰጣቸው ነገሮች እንዲመለሱለት በስጦታው ውስጥ የውል ቃል ለማግባት
ይችላል፡፡
(2) በግልጽ የተነገረ ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር ተቀባዩ ወደታች የሚቈጠሩ ተወላጆች ትቶ የሞተ እንደሆነ ስጦታዎቹ
እንዲመለሱ የመጠየቅ መብት ሊሠራበት አይቻልም፡፡

(3) ስጦታ የተደረገው ስጦታዎቹ ለሰጭ እንዲመለሱ ውል ከማድረግ ጋራ የሆነ እንደሆነ የተሰጡት ንብረቶች እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ
የሚያደርግ የውል ቃል ውጤት አለው፤ የዚህም ዐይነት ውል የሚፈጸምበትን ደንብ የሚከተል ይሆናል፡፡

ቊ 2461፡፡ ምትክነት፡፡

(1) ተቀባይ የተሰጡትን ንብረቶች ጠብቆ አቈይቶ እሱ ሲሞት ወይም አንድ የተወሰነ ጊዜ ሲያልፍ ወይም አንድ ሁኔታ ሲፈጸም በስጦታ
የተቀበላቸውን ንብረቶች ለሚተኩ ለአንድ ወይም ለብዙ ሰዎች ማስተላለፍ አለበት የሚል ቃል ሰጭ በስጦታው ውል ውስጥ ማግባትና
በስጦታ ተቀባይ የሚተኩ ሰዎች እንዲቀሩ ለማድረግ ይችላል፡፡

(2) እንደዚህ ያለው የውል ቃል በኑዛዜ የተነገረውን ምትክነት ስለሚመለከት ነገር በዚህ ሕግ በተጻፉት ሥርዐቶች ፎርማሊቴዎች መንገድና
ግዴታዎች መሠረት ውጤት ይኖረዋል፡፡

ቊ 2462፡፡ ግዴታ ስለ መፈጸም፡፡

(1) ሰጭ በስጦታ ውስጥ ያለው ግዴታ ያለበት ውል እንዲፈጸም ለማስገደድ ይችላል፡፡


(2) ውል የተደረገለት ሰው ወይም ግዴታውን እንዲያስፈጽምለት ሰጭ የመረጠው ሰው ወይም የሰጪው ወራሾች ይህ የማስገደድ መብት
አላቸው፡
(3) ተቀባዩ ግዴታውን መፈጸም ያለበት ስጦታው በተደረገለት ቀን በነበረው ግምት መጠን ብቻ ነው፡፡

ቊ 2463፡፡ ለበጎ አድራጎት ወይም ለሕዝብ አገልግሎት ድርጅት ስለሚደረግ ስጦታና ስለ አደራ ንብረት ጠባቂ (ፊዴዩኮሚ)፡፡
በሕግ የሰው መብት ስለ ተሰጣቸው ድርጅቶችና ለልዩ አገልግሎት ስለ ተመደቡ ንብረቶች በሚለው አንቀጽ በተነገሩት ድንጋጌዎች
መሠረት ሰጪው ለበጎ አድራጎት ወይም ለሕዝብ አገልግሎት ድርጅት የሚደረጉ ስጦታዎችንና የአደራ ንብረት ጥበቃን ለማቋቋም
ይችላል፡፡
ቊ 2464፡፡ ግዴታን ባለመፈጸም ምክንያት የስጦታው መሻር፡፡

(1) ተቀባይ፤ ግዴታዎቹን ባመፈጸሙ ምክንያት፤ ከዚህ በላይ በተጻፈው ቊጥር በተመለከቱት ሰዎች ጥያቄ፤ ስጦታው ሊሻር ይችላል፡፡

(2) ተቀባይ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ስጦታው ይሻራል ብሎ ሰጭ በስጦታው ውል በግልጽ ያላመለከተና የስጦታውም መሻር
የሚያመጣውን ነገር የወሰነ ካልሆነ በቀር በሰጪው ወራሾች ጠያቂነት ስጦታው ሊፈርስ አይችልም፡፡

(3) የተደረገውን ስጦታ ለመሻር ይቻላል ተብሎ ፍርድን ስለ መስጠት የሚነገሩ ምክንያቶችና የስጦታው መሻር ውጤቶች፤ ውሎችን
ስለመሻርና ስለ መሰረዝ በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ በተነገሩት ደንቦች መሠረት ይፈጸማል፡፡

ቊ 2465፡፡ መድን ስለ መሆን፡፡

(1) ሰጭ ያደረገውን ስጦታ የኔ ነው ባይ ሲመጣ መድን ለመሆን በግልጽ ውል ገብቶ እንደሆነ፤ ወይም የተሰጠው ነገር የኔ ነው ባይ
የመጣው በሰጭ ተንኰል ወይም በሰጭ የግል ሥራ ምክንያት የሆነ እንደሆነ ስጦታ ላደረጉለት ሰው መድን ይሆናል፡፡

(2) ስጦታውን አስለቃቂ ሲመጣ የሰጭ መድንነት ነገር በሺያጭ ጊዜ ስለ መድን በተሠራው በዚህ ሕግ ደንቦች መሠረት ይፈጸማል፡፡

(3) ስጦታ የተደረገለት ሰው የተደረገለትን ስጦታ የኔ ነው ባይ ያስለቀቀው እንደሆነ ከተሰጠው ንብረት ላይ አላባ አግኝቶ በአላባው
የተቻቻለ ካልሆነ በቀር በስጦታው ምክንያት ያደረገው ወጪ በነዚህ ደንቦች እንዲመለስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2466፡፡ ስለ ጒድለት የሚሰጥ የመድንነት ቃል፡፡

(1) ሰጭ በተሰጠው ነገር ጒድለት አላፊ መድን ሊሆን በግልጽ ቃል ካልገባ ወይም አንድ የተንኰል ሥራ ካልሠራ በቀር ስለ ተባለው
ጒድለት አላፊ መድን አይሆንም፡፡

(2) እንደዚህም በሆነ ጊዜ የጒድለቱ መድንነት ነገር ስለ ሽያጭ ውል በዚህ ሕግ የተነገረው ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ (ከቊ 22)(6 እስከ
23)9)፡፡

(3) በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ስጦታ ተቀባዩ በስጦታ የወሰደው ሀብት ጒድለት ያለበት በመሆኑ ምክንያት ያደረሰበትን ጉዳት ከዚሁ
ሀብት ላይ ያገኘው አበል ያልተካለት ሲሆን በነዚሁ ደንቦች መሠረት በስጦታ የወሰደው ነገር ያደረሰበት ኪሣራ እንዲከፈለው ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
ቊ 2467፡፡ ገንዘብ ጠያቂ ስለሚያቀርበው ክስ፡፡

(1) ከሰጪው ላይ ገንዘብ ጠያቂ የሆኑ ሰዎች መብታቸውን ለመጉዳት ሰጪው በተንኰል ያደረገውን ስጦታ ለመቃወም ይችላሉ፡፡

(2) ይህን ስለሚመለከተው ነገር በዚህ ሕግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚለው አንቀጽ የተጻፉት ደንቦች ይፈጸማሉ፡፡

ቊ 2468፡፡ የመጦሪያ መብት ስላላቸው ሰዎች (1) መሠረቱ፡፡


ከሰጪው ውርስ ላይ የመጦሪያ መብት ያላቸው ሰዎች ይህ የውርስ ሀብት የማይበቃ ሆኖ ሲገኝ ሰጪው ከመሞቱ ከሦስት ዓመት በፊት
የሟቹን ስጦታ ከተቀበሉ ሰዎች ላይ የመጦሪያ መብታቸውን ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቊ 2469፡፡ (2) የሚገመተው ዋጋ፡፡


(1) ስጦታ የተደረገለት ሰው የሚገደደው በተቀበላቸው ንብረቶች ዋጋ መጠን ብቻ ነው፡፡

(2) ግምቱም የሚደረገው ስጦታ በተደረገበት ቀን በነበረው ዋጋ ነው፡፡

(3) አስፈላጊ ሲሆንም በስጦታ ተቀባዩ ላይ የተጣሉት ግዴታዎች ዋጋ ተቀናሽ ይሆናል፡፡

ቊ 2470፡፡ ለብዙ ሰዎች የተደረጉ ስጦታዎች፡፡

(1) ሟቹ ከመሞቱ አስቀድሞ ባለፉት ሦስት ዓመቶች ውስጥ፤ ለብዙ ሰዎች ስጦታዎች አድርጎ እንደሆነ፤ ስጦታ የተደረገላቸው ሰዎች
እያንዳንዱ፤ በየተሰጧቸው ንብረቶች መጠን፤ የጡረታ መብት ላላቸው ሰዎች የሚከፈለውን ገንዘብ ማውጣት አለባቸው፡፡

(2) በልዩ ልዩ የተደረጉት ስጦታዎች እየአንዳንዳቸው የተሰጡበት ጊዜ በግምት ውስጥ አይገባም፡፡


ምዕራፍ 4፡፡
የሚያልቅ ነገር ብድር፡፡
ቊ 2471፡፡ (1) ትርጓሜ፡፡
የሚያልቅ ነገር ብድር ማለት ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን አበዳሪው፤ ሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ነገር በዐይነቱ ለመመለስ ተገዳጅ
በማድረግ ገንዘብ ወይም በማገልገል የሚያልፍ ሌላ ነገር ለተበዳሪው ለመስጠትና ሀብትነቱን ለማስተላለፍ የሚገደድበት ውል ነው፡፡

ቊ 2472፡፡ (2) የብድር ማስረጃ፡፡

(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ $500 የኢትዮጵያ ብር በላይ ሲሆን የብድሩን ውል በጽሑፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል
ወይም መሐላ ካልሆነ በቀር ለማስረዳት አይቻልም፡፡

(2) ለብድር ውል ማናቸውም ሌላ ዐይነት ማስረጃ ለማቅረብ አይቻልም፡፡

(3) እንደዚሁም ከ$500 የኢትዮጵያ ብር የበለጠ ገንዘብ የመከፈል ነገር በዚህ ዐይነት ይፈጸማል፡፡

ቊ 2473፡፡ (3) በባለ ባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ስላሉ ግንኙነቶች፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች የተነገረው ድንጋጌ ዋነኛው ሥራቸው የባንክ ሥራ በሆነ ሰዎች ወይም ማኅበሮችና በደንበኞቻቸው
መካከል ያለውን ግንኙነት በሚመለከት ጒዳይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

(2) የነዚህ ሰዎች መካከል ባለው ግንኙነት የብድርን ውል ወይም የተበደረውን ገንዘብ መልሶ መክፈልን በምስክሮች ወይም በአእምሮ
ግምት ማስረጃ ለማስረዳት ይቻላል፡፡
ቊ 2 ሺ 474፡፡ የአበዳሪው ግዴታ፡፡
(1) በሽያጭ ውል ምዕራፍ የተነገሩት፤ የሻጭን ግዴታዎች የሚመለከቱ ደንቦች በአበዳሪ ላይ የሚፈጸሙ ይሆናሉ፡፡

(2) ነገር ግን ብድሩ እንዲያው ያለ ዋጋ ተደርጎ እንደሆነ፤ የአበዳሪው ግዴታዎች በቀላሉ የሚገመቱ ይሆናሉ፡፡

(3) በዚህ ጊዜ፤ ባበደረው ነገር ላይ ለሚገኘው እርሱ ለሚያውቀው ጒድለት ብቻ ካልሆነ ዋቢ መሆን የለበትም፡፡

ቊ 2475፡፡ ተበዳሪው ዕዳውን ለመክፈል ስላለመቻሉ፡፡

(1) ውሉ ከተደረገ በኋላ ተበዳሪው የመክፈል ችሎታ ማጣት የደረሰበት እንደሆነ፤ አበዳሪው በብድር ሊሰጠው ቃል የገባለትን ነገር
ለመከልከል ይችላል፡፡

(2) ይህ ለመክፈል አለመቻሉ ውሉ ከመደረጉ በፊት ደርሶ እንደሆነና አበዳሪው ውሉ ከተደረገ በኋላ ነገሩን ቢያውቀውም እንኳን
አልሰጥም የማለት መብት አለው፡፡

ቊ 2476፡፡ ስለ ወጪና የዕቃው ጥበቃ፡፡


(1) ስለ ወጪና ስለ ዕቃው አጠባበቅ ተዋዋዮቹ ያሉባቸውን ግዴታዎች የሚመለከቱት፤ በሽያጭ ውል ምዕራፍ የተጻፉት ደንቦች በሚያልቅ
ነገር ብድርም ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

(2) በዚህ ነገር ባበዳሪው ላይ የሻጭ ግዴታዎች በተበዳሪው ላይ የገዢው ግዴታዎች ይፈጸማሉ፡፡

ቊ 2477፡፡ ሊደርስ የሚችል አደጋ፡፡

(1) ተበዳሪው ለተበደረው ነገር ባለሀብት ይሆናል፡፡

(2) የተበደረው ነገር የጠፋ ወይም የተበላሸ እንደሆነ ከተቀበለበት ጊዜ አንሥቶ በነገሩ የሚደርሰውን የጥፋት ወይም የመበላሸት አደጋ
የሚችል እርሱ ይሆናል፡፡

ቊ 2478፡፡ ወለድ፡፡ (1) የሚከፈልበት ጊዜ፡፡


ተበዳሪው ወለድ እንዲከፍል የውል ቃል ከሌለ በቀር ላበዳሪው ወለድ መክፈል የለበትም፡፡
ቊ 2479፡፡ (2) የወለዱ ልክ፡፡

(1) ተዋዋዮቹ በወለድ የሚከፈለውን ገንዘብ በዓመት በመቶ ከዐሥራ ሁለት በላይ እንዲሆን ለመዋዋል አይችሉም፡፡

(2) ብድሩ በወለድ እንዲሆን ውል ቢኖር በወለድ የሚከፈለው ገንዘብ ግን ከፍተኛ እንዲሆን በጽሑፍ የተደረገ ውል የሌለ እንደሆነ
ተበዳሪው ዘጠኝ በመቶ በዓመት ወለድ መክፈል ይገባዋል፡፡

(3) በወለድ የሚከፈለው ገንዘብ በመቶ ከአሥራ ሁለት በላይ በዓመት እንዲሆን በጽሑፍ የተደረገ ውል ቢኖር እንኳ ተበዳሪው፤ በመቶ
ዘጠኝ ብቻ በዓመት ወለድ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2480፡፡ (3) የመክፈል አስገዳጅነት፡፡


ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር፤ ወለዱ ውሉ ከተደረገበት አንሥቶ በሚቈጠር በየዓመቱ መጨረሻ መከፈል አለበት፡፡
ቊ 2481፡፡ የወለድ ወለድ፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ወለዱ ከዋናው ገንዘብ ጋራ ተጨማሪ ሆኖ ወለድ ይወልዳል ብለው አስቀድመው ለመዋዋል አይችሉም፡፡

(2) ስለ ተመላላሽ ሒሳብ የወለድ ወለድ አስተሳሰብ ደንቦች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2482፡፡ የብድር መመለሻ ጊዜ፡፡ (1) በውሉ የተወሰነ ጊዜ፡፡

(1) ተበዳሪው፤ የተበደረውን ነገር በብዛቱና በዐይነቱ ልክ፤ በውሉ በተወሰነው ጊዜ ለመመለስ ይገደዳል፡፡

(2) ብድሩ በወለድ ያልሆነ እንደሆነ፤ ተበዳሪው የተበደረውን ለመመለስ ማሰቡን ከአንድ ወር በፊት ላበዳሪው አስታውቆ ከተወሰነው ጊዜ
በፊት ሊመልስለት ይችላል፡፡

(3) ከዘጠኝ በመቶ በላይ በሆነ ወለድ ተደርጎ እንደሆነ፤ ምንም እንኳ ማናቸውም የውል ቃል ቢኖር ከዚህ በላይ እንደተባለው ይፈጸማል፡፡

ቊ 2 ሺ 483፡፡ (2) የተወሰነ ጊዜ አለመኖር፡፡

(1) ብድሩ የሚመለስበት አንዳችም ጊዜ ያልተወሰነ እንደሆነ፤ አበዳሪው መልስልኝ ሲል ከጠየቀበት ቀን አንሥቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
ተበዳሪው የተበደረውን ነገር መመለስ አለበት፡፡

(2) እንዲሁም በሆነ ጊዜ ተበዳሪው የተበደረውን ነገር ላበዳሪው ለመመለስ አሳቡን ከአንድ ወር በፊት ካስታወቀ በኋላ ሊመልስለት
ይችላል፡፡
ቊ 2484፡፡ ልዩ የሆነ የውል ቃል፡፡
ተበዳሪው እንደተቻለው፤ ወይም ገንዘብ እንዳገኘ ሊመልስ ውል ያለ እንደሆነ፤ ዳኞቹ የነገሩን ሁኔታ በማመዛዘን ከስድስት ወር በላይ
የማያልፍ የሚከፍልበትን ጊዜ ሊወስኑለት ይችላሉ፡፡

ቊ 2485፡፡ የሚመለሰው ነገር፤ (1) በኢትዮጵያ ብር፡፡

(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ በኢትዮጵያ ብር የሚታሰብ እንደሆነ፤ ተበዳሪው የተበደረውን ገንዘብ በሚከፍልበት ቀን የሕግ መገባያያ ሆኖ
የሚገኘውን ኖትም ሆነ ዝርዝር በተበደረው መጠን በመክፈል ነፃ ይሆናል፡፡

(2) ተበዳሪው ገንዘቡ በብድር ከተሰጠበት ጊዜ ወዲህ በዚህ ገንዘብ ግዥ ላይ የደረሰውን የዋጋ መለዋወጥ ማሰብ የለበትም፡፡

(3) እንዲሁም ገንዘቡ በብድር ከተሰጠበት ጊዜ ወዲህ ስለ ኢትዮጵያ ብር የተሰጠውን ትርጓሜ መለወጥ ማሰብ የለበትም፡፡

ቊ 2486፡፡ (2) ብድሩ በውጭ አገር ገንዘብ ስለ መሆኑ፡፡

(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ በውጭ አገር ገንዘብ የተጻፈ ሲሆን፤ ተበዳሪው የተበደረውን ገንዘብ በሚከፍልበት ቀን፤ በተባለው ገንዘብ
አገር ውስጥ የሕግ መገበያያ ሆኖ የሚገኘውን ያንኑ የውጭ አገር ገንዘብ በተበደረው ቊጥር ልክ ኖት ዝርዝር በመስጠት ነፃ ይሆናል፡፡

(2) የሚፈቅድም እንደሆነ በሚከፍልበት ቀን ከዚህ ከተበደረው ገንዘብ ጋራ እኩል የሚቈጠር የኢትዮጵያ ብር በመክፈል ነፃ ይሆናል፡፡

ቊ 2487፡፡ (3) የንግድ ዕቃዎች ወይም እንክብል ገንዘቦች፡፡

(1) በብድር የተሰጡ ነገሮች ወይም እንክብሎች ወይም ለምግብ የሚሆኑ ነገሮች ወይም ሸቀጦች ሲሆኑ ተበዳሪው በተበደረው ልክ
ብዛቱንና ዐይነቱን በመክፈል ነፃ ይሆናል፡፡

(2) ከብድሩ ጊዜ ወዲህ የሆነው የነዚህ የእንክብሎች ለምግብ የሚሆኑ ነገሮችና የሸቀጦች ዋጋ መለዋወጥ ከግምት አይገባም፡፡

(3) ተበዳሪው፤ የተበደረውን ነገር ለመመለስ የማይቻለው ሲሆን፤ ወይም በርሱ ጥፋት ምክንያት መመለሱ እጅግ አስቸጋሪ ሲሆንበት፤
ዕዳው በሚከፈልበት ቀንና ቦታ ላይ (የተገመተ) የብድሩን ግምት ላበዳሪው በመስጠት ከዕዳው ነፃ ይሆናል፡፡

ቊ 2488፡፡ የተበዳሪው መዘግየት (1) ውሉን ማፍረስ፡፡

(1) ተበዳሪው አንድ ላይ ሲታሰብ ሁለት ጊዜ በማከታተል የተዘለለው ወለድ የዋና ገንዘብ ዐሥረኛ ካልሆነ በቀር አበዳሪው ወለድ
ሳይከፈለኝ ቀረ በማለት በብድር የሰጠው ነገር እንዲመለስለት ለማስገደድ አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም በብድር የተሰጠው ዋናው ገንዘብ በየጊዜው በከፊል እንዲመለስ ስምምነት ሲኖር ከዚህ በላይ የተነገረው ደንብ ተፈጻሚ
ይሆናል፡፡

(3) ለዚህ ተቃራኒ የሚሆን ማንኛቸውም የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2489፡፡ ኪሣራ፡፡

(1) ተበዳሪው የተበደረውን ነገር ከመመለስ ወይም የሚገባውን ወለድ ከመክፈል የዘገየ እንደሆነ፤ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚል አንቀጽ
በተሰጡት ውሳኔዎች መሠረት ጊዜ በማስተላለፍ የሚከፈለውን ወለድ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡

(2) ይህን ግዴታ የሚያከብድ ማንኛቸውም የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡


ምዕራፍ 5፡፡
መጦሪያን ስለ ማቋቋም፡፡
ቊ 2490፡፡ ትርጓሜ፡፡

(1) መጦሪያን የማቋቋም ውል ማለት አንድ ንብረትን በለውጥ በማስተላለፍ ወይም አንድ ዋና ገንዘብ በመተው ይህን ያህል የሚባል
ገንዘብን ወይም ብዛታቸው ይህን ያህል የሚሆኑ የሚያልቁ ዕቃዎችን በየጊዜው ለማስከፈል፤ የማስገደድ መብትን አንዱ ወገን ለአንዱ
የሚሰጥበት ውል ነው፡፡
(2 ) የመጦሪያ የውል ቃል በስጦታ ላይ እንደሚደረግ ግዴታ ሆኖ ስምምነት ሊደረግበት ይቻላል፡፡
ቊ 2 ሺ 491፡፡ ዕዳውን ስለሚያመለክት ሰነድ፡፡
(1) ሰነዱን በእጁ ከያዘ ዘጠኝ ዓመት ያለፈ እንደሆነ ዕዳ አስከፋዩ አዲስ ሰነድ እንዲሰጠው ዕዳ ከፋዩን ሊያስገድድ ይችላል፡፡

(2) አዲሱ ሰነድ የሚዘጋጀው በዕዳ አስከፋይ ኪሣራ ነው፡፡

ቊ 2492፡፡ ዘለዓለም ስለሚኖር መጦሪያና እስከ ዕድሜ ልክ ስለሚቈይ መጦሪያ፡፡


መጦሪያ ለዘለዓለም ወይም እስከ ዕድሜ ልክ ሆኖ መቋቋም ይችላል፡፡
ቊ 2493፡፡ መከፈል ያለበትን ገንዘብ ስለ መክፈል፡፡

(1) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ የመጦሪያ ገንዘብ ውሉ ከተፈጸመበት አንሥቶ በየዓመቱ መጨረሻ ይከፈላል፡፡

(2) ተዋዋዮቹ ያልተከፈለ የመጦሪያ ገንዘብ ወለድ ይሰጣል ብለው አስቀድመው መስማማት አይችሉም፡፡

ቊ 2494፡፡ ወደ ብድር ደንቦች ስለ መምራት፡፡


ከዚህ በላይ ባለው ምዕራፍ የተደነገጉት ውሳኔዎች በመጦሪያ ማቋቋም ውል ላይም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ቊ 2495፡፡ የተጠበቁ ደንቦች፡፡
በመንግሥት ወይም በሌሎች በሕዝብ አገልግሎት መሥሪያ ቤቶች፤ ስለ መጦሪያዎች የተመለከቱ ደንቦች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡
ክፍል 1፡፡
ለዘለዓለም ስለሚኖር መጦሪያ፡፡
ቊ 2496፡፡ መልሶ ስለ መግዛት ችሎታ (1) መሠረቱ፡፡
ምንም እንኳ ተቃራኒ የውል ቃል ቢኖር ለዘለዓለም የተቋቋመውን መጦሪያ ዕዳ ከፋይ እንደገና ሊገዛው ይችላል፡፡
ቊ 2497፡፡ (2) የሚቻሉ ውሳኔዎች፡፡

(1) ሆኖም ዕዳ ጠያቂው ከመሞቱ በፊት ወይም ዐሥር ዓመት ከማይበልጥ ጊዜ በፊት መልሶ መግዛት አይቻልም ብለው ተዋዋዮቹ
ስምምነት ለማድረግ ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም የአንድ ዓመት ማስጠንቀቂያ ለዕዳ ጠያቂው ካልተሰጠው በቀር መልሶ መግዛት የማይቻል መሆኑን ተዋዋዮቹ ለመዋዋል
ይችላሉ፡፡
(3) ከዚህ የበለጡ ጊዜዎች በውሉ ተጽፈው እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ ባሉት (ኀይለ ቃሎች) የተለከቱት ከፍተኞች የሆኑ ጊዜዎች
ይተኩባቸዋል፡፡
ቊ 2498፡፡ መልሶ የመግዛት ግዴታ፡፡
ለዘለዓለም የተቋቋመን መጦሪያ ዕዳ ከፋይ መልሶ እንዲገዛ የሚገደደው፤
(ሀ) ሁለት ዓመት ግዴታዎቹን ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ፤

(ለ) ለዕዳ ጠያቂው በውሉ ተስፋ የተሰጡትን ማረጋገጫዎች ወይም እነዚህ ከሌሉ የሚገዳደሩ አዲስ ማረጋገጫዎች ያልሰጠ እንደሆነ፤

(ሐ) ባለዕዳው የመክፈል ችሎታ ማጣቱ በፍርድ የተረጋገጠ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 2499፡፡ መልሶ ሲገዛ የሚሰጠው ዋና ገንዘብ፡፡


(1) መጦሪያውን መልሶ በገዛ ጊዜ ዕዳ ከፋዩ (ስለ ወለድ) በሕግ በተወሰነው ወለድ መሠረት የመጦሪያውን ዋና ገንዘብ የሚገዳደር ገንዘብ
ለዕዳ ጠያቂው መክፈል አለበት፡፡

(2) ስለዚህ ጒዳይ የዕዳ ከፋዩን ሁኔታ የሚያከብድ የውል ቃል ሁሉ ፈራሽ ነው፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
እስከ ዕድሜ ልክ ስለሚቈይ መጦሪያ፡፡
ቊ 2500፡፡ መጦሪያው የሚቈይበት ጊዜ፡፡ (1) የአንድ ሰው ዕድሜ፡፡

(1) እስከ ዕድሜ ልክ የሚቈይ መጦሪያ በዕዳ ጠያቂው ዕድሜ በዕዳ ከፋዩ ወይም በአንድ ሦስተኛ ወገን ዕድሜ ልክ መቋቋም ይችላል፡፡

(2) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በዕዳ ጠያቂው ዕድሜ ልክ እንደተቋቋመ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2501፡፡ (2) የብዙ ሰዎች ዕድሜ፡፡

(1) ዕድሜ ልክ የሚቈይ መጦሪያ በብዙ ሰዎች ዕድሜ ልክ ለመቋቋም ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ዕዳ ጠያቂው የሞተ እንደሆነ በሌላ ሰው ላይ ይተላለፋል የሚል የውል ቃል ማግባት ይቻላል፡፡

ቊ 2502፡፡ የሚፈርስበት ሁኔታ፡፡

(1) ጡረታው የተቋቋመባቸው ሰዎች የመጦሪያ ውል በተቋቋመበት ቀን አንዳቸውም በሕይወት የሌሉ እንደሆነ መጦሪያውን
የሚያቋቁመው ውል ፈራሽ ነው፡፡

(2) መጦሪያው ለሌላ ሰው ይተላለፋል የሚል ቃል ያለ እንደሆነ የመጦሪያው ውል በሚቋቋምበት ቀን ይተላለፍለታል የተባለው ሰውዬው
በሕይወት ከሌለ መጦሪያውን የሚያስተላልፈው የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2503፡፡ ስለ ማስተላለፍ፡፡
ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በዕዳ ከፋዩ ወይም በአንድ ሦስተኛ ወገን ላይ የተቋቋመ መጦሪያ ለዕዳ ጠያቂዎች ወራሾች ይተላለፋል፡፡
ቊ 2504፡፡ ለመጦሪያ ለሚከፈለው ገንዘብ በሕግ ከተወሰነው ወለድ በላይ የሆነ አራጣ፡፡

(1) እስከ ዕድሜ ልክ የሚቈይ መጦሪያ አንድ ዋና ገንዘብን በመክፈል ለውጥ የተቋቋመ እንደሆነ፤ ዕዳ ከፋዩ የሚሰጣቸው ገንዘቦች ከዚህ
ዋና ገንዘብ ከመቶ ሓያ የሚበልጡ ለመሆን አይችሉም፡፡

(2) አንድ ከፍ ያለ ወለድ በጽሑፍ ውል የሌለ እንደሆነ ወይም ከመቶ ኻያ የሚበልጥ ወለድ በስምምነት ተደርጎ እንደሆነ ወለዶቹ
የሚከፈሉት በመቶ ዐሥራ ሁለት ነው፡፡

ቊ 2505፡፡ ስለ ውሉ መፍረስ፡፡
አቋቋሚው ሰው ስለ ውሉ አፈጻጸም በውል ቃል የተነገሩትን ማረጋገጫዎች ያልሰጠው እንደሆነ እስከ ዕድሜ ልክ የሚቈየው መጦሪያ
የተቋቋመለት ሰው፤ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2506፡፡ ገንዘቦችን ስለ አለመክፈል፡፡

(1) የመጦሪያ ገንዘቦችን ያለመክፈል፤ መጦሪያው የተቋቋመለት ሰው ዋናው ገንዘብ እንዲመለስለት ወይም ያስተላለፋቸው ሀብቶች በእጁ
እንዲገቡ ለመጠየቅ አይፈቅድለትም፡፡

(2) የዕዳ ከፋዩን ሀብቶች ማስያዝና ማሸጥ ከሽያጩም ዋጋ ላይ እንዲታዘዝለት ወይም እንዲፈቀድለት ማድረግ፤ ለገንዘቦች ሥራም በቂ
የሚሆን ገንዘብ የመውሰድ መብት አለው፡፡

ቊ 2507፡፡ መልሶ የመግዛት ችሎታ አለመኖር፡፡


(1) ዋናውን ገንዘብ እመልሳለሁ በማለትና የከፈላቸውንም ገንዘቦች በመተው ዕዳ ከፋዩ መጦሪያውን ከመክፈሉ ነፃ ለመውጣት
አይችልም፡፡
(2) የተጠዋሪ ወይም መጦሪያው የተቋቋመባቸው ሰዎች ዕድሜ በሚቈይበት ጊዜ የመጦሪያው አከፋፈል ምንም እንኳ ከፍ ያለ ወጪ
የሚያስፈልገው ቢሆን ዕዳ ከፋዩ መጦሪያውን መስጠት አለበት፡፡

ቊ 2508፡፡ ለመድረስ የሚችል ጉዳት፡፡

(1) እስከ ዕድሜ ልክ የሚሆነው መጦሪያ ለዕዳ ጠያቂው የሚከፈለው መጦሪያ በተቋቋመበት ሰው ዕድሜ ልክ ነው፡፡

(2) ሆኖም አስቀድሞ የሚከፈል ለመሆኑ ስምምነት ያለ እንደሆነ አከፋፈሉ በሚደረግበት ቀን ገንዘቦች ተከፋይ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2509፡፡ መብትን ስለ ማስተላለፍና ስለ መያዝ፡፡

(1) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ ዕዳ ጠያቂው መብቶቹን ለማስተላለፍ ይችላል፡፡

(2) ለአንድ ሦስተኛ ወገን ጥቅም መጦሪያው ያለ ዋጋ የሚያቋቁም ሰው መጦሪያውን በሚአቋቁምበት ጊዜ ከዚሁ ሦስተኛ ሰው ላይ ዕዳ
የሚጠይቁ ሰዎች የመጦሪያውን ገንዘብ ለመያዝ አይችሉም ሲል በውል ቃል ውስጥ ለመጻፍ መብት አለው፡፡

ቊ 2510፡፡ ስለ ገንዘብ ጠያቂነት መብት ማስረጃ፡፡


እስከ ዕድሜ ልክ የሚቈይ የመጦሪያ ዕዳ ጠያቂው በሕይወቱ መኖሩን ወይም መጦሪያ የተቋቋመበት ሰው መኖሩን ማስረጃ ካላቀረበ
ገንዘቦችን ለመጠየቅ አይችልም፡፡

ቊ 2511፡፡ በአሹራንስ መሠረት የሚከፈል መጦሪያ፡፡


እስከ ዕድሜ ልክ የሚቈይ መጦሪያ በአሹራንስ መሠረት የሚከፈል የሆነ እንደሆነ የአሹራንስን ውል የሚመለከቱ ደንቦች እንደተጠበቁ
ናቸው፡፡

አንቀጽ 16፡፡
የሥራዎች አገልግሎት መስጠትን የሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ስለ ሥራ ውል በጠቅላላው፡፡
ቊ 2512፡፡ (1) ትርጓሜ፡፡

የሥራ ውል ማለት ከተዋዋዮቹ ወገን አንዱ፤ ሠራተኛው፤ ለሌላው ወገን ለአሠሪው፤ አንድ ግዙፍነት ያለው ወይም የአእምሮ ሥራ በተወሰነ
ወይም ባልተወሰነ ጊዜ ውስጥ አሠሪው ሊከፍለው በተገደደበት አንድ ደመወዝ በርሱ አገልግሎትና በርሱ መሪነት ሥራውን ለማከናወን
ግዴታ የገባበት ውል ነው፡፡

ቊ 2513፡፡ (2) የመንግሥት ሹማምቶችና ሠራተኞች፡፡

(1) የሕዝብ ባለሥልጣኖች ከሹማምቶች ጋራ ባሏቸው ግንኙነቶች ላይ የዚህ ምዕራፍ ድንጋጌዎች አይፈጸሙባቸውም፡፡

(2) በልዩ ሕጎች ተቃራኒ ውሳኔዎች ከሌለ በቀር ከኢንዱስትሪኤል ወይም ከንግድ ሥራ ማካሄጃዎች ጋራ በመንግሥት ወይም በአስተዳደር
(በኢድሚኒስትራቲብ) ወይም በቴክኒክ ክፍሎቹ መሪነት በሚደረጉ የሥራ ውሎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
ቊ 2514፡፡ (3) የማይነኩ ልዩ ሠራተኞች፡፡

የሠራተኞችን አንዳንድ ልዩ ሁኔታ የሚመለከቱ ልዩ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

ክፍል 1፡፡
ስለ ውሉ አፈጻጸም፡፡
ቊ 2515፡፡ የውል አፈጻጸም፡፡

ለሥራ ውል አፈጻጸም ማናቸውም የተለየ ፎርም አያስፈልገውም፡፡

ቊ 2516፡፡ የኅብረት ስምምነቶች (1) መሠረቱ፡፡

አሠሪዎች ወይም የአሠሪዎች ስብሰባ ባንድ ወገን የሠራተኞች ስብሰባ በሌላው ወገን፤ ከኅብረት ስምምነቶች ውስጥ እነዚሁኑ የሚመሩ
የእያንዳንዳቸው የሥራ ውል የሚደረጉበትን ሁኔታዎች መወሰን ይችላሉ፡፡

ቊ 2517፡፡ (2) ውሉ የሚጸናበትና የሚቈይባቸው ሁኔታዎች፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከቱት የጋራ ስምምነቶች በጽሑፍ ካልሆኑና ደንበኛ በሆኑ የሕዝብ ባለሥልጣኖች ካልጸደቁ በቀር
ዋጋ የላቸውም፡፡

(2) ቢሆንም ማንኛውም ተቃራኒ የውል ቃል ቢኖር እንኳ፤ ውሉ ከተደረገ አንድ ዓመት ካለፈ በኋላ በማናቸውም ጊዜ የ 6 ወር
ማስታወቂያ ተሰጥቶ የኅብረቱ ስምምነት ቀርቷል ብሎ ለማስታወቅ ይቻላል፡፡

ቊ 2518፡፡ (3) ውጤቶች፡፡

(1) ለሠራተኛው የበለጠ የሚጠቅሙ ካልሆኑ በቀር የእያንዳንዳቸው የሥራ ውሎች ቃል ከኅብረት ስምምነት ጋራ የማይስማሙ ሲሆን
ፈራሾች ናቸው፡፡

(2) ፈራሾች የሆኑት የየአንዳንድ የሥራ ውል ቃል በኅብረት ስምምነት በተመለከቱት ቃል የሚተኩ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2519፡፡ ለዐይነት የሚሆኑ ውሎች (1) መሠረቱ፡፡


(1) የሕዝብ ባለሥልጣኖች ልዩ ልዩ ለሆኑ የሥራ ውሎች ዐይነት የሚሆኑ ውሎች ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡

(2) የተዘጋጁትም የውል ዐይነቶች ውሎች ዋጋ ያላቸው የሚሆኑት በሚገባ ታትመው በግልጽ በወጡ ጊዜ ነው፡፡

ቊ 2520፡፡ (2) ውጤቶች፡፡

(1) የእያንዳንዳቸው የሥራ ውል በዐይነት ውሎች ሁኔታዎች እንደተደረጉ ይገመታሉ፡፡

(2) ተዋዋይ ወገኖች በዐይነት ውሎች ውስጥ የተመለከቱትን ሁኔታዎች በጽሑፍ መለወጥ ይችላሉ፡፡

ቊ 2521፡፡ የሥራ ማካሄጃው የውስጥ ደንብ፡፡

(1) በሥራ ማካሄጃ ውስጥ አሠሪው ያዘጋጀው የውስጥ ትእዛዝ ደንብ በጽሑፍ የተደረገ ሆኖ ከመቀጠሩ በፊት ካልተሰጠው በቀር
ሠራተኛውን አያስገድደውም፡፡

(2) በዚህ ደንብ አፈጻጸም አሠሪው በሠራተኛው ላይ ያደረጋቸው ቅጣቶች በሕግ ወይም ለሚገባ ፍርድ ተቃራኒ የሆኑ እንደሆነ፤ እንደገና
በዳኞች ለመሻሻል (መታየት) ይችላሉ፡፡

ቊ 2522፡፡ ሠራተኛውን የሚጎዳ የውል ቃል፡፡

(1) በዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች ከተጻፈው በአነሰ አኳኋን ለሠራተኛው የሚጠቅም የሥራ የውል ቃል በሕግ ግልጽ ሆኖ ካልተፈቀደ በቀር ዋጋ
የለውም፡፡
(2) ይህም የውል ቃል በጽሑፍ ካልተደረገ በቀር ፈራሽ ይሆናል፡፡

ክፍል 2፡፡
ስለ ሠራተኛው ሥራ፡፡
ቊ 2523፡፡ ግዴታው የራሱ ስለመሆኑ፡፡

በውሉ ወይም በሁኔታዎቹ ተቃራኒ ነገር ከሌለ በቀር ሠራተኛው ሊሠራው ቃል የሰጠበትን ሥራ ራሱ መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 2524፡፡ የትጉህነት አሠራር ግዴታ፡፡

(1) ሠራተኛው ሥራውን በጥንቃቄ መሥራት አለበት፡፡


(2) አስቦ ወይም በቸልተኛነት ወይም ባለመጠንቀቅ በአሠሪው ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አላፊ ነው፡፡

(3) አላፊነት አለበት ወይም የለበትም ብሎ ለመገመት የሚቻለው አሠሪው ለሠራተኛው ቃል የሰጠበትን ሥራ ዐይነት እንዲሁም
የሠራተኛውን የትምህርት ደረጃ ችሎታዎችና የሥራ ደረጃውን አሠሪው የሚያውቀው ወይም ይገባው የነበረውን ማወቅ መሠረት
በማድረግ ነው፡፡

ቊ 2525፡፡ የሥራው ሥነ ሥርዐት (ዲሲፕሊን)፡፡

የሥራውን አፈጻጸም የሚመለከቱ የአሠሪው ትእዛዞች፤ ለውሉ ለሕጉና ለመልካም ጠባይ አንዳችም ተቃራኒነት ከሌላቸውና እነዚህንም
መፈጸም አደጋ የማያመጣ ከሆነ ሠራተኛው መታዘዝ አለበት፡፡

ቊ 2526፡፡ መሠራት የሚገባው ሥራ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

ሠራተኛው ሊሠራው ግዴታ የገባበትን ሥራ ብቻ መሥራት አለበት፡፡

ቊ 2527፡፡ (2) ስለ ሥራ መለወጥ፡፡

(1) ቢሆንም ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር አሠሪው ስለ ሥራው ማካሄጃ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ የሠራተኛውን ደመወዝ የሚቀንስ ወይም
ከሁኔታው ዋና ነገር የሚለዋወጥ ካልሆነ በቀር ሌላ ልዩ ሥራ መስጠት ይችላል፡፡

(2) አዲሱ ሥራ ሠራተኛው ከተቀጠረበት ሥራ ይበልጥ ከፍ ያለ ደመወዝ ያለው እንደሆነ፤ ሠራተኛው ይህን ደመወዝ ለማግኘት መብት
አለው፡፡

ቊ 2528፡፡ (3) ስለ ተጨማሪ ሥራ፡፡

(1) አሠሪው በውሉ ከተመለከተው በላይ የሥራ ፍሬ እንዲሰጥ ሠራተኛውን መጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ሠራተኛው ይህን ተጨማሪ ሥራ መሥራት ከቻለና አልሠራም ማለቱም ለቅን ልቡና አሠራር ተቃራኒ የሆነ እንደሆነ፤ ሠራተኛው ይህን
ተጨማሪ ሥራ መሥራት አለበት፡፡

(3) ሠራተኛውም አስቀድሞ በተስማሙበት ደመወዝ አንጻር በተወሰነውና በሁኔታዎቹ ዐይነት ለዚህ ተጨማሪ ሥራ ተጨማሪ የሥራ ዋጋ
ለማግኘት መብት አለው፡፡

ቊ 2529፡፡ (4) በቊጥር ወይም በሙሉ ሥራን ስለ መሥራት፡፡


(1) በቊጥር ወይም በሙሉ ሥራው ደመወዝ የሚከፈለው ሠራተኛ አሠሪው ከሆነው ሰው ውሉ በሚጸናበት ጊዜ ሁሉ በቂ የሆነ ብዛት
ያለው ሥራ እንዲሰጠው ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) በቊጥር ወይም በሙሉ የሚሠራ ሥራ፤ ለመስጠት ካልቻለ አሠሪው በሰዓት ወይም በቀን ሠራተኛውን ሊያሠራው ይችላል፡፡

ቊ 2530፡፡ መሣሪያዎችን መሥሪያዎችን (1) ስለማቅረብ፡፡

(1) ተቃራኒ የውል ቃል ወይም ልማድ ከሌለ በቀር ለሥራው አስፈላጊ የሚሆኑትን መሥሪያዎችና መሣሪያዎች ለሠራተኛው የሚያቀርበው
አሠሪው ነው፡፡

(2) ሠራተኛው ግዴታ ሳይኖርበት በሙሉ ወይም በከፊል ያቀረባቸው እንደሆነ፤ አሠሪው ኪሣራውን ይከፍለዋል፡፡

ቊ 2531፡፡ (2) በጥበቃ ስለ ማኖር፡፡

ሠራተኛው ለሥራው አፈጻጸም የተሰጡትን ነገሮች በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡

ቊ 2532፡፡ ሠራተኛው ስለሚፈጥረው ነገር፡፡

(1) ለአሠሪው ሥራ ሲል ሥራውን በሚሠራበት ጊዜ ቢሆንም እንኳ ሠራተኛው ፈጥሮ ያወጣው ነገር የራሱ ነው፡፡

(2) ነገር ግን ሠራተኛው ፈጥሮ ወይም ፈልጎ እንዲያወጣ በተለይ ተቀጥሮ እንደሆነ ለአሠሪው ይሆናል፡፡

ቊ 2533፡፡ የሥራ ማካሄጃን ስለሚመለከቱ መግለጫዎች፡፡

(1) ሠራተኛው የሥራው ውል ካለቀ በኋላም ቢሆን በሥራው ጊዜ ያወቃቸውን የአሠሪውን ምስጢሮች መጠበቅ አለበት፡፡

(2) በአሠሪው ላይ ጉዳት በማድረግ ዐይነት በሥራው ጊዜ ያገኛቸውን መግለጫዎች ሊሠራባቸው አይገባውም፡

ክፍል 3፡፡
ለሠራተኛው ስለሚገባው ደመወዝ፡፡
ቊ 2534፡፡ ስለ ደመወዝ መብት፡፡

ይህ ሥራ ያለ ዋጋ እንዲሠራ ልምድ ካልሆነ ወይም ይህን ሥራ በሚሠራ ሰው ሞያ ውስጥ የሚገባ ከሆነ፤ ሥራ ሁሉ በደመወዝ እንደተሠራ
ይገመታል፡፡
ቊ 2535፡፡ የደመወዙ ልክ፡፡

(1) በተስማሙበት ወይም በኅብረት ስምምነቶች ያለውን ወይም ለአሠሪው አስገዳጅ በሆኑ ዐይነት ውሎች መሠረት ሠራተኛው ደመወዝ
ለማግኘት መብት አለው፡፡

(2) እነዚህ የውል ቃሎች ከሌሉ የደመወዝ ውል በልማድ ሞያዎች ወይም ሥራው በሚሠራበት ቦታ ልምዶች የተወሰነ ይሆናል፡፡

(3) ልምዶች ከሌሉ ግን በርትዕ መሠረት ዳኞች ይወስኑታል፡፡

ቊ 2536፡፡ ስለ ደመወዝ አወሳሰን፡፡

(1) ደመወዝ ላንድ ለተወሰነ ጊዜ፤ በሰዓት፤ በቀን፤ በሳምንት፤ በዐሥራ አምስት ቀን፤ በወር ወይም በዓመት ሊወሰን ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ባንድ በተወሰነ ገንዘብ ወይም በቊጥር ሥራ ወይም በሙሉ ሥራ ሠራተኛው ለአሠሪው በሚሰጠው ሥራ መጠን ለመሆን
ይችላል፡፡

ቊ 2537፡፡ ከትርፍ ተከፋይ ስለ መሆን፡፡

(1) ደመወዙ በሙሉ ወይም በከፊል፤ አሠሪው ካገኛቸው ትርፎች ካንድ ድርሻ ውስጥ ወይም ከሥራ ማካሄጃ የንግድ ክንውን ውስጥ
ወይም በሥራ ማካሄጃው ውስጥ ከተገኘው የቁጠባ ገንዘብ ካንድ ድርሻ ውስጥ ወይም ይህንኑ ከመሰለ ከሌላ ከሥራ ዋጋ ውስጥ በመቶ
ይህን ያህል ተበሎ ለመወሰን ይቻላል፡፡

(2) እንዲህም በሆነ ጊዜ እያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር መዝገብ (ኢንቫንቴር) ካደረገ በኋላ አሠሪው ለሠራተኛው ሊከፍለው የሚገባውን ሒሳብ
ያስረክበዋል፡፡
(3) ሠራተኛውም በተዋዋሉት ስምምነት መሠረት የተመረጠው አንድ ሦስተኛ ወገን ወይም ይህ ስምምነት ባይኖር ዳኞች የመረጡት ሰው
የተሠራውን ሒሳብ እንዲመረመርለት ለማስደረግ ይችላል፡፡

ቊ 2538፡፡ ጒርሻዎች፡፡

ደመወዝም በሙሉ ወይም በከፊል ደንበኞች ለሠራተኛው ከከፈሉት ጒርሻዎች ውስጥ ወይም ስለ ሠራተኞቹ አሠሪው ከተቀበላቸው
ውስጥ መሆን ይችላል፡፡

ቊ 2539፡፡ የመክፈያው ጊዜ፡፡


(1) ግዙፍነት ያለውን ሥራ ለመሥራት የተገደዱ ሠራተኞች ደመወዝ የሚከፈለው፤ በቀን መቊጠሪያው በየዐሥራ አምስት ቀን መጨረሻ
ወይም በውሉ አጭር ሆኖ በተወሰነው ጊዜ መጨረሻ ነው፡፡

(2) ለጸሓፊዎችና ለቢሮ ወይም ለማጋዘን ሠራተኞች የሚከፈለው በየወሩ መጨረሻ ወይም በውሉ አጭር ሆኖ በተወሰነው ጊዜ መጨረሻ
ነው፡፡
(3) የሥራው ውል ሲያልቅ በማናቸውም ሁኔታ ደመወዝ ተከፋይ ይሆናል፡፡

ቊ 2540፡፡ ሥራ ስለ ማቆም፡፡

የሚከተሉት ሁለት ቊጥሮች እንደተጠበቁ ሆነው ሥራውን ላልሠራባቸው ቀኖች ሠራተኛው ደመወዝ ለማግኘት መብት የለውም፡፡

ቊ 2541፡፡ የሥራ አለመኖር፡፡

(1) ሠራተኛው አንድም የሥራ አገልግሎት ባይሰጥም እንኳ ይኸውም ሁኔታ አሠሪው ሥራ ሳይሰጠው በመቅረቱ ወይም አሠሪው
እንዳይሠራ ከመከልከሉ የተነሣም የሆነ እንደሆነ፤ ደመወዙን ለማግኘት መብት አለው፡፡

(2) ሠራተኛው የሥራ አገልግሎት ሳይሰጥ በመቆጠብና ሌላ ሥራ በመፈጸም ያገኛቸውን ጥቅሞች አሠሪው ከደመወዙ ለመቀነስ ይችላል፡፡

(3) የሥራው አለመኖር በአሠሪው ጥፋት ያልሆነ እንደሆነ፤ ሠራተኛው በቅን ልቡና ሌላ ሥራ በመፈጸም ሊያገኝ ይችል የነበረውን
ጥቅሞች አሠሪው እንደዚሁ ከደመወዙ ለመቀነስ ይችላል፡፡

ቊ 2542፡፡ ስለ ሠራተኛው መታመም (1) መሠረቱ፡፡

(1) ሠራተኛው እጅግ ቢያንስ የሦስት ወር የሥራ አገልግሎት ሰጥቶ ሆነ ብሎ ሳይሆን በበሽታ ምክንያት አገልግሎት እንዳይሰጥ የታወከ
እንደሆነ፤ የደመወዙን ግማሽ ለማግኘት መብት አለው፡፡

(2) ሠራተኛው ለአሠሪው አንድ ዓመት ወይም ይበልጥ ሥራውን ከመተው በፊት ሠርቶ እንደሆነ፤ የደመወዙ መብት ካንድ ወር በኋላ
ይቀራል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን ካሥራ አምስት ቀን በኋላ ቀሪ ይሆናል፡፡

(3) አሠሪው አስገዳጅ በሆነው ሕጋዊ አሹራንስ መሠረት ለሠራተኛው ሥራውን በመተው ምክንያት የተከፈሉትን ገንዘቦች ከዕዳው
ለመቀነስ መብት አለው፡፡

ቊ 2543፡፡ (2) ለያንዳንድ ሥራ በቊጥር የሚከፈል ደመወዝ ወይም ጒርሻ፡፡

(1) ደመወዝ በያንዳንዱ ሥራ በቊጥር ወይም በመላው ሥራ የሚከፈል እንደሆነ፤ ከዚህ በፊት ያለውን ቊጥር እንዲሠራበት ለማድረግ
በበሽታ ምክንያት የታወከው ሠራተኛ ይሠራው የነበረውን ሥራ ዐይነት የሚፈጽሙ በሥራው ማካሄጃ ውስጥ ባሉት ሠራተኞች
በሚከፈለው መካከለኛ ደመወዝ ግምት ይወሰናል፡፡
(2) እንዲሁም ደግሞ ሥራውን ከመተው አስቀድሞ የነበረው ወር ውስጥ ታሞ የነበረው ሠራተኛ ይቀበለው የነበረው ደመወዝ በግምት
ውስጥ ይገባል፡፡

(3) የሚከፈለውም ደመወዝ በሙሉ ወይም በከፊል በጒርሻዎች የሆነ እንደሆነ፤ ስለ ሠራተኞቹ ወይም በማናቸውም ሌላ ዐይነት
ለመቈጣጠር በሚቻል አኳኋን አሠሪው የሚቀበላቸው ጒርሻዎች ብቻ በግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡

ቊ 2544፡፡ ደመወዝን ስለ መያዝ ወይም ስለ ማስተላለፍ፡፡

(1) በፍትሐ ብሔር ሕግ ሥነ ሥርዐት በተወሰነው አደራረግ ካልሆነ በቀር የሠራተኛ ደመወዝ በገንዘብ ጠያቂዎቹ በኩል ለመያዝ
አይችልም፡፡

(2) እንደዚህ ባለ አኳኋን ካልሆነ በቀር ላንድ ሦስተኛ ሰው ሠራተኛው ለማስተላለፍ አይችልም፡፡

ቊ 2545፡፡ ከደመወዝ ላይ አስቀድሞ ስለ መውሰድ፡፡

(1) ከሠራተኛው ችግር የተነሣና ለአሠሪውም ምንም ጉዳት የሚያመጣበት ካልሆነ በሠራው ሥራ ለሠራተኛው አስፈላጊ የሆነውን ገንዘብ
አሠሪው አስቀድሞ መስጠት አለበት፡፡

(2) ሠራተኛው ደመወዙን ለሌላ ለማስተላለፍ በሚችልበት መጠን ካልሆነ በቀር ገና ባልተፈጸመ ሥራ ምክንያት ለሠራተኛው አስቀድሞ
ገንዘብ መክፈል ሊፈቀድ አይቻልም፡፡

ቊ 2546፡፡ ስለ ማቻቻል፡፡

(1) ሠራተኛው ደመወዙን ለሌላ ሰው ማስተላለፍ በሚችልበት መጠን ካልሆነ በቀር አሠሪው በሠራተኛው ስም ለሌላ የከፈለውን ገንዘብ
ማቻቻያ አድርጎ ሠራተኛውን ለመቃወም አይችልም፡፡

(2) ስለሆነም ሠራተኛው አስቦ በአሠሪው ላይ ላደረገው ጉዳት ምክንያት ሊከፍለው የሚገባውን ኪሣራ መቻቻያ አድርጎ ያላንዳች ወሰን
ሠራተኛውን ሊቃወመው ይችላል፡፡

ቊ 2547፡፡ ከደመወዝ ላይ ስለ መያዝ፡፡

(1) ከደመወዝ ላይ ይያዛል ተብሎ ስምምነት ተደርጎ እንደሆነ ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር ሠራተኛው በአጋጣሚ አሠሪውን
ሊያደርስበት የሚችለውን ጉዳት ለመካስ እንደተያዘ ሆኖ ይገመታል፡፡

(2) ደመወዙን ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በሚቻልበት መጠን ካልሆነ በቀር ይህ የደመወዝ መያዝ አይፈቀድም፡፡

(3) ደመወዙም ከተያዘበት ቀን አንሥቶ ወለድ መከፈል አለበት፡፡


ክፍል 4፡፡
ስለ አሠሪው የጸጥታ አጠባበቅ ግዴታ፡፡
ቊ 2548፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) የሠራተኛውን ሕይወት፤ ሙሉ ሰውነቱን ጤንነቱንና የሕሊና (የሞራል) ክብሩን በመጠበቅ ረገድ አሠሪው ለሥራው ልዩ ሁኔታዎች
ተገቢ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡

(2) በልማድና በቴክኒክ ሥራዎች መሠረት በዚሁ ግብ ለሥራው ማካሄጃ ቦታዎችን ማቋቋምና አስፈላጊ መሣሪያን በተለይ ማደራጀት
አለበት፡፡
ቊ 2549፡፡ በሥራ ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎች፡፡
በሥራው ምክንያት በሠራተኛው ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች አሠሪው አላፊ ነው፡፡
ቊ 2550፡፡ ለሥራው ተመሳሳይ ስለሚሆን ሌላ ሥራ፡፡
ይህ ሥራ በአሠሪው የታዘዘም ባይሆን ለሥራ ማካሄጃው ጥቅም ሠራተኛው በሚሠራው ሥራ ማካሄድ ምክንያት ለሚደርሱበት አደጋዎች
አሠሪው አላፊ ነው፡፡

ቊ 2551፡፡ በሥራው ጊዜና ቦታ ስለሚሆኑ አደጋዎች፡፡

(1) ሠራተኛው ባንድ በተወሰነለት መሬት ወይም ቦታ ውስጥ የሥራውን አገልግሎት ሲፈጽም የሆነ እንደሆነ በሥራው ጊዜና ቦታ
በሠራተኛው ለሚደርሱበት አደጋዎች አሠሪው አላፊ ነው፡፡

(2) በሥራው ሰዓት የሚፈቀደው የዕረፍት ጊዜ እንደ ሥራ ጊዜ ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(3) በነዚሁ ዕረፍት ጊዜ ለሠራተኞች ማረፊያ የተዘጋጁት ቦታዎች እንደ ሥራ ቦታ ክፍል ሆነው ይቈጠራሉ፡፡

ቊ 2552፡፡ በሞያ ሥራዎች ላይ ስለሚደርሱ በሽታዎች፡፡

(1) በሠራተኛው ላይ በሥራው ምክንያት ለሚደርሱበት በሽታዎች አሠሪው አላፊ ነው፡፡

(2) ምንም ተቃራኒ ማስረጃ ቢኖር እንኳ ያስተዳደር ደንቦች በልዩ ልዩ ኢንዱስትሪዎች የሚደርሱትን በሥራ ላይ እንደደረሱ የሚቈጠሩትን
በሽታዎች ይወስናሉ፡፡

(3) ከነዚህ በሽታዎች ዝርዝር ውጭ ለሆነው ወይም የእነዚህ ዝርዝር በሌለ ጊዜ ሠራተኛው በሥራው ምክንያት በሽታው የደረሰበት
ለመሆኑ በማናቸውም ጊዜ ለማስረዳት ይችላል፡፡

ቊ 2553፡፡ ስለ አሠሪው ከአላፊነት መዳን፡፡

(1) ጉዳት የደረሰበት ሰው ጥፋት፡፡

(1) አደጋው ወይም በሽታው የደረሰበት ሰው አስቦ ባደረገው ጥፋት መሆኑን አሠሪው ካስረዳ ከዚህ በፊት ባሉት ቊጥሮች ከተወሰነው
አላፊነት አሠሪው ነጻ ይሆናል፡፡

(2) እንዲሁም አደጋው ወይም በሽታው የደረሰበት ሠራተኛው በግልጽ በጽሑፍ የተሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፍ መሆኑን ካስረዳ አሠሪው
ነጻ ይሆናል፡፡

ቊ 2554፡፡ (2) ከሥራው ጋራ ግንኙነት ስለ አለመኖር፡፡


አደጋው ከሠራተኛው ሥራ ጋራ ወይም ሠራተኛው ግንኙነት ካለው ከሥራው ውል ጋራ ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑን ካስረዳ
አሠሪው አላፊነት የለበትም፡፡
ቊ 2555፡፡ (3) ሌሎች ምክንያቶች፡፡
አሠሪው በሌላ በማናቸውም ምክንያት ከአላፊነት አይድንም፡፡
ቊ 2 ሺ 556፡፡ የአላፊነት መጠን፡፡ (1) የሕክምናና የሌሎች ወጪዎች፡፡

(1) አሠሪው ስለ ሕክምና መድኀኒቶች ሆስፒታልና ሌሎችም አደጋው ወይም በሽታው ሠራተኛውን የሚያስገድዱትና በሚገባ አኳኋን
የተደረጉትን ወጪዎች ሁሉ መክፈል አለበት፡፡

(2) በአደጋው ወይም በበሽታው ጠንቅ ሠራተኛው የሞተ እንደሆነ፤ በዚሁ አኳኋን ለመቃብር ሥርዐቶች አስፈላጊ የሆኑትን ወጪዎች
አሠሪው መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2 ሺ 557፡፡ (2) የደመወዝ ክፍል፡፡

(1) በአደጋው ወይም በበሽታው ምክንያት ሠራተኛው ለመሥራት የታወከ እንደሆነ፤ ሠራተኛው ሥራውን ከተወበት ጊዜ አንሥቶ እስከ
አንድ ዓመት ከደመወዙ ከመቶ ሰባ አምስት አሠሪው መክፈል አለበት፡፡

(2) ከሠራተኛው ደመወዝ የበለጠ ሳይሆን አሠሪው የሚሰጠው ገንዘብ ሠራተኛው በአሠሪው ሥራ ላይ ለቈየበት ለያንዳንድ ዓመት በመቶ
አምስት ይጨመራል፡፡

(3) ሆኖም በወር ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የሚበልጥ ገንዘብ ለመሆን አይችልም፡፡

ቊ 2558፡፡ (3) ስለ ቀለብ ግዴታ፡፡

(1) ከዚህ በፊት ባለው ቊጥር የተመለከተው ጊዜ ካለቀ በኋላና ሠራተኛው ከአደጋው ወይም ከበሽታው የተነሣ ግማሹን ወይም የሚበልጥ
የሥራ ችሎታውን በጭራሽ ያጣ ሆኖ ሲገኝ አሠሪው ለሠራተኛውና አካለ መጠን ላላደረሱ ልጆቹ የቀለብ መክፈል ግዴታ አለበት፡፡

(2) አሠሪው ይህ ግዴታ የሚደርስበት በምትክነት ስለሆነ፤ ሠራተኛው ከቤተ ዘመዱ አባሎች ይህን የቀለብ ርዳታ ለማግኘት ያልቻለ
እንደሆነ ነው፡፡

(3) ይህ ግዴታ በዚህ ሕግ ስለ ቤተ ዘመድ በተነገረው መጽሐፍ በተመለከቱት ደንቦች ይወሰናል፡፡

ቊ 2559፡፡ (4) ስለ አሠሪው ከባድ ጥፋት ወይም አታላይነት፡፡

(1) በሠራተኛው ላይ የደረሰው ጉዳት ወይም በሽታ በአሠሪው አታላይነት ወይም ከባድ ጥፋት የሆነ እንደሆነ ከዚህ በፊት ያሉት የሁለቱ
ቊጥሮች ውሳኔዎች ተፈጻሚ አይሆኑም፡፡

(2) በዚህ ሕግ ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት በሚለው ምዕራፍ ውሳኔዎች መሠረት ሠራተኛው ቤተ ዘመዱና ወራሾቹ የደረሰባቸውን
የጒዳት ካሣ አሠሪውን ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

(3) አሠሪው ስሕተት፤ አለመጠንቀቅ፤ ወይም ችላ ባይነት ሲያደርግና ይኸውም በነዝኅላልነት በድፍረት ወይም ለሠራተኞቹ ሕይወት
ወይም ጤንነት ግድ የሌለው ሆኖ ሲተረጐም ከባድ ጥፋት ይሆናል፡፡
ክፍል 5፡፡
ለሠራተኞች የሚገባ የዕረፍት ጊዜ፡፡
ቊ 2560፡፡ የተለመዱ ሰዓቶችና ቀኖች፡፡
አሠሪው ለሠራተኛው የተለመዱትን የዕረፍት ሰዓቶችና ቀኖች መፍቀድ አለበት፡፡
ቊ 2561፡፡ የዓመት የዕረፍት ፈቃድ፡፡
ሥራ አሠሪው የሠራተኛውን ጊዜ ወይም ከጊዜው ዋነኛውን ክፍል የተገለገለበት ሲሆን ለሠራተኛው የዓመት የዕረፍት ፈቃድ መስጠትና
ለዕረፍት በሚሰጠውም ጊዜ ደመወዙን መክፈል አለበት፡፡
ቊ 2562፡፡ ዕረፍቱ የሚቈይበት ጊዜ፡፡

(1 ) ሠራተኛው በአሠሪው ሥራ ውስጥ ወይም በአንድ የሥራ ማከናወኛ ክፍል ከአንድ ዓመት እስከ 5 ዓመት ሠርቶ እንደሆነ የዕረፍቱ ጊዜ
የሚሰጠው መደዳውን ዐሥር ቀን ይሆናል፡፡

(2) ሠራተኛው በአሠሪው ሥራ ውስጥ ወይም በአንድ የሥራ ማከናወኛ ክፍል ሲሠራ ከአምስት እስከ 0 ዓመት ቈይቶ እነደሆነ የዕረፍቱ
ጊዜ መደዳውን ዐሥራ አምስት ቀን ይሆናል፡፡

(3) ሠራተኛው በአሠሪው ሥራ ውስጥ ወይም ባንድ የሥራ መከናወኛ ክፍል ሲሠራ ዐሥራ አምስት ዓመት ወይም ከዚህ ይበልጥ ሆኖት
እንደሆነ የዕረፍቱ ጊዜ የሚቈየው መደዳውን ኻያ ቀን ይሆናል፡፡

ቊ 2563፡፡ ስለ ውሉ ማለቅ፡፡
የሥራው ውል ባለቀ ጊዜ ሠራተኛው ለአሠሪው በዓመቱ ውስጥ የሠራበት ጊዜ ተገምቶ የሚገባውን የዕረፍት ጊዜ ለማግኘት መብት
አለው፡፡
ቊ 2564፡፡ ስለሚቀነሱ ቀኖች፡፡

(1) በሠራተኛው ጥያቄ ወይም አስቀድሞ ከዕረፍቱ ላይ የተሰጡትን የዕረፍት ቀኖች አሠሪው ለሠራተኛው ከሚገባው ከዓመት የዕረፍት
ቀኖች ላይ ይቀንሳል፡፡

(2) ሠራተኛው በሌላ ምክንያት ያልሠራባቸውን ቀኖች አሠሪው ለመቀነስ አይችልም፡፡

ቊ 2565፡፡ የዕረፍት ጊዜ፡፡

(1) የዕረፍቱም ጊዜ ከዓመቱ ውስጥ ምቹ በሆነ ወራት ይፈቀዳል፡፡

(2) ይኸውም የሥራውን ዐይነት የአሠሪውንና የሠራተኛውን ጥቅሞች እንደተቻለ በማስማማት ነው፡፡

(3) ዕረፍቱን የሚያገኝበት ጊዜ እጅግ ቢያንስ ለሠራተኛው ካንድ ወር በፊት ይነገረዋል፡፡

ቊ 2566፡፡ ለመውለድ ስለሚሰጥ ዕረፍት፡፡

(1) ልጅ ለመውለድ የምትጠባበቅ ሠራተኛ በመውለጃዋ ጊዜ ያንድ ወር ዕረፍት ለማግኘት መብት አላት፡

(2) በዚሁ የዕረፍት ጊዜ አሠሪው ግማሽ ደመወዝዋን መክፈል አለበት፡፡


ክፍል 6፡፡
ውልን ስለ ማቋረጥ፡፡
ቊ 2567፡፡ ጊዜው የተወሰነ ውል፡፡

(1) የሚቈይበት ጊዜ የተወሰነ የሥራ ውል የተወሰነው ጊዜ ሲፈጸም ያለቀ ይሆናል፡፡

(2) የተወሰነ ሥራን ለመፈጸም የተደረገ ውል በስምምነት የሆነው ሥራ ሲፈጸም ያለቀ ይሆናል፡፡

(3) የተፈጸመውን ውል አልቋል ለማለት ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር ማናቸውም ማስታወቂያ አስፈላጊ አይደለም፡፡

ቊ 2568፡፡ ውሉ የሚቈይበት ከፍተኛ ጊዜ፡፡

(1) ከአምስት ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ የአገልግሎትን ሥራ ለመዋዋል አይቻልም፡

(2) ከተዋዋዮቹ ባንዱ ወገን ዕድሜ ልክ ወይም ከ 5 ዓመት ለበለጠ ጊዜ የሚደረግ የሥራ ውል ተዋዋዮቹን ሊያስገድዳቸው አይችልም፡፡

(3) ይህ ጊዜ ካለፈ የስድስት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ተዋዋዮቹ ውሉን ቀሪ ለማድረግ ይችላሉ፡፡


ቊ 2569፡፡ ስለ ውል ማደስ፡፡
ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ የሥራ ውል የተወሰነው ጊዜ ካለቀ በኋላ አሠሪው ሳይቃወመው ሠራተኛው ሥራውን የቀጠለ እንደሆነ ላልተወሰነ
ጊዜ ውሉ እንደታደሰ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2570፡፡ የሚቈይበት ጊዜ ያልተወሰነ ውል፡፡

(1) ውሉ የሚቈይበት ጊዜ ያልተወሰነ እንደሆነና የተጠየቀው የሥራው ዐይነት ወይም ማናቸውም ሌላ ሁኔታ ውሉ የሚቈይበትን ጊዜ
የሚያመለክቱ ያልሆኑ እንደሆነ እያንዳንዳቸው ተዋዋዮች በማናቸውም ጊዜ ውሉን ቀሪ ለማድረግ ይችላሉ፡፡

(2) ስለሆነም ውሉን ቀሪ ለማድረግ አሠሪው ወይም ሠራተኛው ማስጠንቀቂያ አስቀድሞ መስጠት አለበት፡፡

ቊ 2571፡፡ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት አስፈላጊ የሆነው ጊዜ፡፡

(1) ማስጠንቀቂያው እጅግ ቢያንስ ከሰባት ቀን በፊት መሰጠት አለበት፡፡ ውጤትም የሚያገኘው ከሚከተለው የደመወዝ መክፈያ ቀን
አንሥቶ ነው፡፡

(2) የሥራው ውል ካንድ ዓመት በላይ ቈይቶ እንደሆነ ለወሩ መጨረሻ ሆኖ ማስጠንቀቂያው እጅግ ቢያንስ ከሁለት ወር አስቀድሞ
መሰጠት አለበት፡፡

(3) ከዚህ በፊት ባሉት ኀይለ ቃሎች ለተወሰነው ጊዜ ለሠራተኛው ደመወዙን ወዲያውኑ የሰጠው እንደሆነ አሠሪው ማስጠንቀቂያ
መሰጠቱ ይቀርለታል፡፡

ቊ 2572፡፡ ውሉ የሚቀርበት ምክንያት፡፡


የሚቈይበት ጊዜ ያልተወሰነውን የሥራ ውል ቀሪ ያደረገበትን ወይም የሚቈይበት ጊዜ የተወሰነለትን የሥራ ውል የሚያድስበትን ምክንያት
ሠራተኛው የጠየቀ እንደሆነ አሠሪው በጽሑፍ ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2573፡፡ ከሥራ በማሰናበት ስለሚሰጥ ኪሣራ፡፡


አሠሪው ውሉን ቀሪ በማድረግ ወይም አላድስም በማለት ይህን ውሳኔ በግልጽ የሚያረጋግጥ በቂ ምክንያት የሌለው እንደሆነ ሠራተኛው
ተገቢ የሆነ ኪሣራ ለማግኘት መብት አለው፡፡

ቊ 2574፡፡ የኪሣራው ልክ፡፡

(1) የዚህን ተገቢ የሆነውን የኪሣራ ገንዘብ ለመወሰን የሠራተኛውን የአገልግሎት ጊዜና የሥራውን ዐይነት የሚያስወቅሱትንም ጥፋቶች
ከባድነት፤ የሥራ ማካሄጃውን ገንዘብ ሁኔታና አስፈላጊ የሆኑትን ማናቸውንም ግልጽ ሁኔታዎች ሁሉ ዳኞች ይመረምራሉ፡፡

(2) ኪሣራውም ሠራተኛው ባለፈው ሦስት ወር ከተቀበለው ደመወዝ ሊበልጥ አይችልም፡፡

ቊ 2575፡፡ በቂ ምክንያቶች፡፡

(1) ከውሉ ዐይነት የተነሣ ውሉ እንዲታደስ ወይም አንዲራዘም ባሉት ሁኔታዎች መሠረት ለአእምሮ በቂ የሆነ ምክንያት ባልተገኘ ጊዜ
አሠሪው የወሰነው ውሳኔ፤ በቂ ምክንያት እንዳለው ሆኖ ይገመታል፡፡

(2) እንዲሁም በሥራው አፈጻጸም ላይ በአእምሮ ግምት የሚፈለገውን የቴክኒክ ዕውቀቶቹን ቅን ሕሊና ያለው መሆኑን፤ ትክክለኛነቱን፤
ወይም ፈጣንነቱን፤ በሥራው ያላሳየ እንደሆነ አሠሪው የወሰነው ውሳኔ፤ በቂ ምክንያት እንዳለው ይገመታል፡፡

(3) ሠራተኛው የሚሠራው ሥራ በቅን ልቡና ቀሪ የተደረገ እንደሆነ አሠሪው የወሰነው ውሳኔ በቂ ምክንያት እንዳለው ይቈጠራል፡፡

ቊ 2576፡፡ ውሉን ያስቀረው ሠራተኛው ስለ መሆኑ፡፡

(1) ውሉን ያስቀረው አሠሪው ባይሆንም እንኳ ሠራተኛው ውሉን እንዲያፈርስ አሠሪው በአድራጎት ገፋፍቶት እንደሆነ ከሥራ በማሰናበቱ
የሚወሰንለትን ኪሣራ እንዲሰጠው ለማድረግ ይቻላል፡፡
(2) በተለይም አሠሪው ሠራተኛውን በማይገባ ሁኔታ ያጉላላው እንደሆነ ወይም የውሉን ዋና ፍሬ ነገር በመንካት ወይም የውሉን ቃል
በመደጋገም የጣሰ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተነገረው ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 2577፡፡ ስለ እምነት ሥራዎች፡፡

(1) የሥራው ውል ልዩ የሆኑ ችሎታዎችን የሚጠይቁ የእምነት ሥራዎች የሆኑ እንደሆነ አሠሪው ውሉን ቀሪ የሚያደርግበትን ወይም
የማያድስበትን ምክንያት ለማስታወቅ አይገደድም፡፡

(2) እንዲህም ሲሆን ውሉ እንዲቀር የተደረገው በማይገባ ጊዜና አንደኛውን ወገን ለመጉዳት ወይም ሊደርስበት የሚችለውን ጉዳት
ባለማሰብ መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር የውሉ መቅረት ኪሣራ መከፈልን አያስከትልም፡፡

ቊ 2578፡፡ ስለ ውሉ ፈራሽነት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


ለመፍረስ ትክክለኛ የሆነ ምክንያት የኖረ እንደሆነ አሠሪው ወይም ሠራተኛው ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሥራውን ውል ወዲያውኑ ቀሪ
ለማድረግ ይችላል፡፡

ቊ 2579፡፡ (2) ግዴታዎችን ስላለመፈጸም፡፡


ባንድ ወገን በውሉ ውስጥ ያሉ ግዴታዎች አለመፈጸም በሁኔታዎችና በልምዶች አንጻር በቂ የሆነ ከባድ ጠባይ ካላሳየ በቀር ውሉን
ለማፍረስ ትክክለኛ ምክንያት አይሆንም፡፡

ቊ 2580፡፡ (3) ያለ ፈቃድ ሥራን ስለ መተው፡፡


ሁኔታው ለሠራተኛው ጥፋት ካልሆነ በቀር በበሽታ ምክንያት ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ሠራተኛው እንዳይሠራ የተከለከለበት
ሁኔታ ለአሠሪው ውሉን ለማፍረስ ትክክለኛ ምክንያት አይሆንም፡፡

ቊ 2581፡፡ (4) የሥራ አድማ፡፡

(1) ላንድ የሥራ ማቆም አድማ የሠራተኛው ተካፋይ መሆን የሥራ ማቆም አድማ የተደረገው አሠሪውን ለመጉዳት ብቻ የሆነ እንደሆነ
ወይም በሕግ ወይም በሕዝብ ባለሥልጣኖች የተከለከለ የሆነ እንደሆነ ውሉን ለማፍረስ ለአሠሪው ትክክለኛ ምክንያት ይሆናል፡፡

(2 ) ከነዚህ ሁኔታዎች ውጭ የሥራ ማቆም አድማ ውሉን ለማፍረስ ትክክለኛ ምክንያት አይሆንም፡፡

ቊ 2582፡፡ (5) የአሠሪው መክሠር ወይም የመክፈል ችሎታ ማጣት፡፡


አሠሪው የከሠረ ወይም ለመክፈል ያልቻለ እንደሆነ ሠራተኛው ስለ ደመወዙ ዋስትና የጠየቃቸው ማረጋገጫዎች ዋሶች በቂ በሆነ ጊዜ
ውስጥ ያልተሰጡት እንደሆነ ውሉን ለማፍረስ ይችላል፡፡

ቊ 2 ሺ 583፡፡ ስለ ኪሣራ ግዴታ፡፡ (1) አላገባብ ውልን ስለ ማፍረስ፡፡


ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን በማይገባ ሁኔታ ውሉን ያፈረሰ እንደሆነ በማይገባ ውሉን ስላቋረጠ ውል አፍራሹ በተዋዋዩ ላይ ለደረሰበት ጉዳት
ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2584፡፡ (2) በሚገባ ውልን ስለ ማፍረስ፡፡


አንዱ ወገን ውሉን ለማፍረስ የሚያደርሰው ትክክለኛ ምክንያት ውልን በመጣስ ወይም ይህን ከመሰለ መጣስ ጋራ ግንኙነት ያለው
እንደሆነ ግዴታዎቹን ያልፈጸመው ወገን ውሉን በመተው በተዋዋዩ ላደረሰበት ጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2585፡፡ ስለ ሠራተኛው መሞት፡፡

(1) የሠራተኛው መሞት የሥራውን ውል ቀሪ ያደርገዋል፡፡

(2) የሠራተኛው ወራሾች በውሉ ምክንያት ምንም የግል ግዴታ አይደርስባቸውም፡፡

ቊ 2586፡፡ ስለ አሠሪው መሞት፡፡


(1) ስምምነቱ የተደረገው አሠሪውን በመመልከት ካልሆነ በቀር በአሠሪው መሞት የሥራው ውል ቀሪ አይሆንም፡፡

(2) በአሠሪው መሞት የሥራው ውል ቀሪ የሆነ እንደሆነ በዚሁ ቀን ጊዜው ላልተወሰነ የሥራ ውል ማስታወቂያ እንደተቀበለ ያህል ተቈጥሮ
አሠሪው ከሞተ በኋላ ሠራተኛው ደመወዙን ለማግኘት መብት አለው፡፡

ቊ 2587፡፡ የሥራ ማካሄጃን ስለ ማስተላለፍ፡፡

(1) አሠሪው የሥራ ማካሄጃውን ለሌላ ያስተላለፈ እንደሆነ እሱ ያደረጋቸው የሥራ ውሎች በሠራተኞቹና የሥራ ማካሄጃውን በገዛው ሰው
መካከል ይቀጥላሉ፡፡

(2) ሠራተኞቹ የሥራው መካሄጃ ከመተላለፉ በፊት ያገኙዋቸውን የነባርነት መብቶች እንደ ያዙ ይሆናሉ፡፡

(3) የሥራው ማካሄጃ በተላለፈለት ጊዜ አንድ ሠራተኛ ለሠራው ሥራ ሊከፈል ለሚገባው ገንዘብና እንዲሁም አስተላላፊው ውሉን
በማፍረሱ ሊከፍል ለሚገባው ገንዘብ ጭምር እነዚህ ገንዘቦች ሊከፈሉ የሚገባ መሆኑን የሚያውቅ እንደሆነ ወይም ለሠራተኛው፤
ሊከፈለው የሚገባው ገንዘብ በተላለፈው የሥራ ማካሄጃ መዝገብ ወይም በሠራተኛው የሥራ ደብተር ተጽፎ የተገኘ እንደሆነ ገዢው
ካስተላለፈው ጋራ ባንድነት ይገደዳል፡፡

ቊ 2568፡፡ ስለ ተሠራው ሥራ የምስክር ወረቀት፡፡

(1) ሠራተኛው የውሉ ጊዜ ሲያልቅ የሥራውን ዐይነትና ሥራዎቹ የቈዩበት ጊዜ ብቻ እንዲሁም የአሠሪው ስምና አድራሻ ያለበት የምስክር
ወረቀት እንዲሰጠው አሠሪውን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) ለጠባዩና ለፈጸመው ሥራ ዐይነት ያስተያየት ግምት በምስክር ወረቀት ላይ እንዲሰጠው ሠራተኛው አሠሪውን በግልጽ ካልጠየቀው
በቀር የምስክሩ ወረቀት የዚህ ዐይነት አስተያየት አይገኝበትም፡፡

ቊ 2569፡፡ መወዳደር እንዳይደረግ የሚደረግ የውል ቃል (1) መሠረቱ፡፡

(1) ለሠራተኛው የተሰጠው ሥራ የአሠሪውን ደንበኞች ለማወቅ ወይም ለጒዳዮቹ ምስጢር ውስጥ ለመግባት የፈቀደለት እንደሆነ
ሠራተኛው ውሉ ቀሪ ከሆነ በኋላ በራሱ ስም አሠሪውን ለመወዳደር እንዳይችል በናቸውም ዐይነት ሁኔታ አሠሪውን በሚወዳደር የሥራ
ማካሄጃው ውስጥ ተካፋይ እንዳይሆን ሁለቱም ወገኖች መዋዋል ይችላሉ፡፡

(2) ይህ የውል ቃል በግልጽና በጽሑፍ ካልሆነ በቀር ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 2590፡፡ (2) ስለ ስምምነቱ ወሰን፡፡

(1) መወዳደርን የሚከለክለው ስምምነት ዋጋ ያለው የሚሆነው ለአሠሪው ተገቢ የሆኑት ጥቅሞች ለመጠበቅ አስፈላጊ በሆነው መጠንና
ለሠራተኛው የወደፊት አኗኗር ዕድል በርትዕ መሠረት ተቃራኒ ያልሆነ እንደሆነ ነው፡፡

(2) በተለይም ይህ ስምምነት የሚጸናው ለሠራተኛው የተከለከለው ሥራ ዐይነት ስፍራውና ጊዜው የተወሰነ ሲሆን ነው፡፡

ቊ 2591፡፡ (3) ስለ ቅጣት፡፡

(1) የተከለከለውን የመወዳደር ስምምነት የጣሰ ሰው ስምምነቱን በመጣሱ ለሚደርሰው የጉዳት ኪሣራ አላፊ ነው፡፡

(2) ክልከላውን የጣሰ ይቀጣል ብለው ተዋውለው እንደሆነ ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ሠራተኛው ለአሠሪው የተወሰነውን
መቀጫ በመክፈል ነጻ ለመውጣት ይችላል፡፡

(3) ይህ መብት ለራሱ እንዲጠበቅ በጽሑፍ በግልጽ ተወስኖ እንደሆነ ከጉዳት ኪሣራ በቀር አደጋ በደረሰባቸው ወይም ያደርስባቸዋል
ተብለው በሚያሠጉት ጥቅሞች ትልቅነት መጠንና ከሠራተኛው አሠራር የተነሣ ውሳኔው ተገቢ ሆኖ ሲታይ ይህ ሠራተኛው ያደረገው
የውል መተላለፍ ሥራ እንዲቀር አሠሪው ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 2592፡፡ (4) ስለ ውሉ ቃል ፈራሽነት፡፡


(1) የመወዳደር ክልከላ እንዲጠበቅ ለማድረግ አሠሪው እርግጠኛ ጥቅም የሌለው መሆኑ ሲታወቅ የመወዳደሩ ክልከላ ስምምነት ቀሪ
ይሆናል፡፡
(2) በሠራተኛው ላይ ትክክለኛ ምክንያት ሳያገኝበት አሠሪው የሥራውን ውል ያፈረሰ ወይም ለማደስ እንቢ ያለ እንደሆነ አሠሪው
ውድድርን በሚከለክለው ውለታ ለመጠቀም አይችልም፡፡

(3) እንዲሁም ሠራተኛው ውሉን እንዲያፈርስ ትክክለኛ ምክንያት የሰጠው አሠሪው የሆነ እንደሆነ ውድድሩን በሚከለክለው ውለታ
አሠሪው ሊጠቀምበት አይችልም፡፡

ቊ 2593፡፡ የቀሪ ሒሳብ የመጨረሻ ደረሰኝ፡፡

(1) ሠራተኛው የፈረመበት የቀሪ ሒሳብ የመጨረሻ ደረሰኝ አሠሪው ለሚሰጠው ደመወዝ ብቻ እንደተጻፈ ይቈጠራል፡፡

(2) ሠራተኛው ከአሠሪው ላይ ሊያገኛቸው የሚችለው ሌሎች ገንዘቦች የተከፈሉ ሆነው የሚገመቱት አሠሪውን ነጻ የሚያደርጉት ልዩ ልዩ
ደረሰኞች ሆነው አከፋፈላቸውን የሚያመለክቱ ወይም የሠራተኛውን አልፈልግም ማለትን የሚያስረዱ ሰነዶች በተገኙ ጊዜ ነው፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
ስለ አንዳንድ ልዩ ልዩ የሥራ ውሎች፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ ሞያ ሥራ መልመጃ ውል፡፡
ቊ 2594፡፡ አሠሪው ለሥራ ለማጁ የሚሰጠው ትምህርት፡፡

(1) በሥራ መልመጃ ውል መሠረት አሠሪው ለሥራ ለማጁ የሞያ ሥራ ትምህርትን በሚያስፈልገው ጥንቃቄ ሁሉ መስጠት ይገባዋል፡፡

(2) በውሉ ላይ ከተለከተው የሞያ ሥራ ጋራ ግንኙነት ባላቸው ሥራዎች ላይ ብቻ አሠሪው ሥራ ለማጁን ያውለዋል፡፡

ቊ 2595፡፡ ትምህርት ቤቶችን ስለ ማዘውተር፡፡

(1) ሥራ ለማጁ የግዴታ ትምህርት ቤቶችን እንዲያዘወትር አሠሪው ይጠባበቃል፡፡

(2) አሠሪውም ትምህርት ቤቶችንና የሞያ ሥራዎችን ትምህርት እንዲሁም በሥራ ለማጆች ፈተና ተካፋይ ለመሆን እንዲችል፤ ለሥራ
ለማጁ አስፈላጊውን ጊዜ ይፈቅድለታል፡፡

ቊ 2596፡፡ የተከለከሉ ሥራዎች፡፡


ከሁኔታዎች የተነሣ የሚገባ ልዩ ምክንያት ካልተገኘ በቀር አሠሪው፤ ሥራ ለማጁ በሌሊት ወይም በእሑድ እንዲሠራ ለማድረግ
አይችልም፡፡
ቊ 2597፡፡ ወደ ሥራ ውል ደንቦች ስለ መሠራት፡፡
እንዲሁም ደግሞ የሥራ ውል ደንቦች በሥራ መልመጃ ውል ላይ ይጸናሉ፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ሥራ ሙከራ ውል፡፡
ቊ 2598፡፡ በሙከራ ስለ መቅጠር፡፡

(1) ሠራተኛውን በሙከራ ለመቅጠር ይቻላል፡፡

(2) ይህንን ሁኔታ ከሚያረጋግጥ ጽሑፍ የሌለ እንደሆነ በሙከራ የተቀጠረው ሠራተኛ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠረ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2599፡፡ የሕሊና ግምት፡፡


ከአሽከሮች ጋራ የተደረገ የሥራ ውል ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንቶች እንደ ሙከራ ጊዜ ሆነው ይቈጠራሉ፡፡
ቊ 2600፡፡ ለሙከራ የተደረገን ውል ስለ ማፍረስ፡፡

(1) በሙከራው ጊዜ እያንዳንዱ ወገን ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ሳይገደድ ወይም ኪሣራ ሳይከፍል ውሉን ለማፍረስ ይችላል፡፡

(2) የሆነ ሆኖ ሙከራው አስፈላጊ ለሆነ አነስተኛ ጊዜ የተመለከተ እንደሆነ ይህ አነስተኛ ጊዜ ከመፈጸሙ በፊት ውሉን ለማፍረስ
አይቻልም፡፡
ክፍል 3፡፡
በቤተሰብ አስተዳደር ውስጥ ስለሚኖር አሽከር የሥራ ውል፡፡
ቊ 2601፡፡ ስለ ሠራተኛው ጤናና ግብረ ገብነቱ፡፡
ሠራተኛው ከአሠሪው ቤተሰብ ጋራ የሚኖር እንደሆነ አሠሪው የመኖሪያ ቦታዎችን የምግብን የሥራና የዕረፍት ጊዜዎችን የሚመለከቱትን
የሠራተኛውን ጤና ግብረ ገብነቱን የሚጠብቁትን በአእምሮ ግምት አስፈላጊ የሆኑትን ዝግጅቶች ማድረግ አለበት፡፡

ቊ 2602፡፡ ሠራተኛውን የማስታመም ግዴታ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) በአሠሪው ቤተሰብ ውስጥ የሚኖረውና እርሱም የሚጠብቀው አሽከር የታመመ እንደሆነ ውሉ በሚቈይበት ጊዜ ለታመመው ሠራተኛ
የሚያስፈልገውን ሕክምናዎች በቤቱም ሆነ ወይም ባንድ ሆስፒታል ለማስታመም አሠሪው አስፈላጊውን ማድረግ አለበት፡፡

(2) ውሉ ከተጀመረ ቢያንስ ከአንድ ዓመት በኋላ በሽታው የደረሰበት እንደሆነ ለአንድ ወር በሚቈይ ጊዜ እንዲሁም ውሉ ከተጀመረ
ከሦስት ወር በኋላ የደረሰበት እንደሆነ ለዐሥራ አምስት ቀን በሚቈይ ጊዜ፤ ይህ የማስታመም ግዴታ የተወሰነ ነው፡፡

(3) በበሽታው ጊዜ ያደረጋቸውን ወጪዎች አሠሪው ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ ለመቀነስ ይችላል፡፡

ቊ 2603፡፡ (2) ነጻ ስለሚያደርጉ ምክንያቶች፡፡

(1) ሠራተኛው ሆነ ብሎ አስቦ በሽታው እንዲይዘው አድርጎ እንደሆነ አሠሪው ከዚህ በፊት ባለው ቊጥር ከተመለከቱት ግዴታዎች ነጻ
ይሆናል፡፡
(2) በሽታውን ተቃዋሚ ከሚሆን ካንድ አስገዳጅ አሹራንስ የመነጨን አንድ መብት በመፈጸም ባንድ ሆስፒታል ውስጥ ሠራተኛው የገባ
እንደሆነ የአሠሪው ግዴታ እንዲሁ ቀሪ ይሆናል፡፡

(3) በሠራተኛው በሽታ ምክንያት ውሉን በማፍረስ ከዚህ በፊት ባለው ቊጥር ከተለከቱት ግዴታዎች አሠሪው ነጻ ለመሆን አይችልም፡፡

ቊ 2604፡፡ ስለ ደመወዝ አከፋፈል፡፡

(1) የሥራው ውል ያነሰ ጊዜ ካልወሰነ በቀር ከአሠሪው ቤተሰብ ጋራ በአሽከርነት የሚኖሩ ሠራተኞች ደመወዝ የሚከፈላቸው በየሦስት ወር
መጨረሻ ነው፡፡

(2) በማናቸውም ሁኔታ ውሉ ቀሪ ሲሆን ደመወዝ ተከፋይ ይሆናል፡፡


ክፍል 4፡፡
ስለ እርሻ ሥራ ውል፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ስለ እርሻ ውል፡፡
ቊ 2605፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) የእርሻ ሥራ ውል በጠቅላላው የሚመራው ከዚህ በላይ ባለው ምዕራፍ ድንጋጌዎችና በተለይም አስፈላጊ ሲሆን ከዚህ በላይ ባሉት
ንኡስ ክፍሎች ድንጋጌዎች መሠረት ነው፡፡
(2) ስለሆነም፤ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ድንጋጌዎች የሚፈጸሙበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2606፡፡ ጊዜው ያልተወሰነ ውል፡፡

(1) ጸንቶ የሚቈይበት ጊዜ ባልተወሰነ ውል መሬቱን ያከራየ ባመሬት ውሉን የሚያፈርስ መሆኑን ከሦስት ወር በፊት ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው ኃይለ ቃል የተሰጠው የጊዜ ውሳኔ ገበሬው በመሬቱ ላይ በኖረበት ለየአንዳንዱ ዓመት የአንድ ወር ተጨማሪ ጊዜ
ይኖረዋል፡፡

(3) ስለ ገበሬው መሰናበት የተሰጠው የጊዜ ውሳኔ ግን ከመጋቢት 1 ቀን ካለው ቀን በፊት ማናቸውንም ውጤት አያስከትልም፡፡

ቊ 2607፡፡ ባለመሬቱ ገበሬውን ለመመገብ ስላለበት ግዴታ፡፡

(1) የእርሻ ሥራ ገበሬ በተወሰነ የእርሻ ስፍራ ዐሥር ዓመት ሙሉ የሠራ እንደሆነ ባለመሬቱ ለዚህ ገበሬ ምግብ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

(2) ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ በዚህ ግዴታ ላይ የዚህ ሕግ ስለ ሥጋ ዝምድናና ስለ ጋብቻ ዝምድና
በተመለከተው አንቀጽ የተባሉት ድንጋጌዎች ይጸኑበታል፡፡

ቊ 2608፡፡ ይህ ግዴታ ሁለተኛ ደረጃ ግዴታ ስለ መሆኑ፡፡

(1) ባለመሬቱ ሊመግባቸው የሚገደድበት ሌሎች የሥጋ ዘመዶችና ወይም የጋብቻ ዘመዶች ያሉት እንደሆነ እነሱን በመጉዳት ገበሬው
አሠሪውን ባለመሬት ቀለብ እንዲሰጠው ለማስገደድ አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም ገበሬው ምግብ ሊሰጡት የሚችሉ የሥጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች ያሉት እንደሆነ ባለመሬቱን ምግብ እንዲሰጠው
ለማስገደድ አይችልም፡፡

ቊ 2609፡፡ የጊዜው ወሰን፡፡


ባለመሬቱ ገበሬውን ለመመገብ ያለበት ግዴታ የእርሻ ሥራው ውል ከተፈጸመ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚቀር ይሆናል፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ ሥራ ውል፡፡
ቊ 2610፡፡ ትርጓሜ፡፡

የሥራ ማከናወኛ ውል ማለት አሠሪው በገባው ውለታ ለ 1 ኛው ወገን የሥራውን ዋጋ ሊከፍለው ሥራ ተቋራጩም በኀላፊነት የተሰጠውን
አንድ ሥራ በገባበት ውለታ ሊፈጽም በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገ ውል ነው፡፡

ቊ 2611፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ሥራ ማከናወኛዎች፡፡

(1) የሥራ ማከናወኛው ዓላማ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሆነ እንደሆነ፤ የማከናወኛውን ውል የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የማይንቀሳቀሱትን
ንብረቶች በሚመለከተው በዚሁ ሕግ አንቀጽ ውስጥ ተመልክተዋል፡፡

(2) የሚሠራው ሥራ ጠቅላላ ዋጋ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የማይበልጥ ከሆነ ግን የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2612፡፡ በዝምታ መቀበል፡፡

(1) አንድ ሥራ ለመፈጸም በግልጽ ያስታወቀ ሰው ወይም የዚሁ ሥራ አፈጻጸም በሙያ ሥራው ክንውን ውስጥ የገባ ሲሆን ይህ ሰው
የሥራውን ማቅረብ ተቀብሎ የታዘዘለትን ሥራ ለመፈጸም ወዲያውኑ እንቢታውን ካላስታወቀ የማከናወኛው ውል የተፈጸመ ይሆናል፡፡

(2) አንድ ሰው አንድ ሥራ ለመፈጸም በባለሥልጣኖች የተመረጠ ሲሆንና ለመፈጸም አለመፈለጉን ወዲያውኑ ካላስታወቀ እንደዚሁ ውሉ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 2613፡፡ መሣሪያዎችና መሥሪያዎች፡፡


(1) ሥራ ተቋራጩ ሥራን ለመፈጸም አስፈላጊ መሣሪያዎችንና መሥሪያዎችን የሚያቀርበው በራሱ ኪሣራ ነው፡፡

(2) ነገር ግን መሣሪያዎችንና መሥሪያዎችን አሠሪው እንዲሰጥ ሆኖ ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ብቻ እንዲሠራ ለመዋዋል ይችላል፡፡

ቊ 2614፡፡ ሥራ ተቋራጩ የሚያቀርባቸው መሥሪያዎች፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ ለሚያቀርባቸው መሥሪያዎች መልካምነት አላፊ ነው፡፡

(2) ስለ መሥሪያዎቹ መልካምነት ሻጩ አላፊ እንደመሆኑ ሥራ ተቋራጩም አላፊ ነው፡፡

(3) አንድ ተዋዋይ የገባበት የዕውቀት የሥራ ውለታ ተዋዋይ የተዋዋለበት ነገር በሚሰጣቸው ዕቃዎች ግምት መጠን ሥራው ተጨማሪ ሆኖ
የሚታይ እንደሆነ፤ የሽያጭ ውል እንጂ የሥራ ማከናወኛ ውል አይሆንም፡፡

ቊ 2615፡፡ አሠሪው ያቀረባቸው መሥሪያዎች፡፡

(1) መሥሪያዎቹን ያቀረባቸው አሠሪው ሲሆን ሥራ ተቋራጩ በጥንቃቄ ሊሠራባቸው ይገባል፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ የሠራባቸውን መሥሪያዎች ለአሠሪው ገልጾ ሥራውን ከተፈጸመ በኋላ የተረፈውን ይመልስለታል፡፡

(3) አሠሪው ያቀረባቸው መሥሪያዎች የተበላሹ ሲሆኑ ሥራ ተቋራጩ ወዲያውኑ ለአሠሪው ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2616፡፡ የሥራ ተቋራጭ ነጻነት፡፡

(1) የኪነ ጥበብን ደንቦች በማክበር ሥራ ተቋራጩ እንደሚመስለው ሥራውን ይፈጽማል፡፡

(2) ውሉን ባደረገ ጊዜ እንደተስማማበት መጠን ካልሆነ በቀር በአሠሪው ትእዛዞች ለመሄድ አይገደድም፡፡

ቊ 2617፡፡ ራሱ ባለቤቱ ስለሚፈጽመው ሥራ፡፡


ከታዘዘው ሥራ ዐይነት የተነሣ የሥራ ተቋራጩ ችሎታ ለአሠሪው ቁም ነገር የሌላቸው ካልሆኑ በቀር ሥራ ተቋራጩ ራሱ ሥራውን
መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 2618፡፡ ስለ ሥራ አፈጻጸም ማዘግየት፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ሳይጀምር በመቈየቱ በውሉ በተወሰነው የቀጠሮ ጊዜ ለመፈጸም የማይችል መሆኑ ግልጽ ሲሆን ሥራውን
የሚጀምርበትን በቂ የሆነ ጊዜ አሠሪው ሊወስንለት ይችላል፡፡

(2) ይህ የቀጠሮ ጊዜ አልፎ ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ያልጀመረ ሲሆን ወይም ለቅን ልቡና ተቃራኒ በሆነ አኳኋን ያቋረጠ እንደሆነ፤ ስለ
ሥራው አፈጻጸም የተወሰነውን ጊዜ ሳይጠብቅ አሠሪው ውሉ ፈርሷል ብሎ ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(3) እንዲህም ሲሆን ከዚህ በቀር አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ፤ አሠሪው ከሥራ ተቋራጩ ላይ ኪሣራ መጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2619፡፡ ጊዜ ስላልተወሰነበት ጒዳይ፡፡

(1) በውሉ ማንኛውም ጊዜ ያልተመለከተበት እንደሆነ ሥራ ተቋራጩ ወዲያውኑ ሥራውን ጀምሮ በአሠራር ልምድ መሠረት በቂ በሆነ ጊዜ
ይህንኑ ሥራ መፈጸም አለበት፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ወዲያውኑ ያልጀመረ ወይም ይህን አፈጻጸም ያቋረጠ እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተደነገጉት
ውሳኔዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2620፡፡ ሥራን ደኅና አድርጎ ስላለመሥራት፡፡

(1) ውሉ ጸንቶ በሚቈይበት ጊዜ ውስጥ ሥራው በመጥፎ አኳኋን ወይም ለውሉ ተቃራኒ በመሆን የሚፈጸም ሆኖ ሲታይ አሠሪው
ለተመለከተው ጒድለት ማሻሻል በቂ የሆነ ጊዜ ለሥራ ተቋራጩ ለመወሰን ይችላል፡፡
(2) በውሉና በኪነ ጥበብ ደንቦች መሠረት በዚሁ ጊዜ ውስጥ ሥራ ተቁራጩ ሥራውን ያላደሰ እንደሆነ አሠሪው መብቶቹን ለማስከበር ስለ
ሥራው መጨረሻ ጊዜ የተመለከተውን የውል ቃል ሳይጠብቅ ውሉ ፈርሷል ብሎ ማስታወቅ ይችላል፡፡

(3) ከዚህም በቀር አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ፤ አሠሪው ከሥራ ተቋራጩ ላይ ለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ መጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2621፡፡ ሥራን ለአሠሪው ስለ ማስረከብ፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ ሥራውን በጨረሰ ጊዜ በውሉ በተመለከተው ቦታ ወይም ይህ ቦታ በውሉ ውስጥ ባይገኝ የሥራ ተቋራጩ የሥራ
ማከናወኛ ቦታ ወይም መኖሪያ ቤት በአለበት ቦታ ለአሠሪው ያስረክባል፡፡

(2) ለጒዳዮቹ እንደተለመደው የሥራ አካሄድ አሠሪው ሥራውን በፍጥነት ይቀበላል፡፡

ቊ 2622፡፡ የጒድለት ዋስትና፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ ሥራው የተከናወነው በውሉ ላይ በተመለከተው መሠረት በትክክል ስለ መሆኑና ጒድለትም የሌለበት ስለ መሆኑ
ለአሠሪው አላፊ መድን የመሆን ግዴታ አለበት፡፡

(2) በአንድ ነገር ላይ የሚደርስ ጒድለትን አላፊ መድንነት የሚመለከተው በዚህ ሕግ ስለ ሽያጭ በተነገረው ምዕራፍ የተመለከቱት ደንቦች
በሥራ ተቋራጩና በአሠሪው መካከል ስላሉት ግንኙነቶች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2623፡፡ የመክፈያ ጊዜ፡፡

(1) ሥራው የተፈጸመ ሆኖ አሠሪው ከተረከበ (ከተቀበለ)፤ ለሥራ ተቋራጩ ዋጋው ተከፋይ ይሆናል፡፡

(2) ሥራዎቹን በከፊል ለማስረከብና ክፍያዎቹም በከፊል እንዲሆኑ ስምምነቶች ተደርገው እንደሆነ፤ ይህንኒ ሥራ አሠሪው ሲረከብ
(ሲቀበል) ለዚሁ ሥራ የተመደበው ዋጋ ተከፋይ ይሆናል፡፡

ቊ 2624፡፡ በቊርጥ የተወሰነ ዋጋ፡፡

(1) ዋጋው በቊርጥ የተወሰነ ሲሆን አሠሪው ይህን ዋጋ መክፈል አለበት፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ የበለጠ ሥራ አስፈለገው በማለት ወይም ከተመለከተው በላይ ውድ ዋጋ አወጣ በለት፤ ከተወሰነው ዋጋ በላይ
ለሥራው ተጨማሪ ገንዘብ መጠየቅ አይችልም፡፡

(3) አሠሪው ያነሰ ሥራ አስፈለገው በማለት ወይም ከተመለከተው በታች ያነሰ ዋጋ አወጣ በማለት ከተወሰነው ዋጋ ይቀንስልኝ ብሎ
መጠየቅ አይችልም፡፡

ቊ 2625፡፡ ስምምነት የተደረገበትን ሥራ ስለመለወጥ፡፡

(1) ስለ ሥራው አፈጻጸም ሁኔታ በፊት የተስማሙትን ሁለቱ ወገኖች በአዲስ ስምምነት ቢለውጡት እንኳ ለሥራው የተወሰነ ቊርጥ ዋጋ
ያው እንደሆነ ይቀራል፡፡

(2) እንዲሁም ስምምነት ካልተደረገ በቀር በዚሁ መለወጥ፤ ዋጋ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ አይቻልም፡፡

ቊ 2626፡፡ አስቀድሞ ያልተወሰነ ዋጋ፡፡

(1) ዋጋው በውሉ ያልተወሰነ እንደሆነ በሙያ ሥራዎች ታሪፍና (የዋጋ ልክ) በልማድ መሠረት ሥራ ተቋራጩ ይወስናል፡፡

(2) የሙያ ሥራዎች ታሪፍና ልማድ በሌለ ጊዜ ሥራ ተቋራጩ ለሥራ ያዋለውን መሥሪያዎች ዋጋ፤ ሥራውን ለመፈጸም አስፈላጊ የሆነ
ደንበኛ ሥራና የተቋራጩን ወጪዎች በመገመት ይወስናል፡፡

ቊ 2627፡፡ በተቃረበ ግምት ዋጋን ስለ መወሰን፡፡


ውሉ በሚወሰንበት ጊዜ ስለ ዋጋው በተቃረበ ግምት ስምምነት ተደርጎ እንደሆነ ከተደረገው ግምት ዋጋው ከመቶ ሓያ ሊበልጥ
አይችልም፡፡
ቊ 2628፡፡ የመያዝ መብት፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ የሠራቸው ወይም ያደሳቸውና በጁ የሚገኙትን የአሠሪው የሆኑትን ተንቀሳቃሽ ዕቃዎች በውሉ መሠረት በአሠሪው ላይ
ስላለው ገንዘብ ዋስትና ለመያዝ መብት አለው፡፡

(2) አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ የሰጣቸው ዕቃዎች የሦስተኛ ወገን የሆኑ እንደሆነ፤ የተሰጡት ዕቃዎች ሦስተኛው ወገን ሳያውቀው ወይም
ከፈቃዱ ውጭ መሆኑን ያወቀ ወይም ሊያውቅ የሚገባው ካልሆነ በቀር ሥራ ተቋራጩ ስለ መያዝ መብቱ ይህንን ሦስተኛ ወገን
ለመቃወም ይችላል፡፡

ቊ 2629፡፡ ሊደርስ ስለሚችል አደጋ፡፡

(1) ሥራው በሚፈጸምበት ጊዜ አስፈላጊዎች መሥሪያዎች ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል የጠፉ እንደሆነ ኪሣራው መሥሪያዎቹን ባቀረበው
ወገን ላይ ነው፡፡

(2) ከዚህም በቀር የአደጋን አላፊነት ስለ ማስተላለፍ በዚህ ሕግ ስለ ሽያጭ በተነገረው ምዕራፍ የተመለከቱትን ደንቦች መሠረት አድርጎ
መያዝ ይቻላል፡፡

ቊ 2630፡፡ ስለ ሥራ ተቋራጩ መሞት፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ የሞተ እንደሆነ፤ ወይም ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል ሥራውን ለመፈጸም የማይችል የሆነ እንደሆነ፤ ውሉ የተደረገው
የሥራ ተቋራጩን የግል ችሎታዎች በመገመት እንደሆነ ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) ሊሠራባቸው ከቻለ አሠሪው በከፊል የተፈጸሙትን ሥራዎች እንዲረከብና (እንዲቀበልና) የነዚህንም ዋጋ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡

(3) ትክክል የሆነ ግምት ከፍሎ ለዚሁ ሥራ አፈጻጸም የተሰናዱት መሥሪያዎችና ፕላን እንዲሰጡት አሠሪው ማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 2631፡፡ አንዱ ወገን ብቻ ውልን ስለ ማፍረሱ፡፡

(1) አሠሪው በማናቸውም ጊዜ ውሉን ለማፍረስ ይችላል፡፡

(2) በዚህም ጊዜ ሥራ ተቋራጩ በስምምነት የተደረገውን ዋጋ ለማግኘት መብት አለው፡፡

(3) ቢሆንም ሥራ ተቋራጩ ውሉ ከመፍረሱ የተነሣ የቀረበለትን ወጪና በሌላ ሥራ ያገኘውን ወይም ለማግኘት ይችል የነበረውን በክፉ
ልቡናና በቸልተኛነት ሳያገኝ የቀረው ሁሉ ተቀናሽ ይሆናል፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
ስለ ዕውቀት ሥራ ማከራየት ውል፡፡
ቊ 2632፡፡ የሚፈጸሙ ድንጋጌዎች፡፡

(1) የዕውቀት ጠባይ ሥራዎች አገልግሎት ዓላማ ያለው ውል በሚከተሉት ድንጋጌዎች ተወስኗል፡፡

(2) ከነዚሁ ውሳኔዎች ጋራና ከተመለከተው ግንኙነት ዐይነት ጋራ ለመስማማት በሚችሉበት መጠን ከዚህ በፊት ባለው ምዕራፍ
ድንጋጌዎች እንደዚሁ ይፈጸማሉ፡፡

(3) የልዩ ልዩ ሞያዎችን ተግባር የሚመለከቱ የልዩ ሕጎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2633፡፡ ግዴታው የግል ስለ መሆኑ፡፡

(1) የዕውቀት ሥራውን የተዋዋለ ሰው ግዴታዎቹን ራሱ መፈጸም አለበት፡፡

(2) ተባብሮ መሥራት በውሉ ወይም በልማድ የተፈቀደ ሲሆንና ከሥራ አገልግሎት መስጠት ዓላማ ጋራ የሚስማማ ከሆነ በሱ መሪነትና
አላፊነት ረዳቶችን ማሠራት ይችላል፡፡
ቊ 2634፡፡ አሠሪው አስቀድሞ ስለሚከፍለው ገንዘብ፡፡

(1) ስለ ሥራ አፈጻጸም አስፈላጊ ወጪዎችን አሠሪው ለተዋዋዩ አስቀድሞ ይከፍላል፡፡

(2) እንደዚሁ በልማድ መሠረት ከሥራ ዋጋ በከፊል አስቀድሞ ሊሰጠው ይገባዋል፡፡

ቊ 2635፡፡ ከመጠን በላይ ስለሚደረገው የሥራ ዋጋ፡፡


በሁለት ወገኖች መካከል ስምምነት የተደረገበት የሥራ ዋጋ ከመጠን በላይ መሆኑ ግልጽ ሆኖ ሲገኝ የዕውቀት ሥራውን ለሚያዋውለው
ሰው የሞያ ሥራ ተግባር ክብር ተቃራኒ የሆነ እንደሆነ ዳኞች ሊቀንሱት ይችላሉ፡፡

ቊ 2636 ፡፡ ስለሚጠየቅበት ጥንቃቄና አላፊነት፡፡

(1) በውቀት ሥራው የሚዋዋል ሰው በልማድና በሙያ ሥራ ድንጋጌዎች መሠረት ከልብ በመሥራት ለአሠሪው ጥቅሞች በሚሻል አኳኋን
ሥራን ለመፈጸም ግዴታ እንደገባ ይቈጠራል፡፡

(2) የኪነ ጥበብን ደንቦች በማፍረስ ጥፋት ካላደረገ በቀር በአሠሪው በኩል ሥራ ተቋራጩን አላፊነት አይነካውም፡፡

(3) ሳይሠራ ከመቅረቱ የተነሣ እንዲሁም በአሠሪው ላይ ጉዳትን የሚያመጣ ሥራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል ይቻላል፡፡

ቊ 2637፡፡ ስለ ውል መፍረስ፡፡ (1) የአሠሪው ውል ማፍረስ፡፡

(1) አሠሪው በማናቸውም ጊዜ ውሉን ማፍረስ ይችላል፡፡

(2) በዚህ ጊዜ ለተዋዋዩ ስለ ወጪዎቹ ኪሣራን እንዲሰጥና ለፈጸመው ሥራ በርትዕ የሚገባውን ዋጋ እንዲከፍል ይሆናል፡፡

ቊ 2638፡፡ (2) የሠሪው ውል ማፍረስ፡፡

(1) የዕውቀት ሥራውን ያዋዋለ ሰው በማናቸውም ጊዜ ውሉን ማፍረስ ይችላል፡፡

(2) በዚህ ጊዜ ከሥራው ዋጋና ወጪዎች ላይ አስቀድሞ የተቀበላቸውን ለአሠሪው ይመልሳል፡፡

(3) ውሉ ሲፈርስ አሠሪውን ከዚህ የተነሣ የሚያገኘው ጉዳት ከሁሉ ያነሰ ካልሆነ በቀር ኪሣራ ሊከፍለው ይገባል፡፡
ምዕራፍ 5፡፡
ስለ ሕክምና ወይም ስለ ሆስፒታል ውል፡፡
ቊ 2639፡፡ የሕክምና ውል ትርጓሜ፡፡
የሕክምና ውል ማለት አንድ ሐኪም ውለታ ገብቶ የሚገባውን ገንዘብ በመቀበል ላንድ ሰው የሕክምና ሥራዎችን እንዲያደርግለትና
በተቻለውም በመልካም ጤና እንዲቈይ ወይም ሊያድነው የሚደረግ ውል ነው፡፡

ቊ 2640፡፡ የሕክምና ሞያ፡፡

የሕክምና ውልን የሚመለከቱ ደንቦች ለቀዳጆች፤ ለጥርስ ሐኪሞች፣ ለአእምሮ በሽታ ሐኪሞች፤ (ለራዲአሎን)፤ ለአዋላጅ ሴቶች
ለአስታማሚዎችና ሰዎችን ከማከም ኪነ ጥበብ ጋራ ተያይዘው የሞያዎች ተግባርን የመሳሰሉን በሚሠሩ ሌሎች ሰዎችም ላይ
ይፈጸምባቸዋል፡፡
ቊ 2641፡፡ የሆስፒታል ውል ትርጓሜ፡፡
የሆስፒታል ውል ማለት አንድ የሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት ስለ አንድ የታወቀ በሽታ ብዙ ሐኪሞች ወይም አንድ ሆኖ ላንድ ሰው የሕክምና
ሥራዎች ሊያደርግለት የሚደረግ ውል ነው፡፡

ቊ 2642፡፡ ስለ ውሉ መፈጸም፡፡

(1) ውሉ በቀጥታ በሚታከመው ሰውና በሐኪሙ ወይም በሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት መካከል ሊደረግ ይቻላል፡፡
(2) እንዲሁም በሚታከመው ሰው ፋንታ ከሐኪሙ ወይም ከሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት ጋራ ሦስተኛ ሰው ውሉን ሊያደርግ ይችላል፡፡

ቊ 2643፡፡ ስለ ታከመው ሰው ግዴታ፡፡


በርሱ ፈንታ ሦስተኛ ሰው ውሉን ያደረገለት እንደሆነ የታከመው ሰው ለሐኪሙ የሚገባውን ገንዘብ ወይም ለሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት
ዋጋውን የሚከፍለው፤

(ሀ) በርሱ ፈንታ ውሉን ያደረገው ሰው አባቱ እናቱ ወይም በሕጉ መሠረት ወይም በውል ስለ ጤናው አጠባበቅ ግዴታ ያለበት ሰው
ሲሆን፤
(ለ) ውሉም በተደረገ ጊዜ ፈቃደኛነቱን ለማስታወቅ ያልቻለ ወይም በዚሁ ጊዜ ሕክምና ሊደረግለት አስቸኳይ ሲሆን ነው፡፡

ቊ 2644፡፡ ሐኪሙን ስለጠራው ሰው ግዴታ፡፡


ለሌላው ሰው ብሎ ከሐኪሙ ወይም ከሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት ጋራ ውል ያደረገ ሰው ለሐኪሙ ስለሚገባው ገንዘብና ስለ ሆስፒታሉ
መሥሪያ ቤት ዋጋ አከፋፈል የሚገደደው፤

(ሀ) ሕክምና ለተደረገለት ሰው በሕጉ መሠረት ወይም ስለ ጤናው አጠባበቅ ውል ያደረገ ሲሆን፤

(ለ) ለሐኪሙ ወይም ለሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት ራሱ አላፊ መሆኑን በግልጽ የተስማማ ሲሆን ነው፡፡

ቊ 2645፡፡ ክስ ስለ ማቅረብ፡፡
ለሐኪሙ ወይም ለሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት ከከፈለ በኋላ ሕክምና በተደረገለት ሰው ላይ ክስ የማቅረብ መብት አለው፡፡
ቊ 2646፡፡ የሚከፈል ዋጋ፡፡

(1) ለሐኪሙ የሚገባው ገንዘብና ለሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት የሚከፈለው ዋጋ በውሉ ውስጥ ይወሰናል፡፡

(2) በውሉ ውስጥ ያልተመለከተ እንደሆነ በልማድ መሠረት ይወሰናል፡፡

(3) ይህ የሚከፈለው ገንዘብ ወይም ዋጋ ከመጠን በላይ በመሆኑ የሕክምናን ሞያ ክብር ተቃራኒ ሲሆን ዳኞች ሊያሻሽሉት ይችላሉ፡፡

ቊ 2647፡፡ ስለ ሐኪም አላፊነት፡፡

(1) በኪነ ጥበብ ደንቦች መሠረት ጥፋት ካላደረገ በቀር ሐኪሙ ለመታከም ለተዋዋለው ሰው አላፊነት የለበትም፡፡

(2) ሳይሠራ ከመቅረቱ ወይም ከመሥራቱ የተነሣ በአከመው ሰው ላይ ጉዳት የሚያመጣ ሥራ ያደረገ እንደሆነ አጥፊ ነው ለመባል
ይቻላል፡፡
(3) እንዲሁም ሕክምና ሊያደርግለት የተቀበለውን ሰው በቂ ባልሆነ ምክንያት የተወ፤ በልማድ መሠረትም በርሱ ፋንታ የሚተካውን ሰው
ያልሰጠ ሐኪም አላፊ ነው፡፡

ቊ 2648፡፡ የማዳን ዋስትና፡፡


ሐኪሙ ላደረጋቸው ሕክምና መልካም ውጤት ለመስጠት በግልጽ በጽሑፍ ያላፊነትን ግዴታ ካልሰጠ በቀር አይጠየቅም፡፡
ቊ 2649፡፡ ግዴታው የግል ስለ መሆኑ፡፡

(1) ለአንድ ሰው ሕክምናን ለማድረግ ግዴታ የገባ ሐኪም ራሱ ግዴታዎቹን መፈጸም ይገባዋል፡፡

(2) ይሁን እንጂ፤ በሱ መሪነትና ሙሉ አላፊነት በረዳቶች ማሠራት ይችላል፡፡

(3) ከረዳቶቹ በአንዱ ጥፋት ሕክምና በተደረገለት ሰው ለደረሰበት ጉዳት ከውል ውጭ ስለሚደርስ አላፊነት በሚለው ምዕራፍ በተጻፉት
ቊጥሮች መሠረት አላፊ ይሆናል፡፡

ቊ 2650፡፡ በሦስተኛ ሰው ዘንድ ኀላፊ ስለ መሆን፡፡


(1) በሽተኛዋ ባል ወይም የበሽተኛው ሚስት ወላጆቻቸውና ተወላጆቻቸው ብቻ በታመመው ሰው ሞት ምክንያት ለሚደርስባቸው ጉዳት
ሐኪሙን ካሣ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

(2) የበሽተኛው ሞት የደረሰው በሐኪሙ አስቦ ጥፋት ማድረግ ካልሆነ በቀር በነዚሁ ሰዎች በደረሰው የሕሊና ጉዳት ምክንያት ካሣ
አይሰጥም፡፡
(3) ምንም ሟቹ ለሕይወታቸው አስፈላጊ ነገርን ይሰጣቸው እንደነበረና ወይም በርሱ ጥበቃ ውስጥ እንደነበሩ ቢያስረዱም ሌሎች ሰዎች
በበሽተኛው መሞት ምክንያት በራሳቸው ስም ምንም የጉዳት ካሣ ለመጠየቅ አይችሉም፡፡

ቊ 2651፡፡ ስለ ሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት አላፊነት፡፡ (1) ስለ ሕክምናው አፈጻጸም፡፡


በሐኪሞች ወይም እሱ ባሠራቸው ረዳት ሠራተኞች ጥፋት በበሽተኛው ላይ ለደረሰው ጉዳት የሆስፒታሉ መሥሪያ ናበት በፍትሐ ብሔር
ረገድ አላፊ ነው፡፡

ቊ 2652፡፡ (2) ስለ ሆቴሉ ሥራ አፈጻጸም ጥንቃቄ፡፡


በሽተኛው ስለ ሕክምናው ጥቅም በማለት በሆስፒታሉ መሥሪያ ቤት የተመገበና የተቀመጠ እንደሆነ ስለዚሁ መቀመጥና ስለዚሁ መመገብ
አላፊነቱንና ግዴታዎቹን የሚመለከት የሆቴል ሥራን ውል በሚመሩት በዚህ ሕግ ደንቦች ጽሑፎች መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
ምዕራፍ 6፡፡
ስለ ሆቴል ሥራ ውል፡፡
ቊ 2653፡፡ ትርጓሜ፡፡

(1) የሆቴል ሥራ ውል ማለት አንድ ሰው የሆቴልን ሥራ የሞያ ተግባሩ በማድረግ ሰውን ለአንድ ሌሊት ወይም ለብዙ ሌሊት ለማኖር
የሚደረግ ውል ማለት ነው፡፡

(2) ቤቱ ላንድ ወር ወይም ካንድ ወር ለሚበልጥ ጊዜ በውል የተሰጠ እንደሆነ፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራይ ውል እንጂ፤ የሆቴል ሥራ
ውል አይባልም፡፡
ቊ 2 ሺ 654፡፡ ውሉ የሚቈይበት ጊዜ፡፡
(1) ተቃራኒ የሆነ ውል ከሌለ በቀር የሆቴሎች ክፍል ቤቶች የሚከራዩት ከእኩለ ቀን አንሥቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ነው፡፡

(2) ሰውዬው እንደገና ያልተከራየውን ክፍል ቤት ባለሆቴሉ በእኩለ ቀን እንዲለቅለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 2655፡፡ ስለ ውል ማደስ፡፡

ተከራዩ ወይም ባለሆቴሉ ውሉን ላለመቀጠል (ላለማርዘም) ሐሳባቸውን ከእኩለ ቀን በፊት ያላስታወቁ እንደሆነ ባንድ ደንበኛ የተያዘ
ክፍል ቤት ላንድ ተጨማሪ ቀን እንደተከራየ ያህል ይቈጠራል፡፡

ቊ 2656፡፡ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ስለ መስጠት፡፡


ቤትን ከማከራየት በላይ ለቤቱ ተጨማሪ ነገሮችን በመስጠትና የቤት ዕቃን በሆቴሉ ደረጃና በልማድ መሠረት መብራትን የመሳሰለ
ባለሆቴሉ ለተከራየው ሰው መስጠት ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 2657፡፡ ስለ መንገደኛው ዕቃዎች አጠባበቅ፡፡


ተጨማሪ ዋጋ ለመጠየቅ መብት ሳይኖረው ክፍለ ቤቱ ከተከራየበት ቀን ጧት ጀምሮ የኪራዩ ጊዜ እስካለቀበት ቀን ማታ ድረስ ባለሆቴሉ
ተከራዩን ተቀብሎና ዕቃዎቹንም ሊጠብቅ ግዴታው ነው፡፡

ቊ 2658፡፡ ባለሆቴሉ ስለሚሰጠው ዋስትና፡፡

(1) ባለሆቴሉ ያከራያቸውን ቤቶችና ለሁሉ የሚያገለግሉ ክፍሎችን ለመቀመጫ ተገቢ ጤናማና ጉዳት የማያመጡ ለመሆናቸው ለተከራዩ
ዋስትናውን ያረጋግጣል፡፡
(2) ለተከራዩ መብል ወይም መጠጥ የሰጠ እንደሆነ ስለ ጤናማ ጠባያቸውና መርዛም ላለመሆናቸውም እንዲሁ አላፊ ነው፡፡

(3) አደጋው የደረሰው ከዐቅም በላይ በሆነ በማይታለፍ ኀይል ወይም በተጎጂው ስሕተት ምክንያት ካልሆነ በቀር ከዚህ አላፊነቱ ለመዳን
አይችልም፡፡
ቊ 2659፡፡ ስለ ባለመብል ቤቶችና ስለ ቡና ቤቶች፡፡
ባለመብል ቤቶችና ባለቡና ቤቶች ለሚሰጡት መብልና መጠጥ ጤናማ ለመሆናቸውና መርዛማ ላለመሆናቸው ለደንበኞቻቸው አላፊዎች
ናቸው፡፡
ቊ 2660፡፡ ክፍለ ቤቶችን ስለ መያዝ፡፡

(1) ለታወቀ ቀን አንድ ክፍል ቤት የያዘ ተከራይ በባለሆቴሉ ክፍለ ቤቱ የተያዘለት ለመሆኑ ማስታወቂያ ከደረሰው በኋላ ከዐቅም በላይ
በሆነ ኀይል ምክንያት ባይገባበት እንኳ ለዚሁ ክፍለ ቤት ያንድ ቀን ዋጋ መክፈል አለበት፡፡

(2) ከዚህ ግዴታ ነጻ የሚሆነው በቂ በሆነ ጊዜ የመኝታ ክፍሉን መልቀቁን ለባለሆቴሉ አስታውቆና ባለሆቴሉም ይህን ማስታወቂያ
ተቀብሎ የተያዘውን ክፍለ ቤት ላንድ ሦስተኛ ሰው ማከራየት የቻለ እንደሆነ ነው፡፡

(3) ተቃራኒ የሆነ ውል ከሌለ በቀር ክፍለ ቤቱ የተያዘው ለብዙ ቀን ቢሆንና የገንዘቡም አከፋፈል በሳምንት ወይም በወር ሆኖ ቢመለከትም
የጉዳት ኪሣራ የሚከፈለው ላንድ ቀን ብቻ ነው፡፡

ቊ 2661፡፡ የውል መፍረስ፡፡

(1) ክፍለ ቤቱን ለብዙ ቀን የተከራየ እንደሆነና ተከራዩ እሱ ባለው ቀን ያልያዘው እንደሆነ ውሉ ይፈርሳል፡፡

(2) ከተከራዩ ወይም በርሱ ምትክ ከሆነው ሰው ተከራዩ መከራየቱን አልተውም የሚል ማስታወቂያ ካልደረሰው በቀር ባለሆቴሉ በዚሁ
ጊዜ ክፍለ ቤቱን ለሌላ ሰው ቢያከራይ አንድም አላፊነት አይነካውም፡፡

(3) ባለሆቴሉ አስቀድሞ ገንዘብ ተቀብሎ እንደሆነ የተቀበለው ገንዘብ ለኪራዩ ዋጋ በቂ እስከሚሆንበት ቀን ድረስ ለተከራዩ ክፍለ ቤቱን
ጠብቆ ማስቀመጥ አለበት፡፡

ቊ 2662፡፡ የመያዝ መብት ፡፡

(1) ተከራዩ በሆቴል ውስጥ የቈየበትን ጊዜ በመገመት የሚከፈለውን ገንዘብ በሙሉ እስከ ከፈለ ድረስ ያመጣቸውን ዕቃዎች ባለሆቴሉ
መያዝ ይችላል፡፡

(2) ለነዚሁ ዕቃዎቹ ባለሆቴሉ ዕቃ ይዞ የሚያበድር ሰው መብትና ቀደምትነት አለው፡፡

ቊ 2663፡፡ የአላፊነት መሠረት፡፡

(1) ደንበኞቹ በሆቴሉ ውስጥ ላስቀመጧቸው ዕቃዎች ባለሆቴሉ እንደ አንድ ደመወዘኛ አደራ አስቀማጭ ይገደዳል፡፡

(2) አንድ ደንበኛ፤ ዕቃዎቹን ወደ ሆቴሉ ውስጥ ለማምጣቱ ማናቸውንም ዐይነት ማስረጃ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

ቊ 2664፡፡ ቊርጥ ዋጋ ስለ መወሰን፡፡


የባለሆቴሉ ኀላፊነት 5 የኢትዮጵያ ብር በሆነ ገንዘብ የተወሰነ ሆኗል፡፡
ቊ 2665፡፡ ስላልተወሰነ አላፊነት፡፡ (1) በአደራ ዕቃ ሲቀመጥ ወይም ጥፋት ሲገኝ፡፡
የሆነ ሆኖ የባለሆቴሉ ኀላፊነት ያልተወሰነ የሚሆነው፤
(ሀ) የተደረገው ጉዳት በባለሆቴሉ ወይም ከቤተሰቡ ወይም ከሠራተኞቹ በአንዱ ጥፋት የሆነ እንደሆነ፤

(ለ) ጉዳቱ የደረሰው ደንበኛው ለባለሆቴሉ በተለይ በአደራ በሰጣቸው ዕቃዎች ላይ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 2666፡፡ (2) አደራ ማስቀመጥን እንቢ ስለ ማለት፡፡

(1) ባለሆቴሉ ትክክል ባልሆነ ምክንያት በአደራ ለማስቀመጥ አልቀበልም ያላቸውን ዕቃዎች ጉዳት ያገኛቸው እንደሆነ እንዲሁ የባለሆቴሉ
ኀላፊነት ያልተወሰነ ነው፡፡

(2) እንደ ሆቴሉ ማዕረግና እንዳሉት ክፍሎች መጠን ዕቃው ያለ መጠን ዋጋ ያለው ወይም ለማኖር የማይመች ሁኔታ ያለው እንደሆነ
ለእንቢታው ትክክል ምክንያት ይሆነዋል፡፡

ቊ 2667፡፡ ኀላፊነት የሚቀርበት፡፡

(1) ኀላፊነቱ የሚቀረው ዕቃው የተሠረቀው የጠፋው ወይም የተበላሸው በደንበኛው በራሱ ጥፋት ወይም ደንበኛውን በሚጠይቁት
በሚከተሉት ወይም እሱን በሚያገለግሉ ሰዎች ጥፋት መሆኑን ባለሆቴሉ ያስረዳ እንደሆነ ነው፡፡

(2) እንዲሁም የዕቃው መጥፋት ወይም መበላሸት በዕቃው ዐይነት ወይም ጒድለት ወይም ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል የሆነ እንደሆነ
ከኀላፊነት ነጻ ነው፡፡

ቊ 2668፡፡ ስለ ማስታወቅ ግዴታ፡፡


ደንበኛው፤ ጉዳቱን እንዳወቀ ወዲያውኑ ካላስታወቀ በቀር ባለሆቴሉ ከኅላፊነት ነጻ ነው፡፡
ቊ 2669፡፡ ኀላፊነትን የሚያስቀር ስምምነት፡፡
የባለሆቴሉን ኀላፊነት ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ የሚደረግ የውል ቃል ሁሉ አይጸናም፡፡
ቊ 2670፡፡ ሕጉ የሚጸናበት ወሰን፡፡

(1) ደንበኛው ዕቃዎቹን አስቀድሞ ልኮ እርሱ ካልቀረ በቀር ዕቃዎቹ በሆቴሉ ውስጥ ከገቡ ወዲህ የዚሁ ምዕራፍ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ
ይሆናሉ፡፡
(2) እንዲሁም በሆቴሉ ክፍሎች ውስጥ ወይም በሆቴሉ ለደንበኞች በሆኑ ቦታዎች ውስጥ ያሉ እንደ ተሽከርካሪዎች ኦቶሞቢሎች
በሕይወት ያሉ እንስሳዎች ዕቃዎችም ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2671፡፡ እንደ ሆቴሎች የሚቈጠሩ ቤቶች፡፡


የዚህ ምዕራፍ ደንቦች በሆስፒታል መሥሪያ ቤቶች በዕረፍት ቤቶች በሕዝብ መደሰቻዎች በመታጠቢያ ቤቶች በኪራይ በሚመገቡ ሰዎች
መኖሪያ ቤቶች በምግብ ቤቶች አልጋ ባለባቸው የማደሪያ (የባር) ክፍል ቤቶች ለሕዝብ በተሠሩ በረቶችና ሌሎች እነዚሁን በመሳሰሉ
ሥራዎች በሚካሄዱ ቦታዎች ላይ ሁሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
ምዕራፍ 7፡፡
አትሞ የማውጣት (ፐብሊሺንግ) ውል፡፡

ቊ 2672፡፡ ትርጓሜ፡፡
አትሞ የማውጣት ውል ማለት አንዱ ወገን ደራሲ ተብሎ የሚጠራው ባንድ የድርሰት ሥራ ወይም ኪነ ጥበብ ላይ ያለውን ግዙፍነት
የሌለውን የባለሀብትነት መብቶች ወይም ከነዚሁ መብቶች በከፊል አትሞ አውጪ (ፐብሊሺር) ተብሎ ለሚጠራው ለሌላው ወገን
የሚሰጥበት አትሞ አውጪውም ድርሰቱን ለማተም ለማሳየት ወይም ለማባዛት ወይም ለሕዝብ ለመንዛት ግዴታ የሚገባበት ውል ነው፡፡

ቊ 2673፡፡ የማስታወቅ ግዴታ፡፡


ሥራው በሙሉ ወይም በከፊል ላንድ ሌላ አትሞ አውጪ ተሰጥቶ እንደሆነ ወይም ድርሰቱን ደራሲው ዐውቆት ለሕዝብ ታትሞ ተገልጾ
እንደሆነ ይህ ደራሲ ውሉን ከማድረጉ በፊት አትሞ ለሚያወጣው ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2674፡፡ የውሉ ዐይነት (ፎርም)፡፡


ሥራውን ለማባዛት ወይም ለማሳየት ደራሲው አትሞ ለሚያወጣው የሰጠው ፈቃድ ግልጽ መሆን አለበት፡
ቊ 2675፡፡ ወደፊት በሚወጡት ሥራዎች ላይ ያለውን መብት ስለ ማስተላለፍ፡፡
1 ወሰን፡፡
(1) አእምሮ ባለው ሰው አስቀድሞ በመመልከት ተግባር ከሁለት ዓመት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ በደራሲው ለመፈጸፀም የሚችሉ
መሆናቸው ከታወቁ ደራሲው ገና ያላለቀ በቂ በሆነ አኳኋን የተለየ በአንድ ወይም በብዙ ሥራዎች ላይ ያለውን መብት ለማስተላለፍ
የሚዋዋለው ውል ዋጋ ያለው ነው፡፡

(2) ከዚህ ወሰን አልፎ ወደፊት በሚወጡት ሥራዎች ላይ ደራሲው መብቶቹን ለማስተላለፍ የተዋዋለ እንደሆነ ምንም ተቃራኒ የውል ቃል
ቢኖር እንኳ አትሞ ከሚያወጣው የተቀበለውን ገንዘብ እንደ ያዘ አስቀርቶ በማናቸውም ጊዜ ውሉን ማፍረስ ይችላል፡፡

ቊ 2676፡፡ (2) አትሞ አውጪው ያለው የቀደምትነት መብት፡፡

(1) ይፍረስ ያለው ደራሲ ውሉ ከፈረሰበት ጊዜ አንሥቶ ቢበዛ እስከ አምስት ዓመት ጊዜ ድረስ አትሞ ማውጣቱን ተዋውሎት ለነበረው
ሰው ከሌሎች ሰዎች በፊት የቀደምትነት መብቱን ሊሰጠው ግዴታ አለበት፡፡

(2) እነዚህንም መብቶች ለማግኘት ሦስተኞች ወገኖች ያቀረቡለትን የውለታ ሁኔታዎች ለአታሚው ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) በቀደምትነት፤ መብቱን ሊሠራበት መፈለጉን አትሞ አውጪው በሚገባ ጊዜ ውስጥ ካላስታወቀ ይህ መብት ይቀርበታል፡፡

ቊ 2677፡፡ የውሉ ውጤት፡፡

(1) በዚህ አንቀጽ በተደነገጉት ውሳኔዎች መሠረት የውሉ አፈጻጸም እንደሚያስገድደው መጠን ደራሲው በሥራው ላይ ያሉትን መብቶች
ለአትሞ አውጪው ያስተላልፍለታል፡፡

(2) እነዚህን ድንጋጌዎች ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል በግልጽ ለመጻፍ ሕጉ ያልከለከለ እንደሆነ ተዋዋዮቹ እነዚህን ውሳኔዎች ለመለወጥ
ይችላሉ፡፡

(3) የሚያጠራጥር የሆነ እንደሆነ የማተም የውል ቃሎች ለደራሲው ጥቅም እንደሚሆኑ የሚተረጐሙ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2678፡፡ በጠባቡ ስለ መተርጐም፡፡

(1) ባንድ ዐይነት ሁኔታ ሥራውን እንዲሠራ ለአትሞ አውጪው የተሰጠው ፈቃድ በጠባቡ መተርጐም አለበት፡፡

(2) አትሞ አውጪው በውሉ ውስጥ ከተመለከተው አሠራር ዐይነት ውጭ በሌላ አሠራር ዐይነት ሊጠቀምበት አይችልም፡፡

ቊ 2679፡፡ በሥራው ለመጠቀም የተፈቀደ የአሠራር ዐይነት፡፡

(1) የውሉ ቃሎች ምንም በጠቅላላ አነጋገር ቢነገሩም እንኳ ውሉ በተደረገበት ጊዜ ተዋዋዮቹ አስበውት በነበረ ወይም ሊያስቡት ይገባቸው
በነበረ አሠራር ዐይነት ካልሆነ በቀር አትሞ አውጪው በሌላ ዐይነት አሠራር ለመጠቀም መብት የለውም፡፡

(2) እንደዚህ በሆነ ጊዜ አእምሮ ያለው ሰው በሚገምተው ዐይነት ማመዛዘን ይገባል፡፡

ቊ 2680፡፡ መለዋወጥና መተርጐም፡፡


አንድ ሥራን ለማባዛት ወይም ለማሳየት የተሰጠ ፈቃድ መለዋወጥን ወይም እንዲተረጐም መፍቀድን በሌላ ዐይነት ሥራ ማስማማትን
አይፈቅድም፡፡
ቊ 2681፡፡ በራዲዮ የተነገሩትን ሥራዎች ስለ መመዝገብ፡፡
አንድ ሥራ በራዲዮ እንዲነገር የተሰጠ ፈቃድ፤ በራዲዮ የተነገረውን ሥራ ድምፅን ወይም ሥዕልን ተቀብለው ለማስቀረት በሚችሉ
መሣሪያዎች እንዲመዘገብ መፍቀድን አይጨምርም፡፡

ቊ 2682፡፡ የተለያዩ ሥራዎችና ሙሉ የሆኑ ሥራዎች፡፡


(1) ያንድ ደራሲ ሥራዎችን ለየብቻ አትሞ የማውጣት መብት ሁሉንም አንድ ላይ የማውጣትን መብት አይጨምርም፡፡

(2) ያንድ ደራሲን ሙሉ ሥራዎች ወይም ከሥራዎች አንዱን ዐይነት ክፍል አትሞ የማውጣት መብት ልዩ ልዩ ሥራዎች የያዙትን ለየብቻ
የማውጣትን መብት አትሞ ለሚያወጣው አይሰጠውም፡፡

ቊ 2683፡፡ የደራሲው መድንነት፡፡


አትሞ ከማውጣት ውል የተነሣ ደራሲው አትሞ ለሚያወጣው ሰው የሚያስተላልፋቸው የድርሰት የኪነ ጥበብ መብቶች እንዳሉትና
እነዚህንም ለማስተላልፍ ባለመብት ለመሆኑ አትሞ ለሚያወጣው ሰው መድን ነው፡፡

ቊ 2684፡፡ አትሞ ለሚያወጣው ሰው የተላለፈ መብት፡፡

(1) አትሞ የሚያወጣው ሰው አትሞ ያወጣቸው ድርሰቶች እስካለቁ ድረስ ደራሲው ሥራውን በሙሉ ወይም ከነዚሁ አንዱን ክፍል አትሞ
የሚያወጣውን ሰው በሚጎዳ አኳኋን ሊያዝበት አይችልም፡፡

(2) በኅብረት ከተደረሰ ድርሰት ወይም ከተጻፈ ቃል አንዱን ክፍል የማውጣቱ ተግባር ከተፈጸመ ሦስት ዓመት ካላለፈ በቀር ደራሲው
እንደገና ለማውጣት አይችልም፡፡

ቊ 2685፡፡ በሁለት አትሞ አውጪዎች መካከል ስለሚነሣ ክርክር፡፡

(1) አንድ ደራሲ መብቶቹን ላንድ አትሞ አውጪ ካስተላለፈ በኋላ እነዚሁኑ መብቶች ለሌላ አትሞ አውጪ ያስተላለፈ እንደሆነ ሁለተኛው
ባለውል የመጀመሪያውን ውል ካላወቀ በቀር የሚያደርገው ውል ዋጋ ያለው ይሆናል፡፡

(2) ደራሲው በያንዳንዳቸው ተዋዋዮች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2686፡፡ ድርሰቱን አትሞ ስለ ማውጣት፡፡

(1) አትሞ አውጪው ድርሰቱን ሳያሳጥር ሳይጨምር እንዲሁም ሳይለዋውጥ ተገቢ በሆነ ፎርም ማውጣት አለበት፡፡

(2) ድርሰቱንም ሕዝብ እንዲያውቀውና የተመዱትንም የማስታወቂያ አሠራር ማድረግ አለበት፡፡

(3) የመሸጫውንም ዋጋ ይወስናል፡፡

ቊ 2687፡፡ ደራሲው ስለሚያደርገው እርማት (ማረም)፡፡

(1) ያትሞ አውጪውን ጥቅሞች ካላበላሹ ወይም ኀላፊነትን የሚጨምርበት ካልሆነ በቀር ደራሲው በማናቸውም ጊዜ ድርሰቱን ለማረምና
ለማሻሻል ይችላል፡፡

(2) በዚሁም ምክንያት አትሞ አውጪው ያደረጋቸውን ወጪዎች መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2688፡፡ እንደ ገና አትሞ ስለ ማውጣት፡፡


አትሞ አውጪው እንደገና አትሞ ከማውጣቱ በፊት ደራሲው ድርሰቱን ለማሻሻል እንዲችል የሚያስፈልገውን ማድረግ አለበት፡፡
ቊ 2689፡፡ እንዲታተሙና እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ድርሰቶች፡፡

(1) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር አትሞ አውጪው ለማውጣት መብት ያለው በመጀመሪያው አትሞ ያወጣቸውን ብቻ ነው፡፡

(2) አትሞ ለማውጣት ምን ያህል ቅጂዎች መሆናቸውን ውሉ ለይቶ ያላመለከተ እንደሆነ ብዛቱን የሚወስነው አትሞ አውጪው ነው፡፡

ቊ 2690፡፡ ታትሞ የወጣው ስለ ማለቁ፡፡

(1) በብዙ ጊዜ እያተመ ወይም የሚታተመውን ሁሉ ድርሰት ለማውጣት ላትሞ አውጪው ውሉ የፈቀደለት እንደሆነ ደራሲው ስለ ድርሰቱ
በመጨረሻው ታትሞ የወጣው ካለቀ እንደ ገና አትሞ እንዲያወጣ ያንድ ዓመት የተወሰነ ጊዜ ሊወሰንበት ይችላል፡፡

(2) በዚህ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሥራውን ካልፈጸመ አትሞ አውጪው መብቶቹን ያጣል፡፡
(3) ይህን ውሳኔ ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ሁሉ ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2691፡፡ ተከታትለው ታትመው ስለሚወጡ ድርሰቶች የሚደረግ የውል ስምምነት፡፡

(1) አትሞ አውጪው ብዙ ጊዜ አትሞ ለማውጣት መብት ያለው እንደሆነ በሚከተሉት አንዳንድ ታትመው በሚወጡት ላይ
የመጀመሪያው አትሞ ማውጣት ስምምነቶች ቃል እንዲሠራባቸው እንደተወሰነ ይቈጠራል፡፡

(2) በተይም የደራሲውን የሥራ ዋጋ የሚመለከቱ የውል ቃሎች በዚሁ ይፈጸማሉ፡፡

ቊ 2692፡፡ የደራሲው የሥራ ዋጋ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የሥራውን ዋጋ ሁሉ ለመተው ስምምነት አድርጓል ለማለት አካባቢው ሁኔታዎቹ በሚፈቅዱበት ጊዜ ታትሞ የሚወጣን ድርሰት የሰጠ
ደራሲ ለሥራ ዋጋ መብት እንዳለው ሆኖ ይቈጠራል፡፡

(2) ተዋዋዮቹ ያልተስማሙበት እንደሆነ ለደራሲው ተገቢ የሆነውን የሥራ ዋጋ በርትዕ ዳኞች ይወስናሉ፡፡

ቊ 2693፡፡ (2) ያለ ዋጋ የሆኑ ቅጂዎች፡፡

(1) ደራሲው የተወሰነ ብዛት ያለውን የድርሰቱን ቅጂዎች ያለ ዋጋ ለማግኘት መብት አለው፡፡

(2) የውል ቃል ከሌለ የነዚሁኑ ቅጂዎች ብዛት ዳኞች በርትዕ ይወስናሉ፡፡

ቊ 2694፡፡ (3) ስለ መክፈል፡፡

(1) ድርሰቱ ለመሸጥ ዝግጁ ሲሆን የደራሲው የሥራ ዋጋ ወዲያውኑ ተከፋይ ይሆናል፡፡

(2) ከሽያጩ ውጤት በሙሉው ወይም በከፊል የደራሲውን የሥራ ዋጋ ለመክፈል ተዋዋዮቹ ስምምነት አድርገው እንደሆነ፤ አትሞ
አውጪው በተስማሙባቸው ጊዜ ውስጥ የሽያጩን ውጤቶች ለደራሲው ማስረዳት አለበት፡፡

(3) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ ያትሞ አውጪው ሒሳብ በያመቱ መጀመሪያ ወር ለደራሲው መሰጠት አለበት፡፡

ቊ 2695፡፡ ስለ ድርሰቱ መጥፋት፤ (1) ታትሞ ከመውጣቱ በፊት፡፡

(1) ድርሰቱ ለአሳትሞ አውጪው ከተሰጠ በኋላ ታትሞ ከመውጣቱ በፊት በድንገተኛ ነገር የጠፋ እንደሆነ አትሞ አውጪው ለደራሲው
የሥራ ዋጋውን መክፈል አለበት፡፡

(2) ደራሲው የጠፋው ድርሰት ቅጂው በጁ እንደሆነ ለአትሞ አውጪው መስጠት አለበት፡፡

(3) እንዲህ ካልሆነም ድርሰቱ የማያስቸግር የሆነ እንደሆነና አትሞ አውጪውም ሲጠይቀው ደራሲው የሚገባ ገንዘብ ተቀብሎ እንደገና
ድርሰቱን አዘጋጅቶ መስጠት አለበት፡፡

ቊ 2696፡፡ (2) ታትሞ ከወጣ በኋላ፡፡

(1) አትሞ አውጪው ያሰናዳው ከታተመ በኋላ በሙሉ ወይም በከፊል በድንገተኛ ነገር የጠፋ እንደሆነ አትሞ አውጪው የጠፉትን
ቅጂዎች በኪሣራው እንደገና ለማሠራት መብት አለው፡፡

(2) ኪሣራው ከመጠን በላይ ሳይሆን ለማድረግ የቻለ እንደሆነ አትሞ አውጪው እነዚሁኑ ቅጂዎች መተካት አለበት፡፡

ቊ 2697፡፡ ስለ ውሉ ቀሪነት፡፡

(1) ሥራው ከመፈጸሙ በፊት ደራሲው የሞተ ችሎታ ያጣ ወይም ጥፋት ሳይኖርበት ለመጨረስ ያልተቻለው የሆነ እንደሆነ የማተሙ ውል
ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) ያትሞ አውጪው መሞት ወይም የደረሰበት የችሎታ ማጣት ውሉን ቀሪ አያደርገውም፡፡
(3) አትሞ አውጪው የከሠረ እንደሆነ መከሠሩ በሚገለጽበት ጊዜ የተወሰነ ጊዜ ገና ያልደረሰባቸውን ግዴታዎች ለመፈጸም ዋስትና
ካልተሰጠው በቀር ደራሲው ሥራውን ለሌላ አትሞ አውጪ መስጠት ይችላል፡፡

አንቀጽ ዐሥራ ሰባት፡፡


የዕቃ ጥበቃን በዕቃ መገልገልን ወይም በዕቃ መጠቀሙን የሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 2698፡፡ የዚህ አንቀጽ ደንብ አፈጻጸም፡፡

(1) አንድ ተንቀሳቃሽ ዕቃ እንዲጠብቅ ወይም በዚሁ እንዲጠቀምበት ከተዋዋዩ ወገን በውል ተስሣመቶ በመረከቡ ይህ ዕቃ በእጁ የሚገኝ
ሰው ከተዋዋዩ ጋራ በሚኖረው ግንኙነት ጒዳይ በዚህ አንቀጽ የተመለከቱት መብቶችና ግዴታዎች አሉት፡፡

(2) በተንቀሳቃሹ ዕቃ ባለቤትና ዕቃው በእጁ በሚገኘው ሰው መካከል ያለውን ግንኙነት ስለሚመለከተው ጒዳይ፤ በሕጉ ላይ በተገለጸው
መሠረት፤ ከማንኛውም ውል በሆነውም ነገር እንዲሁ እነዚሁ ድንጋጌዎች የሚጸኑ ናቸው፡፡

ቊ 2699፡፡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፡፡

(1) የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ኪራይ የሚመለከቱት ደንቦች በዚህ ሕግ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች በተጻፈው
አንቀጽ ውስጥ ተገልጸዋል፡፡

(2) በማይንቀሳቀስ ንብረት መገልገልና መጠቀም ለሌላ ሰው የተሰጠው ያለ ዋጋ በሆነ ጊዜ ያገልግሎት ትውስትን የሚመለከቱት የዚህ
አንቀጽ ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2700፡፡ ባለቤት፡፡

(1) ባለሀብት (ባለቤት) የሚል ቃል በዚህ ምዕራፍ ላይ የተጻፈው ዕቃውን አሳልፎ በባለይዞታው እጅ እንዲገኝ አድራጊውን ሰው
ለማመልከት ነው፡፡

(2) ባለይዞታው በዚህ ዕቃ ላይ ያለው ወይም አለኝ የሚለው መብት ከባለሀብትነት መብት ውጭ በሆነ ሌላ ዐይነት መብት ሲሆን በዚህ
ምዕራፍ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች በተመሳሳይነት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2701፡፡ የማስረከብ ግዴታ፡፡

ባለሀብቱ ዕቃውን ለባለይዞታው በሚሰጥበት ጊዜ በውሉ ላይ ለተመለከተው ጒዳይ ወይም የዕቃው ተፈጥሮ ጠቃሚ አገልግሎት ሊሰጥ
በሚችልበት ዐይነት እንዲያገለግል ከተጨማሪው ጋራ አድርጎ በመልካም ሁኔታ ማስረከብ አለበት፡፡
ቊ 2702፡፡ ወደ ሽያጭ ደንብ ስለ መምራት፡፡

የዕቃው ማስረከቢያ ስፍራና ዘመን እንዲሁም የዕቃው መለዋወጫ የሆኑትን ተጨማሪ ነገሮች የመጥቀስ ጒዳዮች የሚከናወኑት ስለ ሽያጭ
ደንብ በወጣው ድንጋጌ መሠረት ነው፡፡

ቊ 2703፡፡ በዕቃው ላይ የሚገኝ ጒድለት፡፡ (1) ስለ ውል መፍረስ፡፡

(1) ዕቃው ተላልፎ በሚሰጥበት ጊዜ ለባለይዞታው ሊያገለግል የነበረውን ከፍ ያለ ግምት ሊያሳጣው የሚችል ጒድለት ያለበት ሆኖ የተገኘ
እንደሆነ ወይም ይህን ዕቃ ለማኖር ወይም ለመጠበቅ ከፍ ያለ ችግር የሚያመጣበት፤ ወይም እጅግ ከፍተኛ ወጪ የሚያደርስበት ሆኖ
ሲገኝ ባለይዞታው ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ዕቃው ጒድለት የተገኘበት ወይም ጒድለት የተገለጸበት ተላልፎ ከተሰጠው በኋላም ቢሆን ለባለይዞታው የዚሁ ዐይነት
መብት ይኖረዋል፡፡

(3) የውሉ ስምምነት በተደረገ ጊዜ ባለሀብቱ ይህ ጉድለት መኖሩን የሚያውቅ ወይም ማወቅ ይገባው የነበረ ካልሆነ በቀር ባለይዞታው
በዕቃው አገልግሎት ማግኘት ይገባው የነበረው ልዩ ጥቅም በግምት፤ ውስጥ አይገባም፡፡

ቊ 2704፡፡ (2) ኪሣራ፡፡

(1) ባለሀብቱ ዕቃውን ባስረከበበት ጊዜ ጒድለት ያለበት መሆኑን የሚያውቅ ወይም ሊያውቅ የሚገባው እንደነበረና ይህ ጒድለት
መኖሩንም ለባለይዞታው ሳያስታውቅ ችላ ብሎ እንደሆነ ጒድለቱ በባለይዞታው ላይ ላደረሰበት ጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(2) ጒድለቱ የደረሰው ውሉ በመፈጸም ላይ በሚገኝበት ጊዜ ሆኖ የደረሰውም ከባለሀብቱ ጥፋት የተነሣ እንደሆነም አፈጻጸሙ በዚሁ
ዐይነት ነው፡፡

ቊ 2705፡፡ (3) የውሉ ስምምነት መድን፡፡

ባለሀብቱ ይህ ዕቃ የዚህ ዐይነት ጠባይ አለው ብሎ እንዳረጋገጠው ሳይሆን፤ አለው የተባለው ጠባያዊ ዐይነት ያልነበረው ወይም የሌለው
ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ውሉ እንዲፈርስ የዕቃው ጒድለትም ላደረሰበት ጉዳት ባለይዞታው ኪሣራ ሊጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2706፡፡ (4) ባለይዞታው ያወቃቸው ጒድለቶች፡፡

(1) የውሉ ስምምነት በተደረገ ጊዜ፤ ባለይዞታው፤ በዕቃው ላይ ጒድለት እንደነበረበት የሚያውቅ መሆኑን ባለሀብቱ ካስረዳ፤ በዕቃው ላይ
ስለተገኘው ጒድለት አላፊ መድን አይሆንም፡፡
(2) በእንደዚህ ያለው ነገር ባለሀብቱ የሰጠው ግልጽ የሆነ ዋስትና ቢኖርም እንኳ ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 2707፡፡ (5) አደገኛ ጒድለት፡፡

(1) ዕቃው በባለይዞታው ሕይወት ወይም በጤንነቱ ላይ ወይም ከሱ ጋራ በሚኖሩ ሰዎች ወይም በሠራተኞቹ ሕይወት ወይም
በጤንነታቸው ላይ አደጋ ለማድረስ የሚችል ጒድለት የተገኘበት እንደሆነ ዕቃው የዚህ ዐይነት ጒድለት ያለበት መሆኑን ያወቀው የውሉን
ስምምነት ባደረገበት ጊዜም ቢሆን እንኳ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ይህን ደንብ ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ሁሉ ቀሪ ነው (ዋጋ የለውም)፡፡

ቊ 2708፡፡ (6) አላፊነት የለብኝም ተብሎ ስለሚደረግ የውል ቃል፡፡

ባለሀብቱ በዕቃው ላይ ያለውን ጒድለት ሳይገልጽ የደበቀው በማታለል እንደሆነ ወይም የዕቃው ጒድለቶች ለባለይዞታው የሚሰጡትን
ጠቃሚ አገልግሎት ፈጽሞ የሚያጠፉበት (የሚያፈርሱበት) ሆነው የተገኙ እንደሆነ ባለሀብቱ በዕቃው ጒድለቶች ምክንያት ከሚያደርስበት
አላፊነት ለመዳን አላፊነቱን የተወሰነ ለማድረግ በውሉ ውስጥ የጠቀሰው የስምምነት ቃል (ዋጋ የለውም) ቀሪ ነው፡፡

ቊ 2709፡፡ ሰላማዊ መጠቀም፡፡

ውሉ ጸንቶ በሚቈይበት ዘመን፤ ባለይዞታው በዕቃው ሰላማዊ ጥቅም ለማግኘት እንዲችል ባለሀብቱ አላፊ መድን መሆን አለበት፡፡

ቊ 2710፡፡ በዕቃው ላይ ስለሚደርሰው መለወጥ፡፡

ባለሀብቱ የዕቃውን የአገልግሎት ጥቅም ለመቀነስ ወይም በባለይዞታው ላይ ከፍ ያለ ወጪ ሊያመጣ የሚችል ማንኛውም የመለወጥ ጠባይ
በዕቃው ላይ እንዲደርስ ማድረግ አይገባውም፡፡

ቊ 2711፡፡ ድንገተኛ ሁከት፡፡

(1) በዕቃው ላይ መብት አለን የማይሉ ሌሎች ሰዎች በዚሁ ዕቃ ምክንያት ስለሚያደርሱት ሁከት ባለሀብቱ አላፊ መድን እንዲሆን
አይገደድም፡፡
(2) ባለይዞታው በእነዚህ ሦስተኛ ወገኖች ላይ በራሱ ስም ወቃወሚያ ለማቅረብ ይችላል፡፡

ቊ 2712፡፡ ግዴታና ግብር፡፡


በዕቃው ላይ የሚጠየቀውን ግዴታና የሚከፈለውን ግብር የሚችል ባለሀብቱ ነው፡፡

ቊ 2713፡፡ ዕቃውን ስለ መጠበቅና ስለ ማኖር፡፡

(1) ባለይዞታው ስለ ዕቃው ጥበቃና ስለ ማኖሩ ጒዳይ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡

(2) ባለሀብቱ ካልፈቀደለት በቀር የዕቃውን አገልግሎት ለሌላ ጒዳይ ሊያውለው አይችልም፡፡

ቊ 2714፡፡ ለባለሀብቱ የማስታወቅ ግዴታ፡፡

ለዕቃው መልካም አያያዝና ጥበቃ ባለሀብቱ እንዲደርስ አስፈላጊ የሚሆኑበትን ጒዳዮች እንደ አስቸኳይ የሆኑ የማደስ ሥራዎች ያሉትን
ነገሮችና ድንገት የሚገኙበትን ጒድለቶች በሌሎች ሦስተኛ ወገኖች በኩል የሚደርስበትን የመውሰድ የሁከት ወይም ጉዳት ይህን የመሳሰለ
ነገር እንደደረሰ ወዲያውኑ የዕቃው ባለይዞታ ለባለሀብቱ ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2715፡፡ ዕቃውን ለማኖርና በመልካም አያያዝ ለመጠበቅ የሚያስፈልግ ወጪ፡፡

(1) ዕቃውን ለማኖርና ለመጠበቅ ላያያዙ ወጪ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ የዚህን ዐይነት ወጪ መቻል ያለበት ባለይዞታው ባልሆነ ጊዜ
ይህ ወጪ ማስፈለጉን ለባለሀብቱ ማስታወቅ ይገባዋል፡፡

(2) ለዚሁ ጒዳይ አስቸኳይ የሆነ ወጪ አስፈልጎ ባለይዞታው ይህን አስፈላጊ ወጪ እንዳደረገ ወዲያውኑ ለባለሀብቱ አስታውቆ እንደሆነ
ያወጣው ገንዘብ እንዲመለስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2716፡፡ የባለሀብቱ ተቈጣጣሪነት፡፡

(1) ባለይዞታው እሱን የሚመለከቱትን ግዴታዎች በሚገባ የሚፈጽምና የማይፈጽም መሆኑን ለማረጋገጥ ባለሀብቱ በማንኛውም ጊዜ
ምርመራ ለማድረግ መብት አለው፡፡

(2) ይህ ምርመራ ግን በባለይዞታው ላይ ከፍ ያለ ሁከትና የማበሳጨት ስሜት በማያደርስበት ሁኔታ ትክክለኛነት ያለው ሆኖ እንዲፈጸም
ያስፈልጋል፡፡

ቊ 2717፡፡ በዕቃው ላይ መብት አለኝ ስለሚል ሦስተኛ ወገን፡፡

(1) ሌላ ሦስተኛ ወገን ዕቃው የኔ ነው ወይም በዕቃው ላይ መብት አለኝ ብሎ የተነሣ እንደሆነ ባለይዞታው ይህን ጒዳይ ወዲያውኑ
ለባለሀብቱ ማስታወቅ አለበት፤ ሳያስታውቅ ቢቀር ግን ኪሣራ ይከፍላል፡፡
(2) ይህም ሦስተኛ ወገን ክስ አቅርቦ እንደሆነ ክርክሩ በከሳሹና በባለሀብቱ መካከል እንዲፈጸምና ባለይዞታው ከነገሩ ውጭ እንዲሆን
ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ጊዜ ዕቃውን ዳኞች ባዘዙት ሁኔተ ባመለከቱት ስፍራ በባለሀብቱ ኪሣራ መልሶ በማስረከብና በማስቀመጥ
በውሉ ከገባበት ግዴታ ነጻ ለመውጣት ይችላል፡፡

ቊ 2718፡፡ መልሶ የመስጠት ግዴታ፡፡

(1) ባለይዞታው ዕቃውን መልሶ መስጠት የሚገባው በተረከበበት ጊዜ በነበረበት ሁኔታና በተረከበበት ስፍራ ነው፡፡

(2) በተረከበበት ጊዜ ዕቃው በምን ሁኔታ ይገኝ እንደነበረ የሚታወቀው ተዋዋዮች ወገኖች ስምምነቱን ሲያደርጉ በሰጡት ዝርዝር
መግለጫ መሠረት ነው፡፡

(3) የዚህ ዐይነት ዝርዝር መግለጫ የሌለ እንደሆነ ባለይዞታው ዕቃውን በተረከበ ጊዜ በመልካም ሁኔታ እንደነበረ ሆኖ ይታሰባል፡፡

ቊ 2719፡፡ ከባለይዞታው የተወሰደበት ዕቃ፡፡

(1) ራሱን ተጠያቂ በማያደርገው አጋጣሚ ምክንያት ዕቃው ከባለይዞታው ላይ ተወስዶ እንደሆነ ከመመለስ ግዴታ ነጻ ይወጣል፡፡

(2) ይህ ዕቃ ከእጁ የወጣበትን ምክንያትና ባለይዞታ መሆኑ የቀረበትን አጋጣሚ ነገር ወዲያውኑ በፍጥነት ለባለሀብቱ ማስታወቅ
ይገባዋል፡፡
ሳያስታውቅ ቢቀር ግን ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡
(3) ይህ ዕቃ ከባለይዞታው ስለተወሰደበት በምትኩ የሚሰጠውን ልዋጭ ዕቃ የመቀበል መብትና በባለይዞታው መብት ተተክቶ ባለገንዘቡ
የመጠየቅ መብት አለው፡፡

ቊ 2720፡፡ የዕቃው መጥፋት ወይም መበላሸት፡፡ (1) ጥቅም ያለው ጥበቃ፡፡

(1) ባለይዞታው ዕቃውን ለመጠበቅ ዋጋ ይከፈለው እንደሆነ ወይም እንዲገለገልበት ተፈቅዶለት እንደሆነ ወይም በዚህ ዕቃ በመገልገል
እርግጠኛ ጥቅም የሚያገኝበት ሲሆን ዕቃውን ከተረከበ በኋላ ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ ባለይዞታው አላፊ ነው፡፡

(2) ዕቃው የጠፋው ወይም የተበላሸው በዕቃው እንዲገለገልበት አሳልፎ በሰጠው በሌላ ሰው ምክንያት እንደሆነና ለጊዜው ብቻ ቢሆንም
እንኳ በተለይ በዚህ ሁኔታ ለጠፋው ወይም ለተበላሸው ዕቃ አላፊ ነው፡፡

ቊ 2721፡፡ (2) የአላፊነቱ ወሰን፡፡

(1) ባለይዞታው አላፊነቱ የሚቀርለት የዕቃው መጥፋት ወይም መበላሸት የደረሰው ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል ምክንያት ለመሆኑ ማስረጃ
በቀረበ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
(2) እንዲሁም ለዕቃው መጥፋት ወይም ለመበላሸቱ ምክንያት የሆነው ከእርጅና ወይም ከዕቃው ጒድለት የተነሣ መሆኑን ባስረዳ ጊዜ
ከአላፊነት ለመዳን ይችላል፡፡

(3) ዕቃው በሚሰጠው መጠነኛ አገልግሎት በመጠቀም ወይም ለዕቃው መገልገያ በተፈቀደው ተገቢ ሁኔታ ሲገለገልበት ቢበላሽ
ባለይዞታው አላፊነት አያገኘውም፡፡

ቊ 2622፡፡ (3) ጥቅም የሌለው ጥበቃ፡፡

(1) ባለይዞታው በዕቃው ምንም የማይጠቀምበት ሲሆንና ጥበቃውንም የሚያከናውነው በፍጹም ለባለሀብቱ ጥቅም ብቻ እንደሆነ ዕቃው
የጠፋው ወይም የተበላሸው ራሱ ባደረሰው ጥፋት ካልሆነና ወይም ለባለሀብቱ እንዲመለስ የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ ከተሰጠው በኋላ
ካልሆነ በቀር የዕቃው መጥፋት ወይም መበላሸት በአላፊነት አያስጠይቀውም፡፡

(2) የዕቃውን አጠባበቅና አያያዝ እንደ ራሱ ዕቃ አጠባበቅና አያያዝ አድርጎ ከመጠበቅ የተቀነሰ ጥንቃቄ ካላደረገ በቀር ባለይዞታው
ማንኛውም አላፊነት አይደርስበትም፡፡

ቊ 2723፡፡ ማስጠንቀቂያ የደረሰው ባለይዞታ፡፡

(1) ባለይዞታው ዕቃውን እንዲመልስ ማስጠንቀቂያ ቢደርሰውም እንኳ ዕቃውን ቢመልስም ባይመልስም ከመጥፋት ወይም ከመበላሸት
ለማዳን የማይችል መሆኑን ካስረዳ፤ እንዲያውም ተገቢ በሆነ ጊዜ ለባለሀብቱ እንደመለሰ ያህል የሚገመት ከሆነ በአላፊነት መጠየቁ
ይቀርለታል፡፡

ቊ 2724፡፡ ለዕቃው የተደረገለት ማሻሻያ፡፡ (1) ኪሣራ የመቀበል መብት፡፡

(1) ባለይዞታው ለዕቃው ስላደረገው የማሻሻል ሥራ ማንኛውንም ኪሣራ የመጠየቅ መብት የለውም፡፡

(2) ቢሆንም ለዕቃው መሻሻል የተደረገው ሥራ የተፈጸመው በባለሀብቱ ፈቃድ እንደሆነ ባለይዞታው፤ ባንድ በኩል ለዚሁ ጒዳይ ወጪ
ያደረገውን በሌላ በኩል ደግሞ ይህን ዕቃ ለባለሀብቱ በሚያስረክብበት ጊዜ የዕቃውን ዋጋ ግምት ከፍተኛ ለማድረግ የቻለው በመታደሱ
ምክንያት ሲሆን የዚህኑ ግምት እስከ መጨረሻው ዝቅተኛ ሒሳብ ድረስ መልሶ ገቢ እንዲያደርግለት ባለሀብቱን በሕግ አግባብ
ሊያስገድድው ይችላል፡፡

ቊ 2725፡፡ (2) መቻቻልና አንሥቶ የመውሰድ መብት፡፡

(1) ባለይዞታው ማንኛውም ኪሣራ የመጠየቅ መብት ባይኖረውም እንኳ የራሱን አላፊነት በሚመለከተው ጒዳይ ሆኖ በሱ ጥፋት በሆነ
ምክንያት ያጐደለውን የዕቃ ዋጋና በራሱ ኪሣራ ሊያድስ ከሚገደድበት ወጪ በቀር ያለውን የሒሳብ ግምት ሊያቻችል ይችላል፡፡

(2) በሌላ በኩል ደግሞ፤ ባለይዞታው ለዕቃው ማሻሻያ ያደረገው ተጨማሪ ነገር ከላዩ ተለይቶ ቢወሰድ በዋናው ዕቃ ላይ ጉዳት
የማያደርስበት ከሆነ የጨመረውን አንሥቶ ለመውሰድ ይችላል፡፡
ቊ 2726፡፡ በመያዣ የማቈየት መብት፡፡

(1) ባለይዞታው በዚሁ ምዕራፍ ውስጥ በተመለከተው ድንጋጌ መሠረት፤ ለመጠየቅ የተሰጠውንና ሊከፈለው የሚገባውን ሒሳብ ባለሀብቱ
አጠናቆ እስኪከፍለው ድረስ ዕቃውን ሳይመልስ ለዚሁ መብቱ መያዣ አድርጎ ለማቈየት ይችላል፡፡

(2) ከዚህ ውጭ በሆነ በሌላ ምክንያት ለሱ የሚሰጠውን ገንዘብ በመጠየቅ እስኪከፈለኝ ድረስ ዕቃውን አልመልስም ለማለት አይችልም፡፡

(3) ለባለይዞታው የምከፍለው ገንዘብ የለብኝም ያለ እንደሆነ ሊከፍል የሚገባው ሆኖ ሲገኝ ግዴታውን ለመፈጸም የሚበቃ ዋስ ሰጥቶ
ዕቃው ወዲያውኑ እንዲመለስለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
ስለ ዕቃ ማከራየት፡፡
ክፍል 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌ፡፡
ቊ 2727፡፡ ትርጓሜ፡፡

ያንድ ዕቃ ኪራይ ሲባል አከራይ ተብሎ የሚጠራው አንደኛው ወገን ተከራይ ተብሎ የሚጠራው ሁለተኛ ወገን ላንድ ለተወሰነ ጊዜ ባንድ
ነገር እየተጠቀመ ለዚሁ ልውጫ ኪራይ ተብሎ የሚጠራ ገንዘብ እንዲከፍል የሚስማሙበት ውል ማለት ነው፡፡

ቊ 2728፡፡ ኪራይና ሽያጭ፡፡

(1) የተከራየው ነገር ባለሀብትነት የአከራዩ ሆኖ ቈይቶ የውሉ የጊዜ ውሳኔ ሲፈጸም ላከራዩ ይመለስለታል፡፡

(2) ተከራዩ ለተከራየው ዕቃ ለተወሰኑ የመከፈያ ጊዜያቶች ኪራዩን ሲከፍል ቈይቶ የዕቃው ባለቤት ይሆናል የሚል ስምምነት በውሉ ላይ
ተጠቅሶ እንደሆነ፤ ተዋዋዮቹ ውሉን የኪራይ ውል ነው ቢሉትም እንኳ የሽያጭ ውል ነው፡፡

ቊ 2729፡፡ ክራይና ትውስት፡፡

በውሉ ውስጥ ማንኛውም የኪራይ ገንዘብ አልተወሰነ እንደሆነ የተውሶ ዕቃ ጒዳይን የሚመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2730፡፡ ከመጠን አሳልፎ ስለ መጠቀም፡፡


(1) ተከራዩ በውሉ ስምምነት በተመለከተው መሠረት ወይም እንደልማዳዊው ሕግ ሳይሆን በተከራየው ዕቃ ያላገባብ በመገልገሉ በዕቃው
ላይ ሊታደስ የማይችል ጉዳት ይደርስበታል ተብሎ የሚያሠጋ ሆኖ የታየ እንደሆነ አከራዩ ውሉ ወዲያውኑ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ከመጠየቁም በፊት ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ ወይም የውሉ መፍረስ የሚያጎዳው ሲሆን አከራዩ ኪሣራም ጭምር የመጠየቅ መብት
አለው፡፡
ቊ 2731፡፡ የዕቃው ጠበቃ፡፡

(1) ተከራዩ ዕቃውን በመልካም አያያዝ መጠቀም አለበት፡፡

(2) የዚህንም የጠበቃ ወጪ የሚችል ራሱ ነው፡፡

ቊ 2732፡፡ የኪራይ አከፋፈል፡፡

(1) ተከራዩ ለኪራይ መክፈያ በየተወሰነለት ጊዜ ወይም ከልማዳዊው ሕግ ጋራ ተመሳሳይ በሆነው ዐይነት ኪራዩን መክፈል አለበት፡፡

(2) ስለ ኪራዩ አከፋፈል የጊዜ ውሳኔ ስምምነት የሌለ ሲሆን ወይም ተቃራኒ ልማድ የሌለ እንደሆነ የኪራዩ ሒሳብ የሚከፈለው
በየተወሰነው ጊዜ ልክ በሦስት በሦስት ወር መጨረሻ ላይ ነው፡፡

ቊ 2733፡፡ ክፍያውን ስለ ማዘግየት፡፡

(1) ተከራዩ ሊከራይ መክፈያ የተወሰነለት ጊዜ ካለፈ በኋላ ክፍያውን ያዘገየ እንደሆነ አከራዩ ያሥር ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥቶት በዚሁ ጊዜ
ውስጥ ያልተከፈለ እንደሆነ አከራዩ ውሉ ቀሪ ይሆናል ብሎ ለተከራዩ ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) ቀኑም የሚቈጠረው ለተከራዩ ማስጠንቀቂያው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ነው፡፡

ቊ 2734፡፡ ተከራይቶ ማከራየት፡፡


ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር ተከራዩ አከራዩን ሳያስፈቅድ የተከራየውን ዕቃ አሳልፎ ለማከራየት ወይም ውሉን አሳልፎ ለመስጠት
አይችልም፡፡
ቊ 2735፡፡ የውሉ ማለቂያ ጊዜ፡፡

(1) ላንድ ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል ጊዜው የሚያልቀው፡፡ ተዋዋዮች ወገኖች የተስማሙበት የጊዜ ውሳኔ ሲደርስ ነው፡፡

(2) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር ተዋዋዮች ቢሞቱ ወይም ችሎታ ቢያጡም እንኳ የተወሰነው ዘመን ከማለቁ በፊት አያልቅም፡፡

(3) ቢሆንም ተከራዩ የከሠረ እንደሆነ ላለፈውም ሒሳብ ሆነ ወደ ፊት ለሚመጣው የኪራይ መክፈያ ዘመን ሒሳቡን በሚስማማ ጊዜ
ውስጥ የሚከፍል ለመሆኑ ማረጋገጫ የሚሆን በቂ ዋስትና ካልሰጠው በቀር አከራዩ፤ ውሉ እንዲሰረዝ ለማድረግ ይችላል፡፡

ቊ 2736፡፡ ጊዜ ያልተወሰነላቸው ውሎች፡፡

(1) የኪራይ ዘመን ጸንቶ የሚቈይበት ጊዜ በስምምነቱ ላይ ሳይመለከት የቀረ እንደሆነ ከሁለቱ ወገን ተዋዋዮች አንዱ፤ በማንኛውም ጊዜ
ቢሆን ውሉ እንዲያልቅ ለማድረግ ይችላል፡፡

(2) እንደዚህም በሆነ ጊዜ 1 ኛው ወገን ተዋዋይ የተከራየውን ዕቃ ስለ መመለስ ያለበትን ግዴታ ለመፈጸም ወይም የቀረበውን ለማስረከብ
(ለመረከብ) በአእምሮ ግምት በቂ ነው የሚባል ጊዜ የማግኘት መብት ይኖረዋል፡፡

ቊ 2737፡፡ መልሶ በማስረከብ ላይ የሚደረግ መዘግየት፡፡

(1) ተከራዩ ዕቃውን እንዲመልስ ማስጠንቀቂያ ከደረሰው በኋላ ሳይመልስ የዘገየ እንደሆነ ዕቃውን እስከ መለሰበት ጊዜ ያለውን የኪራይ
ሒሳብ መክፈል አለበት፡፡
(2) እንዲሁም የመዘግየቱ ጒዳይ በአከራዩ ላይ ላደረሰው ጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2738፡፡ የውሉ ዘመን መቀጠል (መርዘም)፡፡

(1) ላንድ ለተወሰነ ዘመን እንዲጸና በተደረገ የኪራይ ውል ስምምነት አንደኛው ወገን ተዋዋይ የተከራየውን ዕቃ እንዲመልስለት
ሳይጠይቀው የጊዜው ውሳኔ ካለፈ በኋላ ዕቃው በተከራዩ ባለይዞታነት የቈየ እንደሆነ የኪራዩ ውል በመጀመሪያው (በዋነኛው) ውል
በተስማሙበት ሁኔታና መሠረት ላልተወሰነ ጊዜ ጸንቶ እንዲቈይ ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች እንደተስማሙበት ያህል ይቈጠራል፡፡

(2) ቢሆንም በእንደዚህ ያለው አጋጣሚ ሁኔታ ስለ መጀመሪያው (ስለ ዋነኛው) ውል መልካም አፈጻጸም ዋሶች የነበሩት ሦስተኛ ወገኖች
ከግዴታው ነጻ ይሆናሉ፡፡
ክፍል 2፡፡
እንስሳን ስለ መከራየት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ባንድ የርሻ መሬት ሥራ ኪራይ ውስጥ ከብትን ጭምር ስለ መከራየት፡፡
ቊ 2739፡፡ የነዚህ ደንቦች አፈጻጸም፡፡

ገበሬው የተጋዛው (የተከራየው) የርሻ መሬት ሥራ ከብቶች ያሉበት የሆነ እንደሆነ፤ በሁለቱም ወገኖች ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር
ከዚህ በሚከተሉት ቊጥሮች የተመለከቱት ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2740፡፡ የከብት ሽያጭ፡፡ (1) የገበሬው መብት፡፡

(1) ተጋዡ ገበሬ የርሻ መሬት ክፍል የሆኑትን ከብቶች ለመሸጥ ይችላል፡፡

(2) ስለሆነም ገበሬው በመሬቱ ላይ ተቀብሎ እንደነበረው በብዛትና በዐይነት የሚተካከል ዘር ያለው የርቢ ከብት ማኖር አለበት፡፡

(3) አከራዩ የርቢው ከብት የበረከተ (የበዛ) ቢሆንም ከብቶቹን እንዲሸጥ ተጋዡን ገበሬ ለማስገደድ አይችልም፡፡

ቊ 2741፡፡ (2) ያከራዩ መብት፡፡

(1) አከራዩ የርሻው መሬት ክፍል የሆኑትን ከብቶች ለመሸጥ አይችልም፡፡

(2) አከራዩ በየዓመቱ ከመሬቱ ላይ የሚገኘውን የርቢ ከብት ዝርዝር እንዲሰጠው ገበሬውን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(3) አከራዩ በገበሬው አሠራር ምክንያት የርቢው ከብት ካንድ እሩብ በሚበልጥ የተቀነሰ መሆኑን የተመለከተ እንደሆነ የኪራዩን ውል
ለመሻር ይችላል፡፡

ቊ 2742፡፡ የከብቶች ጥቅም፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ከዚህ (የሚቀጥሉት) ቊጥሮች የተጠበቁ ሆነው፤ ገበሬው ከከብቶቹ በሚገኙት ነገሮች (በቁርበቶቻቸው) በቆዳዎቻቸውና በብዛታቸው
በመርባታቸው በነጻ ሊገለገልባቸው ይችላል፡፡

(2) ገበሬው የሚከፍለው የኪራይ ዋጋ ከነዚሁ ጥቅሞች ድርሻ ውስጥ የሆነ ወይም እነዚሁኑ ጥቅሞች በመገመት የተወሰነ የሆነ እንደሆነ
የሥራውን አካሄድ ለአከራዩ ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2743፡፡ (2) የበግ ጠጒር፡፡

(1) ገበሬው የሥራውን ክንውን መሪነት የያዘ ወይም መንጋው ከአምሳ ያነሰ ከሆነ የበጎቹን ጠጒር ብቻ ለመሸጥ ይችላል፡፡

(2) ሥራውን የሚመራ አከራዩ በሆነ ጊዜ የበጎቹም መንጋ ከአምሳ በላይ ሲሆን የበጎቹን ጠጒር ለመሸጥ የሚችለው አከራዩ ብቻ ነው፡፡

ቊ 2744፡፡ (3) ፍግ፡፡


የከብቶቹ ፍግ በማናቸውም ሁኔታ በተለይ ስለ መሬቱ ሥራ ብቻ መዋል አለበት፡፡
ቊ 2745፡፡ (4) ርቢ፡፡
በሚሞቱ ወይም በታረዱ ከብቶች ልክ የርቢ ከብቶች መተካት አለባቸው፡፡
ቊ 2746፡፡ መልሶ የመስጠት ግዴታ፡፡

(1) የኪራዩ ውል ሲያልቅ ገበሬው እመሬቱ ላይ ተቀብሎ እንደነበረው በዘር በብዛትና በዐይነት የሚተካከል የርቢ ከብት መተው አለበት፡፡

(2) የርቢው ከብት ምንም እንኳ በኪራዩ ውል ውስጥ በግምት የገባ ቢሆንም ይህ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

ቊ 2747፡፡ ጒድለት፡፡ (1) የአከራዩ ኪሣራ፡፡

(1) ጒድለት ያለው ሆኖ የሚከፈለውም የኪራይ ዋጋ ካንድ ከተወሰነ ጥቅም ድርሻ ወይም ከተወሰነ ከከብቶች ጥቅም ውስጥ የሆነ እንደሆነ
ኪሣራው የአከራዩ ነው፡፡

(2) የከብቶቹ ኪሣራ በገበሬው ጥፋት ወይም ራሱ አላፊ በሆነለት ሰው ካልሆነ በቀር በዚህ ጒድለት ገበሬው አላፊ አይሆንም፡፡

ቊ 2748፡፡ (2) የገበሬው ኪሣራ፡፡


ለኪራዩ የሚከፈለው ዋጋ በተለይ ከከብቶቹ ጥቅም ጋራ ግንኙነት በሌለው አኳኋን የተወሰነ እንደሆነ፤ ገበሬው ላላቀረባቸው ከብቶች ዋጋ
(ግምት) አላፊ ነው፡፡

ቊ 2749፡፡ (3) የአላፊነቱ መጠን፡፡

(1) ገበሬው ያላቀረባቸው ከብቶች ዋጋ በሁለቱ ወገኖች በሚደረገው ግምት መሠረት ይሆናል፡፡

(2) ይህን የመሰለ ግምት ያልተደረገ እንደሆነ፤ የኪራዩን ውል የሚቀርቡት ከብቶቹ የሚያወጡት ግምት ልክ ገበሬው መክፈል አለበት፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
የከብቶቹ ኪራይ ዋና በሆነ ጊዜ፡፡
ቊ 2750፡፡ የነዚህ ደንቦች አፈጻጸም፡፡

(1) የኪራዩ ውል ዋና ዓላማ ለእርሻ ወይም ለንግድ ጥቅም ለመስጠት በሚችሉ ከብቶች ወይም ሌሎች እንስሳዎች የተቋቋመ ሲሆን ከዚህ
የሚከተሉት ቊጥሮች ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

(2) ልማደ ሀገር የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2751፡፡ ለዐይነት የሆኑ ውሎች፡፡

(1) ለዐይነት የሆኑ ውሎች አንዳንድ ዐይነት (ዘር) ከብቶችን በሚመለከት ወይም ባንዳንድ የኢትዮጵያ ግዛት አውራጃዎች ውስጥ መፈጸም
ያለባቸው ለዐይነት የሚሆኑ ውሎችን የርሻ ሚኒስቴር ሊያደራጃቸው ይችላል፡፡

(2) የከብት ዐይነቶችን ወይም ለዐይነት የተደራጅት ውሎች ከሚመለከቷቸው መሬቶች ከአንዱ ላይ የሚደረጉ ውሎች ለዐይነት በተሠሩት
ውሎች ሁኔታዎች መሠረት እንደተደረጉ ይቈጠራሉ፡፡

(3) ሁለቱ ወገኖች በሚያደርጉት ግልጽ ስምምነት ለዐይነት የተሠሩትን ውሎች ሁኔታ ሊለውጡት ይችላሉ፡፡

ቊ 2752፡፡ ውሉ የሚቈይበት ጊዜ (ዘመን)፡፡

(1) ተቃራኒ የሆነ ነገር ቃል በውሉ ውስጥ በግልጽ ካልተጻፈ በቀር ውሉ ለአራት ዓመት እንደተደረገ ይገመታል፡፡

(2) የአራቱ ዓመት መቈጠር የሚጀመረው ውሉ ከተደረገበት ቀን አንስቶ ነው፡፡


ቊ 2753፡፡ ለመሬቱ ባለቤት ስለ ማስታወቅ፡፡

(1) የርቢው ከብት በኪራይ የተሰጠው ለሌላ ሰው ገበሬ የሆነ እንደሆነ፤ ገበሬው ለሚሠራበት መሬት ባለሀብት ማስታወቅ አለበተ፡፡

(2) ይህ ማስታወቂያ ያልደረሰው እንደሆነ፤ ተቃራኒ ልማድ ቢኖርም እንኳ አከራዩ ከተጋዡ ላይ ያለው ገንዘብ እንዲከፈለው የርቢውን
ከብት የማስያዝ ወይም በማቈየት መብቱ ሊሠራበት ይችላል፡፡

(3) ከብቶቹ የገበሬው ሀብት አለመሆናቸውን ያውቅ ነበር ወይም ማወቅ ነበረበት ብሎ ማመካኘት አይቻልም፡፡

ቊ 2754፡፡ የርቢው ከብት ግምት፡፡

(1) በኪራዩ ውል ውስጥ ለርቢው ከብት የተደረገው ግምት ለተከራዩ ሀብትነቱን አያስተላልፍም፡፡

(2) የግምቱ መገለጽ የኪራዩ ውል በሚቀርበት ጊዜ ኪሣራውን ወይም ጥቅሙን የመውሰድ ዓላማ ከመሆኑ በቀር ሌላ የለውም፡፡

ቊ 2755፡፡ ስለ ርቢው ከብት አጠባበቅ፡፡

(1) ተከራዩ ስለ ርቢው ከብት አያያዝና አጠባበቅ የተለመደውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ አለበት፡፡

(2) ተከራዩም ለዚህ አጠባበቅ ራሱ ወጪውን መቻል አለበት፡፡

ቊ 2756፡፡ የርቢ ከብቶች ውላጆች፡፡


በርቢ የተሰጡ ከብቶች ልጆች የአከራዩና የተከራዩ የጋራ ሀብት ናቸው፡፡
ቊ 2757፡፡ የከብቶቹ ጥቅም፡፡
ተከራዩ ለርቢ በተሰጡት ከብቶች ወተት ፍግና ሥራ ብቻውን ይጠቀማል፡፡
ቊ 2758፡፡ የበግ ጠጒር፡፡

(1) ለርቢ የተሰጡ በጎች ጠጒር በአከራዩና በተከራዩ መካከል እኩል ይከፋፈላል፡፡

(2) ተከራዩ የሚሸልትበትን ቀን ለአከራዩ ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2759፡፡ ስለ ከብቶች መሸጥ፡፡

(1) ተከራዩ ያለ አከራዩ ፈቃድ በተሰጡት ከብቶች ሆነ በርቢ ከተገኙት ልጆች ሆነ፤ ከመንጋው ውስጥ አንድም ከብት ለመሸጥ አይችልም፡፡

(2) አከራዩም ያለ ተከራዩ ፈቃድ ለመሸጥ አይችልም፡፡

ቊ 2760፡፡ ስለ ከብቶች መጥፋት፡፡

(1) ተከራዩ ስለ ከብቶቹ መሞት መጥፋት አላፊ የሚሆነው በራሱ ጥፋት ሲሆን ነው፡፡

(2) ይህን ጥፋት ማስረዳት ያለበት አከራዩ ነው፡፡

(3) ተከራዩ የሞቱትን ከብቶች ቆዳ ዘወትር ለአከራዩ ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2761፡፡ ሒሳብ ስለ መተሳሰብ፡፡

(1) አከራዩ፤ ገበሬው የርቢ ከብቶቹን ዝርዝር ቊጥር በያመቱ እንዲሰጠው ለመጠየቅ የዓመቱንም ሒሳብ እንተሳሰብ ሊለው ይችላል፡፡

(2) የገበሬው ነው በሚባል ምክንያት የርቢዎቹ ከብቶች ከሩብ በላይ የቀነሱ የመሰለው እንደሆነ፤ አከራዩ ውሉን ለማፍረስ ይችላል፡፡

ቊ 2762፡፡ ስለ ውሉ ማለቅ፡፡
(1) ውሉ በሁለቱ ወገኖች መካከል በስምምነት እንዲያልቅ በተደረገበት ጊዜ ወይም በሕጉ በተወሰነው ቀን የሚቀር ይሆናል፡፡

(2) ስለሆነም ውሉ እንዲቀር የሚፈልገው ወገን እጅግ ቢያንስ ከስድስት ወር አስቀድሞ የማስቀረት ሐሳቡን ለሌላው ወገን ማስታወቅ
አለበት፡፡
ቊ 2763፡፡ ስለ ሁለቱ ወገኖች መሞት፡፡

(1) ውሉ በአከራዩ ወይም በተከራዩ መሞት የሚቀር አይሆንም፡፡

(2) ተከራዩ የሞተ እንደሆነ እርሱ በሞተ በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ ሐሳባቸውን ለአከራዩ በመግለጽ ውሉ እንዲቀር ማድረግ ይችላል፡፡

(3) በእንደዚህ ያለው ጊዜ ውሉ የሚያልቀው አከራዩ የተከራዩ ወራሾች ሐሳብ በደረሰው ቢያንስ ከስድስት ወር በኋላ ካለው መጋቢት 1
ቀን ጀምሮ ነው፡፡

ቊ 2764፡፡ ስለ ውሉ ሒሳብ መጣራት፡፡

(1) የኪራዩ ውል ሲያልቅ ወይም በሚፈርስበት ጊዜ አዲስ የርቢው ከብት ግምት ይደረጋል፡፡

(2) አከራዩ የመጀመሪያው ግምት እስከሚስተካከል ድረስ ከያንዳንዱ ዐይነት ከብቶች መውሰድ ይችላል፡፡

(3) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር ትርፍ የሆነው በአከራዩና በተከራዩ መካከል እኩል በእኩል ይከፋፈላል፡፡

ቊ 2765፡፡ የማይበቃ የርቢ ከብት፡፡

(1) የመጀመሪያውን ግምት ለመሙላት በቂ ከብቶች የሌሉ እንደሆነ፤ አከራዩ የተረፉትን ወስዶ በጠፋው ሁለቱም ወገኖች ውሳኔ
ያደርጋሉ፡፡

(2) የከብቶቹ መጒደል በተጋዡ ወይም እሱ አላፊ በሚሆነው ሰው ጥፋት ካልሆነ በተጋዡ አይታሰቡበትም፡፡

ቊ 2766፡፡ ፈራሽ የሆኑ የውል ቃሎች፡፡

(1) ተከራዩ ባልታሰበ ድንገተኛ ምክንያት ያለ ጥፋቱ የደረሰበትን የርቢ ከብት መጥፋት በሙሉ ይከፍላል የሚል የውል ቃል ሁሉ ፈራሽ
ነው፡፡

(2) እንዲሁም ተከራዩ ከሚያገኘው ትርፍ የበለጠ ኪራይ ይከፍላል የሚል የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

(3) እንዲሁም አከራዩ የኪራዩ ውል ሲቀር ከሰጠው የርቢ ከብት በላይ ይወስዳል የሚል የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለ መገልገያ ብድር ወይም ትውስት፡፡
ቊ 2767፡፡ ትርጓሜ፡፡
ለመገልገያ መዋስ ሲባል አዋሽ ተብሎ የሚጠራው አንደኛው ወገን ተዋሹ የሚባለው ሁለተኛው ወገን ተዋዋይ አንድ ነገር ያለ ዋጋ ወስዶ
በነጻ እንዲገለገልበት የውል ግዴታ የሚገባበት ውል ማለት ነው፡፡

ቊ 2768፡፡ ውሉ ያለ ዋጋ የሚሰጥ ስለመሆኑ፡፡

(1) ውሰት በፍጹም ዋጋ የማይከፈልበት በነጻ የሚሰጥ ነው፡፡

(2) አዋሹ ላዋሰው ዕቃ አበል ይከፈለዋል የሚል ቃል በውሉ ላይ በተመለከተ ጊዜ ግን ስለ ዕቃ ኪራይ የተሰጠው ድንጋጌ ተፈጻሚ መሆን
አለበት፡፡
ቊ 2769፡፡ የዕቃው ባለሀብትነት፡፡
(1) አዋሹ ላዋሰው ዕቃ ባለሀብት ሆኖ ይቈያል፡፡

(2) የውሉ ዘመን ሲፈጸም ተዋሹ ዕቃውን ሊመልስለት ይገባዋል፡፡

ቊ 2770፡፡ የዕቃው አያያዝ፡፡

(1) ተዋሹ ዕቃውን በሚገባ ጥበቃ መያዝ አለበት፡፡

(2) የዚህንም የአያያዝ ወጪ የሚችል ራሱ ነው፡፡

ቊ 2771፡፡ የዕቃው አገልግሎት፡፡

(1) ተዋሹ በዕቃው እንዲገለገልበት በውሉ ስምምነት ላይ ከተመለከተው ውጭ በሆነ በሌላ ዐይነት ሊገለገል ወይም በውሉ ላይ የተለየ
ስምምነትም ባይኖር የዕቃው ተፈጥሮ ዐይነት ከሚፈቅድለት ውጭ በሆነ ሁኔታ ሊገለገልበት አይችልም፡፡

(2) አዋሹ ካልፈቀደለት በቀር በተዋሰው ዕቃ ሌሎች እንዲገለገሉበት አሳልፎ ለመስጠት አይፈቀድለትም፡፡

ቊ 2772፡፡ ዕቃውን ስለ መመለስ፡፡

(1) ተዋሹ በውሉ ላይ በተወሰነው ጊዜ ዕቃውን መመለስ አለበት፡፡

(2) ለዕቃው መመለሻ የተወሰነ ጊዜ የሌለ እንደሆነና ተዋሹ ዕቃውን መመለስ ስለሚገባው ጒዳይ ልማዳዊ አሠራር የሌለ ሲሆን፤ አዋሹ
እንዲመልስለት ሲጠይቀው ወዲያውኑ መመለስ አለበት፡፡

ቊ 2773፡፡ ከተወሰነው ጊዜ በፊት ስለ መመለስ፡፡ (1) የተዋሹ መብት፡፡


በውሉ ላይ የተወሰነው ጊዜ ከማለቁ በፊት ዕቃው ቢመለስለት ባዋሹ ላይ ጉዳት የማያደርስበት ከሆነ ተዋሹ የውሉ ዘመን ከመድረሱ
በፊትም ቢሆን ዕቃውን ለመመለስ መብት አለው፡፡

ቊ 2774፡፡ (2) ያዋሹ መብት ፡፡


ተዋሹ በውሉ ከተፈቀደለት አገልግሎት ውጭ በሆነ ዐይነት በዕቃው የተገለገለበት እንደሆነና ዕቃውን ያበላሸው እንደሆነ ሌላ ሰው
እንዲገለገልበት አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ፤ ወይም ደግሞ አዋሹ በቃው ራሱ እንዲገለገል የሚያስፈልግ አስቸኳይና ድንገተኛ ያልታሰበ ጒዳይ
የደረሰበት እንደሆነ፤ በውሉ ላይ የተወሰነው ዘመን ከመድረሱ በፊትም ቢሆን አዋሹ ዕቃው እንዲመለስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2775፡፡ የተዋሹ መሞት፡፡


ተዋሹ የሞተ እንደሆነ ለተዋሹ ረጅም ጊዜ የፈቀደለትም ሆኖ ይህ ጊዜ ከመድረሱ በፊትም ቢሆን የተዋሹ ወራሾተ ዕቃውን ወዲያውኑ
እንዲመልሱለት አዋሹ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2776፡፡ ያለመጠን ስለ መገልገል፡፡

(1) ተዋሹ በዕቃው ያለመጠን በመገልገሉ ወይም ሌላ ሰው ያላገባብ እንዲገለገልበት አሳልፎ በማይገባ በመስጠቱ ዕቃው የተበላሸ እንደሆነ፤
የዕቃው መበላሸት ያስከተለው ሊታለፍ በማይቻል ከዐቅም በላይ የሆነ ምክንያት ቢሆንም እንኳ ተዋሹ ስለ ዕቃው መበላሸት አላፊ
ይሆናል፡፡

(2) ያለበትን ግዴታ ቢያፈርስም እንኳ ዕቃው ከመጥፋት ወይም ከመበላሸት የማይድን እንደነበረ በቂ ማስረጃ ካላቀረበ በቀር ከዚህ
አላፊነት ለመዳን አይችልም፡፡

ቊ 2777፡፡ ሊቀር የሚቻል ጥፋት፡፡


ሊታለፍ በማይችል ከዐቅም በላይ በሆነ ምክንያትም ቢጠፋ እንኳ፤ ከተዋሰው ዕቃ ይልቅ የራሱ ዕቃእንደሚሻል ገምቶ የራሱን ዕቃ አሳልፎ
ለጥፋት ባለመስጠት፤ ከሁለቱ አንደኛውን ብቻ ከጥፋት ለማዳን ሲችል የራሱን ዕቃ ለማዳን መርጦ እንደሆነ፤ በዚህ ምክንያት ለጠፋው
ዕቃ ተዋሹ አላፊ መሆኑ አይቀርለትም፡፡
ቊ 2778፡፡ በውሉ ላይ የተገመተ ዕቃ፡፡
የውሉ ጽሑፍ በተደረገበት ጊዜ የዕቃውን ግምት አመልክቶ እንደሆነ ይህ ዕቃ በማናቸውም ሁኔታ ቢጠፋ ተዋሹ በአላፊነት መጠየቅ
አለበት፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
አ ደ ራ፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ አደራ በጠቅላላው፡፡
ቊ 2779፡፡ ትርጓሜ፡፡
አደራ ማለት አደራ ተቀባይ የተባለው አደራ አስቀማጭ የተባለውን የሌላ ሰው ዕቃ ተቀብሎ በአደራ ጠባቂነት እንዲየስቀምጥለት
የሚገባበት የውል ግዴታ ማለት ነው፡፡

ቊ 2780፡፡ አደራ፤ በሁኔታ ስለሚደረግ ሽያጭ ስለ ሥራ፡፡

(1) አደራ ተቀባዩ እንደ ውሉ ስምምነት ለዕቃው ማስቀመጥ ዋጋ እንዲከፈልበት ተፈቅዶለት እንደሆነ ተፈጻሚ የሚሆነው የአደራ
ማስቀመጥ ደንብ ሳይሆን ስለ ሁኔታ ሽያጭ በተወሰነው ድንጋጌ ነው፡፡

(2) አደራ ተቀባዩ ዕቃውን እንዲያድስ ወይም በሌላ ዐይነት እንዲለውጠው የሚገደድ እንደሆነ፤ ተፈጻሚ የሚሆነው ድንጋጌ ያደራ
ማስቀመጥ ደንብ ሳይሆን የውልና የሥራ ደንብ ነው፡፡

ቊ 2781፡፡ የዕቃው ባለቤትነት፡፡

(1) አደራ ሰጪው የዕቃው ባለቤት ሆኖ ይቈያል፡፡

(2) አደራ ተቀባዩ ለአደራ ማስቀመጥ የተወሰነው የውሉ የጊዜ ውሳኔ ሲደርስ ዕቃውን ለአደራ ሰጪው ሊመልስለት ይገባዋል፡፡

ቊ 2782፡፡ በአደራ የተቀመጠ አላቂ ዕቃ፡፡

(1) ለአደራ ተቀባዩ የተሰጠው ዕቃ ጥሬ ገንዘብ ወይም በማገልገል የሚያልቅ አንድ የተወሰነ ብዛት ያለው እንደሆነና አደራ ተቀባዩም
እንዲገለገልበት ተፈቅዶለት እንደሆነ፤ ስለ እንደዚህ ያለው ጒዳይ የአላቂ ነገርን ብድር የሚመለከቱት ደንቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

(2) ለአደራ ተቀባዩ የተሰጠው ዕቃ ጥሬ ገንዘብ እንደሆነና የተረከበውም ሳይታሸግና ሳይዘጋበት እንደሆነ፤ እንዲጠቀምበት ፈቃድ
እንደተሰጠው ሆኖ ይገመታል፡፡

ቊ 2783፡፡ አደራ በተቀመጠው ዕቃ ስለ መገልገል፡፡

(1) አደራ የተቀጠው ዕቃ ሌላ ነገር በሆነ ጊዜ አደራ ሰጪ ካልፈቀደለት በቀር አደራ ተቀባዩ ሊገለገልበት አይችልም፡፡

(2) ይህን ደንብ የጣሰ እንደሆነ ስለ ዕቃ ኪራይ የተሰጠው ደንብ በራሱ ኪሣራ ይጸናበታል፡፡

(3) አደራ ሰጩ የዕቃው ኪራይ እንዲከፈለው አደራ ተቀባዩን ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ኪራዩም የሚወሰንለት በትክክለኛ ግምት መሠረት
ነው፡፡
ቊ 2784፡፡ ያለ ዋጋ ወይም በደመወዝ የሚሰጥ አደራ፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ወገኖች ለአደራ ተቀባዩ አንድ የድካም ዋጋ እንዲከፈለው በውላቸው ላይ ማናቸውንም ስምምነት ካላደረጉ በቀር በአደራ
የሚቀመጥ ዕቃ ዋጋ የማይከፈልበት ነው፡፡
(2) ስለ እንደዚህ ያለው ጒዳይ የአደራ ተቀባዩን ልዩ የሞያ ሥራ ዐይነተኛ ነገርና ሌሎቹንም አጋጣሚ ምክንያቶች ሁሉ መሠረት አድርጎ
መገመት ይገባል፡፡

ቊ 2785፡፡ የአደራ መስቀመጥን አጋጣሚ ጒዳይ ስለ መለወጥ፡፡

(1) አስቸኳይ የሆነ ድንገተኛ አጋጣሚ ነገር የሚያስገድደው በሆነ ጊዜ አደራ ተቀባዩ ስለ ዕቃው አቀማመጥ በስምምነቱ ላይ ከተመለከተው
ውጭ በሆነ ዐይነት ሊጠብቅ ወይም በዕቃው ላይ እርግጠኛ የሆነ የማይቀር ጥፋት ወይም የመበላሸት አደጋ የሚደርስበት እንደሆነ፤
በተለይ ለሌላ ሰው አሳልፎ በአደራ ለመስጠት ወይም ለመሸጥ ይችላል፡፡ (ይገባዋልም)፡፡

(2) ይህንንም እንዳደረገ ወዲያውኑ ለአደራ ሰጪው ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2786፡፡ የአደራ ማስቀመጡ ጊዜ ማለቅ፡፡ (1) የአደራ ሰጪው መብት፡፡

(1) ለአደራ ተቀባዩ ጥቅም ሲባል አደራ የተቀመጠውን ዕቃ ስለመመለስ በውሉ ስምምነት ላይ የተወሰነ ጊዜ ከሌለ በቀር አደራ ሰጪው
እንደጠየቀ ወዲያውኑ ዕቃው ሊመለስለት ይገባል፡፡

(2) በተስማሙበት የጊዜ ውሳኔ መሠረት አደራ ተቀባዩ ዕቃውን ለመጠበቅና ላያያዙ ያደረገውን ወጪ አደራ ሰጪው እንዲከፍል
ይገደዳል፡፡

ቊ 2787፡፡ (2) የአደራ ተቀባዩ መብት፡፡

(1) ለአደራ ሰጪው ጥቅም ሲባል አደራ የተቀመጠውን ዕቃ መልሶ ስለ መውሰድ በውሉ ስምምነት ላይ የተወሰነ ጊዜ ከሌለ በቀር አደራ
ተቀባዩ አደራ ሰጪው ዕቃውን መልሶ እንዲወስድ በማንኛውም ጊዜ ሊጠይቀው ይችላል፡፡

(2) ማንኛውም የተወሰነ ጊዜ በስምምነታቸው ላይ ያልተመለከተ ቢሆንም እንኳ አደራ ሰጪው ዕቃውን መልሶ ለመውሰጃ በቂ ጊዜ
ዳንዲኖረው ዳኞች በአስተያየት ጊዜውን ሊወስኑለት ይችላሉ፡፡

ቊ 2788፡፡ ስለ ብዙ አደራ ሰጪዎች፡፡

(1) ዕቃውን ለአደራ ተቀባዩ የሰጡት ብዙ አደራ ሰጪዎች እንደሆኑና ይህ ዕቃ በምን ዐይነት ተመልሶ ሊወሰድ እንደሚገባ ያልተስማሙበት
ሲሆን፤ ይህን ውሳኔ የመስጠቱ መብት የዳኞች ነው፡፡

(2) አደራ ተቀባዩ ብዙ ወራሾች ትቶ በሞተ ጊዜና ዕቃውም የማይከፋፈል በሆነ ጊዜ መልሶ የመውሰዱን ደንብ የሚወስኑት ዳኞች ናቸው፡፡

ቊ 2789፡፡ ለሦስተኛ ወገን ጥቅም የተቀመጠ አደራ፡፡

(1) በአደራ የተቀመጠው ዕቃ ለሦስተኛ ወገን ጥቅም ሆኖ ይህም ሦስተኛ ወገን ላደራ ሰጪውና ለተቀባዩ ስምምነቱን አስታውቋቸው
እንደሆነ፤ ይህ ሦስተኛ ወገን ሳይፈቅድ አደራ ተቀባዩ ዕቃውን ለአደራ ሰጪው መልሶ ሊሰጥ አይችልም፡፡

ቊ 2790፡፡ ስለ ዕቃው መመለስ፡፡

(1) አደራ ተቀባዩ ይህን ዕቃ ባንድ በተወሰነ ቦታ እንዲያስቀመጥና እንዲጠብቅ በስምምነቱ ላይ የተመለከተ ነገር እንዳለ፤ ዕቃው ተመልሶ
ሊሰጥ የሚገባው በዚሁ በተወሰነው ስፍራ ነው፡፡

(2) በማናቸውም ምክንያት ስለ ዕቃው መመለስ የሚደርሰው ወጪና ጉዳት የአደራ ሰጪው ነው፡፡

ቊ 2791፡፡ ፍሬውን ስለ መመለስ፡፡


አደራ ተቀባዩ በአደራ ካስቀመጠው ዕቃ ላይ ያገኘው ፍሬ ሁሉ ለባለቤቱ መመለስ አለበት፡፡
ቊ 2792፡፡ ዕቃው ለማን መመለስ እንደሚገባው፡፡

(1) አደራ ተቀባዩ በአደራ ያስቀመጠውን ዕቃ ለአደራ ሰጪው ወይም ይቀበልልኝ ብሎ ላመለከተው ሰው መመለስ አለበት፡፡
(2) አደራ ሰጪው ላስቀመጠው ዕቃ ባለቤት ስለመሆኑ ማስረጃ እንዲያቀርብለት አደራ ተቀባዩ ሊጠይቀው አይችልም፡፡

ቊ 2793፡፡ የአደራ ሰጪው ግዴታዎች፡፡

(1) አደራ ሰጪው በውሉ ላይ የተስማሙበትን የአደራ ጠባቂነት የድካም ዋጋ ለአደራ ተቀባዩ መክፈል አለበት፡፡

(2) ዕቃውንም በመልካም አያያዝ ለማኖር ያደረገውን ወጪ ሁሉ ሊከፍለው ይገባል፡፡

(3) ጉዳት የደረሰበት በአደራ ተቀባዩ ወይም እሱ አላፊ በሚሆንበት ሰው ጥፋት (ጒድለት) ካልሆነ በቀር የአደራ ማስቀመጡ ጒዳይ
ላደረሰበት ጉዳት ሁሉ አደራ ሰጪው ኪሣራ መክፈል ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 2794፡፡ በመያዣ የማቈየት መብት፡፡


አደራ ተቀባዩ በአደራ ስላስቀመጠው ዕቃ ሊከፈለው የሚገባው ሒሳብ በሙሉ እስኪሰጠው ድረስ በአደራ የተቀመጠውን ዕቃ በእጁ
ለማቈየት ይችላል፡፡

ቊ 2795፡፡ የአደራ ተቀባዩ ወራሽ፡፡

(1) ያደራ ተቀባዩ ወራሽ ዕቃው በአደራ የተቀመጠ መሆኑን ሳያውቅ በቅን ልቡና ሸጦት ወይም ለውጦት እንደሆነ፤ እንዲመልስ የሚገደደው
ዋጋውን ብቻ ነው፡፡

(2) የዕቃውም ዋጋ ገና አልተከፈለ እንደሆነ አደራ ሰጪው በሻጩ ወራሽ መብት ተተክቶ ገዢውን በቀጥታ ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ክፍል 2፡፡
በትእዛዝ የተቀመጠ አደራ፡፡
ቊ 2796፡፡ ትርጓሜ፡፡
አንድ ዕቃ ሕጋዊ ሁኔታው በክርክር ላይ ያለ ወይም የሚያጠራጥር የሆነ እንደሆነ፤ ዕቃው ለሦስተኛ ወገን ተሰጥቶ ይህ በትእዛዝ አስቀማጭ
የሚባለው ባለአደራ በዕቃው ላይ የተደረገው ጥርጣሬ ከተገለጸ በኋላ ባለመብት ነው ለተባለው ሰው እንዲመልስ የተደረገ እንደሆነ፤
በትእዛዝ የተቀመጠ አደራ ይባላል፡፡

ቊ 2797፡፡ የትእዛዝ ባለአደራን ስለ መምረጥና አላፊነቱን ስለ ማስወረድ፡፡

(1) የትእዛዝ ባለአደራ የሚመረጠው በሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች ስምምነት ነው፡፡

(2) ሁለቱ ወገኖች ያልተስማሙ እንደሆነ ዳኞች ይመርጡታል፡፡

(3) ሁለቱ ወገኖች በጒዳዩ ካልተስማሙበትና በቂ ምክንያት ከሌለ በቀር የትእዛዝ ባለአደራው የተሰጠውን ልዩ ትእዛዝ ጊዜው ከመፈጸሙ
በፊት አላፊነቱን ሊያስወርድ አይችልም፡፡

ቊ 2798፡፡ ስለ ዕቃው መመለስ፡፡


የትእዛዝ ባለአደራው በጒዳዩ ጥቅም ያላቸው ሁሉ ካልተስማሙበት ወይም ዳኞች ካላዘዙት በቀር ዕቃውን ለመመለስ አይችልም፡፡
ቊ 2799፡፡ ወደ አደራ ማስቀመጥ ደንብ ስለ መመራት፡፡
ከዚህ የተረፈው ጒዳይ ስለ አደራ ዕቃ አቀማመጥ በተወሰነው ደንብ ይፈጸማል፡፡
ክፍል 3፡፡
አስፈላጊ የሆነ አደራ፡፡
ቊ 2800፡፡ ትርጓሜ፡፡
አንድ ሰው የራሱ ንብረት በሆኑት ዕቃዎቹ ላይ የማይታገድ እርግጠኛ አደጋ የሚደርስባቸው በሆነ ጊዜ እነዚህን ዕቃዎች ከቀረበው አደጋ
ለማሸሽ ሲል ሌላ ሰው በአደራ ተቀብሎ እንዲያስቀምጥለት የሰጠ እንደሆነ፤ ይህ አድራጎት አስፈላጊ የአደራ ማስቀመጥ ይባላል፡፡

ቊ 2801፡፡ አስፈላጊ የአደራ ማስቀመጥ ልዩ ደንቦች፡፡

(1) የዚህን ዐይነት አስፈላጊ አደራ ማስቀመጥ ጒዳይ እንዲፈጽም የአደራው ዕቃ የቀረበለት ሰው ትክክለኛ ምክንያት ካልኖረው በቀር
አልቀበልም ማለት አይችልም፡፡

(2) የአደራ ማስቀመጡ ከአንድ ሳምንት የበለጠ ተራዝሞ የሚቈይ ሲሆን የድካም ዋጋ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) የአደራ ማስቀመጡ የድካም ዋጋ በስምምነት የተወሰነው አደራው በተሰጠ ጊዜ የሆነ እንደሆነ ዳኞች ገንዘቡን ሊቀንሱ ይችላሉ፡፡

ቊ 2802፡፡ የአሠራሩ ፎርምና ማስረጃ፡፡

(1) አስፈላጊ የአደራ ማስቀመጥ ጒዳይ ከማናቸውም ያሠራር ሥርዐት ነጻ ነው፡፡

(2) በማናቸውም ዐይነት መንገድ ማስረጃ ለማቅረብ ይቻላል፡፡

ቊ 2803፡፡ ስለ አደራ ማስቀመጥ የተሰጠውን ደንብ ስለ ማጽናት፡፡


ከዚህ ለሚተርፈው ጒዳይ ያስፈላጊ አደራ ማስቀመጥ ሥርዐት፤ ስለ አደራ ማስቀመጥ ደንብ በተሰጠው ድንጋጌ መሠረት ይመራል፡፡
ክፍል 4፡፡
ባለቤቱ ሳያውቅ የተገኙ ዕቃዎች ወይም ሌላ ሰው ዘንድ የተቀመጡ ዕቃዎች፡፡
ቊ 2804፡፡ ያግኝው መብትና ግዴታ፡፡

(1) አንድ ዕቃ አግኝቶ የዚሁ ዕቃ ባለይዞታ የሆነ ሰው በሕጉ መሠረት፤ ልክ እንደ አደራ ተቀባይ ሆኖ የሚቈጠር ነው፡፡

(2) በዚህ ሕግ የግል ባለሀብትነት በተባለው አንቀጽ ለዚህ ጒዳይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2805፡፡ ሰውዬው ሳያውቅ ወይም ያለ ፈቃዱ በአደራ የተቀመጠ ዕቃ፡፡

(1) ሰውዬው ሳያውቅ ወይም ያለ ፈቃዱ አንድ ዕቃ በሌላ ሰው እጅ ተቀምጦ እንደሆነ የአደራ ማስቀመጥ ደንብ ላስቀማጩ አይረጋለትም፡፡

(2) በዚህ ዐይነት ይህን የመሰለውን ዕቃ አስቀማጭ የሆነ ሰው በማንኛውም አላፊነት ተጠያቂ አይሆንም፡፡ (ማንኛውም ግዴታ
አይደርስበትም)
ምዕራፍ 5፡፡
የዕቃ ማከማቻ ቦታ፡፡
ቊ 2806፡፡ ትርጓሜ፡፡
የዕቃ ማከማቸት ማለት ሸቀጦችን እየተቀበለ በማከማቻ ስፍራ እንዲያስቀመጥ ከሕዝብ አገልግሎት መሥሪያ ቤት ባለሥልጣኖች ለዙህ
ዐይነት የንግድ ሥራ ፈቃድ የተሰጠው ዕቃ አከማች የተባለ ሰው ይህን ዕቃ የገዛው ወይም በመያዣ የተቀበለው የማከማቻ ዕቃ ሰጭ ተብሎ
ለሚጠራው ሰው ጥቅም፤ ዕቃውን ተቀብሎ በማከማቻው ስፍራ እንዲየስቀምጥለት በውል ግዴታ የሚገባበት ውል ማለት ነው፡፡

ቊ 2807፡፡ የሸቀጡ መጥፋትና መበላሸት፡፡

(1) ዕቃውን በማከማቻ ስፍራ እንዲያስቀምጥ የተረከበው አስቀማጭ ስለ ሸቀጡ መጥፋትና መበላሸት አላፊ ይሆናል፡፡

(2) ሸቀጡን ከመጥፋት ወይም ከመበላሸት ያደረሰው ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል መሆኑ ወይም በሸቀጡ ተፈጥሮ ዐይነትና ጒድለት ወይም
ካጠቃለሉ መጥፎነት የተነሣ መሆኑን ካላስረዳ በቀር በአላፊነት ከጠየቅ አይድንም፡፡

ቊ 2808፡፡ ለዕቃ ሰጪው የማስታወቅ ግዴታ፡፡


የሸቀጡ የተፈጥሮ ጠባይ የመለወጥ ነገር በታየበት ጊዜ ሌላ ዐይነት ጥንቃቄ እንዲደረግበት አስፈላጊ መሆኑን በዕቃ መከማቻ ስፍራ
አስቀማጭ የሆነው ሰው ለሸቀጥ ሰጪው ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2809፡፡ ዕቃውን መልሶ ሰለ መስጠት፡፡

(1) ለሸቀጡ ማስቀመጥ የተወሰነው ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ተረካቢው በማከማቻ ስፍራ ሸቀጡን ማኖር አለበት፡፡

(2) አስቀማጭ የሆነ ሰው ያልታሰበ አጋጣሚ ነገር ከደረሰበት ለሸቀጡ ማስቀመጥ የተወሰነው ጊዜ ከመድረሱ በፊት ባለአደራው ዕቃውን
ለባለቤቱ መመለስ ይችላል በሚለው ሰበብ ለመከራከር አይችልም፡፡

ቊ 2810፡፡ ሸቀጡን ከሌላ ሸቀጥ ጋራ ስለ ማደባለቅ፡፡

(1) ይህ መብት ተለይቶና ተገልጾ በውሉ ስምምነት ላይ ካልተሰጠው በቀር፤ በሸቀጥ ማከማቻ ስፍራ አስቀማጭ የሆነው ሰው
የተረከባቸውን ዕቃዎች ተፈጥሮዋቸውና ዐይነታቸው ተመሳሳይ ቢሆንም ካላቂ ዕቃዎች ጋራ አደባልቆ ለማስቀመጥ አይችልም፡፡

(2) በእንደዚህ ያለ ዐይነት ሸቀጦች ተቀላቅለው በተገኙ ጊዜ አደራ ሰጪው ተገቢ የሆኑትን ከፊል ድርሻዎች እንዲሰጡት ለመጠየቅ
ይችላል፡፡

(3) ይህ ሲሆን ሸቀጡን አከማች የሆነው ሰው፤ ለአደራ ሰጪው ድርሻውን ሌሎችን ሳይጠይቅ ሊመልስለት ይችላል፡፡

ቊ 2811፡፡ የሸቀጥ ሽያጭ፡፡

(1) በስምምነታቸው ላይ የተመለከተው የጊዜ ውሳኔ ካለፈ አደራ ሰጪው ሸቀጡን ሳይወስድ የቀረ እንደሆነ ሸቀጥ አስቀማጩ ማስታወቂያ
ከሰጠው በኋላ ሸቀጦቹን ለመሸጥ ይችላል፡፡

(2) በስምምነቱ ላይ ማናቸውም ጊዜ ሳይወሰን ቀርቶ ሸቀጡ በአደራ ከተቀመጠ አንድ ዓመት ባለፈውም ጊዜ የዚሁ ዐይነት መብት አለው፡፡

(3) እንዲሁም ደግሞ ሸቀጦቹ የመበላሸት አደጋ ይደርስባቸዋል ተብሎ የሚያሠጉ ሆነው የተገኙ እንደሆነ ሊሸጣቸው ይችላል፡፡

ቊ 2812፡፡ የዋጋው አወሳሰድ፡፡


ሸቀጡን ለመሸጥ የተደረገው ወጪና ለአስቀማጩ ሊከፈለው የሚገባው ሌላው ሒሳብ ተቀናሽ ሆኖ ዕቃው የተሸጠበት ዋጋ ለባለመብቶቹ
ተቀማፀጭ ሆኖ መቈየት አለበት፡፡

ቊ 2813፡፡ ደረሰኝና የመያዣ የምስክር ወረቀት፡፡

(1) አደራ ሰጪው በማከማቻ ስፍራ ላስቀመጠው ሸቀጥ ደረሰኝ የጠየቀ እንደሆነ ተቀባዩ መስጠት አለበት፡፡

(2) በደረሰኙ ላይ የተጻፈው ሁሉ ያለበት የመያዣ የምስክር ወረቀት ከደረሰኙ ጋራ ተያይዞ መሰጠት አለበት፡፡

(3) ደረሰኙና ይህ የመያዣ የምስክር ወረቀት፤ ከሸቀጥ ተረካቢው እጅ ተቀማጭ ሊሆን ከሚገባው አንድ ቀሪና ሂያጅ ካለው ደብተር ላይ
ተጎርዶ ላስረካቢው ይሰጣል፡፡

ቊ 2814፡፡ በደረሰኙና በመያዣ መስቀመጫውም የምስክር ወረቀቶች ላይ የሚጻፍ ዝርዝር፡፡

በደረሰኙና በመያዣ ማስቀመጫው የምስክር ወረቀቶች ላይ ሊመለከትባቸው የሚገባው፡-

(ሀ) የአስቀማጩ ስምና የአባት ስም፤ ወይም የማኅበሩ ስም ዋና መኖሪያው፤

(ለ) የማከማቻው ቤት ያለበት ስፍራ፤

(ሐ) በተከማችነት የተሰጡት ሸቀጦች ዐይነትና የተፈጥሮ ጠባይ እንዲሁም ተለይተው ሊገለጹ የሚቻልበት ዝርዝር ማመልከቻ ሁሉ፤

(መ) ስለ ንግድ ዕቃ የጉምሩክ ቀረጥ ተከፍሎ እንደሆነና ዕቃዎቹም አሹራንስ የተከፈሉባቸው መሆኑ ነው፡፡

ቊ 2815፡፡ በነዚህ ሰነዶች ተጠቃሚዎች፡፡


(1) የደረሰኝና የመያዣ ማስቀመጫው የምስክር ወረቀት በአስረካቢው ወይም ይኸው አስረካቢው ለእገሌ ይሰጥልኝ ብሎ ባመለከተው
በሦስተኛ ወገን ስም ተጽፈው ሊሰጡ ይቻላል፡፡

(2) አባሪ በመሆንም ሆነ በመነጣጠል በነዚህ ሰነዶች ጀርባ ላይ ተፈርሞባቸው ለሌላ እንዲተላለፉ ለማድረግ ይቻላል፡፡

ቊ 2816፡፡ የሁለቱ ሰነዶች ባለይዞታ መብት፡፡

(1) የደረሰኝና የማያዣውን ማስቀመጫ የምስክር ወረቀት ሰነዶች ሁለቱንም ባንድነት የያዘ ሰው፤ በሸቀጥ ማከማቻ ቦታ የተቀመጡት
ዕቃዎች እንዲሰጡት ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም እነዚህ ዕቃዎች በራሱ ኪሣራ በብዙ ክፍል እንዲመደቡና ለእነዚህም ለያንዳንዱ ብዙ መደቦች ዕቃ ተቀባዩ በመጀመሪያው
ደረሰኝና የምስክር ወረቀት ሰነድ ምትክ አንዳንድ ልዩ ደረሰኝና አንዳንድ የመያዣ ማስቀመጥ የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
ቊ 2817፡፡ የመያዣ የምስክር ወረቀት ባለይዞታ መብት፡፡
የመያዣ የምስክር ወረቀቱ ሰነድ ብቻ ባለይዞታ የሆነ ሰው ዕቃ አስቀማጩ ዘንድ በተቀመጡት የንግድ ዕቃዎች ላይ የመያዣ መብት
አለው፡፡
ቊ 2818፡፡ የመያዣውን የምስክር ወረቀት ስለ ማስተላለፍ፡፡

(1) በመያዣው የምስክር ወረቀት ሰነድ ጀርባ ላይ በመጀመሪያ የማስተላለፍ ጽሑፍ በሚመለከትበት ጊዜ የዕዳውን ልክና ወለዱን
እንዲሁም የሚከፈልበትን ቀን ለይቶ ማመልከት አስፈላጊ ነው፡፡

(2) በመያዣው ወረቀት በጀርባው የመጻፍ ዝርዝር መግለጫና የዚሁኑ ዝርዝር የማመልከቱ ጽሑፍ በደረሰኙ ላይ ተደርጎ የዚሁ ጽሑፍ
ተጠቃሚ የሆነው ሰው እንዲፈርምበት ያስፈልጋል፡፡

ቊ 2819፡፡ ተገቢውን መግለጫ ስላለማመልከት፡፡

(1) በመያዣ መስጫው የምስክር ወረቀት ጀርባ ላይ የተረገው ጽሑፍ በዕዳ ተጠይቆ እንዲከፈል የሚገባውን የገንዘብ ልክ ወስኖ
ያላመለከተ ሲሆን በማከማቻው ስፍራ ተቀማጭ የሆኑት ዕቃዎች በሙሉ ግምታቸውና ሙሉ ዋጋቸው ለተጠያቂው ዕዳ ዋስትና
እንደተሰጡ ያህል ይቈጠራሉ፡፡

(2) ደረሰኙ በስሙ የተሰጠው ሰው ወይም የዚሁ ደረሰኝ ባለይዞታ የሆነው ሰው ሊከፈል የማይገባውን ገንዘብ ከፍሎ እንደሆነ በመጀመሪያ
ጊዜ በደረሰኙ ጀርባ በጻፈው ሰውና በክፉ ልቡና የመያዣ ዕቃውን የምስክር ወረቀት ባለይዞታ በሆነው ሰው ላይ ክሱን አቅርቦ ሊቃወም
ይችላል፡፡
ቊ 2820፡፡ የደረሰኙ ሰነድ ባለይዞታ መብት፡፡

(1) የዕቃው ደረሰኝ ሰነድ ብቻ ባለይዞታ የሆነው ሰው፤ በዕቃ ማከማቻ ስፍራ የተቀመጡትን የንግድ ዕቃዎች የመመርመር መብት አለው፡፡

(2) ለዕቃ ማስቀመጡ የተወሰነው ጊዜ ሲፈጸም ዕቃውን በመያዣ ስም ለያዘው ሰው የሚገባውን ገንዘብ ለዕቃ ተረካቢው ወይም ለትእዛዝ
ባአደራው በመስጠት በማከማቻው ስፍራ የተቀመጡትን ዕቃዎች ለመውሰድ ይችላል፡፡

ቊ 2821፡፡ መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ ዕቃውን ስለ መሸጡ፡፡

(1) የመያዣው የምስክር ወረቀት ባለይዞታ የሆነ ሰው ሊከፈለው የሚገባውን ገንዘብ በተወሰነው ጊዜ ሳይከፈለው የቀረ እንደሆነና ስለ
ንግድ ወረቀቶች በሕግ በተወሰነው ድንጋጌ መሠረት ያለመክፈሉን መግለጫ (ፕሮቴ) አቅርቦ እንደሆነ ለመክፈያው የተወሰነው ጊዜ ባለፈ
በስምንተኛው ቀን በማከማቻው ስፍራ የተቀመጡትን ዕቃዎች ለመሸጥ ይችላል፡፡

(2) የመያዣው የምስክር ወረቀት ባለይዞታ የሆነው የሚጠይቀውን ሒሳብ በገዛ ፈቃዱ የከፈለ በዚሁ በምስክር ወረቀት ጀርባ ፈራሚ
በዚህኛው መብት ተተክቶ የከፈለውን ገንዘብ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) ዕዳው እንዲከፈል የተወሰነው ዘመን ካለፈ ከስምንት ቀን በኋላ የሸቀጦችን ሽያጭ ለማከናወን መብት አለው፡፡
ቊ 2822፡፡ በማከማቻ ስፍራ የተቀመጡት ሸቀጦች መሸጥ፡፡
ሸቀጦችን ተረካቢ የሆነው ወይም የመያዣው የምስክር ሰነድ ባለ ይዞታ የሆነው ሰው ተይዘው በማከማቻው ስፍራ የተቀመጡትን ሸቀጦች
በሚያሸጥበት ጊዜ ስለ እንደዚህ ያለው ጒዳይ በዚህ አንቀጽ ውስጥ ስለ መያዣ ዕቃ ደንብ በተመለከተው ምዕራፍ ላይ በተሰጠው ድንጋጌ
መሠረት ያሻሻጡ ሥርዐት መፈጸም አለበት፡፡

ቊ 2823፡፡ በሰነዱ ጀርባ የፈረሙትን ስለ መጠየቅ፡፡

(1 ) የመያዣው የምስክር ወረቀት ባለይዞታ የሆነው ሰው የያዛቸውን ሸቀጦች ሽያጭ ከመፈጸሙ በፊት በምስክር ወረቀት ጀርባ የፈረሙትን
ሰዎች ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(2) በምስክር ወረቀት ጀርባ ተከታታይ ፈራሚዎች በሆኑት ላይ ጥያቄ ለማቅረብ የሚቻልበት የጊዜ አወሳሰን ደንብ ስለ ንግድ ወረቀት
በተወሰነው ድንጋጌ ላይ እንደተመለከተው ነው፡፡

(3) ጊዜውም መታሰብ የሚጀምረው ሸቀጦቹ ከተሸጡበት ቀን አንሥቶ ነው፡፡

ቊ 2824፡፡ በደንብ የታዘዘውን ሥርዐት (ፎርማሊቴ) ስለ ለመፈጸም፡፡

(1) የመያዣው የምስክር ወረቀት ባለይዞታ የሆነው ሰው፤ የሚጠይቀው፤ ሒሳብ እንዲከፈለው የተወሰነለት ጊዜ ካለፈ በኋላ ያለ መከፈሉን
መግለጫ (ፕሮቴ) ካላቀረበ ወይም ባቀረበ ባሥራ አምስቱ ቀን ውስጥ ሸቀጦቹ እንዲሸጡ ለማድረግ አስፈላጊውን ሥርዐት ካልጀመረ በቀር
በሰነዱ ጀርባ በፈረሙት ሰዎች ላይ ሊያቀርብ የሚችለውን የመጠየቅ መብት ያጣል፡፡

(2) ስለሆነም በደረሰኙ ሰነድ ጀርባ የፈረሙትንና ባለዕዳውን ስለ መጠየቅ ያለውን መብት እንደያዘ ይቈያል፡፡

(3) ይህን ጥያቄ ስለማቅረብ የተወሰነው ይርጋ ዘመን የሚጸናው እስከ ሦስት ዓመት ነው፡፡
ምዕራፍ 6፡፡
ስለ መያዣ ውል፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለ መያዣ ውል በጠቅላላው፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
የሚጸናባቸው ሁኔታዎች፡፡
ቊ 2825፡፡ የመያዣ ውል ትርጓሜ፡፡

(1) የመያዣ ውል ማለት አንድ ባለዕዳ፤ በባለገንዘቡ በኩል የገባውን ግዴታ ለመፈጸም መቻሉን በማረጋገጥ መያዣ ተብሎ የሚጠራውን
ዕቃ ለመስጠት የሚገደድበት ውል ማለት ነው፡፡

ቊ 2826፡፡ መያዣ ሰጪው፡፡


ለሌላው ሰው ዕዳ ዋስ እንዲሆን ሦስተኛ ወገን ከባለገንዘቡ ጋራ የመያዣውን ውል ለመዋዋል ይችላል፡፡
ቊ 2827፡፡ ዋስትና የተሰጠበት ዕዳ፡፡
ወደፊት ስለሚፈጸም ግዴታ ወይም ሁኔታ ስላለበት ግዴታ በመያዣ ውል ለመዋዋል ይችላል፡፡
ቊ 2828፡፡ የአሠራሩ ሁኔታ ፎርም፡፡

(1) ዋስትና የተሰጠበት ግዴታ ከፍተኛው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በማንኛቸውም ሁኔታ ቢሆን በግልጽ ተጠንቅቆ በመያዣው ውል
ውስጥ መመልከት ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውሉ ፈራሽ ይሆናል፡፡
(2) የመያዣው ውል ከ 5 ብር በላይ የሆነ እንደሆነ ውሉ በጽሑፍ ካልተደረገና ይኸውም ጽሑፍ እርግጠኛ ቀን ካገኘበት ዘመን ጀምሮ
ካልሆነ በቀር አይጸናም፡፡

ቊ 2829፡፡ በመያዣ የተሰጠ ነገር፡፡

(1) በመያዣነት የሚሰጠው አንድ ተንቀሳቃሽ ንብረት፤ ወይም በጠቅላላው ዕቃ ተብለው ከሚጠሩ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች አንዱ ወይም
አንድ የገንዘብ መጠየቂያ መብት ሰነድ ወይም ባንድ ተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ ያለ የመብት መጠየቂያ ሰነድ ለመሆን ይችላል፡፡

(2) ተለያይቶ በደባባይ በሐራጅ ለመሸጥ የሚቻል ነገር መሆን አለበት፡፡

ቊ 2830፡፡ መያዣው በባለገንዘቡ እጅ ስለ መሆኑ፡፡

(1) በዕቃው ለማዘዝ የሚያስችሉት ሰነዶች ከተሰጡት፤ ባገንዘቡ መያዣውን እጅ እንዳደረገ ያህል ይቈጠራል፡፡

(2) እንዲሁም በማከማቻው ስፍራ የተቀመጠው የሸቀጥ መያዣ ምስክር ወረቀት ወይም የሸቀጡ መላኪያ ሸኝ ደብዳቤ፤ ወይም በጒዞ ላይ
ያሉትን የተጫኑ ሸቀጦች የሚያመለክተው መሸኛ ወረቀት በስተጀርባው በባለገንዘቡ ስም ተጽፎ ከተሰጠው መያዣው በእጁ እንዳለ ሆኖ
ይቈጠራል፡፡

ቊ 2831፡፡ በተዋዋዮቹ ስምምነት መያዣው በሦስተኛ ሰው እጅ ስለ መቀመጡ፡፡

(1) መያዣው በሦስተኛ ሰው እጅ እንዲቀመጥ ተዋዋዮቹ ሊስማሙ ይችላሉ፡፡

(2) የሦስተኛ ወገን መብቶችና ግዴታዎች ስለ አደራ ወይም ስለ ዕቃ ማከማቻ በወጣው ድንጋጌ መሠረት ይከናወናል፡፡

ቊ 2832፡፡ መያዣው በባለዕዳው እጅ ስለ መሆኑ፡፡

(1) በሕጉ ላይ ተገልጾ ካልተፈቀደ በቀር በመያዣ ተሰጥቶ ተይዞዋል የተባለው ዕቃ ከባለዕዳው እጅ ሳይወጣ በመያዣ እንደተሰጠ ሆኖ
ሊቈጠር አይችልም፡፡

(2) በሕግ ከተፈቀደው በቀር መያዣው በባለዕዳው እጅ ይሆናል ብለው ቢዋዋሉ ውሉ አይጸናም፡፡

ቊ 2833፡፡ የመያዣ ውል አፈጻጸም ደንብ፡፡

(1) የመያዣ አሰጣጥን ውል የሚመለከቱ የውል አፈጻጸም ደንቦች በዚህ ምዕራፍ ላይ ከተሰጠው ድንጋጌ በቀር ስለ እንደዚህ ያለው ውል
አጻጻፍና አፈጻጸም በሚሰጥ ልዩ ደንብ ውስጥ ወይም መያዣ እየተቀበሉ እንዲያበድሩ ተፈቅዶላቸው ስለሚቋቋሙ ማኅበሮች በሚወጣ
ልዩ ደንብ ውስጥ ገብቶ የሚደነገግ ጒዳይ ነው፡፡

(2) በማከማቻ ስፍራ በተቀመጡት ሸቀጦች ስለ መዋዋል ጒዳይ ከዚህ በላይ በተጻፈው በማከማቻ ስፍራ ስለሚቀመጥ ዕቃ በሚለው
ምዕራፍ ውስጥ ተነግሮአለ፡፡

ንኡስ ክፍል (2)፡፡


የመያዣ ሰጪው መብትና ግዴታ፡፡
ቊ 2834፡፡ የመያዣው ዕቃ ባለሀብት፡፡

(1) በመያዣው ውል ውስጥ በዕቃው ላይ ባለመብት የሚሆነውን ለይተው ካልተዋዋሉ በቀር አስያዡ በመያዣነት ለሰጠው ዕቃ ባለቤት
ሆኖ የመቈየት መብት አለው፡፡

(2) በዚህም መብቱ እንደፈቀደው ሊያዝበት በተለየም መያዣውን ሊሸጠው ወይም ለሌላ ሰው ተተኪ መያዣ አድርጎ አሳልፎ ሊያሲዘው
ይችላል፡፡
ቊ 2835፡፡ መያዣውን ለመጠበቅና በመልካም ለመያዝ የሚደረግ ወጪ፡፡
ዕቃውን በመያዣ የተቀበለው ባገንዘብ የያዘውን ዕቃ ለመጠበቅና በመልካም ሁኔታ ለመያዝ ያደረገውን ወጪ አሲያዡ መክፈል አለበት፡፡
ቊ 2836፡፡ ባለገንዘቡ የሚያደርገው ከመጠን ማለፍ፡፡
ዕቃውን በመያዣ ስም የተረከበው ባለገንዘብ በመያዣው ላይ መብቱ ከሚፈቅድለት በለፍ አላገባብ ሠርቶ የተገኘ እንደሆነ ባለ ዕዳው
የመያዣው ዕቃ ከባለገንዘቡ እጅ ወጥቶ የትእዛዝ ባላደራ በሆነ ሰው እጅ ተዛውሮ እንዲቀመጥ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2837፡፡ ዕዳውን አስቀድሞ ስለ መክፈል፡፡

(1) ዕቃ አስያዥ የሆነው ባለዕዳው ዕቃው የተያዘበትን ገንዘብ በማናቸውም ጊዜ በመክፈል የተያዘው ዕቃ እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት
አለው፡፡
(2) ይህን ደንብ ተቃራኒ የሆኑ ስምምነት ሁሉ አይጸናም፡፡

ቊ 2838፡፡ ሦስተኛ ወገን የሰጠው መያዣ፡፡

(1) መያዣውን የሰጠው ሦስተኛ ወገን በሆነ ጊዘ የማስያዙ ጒዳይ ከተፈጸመ በኋላ በባለገንዘቡና በባለዕዳው መካከል የተደረገው ውል
የዚህን የዕቃ አስያዡን ሁኔታ ሊያብስበት (ሊጎዳው) አይችልም፡፡

(2) ዋናው ባለዕዳ በዚህ ኢልከራከርም ብሎ ነበር በለት ለመቃወም ሳይቻል ባለዕዳው ሊከራከርበት የሚገባውን መብት ሁሉ መያዣ
የሰጠው ሰው ሊከራከርበት ይችላል፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
ዕቃውን የያዘ የባለገንዘብ መብቶችና ግዴታዎች፡፡
ቊ 2839፡፡ ጠቅላላ መሠረቱ፡፡

(1) መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ በባለዕዳው ሀብት ላይ ለሌሎቹ ባለ ገንዘቦች ያላቸው መብት ለሱም ይኖረዋል፡፡

(2) ከዚህም በቀር የመያዣውን ዕቃ ስለሚመለከተው ነገር በዚህ ምዕራፍ ላይ የተገለጸው ልዩ መብት አለው፡፡

ቊ 2840፡፡ የመያዣው ዕቃ አገልግሎት፡፡


መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ መያዣ ሰጪው ባለዕዳ ካልፈቀደለት ወይም ለተያዘው ዕቃ አጠባበቅ አገልግሎት ፍጹም አስፈላጊ ሆኖ
ካልተገኘ በቀር በተያዘው ዕቃ ለመገልገል አይችልም፡፡

ቊ 2841፡፡ የመያዣው ፍሬ፡፡

(1) መያዣው ፍሬ የሚሰጥ እንደሆነ ፍሬውን መሰብሰብ የሚገባቸው ገንዘብ ጠያቂው ወይም ጠባቂው ናቸው፡፡

(2) መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ ከመያዣው ለተገኘ ፍሬ ባለሀብት ይሆናል፡፡

(3) መያዣው የሚሰጠው ፍሬ በቅደም ተከተል ለጥበቃውና ለአያያዙ ለተደረገው ወጪ መያዣው ለተያዘበት ገንዘብ ወለድ ለዋናውም
ገንዘብ እየታሰበ ይቀነሳል፡፡

ቊ 2842፡፡ የእጅ ክስ፡፡

(1) መያዣውን የተቀበለ ባለገንዘብ ስለ መያዣው የእጅ ክስ ለማቅረብ ይችላል፡፡

(2) መያዣውን የሚጠብቀው ሰው ይህንን ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ለባለገንዘቡና መያዣውን ለሰጠው ሰው ሳይዘገይ
ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 2843፡፡ መያዣው የኔ ነው ስለሚል ሦስተኛ ወገን፡፡


መያዣ የተቀበለ ባለገንዘብ ይህን መያዣ የተቀበለው የባለቤትነት መብት ከሌለው ሰው ላይም ቢሆን እንኳ፤ የመያዣው ውል በሚሰጠው
መብት ሊሠራበት ይችላል፡፡
ቊ 2844፡፡ ልዩነት፡፡

(1) ምን ጊዜም ቢሆን የመያዣው ባለቤት የመያዣው ውል በተደረገ ጊዜ መያዣውን የተቀበለው ባለገንዘብ፤ መያዣ ሰጪው የባለቤትነት
መብት የሌለውና ውል ለማድረግ የማይችል መሆኑን እያወቀ ወይም ሊያውቅ ሲገባው የያዘ መሆኑን ካስረዳ የተያዘውን ዕቃ መልሶ
ለመውሰድ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ደግሞ ዕቃው በዋስትና የተያዘበትን ዕዳ በመክፈል መልሶ ለመውሰድ መብት አለው፡፡

ቊ 2845፡፡ መያዣውን ስለ መመለስ፡፡

(1) ገንዘቡ በመከፈሉ ወይም በማንኛውም ሌላ ምክንያት የመያዣው ውል ሲያልቅ መያዣውን የተቀበለ ባለገንዘብ ለዕቃ አስያዡ ወይም
እርሱ ይቀበልልኝ ላለው ሰው ዕቃውን መመለስ አለበት፡፡

(2) መያዣውን የተቀበለው ባለገንዘብ መያዣ የሆነውን ዕቃ እስኪመልስ ድረስ በአንድ ዕቃ ጥቅም በሚያገኝ ባለይዞታ ላይ በሚፈጸመው
ደንብ መሠረት ስለዕቃው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ይሆናል፡፡

ቊ 2846፡፡ ይዞ የማቈየት መብት፡፡


በዚህ ምዕራፍ ላይ በተወሰነው ድንጋጌ መሠረት መያዣውን የተቀበለ ባለገንዘብ ሊከፈለው የሚገባው ሁሉ በሙሉ እስኪከፈለው ድረስ
የመያዣውን ዕቃ በእጁ የማቈየት መብት አለው፡፡

ቊ 2847፡፡ የመያዣው መጥፋት ወይም መበላሸት፡፡


መያዣውን ተረክቦ የሚጠብቀው ባለገንዘቡ እንደሆነ በዚህ አንቀጽ በተለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት፤ ስለ መያዣው መጥፋትና
በመበላሸት አላፊ የሚሆነው ራሱ ነው፡፡

ቊ 2848፡፡ ስለ ዕቃ መተካት፡፡
መያዣው በማናቸውም ምክንያት ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ፤ መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ መብት የሚተካው፤ ስለ ዕቃው መጥፋት ወይም
መበላሸት አላፊ የሆነው ሰው ሊከፍል በሚገባው ኪሣራ፤ ወይም የዕቃውን አሱራንስ ያደረገው በሚከፍለው ገንዘብ ወይም ደግሞ ዕቃውን
የወሰደው ባለሥልጣን ሊከፍለው በሚገባው ገንዘብ ነው፡፡
ንኡስ ክፍል 4፡፡
የመያዣ ውል የሚቀርበት፡፡
ቊ 2849፡፡ ውሉ በተጨማሪ ዐይነት ስለ መሆኑ፡፡
ዕቃው የተያዘበት የዋስትና ዕዳ የተፈጸመ እንደሆነ፤ የመያዣው ውል ቀሪ ሆኖ የተያዘውም ዕቃ ላስያዡ ይመለሳል፡፡
ቊ 2850፡፡ መያዣው የማይከፋፈል ስለ መሆኑ፡፡
የብድሩ ገንዘብና የመያዣው ዕቃ ለመከፋፈል የሚችል ቢሆንም እንኳ፤ መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ ሊከፈለው የሚገባው ነገር በሙሉ
ካልተከለው በቀር መያዣውን በሙሉም ሆነ በከፊል እንዲመልስ አይገደድም፡፡
ንኡስ ክፍል 5፡፡
የመያዣ ውል አፈጻጸም፡፡
ቊ 2851፡፡ መያዣን ይዞ ለመቅረት ስለሚደረግ ስምምነት፡፡

(1) ዕዳው በሚከፈልበት ቀን ባለዕዳው ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ፤ ባለ ገንዘቡ በሕጉ የተደነገገውን ሥርዐት ፎርማሊቴ ሳይፈጽም
መያዣውን መሸጥ ወይም ለራሱ ማስቀረት ይችላል ብለው ቢስማሙ፤ ስምምነቱ መያዣው ከተሰጠበት ቀን በኋላ ቢሆንም አይጸናም፡፡

(2) ለዕዳው መክፈያ የተወሰነው ጊዜ ከደረሰ በኋላ ግን ባለዕዳው ለባለገንዘቡ ስለ ገንዘቡ ምትክ መያዣውን እንዲለቅ ሊስማሙ ይችላሉ፡፡
ቊ 2852፡፡ የመያዣው ውል ለሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ስለ መሆኑ፡፡

(1) የመያዣው ውል ለሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ለመሆን እንዲችል ባለገንዘቡ በመያዣው ላይ መብት አለኝ በሚልበት ጊዜ መያዣው
በባለገንዘቡ ወይም ተዋዋዮቹ በመረጡት ሰው እጅ እንዲገኝ ያስፈልጋል፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው ጊዜ የዕዳ ዋስትና መያዣ የሆነው ዕቃ ከባለዕዳው እጅ ካልወጣ፤ ወይም በባለገንዘቡ ፈቃድ ከባለዕዳው እጅ ተመልሶ
ከገባ፤ ወይም ደግሞ ባለገንዘቡ አምጣ ብሎ ለመጠየቅ መብት በሌለው በሦስተኛ ወገን እጅ የሚገኝ ከሆነ የመያዣው ውል ምንም ዐይነት
ዋጋ ሊሰጥ አይችልም፡፡

ቊ 2853፡፡ ስለ ማስጠንቀቂያ አሰጣጥ፡፡

(1) መያዣውን የያዘው ባለገንዘብ የያዘውን ዕቃ ከመሸጡ በፊት አስያዡ ባለዕዳ የገባውን ግዴታ እንዲፈጽም ሳይፈጽም ቢቀር ግን ዕቃውን
የሚያሸጥበት መሆኑን አስቀድሞ በማስጠንቀቅ ማስታወቂያ መስጠት አለበት፡፡

(2) የዚህም ዐይነት ማስጠንቀቂያ መያዣውን ሰጭ ለሆነው ሦስተኛ ወገን ሊሰጠው ይገባል፡፡

ቊ 2854፡፡ የመያዣው መሸጥ፡፡

(1) ማስጠንቀቂያው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ እስከ ተከታዩ ስምንት ቀን ድረስ ማንኛውም መቃወሚያ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ወይም
የቀረበው መቃወሚያ መሠረት የሌለው መሆኑ የታወቀ እንደሆነ ባለገንዘቡ መያዣውን በአደባባይ በሐራጅ ለማሸጥ ይችላል፡፡

(2) መያዣ የሆነው ነገር በሕግ ወይም በዕለት ገበያ የተወሰነ ዋጋ እንዳለው ይህን የመሰለውን ዕቃ እንዲሸጥ በተፈቀደለት ሰው አማካይነት
ዕቃው እንዲሸጥ ለማድረግ ይቻላል፡፡

ቊ 2855፡፡ ዳኞች የሚያደርጉት አወሳሰን፡፡


መያዣ ሰጪው መቃወሚያ አቅርቦላቸው እንደሆነ ዳኞች የመያዣው ዋጋ የባለገንዘቡን ዕዳ ለመክፈል የሚበቃውን አንድ የተወሰነ ዕቃ
እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል የባገንዘቡን መብት በዚሁ ብቻ ሊወስኑበት ይችላሉ፡፡

ቊ 2856፡፡ መያዣው ለገንዘብ ጠያቂው (ለባለገንዘቡ) የሚሰጥበት ሁኔታ፡፡


ባለገንዘቡ ስለ ገንዘቡ መያዣ በዋስትና የተቀበለውን ዕቃ፤ በልዩ ዐዋቂዎች በተሰጠው ግምት መጠን ወይም በዕለት ገበያ በተወሰነው ዋጋ
ልክ ተገማምቶ ሊከፈለው ከሚገባው ሒሳብ ጋራ ተመዛዛኝ የሚሆነውን መያዣ ስለ ዕዳው ለራሱ እንዲያስቀረው እንዲፈቀድለት ዳኞችን
ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2857፡፡ የቀዳሚነት መብት፡፡

(1) መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ ከመያዣው ሽያጭ ዋጋ ከሌሎቹ ባለገንዘቦች ቀድሞ የመቀበል መብት አለው፡፡

(2) የመያዣው ዋስነት በውሉ ላይ ለተመለከተው ለዋናው ዕዳና ለወለዱ፤ ጊዜው በማለፍ ለሚከፈለው ወለድ፤ መያዣውን ለመጠበቅና
በመልካም አያያዝ ለማኖር ወይም ለመሸጥ ለሚደረገው ወጪ ሁሉ ነው፡፡

ቊ 2858፡፡ የባለገንዘቡ መብቶች ወሰን፡፡

(1) ባለገንዘቡ በመያዣው ውል ከተወሰነው ከፍተኛ ገንዘብ በላይ ባለው ትርፍ ነገር መብት አለኝ ብሎ ሊከራከርበት አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም የመያዣው ውል ከተደረገ በኋላ የተገኘ፤ ከባለዕዳው ወይም ከዕቃ አስያዡ ላይ የሚጠይቀው ሌላ ገንዘብ ቢኖረውም
በመያዣው ላይ የቀዳሚነት መብት አለኝ ብሎ ሊከራከር አይችልም፡፡

ቊ 2859፡፡ የዋጋው አሰጣጥ፡፡

(1) የመያዣው ሽያጭ ዋጋ ለባለገንዘቡ ሊከፈለው እስከሚገባው ተመዛዛኝ ሒሳብ ድረስ ተሰጥቶ ዕቃ አስያዡ ዕዳውን እንደከፈለ ያህል
ይቈጠራል፡፡
(2) ከዕዳው ሒሳብ የተረፈው የሽያጩ ዋጋ ለዕቃ አስያዡ ይሰጣል፡፡

ቊ 2860፡፡ መያዣ ስለ ተቀበሉ ብዙ ባለገንዘቦች፡፡

(1) ዕቃው ብዙ የመያዣ መብት ጠያቂ ያለበት እንደሆነ ባለገንዘቦቹ ሒሳባቸው የሚከፈላቸው እንደ ቅድሚያ ደረጃቸው ነው፡፡

(2) የቅድሚያ ደረጃቸውም የሚመደበው መያዣውን ባደረጉበት ቀን ቅደም ተከተል ነው፡፡

ቊ 2861፡፡ የገዥው መብቶች፡፡

(1) መያዣውን የገዛው ሰው ለዕቃው ባለቤትነቱ ከማናቸውም ዕዳ ነጻ በሆነ አኳኋን ነው፡፡

ቊ 2862፡፡ የባለገንዘቡ አላፊነት፡፡


የመያዣው ውል በተጻፈበት ጊዜ የዚህ ዐይነት ነገር መኖሩን የሚያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው ካልሆነ በቀር በመያዣ የተቀበለውን
የሌላውን ዕቃ የሚሸጥ ባገንዘብ ዕቃውን በመሸጡ ማንኛውም አላፊነት አይደርስበትም፡፡
ክፍል 2፡፡
የገንዘብ መጠየቂያ ሰነዶችን ወይም ግዙፍ ያልሆኑ ሌሎች ሀብቶችን ስለ ማስያዝ
ቊ 2863፡፡ በመያዣ ሰጪውና በባለዕዳው መካከል ስላሉ ግንኙነቶች፡፡
በዋሱና በዋናው ባለዕዳ መካከል ያለውን ግንኙነት ስለሚመለከተው ደንብ የተሰጠው ድንጋጌ ዕቃውን ባስያዘው በሦስተኛው ወገንና
በዋናው ባለዕዳ መካከል ያለውን ግንኙነት በሚመለከተውም ጒዳይ ተፈጻሚ ሆኖ የሚጸና ነው፡፡

ቊ 2864፡፡ የሰነድ ማስረጃ የሌለው ገንዘብ፡፡

(1) በሰነድ ላይ ያልተገለጸ የገንዘብ መጠየቅ መብት ሰነድ በመያዣ ሲሰጥ ዋስትና የሚሰጥበት ገንዘብ ማንኛውም ብዛት ቢኖረው፤
በመያዣው የተሰጠው የገንዘብ መጠየቅ መብት ማስረጃ የምን ያህል ገንዘብ እንደሆነና ዋስትና የሚሰጥበት ገንዘብ ስንት እንደሆነ
አብዛኛውን ልክ በግልጽ የሚያመለክት የጽሑፍ ማስረጃ እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡

(2) በመያዣ የተሰጠው የገንዘብ መጠየቂያ መብት የመያዣው ገንዘብ ባለዕዳ እዲያውቀው ካልተደረገ ወይም እሱ የተረጋገጠ ቀን
በተመለከተበት ጽሑፍ ውሉን ካልተቀበለ የተሰጠው መያዣ አይጸናም፡፡

ቊ 2865፡፡ በሰነድ ላይ ያልተገለጸ መብት፡፡

(1) የገንዘብ መጠየቂያ መብት ያልሆነና በሰነድ ያልተገለጸ ሌላ ዐይነት መብት በመያዣ ሲሰጥ፤ የመያዣው ውል የሚከናወነው ለነዚህ
መብቶች ማስተላለፍ በተደነገገው ሥርዐት (ፎርም) ነው፡፡

(2) በመያዣ የተሰጠውን የመብት ዐይነትና ዋስትና የሚሰጥበትን የገንዘብ መጠየቂያ ሰነድ በቂ በሆነ ዐይነት በመዘርዘር የሚገልጽ ቀኑ
የተረጋገጠ የጽሑፍ ማስረጃ እንዲኖር፤ በማንኛውም አጋጣሚ ሁኔታ ሲሆን ፍጹም አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ዐይነት ሳይፈጸም ቢቀር ግን
ፈራሽ ነው፡፡

(3) አንዳንዶቹ መብቶች በመያዣነት ሲሰጡ የሚሠራባቸው ድንጋጌዎች የተጠበቁ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2866፡፡ በሰነድ የተገለጸ መብት ወይም ገንዘብ፡፡

(1) በመያዣነት የተሰጠው ገንዘብ ወይም መብት በዕዳ መተማመኛ ሰነድ ወይም የንግድ መለዋወጫ ባልሆነ በሌላ ሰነድ የተጻፈ ሲሆን፤
ይህ ሰነድ መያዣ በተቀበለው ባለገንዘብ ወይም በመያዣው ውል በተስማሙበት ሰው እጅ ሊቀመጥ ይገባል፡፡

(2) የንግድ መለዋወጫ መሆናቸው በጽሑፍ የተገለጹትን የገንዘብ መጠየቂያ መብት የሆኑትንና ሰነዶች በመያዣ የመሰጠቱ ሥርዐት
የሚፈጸመው በንግድ ሕግ ላይ በተመለከቱት ደንቦች መሠረት ነው፡፡

ቊ 2867፡፡ በተወሰነ ጊዜ የገቢ ጥቅም የሚሰጡ የገንዘብ መብት ሰነዶች፡፡ (1) የመያዣው ወሰን፡፡
(1) እንደ ጥቅም ድርሻ (ዲቢዳንድ) የሆኑ በተወሰነ ጊዜ ወለድ ወይም ሌላ ጥቅም የሚያስገኙ የገንዘብ መጠየቂያ ሰነዶች በመያዣ በተሰጡ
ጊዜ ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ካልኖረ በቀር መያዣነታቸው የሚጸናው ወደፊት በሚያስገኙት ትርፎች ላይ ነው እንጂ፤ የመከፈያቸው ጊዜ
ባለፉት ትርፎች ላይ አይደለም፡፡

(2) እነዚህ ተጨማሪ ትርፎች በልዩ ሰነዶች ላይ ተለይተው በመዘርዘር የተመለከቱ ከሆኑ በሕጉ ላይ በተፈቀደው ደንብ መሠረት ራሳቸው
መያዣ ሆነው ካልተሰጡ በቀር በመያዣው ውል ውስጥ እንደገቡ አይቈጠሩም፡፡

ቊ 2868፡፡ (2) መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ መብትና ግዴታ፡፡

(1) መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ ስለ ዋስትና የተቀበለው የገንዘብ መጠየቂያ ሰነድ የሚያስገኘውን ወለድና እንደዚሁም የዚሁ የገንዘብ
መቀበያ ሰነድ ባለዕዳ የሆነው ሰው በየጊዜው መከፈል የሚገባቸውን ሌሎቹን ገቢዎች መቀበል አለበት፡፡

(2) በዚህ ዐይነት ያገኘውንም ለእሱ ራሱ ከሚከፈሉት ገንዘቦች ሊቀነስ የሚገባው አስቀድሞ ስላደረጋቸው ወጪዎች ቀጥሎ
ስለሚቀበላቸው ወለዶች በመጨረሻም ከዋናው ገንዘብ ላይ ነው፡፡

(3) አስያዡ የዚህን ዐይነት አከፋፈል ለመቃወም አይችልም፡፡

ቊ 2869፡፡ መጠበቂያ የሚሆኑ ተግባሮች፡፡


መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ በመያዣ የተረከባቸውን መብቶች ለመጠበቅ የሚያስፈልገውን ተግባር መፈጸም አለበት፡፡
ቊ 2870፡፡ በመያዣ የተሰጡ አክሲዮኖች፡፡
አክሲዮኖች በመያዣ በተሰጡ ጊዜ በአክሲዮኔሮች ጉባኤ ላይ የሚቀመጠው አክሲዮኔሩ ራሱ ነው እንጂ፤ አክሲዮን በመያዣ የተቀበለው
ባለገንዘብ አይደለም፡፡

ቊ 2871፡፡ በመያዣ ስለተሰጠው የገንዘብ ሰነድ የባለዕዳው መብቶች፡፡

(1) በመያዣ የተሰጠው ገንዘብ መጠየቂያ ሰነድ ባለዕዳ የሆነው ሰው ከእሱ ገንዘብ ፈላጊ የሆነውን ሰው የሚከራከርበትን መብት መያዣ
የተቀበለውን ሌላውንም ባለገንዘብ ሊከራከርበት ይችላል፡፡

(2) ስለሆነም የመያዣ መስጫውን ውል ያቋቋመውን ስምምነት ያላንዳች ክርክር ባለዕዳው ፈቅዶ ተቀብሎ እንደሆነ፤ በእሱና ከእሱ ላይ
ገንዘብ በሚፈልገው መካከል በነበረው ግንኙነት የሆነውን የዕዳ መቻቻል ሊከራከርበት አይችልም፡፡

ቊ 2872፡፡ በመያዣ የተሰጠው ሰነድ የሚያመጣውን ገንዘብ ስለ መቀበል፡፡

(1) መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ የሚጠይቀው መብት እንዲከፈለው የተወሰነለት ጊዜ ሲደርስ፤ በመያዣ የተቀበለው ሰነድ የሚያመጣውን
ገንዘብ መቀበል አለበት፡፡

(2) ስለሆነም ዕዳው በዚህ ዐይነት እንዳይከፈል መያዣ ሰጪው የተቃወመ እንደሆነ ባለዕዳው የሚጠየቀውን ገንዘብ ገቢ ካላደረገ ወይም
ሊከፍል የሚገባውን ነገር ካላስረከበ በቀር ከዕዳው ነጻ ለመሆን አይችልም፡፡

(3) ስለ ዕዳው ክፍያ የተሰጡት ገቢ ገንዘቦች ወይም አላቂ የሆኑ ሌሎች ነገሮች የሚቀመጡበት ስፍራ የሚመረጠው በሁለቱ ወገኖች
ስምምነት፤ ይህ ስምምነት ባይኖር፤ በዳኞች ነው፡፡

ቊ 2873፡፡ የገንዘብ መጠየቂያውን መብት ሰነድ፤ ወይም በመያዣ የተሰጠውን መብት ስለ መሸጥ፡፡
ዋስትና የተሰጠበት ዕዳ እንዲከፈል የመጠየቂያው ጊዜ ደርሶ እንደሆነ መያዣ የተቀበለው ባለገንዘብ በያዣ የተቀበለውን የገንዘብ መጠየቂያ
መብት ሰነድ ወይም በመያዣ የተሰጠውን መብት ወይም፤ ባለዕዳው ስለ ዕዳው ክፍያ ያስረከባቸውን ዕቃዎች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ከዚህ
በላይ በተመለከተው ክፍል የተመለከተውን ሥርዐት መሠረት አድርጎ ለማሸጥ ይችላል፡፡

ቊ 2874፡፡ በላይኛው ክፍል ወደ ተመለከተው ድንጋጌ ስለ መመራት፡፡


የገንዘብ መጠየቂያ መብት ሰነዶችን ወይም ግዙፍ ያልሆኑ ሀብቶችን በመያዣ የመስጠትን ሥርዐት ስለሚመለከተው ደንብ አፈጻጸም በዚህ
ክፍል ላይ ላልተመለከተው ደንብ ሁሉ፤ በጠቅላላው የመያዣን ውል አፈጻጸም ስለሚመለከተው ደንብ ከዚህ በላይ ባለው ክፍል ውስጥ
የተሰጠው ድንጋጌ ይጸናል፡፡

አንቀጽ ዐሥራ ስምንት፡፡


የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለ ሚመለከቱ ውሎች፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ፡፡
ቊ 2875፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ የሚመራው በዚሁ ሕግ ያንድ ነገርን
ባለሀብትነት ማስተላለፍን ስለሚመለከቱ ውሎች በተደነገገው አንቀጽ በተመለከተው ደንብ መሠረት ነው፡፡

ቊ 2876፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መሥራትና መሸጥ፡፡

አንዱ ወገን ተዋዋይ ለሌላው ወገን ተዋዋይ አንድ ቤት፤ አንድ የቤት ክፍል ወይም ገና የሌለ አንድ የሚሠራ ሕንጻ ለመስጠት ግዴታ
የሚገባበት ውል፤ የአንድ ሕንጻ ሥራ ውል ይባላል እንጂ፤ የሽያጭ ውል ሊባል አይችልም፡፡

ቊ 2877፡፡ የውሉ ፎርም፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ ሳይደረግ የቀረ እንደሆነ ፈራሽ ይሆናል፡፡

ቊ 2878፡፡ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ስለ ማጻፍ፡፡

ያንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ንብረቱ ባለበት አገር በሚገኘው በማይንቀሳቀስ ሀብት መዝገብ ካልተጻፈ በቀር በሦስተኛ ወገኖች
ዘንድ ውጤትን ሊያስገኝ አይችልም፡፡

ቊ 2879፡፡ የንብረቱ ሻጭ የነገሩ ተካፋይ እንዲሆን አስፈላጊ ስለ መሆኑ፡፡

(1) ገዢው የገዛውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሀብትነት በስሙ ለማዛወርና በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ለማጻፍ እንዲችል ሻጩ
የንብረቱን ሰነድና ማንኛውንም ማስረጃ ሁሉ ሊሰጠው ይገባል፡፡

(2) ይህ ግዴታም ለሽያጩ ውል እንደ ዋና ስምምነት ሆኖ የሚገመት ነው፡፡


ቊ 2880፡፡ ሻጩ አንዳንድ መብቶችን መግለጽ ግዴታ ያለበት ስለ መሆኑ፡፡

(1) በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ላይ ሳይጻፉ በገዥ ላይ መቃወሚያ ሊሆኑበት የሚችሉትን የተሸጠውን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት
የሚመለከቱትን የ 3 ኛ ወገኖች መብቶች ሻጩ ለገዥ ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ ለሦስተኛ ወገኖች ጥቅም በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ የተጻፉትን መብቶች ሻጩ ለገዢው ገልጾ
እንዲያስታውቀው ውሉ ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 2881፡፡ የተመዘገቡ መብቶችና ግዴታዎች፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

ገዢው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት በሚገኝበት ስፍራ ባለው መዝገብ ውስጥ የተጻፉትን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የሚመለከቱትን
መብቶችና ግዴታዎች ሁሉ እንደሚያውቅ ሁኖ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2882፡፡ (2) የሻጩ ግልጽ ዋስትና፡፡

(1) በዚህ አንቀጽ የተመለከቱትን መብቶች በሚመለከት ምክንያት በሸጥኩት የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የመነቀል ነገር ሊደርስ አይችልም
ብሎ ሻጩ መድን ሊሆን ቃለ ካልገባ በቀር ገዢው የማስለቀቅን ዋስትና በሚመለከቱት ድንጋጌዎች ሊከራከርባቸው ሊጠቀምባቸው
አይችልም፡፡

(2) ይህም የአላፊነት ዋስትና ሊገኝ የሚችለው በሽያጩ ውል ላይ በግልጽ የተመለከተ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

ቊ 2883፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣና የወለድ አግድ፡፡

የማይንቀሳቀሰው ንብረት፤ መያዣ ባለው ገንዘብ ጠያቂ ወይም ንብረቱን (በዕዳ ገንዘብ) በወለድ አግድ በያዘው ሰው ጠያቂነት በፍርድ
ተይዞ እንዲሸጥ የተደረገ እንደሆነ ገዢው ስለ መነቀሉ ሻጩ በመድንነቱ እንዲያልፍ ለመጠየቅና በዚሁም መብቱ ለመከራከር ይችላል፡፡

ቊ 2884፡፡ የሌላውን ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት ስለ መሸጥ፡፡

(1) የተሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት በሙሉ ወይም በከፊል የሻጩ ሀብት ሳይሆን የቀረ እንደሆነ የመነቀልን የአላፊነት ዋስትናን
የሚመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

(2) ገዢው የገዛውን ንብረት እንዲለቅ መደረጉን ሳይጠብቅ በዚህ የመነቀል የአላፊነት ዋስትና ደንብ አስቀድሞ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡

(3) ስለሆነም የገዥነት መብቱን እንዳያጣ ዳኞች ፍርድ ሊሰጡ በደረሱበት ጊዜ የመነቀሉም ጒዳይ የማያስፈራው ከሆነ በነዚህ ደንቦች
ሊጠቀምባቸው አይችልም፡፡
ቊ 2885፡፡ በቀዳሚነት ይገባኛል የማለት መብት፡፡

በውሉ ላይ የተጻፈ ግልጽ የሆነ ስምመነት ከሌለ በቀር የተሸጠውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ገዢው በቀደምትነት ለመግዛት ሕጋዊ መብት
አለኝ ለሚል ሰው እንዲለቅ የተደረገ እንደሆነ ሻጩ ለገዢው የጉዳት ካሣ መክፈል የለበትም፡፡

ቊ 2886፡፡ የሻጩ አላፊነት፡፡

ገዢው የገዛውን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሙሉ ወይም በከፊል እንዲለቅ የተደረገ እንደሆነ ከዋጋውና በውሉ ካደረገው ወጪ በላይ ገዢው
ይህን ንብረት ለማልሚያ ያወጣውን ገንዘብ እንዲመልስለት ሻጩን በአላፊነት ይጠይቃል፡፡

ቊ 2887፡፡ ጉዳት፡፡

የማይንቀሳቀስ የንብረትን ሽያጭ ገዢው ወይም ሻጩ ተጎዳሁ በማለት ምክንያት ሊያፈርሱት አይችሉም፡፡

ቊ 2888፡፡ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ውስጥ ስለሚገኘው ሀብት የሚሰጥ ዋስትና፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

የማይንቀሳቀሰው ንብረት ስፋት በውሉ ውስጥ የተመለከተ ከሆነ ሻጩ በዚህ በንብረት ውስጥ ስለሚገኘው ነገር ሁሉ አላፊ ዋስ ነው፡፡

ቊ 2889፡፡ (2) የገዢው መብት፡፡

(1) በማይንቀሳቀሰው ንብረት ውስጥ የተገኘው ሀብት ይገኛል ተብሎ ከተረጋገጠው በታች የሆነ እንደሆነ ገዢው በዚሁ በጐደለው ሀብት
መጠን የዋጋ ቅናሽ እንዲደረግለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) በማይንቀሳቀሰው ንብረት ውስጥ ያለው ሀብት በውሉ ላይ ከተመለከተው ዋጋ እጅግ ቢያንስ ከዐሥር አንድ ያነሰ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ
ወይም ሻጩ እንደገለጸው ንብረቱ ለተመደበበት ጒዳይ የማያገለግል ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ገዢው ውሉ እንዲሰረዝለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2890፡፡ (3) ሁኔታና የጊዜ ውሳኔ፡፡

በማይንቀሳቀሰው ንብረት ውስጥ ባለው ሀብት ጒድለት ምክንያት ላይ የተመሠረተው የገዢው የክስ አቤቱታ መቅረብ የሚገባው በጒድለቱ
ማረጋገጫ ዋስትና ላይ በተመሠረተው ሁኔታና ለዚያው በሚጸናው የጊዜ ውሳኔ መሠረት መሆን አለበት፡፡
ቊ 2891፡፡ (4) የሻጩ መብት፡፡

(1) የተሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ልክ በውሉ ላይ ከተመለከተው በላይ ከፍ ያለ ሆኖ ቢገኝም እንኳ ሻጩ ዋጋ እንዲጨመርለት
ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(2) ሻጩ ስሕተት የደረሰበት በገዢው ወይም በእንደራሴው አታላይነት የሆነ እንደሆነ (ሻጩ) መብቱን የሚጠይቅበት ደንብ
እንደተጠበቀለት ይሆናል፡፡

ቊ 2893፡፡ ውሉ በግዴታ የሚፈጸምበት ሁኔታ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የገዛ ሰው ውሉ እንደ ቃሉ ዐይነት እንዲፈጸምለት ለማድረግ የተለየ ጥቅም እንዳለው ሆኖ ይገመታል፡፡

(2) ስለዚህ ውሉ እንደ ቃሉ ዐይነት እንዲፈጸምለት ለማስገደድ ይችላል፡፡

(3) ስለሆነም ሻጩ ውሉን እንደ ውሉ ቃል ከመፈጸም መዘግየቱን ከተረዳበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ውሉ እንዲፈጸምለት
ካልጠየቀ በቀር ገዢው ውሉ በግዴታ እንዲፈጸም የማድረግ መብቱን ያጣል፡፡

ቊ 2894፡፡ መልሶ የመግዛትን መብት አስጠብቆ ስለሚደረግ ሽያጭ፡፡

(1) ሻጩ የሸጠውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ከገዢው ላይ እስከ አንድ የተወሰነ ጊዜ መልሶ ለመግዛት የሚችልበትን መብቱን በሽያጩ ውል
ውስጥ አስጠብቆ ለመዋዋል ይችላል፡፡

(2) የጋራ ሀብትነትን የአላባ ተቀባይነትንና የሌሎች ግዙፍ መብቶችን በማመለከቱት አንቀጾች ለመሸጥ የተስፋ ቃል መስጠትን
የሚመለከቱት ድንጋጌዎች በዚህም ስምምነት ተፈጻሚችን ናቸው፡፡

ቊ 2894፡፡ ከሽያጭ ጋራ የተዛመዱ ውሎች፡፡

የልዋጭን ውል፤ ከሀብትነት በቀር መብቶችን ማስተላለፍንና የኪራይ ሽያጭን መብት ስለሚያስተላልፉ ውሎች ጒዳይ በተነገረው አንቀጽ
የተመለከቱት ድንጋጌዎች የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከቱት ጒዳዮችም ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2895፡፡ የኪራይ ሽያጭ በተደረገ ጊዜ መዝገብ ስለ ማጻፍ፡፡

የኪራይ ሽያጭ በተደረገ ጊዜ ተከራዩ ገዥ በውሉ የተሰጠውን የቀደምትነት መግዛት መብቱን ንብረቱ በሚገኝበት አገር ባለው
የማይንቀሳቀስ ንብረት መጻፊያ መዝገብ ላይ ለማጻፍ ይችላል፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
ስለ ኪራይ፡፡
ክፍል 1፡፡
ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይ በጠቅላላው፡፡
ቊ 2896፡፡ ትርጓሜ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ሀብት ኪራይ ማለት አከራይ ተብሎ የሚጠራው አንዱ ወገን ተከራይ ተብሎ ለሚጠራው ለሌላው ወገን፤ ላንድ ለተወሰነ
ጊዜ ተከራይ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሌላ ነገር ኪራይ እየከፈለ ባንድ በማይንቀሳቀስ ሀብት እንዲጠቀም ወይም እንዲገለገል የሚረጋገጥበት
የውል ስምምነት ማለት ነው፡፡

(2) የንግድ ወይም የእንዱስትሪ ሥራ የሚከናወንባቸውን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ኪራይ የሚመለከቱትና በንግድ ወይም ልዩ ሕጎች
የተወሰኑት ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2897፡፡ ኪራይና ሽያጭ፡፡

ተከራዩ ለተወሰነ ጊዜ ኪራይ ከከፈለ በኋላ ለተከራየው የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት ይሆናል የሚል ቃል በኪራዩ ውል ውስጥ
ተመልክቶ እንደሆነ ሁለቱ ተዋዋዮች ስምምነታቸውን እንደ ኪራይ ውል ብለው ቢሰይሙትም እንኳ ውላቸው እንደ ሽያጭ ውል
ይቈጠራል፡፡

ቊ 2898፡፡ የውሉ ማስረጃ፡፡

(1) አንድ የማይንቀሳቀስ ሀብት ተከራይቶ ነበረ ብሎ ለማስረዳት የሚቻለው የመከራየቱ ሁኔታና ጊዜ ከመጀመሩ በፊት የጽሑፍ ማስረጃ
በማቅረብ፤ ወይም በፍርድ ችሎት ፊት በተሰጠ የቃል መተማመን ወይም በፍርድ ላይ በተሰጠ የመሐላ ቃል አስረጅነት ብቻ ነው፡፡

(2) እንዲህ ያለ ውል አለ ብሎ ለማስረዳት ከዚህ በላይ በተጻፉት ማስረጃዎች ሌላ ለማቅረብ አይቻልም፡፡

(3) ቢሆንም የኪራዩ ውል የመከናወኑን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይህ ውል መኖሩን ምስክሮች በማቅረብ ወይም በግምት አስተያየት
ለማስረዳት ይቻላል፡፡

ቊ 2899፡፡ በማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መዝገብ ስለ መጻፍ፡፡

(1) ከ 5 ዓመት ለበለጠ ጊዜ የተደረጉ የማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራይ ውሎች ንብረቶቹ በሚገኙበት አገር ባለው የማይንቀሳቀስ ንብረት
መዝገብ ካልተጻፉ በቀር ለሦስተኛ ወገኖች መቃወሚያ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

(2) ከአምስት ዓመት ለበለጠ ጊዜ የተደረገ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ውስጥ ያልተጻፈ የኪራይ ውል የተረጋገጠ ቀን ያለው ከሆነ
በዚሁ ንብረት ላይ ያላቸውን መብት ያጻፉትን ሦስተኛ ወገኖች መብታቸውን ካጻፉበት ቀን አንሥቶ እስከ 5 ዓመት ድረስ መቃወሚያ
ሊሆን ይችላል፡፡

(3) እንደዚህ ያልሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራይ ውል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ይቈጠራል፡፡


ቊ 2900፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት ስለ ማስረከብ፡፡

(1) አከራዩ ያከራየውን የማይንቀሳቀስ ሀብት ከተጨማሪ ዕቃዎቹ ጋራና በውሉ መሠረት ወይም በሀብቱ ተፈጥሮ መሠረት ለተመደበበት
ጒዳይ ሊያገለግል በሚችልበት ሁኔታ አሟልቶ ለተከራዩ ማስረከብ አለበት፡፡

(2) የማስረከቢያው ጊዜና ስፍራ የሚወሰነው ስለ ሽያጭ ውል በተነገረው ድንጋጌና ደንብ መሠረት ነው፡፡

ቊ 2901፡፡ የሥራዎች ሁኔታና የዕቃ ዝርዝር መዝገብ (1) መሠረቱ፡፡

(1) አንደኛው ወይም ሌላው ወገን ተዋዋዮች ለተከራዩ አገልግሎትና ጥቅም የተሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚገኝበት ሁኔታና
እንዲሁም ከተከራየው ሀብት ጋራ ተያይዞ የሚገኘው የተንቀሳቃሽ ዕቃ ዝርዝርና የዋጋው ግምት ጭምር ተዘጋጅቶ ጥያቄው እንደተደረገ
ወዲያውኑ ለተከራዩ መሰጠት አለበት፡፡

(2) ይህን ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ሁሉ ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 2902፡፡ (2) ወጪ፡፡

(1) ለተከራየው ሀብት የስፍራ ሁኔታና ለዕቃው ዝርዝር መጻፊያ የሚደረገውን ወጪ የሚችሉት ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ናቸው፡፡

(2) ተከራዩ ለዚህ ጒዳይ የሚያስፈልገውን ገንዘብ አስቀድሞ ወጪ አድርጎ እንደሆነ፤ ለአከራዩ ከሚከፍለው የኪራይ ገንዘብ ላይ እንደ
ሒሳብ ቀንሶ ለማስቀረት ይችላል፡፡

ቊ 2903፡፡ (3) ቅጣት፡፡

(1) ከተዋዋዮቹ ወገኖች አንደኛው የስፍራውን ሁኔታና የዕቃውን ዝርዝር የሚያመለክተውን ሰነድ በአንድነት ሁኖ ለማዘጋጀት ሳይቀርብ
የቀረ እንደሆነ ሌላው ወገን ብቻ በራሱ ሠርቶ ወይም አሠርቶ ለተዋዋዩ ሊያስታውቀው ይችላል፡፡

(2) ይህኛውም ወገን የሚያደርጋቸውን መቃወሚያዎችና ይጠበቅልኝ የሚለውን መብቱን በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ ላንደኛው
ተዋዋዩ ካላስታወቀ ይህን የቦታ ሁኔታ መግለጫና ዝርዝሩን ፈቅዶ እንደተቀበላቸው ይቈጠራል፡፡

(3) አንደኛው ወገን ተዋዋይ የሚያቀርባቸው መቃወሚያዎችና ይጠበቁልኝ የሚላቸው መብቶች ዋጋ የሚኖራቸው ማስታወቂያው
ከደረሰው ቀን አንሥቶ በ 6 ወሮች ውስጥ በራሱ ኪሣራ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ሁኔታና የዕቃ ዝርዝር መዝገብ ያዘጋጀ እንደሆነ ብቻ
ነው፡፡

ቊ 2904፡፡ የዕቃው ጒድለት (1) የውሉ መፍረስ፡፡


(1) የመረካከቡ ጒዳይ በሚፈጸምበት ጊዜ የተከራየው ሀብት የተመደበበትን አገልግሎት እንደሚቀንስ ዐይነት ከፍተኛ ግምት ያለው
ጒድለት የተገኘበት እንደሆነ ተከራዩ ውሉ እንዲፈርስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ከተረከበ በኋላ የዚህ ዐይነት ጒድለት የደረሰ ወይም የተገኘበት እንደሆነ ተከራዩ ውሉ
እንዲሰረዝልኝ የማለት መብት ይኖረዋል፡፡

(3) ውሉ በተደረገበት ጊዜ አከራዩ ይህን ጒዳይ ለይቶ የሚያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው ካልሆነ በቀር ተከራዩ በተከራየው ሀብት ላይ
ያለው ልዩ ጥቅም ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡

ቊ 2905፡፡ (2) የጉዳት ኪሣራ፡፡

(1) አከራዩ የተከራየውን ሀብት ለተከራዩ ባስረከበበት ጊዜ የተከራየው ሀብት ጒድለት እንደነበረበት ሲያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው
ሲሆን በንብረቱ ላይ ያለውን ጒድለት ለተከራዩ ሳያስታውቅ በቸልታ ዝም ብሎ አስረክቦ እንደሆነ በዚህ ጒደለት ምክንያት በተከራዩ ላይ
ለሚደርሰው ጉዳት፤ አላፊ ሆኖ የጉዳት ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(2) እንዲሁም የውሉ ዘመን በመፈጸም ላይ ባለበት ጊዜ የዚህ ዐይነት ጒድለት በአከራዩ ስሕተት ምክንያት የደረሰ እንደሆነ በተከራዩ ላይ
ለደረሰው ጉዳት ካሣ መክፈል አለበት፡፡

ቊ 2906፡፡ (3) ከውሉ መፍረስ ጋራ ስላለ ግንኙነት፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር ውስጥ የተመለከተው የጉዳት ኪሣራ ከውሉ መፍረስ ጋራ ምንም ግንኙነት የለውም፡፡

(2) ውሉን ማፍረስ አስፈላጊ ባይሆንም እንኳ ኪሣራው እንዲከፈል ለማድረግ ይቻላል፡፡

(3) የውሉ መፍረስ በሚወሰንበት ጊዜ ይልቁንም በውሉ መፍረስ ምክንያት የደረሰውን ጉዳት ለመካሥ ሲባል የጉዳቱ ኪሣራ እንዲከፈል
ለማድረግ ይቻላል፡፡

ቊ 2907፡፡ (4) የሚታይ ጒድለት፡፡

ተከራዩ የሚከራከርበት ጒድለት የሚታይ ጒድለት እንደሆነና ይህንንም ጒድለት ውሉን በፈረመበት ጊዜ የሚያውቀው ወይም ማወቅ
የሚገባው የሆነ እንደሆነ ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተውን የመከራከሪያ መብቱን ሊጠቀምበት አይችልም፡፡

ቊ 2908፡፡ (5) አደገኛ ጒድለት፡፡

(1) ስለሆነም የተከራየው ሀብት በተከራዩ ሕይወት ወይም በጤንነቱ ላይ ወይም አብረው በሚኖሩት ቤተሰቦቹ ወይም በሠራተኞቹ
ሕይወትና ጤንነት ላይ ከባድ ሆኖ የሚገመት አደጋ የሚያደርስ የሆነ እንደሆነ፤ ይህ ጒድለት የሚታይ ጒድለት ቢሆን ወይም የዚህ ዐይነት
ጒድለት መኖሩን ውሉን በተዋዋለበት ጊዜ የሚያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው ቢሆንም እንኳ ተከራዩ የውሉን መፍረስ ውሳኔ የመጠየቅ
መብት አለው፡፡
(2) ይህን ተቃራኒ የሆነ ማንኛውም ስምምነት ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2909፡፡ (6) አላፊነትን የሚያስወግድ ስምምነት፡፡

በተከራየው ሀብት ላይ ያለውን ጒድለት አከራዩ በመጥፎ ልቡና ደብቆ ሳይገልጽ የቀረ እንደሆነ ወይም እነዚህ ጒድለቶች ተከራዩ
የተከራየውን ሀብት ጠቃሚነት የሚያስቀሩ የሆኑ እንደሆነ፤ በንብረቱ ጒድለት ምክንያት የሚደርስበትን አላፊነት የሚያስወግዱ ወይም
አላፊነቱን የተወሰነ የሚያደርጉ ማንኛቸውም ስምምነቶች ፈራሾች ናቸው፡፡

ቊ 2910፡፡ (7) በውሉ ስምምነት የተሰጠ ዋስትና፡፡

(1) የተከራየው ሀብት አለው ብሎ አከራዩ በግልጽ ያረጋገጠው ዐይነተኛ ነገር በሀብቱ ላይ የሌለ ወይም ሳይኖር የቀረ እንደሆነ፤ ተከራዩ
ውሉ እንዲፈርስለት ለመጠየቅና እንዲሁም በዚህ ጒድለት ምክንያት ስለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ እንዲከፈለው ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

(2) ይህን መብት በመቀነስ ከዚህ በላይ በተጻፉት ቊጥሮች ውስጥ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች አከራዩ ሊከራከርባቸው አይችልም፡፡

ቊ 2911፡፡ በተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት በሰላም ስለ መገልገል፡፡

ተከራዩ በተከራየው የማይንቀሳቀስ ንበረት የኪራዩ ዘመን ጸንቶ እስከሚቈይበት ጊዜ ድረስ በሰላም ሊጠቀምበት እንዲችል አከራዩ ዋስትና
ይሰጠዋል፡፡

ቊ 2912፡፡ የተከራየውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ስለ መለወጥ፡፡

አከራዩ ካልፈቀደለት በቀር የኪራዩ ውል ጸንቶ እስከሚቈይበት ጊዜ ድረስ ተከራዩ የተከራየውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁኔታ ለመለወጥ
አይችልም፡፡

ቊ 2913፡፡ በተከራየው ሀብት ላይ መብት አለኝ በማለት ሦስተኛ ሰው የሚያቀርበው ክርክር፡፡

(1) የተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት የኔ ነው ወይም በዚሁ ንብረት ላይ መብት አለኝ ብሎ ሦስተኛ ሰው ክርክር ያነሣ እንደሆነ ተከራዩ
ወዲያውኑ ላከራዩ ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ይህ ሦስተኛ ሰው ክርክሩን በፍርድ ፊት ያቀረበ እንደሆነ የተነሣው ክርክር በሦስተኛው ሰውና ባከራዩ መካከል እንዲፈጸምና ተከራዩ
ከነገሩ ውጭ እንዲሆን ለመጠየቅ ይችላል፡፡
(3) በዚሁ በተነሣው ክርክር ምክንያት በተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚገለገልበት ጥቅሙ ተቋርጦ እንደሆነ፤ ይህ ሁከትና ችግር
የደረሰበት መሆኑን ለአከራዩ ካስታወቀ ጥቅሙ ለተቋረጠበት ጊዜ ካለው ሑሳብ ጋራ ተመዛዛኝ በሚሆን መጠን ከኪራዩ ላይ ቀንሶ
ማስቀረት ይችላል፡፡

ቊ 2914፡፡ ቀላል የሆነ አድራጎት ሁከት፡፡

(1) በተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የባለቤትነት መብት ወይም ሌላ መብት አለን በማይሉ በሦስተኛ ወገኖች አድራጎት ለሚነሣው
ሁከት አከራዩ ዋስትና እንዲሰጥ አይገደድም፡፡

(2) ይህን የመሰለውን ሁከት ለማስወገድ ተከራዩ በራሱ ስም ለመከራከር ይችላል፡፡

ቊ 2915፡፡ ቀረጥና ግብር፡፡

ከተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚጠየቀውን ቀረጥና ግብር የሚከፍል አከራዩ ነው፡፡

ቊ 2916፡፡ ስለ ማሳደስ (1) ያከራዩ ግዴታዎች፡፡

አከራዩ የተከራየውን የማይንቀሳቀስ ንብረት በሚገባ መጠበቅና የኪራዩ ውል ዘመን ጸንቶ እስከሚቈይበት ጊዜ ድረስ ለንብረቱ ማደሻ
አስፈላጊ የሆነውንና በኪራዩ ውስጥ የማይታሰበውን የማደሻ ወጪ ሁሉ መቻል አለበት፡፡

ቊ 2917 ፡፡ (2) ለአከራዩ የማስታወቅ ግዴታ፡፡

የተከራየው ንብረት ስለ ጥበቃውና ስለ አያያዙ የማደሻ ወጪ የሚያስፈልገው ሁኖ ይህንንም ወጪ የሚችለው ተከራዩ ባልሆነ ጊዜ ተከራዩ
ይህን ሁኔታ ላከራዩ ማስታወቅ ግዴታ ነው፡፡

ቊ 2918፡፡ (3) የማደሱ ሥራ የሚያስከትለውን የመቻል ግዴታ፡፡

የተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት የማደስ ሥራ የሚያሻው ሲሆንና የኪራዩ ውል እስኪያልቅ ድረስ ለመጠበቅ የማይቻል የሆነ እንደሆነ
ይህ ሥራ የሚያስከትለው መሰናክል ማንኛውም ዐይነት ቢሆንና የማደሱ ሥራ በሚፈጸምበት ጊዜ ከተከራየው ንብረት በከፊሉ
አገልግሎቱን የሚያቋርጥበት ቢሆንም ተከራዩ ሥራው እስኪሠራ መታገሥ አለበት፡፡

ቊ 2919፡፡ (4) የአከራዩ ግዴታ ወሰን፡፡


አከራዩ ላከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም የእርሻ መሬት ማደሻ የሚያወጣው ገንዘብ በሦስት ዓመት ውስጥ ከሚያገኘው ኪራይ
የበለጠ ሒሳብ የሆነ እንደሆነ እነዚህን የማደስ ሥራዎች እንዲፈጽም ሊገደድ አይቻልም፡፡

ቊ 2920፡፡ የአከራዩ ግዴታዎችን አለመፈጸም የሚያስከትለው፡፡

(1) አከራዩ ሊፈጽማቸው የሚገባውንና ለተከራዩ ጥቅም የሚሆኑት የማደስ ሥራዎች ጊዜ ሳይፈጅ ሳይፈጽማቸው የቀረ እንደሆነ፤ ተከራዩ
እነዚህን ሥራዎች በራሱ ኪሣራ ለማሠራትና ያወጣውን ወጪ ከሕጋዊ ወለዱ ጋራ ከኪራዩ ሒሳብ ላይ ቀንሶ ለማስቀረት ይችላል፡፡

(2) ከፈቀደም እንደ ጊዜውም አጋጣሚ ሁኔታ ተከራዩ ለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ ለመጠየቅና አስፈላጊም ከሆነ ውሉ እንዲሰረዝለት
ለማድረግ መብት አለው፡፡

ቊ 2921፡፡ ተከራዩ በተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚጠቀምበት ሁኔታ፡፡

(1) ተከራዩ በተከራየው የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚጠቀመው አስፈላጊውን የጥበቃ ጥንቃቄ በማድረግና በኪራዩ ውል ላይ ንብረቱ
የተመደበበትን አገልግሎት መሠረት በማድረግ ነው፡፡

(2) በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ውሉ ካለቀ በላይ ውጤቱን የሚቀጥል መለዋወጥ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ሁኔታና ንብረቱ የተመደበበት
የፍሬ አሰጣጥ ጒዳይ ላይ ለመፈጸም አይችልም፡፡

ቊ 2922 ፡፡ የአከራዩ መቈጣጠር፡፡

(1) አከራዩ በማናቸውም ጊዜ ቢሆን የሚመለከቱትን ግዴታዎች ተከራዩ አክብሮ የሚጠብቅ መሆኑን ለመቈጣጠር ይችላል፡፡

(2) ይህም የመቆጣጠር ጒዳይ ሊፈጸም የሚገባው በአእምሮ ግምት በተከራዩ ላይ አንዳችም ችግር በማያመጣና ትክክለኛ ነው በሚባል
ሁኔታ ተከራዩንም በማያበሳጭ ዐይነት ነው፡፡

ቊ 2923፡፡ የኪራዩ አከፋፈል፡፡

(1) ተከራዩ በኪራዩ ውል በተወሰኑት ጊዜዎች የንብረቱን ኪራይ ወይም የርሻ አበል መክፈል አለበት፡፡

(2) የኪራይ መክፈያውና ዘመን በውሉ ላይ ያልተመለከተ ሲሆን በሕግ በተወሰኑት ጊዜዎች መከፈል አለበት፡፡

ቊ 2924፡፡ የአከራዩ ይዞ የማቈየት መብት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


ያንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አከራይ የሆነ ሰው ባለፈው ዓመት ላልተከፈለው ኪራይና ባለበትም ዓመት ስድስት ወር ሊከፈለው
ለሚገባው ኪራይ ዋስትና ለቤቱ ማጌጫ ከሚያገለግሉት ዕቃዎችም ሆነ ለስፍራው ማልሚያ ከሚጠቅሙት መሣሪያዎች ውስጥ የመያዣ
መብት አለው፡፡

ቊ 2925፡፡ (2) መብቱ የሚፈጸምባቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፡፡

(1) አከራዩ የዕቃዎቹ ባለሀብትነት የተከራዩ አለመሆኑን ዐውቆ እንደሆነ ወይም ማወቅ ይገባው ኑሮ እንደሆነ በዕቃዎቹ ላይ የመያዣ መብቱ
ሊፈጸም አይቻልም፡፡

(2) አከራዩ፤ ተከራዩ ወደ ተከራየው ስፍራ ያመጣቸው የሚንቀሳቀሱ ሀብቶች የራሱ አለመሆናቸውን ያወቀው ውሉ ጸንቶ በሚቈይበት ጊዜ
የሆነ እንደሆነ ውሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንዲፈርስ ካላመለከተ በቀር በእነዚህ ዕቃዎች ላይ ይዞ የማቈየት መብቱ ይቀርበታል፡፡

ቊ 2926፡፡ (3) ውጤቱ፡፡

(1) ይዞ የማቈየት መብት ባለው መሠረት፤ በዳኞቹ ፈቃድ፤ ተከራዩን በተከራየው በማይንቀሳቀስ ንብረት ውስጥ፤ ኪራዩን ወይም የርሻውን
አበል ለመክፈል ዋስትና እንዲሆኑት አስፈላጊ የሆኑትን የማይንቀሳቀሱ ዕቃዎች እንዲተው አከራዩ ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) በስውር ወይም በኀይል የተወሰዱትን ዕቃዎች ከነበሩበት ስፍራ ከተዛወሩ በኋላ አከራዩ በዐሥር ቀን ውስጥ በፍርድ ያሲያዛቸው
እንደሆነ የአከራዩን መብቶች በቀደምትነት መክፈያ ይሆናሉ፡፡

ቊ 2927፡፡ ውሉ የሚጸናበት ጊዜ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይ፤ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ሊደረግ ይችላል፡፡ ስለሆነም፡፡

(2) ከሃምሳ ዓመት ለበለጠ ጊዜ ሊደረግ አይችልም፡፡

(3) ከሃምሳ ዓመት ለበለጠ ጊዜ ለሚቈይ ዘመን የተደረገ የማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይ ውል ለአምሳ ዓመት ጊዜ እንደተደረገ ያህል
ይቈጠራል፡፡

ቊ 2928፡፡ ያከራይ ወይም የተከራይ መሞት፡፡

(1) የኪራዩ ውል በአከራይ ወይም በተከራይ መሞት ወይም በአከራዩ ወይም በተከራዩ ላይ በሚደርሰው የችሎታ ማጣት ምክንያት
አይፈርስም፡፡
(2) ስለ መሬት ኪራይ የተጻፉት ልዩ ደንቦችና እንዲሁም ስለ ተከራዩ መክሠር በንግድ ሕግ የኪሣራን ደንብ የሚመለከቱት ድንጋጌዎች
የተጠበቁ ናቸው፡፡
ቊ 2929፡፡ በኪራይ የተሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ስለ መጥፋት፡፡

(1) በኪራይ የተሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራዩ ውል በሚቈይበት ጊዜ ውስጥ ባልታሰበ ምክንያት በሙሉ የጠፋ እንደሆነ፤ ውሉ ያለ
ክርክር ያለ አንዳች ፎርማሊቴ) ይፈርሳል፡፡

(2) የማይንቀሳቀሰው ንብረት የጠፋው በከፊል ብቻ እንደሆነ ግን፤ ተከራዩ እንደ አካባቢዎቹ ምክንያቶች ዋጋው እንዲቀነስለት ወይም
ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) በነዚህ በሚጠይቃቸው ነገሮች በሁለቱም ጊዜ ቢሆን አንዳች ኪሣራ ሊጠይቅ አይችልም፡፡

ቊ 2930፡፡ አከራዩ ግዴታዎቹን ስለ አለመፈጸሙ፡፡

(1) የማይንቀሳቀሰው ንብረት ጠቃሚነት ወይም አገልግሎት ከፍ ባለ በሚያጐድል አኳኋን አከራዩ ግዴታዎቹን ያልፈጸመ እንደሆነ
ተከራዩ፤ የኪራዩ ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ከዚህም በቀር ወይም ከውሉ መፍረስ ሌላ፤ አከራዩ ግዴታዎቹን ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰበት ጉዳት ተከራዩ ተመዛዛኝ የሆነ
ኪሣራ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2931፡፡ ተከራዩ ግዴታዎችን ስለ አለመፈጸሙ፡፡

(1) የአከራዩን መብት አደጋ በሚደርስበት አኳኋን ተከራዩ ግዴታዎቹን ያልፈጸመ እንደሆነ፤ አከራዩ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ከዚህም በቀር ወይም ከውሉ መፍረስ ሌላ ተከራዩ ግዴታዎቹን ባለመፈጸሙ ምክንያት በሚያደርስበት ጉዳት ተመዛዛኝ የሚሆን
የጉዳቱን ኪሣራ አከራዩ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2932፡፡ የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት በሚሆን ሰው ላይ የኪራይ ውል መቃወሚያ ስለ መሆኑ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) በአከራዩና በተከራዩ መካከል ግልጽ በሆነ ዐይነት የተነገረ የውል ቃል ከሌለ በቀር የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ተከራዩ ከተረከበው በኋላ
የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት ወይም አላባ ተቀባይ ለሚሆነው ሰው የኪራዩ ውል መቃወሚያ ለመሆን ይችላል፡፡

(2) የማይንቀሳቀሰው ንብረት ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ የሚለቀቅበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2933፡፡ (2) የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚጻፍበት መዝገብ ያልተጻፈ የኪራይ ውል፡፡

(1) የማይንቀሳቀሰው ንብረት በሚገኝበት ቦታ የርስት መዝገብ ያልተጻፈ ሲሆን፤ ንብረቱን የገዛው ወይም ያገኘው ሰው የኪራዩን ውል
ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ ውል አድርጎ ለመገመት መብት አለው፡፡
(2) ስለሆነም የኪራዩ ውል የተረጋገጠ ቀን ያለው እንደሆነ ገዢው ውሉን በርስት መዝገብ ካጻፈበት ቀን አንሥቶ እስከ አምስት ዓመት
ተከራዩ የኪራዩን ውል ለገዢው መቃወሚያ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ቊ 2934፡፡ ይህን ግምት ስለሚመለከተው የውል ቃል፡፡ (1) ውጤት፡፡

(1) የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘው ወይም የገዛው ሰው፤ የኪራይ ውል እንዳይቀጥል ለማድረግ የሚችል ስለመሆኑ፤ በአከራዩና
በተከራዩ መካከል ስምምነት ተደርጎ እንደሆነ፤ ውሉን እንዳይቀጥል የሚፈልግ እንደሆነ ተከራዩ ንብረቱን ለገዛው ወይም ላገኘው ሰው
ጥያቄ ካቀረበለት በኋላ፤ የገዛው ወይም ያገኘው ሰው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ በዚህ መብት የመሥራት ፈቃድ እንዳለው ወይም
እንደሌለው ለተባለው ተከራይ ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) በዚህ በተባለው ጊዜ ውስጥ በተሰጠው መብት ያልሠራበት እንደሆነ ንብረቱን የገዛው ወይም ያገኘው ሰው መብቱ ይቀርበታል፡፡

ቊ 2935፡፡ (2) መልሶ ለመግዛት ውለታ አድርጎ ስለሚደረገው ሽያጭ፡፡

የሸጠውን ንብረት መልሶ ለመግዛት ውል አድርጎ ንብረቱን የሸጠ ሰው መልሶ ለመግዛት የተወሰነው ጊዜ አልቆ ፍጹም ባለሀብት እስኪሆን
ድረስ፤ ባለይዞታውን ለማስለቀቅ ባለው መብቱ ሊሠራበት አይችልም፡፡

ቊ 2936፡፡ ንብረቱን የመመለስ ግዴታ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የኪራዩ የውል ጊዜ ሲያልቅ ተከራዩ በኪራይ የያዘውን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለአከራዩ መመለስ አለበት፡፡

(2) እንደዚሁም ከማይንቀሳቀሰው ንብረት ጋራ የተቀበላቸውን የተፈጥሮ ዐይነታቸውን እንደ ያዙ የሚገኙትን ነገሮች ሁሉ የተፈጥሮ
ዐይነታቸውን እንደ ያዙ ለአከራዩ መመለስ አለበት፡፡

ቊ 2937፡፡ (2) ለኪራይ ከተሰጠው ንብረት ሁኔታ ወይም ከዕቃው ዝርዝር ጋራ ትክክለኛ ስለ መሆኑ፡፡

በአከራይና በተከራይ መካከል ስለ ንብረቱ ሁኔታ ወይም ስለ ዕቃው ዝርዝር የተደረገ ስምምነት እንዳለ፤ ተከራዩ፤ ስለ ንብረቱ ሁኔታና ስለ
ዕቃው ዝርዝር በተነገረው ስምምነት መሠረት የተቀበለውን ነገር እንዳለ አድርጎ መመለስ አለበት፡፡

ቊ 2938፡፡ (3) ስለ ንብረቱ ሁኔታ ወይም ስለ ዕቃው ዝርዝር በተዋዋዮቹ መካከል ስምምነት አለመኖር፡፡

(1) ስለ ንብረቱ ሁኔታ በአከራይና በተከራይ መካከል የተደረገ የመተማመኛ ጽሑፍ የሌለ እንደሆነ፤ ተከራዩ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት
በመልካም ሁኔታ እንደተቀበለው ይገመታል፡፡
(2) ስለ ዕቃው ዝርዝር በተዋዋዮቹ መካከል የተደረገ የመተማመኛ ጽሑፍ የሌለ እንደሆነ የማይንቀሳቀሰው ንብረት ተጨማሪ ነገሮች
እንዳልነበሩበት ሁኖ ይገመታል፡፡

(3) በነዚህ ግምቶች ላይ ተቃራኒ ማስረጃ ለማቅረብ ይቻላል፡፡

ቊ 2939፡፡ (4) የዳኞች አመዛዘን፡፡

ስለ ንብረቱ ሁኔታ ወይም ስለ ዕቃው ዝርዝር፤ የተሰናዳው ጽሑፍ በአንድ ወገን ተዋዋይ ብቻ ሆኖ ሌላው ወገን ያልተቀበለው እንደሆነ፤
ዳኞች አካባቢዎቹን ምክንያቶች በመመልከት ስለ ንብረቱ ሁኔታ ወይም ስለ ዕቃው ዝርዝር ለሚሆነው ስምምነት የሚገባ መስሎ
የሚታያቸውን ግምት ይሰጡታል፡፡

ቊ 2940፡፡ የተከራየው ነገር መጥፋት ወይም መበላሸት፡፡

(1) ተከራዩ የተከራየውን ነገር ከተቀበለ በኋላ ነገሩ የጠፋ ወይም የተበላሸ እንደሆነ ኀላፊ ይሆናል፡፡

(2) በተለይም፤ የተባለውን ጥፋት ወይም መበላሸት ያደረሰው በቤተሰቡ ወይም ወደማይንቀሳቀሰው ንብረት ውስጥ ባስገባው ሰው
ምክንያት የሆነ እንደሆነ፤ በኀላፊነት ይጠየቃል፡፡

ቊ 2941፡፡ የኀላፊነቱ ወሰን፡፡

(1) ተከራዩ የተከራየው ነገር መጥፋት ወይም መበላሸት በአከራዩ ወይም በድንገተኛ ሁኔታ ምክንያት መሆኑን ያስረዳ እንደሆነ ኀላፊነቱ
ይቀርለታል፡፡

(2) እንደዚሁም የጠፋው ወይም የተበላሸው ነገር ከማርጀቱ ወይም ከማናቸውም በነገሩ ከተገኘው ጒድለት የተነሣ መሆኑን ያስረዳ
እንደሆነ ኀላፊነት ይቀርለታል፡፡

(3) የነገሩ መበላሸት ነገሩን በደንበኛ አገልግሎት ላይ በማዋልና በተፈቀደው አደራረግ ሲሆን፤ ተከራዩ ኀላፊነት የለበትም፡፡

ቊ 2942፡፡ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ተከራይ፡፡

የተቀበለውን ነገር እንዲመልስ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ተከራይ፤ የተባለው ነገር የጠፋው ወይም የተበላሸው ይህንኑ ነገር በአስፈላጊው
ጊዜ ለአከራዩ መልሶለት ቢሆን ኑሮ ከመጥፋቱ ወይም ከመበላሸቱ ሁኔታ የማይድን መሆኑን ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ ኀላፊነቱ
ይቀርለታል፡፡

ቊ 2943፡፡ የጉዳቱ ኪሣራ መጠን፡፡


(1) ለመመለስ ያልቀረቡት ነገሮች በሁለቱ ወገኖች መካከል ቀድሞውኑ ተገምተው እንደሆነ፤ ተከራዩ ለነዚህ ነገሮች የተሰጠውን ግምት ዋጋ
ለመክፈል ይገደዳል፡፡

(2) አከራዩ፤ ተከራዩ እነዚህን ነገሮች ከተሰጣቸው ግምት ዋጋ በላይ መሸጥ መለወጡን ያስረዳ እንደሆነ ተጨማሪዎች የሆኑትን የጉዳት
ኪሣራዎች ለመቀበል ይችላል፡፡

(3) እንዲህም ስለ ተባለ፤ በተከራዩ በኩል የተደረገው የነገሩ መሸጥ መለወጥ፤ አከራዩና ተከራዩ፤ የኪራዩ ውል በተፈጸመበት ጊዜ ሁለቱም
በተስማሙበት አሳብ፤ መሠረት ለሥራው ደንበኛ የአስተዳደር ተግባር እንደሆነ ከዚህ አስቀድሞ ባለው ኀይለ ቃል የተነገረው ደንብ
ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

ቊ 2944፡፡ በተከራዩ ጥፋት ስለሚደርስ የውል መፍረስ፡፡

በተከራዩ ጥፋት ምክንያት ውሉ የፈረሰ እንደሆነ የተደረገው ጥፋት ሊያስከትለው የሚችል ኪሣራን መክፈሉ ሳይቀርለት በኪራዩ ውል ላይ
ተወስኖ የነበረው ቀን እስኪደርስ ንብረቱን እንደገና ለማከራየት አስፈላጊ በሆነው ጊዜ መካከል ያለውን የቤቱን ኪራይ ወይም የርሻ አበል
ለመክፈል ይገደዳል፡፡

ክፍል 2፡፡
የቤትን ኪራይ የሚመለከቱ ልዩ ደንቦች
ቊ 2945፡፡ የዚህ ክፍል ተፈጻሚነት፡፡

(1) የአከራይና የተከራይ ውል፤ ቤትን ከነዕቃው ወይም ያለ ዕቃ ወይም አንድ ባለክፍሎች ቤት፤ ወይም አንድ ክፍል ቤት ወይም
ማናቸውንም አንድ ሌላ ሕንጻ ወይም የሕንጻ አንዱን ክፍል ለመከራየት ሲሆን፤ የዚህ ክፍል ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) በዚህ ሕግ አገልግሎት መሰጠትን ስለሚመለከቱ ውሎች የተነገሩት ስለ ሆቴል ውል የተደነገጉት ደንቦች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2946፡፡ ለዐይነት የሆኑ ውሎች፡፡

(1) በታወቀ ቀበሌ መሬት ላይ የሚገኙትን ቤቶች ወይም ክፍለ ቤቶች ኪራይ የሚመለከቱ ሲሆኑ፤ ለዐይነት የሆኑ ውሎችን የማዘጋጃ ቤት
ባለሥልጣኖች ሊያደራጁ ይችላሉ፡፡

(2) እነዚህን ቤቶችና ክፍለ ቤቶች የሚመለከቱ በያንዳንድ ሰዎች መካከል የሚደረጉ ውሎች ከዚህ በላይ በተነገሩት ለዐይነት በተደራጁት
ውሎተ ሁኔታ መሠረት እንደተደረጉ ሆነው ይገመታሉ፡፡

(3) ተዋዋዮቹ በሚያደርጓቸው ግልጽ ስምምነቶች ለዐይነት ከተደራጁት ውሎች የተለዩ ስምምነት ለማድረግ ይችላሉ፡፡

ቊ 2947፡፡ በከፊል ስለሚደረግ የሕንጻ ኪራይ፡፡ (1) የአከራዩ ግዴታዎች፡፡


(1) ለአንድ ተከራይ በኪራይ የተሰጠው ሕንጻ በከፊል ብቻ ሲሆን አከራዩ የዚህን ሕንጻ ሌሎች ክፍሎች በሚያከራይበት ጊዜ ልማድን
በመከተልና የቦታዎቹን ተፈጥሮ በመመልከት የመጀመሪያውን ተከራይ ጥቅም መጠበቅ አለበት፡፡

(2) ሌሎቹን ተከራዮች ሲመርጥ እንዲሁም ከነዚህ ተከራዮች ጋራ በሚያደርጋቸው ውሎች ውስጥ ለሚያገባቸው የውል ቃሎች አከራዩ
ከዚህ በላይ የተባለው ግዴታ ይኖርበታል፡፡

ቊ 2948፡፡ (2) የተከራይ ግዴታዎች፡፡

(1) ተከራዩ፤ በከፊል ከተከራየው ቤት በሌላው ክፍል ለሚኖሩት ሌሎች ሰዎች የሚገባው አክብሮት እንዲኖረው ይገደዳል፡፡

(2) ተከራዩ ወይም ከርሱ ጋራ የሚኖሩት ሰዎች፤ ወይም በተከራየው ሕንጻ ውስጥ እርሱ የሚያስገባቸው ሰዎች በሁኔታቸው (በአካሄዳቸው
ወይም በኑሮዋቸው ዐይነት ሕንጻውን የተከራዩትን የሌሎች ሰዎች መልካም ኑሮ ያወኩ እንደሆነ አከራዩ የውሉን መፍረስ ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
(3) ለአዋኪዎቹ ምክንያት ሰለ ደረሰባቸው ጉዳት እነዚህ ሌሎች ተከራዮች የጉዳትን ኪሣራ የመጠየቅ መብት እንደተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2949፡፡ ተከራዩ በተከራየው ቤት ውስጥ ዕቃ ለማስገባት ስለ አለበት ግዴታ፡፡

(1) ተከራዩ እንደ ቤቱ አገልግሎትና እንደ ቦታው ልማድ በተከራየው (በማይንቀሳቀስ) ቤት ውስጥ ዕቃ ማግባት አለበት፡፡

(2) ተከራዩ ዕቃዎች ያሏቸውን ቤቶች ተከራይቶ እንደሆነ ወይም ለተወሰነው ጊዜ ኪራዩን አስቀድሞ ከፍሎ እንደሆነ ወይም ለኪራዩ ዋስ
ጠርቶ ወይም ሌላ ማረጋገጫ ሰጥቶ እንደሆነ ከዚህ በላይ በተነገረው ግዴታ በተከራዩ ላይ አይፈጸምበትም፡፡

ቊ 2950፡፡ የኪራዩ ልክ፡፡

(1) የኪራዩ ልክ በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስምምነት ይወሰናል፡፡

(2) በሚያጠራጥር ጊዜ፤ የማዘጋጃ ቤት ባለሥልጣኖች በወሰኑት ታሪፍ መሠረት ወይም የተወሰነ ታሪፍ የሌለ እንደሆነ የቦታዎቹን ልማድ
በመከተል ይወሰናል፡፡

ቊ 2951፡፡ ኪራዩ የሚከፈልበት ጊዜ፡፡

(1) የኪራዩ ውል ለአንድ ወይም ለብዙ ዓመታት ተደርጎ እንደሆነ ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ ኪራዩ በየሦስት ወር መጨረሻ
የሚከፈል ይሆናል፡፡

(2) ውሉ በጣም አጭር ለሆነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ በየወሩ መጨረሻ የሚከፈል ይሆናል፡፡

(3) በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን ግን ኪራዩ የውሉ ጊዜ ሲያልቅ (ሲያቆም) መከፈል አለበት፡፡
ቊ 2952፡፡ የተከራዩ ሳይከፍል መቈየት፡፡

(1) የኪራዩ መከፈያ ጊዜ ደርሶ ተከራዩ በተባለው ጊዜ ከመክፈል የዘገየ እንደሆነ፤ የኪራዩ ውል ለአንድ ዓመት ወይም ከአንድ ዓመት
ለሚበልጥ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ አከራዩ የሠላሳ ቀን ጊዜ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ውሉ ለአነስተኛ ጊዜ እንደሆነም የዐሥራ አምስት ቀን ጊዜ
ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ በተወሰነው ጊዜ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ውሉ የሚፈርስ መሆኑን ለተከራዩ ሊያስታውቀው ይችላል፡፡

(2) የጊዜው መቈጠር የሚጀመረው ተከራዩ የአከራዩን ማስታወቂያ ከተቀበለበት ቀን አንሥቶ ነው፡፡

(3) እነዚህን ጊዜዎች የሚያሳጥሩ ወይም ኪራዩ ባለመክፈሉ ምክንያት ወዲያው ውሉን የማፍረስ መብት ለአከራዩ የሚሰጡ የውል ቃሎች
ፈራሾች ናቸው፤ (ዋጋ የላቸውም)፡፡

ቊ 2953፡፡ ቤቶቹን ስለ ማደስ፡፡ (1) የተከራዩ ግዴታዎች፡፡

ተከራዩ ሊያድሳቸው የሚገባውን የተከራያቸውን ቤቶች በራሱ ኪሣራ ለማደስ ይገደዳል፡፡

ቊ 2954፡፡ (2) የማደስ ትርጒም፡፡

(1) ተከራዩ ቤቶችን ማደስ ይገባዋል የተባሉት (የሚባለው) በኪራዩ ውል ተከራዩ ይፈጽማቸዋል ተብሎ የተወሰኑት ናቸው፡፡

(2) ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት ከሌለ በቀር ቤቶችን የማደስ ሥራዎች ተብለው የሚቈጠሩት መዝጊያዎችን ወይም መስኮቶችን የቤት
ወለሎችን ወይም ንጣፎቹን የውሃ መቅጃ መዘውሮችንና የውሃ መስደጃዎችን ለማደስ አስፈላጊዎች የሆኑት ተግባሮች ናቸው፡፡

(3) እንደዚሁም በተከራየው ቤት ለመጠቀም አስፈላጊ የሆኑትን ቤቶችን የማጥዳትና በደንብ የመያዝ ሥራዎች ቤትን እንደ ማደስ ያሉ
ተግባሮች ናቸው፡፡

ቊ 2955፡፡ (3) በማርጀት ወይም ካቅም በላይ በሆነ ነገር መበላሸት፡፡

(1) ቤቶቹ በማርጀት ወይም ካቅም በላይ በሆነ ነገር ብቻ የተበላሹ ሲሆኑ ተከራዩ ማናቸውንም ቤቶችን የማደስ ሥራዎች መፈጸም
የለበትም፡፡

(2) ስለሆነም በኪራይ ውል ውስጥ ግልጽ ሆኖ በገባ የውል ቃል ምክንያት ይህን ደንብ ሊለውጥ ይችላል፡፡

ቊ 2956፡፡ በማደስ ምክንያት በቤቱ ሳይገለገሉ ስለ መቈየት፡፡


(1) በኪራይ ውል ጊዜ፤ አከራዩ ተንቀሳቃሽ ባልሆነው ንብረት ላይ የሚፈጽማቸው ቤትን የማደስ ሥራዎች ከዐሥራ አምስት ቀን የበለጠ
ጊዜ የቈዩ እንደሆነ ተከራዩ ለዚህ ለተወሰነው ቀንና ሳይገለገልበት ለቈየው ክፍል የኪራዩን ዋጋ ይቀንሳል፡፡

(2) የማደሱ ሥራዎች ዐይነት ለተከራዩና ለቤተሰቡ አስፈላጊ የሆነውን መኖሪያ ሊቀመጡበት የማይቻል ያደረገው እንደሆነ፤ ተከራዩ
የኪራዩ ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2957፡፡ የተከራዩትን ስለ ማከራየት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ተከራዩ እርሱ የተከራየውን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት በሙሉ ወይም በከፊል ለማከራየት ይችላል፡፡

(2) የተከራየውን ለማከራየት ከመፍቀዱ በፊት ተከራዩ አሳቡን ለአከራዩ ማስታወቅና አከራዩ በዚሁ ጒዳይ ላይ ሊኖረው የሚችለውን
ተቃዋሚነት ማወቅ አለበት፡፡

ቊ 2958፡፡ (2) የአከራይ ተቃዋሚነት፡፡

(1) በተከራዩ በኩል የሚደረገው ማከራየት አከራዩ ይህንኑ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለሌሎች ተከራዮች ሲያከራይ ለገባው የውል ቃል
ተቃራኒ ሆኖ ሲገኝ ወይም የተባለው ማከራየት በማናቸውም ምክንያት እርግጠኛ ጉዳትን የሚያመጣበት ሆኖ ሲገኝ ይህን ተከራዩ
የሚያደርገውን ማከራየት ለመቃወም ይችላል፡፡

(2) ተከራዩ በዚህ ጊዜ ውሉን ለማፍረስ ይችላል፡፡

(3) የኪራዩ ውል ስምምነት በተፈረመ ጊዜ ተቃዋሚነትን ያስከተለውን ነገር ተከራዩ የሚያውቅ ወይም ማወቅ የሚገባው የሆነ እንደሆነ
የጉዳት ካሣ የመጠየቅ መብቱ ለአከራዩ የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2959፡፡ (3) የተከራዩን አከራይነት የሚያጠብ የውል ቃል፡፡

(1) የኪራዩ ውል ተከራዩ የተከራየውን ቤት እንዳያከራይ፤ ወይም ተከራዩ ከማከራየቱ በፊት የአከራዩን ፈቃድ መቀበል ያስፈልጋል ሲል
ለመወሰን ይችላል፡፡

(2) የኪራዩ ውል ተከራዩ የተከራየውን ቤት ከማከራየቱ በፊት ሌላውን ተከራይ ሲያከራይ አከራይ ወዶ እንዲቀበለው ያስፈልጋል የሚል
እንደሆነና አከራዩ ያለ ምክንያት ፈቃዱን የከለከለ እንደሆነ ተከራዩ የኪራይ ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2960፡፡ (4) የተከራይ ግዴታዎች፡፡

(1) የተከራየውን ቤት በሙሉ ወይም በከፊል ያከራየ ሰው በኪራይ ውል ምክንያት ለአከራዩ ለገባቸው ግዴታዎች ተገዳጅ ይሆናል፡፡

(2) አከራዩ የተከራየውን አከራይነት ፈቅዶም እንደሆነ እንኳ ተከራዩ ያሉበት ግዴታዎች አይቀሩለትም፡፡

(3) ተከራዩ ካሉበት ግዴታዎች ነጻ የሚሆነው በርሱና በአከራዩ መካከል ግልጽ የሆነ ስምምነት ተደርጎ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 2961፡፡ (5) ከተከራይ የተከራየ ሰው ግዴታዎች፡፡

(1) ከተከራይ የተከራየው ሰው በኪራይ የተሰጡትን ቦታዎች ጥቅም በሚመለከት ሁሉ የዋናውን የኪራይ የውል ቃሎች በሙሉ ማክበር
አለበት፡፡

(2) እነዚህን የውል ቃሎች እንዲያከብር ከተከራዩ የተከራየውን ሰው አከራዩ በቀጥታ ሊጠይቀው ይችላል፡፡

(3) ከተከራይ ላይ የተከራየው ሰው እነዚህን ውሎች ሳያውቅ ቀርቶ እንደሆነ ወይም እንዳይጠብቃቸው ተከራይ ፈቅዶለት እንደሆነ ይህ
ከተከራይ ላይ የተከራየው ሰው በአከራየው ሰው ላይ የክስ ማቅረብ መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 2962፡፡ (6) አከራዩ ስለሚያቀርበው ቀጥታ ክስ፡፡

(1) ከተከራይ ላይ የተከራየው ሰው እርሱ ከተስማማበት የኪራይ ዋጋ በላይ ላለው ተጠያቂ አይሆንም፡፡

(2) ዋናው አከራይ ከተከራይ ላይ የተከራየውን ሰው የተከራየበትን ዋጋ በቀጥታ በእጁ ለርሱ እንዲከፍለው ለማስገደድ ይችላል፡፡

(3) ከተከራይ ላይ የተከራየው ሰው ለዋናው ኪራይ ላለበት ጊዜ ከሚከፍለው ዋጋ በቀር አስቀድሞ ለአከራየኝ ከፍያለሁ በማለት ዋናውን
አከራይ ለመቃወም አይችልም፡፡

ቊ 2963፡፡ (7) ይዞ የማቈየት መብት፡፡

ከተከራይ ላይ የተከራየው ሰው ወደ ተከራየው ቦታ ባመጣቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ላይ ዋናው አከራይና ተከራይ ይዞ በማቈየት
መብታቸው ለመሥራት ይችላሉ፡፡

ቊ 2964፡፡ (8) የኪራይ ውል ስለ መፍረስ፡፡

(1) ዋናው የኪራይ ውል ቀሪ ሲሆን ተከራይ ያደረገው የኪራይ ውል ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) ስለሆነም አከራዩ በግልጽ ተከራዩ እንዲያከራይ ፈቅዶ እንደሆነ ዋናውን የኪራይ ውል ለመፈጸም ሁለተኛ ተከራይ የሆነው ሰው
በዋናው ተከራይ ፋንታ ሊተካ ይችላል፡፡

ቊ 2965፡፡ ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል ስለ ማለቅ፡፡

ስለ ኪራይ የተወሰነው ጊዜ ሲያልቅ ልዩ ማስጠንቀቂያ መስጠት አስፈላጊ ሲሆን ያለ አንዳች ፎርማሊቴ ውሉ ቀሪ ይሆናል፡፡
ቊ 2966፡፡ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውል ስለ ማለቅ፡፡

(1) የኪራይ ውል የተደረገው ላልተወሰነ ጊዜ እንደሆነ አከራዩ ተከራዩን ለማስታወቅ ወይም ተከራዩ አከራዩን ለማስታወቅ ይችላል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ውሉ አለቀ የሚባለው በኪራዩ ውል ወይም በሕጉ መሠረት ተከታዩ የኪራይ ዘመን ዋጋ በሚከፈልበት ቀን ወይም
የኪራዩ ውል ስለማለቅ ማስታወቁን ባይሰጥ ኑሮ ኪራዩ ሊከፈልበት ይገባው በነበረበት ቀን ነው፡፡

ቊ 2967፡፡ ቤቱን የሚያገኝ ወይም የሚገዛ ሰው፡፡

(1) ቤቱን የሚገዛ ወይም የሚያገኝ ሰው የኪራዩን ውል ለማቋረጥ እንዲችል መብት ተሰጥቶት እንደሆነና የኪራዩ ውል እንዲቋረጥ የፈለገ
እንደሆነ ከዚሀ በላይ ባለው ቊጥር የተወሰነውን ጊዜ መጠበቅ አለበት፡፡

(2) ለዚህ ተቃራኒ የሚሆን ማናቸውም የውል ስምምነት ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 2968፡፡ ስለ ኪራይ ውል መራዘም፡፡

(1) የኪራይ ውል ሲያልቅ ተከራዩ የተከራየውን ነገር ከአከራዩ ዐውቆና ፈቅዶለት እንደ ያዘ የተቀመጠ እንደሆነ የኪራዩ ውል ላልተወሰነ ጊዜ
እንደታደሰ ይቈጠራል፡፡

(2) ስለ ሌላው ነገር የሁለት ወገን ተዋዋዮች መብትና ግዴታዎች አስቀድሞ በተነገረው ውል በተነገሩት ውለታዎች መሠረት ይፈጸማሉ፡፡

(3) ስለሆነም ስለ መጀመሪያ ውል የተሰጠው ዋስትና ነጻ ይሆናል፡፡

ቊ 2969፡፡ አከራዩ ቤቱን መልሶ ስለ መውሰድ፡፡

(1) ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት ከሌለ በቀር አከራዩ እኔው ራሴ እቀመጥበታለሁ ቢል እንኳ የኪራዩን ውል ለማፍረስ አይችልም፡፡

(2) በኪራዩ ውል ውስጥ አከራዩ ቤቱን እርሱ ራሱ ሊቀመጥበት የሚችል መሆኑን የሚናገር ስምምነት እንዳለ የተባለው አከራይ ላልተወሰነ
ጊዜ የተደረጉትን የኪራይ ውሎች ለማቋረጥ የተወሰኑትን ጊዜዎች መጠበቅና ለተከራዩም ማስጠንቀቂያ ለመስጠት አከራይ ይገደዳል፡፡

ቊ 2970፡፡ ስለ ቤቱ መቃጠል (1) መሠረቱ፡፡

ተከራዩ በቤቱ ላይ የደረሰው ቃጠሎ ከዐቅም በላይ በሆነ ኀይል ወይም በቤቱ ሥራ ጐዶሎነት ወይም ቃጠሎው ከጎረቤቱ ቤት መያያዝ
የተነሣ መሆኑን ካላስረዳ በቀር ተከራዩ ለአከራዩ ኀላፊ ነው፡፡

ቊ 2971፡፡ (2) ስለ ብዙ ተከራዮች፡፡

(1) ተከራዮቹ ብዙዎች የሆኑ እንደሆነ በተከራይነት በያዙዋቸው ቤቶች ክፍል ዋጋ መጠን ሁሉም ለቃጠሎው በኀላፊነት ይጠየቃሉ፡፡
(2) ቃጠሎው ከነርሱ መካከል አንደኛ ተከራይ ባለበት ቤት የጀመረ ለመሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ የተባለው ተከራይ ብቻ ኀላፊ ይሆናል፡፡

(3) ከተከራዮቹ መካከል አንዳንዶቹ ቃጠሎው እነርሱ ባሉበት ዘንድ ያለመጀመሩን ያስረዱ እንደሆነ እነዚህ ተከራዮች ኀላፊዎች
አይሆኑም፡፡
ቊ 2972፡፡ አከራዩ በከፊል ስለሚኖርበት ቤት፡፡

(1) አከራዩ የሚኖርበት ከተቃጠለው ቤት በአንዱ ክፍል በሆነም ጊዜ ከዚህ በላይ የተነገረው ደንብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

(2) በእንደዚህ ያለው ጊዜ አከራዩ የሚቀመጥበትን ክፍል እርሱ ራሱ ቤቱን እንደተከራየው ይቈጠራል፡፡

ቊ 2973፡፡ በቤቱ ላይ ስለሚደረግ ማሻሻል (1) የወጪ መካፈል መብት፡፡

(1) ተከራዩ ያላከራዩ ፈቃድ በተከራየው ቤት ላይ ስላደረገው ማሻሻያ አንዳች ወጪ እንዲከፍለው የመጠየቅ መብት የለውም፡፡

(2) ማሻሻያውን ያደረገው በአከራዩ ፈቃድ እንደሆነ ተከራዩ ያደረጋቸውን ወጪዎች ሁሉ እንዲከፈለው አከራዩን ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 2974፡፡ ማቻቻልና አንሥቶ የመውሰድ መብት፡፡

(1) ምንም እንኳ ተከራዩ አንዳች ኪሣራ የመጠየቅ መብት ባይኖራቸው የቤቱን ባለዋጋነት ከፍ ያደረጉትን ሥራዎችና በርሱ ጥፋት ሳይሆን
ኀላፊ ለሆነባቸው የቤቱን ዋጋ ዝቅ ያደረጉትን መበላሸቶች ለማቻቻል ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም አሠራሩ ቤቱን ሳይጎዳ ሊፈጸም የሚቻል እንደሆነ ተከራዩ ያደረጋቸውን ማሻሻያዎች አንሥቶ ለመውሰድ ይችላል፡፡
ክፍል 3፡፡
ስለ መሬት የተሰጡት ልዩ ደንቦች፡፡
ቊ 2975፡፡ የዚህ ክፍል ተፈጻሚነት፡፡

(1) የኪራይ ውል የሚመለከተው ዋናው ዓላማ አንድ መሬትን በሆነ ጊዜና ተከራዩም መሬቱን የሚያለማው ሲሆን የዚህ ክፍል ደንቦች
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 2976፡፡ ለዐይነት የሚሆኑ ውሎች፡፡

(1) ለዐይነት የሚሆኑትን ውሎች፤ ለአንዳንድ የግብርና አገልግሎት የሚውሉ መሬቶች ወይም በአንዳንድ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት
መንግሥት አውራጃዎች የሚገኙትን መሬቶች የሚመለከቱትን ለዐይነት የሚሆኑትን ውሎች የእርሻ ሚኒስቴር ሊደነግጋቸው ይችላል፡፡

(2) እነዚህን መሬቶች የሚመለከቱት በያንዳንድ ሰዎች መካከል የሚደረጉት ውሎች ከዚህ በላይ በተነገሩት ዐይነት በተደራጁት ውሎች
ሁኔታ እንደተደረጉ ሆነው ይገመታሉ፡፡

(3) ተዋዋዮቹ በሚያደርጉዋቸው ግልጽ ስምምነቶች ለዐይነት ከተደራጁት ውሎች የተለዩ ስምምነቶች ለማድረግ ይችላሉ፡፡

ቊ 2977፡፡ መሬት ስለሚሰጠው ጥቅም የሚደረግ አመራር፡፡ (1) መብቱ፡፡

(1) የመሬቱ ልማት ሥራ የሚመራው በሁለቱ ወገን ተዋወዮች ስምምነት መሠረት ነው፡፡

(2) የመሬቱ ኪራይ የሚከፈለው በሙሉ ወይም አብዛኛው ከመሬቱ ሰብሎች በአንድ በተወሰነ መጠን ልክ በሆነ ጊዜ ወይም መሬቱ
ከሚያፈራቸው በአንዳንድ ሰብሎች የሆነ እንደሆነ ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት ወይም ልማድ ከሌለ በቀር የመሬቱ ሥራ አመራር የአከራዩ
ነው፡፡

(3) የመሬቱ ኪራይ የሚከፈለው በሙሉ ወይም አብዛኛው ለአከራዩ በእጁ በገንዘበ የሚከፈለው እንደሆነ ተቃራኒ ስምምነት ወይም
ልማድ ከሌለ በቀር የመሬቱ ልማት ሥሪ አመራር የገበሬው ነው፡፡

ቊ 2978፡፡ (2) የአንደኛው ወገን (ተዋዋይ) መብት፡፡


(1) የታሰቡት ውሳኔዎች ውጤቶቻቸው የኪራዩ ውል ካለቀ በኋላ የሚቀጥል በሆነ ጊዜ የሥራው መሪ ለአንደኛው ወገን ማማከር አለበት፡፡

(2) ይህ የተባለው አንደኛው ወገን በሚገባ ጊዜ ውሳኔውን ሳያስታውቅ የቀረ እንደሆነና መጠበቁም ከፍ ያለ ጉዳት የሚያስከትል የሆነ
እንደሆነ የተባለው (የሥራ መሪው) ለአንደኛው ወገን ተዋዋይ በዚሁ ሰው ፈንታ ውሳኔውን ለመቀበል ይችላል፡፡

ቊ 2979፡፡ መሬቱን የማልማት ግዴታ፡፡

(1) ገበሬው (ተጋዡ) መሬቱ ጥቅም እንዲሰጥ ለማድረግና በፍሬያማነት መልካም ሁኔታ እንዲገኝ አድርጎ ለመያዝ ይገደዳል፡፡

(2) ተከራዩ ይህን ግዴታ ያልፈጸመ እንደሆነ አከራይ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 2980፡፡ የተክሉ ዐይነትና አደራረግ፡፡


በውሉ መሠረት የመሬቱ ልማት ሥራ መሪነት የተሰጠው ወገን የሚደረገውን የግብርና ዐይነት አሠራር ይወስናል፡፡
ቊ 2981፡፡ የሥራዎች ወቅት፡፡

(1) በማናቸውም ሁኔታዎች የግብርናውን ሥራዎች ወይም ሌሎች ተግባሮች የሚፈጸሙበትን ጊዜ የሚወስን ገበሬው (ተከራዩ) ነው፡፡

(2) በዚህ ጒዳይ አከራዩ ገበሬውን ከማስጠንቀቅ በቀር ሌላ ነገር ማድረግ አይችልም፡፡

ቊ 2982፡፡ መሬቱን ለማልማት ስለሚደረገው ወጪ፡፡

(1) መሬቱን ለማልማት የሚደረገው ተራ የሆነ ወጪ በገበሬው ላይ የሚታሰብ ነው፡፡

(2) ስለ መሬቱ የሚከፈለው ኪራይ መሬቱ ከሚያፈራቸው ነገሮች አንዱን ክፍል ወይም መሬቱ የሚያፈራቸውን አንዳንድ ሰብሎች
በመስጠት እንደሆነ ገበሬው (ተጋዡ) ለዘር የሚሆን ወጪ ገንዘብ ለማድረግ በማይችልበት ሁኔታ ሲገኝ አከራዩ ይህን ለዘር የሚሆነውን
ወጪ ያለ ወለድ አስቀድሞ በብድር መሰጠት አለበት፡፡

(3) በዚህ ዐይነት በብድር የተሰጠው ሒሳብ በመጪው ጊዜ ከሚገኘው ሰብል ላይ ለአከራዩ ይከፈላል፡፡

ቊ 2983፡፡ ስለ ማደስና ስለ መልካም አያያዝ፡፡

(1) ተከራዩ በኪራይ ተሰጥተውት የሚገለገልባቸውን መኖሪያ ቤት የእህልና የገለባ ቤቶች በረቶች ስለሚመለከቱ ቦታዎች በዚህ ምዕራፍ
አስቀድሞ በተጻፈው ክፍል የተነገሩትን የቤት ማደስ ሥራዎች ለመፈጸም ይገደዳል፡፡

(2) ከዚህም በቀር በቦታዎቹ (በአገሬዎቹ) ልማድ መሠረት በኪራይ የተሰጠ መሬት ክፍል የሆኑትን መንገዶች የውሃ ጒድጓዶች አጥሮች
የውሃ መንገዶች የውሃ ቦዮችና ግድቦች በቦታዎቹ ልማድ (በአገሬዎቹ) መሠረት በደንብ ለመያዝ (ለመጠገን) ይገደዳል፡፡

ቊ 2984፡፡ ማርጀት ወይም ከዐቅም በላይ የሆነ ኀይል፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተው የማደሱ ሥራ በማርጀት ወይም ከዐቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቢሆንም በገበሬው
(በጢሰኛው) ኪሣራ ይሆናል፡፡

(2) እንደዚሁ ገበሬው (ጢሰኛው) በማርጀት ወይም ከዐቅም በላይ በሆነ ምክንያት የጠፉትን ዕቃዎች ወይም መሣሪያዎች መተካት
አለበት፡፡
ቊ 2985፡፡ ልዩ የሆነ ወጪ፡፡

ገበሬው (ጢሰኛው) ልዩ ሆኖ በደረሰ አደጋ መሬቱን ለማደስ (ለማቋቋም) የሚደረገውን ኪሣራ እንዲያወጣ አይገደድም፡፡

ቊ 2986፡፡ የመሬት ቊራጭ (ክፍል) ስለ መለዋወጥ፡፡

(1) ከሁለቱ ወገኖተ የመሬቱን ማልማት ሥራ መሪነት የያዘው ወገን የሥራውን ክንውን ለማካሄድ ቀና እንዲሆን ከሌሎች ባለሀብቶች
(ባለርስቶች) ወይም ገበሬዎች (ጢሰኞች) ጋራ የመሬት ክፍልን (ቊራጭን) ልውጫ ለማድረግ ይችላል፡፡
(2) ይህ ልውጫ የገበሬው ተግባር የሆነ አንደሆነ ከነዚህ የመሬት ክፍል ቊራጭ አገልግሎት በቀር የርስትነትን መብት ሊነካ አይችሉም፡፡

(3) ልውጫውን አከራዩ ካልወሰነው ወይም አከራዩ ካልፈቀደ በቀር፤ ውሉ ሲያልቅ ያለ አንዳች አሠራር ውጤት መስጠታቸው ቀሪ
ይሆናል፡፡
ቊ 2987፡፡ መሬቱን ስለ ማደራጀት፡፡

ገበሬው (ጢሰኛው) በኪራይ የተሰጠውን መሬት አእምሮ በሚቀበለው ዐይነት ለሚደረገው ክንውን እንቅፋት የሚሆኑትን ዳገቶች
(አረሆች) ጉብታዎች ቦዮች ወይም አጥሮችን ለማፍረስ ይችላል፡፡

ቊ 2988፡፡ የሚከፈለው የኪራይ ዐይነት፡፡

(1) የሚከፈለው ኪራይ ባንድ በተወሰነ ገንዘብ ወይም ባንድ በተወሰነ ከግብርና በሚገኘው ሰብል ወይም በተወሰኑ ሰብሎች እንደ ጊዜው
ሸመታ ዋጋ በሚወሰን ገንዘብ ለመሆን ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም የሚከፈለው ኪራይ በኪራይ ከተሰጠው መሬት ከሚገኘው ከተወሰነ ሰብል ወይም ልዩ ልዩ ፍሬዎች ውስጥ መሆን
ይችላል፡፡
ቊ 2989፡፡ የሚከፈለው የኪራይ ልክ፡፡
የሚከፈለው የኪራይ ልክ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ይወሰናል፡፡
ቊ 2990፡፡ ሕጋዊ የሆነ የሕሊና ግምት፡፡

(1) ተቃራኒ የሆነ ልማድ ከሌለ በቀር የሚከፈለው ኪራይ በኪራይ ከተሰጠው መሬት ከሚገኘው ሰብል ግማሽ ይሆናል፡፡

(2) ተቃራኒ የሆነ ልማድ ከሌለ በቀር ይህ ሰብል ባከራዩና በገበሬው (በጢሰኛው) መካከል በዐይነት የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

(3) ገበሬው (ጢሰኛው) ማናቸውም ክፍያ ከመደረጉ በፊት ለሚመጣው ሰብል አስፈላጊ የሆነውን ዘር ለማስቀረት ይችላል፡፡

ቊ 2991፡፡ ሕጋዊ ከፍተኛ ድርሻ፡፡

(1) ለአከራዩ የሚሰጠው ሰብል መጠን በማናቸውም ሁኔታ ከሦስት ሩብ ለመብለጥ አይችልም፡፡

(2) በውል ውስጥ ከዚህ የበለጠ ድርሻ የተመለከተ እንደሆነ ይህ ውል ፈራሽ ሆኖና ሰብሉ ባከራዩና በገበሬው መካከል እኩል የሚከፋፈል
ይሆናል፡፡
ቊ 2992፡፡ ለቀለብ አስፈላጊ የሆነ ሰብል (1) መሠረቱ፡፡

(1) ገበሬው በማናቸውም ሁኔታ ለቀለቡና ከእርሱ ጋራ ለሚኖሩት ቀለብ አስፈላጊ የሆነውን የሰብል ድርሻ ማስቀረት (መያዝ) ይችላል፡፡

(2) ምን ጊዜም ቢሆን ግን ሰብሉ ለአከራዩ ቀለብና ከእርሱ ጋራ ለሚኖሩት ሰዎች ቀለብ እንዲሁ አስፈላጊ የሆነ እንደሆነ በዚህ ዐይነት
አይፈጸምም፡፡
(3) እንደዚህ በሆነ ጊዜ ሰብሉን አከራዩና ገበሬው አኩል ይካፈላሉ፡፡

ቊ 2993፡፡ የአከራዩ የተጠበቁ መብቶች፡፡


ከዚህ በላይ ባሉት ቊጥሮች አፈጻጸም ምክንያት አከራዩ የሚገባውን ሙሉ የሰብል ድርሻውን ሳያገኝ የቀረ እንደሆነ ከተከታዩ ዓመት ሰብል
ላይ ድርሻውን የማግኘት መብት አለው፡፡

ቊ 2994፡፡ ሰብል፡፡

(1) የሚከፈለው ኪራይ ከዚሁ ሰብል ድርሻ ውስጥ ወይም ይኸንኑ ሰብል በመመልከት የተወሰነ እንደሆነ ገበሬው ሰብሉን ከመሰብሰቡ
በፊት በተቻለ መጠን ለአከራዩ ማስታወቅ አለበት፡፡
(2) በውሉ መሠረት ለአከራዩ የሚደርሰው የሰብል ድርሻ እስከሚሰጠው ጊዜ ድረስ ገበሬው ይህን ሰብል መጠበቅና ማስቀመጥ አለበት፡፡

ቊ 2995፡፡ ኪራይ የሚከፈልበት ጊዜ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የሚከፈለው በገንዘብ ወይም ከግብርናው በሚገኘው በተወሰነ ሰብል የሆነ እንደሆነ ኪራዩ በያንዳንዱ ዓመት መጨረሻ የሚከፈል
ይሆናል፡፡

(2) የኪራዩ ውል አከራዩ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለገበሬው ካስረከበበት ቀን አንሥቶ ይቈጠራል፡፡

ቊ 2996፡፡ የገበሬው ሳይከፍል መዘግየት፡፡

(1) ገበሬው ያለፈውን ጊዜ ኪራይ ሳይከፍል የዘገየ እንደሆነ አከራዩ የስሳ ቀን ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ይህ ጊዜ ካለፈ በኋላ ሳይከፍል
ቢቀር ውሉ የሚፈርስ መሆኑን (ያስታውቀዋል) ሊያስገነዝበው ይችላል፡፡

(2) ይህ የማስጠንቀቂያ ጊዜ የሚጀመረው ገበሬው የአከራዩ ማስታወቂየ ከደረሰው ቀን አንሥቶ ነው፡፡

(3) ይህን የማስታወቂያ ጊዜ የሚቀንሱ ወይም የሚከፈለው ኪራይ ባለመከፈሉ ምክንያት ወዲያውኑ ለአከራዩ የማፍረስ መብትን የሚሰጡ
ማንኛዎቹም የውል ቃሎች ወይም ልማዶች ሁሉ ፈራሾች ናቸው፡፡

ቊ 2997፡፡ ስለ መሬቱ አበል ሁኔታ፡፡

(1) የሚከፈለው ኪራይ በኪራይ ከተሰጠው መሬት ሰብል ውስጥ ወይም ከተወሰነ ሰብል ውስጥ በመጠን የሆነ እንደሆነ ይህ ሰብል
ከመሬቱ ላይ ከተነሣ በኋላ ለአከራዩ የሚገባው ድርሻ ወዲያው ጥያቄ እንዳደረገ የሚሰጠው መሆን አለበት፡፡

(2) ይህን ተቃራኒ የሆኑ ልማዶች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 2998፡፡ (የሚከፈለውን የኪራዩን ዋጋ ስለ መለዋወጥ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የሚከፈለው የመሬት ኪራይ ዋጋ በገንዘብ ወይም አስቀድሞ በተወሰነ ሰብል የሆነ እንደሆነ ገበሬው በአንበጣ ወረራ ልዩ በሆነ ድርቅ
ወይም ሌላ አደጋ ወይም ይኸንኑ በመሰለ ልዩ መዓት ላንድ ዓመት የተመደበው የሰብል (የሀብት) ገቢ ከደንበኛው መጠን ግማሽ ሆኖ
የተቀነሰ እንደሆነ ዕዳውን በከፊል ይቅርልኝ ለማለት ወይም የዕዳው መክፈያ ጊዜ እንዲሰጠኘ ሲል ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ይህን ተቃራኒ የሆኑ ማንኛዎቹም ውሎችና ልማዶች ሁሉ ፈራሾች ናቸው፡፡

ቊ 2999፡፡ (2) ለመጠየቅ ስላለመቻል፡፡

(1) የሰብሉ መጥፋት የደረሰው ከመሬቱ ከተነሣ በኋላ የሆነ እንደሆነ ገበሬው ዕዳው ይቅርልኝ ብሎ ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(2) ውሉ በተደረገ ጊዜ ጉዳት የሚያደርሰው ምክንያት ያለና በዚያኑ ጊዜ የታወቀ የሆነ እንደሆነ ገበሬው እንደዚሁ ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(3) እንደዚሁም ገበሬው በራሱ የደረሰበት ጉዳት በአንዱ አሹራንስ ወይም በሌላ አኳኋን የተጠበቀ የሆነ እንደሆነ የዘገየ ጊዜ ለመጠየቅ
አይችልም፡፡
ቊ 3000፡፡ (3) ቀሪ የሚሆነው የዕዳ ልክ፡፡

(1) ገበሬው ሊቀነስልኝ ይገባኛል ሲል የሚጠይቀውን የዕዳ ልክ ለመገመት የተመደውን (የሰብል) የሀብት) ገቢና የደረሰበትን ጉዳት
ትልቅነት በማመዛዘን ይደረጋል፡፡

(2) እንዲሁም ገበሬው ባለፉት ዓመታት ሰብል ሊያገኝ ያልቻለውን ጥቅም ወይም ወደፊት ውሉ እስከሚያልቅ ድረስ በቀሩት ዓመታት
ውስጥ አገኛለሁ የሚለውን የሰብል ትርፍ በገመት ነው፡፡

(3) ርትዕ ካላስገደደና የውሉ መለዋወጥ፤ ገበሬውን ከቤተሰቡ ጋራ ለማኖር ወይም ሥራውን እንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስፈልግ ካልሆነ
በቀር የውሉን ግዴታዎች መለወጥ አይችሉም፡፡

ቊ 3001፡፡ የተከራይ አከራይ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


(1) ይህን ተቃራኒ የሆነ ልማድ ከሌለ በቀር ገበሬው የተከራየውን መሬት ያለ አከራዩ ፈቃድ ለማከራየት መብት የለውም፡፡

(2) ተከራዩ መሬቱን አሳልፎ ለሌላ ለማከራየት አከራዩ ያለ አንዳች ምክንያት የከለከለው እንደሆነ ገበሬው ውሉ እንዲሻር ለመጠየቅ
ይችላል፡፡
ቊ 3002፡፡ (2) ልዩነት፡፡

(1) ስለሆነም በአከራዩ ላይ ጉዳት የማያስከትል ከሆነ ገበሬው በውል በተቀበለው ነገር ውስጥ ያሉትን ቤቶች ለሌላ ለማከራየት ይችላል፡፡

(2) ከዚህ በፊት ባለው ክፍል የተከራይ አከራዩን፤ የሚመለከቱ ደንቦች ይህን በመሳሰለው ላይ የጸኑ ይሆናሉ፤ እንዲሁም አሳልፎ
ማከራየቱን አከራዩ በፈቀደም ጊዜ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 3003፡፡ የውሉ ማለቅ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ለኪራዩ ውል የተወሰነው ጊዜ ከማለቁ በፊት አንዱ ወገን ለሌላው ወገን እጅግ ቢያንስ የስድስት ወር ጊዜ ሰጥቶ ስንብቱን ካስታወቀ
በተወሰነው ቀን ውሉ የሚያልቅ ይሆናል፡፡

(2) ይህን ተቃራኒ የሆኑ ልማዶች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 3004፡፡ (2) ስለ ውሉ መታደስ፡፡

(1) ከዚህ በፊት ባለው ቊጥር የተመለከተው ስንብት ያልተሰጠ እንደሆነ ወይም ይህ ስንብት ከተሰጠ በኋላ ገበሬው አከራዩ እያወቀ
ሳይቃወመው በመሬቱ መጠቀሙን የቀጠለ እንደሆነ ይህን ተቃራኒ የሆነ ልማድ ከሌለ በቀር የኪራዩ ውል በተጨማሪ ለአራት ዓመት ጊዜ
የታደሰ ይሆናል፡፡

(2) ለቀረበው ጒዳይ ሁሉ የሁለቱ ወገኖች መብትና ግዴታዎች አስቀድመው ባደረጉት ውል መሠረት የሚፈጸሙ ይሆናሉ፡፡

(3) ስለሆነም አስቀድሞ ለነበረው ውል የተሰጠው ዋስትና ነጻ ይሆናል፡፡

ቊ 3005፡፡ (3) ለረዥም ጊዜ የተደረጉ ውሎች፡፡

(1) የኪራዩ ውል ባንድ ሰው ዕድሜ ወይም ከዐሥር ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ የተደረገ እንደሆነ መሬቱን ከተረከበ ዐሥር ዓመት ያለፈ ሲሆን
ገበሬው በራሱ ፈቃድ ብቻ የውሉን ዘመን ለመለዋወጥ ይችላል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ውሉ የሚያልቀው ገበሬው ውሉን ለመሰረዝ የመፍቀዱ ማስታወቁያ ከአከራዩ ከደረሰው ከአራት ዓመት በኋላ
የኪራዩ ውል በመጋቢት አንድ ቀን ያልቃል፡፡

(3) በንኡስ ቊጥር 1 የተጻፈውን ተቃራኒ የሆነ ማናቸውም የውል ቃል ወይም ልማድ ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 3006፡፡ (4) ጊዜው ያልተወሰነ ኪራይ፡፡

(1) ጸንቶ የሚቈይበት ጊዜ ባልተወሰነ ውል የተደረገ ኪራይ፤ የመሬቱ ይዞታ በገበሬው እጅ ከገባበት ቀን አንሥቶ እስከ አራት ዓመት
ለሚጸና ጊዜ እንደተደረገ ያህል ይቈጠራል፡፡

(2) ይህን ተቃራኒ የሆኑ ልማዶች የተጠበቁ ናቸው፡፡

ቊ 3007፡፡ (5) የማይንቀሳቀስ ንብረትን ስለ መተው፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚገዛ ወይም የሚያገኝ ሰው የኪራዩ ውል እንዲቋረጥ የፈለገ ሆኖ ይህ መብት ለርሱ ተሰጥቶት እንደሆነ
ንብረቱን ከገዛበት ወይም ካገኘበት አንሥቶ በሚከተለው ሦስት ወር ውስጥ ለገበሬው ስንብት መስጠት አለበት፡፡

(2) የኪራዩ ውል ይህ ስንብት ከተሰጠበት ን አንሥቶ ቢያንስ ከሦስት ወር በኋላ በመጋቢት አንድ ቀን ፈራሽ ይሆናል፡፡

(3) ይህን ተቃራኒ የሆኑ ማናቸውም የውል ቃሎች ወይም ልማዶች ፈራሾች ናቸው፡፡
ቊ 3008፡፡ (6) የተከራዩ መብት፡፡

(1) የስንብት ማስታወቂያ የተሰጠው (የተነገረው) ገበሬ ለአከራዩ፤ ንብረቱን ለገዛው፤ ወይም ለአገኘው ሰው ሐሳቡን በማስታወቅ ውሉ
የሚያልቅበትን ቀን ለማሳጠር ይችላል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ አከራዩ ወይም ንብረቱን የገዛው ወይም ያገኘው ሰው የገበሬው ሐሳብ ማስታወቂያ ከደረሰው እጅግ ቢያንስ ከአንድ
ወር በኋላ ገበሬው በወሰነው ቀን ውሉ የሚቋረጥ ይሆናል፡፡
ቊ 3009፡፡ ስለ ገበሬው ወይም ስለ አከራዩ መሞት፡፡
(1) ገበሬው የሞተ እንደሆነ የርሱ ወራሾች መብቱን ያቈየላቸው ሰው ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ በሚከተሉት ስድስት ወር ውስጥ ለአከራዩ
ስንብት በመስጠት የኪራዩ ውል እንዲቋረጥ ለማድረግ ይችላሉ፡፡

(2) አከራዩ የሞተ እንደሆነ የሥራው ክንውን መሪነት በኪራዩ ውል ለአከራዩ ተሰጥቶ እንደሆነ አከራዩ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ በሚከተሉት
ስድስት ወር ውስጠ ለአከራዩ ወራሾች ስንብት በመስጠት ገበሬው የኪራዩ ውል እንዲቋረጥ ለማድረግ ይችላል፡፡

(3) ከዚህ በፊት በተመለከቱት ሁለት ኀይለ ቃሎች ውሉ በሚከተለው መጋቢት አንድ ቀንና አከራዩ ወይም ወራሾቹ የገበሬውን ወይም
የገበሬውን ወራሾች ስንብት ከተቀበሉ በኋላ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ፈራሽ ይሆናል፡፡

ቊ 3010፡፡ ስለ ገበሬው መታመም፡፡ (1) የገበሬው መብት፡፡

(1) ገበሬውን ራሱን ወይም ከቤተሰቡ አንዱን ሥራውን በደንበኛው ሁኔታ ለመቀጠል የማያስችለው በሽታ የያዘው እንደሆነ በውሉ ወይም
በሕጉ ከተወሰነው ጊዜ በፊት የኪራዩን ውል ለመሻር ይችላል፡፡

(2) ገበሬው በዚህ መብት የተገለገለበት እንደሆነ ለአከራዩ አንዳችም የጉዳት ካሣ መክፈል የለበትም፡፡

(3) ውሉም የሚያልቀው የገበሬው ማስታወቂያ ለአከራዩ ከደረሰው ከስድስት ወር በኋላ ነው፡፡

ቊ 3011፡፡ (2) የአከራዩ መብት፡፡

(1) ገበሬውን ወይም ከገበሬው ቤተሰብ አንዱን ሥራውን በደንበኛ ሁኔታ ለመቀጠል የማያስችለው በሽታ የያዘው እንደሆነ የሚከፈለው
የኪራይ ዋጋ ከተወሰነ የሰብል ድርሻ ወይም ከተወሰነ ከመሬቱ አበል ውስጥ የሆነ እንደሆነ አከራዩ በውሉ ወይም በሕጉ የተወሰነው ጊዜ
ከመድረሱ በፊት የኪራዩን ውል ለመሻር ይችላል፡፡

(2) አከራዩ በዚህ መብት የተገለገለበት እንደሆነ ለገበሬው ከአንድ ዓመት መጠነኛ የኪራይ ዋጋ ውስጥ ግማሹን መክፈል አለበት፡፡

(3) ውሉም የሚያልቀው ለገበሬው የአከራዩ ማስታወቂያ ከደረሰው ከስድስት ወር በኋላ ነው፡፡

ቊ 3012፡፡ ቃጠሎ፡፡
የተከራየው ነገር በእሳት መጥፋቱን ወይም መበላሸቱን የሚያመለክተው ከዚህ በፊት ያለው ክፍል ድንጋጌዎች ለገበሬው በኪራይ
በተሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ክፍል በሆኑ የመኖሪያ ቤትና ሌሎች ሕንጻዎች ላይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 3013፡፡ ውሉ ሲቋረጥ የሚደረግ ሥርዐት (1) ጒዝጓዝ ሣርና ፍግ፡፡

(1) መሬቱን ለቆ የሚወጣው ገበሬ ስለ መሬቱ ደንበኛ አሠራር በሚያስገድደው ጥንቃቄ መሠረት የመጨረሻውን ዓመት ገለባ ሣሩንና ፍጉን
መተው አለበት፡፡

(2) ገበሬው መሬቱን ሲረከብ አነስተኛ መጠን የተቀበለም ቢሆን ትርፍ ሆኖ ለሚገኘው መጠን ኪሣራ ለመቀበል መብት አለው፡፡

(3) ገበሬው ይበልጥ ተቀብሎ እንደሆነ ይህን ተቃራኒ የሆነ ልማድ ከሌለ በቀር ለጐደለው ኪራሣ መከፈል አለበት፡፡

ቊ 3014፡፡ (2) ዘር፡፡


ይህን ተቃራኒ የሆነ ልማድ ከሌለ በቀር መሬቱን ለቆ የሚወጣ ገበሬ ለሚመጣው ዓመት ሰብል ዘር እንዲተው አይገደድም፡፡
ቊ 3015፡፡ (3) የግብርና ሥራ ወጪ (ኪሣራ)፡፡

(1) ገበሬው ውሉን በሚተውበት ጊዜ ያልተለቀሙ ፍሬዎችን ለማግኘት መብት የለውም፡፡

(2) ስለሆነም ርትዕ የሚያስገድድ የሆነ እንደሆነ ዳኞች፤ ላደረጋቸው የተክል ሥራዎች ወጪ ኪሣራ እንዲቀበል ለማድረግ ይችላል፡፡

(3) ይኸውም ኪሣራ አከራዩ ከሚያገኛቸው ፍሬዎች ዋጋ በላይ ለመሆን አይችልም፡፡

ቊ 3016፡፡ በመሬቱ ላይ ስለ ተደረገው ማሻሻል፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የኪራዩ ውል የተቋረጠው በማናቸውም ምክንያት ቢሆን በራሱ ሥራ ወይም እሱ ባደረጋቸው ወጪዎች በመሬቱ ላይ የማሻሻል ሥራ
የፈጸመ ገበሬ ውሉ በሚያልቅበት ጊዜ ኪሣራ ለማግኘት መብት አለው፡፡

(2) እንደዚሁ በተከራየው መሬት ላይ ውሉ በሚፈቅድለት መሠረት ቤቶች የሠራ እንደሆነ፤ ገበሬው ኪሣራ (ግምት) ለማግኘት መብት
አለው፡፡

ቊ 3017፡፡ (2) የኪሣራው (የግምቱ) ክፍል፡፡

(1) የሚከፈለው ኪሣራ ልክ ከተደረጉት ማሻሻያዎች ወይም ከተሠሩት ቤቶች፤ የተነሣ መሬቱ ያገኘው ብልጫ ለ 9 ዓመት ከሚታሰበው
ጋራ የሚተካከል ነው፡፡

(2) ለዚህ ኪሣራ አከፋፈል ዳኞች ለአከራዩ ጊዜ መስጠት (መፍቀድ) ይችላሉ፡፡

ቊ 3018፡፡ (3) አንሥቶ የመሄድ (የመውሰድ) መብት፡፡


ገበሬው ከመረጠ በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለማድረግ የተቻለ ከሆነ ያደረጋቸውን የማሻሻል ሥራዎች አንሥቶ
ለመውሰድ ወይም ቤቶችን ለማፍረስ ይችላል፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
ስለማይንቀሳቀስ ንብረት የሥራ ውል፡፡
ቊ 3019፡፡ ተፈጻሚነት ያላቸው ደንቦች፡፡

(1) የሥራ ተቋራጭነቱ ውል የተደረገው የሕንጻን ሥራ ለመሥራት የተሠራውን ለማደስ፤ ወይም አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማደራጀት
እንደሆነ ከዚህ በታች በተነገሩት ድንጋጌዎች የሚመራ ይሆናል፡፡

(2) እንደዚሁም በዚህ ሕግ የሥራ አገልግሎት መስጠትን ስለሚመለከቱ ውሎች በሚለው አንቀጽ የሥራ ተቋራጭነትን የሚመለከቱት
ደንቦች በተባሉት ድንጋጌዎች የተወገዱ ሆኖ በይገኙበት መጠን ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 3020፡፡ የውሉ መፈጸም አስረጅነት፡፡

(1) ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ስለሚፈጽሙት ሥራዎችና ስለ ዋጋው ካልተስማሙ በቀር የተቋራጭነት ውል አለ አይባልም፡፡

(2) የሥራው ተቋራጭ አሠሪው እያወቀ ሥራዎቹን ለመሥራት ጀምሮ እንደሆነ ወይም ከዋጋው ላይ አስቀድሞ ገንዘብ ተቀብሎ እንደሆነ
ውል ለመኖሩ በቂ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡

ቊ 3021፡፡ የሚፈጸሙ ሥራዎች፡፡ (1) በቂ የሆነ የሥራዎች ዝርዝር፡፡

(1) የሚሠሩት ሥራዎች ዐይነት በፕላን በንድፍ ወይም በሌላ አስረጂዎች ሊለይ ይችላል፡፡

(2) የሥራው ተቋራጭ በእንደዚህ ያለው ጊዜ በእንደዚህ ያሉት አስረጂዎች የተለከቱትን ነገሮች አጥብቆ መከተል አለበት፡፡
ቊ 3022፡፡ (2) በጠቅላላው ስለ መወሰን፡፡

(1) የሚሠሩት ሥራዎች የተነገሩት በጠቅላላው አኳኋን ብቻ እንደሆነ፤ የነዚህን ሥራዎች ብዛት ስለሚመለከተው ጒዳይ ውሉ በጠባብ
ዐይነት መተርጐም አለበት፡፡

(2) ደግሞም የሥራው ተቋራጭ አንድ ሥራ ከመፈጸሙ በፊት ለአእምሮ ግምት አስፈላጊ መስሎ በሚታየው መጠን ያሠሪውን ፈቃድ
መጠየቅ አለበት፡፡

ቊ 3023፡፡ የዋጋው አወሳሰን ዐይነት፡፡

(1) የሥራው ተቋራጭ ለመፈጸም የተዋዋላቸው ሥራዎች ዋጋ በጅምላ ሊሆን ይችላል፡፡

(2) የሥራዎቹ ዋጋ አቅራቢያ በሆነ ግምትም ለመሆን ይችላል፡፡

(3) ዋጋው በጅምላ፤ ወይም በአቅራቢያ ግምት ያልተወሰነ እንደሆነ፤ የሥራው ዋጋ የሚገመተው ለሥራ በዋሉት ነገሮችና ግምት ለሥራው
አፈጻጸም አስፈላጊ በሆነው ሥራ ግምት መሠረት ነው፡፡

ቊ 3024፡፡ በአቅራቢያ ግምት የሚደረግ ዋጋ፡፡

(1) የሥራው ዋጋ በአቅራቢያ የተወሰነ እንደሆነ የሥራው ተቋራጭ በጅምላ ዋጋ እንደተዋዋለ ታስቦ ሥራውን ለመፈጸም ይገደዳል፡፡

(2) የሥራው ተቋራጭ በደረሰበት ወጪና አስቸጋሪ ነገሮች ምክንያት የሚወሰነው ዋጋ እንደ አቅራቢያ ግምት ተብሎ ከተስማማበት ዋጋ
ሓያ በመቶ ካልበለጠ በቀር የመጨረሻውንዋጋ እንደፈለገ ለመወሰን ይችላል፡፡

(3) ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ከሌለ በቀር የሥራው ተቋራጭ ስለ ሥራው ዋጋ ባደረገው ውሳኔ ላይ አሠሪው አንዳች አስረጅ ሊጠይቀው
ወይም ክስ ሊያቀርብበት አይችልም፡፡

ቊ 3025፡፡ በጅምላ ወይም በአቅራቢያ ግምት የተወሰነ ዋጋ (1) የማስታወቅ ግዴታ፡፡

(1) የሥራው ዋጋ ለሥራ የሚውሉትን ነገሮችና ሥራ በመመልከት የሚወሰን የሆነ እንደሆነ ምንም እንኳ ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ቢኖር
የሥራው ተቋራጭ ሥራዎቹ የደረሱበትን ሁኔታና ያደረገውን ወጪ ላሠሪው ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) በውሉ የተነገረ ተቃራኒ ቃል የሌለ እንደሆነ በየወሩ መጨረሻ ማስታወቅ አለበት፡፡

ቊ 3026፡፡ (2) የሥራ ተቋራጩ የሥራው ዋጋ፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ 2 ቱ ወገን ተዋዋዮች የተስማሙበትን የሥራ ዋጋ ከአሠሪው ለመቀበል መብት አለው፡፡

(2) ስለዚህ ነገር የተነገረ የውል ቃል የሌለ እንደሆነ፤ ሥራ ተቋራጩ ለአሠሪው በሰጠው ሒሳብ ላይ ለሥራው የሚሆን ደመወዝ
ሊያገባበት ይችላል፡፡

ቊ 3027፡፡ (3) ላሠሪው ያለው መብት፡፡


አሠሪው የሥራ ተቋራጩን ሒሳብ በማናቸውም ጊዜ ልዩ ዐዋቂዎች እንዲመረምሩት ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 3028፡፡ የሥራ ምርመራ፡፡
አሠሪው በማናቸውም ጊዜ ቢሆን ሥራዎቹ የደረሱበትን ሁኔታ በሥራው ላይ የዋሉትን መሥሪያዎች ዐይነትና የተሠራውን ሥራ ዐይነት
በልዩ ዐዋቂዎች ለማስመርመር ይችላል፡፡

ቊ 3029፡፡ ሥራውን ስለ መቀበልና ዋጋ ስለ መክፈል፡፡

(1) ዋጋውን መክፈል፤ ሥራው እንደ ተመረመረና አሠሪው እንደተቀበለው የሚያስገምት ነው፡፡
(2) ስለሆነም የተከፈሉት ገንዘቦች ከዋጋው ላይ በቅድሚያ እንደተከፈሉ የሚገመት የሆነ እንደሆነ ከዚህ በላይ ባለው ኀይለ ቃል የተሰጠው
አገማመት የሚጸና አይሆንም፡፡

ቊ 3030፡፡ በከፊል ሥራውን ስለ መቀበልና ዋጋውን ስለ መክፈል፡፡

(1) ውሉ በደረጃ እንዲፈጸም ስምምነት ተደርጎ እንደሆነ እያንዳንዱ ደረጃ ሥራ በተፈጸመ ቊጥር ምርመራውና የአቀባበሉ ሥነ ሥርዐት
ይፈጸማል፡፡

(2) የያንዳንዱ የሥራ ደረጃ በተፈጸመበት ጊዜ ሥራ ተቋራጩ በተፈጸሙት ሥራዎች መጠን ከሥራው ዋጋ ላይ አንዱ ክፍል እንዲከፈለው
ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 3031፡፡ አሠሪው የሚጠይቃቸው የሥራ መለዋወጥ፡፡ (1) የአሠሪው መብት፡፡


የተጠየቁት የሥራ መለዋወጥ በቴክኒክ ረገድ ሊፈጸሙ የሚቻልና የሥራውንም ጥንካሬ ከማይጎዱ ከሆኑ አሠሪው አስቀድሞ ከተስማማበት
የሥራ ዐቅድ አንዳንድ መለዋወጥ እንዲፈጸሙ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 3032፡፡ (2) የሚያስከትለው ውጤት፡፡

(1) ከሚሠራው ሥራ ላይ እንዲቀነስ ሥራ አሠሪው የጠየቀው የሥራ መለዋወጥ የሥራ ተቋራጩን ወጪ በቀነሰለት መጠን በውል ተወስኖ
ከነበረው ዋጋ ላይ እንዲቀነስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ደግሞ አሠሪው በጠየቀው የሥራ መለዋወጥ ምክንያት የሥራ ተቋራጩን ወጪ የሚያበዛ ወይም በተጨማሪ ሥራ
የሚያስከትል ወይም አላፊነቱን የሚያከብድበት በመሆኑ መጠን ለዚህ ለተጨማሪው ሥራ ዋጋውና የሚከፈለው አበል ተጨምሮ
እንዲከፈለው አሠሪውን ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(3) በሚቀነሰው ወይም በሚጨመረው የዋጋ አከፋፈል ሒሳብ ላይ ሁለቱ ወገን ተዋዋዮች ያልተስማሙ እንደሆነ በተጨማሪ ወይም
ተቀናሽ ሥራ የሚከፈለውን ሒሳብ ሁለቱ ወገኖች የሚመርጡዋቸው የሽምግልና ዳኞች እነዚህም ባይኖሩ ዳኞች ይወስኑታል፡፡

ቊ 3033፡፡ (3) የሥራ ተቋራጩ እንቢታ፡፡

(1 ) አሠሪው የጠየቃቸው የሥራ መለዋወጥ ስምምነት የተደረገባቸውን ፕላኖች ንድፎች ወይም ሌላ ሰነዶች የሚነኩ የሆነ እንደሆነ ሥራ
ተቋራጩ አልቀበልም ለማየት ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ሥራ ተቋራጩ አሠሪው የጠየቃቸው መለዋወጥ በብዛታቸውም ወይም በዐይነታቸው ስምምነት ከተደረገበት ሥራ
በአፈጻጸማቸው ሌላ ልዩ ሥራ የሚያስከትሉ የሆነ እንደሆነ አልቀበልም ለማለት ይችላል፡፡

(3) ሥራው በተለይ በፍጹም እንደ ልዩ ሆኖ የሚገመተው አስቀድሞ ከታሰበው ሥራ ግምት ወይም ሊገመት ከሚቻለው ከመቶ ሓያ በላይ
መለዋወጥን የሚያስከትል ሲሆን ነው፡፡

ቊ 3034፡፡ ሥራ ተቋራጩ የሚያቀርባቸው መለዋወጥ፡፡

(1) በቴክኒክ ምክንያት ስምምነት የተደረገበት ዕቅዱ እንዲለዋወጥ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፤ አስቸኳይ ካልሆነ በቀር ሥራ ተቋራጩ
ለአሠሪው ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) የታሰበው መለዋወጥ አሠሪው አንድም ተጨማሪ ዋጋ ለመክፈል የሚያስገድደው ባይሆንም እንኳ ሥራ ተቋራጩ የማስታወቅ ግዴታ
አለበት፡፡

ቊ 3035፡፡ ውሉን ስለ ማስቀረት፡፡


አሠሪው፤ ሥራ ተቋራጩ አንዳችም ጥፋት ባያደርግም እንኳ የፈረመውን ውል ለማፍረስ ይችላል፡፡
ቊ 3036፡፡ የሥራ ተቋራጩ መብት፡፡ (1) ዋጋው በጅምላ ወይም በአቅራቢያ ግምት የተደረገ ሲሆን፡፡
(1) አሠሪው በዚህ አኳኋን ውሉን ያፈረሰ እንደሆነ፤ ሥራ ተቋራጩ ስምምነት የተደረገበትን የጅምላ ዋጋ ወይም የአቅራቢያ ግምት ዋጋ
ለማግኘት መብት አለው፡፡

(2) ስለሆነም በውሉ መሻር ምክንያት ሥራ ተቋራጩ ከማውጣት የቀረለት ወጪ ከዚህ ዋጋ ላይ ተቀናሽ መሆን አለበት፡፡

(3) አቅራቢያ በሆነ ግምት ዋጋው ተወስኖ እንደሆነ፤ ከዚህ በላይ ባሉት ሁለት ኀይለ ቃሎች መሠረት አሠሪው መክፈል ያለበትን ገንዘብ
እስከ ሓያ በመቶ ድረስ በማብዛት ሥራ ተቋራጩ ሊጠይቅ ይችላል፡፡

ቊ 3037፡፡ (2) ሌላ ዐይነት ዋጋዎች፡፡

(1) የሥራው ዋጋ በመሥሪያዎቹና ሥራውን ለመፈጸም አስፈላጊ በሚሆነው ሥራ ዋጋ መሠረት የተወሰነ የሆነ እንደሆነ የውሉ መፍረስ
ማስታወቂያ ለሱ ከመድረሱ በፊት አስቀድሞ ለተሠራባቸው መሥሪያዎችና ለተሠሩት ሥራዎች ተቋራጩ የዋጋ ግምት ለማግኘት መብት
አለው፡፡

(2) እንዲሁም አሠሪው ስለ ሥራው አፈጻጸም በቅን ልቡና ከተወሰነው ጊዜ በፊት ሥራ ተቋራጩ ላደረጋቸው ውሎች በራሱ ሒሳብ
ማሰብ አለበት ወይም በነዚሁ ውሎች መሻር ምክንያት ለሥራው ተቋራጭ የሚደርስበትን ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(3) በመጨረሻም ሥራ ተቋራጩ አሠሪው ሊከፍለው ግዴታ የገባበትን ጠቅላላ የድካም ዋጋ እንዲሰጠው ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 3038፡፡ የውሉ መፍረስ፡፡

(1) የውሉ መፍረስ በሥራ ተቋራጩ ጥፋት የሆነ ወይም አሠሪው በሚገባ የጠየቀውን መለዋወጥ ለመፈጸም ባለመቀበል የሆነ እንደሆነ
አስቀድመው በተሠሩት ሥራዎች ብዛት መጠን ሥራ ተቋራጩ ስምምነት ከተደረገበት የሥራ ዋጋና የአገልግሎት ዋጋ ለማግኘት መብት
አለው፡፡

(2) ስለሆነም ሥራ ተቋራጩ ግዴታዎቹን ባለመፈጸሙ ምክንያት ለሚደርሰው ጉዳት የአሠሪው የኪሣራ መጠየቁ መብት እንደተጠበቀ
ነው፡፡
ቊ 3039፡፡ ሥራ ተቋራጩ የሚሰጠው መድን፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ቀን ጀምሮ ስለ መልካም አሠራሩና ስለ ሥራው ስለ ጠንካራነቱ ለዐሥር ዓመት ጊዜ መድን ነው፡፡

(2) በዚሁም ጊዜ ውስጥ በሥራ ጒድለት ወይም በተሠራበት መሬት ዐይነት ምክንያት በተሠራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም
መበላሸት አላፊ ነው፡፡

(3) ማናቸውም ይህን ጊዜ የሚያሳጥር ወይም መድንነቱን የሚሽር የውል ቃል ሁሉ አይጸናም፡፡

ቊ 3040፡፡ የምክትል ሥራ ተቋራጮችና ሠራተኞች በቀጥታ ያላቸው የክስ መብት፡፡


በአንድ የሕንጻ ሥራ ተቋራጭነት ውስጥ የሚሠሩ ሥራ ተቋራጮች ወይም ሠራተኞች የሠሩበትን ሥራ ዋጋ ለመከፈል ክሳቸውን
ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን ባሠሪው ላይ በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት
አላቸው፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
ስለማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣና ስለ ወለድ አግድ
ክፍል 1፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ አቋቋም፡፡
ቊ 3041፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን የማቋቋሚያው ሰነድ፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በቀጥታ በሕግ ወይም በፍርድ ወይም በውል ወይም ደግሞ በኑዛዜ ሊቋቋም ይችላል፡፡
ቊ 3042፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሻጭ ለሆነ ሰው ሕግ የሚሰጠው መያዣ፡፡
አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሸጠ፤ ያስተላለፈ ሰው ለተዋዋለበት ንብረት ዋጋ አከፋፈል ዋስትናና በሽያጩ ስምምነት ውስጥ
ለተመለከቱት ሌሎች ግዴታዎች ዋስትና እንዲሆነው በሕጉ መሠረት በዚህ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የመያዣ መብት አለው፡፡

ቊ 3043፡፡ ለማይንቀሳቀሰው ንብረት የጋራ ተካፋይ የሆነ ሰው ሕግ የሚሰጠው መያዣ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ተካፋይ የሆነ ሰው፤ በክፍያው መሠረት በሌሎቹ የጋራ ተካፋዮች ድርሻ ውስጥ ሕግ የሚሰጠው የመያዣ መብት
አለው፡፡

(2) ይህም የመያዣ መብት የሚሰጠው ከክፍያው ውስጥ ለሚጐልበት ድርሻውና ምናልባትም በክፍያ ያገኛቸውን ሀብቶች እንዲለቅ
ቢፈረድበት፤ የጋራ ተካፋዮቹ ሊከፍሉት ለሚገባው ኪሣራ ዋስትና ነው፡፡

ቊ 3044፡፡ በፍርድ የሚሰጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ፡፡

(1) ዳኞች በዳኝነት የሰጡት ፍርድ ሽማግሎች በሽምግልና ዳኝነት የሰጡት ብይን ወይም የሰጡት ትእዛዝ ተፈጻሚነት እንዲያገኝ
ለማረጋገጥ አንዱ ወገን በሌላው ወገን በማይንቀሳቀስ በአንድ ወይም በብዙ ንብረቶች ላይ የመያዣ መብት እንዲኖረው ለመወሰን
ይችላሉ፡፡

(2) ይህም የፍርድ ውሳኔ ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይን የዋስትና መያዣ የተሰጠበትን የዕዳ ልክና ስለዚህም ዕዳ በመያዣ የተሰጠውን
ንብረት ወይም ንብረቶች ለይቶ ያመለክታል፡፡

ቊ 3045፡፡ የማይንቀሳቀሰው ንብረት መያዣ የሚቋቋምበት ሰነድ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን የሚያቋቁም ውል ወይም ሕጋዊ ሰነድ በጽሑፍ ካልተደረገ በቀር ዋጋ የለውም፡፡

(2) መያዣ የተሰጠበት ገንዘብ ልክ በኢትዮጵያ ገንዘብ ካልተመለከተ በቀር ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 3046፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ ዋስትና የተሰጠው ዕዳ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ፤ አሁን ለተደረገ ለወደፊቱ ለሚደረግ በውለ ገብነት ለሚደርስ ወይም ይደርሳል ለሚባል ገንዘብ ልክ
ዋስትና ሊቋቋም ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም በትእዛዝ ወይም ለአምጪው በሚከፈል ሰነድ ላይ ለተመለከተው ገንዘብ ዋስትና እንዲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ
ውል ሊቋቋም ይችላል፡፡

ቊ 3047፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ሊሆኑ የሚችሉ ንብረቶች፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ሊቋቋም የሚቻለው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ብቻ ነው፡፡

(2) ልዩ ልዩ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች እንደማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ የተወሰነው ድንጋጌ የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 3048፡፡ መያዣ የሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት፡፡

(1) በመያዣነት መሰጠቱ የተመዘገበ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣውን በሚያቋቁመው ሰነድ ላይ በግልጽ መጠቀስ አለበት፡፡

(2) ሰነዱም የማይንቀሳቀሰው ንብረት የሚገኝበትን ወረዳ የንብረቱን ዐይነት የሚቻልም ቢሆን በርስት መዝገብ የተጻፈበትን የካርታ ቊጥር
በተለይ ማመልከት ይገባዋል፡፡

(3) የማይንቀሳቀሰው ንብረት የሚገኘው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መዝገብ ባልተቋቋመበት አውራጃ ውስጥ በሆነ ጊዜ ሰነዱ እጅግ ቢያንስ
ሁለቱን አዋሳኞቹን ገልጾ ማመልከት ይገባዋል፡፡

ቊ 3049፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ለመስጠት የሚያስፈልግ ችሎታ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በባለዕዳው፤ ወይም ስለ ሌላ ሰው ዕዳ መያዣ ሰጥቶ በሚዋዋል ሦስተኛ ሰው፤ ሊቋቋም ይችላል፡፡
(2) ለራሱ ዕዳ ዋስትና እንዲሆን አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለዕዳ በመያዣነት ለመስጠት የሚቻለው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት
ለመሸጥ ችሎታ ያለው እንደሆነ ነው፡፡

(3) ለሌላ ሰው ዕዳ ዋስትና እንዲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረትን ለመያዣ መስጠት የሚቻለው ይህንኑ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ዋጋ
ሳይቀበል በችሮታ ለማስተላለፍ ሊያዝበት ችሎታ ያለው ሲሆን ነው፡፡

ቊ 3050፡፡ የፍትሐ ብሔር ቅጣት፡፡

(1) ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር ውስጥ የተጻፈው ችሎታ የሌለው ሰው የሰጠው የመያዣ ውል ዋጋ የለውም (አይጸናም)፡፡

(2) ይህ ችሎታ የሌለው ሰው ሀብቱን በመያዣ ከሰጠ በኋላ ይህንኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሊያዝበት ችሎታ ቢያገኝም እንኳ አስቀድሞ
ሰጥቶት የነበረው መያዣ ዋጋ ያለው አይሆንም፡፡

(3) እንዲሁም ወደፊት ይሠራሉ የሚባሉትን ሕንጻዎች መያዣ መስጠት ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 3051፡፡ (1) በባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የታወቀ ንብረት፡፡

(1) የአስተዳደር ክፍል፤ የአንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት መሆኑን ዐውቆለት የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት ከሰጠው ሰው ጋራ
የተደረገ የንብረት መያዣ ውል የሚጸና ነው፡፡

(2) የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የተሰጠበት ማስረጃ ፍርስ ሆኖ የተሰረዘ ቢሆንም በመያዣው የሚከራከረው ሰው በቅን ልቡና
አለመሆኑ ካልተገለጸ በቀር የርስት መያዣው ውል የሚጸና ነው፡፡

(3) የርስት የምስክር ወረቀት በሚሰጥበት ጊዜ በአስተዳደር ክፍል ደንብ መሠረት ከምስክር ወረቀት መስጫው ታክስ ጋራ ከሚከፈለው
ለመጠባበቂያ ዋስትና ከተመደበው ገንዘብ በዕዳ የተያዘውን የማይንቀሳቀስ ንብረቱን ዕዳ ከፍሎ ንብረቱን ላስለቀቀው ባለሀብት
ይከፈለዋል፡፡

ቊ 3052፡፡ የማጻፍ አስፈላጊነት፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በማናቸውም ዐይነት ሰነድ ላይ የተመሠረተ ቢሆን ከተጻፈበት ቀን አንሥቶ የማይንቀሳቀሰው ንብረት
በሚገኝበት አገር ባለው በማይንቀሳቀስ ርስት መዝገብ ካልተጻፈ በቀር ማንኛውንም ዐይነት ውጤት አያስገኝም፡፡

ቊ 3053፡፡ የአጻጻፉ ሥርዐት፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረትን መያዣ እንዲመዘግብ ጥያቄ የቀረበለት የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ሠራተኛ፤ የውሉን አመዘጋገብ ሥርዐት
የሚፈጽመው በዚህ ሕግ ስለማይንቀሳቀሱ ንብረቶች አመዘጋገብ ሥርዐት በሚመለከተው አንቀጽ በተደነገገው ደንብ መሠረት ነው፡፡

(2) የዚሁም አንቀጽ ደንብ አመዘጋገብ የሚሻሻልበትንና የሚለወጥበትን ሥርዐት ወስኗል፡፡

ቊ 3054፡፡ የማስመዝገቢያው ወጪ፡፡

(1) የማስመዝገቢያውን ወጪ የሚችለው በመጨረሻው ባለዕዳው ብቻ ነው፡፡

(2) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን ያስመዘገበና ለዚህም ወጪውን አስቀድሞ የከፈለ ሰው የከፈለውን ገንዘብ ባለዕዳው እንዲከፍለው
ለመጠየቅ ይችላል፡፡

ቊ 3055፡፡ የገንዘብ መብት መቀነስ፡፡

(1) ባለዕዳው ከዕዳው ጠቅላላ ሒሳብ ላይ ሩቡን ከከፈለ በኋላ ከመዝገቡ ላይ የተጻፈው እንዲተካከልለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ገንዘብ ጠያቂውም ይህን የመዝገብ መተካከል ጒዳይ መፍቀድ አለበት፡፡

(3) ባለዕዳው ከተበደረው ገንዘብ በከፊሉ በመክፈል፤ በመያዣ ካስያዛቸው የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ውስጥ በዚሁ መጠን በከፊል
እንዲለቀቅለት ለመጠየቅ አይፈቀድለትም፡፡
ቊ 3056፡፡ የገንዘብ መብት መጨመር፡፡

(1) በመጀመሪያ በመዝገቡ ላይ የተጻፈውን የገንዘብ ልክ በማስተካከል ብቻ የገንዘቡን ልክ ለመጨመር አይቻልም፡፡

(2) በመጀመሪያ በመዝገቡ ላይ ከተጻፈው የገንዘብ ልክ በላይ ያለው ገንዘብ ማረጋገጫ እንዲኖረው ከተፈለገ ይህንኑ በመዝገቡ ላይ
እንደገና ማስመዝገብ አስፈላጊ ነው፡፡

ቊ 3057፡፡ ለማስመዝገብ የተወሰነ ጊዜ፡፡

(1) የማይንቀሳቀሰው ንብረት የተያዘበትን ዕዳ የመክፈል ግዴታ የሌለበት ሦስተኛ ወገን የሆነ ሰው በዕዳ ተይዟል የተባለውን ይህንኑ
የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ገዝቶ ግዥውን በማይንቀሳቀስ ንብረት መጻፊያ መዝገብ ውስጥ ካጻፈ በኋላ የተመዘገበውን የማይንቀሳቀስ
ንብረት በመያዣ ማጻፍ ዋጋ የለውም፡፡

(2) እንዲሁም የማይንቀሳቀሰው ንብረት እንዲያዝ በፍርድ ሥነ ሥርዐት መወሰኑ በመዝገብ ከተጻፈ በኋላ ወይም ባለዕዳው መክሠሩ
ከተገለጸ በኋላ የሚደረግ የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ መጻፍ ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 3058፡፡ የተወሰነው ጊዜ ሲያልፍ መብት የሚቀርበት ሁኔታ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት ውጤት የሚኖረው፤ ከተጻፈበት ቀን አንሥቶ እስከ ዐሥር ዓመት ድረስ ነው፡፡

(2) ይህ የተወሰነው ጊዜ ከማለፉ በፊት ይህ ውል እንዲታደስ አዲስ የመዝገብ ማጻፍ ጒዳይ የተፈጸመ እንደሆነ ጸንቶ የሚቈይበት ዘመን
ይራዘማል፡፡

(3) እንዲህም በሆነ ጊዜ አስቀድሞ የተመዘገበው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል አዲሱ የመዝገብ ማስጻፍ ጒዳይ ከተፈጸመበት ቀን
አንሥቶ ወደፊትእስከ ዐሥር ዓመት ውጤት ያለው ይሆናል፡፡
ክፍል 2፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውጤቶች፡፡

ቊ 3059፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ፤ መያዣው የሚመለከተውን የማይንቀሳቀስ ንብረት፤ ገንዘብ ጠያቂዎች
ያስያዙት እንደሆነ ከንብረቱ ዋጋ ላይ የሚጠይቀው ገንዘብ ከሌሎቹ ገንዘብ ጠያቂዎች በፊት ለርሱ በቀዳሚነት እንዲከፈለው የመጠየቅ
መብት አለው፡፡

(2) እንዲሁም የመጀመሪያው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት ከተመዘገበ በኋላ፤ መብቱን ላስመዘገበ ለሌላ ሦስተኛ ወገን ባለዕዳው
የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ቢሸጥ ቢያስተላልፍም እንኳ የመያዣ መብቱን ያስመዘገበው ገንዘብ ጠያቂ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት
ለማስያዝ ይችላል፡፡

(3) ከዚህም በቀር ባለመያዣ የሆነ ገንዘብ ጠያቂ ለማንኛቸውም ሌሎች ተራ ገንዘብ ጠያቂዎች ያላቸው መብት ሁሉ ይኖረዋል፡፡

ቊ 3060፡፡ ንብረትን የማስቀረት ስምምነት፡፡

(1) ዕዳው እንዲከፈል በተወሰነበት ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂው የመያዣ መብት ያገኘበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት
ይወስዳል፡፡ ወይም በሕጉ የተመለከተውን ሥርዐት (ፎርማሊቴ) ሳይጠብቅ ሊሸጠው ይችላል የሚል ስምምነት ሁሉ የመያዣው መብት
ከተመዘገበ በኋላ የተደረገ ስምምነት ቢሆንም እንኳ ፈራሽ ነው፡፡

(2) ስለሆነም ለዕዳው መክፈያ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ በኋላ ገንዘብ ጠያቂው የመያዣ መብት ያገኘበትን የማይንቀሳቀስ ንብረት፤ የዕዳው
መክፈያ አድርጎ ባለዕዳው ለገንዘብ ጠያቂው ለመስጠት (ይችላል ብሎ) መስማማት ይችላል፡፡

ቊ 3061፡፡ ክስ ስለ ማቅረብ (1) ሥልጣን፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን አመዘጋገብ፤ ወይም መያዣ የተሰጠበትን የማይንቀሳቀስ ንብረትን ስለ መሸጥ የሚመለከቱትን ጒዳዮች
ሁሉ፤ ለማየት ሥልጣን የተሰጣቸው ይኸው ንብረት በሚገኝበት ቦታ የሚገኙት ፍርድ ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡

ቊ 3062፡፡ (2) መኖሪያ ቦታን ለይቶ ስለ ማስታወቅ፡፡

(1) በማናቸውም ባለጒዳይ ጥያቄ አቅራቢነት በንብረቱ ላይ የመያዣ መብት የተሰጠውና ንብረቱንም በመያዣ ሰጭ የሆነ ሁለቱም ወገኖች
የመኖሪያ ቦታቸውን እነዚህ ፍርድ ቤቶች በሚገኙበት ክፍል ለይቶ ማስታወቅ አለባቸው፡፡

(2) ሕጋዊ የመኖሪያ ቦታቸውን እንዲመርጡ ከተጠየቁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አንድ ወር ድረስ ሳይመርጡ የቀሩ እንደሆነ ዳኞች
የማይንቀሳቀሰውን ንብረት መያዣ የሚመለከቱት ጒዳዮች በሚገባ ከቀረቡላቸው በኋላ የባለጒዳዮቹን ሕጋዊ መኖሪያ ቦታ መርጠው
ለመወሰን ይችላሉ፡፡

ቊ 3063፡፡ (3) (ወኪል) የንብረት ጠባቂ፡፡


እንዲሁም በማናቸውም ባለጒዳይ ጥያቆ አቅራቢነት ስሙና መኖሪያ ቤቱ ላልታወቀ ገንዘብ ጠያቂ ይህ ገንዘብ ጠያቂ በክርክሩ ላይ ራሱ
እንዲኖር በሕጉ ላይ ተመልክቶ እንደሆነና አንድ አስቸኳይ ውሳኔ መስጠት የሚያስፈልግ ሲሆን ዳኞች ለዚህ ገንዘብ ጠያቂ አንድ ንብረት
ጠባቂ ለመሾም ይችላሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ፡፡
ቀደምትነት የብልጫ መብት፡፡
(ሀ) ይህ መብት የሚመለከታቸው ንብረቶች፡፡

ቊ 3064፡፡ ከንብረቱ ጋራ አንድ የሆነና ተጨማሪ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይና ከንብረቱ ጋራ አንድነት ባላቸው ክፍሎች እንዲሁም ተጨማሪ
ክፍሎችንም ጭምር የሚጠቀልል ነው፡፡

(2) በመያዣው ውል ላይ እንደ ንብረቱ ተጨማሪ ሆነው በግልጽ የተመለከቱት ዕቃዎች በዚሁ ዐይነት ይቈጠራሉ፡፡

(3) ተቃራኒ ማስረጃ የማቅረብ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

ቊ 3065፡፡ የሦስተኛ ወገኖች መብት፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ያለው ገንዘብ ጠያቂ የመያዣው መብት ከሚመለከተው ከማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ በተለዩትና
ባለሀብትነታቸውም ለሦስተኛ ወገኖች በተዛወሩት ክፍሎች ወይም ተጨማሪ ዕቃዎች ላይ የባለመያዣነት መብቱን ሊሠራበት አይችልም፡፡

(2) እንደዚህ ያለ ሁኔታ በአጋጠመ ጊዜ መያዣ የሆነው የማይንቀሳቀስ ንብረት ዋጋ ቢቀነስ ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ በዚህ ሕግ አንቀጾች
በታወቁለት መብቶቹ ብቻ ሊገለገልባቸው ይችላል፡፡

ቊ 3066፡፡ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት አዲስ ሥራ ስለ መሥራትና ስለ ማሻሻል፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዝ መብት የመያዣው መብት በሚመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረትና እንዲሁም በዚሁ ንብረት ላይ
የሚሠሩትን አዳዲስ ሥራዎች፤ ተክሎችና ሰብሎች የሚጠቀልል ነው፡፡

ቊ 3067፡፡ (2) የሥራ ተቋራጮችና የዕቃ አቅራቢዎች ልዩ መብት፡፡

(1) ስለሆነም ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተጠቀሰውን በማደስ የማሻሻል ሥራና የሕንጸሥራ የፈጸሙ ሥራ ተቋራጮችና ለሥራው
አስፈላጊ የሆነውን የማደሻውን ዕቃ የሸጡ አትክልት ዘር ወይም የሰብል ፍሬ ያቀረቡ ዕቃ አቅራቢዎች፤ ለፈጸሙት ሥራና ላቀረቡት ዕቃ
ስለሚከፈላቸው ገንዘብ ጒዳይ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት ካላቸው ገንዘብ ጠያቂዎቹ (ብልጫ) ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

(2) በዚህም በክፍያ ክርክር የተነሣ እንደሆነ ዳኞች የድርሻውን ልክ ይወስናሉ፡፡


(3) እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በልዩ ልዩዎች ሥራ ተቋራጮችና በዕቃ አቅራቢዎች መካከል የሚደረገውን የክፍያ ጒዳይ ይወስናሉ፡፡

ቊ 3068፡፡ የቤትና የእርሻ መሬት ኪራይ፡፡

(1) በኪራይ የተሰጠውን የማይንቀሳቀስ ንብረት የሚመለከተው የመያዣ መብት ንብረቱ በፍርድ ከተያዘበት ቀን አንሥቶ የሚታሰበውን
የቤትና የርሻ ኪራይን ይጠቀልላል፡፡

(2) ቤት ተከራዮችና የእርሻ መሬት ተከራዮች መያዣ የተሰጠበት የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍርድ መያዙ ማስታወቂያ ከተሰጣቸው በኋላ
የቤቱን ወይም የመሬቱን ኪራይ ዋጋ ለማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለሀብት በሚጸና አኳኋን ሊከፍሉ አይችሉም፡፡

ቊ 3069፡፡ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የተመደበ ኪሣራ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት፤ ንብረቱ በጠፋ ወይም በተበላሸ ጊዜ ለዚሁ ሊከፈል የሚገባውን አሹራንስ ወይም በአላፊነት
የሚከፈል የኪሣራን ሒሳብ የሚጠቀልል ነው፡፡

(2) እንዲሁም የማይንቀሳቀሰው ንብረት መያዣ ንብረቱ በሚወሰድበት ጊዜ ለባለዕዳው (ለባለሀብቱ) የሚከፈለውን ግምት የሚጠቀልል
ነው፡፡
ቊ 3070፡፡ (2) ስለ አከፋፈሉ የገንዘብ ጠያቂው ፈቃድ፡፡

(1) በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ የመያዣ መብታቸውን ያስመዘገቡት ገንዘብ ጠያቂዎች ሁሉ ካልፈቀዱ በቀር፤ በአሹራንስ በኀላፊነት
ወይም ንብረት በመልቀቅ ምክንያት መያዣውን ለሰጠው ባለዕዳ የሚከፈሉት ኪሣራዎች ሊሰጡት አይቻልም፡፡

(2) ይህን የመሰለ ኪሣራ ሊከፈለው የሚገባው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የሰጠ ባለዕዳ ለተመዘገቡት ገንዘብ ጠያቂዎች የኪሣራውን
ልክና ምክንያት እንዲሁም የሚከፍለውን ሰው ስምና አድራሻ ያስታውቃል፡፡

(3) ለዚህ አከፋፈል ይህ ማስታወቂያ ከተደረገበት ቀን አንሥቶ በሠላሳ ቀን ጊዜ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ ባለመብት የሆኑ
ገንዘብ ጠያቂዎች መቃወማቸውን ያልገለጹ እንደሆነ ኪሣራው ለባለዕዳዎች እንዲከፈል እንደተስማሙ ያህል ይገመታሉ፡፡

ቊ 3071፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረትን መያዣ የሰጠ ባለዕዳ መብት፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረትን የመያዣ መብት ለሰጠ ባለዕዳ የሚከፈለው ኪሣራ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር ያልበለጠ እንደሆነ ለሱው
እንዲከፈለው ለማስገደድ ይችላል፡፡

(2) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት የሰጠ ባለዕዳ በኪሣራው ገንዘብ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት እንደገና ለመሥራት ወይም
ለማደስ የሚያውለው ለመሆኑ ግዴታ የገባ እንደሆነና ተስፋ የሰጠበትንም ነገር ለመፈጸም ማረጋገጫ እንዲሆን በቂ ሆነው የሚገመቱ
ዋስትናዎች ወይም ሌሎች መያዣዎች ያቀረበ እንደሆነ ለኪሣራ የሚከፈለው ገንዘብ እንዲሰጠው ለማስገደድ ይችላል፡፡

(3) በማናቸውም አኳኋን ቢሆንም የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የመያዣ መብት የሰጠ ባለዕዳ ለሱ የሚከፈለውን ኪሣራ ዳኞች በመረጡት
በትእዛዝ ባለአደራ ተይዞ እንዲቀመጥ ለማስገደድ ይችላል፡፡

ቊ 3072፡፡ በስመ ርስቱ ላይ የሚደረግ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ስለ መስጠት፡፡


በስመ ርስት ላይ የሚደግ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ አላባው ባለቀ ጊዜ በሙሉ በርስቱ ላይ የሚጠቀለል ይሆናል፡፡
ቊ 3073፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረትን ዋጋ ስለ ማጓድል፡፡ (1) የባለዕዳው አድራጎት፡፡

(1) ባለዕዳው በራሱ አድራጎት ወይም ቸልተኛነት የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበትን ንብረት ዋጋ እንዲቀነስ ወይም እንዲጎዳ ያደገ
እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂው አዲስ ዋስትና እንዲሰጠው ለማስገደድ ይችላል፡

(2) ለገንዘቡ ተገቢ ሆኖ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ዕዳ ከፋዩ እነዚህን መያዣዎች ያላቀረበ እንደሆነ፤ ለዕዳ መክፈያው ከተወሰነው ቀን
አስቀድሞ ባለገንዘቡ ለዋስትናው በቂ የሆነ ገንዘብ መልሶ እንዲሰጠው ለመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡

ቊ 3074፡፡ ንብረቱን የሚገዛ የሦስተኛ ሰው አድራጎት፡፡


ከባለዕዳው ላይ ንብረቱን በገዛ በሦስተኛ ሰው አድራጎት ወይም ቸልተኛነት የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበት ንብረት ዋጋ የተቀነሰ
ወይም የተጎዳ እንደሆነ የማይንቀሳቀሰው ንብረት መያዣ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ በባለዕዳው ላይ እንዲሠራባቸው ባለፈው ቊጥር
የተመለከቱት መብቶች ይኖሩታል፡፡

ቊ 3075፡፡ ሌሎች ምክንያቶች፡፡


ሌላ ምክንያት ያለበት የዋጋ መቀነስ ወይም ዋጋ ያስቀንሳል ተብሎ የሚያስፈራ ጒዳይ ከባለዕዳው አዲስ ዋስትናዎችን ለመጠየቅ ወይም
መያዣ የተሰጠበትን ዕዳ በከፊልም ሆነ እንዲከፈለው ለመጠየቅ ለባለ ገንዘቡ መብት አይሰጠውም፡፡

(ለ) ቀደምትነት ያላቸው የገንዘብ መጠየቂያ መብቶች፡፡

ቊ 3076፡፡ የተመዘገበ የገንዘብ መጠየቂያ መብት ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡፡


በማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መዝገብ ውስጥ የተመዘገበውን ገንዘቡን ከሌሎች ገንዘብ ጠያቂዎች በፊት በቀደምትነት እንዲከፈለው
የማይንቀሳቀሰው ንብረት መያዣ ለገንዘብ ጠያቂው መድን ነው፡፡

ቊ 3077፡፡ የዋናው ገንዘብ ወለድ፡፡

(1) እንዲሁም በማይንቀሳቀሰው ንብረት መያዣ መዝገብ ውስጥ በተመዘገበው የወለድ መጠን የዋናውን ገንዘብ ወለድ ከሌሎች ገንዘብ
ጠያቂዎች አስቀድሞ ለመክፈል የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ለባለገንዘቡ መድን ነው፡፡

(2) ስለሆነም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ በዚህ መብተ መሠረት ከሁለት ዓመት ለበለጠ ጊዜ ወለዱ
በቀደምትነት እንዲከለው ለመጠየቅ አይችልም፡፡

(3) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት በሚመዘገብበት ጊዜ ወለዱ በቀደምትነት የሚከፈልበት ከሁለት ዓመት ለበለጠ ጊዜ ይሆናል
ተብሎ ሊጻፍ አይቻልም፡፡

ቊ 3078፡፡ አስፈላጊ ወጪዎችና ለአሹራንስ የሚከፈል ዋጋ፡፡


እንዲሁም ባለዕዳው ሊከፍላቸው የሚገባ ሁኖ ሳለ፤ ገንዘብ ጠያቂው ለማይንቀሳቀሰው ንብረት ጥበቃ ያደረጋቸውን አስፈላጊ ወጪዎችና
ለንብረቱ አሹራንስ የከፈላቸውን ዋጋዎች ከሌሎቹ ገንዘብ ጠያቂዎች በፊት በቀደምትነት ለመከፈል ያው የማይንቀሳቀሰው ንብረት መያዣ
መድኑ ነው፡፡

ቊ 3079፡፡ በፍርድ ለማሲያዝ የሚደረጉ የተለመዱ ወጪዎች፡፡


እንዲሁም ገንዘብ ጠያቂው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት መያዣ በፍርድ ለማሲያዝ ያደረጋቸውን ወጪዎች ከሌሎች ባለገንዘናበች በፊት
በቀደምትነት ለመከፈል የማይንቀሳቀሰው ንብረት መድኑ ነው፡፡

ቊ 3080፡፡ ሕጋዊ ወለድ፡፡

(1) ከዚህ በፊት ባሉት አራት ቊጥሮች የተመለከቱት ገንዘቦች፤ የመያዣ መብት የተሰጠበት የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍርድ ከተያዘበት ቀን
አንሥቶ ሕጋዊ የሆነ ወለድን ይሰጣሉ፡፡

(2) በመያዣ የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍርድ ተይዞ ሐራጅ እስከተፈጸመበት ቀን ድረስ ባለው ጊዜ ለሚታሰበው የወለድ ገንዘብ
በመያዣ የተሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት መድኑ ነው፡፡

(ሐ) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት ያስመዘገቡ ብዙዎች ገንዘብ ጠያቂዎች፡፡

ቊ 3081፡፡ መሠረቱ፡፡

(1) ባንድ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ብዙ ገንዘብ ጠያቂዎች የመያዣ መብት አስመዝግበው እንደሆነ የቀደምትነት መብታቸውን
የሚሠሩበት ተራ የሚወሰነው መብታቸውን ያስመዘገቡበትን ቀን በመከተል ነው፡፡

(2) የገንዘብ መጠየቂያ መብታቸው እርግጠኛ የሆነበት ወይም እንዲከፈል ለመጠየቅ የሚቻልበት ቀን በግምት ውስጥ አይገባም፡፡
ቊ 3082፡፡ ባንድ ቀን የተመዘገቡ ገንዘብ ጠያቂዎች፡፡
ባንድ ቀን ውስጥ የተመዘገቡ ገንዘብ ጠያቂዎች በየመጠናቸው ይከፋፈላሉ፡፡
ቊ 3083፡፡ ስለ መተካት፡፡

(1) ማናቸውም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት ያለው ገንዘብ ጠያቂ ከርሱ በፊት ቀደምትነት ያለውን ገንዘብ ጠያቂ አስፈቅዶ
የቀደምትነቱን ተራ ለመውሰድ ይችላል፡፡ በተራ ተከታይ የሆነው ገንዘብ ጠያቂ ባደረገው ጥያቄ መሠረት የመያዣ መብት የተሰጠበትን
የማይንቀሳቀሰውን ንብረት በፍርድ እንዲያዝ አድርጎ እንደሆነ ግን ከርሱ በፊት ተራ የነበረውን ገንዘብ ጠያቂ ማስፈቀድ አስፈላጊው
አይደለም፡፡

(2) እንዲህም በሆነ ጊዜ በቀደምትነት ተራ የሚተካው ገንዘብ ጠያቂ ከርሱ በፊት የነበረው የገንዘብ ጠያቂው የቀደምትነት ተራ ይኖረዋል፡፡
2 የመከታተል መብት፡፡
(ሀ) ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡

ቊ 3084፡፡ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት የመሸጥ የመለወጥ መብት፡፡

(1) በንብረቱ ላይ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት መያዣ የሰጠ ሰው ይኸንኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ለመለወጥ መብት አለው፡፡

(2) ይህን ተቃራኒ የሆነ ማናቸውም የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 3085፡፡ በገንዘብ ጠያቂው ላይ መቃወሚያ ስላለመሆኑ፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት ያለው ባለገንዘብ የንብረቱ የመሸጥ መለወጡ ጽሑፍ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገቦች ከመጻፉ
በፊት የመያዣ መብቱን አስመዝግቦ እንደሆነ ንብረቱን ከገዢው እጅ በፍርድ ሊያስዝ ይችላል፡፡

ቊ 3086፡፡ በፊተኛው ባለዕዳ ላይ ያለው ውጤት፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበት ንብረት መሸጥ መለወጥ በጠቅላላው በፊተኛው ባለዕዳ ግዴታ ላይ አንድም መለዋወጥ
አያጣም፡፡

(2) ስለሆነም ገዢው ዕዳውን እከፍላለሁ ብሎ እንደሆነባለ ገንዘቡ በፊተኛው ባለዕዳው ላይ ያለውን መብት የማይተው መሆኑን በጽሑፍ
ካላስታወቀ በቀር የቀድሞው ባለዕዳ ነጻ ይሆናል፡፡

(3) የተደረገው የመሸጥ የመለወጥ ስምምነት ለገንዘብ ጠያቂው እንዲያውቀው ከተደረገበት ቀን አንሥቶ በአንድ ዓመት ውስጥ
መግለጫው ካልተላከ በቀር ዋጋ የሌለው ይሆናል፡፡

ቊ 3087፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የማይከፋፈል ስለ መሆኑ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የማይከፋፈል ነው፡፡

(2) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ከተሰጠበት ንብረት አንዱ ክፍል የተሸጠ የለወጠ እንደሆነ፤ ወይም ንብረቱ የተከፋፈለ እንደሆነ፤
የንብረቱ እያንዳንዱ ክፍል መያዣ ለተሰጠበት ሙሉ ዕዳ መክፈያ መሆኑ አይቀርለትም፡፡

ቊ 3088፡፡ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ግዙፍ መብትን ስለ ማቋቋም፡፡

(1) በንብረቱ ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት የሰጠ በዚሁ ንብረቱ ላይ በአላባ የመጠቀም፤ የንብረት አገልግሎት፤
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣዎች ወይም ሌሎች ግዙፍ መብቶች ሊያቋቁም ይችላል፡፡

(2) ይህን ተቃራኒ የሆነ ማናቸውም የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡

ቊ 3089፡፡ በገንዘብ ጠያቂው ላይ መቃወሚያ ስለ አለመሆኑ፡፡


(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ያለው ገንዘብ ጠያቂ መብቱን ካስመዘገበበት ቀን በኋላ በማይንቀሳቀሰው ንብረት የተመዘገቡ ግዙፍ
መብቶች መቃወሚያ ሊሆኑት አይችሉም፡፡

(2) እነዚህን ግዙፍ መብቶች እንዳልተቋቋሙ አድርጎ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ሊያሸጥ ይችላል፡፡

(3) ባለግዙፍ መብት የሆነው ሰው የማይንቀሳቀሰው ንብረት በፍርድ እንዲያዝ ተደርጎ እንደሆነ ከሱ በኋላ መብታቸውን ካስመዘገቡት
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ካላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች በፊት በቀደምትነት የመብቱ ዋጋ እንዲከፈለው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(ለ) ገዥ የሆነ የሦስተኛ ወገን ሁኔታ፡፡

ቊ 3090፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍርድ ስለ መያዝ፡፡ (1) እንደ ዋስ ስለመቈጠር፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት የተሰጠበትን ንብረት የገዛ ሰው የመያዣው መብት ከተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ ጋራ ስላለው ግንኙነት
በዚህ ሕግ በጠቅላላው ስለ ውሎች በሚለው አንቀጽ ውስጥ ስለ ዋስ በተሰጡት መብቶች ሊሠራባቸው ይችላል፡፡

ቊ 3091፡፡ (2) ቤቶችን ስለ ማሻሻል ወይም ስለ መሥራት፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት የተሰጠበትን ንብረት የገዛ ሰው ቤት በመሥራት ወይም በማሻሻል ተክል ወይም ሰብል በማድረግ
የዚህን የማይንቀሳቀስ ንብረት ዋጋ እንዲጨመር አድርጎ እንደሆነ የሽያጩን ጽሑፍ በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ካስመዘገበበት ቀን
በኋላ ንብረቱ እንዲያገኝ ያደረገውን የዋጋ ብልጫ ከንብረቱ ሽያጭ ዋጋ ላይ እንዲቀንስ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ገዢው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ከመግዛቱ በፊት በንብረቱ ላይ የነበሩት የንብረት አገልግሎትና ግዙፍ መብቶች እንደገና
ሊሠራባቸው ያልተቻለ እንደሆነ ኪሣራ እንዲያገኝ ያደርጉለታል፡፡

ቊ 3092፡፡ (3) የማይንቀሳቀሰው ንብረት መጥፋት ወይም መበላሸት፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት የተሰጠበትን ንብረት የገዛ ሰው በጠቅላላው ስለ ንብረቱ መጥፋት ወይም መበላሸት
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት ላላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች አላፊ አይሆንም፡፡

(2) ለዚህ መጥፋትና ለዚህ መበላሸት አላፊ የሚሆነው በሱ አድራጎት ወይም ቸልተኛነቱ የሆነ እንደሆነና ይኸውም የሆነው ንብረቱን
በፍርድ የማስያዝ ሥነ ሥርዐት የተጀመረና ማስታወቂያ የተላከበት እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 3093፡፡ (4) አላባ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት የተሰጠበትን ንብረት የገዛ ሰው ንብረቱ በፍርድ ከመያዙ በፊት ከንብረቱ ላገኘው አላባ መጠየቅ
የለበትም፡፡

(2) ገዢው ንብረቱ ከእጁ እንዳለ በፍርድ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ የአላባው ባለሀብት መሆኑ ይቀራል፡፡

ቊ 3094፡፡ (5) በመድኑ ላይ ስለሚቀርበው ክስ፡፡

(1) የማየንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት የተሰጠበትን ንብረት የገዛ (ያገኘ) ሰው ይህ ንብረት ከእጁ ባለ ጊዜ በፍርድ የተያዘበት እንደሆነ
ንብረቱን ባስተላለፈለት ሰው ላይ በመድንነቱ ላይ ክስ ሊያቀርብበት ይችላል፡፡

(2) ንብረቱን ያገኘው ሰው ያለ ዋጋ ቢሆንም፤ እንኳ ይህ ክስ የማቅረብ መብት ይኖረዋል፡፡

(3) በመሸጥ በመለወጥ ውል ውስጥ በጽሑፍ ግልጽ በሆነ የውል ቃል ካልሆነ በቀር ክሱ ሊወገድ አይቻልም፡፡

ቊ 3095፡፡ (6) መተካት፡፡

(1) ከእጁ ንብረቱ የተያዘበት የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት የተሰጠበትን ንብረት ያገኘ ሰው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት
በተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ መብቶች የሚተካ ይሆናል፡፡
(2) ስለሆነም ከባለዕዳው ወይም ከባለዕዳው ዋስ ላይ ለዕዳው መድን የሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት በገዙት በ 3 ኛ ወገኖች ላይ
በተባለው መተካት ሊሠራባቸው አይችልም፡፡

ቊ 3096፡፡ (7) የትእዛዝ ባለአደራ ስለ መምረጥ፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ መብት የተሰጠበትን ንብረት የገዛ ያገኘ ሰው የመያዣ ዋስትና የተሰጠባቸውን ዕዳዎች እሱ ከራሱ
ለመክፈል በማይገደድበት ጊዜ ንብረቱን በፍርድ ለማስያዝ ከሚደረገው ሥነ ሥርዐት ውጭ እንዲሆን ለመጠየቅ ይቻላል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ የመያዙ ሥነ ሥርዐት የሚፈጸምበት አንድ ባለአደራ ይመርጣል ወይም ዳኞቹ እንዲመርጡ ይጠይቃል፡፡

(3) የትእዛዝ ባለአደራው፤ የመያዙን ውሳኔ ለመስጠት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት ባለበት ስፍራ ነዋሪ መሆን ወይም በዚሁ ስፍራ
መኖሪያውን መሰየም አለበት፡፡

ቊ 3097፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት ላላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች ፈቅዶ ገንዘብ ስለ መክፈል፡፡

(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበት ንብረትን ሀብትነት ያገኘ ሰው በዚሁ ንብረት ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት
ካለው ሰው ተስማምቶ ወይም ንብረቱ በዚሁ ባለገንዘብ ጥያቄ በፍርድ እንዲያዝ ተደርጎ እንደሆነ ገንዘብ ጠያቂው ባይስማማም ገንዘቡን
ለገንዘብ ጠያቂው ሊከፍለው ይችላል፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ መብትህ ተቀላቅሏል የማለት መቃወሚያ ሊቀርብበት ሳይቻል ገንዘቡ በተከፈለው ገንዘብ ጠያቂ ምትክ
በማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት ይገባል፡፡

ቊ 3098፡፡ ከመያዣነት ስለ ማስለቀቅ፡፡ (1) የሚቻል ስለ መሆኑ፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበትን ንብረት ያገኘ ሰው እሱ ራሱ መያዣ የተሰጠባቸውን ዕዳዎች ለመክፈል የሚገደድ ካልሆነ በቀር
መያዣ የተሰጠባቸውን ዕዳዎች ከፍሎ ንብረቱን ነጻ ለማድረግ ይችላል፡፡

ቊ 3099፡፡ (2) ከመያዣነት ነጻ ለማድረግ ሐሳብ ስለ ማቅረብ፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበትን ንብረት መያዣነቱን ነፃ ለማድረግ የሚፈልግ ንብረቱን ያገኘ ሰው የመያዣ መብታቸውን
ላስመዘገቡት ገንዘብ ጠያቂዎችና እንዲሁም መብቱን ላስተላለፈለት ባለሀብት ቀጥሎ ያለው ቃል የተዘረዘረበትን ጽሑፍ ያስታውቃቸዋል፡፡

(ሀ) የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘበትን የማስረጃ ጽሑፍ የማስረጃውን ጽሑፍ ያገኘበትን ቀንና ይህንኑም በማይንቀሳቀስ ንብረት
መዝገብ ያስመዘገበበትን ቀን፤

(ለ) እርሱ ያገኘውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ተገቢ የሆነው መግለጫ ቃል በተለይም ይህ የተባለው ንብረት
የሚገኝበት ቦታና በርስት መዝገብ ውስጥ ያለውን ቊጥር የሚያመለክት (መግለጫ) ቃል፤

(ሐ) ንብረቱ የተገዛበትን ዋጋ ወይም ንብረቱን ያገኘው በችሮታ ስም የሆነ እንደሆነ ለዚህ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የሚሰጠውን ግምት፤

(መ) ይህንኑ ዋጋ ወይም ግምት ለመክፈል የሚያቀርበውን ጥያቄ፤

(ሠ) በንብረቱ ላይ ተሰጥተው የተመዘገቡትን የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብቶች ዝርዝር እንዲሁም የተመዘገቡበትን ቀን፤

(ረ) ይህ የማይንቀሳቀስ ንብረት በፍርድ የሚያዝበት ጊዜ ውሳኔ ለመስጠት የሚችል ባለሥልጣን የሆነው ፍርድ ቤት በሚቀመጥበት ስፍራ
ይህን የተባለውን ንብረት ያገኘውን ሰው የመኖሪያ ቦታ፡፡

ቊ 3100፡፡ (3) ለመክፈል የሚቀርበው (ጥያቄ) ቃል የማይመለስ ስለ መሆኑ፡፡

(1) ከመያዣነት ነጻ ለማድረግ ለመክፈል ቃል የሰጠውን ሰው እስከ ስሳ ቀን ድረስ የሰጠው ቃል ተገዳጅ ያደርገዋል፡፡

(2) ጥያቄውን ካቀረበላቸው ሰዎች ያቀረበውን ጥያቄ ለመመለስ አይችልም፡፡

ቊ 3101፡፡ (4) የቀረበውን ጥያቄ ስለ መቀበል፡፡


(1) መያዣን ስለ ማስለቀቅ የሚቀርበውን ጥያቄ በስሳ ቀን ውስጥ አንቀበለውም ሲሉ ያልመለሱት እንደሆነ፤ ጥያቄው የቀረበላቸው ገንዘብ
ጠያቂዎች ሁሉ እንደተቀበሉ ይገመታሉ (ይቈጠራሉ)፡፡

(2) እንዲህ በሆነ ጊዜ ንብረቱን ያገኘው ሰው ለመክፈል ያቀረበውን ገንዘብ ጠያቂዎቹ እንደተራቸው ይካፈሉታል፡፡

ቊ 3102፡፡ (5) መያዣን ስለ ማስለቀቅ የሚቀርበውን ጥያቄ አለመቀበል፡፡

(1) አንድ ገንዘብ ጠያቂ፤ ባለሀብቱ መያዣን ስለ ማስለቀቅ ያቀረበለትን ጥያቄ አልቀበልም ያለ እንደሆነ፤ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሐራጅ
እንዲሸጥ ይደረጋል፡፡

(2) መያዣን ስለ ማስለቀቅ የቀረበውን ጥያቄ አንቀበልም የሚሉ ገንዘብ ጠያቂዎች በሐራጅ ለማሸጥ የሚደረገውን ወጪ አስቀድመው
ለመክፈል ይገደዳሉ፡፡

ቊ 3103፡፡ (6) በሐራጅ የመሸጥ ወጪ፡፡

(1) ይህን የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘ ሰው ለመክፈል ካቀረበው ገንዘብ ልክ በልጦ የተባለው ንብረት ከመቶ ዐሥር በላይ ብልጫ
በማድረግ ወሳጅ ያገኘ እንደሆነ፤ ለሐራጅ የወጣው ገንዘብ ንብረቱን ባገኘው ሰው ላይ ይታሰብበታል፡፡

(2) እንደዚህ ያልሆነ እንደሆነ ግን፤ ኪሣራው መያዣውን ስለ ማስለቀቅ የቀረበውን ጥያቄ አንቀበልም ባሉት ገንዘብ ጠያቂዎች ይታሰባል፡፡

ቊ 3104፡፡ (7) መያዣን የማስለቀቅ መብት ስለ መቅረት፡፡


የተባለው ንብረት በፍርድ የመያዣ ሥነ ሥርዐት በተጀመረና ይኸውም በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ መያዣ ጽሕፈት ቤት ተመዝግቦ
እንደሆነ ንብረቱን ያገኘው ሰው መያዣ የነበረውን መብት ለማስለቀቅ ያለው መብቱ ይቀርበታል፡፡

(ሐ) የንብረት ዋስትናን የሰጠ ሰውን ውል የሚመለከቱ ልዩ ድንጋጌዎች፡፡


ቊ 3105፡፡ የሕሊና ግምት፡፡
ማንም ሰው ሌላ ሰው ለሚከፍለው ዕዳ በንብረቱ ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የሰጠ እንደሆነ፤ በሌሎቹ ንብረቶቹ ላይ ግዴታ
ገብቷል ተብሎ አይገመትም፡፡
ቊ 3106፡፡ ንብረቱን አሲዞ ዋስ ስለሆነ ሰው ሁኔታ፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት የሁለቱ ቊጥሮች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ንብረት አሲዞ ዋስ የሚሆን ሰው መያዣ የተሰጠበትን የማይንቀሳቀስ
ንብረት እንደገዛ ሦስተኛ ወገን ይቈጠራል፡፡
ቊ 3107፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት መጥፋት ወይም መበላሸት፡፡
(1) ግዙፍ ዋስትና የሰጠው ሰው በራሱ አድራጎት ወይም ቸልተኛነት የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበትን ንብረት ዋጋ እንዲቀነስ
ወይም እንዲጎዳ ያደረገ እንደሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ አዲስ ዋስትና እንዲሰጠው ግዙፍ ዋስትና ሰጥቶት
የነበረውን ሰው ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠበት ንብረት ዋጋ ንብረቱን ግዙፍ ዋስትና አድርጎ ከሰጠው ሰው በገዛ 3 ኛ ወገን
አድራጎት ወይም ቸልተኛነት የተቀነሰ ወይም የተጎዳ እንደሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ ይኸውም
መብት ይኖረዋል፡፡
ቊ 3108፡፡ ሌሎች ልዩነቶች፡፡
(1) ንብረቱን አሲዞ ዋስ የሆነ የማይንቀሳቀሰው ንብረት ከእጅ የተያዘበት እንደሆነ፤ ቀድሞ ይህን ንብረት ባስተላለፈለት ሰው ላይ
ማናቸውንም ጥያቄ ሊያቀርብ አይችልም፡፡

(2) የመያዙ ሥነ ሥርዐት በሚፈጸምበትም ጊዜ ከነገሩ ውጭ ልሁን ብሎ ሊጠይቅ አይችልም፡፡

(3) እንዲሁም በንብረት ላይ የተሰጠውን የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ዕዳ ከፍሎ መያዣውን ለማስቀረት አይችልም፡፡
ክፍል 3፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ስለ መቅረት፡፡
ቊ 3109፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተመዘገበበት ጽሑፍ በተሰረዘ ጊዜ ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) ያሰራረዙ አኳኋን በዚህ ሕግ ስለ ርስት መዝገብ በሚለው አንቀጽ ተደንግጓል፡፡


ቊ 3110፡፡ የመሰረዝ ምክንያቶች፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ ጽሑፍ እንዲሰረዝ አግባብ ያለው ማናቸውም ባለጕዳይ ለመጠየቅ የሚችለው፡-

(ሀ) መያዣው የሚመለከተው የገንዘብ መጠየቂያ መብት ቀሪ ሲሆን፤

(ለ) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ የመያዣውን መብት ይቅርብኝ ብሎ ሲተው፤

(ሐ) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መብት የተሰጠበት ንብረት በፍትሕ በሐራጅ ተሸጦ ዋጋው ለባለመብቶቹ የተከፈለ ሲሆን፤

(መ) መያዣው እንዲለቀቅ ጥያቄ በቀረበበት ጊዜ የቀረበውን ገንዘብ፤ ገንዘብ ጠያቂዎቹ ተቀብለው በባለመብቶቹ መካከል ገንዘቡን
የተከፋፈሉ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 3111፡፡ በማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣነት ስለሚሰጥ የአላባ መብት፡፡
(1) በማይንቀሳቀስ ንብረት የአላባው መብት ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ተቋቁሞ እንደሆነ፤ አላባው በሚቀርበት ጊዜ አግባብ ያለው
ማናቸውም ባለጕዳይ የመያዣው መብት እንዲሰረዝ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የተሰጠውን ገንዘብ ጠያቂ በመጉዳት የአላባ ጥቅም ተቀባዩ የአላባውን መብት በሚጸና አኳኋን ለመተው
አይችልም፡፡
ቊ 3112፡፡ የመያዣውን መብት ይቅርብኝ ብሎ ስለ መተው፡፡
(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብትን የባለገንዘቡ ይቅርብኝ ብሎ መተው፤ በተገለጸ ዐይነትና በጽሑፍ ካልተደረገ በቀር ዋጋ
የለውም፡፡
(2) ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር የመያዣውን መብት የባለገንዘቡ ይቅርብኝ ማለት የሚጠይቀውን ገንዘብ እንደ ተወ
አያስቈጥረውም፡፡
ቊ 3113፡፡ በባለመያዣ ገንዘብ ጠያቂ አጥፊነት ምክንያት መተካት ስለማይችል፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ የሚመለከተው የባለዕዳው ያልሆነውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ሆኖ በገንዘብ ጠያቂው ጥፋት
የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብት በዚሁ ገንዘብ ጠያቂ መብቶች ለመተካት ያልቻለ እንደሆነ የመያዣው መብት እንዲሰረዝ ለመጠየቅ
ይቻላል፡፡
ቊ 3114፡፡ የመሰረዝ ምክንያት፡፡
(1) በዳኞች ትእዛዝ ካልሆነ በቀር የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት ሊሰረዝ አይችልም፡፡

(2) የማይንቀሳቀስ ንብረት መብት ያለው ገንዘን ጠያቂ መብቱ እንዲሰረዝ መፍቀዱን በጽሑፍ ሰጥቶ እንደሆነ ዳኞች መሰረዙን ማዘዝ
አለባቸው፡፡

(3) ገንዘብ ጠያቂው፤ በማይገባ መሰረዝን ያልፈጸመ እንደሆነ በዚህ ነገር በአላፊነት የሚያስጠይቀው ይሆናል፡፡
ቊ 3115፡፡ የመሰረዙ ውጤቶች፡፡
(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት መሰረዝ ከዚህ መብት በኋላ በተራ ለተመዘገቡት ገንዘብ ጠያቂዎች የሚጠቅም ይሆናል፡፡
(2) ባለሀብቱ በተሰረዘው መያዣ ቦታና ስፍራ አዲስ የመያዣ መብት ለማቋቋም አይችልም፡፡
ቊ 3116፡፡ ያለ መብት የተደረገው መሰረዝ፡፡
(1) በማይገባ የተደረገም ቢሆን፤ የመያዣ መብት መሰረዝ፤ በማናቸውም አንዳች ሁኔታ ሊሻር አይችልም፡፡

(2) በማይገባ የተሰረዘው የመያዣ መብት ይጻፍና እንደገና ተመዝግቦ የሚጸናውም ከዚሁ ከተመዘገበበት ቀን አንሥቶ ነው፡፡

(3) በማይገባ በተፈጸመው መሰረዝ አላፊዎች በሆኑ ሰዎች ላይ ክስን የማቅረቡ መብቶች የተጠበቁ ናቸው፡፡
ክፍል 4፡፡
ስለ ወለድ አግድ ‹‹አንቲክሬዝ፡፡››
ቊ 3117፡፡ ትርጓሜ፡፡
ወለድ አግድ ማለት አንድ ባለዕዳ ግዴታውን ለመፈጸም ማረጋገጫ በማድረግ ለገንዘብ ጠያቂው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ለማስረከብ
የሚገደድበት ውል ነው፡፡

ቊ 3118፡፡ የወለድ የግድ መቋቋም፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን መቋቋም የሚመለከቱት የዚህ ያሁኑ አንቀጽ ድንጋጌዎች የሚከተለው ቊጥር የተጠበቀ ሆኖ ስለ ወለድ
አግድ ውል አፈጻጸም ላይም ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 3119፡፡ (2) ልዩ የሆኑ ደንቦች፡፡

(1) ወለድ አግድ በውል ካልሆነ በቀር ሊቋቋም አይችልም፡፡

(2) ለአምጪው ወይም በትእዛዝ ለሚተላለፍ የገንዘብ መጠየቂያ መብት የወለድ አግድ ውል ለማድረግ አይቻልም፡፡

(3) የማይንቀሳቀስ ንብረት ሌጣ ርስት ባለሀብት የሆነ ሰው ወለድ አግድ ሊያቋቁም አይችልም፡፡
ቊ 3120፡፡ በሁለቱ ወገኖች ተዋዋዮች መካከል ስላለው ግንኙነት፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ቊጥሮች የተጠበቁ ሆነው፤ አከራይንና ተከራይን ወይም ገበሬን የሚያገናኙትን ነገሮች በሚመለከቱት ደንቦች በወለድ
አግድ የተዋዋሉት ሁለቱ ወገኖች አንዱ ለአንደኛው ባላቸው መብትና ግዴታ የሚመሩ ይሆናሉ፡፡
ቊ 3121፡፡ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ስለ ማስረከብ፡፡
(1) (የተባለውን) ወለድ አግዱን ያቋቋመው (የተዋዋለው) ሰው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ከተጨማሪዎቹ ነገሮች ጋራ በወለድ አግድ
ለሚይዘው ሰው ወይም በውሉ ለተመለከተው ሰው ማስረከብ አለበት፡፡

(2) የተባለው ማስረከብ፤ ሳይፈጸም እስከ ቈየበት ድረስ ወይም የማይንቀሳቀሰው ንብረት ወደ ባለዕዳው እጅ የገባ እንደሆነ ወለድ አግዱ
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውጤት ይኖረዋል፡፡
ቊ 3122፡፡ የንብረቱ ጕድለቶች መድንነት፡፡
(1) የማይንቀሳቀሰው ንብረት ባለበት ሁኔታ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

(2) ንብረቱን በወለድ አግድ የሚሰጠው ሰው በዚህ በንብረት በሚገኙት ጕድለቶች ምክንያት መድን እንዲሆን አይገደድም፡፡

(3) ነገር ግን ኀላፊነት የሚያገኘው ውሉ ሲደረግ እነዚህ ጕድለቶች መኖራቸውን እያወቀ ሳይገልጻቸው ቀርቶ እነዚህ የተባለው ንብረት
ጕድለቶች ይህን የማይንቀሳቀስ ንብረት እጅ ላደረገው ሰው ወይም አብረውት ለሚኖሩ ሰዎች ወይም ለሠራተኞቹ ሕይወት ወይም ጤና፤
ከፍ ያለ የአደጋ አሥጊነት ያላቸው እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
ቊ 3123፡፡ ስለ ማደስ ሥራ፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረቱን በወለድ አግድ የሚሰጥ ሰው በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ አንዳች የማደስን ሥራ ለማድረግ አይገደድም፡፡
ቊ 3124፡፡ ስለ ዕዳው ወለድ፡፡
(1) በወለድ አግድ የማይንቀሳቀስ ንብረትን የያዘ ገንዘብ ጠያቂ ንብረቱን በወለድ አግድ ለሰጠው ሰው አንዳች ኪራይ ወይም የርሻ ኪራይ
አይከፍልም፡፡

(2) በተባለው ንብረት መገልገሉና ከዚህ ንብረት የሚያገኛቸው ፍሬዎችና ጥቅሞች ለሚጠየቀው ለገንዘብ ወለድ ናቸው፡፡

(3) ከዚህ ከሚገለገልበትና ከሚጠቀምበት ነገር በላይ ወለድን የሚፈቅድለት የውል ቃል ፈራሽ ነው፡፡
ቊ 3125፡፡ በኪራይ የተሰጡትን ቦታዎች ስለ ማደርጀት፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት በወለድ አግድ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ በኪራይ የተሰጡትን ቦታዎች ለማዘጋጀት አይገደድም፡፡
ቊ 3126፡፡ በወለድ አግድ ስለሚሰጥ መሬት፡፡
ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር፤ በወለድ አግድ የተሰጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት መሬት እንደሆነ የተባለው መሬት ጥቅም
እንዲሰጥ የማድረግ መሪነት ንብረቱ በወለድ አግድ ለተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ ነው፡፡
ቊ 3127፡፡ የመብት ማስተላለፍ፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት በወለድ አግድ የሰጠው ሰው ሳይፈቅድ ወለድ አግድ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂው የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ወይም
መብቱን ለሌላ ሦስተኛ ሰው ለማስተላለፍ አይችልም፡፡
ቊ 3128፡፡ አንደኛው ወገን ብቻ ወለድ አግዱን ስለ መሰረዙ፡፡
(1) ወለድ አግድ የተሰጠው ገንዘብ ጠያቂ በማናቸውም ጊዜ የወለድ አግድ መብቱን ለመተው ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ተቃራኒ የሚሆን የውል ቃል ከሌለ በቀር የተባለው ወለድ አግድ የተቋቋመበትን ግዴታ በመፈጸም ባለዕዳው በማናቸውም
ጊዜ ወለድ አግዱ እንዲቀር ለማድረግ ይችላል፡፡
ቊ 3129፡፡ ወለድ አግድ በተሰጠው ገንዘብ ጠያቂውና በሌሎች ሦስተኛ ወገኖች መካከል ስላለው ግንኙነቶች፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ አመዘጋገብና የመያዣውንም ውጤቶች የሚመለከቱት የዚህ አንቀጽ ደንቦች በወለድ አግድ ውልም ላይ
ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡

ቊ 3130፡፡ የወለድ አግድ (የአንቲክሬዝ) መሰረዝ፡፡


እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት መቅረትንና መሰረዝን የሚመለከቱት የዚህ አንቀጽ ደንቦች በወለድ አግድም ላይ፤
ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ ዐሥራ ዘጠኝ፡፡


የአስተዳደር ክፍል መሥሪያ ቤቶች (አድሚኒስትራሲዮኖች) የሚያደርጓቸው ውሎች፡፡

ምዕራፍ 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች
ቊ 3131፡፡ የአስተዳደር ክፍል መሥሪያ ቤቶች በሚያደርጓቸው ውሎች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ደንቦች፡፡
(1) መንግሥት፤ ወይም ሌሎች የአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች የሚዋዋሏቸው ውሎች ስለ ውሎች በጠቅላላውና ስለ ልዩ ልዩ ውሎች
የተሰጡት የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች በጠቅላላው ይጸኑባቸዋል፡፡

(2) ውሉ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውል ጠባይ ያለው በሆነ ጊዜ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች ከዚህ በላይ፤ የተባሉትን ደንቦች የሚያሟሉ
ወይም በነሱ ፈንታ የሚተኩ ይሆናሉ፡፡

ቊ 3132፡፡ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውሎች፡፡

አንድ ውል እንዳስተዳደር መሥሪያ ቤት ውል ሆኖ የሚቈጠረው፤


(ሀ) ሕግ ወይም ተዋዋዮቹ ግልጽ በሆነ ቃል የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውል ነው ያሉት ሲሆን፤

(ለ) ውሉ ከሕዝብ አገልግሎት ሥራ ጋራ የተያያዘና ለሥራውም አፈጻጸም የተዋዋዩን የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱን ሥራ ተካፋይነት
ሳይቋረጥ የሚጠይቅ ሲሆን፤

(ሐ) በውሉ ውስጥ ለጠቅላላ ጥቅም አስቸኳይ በመሆናቸው ብቻና የግል ሰዎች በሚያደርጓቸው ውሎች ውስጥ የማይገኙ አንድ ወይም
ብዙ ውለታዎች ያሉበት ሲሆን ነው፡፡

ቊ 3133፡፡ ደንቡ ባንዳንድ ማኅበሮች ላይ የሚጸና ስለ መሆኑ፡፡

ከሕዝብ ገንዘብ ለማግኘት ጥሪ የሚያደርጉ ወይም አክሲዮኖቸውን ወይም የግዴታ ወረቀታቸውን ለሕዝብ የሚሸጡ የንግድ ማኅበሮችን
ውል በሚፈራረሙበት ጊዜ ለአስተዳደር መሥሪያ ቤት በሕግ የተመደቡትን ሥነ ሥርዐትና ፎርሞች እንዲከተሉ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት
ለማስገደድ ይችላል፡፡

ክፍል 1፡፡
ስለ ውሎች ሥርዐት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ፈቃድን ስለ ማስጠት፡፡
ቊ 3134፡፡ የመቀበሉ ፎርም፡፡

(1) በአስተዳደር ሕግ ወይም ደንብ የተመለከተ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር፤ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውሉን ተቀብሎታል የሚባለው
ግልጽ በሆነ አኳኋን መቀበሉን ሲያስታውቅ ነው፡፡

(2) የክፍሉ ባለሥልጣን ስለ አንድ ውል ማጽደቅ ጕዳይ ዝም ማለቱ ግልጽ የሆነ ድንጋጌ ከሌለ ውሉን እንደ አጸደቀው የሚያስገምት
አይደለም፡፡

(3) ከዚህ በላይ ባሉት ኀይለ ቃሎች የተመለከቱት ድንጋጌዎች አንድ ውል ለማራዘም ወይም ያንድ ውል ቃል ለመለወጥ በሚመለከቱት
ጕዳይ ላይ ተፈጻሚዎች ናቸው፡፡
ቊ 3135፡፡ ለአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ጠቅላላ ሁኔታዎች (ግዴታዎች) (1) የውሎቹ አጻጻፍ፡፡

ሥራዎች የሚፈጸሙባቸውን አኳኋን የሚያመለክቱ ለዐይነት የሆኑ ደብተሮችን (ከዬደሻርዥቲፕ) ጠቅላላ ውለታዎችንና ደንቦችን
የሚያመለክቱ ደብተሮችን፤ አጠቃላይ የሆኑ ውሳኔዎች ያሉባቸውን ደብተሮች፤ ሥራው የሆነው እያንዳንዱ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት
ሊያዘጋጃቸውና በሚኒስቴሩ ትእዛዝ ሥራዎቹ የሚፈጸሙት በነዚህ መሠረት ነው፡፡ ተብሎ ሊወሰን ይቻላል፡፡

ቊ 3136፡፡ (2) ትርጓሜ፡፡

(1) ሥራዎቹ የሚፈጸሙባቸውን አኳኋን የሚያመለክት ለዐይነት የሆነው ደብተር ለሕዝብ አገልግሎት ኮንሴሲዮኖች ለሥራው አፈጻጸም
መሪ እንዲሆን አስቀድሞና በጠቅላላ አኳኋን የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ያዘጋጀው ነው፡፡

(2) ጠቅላላ ውለታዎችን ደንቦችን የሚያመለክቱት ደብተሮች፤ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት በሚሰጣቸው የሥራ ውሎች ወይም በአንዳንድ
ዐይነት የሥራ ውሎች ላይ ሁሉ ተፈጻሚ የሚሆኑትን ደንቦች የሚወስኑ ናቸው፡፡

(3) አጠቃላይ የሆኑትን ውሳኔዎች የያዙት ደብተሮች አንድ ዐይነት የሆኑ ሥራዎች ወይም የዕቃ ማቅረብን በሚመለከቱ ጕዳዮች ላይ
በቴክኒክ በኩል በውሎቹ ላይ ሁሉ የሚፈጸሙትን ደንቦች የሚወስኑ ናቸው፡፡

ቊ 3137፡፡ የደብተሮቹ ውጤት፡፡ (1) ውሉን ስለ መፈረም፡፡

(1) ለውሉ አፈራረም የአስተዳደር መሥሪያ ቤት መከተል ስለ አለበት ጕዳይ በሚመለከተው ረገድ፤ ለሥራዎቹ ዕጩ የሆኑት የግል ሰዎችና
በተለየም ሥራው በጨረታ በተሰጠ ጊዜ በጨረታው ተካፋይ የሆኑት ሰዎች ጠቅላላ ውለታዎችንና ደንቦችን በሚመለከተው ደብተር
ውስጥ ያለውን ደንብ ሊጠቅሱ ይችላሉ፡፡

ቊ 3138፡፡ (2) በውሉ ውስጥ የሚገኘው ቃል፡፡

(1) ሥራዎች የሚፈጸሙባቸውን አኳኋን የሚያመለከተው ደብተር፤ ወይም ጠቅላላ ውለታዎችና ደንቦች ያሉበት ደብተር አጠቃላይ
የሆኑት ውሳኔዎች ያሉበት ደብተር አንድ ውል ሲደረግ ወደ እነሱ የሚመራ በግልጽ የተጻፈ ቃል ከሌለበት በቀር ስለ ውሉ አተረጓጐም
ወይም በውሉ ውስጥ ስላለው ቃልና ስለ ውሉ አፈጻጸም በነዚህ ደብተሮች ውስጥ ያለው ደንብ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

(2) ስለ አንድ ኮንሴሲዮን ወይም ስለ አንድ የተወሰነ ሥራ ሥራዎቹ የሚፈጸሙባቸውን አኳኋን የሚያመለክተው ልዩ ደብተር የሌሎቹን
ደብተሮች ድንጋጌዎች ላይከተል ይችላል፡፡

ቊ 3139፡፡ በደብተሩ ውስጥ ያለውን ስለ መለዋወጥ፡፡


(1) የተዋዋዮቹ መብቶትና ግዴታዎች የተወሰኑት ሥራ የሚፈጸምበትን አኳኋን የሚመለከተውን አንድ ደብተር ወይም ጠቅላላ
ውለታዎችንና ደንቦችን ወይም አጠቃላይ ውሳኔዎች ያሉበትን ደብተር በመጥቀስ የሆነ እንደሆነ፤ ውሉ በተፈረመበት ጊዜ ደብተሩ ተጽፎ
የነበረበትን አኳኋን መመልከት ያስፈልጋል፡፡

(2) የውሉ ስምምነት ከተደረገ በኋላ የደብተሩ ቃል ቢለዋወጥ የተዋዋዮቹን መብቶችና ግዴታዎች የሚነካ አይደለም፡፡

ቊ 3140፡፡ ለአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት የሚፈቀድ የገንዘብ ወጪ፡፡

(1) ለአንድ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት የባጀት ባለሥልጣኖች የሚፈቅዱለት የገንዘብ ወጪ በመፈቀዱ ብቻ ገንዘቡ ሥራ ላይ እንዲውል
ለማስደረግ ለግል ሰዎች መብት አይሰጣቸውም፡፡

(2) ውሉን ለመፈራረም ፈቃድ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ለአስተዳደር መሥሪያ ቤት አንድ ሥራ እንዲያሠራ የተሰጠው ፈቃድ ውሉን
እንዲፈራረም ፈቃድ እንደተሰጠው ሆኖ አይቈጠርም፡፡

ቊ 3141፡፡ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ውል ለማድረግ ስላለው ነጻነት፡፡

(1) አንድ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውል እንዲዋዋል የተሰጠው ፈቃድ ውሉን እንዲፈራረም አያስገድደውም፡፡

(2) ውል እንዲዋዋል የተሰጠው ፈቃድ የአስተዳደሩን መሥሪያ ቤት ውል ለመዋዋል እንዲችል ብቻ የሚያደርግ ነው፡፡

ቊ 3142፡፡ ገንዘብ አለመኖር፡፡

ሥራዎቹን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉት ገንዘቦች ያልተሰጡት ቢሆንም እንኳ በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት
የተዋዋለው ውል የጸና ነው፡፡

ቊ 3143፡፡ ለመዋዋል ያልተፈቀደለት ያስተዳደር መሥሪያ ቤት፡፡

(1) በአስተዳደር ሕጎች ወይም ደንቦች መሠረት ውል ለመዋዋል ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ሆኖ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ፈቃድ ሳይቀበል
ውሉን የፈረመ እንደሆነ ውሉ ፈራሽ ነው፡፡

(2) የውሉ ዓላማ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚያስከትለውን ፈራሽነት ስለ ውሎች በጠቅላላው በተባለው አንቀጽ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ከዚህ
በላይ ያለው ኀይለ ቃል በሚመለከተው የውል መፍረስ ጕዳይ ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 3144፡፡ ውሉን ስለ ማጽደቅ፡፡


(1) ውሉ እንዲረጋ ከተፈረመ በኋላ ባለሥልጣን እንዲያጸድቀው አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ይህ የማጽደቅ ተግባር እስከተፈጸመ ድረስ ውሉ
የመጨረሻ አስገዳጅነት አያገኝም፡፡

(2) ውሉን የተዋዋለው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውሉ እንዲጸድቅ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑትን አሠራሮች ሁሉ መፈጸም አለበት፡፡

(3) ይህን የውል ማጽደቂያ ፈቃድ የሚያሰናክል ወይም የሚያውክ አሠራር መፈጸም አይገባውም፡፡

ቊ 3145፡፡ የዘገየ የውል ማጽደቅ፡፡

ከአስተዳደር መሥሪያ ቤት ጋራ አንድ ውል የተዋዋለ ሰው ያደረገው ውል እስከ ስድስት ወር ድረስ ወይም በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል
እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ የማጽደቁ ነገር ያልተፈጸመ እንደሆነ ለተዋዋዩ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት አንድ ማስታወቂያ በመስጠት ብቻ ከውሉ
ግዴታዎች ውጭ ለመሆን ይችላል፡፡

ቊ 3146፡፡ ውሉ ፍጻሜ ሳያገኝ ሲቀር የሚደርስ አላፊነት፡፡

(1) የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ውሉን ሳይፈራረም የቀረ እንደሆነ፤ ውሉ ከመፈረሙ በፊት በተደረገው ንግግር ባሳየው ሁኔታ ምክንያት
በአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ጥፋት ተዋዋዩ ውሉ ይፈጸማል በማለት ላደረጋቸው ወጪዎች ኪሣራ መክፈል አለበት፡፡

(2) የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት አንዳች ጥፋት ባያደርግም እንኳ ከተዋዋዩ ሥራ ተቋራጭ ጋራ ባደረገው የውል ቃል ድርድር መሠረት
ተዋዋዩ ለሚፈጽመው ሥራ ጥናት አድርጎ፤ ፕላን አዘጋጅቶ ሥራውን ጀምሮ ወይም ወጪ አድርጎ እንደሆነና ይኸንንም ኪሣራና ወጪ
ያደረገው በመሥሪያ ቤቱ ፈቃድ ሆኖ በዚህም ወጪ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ተጠቅሞበት እንደሆነ ሥራ ተቋራጩ ያደረገውን ወጪ
በመክፈል ኪሣራውን መመለስ አለበት፡፡

ንኡስ ክፍል 2፡፡


የጨረታ ሥነ ሥርዐት፡፡
ቊ 3147፡፡ ይህን ሥነ ሥርዐት በሥራ ላይ ስለ ማዋል፡፡

(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች የሚያደርጋቸው ውሎች በጨረታ ሥርዐት ሊፈጽሙ ይቻላል፡፡

(2) ሕጉ በእንደዚህ ያለ ሥርዐት እንዲፈጸም የሚያዝ በሆነ ጊዜ ውሎቹ በጨረታ ካልተሰጡ ፈራሽ ናቸው፡፡

ቊ 3148፡፡ የጨረታ ማስታወቂያ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

በጨረታ የሚፈጸመው ነገር ሁሉ በአስተዳደር መሥሪያ ቤት የውስጥ ደንብ በተመለከተው መሠረት ወይም ይህ ደንብ ባይኖርም ተገቢ
ነው ተብሎ በሚገመተው ግልጽ በሆነ ዘዴ ለሕዝብ መገለጽ አለበት፡፡
ቊ 3149፡፡ (2) በጨረታው ማስታወቂያ የሚገለጸው ቃል፡፡

የጨረታው ማስታወቂያ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነገሮች ማስታወቅ አለበት፡፡


(ሀ) ሥራው የሚፈጸምበትን አኳኋን የሚያመለክተውን ደብተር ለማየት የሚቻለበትን ቦታ፤

(ለ) ጨረታ የሚያደርጉትን ባለሥልጣኖች፤

(ሐ) ስለ ጨረታው መልስ የሚቀርብበትን ጊዜ፤

(መ) ለጨረታው የተወሰነውን ስፍራ ቀንና ሰዓት፤

(ሠ) ተጫራቾቹ የሚያቀርቡትን የዋስትና ገንዘብ ልክ ወይም ሌሎች የዋስትና ማረጋገጫዎች

ቊ 3150፡፡ (3) የጊዜ ውሳኔ፡፡

የሚያስቸኵል ምክንያት ከሌለ በቀር ለጨረታው መልስ መስጫ ከተወሰነው ጊዜ እጅግ ቢያንስ ከአንድ ወር በፊት የጨረታው ማስታወቂያ
ለሕዝብ እንዲገለጽ መደረግ አለበት፡፡

ቊ 3151፡፡ የጨረታው ማስታወቂያ የሚያስከትለው ውጤት፡፡

እንደገና በአዲስ ማስታወቂያ ካልተገለጸ በቀር የመጀመሪያው የጨረታ ማስታወቂያ ከተደረገ በኋላ ሥራው የሚፈጸምበትን አኳኋን
የሚያመለክተውን ደብተር መለዋወጥ አይቻልም፡፡

ቊ 3152፡፡ ሥራው የሚፈጸምበትን አኳኋን የሚያመለክት ደብተር፡፡

(1) ሥራው የሚፈጸምበትን አኳኋን የሚያመለክተው ደብተር ተጫራቾቹ ያለባቸውን የግዴታ ዝርዝር ገልጾ ያመለክታል፡፡

(2) በዚህም ደብተር ውስጥ የአስተዳደሩ መሥሪያ ተፈላጊ መስሎ የሚታየውን የተጫራቾቹን የቴክኒክና የሞያ ሥራ ችሎታ ይወስናል፡፡

(3) አስፈላጊም ሲሆን ባንድ ጨረታ ውድድር ውስጥ ለመግባት ማቅረብ የሚያስፈልገውን የማስረጃ ዐይነትና እንዲሁም የቀረቡት የሥራ
ዐቅድ (ፕላኖች) ወይም የዕቃ ዐይነቶች ተገቢ አይደሉም ተብለው አቅራቢዎቹ ከውድድሩ ውስጥ የሚወገዱበትን ሁኔታ ገልጾ ይወስናል፡፡

ቊ 3153፡፡ መቅረብ የሚገባቸው አስረጅ ጽሑፎች፡፡

በጨረታው ውድድር ውስጥ ለመግባት የሚፈቅዱት ሥራ ተቋራጮች ወይም ዕቃ አቅራቢዎች አስቀድሞ በተዘጋጀው ሥራው
የሚፈጸምበትን አኳኋን በሚገልጸው ደብተር ላይ በተመለከተው ስፍራና በተወሰነው ቀን በጨረታው ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ
መሆናቸውንና የሚሰጡትን መልስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ቊ 3154፡፡ የጨረታው ዋጋ ለማቅረብ አሳብ አለኝ ሲባል የሚሰጥ ማስታወቂያ፡፡

(1) በጨረታው ውስጥ ለመግባት ሐሳብ መኖሩን የሚያመለክተው ማስታወቂያ የዕጩውን የቤተ ዘመድ ስም የግል ስም ሥራውንና
መኖሪያ ቦታውን መግለጽ አለበት፡፡

(2) ይህ መግለጫ አስፈላጊ የሆኑትን ማስረጃዎችና ሥራው የሚፈጸምበትን አኳኋን በሚያመለክተው ደብተር ላይ መቅረብ አስፈላጊው
ነው ተብሎ እንደሆነም ደንበኛ ከሆነ የዋስትና ጽሑፍ ጋራ መቅረብ አለበት፡፡

ቊ 3155፡፡ የጨረታው አቀራረብ፡፡ (1) በጨረታ ማቅረቢያው ጽሑፍ የሚመለከተው ነገርና ፎርም፡፡

(1) የጨረታው ማቅረቢያ ጽሑፍ ዕጩው ያቀረበውን ዋጋና የሚገባበትን ግዴታ ገልጾ ያመለክታል፡፡

(2) የሚቀርበውም፤ ሥራው የሚፈጸምበትን አኳኋን በሚያመለክተው ደብተር ላይ ተገልጾ በታዘዘው መሠረት በተዘጋና በታሸገ
አምቦሎፕ ውስጥ ሆኖ ነው፡፡

ቊ 3156፡፡ የቀረበውን ጨረታ የመፈጸም ግዴታ፡፡

(1) የጨረታው ውጤት እስከ ተነገረ ድረስ ለጨረታ የቀረበው ሥራ ተቋራጭ ያቀረበውን የጨረታ ውድድር ትቻለሁ ለማለት ወይም
ለመለዋወጥ አይችልም፡፡

(2) ስለሆነም ለጨረታ ባቀረበው ጽሑፍ ላይ የሚገደድበትን የጊዜ ልክ ሊወስን ይችላል፡፡

ቊ 3157፡፡ የጨረታ ከፍል ጽሕፈት ቤት፡፡

የጨረታ ክፍል መሥሪያ ቤት የሚቋቋመው በልዩ ልዩ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች በተሰጠው የውስጥ ደንብና ጽሑፍ መሠረት ነው፡፡

ቊ 3158፡፡ ጨረታውን ስለ ማስታወቅ፡፡

የጨረታው ሥራ የሚፈጸመው በግልጽ ጉባኤ ነው፡፡

ቊ 3159፡፡ ተጫራቾችን ስለ መቀበል፡፡ (1) የጽሕፈት ቤቱ ሥራ፡፡

(1) የጨረታው ጽሕፈት ቤት በመጀመሪያ ተጫራቾቹ የሥራው ተካፋይ ለመሆን የሚሰጡትን መግለጫ ይመለከታል፡፡
(2) የጨረታው መግለጫ በሚገባ የቀረበ መሆኑንና ተጫራቾቹም ለጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚያበቃቸው አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎች
(ግዴታዎች) ሁሉ ያሏቸው መሆናቸውን ይመረምራል፡፡

ቊ 3160፡፡ የመምረጥ ሥልጣን፡፡

(1) ጽሕፈት ቤቱ ከተጫራቾቹ ወይም ከዕቃ አቅራቢዎቹ በገንዘብ ረገድ ወይም በሞያ ሥራቸውም ረገድ የሚፈለጉት መድኖች ያሏቸውን
ካልሆነ በቀር አይቀበላቸውም፡፡

(2) ሥራዎቹ የሚፈጸሙባቸውን አኳኋን በሚያመለክተው ደብተር ላይ ተቃራኒ ቃል ከሌለ በቀር የማይቀበላቸውን ተጫራቾች ጽሕፈት
ቤቱ ሊሰማቸው አይገደድም፡፡

(3) ውሳኔውንም የሰጠበትን ምክንያት እንዲገለጽ ግዴታ የለበትም፡፡

ቊ 3161፡፡ የተሰጠውን ውሳኔ ለመለወጥ የማይቻል ስለ መሆኑ፡፡

የጨረታውን መልስ የያዙ አምቦሎፖች ከተከፈቱ በኋላ ሥራ ተቋራጭ ወይም ዕቃ አቅራቢ የሆነው ሰው በጨረታው ተካፋይ እንዲሆን
የተፈቀደበትን ውሳኔ ለመለወጥ አይቻልም፡፡

ቊ 3162፡፡ የጨረታ ማቅረቢያ ወረቀት ንባብ፡፡

(1) የጨረታውን መልስ የያዙት አምቦሎፖች የሚከፈቱት ሕዝብ ባለበት ነው፡፡

(2) የሚነበበውም በከፍተኛ ድምፅ ነው፡፡

ቊ 3163፡፡ የጨረታ ፕሮሴቬርባል፡፡

የጨረታው ውጤት የዚሁኑ ሥራ አፈጻጸም ጠቅላላ ሥርዐት በሚገለጽ ቃለ ጉባኤ (ፕሮሴቬርባል) ይጻፋል፡፡

ቊ 3164፡፡ ለጊዜው የሚሆን አንድ ተጫራች ስለ መምረጥ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የጨረታ ጽሕፈት ቤት ከተጫራቾቹ መካከለ ለመሥሪያ ቤቱ ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ዋጋ ያቀረበውን ለጊዜው የጨረታው አሸናፊ ነው
ብሎ ያስታውቃል፡፡

(2) ይህንንም ሲያደርግ ጽሕፈት ቤቱ የቀረበለትን ዋጋና ሥራው የሚፈጸምበትን ሁኔታ በሚገልጸው ደብተር ላይ በተመለከተው መሠረት
መፈጸሙን ይመለከተል፡፡
ቊ 3165፡፡ (2) ማስታወቁን ስለ ማዘገየት፡፡

(1) በጨረታው ደንቦች ላይ ያስተዳደሩ መሥሪያ በት ከአንድ ከተወሰነ ዋጋ በላይ አልፎ ሊዋዋል አይፈልግም ተብሎ ተነግሮ እንደሆነ
ጽሕፈት ቤቱ ለጊዜው የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለውን ሰው ላያስታውቅ ይችላል፡፡

(2) ይህን የተወሰነ ዋጋም ተጫራቾቹ እንዲያውቁት አይደረግም፡፡

ቊ 3166፡፡ (3) የብዙ ዋጋ አቀራረብ እኩልነት፡፡

(1) ከተጫራቾቹ መካከል ብዙዎቹ ተመሳሳይ የሆነ ዋጋ አቅርበው እንደሆነና ጽሕፈት ቤቱም ከነዚሁ መካከል ለመምረጥ የማይቻለው
የሆነ እንደሆነ የጨረታው ደንብ ከነዚሁ መካከል በዕጣ የደረሰው የሥራውን ውል ሊወስድ ይችላል የሚል ቃል ሊኖርበት ይችላል፡፡

(2) በደንቡ ላይ የዚህ ዐይነት ድንጋጌ የሌለ እንደሆነ እንደገና አዲስ ጨረታ ይደረጋል፡፡

ቊ 3167፡፡ (4) ውጤቱ፡፡

(1) አሸናፊ የሆነውን ተጫራች ለጊዜው ጽሕፈት ቤቱ ቢመርጥ ውሉ እንደተፈጸመ አያስነቈጥረውም፡፡

(2) አሸናፊውን ተጫራች ለጊዜው መምረጥ ውሉን ለመፈራረም የሚችለውን ተጫራች የማመልከት ውጤት ብቻ ይኖረዋል፡፡

(3) እንዲሁም ያንዱ ተጫራች መመረጥ የጨረታ ዋጋ አቅርበው የነበሩትን ሌሎቹን ተጫራቾች ከግዴታቸው ውጭ ያደርጋቸዋል፡፡

ቊ 3168፡፡ ያስተዳደር መሥሪያ ቤት የሚያደርገው ማጽደቅ፡፡

(1) የጨረታውን ሥርዐት ያስፈጸመው ያስተዳደር መሥሪያ ቤተ የጨረታውን ውጤት ለማጽናት ወይም ላለማጽናት ሙሉ ነጻነት አለው፡፡

(2) ውሉም ተፈጸመ የሚባለው ይህ ማጽደቅ ከተደረገ በኋላ ነው፡፡

ቊ 3169፡፡ ስምምነት፡፡

(1) በጨረታ የሚሠሩ ሥራዎች ሁለቱ ወገን እርስ በራሳቸው እየተስማሙ በጨረታው ዋጋ ላይ ስምምነት ሊያደርጉበት ይችላሉ፡፡

(2) እንዲሁም የውሉ ዘመን ሲፈጸም በተዋዋዮቹ መካከል በሚደረግ ስምምነት በየጊዜው ለመታደስ ወይም ቀኑን ለማራዘም ይቻላል፡፡

ንኡስ ክፍል 3፡፡


የውል ምክንያት፡፡
ቊ 3170፡፡ ምክንያት የሌለው ውል፡፡

የውሉ ስምምነት በተደረገበት ጊዜ ለውል ሰጪው ያስተዳደር መሥሪያ ቤት፤ ይህ የተደረገው ውል ወደ ታሰበው ግብ ለመድረስ
የሚያስችለው ምክንያት ሊያገኝ የማይችል መሆኑንና አድሚኒስትራሲዮኑ ያሰበውን ውጤት ለማስገኘት የማይችል መሆኑንና
አድሚኒስትራሲዮኑ ያሰበውን ውጤት ለማስገኘት የማይችል የሆነ እንደሆነና ይህንኑም ተዋዋዩ ወገን የሚያውቀው እንደነበረ የተገለጸ
ሲሆን ውሉ አንዳችም ዋጋ የሌለው ሆኖ ፈራሽ ይሆናል፡፡

ቊ 3171፡፡ ሕገ ወጥ ምክንያት፡፡

(1) ያስተዳደር መሥሪያ ቤት የውሉን ስምምነት ያደረገው ሕገ ወጥ ለሆነ ግብ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ ሕገ ወጥ ለሆነው ምክንያት የተደረገው
ውል ፈራሽ ነው፡፡

(2) እንዲሁም የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ይህን ሕገ ወጥ ውል ያደረገው ለጠቅላላው ጥቅም ሳይሆን ለተዋዋዩ የግል የገንዘብ ጥቅምን
ለማስገኘት ታቅዶ የሆነ እንደሆነ ውሉ ዋጋ የሌለውና ፈራሽ ይሆናል፡፡

ክፍል 2፡፡
ውል ስለሚያስከትለው ውጤት፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ስለ ውሎች ደንበኛ አፈጻጸም፡፡
ቊ 3172፡፡ በውሉ ውስጥ ሊመለከት የሚገባው ነገር፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ወገኖች በውሉ ስምምነት ላይ እንደተመለከተው አድርገው ግዴታቸውን መፈጸም አለባቸው፡፡

(2) በውሉ ስምምነት ላይ የተመለከተውንም ነገር ትክክል አድርጎ በዘመኑ በሚሠራበት የጥበባዊ ሥራ አፈጻጸም መሠረተ አስደሳች በሆነ
ዐይነትና ጥቅም አለው ተብሎ በተመደበው የአሠራር ዘዴ መፈጸም ይገባቸዋል፡፡

(3) እንዲሁም በትጋት በጥንቃቄ መፈጸም አለባቸው፡፡

ቊ 3173፡፡ ግዴታዎች የሚፈጸሙበት ሁኔታ፡፡

(1) ተቃራኒ የሆነ ስምምነት ከሌለ በቀር ተዋወዩ ወገን በስምምነቱ የገባበትን ግዴታ ለመፈጸም እንዲችል አስፈላጊ የሆኑትን ዕቃዎችና
መሥሪያዎች ለመግዛት ራሱ የፈለጋቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ለማምጣት ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ግዴታዎቹን ለመፈጸም በራሱ አላፊነት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን የዕለት ሠራተኞች
ወይም ሌሎች ሠራተኞችንም መርጦ ለመቅጠር ይችላል፡፡
ቊ 3174፡፡ ስለ ጊዜ ውሳኔ (1) መሠረቱ፡፡

(1) እያንዳንዱ ወገን ተዋዋይ በውሉ ውስጥ በተወሰነው ጊዜ ግዴታዎቹን መፈጸም አለበት፡፡

(2) በውሉ ላይ ተወስኖ በግልጽ የተመለከተ ጊዜ የሌለ እንደሆነ የገባበትን ግዴታ በአእምሮ ግምት በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ መፈጸም
አለበት፡፡

ቊ 3175፡፡ (2) ያስተዳደሩ መሥሪያ ቤት መብት፡፡

በውሉ ውስጥ በግዴታዎቹ አፈጻጸም ከተወሰነው ጊዜ ሌላ በሥራ ትእዛዝ ያስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ሊወስን መብት አለው ተብሎ
ካልተመለከተ በቀር ያስተዳደሩ መሥሪያ ቤት በስምምነት ከተመለከተው የሥራ ማስፈጸሚያ ጊዜ ሌላ በራሱ ሥልጣን ብቻ ተዋዋዩን
ሊያስገድደው አይችልም፡፡

ቊ 3176፡፡ የዋጋ አከፋፈል፡፡

ያስተዳደሩ መሥሪያ ቤተ ሊከፍል የሚገባው ገንዘብ በፋይናንስ ሕግ በመንግሥት ሒሳብ አያያዝ ደንብ መሠረት ይፈጸማል፡፡

ቊ 3177፡፡ ግዴታ አልተፈጸመም ማለትን መከራከሪያ ስለ ማድረግ፡፡

(1) ያስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ያለበትን ግዴታ አለመፈጸሙ ይህ አድራጎት ውሉን ለመፈጸም እንዳይችል ካላደረገው በቀር ተዋዋዩ ያሉበትን
ግዴታዎች አልፈጽምም ለማለት ምክንያት ሊሆነው አይችልም፡፡

(2) የውሉን አፈጻጸም የሚያስችለው ከሆነ ያስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ያደረገውን የውለታ ጥፋት ምክንያት በማድረግ ተዋዋዩ የውሉን
አፈጻጸም ሊያቋርጥ አይችልም፡፡

ቊ 3178፡፡ ስለ ማቻቻል፡፡

ተዋዋዩ ዕዳ ይቻቻልልኝ ብሎ ያስተዳደሩን መሥሪያ ቤት ለመጠየቅ የሚችለው ይቻቻልልኝ የሚለው ዕዳ የቀረጥ ዕዳን የሚመለከት
ያልሆነ እንደሆነ ነው፡፡

ንኡስ ክፍል 2፡፡


ስለ ውሎች ምርመራ፡፡
(ሀ) ላስተዳደር መሥሪያ ቤት በተለይ የተፈቀዱለት መጠቀሚያዎች፡፡
ቊ 3179፡፡ መሠረቱ፡፡
ለአስተዳደር መሥሪያ ቤት በውሉ በዝምታ የታለፈውንም ቢሆን ባንድ ወገን በሆነ አፈጻጸም በውሉ አንዳንድ መሻሻያዎች አድርጎ ተዋዋዩን
ለማስገደድ ይቻለዋል፤ ይህም አንድ አጋጣሚ የሆነ መለዋወጥ እኒሁ መሻሻያዎች ለሕዝባዊ ጥቅም አስፈላጊ መሆናቸውን ባስረዳው ጊዜ
ነው፡፡

ቊ 3180፡፡ ውልን ስለ ማፍረስ፡፡


ተዋዋዩ ጥፋት ባይኖርበትም የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውሉን ሊያፈርስ ይቻለዋል፡፡ ይህም ውሉ ለሕዝባዊ አገልግሎት የሚጠቅም
ሳይሆን ሲቀር ወይም ለፍላጎቱ የማይስማማ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
ቊ 3181፡፡ ስለ ኪሣራ፡፡
(1) ካስተዳደር መሥሪያ ቤት ጋራ ተዋዋይ የሆነው ሰው በውሉ መሻሻል ወይም መሰረዝ ምክንያት በሚደርስበት ጉዳት ልክ ኪሣራ
ለማግኘት መብት አለው፡፡

(2) ኪሣራው ሲታሰብ ተዋዋዩ በውሉ ለማግኘት የለባቸውን ትርፎች ሁሉ መገመት ይገባል፡፡

(3) ዳኞች ግን ለተዋዋዩ ስለቀሩበት ትርፎች የኪሣራውን ገንዘብ በማሳነስ ለመወሰን ይችላሉ፡፡ እንደዚህም የሚሆነው ውሉ እንዲሻሻል
ወይም እንዲሰረዝ የተደረገው ውሉን በተዋዋለው ያስተዳደር መሥሪያ ቤት ጥፋት ሳይሆን በሌላ ምክንያቶች መሆኑ በታወቀ ጊዜ ነው፡፡
ቊ 3182፡፡ በተዋዋዩ ጥያቄ ውልን ስለ ማፍረስ፡፡
(1) ተዋዋዩ ባስተዳደር መሥሪያ ቤት ጣልቃ መግባት የውሉን ጠቅላላ ገንዘብ ቁጠባ የሚለውጠው ወይም የሚገለባብጠው ሆኖ በተገኘ
ጊዜ ውሉ እንዲፈርስለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) መሥሪያ ቤቱ በውሉ ያደረገው ማሻሻል ብዛቱ ውሉ በተደረገ ጊዜ ስለዚሁ ጕዳይ ከታሰበው መብለጥ አለመብለጡን ማመዛዘን
የሚችሉት ዳኞች ናቸው፡፡

(3) ተዋዋዩ በገዛ ፈቃዱ ውሉን ለማፍረስ የሚፈቅድለት አንቀጽ ካልኖረው በቀር ውሉን ለማፍረስ አይችልም፡፡

(ለ) አስቀድሞ ሳይታሰብ ስለ መቅረት፡፡


ቊ 3183፡፡ መሠረቱ፡፡
(1) ውሉ በተደረገ ጊዜ አስቀድሞ ሳይታሰቡ የቀሩት አጋጣሚ ሁኔታዎች የውሉን ሚዛን ምናልባት ገለባብጠውት ቢገኙ ካስተዳደር
መሥሪያ ቤት ተዋዋይ የሆነው ሰው ግዴታዎቹን የኒህም አፈጻጸም በመሣሪያ ረገድ የሚቻል ሆኖ ሲገኝ ግድ መፈጸም አለበት፡፡

(2) ከአስተዳደር መሥሪያ ቤት ተዋዋይ የሆነው ከወደቀበት ጉዳት የተዋዋለው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በከፊል ችሎ እንዲረዳው
ለመጠየቅ ይችላል፡፡
ቊ 3184፡፡ ስለ ውሉ መናወጥ፡፡
የውሉ ሚዛን የሚናወጠው አዲስ የተፈጠሩ አጋጣሚ ሁኔታዎች ከአስተዳደር መሥሪያ ቤት ጋራ የተዋዋለውን ሰው ግዴታዎች ከፍ
ሲያደርጉትና ይኸም ሁለቱ ወገኖች ሲዋዋሉ ከሰጡት አገማመት የመጨረሻ ወሰኑን ተላልፎ የበለጠ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 3185፡፡ አስቀድሞ ሳይታሰብ ስለ መቅረት፡፡
(1) አስቀድሞ ሳይታሰብ የቀረ ሆኖ የሚቈጠር አንድ ሁኔታ ውሉን ሲዋዋሉ ሁለቱ ወገኖች በአእምሮ ግምት ለመገንዘብ ሳይቻላቸው
የቀረው ነው፡፡

(2) አንድ ሁኔታ አስቀድሞ ሳይታሰብ የቀረ ነው ተብሎ ሊቈጠር የማይቻለው ለጥቅሙ ባደረገው ሰው አሠራር የሆነው ነው፡፡
(3) አስቀድሞ ሳይታሰብ መቅረትን ለመጥቀስ የሚቻለውም ባልታሰቡ ምክንያቶች ስለሚደርሱት ሁኔታዎች ወይም ባልታሰበ የልክ
መተላለፈና በውሉም ጊዜ ቀድሞ በተፈጸሙት ጕዳዮች ነው፡፡
ቊ 3186፡፡ ዋጋዎችን ለመለዋወጥ ወይም እንደገና ለማሻሻል የተደረጉ የውል ቃሎች፡፡
በውሉ ውስጥ ዋጋዎችን ለመለዋወጥ ወይም እንደገና ለመመርመርና ለማሻሻል የሚፈቅድ የውል ቃል ቢኖርም ቀጥሎ ያሉት ምክንያቶች
ሲኖሩ ኪሣራ ማግኘት የሚገባ መሆኑን አያስቀርም፡፡

(ሀ) በጕዳዩ የተመለከተውን የውል ቃል በሥራ ላይ ለማዋል ሳይቻል ሲቀር፤

(ለ) በውሉም ቃል አፈጻጸም ለምሳሌ፤ በዋጋ መለዋወጥ አንቀጽ ውስጥ ከተመለከቱት ነገሮች ውጭ በሆኑ ነገሮች ምክንያት በሚደርሰው
የዋጋ መለዋወጥ የውሉን የቁጠባ ኤኮኖሚ መናወጥን ለማቃናት የማይበቃ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 3187፡፡ የወጪ ብልጫ መኖር የሚያሻ ስለ መሆኑ፡፡
በጊዜው አጋጣሚ ሁኔታዎች ምክንያት በተዋዋዩ ላይ የወጪ ብልጫ ኪሣራ ሳይደርስበት ትርፎቹ በመቀነሳቸው ወይም ትርፍ በማጣት
ብቻ ኪሣራ ለመጠየቅ አይቻልም፡፡
ቊ 3188፡፡ ስለ ኪሣራ ገንዘብ፡፡
(1) የሚከፈለውም ኪሣራ በጊዜው አጋጣሚ ሁኔታዎች ምክንያት ከደረሰው ጉዳት አንደኛውን ክፍል ተዋዋዩ ራሱ እንዲችል በማድረግ
ነው፡፡
(2) በዚሁም ረገድ መገንዘብ የሚያስፈልገው ተዋዋዩ ችግሩን ለመወጣት ያደረገውን ጥረት ሁሉ የሥራውን ድርጅት ጠቅላላ አኳኋኑን
እንዲሁም ሌላ ማናቸውንም ርትዕ የሆኑ ሁኔታዎችን ሁሉ ነው፡፡
ቊ 3189፡፡ አስቀድሞ ያልታሰበ ነገር በሚቀርበት ሁኔታ፡፡
(1) አስቀድሞ ያልታሰበ ነገር መቅረት የሚገባው የውሉ ሚዛን በተቃና ጊዜ ነው፡፡

(2) የውሉ ሚዛን መቃወስ ፍጹም ሆኖ ከተገኘ እያንዳንዱ ተዋዋይ በዚሁ ረገድ የተፈጠረውን ሁኔታ እንዲያውቁለት ለዳኞች ሊያመለክት
ይችላል፡፡
(3) ውሉ በስምምነት እንዲሻሻል ለማድረግ ካልተቻለ ዳኞች ውሉ እንዲፈርስ ያደርጋሉ፡፡

(ሐ) የመንግሥት ሥርዐት፡፡

ቊ 3190፡፡ ጠቅላላ ጥንቃቄዎች፡፡ (1) በውሉ ውስጥ የተለከተውን ስለ መንካት፡፡

(1) መንግሥት ያወጣቸው ሕጎች ደንቦች፤ ትእዛዞችና እንዲሁም ሌላ ጠቅላላ የሆኑ ውሳኔዎች እነዚህም ውሳኔዎች የውሉን ቃሎች በቀጥታ
የሚለውጡ ወይም የውሉን አንዳንድ ቃሎች ለመፈጸም እክል የሚሆኑ ወይም ውሉ ያለ ጊዜው እንዲቆም የሚያደርጉ ሲሆኑ ከአስተዳደር
መሥሪያ ቤት ተዋዋይ የሆነው ሰው ኪሣራ እንዲያገኝ ያደርጉለታል፡፡

(2) በዚሁም ረገድ ጣልቃ የገባው ጠቅላይ የሆነው ውሳኔ ኪሣራ ለማግኘት አለመቻሉን ካልጠቀሰ በቀር ኪሣራውን ለመከልከል
አይቻልም፡፡
ቊ 3191፡፡ (2) የውሉን አፈጻጸም በጣም ውድ የሚያደርጉ ውሳኔዎች፡፡

(1) መንግሥት በሚያወጣቸው ጠቅላይ የሆኑ ውሳኔዎች የውሉ ቃሎች ሳይነኩ ያፈጻጸሙን አኳኋን ብቻ ቢለውጡ አፈጻጸሙንም በጣም
አስቸጋሪና ውድ ቢያደርጉትም ኪሣራ ሊገኝባቸው አይቻልም፡፡

(2) ጣልቃ በገባው ውሳኔ ወይም በውሉ ለዚሁ ዐይነት ሁኔታ ኪሣራ የሚገባው ነው ተብሎ ተመልክቶ እንደሆነ ኪሣራ ማግኘት
ይገባዋል፡፡
ቊ 3192፡፡ በተለይ የሆኑ ጥንቃቄዎች፡፡ (1) ባለሥልጣን የሆነው ተዋዋይ ያደረጋቸው የጥንቃቄ ውሳኔዎች፡፡
(1) ባለሥልጣን የሆነው ተዋዋይ ያደረጋቸው በተለይ የሆኑ የጥንቃቄ ውሳኔዎች የውሉን ቃሎች የሚነኩ እንደሆነ ወይም አፈጻጸሙን ብቻ
የሚያዳግቱ ወይም በጣም የሚያስወድዱ እንደሆነ ከአስተዳደር መሥሪያ ቤት ጋራ ተዋዋይ የሆነውን ኪሣራ ለማግኘት የሚገባው
ያደርጉታል፡፡
(2) የተደረጉት ጥንቃቄዎች ግን ከወገኖቹ ውጭ የሆነውን ለማምለጥ የማይቻለውን የቁጠባ (የኤኮኖሚ) ሁኔታ ለማረጋገጥ ሲሆን፤
አንዳችም ኪሣራ ሊጠየቅ አይቻልም፡፡

ቊ 3193፡፡ (2) በሌላ ባለሥልጣን የተደረጉ የጥንቃቄ ውሳኔዎች፡፡

(1) ጉዳት ያመጣውን ሥራ ፈጻሚው ተዋዋይ ባለሥልጣኑ ሳይሆን አንድ ሌላ ባለሥልጣን ሲሆን፤ አንዳችም ኪሣራ ሊከፈል አይገባም፡፡

(2) ይህን የመሰለው ጕዳይም የሚፈጸመው አስቀድሞ ሳይታሰብ ስለቀረ ነገር ወይም በሕዝብ ባለሥልጣን ኀላፊነት በተሠሩት ደንቦች
መሠረት ነው፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
ስለ ውሎች ያለመፈጸም፡፡
ቊ 3194፡፡ ውልን በግድ ስለ ማስፈጸም፡፡
(1) ዳኞች የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ግዴታውን ይፈጽም ዘንድ ሊያስገድዱት አይችሉም፡፡

(2) የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ግዴታውን ለመፈጸም ሳይወድ ቢቀር ዳኞች ኪሣራ ለማስከፈል ፍርድ ለመስጠት ይችላሉ፡፡

(3) ዳኞች የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ያወጣቸውን መጠንቀቂያ ውሳኔዎች ራሱ ከተዋዋላቸው ግዴታዎች ጋራ ተቃራኒ ሲሆኑ ተቃራኒ
የሆነ ሕጋዊ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ለመሰረዝ ይችላሉ፡፡
ቊ 3195፡፡ በትእዛዝ የመውሰድ ‹‹ሬኪዚሲዮን›› መብቶች፡፡

(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ራሱ ያደረገውን ውል ‹‹በሬኪዚሲዮን›› በትእዛዝ መብት ወስዶ ለማስፈጸም አይችልም፡፡

(2) የሠራተኞችን የሥራ ማቆም አድማ ለማስወገድ የመንግሥት መሥሪያ በቶችን ሠራተኞች ‹‹በሬኪዚሲዮን›› ለመውሰድ ግን ይችላል፡፡
ቊ 3196፡፡ ሳይከፈሉ ስለ ቀሩ ገንዘቦች ወለድ፡፡
ሳይከፈል ለቀረው ገንዘብ የሚገባው ወለድ ማስጠንቀቂያ የመስጠት አስፈላጊነት ሳይኖረው ከአስተዳደር መሥሪያ ቤት ላይ በሙሉ መብት
ተፈላጊ የሚሆነው፤

(ሀ) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በውሉ በተመለከተው መሠረት ከዐሥራ አምስት ቀን በኋላ ለተዋዋዩ ስለ ገንዘቡ አከፋፈል
የሚያስፈልገውን የማረጋገጥ ሥራ ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ ወይም፤

(ለ) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት የሚፈለግበትን ገንዘብ የማረጋገጡ ሥራ በተፈጸመ በሦስት ወር ውስጥ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 3197፡፡ ኀላፊነት እንዳይኖር የተደረገ የውል ቃል፡፡
ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ቢኖርም ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የተዋዋለው ሰው መሥሪያ ቤቱ ሳይከፍለው ላቈየበት ገንዘብ ወለድ ወይም
ኪሣራ ለመጠየቅ የሚችለው፡-

(ሀ) ሳይከፈል የቈየበት ጊዜ ከስድስት ወር በላይ ሲሆን፤

(ለ) ውሉን ያደረገው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ለመጉዳት ብሎ ያደረገው ወይም ከባድ በሆነ ቸልተኛነትና ወይም ጥፋት ያደረገው ሲሆን
ነው፡፡
ቊ 3198፡፡ ስለ ማስጠንቀቂያው ውድቅነት፡፡
(1) አንድ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ከተዋዋዩ ጋራ በመገናኘት ስለ ሥራው በሌላ የውል ግዴታዎች መሠረት
ንግግር ለማድረግ ቢጀምር ማስጠንቀቂያው ውድቅ ስለሚሆን ማስጠንቀቂያውን እንደገና ማደስ ያስፈልገዋል፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ አንድ የቅጣት ውሳኔ ሳያደርግ ብዙ ጊዜ ቢያሳልፍ ወይም ከተዋዋዩ ጋራ የንግድ
ግንኙነትን ቢቀጥል በተዋዋዩ ላይ የቅጣት ውሳኔ መፈለጉን ትቷል የሚያሰኘውና እንደገና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ የሚያስገድደው
አይሆንም፡
ቊ 3199፡፡ ስለ አቅራቢዎች መዘግየትና ጕድለት፡፡
(1) አንድ ተዋዋይ የሆነ በገዛ አቅራቢዎቹ መዘግየትና ጕድለት በሚደርሰው ጥፋት ሊከለክሉት በማይቻል ከዐቅም በላይ በሆነ ሕግ
መሠረት ለመከራከር አይችልም፡፡

(2) አንድ ተዋዋይ የሆነ የገዛ አቅራቢዎቹ መዘግየትና ጕድለት ሊከለክሉት የማይቻል ከዐቅም በላይ እንደሆነ ኀይል ተቈጥሮ ውሉን
ባለመፈጸም ከሚደርስበት አላፊነት ሊያድነው አይችልም፡፡

ቊ 3200፡፡ የቅድሚያ ልዩ መብት ስላለመኖር፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ተዋዋዩ ውሉን ባለመፈጸሙ የሚያስቀጣ ጥፋት አድርጓል፡፡ በማለት በገዛ ራሱ አንድ ውሳኔ ለማድረግ
አይችልም፡፡
(2) እንዲሁም የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ተዋዋዩ ግዴታዎቹን ባለመፈጸሙ ወይም ለመፈጸም በመዘግየቱ ምክንያት የሚፈለግበትን
ኪሣራ ልክ በገዛ ራሱ ለመወሰን አይችልም፡፡

(3) ዳኞች የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ከመብቱ ተቃራኒ በሆነ አኳኋን በተዋዋይ ላይ ባደረገው ውሳኔ (ቅጣት) ለደረሰበት ጉዳት ኪሣራ፤
ይከፍለው ዘንድ ሊፈርዱበት ይችላሉ፡፡
ንኡስ ክፍል 4፡፡
ውሎችን ለሌላ ሰው ስለ መልቀቅና ከዋናው ተቋራጭ ስለ ተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ፡፡
ቊ 3201፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) ውሎችን ለሌላ መልቀቅ ማለት ተዋዋዩ ውሉን በሙሉ እንዲፈጽምለት ላንድ ሦስተኛ ወገን ለሆነ ሲያስተላልፍ ነው፡፡

(2) ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ የሚባለውም ከተዋዋዩ ውሉን በከፊል ለማስፈጸም ካንድ ሦስተኛ ወገን ከሆነ ሰው ጋራ
የሚደረግ ውል ነው፡፡
ቊ 3202፡፡ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ፈቃድ አስፈላጊነት፡፡
(1) ተዋዋዩ ያደረጋቸው ውሎችን ለሌላ ለመልቀቅና ከሁለተኛ ተቋራጭ ጋራ የተደረጉ ውሎች አስቀድሞ ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ
እንዲፈቀድ ያስፈልጋል፡፡

(2) ውልን ለሌላ ስለ መልቀቅ ወይም ከሁለተኛ ተቋራጭ ጋራ የተደረገውን ውል ለመፍቀድ መብት ያለው ባለሥልጣን ተቃራኒ የሆነ ቃል
ካልኖረ በቀር ውሉን ለመዋዋል የተፈቀደለት ባለሥልጣን ነው፡፡
ቊ 3203፡፡ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ግዴታና ችሎታ፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ውልን ለሌላ ለመልቀቅ ወይም ለሁለተኛ ተቋራጭ ለማድረግ ለሚቀርብለት የፈቃድ ጥያቄ መልሱን
በአእምሮ ግምት ተገቢ በሆነ ጊዜ ውስጥ መስጠት አለበት፡፡

(2) ውልን ለሌላ ለመልቀቅ ወይም የሁለተኛ ተቋራጭ ሆኖ የተዋዋለው የሕዝባዊ አገልግሎት ሥራ ባለኮንሴሲዮን በሆነ ጊዜ የአስተዳደር
መሥሪያ ቤቱ ይህ አዲስ የታጨው ባለኮንሴሲዮን (በቴክኒካዊ ወይም) በገንዘብ ችሎታ ማነስ ምክንያት ካልሆነ ፈቃዱን ለመከልከል
አይችልም፡፡
(3) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ለሌላ ውሎች ውስጥ ስለ ውሎች ለሌላ ማሳለፍ ወይም ስለ ሁለተኛ ተቋራጭ ረገድ የመከልከል ወይም
የመፍቀድ በተለይ የሆነ መብት አለው፡፡
ቊ 3204፡፡ ቅጣት፡፡
(1) ሳይፈቀድለት የተደረገው ውልን ለሌላ መለቀቅ ወይም ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ አስተዳደር መሥሪያ ቤቱን
መቃወሚያ ሊሆን አይችልም፡፡

(2) እነዚህም ስለ ውል ጥፋት ተቈጥረው በተዋዋዩ ጕድለት ውልን የሚያፈርሱ ይሆናሉ፡፡

ቊ 3205፡፡ ፈቃዱ የሚሰጠው ውጤት፡፡ (1) ለሌላ ስለ መልቀቅ፡፡

(1) ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ውልን ለሌላ ለመልቀቅ የሚሰጠው ፈቃድ ውል በተሰጠው በቀድሞ ተዋዋይ ምትክ ያደርገዋል፡፡

(2) ተቃራኒ የሆነ ውል ካልኖረ በቀር የቀድሞው ተዋዋይ ስለ ውሉ አፈጻጸም ኀላፊነት ነጻ ነው፡፡

(3) የቀድሞው ተዋዋይ ለአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የሰጠው ዋስትና በመሥሪያ ቤቱ እጅ የሚቈየው በመካከላቸው ባሉት ክርክሮች መጠን
ብቻ ነው፡፡

ቊ 3206፡፡ (2) ከዋናው ተቋራጭ የተስማማ ሁለተኛ ተቋራጭ፡፡

(1) ከአስተዳደር መሥሪያ ቤት ከዋናው ተቋራጭ ለተስማማው ለሁለተኛው ተቋራጭ የሚሰጠው ፈቃድ፤ በተዋዋዩና በመሥሪያ ቤቱ
መካከል ያለውን የውል ማሰሪያ እንዳለ ሆኖ እንዲኖር ይተወዋል፡፡

(2) የቀድሞው ተዋዋይ፤ ሁለተኛው ተዋዋይ ለፈጸማቸው ሥራዎችና ዕቃዎች ራሱ እንደፈጸማቸው ተቈጥረው ኀላፊነት ይኖርበታል፡፡

(3) ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ስለ ሁለተኛው ተዋዋይ የተሰጠው ፈቃድ በመዘግየት ምክንያት ከሚወድቀው ቅጣት የመዘግየቱ ነገር
በሁለተኛው ተዋዋይ ጥፋት በሆነ ጊዜ የቀድሞውን ተዋዋይ አይነካውም፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
ስለ ሕዝብ አገልግሎት ሥራ ኮንሴሲዮን፡፡
ቊ 3207፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) አንድ የሕዝብ አገልግሎት ሥራ የሚባለው መንግሥት ይኸን ሥራ የግል የሆነ ድርጅት በሚገባ ለማካሄድ የማይችለው ነው ብሎ ወስኖ
በጠቅላላ ለሕዝቡ አስፈላጊነት ያለው ነው በማለት ራሱ የሚያካሂደው ነው፡፡

(2) የሕዝብ አገልግሎት የመንግሥት ሥራ ኮንሴሲዮን የሚባለውም አንድ ባለኮንሴሲዮን የሕዝባዊ አገልግሎት ሥራን ስለ አገልግሎቱ
የሚከፈለውን ከሚገለገሉበት ሰዎች በመቀበል ለማካሄድ ካንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ጋራ ያደረገው ውል ነው፡፡

ቊ 3208፡፡ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት የመቈጣጠር መብት፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) የሕዝብ አገልግሎት ሥራ በደኅና እንዲካሄድ ኅላፊነት ያለው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውሉ በሚፈጸምበት በማናቸውም ጊዜ ሁሉ
ለመቈጣጠር መብት አለው፡፡

(2 ) ባለኮንሴሲዮኑ ኮንሴሲዮኑን ለሰጠው የሥራውን ሁኔታ ገልጾ ማስረዳትና እንዲሁም መቈጣጠሩን እንዲፈጽም አስፈላጊውን ሁሉ
ማድረግ አለበት፡፡

ቊ 3209፡፡ (1) በደንብ ስለ መወሰን፡፡

(1) ባለኮንሴሲዮኑን ለመቈጣጠር የሚፈጸመው አሠራር በደንብ በተደረነገጉትና ተዋዋዮቹም በተስማሙባቸው ውሳኔዎች መሠረት ነው፡፡

(2) ከዚህ በታች ባሉት ቊጥሮች ውስጥ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ቢኖርም እንኳ ተፈጻሚ ናቸው፡፡
ቊ 3210፡፡ (3) የመቈጣጠሩ ወሰን፡፡

(1) አኮንሴሲዮኑ መቈጣጠር ኮንሴሲዮኑን አበላሽቶ ሥራው በአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት በቀጥታ እንደሚመራ አድርጎ የሚለውጠው
እንዳይሆን ያስፈልጋል፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ባለኮንሴሲዮኑ አንዱን የሥራ ክፍል በሙሉ አስቀድሞ እያስፈቀደ እንዲሠራ ለማድረግ አይቻለውም፡፡

(3) በውል የተወሰነው እንደተጠበቀ ሆኖ ባለኮንሴሲዮኑ ውሉን የሚፈጽምበትን አኳኋን በነጻነት ራሱ ይመርጣል፡፡

ቊ 3211፡፡ (4) ስለ ውሉ አተረጓጐም፡፡

(1) የውሉን ቃሎች ለኮንሴሲዮኑ ሥራ አካሄድ መቈጣጠርም ሆነ ስለ ሕዝባዊ ሥርዐት ጸጥታ ጥበቃም ሆነ አዲስ ለሆኑት ደንቦች አፈጻጸም
አሰናካይ እንዲሆኑ አድርጎ በፍጹም ትርጕም ሊሰጣቸው አይቻልም፡፡

(2) ስለሆነም የአስተዳደሩ ባለሥልጣን ከተዋዋዩ ጋራ በውል የተስማማባቸውን ግዴታዎች ለመለወጥም ሆነ ለመቈጣጠር በፖሊስ ደንቦች
ኀይል መሠረት ለመፈጸም አይችልም፡፡

ቊ 3212፡፡ ዋጋዎችንና የዋጋ ልክ ማስታወቂያዎችን በውል ስለ መለወጥ (1) መሠረቱ፡፡


በኮንሴሲዮኑ ውስጥ በውሉ የተመለከቱት ዋጋዎችና የዋጋ ልክ ማስታወቂያዎች በቁጠባ ረገድ መለዋወጥ በደረሰበት ጊዜ ሊለወጡ ይቻላል
የሚል ቃል በውል ውስጥ ሊገባ ይቻላል፡፡

ቊ 3213፡፡ (2) የመለዋወጥ የውል ቃሎች፡፡

(1) በያንዳንድ ዕቃዎች ሥራዎች ላይ በሚደርስባቸው የዋጋ መለዋወጥ መጠን ዋጋዎቹ ዐውቀው ወዲያውኑ ተለውጠው በሥራ ላይ
ይውላሉ ብሎ አስቀድሞ በኮንሴሲዮኑ ውስጥ ሊወሰን ይቻላል፡፡

(2) ያዲሶች ዋጋዎች ወይም የዋጋ ልክ ማስታወቂያዎች አወሳሰን ባንድ የመለዋወጥ የውል ቃል መሠረት ዐውቆ ተለዋጭ ሲሆን ክርክርም
ቢነሣ በዚሁ በተጠቀሰው የመለዋወጥ የውል ቃል መሠረት ዳኞች አዲሶችን ዋጋዎችና የዋጋ ልክ ማስታወቂያዎችን ይወስናሉ፡፡

ቊ 3214፡፡ (3) የማሻሻያ የውል ቃል፡፡

(1) በውሉ በቁጠባው ሁኔታዎች በጣም ከፍ ያለ መለዋወጥ በደረሰ ጊዜ ስለ ዋጋዎችና የዋጋ ልክ ማስታወቂያዎች ማሻሻል መሠረቱን ጕልህ
አድርጎ ሳይገልጽ መሻሻል ይገባቸዋል የሚል ቃል ሊጻፍ ይቻላል፡፡

(2) እንደዚህም በሆነ ጊዜ በውሉ የተጠቀሱት ሁኔታዎች በደረሱ ጊዜ ተዋዋዮቹ ተከራክረው ለውሉ አንድ የስምምነት ተጨማሪ ማድረግ
ግድ ይኖርባቸዋል፡፡

(3) ተዋዋዮቹ ሳይስማሙ ቢቀሩ ግን ዳኞች ለባለኮንሴሲዮኑ ርትዕ የሆነ ዋጋ መቀበያ የሚሆነው አንድ የዋጋ ልክ ማስታወቂያ ወስነው
ማውጣት አለባቸው፡፡

ቊ 3215፡፡ (4) ስለ ውል ቃሎቹ የጊዜ አፈጻጸም፡፡

(1) በውሉ ተቃራኒ የሆነ ቃል ካልኖረ ተዋዋዩ ሥራውን ከተቀበለበት ቀን ጀምሮ የዋጋዎችን መለዋወጥና የማሻሻያ የውሎችን ቃል
ለመጥቀስ ይችላል፡፡

(2) ተዋዋዩ እነዚህኑ የውል ቃሎች በውሉ የተመለከቱትን ግዴታዎችን ለመፈጸም ከተወሰነለት ጊዜ በኋላ ከመሥሪያ ቤቱ የተጨመረለት
ጊዜ ካልኖረው በቀር ለመጥቀስ አይችልም፡፡

ቊ 3216፡፡ ባንድ ወገን ብቻ ስለሚደረግ የውል መለዋወጥ፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ኮንሴሲዮን ሰጭ የሆነው መሥሪያ ቤት ውሉ በሚጸናበት ጊዜ ስለ ሥራው መልካም አካሄድ ወይም ስለተሰጠው አገልግሎት ሥራ
መሻሻል አስፈላጊ መስሎ የታየውን ማንኛዎችንም ግዴታዎች በባለኮንሴሲዮኑ ላይ ሊጥልበት ይችላል፡፡
(2) እንዲሁም በኮንሴሲዮኑ ውል ወይም የሥራውን አኳኋን በሚያመለክተው በግዴታዎቹ ደብተር የተመለከተውን ያገልግሎት ሥራ
ድርጅት እንዲለውጥ ባለኮንሴሲዮኑን ለማስገደድ ይችላል፡፡

(3) ማናቸውም ይህን ተቃራኒ የሆነ ቃል ዋጋ የለውም፡፡

ቊ 3217፡፡ (2) ለመለዋወጥ የሚቻሉ የስምምነት ቃሎች፡፡

(1) ለመለዋወጥ የሚቻሉት አገልግሎት ሥራንና አፈጻጸሙን የሚመለከቱ ቃሎች ብቻ ናቸው፡፡

(2) እንዲሁም መሥሪያ ቤቱ ባለኮንሴሲዮኑ ማቅረብ የሚገባውን ሀብት ብዛት ከፍ ለማድረግ ወይም ዝቅ ለማድረግ ወይም ያገልግሎት
ሥራውን እንዲያስፋፋ ለማድረግ ይችላል፡፡

ቊ 3218፡፡ (3) ስለ መለዋወጡ ወሰኖች፡፡

(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የአገልግሎት ሥራን ድርጅት ዐይነቱን ወይም ውሉን ፍጹም ሌላ መልክ የሚሰጥ መለዋወጥ እንዲደረግ
ለማስገደድ አይችልም፡፡

(2) እንዲሁም የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ኮንሴሲዮኑን በመንግሥት መሪነት በሚሠራ ሥራ አስተዳደር ዐይነት ለማስተዳደር አይችልም፡፡

(3) እንዲሁም የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ባለኮንሴሲዮኑ ከተሰጠው ያገልግሎት ሥራ ልዩ የሆነ አንድ ሥራ ወይም ጭራሹን አንድ አዲስ
ሥራ ወይም ከችሎታው በላይ የሆነ አንድ ሥራ ለማሠራት አይችልም፡፡

ቊ 3219፡፡ (4) ለመለወጥ የማይቻሉ የስምምነት ቃሎች፡፡

(1) የኮንሴሲዮኑ ውል ለባለኮንሴሲዮኑ በገንዘብ ረገድ የሚያስገኘውን ጥቅም ሁሉ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በበኩሉ ለብቻ ለመለዋወጥ
አይቻለውም፡፡
(2) እንዲሁም የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ለባለኮንሴሲዮኑ የተሰጠውን የብቻነት ልዩ ጥቅም ለመንካትም አይችልም፡፡

(3) የኮንሴሲዮኑ ሰጭ በበኩሉ ለብቻው የዋጋዎቹን ማስታወቂያ በመለወጥ ሊያስገድደው ይችላል፡፡ ግን በዚሁ መለዋወጥ
በባለኮንሴሲዮኑ ለሚደርሰው ጉዳት መካሥ ይገባዋል፡፡

ቊ 3220፡፡ (5) ለባለኮንሴሲዮኑ ስለሚከፈለው ካሣ፡፡

(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በበኩሉ ለብቻው ያለውን የመለዋወጥ መብት የፈጸመ እንደሆነ፤ በዚሁ ረገድ ለሚደርሰው ጉዳት ሁሉ
ለባለኮንሴሲዮኑ ኪሣራ መክፈል ይገባዋል፡፡

(2) ለባለኮንሴሲዮኑ የሚከፈለውም ካሣ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት የበለጠ ግዴታ እንዲፈጸም ባደረገው ሥራ በሚደርሰው ኪሣራ ልክ
ነው፡፡
ቊ 3221፡፡ ከደንበኞቹ ጋራ ስለሚደረገው ግንኙነት (1) የዋጋ ማስታወቂያ ስለ ማውጣት፡፡

ለባለኮንሴሲዮኑ በኮንሴሲዮኑ ውል ከደንበኞቹ ላይ የሚቀበለው ቀረጥ (ታክስ) ባንድ የዋጋ ማስታወቂያ መደብ (ታሪፍ) የብዛቱ ልክ
ተወስኖ ተፈቅዶለት እንደሆነ፤ ባለኮንሴሲዮኑ ከዚሁ ከተፈቀደለት ከፍተኛ ወሰን ሳያልፍ የዋጋ ማስታወቂያውን ራሱ ዐውቆ ለማውጣት
ይችላል፡፡
ቊ 3222፡፡ (2) የዋጋ ማስታወቂያን (ታሪፍ) ስለ መለዋወጥ፡፡
ኮንሴሲዮን ሰጪው የመደበው የዋጋ ማስታወቂያ ወይም ግዴታዎች የተለወጡ እንደሆነ ያዲሱ የዋጋ ማስታወቂያ ወይም ግዴታዎች
ወዲያውኑ በሥራ ላይ ይውላሉ ግን በባለኮንሴሲዮኑና በደንበኞቹ መካከል ባሉት ውሎች ላይ ወደ ኋላ ተመልሰው ሊጸኑባቸው
አይችሉም፡፡

ቊ 3223፡፡ (3) ኮንሴሲዮኑ እንደ ሕዝባዊ ሥርዐት (ጸጥታ) ዐይነት ለመሆኑ፡፡


ባለኮንሴሲዮኑ ካንድ ደንበኛ ጋራ ባደረገው የግል ውል መሠረት በኮንሴሲዮኑ ውል ወይም በግዴታዎቹ ደብተር የተወሰኑትን ጠቅላላ
ደንቦች ለመለወጥ አይቻለውም፡፡
ቊ 3224፡፡ ስለ ደንበኞቹ እኩልነት፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤትም ሆነ ባለኮንሴሲዮኑ በደንበኞቹ መካከል የከፍተኝነትና የዝቅተኝነት ተግባር በመወሰን የነርሱን እኩልነት
ለማጥፋት አይችሉም፡፡

(2) የአገልግሎቱም ሥራ ዋጋ ማስታወቂያ በደንበኞቹ ደረጃ መካከል ልዩነት ሊኖረው የሚችለው እኒህም ልዩነቶች በሕዝባዊ አገልግሎት
ሥራ ፊት ለደንበኞቹ ልዩ ልዩ ከሆኑ ሁኔታዎች ጋራ ተመሳሳይ ሆነው ሲገኙ ነው፡፡

(3) የንግድና ኢንዱስትሪ ሕዝባዊ አገልግሎት ሥራዎች የሚተዳደሩት በግል መብት ደንቦች መሆኑ በሕግ የታወቀላቸውም ቢሆን ከላይ
የተጠቀሰውን መሠረታዊ የሆነ አደራረግን ማክበር አለባቸው፡፡

ቊ 3225፡፡ (5) የደንበኞችና የባለኮንሴሲዮኑ ግንኙነቶች፡፡

(1) በዋጋ መደብ ወይም ግዴታዎች አፈጻጸም የሚደረጉት ስሕተቶች ሁሉ መቃናት አለባቸው፡፡

(2) ደንበኛው ባለካንሴሲዮኑ አላገባብ የተወሰደበትን ገንዘብ ለማስመለስ ክሱን አላገባብ ከተወሰደበት ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት
ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡

(3) እንዲሁም ባለኮንሴሲዮኑ የዋጋ ተጨማሪ ለመቀበል አላገባብ ከከፈለበት ቀን አንሥቶ እስከ አንድ ዓመት ክሱን ማቅረብ አለበት፡፡

ቊ 3226፡፡ (6) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት የደንበኞች ወኪል ስላለመሆኑ፡፡


የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ባለኮንሴሲዮኑን የውሉን ግዴታዎች ጠንቅቆ ባለመጠበቁ ምክንያት በአገልግሎት ሥራ ደንበኞች ላይ
ላደረሰባቸው አንድ ጉዳት ኪሣራ ለመጠየቅ አይችልም፡፡
ቊ 3227፡፡ የኮንሴሲዮኑ ጊዜ ልክ፡፡
(1) ኮንሴሲዮኑ የሚጸናበት ጊዜ ልኩ በውሉ ይወሰናል፡፡

(2) የኮንሴሲዮኑም ጊዜ ከስሳ ዘመን በላይ ሊሆን አይችልም፡፡

(3) የውል ቃል የሌለ እንደሆነ ኮንሴሲዮኑ ለሰባት ዓመት እንደተደረገ ይቈጠራል፡፡


ቊ 3228፡፡ ስለ ኮንሴሲዮኑ መታደስ፡፡
(1) የኮንሴሲዮኑ ውል መፈጸሚያው ሁለት ዓመት ሲቀረው ወይም ውሉ እንደሚያዝዘው አድርጎ ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ካልኖረ በቀርና
አንደኛው ወገን ለሁለተኛው ወገን ውሉ እንዲቀር ካላስጠነቀቀው በቀር ውሉ ዐውቆ የታደሰ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

(2) በዚሁም ምክንያት ውሉ ለሰባት ዓመት ወይም ተዋዋዮቹ ወገኖች አስቀድሞ በወሰኑት አጭር ጊዜ ታድሶ ይቀጥላል፡፡

ቊ 3229፡፡ የኮንሴሲዮኑን ሒሳብ ስለ ማጣራት (1) መሠረቱ፡፡

(1) የሕዝባዊ አገልግሎት ሥራ ኮንሴሲዮን ማለቅ በባለኮንሴሲዮኑና በኮንሴሲዮን ሰጪው መካከል ያሉት ሒሳቦች ተጣርተው እንዲፈጸሙ
ያደርጋል፡፡
(2) የሒሳብ ማጣራቱም ተግባር የሚፈጸመው በግዴታዎች ደብተር በተመለከቱት ውሳኔዎች መሠረት ነው፡፡

(3) የስምምነት ውል ቃል ካልኖረ በቀር የሒሳቡ ማጣራት ቀጥሎ በሚመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ይፈጸማል፡፡

ቊ 3230፡፡ (2) የባለኮንሴሲዮኑ ግዴታዎች፡፡

(1) ባለኮንሴሲዮኑ ስለ ኮንሴሲዮኑ ሥራ መቀጠል አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ለኮንሴሲዮን ሰጪው ማስታወቅ አለበት፡፡
(2) ባለኮንሴሲዮኑ በነጻ ወይም ኪሣራ ተከፍሎባቸው ተመላሽ የሆኑትን የኮንሴሲዮኑን ሥራዎችና መሣሪያዎች ሁሉ እንዳሉ በደኅና ሁኔታ
ለኮንሴሲዮኑ ሰጭ ማስረከብ አለበት፡፡

ቊ 3231፡፡ (3) ተመላሽ የሆኑ ንብረቶች፡፡

(1) ኮንሴሲዮን ሰጭ ኪሣራ ሳይከፍልባቸው የኮንሴሲዮኑን የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መልሶ ይረከባል፡፡

(2) እንደዚሁም ኮንሴሲዮን ሰጭ በግዴታዎች ደብተር ውስጥ ኪሣራ ሳይከፈልባቸው ተመላሽ ይሆናሉ ተብሎ የተመለከቱትንም
ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ኪሣራ ሳይከፈልባቸው ይረከባል፡፡

ቊ 3232፡፡ (4) እንደ ገና ሥራ መቀጠያ የሆኑ ንብረቶች፡፡

(1) ኮንሴሲዮን ሰጭ የቀሩትን ለኮንሴሲዮኑ ሥራ የሚያገለግሉትን ንብረቶች ኪሣራ ከፍሎ ለመውሰድ ይችላል፡፡

(2) ኮንሴሲዮን ሰጭ ለኮንሴሲዮኑ ሥራ አካሄድ የሚያገለግሉትን ንብረቶች መልሶ ለመውሰድ ተገዳጅነት የሚኖረውም በግዴታዎች
ደብተር ውስጥ ተገዳጅነቱ ተጠቅሶ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 3233፡፡ (5) ስለሚከፈለው ካሣ ገንዘብ፡፡

(1) ቀደም ብሎ በሚገኘው ቊጥር የተጠቀሰው የኪሣራ ገንዘብ የሚያከራከር በሆነ ጊዜ ልኩን ሁለቱ ወገኖች የመረጧቸው ሽማግሌዎች
ያለዚያም ዳኞች እንዲወስኑት ይደረጋል፡፡

(2) ባለኮንሴሲዮኑ ወይም ኮንሴሲዮን ሰጭ ንብረቶቹ ባወጡት ዋጋ መሠረት እንዲሆን ከወሰኑ ኪሣራው በዚሁ ዋጋ መሠረት ሆኖ
የመበላሸትና የእርጅና ተቀንሶለት መወሰን አለበት፡፡

(3) ለንብረቶቹ የወጡላቸው ዋጋዎች ልኩ ሊታወቅ ካልተቻለ ኪሣራው ለንብረቶቹ በመረከቢያው ጊዜ በሚሰጣቸው ዋጋ ግምት መሠረት
መወሰን አለበት፡፡

ቊ 3234፡፡ (6) ውሎች፡፡

(1) ባለኮንሴሲዮኑ ለኮንሴሲዮኑ ጠቃሚነት ያላቸውንና በሥራም ላይ ያሉትን ውሎች ሁሉ ለኮንሴሲዮን ሰጪው ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) ኮንሴሲዮን ሰጪው በነዚሁ ውሎች የባለኮንሴሲዮኑን ቦታ የሚይዝ በመሆኑ ለመሻር የሚፈልገውን ውል መኖሩን በተረዳበት ወር
ውስጥ ለባለኮንሴሲዮኑ ወይም ለተዋዋዩ ኮንሴሲዮን ሰጪው ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) ባለኮንሴሲዮኑ በውሉ ቀዋሚ የሆነ ግዴታ ካልኖረበት በቀር ስለ ውሉ ሽረት በተዋዋዩ ፊት አንዳችም ኀላፊነት ሊያገኘው አይችልም፡፡

ቊ 3235፡፡ (7) ዋስትናዎች፡፡


በኮንሴሲዮን ሰጪውና በባለኮንሴሲዮኑ መካከል ያሉት ሒሳቦች እንደተፈጸሙ ወዲያኑ ባለኮንሴሲዮኑ ያስያዘው መያዣ ተመላሽ ሆኖለት
የዋሶቹም ዋስትናቸው እንዲወርድ ይደረግላቸዋል፡፡

ቊ 3236፡፡ ኮንሴሲዮኑን መልሶ ስለ መግዛት (1) መሠረቱ፡፡

(1) መልሶ መግዛት ማለት ኮንሴሲዮኑን ከመፈጸሚያው ጊዜ በፊት ለማቆም ከባለኮንሴሲዮኑ ማናቸውም ጥፋት ውጭ የሆነ የአስተዳደር
መሥሪያ ቤት ውሳኔ ነው፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት የሕዝባዊ አገልግሎት ሥራን ለማቆም ወይም እንደገና ለማደራጀት በማናቸውም ጊዜ ኮንሴሲዮኑን መልሶ
ለመግዛት ይችላል፡፡

(3) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ግን ለሌላ ባለኮንሴሲዮን ለመስጠት ኮንሴሲዮኑን ከባለኮንሴሲዮኑ መልሶ ለመግዛት መብት የለውም፡፡

ቊ 3237፡፡ (2) ውጤቶች፡፡

(1) ኮንሴሲዮኑ መልሶ በተገዛ ጊዜ ከላይ በተጠቀሱት ሐሳቦች መሠረት መጣራት አለበት፡፡
(2) ባለኮንሴሲዮኑ መልሶ በመግዛት ለሚያገኘው ጉዳት ሁሉ በተለይም ለኮንሴሲዮን ሰጪው ባስተላለፈባቸው በነዚያ ዋጋቸውን ቀስ
በቀስ አድርጎ ለመመለስ ጊዜ ሳያገኝ በቀረባቸው ንብረቶች ረገድ በሚያገኘው ጉዳት መካስ ይገባዋል፡፡

(3) ለባለኮንሴሲዮኑ አገኛለሁ ብሎ አስቦት የነበረውን ትርፍ በመገንዘብ ይኸንኑም መልሶ በመግዛቱ ምክንያት በማጣቱ ርትዕ የሆነ ካሣ
ሊሰጠው ይቻላል፡፡

ቊ 3238፡፡ ስለ ባለኮንሴሲዮኑ መብት እጦት (1) ስለ መበየን፡፡

(1) የባለኮንሴሲዮኑ መብት እጦት መበየን የሚቻለው ባለኮንሴሲዮኑ በተለይ ከባድ የሆነ ጥፋት በሠራ ጊዜ ነው፡፡

(2) የመብት እጦቱም መበየን የሚገባው የኮንሴሲዮኑ ውል የመበየኑ ሥልጣን ለአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ካልተፈቀደለት በቀር በዳኞች
ብቻ ነው፡፡

ቊ 3239፡፡ (2) ውጤቶች፡፡

(1) የመብት ማጣት ውሉን በጭራሽ ያፈርሰዋል፡፡

(2) የመብት ማጣት የደረሰበት ባለኮንሴሲዮን የሕዝባዊ አገልግሎት ሥራ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ለማድረግ በውድ የሚከፈለውን ገንዘብ
ራሱ መቻል አለበት፡፡

ቊ 3240፡፡ (3) መብቱን ስላጣ ባለኮንሴሲዮን መብቶች፡፡

(1) ኮንሴሲዮኑ በባለኮንሴሲዮኑ ኀላፊነት በሐራጅ ይሸጣል፡፡

(2) መብቱን ያጣው ባለኮንሴሲዮን በኮንሴሲዮኑ ላይ ስላሉት መብቶች ሁሉ ምትክ እንዲሆነው በሐራጅ የተወሰነውን ዋጋ ከአዲሱ ባለ
ኮንሴሲዮን ይቀበላል፡፡

ቊ 3241፡፡ ስለ ማስያዝ (1) ግዴታዎች፡፡

(1) ኮንሴሲዮኑ እንዲያዝ መበየን የሚቻለው በባለኮንሴሲዮኑ ደካማነት ጕድለት ወይም ችሎታ ማነስ የአገልግሎት ሥራውን በከፊል
ወይም መላውን ያቆመ እንደሆነ ነው፡፡

(2) እንደዚሁም እንዲያዝ ለመበየን የሚቻለው በባለኮንሴሲዮኑ ማናቸውም ጥፋት ባይኖርም ባለኮንሴንሰዮኑ ያገልግሎት ሥራን
ለማካሄድ የማይዘልቀው መስሎም በታየ ጊዜ ነው፡፡

ቊ 3242፡፡ (2) ውጤቶች፡፡

(1) እንዲያዝ መደረጉ በኮንሴሲዮኑ ውል በነበሩት መብቶች ለጊዜው እንዳይሠራባቸው ባለኮንሴሲዮኑን ያግደዋል፡፡

(2) እንዲያዝ የተደረገው ባለኮንሴሲዮኑን ስለ ደካማነት ወይም ስለጥፋቱ ለመቅጣት የሆነ እንደሆነ ያገልግሎቱ ሥራ በኮንሴሲዮን ሰጭ
ወይም እርሱ በመረጠው አንድ የሥራ አስኪያጅ አማካይነት በባለኮንሴሲዮኑ ኪሣራና ኀላፊነት እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡

(3) ኮንሴሲዮኑ እንዲያዝ የተደረገው በእንደዚህ ያለ ምክንያት ያልሆነ እንደሆነ የማስያዙ ወጪ በኮንሴሲዮን ሰጪው ላይ ይሆናል፡፡
ቊ 3243፡፡ ስለ ዳኞች ተቈጣጣሪነት፡፡
(1) ዳኞች የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ባንድ የሕዝባዊ አገልግሎት ሥራ ባለኮንሴሲዮን በሆነው ላይ የፈጸመውነ ማሲያዝ በሥራ መሪ
ውስጥ ማድረግን መብት ማስቀረትን መሰረዝን እንደዚህ ያለውን ግዴታን የማስፈጸሚያ ማስገደጃ ወይም የውል ማፍረስ ውሳኔ (ቅጣት)
በሚገባ የተደረገ መሆኑን የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ካላስረዳ በቀር ዳኞች ለመሻር ይችላሉ፡፡

(2) ከዚህ በቀር የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በማይገባ የቅጣት ውሳኔ አድርጎ በተዋዋዩ ላይ ጉዳት ቢያደርስበት ለአደረሰበት ጉዳት ኪሣራ
እንዲከፍለው በአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ላይ ዳኞች ሊፈርዱበት ይችላሉ፡፡
ምዕራፍ 3፡፡
የመንግሥት ሥራዎችን የመቋረጥ ውል፡፡
ቊ 3244፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) የመንግሥት ሥራዎች ውል የሚባለው አንድ ተቋራጭ የሆነ ሰው ካንድ የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን ጋራ በዋጋ ተስማምቶ
አንድ የመንግሥት የሆነ ሕንጻ ሥራን ለመሥራት ለመጠበቅ ወይም ለማደስ የሚያደርገው ውል ነው፡፡

(2) የመንግሥት ሥራዎች ውል መባሉ ቀርቶ የአቅራቢነት ውል የሚባለው ውል ከሚሠራው የመንግሥት ሥራ ተካፋይነት ሳይኖረው
አቅራቢው ለሥራው አስፈላጊነት ያላቸውን ነገሮች ብቻ የማቅረብ ሲሆን ነው፡፡
ቊ 3245፡፡ ስለ ጥበባዊ ሥራዎች ገበያዎች፡፡
(1) በዚህ ምዕራፍ ለመንግሥት ሥራዎች ውል የተሠሩት ድንጋጌዎች ከአስተዳደር መሥሪያ ቤት ጋራ በሚደረጉትም የጥበብ ሥራዎች ውል
ላይ የሚፈጸሙ ናቸው፡፡

(2) የጥበባዊ ሥራ ውል ማለት በአሠራራቸውም ብዙ ዐይነትና ለመሥሪያ ቤቱም የተለየ አስፈላጊነት ያላቸው ነገሮች የሆኑት ናቸው፡፡
ክፍል 1፡፡
ውልን ስለ ማዘጋጀት
ቊ 3246፡፡ ውድድር፡፡ (1) መሠረቱ፡፡
የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት የጥበብ ሰዎች የሆኑትን፤ ወይም የልዩ ሥራዎች ተቋራጭ የሆኑትን ቤቶች ያንድ ሕንጻን ዐቅድ ለማሠራት
ማወዳደር ይችላል፡፡

ቊ 3247፡፡ (2) የግዴታዎች አወሳሰን፡፡

(1) የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ተወዳዳሪዎቹ ዐቅዶቻቸውን የሚያቀርቡበትን የጊዜ ልክ እነዚሁም ዐቅዶች በመልክና በውስጥ መሆን
የሚገባቸውንና ሌላም ማናቸውንም የውድድር ግዴታዎችን እንደፈቃዱ ለመወሰን ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ እንደ ፈቃዱ የተወዳዳሪዎቹ በማንና በምን ዐይነት እንደሚወሰኑ ወይም የደረጃ ተራ ማዕረግ
እንደሚሰጣቸውም ይቈርጣል፡፡

(3) መሥሪያ ቤቱ በውድድሩ ተካፋይ የሚሆኑትን ሰዎች እንደ ፈቃዱ ይመርጣል፤ ለምርጫውም ምክንያት መስጠት የለበትም፡፡

ቊ 3248፡፡ (3) የውድድርን ደንብ የማክበር ግዴታ፡፡


የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ራሱ ያወጣውን የውድድር ደንብ ለማክበር የጠበቀ ግዴታ አለበት፡፡
ቊ 3249፡፡ ስለ ውሉ አፈጻጸም፡፡
የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ ደረጃ ያገኘውን ተወዳዳሪ ለመምረጥ ቃል የገባ ካልሆነ በቀር መልካም ከመሰለው ጋራ ለመዋዋል ነጻ
ነው፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ውል ደንበኛ የሆነ አፈጻጸም፡፡
ንኡስ ክፍል 1፡፡
ስለ ሥራዎች የበላይ ተጠባባቂነት፡፡
ቊ 3250፡፡ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ መብት፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የሥራዎቹን አፈጻጸም ለመጠባበቅ (ለመቈጣጠር) ይችላል፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ሥራው በሚፈቅደው ዐይነት እንዲፈጸም የሥራ ተቋራጩን ለማዘዝ ይችላል፡፡
(3) በውሉ ተቃራኒ የሆኑ ስምምነቶች ካልኖሩ በቀር የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱን የተቈጣጣሪነትና የበላይነት ሥልጣን ከዚህ በታች ባሉት
ቊጥሮች የተመለከቱት ድንጋጌዎች ይወስናሉ፡፡
ቊ 3251፡፡ ስለ መጠባበቅ መብት፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ወኪሎች በሥራ ቦታዎች ዘወትር ገብተው ከሥራ ተቋራጩ ስለ መቈጣጠር የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ
ለመጠየቅ ይችላሉ፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ስለ ሥራ ቦታዎች መልካም ሥርዐትና ጸጥታ ጥበቃ ያወጣቸውን ደንቦች በሚገባ መጠበቅ
አለበት፡፡
(3) ይህን ተቃራኒ የሆነ ውል ሁሉ ፍርስ ነው፡፡
ቊ 3252፡፡ ስለ ሥራዎች የበላይ ተጠባባቂነት፡፡
(1) የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት የሥራ ትእዛዞች እየሰጠ የሥራዎቹን አካሄድ ይወስናል፡፡ እኒሁም ሥራዎች በሚፈቅደው ዐይነት
እንዲፈጸሙ ሥራ ተቋራጩን ያዛል፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ በተሰጡት ፕላኖች ዐይነቶች የዋጋና ሥራ ማስታወቂያው መሠረት ጠንቅቆ መሥራት
አለበት፡፡
ቊ 3253፡፡ ስለ ሥራዎች አካሄድ፡፡
(1) በውል የተደረገው የስምምነት ቃል ሳይነካ መሥሪያ ቤቱ ባንድ ጊዜ ጠቅላላውን ጊዜና እያንዳንዱ የሥራው ክፍል የሚፈጸሙበትን
ጊዜዎች ወይም ለያንዳንዱ ክፍል በተለይ የሆኑትን ጊዜዎች ብቻ ለመወሰን ይችላል፡፡

(2) በውሉ፤ ሥራዎቹ በሙሉ የሚፈጸሙበት ጠቅላላው ጊዜ ብቻ ተወስኖ እንደሆነ፤ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ሥራዎች የሚጀመሩበትን
ጊዜ ዘርዝሮ ማስታወቅ አለበት፡፡

(3) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የሥራዎቹን አከታተልና አካሄድ በውሉ በተመለከተው ጠቅላላ ጊዜ ውስጥ ይወስናል፡፡
ቊ 3254፡፡ ስለ ጊዜዎች መነሻ፡፡
(1) የጊዜዎቹ መነሻ እንደተለመደው የሥራው ውል እንዲታወቅ የተደረገበት ቀን ነው፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ ግዴታዎቹን ለመፈጸም የሚጀምርበት ጊዜ የሚቈጠረው የመሥሪያ ቤቱን ውሳኔ ወይም መሥሪያ ቤቱ ሊያደርግ
የሚገባውን አደራረግ መጠበቅ ያለበት ሲሆን እነዚህ ተግባሮች መፈጸም የተጀመሩበት ቀን ነው፡፡
ቊ 3255፡፡ የተቋራጩ መሥሪያ ቤት ሠራተኞችና መሥሪያዎች፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ለሥራው የሚያስፈልገውን ሠራተኛና በሥራ ላይ የሚውለውን መሥሪያ ብዛት ለመወሰን ይችላል፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ሠራተኞችን ይቈጣጠራል፡፡ ሠራተኞች እንዲለወጡ ወይም ከሥራ እንዲወጡ ይደረጋል፡፡

(3) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በሥራ ላይ የሚውሉትን መሥሪያዎች ይቈጣጠራል፡፡ እንዳይሠራባቸውም ለመከልከል ይችላል፡፡
ቊ 3256፡፡ ብልሹ ስለሆነ ሥራ፡፡
የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በውሉ መፈጸሚያ ጊዜ ውስጥ ብልሹ የሆኑትን ሥራዎች ሥራ ተቋራጩ በኪሣራው እንዲያፈርስና እንደገና
እንዲሠሩ ለማስደረግ ይችላል፡፡
ቊ 3257፡፡ በጽሑፍ ወይም በቃል ስለሆኑ ትእዛዞች፡፡
(1) ሥራ ተቋራጩ የሥራ ትእዛዞችን መፈጸም ያለበት እነዚሁ ትእዛዞች በጽሑፍ ሆነው በተሰጡት ጊዜ ብቻ ነው፡፡
(2) የቃል ትእዛዞች በሥራ ተቋራጩ ላይ ዋጋ የሚኖራቸው በሥራው ለውጥ ነገር ሳይገባ በሥራ ዝርዝር ማስታወቂያ መሠረት ስለ ሥራው
አፈጻጸም ብቻ በሆነ ጊዜ፤ ወይም ሥራ ተቋራጩ በውሉ ይህንኑ ለመፈጸም ግዴታ ገብቶ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 3258፡፡ ስለ ሥራ ተቋራጩ አበቱታ፡፡
ሥራ ተቋራጩ እንዲሠራ ታዞ ሳይፈርም በቀረው ወይም መብቱን ጠብቆ ለፈረመው ሥራ ካልሆነ በቀር በቂ የሆነ አቤቱታ ለማቅረብ
አይችልም፡፡
ቊ 3259፡፡ የሥራ ተቋራጩ የኪሣራ ማግኘት መብት፡፡
(1) በውሉ በተወሰነው መጠን የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ደንበኛ የሆኑትን የተቈጣጣሪነት ችሎታዎችን ቢፈጽም ለተቋራጩ የኪሣራ
መብት አይሰጠውም፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ በራሱ ጥፋት አንድ ጉዳት አድርሶበት እንደሆነ፤ወይም ከልክ በተላለፉ ነገሮች አጠያየቅ ጎድቶት እንደሆነ
ወይም ውሉን ለጊዜው እንዳይፈጽም አግዶት እንደሆነ ሥራ ተቋራጩ አንድ ኪሣራ ለማግኘት መብት አለው፡፡

(3) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ጥፋት ወይም ከመብት መተላለፍ ባያደርግም አድራጎቱ የሥራ ተቋራጩን ሥራ ደንበኛ አፈጻጸም ከባድ
ያደረገበት እንደሆነ ኪሣራውን መክፈል አለበት፡፡
ቊ 3260፡፡ ስለ ሥራ ተቋራጩ ኀላፊነት፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ተቈጣጣሪነት ሥራ ተቋራጩን ከኀላፊነቱ ነጻ አያደርገውም፡፡

(2) የሥራ ተቋራጩ ኀላፊነት የሚቀረው በሥራ ማዘዣዎች ታዞ በሠራ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

(3) ሥራ ተቋራጩ በአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ተቈጣጣሪነት ሥር ሆኖ በራሱ ሐሳብ ባከናወናቸው ሥራዎች መጠን ኀላፊነት
ይኖርበታል፡፡
ንኡስ ክፍል 2፡፡
ስለ ዋጋ አከፋፈል፡፡
ቊ 3261፡፡ ስለ ሥራ ተቋራጭ የሥራ ዋጋ (1) በቊርጥ ዋጋ ለማሠራት ስለ መዋዋል፡፡
ለሥራ ተቋራጩ የሚከፈለው ዋጋ በቊርጥ ለመሆን ይችላል፡፡
ቊ 3262፡፡ (2) በዝርዝር ተራ ዋጋ ለማሠራት ስለ መዋዋል፡፡
ውሉ በሚደረግበት ጊዜ የሚፈጸመውን ሥራ ልክ ለይቶ ሳይወሰን በሥራ መዋዋያው ውል ውስጥ ለሚገኙት ለያንዳንዱ ሥራዎች ውሉ
ልዩ ልዩ የሆኑትን ዋጋዎች ብቻ ለመወሰን ይችላል፡፡

ቊ 3263፡፡ (3) በሥዕል ዝርዝር ማስረጃ፤ ወይም በመለኪያ ልክ እየተላከ ለመክፈል ስለሚደረግ ውል፡፡
የሚፈጸሙትን ሥራዎች ልክና ለየሥራውም ዐይነት የሚከፈለውን የዋጋ ዝርዝሮችን ውሉ ባንድነት ለመወሰን ይችላል፡፡
ቊ 3264፡፡ (4) ወጪዎችን እየተቈጣጠሩ ለመከፈል ስለሚደረግ የሥራ ውል፡፡
ለሥራ ተቋራጩ ለሥራው ያወጣቸውን ዋና ዋና ወጪዎቹን በሚገባ በመቈጣጠር እንዲከፈለውና ለቀረውም ወጪውና ለራሱም በቂ
የሆነ ጥቅም ለማስገኘት በቊጥር የሆነ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲወሰንለት አድርጎ ለመዋዋል ይቻላል፡፡

ቊ 3265፡፡ (5) በትእዛዝ ስለሚፈጸም የሥራ ውል፡፡

(1) የጊዜው ሁኔታ አስገዳጅ በሆነ ጊዜ አስፈላጊነት ላላቸው ሥራዎች ወይም ስለ ውሉ አፈጻጸም ቴክኒካዊ መለዋወጥ ረገድ ውሉ ለጊዜው
አንድ ዋጋ ለመወሰን ይችላል፡፡

(2) እንደዚህ በሆነ ጊዜ ለውሉ መፈጸሚያ የተወሰነው ጊዜ አንደኛው ሩብ ጊዜው ከመፈጸሙ በፊት የመጨረሻውን ዋጋ ልክ ወይም ስለ
ዋጋው አወሳሰን ትክክለኛ የሆኑትን ግዴታዎች የሚወስን ተጨማሪ ስምምነት መደረግ አለበት፡፡
(3) ተዋዋዮቹ ሳይስማሙ ቢቀሩ ግን የሥራ ተቋራጭ ለዳኞች የማመልከት መብት የተጠበቀለት ሆኖ የዋጋውን ልክ የአስተዳደር መሥሪያ
ቤቱ በሦስት ወር ውስጥ ይወስናል፡፡

ቊ 3266፡፡ (6) ስለ ተጨማሪ ሥራዎች፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ አስቀድሞ በሥራው ውል ያልተቋረጣቸውን ሥራዎች ለመሥራት ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ቢታዘዝ መሥራት
ግዴታ አለበት፡፡

(2) ተጨማሪ የሆኑትን ሥራዎች ዋጋ የሚወሰነው ተጨማሪ ስምምነት በሦስት ወር ውስጥ መወሰን አለበት፡፡

(3) ተዋዋዮቹ ሳይስማሙ ቢቀሩ ግን የሥራ ተቋራጩ ለዳኞች የማመልከት መብቱ የተጠበቀለት ሆኖ ዋጋውን የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ
በተከታዩ አንድ ወር ይወስናል፡፡
ቊ 3267፡፡ የዋጋው አከፋፈል፡፡
የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ባንድ የሥራውን አፈጻጸም ሁኔታ በሚያመለክቱት የግዴታዎች ደብተር ውስጥ ወይም ሥራ በተሰጠበት ውል
ውስጥ በኀዋላ ወይም በየዓመቱ የሚከፈል ድርሻ አከፋፈል ካለሆነ በቀር በሌላ ዐይነት የሆነ አንድ ያከፋፈል ቃል እንዳያገባ ክልክል ነው፡፡
ቊ 3268፡፡ ስለ መክፈያ ጊዜ፡፡
(1) የተሠሩትን ሥራዎች መመርመርና ማረጋገጥ ስለ ዋጋው አፈጻጸም ቀዳሚ ጕዳይ የሆነ እንደሆነ፤ ይህ ምርምርና ማረጋገጥ በሥራው
ውል በተወሰነበት ጊዜ ውስጥ መፈጸም አለበት፡፡

(2) የተወሰነው ጊዜ ካለቀ ከዐሥራ አምስት ቀን በኋላ ሥራውን መርምሮ የማረጋገጡ ሥራ ሳይደረግ ቢቀር ይህም የሆነበት በአስተዳደር
መሥሪያ ቤቱ ኀላፊነት የሆነ እንደሆነ መክፈልን በማዘግየት የሚታሰበውን ወለድ እንዲያገኝ መብት ይሰጣል፡፡
ቊ 3269፡፡ ከሒሳብ ላይ የሚታሰብ ገንዘብ አስቀድሞ የመቀበል መብት፡፡
ሥራ ተቋራጩ፡- ፡፡

(ሀ) የተቋረጣቸውን ሥራዎች ለመሥራት በሥራው ቦታላይ አንጡራ ገንዘቡ የሆኑትን የመኪና መሥሪያ ወይም የፋብሪካ ቤትና ለሥራው
የሚያገለግሉ ዕቃዎች አከማችቶ እንደሆነ፤

(ለ) የተቋረጣቸውን ሥራዎች ለመሥራት በተለይ በገዛ ራሱ ለቀጠራቸው ሠራተኞች ቀለባቸውን ከፍሎ እንደሆነ፤ ከሒሳቡ ላይ አስቀድሞ
ገንዘብ እንዲከፍለው ለመጠየቅ መብት አለው፡፡
ቊ 3270፡፡ ከሒሳብ ስለሚታሰቡ ገንዘቦች አከፋፈል፡፡
(1) በሥራ ተቋራጩ ጥያቄ ከሒሳብ ላይ አስቀድሞ ስለሚሰጡ ገንዘቦች አከፋፈል መሠረት ይሆን ዘንድ በየወሩ መጨረሻ የተሠሩትን
ሥራዎች ዝርዝርና ሥራ ተቋራጩም ወጪ ያደረጋቸውን ገንዘቦች ልክ የሚያመለክት ዝርዝር ማስታወቂያ ያዘጋጃል፡፡

(2) በውሉ ውስጥ ይህን የሚወስን የስምምነት ቃል ካልኖረ በቀር ከሒሳብ የሚታሰቡት አስቀድሞ የሚከፈሉት ገንዘቦች የሚሰጡት
በየሦስት ወር ነው፡፡

(3) ከሒሳብ ላይ አስቀድሞ የሚከፈለው ገንዘብ ልክ ከዚህ ቀድሞ ባለው ቊጥር እንደተመለከተው ለሥራው ከሚያገለግሉ ዕቃዎች
ወይም ከታወቁት ደመወዞች ዋጋ እኩል መሆን አለበት፡፡
ቊ 3271፡፡ ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ አስቀድሞ ስለሚከፈለው ገንዘብ፡፡
(1) ሥራ ተቋራጩ ከመሥሪያ ቤቱ ጋራ ስለ ተዋዋለው ሥራ አስቀድሞ ገንዘብ ለመቀበል የሚችለው ለዚሁ አስቀድሞ ለሚከፈለው ገንዘብ
እጅግ ቢያንስ ግማሹን መልሶ ለመክፈል የሚችል አንድ ዋስ ወይም ሌላ ዋስትና ከሰጠ በኋላ ነው፡፡

(2) ይኸውም አስቀድሞ የሚከፈለው ገንዘብ በሥራው ውል ጊዜ በተወሰነው መሠረት ወደፊት ሥራ ተቋራጩ ከሚፈልጋቸው ቀሪ
ገንዘቦች ላይ ተቀናሽ ይሆናሉ፡፡
ቊ 3272፡፡ መጨረሻ ሒሳብን በዝርዝር ስለ መተሳሰብ፡፡
(1) የመጨረሻ ሒሳብን በዝርዝር መተሳሰብ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱን ዕዳዎች የሚወስንና ወገኖቹንም በማይሻር አኳኋን የሚያስገድድ
የሒሳብ ውሳኔ ነው፡፡

(2) ይህንም መጨረሻ ሒሳብ ሥራ ተቋራጩ የተቀበለው እንደሆነ ሕጋዊ ውጤት ያለው ይሆናል፡፡

(3) የመጨረሻ ሒሳብን በዝርዝር መተሳሰብ የሚቻለው በውሉ መሠረት ሥራዎቹ ተፈጽመው ከማለቃቸው በፊት የተወሰኑ ጊዜዎች
ካለፉና ከሥራዎቹም አንደኛው ክፍል ከተፈጸመ በኋላ ነው፡፡
ቊ 3273፡፡ የተስማሙበትን ሒሳቦች እንደገና ስለ መመርመር፡፡
(1) ወገኖቹ በስምምነት የተቀበሏቸውን ሒሳቦች የሒሳብ ስሕተት፤ ዝንጋታ፤ ሐሰት (ሸፍጥ) ወይም በአጠፌታ የመታሰብ ነገር
ካልተገኘባቸው በቀር እንደገና ለመመርመር አይቻልም፡፡

(2) ከዚህ ቀደም ብሎ ባለው ቊጥር የተመለከቱት የሒሳብ ዝንጋታዎችን ስሕተቶችን ማስተካከል የሥራ ልክን ወይም የዋጋን ወይም
የውልን ክርክር የሚያስከትል አይደለም፡፡
ንኡስ ክፍል 3፡፡
ስለ ሥራዎች ርክክብ፡፡
ቊ 3274፡፡ ለጊዜው ስለሆነ ርክክብ፡፡ (1) ለጊዜው የሆነ ርክክብ አኳኋን፡፡

(1) ለጊዜው የሆነ ርክክብ ማለት ሥራዎቹ ተሠርተው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ባሉበት በሥራው ላይ የሚደረግ የምርመራ
ማረጋገጫ ነው፡፡

(2) መብትን በመጠበቅ ተደርጎ ለጊዜው የሆነ ርክክብ በትክክል በእጅ አግብቶ መያዝን የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ቊ 3275፡፡ (2) ስለ ውጤቶች፡፡

(1) ለጊዜው የሆነ ርክክብ ከተደረገ በኋላ ለሚገለጹት የተበላሹ ሥራዎች የርክክቡ ሥራ ተቋራጩን ከአላፊነት ሊያድነው አይችልም፡፡

(2) ለጊዜው የሆነ ርክክብ፤ ሥራ ተቋራጩ ለሥራው የታቀደውን ዐቅድ በመለወጥ የሠራው ሥራ ቢኖር፤ በዝምታ እንደተቀበሉት አድርጎ
የሚያስቈጥር ነው፡፡

(3) ለጊዜው የሆነ ርክክብ ለሥራው መድን ለመሆን የተወሰነው ጊዜ መከፈቱን (መጀመሩን) የሚያመለክት ነው፡፡ ለመድንነት
የተወሰነውም ጊዜ በተፈጸመ ጊዜ የመጨረሻው ርክክብ ይደረጋል፡፡

ቊ 3276፡፡ (3) ስለ ጥፋትና ብልሽት የአደጋ ኪሣራን ስለ መቻል፡፡

(1) ከፍተኛ የሆነ ኀይል ምክንያት መፈራረስ ወይም ጉዳቶች ቢደርሱ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ለጊዜው በሆነ ርክክብ ሥራዎቹን
ካልተረከባቸው በቀር ኪሣራው የሥራ ተቋራጩ ነው፡፡

(2) የጠቅላላ ሁኔታዎችንና ሥራ ተቋራጭ የሚፈጽማቸውን የሚያመለክቱ የግዴታዎች ደብተሮች ከዚህ ደንብ ሊነጠሉ ይችላሉ፡፡

(3) እንደዚህ በሆነ ጊዜ ለሥራ ተቋራጩ የሚገባውን የኪሣራ ልክ የመጠየቂያውንም ጊዜና ሥርዐቱን ይወስኑታል፡፡

ቊ 3277፡፡ የመድንነት ጊዜ (1) የመድንነት ጊዜ አኳኋን፡፡

(1) የመድንነት ጊዜ የተባለው የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ሥራዎቹን በጭራሽ ከመረከቡ በፊት ሥራዎቹ በደኅና ስለ መሠራታቸው
ለመመርመር የሚያስችለው ጊዜ ነው፡-

(2) ለጊዜውም ልክ በውሉ የተወሰነ ነው፡፡


ቊ 3278፡፡ (2) ስለ ውጤቶች፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ ለሥራው ማድንነት ባለበት ጊዜ ውስጥ ሥራው በመልካም ሁኔታ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ ለተበላሹ ሥራዎች መድን ነው፡፡ ስለዚሁም ከአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት እንዲያድሳቸው ትእዛዝ በደረሰው ጊዜ ማደስ
ግዴታ አለበት፡፡

ቊ 3279፡፡ ስለ መጨረሻ ርክክብ፡፡ (1) የሚፈጸምበት አኳኋን፡፡

(1) የመጨረሻ ርክክብ ማለት የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ሥራ ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደኅና የፈጸመ መሆኑን ከተረዳው በኋላ
ሥራዎቹን በጭራሽ በእጁ የሚያደርግበት አፈጻጸም ነው፡፡

(2) መጨረሻው ርክብብ የሚፈጸመው ወገኖቹ ባሉበትና በፕሮሴቬርባል ተጽፎ ነው፡፡

ቊ 3280፡፡ (2) ስለ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ አለመቅረብ፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ያልቀረበ እንደሆነ፤ ሥራው ለመቀበል በሚቻል ሁኔታ ላይ መሆኑ ታይቶ ዳኞች
እንዲያረጋግጡ ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) እንደዚህም ሲሆን የመጨረሻው ርክክብ ስለ መድንነት በተወሰነው ጊዜ መፈጸሚያ ላይ ወይም ስለ መድንነት የተወሰነ ጊዜ የሌለ
እንደሆነ፤ ዳኞች በወሰኑት ቀን እንደተደረገ ሆኖ ይቈጠራል፡፡

ቊ 3281፡፡ (3) ስለ ውጤቶች፡፡

(1) የመጨረሻው ርክክብ ሥራ ተቋራጩ ስለ ሥራው መልካም አያያዝ ያለበትን ግዴታ ያወርድለታል፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ ከዋጋው ቀሪ ሒሳቡ እንዲከፈለውና ለዋስትና መያዣ የተያዙበት ገንዘቦችም ይመለሱለት ዘንድ መብት አለው፡፡
ቊ 3282፡፡ ስለ አሠራር ጕድለት መድንነት፡፡
(1) ሌላ ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ካልኖረ በቀር ሥራ ተቋራጩ መሥሪያ ቤት ሥራዎቹን ከተረከባቸው ቀን አንሥቶ ወደፊት እስከ ዐሥር
ዓመት ድረስ ስለ ሥራው አሠራር ጕድለት ለአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ኀላፊ መድን ነው፡፡

(2) ስለሆነም ይህ መድንነቱ በሥራው የመጨረሻ ርክክብ ጊዜ ይታዩ ለነበሩት ጕድለቶች የተሰጠ አይደለም፡፡

(3) መድንነት ያላቸው ጕድለቶች ሥራው ሊያገለግል የተሠራበትን በውሉ ውስጥ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለመሥራት የሚያውኩ፤
ወይም በጣም አክሣሪ የሆኑ ወይም ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ጕድለቶች ናቸው፡፡
ክፍል 3፡፡
ውልን ስለ ማሻሻል፡፡
ቊ 3283፡፡ ውሉን ለብቻ ስለ ማሻሻል፡፡ (1) የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት መብት፡፡

(1) ለመንግሥት ሥራዎች ውል በሚፈጸምበት ጊዜ ተቃራኒ የሆነ ውል ቢኖርም እንኳ አስቀድሞ በግዴታዎች ደብተር የተመለከተ ውንና
በመገበያያውም ውል የተወሰነውን ለማስለወጥ በራሱ ፈቃድ ብቻ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ሥራ ተቋራጩን ሊያዘው ይችላል፡፡

(2) እኒህ የሚለወጡ ሥራዎች ለመንግሥቱ ሥራዎች መልካም አቀማመጥ ጠቃሚ መሆን አለባቸው፡፡

(3) እነርሱም በውሉ የተስማሙበትን የገንዘብ ግዴታዎች ለመንካት አይችሉም፡፡

ቊ 3284፡፡ (2) ስለ አዳዲስ ሥራዎች፡፡

(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት በውሉ ውስጥ ያልተመለከቱትን ሥራዎች በአንድ አዲስ በሆነ ዋጋ እንዲሠራው ሥራ ተቋራጩን ለማዘዝ
ይችላል፡፡
(2) ቢሆንም መሥሪያ ቤቱ በውሉ ከተመለከተው ሥራ ፍጹም ልዩ የሆነና ወይም ከዚሁ ሥራ ጋራ ግንኙነት የሌለውን ሥራ እንዲሠራ
ሥራ ተቋራጩን ሊያዘው አይችልም፡፡

(3) እንዲሁም በውሉ ውስጥ ከተመለከቱት ፍጹም ልዩ በሆኑ ግዴታዎች መሠረት አንድ ሥራ እንዲሠራ ያስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ሥራ
ተቋራጩን ሊያዘው አይችልም፡፡

ቊ 3285፡፡ (3) የሥራ ተቋራጩ መብቶች፡፡

(1) ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የታዘዙት የሥራዎች መጨመር ወይም መጕደል በውሉ ከታሰበው ሥራ ከስድስቱ እጅ በላይ የሆነ ልዩነት
ያስከተለ እንደሆነ ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ካልኖረ በቀር ሥራ ተቋራጩ ውሉን ለማፍረስ መብት አለው፡፡

(2) ሥራ ተቋራጩ ከሚሠራው ሥራ ላይ ጠቅላላ አቀናነስ የተደረገ እንደሆነ ውሉ በመለዋወጡ ምክንያት ለደረሰበት ጉዳትና ሊያገኝ
ይገባው በነበረው ትርፍ ልክ የሆነ ኪሣራ የማግኘት መብት አለው፡፡

(3) የውሉን መለዋወጥ ያስከተለው ምክንያት ውሉን ባደረገው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ጥፋት ሳይሆን ከዚህ ውጭ በሆነ ምክንያት
መሆኑን ዳኞች የተረዱት እንደሆነ ሥራ ተቋራጩ ለቀረበት ሊያገኝ ለነበረው ትርፍ የሚከፈለው ኪሣራ የተወሰነ እንዲሆን ሊቈርጡ
ይችላሉ፡፡
ቊ 3286፡፡ ስለ ድንገተኛ እክሎች፡፡ (1) መሠረቱ፡፡

(1) ሥራ ተቋራጩ ውሉን በሚፈጽምበት ጊዜ ታይቶ የማይታወቅ ውሉም በተደረገ ጊዜ ያልታበበ እክል ያጋጠመው እንደሆነ ውሉ
እንዲሻሻልለት ለመጠየቅ ይችላል፡፡

(2) ከሥራ ተቋራጩ ውሉን የተዋዋለው የአስተዳደር መሥሪያ ቤት ውሉ እንዲሰረዝ ካልፈቀደ በዚሁ ባልታሰበ ድንገተኛ እክል
ከተፈጠረው ወጪ አንዱን ክፍል ራሱ መቻል ይገባዋል፡፡

(3) ይህም ጕዳይ በዚሁ አንቀጽ ስላልታሰቡ ነገሮች በተወሰኑት ደንቦች የሚፈጸም ነው፡፡

ቊ 3287፡፡ (2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱን ምክር የመጠየቅ አስፈላጊነት፡፡

(1) በውሉ ያልተመለከተውን ሥራ ለመሥራት ባጋጠመው እክል ምክንያት ሥራ ተቋራጩ ተገዳጅ የሆነ እንደሆነ ይህንኑ ለመሥራት
የሚችለው ከመሥሪያ ቤቱ ይህን የተባለውን ሥራ ለመፈጸም ትእዛዝ እንዲተላለፍለት ካመለከተ በኋላ ነው፡፡

(2) የተባለውን ሥራ ስለ ውሉ አፈጻጸም ፍጹም አስፈላጊነት ያለውና አስቸኳይነትም ያለው ከሆነ ከአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ትእዛዝ
ባይኖርም ሥራ ተቋራጩ መሥራት ይችላል፡፡

(3) እንደዚህም በሆነ ጊዜ ስለ ሥራዎች አመራር ነገር በዚሁ ሕግ በተወሰነው መሠረት ሥራ ተቋራጩ ኪሣራ ለማግኘት መብት አለው፡፡
ክፍል 4፡፡
ስለ ውል አለመፈጸም፡፡
ቊ 3288፡፡ በሥራ መሪ ሥር ስለ ማድረግ (1) ግዴታዎች፤ (ሁኔታዎች)፡፡

(1) በመንግሥት ሥራ ውል ሥራ ተቋራጩ ያሉበትን ግዴታዎች ሳይፈጽማቸው የቀረ እንደሆነ ሥራው በሥራ መሪ ውስጥ ሆኖ እንዲሠራ
ይደረጋል፡፡

(2) ተቃራኒ የሆነ የውል ቃል ቢኖርም እንኳ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ለሥራ ተቋራጩ ግዴታዎቹን እንዲፈጽም ካስጠነቀቀው በኋላ
ባጭሩ ዐሥር ቀን ካልሆነው በቀር ሥራውን በሥራ መሪ ውስጥ ለማድረግ አይቻለውም፡፡

(3) ሥራው በሥራ መሪ ሥር እንዲሆን አስፈላጊ የሆነው አንዱን ክፍል ሲሆን በሥራ መሪ ሥር ለማድረግ የሚቻለውም የሥራዎቹን
አንዱን ክፍል ነው፡፡

ቊ 3289፡፡ (2) ስለ ውጤቶች ፡፡


(1) ሥራው በሥራ መሪ ሥር በተደረገ ጊዜ ሥራ ተቋራጩ ለጊዜው ሥራ ከተቋረጠበት የተላቀቀ ሆኖ ይገኛል፡፡

(2) ሥራ አመራሩ የሚከናወነው በሥራ ተቋራጩ ወጪና ኪሣራ ነው፡፡

ቊ 3290፡፡ (3) ስለ ማቆም፡፡


ሥራ ተቋራጩ ሥራዎቹ በሥራ መሪ ሥር መሆናቸው ቀርቶ በደኅና ከፍጻሜ ለማድረስ የሚያስችሉት አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች እንዳለው
ለማረጋገጥ ከቻለ በሥራ መሪ ሥር ያለው ሥራ እንዲለቀቅለት ይደረጋል፡፡
ቊ 3291፡፡ እንደገና ስለ ማጫረት፡፡
(1) የመንግሥቱ ሥራ ውል ሊሰረዝ መቻሉ በግልጽ በውሉ ታውቆለት እንደሆነ፤ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ እንደገና በሐራጅ ለማጫረት
ወይም ላንድ ሌላ አዲስ ሥራ ተቋራጭ በስምምነት ሥራውን ለመስጠት ይችላል፡፡

(2) ከሥራ ውጭ የተደረገው ሥራ ተቋራጭ በዚህ አኳኋን አዲሱ የሥራ ውል ለመሥሪያ ቤቱ የሚያስከትለውን ከባድ የሆነውን ወጪ
ራሱ መቻል አለበት፡፡
ቊ 3292፡፡ ስለ ዳኞች ተቈጣጣሪነት፡፡
(1) የመንግሥት ሥራዎች ተዋዋይ የሆነው ሰው የሚገባውን እንዲፈጽም የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ያደረገውን የማስገደጃ ወይም የውል
ማፍረስ ውሳኔ (ቅጣት) ዳኞች ሊሽሩት አይችሉም፡፡

(2) ዳኞች ማድረግ የሚችሉት ውሎቹን በመመርመር ይህ ውሳኔ (ቅጣት) አላገባብ ተደርጎ እንደሆነ ሥራ ተቋራጩ ኪሣራ የሚያገኝበት
መብት ያለው መሆኑን ብቻ ነው፡፡
ክፍል 5፡፡
ውልን ለዋስትና መያዣነት ስለ ማስተላለፍ፡፡
ቊ 3293፡፡ የመንግሥት ሥራ የተቋረጠበትን ውል በዋስትና ስለ ማስያዝ፡፡
ሥራ ተቋራጩ ወይም መሥሪያ ቤቱ ያወቃቸው ከዋናው ተቋራጭ ውስጥ ሁለተኛ ተቋራጮች የሆኑት የመንግሥትን ሥራ
የተቋረጡባቸውን ውሎች ለዕዳ መያዣ ሊሰጧቸው ይችላሉ፡፡
ቊ 3294፡፡ የመንግሥትን የሥራ ውል ስለ ማስተላለፍ፡፡
የመንግሥት ሥራ ውል በደንብ መሠረት እንዲተላለፍ ተደርጎ እንደሆነ ዋጋውን ለመቀበል መብት ያለው አስተላላፊው ብቻ ነው፡፡
ቊ 3295፡፡ ከዋናው ተቋራጭ ውስጥ ተቋራጭ የሆነው ሰው መብቶች፡፡
(1) በአስተዳደር መሥሪያ ቤት የታወቀ ከዋና ተቋራጭ ውስጥ ሁለተኛ ተቋራጭ የሆነ ሰው ስለፈጸማቸው ሥራዎች ዋጋውን በቀጥታ
ከመሥሪያ ቤቱ ለመቀበል ይችላል ይህም ዋናው ተቋራጭ የፈቀደለት ሲሆንና በውሉም ሁለተኛው ሥራ ተቋራጩ የሚሠራው የሥራ
ዐይነትና የሥራውም ዋጋ በግልጽ የተመለከተ በሆነ ጊዜ ነው፡፡

(2) ሁለተኛው ሥራ ተቋራጭ የፈጸማቸውን ሥራዎች የሚያስረዱ የዝርዝር ማስታወቂያዎቹን የውሉ ባለቤት እንዲቀበላቸው አስፈላጊ
ነው፡፡

(3) ከሁለተኛው ሥራ ተቋራጭ ጋራ በቀጥታ ለመተሳሰብ የሚይቻል የሚሆነው ዋናው ተቋራጭ ውሉን በመያዣነት በሰጠው ጊዜ ነው፡፡
ቊ 3296፡፡ ከሒሳብ አስቀድሞ የሚከፈል ገንዘብን መከልከል፡፡
ሁለተኛ ሥራ ተቋራጭ የሆነው በማናቸውም አኳኋን ቢሆን ከሒሳብ አስቀድሞ የሚከፈል ገንዘብ ለመቀበል አይችልም፡፡
ምዕራፍ 4፡፡
ስለ ዕቃዎች ማቅረብ ውል፡፡
ቊ 3297፡፡ ስለ ውል አፈጻጸም፡፡
(1) ዕቃ አቅራቢው ስለ ውሉ አፈጻጸም የሚያስፈልገውን ለማድረግ ምርጫና ቅድሚያ አለው፡፡

(2) ዕቃ አቅራቢው ያሉበትን ግዴታዎች ለመፈጸም አስፈላጊ የሆኑትን ዕቃዎች ከሚፈቅዳቸው ሰዎች ላይ ለመግዛት ይችላል፡፡
ቊ 3298፡፡ ስለ አደጋ፡፡
(1) ዕቃውን የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ እስኪረከበው በመካከሉ ባንድ ከዐቅም በላይ በሆነ ከፍተኛ ኀይል ምክንያት በዕቃው ላይ
ለሚደርስበት አደጋ ኪሣራውን የሚችለው ራሱ አቅራቢው ብቻ ነው፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የቀረቡለትን ዕቃዎች ተቀብሎና በዕቃ ማከማቻ ቤቱ ካስቀመጠበት ቀን አንሥቶ ዕቃዎቹን ለመረከብ
ወይም ተመላሽ ለማድረግ አንድ የመጨረሻ ውሳኔ እተሰጠበት ቀን ድረስ የዕቃ አደራ ከታቾች እንዳለባቸው ኀላፊነት ይኖርበታል፡፡
ቊ 3299፡፡ ስለ ዕቃዎች ርክክብ፡፡
የዕቃዎች ርክክብ በውሉ ውስጥ በተመለከተው አኳኋንና በተወሰነውም ጊዜ ውስጥ የሚፈጸም ነው፡፡
ቊ 3300፡፡ የርክክቡን ጊዜ ስለ ማስተላለፍ፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤት የቀረቡለትን ዕቃዎች የተበላሹ ከሆኑ የርክክቡን ጊዜ ለማስተላለፍ ይችላል፡፡

(2) እንደዚህም በሆነ ጊዜ መሥሪያ ቤቱ ላቅራቢው ስለ ተበላሹት ዕቃዎች የሚያሻሽልበትን ጊዜ ልክ ወስኖ ያስታውቀዋል፡፡
ቊ 3301፡፡ ዋጋ ስለሌላቸው ዕቃዎች፡፡
የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ በትክክል እንደተስማማበት ዐይነት ያልሆኑትን ዕቃዎች የኒህም ጕድለታቸው ለመሥሪያ ቤቱ የሚቀርቡትን
ዕቃዎች ጥቅም የሚያጠፋና አቅራቢውም በተፈለገበት ጊዜ ይህንን ጕድለት ለማሻሻል ያልቻለ ወይም ያልፈለገ እንደሆነ ሊቀበላቸው
አይችልም፡፡
ቊ 3302፡፡ ስለ ዕቃዎች ምርመራ ኪሣራ፡፡
(1) በአቅራቢው ቤት የሚደረገው የዕቃዎች ምርመራ በአቅራቢው ኪሣራ ነው የቀረው ግን በአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት ኪሣራ ነው፡፡

(2) አቅራቢውም በምርመራዎቹ ጊዜ በቦታው ላይ የመገኘት መብት አለው፡፡

(3) ስለ ምርመራው አፈጻጸም የተወሰነውን ጊዜ ለአቅራቢው እንዲነግረው አስፈላጊ ነው፡፡ አሳቡንም ይሰጥ ዘንድ ይፈቀድለታል፡፡
ቊ 3303፡፡ ስለ አቅራቢው ኀላፊነት፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ያደረገው የመጠባበቅ ተግባር ያቅራቢውን ሙሉ ኀላፊነት አይቀንስለትም፡፡

(2) እንዲሁም የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ዕቃዎቹን በተረከበበት ጊዜ ተበላሽተው የተገኙትን ዕቃዎች ሳይቀበል ወይም በተወሰነው
የመድንነት ጊዜ ውስጥ የተበላሹትን ለማሳደስ ያለውን መብት ሊያስቀርበት አይችልም፡፡
ቊ 3304፡፡ በሌለበት ማስፈጸም፡፡
(1) በዕቃ ማቅረብ ውል አቅራቢው በፍጠነት እንዲያቀርብ የታዘዘውን ሳያቀርብ በመቅረቱ ወይም አንድ የዕቃ ማቅረብ ውል የተሰረዘ
እንደሆነ በሌለበት ለማስፈጸም ማስደረግ ይቻላል፡፡

(2) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ሳያቀርብ በቀረው ዕቃ አቅራቢ ተተክቶ ዕቃዎቹን ከሌለ አቅራቢ ዘንድ ገዝቶ ወይም በራሱ ፋብሪካ አሠርቶ
ያቀርባል፡፡

(3) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱም ውሉን ሳይፈጽም ከቀረው አቅራቢ ላይ ኪሣራ ለመከፈል መብት አለው፡፡
ቊ 3305፡፡ ለዳኞች አቤቱታ ስለ ማቅረብ፡፡
(1) የአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ የዕቃ አቅራቢነት ውል ተዋዋይ የሆነው የሚገባውን ግዴታ እንዲፈጽም ያደረገውን የማስገደጃ ወይም የውል
ማፍረስ ውሳኔ ቅጣት ዳኞች ሊሽሩት አይችሉም፡፡

(2) ዳኞች ማድረግ የሚችሉት ውሎቹን በመመርመር ይህ ውሳኔ (ቅጣት) አላገባብ ተደርጎ እንደሆነ አቅራቢው ኪሣራ የሚያገኝበት
መብት ያለው መሆኑን ብቻ ነው፡፡

(3) ከዚህም ቀጥሎ ባለው ቊጥር የተመለከተው ድንጋጌ የተጠበቀ ነው፡፡


ቊ 3306፡፡ ለአስተዳደሩ መሥሪያ ቤት አስቀድሞ አቤቱታ ሰለ ማቅረብ፡፡
(1) ተዋዋዩ ይህን ተቀዳሚ ሥነ ሥርዐት እንዲከተል ውሉ በሚያስገድደው መጠን አስቀድሞ አቤቱታውን ለአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ
ባለሥልጣኖች ማቅረብ አለበት፡፡

(2) ይህን ግዴታ የሆነውን ለመሥሪያ ቤቱ የሚቀርበውን አቤቱታ ሳያስቀድም ለዳኛ የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት ሊያገኝ
አይችልም፡፡
(3) ውሉ ለአስተዳደር መሥሪያ ቤቱ ስለሚቀርበው አቤቱታ ጊዜ ወስኖ እንደሆነ ተዋዋዩም ይኸንኑ የተወሰነውን ጊዜ አሳልፎ አቅርቦ
እንደሆነ ጊዜው በመተላለፉ አቤቱታው የማይቅበሉት ይሆናል፡፡ ለዳኛም የሚቀርበው አቤቱታ ተቀባይነትን ሊያገኝ አይችልም፡፡

አንቀጽ ኻያ፡፡
ስለ ግልግልና ስለ ስምምነት የሚደረግ ውል፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ስለ ግልግል
ክፍል 1፡፡
ስለ ግልግል በጠቅላላው፡፡
ቊ 3307፡፡ ትርጓሜ፡፡

ግልግል ማለት ተዋዋይ ወገኖች፤ አንዱ ላንዱ አንድ ነገር ትቶ ወይም ሰጥቶ የተጀመረውን ክርክር የሚያቆሙበት ወይም የሚፈጠረውን
ክርክር አስቀድመው የሚያስቀሩበት አንድ ውል ነው፡፡

ቊ 3308፡፡ (2) የፎርሙ ግዴታ፡፡

(1) ግልግል በመብት ምክንያት የሚያገኙዋቸውን ነገሮች የመፍጠር የመለዋወጥ ወይም የማስቀረት ውጤት ሊኖረው ይችላል፡፡

(2) የነዚህንም ግንኙነቶች ያለ ዋጋ ለመፍጠር ለመለዋወጥ ወይም ለማስቀረት በሕግ የተደነገጉት የፎርም ግዴታዎች መጠበቅ አለባቸው፡፡

ቊ 3309፡፡ አተረጓጐም፡፡ (1) መሠረቱ፡፡


ስለ መብት መተው የሚደረጉ የግልግል ቃሎች በጠባብ አኳኋን መተርጐም አለባቸው፡፡
ቊ 3310፡፡ (2) አፈጻጸም፡፡
(1) ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን የክስና የይገባኛል ባይነቱን መብቶች ሁሉ የተወ እነደሆነ ግልግሉ የሚያስቀራቸው ከግልግል ለመግባት
ምክንያት የነበሩትን የክስ መብቶችና የይገባኛል ባይነቱን መብቶች ብቻ ነው፡፡

(2) በራሱ በነበረው ባንድ መብት ላይ መገላገሉ ከሌላ ከአንድ ሰው ይኸንኑ የመሰለ መብት ያገኘ እንደሆነ፤ አዲስ የተገኘው መብት
ካለፈው ግልግል ጋራ የተሳሰረ አይሆንም፡፡
ቊ 3311፡፡ ግልግሉ የሚጸናበት፡፡
ከባለጕዳዮቹ ባንዱ የተደረገ ግልግል ሌሎቹን ባለጕዳዮች አያስገድድም እነርሱም መቃወሚያ ሊያደርጉት አይችሉም፡፡
ቊ 3312፡፡ የመብት ስሕተት፡፡
(1) ግልግል በተዋዋይ ወገኖች መካከል ይግባኝ ሳይኖረው መጨረሻ ሆኖ እንደተፈረደ ፍርድ ሥልጣን አለው፡፡

(2) ግልግል ያደረጉበትን መብቶች በመመልከት በተዋዋይ ወገኖች ወይም ከነርሱ ባንዱ በተደረገው ስሕተት ምክንያት ግልግል ሊነካ
አይቻልም፡፡
ቊ 3313፡፡ ዋነኛ ስሕተት፡፡
(1) ፍርስ ወይም ሐሰተኛ የሆኑ ሰነዶች፡፡

(1) ከስሕተት የተነሣ ግልግልን ለማፍረስ የሚቻለው፤ ለመፈጸም ግዴታ የገቡበት ሰነድ ራሱ ፍርስ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡

(2) እንዲሁም የተዋዋይ ወገኖች ወይም ከነርሱ ያንዱ ፈቃድ የተገኘው ሐሰተኛነቱ በታወቀ ባንድ ሰነድ መሠረት እንደሆነ ግልግሉን
ለማፍረስ ይቻላል፡፡

(3) በውሉ ጊዜ ተዋዋይ ወገኖች ሰነዱ ፈራሽ ወይም ሐሰተኛ ለመሆን መቻሉን አስበው የተገላገሉ እንደሆነ በሁለቱም ጊዜ ግልግሉ
እንደጸና ይቀራል፡፡

ቊ 3314፡፡ (2) ያልታወቀ ፍርድ፡፡

(1) ተዋዋዮቹ ወይም ከነርሱ አንዱ ሳያውቁት ከግልግሉ በፊት መጨረሻ በሆነ በፍርድ ጕዳዩ አልቆ እንደሆነ ግልግሉን ለማፍረስ ይቻላል፡፡

(2) በተዋዋይ ወገኖች ወይም ከነርሱ ባንዱ ያልታወቀው ፍርድ በደንበኛው ይግባኝ መንገድ ለመቅረብ የሚቻል ሲሆን ግልግሉ ዋጋ ያለው
ሆኖ ይቈያል፡፡

ቊ 3315፡፡ (3) ጠቅላላ ስምምነትን የሚያስከትል ግልግል፡፡

(1) ተዋዋይ ወገኖች አንድነት በሚኖሩዋቸው ነገሮች ሁሉ ላይ በጠቅላላው የተገላገሉ እንደሆነ፤ ለተዋዋይ ወገኖች ወይም ላንዱ ግልግሉ
በሚፈጸምበት ጊዜ ያልታወቁ ሰነዶች በመጨረሻው የተገለጹ በመሆናቸው ምክንያት ግልግሉ ፍርስ ለመሆን አይችልም፡፡

(2) ነገር ግን ውሉ በሚፈጸምበት ጊዜ የተባሉት ሰነዶች ከተዋዋይ ወገኖች ባንዱ ወገን ሳይገለጹ ቀርተው እንደሆነ ግልግሉ ፍርስ ለመሆን
ይችላል፡፡
ቊ 3316፡፡ ሕገ ወጥ የሆነ ግብ፡፡
ግልግሉ ለሕግ ወይም ለመልካም ተግባር ተቃራኒ ከሆነ፤ ከአንድ ውል ጋራ ግንኙነት ያለው እንደሆነ ፍርስ ነው፡፡
ቊ 3317፡፡ በሁለቱ ወገኖች መስጠት የሚገባው መድን፡፡
(1) በግልግል ስምምነት ውስጥ አንደኛው ወገን በሚያደርገው የመብት መተው፤ ግልግሉ የሚያስከትለው ውጤት መብት መኖሩን መግለጽ
ብቻ ነው፡፡

(2) ስለሆነም የተተወውን መብት ለማስተላለፍ አስፈላጊ የሆኑት የችሎታና የፎርም ግዴታዎች ሊጠበቁ ይገባቸዋል፡፡
(3) ግልግሉን ያደረጉት ወገኖች ለራሳቸው ሥራና በግልጽ በውላቸው ለተጻፈው ጕዳይ ካልሆነ በቀር ለነዚሁ መብቶች አንዱ ላንዱ መድን
መሆን የለበትም፡፡
ክፍል 2፡፡
ስለ ዕርቅ፡፡
ቊ 3318፡፡ አስታራቂ ስለ መምረጥ፡፡
(1) ተዋዋይ ወገኖች ላንድ ሦስተኛ ሰው እንዲያስታርቃቸውና ቢቻልም በመካከላቸው አንድ ግልግል እንዲያደርግላቸው ሥልጣን
ሊሰጡት ይችላሉ፡፡

(2) በተዋዋይ ወገኖች ጥያቄ አስታራቂው ባንድ ድርጅት ወይም ባንድ ሦስተኛ ወገን ሊመረጥ ይቻላል፡፡

(3) አስታራቂ ሆኖ የተመረጠው ሰው ይኸንን ሥራ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ነጻነት አለው፡፡


ቊ 3319፡፡ የተዋዋይ ወገኖች ግዴታዎች፡፡
(1) ተዋዋይ ወገኖች ለሥራው አፈጻጸም የሚሆኑትን መረጃዎች ለአስታራቂው ማቅረብ አለባቸው፡፡

(2) የአስታራቂውን ሥራ የማይቻል ወይም በጣም አስቸጋሪ ከሚያደርገው ሥራ መራቅ (መወገድ) አለባቸው፡፡
ቊ 3320፡፡ የአስታራቂው ግዴታዎች፡፡
(1) አስታራቂው የመጨረሻ ውሳኔዎቹን ከመግለጹ በፊት ለተዋዋይ ወገኖች አስተያየታቸውን በሙሉ እንዲያቀርቡ መፍቀድ አለበት፡፡

(2) አስታራቂው የግልግል ቃሎችን ይጽፋል ወይም ለመገላገል ካልቻለ ዕርቅ ስላለመደረጉ አንድ ፕሮሴቬርባል ያዘጋጃል፡፡

(3) እነዚህንም ጽሑፎች ለተዋዋይ ወገኖች ይሰጣል፡፡


ቊ 3321፡፡ የተወሰነ ጊዜ፡፡
(1) አስታራቂው በውል በተመለከተው የተወሰነ ጊዜ ውስጥ ወይም ጊዜው ያልተወሰነ እንደሆነ ከተመረጠበት ቀን አንሥቶ በስድስት ወር
ውስጥ ተግባሩን መፈጸም አለበት፡፡

(2) በዚሁ ጊዜ ተዋዋይ ወገኖች የመብቶቻቸውን የጥበቃ ተግባሮች ለመፈጸም ይችላሉ፡፡

(3) አስታራቂው ዕርቅ ስላለመደረጉ አንድ ፕሮሴቬርባል ካላዘጋጀ በቀር ተዋዋይ ወገኖች ይህ ጊዜ ከማለቁ በፊት ስለ ክርክራቸው በዳኞች
ፊት ለመቅረብ አይችሉም፡፡
ቊ 3322፡፡ የአስታራቂው ሥልጣን፡፡
(1) የአስታራቂው ሥልጣን ጠባብ በመሆን መተርጐም አለበት፡፡

(2) ተዋዋይ ወገኖች አስታራቂው ያደረጋቸውን የግልግል ቃሎች ለማረጋገጥ በጽሑፍ በግልጽ ግዴታ ካልገቡ ሊገደዱ አይችሉም፡፡
ቊ 3323፡፡ የአስታራቂው ወጪዎችና የድካም ዋጋዎች፡፡
(1) አስታራቂው ለሥራው አፈጻጸም በሚገባ ሁኔታ ያደረጋቸውን ወጪዎች ተመላሽ እንዲደረጉለት ለመጠየቅ መብት አለው፡፡
ተቃራኒ የሚሆን ግልጽ ስምምነት ከሌለ በቀር አስታራቂው የሥራ ዋጋ ለማግኘት መብት የለውም፡፡
ቊ 3324፡፡ የግልግል ደንቦች ተፈጻሚ ስለ መሆናቸው፡፡
በአስታራቂው አማካይነት ግልግል በተፈጸመ ጊዜ ለቀሪው አሠራር ሁሉ ባለፈው ክፍል የተደነገጉት ውሳኔዎች ይጸናሉ፡፡
ምዕራፍ 2፡፡
በዘመድ ዳኛ የመጨረስ ስምምነት፡፡
ቊ 3325፡፡ ትርጓሜ፡፡
(1) የግልግል ስምምነት ማለት ተዋዋይ ወገኖች ያንድ ክርክርን ውሳኔ ለአንድ የዘመድ ዳኛ ለሆነው ለአንድ ሦስተኛ ሰው አቅርበው የዘመድ
ዳኛው ውል በሕግ አግባብ መሠረት ይኸንኑ ክርክር ለመቊረጥ የሚያደርገው ውል ነው፡፡

(2) የዘመድ ደኛው በሕግ በኩል ነገሩ የሚያስከትለውን ውጤት ሳይወስን አንድ የተለይ ጕዳይ ብቻ እንዲያረጋግጥ ሊመረጥ ይችላል፡፡

ቊ 3326፡፡ ችሎታና ፎርም (1) መሠረቱ፡፡

(1) መብትን ያለ ዋጋ ለመስጠት ስለ መቻል የሚያስፈልገው ችሎታ በዚሁ መብት የተነሣውን ክርክር በዘመድ ዳኛ ለመጨረስ
ለሚደረገውም ውል አስፈላጊ ነው፡፡

(2) በዘመድ ዳኛ ለመጨረስ የሚደረገው ስምምነት በሕግ ይህንኑ መብት ያለ ዋጋ ለመስጠት አስፈላጊ በሆነው ፎርም ዐይነት መፈጸም
አለበት፡፡
ቊ 3327፡፡ (2) የተጠበቀ ሁኔታ፡፡

(1) ከዚህ በላይ ያለው ቊጥር ድንጋጌዎች ይህ ሕግ ወደ ሽምግልና ዳኝነት እንዲቀርብ በግልጽ ባዘዘው ጕዳይ ተፈጻሚ አይሆኑም፡፡

(2) ለእንደዚህ ያለው ጕዳይ በሽምግልና ዳኝነት የመጨረሱን ስምምነት አካለ መጠን ባላደረሰው ወይም በተከለከለው ሰው ስም ሞግዚቱ
ሊፈጽም ይችላል፡፡

(3) በሽምግልና ዳኝነት ለመጨረስ የሚደረገው ስምምነት ማናቸውንም ፎርም መከተል የለበትም፡፡
ቊ 3328፡፡ የደረሰና ያልደረሰ ክርክር በዘመድ ዳኛ ለመጨረስ ስለሚደረግ ስምምነት፡፡
(1) ለዘመድ ዳኛ የቀረበው ክርክር ቀድሞውኑ የነበረ ክርክር መሆን ይችላል፡፡

(2) እንዲሁም አንድ ውል በሚደረግበት ጊዜ ተዋዋይ ወገኖች በአጋጣሚ በዚህ ውል ለመነሣት የሚችለውን ክርክር ለዘመድ ዳኛ
ለማቅረብ ይችላሉ፡፡

(3) ወደፊት የሚነሡትን ክርክሮች ለዘመድ ዳኛ ለማቅረብ ሲባል የሚደረገው ስምምነት ዋጋ ያለው የሚሆነው ስምምነቱ በአንድ ውል
ወይም በተለየ በመብት ገዥነት ላይ የሆነ እንደሆነ ነው፡፡
ቊ 3329፡፡ አተረጓጐም፡፡
የዘመድ ዳኛ ሥልጣንን የሚመለከቱ የዘመድ ዳኛ ስምምነት ቃሎች በጠባቡ መተርጐም አለባቸው፡፡
ቊ 3330፡፡ የተሰጠው ሥልጣን ስላለው ሥልጣን፡፡
(1) የዘመድ ዳኛው ስምምነት፤ የዚሁ ስምምነት አተረጓጐም ያነሣሣውን ችግር በሥልጣኑ እንዲወሰን ለዘመድ ዳኛው ሊፈቅድለት
ይችላል፡፡

(2) በተለይም የራሱን ሥልጣን የሚመለከቱትን ክርክሮች በሥልጣኑ እንዲወሰን ለዘመድ ዳኛው ሊፈቅድለት ይችላል፡፡

(3) የዘመድ ዳኛው በማናቸውም ሁኔታ የዘመድ ዳኛ ስምመነት ዋጋ ያለው ወይም የሌለው ነው ብሎ በሥልጣኑ ሊወስን አይችልም፡፡

ቊ 3331፡፡ የዘመድ ዳኛ ስለ መምረጥ፡፡ (1) በተዋዋይ ወገኖች ስለ መመረጥ፡፡

(1) የዘመድ ዳኛው በዘመድ ዳኛው ስምምነት ውስጥ ሆኖ ወይም ከዚሁ ስምምነት በኋላ መመረጥ ይችላል፡፡

(2) ስምምነቱም አንድ ወይም ብዙ የዘመድ ዳኞችን የሚኖሩ መሆናቸውን አስቀድሞ ለመወሰን ይችላል፡፡
(3) የዘመድ ዳኞች ስንት እንደሚሆኑ ወይም እንዴት እንደሚመረጡ ስምምነቱ ያላመለከተ እንደሆነ እያንዳንዱ ወገን አንድ የዘመድ ዳኛ
ይመርጣል፡፡
ቊ 3332፡፡ (2) በዘመድ ዳኞች ወይም በዳኞች ስለ መመረጥ፡፡

(1) ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር የዘመድ ዳኞች ብዛት በጥንድ የሚቈጠሩ እንደሆነ በሥራው ከመግባት በፊት አንድ ሌላ የዘመድ ዳኛ
ይመርጣሉ፡፡ ይኸውም የተመረጠው የዘመድ ዳኛ ለዘመድ ዳኝነቱ ሰብሳቢ ይሆናል፡፡

(2) ብዛታቸው በጥንድ የማይቈጠሩ የሆኑ እንደሆነ የዘመድ ዳኞቹ ከመካከላቸው ለዘመድ ዳኝነቱ ሰብሳቢ የሚሆነውን ይመርጣሉ፡፡

(3) በዘመድ ዳኞቹ መካከል ስምምነት የሌለ እንደሆነ ከተዋዋይ ወገኖች አንዱ በሚያቀርበው ጥያቄ እነዚህ ምርጫዎች በዳኞች የሚደረጉ
ይሆናሉ፡፡
ቊ 3333፡፡ (3) የምርጫው ሥነ ሥርዐት፡፡

(1) አስፈላጊ ሲሆን የዘመድ ዳኛውን ስምምነት የሚጠይቀው ወገን የሚያነሣውን ክርክር ገልጦ አንድ የዘመድ ዳኛ ይመርጣል፡፡

(2) እንዲህም በሆነ ጊዜ ላንደኛው ወገን ወይም በዘመድ ዳኝነት ስምምነት መሠረት የዘመድ ዳኛውን እንዲመርጥ ለተደረገው ሰው
ማስታወቂያ ይሰጣል፡፡

ቊ 3334፡፡ (4) የተወሰነ ጊዜ፡፡

(1) አንደኛው ወገን ወይም አንድ የዘመድ ዳኛ እንዲመርጥ የተጠየቀው ሰው በሙሉ በሠላሳ ቀን ጊዜ ውስጥ ያልመረጠ እንደሆነ ዳኞች
ይህን የዘመድ ዳኛውን ይመርጣሉ፡፡

(2) ጊዜው መቈጠር የሚጀምረው ከዚህ በላይ ባለው ቊጥር የተመለከተው ማስታወቂያ ከደረሰበት አንሥቶ ነው፡፡

(3) የዘመድ ዳኛ ስምምነት እነዚህን ደንቦች ለመለዋወጥ ይችላል፡፡

ቊ 3335፡፡ (5) የተዋዋይ ወገኖች ትክክለኛነት፡፡


የዘመድ ዳኛው ስምምነት የዘመድ ዳኞች ስለ መምረጥ በሚመለከተው ጕዳይ ከተዋዋይ ወገኖች ላንዱ ልዩ የሆነ አንድ የበለጠ የመብት
ሁኔታ የፈቀደለት እንደሆነ ዋጋ ያለው አይሆንም፡፡

ቊ 3336፡፡ ስለ አንድ የዘመድ ዳኛ መቅረት (1) መተካት፡፡

(1) አንድ የዘመድ ዳኛ የዘመድ ዳኛ ሆኖ መመረጡን አልፈልግም ያለ እንደሆነ ወይም የሞተ ወይም ችሎታ ያጣ ወይም ስንብት የጠየቀ
እንደሆነ፤ ከዚህ በፊት ባሉት ቊጥሮች መሠረት እርሱ እንደተመረጠው ዐይነት በርሱ ምትክ ሌላ ይመረጣል፡፡

(2) የዘመድ ዳኛው የተሻረ እንደሆነ አዲሱን የዘመድ ዳኛ ዳኞች ይመርጣሉ፡፡

(3) የዚህ ቊጥር ውሳኔዎች በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ሊለዋወጡ ይችላል፡፡

ቊ 3337፡፡ (2) የስምምነቱ ቀሪነት፡፡

(1) የሆነ ሆኖ ዘመድ ዳኛው ስሙ ተጠርቶ በዘመድ ዳኛ ስምምነት ውስጥ የተመረጠ ሆኖና ተዋዋይ ወገኖች በርሱ ምትክ ለማድረግ
ያልተስማሙ እንደሆነ የዘመድ ዳኛ ስምምነት ቀሪ ይሆናል፡፡

(2) ቢሆንም ወደፊት ለሚደርስ ክርክር ይኸውም ክርክር በደረሰ ጊዜ የዘመድ ዳኛውን መሰናክል የሆነው ነገር ቀርቶ እንደሆነ የዘመድ
ዳኛው ስምምነት የሚረጋ ይሆናል፡፡

(3) የዚህ ቊጥር ውሳኔዎች በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ለመለዋወጥ ይችላሉ፡፡


ቊ 3338፡፡ ከተዋዋይ ወገኖች ያንዱ መሞት፡፡
ተዋዋይ ወገኖች በሌላ ሁኔታ የውል ቃል ካላገቡ በቀር ያንደኛው ወገን መሞት የመረጡትን የዘመድ ዳኛ ተግባር አያስቀረውም፡፡
ቊ 3339፡፡ የተገላጋዩ ተግባር፡፡
(1) ማንኛውም ሰው ሁሉ የዘመድ ዳኛ ሆኖ ለመመረጥ ይችላል፡፡

(2) የዘመድ ዳኛው ዜግነት ለመመረጥ ከግምት አይገባም፡፡

(3) ለዘመድ ዳኝነት የተመረጠው ሰው ይህን ሥራ ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ነጻ ነው፡፡

ቊ 3340፡፡ የዘመድ ዳኛውን ስለ ማስወገድ (1) ምክንያቶች፡፡

(1) አንድ የዘመድ ዳኛ አካለ መጠን ያልደረሰ እንደሆነ ወይም በርሱ ላይ በደረሰበት በአንድ ቅጣት ምክንያትም ቢሆን፤ ወይም ክፉና ደጉን
መለየት ባለመቻሉ በበሽታ፤ በመጥፋት፤ ወይም በማናቸውም ሌላ ምክንያት ተገቢ በሆነ የተወሰነ ቀን ውስጥም ቢሆን ለማስወገድ
ይቻላል፡፡

(2) በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ወይም ባንድ ሦስተኛ ወገን የተመረጠው የዘመድ ዳኛ ባለማዳላቱ ወይም በነጻነቱ ላይ ጥርጣሬን
ለማስገባት የሚችል አንዳንድ አካባቢ ምክንያት ካለ ሊወገድ ይችላል፡፡

(3) በዘመድ ዳኝነት ሰብሳቢ የሆነውም ሰው ይኸንኑ በመሰለ ምክንያት ሊወገድ ይቻላል፡፡

ቊ 3341፡፡ (2) ጥያቄን ስላለመቀበል፡፡


ተቃራኒ የውል ቃል ከሌለ በቀር አንዱ ወገን ራሱ የመረጠውን የዘመድ ዳኛ ከዚህ ምርጫ በኋላ ለደረሰው ምክንያት ወይም ይህ ምርጫ
ከሆነ በኋላ ምክንያቱን ማወቁን ካላረጋገጠ ሊያስገድደው አይችልም፡፡

ቊ 3342፡፡ (3) ሥነ ሥርዐት፡፡

(1) የማስወገዱ ጥያቄ መቅረብ፤ ለዘመድ ዳኝነት ባለሥልጣኖች ለሆኑት ውሳኔያቸውን ከመስጠታቸው በፊትና ጥያቄውንም የሚያቀርበው
ወገን ምክንያቱን እንዳወቀው ወዲያውኑ መሆን አለበት፡፡

(2) ተዋዋይ ወገኖች የመወገዱ ጥያቄ ለሌላ ባለሥልጣን ይቀርባል ብለው መስማማት ይችላሉ፡፡

(3) የቀረበውን የመወገድ ጥያቄ አንቀበልም ተብሎ የተወሰነ እንደሆነ ይህኑ ውሳኔ እስከ ዐሥር ቀን በዳኞች ላይ ለመቃወም ይቻላል፡፡
ቊ 3343፡፡ የዘመድ ዳኛውን ስለ መሻር፡፡
አንድ የዘመድ ዳኛ ሥራውን ተቀብሎ ከመፈጸም በማይገባ የዘገየ እንደሆነ በተዋዋዮቹ ስምምነት የተመረጠው ባለሥልጣን ወይም በዚሁ
ስምምነት አላደረጉ እንደሆነ ከተዋዋዮቹ አንዱ ወገን ባቀረበው ጥያቄ ዳኞች የዘመድ ዳኛውን ለመሻር ይችላሉ፡፡
ቊ 3344፡፡ ባለመፈጸም ስለሚደረግ ቅጣት፡፡
(1) ለዘመድ ዳኝነት ስምምነት ካደረጉት አንዱ ወገን በዚሁ ስምምነት ውስጥ ለተመለከተ ክርክር ወደ ዳኞች የሄደ፤ ወይም የዘመድ ዳኝነት
ለማደራጀት አስፈላጊ የሆኑትን ተግባሮች ለመፈጸም እንቢ ያለ፤ ወይም በዘመድ ዳኛ ስምምነት የተያዝኩ አይደለሁም ባይ የሆነ እንደሆነ
ሌላው ወገን እንደመረጠው በዘመድ ዳኝነት የተደረገውን ስምምነት እንዲፈጸም ለማስገደድ ወይም በተለይ ለተነሣው ክርክር ስምምነተ
ቀሪ እንደሆነ ለመቊጠር ይችላል፡፡

(2) አንዱ ወገን ስለ አንድ የዘመድ ዳኛ ስምምነት አንድ የአጠባበቅ ጥንቃቄ ዳኞችን ለመጠየቅ ያደረገው ተግባር የዚህን ስምምነት ቀሪነት
አያስከትልም፡፡
ቊ 3345፡፡ ወደ ሥነ ሥርዐቱ ሕግ ስለ መምራት፡፡
(1) የዘመድ ዳኝነት የሚከተለው ሥነ ሥርዐት በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዐት ሕግ ተደንግጓል፡፡

(2) እንዲሁም የዘመድ ዳኛ ውሳኔ አፈጻጸምን ወይም ለዚሁ ውሳኔ ተቃራኒ የሆኑ አቤቱታዎችን ለሚመለከቱ ነገሮችም ይኸው ሕግ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ቊ 3346፡፡ የዘመድ ዳኝነት አሠራር፡፡
በዚህ ምዕራፍ ‹‹የዘመድ ዳኛ ስምምነት›› ‹‹ወይም›› የተዋዋዮቹ ስምምነት የተባሉት ቃሎች ተዋዋዮቹ ለመጥቀስ የፈለጉትን የዘመድ ደኛ
አሠራር ድንጋጌዎችን ይጠቀልላሉ፡፡

አንቀጽ 21፡፡
በቀድሞው ሕግና በዚህ በአሁኑ ሕግ መካከል ስላለው ግንኙነት
ምዕራፍ 1፡፡
ጠቅላላ ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 3347፡፡ የተሻሩት የቀድሞ ሕጎች፡፡

(1) ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር በዚህ በፍትሐ ብሔር ሕግ ውስጥ ለተመለከቱት ጒዳዮች፤ ከዚህ በፊት በልማድ ወይም
ተጽፈው ይሠራባቸው የነበሩት ደንቦች ሁሉ ይህ የፍትሐ ብሔር ሕግ ስለ ተተካ ተሽረዋል፡፡

(2) በተለይም፡፡

(ሀ) የካቲት 21 ቀን 19 ፵ ዓ.ም. የይርጋ ሕግ፡፡

(ለ) የ 1916 ዓ.ም. የብድር ሕግ፤ ተሽረዋል፡፡

ቊ 3348፡፡ በተሻሩት ሕጎች መሠረት ተገኝተው ለነበሩት መብቶች፡፡

(1) ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር፤ ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት የነበሩትን ሕጋዊ ሁኔታዎችን ለማስገኘት አዲሱ ሕግ
የሚጠይቃቸው አቋሞች ከዱሮው የተለዩ ቢሆኑም እንኳ፤ በተሻረው ሕግ መሠረት ተገኝተው የነበሩት ሕጋውያን ሁኔታዎች ሁሉ
እንደተጠበቁ ናቸው፡፡

(2) ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር፤ ይህ ሕግ ከመጸናቱ በፊት በተሻረው ሕግ መሠረት ተገኝተው የነበሩት ሕጋውያን ሁኔታዎች
ያስገኟቸውን ውጤቶች ይህ ሕግ አይለውጣቸውም፡፡

ቊ 3349፡፡ በከፊል ስለ ተፈጸመ ሕጋዊ ሁኔታ፡፡

(1) ግልጽ የሆነ ድንጋጌ ከሌለ በቀር፤ ሕጋዊ ሁኔታን የሚያስገኙ አቋሞች በልዩ ልዩ ጊዜ ለመገኘት የሚችሉ ወይም የሚያስፈልጉ ሲሆኑ፤
ይህ ሕግ ከመጸናቱ በፊት በከፊል ሳይፈጸም በቀረው ሕጋዊ ሁኔታ ብቻ የዚህ ሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

(2) ይህንኑ ሁኔታ በሚመለከት ጒዳይ በዚህ ሕግ የተጠቀሰውን ሕጋዊ ሁኔታ ለማስገኘት የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ነገር ሁሉ ይህ ሕግ
ሊመራ ይችላል፡፡

ቊ 3350፡፡ የጊዜውን ውሳኔ ስለማሻሻል፡፡


(1) ይህ ሕግ ከመጸናቱ በፊት በሕግ ተወስኖ የነበረው ያለቀው የጊዜ ውሳኔ እንደጸና ይቈጠራል፡፡

(2) ይህ ሕግ የጊዜን ውሳኔ የሚያራዝም ሲሆን የዚህ ሕግ ድንጋጌ ተፈጻሚ ይሆናል፤ ስለሆነም ይህ ሕግ ከመጸናቱ በፊት ያለፈው ጊዜ
መቀነስ ይገባዋል፡፡

(3) ይህ ሕግ የጊዜን ውሳኔ የሚያሳጥር ሲሆን ይህ ሕግ ከመጸናቱ በፊት ያለፈው ጊዜ እየተቈጠረ በድሮው ሕግ የተወሰነው የጊዜ ውሳኔ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ቊ 3351፡፡ ሕጋዊ ሁኔታ ስለሚያስከትለው ውጤት፡፡

(1) ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በቀር ይህ ሕግ ለሚወስነው ከውል ውጭ ለሆነው ሕጋዊ ሁኔታ የሚያስከትለውን ውጤት ሕጉ
በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ለተገኙት ሕጋውያን ሁኔታዎች ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

(2) ይህ ሕግ በጸናበት ጊዜ ዘመኑ ያላለቀለት ውል በማታለል በኀይል ዐይነት የተደረገ ነው ተብሎ በዚህ ሕግ በተወሰነው ጊዜና ሁኔታ
እንዲፈርስ ካልተጠየቀ በቀር ውሉ በተደረገበት በቀድሞው ሕግ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ምዕራፍ 2፡፡
ልዩ ድንጋጌ፡፡
ቊ 3352፡፡ ችሎታን ስለ ማጥበብ፡፡

ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት ችሎታን የሚመለከቱ ስምምነቶች በቊ 195 መሠረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

ቊ 3353፡፡ ችሎታ ስለሌላቸው ሰዎች ጥበቃ፡፡

ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት ተመርጠው ሥራ የጀመሩ አሳዳሪዎች፤ ሞግዚቶች፤ ምትክ ሞግዚቶች ወይም ረዳት ሞግዚቶች ሁሉ በዚህ ሕግ
መሠረት ለዚህ ሥራ ለመመረጥ የማይችሉ ቢሆኑም እንኳ በዚህ ሕግ መሠረት እንደተመረጡ ተቈጥረው ሥራቸውን መቀጠል ይችላሉ፤
በዚህ ሕግ የተሰጣቸውንም ተግባር መፈጸም አለባቸው፡፡

ቊ 3354፡፡ ስለ ውርስ (1) ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት ስለ ተጀመረ ውርስ፡፡

ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት የተጀመረው ውርስ የሚተላለፈውና ሒሳቡ የሚጣራው በቀድሞው ሕግ መሠረት ነው፡፡

ቊ 3355፡፡ (2) ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት ስለ ተደረገ ኑዛዜ፡፡

ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት የተደረገ ኑዛዜ የሚጸናው፡-


(ሀ) በተሻረው ሕግ መሠረት የሚጸና የሆነ እንደሆነ፤ ወይም፤

(ለ) ይህ ሕግ በሚጠይቀው ደንብ መሠረት የተደረገ እንደሆነ ነው፡፡

ቊ 3356፡፡ አትሞ የማውጣት ውል፡፡

ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት የተፈጸመውን አትሞ የማውጣት ውል ሕጉ ከጸናበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ሳይሞላ ደራሲው ውሉን
ለማፍረስ አይችልም፡፡

ቊ 3357፡፡ የአገልግሎት ጊዜ ስለ መቊጠር፡፡

ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት ሠራተኛው በአሠሪው ወይም በድርጅቱ ዘንድ የሠራበት ዘመን የሚቈጠርለት ስለሆነ ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት
ከአሠሪው ወይም ከድርጅቱ ዘንድ የቈየበት የአገልግሎት ዘመን ለዚህ ሕግ አፈጻጸም ይታሰብለታል፡፡

አንቀጽ 22፡፡
መሸጋገሪያ ሕግ፡፡
ምዕራፍ 1፡፡
ሰዎችንና ውርስን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 3358፡፡ ስለ ቤተ ዘመድ ስም አሰጣጥ (1) ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት የተወለደ ሰው፡፡

(1) ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት የተወለደ ማናቸውም ሰው አንድ የቤተ ዘመድ ስም እንዲኖረው አይገደድም፡፡

(2) ይህ ሕግ ከመጽናቱ በፊት የተወለደ ሰው የቤተ ዘመድ ስም እንዲኖረው የፈለገ እንደሆነ የቤተ ዘመድ ስም አድርጎ የሚይዘው የአባቱን
ስም ነው፤ ስለሆነም ይህ ሕግ በሚጸናበት ጊዜ ከቤተ ዘመዶቹ ሁለት ወይም ብዙ ትውልዶች በሕይወት ያሉ ሲሆን የቤተ ዘመድ ስም
ለማግኘት የሚፈልገው ሰው የቤተ ዘመድ ስም አድርጎ የሚይዘው ወደ ላይ ከሚቈጠሩ ወላጆች በዕድሜ ታላቅ የሆነውን ወላጅ ስም ነው፡፡

(3) አባቱ የተካደ ያልታወቀ ሰው የቤተ ዘመድ ስም አድርጎ የሚይዘው የእናቱን አባት ስም ነው፡፡

ቊ 3359፡፡ (2) ይህ ሕግ ከጸና በኋላ የተወለደ ሰው፡፡

(1) ይህ ሕግ ከጸና በኋላ የሚወለድ ሁሉ አንድ የቤተ ዘመድ ስም መያዝ አለበት፡፡

(2) ከዚህ በላይ በተጻፉት ድንጋጌዎች መሠረት ልጁ የቤተ ዘመድ ስም የሌለው እንደሆነ የቤተ ዘመድ ስም አድርጎ የሚይዘው የአባቱን ስም
ነው፡፡

(3) የተካደ ወይም አባቱ ያልታወቀ ልጅ ሲሆን የቤተ ዘመድ ስም አድርጎ የሚይዘው የቤተ ዘመድ ስም እንዳላት የእናቱን የቤተ ዘመድ ስም
ወይም የእናቱን አባት ስም ነው፡፡
ቊ 3360፡፡ ውጤት፡፡

ከዚህ በላይ የተመለከቱት ሁለት ቊጥሮች በሥራ ላይ የሚውሉበት ጒዳይ በዚሁ መሠረት የተሰጠ የቤተ ዘመድ ስም ሁሉ በቀጥታ
መሥመር ለዚሁ የቤተ ዘመድ ተወላጅ ለሆኑት ሰዎች ሁሉ የቤተ ዘመድ መጠሪያ ስም ሆኖ ይኖራል፡፡

ቊ 3361፡፡ ስለ ክብር መዝገቦች፡፡

(1) በሥራ ላይ የሚውልበት ቀን ተወስኖ በነጋሪት ጋዜጣ ታውጆ ካልወጣ በቀር በቊ 48 እስከ 55፤ በቊ፤ 57 እስከ ፸፤ በቊ 72 እስከ
77፤ በቊ፤ 79 እስከ 131 እና በቊጥር 133 እስከ 145 የተገለጹት ድንጋጌዎች ተፈጻሚዎች አይሆኑም፡፡

(2) ከዚህ በላይ ባለው በንኡስ ቊጥር (1) የተጠቀሱት ቊጥሮች እስከሚጸኑበት ጊዜ ድረስ ልደትን፤ ጋብቻን፤ ሞትን የሚገልጽ ማስረጃ
የሚቀርበው በቊ፤ 146 እስከ 153 በተመለከተው መሠረት በዚህ ሕግ ሕግ በቊ 146 ን/ቊ/(1) የአገር ግዛት ሚኒስቴር የመረጣቸው
ሰዎች ያዘጋጁትን የታወቀውን ጽሑፍ በማቅረብ ነው፡፡

(3) በንኡስ ቊ (1) የተመለከተው ቃል ቢኖርም እንኳ በዚህ ሕግ በቁ/ 121 እስከ 145 የተመለከቱት ድንጋጌዎች በተመሳሳይነት ለታወቁ
ጽሑፎች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 3362፡፡ የማኅበሮች ጽ/ቤት፡፡

በዚህ ሕግ ለማኅበሮች መመዝገቢያ ጽሕፈት ቤቶች የተሰጠው ሥልጣንና ተግባር እነዚሁ ጽሕፈት ቤቶች እስኪቋቋሙ ድረስ ሥራው
በአገር ግዛት ሚኒስቴር ይመራል፡፡

ምዕራፍ (2)፡፡
ስለ ንብረትና የማይንቀሳቀሰውን ንብረት መያዣ
ማድረግን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች፡፡
ቊ 3363፡፡ ስለ ማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መዝገብ፡፡

(1) በዚህ ሕግ በአንቀጽ ዐሥር ስለ ማይንቀሳቀሱ ንብረቶች መዝገብ የተመለከተው ሕግ በሥራ ላይ የሚውልበት ቀን በንጉሠ ነገሥታዊ
ድንጋጌ (ትእዛዝ) ተወስኖ በነጋሪት ጋዜጣ እስኪታወጅ ድረስ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

(2) የአንቀጽ ዐሥር ድንጋጌ የሚጸናበት ቀን እስኪወሰን ድረስ ከዚህ ቀጥሎ በዚህ ምዕራፍ በተመለከቱት ቊጥሮች ውስጥ የሚገኙት
ድንጋጌዎች ይሠራባቸዋል፡፡

ቊ 3364፡፡ ባለሀብትነትን ስለ ማስተላለፍና ስለ ማስቀረት፡፡


የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለሀብትነት ለማስተላለፍ ወይም ለማስቀረት መፈጸም ያለባቸው ልማዳዊ ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 3365፡፡ በንብረት ላይ ስለሚሰጥ አገልግሎትና የባለሀብትነትን መብት ስለ መቀነስ፡፡

በመሬት ላይ ያገልግሎት መብትን ወይም ለመሸጥ ቃል መግባትን ወይም ለመግዛት የቀደምትነት መብትን ወይም ንብረት እንዳይዝ፤
እንዳይሸጥ፤ እንዳይለወጥ፤ የሚያደርጉት ስምምነቶች ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ እንዲሆኑ መፈጸም ያለባቸው ሥርዐቶችን
የሚመለከቱ ልማዳውያን ደንቦች ተፈጻሚዎች ይሆናሉ፡፡

ቊ 3366፡፡ የሻጭ ግዴታዎች፡፡

(1) በዚህ ሕግ መሠረት ሦስተኛ ወገንን መቃወሚያ ለመሆን እንዲችል በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ መመዝገብ የሚያስፈልገውንና
የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ባለሀብትነት መብት የሚቀንሰውን ነገር ሁሉ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ሻጭ ማስታወቅ አለበት፡፡

(2) በተሸጠው በማይንቀሳቀሰው ንብረት ላይ በግልጽ የሚታየውን በመሬት ላይ የአገልግሎት መበት መኖሩን ሻጭ ለገዥ እንዲያስታውቅ
አይገደድም፡፡

(3) ማንኛውም ሰው ስለ ማይንቀሳቀሰው ንብረት ያደረገው ስምምነት በዚህ ሕግ መሠረት በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ መመዝገብ
ያለበት ሲሆን በዚህ ቊጥር መሠረት ሻጭ ማድረግ የሚገባውን እሱም ማድረግ ይገባዋል፡፡

ቊ 3367፡፡ ስለ ማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ፡፡

የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ሦስተኛ ወገኖችን መቃወሚያ እንዲሆን መፈጸም የሚገባቸው ልማዳዊ ደንቦች ይሠራባቸዋል፡፡

You might also like