Professional Documents
Culture Documents
2010
2010
መግቢያ
መንግስት የህ/ሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራ
ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለዉ ሁኔታ በየዘርፉ በርካታ አበረታች ዉጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት
በማስወገድና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ከማሳደግ አኳያ ትክክለኛ ፖሊሲና አቅጣጫ ተቀምጦ ከየትኛዉም ጊዜ
የተሻለ እንቅስቃሴ በመደረጉ ተጨባጭ የሆኑ ዉጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን መልካም
አስተዳደርን ለማስፈንና በተሰሩ ስራዎችም የማይናቁ ለዉጦች ታይተዋል፡፡
መልካም አስተዳርና ፈጣን ልማት የማይነጣጠሉ ከመሆናቸዉ አኳያ ከላይ የተጠቀሱት እና መሰል
የመልካም አስተዳደር ችግሮች ባልተፈቱበት ሁኔታ ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ቀርቶ የተጀመረዉንም ዳር
ማድረስ የሚቻልበት ሁኔታ በፍጹም ሊኖር አይችልም ፡፡
ስለሆነም እስካሁን ያስመዘገብናቸዉን የመልካም አስተዳደር ፍሬዎች ጠብቀን ጎን ለጎን ደግሞ ተገልጋዩ
ህ/ሰብ በችግርነት የሚያሳያቸዉንና በተለያዩ ዘዴዎች ተጠቅመን ያገኘናቸዉን የመልካም አስተዳደር
እጥረቶች በአጭር በመካለኛና በረጀም ጊዜ መፍታት ስለሚገባ ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር
ለመፍታት የሚያገለግል ዕቅድ አቅደናል ፡፡
እቅዱን ለመፈጸም ጥረት አድርጓል፡፡ በሁሉም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃና ት/ቤቶች መንግስት
የቀየሳቸዉን የሪፎርሙን ፕሮግራሞች ተግባራዊ ለማድረግ ስፊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡ በተደረጉ
ጥረቶች መልካም አበረታች ዉጤቶች ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ በጎ ዉጤቶች ያለ ትምህርት አመራርና
ፈጻሚዎች ጥረት የመጡ እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል ፡፡
በድምሩ የለዉጥና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴያችን መሰረታዊ ዉስንነት መንስኤ ሲታይ አመራሩ
የመልካም አስተዳደር ስራችን ትኩረት ሰጥቶን በባለቤትነት መምራት ካለመቻሉ ጋር የሚያያዝ ነዉ ይህ
በመሆኑ አመራሩ ራሱን ጨምሮ ከስሩ ያለዉን ሰራተኛ እና የህዝቡን አመለካከት ፣ክህሎት፣ የአደረጃጀት
፣የአመራርና የአቅርቦት ማነቆዎችን የመፍታት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስራ በዋና በባለቤትነት
ያልሰራበት ሁኔታ በሰፊዉ ታይቷል ፡፡ስለሆነም በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችን የግንዛቤ ችግሮችን በመፍታት
የአመለካከት፣የክህሎትና የአቅርቦት ያለዉን ማነቆ በማስወገድ ከስሩ ያሉትን ሰራተኞችንና ህዝቡን
የአመለካከት ፣የክህሎትና የአቅም ክፍተቶች ቆጥሮ በመለየት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ሰፊ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ፓኬጅን ከምንጊዜዉም በላይ ተግባራዊ
ማድረግ ይገባናል ፡፡
ቀደም ሲል የነበረዉ ስርአት እጅግ ኋላቀር የስራ ባህል የመፈጸም አቅሙም የደከመ
የአገልግሎት አሰጣጡ የቀዘቀዘ የተጠያቂነት ስሜት ያልያዘ ኋላቀር አሰራር ለመቀየር ብዙ
ጥረቶች ተደርገዋል መሻሻሎችም ታይተዋል፡፡ ይህ አበረታች ለዉጥ በተጨባጭ የሚታይ
ቢሆንም ጠንካራ የመፈጸም አቅም ያለዉ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የጸዳ
ለፈጣን አገልግሎት አመች /quik wins/ መሳሪያዎች በተቋማት የስራ ባህሪ አንጻር
አለመሟላት
የተሟላ ዕዉቀት ያለዉ የሰዉ ኃይል አለመሟላት
የመረጃ ሀብት ተጠናክሮ አለመያዝ
ልዩ ልዩ ደንቦችን መመሪያዎችን አደራጅቶ አለመያዝና አለመጠቀም
ለሚመለከታቸዉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ አለመስራቱ
የተመደበዉን በጀት በአግባቡ አለመጠቀም
የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለሚፈልገዉ አገልግሎት በአግባቡ አለመጠቀም
3.4 ዓላማ
ግብ
የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ግቦችን በተሟላ መንገድ
ለማሳካት
ተነሳሽነቱ ከፍተኛ የሆነ በህዝቡ ተቀባይነት በተለይም ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካትን
ለመናድ በጽናት የሚታገል ኃይል መፍጠር
ዉጤታማና ቀልጣፋ እንዲሁም ወጭ ቆጣቢ አገልግሎት በመስጠት መልካም አስተዳደር
እንዲሰፍን ማድረግ
ለተገልጋዮች ፍትሃዊ ግልጽና ዉጤታማ አገልግሎት ለማበርከትና ለፍላጎታቸዉ አፋጣኝ
መልስ መስጠት
የህዝብ አገልጋይነት አመለካከት ማዳበር
በአሰራር አደረጃጀትና በአመለካከት የሚታዩ ክፍተቶች ለይቶ በማዉጣት ዜጎች
የሚፈልጓቸዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለስ
ተደራሽ ያልሆነ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የዜጎችን እንግልት መቀነስ ከመልካም
አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ፈጻሚዎችንና አመራሩን በማነቃነቅ የተጀመረዉን የልማት
ሰራ ግንባታ ተግባር ማጠናቀር
በተለያየ ምክንያት ምላሽ ያልተሰጠዉን ለይቶ በመፍታት የዜጎችን እርካታ ማሳደግ
ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ባለዉ የተቋማችን እርከን የሚስተዋሉ /የሚታዩ/ የመልካም
አስተዳደር ችግሮችን መፍታት
በተለያዩ የመልካም አስተዳር ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ በየደረጃዉ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት
ፈጻሚዎችና አመራሮች ግንዛቤ መፍጠር
ምላሽ ሳያገኙ የተቀመጡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ፈትሾ በአፋጣኝ ምላሽ መስጠት
ለአገልግሎት አሰጣጥ አጋዥ የሆኑ የፈጣን አገልግሎት አምጭ /quick wines/ በቋሚነት ማሟላትና
ሰነዶችን የተሟሉ ማድረግ
በጥናት የተደገፈ ሃሳብ በማቅረብ የቅሬታ ስርአቱ ሀብት ቆጣቢ በሆነ መልኩ በወረዳችን ላይ
ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ
ከተገልጋዮች ጋር የምክክር መድረክ በመፍጠር መብቶቻቸዉና በግዴታቸዉ ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ
ስራ መስራት
የሚፈቱበት ጊዜ
ተ በተቋሙ የተለያዩ የመ/አስ/ችግሮች ለመፍታት የተቀመጡ የመፍትሄ በአጭር በመካከለኛ በረጅም ፈጻሚ
. ሀሳቦች ጊዜ ጊዜ ጊዜ አካላት
1 በተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ ለፈጻሚዎች ትምህርት
ኦሬንቴሽን መስጠት ጽ/ቤት
2 ምላሽ ሳያገኙ የተቀመጡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ፈትሾ ምላሽ መስጠት ›
3 ለአገልግሎት አሰጣጥ አጋዥ የሆኑ ታፔላችንና ሌሎች አሰራሮች ››
ማስተካከል ›
4 አስተዳደር ፍ/ቤቱን ወረዳችን ላይ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ √ ›
5 ከተቋሙ ተገልጋዮች ጋር የምክክር መድረክ በመፍጠር ››
ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት ›
6 በትምህርት ቤቶች የሰዉ ኃይል አስተዳደር መመሪያና አፈጻጸም መካል ›
ያለዉን ክፍተት እንዲሞላ ለዞን ትምህርት መምሪያ ማሳወቅ ›
7 ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመገናኜት የአዲስ ቅጥር ›
ሰራተኞችን ጥያቄ መፍታት ›
ማሳሰቢያ ፡- በአጭር ጊዜ የሚፈታ ማለት እስከ ጥቅምት 30/2010 ዓ.ም የመካከለኛ ጊዜ
ማለት እስከ ጥር 30 ሲሆን የረጅም ጊዜ ማለት ደግሞ እንደ ሁኔታዉ እስከሚቀጥለዉ
ዓመት አጋማሽ ድረስ የሚፈቱ ማለት ነዉ፡፡
1.9 መፍትሄዎች
ከወረዳ እስከ ቀበሌ የተደራጁትን የተለያዩ ኮሚቴዎች በማጠናከርና የልማት ሰራዊት
አደረጃጀቶችን በማሳለጫነት መጠቀም
በመልካም አስተዳር አፈጻጸምና ችግሮች ላይ የተሟላ ግንዛቤ መፍጠር
የመልካም አስተዳር ምንጮችን በመለየትና ባለቤት ሰጥቶ መፍትሄ የመስጠት ስራ
መስራት
ለመልካም አስተዳር ስኬታማነት ስራ የሚያግዝ ማረቂያ ስትራቴጂ መንደፍ
በሁሉም ስራዎቻችን ግልጽና ተጠያቂነት የተላበሰ ስርአት በመዘርጋት ሙስናንና አድሎን
መሸከም የማይችል ዜጋ መፍጠር
ቀጣይነት ተከታታይነት ያለዉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ መስራት
ማጠቃለያ