You are on page 1of 9

ረቂቁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገመንግሰት ላይ ያለኝ የግል አስተያየት

ክፍል 1

ሕገመንግሰት የመስራቾች ቃል ክዳን፤መስራቾች ስልጣናቸዉን የሚያከፋፍሉበትና በመካከላቸዉ የሚኖረዉን


ግንኙነት ቀድመዉ የሚወስኑበት የዉል ሰነድ ነዉ፡፡የቀድሞዉ ደቡብ ክልል ፈርሶ 2 ክልሎች ቀድመዉ የተዋቀሩ
ስሆን ቀርዎቹ ሁለት ክልሎች በምስረታ ህደት ላይ ናቸዉ፡፡ከምስረታ ህደቶች ዋነኛዉ የሆነዉ የክልሉን
ህገመንግሰት የማርቀቅ እና የማጸደቅ ህደት አንዱ ስሆን በፌደረሽን ም/ቤት 12 ኛ ክልል ሆኖ እንድደራጅ
የተወሰነዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ በቀድሞዉ ደቡብ ክልል የስልጣን ርክክብ ተደርጎ ወደ
ህገመንግስት ዉይይት መገባቱን በተለያዩ ሚዲያዎች ከሚጋሩ መረጃዎች እና ከሚናገኛቸዉ ግለሰቦች
እንሰማለን፡፡

የህገመንግስቱን ረቂቅ ዛሬ ያገኘሁ ስሆን ሀገመንግስቱ በዉይይት ላይ ስላለ እና ዉይይቱ ያስፈለገዉም በረቂቁ
ላይ አስተያየት ተሰጥቶ መስተካከልና መታረም ያለባቸዉ ነጥቦች እንድታረሙ በማሰብ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ
በቀጥታ ዉይይቱ ላይ የመሳተፍ ዕድል የማያገኙ ሰዎች አስተያየታቸዉን በተለያየ መንገድ ማቅረብ ይችላሉ
የሚለዉን ታሳቢ በማድረግ በረቂቁ ላይ ምልከታዬን ለማጋራት ወደድኩ፡፡ የህገመንግስቱ አርቃቂዎችም ሆነ
አስተያየቶችን ሰብስባችሁ ግብዓት የሚታቀርቡ ሰዎች እነዚህን ነጥቦች እንድትመለከቷቸዉና ጠቃሚ ከሆኑ
እንድትተገብሩ አደራ እላለሁ፡፡ የሚንመራበት እና የሚንተገብረዉ ሕገመንግሰት ላይ የመወያየት ዕድል ያላገኘን
ዘጎች ህገመንግስቱ የጋራችን ስለሆነ በዚህ መንገድ ዕይታችንን አስተያየታችንን ብናጋራ ይደርሳቸዋል ብለን
እናስባለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ የክልል ማዕከል ሰራተኞች ላለፉት በርካታ ዓመታት ስሰሩበት የነበረዉ ክልል ፈርሶ እንደአዲስ
በሚደራጅበት ህደት ላይ የመወያየትም አስተያየት የመስጠትም ዕድል ብዙ ያገኙ አይመስለኝም የቀድሞዎቹን
ሁለቱ ክልሎች የወጡበት ህደት ላይ የነበረዉን ዝርዝር ሁኔታ ባላዉቅም፡፡ ህዝቤ ዉሳኔዉ ላይ የሚሳተፉበት
ዕድል አለመመቻቸቱ(የተሳተፉ ተቋማት ስለመኖራቸዉ መረጃ የለኝም) እና አሁን ደግሞ በህገመንግስቱ ላይ
የመወያየት እና አስተያየት የመስጠት ዕድል አለመመቻቸቱ ምናልባት ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት የሆኑት የታች
መዋቅሮች ስለሆኑ ይሆናል፡፡ ምናልባት እስከ ቀበሌ ያለዉን ዉይይት ስጨርሱ የክልል ማዕከል ሰራተኞችን
በህገመንግስቱ ጉዳይ ላይ ያወያያሉ ብለን እጠብቃለሁ፡፡

ወደተነሳሁበት ነጥብ ስመለስ በህገመንግስቱ ረቂቅ ላይ ያለኝን ምልከታ

1) አንቀጽ 1.የክልሉ መንግስት መቋቋም እና ስያሜ

በዚህ ህገ መንግስት ዲሞክራሲያዊ አወቃቀር ሥርዓትን የሚከተል “የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል
መንግስት” ተብሎ የሚጠራ መንግስት ተቋቁሟል፡፡
ይህ አንቀጽ ከርዕሱ ጀምሮ ለመግለጽ የተፈለገዉን ሐሳብ ገላጭ አይደለም፡፡ “የክልሉ መንግሰት ስያሜ” የሚል
ርዕስ ተሰጥቶት ደሞክራስያዊ የአስተዳደር ስርዓት የሚከተል የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ተብሎ የሚጠራ
መንግሰት በዚህ ህገመንግሰት ተቋቁሟል” ብባል የተሸለ ገላጭ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ የቃላት ቅደም ተከተሉ
እና በተለይም “አወቃቀር” የሚለዉ ቃል አስፈላጊ አይመስልም፡፡ ደሞክራሲ አወቃቀር ሳይሆን የአስተዳደር
ስርዓት ነዉ፡፡

በዚህ አንቀጽ ላይ ሌላዉ አስተያየቴ የክልሉ ስያሜ ነዉ፡፡ በፌደረሽን ም/ቤት የክልሉ ምስረታ በጸደቀበት ወቅት
የም/ቤቱ አፈጉባኤ የክልሉ ስያሜ በመስራች ጉባዔዉ ልስተካከል እንደሚችል ስገልጹ የሰማሁ ይመስለኛል፡፡
ቀድሞ የፌደረሽኑ አባል ሆኖ የተደራጀዉ ክልል “ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ ይዞ የተደራጀ
ስለሆነ የአሁኑን “ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” በሚል ስያሜ ማደራጀት አሳሳች ስያሜን መምረጥ ይሆናል፡፡
የግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት ጭምር አሳሳች እንዳይሆኑ ጥንቃቄ የሚደረግ ስሆን ክልልን የሚያክል ተቋም
አንዱ ደቡብ ኢትዮጵያ ሌላዉ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ መሆኑ አሳሳች ስለሚያደርገዉ አማራጭ ስሞች
ተዘጋጅተዉ የፌደረሽንም/ቤቱ አፈጉባኤ እንዳሉት በክልሉ መስራች ጉባኤ እንድጸድቅ ብደረግ የሚል
አስተያየት አለኝ፡፡ ስያሜ ባልጠፋበት አሳሳችና የሚመሳሰል ስያሜ መስጠት ተገቢ አይመስልም፡፡

3) አንቀጽ 6. ርዕሰ ከተማ

የክልሉ መንግስት ከአንድ በላይ ርዕሰ ከተሞች ይኖሩታል፡፡ ተጠሪነት፣ብዛት እና የአስተዳደራዊ ጉዳይ የክልሉ
ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚያወጣው ህግ ይወሰናል፡፡

የዚህ ድንጋጌ ሁለተኛ አንቀጽ ለማለት የተፈለገዉን ገላጭ አይደለም፡፡ ስለዚህ “የከተሞቹ
ብዛት፣ተጠሪነታቸዉ እና አስተዳደራቸዉ የክልሉ ም/ቤት በሚያወጣዉ ሕግ ይወሰናል” የሚል ቅርጽ ብኖረዉ
ጥሩ ይመስላል፡፡

4. የክልል ም/ቤት ወይስ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት

በረቂቁ ላይ አንዳንድ ቦታ “የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት” የሚል ስሆን አንዳንድ ቦታ ደግሞ “የክልል
ም/ቤት” በሚል ይገልጻል፡፡ ስለዚህ አንድም የፌደራል መንግሰት ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚል አጠራር
ስለሚጠቀም እና አሁን አድሱን ክልል የሚመሰርቱት ተወካዮች የተመረጡትም የክልል ም/ቤት በሚል ስለሆነ
ከሁሉም በላይ ደግሞ በፌደራሉ ህገመንግሰት የክልል ም/ቤት በሚል የተገለጸ ስለሆነ ተስተካክሎ ወጥ የሆነ
“የክልል ም/ቤት” የሚል አጠራር ብገባ የሚል አስተያየት አለኝ፡፡
5) አንቀጽ 47 የክልሉ መንግሰት መስራቾች

የብሄር ብሄረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ዓለም አቀፍ መብት ነዉ፡፡ የክልል መንግሰት ምሰረታ ራስን
በራስ የማስተዳደር መብት ነዉ፡፡ በኢትዮጵያ ህገመንግሰትም ሆነ በቀድሞዉ የደቡብ ክልል ህገመንግሰት
መሰረት ራስን በራስ የማስተዳደርም ሆነ ክልል የመመስረት መብት የተሰጠዉ ለብሄር ብሔረሰብ እና ህዝብ
ነዉ፡፡ ህገመንግስቱ ክልል የመመስረት መብት የሰጣቸዉና ያንን መብታቸዉን ተጠቅመዉ በየብሄረሰብ
ም/ቤቶቻቸዉ ወስነዉ ክልሉን ለመመስረት የጠየቁት ብሄሮቹ እንጂ መዋቅሮቹ አይደሉም፡፡ ነገር ግን
በህገመንግስቱ ረቂቅ ላይ የክልሉ መስራቾች ተብለዉ የተዘረዘሩት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ናቸዉ፡፡

ስለዚህ የክልሉ መስራች ልሆኑ የሚችሉት የክልሉ ብሄረሰቦች እንጂ የክልሉ መዋቅሮች አይደሉም፡፡ መዋቅሮች
እና ብሄሮች የተለያዩ ስሆኑ መዋቅር ግዜያዊ ስሆን ብሔሮች ዘላቂ ስለሆኑ የክልሉ መስራቾች በሚል መገለጽ
ያለበት ዘላቂ የሆነዉ የብሄሮች ስያሜ እንጂ የሕዝብ ጥያቄን መሠረት አድርጎ በየጊዜዉ ተለዋዋጭ የሆነዉ
የመዋቅሮች ስያሜ አይደለም፡፡ ስለዚህ ክልሉን የመሰረቱ ብሔሮች በስም የክልሉ መስራች በሚለዉ አንቀጽ
47 ላይ ብካተቱ የሚል ዕይታ አለኝ፡፡ የፌደራሉ ህገመንግሰት አንቀጽ 47 እንደመነሻ ተወስዶ ከሆነ የሚለዉ
“የፌደረሽኑ አባላት” እንጂ “መስራቾች” አይደለም፡፡ የፌደረሽኑ መስራቾች ብሄር፣ብሄረሰቦች እና ህዝቦች
መሆናቸዉን ከፌደራሉ ህገመንግሰት መግቢያ መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እኩል መብት ያላቸዉ እንደሆነ የፌደራል መንግሰትም ሆነ
ይህ ረቂቅ ሕገመንግስት ይደነግጋል፡፡ ዞን እና ልዩ ወረዳ ብሎ በህገመንግስቱ መዋቅሮችን ለይቶ መዘርዘር
የእኩልነት መርህን የሚጥስ እና የመዋቅሮች መበላለጥን የሚያሳይ ይመስላል፡፡ የኢፌድሪ ህገመንግስት
የፌደረሽኑን አባል ክልሎች በሚዘረዝርት ግዜ ሁሉንም “ክልል” ብሎ ነዉ የሚዘረዝር ስሆን በክልሎቹ መሀል
ግን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፋፍ ልዩነቶች ይታያሉ፡፡ ስለዚህ ሕገመንግሰት የህጎች ሁሉ የበላይ እና መነሻ
እንደመሆኑ መጠን በተቻለ መጠን የእኩልነት መሪህን የሚያሳይ ይዘት ልኖረዉ ይገባል የሚል ምልከታ አለኝ፡፡

አንቀጽ 2.የክልሉ አስተዳደር ወሰን

1.የክልሉ አስተዳደር ወሰን በክልሉ ባሉ የዞንና የልዩ ወረዳ የአስተዳደር መዋቅሮች ውስጥ የሚገኙ
ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሰፈሩበት መልክዓ ምድር ከሌሎች ክልሎች እና በክልሉ በኩል ኢትዮጵያ
ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ወሰን ሆኖ ፡-

ሀ/ በሰሜንና በምሥራቅ በኩል ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣

ለ/ በሰሜን ምዕራብ በኩል ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣

ሐ/ በደቡብ በኩል ኬኒያ፣

መ/ በደቡብ ምዕራብ በኩል ከደቡብ ሱዳን፣

ሠ/ በደቡብ ምሥራቅ በኩል ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣


ረ/ በምዕራብ በኩል ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ያዋስኑታል ፡፡

ይህ አንቀጽ ድግግሞሽ ነዉ፡፡ ከላይ የአስተዳደር ወሰኑን ያስቀምጥና ታች ወርዶ እንደገና ይዘረዝራል፡፡
መግቢያዉም ዝርዝሩም አንድ ስለሆኑ ከሁለቱ አንዱ አስፈላጊ አይሆንም፡፡

6 አንቀጽ 48. አዳዲስ አደረጃጀቶችን ስለመመስረት

1.የክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በማናቸዉም ጊዜ የራሳቸውን የአደረጃጀት መዋቅር የማቋቋም


መብት አላቸው፤

2.የክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የራስ ክልል የመመስረት መብት ሥራ ላይ የሚዉለዉ በኢትዮጵያ
ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት በተደነገገዉ አግባብ ይሆናል፤

3.የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄዉ በደረሰዉ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምላሽ ካልሰጠ ወይም
ጠያቂው በተሰጠው ምላሽ ካልተስማማ የጠያቂዉ ብሔር፣ብሔረሰብ ወይም ህዝብ ምክር ቤት ተገቢውን
የህግ አግባብ ተከትሎ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ ወይም ይግባኝ የማቅረብ መብት አለዉ፤

ይህ ድንጋጌ አንቀጽ 1 ለመግለጽ የፈለገ የሚመስለዉ በክልሉ ዉስጥ ሆኖ ብሄሮች ስለሚያዋቅሩት የራስ
አስተዳደር መዋቅር ስሆን አንቀጽ 2 እና 3 ደግሞ ከክልሉ ወጥቶ የራስን ክልል ስለመመስረት ነዉ፡፡ በንዑስ 1
ላይ ያለዉንና በክልሉ ዉስጥ አድስ መዋቅር ስለምዋቀርበት ሁኔታ ያልተቀመጠ ከመሆኑም በላይ በሌላ ዝርዝር
ህግ እንመሚወሰን የሚጠቁም ነገር የለም፡፡

በዚህ ድንጋጌ አንቀጽ 2 ላይ የፌደራሉ ህገመንግሰት ያስቀመጠዉን ህደት እንደሚከተል ከደነገገ በኋላ ተመልሶ
በንዑስ አንቀጽ 3 ላይ ራሱ ወደ ዝርዝር ይገባል፡፡በፌደራሉ ህገመንግስት በአንድ ዓመት ጊዜ ምላሽ ካልተሰጠ
ምን ይሆናል የሚለዉ ዝርዝር ያልተቀመጠ በመሆኑ መፍትኄ ለማስቀመጥ ያለመ ድንጋጌ ብመስልም
ከፌደራልና ከክልል የሚለቃቅም ህደት ከማስቀመጥ ሙሉ አጠቃላይ ሕደቱን መዘርዘና በፌደራሉ ህገመንግሰት
ያለዉን ክፍተት አሟልቶ መደንገጉ የተሻለ ይሆናል፡፡

ክፍል 2

አንቀጽ 13. የመንግስት አካላት የሥልጣን ክፍፍል

1.የክልሉ መንግስት የሥልጣን ክፍፍል በህግ አውጭ፣በህግ አስፈጻሚ እና በህግ ተርጓሚ አካላት የተደራጀ
ይሆናል፤

2.በንዑስ አንቀጽ አንድ ለህግ ተርጓሚ የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት
ህገ መንግስቱን የመተርጎም ሥልጣን አለው፤

3.የመንግስት አካላት አንዱ በሌላው ሥልጣንና ተግባር ላይ ጣልቃ አይገባም፤


4.በንዑስ አንቀጽ ሦስት የተደነገገው ቢኖርም በመንግስት አካላት መካከል በህግ ተለይቶ የተደነገገን የቁጥጥርና
ክትትል ሥርዓትን አያስቀርም፡፡

ይህ ድንጋጌ በዚህ ክፍል ዉስጥ የሚካተት አይደለም፡፡ ትክክለኛ ቦታዉ የመንግሰት አደረጃጀትን የሚያወራዉ
ክፍል ነዉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ያለዉ አገላለጽ የህግ ተርጓሚን ስልጣን የሚዘረዝር ይዘት
በንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ያለ ያስመስለዋል፡፡ንዑስ አንቀጽ 2 መግባት የሚችለዉ የክልሉን የዳኝነት መዋቅር
ስልጣን የሚደነግገዉ ክፍል ነዉ፡፡ ሕግ አዉጪ አስፈጻሚ እና ተርጓሚ የሶስቱ የመንግስት አካልነት ላይ ምንም
ልዩ ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ ሙሉ ድንጋጌዉ ያለቦታዉ በሌላ ክፍል ዉስጥ የገባ ከመሆኑም በላይ ንዕስ አንቀጽ 2
በዚህ አንቀጽ ዉስጥ መግባት የለበትም፡፡

1) ይግባኝ/አቤቱታ ለፌደሬሽን ም/ቤት ስለማቅረብ

በህገመንግሰት ረቂቁ ላይ ለፌደረሽን ም/ቤት አቤቱታ ወይም ይግባኝ ያቀርባል የሚሉ ድንጋጌዎች ተካተዋል፡፡
የፌደረሽን ም/ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚቀርብ ይግባኝ/አቤቱታ ተቀብሎ ይወስናል የሚል የፌደረሽን ም/ቤት
ስልጣንና ተግባር ዉስጥ ወይም የሚመራበት ልዩ ህግ ዉስጥ መኖር አለበት፡፡ ለምሳሌ የመዋቅር ጥያቄን
በተመለከተ ብሄሮች ለፌደረሽን ም/ቤት አቤቱታ/ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችሉ ረቂቁ ላይ ተቀምጧል፡፡
በብሄረሰቦች ም/ቤት በተሰጠዉ ህገመንግሰት ትርጉም ያልረካ ወገን ለፌደረሽን ም/ቤት ይግባኝ የማቅረብ
መብት እንዳለዉ ይገልጻል፡፡

የፌደረሽን ም/ቤት በፌዴራሉ ህገመንግሰት አንቀጽ 62 ላይ የተሰጠዉ ስልጣን በክልሎች ዉስጣዊ መዋቅራዊ
አደረጃጀት ላይ የሚነሱ ጉዳዮችን በይግባኝ የማየት አይመስልም፡፡ አዋጅ ቁጥር 251/93 አንቀጽ 19 እና
ተከታዮቹን በማንበብ መረዳት ይቻላል፡፡ የፌዴራሉ ህገመንግሰት በክልሎች ዉስጣዊ አደረጃጀት ጉዳይ
ለፌዴረሽን ም/ቤት ስልጣን ያልሰጠ ከመሆኑም በላይ በአንቀጽ 50/4 መሠረት ክልሎች ዉስጣዊ
አደረጃጀታቸዉን እንድያደራጁ ስልጣን ስጥቷል፡፡ ስለዚህ የፌደረሽን ም/ቤት ያልተሰጠዉን ስልጣን እንድሰራ
ከክልል ይግባኝ እንድቀርብለት መደንገግ ወደላይ ማዘዝ ይመስላል፡፡

የህገመንግሰት ትርጉምን በተመለከተ የፌዴረሽን ም/ቤት እንድተረጉም የፌዴራሉ ህገመንግስት የደነገገዉ


የፌዴራሉን ህገመንግሰት ነዉ፡፡ ባልተሰጠዉ ስልጣን የክልልን ህገመንግሰት እንድተረጉም ይግባኝ ለፌደሬሽን
ም/ቤት እንድቀርብ መደንገግም ወደላይ ማዘዝ ይሆናል፡፡

ስለዚህ የፌደረሽን ም/ቤት እንድያከናዉን በህግ ያልተደነገጉ ተግባራትን እንድያከናዉን ማዘዝ የፌደራሉን
ህገመንግሰት የሚቃረን ስለሆነ በዉስጥ አደረጃጀት ጉዳይም ሆነ በክልል ሕገመንግሰት ትርጉም ላይ ለፌደረሽን
ም/ቤት ይግባኝ ልቀርብ የሚችልበት ህደት የለም፡፡ ይህ እድሆን የፌደረሽን ም/ቤትን ስልጣን በሚደነግገዉ
ክፍል ላይ --“ከክልል በይግባኝ/በአቤቱታ የሚመጡ ጉዳዮች ላይ መወሰን” የሚል መኖር ነበረበት፡፡ በፌዴራል
ህገመንግስቱ አንቀጽ 62 እና አዋጅ ቁጥር 251/93 በክልል ዉስጥ የሚፈጠሩ የዉስጥ አደረጃጀት
ጥያቄዎችን፣የዉስጥ የድንበር ግጭቶችን እና የክልል ህገመንግስትን የመተርጎም ስልጣንም ግደታም
በፌዴረሽን ም/ቤት ላይ የሌለ ስለሆነ ተፈጻሚነት የማይኖራቸዉ ድንጋጌዎች ይመስላሉ፡፡
2) አንቀጽ 48. አዳዲስ አደረጃጀቶችን ስለመመስረት

ይህ ድንጋጌ በዋናነት ለማስተላለፍ የፈለገዉ ክልል ዉስጥ ስለሚደራጁ አዳድስ አደረጃጀቶች ይመስላል፡፡
ምክንያቱም ቀድሞት ባለዉ ድንጋጌ ላይ የተዘረዘሩት ዉስጣዊ አደረጃጀቶች ከመሆናቸዉም በላይ የዚህ
ድንጋጌ ርዕስ ራሱ በክልሉ ዉስጥ አዳዲስ አደረጃጀቶችን ስለመመስረት እንደሆነ ገላጭ ይመስላል፡፡

አንቀጽ 48/1 ላይ ብሄሮች በማንኛዉም ጊዜ የራሳቸዉን የአደረጃጀት መዋቅር የማቋቋም መብት አላቸዉ
የሚል ድንጋጌ የተቀመጠ ስሆን የራሳቸዉን መዋቅር የመመስረቻ ህደት በህገመንግስቱ አልተገለጸም፡፡ ረቂቁ
ይህን በማድረግ ፈንታ በፌዴራሉ ህገመንግሰት የተሸፈነዉን ክልል የመመስረት ህደት ይዘረዝራል፡፡ በፌደራሉ
ህገመንግሰት የነበረዉን ክፍተት በሚሞላ መልኩ ስለክልሎች አደረጃጀት መደንገጉ ባይነቀፍም የክልሉ
ህገመንግስት ዋና ራስ ምታት መሆን የነበረበት ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የተቀመጠዉን መብት ብሔሮች
የሚተገብሩበት ሁኔታ ነዉ፡፡ የፌደራሉ ህገመንግሰት ስለክልሎች አመሰራረት ህደት ከደነገገ የክልሉ
ህገመንግሰት ስለዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አመሰራረት ሕደት መደንገግ ነበረበት፡፡

በሌላ በኩል ብሄርን መሠረት አድርገዉ የሚቋቋሙት አደረጃጀቶች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ስሆኑ ወረዳ፣ከተማ
አስተዳደር እና ቀበሌ በዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ዉስጥ የሚመሰረቱ ስለሆነ የአመሰራረት ህዴታቸዉ ተመሳሳይ
ልሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ብሄሮች በማንኛዉም ጊዜ የራሳቸዉን መዋቅር እንደሚመሰርቱ ብቻ ሳይሆን
መመስረት ስለሚችሉት መዋቅር እና የአመሰራረት ህደቱ በዝርዝር ልደነገግ ይገባል፡፡ በሌላ አካል የሚመራዉን
የክልል አወቃቀር ህደት በዝርዝር ደንግጎ የራስ ተግባር የሆነዉን የዞን እና ልዩ ወረዳ አጠያየቅ እና ምስረታ ህደት
አለመደንገግ ትክክል አይመስልም፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በረቂቁ አንቀጽ 48 ላይ የክልል ጥያቄም ሆነ ሌሎች መዋቅሮች እንደሚመሰረቱ


ተደንግጓል፡፡ መዋቅሮቹ ልመሰረቱ የሚችሉትም በብሄር ም/ቤቶች ጥያቄ ስቀርብ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ነገር
ግን የዞን/ልዩ ወረዳ ም/ቤቶች ስልጣን በሚለዉ ክፍል ላይ ም/ቤቱ የመዋቅር/አደረጃጀት ጥያቄ ማቅረብ
እንደሚችል ስልጣን አልሰጠዉም፡፡ ስለዚህ የዞን/ልዩ ወረዳ ም/ቤቶች ስልጣን ላይ ይህ ስልጣን መጨመር
ያለበት ይመስላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የዞን/ልዩ ወረዳ ም/ቤት አወቃቀር የሚለዉ ክፍል ላይ የም/ቤት አባላት አመራረጥን ስደነግግ
“ለክልል ም/ቤት የተመረጡትን ጨምሮ ከየወረዳዉ ለዞን/ልዩ ወረዳ ም/ቤት የሚመረጡበት አባላት ያሉበት
ሆኖ ይቋቋማል” ይላል፡፡ ይህ ድንጋጌ ዞንን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ስሆን ልዩ ወረዳ በስሩ ወረዳዎች የለሉት ስለሆነ
የዞን ም/ቤት አባላት አመራረጥ እና የልዩ ወረዳ ም/ቤት አባላት አመራረጥ ተመሳሳይ ልሆን አይችልም፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የክልሉን ንዑስ ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አወቃቀር በደነገገዉ ክፍል የዞንና ልዩ ወረዳ
ፍ/ቤቶች አወቃቀር የተለያዩ መሆኑን ታሳቢ ያላደረገ ይመስላል፡፡

3) የክልል ም/ቤት ስልጣን ወይስ የብሄረሰቦች ም/ቤት

የቀድሞዉ የደቡብ ክልልም ሆነ አሁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደረጃጀታቸዉ የፌደረሽን ቅርጽ ይይዛል፡፡
በፌደሬሽን የላይኛዉ ም/ቤት ወይም ፌደረሽኑን የመሰረቱ አባላት የሚወከሉበት ስሆን የታችኛዉ ም/ቤት
ህዝብ የሚወከልበት ነዉ፡፡ የላይኛዉ ም/ቤት የፌደረሽኑ ጠባቂ እና ፌደረሽኑን የሚመለከቱ ጉዳዮችን
የሚወስን ነዉ፡፡ በመመስረት ላይ ያለዉ የደቡብ ኢትዮጵያም የፌደረሽን ቅርጽ የያዘ በፌደራሉ መንግሰት
ሉዓላዊነታቸዉ የተረጋገጠላቸዉ ብሔር ብሔረሰቦች እንደገና በክልል ደረጃም በፌደሬሽን መልክ የተዋቀሩበት
ክልለ ነዉ፡፡ ስለዚህ ፌደረሽኑን የሚመለከቱ ጉዳዮች መወሰን ያለባቸዉ በላይኛዉ ም/ቤት ነዉ፡፡
ፌዴረሽኑን/ክልሉን የሚመሰርቱ አካላት የሚወከሉበት የላይኛዉ ም/ቤት የብሄረሰቦች ም/ቤት ነዉ፡፡ ስለዚህ
ክልሉ እንደፈደረሽን ተወስዶ በክልሉ ዉስጥ የሚነሱ ዉስጣዊ አደረጃጀቶችን የመፍታት ስልጣን ልሰጠዉ
የሚገባዉ ለብሄረሰቦች ም/ቤት ነዉ፡፡ በረቂቁ ህገመንግሰት የዉስጥ አደረጃጀትም ሆነ ክልል የመሆን ጥያቄን
በአንቀጽ 48 መሠረት የሚነሱ የአደረጃጀትን ጥያቄዎችን በሚል ለክልል ም/ቤቱ ይሰጥና እንደገና በሌላ
ድንጋጌ ለብሄረሰቦች ም/ቤት ይሰጣል፡፡ ስለዚህ በፌደራሉ ህገመንግስት እንደተገለጸዉ ክልል ለመሆን የሚነሱ
ጥያቄዎችን ካልሆነ ሌሎች የአደረጃጀት ጉዳዮች የብሄረሰቦች ም/ቤት ተደርገዉ ልደነገጉ ይገባል የሚል ሀሳብ
አለኝ፡፡

4) አንቀጽ 22. የተከሰሱ ሰዎች መብት

1. የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸዉ በኃላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት
ለህዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመሰማት መብት አላቸው፤

2. ለሕፃናት ልዩ ጥቅምና ደህንነት ሲባል በወንጀል የተከሰሱ ህጻናት የክስ መሰማት ሂደት በዝግ ችሎት
መሆን አለበት፤

የተከሰሱ ሰዎች በግልጽ ችሎት ክሳቸዉ እንድሰማ ያስፈለገዉ ለተከሳሹ ጥቅም ነዉ፡፡ ምክንያቱም ግልጽ
ባልሆነ ችሎት የተከሰሱ ሰዎች ያለአግባብ ልበደሉ ስለምችሉ እና በግልጽ ችሎት ጉዳዩ መታየቱ ዳኞች
የሚወስኑትን ዉሳኔ ተገማች እንድያደርጉ ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡

የህጻናትን ችሎት በዝግ ማድረግ ለህጻኑ ጥቅም ነዉ ወይስ ጉዳት ነዉ ስጀመር ግልጽ ችሎት ለተከሳሹ ጥቅም
ከሆነ የህጻናትን ችሎት ዝግ ማድረግ ለህጻኑ ጥቅም እንደት ልሆን ይችላል

ህጻኑን መጥቀም የሚሆነዉ ለአዋቂ እንኳን የተፈቀደዉን ግልጽ ችሎት መከልከል ሳይሆን ለአዋቂ የማይፈቀዱ
ልዩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነዉ፡፡

ይህ ድንጋጌ ልያስከድ የሚችለዉ የወንጀል ተጎጂዎች ወይም ምስክሮች ህጻናት በሚሆኑበት ጊዜ ችሎቱ ዝግ
እንድሆን ብገረግ ነዉ፡፡ በዚህ ጊዜ የተከሳሽ በግልጽ ችሎት የመሰማት መብት በልዩ ሁኔታ ተገድቦ በዝግ ችሎት
እንድሆን ይደረጋል እንጂ ተከሳሽ ህጻን ከሆነ ዝግ ማድረግ አዋቂ ያለዉን መብት ህጻንን በልዩ ሁኔታ መንፈግ
እንጂ ህጻኑን መጥቀም አይሆንም፡፡

5) አንቀጽ 30. በሰብአዊነት ላይ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች

በዚህ ድንጋጌ ርዕሱ እንደገና ዝርዝሩ ዉስጥ ተካቷል፡፡ ስለዚህ ሁሉንም ልያክትት የሚችል የአንቀጹ ርዕስ ብሆን
ይመረጣል፡፡ ርዕሱ ራሱ የዝርዝሩ አካል ከሆነ ሙሉ ዝርዝሩን ገላጭ አይሆንም፡፡
ከዚህ ጋር በተመሳሳይ በረቂቁ ላይ ብሄር ብሄረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር አንዱ አካል የሆነዉን ምዛናዊ
ዉክልና የማግኘት መብትን የሚደነግገዉ ክፍል ላይ ለፌደራሉ መንግስት ግዴታ ይጥላል፡፡በዚህ ህገመንግሰት
መሰረት ልሰጥ የሚቸለዉ መብት ይህን ሕገመንግሰት ጠቅሰዉ ሰዎች ተከራክረዉ ማግኘት የሚችሉት ብቻ
ነዉ፡፡ በፌደራል መንግሰት ሚዛናዊ ዉክልና የማግኘት መብት እነዳላቸዉ በክልል ህገመንግሰት ተደንግጎ
ልፈጸም አይችልም፡፡ የፌደራሉ ህገመንግስት ይህንን መብት ስላረጋገጠ የክልሉ ህገመንግሰት በክልል እና ከክልል
በታች ባሉ መዋቅሮች የብሄሮች ምዛናዊ ዉክልና እንድረጋገጥ የማድረግ ሓላፊነት ስላለባቸዉ ይህን ማድረግ
ይችላሉ፡፡ ነገር ግን አልፎ በፌደራል መንግሰት ምዛናዊ ዉክልና የማግኘጥ መብት አላችሁ ብሎ መደንገግ
አስፈላጊነቱ አይታይም

ፍ/ቤቶችንም በተመለከተ በተመሳሳይ በፌደራል መንግሰት ይሁንታ ላይ የሚመሰረቱ ጉዳዮችን እንደመብት


ደንግጓል፡፡ ለምሳሌ የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት እስክቋቋም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት
ስልጣንን በዉክልና እንድሰራ የተሰጠዉ ስሆን አሁን የደቡብ ክልል ላይ ጠቅላይ ፍ/ቤት በፌዴራል ጉዳዮች ላይ
የመጀመሪያ ደረጃ የዳንነት ስልጣን የለዉም፡፡ ስለዚህ የፌደራል መንግስት ስፈልግ እየጠ ስፈልግ የሚያነሳዉን
ጊዜያዊ ዉጤት ያለዉን ድንጋጌ ህገመንግሰት ዉስጥ ማካተት አስፈላጊ አይመስልም፡፡

አንቀጽ 91.የዞን ወይም የልዩ ወረዳ ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር

የዞን ወይም የልዩ ወረዳ ምክር ቤት ለክልል ምክር ቤት የተመረጡትን አባላት ጨምሮ ከየወረዳው ለዞን ወይም
ለልዩ ወረዳ ምክር ቤት የሚመረጡ አባላት ያሉበት ሆኖ ይቋቋማል፤

የቀድሞዉ ደቡብ ክልልም ሆነ አሁን የሚደራጀዉ ክልል በፌዴረሽን ዉስጥ ያለ ሌላ ፌዴሬሽኝ ልባል የሚችል
አይነት ነው፡፡ ምክንያቱም በፌደራሉ ህገመንግስት የተሰጡ በክልሉ ህገመንግስት ልከለከሉ የማይችሉ መብቶች
ያሏቸዉ ብሔሮች የሚመሰርቱት ክልል ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ብሄሮች በፌደራሉ ህገመንግስት የተሰጣቸዉን
መብቶች እንደያዙ የሚመሰርቱት ክልል እስከሆነ ድረስ ክልሉ በፌዴረሽን ዉስጥ ያለ ሌላ ፌደረሽን ይሆናል፡፡
በክልሉ የሚኖሩ አደረጃጀት መዋቅሮች ብሄርን መሰረት ያደረጉ እና ያላደረጉ ልሆኑ ይእላሉ፡፡ ነገር ግን አንድ
ብሄር በፌደራሉ ህገመንግስትም ሆነ ዓለም አቀፍ ህጎች የተሰጡትን ብሄር በመሆኑ የሚያገኛቸዉን መብቶች
የሚተገብርበት መዋቅር ልኖረዉ ይገባል፡፡ በዚህ ረቂቅ ህገመንግስትም ሆነ በፌደራሉ ህገመንግሰት ብሄሮች
ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤቶች ናቸዉ፡፡የክልሉ መንግሰት በዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የተዋቀረ ነዉ፡፡

አንቀጽ 49. የአስተዳደር እርከኖች የወሰን አከላለል


1.በክልሉ ውስጥ የአስተዳደር እርከን ወሰንን አከላለል የህዝቦችን ታሪክ፣ባህል፣ቋንቋ ፣የማህበረሰባዊ
መስተጋብር ፣አሰፋፈርና ፍላጎት እንዲሁም የጥቅም ቁርኝት መሰረት በማድረግ ወይም ሌሎች ተገቢ የሆኑ
መስፈርቶችን የተከተለ ይሆናል፤

2.በክልሉ ውስጥ የአስተዳደር እርከን ወሰንን በሚመለከት አለመግበባት የተነሳ እንደሆነ በሚመለከታቸው
መዋቅር ውስጥ ባሉ የአከባቢው ማህበረሰብ አካላት በስምምነት ይፈታል፤

3.በንዑስ አንቀጽ ሁለት በተደነገገው አግባብ ጉዳዩ ካልተፈታ በየእርከኑ ባለው የአስተዳደር መዋቅር የሚፈታ
ይሆናል፤4.በንዑስ አንቀጽ ሦስት ያለመግባባቱ ካልተፈታ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ጉዳዩ በቀረበ በአንድ
ዓመት ጊዜ ውስጥ በንዑስ አንቀጽ አንድ የተቀመጠውን መስፈርት በመከተል ውሳኔ ይሰጣል፤

5.በንዑስ አንቀጽ አራት መሰረት በብሔረሰቦች ምክር ቤት በተሰጠው ውሳኔ ያልተስማማ ወይም
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምላሽ ያላገኘ አካል ይግባኙን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል፡፡

ህገመንግስት ስለማሻሻል

ህገመንግሰትን ሰለማሻሻል በሚለዉ ክፍል ንዑስ 1 ላይ የፌደራሉ ህገመንግሰት ባስቀመጠዉ መሠረት ይላል፡፡
የፌደራሉ ህገመንግሰት ስክልል ህገመንግሰት መሻሻል ልያወራ አይችልም፡፡

በሌላ በኩል ህገመንግሰትን ስለማሻሻል የሚደነግገዉ ክፍል በፌደራሉ ህገመንግሰት ለብሄሮች የተሰጠዉን
መብት ያጣበበ ነዉ፡፡ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የብሄር መዋቅሮች ስለሆኑ የፌደራሉ ህገመንግስት
በህገመንግሰት ማሻሻያ ላይ የእነሱ ይሁንታ እንድኖር ደንግጓል፡፡ ነገር ግን በረቂቁ ህገመንግሰት የብሄሮችን
ተሳትፎ በመገደብ አብዛኛዉ ድንጋጌ በሁለቱ ም/ቤቶች የሚሻሻል እንድሆን አድርጓል፡፡ የክልል ህገመንግሰት
በፌደራሉ ህገመንግሰት ከተሰጠዉ መብት ተጨማሪ መብት መስጠት ወይም መብትን ማስፋት ይችላል እንጂ
በፌረራል ህገመንግሰት የተሰጠዉን መብት መገደብ አይችልም፡፡ ኢ ህገመንግስታዊ ነው፡፡

You might also like