Professional Documents
Culture Documents
ውህደት ማለት የስውር ግልፅ አሀዳዊነት ማለት እንደሆነ ተረጋገጠ
ውህደት ማለት የስውር ግልፅ አሀዳዊነት ማለት እንደሆነ ተረጋገጠ
ስለዚ የአፋር ፖለቲካ ድርጅት ተዋሀደ ማለት የአፋር ህዝብ መብት ለብልፅግና
ፓርቲ አሳልፎ ሰጠ ማለት ነው፡፡ የጋምቤላ፣ የቤንሻንጉል፣ የሶማሌ፣ የሀረሬ፣
የደቡብ ፖለቲካ ፓርቲዎችም ተዋሀዱ ማለት የየክልላቸው ህዝብ መብት ኣሳልፈው
ለብልፅግና ፓርቲ ሰጡ ማለት ነው፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ማለት ደግሞ የሁሉም ብሄር
ብሄረሰቦች ፓርቲ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በየራሳቸው ጉዳይ
ሳይሆን በሁሉም ጉዳይ ገብተው ይፈተፍታሉ፣ ይወስናሉ ማለት ነው፡፡
በሌላ አነጋገር ባለፉት 28 ዓመታት የነበረውን የየክልሉ ህዝብ በራሱ ክልል ህዝብ
የመወሰን ስልጣን አሳልፎ ለብልፅግና ፓርቲ ወይም ለአንድ ፓርቲ መስጠት ማለት
ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ የበለጠ የአሀዳዊ ፓርቲ መገለጫ ምን ይምጣ ?