You are on page 1of 4

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት

ደቡብ ምዕራብ ነጋሪት ጋዜጣ


SOUTHWEST NEGARIT GAZETA
OF THE SOUTHWEST ETHIOPIA PEOPLES’ REGIONAL STATE

……. ዓመት ቁጥር…… ………th Year No ………


…….. ቀን……./2014 ………..th ……., 2021

ማውጫ

አዋጅ ቁጥር ……..2014 ዓ.ም

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ለመደበኛ መንግስታዊ ሥራዎች በነባሩ
ክልል የወጡ አዋጆች ተፈጻሚነት እንዲቀጥል ለመፍቀድ የወጣ አዋጅ ቁጥር ……/2014
……………….. ገጽ ፩

አዋጅ ቁጥር ……. /2014

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ለመደበኛ መንግስታዊ ሥራዎች በነባሩ
ክልል የወጡ አዋጆች ተፈጻሚነት እንዲቀጥል ለመፍቀድ የወጣ አዋጅ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት የተደራጀበት ጊዜ አጭር ከመሆኑ የተነሳ
መደበኛ መንግስታዊ ሥራዎችን ለማስቀጠል የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ሕጎችን አዘጋጅቶ ሥራ
ላይ ለማዋል ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግ ከመሆኑ በላይ ያለ ሕግ ማዕቀፍ መንግስታዊ
ሥራዎችን መፈጸም አስቸጋር በመሆኑ፣

በክልሉ ለመደበኛ መንግስታዊ ሥራዎች የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ሕጎች በተደረጀ ሁኔታ


እየተዘጋጁ እና እየጸደቁ ሥራ ላይ እስከሚውሉ ድረስ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
ክልል መንግስት ለመደበኛ መንግስታዊ ሥራዎች የወጡና በሥራ ላይ የሚገኙ ሕጎች በደቡብ
ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ውስጥ ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል የሚፈቅድ
ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፣
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 56 ንዑስ አንቀጽ 3 (ሀ)
መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

1. አጭር ርዕስ

ይህ አዋጅ “በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ለመደበኛ መንግስታዊ


ሥራዎች በነባሩ ክልል የወጡ አዋጆች ተፈጻሚነት እንዲቀጥል ለመፍቀድ የወጣ አዋጅ
ቁጥር ……. /2014” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያስጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-

1. “መደበኛ መንግስታዊ ሥራ” ማለት እያንዳንዱ የመንግስት አስፈጻሚ ወይም ሕግ


ተርጓሚ አካል የተቋቋመበትን ዓላማ እና ተልዕኮ ለማሳካት የሚሰራው የውስጥ እና
ወደ ተቋሙ የመጣ ተገልጋይን በአግባቡ ለማስተናገድ የሚፈፅመው ሥራ ነው፡፡
2. “ነባሩ ክልል” ማለት የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ነው፡፡
3. “አዲሱ ክልል” ማለት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ነው፡፡
4. “እንደ አግባብነቱ” ማለት በነባሩ ክልል የወጡ አዋጆች ስያሜያቸው ወይም ይዘታቸው
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ህገ መንግስት ጋር ሊጣጣሙና ተፈጻሚ
ሊሆኑ በሚገባቸው መጠን ብቻ ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚገባ የሚገልጽ ሐረግ ነው፡፡

3. ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል የተፈቀዱ አዋጆች

በነባሩ ክልል መንግስት መደበኛ መንግስታዊ ሥራዎችን ለማስኬድ የወጡና ስማቸውና


ብዛታቸው ከዚህ አዋጅ ጋር አባሪ የተደረጉ አዋጆች እንደ አግባብነታቸው በአዲሱ ክልል
ለሚሰሩ መደበኛ መንግስታዊ ሥራዎች ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል በዚህ አዋጅ
ተፈቅዷል፡፡

4. አጠቃቀምን በሚመለከት

በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 መሰረት ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል የተፈቀዱ በነባሩ ክልል የወጡ
አዋጆች ከተፈጻሚነት ወሰን፣ ከፈጻሚ ተቋማት አደረጃጀት፣ ከአስተዳደር እርከን፣ ከርዕሰ
ጉዳዩች ይዘትና አግባብነት አንጻር ለአዲሱ ክልል በሚመጥን መልኩ ሥራ ላይ የሚውሉ
ይሆናል፡፡

5. ደንብና መመሪያ ስለማውጣት

1. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 3 ላይ በተደነገገው መሠረት ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል


የተፈቀዱ አዋጆችን ለማስፈጸም ወይም ለአዲሱ ክልል ለመደበኛ መንግስታዊ ሥራ
አግባብነት ያላቸው በነባሩ ክልል የወጡ ደንቦች ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል የሚፈቅድ
ደንብ በመስተዳደር ምክር ቤት ይወጣል፡፡
2. በነባሩ ክልል የወጡ አዋጆችን ወይም ደንቦችን ለማስፈጸም የወጡ መመሪያዎች
ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል የሚፈቅድ መመረያ በእያንዳንዱ አስፈጻሚ ተቋም
ይወጣል፡፡
5. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ

ይህ አዋጅ ከ ………/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

………….……… ከተማ

…..………… ቀን 2014 ዓ.ም

አቶ/ወ/ሮ ……………………..

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት

ርዕሰ መስተዳደር
በዚህ አዋጅ ተፈጻሚነታቸው እንዲቀጥል የተፈቀዱ ህጎች አባሪ

1. የተሻሻለው የክልል ምክር ቤት የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 16/2008


2. የፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 43/94፣ የተሻሻለው የፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 85/96
እና የተሻሻለው የፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 130/2002
3. የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 42/94
4. ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 177/2011
5. የተሻሻለው የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 142/2004
6. የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 176/2011 እና የማሻሻያ አዋጅ
ቁጥር 189/2013
7. የተሻሻለው የፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 157/2006
8. የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 175/2011
9. የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 166/2009
10. የገቢ ግብር አዋጅ ቁ.165/2009
11. በክልሉ ፍርድ ቤቶች ስለሚሰሩ ጠበቆችና የግል የህግ ጉዳይ ጸሐፊዎች ፈቃድ
አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 164/2008
12. የይቅርታ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥ 157/2007
13. ከኃላፊነት የተነሱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላትና ዳኞች መብቶችና
ጥቅሞች ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 148/2004
14. ስለደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 147/2004
15. የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 146/2004
16. ሀብትን ለማሣወቅና ለማስመዝገብ የወጣ አዋጅ ቁጥር 138/2003
17. የቴምበር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር 135/2003
18. የተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ ቁጥር 57/1995 እና ማሻሸያ አዋጅ ቁጥር 134/2003
19. የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 128/2002
20. የገጠር መሬት መጠቀሚያ ክፍያና የግብርና ሥራ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 122/2000
21. የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 110/1999
22. የጋራ ሕንፃ ባለቤትነት አዋጅ ቁጥር 102/1999
23. የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/1996

You might also like