You are on page 1of 147

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሚያዝያ 2004 ዓ.ም


አዲስ አበባ
ማውጫ

I. መግቢያ 1

II. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ አስፈላጊነት 4


ክፍል አንድ - የስትራቴጂው መነሻ ሁኔታ ትንተና 20
1. መሰረታዊ ካርታ 20
1.1. የመሰረታዊ ካርታ መሰረታዊ ሀሳቦች 20
1.2. የሀገሪቱ የመሰረታዊ ካርታ አዘገጃጀት ነባራዊ ሁኔታዎች 22
1.3. በቅየሳና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት የሀገሪቱ የተቋማት ብቃት ዝንባሌ ትንተና /Trend Analysis/ 25
1.4 ከመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ቁልፍ ችግሮች 32
2. መዋቅራዊ ፕላን 32
2.1. የመዋቅራዊ ፕላን መሰረተ ሀሳቦች 32
2.2. የሀገሪቱ የመዋቅራዊ ፕላን አዘገጃጀት ነባራዊ ሁኔታ ትንተና 83
2.3. በመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት የሀገሪቱ የተቋማት ብቃት ዝንባሌ ትንተና /Trend Analysis/ 104
2.4 ከመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ቁልፍ ችግሮች 106
3. የአካባቢ ልማት ፕላን 107
3.1. የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት መሰረተ ሀሳቦች 107
3.2. የሀገሪቱ የአካባቢ ልማት ፕላን አዘገጃጀት ነባራዊ ሁኔታዎች 111
3.3. በአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት የሀገሪቱ የተቋማት ብቃት ዝንባሌ ትንተና /Trend Analysis/ 113
3.4 ከአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ቁልፍ ችግሮች 115
4. የመሰረታዊ ካርታ፣ መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ ልማት ፕላን የጋራ ጉዳዮች 116
4.1. የሕዝብ ተሳትፎ በከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ 116
4.2. ክትትል፣ ግምገማና ግብረ መልስ 120
4.3. የከተማ ፕላን መረጃ አያያዝ 121
4.4. የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ 122
4.5. የተቀናጀ የመሰረተ ልማት አቅርቦት 122
4.6. የፌዴራል፣ ክልሎችና የከተሞች ሚና በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ 123
4.7. የመሬት አጠቃቀሞቹ የሚፈጥሩት ቅንጅታዊ መስተጋብር 125
5. የስትራቴጂው ራዕይ፣ ዓላማና መርሆዎች 126
5.1. የስትራቴጂው ራዕይ 126
5.2. የስትራቴጂው ዓላማዎች 126
5.3. የስትራቴጂው መርሆዎች126
ክፍል ሁለት - የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ስትራቴጂ 127
1. ትኩረት የሚሹ የፖሊሲ/ ስትራቴጂ ጉዳዮች 127
2. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ስትራቴጂ አቅጣጫዎችና ስልቶች 132
3. የከተማ ፕላን ትግበራ/አፈጻጸም ስርዓትን ማሻሻል 148
3.1. የመዋቅራዊ ፕላን ማስተግበሪያ የዝርዝር ፕላን ዝግጅት ስርዓትን ማሻሻል 149
3.2. የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ስርዓትን ማሻሻል 151
4. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጸም ክትትል፣ ግምገማና ግብረ-መልስ ስርዓት
ማሻሻል 152
4.1. የክትትል ግማገማና ግብረመልስ አሰራርን ጥራቱን የጠበቀና ተደራሽ ማድረግ 153
4.2. በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የሕበረተሰብ ተሳትፎ ማሳደግ 154
5. በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የማስፈጸም ብቃትን ማሳደግ 158
5.1. ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት 159
5.2. የቴክኖሎጂ እና መረጃ አቅርቦት ማሻሻል 160
5.3. የተሟላ ተቋማዊ አደረጃጀት መዘርጋት 162
ክፍል ሶስት - ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት 163
1. ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚከናወኑ ተግባራት 163
2. በስትራቴጂው አፈጻጸም የባለድርሻ አካላት ሚና 163
3. ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው ጊዜ 164
4. የስትራቴጂው አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ 165
ክፍል አራት - ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚያስፈልግ የአደረጃጀትና የአመራር ስርዓት 166
1. ሊያሰራ የሚችል ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር 166
2. የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ክፍተቶችን ማሟላትና ተፈጻሚነታቸውን መከታተል 167
III. ማጠቃለያ 169
ዕዝል - የስትራቴጂ አፈጻጸሙ መርሀ ግብር 171
ዋቢ ሰነዶች 172
የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

I. መግቢያ

የከተማነት ሂደት በኢትዮጵያ ረጅም ዘመን ቢያስቆጥርም ዕድገቱ ካሳለፈው የጊዜ ርዝመት አንፃር ሲታይ
ዘገምተኛ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የከተሞች መቆርቆር የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በመጀመርያው
ዓመተ ዓለም ለመሆኑ እንደነበር የየሃና የአክሱምን ታሪክ እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ዘግየት ብሎም
ላሊበላ ጎንደርና ሐረርን ጨምሮ ወደ ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍሎች የከተሞች መስፋፈት ተከትሎ በአስራ
ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ላይ በዐፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት አዲስ አበባ በእንጦጦ
ኮረብታ ላይ እንድትቆረቆር ምክንያት ሆኗል፡፡ የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር መዘርጋትን ተከትሎ
እንዲሁም ከጣልያን ወረራ በኋላ የከተማነት ሂደት አስቀድሞ ከነበረበት በእጅጉ ተፋጥኗል፡፡

አዲስ አበባ ከተቆረቆረች በኋላ፤ በቀዝቃዛዎቹ ወራት ዐፄ ሚኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ወደ ፍልውሃን
ከማዘውተራቸውና በእቴጌይቱ አሳሳቢነት እ.ኤ.አ. በ 1886 ዓ.ም የሚኒሊክ ቤተመንግስትም በዚሁ አካባቢ
ከመገንባት ጋር ተያይዞ አስቀድሞ በተዘጋጀ የሰፈራ ፕላን መሰረት በመጀመሪያ ለከፍተኛ የጦር አበጋዞችና
የሲቪል ባለሟሎች በቤተመንግስቱ ዙርያ ሰፋፊ ቦታዎች ተደለደሉ፡፡ ቀጥሎም ከፍተኛ ባለስልጣኖቹ
በተራቸው ከስራቸው ለሚገኙት ሹማምንትና የሲቪል ማህበረሰብ ቦታቸውን እየሸነሸኑ ከሰጡ በኋላ
የመጀመርያው የመሬት አጠቃቀም መልክ (pattern) ተፈጠረ፡፡ ይህ የሰፈራ ፕላን የጣይቱ ፕላን በመባል
ይታወቃል፡፡ (Techeste, 1986፡1፣ በ Abercrombie,1956፡56 ውስጥ የተጠቀሰ)፡፡

ይሁንና፤ ዘመናዊ የከተማ ፕላን ዝግጅት በኢትዮጵያ የተጀመረው ከሰባት አሰርት ዓመታት በፊት በጣልያን
ወረራ ወቅት ነው፡፡ ቀዳሚውን ፕላን ያዘጋጀውም የስዊስና ፈረንሳይ ዜግነት ያለው ለኩርቡዜር የተባለው
መሃንዲስ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ፕላኑ አጠቃላይ ንድፍን ብቻ የሚያሳይና ተዘርዝሮ ያልቀረበ
እንደነበረም ይታወቃል፡፡ ብዙም ሳይቆይ ደገሞ በሁለት የኢጣሊያ የሥነ ሕንፃ ሙያተኞች የተሻለ ፕላን
ሊዘጋጅ በቅቷል፡፡ ይሁንና ለአዲስ አበባ በወቅቱ የተዘጋጁት እነዚህ ፕላኖች ነጮች አበሾችና የተለያዩ
ጎሳዎች የሚኖሩባቸውንና የሚጠቀሙባቸውን አካባቢዎች በመለየት ላይ ያተኮሩ ነበሩ (Techeste, 1986፡
6-7)፡፡ ከነፃነት በኋላም፤ በውጭ ሀገር ባለሙያዎች የከተማ ፕላን የማዘጋጀቱ ስራ የቀጠለበት ሁኔታ
ታይቷል፡፡ ሆኖም ግን ለአዲስ አበባ ጭምር ፕላኖቹ በአብዛኛው በአንድ ሲበዛ ደግሞ በሁለት የከተማ ፕላን
ሙያተኞች ብቻ መዘጋጀታቸው የሚፈለገውን ውጤት ሊያስገኝ አልቻለም፡፡ በተጨማሪም በማህበረ-
ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች ላይ ያልተመሰረተና ፊዚካል ፕላኖች መሆናቸው ከቶፖግራፊ ካርታዎች ችግርና
ከሌሎች ምክንያቶች ጋር ተዳምሮ የአፈፃፀም ደረጃውን በአብዛኛው ዝቅተኛ ሊያደርገው ችሏል፡፡ (ከላይ
የተጠቀሰው ምንጭ ገፅ 14)፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒሰቴር ገፅ 1


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከ 1979 ዓ.ም ጀምሮ የከተማ ፕላን ተቋማዊ ቅርፅ ይዞ በአገር ውስጥ ባለሙያዎች መዘጋጀት መጀመሩ እና
የተለያዩ ባለሙያዎችን ግብአት ለማካተት የተደረገውም ጥረት አዎንታዊ እርምጃ ቢሆንም በሽፋንም ሆነ
በጥራት ሲታይ፤ የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ ነበር ለማለት ግን አይቻልም፡፡ የመሠረታዊ ካርታ
በተፈለገው ብዛትና ጥራት አለመዘጋጀት፤ የሰለጠነ የሰው ኃይልና በአጠቃላይ የአቅም ውስንነት፣ የመረጃ
እጥረትና የመሳሰሉትም ለችግሩ አስተዋጽኦ ያላቸው ምክንያቶች ቢሆኑም በዋነኛነት የተዘጋጁት ፕላኖች
በካርታ ዝግጅት (ፊዚካል ፕላን) ላይ ያተኮሩና የነዋሪውን ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ግምት ውስጥ
ያስገቡ አልነበሩም። በተጨማሪም የማህበረሰብና የባለድርሻ አካላትም ተሳትፎ ዝቅተኛ ስለነበር፤ የፊዚካል
ፕላኑ የአፈጻጸም ደረጃም እንኳን ዝቅተኛ ነበር፡፡

ሌላ ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ችግር በሃገራችን በተለያዩ ክልሎችና የመንግስት እርከኖች ላይ ያሉ


አካላት በመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትም ሆነ ትግበራ ወቅት ቅንጅት አለመኖሩ ነው። ምንም እንኳን
የከተማ ፕላን አዋጁ መጣጣም የሚገባው የፕላን ተዋረድ መኖር እንዳለበት ቢደነግግም በተግባር ግን
እያንዳንዱ ፕላን የሚያዘጋጅ አካል በፈለገው አቅጣጫ እየሰራ ይገኛል። በከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን
ዝግጅትና ትግበራ የአጎራባች ክልሎችን ጥረት የሚያስተባብር የጋራ የፕላን ኮሚሽን የለም። አጎራባች
የሆኑ ከተሞች በተለያዩ የክልል አስተዳደሮች ስር በሚገኙበት ሁኔታ አብሮ/ተናቦ ማቀድ ካልተቻለ በሀገሪቱ
የከተማ ልማት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል።

በበርካታ ጥናቶች እንደተረጋገጠው የአንድ አገር ዕድገት ከከተሞች ልማትና ዕድገት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ
ነው። በዚህም ምክንያት ነው ‘ከተሞች የዕድገት ሞተሮች ናቸው’ የሚባለው። ይህን በመገንዘብም
የከተማ ልማት ፖሊሲውም “ከተሞች የገበያ የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ማዕከል ሆነው ማደግ ካልቻሉ
የገጠሩም ልማት መጓተቱ” እንደማይቀር ያስገነዝባል። በአምስት ዓመቱ (2003 – 2007) የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድም በከተሞች ከመሰረተ ልማት፣ ከአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ከኢንዱስትሪና
ኮንስትራክሽን ጋር በተያያዘ ሰፊ ዕቅድ ተነድፏል። የከተሞችንም ልማትና ዕድገት በፕላን ለመምራት፤
በከተማ ፕላን ንዑስ ዘርፉም እንደዚሁ ሰፊ ዕቅድ ተይዟል።

ነገር ግን ንዑስ ዘርፉ በርካታ ውስብስብ ችግሮች ስላሉበት ያጋጠሙትን ሁለንተናዊ ችግሮች መፈተሸና
መሰናክሎችን ከወዲሁ ለማቃለል ሊረዱ የሚችሉ ሀሳቦችን ማቅረብ የዚህ ስትራቴጂ ጥናት ዋና ዓላማ
ነው፡፡ ጥናቱ የተዘጋጀው በከተማ ፕላን ዘርፍ የሚገኙ ሰነዶችን በመፈተሽና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች
በተገኙ መረጃዎች ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ ለዚሁም፤ ከሁለት ክልሎች በስተቀር ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች
እንዲሁም ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ የከተማ ፕላን ባለሙያዎች ለአንድ
ወር ያህል በደብረዘይት የስራ አመራር ኢንስቲትዩት እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 2


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሰነዱ የስትራቴጂውን አስፈላጊነት ካብራራ በኋላ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን


የመጀመሪያው ክፍል የስትራቴጂው መነሻ ሁኔታ ትንተና በከተማ የመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና
አፈፃፀም ዙሪያ የሚገኙ ዋና ዋና መሰረተ-ሀሳቦችን የሚያብራራ ሲሆን ይህም በሚቀጥሉት ክፍሎች
ለሚነሱ ጉዳዮች ከወዲሁ ግንዛቤን ለማዳበር ይረዳል የሚል እምነት አለ፡፡ ክፍል ሁለት የከተማ መሬት
አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂው ሲሆን በውስጡ በዋናነት ትኩረት የሚሹ የፖሊሲና
የስትራቴጂ ጉዳዮችን እንዲሁም የስትራቴጂ አቅጣጫዎችንና ስልቶችን ያብራራል፡፡ ክፍል ሶስት በክፍል
ሁለት የተቀመጡ ስልቶችን ወደ መሬት ለማውረድ መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት ይዘረዝራል፡፡ ክፍል
አራት ስትራቴጂውን ለማስፈፀም የሚያስችል የአደረጃጀት ስርዓት የሚያመለክት ሲሆን በመጨረሻም
ማጠቃለያ ሀሳቦችን ያቀርባል፡፡

II. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ


አስፈላጊነት

የከተማ ሕዝብ ዕድገትን በተመለከተ እ.አ.አ. በ 2009 ዓ.ም የተለቀቀ የተባበሩት መንግስታት መረጃ (UN,
2010) እንደሚያሳየው የከተማ ሕዝብ ድርሻ በአፍሪካ 40 ከመቶ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ገና 17 ከመቶ ብቻ
እንደነበር ያሳያል በሀገሪቱ የከተማ ሕዝብ ድርሻ ዝቅተኛ መሆን የራሱ ቀላል የማይባል እንደምታ አለው።
ይኸውም ፈጣን የከተሞች ዕድገት ሊኖር እንደሚችል ያመላክታል። ይህ ዕድገት በፕላን እንዲመራ በሀገር
አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች ግቦችና ዕቅዶች ተቀርጸው ተግባራዊ በመሆን ላይ
ይገኛሉ።

በዚህ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ አስፈላጊነት ርእሰ ጉዳይ ትንታኔ
ውስጥ ስትራቴጂው ከኢትዮጵያና ከከተሞቻችን ህዳሴ ከምእተ አመቱ ግቦች ከሀገር አቀፉና ከዘርፉ
ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ከኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ
እንዲሁም ከዘርፉ አረንጓዴ ልማትና አገልግሎት አሰጣጥ ስትራቴጂ አንጻር ያለውን አስፈላጊነት ከዚህ
በታች በተመለከተው ሁኔታ ለመግለጽ ተሞክሯል።

2.1 የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራተጂ እና የኢትዮጵያና የከተሞቻችን ህዳሴ

በአጠቃላይ ከአገራችን ህዝብ ውስጥ 17 ከመቶ ያህል ህዝብ ይኖራል ተብሎ የሚገመተው በከተሞች
ውስጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ እጅግ በጣም አብዛኛው በልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ ሊጠቀም
የሚችልና የሚገባው ነው፡፡ ሰፊው የከተማ ህዝባችን ከድህነትና ኋላቀርነት የመላቀቅ ፅኑ ፍላጎት ያለው

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 3


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በመሆኑና መንግስትም ይህንኑ በመገንዘብና በልማታዊ መንግስት ፕሮግራም እንደሚሳካ በማመን ተግባራዊ
ለማድረግ በሚያስችል ጠንካራና ፅኑ አቋም እየመራ ይገኛል፡፡

የከተሞቻችን ልማትና የህዳሴ ጉዞን ማፋጠን የሚቻለው ያለንን ሰፊ ጉልበትና ውሱን ካፒታል ውጤታማ
በሆነ ሁኔታ መጠቀም ሲቻል ነው፡፡ የከተሞቻችንን ልማትና ህዳሴም ለማፋጠን ወሳኞቹ ዘርፎች
የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልማትና የቤቶች ግንባታ ሲሆኑ ከሁለቱም ዘርፎች በህዳሴያችን ላይ
የላቀውን ሚና የሚጫወተው የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እንቅስቃሴ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያም በዋናነት
በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ላይ ያተኮረ የልማት አቅጣጫን ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ በመሆኑ ይሄውም
እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ሰፊ እድል የሚከፍት ሲሆን
ሌሎችንም ጥቅሞች የሚያስገኝና ሰፊ ጉልበትን ሊቀጥር የሚችል የኮንስትራክሽን ዘርፍን የሚያነቃቃ
የቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ተቀርጾ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም በነዚህ ብቻ የማይሸፈነው
የልማት ስራችንን የተሟላና ፈጣን እንዲሆን ለማድረግ ለመካከለኛና ትላልቅ ተቋሞች ልማት በቂ ትኩረት
በመስጠትና በቅደም ተከተላቸው አስተሳስሮ መፈጸም የህዳሴውን ጉዞ በእጅጉ የተሳለጠ እንዲሆን
ያደርገዋል፡፡

አብዛኛዎቹ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የልማት ስራቸውን ለማከናወን ከሚያስፈልጓቸው መሰረታዊ


ጉዳዮች መካከል ለልማት ስራው ቁርጠኝነት፣ የተወሰነ ስራ ለመስራት የሚያስችል ክህሎትና የንግድ
አመራር ጥበብ መጨበጥ፣ ውስን ካፒታልና ለማምረቻና ለመሸጫ የሚሆን መሬት ማግኘት ናቸው፡፡
ማምረቻና መሸጫ መሬት ካላገኙ የልማት ስራዎች ላይ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ የተሟላ አይሆንም፡፡
በመሆኑም እንደየምርቱ ዓይነት ምቹ የሆነ መሬት ሊቀርብላቸው ይገባል፡፡ ይህ ሲባል ግን መሬት
በጊዜያዊነትም ይሁን በቋሚነት ሲሰጣቸው በዘፈቀደ ወይም ክፍት ቦታ በተገኘ ቁጥር ሊሆን አይገባም፡፡
በከተማው የመሬት አጠቃቀም ፕላን ላይ በተጠና ሁኔታ የተመለከተውን መሬት ከአካባቢው ጋር
በተጣጣመ መልክ በመሸንሸንና በመደልደል ሊሆን ይገባል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም አልፎ አልፎ የኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከት ያላቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ሊከሰቱ ስለሚችሉ መሬትን ለሌላ አካል
እንዳያስተላልፉትና የታሰበው አቅጣጫ እንዳይሰናከል የክትትል ስርአታችን ጠንካራ ሊሆን ይገባል፡፡
ለዚህም ነው መሬት ውስን ሀብታችን ስለሆነ በፕላን በተመሰረተ ሁኔታ በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል
የህዳሴ ጉዟችንን የተሳካ እናድርገው የምንለው፡፡ እነዚህ ተቋማት ለልማቱ ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆኑ
በፕላን በተመሰረተ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያሳኩ ካደረግን የከተሞቻችን ህዳሴ በተሻለና ውጤታማ በሆነ
ሁኔታ የተሳካ ይሆናል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከላይ ሊገለጽ እንደተሞከረው ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ሰፊ እድል የሚከፍትና
የመኖሪያ ቤት ጥቅምን የሚያስገኝ ብሎም የከተሞችን ህዳሴ የሚያሳልጥ የቤቶች ግንባታም የሚከናወነው

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 4


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በመሬት ላይ በመሆኑ ይሄም መስተናገድ የሚገባው በተጠና ሁኔታ በከተማው የመሬት አጠቃቀም ፕላን
ላይ በተመለከተው ሁኔታ ሲስተናገድ ብቻ ነው፡፡ የመኖሪያ ቤት ቦታ በከተማ የመሬት አጠቃቀም ፕላን ላይ
ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ በመሆኑና ለሰው ልጆችም አንዱና መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ከመኖሪያ ጋር
ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን በማካተት በከተማ ፕላን ላይ የሚመለከት ነው፡፡ በአንዳንድ ከተሞች ለሌሎች
አገልግሎቶች የተያዙትን ቦታዎች በስፋት ለሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች ሲውሉ የሚታይ ሲሆን ይህም የመሬት
አጠቃቀም መስተጋብሩን ያዛባዋል፡፡

የመካከለኛና ከፍተኛ የማምረቻ ተቋማት ሰፊ የሰው ሀይል በማሳተፍ ሰፊ የስራ እድል ስለሚፈጥሩና
በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ሊሰሩ የማይችሉትን ስራዎች በመስራት በኢኮኖሚው ውስጥ ሊፈጠር
የሚችለውን ክፍተት በመሙላት ለፈጣን የከተሞች ህዳሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስለሚያበረክቱ
እንደየከተሞቹ ሁኔታ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላኑ ለነዚሁ በቂ ቦታ መያዝና በዚሁ መሰረት መስተናገድ
ይኖርባቸዋል፡፡

ስለዚህ በቅድሚያ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልማት ቀጥሎም የቤቶች ግንባታ እንዲሁም የመካከለኛና
ከፍተኛ ተቋማት ልማት በከተማ የመሬት አጠቃቀም ፕላን ስትራተጂ መሰረት የሚደገፉ ከሆነ የከተሞችን
ህዳሴ የተሻለ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማሳለጥ የሚቻል ይሆናል፡፡ ይሄው በመሬት አጠቃቀም ፕላንና
ስትራቴጂ የተሳለጠ የህዳሴ ጉዞም በዚያው ሰፊው ህዝብ እንዲሁም ሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች በየደረጃው
ከልማቱ ፍትሀዊ በሆነ አኳኋን እንዲጠቀሙ ለማድረግ ያስችላል፡፡ ለዚህም መገለጫ የሚሆነው አንደኛ
በዚሁ አቅጣጫ በምንመራው ሂደት በከተማ ውስጥ የሚፈጠረው የስራ እድል ከፍተኛ በመሆኑ የአብዛኛው
የከተማ ነዋሪ የገቢ መጠን ስለሚጨምር አጠቃላይ የሀብት ክፍፍሉ ፍትሀዊ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ
የከተማ ልማት ስራችን በፈጣን የግብርና ልማት ስራ የሚረጋገጥ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የገጠሩ
አርሶአደር በፈጣን የገጠር ልማቱ ሳቢያ ገቢው የሚጨምር በመሆኑ ከፍላጎትም ሆነ ለምርቱ ግብአት
ከማሟላት ጋር ተያይዞ የመግዛት አቅሙም በዚሁ መሰረት ይጨምራል፡፡ ለአርሶ አደሩ የሚጠቅሙት
ግብአቶች የሚመረቱት ወይም የሚከፋፈሉት ደግሞ እንደየከተሞቹ ደረጃ በከተሞች አካባቢ ለስራ
በተሰማሩት በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አማካይነት ነው፡፡ ለአርሶአደሩ በቀረቡት አነስተኛ ከተሞች
አካባቢ የሚገኙት የተወሰኑ አገልግሎቶችና ሸቀጦች ሲሆኑ በመካከለኛና ከፍተኛ ከተሞች ደግሞ በተሻለ
ሁኔታ በይበልጥ የተሟላና ሰፋ ያለ አገልግሎትና ሸቀጦች ይቀርባሉ፡፡ በመሆኑም የተለያዩ ከተሞች
እንደየደረጃቸውና እንደሚያቀርቡት አገልግሎት መጠን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚነታቸው
ይረጋገጣል፡፡

2.2. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራተጂ እና የከተማ ልማት ፖሊሲዎቻችን

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 5


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የከተማ ልማት ፖሊሲ እንደትኩረት አቅጣጫ ከለያቸው ሁለት ጉዳዮች
ማለትም ፈጣንና ፍትሀዊ ልማት የማረጋገጥ ስራዎች እንዲሁም የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር
ተግባራት መካከል በመጀመሪያው የትኩረት አቅጣጫ ላይ የከተሞች ፕላንና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን
ማጠናከር እንደ አንድ ጉዳይ አጉልቶ አውጥቶታል፡፡ የከተማ ፕላን ዝግጅትን አስመልክቶ ፖሊሲው
ማንኛውም የከተማ ፕላን ሲዘጋጅ የገጠርና ከተማ እንዲሁም ከተማና ከተማ ትስስር መሰረት ያደረገና
የሚያጠናክር፣ የልማት ዕቅድንና የመሬት አጠቃቀምን የሚያቀናጅ፣ የሀገርና የክልል የልማት ዕቅዶችን
መነሻ የሚያደርግ መሆን እንዳለበት እንደ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን በይዘትም ደረጃ ፈጣንና ፍትሀዊ
ልማትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን የመንግስት፣ የባለሀብትና የህዝብን ሚና የለየና ያቀናጀ እንዲሁም
በማማከር የሚያሳትፍና ተጠቃሚነታቸውንም የሚያረጋግጥ፣ ህዝቡ የስራው ባለቤት መሆኑን ማረጋገጥ
እንዳለበት ያመለክታል፡፡ የከተማ ፕላንም በተመሳሳይ በከተማ ልማት ፖሊሲው ላይ ለተለዩት የተለያዩ
የልማት፣ የዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማሳካት ጉልህ ሚና የሚጫወት ሆኖ ይገኛል፡፡
በከተማና የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ላይም የከተማ ፕላንን አስመልክቶ ከመሬት እደላ በፊት የመሬት
መጠንና አይነት በአግባቡ ታውቆና አጠቃቀሙ በፕላን የሚመራ እንዲሆን ያመለክታል፡፡

ከላይ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ እና የከተሞቻችን ህዳሴ፣ የከተማ
ልማት ፖሊሲና የከተማና ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ከከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ጋር ያላቸውን
ትስስር ለማየት የተሞከረ ሲሆን በመቀጠል የከተማ ፕላን ስትራቴጂ ለምእተ ዓመቱን ግቦች፣ ለሀገር
አቀፍ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ ለክፍለ ኢኮኖሚው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
እንዲሁም ለአረንጓዴ ስትራቴጂ መሳካት የሚኖረው አስፈላጊነት እንደሚከተለው ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

2.3 የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራተጂ እና የምዕተ ዓመቱ ግቦች

የምእተ ዓመቱን ግቦች ለማሳካት ወደ እንቅስቃሴ ከገቡት ሀገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ስትሆን
እንደሚታወቀው በምእተ አመቱ ግቦች ውስጥ ርሀብንና ድህነትን ማስወገድ፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርትን
ለሁሉም ማዳረስ፣ ሴቶችን ማብቃትና የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ፣ የህጻናት ሞትን መቀነስ፣ የእናቶች
ጤንነትን ማሻሻል፣ ኤች አይ ቪ ኤድስን፣ ወባንና ሌሎች በሽታዎችን መዋጋት እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ
ዘላቂነትን ማረጋገጥ በቅደም ተከተል ይገኙበታል፡፡

የምዕተ አመቱ የመጀመርያ ግብ የሆነውን የገቢ መጠናቸው በቀን ከ 1 የአሜሪካን ዶላር በታች የሆኑና
በረሀብ የሚቸገሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች በግማሽ በመቀነስ ሥር የሰደደ ድህነትንና ረሀብን ማጥፋትን
ከማሳካት አኳያ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የስራ ዕድልን በመፍጠርና ፍትሀዊ
የሀብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን በማስፋፋት በኩል ሰፊ ዕቅድ የተያዘ መሆኑ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 6


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ይታወቃል፡፡ ረዘም ላሉ ጊዜያት የከተማ ፕላን ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት በመሬት አጠቃቀም ፕላን
ሪፖርቱ ውስጥ የአካባቢ ኢኮኖሚ ልማት (Local Economic Development) ጥናት በማካሄድ ወይንም
በተደረጉ ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ የአካባቢውን ኢኮኖሚ አወቃቀር/ቅርፅ፣ ተግዳሮቶች፣ የፋይናንስ
አቅርቦትን፣ የተሰማራውን የሰው ሀይልና ሌሎችንም በመለየት የፕሮጀክት ሀሳቦችን እስከ መንደፍ
ይደርሳል፡፡ እንደ የአካባቢው ሁኔታም በመሬት ላይ ተስማሚ ቦታዎች እንዲያዙ ያደርጋል፣ ለክላስተር
ልማትም ቦታ ይከልላል፡፡

ከተሞች የሚፈጥሩትን የስራ እድል ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግ የከተሞችን የፋይናንስ አቅም
በማጥናት የሚሻሻልበትን ሁኔታ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ጥናት ይጠቁማል፡፡ ከላይ ለከተሞች
ህዳሴ መሰረቱ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መስፋፋት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን እነዚህኑ ተቋማት
በማስፋፋትና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በመንግስትና በግል አልሚዎች ጥረት በከፍተኛ ፍጥነት
እንዲያድግ ለማድረግ በከተማ የመሬት አጠቃቀም ፕላን በተደገፈ ሁኔታ የመሬት አቅርቦት በማመቻቸት
የስራ እድል በተሻለ ሁኔታ ማሳካት ይቻላል፡፡ በመሬት አጠቃቀም ፕላን በተደገፈ ሁኔታ የሚመሰረቱት
የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የሚፈጥሩት የስራ እድል ዘለቄታነት ያለው በመሆኑና አብዛኛውን የከተማ
ህዝብ የሚያሳትፍ በመሆኑ በከተማ ውስጥ የሚገኘው ነዋሪ ገቢው ስለሚጨምር ተጠቃሚነቱም በተሻለ
ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡ ለሀገራችን ድህነት መንስኤ ከሚሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ ስር የሰደደ ኪራይ
ሰብሳቢነት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘርፍ ማለትም ከመሬት ጋር በተያያዙ ስራዎቻችን ላይ
የሚስተዋል በመሆኑ መሬት በፕላን ላይ ተከልሎና የተመደበበት አገልግሎት ተለይቶ ግልፅ በሆነ መንገድ
ለተጠቃሚው ማስተላለፍ ሲቻል የኪራይ ሰብሳቢነትን በር ጎን ለጎን መግታት ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት የኢመደበኛ የኢኮኖሚ ዘርፍ
(informal sector) ከፍተኛ የሰው ሀይል በማሰማራት ድህነትን በመቀነስ ትልቅ ሚና ከመጫወቱም በላይ
እንደውም በአንዳንድ ሀገራት እስከ 90 ከመቶ የሚደርሰው አዳዲስ የስራ ዕድሎች የሚፈጠርበት ሴክተር
ነው፡፡ በኢትዮጵያ እ.አ.አ መጋቢት 2010 በማዕከላዊ ስታትስቲክ ኤጀንሲ በተሰበሰበው የስራ ሁኔታ መረጃ
መሠረት በሥራ ላይ ከተሠማራው የከተማ ሕዝብ 34 ከመቶ የሚሆነው በኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንደሚገኝ
ያመለክታል፡፡ በመሆኑም በከተማ ፕላን ለዘርፉ ቦታዎች ተከልለው ይያዛሉ፡፡ በቀድሞዎቹ ጊዜያት ይህ
የስራ ዘርፍ ከመደበኛው ኢኮኖሚም ሆነ ከመንግስት አስተዳደር ጋር ግንኙነት እንደሌለው ተደርጎ ይወሰድ
ስለነበር ዕውቅና ሳያገኝ እንደ ሕገ-ወጥ ሲቆጠር ቆይቷል፡፡

የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ማዳረስ የምዕተ አመቱ አንዱ ሌላ ግብ እንደመሆኑ መጠን ይሄውም
በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ላይ በማካተት ለትምህርት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መሆኑ
ይታወቃል፡፡ ይህን ጥረት ለማገዝ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን በከተማውና እንደሁኔታውም

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 7


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በአካባቢው የትምህርት አገልግሎቶች፤ በወጡ መስፈርቶች መሰረት፤ በፕላን ዘመኑ የሚያስፈልጉትን


የተቋማት ብዛት በመወሰን ለነሱም የሚሆኑ ተስማሚ ቦታዎችን መርጦ ይይዛል፡፡ ለነባሮችም ያሉበትን
ሁኔታ በማገናዘብ እንደአስፈላጊነቱም ተጨማሪ ቦታዎችን እንዲያካትቱ ያደርጋል፡፡ ከዚያም አልፎ
በአካባቢው የትምህርት ሂደቱን ሊያደናቅፉ ይችላሉ ተብለው በጥናት ለሚለዩ ችግሮች በፕላን ሪፖርት
በማካተት የሚቀረፉበትን የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ ለትምህርት ሂደት መሳለጥ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡

ከጤና ጋር በተያያዘም በተለይ የእናቶችን ጤና በማሻሻል ሞትን በሶስት አራተኛ መቀነስ፣ የህፃናት ሞትን
በሁለት ሶስተኛ መቀነስ፣ እንዲሁም የወባ ወረርሽኝንና የኤች አይ ቪ ኤይድስን ስርጭት ለማቆምና
ለመግታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን በተለያዩ እርከኖች በፕላን
ዘመኑ ለሚያስፈልጉ የጤና ተቋማት፤ በወጡ መስፈርቶች አማካኝነት፤ ተስማሚ ቦታ ከመያዝም
በተጨማሪ በጥናትና በስታንዳርዶች ላይ በመመርኮዝ በአካባቢው ያሉ ሁኔታዎችን በማገናዘብ የመፍትሄ
ሀሳቦችን ያቀርባል፡፡ የነባሮቹ ተቋማትንም ሁኔታና የከተሞቹንም እድገት ግምት ውስጥ በማስገባት
የማስፋፊያ ቦታዎችን ያካልላል፡፡ እንዲሁም ለሕብረተሰብ ጤና ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ አገልግሎቶችን
ግምት ውስጥ በማስገባት ከመኖርያ አካባቢዎች በተለየ አካባቢ እንዲመደቡ ቦታ ይይዛል፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ዘላቂነትን (environmental sustainability) ማረጋገጥ በምዕተ አመቱ ግቦችም ሆነ
በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘና ከከተማ ፕላን ጋርም ጥብቅ ዝምድና ያለው
አንድ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡ ከፋብሪካዎች፣ ከተሽከርካሪዎች፣ ከደኖች ቃጠሎና ከሌሎችም የሰው ልጅ ልዩ ልዩ
ተግባራት የሚለቀቀው የጭስ/የጋዝ ብክለት ለአካባቢና ብሎም ለሕብረተሰብ ጤና አሳሳቢ እየሆነ
መጥቷል፡፡ ሌላው የአካባቢ ችግርም የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሲሆን የማዕከላዊ
ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በ 1999 ዓ.ም በሰበሰበው መረጃ መሠረት በሃገሪቱ ከተሞች ከሚፈጠረው ደረቅ
ቆሻሻ የሚሰበሰበው በአማካኝ 29.2 በመቶ ብቻ እንደነበርና ቀሪው ወደ 7 ዐ በመቶ የሚሆነው በየመንገዱ
ዳርቻ፣ በውሃ መፋሰሻ ቦዮች፣ በወንዞችና በማንኛውም ክፍት ቦታዎች እንደሚጣል ያሳያል፡፡ አካባቢን
በዘላቂነት በመጠበቅ በኩል የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ሰፊ ሚና ይኖረዋል፡፡ በመጀመርያ የስራቸው
ባህሪ ከመኖርያ አካባቢዎች ጋር የማይጣጣሙ ተቋማትን ለብቻ በተለየ የመሬት አጠቃቀም በመመደብ ቦታ
ይይዛል፡፡ ቀጥሎም ማንኛውም በጥብቅ ቦታዎች የሚከናወኑ የከተማ ልማት ስራዎች፤ ትላልቅ ማምረቻ
ተቋማት፣ የአመት የእርድ መጠናቸው ከ 100,000 በላይ የሆኑ ቄራዎች፤ የቆሻሻ መድፊያ ቦታዎች፣
በስፋት የሚገነቡ የጋራ መኖርያዎች ወዘተ… ሲታቀዱ በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትላሉ ተብለው
የሚታሰቡ ከሆነ ወይም ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ያስፈልጋቸዋል ተብለው
የተመደቡ ከሆነ፤ ብክለትን የሚቆጣጠሩበት መንገድ እንዲኖር የከተማ ፕላን ያስገድዳል፡፡ በተጨማሪም
በአንዳንድ ከተሞች እንደአስፈላጊነቱ ለደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚያገለግሉ የገንዳ ማረፍያ ቦታዎችን
በመወሰን በየሰፈሩ እንዲመላከቱ ከማድረግም በላይ ከሁሉም አካባቢ ለሚሰበሰበው ቆሻሻም ተስማሚ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 8


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

መድፊያ ቦታ(ዎች)ን (Land Fill sites) መርጦ ይይዛል፡፡ በአዲስ አበባና አንዳንድ መካከለኛ ከተሞች
የፍሳሽ ቆሻሻ መስመሮችንም ሆነ የማከማቻ ቦታዎች በጥናት በመወሰን በፕላን ያሳያል፡፡

ከዚሁም ጋር በተያያዘ ተፋሰሶችን ለመጠበቅ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን የተለያዩ የውሳኔ ሃሳቦችን
የሚጠቁም ሲሆን ይሄንን ተግባራዊ ለማድረግ በከተማ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ሰፋ ካሉ ሌሎች አጎራባች
አካባቢዎችም ጋር በቅንጅት መስራትን ይጠይቃል፡፡ የተፋሰስ ቦታዎች ብዙውን ጊዜ የተፈጥሮ ውኃ አካላት
ፍሰት መነሻዎች የሆኑና የተለያየ ደረጃ ያለው የተዳፋትነት ገጽታ ያላቸው የመሬት ክፍሎች ሲሆኑ
ለመሬት መንሸራተትና ለጎርፍ አደጋዎች የተጋለጡ በመሆናቸው በከተሞች ላይ ችግሮችን
ከማስከተላቸው በፊት የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን እነዚህ አካባቢዎች በፕላን ላይ በመመስረት
በደኖች እንዲሸፈኑ ወይም ሌሎች አማራጮችን በማመላከት አስቀድሞ የመከላከያ እርምጃ እንዲወሰድ
መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

2.4 የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራተጂ እና የሀገር አቀፉና የዘርፉ የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅዶች

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ በዋናነት የተመለከቱት ጉዳዮች በሁለት የተከፈሉ
ሲሆን አንደኛው የኢኮኖሚ ዘርፍን የሚመለከት ሌላኛው ደግሞ የማህበራዊ ዘርፍን የያዘ ነው፡፡ ከኢኮኖሚ ዘርፍ አንጻር
በዕቅዱ የተመለከቱት የኢንዱስትሪ፣ የንግድ፣ የመሰረተ ልማት ማለትም መንገድ፣ የባቡር መሰመር፣ የቴሌኮሚዩኒኬሽን፣
ንጹህ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት፣ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሁም የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ስራዎች ሲሆኑ
ከማህበራዊ ዘርፍ አንጻር ደግሞ በእቅዱ የተመለከቱት የትምህርትና ስልጠና እና የጤና አገልግሎቶች ናቸው፡፡

በኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፎች ስር የተያዙትን እቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ የመሬት አቅርቦት አስፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡፡
የሚዘጋጀው መሬት በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ነው፡፡ በመሆኑም እነዚሁ ዘርፎች በየትኛውም ከተማ በዘፈቀደ
የሚመደቡ ሊሆን አይገባም፡፡ ከዚህ አንጻር ሁሉም ከተሞች በእቅዱ የተመለከቱትን አገልግሎቶች በተጠናና ተስማሚ
በሆኑ በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ሊመድቡ ይገባል፡፡ የአገልግሎቶቹን የምደባ ሁኔታም ተግባራዊ ለማድረግ የተጠና
መሬት አጠቃቀም ፕላን ለከተሞች አስፈላጊ ነው፡፡ እንደሚታወቀው መሬት አንዱና ትልቁ ለኪራይ ሰብሳቢነት ምንጭ
በመሆን ከሚታወቁት ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ሲሆን በፕላን ላይ እያንዳንዱን የከተማ ክፍል የቦታ አጠቃቀም በግልጽ
በመመደብ ለታሰበለት አላማ ብቻ እንዲውል በማስገደድ የኪራይ ሰብሳቢነት በር ለመዝጋት ያስችላል፡፡ በአብዛኛው
የከተሞቻችን ክፍል በስፋት የሚታይ ሌላው ጉዳይ የደቀቁና ያረጁ የከተማ ክፍሎች መገኘት ሲሆን
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይም በአዲስ አበባ ብቻ እነዚሁኑ የከተማ ክፍሎች በ 50% ለመቀነስ
በእቅድ ተይዟል፡፡ በዚህ ሂደትም አካባቢውን መልሶ ለማልማት የአካባቢ የመሬት አጠቃቀም ፕላን በቅድሚያ
የሚዘጋጅ በመሆኑ በዚህ ሁኔታ የሚጠናው ፕላን ለከተሞች አስፈላጊ ይሆናል፡፡ አካባቢው መልሶ በሚለማበት ወቅትም

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 9


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የሚገነቡት ግንባታዎች በፕላን የተቀመጡ ስታንዳርዶችን መሰረት አድርገው ስለሚሆን የህዝቡን የአኗኗር ደረጃ በማሻሻል
የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የመልሶ ማልማት ፕላኑ ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡

በሀገር አቀፉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ በመመስረት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፉ የራሱን የአምስት
አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያዘጋጀ ሲሆን ዕቅዱም ከአምስት የትኩረት መስኮች ማለትም ከጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ከካዳስተር፣ ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ፣ ከአሰራርና አመራር እና ከማዘጋጃ ቤታዊ
አገልግሎቶች ጋር የተያያዙ የአቅም ግንባታ ጉዳዮችን በመለየት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ጀምሯል፡፡
በዚህም መሰረት የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራተጂ ዕቅዶቹን ከማሳካት
አኳያ የሚኖረው አስፈላጊነት እንደሚከተለው ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

በተለያየ የአቅም ደረጃ ለሚገኘው የከተማ ነዋሪ የመኖርያ ቤቶችን ማቅረብ ድህነትን ከመቀነስና ኑሮን
ከማሻሻል አኳያ አስተዋፅኦ ከሚያበረክቱ አንዱና መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት
የከተማ ፕላን ደሳሳ/የቆሸሹ ሰፈሮችን በማሻሻል፣ ፍትሀዊ የመኖርያ ቤቶች ስርጭትና ቅይጥ (Mixed
Landuse) የመሬት አጠቃቀምን በማረጋገጥ በኩል ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ
አበባ 150,000 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ በተለያዩ አካላት ከ 500 ሺ በላይ ቤቶች
እንደሚገነቡ በዕቅድ የተያዘ ሲሆን ለነዚሁ የመኖርያ ቤቶችና ተጓዳኝ አገልግሎቶች ግንባታ የሚሆን
ተስማሚና ከአካባቢው አገልግሎቶች ጋር የሚጣጣሙ ቦታዎችን ለማዘጋጀት የከተማ ፕላን ያስፈልጋል፡፡

በተጨማሪም የከተማ ፕላን የሚጣጣሙ የመሬት አጠቃቀም አገልግሎቶችን በጥናት በመለየትና ምን


ከምን ጋር እንደሚቀየጥ በመወሰን የቅይጥ መሬት አጠቃቀም ቦታዎችንና ሌሎችንም በመመደብ ልማትን
ይመራል፡፡ በከተማ አቀፍ ደረጃና በተለይም በመኖርያ አካባቢዎች፤ ተዋረድን የተከተለ የገበያ አገልግሎት፣
ለምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት የመንገድ ተደራሽነትን፣ የመዋዕለ ህፃናትን፣ ከብክለት ነጻ የሆኑ
የወፍጮና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች ነዋሪው እንዲያገኝ የከተማ ፕላን ያመቻቻል፡፡ የተመጣጠነ
የአገልግሎት ስርጭት በማይኖርበት ጊዜ በተለይ የሚጎዱት ሴቶች እንደመሆናቸው መጠን፤ የከተማ ፕላን
ፍትሀዊ የአገልግሎት ስርጭትን በማስፈን በተለይ የሴቶችንና ተጋላጭ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን
ችግሮች በማቃለል ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘም በአገር አቀፍ ደረጃ ከ 3 ሚሊየን በላይ በጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕይዞች የተደራጁ አንቀሳቃሾች ወደስራ እንደሚገቡ በእቅድ የተያዘ ሲሆን ለእነዚህም
አንቀሳቃሾች ከ 146 ሚሊየን ካሬ ሜትር በላይ መሬት ማዘጋጀት የሚጠበቅ በመሆኑ ይህንኑ ማስተናገድ
እንዲቻል በከተሞች የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን መኖሩ ወሳኝ ሆኖ ይገኛል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 10


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

እንደ ሌሎች ብዙ ሀገራት ኢትዮጵያም መንትያ የዕድገት አቅጣጫን እየተከተለች ትገኛለች፡፡ በአንድ በኩል
መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለሁሉም አካባቢዎች ለማዳረስ መሞከር ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱን
ልማት በማፋጠን በኩል ለወደፊት ከፍተኛ ምርታማነት ብሎም ፈጣን ዕድገትን ሊያመጡ የሚችሉ
የተወሰኑ አካባቢዎችን (Growth Corridors) መርጦ ከፍ ያለ መዋዕለ ነዋይን በማፍሰስ ማልማት ነው፡፡
በነዚህ አካባቢዎችም ያሉ ከተሞች የሚታሰበው ዕድገት ማዕከል (Growth Pole) መሆናቸው ስለማይቀር፤
የሚጠበቀውን የተፋጠነ ዕድገታቸውን በመምራት በኩል የከተማ ፕላን አስፈላጊነት በይበልጥ የጎላ ነው፡፡
በተለይ ፈጣን ዕድገትን በፕላን መምራት ካልተቻለ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ መዘዝ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩል
የከተሞቹ ጤናማ ዕድገት በተራው በቀጠናው ልማትና ዕድገት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ጥርጥር
የለውም፡፡

በከተማ ፕላን ዝግጅት ዙሪያም የከተማና ገጠር ትስስርን ከማጠናከር አንጻር እንዲሁም ባለሀብት መሆን
የጀመረውን አርሶ አደር በከተማ ልማት ዘርፍ እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በአምስት አመት
ውስጥ ለ 750 አነስተኛ ከተሞች እና ለመካከለኛና ከፍተኛ ከተሞች የከተማ ፕላን እንደሚዘጋጅ በዕቅድ
ተይዟል፡፡ በከተማ ደረጃ የሚዘጋጀው ፕላን ተግባራዊ የሚደረገው ለየአካባቢው በሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት
ፕላኖች (Local Development Plan) አማካኝነት ሲሆን፤ በከተማው አዳዲስ የመስፋፊያ አካባቢዎችም
ሆነ በነባሩ የከተማው ክፍል የአካባቢውን ሕዝብ በማሳተፍ የሚዘጋጁ ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም ይህን እቅድ
ከማሳካት አኳያ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራተጂ ነድፎ መተግበር አስፈላጊ
ሆኖ ይገኛል፡፡

2.5 የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ እና የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ
የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ
(Ethiopia’s Climate - Resilient Green Economy Strategy) በዋናነት አራት ጉዳዮችን ያመላከተ
ሲሆን እነዚህም ግብርናን በማሻሻል የካርቦን ልቀትን መቀነስ፣ የደን ጥበቃና ልማት፣ ከታዳሽ የኃይል ምንጭ
የኤሌክትሪክ ሀይልን ማስፋፋት እና ዘመናዊና ሀይል ቆጣቢ ትራንስፖርት፣ ኢንዱስትሪና ህንጻ ናቸው፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው በአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ግብርናን
በማሻሻል የካርቦን ልቀትን መቀነስ አንዱ ሲሆን ይህንንም ከማሳካት አኳያ በሀገር አቀፍ፣ በክልል እና
በከተሞች ደረጃ መሬትን ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ እነዚህኑ እርከኖች መሰረት ያደረገ የመሬት
አጠቃቀም ፕላኖች ማዘጋጀት ወሳኝ ነው፡፡ የከተማ ግብርና በብዙ ሀገራት ለምግብ ዋስትና የበኩሉን ድርሻ
ከማበርከቱም በላይ የስራ ዕድል በመፍጠር ለድህነት ቅነሳ የሚያግዝ አንድ አይነተኛ ዘርፍ ነው፡፡ የከተማ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 11


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ግብርና የከተማ አረንጓዴነት ሽፋን ከማሳደግ አንጻር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ሲሆን ለከተማ ነዋሪው
የጓሮ አትክልቶችንም በማቅረብ ይታወቃል፡፡ በእነዚህና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ረዘም ላሉ ጊዜያት
የነባርና አዳዲስ የከተማ ግብርና አካባቢዎችን በመለየትና እንዲጠበቁ በማድረግ የከተማ መሬት አጠቃቀም
ፕላን ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ደንን መጠበቅና መልሶ ማልማት ሌላው በአረንጓዴ ስትራቴጂ ውስጥ የተካተተ ጉዳይ ሲሆን የደን ልማት
ብዝሃ ህይወትን ከመጠበቅና ካርቦንን ከመሰብሰብ አኳያ የሚያበረክቱት አስተዋጽዎ ከፍተኛ ነው፡፡ ከላይ
እንደተገለጸውም በተለያየ እርከን የሚዘጋጁ ፕላኖች ለዚሁ አገልግሎት የሚሆን ቦታ እንዲይዙ የሚጠበቅ
በመሆኑ ይህም ለአረንጓዴው ስትራቴጂ መሳካት ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ከታዳሽ ሀይል የኤሌክትሪክ ሀይልን ከማመንጨት ጋር ተያይዞም አንዱ አማራጭ የሚወገድ ቆሻሻን
መሰረት በማድረግ ሲሆን ይህንኑ ቆሻሻ በበቂ መጠን ለማከማቸት በተጠና ሁኔታ ቦታ መያዝ አስፈላጊ
ሲሆን ይህም ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው በፕላን ሲመላከት ነው፡፡

ከከተሞች ውበት አንጻር ከተሞች ውብና ለኑሮ ምቹ ሊሆኑ የሚችሉት በተቀናጀና በታሰበ መልክ በፕላን
ሲታገዙ ነው፡፡ በተበታተነና በተናጠል በሚደረግ ጥረት ብቻ አጠቃላይ ውበትንና ምቾትን ዕውን ማድረግ
አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለሆነም መጀመርያ ከተማ አቀፍ፣ በመቀጠልም የአካባቢ ልማት ፕላን እንዲሁም
ለተመረጡ አካባቢዎች ከተጠቀሱት ፕላኖች ጋር የሚጣጣም የዲዛይን (Urban Design) ፕላን በማዘጋጀት
ውበትን እንዲሁም ምቾትን መፍጠር ይቻላል፡፡ የከተማ ዲዛይን ፕላን በተወሰነ የከተማ አካባቢ ውበትን
ለመፍጠር/ለማጎልበት የሚዘጋጅ ዝርዝር ፕላን ሆኖ የአካባቢውን ውበትና ምቾት ከመፍጠርም አልፎ
የንብረት ዋጋም እንዲጨምር አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

የከተማ አረንጓዴ ዕፀዋት ውበትን ከመፍጠር እንዲሁም ከፍተኛ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም
ከመስጠትም በላይ ለሰው ልጅ ሕይወት ያላቸውን ጠቀሜታ በሚገልፅ የትርጉም ሐረግ ‘የከተማ ሳንባዎች’
በመባል ይታወቃሉ፡፡ እዚህ ላይ ሊጠቀስ የሚገባው ነገር ቢኖር የሀገሪቱ ለም አፈርና የአየር ሁኔታ በበርካታ
ከተሞች የአረንጓዴ ልማትን ለማካሄድ ምቹ መሆኑ ነው፡፡ በአረንጓዴ ልማት ስር ከሚጠቃለሉት በርካታ
ጉዳዮች መሀከል ፓርኮች፣ የመንገድ አካፋዮችና ዳርቻዎች፣ የፕላዛና ክብረበዓል ቦታዎች፣ የወንዝ
ዳርቻዎች፣ የከተማ ግብርናና ደኖች የሚገኙበት ሲሆን የከተማ ፕላን ያሉት ተጠብቀው እንዲቆዩ
ያደርጋል፣ በጥናት ላይ በመመርኮዝም ለሌሎችም የከተማውን የሥነ-ምህዳር ቀጠና እና ሌሎች ነባራዊ
ሁኔታዎችን ያገናዘበ የአረንጓዴ ቦታዎችን ይይዛል፡፡

በአገራችን ከተሞች የሚገኙት የወንዝ ዳርቻ ቦታዎች ከላይ እንደተጠቀሰው ለከተማው ስነ ምህዳርና
ብዝሃ ህይወት ጥበቃ የሚያበረክቱት አሰተዋጾ ከፍተኛ ቢሆንም ከትኩረት ማነስ የተነሳ የቆሻሻ መድፊያ፣

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 12


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የህገወጥ ቤቶች መገንቢያ፣ የመጸዳጃ ቦታዎች በመሆን በከተሞቻችን ገጽታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ
ከማሳደራቸውም በላይ ለህበረተሰቡ የጤና ጠንቅ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የወንዝ ዳርቻ ቦታዎች
በከተሞች ያሉት የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶችን ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም ለዱር እንስሳት
የሚመቻቸውን አካባቢዎች ፍለጋ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ መንገድ እንደሚሆኑ በመገንዘብ በከተማ ፕላን
ከወንዞች ግራና ቀኝ ያሉ ቦታዎች ከማንኛውም ግንባታ ነፃና ክፍት ሆነው አረንጓዴ ልማት
እንዲካሄድባቸው ይደረጋል፡፡

አንዱና ዋናው የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ሚና በየጊዜው ቁጥራቸው እየጨመረ የሚመጡ
ከተሞችን በፕላን መምራት እንዲሁም በነባር ከተሞች እያደገ የሚመጣውን የከተማ ሕዝብ ብዛት ፍላጎት
የሚያስተናግዱ ተጨማሪ ቦታዎችን መያዝ ነው፡፡ የተለያዩ ዕቅዶችን ማሳካት እና የከተማ ፕላን ዝግጅትና
ትግበራን ይበልጥ አስቸጋሪ የሚያደርገው ሌላው ጉዳይ በተለይም በከተሞች በፍጥነት እያደገ የሚሄደው
የሕዝብ ብዛት ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ የከተማ ሕዝብ ድርሻ (proportion) ከጠቅላላው
ሕዝብ ጋር ሲነፃፀር በዓለም ላይ በጣም ዝቅተኛ ከሚባሉት አንዱ ነው።

ስለሆነም፤ በሀገሪቱ የከተማ ሕዝብ ድርሻ ዝቅተኛ መሆኑና ገና የከተማነት ሽግግርም (urban transition)
በቅጡ ስላልተጀመረ ከፍተኛ የከተማ ሕዝብና የከተሞች ቁጥር ዕድገት እንደሚኖር ያመላክታል። ከተሞች
የዕድገት ማዕከል በመሆናቸው ምክንያት የኢኮኖሚ ዕድገት የከተማን ሕዝብ ብዛት በማሳደግ ቀጥተኛ
ተፅዕኖ ቢኖረውም የብዙ ያልበለፀጉ ሀገራት ልምድ እንደሚያሳየው ዕድገት እንኳን በሌለበትም ቢሆን
በተለያዩ ምክንያቶች የከተማ ሕዝብ ድርሻ በአብዛኛው እያደገ መምጣቱ ታይቷል፡፡ በሌላ በኩል የከተማ
ሕዝብ ድርሻ አሁን ባለበት (17%) እንኳን ቢቆይ ወይንም ባይጨምር አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር በመጨመሩ
ብቻ የከተማ ሕዝብ ብዛት እንደሚያድግ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በአገሪቱ እየታየ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት
በዘላቂነት ከቀጠለ ፈጣን የከተማ ሕዝብ ዕድገት እንደሚኖር ይገመታል፡፡ ይህን የሚጠበቅ ፈጣን የከተማ
ሕዝብ ቁጥር ዕድገት እና ተያይዞ የሚመጣ ፈላጎትን በፕላን መምራት ካልተቻለ በሀገሪቱ ልማት ላይ
አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው መታወቅ ይኖርበታል፡፡

2.6 የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ የከተማ መሬት ልማትና
ማኔጅመንት ስርዓትን ለማስተካከል ያለው ፋይዳ

ለአገራችን ከተሞች መሬት የዕድገት መሠረታቸውና ለልማታቸውም ዓብይ ግብዓት እንደሆነ ይታመናል፡፡
የከተሞቻችን አብዛኛው ማዕከላዊ ክፍሎቻቸው ያረጁ ከመሆናቸውም ባሻገር በመስፋፊያ አካባቢ ጭምር ሳይቀር
ህገወጥ መጠለያዎች በመፈጠራቸው ለኑሮም ሆነ ለስራ ያላቸው ተስማሚነት ዝቅተኛ ሆኗል፡፡ የዚህ ችግር
መንስኤዎች የተለያዩ ቢሆኑም በተለይም ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 13


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በአዋጅ 47/67 የተወረሱ ቤቶችና ይዞታዎች ከግል ይዞታዎች ጋር ተቀላቅለው የሚገኙ ሲሆን በህግ ከተደነገገው የከተማ
ቦታ (ይዞታ) የስፋት ደረጃ በታችና በላይ የሆኑ በመኖራቸው ለከተሞች ልማት እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ
በተለይ እንደ አዲስ አበባ ባሉ የአገራችን ትልልቅ ከተሞች የመሬት አቅርቦትንና ልማትን ለማሳለጥ እንዲሁም የከተሞችን
ውበትና ፕላን ግምት ውስጥ በማስገባት ቅርጽ የለሽ የሆኑና ከደረጃ በታችና በላይ የሆኑ ይዞታዎችን በማቀላቀልና መልሶ
ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በብሎክ በመሸንሸን (በማደራጀት/በማስተካከል) ለመሠረተ ልማት አውታር ዝርጋታና
ለተፋጠነ መሬት ልማት ምቹ ማድረግ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን አንዱ ተግባር ነው፡፡

በመሬት የልማትና ማኔጅመንት፣ የፋይናንስና የግብይት ስርዓቱም ቅልጥፍናና ግልጽነትን በማረጋገጥ


የኪራይ ሰብሳቢነትን መሰረት ከስሩ ለመናድ የሚያስችሉ ስራዎች ተጀምረውና የሊዝ ህግም ወጥቶለት
አበረታች እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት አንጻር ለከተማ
መሬት ልማት ባንክ ግብይት፣ ለመሬት ሀብት ኢንቬንቶሪ፣ ለግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር፣ ለከተማ መሬት
ይዞታ አስተዳደር፣ ለካዳስተር፣ የከተሞችን አድራሻ ስርዓት ለመዘርጋት፣ የፈቃድ አልባ ግንባታዎችን ችግር
ለመፍታት፣ ሰነድ አልባ የሆኑ ይዞታዎችን በጥንቃቄ በመለየትና ጎን ለጎን ባለመብቱን ለመደንገግ፣ ህገወጥ
ይዞታዎችን ለመለየትና እንደአስፈላጊነቱ ሬጉላራይዝ ለማድረግ፣ ሽንሸና አልባ ይዞታዎችን ለማስተካከል፣
ለመለካትና ለመመዝገብ ብሎም የይዞታ ማረጋገጫ ለመስጠት እንዲሁም በእነዚህ የከተማ ክፍሎች ያሉ
ቤቶች አስፈላጊውንና ተመጣጣኝ የግንባታ ፈቃድ እንዲያገኙ በማድረግ የመጠለያዎቹን ደረጃ ከፍ የማድረግ ሥራ
በቅንጅት ለመስራት እና ከከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ፖሊሲ ጋር በተጣጣመ መልኩ ለመፈጸም የከተማ መሬት
አጠቃቀም ፕላን አስፈላጊ ነው፡፡

2.7 የልማት ማነቆዎችን ከመፍታት አኳያ ያለው ፋይዳ

በአጠቃላይ በሀገራችን ባለው ሁኔታ ለከተማ ፕላን የሚሰጠው ትኩረት እጅግ አናሳ ሆኖ ይታያል፡፡ ለዚህም
ተጠቃሽ የሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ የአመለካከት ችግር ሲሆን መገለጫውም የመሬት አቅርቦት
ጥያቄዎች በሚቀርቡበት ጊዜ የፕላኑን እሳቤ ወደ ጎን በመተው የተጠየቀውን አገልግሎት በማሰተናገድ
የፕላን ጥሰት መፈጸም፣ በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት ለሕብረተሰብ ተሳትፎ አናሳ ግምት መስጠት፣
ከተማ ፕላን የከተሞች ልማት በመምራት ረገድ የሚኖረውን ሚና እጅግም ግምት ውስጥ አለማስገባትና
በከተማው ፕላን አለመመራት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ከክህሎት አንጻርም በክልልም ሆነ በከተሞች በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም የሚሳተፉ ባለሙያዎች
በዘርፉ በቂ ክህሎት የሌላቸው ሲሆን በተጨማሪም የከተማ አመራሩ ስለ ከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም
በቂ ግንዛቤ አለው የሚባልበት ደረጃ ላይ አይደለም፡፡ ለከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም የሚያስፈልገውን
ግብዓት ከማሟላት አኳያም በርካታ ችግሮች ይታያሉ፡፡ ከሰው ሀይል አንጻር ለከተማ ፕላን ዝግጅትና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 14


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አፈጻጸም በቂ የሆነ የሰው ሀይል ካለመኖሩም በተጨማሪ በመዋቅር ወይንም በአደረጃጀት ለመደገፍ
የሚደረገው ጥረት አናሳ ነው፡፡ የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም በበቂ ማቴሪያል መደገፍ የሚገባው
ሲሆን በከተሞች አካባቢ ለነዚህ አቅርቦቶች አነስተኛ ግምት እየተሰጠው ይገኛል፡፡ እንዲሁም ከበጀት
አንጻር ለዘርፉ ክልሎችም ሆኑ ከተሞች በቂ በጀት የማይመድቡ በመሆኑ አብዛኛው የሀገሪቱ ከተሞች
የፕላን ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡

ከፌዴራል እስከ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ
የሚደረጉ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ትኩረት ስለማይሰጣቸው የከተማ ፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጸም
ስርዓት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ ሊሆን አልቻለም፡፡ ሌላው ሊጠቀስ የሚገባው ችግር በተለያዩ
ደረጃዎች በሚገኙ የመንግስት ተቋማት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ጠንካራ አለመሆኑ ነው፡፡

በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ምንም እንኳን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በተወሰነ
ደረጃ እየታየ ቢሆንም በሀገሪቱ ካሉት የከተሞች ብዛት አንጻር የተሳትፎ ሚናው በሚፈለገው ደረጃ ላይ
አይደለም፡፡ በተመሳሳይም በከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ ላይ የመንግስት፣ የሕዝብና የግሉ ዘርፍ ቅንጅት
አስፈላጊ መሆኑ በተለያየ ጊዜ ቢገለጽም በቅንጅት የመስራቱ ሁኔታ አበረታች አይደለም፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ በፕላን ትግበራ ወቅት በመሰረተ ልማት አውታር አቅራቢ ድርጅቶች መካከል ቅንጅታዊ አሰራር
ባለመኖሩ አንዱ የሰራውን ሌላው በማፍረስ የሀብት ብክነት እየተከሰተ ይገኛል፡፡ የከተማ መሬት አጠቃቀም
ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራተጂ ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት እንደዋነኛ መሳሪያ
ሆኖ ያገለግላል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትና የሌሎችም ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ሄዶ ሄዶ ተግባራዊ የሚሆነው በመሬት


ላይ በመሆኑ የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ሁሉንም በማቀናጀት ትልቅና የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡
ሌላ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ከላይ የተገለፁት ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በከተማ ደረጃ ብቻ ታጥረው
የሚቀሩ ባለመሆናቸው በከተማ ፕላን አዋጁ መሰረት የፕላን ተዋረድ የግድ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ማለት
ከሀገር-አቀፍ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከተማ ድረስ የሚወርድ በየእርከኑ ተጣጥመውና ተናብበው የሚዘጋጁ
የመሬት አጠቃቀም ፕላኖች/ዕቅዶች መኖር ይገባቸዋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 15


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ክፍል አንድ - የስትራቴጂው መነሻ ሁኔታ ትንተና

1. መሰረታዊ ካርታ

1.1. የመሰረታዊ ካርታ መሰረታዊ ሀሳቦች

መሠረታዊ ካርታ ማለት የአንድን አካባቢ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥና ገጽታ እንዲሁም ዋና ዋና
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፊዚካላዊና ጂኦግራፊያዊ መረጃዎች የሚያካትት የካርታ አይነት ነው፡፡ ካርታው
ለአገልግሎት እንደሚውልበት ዓላማ በተለያየ መስፈርት የሚዘጋጅ ሲሆን በኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጄንሲ
በኩል ከ 1950 ቹ ጀምሮ ከ 1፡2,000,000 እስከ 1፡2,000 መስፈርት ድረስ የቶፖግራፊክ፣ የአየር ፎቶና
የሳታላይት ምስል በመጠቀም መሠረታዊ ካርታዎች ይዘጋጃሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ከተሞች አሁን እየተዘጋጀ
ያለው ባለ 1፡2,000 እና ባለ 1፡5,000 መስፈርት ባለመስመርና አሃዛዊ መሠረታዊ ካርታዎች ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ 1፡10,000 መስፈርት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ይሁንና መስፈርቱ
የሚወሰነው እንደ ከተሞቹ የዕድገት ደረጃና የቆዳ ስፋት እንዲሁም የመሰረታዊ ካርታው በሚውልበት
አገልግሎት መሰረት ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ለመሬት ምዝገባና የካዳስተር ሥራዎች እንዲሁም ለመሬት
ሽንሻኖና ለዝርዝር ላንድ ስኬፕ ዲዛይን ስራዎች በ 1፡500 ኛና በ 1፡200 ኛ መስፈርት ሊዘጋጅ ይችላል፡፡

የከተማ ፕላን ዝግጅት እንደሌሎቹ የልማት ሥራዎች ሁሉ የመሰረታዊ ካርታን በግብዓትነት ይጠቀማል፡፡
ለከተማ ፕላን ዝግጅት አገልግሎት ግብዓት የሚሆን መሠረታዊ ካርታ በውስጡ ቢያንስ ዋና ዋና የግንባታ
ብሎኮችን በዓይነት፣ የመንገድ መረቦችን፣ የውሃማ አካላትን፣ ከፍታን፣ የመልከአ ምድር ገጽታዎችን
(ሸለቆዎች፣ ተራሮች፣ ሸንተረሮች)፣ የደን ቦታዎችን፣ የስልክ፣ የመብራት፣ የፍሳሽ ቆሻሻ መስመሮችን እና
የአስተዳደር ድንበር መረጃዎች ሊኖሩት ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ካርታውን በቀላሉ አንብቦ ለመረዳት
የሚያስፈልጉ የካርቶግራፊክ ኢለመንትስ ማለትም የካርታውን አቀማመጥ፣ ስም፣ አቅጣጫ፣ መጠን፣
መስፈርት ከነመስመሩ፣ የምልክቶች ትርጉም ማውጫ፣ ቁጥር፣ ግሪድ፣ የአስተዳደር ክልል፣ የአዘጋጁ
ድርጅት ስም፣ የኮኦርዲኔት ሥርዓት፣ የፕሮጀክሽን ዓይነት፣ ወዘተ ማካተት ይኖርበታል፡፡
የመሠረታዊ ካርታዎቹ የሚዘጋጁት የተለያዩ የቅየሳ ዘዴዎችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እንደ
ኢኮኖሚ/ቴክኖሎጂ እድገት ደረጃ ቀላል የቅየሳ መሳሪያዎችን ከመጠቀም አንስቶ እስከ ከፍተኞቹ የዲጂታል
ቶታል ስቴሽን እና ጂፒኤስን ለመሬት ላይ ቅየሳ በመጠቀም መሠረታዊ ካርታዎችን ያዘጋጃሉ፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ በጂኦ ስፓሻል መረጃ ምንጭነታቸውና አቅማቸው የረቀቁ የሳተላይት ምስል እና የአየር ፎቶ
ግራፎችን በሪሞት ሴንሲንግና ፎቶግራሜትሪ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በተለያየ የመረጃ ጥራት ደረጃ
መስፈርት የመሠረታዊ ካርታዎቹ ሊዘጋጁ ይችላሉ፡፡ የመሠረታዊ ካርታዎቹን ለማዘጋጀት የሚከናወነው
የቅየሳ ሥራ ከአገር አቀፍ የጂኦዴቲክ መረብ ጋር ተሳስረው ከተዘጋጁ የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች በመነሳት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 16


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ይሆናል፡፡ ይህም በመሠረታዊ ካርታው ላይ የተካተቱ መረጃዎች በመሬት ላይ ከሚገኘው እውነታ ጋር


ባልተዛባ መልኩ ማግኘት እንዲያስችል ይረዳል፡፡

በመሆኑም ለከተማ ፕላን ግብዓት የሚሆን የመሠረታዊ ካርታ ለማዘጋጀት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች
ወጭንና ጊዜን እንዲሁም የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ብዛትና የሙያ ደረጃ ለመወሰን ግምት ውስጥ
መግባት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል የፕሮጀክቱን ዓላማ፣ የሚሸፍነው የቆዳ ስፋት፣ የመልከዓ ምድር
አቀማመጥ፣ የቦታ ስፋትና ቅርጽ፣ የአየር ሁኔታ በተለይም የደመና ሽፋንና የቴክኖልጂ አቅርቦት ወዘተ ዋና
ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከተሞች የራሳቸው የተለየ ወሰን የሚስፈልጋቸው ሲሆን እንደ ከተሞቹ የእድገት ደረጃና የልማት
ማዕከልነታቸውን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ሁለት አይነት የከተማ ወሰን አከላለል ይኖራል፡፡ ይህም
የአንድን ከተማ መሠረታዊ ካርታ ለማዘጋጀት የሚደረገውን የቅየሳ ሥራ ለማሳለጥና በቀላሉ ለማከናወን
ይረዳል፡፡ በተለይም የከተማውን የአስተዳደር ድንበር ምንነት በውል ከመገንዘብ ባሻገር የፕላን ወሰንን
በግልጽ መረዳት ግድ ይላል፡፡ የመጀመሪያው የፕላን ወሰን ዓይነት በአንድ የፕላን ዘመን በቀጥታ ለተለያዩ
የመሬት አጠቃቀም አገልግሎቶች የሚከለል የከተማ ፕላን ወሰን (Urbanization Promotion Area)
ተብሎ የሚጠራው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፕላን ዘመኑ በቀጥታ ለልማት አገልግሎት ባይውልም
በጥብቅ ክልል ውስጥ የሚታይ (Urbanization Control Area) በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም በጥብቅ ወሰን
የሚያስፈልገው የወደፊት የከተማውን ማስፋፊያ ቦታዎች አግባብነት በሌለው መንገድ የሚደረጉ
ሰፈራዎችን ለመከላከል፣ የተለያዩ የአካባቢ ጥበቃ እንክብካቤ ስራዎች /የአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ የደን ተከላ፣
የእርከን ስራዎች፣ የውሃ መገኛ ቦታዎችን መጠበቅና መንከባከብ እና የመሳሰሉትን/ ለማካሄድ እና
የቱሪዝም ልማት ሊያጎለብቱ የሚችሉ ጉዳዮችን ማካሄድ እንደሚኖርባቸው /ለምሳሌ የታሪካዊ ወይም
የቅርስ ቦታዎችን ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ለማስተዋወቅ/ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ በፕላን ላይ
የተከለለ ወሰን በከተማው አስተዳደር አማካኝነት በመሬት ላይ መመላከት አለበት፡፡ በከተማ ፕላን አዋጅ
አንቀፅ 6 መሰረት አንድ ከተማ የራሱ ወሰን ቢኖረውም ‘የእድገት ማዕከል’ ሆኖ ከተመረጠ በአካባቢው
ያሉትን ቦታዎችም ሊያካትት እንደሚችል ይደነግጋል፡፡

የማስፋፊያ ቦታ ማለት በከተማ የፕላን ጊዜ ውስጥ ለከተማው እድገት ወይም መስፋፊያ የሚውል መሬት
ሲሆን ቦታው የተለያዩ የመሬት አጠቃቀም እንቅስቃሴዎችን ማስተናገድ ይችል ዘንድ የማስፋፊያ ቦታዎች
መረጣ በጥንቃቄ ማከናወን ያስፈልጋል፡፡ በማስፋፊያ ቦታዎች መረጣ ጊዜ ግምት ውስጥ መግባት ካለባቸው
ጉዳዮች መካከል፣ የመሬቱ አቀማመጥ፣ የተፋሰስ ሁኔታ፣ የአካባቢው የአየር ጸባይ፣ የከተማው ቅርጽ፣
የአፈር አይነት፣ የመስፋፈፊያ ቦታው ለመሰረተ ልማት /ለመንገድ፣ ለመብራት፣ ለቴሌፎን፣ ለውሀ መስመር
ወዘተ…/ እና ማህበራዊ አገልግሎቶቸ ያለው ቀረቤታ፣ ነባራዊው የመሬት አጠቃቀም፣ የሕብረተሰቡ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 17


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ፍላጎት፣ ነባራዊ ሰውሰራሽና የተፈጥሮ ማነቆዎች ዋና ዋነዎቹ ናቸው፡፡ በመስፋፊያ ቦታ መረጣ ጊዜ ለም


የሆኑ የእርሻ ቦታዎችን በተቻለ መጠን ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ ለከተማ መስፋፊያነት እንዳይውሉ ጥንቃቄ
ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የማስፋፊያ ቦታ መጠን የሚወሰነው በህዝብ ቁጥር ትንበያ መሰረት በፕላን ዘመኑ
ውስጥ ለሚያስፈልጉ የተለያዩ አገልግሎቶች በሚያስፈልገው ቦታ መጠን ላይ በመመስረት ሲሆን፤
ለተሳለጠ ግንኙነትና ልማት የከተማው ቅርፅ ወደ ክብነት የሚያደላ (compact shape) እንዲሆን
ይፈለጋል፡፡

1.2. የሀገሪቱ የመሰረታዊ ካርታ አዘገጃጀት ነባራዊ ሁኔታዎች

ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር ዓመታዊ ሪፖርት ላይ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው እስከ
2003 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከአጠቃላይ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች ውስጥ 62 በመቶ አካባቢ ፕላን
የተዘጋጀላቸው መሆኑን በዚሁ አንጻር የመሠረታዊ ካርታም እንደተዘጋጀላቸው ይገመታል፡፡ ይሁንና ባለፉት
ዓመታት ከተሞቹ ካሳዩት ፈጣን ዕድገት አኳያ ግዙፍ የቆዳ ስፋት መስፋፋት አሳይተዋል፡፡ በዚህ ሂደት አሁን
ያላቸው መሠረታዊ ካርታ የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የሚያንጸባርቅ ሆኖ አልተገኘም፡፡
በመሆኑም ከመሰረታዊ ካርታ ጋር በተያያዘ ከሚነሱት ችግሮች መካከል ሽፋን አንዱ ሲሆን የጥራት
ችግርም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሌላው ችግር ነው፡፡ ይህም በሚዘጋጁ እና ተዘጋጅተው በአፈጸጸም ላይ
ያሉ የከተማ ፕላኖች ትግበራ ላይ ከፍተኛ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ከጥራት ጋር ከተያያዙት ችግሮች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የቅየሳ የልኬት ዝንፈት፤ እየተሰራበት ያለው የቅየሳና
መሰረታዊ ካርታ አዘገጃጀት ዘዴ (በተለይም የመሬት ላይ ቅየሳ በማከናወን እየተካሄደ ያለው የመሰረታዊ
ካርታ ዝግጅት) ውድ፣ አድካሚ፣ ብዙ የሰው ኃይል እና እረጅም ጊዜ የሚወስድ መሆን እና የሚዘጋጁ
መሰረታዊ ካርታዎች ወጥነት የሌላቸውና ከብሄራዊ የጂኦዴቲክ መረብ ጋር የማይናበቡ በመሆናቸው
ለመረጃ ውህደትና ቅንጅት ሥራ አስቸጋሪ መሆን ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመሠረታዊ ካርታዎቹ
የመረጃ ይዘት ዓይነትና ጥልቀት ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታና በትክክል አለማስቀመጡ በሚዘጋጁ የከተማ
ፕላኖች ጥራት ላይ የራሳቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ጊዜያትና
አካላት የተዘጋጁ መሠረታዊ ካርታዎች ያሉ ሲሆን እነዚህም የሶፍራቶፕ፣ የኖርቴክ፣ የጂ.አይ.ኤስ. እና
የላይን ማፕ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ በነዚህ ካርታዎች መሀከል የእርስበርስ አለመጣጣምና ዝንፈት ችግሮች
ያሉባቸው ሲሆን ይህም በከተማው ፕላን ዝግጅትና አፈፃፀም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡
የአብዛኛዎቹ የሌሎች ከተሞቻችን መሰረታዊ ካርታዎች አካባቢያዊ የቅየሳ መቆጣጠሪያ በመሬት ላይ
ቅየሳ ዘዴ የተዘጋጁ ሲሆን እነዚህም ካርታዎች መሬት ላይ ካለው ሁኔታ ጋር ሲገናዘቡ ችግር ያለባቸው
መሆኑ ታይቷል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 18


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከላይ ከተጠቀሱት የቅየሳና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች መንስኤዎች ዋና ዋናዎቹ
ከሽፋን አንጻር አደረጃጀትን በሚፈለገው ደረጃ ያልተማከለ አለመሆኑ ያሉትም የተጠናከሩ አለመሆን፣ በቂ
ባለሙያና የሙያ ስብጥር እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አለመኖር፣ የግሉ ዘርፍ አቅምና ተሳትፎ
አለመጠናከር፣ የመሠረታዊ ካርታዎች ዝግጅት ግልጽ የሕግ ማዕቀፍና የአሰራር ስታንዳርድ ሰነድ አለመኖር
ሁነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ከጥራት አንጻር ለተለዩት የመሰረታዊ ካርታ ችግሮች ደግሞ የቅየሳና መሠረታዊ
ካርታ ዝግጅት የቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች አቅርቦትና ተጠቃሚነት ደካማ መሆን፣ የቅየሳ አፈጻጸሙ እና
የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅቱ ላይ ወቅታዊና አስፈላጊ የክትትልና የግምገማ ስርዓት አለመዘርጋቱ፣ የባለሙያ
ክህሎት ዝቅተኛ መሆን እና ለከተሞች ፕላን ዝግጅት የሚያግዝ ደህንነታቸው የተጠበቀ የቅየሳ መነሻ
መቆጣጠሪያ ነጥቦች በበቂ ቁጥርና ጥግግት መጠን አለመኖር ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡

የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት በዋናነት ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች የሚታዩበት ቢሆንም ክልሎች የራሳቸውን
ከተሞች መሰረታዊ ካርታ በራሳቸው አቅም ማዘጋጀት መጀመራቸው በተለይም ዘመናዊ የሆነ የቅየሳ
ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለምሳሌ የጥራት ደረጃቸው የተሻሉ የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም
እየተዘጋጁ ያሉት የመሰረታዊ ካርታ አዘገጃጀት ጅምሮች አበረታች ውጤት እያሳዩ ሲሆን በዘርፉ ያለውን
የአሰራር ዘዴ እምርታዊ ለውጥ እንዲያመጣ የሚያግዙ መልካም ተሞክሮዎችና ጠንካራ ጎኖች ናቸው፡፡

በሌላ መልኩ የከተማ አስተዳደር ወሰን አከላለል የአፈጻጸም ሥነ-ስርዓት እና ሥራው የሚፈጸምበት
መስፈርት ባለመኖሩ ምክንያት ወጣ ገባ የሆነ አሰራር እንዲሰፍን ከማድረጉም ባሻገር አንዳንድ ክልሎች
ከከተማው የፕላን ድንበር አንስቶ 2.5 ኪ.ሜ. ዙርያ ያለውን ቦታ በከተማው አስተዳደር ውስጥ ሲያካትቱ
አንዳንዶች ደግሞ 5 ኪ.ሜ. እና ከዚያ በላይ የሆነ ቦታ ያካትታሉ፡፡ የከተማ አስተዳደር ወሰን መከለል ዋናው
አላማ ህገወጥ ሰፈራዎችን ለመቆጣጠር ቢሆንም አከላለሉ ለመወሰን የሚያስችል ወጥ የሆነ የአፈጻጸም
ሥነ-ስርዓት የለም፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዳድ ከተሞች የከተማ ደረጃቸው ከፍ እንዲል በማሰብ በጣም
ሰፊ የሆነ መሬት በከተማው አስተዳደር ስር እንዲሆን ሲያደርጉ የሚስተዋል ሲሆን ይህም በመሰረታዊ
ካርታ ዝግጅት ላይ አላስፈላጊ ወጪ እንዲወጣ ምክንያት ከመሆኑም ባሻገር ምርታማ የሆኑ የእርሻ
መሬቶች ከደረጃ በታች ጥቅም ላይ እንዲውሉና ለህገወጥ ግንባታዎች መስፋፋት መንስኤ ሆኗል፡፡ ከዚህ
ጋር በተያያዘ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች ከተሞች የድንበር ወሰን የማካለል ችግር ሲፈጠር
ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት የለም፡፡

በቅየሳ አፈጻጸምና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ወቅት ህብረተሰቡ ተገቢው የቅድመ ግንዛቤ ማስጨበጫ
አሰራር ተዘርግቶለት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ባለመበረታታቱ የተሳትፎ ደረጃው ውስን እንዲሆን
አድርጎታል፡፡ የከተሞችን የፕላን ወሰን ክለላና ለፕላን ዝግጅት የሚያግዝ መሠረታዊ ካርታ በማዘጋጀት
ሂደት ውስጥ ህብረተሰቡ በንቃት ሳይሳተፍ በመቅረቱ በመስፋፊያ አካባቢ የከተሞች ድንበር ክለላ ላይ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 19


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የተተከሉ የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦችን ሳይቀር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተነቅለው ይጠፋሉ፡፡ የችግሩ
መንስኤዎች ከአዘጋጁ፣ ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከተሳታፊው እና ከሬጉላቶሪና ድጋፍ ሰጪ አካላት የመነጩ
ናቸው፡፡

1.3. በቅየሳና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት የሀገሪቱ የተቋማት ብቃት ዝንባሌ ትንተና /Trend
Analysis/

ለከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጸጸም አገልግሎት እንዲውል የሚከናወነው የቅየሳ እና የመሠረታዊ ካርታ
ዝግጅት አጠቃላይ የአፈጻጸም ብቃት መሻሻል እያሳየ ቢሆንም በአለም ላይ ከሚታየው ዕድገት አንጻር
ሲታይ በተለይም ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ከአሰራርና ከመረጃ ጥራት አኳያ የዘርፉ ዕድገት አዝጋሚ ነው
ማለት ይቻላል፡፡ ይሁንና የፌዴራል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 38/1997 ከተቋቋመበት
ጀምሮ እስከ 1999 ዓ/ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በአዋጁ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመሬት ላይ ቅየሳና
በተወሰነ ደረጃ የአየር ፎቶግራፍን በመጠቀም የመሠረታዊ ካርታዎችን የአውቶካድና ጂ.አይ.ኤስ. መረጃ
ማቀናበሪያና ማደራጃ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ለከተማ ፕላን አገልግሎት የሚውሉ መሰረታዊ
ካርታዎችን ያዘጋጅ ነበር፡፡ ከዚህ ውጭ ለዚህ አላማ ሲባል የቅየሳ አፈጻጸምና የመሠረታዊ ካርታ ይዘጋጅ
የነበረው በዋናነት በኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ /ኢ.ካ.ሥ.ኤ./ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ባለ
1:2,000,000፣ 1:1,000,000 እና 1:250,000 መስፈርት መላ ሀገሪቱን የሚሸፍኑ ለመሠረታዊ ካርታ
ዝግጅት መነሻ የሚሆኑ የቶፖግራፊ ካርታዎች ተሰርተዋል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን ኤጀንሲው የተለያዩ ሀገራዊ
የልማት ዕቅድና መርሃ ግብር ለመንደፍ የሚረዱ ባለ 1:50,000 መስፈርት ቶፖግራፊ ካርታ በመሥራት ላይ
ሲሆን እስከ አሁን የሀገሪቱን 80 በመቶ ያህል የቆዳ ሽፋን ለማዘጋጀት ችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
መስፈርቱን ለማሳደግ የባለ 1፡25,000 እና የባለ 1፡10,000 መስፈርት ቶፖግራፊ ካርታ ለማዘጋጀት ቅድመ
ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ከኢ.ካ.ሥ.ኤ. የተገኘ መረጃ ይጠቁማል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ u}KÁ¿ ²S“ƒ ¾}’c< SL GÑ]~” ¾T>gõ’< uvK 1:40,000 እና vK 1:50,000
Seð`ƒ ¾›¾` ö„Ó^ö‹ ›K<ƒ:: ከዚህ በተጨማሪ KŸ}T ýL” ዝግጅትና ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ
ለካዳስትራል ቅየሳ ተግባራት አገልግሎት ላይ የሚውሉ መሠረታዊ ካርታዎች ለገጠር በባለ 1:10,000
መስፈርት እና ለከተማ በባለ 1:2,000 እና ባለ 1:5,000 መስፈርት በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡ የቅየሳ
አፈጻጸሙንም ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ GÑ]~” ¾T>gõ” }ÚT] ¾Í=*È+¡ ¾›ÓÉSƒ“ Ÿõ ታ
Sq×Ö`Á ’Øx‹ S[w }²`Ó…M:: u}Kà u›G<’< ¨pƒ ¯KU ›kõ ¾Í=*È+¡ S[w KS²`Òƒ Ÿõ}—
”penc? ¾}Å[Ñ c=J” u²=IU እ Á”Ç”Æ GÑ` HÁ ›^ƒ c¯ƒ ¾T>c^ u=Á”e ›”É ¾Í=*Å+
¡ Sq×Ö]Á (CORS – Continuously Operational Reference Station) uSvM ¾T>ታ¨k¨<” ×u=Á
እ”Ç=ÁslU ይጠበቅበታል:: u²=I [ÑÉ በአገር አቀፍ ደረጃ up`u< }slS¨< Y^ ¾Ë መ\ ›^ƒ ×u=Á‹
/u›Ç=e ›uv' É_Ū' Ô”Å` እ“ ጅ T/ ያሉ ሲሆን እንዲሁም በተጨማሪ አምስተኛ ጣቢያ በአሶሳ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 20


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ለማቋቋም የዝግጅት ሥራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ይሁንና በዚህ ረገድም ወደ 20 የሚጠጉ ተጨማሪ


የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በአገር አቀፍ ደረጃ በአምስት አመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን
እንደሚቋቋሙ እቅድ የተያዘ መሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በክልል እና ከተማ ደረጃ ያሉ የከተማ ፕላን
ኢንስትቲዩቶችም በራሳቸው አቅም በቅየሳ አፈጻጸምና የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ከቴክኖሎጂ
አጠቃቀም አንጻር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳዩ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በዘርፉ ያለውን የቅየሳ አፈጻጸምና
የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት የመሬት ላይ ቅየሳን ደረጃ በደረጃ በመቀነስ ወደ ርቀት ምርመራ (Remote
Sensing) እና የአየር ፎቶግራፍ (photogrametry) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ካርታዎቹን ከባለ 2 ጎንዮሽ
እስከ ባለ 3 ጎንዮሽ የመረጃ ይዘት ባላቸው በአሃዛዊ (Digital) መረጃ እንዲደራጁ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በመሆኑም u²`ñ እየታየ ያለው ¾°Éу አዝማሚያ እንደሚጠቁመው የወረቀት ካርታዎችን ወደ ›H³©
¾Í=*-ስፓሺያል ›=”ö`T@i” S[Í wKAU ¨Å አሃዛዊ T>Ç=Á uSK¨Ø SÖkU ¾T>Áe‹M ‚¡•KAÍ=
Là ƒŸ<[ƒ” uTÉ[Ó ውጤታማ፣ ቀልጣፋ እና ወጪ ቆጣቢ የቅየሳ አፈጻጸምና የመሠረታዊ ካርታ
ዝግጅትን በማከናወን አገልግሎቱን በ Ø^ƒ }Å^i KTÉ[Ó ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን መረዳት
ይቻላል፡፡ ÃG<”“ u²`ñ በአጠቃላይ እየተመዘገበ ያለው ዕድገት ተስፋ ሰጪ ቢሆንም አሁንም ቢሆን
ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ከአሰራር እና ሰው ኃይል ልማት ረገድ መሻሻል የሚገባቸው ብዙ ጉዳዮች እንዳሉ
መረዳት ይቻላል፡፡

ከላይ የተገለጸው የሀገሪቱ የቅየሳ አፈጻጸምና የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ብቃት ዝንባሌ/አዝማምያ
እየተሻሻለ መምጣቱን የሚጠቁም ቢሆንም አሁንም ከቅየሳ አፈጻጸምና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ጋር
ተያያዥ የሆኑ በርካታ ችግሮች ያሉ ሲሆን በነባራዊ ሁኔታዎች ትንተና በቅየሳ አፈጻጸምና መሰረታዊ ካርታ
ዝግጅት ዙሪያ የተለዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች መሀከል ዋና ዋናዎቹን ዘርዘር ባለ መልኩ እንደሚከተለው
ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከተማ ልማት ፖሊሲ፣ የከተማ ፕላን ህግ፣ የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጅንሲ
ማቋቋሚያ አዋጅ እና በኤጄንሲው አማካኝነት በሚንስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ታቅዶ የተዘጋጀ
የቅየሳ አፈጻጸም ረቂቅ ደንብ እንዲሁም ረቂቅ ስታንዳርድ ሰነድ መዘጋጀታቸውና በዚህም መሰረት
ለአገሪቱ ከተሞች የቅየሳ አፈጻጸም እና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ለማከናወን እየተደረገ ያለው ጥረት
ከፖሊሲና ህግ ማዕቀፎቸ አንጻር እንደ ጠንካራ ጎን የሚታይ ቢሆንም በስራ ላይ በዋሉት የህግ ማዕቀፍ
ሰነዶችና የአሰራር ማኑዋልና ስታንዳርዶች ላይ ለዚህ ጥናት አላማ ሲባል በተደረገው ዳሰሳ ሰነዶቹ ላይ
አንዳንድ ክፍተቶች እንዳሉባቸው ተረጋግጧል፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ በክልልም ይሁን በፌዴራል ደረጃ ያሉ ከቅየሳ አፈጻጸምና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት አንጻር
የወጡ ህጎች በዝርዝር የተዳሰሱ ሲሆን በዋናነት በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጀው የከተማ ፕላን አዋጅ ቁጥር

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 21


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

574/2000 ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ በፌደራል አዋጁ ስለመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት የተቀመጠ አንቀጽ
ባይኖርም የፌደራል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩትን ለመሻር በወጣው አዋጅ ላይ ቀደም ሲል
የኢንስቲትዩቱ የነበሩ ስልጣንና ኃላፊነቶች ወደ ስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር መሸጋገራቸውን እንዲሁም
በአብዛኞቹ ክልላዊ መንግስታት የከተማ ፕላን ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ወስጥ በመሬት ላይ ቅየሳና
የሳታላይት ምስልን እንደ አስፈላጊነቱ በመጠቀም ቅየሳ በማከናወን ለከተማ ፕላን ግብዓት የሚሆን
የመሠረታዊ ካርታ እንደሚያዘጋጁ ተደንግጓል፡፡ ለምሳሌ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተሞች
ፕላን ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 147/1999 በአንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ
ለከተማ ፕላን አገልግሎት ግብዓት የሚሆን የመሰረታዊ ካርታ አዘገጃጀትን በተመለከተ በግልጽ ተደንግጓል፡፡
ለመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ ሳይቀር ስለከተሞች
የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ጸድቆ በሥራ ላይ ያለ ደንብና መመሪያ የሌለው እና የቅየሳ አፈጻጸሞችን
በዝርዝር የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲፈጸሙ የሚያስችል ስታንዳርድ ሰነድ ባለመኖሩ እንዲሁም
አሰራሩን ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት እስከ ታችኛው የአስተዳደር እርከን ድረስ
አልተዘረጋም፡፡ ይሁንና በአገራችን በተለያየ የጥራት ደረጃና የአሰራር ዘዴ የተለያዩ የመንግስት ተቋማትና
የግል አማካሪ ድርጅቶች ቅየሳ በማከናወን ለተለያየ አላማ የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ላይ ተሰማርተው
ይገኛሉ፡፡ ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የስፓሻል መረጃ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ጥረት ላይ
የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ከመፍጠሩም በላይ በዘርፉ በተሰማሩ ተቋማት መካከል የመረጃ ልውውጥን
በማመቻቸትና በማጠናከር ተመሳሳይ መረጃን ለመሰብሰብና ለማደራጀት የሚደረገውን አላስፈላጊና
ተደራራቢ የወጪና የጊዜ ብክነት ከመቀነስ አኳያ በሚኖረው ድርሻ ላይ ጥላውን እንዲያጠላበት አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ዝግጅትና መረጃ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ
ላይ ለከተማ ፕላን አገልግሎት ግብዓት የሚሆን የመሰረታዊ ካርታ አዘገጃጀትን በተመለከተ በግልጽ
ተደንግጓል፡፡ ይሁንና በአንዳንድ ክልላዊ መንግስታት የከተማ ፕላን ተቋማትን ለማቋቋም የሚደነግጉ
አዋጆችና የከተማ ፕላን ነክ አዋጆች ሲዘጋጁ የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት በተሟላ መልኩ በግልጽ
አልተቀመጠም፡፡ በአጠቃላይ ይህ የሚያሳየው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፤ በአገር አቀፍ ደረጃ በወጣው
የከተማ ፕላን አዋጅ እንዲሁም የኢ.ካ.ሥ.ኤ. ማቋቋሚያ አዋጅ በግልፅ ከተሰጣቸው ስልጣንና ሀላፊነት
ውጪ በየራሳቸው አዋጆች ደንግገው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ሥራ መሰራቱ አንድ ነገር ሆኖ ነገር ግን
ከሥራው ጥራት አንጻር እና ሌሎች ተያያዥ አስተዳደራዊና የህግ ድንጋጌዎች አንጻር ከላይ በተገለጸው
አግባብ የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 691/2003 እንደገና በአዲስ መልክ ከተደራጀ
በኋላ በሀገሪቱ የአምስት አመት ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተመለከቱትን ሀገራዊ አቅጣጫዎችና
ግቦች መሰረት በማድረግ የአምስት አመት ክፍለ ኢኮኖሚያዊ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 22


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ ሰነድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ለ 750 አነስተኛ ከተሞች
የመሠረታዊ ካርታና ፕላን እንደሚዘጋጅ በግልጽ ተቀምጧል፡፡

ለ kt¥ P§N ZGJT xfÚ[M ግብዓት በ¸çN yQyú m\r¬êE µR¬ ZGJ ት z#¶Ã ên¾ têÂY yçn#T
bØ ዴ‰L dr© bêÂnT የኢ.ካ.ሥ.ኤ. ሲሆን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እንዲሁም
አንዳንድ የግል ድርጅቶችም y‰úcWN DRš btwsn dr© Xytw-# Yg¾l#ÝÝ

በብሄራዊ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት የማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 317/1979 እና በፌዴራል የከተሞች
ፕላን ኢንስቲትዩትን የማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 38/1997 በተሰጠ ስልጣን መሰረት ኢንስቲትዩቱ በራሱ
የሰው ኃይል የመሬት ላይ ቅየሳ፣ የአየር ፎቶግራፎችንና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም እስከ 1999 ዓ/ም.
ድረስ ከ 120 በላይ ለሚሆኑ ከተሞች ለከተማ ፕላን ዝግጅት የሚውሉ መሰረታዊ ካርታዎችን ማዘጋጀቱን
ሪፖርቶች ያረጋግጣሉ፡፡

ይሁንና በ 1999 ዓ.ም ሚኒስቴር መ/ቤቱ የአሰራር ስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ ትኩረቱን የፓሊሲ፣ የህግ
ማዕቀፎችን፣ ስታንዳርዶችንና የአሰራር ሥርዓቶች መቀየስ እንዲሁም የአቅም ግንባታ፣ የክትትል፣
ግምገማና ግብረ-መልስ ሥርዓት ዝርጋታ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከመስከረም
2003 ዓ/ም ጀምሮ ሚ/ር መ/ቤቱ በአዲስ መልክ ሲደራጅ ተቋሙን የከተማ ፕላን፣ ጽዳትና ውበት ቢሮ
በሚል ስያሜ በአራት አላማ አስፈጻሚ መምሪያዎች አደራጅቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል በፌዴራል ደረጃ በዘርፉ ትኩረት ከሚሰጣቸው ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ
ኤጀንሲ አንዱ ነው፡፡ ኤጀንሲው የተጣለበትን አገራዊ ተልዕኮ እና ገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ የሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 21/2003 ዓ.ም. “ልማታዊ የከተማ መሬት አስተዳደር ሥርዓት አቅጣጫና
የአፈፃፀም ዕቅድ” በሚል ርዕስ ባስቀመጠው መሠረት ከዚህ በታች የተቀመጡትን ቁልፍ ተግባራት የራሱ
የመርሃ ግብር አካል በማድረግ እንዲያከናውን አገራዊ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ከአገር አቀፉ የጂኦዴቲክ መቆጣጠሪያ ነጥቦች መረብ (National Geodetic Network) ጋር በተያያዘ መልኩ
ለሁሉም ከተሞች የቅየሣ መቆጣጠሪያ ነጥቦች በመመሥረት በየከተሞቹ የሚሠሩ ቀጣይ የልማት
እንቅስቃሴዎች እነዚህን ነጥቦች መነሻ በማድረግ እንዲሠሩ በማድረግ እርስ በርሱ ተናባቢ የሆነ የመረጃ
ማምረት ሥራ እንዲሠራ ለማስቻል መሠረት መጣል፤ የመሠረታዊ ካርታ በ 1፡2,000 እና በ 1፡5,000
መሥፈርት በአምስት አመት ዕቅዱ ለተያዙት ከተሞች የማዘጋጀት የመሪነት ሚና ይጫወታል፤ ለከተማ
ፕላን ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ የመሠረታዊ ካርታዎች ዝግጅትና አጠቃቀም ውጤቱ ተመሳሳይና ተናባቢ
እንዲሆን ይህን ሥራ የሚያከናውኑ ባለሙያዎችን ለመመዘንና እውቅና ለመሥጠት የሚያስችል ሥርዓት
በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግና ተፈጻሚነቱንም መቆጣጠር በሃላፊነት ይፈፅማል፤ የምድር መረጃ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 23


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አመራረት ስታንዳርድ አተገባበርን፣ የምድር መረጃ ለማምረት ጥቅም ላይ የሚውሉ መሣሪያዎችን


ትክክለኛነት በማረጋገጥና ሰርተፍኬት በመስጠት በሃገር ደረጃ አግባብ ያለው አደረጃጀት ወይም የውክልና
ቁጥጥር ሥርዓት በመመስረት ተግባራቱን ያከናውናል፤ አገራዊ 24 ሰዓት የማያቋርጥ የጂኦደቲክ
መቆጣጠርያ ነጥቦች አገልግሎት ሲተገበር በሃገር ደረጃ አገልግሎቱን የሚሰጥበትን አቅምና ሥርዓት ፈጥሮ
ይተገብራል።

ይሁንና ኤጀንሲው ያለው አደረጃጀት እስከታችኛው የአስተዳዳር እርከን ድረስ ባልተማከለ አስተዳደር
መርህ ሙሉ በሙሉ ባለመዘርጋቱ ለከተሞች ፕላን አገልግሎት የሚውል መሠረታዊ ካርታ አገልግሎቱ
ተደራሽ እንዳይሆን ምክንያት ሲሆን በዚህ ረገድ በክልሎች፣ ከተሞችና በግሉ ዘርፍ እየተካሄደ ያለውን ወጥ
ያልሆነ አሰራር አቀናጅቶ በመምራትና በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ክፍተቶች ይታያሉ፡፡

በክልሎች ያለው የቅየሳና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ተቋማዊ አደረጃጀት የተለያየ ሲሆን በአንዳንድ
ክልሎች በኢንስቲትዩት ውስጥ በሥራ ሂደት ደረጃ በአንዳንዶች ደግሞ በተለያዩ የክልል ከተማ ልማት
ቢሮዎች ሥር በኬዝ ቲም (በቡድን) ደረጃ ተደራጅተው ይገኛሉ፡፡ የውስጥ አደረጃጀት ላይ የተደረገው ዳሰሳ
እንደሚጠቁመው በክልሎች ያሉ አደረጃጀቶች ከስያሜ፣ በውስጣቸው ከሚያካትቷቸው የሥራ ሂደቶች
ወይም ቡድኖቹ እንዲሁም ከክልል እስከ ከተማ በተዘረጋው የቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅትና አፈፃፀም
መዋቅር አንፃር ወጥነት የሌላቸው ሲሆን በአንጻሩ በትላልቆቹ ክልሎች ያለው አደረጃጀት ከታዳጊዎቹ
የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በክልሎች ለቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ሥራ ዝግጅት የሚያግዙ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በተለያየ


የአቅርቦትና አጠቃቀም ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ክልሎች በዞንና በከተማ ደረጃ ባሏቸው ቅርንጫፍ
ጽ/ቤቶች ጭምር አቅም በፈቀደ መልኩ አስፈላጊ መሳሪያዎችን ለማሟላት ጥረት በማድረግ ላይ ቢሆኑም
ተቋማቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነትና ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያስችላቸውን bqE yzmÂêE
t&KñlÖ©! mú¶ÃãC xQRïT WSNnT bmñ„ b¸flgW m-N F_nT yzRûN F§¯T ለ¥à§T ያልተቻለ
ሲሆን ችግሩ በታዳጊ ክልሎች ደግሞ የጎላ ነው ÝÝ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ አስተዳደር የከተማ ፕላንና
መረጃ ኢንስቲትዩት ከአደረጃጀት አንፃር ከማዕከል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ የተዘረጋ ተቋማዊ አደረጃጀት
ያለው ከመሆኑም ባሻገር በሰው ኃይል ብዛትም ሆነ በሙያ ስብጥር እንዲሁም በቁሳቁሶችና የቴክኖሎጂ
መሣሪያዎች ግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀም ከሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት አንፃር ሲታይ በተሻለ አደረጃጀት
ላይ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ በፌደራል፣ በክልልና በከተሞች ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ ተቋማቱ ለቅየሳና መሰረታዊ
ካርታና ዝግጅትና አፈጻጸም የሚያግዝ እስከ ታችኛው የአስተደደር እርክን ድረስ ወጥ የሆነ መዋቅራዊ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 24


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አደረጃጀት ካለመኖሩም ባሻገር በመዋቅሩ ያለው የሰው ኃይል የላቀና የተሟላ ዕውቀት አለመኖር
እንዲሁም የዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦት እጥረት በአሰራር ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ቁልፍ
ችግሮች ናቸው፡፡

በመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ዙሪያ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተወዳዳሪ
አገልግሎት ለከተሞች በማቅረብ የከተሞችን ልማት መደገፍ ይጠበቃል፡፡ ይሁንና የከተማ ፕላን ከቅየሳና
መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ጋር አጣምረው አገልግሎት የሚሰጡ የግል አማካሪ ድርጅቶች በበቂ መጠን
ያለመኖርና ያላቸው ልምድም ውስን ከመሆን የተነሳ ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ እየተደገፈ አይደለም፡፡
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ጅምር ተሳትፎ ቢኖርም በዘርፉ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አንጻር እየተደረገ ያለው
ድጋፍ ከቁጥር የሚገባ አይደለም፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው ልምድ እንደሚያሳየው
የሙያ ማህበራት በቅየሳ አፈጻጸም እና የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ላይ ያላቸው ሚና ጉልህ ቢሆንም
በአገራችን በዘርፉ ተደራጅተው የሚገኙ የሙያ ማህበራት ያላቸው አስተዋጽኦ ከዚህ ግባ የሚባል
አይደለም፡፡

1.4 ከመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ቁልፍ ችግሮች


 ካርታዎች ሽፋንና ጥራት ዝቅተኛ መሆን፣
 የሚዘጋጁ መሰረታዊ ካርታዎች ወጥነት የሌላቸውና ከብሄራዊ የጂኦዴቲክ መረብ ጋር የማይናበቡ፣
 የቅየሳ መቆጣጠርያ ነጥቦች በቁጥር አናሳ መሆንና በሚፈለገው ጥግግት አለመገኘት
 የቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት የቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች አቅርቦትና ተጠቃሚነትን ደካማ
መሆን፣
 ግልጽ የሕግ ማዕቀፍና የአሰራር ስታንዳርድ ሰነድ አለመኖር፡፡

2. መዋቅራዊ ፕላን

2.1. የመዋቅራዊ ፕላን መሰረተ ሀሳቦች

2.1.1. የከተማ ፕላን ዓይነቶችና ውጤቶች

የከተማ ፕላን ዓይነቶች

የከተማ ፕላን ማለት አስቀድሞ ለሚወሰን ዘመን የአንድን ከተማ እና አካባቢውን የወደፊት ዕድገት/ልማት
በሚፈለገው ዓላማ መሰረት እንዲመራ የሚዘጋጅ ዕቅድ ሲሆን በይዘት ደረጃ የከተማውን መሬት
አጠቃቀም፣ የትራንስፖርት ስርዓትን፣ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ፣ ታሪካዊ፣ የፊዚካላዊና ሌሎች ጉዳዮችን
ሊያካትት ይችላል፡፡ የፕላኑ ውጤት (output) የሚገለፀው በካርታና በዝርዝር የፅሑፍ ሰነዶች ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 25


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በዓለም ላይ በርካታ የፕላን አይነቶች ሲኖሩ አሁን በኢትዮጵያ እንዲሰራባቸው የተፈቀዱት ሶስት ዓይነት
ፕላኖች ማለትም መዋቅራዊ ፕላን (Structure Plan)፣ የአካባቢ ልማት ፕላንና (Local Development
Plan) መሰረታዊ ፕላን (Basic Plan) የሚባሉት ናቸው፡፡ ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ በአብዛኛው የመሬት
አጠቃቀሙን ለማስፈፀም የየአካባቢው ዝርዝር ፕላኖች የሚያስፈልጉ ሲሆን የማህበረ-አኮኖሚያዊ
ጉዳዮችን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንና ፕሮግራሞችን መንደፍ ያስፈልጋል፡፡

ሀ.መዋቅራዊ ፕላን (Structure Plan)

በከተማ ፕላን አዋጅ 574/2000 መሰረት መዋቅራዊ ፕላን በከተማ አቀፍ ደረጃ እስከ 10 ዓመት የፕላን
ዘመን ለሚደርስ ጊዜ የሚዘጋጅ ስትራቴጂካዊ የፕላን ዓይነት ሆኖ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አጠቃላይ የፊዚካል
የልማት አካላትን ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡

ሀ) ከተማው የሚያድግበትን መጠንና አቅጣጫ፣

ለ) ዋና ዋና የመሬት አጠቃቀም ምድቦች፣

ሐ) ዋና ዋና ማሕበራዊና ፊዚካላዊ የመሰረተ ልማት አውታሮች የሚዘረጉበትንና


የሚደራጁበትን እንዲሁም

መ) መልሶ የማልማት እርምጃን የሚጠይቁ የከተማውን አካባቢዎችና የአካባቢ ጥበቃ ነክ


ጉዳዮች ናቸው፡፡

መዋቅራዊ ፕላን ከ 20,000 የሕዝብ ቁጥር በላይ ላላቸው ከተሞች የሚዘጋጅ ሆኖ ቀድሞ ይሰራበት
ከነበረው ማስተር ፕላን የሚለይበት መሰረታዊ ነገር አለ። ማስተር ፕላን በአፈፃፀም ላይ፤ በማንኛውም
የከተማ ክፍል በፕላኑ አስቀድሞ ከተቀመጠው ውጭ ተግባራዊ እንዲሆን ስለማይፈቅድ ግትር (rigid)
ነው። በአንጻሩ መዋቅራዊ ፕላን ከዋና ዋና የከተማ መዋቅሮች/አውታሮች በስተቀር የከተማን አካባቢዎች
ከፊል በከፊል አቅምንና በወቅቱ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብና የአካባቢውን ሕዝብ በማሳተፍ
ተግባራዊ የሚደረግ በመሆኑ እንደ ሁኔታው ሊዘጋጅ የሚችል (flexible) ፕላን ነው።

ለ. መሰረታዊ ፕላን (Basic Plan)

መሰረታዊ ፕላን ማለት ከ 20,000 ህዝብ በታች ላላቸው አነስተኛ ከተሞች ከአምስት ዓመት ላልበለጠ
ዘመን፣ በአነስተኛ የሰው ኃይልና አጠር ላለ ጊዜ ጥልቅ የማህበረ-ኢኮኖሚ ጥናት ሳያስፈልግ እንዲዘጋጅ
በመንግስት የተወሰነ ውስብስብ ያልሆነ ዘርዘር ያለ የፊዚካል/ስፓሻል ፕላን ነው፡፡ ዋናው ዓላማም አነስተኛ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 26


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከተሞች መዋቅራዊ ፕላን እስኪዘጋጅላቸው ድረስ ካለ ሥርዓት አድገው የወደፊት ልማታቸው ላይ


ዕንቅፋት ከመፈጠሩ በፊት ከወዲሁ ዕድገታቸውን በስነ ሥርዓት እንዲመሩ የሚያስችል የፊዚካል (የመሬት
አጠቃቀምንና የመሰረተ-ልማት ዕቅድን የሚያሳይ) ፕላን ነው፡፡

መሰረታዊ ፕላን እንደ መዋቅራዊ ፕላን ዝርዝር ፕላን ሳያስፈልገው በራሱ ተፈፃሚ እንዲሆን የሚዘጋጅ
ነው ፡፡ በአገራችን የአነስተኛ ከተሞች ቁጥር በርካታ በመሆኑ፤ በአካባቢያቸው ካለው ገጠር ጋር
ተቆራኝተው የከተማ-ገጠር ትስስርን ለማጠናከር እንዲያግዙ የሚዘጋጅ ነው፡፡ ፕላኑን ተግባራዊ ሊሆን
የሚችለው በተለያዩ የመንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት በሕብረተሰቡ የተቀናጀ ጥረት ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት በአገራችን እየተሰራባቸው የሚገኙ ፕላኖች ተዘጋጅተው በሚመለከታቸው አካላት


ከፀደቁ በኋላ ሕጋዊ ሰነድ ስለሚሆኑ፤ ዋናዎቹን ፕላኖችም ሆነ በነሱ ላይ ተመርኩዘው የሚዘጋጁ ዝርዝር
ፕላኖችን የጣሰ ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

የከተማ ፕላን ውጤቶች

የአንድ ከተማ ፕላን ሲዘጋጅ፤ ቀደም ብሎ እንደተጠቆመው፤ ለአስፈፃሚዎቹ መመርያ እንዲሆኑና


ለወደፊትም በሰነድነት እንዲቀመጡ በአብዛኛው ሁለት ዓይነት ሰነዶች ይዘጋጃሉ፡፡ በአንዱ ስብስብ
የተለያዩ ዓይነትና መስፈርት ያላቸው የነባራዊና የወደፊት የመሬት አጠቃቀምና የመሰረተ-ልማት ስርጭት
ካርታዎች (maps/graphic documents) ሲሆኑ፤ በሌላው ስብስብ ደግሞ የፅሑፍ ሰነዶች ይገኛሉ። የፅሑፍ
ሰነዶቹ የካርታዎችን ማብራርያ፣ የማህበረ-ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ጥናቶችን ያጠቃልላሉ፡፡

ብዙ ጊዜ ፕላኖችን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት የሚደረገው ካርታዎችን ብቻ በማየት እንጂ የፅሑፍ ሰነዶቹ
ጥቅም ላይ አይውሉም። ለአብነት “ቅይጥ የመሬት አጠቃቀም” በካርታ ላይ በአብዛኛው ሰፊ ቦታን
ይሸፍናል። ነገር ግን በዚህ ቅይጥ የመሬት አጠቃቀም በሚባለው ውስጥ ምን ከምን ጋር እንደሚጣጣምና
እንደሚቀየጥ ማብራሪያው የሚገኘው የፅሑፍ ሪፖርቱ (Text Report) ውስጥ ነው። ሌሎችም
የፕሮግራምና ፕሮጀክት ዝርዝር ሀሳቦች (proposals) እንዲሁም የትግበራ ምዕራፎች (phasing) እና
ሌሎችም የሚገኙት ከሪፖርቶች መሆኑ ብዙ ጊዜ ይዘነጋል።

2.1.2. የመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት

የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም የተለያዩ ሂደቶች ያሉት ሲሆን እነዚህንም በአብዛኛው በሁለት ከፍሎ
ማየት ይቻላል፤ እነዚህም የቅድመ ዝግጅት እንዲሁም የፕላን ዝግጅትና አፈፃፀም ደረጃዎች ናቸው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 27


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ቅድመ ዝግጅት፡- ስሙ እንደሚጠቁመው የፕላን ዝግጅት ዋናው ስራ ከመጀመሩ በፊት መከናወን


ያለባቸው ስራዎችን የሚያካትት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ

1. ስለ ፕላን ዝግጅት አስፈላጊነት ሀሳብ ማመንጨት፣

2. ለፕላን ዝግጅት አስፈላጊ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣

3. ዋና ዋና የፕላን ጉዳዮችን በቅደም ተከተል መለየትና፣

4. የመነሻ ራዕይ፣ ግብና ዓላማዎችን ማስቀመጥን ያካትታል፡፡ በተጨማሪም የዝክረ ተግባር ዝግጅት ለፕላን
ዝግጅት አስፈላጊ የሆኑ አደረጃጀቶችን ማቋቋም የቅድመ ዝግጅቱ ተግባራት ተደርገው ሊወሰዱ
ይችላሉ፡፡

የፕላን ዝግጅት፡-የፕላን ዝግጅት ከተጀመረ በኋላ ቀጣዮቹ ሂደቶች በቅደም ተከተል የሚከተሉት ይሆናሉ

5. የመረጃ ስብሰባ የሚያካትታቸው ዋና ዋና ተግባራት የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጾች ዝግጅት፣ ለፕላን


ዝግጅት አስፈላጊ የሆኑትን የሶሾዮ ኢኮኖሚ፣ ፊዚካልና ስፓሻል መረጃዎችን መሰብሰብ፣
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በየደረጃው ውይይቶችን ማድረግ፣ መረጃዎችን በማደራጀት ለትንተና
ዝግጁ ማድረግ ናቸው፡፡

6. የተሰበሰቡ መረጃዎች የመተንተን እና በትንተናው ላይ በመመስረት የትንተና ውጤቶችን የመተርጎም፣


ለመሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት ግብዓቶችን የማዘጋጀትና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን የመለየት
ስራዎችን ያካትታል፡፡ በተጨማሪም በትንተና ለተለዩ ለእያንዳንዱ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ግቦችን
እና ግቦቹን ለማሳካት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች የመንደፍ ስራዎችን እንዲሁም ስትራቴጂዎች ወደ
ተግባር መለወጥ የሚያስችሉ የፕሮጀክት ሀሳቦች ዝግጅትን ያካትታል፡፡

7. በሶሺዮ ኢኮኖሚ፣ ፊዚካልና ስፓሻል መረጃዎች ትንተና ላይ በመመስረት የጽንሰ ሀሳብ ፕላን ይዘጋጃል።

8. የመዋቅራዊ ፕላኑ ዝግጅት ዋና ዋና የመሬት አጠቃቀም ምድቦችን ዋና ዋና ማህበራዊና ፊዚካላዊ


የመሰረተ ልማት አውታሮችንና የመስፋፊያ ቦታዎችን ወዘተ ይይዛል፡፡

9. የፕላን ማስተቸትና ማጸደቅ በውስጡ ሁለት ዋና ዋና ተግባራትን ማለትም የፕላን ማስተቸት እና


የፕላን ማጸደቅ ተግባራትን የያዘ ነው፡፡ በፕላን ማስተቸት ወቅት ፕላን ከመፅደቁ በፊት የፕላኑ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 28


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ብቃትና ጥራት በተለያዩ ደረጃ በሚገኙ የሚመለከታቸው አካለት ይፈተሽና ጥራቱና ብቃቱ ሲረጋገጥ
ፕላኑን የማጸደቅ ስራ ይከናወናል፡፡

የፕላን አፈጻጸም፡-

10. ፕላን ዝግጅት ከተጠናቀቀና ከጸደቀ በኋላ ቀጣይ ስራ ፕላኑን መተግበር በመሆኑ በፕላን ዝግጅትና
አፈጻጸም ሂደት የትግበራ አካልን ማደራጀት፣ ለባለሙያዎች ስልጠና መስጠት፣ ዝርዝር የአካባቢ
ልማት ፕላኖችን ማዘጋጀት፣ የትግበራ መርሀግብር ማዘጋጀት እና ፕላኑን የመተግበር የመሳሰሉ ዋና
ዋና ተግባራትን ያካትታል፡፡

በተጨማሪም፤ በፕላን ትግበራ ወቅት ክትትል ማድረግንና የግምገማ ስራዎችን የሚያካትት ሲሆን ለዚህም
ስራ ራሱን የቻለ ተቋማዊ አደረጃጀት ያስፈልገዋል፡፡ በፕላን ዝግጅት ወቅት ፕላኑ በሚፈለገው የጥራት
ደረጃ መዘጋጀቱንና ለትግበራ አመቺ መሆኑን በቡድን፣ በቤት ውስጥና በመስክ ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር በሚደረጉ ውይይቶች እንዲሁም በቴክኒካል ኮሚቴ ግምገማ ስለመዳበራቸው ክትትልና ግምገማ
ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን ፕላኑ ከተዘጋጀ በኋላ ደግሞ አፋጻጸሙን አስመልክቶ በየጊዜው ክትትል ማድረግና
መገምገም ችግሮችን በሰዓቱ ለመለየትና የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያስችላል፡፡

2.1.3. ለከተማ ፕላን ዝግጅት የሚካሄድ ጥናት

ሀ. የታሪክና ቅርስ ጥናት

ቅርስ ማለት የተለያዩ ጉዳዮችን የሚመለከት ሲሆን ግዙፍነት የሌለው ቅርስና ግዙፍነት ያለው ቅርስ
በመባል ይለያያሉ፡፡ ግዙፍነት የሌለው ቅርስ በእጅ ለመዳሰስ የሚያዳግት ነገር ግን በአይን ለማየት፣ በጆሮ
ለመስማት የሚቻል ቅርስ ሲሆን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልዩ ልዩ ትርዒትና ጨዋታዎች፣ ሥነ-
ቃል፣ የሃይማኖት እምነት፣ የጋብቻ፣ የሐዘን ሥነ ሥርዓት፣ ሙዚቃ ድራማና ሌሎች ተመሳሳይ ባህላዊ
እሴቶች፣ ወግና ልማድን ይጨምራል፡፡

በሌላ በኩል ግዙፍነት ያለው ቅርስ ማለት በእጅ የሚዳሰሱ፣ በአይን የሚታዩ፣ የሚንቀሳቀሱና
የማይንቀሳቀሱ ባህላዊና ታሪካዊ ወይም ሰው ሰራሽ ቅርሶችን ይጨምራል፡፡ የማይንቀሳቀስ ቅርስ ማለት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 29


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከቦታ ለማንቀሳቀስ የማይቻሉ፣ በመሠረት ተገንብተው ቋሚ ከሆኑ ነገሮች ጋር የተያያዙና ከቦታ ወደ ቦታ


ለማዘዋወር የሚቻለውም በማፍረስ ብቻ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

መካነ ቅርሶች የተገኙባቸው ቦታዎች፣ የፖሊዮንቶሎጂ የታሪክ፣ የቅድመ ታሪክና የአርኪዎሎጂ ሥፍራዎች፤
ሕንፃ፣ የመታሰቢያ ቦታ፣ ሃውልት፣ ቤተ-መንግሥት፤ የጥንታዊ ከተማ ፍርስራሽ፣ ጥንታዊ የመቃብር ቦታ
የዋሻ ስዕሎችና ፅሁፎች፤ ቤ/ክርስቲያን፣ ገዳም፣ መስጊድ፣ ወይም ማናቸውም የማምለኪያ ሥፍራ፣ ወዘተ.
ናቸው፡፡ የሚንቀሳቀስ ቅርስ ማለት ከቋሚ ነገሮች ጋር በመሠረት ያልተገነቡና ከቦታ ወደ ቦታ ያለምንም
ችግር በቀላሉ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ፣ ከትውልድ ትውልድ ተላልፈው የደረሱ ቅርሶች ሲሆኑ የሚከተሉትን
ያካትታል፡፡ የብራና ፅሑፍ፣ የድንጋይ ላይ ፅሑፎችና ስዕሎች፣ የድንጋይ መሣሪያዎች፣ ከወርቅ፣ ከብር፣
ከነሐስ ወይም ከብረት ወይም ከመዳብ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች ከእንጨት፣ ከድንጋይ፣ ከቆዳ፣ ከዝሆን ጥርስ፣
ከቀንድ፣ ከአጥንትና ከአፈር ወይም ከሌሎች ነገሮች የተሰሩ ቅርፆችና ምስሎች እንዲሁም የአርኪዎሎጂ
እና የፓሊዮንቶሎጂ ቅሪቶች፤ ፅሑፍና የግራፊክ ዶክመንት ወይም የሲኒማቶግራፊና የፎቶግራፍ
ዶክመንት፣ የድምፅ ወይም የቪዲዮ ቅጂ ዶክመንት፤ ከወርቅ፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከመዳብ ወይም ከሌሎች
ነገሮች የተሰራ ገንዘብ፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መገልገያ ጌጥ ወይም ባህላዊ እቃ ያካትታል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ድርጅት አማካኝነት
ቅርስን በሚከተለው መልኩ አስቀምጦታል፡፡ ሃውልቶች፣ የሥነ ሕንፃ ሥራዎች፣ የትርዒት ቅርስና የስዕል
ሥራዎች፣ የሥነ-ምህዳር ሥራዎት፣ የድንጋይ ላይ ፅሑፎች፣ ዋሻዎች እና ማንኛውም ታሪካዊና ጥበባዊ
ዋጋ ያላቸው ነገሮች፤ ታሪካዊ ቤቶች ካላቸው የተለየ የሥነ-ሕንፃ ምህንድስና፣ የታሪክ ጥበባዊ ሥራዎች
አንፃር፤ ታሪካዊ ሥፍራዎችን ጨምሮ የአካባቢውን ወይም የቦታውን ታሪካዊነትንና ባህላዊ ጥበብና
የአካባቢውን ማህበረሰብ አስደናቂ የታሪክና ባህል እሴቶችን ያካተተ ከሆነ ቅርስ ተብለው ይጠራሉ ሲል
ገልፆታል፡፡ (በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን በተመለከተ ከተደረገ ዝርዝር ጥናት ሰነድ
የተወሰደ, አዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ 2004)

ፕላን የሚዘጋጅለት ከተማ ከመቆርቆሩ በፊት ጀምሮ የነበሩ ታሪካዊ ክስተቶች፣ ድርጊቶች፣ የሰው
ሰራሽም ሆነ ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎችና አቀማመጦች፣ የህዝብ አሰፋፈርና የአመሰራረት መልክና
(በግብታዊነት ወይም በጥናታዊ ሂደት መሆኑ) ቅደም ተከተላዊ ሂደቶች፣ የማዘጋጃ ቤታዊና የከተማዊ
አገልግሎቶች አጀማመርና እድገት መቼ፣ የትና እንዴት እንደሆነ የሚዳሰስበት ነው፡፡ በአጠቃላይም
የከተማው ታሪካዊ የእድገት ጉዞ የቅርስና የቱሪዝም መስህብ ገጽታዎችንና የመሳሰሉትን በሚመለከት
ጥናታዊ ትንታኔዎች የሚቀርቡበት ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 30


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ይህም በከተማ ፕላን ዝግጅት ላይ አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት ከተማው ታሪካዊ አመጣጥና የእድገት
ፈለግ አኳያ የከተማው የእድገትና የመስፋፋት አቅጣጫን በቀላሉ ለማሳየት፣ እምቅ የታሪካዊና የቅርስ
(archaeological) ቦታዎችን በትክክል ለይቶ ለማመላከት፣ የቱሪስት መስህብና እምቅ ቦታዎችን
ለመለየትና ለማመላከት ያስችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተከልለው መያዝና መጠበቅ የሚገባቸው የታሪክና
ቅርስ ቦታዎችን ለመጠቆም፣ ለቱሪዝም ልማት አመቺ ወይም ተስማሚ የሆኑ ቦታዎችንና አቅጣጫዎችን
ለመጠቆም፣ ታሪካዊ ድጋፍና ተቀባይነት ያላቸውን የከተማ ማስፋፊያ አቅጣጫዎችን ለይቶ ለማመላከትና
ለመጠቆም፣ ለባህላዊ፣ ታሪካዊና አርኪዮሎጂያዊ ቅርሶች መጠበቂያ ሙዚየሞች ግንባታ የሚሆን በፕላኑ
ላይ ተገቢው ቦታ እንዲያዝ ለማድረግ ይረዳል፡፡

ለ. የሥነ-ሕዝብና ማህበራዊ ጉዳዮች ጥናት

የሥነ-ሕዝብና ማህበራዊ ጉዳዮች ጥናት ስሙ እንደሚጠቁመው የህዝብ ብዛት፣ የእድሜ፣ ጾታ፣ የብሔርና
የሃይማኖት ስርጭትን እንዲሁም የሕዝብ ቁጥር ትንበያን የሚያካትት ሲሆን የማህበራዊ ጉዳይ ደግሞ
የማህበራዊ አገልግሎቶችን/ጤና፣ ትምህርት፣ መኖሪያ ቤት፣ የመዝናኛ ቦታዎች፣ የአምልኮና የቀብር
ቦታዎች እና ማሕበራዊ ችግሮችን/ጎዳና ተዳዳሪነት፣ ልመና፣ ስራ አጥነት..ወዘተ/ የሚመለከት ነው፡፡

በአጠቃላይ በፕላን ዝግጅት ጊዜ የሥነ-ሕዝብና ማህበራዊ ጉዳዮች ጥናት የሚያስፈልገው በፕላን ዘመን
/10 ዓመት/ መጨረሻ ሊኖር የሚችለውን የህዝብ ቁጥር በጾታ፣ በእድሜ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ
በሃይማኖት እና በብሔር ለመተንበይ ሲሆን ጥቅሙም በፕላን ዘመኑ የሚያስፈልጉ የማህበራዊ
አገልግሎቶችን ብዛት ለመወሰንና በፕላን ላይ ቦታ ለነዚሁ አገልግሎቶች ለመያዝ ነው፡፡

ሐ. የፊዚካል፣ ጂኦሎጂ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ጥናት

የፊዚካል ጥናት

በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት የፊዚካል ሁኔታ ጥናት የሚያካትተው የአንድን ከተማ ጂኦግራፊያዊ መገኛ፣
የመሬት አቀማማጥና የተዳፋት ሁኔታ፣ የከተማ ቅርጽና የማሰፋፊያ አቅጣጫ፣የአየር ንብረት፣ የእጽዋት
ሽፋን፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ማነቆዎች፣ ወዘተ ሁኔታዎችን ነው፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ የከተማውን
የተጽዕኖ ክልል (Influence Area) የሚያካትት ሲሆን ከተማው ከአካባቢው ጋር ያለውን የመሰረተ ልማትና
ትራንስፖርት ቁርኝት፣ የህዝብ አሰፋፈርና ጥግግት፣ የአከታተም ሥርዓትና የከተሜነት ደረጃ፣ የአየር
ንብረትና የተፈጥሮ ሀብት፣ ወዘተ ትንተናን ያጠቃልላል፡፡ የፊዚካል ጥናት የወደፊት የመሬት አጠቃቀም
እቅድን ከመሬት አቀማመጥና ተዳፋት (slope) ጋር ለማቀናጀትና በወደፊቱ የከተማው እድገት ላይ
የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለይቶ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥም ጭምር ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 31


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የጂኦሎጂ ጥናት

በጂኦሎጂ ጥናት ውስጥ የሚካተቱ ነገሮች፡ የአለትና የአፈር አፈጣጠርና አሁን ያሉበት ሁኔታ፣ ጂኦሎጂያዊ
የመሬት አፈጣጠርና አቀማመጥ፣ በመሬት ላይ የሚካሄዱ ጂኦሎጂያዊ ሂደቶች ሁኔታ፣ የከርሰ-ምድርና
የገጸ-ምድር ውኃ ሀብት መገኛ ስፍራዎች፣ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ማዕድናት፣ የከተማውን የዕድገት
ሁኔታ ሊገቱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ክስተት ሁኔታ፣ ወዘተ ናቸው፡፡ በከተማ
ፕላን ዝግጅት ወቅት የጂኦሎጂ ጥናት የተፈጥሮ ሀብቶች ማለትም የተለያዩ ማዕድናትን ለይቶ በማወቅ
ጥቅም ላይ ሊዉሉ የሚችሉበትን መንገድ መጠቆም፣ ሊከሰቱ የሚችሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን በመለየት
የመፍትሄ ሀሳቦችን ማቅረብ እና የገጸ-ምድርና የከርሰ-ምድርን አጠቃላይ ይዘት (አፈር፣ ድንጋይ፣ ወዘተ)
በማጥናት በግንባታ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሁኔታዎችን ማመላከት ናቸው፡፡

የአካባቢያዊ ጉዳዮች ጥናት

የከተማው የአካባቢ ሁኔታ ጥናት ውስጥ የሚካተቱት በዋናነት የፍሳሽና የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፣
አረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ብክለት ሁኔታ ናቸው፡፡ ከከተሞች እድገትና መስፋፋት ጋር በተያያዘ ሊመጡ
የሚችሉ አካባቢያዊ ችግሮችን በማጥናትና በመተንበይ ተገቢውን ቅድመ-ዝግጅት ለማድረግና ለአካባቢ
ጥበቃ ትኩረት የሰጠ የቦታ አመዳደብ ለማድረግ ነው፡፡

መ. የከተማና ገጠር ኢኮኖሚ ጉዳዮች ጥናት

በከተማ ፕላን ዝግጅት የአኮኖሚ ጉዳዮች ጥናት የሚያተኩረው በከተማዋና በአካባቢዋ ያለው የገጠር
አኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ላይ ነው፡፡ በገጠሩ ኢኮኖሚ ጥናት ውስጥ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች
በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ተጽዕኖ ሊያመጡ የሚችሉ እንደ እህልና የከብት ሀብት የመሳሰሉ
የግብርና ምርቶች ሲሆኑ፣ የከተማ ኢኮኖሚ ዘርፍ ጥናት ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮች ደግሞ በከተማ
ውስጥ በሚካሄዱ የሸቀጣሸቀጥ ንግድና አገልግሎቶች፣ ፋብሪካና ኢንዱስትሪ፣ መደበኛ ያልሆነው
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ፣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴና አካባቢ፣ የከተማ
ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ግንባታ፣ የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎት ተቋማዊ አቅምና የመልካም አስተዳደር
ሁኔታዎች ላይ ነው፡፡

የከተማና አካባቢ ኢኮኖሚያዊ ጥናት በከተማ ፕላን ዝግጅት ላይ አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት የከተማና
አካባቢው ዋና የኢኮኖሚ መሠረት እንዲሁም የወደፊት የከተማዋን ሚና ለመለየት፣ በከተማዋ አሁን
ላሉትም ሆነ ወደፊት ለሚፈጠሩ ኢኮኖሚያዊና የንግድ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊውን ቦታ እንዲሁም

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 32


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ጂኦግራፊያዊ አቅጣጫዎችና ፍላጎቶችን ለመለየት እና ለመወሰን ነው፡፡ በተጨማሪም፤ በከተማ ኢኮኖሚ


ዘርፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ቅልጥፍናና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ መንገዶችን ለመጠቆም፣
ከገጠር ለሚመጡ የግብርና ምርቶች ገበያ /የእህል፣ የከብት/ እና መጋዘኖች የሚሆኑ በቂ ቦታዎችን በፕላን
ላይ ለመያዝ ነው፡፡

ሠ. የስፓሻል ጥናት

ስፓሻል ማለት መሬትና መሬት ነክ የሆኑ ጉዳዮችን የሚያጠቃልል ሲሆን በውስጡ የሚያካትታቸው ዋና
ዋና ጉዳዮች የመሬት አጠቃቀም እና የመንገድ ስርጭት ናቸው፡፡ የመሬት አጠቃቀም በዚሁ ክፍል የከተማ
ፕላን የመሬት አጠቃቀም ይዘት በሚለው ንዑስ ክፍል ውስጥ የተመለከቱትን /መኖሪያ፣ ንግድና ቢዝነስ፣
አስተዳደርና ማህበራዊ አገልግሎት፣ ማምረቻና መጋዘኖች እና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች/ የሚያካትት ሲሆን
በፕላን ዝግጅት ውቅት የነባራዊ የመሬት አጠቃቀም ካርታ ላይ በመመስረት ከመሬት አጠቃቀም ጋር
ተያያዥ የሆኑ ችግሮች ይለያሉ፡፡ የወደፊት የመሬት አጠቃቀም ፕላን በሚዘጋጅበት ጊዜ በነባራዊ የመሬት
አጠቃቀም ፕላን ላይ ለተለዩት ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በፕላን ዘመኑ ውስጥ
ለሚያስፈልጉት ተጨማሪ አገልግሎቶች በወደፊት የመሬት አጠቃቀም ፕላኑ ላይ በስታንዳርድ መሰረት
በቂና ተስማሚ ቦታ እንዲያዝ ይደረጋል፡፡

የስፓሻል ጥናት ከሚያካትታቸው ጉዳዮች ሌላው የመንገድ ስርጭት ፕላን ሲሆን ልክ እንደ የመሬት
አጠቃቀም ፕላን በነባራዊው የመንገድ ስርጭት ፕላን ላይ ዳሰሳ በማድረግ ከመንገድ ጋር የተያያዙ ችግሮች
ይለዩና የወደፊት የመንገድ ስርጭት ፕላን ሲዘጋጅ ችግሮቹን በሚፈታበት እና በፕላን ዘመኑ የሚያስፈልጉ
ተጨማሪ መንገዶችን ባካተተ መልኩ ይሆናል፡፡

ረ. የከተሞች መንገድ የተፋሰስ ጥናት

በከተሞች የሚኖረው የመንገድ ተፋሰስ በዙሪያቸው ያለው ተፋሰስ አካል ሲሆን በከተሞች ውስጥ
የሚገኙትን የመንገድና ወንዝ ተፋሰሶች መሰረት አድርገው በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኘውን ትርፍ ውሃ
(ጎርፍን ጨምሮ) በከተማው ነዋሪና ንብረት ላይ አደጋ በማይፈጥርበት ሁኔታ እንዲፈስ ተገቢውን አያያዝና
አወጋገድ የሚደረግበት ሥርዓት ነው፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል
የተፋሰሱን አቅጣጫ፣ ፍሳሽ የሚሰበሰብበት የቆዳ ስፋት፣ የውሃ መጠን፣ የፍሰት ፍጥነት መጠን እንዲሁም
ከጎርፍ አደጋ ጋር የተያያዙ ታሪካዊ ክስተቶችን መነሻ በማድረግ ትንበያ ማካሄድን ያካትታል፡፡ በዘርፉ
የተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በከተሞች ከ 20 እስከ 25 በመቶ የሚሆነው ኢኮኖሚያዊ
ውድመት የሚመነጨው በጎርፍ አደጋ ምክንያት እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም የከተሞች መንገድ
ተፋሰስ ሥርዓት በተለይም በከተሞች የሚፈጠረውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ፣ የነዋሪውን ደህንነት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 33


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ለማረጋገጥ፣ በውድ ዋጋና ከፍተኛ ወጪ የተሰሩ መንገዶች ያለጊዜያቸው በጎርፍ አደጋ ተሸርሽረው
ከጥቅም ውጪ እንዳይሆኑ ለመከላከልና የአካባቢን ንጽህና ለመጠበቅ ስለሚያስችሉ የመንገድ ተፋሰስ
ሥርዓቱ ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ ከሌሎች የመሠረተ ልማት አውታሮች ጋር በቅንጅት መሰራት ያለበት
ተግባር ነው፡፡

2.1.4. መዋቅራዊ ፕላን ለማዘጋጀት የሚያስፈልገው አደረጃጀት፣ የባለሙያ ብዛት፣ ስብጥር እና


ጊዜ

የከተሞች ፕላን እየተዘጋጁ የሚገኙት በክልል ደረጃ በሚገኙ ተቋማት በመሆኑ ለከተማ ፕላን ዝግጅት
የሚያስፈልገው መዋቅራዊ አደረጃጀት አቅምን የሚጠይቅ በመሆኑ እንደ ክልሉ ትልቅነትና አነሰተኛነት
ሊለያይ ይችላል፡፡ በሀገሪቱ ትላልቅና ታዳጊ ክልሎች እንዲሁም የቻርተር ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ
ሲሆን በሁሉም ተመሳሳይ አደረጃጀት መፍጠር አዋጭ ባለመሆኑ እንደየ ክልሎቹ የእድገት ደረጃ፣
የከተሞች ብዛት፣ የከተሞች ደረጃ ለየክልሎቹ ተስማሚ የሆኑ አደረጃጀቶች ሊኖሩ ይገባል፡፡ በዚህም
መሰረት ምንም እንኳን ለየክልሎቹ የሚያስፈልገው ተቋማዊ አደረጃጀት በጥናት መደገፍ ያለበት ቢሆንም
ለጊዜው ወጥ የሆነ አሰራርን ከመዘርጋት አኳያ በአራቱ ትላልቅ ክልሎች ተመሳሳይ አደረጃጀት ለምሳሌ
በኢንስቲትዩት ደረጃ የከተማ ፕላን ተቋም ማደራጀት /ከፕላን ዝግጅት በተጨማሪ ጥናትና ምርምር፣
የአቅም ግንባታ ስራዎች እንዲሁም የክትትልና ግምገማ ስራዎችን የሚያከናውን/ እንዲሁም በአራቱ
ታዳጊ ክልሎች በወሳኝ የስራ ሂደት ደረጃ ተመሳሳይ አደረጃጀት መፍጠር /በዋንኛነት የከተማ ፕላን
ዝግጅትና የክትትልና ግምገማ ስራዎችን የሚያከናውን/ የሚቻል ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ አዲስ አበባና
ድሬዳዋ መስተዳድር እና የሀረሪ ክልል እያንዳንዳቸው አንድ ከተሞች ያላቸው ቢሆኑም አዲስ አበባ የተለየ
በመሆኑ አሁን ባለበት በኢንስቱትዩት ደረጃ እንዲቀጥል በማድረግ የድሬዳዋንና የሀረሪን በስራ ሂደት ደረጃ
በተመሳሳይም ከ 20,000 ሕዝብ በላይ ያላቸውን ከተሞች እንደ የደረጃቸው በመለየት የፕላን ዝግጅት
አሀድ በስራ ሂደት ደረጃ ማዋቀር ይቻላል፡፡

የፕላን ዝግጅት ተቋማት እንደ ተቋሙ ተግባርና ሀላፊነት የተለያዩ ቡድኖች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ተቋሙ
በኢንስቲትዩት ደረጃ ከተቋቋመ ቢያንስ ሁለት የስራ ሂደቶች ሊኖሩት የሚገባ ሲሆን እነዚህም የከተማ
ፕላን ዝግጅት የስራ ሂደት እና የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት የስራ ሂደት ናቸው፡፡ የከተማ ፕላን ዝግጅት የስራ
ሂደት በውስጡ የከተማ ፕላን ዝግጅት፣ የጥናትና አቅም ግንባታ እንዲሁም የክትትልና ግምገማ ቡድኖች
ሊኖሩት ይችላል፡፡ ቡድኖቹ ሊይዙ የሚገባቸው የባለሙያ ብዛት በአመት በተቋሙ ሊሰሩ በሚታቀዱ
ስራዎች ላይ የሚመሰረት ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በስራ ሂደት ደረጃ ለሚዋቀሩት ተቋማት ዋንኛ
ስራቸው ፕላን ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ቡድን ማደራጀት የሚቻል ሲሆን በየቡድኑ የሚኖረው

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 34


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የባለሙያ ብዛት ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የሚወሰነው በአመት የሚታቀደው የስራ መጠን መሠረት
ይሆናል፡፡

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ለአንድ የከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋም የሚያስፈልገው የሰው ኃይል
የሚወሰነው በአመት በሚታቀደው የስራ መጠን ላይ የተመሰረተ ሲሆን ለአንድ ከተማ የመዋቅራዊ ፕላን
ዝግጅት የሚያስፈልገው የባለሙያ ብዛትና ስብጥር ደግሞ እንደሚዘጋጀው ፕላን ዓይነት ይለያያል፡፡ ከላይ
ለመግለጽ እንደተሞከረው በሀገሪቱ የሚዘጋጁ ፕላኖች ለትላልቅ ከተሞች መዋቅራዊ ፕላን ሲሆን የህዝብ
ቁጥራቸው ከ 20 ሺ በታች ለሆኑ አነስተኛ ከተሞች ደግሞ መሰረታዊ ፕላን ነው፡፡ በዚሁ መሰረት
ለመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እንደ ሁኔታው እስከ 7 ባለሙያዎች /በተለያዩ የሙያ ዘርፎች/ ማለትም
የታሪክ፣ የስነ ህዝብ፣ የኢኮኖሚ፣ የፊዚካልና ኢንቫይሮንሜንት፣ የጂኦሎጂ፣ የተፋሰስ እና የስፓሻል ጥናት
ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ሲሆን ለመሰረታዊ ፕላን ዝግጅት ደግሞ የሶሺዮ-ኢኮኖሚ፣ የፊዚካልና
የስፓሻል በጥቅሉ 3 ባለሙያዎች እንደመነሻ ያስፈልጋሉ ብሎ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡

ለከተሞች ፕላን ዝግጅት የሚያስፈልገው ጊዜ እንደ ከተሞቹ ደረጃና እንደሚዘጋጀው የፕላን ዓይነት
የሚለያይ ሲሆን የህዝብ ቁጥራቸው ከ 20 ሺ በታች ለሆኑ ከተሞች የሚዘጋጀው የፕላን ዓይነት መሰረታዊ
ፕላን ሲሆን የሚያስፈልገውም ጊዜ ከአራት ወራት ያልበለጠ ነው፡፡ የህዝብ ቁጥራቸው ከ 20 ሺ በላይ የሆኑ
ከተሞች በህዝብ ብዛታቸው መጠን መካከለኛ፣ ትላልቅ እና ከፍተኛ ሜትሮፖሊታን በመባል የተለዩ ሲሆን
በደረጃቸው መሰረት በመዋቅራዊ ፕላን ማኑዋል /ምንም እንኳን ማኑዋሉ ክለሳ የሚያስፈልገው ቢሆንም/
ላይ የተቀመጠው ጊዜ በቅደም ተከተል ስድስት፣ ስምንት፣ አስር እና አስራ ሁለት ወራት ነው፡፡

2.1.5. የከተማ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ይዘት

ሀ. የመኖሪያ ቤት አገልግሎት

የመኖሪያ ቤት አገልግሎት ለከተማ ነዋሪዎች አንድ ወሳኝ መሠረታዊ ፍላጎትና የማህበራዊ አገልግሎት
ከመሆኑም በላይ በከተሞች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ዕድገት ውስጥ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ በተለይም
በኢመደበኛ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ውስጥ የኑሮ መሰረታቸውን አድርገው ለሚንቀሳቀሱ ዝቅተኛ ገቢ
ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት መጠለያ ብቻ ሳይሆን የማምረቻና የንግድ ቦታቸው፣ የመዝናኛ
ማዕከላቸው፣ የገንዘብ ተቋማትና የችርቻሮ ገበያ ቦታቸው ወዘተ ጭምር ነው፡፡ የመኖሪያ ቤት አገልግሎት
ዘርፍ ዕድገት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ከማድረጉም በተጨማሪ በግንባታ
እቃዎችና መሳሪያዎች፣ የቤት እቃዎችና ቁሳቁሶች አቅርቦት ዕድገት እንዲመዘገብ ከፍተኛ ሚና
ይጫወታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሲሉ ካላቸው ውሱን ገቢ
እንዲቆጥቡ በማበረታታት ገንዘባቸውን በመደበኛ የባንክ ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፍ ስለሚደረግ ፈጣንና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 35


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ተደማሪ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት በከተሞች እንዲመዘገብ ይረዳል፡፡ በአጠቃላይ አለም አቀፍ ጥናቶች
እንደሚጠቁሙት የቤት ልማት ዘርፍ ከከተሞች አጠቃላይ የኢንቨስትመንት ፍሰት ውስጥ ከ 20 እስከ 25
በመቶ ድርሻ እንዳለው ተረጋግጧል፡፡

ከመሬት አጠቃቀም አኳያ በአገራችን የከተሞች መዋቅራዊ ፕላን ላይ ሁለት ዓይነት አበይት የመኖሪያ ቦታ
አጠቃቀም ሲኖሩ እነሱም ለመኖሪያ አገልግሎት ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል የተከለለ የመሬት ዓይነት
(pure residence) አንደኛው ሲሆን ይህም ሌሎች አገልግሎቶችን በመቀላቀል ለምሳሌ የንግድ ሱቆች፣
ኪዎስኮች፣ ሱፐር ማርኬቶች እንዲሁም ከባድ የድምጽ ብክለት የማያስከትሉ የጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንዱስትሪዎች፣ የንግድና አገልግሎት ዘርፎችን ሊያካትት በሚችል ሁኔታ በማካተት የሚካለል ሲሆን
በተመሳሳይ ህንፃ ውስጥ ወይም ብሎክ ውስጥ ከመኖርያ ውጭ ያሉ አገልግሎቶችን የሚጨምር ቅይጥ
የቦታ ምደባ (mixed use) ሌላው ዓይነት ነው፡፡ በአንድ ከተማ ውስጥ አጠቃላይ ለግንባታ ከዋለው የመሬት
ስፋት ውስጥ እንደ ከተሞቹ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር ከ 40 እስከ 60 በመቶ
ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት ሽፋን እንዲኖረው ተደርጎ መሬት መያዝ አለበት፡፡ ለዚሁ አገልግሎት
የሚውለውን የመሬት መጠን ለመወሰን ከሚያስፈልጉ ነገሮች መካከል በከተማው በፕላን ዘመኑ ውስጥ
የሚያስፈልግ የተተነበየ የቤት ፍላጎት (በክምችት ያለውን ጨምሮ) በብዛት፣ በዓይነት፣ በመጠንና ተያያዠ
ጉዳዮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አገር አቀፍ የከተማ ልማት ፖሊሲዎችና
የስትራተጂ አቅጣጫዎችን እንዲሁም የየክልሎቹና የከተሞቹ ውስጣዊ የልማት ፖሊሲዎችና
አቅጣጫዎች ጭምር በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ስለሚኖራቸው ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት ተገቢውን
ትኩረት ሊያገኙ ይገባል፡፡

በሌላ በኩል የቤቶች አቀማመጥ በመኖሪያ አካባቢያቸው ወይም መንደራቸው ውስጥ ያላቸው ኢኮኖሚያዊ
ትስስርና ከሌሎች ዓይነት የከተሞች የመሬት አጠቃቀም ጋር ያላቸው መስተጋብር በአጠቃላይ የከተማው
ዕድገት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አለው፡፡ ለዚህም አንዱ መገለጫው የመኖሪያ ቤቶች ዓይነት በከተሞች
አጠቃላይ ቅርጽ ላይ የሚኖራቸው እንድምታ ነው፡፡ ይህም ሰማይ ጠቀስ ፎቆች የሚበዙበት ከተማ
በአንጻራዊነት በብዛት ራሳቸውን የቻሉ ግቢ ካላቸው የቤት ዓይነቶች ከሚገኙበት ከተማ በተሻለ መልኩ
ሰብሰብ ያለ የከተማ ቅርጽ እንዲኖረው ያስችላል፡፡ ይህም በከተሞች የትራንስፖርት ሥርዓት ላይ ቀጥተኛ
ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ በመሆኑም ከቤቶች ዓይነት አንጻር ወደ ጎን የተለጠጠ የከተማ ቅርጽ ያላቸው ከተሞች
ለመሠረተ ልማት አውታር ዝርጋታ ለከፍተኛ ወጪ ይዳርጋሉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ቅርጽ ባላቸው ከተሞች
ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች ለአላስፈላጊ የትራንስፖርት ገንዘብ ወጪና የጊዜ ብክነት ከማስከተሉም በላይ
በኢኮኖሚው ውስጥ የሚኖራቸውን ምርታማነት ዝቅተኛ እንዲሆን ያስገድዳል፡፡ ስለሆነም በመዋቅራዊና
መሰረታዊ የከተማ ፕላኖች ላይ ለመኖሪያ ቤቶች አገልግሎት እንዲውሉ የሚያዙ ቦታዎች በሁሉም
የከተማ አቅጣጫዎች ፍትሃዊ ስርጭት እንዲኖራቸው መደረግ አለበት፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 36


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሌላው ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ጉዳይ ቤቶች ካላቸው አካላዊ ግዝፈትና የውስጥ ክፍፍል (መጸዳጃ፣
ማብሰያ፣ መታጠቢያ፣ መኝታ ወዘተ) በተጨማሪ በቅጥር ግቢያቸውና በዙሪያቸው ወይም በአቅራቢያቸው
ከሚገኙ ሌሎች አገልግሎቶች ጋር መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ የውሃና ፍሳሽ፣
የመብራትና ስልክ አገልግሎት እንዲሁም ሁሉም የቤት መገንቢያ ቦታዎች ቢያንስ በአንድ አቅጣጫ ወደ
ዋና ጎዳና የመዳረሻ መንገድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በሌላ በኩል ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት እንዲውል
የሚመረጠው ቦታ የመሬት አቀማመጥ ተዳፋታማነቱ እጅግ ቢበዛ ከ 20 በመቶ በላይ መሆን የለበትም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በተቻለ መጠን ለከተሞች መስፋፋት ማነቆዎች ከሚሆኑ የተፈጥሮም ይሁን ሰው ሰራሽ
ክስተቶች ውጪ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህም ከጥቁር መረሬ አፈር፣ ከመሬት መንሸራተት፣ ከድንጋይ ናዳ፣
ከጎርፍ መጥለቅለቅ፣ ከረግረግማ ቦታዎች፣ ከትላልቅ የመብራት ኃይል ተሸካሚ ምሶሶዎች፣ ከአገር
ደህንነትና ወታደራዊ ተቋማት አካባቢ የራቁ መሆን ይገባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል አንድ አካባቢ ለመኖሪያ ሲዘጋጅ፤ በተዘጋጀው የሽንሻኖ መመሪያ መሰረት መሆን ይገባዋል፡፡
በመሆኑም የሚዘጋጁት የብሎክ ሰፈሮች እርዝማኔ በመሰረተ ልማት አውታር ዝርጋታ ወጪ ላይ ቀጥተኛ
ተጽዕኖ ስላላቸው ሽንሻኖው በጥንቃቄ መከናወን አለበት፡፡ ለውጤታማ የመሬት አጠቃቀም የአንድ ቦታ
መጠን አጭሩ ወርድ 6 ሜትር ሲሆን ተጓዳኝ ርዝመቱ ከ 12-30 ሜትር (ከወርዱ ከ 2-5 እጥፍ) ብቻ መሆን
ይገባዋል፡፡ የእግረኛ ነዋሪዎችንና ተሽከርካሪዎችን የትራፊክ እንቅስቃሴና ፍሰት ከማሳለጥ አኳያ
የሚዘጋጁት ብሎኮች እርዝማኔ ከ 80 ሜትር ያላነሰና ከ 150 ሜትር ያልበለጠ መሆን ይገባዋል፡፡ ሆኖም
አስገዳጅ ሁኔታዎች ማለትም በባህሪያቸው ሰፋፊ ቦታ የሚፈልጉ ትልልቅ ተቋማት በሚኖሩበት ወቅት
በተቋማቱ የቦታ ፈላጐት ስታንዳርድ መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እንደ ከተሞቹ ሁኔታ
በሄክታር ከ 200 እስከ 600 የቤቶች እፍግታ (net density) ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በአጠቃላይ ስለመኖሪያ ቤት
አገልግሎት ስናቅድ ለቤት ልማት ቦታ ከመለየትና ከመያዝ አንስቶ ማልማትን፣ ማቅረብን፣ ለተጠቃሚዎች
ማስተላለፍን፣ መጠገንና ማስተዳደርን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በጥልቀትና በተቀናጀ መልኩ በመመርመር
መሆን ይገባዋል፡፡ በአብዛኛው ሁኔታ የከተሞች የመንገድ ስፋት ከፍተኛ በሆነበት አካባቢ የመሬት ዋጋው
ከፍተኛ ስለሚሆን የቦታውን ጥቅም አሟጦ ለመጠቀም ከመንገዶቹ ስፋት መጨመር ጋር የመኖሪያ ቤቶቹ
ከፍታ በቀጥተኛ ሁኔታ ተያያዥ በመሆን ሊተገበር ይገባል፡፡ በስፋት የሚከናወኑ የጋራ መኖርያ ቤቶች
ግንባታ በሚከናወንበት ወቅትም የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ጥናት መደረግ አለበት፡፡

ለ. የቢዝነስ፣ ንግድና የገበያ አገልግሎቶች

የከተማ ፕላን ከሚያካትታቸው የመሬት አጠቃቀም ዓይነቶች ውስጥ አንዱ የቢዝነስ፣ የንግድ ማእከላትና
የገበያ ቦታዎች አገልግሎት በመባል የሚጠራው ሲሆን ይህም በውስጡ የተለያዩ ሱቆችና ሱፐርማርኬቶች፣
የገበያ ማእከላት፣ ለቢሮና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የንግድ ህንጻዎች፣ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 37


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ድርጅቶች፣ ሆቴሎች፣ ቡና ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ …ወዘተ ያጠቃለለ ነው። በአንድ የከተማ ፕላን
ዝግጅት ወቅት ለወደፊት ለከተማዋ ዕድገት ተብሎ ከሚያዘው ጠቅላላ ቆዳ ስፋት ውስጥ ለአነስተኛና
መካከለኛ ከተሞች ከ 5—10 በመቶ፣ ለትላልቅና ሜትሮፖሊታን ከተሞች ደግሞ ከ 10—20 በመቶ
የሚሆነው ቦታ ለዚሁ አገልግሎት መዋል እንዳለበት እየተዘጋጀ ባለው ስታንዳርድ ማኑዋል ላይ ተጠቅሷል።
በአጠቃላይ የቢዝነስ፣ የንግድና የገበያ አገልግሎቶች በከተሞች ውስጥ መስፋፋት የሚያመጡት የኢኮኖሚ
ዕድገትና እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀላል ለማይባል የሰው ሃይል የስራ ዕድል የሚፈጥሩ መሆናቸው
ግልፅ ነው፡፡ በዚህም መሰረት እንደ ከተማው መጠን በአንድ ከተማ ውስጥ በአንድ አካባቢ ተስፋፍቶ የሚገኝ
የማዕከል የንግድ ቀጠና (Central Business District) ወይም ከተማው ሰፊ ሲሆን የማዕከል የንግድ
ቀጠናውን ጨምሮ በተለያዩ የከተማ ንዑሳን ክፍሎች የተለያዩ የንግድ ማዕከላት እንዲሁም በየመንደር
(neighborhood) ደረጃ እንዲኖሩ ተደርገው በከተማው ፕላን ውስጥ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ስለዚህ ለነዚህ
አገልግሎቶች ከላይ በተገለፀው ቁጥር መሰረት ቦታ መከለልና መያዝ እንደሚያስፈልግ የታወቀ ሆኖ በዚህ
ውስጥ የሚካተቱትን አገልግሎቶች እንደሚከተለው በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

ሱቆችና ሱፐርማርኬቶች

ህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ተግባር አድርጎ ከሚጠቀምባቸው አገልግሎቶች መካከል ሱቆችና


ሱፐርማርኬቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ስለዚህ አንድ የከተማ ፕላን በሚዘጋጅበት ወቅት እነዚህን አገልግሎቶች
በቀላሉ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ሊሆኑ በሚችሉበት አካባቢ መቀመጥ መቻል አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት
ለአገልግሎቶቹ የሚሆኑ ቦታዎችን በመያዝ በዋና ዋና መጋቢ መንገዶች ተከትሎ፣ ለዋና መንገድ ቅርብ
በሆኑ ቦታዎች፣ በመኖሪያ አካባቢዎች መሀልና በማእዘን ቦታዎች /Block corners/፣ የመሬት ጠቀሜታ
ከፍተኛ በሆነበት አካባቢ እንዲሁም በመገናኛ መንገዶች ማስተናገድ ይቻላል፡፡

ሆቴሎች፣ ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች

ለአንድ የከተማ ነዋሪ ህዝብና ወደ ከተማዋ ለሚመጡት እንግዶች ከሚያስፈልጓቸው አገልግሎቶች


መካከል አንዱ የሆቴሎች፣ ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች መኖር ነው፡፡ በመሆኑም ለከተማዋ ነዋሪዎች የስራ
ዕድል የሚፈጥሩና ለከተማዋ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት
የከተማ ፕላኑ ለነዚህ አገልግሎቶች የሚውሉ ቦታዎችን በሚመረጡ የከተማ ማዕከሎች አካባቢና የህዝብ
እንቅስቃሴ የሚጎላባቸው አካባቢዎች በቂና አመቺ በሆነ አኳኋን መከለል ይኖርበታል፡፡ አቀማመጣቸውም
ዋና ዋና መንገድ የተከተሉ፣ ለዋና መንገድ ቅርብ የሆኑ፣ ከመኖሪያ አካባቢዎች በጣም ያልራቁና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 38


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከባህርያቸው አንጻር እንደ አስፈላጊነቱ ከመሀል ከተማ ወጣ ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በተለይ ደግሞ ለባለ
ኮከብ ሆቴሎችና ለትላልቅ ምግብ ቤቶች እንደየ ፕሮጀክታቸው ሁኔታ እየታየና እንደአስፈላጊነቱ
በሚለያይ የቦታ መጠን መሰረት ተደርጎ መስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡ እያንዳንዳቸው አገልግሎቶች ደግሞ
ከንፅህና ጋር በተያያዘ የየራሳቸው የሆነ መፀዳጃ ቤትና የፍሳሽ ማጠራቀሚያ እንዲሁም የመኪና ማቆምያ
ቦታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ባንኮችና የኢንሹራንስ ድርጅቶች

ባንኮችና የኢንሹራንስ ድርጅቶች ለህብረተሰቡ ከሚያስፈልጉ አገልግሎቶች መካከል ናቸው፡፡ በዚህም


መሰረት ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለአንድ ከተማ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያበረክቱት
አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ለነዚህ ድርጅቶች በከተማ ፕላን ስራ ላይ የመስሪያ ቦታ በበቂ ሁኔታ መከለል
አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ስለሆነም የከተማውን ዋና ዋና መንገድ በመከተል፣ ማእከላዊ የንግድ ቀጠናዎች
/Central Business District/ በሆኑ የከተማው አካባቢዎች፣ ለዋና ዋና መንገድ ቅርብ በሆኑ አካባቢዎችና
በመሳሰሉት በማድረግ ማስተናገድ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ሊጠቀሙባቸው
የሚችሉ የኤቲኤም /ATM/ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች በከተማው ፕላን ላይ መቀመጥ እንዳለባቸውና
እነዚህም በትላልቅ የገበያ ማእከላት፣ በዋና ዋና መንገዶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግቢ ውስጥ፣ የሕዝብ
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው መንገዶች ታዋቂ በሆነ ህንፃ ማስተናገድ ይቻላል፡፡

የገበያ ማእከላት

ለአንድ ከተማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ዕድገት ከሚያስፈልጉ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች አንዱ የገበያ
ቦታዎች መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የገበያ ቦታዎቹ ለነዋሪዎቹ በቀላሉ ተደራሽ የሚሆኑና
ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም በከተማው ፕላን ስራ ለነዚህ አገልግሎቶች የሚያዙ
ቦታዎች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የገበያ ማእከላቱ በሁለት የተከፈሉ ናቸው፡፡ እነሱም
የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች የሚገዙባቸውና የሚሸጡባቸው እና የእንስሳት የገበያ ቦታዎች ሲሆኑ ደረጃቸው
እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡

የሸቀጣሸቀጥ ገበያ፡ የመጀመሪያ ደረጃ ገበያ /Primary market/ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት ከ 7—11
ሄክታር ሆኖ ለትላልቅ ሱፐር ማርኬቶች፣ ለተለያዩ ሱቆችና ለመሳሰሉት የሚያገለግል እስከ አምስት ፎቅ
ያላቸው ህንጻዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ ገበያው ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ገበያተኞችን
የሚያስተናግድና አቀማመጡም ንግድና ቢዝነስ በሚከናወንባቸው ስፍራዎች እንዲሁም ለዋና መንገድና
ለህዝብ ትራንስፖርት ቅርብ የሆነ ቦታ መሆን ይገባዋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 39


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሁለተኛ ደረጃ ገበያ /Secondary market/ ደግሞ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት ከ 4—6 ሄክታር ሆኖ
ለትናንሽ ሱፐር ማርኬቶችና ለመሳሰሉት የሚያገለግል እስከ ሦስት ፎቅ ያላቸው ህንጻዎችን
የሚያጠቃልል ነው፡፡ ከ 2.5—7 ኪሎ ሜትር ባለው ዙሪያ ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች
የሚጠቀሙበትና አቀማመጡም በመሀል ከተማውና እንዲሁም ለዋና መንገድና ለህዝብ ትራንስፖርት
ቅርብ የሆነ ቦታ መሆን አለበት፡፡

ሦስተኛ ደረጃ ገበያ /Tertiary market/ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት ከ 1—2.5 ሄክታር ሆኖ በከፊል
የተሸፈነና ክፍት የሆነ እስከ ሦስት ፎቅ ያላቸው ህንጻዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ ከ 1—2 ኪሎ ሜትር
ባለው ዙሪያ ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙበትና አቀማመጡም ለመጋቢ መንገዶች
ቅርብ የሆነና በከተማው ውስጥ መሀል ቦታ ሲሆን አራተኛ ደረጃ ገበያ /Local market/ ደግሞ
የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት ከ 0.25—0.5 ሄክታር ሆኖ በከፊል የተሸፈነና ክፍት የሆነ ነው፡፡ ከ 0.5—1 ኪሎ
ሜትር ባለው ዙሪያ ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙበትና አቀማመጡም በመኖሪያ
አካባቢዎች ውስጥ መሆን አለበት፡፡ በአጠቃላይ የገበያ ማእከላቱ በቀላሉ በድምፅ ሊረበሹ ከሚችሉ
ተቋማት ማለትም ከትምህርት ቤቶች፣ ከቤተ መጽሐፍቶች፣ ከሆስፒታሎችና…ወዘተ መራቅ አለባቸው፡፡
የሚመረጥላቸው ቦታም በተቻለ መጠን ሜዳማ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም እንደ የከተሞቹ ባሕሪ
ለመኪናና ቀላል የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች በእንሰሳት ለሚሳቡ ተሽከርካሪዎች ማቆምያ እንዲሁም
ለትራንስፖርት አገልግሎት ለሚውሉ እንሰሶች ቦታ ሊጠበቅላቸው ይገባል፡፡

የእንስሳት ገበያ፡ የከብት ገበያ /Cattle market/፦ ለገበያ የሚቀርቡ የተለያዩ እንስሳት የሚስተናገዱበት ቦታ
ነው፡፡ እነዚህም በአራት ደረጃ ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ የእንስሳት ገበያ /Primary
market/ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት 2.17 ሄክታር ሆኖ ከ 7‚000 በላይ እንስሳት የማስተናገድ አቅም
ሲኖረው ሁለተኛ ደረጃ የእንስሳት ገበያ /Secondary market/ ደግሞ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት ከ 1.17-
1.51 ሄክታር ሆኖ 5‚060 እንስሳት የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል፡፡ ሦስተኛ ደረጃ የእንስሳት ገበያ /Tertiary
market/ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት ከ 0.62—0.83 ሄክታር ሆኖ 3‚040 እንስሳት የማስተናገድ አቅም
ሲኖረው አራተኛ ደረጃ የእንስሳት ገበያ /Local market/ ደግሞ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት 0.42 ሄክታር
ሆኖ 1‚520 እንስሳት የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል፡፡ በአጠቃላይ የእንስሳት ገበያዎቹ አቀማመጣቸው
የከተማውን ወሰን ወይም ጫፍ የያዙና የመኪና መንገድና የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያሉባቸው፣ ቄራ አጠገብ
የሆኑ፣ እንስሳቶቹ በብዛት የሚመጡበት አካባቢ ቅርብ የሆነና ከተማው እየሰፋ ሲሄድ ደግሞ በየአቅጣጫው
በማድረግ፣ ከትምህርት ቤት፣ ከጤና ተቋም፣ ከአምልኮ ቦታ፣ ከመኖሪያ አካባቢ የራቁና በጣም ተዳፋት
ያልሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 40


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሐ. ማሕበራዊ አገልግሎቶች

የከተማ ማሕበራዊ አገልግሎቶች በሚል የሚካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ለከተማዋም ሆነ ለአጎራባች የገጠርና


ከተማ አካባቢ ነዋሪ ህዝብ የሚሰጡ እንደ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች (የስፖርት፣
የመዝናኛ፣ የእምነትና የዘላቂ ማረፊያ ስፍራዎች) እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ናቸው፡፡

በመሬት አጠቃቀም ፕላን በእነዚህ አገልግሎቶች የሚሸፈነው ቦታ ከአጠቃላይ የከተማው የመሬት ስፋት
ከ 10 በመቶ የሚበልጥና አልፎ አልፎም እንደከተማዋ እድገት ደረጃ ከ 20 በመቶ ሊዘል የሚችል ሲሆን
ምናልባት ዘርዘር ሲደረግ ለአነስተኛ (small towns)፣ መካከለኛ ከተሞች (middle towns) እና ለትላልቅ
ከተሞች (large towns) ከ 5-10 በመቶኛ እንዲሁም ለከፍተኛ ከተሞች እና ከከተማ ውጭ ያሉትን
አካባቢዎች የሚያጠቃልሉ/የሚያስተዳድሩ ከተሞች ከ 10-20 በመቶኛ ይሆናል፡፡

በማህበራዊ አገልግሎቶች ውስጥ የሚጠቃለሉ የትምህርት፣ የጤና፣ የስፖርትና የመዝናኛ አገልግሎቶች እና


የእምነት ተቋማትና የዘላቂ ማረፊያ ሥፍራዎች ፕላን በሚዘጋጅለት ከተማ፣ በአጎራባች ከተሞችና የገጠር
አካባቢዎች ለሚገኙ በተለያየ ዕድሜና ማህበራዊ ሁኔታዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት
የሚሰጡ ናቸው፡፡ የእነዚህን ተቋማትና አገልግሎቶች ቁጥር፣ ስርጭትና እንዲሁም የአገልግሎቶቹ አሰጣጥ
ጥራትና ውጤታማነትን በተመለከተ ጥናታዊ ትንተና በማድረግ አገልግሎቶቹ ከህዝቡ ብዛት አኳያ
ተመጣጣኝ ቁጥርና ፍትሃዊ የቦታ ስርጭት እንዲኖራቸውና የአገልግሎት አሰጣጣቸውም የተሻለ ጥራት
እንዲኖረው ማስቻል አስፈላጊና ወሳኝም ነው፡፡

ከላይ ለመግልጽ እንደተሞከረው በማህበራዊ አገልግሎት ስር የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች ማህበረሰባዊ


አገልግሎቶች (የስፖርት፣ የመዝናኛ፣ የእምነትና የዘላቂ ማረፊያ ስፍራዎች) እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት
አገልግሎቶች ያሉ ሲሆን እያንዳንዱ አገልግሎት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የትምህርት አገልግሎት

ትምህርት ቤቶች በክፍል ደረጃዎች የሚከፋፈሉ ሲሆን ይኸውም የቤተ-ሕጻናትና የአጸደ-ሕጻናት፣


የአንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የመሰናዶና የሙያ
ስልጠና ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ከአጸደ ህጻናት ደረጃ በላይ የሆኑ ት/ቤቶች የስፖርት ሜዳዎች፣ ቤተ
መጽሀፍት፣ አጥር፣ መጸዳጃ ቤት፣ የመብራት፣ የውሃ፣ የቴሌፎን አገልግሎቶች ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን
በአጸደ ህጻናት ደረጃ ያሉ ደግሞ ከላይ ከተዘረዘሩት አገልግሎቶች በተጨማሪ የህጻናት መዝናኛ አገልግሎት
ሊኖራቸው ይገባል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 41


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ትምህርት ቤቶች አቀማመጣቸው የጸሀይ መውጫን ግምት ውስጥ ያስገባ፣ ዋናው መግቢያ በር ከዋና
መንገድ ትይዩ ያልሆነና ተማሪዎች ትራፊክ የሚበዛበትን መንገድ ሳያቋርጡ ወደ ት/ቤት የሚገቡበትና
የሚወጡበት ሁኔታን ግምት ውስጥ ያስገባ፣ ተደራሽና ፀጥታማ አካባቢ የሆነ፣ ሜዳማ የመሬት አቀማመጥ
ያለው፣ ከተቻለ በአካባቢው መጫወቻና ፓርክ የሚገኝበት መሆን አለበት፡፡

የቤተ-ሕጻናት እና የአጸደ ህጻናት አገልግሎት፡ የቤተ-ሕጻናት አገልግሎት በአራት መቶ ሜትር የአገልግሎት


ሽፋን (catchment area) አካባቢ ውስጥ ለሚገኙ ለሁለትና ለሶስት ዓመት ዕድሜ ሕጻናት የትምህርት ነክ
ጨዋታዎች የሚሰጥበት የአገልግሎት አይነት ነው፡፡ የአጸደ ህጻናት አገልግሎት ከ 4-6 ዓመት ዕድሜ ላሉ
የአካባቢ ሕጻናት የትምህርትና የጨዋታ አገልግሎት የሚሰጥበት ሲሆን የቦታ አቀማመጡም በመኖሪያ
አካባቢና በአንድ ኪሎ ሜትር አገልግሎት ሽፋን አማካይ ቦታ መሆን ይኖርበታል፡፡ ቤተ-ሕጻናት በተመሳሳይ
አካባቢና አቀማመጥ ወይም በአጸደ-ሕጻናት ቅጥር ግቢ ውስጥና ከመስሪያ ቦታዎች አቅራቢያና እንዲሁም
ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ ከበካይ ድምጾችና ከጤና አገልግሎቶች ቢያንስ በ 100 ሜትር ያህል ርቀት ሊሰራ
ይገባዋል፡፡ የቦታ ስፋታቸውን በተመለከተ ለቤተ-ሕጻናት ከ 70-175 ሜትር ካሬ ለአጸደ-ሕጻናት ደግሞ
ከ 500-3000 ሜትር ካሬ ቦታ እንዲሰሩ ይፈቀዳል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ 7-14 ዓመት ዕድሜ ክልል ለሚገኙ
ታዳጊ ሕጻናት ከ 1 ኛ-8 ኛ ክፍል የትምህርት አገልግሎት የሚሰጥበት ነው፡፡ የቦታ አቀማመጡም በመኖረያ
አካባቢ ባሉ መጋቢ መንገዶች አቅራቢያ በሁለት ኪሎ ሜትር የአገልግሎት ሽፋን (catchment area)
አማካይ ቦታ ሆኖ ከአውራ ጎዳናዎች፣ ከቡና ቤቶች፣ የትራፊክ መጨናነቅ ካለባቸውና ከገበያ ቦታዎች፣
ድምጽ ካላቸው ኢንዱስትሪዎች፣ ከጤና ተቋማት፣ ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ፣ ከወንዝ፣ ከሸለቆዎችና ከቪዲዮ
ቤቶች ቢያንስ በ 100 ሜትር ያህል መራቅ ሲኖርበት የግቢው ስፋትም ከ 1.5 – 2.5 ሄክታር ሆኖ በውስጡ
የመጫወቻ ቦታዎችን ያካተተ መሆን አለበት፡፡

የመጀመሪያ ሳይክል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ የመጀመሪያ ሳይክል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ከ 15-16 ዓመት ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ታዳጊ ሕጻናት የ 9 ኛ-10 ኛ ክፍል የትምህርት አገልግሎት
የሚሰጥበት ነው፡፡ የቦታ አቀማመጡም በመኖረያ አካባቢ ባሉ መጋቢ መንገዶች አቅራቢያ ከሶስት እስከ
አምስት ኪሎ ሜትር አገልግሎት ሽፋን አማካይ ቦታ ሆኖ ከአውራ ጎዳናዎች፣ ከቡና ቤቶች፣ የትራፊክ
መጨናነቅ ካለባቸውና ከገበያ ቦታዎች፣ ድምጽ ካላቸው ኢንዱስትሪዎች፣ ከጤና ተቋማት፣ ከቆሻሻ
ማጠራቀሚያ፣ ከወንዝና ሸለቆዎች እንዲሁም ከተለያዩ ወጣቱን ከሚያማልሉ ተቋማት ቢያንስ በ 100
ሜትር ያህል ርቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ የትምህርት ቤቱ መጫወቻ ቦታዎችን ጨምሮ የግቢው ስፋት ከ 3-6
ሄክታር መሆን አለበት፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 42


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የመሰናዶና ትምህርት ቤት፡ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ከ 17-18 ዓመት ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ታዳጊ
ወጣቶች ከ 11 ኛ-12 ኛ ክፍል የትምህርት አገልግሎት የሚሰጥበት ነው፡፡ የቦታ አቀማመጡም በዋና መጋቢ
መንገዶች አቅራቢያ ከ 3-5 ኪሎ ሜትር የአገልግሎት ሽፋን ክልል ውስጥ ሆኖ በመገናኛ መንገዶች፣ በህዝብ
ትራንስፖርት፣ መና þ ሪያና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትና የመሰረታዊ አገልግሎቶች በሚኖሩበት
አካባቢ ነው፡፡ አገልግሎቱ ከፍተኛ ድምጽ ካላቸው ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች በካይ እንቅስቃሴዎች፣ ለአደጋ
ከተጋለጡ አካባቢዎችና ከቆሻሻ ማጠራቀሚያ ስፍራዎች መራቅ ሲኖርበት የግቢው ስፋትም ከ 2.5-6
ሄክታር መሆን አለበት፡፡

ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ቤት፡ የቴክኒክ ትምህርት ቤት ከ 17-18 ዓመት ዕድሜ ክልል ለሚገኙ ወጣቶች
ከ 10 ኛ ክፍል በላይ የሙያ ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥበት ነው፡፡ አገልግሎቱ እንዲሰጥ የሚፈለግበት የቦታ
አቀማመጥ ከሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርብ የእግር ርቀት ያለ በ 3-5 ኪሎ ሜትር የአገልግሎት
ሽፋን አካባቢ ሆኖ ከዋና የትራፊክ ጣቢያዎች በ 100 ሜትር የራቀና በስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት
አቅራቢያ የሚመረጥ ሆኖ የግቢ ስፋቱም ከ 2.5-6 ሄክታር መሆን ይኖርበታል፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፡ በፕላን ዝግጅት ጊዜ ለሁሉም ከተሞች ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቦታ
አይያዝም፡፡ ምክንያቱም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁሉም የአገሪቱ ከተሞች መገንባት ስለማይቻል
ነው፡፡ ነገር ግን ፍላጎቱ ኖሮ የቦታ ጥያቄ ሲነሳ በፕላን ላይ ላልታሰቡ አገልግሎቶች የሚውል ቦታ ስለሚያዝ
ከነዚህ ቦታዎች ውስጥ ተስማሚውን በመምረጥ ጥያቄውን ማስተናገድ ይቻላል፡፡

የጤና አገልግሎት

በተለያየ ደረጃ የሚጠቀሱ የጤና ተቋማት ያሉ ሲሆን እነሱም የጤና ኬላ፣ የጤና ጣቢያ የጤና ማዕከል
/Health Center/፣ ዲስትሪክት ሆስፒታል፣ ሪጅናል ሆስፒታል፣ ሪፈራል ሆስፒታል እና ስፔሻላይዝድ
ሆስፒታል ናቸው፡፡

በሁሉም ደረጃ ያሉ ከፍተኛ የጤና ተቋማት በርካታ ሕዝብ በሚኖርበት ነገር ግን ከመሃል የከተማ ክፍል
ወጣ ባለ አካባቢ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች በተሟሉባቸውና ከቆሻሻ ማከማቻና ከድምጽ ብክለት ነጻ
ሆነው ከህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርብ የእግር ርቀት ባሉ የመጋቢ መንገዶች መዳረሻ አቅራቢያ
እንዲቋቋሙ ይፈለጋል፡፡ ተቋማቱን ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸው የቦታ ስፋት እንደየደረጃቸው የሚለያይ
ሲሆን፣ የተቋማቱ ግንባታ ቦታ አቀማመጥ ደልዳላና ለተፋሰስ አመቺነት ሲባል በመጠኑ ቆልቆል ያለ ስፍራ
መሆኑ ይመረጣል፡፡ በቂ የትራንስፖርት አገልግሎትና ከጎርፍና ከማንኛውም ዓይነት የአየር፣ የውሃና የአካባቢ
ብክለት የጸዳ ቦታ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 43


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የጤና ኬላ /Health Post/ እና የጤና ጣቢያ /Health Center/ በአነስተኛ መሃከለኛና ትላልቅ ከተሞች
ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሲሆኑ ጤና ኬላ ከ 3,000 - 5,000 እንዲሁም ጤና ጣቢያ ደግሞ
15,000- 25,000 ለሚደርስ ህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ይጠበቃል፡፡ የከተማው ነዋሪ ህዝብ በጨመረ
ቁጥር በዚሁ ስሌት ሊያስተናግዱ ለሚችሉ ተቋማት ቦታ ሊያዝ ይገባል፡፡ በሁለቱም ደረጃ የሚሰጡ
አገልግሎቶች በርካታ ሕዝብ በሚኖርበትና ጸጥታ በሰፈነበት የመኖሪያ አካባቢ ባሉ የመንገድ መገናኛ ወይም
ግንባር ቦታዎች ሆነው የግቢ ስፋታቸው ለጤና ኬላ በ 600 ካሬ ሜትር ለጤና ጣቢያ ደግሞ 10,000 ካሬ
ሜትር መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ከጤና ጣቢያ በላይ የሚሰጡ አገልግሎቶች የሆስፒታል አገልግሎቶች ሲሆኑ በሶስት ደረጃዎች ይከፈላሉ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመካከለኛ ከተሞች ከ 60‚000 እስከ 100‚000 ለሚደርስ ህዝብ በትላልቅ
ከተሞች ደግሞ ለ 40,000 ህዝብ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥበት ሲሆን ስፋቱም 15,000 ካሬ ሜትር
ማነስ የለበትም፡፡ ጠቅላላ እና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች በትላልቅ ከተሞች ብቻ የሚኖሩ ሲሆን
የሚያገለግሉትም ህዝብ ብዛት በቅደም ተከተል ከ 1,000,000 እስከ 1,500,000 እና ከ 3,500,000 እስከ
5,000,000 ሆኖ ከፍተኛ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ የሚቋቋም ነው፡፡ ሆስፒታሎቹ እያንዳንዳቸው
30‚000 ስኩዌር ሜትር ያላነሰ ስፋት ያለው ቦታ እንደሚያስፈለግ አሁን በቅርቡ /2004 ዓ.ም/ ከጤና
ጥበቃ ሚ/ር የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

መ. ሌሎች ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶች

የቄራ አገልግሎት

የተለያዩ የቄራ አገልግሎቶች በአንድ ላይ፣ በተያያዥ ግቢ ወይም በተለያዩ ቦታዎች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ ሥጋ
ተመጋቢውን ህብረተሰብ ከምግብ ወለድ የጤና ችግሮች ለመከላከል ደረጃውን የጠበቀ የቄራ አገልግሎት
በከተሞች ውስጥና በአካባቢው እንዲስፋፋ ማድረግ ይገባል፡፡ የቄራዎች የእርድ መጠንና የሚሰጡትን
የአገልግሎት ዓይነት መሰረት በማድረግ አነስተኛ፣ መካከለኛ፣ ከፍተኛ፣ የኤክስፖርት እንዲሁም የበግና ፍየል
ተብለው ይከፈላሉ፡፡ የአመት የዕርድ መጠናቸው ከ 100,000 እንሰሳት በላይ የሆኑ ከተሞች የአካባቢ ተፅእኖ
ግምገማ ጥናት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡

አነስተኛ ቄራ በአማካኝ በቀን ከ 50-120 የዕርድ ከብት እንዲሁም እስከ 300 የፍየልና የበግ የእርድ
አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ከ 1-1.5 ሄክታር ቦታ ያስፈልገዋል፡፡ መካከለኛ ቄራ በቀን እስከ 400 የዕርድ ከብት
እንዲሁም እስከ 800 የበግና የፍየል እርድ የሚያከናወንበት ሲሆን ከ 4-5 ሄክታር ቦታ ያስፈልገዋል፡፡ ከፍተኛ
ቄራ በቀን እስከ 4,000 የከብት እንዲሁም እስከ 5,000 ፍየልና በግ የእርድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ከ 15-
20 ሄክታር ቦታ ያስፈልገዋል፡፡ ይህ ቄራ 4 የዕርድ መስመር ኖሮት እያንዳንዱ በሰዓት እስከ 150 ከብት እና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 44


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

እስከ 1000 በግና ፍየል ዕርድ ይከናወንበታል፡፡ የኤክስፖርት ቄራ ከከፍተኛ ቄራ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ በአንድ
የእርድ መስመር በሰዓት እስከ 240 የከብት እና እስከ 2,000 የበግና የፍየል ዕርድ ሊከናወን እንደሚችል
ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በአጠቃላይ በከተማ ፕላን ላይ ለቄራዎች የሚያዘው ቦታ በከተማ ዳርቻ፤ ከመኖሪያ አካባቢ፣ ከት/ቤት፣
ከማምለኪያ ቦታዎች፣ ወዘተ የራቀ፤ ከከተማው ማስፋፊያ ውጭ የሆነ፤ በቂ የመሠረተ ልማት አቅርቦት
ያለው (መብራት፣ ውሀና መንገድ)፤ ከውሃ ምንጮች አካባቢ ቢያነስ 2 ኪ.ሜ. ርቀት ያለው፤ ከአውሮፕላን
ማረፊያ (መነሻና ማረፊያ አቅጣጫን አካቶ) በሲቪል አቬሽን ስታንዳርድ መሰረት በቂ ርቀት ያለው፤
የነፋስን አቅጣጫ ያገናዘበ፤ ወዘተ መሆን አለበት፡፡ ሆኖም ግን ቄራን ከአካባቢ ንጽህና አንጻር በአግባቡ
ማስተዳደር ከተቻለና በአካባቢ ላይ መጥፎ ሽታ የማያመጣ እንዲሁም የእርድ ተረፈ ምርትን
የሚለቃቅሙ በሰማይ ላይ የሚያንዣብቡ አእዋፋትም ሆነ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ የቤትም ሆነ የዱር
እንስሳትን ወደ ግቢው የማይስብ ከሆነ ከላይ ከተዘረዘሩት አገልግሎቶች መራቅ ላያስፈልገው ይችላል፡፡

የእሳት አደጋ ጣቢያ

የእሳት አደጋ ጣቢያ በአንድ ከተማ ወይም በከተማ ክፍል ውስጥ የሚደርስ የእሳት አደጋ/ቃጠሎና ተዛማጅ
አደጋዎችን ለመከላከል የሚቋቋም ድርጅት ነው፡፡ በከተማ ፕላን ውስጥ ከ 2500 - 5000 ካ.ሜ ቦታ
ይያዝላቸዋል፡፡ በትልልቅ ከተሞች ከአንድ በላይ ጣቢያዎች የሚኖሩ ከሆነ አንዱ ጣቢያ ከ 2.5-5 ኪ.ሜ
ርቀት ውስጥ ላሉ አካባቢዎች እንደሚያገለግል ታሳቢ ተደርጎ ቦታ ይያዛል፡፡

የህዝብ መጸዳጃና ገላ መታጠቢያ

የከተማ የህዝብ መጸዳጃና መታጠቢያ አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ባለመኖሩ ምክንያት በአሳቻ ቦታዎች እና
በወንዝ አካባቢዎች የመፀዳዳት ሁኔታ ይታያል፡፡ ይህ ችግር አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞቻችን
በእጅጉ ጎልቶ የሚታይ ችግር ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት አገልግሎቶች ከተወሰኑ አመታት በፊት በተለይም
ከደርግ አገዛዝ ቀደም ባለው የንጉሱ ዘመን ቢያንስ በትላልቅ ከተሞች በተወሰነ ደረጃ በተለያዩ የከተሞች
አካባቢ ተገንብተው አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ቢሆንም ከጊዜ በኋላ እየፈራረሱ አገልግሎት መስጠት
ማቋረጥ ብቻ ሳይሆን ቦታዎቻቸውም ለሌሎች አገልግሎቶች እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

የኋላኋላም አንዳንድ መንግስታዊ ያልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በዚህ ላይ ትኩረት ሰጥተው በተለያዩ
የከተማ አካባቢዎቸ በተለይም በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሚበዙባቸው አካባቢዎች
በርካታ የመጸዳጃ ቤት አገልግሎቶችን ገንብተው ለአካባቢው ማሕበረሰብ በማስረከብ አገልግሎት
እንዲሰጡ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ይህ ዓይነት ጥረት አልፎ፣ አልፎ በመደረግ ላይ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 45


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሲሆን ተጠናክሮ በስፋት መቀጠል ያለበት መሆኑም በአብዛኛው ሕብረተሰብ ዘንድ ግንዛቤ እያገኘ
መጥቷል፡፡

የህዝብ ገላ መታጠቢያ አገልግሎቶችን በተመለከተ በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ በተለያዩ የከተማ
አካባቢዎች የግል የገላ መታጠቢያ ቤቶች ተከፍተው በመጠነኛ ዋጋ አገልግሎት የሚሰጡበት ሁኔታ ያለ
ቢሆንም አገልግሎቱን ከሚፈልገው የከተማ ነዋሪ ህብረተሰብ ብዛት አኳያ ከቁጥርም የሚገቡ አይደሉም፡፡
በአሁን ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ ያሉ አብዛኞቹ ድርጅቶች ቀስ በቀስ የአገልግሎት ዋጋቸውን
በመጨመራቸው ምክንያት ሕብረተሰቡ በተለይ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ያለውና ቤት አልባው ክፍል በአቅሙ
ከፍሎ ለመጠቀም በማይችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ችግሩ አሳሳቢና ሰፊ የመንግስት ትኩረት እንዲያሻው
አድርገውት ይገኛሉ፡፡

የከተማ የህዝብ መጸዳጃ አገልግሎቶች ሊስፋፉባቸው የሚገቡ ቦታዎችን በተመለከተ ቦታዎቹን ለመለየት
የተለያዩ ባህርያትን ማጤን የሚያስፈልግ ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ሕዝብ ዘወትር በብዛት
በሚታይባቸው አካባቢዎች ማለትም የሕዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ ጣቢያዎችና የተሽከርካሪ ማቆሚያ
ፓርኮች፣ የከተማና ክፍለ ከተሞች ማእከላዊ አካባቢዎች፣ የገበያ ቦታዎችና የአካባቢ ንግድ ማዕከሎች
ወይም መደብሮች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ስቴዲየም፣ ፓርኮች፣ ወዘተ… ያሉበት አካባቢዎች እንዲሁም
እፍግፍግ ያሉ መኖሪያ ቤቶች በሚገኙበት አካባቢ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኝ የሕብረተሰብ
ክፍል በየመንደሩ የጋራ መጸዳጃ ቤቶች ያስፈልጋሉ፡፡

የህዝብ ገላ መታጠቢያ አገልግሎቶች ደግሞ በመኖሪያ ቤቶች እንዲሁም በስፖርት ማዘውተሪያ አካባቢዎች
የሚያስፈልጉ ሲሆን በተለይ የከተማው አየር ጸባይ ሞቃት ከሆነ በየቀበሌው ቢያንስ አንድ የጋራ የገላ
መታጠቢያ የሚያሰፈልግ ሲሆን ለገላ መታጠቢያም ሆነ ለመጸዳጃ አገልግሎት የሚያዙ ቦታዎች ለወንጀል
አመቺ ያልሆኑ በግልጽ የሚታዩ ከመጠጥ ውሃ ጉድጓዶች የራቁ መሆን አለባቸው፡፡

መ. አረንጓዴና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች

አረንጓዴ ቦታዎች

የከተማ አረንጓዴ ቦታዎች ልማት በተለያዩ አገሮች የተለያየ የትርጉም፣ የይዘትና የመጠን ልዩነት ያለው
ቢሆንም በአገራችን ሁኔታ ይዘቱ የተለያዩ ፓርኮችን፣ የሠፈር ውስጥና የአካባቢ (neighbourhood)
አረንጓዴ ቦታዎችን፣ የእግረኛና ዋና ዋና የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ አካፋዮችን፣ አደባባዮችን፣
መናፈሻና መዝናኛ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎችን፣ የወንዝና የሐይቅ ዳርቻዎችን፣ የተለያዩ
ተቋማት/ድርጅቶች ግቢዎች፣ በመኖሪያ ቤት ግቢዎች ውስጥ የሚገኙ አረንጓዴ ቦታዎችን፣ የዘላቂ ማረፊያ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 46


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ቦታዎችን፣ የከተማ እርሻን፣ የችግኝ ማፍያዎች፣ የደን/ዛፍ ቦታዎችን፣ የአገልግሎት መለያ ቦታዎችን
(buffer zone)፣ ጥብቅ ቦታዎችንና ተዳፋትና ተራራማ ቦታዎችን ልማት ያጠቃልላል፡፡

አረንጓዴ ቦታዎች ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር በትንሽ ቦታ ላይ ተፋፍጎ/ተሰባስቦ በሚኖርባቸው ከተሞች እንደ
መተንፈሻ ሳንባ ከማገልገላቸው በተጨማሪ የተለያዩ ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊ፣ አካባቢያዊና ኢኮሎጂአዊ
ፋይዳቸው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ተገቢውን የአረንጓዴ እጽዋት ሽፋን የሌላቸው ከተሞች በበረሃ ውስጥ
ከተገነባ የህንጻ ስብስብ ተለይተው የማይታዩና ለነዋሪዎቻቸው የማይመቹ ናቸው፡፡ አረንጓዴ እጽዋት
የከተሞችን አየር ንብረት በማሻሻል ረገድ ምትክ የለሽ ሚና አላቸው፡፡ በተመሳሳይም አረንጓዴ እጽዋት
የከተሞችንም ውበት በመጨመር ለነዋሪዎቻቸው ምቾትንና እርካታን ይጨምራሉ፡፡ ስለዚህ እየጨመረ
የመጣውን የከተሞችን የአየር ንብረት ሙቀት (Urban Macro Climate) ለማሻሻል በከተሞች አረንጓዴ
ቦታዎችን በመከለል ማልማት ያስፈልጋል፡፡ ለማንኛውም ከተማ ወይም ጥንስስ ከተማ ፕላን ሲዘጋጅ
የከተማውን ኢኮሎጂያዊ ሥነምህዳር እና የከተሞቹን ዕድገትና ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ የአረንጓዴ
ቦታዎች መያዝ ይገባል፡፡ የአረንጓዴ ቦታዎች መጠንም ለእያንዳንዱ ነዋሪ ከ 9 ካሬ ሜትር ያነሰ መሆን
የለበትም፡፡ በከተማ ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችም በተቻለ መጠን ለአረንጓዴ ልማት መጠበቅ ተመራጭ
ይሆናል፡፡ ለከተማው ውበትም የተሻለ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ የአንድ ከተማ አረንጓዴ
ቦታዎች ሽፋን ከጠቅላላው የመሬት አጠቃቀም ውስጥ ቢያነስ ከ 15-25% ማነስ የለበትም፡፡ ሆኖም
የሚከለሉት አረንጓዴ ቦታዎች ከቤት ውስጥ እና ውጭ የሚዘወተሩ የመዝናኛና መጫዎቻ ሜዳዎችን
የሚያካትት ሲሆን መጠኑ ሊጨምር ይገባል፡፡ ከተሞችም ሆኑ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለአረንጓዴ ልማት
ከፍተኛ ትኩረትና ቅድሚያ ሊሰጡትና የልማት አጀንዳ አድርገው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የእምነት ተቋማትና ዘላቂ ማረፊያ ስፍራዎች

የእምነት ተቋማት

የእምነት ቦታዎች ጥያቄ በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች እያደገ የመጣ ጥያቄ ሲሆን በተለይ በየመኖሪያ
አካባቢዎች የእምነት ተቋማት እየተስፋፉ ለአገልግሎትም አስቸጋሪ የሆንበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
በመሆኑም ለእምነት ተቋማት ቦታዎች ለማዘጋጀት ሲታሰብ የተወሰኑ መሰረታዊ ጉዳዮችን ማጤን ተገቢ
ይሆናል፡፡ ይኸውም የእምነት ተግባራቱ ባህርያት፣ የአገልግሎቱ ሽፋንና በአካባቢው ያሉ የተገልጋዮች ብዛት
ከተመሳሳይ የእምነት አገልግሎት ያለው የቦታ ርቀት፣ የጥብቅ ቦታ ሁኔታና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ለእምነት
ተቋማት ቦታ ለመያዝ ሲፈለግ የከተማውን ሁኔታና የመሳሰሉትን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ተግባራዊ
ለማድረግ የሚያስችሉ ቀደም ሲል የተዘጋጁ እንዲሁም በመከለስም ላይ የሚገኙ ስታንዳርዶች አሉ፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 47


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የዘላቂ ማረፊያ ቦታዎች

የዘላቂ ማረፊያ ቦታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ከስርዓት ውጪ እየተስፋፉና እጅግ ሰፊ መሬት እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
በአገልግሎት ላይ ያሉትም ኋላ ቀርና በዘመናዊ ፕላን የታገዙ አይደሉም፡፡ በፕላን ያልተዘጋጁ ዘላቂ ማረፊያ
ስፍራዎች በመኖሪያ አካባቢዎች አስከፊ ገጽታና ብክለት እየፈጠሩ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሐውልት
ግንባታ አላስፈላጊና ከፍተኛ የሆነ ወጪ በሟች ቤተሰቦች ላይ እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን የመሰሉ
ችግሮች ለማስወገድና የዘላቂ ማረፊያ ቦታዎችን በስርዓት ለመምራት ተገቢ ስታንዳርድና ደንብ መኖሩ
የግድ በመሆኑ የአንድ ዘላቂ ማረፊያ ቦታ የአገልግሎት ሽፋን ሬዲየሱ ከ 2.5-5 ኪሎ ሜትር ሆኖ የተገልጋይ
ሽፋን ቢያንስ ከ 25,000-30,000 ለሚሆን ህዝብ እንዲሆንና ለአንድ ግለሰብ የሚሰጥ የቀብር ቦታ ደግሞ 2
ሜትር በ 0.80 ሳንቲሜትር እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ በአንድ የከተማ በፕላን ጊዜ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጥ
የሚዘጋጀው የዘላቂ ማረፊያ ቦታ ጠቅላላ ስፋት የሚወሰነው በአመታዊ የሞት መጠን ግምት፣ የእምነቱ
ተከታይ የህዝብ ብዛት፣ ለአንድ ግለሰብ በሚፈቀድ የቀብር ቦታ መጠን ሲሆን በመሬት ለሚዘጋጅ ለአንድ
የቀብር ቦታ በአማካይ የሚሰጠው ጠቅላላ የቦታ ስፋት ከሐውልት ግንባታ ጋር 5.38 ካሬ ሜትር ያለ
ሐውልት ደግሞ 3.38 ካ.ሜ. ነው፡፡

የቀብር ስፍራዎች ከከተማ መኖሪያ አካባቢዎች፣ ከመዝናኛ አካባቢዎች፣ ከሆስፒታሎች፣ ከስፖርት


ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ከትምህርት ቤቶች አካባቢ ቢያንስ 100 ሜትር ያህል የአረንጓዴ ጥብቅ ሰርጥ
/green buffer strip/ መተው አስፈላጊ ነው፡፡ የዘላቂ ማረፊያ ቦታው ከዋና መንገድ ወደ 20 ሜትር ያህል
ወደ ኋላ መሸሽና ለመጋቢና የውስጥ ገባር መንገዶች ተደራሽነት ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ የቦታ
ዝግጅቱም ከ 10 በመቶ ተዳፋት /slope/ ያነሰ ቢሆን የሚመረጥ ሲሆን የመሬት ጥበት ባለባቸው ከተሞች
ከ 10 በመቶ ከፍ ያለ ተዳፋት /slope/ መጠቀም ይቻላል፡፡ ነባር የቀብር ስፍራዎችን ከልሶ የመጠቀም
/Recycling/ እና የፉካ ቀብር አፈጻጸም ዘዴ መጠቀም አስፈላጊ ሲሆን የግለሰቦች ቀብር ከተፈጸመ ሰባት
ዓመት በኋላ የሟች ቤተሰቦች ባሉበት አጽሞችን በክብር ሰብስቦ ወደ ዘላቂ የክብር ማረፊያ ስፍራ የማኖር
ስርዓት እንዲሁም ጉልበትና ወጪ ቆጣቢና ጤናማ የሆነ የቀብር አፈጻጸም ሂደት በፕላን ከታገዘ ከመሬት
አጠቃቀም ጋር አቀናጅቶ ማካሄድ አይነተኛ የችግሮች መፍትሄ ነው፡፡ በተመሳሳይም የቀብር ቦታዎችን ወደ
ፓርክነት የመለወጥ ስርዓትም ሌላው ዘዴ ይሆናል፡፡

የቦታ አቀማመጥን በተመለከተ ዘላቂ የማረፊያ ስፍራዎች ከመሃል የከተማ ክፍሎች የራቁና ለወደፊት
የማስፋፊያ ቦታዎች ተብለው በሚያዙ ቦታዎች ላይ ሊዘጋጁ አይገባም፡፡ አመቺ ሆኖ ከተገኘ ሰፊ ቦታ
ባላቸው የዕምነት ቦታዎች ውስጥ ተካተው ወይም ተያይዘው ቢዘጋጁ ይመረጣል፡፡ የቴሌፎንና የኤሌክትሪክ
መስመሮችና የውሃ ቧንቧዎች በቀብር ቦታዎቸ መሃል አቋርጠው ሊዘረጉና አለታማ በሆነ ቦታና ለጎርፍ
በተጋለጡ ቦታዎችና ረግረጋማ ስፍራዎች ሊመሩ ወይም ሊዘጋጁ አይገባም፡፡ የዘላቂ ማረፊያ ስፍራዎች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 48


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ስርጭት ፍትሃዊነት ያለውና በተለይ ደግሞ በከተማ ውበትና በሌሎች የአካባቢ እንቅስቃሴዎች ላይ
አሉታዊ ተጽዕኖ የማያስከትል እንዲሆን ከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባል፡፡

የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች

በሀገራችን በተለያየ ደረጃ የሚዘጋጁ ሁለት ዓይነት የስፖርታዊ አገልግሎቶች ማለትም ማህበረሰባዊ
የስፖርት አገልግሎቶችና መደበኛ የስፖርት አገልገሎቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡ በአብዛኞቹ ከተሞች
ለእነዚህ አገልግሎቶች የሚዘጋጁ ቦታዎች ሽፋን በመቶኛ ከከተማ ከተማ ይለያያል፡፡ በአብዛኛው ከ 2-8
በመቶ ሲሆን በአንዳንዶቹ በተለይም የስፖርትና መዝናኛ በተለይ የሚዘወተርባቸው ከተሞች ሽፋኑ ከ 10
በመቶ በላይ ሊሆን ይችላል፡፡

በተለያየ ደረጃ የሚጠቀሱ የስፖርት አገልግሎቶች ያሉ ሲሆን እነሱም የሠፈር መጫወቻ ስፍራ /Play lot/፣
የሠፈር መጫወቻ ሜዳ /Playground/፣ የቀበሌ የእግር ኳስ ሜዳ / Kebele level football field/፣ የወረዳ
የእግር ኳስ ሜዳ /Woreda level football field/፣ የዞናል ስቴድዮም /Zonal level football /stadium/
እና ብሔራዊ ስታዲዮም /National level football stadium/ ናቸው፡፡ የእግር ኳስ ሜዳዎቹ ለተለያዩ
ሌሎች ስፖርቶችም ማዘውተሪያነትና ለተለያዩ የማሕበረሰብ መሰብሰቢያዎች ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡1

የሠፈር መጫወቻ ስፍራ /Play lot/ ቁጥሩ ከ 1‚250 እስከ 1‚750 ለሚደርስ የከተማ ሕዝብ በማኅበረሰባዊ
ጉርብትና ደረጃ በ 120 ሜትር ሬዲየስ የሽፋን ቦታ (catchment area) በማዕከላዊ ስፍራ አካባቢ
ማናቸውም የስፖርት ነክ ጨዋታዎችን ለማካሄድ በመኖሪያ አካባቢ ከመጋቢ መንገዶች ትይዩ ባልሆኑ
ቦታዎች ከ 0.1-0.2 ሄክታር ቦታ ስፋት ላይ የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡

የሠፈር መጫወቻ ሜዳ / Playground / ቁጥሩ 5‚000 እስከ 7‚500 ሕዝብ ለሚደርስ የከተማ ሕዝብ
በ 400 ሜትር የማዕከላዊ አገልግሎት ሽፋን አካባቢ ማናቸውም የስፖርት ነክ ጨዋታዎችን ለማካሄድ
በመኖሪያ አካባቢ ከ 0.3-0.42 ሄክታር ቦታ ስፋት ላይ የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡

የቀበሌ የእግር ኳስ ሜዳ /Kebele level football field/ ቁጥሩ ከ 5‚000 እስከ 10‚000 ለሚደርስ የከተማ
ሕዝብ በአንድ ኪሎ ሜትር አገልግሎት ሽፋን አካባቢ ከማዕከላዊ የከተማ ክፍል ወጣ ባለ ቦታ ለእግር ኳስ
መጫወቻ በ 8,064 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት ላይ የሚዘጋጅ አገልግሎት ነው፡፡

1
እዚህ የተዘረጉት ስታንዳርዶች የፌዴራል የስፖርት ኮሚሽን በ 1992 ዓ.ም ካዘጋጀው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ስታንዳርድ የተወሰዱ ሲሆን፤ አሁን
በተገኘው መረጃ መሠረት ገና እየተዘጋጀ ባለው አዲስ መመሪያ ስታንዳርዶቹ ከፍ እንደሚሉ ተገልጿል፡፡ ስለሆነም የተጠቀሱት ስታንዳርዶች እንደዝቅተኛ
እርከን ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 49


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የወረዳ የእግር ኳስ ሜዳ / Wereda level football field / ቁጥሩ ከ 60‚000 እስከ 120‚000 ለሚደርስ
በወረዳ ክልል በሚሸፈን ቦታ ለሚኖር ሕዝብ ከማዕከላዊ የከተማ አካባቢ ወጣ ባለ የወረዳው ክልል የእግር
ኳስ ጨዋታዎችን ለማካሄድ በ 11,935 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት ላይ የሚዘጋጅ አገልግሎት ነው፡፡

የዞን የእግር ኳስ ሜዳ / Zonal level football field /ቁጥሩ ከ 300‚000 እስከ 600,000 ለሚደርስ
በአስተዳደራዊ ዞን ወይም ክፍለ ከተማ በሚሸፈን ቦታ ለሚኖር ሕዝብ ከማዕከላዊ የከተማ አካባቢ ወጣ ባለ
የዞኑ ወይም ክፍለ ከተማው ክልል የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለማካሄድ በ 11,935 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት
ላይ የሚዘጋጅ አገልግሎት ነው፡፡

የክልል የእግር ኳስ ሜዳ / Regional level football stadium / በትላልቅ ከተማ ወይም በክልል ደረጃ
ለሚገኝ ሕዝብ ከማዕከላዊ የከተማ አካባቢ ወጣ ብሎ የተዘጋጀ ቦታ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለማካሄድ
በ 13,120 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት ላይ የሚዘጋጅ አገልግሎት ነው፡፡

የብሔራዊ የእግር ኳስ ስታዲየም /National level football stadium/ በጠቅላላ ሀገሪቱና በአለም አቀፍ
ደረጃ ዲዛይን ተደርጎ ከማዕከላዊ የከተማ አካባቢ ወጣ ብሎ በተገነባ ስቴዲዮም የእግር ኳስ ጨዋታዎችንና
ሌሎች የአትሌቲክስ ውድድሮችን ለማካሄድ በ 40‚000 ካሬ ሜትር የቦታ ስፋት ላይ የሚዘጋጅ አገልግሎት
ነው፡፡

የመዝናኛ አገልግሎት በመባል የሚጠራው በውስጡ ክፍት ቦታዎች፣ የውጭና የቤት ውስጥ መጫወቻና
መናፈሻ ቦታዎችን ያጠቃለለ ነው። በአንድ የከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት ለወደፊት ለከተማዋ ዕድገት
ተብሎ ከሚያዘው የመሬት አጠቃቀም ውስጥ ለዚሁ አገልግሎት የሚሆን ቦታ መከለል ያስፈልጋል፤ በተለይ
ደግሞ የተሻለ ደረጃ ጠብቀው ለሚሰሩ ትላልቅ የመናፈሻ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በሚያቀርቡት
የፕሮጀክት ንድፍ መሰረት ታይቶ መስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡

ሠ. የአስተዳደር አገልግሎት

አንድ የከተማ ፕላን ሲዘጋጅ ከሚያካትታቸው ዋና ዋና ክፍሎች መካከል ለአስተዳደር አገልግሎት የሚውሉ
ቦታዎች አንዱ ነው። በዚህም መሰረት መንግሰታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት መስሪያ ቤቶች፣
የተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶች ፅ/ቤቶች፣ የፖሊስ ፅ/ቤቶች፣ የፍርድ ቤትና የፍትህ መስሪያ ቤቶች እንዲሁም
የማረሚያ ቤት ፅ/ቤቶች በአስተዳደር ክፍል ከሚመደቡት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ስለዚህ በከተማ
ፕላን ዝግጅት ወቅት በቂና አመቺ ቦታ በመያዝ መስሪያ ቤቶቹ ወይም ፅ/ቤቶቹ በቀላሉ ለህብረተሰቡ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 50


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ተደራሽ የሚሆኑ፣ በአቀማመጣቸው የተመቹ፣ በስርጭታቸው ፍትሀዊ የሆኑ፣ በመጠናቸው


ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ እና ለእያንዳንዱ መስሪያ ቤት ለስራው ተስማሚ የሆነ ቦታ በመከለል ትኩረት
ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል።

ተመሳሳይ አገልግሎት ያላቸውን መ/ቤቶች በክላስተር አንደ አካባቢ በማድረግ አስፈላጊ ሲሆን ክላስተሮችን
ፍትሃዊ ስርጭትን ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ማስቀመጥ ይገባል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ ለተዘረዘሩት ተቋማትን በማእከል የንግድ ቀጠና ውስጥ፣ በዋና መጋቢ መንገዶች
አቅራቢያ፣ አማካይ በሆነ አከባቢ፣ የትራፊክ መጨናነቅ ካሉባቸውና ከገበያ ቦታዎች በራቁ፣ ከፍተኛ ድምፅ
ካላቸው ኢንዱስትሪዎች በራቁ፣ ለትራንስፖርት ምቹ በሆኑ አካባቢዎች ቦታ እንዲያዝላቸው በማድረግ
ማስተናገድ ይቻላል፡፡

ረ. ፋብሪካዎች /ኢንዱስትሪዎች፣ ማከማቻ ቦታዎች እና የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት

ፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎች እና ማከማቻ ቦታዎች

የዚህ ዘርፍ ዋና ዋናዎቹ ክፍሎች ከባድና ቀላል ኢንዱስትሪዎችን/ፋብሪካዎችን፣ ማከማቻ መጋዘኖችንና


ዲፖዎችን፣ ወርክሾፖችን እና ጋራዦችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ በከተማ የመሬት አጠቃቀም ቦታ ምደባ
መሠረት ባመዛኙ ራሳቸውን ችለው የተለየ ቦታ ይያዝላቸዋል፡፡

ፋብሪካዎች /ኢንዱስትሪዎች እና ማከማቻዎች (manufacturing and warehouses) በአጠቃላይ ለአንድ


ከተማ ከሚመደበው አጠቃላይ የመሬት አጠቃቀም እቅድ ውስጥ በአነስተኛ ከተሞች ከ 5-10 በመቶ፣
በመካከለኛና ትላልቅ ከተሞች 10-15 በመቶ እና በሜትሮፖሊታን አካባቢዎች 10-20 በመቶ የሚሆን
ድርሻ ይይዛሉ፡፡

ፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆን ከእርሻ መር


ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለሚደረገው ሽግግርም መሠረት ናቸው፡፡ በከተሞችም የሥራ
እድል ከመፍጠር ባሻገር ድህነትን በመቀነስ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡
ስለዚህ የፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎች እና ማከማቻዎች ጉዳይ በከተሞች ፕላን ዝግጅት ውስጥ ከፍተኛ
ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡

የፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎችና ማከማቻዎች ቦታዎች በአብዛኛው ከሌሎች የመሬት አጠቃቀም ቦታዎች


የተለዩና የጥሬ ዕቃ አቅርቦትን፣ የሠራተኛውን የመኖሪያ አካባቢና ትራንስፖርትን፣ የመሠረተ ልማት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 51


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አቅርቦትን (ውሃ፣ መብራት፣ መንገድ፣ ወዘተ)፣ የአካባቢ ሥነምህዳር ብክለትን፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ
አወጋገድን፣ የጥሬ ዕቃና የፋብሪካ ምርት የትራንስፖርት አገልግሎትን፣ በቂ የወደፊት ማሰፋፊያ ቦታን
ያገናዘበ እና የወደፊት የመሬት አጠቃቀም አገልግሎቶች ላይ ችግር ሊያስከትል በማይችልበት አካባቢ
የሚመደብ መሆን አለበት፡፡ በተመሳሳይም ከአንድ የከተማ ክልል ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ በተለይም
የጥሬ ዕቃና የትራንስፖርት አቅርቦት በሚገኝበት አካባቢ ሊመደብ ይችላል፡፡

ፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎች፡ ፋብሪካዎች /ኢንዱስትሪዎች በሶስት ደረጃ የሚከፈሉ ሲሆን እነዚህም የጎጆ


ኢዱስትሪዎች፣ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች እና መካከለኛና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ተብለው ይጠራሉ፡፡
የጎጆ ኢንዱስትሪ በአብዛኛው በቤተሰብ አባላትና በትንሽ የሰው ሃይል በመኖርያ ቤት ውስጥ የሚከናወን
የማምረት ተግባር ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ተቋማት በመኖሪያና ንግድ አካባቢዎች መሆን የሚችሉ ሲሆን
ስፋታቸውም ከ 500-2,500 ሜ.ካሬ መሆን አለበት፡፡ አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች የድምጽ ብክለት
የማያስከትሉ ከሆነ በመኖሪያና ንግድ አካባቢዎች ቢሆኑ ይመረጣል፤ የቦታ መጠናቸውም እንደ
ኢንዱስትሪው ዓይነት ከ 5,000-10,000 ሜ.ካሬ መሆን ይገባዋል፡፡ የመካከለኛና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች
ቦታ በከተሞች ዳርቻ እና ከዋና መጋቢ እና አውራ ጎዳና መንገዶች በቅርብ ርቀት ላይ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡
የእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ቦታ በተለይ አካባቢን በመጥፎ ሽታ፣ በድምጽ እና ብናኝ የሚበክል ከሆነ ርቀትና
የነፋስ አቅጣጫ ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ሲሆን የሚያዘው ቦታም ከ 10,000-15,000 ሜ.ካ ነው፡፡
በተጨማሪም ማናቸውም ፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎች ነባርም ሆኑ አዲስ የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ጥናት
ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማከማቻና ዲፖች፡ ከሌሎች የከተማ አገልግሎቶች ተለይተው በገበያና ማምረቻ አካባቢዎች ቦታ


ቢያዝላቸው ይመረጣል፡፡ በተጨማሪም የአካባቢውን ምርት ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለከፍተኛ የትራንስፖርት
አውታሮች (ለባቡር መስመሮች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ ለደረቅ ወደቦች፣ ወዘተ) ቅርብ መሆን አለባቸው፡፡
የሚያዝላቸው ቦታ ለአነስተኛ ማከማቻዎች እስከ 500 ካ.ሜ. ሲሆን በንግድ አካባቢ፣ በከተማ ማዕከላዊ
ሥፍራና ለዋና መጋቢ መንገድ ተደራሽ በሆነ አካባቢ መሆን አለበት፡፡ ለመካከለኛ ማከማቻ ከ 500-5,000
ካ.ሜ. ቦታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ከመሃል ከተማ ወጣ ብሎ አማካይ ቦታ ላይ ለዋና መስመር ቅርብ እና
መጋጠሚያ ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ ለትላልቅ ማከማቻዎች 5,000-10,000 ካ.ሜ. ቦታ
የሚያስፈልጋቸው ሲሆን በከተማ ዳርቻ አካባቢዎች፣ ከዋና መስመር የሚገናኝ እና በመካከለኛና ትላልቅ
ኢንዱስትሪዎች አካባቢ ቢሆን ይመረጣል፡፡

የደረቅ ወደብን በተመለከተ ሀገር አቀፍ ጠቀሜታ ያለው ጉዳይ በመሆኑ ከከተማ ክልል ውጭ የሚታይ
ሲሆን የቦታ አመራረጡም ከውጭ ሀገራት ጋር የትራንስፖርት ግንኙነት በሚደረግባቸው መስመሮች ላይ
ሊሆን ይገባል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 52


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የነዳጅ ዲፖዎች በተለየ ባህሪያቸው ምክንያት በከተማ ዳርቻና ምርቱ የሚመጣበትን አቅጣጫ መሠረት
በማድረግ ከሌሎች አገልግሎቶች ተለይተው ቦታ የሚያዝላቸው ሲሆን ለከፍተኛ የትራንስፖርት
አውታሮች (ለባቡር መስመሮች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ ወዘተ) የተገናኙ ወይም በቅርብ ርቀት መሆን
አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን በከተማው የመስፋፊያ ክልል ውስጥ ሊቀመጡ አይገባም፡፡ በተመሳሳይም ከከተማ
ክልል ውጭ በሚመረጥ ቦታ ላይ ሊመላከቱ ይችላሉ፡፡

ነዳጅ ማደያዎች ደግሞ በመሃል ከተማና ዋና ዋና መንገዶች ዳርቻ እና እንደ ሁኔታው በዋና ዋና የንግድ
ማዕከላት አካባቢም መያዝ ይቻላል፡፡ ሆኖም ከህዝባዊ ተቋማት (ከት/ቤት፣ ከቤተክርስቲያን፣ ከሆስፒታል፣
ከቤተመጻህፍት፣ ከመጫወቻ ሜዳዎች፣ ወዘተ) ቢያንስ 150 ሜትር መራቅ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም
ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አመቺ የሆነና የትራፊክ መጨናነቅ የሌለበትና ተሽከርካሪዎችን እንደልብ
መግባትና መውጣት የሚያስችል ሆኖ እስከ 1,100 ካ.ሜ. የቦታ ስፋት ሊኖረውና በዋና መንገድ ላይ መሆን
ይገባዋል፡፡ ይህ ቦታ እይታን ከሚጋርድ መታጠፊያ/ማዞሪያ አካባቢ የራቀ፣ ከከተማው መውጫና መግቢያ
መስመሮች ጋር በተያያዘ የሚገኝ ቦታ ላይ፣ ሜዳማ አካባቢ፣ የውሃ አካላትን (ወንዞችንና፣ ሀይቆችን፣
ኩሬዎችን ወዘተ) ሊበክል በማይችልበት አካባቢ መገንባት ይኖርበታል፡፡

ጋራዥና ወርክሾፖች፡ አብዛኛዎቹ ጋራዦችና ወርክሾፖች በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በአካባቢቸው ላይ


ከፍተኛ የድምጽ እና የውሃ ብክለት የሚያስከትሉ በመሆናቸው የተለየ ምደባ ያስፈልጋቸዋል፤ ለዋና እና
መጋቢ መንገዶች ተደራሽ በሚሆኑ አካባቢዎች፣ በኢንዱስትሪዎችና ማከማቻ አካባቢዎች ቢሆኑ
ይመረጣል፡፡ ሆኖም ዘመናዊና የድምጽ ብክለት የማያስከትሉ ጋራዦችና ወርክሾፖች በማንኛውም
ለትራንስፖርት አመቺ በሆነ አካባቢ ቦታ ሊያዝላቸው ይገባል፡፡

በአጠቃላይ አገሪቱ ከነደፈችው የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንጻር የከተማ ፕላን
ዝግጅትና አፈጻጻሙ የኢንዱስትሪ ልማትን መደገፍ ይገባዋል፡፡ ለዚህም ተስማሚ የሆኑ የማምረቻ ዞኖችን
በተለይም የአካባቢ ጥበቃን ማዕከል ያደረገ እና አለማቀፍና አገራዊ ስታንዳርድን በጠበቀ መልኩ
የኢንዱስትሪና ማምረቻ ፓርክ (Industrial park) በፕላን በማመላከት/ከልሎ በሥራ ላይ እንዲውሉ እና
በፕላን እንዲመሩ ማድረግ ይገባል፡፡ በተጨማሪም ስታንዳርዱን የጠበቀ የምርት ማከማቻና ዲፖዎችን፣
የጋራዥና ወርክሾፖች ቦታዎችን በፕላን በመያዝ ችግሮቹን ለዘለቄታው መቅረፍ ይገባል፡፡

የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት

የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት መስፋፋት ለአንድ አገር ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ግልፅ ነው፡፡
በመሆኑም በከተማ ፕላን ዝግጅት ውስጥ ለነዚህ ተቋማት የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች በመከለል ትኩረት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 53


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨርቃ ጨርቅ፣ የእንጨትና ብረታብረት ስራ፣
የምግብ ዝግጅት፣ የግንባታ ስራዎች፣ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እና የከተማ ግብርናን ያካትታሉ፡፡

አብዛኛዎቹ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የልማት ስራቸውን ለማከናወን ከሚያስፈልጓቸው መሰረታዊ


ጉዳዮች መካከል ለልማት ስራው ቁርጠኝነት የተወሰነ ስራ ለመስራት የሚያስችል ክህሎትና የንግድ
አመራር ጥበብ መጨበጥ፣ ውስን ካፒታልና ለማምረቻና ለመሸጫ የሚሆን መሬት ማግኘት ናቸው፡፡
ማምረቻና መሸጫ መሬት ካላገኙ የልማት ስራዎች ላይ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ የተሟላ አይሆንም፡፡
በመሆኑም እንደየምርቱ ዓይነት ምቹ የሆነ መሬት ሊቀርብላቸው ይገባል፡፡ ይህ ሲባል ግን መሬት
በጊዜያዊነትም ይሁን በቋሚነት ሲሰጣቸው በዘፈቀደ ወይም ክፍት ቦታ በተገኘ ቁጥር ሊሆን አይገባም፡፡
በከተማው የመሬት አጠቃቀም ፕላን ላይ በተጠና ሁኔታ የተመለከተውን መሬት ከአካባቢው ጋር
በተጣጣመ መልክ በመሸንሸንና በመደልደል ሊሆን ይገባል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም አልፎ አልፎ የኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከት ያላቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ሊከሰቱ ስለሚችሉ መሬትን ለሌላ አካል
እንዳያስተላልፉትና የታሰበው አቅጣጫ እንዳይሰናከል የክትትል ስርአታችን ጠንካራ ሊሆን ይገባል፡፡
ለዚህም ነው መሬት ውስን ሀብታችን ስለሆነ በፕላን በተመሰረተ ሁኔታ በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል
የህዳሴ ጉዟችንን የተሳካ እናድርገው የምንለው፡፡ እነዚህ ተቋማት ለልማቱ ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆኑ
በፕላን በተመሰረተ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያሳኩ ካደረግን የከተሞቻችን ህዳሴ በተሻለና ውጤታማ በሆነ
ሁኔታ የተሳካ ይሆናል፡፡

ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት የሚያዙ ቦታዎች ከድምፅ ብክለት ነፃ ለሆኑት ለምሳሌ ካፌ፣ ምግብና
መጠጥ ቤቶች፣ የዕለት ተዕለት ሸቀጣሸቀጦች የሚሸጡባቸው ሱቆች፣ ፎቶ ኮፒ ቤቶች፣ የውበት ሳሎን
ስራዎች፣ የአልባሳት መስሪያ ቤቶች፣ ኢንተርኔት ካፌ፣…ወዘተ በክላስተር መልክ በማድረግ የሕዝብ
እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች፣ በመኖሪያ አካባቢዎችና ማእዘን በሆኑ ቦታዎች ላይ ሲሆን /Block
corners/፣ ከድምፅና ከሽታ ብክለት ጋራ የተያያዙትን የእንጨትና ብረታ ብረት ድርጅቶች፣ ቆዳና የቆዳ
ውጤቶች፣ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣…ወዘተ ደግሞ ከመኖሪያ አካባቢ በማራቅ በከተማ ፕላን ላይ
በኢንዱስትሪ ዞንና አገልግሎቱ በሚፈቅድለት ቦታ ማስተናገድ ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ ከላይ የተዘረዘሩት አገልግሎቶች በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት በቀላሉ ለህብረተሰቡ
ተደራሽ የሚሆኑ፣ በአቀማመጣቸው የተመቹ፣ በስርጭታቸው ፍትሀዊ የሆኑ፣ በመጠናቸው
ስታንዳርዳቸው የጠበቁ እና ለእያንዳንዱ አገልግሎት ለስራው ተስማሚ የሆነ ቦታ በማመላከትና የመኪና
ማቆሚያ ቦታ /Parking/ በመከለል ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል። ከነዚህ አገልግሎቶች ጋር አብረው
የማይሄዱና የማይጣጣሙ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችና መጋዘኖች፣ መካነ መቃብሮች፣ የቆሻሻ መድፊያ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 54


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ቦታዎች፣ የወታደራዊ ማሰልጠኛዎችና አገልግሎቶች እንዲሁም የተለያዩ ከባድ ድምፅና ሁከት የሚፈጥሩ
ሌሎች አገልግሎቶች ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የከተማ ፕላን በሚሰራበት ወቅት ከማይጣጣሙት ጋራ ጎን
ለጎን እንዳይሆኑ ተደርገው መቀመጥ አለባቸው፡፡

ሰ. መንገድ፣ ትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት አገልግሎቶች

ለአንድ ከተማ ከተማነት ከሚያስፈልጉት በርካታ ጉዳዮች ውስጥ መንገድ፣ ትራንስፖርት እና መሰረተ
ልማት አውታሮች ዋንኞቹ ናቸው፡፡ የከተሞች የተሳለጠ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ሊኖር
የሚችለው የመንገድ፣ የትራንስፖርትና የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች ሲኖሩ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቶቹ
በሚፈለገው የጥራትና የሽፋን ደረጃ ሲገኙ ነው፡፡

በከተማ ፕላን ዝግጅት መንገድ በአራት ዋና ዋና ደረጃዎች በመክፈል አንደኛ ደረጃ መንገድ፣ ሁለተኛ ደረጃ
መንገድ፣ ሰብሳቢ መንገዶችንና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ሲያካትት ትራንስፖርት ደግሞ የአውቶብስ
መናኸሪያ፣ የታክሲ ማቆሚያ፣ የጭነት መኪናዎች ማቆሚያ፣ የማንኛውም መኪና ማቆሚያ ቦታዎች
/Parking/፣ አየር ማረፊያዎችን የሚያካትት ሲሆን የመሰረተ ልማት ደግሞ መንገድን ጨምሮ የውሀ፣
የኤሌክትሪክ፣ የቴሌፎን፣ የቆሻሻ ውሃ ማስወገጃ መስመሮችን ወዘተ ያካትታል፡፡ ከአጠቃላይ የመሬት
አጠቃቀም መንገድ፣ ትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ድርሻ እንደ ከተሞቹ ደረጃ በመቶኛ ከ 15-25
ይይዛል፡፡

መንገድ

በከተማ ውስጥ በእግርም ሆነ በተሽከርካሪ የተሳለጠ፣ ቀልጣፋ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንቅስቃሴ


ለማድረግ መንገድ የከተማ የደም ስርና አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር ለከተሞች ፊዚካላዊ፣ ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡

የመንገዶች ተዋረድ፡ የከተማ ውስጥ መንገዶች ተዋረድ በአራት ደረጃዎች የሚከፈሉ ሲሆን እነዚህም
አንደኛ ደረጃ መንገድ /Principal Arterial/፣ ሁለተኛ ደረጃ መንገድ /Sub-Arterial/፣ መጋቢ መንገድ
/Collector road/ እና የውስጥ ለውስጥ መንገድ /Local road/ በመባል ይጠራሉ፡፡ ምንም እንኳን
በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ደረጃውን የጠበቀ አገር አቋራጭ መንገድ (express way) ባይኖርም ይህ
የመንገድ አይነትም በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ የመንገድ አይነት ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ መንገድ አዲስ አበባን
ከአዳማ ለማገናኘት የተጀመረውን የመንገድ ዓይነት ያካትታል፡፡ በተመጨማሪም ከውስጥ ለውስጥ
መንገዶች ጋር በተያያዘ አነስተኛ ርዝመት ያላቸው መዳረሻ መንገዶች ይገኙበታል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 55


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አንደኛ ደረጃ መንገዶች /Principal Arterial/ የከተማ ክፍሎችን፣ የከተማ ማዕከል ወይም ንዑስ
ማዕከላትን የሚያገናኙ ናቸው፡፡ በነዚህ መንገዶች ላይ መኪና ማቆም፣ መጫንና ማራገፍ የተከለከለ ሲሆን
እግረኞች መንገዱን ማቋረጥ የሚችሉት ምልክት በተደረገባቸው ማቋረጫዎች፣ መንገዶች በሚገናኙበት
አካባቢ፣ መሿለኪያና የእግረኞች ድልድዮች ላይ ብቻ ነው፡፡ ሁለተኛ ደረጃ መንገዶች /Sub-Arterial/
አንደኛ ደረጃና መጋቢ መንገዶችን የሚያገናኙ ናቸው፡፡ እነዚህ መንገዶች ከአንደኛ ደረጃ ጋር ሲነጻጸሩ
አነስተኛ የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተናግዱ ሲሆኑ በመንገዶቹ ላይ መኪና ማቆም፣
መጫንና ማራገፍ የሚፈቀደው ለየት ያሉ ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው፡፡ እግረኞች መንገዱን ማቋረጥ
የሚችሉት ምልክት በተደረገባቸው ማቋረጫዎች እና መንገዶች በሚገናኙበት አካባቢ ብቻ ነው፡፡ መጋቢ
መንገዶች /Collector road/ ሁለተኛ ደረጃ መንገድንና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የሚያገናኙ ሲሆን
በነዚህ መንገዶች እግረኞች ማቋረጥ ይችላሉ፡፡ የመኪና መጨናነቅ ከሚበዛበት ሰዓት ውጭ በመንገዶቹ ዳር
መኪና ማቆም፣ መጫንና ማራገፍ አይከለከልም፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገድ /Local road/ ወደ የመኖሪያ
ቤት፣ ንግድና ማምረቻ ቦታ የሚወስዱ መንገዶች ሲሆኑ በነዚህ መንገዶች ላይ የትራፊክ ብዛት አነስተኛ
ሲሆን የህዝብ ትራንስፖርት መስመር የማይኖርባቸው ናቸው፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለእግረኛች፣
ለመኪና ማቆም፣ ጭነት መጫንና ማራገፍ የተፈቀዱ ናቸው፡፡

የመንገዶች ስፋት፡ የመንገድ ስፋት እንደ መንገዱ ደረጃ እና መንገዱ የሚሰራበት አካባቢ /Core areas,
Intermediate Zone, Expansion Areas / የሚለያይ ሲሆን የአንደኛ ደረጃ መንገድ /Principal Arterial/
ስፋት ከ 30 -120 ሜትር፣ የሁለተኛ ደረጃ መንገድ /Sub-Arterial/ ስፋት ከ 20 - 25 ሜትር፣ መጋቢ
መንገዶች /Collector road/ ከ 11 - 20 ሜትር እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶች /Local road/ ከ 4 -
12 ሜትር ሊሆን የሚችል ሲሆን ትክክለኛ ስፋት ግን በተቀመጠው ወሰን ውስጥ ሆኖ በአካባቢው በቂ ቦታ
መኖርና በመንገዱ ተፈላጊነት ደረጃ ላይ ይወሰናል፡፡

በመንገዶች መሀከል ሊኖር የሚገባው ርቀት፡ በመንገዶች መሀከል የተወሰነ ርቀት መኖር ያለበት ሲሆን
ርቀቱም እንደ መንገዶቹ ደረጃ ይለያያል፡፡ በአንደኛ ደረጃ መንገዶች /Principal Arterial/ መሀከል ርቀቱ
ከ 1.5 ኪሎ ሜትር መብለጥ የሌለበት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ መንገዶች /Sub-Arterial/ መሀከል ከ 0.8-1.5
ኪሎ ሜትር፣ በመጋቢ መንገዶች /Collector road/ መሀከል 300-800 ሜትር እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ
መንገዶች መሀከል የሚኖረው ርቀት ከ 150 ሜትር በታች ነው፡፡

የመንገዶች መገናኛ/Road Junction/፡ በአንድ ከተማ ውስጥ የሚገኙ መንገዶች አንዱ ከሌላው ጋር
የሚገናኝበት በርካታ ቦታዎች ያሉ ሲሆን እነዚህ ቦታዎች T-Junction /ሁለት መንገዶች ሳይተላለፉ አንድ
ቦታ ብቻ ሲገናኙ/, Cross-Junction /መስቀለኛ መንገዶች/, Multiple-Junction/Grade-separated-
Junction /ከሁለት በላይ መንገዶች የሚገናኙበት/ እና Round Abouts /አደባባዮች/ ተብለው በአራት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 56


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ይከፈላሉ፡፡ “Junction” የትራፊክ ፍሰት፣ ፍጥነትና ደህንነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ስለሆነ ዲዛይን ሲደረጉ
የትራፊክ እንቅስቃሴን በማያውኩበት፣ እይታን በማይጋርዱበት፣ ለአሽከርካሪዎች ግልጽ በሆኑበት
እንዲሁም ለአደጋ አጋላጭነታቸው አነስተኛ መሆን አለበት፡፡

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ ላይ ሊኖር የሚገባው የ “ Junction” ዓይነት የትራፊክ
ፍሰት መጠን፣ የተሽከርካሪ ፍጥነት፣ የቦታው ለእይታ አመቺነት ላይ የሚወሰን ሲሆን ማንኛውም
“Junction” በሚኖርበት አካባቢ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ከሌለ በስተቀር መንገዶች በ 90 ዲግሪ መገናኘት
አለባቸው፤ መንገዶቹ የሚገናኙበት ቦታም ተዳፋታምነት ከ 3 በመቶ መብለጥ የለበትም፤ በዋና መንገዶች
ላይ በሚኖሩት “Junctions” መሀከል ቢያንስ የ 500 ሜትር ርቀት መኖር ያለበት ሲሆን የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች “Junctions” መጠጋጋት የሌለባቸውና እንዲሁም እይታን አለመጋረዳቸው ግምት ውስጥ
መግባት አለበት፡፡ የሌሎች አገሮች ተሞክሮ እንደሚጠቁመው የመጀመሪያ ሶስቱን ዓይነቶች “Junctions”
ወደ አራተኛው ዓይነት ማለትም ወደ “Round Abouts” ወይም አደባባዮች መለወጥ ቢቻል ሊከሰቱ
የሚችሉ የመኪና አደጋዎችን በ 80 በመቶ መቀነስ ይቻላል፡፡

የመንገድ ጥግግት /Density/፣ መንገድ ከአጠቃላይ የመሬት አጠቃቀም የሚኖረው ድርሻ እና የተዳፋታማነት
/Slope/መጠን፡ የመንገድ ጥግግት መጠን ማለትም አጠቃላይ የመንገድ ርዝመት ከአጠቃላይ የመሬት
አጠቃቀም በመቶኛ የሚኖረው ድርሻ ሲሆን ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው አነስተኛው
መጠን 15 በመቶ ነው፡፡ የከተማ ውስጥ መንገዶች አጠቃላይ ስፋታቸው/Area/ ከጠቅላላው የመሬት
አጠቃቀም ስፋት ከ 15-22 በመቶ መሆን ሲገባው የመንገድ ተዳፋታማነት መጠን ከ 12 በመቶ መብለጥ
የለበትም፡፡

የእግረኞች መንገድ፡ አብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ህዝብ ዋነኛ መጓጓዣ እግር እንደመሆኑ መጠን በከተሞች
የሚሰሩ መንገዶች የእግረኛ መንገድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በመዋቅራዊ ፕላን በከተማ ውስጥ ዋና ዋና
መንገዶች በግራና በቀኝ በኩል በመግለጫ (Legend) ላይ የእግረኛ መንገድ ማሳየት የሚጠበቅበት ሲሆን
የመጋቢና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ደግሞ ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላኖች ሲዘጋጁ የእግረኛ መንገድን
ስፋት ጨምሮ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የእግረኛ መንገዶች ከመኪና መንገዶች ከ 15-20 ሴንቲ ሜትር ከፍታ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን ፍሳሽን
ለማስወገድ ተዳፋታማነታቸው በ 2.5 መቶኛ ማነስ እንደሌለባቸው እንዲሁም ከመሬት ወደ ላይ ቢያንስ
2.3 ሜትር ያህል ከማንኛውም መሰናክል ክፍት/ነጻ መሆን ይገባቸዋል፡፡ የመንገድ ላይ ማስታወቂያ
ምልክቶች እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም የግንባታ ቁሳቁሶች የመንገድ ተጠቃሚውን እንቅስቃሴ ማወክ
ወይንም እንቅፋት መሆን የለባቸውም፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 57


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የእግረኞች መንገድ ስፋትን በተመለከተ ለአንደኛ ደረጃ መንገድ /Principal arterial/ በመንገዱ ግራና ቀኝ
በእያንዳንዱ በኩል ከ 3.5 - 5 ሜትር በጠቅላላው በሁለቱም በኩል ከ 7-10 ሜትር ስፋት ሊኖረው የሚገባ
ሲሆን ለሁለተኛ ደረጃ መንገዶች /Sub-arterials/ በአንዱ በኩል ከ 2.5 - 4 ሜትር በጠቅላላው በሁለቱም
በኩል ከ 5-8 ሜትር ስፋት ሊኖር ይገባል፡፡ ለመጋቢ መንገዶች የሚያስፈልገው የእግረኛ መንገድ ስፋት ከ 2
ሜትር በሁለቱም የመንገዱ አቅጣጫዎች ከ 4 ሜትር ማነስ የለበትም፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች
የሚያስፈልገው የእግረኛ መንገድ ስፋት የሚወሰነው በአካባቢው ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ሲሆን Urban
motorway የእግረኛ መንገድ አያስፈልጋቸውም፡፡

በዋና ዋና መንገዶች /Principal arterial and Sub-arterials/ ዳርና ዳር የሚኖረው የእግረኞች መንገድ
አማካኝ ስፋት እንደ አካባቢው እንቅስቃሴ የሚለያይ ሲሆን የኢንዱስትሪ አካባቢ 1.8 ሜትር፣ ሱቆች
ፊትለፊት ከ 3.7 - 4.5 ሜትር፣ የንግድ ቦታዎች አካባቢ 3-5 ሜትር እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶች
ባሉበት አካባቢ ደግሞ 2.7 ሜትር ይሆናል፡፡ የእግረኛ መንገድ ሲዘጋጅ ለጥላና ለውበት አገልግሎት
እንዲውሉ የተመረጡ ተክሎች ሊተከሉ ይገባል፡፡ እንዲሁም ከማስታወቅያ ሰሌዳዎች ነፃና ለእግር
እንቅስቃሴ ምቹ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

የብስክሌት መንገድ፡ የመሬቱ አቀማመጥ አመቺና ሜዳማ በሆኑባቸው ከተሞች እንደ አስፈላጊነቱ
ለብስክሌቶች የሚያገለግሉ መንገዶች በፕላን ውስጥ ማካተት አስፈላጊ ሲሆን የመንገዱ ስፋት 2 ሜትር፣
ተዳፋታማነቱ ከ 5 በመቶ በታች ሆኖ ለአጭር ርቀት ማለትም ለ 20 ሜትር 5 በመቶ እንዲሁም ለ 50
ሜትር 3.5 በመቶ ሊሆን ይችላል፡፡ መንገዱ እይታ ከሚከልሉ፣ ከቦይ፣ ከዛፍ ስሮችና ከማንኛውም
እንቅፋቶች ቢያንሰ ከግማሽ ሜትር መራቅ ያለበት ሲሆን ከማንኛውም መሰናክል ከመሬት ወደ ላይ ቢያንስ
2.25 ሜትር ያህል ክፍት/ነጻ መሆን አለበት፡፡

ትራንስፖርት

ትራንስፖርት ነዋሪው ከመኖሪያ ወደ ስራ ቦታ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት፣ የንግድ ተቋማትና


ሌሎች ማህበራዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች መንቀሳቀስ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን ለአንድ ከተማ
ማህበራዊና ኢኮኖሚያ እድገት የጀርባ አጥንት ነው፡፡ ትራንስፖርትን በሁለት ዋና ዋና ምድቦች ማለትም
በሞተር የሚታገዙና የማይታገዙ ብሎ በመክፈል ማየት ይቻላል፡፡ በሞተር የሚታገዙ የሞተር
ተሽከርካሪዎችን ሲያካትት በሞተር የማይታገዙት ደግሞ የብስክሌትና የእግር ትራንስፖርትን ያመለክታል፡፡
ለሁለቱም የትራንስፖርት ዓይነቶች ከመንገድ አንጻር የከተማ ፕላን ሊያካትታቸው የሚገቡ ጉዳዮች
በዝርዝር አስቀድሞ የተገለጸ ሲሆን በዚህ ንዑስ ክፍል ውስጥ በሞተር ለሚታገዙ የትራንስፖርት
አገልግሎቶች /Motorized Transportation/ የሚያስፈልጉ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 58


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የአውቶበስ መናኸሪያ፡ የአውቶብስ መናኸሪያ በከተማው ስፋት፣ በመኪናዎች ብዛት፣ ለተሳፋሪዎች


መብዛት ምክንያት በሆኑት የከተማው የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ከተማው
ከሌሎች ከተሞች ጋር ባለው ግንኙነት መሰረት በአራት ደረጃዎች ማለትም አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ እና
አራተኛ ደረጃ በመባል የሚከፈል ሲሆን ስፋታቸውም በቅደም ተከተል በሄክታር 0.37- 0.61፣ 0.63- 1.02፣
1.04- 1.82፣ 1.86- 2.67 ሲሆን በፕላን ላይ የሚቀመጡበት ስፍራም በከተማ ማዕከል ወይም ንዑስ
ማዕከል፣ ዋና ገበያ አካባቢ፣ ተዳፋታማነቱ ከ 5 በመቶ በማይበልጥ ቦታ፣ የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ደረጃ
መንገድ ላይ ሆኖ ከትምህርት ቤት፣ ከጤና ተቋማት፣ ከቤተ መጻህፍት፣ ወዘተ ራቅ ብለው ይሆናሉ፡፡
በትላልቅ ከተሞች የአውቶብስ መናኸሪያ ቦታዎች ያልተማከለ ስርዓት አስተዳደርን መሰረት አድርገው
ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ ይህም የመውጫ ወይም የመግቢያ አቅጣጫን ግምት ውስጥ በማስገባት መሆን አለበት፡፡
መናኸሪያ በማያስፈልጋቸው አንዳንድ ትናንሽ ከተሞች፤ ከተማውን አቋርጠው የሚሄዱ የህዝብ
ትራንስፖርት መኪናዎች በሚኖሩበት ጊዜ በከተማው የማዕከል ክፍል በሚገኝ መንገድ ዳር ሰው
የሚጭኑበትና የሚያወርዱበት የአውቶብስ ማቆሚያ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

የጭነት መናኸሪያ፡ የጭነት መናኸሪያም ልክ እንደ የአውቶብስ መናኸሪያው በአራት ደረጃዎች ይከፈላል፡፡
ስፋታቸውም በቅደም ተከተል በሄክታር 0.48-0.9፣ 1.03-1.6፣ 1.63-3.0 እና 3.73-4.40 ሲሆን
ስፋታቸውም የሚወሰነው በመኪናዎች ብዛት፣ ለቢሮዎች፣ ለመኪናዎች እና እንዲሁም ለእግረኞች
እንቅስቃሴ በሚያስፈልገው ቦታ መሰረት ነው፡፡ የጭነት መናኸሪያዎች በፕላን ላይ የሚቀመጡበት ስፍራ
የኢንዱስትሪዎችና መጋዘኖች በብዛት የሚገኙበት አካባቢ በከተማው መውጫና መግቢያ በሮች አካባቢ፣
በከተማው አውራ ጎዳና አጠገብ፣ የቀለበት መንገድና ከቀለበት መንገዱ ጋር የሚገናኙ መንገዶች
መጋጠሚያ አካባቢ ሆኖ ከመኖሪያ ቤቶች፣ ከትምህርት ቤት፣ ከጤና ተቋማት፣ ከቤተ መጽሀፍት፣ ወዘተ
ራቅ ብለው ነው፡፡ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ መናኸሪያቸው ሲገቡም ሆነ ሲወጡ እንዲሁም ከተማን
ሲያቋረጡ በተቻለ መጠን የሕዝብ እንቅስቃሴ የሚበዛባቸውን ቦታዎችንና ዋና ዋና መንገዶችን ሳያቋርጡ
ቢሆን ተመራጭ ይሆናል፡፡

የአውሮፕላን ማረፊያ፡ የአውሮፕላን ማረፊያ ቦታ መረጣን በተመለከተ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታይ ጉዳይ
ሆኖ የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ባወጣውና በሚያወጣው ስታንዳርድ መሰረት ተፈፃሚ የሚሆን ነው፡፡
በከተማ ክልል ውስጥ የቦታ መረጣ ሲከናወን የአውሮፕላን ማረፊያ ቦታ እና ስፋት እንደ ማረፊያው አይነት
/አለም አቀፍ፣ ብሄራዊና የአካባቢ/ የሚለያይ ቢሆንም ቦታው ሲመረጥ ጭስ ከሚያመነጩ ፋብሪካዎች፣
አእዋፋትን ከሚሰበስቡ ቦታዎች /ቄራ፣ ቆሻሻ መጣያ ቦታዎች…ወዘተ/፣ ከተራራ፣ ትላልቅ ህንጻዎችና
ከመኖሪያ ቦታዎች የራቀ መሆን አለበት፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 59


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች /Parking/፡ ሁለት ዓይነት የመኪና ማቆሚያ አገልግሎቶች ያሉ ሲሆን እነሱም
የመንገድ ላይ የማቆም አገልግሎት /On street parking facilities/ እና ከመንገድ ውጭ የማቆም
አገልግሎት /Off-street parking facilities/ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ሁለቱም ዓይነት የመኪና ማቆሚያ
አገልግሎቶች እያንዳንዳቸው በሁለት የሚከፈሉ ሲሆን የመንገድ ላይ አገልግሎት የተገደቡና /restricted/
እና ያልተገደቡ /unrestricted/ በመባል ሲከፈሉ የተገደቡት የትራፊክ ፖሊስ የሚቆጣጠራቸው ናቸው፡፡
ከመንገድ ውጭ አገልግሎቶች ደግሞ የመሬት ላይ እና የህንጻ ላይ/ ውስጥ በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡

በየአካባቢው የሚያዘው የመኪና ማቆሚያ መጠን/ስፋት በአካባቢው እንደሚገኙ አገልግሎቶች የሚለያይ


ሲሆን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉበት አካባቢ ለአንድ ቤት አንድ የማቆሚያ ቦታ ስሌት ሁሉም መኖሪያ
ቤቶች የመኪና ማቆሚያ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡ በተመሳሳይ ትያትር ቤት፣ ስታዲዮም፣ ሬስቶራንት፣
ቡና ቤቶች አካባቢ ደግሞ የመኪና ማቆሚያው ብዛት የሚወሰነው በሚስተናገደው ሰው መጠን ሲሆን
በዚሁም መሰረት ለ 10 ሰዎች አንድ የማቆሚያ ቦታ ስሌት መሠረት ጠቅላላ የሚያስፈልገው ቦታ
ይወሰናል፡፡ ለዩኒቨርስቲዎች ለ 5 ሰራተኞች አንድ የማቆሚያ ቦታ፤ ለሆስፒታሎች፣ ሙዚየምና የሕዝብ
ቤተ መጽሐፍቶች እንደየስፋታቸው ልክ ለ 40 ስኩዌር ሜትር አንድ የማቆሚያ ቦታ፤ ለሆቴሎች ለ 5
አልጋዎች አንድ የማቆሚያ ቦታ፤ ለትምህርት ቤቶች ለ 2 መማሪያ ክፍሎች አንድ የማቆሚያ ቦታ፣
ለመስሪያ ቤቶች እንደ ስፋታቸው መጠን ለ 40 ስኩዌር ሜትር አንድ የማቆሚያ ቦታ እንዲሁም ለሱፐር
ማርኬቶች፤ ለመጋዘኖች በስፋታቸው መጠን ለ 60 ካሬ ሜትር አንድ የማቆሚያ ቦታ ሂሳብ ለጠቅላላው
የሚያስፈልገው ቦታ ይያዛል፡፡ ለአንድ መኪና የሚያስፈልገው የማቆሚያ ቦታ ስፋት 14.75 ካሬ ሜትር /2.5
ሜትር x 5.9 ሜትር/ ነው፡፡ በማንኛውም የሕንፃ ዲዛይን የማፅደቅ ሂደት ለመኪና ማቆምያ
የሚያስፈልገው የቦታ መጠን መካተቱ መረጋገጥ አለበት፡፡ በተመሳሳይም በከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ
የማሀከል ክፍሎችና እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው አካባቢዎች ራሱን የቻለ የመሬት ላይ ወይም የሕንፃ ውስጥ
የማቆሚያ ቦታ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡

የተሽከርካሪዎች ፍጥነት፡ ተሽከርካሪዎች በከተማ ውስጥ እንደሚጓዙበት መንገድ ደረጃ ፍጥነታቸው


የተወሰነ ሲሆን ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ መንገድ /Principal and sub arterial roads / ፍጥነታቸው
በሰዓት ከ 40 እስከ 60 ኪ/ሜ፣ ለመጋቢ መንገዶች/Collector roads/ በሰዓት 30 ኪ/ሜ እንዲሁም
ለውስጥ ለውስጥ መንገዶች /Local roads/ በሰዓት ከ 20 እስከ 30 ኪ/ሜ ነው፡፡

መሰረተ ልማት አውታር መስመሮች /Utilitites/

የመሰረተ ልማት አውታሮች የውሃ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌፎን፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመሮችን
ያካትታሉ፡፡ መሰረተ ልማት አገልግሎቶች ስታንዳርዳቸውን ጠብቀው የመንገድ ደህንነት፣ ግንባታን ጥገና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 60


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የመሳሰሉትን በማያውኩበት ሁኔታ መንገድ በሚሰራበት ጊዜ ከመንገዱ ጋር አብረው መካተት


ይኖርባቸዋል፡፡ የመስመር ዝርጋታው በከተማ ገጽታ ላይም ሆነ ዕይታ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ በጣም
አነስተኛ መሆን እንዲሁም መስመሮች ከማንኛውም ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መጠበቅ
ይኖርባቸዋል፡፡ የመስመሮቹ ዝርጋታ በተቻለ መጠን በትራፊክ ጉዳት ሊደርስባቸው በማይችልበት
እንዲሁም ለቁጥጥርና ጥገና አመቺ በሆነ መልኩ መሆን አለበት፡፡ በአብዛኛው ያደጉት ሀገሮች የመሰረተ
ልማት መስመሮች ከመንገድ ግንባታ ጋር በመሬት ውስጥ የሚዘረጉ ሲሆን በታዳጊ ሀገሮች ግን የቴሌፎንና
የመብራት መስመሮች በመሬት ውስጥ እንዲሁም ከመሬት በላይ በአየር ላይ ይዘረጋሉ፡፡ በመሬት አጠቃቀም
ፕላን ላይ መንገድና መሠረተ ልማት አውታር መዘርጊያ የሚጠበቁ ቦታዎች እስኪለሙ ድረስ ቦታዎቹን
በአረንጓዴ ቦታነት በማልማት ጠብቆ ማቆየት ያስፈልጋል፡፡

የመሬት ውስጥ መስመር ዝርጋታ ከወጪ አንጻር ውድ ቢሆንም የመስመሩም ሆነ የሰው ለአደጋ ተጋላጭነት
ከመቀነስ፣ ከመሬት በላይ ያለውን ቦታ ለሌላ አገልግሎት ከመጠቀም፣ ሌሎች ግንባታዎች ላይ ተጽዕኖ
ካለማሳደር እንዲሁም የተዋበ እይታ ከመፍጠር አንጻር የተሻለ ሆኖ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በማንኛውም
የአገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ የመስመር ዝርጋታዎች በመሬት ውስጥ መቀበር ይኖርባቸዋል፡፡

የመሰረተ ልማት አውታሮች መስመሮችን /የውሀ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌፎን፣ የቆሻሻ ውሃ ማስወገጃ


መስመሮች/ በከተማ ፕላን ላይ አብዛኛውን ጊዜ ማካተት የተለመደ አይደለም፡፡ ይህም የአገልግሎቱ
ፊዚካላዊ ስርጭትን በቀላሉ ለማወቅ አስቸጋሪ ከመሆኑ በተጨማሪ የእድሳት ስራዎችን ለማከናወን
በሚፈለግበት ጊዜ መስመሮቹ የሚለዩት መስመሮቹ ሲዘረጉ በነበሩና ባዩ ሰራተኞች አማካኝነት ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህንና ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮችን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ የመሰረተ ልማት መስመሮች በፕላን
ላይ ማስቀመጥና በየጊዜው ለውጥ ሲኖርም ፕላኑን ማሻሻል አስፈላጊ ነው፡፡ እያንዳንዱ የመሰረተ ልማት
አቅራቢ ድርጅት የራሱ ፕላን ሊኖረው የሚገባ ሲሆን ፕላኑ ከመሰረተ ልማት መስመሮች በተጨማሪ
የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን፣ የውሃ ጉድጓዶችን፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎችን…ወዘተ
ማካተት ይኖርበታል፡፡ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ፕላኖች ሲዘጋጁ በከተማ ደረጃ የተዘጋጀውን የመንገድ
መረብን ተከትለው መሆን ስላለባቸው በፕላን ዝግጅት ወቅት ተቀናጅተውና ተናበው መዘጋጀት
ይገባቸዋል፡፡ በተለይ የማከፋፈያ ጣቢያዎች ቦታ መረጣ በሚከናወንበት ወቅት፤ የከተማውን ነባር ክፍልም
ሆነ የማስፋፊያ አካባቢ ውስጥ ከፍተኛ ሀይል ተሸካሚ መስመሮች እንዳያቋርጡ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
በዲዛይን ደረጃም ከከተማው ጋር ምክክር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የውሃ መስመሮች፡ የንፁህ ውሃ ጉድጓዶች፤ ከሴፕቲክ ታንክ እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር ቢያንስ 15
ሜትር እንዲሁም ከፍሳሽ ማጠራቀሚያ (cesspools) 45 ሜትር መራቅ አለባቸው፡፡ የውሃ መስመር

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 61


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከጎርፍ ማስወገጃ መስመር 1.5 ሜትር፣ ከኤሌክትሪክና ቴሌፎን መስመሮች 0.7 ሜትር እንዲሁም ከነዳጅ
መስመር 1 ሜትር መራቅ ይኖርበታል፡፡

ከመሬት በታች የውሃ መስመሮች ለዋናው መስመር ቢያንስ 100 እና 150 ሴንቲ ሜትር መቀበር ሲኖርበት
ለሁለተኛ ደረጃ መስመሮች ከ 80 ሴንቲ ሜትር ማነስ የለበትም፡፡

የኤሌክትሪክ መስመሮች፡ በመንገድ ትይዩ በአየር ላይ የሚዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ከመሬት


የሚኖራቸው የከፍታ ርቀት እንደ ቮልቱ መጠን የሚለያይ ሲሆን ለ 0.4 ኪሎ ቮልት ያልተሸፈነ መስመር 450
ሴንቲ ሜትር፣ ለ 0.4 ኪሎ ቮልት የተሸፈነ መስመር 400 ሴንቲ ሜትር እንዲሁም ለ 15 ኪሎ ቮልት
ያልተሸፈነ መስመር 600 ሴንቲ ሜትር ነው፡፡ መንገድ የሚያቋርጡ መስመሮች ደግሞ እንደ ሚሸከሙት
ቮልት መጠን በመንገድ ትይዩ ከሚዘረጉበት ከፍታ ቢያንስ በ 50 ሴንቲ ሜትር ከፍ ማለት አለባቸው፡፡

በዋና መንገድ እና በባቡር መንገድ ትይዩ የሚዘረጉ የሀይል ተሸካሚ መስመሮች ከመሬት ወደ ላይ
የሚኖራቸው ከፍታ ለ 0.4 ኪሎ ቮልት 800 ሴንቲ ሜትር ሲሆን ባለ 15 ኪሎ ቮልት ከሆነ ደግሞ 850 ሴንቲ
ሜትር ከመሬት ከፍ ማለት አለበት፡፡ በሌሎች መንገዶች የሚዘረጉ መስመሮች ለ 0.4 ኪሎ ቮልት ገመዱ
ያልተሸፈነ ከሆነ 550 ሴንቲ ሜትር የተሸፈነ ከሆነ 500 ሴንቲ ሜትር ሲሆን ያልተሸፈነ ባለ 15 ኪሎ ቮልት
ደግሞ 600 ሴንቲ ሜትር ከመሬት ከፍ ማለት አለበት፡፡

በአየር ላይ የሚዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች እና ከመስመሩ በታች ከስር ከሚያድጉ ማንኛውም


እጽዋቶች መሀከል ሊኖር የሚገባው ክፍተት ላልተሸፈኑ 0.4 እና 15 ኪሎ ቮልት መስመሮች 250 ሴንቲ
ሜትር ሲሆን ምናልባት ክፍተቱ ከ 250 ሴንቲሜትር ካነሰ የጎንዮሽ ርቀታቸው ቢያንስ 400 ሴንቲ ሜትር
መሆን አለበት፡፡ 15 ኪሎ ቮልት የሚሸከሙ መስመሮች ከህንጻ ሊኖራቸው የሚገባው የጎንዮሽ ርቀት ከ 300
ሴንቲ ሜትር ማነስ የለበትም፡፡

ቮልቴጃቸው አነስተኛ የሆኑ ያልተሸፈኑ መስመሮች ከማንኛውም የህንጻ ክፍል የሚኖራቸው የጎንዮሽ
ክፍተት ከ 200 ሴንቲሜትር ካነሰ ከፍታቸው ከተጠቀሰው የህንጻ ክፍል ቢያንስ 300 ሴንቲ ሜትር መራቅ
ሲኖርበት የተሸፈኑ መስመሮች ደግሞ ከማንኛውም የህንጻ ክፍል ያላቸው የጎንዮሽ ርቀት ከ 50 ሴንቲ
ሜትር ያነሰ ከሆነ ከፍታቸው ቢያንስ 200 ሴንቲ ሜትር መሆን አለበት፡፡ ወደ 5 ሜጋ ዋት ንዑስ ጣቢያዎች
የሚገቡ ከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮች ከማንኛውም ነገር በግራና በቀኝ በድምሩ 32 ሜትር መከለል
(Buffer Zone) ይኖርባቸዋል፡፡ ከ 330-500 ኪሎ ቮልት ሀይል ተሸካሚ መስመሮች በድምሩ 10 ሜትር፣
ከ 220-330 ኪሎ ቮልት መስመሮች በድምሩ 8 ሜትር፣ ከ 150-200 ኪ. ቮልት በድምሩ 6 ሜ፣ ከ 110-150
ኪ.ቮ 5 ሜ፣ ከ 35-110 ኪ.ቮ 4 ሜ እንዲሁም እስከ 20 ኪ. ቮልት በድምሩ 2 ሜትር ከማንኛውም ነገር
መራቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የመንገድ መብራቶች ከመሬት 470 እና 550 ሴንቲ ሜትር ከፍታ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 62


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ባለ 0.4 ቮልት ኃይል ተሻካሚ መስመር የመጨረሻው ጫፍ ወደ ማንኛውም ህንጻ/ግቢ ሲገባ ከመስኮት፣
ከጣሪያ ጠርዝ ከመሳሰሉት መስመሩ የተሸፈነ ከሆነ 50 ሴንቲ ሜትር ያልተሸፈነ ከሆነ ደግሞ 100 ሴንቲ
ሜትር መራቅ ይኖርበታል፡፡

በመሬት ውስጥ የሚዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ከተቀበሩ በኋላ ያንያህል ጥገና አያስፈልጋቸውም፡፡
ከፍተኛ ቮልት ተሸካሚ መስመሮች በመሬት ውስጥ ከተቀበሩ በኋላ ያለምንም ጥገና እስከ 30 ዓመት
ማገልገል ይችላሉ፡፡ መስመሮቹ መሬት ውስጥ የሚቀበሩበት ጥልቀት ከ 0.5 ሜትር ማነስ የሌለበት ሲሆን
ለመንገድ እና ትራፊክ መብራቶች የተለየ መስመር መዘርጋት አለበት፡፡ የኤሌክትሪክ መስመሩ አስፋልት
መንገድ የሚያቋርጥ ከሆነ በ 20 ሴንቲ ሜትር ዲያሜትር ኮንክሪት ተሸፍነው 100 ሴንቲ ሜትር መቀበር
ይኖርባቸዋል፡፡ መስመሩ የሚዘረጋው በእግረኞች መንገድ ላይ ከሆነ ጥልቀቱ ቢያንስ 100 ሴንቲ ሜትር ሆኖ
ከመንገዱ ጠርዝ የሚኖረው ርቀት 1.5 ሜትር መሆን አለበት፡፡

የኤሌክትሪክ መስመር ከቴሌፎን መስመሮች 0.5 ሜትር የጎንዮሽ ርቀት ሊኖረው የሚገባ ሲሆን ከፍሳሽ
ቆሻሻ እና ከነዳጅ መስመሮች 1 ሜትር እንዲሁም ከውሃ መስመር 0.7 ሜትር መራቅ ይኖርበታል፡፡

የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች (sub-stations) ግንባታ በዘፈቀደ ሳይሆን በዚሁ ሰነድ በመሰረተ ልማት
አውታር ዝርጋታ ላይ በተመለከተው መሠረት በጥንቃቄና የከተማውን የወደፊት መስፋፊያ ግምት ውስጥ
ያስገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

የቴሌ ኮሙኒኬሽን /ቴሌፎን፣ ቴሌግራም/ መስመሮች፡ የአየር ላይ ኬብሎች ከሚደግፋቸው ምሶሶ አናት 50
ሴንቲሜትር ዝቅ ብለው ይዘረጋሉ፡፡ በፖሎች መሀከል የሚኖረው ርቀት 40 ሜትር አካባቢ ሲሆን ተጨማሪ
ድጋፍ ካልተደረገላቸው በቀር ከ 50 ሜትር በላይ መራራቅ የለባቸውም፡፡ መስመሮቹ ከመሬት በላይ
ከፍታቸው በመንገድ ትይዩ 450 ሴንቲ ሜትር ሲሆን መንገድ የሚያቋርጡ ከሆነ ደግሞ 550 ሴንቲ ሜትር
መሆን አለበት፡፡

በመሬት ውስጥ የሚዘረጉ መስመሮች መሬት ውስጥ የሚኖራቸው ጥልቀት በእግረኛ መንገድ፣ እርሻ
ቦታዎችና ደኖች አካባቢ ቢያንስ 80 ሴንቲሜትር ሲሆን የመኪና መንገድ ላይ ደግሞ ከ 1 ሜትር ማነስ
የለበትም፡፡ መስመሮቹ ከሌሎች መስመሮች ማለትም ከመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ
መስመሮች ጎን ለጎን ከሆኑ 30 ሴንቲ ሜትር፣ በላይና በታች የሚተላለፉ ከሆነ 15 ሴንቲ ሜትር መራራቅ
ሲጠበቅባቸው ከኤሌክትሪክ መስመር ደግሞ ጎን ለጎንም ሆነ በላይና በታች የሚተላለፉ ከሆነ 45 ሴንቲ
ሜትር መራራቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ለኬብል ዝርጋታ በሚቆፈሩ ሁለት manholes መሀከል የሚኖረው ርቀት ከ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 63


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

200 ሴንቲ ሜትር መብለጥ የለበትም፡፡ ቦታ ከመቆጠብ አንጻር ኬብሎች chambers or cable
vaults/trenches ውስጥ ይቀመጣሉ፡፡

የጎርፍ ማስወገጃ መስመሮች፡ የጎርፍ ማስወገጃ መስመር ምንግዜም ከውሃ መስመር በላይ መዘርጋት
ያለበት ሲሆን ጫናን ከመቋቋም አንጻር የጉድጓዱ ጥልቀት 1.25 ሜትር ቢሆን በቂ ሲሆን basements
በሚገኝበት የከተማው ክፍሎች የጉድጓዱ ጥልቀት ከመሬት በታች ከ 2 እስከ 2.5 ሜትር መሆን
ይጠበቅበታል፡፡ የጎርፍ ማስወገጃ መስመር ከውሃ መስመር 1.5 ሜትር እንዲሁም ከሌሎች ማንኛውም
መስመሮች 1 ሜትር መራቅ አለበት፡፡ የጎርፍ ማስወገጃ Manholes የጎርፍ እና የተዳፋታማነት መጠን
በሚጨምርባቸው አካባቢዎች፣ መስመሩ በሚታጠፍባቸው ቦታዎች እንዲሁም ገባሪ ጎርፍ መስመሮች
በሚገኙበት ቦታዎች ላይ ከ 150 ሜትር ባልበለጠ ርቀት መገንባት ይኖርባቸዋል፡፡

የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ፡ በኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ ዋና ዋና ከሆኑት ችግሮች መሀከል አንዱ የቆሻሻ
አያያዝ/ አስተዳደር ነው፡፡ የቆሻሻ አያያዝ/አስተዳደር በሥሩ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎችን ማለትም የደረቅ
ቆሻሻ እና የፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝን ያካትታል፡፡ የተሟላ የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት መኖር
ለአንድ ከተማ ነዋሪዎች ጤንነት መጠበቅ ወሳኝ ከመሆኑም ባሻገር ምርታማነትን ይጨምራል፤
የከተማውንም ገጽታ በማስዋብ ለመኖሪያና ለሥራ የተመቻቸ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በተለይም ታሪካዊ፣
የመዝናኛ እና ሌሎች ትላልቅ የንግድና የአገልግሎት መስጫ ማዕከል የሆኑ ከተሞች ጽዳትና ውበታቸው
ሲጠበቅ የቱሪስት ፍሰትን በማበረታታት ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

ከደረቅ ቆሻሻ ጋር በተገናኘ በፕላን ዝግጅት ወቅት መካተት ካለባቸው ጉዳዮች ውስጥ ለትልልቅ ከተሞች
እስታንዳርዱን የጠበቀ የደረቅ ቆሻሻ የገንዳ ማስቀመጫዎች፣ የቅብብሎሽ ጣቢያዎች፣ ማስወገጃ ቦታዎች
(dump site or sanitary landfill) እና ለመልሶ ጥቅም አገልግሎት ማዘጋጃ የሚሆኑ ቦታዎች ናቸው፡፡
የደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት መስጫ ገንዳዎች ቦታ በመኖሪያ፣ ንግድ አካባቢ፣ የተለያዩ ተቋማት አካባቢ ሲሆኑ
አካባቢዎቹ/ቦታዎቹ መኪና በቀላሉ የሚገባባቸው፣ ከመንገድ ገባ ያሉና የራሳቸው ከለላ (Buffer)
አለባቸው፡፡ በተጨማሪም እንደ አ/አ ላሉ ትላልቅ ከተሞች የቅብብሎሽ ጣቢያ የሚያስፈልግ ጣቢያው
ደረቅ ቆሻሻ ወደ ማስወገጃ ሥፍራ ከመጓጓዙ በፊት በአነስተኛ ተሸከርካሪዎች ማዕከላዊ በሆነ ሥፍራ
እየተሰበሰበ በመኖሪያ ቤት የሚጠራቀመውን ቆሻሻ ከመቀነስ በተጨማሪ የመለየት ሥራ የሚሰራበት እና
የቀልዝና መልሶ መጠቀም ሥራን ያካተተ ጊዜያዊ ማቆያ ቦታ ነው፡፡ ይህ ሥፍራ የደረቅ ቆሻሻ ማሰባሰቢያ
መስመሮችን ባማከለ ሥፍራ፣ ከመኖሪያና ሥራ አካባቢ በቂ ርቀት ያለው፣ ረግረጋማ ያልሆነ መሬት፣
ሜዳማ አካባቢ፣ ከለላ (Buffer) ያለው፣ ወዘተ መሆን ይገባዋል፡፡ ዝርዝሩ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ
ስትራቴጂ ላይ ተጠቁሟል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 64


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ (dump site or sanitary landfill) ቦታዎች በከተማ ዳርቻ ከመኖሪያና ሌሎች
የከተማ አገልግሎቶች ተለይተው በአካባቢ ላይ ብክለት ሊያስከትሉ በማይችሉበት አካባቢ መሆን
ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተስማሚ የመሬት አቀማመጥ/ተዳፋት፣ ጂኦሎጂአዊ ችግር የሌለበት አካባቢ፣
የመሬት መንሸራተትና መናድ አደጋ የሌለበት አካባቢ፣ ጎርፍ የማያጠቃው አካባቢ፣ ከመኖሪያና ሌሎች
አካባቢዎች በቂ ርቀት ያለው፣ ከከተማው ማስፋፊያ አቅጣጫ እና ከንፋስ መምጫ አቅጣጫ በተቃራኒው፣
የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሃን በማይበክልበት አካባቢ፣ ወዘተ መሆን ይገባዋል፡፡ ከመደበኛ ደረቅ ቆሻሻ
ማስወገጃ ቦታ በተጨማሪም በትላልቅና የኢንዱስትሪ ከተሞች እንደ ከተሞቹ ተጨባጭ ሁኔታ ልዩ
ጥንቃቄ ለሚፈልጉ አደገኛ ቆሻሻ ተብለው ለሚመደቡ ደረቅ ቆሻሻዎች በዚያው አካባቢ ቦታ መያዝ
ይገባዋል፡፡ ከተሞቹ አነስተኛና መካከለኛ በሚሆኑበት ወቅት ቆሻሻን በተለያዩ ዘዴዎች (በማዳበርያ፣ በሰው
በሚገፋ ጋሪ፣ በእንሰሳት በሚጎተቱ ተሽከርካሪዎች፣ ወዘተ) በማሰባሰብ ወደ ቆሻሻ ማከማቻ በማጓጓዝ
እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ ዝርዝሩ በደረቅ ቆሻሻ ማኔጅመንት ስትራቴጂ ላይ ተጠቁሟል፡፡

ከፍሳሽ ቆሻሻ ጋር በተያያዘ በከተሞች የማህበረሰብና የህዝብ መጸዳጃ ቦታዎች (community & public
toilets) ህዝብ በብዛት በሚሰባሰብባቸው አካባቢዎች፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጠራቀሚያና ማጣሪያ ቦታዎች
ደግም ከከተማ ወጣ ባለ አካባቢና አካባቢን በማይበክልበት አግባብ መሆን ይገባዋል፡፡ በተጨማሪም የፍሳሽ
ቆሻሻ ማስወገጃ ስርዓት /ሲዎሬጅ ሲስተም/ በትላልቅ ከተሞች የሚዘረጋበት ቦታዎችን በፕላን ላይ
ማመላከት ይገባል፡፡

ሸ. ሌሎች አገልግሎቶች /Special Functions/

በከተማ ፕላን በጉልህ ከሚታወቁት የመሬት አጠቃቀም ዓይነቶች በባህሪያቸውና በተፈጥሮአቸው ከሌሎቹ
ለየት ላሉት የሚከለል ቦታ ልዩ አገልግሎት ሰጪ (Special Function) በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ልዩ
አገልግሎት ሰጪ የሚባል የመሬት አጠቃቀም በውስጡ ከሚያካትታቸው ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የተፈጥሮና
ሰው ሰራሽ ጥብቅ አካባቢዎች (ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ አርክዮሎጂያዊ፣ ወዘተ አካባቢዎች)፣ በተፈጥሮ አደጋ
የሚጠቁ አካባቢዎች (በጎርፍ፣ የድንጋይ ናዳ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ድንጋያማ ቦታዎች፣ ወዘተ)፣
የተከለከሉ አካባቢዎች (ኤምባሲዎች፣ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች፣ የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ የኤሌክትሪክ
መስመሮች፣ ወዘተ.)፣ የገጸ-ምድርና የከርሰ-ምድር ውኃ ሀብት (ወንዞች፣ ረግረግማ ስፍራዎች፣ ወዘተ.)፣
ላልታሰቡ አገልግሎቶች የሚውሉ መጠባበቂያ ቦታዎች ናቸው፡፡ በልዩ ልዩ አገልግሎት ስር የሚጠቃለሉ
የመሬት አጠቃቀም አይነቶች ከጠቅላላው የመሬት አጠቃቀም ውስጥ የሚሸፍኑት በመቶኛ ሲሰላ ከ 15-20
በመቶ ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 65


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከለለው የመሬት አጠቃቀም ክፍል የተለያዩ
ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይታመናል፡፡ እነርሱም አንደኛ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ የአርክዮሎጂ ወዘተ የመሳሰሉ
ቦታዎች የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎችን በመሳብ ለከተማው የኢኮ-ቱሪዝም ገቢን በማስገኘት ከፍተኛ
ጠቀሜታ አላቸው፡፡ ሁለተኛ በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት በጎርፍ፣ በድንጋይ ናዳ፣ በመሬት መንሸራተትና
በመሳሰሉት የተፈጥሮ አደጋ ሊጠቁ የሚችሉ አከባቢዎችን ለይቶ በማመላከት አደጋ በተከሰተ ጊዜ ሊደርስ
የሚችለውን የህይወት፣ የንብረት ውድመት እና የአየር ብክለት ለመቀነስ ብሎም ለማስቀረት ይረዳል፡፡
ሦስተኛ ወታደራዊ ካምፖች፣ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወዘተ አካባቢዎችን ለብቻ ከልሎ
በፕላን ላይ ማመላከት አስፈላጊ የሆነበት ዋናው ምክንያት እነዚህ ተቋማት ከመኖሪያ ቤቶች፣ ከንግድ
ቤቶች፣ የህዝብ መሰብሰቢያ፣ ወዘተ ስፍራዎች በተወሰነ ርቀት ላይ መቀመጥ ስላለባቸው ነው፡፡ አራተኛ
የገጸ-ምድርና የከርሰ-ምድር ውሃ ሀብት ክምችት ያለባቸው ስፍራዎች በትክክል ተለይተው በፕላን
ማመላከት አስፈላጊ የሆነበት ዋናው ምክንያት ይህ ስፍራ ለከተማው ነዋሪ በመጠጥ ውኃና ሌሎች
አገልግሎቶች ማለትም ለከተማ ግብርናና ለመሳሰሉት ጥቅሞች ስለሚውል ነው፡፡ አምስተኛ ለልዩ ልዩ
ተግባራት እንዲውሉ ታስበው በፕላን ላይ የሚከለሉ ቦታዎች በከተማው ደራሽ የሆኑና ቀድሞ ያልታሰቡ
የልማት ወይም ሌሎች አስፈላጊ ጥያቄዎች ሲከሰቱ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡

2.1.6. ሌሎች ከመዋቅራዊ ፕላን ጋር ተያያዥ የሆኑ መሰረታዊ ሀሳቦች

ሀ. የከተማ - ከተማ እና የከተማ - ገጠር ትስስር

ከተሞች ከሌላው አካባቢ ተነጥለው ብቻቸውን ሊያድጉ የሚችሉ አካላት አይደሉም፡፡ የከተማ ፕላን
ዝግጅት ስራ ከመጀመሩ በፊት ፕላን በሚዘጋጅበት ከተማ ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ
የሚችሉ አካባቢዎች ወይም የተጽዕኖ ክልሎች ይለያሉ፡፡ ከተሞች በአካባቢያቸው ከሚገኙ ከተሞችና
የገጠር አካባቢዎች /የተጽዕኖ ክልሎች/ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በአስተዳደራዊ ወዘተ የተሳሰሩ
በመሆናቸው ከአካባቢያቸው ጋር ተደጋግፈው ሊያድጉ የሚችሉበትን ሁኔታ ማጥናት አስፈላጊ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የከተማ ልማት ስራችን በፈጣን የግብርና ልማት ስራ የሚረጋገጥ መሆኑ የሚታወቅ
ሲሆን የገጠሩ አርሶአደር በፈጣን የገጠር ልማቱ ሳቢያ ገቢው የሚጨምር በመሆኑ ከፍላጎትም ሆነ ለምርቱ
ግብአት ከማሟላት ጋር ተያይዞ የመግዛት አቅሙም በዚሁ መሰረት ይጨምራል፡፡ ለአርሶ አደሩ
የሚጠቅሙት ግብአቶች የሚመረቱት ወይም የሚከፋፈሉት ደግሞ እንደየከተሞቹ ደረጃ በከተሞች
አካባቢ ለስራ በተሰማሩት በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አማካይነት ነው፡፡ ለአርሶአደሩ በቀረቡት አነስተኛ
ከተሞች አካባቢ የሚገኙት የተወሰኑ አገልግሎቶችና ሸቀጦች ሲሆኑ በመካከለኛና ከፍተኛ ከተሞች ደግሞ
በተሻለ ሁኔታ በይበልጥ የተሟላና ሰፋ ያለ አገልግሎትና ሸቀጦች ይቀርባሉ፡፡ በመሆኑም የተለያዩ ከተሞች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 66


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

እንደየደረጃቸውና እንደሚያቀርቡት አገልግሎት መጠን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተጠቃሚነታቸው


ይረጋገጣል፡፡

በመሆኑም ፕላን የሚዘጋጅለት ከተማ በተጽዕኖ ክልሉ ውስጥ ለተካተቱ ከተሞች እና የገጠር አካባቢዎች
የሚሰጣቸው ማንኛውም የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የአስተዳደራዊ ወዘተ አገልግሎቶች እንዲሁም
ከተማው ከከተሞቹና የገጠር አካባቢዎች የሚያገናኛቸው አገልግሎቶች ከተዳሰሱ በኋላ በፕላን ሊፈቱ
የሚገባቸው ጉዳዮች በፕላን እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ ከገጠሩ አካባቢ ከፍተኛ የእህል ምርትና ከብቶች
ወደ ከተማው የሚገቡ ከሆነ በከተማው ውስጥ የእህልና የከብት ገበያዎች እንዲሁም መጋዘኖች ግንባታ
የሚሆን ቦታ በፕላኑ ላይ መያዝ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ለ. የፕላን ትግበራ ቅደም ተከተል ፕላን /Phasing Plan/

የከተሞች መዋቅራዊ ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ ቀጣይ ስራ ፕላኑን መተግበር መሆኑ ይታወቃል፡፡ መዋቅራዊ
ፕላን ደግሞ የሚተገበረው የአካባቢ ልማት ፕላኖችን በተመረጡ ስትራቴጂያዊ አካባቢዎች በማዘጋጀት
ሲሆን ይኸውም በመስፋፊያና በከተማው ውስጥ ያረጁ አካባቢዎች ላይ የሚያተኩሩ ፕላኖችን ያካትታል፡፡
መዋቅራዊ ፕላኑን ለመተግበር የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላኖች በአንድ ጊዜ ለሁሉም የከተማው ክፍል
ወይም ለመዋቅራዊ ፕላኑ ሙሉ ለሙሉ ማዘጋጀት ከአቅም አንጻር የሚቻል ካለመሆኑም በተጨማሪ
ያንያህል አስፈላጊ ባለመሆኑ መልማት የሚገባቸውን አካባቢዎች ቅደም ተከተል በማውጣትና ይህንኑ
ቅደም ተከተል በመዋቅራዊ ፕላኑ ላይ ከልሎ ወይም ለይቶ በማስቀመጥ በቅደም ተከተሉ መሰረት
መጀመሪያ መልማት ለሚገባው አካባቢ የአካባቢ ልማት ፕላን በማዘጋጀት አካባቢውን ማልማት
ያስፈልጋል፡፡ ለተለያዩ አካባቢዎቸ በቅደም ተከተሉ መሰረት የአካባቢ ልማት ፕላን በሚዘጋጅበት ወቅት
ፕላኖቹ ከመዋቅራዊ ፕላኑ ጋር የሚናበቡና የሚጣጣሙ መሆኑ መረጋገጥ ያለበት ሲሆን ከዚህም
በተጨማሪ አንድ የአካባቢ ልማት ፕላን ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ከጎኑ ሌላ የአካባቢ ልማት ፕላን
ሲዘጋጅ ይህ ፕላን ቀድሞ ከተሰራው ከጎኑ ካለው የአካባቢ ልማት ፕላን ጋር የሚጣጣምና የሚናበብ መሆን
አለበት፡፡

2.2. የሀገሪቱ የመዋቅራዊ ፕላን አዘገጃጀት ነባራዊ ሁኔታ ትንተና

2.2.1. ክፍለ ኢኮኖሚያዊ የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 691/2003 እንደገና በአዲስ መልክ ከተደራጀ
በኋላ በሀገሪቱ የአምስት አመት ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተመለከቱትን ሀገራዊ አቅጣጫዎችና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 67


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ግቦች መሰረት በማድረግ የአምስት ዓመት ክፍለ ኢኮኖሚያዊ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
አዘጋጅቷል፡፡

በዚሁ ሰነድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና
አፈጻጸም በተሟላ የህግ ማዕቀፍ አደረጃጀትና አሰራር እንዲመራ የሚደረግ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ይህንንም
ለማስፈጸም በጥናትና ምርምር የተደገፉ የተለያዩ ከከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ጋር እንዲሁም
ከጽዳት፣ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጋር የተያያዙ የተሟሉ የአሰራር ማንዋሎችና ስታንዳርድ ሰነዶች
እንደሚዘጋጁ ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሀገር አቀፍ የልማት ቀጣና እና የልማት ማዕከላትን ታሳቢ
ያደረገ የከተማ ልማት ስኪም ጥናት እንደሚሰራና ተግባራዊ እንደሚደረግ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ በከተማ
መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት ዙሪያም የከተማ ገጠር ትስስርን ከማጠናከር አንጻር እንዲሁም ባለሀብት
መሆን የጀመረውን አርሶ አደር በከተማ ልማት ዘርፍ እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በአምስት
አመት ውስጥ ለ 750 አነስተኛ ከተሞች እና ለመካከለኛና ከፍተኛ ከተሞች የከተማ ፕላን እንደሚዘጋጅ
በዕቅድ ተይዟል፡፡ በተመሳሳይም ለከንቲባዎች፣ ሥራ አስኪያጆችና ባለሙያዎች ስለከተማ ፕላን
አዘገጃጀትና አተገባባር የተጠናከረ የአቅም ግንባታና ድጋፍ ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ
ያረጋግጣል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በመንግስት የፕላን ዝግጅት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች
በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፊዚካላዊ፣ ስፓሻልና ጂ.አይ.ኤስ. ሙያ ዘርፍ በተከታታይ የአቅም ግንባታ
ስልጠና ይሰጣል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በከተሞች ለሚዘጋጁ መዋቅራዊ ፕላኖችና የአካባቢ ልማት
ፕላኖች ላይ የክትትል፣ ግምገማና ግበረ መልስ በማካሄድ በሥራው ላይ ለሚሳተፉት ክልሎች፣ ከተሞችና
የግሉ ዘርፍ አቅማቸው እንዲጎለበት እንደሚደረግ የሚያብራራ ሲሆን ይህን ዕቅድ ለማሳካት ይህ ስትራቴጂ
አስፈላጊ በመሆኑ ስትራቴጂውን ለማዘጋጀት የተደረጉ የውጫዊና ውስጣዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ
እንደሚከተለው ቅርቧል፡፡

በአገራችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ቴክኖሎጂያዊና


አካባቢያዊ ሁኔታዎች በመሰረታዊ ካርታ እና ከተማ ፕላን ዝግጅት ዙሪያ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉ
ውጫዊ ስጋቶችና መልካም አጋጣሚዎችም ያሉ ሲሆን እነሱም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

አገሪቱ ያልተማከለ አስተዳደራዊ መዋቅር መዘርጋቷና በመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት መመራቷ
ከተሞች በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ጉልህ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ የከተማ ምክር ቤቶች
የሚያስተዳድሯቸውን ከተሞች ፕላን አጽድቆና አሻሽሎ ልማታቸውን እንዲመሩ ስልጣን መስጠቱ
ለከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጻም ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ በዚህ ሂደት በአገር ደረጃም ሆነ በክልልና
ከተሞች ሰላምና መረጋጋት በመኖሩ የከተማ ምክር ቤቶች የልማት ስራዎቻቸውን በብቃት ለማከናወን
እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለይ በበላይ አመራር ደረጃ የከተማ መሬት ልማት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 68


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በፕላን እንዲመራና የፖለቲካል ኢኮኖሚ አስተሳሰቡ ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ ተላቆ ወደ ልማታዊ
ፖለቲካል ኢኮኖሚ እንዲያመራ በተዋረድ ያለው አመራር ቁርጠኛ አቋም እንዲይዝበት ጥረት መደረጉ
ለከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም መሳካት ሌላው ምቹ ሁኔታ ነው፡፡ በአንጻሩ የተፈጠረው ያልተማከለ
አስተዳደር እና አደረጃጀት በአግባቡ ካልተመራና በሥራ ላይ ካልዋለ የኃላፊነት መደራረብና አንዱ በአንዱ
ኃላፊነት ጣልቃ በመግባት በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል፡፡
የከተማ ምክር ቤቶች በተለይም ከፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም አንጻር ኃላፊነታቸውን በተገቢው ተገንዝበው
የሚጠበቅባቸውን ሚና መጫወት ካልቻሉ በመስኩ ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊፈጥር ይችላል፡፡
በየደረጃው በከተማ መሬት ላይ ተንሰራፎቶ ያለው የኪራይ ሰብሳቢነት የፖለቲካል ኢኮኖሚ አስተሳሰብ
ወደ ልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ እንዲያመራ እየተደረገ ያለው ትግል በጥንቃቄ ካልተመራ በሚፈለገው
ፍጥነትና አቅጣጫ ውጤት ላያስመዘግብ ቢችል በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጸጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ
ሊፈጥር ይችላል፡፡

ከኢኮኖሚ አንጻር አገሪቱ በየዓመቱ ከፍተኛ የሚባል የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች እነደሆነ ይታወቃል፡፡
ከአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከተሞች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ ያለ
በመሆኑ የኢኮኖሚ እድገቱ ለከተሞች እድገት አስተዋጽዎ ስለሚያደግ ይህም በአንድ በኩል የከተሞች
ፕላን ፍላጎትን የሚጠቁም ሲሆን በሌላ በኩል የከተሞች በራሳቸው አቅም/ወጪ ፕላን ማዘጋጀት
እንዲችሉ እድል ሊፈጥር መቻሉ እንደ መልካም አጋጣሚ / እድል ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ በሌላ መልኩ
በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ እየተከሰተ የሚገኘው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት በሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት ላይ
እንዲሁም በከተሞች አቅም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ በማሳደር ለከተሞች ፕላን ዝግጅት አስፈላጊ በሆኑ
የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ላይ የዋጋ ንረት ማስከተል የሚችል መሆኑ እንደ ስጋት ሊታይ የሚችል ጉዳይ
ነው፡፡

ቴክኖሎጂን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ለመሠረታዊ ካርታና ከተማ ፕላን ሥራ የሚያገለግሉ
የቴክኒክ መሳሪያዎች ከጂ.አይ.ኤስ እና ሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጂ ጋር በአስደናቂ ፍጥነት እያደጉ
በመምጣታቸው የሳታላይት ምስልና የአየር ፎቶግራፎችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወጪ ቆጣቢና
ጥራት ያለው የከተማ ፕላን ማዘጋጀት መቻሉ እንዲሁም የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ
ቅናሽ እያሳየ መምጣቱ በከተማ ፕላን ዘርፍ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያስችል
መሆኑ ውጫዊ የሆነ ምቹ አጋጣሚ ሲሆን በአንጻሩ በአገር ውስጥ የካበተ ልማድ ባለመኖሩ በቴክኖሎጂ
አቅራቢው ድርጅት የሚቀርቡትን የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች የጥራት ደረጃ በአግባቡ የመለየት አቅም አናሳ
በመሆኑ ምክንያት የሚፈለገውን ጥራት የጠበቀ ቴክኖሎጂ ያለማቅረብ እንደ ስጋት የሚታይ ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 69


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከማሕበራዊ ጉዳዮች አንጻር በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ ቁጥር በፍጥነት እያደገ መምጣቱ የከተሞችና
የከተማ ነዋሪዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እያደገ እንዲመጣ ስለሚያደርግ የከተማ ፕላን ፍላጎት ከጊዜ ወደ
ጊዜ እየጨመረ እንዲመጣ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ከተሞች ከዕድገታቸው ጋር ያልተመጣጠነ
የህዝብ ቁጥር መጨመርና በገጠር አማራጭ የሥራ ዕድል አለመስፋፋት የገጠር ከተማ ህዝብ ፍልሰት
ሊያስከትል መቻሉና በከተሞች ማዕከላዊ ቦታዎች ያሉ መኖሪያ ቤቶች፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና
መሠረተ ልማት አውታሮች በእርጅና ምክንያት እየደቀቁ መምጣታቸው የራሱን ችግር እየፈጠረ
ከመሆኑም በተጨማሪም በከተማ ዳርቻዎችና ማስፋፊያ አካባቢዎች ህገ ወጥ ግንባታዎች እንደ እንጉዳይ
በየጊዜው እየተፈጠሩና እየተስፋፉ መምጣታቸው እንደ አንድ ስጋት ይታያል፡፡ ሌላው በአገር ውስጥ በግልና
በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘርፉ በብዛት የሰው ኃይል እየሰለጠነ መሆኑ መልካም አጋጣሚ
ሲሆን በዚህ ረገድ ለሚደረገዉ ትግል ስኬታማነት የሚኖረው አስተዋጽኦ ቀላል እንደማይሆን ይገመታል፡፡
በሌላ በኩል በዘርፉ የተሰማራው የሰለጠነ የሰው ሃይል በግሉ ዘርፍና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ሊሳብ
መቻሉ ሊያጋጥም የሚችል ስጋት ነው፡፡

የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች (Evironmental Issues) በዓለም አቀፍ፣ በአህጉር እና በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ
ትኩረት ያገኘ አጀንዳ መሆኑ፤ ተቀባይነቱም እያደገ መምጣቱና እንዲሁም የአካባቢ ችግሮችን በጋራ
ለመቋቋም አህጉራዊና አለማቀፋዊ ትብብር እየዳበረ መምጣቱ ወደፊት ከአካባቢ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ
መልኩ በከተማ ፕላኖች ላይ የሚጠኑ ጥናቶችና ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ
እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ ነው፡፡

ከላይ ለማቅረብ የተሞከረው የውጫዊ ሁኔታዎች ትንተና ሲሆን በከተማ ፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጸም
ዙሪያ በሀገሪቱ ያለው ውስጣዊ ሁኔታዎች ትንተና እንደሚከተለው ቀርቧል፡

2.2.2. የህግ ማዕቀፎች /አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ማኑዋሎች/

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከተማ ልማት ፖሊሲ፣ የከተማ ፕላን ህግ፣ የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም
ማኑዋልና ስታንዳርዶች መዘጋጀታቸውና በዚህም መሰረት የአገሪቱን ከተሞች በፕላን ለመምራት
እየተደረገ ያለው ጥረት ከፖሊሲና ህግ ማዕቀፎቸ አንጻር እንደ ጠንካራ ጎን የሚታይ ቢሆንም በስራ ላይ
በዋሉት የከተማ ፕላን ህግ፣ የከተማ ፕላን ማኑዋልና ስታንዳርዶች ላይ የተደረገው ዳሰሳ አንዳንድ ችግሮች
እዳሉባቸው ይጠቁማል፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ በክልልም ይሁን በፌዴራል ደረጃ ያሉ ከተማ ልማት ነክ ህጎች በዝርዝር የተዳሰሱ ሲሆን
በዋናነት በፌዴራል ደረጃ የተዘጋጀው የከተማ ፕላን አዋጅ ቁጥር 574/2000 ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ አዋጁ
በሀገሪቱ እንዲሰራባቸው ስለተፈቀዱ የፕላን ዓይነቶች፣ ፕላንን ስለማፅደቅና ልማትን ስለመፍቀድ፣ ያረጁ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 70


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አካባቢዎችን በፕላን መልሶ ስለማልማት እንዲሁም ከከተማ አስተዳደር ጀምሮ በተለያዩ እርከን የሚገኙ
የመንግስት አካላት ሥልጣንና ኃላፊነትን ያብራራል፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 56 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ የክልል
መንግስታት የከተማ ፕላኖችን በአግባቡ ስለመፈጸማቸው እንደሚከታተሉ፣ እንደሚገመግሙና
እንደሚያረጋግጡ ሥልጣንና ተግባር ተሰጥቷቸዋል፡፡ በተመሳሳይ በአዋጁ አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ
የፌዴራል መንግስት ተጠሪ የሆኑ ከተሞች እንደየአግባቡ ከክልልና አገር አቀፍ የከተማ ልማት ዕቅዶች ጋር
የተጣጣሙ የከተማ አቀፍ መዋቅራዊና የአካባቢ ልማት ፕላኖች እንዲያዘጋጁ ሥልጣንና ተግባር
ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሆኖም ግን የክልልና አገር አቀፍ የከተማ ልማት ዕቅዶች ወጥ በሆነ መልኩ
ባለመዘጋጀታቸው የከተማ ፕላኖች በተናጠል ማለትም የአገር አቀፍም ሆነ የክልል እቅዶችን ግምት ውሰጥ
ሳያስገቡ በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ፡፡

የከተማ ፕላን አዋጅ ቁጥር 574/2000 ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል በክልሎች እየወጣ ያለ ደንብና
መመሪያ ተጠናቆ ሙሉ ለሙሉ ለስራ ዝግጁ ባለመሆኑ ወጥነት ያላቸው የፕላን ዓይነቶች አዘገጃጀት ላይ
ክፍተት ፈጥሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአዋጁ የከተማ ዲዛይን ዝርዝር ፕላን ጉዳይ ተገቢው ትኩረት
የተሰጠው ባለመሆኑ በዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች እንኳን የከተማ ዲዛይን ስራዎች በማኑዋል የተደገፉ
አይደሉም፡፡

አገር አቀፍ የከተማ ፕላን አዋጁን ለማስፈጸም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተዘጋጅተው የሚገኙት ሞዴል
ረቂቅ ደንብና መመሪያ የተዳሰሱ ሲሆን ማብራሪያ የሚፈልጉ አንዳንድ አንቀጾች በረቂቆቹ በተገቢው
ሳይብራሩ እንዳሉ መቀመጣቸው በዳሰሳው ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በረቂቆቹ ውስጥ የሀሳብ
ድግግሞሽና በአጠቃላይ ግልጽነት የሚጎድላቸው ማብራሪያዎች መኖራቸው ዳሰሳው ያረጋግጣል፡፡ በከተማ
ፕላን አዋጁ ውስጥ ያልተካተተ ነገር ግን በአንዳንድ ክልሎች ውስጥ ለአነስተኛ ከተሞች እየተዘጋጀ
የሚገኘው የመሰረታዊ ፕላን ጉዳይ ተንጠልጥሎ መቅረቱ ሌላው የሚጠቀስ ችግር ነው፡፡ አዋጁ ስለ ከተማ
ፕላን ክትትልና ግምገማ የሚያነሳው አንቀጽ ካለመኖሩ በተጨማሪ በከተማ ፕላን ትግበራ ወቅት መሬትን
ፕላኑ ከሚፈቅደው ውጪ ለሌላ አገልግሎት በማዋል በአስፈጻሚ፣ ፈጻሚና ባለድርሻ አካላት የሚከሰተውን
የሕግ ጥሰት ለመከላከል የሚያስችል ግልጽና ጠንካራ የሕግ እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ አንቀፆችን
አያካትትም፡፡

በሌላ በኩል በየደረጃው ያሉ ለከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ ተዘጋጅተው በሥራ ላይ የሚገኙት
ማንዋሎችና የስታንዳርድ ሰነዶች ያልተሟሉና ወጥነት የሚጎድላቸው በመሆናቸው በሚፈለገው ጥራት
ሊያሰሩ የሚችሉ አይደሉም፡፡ በመሆኑም በሚዘጋጁ ፕላኖች ጥራትና አፈጻጸም ላይ ትልቅ ችግር እየታየ
ነው፡፡ ከማኑዋል ጋር ተያይዞ ሊነሳ የሚገባው ሌላ ጉዳይ በየጊዜው እያቆጠቆጡ ለሚፈጠሩ ከተሞች፣
ለገጠር ቀበሌ ማዕከላት እንዲሁም አዲስ ለሚመሰረቱ ከተሞች የፕላን አዘገጃጀት መመሪያም ሆነ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 71


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ማኑዋል አለመኖሩ ነው፡፡ በአገሪቱ በሺህ የሚቆጠሩ የገጠር ቀበሌ ማዕከላት ያሉ ሲሆን እነዚህም ማዕከላት
የወደፊት ከተሞች መሰረት ወይም ጥንስስ በመሆናቸው ከወዲሁ ማለትም ውስብስብ ሁኔታዎች
ከመፈጠራቸው በፊት ማዕከላቱን በፕላን መምራት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በስራ ላያ የሚገኙት
ማኑዋሎች ለነባር ከተሞች የተዘጋጁ በመሆናቸው ለገጠር ቀበሌ ማዕከላትና አዲስ ለሚመሰረቱ ከተሞች
የፊዚካል ዕድገታቸውን መምራት የሚያስችል ፕላን ዝግጅት ማኑዋል መዘጋጀት አለበት፡፡

በሀገር አቀፉ የከተማ ፕላን አዋጅ ላይ በተደረገው ዳሰሳ መሰረት ሊጠቀሱ ከሚችሉት ሌሎች ጉዳዮች
ውስጥ ስለ ከተማ ፕላን ክለሳና ማሻሻል እንዲሁም ስለ ከተማ ማደስና ማሻሻል የተጠቀሱት አንቀጾች
አሻሚና ግልጽ አለመሆን፣ የሕዝብ ተሳትፎ በፕላን ሂደት በግልጽ አለመቀመጡ፣ ምክር ቤት ወይም ከተማ
አስተዳደር የሌላቸው ከተሞች ፕላናቸውን በማን መጽደቅ እንዳለባቸው አለመጠቆሙ፣ የገጠር ቀበሌ
ማዕካላት ፕላን ዝግጅትን አስመልከቶ የተጠቀሰ አንቀጽ አለመኖር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

2.2.3. ተቋማዊ አደረጃጀት፣ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅርቦት

በከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት በፌደራል ደረጃ የከተማ ልማትና
ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር /የፖሊሲ ህግ ማዕቀፍና አሰራር ሥርዓትን በመቅረጽ የሪጉላቶሪና አቅም ግንባታ
ሥራዎችን ማከናወን/፣ በክልሎች የክልል ከተማ ፕላን ተቋማት /ፕላን ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ/ እና የከተማ ልማት
ቢሮዎች /ሬጉላቶሪ፣ ድጋፍ ስራዎች እና ፕላን ዝግጅት/ እንዲሁም ከተሞች /በዝርዝር ፕላን ዝግጅትና ትግበራ/ ሲሆኑ
በተቋማቱ አደረጃጀት፣ የሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ አቅርቦት ላይ የተደረገው ነባራዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡

በፌዴራል ደረጃ

በ 1999 ዓ.ም ሚኒስቴር መ/ቤቱ የአሰራር ስትራቴጂ ለውጥ በማድረግ ትኩረቱን የፓሊሲ፣ የህግ
ማዕቀፎችን፣ ስታንዳርዶችንና የአሰራር ሥርዓቶች መቀየስ እንዲሁም የአቅም ግንባታ፣ የክትትል፣
ግምገማና ግብረ መልስ ሥርዓት ዝርጋታ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከመስከረም
2003 ዓ/ም ጀምሮ ሚ/ር መ/ቤቱ በአዲስ መልክ ሲደራጅ ተቋሙን የከተማ ፕላን፣ ጽዳትና ውበት ቢሮ
በሚል ስያሜ በአራት አላማ አስፈጻሚ መምሪያዎች አደራጅቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ÃlW ysW `YL
B²T ና SB_RM kä§ ¯dL b¸flgW dr© §Y Yg¾LÝÝ

ይሁንና ያለው የሰው ኃይል በተወሰነ ደረጃ የአቅም ውሱንነት የሚታይበት ሲሆን በተለይም ወቅታዊና
ከእድገት ጋር ተያይዘው የሚመጡ አለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችና አዳዲስ አሰራሮችን ለይቶና አጥንቶ
ወደ አገሪቱ ከተሞች እንዲስፋፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የተጠናከረ ሥርዓት የለም፡፡ b!éW

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 72


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

lKLlÖC ktäC yxQM GNƬ y¶g#§è¶ |‰ãCN l¥kÂwN y¸ÃSCl# WSN q$úq$îCÂ
yt&KñlÖ©! mú¶ÃãC ያሉት bmçn# lktäC KLlÖC በ kt¥ P§N ZGJT xfÚ[M §Y xSt¥¥"
አቅም ለመፍጠር የአቅም ውስንነት ያለ ሲሆን የሚሰጡ ስልጠናዎች የከተሞች ርዕሰ ጉዳዮችም በየጊዜው
ሊከለሱ የሚገባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ያለው ባለሙያ ተቋማዊ ተልዕኮን በአግባቡ ተገንዝቦ
በመንቀሳቀስ ውጤት ለማስመዝገብ ያለው ተነሳሽነት ውስን መሆኑ ይታያል፡፡ ለመሰረታዊ ካርታና ፕላን
ዝግጅት አሰራር የሚረዳ የተሟላ የስታንዳርድና የማስፈጸሚያ ማንዋሎች አለመኖር እንዲሁም በውጤት
ላይ የተመሠረተ የአፈጻጸም፣ ክትትል፣ ግምገማና ግብረ መልስ ሥርዓት አለመዳበሩ የከተሞችንና
ክልሎችን አቅም በመደገፍ ረገድ ሰፊ ክፍተት መኖሩ ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡

በክልል ደረጃ

በክልሎች ያለው የከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማዊ አደረጃጀት የተለያየ ሲሆን በአንዳንድ ክልሎች
በኢንስቲትዩት ደረጃ በሌሎች ደግሞ በሥራ ሂደት ደረጃ በተለያዩ የክልል ከተማ ልማት ቢሮዎች ሥራ
ተደራጅተው ይገኛሉ፡፡ የውስጥ አደረጃጀት ላይ የተደረገው ዳሰሳ እንደሚጠቁመው በክልሎች ያሉ
አደረጃጀቶች ከስያሜ፣ በውስጣቸው ከሚያካትቷቸው የሥራ ሂደቶች ወይም ቡድኖቹ እንዲሁም ከክልል
እስከ ከተማ በተዘረጋው የፕላን ዝግጅትና አፈፃፀም መዋቅር አንፃር ወጥነት የሌላቸው ሲሆን በአንጻሩ
በትላልቆቹ ክልሎች ያለው አደረጃጀት ከታዳጊዎቹ የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በየተቋማቱ አሁን ተመድቦ ያለው የሰው ኃይል በመዋቅር ከተፈቀደው በአማካኝ 61 በመቶ ሲሆን
የጋምቤላ ክልል ከ 50 በመቶ በላይ በሰው ሃይል ያልተሞላ ክፍት መደብ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከሙያ ስብጥርና
ብዛት አንጻር በክልሎች መሀከል ልዩነት የሚታይ ሲሆን አንድን የከተማ ፕላን ለማዘጋጀት በአንዳንድ
ክልሎች ሁለት ባለሙያዎች ብቻ ሲሳተፉ በአንድ ክልሎች ግን የተሟሉ ሰባት ባለሙያዎችን
እንደሚያሰማሩ በዳሰሳው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ ከሰው ሀይል ጋር ከተያያዙ ችግሮች መሃከል ዋናዎቹ
በፕላን ዝግጅት የሚያስፈልገው የቡድን አወቃቀርና የሰው ኃይል ብዛትና የሙያ ስብጥር ላይ ወይነት
አለመኖር ናቸው፡፡

በክልሎች ለከተማ ፕላን ዝግጅት የሚያግዙ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በተለያያ የአቅርቦትና አጠቃቀም
ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ክልሎች በዞንና በከተማ ደረጃ ባሏቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጭምር አቅም
በፈቀደ መልኩ አስፈላጊ መሳሪያዎችን ለማሟላት ጥረት በማድረግ ላይ ቢሆኑም ተቋማቱ የተጣለባቸውን
ኃላፊነትና ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያስችላቸውን bqE yzmÂêE t&KñlÖ©! mú¶ÃãC xQRïT
WSNnT bmñ„ b¸flgW m-N F_nT yzRûN F§¯T ለ¥à§T ያልተቻለ ሲሆን ችግሩ በታዳጊ ክልሎች
ደግሞ የጎላ ነው ÝÝ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 73


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በከተማ ደረጃ

በማንኛውም አካል የሚዘጋጁ ፕላኖች የሚተገበሩት በከተማ አስተዳደሮች አማካኝነት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ከፕላን አፈፃፀም እና ክትትል አንጻር አብዛኞቹ ከተሞች ተመሳሳይ ቢሆኑም ከሰው ኃይል፣
ከመሳሪያዎችና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንጻር በመሀከላቸው ልዩነት ያለ ሲሆን በተለይ በአገሪቱ ከተሞች
ውስጥ በቁጥራቸው ትልቁን ድርሻ በሚይዙት በአነስተኛ ከተሞች ላይ ችግሩ የጎላ እንደሆነ በሚ/ር መ/ቤቱ
አማካኝነት የተካሄዱ የፕላን አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ
አስተዳደር የከተማ ፕላንና መረጃ ኢንስቲትዩት ከአደረጃጀት አንፃር ከማዕከል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ
የተዘረጋ መዋቅር ያለው ከመሆኑም ባሻገር በሰው ኃይል ብዛትም ሆነ ሥብጥር እንዲሁም በቁሳቁሶችና
የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ከሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት አንፃር ሲታይ በተሻለ አደረጃጀት ላይ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ በፌደራል፣ በክልልና በከተሞች ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ ተቋማቱ ለከተማ ፕላን ዝግጅትና
አፈጻጸም የሚያግዝ እስከ ታችኛው የአስተደደር እርክን ድረስ ወጥ የሆነ መዋቅራዊ አደረጃጀት
ካለመኖሩም ባሻገር በመዋቅሩ ያለው የሰው ኃይል የላቀና የተሟላ ዕውቀት አለመኖር እንዲሁም የዘመናዊ
ቴክኖሎጂ መሳሪያዎች አቅርቦት እጥረት በአሰራር ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች ናቸው፡፡

የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ

በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተወዳዳሪ
አግልግሎት ለከተሞች በማቅረብ የከተሞችን ልማት መደገፍ ይጠበቃል፡፡ ይሁንና የከተማ ፕላን ዝግጅት
አገልግሎት የሚሰጡ የግል አማካሪ ድርጅቶች በበቂ መጠን ያለመኖርና ያላቸው ልምድም ውስን መሆን
እንዲሁም የአመለካከት ችግሮች በመኖራቸው የተነሳ ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ በመደገፍ ላይ
አይስተዋሉም፡፡ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ጅምር ተሳትፎ ቢኖርም በዘርፉ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አንጻር
እየተደረገ ያለው ድጋፍ ከቁጥር የሚገባ አይደለም፡፡ በሁሉም ክልሎች በግሉ ዘርፍ የተሠሩት መዋቅራዊ፣
መሠረታዊና የአካባቢ ልማት ፕላኖች በጠቅላላው በቁጥር ከ 50 የማይበልጡ ሲሆን ይህም በሀገሪቱ ፕላን
ከተዘጋጀላቸው ከተሞች 7 በመቶውን ያህል ብቻ ይሸፍናል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ደረጃ
ያለው ልምድ እንደሚያሳየው የሙያ ማህበራት በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ላይ ያላቸው ሚና
ጉልህ ቢሆንም በአገራችን በዘርፉ ተደራጅተው የሚገኙ የሙያ ማህበራት ያላቸው አስተዋጽኦ ከዚህ ግባ
የሚባል አይደለም፡፡

የከተማ ልማት ስራዎች ላይ የመንግትስና የግሉን ዘርፍ ትብብርን በማጠናከር በተለይም የመንግስትን ሚና
በሪጉላቶሪና አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ሆኖ የግሉ ዘርፍን በከተማ ፕላን ስራ ጉልህ ሚና እንዲኖረው
ከማድረግ አኳያ ብዙ ሊሰራ የሚገባው ጉዳይ ይኖራል፡፡ ይህም በቅድሚያ የግሉ ዘርፍን በስፋት የሚያሳትፍ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 74


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስራ በበቂ መጠንና ስፋት መኖሩ ማለትም የገበያው ፍላጎት መኖሩ
በጥናት ተፈትሾ መለየት ይኖርበታል፡፡ የገበያ ፍላጎቱ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በምን አይነት መንገድ፣
ደንብና ስርዓት የግሉን ዘርፍ ወደስራው ማሰማራት እንደሚገባና እንደሚቻል ተጠንቶ በህግ ማዕቀፍ
ወይም በደንብ የተደገፈ የአሰራር ዘዴና የክትትልና ቁጥጥር አግባብ ፈጥሮ ስራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ረገድ ብዙ የተሰራበት ሁኔታ የለም፡፡ እስከዛሬ በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የተከናወኑ የከተማ ፕላን ዝግጅት
ስራዎች ወይም ውጤቶች በስርአት ተገምግመው የተወሰደ የግብረ መልስ ግብዓት የለም፡፡

2.2.4. የአገልግሎት አሰጣጥና አሰራር ሥርዓት

በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የፕላን ሕግ ላይ በሀገሪቱ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች መዋቅራዊ ፕላንና
የአካባቢ ልማት ፕላን መሆናቸው በግልጽ ተመልክቷል፡፡ መዋቅራዊ ፕላን ህጋዊ አስገዳጅነት ያለውና
የከተማውን ዋና ዋና የመሬት አጠቃቀም መሪ ሀሳቦችን የያዘ እንደዚሁም በከተማው የተለያዩ ክፍሎች
ለዋና ዋና የከተማው ተግባራት መጠባበቂያ የተባሉ ቦታዎችንና የነዋሪዎቹን ፍላጎት እንዲያሟሉ
የሚያስፈልጉ ቦታዎችን የሚያመለክት የከተማ ፕላን ሰነድ ነው፡፡ ዋና አላማዉም የከተሞችን የወደፊት
ዕድገት ለመምራት የሚያስችል አጠቃላይ አቅጣጫዎችን፤ መሰረተ ልማት ዝርጋታ፤ የቦታ አጠቃቀምና
አደረጃጀት ማስቀመጥ ወይም ማመላከት ነው፡፡ በአንጻሩ የአካባቢ ልማት ፕላን (LDP) ደግሞ ለተወሰነ
የከተማው ክፍል ብቻ የሚዘጋጅ ዝርዝር ፕላን ነው፡፡ ይህ ፕላን በውስጡ የአካባቢ መልሶ ማልማትን፣
ማሻሻልን እንዲሁም የሽንሻኖ ዝርዝሮችን ያጠቃልላል፡፡

የአካባቢ ልማት ፕላኖች ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ልማት ከመገባቱ በፊት ዝርዝር ፕላንና የከተማ ዲዛይንን
ማዘጋጀት አስፈላጊ ቢሆንም ይህ አሰራር በአገሪቱ ውስጥ የተለመደ አይደለም፡፡ አብዛኞቹ የአካባቢ ልማት
ፕላኖች የሚተገበሩት የማስፈጸሚያ ህጎች ወይም የከተማ ዲዛይን ሳይዘጋጅላቸው ሲሆን ለዚህም
እንደዋነኛ ምክንያት ሊጠቀስ የሚችለው የከተማ ፕላን አዋጁ የከተማ ዲዛይን ዝግጅትን /ለትላልቅ
ከተሞች/ የማያካትትና ለዲዛይን ዝግጅት የተዘጋጁ መመሪያዎች፣ የአሰራር ስታንዳርድ እና ማንዋሎች
አለመኖራቸው ነው፡፡

የከተማ ፕላን ዝግጅት አሰራር ሥርዓት

ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር ዓመታዊ ሪፖርት ላይ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው እስከ
2003 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከአጠቃላይ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች ውስጥ 62 በመቶ የከተማ ፕላን
የተዘጋጀላቸው ቢሆንም ፕላን ከተዘጋጀላቸው ከተሞች ውስጥ የፕላን ጊዜያቸው ተጠናቆ ክለሳ
የሚፈልጉ በርካታ ከተሞች ከመኖራቸውም ባሻገር በየጊዜው የሚያቆጠቁጡ ከተሞች መኖር እንዲሁም
በርካታ የገጠር ቀበሌ ማእከላት በፕላን እንዲመሩ ፍላጎት መኖሩ ሽፋኑን ዝቅተኛ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 75


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የከተሞች ፕላን ሽፋን ዝቅተኛ መሆን ፕላን የሌላቸው ከተሞች መሬታቸውን በአግባቡ እንዳይጠቀሙ
በማድረግ በአካባቢያቸው ያለውን ለም የእርሻ መሬት በመሻማት ያለጥናትና ያለ ፕላን ከቁጥጥር ውጭ
የሆነ የአከታተም ሥርዓት እንዲከተሉና ለከባቢ ብክለት/ሥነምህዳር መዛነፍ ምክንያት እንዲሆኑ
ያደርጋቸዋል፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት ከከተማ ፕላን ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች መንስኤዎች ዋና ዋናዎቹ ከሽፋን
አንጻር አደረጃጃትን በሚፈለገው ደረጃ ያልተማከለ አለመሆኑ ያሉትም የተጠናከሩ አለመሆን፣ በቂ
ባለሙያና የሙያ ስብጥር እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አለመኖር፣ የግሉን ዘርፍ አቅምና ተሳትፎ
አለመጠናከር፣ የመሠረታዊ ካርታዎች ዝግጅት ሽፋን ዝቅተኛ መሆን ናቸው፡፡ ከጥራት አንጻር የከተማ
ፕላን የጥናት ሰነድ ጥራት ሲገመገም ሰነዱ ለጥናት አስፈላጊ የሆኑ የተሟሉ፣ የተረጋገጡና አስተማማኝ
መረጃዎችን የማያካትትና በተለይም ማሕበራዊና ኢኮኖሚዊ ለሆኑ ቁልፍ ችግሮች መፍትሄ የማይሰጥ
እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ዕቅድ ጋር የማይቆራኝ ነው፡፡ በታዳጊ ሀገሮች ከተሞች ፕላን ላይ የተደረገ ጥናት
እንደሚጠቁመው በነዚህ ሀገሮች የሚዘጋጁ ፕላኖች ተመሳሳይ ችግሮች የሚታይባቸው ሲሆን ይህም
ፕላኖቹ በመሬት አጠቃቀም ላይ እና በፕላን ላይ በሚቀመጡ ፊዚካላዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ በማተኮር
ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍትሄ የማይሰጡ ናቸው፡፡ የከተማ ልማት ፖሊሲው የከተማ ፕላን
ሲዘጋጅ ከከተማ ልማት ዕቅድ ጋር መያያዝ እንዳለበት የሚጠቅስ ቢሆንም በተግባር የሚታየው ግን
ለከተሞች የሚዘጋጀው ስፓሻል ፕላን ብቻ ነው፡፡ ስፓሻል ፕላን ብቻውን የከተሞችን ልማት በሚፈለገው
ደረጃ የማያመጣ በመሆኑ የከተማ ፕላን ሲዘጋጅ የከተሞችን/የማዘጋጃ ቤትን/ የሶሺዮ ኢኮኖሚ ልማት
ዕቅድ ጋር መያያዝ ይኖርበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፕላኖቹ የሕብረተሰቡን በተለይም ዝቅተኛውን
የሕብረተሰብ ክፍል ፍላጎት ከግምት ውስጥ የማያስገቡ ሲሆን የማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናቶች
ቢደረጉም እንኳን ጥናቶቹ ለመሬት አጠቃቀም ፕላኑ ግብአት የሚሆኑ ፊዚካላዊ ጉዳዮች ቦታ ለመያዝ
እንጂ የማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት አይደለም /Taylor & Williams, 1982 :26 and
27/፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ የውይይት መድረኮች የተገኙ ገንቢ ሀሳቦችን በሰነዱ ውስጥ በተሟላ
መልኩ አለማካተትና የፕላን ማስፈጸሚያ ስልቶችን አለመጠቆማቸው በጥናት ሰነዶች ላይ የሚታዩ ዋና
ዋና ችግሮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የመሬት አጠቃቀም ፕላን ጥራትን በተመለከተ የሚነሱ ዋና ዋና ችግሮች
የኮድ፣ ስታንዳርድ፣ ሌጀንድ፣ ወዘተ ወጥነት አለመኖር፤ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ አለማሳየቱ
እንዲሁም የማይጣጣሙ አገልግሎቶች ጎን ለጎን መቀመጥ፣ የመንገድ ተዋረድ አለመጠበቅ /የሚዘጉ፣
የሚጠቡ፣ ወዘተ…/፣ የሶሾ-ኢኮኖሚ ጥናቶችን አለማንጸባረቅ፣ የገጠርና ከተማ ትስስርን እንዲሁም ጥብቅ
ቦታዎችና ማነቆዎችን፣ ግምት ውስጥ አለማስገባትና የኮንቱር አለመናበብ ናቸው፡፡

የከተማ ፕላን አሠራርን በተመለከተ ከተለዩት ችግሮች መሀከል ዋና ዋናዎቹ አንድ አይነት የሆኑ ፕላኖች
በአዲስ አበባም ሆነ በተለያዩ ክልሎች የተለያዩ ሥያሜዎች መስጠቱ፣ በሕዝብ ብዛታቸውም ሆነ በቆዳ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 76


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ስፋታቸው ተመሳሳይ ለሆኑ ከተሞች የተለያዩ የፕላን አይነቶች መዘጋጀታቸው እንዲሁም እንደየከተሞቹ
ደረጃ የሚዘጋጁ የፕላን አይነቶች አለመለየታቸው በአጠቃላይ የከተሞች ፕላን ዓይነት፣ አዘገጃጀት፣ ሂደት፣
ይዘትና ለዝግጅት የሚወስዱት ጊዜ ላይ ወጥነት አለመኖር ናቸው፡፡ በተጨማሪም የሚዘጋጁ ፕላኖች
ለፊዚካልና ስፓሻል ጉዳዮች ብቻ ትኩረት በመስጠት በአንፃሩ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን
ግምት ውስጥ የማያስገቡ ናቸው፡፡

የከተማ ፕላንን ለማዘጋጀት የሚያስፈልገው የጊዜ በጀት እና አጠቃቀም እንደየከተሞቹ የእድገት ደረጃ፣
የሕዝብ ብዛትና የቆዳ ስፋት ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን በክልሎች መሀከል የህዝብ
ቁጥራቸው ተመሳሳይ ለሆኑ ከተሞች የተለያየ የጊዜ በጀት እንደሚወጣላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ለአብነት በአማራው ክልል የህዝብ ቁጥራቸው ከ 20 ሺ በታች ለሆኑ ከተሞች የፕላን ዝግጅት /መዋቅራዊ
ፕላን በተወሰኑ ቦታዎች የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅትን ጨምሮ/ የሚወስደው ጊዜ 45 ቀናት በኦሮሚያ
ደግሞ እስከ 4 ወራት የሚወስድ እንደሆነ በየክልሉ የተካሄዱ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ጥናት ሰነዶች ላይ
ተቀምጠዋል፡፡ በሚ/ር መ/ቤቱ የከተማ ፕላን ማስተባበሪያ ቢሮ የተዘጋጀው የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ
ጥናት መሰረት የአነስተኛ ከተሞች ፕላን ዝግጅት 4 ወራት እንደሚወስድ የተቀመጠ ሲሆን በአማራ ክልል
የአነስተኛ ከተሞችን ፕላን የአካባቢ ልማት ፕላንን ጨምሮ በ 45 ቀናት ውስጥ መዘጋጀቱ በጥራት ላይ
የራሱ የሆነ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል፡፡

ከባለሙያ ስብጥር አንጻርም የአንድ ትልቅ ከተማን የመዋቅራዊ ፕላን ለማዘጋጀት ቢያንስ ሰባት
ባለሙያዎች /የታሪክ፣ የፊዚካል፣ የጂኦሎጂ፣ የኢኮኖሚክ፣ የስፓሻል፣ የተፋሰስ፣ የዲሞግራፊ /ሶሾሎጂ/
የሚያስፈልጉ ሲሆን በባለሙያ እጥረት ምክንያት በአብዛኛው ክልሎች የከተሞች ፕላን ዝግጅት
የተጠቀሱትን ባለሙያዎች በተሟላ መልኩ አይካትትም፡፡ በዚህም ምክንያት የሚዘጋጁ ፕላኖች
የሚገባውን ጥራት የጠበቁ አይደሉም፡፡ ለባለሙያ እጥረት ዋንኛው ምክንያት ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ
ፍልሰት መኖሩ ሲሆን ይህም የሚከሰተው ለከተማ ፕላን የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑና ባለሙያን
ለማቆየት የሚደረግ ጥረት ባለመኖሩ ነው፡፡

ከተሞች የገበያ፣ የአገልግሎትና የኢንዱስትሪ ማዕከልነታቸውን አጠናክሮ በማስቀጠል ከገጠሩ ጋር


ያላቸውን ትስስር ማጠናከር ተገቢ ነው፡፡ ይሁንና ይህን ሚና በከፍተኛ ሁኔታ የሚጫወተው የከተማ ፕላን
ዝግጅትና አፈጻጸም በሚገባው ደረጃ እየተከናወነ ባለመሆኑ በፕላን ዕድገታቸውን የማይመሩ ከተሞች
ብዛት ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር በተጎራባች ክልሎችና ከተሞች መካከል ያለው ያልተቀናጀና በተናጠል
የሚከናወን የከተማ ፕላን አሰራርና አፈጻጸም ሰፊ ችግር ሆኖ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ በመሰረተ ልማት
አውታር ዝርጋታ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በመሬት አጠቃቀም፣ በትራንስፖርት፣ ወዘተ ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር
በማጎለበት የህብረተሰቡን ፍላጎት ማርካት አልተቻለም፡፡ በአጎራባች ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 77


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በተናጠል እየተካሄደ የሚገኘው ያልተናበበ የከተማ ልማት የሃብት ብክነት ከማስከተሉም በላይ በሀገሪቱ
የከተማ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማስከተሉ አይቀርም። ለአብነት በአዲስ አበባ ከተማና በአካባቢዋ
የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ባላቸው ቅርበት ምክንያት ጥብቅ ቁርኝት ቢኖርም፤ በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ
አበባ መስተዳድር መካከል በቅንጅት የሚሰሩበት ስርዓት የለም። አካባቢው በአንድ ክልላዊ/ሪጅናል/ ፕላን
መመራት ቢኖርበትም፤ በሁለት የተለያዩ አስተዳደሮች ስር የሁለቱም በተናጠል መስራት በአካባቢው ላይ
ብቻ ሳይሆን በአገሪቱም የከተማ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያስከትላል። በደቡብና ኦሮሚያ (የአዋሳና
የሻሸመኔም ጉዳይ) ተመሳሳይ ነው። በተመሳሳይ ክልል ውስጥ ያሉ ከተሞች ራሳቸው ለምሳሌ በኦሮሚያ
ክልል ዱከምና ቢሾፍቱ ተጎራባች ሆነው ሳለ ፕላኖቻቸውን ሲያዘጋጁ የመናበብ ሁኔታ አይታይም፡፡
የድሬዳዋ-ሐረር ቀጠናም በአራት የተለያዩ መስተዳድሮች ስር በመሆኑ የአካባቢውን ንዑስ የከተማ ስርዓት
በአንድ ወጥ የአካባቢ ፕላን የሚመራበት ስርዐት የለም።

የከተማ አስተዳደር ወሰን አከላለል መስፈርት ባለመኖሩ ምክንያት አንዳንድ ክልሎች ከከተማው የፕላን
ድንበር አንስቶ 2.5 ኪ.ሜ ዙርያ ያለውን ቦታ በከተማው አስተዳደር ውስጥ ሲያካትቱ አንዳንዶች ደግሞ 5
ኪ.ሜ እና ከዚያ በላይ የሆነ ቦታ ያካትታሉ፡፡ የከተማ አስተዳደር ወሰን መከለል ዋናው አላማ ህገወጥ
ሰፈራዎችን ለመቆጣጠር ቢሆንም አከላለሉ ለመወሰን የሚያስችል ወጥ የሆነ አሰራር የለም፡፡ በዚህም
ምክንያት አንዳንዳድ ከተሞች የከተማ ደረጃቸው ከፍ እንዲል በማሰብ በጣም ሰፊ የሆነ መሬት በከተማው
አስተዳደር ስር እንዲሆን ሲያደርጉ የሚስተዋል ሲሆን ይህም በመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ ወጪ
እንዲወጣ ምክንያት ይሆናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች ከተሞች
ድንበር ወሰን የማካለል ችግር ሲፈጠር ችግሩን ለመፍታ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት የለም፡፡

ላለፉት ስምንት ተከታታይ አመታት በአገራችን እየተመዘገበ ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የከተማ-
ገጠርንና የከተማ- ከተማ ትስስርን በማጠናከር ረገድ ያለው አውንታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም
ከተሞቻችን ይህን ፈጣን ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ እና የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ
ለማስቻል የከተሞቻችንን ዕድገት አቅጣጫና የአከታተም ሥርዓት ካላቸው ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት አንጻር
በመቃኘት የአካባቢው የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የገበያ፣ የኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት፣ የባህልና ቴክኖሎጂ
ማዕከልነታቸውንና የእርስ በእርስ ተወዳዳሪነታቸውን በዘላቂነት ማስቀጠል ያስፈልጋል፡፡ ይህን አገራዊ
ራዕይ እውን ለማድረግ ከተሞች በፕላን እንዲመሩና የሚዘጋጁት የከተማ ፕላን ከአገሪቱ የከተሞች ልማት
ስኪምና ከየክልሎቹ የከተሞች ልማት ፕላን ጋር የተጣጣመ መሆን ይገባዋል፡፡

ቅንጅታዊ አሰራርን በተመለከተ በፌደራል፣ በክልል የከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማትና ከተማ አስተዳደሮች
መካከል በሚካሄዱ የስልጠና፣ የጥናት /ለምሳሌ ማንዋል ዝግጅት/ እና የፕላን አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 78


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ተግባራት ስራዎች ላይ የመናበብ፣ ተቀናጅቶ የመስራትና ቀልጣፋ የሆነ የመረጃዎችና ሰነዶች ልውውጥ
ያለመኖር /ማን፣ ምን፣ መቼና እንዴት መስራት እንዳለበት ያለመታወቅ/ ችግር በግልጽ የሚታይ ነው፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት ከከተማ ፕላን ዝግጅት ጥራት ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮች መንስኤዎች ወይም
ምክንያቶች ውስጥ የፕላን ዝግጅት ክትትል፣ የግምገማና የግብረ መልስ ስርዓት አለመዘርጋት፣
እየተሰራባቸው የሚገኙትን አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎች የተሟሉ አለመሆን፣
የመሰረታዊ ካርታ ጥራትና የባለሙያ ክህሎት ዝቅተኛ መሆን፣ የከተማ ፕላን ዝግጅትን በጥናትና ምርምር
አለመደገፍ፣ የመሠረታዊ ካርታ ጥራት ደካማ መሆን እና በፌዴራል፣ በክልሎችና በከተሞች መሀል ተገቢ
ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት አለመዘርጋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከከተማ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ይዘቶች /Major Land Use Functions/ ጋር የሚታዩ ችግሮች

የከተማ ፕላን መሬት አጠቃቀም ይዘት /Major Land Use Functions/ በስድስት ዋና ዋና የመሬት
አጠቃቀም አገልግሎቶች የሚከፈል ሲሆን ከመሬት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ መልኩ የሚታዩ ችግሮችን
እንደሚከተለው ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

የመኖሪያ ቤት አገልግሎት፡- በአገር አቀፍ ደረጃ በከተሞች ያለው የመኖሪያ ቤት አግልግሎትና አቅርቦት
ክፍተት እስከ 1 ሚሊዮን ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ አሁን ካለው የመኖሪያ ቤት ክምችት ውስጥ 30
በመቶው ብቻ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ሲሆን 25 በመቶው ፈርሶ መገንባት ያለባቸው ናቸው፡፡ መኖሪያ
ቤቶቹ ለጤናና እንዲሁም ለእይታ ምቹ ያልሆኑና የተፋፈጉ መሆናቸው አንድ ጉዳይ ሆኖ በአብዛኞዎቹ
የአገሪቱ ከተሞች ማዕከላዊና ዋጋው ከፍተኛ የሆነውን የመሬት ክፍል የያዙ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2004 ዓ.ም.
የተከናወነው የከተማ ዘርፍ የሚሊኒየም ልማት ግብ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ውጤት እንደሚያመላክተው
በአገሪቱ ውስጥ ከከተሞች እድገት ጋር ተያይዞ በህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት የሚከሰተውን የመኖሪያ
ቤት ፍላጎት ለማስተናገድ እስከ 2015 ዓ/ም በየአመቱ በመንግስትና በሌሎች አካላት ወደ 225,000 ቤቶችን
መገንባትን ያስፈልጋል (UNHABITAT, 2010)፡፡

በመንግስት እየተካሄደ ባለው የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም እስከ 2002 ዓ/ም መጨረሻ ድረስ
ለመገንባት የተቻለው 200,000 ቤቶች ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ያለው የመኖሪያ ቤት አቅርቦት
ከሚታየው ፍላጎት አንጻር እጅጉን ያልተጣጣመና በተለይም ከዜጎች የመክፈል አቅም ጋር የማይመጣጠን
በመሆኑ የከተማ ነዋሪዎች ከመደበኛ የቤት አቅርቦት መስመር ውጭ በመንቀሳቀስ የራሳቸውን ህገ ወጥ
መፍትሄ በመቀየስ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ህገወጥ መንደሮችን ሲመሰርቱ ይታያሉ፡፡ በሪል እስቴት አልሚ
ድርጅቶች እየተገነቡና ለገበያ በግዥ እየቀረቡ ያሉት የመኖሪያ ቤቶች በቁጥርም ይሁን በዓይነት ውሱን
ሲሆኑ አቅርቦቱም ከፍተኛ ገቢ ላላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 79


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከላይ ከመኖሪያ ቤት ጋር ተያይዘው የተነሱ ችግሮች በከተማ ፕላን ላይ ለመኖሪያ አገልግሎት ተብሎ
የተያዘውን የቦታ መጠን የሚያዛቡና አጠቃላይ የመሬት አጠቃቀም ስርዓቱን የተዛባ እንዲሆን ሊያደርጉ
እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም፡፡ በፕላን ላይ ለመኖሪያ አገልግሎት የሚያዘው ቦታ የመሬት ዋጋን
መሰረት ባደረገ ሁኔታ መቃኘት ይገባዋል፡፡ የመሬት ዋጋ ከፍተኛ በሆነበት አካባቢ የመሬትን ጥቅም አሟጦ
መጠቀም በሚቻልበት ደረጃ ከፍታቸው ትላልቅ የሆኑ ህንጻዎችን ማስተናገድ እንዲቻል በተመሳሳይም
የመሬት ዋጋ አነስተኛ የሆኑ አካባቢዎችን አብዛኛውን የገቢ መጠኑ ዝቅተኛ የሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል
ማስተናገድ የሚያስችል የመኖሪያ ቤት ቦታ አያያዝ ስርዓት አልዳበረም፡፡

ለነዚህ ችግሮች መከሰት ዋናው መንስኤ ገበያ መር የሆነው የመኖሪያ ቤቶች ልማትና አቅርቦት ከአብዛኛው
የከተማ ነዋሪዎች ገቢ አንጻር ውድና ተደራሽ ካለመሆኑም በላይ የመሬት ዝግጅቱ ከመኖሪያ ቤት አቅርቦት
በተጨማሪ በመሰረተ ልማት አውታር የለማ አለመሆኑ፣ የደቀቁ አካባቢዎችን በጥናት መልሶ የማልማት
ስራዎች አለመከናወን፣ የመኖሪያ ቤት አልሚዎች ቁጥር አናሳ መሆንና ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ላይ
ብቻ ማተኮር፣ ለቤት ግንባታ የሚውል ፋይናንስ አቅርቦት እጥረት፣ የከተማ ነዋሪዎች ቁጠባ ባህል
አለመዳበር፣ ወጪ ቆጣቢ የግንባታ ቴክኖሎጂ እና የከተማ ውበትና ገጽታን የሚጠብቁ የቤቶች ዲዛይን
ውሱንነት፣ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት እጥረትና በየጊዜው የሚስተዋለው የዋጋ መናር እንዲሁም
የማስፈጸም አቅም ውሱን መሆን ናቸው፡፡

የቢዝነስ፣የንግድና የገበያ ቦታዎች፡- ከየቢዝነስ፣ የንግድና የገበያ ቦታዎች ጋር የሚታዩ ችግሮች ውስጥ ዋና
ዋናዎቹ ከመጀመሪያው ጀምሮ በስታንዳርድ መሰረት ለአገልግሎቶቹ በቂና አመቺ ቦታ አለመያዝ፣ ተጓዳኝ
የሆኑ ጉዳዮችን /ለምሳሌ ፓርኪንግ/ ግምት ውስጥ አለማስገባት፣ ያልተመጣጠነ ስርጭት መኖርና የመሰረተ
ልማት ዝርጋታ አለመሟላት፣ እንዲሁም በአተገባበር ወቅት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የፕላን ጥሰት
ማለትም በፕላን ላይ ከተቀመጠው አገልግሎት ውጭ ቦታን ለሌላ አገልግሎት ማዋል ናቸው፡፡

ማሕበራዊ አገልግሎቶች፡- በከተሞች የትምህርት፣ ጤና አገልግሎት፣ የስፖርትና የመዝናኛ አገልግሎቶች፣


የእምነት ተቋማትና ዘላቂ ማረፊያ ስፍራዎችና አገልግሎቶች ጋር ተያያዥ ከሆኑት ችግሮች ውስጥ ዋና
ዋናዎቹ የአገልግሎቶቹ ብዛት የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ ከሆነው የከተማው ነዋሪ ብዛት ጋር የተመጣጠኑ
አለመሆን፣ ከስፋት አንጻር በቂ ቦታ ያለመያዝ፣ ቦታው ከተያዘ በኋላም የሚገነባው ግንባታ የአገልግሎት
ስታንዳርዱን ያልጠበቀ መሆን፣ የቦታ ስርጭቱም ፍትሃዊነት የሌለው በመሆኑና ከርቀትም አኳያ ተደራሽ
አለመሆን ናቸው፡፡ ለነዚህ ችግሮች በዋና ምክንያትነት የሚጠቀሱት በከተማ አመራሩና አስፈጻሚዎች
በኩል ለመሬት አጠቃቀም ፕላን ያላቸው ዝቅተኛ ግንዛቤና የአፈጻጸም ክህሎት ማነስ፣ በመሬት ላይ ያለው
የኪራይ ሰብሳቢነትና የጥገኝነት አመለካከት፣ በፕላን ዝግጅት ወቅት በባለሙያዎች ችግር ምክንያት
በመረጃ የተደገፈ ትክክለኛ የቦታ መጠን ያለማሰቀመጥና የመሳሰሉት ሲሆኑ የእነዚህ ችግሮች ድምር

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 80


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ውጤቶች ደግሞ የአገልግሎት ሽፋኑና ጥራት ዝቅተኛ መሆንና የወደፈት ጤናማ አምራች ዜጋ
ለማፍራትና ልማትን በማፋጠንና ድህነትን በማስወገድ ለህብረተሰቡ የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር
የተያዙ ግቦችን በአግባቡ ለማሳካት ያለመቻልና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ፋብሪካዎች፣ ኢንዱስትሪ፣ የማከማቻ ቦታዎችና ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት፡- ከፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪ


እና ማከማቻ ጋር የተያያዘ ቁልፍ ችግር በከተማ ፕላን የሚመራና በመሰረተ ልማት የለማ መሬት አቅርቦት
እጥረት መኖሩ ሲሆን ለአዳዲስ የፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት እድገት በፍጥነት ለማምጣትም
እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም አሁን በስራ ላይ ያሉት አንዳንድ ኢንዱስትሪዎችም ኋላቀር
በመሆናቸው ለምሳሌ እንደ ቆዳና ጨርቃጨርቅ የመሳሰሉ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች በአካባቢያቸው
ስነ-ምህዳር (ውሀ፣ አፈርና አየር) ላይ ከፍተኛ ብክለት በማስከተል በከተማና በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ
የጤና ችግር መንስኤዎች እና ለከተሞች ገጽታ መበላሸትም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ለዚህም ምክንያቱ አብዛኛዎቹ ቀደም ብለው የተስፋፉት ፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪዎች ከመኖሪያም ሆነ
ከሌሎች የመሬት አጠቃቀም ጋር መቀላቀላቸውና በቂ ርቀት (buffer zone) የሌላቸው መሆናቸው ነው፡፡
በተጨማሪም የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርአታቸው ኋላ ቀርና ደረጃውን የጠበቀ አለመሆን
ናችው፡፡

መንገድ፣ ትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት፡- ከመንገድ፣ ትራንስፖርትና መሰረተ ልማት አገልግሎቶች ጋር


በተያያዘ መልኩ የሚነሱ ችግሮች ከከተማ ከተማ የሚለያዩ ቢሆንም በአብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች
የሚታዩትን እንደሚከተለው ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

መንገድ፡ የመንገድ ሽፋንና ጥራት በአጠቃላይ ዝቅተኛ ነው፡፡ የሽፋኑ ዝቅተኛ መሆን መገለጫዎቹ የመንገድ
መረብ/Network/ ደካማ መሆን፣ የመንገድ መዘጋት፣ የመንገድ ተዋረድ አለመጠበቅ፣ የመንገዶች መጥበብ፣
ነባር እና መስፋፊያ አካባቢዎች በመንገድ መረብ አለመያያዝ፣ በመንገዶች በረዣዥም ብሎኮች ምክንያት
ቅርብ ቦታ ለመሄድ ረዥም መንገድ መጓዝ፣ መንገዶች የሚገናኙባቸው ቦታዎች /ለምሳሌ አደባባዮች፣
መስቀለኛ መንገዶች/ መጥበብና ተስማሚ አለመሆን የመሳሰሉት ሲሆኑ የጥራቱ ዝቅተኛነት መገለጫዎች
ደግሞ በአጠቃላይ በአስፋልትና በጠጠር የተሸፈኑ መንገዶች መጠን ዝቅተኛ መሆንና በአስፋልት ብቻ
የተሸፈኑት ደግሞ እጅግ ዝቅተኛ መሆናቸው ሲሆን በአስፋልትና በጠጠር የተሰሩት ራሳቸው በደካማ
ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆኑ ነው፡፡

ትራንስፖርት፡ ከትራንስፖርት ጋራ ተያይዘው የሚነሱ ችግሮች በአብዛኛው የትላልቅ ከተሞች ችግሮች


ሲሆኑ እነዚህም የእግረኞች መንገድ አለመኖርና ትኩረትም አለመስጠት፣ የመሬት አቀማመጣቸው አመቺ
በሆኑ አንዳንድ የአገሪቱ ከተሞች የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎች መንገድ አለመኖር፣ የአውቶብስ መናኸሪያ፣

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 81


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የታክሲ ማቆሚያ፣ የጭነት መኪናዎች ማቆሚያ፣ የማንኛውም መኪና ማቆሚያ ቦታዎች እጥረትና
ለነዚህ አገልግሎቶች ቦታ ሲያዝ መስፈርቶችን ግምት ውስጥ አለማስገባት /ስፋት፣ የመሬት
ተዳፋታምነት፣ ማዕከላዊነት፣ ከአካባቢ ጋር የመጣጣም ሁኔታ፣ ስርጭት፣ ተደራሽነት /accessibility/…
ወዘተ/ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህም ችግሮች የትራፊክ መጨናነቅ፣ የትራፊክ አደጋ፣ የአየር ብክለት፣ ጉዞ
ረዥም ሰዓት መውሰድ፣ መንገድ ለከፍተኛ ጫና/ክብደት መጋለጥ የመሳሰሉትን ችግሮች ያስከትላሉ፡፡

መሰረተ ልማት፡ የመሰረተ ልማት አገልግሎት በተመለከተ ከሚታዩት ችግሮች ውስጥ አገልግሎቶቹ
ተቀናጅተው አለመዘርጋታቸው፣ የተዘረጉትም ሽፋናቸው ዝቅተኛ መሆን፣ ህገ ወጥ ሰፈራዎች አካባቢ
አገልግሎቶቹን ማቅረብ እንዲሁም በፕላን ዝግጅት ወቅት ለሁሉም አገልግሎቶች መስመሮችን
በመሀከላቸው መኖር የሚገባ ተገቢው ርቀት፣ ቅደም ተከተላቸውን እንዲሁም መሬት ውስጥ ሊኖራቸው
የሚገባውን ጥልቀት ባመላከተ መልኩ ፕላን ላይ አለማስቀመጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች መከሰት ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የተዘጋጁ ፕላኖችን በፕላኑ
መሰረት አለመተግበር፣ በፕላን ዝግጅት ጊዜ ተገቢው ጥናት አለመደረግ፣ በመሰረተ ልማት አቅራቢ
ተቋማት መሀከል ተቀናጅቶና ተናቦ አለመስራት፣እንዲሁም የከተሞች የአቅም ውስንነት ሲሆኑ ችግሮቹ
ካስከተሏቸው ውጤቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የተቀላጠፈ የእግረኞችም ሆነ የተሽከርካሪ ፍሰት አለመኖር፣
የትራፊክ መጨናነቅ፣ በንብረትና በሰው ላይ አደጋዎች መከሰት፣ የሀብት ብክነት፣ የመሰረተ ልማት
አገልግሎት መስመሮች ለአደጋ ተገላጭ መሆን፣ በከተሞች ውበት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ መከሰት
የመሳሰሉት ሲሆን ይህም በከተሞች ልማት ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ያሳድራል፡፡

ልዩ ልዩ አገልግሎቶች (Special Functions) ፡- ከልዩ ልዩ አገልግሎት ሰጪ ቦታዎች ጋር በተያያዘ የሚታዩ


ችግሮች ውስጥ ታሪካዊ፣ ባህላዊና አርኪዮሎጂካዊ አካባቢዎችን ከመጠበቅ አንጻር በፕላን ላይ በተገቢው
ርቀት እንዲከለሉ የማድረግ ስራ እምብዛም የማይታይ መሆኑ፣ በታሪካዊነት መመዝገብ ስላለባቸው
ቦታዎችና ግንባታዎች መለያ ዘዴ አለመኖር፣ የውኃ አካላትን ከብክለት ለመከላከል እንዲቻል ከመኖሪያ፣
ከፋብሪካና ከሌሎች ብክለት ሊያመጡ ከሚችሉ የመሬት አጠቃቀም ዓይነቶች በተገቢው ርቀት ላይ
አለመከለል፣ በአንዳንድ ከተሞች ውስጥ የሚሊቴሪ ካምፖች በጣም ሰፊ ቦታዎችን ይዞ መገኘት ዋና
ዋናዎቹ ናቸው፣

2.2.5. ስትራቴጂ፣ የስራ ዓመራር ዘይቤና የጋራ እሴት

ከስትራቴጂ አንጻር በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የሚያመለክተው አብዛኛዎቹ መስሪያ ቤቶች
የአምሰት ዓመት ስትራቴጂ እቅድ በማዘጋጀት በየዘርፋቸው ያሉትን ችግሮች በስትራቴጂ በመፍታት
ስራቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን በከተማ ፕላን ዝግጀትና አፈጻጸም ዘርፍ የተሰማሩ መስሪያ ቤቶችም

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 82


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አጠቃላይ ስራቸውን የሚመሩት በተመሳሳይ ሁኔታ መሆኑ እንደ ጠንካራ ጎን የሚታይ ነው፡፡ ሆኖም ዘርፉ
ከከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ ችግሮች ያሉበት ሲሆን እነዚህን ችግሮች
ስር ነቀል በሆነ መልኩ በመፍታት የከተሞች ዕድገት በፕላን እንዲመራ ለማድረግ የሚያስችል የተሟላ
የከተማ ፕላን ስትራቴጂ ያልነበረ መሆኑ እንደ ክፍተት የሚታይ ቢሆንም ይህ ስትራቴጂ መዘጋጀቱ ራሱ
የከተማ ፕላን ከተተበተበበት ችግሮች በማላቀቅ ለከተሞች እድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዎ ሊያበረክት
እንደሚችል ይታመናል፡፡

በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የተሰማሩ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን የስራ አመራር ዘይቤ በተመለከተ
አሁን ባለው የዲሞክራታይዜሽንና ያልተማከለ አሰራር ለውጥ ጋር ተያይዞ በፌደራል፣ በክልልም ሆነ
በከተማ ደረጃ ያሉ አመራሮች ከእቅድ አወጣጥ ጀምሮ እስከአፈጻጸሙ ድረስ በአሳታፊነት እና በውክልና
ሀላፊነትን በመስጠት ሰራተኛን ለማሰራት የሚደረግ ጥረት እንዳለ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ያለው የአመራር
ዘይቤ ገና በጅምር ላይ ያለ በመሆኑ ይበልጥ የተሻለ ለማድረግ ብዙ መሰራት እንዳለበት የሚጠቁሙ
ሁኔታዎቸ አሉ፡፡ በመስሪያ ቤት ደረጃ የሚታቀዱ እቅዶችን ከሰራተኛው ጋር አብሮ ከማቀድ ይልቅ እቅዱ
በአንድ ወይም በሁለት ባለሙያዎች ከተዘጋጀ በኋላ የማሳወቅ ሁኔታዎች፣ በእቅዱ ላይ ክለሳ ወይም
ማስተካከያ ሲደርግ ባግባቡ አለማሳወቅ፣ ሀላፊዎች ሰራተኛን ከማገዝና ከማብቃት ይልቅ በቁጥጥር ላይ
ብቻ ማተኮር፣ በሀላፊዎች መከናወን ያለባቸውን ተግባራት ለሰራተኛው በመተው ሀላፊነታቸውን
አለመወጣት፣ ሰራተኞችን በአንድ አይን ከማየት ይልቅ በመከፋፈል ልዩነት መፍጠር፣ የመሳሰሉት ከስራ
አመራር ዘይቤ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው፡፡

የጋራ እሴቶች ማለትም ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም
ያለማቋረጥ በመማር ራስን መለወጥና ማብቃትን በተመለከተ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሰረታዊ የአሰራር
ሂደት ለውጥ ጥናት መሰረት አንዳንድ ለውጦች እየታዩ ቢሆንም አልፎ አልፎ የመቀዛቀዝ ሁኔታ የሚታይ
በመሆኑ በመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ ጥናቱ መሰረት ስራዎች እየተከናወኑና የደንበኞች ፍላጎት
እየተሟላ መሆኑን አስመልክቶ የማያቋርጥ፣ ተከታታይነት ያለው የቅርብ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በውስጣዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ ላይ በተለዩት ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም በውጫዊ ሁኔታዎች
ዳሰሳ በተለዩት ስጋትና ምቹ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት የአስቻይና ፈታኝ ሁኔታዎች ትንተና የተደረገ
ሲሆን ፈታኝ ሁኔታዎች ነባራዊውን ደካማ ጎኖች ሊያባብሱ የሚችሉ ውጫዊ ስጋቶች ሲሆኑ በአንጻሩ
ደግሞ አስቻይ ሁኔታዎች ደግሞ በውስጣዊ ሁኔታ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ ለማጎልበት የሚያስችሉ
ውጫዊ ምቹ ሁኔታዎች ናቸው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 83


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ፈታኝ ሁኔታዎች፡ በስትራቴጂ ትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈታኝ ሁኔታዎች መሀከል ዋና ዋናዎቹ
በየተቋማቱ በዘርፉ የላቀ እውቀት እና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል በበቂ ደረጃ አለመኖሩና ልምድ ያለው
ውሱን የሰው ኃይል ከከተማ ፕላን ዘርፍ ውጪ ወዳሉ መስሪያ ቤቶች ፍልሰት መጨመር፤ የአመራሩና
ባለሙያው የአመለካከት፣ የቁርጠኝነትና የተነሳሽነት ውስንነት በመኖሩ የማስፈጸም አቅም እንዲዳከም
ማድረጉና በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ተመሳሳይ ችግሮች የሚታዩ መሆናቸው፤ በየተቋማቱ
የሚታየው የፋይናንስ አቅም ውሱንነት በአለም ላይ ከሚታየው የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ጋር ተዳምሮ
በዘርፉ የሚያሰፈልገውን የቴክኖሎጂ አቅርቦት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር መቻሉ ናቸው፡፡

አስቻይ ሁኔታዎች፡ በስትራቴጂው ትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈታኝ ሁኔታዎች እንዳሉ ሁሉ
አስቻይ ሁኔታዎችም ያሉ ሲሆን ከነዚህም መሀከል ዋና ዋናዎቹ ለዘርፍ በመንግስት ከፍተኛ አመራር በኩል
የላቀ ቁርጠኝነትና የተሻለ አመለካከት እየዳበረ መምጣቱ ይህንንም ለማስፈጸም የፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎች፣
ህግ ማዕቀፍ፣ አደረጃጀትና የሰው ኃይል ልማት አስፈላጊ ዝግጅቶች መደረጋቸው፤ በመንግስት የተቀየሰው
የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የክፍለ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲመጣ አልሞ እየሰራ በመሆኑ
ከተሞች በመጠንም ይሁን በቁጥር ፈጣን እድገት ሊያሳዩ እንደሚችሉ የሚገመት ሲሆን ያልተማከለ
የአደረጃጀት ፖሊሲን በመንተራስ የተጀመረው ያልተማከለ የከተማ ፕላን ተቋማት አደረጃጀት
እየተጠናከረ ሊሄድ መቻሉ የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፤ በዘርፉ
የዘመናዊ ቴከኖሎጂ ተጠቃሚነት እያደገ መሆኑና የባለሙያዎችም የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች አጠቃቀም
ልምድ እየተሻሻለ መምጣቱ በተጨማሪም የመሠረታዊ ካርታና ከተማ ፕላን ዝግጅት አፈጻጸምን
ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የዘመናዊ የቅየሳና ጂኦ-ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
አቅርቦት በሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ገበያዎች በአስተማማኝ ደረጃና በተመጣጣኝ ዋጋ ገበያ ላይ ሊገኝ
መቻሉ ናቸው፡፡

2.3. በመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት የሀገሪቱ የተቋማት ብቃት ዝንባሌ ትንተና /Trend
Analysis/

በሀገሪቱ የፕላን ዝግጅት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ያሉት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የሀገሪቱ የፕላን
ዝግጀት ዝንባሌ/አዝማሚያ /Trend/ ከሚዘጋጁ የፕላን አይነቶች፣ ከቴክኖሎጂ፣ ከሰለጠነ የሰው ሀይል፣
በአመት ከሚዘጋጁት ፕላኖች ብዛት፣ ከወጪ እና የፕላን ዝግጅት ከሚወሰደው ጊዜ አንጻር እየተሻሻለ
እንደመጣ ነው፡፡

ከሚዘጋጁ የፕላን አይነቶች አንጻር ሲታይ አሁን የሚዘጋጁ ፕላኖች ከቀድሞዎቹ በተወሰነ ደረጃ አሳታፊ
መሆናቸው፣ የሶሾ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ ማስገባታቸው፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለመለየት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 84


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

መሞከሩ፣ የአካባቢ ልማት ፕላኖች መዘጋጀት መጀመራቸው፣ እንደ አስፈላጊነቱ ተለዋዋጭ /ፍሌክሲብል/
መሆናቸው የፕላን ዝግጅት እየተሻሻለ መምጣቱን ይጠቁማሉ፡፡

ከቴክኖሎጂ አንጻር ሲታይ ከቅርበ ጊዜ በፊት ፕላኖች ይዘጋጁ የነበሩት በትሬሲንግ ወረቀት ላይ በእጅ
በማስመርና በማሳተም ሲሆን አሁን ግን በኮምፒዩተር አማካኝነት በአውቶ ካድና ጂ አይ ኤስ ሶፍትዌሮች
በመጠቀም በፕሎተር በማተም መሆኑ እንዲሁም በፊት የተለያዩ የመሬት አጠቃቀም አይነቶችን ስፋት
መጠን /area/ ስሌት፣ የተለያዩ የመሬት አጠቃቀሞችን በተለያዩ መስመሮች የመለየት /hatching/፣
የተዳፋት ካርታ የማዘጋጀት ስራዎች ይከናወኑ የነበሩት በእጅ በማስላት፣ በማስመር፣ ወዘተ ሲሆን ይህም
ረዥም ጊዜ ይወስድ ነበረ፡፡ በአሁን ሰዓት ግን ስራው በኮምፒዩተር አማካኝነት በአጭር ጊዜ ውሰጥ መሰራት
መቻሉ እንዲሁም ፕላኖችን በሶፍት ኮፒ ማግኘት መቻሉ ከቴክኖሎጂ አንጻር መሻሻል መኖሩን
ይጠቁማል፡፡

ሌሎች ሊጠቀሱ የሚገባቸው ጉዳዮች በፕላን ዝግጅት ዙሪያ በየማሰልጠኛ ተቋማት በርካታ ባለሙያዎችን
ማፍራት መቻሉ፣ የፕላን ዝግጅትን ከተማከለ አሰራር ወደ አልተማከለ አሰራር በመለወጥ ክልሎች
ማዘጋጀት መጀመራቸውና ከበፊቱ እጅግ በጣም በተሻሻለ ሁኔታ በአመት የበርካታ ከተሞችን ፕላን
ማዘጋጀት መቻሉ፣ ከአመት በላይ ይወስድ የነበረውን የአንድ ከተማ ፕላን ዝግጅት በጥቂት ወራት ውስጥ
ማዘጋጀት መቻሉ የከተማ ፕላን ዝግጅት አዝማሚያው እያደገ ወይም እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቋሚ
ነው፡፡

የወደፊቱን አዝማሚያ በተመለከተ የቴክኖሎጂ እደገት፣ ያልተማከለ አደረጃጀት ፖሊሲ መኖር፣ በዘርፉ
ከማሰልጠኛ ተቋማት እየሰለጠኑ የሚወጡ ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ የሚሄድ መሆኑ ጋር ተያይዞ
ሊተገበሩ የሚችሉ ጥራት ያላቸው ፕላኖችን፣ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች ማዳረስና
አፈጻጸማቸውንም ሊከታተሉ የሚችሉ ተቋማትን መፍጠር እንደሚቻል አሁን ያለው አጠቃላይ የሀገሪቱ
የፕላን ዝግጅት አዝማሚያ/ዝንባሌ ጠቋሚ ነው፡፡

ከላይ የተገለጸው የሀገሪቱ የፕላን ዝግጅት ብቃት ዝንባሌ/አዝማሚያ እየተሻሻለ መምጣቱን የሚጠቁሙ
ቢሆንም አሁንም ከፕላን ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ ችግሮች ያሉ ሲሆን በነባራዊ ሁኔታዎች
ትንተና በመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የተለዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች መሀከል ዋና ዋና
የሆኑትን እንደሚከተለው ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

የፕላን ዝግጅት ያልተማከለ መሆኑና በየክልሉ የፕላን ዝግጅት ተቋማት ተደራጅተው የየክልላቸውን
ከተሞች ፕላን ማዘጋጀት መጀመራቸው፣ ለፕላን ዝግጅት ትኩረት መሰጠቱ፣ በአንዳንድ ክልሎች
መዋቅራዊ ፕላንን ከከተሞች የማሕበራዊና ሶሾዮ ኢኮኖሚ እቅድ ጋር ለማቀናጀት እየተሞከረ ያለው

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 85


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ጥረት፣ የፕላን ዝግጅቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለሁሉም ከተሞች የፕላን ተደራሽነትን
ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት እንደ ጠንካራ ጎኖች የሚታዩ ናቸው፡፡

መረጃ አያያዝና ልውውጥን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና መረጃ ኢንስቲትዩት ራሱን የቻለ
የመረጃ ንዑስ የሥራ ሂደት የሚገኝ ሲሆን በውስጡ የ GIS, IT, Documentation እና Audiovisual
ቡድኖች ሲኖሩት ከማዕከል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ የመረጃ አያያዝና ልውውጥ ስርዓት በመዘርጋቱ
በመረጃ አያያዝም ጥሩ ጅምር ይታያል፡፡

የክትትል ግምገማና ግብረ መልስ ስርዓትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከተማ ፕላን ዝግጅትና መረጃ
ኢንስቲትዩት በክትትልና ግምገማ ረገድ ከወረዳ እስከ ማእከል ባሉ የመሬት አስተዳደርና ግንባታ ፈቃድ እና
በከተማ ፕላን ዝግጅትና መረጃ ጽ/ቤት መሀከል የመረጃ ልውውጥ በ”hard copy” እና “soft copy”
የሚደረግ ሲሆን ችግሮችን በመለየት እርምት/ማስተካከያ እንዲደረግ የሚያስችል የአሰራርና ቁጥጥር
ሥርዓት ጥሩ ጅማሮ አለ፡፡

2.4 ከመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ቁልፍ ችግሮች

በከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ከላይ የተገለጹት ጠንካራ ጎኖች ያሉት
ቢሆንም ሊፈቱ የሚገባቸው በርካታ ችግሮች ያሉ ሲሆን በነባራዊ ሁኔታዎች ትንተናው መሰረት የተለዩ
ችግሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

 ፀድቀው በስራ ላይ የዋሉ አዋጆች የማስፈሚያ ደንብ እና መመሪያ የሌላቸው መሆኑ፣


 የተሟላ የአሰራር ማንዋሎችና የስታንዳርድ ሰነዶች አለመኖር፣
 በየጊዜው እያቆጠቆጡ የሚገኙ አዳዲስ፣ አነስተኛ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌ ማዕከላት የፕላን
አዘገጃጀት እና አፈፃፀም በሚመለከት የተቀመጠ ወይም የተዘጋጀ መመሪያ ያለመኖር፣
 የከተማ አስተዳደር ወሰን አከላለል መስፈርት የአፈጻጸም ስነ ስርዓት ደንብ አለመኖር እንዲሁም
በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች ከተሞች በቅንጅት ፕላን የማዘጋጀት ችግር መኖርን
ያካትታል፡፡
 በቂ የሰው ኃይል ያለመኖር፣
 ለከተማ ፕላን የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የባለሙያ ፍልሰት በፕላን ዝግጅት
ትቋማት መኖሩ፡፡
 አመቺ ተቋማዊ አደረጃጀት እና ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር፣
 የተሟላ የቴክኖሎጂ አቅርቦት እና አጠቃቀም ያለመኖር፣
 የፋይናንስ አቅም ውስንነትና የአጠቃቀም ችግር፣
 ደካማ የመረጃ አያያዝ፣ አደረጃጀት እና ልውውጥ ሥርዓት መኖር፣

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 86


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

 በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈፃፀም ላይ የግል ባለሃብቶች ተሳትፎ ውስንነት፡፡


 የከተሞች ፕላን ሽፋንና ጥራት ዝቅተኛ መሆን፣
 የከተሞች ፕላን ዓይነት፣ አዘገጃጀት፣ ሂደት፣ ይዘትና ለዝግጅት የሚወስዱት ጊዜ እንዲሁም
አደረጃጀት ላይ ወጥነት አለመኖር፣
 የከተማ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ይዘቶች /Major Land Use Functions/ በስታንዳርድ መሰረት
አለመቀመጥ፣
 በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ዝቅተኛነት/በቂ አለመሆን፣
 የክትትል፣ የግምገማና የግብረ መልስ ስርዓቱ በውጤት ላይ ያልተመሰረተ እና ተጠያቂነትን
በሚያሰፍን መልኩ የተቃኘ አለመሆኑ፣
 በፕላን ትግበራ ወቅት የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶች መከሰት፣
 የከተማ ፕላን ዝግጅትን በጥናትና ምርምር አለመደገፍ፣
 የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች በይዘታቸው ስፓሻል ፕላን ላይ ያተኮሩ መሆናቸውና ለማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በቂ ትኩረትና መፍትሄ የማይሰጡ እንዲሁም በከተማ ልማት ፖሊሲው መሰረት
የከተሞችን /የማዘጋጃ ቤት የልማት ዕቅድ ጋር የማይያያዙ መሆናቸው፣
 በተጎራባች ክልሎችና ከተሞች መካከል ያልተቀናጀና በተናጠል የሚከናወን የከተማ ፕላን ዝግጅት
በከተሞች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ፣
 ብሄራዊ የከተሞች እድገት ንድፍ/ scheme /እና የክልል ከተሞች እድገት ፕላን ሳይዘጋጅላቸው
የከተሞች ፕላን መዘጋጀቱ፣
 የአዳዲስ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌ ማዕከላት ፕላን ዝግጅትን አስመልክቶ ማኑዋል አለመኖር፣

3. የአካባቢ ልማት ፕላን

3.1. የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት መሰረተ ሀሳቦች

የአካባቢ ልማት ፕላን በከተማ አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀውን መዋቅራዊ ፕላን ተግባራዊ ለማድረግ ሲባል
አቅምንና በወቅቱ ያለውን ሁኔታ አገናዝቦ የሚዘጋጅ የአንድ ከተማ ከፊል አካባቢ ፕላን ሲሆን ተፈፃሚ
የሚደረገውም መዋቅራዊ ፕላኑ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ በከተማ ፕላን አዋጁ ወስጥ
ተመልክቷል፡፡ አንድ መዋቅራዊ ፕላን በርካታ የአካባቢ ፕላኖች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ የአካባቢ ልማት ፕላን
በፕላን አዋጁ መሰረት የሚከተሉትን እንዲያካትት ይጠበቃል፡፡

 የመሬት አጠቃቀም ዓይነትና የሕንፃ ከፍታ፣


 የአካባቢ መንገዶች፣ ዋና ዋና የመሰረተ ልማት አውታሮችና የትራንስፖርት ስርዓት፣
 የቤቶችን አደረጃጀት፣ የመንደሮችን ዓይነት፣ አረንጓዴና ክፍት ቦታዎችን፣
 የከተማ ማደስ፣ ማሻሻል፣ እንደገና መደልደል እና ሌሎች የአካባቢ ጉዳዮችን

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 87


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከባለሙያ ስብጥር አንጻርም አንድ የአካባቢ ልማት ፕላንን ለማዘጋጀት ቢያንስ ሶሰት ባለሙያዎች /ስፓሻል
ፕላነር፣ ፊዚካል ፕላነር እና የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ፕላነር/ የሚያስፈልጉ ሲሆን እንደ አካባቢው
ሁኔታ፣ደረጃና ተፈላጊነት ሌሎች ዓይነት ባለሙያዎችንም ሊያካትት ይችላል፡፡ የአካባቢ ልማት ፕላንን
መሰረት አድርገው የሚዘጋጁ ፕላኖችም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ/ መልሶ ማልማት

በከተማ ፕላን አዋጁ መሰረት መልሶ ማልማት ማለት ከተማ ነክ ችግሮችን ለማቃለል፣የኑሮ ደረጃን
ለማሻሻልና የተሳለጠ የመሬት አጠቃቀምን ለማስፈን የሚወሰድ እርምጃ ሲሆን፤ የከተማ እድሳትን
(urban renewal)፣ ማሻሻልንና (urban upgrading) የመሬት እንደገና መደልደልን (land reallocation)
ያካትታል። የከተማ ፕላን አዳዲስ የመስፋፊያ አካባቢዎችን ብቻ ሳይሆን ነባር የከተማ ክፍሎችንም መልሶ
የማልማት ተግባርም ያከናውናል፡፡

በአዋጁ አንቀፅ 41 መሰረት የከተማ እድሳት (Urban Renewal) ማለት በአንድ ከተማ ውስጥ የፈራረሱ፣
ያረጁና የተተዉ መዋቅሮችን (structures) በከፊል ወይም በሙሉ በማስወገድ ምቹ የመኖርያና የሥራ
አካባቢ ለማድረግ እንዲሁም የአካባቢውን ገፅታም ጭምር ለመቀየር የሚከናወን እንቅስቃሴ ነው። የከተማ
ማደስ በከፊል ወይም በሙሉ ያሉትን ነዋሪዎች ከአካባቢው አንስቶ ወደ ሌላ ቦታ ማስፈርን ያካትታል፡፡

በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 43 መሠረት ደግሞ የከተማ ማሻሻል (Urban Upgrading) ማለት በአንድ ከተማ
ውስጥ የሚታዩትን ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸውን መዋቅሮች በማደስና በከፊል በማስወገድ እንዲሁም
የመሰረተ ልማትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ አውታሮችን በመዘርጋት ወደ ምቹ/ወደ ተሻለ የመኖርያና
የመስሪያ አካባቢ የማሻሻል እንቅስቃሴ ነው። ከመሰረተ ልማት አቅርቦት በተጨማሪ የመኖሪያ ቤቶችን፣
የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሁኔታዎችንም በማሻሻል በአካባቢው ያለውን ነዋሪ የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚደረግ
ክንውን ነው፡፡

ለ/ የከተማ ዲዛይን ፕላን

መዋቅራዊ ፕላን ተግባራዊ የሚሆነው በአካባቢ ልማት ፕላን አማካኝነት እንደሆነ ቀደም ብሎ የተገለፀ
ሲሆን የአካባቢ ልማት ፕላን በዝርዝር ሲዘጋጅ ደግሞ ለተመረጡ አንዳንድ አካባቢዎች ብቻ የከተማ
ዲዛይን ፕላን ይዘጋጃል፡፡ ይህ ፕላን በተወሰነ የከተማ አካባቢ ውበትን ለመፍጠር/ለማጎልበት የሚዘጋጅ
ዝርዝር ፕላን ነው፡፡ የከተማ ዲዛይን ሥራ የከተማ ፕላን፣ የስነ-ህንፃና የላንድስኬፕ ሙያዎች ውህደት ነው
ለማለት ይቻላል። ከሚመለከታቸው መሀከል የሕንፃ መመሪያዎች/ስታንዳርዶች (ምሳሌ፡ ሕንፃዎች
የሚሰሩባቸው ቁሳቁሶች፣ አቀማመጥ፣ ከፍታ) የሕዝብ መጠቀሚያ ቦታዎች፣ ክፍት ቦታዎች፣ አደባባዮች፣

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 88


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የተሽከርካሪና የእግረኛ መንገዶች፣ የትራፊክ መብራት፣ የመንገድ መብራት፣ የእግረኞች ማቋረጫ


ይገኙባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የህንጻ ቀለምን፣ አጥርና አረንጓዴ ዕጽዋቶችን በመወሰን የአካባቢውን ውበት፣
ብሎም የንብረት ዋጋ እንዲጨምር አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

የከተማ ዲዛይን ለተለያዩ የከተማ ክፍሎች ማለትም ለከተማ ማዕከል፣ የጋራ መገልገያዎች ለሚገኙባቸው
የመኖሪያ አካባቢዎች፣ ለቅይጥ የመሬት አጠቃቀም አካባቢዎች፣ ለልዩ ቦታዎች ወዘተ. ሊዘጋጅ ይችላል፡፡
በሙያው ካለው ውሱን የሰው ሀይል አንፃር እንዲህ ዓይነት ፕላን በአገራችን እንዲዘጋጅ የሚፈለገው
ለሁሉም ከተሞች ሳይሆን የሕዝብ ቁጥራቸው ከ 20,000 በላይ ለሆኑና በተለይም ስራውንም
ከማስተዋወቅ አንፃር አሁን ካሉን ከተሞች አንፃር ከ 100,000 ሕዝብ በላይ ላላቸው ትላልቆቹ የአገሪቱ
ከተሞች አስገዳጅ እንዲሆን ያስፈልጋል። በነዚህ ከተሞች አዲስ ለሚዘጋጁት የከተማ ፕላንም ሆነ በፊት
ተዘጋጅተው ነገር ግን ገና አዳዲስ የአካባቢ ልማት ፕላኖች ለሚዘጋጅላቸው የተወሰኑ አካባቢዎች የዲዛይን
ፕላን የሚያካትቱበት ሁኔታ መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

ሐ/ የመሬት ሽንሸና (parcellation)

የአካባቢ ልማት ፕላን ተዘጋጅቶ ከፀደቀ በኋላ ፕላኑን ለማስፈፀም መከናወን ከሚገባቸው ተግባራት አንዱ
ፕላኑ ላይ በተቀመጠው የመሬት አጠቃቀም መሰረት ለመኖሪያም ሆነ ለሌሎች አገልግሎቶች ለአልሚዎች
የሚታደሉ ቦታዎችን መሸንሸንና ካርታ ማዘጋጀት ነው። በአብዛኛው የሽንሸና ስራ የፕላን ዝግጅቱ አካል
ሳይሆን በአፈፃፀም ወቅት በከተማው ማዘጋጃ ቤት የሚከናወን ተግባር ነው። ይህን ስራ ለማከናወን
የከተማ ማዘጋጃ ቤቱ ከቻለ በራሱ ቀያሾች ወይንም በግሉ ዘርፍ በተሰማሩ ድርጅቶች ወይንም ሁለቱንም
አማራጮች በመጠቀም ስራውን ማከናወን ይችላል።

ከሽንሸናው ጎን ለጎንና ቦታዎች ለአልሚዎች ከመታደላቸው በፊት የመንገድ፣ የውሀ፣ የኤሌክትሪክና የቴሌ
መስመሮችን አስቀድሞ መዘርጋት እንዲሁም ለማህበራዊ አገልግሎቶችም ከወዲሁ ቦታ መያዝ/መከለል
ያስፈልጋል፡፡ ቤቶች ከተገነቡ በኋላ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ባልተቀናጀ ሁኔታ መዘርጋት የነዋሪውን
ምቾት ከመቀነስ አልፎ ከፍተኛ የሃብት ብክነት እንደሚያስከትል በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። በመሆኑም
የመሬት ሽንሻኖው ከመሰረተ ልማት አውታር ዝርጋታ ጋር ተቀናጅቶ መሰራት ያለበትና መሬቱም የመሬት
ልማት አሰራሩ በሚፈቅደው አግባብ ለአልሚዎች መተላለፍ ይኖርበታል፡፡

የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት የሚያካትታቸው ጥናቶችና የሰው ሀይል

የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት ሂደት ከሞላጎደል የመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት ከሚያልፍበት ሂደት ጋር
ተመሳሳይ ሲሆን በዝግጅቱ ወቅት የሚካሄዱ ጥናቶች የአካባቢ ልማት ፕላኑ እንደሚዘጋጅበት ቦታ ሊለያይ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 89


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ይችላል፡፡ የአካባቢ ልማት ፕላኑ የሚዘጋጀው በመስፋፊያ አካባቢዎች ከሆነ ጥልቀት ያለው የሶሺዮ
አኮኖሚና ፊዚካል ጥናቶችን ሳያስፈልጉ በአካባቢው ላይ የሚያስፈልጉ መኖሪያ ቤቶች፣ ማህበራዊና
የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን በመለየት ወይም በመተንበይ ብቻ ፕላኑን ማዘጋጀት የሚቻል ሲሆን ነገር
ግን የአካባቢ ልማት ፕላኑ የሚዘጋጀው በነባር አካባቢዎች ላይ ከሆነ የሚፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች
የሚኖሩ በመሆኑ ጠለቅ ያለ የሶሺዮ አኮኖሚና ፊዚካል ጥናቶችን ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡

የሙያ ስብጥርን በተመለከተ የአካባቢ ልማት ፕላኑ የሚዘጋጀው በመስፋፊያ አካባቢዎች ከሆነ ለትናንሽ
ከተሞች ቢያንስ ሁለት ባለሙያዎች ማለትም የሶሺዮ ኢኮኖሚና የስፓሻል ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ
ሲሆን የአካባቢ ልማት ፕላኑ የሚዘጋጀው በነባር አካባቢዎች ላይ ከሆነ ቢያንስ ሶስት ባለሙያዎች /የሶሺዮ
ኢኮኖሚ፣ የፊዚካልና የስፓሻል/ ያስፈልጋሉ፡፡ የትላልቅ ከተሞች የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት ጊዜ
በስትራክቸር ፕላን ዝግጅት ወቅት የሚያስፈልጉት ባለሙያዎች ቢሳተፉ መልካም ነው፡፡

የካሳ ክፍያ

አንድ የከተማ ፕላን ዝግጅቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚቀጥለው ስራ በአካባቢ ልማት ፕላኑ አማካኝነት ፕላኑን
መተግበር ነው፡፡ ከፕላን ትግበራ ጋር በተያያዘ ጎልተው ከሚወጡና ከሚነሱ ጉዳዮች ውስጥ ደግሞ አንዱና
ዋነኛው የካሳ ክፍያ ጉዳይ ነው፡፡ የካሳ ክፍያ ማለት ለልማት ስራዎች ተብለው በተመረጡ ቦታዎችና
አካባቢዎች ለሚነሱ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሌሎች አካላት የገንዘብ ግምት እና ምትክ ቦታ በመስጠት
የሚስተናገዱበት ስርዓት ነው፡፡ ለዚህም የራሱ የሆነ ደንብና መመሪያ አለው፡፡ በዚህም መሰረት በከተማ
ፕላን ትግበራ ወቅት በተለይ ደግሞ በነባር/አሮጌ የከተማ አከባቢዎች በሚደረጉ የመንገድ ከፍታ ወይም
የመልሶ ማልማት ስራዎች በከፊል ወይንም ሙሉ በሙሉ የሚፈርሱ ቤቶች እንዲሁም በመስፋፊያ
አካባቢዎች ለሚፈናቀሉ የግብርና ይዞታዎች የከተማው አስተዳደር ከሕብረተሰቡ ጋር ውይይት በማድረግ
መግባባት ላይ በመድረስ ተገቢው የካሳ ክፍያ አስቀድሞ ማዘጋጀት አለበት፡፡

3.2. የሀገሪቱ የአካባቢ ልማት ፕላን አዘገጃጀት ነባራዊ ሁኔታዎች

መዋቅራዊ ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ ፕላኑን ወደ መሬት ማውረድ የሚቻለው በአካባቢ ልማት ፕላን
አማካይነት እንደሆነ ቀደም ብሎ ተገልጿል፡፡ የአካባቢ ልማት ፕላን በመዋቅራዊ ፕላኑ ውስጥ ተለይቶ
ለሚመለከት የከተማ ክፍል የሚዘጋጅ ዝርዝር ፕላን ሲሆን ፕላኑ የአካባቢ መልሶ ማልማትን፣ መልሶ
ማሻሻልንና ለአካባቢ የሚሰሩ ዝርዝር ፕላኖችን ያጠቃልላል፡፡ በዚህ ሰነድ ውስጥ ከከተማ ፕላን ዝግጅት ጋር
በተያያዘ የተነሱት ጉዳዮች ሁሉ የአካባቢ ልማት ፕላንንም የሚመለከቱ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ
በአካባቢ ልማት ፕላን ላይ ብቻ የተደረገ ዳሰሳ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ የከተሞች መዋቅራዊ ፕላን
እየተዘጋጀ የሚገኘው በክልል ከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማት እና አልፎ አልፎም በግል አማካሪ ድርጅቶች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 90


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሲሆን ፕላኑ ሲዘጋጅ ከሁለት ያልበለጡ የአካባቢ ልማት ፕላኖችን በማዘጋጀት ቀሪ የአካባቢ ልማት
ፕላኖችንና ዝርዝር ፕላኖች የማዘጋጀትና የመተግበር ስራዎች ከተሞች እንዲቀጥሉበት ይተውላቸዋል፡፡
አብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች የኢኮኖሚ ሁኔታ ደካማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከተሞቹ የተዘጋጀላቸውን
መዋቅራዊ ፕላን ለመተግበር የአካባቢ ልማት ፕላኖችንና ዝርዝር ፕላኖችን ለማዘጋጀት ከፍተኛ የባለሙያ፣
የመሳሪያዎች እንዲሁም የአሰራር ማኑዋሎችና ስታንዳርዶች እጥረት ይታይባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት
ዝርዝር ፕላኖች ሳይዘጋጁ ፕላኖችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚሞክሩ ሲሆን አልፎ አልፎ በትላልቅ ከተሞች
የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት በተወሰነ ደረጃ ቢኖርም በበርካታ ችግሮች የታጀቡ ናቸው፡፡ በአካባቢ ልማት
ፕላን ዝግጅት ጊዜ ከሚታዩት ችግሮች መካከል ቀድሞ የተዘጋጀ የአካባቢ ልማት ፕላን ከጎኑ ሌላ የአካባቢ
ልማት ፕላን ሲዘጋጅ ይህ ፕላን ቀድሞ ከተሰራው ከጎኑ ካለው ፕላን ጋር ያለመጣጣምና ያለመናበብ ችግር
ዋንኛው ነው፡፡

በክልል ከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማት የሚዘጋጁት የአካባቢ ልማት ፕላኖች ከጊዜ አንጻር ሲታዩ ወጥነት
የሌላቸው ሲሆን ለምሳሌ በአማራ ክልል ለመሀከለኛ ከተሞች መዋቅራዊ ፕላኑን ጨምሮ የአካባቢ ፕላኖች
ዝግጅት በሁለት ወራት ውስጥ የሚዘጋጅ ሲሆን በአዲስ አበባ ለአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት ብቻ እስከ
አራት ወራት ጊዜ የሚያዝበት ሁኔታ አለ፡፡

ከባለሙያ ስብጥር አንጻርም አንድ የአካባቢ ልማት ፕላንን ለማዘጋጀት ቢያንስ ሶሰት ባለሙያዎች /ስፓሻል
ፕላነር፣ ፊዚካል ፕላነር እና ሶሺዮኢኮኖሚክ ፕላነር/ የሚያስፈልጉ ሲሆን በአብዛኛው የተጠቀሱት
ባለሙያዎች በተሟላ መልኩ አይገኙም፡፡ በብዙዎቹ ክልሎች የአካባቢ ልማት ፕላን የሚዘጋጀው
በአርክቴክት ወይም በከተማ ፕላን ባለሙያው ብቻ በመሆኑ ፕላኖቹ በሚዘጋጁበት ወቅት ለማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ወይም ችግሮች ትኩረት አይሰጡም፡፡ ሌላው የሚስተዋለው ችግር የአካባቢ ልማት
ፕላን ዝግጀቱ የአካባቢውን ሕብረተሰብ በሚፈለገው መልኩ በማሳተፍ ፍላጎታቸውን ለማሟላት
አለመቻሉ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና መረጃ ኢንስቲትዩት እስካሁን እየተዘጋጁ ያሉት አብዛኞቹ
የአካባቢ ልማት ፕላኖች በመሬት አጠቃቀም/Spatial/ እና በፊዚካላዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ በመሆናቸው
ብዙም የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በማቃለል መሻሻል ወይም ለውጥ ማምጣታቸው አይስተዋልም፡፡

ከአካባቢ ልማት ፕላን ትግበራ ጋር ተያይዞ ከሚከሰቱ ችግሮች መሀከል ዋንኛው የከተሞች የመሬት
አጠቃቀም በአብዛኛዉ በፕላን በተደነገገዉ መሰረት ባለመተግበሩ ለዋና ዋና ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና
ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶቸ በተያዙ ቦታዎች ላይ የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶች እየተከሰቱ መገኘቱ ነው፡፡
ለአብነት ያህል የአረንጓዴ ቦታዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያና መዝናኛ ቦታዎች፣ የበአላት ማክበሪያ ቦታዎች
በፕላኑ ከተመለከተዉ ድንጋጌ ውጭ በግለሰቦች እና በፈጻሚዎች ለሌላ አገልገሎት ማዋል በብዛት
የሚስተዋሉ ችግሮች ሲሆኑ እንደዚህ አይነቶቹን የፕላን ጥሰቶች በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ አግባብ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 91


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ተከታትሎ የሚያርም እና የሚያስተካክል አሰራር አለመኖርና የማስፈጸም አቅም ደካማ መሆን ችግሩን
በእጅጉ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ከፕላን ትግበራ ጋር በተያያዘ ከሚጠቀሱ ሌሎች ዋና ዋና ችግሮች መሀል
የፕላን ትግበራ ስትራቴጂ ሳይነደፍ ትግበራ ማካሄድ፣ በየጊዜው የመሬት አጠቃቀም ለውጥ (Zoning
change) ማድረግ፣ ፕላኖች በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት መተግበር አለመቻላቸው፣ በፕላን ትግበራ
ወቅት ለሚፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢው ካሳ በተገቢ ጊዜ ባለመከፈሉ ምክንያት በልማት
ስራዎች ላይ መጓተት መፈጠሩ፣ እንዲሁም በሚዘጋጁ ፕላኖች ጥራት ዝቅተኛነት ምክንያት ፕላኖችን ወደ
መሬት ለማውረድ አስቸጋሪ መሆን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ከመኖሪያ ቤት ጋር ተቀይጠው አገልግሎት እንዲሰጡ በተፈቀዱ የንግድና ማምረቻ አገልግሎቶች ሰበብ


በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የድምጽ፣ የሽታ እና ከማምረቻ ተቋማቱ በሚወጡ ብናኞች ብክለት ችግር
እየተፈጠረ መሆኑ ከትግበራ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ሌላው ችግር ነው፡፡

በአንዳንድ ክልሎች የመሬት ይዞታ በጎሳ እጅ በመሆኑ ማዘጋጃ ቤቶች በሚያስተዳድሩት መሬት ላይ
ቀጥተኛ የባለቤትነት መብት ስለሌላቸው የተዘጋጁ ፕላኖችን በመተግበር ረገድ ከፍተኛ ችግሮች
እየገጠሟቸው ይገኛል፡፡ ይህ ጉዳይ ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጋር ተያያዥ በመሆኑ ችግሩን ለምፍታት
የሚያስችሉ በጥናት የተደገፉ ስልቶችን መንደፍ ያስፈልጋል፡፡

ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ በፕላኑ መሰረት በመሬት ላይ የልማት ስራዎች በወቅቱ የማይከናወኑ ሲሆን ለዚህም
ዋንኛው ምክንያት በፕላኑ ለተለያዩ አገልግሎት የሚያዙ ቦታዎችን ፕላን አዘጋጁ ለሚመለከታቸው አካላት
አለማሳወቅና በሚመለከታቸው አካላት ሲጠየቅም ፈጣን ምላሽ አለመስጠት ነው፡፡ የሚመለከታቸው
አካላትም ቢሆኑ በፕላን ላይ የተያዘላቸውን ቦታ ተከታትለው ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት አነስተኛ
በመሆኑ በፕላን ለተለያዩ አገልግሎት የተያዙ ቦታዎች ሳይለሙ ይቆያሉ፡፡

3.3. በአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት የሀገሪቱ የተቋማት ብቃት ዝንባሌ ትንተና /Trend
Analysis/

በመሰረቱ የአካባቢ ልማት ፕላን መዘጋጀት ያለበት በራሱ ፕላን በሚዘጋጅለት ከተማ አስተባባሪነትና
መሪነት በዛው በከተማው ውስጥ መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚሁም ዋናው ምክንያት የአካባቢው ሕዝብ
እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተሟላ በፕላን ዝግጅቱም ሆነ ትግበራ በቀጣይነት መሳተፍ እንዲችሉና
የፕላኑም የተፈፃሚነት ደረጃ ከፍ እንዲል ነው፡፡ ምንም እንኳን ቀደም ብሎ እንደተገለፀው የሕብረተሰብ
ተሳትፎ በማንኛውም የፕላን ዝግጅት ሂደት በቀጣይነት መከናወን ያለበት ተግባር ቢሆንም ዋነኛው
መገለጫውና ይበልጥ ውጤታማም የሚሆነው በአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅትና ትግበራ አማካኝነት
እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 92


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ማንኛውም የከተማ ፕላን የአፈፃፀም ደረጃ የሚለካው በከተሞች በየአካባቢው በሚፈፀሙ ድምር
ውጤቶች አማካኝነት በመሆኑ የአካባቢ ልማት ፕላን ልዩ ትኩረት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን በአገራችን ከአዲስ
አበባ ውጭ ባሉት ከተሞች የመዋቅራዊና ብሎም የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅትም ሆነ በተለይም ትግበራ
ገና በቅርቡ የተጀመረ በመሆኑና በዚህም አቅጣጫ ልምዱም የሳሳ ስለሆነ ጎልቶ የሚታይ ውጤት
ተመዝግቧል ለማለት አያስደፍርም፡፡ ስለ መዋቅራዊም ሆነ የአካባቢ ልማት ፕላን የሚደነግገው የከተማ
ፕላን አዋጅ እንኳን የፀደቀው በ 2000 ዓ.ም መጨረሻ ገደማ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ባሉት ጥቂት ጊዜያት
ውስጥ የከተማ ፕላን አሀዶች ባሉባቸው አራት ክልሎች በሚገኙ የፕላን ተቋማት እንዲሁም በጣም
በተወሰነ ደረጃ በግሉ ዘርፍ የአካባቢ ፕላኖች ተዘጋጅተዋል፡፡ በአጠቃላይ የተዘጋጁት ቁጥራቸው ጥቂት
ከመሆኑም ባሻገር የሚበዙት መዋቅራዊ ፕላኖች ሲዘጋጁ አብረው የተዘጋጁ ናቸው፡፡

ሰፋ ያለ ልምድ አለው በሚባለው በአዲስ አበባም ቢሆን ከ 1994 ዓ.ም. የፕላን ክለሳ በኋላ ፕላኑን
ለማስፈፀም 42 የአካባቢ ልማት ፕላኖች የተዘጋጁ ቢሆንም በተለይ ለከተማዋ ስትራቴጂካዊ
አቅጣጫዎችና ለንዑስ ማዕከላት የተዘጋጁት ተግባራዊ እንዳልሆኑ ወይንም አንዳንዶቹ ተግባራዊ
የሆኑትም በሕንፃ ፈቃድ አማካኝነት ብቻ እንደሆነ በቅርቡ የወጣ የማስተር ፕላኑ ግምገማ ሪፖርት
ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለከተማዋ የተዘጋጁት የአካባቢ ልማት ፕላኖች የአካባቢውን
ሕብረተሰብ ማሳተፍ እንዳልቻሉ ተገልጿል (LTPA, 2010: ገፅ 23)፡፡ ሌላው የተጠቀሰው ደካማ ጎን ደግሞ
ገና የአካባቢ ልማት ፕላንን ለማዘጋጀት የሚያስችል ዕውቀት፣ ልምድና ክህሎት ለሌላቸው ክፍለ
ከተሞችም የአካባቢ ልማት ፕላንን እንዲያዘጋጁ ስልጣን መሰጠቱ ነው፡፡ ከዚሁም ጋር በተያያዘ በክፍለ
ከተማና ወረዳ ደረጃ ተጓዳኝ ክህሎትና አቅም በሌለበት ያልተማከለ አሰራርን በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ
እንደተሞከረ ያሳያል (ቀድሞ በተጠቀሰው ምንጭ)፡፡

በሌላ በኩል የአካባቢ ልማት ፕላኖች ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ልማት ከመገባቱ በፊት ዝርዝር ፕላንና የከተማ
ዲዛይንን ማዘጋጀት አስፈላጊ ቢሆንም ይህ አሰራር በአገሪቱ ውስጥ የተለመደ አይደለም፡፡ አብዛኞቹ
የአካባቢ ልማት ፕላኖች የሚተገበሩት የማስፈጸሚያ ህጎች፣ የከተማ ዲዛይን እንዲሁም ዝርዝር የሽንሸና
ፕላን ሳይዘጋጅላቸው ሲሆን ለዚህም ዋናዎቹ ሊጠቀሱ የሚችሉ ምክንያቶች የከተማ ፕላን አዋጁ የከተማ
ዲዛይን ዝግጅትን /ለትላልቅ ከተሞች/ የማያካትትና ለዲዛይን ዝግጅት የተዘጋጁ መመሪያዎች፣ የአሰራር
ስታን ዳርድ እና ማንዋሎች አለመኖራቸው ነው፡፡

በሌላ በኩል በአካባቢ ልማት ፕላን አማካኝነት የአንዳንድ የተረሱ አካባቢዎችን መሰረተ ልማት
በመዘርጋትና እንዲሁም የቅርስ ቦታዎችንም እንዲጠበቁ በማድረግ በኩል በአዲስ አበባ ጥረቶች
መታየታቸው እንደጠንካራ ጎን ሊታይ የሚችል ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 93


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የመዋቅራዊና ብሎም የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅትና ትግበራ ገና በተሟላ መልክ ተግባራዊ ሆኗል
ለማለት ባይቻልም የተያዘው መንገድ ግን በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ ይገኛል፡፡ በአዲሱ የከተማ ፕላን ስራ
አስተሳሰብ (paradigm shift in urban planning) የመዋቅራዊ ፕላን ማዘጋጀትና ለእሱም ማስተግበሪያ
ከአቅም ጋር እየተገናዘበ እንደአስፈላጊነቱና በጊዜው ያለውን የአካባቢውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት
የአካባቢ ልማት ፕላኖች ማዘጋጀት የስትራቴጂክ ፕላን አሰራር ስርዓትን ይከተላል፡፡ ስለሆነም ይህ አዲስ
አስተሳሰብና አሰራር አገሪቱ ከተለመችው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫ ጋር የሚጣጣም በመሆኑ
የወደፊቱ ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም አዝማምያ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡

3.4 ከአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት ጋር ተያያዥ የሆኑ ቁልፍ ችግሮች

በአጠቃላይ ከአካባቢ ልማት ፕላን ጋር በተያያዘ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1. በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ዝቅተኛነት/በቂ አለመሆን፣


2. በአካባቢ ልማት ፕላን ፕላን ትግበራ ወቅት የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶች መከሰት፣
3. የአካባቢ ልማት ፕላን ለሚዘጋጅላቸው ትላልቅ ከተሞች የከተማ ዲዛይን (Urban Design)
አለመካተቱ፣
4. በማዘጋጃ ቤት እና በመሠረተ ልማት አውታር አቅራቢ ድርጅቶች መሃከል እንዲሁም በመሠረተ
ልማት አውታር አቅራቢ ድርጅቶች መሃከል /እርስ በእርሳቸው/ ቅንጅታዊ አሰራር ባለመኖሩ
ምክንያት በፕላን ትግበራ ወቅት የሚከሰት የሀብት ብክነት፣
5. የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅትን በጥናትና ምርምር አለመደገፍ፣
6. የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች በይዘታቸው ስፓሻል ፕላን ላይ ያተኮሩ መሆናቸውና ለማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በቂ ትኩረትና መፍትሄ የማይሰጡ እንዲሁም በከተማ ልማት ፖሊሲው
መሰረት የከተሞችን /የማዘጋጃ ቤት የልማት ዕቅድ ጋር የማይያያዙ መሆናቸው፣
7. የአካባቢ ልማት ፕላን ባልተዘጋጀበት ሁኔታ መዋቅራዊ ፕላንን ለመተግበር መሞከር፣
8. አልፎ አልፎ ጎን ለጎን የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላኖች የማይናበቡ መሆናቸው፣
9. ከመኖሪያ ቤት ጋር ተቀይጠው አገልግሎት እንዲሰጡ በተፈቀዱ የንግድና ማምረቻ አገልግሎቶች
ሰበብ አልፎ አልፎ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የድምጽ፣ የሽታ እና ከማምረቻ ተቋማቱ በሚወጡ
ብናኞች ብክለት ችግር መፈጠር፣
10. ለተለያዩ አገልግሎት የሚያዙ ቦታዎችን ፕላን አዘጋጁ ለሚመለከታቸው አካል አለማሳወቅ፣
የሚመለከታቸው አካላትም ቦታውን አለማልማት፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 94


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

4. የመሰረታዊ ካርታ፣ መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ ልማት ፕላን የጋራ ጉዳዮች

4.1. የሕዝብ ተሳትፎ በከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ

ምንም እንኳን በሀገራችን ገና ተግባራዊ ሆኗል ለማለት ባያስደፍርም ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት
በዓለማችን ላይ በከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ ከተደረጉ መሰረታዊ ለውጦች (paradigm shift) አንዱ
የከተማ ፕላን በባለሙያ ብቻ መመራት ያለበት ቴክኒካል ተግባር ነው ከሚለው አስተሳሰብ ወደ
የማህበረሰቡንና የባለድርሻ አካላትን ግብአት የሚያካትት ሰፋ ያለ ውይይት ላይ የተመረኮዘ ተግባር መሆን
አለበት ወደሚለው መሸጋገሩ ነው። በተለይም የፖለቲካ አመራሩ ይህን ውጤታማ በማድረግ የማይተካ
ሚና እንደሚጫወት ጎልቶ መውጣቱ የአስተሳሰብ ለውጥ አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 43 ንዑስ አንቀፅ 2 እና አንቀፅ 89 ንዑስ አንቀፅ 6 በብሔራዊ ልማት
ፕሮግራሞችና ፖሊሲዎቸ ላይ ሕብርተሰቡ የመሳተፍ መብት እንዳለውና መንግስትም የተሳትፎ
እንቅስቃሴዎችን የመደገፍና የማመቻቸት ሀላፊነት እንዳለበት ይደነግጋሉ። የከተማ ፕላን አዋጁም
ይበልጥ ተጨባጭ በሆነ መንገድ በከተማ ፕላን ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በዝግጅቱም ሆነ በትግበራ ሂደት
በሙሉ ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ያብራራል።
ነገር ግን በአብዛኛው በከተማ ፕላን ስራ የአሳታፊነት ሂደት በተጨባጭና በዘላቂነት ተግባራዊ ሊሆን
አልቻለም፡፡ ለመሆኑ አሳታፊነት ምን ማለት ነው? ለምንስ አስፈለገ?

አሳታፊነት ማለት የተወሰኑ የሕብረተሰብ አባላትን ብቻ ለተወሰነ ጊዜ በማሰባሰብ የሚደረግ ውይይት ብቻ


አይደለም፡፡ አሳታፊነት ውጤታማ የሚሆነው ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላትን
በአብዛኛው በውክልና፣ በተደራጀና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ከፕላን ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በዝግጅትና
አፈፃፀም ወቅት መረጃ ከመሰብሰብ ጀምሮ በጋራ ውሳኔ እስከ መስጠት ድረስ በየደረጃው የሚያሳትፍ
ሂደት ሲሆን ነው፡፡ አሳታፊነት ካስፈለገባቸው በርካታ ምክንያቶችም ጥቂቶቹ ነዋሪው የባለቤትነት ስሜት
እንዲኖረው፣ የህብረተሰቡ ፍላጎት በተጨባጭ እንዲያካትት፣ ፕላኑም ተግባራዊ የመሆን ዕድሉ እንዲሰፋና
እንዲረጋገጥ እንዲሁም ሕገ-መንግስታዊ መብትም ስለሆነ ጭምር ነው።

አሳታፊነትን ተጨባጭና ውጤታማ ለማድረግ መወሰድ ከሚገባቸው በርካታ እርምጃዎች አንዱ የፕላን
ዝግጅትና ትግበራ ሂደቱ የፕላን ሀሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ በዝግጅቱም ሆነ በትግበራ ወቅት ፕላኑ
የሚዘጋጅለት የከተማ አስተዳደር/ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት እንዲመራ ማድረግ ነው፡፡ አስቀድሞ
እንደሚደረገው የፕላን ዝግጅት ሂደቱ የሚመራው በሌላ ፕላን በሚያዘጋጅ አካል ከሆነ የተሳትፎ ሂደቱ
ቀጣይና ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ በተጨማሪም የሕዝብ ግንኙነት ስራዎችን ከመጀመሪያው ጀምሮ
ማከናወን ለውይይት በቂ ጊዜና ምቹ ቦታ ማዘጋጀት፣ ሁሉም አካል መወከሉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 95


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከላይ የተጠቀሱት ጠቅለል ያሉ የሕግ አንቀፆች/ሀሳቦች ቢኖሩም በከፊልም ዝርዝር አንቀፆች/ደንቦች


ባለመኖራቸው በአብዛኛው የከተማ ፕላን ስራ የአሳታፊነት ሂደት በተጨባጭና በዘላቂነት ተግባራዊ ሊሆን
አልቻለም፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ለመሆኑ ተሳትፎን በዘላቂነት ተግባራዊ ማድረግስ ይቻላል ወይ? የሚል
ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ የብዙ ሀገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየው በዋናነት ግንዛቤና ቁርጠኝነት ካለ
አሳታፊነትን ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡

አሳታፊነት ማለት በሀገራችን እስካሁን እንደሚደረገው አንዴ ወይም ሁለቴ የተወሰኑ ሰዎችን በማሰባሰብ
ለአጭር ጊዜ /አንድ ቀን/ የሚደረግ ውይይት ብቻ አይደለም፡፡ አሳታፊነት ማለት በተደራጀና ቀጣይነት
ባለው መልኩ መረጃ እና አስተያየቶችን ከመሰብሰብ ጀምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ውሳኔዎች ላይ
እስከ መድረስ የሚያጠቃልል ረጅምና ውስብስብ ሂደት ነው (FUPI, 2009)፡፡ የፕላን ዝግጅት ገና ሲታሰብ
ጀምሮ በዝግጅቱም ሆነ በትግበራ ወቅት መካሄድ ያለበት የማያቋርጥ ሂደት መሆኑ ቀደም ሲል ተገልጿል፡፡
በሂደቱም ውስጥ እንደ ሁኔታው የተሳትፎውም መልክ ሊቀያየር እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በመሠረታዊ ካርታና በከተማ ፕላን ዝግጅት፣ አፈፃፀምና ክትትል ሂደት ህብረተሰቡ ተገቢው የቅድመ
ግንዛቤ ማስጨበጫ አሰራር ተዘርግቶለት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ባለመበረታታቱ የተሳትፎ ደረጃው
ውስን እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የችግሩ ምክንያቶችም ከፕላን አዘጋጁ፣ ከፕላኑ ባለቤት፣ ከተሳታፊው እና
ከሬጉላቶሪና ድጋፍ ሰጪ አካላት የመነጨ መሆኑ ተብራርቷል፡፡ የከተሞችን የፕላን ወሰን ክለላና ለፕላን
ዝግጅት የሚያግዝ መሠረታዊ ካርታ በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ ህብረሰቡ በንቃት ሳይሳተፍ በመቅረቱ
በማስፋፊያ አካባቢ የከተሞች ድንበር ክለላ ላይ የተተከሉ የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦችን ሳይቀር በአጭር
ጊዜ ውስጥ ተነቅለው ይጠፋሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በከተማ ፕላን ዝግጅት ሂደት የህብረተሰቡን ፍላጎትና ችግሮች ከመለየት ጀምሮ ትኩረት
የሚሹ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ትክክለኛ መረጃንና ውሳኔዎችን በመስጠት ህብረተሰቡን
በሚፈለገው ደረጃ የማሳተፍ ልምድና ግንዛቤ የለም፡፡ በተወሰነ ደረጃ በፕላን ዝግጅት ሂደት የማሳተፍ
አዝማሚያ ቢኖርም ያልተስተካከለ የተሳታፊ አካላት አመራረጥና የውክልና ስብጥር ፍትሀዊነት
የሚጎድለው በመሆኑ በተለይም ችግሩ የሚመለከታቸው ተጋላጭ /ለምሳሌ የአካል ጉዳተኞች/ እና ዝቅተኛ
የህብረተሰብ ክፍሎችን ቢያንስ በውክልና በማሳተፍ ችግርና ፍላጎቶቻቸውን በአግባቡ በፕላኑ
እንዲንጸባረቅ የሚያደርግ አሰራር አልሰፈነም፡፡ በፕላን አፈጻጸም ሂደትም ቢሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ
የለም ሊባል በሚችልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ ለውይይት በሚቀርቡ የፕላን እሳቤዎች (Proposal) ላይ
በውሳኔ አሰጣጥ ስለማይሳተፍ የባለቤትነት ድርሻውን በሚገባ ሊወጣና ህገወጥ አስራሮችንም በጋራ
መዋጋት አልቻለም፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 96


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በፕላን ዝግጅትም ሆነ በአፈጻጸም ወቅት ለተሳታፊነት በሚጋበዙ ጥቂት አካላትና ግለሰቦች የተሳትፎውን
እድልና መድረክ በመገደብ የብዙሀኑን ፍላጎት የመጫን ሁኔታና በህብረተሰቡም በኩል የተሳትፎ ፍላጎት
የማጣት ችግር ይታያል፡፡ ሕብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ከፕላን ዝግጅት ምዕራፎች ውስጥ ወጥ በሆነ
መልኩ በቋሚነት የሚሳተፉበት ሁኔታ የሌለ ሲሆን በአንድ የፕላን ዝግጅት ምዕራፍ የተሳተፉትን
በቀጣይነት በሁሉም የፕላን ዝግጅት ምዕራፎች በማሳተፍ ፈንታ በተለያዩ ምዕራፎች የተለያዩ
ተሳታፊዎች እንዲሳተፉ መደረጉ በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ሌላው ችግር ነው፡፡ በፕላን ዝግጅትና
አፈጻጸም የህዝብ ተሳትፎ ማንዋል ተዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት በተገቢው አለማዳረሱ
ለህብረተሰብ ተሳትፎ ማነስ እንደ አንድ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ በአጠቃላይ በመሰረታዊ ካርታ፣ በፕላን
ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ያለውን አመለካከት ለመቀየር የህብረተሰቡን፣ የባለድርሻ አካላትንና የልማታዊ
ባለሀብቱን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ጥረት በቂ አይደለም፡፡

የህብረተሰቡም ሆነ የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ በሀገራችን በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ሊሆን
ያልቻለባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንዱ እና ዋናው ምክንያት በተለያዩ የመንግስት/የአስተዳደር
እርከኖች ላይ ያሉ አካላት በተለይም በየከተሞች የሚገኙ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች አሳታፊነትን
በተመለከተ ያላቸው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን ነው፡፡ ጊዜያዊና ቋሚ የተሳትፎ መድረኮች አለመኖር፣
ለተሳትፎ ሂደቱ በጀት አለመመደብ፣ በውይይትና በመድረክ አመራር የሰለጠኑ ባለሞያዎች (facilitators)
እንዲሁም የተሟላ የሕግ ማዕቀፍና የስራ መመሪያዎች በብዛት አለመኖር ሌሎች ተጠቃሽ ምክንያቶች
ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና መረጃ ኢንስቲትዩት በአብዛኛው በሚዘጋጁት የአካባቢ ልማት ፕላኖች የፕላኑ
ባህሪ መልሶ ማልማትና ማሻሻል በመሆኑ በፕላኑ ትግበራ ጊዜ የሚያፈናቅለው የሕብረተሰብ ክፍል ፍላጎት
ከማሟላት አንጻር ክፍተቶች እንዳሉበት ከዚህ ቀደም ከተዘጋጁትና ከተተገበሩት የአካባቢ ልማት ፕላኖች
ውጤት ለመረዳት ተችሏል፡፡

በፕላን ዝግጅት የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ከላይ የተጠቀሱት በርካታ ችግሮች የሚታዩበት ቢሆንም
በተዘጋጀው ፕላን ላይ የተወሰነ የሕብረተሰቡ ክፍል አስተያየቱን እንዲሰጥ መደረጉና በዚሁም መሰረት
ገንቢ አስተያየቶች በፕላኑ ውስጥ እንዲንጸባረቁ እየተደረገ ያለው ጥረት እንደጠንካራ ጎን የሚታይና
ሊጎለብት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 97


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

4.2. ክትትል፣ ግምገማና ግብረ መልስ

የክትትልና ግምገማ ስርዓት ከተሞች ፕላን ሲዘጋጅላቸው ሂደቱን ለመከታተልና ከተዘጋጀላቸውም በኋላ
የተዘጋጀው ፕላን በትክክል ተግባራዊ ስለመሆኑና የሚፈለገውንም ውጤት ስለማምጣቱ በየደረጃው
መከታተያና መመዘኛ መሳሪያ ነው፡፡

የክትትል ሥራ የፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም እንቅስቃሴን በተከታታይ መረጃ በመሰብሰብ የምንከታተልበት


እና እርምት የሚደረግበት አሠራር ሲሆን ግምገማ ደግሞ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚከናወን የፕላን
ዝግጅትና አፈጻጸም ዕቅድ ክንውን አፈጻጸም የሚፈተሽበትና የሚለካበት እንዲሁም ግብረመልስ
የሚሰጥበት አሠራር ነው፡፡

ስለዚህ ክትትል፣ ግምገማና ግብረ መልስ በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት ውስጥ አንዱ ቁልፍ ምዕራፍ
በመሆኑ አስፈላጊውን መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ግልጽ የአሠራር ቅደም ተከተልና ሪፖርት አደራረግ፣
ትክክለኛ መርሀግብር፣ መለኪያ እና የክትትልና ግምገማ መስፈርት /ቼክሊስት ተዘጋጅቶለት በሥራ ላይ
ሊውል የሚገባ ሲሆን በክትትልና ግምገማ ለሚለዩ ግድፈቶች የግበረ-መልስ አሰጣጥ ስርዓትም መዘርጋት
ያስፈልጋል፡፡ በክትትልና ግምገማ ወቅት ከሚለዩት ችግሮች ውስጥ ዋንኛው የመሬት አጠቃቀም ጥሰት
ማለትም በፕላን ላይ ለአንድ የተወሰነ አገልግሎት የተመደበ መሬትን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ለሌላ
አግልግሎት ማዋል ሲሆን ይህ ችግር በሀገሪቱ ከተሞች በስፋት የተንሰራፋ በመሆኑ ከችግሩ አሳሳቢነት አኳያ
ጥሰቱን ያከናወኑ አካላት በእስራትና በገንዘብ ተጠያቂ የሚሆኑበት ደንብና መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ
ነው፡፡

በሀገራችን በየደረጃው በከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ ወቅት የሚደረገው የክትትል፣ የግምገማና የግብረ
መልስ ሥራን በተመለከተ የግንዛቤና የአቅም እጥረት፣ ወጥ፣ ተከታታይ፣ የተቀናጀና ወቅቱን የጠበቀ
አለመሆን በፕላን ዝግጅትና ትግበራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ ለከተማ ፕላን ዝግጅት
የሚረዳ የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት የክትትል፣ ግምገማና ግብረ-መልስ ሥርዓት ያልተዘረጋለት በመሆኑ
በተለያዩ አካላት የሚዘጋጁ ካርታዎች ያሉባቸው ጥንካሬና ክፍተቶች ተለይተው የተሻሉ ተሞክሮዎችን
ለማስፋትና ድክመቶችንም በማረም በፕላን ዝግጅትና ትግበራ ጥራቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን
አሉታዊ ተፅዕኖ በማስቀረት ረገድ ውስንነት ይታይበታል፡፡ የከተማ ፕላኖች የፕላን ዘመናቸውን
እንዳጠናቀቁ ለከተማው ዕድገት ያስመዘገቡት ውጤት በሚገባ ተገምግሞ ድክመቶቻቸውና
ጥንካሬዎቻቸው ተለይቶ ወቅታዊ ክለሳ አይደረግላቸውም፡፡ የክትትል፣ የግምገማና የግብረ-መልስ ሥርዓቱ
ለሁሉም ፕላን የተዘጋጀላቸው ከተሞች ተደራሽ አይደለም፡፡ በጅምር ያለው የፕላን አዘገጃጀትም ሆነ
አፈጻጸም የክትትል፣ የግምገማና የግብረ-መልስ አሰራር ስርዓትም ችግሮቹን በዝርዝር ለይቶ ተጠያቂነትን
በሚያሰፍን መልኩ ያልተቃኘ ሲሆን እንዲሁም መልካም ተሞክሮዎች ተቀምረው ወደ ሌሎች ከተሞች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 98


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ለማዳረስ ተገቢው ስትራቴጂ ተቀይሶ እየተሰራበት አይደለም፡፡ ሌላው ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ችግር
የህብረተሰቡ ተሳትፎ በከተማ ፕላን ትግበራ ወይም አፈጻጸም ላይ በክትትልና ግምገማ ሂደት ውስጥ
ጨርሶውኑ አለመኖሩ ነው፡፡

በከተማ ፕላን ዙሪያ የሚካሄዱ የክትትልና ግምገማ ስራዎች በብዛት የሚያተኩሩት የተዘጋጁ ፕላኖችን
ትግበራ ወይም አፈጻጸም ላይ ሲሆን በፕላን አዘገጃጀት ላይ የሚደረግ ክትትልና ግምገማ ግን ያን ያህል
የጎላ አይደለም፡፡ በመሆኑም በሚዘጋጁ ፕላኖች ጥራት እና አፈጻጸም ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ
ያሳድራል፡፡

ከላይ ለተዘረዘሩት ችግሮች መከሰት እንደ መንስኤ ከሚጠቀሱት መሀከል ዋና ዋናዎቹ የፕላን አፈጻጸም
ክትትልና ግምገማ ቋሚ አደረጃጀት አለመኖር፣ በፌደራል፣ በክልልና በከተሞች መሀል ወጥ የሆነ
የቅንጅታዊ አሰራር ስርዓት አለመኖር፣ በየደረጃው ሊያሰራ የሚችል የክትትል ግማገማና ግብረመልስ
ደንብ፣ መመሪያና ማኑዋል እንዲሁም ቼክሊስት አለመኖር፣ በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም
የህብረተሰቡ ተሳትፎ ትኩረት አለመሰጠቱ ናቸው፡፡

4.3. የከተማ ፕላን መረጃ አያያዝ

ከከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ጋር ተያያዥ የሆኑ መረጃዎች አያያዝና ልውውጥ ስርዓትን መዘርጋት
በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም በከተማ ፕላኑ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በመለየት የማሻሻያ እርምጃዎችን
ለመውሰድ የሚቻለው መረጃዎች በሚፈለገው መልኩ ተደራጅተው በሚፈለገው ጊዜ ማግኘት ሲቻል
ነው፡፡ የከተማ ፕላን መረጃ አያያዝ ውስጥ መካተት ያለባቸው ጉዳዮች መሠረታዊ ካርታ፣ የተለያዩ የመሬት
አጠቃቀም ካርታዎች፣ ፕላኑን በጽሑፍ የሚያብራሩ ሰነዶች፣ የጥናት ሪፖርቶች ወዘተ በዲጂታልና
በአናሎግ ናቸው፡፡ ስለዚህ በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና ልውውጥ ዘዴን
በመዘርጋት መረጃዎችን በጥንቃቄ መያዝና ቀልጣፋ የሆነ ልውውጥ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሆኖም በተግባር እንደሚታየው ከፌደራል ጀምሮ እስከ ከተሞች ድረስ ያሉ የኘላን ዝግጅትና አፈፃፀም
ባለድርሻ አካላት የመረጃ አደረጃጀት፣አያያዝና ልውውጥ ሲታይ በተሟላ መልኩ የተዘረጋ ስርአት የለም፡፡
በከተሞች ደረጃ የአመራር ለውጥ ሲደረግ መረጃዎቹ አብረው ይጠፋሉ፡፡ በክልልም ሆነ በማዕከል ደረጃ
ለከተሞች የተዘጋጁ ፕላኖች ተደራጅተው አይገኙም፡፡ ከዚህም ባሻገር ሥርዓቱ በዳታቤዝ ማኔጅመንት
ዘዴ (Database Management System) የተቃኘና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ አይደለም፡፡ በመሆኑም
በየክልሉ የሚዘጋጁት የመሠረታዊ ካርታና ከተማ ፕላን መረጃ አያያዝንና አደረጃጀት ለአደጋ
ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ የሆነና ለአጠቃቀምም በቀላሉና በአጭር ጊዜ ተደራሽ ያልሆኑ ናቸው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 99


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

4.4. የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ

በከተማ ፕላን አፈጻጸም ወቅት ሌላው ትኩረት የሚሻ ጉዳይ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ነው፡፡ የአካባቢ
ተጽዕኖ ግምገማ የአንድ ፕሮጀክት ወይም የልማት ሀሳብ ንድፍ ሲዘጋጅ ቦታው ሲመረጥ፣ ሲገነባ እና
እንዲሁም በእንቅስቃሴ ላይ እያለ በአካባቢ (በአየር፣ በውሀ፣ በህይወት፣ ወዘተ) ላይ ሊያደርስ የሚችለውን
ተጽዕኖ/አፍራሽ ውጤት በቅድሚያ ለማወቅና ለመመዘን እንደ ሁኔታውም መፍትሄ ለማስቀመጥ
የሚያስችል ጥናት ነው፡፡ ስለዚህ ማናቸውም ፕሮጀክቶች /የቆሻሻ መድፊያ ቦታ፣ ትላልቅ ቄራዎች
(በዓመት ከ 100000 በላይ እርድ የሚያከናውኑ)፣ የኢንዱስትሪ ዞን፣ ካባ ወይም የግንባታ ድንጋይ ማምረቻ
ቦታዎች፣ በጥብቅ ቦታዎች የሚከናወኑ ማናቸውም የከተማ ልማት ስራዎች፣ በስፋት የሚገነቡ የጋራ
መኖሪያዎች ወዘተ…/ ሲታቀዱ በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትላሉ ተብለው የሚታሰቡ ከሆነ
ወይም በአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የተመደቡ ከሆነ
የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.5. የተቀናጀ የመሰረተ ልማት አቅርቦት

የመሰረተ ልማት አውታሮች የሚባሉት የሕብረተሰቡን ኑሮ ምቹ እንዲሆን የሚያሳልጡና የተያያዙ


በአብዛኛው የመንገድ፣ የቆሻሻና የጎርፍ ውሃ ማስወገጃ ፣ የኤሌትሪክ፣ የውሃና የቴሌ መስመሮችን
የሚያጠቃልሉ ናቸው፡፡ ከመንገድ ውጭ ያሉት የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች መስፈርቶችን ጠብቀው
የመንገድ ደህንነት፣ ግንባታና ጥገና የመሳሰሉትን በማያውኩበት ሁኔታ ተቀናጅተውና መንገዶችን
ተከትለው መዘርጋት ይኖርባቸዋል ፡፡ የመሰረተ ልማት አውታሮቹ ሲዘረጉ፤ ዕይታን እንዳያውኩና ገፅታንም
እንዳያበላሹ ጥንቃቄ ማድረግና ከማንኛውም ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮችም እንዲጠበቁ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ ከመንገድ በስተቀር ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮችን በከተማ ፕላን ላይ ማካታት
አስፈላጊ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የተለመደ አይደለም፡፡ መሰረተ ልማት አገልግሎቶችን በፕላን ላይ
ከማስፈር በተጨማሪ የአገልግሎቶቹን አቅራቢ ድርጅቶች በፕላኑ መሰረት የጋራ ዕቅድ በማውጣት
ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች መሀከል የመናበብ
ወይም ተቀናጅቶ የመስራት ችግር በሰፊው የሚታይ ነው፡፡ ተቀናጅተው ባለመስራታቸው ምክንያት አንዱ
ያለማውን ሌላው ማፍረሱ በየጊዜው የሚታይ ክስተት ሲሆን ይህም ለሀብት/ገንዘብ ብክነትም ምክንያት
ሆኗል፡፡ ችግሩን ለማቃለል የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፕላን ማዘጋጀትና የከተማ መስተዳድሮችም
/ማዘጋጃ ቤቶችም የመሰረተ ልማት አቅራቢዎችን ተቀናጅተው እንዲሰሩ ማስተባበር ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.6. የፌዴራል፣ ክልሎችና የከተሞች ሚና በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ

ከተሞች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 100


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የከተሞች ፕላን አዋጅ መሰረት የከተሞችን ፕላን ማዘጋጀት ስልጣን
የተሰጠው ለከተሞች ነው፡፡ ሆኖም ግን አብዛኞቹ የሀገሪቱ ከተሞች የራሳቸውን ፕላን በራሳቸው
ለማዘጋጀት የአቅም ውሱንነት ያለባቸው በመሆኑ ፕላኖቻቸው በክልል ደረጃ በተደራጁ የከተማ ፕላን
ዝግጅት ተቋማትና በነሱ አስተባባሪነት በአማካሪዎች እየተዘጋጁ ይገኛሉ፡፡ ፕላኖች ከተዘጋጁ በኋላ
የሚተገበሩት ከተሞች ላይ ስለሆነ ትግበራው ማለትም ዝርዝር ፕላኖች ማዘጋጀት፣ መሬት የማዘጋጀትና
የመስጠት ስራዎች የሚከናወኑት በከተሞች ሲሆን የባለሙያ እጥረት በሚኖርባቸው ከተሞች በከተማ
ልማት ቢሮዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡

ክልል ከተማ ልማት ቢሮዎች

በአገራችን የሚገኙ የክልል የከተማ ልማት ቢሮዎች በአገር አቀፍ ከተሰጣቸው ተግባርና ሀላፊነት አንጻር
በከተማ ፕላንና አፈጻጸም ዙሪያ የፕላን ዝግጅት ክትትልና ግምገማ፣ ድጋፍና ስልጠና እንዲሁም ጥናትና
ምርምር ስራዎችን እንደሚያከናውኑ በአዋጆቻቸው ስልጣን የተሰጣቸው ቢሆንም ከተሞቻቸው
ራሳቸውን ችለው የራሳቸውን ፕላን ማዘጋጀት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናቸው አራቱ ትላልቅ
ክልሎች የከተማ ፕላን ተቋማትን በማደራጀት የየክልሎቻቸውን የከተማ ፕላን የሚያዘጋጁ ሲሆን ልዩ
ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ደግሞ የየክልሎቹ ከተሞች ፕላኖች የሚዘጋጁት በክልሎቹ ከተማ ልማት ቢሮዎች
አማካኝነት ነው፡፡

yØÁ‰L kt¥ L¥T ÷NST‰K>N ¸n!St&R

በፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ውስጥ ከተዋቀሩት ቢሮዎች የከተማ ፐላን፣ ጽዳትና
ውበት ቢሮ አንዱ ሲሆን ቢሮው በአራት መምሪያዎች የተዋቀረ ነው፡፡ እነዚህም፡- ከተማ ፕላን ፅዳትና
ውበት ጥናትና ምርምር መምሪያ፣ ከተማ ፕላን ፅዳትና ውበት ሥልጠና መምሪያ፣ ከተማ ፕላን ፅዳትና
ውበት አፈጻጸም ክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ መምሪያ እና የከተሞች ጽዳትና ውበት ሕግና ስታንዳርድ
ክትትል ግብረ መልስ መምሪያ መምሪያ ናቸው፡፡ በእነዚህ መምሪያዎች የሚከናወኑ ተግባራትም
የመምሪያዎቹ ስሞች እንደሚጠቁሙት በዋነኛነት በሪጉላቶሪና የአቅም ግንባታ ድጋፍ አገልግሎቶች ላይ
ያተኮሩ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከሌሎች የፌደራል አካላት ጋር በመተባበር ብሔራዊ
የከተማ ልማት ዕቅድ የማዘጋጀት ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

የሴክተር መሥሪያ ቤቶች እና ሕብረተሰቡ

ys@KtR mS¶Ã b@èC X y?Brtsb# bkt¥ P§N ZGJT £dT WS_ y¯§ túTæ y¸ñ‰cW s!çN
túT ፏ cWM mr©ãCN bmS-T½ ykt¥WN q$LF C ግ éC bmlyT½ lkt¥W b¸zUjW ymÊT x-”qM

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 101


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

XÂ ymNgD SR+T P§N §Y xStÃyèÒcWN mS-T XNÄ!h#M q$LF C ግ éCN lmF¬T b¸ndû
SLèC PéjKèC §Y Ñ ያ êE DUF mS-T YçÂLÝÝ በተጨማሪም ፕላኑ በታሰበው መንገድ ተግባራዊ
እንዲሆን ድርሻቸውን ወስደው በከተማ መስተዳድሩ/ማዘጋጃ ቤቱ አስተባባሪነት ፕሮጀክቶችን በተቀናጀ
ሁኔታ መንደፍና ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.7. የመሬት አጠቃቀሞቹ የሚፈጥሩት ቅንጅታዊ መስተጋብር

ከላይ ለማየት እንደተሞከረው የመሬት አጠቃቀም ፕላን በሚዘጋጅበት ጊዜ በተለያዩ የመሬት አጠቃቀም
አገልግሎቶች መካከል መጣጣም መኖሩ መረጋገጥ ብቻ ሳይሆን አገልግሎቶቹ ከብዛት አንጻር በቂ
መሆናቸው፣ እንዲሁም የሚይዙት የቦታ ስፋት በቂ መሆኑ፣ የሚቀመጡበት አካባቢ ተዳፋታማነት አመቺ
መሆኑ፣ ቦታው ተገቢው ርቀት ላይ መሆኑ፣ ስርጭታቸው ፍትሀዊ መሆኑ፣ አስፈላጊው የመሰረተ ልማት
አውታር ለምሳሌ መዳረሻ መንገድ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡

የከተማ ፕላን በአንድ ከተማ ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉ ማንኛውንም የልማት ዓይነት የቤት ልማት፣ የንግድ፣
የማሕበራዊ አገልግሎቶች፣ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የከተማ ግብርና፣ ወዘተ…ማስተናገድ የሚችሉ
የመሬት አጠቃቀሞች የሚያካትት ነው፡፡ ፕላኑ ከተዘጋጀ በኋላ መሬቱን ለልማት ዝግጁ በማድረግ በፕላኑ
መሰረት ቦታ በመስጠት የልማት ስራዎች ይከናወናሉ፡፡ በመሆኑም በልማት ስራዎቹ መሀከል መጣረስ
ወይም አለመጣጣም እንዳይከሰት ለልማት ስራዎች ቦታ በሚሰጥበት ጊዜ በፕላኑ መሰረት መሆኑን
ማረጋገጥ ከግንባታ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የሀብት ብክነቶችን ለማስቀረት ያስችላል፡፡

የሚዘጋጀው ፕላን የማህበረ ኢኮኖሚያዊ፣ ፊዚካላዊ፣ ስፓሻል ወዘተ ጥናቶችን መሠረት አድርጎ ከተማው
በጤናማ መንገድ እንዲመራ የሚያደርግ የፖሊሲ ወይም የሕግ ሰነድ በመሆኑ በፕላን ሕግ ላይ
በተመለከተው መሰረት በከተማው ም/ቤት እንዲፀድቅ ይደረጋል፡፡ በመሆኑም ፕላንን እንደ ሕጋዊ ሰነድ
መቁጠር ግዴታ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በፕላን ላይ የተመለከቱ የመሬት አጠቃቀሞችንና የመንገድ መርበብ
በሚመለከት የፕላን ጥሰት ቢፈጠር ጥሰቱን በፈፀሙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

በአንድ ከተማ የሚፈለገው እድገት እንዲመጣ ከሚያስችሉት ሁኔታዎች መሀከል አንዱና ዋንኛው ከላይ
የተጠቀሱት የልማት ስራዎች እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉና ተቀናጅተው በመጣጣም ሊሄዱ ሲችሉ ሲሆን
ነገር ግን የአንዱ ልማት ሌላው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ከሆን የሚፈለገው አጠቃላይ ውጤት ላይ
መድረስ አይቻልም፡፡ አንድን ከተማ ባሕሪ እንደሰው አካል ማየት ይቻላል፡፡ ሰው ጤናማ ሆኖ እለታዊ
እንቅስቃሴውን ማካሄድ የሚችለው እያንዳንዱ የሰውነቱ ክፍል ሌላውን ሳያውክ በመደጋገፍ የራሱን ስራ
ጤነኛ ሆኖ ሲያከናውን ነው፡፡ ከሰውነታችን ክፍል አንዱ ቢታወክ የሚጠበቅበትን ተግባራት ማከናወን
የሚሳነው ሲሆን ይህም አጠቃላይ ሰውዬ/ሴትየዋ ስራ ላይ እንዲሁም ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 102


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በተመሳሳይ ከተሞችም በውስጣቸው በሚያስተናግዷቸው የተለያዩ የልማት ሥራዎች መሀከል ጤናማ


ቅንጅታዊ መስተጋብር ከተፈጠረ ከተሞች በሚፈለገው ደረጃ ማደግ ይችላሉ፡፡

5. የስትራቴጂው ራዕይ፣ ዓላማና መርሆዎች

5.1. የስትራቴጂው ራዕይ


“ሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች ዕድገታቸውን በፕላን የሚመሩ፣ ለኑሮ እና ለሥራ ምቹና
ተወዳዳሪ ሆነው ማየት!”

5.2. የስትራቴጂው ዓላማዎች


 የከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ በሕግ ማዕቀፍና በአሰራር ስታንዳርድ እንዲመራ
ማድረግ፣
 በፕላን ዝግጅትና አፈፃፀም የተሰማሩ አካላትን ሁለንተናዊ አቅም መገንባትና ቅንጅታዊ
አሠራርን ማጠናከር፣
 ወጪ ቆጣቢ ቀልጣፋና ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት መገንባት ናቸው፡፡

5.3. የስትራቴጂው መርሆዎች


 የከተሞች ፕላን ከተሞች ዕድገታቸውን የሚመሩበት ሕግ ነው፤
 የከተሞች ፕላን ዝግጅት እና አፈፃፀም አሳታፊ፣ ተጠያቂነትና ግልፅነትን የተላበሰ
ይሆናል፤
 የከተሞች ፕላን የሕብረተሰቡና የልማት አጋሮችን ፍላጐት ያማከለ ይሆናል፤
 የከተሞች ፕላን ዝግጅት የመንግስትና የግሉን ዘርፍ ሽርክና ያማከለ ይሆናል፤
 የከተሞች ፕላን ዝግጅትና አፈፃፀም ስትራቴጂያዊ አካሄድን ይከተላል፤
 የከተሞች ፕላን ዝግጅት የተሰባሰበ /Compact settlement/ አሰፋፈርን መሰረት
ያደርጋል፤
 የከተሞች ፕላን የፊዚካል፣ ስፓሻል እና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በሚፈታ
መልኩ ይዘጋጃል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 103


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ክፍል ሁለት - የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ስትራቴጂ

ይህ ክፍል በመሰረታዊ ካርታ እና ከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ በተደረገው የነባራዊ ሁኔታዎች
ትንተና ላይ በመመስረት የተዘጋጁ ትኩረት የሚሹ የፖሊሲ ጉዳዮች እና ስልቶችን የሚያቀርብ ሲሆን
በዚህ ሰነድ የፖሊሲ ጉዳዮችና ስልቶች ማለት ምን ማለት እንደሆኑ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ትኩረት የሚሹ የፖሊሲ/ የስትራቴጂ ጉዳዮች፡- በነባራዊ ሁኔታ ትንተና ከከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን
ዝግጅትና አፈጻጸም ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ ችግሮች የተለዩ ሲሆን ችግሮቹ ከመሰረታዊ ካርታ
ዝግጅት፣ ከከተማ ፕላን ዝግጅት፣ ከከተማ ፕላን ትግበራ / አፈጻጸም፣ ከከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም
ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ከአፈጻጸም አቅም ጋር የተያያዙ በመሆናቸው በዚሁ መሰረት እንደገና
በመከፋፈል ስድስት ትኩረት የሚሹ የፖሊሲና ስትራቴጂ ጉዳዮችን ለመለየት የተሞከረ ሲሆን እነዚህም
የፖሊሲና ስትራቴጂ ጉዳዮች እንዲሁም በስራቻው ያካተቷቸው ቁልፍ ችግሮች በዚህ ክፍል ቀርበዋል፡፡

ስልቶች፡- ስልቶች ከላይ የተቀመጡትን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ወይም ለማሳካት የምንከተላቸው
መንገዶች ሲሆኑ ለእያንዳንዱ ግብ የተለያዩ ስልቶች ተቀምጠዋል፡፡ ስልቶቹ የመነጩት በየስትራቴጂ
አቅጣጫዎቹ ስር የተቀመጡትን ቁልፍ ችግሮች እና የችግሮቹ ምክንያቶች ላይ በመመስረት ነው፡፡
የመሰረታዊ ካርታና ከተማ ፕላን ተያያዥ እንደመሆናቸው መጠን ለከተማ ፕላን የተቀመጡት
ከአደረጃጀት ጋር ተያያዥ የሆኑ ስልቶች መሰረታዊ ካርታንም የሚመለከቱ ናቸው፡፡

1. ትኩረት የሚሹ የፖሊሲ/ ስትራቴጂ ጉዳዮች

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በነባራዊ ሁኔታ ትንተና ላይ በመመስረት ከከተማ መሬት አጠቃቀም
ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ ችግሮችን በስድስት ትኩረት የሚሹ የፖሊሲ/
ስትራቴጂ ጉዳዮች ለመለየት የተሞከረ ሲሆን እነዚህም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

የከተሞች የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅትን በተመለከተ

የመጀመሪያው የፖሊሲ ወይም የስትራቴጂ ጉዳይ የከተሞች የመሰረታዊ ካርታ ዝግጅትን የሚመለከት
ሲሆን ይህ የስትራቴጂ ጉዳይ ጠቅለል ባለ መልኩ ከሚያካትታቸው ችግሮች ውስጥ የመሠረታዊ ካርታዎች
ሽፋን ዝቅተኛ መሆን፣ የመሠረታዊ ካርታዎች ጥራት ዝቅተኛ መሆን፣ እየተሰራበት ያለው የመሬት ላይ
ቅየሳ ዘዴ ውድ፣ አድካሚ፣ ብዙ የሰው ኃይል እና ረጅም ጊዜ የሚወስድ መሆኑ፣ የሚዘጋጁ መሰረታዊ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 104


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ካርታዎች ወጥነት የሌላቸውና ከብሄራዊ የጂኦዴቲክ መረብ ጋር የማይናበቡ፣ ያሉትም የቅየሳ መቆጣጠርያ
ነጥቦች በቁጥር አናሳ መሆንና በሚፈለገው ጥግግት አለመገኘት እንዲሁም በቀላሉ ለመነቀል በሚችሉበት
ሁኔታ ውስጥ መገኘታቸው እና ለመረጃ ውህደትና ቅንጅት ሥራ አስቸጋሪ መሆናቸው ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችን በሁለት በመክፈል ማየት የሚቻል ሲሆን ከሽፋን
አንጻር ለታዩት ችግሮች መንስኤዎች ዋና ዋናዎቹ አደረጃጃት በሚፈለገው ደረጃ ያልተማከለ አለመሆኑ፣
በቂ ባለሙያና የሙያ ስብጥር እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አለመኖር፣ እየተሰራበት ያለው ዘዴ ረጅም
ጊዜ የሚወስድ መሆኑ፣ የግሉን ዘርፍ አቅምና ተሳትፎ አለመጠናከር ናቸው፡፡ ከጥራት አንጻር ለታዩት
ችግሮች ዋና ዋናዎቹ መንስኤዎች ደግሞ ለቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት የቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች
አቅርቦት ተጠቃሚነት ደካማ መሆን፣ ለመሠረታዊ ካርታዎች ዝግጅት ግልጽ የሕግ ማዕቀፍና የአሰራር
ስታንዳርድ ሰነድ አለመኖር፣ ለመሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ክትትልና የግምገማ ስርዓት አለመዘርጋት፣
የባለሙያ ክህሎት ዝቅተኛ መሆን፣ ለከተሞች ፕላን ዝግጅት የሚያግዝ የቅየሳ መነሻ መቆጣጠሪያ ነጥቦች
አለመኖር ናቸው፡፡ ነጥቦቹ በደህንነት ስጋት ውስጥ የመገኘታቸው መንስኤ የአካባቢው ሕብረተሰብ በቂ
ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችል መረጃ ስለማይሰጠው ነው፡፡

የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት አሰራርን በተመለከተ

ሁለተኛው የፖሊሲ ወይም የስትራቴጂ ጉዳይ የከተማ ፕላን ዝግጅት አስራርን የሚመለከት ሲሆን በዚህ
የስትራቴጂ ጉዳይ ከሚያካትታቸው ችግሮች መሀከል ዋና ዋናዎቹ የከተሞች ፕላን ሽፋን ዝቅተኛ መሆን፣
የከተሞች ፕላን ጥራት ዝቅተኛ መሆን፣ የከተሞች ፕላን ዓይነት፣ አዘገጃጀት፣ ሂደት፣ ይዘትና ለዝግጅት
የሚወስዱት ጊዜ ላይ ወጥነት አለመኖር፣ ከከተማ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ይዘት /Major Land Use
Functions/ በስታንዳርድ መሰረት ያለመቀመጥ ችግሮች፣ አልፎ አልፎ ጎን ለጎን የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት
ፕላኖች የማይናበቡ መሆናቸው፣ከመኖሪያ ቤት ጋር ተቀይጠው አገልግሎት እንዲሰጡ በተፈቀዱ የንግድና
ማምረቻ አገልግሎቶች ሰበብ አልፎ አልፎ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የድምጽ፣ የሽታ እና ከማምረቻ
ተቋማቱ በሚወጡ ብናኞች ብክለት ችግር መፈጠር፣ በተጎራባች ክልሎችና ከተሞች መካከል ያልተቀናጀና
በተናጠል የሚከናወን የከተማ ፕላን አሰራር በከተሞች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ፣ የከተማ አስተዳደር
ወሰን አከላለል መስፈርት እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች ከተሞች ድንበር ወሰን
የማካለል ችግር አፈታት ስርዓት አለመኖር ናቸው፡፡

ከሽፋን አንጻር ለተለዩት ችግሮች መንስኤዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ አደረጃጃትን በሚፈለገው ደረጃ
ያልተማከለ አለመሆኑ ያሉትም የተጠናከሩ አለመሆን፣ በቂ ባለሙያና የሙያ ስብጥር እንዲሁም

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 105


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አለመኖር፣ ለፕላን ዝግጅት የሚፈጀውን ረዥም ጊዜ ማሳጠርና ጊዜን በአግባቡ
አለመጠቀም፣ የግሉ ዘርፍ አቅምና ተሳትፎ አለመጠናከር ናቸው፡፡

ከጥራት አንጻር ለተለዩት ችግሮች መንስኤዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የፕላን ዝግጅት ክትትል፣ የግምገማና
የግብረ መልስ ስርዓት አለመዘርጋት፣ እየተሰራባቸው የሚገኙትን አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ስታንዳርድና
ማንዋሎች የተሟሉ አለመሆን፣ አዳዲስ ከተሞችና የገጠር ቀበሌ ማዕከላት የፕላን አዘገጃጀት እና
አፈፃፀም በሚመለከት መመሪያ አለመኖር፣ የ ã ርባን ዲዛይን (Urban Design) መመሪያ አለመኖር፣
የባለሙያ ክህሎት ዝቅተኛ መሆን፣ ለከተማ ፕላን የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ
የባለሙያ ፍልሰት በፕላን ዝግጅት ተቋማት መኖሩ፣ የከተማ ፕላን ዝግጅትን በጥናትና ምርምር
አለመደገፍ፣ ጥራቱና አስተማማኝነቱ በግልጽ ባልተረጋገጠ መሰረታዊ ካርታ ላይ የፕላን ዝግጅት
ማከናወን፣ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች በይዘታቸው ስፓሻል ፕላን ላይ ያተኮሩ መሆናቸውና ለማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በቂ ትኩረትና መፍትሄ የማይሰጡ እንዲሁም በከተማ ልማት ፖሊሲው መሰረት
ከከተሞች /የማዘጋጃ ቤቶች የልማት ዕቅድ ጋር የማይያያዙ መሆናቸው፣ ብሄራዊ የከተሞች እድገት ንድፍ/
scheme /እና የክልል ከተሞች እድገት ፕላን ሳይዘጋጅላቸው የከተሞች ፕላን መዘጋጀቱ የሚሉት
ይገኙበታል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የፕላን ዓይነቶችን፣ ሂደት፣ ይዘትና የሚወስዱትን ጊዜ አስመልክቶ ወጥ የሆነ አሰራር
ለመዘርጋት የተደረገ ጥረት አነስተኛ በመሆኑ በሀገሪቱ ውስጥ ወጥ የሆነ የፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጸም
ስርዓት አለመኖር ናቸው፡፡

የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን አፈጻጸም ሥርዓትን በተመለከተ

በሶስተኛው የፖሊሲ/ የስትራቴጂ ጉዳይ ስር ከተካተቱት ችግሮች መሀል ዋና ዋናዎቹ በትግበራ ወቅት
የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶች መከሰት፣ ፕላኖችን ወደ መሬት ለማውረድ አስቸጋሪ መሆን፣ ፕላኖች
በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት መተግበር አለመቻላቸው፣ በመሠረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶችና በማዘጋጃ
ቤት መሃከል ቅንጅታዊ አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት በፕላን ትግበራ ወቅት የሚከሰት የሀብት ብክነት፣
ለተለያዩ አገልግሎት የሚያዙ ቦታዎችን ፕላን አዘጋጁ ለሚመለከታቸው አካላት አለማስተላለፍ
/አለመስጠት የሚመለከታቸው አካላትም ቦታውን ተከታትለው አለማልማት ናቸው፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች መንስኤዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የፕላን ትግበራ ራሱን የቻለ ቋሚ
አደረጃጀት አለመኖር፣ የተጠያቂነት ስርዓት አለመኖር፣ የሚዘጋጁ ፕላኖች ጥራት ዝቅተኛነት ፣ የፕላን
ትግበራ ማስፈጸሚያ ስልት አለመዘጋጀቱ፣ የከተማ ፕላን አፈጻጸም መከታተያ ማኑዋል አለመኖር፣

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 106


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በመሠረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶችና በማዘጋጃ ቤት መሃከል ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር፣ የተነሳሽነት
አለመኖርና ቸልተኝነት እና የሰለጠነ የሰው ሀይልና የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች እጥረት ናቸው፡፡

መዋቅራዊ ፕላንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚዘጋጁ ዝርዝር ፕላኖች ዝግጅት ሥርዓትን በተመለከተ

አራተኛው የፖሊሲ/ የስትራቴጂ ጉዳይ መዋቅራዊ ፕላን ማስተግበሪያ ዝርዝር ፕላኖች ዝግጅትን
በተመለተ ሲሆን ይህ ጉዳይ ከሚያካትታቸው ችግሮች መሀከል ዋናዎቹ ከተሞች ዝርዝር የአካባቢ ልማት
ፕላን ሳያዘጋጁ መዋቅራዊ ፕላኑን መተግበራቸው እንዲሁም አልፎ አልፎ የአካባቢ ልማት ፕላን
የሚዘጋጅበት አጋጣሚ ቢኖርም ፕላኑ በቀጥታ ሲዘጋጅ የፊዚካላዊና ማሕበራዊ መሰረተ ልማት አቅርቦትን
ግምት ውስጥ ያለማስገባቱ ሲሆኑ በዚህም ምክንያት በከተሞች ላይ የአገልግሎቶች በተገቢው ቦታ ላይ
ተገቢው መስፈርቶችን አሟልቶ ያለማሰቀመጥ፣ የቦታ ብክነት፣ በመኖሪያ ቤት አካባቢ አስፈላጊ ለሆኑ
አገልግሎቶችን ቦታ አለመያዝ የመሳሰሉት ችግሮች የሚከሰቱ ሲሆን የችግሮቹ መንስኤዎችም የፕላን
ትግበራ ራሱን የቻለ ቋሚ አደረጃጀት የሌለው መሆኑ፣ የፕላን ትግበራ ማስፈጸሚያ ስልት አለመዘጋጀቱ /
ዝርዝር የሽንሻኖ ፕላን፣ ለትላልቅ ከተሞች የከተማ ዲዛይን ፕላን፣ የፌዚንግ ፕላን፣ የሽንሻኖ ስታንዳርድ፣
የሽንሻኖ ማኑዋል፣ የድርጊት መርሀ ግብር/ እና የማስፈጸም አቅም ደካማ መሆን ናቸው፡፡

የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ሥርዓትን በተመለከተ፡-

አምስተኛው የፖሊሲ ወይም የስትራቴጂ ጉዳይ ከሚያካትታቸው ችግሮች መሀከል ዋና ዋናዎቹ ጥራትን
ከማስጠበቅ አንጻር በመሰረታዊ ካርታና ከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት የሚደረጉ የክትትልና ግምገማ
ስራዎች ደካማ መሆን፣ ክትትልና ግምገማ ስራዎች ሽፋን በጣም ዝቅተኛ መሆን፣ የፕላን ትግበራ /
አፈጻጸም ላይ የሚደረግ የክትትል፣ የግምገማና የግብረ መልስ ስርዓቱ በውጤት ላይ ያልተመሰረተ እና
ተጠያቂነትን በሚያሰፍን መልኩ ያልተቃኘ መሆኑ፣ የከተማ ፕላን ጥሰት ላይ የሚወሰድ የማስተካከያ
እርምጃ የሌለ መሆኑ፣ በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆን ወይም
አለመኖር ናቸው፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት ችግሮች ምክንያቶች መሀከል ዋና ዋናዎቹ የፕላን አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ቋሚ
አደረጃጀት አለመኖር፣ በፌደራል፣ በክልልና በከተሞች መሀል ወጥ/ተናባቢ የሆነ የቅንጅታዊ አሰራር ስርዓት
አለመኖር፣ በየደረጃው ሊያሰራ የሚችል የክትትል ግማገማና ግብረ-መልስ ደንብ፣ መመሪያ፣ ማኑዋልና
ቼክሊስት አለመኖር እና በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ለህብረተሰቡ ተሳትፎ ትኩረት አለመሰጠቱ
ናቸው፡፡

የማስፈጸም ብቃትን በተመለከተ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 107


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ስድስተኛው የፖሊሲ ወይም የስትራቴጂ ጉዳይ የማስፈጸም ብቃትን የሚመለከት ሲሆን በዚህ የስትራቴጂ
ጉዳይ ስር ከተካተቱት ችግሮች መሀል በቂ የሰው ኃይል ያለመኖር፣ አመቺ ተቋማዊ አደረጃጀት እና
ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር፣ የተሟላ የቴክኖሎጂ አቅርቦት እና አጠቃቀም ያለመኖር፣ የፋይናንስ አቅም
ውስንነትና የአጠቃቀም ችግር፣ ደካማ የመረጃ አያያዝ፣ አደረጃጀት እና ልውውጥ ሥርዓት መኖር፣
የአመራሩና ባለሙያው ሥነ-ምግባር ችግር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

2. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ስትራቴጂ አቅጣጫዎችና ስልቶች


1) የከተሞች የቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ሥርዓትን ማሻሻል

S ሠ[ታ© "` K›”É Ÿ}T K}KÁ¿ Ów¯„‹ K=ው M ¾T>‹M ¾ አካላዊ Í=*Ó^òÁ© S[Í U”ß uSJ”
Ÿõ}— ›e}ªï ኦ ›K ው:: u}Kà የከተማ ፕላን ከመዘጋጀቱ uòƒ አስፈላጊውን የቅየሳ ሥራ በማከናወን
የመሠረታዊ ካርታ T²Ò˃ upÉS G<’@ታ ¾T>Ÿ“¨” }Óv` uSJ’< KT>²ÒË ው ¾ ከተማ ፕላን ª’—
Ów¯ƒ uSJ” ÁÑKÓLM:: የአብዛኞቹ ከተሞች መሰረታዊ ካርታ ¾Ø^ƒ Å[Í ´p}— ከመሆኑም ባሻገር
¨p ታ© ማሻሻያ/ክለሳ ¾Tß“¨”L†ው uSJ“†ው ¾T>ò<ƒ ¾S[Í Ø^ƒ እና ጥልቀት ¨<e”’ƒ ያለበት
መሆኑ በተደረገው የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ተረጋግጧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በብሄራዊ የከተሞች ፕላን
ኢንስቲትዩት ሲዘጋጁ የቆዩ መሠረታዊ ካርታዎች እና በአሁኑ ሰዓት በአንዳንድ የክልል ፕላን ተቋማት
የመሬት ላይ ቅየሳ በማድረግ እየተዘጋጁ ያሉት መሠረታዊ ካርታዎች የጂኦግራፊያዊ መረጃ አሰባሰብና
አተናተን ዘዴው ውድ፣ አድካሚ፣ ብዙ የሰው ኃ ይል እና ረጅም ጊዜ የሚወስድ ከመሆኑም በላይ ወጥነት
የሌለውና ከብሄራዊ የጂኦዴቲክ መረብ ጋር የማይናበብ፣ ለመረጃ ውህደትና ቅንጅት ሥራ አስቸጋሪ
መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህንን መሠረት አድርገው የተዘጋጁ የከተማ ፕላኖችን ይዘው ከተሞቹ ወደ
ትግበራ በሚገቡበት ወቅት በፕላኖቹ አፈጻጸም ላይ ትልቅ ተግዳሮት የገጠማቸው ሲሆን ይህም አንድ
የአሰራር ማነቆ ሆኗል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመሰረታዊ ካርታ አቅርቦት/ሽፋን ከፍላጎት አንጻር ሲታይ
አነስተኛ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት የከተሞች የቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት
ሥርዓትን ማሻሻል እንደ ስትራቴጂ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ይህ የስትራቴጂ አቅጣጫ በውስጡ ሁለት ዋና
ዋና ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን እነዚህን ጉዳዮች ለማሳካት የሚያስችሉ ስልቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1.1. የከተሞች የቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ሽፋንን ማሻሻል

በነባራዊ ሁኔታ ትንተና ለማየት እንደተቻለው የአገሪቱ የከተማ ፕላን አቅርቦት ካለው ፍላጎት አንጻር
ሲታይ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በመሆኑም የከተሞች የቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ሽፋንን ማሻሻል
አስፈላጊ ሲሆን ይህን ግብ ተግባራዊ ለማድረግ ከተቀመጡ ስልቶች መሀከል ዋና ዋናዎቹ የከተማ ፕላን
ዝግጅት አደረጃጀትን ማጠናከርና አሁን ካለበት በተሻለ መልኩ ያልተማከለ ማድረግ፣ በቂ ባለሙያዎች
ማሰማራት፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማጠናከር፣ እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ረዥም

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 108


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ጊዜ የሚወስደውን አሰራር ማሳጠርና ጊዜን ባግባቡ መጠቀም ናቸው፡፡ ስልቶቹ ከፕላን ዝግጅት ሽፋን
ማሳደጊያ ስልቶች ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው የስልቶቹ ዝርዝር በከፕላን ዝግጅት ሽፋን ማሳደጊያ
ስልቶች ስር በዝርዝር ቀርቧል፡፡

1.2. የከተሞች የቅየሳና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ጥራትን ማሻሻል

ከመሰረታዊ ካርታ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚነሱት ችግሮች አንዱ የጥራት ችግር ሲሆን ይህም በሚዘጋጁ
ፕላኖች ትግበራ ላይ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከጥራት ጋር ከተያያዙት ችግሮቹ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የቅየሳና
የልኬት ዝንፈት፣ የሚዘጋጁ መሰረታዊ ካርታዎች ወጥነት የሌላቸውና ከብሄራዊ የጂኦዴቲክ መረብ ጋር
የማይናበቡ በመሆናቸው ለመረጃ ውህደትና ቅንጅት ሥራ አስቸጋሪ መሆናቸው ናቸው፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ የመሠረታዊ ካርታዎቹ የመረጃ ይዘት ዓይነትና ጥልቀት በበቂ ሁኔታና በትክክል አለማስቀመጡ
በሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች ጥራት ላይ የራሳቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ግብ
በማሳካት ችግሮቹን መፍታት ይቻል ዘንድ የሚከተሉት ስልቶች ተቀምጠዋል፡፡

ስልት 1.2.1. ለከተሞች መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት የሚያግዝ የቅየሳ መነሻ መቆጣጠሪያ
ነጥቦች ምስረታና ጥበቃ

የከተማ መሠረታዊ ካርታ ዝግጅትና አጠቃቀም በተቀናጀ መልኩ ተናባቢ ለማድረግ ከዋና ዋና ግብዓቶች
አንዱ ለከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም አግልግሎት የሚውል አገራዊ የቅየሳ መቆጣጠሪያ መረብ መነሻ
አድርጎ የሚከናወን የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥብ የማስፋፊያና ምስረታ ሥራ ነው፡፡ ይህን ጠቃሚ የምድር
መረጃ ልኬት መውሰድ፣ ስሌት መስራት፣ መረጃ ማቀናበር እና በአግባቡ አደራጅቶ መያዝ በበቂ ጥናት
መደገፍ አለበት፡፡ የቅየሳ መሳሪያዎችና መረጃ ማቀናበሪያ ሶፍትዌር አቅርቦትን በማሳደግ ¾ አ ÓÉSƒ“
¾ ከ õ የቅየሳ መነሻ መቆጣጠሪያ ነጥቦች ምስረታና ማስፋፊያ ሥራን በከተሞች ማካሄድ ግድ ስለሚሆን
ይህ ስልት ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የከተማ ፕላን ለሚዘጋጅላቸው ሁሉም የአገሪቱ ከተሞች የመሰረታዊ
ካርታ ዝግጅቱን ለማፋጠን የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦችን የጥግግት መጠናቸውን መጨመር ወሳኝ በመሆኑ
በሁሉም ደረጃ ላሉ ከተሞች አሁን ካሉት የቅየሳ መነሻ መቆጣጠሪያ ነጥቦች በተጨማሪ አዳዲስ
መመስረት፣ ¾ ቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች ምልክቶች ደ I”’ƒ ን Øun ለማጠናከር ደ”w ተዘጋጅቶ
እንዲፈጸም በማድረግ ለተመሰረቱት መቆጣጠሪያ ነጥቦች የደህንነት ጥበቃ ሥርዓት እንዲዘረጋ ይደረጋል፡፡

ስልት 1.2.2. የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ልማትና አቅርቦትን ማሻሻል

እስከ አሁን ድረስ ስንከተለው የነበረውን የቅየሳ አፈጻጻምና የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት አሰራር ሥር ነቀል
በሆነ መልኩ ለመቀየርና እምርታዊ ውጤት ለማስመዝገብ ዘመኑ ያፈራቸውን የቅየሳ መሳሪያዎች እና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 109


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ለመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ወሳኝ የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች አቅርቦትን አቅም በፈቀደ መልኩ ማሻሻል
የስትራቴጂው ማስፈጸሚያ አንዱ መንገድ ሆኖ ተቀይሷል፡፡

በመሆኑም የህዝብ ቁጥራቸው ከ 20,000 በታች ለሆኑ አነስተኛ ከተሞች የሳታላይት ምስል የመሬት ላይ
የቅየሳ ዘዴ እና ከ 20,000 በላይ የህዝብ ቁጥር ላላቸው ከተሞች የአየር ፎቶግራፍን መሠረት ያደረገ
መሠረታዊ ካርታ እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡ በዚሁ አቅጣጫ ለመሠረታዊ ካርታ ዝግጅትና አጠቃቀም አጋዥ
የሚሆን የሳታላይት ምስልና የአየር ፎቶግራፍ ግዥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በእነዚሁ
ከተሞች ውስጥ አዲስ ለሚመሰረቱ የአግድመትና የከፍታ የቅየሳ መቆጣጠርያ ነጥቦች የማስፋፋት ሥራ
እና የሳታላይት ምስል መረጃዎችን በምድር ላይ በትክክል መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚያገለግል ዘመናዊ
GNNS Receivers GPS ግዥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከተሞችን አቅም ባገናዘበ መልኩ
የመሬት ላይ ቅየሳ በማከናወን መሰረታዊ ካርታ እንዲዘጋጅ የቶታል ስቴሽን የቅየሳ መሳሪያ ግዥ ተፈጽሞ
ከተሞች እንዲደገፉ ይደረጋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለሳተላይት ምስል እና የአየር ፎቶግራፍ ትርጎማና
መሠረታዊ ካርታ ዝግጅትና አጠቃቀም አስፈላጊ የሆኑ የሀርድዌርና ሶፍትዌር ግዥ በመፈጸም በየደረጃው
በመስኩ ለተሰማሩ ተቋማት ድጋፍ ማድረግና አቅማቸውን ለማጠናከር ጥረት ይደረጋል፡፡

ይህን ስልት ለማስተግበር ለአነስተኛ ከተሞች የሳተላይት ምስል፣ ለትላለቅ ከተሞች የአየር ፎቶግራፍ፣
ይህን ሥራ ለሚያከናውኑ የክልልና ፌዴራል ተቋማት የትርጉም ሀርድዌርና ሶፍትዌር መሳሪያዎች ግዥ
በመፈጸም ድጋፍ ይደረጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዲጅታል መሠረታዊ ካርታ ዝግጅትና አጠቃቀምን
ለማጠናከር ከክልልና ፌዴራል ተቋማት ለተውጣጡ በመስኩ ለተሰማሩ ባለሙያዎች በቴክኖሎጂዎቹና
መሳሪያዎቹ አጠቃቀምና አያያዝ ላይ የስልጠና ድጋፍ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ለከተማ ፕላን ዝግጅት
አስፈላጊ በሆኑ የ GIS ሶፍትዌሮች ላይ ለክልል የከተማ ፕላን ባለሙያዎች /Architect or Urban
Planners, Surveyors, Draft Persons/ ስልጠና ይሰጣል፡፡

ስልት 1.2.3. ግልጽ የሕግ ማዕቀፍና የአሰራር ስታንዳርድ ሰነድ ዝግጅት

በተለያዩ ከተሞች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዘጋጁት የመሠረታዊ ካርታዎች እንዴትና በማን


እንደሚዘጋጁ ስልጣንና ኃላፊነትን በግልፅ የሚያስቀምጥ የተሟላ የህግ ማእቀፍ እንደዚሁም ወጥ የሆነ
አገር አቀፍ የቅየሳ አፈጻጸምና መሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ስታንዳርድ ›K ማለት አይቻልም፡፡ በመሆኑም
በተለያየ ወቅት በተለያዩ ተቋማት የተሰሩት የመሠረታዊ ካርታዎችም ሆነ የከተማ ፕላኖች ጥራትና
ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሁም የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት ተዘርግቶላቸው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ
ባለመደረጉ የደረጃ መጓደል እና የመረጃ ተና vu=’ƒ ችግሮች ሲከሰቱ ቆይቷል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 110


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በመሆኑም የመሠረታዊ ካርታና የከተማ ፕላኖች አዘገጃጀትና አጠቃቀም፣ የቅየሳ መነሻ መቆጣጠሪያና
የከተሞች ፕላን ወሰን ምልክቶች ደህንነት ጥበቃ እንዲሁም የቅየሳ አፈፃፀምና የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት
ደንቦችና e ታ”Ç`Ê‹ T²Ò˃ ና በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ u መስኩ ¾T>ታ¿ƒ” ‹Óa‹ ስርነቀል በሆነ
መልኩ ለመቅረፍ ያስችላል:: ስለሆነም ይህን ስልት ለማስተግበር የቅየሳ አፈጻጸምና የመሠረታዊ ካርታ
ዝግጅትና አ ÖnkU በግልጽ የህግ ማዕቀፍ እንዲመራ የሚያስችል ደንብ ተዘጋጅቶ እንዲጸድቅ በማድረግ
ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቅየሳ አፈጻጸምና የመሠረታዊ ካርታ አዘገጃጀት ስታንዳርድ ሰነድ፣
የከተማ አስተዳደር ወሰን አከላለል መስፈርት እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች
ከተሞች ድንበር/ ወሰን ማካለያ መመሪያ ተዘጋጅቶ በሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል፡፡

2) የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት አሰራርን ማሻሻል

በነባራዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ እንደተጠቆመው በአጠቃላይ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች ፕላን የተዘጋጀላቸው 62
በመቶ አካባቢ ብቻ ሲሆኑ ይህም ለሁሉም ከተሞች የፕላን ፍላጎት ምላሽ ከመስጠት አንጻር ሽፋኑ
ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፕላን ከተዘጋጀላቸው ከተሞች ውስጥ የፕላን ጊዜያቸው
ተጠናቆ ክለሳ የሚፈልጉ በርካታ ከተሞች ከመኖራቸውም ባሻገር በየጊዜው የሚያቆጠቁጡ ከተሞች
መኖር እንዲሁም በርካታ የገጠር ቀበሌ ማእከላት በፕላን እንዲመሩ ፍላጎት መኖሩ ሽፋኑን ዝቅ እንዲል
ያደረገዋል፡፡ በሌላ በኩል የከተማ ፕላን የጥናት ሰነድ ጥራት ሲገመገም ሰነዱ ለጥናት አስፈላጊ የሆኑ
የተሟሉ፣ የተረጋገጡና አስተማማኝ መረጃዎችን የማያካትትና በተለይም የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች
በይዘታቸው ስፓሻል ፕላን ላይ ያተኮሩ መሆናቸውና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በቂ ትኩረትና
መፍትሄ የማይሰጡ እንዲሁም በከተማ ልማት ፖሊሲው መሰረት የከተሞችን /የማዘጋጃ ቤት የልማት
ዕቅድን የማያካትቱ መሆናቸው ከከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት ጋር ተያይዘው የሚገለጹ
ችግሮች ናቸው ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ የውይይት መድረኮች የተገኙ ገንቢ ሀሳቦችን በሰነዱ ውስጥ በተሟላ መልኩ
አለማካተትና የፕላን ማስፈጸሚያ ስልቶችን አለመጠቆማቸው በጥናት ሰነዶች ላይ የሚታዩ ዋና ዋና
ችግሮች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የመሬት አጠቃቀም ፕላን ጥራትን በተመለከተ የሚነሱ ዋና ዋና ችግሮች
መሀከል የኮድ፣ ስታንዳርድ፣ ሌጀንድ፣ ወዘተ ወጥነት አለመኖር፤ በመሬት ላይ ያለውን እውነታ አለማሳየቱ
እንዲሁም የማይጣጣሙ አገልግሎቶች ጎንለጎን መቀመጥ፣ የመንገድ ተዋረድ አለመጠበቅ /የሚዘጉ፣
የሚጠቡ፣ ወዘተ…/፣ የሶሾ-ኢኮኖሚ ጥናቶችን አለማንጸባረቅ፣ የገጠር-ከተማ እና የከተማ-ከተማ ትስስርን
እንዲሁም ጥብቅ ቦታዎችና ማነቆዎችን፣ ግምት ውስጥ አለማስገባትና የኮንቱር አለመናበብ ተጠቃሾች
ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮቹች ለመፍታት የከተሞች መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት አሰራርን

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 111


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ማሻሻል እንደ አንድ የስትራቴጂ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ይህ የስትራቴጂ አቅጣጫ በውስጡ ሁለት ዋና ዋና
ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን እነዚህን ጉዳዮች ለማሳካት የሚያስችሉ ስልቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

2.1. የከተሞች መሬት አጠቃቀም ፕላን ሽፋንን ማሳደግ

በነባራዊ ሁኔታ ትንተና ለማየት እንደተቻለው የአገሪቱ የከተማ ፕላን አቅርቦት ካለው ፍላጎት አንጻር
ሲታይ ዝቅተኛ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ የገጠር ቀበሌ ማዕከላት በፕላን እንዲመሩ
ፍላጎት መኖር እና በተመሳሳይ መልኩ ምላሽ መስጠት አለመቻል አጠቃላይ የፕላን ሽፋኑን በጣም ዝቅተኛ
ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ የከተማ ፕላን ሽፋን በማሳደግ ሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ ለማድረግ
የሚከተሉት ስልቶች ተነድፈዋል፡፡

ስልት 2.1.1. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት አደረጃጀት ማጠናከርና አሁን

ካለበት በተሻለ መልኩ ያልተማከለ ማድረግ

ከአስር አመት በፊት የከተማ ፕላን ዝግጅት በማዕከል ይከናወን የነበረ በመሆኑ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን
የከተሞች የፕላን ፍላጎት ማሟላት ባለመቻሉ ምክንያት ክልሎች የየከተሞቻቸውን ፕላኖች እንዲያዘጋጁ
በመደረጉ ምክንያት በአመት በርካታ ፕላኖችን ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡ ሆኖም አሁንም በሚፈለገው መልኩ
የከተሞች ፕላን ሽፋንን ማሳደግ ባለመቻሉ ምክንያት ሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ
ለማድረግ እንዲሁም ከፕላን አፈጻጸም/አተገባበር ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ይቻል ዘንድ
በክልል ደረጃ ያለውን የፕላን ዝግጅት አደረጃጀት ያልተማከለ በማድረግ በዞን ደረጃ እንዲሁም በሂደት
በወረዳ እና በመጨረሻም በከተሞች ደረጃ እንዲወርድ ይደረጋል፡፡

ስልት 2.1.2. በቂ ባለሙያዎች ማሰማራት

ለከተማ ፕላን ሽፋን አነስተኛ መሆን አንዱ ምክንያት በቂ ባለሙያዎች በፕላን ዝግጅት ተቋማት
አለመኖራቸው ነው፡፡ ምክንያቱም በርካታ ባለሙያዎች ካሉ በርካታ ፕላኖች ማዘጋጀት የሚቻል መሆኑ
ነው፡፡ በፕላን ዝግጅት ተቋማት በቂ ባለሙያ የማይኖርበት ዋና ዋናዎቹ ምክንያቶች የአደረጃጀቱ መዋቅር
የጠበበ መሆን፣ ባለሙያን ለመቅጠር አቅም አለመኖር፣ የባለሙያዎች በከፍተኛ ሁኔታ መፍለስ ናቸው፡፡
በመሆኑም ችግሩን ዘላቂነት ባለው መልኩ መፍታት ይቻል ዘንድ ለፕላን ዝግጅት የሚያስፈልገውን
አደረጃጀትና የሰው ሀይል በማዘጋጀት፣ በአደረጃጀቱ መሰረት ባለሙያዎች እንዲቀጠሩ የማድረግ ስራዎችን

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 112


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በመስራት እንዲሁም ለባለሙያ ፍልሰት ምክንያት የሆኑትን ሁኔታዎች በመለየትና ማቆየት የሚቻልበትን
ሁኔታዎች በማመቻቸት በፕላን ዝግጅት ስራዎች በቂ ባለሙያዎች እንዲሰማሩ በማድረግ ለከተማ ፕላን
ሽፋን ማደግ አስተዋጽዎ ይደረጋል፡፡

ስልት 2.1.3. የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማጠናከር

በመሰረታዊ ካርታ እና በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተወዳዳሪ
አግልግሎት ለከተሞች ለማቅረብ በመንግስት አካላት ብቻ የሚቻል ባለመሆኑ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ
ማሳደግ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ የከተማ ፕላን ከቅየሳና መሰረታዊ ካርታ ዝግጅት ጋር አጣምረው
አገልግሎት የሚሰጡ የግል አማካሪ ድርጅቶች በበቂ መጠን መፍጠርና በቂ የአፈጻጸም አቅም፣ ልምድና
ከጥገኝነትና ኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ አመለካከት ኖሯቸው ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ መደገፍ እንዲችሉ
ማብቃት ያስፈልጋል፡፡ ይህም በአደረጃጀትና አሰራር ስርዓት፣ በሰው ኃይልና በቴከኖሎጂ አጠቃቀም
ያላቸውን ውስጣዊ አቅም ማጠናከርና በዘርፉ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት አንጻር በርካታ የግሉ ዘርፍ ተቋማት
ወደ ገበያው ገብተው ጉልህ ድርሻና አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ሁኔታዎችን የማመቻቸትና የማበረታታት
ጥረትን ያካትታል፡፡

ለዚህም የግሉን ዘርፍ ወደ መሰረታዊ ካርታና የከተማ ፕላን ዝግጅት ስራው እንዲገባ ከማበረታታት አኳያ
ቀደም ሲል የተጀመረው በምዝገባና መምረጫ መስፈርት መሰረት አዳዲስ አማካሪ አሃዶችን መዝግቦ፣
መርጦና ስልጠና ሰጥቶ በማደራጀት ወደ ስራው እንዲገቡ የማስቻል ስራው መቀጠል አለበት፡፡ ለዚህም
በተለይ ከክልሎችና ከከተሞች ጋር በመተባበር ተመርጠው እንዲደራጁ የተደረጉት አሃዶች በየአካባቢያቸው
ካሉ የአነስተኛ ብድር ተቋማት የብድር አገልግሎት በማግኘት የቢሮና ቁሳዊ አደረጃጀታቸውን
እንዲያሟሉና ቀጣይነት ካለው ስራ ጋር የሚተሳሰሩበትን ሁኔታ የማመቻቸት ስራ ይሰራል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በተለይ በክልልና በከተሞች ደረጃ ለግሉ ዘርፍ የመሰረታዊ ካርታና የፕላን ስራዎችን
በአስተማማኝ ሰጥቶ ለማሰራት የሚያስችል የበጀት አቅም መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ ይኸውም የከተሞችን
የአመታዊ ገቢዎችን ለማሳደግ የገቢ መሰረቶችን ወይም ምንጮችን (Revenue basis) በሚገባ ፈትሾ
ወይም አጥንቶ የመለየትና እንዲሁም ቀልጣፋ የአገልግሎቶች ክፍያና የታክስ አሰባሰብ ስርዓትን የመፍጠር፣
ከክልሎች ጋር ወጪን የመጋራት ዘዴን የመከተልና እንዲሁም በፌዴራል በኩል እንደፒስካፕና የጂ አይ ዜድ
ወዘተ ድጋፍን ትኩረት ወደ ከተሞች ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ከለጋሽ
ድርጅቶች ጋር በመመካከር ማመቻቸት የሚቻልበት መንገድ መታሰብ አለበት፡፡

ስልት 2.1.4. ረዥም ጊዜ የሚወስደውን አሰራር ማሳጠርና ጊዜን በአግባቡ መጠቀም

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 113


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከተሞች በቆዳ ስፋታቸውና በህዝብ ብዛታቸው መጠን የሚለያዩ በመሆኑ ለፕላን ዝግጅት የሚወስዱት
ጊዜ በዚሁ መሰረት የሚለያይ ቢሆንም በቆዳ ስፋታቸውና በህዝብ ብዛታቸው ተመሳሳይ የሆኑ ከተሞች
ፕላን ዝግጅት ተመሳሳይ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ ሆኖም ግን በነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ለማየት እንደተቻለው
ተመሳሳይ ከተሞች የተለያየ ጊዜ እየወሰዱ በመሆናቸው ከሚፈለገው ጊዜ በላይ መውሰድ በወጪም ሆነ
በሚዘጋጁ ፕላኖች ብዛት አንድ ቡድን በአራት ወራት ውስጥ ማዘጋጀት ያለበት ፕላን ስምንት ወር
ወሰደበት ማለት ቡድኑ በስምንት ወር 2 ፕላኖች ማዘጋጀት ሲጠበቅበት አንድ ብቻ አዘጋጀ ማለት ስለሆነ
ይህም በሽፋን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ በመሆኑም ረዥም ጊዜ የሚወስደውን አሰራር በማሳጠር፣
ጊዜን ባግባቡ በመጠቀምና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለከተማ ፕላን ሽፋን እድገት አስተዋጽኦ
ይደረጋል፡፡

2.2. የከተሞች መሬት አጠቃቀም ፕላን ጥራትን ማሳደግ

የከተማ ፕላን ጥራት የሚለካው በስፓሻል ፕላኑ/የመሬት አጠቃቀም ፕላን/ እና በጥናት ሰነዱ /የሶሺዮ
ኢኮኖሚ፣ ፊዚካልና ስፓሻል ጥናት ሰነድ/ ጥራት ሲሆን የመሬት አጠቃቀም ፕላን ጥራትን በተመለከተ
የሚነሱ ዋና ዋና ችግሮች የኮድ፣ ስታንዳርድ፣ ሌጀንድ፣ ወዘተ ወጥነት አለመኖር፤ በመሬት ላይ ያለውን
እውነታ አለማሳየቱ እንዲሁም የማይጣጣሙ አገልግሎቶች ጎንለጎን መቀመጥ፣ የመንገድ ተዋረድ
አለመጠበቅ /የሚዘጉ፣ የሚጠቡ፣ ወዘተ…/፣ የሶሾ-ኢኮኖሚ ጥናቶችን አለማንጸባረቅ፣ የገጠርና ከተማ
ትስስርን እንዲሁም ጥብቅ ቦታዎችና ማነቆዎችን፣ ግምት ውስጥ አለማስገባትና የኮንቱር አለመናበብ
ናቸው፡፡

በሌላ በኩል የከተማ ፕላን የጥናት ሰነድ ጥራት ሲገመገም ሰነዱ በአብዛኛው ለጥናት አስፈላጊ የሆኑ
የተሟሉ፣ የተረጋገጡና አስተማማኝ መረጃዎችን የማያካትትና በተለይም ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለሆኑ
ቁልፍ ችግሮች መፍትሄ የማይሰጥ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ዕቅድ ጋር የማይቆራኝ ነው፡፡ የከተማ ልማት
ፖሊሲው የከተማ ፕላን ሲዘጋጅ ከከተማ ልማት ዕቅድ ጋር መያያዝ እንዳለበት የሚጠቅስ ቢሆንም
በተግባር የሚታየው ግን ለከተሞች የሚዘጋጀው ስፓሻል ፕላን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ
የውይይት መድረኮች የተገኙ ገንቢ ሀሳቦችን በሰነዱ ውስጥ በተሟላ መልኩ አለማካተትና የፕላን
ማስፈጸሚያ ስልቶችን አለመጠቆማቸው በጥናት ሰነዶች ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች ሲሆኑ እነዚህም
ችግሮች በፕላኑ ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽእኖዎችን አሳድረዋል፡፡ ስለዚህ ከጥራት ጋር የተያያዙ ችግሮችን
ዘላቂነት ባለው መልኩ መፍታት ይቻል ዘንድ የሚከተሉት ስልቶች ተነድፈዋል፡፡

ስልት 2.2.1. የፕላን ዝግጅት የጥራት ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት፣

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 114


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን መረጋገጥ አለበት፡፡ ሆኖም በየክልሉ የሚዘጋጁት ፕላኖች
ተግባራዊ ከመሆናቸው በፊት የጥራት ቁጥጥር ስርዓትን የሚያልፉበት ሁኔታ ተዘርግቷል ማለት
አይቻልም፡፡ በመሆኑም ፕላን የሚሰራው በቡድን በመሆኑ ፕላንኑን ለቡድን ውይይት በማቅረብ፣ የቡድን
መሪዎችና የመምሪያ/የስራ ሂደት ሀላፊዎች የፕላኑን ጥራት የሚገመግሙበት ሁኔታ በማመቻቸት፣ ፕላኑን
ለቤት ውሰጥ ውይይት /ለሚመለከታቸው የመስሪያ ቤት ባለሙያዎች /በማቅረብ፣ በመስሪያ ቤቱ ውሰጥ
የቴክኒካል ኮሚቴ በማቋቋም ከሚቴው ፕላኑን የሚገመግምበት ሁኔታ በመፍጠር እንዲሁም ፕላኑ
ከሚዘጋጅለት ከተማ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳ፣ ከከተማው ማዘጋጀ ቤት ባለሙያዎች ለሚውጣጡ የቴክኒክ
ኮሚቴ በማቅረብ፣ ለከተማ የተወካዮች መድረክ በማቅረብ ገንቢ ሀሳቦችን በማካተትና መስተካከል
የሚገባቸውን ጉዳዮች በማስተካከል የከተማ ፕላን ጥራት የሚጠበቅበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

ስልት 2.2.2. እየተሰራባቸው የሚገኙትን አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎች መከለስ

ለከተሞች ፕላን ጥራት ዝቅተኛ መሆን ከሚጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ በከተማ ፕላን
አዋጁ ያልተካተቱ ጉዳዮች መኖራቸው እንዲሁም ጠቅለል ባለ ሁኔታ የተካተቱ ቢኖሩም በደንብና መመሪያ
በዝርዝር ሊብራሩ የሚገባቸው ጉዳዮች ደንብና መመሪያ ያልተዘጋጀላቸው መሆኑ፣ እየተሰራባቸው ያሉ
የከተማ ፕላን ማኑዋሎችና ስታንዳርዶች የተሟሉና ግልጽ አለመሆናቸው በመሆኑ እነዚህን አዋጅ፣ ደንብ፣
መመሪያ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎች በመከለስ የከተሞች ፕላን ጥራት እንዲጠበቅ ይደረጋል፡፡

ስልት 2.2.3. የባለሙያ ክህሎት በስልጠና ማሳደግ

በከተሞች ፕላን ጥራት ላይ የባለሙያ ክህሎት ተጽዕኖ ያለው መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ በክልል ከተማ
ፕላን ዝግጅት ተቋማት የሚቀጠሩ ባለሙያዎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም በተግባር ግን የፕላን
ዝግጅት ልምዱ የሌላቸው በመሆኑ ገና እንደተቀጠሩ የስራ ላይ ስልጠና ሳይሰጣቸው ወደ ፕላን ዝግጀት
ስራ የሚገቡ በመሆኑ በሚዘጋጁ ፕላኖች ላይ የጥራት ጉድለት ይከሰታል፡፡ በፌደራል ደረጃ ለክልል
ባለሙያዎች በየወቅቱ ክህሎት ማሳደጊያ የቤት ውስጥና የስራ ላይ ስልጠና የሚሰጥ ቢሆንም በቂ ባለመሆኑ
በተደራጀ መልኩ በፌዴራልና በክልል ደረጃ የባለሙያ ክህሎትን የማሳደግ ስራ ይሰራል፡፡

ስልት 2.2.4. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትን በጥናትና ምርምር መደገፍ

በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስራዎችን በጥራት ለማከናወን ከሚያግዙ ስልቶች
ውስጥ አንዱ ስራውን በጥናትና ምርምር መደገፍ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ
ከኢንተርኔትና ከተለያዩ ሰነዶች ለመፈተሽ የተደረገ ጥረት ቢኖርም የአንድን አገር መልካም ተሞክሮ
ለመቅሰም ዝርዝር መረጃ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ከጥራትም ሆነ ከጊዜና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 115


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ከወጪ አንጻር የተሻለ አሰራርን መዘርጋት ይቻል ዘንድ ሀገር ውስጥ ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ የሌሎች
ሀገሮችን ልምድ ለመቅሰም ስልጠናዊ የውጭ ሀገር ጉብኝቶች ይደረጋሉ፡፡

ስልት 2.2.5. ፕላኖች ከማዘጋጃ ቤት የልማት ዕቅድ ጋር እንዲያያዙ ማደረግ

በሀገሪቱ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች ስፓሻል ተኮር የሆኑና ለማሕበራዊና ኢኮኖሚዊ ለሆኑ ቁልፍ ችግሮች
መፍትሄ የማይሰጡ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤት ዕቅድ ጋር የማይቆራኙ ናቸው፡፡ የከተማ ልማት ፖሊሲው
የከተማ ፕላን ሲዘጋጅ ከከተማ ልማት ዕቅድ ጋር መያያዝ እንዳለበት የሚጠቅስ ቢሆንም በተግባር
የሚታየው ግን ለከተሞች የሚዘጋጀው ፕላን ስፓሻል ፕላን ብቻ ነው፡፡ ስፓሻል ፕላን ብቻውን የከተሞችን
ልማት የማያመጣ በመሆኑ የከተማ ፕላን ሲዘጋጅ የከተሞችን/የማዘጋጃ ቤትን/ የሶሺዮ ኢኮኖሚ ልማት
ዕቅድ ጋር መያያዝ የሚኖርበት ሲሆን ይህም በፕላን ዝግጅት ማኑዋል ውስጥ እንዲካተት/እንዲንጸባረቅ
ይደረጋል፡፡

ስልት 2.2.6. የ ã ርባን ዲዛይን (Urban Design) ማኑዋል ማዘጋጀት

መዋቅራዊ ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ ፕላኑን ተግባራዊ የሚደረገው የአካባቢ ልማት ፕላን በማዘጋጀት ሲሆን
ፕላኑ የሚዘጋጀው ለትላልቅ ከተሞች ከሆነ ዝርዝር ፕላን ሲዘጋጅ የከተማ ዲዛይን ፕላንም ማዘጋጀት
አስፈላጊ ቢሆንም በአብዛኛው የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች እንደማይዘጋጅና የሚዘጋጅበትም አጋጣሚ ቢኖር
በማኑዋል እና ስታንዳርድ ላይ ባልተመሰረተ ሁኔታ ስለሆነ ወደፊት የሚዘጋጁት የከተማ ዲዛይኖች
ጥራታቸውን የጠበቁ ይሆን ዘንድ የከተማ ዲዛይን ማኑዋልና ስታንዳርድ ሰነድ ይዘጋጃል፡፡

ስልት 2.2.7. የከተሞች መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅት የብሄራዊ እና የክልል የከተሞች እድገት ዕቅድን
ግምት ውስጥ እንዲያስገባ ማድረግ ፣

በሀገር አቀፍ የከተማ ልማት ፖሊሲ ውስጥ እንደተቀመጠው ማንኛውም የከተማ ፕላን ሲዘጋጅ በብሄራዊ
እና ክልላዊ ደረጃ የሚታቀዱ እቅዶችን ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡ ምክንያቱም በሀገር አቀፍና
በክልል ደረጃ የሚታቀዱ እቅዶች ፕላን በሚዘጋጅለት ከተማ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ነው፡፡
ለምሳሌ በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የሚታቀዱ አገር አቋራጭ የባቡር ወይም የመኪና መንገዶች ፕላን
በሚዘጋጅለት ከተማ ውስጥ ሊያልፉ ስለሚችሉ፣ ወይም ከተማዋ ለኢንዲስትሪ ማዕከልነት ወይንም
ለደረቅ ወደብነት የተመረጠች ልትሆን ስለምትችል ይህንን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ፕላን ማዘጋጀት በሀገር
አቀፉ ወይም በክልል ደረጃ የታቀዱ እቅዶች ተግባራዊ ሲሆኑ በከተማዋ ውስጥ የለሙ ቦታዎች የማፍረስ፣
የሀብት ብክነትና ሌሎች ችግሮች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ማንኛውም ፕላን በሚዘጋጅበት ወቅት ፕላን

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 116


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ዝግጅቱ በሀገር አቀፉ እና በክልል ደረጃ የሚታቀዱ የከተማ ልማት እቅዶችን ግምት ውስጥ እንዲያስገባ
ይደረጋል፡፡

ስልት 2.2.8. የአዳዲስ ከተሞች እና የገጠር ቀበሌ ማዕከላት ፕላን ዝግጅት ማኑዋል ማዘጋጀት ፣

በስራ ላይ የሚገኙት ማኑዋሎች የነባር ከተሞችን ፕላን ለማዘጋጀት ታስቦ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ በየክልሉ
በየጊዜው እያቆጠቆጡ የሚፈጠሩ ከተሞች፣ በፕላን መመራት ያለባቸው በሺ የሚቆጠሩ የገጠር ቀበሌ
ማዕከላት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች አዲስ እንዲመሰረቱ የሚፈለጉ ከተሞች ያሉ በመሆኑ ለነዚህ
ከተሞች ፕላን ዝግጅት የሚሆን መመሪያም ሆነ ማኑዋል የለም፡፡ በአገሪቱ ያሉት በርካታ የገጠር ቀበሌ
ማዕከላት ወደፊት ወደ ከተማነት ሊያድጉ የሚችሉ ጥንስስ በመሆናቸው ከወዲሁ ማለትም ውስብስብ
ሁኔታዎች ከመፈጠራቸው በፊት ማዕከላቱን በፕላን መምራት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በስራ ለገጠር ቀበሌ
ማዕከላትና አዲስ ለሚመሰረቱ ከተሞች የፊዚካል ዕድገታቸውን መምራት የሚያስችል ማኑዋል
እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡

ስልት 2.2.9. በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች ከተሞችን ፕላን በጋራ የሚያቅድ የጋራ የፕላን
ኮሚሽን ማቋቋም ፣

በተጎራባች ክልሎችና ከተሞች መካከል ያለው ያልተቀናጀና በተናጠል የሚከናወን የከተማ ፕላን አሰራርና
አፈጻጸም ትልቅ ችግር ሆኖ ይገኛል፡፡ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች ከተሞች በተናጠል
እየተካሄደ የሚገኘው የከተማ ፕላን ዝግጅትም ሆነ ልማት ያልተናበበና ያልተቀናጀ በመሆኑ የሃብት ብክነት
ከማስከተሉም በላይ በከተሞቹ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማስከተሉ አይቀርም። ለአብነት በአዲስ አበባ
ከተማና በአካባቢዋ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ባላቸው ቅርበት ምክንያት ጥብቅ ቁርኝት ቢኖርም
በኦሮሚያ ክልልና በአዲስ አበባ መስተዳድር መካከል በቅንጅት የሚሰሩበት ስርዓት የለም። በደቡብና
ኦሮሚያ (የአዋሳና የጥቁር ውሀ ጉዳይ) ተመሳሳይ ነው። ስለዚህ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ
ተጎራባች ከተሞች እንዲሁም በአንድ ክልል ውስጥ የሚገኙ ተጎራባች ከተሞች /ለምሳሌ ዱከምና ቢሾፍቱ
በኦሮሚያ/ ፕላኖቻቸውንና በጋራ የሚያቅዱበት የጋራ የፕላን ኮሚሽን ይቋቋማል፡፡

2.3. ውጤታማና የተቀናጀ የከተማ የመሬት አጠቃቀም /Major Land Use Functions/ ስርዓት
መዘርጋት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 117


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ስልት 2.3.1. ለአገልግሎቶች ቦታ የመመደብ ስርአትን ማሻሻል

የከተማ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ይዘት ሰፋፊ በሆኑ በስድስት ዋና ዋና ምድቦች ማለትም የመኖሪያ ቤት
አገልግሎት፣ የቢዝነስ፣ የንግድና የገበያ ቦታዎች፣ የማሕበራዊ አገልግሎቶች፣ የፋብሪካዎች/ኢንዱስትሪ እና
ማከማቻ ቦታዎች፣ የመንገድ ትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎቶች በመባል
የሚከፈል ሲሆን እያንዳንዱ ምድብ በውስጡ በርካታ አገልግሎቶችን ይዟል፡፡ በመሬት አጠቃቀም ይዘቶቹ
ላይ በተደረገው የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ አብዛኛው አገልግሎቶች ለነዋሪው በቂ አለመሆናቸው፣ አንዳንድ
አገልግሎቶች ጭራሹኑ አለመኖራቸው፣ ያሉትም አገልግሎቶች አብዛኞቹ ቦታ ሲያዝላቸው መስፈርቶችን
/ስፋት፣ የመሬት ተዳፋታምነት፣ ማዕከላዊነት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ ከአካባቢ ጋር የመጣጣም ሁኔታ፣
ስርጭት፣ ተደራሽነት /accessibility/…ወዘተ/ ግምት ውስጥ የማያስገቡ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ችግሮችን ለመፍታት ይቻል ዘንድ በፕላን ላይ ቦታ በሚያዝበት ጊዜ በስትራክቸር ፕላን
ስታንዳርድ ማኑዋል መሰረት ተገቢው ስፋት እንዲኖራቸው፣ ተዳፋታማነት በማያስቸግርበት በተገቢው
ቦታ ላይ እንዲቀመጡ፣ መዳረሻ መንገድ እንዲኖራቸው፣ እንደየአገልግሎቶቹ ፀባይ ማዕከላዊ ቦታ ላይ
መሆን የሚገባቸውን ማዕከላዊ ቦታ ላይ እንዲቀመጡ፣ በሁሉም የከተማ ክፍል መኖር የሚገባቸውን በዚሁ
መሰረት እንዲቀመጡ እንዲሁም አካባቢን በመጥፎ ሽታ በካይ የሆኑትን የንፋስ አቅጣጫን ግምት ውስጥ
በማስገባት ከተማ ዳር ላይ እንዲቀመጡ አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ
የመሬት አጠቃቀሞችን በፕላን ላይ በሚቀመጡበት ጊዜ አንዱ ከሌላው ጋር የሚጣጣሙ መሆኑን
ማረጋገጥ አሰፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ ትምህርት ቤትንና ከፍተኛ ድምጽ የሚያወጣ ፋብሪካን ጎን ለጎን
እንዳይቀመጡ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ሲሆን የአገልግሎቶቹ ብዛት ወይም ቁጥራቸው በስታንዳርድ
መሰረት ለከተማ ነዋሪ ህዝብ በቂ መሆኑን እንዲሁም አገልግሎቶቹ በከተማ ውስጥ ፍትሀዊ ስርጭት
ያላቸው መሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡

ስልት 2.3.2. መንገድ፣ ትራንስፖርትና መሰረተ ልማትን በተመለከተ

ከመንገድ ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት በመጀመሪያ በሚፈለገው መልኩ የተደራጀ የመንገድ
ስርጭት ፕላን ማዘጋጀት አስፈላጊ ሲሆን የመንገድ ስርጭት ፕላኑ በዋና ዋና መንገዶች ግራና ቀኝ
የእግረኞች መንገድ እና እንደ ከተማው የመሬት አቀማመጥና ተጨባጭ ሁኔታ የብስክሌት መንገድንም
ማካተት አለበት፡፡ በመንገድ ስርጭት ፕላኑ ላይ በመመስረት የከተማውን ጎርፍ መቆጣጠር ይቻል ዘንድ
በቅድሚያ የጎርፍ ማስወገጃ ፕላን መዘጋጀት አለበት፡፡ የተዘጋጀው የመንገድ ስርጭት ፕላን ነባራዊው
የመንገድ ስርጭት ፕላን ላይ የሚታዩ ችግሮችን ማለትም የጠበቡ መንገዶች፣ የተዘጉ መንገዶች፣ ከሌላው
አካባቢ ጋር የማይገናኙ መንገዶች፣ መተላለፊያ የዘጉ ረዣዥም ብሎኮች፣ የጠበቡ መስቀለኛ መንገዶች
የሚገናኙበት intersections እና አደባባዮች ወዘተ… መፍትሄ መስጠት አለበት፡፡ በየትኛውም የከተማ ክፍል

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 118


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ለወደፊት የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ቦታነት የሚመደቡ ቦታዎች እስኪለሙ ድረስ በአረንጓዴ ቦታነት
ጠብቆ ማቆየት ይገባል፡፡

የመንገድ ስርጭቱ ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ እንደ ከተማው አቅም መንገዶች መገንባት የሚያስፈልግ ሲሆን
መንገዶችን እንደ ደረጃቸው ቅድሚያ ትኩረት የሚሹትን በመለየት ዋና ዋና መንገዶችን በአስፋልት፣
ሁለተኛ ደረጃ መንገዶችን በኮብል ስቶን እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በጠጠር በመገንባት
የከተማው አቅም እያደገ ሲሄድ የመንገዶቹን ደረጃ ከፍ ማድረግ የሚቻል ሲሆን መንግስት ብቻውን
ሁሉንም የልማት ስራዎች መስራት ስለማይችል በሕብረተሰቡ ተሳትፎ የአካባቢ ልማት ስራዎች
እንዲከናወኑ ጥረት መደረግ አለበት፡፡ ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ መዘንጋት የሌለበት የጎርፍ ማስወገጃ
መስመሮች፣ የእግረኞች መንገድ እንዲሁም የመሬቱ አቀማመጥ በሚፈቅድላቸው ከተሞች የብስክሌት
መንገዶች ግንባታዎች ናቸው፡፡ መንገዶች ከተገነቡ በኋላ ክትትል ማድረግና ሲጎዱ ጥገናዎችን ማድረግ
መንገዶቹ ለረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ከማስቻሉ በተጨማሪ አደጋዎች እንዳይከሰቱ፣ የትራፊክ
መጨናነቅ እንዳይኖር፣ መኪናዎችም እንዳይጎዱ ይረዳል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የጎርፍ ማስወገጃ መስመሮች
ከተገነቡ በኋላ በቆሻሻ እንዳይዘጉ በየጊዜው ክትትል በማድረግ ማጽዳት አስፈላጊ ነው፡፡

ከትራንስፖርት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት በስትራክቸር ፕላን ስታንዳርድ ማኑዋል ላይ


በመመስረት የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን/Parking/ በመሬት ላይ እንዲሁም ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ
ሕንጻዎች ግንባታ የሚውል ቦታ ማዘጋጀት፣ ለጭነት መኪና ተርሚናሎችን ማዘጋጀት፣ ለአውቶብሶች
መናኸሪያዎችን ማዘጋጀት፣ በመንገዶች ላይ የትራፊክ መብራት፣ ምልክት፣ የእግረኞች ማቋረጫ
ምልክቶች ማዘጋጀት፣ አካባቢ ከመጠበቅ አንጻር በካይ እና ረዥም እድሜ ያስቆጠሩ መኪናዎች ወደ አገር
ውስጥ እንዳይገቡ ማድረግ፣ የሕብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ፣ የማስፈጸም አቅም መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
በመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች መሀከል የሚታየው በተናጠል አቅዶ መስራት የሀብት ብክነትና
የልማት መጓተት እያስከተለ በመሆኑ ድርጅቶቹ በጋራ በማቀድ ተቀናጅተው የሚሰሩበት ሁኔታ መፍጠር፣
የመሰረተ ልማት መስመሮችን በፕላን ላይ ማስፈር፣ መስመሮችን በስታንዳርድ መሰረት መሬት ውስጥ
መቅበር አስፈላጊ ነው፡፡

ስልት 2.3.3. የመኖሪያ ቤትን አቅርቦት ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ በቂና ፍትሃዊ እንዲሆን ማድረግ

ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው መስጠት ከሚጠበቅባቸው አገልግሎቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የመኖሪያ ቤት


አቅርቦት በመሆኑ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ወደሚፈለገው ደረጃ በብቃት ለማድረስ ጥረት መደረግ
ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም አሁን እየታየ ያለውን የመኖሪያ ቤት አገልግሎት እጥረት፣ በክምችት ያሉ የደቀቁና
ለኑሮ አመቺ ያልሆኑ ቤቶች እንዲሁም ከከተማው ነዋሪ ገቢ ጋር የተመጣጠነ የቤት አቅርቦት እንዲኖር
ለማስቻል ወጪ ቆጣቢ የሆኑ አዳዲስ ቤቶችን መገንባና የአቅርቦቱን ቁጥር መጨመር እንዲሁም በእርጅና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 119


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ምክንያት የደቀቁትን ከመጠገንና ይዞታቸውን ማሻሻል በተጨማሪ ሙሉ በሙሉ አፍርሶ መተካት ድረስ
ሥራ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ለከተማ ነዋሪው የቤት አቅርቦቱ የሚከናወነው በመንግስት፣ በማህበራት፣
መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በግሉ ዘርፍ ሆኖ በተለይ የግሉ ዘርፍና የቤት ማህበራት በቤት አቅርቦት
የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ ለማድረግ የለማ መሬት አቅርቦትን ከማሻሻል አንስቶ የከተማ
ነዋሪዎችን ቁጠባ ባህል በማበረታታት ለቤት ግንባታ የሚውል ፋይናንስ አቅርቦትን ማሻሻል ይጠይቃል፡፡

የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እንደ አገልግሎት ለማሟላት እንዲቻል በመስፋፊያ ቦታዎች የመሰረተ ልማት
የተሟላለት የመሬት አቅርቦትን ማሻሻል፣ በህገ ወጥ መንገድ ከፕላን ውጭ ግንባታዎች እንዳይከናወኑ
መከልከል፣ የተሰሩ ቤቶች ካሉም እንዲፈርሱ ማድረግና አዳጋች በሆነ ወቅትም በፕላኑ የሚደገፉ ከሆነና
ለመኖሪያ በተያዘ ቦታ ላይ ከተገነቡ ከፕላን ጋር ተጣጥመው የሚቀጥሉበትን ስልት የመቀየስና የመተግበር፣
ቀልጣፋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር፣ የከተሞች አቀፍና ዝርዝር ፕላኖች እንደ ከተሞቹ የዕድገት ደረጃ
የከተማ ዲዛይንን ጨምሮ ተፈጻሚነታቸውን ማረጋገጥ፣ በተጓዳኝም የከተማ ማደስና መልሶ ማልማት
ለችግሩ መፍቻ መንገዶች ሆነው መወሰድ ይገባቸዋል፡፡ ይህም በተቻለ መጠን ከተሞች እንዳሉበት የእድገት
ደረጃና የከተማ ነዋሪዎችን የገቢ ልዩነትን መሰረት ያደረገ እንዲሁም ወደ ጎን የተለጠጠ መስፋፋትን
በመግታት ጎን ለጎን ወይም በቅልቅል ተባብረው የሚሄዱ የተለያዩ የመሬት አጠቃቀም ዓይነቶችንና
አገልግሎቶችን በመያዝ ከፍታ ያላቸው ህንጻዎች መገንባት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከተሞች
በመሬት አጠቃቀም ፕላን የተመጠነ ቅርጽ እንዲኖራቸው በማድረግ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን
የመሰረተ ልማት አውታር ዝርጋታ ወጪን መቀነስ በሚያስችል መልኩ እንዲቃኝ በማድረግ የከተሞችን
መኖሪያ አካባቢ ጤናማና ለኑሮ ምቹ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም
በከተሞቻችን የተለያየ የገቢ ደረጃ ያላቸውን ነዋሪዎች አቅማቸውንና የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ባገናዘበ
መልኩ ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውለውን መሬት አጠቃቀም ዓይነት በግልጽ እንዲያመላክቱ በማድረግና
አቅርቦቱም ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ በቂና ፍትሃዊ እንዲሆን በማድረግ የከተሞችን እድገት እንዲደግፍ
ይደረጋል፡፡ የአብዛኛው ህብረተሰብ የገቢ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ የመሬት ዋጋን ግምት ውስጥ ያስገባ
የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ስልት መከተል ያስፈልጋል፡፡ የመሬት ዋጋ ከፍተኛ በሆነበት አካባቢ የመሬቱን አቅም
አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በተመሳሳይ የመኖሪያ ቤት አካባቢ ፕላን /Neihgbourhood plan/ ሲዘጋጅ
የፊዚካልም ሆነ ማህበራዊ መሰረተ ልማት ያካተተ ፕላን እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡

ስልት 2.3.4. ከሶሾ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ችግሮችን መፍታት

ከከተማ ፕላን የመሬት አጠቃቀም ይዘቶች /Major Land Use Functions/ ላይ በተደረገው ትንተና
የተለዩት ችግሮች ስፓሻል እና ፊዚካላዊ ብቻ ሳይሆኑ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮችንም የሚያካትቱ
ሲሆን ከስፓሻል እና ፊዚካላዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙት ችግሮች መፍቻ ስልቶች ከላይ ለመግለጽ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 120


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ተሞክሯል፡፡ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮች ማለትም ስራ አጥነት፣ ማህበራዊ ችግሮች፣ የትምህርትና


ጤና አገልግሎት ጥራት ዝቅተኛ መሆን፣ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንና ጥራት ዝቅተኛ መሆን የመሳሰሉት
ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ስልቶች በየሚመለከታቸው ዘርፎች/Sectoral Organaiztions/ የሚገኙ
ስለሆነ /ለምሳሌ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ በትምህርት ሚ/ር የተዘጋጁ ስትራቴጂዎች ወይም ስልቶች
አሉ/ በፕላን ዝግጅት ነባራዊ ሁኔታዎች ዳሰሳ ወቅት እነዚህ ችግሮች እንደ ቁልፍ ችግር ከተመረጡ
ችግሮቹን ለመፍታት የሴክተር መ/ቤቶቹን ስትራቴጂዎች መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡

3. የከተማ ፕላን ትግበራ/አፈጻጸም ስርዓትን ማሻሻል

መዋቅራዊ ፕላን ከተዘጋጀ በኋላ ፕላኑ ተግባራዊ የሚደረገው ዝርዝር ፕላኖችን ማለትም ያካባቢ ልማት
ፕላኖችን በማዘጋጀት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን መዋቅራዊ ፕላን ሲዘጋጅ በአዘጋጁ አካል /ክልል
የከተማ ፕላን ተቋም ወይም የግል አማካሪዎች/ የአካባቢ ልማት ፕላን የሚዘጋጀው ከሁለት ላልበለጠ
አካባቢዎች ብቻ በመሆኑ የከተማው የሌሎች አካባቢዎች የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅት የሚተወው
ለከተሞች ነው፡፡ ነገር ግን ከተሞች የመሳሪያም ሆነ የሰው ሀይል አቅም የሌላቸው በመሆኑ ዝርዝር የአካባቢ
ልማት ፕላን ሳያዘጋጁ መዋቅራዊ ፕላኑን እንደሚተገብሩ ይህም የመሬት አጠቃቀም ብክነት፣ የመሬት
አጠቃቀም አለመጣጣምና መኖሪያ ቤት አካባቢ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች ያለመኖር ምክንያት ሆኗል፡፡
አልፎ አልፎ የአካባቢ ልማት ፕላን የሚዘጋጅበት አጋጣሚ ቢኖርም ፕላኑ ሲዘጋጅ የፊዚካላዊና ማሕበራዊ
መሰረተ ልማት አቅርቦትን ግምት ውስጥ እንደማይገባ ከላይ ለመግለጽ ተሞክሯል፡፡ በከተሞች ዝርዝር
ፕላኖችን የማዘጋጀት አቅም ውስንነት ምክንያት ፕላኖች በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት መተግበር
አልተቻለም፡፡

መዋቅራዊ ፕላንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያሰችሉ ዝርዝር የአካባቢ ፕላኖች ከተዘጋጁ በኋላ ቀጣይ ስራ
በዝርዝር ፕላኑ መሰረት የመሬት ላይ ቅየሳ ስራዎችን በማካሄድ እና አስፈላጊ መሰረተ ልማት አውታሮችን
በማቅረብ ለአልሚ ቦታ መስጠት ነው፡፡ የመሬት ዝግጅት፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት እና የመሬት አቅርቦት
ስራዎች ከዚህ ቀደም ይከናወኑ የነበሩት ራሱን በቻለ ለዚሁ አገልገሎት በተደራጀ አካል ሳይሆን ዝርዝር
ፕላን በሚያዘገጀው አካል የነበረ ሲሆን ይህም አካል በከተሞች ማዘጋጀ ቤቶች ውስጥ የቴክኒክ ክፍል
በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ ሆኖም ግን የስራ መደራረብን ከመቀነስ እና የፕላኖችን ትግበራ/አፋጻጸም
ከመከታተል አንጻር የዝርዝር ፕላን ዝግጅቱና የመሬት አቅርቦቱን በተለያዩ አካላት ማከናወን አስፈላጊ
መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም ፕላን የሰራው አካል ራሱ ቦታ የሚያቀርብ ከሆነ በፕላን ትግበራ ወቅት
የሚከሰቱ የአፈጻጸም ችግሮች/ በፕላኑ መሰረት የመሬት አቅርቦት ስለ መከናወኑ/ ሊደበቁ ስለሚችሉ
ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ያደበዝዛል፡፡ ከፕላን አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ሌሎች ጉዳዮች በፕላኑ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 121


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

መሰረት ለወደፊት የመሬት አጠቃቀም ለተለያዩ አገልግሎቶች የተያዙ በቦታዎችን ፕላኑን ከሚያዘው
ውጭ የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶች መከሰት፣ በሚዘጋጁ ፕላኖች ጥራት ዝቅተኛነት ምክንያት ፕላኖችን
ወደ መሬት ለማውረድ አስቸጋሪ መሆን፣ የመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች በፕላን መሰረት መጀመሪያ
መልማት ያለባቸው አካባቢያቸውን ቅድሚያ በመስጠት ተቀናጅተው አግልግሎቶችን አለማቅረባቸው
ናቸው፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት የከተሞች ፕላን ትግበራ/አፈጻጸም ስርዓትን ማሻሻል እንደ
ስትራቴጂ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ይህ የስትራቴጂ አቅጣጫ በውስጡ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን
እነዚህን ጉዳዮች ለማሳካት የሚያስችሉ ስልቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

3.1. የመዋቅራዊ ፕላን ማስተግበሪያ የዝርዝር ፕላን ዝግጅት ስርዓትን ማሻሻል

በዓላማ 3 ስር የተጠቀሱት ከስትራክቸር ፕላን ማስተግበሪያ ዝርዝር ፕላን ዝግጅት ጋር የተያያዙ ችግሮች
መንስኤዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የፕላን ትግበራ ራሱን የቻለ ቋሚ አደረጃጀት የሌለው መሆኑ፣ የፕላን
ትግበራ ማስፈጸሚያ ስልት አለመዘጋጀቱ /ዝርዝር የሽንሻኖ ፕላን፣ ለትላልቅ ከተሞች የከተማ ዲዛይን
ፕላን፣ የፌዚንግ ፕላን፣ የሽንሻኖ ስታንዳርድ፣ የሽንሻኖ ማኑዋል፣ የድርጊት መርሀ ግብር/፣ የአመራሩና
ሀላፊዎች አመለካከት ችግሮች እና የማስፈጸም አቅም ደካማ መሆን ሲሆኑ እነዚህን ችግሮቹ ለመፍታት
የስትራክቸር ፕላን ማስተግበሪያ የዝርዝር ፕላን ዝግጅት ስርዓትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስልቶች
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

ስልት 3.1.1. የዝርዝር ፕላን ዝግጅት ቋሚ አደረጃጀት መፍጠር

በማንኛውም አካል የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች የሚተገበሩት በከተማ አስተዳደሮች አማካኝነት መሆኑ
ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን ከፕላን አፈፃፀም አኳያ አብዛኛዎቹ ከተሞች ከሰው ሀይል አንጻር ሲታይ
በመሀከላቸው ልዩነት ያለ ሲሆን በተለይ በአገሪቱ ከተሞች ውስጥ በቁጥራቸው ትልቁን ድርሻ በሚይዙት
በአነስተኛ ከተሞች ላይ ችግሩ የጎላ እንደሆነ በሚ/ር መ/ቤቱ አማካኝነት የተካሄዱ የፕላን አፈጻጸም
ክትትልና ግምገማ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ ስለዚህ ለከተማ ፕላን ትግበራ ዝርዝር ፕላኖችን የሚያዘጋጅ
አካል ወይም መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወንና አደረጃጀቱ
ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም በመዋቅሩ የሚኖረው የሰው ኃይል የላቀና የተሟላ ዕውቀት
እንዲኖረው ይደርጋል፡፡

ስልት 3.1.2 የማስፈጸሚያ ስልት ማዘጋጀት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 122


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የከተማ ፕላን ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ የማስፈጸሚያ ስልት በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባት የተለመደ
አይደለም፡፡ በአብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ትግበራ የሚካሄደው ለትግበራው አስፈላጊ የሆኑ የማስፈጸሚያ
ስልቶች ባልተዘጋጁበት ሁኔታ ነው፡፡ የማስፈጸሚያ ስልቶች ከሚያካትቷቸው ዋና ዋና ስራዎች መሀከል
ስትራክቸር ፕላኑን ማስተግበሪያ የአካባቢ ልማት ፕላን/ለነባር አካባቢና ለመስፋፊያ አካባቢ/፣ የአካባቢ
ልማት ፕላኖች በብሎክ ደረጃ ስለሚዘጋጁ ዝርዝር የሽንሻኖ ፕላን፣ ለትላልቅ ከተሞች የከተማ ዲዛይን
ፕላን፣ የፌዚንግ ፕላን፣ የሽንሻኖ ስታንዳርድ፣ የሽንሻኖ ማኑዋል፣ የድርጊት መርሀ ግብር ሲሆኑ እነዚህን
በጥናትና በምርምር አስደግፎ በማዘጋጀትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን የከተማ ፕላን
ትግበራ እንዲሻሻል ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ጎን ለጎን የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላኖች
ያለመናበብ ችግርን እንዲሁም ከመኖሪያ ቤቶች ጋር ተቀይጠው አገልግሎት እንዲሰጡ በተፈቀዱ የንግድና
ማምረቻ አገልግሎቶች ሰበብ አልፎ አልፎ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የሚፈጠር የድምጽ፣ የሽታ እና
ሌሎችም ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት የአካባቢ ልማት ፕላን ማኑዋሉን በመከለስ ለእነዚህ ችግሮች
ትኩረት እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

በመስፋፊያ ቦታዎችና መልሰው በሚለሙ ነባር ቦታዎች ላይ መሬት ዝግጅት ከተከናወነ በኋላ የተቀናጀ
የመሰረተ ልማት አቅርቦት ስራዎችን ይከናወናሉ፡፡ እንዲሁም በተዘጋጀው ፕላን መሰረት የቦታ አቅርቦት
እና የግንባታ ፈቃድ መስጠት ስራዎች ይከናወናሉ፡፡ በተጨማሪም በፕላን ላይ ለተለያዩ አገልግሎት የሚያዙ
ቦታዎችን በተገቢው ጊዜ ማልማት ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት በፕላን ላይ የተያዘላቸውን ቦታ
የማሳወቅና ሳይት ፕላኑን የመስጠት ስራዎች ይከናወናሉ፡፡

3.2. የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ስርዓትን ማሻሻል

በዚሁ ሰነድ ውስጥ እንደተገለፀው ከመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ጋር የተያያዙ ችግሮች መንስኤዎች መካከል
ዋና ዋናዎቹ የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ራሱን የቻለ ቋሚ አደረጃጀት የሌለው መሆኑ፣ በዝርዝር ፕላን
አዘጋጅ አካልና በመሬት ዝግጅት አካል የስራ ድርሻ ተለይቶ አለመቀመጡ፣ የሚዘጋጁ ዝርዝር ፕላኖች
ጥራት ዝቅተኛ መሆን፣ የዞኒንግ /የመሬት አጠቃቀም/ ለውጥ አሰራር ስርዓት አለመኖር፣ የአመራሩና
ኃላፊዎች የአመለካከት ችግሮች፣ በመሠረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶችና በማዘጋጃ ቤት መሃከል ቅንጅታዊ
አሰራር አለመኖር እና የማስፈጸም አቅም ደካማ መሆን ሲሆኑ ችግሮቹን በመፍታት የመሬት ዝግጅትና
አቅርቦት ስርዓትን ማሻሻል ይቻል ዘንድ የሚከተሉት ስልቶች ተነድፈዋል፡፡

ስልት 3.2.1 የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ቋሚ አደረጃጀት መፍጠር

የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ከሚያካትታቸው ስራዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ በተዘጋጁ ዝርዝር ፕላኖች
መሰረት የመሬት ላይ ቅየሳ ስራዎችን ማካሄድ፣ አስፈላጊ መሰረተ ልማት አውታሮችን ማቅረብ እና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 123


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ለአልሚ ቦታ መስጠት ናቸው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የስራ መደራረብን ከመቀነስ እና


የፕላኖችን ትግበራ/አፈጻጸም ከመከታተል አንጻር የዝርዝር ፕላን ዝግጅቱና የመሬት አቅርቦቱን በተለያዩ
አካላት ማከናወን አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም የመሬት ላይ ቅየሳ ስራዎችን፣ የመሰረተ ልማት አውታሮች
አቅርቦትና ለአልሚ ቦታ የመስጠት ስራዎችን የሚያከናውን፣ የተሰጡ መሬቶች ለታሰበላቸው ዓላማ
መዋላቸውን የሚከታተል፣ ህንጻዎች በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ስለመገንባታቸው የሚቆጣጠር አካል
ወይም ተቋማዊ አደረጃጀት ይፈጠራል፤ አደረጃጀቱን የሚመለከት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነትም ይዘጋጃል፡፡

ስልት 3.2.2 የመሬት አጠቃቀም ለውጥና የመሬት አጠቃቀም ጥሰትን

በተመለከተ መመሪያ ማዘጋጀት

በከተማ ፕላን አፈጻጸም ወቅት በየከተሞቹ የመሬት አጠቃቀም ጥሰት በተለይ ለአረንጓዴ ቦታዎች፣
ለስፖርት ማዘውተሪያና ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በሚያዙ ቦታዎች ላይ በዞኒንግ ለውጥ ሰበብም ሆነ
ከዚያ ውጭ በሆኑ ምክንያቶች የሚከሰት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ጥሰቱ ሲከሰት ለጥሰቱ ምክንያት የሆነው
አካል ተጠያቂ የሚሆንበት አሰራር የሌለ ከመሆኑ በተጨማሪ ጥሰቱን የሚፈጽም አካል ላይ መወሰድ
ያለበትን ህጋዊ እርምጃ በጽሁፍ አልተቀመጠም፡፡ ስለዚህ ይህን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ተጠያቂነትን
የሚያመላክት፣ የዞኒንግ ለውጥ እንዴትና በማን መከናወን እንዳለበት የሚያሳይ፣ አግባብ የሌለው የመሬት
አጠቃቀም ጥሰት ሲከናወን መወሰድ ያለበትን እርምጃ የሚያካትት መመሪያ ይዘጋጃል፡፡

ስልት 3.2.3 በመሠረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶችና በማዘጋጃ ቤት መሃከል

ቅንጅታዊ አሰራርን መፍጠር

ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ከፕላን አፈጻጸም ጋር ከሚታዩት ችግሮች መሀከል በመስፋፊያ አካባቢ
የመሬት ላይ ሽንሻኖ ከተካሄደ በኋላ መሰረተ ልማቶችን /መንገድ፣ መብራት፣ ውሀ፣ ወዘተ…/ አለማቅረብና
በመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች መሀከል ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር ነው፡፡ የመሰረተ ልማት አቅራቢ
ድርጅቶች በፕላን መሰረት መጀመሪያ መልማት ያለባቸው አካባቢዎችን ቅድሚያ በመስጠት ተቀናጅተው
አገልግሎቶችን አያቀርቡም፡፡ በመሰረተ ልማት አቅራቢ ድርጅቶች መሀከል ያለውን ያልተቀናጀና በተናጠል
የሚከናወን አሰራር ችግርን እንዲሁም ከላይ የተጠቀሰውን ችግር ለመፍታት በመሰረተ ልማት አቅራቢ
ድርጅቶችና በከተሞቹ መካከል ቅንጅት ፈጥሮ መስራት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ፣ የአደረጃጀት መዋቅርና
የቅንጅታዊ አሰራር ስርዓት መመሪያ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 124


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

4. የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጸም ክትትል፣ ግምገማና ግብረ-


መልስ ስርዓት ማሻሻል

የክትትልና ግምገማ ሥራዎች በውል ተለይተውና ተደጋጋፊነት ባለው ሁኔታ ማለትም ወጥነትን፣
ተከታታይነትን፣ ወቅታዊነትን፣ ቅንጅታዊ አሠራርን ባማከለ እና ወጥ መለኪያና መስፈርቶች ተዘጋጅተው
ከፌዴራል እስከ ከተማ የተዘረጋ አሠራር ባለመኖሩ በተለያዩ ተቋማት የሚዘጋጁ ፕላኖችን እና የከተሞች
ፕላን አፈጻጸም ድክመቶች በወቅቱ ለማረም እንዲሁም መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት የሚደረገው
ጥረት አጥጋቢ ሆኖ አልተገኘም፡፡ በተለይም የከተሞች ፕላን አተገባበር ክትትልና ግምገማ ሁሉንም ፕላን
የተዘጋጀላቸውን ከተሞች ካለመሸፈኑም ባሻገር የፕላን ጊዜአቸውን ያገባደዱ/ያጠናቀቁ ከተሞች
ያስመዘገቡት ውጤት ተገምግሞ ድክመትና ጥንካሬአቸው ተለይቶ ክለሳ የሚደረግበት አሠራር የለም፡፡
ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር በመሰረታዊ ካርታና ከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት የሚደረጉ የክትትልና
ግምገማ ስራዎች ደካማ ናቸው፡፡ እየተካሄደ ያለው ውሱን ያልተቀናጀ የክትልና ግምገማ ሥራ ወቅቱን
የጠበቀ ግብረመልስ የሚሰጥበት አግባብ የለውም፡፡ ባጠቃላይ አሁን ያለው አሠራር የአደረጃጀት ተዋረዱን
ጠብቆ ማን ምን፣ መቼ፣ እንዴት ክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ መደረግ እንዳለበት የጋራ አሠራር ስለሌለ
የከተማ ፕላን ዝግጅትና አተገባበር ውጤትና ስኬትን በትክክል ለመለካት የሚያስችል እና ተጠያቂነትን
የሚያስከትል ሆኖ አልተገኘም፡፡ ለነዚህ ችግሮች መንስኤ ከሆኑት ውስጥ የፕላን አፈጻጸም ክትትልና
ግምገማ ቋሚ አደረጃጀት አለመኖር፣ በፌዴራል፣ በክልልና በከተሞች መካከል ወጥ የሆነ የቅንጅታዊ አሰራር
ስርዓት አለመኖር፣ በየደረጃው ሊያሰራ የሚችል የክትትል ግማገማና ግብረመልስ ማኑዋል አለመኖር
የመሳሰሉት ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ችግሮቹን ለመፍታት የከተማ ፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጸም ክትትል፣
ግምገማና ግብረመልስ ስርዓትን ማሻሻል እንደ የስትራቴጂ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ይህ የስትራቴጂ አቅጣጫ
በውስጡ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን እነዚህን ጉዳዮች ለማሳካት የሚያስችሉ ስልቶች
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

4.1. የክትትል ግማገማና ግብረ-መልስ አሰራርን ጥራቱን የጠበቀና ተደራሽ ማድረግ

በከተማ ፕላን አፈጻጸም ላይ ጥራት ያለው ስራን ለማከናወን የሚያስችል የተሟላ ማኑዋል ካለመኖሩ
በተጨማሪ ክትትልና ግምገማ የሚደረግባቸው ከተሞች ሽፋን እጅግ በጣም አነስተኛ ሲሆን ክትትሉም
በየጊዜው መደረግ ሲገባው የሚደረገው ግን በዓመት አንዴ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በክትትልና ግምገማው
ውጤት ላይ በመመስረት የሚከናወኑ የግብረ መልስ ስራዎች የሉም ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ይህን ችግር
በዘላቂነት ለመፍታት የሚከተሉት ስልቶች ተቀምጠዋል፡፡

ስልት 4.1.1. የፕላን አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ቋሚ አደረጃጀት መፍጠር

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 125


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ለሚታቀዱ ግቦች እንዲሁም በየደረጃው ለሚሰጡ አገልግሎቶች
ስኬታማ ለማድረግ የክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ ሥራን የሚያከናውን ከፌደራል እስከ ከተማ ተናባቢና
በቅንጅትና በጋራ ኃላፊነት የሚሠራ ሞዴል አደረጃጀት በማዘጋጀት፣ ግንዛቤ ማሰጨበጫ ስራዎች
በማከናወን እና ሞዴል አደረጃጀቱን በሁሉም ክልሎችና ከተሞች በተዋረድ ተግባራዊ በማድረግ ጥራቱን
የጠበቀና ተደራሽ የሆነ የክትትልና ግብረመልስ ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ስልት 4.1.2. የክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ ማኑዋል ማዘጋጀት

የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስፈልጉ መረጃዎች የትኞቹ እንደሆኑና እንዴት መሰብሰብ
እንዳለባቸው፣ መረጃዎቹን እንዴት መተንተን እንሚገባቸው፣ በትንተናው ላይ በመመስረት የግብረመልስ
አሰጣጥ በምን አግባብ መከናወን እንዳለበት የሚመራ እንዲሁም በክትትልና ግምገማው የፌደራል ከተሞች
ፕላን ማስተባበሪያ ቢሮ፣ የክልል ከተማ ልማት ቢሮዎች፣ የክልል የከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማትና
ከተሞች ተቀናጅተው የሚሰሩበትን ሁኔታ የሚያሳይ ማኑዋል ይዘጋጃል፡፡

4.2. በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የሕበረተሰብ ተሳትፎ ማሳደግ

በከተማ ፕላን ዝግጅት ሂደት የህብረተሰቡን ፍላጎትና ችግሮች ከመለየት ጀምሮ ትኩረት የሚሹ የመፍትሄ
አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ሂደት ትክክለኛ መረጃንና ውሳኔዎችን በመስጠት ህብረተሰቡን በሚፈለገው
ደረጃ የማሳተፍ ልምድና ግንዛቤ የለም፡፡ በተለይም ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቢያንስ በውክልና
በማሳተፍ ችግርና ፍላጎቶቻቸውን በአግባቡ በፕላኑ ውስጥ እንዲንጸባረቅ የሚያደርግ አሰራር አልሰፈነም፡፡
በፕላን አፈጻጸም ሂደትም ቢሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ የለም ሊባል በሚችልበት ደረጃ ላይ መገኘቱ
በውሳኔ አሰጣጥ ላይም ተጽእኖ የማድረግ አቅም የሌለው በመሆኑ ህብረተሰቡ የባለቤትነት ድርሻውን
በሚገባ ሊወጣና ህገወጥ አስራሮችንም በጋራ ሊዋጋ አልቻለም፡፡

የህብረተሰቡ ተሳትፎ በሀገራችን በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ሊሆን ያልቻለባቸው በርካታ ምክንያቶች
አሉ፡፡ ለዚህም አንዱ እና ዋናው ምክንያት በተለያዩ የመንግስት/የአስተዳደር እርከኖች ላይ ያሉ አካላት
በተለይም በየከተሞች የሚገኙ ባለስልጣኖች እንዲሁም ባለሙያዎች አሳታፊነትን በተመለከተ ያላቸው
ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን ነው፡፡ ጊዜያዊና ቋሚ የተሳትፎ መድረኮች አለመኖር፣ ለሂደቱ በጀት አለመመደብ፣
በውይይትና በመድረክ አመራር የሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዲሁም የተሟላ የሕግ ማዕቀፍና የስራ
መመሪያዎች በሚፈለገው ደረጃ አለመኖር ሌሎች ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ በፕላን ዝግጅትና
አፈጻጸም ዙሪያ ተሳትፎን በማሳደግ ሕብረተሰቡ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ለማድረግ የሚከተሉት ስልቶች
ተነድፈዋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 126


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ስልት 4.2.1. የአስፈፃሚ አካላትን ግንዛቤ ማሳደግ

በተለያዩ የመንግስት/የአስተዳደር እርከኖች የሚገኙ ባለስልጣኖች ስለ ተሳትፎ ያላቸው ግንዛቤ ከፍ ካላለ


በስተቀር አሳታፊነት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ብሎ ለማሰብ ያስቸግራል። ስለሆነም
በተለይ ከንቲባዎችንና ሌሎች የከተማ ባለስልጣኖች በከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራ እንዲሁም
የሕብረተሰቡና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የሚጫወተውን ሚናና ከዚሁም ጋር ተያይዞ በዓለማችን
ስለተከሰተው አዲሱ አስተሳሰብ (paradigm shift) ግንዛቤ መፍጠርና ማዳበር ያስፈልጋል። በከተማ ፕላን
ዝግጅትና አፈፃፀም አሳታፊነትን ተግባራዊ ለማድረግ እና ትክክለኛው ግንዛቤ ለመፍጠር የአስፈጻሚ
አካላትን ግንዛቤ ማሳደግ በመንግስት በኩል ለሚፈለገው ቁርጠኝነትን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት
ይታመናል፡፡

ስልት 4.2.2. የፕላን ዝግጅትና ትግበራ በማዘጋጃ ቤት እንዲመራ ማድረግ

ፕላን በማንኛውም አካል ቢዘጋጅም ሂደቱን ከፕላን ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ፣ በዝግጅቱም ሆነ በትግበራ
ወቅት በባለቤትነት መምራት ያለበት ፕላኑ የሚዘጋጅለት የከተማ አስተዳደር/ማዘጋጃ ቤት ነው፡፡ በከተማ
ፕላን አዋጅ አንቀፅ 14 መሰረት የከተማ ፕላን ማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ የማድረግ ስልጣንና ተግባር
የተሰጠው ለከተሞች ነው፡፡ የአሳታፊነት ሂደቱንም ቀጣይነት ኖሮት ውጤታማ እንዲሆን ከመጀመሪያ
ጀምሮ በሀላፊነት ማደራጀትና መምራት ያለበት የከተማው አስተዳደር ሲሆን ፕላን የሚያዘጋጅ
ማንኛውም አካል መስተዳድሩ በሚያዘጋጀው መርሀ-ግብር/ፕሮግራም ውስጥ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
አስቀድሞ እንደሚደረገው የፕላን ዝግጅት ሂደቱ የሚመራው በሌላ ፕላን በሚያዘጋጅ አካል ከሆነ የተሳትፎ
ሂደቱ ቀጣይና ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡

ስልት 4.2.3. ቋሚና ጊዜያዊ የተሣትፎ መድረኮችን ማዘጋጀት/ማመቻቸት

የአሳታፊነት መሰረተ ሃሳብ የሚመነጨው ሕዝቡ የልማት ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ልማቱንም


የሚያመጣው እሱ መሆኑን ከማመን ነው። ስለሆነም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና ባለድርሻ አካላት
የሚሳተፉበትን መንገድ ለማረጋገጥ በተለይ በመሀከለኛ ከተሞች ተሳትፎን ቢያንስ በሁለት እርከን/ደረጃ
ማካሄድ ያስፈልጋል። ይህን ለማድረግ ቋሚና ጊዜያዊ መድረኮችን ማደራጀት የግድ ነው። በከፍተኛው
ወይንም በከተማ አቀፍ ደረጃ (Municipal Level) በብዙ ከተሞች ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ስላለና ህዝቡን
በሙሉ ማሳተፍ ስለማይቻል ተሳትፎ የሚደረገው በውክልና ነው። በመሆኑም በከተማ አቀፍ ደረጃ አንድ
ቋሚ የተወካዮች የውይይት መድረክ መቋቋም ያለበት ሲሆን በአብዛኛው ውይይቱ የሚደረገው በከተማ
አቀፍ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 127


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በዝቅተኛው ወይም በቀበሌ ደረጃ (Grassroot Level) ተሳትፎ አስፈላጊ ሲሆን በየአካባቢው ያለውን
ሕብረተሰብና የተለያዩ የሙያ ማህበራት አባላትም በማህበራቸው አማካኝነት ጊዜያዊ መድረኮችን
በየአካባቢው በማዘጋጀት ማሳተፍ ይገባል፡፡ በአካባቢ/ በቀበሌ/በማህበራት ደረጃ ተሳትፎ የሚደረግባቸው
ምክንያቶች መጀመርያ በፕላን ዝግጅቱ ሊታዩ የሚገባቸውን የአካባቢ ችግሮች ለመለየትና በፕላን
ትግበራውም ወቅት ፕሮጀክቶችን ለመከታተልና ለማስፈፀም ሲሆን በሁለተኛም ለከተማ አቀፉ መድረክ
ወኪሎችን ለመምረጥ ነው፡፡ በትላልቅ ከተሞች ተሳትፎን በሶስት (በከተማ አቀፍ፣ በዞን እና በቀበሌ ደረጃ)
ወይም ከዛ በላይ በሆኑ እርከኖች ማደራጀት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በፌዴራልና በክልል ደረጃ
የተሳትፎን ጉዳይ የሚከታተሉ አሀዶች/ዴስኮች ማቋቋም ያስፈልጋል፡፡

ስልት 4.2.4. ውይይቶችን የሚመሩ/የሚያሳልጡ ባለሞያዎች (Facilitators) ማሰልጠን

ውይይቶችን የሚመሩ/የሚያሳልጡ ሰዎችን (Facilitators) ማሰልጠን/ማዘጋጀት ቀላል የሚመስል ግን


ደግሞ ምንም ያልተሰራበትና ቁልፍ ከሚባሉት ተግባራት አንዱ ነው። አሳታፊነት በባሕሪው የተለያዩ
የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካተቱ በርካታ ውይይቶችን በማካሄድ ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ መጠን
በውይይት አካሄድ የሰለጠኑ ሰዎች የግድ ያስፈልጋሉ። በተለይ በከተማ አቀፍ ውይይቶች ላይ የከተማ
ከንቲባ ወይም ሌላ አመራር በአብዛኛው በውይይት መክፈቻና መዝጊያ ላይ የስነስርዓት ሚና ከመጫወት
በስተቀር ውይይቶችን መምራት የሚገባቸው አሳላጮቹ (Facilitators) ናቸው። ሁሉም ተሳታፊዎች
የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና ተሳታፊው ሳይሰላች ውይይቶች እንዲቋጩ
በማድረግ ረገድ የውይይት መሪዎች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። እነሱ በሌሉበት አሳታፊነትን ማካሄድ እጅግ
አስቸጋሪ ነው።

በዚህ ሞያ የሰለጠኑ ብዙ ሰዎች ቢያስፈልጉም አሁን ሊኖሩ የሚችሉት ምናልባትም ከጥቂት እንደማይዘሉ
መገመት ይቻላል። ስለሆነም በከተማ ፕላን ስራ አሳታፊነትን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ
ከተፈለገ በውይይት ማሳለጥ (facilitation) ሰፊ ስልጠና መስጠትን ይጠይቃል።

ስልት 4.2.5. ለተሳትፎው ሂደት በጀት መመደብ

ብዙ ጊዜ ስለአሳታፊነት ሲነሳ የጊዜና የገንዘብ/ሀብት ጉዳይ አይታሰብም፡፡ ሀቁ ግን አሳታፊነት ጊዜና ሀብት


ይጠይቃል፡፡ በሀገራችንም ለሕዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው የተቀናጀ የከተማ ልማት ፕላንን
(LDP) ዝግጅትና አፈፃፀም ተግባራዊ ለማድረግ በተሞከረበት ወቅት በከፊል አዲስ አስተሳሰብ በመሆኑ
ከግንዛቤ ማነስ የተነሳ ሂደቱ የሚጠይቀው ጊዜና ገንዘብ ግምት ውስጥ ገብቶ አያውቅም ነበር፡፡ ምንም
እንኳን በአንድ በኩል ለአሳታፊነት ሂደት የሚፈለገው ጊዜና ሀብት ቀላል ነው ባይባልም በሌላ በኩል ብዙ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 128


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ገንዘብና ጊዜ ፈሶባቸው ነገር ግን የአፈፃፀም ደረጃቸው ዝቅተኛ ከሆኑት ፕላኖች አንፃር የሚያስገኘው
ውጤት ሲታይ፤ የሚጠይቀው ሀብትና ጊዜ ምክንያታዊ ነው ለማለት ይቻላል፡፡

ምንም እንኳን ተሳትፎ ለራሱ ለሕብረተሰቡ ጥቅም ሲባል የሚደረግ ሂደት መሆኑን የሕብረተሰቡን ግንዛቤ
ማሳደግ መሰረታዊ ጉዳይ ቢሆንም፤ አሳታፊነት በባህሪው በተለያዩ ደረጃዎች በርካታ ውይይቶችን
(interactive discussions) ስለሚያስተናግድ ብዙ ቁሳቁስ ከማስፈለጉም በላይ ለመስተንግዶ፣
ለትራንስፖርትና በስብሰባ ምክንያት ከስራ ገበታቸው በመቅረታቸው ገቢ/ደሞዝ ለሚያጡ ቢያንስ
ለቀን/ዝቅተኛ ሰራተኞች ገቢ መተካትና የመሳሰሉት ወጪዎች ማስፈለጋቸው አይቀርም፡፡ ስለሆነም
የአሳታፊነት ሂደትን ተግባራዊ ለማድረግ በጀት መያዝ ግዴታ ይሆናል፡፡

ስልት 4.2.6. በስራ ላይ ያለውን የተሳትፎ ማኑዋል መከለስ

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተማ ፕላን፣ ፅዳትና ውበት ቢሮ አማካይነት የተዘጋጀው
የተሳትፎ መመሪያ (Participation Manual) ቢኖርም እሱን መከለስና በአካበቢ ቋንቋዎች ተርጉሞ
ተደራሽነታቸውን ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች መመሪያዎችንም በአካባቢ ቋንቋዎች
እንዲዘጋጁ ማድረግ የግንዛቤ ሽፋኑን ብቻ ሳይሆን የአሰራር ስልትንም ለማሳደግ ይረዳል፡፡

ስልት 4.2.7. ተሳትፎን በተመለከተ ደንብና መመሪያ ማዘጋጀት

ምንም እንኳን ጠቅለል ያሉ የፖሊሲና የሕግ ድንጋጌዎች ቢኖሩም በከፊልም ቢሆን ዝርዝር አንቀፆች
ወይንም ደንብና መመሪያ ባለመኖራቸው በአብዛኛው በከተማ ፕላን ስራ የአሳታፊነት ሂደት በተጨባጭና
በዘላቂነት ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም፡፡ ስለሆነም የከተማ ፕላን አዋጁ ሲከለስ ተጨማሪ አንቀፆች
መጨመርና እንዲሁም ተሳትፎን በተመለከተ ደንብና መመሪያ(ዎችን) ማውጣት የግድ ያስፈልጋል፡፡

5. በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ የማስፈጸም ብቃትን ማሳደግ

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፌዴራል እስከ ከተማ አስተዳደር ባለው አደረጃጀት የመሠረታዊ ካርታና ፕላን
ዝግጅትና አፈጻጸም አገልግሎቶችን በተቀላጠፈና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ
ለመስጠት እንዲቻል በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት ሁለንተናዊ የማስፈጸም ብቃት ሊኖራቸው ግድ ነው፡፡
የተቋማቱ የማስፈጸም ብቃት ወይም አቅም በመሰረታዊነት የሚገለጸው ቀልጣፋና ውጤታማ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 129


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አገልግሎቶችን በመስጠት የተገልጋዩን ሕብረተሰብ/አካላት ወይም የከተሞችን ፍላጎት ማርካት በመቻል


ሲሆን ይህም የሚሆነው እያንዳንዱ ተቋም በብዛትም ሆነ በጥራት በቂ የሆነና መልካም ስነምግባርና
አመለካከት ያለው የሰው ኃይል፣ ወጥ በሆነና ተናባቢነት ያለው አደረጃጀትና የአሰራር ስርዓት፣ በመረጃ
አያያዝና አደረጃጀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የጎለበተ የአፈጻጸም አቅም ሲኖረው ብቻ መሆኑ
ግልጽ ነው፡፡

በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም በከተሞች የሚታየውን ከሰው ኃይል፣ ከአደረጃጀት፣ ከቴክኖሎጂ ጋር
የተያያዙ የማስፈጸም አቅም ችግሮችን ለመፍታት የማስፈጸም ብቃትን ማሳደግ እንደ የስትራቴጂ
አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ይህ የስትራቴጂ አቅጣጫ በውስጡ ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን እነዚህን
ጉዳዮች ለማሳካት የሚያስችሉ ስልቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

5.1. ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት

በነባራዊ ሁኔታዎች ትንተና ከተለዩት ችግሮች መሀከል አንዱ በክልሎች ያሉ የፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም
ተቋማት ውስጥ የልምድና ክህሎት ማነስ እንደሆነና ይህም በሚዘጋጁ ፕላኖች ጥራት ላይ የራሱ የሆነ
አሉታዊ ተጽዕኖዎች እያሳደረ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከስነ ምግባር ጋር በተያያዘ መልኩ
በአመራሩና በባለሙያዎች በሚፈጠሩ ችግሮች የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶች በየከተሞቹ እየተከሰቱ
እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በባለሙያዎችና በአመራሩ መሀከል ያለውን የክህሎት ክፍተትና የስነ
ምግባር ችግሮች መፍታት ይቻል ዘንድ የሚከተሉት ስልቶቸ ተነድፈዋል፡፡

ስልት 5.1.1 የባለሙያን እውቀትና ክህሎት ማሳደግና ማቆየት

በመሠረታዊ ካርታና ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ላይ በተሰማሩ በየደረጃው ያሉ ተቋማት ውስጥ የሚገኘው
የሰው ሀይል በሚፈለገው መጠንም ሆነ ጥራት እንዲሟላ ይደረጋል፡፡ የሰው ኃይል እጥረት እንዲሁም
የእውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት በሚያስችል መልኩ በጥናት የተቃኘና መደበኛ የሆነ የሰው
ሃይል ልማት ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ መዘርጋት ይኖርበታል፡፡

እንደማናቸውም ታዳጊ ሀገሮች በሀገራችን በሚገኙ በከተማ ፕላን ላይ ትምህርትና ስልጠና የሚሰጡ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሰረታዊ ካርታና የከተማ ፕላን ዝግጅት ስርዓተ ትምህርት መከለስ ወይም
መለወጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህም በዚህ ወቅት በከተማ ፕላን አዘገጃጀትና አፈጻጸም ሥር ካሉት
ተግዳሮቶችና አዳዳስ ሀሳቦች ጋር አብሮ ለመጓዝ የሚያስችል ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ከዚሁ ጋርም የተቃኘ
ውጤታማ የክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ለነባርና ለአዳዲስ የመስኩ ባለሙያዎች በመስጠት የሙያ ብቃት
ማረጋገጫ የሚሰጥበት ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በየደረጃው ባሉ የመሰረታዊ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 130


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ካርታና የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ላይ የተሰማሩ ተቋማት በተዘጋጀላቸው ድርጅታዊ መዋቅር
መሰረት የሰው ሃይል ከማሟላት ጎን ለጎን ከስራው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ፣ ጥቅማጥቅምና
ማነቃቂያዎችን በማመቻቸትና የተመቻቸ የስራ አካባቢ በመፍጠር ባለሙያዎችን በስራ ላይ ማቆየት
የሚቻልበትን ሁኔታ መፈጠር አለበት፡፡

ስልት 5.1.2 ሙያዊ ሥነ-ምግባር ያለው አመራርና ባለሙያ ማፍራት

የፕላን ትግበራ ስትራቴጂ ሳይነደፍ ትግበራ ማካሄድ፣ በየጊዜው የዞኒንግ ለውጥ ማድረግ፣ የፖለቲካ
አመራሮች አላስፈላጊ የሆነ ጣልቃ ገብነትና ከካሳ ክፍያ ጋር የሚነሱ አብዛኞቹ ችግሮች ከፖለቲካ አመራር
እንዲሁም ከባለሙያዎች የአመለካካትና ስነ ምግባር ችግር ጋር ተያይዘው ከተጠቀሱ ችግሮች ዋነኞቹ
ናቸው፡፡

የከተማ ፕላን የከተሞቹን እድገት ጠቋሚ፣ መሪና ደንብ ማስከበሪያ መሆኑ ለማረጋገጥና በህግ/በፕላን
ሽፋን ለህገ-ወጥ የመሬት ሽንሸና፣ የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶችንና ለኪራይ ሰብሳቢነት መሳሪያ ሆኖ
ማገልገሉን ለማስቀረት የከተማ ፕላን አተገባበር አስገዳጅና የተጠያቂነት አሰራር ማስፈንና ሙያዊ ሥነ
ምግባር ያለው የፖለቲካ አመራርና ባለሙያ ማፍራት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ የክትትል ስርዓቱም በየደረጃው
ባለ የአስተዳዳር እርከን የሚከናወን ሲሆን የቀበሌውን፣ ወረዳ፣ የወረዳውን ክ/ከተማ፣ የክ/ከተማውን
ከተማ፣ የከተማውን ክልል፣ የክልልን ፌዴራል፣ የፌዴራል ከተሞች ለተወካዮች ም/ቤት ሪፖርት
የሚደረግበት አሰራርም ይፈጠራል፡፡ ለዚህም ቀጣይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና የመስጠትና
የህግ አስገዳጅነትን የማጠናከር ሰፊ ስራ ማከናወን ይጠበቃል፡፡

5.2. የቴክኖሎጂ እና መረጃ አቅርቦት ማሻሻል

በነባራዊ ሁኔታዎች ትንተና ከተለዩት ችግሮች መካከል በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ያለው
የቴክኖሎጂ አቅርቦትና አጠቃቀም ዝቅተኛ መሆኑ እንዲሁም በመረጃ አያያዝና ልውውጥ ላይ ከፍተኛ የሆነ
ክፍተት መኖሩ ሲሆን እነዚህም ችግሮች በሚዘጋጁ ፕላኖች ጥራትና መጥን ላይ የራሳቸው የሆነ አሉታዊ
ተጽዕኖዎች እያሳደሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ችግሮች በመፍታት በመጠንም ሆነ በጥራት
በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ለውጥ ማምጣት ይቻል ዘንድ የሚከተሉት ስልቶች ተነድፈዋል፡፡

ስልት 5.2.1 የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ልማትና አቅርቦትን ማሻሻል

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 131


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

እስከ አሁን ድረስ ስንከተለው የነበረውን የቅየሳ አፈጻጻምና የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት አሰራር ሥር ነቀል
በሆነ መልኩ ለመቀየርና እምርታዊ ውጤት ለማስመዝገብ ዘመኑ ያፈራቸውን የቅየሳ መሳሪያዎች እና
ለመሠረታዊ ካርታ ዝግጅት ወሳኝ የሆኑ የቴክኖሎጂዎች ግብዓት አቅርቦትን አቅም በፈቀደ መልኩ ማሻሻል
የስትራቴጂው ማስፈጸሚያ አንዱ መንገድ ሆኖ ተቀይሷል፡፡

በመሆኑም የህዝብ ቁጥራቸው ከ 20,000 በታች ለሆኑ አነስተኛ ከተሞች እና ከ 20,000 በላይ የህዝብ
ቁጥር ላላቸው ከተሞች የመሠረታዊ ካርታ ዝግጅትና አጠቃቀም አጋዥ የሚሆን የሳተላይት ምስልና
የአየር ፎቶግራፍ ግዥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በእነዚሁ ከተሞች ውስጥ አዲስ
ለሚመሰረቱ የአግድመትና የከፍታ የቅየሳ መቆጣጠርያ ነጥቦች የማስፋፋት ሥራ እና የሳተላይት ምስል
መረጃዎችን በምድር ላይ በትክክል መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚያገለግል ዘመናዊ GNNS Receivers
GPS ግዥ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የከተሞችን አቅም ባገናዘበ መልኩ የመሬት ላይ ቅየሳ
በማከናወን መሰረታዊ ካርታ እንዲዘጋጅ የቶታል ስቴሽን የቅየሳ መሳሪያ ግዥ ተፈጽሞ ከተሞች
እንዲደገፉ ይደረጋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለሳተላይት ምስል እና የአየር ፎቶግራፍ ትርጎማና መሠረታዊ
ካርታ ዝግጅትና አጠቃቀም አስፈላጊ የሆኑ የሀርድዌርና ሶፍትዌር ግዥ በመፈጸም በየደረጃው በመስኩ
ለተሰማሩ ተቋማት ድጋፍ ማድረግና አቅማቸውን ለማጠናከር ጥረት ይደረጋል፡፡

ይህን ስልት ለማስተግበር ለአነስተኛ ከተሞች የሳተላይት ምስል፣ ለትላለቅ ከተሞች የአየር ፎቶግራፍ፣
ይህን ሥራ ለሚያከናውኑ የክልልና ፌዴራል ተቋማት የትርጉም ሀርድዌርና ሶፍትዌር መሳሪያዎች ግዥ
በመፈጸም ድጋፍ ይደረጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዲጅታል መሠረታዊ ካርታ ዝግጅትና አጠቃቀምን
ለማጠናከር ከክልልና ፌዴራል ተቋማት ለተውጣጡ በመስኩ ለተሰማሩ ባለሙያዎች በቴክኖሎጂዎቹና
መሳሪያዎቹ አጠቃቀምና አያያዝ ላይ የስልጠና ድጋፍ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ለከተማ ፕላን ዝግጅት
አስፈላጊ በሆኑ የ GIS ሶፈትዎሮች ላይ ለክልል የከተማ ፕላን ባለሙያዎች /Architect or Urban
Planners, Surveyors, Draft Persons/ ስልጠና ይሰጣል፡፡

ስልት 5.2.2. ቋሚ የመረጃ አያያዝ፣ አደረጃጀትና ልውውጥ ስርዓት መፍጠር

ከፌደራል ጀምሮ እስከ ከተሞች ድረስ ባሉና በኘላን ዝግጅትና አፈፃፀም ተሳታፊ በሆኑ ባለድርሻ አካላት
መካከል በዳታቤዝ ማናጅመንት ዘዴ (Database Management System) የተቃኘና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ
የታገዘ የመረጃ አደረጃጀት፣ አያያዝና ልውውጥ ስርአት በመዘርጋት የመሠረታዊ ካርታና ከተማ ፕላን
መረጃ ህግን መሰረት አድርጎ በቀላሉና በአጭር ጊዜ ለተጠቃሚው ተደራሽ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ ይህንኑ
ስልት ተግባራዊ ለማድረግ ሞዴል አደረጃጀት በማዘጋጀት፣ በሞዴል አደረጃጀቱ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ሥራዎችን በማከናወን አደረጃጀቱ ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 132


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

5.3. የተሟላ ተቋማዊ አደረጃጀት መዘርጋት

ይህ ግብ ከላይ ለመሰረታዊ ካርታ፣ ለፕላን ዝግጅት፣ ለፕላን ትግበራ እንዲሁም ለክትትልና ግምገማ
የሚያስፈልጉትን አደረጃጀቶችን የሚመለከት ሲሆን በመሠረታዊ ካርታና ፕላን ዝግጅት አፈጻጸም
ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት በዘርፉ ያሉትን ተቋማት አደረጃጀት ላይ ተገቢውን ማስተካከያ
በማድረግ በፕላን ዝግጅት፣ ትግበራ እና ክትትልና ግምገማ አሰፈላጊና ሊያሰሩ የሚችሉ አደረጃጀቶችን
እስከታችኛው እርከን /ከተሞች/ ድረስ መዘርጋት አስፈላጊ ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ በየደረጃው ያሉ ተቋማት እንደየራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አሻሽለው ሊጠቀሙበት


የሚችሉት ሞዴል አደረጃጀት ማዘጋጀት፣ ሞዴል አደረጃጀቱን በማወያየት ተግባራዊ የሚሆንበትን ሁኔታ
ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 133


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ክፍል ሶስት - ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

በከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ
ስትራቴጂው ወደ መሬት በማውረድ መተግበር አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም ስትራቴጂውን ተግባራዊ
ለማድረግ መከናወን ያለባቸውን ዋና ዋና ተግባራትን መለየት፣ በትግበራው ወቅት የባለድርሻ አካላት
የሚኖራቸውን ሚና መለየት፣ የትኛው ተግባር መቼ መከናወን እንዳለበት ማስቀመጥ፣ የስትራቴጂው
አፈጻጸምን መከታተልና የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስፈልግ ሲሆን እነዚህም
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1. ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚከናወኑ ተግባራት

ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ መከናወን ከሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት መሀከል ሀገር አቀፍ የአውደ
ጥናት መድረኮንችን በማዘጋጀት ማስተዋወቅና ማዳበር፣ ሰነዱ የመጨረሻውን ቅርጽ ከያዘ በኋላ
ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት፣ በየክልሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት እንዴት
ስትራቴጂውን መተግበር እንዳለባችው ውይይት ማካሄድ፣ ስልጠናም መስጠት፡፡ ስትራቴጂው የሚዲያ
ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ፣ ፕሮጀክት ሊቀረጽላቸው የሚገባ ስልቶችን በመለየት ፕሮጀክቶችን
በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ፣ ለፕሮጀክት ትግበራ የሚሆን በጀት ማፈላለግ፣ አፈጻጸሙ ላይ ክትትልና
ግምገማ በማድረግ የማስተካከያ ስራዎችን ማከናወን ናቸው፡፡

2. በስትራቴጂው አፈጻጸም የባለድርሻ አካላት ሚና

በስትራቴጂው አፈጻጸም ላይ ከሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት መካከል ዋንኞቹ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን
ሚኒስቴር፣ የክልል መስተዳድሮች፣ የክልል ከተማ ልማት ቢሮዎች፣ የክልል ከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማት
እና ከተሞች ናቸው፡፡

በመሆኑም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኩል የከተሞች ፕላን፣ ጽዳትና ውበት ቢሮ
አማካኝነት ሰነዱ የመጨረሻ ቅርጹን ከያዘ በኋላ ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት፣ የአውደ ጥናት
መድረኮችን በሀገር አቀፍና ክልል ደረጃ በማካሄድ ስትራቴጂውን እንዴት መተግበር እንዳለባችው ስልጠና
ነክ ውይይቶችን ማካሄድ፣ ስትራቴጂው የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ እና በስትራቴጂው አፈጻጸም
ላይ ክትትልና ግምገማ ማድረግ ናቸው፡፡

የክልል ከተማ ልማት ቢሮዎች እና የከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማት በጋራ በመሆን በስትራቴጂ ሰነዱ
የተለዩትን ግቦች ተግባራዊ ለማድረግ የተቀመጡ ስልቶችን ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስችሉ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 134


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ፕሮጀክቶችንና ዝርዝር ተግባራትን ማዘጋጀት እና መተግበር የሚጠበቅባቸው ሲሆን የክልል መስተዳድሮች


ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን / የሰው ሀይል፣ በጀት/ ማሟላት
የሚጠበቅባቸው ሚና ነው፡፡ ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ የክልል ከተማ ልማት ቢሮዎች የስትራቴጂ
ሰነዱን በክልላቸው ውስጥ ማስተዋወቅ፣ በስትራቴጂው ትግበራ ላይ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ የስትራቴጂ
ትግበራ ውጤት የሆኑ ሰነዶችን ማሰራጨትና ማስተዋወቅ እንዲሁም በስትራቴጂው መሰረት በክልል ደረጃ
ክለሳ የሚያስፈልጋቸውን ከከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ጋር ተያያዥ የሆኑ አደረጃጀቶችን መከለስ
የሚጠበቅባቸው ሲሆን የክልል ከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማት ደግሞ የስትራቴጂው ትግበራ ውጤት በሆኑ
ሰነዶች ማለትም ስታንዳርዶች፣ ማኑዋሎች ወዘተ መሰረት ያደረጉ ፕላኖችን ማዘጋጀትና ተመሳሳይ
ስራዎችን ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡

በስትራቴጂ ሰነዱ ትግበራ ላይ ከተሞች የሚኖራቸው ሚና መዋቅራዊ ፕላኑን ተግባራዊ ለማድረግ


የሚያስፈልጉ አደረጃጀቶችን መፍጠር ሲሆን እነዚህም ዝርዝር ፕላኖችን የሚያዘጋጅና በፕላኑ መሰረት
ትግበራ እየተካሄደ መሆኑን የሚከታተልና ሪፖርት የሚያደርግ ክፍል/ቡድን እና በተዘጋጀው ዝርዝር ፕላን
መሰረት ትግበራ የሚያካሂድ /መሬት ማዘጋጀት፣ መሬትና የግንባታ ፍቃድ መስጠት፣ ግንባታውን መከታተል
ወዘተ…/ ክፍል/ቡድን ማቋቋም ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሚቋቋሙት ቡድኖች ስራቸውን በዚህ
የስትራቴጂ ሰነድ ውጤት በሚሆኑት ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ማኑዋሎችና ስታንዳርዶች መሰረት ማከናወን
ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልገው ጊዜ

ይህ የስትራቴጂ ሰነድ የተዘጋጀው የክፍለ ኢኮኖሚውን የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
ለማሳካት በመሆኑ ጠቅለል ባለመልኩ የስትራቴጂ ሰነዱ ከሶስት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እስከ 2006
ዓ/ም ድረስ ተግባራዊ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን ዝርዝር የጊዜ መርሀ ግብሩ በዚህ ሰነድ ዕዝል ስር
ተቀምጧል፡፡

4. የስትራቴጂው አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ

የከተማ ፕላን ስትራቴጂው ትግበራ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆኑን ለማረጋገጥ እንዲሁም መሰናክሎች
ካጋጠሙት በሰዓቱ የማስተካከያ እርምቻዎችን መውሰድ ይቻል ዘንድ አፈጻጸሙ ላይ ክትትልና ግምገማ
ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ በፌዴራል፣ በክልል እና በከተሞች ያሉ በስትራቴጂው
ትግበራ ላይ ሚና ያላቸው የባለድርሻ አካላት በዋና ስራዎቻቸው እቅድ ውስጥ የክትትልና ግምገማ
ስራዎችን በማካተት በየደረጃቸው በስትራቴጂው ትግበራ ክትትልና ግመገማ ላይ መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 135


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በክትትልና ግምገማው የሚሳተፉት አካላት ከላይ የተገለጹት ሲሆኑ የክትትልና ግምገማ ስራን ለማከናወን
መረጃዎችን በየጊዜው በመሰብሰብ መተንተንና ክፍተቶችን መለየት ያስፈልጋል፡፡ ለክትትልና ግምገማ
የሚያስፈልጉ መረጃዎችን መለየት በመጀመሪያ መከናወን ያለበት ተግባር ሲሆን በቅድሚያ ክትትልና
ግምገማ የሚካሄድባቸውን ስራዎች መለየት፣ የስራዎቹን ውጤቶች መለየት፣ የእያንዳንዱን ስራ ውጤት
ከመጠን አንጻር በሚለካ መልኩ ማሰቀመጥ፣ እያንዳንዱ ስራ የሚጠይቀውን ጊዜ /ከተቻለ ወጪና ጥራት/
ማስቀመጥና በዚሁ መሰረት በነዚህ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን መሰብሰብ /በየወሩ፣ በየሩብ ዓመቱ፣
በየመንፈቁ እና በየዓመቱ/ አለበት፡፡

መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ መልክ ባለው ሁኔታ በማደራጀት ትንተና ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆን
የተሰበሰቡት መረጃዎች ከመጠን፣ ከጊዜ እንዲሁም የሚያስኬድ ከሆነ ከጥራትና ወጪ አንጻር የትግበራውን
የአፈጻጸም ሁኔታ ወይንም አፈጻጸሙ የሚገኝበትን ደረጃ የሚጠቁሙ በመሆኑ ነበራዊውን የአፈጻጸም
ሁኔታ በእቅድ ከመጠን፣ ከጊዜ፣ ከጥራትና ወጪ አንጻር ከተቀመጠው ጋር በማነጻጸር ክፍተቶችን መለየት
ይቻላል፡፡ ከዚያም በተለዩት ክፍተቶች ላይ በመመስረት በግበረ መልስ መልክ የማስተካከያ እርምጃዎችን
በመውሰድ የስትራቴጂ ትግበራውን ማሳካት ይቻላል፡፡

ክፍል አራት - ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚያስፈልግ የአደረጃጀትና


የአመራር ስርዓት
1. ሊያሰራ የሚችል ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር

ሀ. የከተማ ፕላን ዝግጅት አደረጃጀትን አሁን ካለበት በተሻለ መልኩ ያልተማከለ ማድረግ

የከተማ ፕላን ዝግጅት በአገሪቱ ከተጀመረ አንስቶ ለበርካታ ዓመታት የከተሞች ፕላን ዝግጅት ይከናወን
የነበረው በማዕከል በመሆኑ በሀገሪቱ ውስጥ በዓመት ፕላን የሚዘጋጅላቸው ከተሞች ብዛት በጣም አነስተኛ
ነበር፡፡ በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክልሎች የየከተሞቻቸውን ፕላኖች እንዲያዘጋጁ በመደረጉ በአመት
በርካታ ፕላኖችን ለማዘጋጀት ተችሏል፡፡ ሆኖም አሁንም በሚፈለገው መልኩ የከተሞች ፕላን ሽፋንን
ማሳደግ ባለመቻሉ ሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ ለማድረግ እንዲሁም ከፕላን
አፈጻጸም/አተገባበር ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ይቻል ዘንድ በክልል ደረጃ ያለውን የፕላን
ዝግጅት አደረጃጀት ያልተማከለ በማድረግ በዞን ደረጃ እንዲሁም በሂደት በወረዳ እና በመጨረሻም
በከተሞች ደረጃ እንዲወርድ መደረግ አለበት፡፡

ለ. የመዋቅራዊ ፕላን ትግበራ ዝርዝር ፕላን ዝግጅት ቋሚ አደረጃጀት መፍጠር

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 136


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

የመዋቅራዊ ፕላን ተግባራዊ የሚሆነው የአካባቢ ልማት ፕላንና የሽንሻኖ ፕላኖችን በማዘጋጀት እንደሆነ
ይታወቃል፡፡ ሆኖም በአገሪቱ እየተዘጋጁ የሚገኙት በማንኛውም አካል የሚዘጋጁ የመዋቅራዊ ፕላኖች
ከሁለት ላልበለጡ የከተማ አካባቢዎች ብቻ የአካባቢ ልማት ፕላን በማዘጋጀት ቀሪውን በከተማ
አስተዳደሮች አማካኝነት እንዲዘጋጁ ይተዋሉ፡፡ ሆኖም ግን ከፕላን አፈፃፀም አኳያ አብዛኛዎቹ ከተሞች
ከሰው ሀይል አንጻር ሲታይ በመሀከላቸው ልዩነት ያለ ሲሆን በተለይ በአገሪቱ ከተሞች ውስጥ በቁጥራቸው
ትልቁን ድርሻ በሚይዙት በአነስተኛ ከተሞች ላይ ችግሩ የጎላ እንደሆነ በሚ/ር መ/ቤቱ አማካኝነት
የተካሄዱ የፕላን አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡ ስለዚህ ለከተማ ፕላን ትግበራ
ዝርዝር ፕላኖችን የሚያዘጋጅ አካል ወይም መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስራዎችን ማከናወንና አደረጃጀቱ ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም በመዋቅሩ የሚኖረው የሰው
ኃይል የላቀና የተሟላ ዕውቀት እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 137


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ሐ. የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ቋሚ አደረጃጀት መፍጠር

የመሬት ዝግጅትና አቅርቦት ከሚያካትታቸው ስራዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ በተዘጋጁ ዝርዝር ፕላኖች
መሰረት የመሬት ላይ ቅየሳ ስራዎችን ማካሄድ፣ አስፈላጊ መሰረተ ልማት አውታሮችን ማቅረብ እና
ለአልሚ ቦታ መስጠት ናቸው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የስራ መደራረብን ከመቀነስ እና
የፕላኖችን ትግበራ/አፋጻጸም ከመከታተል አንጻር የዝርዝር ፕላን ዝግጅቱና የመሬት አቅርቦቱን በተለያዩ
አካላት ማከናወን አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም የመሬት ላይ ቅየሳ ስራዎችን፣ የመሰረተ ልማት አውታሮች
አቅርቦትና ለአልሚ ቦታ የመስጠት ስራዎችን የሚያከናውን አካል ወይም ተቋማዊ አደረጃጀት ይፈጠራል፣
አደረጃጀቱን የሚመለከት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነትም ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡

መ. የፕላን አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ቋሚ አደረጃጀት መፍጠር

በከተማ ፕላን ትግበራ ጊዜ የሚፈጠሩ ቴክኒካዊ ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃዎችን


ለመውሰድ እንዲሁም በፕላን ላይ የተቀመጡ የመሬት አጠቃቀም ጥሰቶችን ለመከላከልና ተጥሰውም
ሲገኙ ህጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ይቻል ዘንድ የፕላን አፈጻጸም ጠንካራ የክትትልና ግምገማ ስራዎች
ያስፈልጉታል፡፡

በመሆኑም በፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ለሚታቀዱ ግቦች እና በየደረጃው ለሚሰጡ አገልግሎቶች
ስኬታማነት የክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ ሥራን የሚያከናውን ከፌደራል እስከ ከተማ ተናባቢና
በቅንጅትና በጋራ ኃላፊነት የሚሠራ ቋሚ አደረጃጀት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡

2. የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ክፍተቶችን ማሟላትና ተፈጻሚነታቸውን መከታተል


ሀ. እየተሰራባቸው የሚገኙትን አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎች መከለስ

ለከተሞች ፕላን ጥራት ዝቅተኛ መሆን ከሚጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ በከተማ ፕላን
አዋጁ ያልተካተቱ ጉዳዮች መኖራቸው እንዲሁም ጠቅለል ባለ ሁኔታ የተካተቱ ቢኖሩም በደንብና መመሪያ
በዝርዝር ሊብራሩ የሚገባቸው ጉዳዮች ደንብና መመሪያ ያልተዘጋጀላቸው መሆኑ፣ እየተሰራባቸው ያሉ
የከተማ ፕላን ማኑዋሎችና ስታንዳርዶች የተሟሉና ግልጽ አለመሆናቸው ሲሆኑ እነዚህን አዋጅ፣ ደንብ፣
መመሪያ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎች በመከለስ የከተሞች ፕላን ጥራት እንዲጠበቅ ይደረጋል፡፡

ለ. የመዋቅራዊ ፕላን የማስፈጸሚያ ስልት ማዘጋጀት


የመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት ከተጠናቀቀ በኋላ የማስፈጸሚያ ስልት በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባት
የተለመደ አይደለም፡፡ በአብዛኛው የአገሪቱ ከተሞች ትግበራ የሚካሄደው ለትግበራው አስፈላጊ የሆኑ
የማስፈጸሚያ ስልቶች ባልተዘጋጁበት ሁኔታ ነው፡፡ የማስፈጸሚያ ስልቶች ከሚያካትቷቸው ዋና ዋና
ስራዎች መሀከል ስትራክቸር ፕላኑን ማስተግበሪያ የአካባቢ ልማት ፕላን/ለነባር አካባቢና ለመስፋፊያ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 138


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

አካባቢ/፣ የአካባቢ ልማት ፕላኖች በብሎክ ደረጃ ስለሚዘጋጁ ዝርዝር የሽንሻኖ ፕላን፣ ለትላልቅ ከተሞች
የከተማ ዲዛይን ፕላን፣ የፌዚንግ ፕላን፣ የሽንሻኖ ስታንዳርድ፤ የሽንሻኖ ማኑዋል፣ የድርጊት መርሀ ግብር
ሲሆኑ እነዚህን በጥናትና በምርምር አስደግፎ በማዘጋጀትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን
የከተማ ፕላን ትግበራ እንዲሻሻል ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ጎን ለጎን የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት
ፕላኖች ያለመናበብ ችግርን እንዲሁም ከመኖሪያ ቤቶች ጋር ተቀይጠው አገልግሎት እንዲሰጡ በተፈቀዱ
የንግድና ማምረቻ አገልግሎቶች ሰበብ አልፎ አልፎ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የሚፈጠር የድምጽ፣ የሽታ
እና ሌሎችም ተያያዥ ችግሮችን ለመፍታት የአካባቢ ልማት ፕላን ማኑዋሉን በመከለስ ለእነዚህ ችግሮች
ትኩረት እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

በመስፋፊያ ቦታዎችና መልሰው በሚለሙ ነባር ቦታዎች ላይ የመሬት ዝግጅት ከተከናወነ በኋላ የተቀናጀ
የመሰረተ ልማት አቅርቦት ስራዎች ይከናወናሉ እንዲሁም በተዘጋጀው ፕላን መሰረት የቦታ አቅርቦት እና
የግንባታ ፍቃድ የመስጠት ስራዎች ይሰራሉ፡፡ በተጨማሪም በፕላን ላይ ለተለያዩ አገልግሎት የሚያዙ
ቦታዎችን በተገቢው ጊዜ ማልማት ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት በፕላን ላይ የተያዘላቸውን ቦታ
የማሳወቅና ሳይት ፕላኑን የመስጠት ስራዎች ይከናወናሉ፡፡

ሐ. የክትትል፣ ግምገማና ግብረመልስ ማኑዋል ማዘጋጀት

የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ለማከናውን የሚያስፈልጉ መረጃዎች የትኞቹ እንደሆኑና እንዴት መሰብሰብ
እንዳለባቸው፣ መረጃዎቹ እንዴት መተንተን እንሚገባቸው፣ በትንተናው ላይ በመመስረት የግብረ-መልስ
አሰጣጥ በምን አግባብ መከናወን እንዳለበት የሚመራ እንዲሁም በክትትልና ግምገማው የፌደራል ከተሞች
ፕላን ማስተባበሪያ ቢሮ፣ የክልል ከተማ ልማት ቢሮዎች ፣ የክልል የከተማ ፕላን ዝግጅት ተቋማትና
ከተሞች ተቀናጅተው የሚሰሩበትን ሁኔታ የሚያሳይ ማኑዋል ይዘጋጃል፡፡

III. ማጠቃለያ

ባለፉት ተከታታይ አመታት በአገራችን እየተመዘገበ ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የከተማ- ገጠርንና
የከተማ- ከተማ ትስስርን በማጠናከር ረገድ ያለው አውንታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም
ከተሞቻችን ይህን ፈጣን ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ እና የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ
ለማስቻል የከተሞቻችንን ዕድገት አቅጣጫና የአከታተም ሥርዓት ካላቸው ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብትና
ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ አንጻር በመቃኘት በፕላን እንዲመሩ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ውጤቱም
ከተሞቻችን በዘላቂነት የአካባቢው የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የገበያ፣ የኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት፣ የባህልና
ቴክኖሎጂ ማዕከልነታቸውንና የእርስ በእርስ ተወዳዳሪነታቸውን ማስቀጠል ይሆናል፡፡ ይሁንና እስካሁን
ድረስ ከተሞቻችን በፕላን እንዲመሩ በተወሰነ ደረጃ ጥረት ቢኖርም ሂደቱ የራሱ የሆኑ ክፍተቶች ያሉበት

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 139


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

መሆኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተረጋግጧል፡፡ ከነዚህም መካከል በአገር አቀፍ ደረጃ ከተሞች ወጥ በሆነ
የከተማ ፕላን ዝግጅት ባለመመራታቸውና በትግበራ ወቅትም የክትትልና ግምገማ ስርዓቱ ደካማና
በመደበኝነት ተጠያቂነትን በሚያሰፍን መልኩ የሚከናወን ባለመሆኑ የመሬት አጠቃቀሙ በፕላኑ ላይ
በተቀመጠው መልክ ሳይሆን በዘፈቀደ ተግባራዊ ሲደረግና የፕላን ጥሰቶች ሲፈጸሙ ይሰተዋላል፡፡ ይህ
ደግሞ የከተሞቻችንን ገፅታ ከማበላሸቱም በላይ የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎትና ተጠቃሚነት ባለረጋገጠ
መልኩ እንዲሁም የከተሞችን ተጨባጭ የዕድገት አቅጣጫ የማያመላክት ከመሆኑም ባሻገር ውጤታማና
ዘላቂ የመሬት አጠቃቀም እንዳይኖር ማነቆ ሆኗል፡፡

በተጨማሪም ከኢኮኖሚ ዕድገቱ ጋር ተያይዞ “የነገዎቹ ከተሞች” የሚባሉት የገጠር ማዕከላት በቁጥርም
ሆነ በመጠን መበራከት እና በፕላን ልማታቸውን የመምራት ፍልጎት መኖሩ እንደ መልካም አጋጣሚ
የሚወሰድ ቢሆንም ፈጣንና ዘላቂ ምላሽ ባለመሰጠቱ በአገር አቀፍ ደረጃ የከተማ- ከተማ እና የከተማ-
ገጠር ትስስር በሚፈለገው ደረጃ ላይ እንዳይገኝ አድርጎታል፡፡ በአንጻሩ ይህንን ፍላጎት ለማሳካት በሁሉም
ከተሞቻችን የአቅም ውስንነት በሰፊው ይታያል፡፡ በሌላ በኩል ፕላን የተሰራላቸው ከተሞቻችንም ፕላኑን
ከመተግበር አንፃር የአመለካከት እና ኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ መኖር ከማስፈጸም አቅም ውሱንነት ጋር
ተዳምረው ፕላኑ በታቀደው መሠረት ተግባራዊ እንዳይሆንና ሕገ ወጥ ግንባታዎች እንዲበራከቱ በር
ከፍቷል፡፡ እነዚህን ጥሰቶች ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራና ተፈጻሚነት ያለው የሕግ ማዕቀፍ፣ ተናባቢና
ጠንካራ የሆነ ያልተማከለ ተቋማዊ አደረጃጀትና ደረጃውን የጠበቀ የአሰራር ስርዓት አለመኖሩ ለክፈተቶቹ
መፈጠር አጋዥ ኃይል ሆነዋል፡፡

በመሆኑም መንግስት እነዚህን ችግሮች መኖራቸውን አስቀድሞ በመገንዘቡ ችግሮቹን ስርነቀል በሆነ መልኩ
ለመቀየር የፖሊሲ፣ የስትራቴጂ፣ የህግ ማዕቀፍ፣ የማስፈጸም አቅም ግንባታና የአሰራር ስርዓትን በዚህ
ጥናት መነሻነት በማመላከት በዘርፉ እምርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙትን
የባለድርሻ አካላት ሚናን በለየ መልኩ መፍትሄ አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ የከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራው
ከተሞቻችን አገሪቱ የነደፈችውን ግዙፍ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ውጤታማነትን ለማስተናገድ
በሚችሉበት ቁመና ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ በዘርፉ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡ የሚዘረጋው አሰራር
ስርዓት ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ በግልጽ የህግ ማዕቀፍ፣ ጠንካራ፣ ተናባቢና ያልተማከለ አደረጃጀት እና
አስተማማኝ የማስፈጸም አቅምን በመገንባት ከተሞቻችን ዘላቂ የልማትና የመልካም አስተዳደር ማዕከል
እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅትም የከተማው ክልል የመሬት ሀብት አሳታፊ በሆነ መልኩ
ተለይቶና ታወቆ ፕላኑ እንዲዘጋጅና ነዋሪዎች በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች እንዲያውቁት በማድረግ የፕላን
አፈጻጸሙ የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎትና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ የፕላን ዝግጅቱ
የተመጣጠነና የተቀናጀ ብሄራዊ፣ ክልላዊና አካባቢያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ እንዲያስችል የከተማ ፕላን
ተዋረድን (ደረጃን) እና ዓይነትን ተናባቢነትን ያረጋገጠ ሆኖ አፈጻጸሙም የሶሺዮ ስፓሻል ጉዳዮችን

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 140


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

በቅንጅት የሚፈታ ይሆናል፡፡ በየጊዜው በመጠንና ቁጥር እያደገ ከመጣው ከከተሞቻችን አሀዝ ጋር
የተጣጣመ የፕላን ዝግጅት እንዲኖር በየደረጃው ያለው የመንግሥት መዋቅርን በሰው ሀይል፣
በአመለካከትና በግብዓት አቅርቦት በማጠናከር የከተሞች ፕላን በጥራት ለሁሉም ከተሞች ተደራሽ
ይደረጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በፕላን ዝግጅት ላይ የግል ዘርፉንና ባለሙያዎችን በአሀድ በማደራጀትና
ተከታታይ የአቅም ግንባታ ድጋፎችን በመስጠት ሁሉም ከተሞቻችን በፕላን እንዲመሩ ይደረጋል፡፡

ዕዝል - የስትራቴጂ አፈጻጸሙ መርሀ ግብር

ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት ፈጻሚ አካል ጊዜ የሚጠበቀው ውጤት


1 ሀገር አቀፍ የአውደ ጥናት መድረክ የፌደራል የከተማ ፕላን፣ የ 2004 ዓ.ም 3 ኛ በየደረጃው ግንዛቤ ያገኙ
በማዘጋጀት ሰነዱን ማስተዋወቅ ፅዳትና ውበት ቢሮ ሩብ ዓመት የከተሞችና የከተማ
ልማት/ፕላን ተቋማት
ሀላፊዎችና ባለሙያዎች

2 ሰነዱ የመጨረሻውን ቅርጽ ከያዘ የፌደራል የከተማ ፕላን፣ የ 2004 ዓ.ም 3 ኛ ተባዝተው የተሰራጩ
በኋላ ማሳተምና ፅዳትና ውበት ቢሮ ሩብ ዓመት የስትራቴጂ ሰነዶች
ለሚመለከታቸው አካላት
ማሰራጨት
3 በየክልሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ የክልል ከተማ ልማት የ 2004 ዓ.ም 4 ኛ የተዘጋጁ የግንዛቤ
መድረኮችን በማዘጋጀት እንዴት ቢሮዎችና ፌደራል የከተማ ሩብ ዓመት ማስጨበጫ መድረኮች
ስትራቴጂውን መተግበር ፕላን፣ ፅዳትና ውበት ቢሮ
እንዳለባችው ውይይት ማካሄድ
4 ፕሮጀክት ሊቀረጽላቸው የሚገባ የክልል ከተማ ልማት የ 2004 ዓ.ም 4 ኛ የተለያዩ የፕሮጀክት
ስልቶችን በመለየት ፕሮጀክቶችን ቢሮዎችና የከተማ ፕላን ሩብ ዓመት ሰነዶች
ማዘጋጀት ተቋማት
5 ፕሮጀክቶችን መተግበር የክልል ከተማ ልማት እስከ 2006 ዓ.ም የተተገበሩ ፕሮጀክቶች
ቢሮዎች፣ ከተማ ፕላን መጨረሻ
ተቋማትና ከተሞች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 141


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

6 አፈጻጸሙ ላይ ክትትልና ግምገማ የፌዴራልና ክልል ተቋማት በቀጣይ የክትትልና ግምገማ


በማድረግ የማስተካከያ ስራዎችን የሚከናወን ሰነዶችና የተሰጡ ግብረ
ማከናወን መልሶች

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 142


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

ዋቢ ሰነዶች
Ministry of Works and Urban Development(MWUD) (2008). “Integrated Housing
Development Programme of the Federal Democratic Republic of Ethiopia”, African
Ministerial Conference on Housing and Urban Development, AMCHUD, held in Abuja,
Nigeria, 28-30 July

Federal Urban Planning Institute ( FUPI)(2009). Participation Manual for Urban Planning,
Ministry of Urban Development and Construction, Addis Abeba

Federal Urban Plann Coordinating Bureau ( FUPCB)(2011). Manual on Stamdard and Norms
for Urban Planning (Draft Manual), Ministry of Urban Development and Construction,
Addis Abeba

Lyon Town Planning Agency (LTPA) (2010). Evaluation of the Master Plan (2001-2010),
Addis Abeba, City Government of Addis Abeba, Addis Abeba.

Office for the Revision of the Addis Ababa Master Plan (ORAAMP)(2000). Assessment of
Addis Ababa’s Housing Sector, Key Areas of Intervention, Strategies &Policy Measures
for a Housing Policy, (Draft report), Addis Ababa.

-----------------------(2000). Road and Utility Lines Construction Standard-Preliminary


Proposal, unpublished, Municipality of A.A, Addis Ababa.

-----------------------(2000). Summary Report on the Urban Transport and Road Network of


Addis Abeba

-----------------------(2001). Housing Component, Improvement and Development Strategy:


Guidelines, Regulations, Norms and Standards, Addis Ababa.

-----------------------(2002). Project Proposal for Addis Ababa Transport Sector, Municipality


of A.A, Addis Ababa.

-----------------------(2002). Addis Ababa City Road Network (Final Draft), Addis Abeba.

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 143


የከተማ መሬት አጠቃቀም ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ስትራቴጂ

Taylor, J.L and Williams, D.G. (1982). "Problems and Issues in Asian Urban Areas-and the
Response of Planning Practice", in J.L.Taylor and D.G. Williams(eds.) Urban Planning
Practice in Developing Countries, Pergamon Press, G. Britain.

Techeste Ahderom (1986). “Basic Planning Principles and Objectives Taken in the
Preparation of the Addis Abeba Master Plan, Past & Present”, a paper presented to the
International Symposium on the Centenary of Addis Abeba, Addis Abeba.

UN HABITAT(2009). Planning Sustainable Cities, Earthscan, UK


(http://www.unhabitat.org/content.asp?typeid=19&catid=555&cid=5607)

-------------------(2010). The Ethiopian Case of Condominium Housing: The Integrated


Housing Development Programme. United Nations Human Settlements Programme,
Nairobi.

United Nations (2010). World Urbanization Prospects: The 2009 Revision

(http://esa.un.org/unpd/wup/index.htm)

የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር (1997E.C). የከተማ ልማት ፖሊሲ፣አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ (2000). የከተማ ፕላን አዋጅ ቁ. 574/2000፣አዲስ አበባ፡፡

--------------------------------(2003E.C). የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር ክፍለ- ኢኮኖሚያዊ


የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (2003-2007)፣ አዲስ አበባ፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ገፅ 144

You might also like