You are on page 1of 25

0 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ

የከተማ ቦታን ለአጭር ጊዜ በሊዝ ወይም ኪራይ ውል


ለተጠቃሚዎች ለመፍቀድ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ

ግንቦት 2006 ዓ/ም

ባህር ዳር

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን ለአጭር ጊዜ በሊዝ ወይም
በኪራይ ውል ለተጠቃሚዎች ለመፍቀድ ተሻሽሎ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ

0
በዝቅተኛ ካፒታል የንግድ እንቅስቃሴ በማድረግ ራሳቸውን ለመቻል የሚጥሩ ዜጎችን መሬት የማግኘት ዕድል
በማስፋት ከህገ-ወጥ አሰራር ወጥተው ወደ ህጋዊ ስርዓት በመምጣት ለኢኮኖሚው ማደግ የበኩላቸውን
አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችሉ በማገዝ በከተሞች ውስጥ የተንሰራፋውን ድህነት መዋጋት በማስፈለጉ፤

በከተማ መሬት ልማት ፖሊሲው ላይ እንደተመለከተው ለሁለንተናዊ ዕድገት በግብዓትነት ከሚያገለግሉት


የተፈጥሮ ሀብቶች መካከል ዋናው ሃብት መሬት በመሆኑና ይህንን ግብዓት መሠረታዊ የከተማ ቦታ አስተዳደር
መርህን ሳይለቅ በተለያዩ ስርዓቶች ጥቅም ላይ ማዋል በማስፈለጉ ፤

በክልላችን ከተሞች ለሚኖሩ ዜጐች ሰፊ የስራ ዕድል በመፍጠር የህዝባችንን ገቢ በማሻሻል ድህነትን በመቀነስ
ተወዳዳሪና ቀጣይነት ያለው ፈጣን ልማት ለማስመዝገብና ከመሬት የሚገኘውን ሀብት ማሳደግ በማስፈለጉ፤
ከተሞች በአስተዳደር ወሰናቸው ውስጥ ያለውን ክፍት ቦታ በቋሚነት ልማት ላይ እስኪውል ድረስ በጊዜያዊ የሊዝ
ወይም የኪራይ ውል ለተጠቃሚዎች ተሰጥቶ ጥቅም ላይ እንዲውልና አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ በብዙ መልኩ
የተሻለ ጠቀሜታ እንዳለው በመታመኑ፤

የሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 እና የክልሉን የሊዝ ደንብ ቁጥር 103/2004 በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ እና
በሥራ ላይ የቆየውን የአጭር ጊዜ ቦታ አሰጣጥ የአፈፃፀም መመሪያ በማሻሻል ከከተሞች ነባራዊ ሁኔታ አኳያ
ቦታዎችን በጊዜዊነት ለመጠቀም ከነዋሪዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ማስተናገድ የሚያስችል መመሪያ ማውጣት
በማስፈለጉ፣

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 176/2003
አንቀጽ 11 ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል /ሠ/ እንዲሁም የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር
721/2004 አንቀጽ 33 ንዑስ አንቀጽ 2፣ እና የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተዳደር የክልሉ ደንብ ቁጥር 103/2004
አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ከተማ
ልማት ቢሮ ይህንን የአፈፃፀም መመሪያ አውጥቷል፡፡

ክፍል-- አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የከተማ ቦታን ለአጭር ጊዜ በሊዝ ወይም በኪራ ይ ውል ለተጠቃሚዎች ለመፍቀድ የወጣ
የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 5/2006 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. . ትርጓሜ
3. የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሠጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ፡-

1
1. “አዋጅ” ማለት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 ዓ.ም ነው፤
2. “ደንብ” ማለት የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተዳደር እንደገና ተሻሽሎ የወጣ የክልል መስተዳደር ደንብ ቁጥር
103/2004 ነው፤
3. “ሊዝ” ማለት በጊዜ በተገደበ ዉል መሰረት የከተማ ቦታ የመጠቀም መብት የሚገኝበት የመሬት ይዞታ
ስሪት ነው፤
4. “የአጭር ጊዜ ኪራይ ውል” ማለት ወደ ሊዝ ስሪት ባልገቡ ከተሞች በጊዜ በተገደበ ውል ቦታ ለአጭር
ጊዜ የሚሰጥበት አግባብ ነው፤
5. “የቦታ ምደባ” ማለት በጨረታ ሊስተናገዱ ለማይችሉ ተቋማት የከተማ ቦታ በሊዝ ወይም ኪራይ ውል
የሚፈቀድበት ስልት ነው፤
6. “ለአጭር ጊዜ በሊዝ ወይም ኪራይ የሚፈቀድ ቦታ” ማለት ለከተማ ግብርና እስከ አስራ አምስት
ዓመት እንዲሁም ለሌሎች የአጭር ጊዜ የቦታ አገልግሎት ለአምስት ዓመትና ከዚያ በታች ለማምረቻ
፣ለማከማቻ ፣ለመሸጫ ፣ ለአገልግሎት ማቅረቢያ ወይም ለሌሎች አገልግሎቶች እንዲዉል በጊዜያዊ
ዉል የሚሰጥ ቦታ ነው፤
7. “ጊዜያዊ የሊዝ ወይም የኪራይ ክፍያ” ማለት በጊዜ ተወስኖ ለአጭር ጊዜ መጠቀሚያ ለተፈቀደ
የከተማ ቦታ በኪራይ ተመን ወይም በሊዝ ዋጋ መሠረት የሚከፈል ዓመታዊ ክፍያ ነው፤
8. “ክላስተር” ማለት በአንድ አካባቢ ተሰባስበው ብዛት ያላቸውንና ተመጋጋቢ የሆኑ የተለያዩ ምርቶችና
አገልግሎቶችን የሚያቀርቡና ተመሳሳይ ስጋትና መልካም አጋጣሚውንም የሚጋሩ ተቋማት ስብስብ
ነው፤
9. ”ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ”ማለት ከፖሊሲና ስትራቴጅ መሻሻል ጋር የሚኖር የትርጓሜ ለውጥ
እንደተጠበቀ ሆኖ የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞች ጨምሮ እስከ
አምስት ሰዎች ቀጥሮ የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ
ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ወይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ያልበለጠ
ኢንተርፕራይዝ ነው፤
10. ”አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ” ማለት ከፖሊሲና ስትራቴጅ መሻሻል ጋር የሚኖር የትርጓሜ ለውጥ
እንደተጠበቀ ሆኖ የኢንተርፕራይዙን ባለቤት፤ የቤተሰብ አባላትና ተቀጣሪ ሰራተኞችን ጨምሮ
ከስድስት እስከ ሰላሳ ሰዎች የሚያሰማራና የጠቅላላ ካፒታሉ መጠን ህንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት
ዘርፍ ከብር 50,001 (ሃምሳ ሺህ አንድ) እስከ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ወይም በኢንዱስትሪ
ዘርፍ ከብር 100,001 (አንድ መቶ ሺህ አንድ) እስከ 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ)
ያልበለጠ ኢንተርፕራይዝ ነው፤

2
11. “ሼድ” ማለት እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በተዘጋጀው ዲዛይን መሰረት የሚሰራና በቋሚነት
ወይም ለተወሰነ ጊዜ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ምርት ማምረቻና መሸጫ የሚያገለግል
ግንባታ ነው፤
12. #ጊዚያዊ ግንባታ; ማለት የጊዜ ገደብ ተቀምጦለት የሚገነባ እና የተሰጠው የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ በቀላሉ
የሚነሳ ግንባታ ነው፤
13. “አግባብ ያለው አካል’’ ማለት የከተማ መሬትን ለማስተዳደር እና ለማልማት በህግ ስልጣን የተሰጠው አካል
ነዉ፤
14. “ከተማ” ማለት ማዘጋጃ ቤት የተቋቋመበት ወይም ሁለት ሺህ ወይም ከዚያ በላይ የህዝብ ቁጥር
ያለውና ከዚህ ውስጥ ሃምሳ በመቶ (50%) በላይ የሚሆነው ነዋሪ ከግብርና ውጭ በሆነ ሥራ ላይ
የተሰማራ ሆኖ የሚገኝበት አካባቢ ነው፤
15. “የከተማ ቦታ” ማለት በከተማ የአስተዳደራዊ ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኝ መሬት ነው፤
16. “ቢሮ” ማለት የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ማለት ነው፤
17. ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ይጨምራል፡፡

3. የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በሚገኙ ከተሞች በአዋጁ አንቀፅ 18 ንዑስ አንቀጽ 2
ፊደል ተራ /ለ/ እንዲሁም በደንቡ አንቀፅ 25 በተጠቀሰው መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ በቋሚነት ጥቅም ላይ
በማይውሉ የከተማ ቦታዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

4. የከተማ ቦታ በአጭር ውል ጊዜ የሚሠጥበት መርህ


1. ለአጭር ጊዜ ውል የሚሰጥ ማንኛውም የከተማ ቦታ በተቻለ መጠን የከተማውን የፕላን ምደባ
ተከትሎ የሚከናወን ይሆናል፡፡
2. ለአጭር ጊዜ የሚሰጥ ቦታ እንደ ከተሞቹ ሁኔታ በሊዝ ወይም በኪራይ አግባብ ለተጠቃሚ
የሚተላለፍ ሆኖ በአካባቢው ካለው የአገልግሎት ዓይነት ጋር የሚጣጣም መሆን አለበት፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተጠቀሰው ቢኖርም በጊዜው ለሌላ ቋሚ አገልግሎት ጥቅም ላይ
የማይውሉ፣ በክፍትነት ያሉ እንዲሁም ራሳቸውን ችለው የማይለሙ የከተማ ቦታዎችን ጥቅም ላይ
ለማዋል መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡

3
4. ለአጭር ጊዜ ሊዝ ወይም ኪራይ የሚሰጡ ቦታዎች የስራ ዕድል ፈጠራን ትኩረት ባደረገ፣ በጥቃቅንና
አነስተኛ ተደራጅተው ለሚቀርቡ ስራ ፈላጊዎች ወይም በግል ለሚቀርቡ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ
ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆን አለበት፡፡
5. በአጭር ጊዜ ውል የሚሠጡ የከተማ ቦታዎች በተቻለ መጠን መሰረተ ልማት የተሟላላቸው ወይም
በቅርበት የሚገኝባቸው ቦታዎች መሆን አለባቸው፡፡
6. ለአጭር ጊዜ ውል በሚሰጥ ቦታ ላይ የሚያርፍ ግንባታ ወይም ንብረት ወይም የሚሰጥ አገልግሎት
የከተማውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ መሆን ይኖርበታል፡፡
7. በአጭር ጊዜ ውል ለተጠቃሚ በጊዜያዊነት የተላለፈ ቦታ/ሸድ ከውርስ በስተቀር በማንኛውም መንገድ
ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ ወይም በዋስትና ማስያዝ አይቻልም፣

ክፍል ሁለት

በአጭር ጊዜ ውል የሚሠጡ የከተማ ቦታዎች ዓይነት፣ የሚፈቀዱ አገልግሎቶች፣ የቦታ


ዝግጅት፣ ጥያቄ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ፣

5. በአጭር ጊዜ ውል የሚሠጡ የቦታ አይነቶች


1. በከተማው የአስተዳደር ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኙ ቦታዎች፤
2. በከተማው እድገት/መሪ ፕላን ላይ ለጥቃቅንና አነስተኛ አገልግሎት የተመደቡ ቦታዎች፣
3. በቀጣይ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለሌላ ቋሚ ልማት ሊውሉ የማይችሉ ፣ ከይገባኛል ጥያቄ ነፃ እና
ክፍት የሆኑ ቦታዎች፣
4. የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ/ጥናት እየተደረገላቸው የአፈርና ደን፣ የከርሰ-ምድር ውሀ እና በፈር ዞን
ጥበቃን የሚያረጋግጡ አገልግሎቶች ሆነው በወንዞች ዳርቻ የሚገኙ ቦታዎች፣
5. በከተማው መሀል አካባቢ ሆኖ በቦታ መጠናቸው እና በመልክዓ-ምድራዊ አቀማመጣቸው ምክንያት
ራሳቸውን ችለው የማይለሙ ክፍት እና ሌሎች ተመሳሳይ ቦታዎች፣

6. በአጭር ጊዜ የማይሠጡ የከተማ ቦታዎች


1. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት የቦታ
አገልግሎት አይነቶች በጊዜያዊነት ለተጠቃሚ መስጠት/ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
ሀ. በቀጣይ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ በቋሚነት ለማልማት የተለዩ ቦታዎች፣
ለ. ለእምነት ተቋማት መገንቢያ የተመደቡ ቦታዎች፣
ሐ. ለስፖርት ማዘውተሪያነት የሚውሉ ቦታዎች፣

4
መ. መዉጫና መግቢያን በመዝጋት የትራፊክ ዕንቅፋት የሚፈጥሩ ቦታዎች፣
ሠ. በከተማዉ ወይም በአካባቢዉ ነዋሪ ለአረንጓዴ ልማት (Greenery
areas)የተከለሉ ቦታዎች፣
ረ. ታሪካዊና ጥብቅ ቦታዎች/hisorical and reserved areas/ እና ሌሎች ተመሳሳይ ቦታዎች፣
7. በአጭር ጊዜ ውል በሚሰጡ የከተማ ቦታዎች ላይ የሚፈቀዱ የአገልግሎት አይነቶች፣
1. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ለአጭር ጊዜ የሚሠጡ ቦታዎች በአካባቢው
ካለው እንቅስቃሴና አገልግሎት ጋር የተጣጣመ እና በአካባቢው ላይ የብክለትም ሆነ ሌላ ተጽዕኖ
የማያሳድር መሆኑ እየተጠረጋገጠ የሚከተሉትን የኘሮጀክት/አገልግሎት አይነቶች ያካተተ ሊሆን
ይችላል፡፡

ሀ. ለከተማ ግብርና ሥራዎች /አትክልት፣ አበባ፣ እንሰሳት እርባታና ማድለብ ወዘተ.../፣

ለ. ለግንባታ ዕቃዎች ማምረቻ ወይም መሸጫ ወይም ማሳያ ቦታዎች፣

ሐ. ለግንባታ ጊዜ ማሽነሪና ቁሳቁስ ማስቀመጫ ቦታዎች፣

መ. ለግንባታ ድንጋይ ማውጫ እና ለዚሁ ተግባር የሚሆን ማሽነሪ መትከያ ቦታዎች፣

ሠ. ለማስታወቂያ ሰሌዳ መትከያ የሚውሉ ቦታዎች፣

ረ. ለግንባታና ለማገዶ የሚሆን የእንጨት መሸጫ ቦታዎች፣

ሰ. ለአሸዋና ጠጠር ማምረቻ፣ ማከማቻና መሸጫ ቦታዎች፣

ሸ. ለአነስተኛ open restaurants እና ትኩስ ምግቦች መሸጫ ቦታዎች፣

ቀ. ለዕደ ጥበብ/ሸማና ሸክላ ሥራ/ወርክሾፕ ስራ የሚውሉ ቦታዎች፣

በ. ለጋዜጣና መጽሔት ማደያዎች እና መሸጫ ቦታዎች፣

ተ. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ለተለያዩ አገልግሎቶች ማቅረቢያ/መሸጫ እና ማምረቻ ቦታዎች ሊሆኑ ይችላል፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ከ/ሀ/ እስከ /ተ/ የተዘረዘሩ የአገልግሎት አይነቶች እንደተጠበቁ ሆኖ አግባብ
ያለው አካል ለአጭር ጊዜ በሊዝ ወይም ኪራይ ውል ሊሰጡ ይገባል ብሎ የሚያምንባቸውን ሌሎች
ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው የአገልግሎት አይነቶች ሊሰጥ ይችላል::

5
8. የከተማ ቦታን በአጭር ጊዜ ውል ለመጠቀም የሚቀርብ ጥያቄ አቀራረብ እና
ለተጠቃሚዎች የሚተላለፍበት አግባብ
1. የቦታ ጥያቄዉ በግል ወይም በማህበር የሚቀርብ ከሆነ ቦታዉን ለምን አገልግሎት እንደፈለገዉ፣
በቦታዉ ላይ ሊከናወን የተፈለገዉ አገልግሎት ጠቀሜታ፣ ለአገልግሎቱ የሚውለው ጊዜያዊ የግንባታ
ስትራክቸርና የሚጠቀምበትን የጊዜያዊ ግንባታ ቁስ ዓይነት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ንድፍ፣ ስራዉ
የሚጠይቀዉን የቦታ ስፋት፣ ቦታው የሚገኝበትን አድራሻ፣ ቀንና ዓ.ም የተጠቀሰበት የጽሁፍ
ማመልከቻ አግባብ ላለው አካል ያቀርባል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመለከተዉ እንደተጠበቀ ሆኖ የቦታ ጥያቄዉ በአነስተኛና ጥቃቅን
ከተደራጁ ማህበራት የቀረበ ሲሆን የማህበራቱ አደረጃጀት፤ የህጋዊነቱ አግባብ እና ጥያቄዉ
ተቀባይነት ማግኘቱ ማህበራቱን በሚያደራጀዉ በከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
ልማት ጽ/ቤት በኩል እየተረጋገጠ አግባብ ላለው አካል መቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. ለከተማ ግብርና እና ለማዕድን ማውጫ በጊዜያዊነት ለሚሰጡ ቦታዎች የሚቀርቡ ፕሮጀክቶችን
በተመለከተ የቀረበው ፕሮጀክት ዘርፉን በሚመራው ተቋም በኩል ግምገማና ሙያዊ አስተያየት
መሰጠት ይኖርበታል፡፡
4. ከተማው በተመረጡ የእድገት ተኮር የልማት ዘርፎች ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ስራ አጦችና
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወጣቶች፣ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤቱ በኩል በግል ተመልምለው ሲቀርቡ ማስተናገድ ይችላል፡፡
5. በዚህ አንቀጽ በተገለፀው አግባብ በጊዜያዊነት ለሚሰጡ ቦታዎች የሚቀርብ የቦታ ጥያቄ በከተማው
ከንቲባ ኮሚቴ ወይም ማዘጋጃ ቤት ማኔጅመንት ኮሚቴ በኩል እየተወሰነ በምደባ ለተጠቃሚዎች
የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

9. በአጭር ጊዜ ውል የሚሠጡ ቦታዎች ዝግጅትና ውሳኔ አሰጣጥ፣


1. ከተማው በአጭር ጊዜ ውል እንደአስፈላጊነቱ በግል ወይም በማህበር የሚሠጡ ጊዜያዊ
ቦታዎችን በመለየት ያዘጋጃል፡፡በዚህም መሰረት፡-

ሀ. በተቻለ መጠን የመሰረተ ልማት አቅርቦት እንዲሟላላቸው ያደርጋል ፣

6
ለ. ከሶስተኛ ወገን ሙሉ በሙሉ ነፃ ያደርጋል፣
ሐ. ጊዜያዊ ሳይት ኘላን ያዘጋጃል፣
መ. ለእያንዳንዱ ቁራሽ መሬት መለያ ቁጥር በመስጠት የወሰን ድንጋይ በመትከል ቁጥር እንዲሠጣቸው
ያደርጋል፡፡
2. ከተማው ጊዜያዊ ሸድና ክላስተር በመገንባት ወይም ቦታን በማዘጋጀት በአጭር ጊዜ ሊዝ/ኪራይ አግባብ
ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፍ ያደርጋል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 በተገለፀው መሰረት የከተማው ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ
አገልግሎት/መምሪያ/ ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት ተመርጦ በተዘጋጀ ቦታ ላይ የሸድና ክላስተር ግንባታ
ያከናውናል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 በተገለፀው መሰረት ከተማው ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ
አገልግሎት/መምሪያ/ ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት የተገነባውን ጊዜያዊ ሸድ ለከተማው ጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ያስረክባል፡፡
5. የከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት የተገነቡ ክላስተርና ሸዶች በጊዜያዊ ውል
ለተጠቃሚዎች ያስተላልፋል፡፡
6. በዚህ አንቀጽ 5 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት
ጽ/ቤት በውሉ መሰረት ሸድና ክላስተር ይዞታዎችን አጠቃቀም እና ክፍያ አፈፃፀም ይከታተላል፡፡
7. የከተማው ማዘጋጃ ቤት ወይም ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት/መምሪያ/ ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ
ቤት ቦታውን በቋሚነት ማልማት ሲፈለግ ከተጠቃሚዎች ጋር የተያዘው የሊዝ/ኪራይ ውል
እንዲቋረጥ ከስድስት ወር በፊት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት በደብዳቤ
ያሳውቃል፡፡
8. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ከተማው በአጭር ጊዜ ሊዝ/ኪራይ አግባብ
ጊዜያዊ ቦታን በግል ወይም በማህበር ለሚቀርቡ ተጠቃሚዎች እንዲተላለፍ ያደርጋል፡፡
ሀ. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት በኩል ተመልምለውና ተደራጅተው ለከተማው
ማ/ቤት ወይም ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት/መምሪያ/ ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት
ጊዜያዊ ቦታ እንዲያገኙ ጥያቄው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ሲቀርብ
በተገለፀው የቦታ መጠንና የአገልግሎት ዘርፍ መሰረት በቅደም ተከተል ቦታ ይሰጣቸዋል፡፡
ለ. የጊዜያዊ ውሉ በተዘጋጀው የውል ፎርም መሰረት በከተማው ማዘጋጃ ቤት ወይም ኢንዱስትሪ
ልማትና ከተማ አገልግሎት/መምሪያ/ ጽ/ቤት በኩል የሚያዝ ይሆናል፡፡
ሐ. የቦታ አጠቃቀሙና የክፍያ አፈፃጸሙ በከተማው ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት/መምሪያ/
ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት በኩል ክትትል ይደረግበታል፡፡እንደአስፈላጊነቱ የጊዜያዊ ውል እደሳት
የሚደረግ ይሆናል፡፡

7
መ. በተናጥል በጊዜያዊነት የሚሰጡ አገልግሎቶች ለምሳሌ ለግንባታ ጊዜ ቁሳቁስ ማስቀመጫ
፣ለማስታዎቂያ መትከያ ወዘተ አገልግሎቶች ሆነው ለሚቀርቡ ጊዜያዊ የቦታ ጥያቄዎች አግባብ
ያለው አካል እንደአስፈላጊነቱ በጊዜያዊ ውል ቦታ የሚፈቅድ ይሆናል፡፡

10. ለአጭር ጊዜ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች የሚሠጡ ቦታዎች መጠን በአገልግሎት አይነት


1. ለአጭር ጊዜ ሊዝ ወይም ኪራይ ውል ለተጠቃሚዎች የሚሠጠው የቦታ መጠን የቦታ ጠያቂዎችን
ብዛት እና ለአገልግሎት ዓይነቱ የሚፈልገውን የቦታ መጠን ታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡
2. ለጊዜያዊነት በአጭር ጊዜ ውል ለሚሰጡ አገልግሎቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታ መጠን በአገልግሎት
ዓይነት ተለይቶ ተቀምጧል፡፡ ዝርዝሩን አባሪ 1፣ 2 እና 3 ይመልከቱ፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 በአባሪዎች ላይ በአገልግሎት አይነት ተለይቶ የተቀመጠው የቦታ
መጠን ቢኖርም ውጤታማና ፍትሀዊ የቦታ አጠቃቀምን ከማረጋገጥ አኳያ ከተሞች የሚቀርበውን
ፕሮጀክትና የአገልግሎት አይነት በማየትና በመገምገም የቦታ መጠኑን ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

ክፍል ሶስት

በጊዜያዊነ የተሰጡ ቦታዎች አስተዳደርና አጠቃቀምን በተመለከተ

11.በጊዜያዊነት የተሰጡ ነባር ይዞታዎች በተመለከተ


1. ከዚህ በፊት በጊዜያዊነት በአጭር ጊዜ ውል የተሰጡ ነባር ይዞታዎች ከከተማው ኢንዱስትሪ ልማትና
ከተማ አገልግሎት/መምሪያ/ ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት፣ ከቀበሌ አመራሮች እና ከጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርኘራይዝ ልማት ጽ/ቤት በጋራ በሚቋቋም ኮሚቴ ዝርዝር መረጃውን በማሰባሰብ
በመዝገብ እንዲያዝ ይደረጋል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰበሰበው ዝርዝር መረጃና ጥናት መሰረት በጊዜያዊነት ጥቅም ላይ
የሚውል የከተማ ቦታን ያለፈቃድ የያዙ፣ የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ፣ ከውርስ በስተቀር
ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፉ እና ቋሚ ግንባታ የገነቡ ባለይዞታዎች አግባብ ባለው አካል እርምጃ
የሚወሰድ ሲሆን፣

ሀ. በከተማው በኩል በጊዜያዊነት በተሰጡ ቦታዎች ላይ በህገወጥ መንገድ የግንባታ ፈቃድ በመውሰድ
ቋሚ ግንባታ የገነቡ እና ቦታውን እየተጠቀሙ ያሉ ግለሰቦች ቋሚ ግንባታውን በማፍረስ ቦታው
ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርጎ ችግሩን የፈጠረው አካልም አግባብ ባለው ህግ ተጠያቂ
ይሆናል፡፡

ለ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 /ሀ/ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ግለሰቡ የገነባውን ቋሚ


ግንባታ በማፍረስ የግንባታውን ቁሳቁስ የሚያነሳበት የአንድ ወር ጊዜ የሚሰጠው ሲሆን

8
በተሰጠው ጊዜ የማያፈርስና የማያነሳ ከሆነ ከተማው የህገ-ወጥ ግንባታዎችን
በሚያስተናግድበት አግባብ ተፈፃሚ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

ሐ. ለአጭር ጊዜ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ የከተማ ቦታዎችን በተለያየ አግባብ ከሚመለከተው


አካል ፈቃድ ሳያገኙ ይዘው የተገኙ ግለሰቦች/ድርጅቶች ቦታውን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን
ውዝፍ የሊዝ/ኪራይ ክፍያ እንዲከፍሉ ተደርጎ ቦታውን እንዲነጠቁ ይደረጋል፡፡

መ. የከተማ ቦታን በጊዜያዊነት አገልግሎት ላይ ለማዋል አግባብ ካለው አካል ወስደው የአገልግሎት
ለውጥ ያደረጉ ተጠቃሚዎች የአመታዊ የሊዝ/ኪራይ ክፍያውን 3% ቅጣት በማስከፈል
መጀመሪያ ለተፈቀደው የአግልግሎት አይነት እንዲጠቀሙ ይደረጋል፡፡

ሠ. በአጭር ጊዜ ውል የተሰጡ የከተማ ቦታዎች ከውርስ በስተቀር ወደ ሶስተኛ ወገን ተላልፎ


ከተገኘ ተጠቃሚው ቦታውን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የቦታ የሊዝ/ኪራይ ውዝፍ
ክፍያ በማስከፈል ቦታው ተነጥቆ ለሌላ የስራ እድል መፍጠሪያ እንዲውል ይደረጋል፡፡

ረ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 /ሠ/ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ጊዜያዊ ቦታዎች/ሸዶችን


በህጋዊ መንገድ አግባብ ካለው አካል ወስደው አከራይተው የሚጠቀሙ አቅመ ደካማ፣
አካል ጉዳተኞች እና የኤችአይቪ ህመምተኞች ጊዜያዊ ውሉ የማይታደስበት ሁኔታ
ካልኖረ በስተቀር የሚነጠቁ አይሆንም፡፡

3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ፊደል ተራ /ሠ/ እና /ረ/ በተገለፀው አግባብ ቀደም ሲል
በጊዜያዊነት የወሰዱ እና አሁን እንዲጠቀሙበት የተፈቀደላቸው ባለይዞታዎች ውዝፍ የቦታ
ሊዝ/ኪራይ ክፍያ በአንድ ጊዜ አጠቃለው እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡
4. በህጋዊ መንገድ ቦታ በጊዜያዊነት ለማልማት ወስደው ለተፈቀደላቸው አገልግሎ እየተጠቀሙ
የሚገኙ ሆነው በተለያየ ምክንያት ውል ያልያዙ፣ውል ይዘው ያላሳደሱ እና የቦታ ኪራይ/ሊዝ
ክፍያ ያልከፈሉ ተጠቃሚዎች ከተማው ቦታውን ለተለየ ልማት እስካልፈለገው ድረስ ቦታውን
ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ውል እንዲይዙ በማድረግ በውሉ መሰረት ውዝፍ የኪራይ/ሊዝ ክፍያ
እንዲከፈሉ ይደረጋል፡፡

5. በከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተረፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት እና በቀበሌ በኩል ለተጠቃሚ


የተሰጡ ቦታዎች ዝርዝር መረጃና ውል ለቁጥጥርና ክትትል ይረዳ ዘንድ ለከተማው ኢንዱስትሪ
ልማትና ከተማ አገልግሎት መምሪያ/ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡

6. ከዚህ ቀደም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት በጊዜያዊነት የተገነቡ ሆነው
ለተጠቃሚዎች የተላለፉ ሸዶችን መረጃ በዝርዝር ተለይተው ተገቢውን የሰነድና ማስረጃ ርክክብ

9
በመፈጸም የማስተዳደር እና ክፍያ አፈፃፀሙን የመከታተል ስራ በከተማው ኢን/ል/ከተማ
አገል/መምሪያ/ጽ/ቤት/ማ/ቤት በኩል የሚከናወን ይሆናል፡፡

12. በአጭር ጊዜ ውል የሚሰጡ ቦታዎች አጠቃቀምና የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታ

1. ለጊዜያዊነት በአጭር ጊዜ ውል በሚፈቀድ የከተማ ቦታ ላይ የሚከናወን የአገልግሎት አይነት


እንደአስፈላጊነቱ ከከተማው ፕላንና የመሬት አጠቃቀም ጋር የሚጣጣም መሆን አለበት፡፡
2. ለአጭር ጊዜ ጥቅም በሚፈቀድ ቦታ ላይ የሚገነባ ግንባታ የትራፊክ እንቅስቃሴን የማያውክ እና
የአካባቢውን እይታ የሚያበላሽ አለመሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
3. ለአጭር ጊዜ በሊዝ/ኪራይ ውል በተሰጠ ቦታ ላይ የሚገነባ ጊዜያዊ ግንባታ መሰረት በድንጋይና
በኮንክሪት መገንባት የሚቻል ቢሆንም በቀላሉ ፈርሶ ሊነሳ የማይችል የብሎኬት፣ የድንጋይ ወይም
የሸክላ ግድግዳና ጣሪያ ያለው ጊዜያዊ ግንባታ መገንባት በፍጹም አይፈቀድም፡፡የጊዜያዊ ግንባታው
ግድግዳና ጣሪያ ከላይ በተጠቀሱት ቁሳቁሶች ተገንብቶ ቢገኝና ቢፈርስ ለሚደርሰው ኪሳራ ከተማው
ተጠያቂ አይሆንም፡፡
4. በጊዜያዊ ይዞታ ላይ የቋሚ ግንባታ ፈቃድ በስህተት ተሰጥቶ ቢገኝ ፈቃድ ሰጪው አካል በህግ ተጠያቂ
መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግንባታው ያለ ካሳ ክፍያ እንዲፈርስ ተደርጎ ቦታው ወደ መሬት ባንክ
እንዲገባ ይደረጋል፡፡
5. ለአጭር ጊዜ አገልግሎት በተወሰዱ ቦታዎች ላይ የጊዜያዊ ግንባታዎች ከመከናወናቸው በፊት የግንባታ
ፕላን ፤ንድፍ፤ወይም ፎቶግራፍ ከነመግለጫው በህንጻ ሹም ወይም ውክልና በተሰጠው ተቋም በኩል
ቀርቦ መፅደቅ ይኖርበታል፡፡
6. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ለአጭር ጊዜ በሊዝ/ኪራይ በሚሰጡ
ቦታዎች ላይ የሚያርፉ ግንባታዎች ንድፍ/ዲዛይን፡-
ሀ/ ውል ተቀባይ የግንባታውን ንድፍ ወይም ዲዛይን አዘጋጅቶ በማቅረብ ያፀድቃል፡፡
ለ/ ንድፍ ማቅረብ የማይጠይቁ በተንቀሳቃሽነት የሚያገለግሉ መገልገያ ስትራክቸሮች/ቁሳቁሶች በፎቶ
ግራፍና የጽሁፍ መግለጫ አያይዘው በማቅረብ ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡

7. በጊዜያዊ ቦታዎች ላይ ለሚገነቡ ግንባታዎች ቋሚ የግንባታ ስራ ፈቃድ አይጠየቅም ወይም


አይሰጥም፡፡ ይሁን እንጅ በተዘጋጀውና በፀደቀው ንድፍ ወይም ዲዛይን መሠረት በቦታዉ ላይ
ጊዜያዊ ግንባታ ለማከናወን ይቻል ዘንድ ጊዜያዊ ግንባታ ፈቃድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

13. በአጭር ጊዜ የተሰጡ ቦታዎች የክፍያ ጊዜና መጠን

10
1. አንድ ዓመትና በታች ለሆነ ጊዜ በጊዜዊነት የሚፈቀዱ ቦታዎች በየወሩ ወይም
እንደአስፈላጊነቱ ውል ሰጭና ውል ተቀባይ በውል ስምምነታቸው በሚያስቀምጡት ጊዜ
መሰረት የሚከፈል ይሆናል፡፡
2. ለአጭር ጊዜ የተፈቀደው ቦታ ውሉ ከአንድ ዓመት በላይ ከሆነ ክፍያው በየዓመቱ የሚፈፀም
ይሆናል፡፡በጊዜያዊነት ለአጭር ጊዜ የሚሰጡ ቦታዎች ዓመታዊ የክፍያ መጠን በካ/ሜትር እና
በአገልግሎት ዓይነት በዚህ መመሪያ አባሪ 4 ላይ ይመልከቱ፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በአጭር ጊዜ ውል የተሰጠ
ማንኛውም ቦታ ውል ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በየአመቱ ዓመታዊ የሊዝ/ኪራይ ክፍያ የሚከፈል
ይሆናል፡፡ ከአንድ አመት በላይ ውል ላላቸው ቦታዎች አመታዊ ክፍያውን ከሶስት ወርና በላይ ሳይከፍሉ
ከዘገዩ ለሚዘገይበት እያንዳንዱ ወር የአመታዊ ክፍያውን 3 በመቶ ቅጣት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ከሶስት አመት በላይ ውል ለያዙ
ተጠቃሚዎች የሶስት አመት ውዝፍ ካለባቸው ውዝፍ ክፍያውን በማስከፈል ቦታውን እንዲነጠቁ
ይደረጋል፡፡
5. የውል ጊዜው ተጠናቆ አዲስ ውል የሚፈረም ከሆነ እና አዲስ የተደረጉ የዋጋ ማስተካከያዎች ካሉ
ውሉ በተስተካከለው ዋጋ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
6. በከተማ አስተዳደሮች በዚህ መመሪያ አባሪ 4 ላይ የተቀመጠውን ዋጋ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ
ከተሞች ጥናቱን አከናውነው ለቢሮ በማቅረብ አስፈላጊው ግምገማ አስተያየት ተሰጥቶበት
እንዲፀድቅ ይደረጋል፡፡
7. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በማዘጋጃ ቤት እና ታዳጊ ከተሞች
በጊዜያዊነት የሚሰጡ ቦታዎች ሊዝ/ኪራይ ዋጋ ማሻሻያ ጥናት በዞን ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት
መምሪያዎች በኩል ተጠንቶ ጥናቱ ለቢሮው በማቅረብ ሲፀድቅ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ክፍል አራት

ለአጭር ጊዜ የተሰጡ ቦታዎች የውል አፈፃፀምና ክትትል አግባብ

14. ስለ ውል አፈጻጸም ፣ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ እና ክትትል ስለማድረግ


ውል ሰጭ የከተማ ቦታን ለማስተዳደር ስልጣን የተሠጠው አካል እና ውል ተቀባይ ቦታውን በጊዜያዊነት
ለአጭር ጊዜ በሊዝ/ኪራይ ውል የሚወስደው አካል ሲሆን ውል ሰጭ የሚከተሉትን ተግባራት የሚያከናውን
ይሆናል፡፡

11
1. የከተማዉ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት/መምሪያ/ ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት ወይም
ታዳጊ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት የተሰጠዉን ዉሳኔ ቃለ ጉባኤ መሰረት
በማድረግ በተዘጋጀው የዉሉ ቅጽ/ፎርም መሰረት ከውል ተቀባይ ጋር ይዋዋላል፡፡
2. የዉሉ ይዘት ቃለ ጉባኤዉን መነሻ የሚያደርግ እና የዉል ተቀባይ እና ዉል ሰጪን መብት እና ግዴታ
ያካተተ ይሆናል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማ ቦታ የአጭር ጊዜ ሊዝ
ወይም ከራይ የውል አፈፃፀም ዝርዝር ሁኔታ የያዘ ፎርም በቢሮው በኩል የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 የተመለከተዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለድንጋይ ማዕድን ማዉጫነት ለሚዉል
ቦታ የሚፈጸመዉ ዉል ቦታዉን በነበረበት ሁኔታ አፈር በመሙላት እና በማስተካከል መመለስን
የሚያካትት ይሆናል፡፡
5. በዚህ መመሪያ በአባሪነት የተያያዘው ፎርም የመመሪያው አካል ሆኖ ዉል ተቀባይ የከተማዉ የመሬት
ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት ጋር ዉል እንደተፈራረመ ቦታዉን ለተጠቀሰዉ ጊዜ መጠቀም
የሚያስችለዉ ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት/ሰርትፊኬት ለተፈቀደው የውል ዘመን የሚሰጠዉ ይሆናል፡፡
ሆኖም በጊዜያዊነት ለአጭር ጊዜ ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ለሚተላለፉ የክላስተርና ሸድ ቤት
ተከራዮች ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት የሚሰጥ አይሆንም፡፡
6. ለክትትል ይረዳ ዘንድ የከተማዉ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት ከከተማው ጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ሰነዶቹን መነሻ በማድረግ የጊዜያዊ
ሊዝ/ኪራይ ይዞታዎች መረጃ በማህደር የሚያደራጅ ይሆናል፡፡
7. የከተማው መሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና የስራ ሂደት በጊዜያዊነት የተላለፈዉ መሬት በዉሉ
መሰረት በአግባቡ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ እና ከዉል ተቀባዩ ዉጪ ለሌላ አካልም ያልተላለፈ መሆኑን
ክትትል ያደርጋል፤ በዉሉ መሰረት ካልተፈጸመም ቦታዉን መልሶ ይረከበዋል፡
8. ከተማው ጊዜያዊ ሸድ ገንብቶ ለጥቃቅን በሚያስረክብበት ጊዜ ከተጠቃሚዎች ጋር የሚያዘው የኪራይ
ውልና ክፍያ አፈፃፀም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት በኩል ክትትል የሚደረግ
ይሆናል፡፡

15. በአጭር ጊዜ የሚሰጡ ቦታዎች የውል ዘመን


1. በአዋጅ 721/2004 አንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 2 እንዲሁም አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004
አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ 2 ተራ ፊደል (ለ) በተመለከተዉ መሰረት ለከተማ ግብርና 15 ዓመት የዉል ዘመን ሲሆን
የጥቃቅንና አነስተኛን ጨምሮ ሌሎች የአጭር ጊዜ ሊዝ ወይም ኪራይ ይዞታ ውል እስከ 5 ዓመት የተወሰነ
ነው፡፡

12
2. እንደአስፈላጊነቱ ጊዜያዊ የውል እድሳት የሚደረግ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በጥቃቅንና አነስተኛ
ለተደራጁ ግለሰቦች ወይም ማህበራት ለከተማ ግብርና አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ የውል ዘመን ለ 5 ዓመት
ይሆናል፡፡
3. ውል ተቀባይ ቦታዉን ለሌላ ተጨማሪ አመት መጠቀም ከፈለገ የዉል ዘመኑ ለመጠናቀቅ ከአንድ አመት
እስከ ስድስት ወር ሲቀረዉ የውል እድሳት ጥያቄውን ለከተማዉ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዋና
የስራ ሂደት በደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ /3/ በተገለፀው መሰረት ዉል ሰጭ በጊዜያዊ የቦታ ውል ዕድሳት ማመልከቻ ደብዳቤ
መሰረት ጥያቄውን ከደንብና መመሪያ አኳያ አጣርቶ ቦታውን በቋሚነት ለሌላ ልማት የማይውል
መሆኑን በማረጋገጥ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ሲወሰን የሚታደስለት ይሆናል፡፡ የጊዜያዊ ውል
እድሳቱ ለውል ተቀባይ ሲገለጽለት ቀድሞ የነበረዉን ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት ተመላሽ እንዲያደርግ
እና የዉል እድሳት በመፈጸም አዲስ የመጠቀሚያ ጊዜያዊ ምስክር ወረቀት እንዲሰጠዉ ይደረጋል፡፡
5. በከተማው በኩል በጊዜያዊነት ተገንብተው ለከተማው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት
ጽ/ቤት የተላለፉ ጊዜያዊ ሸዶች ጽ/ቤቱ የውል ዕድሳቱን አስፈላጊነት በደብዳቤ ሲያሳዉቅና ቦታዉ ለሌላ
ልማት የማይፈለግ መሆኑ ሲረጋገጥ የሚታደስለት ይሆናል፡፡
6. በጊዜያዊነት ለአጭር ጊዜ የተሰጠ የከተማ ቦታ ውል ሊታደስ የሚችለው ቀደም ሲል ለተሠጠው
አገልግሎት ሲሆን የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄ ከቀረበ በሚመለከተው አካል ሲታመንበት ሊስተናገድ
ይችላል፡፡

7. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 እና 4 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ከተማ
ግብርና አገልግሎት የተሰጠ እና በውሉ መሰረት ጥቅም ላይ እየዋለ ከሚገኝ ቦታ በስተቀር ከአንድ ጊዜ
በላይ ውል እድሳት ማድረግ አይቻልም ፡፡
8. የዉል ዘመኑ የተጠናቀቀ እና ዉል ተቀባይ እድሳት ጥያቄ ያላቀረበ ወይም ውል ሰጭ እድሳቱን ያላመነበት
ከሆነ ቦታዉን ዉሉ በተጠናቀቀ በሶስት ወር ጊዜ ዉስጥ ዉል ተቀባይ እንዲያስረክብ ይደረጋል፡፡ የውል
ተቀባይ የአጭር ጊዜ ይዞታ ባለቤትነት እና የጊዜያዊ መጠቀሚያ የምስክር ወረቀት እንዲሠረዝ ተደርጎ
ቦታዉም በመሬት መረጃ ባንክ ላይ በማንም ያልተያዘ በሚል ተመዝግቦ እንዲያዝ ይደረጋል፡፡
9. ለአጭር ጊዜ የተሰጠ ቦታ የውል ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት ለልማት ሲፈለግ ለውል ተቀባይ ንብረቱን
ለማንሳት የሚያበቃ ግምት ይሰጠዋል፡፡ እንደአስፈላጊነቱ እየታየ ለቀሪው የውል ጊዜ መጠቀሚያ
የሚሆን ምትክ ቦታ ሊሰጥ ይችላል፡፡
10. ከላይ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 7 የተገለጸው ቢኖርም ከከተማው ፕላን ጋር በተጣጣመ፣ የትራፊክ
እንቅስቃሴን በማያውክ፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን በማያደናቅፍ፣ ህንጻዎችንና ሰው ሰራሽ
የተፈጥሮ ቅርሶችን በማይከልልና በማያውክ ሁኔታ መሆኑ እየተረጋገጠ ለመንግስታዊ ተቋማት፣

13
ለኢምባሲዎች እና በተመሳሳይ ለሌሎች በልዩ ሁኔታ መታየት ላለባቸዉ ተቋማት ለማስታወቂያ ሰሌዳ
መትከያ የሚፈቀዱ ቦታዎች በየጊዜዉ ሊታደስላቸዉ ይችላል፡፡

16. የአጭር ጊዜ ሊዝ ወይም ኪራይ ውል የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች

በአጭር ጊዜ የተሰጡ ቦታዎች ውሉ የሚቋረጠው፡-

1. የውል ዘመኑ ሲጠናቀቅና ውሉ ዳግም የማይታደስ ሲሆን፣


2. ውል ተቀባይ በራሱ ምክንያት ውል ማቋረጥ ሲፈልግ፣
3. ውል ሰጭ ቦታውን በመደበኛ መልኩ ለማልማት ሲፈልግ፣
4. ውል ተቀባይ ቦታውን በውሉ ላይ ከተጠቀሰው የአገልግሎት አይነት ውጭ ሲጠቀምበት ሲገኝ፣
5. ውል ተቀባይ መክፈል ያለበትን የሊዝ ወይም ኪራይ ክፍያ ለሶስት አመታት መክፈል ካልቻለ
6. ውል ተቀባይ በጊዜያዊነት የተረከበውን ቦታ ውሉ አግባብ ይዞታውን መጠቀምና ማልማት ካልቻለ፣
7. ውል ተቀባይ ቦታውን በዚህ መመሪያ አንቀጽ 11 /2/ ተራ ፊደል /ሠ/ እና /ረ/ ከተጠቀሰው ውጭ
ለሌላ ሰው አስተላልፎ ሲገኝ ይሆናል፡፡

ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
17. ስለተጠያቂነት

14
በዚህ መመሪያ የተጣለበትን ግዴታ ያልተወጣና ለሊዝ/ኪራይ ውል ተቀባዮች የተሰጠውን መብት በአግባቡ
ያላከበረ አካል በአዋጁ አንቀጽ 35 የተጠቀሰው እንደጠበቀ ሆኖ ወንጀል ህጉ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል::

18. የመተባበር ግዴታ


ማንኛውም ሰው ይህን መመሪያ ለማስፈጸም በሚደረገው ማንኛውም እንቅስቃሴ ሁሉ አግባብ ያለው
ትብብር ሲጠየቅ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
19. ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ህጎችና አሰራሮች
1. በ 1994 ዓ.ም ወጥቶ በስራ ላይ የቆየው የከተማ ቦታን ለአጭር ጊዜ በሊዝ ወይም ከራይ ለማስተዳደር
የወጣው መመሪያ በዚህ መመሪያ ተሽሯል፡፡
2. ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማናቸውም መመሪያ ወይም አሰራር ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ ይህ
ጊዜያዊ የቦታ አሰጣጥ የአፈፃፀም መመሪያ በከተሞች በቋሚነት የሚገነቡ የሸድና ክላስተር
ግንባታዎችን አይመለከትም፡፡
3. በጨረታ ለተጠቃሚዎች ለሚተላለፍ የከተማ ግብርና አገልግሎት ለሚውል ቦታ የቦታ ጥያቄ አግባብ
የሚስተናገድ ሲሆን ከጊዜያዊ የመጠቀሚያ ሰርተፊኬት ውጭ ቋሚ ካርታ አይሰጥም፡፡

23. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ፀድቆ ከወጣበት ግንቦት
15/2006 ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አባሪ-1:- ለጥቃቅን እና አነስተኛ በአጭር ጊዜ ውል የሚሰጡ የመስሪያና መሸጫ ቦታዎች መጠን

15
ተ.ቁ የህንፃው አገልግሎት ጠ/ወለል የቦታዉ ምርመራ
ስፋት(በካ/ሜ) ስፋት(በካ/ሜ)
1 ጨርቃጨርቅና አልባሳት

 ሽመና 120 120


 ልብስ ስፌት 80 80
 የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች 80 80
 ሹራብ ስራ 80 80
 የጥልፍ ስራ 80 80
2 ብረታ ብረትና እንጨት
 ብረታ ብረት ስራ 200 200
 እንጨት ስራ 200 200
3 ምግብ ዝግጅት
 የባልትና ዉጤቶች 80 80
 እንጅራ ዝግጅት 80 80
 ወተትና የወተት ተዋፅኦ 80 80
 ማር ማጣራትና ማሽግ 80 80
 ዳቦ/አንበሻና ድፎ 80 80
4 ኮንስትራክሽን/ ብሎኬት 800 800
ምርት
5 የእደጥበብ ስራዎች 80 80
 ስጋጃ ስራ
 ሽክላ 60 60
 እንጨትና ድንጋይ ቅርፃ 80 80
ቅርፅ
 ቀርቀሃ ስራ 100 100

አባሪ-2፡- ለእንስሳት እርባታና ማድለብ አገልግሎት በአጭር ጊዜ የሚሰጥ ከተማ ቦታ መጠን

ተ. የእንስሳ አይነት የሚያስተናግደዉ ጠ/ወለል የቦታዉ ምርመራ


ቁ እንስሳ ብዛት ስፋት(በካ/ሜ) ስፋት(በካ/ሜ)
1 የወተት ከብት እርባታ
 ኮርማ፣ላም፣ወይፈን ወይም 10-20 1070-2090 1100-2150
ጊደር፣ጥጃ
2 በግ/ፍየል እርባታ

 አወራ፣እናት፣ ግልገል 20-30 200-300 250-350

16
3 የደሮ እርባታ

 ጫጩት(8 ሳምንት 500-1000 400-600 450-650

እድሜ)፣ታዳጊ(9-12 ሳምንት
እድሜ)፣እናት ወይም
አዉራደሮ
4 አሳማ እርባታ

 ኮርማ፣ወላድ(እናት)፣ 20-30 1750-2600 1800-2650

ታዳጊ
4 ማድለብ

 የዳልጋ ከብት 10-20 560-980 600-1000


5 ንብ እርባታ

 ባህላዊ ቀፎ/ ዘመናዊ ቀፎ 10-30 80-90 150-200

አባሪ-3፡- ለፍራፍሬ፤የጓሮ አበባና አትክልት ልማት አገልግሎት የሚሰጥ ቦታ መጠን

ተ. የእፅዋት በከተማ ደረጃ የቦታዉ ስፋት(በካ/ሜ)


ቁ አይነት 1 ኛ ደረጃ 2 ኛ ደረጃ 3 ኛ ደረጃ 4 ኛ ደረጃ 5ኛ 6ኛ ደረጃ
ከተማ ከተማ ከተማ ከተማ ደረጃ ከተማ
ከተማ

1 ለፍራፍሬ 10000 15000 20000 25000 30000 35000

2 ለጓሮ አበባ 5000 10000 15000 20000 25000 30000


እና
አትክልት

አባሪ 4፡- ዓመታዊ የአንድ ሜትር ካሬ ኪራይ ክፍያ በአገልግሎት ዓይነትና ቦታ ደረጃ

የሊዝ/ኪራይ መነሻ ዋጋ በአገልግሎት አይነት (ብር × 1 ካ.ሜ)


የከተማ ደረጃ

ለጥቃቅ ለከተ ለግንባታ ለግንባታ ለድንጋይ/ ለግንባታ ለጋዜጣና ለማስታወ


የቦታ ደረጃ

ንና ማ ዕቃዎች ጊዜ ማዕድን ና ማገዶ መጽሔት ቂያ


አነስተኛ ግብርና ማምረቻ፣ ማሽነሪና ማውጫ እንጨት ማደያዎች መትከያ
ተ.ቁ

ንግድ መሸጫ/ ቁሳቁስ የሚሆን መሸጫ / ቦታ


ሥራዎ ማሳያ ማስቀመጫ ቦታ መሸጫዎ
1 1 1 25 15 20 6 40 20 2.00 10

17
2 25 15 18 6 35 18 1.00 8
3 20 12 15 6 30 16 0.75 6
4 10 10 12 5 25 10 0.50 4
5 8 8 10 5 20 8 0.25 2
2 2 1 20 15 18 5 30 16 1.50 1
2 20 12 15 5 25 10 1.00 8
3 15 10 12 4 20 8 0.75 6
4 8 8 10 3 15 6 0.50 4
5 5 7 8 3 10 4 0.25 2
3 3 1 15 12 15 4 20 10 1.00 6
2 10 10 12 4 15 8 0,75 4
3 8 8 10 3 10 6 0.50 2
4 6 6 8 2 8 3 0.25 1
5 3 4 6 2 5 2 0.15 0.5
4 4 1 8 8 10 3 10 3 0.75 4
2 6 6 8 3 8 2 0.50 2
3 3 4 6 2 6 1 0.25 1
4 2 2 4 1 4 0.50 0.15 0.5
5 5 1 6 6 8 2 8 2 0.50 2
2 3 3 6 1 5 1 0.25 1
3 2 1 2 0.5 2 0.50 0.15 0.5
6 6 1 2 2 3 1 2 0.50 0.25 1
2 1 0.50 1 0.25 1 0.25 0.15 0.25

አባሪ-5፡- በአጭር ጊዜ ውል የሚሰጥ የከተማ ቦታ ሊዝ/ኪራይ ውል ፣

የውል ቁጥር ---------

በአጭር ጊዜ የሚሰጥ የከተማ ቦታ ሊዝ/ኪራይ ውል

የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 እና በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
ምክር ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተዳደር በወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 መሠረት ተፈጻሚ የሚሆን
ውል፡-
18
1.ውል ሰጪ የ--------------------- ከተማ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት/መምሪያ ጽ/ቤት ወይም
ማዘጋጃ ቤት

አድራሻ፡-ከተማ -----------------ወረዳ-----------------ቀበሌ---------ፓ.ሣ.ቁ-----------------ስልክ ቁጥር


-------

2. ውል ተቀባይ፡-ሙሉ ስም--------------------------------------

አድራሻ፡-ዞን------------ወረዳ-----------ከተማ-----------ቀበሌ----------------------የቤት
ቁጥር-------------------ስልክ ቁጥር-----------------------------

3. ውል ስለመፈረም
በዚህ ውል የተጠቀሰውን የከተማ ቦታ/ሸድ ውል ተቀባይ ለአጭር ጊዜ በሊዝ /በኪራይ ውል
ለ------------------አገልግሎት ብቻ ለመጠቀም ከዛሬ ----------------ቀን--------------- ወር----------------
ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ በኋላ ውል ሰጭ እየተባለ በሚጠራው የ-------------- ከተማ ኢንዱስትሪ ልማትና
ከተማ አገልግሎት/መምሪያ ጽ/ቤት ወይም ማዘጋጃ ቤት እና ውል ተቀባይ እየተባለ በሚጠራው
በአቶ/ወ/ሮ/ወሪ/ት/ድርጅት/ተቋም------------------መካከል ተፈርሟል፡፡
4. በአጭር ጊዜ የሊዝ/በኪራይ ውል የሚያዘው ቦታ/ሸድ ዝርዝር ሁኔታ፡-
 ቦታው/ሸዱ የሚገኝበት አድራሻ፡-
ዞን--------------------ወረዳ------------------ከተማ-----------------ቀበሌ---------------ቦታው/ሸዱ የሚገኝበት
አካባቢያዊ ልዩ ስም------

 የቦታው/ሸዱ አዋሳኝ፡-

በሰሜን ----------------------

በደቡብ ----------------------

በምስራቅ---------------------

በምዕራብ --------------------

 በሊዝ ወይም በኪራይ የሚያዘው ጊዜያዊ ቦታ/ሸድ በ-----------------------የፕሎት/ሸድ/ቤት ቁጥር


የተመዘገበ የከተማ ቦታ/ሸድ/ቤት ነው ፡፡
 የቦታው/ሸዱ ጠቅላላ ስፋት------------------------ሜትር ካሬ ነው፡፡
 የህንጻው መሰረትና ግድግዳ የሚሰራበት የቁሳቁስ አይነት ---------------------ነው፡፡

19
 የቦታው የሊዝ/ኪራይ ውል ዘመን---------------------ዓመት ነው፡፡
 በሊዝ ወይም በኪራይ የሚያዘው ቦታ ደረጃ -------------የንዑስ የቦታ ደረጃ----------ነው፡

5. ስለ ሊዝ ወይም ኪራይ ዋጋ መጠን አከፋፈል

 ውል ተቀባይ ከውል ሰጭ የተረከበውን ቦታ/ሸድ ለ------------------ዓመት ከላይ ለተጠቀሰው የአገልግሎት ዓይነት


ብቻ ለማዋል ለአንድ ካሬ ሜትር ዋጋ ብር---------------------------በመክፈል በጊዜያዊ የይዞታ የምስክር ወረቀት
ቁጥር--------------------------የተመዘገበውን ጊዜያዊ ይዞታ/ሸድ/ቤት በሊዝ/ኪራይ ውል ለመጠቀም በተፈቀደዉ
መሰረት ይህ ውል ተፈርሟል፡፡
 በዚህ መሰረት ውል ሰጪው በ----------------- ከተማ-----------------ዞን ------------------------
ወረዳ--------------------- ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን ቦታ የአመታዊ/ወርኃዊ ክፍያ ---------------------------
ብር በመክፈል በሊዝ ወይም በኪራይ የወሰዱት ሲሆን ለ---------------------------ዓመት ውል ከተፈረመበት
ከ-------------- ቀን----------------------ወር-------------------------ዓ.ም እስከ ቀን------------------------
ወር-------------------------ዓ.ም ይሆናል፡፡

 ተከራይ የተገለፀውን የማምረቻና የማሳያ ማዕከላት ወይም ሕንፃ በካሬ ሜትር ……. ብር ሂሳብ
በጠቅላላ ---------------------------- በካሬ ሜትር ብር -------------------------------------- ኪራይ በወር
ለመክፈል ተስማምቷል፡፡

 ከላይ የተጠቀሰውን ክፍያ ተከራይ በየወሩ ወር በገባ እስከ 10 ኛው ቀን ለመክፈል ተስማምቷል፡፡

 በየወሩ ኪራይ የሚከፈለው በአካባቢው የሚገኘው የገቢዎች ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ ነው፡፡ ተከራይ
የተጠቀመበትን የኪራይ ክፍያ እስከ 3 ወር ካልከፈለ በየወሩ የወርሃዊ ክፍያውን 10% ጨምሮ መቀጫ
ይከፍላል፡፡ የቅጣቱን ክፍያም ለገቢዎች ጽ/ቤት ይከፍላል፡፡

 ተከራይ በተከታታይ እስከ ሶስት ወር ድረስ ያለውን ኪራይ ከነመቀጫው ካልከፈለ አከራይ ውሉ
እንዲቋረጥ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ ለማስከፈል በሕግ ይጠይቃል፡፡ ውሉ ከተቋረጠ በኃላ በሕንፃው
ውስጥ ለሚገኝ ንብረት ተጠያቂነት አይኖርበትም፡፡

6. ለአጭር ጊዜ በተፈቀደው ቦታ ላይ ስለሚገነባው ግንባታ በተመለከተ

 ውል ተቀባይ ከውል ሰጭ ለተፈቀደለት ቦታ ላይ መሰረቱ ከ-----------------------ግድግዳው


ከ------------------------------ቁሳቁስ እንደሚገነባ ውሉ ላይ ስምምነት ተደርጓል፡፡

20
 በግንባታ ቁሳቁስ ጉድለት በእርጅና እንዲሁም ከአቅም በላይ በሆኑ ነገሮች በሕንፃው ላይ ጉዳት ቢደርስ ሕንፃውን
አከራይ ይጠግናል፡፡
7. የውል ተቀባይ መብትና ግዴታ

1. የውል ተቀባይ መብቶች ፣


 በጊዜያዊነት በተፈቀደለት ቦታ/ሸድ/ቤት በውሉ ላይ ለተገለፀው የአገልግሎት አይነት በውል
ጊዜው የመጠቀምና ሀብት የማፍራት መብት ይኖረዋል፡፡
 ውል ተቀባይ የዓመታዊ የሊዝ/ኪራይ ክፍያውን አንድ ጊዜ አጠቃሎ መክፈል ይችላል፡፡
 የውል ጊዜው ሲጠናቀቅ የገነባውን ጊዜያዊ ግንባታ አፍርሶ የማንሳት መብት አለው፡፡
 ውል ተቀባይ በቦታዉ ላይ በሚሰጠዉ ጊዜያዊ የግንባታ ፈቃድና በውሉ መሰረት አስፈላጊውን ጊዜያዊ
ግንባታ በማከናወን መጠቀም ይችላል፡፡
 ከህንፃው ባለቤትነት ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን ይከፍላል፡፡
2. የውል ተቀባይ ግዴታዎች
 ውል ተቀባይ በሊዝ ኪራይ የተፈቀደለትን ቦታ ለተፈቀደለት አገልግሎት ብቻ ጥቅም ላይ ማዋል
አለበት ፡፡
 ውል ተቀባይ የቦታዉን ዓመታዊ የሊዝ/ኪራይ ክፍያ በየአመቱየመክፈል ግዴታ አለበት፡፡ በውሉ ላይ
በተቀመጠው ቀን የማይከፍል ከሆነ በዚህ መመሪያ በተቀመጠው የቅጣት ተመን መሰረት ከአመታዊ የሊዝ
ክፍያ ጋር ተጨምሮ ቅጣት ይከፍላል፡፡
 ውል ተቀባይ በዚህ ውል መሠረት ቦታውን ወይም ህንፃውን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ በቤቱ ውስጥ
ለሚገለገለበት የኤሌክትሪክ የውሃና የስልክ የፍጆታ አገልግሎት ዋጋ ክፍያን በወቅቱ የመክፈል ግዴታ
አለበት፡፡
 ከውል ሰጭ በሚሰጠው ጊዜያዊ ግንባታ እድሳት ፈቃድ መሰረት የህንፃ እድሳት ያደርጋል፡፡
 የውል ተቀባይ እንዲጠቀም የተፈቀደለትን ጊዜያዊ ቦታ/ሸድ በዉል ሰጪ ስምምነትና ፈቃድ ዉሉ ካልታደሰ
በስተቀር የተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ የተሰጠውን ጊዜዊ ካርታ እና ውል በመመለስ ያለ ምንም ቅደመ
ሁኔታ የመልቀቅ ግዴታ አለበት፡፡
 ውል ተቀባይ የዉል ጊዜ ሲጠናቀቅ ቦታዉ ላይ የሰፈረዉን ንብረት በራሱ ወጪ የማንሳት ግዴታ ይኖርበታል፡፡

 ውል ተቀባይ ሕንፃውን ወይም ቦታውን መልቀቅ ሲፈልግ የተረከበውን ማንኛውንም ንብረት ሲረከብ
በነበረበት ሁኔታ ለአከራይ የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
8. የውል ሰጪግዴታና የመቆጣጠር ስልጣን

 የውል ተቀባዩን መብቶች የማክበር ግዴታ አለበት፡፡


 ውል ሰጪው ለህዝብ ጥቅም ሲባል ውሉ ከመጠናቀቁ በፊት እንዲቋረጥ ሲያደርግ ለውል ተቀባዩ
እንደአስፈላጊነቱ ለቀሪው ጊዜ ትክ ቦታ/ሸድ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

21
 ለውል ተቀባዩ ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
 በጊዜያዊነት የተፈቀደው ቦታ/ሸድ በአግባቡ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ እና በየዓመቱ የሚከፈለው
ክፍያ ወቅቱን ጠብቆ እየተከፈለ መሆኑን መከታተልና ማረጋገጥ አለበት፡፡
 የሊዝ/ኪራይ ውሉ ከመፈረሙ በፊት ስለ ውሉ ይዘት ማሳወቅ አለበት፡፡
 ቦታው/ሸዱ ለተፈቀደለት አገልግሎት መዋሉን እና መልማት ባለበት አግባብ እለማ መሆኑን
ይቆጣጠራል፡፡

9. የውል መቋረጥ

በውሉ መሰረት በሚከተሉት ምክንያቶች ውል ሊቋረጥ ይችላል፡-

 ውል እዲፈርስ ሁለቱም ወገኖች ሲስማሙ፤


 ውል ተቀባዩ ግዴታውን ካልተወጣ፤
 ቦታው ለህዘብ ጥቅም ሲባል ለሌላ አገልግሎት እንዲውል ሲፈለግ፤
 የሊዝ /ኪራይ ይዞታው ዘመኑ ተጠናቆ ውሉ የማይታደስበት ሁኔታ ሲኖር፤
 ቦታው/ቤቱ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ተላልፎ ሲገኝ፣

10. ስለውሉ መጽደቅ

ይህ ውል ተቀባይ አና ውል ሰጪው ከዚህ በላይ በዝርዝር የተገለፀውን የውል ስምምነት አንብበው እና ተስማምተው
በፊርማቸው አጽድቀው በአራት ኮፒ በማዘጋጀት አንድ ኮፒ ለውል ተቀባይ ፣አንድ ኮፒ ለማይንቀሳቀስ ንብርት ምዝገባ
ተቋም፣አንድ ኮፒ ለግንባታ ፈቃድ ሰጭ ተቋም እና አንድ ኮፒ የውል ተቀባይ ማህደር ውስጥ ተያይዞ ይቀመጣል፡፡

11. የውሉ ህጋዊነት

ይህ ውል በሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ከተፈረመ በኋላ ለ………………ዓመት የጸና ይሆናል፡፡


በ………………………./ከተማ አገ/ጽ/ቤት/ ማዘጋጃ ቤት እና

እኔ…………………ሊዝ ተቀባይ የውሉን ጠቅላላ ይዘት በአግባቡ መርምረን በመገንዘብ በውሉ


መሰረት መብታችንን ስናስከብር ግዴታችንንም ለመፈጸም በፈቃዳችን ተስማምተን በፊርማችን
አጽድቀናል፡

የውል ሰጪ የውል ተቀባይ


ስም_______________ ስም_______________
ፊርማ______________ ፊርማ_______________
ቀን_______________ ቀን_______________

22
አባሪ--6 ፡- ጊዜያዊ የከተማ ቦታ መጠቀሚያ የምስክር ወረቀት

የ ከተማ ኢንዱ/ል/ከ/አገ/መምሪያ/ጽ/ቤት/ማዘጋጃ ቤት/

ጊዜያዊ የከተማ ቦታ መጠቀሚያ የምስክር ወረቀት፤


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የከተማ ቦታ በሊዝ ወይም በኪራይ ስለመያዝ እንደገና በመደንገግ
በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 18 ንዑስ እንቀጽ 2 እንዲሁም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር
ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ/በኪራይ ለማስተዳደር ባወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 ዓ.ም አንቀጽ 25 ንዑስ አንቀጽ 3
መሠረት በ ቁጥር የተመዘገበውና በዚህ ገጽ መጠኑ በግልጽ የተመለከተው የከተማ ቦታ
ለአቶ/ወ.ሮ/ሪት/ድርጅት በሊዝ ወይም በኪራይ ለመያዝ በውል ቁጥር
በመዋዋላቸው ይህ ጊዜያዊ የመጠቀሚያ የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
የፓስፖርት
ጊዜያዊ የመጠቀሚያ የምስክር ወረቀት ቁጥር --------–----- መጠን ያለው
ጉርድ ፎቶ ግራፍ

የቦታው አቀማመጥ

አዋሳኝ:-
በሰሜን -----------------------

በደቡብ ----------------------

በምስራቅ----------------------

በምዕራብ ---------------------

ሚዛን––––––– የተሰጠበት ቀን ––––––––––––––––


ያዘጋጀው ባለሙያ ስም––––––––––––––
ፊርማ ––––––––––––––––––––
ያጸደቀዉ ሀላፊ ስም –––––––––––––––
ፊርማ–––––––––––

23
አባሪ--7፡- በጊዜያዊነት የተሰጡ ቦታዎች መረጃ ማሰባሰቢያ ፎርም/ቅፅ/

ይዞታው የሚገኝበት የቦታ የቦታ የሚሰ የኘ በየአመ የቦታው የሊዝ/ የሊዝ/ የፕላን
አድራሻ ው ው ጠው ሎት ቱ ጠቅላላ ኪራይ ኪራይ ውሉ ምደባ
ደረ ስፋት አገልግ ቁጥ የሚከፈ የሊዝ/ኪራይ ዘመን የሚጠናቀቅ ኮድ
ጃ ሎት ር ለው ክፍያ በት ጊዜ ቁጥር
የሊዝ
ኪራይ
ክፍያ
ዞን ወረዳ ከተማ ቀበሌ/
ልዩ ስም

24

You might also like