You are on page 1of 77

ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ

[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ


የማስተማሪያ ኖት

ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ


ጥናት

በደብረ ፍስሃ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ


ቤተክርስቲያን ውሉደ ብርሃን ሰ/ት.ቤት
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ የማስተማሪያ ኖት

በደብረ ፍስሃ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 2
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

መክስተ አርዕስት (የአርዕስት ማውጫ)

መግቢያ..................................................................................................................................................................................................................................5
ምዕራፍ 1፡- የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት ........................................................................................................................................7-13
1.1 የቃሉ ትርጉም......................................................................................................................................................................................................7
1.2 የመጽሐፍ ቅዱስ ቅድስና.....................................................................................................................................................................................8
1.3 መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ልዩ የሚያደርጉት ነጥቦች.....................................................................................................9
1.4 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅም......................................................................................................................................................................................10
1.5 መጽሐፍ ቅዱስ በነማን፣ መቼ፣ በምን ቋንቋ፣ በየት ቦታ ተጻፈ? ....................................................................................................................11
1.6 የመጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ መተርጎም.................................................................................................................................................11
1.7 የመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር /ቀኖና/cannonization..............................................................................................................................................12
1.8 የምዕራፍ አንድ የክለሳ ጥያቄዎች........................................................................................................................................................................13

ምዕራፍ ፪፡- የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ........................................................................................................................................................13-26


፪.1 መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይነበባል? ...................................................................................................................................................................13
፪.1.1 ከጸሎት እና ከመሻት ጋር ማንበብ......................................................................................................................................................13
፪.1.፪ አዘውትሮ ማንበብ.................................................................................................................................................................................13
፪.1.3 የቤሰተብ የንባብ ጊዜ ወስኖ ማንበብ ................................................................................................................................................. 14
፪.1.4 ከቤተክርስቲያን አባቶች (መምሕራን) ድጋፍ በማግኘት ማንበብ....................................................................................................14
፪.1.5 ምላሽ ፈልጎ (የሕይወት ጥያቄዎችን በማንሳት) ማንበብ...................................................................................................................14
፪.1.6 ህዳግ፣ ግፃዌ እና መዝገበ ቃላትን በማመሳከር ማንበብ.....................................................................................................................14
፪.፪ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ባሕል.........,................................................................................................................................................................14
፪.፪.1 የዕብራውያን ስም አወጣጥ ባሕል........................................................................................................................................................15
፪.፪.፪ የዕብራውያን የአነጋገር ዘይቤ.................................................................................................................................................................17
፪.፪.፪.1 በማራቅ መናገር.....................................................................................................................................................................18
፪.፪.፪.፪ ቃላትን በመደጋገም መናገር .................................................................................................................................................18
፪.፪.፪.3 “ከ...... ጋር ምን አለኝ?”........................................................................................................................................................19
፪.፪.3 የዕብራውያን ኃዘን አገላለጽ ................................................................................................................................................................. 19
፪.፪.4 በዕብራውያን የ ”በኩር ትርጉም .................................................................................................................................................... 19
፪.፪.5 በዕብራውያን የ “ወንድም” ትርጉም ............................................................................................................................................... 20

፪.3 መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይተረጎማል? ...............................................................................................................................................................20


፪.3.1 መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ያስፈለገበት ምክንያት..................................................................................21
፪.3.፪ መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ እንዴት ሊተረጎም ይችላል ..............................................................................................21
፪.3.3 ነጠላ ትርጉም................................................................................................................................................................................22
፪.3.4 ምሳሌያዊ ትርጉም........................................................................................................................................................................22
፪.3.5 ምስጢራዊ ትርጉም....................................................................................................................................................................24
፪.4 የምዕራፍ ሁለት የክለሳ ጥያቄዎች ........................................................................................................................................................................26

በደብረ ፍስሃ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 3
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ምዕራፍ 3፡- የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል ............................................................................................................................... 27-69


3.1 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት .................................................................................................................................... 27
3.1.1 የቃሉ ትርጉም ................................................................................................................................. 27
3.1.፪ የመጻሕፍቱ ብዛት............................................................................................................................. 27
3.1.3 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አከፋፈል....................................................................................................... 28
3.1.3.1 የህግ መጻሕፍት...................................................................................................................................................28
3.1.3፪ የታሪክ መጻሕፍት..............................................................................................................................................30
3.1.3..3 የመዝሙር የጥበብና የቅኔ መጻሕፍት..............................................................................................................37
3.1.3.4 የትንቢት መጻሕፍት..........................................................................................................................................40
3.፪ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት....................................................................................................................................... 47
3.፪.1 የቃሉ ትርጉም.................................................................................................................................. 47
3.፪.፪ የመጻሕፍቱ ብዛት ............................................................................................................................. 47
3.፪.3 የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አከፋፈል ......................................................................................................... 48
3.፪.3.1. ወንጌላት................................................................................................................................................................48
3.፪.3፪ የታሪክ መጽሐፍ.................................................................................................................................................52
3.፪.3..3. መልእክታት .......................................................................................................................................................53
3.፪.3..4 የትንቢት መጻሕፍት...........................................................................................................................................65
3.፪.3..5 የሥርዓት መጻሕፍት.......................................................................................................................................66
1.3 የምዕራፍ ሶስት የክለሳ ጥያቄዎች......................................................................................................................................................................69

ምዕራፍ 4፡- አዋልድ መጻሕፍት ........................................................................................................................................... 69


4.1 የቃሉ ትርጉም .................................................................................................................................................. 69
4.፪ የአዋልድ መጻሕፍት አስፈላጊነት............................................................................................................................ 70
4.3 አዋልድ መጻሕፍትን ጸሐፊዎች.........................................................................................................................................................................70
4.4 የአዋልድ መጽሐፍት የአስራው መጻሕፍት ልጆች መሆናቸው በምን ይታወቃል?........................................................................................70
45 የአዋልድ መጻሕፍት መሰረታቸው ምንድን ነው?..............................................................................................................................................71
46 የቤተክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት ዝርዝር ........................................................................................................................................................71
ሀ. አንድምታ.......................................................................................................................................................................73
ለ. ስንክሳር..........................................................................................................................................................................74
ሐ. የጸሎት መጻሕፍት ......................................................................................................................................................74
መ. ገድላትና ድርሳናት.......................................................................................................................................................75
ሠ. ተኣምራት......................................................................................................................................................................75
47 አዋልድ መጻሕፍትን ስናነብ ልብ ልንላቸው የሚገቡ ነጥቦች...........................................................................................................................76
48 የምዕራፍ አራት የክለሳ ጥያቄዎች.........................................................................................................................................................................76
ማጠቃለያ.............................................................................................................................................................................................................76
ዋቢ መጻሕፍት....................................................................................................................................................................................................78

በደብረ ፍስሃ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 4
መግቢያ
ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም ለእናንተ ይሁን!!! የተወደዳችሁ እና
የተከበራችሁ ተማሪዎች በዚህ ክፍለ ትምህርት እግዚአብሔር ለእኛ ፍቃዱን የገለጠበትንና እኛ ልጆቹ እንመራበት
ዘንድ የሠጠውን ቅዱስ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ) ምንነት እና አጠቃላይ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የቅድስት
ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ በስፋት ለመመልከት እንሞክራለን፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ለመነሻነት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ
ሺኖዳ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የጻፉትን ጽሑፍ ለመግቢያነት እንመልከት፡-

“መጽሐፍ ቅዱስ የመጽሐፎች መጽሐፍ ነው፡፡ እውነትም ታላቅ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፍም ሲባል
የእግዚአብሔር መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃሉ ነው፡፡ በእርሱ አንተን ይናገርበታል፡፡ መጽሐፍ
ቅዱስ በእግዚአብሔር የተገለጠና በቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት አንደበት የተነገረ እውነት ነው፡፡1 ጥቅሙም
እንድትማርበት፣ ለእግዚአብሔር የቀና ልብ እንዲኖርህ በአጠቃላይ የፈጣሪህን ፍቃድ ተከታይ እንድትሆን ለማድረግ
ነው፡፡2 መጽሐፍ ቅዱስ ለአንተ ከእግዚአብሔር የተላለፈልህ መልእክት ነው፡፡ በዚህ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር
በመጣለት መልእክት ደስ የማይለው ማን ነው? በአንድ ወቅት ታላቁ ቅዱስ አባት አባ እንጦስ ከንጉስ ቆስጠንጢኖስ
የተላከ ደብዳቤ ደረሰው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም አባታቸው የንጉስ ደብዳቤ ስለደረሰው እጅግ በጣም ተደሰቱ እርሱ ግን
ምንም የተለየ ግምት ሳይሠጠው ወደ ጎን አለው፡፡ አሁንም ተማሪዎቹ በመደነቅ ብዛት ለማንበብ በጣም ጓጉ አባ
እንጦስ ግን ‹‹ልጆቼ ከሠው ለመጣ ደብዳቤ እንዴት እንደዚህ ደስ ይላችኋል? እነሆ የነገስታት ንጉስ እግዚአብሔር
የብዙ ብዙ ደብዳቤዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልኮልናል ለምን በዚህ መልዕክት አትደሠቱም? ለማንበብስ
እንዴት አልጓጓችሁም?›› ብሎ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ካስተማራቸው በኋላ ደብዳቤውን አነበበ፡፡ ለንጉሱም
የሚያስፈልገውን የበረከት መልስ ሠጠው፡፡ አንተስ ከምትወደውና ከምትናፍቀው ሰው ደብዳቤ ቢደርስህ እጅግ
ተደስተህ በየሰዓቱ ታነበው የለምን? ከሆነ ደግሞ ከእግዚአብሔር ለመጣልህስ ይህን ያህልና የበለጠ መደሰትና
መጓጓት በየሠዓቱ ማንበብ አይገባህም ነበር? ይህ ከእግዚአብሔር ወደ አንተ የተላከው መልእክት በመንፈስ ቅዱስ
የተቃኘ ይመራቸው የነበሩ ነብያት የተነገረ እና ቃሉ ራሱ በመንፈስ ቅዱስ የሆነ መልእክት ነው፡፡ ይህን ደግሞ
በውስጡ ባለው መንፈስና ሕይወት መረዳት ትችላለህ፡፡ ጌታችንም ‹‹እኔ የነገርኳችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም
ነው››3 ሲል ተናግሯል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ተመግበኸው ሕይወት እንድታገኝበት ከእግዚአብሔር የተሠጠህ መንፈሳዊ ምግብ ነው፡፡
ጌታችን ዲያቢሎስ ሊፈትነው በቀረበው ጊዜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሶ እንደተናገረው ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ
በሚወጣው ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም››4 እናም ለስጋዊ ሕይወትህ የሚሆን ስጋዊ ምግብ ትመገባለህ
እንዲሁም በውስጥህ የማይሞት የማይበሰብስ መንፈስ ስላለ መንፈሳዊውንም ምግብ መጽሐፍ ቅዱስን መመገብ
እና ሕይወትን ማግኘት አለብህ ‹‹እውነት እውነት እላችኋለው ቃሌን የሚሠማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም
ሕይወት አለው›› ዮሐ 5፡24 እናም ወንድሜ ሆይ መኖር የምንችለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባለው የሕይወት
ቃል ጭምር እንጂ በእንጀራ ብቻ እንዳልሆነ እርግጠኛ ሁን ‹‹የዕለት ምግባችንን ስጠን ዛሬ››5 እያልን ስንጸልይም
የሕይወት ምግባችንንም የሚያጠቃልል እንደሆነና ስለ ስጋችን ብቻ እንደማትጠይቅ ልብ ልንል ይገባል.... እናም
ዘወትር ቃሉን አጥናው!!! ሁሌም አትርሳው!!! ይህ የበጎ ነገር መጀመሪያ ነውና!!!

...የእግዚአብሔር ሠው ክርስቲያን ሆይ እጅግ ብዙ የተጠቀምክበትና ብዙ ነገር የምታስታውስበት መጽሐፍ


ቅዱስን በእጅህ ላይ ሊታይ ይገባዋል፡፡ ለእይታ ለጌጥ ብቻ ያልሆኑ መጻሕፍት የክርስቲያን መለያዎች ናቸው፡፡
እባክህ ይህንን የሕይወት መጽሐፍ ተጠቀምበት!!! አንብበው!!! አስበው!!! ወደ ጥልቁም ግባና ከነፍስህ ጋር
አዋህደው!!!”6

1
2ጴጥ 1፡21
2
2ጢሞ 3፡16
3
ዮሐ 6፡63
4
ዘዳ 8፡3፣ማቴ 4፡4
5
ማቴ 5፡11-12
6
ጉዞ ወደ እግዚአብሔር ከገጽ 24-27
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

በማለት አባታችን አቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሆነና በሕይወታችን ያለውን የጎላ ድርሻ በማስረዳት
ዘወትር ልናነበው እንደሚገባ ይስረዱናል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም የነፍስ ምግብ ስለሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር
በዚህ ክፍለ ትምህርት የምንመለከት ይሆናል፡፡ ሰው ሁሉ ለመንገዱ ብርሃን ይሆንለት ዘንድ ነፍስም ሕይወትን
አግኝታ እንድትኖርበት ነብያቱንና ሐዋርያቱን ያናገረ የተናገሩትንም በመጽሐፍ እንዲጽፉት ያደረገ አምላካችን
ምስጢርና ጥበቡን ይገልጥልን ዘንድ የእርሱ በጎ ፈቃድ ይሁንልን!!!

መልካም ትምህርት
ተከታታይ ትምህርት ክፍል

ማሳሰቢያ
 ውድ ተማሪዎች በማስተማሪያ ኖቱ ላይ ማብራሪያ ሀሳቦችንና መጣቀሻ መጻሕፍትን በግርጌ ማስታወሻ
ላይ ያሠፈርን በመሆኑ በትምህርቱ ላይ ከግርጌ ስር ካለው ማጣቀሻ ጋር በማጣቀስ እንድታነቡ
 በምዕራፉ መጨረሻ ያሉትን የክለሳ ጥያቄዎች እንድትሰሩ በጥያቄዎቹም ላይ ማብራሪያና ምላሽ
እንደዲሰጡ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች ለመምሕራቹ በማቅረብ ማብራሪያ እንዲሰጡባቸው
እንድታደርጉ

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 6
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ምዕራፍ 1
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት

የተሰጠው ክፍለ ጊዜ ፲4 የትምህርት ቀናት


የትምህርቱ ዓላማዎች፡- ከትምህርቱ መጠናቀቅ በኋላ ተማሪዎች፡
 መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔር መሆኑን ይረዳሉ
 የመጽሐፍ ቅዱስን የአተረጓጎም ዘዴ ያውቃሉ
 የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ያውቃሉ
 የመጸሐፍ ቅዱስን አከፋፈል ይገነዘባሉ
 የአዋልድ መፃሕፍትን አገልግሎቶች ያብራራሉ እና
 በየዕለቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የማንበብ ልምድ ያዳብራሉ፡፡

1.1 የቃሉ ትርጉም


መጽሐፍ ቅዱስ የሚለዉ ሐረግ “መጽሐፍ” እና “ቅዱስ” ከሚሉት ሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን መጽሐፍ ማለት
7

በአንድ ጥራዝ ስር የተሰበሰበ ጽሑፍን ሲገልጽ ቅዱስ8 የሚለው ቃል ደግሞ የግዕዝ ቃል ሲሆን የተለየ፣የተከበረ፣…
የሚል የአማረኛ ትርጉምን ይሠጠናል፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በአንድ ጥራዝ ስር የተሰበሰበ የተለየ፣
የተከበረ ጽሁፍ ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ማለት የተለየ፣ የተቀደሰ እና የተከበረ ዘመን የማለውጠው
ዓለማዊውም ሆነ መንፈሳዊው ዓለም በስፋት የተዳሰሰበት ቀዋሚ የሆነ ገጽታ ያለው ጾታ ዕድሜ እና ነገድ
የማይለየው ለሰው ልጆች ሁሉ የተሠጠ መጽሐፍ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ብቻዉን መቆም
የሚችል እዉነት ነው፡፡ ይህ ማለት የትኛዉም እዉነት በመጽሐፍ ቅዱስ ይረጋገጣል እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን
ማረጋገጥ የሚችል ሌላ እዉነት የለም፡፡
ከዚህ ዉጪ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው ለሚለው ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለህዝቡ
ያስተላለፈው ቅዱስ ቃል ነዉ የሚለዉ ምላሽ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ፡-

ሀ. የመንፈስ ምግብ ነዉ
 “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም”
ማቴ 4÷4፣ ዘዳ 8፡3
 “ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ የሠራዊት አምላክ ሆይ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ
ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ” ኤር 15፡16
 “የሰው ልጅ ሆይ ያገኘኸውንም ብላ ይህንንም መጽሐፍ ብላ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር አለኝ
አፌንም ከፈትኩ መጽሐፉንም አጎረሰኝ እርሱም፡- የሰው ልጅ ሆይ አፍህ ይብላ በምሰጥህም በዚህ
መጽሐፍ ሆድህን ሙላ አለኝ እኔም በላሁት በአፌም ውስጥ እንደማር ጣፈጠ” ሕዝ 3÷1-3
 “ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ” መዝ 118÷103
ለ. ብርሃን ነዉ
 “ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው” መዝ 118÷105
ሐ. ህያዉና የሚሰራ ነዉ
 “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና የሚሠራ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው
ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለይ ድረስ ይወጋል የልብንም ስሜትና ሀሳብ
ይመረምራል” ዕብ 4÷12
መ. ዘላለማዊ ነዉ

7
መጽሐፍ ቅዱስ በግሪክ ቋንቋ “ቢብሎስ/ Byblos/ ወይም “ግራፌ ከሚል ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ቢብሎስ ማለት ከኒቂያ ወደቦች መካከል ከቤይሩት 25
ማይል ርቆ የሚገኝ ከተማ ሲሆን በዛች ከተማ ለመጻፍ የሚያገለግል “ፓፒረስ/ደንገል የተባለው ተክል እንደ ወረቀት አድርገው የሚሠሩበት ቦታ ነው፡፡
ቦታውንም መጀመሪያ ግሪኮች “ቢብሎስ ብለው ይጠሩት ነበር፡፡ ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ ግን ስያሜው ለመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ መጠቀም ጀመረ፡፡
በላቲን ደግሞ “ስክሪፕቸር/ የሚል ስም ሲኖረው ይህም ለሁሉም ጽሑፍና መጽሐፍ ማመላከቻ ሆኖ ከቆየ በኋላ ለመጽሐፍ ቅዱስ ማመላከቻ ብቻ
ሆኖ ከጊዜያት በኋላ ተቀይሯል፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት ደግሞ በተለይ በፍትሐ ነገስት ላይ “መጻሕፍት አምላካውያት”ተብሎ ይጠራል፡፡
8
ቅዱስ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ክዳሽ ፣ በሱርስት “ካዲሽ የሚሉትን ቃላት ይተካልናል፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 7
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 “ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም” ማቴ 24÷35


ሠ. የሰዉ ልጅ ዳግመኛ የሚወለድበት የማይጠፋ ዘር ነዉ
 “ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል
ነውና” 1ጴጥ 1÷23
ረ. የመንፈስ ሰይፍ ነዉ
 “በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን እንደሰው ልማድ አንዋጋም የጦር ዕቃችን
ሥጋዊ አይደለምና” 2ቆሮ 10÷3
 “የዲያቢሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን የጦር እቃ ሁሉ ልበሱ
መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም
ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር ነው እንጂ”
ኤፌ 6፡12

1.፪ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅድስና


መጽሐፍ ቅዱስ የተቀደሰ መጽሐፍ ነው ይህም የተባለበት የራሱ ምክንያቶች አሉት፡፡ ከዚህም በመቀጠል ነጥቦቹን
በዝርዝር እንመለከታለን፡-

ሀ. አስገኚው እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ


መጽሐፍ ቅዱስ በቅዱሳን ሰዎች ለሰው ልጆች የተጻፈ መጽሐፍ ቢሆንም ቅዱሳን ሰዎች ከራሳቸው
አፍልቀውና አመንጭተው የጻፉት መጽሐፍ ግን አይደለም ይልቁኑ በእግዚአብሔር መሪነት የተጻፈ እና የተገኘ
መጽሐፍ ነው፡፡ እናም መጽሐፍ ቅዱስን ያስገኘው እግዚአብሔር ደግሞ በባሕርይው ቅዱስ ነው፡፡
 “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ዘሌ 19÷2
 “የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮዓችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ”
1ጴጥ 1፡15-16
እናም አስገኚው እግዚአብሔር ቅዱስ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስም በጸጋ ቅዱስ ተብሏል፡፡ ለዚህም ነው “ቅዱሳት
መጻሕፍት” ተብሎ የተጠቀሰው9 እናም መጽሐፍ ቅዱስ አስገኚው እግዚአብሔር ቅዱስ በመሆኑ ቅዱስ ተብሏል፡፡
 “በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም አፌ አዝዟልና መንፈሱም ሰብስቧቸዋልና ከእነዚህ
አንዲት አትጠፋም” ኢሳ 34፡16

ለ. በእግዚአብሔር መንፈስ የተመሩ ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት ስለሆነ


መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር አነሳሽነት እና መሪነት በቅዱሳን ሰዎች የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ ሲባል
መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት የቅድስና ማዕረግ የተሰጣቸው ቅዱሳን ነብያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት፣ ቅዱሳን አርድዕት፣
ወዘተ.... ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ይህንን ሲያስረዳ፡-
 “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች
በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ እንጂ” 2ጴጥ 1፡20
መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊትም መጽሐፍ ቅዱስን የተጻፈው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳኑ ላይ
አድሮ ባናገረው መሠረት መሆኑን ሲገልጥ፡-
 “እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ ቃሉም በአንደበቴ ላይ ነበረ” 2ሳሙ 23፡2
ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ ኪዳን አምስት መጽሐፍን የጻፈው ባለ ራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስም ይህንን ሲገልጥ፡-
 “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰርምኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትርያጥሮንም
ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያም ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ
ክርስቲያናት ላክ አለኝ” ራዕ 1፡11
እግዚአብሔርም ሙሴን፡-

9
2ጢሞ 3፡15
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 8
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 እግዚአብሔርም ለሙሴ የአማሌቅን ዝክር ከሠማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህንን


ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው በኢያሱም ጆሮም ተናገር አለው” ዘጸ 17፡14

እናም የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከላይ በዝርዝር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን በመጥቀስ ለመግለጽ
እንደሞከርነው መጽሐፍ ቅዱስን ለመጻፍ የእግዚአብሔር አነሳሽነት እና ገላጭነት እንደሚያስፈልግና መጽሐፍ
ቅዱስ እግዚአብሔር በጠራቸው እና በመረጣቸው ቅዱሳን ሠዎች በእግዚአብሔር ገላጭነት የተፃፈ መጽሐፍ
በመሆኑ ቅዱስ ሊባል ችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን ቅዱስ ያስባለው፡-

ሐ. አንባቢያኑን የሚሰሙትንና ተከታዮቹን ወደ ቅድስና የሚመራ በመሆኑ


መጽሐፍ ቅዱስ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ የእግዚአብሔር ህግና አዋጅ ነው፡፡ የእግዚአብሔር
ሰውም ከዚህ ህግና አዋጅ ጋር ልክ እንደ ቅዱሳን አባቶች ያለው ግንኙነት ቋሚና የጠበቀ መሆን አለበት፡፡ ያን
ባደረገ ሠዓት ህግጋትን በመጠበቅ የሚገኘውን የቅድስና ክብር ያገኛል፡፡
 “የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብጹዕ ነው” ራዕ 22፡7
 “በእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት
በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” 2ጢሞ 3፡16-17

1.3 መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ልዩ የሚያደርጉት ነጥቦች


መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት የሚለይባቸዉ የተለያዩ ነጥቦች አሉ፡፡ እነዚህም፡-

ሀ. በእድሜዉ ርዝማኔና ዘመን የማይሽረው በመሆኑ


መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ላይ ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ግንባር ቀደሙ መጽሐፍ ነዉ፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ
ዉስጥ ቅድሚያ የተጻፈዉ መጽሐፍ መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን የተጻፈዉም በ1486 ዓ.ዓ ነዉ፡፡ ይህም መጽሐፍ
ቅዱስን የመጀመሪያዉ መጽሐፍ ያደርገዋል፡፡ ሌላዉ መጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የማይሽረው መሆኑ ነው፡፡ በተለያዩ
ደራሲያን የተጻፉ መጻሕፍት ለአንድ ወቅት የሚነበቡ አሊያም መወያያ ርዕስ እየሆኑ ለታሪክ ወይም ለመረጃ
ሊቀመጡ የሚችሉ ናቸዉ፡፡ እነዚህ መጻህፍት ወቅትና ጊዜ እየተለወጠ ቴክኖሎጂ እያደገ በሄደ ቁጥር የሚሻሻሉ
(የሚለወጡ) ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ግን በዘመናት መለዋወጥ ሊለወጥ የማይችል ነዉ፡፡
 “ሳሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች”
ኢሳ 40፡8
 “ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም” ማቴ 24፡35
 “የጌታ ቃል ግን ለዘለዓለም ይኖራል” 1ጴጥ 1፡25

ለ. የሚያነቡትንና የሚሰሙትን የሚያንጽ በመሆኑ


በዓለም ላይ ብዙ አይነት ቢኖሩም ከነዚህ መጻሕፍት ቢኖሩም ከእነዚህ መጻሕፍት የምናገኘዉ እዉቀትን
ብቻ ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከእነዚህ የሚለየዉ የሚያነቡትንና የሚሰሙትን ሰዎች ከእውቀት በተጨማሪ
ሕይወት የሚሆናቸዉን ትምህርት የሚያገኙበት መጽሐፍ በመሆኑ ነዉ፡፡
 “ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ የሠራዊት አምላክ ሆይ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ
ሐሤትና ደስታ ይሁኝ” ኤር 15÷16
 “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት
በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል” 2ጢሞ 3÷17

ሐ. ስላለፈዉና ሰለሚመጣው ነገር በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ


ለምሳሌ፡- ሰላለፈዉ ሲናገር ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከርሱ በፊት ስለተፈጸመዉ የሥነ ፍጥረት ታሪክ ሲናገር በ
“ይሆናል” ወይም በ “ሳይሆን አይቀርም” በሚል ግምት ሳይሆን በእርግጠኝነት ነዉ ሌሎች መጽሐፍት የታሪክ
ወይም የምርምር መጽሐፍት ግን በ “ይሆናል” ወይም “ሳይሆን አይቀርም” በሚል ያስቀምጣሉ፡፡ እንዲሁም
መጽሐፍ ቅዱስ ስላለፈዉ ብቻ ሳይሆን ወደፊት የሚመጣዉንም በእርግጠኝነት የሚናገር ልዩ መጽሐፍ ነው፡፡

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 9
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

1.4 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅም


የተወደዳችሁ ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅም እንዲህ በቀላሉ ለመግለጽ መሞከር የማይቻል ቢሆንም
ጠቅለል ባለ መልኩ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የተወሠነውን ለመዘርዘር እንሞክራለን፡-

ሀ. እግዚአብሔርን የበለጠ ለማወቅና ለመቀደስ ይረዳል


እግዚአብሔር በባህርይው የማይመረመር ምጡቅ አምላክ ነው፡፡10 ነገር ግን ለፍጥረታቱ እርሱ በወደደ እና
በፈቀደ መጠን ፍጥረታቱም በሚረዱት መጠን ራሱን ገልጧል፡፡ የሰው ልጅም በተፈጥሮ በተሠጠው ህሊና
የእግዚአብሔርን መኖር ቢረዳም እግዚአብሔር ለሰው በህሊናው ስለእርሱ ከሚያውቀውና ከሚረዳው በተሻለ
ያውቀውና ይረዳው ዘንድ ራሱን በመጽሐፍ ቅዱስ ገልጧል፡፡ እናም የሰው ልጅ በህሊናው ካገኘው እውቀት በበለጠ
እግዚአብሔርን በመጽሐፍ ቅዱስ ሊያውቀውና ሊረዳው ችሏል፡፡ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ወቅት
ከሚያገኘው ዓለማዊ እውቀት ባሻገር በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ መጽሐፍ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ግሩም
እና ድንቅ ሥራዎችን ይረዳል፡፡11 ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ከአሁን በፊት በነበሩትና ወደፊት በሚመጡት
ዘመናት እግዚአብሔር የፈጸመውንና ሊያደርግ ያሰበውን መለኮታዊ ዕቅድ አካቶ የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ ጌታችንም
በመዋዕለ ስጋዌው ይህንን ሲግልጥ፡-
 “እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን
ትመረምራላችሁ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው” ዮሐ 5፡39

ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በቅዱሳን ሰዎች የተጻፈ ቅዱስ መጽሐፍ
በመሆኑ የሚያነቡትን፣ የሚያጠኑትን እና ለጸሎት የሚጠቀሙበትን ሁሉ የሚቀድስ መጽሐፍ ነው፡፡
 “በእውነት ቀድሳቸው ቃልህ እውነት ነው” ዮሐ 17፡17
 “ከቃሉ ጋር አጽንቶ እንዲቀድሳት ራሱን አሳልፎ ሰጠ” ኤፌ 5፡26

ለ. ሠዎች በክርስቶስ በማመን የዘላለም ሕይወትን እንዲወርሱ ይረዳል


እግዚአብሔር አብ ለሰው ልጆች ያለውን መጠን የለሽ ፍቅር የገለጠው ተቀዳሚም ተከታይም የሌለው አንድ
ልጁን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ነው፡፡ የሰው ልጅ ይህንን የእግዚአብሔርን ፍቅር እንዲያውቅና እንዲገነዘብ አውቆና
ተገንዝቦም የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበትን ኢየሱስ ክርስቶስን አምኖ የዘላለም ሕይወትን ይወርስ ዘንድ
የእግዚአብሔር ፍቃድ በመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው የዘላለም ሕይወትን እንዲወርሱ
ተሰጥቷል፡፡ በዚህም መነሻነት አንድ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘውን ሕይወት
ማግኘት ይችላል ማለት ነው፡፡
 “ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ
ነው” ዮሐ 6፡40
 “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ታምኑ ዘንድ አምናችሁም በስሙ
ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል” ዮሐ 20፡31

ሐ. ለሰው ልጅ መመሪያ ይሆናል


መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች እግዚአብሔር በሚወደው እና በሚፈቅደው መንገድ ተጉዘው ዘላለማዊ ድኅነትን
እንዲያገኙ የሚረዳ መጽሐፍ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሰው ልጅ ብርሃኑን ከጨለማው፣ መልካሙን ከመጥፎው
እንዲለይና እንዲያውቅ የሚያደርግ ሕይወቱንም እንዲያቀና የሚረዳ መጽሐፍ ነው፡፡ በዋናነትም መጽሐፍ ቅዱስ
የተጻፈበት አንዱ ዓላማ ይህንኑ ጥቅም ሰዎች ያገኙ ዘንድ ነው፡፡
 “እግዚአብሔር ለሕዝቡ በውስጧም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል”
መዝ 86(87)፡6
 “ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው” መዝ 118(119)፡105
 “አንተን እንዳልበድል ቃልህን ሰወርሁ” መዝ 118(119)፡11

10
ኢዮብ 11፡7-10
11
መዝ 65(66)፡3
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 10
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹም ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ


ያለበትን መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር
ደግሞ ይጠቅማል” 2ጢሞ 3፡16-17
 እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ለአንተ ዛሬ እነሆ አስታወቅሁህ የእውነት ቃል
እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ ለሚጠይቅህም የእውነት ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ በምክርና
በእውቀት የከበረን ነገር አልጻፍሁልህምን?” ምሳ 22፡19-20
ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ፡-
 በሥራችን ስኬታማ ለመሆን............... ኢያ 1፡8-9
 አስተዋይ እና ብሩህ አይምሮ እንዲኖረን........ መዝ 18(19)፡8
 እግዚአብሔር የገባልንን ርስት ለመቀበል....... ሐዋ 20፡32
 መንፈሳዊ ውጊያን ለመዋጋት................... ኤፌ 6፡10-18 የሚጠቅም ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
ውድ ተማሪዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅም ለአብነት ይህንን አነሳን እንጂ ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ተዘርዝረው
የማያልቁ ብዙ ጥቅሞችን ያገኛል፡፡ እናም እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበትን ቅዱስ መጽሐፍ ለማንበብ መትጋት
ይኖርብናል፡፡

1.5 መጽሐፍ ቅዱስ በነማን፣ መቼ ፣ በምን ቋንቋ፣ በየት ቦታ ተጻፈ?


መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች /ሀገሮች/ ከልዩ ልዩ ተግባራት በተጠሩ ከ40 በላይ በሚሆኑ ቅዱሳን
ነብያትና ሐዋርያት ተጽፏል፡፡ ምንም እንኳን መጻሕፍቱ በተለያየ ቦታና ጊዜ ቢጻፉም በመንፈስ ቅዱስ መሪነትና
ገላጭነት በቅዱሳን ሰዎች የተፃፉ በመሆናቸዉ እርስ በእርስ አይጣሉም (አይጣረሱም)፡፡

 “ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች


በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ እንጂ” 2ጴጥ 1፡20
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጠቅለል ባለ ሁኔታ ከ1486 ዓ.ዓ እስከ 400 ዓ.ዓ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተጻፉ
ሲሆን በዚያ ዘመን ውስጥ እንደኖሩበት ቦታ በተለያየ ቋንቋ እና ባሕል እንዲሁም ኑሮ ዘይቤ ተጽፏል፡፡ ትንቢተ
ዳንዔል በአረማይክ /አረማይስጥ/ ቋንቋ12 ሲፃፍ ሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉት በዕብራይስጥ ቋንቋ13
ተጽፈዋል፡፡
የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ የተጻፉት ከ42ዓ.ም እስከ 96ዓ.ም ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ሲሁን አብዛኞቹ
መጻሕፍት በጽርዕ ቋንቋ14 ሲጻፉ የማቴዎስ ወንጌል በዕብራስጥ የማርቆስ ወንጌል ደግሞ በሮማይስጥ ቋንቋ15
ተጽፈዋል፡፡

1.6 የመጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ መተርጎም

መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራይስጥና በጽርዕ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን ከእነዚህ ቋንቋዎች ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች
በተለያዩ ጊዜያት ተተርጉሟል፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በ284 ዓ.ዓ የንጉስ በጥሊሞስ ዘመን በሰባው ሊቃውንት
አማካይነት ከዕብራይስጥ ወደ ጽርፅ ቋንቋ ተተርጉሟል፡፡ በዘመነ አዲስም መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች
ተተርጉሟል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-
 ወደ ላቲን በአባ ጄሮም በ420 ዓ.ም
 ወደ እንግሊዘኛ በዊክሌፍ /1329-1384/ እና ቴንዴል /1494-1536/
 ወደ ጀርመንኛ ደግሞ በ1545 ዓ.ም ተተርጉሟል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በአሁን ሰዓትም ከ200 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉሟል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ህገ
ኦሪትን ከእስራኤል ቀጥላ ከዓለም ሁሉ አስቀድማ በፈቃዷ የተቀበለች ሃገር ናት፡፡ በዚህ እግዚአብሔር በሰጣት

12
የሶሪያ ቋንቋ ነው
13
ዕብራይስጥ የዕብራውያን ቋንቋ ሲሆን በ2ነገ 18፡26 ላይ “የአይሁድ ቋንቋ ተብሎ ተገልጧል
14
የግሪክ ቋንቋ ነው
15
የሮማውያን ቋንቋ ነው
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 11
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ረጅም የሃይማኖት ዘመን ብዙ ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ ቋንቋዋ ተርጉማለች ይኸውም በ980 ዓ.ዓ ገደማ
ከመጀመሪያው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ እስከ ንጉስ ሰለሞን ዘመን ድረስ የተጻፉት መጻሕፍት በቀዳማዊ ምኒሊክ
አማካኝነት መጥተው ከዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተተርጉመዋል ከዚህ በኋላ የተጻፉት ደግሞ በምርኮ ዘመን
በስደት ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ በመጡ አይሁዳውያን ነገስታቱ እየተጻጻፉ በመላላክና እንደ ኢትዮጵያዊው
ጃንደረባ16 ኢየሩሳሌም ተሳልመው የሚመለሱ አበው ይዘው እየመጡ ተተርጉመዋል፡፡ በአዲስ ኪዳንም፡-
 በ330 ዓ.ም በአባ ሰላማ17 ከሱርስት፣ ከዕብራይስጥና ከጽርዕ ቋንቋዎች ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተተርጉሟል፡፡
 ከ480 ዓ.ም ዘጠኙ ቅዱሳን18 ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ከገቡ በኋላ ግዕዝን ተምረው በአቡነ ሰላማ
የተወጠነውን በተለይም አዲስ ኪዳንን ከጽርዕና ከሱርስት ወደ ግዕዝ ተርጉመዋል
 ከዚያም አባ ሰላማ ዘአዜብ /መተርጎም/ ከ1343-83 ዓ.ም/ ከሰባው የአይሁድ ሊቃውንት ትርጉም ጋር
በማነፃፀር ክለሳ አድርገው ከአብረኛ ወደ ግዕዝ ሙሉ ትርጉም ተረጉሙ፡፡
 ወደ አማረኛም በአባ አብርሃም19 በተባሉ መነኩሴ አማካይነት ከ1808ዓ.ም እስከ 1818ዓ.ም ባለዉ
አስር አመታት ዉስጥ ተተርጉሟል፡፡
 በአለቃ ተወልደ መድኀን አማካይነት ወደ ትግረኛ ሲተረጎም በአናሲሞስ አማካይነት ደግሞ ወደ
ኦሮምኛ ተተርጉሟል፡፡

1.7 የቅዱስ መጻሕፍት ቁጥር /ቀኖና/ cannonization


ቀኖና ማለት “ካኖን“ ከሚል የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መለኪያ፣ ዘንግ/ሸንበቆ/፣ መቃ ማለት
ነዉ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት እስከ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተነጣጥለው ይገኙ ነበር፡፡ ይህም መጻሕፍቱ ለየብቻ
ተጠቅለው20 የተቀመጡ (ክርታስ ይባላሉ) ነበሩ፡፡21 ግኖስቲኮች በሐዋርያት ስም የራሳቸውን የክህደት ትምህርት
እየጻፉ ስላስቸገሩ በካርቴጅ /ቅርጣግ/ ጉባዔዎች /395ዓ.ም፣397ዓ.ም፣399ዓ.ም እና 419ዓ.ም/ ቤተክርስቲያን
የቅዱሳት መጻሕፍትን ዝርዝር በቀኖና ወስናለች፡፡22 በቀኖና መወሰን ያስፈለገበት ምክንያቶች አሉ እነሱም ፡-
ሀ. በእግዚአብሔር መንፈስ በነብያትና በሐዋርያት አማካይነት የተጻፉትን ቅዱሳት መጻሕፍት ከሌሎች
ተራ መጻሕፍት ለመለየት
ለ. በቅዱሳን ስም ይጻፉ ከነበሩ የስህተት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር ያለባቸዉን መጻሕፍት
ለመለየት
ሐ. ለቤተክርስቲያን ዕምነትና ትምህርት አብነት የሚሆኑ የተወሰኑ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲኖራት ለማረግ

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቀኖናዋ መሰረት 81 መጻሕፍትን ትቀበላለች፡፡
/ፍት.ነገ.አን 2/ እነዚህም 46 የብሉያትና 35 የሀዲሳት መጻሕፍት ናቸዉ፡፡ ከቤተክርስቲያን ውጪ ያሉ እምነቶችን
ብንመለከት አይሁድ 39 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን ሳምራውያን 5ቱን የሙሴ መጻሕፍት ሲቀበሉ የካቶሊክ
እምነት 73 የግሪክ ኦርቶዶክስ 76 ፕሮቴስታንት 66 እንዲሁም የራስል ተከታዮች /ጆሆሻውያን/ የ1000 ቃላት
እርማት አድርገው 66 መጻሕፍትን ይቀበላሉ፡፡

16
ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ ሲባል ታሪኩን በሐዋርያት ሥራ 8፡27 እናገኘዋለን፡፡
17
አባ ሰላማ ከሶሪያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ አባት ናቸው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመግባታቸው በፊት ፍሪምናጦስ ይባሉ ነበር፡፡ በኢትዮጵያም መጽሐፍ ቅዱስን ወደ
ግዕዝ ከመተርጎማቸውም በተጨማሪ ነገስታቱን ኢዛናንና ሳይዛናን በማጥመቅ ክርስትና የመጀመሪያው ሃይማኖት እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ወንጌል በኢትዮጵያ
እንዲስፋፋ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኤጲስ ቆጶስ ሆነው በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ ተሹመው በመምጣት ታላላቅ ገዳማትን በመገደም የመጀመሪያው ትምህርት
ቤት /ቤተ ቀጢም/ በማቋቋም በኢትዮጵያ ወንጌል እንዲስፋፋ በማድረጋቸው “ከሳቴ ብርሃን ወይም “ብርሃን ገላጭ ተብለው ተጠርተዋል፡፡
18
ወይም ተሰዓቱ ቅዱሳን
19
ሌላኛው ስማቸው አባ ሮሜ ሲባሉ ከጎንደር ወደ ግብፅ ካይሮ በመሄድ በ10 ዓመት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ ቋንቋ ተርጉመዋል፡፡
20
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 270 ይመልከቱ
21
“ክርታስ ማለት ለመጻፊያ የሚያገለግል ወፍራም ወረቀት ከእንሰሳ ቆዳ የሚሰራውም የብራና ጥቅልል ክርታስ ይባላል፡፡ (ኤር34፡4-6) የመጽሐፍ ቅዱስ
መዝገበ ቃላት ገጽ 203
22
እነዚህ መጻሕፍት አስራው መጻሕፍት በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ መጸሕፍት ለሌሎች መጻሕፍት መሰረቶች በመሆናቸው አስራው (መሰረቶች) ተብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ መጻሕፍት በሌላ መጽሐፈ አምላካውያት ተብለዋል፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 12
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

1.8 የምዕራፍ አንድ የክለሳ ጥያቄዎች23


1. መጽሐፍ ቅዱስ ለምን ቅዱስ ተባለ?
2. መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት በምን ይለያል?
3. መጽሐፍ ቅዱስ በቀኖና መወሰን ለምን አስፈለገ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንስ
በቀኖናዋ ስንት መጻሕፍትን ትቀበላለች? ስንት የብሉያት ስንት የሐዲሳት መጻሕፍት ናቸው?
4. መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው?
5. መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጣቸውን ጥቅሞች ዘርዝሩ?

ምዕራፍ ፪
የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ
መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ የሃይማኖት መሰረት ነው፡፡ አምላኩን በአግባቡ እንዲያውቅ፣ እውነቱንም
ከሀሰት እንዲለይ እና ፍጹም ድኅነት የሚገኝበትን መንገድ እንዲያገኝ የሚረዳው ታላቅ መጽሐፍ ነው፡፡ እናም
ይህንን መጽሐፍ ሰናነብ (ስናጠና) እንደሌሎች ተራ መጻሕፍት መሆን የለበትም ይልቁኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ
የሚገኘውን ጥቅም ተጠቃሚ ለመሆን ልንተገብራቸው የሚገቡ ተግባራት አሉ፡፡ እናም የተወደዳችሁ ተማሪዎች
በዚህ ምዕራፍ መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና ልንከተለው የሚገባውን ዘዴ በስፋት ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

፪.1 መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይነበባል?


መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ልንከተላቸው የሚገቡ ነገሮች፡-

፪.1.1 ከጸሎትና ከመሻት ጋር ማንበብ


መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለሰዎች ፍቃዱን የገለፀበት ሰዎች በመልካሚቱ መንገድ ይመሩ ዘንድ እና
በሕይወት ይኖሩ ዘንድ የገለጸው መጽሐፍ ነው፡፡ እናም እግዚአብሔር ሰዎችን በመጽሐፍ ይናገራል፡፡24 ስለዚህ
ይህንን መጽሐፍ በምናነብበት ወቅት እግዚአብሔር ምስጢሩን ለመመርመር አይኖቻችንን ይከፍት ዘንድ እንዲሁም
ማስተዋልንና ጥበብን ይሰጠን ዘንድ ካነበብንም በኋላ ያነበብነውን በሕይወታችን ተግባራዊ ለማድረግ ቃሉን ለመኖር
ይረዳን ዘንድ መጸለይ ይገባናል፡፡ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊትም ተመሳሳይ ጸሎትን ይጸልይ ነበር፡፡
 “ዓይኖቼን ክፈት ከሕግህም ተኣምራትን አያለሁ” መዝ 118(119)፡18
 “አቤቱ መንገድህን አመልክተኝ ፍለጋህን አስተምረኝ” መዝ 24(25)፡4
እና እኛም ልክ እንደ ዳዊት ቅዱስ ቃሉን ይገልጥልን ዘንድ፣ ማስተዋሉን ጥበቡን ይሠጠን ዘንድ
ያንበብነውንም በሕይወት እንድንኖር ይረዳን ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን
ከመሻት ጋር ልናነብ ያስፈልጋል፡፡

፪.1.፪ አዘውትሮ ማንበብ


መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ምግብ ነው፡፡ ይህ ሲባል ነፍሳችን እንዳትራብ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር
መመገብ ይገባታል፡፡ ይህን ምግብ ዘወትር ለነፍሳችን ልንመግባት ካልቻልን መኖር አንችልም፡፡ ጌታችንም በሕያው
ቃሉ ይህንን ሲያረጋግጥልን፡-

 “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም” ማቴ 4፡4


በማለት ነው፡፡ ይህንን ቃል እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን አስቀድሞ ገልጦላቸዋል፡፡25 ከዚህ በተጨማሪም
መጽሐፍ ቅዱስ የመንፈስ ምግብ መሆኑ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተገልጦ እናገኛለን፡፡ እናም ለቁመተ
ሥጋችን ዘወትር መመገብ እንደሚገባን ሁሉ ለነፍሳችንም ዘወትር የእግዚአብሔርን ቃል ልንመገብ ያስፈልጋል፡፡

23
ከማስተማሪያ ኖቱ በተጨማሪ ለጥያቄዎቹ ምላሽና ማብራሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በአባይነህ ካሴ የተጻፈና በማህበረ ቅዱሳን የታተመ መጽሐፍ እና
በሠንበት ትምሕርት ቤታችን የርቀት ክፍል የተዘጋጀውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ መጽሐፍን ይመልከቱ፡፡
24
መዝ 86(87)፡6
25
ዘዳ 8፡3
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 13
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

፪.1.3 የቤተሰብ የንባብ ጊዜ ወስኖ ማንበብ


የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከላይ ባነሳነው ርዕስ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ የነፍስ ምግብ እንደሆነና ዘወትር
ልንመገበው እንደምንገባ ተማምረናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን ይህንን ምግብ የመመገቢያ ቋሚ የመመገቢያ ጊዜ
በመመደብ ከቤተሰብ አባላት ጋር መመገብ ይገባል፡፡
 “እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህንን ቃል በልብህ ያዝ ለልጆችህም አስተምረው በቤትህም
ስትቀመጥ በመንገድህም ስትሄድ ስትተኛም ስትነሳም ተጫወተው” ዘዳ 6፡6-7
 “አኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን” ኢያሱ 24፡15

፪.1.4 ከቤተክርስቲያን አባቶች (መምሕራን) ድጋፍ በማግኘት ማንበብ


መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰው እግዚአብሔር ለእርሱ የሚያስተላልፈውን መልእክት
ሳይዛነፍ መቀበል አለበት፡፡ ነገርግን መጽሐፍ ቅዱስን አንባቢው ወደገዛ ፍቃዱ እንዳይተረጉምና ትክክለኛውን
የእግዚአብሔርን መልእክት ለማወቅ እና ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ወቅት የሚመራ መምሕር
ያስፈልጋል፡፡
ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በጋዛ ተቀምጦ ኢሳይያስ ስለጌታችን ስለመድኃኒታችን ስለኢየሱስ ክርስቶስ በትንቢት
የተናገረውን በሠረገላ ላይ ሆኖ ቢያነብም መንፈስ ቅዱስ ፊሊጶስን ነጥቆ ወደ እርሱ እስኪወስደው ድረስ ነብዩ
ስለምን እንደጻፈ አልተረዳም ነበር፡፡ ይህንንም ራሱ ጃንደረባው በተናገረው ንግግር መገንዘብ ይቻላል በኋላም ቅዱስ
ፊሊጶስ ነብዩ በትንቢት ስለማን እንደተናገረና መቼ እንደተፈጸመ በዝርዝር ካስረዳው በኋላ በኢየሱስ ክርስቶስ
በማመን ሊጠመቅ ችሏል፡፡26 ዛሬም መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ወቅት የቤተክርስቲያን አባቶች እገዛ እጅግ
አስፈላጊ ነው፡፡
፪.1.5 ምላሽ ፈልጎ (የሕይወት ጥያቄዎችን በማንሳት) ማንበብ
በሕይወታችን በእግዚአብሔር እንዲመለስልን የምንሻቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ይኖራሉ፡፡ ከዚህ ወጪ
እግዚአብሔር እንዲሞላልን የምንፈልጋቸው ጉድለቶችም ይኖሩናል፡፡ እናም መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወታችን ለሚነሱ
ጥያቄዎች እና የልባችንን የዘመናት ጥያቄ ጉድለታችንን ሁሉ የሚሞላ የእግዚአብሔር እስትንፋስ በመሆኑ መጽሐፍ
ቅዱስን በምናነብበት ወቅት ሁሉ እነዚህን የሕይወት ጥያቄዎች በማንሳት ምላሽም በመሻት ጉድለታችንንም
ለመድፈን በመፈለግ ማንበብ መቻል አለብን ያን ጊዜ እግዚአብሔር በቃሉ ጉድለታችንን ይሞላል፡፡
 “የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና የሚሰራም ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ
የተሳለ ነው ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል የልብንም
ስሜትና አሳብንም ይመረምራል፡፡” ዕብ 4፡12-13

፪.1.6 ሕዳግ፣ግፃዌ እና መዝገበ ቃላትን በማመሳከር ማንበብ


መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ወቅት ሕዳግን፣ ግፃዌንና የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትን በማመሳከር
ማንበብ ይገባል፡፡ ይህ በተለይ የምናነበውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይበልጥ እንደንረዳ ከማድረጉም በተጨማሪ
ከምናነበው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጋር ተዛማጅነት ያላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አልያም ትንቢቶች ካሉ
እነርሱን እንድንረዳና እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡

፪.፪ መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ባሕል


መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት የራሱ የሆነ ባሕል አለው፡፡ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕል የሚባለው በወቅቱ
መጽሐፉ በሚጻፍበት ወቅት ከነበሩ ሁኔታዎች ጋር ተስማምቶ የሚሄድ በመሆኑ፣ በተጻፈላቸው ሰዎች እና
በጸሐፊዎቹ አካሄድ ላይ ተመሠረተ መሆኑ የራሱ የአጻጻፍ ባሕል እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ ስለዚህ በዓለም ላይ
ያሉ ሕዝቦች የመጽሐፍ ቅዱስን የአጻጻፍ ባሕል መረዳት ይገባል እንጂ ከራሳቸው ባህል ጋር ለማቆራኘት መሞከር
አይገባም፡፡ ለምሳሌ “ወንድም” የሚለው ቃል በመካከለኛው ምስራቅ እና በኢትዮጵያ ተመሳሳይ አተረጓጎም ቢኖረውም
በምዕራባውያን ዘንድ ግን ያለው አተረጓጎም የተለየ ነው፡፡ እናም አንድ ምዕራባዊ ይህንን ቃል በራሱ ባሕል
ሊተረጉመው ቢሞክር ተገቢውን ፍቺ ሊያገኝ አይችልም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በአብዛኛው የሚያመላክተው
የመካከለኛውን ምስራቅ (የእስራኤላውያንን) ባሕል በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእረኛን ጠባይ መጽሐፍ ቅዱስ

26
ሐዋ 8፡26-38
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 14
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

የሚያነብ ኢትዮጵያዊ ሰው እንደ ሀገሩ ባሕል ለመተርጎም ቢሞክር ወደ ስህተት ማምራቱ የማይቀር ነው፡፡
ምክንያቱም እረኛ በእስራኤላውያን ባህል በጎቹን ፊት ለፊት እየመራ የሚሄድ ሲሆን27 በኢትዮጵያውያን ባሕል ግን
እረኛ ከበጎቹ ኋላ ሆኖ እየነዳቸው የሚሄድ ነው፡፡ ስለዚህ ማንም መጽሐፍ ቅዱስን በሚያነብበት ወቅት ከላይ
የተጠቀሱትን ነጥቦች ከግምት ወስጥ በመክተት የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕል በመረዳት ሊያነበው ይገባል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕሎችን ከዚህ ቀጥለን በዝርዝር ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ይህም የእስራኤላውያንን ባሕል መመልከት የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕል ለማወቅ ይረዳል፡፡ ይህም የእስራኤላውያንን
የስም አወጣጥ፣ የአነጋገር ዘይቤ፣ ማሕበራዊ ሕይወትን መመልከት እና መረዳት ይገባል፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ
ቅዱስ የተጻፈው አብዛኛው የእስራኤላውያንን ባሕል መሰረት በማድረግ ስለሆነ ነው፡፡ ይህም በውስጡ
የእስራኤላውያንን የአነጋገር ዘይቤ ተክትሎ የተጻፈ በመሆኑና የተለያዩ የእስራኤላውያንን ማህበራዊ ኑሮ በተመለከተ
በውስጡ ስለሚገልጥ ነው፡፡
በሌላ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ሌላ ዓይነት ባሕል ይንጸባረቅበታል፡፡ ይህም የአጻጻፍ ስልቱን የሚመለከት
ይሆናል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፈርጀ ብዙ ቃላት እንደየአገባባቸው የተለያየ ትርጉምን የሚይዙ አንዳንድ ቃላት
ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ነገር ለመግለጽ ተራ ቋንቋ አይጠቀምም፡፡ ለምሳሌ የአንድን ሴት
ተገድዶ መደፈር ለመግለጥ ቢፈልግ የአድራጊውን ስም በማንሳት እገሊትን አስነወራት ይላል፡፡28 ከዚህ በተጨማሪ
ሌሎችን የመጽሐፍ ቅዱስ ባህል ከዚህ በመቀጠል በዝርዝር የምንመለከት ይሆናል፡፡

፪.፪.1 የዕብራውያን ስም አወጣጥ ባሕል


በዕብራውያን ባሕል ስም ጠባይን ግብርንና ሁኔታን ይገልጣል፡፡ ከዚህ መነሻነት በመጽሐፍ ቅዱስም
የምናገኛቸው አብዛኞቹ ስሞች ከመጠሪያነታቸው ባሻገር ሌሎች ብዙ ጉዳዮችን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ ይህም
ዕብራውያን ለልጆቻቸውና ለቦታዎች ስምን ሲያወጡ ስሙ በሚወጣበት ሰዓት በሀገራቸው፣ በግላቸው ወይም
በቤታቸው ተከስቶ ከነበረው ሁኔታ ጋር በማዛመድ ያወጣሉ፡፡ ይህም ያንን ጊዜና ሁኔታ እንዳይረሱት ይረዳቸዋል፡፡
ለአብነትም የተወሰኑትን እንመልከት፡-

ሀ. ለሰዎች የተሠጠ ስም
 አዳም ፡- በአረማይክ ቋንቋ “መሬት” ማለት ሲሆን ይህም አዳም ከምን እንደተፈጠረ ለማመላከት ነው፡፡30
29

 ሴት፡- ትርጉሙም ምትክ ማለት ሲሆን በአቤል ምትክ የተወለደ በመሆኑ ይህ ስም ተሰጥቶታል፡፡31
 ይስሐቅ32፡- ትርጉሙም “መሳቅ” ማለት ሲሆን አብርሃምና ሳራ እድሜያቸው ገፍቶ እግዚአብሔር ልጅ
ትወልዳላችሁ ባለ ጊዜ ሳራ በልቧ ስለሳቀች ይህን ለማስታወስ ልጃቸውን ይስሐቅ ብለው ጠርተውታል፡፡33
 ያዕቆብ፡- ትርጉሙ “ተረከዝን ይይዛል” ማለት ሲሆን ይህም በተወለደ ጊዜ የወንድሙን የኤሳውን ተረከዝ
ይዞ በመወለዱ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡34
 ሙሴ፡- ትርጉሙም “ከባሕር የወጣ” ማለት ሲሆን ይህም በዘመኑ እስራኤላውያን በግብጽ ፈርዖን35 ትዕዛዝ
ወንድ ልጅ ከተወለደ ይገደል ስለነበር እናቱ ከወለደችው በኋላ መሸሸግ ስላልቻለች በወንዝ ላይ ጣለችው፡፡
የፈርዖኑ ልጅም ልትታጠብ በወንዙ ላይ በወረደች ጊዜ ይህን መልከመልካም ልጅ አገኘችው በዚህ የተነሳ
ሙሴ ተብሎ ተጠርቷል፡፡36

27
ዮሐ 10፡2-5
28
ዘፍ 34፡3-5
29
አዳም ማለት በግዕዝ ያማረ መልካም ማለት ነው፡፡ ይህም አዳም ከፍጥረታት ሁሉ እጅግ ያማረ እና መልካም የሆነ ፍጥረት መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡
(ዘፍ 1፡26-31)
30
ዘፍ 2፡7
31
ዘፍ 4፡25
32
ይስሐቅ የሚለው ቃል በዕብራይስጡ “ሻሐቅ በእንግሊዘኛ አይዛክ የሚል ቃል ይይዛል፡፡
33
ዘፍ 18፡12 እና ዘፍ 21፡3
34
ዘፍ 25፡26
35
በኢትዮጵያ ነገስታት “አጼ የሚል የማዕረግ ስም እንደሚሠጣቸው የግብጽ ነገስታትም ፈርዖን ይባሉ ነበር፡፡
36
ዘጸ 1፡15-2፡10
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 15
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ምናሴ፡- ማለት “ማስረሻ” ማለት ሲሆን ዮሴፍ መከራውንና የአባቱን ቤት በመርሳቱ ይህ ስያሜ
ተሰጥቶታል፡፡37
 ኤፍሬም፡- ማለት ትርጉሙ “ማፍራት” ማለት ሲሆን የዮሴፍ ሁለተኛ ልጁ ነው፡፡ በግብጽ መከራውን ሁሉ
ረስቶ ፍሬ ማፍራቱን (ልጆች መውለዱን) ለመግለጽ ልጁን ኤፍሬም ብሎ ሠይሞታል፡፡38
 ኢካቦድ፡- ማለት “ክብር ከእስራኤል ለቀቀ” ማለት ሲሆን የፊንሐስ ሚስት ልጇን በወለደችበት ሠዓት ታቦተ
ጽዮን የተማረከችበት እና ሁለቱ ወንድማማቾች አፍኒንና ፊንሐስ የተገደሉበት ጊዜ በመሆኑ የልጇን ስም
ኢካቦድ ብላ ጠርታዋለች39
 ዘሩባቤል፡- ማለት “የባቢሎን ዘር” ማለት ሲሆን በተወለደ ጊዜ ሕዝበ እስራኤል በባቢሎን ምርኮ ስለነበርና
የተወለደውም በባቢሎን በመሆኑ ያንን ታሪክ ለመግለጥ ዘሩባቤል ተብሏል፡፡40

የተወደዳችሁ ተማሪዎች ለአብነት እነዚህን አነሳን እንጂ ሌሎች ስሞችም በጊዜው ከነበረው ሁኔታ ጋር
የወጡ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እስራኤላውያን የቦታ ስያሜዎችንም ሲገልጡ በወቅቱ ከተፈጸመው ድርጊት ጋር
በማዛመድ ያወጡ ነበር፡፡ ከዚህ በመቀጠልም የተወሠኑትን ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

ለ. ለቦታዎች የተሠጠ ስም
 ቤቴል፡- ትርጉሙ “የእግዚአብሔር ቤት” ማለት ሲሆን ያዕቆብ በሕልሙ በዛች ስፍራ ላይ እግዚአብሔርን
በማየቱ ቦታዋን ቤቴል ብሎ ሠይሟታል፡፡41
 ብኤል ለሃይሮኢ፡- ትርጉሙም “ሕያው የሆነውን የሚያየኝንም ያየሁበት የውሃ ጉግጓድ” ማለት ሲሆን
በዚህ ስፍራ አጋር42 የእግዚአብሔርን መልአክ በማየቷ ይህን ስያሜ ልትሰጥ ችላለች፡፡43
 መሪባ፡- ማለት “ክርክር” ማለት ነው፡፡ እስራኤላውያን ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ በራፊዲም ሰፍረው ሳለ
በዛች ቦታ ውሃ ባለመኖሩ “ለምን ከግብጽ ምድር አወጣኸን” በማለት ሙሴን ተናገሩት ሙሴም ወደ
እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ እግዚአብሔር ባመላከተው መሰረትም በበትሩ የኮሬብን ዓለቶች መታ በዚያም ሕዝቡ
ከኮሬብ ዓለቶች የፈለቀውን ውሃ ጠጡ በዚህም የተነሳ ስለ እግዚአብሔር ሕዝቡ ከሙሴ ጋር ተከራክረዋልና
ሥፍራውን “መሪባ” ብለው ጠሩት፡፡44
 አቤንዔዘር፡- ማለት ትርጉሙ “እግዚአብሔር እስካሁን ድረስ ረድቶናል” ማለት ሲሆን ነብዩ ሳሙኤል
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከፍልስጤማውያን እጅ ባዳናቸው ወቅት አንድን ድንጋይ አንስቶ በምጽጳና
በሻይን መካከል አቁሞ ቦታውን የጠራበት ስያሜ ነው፡፡45
 ጌልገላ፡- ማለት “ማንከባለያ” ማለት ሲሆን አስራኤል ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ የተወለዱት ወንዶች
አልተገረዙም ነበር፡፡ እናም እግዚአብሔርም ኢያሱን እነዚህ ልጆች እንዲገረዙ አዘዘው፡፡ ኢያሱም
እንደታዘዘው አደረገ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን የግብጽን ነውር ከእርሱ ላይ እንዳንከባለለ ገልጾለታል፡፡
በዚህ የተነሳ ስፍራው ጌልገላ ተብሏል፡፡46
 ጎልጎታ፡- ማለት የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን47 ትርጓሜውም “የራስ ቅል” ማለት ነው፡፡48 የራስ ቅል
የተባለበትም ምክንያት አስቀድሞ የአባታችን የአዳም አጽም የተቀበረበት ሥፍራ በመሆኑ ነው፡፡49

37
ዘፍ 41፡51
38
ዘፍ 41፡52
39
1ሳሙ 4፡21
40
1ዜና 3፡19
41
ቤቴል አስቀድሞ ስሟ ሎዛ ይባል ነበር፡፡ ከኢየሩሳሌምም ርቃ የምትገኝ ስፍራ ናት፡፡ (ዘፍ 28፡10-19)
42
አጋር ይናገራት የነበረውንም የእግዚአብሔር ድምጽ “ኤልሮኢ ብላ የጠራችው ሲሆን ትርጉሙም “የሚያየኝን በውኑ አየሁት ማለት ነው፡፡ (ዘፍ 16፡13)
43
ዘፍ 16፡13-14
44
ዘጸ 17፡1-8
45
1ሳሙ 7፡12
46
ጌልገላ በኢያሪኮና በዮርዳኖስ መካከል የምትገኝ ስፍራ ናት፡፡ (ኢያ 5፡2-9)
47
በግሪክ ቃል “ቀራንዮ ይባላል፡፡
48
ዮሐ19፡17-18
49
አባታችን አዳም በደብረ ቅዱስ ሳለ መካነ ጸሎት ለይቶ ይኖር ነበር፡፡ እርሱ ከሞተ በኋላም የእርሱ ልጆች ዐጽሙን እንደታቦት አድርገው መሥዋዕተ ጸሎት
ያደርጉ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ እስከ ኖኅ ድረስ ዘለቀ ኖኅም ወደ መርከቡ ሲገባ ዐጽሙን ይዞት ገባ በዚያም እንደቀደመው አደረገ፡፡ ኖኅም ከመርከብ ሲወጣ
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 16
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ሐ. ለሰዎች የሚሰጡ ቅጽል ስሞች


ከዚህ ወጪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተመሳሳይ ስም ለሚጠሩ ሰዎች አንዱን ከአንዱ ለመለየት
ግብራቸውን ወይም የተወለዱበትን ቦታ ወይም ቤተሰባቸውን እንደ መለያ በማድረግ ቅጽል ይወጣላቸዋል፡፡ ከዚህ
በመቀጠልም የተወሠኑትን ለመመልከት እንሞክራለን፡-
 መጥምቁ ዮሐንስ፡- የካህኑ ዘካርያስ እና የቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ ሲሆን ቤተሰቦቹ ዮሐንስ ብለው
ጠርተውታል፡፡ ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሌሎች በዮሐንስ ስም የሚጠሩ ሰዎች በመኖራቸውና
ጌታን በማየ ዮርዳኖስ በማጥመቁ “መጥምቁ” የሚለውን ቅጽል አግኝቷል፡፡50
 ፍቁረ እግዚዕ ዮሐንስ፡- ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ሲሆን
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ሌሎች በዮሐንስ ስም ከሚጠሩ ሰዎች ለመለየት ጌታ ይወደው ስለነበር
“ፍቁረ እግዚዕ” (“ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር”) ተብሏል፡፡51
 ቁርበት ፋቂው ስምዖን፡- በኢዮጴ የሚኖር እና ቅዱስ ጴጥርስን በቤቱ ያስተናገደ ሰው ሲሆን ከሌሎች
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በስምዖን ስም ከተጠሩት ለመለየት ይሰራበት በነበረው በቆዳ ስራው የተነሳ
በዚህ ስም ተጠርቷል፡፡52
ከዚህ በተጨማሪ ሌሎችም ሰዎች በተለያዩ ቅጽል ስሞች ከእነርሱ ጋር ተመሳሳይ ስም ካላቸው ጋር
እንዲለዩ በማሰብ ቅጽል ስም ወጥቶላቸዋል፡፡ ለአብነትም፡- ስምዖን አረጋዊ፣ ማርያም መግደላዊት፣ ኢትዮጵያዊው
አቤሜሌክ፣ ስምዖን ቀሬናዊው፣ ቴስቤያዊው ኤልያስ፣ ሞዓባዊቷ ሩት፣ወዘተ...... መጥቀስ ይቻላል፡፡53 ዛሬም
በቤተክርስቲያናችን የተለያዩ ቅዱሳንን በግብራቸው፣ በተክለ ቁመናቸው፣ በመልካቸው፣ ወይም በትውልድ
ሥፍራቸው ቅጽል ስም እየተሰጣቸው ይጠራሉ፡፡ ለአብነትም፡- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ
መለኮት፣ ተፈጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ፣ አባ ሠላማ ከሳቴ ብርሃን፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘላዕላይ ግብጽ፣ ቅዱስ
ባስልዮስ ዘቂሳርያ፣ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ፣ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፣
ወዘተ... መጥቀስ ይቻላል፡፡

፪.፪.፪ የዕብራውያን የአነጋገር ዘይቤ


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በአብዛኛው የምናገኘው የእስራኤላውያንን የአነጋገር ዘይቤን በመሆኑ ማንኛውም
ሰው ይህንን መጽሐፍ በሚያንብበት ወቅት እርሱ ባደገበት እና በሚኖርበት አካባቢ ባለ የአነጋገር ዘይቤ ሊረዳና
ሊገነዘብ አይገባም፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የእስራኤላውያንን የአነጋገር ዘይቤ ጠንቅቆ መረዳት
ያስፈልጋል፡፡ አንባቢው የእስራኤላውያንን አነጋገር ጠንቅቆ የሚረዳ ከሆነ የንግግሩን ፍሬ ሐሳብ ለመረዳት
የሚያስችለው ይሆናል፡፡ እናም ከዚህ በመቀጠል በመጽሐፍ ቅዱስ የሚንጸባረቁትን የአነጋገር ዘይቤዎች
የምንመለከት ይሆናል ተከተሉን፡-
፪.፪.፪.1 በማራቅ መናገር
እስራኤላውያን ትህትናቸውን ለመግለጽ ራስን ዝቅ ለማድረግ ይህንን የአነጋገር ዘይቤ ይጠቀማሉ፡፡ ይህንንም
በዝርዝር ከዚህ ቀጥለን ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

ሀ. አንደኛ መደብን በሦስተኛ መደብ አርቆ መናገር


ዕብራውያን ስለራሳቸው መናገር በፈለጉበት ጊዜ በሁለት ዓይነት መደብ የሚጠቀሙ ሲሆን አንደኛው
ተናጋሪው በቀጥታ አንደኛ መደብን54 በመጠቀም “እኔ”፣ “እኛ” ወይም የሚያነጋግረው ሰውም ካለ “አንተ”፣ “አንቺ”

ላዳነኝ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል በማለት ዐጽመ አዳምን እንደታቦት አድርጎ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረበ ከዚህም በኋላ ኖኅ ልጁን ሴምን ጠርቶ
ዐጽመ አዳምን እግዚአብሔር ካዘዘህ ቦታ ወስደህ አስቀምጥ አለው፡፡ ሴምም መልከ ጸዴቅን አሰናብቶ አጽሙን አሸክሞት ይዞት ሄደ መላዕክትም እየመሩት
ማዕከለ ምድር ቀርንዮ ደረሰ (ይህች ምድር አስቀድሞ አዳም የተፈጠረባት ሥፍራ ስትሆን “ኤልዳ” ተብላ ትጠራለች፡፡) የጌታ መስቀልም ከሚያርፍበት ሥፍራ
ሲደርስ ምድር ተከፈተችለት በዚያም አጽመ አዳምን አኖረ፡፡ መልከ ጸዴቅንም ጠብቅ ብሎት ትቶት ሄደ፡፡ መልከ ጸዴቅም የአዳምን አጽም እንደ ታቦት አድርጎ
መሥዋዕትን ይሰዋ ነበር፡፡
50
ማቴ 3፡1፣ 14፡8፣ ማቴ 16፡14፣ ማር 8፡28
51
ዮሐ 19፡26፣ 21፡20
52
የሐ.ሥራ 9፡43
53
ሉቃ 2፡25፣ 8፡2፣ ኤር 38፡7፣ 1ነገ 17፡1፣ ሩት 2፡21፣ ወዘተ.... ይመልከቱ፡፡
54
First person
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 17
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ወይም “እናንተ” እያለ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ራስን በማራቅ በሦስተኛ መደብ55 የሚናገሩበት ዘይቤ ነው፡፡ ይህም
“አንተ” በማለት ፋንታ “እርሱ” ብለው ይናገራሉ፡፡ ለምሳሌ የተወሰኑትን እንመልከት፡-
 ኢያሱ ቅዱስ ሚካኤልን “ጌታዬ ለባርያው የሚናገረው ምንድን ነው?”56 በማለት ራሱን “ለባሪያው”
በማለት (በሦስተኛ ወገን በመጥራት) ይናገራል፡፡ እንደ እኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ ቢሆን ግን
“ጌታዬ ለባርያህ የምትነግረኝ ምንድን ነው?” ብሎ በተናገረ ነበር፡፡
 ከዚህ በተጨማሪ ቅዱስ ዳዊት ስለራሱ ሲናገር፡- “ቸርነቱን ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ ይሰጣል”57
በማለት ራሱን በሦስተኛ ወገን ይገልጣል እንደኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ ቢሆን ግን “ቸርነቱን
ለቀባኝ ለእኔና ለዘሬ ይሰጣል” ብሎ በተናገረ ነበር፡፡
 በአዲስ ኪዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በፊሊጶስ ቂሳርያ ሐዋርያትን “ሰዎች
የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?”58 በማለት በዚህ የአነጋገር ዘይቤ ሲናገር እናያለን እንደ
እኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ ቢሆን ኖሮ “ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?” ብሎ በተናገረ ነበር፡፡

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ተማሪዎች ለአብነት እነዚህን አነሳን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ
አይነት የአነጋገር ዘይቤ በተለያየ ቦታ ተጠቅሶ የምናገኝ ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ራስን በሦስተኛ ወገን
አርቆ የመናገር ባሕል እንዳለና መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ጊዜ ይህን ባሕል ጠንቅቆ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ስለዚህ እኛም በምናነብበት ጊዜ ይሄንን የአነጋገር ዘይቤ በመረዳት ልናነብ ይገባል፡፡

ለ. ሁለተኛ መደብን በሦስተኛ መደብ አርቆ መናገር


የዕብራውያን ሌላው የአነጋገር ዘይቤ ሁለተኛ መደብን59 በማራቅ በሦስተኛ መደብ መናገር ነው፡፡ ለምሳሌ
የተወሰኑትን ለመመልከት እንሞክር፡-
 አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር በሚነጋገርበት ወቅት “ጌታዬ አይቆጣ”60 በማለት እግዚአብሔርን
ይናገራል ይህም ሁለተኛ መደብን ወደ ሦስተኛ መደብ በማራቅ ይናገራል፡፡ በእኛ ሀገር የአነጋገር
ዘይቤ “ጌታዬ አትቆጣ” ባለ ነበር፡፡
 ቅዱስ ዳዊትም ሳዖልን “የእስራኤል ንጉስ ማንን ለማሳደድ መጥቷል?”61 በማለት በሁለተኛ ወገን
መናገር ሲገባው በሶስተኛ ወገን በማራቅ ሲናገር እናያለን በእኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ ቢሆን ኖሮ
“ሳዖል ሆይ ማንን ለማሳደድ መጥተሃል?” በማለት በተናገረ ነበር፡፡
ስለዚህ ሌላኛው የእስራኤላውያን የአነጋገር ዘይቤ ደግሞ በሁለተኛ መደብ ሊነገር የሚገባውን በሦስተኛ
መደብ በማራቅ መናገር ነው፡፡

፪.፪.፪.፪ ቃላትን በመደጋገም መናገር


በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሌላው የምንመለከተው የአነጋገር ዘይቤ አንድ ቃልን በመደጋገም መናገር ነው፡፡
ይህም በእኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ የሌለ ቢሆንም ዕብራውያን አንድን ሐሳብ በቁርጠኝነት ወይም በአጽንዖት
ለመናገር በሚፈልጉበት ወቅት ሁሉ ቃሉን በመደጋገም ይናገራሉ፡፡ ለአብነትም የተወሰኑትን ለመመልከት
እንሞክር፡-
 “አንተ አባታችን ነህ አቤቱ አንተ አባታችን ነህ” ኢሳ 63፡16
 “ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ነብያትን የምትገድል ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር ዶሮ
ጫጩቶቿን ከክንፎቿ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ
አልወደዳችሁምም” ማቴ 23፡37

55
Third person
56
ኢያ 5፡14
57
መዝ 17(18)፡50
58
ማቴ 16፡13
59
Second person
60
ዘፍ 18፡32
61
1ሳሙ 24፡14
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 18
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 “እውነት እውነት እልሃለው ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔርን


መንግስት ሊገባ አይችልም” ዮሐ 3፡3-5
 “እውነት እውነት እላችኋለው በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው” ዮሐ 6፡47

፪.፪.፪.3 ከ ....... ጋር ምን አለኝ?


መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራውያን ባሕል የተጻፈ መጽሐፍ እንደመሆኑ ዕብራውያን የተጠየቁትን ነገር ለመፈጸም
እንዳይችሉ የሚያደርጋቸው (የሚያግዳቸው) ምንም ምክንያት እንደሌለ ለማስረዳት ወይም ለመግለጽ
የሚጠቀሙበት የራሳቸው የሆነ የአነጋገር ስልት አለ ይህም “ከአንተ /ከአንቺ/ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ?” የሚለው
ጥያቄ አዘል አባባል ነው፡፡ በእኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ ይህ የአነጋገር ዘይቤ ያለተለመደ በመሆኑ “ከአንተ /ከአንቺ/
ከእናንተ ጋር ምን ግንኙነት አለኝ?” ወደሚል ተቃራኒ ትርጉም ወደ አዘለ አባባል የሚተረጎም ይሆናል፡፡
በዕብራውያን የአነጋገር ዘይቤ ግን ይህ አነጋገር ፍቅርን፣ ትህትናን አልያም ታዛዥነትንና ሙሉ ፈቃደኝነትን
የሚገልጽ አነጋገር ነው፡፡ ለአብነትም የሚከተሉትን ምሳሌዎች እንመልከት፡-
 የሰራፕታዋ መበለት ልጇ በሞተባት ጊዜ ወደ ኤልያስ ዘንድ በመሄድ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ
ጋር ምን አለኝ ኃጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደኔ መጥተሃልን?”62 በማለት
ተናግራለች፡፡ በእኛ የአነጋገር ዘይቤ መበለቷ ሴት በዚህ ንግግሯ ነብዩ ኤልያስን ያለችው “የእግዚአብሔር
ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን ጠብ አለኝ ያጠፋሁትስ ምንድን ነው?” ነው፡፡ ይህም ትህትናን ይገልጣል እንጂ
ጸብን አሊያም ጥላቻን አያመላክትም፡፡
 ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በቃና ገሊላ በዶኪማስ ቤት በተሰረገው ሰርግ ላይ እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም የዶኪማስን ጎዶሎ ማንም ሳይነግራት ተመልክታ (ወይኑ ማለቁን አውቃ)
ለጌታችን “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም”63 ብላ በጠየቀችው ሰዓት እርሱም ለተከበረችው እናቱ “አንቺ ሴት
ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?” በማለት መልሶላታል፡፡ እርሷም ለአስተናጋጆቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” በማለት
ነግራቸዋለች፡፡ ይህም በእኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ ከላይ እንደተመለከትነው ፍጹም ተቃርኖን የሚያመላክት
ነው፡፡ ነገርግን ትክክለኛ ትርጉሙን ለመረዳት ሐረጉ የተነገረው በዕብራውያን የአነጋገር ዘይቤ እንደመሆኑ
ወደ እኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ መቀየር ተገቢ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ይህንን ሐረግ በእኛ አነጋገር ዘይቤ
ስንተረጉመው “አንቺ ሴት64 (እናቴ) አንቺ የለመንሽኝን እንዳላደርግ የሚከለክል ምን ጠብ አለኝ?” የሚል
ነው፡፡ ስለዚህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ምን እንዳላትና ለጥያቄዋ አዎንታዊ ምላሽ
እንደሰጣት በመረዳቷ ለአገልጋዮቹ ጌታ የሚያዛቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ አዛቸዋለች፡፡
የተወደዳችሁ ተማሪዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከላይ ያየናቸው የአነጋገር ዘይቤዎችን ብቻ ሳይሆን
ሌሎች በዚህ ክፍል ያልተጠቀሱና ዕብራውያን የሚጠቀሟቸው የአነጋገር ዘይቤዎች ተጠቅሰው እናገኛለን፡፡ እናም
መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ወቅት የዕብራውያንን የአነጋገር ዘይቤ ጠንቅቆ መረዳትና ትክክለኛውን ትርጉም
ማወቅ ይገባል፡፡
፪.፪.3 የዕብራውያን ኃዘን አገላለጽ
በመካከለኛው ምስራቅ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ኃዘናቸውን በተለያየ መንገድ ይገልጡ ነበር፡፡ በዚህም መሠረት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኃዘናቸውን በተለያየ መንገድ ይገልጻሉ፡፡ ለአብነትም ልብስን መቅደድ፣ አመድን (ትቢያን)
መነስነስ፣ ማቅን መታጠቅ፣ ወዘተ... ይገኙበታል፡፡ (ዘፍ 37፡34፣ ኢያ 7፡6፣ 1ሳሙ 4፡12፣ወዘተ....

፪.፪.4 በዕብራውያን የበኩር ትርጉም


በኩር ማለት የመጀመሪያ (ማህጸንን ከፍቶ የሚወጣ) ማለት ነው፡፡65 ከአንድ እናትና አባት የተወለዱ
ሁለትና ከዚያ በላይ ልጆች ቢኖሩ ከነዚህ መካከል የመጀመሪያ የሆነው በኩር ይባላል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው
በኩር ለመሆን የግድ ተከታይ ሊኖረው አይገባም፡፡ ብቸኛ ልጅ ከሆነም በኩር ይባላል፡፡

62
1ነገ 17፡18
63
ዮሐ 2፡3
64
በዕብራውያን “አንቺ ሴት የሚለው አነጋገር የክብር አነጋገር መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ በእኛ ሀገር የአነጋገር ዘይቤ ግን ይህ ቃል ንቀትን ሊያመላክት
ይችላል፡፡
65
ዘኁ 18፡15-16
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 19
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 “ብቸኛ ልጅ ሁሉ የበኩር ልጅ ነው፡፡ የበኩር ልጅ ሁሉ ግን ብቸኛ ልጅ አይደለም”


አባ ጄሮም
ስለዚህ በኩር ማለት የመጀመሪያ ማህጸንን ከፍቶ የሚወጣውን የሚያመላክት እንጂ ሁለተኛ ወይንም ከዚያ
በላይ ልጆች መኖራቸውን የሚያመላክት አይደለም፡፡ ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕል አንፃር በማቴዎስ ወንጌል
ምዕራፍ 1፡25 ላይ ያለውም ቃል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሁለተኛ ልጅ እንዳላት የሚያመላክት
ሳይሆን ይልቁኑ ጌታችን የእመቤታችን የመጀመሪያ ልጇ መሆኑን የሚያመላክት ብቻ ነው፡፡ ሌሎች የመጽሐፍ
ቅዱስ ክፍሎችንም ብንመለከት አንድም ቦታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታችን ከመድኃኒታችን
ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ልጅ እንዳላት አይገልጽም፡፡66

፪.፪.5 በዕብራውያን የወንድም ትርጉም


በመጽሐፍ ቅዱስ “ወንድም” የሚለው ቃል የግድ በእናትና በአባት ለሚገናኙ ብቻ የሚሆን ቃል አይደለም፡፡
ይልቁኑ ይህንን ቃል በተለያየ ምክንያት ለሚቀራረቡ ሰዎች የሚጠቅም ቃል ነው፡፡ ለአብነትም፡-
 የአንድ ሀገር ልጆች ወንድም ይባላሉ፡፡ (ዘጸ 2፡11)
 የአንድ ነገድ ልጆች ወንድም ይባላሉ፡፡ (2ሳሙ 19፡12፣ ዕዝ 3፡2)
 በዝምድና ወንድም ይባላሉ፡፡ (ዘኁ 20፡14)
 በባልንጀርነት ወንድም ይባላሉ፡፡ (2ሳሙ 1፡26)
 የቤተሰብ አባልነት ወንድም ይባላል (ዘፍ 13፡8)
 በሀይማኖት አንድነት ወንድም ይባላል፡፡ (ሮሜ 1፡13፣ ፊሊ 1፡12፣ 3፡1)
ስለዚህ የተወደዳችሁ ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በዕብራውያን ባሕል መሠረትነት በመሆኑ
“ወንድም” የሚለው ቃል የግድ በእናትና በአባት አንድ መሆንን እንደማያመላክት ልብ ልንል ይገባል፡፡ በመጽሐፍ
ቅዱስም ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታ ወንድሞች እንደሆኑ ተገልጸዋል፡፡ ይህም ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ
በመሆኑ67፣ የባሕርይ አባቱ አብ ለእኛ በጸጋ አባታችን ስለሆነ68፣ እንዲሁም በስጋ የወለደችውም እናቱ በዮሐንስ
በኩል ለእኛ እናት ተደርጋ ስለተሠጠች69 ወንድም ተብለው ተገልጸዋል፡፡ (ዮሐ 20፡17፣ ዕብ 2፡13)
ነገር ግን እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕል ባለመረዳት “የጌታ ወንድሞች” ተብለው
የተጠቀሱትን70 ያዕቆብ፣ ዮሳን፣ ስምዖንና ይሁዳን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ከዮሴፍ የወለደቻቸው
መሆናቸውን በመጥቀስ ትልቅ የምንፍቅና ትምህርትን የሚያነሱ አሉ፡፡ ነገር ግን ከላይ ያነሳናቸው ነጥቦች እንዳሉ
ሆኖ አባ ጄሮም ሄሊቪየስ ለተባለ ጸረ ማርያም መናፍቅ ወንድሞቹ የተባለበትን ምክንያት ሲያስረዳው፡-
 “ወንድሞቹ የተባሉት የአክስቱ ልጆች71 ስለሆኑ ነው” በማለት ገልጾለታል፡፡
እንግዲህ የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከላይ በዝርዝርን ለመመልከት እንደሞከርነው መጽሐፍ ቅዱስ
በአብዛኛው በዕብራውያን ባሕል የተጻፈ መጽሐፍ በመሆኑ የራሱ የሆነ ባሕል ያለው ነው፡፡ ነገር ግን እኛ ለማሳያ
የተወሰኑትን ዘረዘርን እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱስ ባሕል ከላይ የጠቀስናቸው ብቻ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ እናም
መጻሕፍትን ስናነብ ይህንን እና በዚህ ክፍለ ትምሕርት ያልተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕሎችን በመረዳት ልናነብ
ይገባል፡፡
፪.3 መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ይተረጎማል?
የመጽሐፍ ቅዱስን የአተረጓጎም ስልት ለመረዳት አስቀድሞ መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የመንፈስ ቅዱስ
አጋዥነት (ረዳትነት) ያስፈለገበትን ምክንያት መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ከዚያ በመቀጠልም የመጽሐፍ ቅዱስ
ትርጉምን አጀማመርና ስልት እንዲሁም አስፈላጊነትን እንደየቅደም ተከተላቸው ለመመልከት እንሞክራለን፡፡

66
ከላይ የጠቀስነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መሠረት በማድረግ “እመቤታችን ቅደስት ድንግል ማርያም ከጌታ በኋላ የወለደቻቸው ልጆች አሉ ብለው”
የሚያነሱ አሉ ነገር ግን ይህን የሚሉበት ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕል ካለመረዳት መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡
67
ዕብ 2፡16
68
ዮሐ 1፡12፣ ማቴ 6፡9
69
ዮሐ 19፡26
70
ማር 6፡3
71
ከላይ ዝምድና ያላቸው ሰዎች “ወንድም እንደሚባሉ አይተናል እናም “የጌታ ወንድሞች የተባሉበትም ምክንያት ይህ ነው እንጂ እውነት የጌታ እናት ሌሎች
ልጆች ኖረዋት አይደለም፡፡ (ማቴ 10፡3)
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 20
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

፪.3.1 መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ያስፈለገበት ምክንያት


የተወደዳችሁ ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ነጂነት (መሪነት) ከአርባ በላይ በሆኑ ቅዱሳን
ሰዎች የተጻፈ መጽሐፍ መሆኑን ተመልክተናል፡፡ እናም እነዚህ ቅዱሳን መጽሐፍ ቅዱስን ሲጽፉ የመንፈስ ቅዱስ
አጋዥነት ያስፈለገበት የራሱ የሆኑ ምክንያቶች አሉ፡፡ እነርሱም፡-
 የሰው ልጅ አስቦ ሊደርስባቸው የማይችላቸውን እጅግ በጣም ጥልቅና ረቂቅ የሆኑ ነገሮችን የያዘ
መጽሐፍ በመሆኑ ለእነዚያ ጥልቅና ረቂቅ የሆኑ ነገሮች ጸሀፊው የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ (ገላጭነት)
ስለሚያስፈልገው
 መጽሐፍቶቹን ያለ ስህተትና ያለ ልዩነት እንዲጻፉ ለማስቻል
 አንድ አይነት የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ
 የመጽሐፉ ይዘት በጸሐፊው እውቀትና ችሎታ ላይ የተገደበ እንዳይሆን ለማድረግ
ስለዚሀ በእነዚህና በመሳሰሉት ምክንያቶች መጽሐፍ ቅዱስን ለመጻፍ የመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት አስፈልጓል፡፡
ከዚህ መነሻነት መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ጥበብ በጥቂቱ የተገለጠበት መጽሐፍ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ
ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ጥበብ ለሰዎች የተገለጠበት መጽሐፍ እንደመሆኑ ሰዎች በቀላሉ
አንብበው ሊረዷቸው የማይችሏቸው ጥልቅና ረቂቅ ሀሳቦችን ያቀፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ድንቅ መጽሐፍ
ሰዎች አንብበውት የእግዚአብሔርን ሀሳብ እንዲረዱና ቃሉን በራሳቸው አተረጓጎም ተርጉመው ወደ ስህተት
እንዳያመሩ ከህዳግ ግጻዌና የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በተጨማሪ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወለዱ መጻሕፍትን72
ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ መጻሕፍትን ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ሲተረጎምም ሆነ በአንድምታ ሲተረጎም ከመንፈስ
ቅዱስ እርዳታ ባሻገር ተርጓሚው ሊከተላቸውና ሊጠብቃቸው የሚገቡ ስልትና ጥንቃቄዎች እንዲሁም ሊኖሩት
የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡

፪.3.፪ የመጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ እንዴት ሊተረጎም ይገባል?


መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ መቼ እና በነማን እንደተተረጎመ በዝርዝር በምዕራፍ አንድ ላይ
ለመመልከት ሞክረናል፡፡ በዚህ ርዕስ ስር ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ሲተረጎም ምን አይነት
የአተረጓጎም ዘዴ መጠቀም እንደሚገባና መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ሲተረጎም ተርጓሚው ሊከተሉትና
ሊኖሩት የሚገቡትን ነገሮች ለመመልከት እንሞክራለን፡፡ አንድን ጽሁፍ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ለመተርጎም የተለያዩ
የትርጉም ዘዴዎችን73 መጠቀም የሚገባ ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስን ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ለመተርጎም ግን ቃል በቃል
የተሰኘውን ዘዴ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ በሚተረጎምበት ጊዜ
ተርጓሚው በመሰረታዊነት ሊኖሩት የሚገቡ ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ እነሱም፡-

ሀ. ፈሪሃ እግዚአብሔር ሊኖረው ይገባል፡- መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ በሚተረጎምበት
ወቅት ተርጓሚው በፈሪሃ እግዚአብሔር የታነጸ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተረጓሚው በፈሪሃ እግዚአብሔር
የታነጸና ታማኝ ካልሆነ የግሉን አስተሳሰብ ሊጨማር አልያም ከመጽሐፉ እርሱ የማያምንበትን ሊቀንስ ይችላል፡፡
ይህም በተለያየ ጊዜ የተለያዩ መናፍቃን ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ ለማሳያም አንድ ምሳሌ መዘን ለመመልከት
እንሞክር፡-
 በዘመናችን መናፍቃን በ2ቆሮ 5፡20 ላይ አንዲት ፊደል በመለወጥ የሀሰት ትምህርታቸውን ለማስረጽ
ሞክረዋል፡፡ የተወደዳችሁ ተማሪዎች ይህ ግልጥ ይሆን ዘንድ እዛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ያሉትን
የፊደል ቅርፆች ማየት ተገቢ ነው፡፡ የተስተካከለው ቃል የሚለው “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ
እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን” ነው ነገር ግን እዛው ክፍል ላይ ከፍ ብለን ቁጥር 18 ላይ
“አገልግሎት” የሚለውን ቃል የፊደል ቅርጽ ልብ እንበል ቀጥሎም ቁጥር 20 ላይ “እንለምናለን” የሚለውን
የፊደል ቅርጽ ልብ እንበል ቀጥሎም ቁጥር 20 ላይ “እንደሚማልድ” የሚለውን ቃል ልብ እንበልና እዚሁ
ቃል ላይ ያለችውን “ል” የተሰኘችውን ፊደል እንመልከት ይህች ፊደል መስተካከል አለመስተካከሏን (“ለ”
የነበረችውን “ል” ተደርጋ መስተካከልዋን አለምስተካከልዋን) ከላይ ለማመሳከሪያነት በጠቅስናቸው የመጽሐፍ

72
አዋልድ መጻሕፍትን
73
የትርጉም ዘዴዎች፡- ቃል በቃል ፣ ዓውደ ምንባባዊ (contextual)፣ ውርስ ትርጉም (adaptation)፣ አሳጥሮ መግለጽ እና
የጽሑፉ ሃሳብ ላይ ማተኮር የሚሉት የትርጉም ዘዴዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 21
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ቅዱስ ቃላት ላይ ማለትም “አገልግሎት” የሚለውን ቃልና “እንለምናለን” የሚለውን ቃል ያሉትን የ “ለ”
እና የ “ል” ፊደላት አቀራረጽ ተመልክተን “እንደሚማልድ” የሚለውን ቃል ስንመለከት “ል” ተስተካክላ
እንደሆነ ግልጽ ይሆንልናል፡፡ ይህም ማለት ቃሉ አስቀድሞ “እንደሚማለድ” እንደነበረና ከጊዜያት በኋላ
የቅዱሳንን አማላጅነትና የጌታችንን ተማላጅነት በሚቃወሙ መናፍቃን እንደተስተካከለ (“እንደሚማለድ”
የነበረው “እንደሚማልድ” ወደሚል)74 ያስታውቃል፡፡ በዚህ መነሻነት “እንደሚማልድ” የሚለው ቃል
ትርጉም አልባ ሁኗል፡፡ ምክንያቱም ከታች “እንለምናለን” ማለታቸው የቅዱሳንን አማላጅነት የሚያመላክት
ሲሆን ከላይ ያለው ቃል አስቀድሞ ስለተማላጁ የተነገረ ነበር፡፡ ነገርግን ቃላቱ በመስተካከሉ ትርጉም አልባ
እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይልቁኑ ይህንን ቃል “እንደሚማለድ (እንደሚለመን)” በሚለው ቃል ተክተን
ብናነበው የአረፍተ ነገሩ አጠቃላይ ሃሳብ ግልጽ ይሆንልናል፡፡75
እናም የተወደዳችሁ ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ በሚተረጎምበት ወቅት ተርጓሚው
ታማኝ እና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ሊኖረው ይገባዋል፡፡ ይህም ተርጓሚው በመጽሐፉ ላይ በመጨመሩም
ሆነ በመቀነሱ ሊመጣበት ካለው መቅሰፍት76 ለመዳን በማሰብ ሊተረጉም ይገባዋል፡፡ ሆኖም ከላይ ለአብነት አንድ
ምሳሌ አየን እንጂ ሌሎችም መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ፈሪሃ እግዚአብሔር የራሳቸው ሃሳብ ያካተቱ ብዙ መናፍቃን
በየዘመኑ ተነስተዋል፡፡

ለ. የቋንቋ እውቀት ሊኖር ያስፈልጋል፡- መጽሐፍ ቅዱስን ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ ለመተርጎም
በቂ የቋንቋ እውቀት ተርጓሚው ሊኖረው ይገባዋል፡፡ ይህ ሲባል ተርጓሚው የሚተረጉምበትንም ሆነ
የሚተረጉምለትን ቋንቋ በበቂ ሁኔታ ሊያውቅ ይገባዋል፡፡ ይህ መሆን ከቻለ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይበረዝና ሳይፈለስ
ዓላማውን እንደጠበቀ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ መተርጎም ይቻላል፡፡ ነገር ግን በዚህም ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ
ቋንቋ በሚተረጎምበት ወቅት ተርጓምያኑ በቂ እውቀት ሳይኖራቸው በመተርጎም ችግር ሲፈጥሩ ታይተዋል፡፡
ለአብነትም አንዳንድ ድርጅቶች በቂ የቋንቋ ዕውቀት ሳይኖራቸው መጽሐፍ ቅዱስን ለመተርጎም ባደረጉት ጥረት
እነዚህ የትርጉም ስህተቶች በጉልህ ታይተዋል፡፡ ለምሳሌ በ2ቆሮ 5፡20 ላይ ያለውን “ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች
ነን” የሚለውን ቃል “ስለ ክርስቶስ አንባሳደሮች ነን” በማለት ለመተርጎም ሞክረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
“መሰረቶቿ” የሚለውን መሰረቶቹ (መሰረቱ) በማለት ተርጉመዋል77፡፡ እንዲህ ያለው ታማኝነት የጎደለው ሥራ
የመተርጉማኑን ሥውር ዓላማና ያለበቂ ዕውቀት እንዲሁም ያለ ፈሪሃ እግዚአብሔር በድፍረት ለመተርጎም
መሞከራቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ከዚህ ውጪ መጽሐፍትን በምናነብበት ወቅት በውስጡ ያሉትን ኃይለ ቃላት ለመረዳት የግድ የመጽሐፉን
ኃይለ ቃል ትርጉም መረዳት ያስፈልጋል፡፡ እናም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ኃይለ ቃላትን የምንተረጉምባቸው
የአተረጓጎም አይነቶች አሉ እነዚህም፡-
፪.3.3 ነጠላ ትርጉም
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በቀጥታ ትርጉም78 የሚወሰዱ እና የተለየ ምሳሌያዊም ሆነ ምስጢራዊ ትርጉም
የሌላቸው በርካታ ኃይለ ቃሎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ሲሞከር፡-
 “እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ” ዘፍ 1፡1
 “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” ማቴ 26፡41
 “እስከመጨረሻ የሚጸና እርሱ ግን ይድናል” ማቴ 24፡13 ወዘተ.....
ለእነዚህና ለመሳሰሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃላት የሚሠጠው ማብራሪያ ነጠላ ትርጉም በመባል
ይታወቃል፡፡
፪.3.4 ምሳሌያዊ ትርጉም
በመጽሐፍ ቅዱስ አንድን ነገር በተሻለና በበለጠ ግልጽ ለማድረግ በምሳሌያዊ ትርጉም ይነገራል፡፡ ይህም
“ነገር በምሳሌ...” እንዲሉ አበው ሃሳቡን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ነገር ግን ምሳሌ ሁልጊዜ ከአማናዊው

74
“ለ ን እዛው ወደ “ል ተቀይሯል መቀየሩም የፊደሉ ቅርጽ ሌሎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጻፉ “ል ዎች በጣም የተለየና አስቀድሞ “ለ የነበረ መሆኑ
የሚያስታውቅ ነው፡፡
75
በተጨማሪ ክርስቶስ ተማላጅ እንጂ አማላጅ መሆኑን የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመልከቱ፡- “ዮሐ 10፡30፣ 16፡15፣ 17፡10፣ 16፡26
76
ራዕ 22፡18-19፣ 2ጴጥ 1፡20
77
መዝ 86 (87)፡1
78
Literal meaning
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 22
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ወይም ከሚመሰልለት ነገር ያንሳል፡፡79 በመጽሐፍ ቅዱስም በምሳሌ የተነገሩ ብዛት ያላቸው ክፍሎች ይገኛሉ፡፡
ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመዋዕለ ስጋዌው ለደቀ መዛሙርቱ ካስተማረባቸው ዘዴዎች አንዱ
በምሳሌ ማስተማር80 ነው፡፡ በዚህም የተነሳ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ተገልጧል፡-
 “መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር፡፡ ያለ
ምሳሌ ግን አልነገራቸውም” ማር 4፡33-34

የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከዚህ በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በርካታ ነገሮች በምሳሌ ተመስለዋል፡፡
ለአብነትም የተወሰኑትን ከዚህ በመቀጠል በዝርዝር ለመመልከት እንሞክራለን፡-

ሀ. የእስራኤል በወይን ቦታ መመሰል፡-


 “አሁን ስለወዳጄና ስለወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለው፡፡ ለወዳጄ በፍሬያማው ኮረብታ ላይ
የወይን ቦታ ነበረው፡፡ በዙርያው ቆፈረ ድንጋዮችንም ለቅሞ አወጣ ምርጥ ሆነውንም ሀረግ
ተከለበት በመካከሉም ግምብ ሰራ ደግሞም የመጥመቂያ ጉድጓድ ማሰበት ወይንንም ያፈራ ዘንድ
ተማመነ ዳሩ ግን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ” ኢሳ 5፡1-2
በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ የተነገረው ስለ ወይን(ስለ ግብርና) ይሁን እንጂ ዋናው መልእክት ግን
ይህ አይደለም፡፡ በምሳሌ ተመስለው የቀረቡልን የወይን ቦታው ወይም እርሻውና የወይኑ ሀረግ የሚመስሉት
(የሚወክሉት) ሌላ ትርጉም አለ፡፡ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ አካሄዱ ነው፡፡ የኃይለ ቃሉ ምሳሌያዊ ትርጉም
የወይን ቦታ የተባሉት ቤተ እስራኤል፣ የደስታውም አትክልት የተባሉት የይሁዳ ሰዎች፣ ወዳጄ የተባለው
እግዚአብሔር ሲሆን ከወይን አትክልቱ አመርቂ ፍሬ እንዲያገኝ በሚገባ የሚንከባከበውን ያህል እግዚአብሔርም
እስራኤልን እንደተንከባከባቸው ኃይለ ቃሉ ያሳየናል፡፡81

ለ. የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና ምሳሌ፡-


 “እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ የተቆለፈ ገነት፤ የተዘጋ ምንጭ የታተመ ፈሳሽ ናት” መኃ 4፡12
ቃሉን ምሰሌያዊ ትርጉም ያለው ነው፡፡ ይህም ማለት በነጠላ ትርጉም ልንተረጉመው አንችልም፡፡ በነጠላ
ትርጉም እንውሰደው ብንል ምን ለማለት እንደተፈለገ ግልጽ አይሆንልንም፡፡ ምክንያቱም ምንጭ ከሆነች ልትዘጋ
አትችልም፡፡ ፈሳሽም ከሆነች ልትታተም አትችልም፡፡ እናም ጠቢቡ ሠለሞን የተናገረው ኃይለ ቃል ምሳሌያዊ
በመሆኑ በቀጥታ እንደወረደ ለመተርጎም አይቻልም፡፡ እናም ሰለሞን በምሳሌ ሊገልጥ የሞከረው የእመቤታችንን
ዘላለማዊ ድንግልና ነው፡፡ በአጠቃላይም በዚህ የመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ በሴት አንቀጽ የተገለጡት
የእመቤታችንና የቤተክርስቲያን ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ነብዩ ሕዝቅኤልም በትንቢቱ የእመቤታችንን
ዘላለማዊ ድንግልና በምሳሌ ገልጧል፡፡
 “ወደ ምስራቅም ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ ዘግቶም ነበር፡፡
እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም ሰውም አይገባበትም የእስራኤል
አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል” ሕዝ 44፡1
የተወደዳችሁ ተማሪዎች ይህን ክፍል በነገረ ማርያም ትምህርታችሁ ላይ ወደ ፊት በዝርዝር
ስለምትመለቱት እዚህ ላይ እናብቃና ወደ ሌላ ምሳሌ እንሸጋገር፡-

ሐ. የጌታችን በበግ መመሰል፡-


በግ ቢሸልቱት፣ ቢመቱት፣ ቢያርዱት እንዲሁም ቢያሰቃዩት ምንም አይናገር፡፡ ጌታችንም አይሁድ መከራን
ቢያበዙበትም ምንም አልተናገረም82፡፡ በዚህም የተነሳ በበግ ተመስሏል፡፡
 “....ተጨነቀ ተሰቃየ አፉንም አልከፈተም፡፡ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹ ፊት ዝም
እንደሚል በግ እንዲሁ አፉንም አልከፈተም” ኢሳ 53፡7

79
በዚህም መነሻነት አበው “ምሳሌ ዘየሐጽጽ ይላሉ፡፡
80
ለምሳሌ በጠፋው ልጅ፣ በበግ እና በድሪም..... ሉቃ 15፡3-32፣ በፈሪሳዊና በቀራጭ ....... ሉቃ 18፡9-14፣ በሰናፍጭ ቅንጣት ....... ማር 4፡30-32፣ ወዘተ...
81
በተጨማሪ፡- ኢሳ 5፡1 (አንድምታ)፣ ኢሳ 5፡7 ዋናው እና አንድምታውን ይመልከቱ፡፡
82
ማቴ 27፡14
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 23
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ“ ዮሐ 1፡29


ከዚህ በተጨማሪም በይስሐቅ ፋንታ የተሰዋው በግም የጌታችን ምሳሌ ነው፡፡ ይህም በጉ በይስሐቅ ፋንታ
እንደታረደ ሁሉ ጌታችንም በአዳም ፋንታ ተገብቶ በመስቀል ላይ ተሰውቷልና ነው፡፡ ከዚህ ወጪ በመጽሐፍ ቅዱስ
ላይ በግ ተብሎ ተጠርቷል፡፡83
ከዚህ በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተለያዩ ምሳሌያዊ አነጋገሮች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡-
 ፃድቃንና ኃጥአን በበግና በፍየል ተመስለዋል......... ዮሐ 10፡3-15፣
 መንግስተ ሠማያት ለልጁ ሠርግን ባደረገ ንጉስ ተመስላለች...... ማቴ 22፡1-13
 የጌታ ደቀ መዛሙርት በጨው ተመስለዋል................ ማቴ 5፡13
 ጌታችን በማዕዘን ድንጋይ፣ በቤተ መቅደስ፣ በዓለት ተመስሏል.............. ዳን 2፡34፣84 1ቆሮ 10፡4፣ ዘጸ
17፡6፣ ዮሐ 2፡19፣ ወዘተ........

፪.3.5 ምስጢራዊ ትርጉም


ምስጢር85 ማለት የተሰወረ፣ የተሸሸገ፣ የተደበቀ፣ በውስጥ ያለ ላይ በላይ የማታይ ማለት ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምስጢርን ማግኘት አሊያም መረዳት ካልተቻለ የኃይለ ቃሉን (የመልእክቱን) ጭብጥ
ማግኘትና መገንዘብ አይቻልም፡፡ እናም የመጽሐፉን ኃይለ ቃል ምስጢር ማግኘት እጅግ አስፈላጊና ተገቢ ነው፡፡
ይህ ትርጉም ሊገኝ የሚችለው በምርምር እና በተገደበው በሰዎች እውቀት ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
ገላጭነት ነው፡፡ ይህም አስቀድሞ ከላይ ለመግለጥ እንደሞከርነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተመርምሮ
የማያልቀውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በጥቂቱ ለመረዳትና ከሰው አዕምሮና ጥበብ በላይ የሆኑ ነገሮችን ለመግለጥ
በነብያት፣ በሐዋርያት እና በአርድዕት ላይ አድሮ መጽሐፍ ቅዱስን አጽፏል፡፡ ይህ ቅዱስ መጽሐፍ በእግዚአብሔር
ጥበብ እንደመጻፉ ሰዎች ተመራምረው የማይደርሱባቸው እጅግ ጥልቅ ጥበብን የያዘ ምስጢራዊ መጽሐፍም ነው፡፡
ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ የማያልቅ ባህር ነው የሚባለው፡፡ ስለዚህ ይህንን ጥልቅ ምስጢር የሰው ልጅ
በተሰጠው ውስን አዕምሮ ተመራምሮ ሊፈታው አይችልም ይልቁኑ ይህንን ምስጢር ይገለጥላቸው ዘንድ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አዕምሮአቸውን ለመረጣቸው ይከፍታል፡፡
 “መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አዕምሮአቸውን ከፈተላቸው” ሉቃ 24፡45
 “በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን... ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ
በምስጢር እንናገራለን” 1ቆሮ 2፡6-7
ስለዚህ ከዚህ የምንረዳው ሰው መጻፍ እና ማዳመጥ ስለቻለ ብቻ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ምስጢር
እንደማይገለጥለት ነው፡፡ በጋዛ በሰረገላ ላይ ተቀምጦ ከነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ከገጠመው የምነረዳው
ይህንኑ ነው፡፡ እናም ከዚህ የምንረዳው መጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራዊ ትርጉም የሚረዱት እግዚአብሔር መንፈስ
ቅዱስ ጥበቡን እና ጸጋው86 ለገለጠላቸው ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ነው፡፡
 “የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽሜ እንድሰብክ እኔ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ሆንሁ ይህም ቃል
ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምስጢር ነው” ቆላ 1፡26

ስለዚህ ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራዊ ትርጉምን ያዘለ በመሆኑ እግዚአብሔር ለመረጣቸውም
የሚገለጥ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡ እናም የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራዊ ትርጉምን ለመረዳት የተለያዩ መንገዶች
አሉ፡፡ ጌታም ለሐዋርያቱ “ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ”
በማለት እንደተናገረው ከመምህራን መማርና “የተቀበላችሁትን” እንዳለ በትውፊትም ትርጓሜ መጻሕፍትን ማግኘት
ይቻላል፡፡ በዚህ መሰረት ቅዱሳን አባቶች ገጽ በገጽ ከሐዋርያት የተማሩትን፣ ያዩትንና የሠሙትን በቀጥታ ለእኛ
አድርሰውልናል፡፡ ከዚያም ሐዋርያው የተቀበላችሁትን እንዳለ በትውፊት (በቅብብሎሽ) መጻሕፍቱንና

83
ዘፍ 22፡13፣ ራዕ 5፡6 እና ቁ.13ነነ፤/፣ 6፡1፣ 7፡10፣ 17፡14፣ 12፡11፣ 14፡1 እና ቁ4፣ ወዘተ.....
84
ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊውም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ድርሰቱ ላይ ይህንን ሲያጎላ፡- “ነብዩ ዳንኤል ያየው ያለእጅ ከረጅም ተራራ የተፈነቀለ ያ ደንጊያ ከአብ
ዘንድ የወጣው ቃል (ኢየሱስ ክርስቶስ) ነውና መጥቶ ያለ ወንድ ዘር ከድንግል ተወልዶ አዳነን”
85
ምስጢር የሚለው ቃል በግዕዙ “አመሠጠረ ወይም “ሠጠረ ከሚለው ቃል የተገኘ ነው፡፡ ቃሉ በዕብራይስጥ “ሳታር”፣ በአረብኛ “ሰተር”፣ በሱርስት “ስታር”፣
በእንግሊዘኛ “ሚስትሪ ይሉታል፡፡
86
ኤፌ 3፡9
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 24
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ትርጓሜያቸውን አግኝተናል፡፡ ይኸውም የጻፏቸውን መልዕክታት ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ምክንያቱም እነርሱ


የጻፏቸው እኛ የምንቀበላቸው በመሆናቸው ነው፡፡
ከዚህ በመቀጠልም በአባቶቻችን አማካይነት የደረሠውን ትርጉም እንደምሳሌ የተለያዩ ክፍሎችን
ለመመልከት እንሞክራለን ይህም በትርጓሜዎች ላይ ተተርጉመው የምናገኛቸው ምስጢራዊውን ትርጉም ነው፡፡

ሀ. “እንጀራህን በውኃ ፊት ጣለው ከብዙ ቀኖች በኋላ ታገኘዋለህ” (መክ 11፡1)


ይህንን ኃይለ ቃል እንደወረደ የምንተረጉመው ከሆነ ትርጉም አልባ ነው፡፡ ምክንያቱም እንጀራን በውኃ
ላይ ጥለን ከብዙ ቀናት በኋላ ብንመጣ እንኳን ልናገኘው ሟምቶ ከአይናችን ይሰወራል፡፡ እናም የዚህን ኃይለ ቃል
ምስጢራዊ ትርጉም መመልከት ሐሳቡን ሳይጣመም ለመረዳት ወሳኝ ነው፡፡ እናም ምስጢራዊ ትርጉሙ ደግሞ
የሚገልጠው ስለ እንጀራ ሳይሆን ስለ ምጽዋት ነው፡፡ ይህም እንዴት ነው ቢባል ትርጉሙን ከዚህ በመቀጠል
ለመመልከት እንሞክራለን፡-
 ከውኃ ውስጥ የጣሉት አይታይም አንተም ለድሆች ሰውረህ መጽውት በኋላ በዳግም ምጽአት ጊዜ
“ተርቤ አብልተኸኛልና” ብሎ በግልጥ ይከፍልሃልና፡፡87
 ከውኃ ላይ የጣሉት እንጀራ ተመልሶ አይገኝም አንተም ምጽዋትን ስትሰጥ ከተቀበለኝ ሰው ዋጋዬን
መልሼ አገኛለው፤ የሠጠሁት ሰው ብድራቴን መልሶ ይከፍልልኛል ብለህ አትመጽውት ሲል88
 ከውኃ ዳር የዘራ ሰው ምርት አያጣም ዝናብ ቀረ ብሎም አይሰጋም አንተም በቸርነት ለመጸወትከው
ምጽዋት ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ዋጋ አታጣም ሲል89

ለ. “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ” (ማቴ 27፡46)


ይህንን የጌታችን ንግግር በነጠላ ትርጉም ብንተረጉመው የተጣመመ መልእክትን ስለምናገኝ ወደ ስህተት
እናመራለን፡፡ እናም ይህ ኃይለ ቃል በምስጢራዊ ትርጉም አተረጓጎም የተተረጎመውን ትርጉም መመልከት
ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ይህንን ቃል የተናገረባቸው ስለ ሶስት ምክንያቶች ነው፡፡ ይህም፡-

 ለእኛ አብነት ይሆን ዘንድ፡- ጌታችንም በተለያየ ጊዜና በተለያየ ቦታ እርሱን አብነት እንድናደርግና እርሱ
የሰራውን እኛም እንድንሰራ አዞናል፡፡90 ከዚህ በተጨማሪም እርሱን አብነት አድርገው በሕይወታቸው
ያሳዩን ቅዱሳን ሐዋርያት እነርሱን አብነት እንድናደርግ አዘውናል፡፡91 ጌታችንም ሰው በመሆኑ
ጾሟል፣ጸልዮዓል፣ አልቅሷል፣አዝኗል92 ፣ ከዚህ በተጨማሪም ስለ ሰዎች ምህረትን ለምኗል93 ወዘተ...
እናም ይህንን ሁሉ ያደረገበት ለእኛ አብነት ለመሆን ነው፡፡ እንጂ እርሱ ንጹሀ ባሕርይ ጉድለት የሌለበት
ሁሉም በእርሱ ፈቃድ የሚሆን እንጂ አንዳች ያለእርሱ ፈቃድ የማይደረግ አምላክ ነው፡፡94 ስለዚህ እርሱ
ቢጾም ቢጸልይ ለእኛ አብነት ለመሆን እንጂ የጎደለበት ነገር ኖሮ ይሞላለት ዘንድ አይደለም፡፡ ስለዚህም
ጌታችን ስለምን “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ አለ ቢባል ለእኛ አብነት ለመሆን ነው፡፡ ይህም እኛ
በሃይማኖት የተነሳ መከራ ቢጸናብን ጌታችን ሁልጊዜ ከጎናችን ሆኖ መከራውንና ስቃዩን ያሳልፍልን ዘንድ
“አትተወን” ማለት እንደሚገባን ለማስተማር (ለእኛ አብነት ለመሆን) በመስቀል ላይ ይህንን ቃል
ተናግሮታል፡፡

87
ማቴ 6፡1-4
88
ሉቃ 14፡13-14
89
ሉቃ 14፡13-14
90
ማቴ 11፡29፣ ዮሐ 13፡12-15
91
1ቆሮ 11፡1
92
ማቴ 4፡1፣ ዮሐ 11፡33፣ ሉቃ 22፡41፣.....
93
እርሱ ለማኝ አብ ተለማኝ ሆኖ ሳይሆን ለእኛ አብነት ይሆንልን ዘንድ ነው፡፡ ይህም ሰዎች መከራን ቢያጸኑብንም ስለእነርሱ ምህረትን መለመን እንደሚገባን
ለማስተማር ነው፡፡ ከእርሱም በኋላ እርሱን አብነት በማድረግ ይህንን የጌታችንን ተግባር ቅዱሳኑ ፈጽመውታል፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ እስጢፋኖስን ማንሳት
ይቻላል፡፡ (የሐዋ. ሥራ 7፡60)
94
ቆላ 1፡15-18
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 25
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ትንቢቱን ለመፈጸም፡- ይህም አስቀድሞ በነብዩ ዳዊት ተነገረውና95 አዳምና የአዳም ልጆች ሁሉ በሲዖል
ውስጥ ሆነው የመሲሁን ወይም የክርስቶስን መምጣት በመናፈቅ የጮሁት ጩኸት ነው፡፡

 ለአቅርቦተ ሠይጣን፡- ይህም ዲያቢሎስ አስቀድሞ ፍጹም ሰው ብቻ ነው96 ብሎ ሊፈትነው ሲቀርበው


አምላካዊ ግብርን እያሳየው ይሸሸው ነበር፡፡ እናም በዚህ የተነሳ ዲያቢሎስ የክርስቶስን ፍጹም ሰው መሆን
ተጠራጥሮ ነበርና፡፡ ይህም ማለት አምላክ መሆኑን ተጠራጥሮ ነበርና አምላክ አለመሆኑንና ሰው ብቻ
መሆኑን አምኖ ይቀርበው ዘንድ ይህንን ቃል ተናግሯል፡፡ በዚያም የተነሳ “አምላኬ አምላኬ” ክርቶስ ሲል
ዲያቢሎስ ስለሰማው ይሄስ አምላክ አይደለም ብሎ በመስቀል ላይ ሊፈትነው ቀርቦታል ያኔም ክርስቶስ
በአራት የነፋስ አውታራት ዲያቢሎስን በማሰር ሲዖል ያሉ ነፍሳትን አውጥቷል፡፡

የተወደዳችሁ ተማሪዎች ለአብነት ይህንን አነሳን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በነጠላ ትርጉም
የማይተረጎሙ ይልቁኑ በምስጢራዊ ትርጉማቸው የሚተረጎሙ ወይም በአንድምታ የሚተረጎሙ እጅግ ብዙ ኃይለ
ቃላት አሉ፡፡ እነዚህ ኃይለ ቃላት በተለይ በዘመናችን የተነሱ መናፍቃን ለሚያነሷቸው የምንፍቅና ጥያቄዎች ምንጭ
ናቸው፡፡ አብዛኞቹም መሰል ጥያቄዎች የሚነሱት የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢራዊ ትርጉም ካለመረዳት የተነሳ ነው፡፡
እናም እናንተም ይበልጥ ግንዘቤያችሁ ይሰፋ ዘንድ በምዕራፉ የክለሳ ጥያቄዎች ላይ የተጠቀሱትን የመጽሐፍ ቅዱስ
ኃይለ ቃላት መምሕራነ ቤተክርስቲያንን በመጠየቅ የኃይለ ቃሉን ትርጉም ለመረዳት እንሞክር፡፡ በበለጠ ደግሞ
ቀጣይ በምትማሯቸው ትምህርቶች ላይ እነዚህ ቃላት በተብራራ መልኩ እንደሚመሱላችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ላሁን ግን ወደ ቀጣዩ ርዕስ እንሸጋገር፡-

፪.4 የምዕራፍ ሁለት የክለሳ ጥያቄዎች97


1. መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንደሚገባ በዝርዝር አስረዱ?
2. ከታች የምትመከለቷቸውን ኃይለ ቃላት በመካከላቸው ያለውን የትርጉም ልዩነት ተወያዩበት?
 “የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል” እና “ደግ ሰው ዘወትር ሲታወስ ይኖራል” መዝ
111(112)፡6
 “ደጋግ ሰዎች ሰዎች በደግነታቸው ሲታወሱ ይኖራሉ” እና “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው”
ምሳ 10፡7
3. ከታች የተዘረዘሩትን በመካከላቸው ያለውን ልዩነት አስረዱ?
 በነጠላ ትርጉም እና በምሳሌያዊ ትርጉም
 በምሳሌያዊ ትርጉምና በምስጢራዊ ትርጉም
 በምስጢራዊ ትርጉምና በነጠላ ትርጉም
4. መጻሕፍት ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ሲተረጎሙ ተርጓሚው ሊኖሩት የሚገቡ ነገሮችን ዘርዝሩ?
5. የሚከተሉትን ኃይለ ቃላት ምስጢራዊ ትርጉም ከመምሕራችሁ አልያም ከአገልጋዮቻችሁ ጠይቃችሁ
በመረዳት ምስጢራዊ ትርጉማቸውን አስረዱ?
 “ስለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም” ማር 10፡18
 “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ
አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው” ዮሐ 20፡17

95
መዝ 21(22) ፡1
96
እሩቅ ብዕሲ ነው
97
ለጥያቄዎቹ በቂ ምላሽ ለማግኘት “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአባይነህ ካሴ የተፃፈና በማህበረ ቅዱሳን 2002 ላይ የታተመውን መጽሐፍ
ይመልከቱ
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 26
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ምዕራፍ ሦስት
የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል
የተወደዳችሁ ተማሪዎች በምዕራፍ አንድ አንድና በምዕረፍ ሁለት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንነትና እንዴት
ማጥናት እንደሚገባን በዝርዝር ተመልክተናል፡፡ በዚህኛው ምዕራፍ ደግሞ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አከፈፈል እና ይዘት
እንዲሁም ስለ ጸሐፊያኑ ማንነት በዝርዝር ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በዋናነት ብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ተብሎ በሁለት ዐበይት ክፍሎች
ይከፈላል፡፡ ብሉይ ኪዳን በውስጡ አርባ ስድስት መጻሕፍትን የያዘ ሲሆን አዲስ ኪዳን ደግሞ ሰላሳ አምስት
መጻሕፍትን የያዘ ነው፡፡ በውስጣቸውም ያሉት መጻሕፍት እንደይዘታቸው በተለያየ አከፋፈል እንከፋፍላቸዋለን፡፡
እናም የተወደዳችሁ ተማሪዎች ለመግቢያ በሁለቱም አከፋፈሎች ውስጥ ያለውን እንዲህ ከተመለከትን በቀጣይ
በውስጣቸው ያሉትን መጻሕፍት አከፋፈልና ይዘት እንዲሁም ስለ ጸሐፊዎቹ ማንነት በዝርዝር የምንመለከት
ይሆናል፡፡
3...1 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
3.1.1 የቃሉ ትርጉም
ብሉይ ማለት ያረጀ፣ ጥንታዊ፣ ቀዳማዊ፣ የድሮ፣ የቀድሞ፣ የፊት፣ወዘተ.... ማለት ሲሆን፤ ኪዳን98 ማለት
ደግሞ ውል፣ ስምምነት፣ ወዘተ... ማለት ነው፡፡ ባጠቃላይ ብሉይ ኪዳን ማለት የጥንት የቆየ የመጀመሪያ ውል
ስምምነት ማለት ነው፡፡ ይህም ያረጀ መባሉ ከሱ የተሻለው ኪዳን አዲስ ኪዳን በመኖሩ ነው እንጂ ኪዳኑ ዛሬም
የጸና ኪዳን ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር የሚገባው ቃል ኪዳን በዘመናት የማይሻር በመሆኑ
ነው፡፡ ከዚሀ በተጨማሪም ብሉይ ኪዳን ያረጀ መባሉ ኪዳኑ የተገባበት ዘመን በማርጀቱ ይህም ማለት ኪዳኑ
የተገባበት ዘመን በኋላ ረጅም ጊዜያት ማለፉን ለማጠየቅ ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን በአጠቃላይ ከጌታ ልደት በፊት የአንድ
አምላክ አማኞች የሆኑትን የእስራኤላውያንን ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ ነው፡፡ በውስጡም በዋናነት ከአምስት ሺ
አምስት መቶ ዘመን በኋላ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በፍጹም ድንግልና የሚወለደውን ጌታ ሕዝቡ
ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ በተለያዩ የነብያት ትንቢትን ይዟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እግዚአብሔር ከወዳጆቹ ጋር
የገባውን ቃል ኪዳን በአጠቃላይ ያካትታል፡፡99

3.1.፪ የመጻሕፍቱ ብዛት


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የካርቴጅ (ቅርጣግ) ጉባኤያትን100 መሰረት አድርጋ በቀኖናዋ
የምትቀበላቸው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ብዛት 46 ሲሆኑ እነዚህን መጻሕፍት የጻፉት ሰላሳ ሁለት የሚደርሱ
ጸሐፍያን ናቸው፡፡ ባጠቃላይ በእነዚህ ጸሐፍያን የተጻፉት መጻሕፍት የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በመባል ይታወቃሉ፡፡
እነርሱም፡-
1. ኦሪት ዘፍጥረት 24. መጽሐፈ ኩፋሌ
2. ኦሪት ዘጸአት 25. መጽሐፈ ተግሳጽ
3. ኦሪት ዘሌዋውያን 26. መጽሐፈ ጥበብ
4. ኦሪት ዘኁልቁ 27. መጽሐፈ መክብብ
5. ኦሪት ዘዳግም 28. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
6. መጽሐፈ ኢያሱ 29. መጽሐፈ ሲራክ
7. መጽሐፈ መሳፍንት 30. ትንቢተ ኢሳይያስ
8. መጽሐፈ ሩት 31. ትንቢተ ኤርሚያስ
9. 1ኛ እና 2ኛ ሳሙኤል 32. ትንቢተ ሕዝቅኤል
10. 1ኛ እና 2ኛ ነገስት 33. ትንቢተ ዳንኤል
11. 1ኛ ዜና መዋዕል 34. ትንቢተ ሆሴዕ

98
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ላይ ኪዳን የሚለውን ቃል ሲተረጉሙት፡- በቁሙ ውል ፣ቁም ነገር፣ የፍቅርና የአንድነት መሐላ፣
ሰላማዊ ህግ፣ ሁለቱን ወገን አንድ የሚያደርግ ስለ ረብና ስለ ጥቅም በተስፋ የቆመ የተጻፈ ሥርዓት ቢያፈርሱት ጉዳትና ጠብ የሚያመጣ ጥቅም የሚያሳጣ
በማለት ተርጉመውታል፡፡ (ገጽ 529) ኪዳን በሁለት አካላት (ውል ሰጪና ውል ተቀባይ) የሚደረግ ውል ሲሆን ብሉይ ኪዳንም እግዚአብሔር ከተለያዩ
ቅዱሳን ጋር የሚያደርገው ወል አሊያም ስምምነት ነው፡፡
99
መዝ 88(89)፡3
100
በ395ዓ.ም፣ 397ዓ.ም፣ 399ዓ.ም እና በ419 ዓ.ም
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 27
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

12. 2ኛ ዜና መዋዕል 35. ትንቢተ አሞጽ


13. መጽሐፈ ኩፋሌ 36. ትንቢተ ሚኪያስ
14. መጽሐፈ ሄኖክ 37. ትንቢተ ኢዩኤል
15. መጽሐፈ ዕዝራ እና ነህምያ 38. ትንቢተ አብድዩ
16. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ እና ዕዝራ ሱቱኤል 39. ትንቢተ ዮናስ
17. መጽሐፈ ጦቢት 40. ትንቢተ ናሆም
18. መጽሐፈ ዮዲት 41. ትንቢተ ዕንባቆም
19. መጽሐፈ አስቴር 42. ትንቢተ ሶፎንያስ
20. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ 43. ትንቢተ ሐጌ
21. ዳግማዊና ሣልሳዊ መቃብያን 44. ትንቢተ ዘካርያስ
22. መጽሐፈ ኢዮብ 45. ትንቢተ ሚልክያስ
23. መዝሙረ ዳዊት 46. ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን

3.1.3 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አከፋፈል


ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ብዛት አርባ ስድስት ሲሆን እነዚህን መጻሕፍት
ከይዘታቸው አንጻር በአጠቃላይ በአራት መሰረታዊ ክፍሎች ከፍለን እንመለከታቸዋለን፡፡ እነሱም፡-
 የሕግ /የኦሪት/ መጻሕፍት ክፍል
 የታሪክ መጻሕፍት ክፍል
 የትምህርት /የጥበብ የመዝሙር/ መጻሕፍትና ክፍል
 የትንቢት መጻሕፍት ክፍል ናቸው፡፡

ክፍል አንድ
የህግ መጻሕፍት/ብሔረ ኦሪት/
ኦሪት የሚለው ቃል የሱርስት ቃል ሲሆን ሕግ ማለት ነው፡፡ ሕግ ማለት ደግሞ ብርሃን ማለት ነው፡፡ ከዚህ
ቃል ጋር ተያይዘው የሚጠሩ መጻሕፍት አምስት ሲሆኑ የተጻፉትም በሊቀ ነቢያት ሙሴ አማካኝነት በሲና ተራራ
በ1500 ዓ.ዓ ነው፡፡ መጻሕፍቱ በዕብራይስጥ ቋንቋ ለእስራኤል ዘስጋ የተጻፉ ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በውስጣቸው
ሦስት ታላላቅ ህግጋትን ይዘዋል፡፡ እነሱም:-
1. የሞራል ህግ
2. የክህነት ህግ
3. የአስተዳደር ህግ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም እነዚህ መጻሕፍት ከህግ በተጨማሪ ታሪክን፣ ትንቢትንና፣ትምህርትን የያዙ መጻሕፍት
ናቸው፡፡ እነዚህም፡-
1 ኦሪት ዘፍጥረት 4 ኦሪት ዘኅልቁ
፪ ኦሪት ዘጸአት 5 ኦሪት ዘዳግም
3 ኦሪት ዘሌዋውያን

1. ኦሪት ዘፍጥረት /ዘልደት/101


በግዕዝ ዘልደት ተብሎ ይታወቃል፡፡ የፍጥረትን ካለመኖር ወደመኖር መምጣትና መገኘትን በማውሳት
ስለሚጀምር በዚሁ ታሪክ በርዕሱ ኦሪት ዘፍጥረት /ዘልደት/ ተብሏል፡፡ መጽሐፉ ከህግ መጻሕፍት የመጀመሪያው
ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ከፍጥረት አገኛኘት ጅምሮ እስከ ህዝበ እስራኤል ወደ ግብጽ መውረድ ድረስ ያለውን ታሪክ
ይገልጣል፡፡ መጽሐፉ 50 ምዕራፎች አሉት፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-5 የሥነ ፍጥረት ስርዓት /የፍጥረት አፈጣጠር/ የሰው ልጅ ውድቀትና የመጀመሪያ
አባቶች ዕድሜ

101
Genesis
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 28
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ከምዕራፍ 6-11 የሰው ልጆች በኃጢአት መክፋትና የደረሰባቸው ቅጣት የባቢሎን ግንብ ታሪክ
 ከምዕራፍ 12-26 የአብርሃም የሃይማኖት ጉዞ የሰዶምና የገሞራ ጥፋት እንዲሁም የይስሃቅ
ታሪክ
 ከምዕራፍ 27-50 የያዕቆብና የዮሴፍ ታሪክ የእስራኤል ወደ ግብጽ መውረድ፡፡

፪. ኦሪት ዘጸአት102
“ጸአት” ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን መውጣት ማለት ነው፡፡ ይህም መጽሐፉ የእስራኤል ሕዝብ በሙሴ
መሪነት ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን በሰፊው የሚያወሳ ስለሆነ በዚሁ ተሰይሟል፡፡ ይህ መጽሐፍ ሕዝበ
እስራኤል ከ430 ዓመት የባርነትና የስቃይ ቆይታ በኋላ በሙሴ መሪነት ከግብጽ ከባርነት ወጥተው እስከ ሲና
ተራራ ድረስ ያለውን ታሪክ ይተርካል፡፡ መጽሐፉ 40 ምዕራፎች አሉት፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-4 ከሙሴ ልደት ነጻ ለማውጣት እስከተጠራበት
 ከምዕራፍ 5-11 በግብጽ ስለወረዱ 10 መቅሰፍቶች
 ከምዕራፍ 12-15 የኤርትራን ባህር በእግዚአብሔር ኃይል መሻገራቸው
 ከምዕራፍ 16-40 እስራኤል መና እንደወረደላቸው የሙሴ በሲና ሕግን መቀበል እንዲሁም
የእስራኤልን ጣዖት ማምለክና መቀጣት የሚገልጽ ታሪክ ይገኛል፡፡

3. ኦሪት ዘሌዋውያን103
ዘሌዋውያን የሚለው ቃል ሌዊ ከተሰኘ የያዕቆብ ልጅ ስም የተገኘ ነው፡፡ የሌዊ ልጆች104 (ትውልድ) ለእስራኤል
ሕዝብ ካህናት እንዲሆኑ የተመረጡ ሲሆኑ በተለይም የሙሴ ወንድም አሮን ሊቀ ካህናት ተብሎ ከተሾመ ጀምሮ
የነበረውን የእነዚህን ካህናት ሥርዓት በዝርዝር ስለሚያስረዳ በዚህ ስም ተሰይሟል፡፡ ይህ መጽሐፍ የእግዚአብሔር
ሕዝብ በሁለንተናው ንጹህ (ቅዱስ) መሆን ስለሚናገር የቅድስና መጽሐፍ ይባላል፡፡105 ይህ መጽሐፍ 27 ምዕራፎች
አሉት፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-10 ስለ መስዋዕትና ስለ ሥርዓተ ክህነት
 ከምዕራፍ 11-16 ስለ መባልዕትና የማንጻት ሥርዓት
 ከምዕራፍ 17-22 ስለ ጋብቻና የክህነት ምርጫ
 ከምዕራፍ 23-27 ህግና በዓላትን ስለማክበር በዚያም የሚገኘውን በረከትን መርገም የሚገልጽ
ሲሆን በውስጥ በርካታ ሕግጋተ እግዚአብሔር ተገልጠዋል፡፡

4. ኦሪት ዘኁልቁ106
በግዕዝ “ኆለቀ” ማለት ቆጠረ ማለት ሲሆን ዘኁለቁ ማለት ደግሞ የቁጥር መጽሐፍ ማለት ነው፡፡ እስራኤል
ከግብጽ ባርነት ከወጡ በኋላ በታሪካቸው ሁለት ጊዜ የተቆጠሩበት መጽሐፍ ነው፡፡ ይህም በመጀመሪያ በሲና ምድረ
በዳ107 ቀጥሎም በሞዓብ ሃገር108 መቆጠራቸውን ስለሚገልጽ በዚህ ስም ተሰይሟል፡፡ ይዘቱም የማርያምንና የአሮንን
ሞት በመጨረሻም ምድረ ርስትን እንዴት እንደሚከፋፈሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ትዕዛዝ ገልጧል፡፡ መጽሐፉ
36 ምዕራፎች አሉት፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-5 ህዝበ እስራኤል በሲና መቆጠራቸዉ
 ከምዕራፍ 6-25 ከሲና ተራራ እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ መጓዛቸዉ፣ 12ቱ ሰላዮች፣ የሙሴ
ኢትዮጵያዊታን ማግባት

102
Exodus
103
Leviticus
104
እነዚህ ለክህነት አገልግሎት የተመረጡና ስለ ህዝቡ ኃጢአትና በደል መስዋዕትን ዘወትር የሚያቀርቡ ከእግዚአብሔር ጋር ሕዝቡን ያስታርቁና
ኃጢአታቸውንም ያስተሰርዩላቸው የነበሩ ናቸው፡፡
105
ዘሌ 19፡2
106
Numbers
107
ዘኁ 1፡1-3
108
ዘኁ 26፡1-3
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 29
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ምዕራፍ 26 የእስራኤላዉያን አለመታዘዝና የ40 ዓመት ጉዞ

5. ኦሪት ዘዳግም109
ዘዳግም ማለት ትርጉሙ የተደገመ ማለት ነው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ከኦሪት ዘጸአት እስከ ኦሪት ዘኁልቁ
ድረስ ያሉትንና የቀሩትን ዋና ዋና ኃይለ ቃሎች በስብከት መልክ ስለሚደግማቸው ዘዳግም(የሚደግም) ተብሏል፡፡
መጽሐፉ 34 ምዕራፎች ሲኖሩት በዮርዳኖስ ምድር ባለችው በሞአብ ሀገር ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው ነው፡፡
ይህም እግዚአብሔር ስለሰጣቸው ደንቦች እንደ አዲስ የሚተረጉምና የወደፊቱን በትንቢት የሚናገር መጽሐፍ ነዉ፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-4 እግዚአብሔር ለህዝቡ ያረጋቸዉን ድርጊቶች መገለጹ፣ በሙሴ መሪነት
የተከናወነ የእስራኤላዉያን ታሪክ
 ከምዕራፍ 5-26 ከእግዚአብሔር የተሰጡ ህግጋት ተደጋግመዉ እንዲነገሩና ህዝቡም
ህግጋቱን እንዲከተሉ ምክር መሰጠቱ
 ከምዕራፍ 27-30 ለሰዎች የተሰጡ ምርጫዎች፣ በመታዘዝ በረከት ባለመታዘዝ መርገም
እንዳለ መገለጹ
 ምዕራፍ 31 ማስጠንቀቂያ
 ከምዕራፍ 32-33 የመጨሻዎቹ የሙሴ መዝሙራትና በረከት
 ምዕራፍ 34 የሙሴ ሞት

ክፍል ሁለት
የታሪክ መጻሕፍት
በዚህ ክፍል 17 መጻሕፍትን እናገኛለን፡፡ በዉስጡም ከመስፍኑ ከኢያሱ ወልደ ነዌ አነሳስ ጀምሮ እስከ ዮሴፍ
ወልደ ኮርዮን ድረስ ያሉትን መጻሕፍት ይይዛል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በአጠቃላይ የሚያወሱትም በእስራኤላዉያንና
በእግዚአብሔር መካከል ስለነበረዉ ግንኙነት110 ነው፡፡ የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከዚህ በመቀጠል የመጽሐፍቱን
ይዘት እና ስለጸሐፊያኑ እንዲሁም አከፋፈላቸውን በዝርዝር ለመመልከት እንሞክራለን ተከተሉን፡-

1. መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ111


ኢያሱ ማለት መድኃኒት ማለት ነው፡፡112 ኢያሱ የመጀመሪያ ስሙ አውሴ በመባል ሲታወቅ ኢያሱ ብሎ
ያወጣለት ሊቀ ነብያት ሙሴ ነው፡፡ የተወለደው ከነገደ ዮሴፍ ሲሆን የእናቱ ስም ባይታወቅም አባቱ ነዌ ይባላል፡፡
መጽሐፉም በስሙ ተሰይሟል መድኃኒት የተባለበትም ምክንያት እስራኤልን መክሮና አስተምሮ ከስህተት በማዳኑና
ጠላትን አጥፍቶ ከጠላት እጅ በማስጣሉ ነው፡፡ ኢያሱ በመንፈሳዊነቱና በአርበኛነቱ የታወቀ በደብረ ሲና ከሙሴ
ጋር ያለ እህል ውሃ ለበርካታ ቀናት የጾመ ሰዉ ነው፡፡ ምድረ ርስትን ለመሰለል ከተላኩት 12 ሰዎች(ሰላዮች)
መካከል አንዱ ሲሆን አስሩ የጠላቶቻቸውን ኃይል አጋነው ህዝቡን ሲያሸብሩ እውነቱን ተናግረው በእግአዚአብሔር
ኃይል ድል አድርገው ምድረ ርስትን እንደሚወርሱ ከካሌብ ጋር የመሰከረ አባት ነው፡፡ ከሙሴ ቀጥሎም
በእግዚአብሔር ፈቃድ ነቢይና መስፍን እንዲሆን በሙሴ እጅ ተሾሟል፡፡ ለእስራኤልም ምድረ ርስትን ካወረሰ በኋላ
በዘመኑ መጨረሻ እንደ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ህዝቡን መክሮ በ110 ዓመቱ አርፏል፡፡113መጽሐፉን የጻፈው ኢያሱ
እንደሆነ ይነገራል፡፡ መጽሐፉ 24 ምዕራፎች ያሉትና በ1300 ዓ.ዓ በዕብራይስጥ ቋንቋ በምድረ እስራኤል እንደተጻፈ
ይነገራል፡፡

109
Deuteronomy
110
ይህም ሲባል ህዝበ እስራኤል የእግዚአብሔርን የአምላካቸውን ህግ ሲያከብሩ ሰላምና ብልጽግና ያገኙ እንደነበር ከአምላካቸው ፈቃድ ሲወጡ ደግሞ
ጦርነትና መዓት እንዲሁም ምርኮ ይገጥማቸው እንደነበር ያወሳሉ፡፡
111
joshua
112
ከኢያሱ ጋር ተመሳሳይ ትርጓሜ ያላቸው ስሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ ኢየሱስ እና ኢሳይያስ ይጠቀሳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢያሱ ህዝበ እስራኤልን በምድረበዳ
መርቶ ቃል ወደተገባላቸው ርስተ ከንዓን በማግባቱ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌም ነው፡፡ ምክንያቱም እስራኤል ዘነፍስ (ክርስቲያኖች)
ርስት መንግስተ ሠማያትን የምንወርሰው በክርስቶስ መሪነት በመሆኑ ነው፡፡
113
ኢያ 24፡29
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 30
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 2-12 ስ እስራኤል ከነዓን መግባት
 ከምዕራፍ 13-22 ምድረ ርስትን ስለመከፋፈላቸው
 ከምዕራፍ 23-24 የኢያሱን የመጨረሻ ምክርና ዕረፍት ይገልጻል፡፡

፪. መጽሐፈ መሳፍንት114
መሳፍንት ማለት ፈራጆች፣ አስተዳዳሪዎች ማለት ነው፡፡ እነዚህም ኢያሱ ከሞተ በኋላ እስከ ንጉስ ሳኦል
ድረስ ለ400 ዓመታት እስራኤልን ያስተዳድሩ ነበር፡፡115 መጽሐፉም ትረካቸውን በመግለጡ በስማቸው ተጠርቷል፡፡
ይህን መጽሐፍ ኢያሱ እንደጻፈው ይታመናል፡፡116 የተጻፈውም ከ1380-1050 ዓ.ዓ እንደሆነ ይታመናል፡፡117
መጽሐፉም 21 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን የእስራኤልን ታሪክ የያዘ እንደመሆኑ በዕብራይስጥ ቋንቋ በምድረ እስራኤል
ተጽፏል፡፡ በዚህ የመሳፍንት ዘመን ለእስራኤል ንጉስ ያልተሾሙበትና በሕገ እግዚአብሔር ጸንተው በሰላምና በፍቅር
የኖሩበት በመሆኑ ዘመኑ መንግስት እግዚአብሔር ይባላል፡፡ በዚህ መጽሐፍ የተጠቀሱት መሳፍንት 13 ሲሆኑ
እነሱም፡-
1. ጎቶንያል /መሳ 3፡7-11/ 8. ኢያዕር /መሳ 10፡3/
2. ናዖድ /መሳ 3፡12-30/ 9. ዮፍታሔ /መሳ 11፡1/
3. ሰሜጋር /መሳ 3፡31/ 10. ኢብጻን /መሳ 12፡11/
4. ዲቦራና ባርቅ /መሳ 4፡8/ 11. ኤሎም /መሳ 12፡8/
5. ጌዴዎን /መሳ 6፡11/ 12. አብዶን /መሳ 12፡33/
6. አቤሜሌክ /መሳ 9፡22/ 13. ሶምሶን /መሳ 13፡1-16/ ናቸው፡፡
7. ቶላ /መሳ 10፡1-2/
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 እስራኤል የእግዚአብሔርን ውለታ ስለመዘንጋታቸው
 ከምዕራፍ 3-16 ስለመሳፍንቱ አነሳስና በእነሱ አማካኝነት ስለተፈጸሙ ታሪኮች
 ከምዕራፍ 17-21 መሳፍንቱ ባልነበሩበት ዘመን ስለተፈጸሙ ታሪኮች

3. መጽሐፈ ሩት118
መጽሐፉ በነቢዩ ሳሙኤል የተጻፈ መጽሐፍ ሲሆን የስያሜው ምክንያት የእርሷን ታሪክ ስለሚተርክ ነው፡፡
ይህቺ ሴት ከአህዛብ ወገን ስትሆን119 ታሪኳ የተጻፈው በደግነቷ እንዲሁም የዳዊት ቅድመ አያት ሆና ከጌታ
ትውልድ ሐረግ በመግባቷ ነው፡፡120 መጽሐፉ 4 ምዕራፎች አሉት፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ኑሃሚን ከባሏና ከሁለት ልጆቿ ጋር ከሀገሯ ስለመሰደዷና ከሩት ጋር ወደሃገሯ
ስለመመለሷ
 ከምዕራፍ 2-3 ሩት የቦዔዝን እርሻ እየቃረመች ኑሃሚንን ስለመርዳቷ
 ምዕራፍ 4 ቦዔዝን አግብታ በዳዊት የዘር ሐረግ መጠቀሷን እናገኛለን፡፡

114
judges
115
አንዳንድ መንጮች እንደሚገልጡት እነዚህ መሳፍትን እስራኤልን ያስተዳደሩበትን ዘመን 430 ነው፡፡
116
መምህር ቸርነት አበበ “መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ገጽ 99 ላይ መጽሐፈ አቡሻኽርን በመጥቀስ እንደገለጹት
የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ መስፍኑ ኢያሱ ነው፡፡
117
የደ/ፍ/መ/ሰ/ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ውሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት የርቀት ማስተማርያ መጽሐፍ ገጽ 24
118
ruth
119
ሞዓባዊት ናት
120
ማቴ 1፡5
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 31
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

4. መጽሐፈ ሳሙኤል
ሳሙኤል ማለት “እግዚብሔር ሰማኝ” ማለት ነው፡፡ አባቱ ሕልቃና እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ በእስራኤል ከተነሱ
መሳፍንት የመጨረሻ መስፍን ነው፡፡ ሳሙኤል121 እስራኤልን ለ20 ዓመታት መርቶ የመጀመሪያው የእስራኤል
ንጉስ ሳዖል ሲነግስ ዘመነ መሳፍንት አብቅቷል፡፡ ይህ ነቢይ ሁለተኛውን የእስራኤል ንጉስ ዳዊትን ቀብቶ አርፏል፡፡
መጽሐፉን ሰባው ሊቃውንት ለሁለት ከመክፈላቸው በፊት አንድ ነበሩ በኋላም በሰባው ሊቃውንት አማካይነት
መጻሕፍቱ ለሁለት በመከፈል መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ እና ካልዕ ተብለዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በነብዩ በሳሙኤል
ስም የተጠራበት ምክንያት፡
 መጽሐፉ የሚጀምረው የሳሙኤልን የህይወት ታሪክ በመተረክ በመሆኑ
 ጸሐፊው ራሱ ነብዩ ሳሙኤል በመሆኑ ነው፡፡

4.1 መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ122


መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊን የጻፈው ራሱ ሳሙኤል ሲሆን123 በዚሁ መጽሐፍ ላይ ነብዩ ሳሙኤል
እንደሞተ ስለሚገልጥ ከዚያ በኋላ ያለውን የመጽሐፍ ክፍል ነብዩ ናታንና ጋድ እንደጻፉት ይታመናል፡፡ መጽሐፉ
31 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በዉስጡም ስለ ነቢዩ ሳሙኤል አጠራር፣ ስለ ቃልኪዳኑ ታቦት መማረክና
የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉስ ስለነበረው ሰለሳዖል ታሪክ በመጨረሻም በዳዊት ስለመተካቱ ይገልጻል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-7 የሳሙኤል ታሪክ፣የዔሊ ልጆች በደልና የታቦተ ጽዮን መማረክ
 ከምዕራፍ 8-15 የሳዖል መመረጥና የሳሙኤል ስንብት
 የዳዊት የንግስና ዘመን፣ የሳሙኤልና የሳዖል አሳዛኝ ሞት

4.፪ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ124


መጽሐፉ ከመጀመሪያው የሳሙኤል መጽሐፍ የቀጠለ ታሪክን ይተርካል፡፡ የጻፉት ነቢዩ ናታንና ጋድ ሲሆኑ
በ1000 ዓ.ዓ አካባቢ እንደተጻፈ ይታመናል፡፡ መጽሐፉ 24 ምዕራፎች ሲኖሩት በዉስጡ ዳዊት እግዚአብሔርን
ስለማሳዘኑና ንስሃ ስለመግባቱ እንዲሁም ለታቦተ ጽዮን የነበረዉን ክብር ይገልጻል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-4 ዳዊት በሳዖልና በዮናታን ሞት ስለ ማዘኑ፣ በዳዊትና በሳዖል ልጅ መሐል
ስለነበረዉ የስልጣን ትግል
 ከምዕራፍ 5-10 የንጉሱ ዳዊት መንግስት መጽናትና መናገሻ ከተማዉንም ኢየሩሳሌም
ማረጉ፣ ቤተ መቅደስ ለማነጽ መፈለጉና እግዚአብሔር አለመፍቀዱ፣ ዳዊት ጠላቶቹን ድል
ማረጉ
 ከምዕራፍ 11-24 ዳዊት የሰራዉ ኃጢአትና የደረሰበት ቅጣት፣ ከልጆቹ ጋር መጣላቱና
በመጨረሻ ዘመናቱ የተነሱበት አመጾች

5. መጽሐፈ ነገስት
የጻፈው ማን እንደሆነ በትክክል ባይታወቅም ነቢዩ ኤርምያስ እንደጻፈው ይነገራል፡፡125 መበሌላ በኩል
ደግሞ ካህኑ ዕዝራ ነው የሚሉም አሉ፡፡ በአጠቃላይ ይህን መጽሐፍ ስንመለከተው ከንጉሥ ሰሎሞን አንስቶ እስከ
ባቢሎን ምርኮ126 የተነሱ የይሁዳና የእስራኤልን ነገስታት ታሪክ እንዲሁም በዘመናቸው ስለተፈጸሙ ታሪኮች
ይገልጣል፡፡ በመሆኑም መጽሐፉ በዚህ ስም ተሰይሟል፡፡

121
ሳሙኤል እናትና አባቱ በስዕለት ያገኙት ልጃቸው በመሆኑ ጡት ሲጥል እናቱ ለቤተመቅደስ ሰጥታዋለች፡፡ በዚያን ወቅት እስራኤልን በመስፍንነትም ሆነ
በካህንነትም ያገለግል የነበረው ነብዩ ኤሊ ነበር፡፡ (1ሳሙ 1፡25፣ 2፡11) ኤሊም ሲያርፍ የመጨረሻው የእስራኤል መስፍን ሆኖ እስራኤልን አስተዳድሯል፡፡
122
1 samuel
123
1ሳሙ 10፡25
124
2 samuel
125
1000-590 ዓ.ዓ ባለው ጌዜ ውስጥ
126
በዘመን ስናስቀምጠው የ400 ዓመት ታሪክ ነው፡፡ (የደ/ፍ/መ/ሰ/ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ው/ብ/ሰ/ት/ቤት የርቀት የማስተማሪያ ኖት)
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 32
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

5.1 መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ127


መጽሐፉ 22 ምዕራፎች ሲኖሩት ከሰሎሞን የንግስና ዘመን በኋላ የእስራኤል መንግስት ለ2 መከፈሉንና
ከዛ በኋላ የተነሱትን የይሁዳ ነገስታት ታሪክ የያዘ ነዉ፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-10 የሰለሞን ዘመነ መንግስት
 ከምዕራፍ 11-22 ስለእስራኤል ለሁለት መከፈል በይሁዳና በእስራኤል ስለነገሱ ነገስታትና
ስለነብያት ታሪክ

5.፪ መጽሐፈ ነገስት ካልዕ128


መጽሐፉ 25 ምዕራፎች ሲኖሩት ከኢዮሳፍጥ ቀጥሎ የተነሱትን የእስራኤል ነገስታት ታሪክ ይተርካል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-10 ስለ ይሁዳና ስለእስራኤል መንግስታት እስራኤል ከአሶር መንግስት እስከ
ተማረኩበት ጊዜ ድረስ ያለውን ታሪክ ይተርካል
 ከምዕራፍ 18-25 ስለይሁዳ መንግስት ታሪክ ኢየሩሳሌም በባቢሎን እስከተማረከችበት ድረስ
ያለውን ይናገራል፡፡

6. ዜና መዋዕል ቀዳማዊ129
ዜና መዋዕል ማለት የዕለት ዜና ማለት ነው፡፡ የተጻፈው ከባቢሎን ምርኮ በኋላ በካህኑ በዕዝራ ነው፡፡
ሁለቱ የዜና መዋዕል መጻህፍት አንድ የነበሩ ሲሆን ከሰባው ሊቃውንት ትርጉም በኋላ ለሁለት ተከፍለዋል፡፡
መጻህፍቱ በይዘታቸው ከመጻሕፍት ነገስት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ መጻሕፍቱ የተጻፉት በ400 ዓ.ዓ ገደማ
ነው፡፡ 1ኛ ዜና መዋዕል 29 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-9 የቤተ እስራኤል የትውልድ ሐረግ ቆጠራ
 ከምዕራፍ 10-29 ስለ ሳዖል መንግስት አወዳደቅ ስለዳዊት መንግስት አነሳስ እንዲሁም በዘመኑ
ስለተፈጸሙ ታሪኮች በመጨረሻም ንጉስ ዳዊት መንግስቱን ለልጁ ለሰሎሞን አስረክቦ ማረፉን
ይገልጻል፡፡

7. 2ኛ ዜና መዋዕል ካልዕ130 እና ጸሎተ ምናሴ


 ሁለተኛ ዜና መዋዕል፡- ሁለተኛ ዜና መዋዕል 36 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-9 ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት እንደሰራና እግዚአብሔርም ስፍራዋን
እንደቀደሳት፣ የንግስተ ሳባ ጉብኝት
 ከምዕራፍ 10-36 ከሮብዓም እስከ ባቢሎን ምርኮ
 ጸሎተ ምናሴ ፡- ምናሴ ማለት “ማስረሻ” ማለት ነው፡፡ በ12 ዓመቱ እስራኤልን ለመምራት የነገሰ ንጉስ
ነዉ፡፡ አባቱ ከዳዊት ቀጥሎ ከነገሱ ነገስታት በመልካምነቱ የተመሰከረለትና በጸሎቱም ከዕድሜዉ ላይ
15 ዓመት የተጨመረለት ሕዝቅያስ ነዉ፡፡131 ነገር ግን ምናሴ የአባቱን አካሄድ አልተከተለም ይልቁኑ
አባቱ ያፈረሳቸዉን ቤተ ጣዖት ድጋሚ አሰርቶ እርሱና ህዝቡ እግዚአብሔርን በደሉ እግዚአብሔርም
በዘመኑ በነበረዉ ነብይ በኢሳይያስ ከጥፋቱ እንዲመለስ ቢያዘዉም በእንቢተኝነቱ በመጽናት ኢሳይያስን
በመጋዝ አስተርትሮ አስገድሎታል፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ለአሶር ንጉስ አሳልፎ ሰጥቶታል፡፡
የአሶሩ ንጉስም ለምናሴ በቁመቱ ልክ የብረት ቀፎ አዘገጅቶ አስሮታል ምናሴም በቀፎዉ ዉስጥ የቀን
ፀሐይ የለሊት ብርዱ ሲፈራረቅበት ስለበደለዉ በደል የጸለየዉ የንስሐ ጸሎት ነው፡፡ መጽሐፉ በሰባዉ
ሊቃዉንት አቆጣጠር መሰረት ከ2ኛ ዜና መዋዕል ጋር ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም በ2ኛ ዜና መዋዕል

127
1 kings
128
2 kings
129
1chronicles
130
1chronicles
131
2ነገ 20፡1-7
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 33
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

33፡18 ላይ ምናሴ እንደጸለየ ስለሚናገር እና ሁለቱ መጻሕፍት በታሪክ ተያያዥነት ስላላቸው እንደ አንድ
ሊቆጠሩ ችለዋል፡፡
8. መጽሐፈ ኩፋሌ
ኩፋሌ ማለት ክፋይ /የተከፈለ/ ማለት ሲሆን የተከፈለውም ከኦሪት ዘፍጥረትና ከኦሪት ዘጸአት የተከፈለ
መጽሐፍ ነው፡፡ ከመጀመሪያው የሥነ ፍጥረት ታሪክ ጀምሮ እስከ እስራኤላዉያን ከግብጽ እስከወጡበት ዘመን
ድረስ ያለውን ታሪክ ከህግጋት ጋር እያዛመደ ጊዜውን በሱባኤ እየቀመረ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ 34
ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በነቢዩ ሙሴ በዕብራይስጥ ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ አጻጻፉም፡-
 ከአዳም እስከ ሙሴ ያለውን የ3830 ዓመታት ታሪክ ይገልጻል
 ታሪኮቹ የተፈጸሙበትን ዘመን በሱባኤ አቆጣጠር ይገልጻል
 ታሪኩን ከህግጋት ጋር እያዛመደ ያስረዳል፡፡ ለምሳሌ፡- አዳምና ሔዋን ከተፈጠሩበት ወደ ገነት
የገቡት በ40 እና በ80 ቀናቸው እንደሆነ በምዕራፍ 4÷8-13 ሲገለጽ ይህንም በዘፍ 2፡7-5
ካለው ታሪክ ጋር አዛምዶ የተፈጸመበትን ጊዜያት በሱባዔ ቆጥሮ ይገልጻል፡፡ /ኩፋ 4÷6/

9 መጽሐፈ ሄኖክ
ሄኖክ ማለት ተሐድሶ ማለት ነው፡፡ ይህ አባት ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ ነው፡፡ በሕይወተ ስጋ ሳለም
እግዚብሔርን በማስደሰቱ ሞትን ሳይቀምስ ብሔረ ሕያዋን የገባ አባት ነው፡፡ በዚያም /በብሔረ ሕያዋንም/ እያለ
የሆነውን እና የሚሆነውን እንዲሁም የተለያዩ ምስጢራት ተገልጾለት ጽፏል፡፡ መጽሐፉ የተጻፈበት ዘመን 1486
ዓ.ዓ ነዉ፡፡ ይህም ከቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ አስቀድሞ የተጻፈ መጽሐፍ ያደርገዋል፡፡ የተጻፈዉም በዕብራይስጥ
ቋንቋ ነዉ፡፡132 መጽሐፉ ከተጻፈ በኋላም 70 ሊቃናት ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ ተርጉመውታል፡፡ ይዘቱም፡-
 ስለጌታችን በዚህ ዓለም መወለድና ማስተማር ሞቶም ሰዎችን ስለማዳኑ ይገልጻል
 ስለቅዱሳን መላእክት አገልግሎት
 ስለጸሐይና ጨረቃ ዑደትና ስለ እጽዋት ምስጢር
 ስለጻድቃን የዘላለም ዋጋና ስለኃጥአን ፍዳ
 በኖህ ዘመን ስለሚፈጸመው ኃጢአትና ቅጣት በሰፊው የሚገልጥ ባለ 42 ምዕራፍ መጽሐፍ
ነው፡፡
፲. መጻሕፍተ ዕዝራ እና መጽሐፈ ነህምያ
ሁለቱ መጽሐፍት በሰማንያ አሐዱ መጽሐፍት ዝርዝር ዉስጥ እንደ አንድ የሚቆጠሩ ናቸዉ፡፡

፲.1 መጽሐፈ ዕዝራ133


ዕዝራ ማለት ረድኤት ማለት ነዉ፡፡ ዕዝራ ከአሮን ቤተሰብ ተወልዶ በባቢሎን በምርኮ ስላደገ ዳግማዊ ሙሴ
ተብሎ ይጠራል፡፡ መጽሐፉ የእስራኤል ሕዝብ ከምርኮ በካህኑ ዕዝራ መሪነት እንደተመለሱና ቤተመቅደስንም
እንዴት እንደሰሩ ያስረዳል ባጠቃላይ ከ537-458 ዓ.ዓ ያለውን ታሪክ ያገልጣል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 ቂሮስ የእግዘኢብሔርን ሕዝብ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ስለመፈለጉና
የተመለሱትን ሕዝብ ብዛት ይገልጻል፡፡
 ከምዕራፍ 3-4 በቂሮስ ዘመን ቤተ መቅደስ መታደስ መጀመሩን በአርጤክስስ ቀዳማዊ ዘመን
ደግሞ ቤተ መቅደስ እንዳይሰሩ ስለመከልከላቸው ይገልጻል፡፡
 ከምዕራፍ 5-10 በሐጌና በዘካያስ ቀስቃሽነት ቤተመቅደሱ ተሰር እንደተፈጸመ ዕዝራና የቀሩት
እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ስለመመለሳቸው እንዲሁም ዕዝራ እስራኤልን ከአህዛብ ጋር
በምንም ዓይነት መንገድ አንድ እንዳይሆኑ ስለመምከሩ ይገልጻል፡፡ መጽሐፉ 10 ምዕራፎች
አሉት፡፡

132
ከዚህ መጽሐፍ ሐዋርያት ለትምህርታቸው ማስረጃነት ጠቅሰዋል፡፡ /ለምሳሌ ይሁዳ 1፡14 ሄኖ 1፡9/
133
Ezra
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 34
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

፲.፪ መጽሐፈ ነህምያ134


ነህምያ ማለት እግዚአብሔር አጽናኝ ማለት ነዉ፡፡ ነህምያ የፋርስ ንጉስ የአርጤክስስ ጠጅ አሳላፊ የነበረ
ሰዉ ነዉ፡፡ የእየሩሳሌምንም ቅፅሮች በ445 ዓ.ዓ የሰራ ሰዉ ነዉ፡፡ የመጽሐፉም ጸሐፊው ራሱ ነህምያ ነው፡፡
መጽሐፉ 13 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 የኢየሩሳሌም ቅጽሮችና በር ወድመው ስለመታየታቸው ነህያም ይህን ሰምቶ
ከንጉሱ ፈቃድ ጠይቆ የኢየሩሳሌምን ቅጽር ለመስራት ጉዞ እንደጀመሩ
 ከምዕራፍ 3-6 ነህምያ ህዝቡን አስተባብሮ ቅጽሮቹንና በሮቹን ስለመስራቱ
 ከምዕራፍ 7-13 የሙሴ ሕግ መጽሐፍ በዕዝራ መነበቡን በመጨረሻም በሃይማኖታቸው
እንዲጸኑና ከክፋታቸው እንዲመለሱ መመከራቸውን ሕዝቡም ንስሃ ገብተው የዳስን በዓል
አክብረው በምድሪቱ መስፈራቸውን ይገልጻል፡፡

፲1. መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ እና መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል


መጽሐፈ እዝራ ካልዕና መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል እንደ አንድ መጽሐፍ የሚቆጠሩ ሲሆኑ ጸሐፊዉም
ካህኑ ዕዝራ ነዉ፡፡
፲1.1 መጽሐፈ እዝራ ካልዕ
ይህ መጽሐፍ ዘጠኝ ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ ነው፡፡ ጸሐፊውም ካህኑ እዝራ ነው፡፡ በይዘቱም፡-
 በሁለተኛ ዜና መዋዕል ከምዕራፍ 35-36
 በመጽሐፈ ነህምያ ከምዕራፍ 7-8
 እንዲሁም በመጽሐፈ ነህምያ ከምዕራፍ 2-8
ድረስ የተጻፉትን ታሪኮች በድጋሚ የሚተርክ መጽሐፍ ነዉ፡፡ ይህም በመጽሐፈ ነገስት ላይ የተገለጸው
ታሪክ በድጋሚ በዜና መዋዕል እንደተገለጸው ማለት ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን አቆጣጠር መሰረት ከመጽሐፈ እዝራ ሱቱኤል ጋር በአንድነት ይቆጠራል፡፡

፲1.፪ መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል


ሱቱኤል (ሰላትያል) የዕዝራ ድርብ ስሙ ነው፡፡ መጽሐፉ 13 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ጸሐፊውም ራሱ
ካህኑ እዝራ ነው፡፡ በይዘቱም፡-
 ዕዝራ በባቢሎን ምርኮ እያለ ስላያቸው ሰባት ራዕዮች
 እንዲሁም ላቀረባቸው ጥያቄዎች በምሳሌ ስለተሰጠው መልስ፣
 በመጨረሻም እግዚአብሔርን በጸሎት ለምኖ የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
ተገልጠውለት እንዲጽፍ በመልአኩ በዑራኤል አማካኝነት የዕውቀት መጠጥ ጠጥቶ 40
ቀንና ሌሊት ጾሞ እንደጻፈ፣
 መላእክትም በሕይወተ ሥጋ እያለ ብሔረ ሕያዋን እንደወሰዱት የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡

፲፪. መጽሐፈ ጦቢት


መጽሐፉ ጦቢት ስለተባለ አንድ ቅዱስ ንጉስ በሰልምናሶር ዘመን ወደ አሶር ከተማረከ በኋላ እርሱና ልጁ
ጦቢያ በችግር በነበሩበት ወቅት እግዚአብሔር በመልአኩ በሩፋኤል አማካይነት እንደረዳዉ የሚገልጽ መጽሐፍ
ነዉ፡፡ መጽሐፉ 14 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በዉስጡም፡-
 ጦቢት በበጎዉ ስራዉ ስላገኘዉ መከራና ለእግዚአብሔር ያቀረበዉ ምስጋና፣
 የመልአኩ ሩፋኤል እርዳታና ጦቢት በእርጅናዉ ጊዜ ልጁን ጦቢያንና የልጅ ልጆቹን
ጠርቶ የሰጣቸዉ ሃይማኖታዊ ምክርና ኑዛዜ በስፋት ይገልጻል፡፡

134
nehemiah
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 35
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

፲3. መጽሐፈ ዮዲት


መጽሐፉን የጻፈው ማን እንደሆነ በትክክል ባይታወቅም በስደት የነበሩ አይሁድ እንደጻፉት ይታመናል፡፡
መጽሐፉ 6 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን የተጻፈው በ600 ዓ.ዓ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ባጠቃላይ ናቡከደነጾር
እስራኤላውያንን ለመውጋት የላከው ሆሎፎርኒስ የተባለው የጦር አዛዥ በእስራኤላውቷ በጦቢት እጅ እንዴት
እንደወደቀና እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዴት እንደታደገ የሚያትት መጽሐፍ ነው፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-7 የሆሊፎርኖስ የጦር ዘመቻና የእስራኤል ልጆች ዘመቻ
 ከምዕራፍ 8-15 ዮዲት እንዴት በጥበብ ወገኖቿን እንዳዳነች
 ምዕራፍ 16 ዮዲት ለጌታ ስላቀረበችው ምስጋናና ስለዕረፍቷ ይገልፃል፡፡

፲4. መጽሐፈ አስቴር135


አስቴር ማለት ኮከብ ማለት ነው፡፡136 አስቴር በምርኮ እያለች አርጤክስስ የተባለ የፋርስ ንጉስ አግብታ
ንግስት ለመሆን የበቃች ስትሆን አጎቷ መርዶክዮስና ሕዝቧ አይሁድ ከጥፋት የዳኑባት አይሁዳዊት ምርኮኛ
ናት፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መጽሐፈ አስቴር በሚል ስም የሚጠሩ ሁለት መጻሕፍት ሲኖሩ ጸሐፊያቸው
መርዶክዮስ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ከነዚህ መጽሐፍት አንዱ በ66ቱ ሌላው ደግሞ በ81 መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ ይዘታቸውም መርዶክዮስ ህልም ስለማለሙ ፣አስቴር እንዴት ንግስት እንደሆነች ፣ሐማ
በመርዶክዮስ ምክንያት አይሁድን ለማጥፋት ስለማሰቡ ፣የመርዶክዮስን ክብር ማግኘት ፣በአስቴር ምክንያት
አይሁድ በጠላቶቻቸው ላይ መሰልጠናቸውና እግዚአብሔርም እነርሱን ያዳነበትን በዓል ማክበር መጀመራቸውን
ያካትታል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በአጠቃላይ ይዘታቸው ቢመሳሰሉም አንዳንድ ልዩነቶች አሏቸው ልዩነታቸውንም
ከዚህ ቀጥለን እንመለከታለን፡፡
መጽሐፈ አስቴር /የ66ቱ/ መጽሐፈ አስቴር /የ81ዱ/
 ስመ እግዚአብሔር አልተጠቀሰበትም - ስመ እግዚአብሔር ተጠቅሶበታል
 ስለ መርዶክዮስ ህልም አይገልጽም - ስለ መርዶክዮስ ህልም በመጽሐፉ
መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ተጠቅሷል
 10 ምዕራፎች አሉት፡፡ - 11 ምዕራፎች አሉት፡፡

መጻሕፍተ መቃብያን
መቃብያን ማለት “ጀግኖች” ማለት ሲሆን በዓለም ላይ በመቃብያን ስም የሚጠሩ ስምንት መጻሕፍት
ይገኛሉ፡፡ መጻሕፍቱ ማን እንደጻፋቸው አይታወቅም ከስምንቱ መጻሕፍትም አራቱ በግሪክ የቀሩት አራቱ ደግሞ
በግዕዝ የተጻፉ ናቸው፡፡ በግዕዙ ተጽፈው ከሚገኙት ውስጥ ቤተክርስቲያናችን መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊና ካልዕን
ከቅዱሳት መጻሕፍት ቆጥራ የምትቀበል ሲሆን መቃብያን ሳልስን ከይዘቱ አንጻር (የብሉይ ኪዳንን ታሪክ እየገለጸ
ፅድቅና ኩነኔን እያነጻጻረ ስለሚሰብክ) ከአዋልድ መጻሕፍት መድባ ትቀበለዋለች፡፡ አራተኛው መጽሐፈ መቃብያን
በሌላ ስሙ መጽሐፈ ዮሴፍ ወልድ ኮርዮን በመባል ይታወቃል፡፡

፲5. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ


መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ 36 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በዋነኝነት የሚገልጸው የመቃቢስ ዘብንያም ልጆች
አብያ ሲላስና ፈንቶስ ከሁለት ወንድሞቻቸው ጋር፡-
 ጺሩጻይዳን የተባለው አመጸኛ ንጉስ ስለ ሃይማኖታቸው ምክንያት እንዳሰቃያቸውና
የተቀበሉትን ሠማዕትነት
 ከብሉይ ኪዳንና ከአዲስ ኪዳን ታሪኮችና ምሳሌዎችን እየጠቀሱ ስለ ትንሳኤ ሙታን
መናገራቸውን
 የሰው ልጅ የነፍስና የሥጋ በረከትና ሕይወት ስለሚያገኝበት መንገድ የመሰከሩትን
ይገልፃል፡፡

135
Esther
136
በፋርሳውያን ቋንቋ
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 36
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

፲6 መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ወሳልስ


ቅድስት ቤተክርስቲያን በቀኖናዋ መሰረት እነዚህ መጻሕፍትን እንደ አንድ መጽሐፍ የምትቆጥራቸው ሲሆን
ከዚህ በመቀጠል በተናጠል የመጻሕፍቶቹን ይዘት እናያለን፡፡

፲6.1 መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ


መቃቢስ የተባለ የሞአብ ንጉስ እስራኤልን ሊቀጣ ተልኮ ስቃይ እንዳጸናባቸው ከዚያም በአንድ ነቢይ
ተመክሮ ንስሃ እንደገባና እርሱ ከሞተ በኋላ ጺሩጻይዳን የተባለ ንጉስ የመቃቢስን ልጆች እንዴት እንዳሰቃያቸው
የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ 21 ምዕራፎች አሉት፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-4 የሞዓብ ንጉስ እስራኤላውያንን ከተወጋ በኋላ በኢየሩሳሌም ላይ ያደረሰውን
ጥፋት፣ በንስሐ ተመልሶ የሰራውን በጎ ሥራና ዕረፍቱ
 ከምዕራፍ 5-12 የመቃቢስ ዘሞዓብ ልጆች በእግዚአብሔር ስላመኑ ጺሩጻይዳን የተባለውን
የከለዳውያን ንጉስ ያደረሰባቸውን መከራ
 ከምዕራፍ 13-21 የመቃቢስ ዘሞዓብ ልጆችን አብነት አድርጎ ትንሳኤ ሙታንን ለማያምኑ
የተሰጠ መልስ

፲6.፪ መጽሐፈ መቃብያን ሳልስ


ይህ መጽሐፍ አስር ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በዋነኝነት መጽሐፉ የብሉይ ኪዳን ታሪኮችን እየጠቀሰ
የጽድቅና የኩነኔ፣ የትንሳኤ ሙታንና ዲያቢሎስ የሰው ልጆችን የሚያሰናክልባቸውን መረቦች በዝርዝር የሚያትት
መጽሀፍ ነው፡፡

፲7. መጽሐፈ ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን


አራተኛ የመቃብያን መጽሐፍ ተብሎ በፍትሐ ነገስት የሚታወቀው ይህ መጽሐፍ በይዘቱ ከአዳም ጀምሮ
እስከ 70 ዓ.ም ድረስ ያለውን ታሪክ አካቶ ይተርካል፡፡ ይህም ከሥነ-ፍጥረት መጀመሪያ አንስቶ እየሩሳሌም በጥጦስ
እስከጠፋችበት ዘመን ማለት ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በሌላ አጠራር “መጽሐፈ ዜና አይሁድ” እንዲሁም “መጽሐፈ
ዜና ሥርው” ተብሎ ይጠራል፡፡ የጻፈውም የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ የሆነው ዮሴፍ ወልደ ኮርዮን ነው፡፡ በስምንት
ክፍሎችም የተከፋፈለ ነው፡፡

ምዕራፍ ሶስት
የመዝሙር ክፍል መጽሐፍት
መዝሙር ማለት ምሥጋና ማለት ሲሆን ዘመረ ከሚለው የግእዝ ግስ የተወሰደ ነው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት
የትምህርት እና የእውቀት መጻሕፍት ተብለው ይታወቃሉ፡፡137 መጻሕፍቱ በግጥም በዝማሬ እንዲሁም በትረካ
መልክ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ዓላማቸውም ሰውን በለሰለሰ መንገድ ማስተማር መሳብና ወደ መልካም ጠባይ መለወጥ
ነው፡፡ ውድ ተማሪዎች በዚህ ክፍል የምንመለከታቸው የመጽሐፍት ብዛት ስምንት ሲሆኑ ጸሐፊዎቹ ደግም አራት
ናቸው፡፡ ከዚህ በመቀጠልም ስለ እያንዳንዱ መጻሕፍት በዝርዝር ለመመልከት እንሞክራለን፡-

1 መጽሐፈ ኢዮብ138
ኢዮብ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ዖፅ በምትባል ሀገር ይኖር የነበረ ጻድቅ ሰው ነው፡፡ ከአኗኗሩና ከሥርዓተ
አምልኮው ተነስተው ከሙሴ ዘመን በፊት አብርሃም አምስተኛ ትውልድ እንደሆነ ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ መጽሐፉ
በአጻጻፉ ከሁለት ምዕራፎች በስተቀር በግጥም መልክ የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ 42 ምዕራፎች አሉት፡፡
ጸሐፊው ማን እንደሆነ አልታወቀም ነገር ግን በአንዳንድ መጻሕፍት ላይ የመጽሐፉ ጸሐፊ ኢዮብ እንደሆነ
ይገልጣሉ፡፡139 አከፋፈሉም፡-

137
በዘመን ሲቀመጥ ከአዳም ጀምሮ እስከ 70 ዓም ድረስ ያለውን ታሪክ ይተርካል፡፡
138
job
139
መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ ገጽ 108
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 37
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ከምዕራፍ 1-3 የኢዮብ ለእግአብሔር መስዋዕት ማቅረብና መፈተን


 ከምዕራፍ 4-37 የጓደኞቹና የኢዮብ ክርክር
 ከምዕራፍ 38-42 የእግዚአብሔር ጥያቄ እና በመጨረሻም ኢዮብ ያገኘው በረከት

፪. መዝሙረ ዳዊት140
ዳዊት ከበግ እረኝነት ለንግስናና ለነብይነት የተመረጠ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዳዊት በነብዩ ሳሙኤል ተቀብቶ
በነገሰ141 ጊዜ ሰባት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን አግኝቷል፡፡ ከእነዚህም አንዱ ሀብተ ትንቢት ነው፡፡ በዚህ ስጦታው
በትንቢት መነጽርነት ያለፈውንና የሚመጣውን ምስጢር ዓለም ተገልጦለት ጽፏል፡፡የተጻፈበት ዘመን 1000 ዓ.ዓ
አካባቢ ነው፡፡ በእስራኤልም ሆነ በክርስቲያኖች ዘንድ ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለግል ጸሎት እጅግ የተወደደ ሲሆን
በይዘቱም መዝሙር፣ ጸሎት፣ ትምህርትና ቅኔ በአንድነት ይገኙበታል፡፡ መጽሐፉን አሁን ባለበት ሁኔታ አሰባስቦ
ያዘጋጀው ካህኑ ዕዝራ ነው፡፡ መዝሙረ ዳዊት ደረቅ ሐዲስ በመባልም ይታወቃል ምክንያቱም ስለ ክርስቶስ ስለ
እመቤታችን ስለ ምዕመናን /ቤተክርስቲያን/ በግልጥና በብዛት ስለሚናገር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በይዘቱ
ከመዝሙረ ዳዊት ሰባት ዋና ዋና መንፈሳዊ ነገሮችን እንማራለን፡-
1. ጠላትን መውደድ /መዝ 16፡4/ 5. ኃጢአትን ማመን /መዝ 37፡4/
2. ትህትና /መዝ 21፡6/ 6. ሰርየተ ኃጢያት /ይቅርታ/ መዝ 50፡2
3. ሃይማኖት /መዝ 21፡10/ 7. ምጽዋት /መዝ 111፡9/
4. ተስፋ መንግስተ ሰማያት /መዝ 26፡13/

መዝሙረ ዳዊት “ከዘላለም እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር ይባረክ አሜን አሜን” በሚለው ቃል ለአምስት
ከፍለን ማየት ይቻላል፡፡ ይህም፡-
 ከምዕራፍ 1-40 ድረስ
 ከምዕራፍ 41-71 ድረስ
 ከምዕራፍ 72-88 ድረስ
 ከምዕራፍ 89-105 ድረስ
 ከምዕራፍ 106-150 ድረስ
በቅድስት ቤተክርስቲያንም ምዕመናን ለጸሎት ከሚጠቀሙባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህም
ሰዎች በዚህ ዓለም ከሚያጋጥሟቸው ሁኔታዎች ሁሉ ምን መጸለይ እንደሚገባቸው የሚያስረዳ መጽሐፍም ስለሆነ
ነው፡፡ የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከዚህ በመቀጠልም የመጽሐፉን ይዘት በሰንጠረዥ መልክ የምንመለከት ይሆናል፡፡
ተከተሉን፡-

ተ.ቁ የሚጸለይበት /የሚዘመርበት/ ሁናቴ እንዲሁም የመዝሙረ ዳዊት ክፍል


ከመጽሐፉ የሚገኙ ትምህርቶች
1 ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ መዝሙር፡- 8፣ 29፣ 33፣ 36፣ 89፣ 94፣ 103፣ 104፣
105፣ 106፣ 111፣ 118፣ 138፣ 145
2 የእግዚአብሔርን የባሕርይ ልዕልና ለመግለጽና መዝሙር፡- 8፣ 19፣ 29፣ 33፣ 47፣ 65፣ 66፣ 68፣
ለማወደስ 76፣ 81፣ 89፣ 92፣ 95፣ 95፣ 96፣ 98፣ 135፣ 136፣
147፣ 148፣ 150
3 አንድ ኃጢአተኛ በንስሐ ከኃጢአቱ ተመልሶ መዝሙር፡- 6፣ 31፣ 37፣ 50፣ 85፣ 101፣ 102፣ 142
የእግዚአብሔር ይቅርታ የሚጠይቅበት
4 ጭንቀት፣ ፈተና፣ ውርደት፣ ሐዘን፣ ስደትና መዝሙር፡- 2፣ 6፣ 13፣ 21፣ 35፣ 41፣ 43፣ 44፣
ጭቆና በሚያጋጥምበት ጊዜ 52፣ 55፣ 56፣ 59፣ 64፣ 66፣ 74፣ 77፣ 79፣ 80፣
83፣ 88፣ 90፣ 94፣ 102፣ 109፣ 140፣ 143

140
pslams
መምህር ቸርነት አበበ “መሰረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት ከሆነ የዳዊት የንግስና ዘመን ከ1011-971 ዓ.ዓ
141

ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡


በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 38
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

5 ፍርሃትና ፈተና ሲያጋጥም


በእግዚአብሔር መዝሙር፡- 11፣ 16፣ 18፣ 20፣ 25፣ 27፣ 28፣ 30፣
ለመተማመን 32፣ 37፣ 46፣ 54፣ 57፣ 62፣ 70፣ 71፣ 91፣ 115፣
124፣ 125፣ 144፣ 146
6 የእግዚአብሔር ሕጉና ቤቱ በሚናፍቅበት ጊዜ መዝሙር፡- 16፣ 17፣ 18፣ 40፣ 41፣ 44፣ 63፣ 72፣
83፣ 119፣ 121፣ 131
7 ካህናት የቤተመቅደስን ደረጃዎች ሲወጡ መዝሙር፡- ከመዝሙር 112 እስከ 135
የሚዘምሯቸው የመዓረግ መዝሙር
8 መሰረተ እምነትንና የእግዚአብሔር ብቸኛ መዝሙር፡- 33፡13፣ 50፣ 86፡8፣ 135፡5፣ 139፡7፣
አምላክነትን የሚያመለክቱ
9 የስላሴን በመለኮት አንድነትን በአካል ሶስትነትን መዝሙር፡- 2፡7፣ 33፡6፣ 45፡6፣ 110
የሚያመላክቱ
10 ስለ ትንሳኤ ሙታንና ከዚያ በኋላ ስለሚሆነው መዝሙር፡- 1፡5፣ 16፡8፣ 116፡15
ፍርድ
11 ስለ ክርስቶስና ስለ ክርስትና ዘመን የተነገሩ መዝሙር፡- 1፡9፣ 22፣ 66፡1፣ 69፡21፣ 72፣ 107፣
ትንቢቶች 109፣ 110፣ 117፣ 118፡22፣ 132፡11
12 ስለ ዳዊትና ስለ ህዝቡ ታሪካዊ ድርጊቶች መዝሙር፡- 78፣ 105፣ 106፣ 135፣ 130

ሠንጠረዥ 1፡- የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ይዘት


3 መጽሐፈ ምሳሌ142
የንጉሱ የዳዊት ልጅ ጠቢቡ ሰሎሞን143 ልክ እንደ አባቱ እስራኤልን 40 ዘመን በጥበብ ገዝቷል፡፡ ሰሎሞን
ማለት መስተሳልም /የሰላም አባት/ ማለት ነው፡፡ ዘመኑ የሰላም ስለነበር ንጉስ ሰሎሞን ከሁሉ በላይ እግዚአብሔር
የለመነው ይህን ታላቅ ሕዝብ መምራት የሚችለበትን ጥበብና ዕውቀት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ጥቂት ሲለምኑት ብዙ
መስጠት የባሕርይው ነውና ሁሉን የሚያውቅበት ጥበብ ሰጥቶታል፡፡ የሰሎሞን ጥበብ እስከ ምድር ዳርቻ በዓለም
ነገስታት ሁሉ ዘንድ የገነነ ነበረ፡፡144
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቀኖና መሰረት ከምንቀበላቸው 46 የብሉይ መጻሕፍት 5ቱን የፃፈው እርሱ ነው፡፡ ከነዚህም
አንዱ መጽሐፈ ምሳሌ አንዱ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ በ950 ዓ.ዓ አካባቢ የተጻፈ ሲሆን 24 ምዕራፎች አሉት፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-9 ስለ ጥበብና ጥበብን መርምረን ማወቅ እንደሚጠቅም
 ከምዕራፍ 10-22 ልብን ለማደስና ሥነ ምግባርን ለማጎልመስ የሚጎዱ ምክሮች
 ከምዕራፍ 22-24 ጥበብን ለማግኘት የሚቻልበትን መንገድ ይመክራል

4 መጽሐፈ ተግሳጽ
ከመጽሐፈ ምሳሌ ጋር ተመሳሳይ አቀራረብ ያለው ሲሆን 7 ምዕራፎች አሉት፡፡ በንጉስ ሰሎሞን በአጉርና
እና በልሙኤል የተነገሩ ሲሆን በ780 ዓ.ዓ በንጉስ ሕዝቅያስ ዘመን ከነቢያት የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ በአማርኛው
በመጽሐፈ ምሳሌ 25፡31 ጀምሮ በቅንፍ “ተግሳጽ” ተብሎ ተገልጧል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-5 የንጉስ ሰሎሞን ምሳሌዎች
 ምዕራፍ 6 የማሳ አገር ሰው አጉር ለኢትኤልና ለኡካል የተናገረው
 ምዕራፍ 7 የማሳ ንጉስ የልሙኤል ቃል

142
proverbs
143
ጠቢቡ ሠሎሞን 3ዐዐዐ ምሳሌዎችና 1ዐዐ5 መዝሙራት የጻፈ ታላቅ የጥበብ አባት ነው፡፡ /1ኛ ነገ 4፣32/
144
1ነገ 3፡6-9
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 39
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

5. መጽሐፈ ጥበብ
የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ ሰሎሞን ሲሆን በ19 ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው፡፡ ከመጽሐፈ ምሳሌ ጋር ተመሳሳይ
ሀሳብ አለው ስለጥበብ በመናገር ሰው ጥበብን እንዲፈልግ ይመክራል፡፡ የተጻፈበት ዘመን ከመጽሐፈ ምሳሌ
አይለይም፡፡ አጠቃላይ ይህ መጽሐፍ ስለ ሦስት ዋና ዋና ነገሮች ይናገራል፡-
1. ስለ መነናውያም
2. ስለ አይሁድ
3. ስለ ሰዶማውያን

6 መጽሐፈ መክብብ145
መክብብ ማለት አለቃ፣ ሹም፣ ሰባኪ ወይም አስተማሪ ማለት ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ የጻፈው ንጉስ ሰሎሞን
ሲሆን በሌላ አጠራር መጽሐፉ ጥበብ ባጉር ይባላል፡፡ ባጉር የሰሎሞን የፍልስፍና ስሙ ሲሆን የዓለምን ከንቱነት
እንዲሁም ከፀሀይ በታች ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ ይናገራል፡፡ የጭንቅና የህይወት ፍፃሜ ሳይደርስ ሁሉ ከንቱ
ስለሆነ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ በማለት ከራሱ ህይወት በመነሳት ያስተምራል፡፡ በአጠቃላይ መጽሐፉ
12 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ከፀሐይ በታች ሁሉም ዞሮ ዞሮ እንደሚመጣና ፍጻሜም እንደሌለዉ
 ምዕራፍ 2 የዚህ አለም ደስታ የሆነዉ ሁሉ ከንቱና ሁሉም ነፋስን እንደመከተል የማያጠግብ እንደሆነ
 ከምዕራፍ 3-11 ዓለም ምንም ውብ ብትሆን ሰው ግን ተስፋውን ሊመሰርትባት እንደማይገባ
 ምዕራፍ 12 አጥጋቢ ደስታ የተትረፈረፈ ሕይወት በዓለም ነገር በማናቸዉም በኩል እንደማይገኝ

7. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን146


መኃልየ መኃልይ ማለት ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር ማለት ነው፡፡147 ይህ መጽሐፍ
ቅ/ጳውሎስ እንደጠቀሰው148 በወንድና በሴት ፍቅረኞች መስሎ የእስራኤልንና የእግዚአብሔርን፣ የሰው ልጆችና
የእግዚአብሔርን፣ የክርስቶስንና የቤተ ክርስቲያንን ፍቅር ይገልፃል፡፡ መጽሐፉ ስምንት /8/ ምዕራፎች ያሉት
ሲሆን የተጻፈበት ዘመን ከተጠቀሱት መጻሕፍት ብዙ አይርቅም፡፡

8. መጽሐፈ ሲራክ
ሲራክ ማለት ጸሐፊ ማለት ነው፣፡ መጽሐፉ በዚህ ቅጽል ስም ይጠራ እንጂ የጸሐፊው ዋና ስም ኢያሱ
ይባላል፡፡ በ80 ዓ.ዓ በግዞት እያለ ጽፎታል ስለ መንፈሳዊና ስለስጋዊ ሕይወት ጥበብና ምክር ይሰጣል፡፡ ሲራክ
ስጋዊና መንፈሳዊ ጥበብን ከእግዚአብሔር ለምኖ ተገልጾለት የጻፈው ነው፡፡ መጽሐፉ 51 ምዕራፎች አሉት፡፡
በአቀራረቡም ከመጽሐፈ ምሳሌ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

ምዕራፍ አራት
የትንቢት ክፍል
ነቢይ149 ማለት አፈ እግዚአብሔር ፣መምህር ፣ወደፊት የሚሆነውንና ከሱ በፊት የሆነዉን የሚናገረው
የሚተነብይ ማለት ሲሆን የሚናገረው ቃል ደግሞ ትንቢት150 ይባላል፡፡ ነቢያት በተለያዩ ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡
 በመጀመሪያ ከትንቢት አገላለጻቸው አንጻር በሁለት ይከፈላሉ
ሀ. የቃል ነቢያት፡- የተናገሩትን ትንቢት በመጽሐፍ ያልጻፉ ታሪካቸው በቅዱሳን መጻሕፍት ተጽፎ
የሚገኙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ኤልያስ፣ ኤልሳዕ፣ ናታን፣ ጋድ ወዘተ… ናቸው፡፡

145
Ecclesiastes
146
Song of solomon
147
መኃ 1፡1
148
ኤፌ 5፡21፡33
149
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ላይ ነብይ የሚለውን ቃል ሲተረጉሙት በተመሳሳይ “መንፈሰ ትንቢት ያደረበት፣ ራዕይ
የሚያይ፣ትንቢት የሚናገር፣ ሰባኪ መምሕር ማለት ነው፡፡ በማለት ይተረጉሙታል፡፡ (ገጽ 620)
150
ትንቢት ማለት በቁሙ ራዕይ ንግግር ገና ወደፊት የሚመጣ ነገር፣ አስቀድሞ የሚታይና የሚገለበጥ፣ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሠጥ ማለት ነው፡፡ (መጽሐፈ
ሰዋሰው ወግስ ገጽ 620)
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 40
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ለ. የጽሑፍ ነቢያት፡- 16ቱን መጽሐፍት የፃፉ ነብያት ናቸው፡፡ እነዚህ ነብያት ደግሞ የተናገሩትን
ትንቢት በመጽሐፍ ያሰፈሩ ናቸው፡፡

 ከዚህ በተጨማሪ ነብያት በጻፏቸው መጻሕፍት ብዛትና በማዕረጋቸው እንዲሁም በፃፉት መጽሐፍ ይዘት
መሰረት ለሁለት ይከፈላሉ፡፡
ሀ. ዐበይት ነብያት፡- በዚህ ክፍል ዉስጥ የሚመደቡት ነብያት አራት ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ነብዩ
ኢሳይያስ፣ ነብዩ ኤርምያስ፣ ነብዩ ህዝቅኤል እና ነብዩ ዳንዔል ናቸዉ፡፡
ለ. ደቂቅ ነብያት፡- በዚህ ክፍል ዉስጥ ቀሪዎቹ 12 ነብያት ይመደባሉ፡፡

 ነብያት ከሚኖሩበት ስፍራ አንፃር በሶስት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡-


ሀ. የይሁዳ ነብያት፡- ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሚክያስ፣ ሚልክያስ፣ አሞጽ፣ ሶፎንያስና ሀጌ ናቸው፡፡
ለ. የሰማርያ ነብያት፡- ሆሴዕ፣ ዮናስ እና አሞጽ ናቸዉ፡፡
ሐ. የባቢሎን ነብያት፡- ሕዝቅዔልና ዳንዔል ናቸው፡፡

 ነብያት ከኖሩበት ዘመን አንጻር በሶስት ይከፈላሉ፡፡ እነርሱም፡-


ሀ. ከባቢሎን ምርኮ በፊት የኖሩ ነብያት፡- ኢሳይያስ፣ ሆሴዕ፣ ኢዩዔል፣አሞፅ፣ ሚክያስ እና አብድዩ
ለ. በባቢሎን ምርኮ ጊዜ የነበሩ ነብያት፡- ኤርምያስ፣ዕንባቆም፣ሕዝቅኤልና ዳንዔል
ሐ. ከባቢሎን ምርኮ በኋላ የነበሩ ነብያት፡- ሐጌ፣ ዘካርያስ፣ ሚልክያስ
የተወደዳችሁ ተማሪዎች በዚህ ክፍል የምንመለከታቸው መጻሕፍት ብዛት አስራ ስድስት ሲሆን እነዚህ
መጻሕፍት የተጻፉት ከላይ በዘረዘርናቸው አስራ ስድስት ነብያት ነው፡፡ እነርሱንም ከዚህ በመቀጠል በዝርዝር
ለመመልከት እንሞክራለን ተከተሉን፡-

1. ትንቢተ ኢሳይያስ151
ኢሳይያስ ማለት መድኃኒት152 ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ “እግዚአብሔር ደህንነት ነው” የሚልም
ትርጓሜ ይሰጣል፡፡ ኢሳይያስ አባቱ አሞጽ ይባላል፡፡ ከዓበይት ነቢያት የሚመደብ ነብይ ነው፡፡ ኢሳይያስ ከዘመነ
አካዝ ጀምሮ ይታወቅ የነበረ በዘመነ ምናሴ በመጋዝ ተተርትሮ ያረፈ የይሁዳ ነቢይ መሆኑ በሊቃውንተ
ቤተክርስቲያን ይነገራል፡፡ የነበረበት ዘመን በ700 ዓ.ዓ አካባቢ ሲሆን 66 ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ ጽፏል፡፡
በትንቢቱም ስለባቢሎን ምርኮና ከምርኮ ስለመመለሳቸው እንዲሁም ጽዮን153 በሚል ስያሜ ስለተጠሩ ስለ
ኢየሩሳሌም፣ ስለ እስራኤል፣ ስለ ቤተክርስቲያን፣ ስለ እመቤታችንና መንግስተ ሰማያት የተነበየ ነብይ ነው፡፡154
ከዚህም በተጨማሪ ስለጌታ ሰው መሆን የተለያዩ ግልጽ ትንቢቶችን ተናግሯል፡፡155 በዚህም ምክንያት በሊቃውንተ
ቤተክርስቲያን “ወንጌላዊው ነቢይ” ሲባል መጽሐፉ ደግሞ “ደረቅ ሐዲስ” ተብሎ ይጠራል፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-12 ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን የሚመለከቱ ትንቢቶች
 ከምዕራፍ 13-23 ከይሁዳና ከእስራኤል ውጪ የሆኑ አሕዛብን የሚመለከቱ ትንቢቶች
 ከምዕራፍ 24-35 በዓለም ላይ ስለሚሆነው የመጨረሻ ፍርድ እና እግዚአብሔር መንግስት
 ከምዕራፍ 36-39 ስለ እስራኤላውያን መሸነፍና የኢየሩሳሌም ህዝብ በባቢሎን ስለመማረካቸው
 ከምዕራፍ 40-55 በባቢሎን ምርኮ ምክንያት በባቢሎን የሚኖሩ አይሁድን የሚያጽናና እና ወደ
ሀገራቸው አየሩሳሌም ለመመለስ የሚያደርጉትን ዝግጅት የሚያሳይ የትንቢት ክፍል
 ከምዕራፍ 56-66 ስለጽዮን (ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም) ዘላለማዊ ክብር የተነገሩ
ትንቢት የክፉዎች መወገድና ስለ እግዚአብሔር ሕዝብ

151
Isaiah
152
አባቶቻችን እንደሚተረጉሙት ከሆነ ኢሳይያስና ኢያሱ በትርጓሜ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የሁለቱም ትርጉም “መድኃኒተ ስጋ ማለት ሲሆን ኢየሱስ ማለት ግን
“መድኃኒተ ስጋ ወነፍስ ማለት ነው፡፡ ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነፍስም የስጋም መድኃኒት መሆኑን የሚያመላክት ነው
153
ጽዮን ማለት አምባ ማለት ነው፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 280)
154
ለምሳሌ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመልከቱ፡- ኢሳ 8፡18፣ 18፡7፣ 24፡23፣ 49፡14፣ 60፡14፣ ወዘተ....
155
ለምሳሌ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመልከቱ፡- ኢሳ 7፡14፣ 9፡6፣ 53፡1
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 41
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

2. ትንቢተ ኤርምያስ156
ኤርምያስ ማለት “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደርጋል” ማለት ነው፡፡157 አባቱ በኢዮስያስ ዘመን የሕጉን
መጽሐፍ ያገኘው ኬልቅያስ መሆኑን ብዙ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያምናሉ፡፡ ከእናቱ ማህጸን የተመረጠና158 በ20
ዓመቱ የነቢይነትን አገልግሎትን የጀመረ ነቢይ ሲሆን የኖረውም ከ600 ዓ.ዓ ጀምሮ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ኤርምያስ
በባቢሎን ምርኮ አብሮ የተማረከ ከምርኮም የእስራኤል ልጆች እየመራ የመጣ በመጨረሻም በድንጋይ ተወግሮ
በሰማዕነት ያረፈ የይሁዳ ነቢይ ነው፡፡159 ትንቢት በሚናገርበት ዘመን ሁሉ መከራ ስለነበረና እያለቀሰ ይናገር
ስለነበር “የሐዘን የሰቆቃ ነቢይ” ሲባል እስራኤል ደግሞ “አልቃሻው ነቢይ” ብለው ይጠሩታል፡፡ መጽሐፉ 52
ምዕራፎች አሉት በይዘቱም ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ ጐረቤት አገሮች፣ ስለ ባቢሎን ምርኮና ህዝቡ ከበደላቸው
እንዲመለሱ ማስጠንቀቅ ነው፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 የነብዩ መጠራት
 ከምዕራፍ 3-20 የሕዝቡ በደልና ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ የሚል ተግሳጽ ያስተላለፈበት
 ከምዕራፍ 21-29 ለህዝቡ ለምርኮኞችና ለሐሰተኛ ነብያት ያስተላለፈው መልዕክትና የተሰጡ
ምልክቶች
 ከምዕራፍ 30-33 እግዚአብሔር ስለህዝቡ ስለ ኢየሩሳሌምና ስለ አዲስ ኪዳን የሰጠው ተስፋ
 ከምዕራፍ 34-39 ስለኢየሩሳሌም መውደቅ
 ከምዕራፍ 40-42 በይሁዳ ከቀሩ ሰዎች ጋር ስለመኖር
 ከምዕራፍ 43-44 በግብጽ ስለመኖሩ
 ከምዕራፍ 45-52 በህዝቡ ላይ ስለተነገሩ ትንቢቶችና ስለኢየሩሳሌም መውደቅ
ከዚህ መጽሐፉ በተጨማሪ አብረው የሚቆጠሩ በእርሱና በደቀመዝሙሩ በባሮክ የተጻፉ መጻሕፍት አሉ፡፡
እነሱም፡-
 ሰቆቃው ኤርምያስ160 ፡- ኤርምያስ ከተማረከ በኃላ በቤሩት አፋፍ ላይ ቆሞ የተናገረዉ የሀዘን ቃል
ነዉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እስራኤላዉያን በባቢሎን ሳይማረኩ በናቡከደነፆር ተከበዉ ሳሉ የጻፈው
እንደሆነ ይነገራል፡፡ መጽሐፉ 5 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በይዘቱም እስራኤል በእግዚአብሔር ፊት
በመበደላቸዉ በባቢሎዉያን የደረሰባቸዉን ጥፋት እና በንስሐ በመመለሳቸዉ ስለተሰጣቸው ተስፋ
እንዲሁም ከምርኮ መልስ ያለውን የኢየሩሳሌም ገጽታ ሃያ ሁለቱን161 አሌፋት መነሻ በማድረግ
የሚተነትን መጽሐፍ ነዉ፡፡
 ተረፈ ኤርምያስ ፡- ይህ መጽሐፍ የኤርምያስ አርአያ መጽሐፍ በመባል ይታወቃል፡፡
 መጽሐፈ ባሮክ ፡- ባሮክ ማለት ብሩክ ማለት ነው፡፡ ባሮክ የነብዩ ኤርምያስ ታማኝ ወዳጅና ጸሐፊ
ነው፡፡ መጽሐፉ የተጻፈው በባሮክ አማካይነት ሲሆን የተጻፈዉም በባቢሎን ምርኮ ለነበሩት
እስራኤላዉያን ነው፡፡ በውስጡም፡- በምርኮ ስላሉት አይሁድ ኑሮ፣ ስለ ንስሃና ስለጸሎት ለአይሁድ
የቀረቡ ምክሮች ይገኙበታል፡፡

3. ትንቢተ ሕዝቅኤል162
ሕዝቅኤል ማለት “እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል” ማለት ሲሆን ከጌታ ልደት በፊት በ6ዐዐ ዓ.ዓ አካባቢ
የነበረ ነብይ ነው፡፡ በልጅነቱ ወደ ባቢሎን የተማረከ ነብይ ነው፡፡163 ካህንም እንደነበረ በመጽሐፉ ጽፏል፡፡ በዚያም
እያለ ለ2ዐ ዓመታት ሲያገለግል ቆይቶ በሰማዕትነት ያረፈ ነቢይ ነው፡፡ መጽሐፉ 48 ምዕራፎች ሲኖሩት
አከፋፈሉም፡-

156
jeremiah
157
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 183
158
ኤር 1፡5
159
በባቢሎን ምርኮ የተማረከውም ለነብይነት በተጠራ ከ40 ዓመት በኋላ ነው፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 183)
160
lamentations
161
ሀያ ሁለቱ አዕሌፋት የሚባሉት የእግዚአብሔር ሕቡዕ ስሞች ናቸው፡፡ እነዚህን ስሞች ከሰቆቃው ኤርምያስ በተጨማሪ በመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 118 ላይ
እናገኛቸዋለን፡፡
162
Ezekiel
163
የባቢሎን ምርኮ የሆነው በ597 ዓ.ዓ ነው፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 25)
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 42
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ከምዕራፍ 1-21 ከኢየሩሳሌም ውድቀት በፊት ስለ እግዚአብሔር ፍርድ የተናገረው


 ከምዕራፍ 25-32 ከኢየሩሳሌም ውጪ ባሉ አሕዛብ ላይ የተነገሩ ትንቢቶች
 ከምዕራፍ 33፡39 ናቡከደነፆር እየሩሳሌምን ከወረረ በኋላ የተነገሩ ከምርኮ መመለስን ተስፋ
የሚያበስሩ ትንቢቶች
 ከምዕራፍ 40-48 ስለ አዲሱ ቤተመቅደስ /ስለ አዲስ ኪዳኑ ቤተመቅደስ/ ስለመንግስተ ሰማያት
የተገለጠ ራዕይ

4. ትንቢተ ዳንኤል164
ዳንኤል ማለት “እግዚአብሔር ፈራጅ /ዳኛ/ ነው”165 ማለት ሲሆን ከነቢዩ ሕዝቅኤል ጋር በምርኮ ጊዜ አብሮ
የነበረ ጓደኛው ነው፡፡ የዳንኤል ሌላ ስሙ ብልጣሶር ሲሆን166 የባቢሎን ነቢይም ይባላል፡፡ መጽሐፉ 12 ምዕራፎች
ሲኖሩት በውስጡም፡- ስለ ሰለስቱ ደቂቅ ታሪክ ነቢዩ ስለራሱ የጻፈው ታሪክ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜዎች የሚፈፀሙ
በምሣሌ ያያቸው ራዕዮች ተካተዋል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 የዳንኤል ወደ ባቢሎን መማረክና መሾም
 ምዕራፍ 2 ዳንኤል አንደኛውን የናቡከደነፆር ሕልም መተርጎሙ
 ምዕራፍ 3 ሰልስቱ ደቂቅ በእቶን እሳት መጣላቸውና መዳናቸው
 ምዕራፍ 4 ዳንኤል 2ኛውን የናቡከደነፆርን ህልም መተርጎሙና ፍፃሜው
 ምዕራፍ 5 ዳንኤል በግድግዳ ላይ ስለብልጣሶር የተጻፈውን ቃል መተርጎሙ
 ምዕራፍ 6 ዳንኤል ዳርዮስን እያገለገለ በአንበሳ ጉድጓድ መጣሉና መዳኑ
 ከምዕራፍ 7-12 ስለ መሲህ መምጣት፣ ስለ ቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት

ከዚህ መጽሐፍ ጋር የሚቆጠሩ ነቢዩ የጻፋቸው ሶስት መጽሐፍት አሉ እነሱም፡-


 ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ፡- ከወላጆቻቸው ጋር በምርኮ ወደ ባቢሎን የወረዱት አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል
የተባሉት ህጻናት ጣዖትን ባለማምለካቸዉ በንጉሱ ትዕዛዝ ወደ እሳት ዉስጥ ተጥለዉ ሳለ እግዚአብሔር
መልአኩን ልኮ ስላዳናቸዉ ያመሰገኑት ምስጋና ነዉ፡፡167
 ተረፈ ዳንኤል ፡- ይህን መጽሐፍ የጻፈው ነብዩ ዳንዔል ሲሆን በቂሮስ ዘመነ መንግስት ዳንዔል ለጣዖት
ባለመስገዱ የተነሳ ወደ አናብስት ጉድገድ መጣሉና በዛም ለ7 ቀናት እንደቆየ የእግዚአብሔር መልአክም
ነብዩ እንባቆምን ምግብ አስይዞ እንደላከዉ ይገልጻል፡፡
 መጽሐፈ ሶስና ፡- ሶስና ሹሻና ወይም ሊሊ የምትባል ሲሆን ትርጉሙም የአበባ አይነት ማለት ነው፡፡
መጽሐፉ ሶስና በ3 መምሕራን የሚደርስባትን በደል የሚያትት ነው፡፡

5 ትንቢተ ሆሴዕ168
ሆሴዕ ማለት “እግዚአብሔር ያድናል” ማለት ሲሆን ከጌታ ልደት በፊት ከ765-725 ዓ.ዓ የነበረ ነቢይ ነው፡፡
በት.ሆሴ 6፡1 11፡1-7 ላይ እንደተጠቀሰው ትንቢቱን በራሱ በሚስቱ169 እና በልጆቹ እየመሰለ በእስራኤልና
በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ግንኙነት ይናገር ነበር፡፡ መጽሐፉ 14 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በውስጡም፡-
እስራኤል ጣዖት በማምለካቸው የእግዚአብሔርን ሕግ ስለመጣሳቸው እንዲሁም ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
ትንቢቶችን ተናግሯል፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-3 የሆሴዕ ሚስት የጎሜር ማመንዘር ለእስራኤል መንፈሳዊ አመንዝራነት

164
Daniel
165
“ዳን ማለት ዳኛ ማለት ሲሆን ኤል ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር ስሙ ነው፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 244 እና 245 ላይ ያሉትን ትርጉሞች
ይመልከቱ)
166
ት.ዳን 1፡7
167
ት.ዳን 3፡24-25
168
Hosea
169
ጎሜር ትባላለች፡፡ ይህች ሴት የዴብላይም ልጅ እና የኢይዝራኤልና የሎሩሃማ የሎዓሚ እናት ስትሆን ውሽሞቿን ተከትላ በባርነት የተሸጠች ነገርግን በሏ
ሆሴዕ ከባርነት የመለሳት ሴት ናት፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 262
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 43
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ከምዕራፍ 4-13 እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ባይመለስ ከፍርድና ከውድቀት እንደማያመልጥ


የተናገረበት
 ምዕራፍ 14 ወደ እግዚአብሔር በመመለስ የሚገኝ ፈውስና በረከት

6 ትንቢተ አሞጽ170
አሞጽ ማለት “ኃይል” ማለት ሲሆን ከእረኝነት የተጠራ የእስራኤል/የሰማርያ/ ነቢይ ነው፡፡ መጽሐፉ ዘጠኝ
ምዕራፎች ያሉት መጽሐፍ ሲሆን በይዘቱም፡- የፍልስጥኤምና የእስራኤል ኃጢአት በመብዛቱ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ፣
በሳምራውያን ላይ የሚመጣ ቁጣና ለእስራኤል የተነገረ ተስፋ ይገልጻል፡፡ መጽሐፉ ዘጠኝ ምዕራፎች ያሉት ሲሆን
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 ፍርድ በእስራኤልና በእስራኤል ጎረቤት ሀገሮች
 ከምዕራፍ 3-6 ፍርድ በእስራኤልና አለመመለስና ኃጢአት ምክንያት
 ከምዕራፍ 7-9 እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ስለሚመጣው ፍርድና በፍጻሜ ዘመን ስላለው
ተስፋ

7 ትንቢተ ሚክያስ 171

ሚክያስ172 ማለት “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?”173 ማለት ሲሆን ከ722 ዓ.ዓ በፊት የነበረ የይሁዳ
ነቢይ ነው፡፡ ነብዩ ሚክያስ የብንያም ነገድ ሲሆን የነቢዩ ኢሳይያስ ጓደኛ የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ነብዩ የጻፈው መጽሐፍ
ሰባት ምዕራፎች ያሉትን የትንቢት መጽሐፍን ሲሆን በይዘቱም፡- ስለ ሠማርያ እና እየሩሳሌም መፍረስ በኋላም
እግዚአብሔር ህዝቡን እንደመንጋ እንደሚሰበስብ እና እየሩሳሌምን ዳግም እንደሚሰራ፣ አህዛብም እግዚአብሔርን
እንደሚፈልጉ ይህም በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚፈጸም ተንብዮዓል፡፡174
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1—3 የሰማርያና የኢየሩሳሌም መፍረስ
 ምዕራፍ 4 የእግዚአብሔር መንግስት መመስረት
 ምዕራፍ 5 ከቤተልሔም የሚወጣ ገዢና እረኛ
 ምዕራፍ 6 እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ያለው ክርክር
 ምዕራፍ 7 ተግሳጽና ተስፋ

8 ትንቢተ ኢዮኤል175
ኢዩኤል ማለት “እግዚአብሔር አምላክ ነው” ማለት ሲሆን ከጌታ ልደት በፊት በ6ዐዐ ዓ.ዓ የነበረ የይሁዳ
ነቢይ ነው፡፡ አባቱ ባቱዔል የሚባል የእስራኤል ነብይ ነው፡፡176 መጽሐፉ 3 ምዕራፎች ሲኖሩት በይዘቱም፡- በህዝቡ
ላይ ሊወርድ ስላለው የአንበጣ መንጋ ህዝቡ በጾምና በጸሎት ወደ አምላኩ እነዲቀርብ ማስጠንቀቅ፣ ስለ ርደተ
መንፈስ ቅዱስ /ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ/ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር ቀን ይገልጣል፡፡177
አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1፡1-12 የአንበጣ መቅሰፍት
 ምዕራፍ 1፡13-2፡27 ንስሐ ለሚገቡ የእግዚአብሔር በረከት
 ምዕራፍ 2፡28-32 የእግዚአበሔር መንፈስ መፍሰስ
 ምዕራፍ 3፡1-15 የዓለም ህዝቦች ፍርድ

170
Amos
171
Micah
172
የሚክያስ ቅጽል ስም “ሞሬታዊው ሚክያስ ሲባል ይህንን ስያሜ ያገኘው “ሞሬሼት ጌት በተባለች ከተማ ነው፡፡ ( ትንቢተ ሚክያስ 1፡1 እና የመጽሐፍ
ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 51
173
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 51
174
ለምሳሌ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመልከቱ፡- ሚክ 1፡6፣ 2፡12፣4፡1-2 ፣7፡14፣ 7፡16
175
Joel
176
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 176
177
ት.ኢዩ 1፡4፣ 3፡14፣ 2፡28
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 44
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ምዕራፍ 3፡16-21 የእግዚአብሔር ብጽዕና

9 ትንቢተ አብድዮ178
አብድዮ ማለት “የእግዚአብሔር አገልጋይ” ማለት ሲሆን ለነብይነት ከመጠራቱ በፊት የእስራኤል ንጉስ
ለነበረው ለአክዓብ የቤቱ አዛዥ ነበር፡፡ ንግስቷ ኤልዛቤልም የእግዚአብሔር ነብያትን ባስገደለች ጊዜ መቶ ነብያትን
የሸሸገ ሰው ነው፡፡ ከጌታ ልደት በፊትም በ6ዐዐ ዓ.ዓ የነበረ የሰማርያ ነቢይ ነው፡፡ የጻፈው መጽሐፍም 1 ምዕራፍ
ሲኖረው ከነቢያት መጽሐፍት በጣም ትንሹ (ትንሽ ምዕራፍ ያለው) መጽሐፍ ነው፡፡ የሚናገረውም ስለ ኤዶምያስ
ነው፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከቁጥር 1-9 በኤዶም ላይ ስለሚፈጸመው ፍርድ
 ከቁጥር 10-14 ኤዶም በእስራኤላውያን ላይ ስለፈጸመችው በደል
 ከቁጥር 15-21 ፍርድ በኤዶምያስና በአህዛብ ላይ የጽዮን መዳን

፲ ትንቢተ ዮናስ179
ዮናስ ማለት የዋህ ርግብ ማለት ነው፡፡ ዮናስ ከጌታ ልደት በፊት 9ዐዐ ዓ.ዓ የነበረ ነብይ ሲሆን ይኖር
የነበረውም በገሊላ በጋትሔፌር ከተማ ነበር፡፡180 መጽሐፉ በአራት ምዕራፎች የተከፈለ ነው፡፡ ዮናስ በቤተክርስቲያን
ሊቃውንት ትምሕርት በነብዩ በኤልያስ ዘመን የነበረና ኤልያስ ከሙታን ያስነሳው የመበልቲቱ ልጅ ነው፡፡ ካስነሳው
በኋላም የኤልያስ ደቀመዝሙር ሆኖ አድጓል፡፡ መጽሐፉ በይዘቱ፡- ዮናስ እግዚአብሔር ወደላከው ሃገር አልሄድም
ብሎ መኮብለሉ፣ በድጋሚ የዮናስ መላክና የነነዌ ንስሀና በንስሀቸዉም ሊደርስ የነበረው ጥፋት መመለሱ በዚህም
ምክንያት የነቢዩ አለመደስት ይገልጻል፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ዮናስ ወደ ተርሴስ መኮብለል
 ምዕራፍ 2 የዮናስ ጸሎትና መመለስ
 ምዕራፍ 3 በዮናስ ስብከት ከንጉሱ እስከ ህዝቡ በንስሀ መመለስ
 ምዕራፍ 4 የዮናስ ቁጣና የእግዚአብሔር መልስ

፲1 ትንቢተ ናሆም181
ናሆም ማለት “መጽናናት” ማለት ነው፡፡ ከጌታ ልደት በፊት በ7ዐዐ ዓ.ዓ የነበረ ነብይ ሲሆን ይኖርባት
የነበረችው ከተማ ኤልቆሽ ትባላለች፡፡ ይህች ከተማ ከይሁዳ ከተሞች የምትመደብ ናት፡፡182 ናሆም እንደ ነብዩ ዮናስ
በነነዌ ያስተማረ ነብይ ሲሆን ያስተማረበት ምክንያትም ከነብዩ ዮናስ አገልግሎት በኋላ በድጋሚ በመበደላቸው
የተነሳ ነው በዚህም የተነሳ እንደ ነብዩ ዮናስ የአህዛብ ነብይ ተብሎ ተጠርቶአል፡፡ መጽሐፉ 3 ምዕራፎች ያሉት
ሲሆን ይዘቱም፡- ስለ ይሁዳ ሕዝብና ስለ እስራኤል ነፃ መውጣት ስለ ነነዌ ዳግም ጥፋት ይገልጻል፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 እግዚአብሔር የፍርድና የበቀል አምላክ መሆኑ
 ምዕራፍ 2 የነነዌ ጥፋት
 ምዕራፍ 3 የነነዌ ጥፋት ምክንያት

፲2 ትንቢተ ዕንባቆም183
ዕንባቆም ማለት “ማቀፍ/እቅፍ/” ማለት ሲሆን ከጌታ ልደት በፊት በ6ዐዐ ዓ.ዓ የነበረ ነቢይ ነው፡፡ መፅሐፉ
በ3 ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን በይዘቱም፡- አይሁድ በኃጢያታቸው የሚደርስባቸውን መከራ ባቢሎናውያን
በሚገዟቸው ላይ ባደረጉት ግፍ የሚደርስባቸውን ቅጣትና ነቢዩ የጸለየውን ጸሎት ያካትታል፡፡ እከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 የነብዩ ዕንባቆም ጥያቄ

178
Obadiah
179
Jonah
180
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 238
181
Nahum
182
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 145
183
Habakkuk
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 45
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ምዕራፍ 2 ነብዩ ለጸለየው ጸሎት እግዚአብሔር የሰጠው መልስ


 ምዕራፍ 3 የነብዩ ዕንባቆም ጸሎት

፲3 ትንቢተ ሶፎንያስ184
ሶፎንያስ ማለት “እግዚአብሔር ሰውሯል” ማለት ሲሆን በ7ዐዐ ዓ.ዓ የነበረ የይሁዳ ነቢይ ነው፡፡ አባቱ ኩሲ
ይባላል፡፡ ሶፎንያስ በይሁዳ ንጉስ በአሞጽ ዘመነ መንግስት የተነሳ ነብይ ነው፡፡ መጽሐፉ 3 ምዕራፎች ሲኖሩት
በይዘቱም፡- አይሁድ እንዲመለሱ ምክርና ማስጠንቀቂያ፣ በኢየሩሳሌም አካባቢ ለሚገኙ ሕዝቦች ማስጠንቀቂያ፣
አህዛብ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ እንዲሁም እግዚአብሔር እስራኤልንና ይሁዳን ከምርኮ እንደሚመልሳቸው
ይገልጻል፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ሁሉም ላይ ስለሚመጣው ፍርድ
 ምዕራፍ 2 በልዩ ልዩ ሕዝቦች ላይ ስለሚመጣው ፍርድ
 ምዕራፍ 3 በይሁዳ ስለሚመጣው ፍርድ እንዲሁም የእስራኤል ከተበተኑበት መሰብሰብና
ከእግዚአብሔር ስለሚያገኙት በረከት

፲4. ትንቢተ ሐጌ185


ሐጌ ማለት “በዓላዊ” ማለት ሲሆን ከምርኮ በኋላ በ520 ዓ.ዓ የነበረ የይሁዳ ነቢይ ነው፡፡ መጽሐፉ በሁለት
ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን በይዘቱም፡- ስለ ቤተ መቅደስ ዳግም መታነጽ እግዚአብሔር ቁጣውን በበረከት
እንደሚመልስ እንዲሁም ስለ ዘሩባቤል ይገልጣል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 የእግዚአብሔርን ቤት ለመስራት ተነሱ የሚል የነብዩ መልእክት የቀረበበትን
 ምዕራፍ 2፡1-9 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይኖራል የሚል ማበረታቻ እንደተሰጠ
 ምዕራፍ 2፡10-23 እግዚአብሔር ይባርካችኋል ያንፃችኋልም የሚል ማበረታቻ እንደተሰጠ
 ምዕራፍ 2፡20-23 ዘሩባቤል ስለመጨረሻው ሰዓት የተናገረው ትንቢት

፲5. ትንቢተ ዘካርያስ186


ዘካርያስ ማለት “እግዚአብሔር ያስታውሳል” ማለት ሲሆን በ5ዐዐ ዓ.ዓ የነበረ የይሁዳ ነቢይ ነው፡፡187
መጽሐፉ በ14 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በይዘቱም፡- ስለ ቅዱሳን መላእክት አማላጅነት፣ እመቤታችን በወርቅ
መቅረዝ መስሎ መናገሩ፣ ስለ ሆሳዕና፣ ስለ ጌታችን ጐን መወጋት እንዲሁም ስለ ትንሳኤ ሙታን ይገልጣል፡፡
አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1፡1-6 ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ የሚል ጥሪ
 ምዕራፍ 1፡6-6፡15 በስምንት ራዕዮች የአለማት ጌታ እግዚአብሔር ጽዮንን ለመስራትና ለማንጻት
ያለውን ሐሳብ መግለጽ
 ምዕራፍ 7-8 በኢየሩሳሌም መፍረስ ጊዜ የተደነገጉ የጾም ቀናት ተለውጠው የደስታ በዓላት
እንዲሆኑ የተሰጠ ትዕዛዝ
 ምዕራፍ 9 እግዚአብሔር ለመፍረድም ለማዳንም ታላቅና የዋህ አምላክ እንደሆነ
 ከምዕራፍ 10-13 ስለማይረቡ እረኞችና ስለመልካም እረኛ
 ምዕራፍ 14 እግዚአብሔር በምድር ላይ ስለመንገሱ

184
Zephaniah
185
Haggai
186
Zechariah
187
ዘካ 1፡12፣ 4፡2፣ 9፡9፣ 14፡10፣ 12፡10
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 46
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

፲6. ትንቢተ ሚልክያስ188


ሚልክያስ “መልዕክተኛ” ማለት ሲሆን በ400 ዓ.ዓ ከጌታ ልደት በፊት የነበረ የይሁዳ ነቢይ ነው፡፡ መፅሐፉ
4 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በይዘቱም፡- ስለ አይሁድ ካህናትና ሕዝብ የተሰጠ ተግሳፅ፣ ስለአስራት በኩራት፣
ስለጌታችን መምጣት እንዲሁም ስለ ዮሐንስ መጥምቅ መላክ ይገልጣል፡፡189 አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1፡1-5 የእግዚአብሔር ፍቅር
 ምዕራፍ 3፡1-6 ከኃጢአት የሚያነፃ የመሲህ መምጣት
 ምዕራፍ 1፡7-12 ተመለሱ የሚል የንስሐ ጥሪ
 ከምዕራፍ 3፡13-4፡3 እግዚአብሔር የሚፈሩትንና የሚነቅፉበትን እንደሚርቅ
 ምዕራፍ 4፡4-6 ስለምታስፈራውና ታላቋ የእግዚአብሔር ቀን

ክፍል ሁለት
የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት190
3.፪.1 የቃሉ ትርጉም
አዲስ ኪዳን ማለት አዲስ ውል ስምምነት ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ወዶ ፈቅዶ ባስነገረው ትንቢት መሰረት191
የፍቅር አምላክ በማይመረመር ጥበቡ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ያደረገው የሰው ልጆችን የማዳን ጉዞና ከእስራኤል
ዘነፍስ /ከክርስትያኖች/ ጋር በክቡር ደሙ ያደረገውን የውል ስምምነት (ኪዳን) ያመለክታል፡፡192 በዚህ ዘመን
የተጻፉት መጻሕፍት የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በመባል ይታወቃሉ፡፡ ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን የማይነጣጠሉና
አንዱ በአንዱ ላይ ህልው ሆኖ የሚኖር ነዉ፡፡
 ብሉይ ኪዳን የአዲስ ኪዳን ንባብ ሲሆን አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ትርጉም ነዉ፡፡
 ብሉይ ኪዳን የአዲስ ኪዳን ትንቢት ሲሆን አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን ፍፃሜ ነዉ፡፡
 ብሉይ ኪዳን የአዲስ ኪዳን ጥላ ሲሆን አዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳን አካል ነዉ፡፡
 አዲስ ኪዳን በብሉይ ኪዳን የተሰወረ ሲሆን ብሉይ ኪዳን ደግሞ በአዲስ ኪዳን የተገለጠ ነዉ፡፡
አዲስ ኪዳን የሚለው ቃል ከዚህ ኪዳን በፊት ኪዳን እንደነበረ የሚያስረዳና የቀደመውን ኪዳን መንደርደሪያ
አድርጎ የተነሳ አዲስ የውል ስምምነት መሆኑን የሚገልጥ ቃል ነው፡፡ የአዲስ ኪዳን ዘመን የሚባለው ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ለድኅነተ ዓለም ቅዱስ ስጋውንና
ክቡር ደሙን ለምዕመናን ለመስጠት አዲስ ውል የተዋዋለበት ዘመን ነው፡፡ ይህም ክፍል ከመጽሐፍ ቅዱስ ሁለት
አበይት ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ የዚህ ክፍል መጻሕፍት የተጻፉበት ጊዜ ከ45 ዓ.ም እስከ 100 ዓ.ም ባለው ጊዜ
ውስጥ ነው፡፡ የእነዚህ መጻሕፍት አቀራረብ በታሪክ በትምህርት ወይንም በትንቢት መልክ ቢሆንም ስለ ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገልጡ ስለሆነና ማዕከላቸው እርሱ ስለሆነ በጥቅሉ ወንጌል ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህም
ሌላ የአዲስ ኪዳን ዘመን ለብሉይ ኪዳን ዘመን ፍፃሜ ስለሆነ በዘመነ ብሉይ የተነገሩ ምሳሌዎችና ትንቢቶች በአዲስ
ኪዳን መጻሕፍት ተጠቅሰው ፍፃሜያቸውና ትርጉማቸው ተገልጧል፡፡193

3.2.2 የመጻሕፍቱ ብዛት


የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከላይ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ለመግለጽ እንደሞከርነው ቅድስት ቤተክርስቲያናችን
የካርቴጅ (ቅርጣግ) ጉባኤያትን መሠረት በማድረግ ሰማንያ አንድ መጻሕፍትን ትቀበላለች፡፡ ከነዚህ መጻሕፍት
መካከል ሰላሳ አምስቱ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
1. የማቴዎስ ወንጌል 19. ወደ እብራውያን ሰዎች
2. የማርቆስ ወንጌል 20. 1ኛ ጴጥሮስ
3. የሉቃስ ወንጌል 21. 2ኛ ጴጥሮስ

188
Milachi
189
ት.ሚል 1፡2፣ 3፡1
190
New testment
191
ኤር 31፡31
192
ማቴ 26፡26 ዮሐ 6፡53-59 1ቆሮ 11፡23-26
193
ይህንን ለመረዳት መጻሕፍቱን ሲያነቡ ከህዳጉ ጋር በማስተያየት ያንብቡ፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 47
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

4. የዮሐንስ ወንጌል 22. 1ኛ ዮሐንስ


5. የሐዋርያት ሥራ 23. 2ኛ ዮሐንስ
6. ወደ ሮሜ ሰዎች 24. 3ኛ ዮሐንስ
7. 1ኛ ቆሮንጦስ 25 የያዕቆብ መልእክት
8. 2ኛ ቆሮንጦስ 26. የይሁዳ መልእክት
9. ወደ ገላትያ ሰዎች 27. የዮሐንስ ራዕይ
10. ወደ ኤፌሶን ሰዎች 28. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶስ
11. ወደ ፊሊጵዮሲስ ሰዎች 29. ትዕዛዝ ሲኖዶስ
12. ወደ ቆላስይስ ሰዎች 30. ግጽው ሲኖዶስ
13. 1ኛ ተሰሎንቄ 31. አብጥሊስ ሲኖዶስ
14. 2ኛ ተሰሎንቄ 32. 1ኛ መጽሐፈ ኪዳን
15. 1ኛ ጢሞቲዎስ 33. 2ኛ መጽሐፈ ኪዳን
16. 2ኛ ጢሞቲዎስ 34. መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ
17. ወደ ቲቶ 35. መጽሐፈ ዲድስቅልያ
18. ወደ ፊሊሞና

323 የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አከፋፈል


እንደ ብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ሁሉ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍትንም በአምስት መደቦች ከፍለን እንመለከታለን፡፡
እነሱም፡-
1. የወንጌል ክፍል 4. የትንቢት ክፍል
2. የታሪክ ክፍል 5. የሥርዓት ክፍል ናቸዉ፡፡
3. የመልእክት /የትምህርት/ ክፍል

ምዕራፍ አንድ
የወንጌል ክፍል
ወንጌል ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን “ኢቫንጊሌዩን”194 ከሚለው ቃል የተገኘ ነው፡፡ ትርጉሙ ብስራት፣ የምስራች፣
ስብከት ማለት ነው፡፡ ወንጌል ደስታ/የምስራች/ የሚገለጥበት ቋንቋ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ እንደነገሰ ዲያብሎስ
እንደተዋረደ ሞተ ሥጋ ወነፍስ እንደጠፋ ያወሳልና ነው፡፡ ይህም ቃል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
የተናገረውን ቅዱሳን ሐዋርያትና አርድዕት ያስተማሩትን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህን ትምህርት ወንጌል
ብሎ የጠራው ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡195 በዚህ ክፍል ውስጥ አራት የወንጌል
መጽሐፍት አሉ፡፡ እነርሱም፡-
1. የማቴዎስ ወንጌል 3. የሉቃስ ወንጌል
2. የማርቆስ ወንጌል 4. የዮሐንስ ወንጌል ናቸው፡፡
በጸሐፊዎቹ ስም መጠራታቸው ጸሐፊዎቹን ለማስታወቅ እንጂ ወንጌሉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ ነው፡፡ መጻሕፍቱን በጸሐፊዎቹ ስም የሰየሙት 318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡ አራቱም
ወንጌላት የሚተርኩት ስለ ጌታችን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆንም በአገላለጥ እንዲሁም በይዘት
አንዱ ከአንዱ ይለያያል፡፡ የማቴዎስ የማርቆስና የሉቃስ በአጻጻፍ ይዘታቸው የሚመሳሰሉ ሲሆኑ ዮሐንስ ደግሞ
ለየት ባለ መልኩ ተጽፈዋል፡፡ በዮሐንስ ወንጌል በአብዛኛው ከጌታ ምድራዊ ልደት አንስቶ ረቀቅ መጠቅ ያሉ
ምስጢራተ መለኮት ተገልጸዋል፡፡ ከአራቱ ወንጌላውያን ማቴዎስና ዮሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት ውስጥ ሲሆኑ
ማርቆስና ሉቃስ ደግሞ ከሰባ ሁለቱ አርድዕት ውስጥ ናቸው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አለው፡፡ ከአርድዕት ወገን
የሆኑት ማርቆስና ሉቃስ እንዲጽፉ የተደረገበት ምክንያት ከአርድዕት ለማስተማር ሲወጡ እናንተ የውጭ ሰዎች
ናችሁ የውስጥማ ሰዎች ብትሆኑ ኖሮ ወንጌልን በጻፋችሁ ነበር ብለው አይሁድ ትምህርታቸውን ከመቀበል
ወደኋላ እንዳይሉ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የአርድዕት ክብር በአይሁድም ሆነ በክርስቲያኖች ዘንድ እንዲታውቅ

194
Evangellion
195
ማቴ24፡14፣ ማቴ26፡13፣ ማር16፡15
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 48
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ነው፡፡ አርድዕት በጌታ ዘንድ የከበሩ መሆናቸውን ወንጌሉን በመጻፋቸው ይታወቃል፡፡ ከሐዋርያት ወገንም ሁለቱ
ወንጌል እንዲጽፉ የተደረገው ስለ ወንጌል ክብር ነው፡፡ በአጠቃላይ ወንጌል በአርድዕት ብቻ ተጽፎ ቢሆን ኖሮ
ይህች ተርታ ህግ ናት ደገኛይቱ ህግ በሐዋርያት ልብ ቀርታለች በማለት አይሁድ ወንጌልን ከመቀበል ወደኋላ
ይሉ ነበር፡፡ ይህ እንዳይሆን ወንጌል በሐዋርያትም በአርድዕትም ተጻፈ፡፡

የዐራቱ ወንጌላት ይዘት


በአራቱ ወንጌላት የተመዘገበው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ እና ስራ ነው፡፡ ይሁንና አንዳቸው ከሌላቸው
የሚለዩበት የታሪክ የትምህርት እና የተዓምራት አመዘጋገብ አለ፡፡ በአንዱ ወንጌል ተመዝግበው በሶስቱ የማይገኙ
አንዳንድ የጌታ ታሪኮችና ሥራዎች አሉ፡፡ ዐራቱ ወንጌላት ከይዘታቸው አንፃር ሲጠኑ በሁለት ይከፈላሉ፡፡
ይኸውም፡-
 ሲኖፕቲክ ወንጌላት፡-196 “ሲኖፕቲክ” የግሪክ ቃል ሲሆን በአንድ መታየት ማለት ነው፡፡ ሲኖፕቲክ ከዐራቱ
ወንጌላት መካከል ለሶስቱ ወንጌላት ማለትም ለማቴዎስ፣ ለማርቆስና ሉቃስ ወንጌል የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡
ሶስቱ ወንጌላት በይዘታቸው በብዙ ክፍል ስለሚመሳሰሉና እርስ በርስ ማስተያየት ስለሚቻል ይህን
ለማስረዳት የተሰጣቸው ስያሜ ነው፡፡
 ዐራተኛው ወንጌል፡- አራተኛው ወንጌል የተባለው የዮሐንስ ወንጌል ነው፡፡ በዚህ ወንጌል የተመዘገበው
እንደሶስቱ ወንጌላት ስለጌታ ታሪክና ሥራ ቢሆንም በሶስቱ ወንጌላት ያሰፈሩትን የጌታችንን ትምህርቶች
በብዛት ይዞ ይገኛል፡፡ ሦስቱ ወንጌላት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የምድር መዋዕለ ዘመን /የሰውነቱን
ነገር/ አጉልተው ሲጽፉ197 ዐራተኛው ወንጌል ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ መውረዱን
/የመለኮቱን ነገር/ አጉልቶ ጽፏል፡፡198 በዚህም ምክንያት ሦስቱ ወንጌላት “ወንጌላት ዘምድር” ሲባሉ
ዐራተኛው ወንጌል ደግሞ “ሰማያዊ ወንጌል” በመባል ይጠራሉ፡፡

1 የማቴዎስ ወንጌል199
ማቴዎስ ማለት “የእግዚአብሔር ስጦታ” ማለት ነው፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ሌዊ ይባላል፡፡200 የአባቱ ስም
ዲቁ /እልፍዮስ/ እናቱ ካሩትሰያ ትባላለች፡፡ ትውልዱ ከ12ቱ ነገደ እስራኤል ከነገደ ይሳኮር ነው፡፡ ለሐዋርያነት
ከመጠራቱ በፊት ቀራጭ ነበር፡፡ አህጉረ ስብከቱ ምድረ እስራኤል፣ ሕንድ፤ ኢትዮጵያ ወዘተ… እንደሆኑ የተለያዩ
የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ያስረዳሉ፡፡ የቅዱስ ማቴዎስ እረፍቱ ጥቅምት 12 ቀን እንደሆነና ያረፈውም
በሰማዕትነት እንደሆነ በመጽሐፈ ስንክሳር እና በገድለ ሐዋርያት እንዲሁም በመቅድመ ወንጌል ላይ ተጽፎ
እናገኛለን፡፡201 ይህ ወንጌላዊ/ማቴዎስ/ ከአራቱ የሥላሴ መንበር ከሚሸከሙ ኪሩቤል በገፀ ሰብዕ/በሰው መልክ/
ይመሰላል፡፡ ምክንያቱም የጌታን ደኃራዊ ልደት /በሥጋ መወለድ/ ከሰው ወገን አንደሆነ “የዳዊት ልጅ የአብርሃም
ልጅ” በማለት ያስረዳልና ነው፡፡202 ወንጌሉ የተጻፈበት ዘመን ከኢየሩሳሌም ጥፋት ቀደም ብሎ ሲሆን ዘመኑም
በመቅድመ ወንጌል ላይ በገላውዴዎስ ቄሣር ዘመነ መንግስት ጌታ ባረገ በዘጠነኛው ዓመት እንደሆነ ይገልፀዋል፡፡
በዘመናዊ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘንድ መጽሐፉ በ58 ዓ.ም እንደተጻፈ ይታመናል፡፡ ስለተጻፈበት ቦታ ደግሞ ሲገልፅ
በፍልስጤም ተጀምሮ በህንድ ሀገር እንደተፈፀመ በመቅድመ ወንጌል ላይ የተገለፀ ሲሆን የተጻፈበት ቋንቋ
እብራይስጥ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ምክንያቱም የተጻፈላቸው ሰዎች አይሁድ /ዕብራውያን/ ስለሆኑ ነው፡፡ ይህንን
ወንጌል ወንጌላዊ ዮሐንስ ለተማሪዎቹ ከእብራይስጥ ቋንቋ ወደ ግሪክ ቋንቋ ተርጉሞላቸዋል፡፡ ማቴዎስ በሀገረ

196
synoptic
197
ማቴ 1፡1-17፣ ማር 8፡32፣ ሉቃ 3፡23-38
198
ዮሐ 1፡1-3፣ 3፡13፣ 6፡4-5፣ 8፡23
199
Matthiew
200
ማቴ 9፡9
201
አንዳንድ የታሪክ ጸሐፊዎች ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ እንዳስተማረና በኢትዮጵያም ሠማዕትነትን እንደተቀበለ ይገልጣሉ፡፡ ነገርግን ይህ
በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ዘንድ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው ምክንያቱም ኢትዮጵያ ከቅዱስ ማቴዎስም ስብከት በፊት አምልኮተ እግዚአብሔርን
የተቀበለች ሃገር ነች፡፡ በንጉስ ሰሎሞንም ዘመን የመጣችው ኢትዮጵያዊት ንግስት ማክዳ (ሳባ) የተናገረችው ንግግር ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ (2ነገ 10፡9) እናም
በዚህም መነሻነት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ቅዱስ ማቴዎስ በኢትዮጵያ ሠማዕነትን እንደተቀበለ አያምኑም፡፡
202
ማቴ 1፡1
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 49
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ፍልስጤም ሲያስተምር አይሁድ ትምህርቱን አምነው ተቀብለውታል ያስተማረውንም ትምህርት በጽሁፍ


እንዲያሰፍርላቸው ጠይቀውት ጽፎላቸዋል፡፡ መጽሐፉ 28 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 የጌታ የትውልድ ሐረግ በግብረ መንፈስ ቅዱስ መፀነሱ ልደቱና ስደቱ
 ከምዕራፍ 3-4 ጥምቀቱ፣ ጾሙ፣” በዲያቢሎስ መፈተኑና ማስተማር መጀመሩ
 ከምዕራፍ 5-7 የተራራው ስብከት
 ከምዕራፍ 8-9 ድውያንን መፈወሱ፣ ነፋሳትን መገሰጹ፣ አጋንንትን ማውጣቱ፣ የማቴዎስ
መጠራትና ሙት ማስነሳቱ
 ምዕራፍ 10 ለሐዋርያት ሥልጣንን መስጠቱ
 ከምዕራፍ 11-16 የዮሐንስ መጥምቅ መልእክትና ሞት፣ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ፣ ጌታ
በውኃ ላይ መሄዱ፣ በረከተ ኅብስት፣ ከነናዊቷ ሴት፣ ሐዋርያት በቂሳርያ መጠየቁ
 ከምዕራፍ 17-18 ደብረ ታቦር፣ ግብር፣ ሕጻናት፣ የጠፋው በግ፣ ይቅርታ
 ከምዕራፍ 19-20 ጋብቻ፣ ባለጠጋ፣ የወይን አትክልት ጌታ፣ የያዕቆብና የዮሐንስ እናት ልመና፣
ሁለቱ ማየት የተሳናቸው
 ከምዕራፍ 21-23 ሆሳዕና፣ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ፣ ትንሳኤ ሙታን፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን
 ከምዕራፍ 24-25 ዳግም መምጣቱ
 ከምዕራፍ 26-28 ምሴተ ሐሙስ፣ ስቅለቱ፣ ሞቱና ትንሳኤው

2 የማርቆስ ወንጌል203
ማርቆስ እናቱ ማርያም አባቱ አርስጦቡሎስ ይባላሉ፡፡ እናቱ ቤቷን ለትምህርተ ወንጌል ከመልቀቋም በላይ
የመጀመሪያ ቤተክርስቲያን የተመሠረተችውም ለቅዱስ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስ የወረደላቸው በዚህችው
ከማርቆስ እናት ቤት ነው፡፡204 ማርቆስ በሌላ ስሙ ዮሐንሰ ተብሎ ይታወቃል፡፡205 ትርጉሙም “ፀጋ እግዚአብሔር”
ማለት ነው፡፡ ማርቆስ ማለት ደግሞ “ንብ” ማለት ነው፡፡ ንብ ማርዋን ለማዘጋጀት አስቀድማ ከተለያዩ አበቦች
እንደምትቀስም ሁሉ ቅዱስ ማርቆስም በመጀመሪያ ከጌታ ቀጥሎም ከሐዋርያት ስለተማረ ነው፡፡ ቅዱስ ማርቆስ
ከጌታ ዕርገት በኋላ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመሆን አገልግሏል፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ አህጉረ ስብከቶች በሆኑት
በሮምና በእስክንድርያ አስተምሯል፡፡ በተለይ ለእስክንድርያና ለሊቢያ ቤተክርስቲያን መስራች አባት እንደሆነ
ይነገርለታል፡፡ በነዚህ አገሮች ክርስትናን አስፋፍቶ ሚያዚያ 3ዐ ቀን 67 ዓ.ም በእስክንድርያ ከተማ በ70 ዓመቱ
በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ በገፀ አንበሳ ይመሰላል፡፡ ምሳሌውም አንበሳ ለላህም ጌታዋ ነው
ይሰብራታል ቅዱስ ማርቆስም በግብጽ የነገሰ አምልኮ ላህምን አጥፍቷልና በዚህ ይመሰላል፡፡ ቅዱስ ማርቆስ
ወንጌሉን የጻፈላቸው ለሮም ሰዎች በሮማይስጥ ቋንቋ ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃ በሮማይስጥ ቋንቋ የሚታወቁት
ቃላት በወንጌሉ ይገኛሉ፡፡206 የተጻፈበት ዘመን እንደ ቤተክርስቲያን ትውፊት ጌታ ካረገ በኋላ በ11ኛው ዓመት
አልቆ በ12ኛው ዓመት ላይ ነው፡፡ መጽሐፉ 16 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በይዘቱም የክርስቶስን የኃይል ሥራ
በማጉላት ከጥምቀቱ እስከ እርገቱ ያለውን ታሪክ አውስቷል፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-3 ጥምቀቱ፣ ድውይ መፈወሱ፣ አጋንንት ማውጣቱ
 ከምዕራፍ 4-5 የዘሪው ምሳሌ፣ ነፋሳትን መገሰጹ፣ ሌጌዎን የነበረበት ሰው፣ ደም የሚፈሳትን ሴት
መፈወሱ፣ የምኩራብ አለቃውን ልጅ ከሞት ማንሳቱ
 ከምዕራፍ 6-8 የዮሐንስ ሞት፣ የሐዋርያት በሥልጣን መላክ፣ በረከተ ኅብስት፣ ድውይ መፈወሱና
በቂሳርያ ሐዋርያትን መጠየቁ
 ከምዕራፍ 9-10 ደብረ ታቦር፣ ጋኔን ማውጣቱ፣ የአይሁድ ጥያቄ፣ አይነ ስውሩ በርጠሜዎስ
 ምዕራፍ 11 ሆሳዕና፣ ፍሬ የጠፋባት በለስ፣ ከቤተ መቅደስ ነጋዴዎችን ማስወጣቱ
 ከምዕራፍ 12-13 የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ፣ ትንሳኤ ሙታን፣ ፈሪሳውያንን መገሰጹ
 ከምዕራፍ 14-16 ነገረ ምጽአት፣ ፋሲካ፣ ስቅለቱ፣ ትንሳኤውና እርገቱ

203
Mark
204
ሐዋ 2፡1
205
ሐዋ 12፡12
206
ማር 5፡9፣ 15፡16
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 50
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

3 የሉቃስ ወንጌል207
ሉቃስ ማለት “ሉካኖስ” ማለት ሲሆን ትርጉሙም “መብራት” ማለት ነው፡፡ አንድም ሉቃስ ማለት “ዐቃቤ
ስራይ (ሃኪም)” ማለት ነው፡፡ ለስብከተ ወንጌል ይፋጠናልና አንድም “መበስር (ነጋሪ)” ማለት ነው፡፡ የሉቃስ
ትውልድ ከአህዛብ ወገን ነው፡፡ አገሩ በገድለ ሐዋርያት ድልማጥያ ነው፡፡ ሲል በሌላ ታሪክ ደግሞ አንጾኪያ ነው
ይላል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ከመጠራቱ በፊት የሚያውቃቸው ሙያዎች ነበሩት፡፡ እነዚህም አንደኛው ባለመድኃኒት
/ሐኪም/ ነበር፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ “የተወደደው ባለመድኃኒት” ብሎ መስክሮለታል፡፡208 ሁለተኛው ደግሞ
ሰዓሊ ነበር፡፡ በትውፊት ታሪክ ቅዱስ ሉቃስ ሰዓሊ እንደነበረ እንዲሁም የእመቤታችንን ምስለ ፍቁር ወልዳ
ስዕልንም የሳለው እሱ እንደሆነ ይነገራል “ከወንጌላውያን አንዱ የሆነው ጥበበኛው ሉቃስ ለሳላት ስእልሽ ሰላምታ
ይገባል፡፡” እንዲል መልክአ ስዕል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ በመቄዶንያ ቅዱስ ጳውሎስ ባስተማራቸው ቦታዎች
በተለይም በሮም አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በኔሮን ዘመን ጥቅምት 22 በ84 ዓመቱ በሰማዕትነት አርፏል፡፡
ከዚያም ሥጋውን ወደ ባህር ቢጥሉት እግዚአብሔር ማዕበል አስነስቶ ወደ አንዲት ደሴት አወጣው በዚያም የመነነ
ክርስቲያን አግኝቶ ገንዞ ቀብሮታል፡፡ ወንጌላዊው ከአራቱ ገፀ ኪሩብ በገጸ ላህም ይመሰላል፡፡ ምክንያቱም የጌታን
በከብቶች በረት መወለድ ይጽፋልና፡፡209 ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈበት ቦታ መቄዶንያ በዮናኒ ቋንቋ እንደሆነና
የተጻፈበት ዘመን ጌታ ባረገ 21ኛው ዓመት ተፈጽሞ በ22ኛው ዓመት እንደሆነ መቅድመ ወንጌሉ ያወሳል፡፡
ዘመናዊው ታሪክ ደግሞ ወንጌሉ ቅዱስ ጳውሎስ በቂሳርያ በታሰረበት ጊዜ በዚያው ቦታ በግሪክ/ጽርዕ/ ቋንቋ
እንደተጻፈ ያስረዳል፡፡ ወንጌላዊው ወንጌሉን የጻፈው ለመቂዶንያ ባለሥልጣን ለነበረው ለቴዎፍሎስ እንደሆነ
ገልጧል፡፡210ይህም ሰው በስብከቱ ያመነ ሰው ነው፡፡ ቴዎፍሎስ ማለት የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው፡፡
አንዳንዶች ከዚህ ትርጉም መነሻነት ወንጌሉ የተጻፈው ለአንድ ግለሰብ ሳይሆን የእግዚአብሔር ወዳጅ የተባሉ
ወንጌሉን እንዲያነቡ ለተጻፈላቸው ሰዎች ሁሉ ነው የሚሉም አሉ፡፡ ይህ ግን ስህተት ነው፡፡ ለጊዜው ለዚህ አንድ
ሰው እንደተጻፈ “የከበርክ ቴዎፎሎስ ሆይ” የሚለው ቃል ላይ ያለው መልእክት በቂ ነው፡፡ የሉቃስ ወንጌል
“ወንጌለ አንዕስት” በመባል ይጠራል ምክንያቱም በሌሎች ወንጌላት የማናገኛቸውን የሴቶች ታሪክ በዚህ ወንጌል
እናገኛለን ለአብነትም፡- የእመቤታችንን፣ የቅድስት ኤልሳቤጥን፣ የማርያም እንተ እፍረትን፣ወዘተ… የመሳሰሉትን
ሴቶች ታሪክ የያዘ በመሆኑ ነው፡፡ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ ደጋግሞ ይገልፃልና “ሰባኪ መንፈስ ቅዱስ” ተብሎም
ይጠራል፡፡ እንዲሁም “የአህዛብ ወንጌል” ተብሎም ይጠራል፡፡ ምክንያቱም ለአህዛብ ስለተጻፈ ነው፡፡ እንደ አህዛብ
ልማድም መጽሐፉ ትረካን ከማብዛቱ በተጨማሪ አህዛብ ሱባኤ የመቁጠር ትንቢት የመጠበቅ ልማድ ስለሌላቸው
ከነብያት ትንቢት በብዛት አልጠቀሰም፡፡ ከዚህም ውጪ ወንጌሉ ከጌታ ጽንሰት ጀምሮ እስከ እርገቱ ድረስ ያደረጋቸው
ተአምራትና ትምህርት በስፋት ይገኙበታል፡፡211 መጽሐፉ 24 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 ልደተ ዮሐንስ፣ ብስራተ መልአክ፣ የጌታ ልደትና አስተዳደግ
 ከምዕራፍ 3-5 ማስተማር መጀመሩ፣ የትውልድ ሐረጉ፣ በዲያቢሎስ መፈተኑ፣ በምኩራብ
ማስተማሩ፣ የሌዊ ግብዣ
 ከምዕራፍ 6-7 ድውይ መፈወሱ፣ አጋንንትን ማውጣቱ፣ ትምህርተ ብጹአን፣ የመቶ አለቃውን
ልጅ ማዳኑ፣ የመበለቷን ልጅ ማስነሳቱ፣ የዮሐንስ መልእክተኞች፣ ማርያም እንተ እፍረት
 ምዕራፍ 8 ማርያም መግደላዊት፣ የዘሪው ምሳሌ፣ ነፋሳትን መገሰጹ፣ ጋኔን ማውጣቱ፣ ደም
ይፈሳት የነበረችውን ሴት ማዳኑ፣ የምኩራብ አለቃውን ልጅ ማዳኑ
 ከምዕራፍ 9-14 ተልዕኮተ ሐዋርያት፣ በረከተ ኅብስት፣ ደብረ ታቦር፣ ደጉ ሳምራዊ፣ ማርያምና
ማርታ፣ ጸሎት፣ ፈሪሳውያን፣ ታማኝ መጋቢ የገሊላውያን ጥፋት፣ ሰንበትና መንግስተ ሰማያት
 ከምዕራፍ 15-17 የጠፋው ልጅ፣ ዓመጸኛው መጋቢ፣ አልአዛር ነዳይ፣ 10 ለምጻሞች፣ ነገረ
ምጽአት
 ከምዕራፍ 18-20 ፈሪሳዊና ቀራጭ፣ ዕውር ማብራቱ፣ ዘኪዎስ፣ 10ሩ ባሮች፣ ሆሳዕና፣ የወይን
አትክልት ምሳሌ፣ ትንሳኤ ሙታን፣ የአይሁድ መገሰጽ
 ከምዕራፍ 21-24 ጸሪቀ መበለት፣ ነገረ ምጽአት፣ ፋሲካ፣ ስቅለት፣ ትንሳኤና እርገት

207
Luke
208
ቆላ 4፡14
209
ሉቃ 2፡1
210
ሉቃ 1፡1-4
211
ከወንጌላት ሁሉ ከጌታ ጽንሰት እስከ እርገት የሚገልጥ መጽሐፍ የሉቃስ ወንጌል ብቻ ነው፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 51
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

4 የዮሐንስ ወንጌል212
ዮሐንስ ማለት “ፍስሃ ወሐሴት/ተድላ ደስታ/” ማለት ነው፡፡ አንድም “የእግዚአብሔር ጸጋ (ስጦታ) ነው”
ማለት ነው፡፡ አንድም “ርህራሄ ወሳህል (ሩህሩህ መሐሪ)” ማለት ነው፡፡ አባቱ ዘብዴዎስ እናቱ ማርያም
ይባላሉ፡፡213 ይህ ወንጌላዊ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት ሲሆን ብዙ መጠሪያዎች አሉት፡፡ “የዘብድዎስ ልጅ”፣
“የነጉድጓድ ልጅ”፣ “የጌታ ወዳጅ”(ፍቁረ እግዚእ)፣ “ታዖሎጎስ” (የመለኮት ምስጢር ተናጋሪ ወይም “ነባቤ መለኮት”)
“አቡቀለምሲስ” /ባለራዕይ/ ይባላል፡፡ ለሐዋርያትነት የተጠራውም ከወንድሙ ከያዕቆብ ጋር ዓሣ በማጥመድ ላይ
ሳለ ነበር፡፡214 ቅዱስ ዮሐንስ ያስተማረበት አገር የተለያየ እንደሆነ ይነገራል በመጀመሪያ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር
በኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ በአንጾኪያ ነበር፡፡ ከዚያም ሎዶቅያ አስተምሯል፡፡ ኤፌሶን የነበረውን የአርጤምስ ጣኦተ
አምልኮ በመቃወም ሲያስተምር ተይዞ በድምጥያኖስ ፍርድ በፍጥሞ ደሴት ታስሯል፡፡ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት
ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስ አርፏልም ተሰውሯዋልም ይባላል፡፡ እረፍቱን ሲገልፁ እድሜ ጠግቦ አርጅቶ ነው ይሉታል፡፡
ተሰውሯል የሚሉት ደግሞ በዮሐ 21፡22 ላይ “እስክመጣ ይኖር ዘንድ ብወድስ አንተ ምን አግደህ” ያለውን ቃል
ይዘው ዮሐንስ ሞትን አልቀመሰም የሚሉም አሉ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በገጸ ንስር ይመሰላል፡፡ ምክንያቱም
ንስር እንደሌሎች እንስሳት በእግሩ ይሽከረከራል ከእነርሱ ተለይቶ በክንፍ መጥቆ ይበራል ዮሐንስም እንደወንድሞቹ
ሐዋርያት የሰው ልጅ ከሰማይ ወረደ እያለ ምድራዊ ልደቱን ይናገራል፡፡ ከእነርሱ ለየት ብሎ የሥላሴ አካል
ከሕልውና ተገልጦለት “በመጀመሪያ ቃል ነበር” ብሎ ይናገራል፡፡215 የንስር ዓይኑ ጽሩይ ነው ወደላይ ወጥቶ ረቦ
ቁልቁል በተመለተ ጊዜ የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ሥጋ እንኳን አትሰወረውም ያቺን አንስቶም ይመገባታል
ዮሐንስም ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስና ንጽሐ ልቦና ተሰጥቶት ረቂቅ ምስጢር ተገልጦለት “በመጀመሪያ ቃል ነበር”
ብሎ ተናግሯልና በገጸ ንስር ይመሰላል፡፡ ዮሐንስ ወንጌሉን ራዕይ ባየበትና በጻፈበት በኤዥያን ባህር ውስጥ
በምትገኘው በፍጥሞ ደሴት እንደጻፈው ስንክሳር ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በወንጌል ትርጓሜ መቅድም ላይ ደግሞ
በኤፈሶን እንደሆነ ይገልጣል፡፡ መጽሐፉ በግሪክ/ጽርዕ/ ቋንቋ ወይም በዮናኒ ቋንቋ ጌታ ባረገ በ3ዐኛው ዓመት
ለኤፌሶን ሰዎች እንደተጻፈ ይነገራል፡፡ ወንጌሉ የተጻፈበት ዓላማ የኤፌሶን ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር
ልጅ እንደሆነ ያምኑ ዘንድ እንዲሁም በመናፍቃን ይታወኩ ስለነበር የእነርሱን ትምህርት ለመቃወም ነው፡፡
የዮሐንስ ወንጌል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ ከቅድምናው አንስቶ አስከ ሥጋዊው /ሰው መሆኑ/ ከዚያ
እስከ እርገቱ ድረስ ያለውን ታሪክ እንዲሁም በዘመነ ሥጋዌው የሰራውን ተዓምራት /ሥራ/ እና ያስተማረውን
ትምህርትን ይዟል፡፡ መጽሐፉ 21 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ስለ ቃል ቀዳማዊነት፣ የዮሐንስ ምስክርነት፣ የሐዋርያት መጠራት
 ከምዕራፍ 2-3 የመጀመሪያው ተኣምር፣ ፋሲካ፣ ንቆዲሞስ፣ የዮሐንስ ምስክርነት
 ከምዕራፍ 4-5 ሳምራዊቷ ሴት፣ መጻጉዕ፣ ትንሳኤ ሙታንና ዘላለማዊ ሕይወት
 ከምዕራፍ 6-9 በረከተ ኅብስት፣ የሕይወት እንጀራ፣ የዳስ በዓል፣ ዘማዊቷ ሴት፣ የዓለም
ብርሃን፣ እውር ሆኖ የተወለደው
 ከምዕራፍ 10-13 አንቀጸ አባግዕ፣ የአላዛር መነሳት፣ ማርያም እንተ እፍረት፣ ሆሳዕና፣ ፋሲካ
 ከምዕራፍ 14-16 ስለ ሞቱና ትንሳኤው፣ ስለ እርገቱና ዳግም መምጣቱ፣ ደቀ መዛሙርቱን
ለአባቱ አደራ መስጠቱ
 ምዕራፍ 17 ስለ እግዚአብሔር አብ
 ከምዕራፍ 18-21 ስቅለቱ፣ ሞቱና ትንሳኤው

ምዕራፍ ሁለት
የታሪክ ክፍል
የተወደዳችሁ ተማሪዎች በዚህ ክፍለ ትምህርት ከአዲስ ኪዳን ዘመን መጻሕፍት ሁለተኛ ክፍል የሆነውንና
በውስጡ አንድ መጽሐፍ የያዘውን የታሪክ ክፍል እንመለከታለን፡፡ በውስጡ የሚካተተው መጽሐፍም የሐዋርያት
ስራ ነው፡፡ ሐዋርያት ማለት “ሖረ” ሄደ፣ ተጓዘ፣ ተላከ፣ መሰከረ፣ አስተማረ፣ ወዘተ.... ከሚለው የግዕዝ ግስ

212
John
213
ማቴ 20፡20
214
ማቴ 4፡21፣ ማር 1፡19
215
ዮሐ 1፡1
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 52
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

የተገኘ ሲሆን ታዛዥ፣ ምስክር፣ መምሕር፣ መልእክተኛ ማለት ነው፡፡ይህ ስያሜ የተሰጣቸው ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመረጣቸው 12ቱ ሐዋርያት ናቸው፡፡ እነዚህ ሐዋርያት ወንጌልን በዓለም ዞረው
ያስተምሩ ዘንድ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተላኩ ናቸው፡፡216

1 ግብረ ሐዋርያት /የሐዋርያት ሥራ/217


የሐዋርያት ሥራ “ዜና ሐዋርያት”፣ “ዜና ግብረ ሐዋርያት”፣ “ዜና ልዑንን”፣ “መጽሐፈ ግብረ ልዑንን”፣
“ነቅዕ ንፁህ”፣ “መጽሐፈ አብረክሲስ” ተብሎ ይጠራል፡፡ ይህን መጽሐፍ የጻፈው ወንጌላዊው ሉቃስ ሲሆን የጻፈው
ወንጌሉን ለጻፈለት ለመቄዶንያው መኮንን ለሆነው ለቴዎፍሎስ ነው፡፡218መጽሐፉን የጻፈው ቅዱስ ጳውሎስ በሮም
እስር በቆየባቸው ሁለት ዓመታት ከ58-6ዐ ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ የጻፈበት ቦታም እዛው ሮም ከተማ
ሲሆን የጻፈበት ቋንቋም በጽርዕ ቋንቋ ነው፡፡ የመጽሐፉ ይዘት ከጌታ እርገት በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደሮም
እስከገባበት ጊዜ ያለውን የመጀመሪያይቱን የቤተክርስቲያን ታሪክ የሚናገር ክፍል ነው፡፡ ይህም በዘመን ሲቀመጥ
ከ34 ዓ.ም እስከ 64 ዓ.ም አካባቢ ድረስ ያለውን የ30 ዓመት የቤተክርስቲያን ታሪክ በተለይ በአራቱ ወንጌላቱ
ከተመዘገበው ታሪክ ቀጥሎ ያለውን የመጀመሪያይቱን የቤተክርስያንን ምሥረታና ሕይወት የሐዋርያትን ተልዕኮ
በተለይ የቅዱስ ጳውሎስን ሥራዎችን እንዲሁም የክርስትናን በዓለም ላይ መስፋፋት የሚተርክ መጽሐፍ ነው፡፡
መጽሐፉ የተጻፈበት ዓላማም “እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኳችውን እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው”219 በተባለው መሠረት
ትምህርተ ወንጌል በሐዋርያት አማካኝነት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በሩቅ ላሉ አገሮች እንዴት እንደተዳረሰ ለመግለጥ
ነው፡፡ በይዘቱም ከጌታ እርገት አንስቶ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ እና የመጀመሪያዎቹ ማኀበረ ምዕመናን ሕይወት
እስከ እስጢፋኖስ ሞት በእስጢፋኖስ ሞት የክርስቲያኖች ስደትና በዚያ ምክንያት የወንጌል መስፋፋት እንዲሁም
የቅዱስ ጳውሎስ መጠራት ቤተክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ወደ ቀሪው ምድረ እስራኤልና ወደ አህዛብ አገር መስፋፋት
እንዲሁም የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞዎች በታናሽ እስያ በግሪክና በሮም እንዴት እንደነበር ይገልጣል፡፡ ነገር ግን የሁሉም
ሐዋርያት ታሪክና ሥራ በዚህ መጽሐፈ ተሟልቶ አለተገለጠም፡፡ መጽሐፉ 28 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ስለ ቤተክርስቲያን መሰረት ዕድገት መኖር
 ምዕራፍ 2 ስለጌታ ደቀመዛሙርት ስራ ከጰራቅሊጦስ በፊት
 ከምዕራፍ 3-5 ስለ ጌታ ደቀ መዛሙርት ስራ ከጰራቅሊጦስ በኃላ
 ከምዕራፍ 6-7 ስለቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
 ምዕራፍ 8 ስለ ወንጌል መልዕክተኛው ፊሊጶስ
 ምዕራፍ 9፡1-31 ስለ ሳውል መመለስ
 ከምዕራፍ 13-14 በቅዱስ ጳውሎስ አማካይነት ወንጌል መስፋፋትና የመጀመሪያው ሐዋሪያዊው ጉዞው
 ምዕራፍ 15፡1-35 በእየሩሳሌም ስለተደረገው ጉበዔ
 ከምዕራፍ 15፡36-18፡22 ሁለተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ
 ከምዕራፍ 18፡23-21፡17 ሶስተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ
 ከምዕራፍ 21፡18-23፡22 ስለ ቅዱስ ጳውሎስ መያዝ
 ከምዕራፍ 23፡23- 26፡32 ስለ ቅዱስ ጳውሎስ እስራት
 ከምዕራፍ 27-28 ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ታስሮ ወደ ሮም መሔድ

ምዕራፍ ሦስት
የትምህርት/የመልእክታት/ መጻሕፍት ክፍል
በዚህ ክፍል ቅዱሳን ሐዋርያት ቀደም ብለው ላስተማሯቸውና በተለያዩ ምክንያቶች ላመኑ ምዕመናን
የጻፉት መልእክታት ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ከማረጉ በፊት የተሰጡ የቤተክርስቲያን መመሪያ ትምህርቶች እንዲሁም
በሐዋርያት ጉባኤ /ሲኖዶስ/ የተሠሩ ሥርዓቶች ይካተታሉ፡፡ ይህ ክፍል በውስጡ 21 መጻሕፍትን ያጠቃልላል፡፡

216
ማቴ 10፡2-7
217
Acts
218
ሉቃ 1፡1 ሐዋ 1፡1
219
ማቴ 28፡20
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 53
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 እነዚህ መልእክታት ከተላከላቸው አካላት አንጻር ለ3 ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-


ሀ. የግል መልእክታት፡- በዚህ ክፍል ውስጥ 6 መጻሕፍት ሲገኙ መጻሕፍቱ የተላኩት ለአንድ ግለሰብ
ሆኖ በቅጂ ለሁሉም እንዲዳረስ የሚባዛ ነው፡፡ መጻሕፍቱም 1ጢሞ፣ 2ጢሞ፣ ቲቶ፣ ፊሊሞና፣ 2ዮሐ እና 3ዮሐ
ናቸው፡፡
ለ. የማህበር መልእክታት፡- በዚህ ክፍል ውስጥ 10 መጻሕፍት ሲገኙ መጻሕፍቱ የተላኩት ለአንድ
ቤተክርስቲያን/ማህበር/ የተላኩ ናቸው፡፡እነዚህ መጻሕፍት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ስላለው ሥነ ምግባራዊ
ተጋድሎ የሚያስተምሩ ናቸው፡፡ መጻሕፍቱም ወደ ሮሜ፣ ወደ ቆላስይስ፣ 1ቆሮ፣ 2ቆሮ፣ ገላ፣ ኤፌ፣ 1ተሠ፣
2ተሠ፣ እብራውያን ናቸው፡፡
ሐ. ዓለም አቀፍ መልእክታት፡- በዚህ ክፍል ውስጥ 5 መጻሕፍት ሲገኙ መጻሕፍቱ የተላኩት ለተወሰነ
ማህበር ወይም ለግለሰብ የተላኩ አይደሉም ይልቁኑ በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ምዕመናን (ለሁሉም) የተላኩ
መልእክታት ናቸው፡፡ መጻሕፍቱም 1ጴጥ፣ 2ጴጥ፣ 1ዮሐ፣ የያዕቆብ መልእክት እና የይሁዳ መልእክት ናቸው፡፡

 እነዚህ መልእክታት ከጸሐፊዎቹ አንፃር በ2 መሠረታዊ ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-


ሀ. 14ቱ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት
ለ. 7ቱ መልእክታት ተብለው ይከፈላሉ፡፡

ሀ. የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት


ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያ ስሙ ሳውል ይባል ነበር፡፡ ትርጉሙም “የእግዚአብሔር
ስጦታ/ሐብተ እግዚአብሔር/” ማለት ነው፡፡ ጳውሎስ የሚለውን ስም ያወጣለት ሰርግዮስ ጳውሎስ የተባለ
ባለሥልጣን ነው፡፡ ጳውሎስ ማለት “ብርሃን” ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን በሮም ግዛት በመወለዱ
የሮም ዜግነትን አግኝቶዓል፡፡ አባቱ ዮስአል ይባላል፡፡ ጳውሎስ ፈሪሳዊ ሲሆን ፈሪሳዊ ለመሆን ያበቃውን የኦሪት
ትምህርት የተማረው ገማልያል ከተባለ መምህረ ኦሪት ነው፡፡ ስለዚህም በዘመኑ አግዚአብሔርን ያገለገለ/ያስደሰተ/
እየመሰለው በክርስቶስ የተመሠረተችውን ቤተክርስቲያን ያሳድድ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የመጀመሪያው የሐዲስ
ኪዳን ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲገደል እንኳን ተባባሪ የነበር ሠው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ምርጫና
በእስጢፋኖስ ጸሎት በድንቅ ተዓምር ለዚህ ታላቅ የሐዋርያነት ሥራ ተጠርቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ባለው ዘመኑ ለ42
ዓመታት በዚህ አገልግሎት ብዙ መከራን የተቀበለ ሐዋርያ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ 3 ሐዋርያዊ ጉዞዎችን
የተገዘ ሐዋርያ ነው፡፡ በሦስቱ ጉዞዎቹ አብዛኛውን የመካከለኛውን ምሥራቅና አውሮፖን አስተምሯል በወገኖቹ
በአይሁድ ብዙ መከራ ደርሶበታል ሁለት ጊዜ በሮም ሀገር ታስሯል፡፡ ከዚህም ሌላ በተለያዩ ቦታዎች መከራ
ተቀብሏል፡፡ በዚህ ሁሉ ተጋደሎ ወንጌልን ለአብዛኛው ክፍለ ዓለም አድርሷል፡፡ በመጨረሻም በዘመነ ኔሮን ቄሳር
ሐምሌ 5 ቀን 67 ዓ.ም በሮም አደባባይ በሰማዕትነት አርፏል “ኦስትያን ጉዳና” በተባለ ቦታም ተቀብሯል፡፡ ቅዱስ
ጳውሎስ መልእክታት 14 የፃፈ ሲሆን ከዚህ ቀጥለን በዝርዝር እናያለን፡፡

1 ወደ ሮሜ ሰዎች የተላከ መልእክት220


ሮም ጥንት ከጥፋት ውኃ በፊት /በዘመነ ኖህ/ “አርስጣጣሊስ” ትባል ነበር ከጥፋት ውሃ በኋላ
የምትታወቀው “እንጣሎስ” የተባለ ኃይለኛ ንጉስ ነግሶባት በአንጣሎስ ኢጣሊያ ተብላለች፡፡ በኋላም “ሮሙላስና”
“ሮማኖስ” የሚባሉ ወንድማቾች ነግሠውባት በእነዚህ ሰዎች “ሮምያ” “ሮማ” ተብላለች፡፡ ይህች ሀገር ዛሬ በአውሮፖ
አህጉር የምትገኝ ናት፡፡ መልእክቱ በተጻፈበት ዘመን ይኖሩባት የነበሩ ሰዎች የሀገሪቱ ተወላጆች /አህዛብ/ ብቻ
ሳይሆኑ በፍልሰት በስደትና በተለያየ ምክንያቶች የገቡም አይሁድ ይኖሩባት ነበር፡፡ የአዲስ ኪዳን መግቢያ ጊዜም
አብዛኛውን ዓለም ትቆጣጠር የነበረች ሀገር ናት፡፡ በዘመነ ክርስትና በዚህች ሀገር ይኖሩ የነበሩ አይሁድ ለበዓል
ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጡ በበዓለ ሃምሣ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደላቸው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ካመኑ
3ሺህ ሰዎች መካከል እነዚህ የሮም ሰዎች /አይሁድና አህዛብ/ አብረው ነበሩ፡፡ ይህንን እምነታቸውን ወደ ሀገራቸው
ሲመለሱ ለሌሎችም አስተምረው ነበር፡፡ ከዚህም ጋር ከሐዋርያት መካከል ለማስተማር ለቅዱስ ጴጥሮስ እጣው
ደርሳው ነበር፡፡ እርሱም ሄዶ ሲያስተምር አይሁድም አህዛብም በአንድነት አመኑ ተጠመቁ ትምህርቱ ካልደረሰበት
ለማድረስ ወጥቶ ሲሄድ ሁለቱም የቀደመ ሕይወታቸውን እያነሱ ይለያዩ ይወጋገዙ ጀመር አይሁድ በአብርሃም

220
Romans
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 54
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ልጅነታቸው በኦሪታቸው እየተመኩ አህዛብን ሲነቅፉ አህዛብ ደግሞ አየሁድ እግዚአብሔርን እያወቁ መበደላቸውን
እርሱ/አህዛብ/ ቢያጠፉም ባለማወቃቸው መሆኑን እያነሱ የአንዲት ቤተክርስቲያን ልጆች በማይረባ ነገር
ተለያይተው ሲኖሩ ይህን ያስተዋሉ አቂላና ጵርስቅላ የተባሉ ባልና ሚስት ፌቨን የተባለች እናት ይህንን ችግር
ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ በወጣ ጊዜ ነገሩት ሁለቱንም አህዛብንም አይሁድንም ለማስታረቅ ሁለቱም የዳኑት
በእግዚአብሔር ቸርነት መሆኑን ለማስረዳት በሃይማኖት በምግባር ለማጽናት አይሁድ በኦሪታቸው መመካታቸውን
አህዛብም ባለማወቅ ማመካኘታቸውን ትተው በወንጌሉ ተመስርተው በሃይማኖት እንዲጸድቁ ለማስተማር በ52
ዓ.ም ጽፎ የክንክራኦስ ቤተክርስቲያንን በምታገለግል በፌቨን እጅ ልኮላቸዋል፡፡ መልእክቱን እርሱ ቢልከውም
የጻፈው ጠርጥዮስ የተባለ ሰው ነው፡፡ መልእክቲቱ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት መረጃነት የተጻፈች ጥቅል ትምህርት
የምትሰጥ ናት፡፡ በአጻጻፋም ከእብራውያን መልእክት ጋር ይመሳሰላል፡፡ የመልእክቱ ይዘትና አከፋፈልም፡-
 ከምዕራፍ 1፡1-17 የመግቢያ ሰላምታ
 ከምዕራፍ 1፡18-3 ስለ አረማውያን፣ ስለአይሁዳውያንና ስለ እግዚአብሔር ጽድቅ
አስፈላጊነት
 ከምዕራፍ 4-5 የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሰው በእምነት የሚገኝ ስለ መሆኑ
 ከምዕራፍ 6-8 ሰው በጽድቅ ሕይወት የሚኖር ከሆነ ኃጢአት ከህግና ከሞት ነፃ ስለመሆኑ
 ከምዕራፍ 9-11 ስለ እስራኤል መመረጥና ተስፋ
 ከምዕራፍ 12፡15-16 ስለ ክርስቲያኖች በዓለም፣ በግልና፣ በቤተክርስቲያን መኖር
 ምዕራፍ 16 ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ሰላምታ፣ የአደራ ምስጋና ጸሎት

2 የመጀመሪያይቱ የቆሮንጦስ መልእክት221


ቆሮንቶስ የምትገኘው በግሪክ ውስጥ ሲሆን የአካይያ ሁለተኛ ከተማ ናት፡፡ ይህችን ቤተክርስቲያን
የመሠረታት ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚህች ከተማ በሁለተኛው ጉዞ በ5ዐ ዓ.ም አካባቢ ገብቶ
አስተምሮበታል፡፡ በ54 ዓ.ም አካባቢ ደግሞ ጢሞቲዎስን ልኮላቸዋል፡፡ ይህችን መልእክት የጻፉት በኤፌሶን እያለ
ነው የጻፈበት ዓመት በ54 ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡ መልእክታቱን ያደረሱት እስጢፋኖስ፣ ፈርዶናጥስ፣ ጢሞቲዎስ
እንዲሁም በአካይቆስ እጅ ልኳል፡፡ ይህችን መልእክት የጻፈበት ምክንያቶች፡-
ሀ. ቅዱስ ጳውሎስ አስተምሯቸው ከሄደ በኋላ በአቄላ አማካኝነት ቅዱስ ጳውሎስ ያጠመቀው የኦሪት ሊቅ
የነበረው አጵሎስ ብሎይን ከሐዲስ እያስማማ ቢያስተምራቸው ብዙ ሰዎች አመኑ በዚህች ቤተክርስቲያን ጌታ
ያደረገውን ተአምራት ያስተማረውን ትምህርት የተካፈሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ ከዚህም ሌላ በበዓለ ሃምሣ ከቅዱስ ጴጥሮስ
ተምረው ያመኑ ምእመናን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሁሉ በተማሩት ትምህርት መጽናት ሲገባቸው “እኔ የጳውሎስ ነኝ እኔ
የኬፋ ነኝ” አያሉ መከፋፈል በመጀመራቸው ይህንን ትተው ሁሉም በክርስቶስ አንድ ሁነው እንዲኖሩ ለመምከር
ለ. የቆሮንቶስ ሰዎች በዝሙት ኃጢአት ይጠቁ ነበር አባታቸው እንኳን በሕይወት እያለ የአባታችውን
ሚስት ያገቡ ነበር፡፡ ይህንን ክፉ ሥራቸውን ትተው በንጽህና እንዲመላለሱ ለመምከር
ሐ. ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ውጪ ሴቶች ሳይከናነቡ እየጸለዩ በጉባኤ እናስተምር እያሉ በማስቸገራቸው
ሥርዓት ይዘው እንዲጓዙ ለመምከር
መ. የቆሮንቶስ ሰዎች የነበሩበትን የአምልኮ ጣዖት ልማድ ወደ ቤተክርስቲያን ለማምጣት መከሩ እንዲሁም
ለቤተክርስቲያን አስራት በኩራት ማውጣት ያልቻሉ ክርስቲያኖች ሥጋ ወደሙ እንዳይቀበሉ ከለከሉ ራሣቸውም
የቁርባኑን ሥርዓት እያበላሹ ከቁርባኑም በኋላ እየበሉ እየጠጡ እየሰከሩ እየተደባደቡ ሌላው እየራበው ወደ ቤቱ
ይመለስ ነበር፡፡ በዚህ ሥራቸው ወቀሳቸው የቁርባንንም ክብር አስረዳቸው
ሠ. ሰው በትዳር ወይም በድንግልና መኖር እንደሚገባው ለጠየቁት ጥያቄ እግዚአብሔር እንደሰጣቸው
ፀጋ እንዲኖሩ ነገር ግን የሚበልጠው እንደርሱ በድንግልና በብቸኝነት መኖር እንደሆነ ለማስረዳት
ረ. በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ቅናት ስለሚቀኑ መቀናናታቸውን ትተው ሁሉም በተሰጣቸው ጸጋ
እንዲያገለግሉ
ሰ. ትንሣኤ ሙታን መኖሩን የማያምኑ ሰዎችም ስለነበሩ ትንሣኤ መኖሩን ካላመኑ በከንቱ እንደሚከደክሙ
ነገር ግን ትንሣኤ ሙታን እንዳለ ካስረዳ በኋላ ትንሣኤ ስለመኖር የክርስቶስ ትንሣኤ ማስረጃ እንደሆነና ይህም
ታላቅ ምሥጢር እንደሆነ ለማስረዳት እና ለሌሎችም ችግሮቻቸው መፍትሔ ለመስጠት ጽፏል፡፡

221
1 Corinthians
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 55
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

መጽሐፉ 16 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን አከፋፈሉም፡-


 ከምዕራፍ 1-4 በመካከላቸው ስለተነሳው ክርክር
 ምዕራፍ 5 በመካከላቸው ስለተነሳው ዝሙት
 ምዕራፍ 6 በመካከላቸው ስለተነሳው ሙግት
 ምዕራፍ 7 ስለ ጋብቻ
 ከምዕራፍ 8-10 ለጣዖት ስለተሰዋ ሥጋ
 ምዕራፍ 11 ስለ ቅዱስ ቁርባን
 ከምዕራፍ 12-14 ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች
 ምዕራፍ 15 የሙታን ትንሳኤና የጌታ ምጽአት
 ምዕራፍ 16 የተቸገሩትን መርዳትና እንደሚገባ ስለግል ሕይወቱ

3 ሁለተኛይቱ የቆሮንጦስ መልእክት222


ሁለተኛይቱን መልእክት የጻፈው መቄዶንያ እያለ ሲሆን የመጀመሪያዋ መልእክት በተጻፈች በዓመቱ /በ55
ዓ.ም /ተጽፋለች፡፡ መልእክቲቱን ያደረሰው ደቀ መዝሙሩ ቲቶ ነው፡፡ ይህች መልእክት 13 ምዕራፎች አሏት፡፡
ይህች መልእክት የተጻፈችበትም ምክንያት፡-
 በመጀመሪያው መልእክቱ ምን ያህል እንደተማሩ ለማወቅ ቲቶን ልኮ ነበር፡፡ ቲቶም በመጀመሪያው
መልእክት ወቀሳ እጅግ እንዳዘኑ ከጥፋታቸውም ተመልሰው በመልካም ሥራ ለችግረኞች
በሚሠጠውም ምጽዋት በርትተው እንደሚሳተፉ ሲነግረው በዚህ ነገር እንዲጸኑ ለመምከርና
ለማበረታታት ያልተመለሱትንም እንዲመለሱ ለመምከር
 ሀሰተኞች መምህራን ገብተው በሐሰትና ባለፈ የኦሪት ትምህርት እየበጠበጡ እንደሆነ ስለነገረው
ከሐሰተኞች መምህራን እንዲጠበቁ ለማስጠንቀቅ
 ለችግረኞች የሚደረገውን ስጦታ በልግስና እንዲያዘጋጁና እንዲጠብቁት ለማሳሰብ ጽፎላቸዋል፡፡

4 ወደ ገላትያ ሰዎች የተላከ መልእክት223


ገላትያ በታናሽ እስያ ውስጥ ከሚገኙ ግዛቶች አንዷ ነች፡፡ ዛሬ የቱርክ ዋና ከተማ አንካራ አካባቢ ትገኛለች፡፡
ገላትያ የተባለችው በመጀመሪያ ይኖሩ በነበሩ “ጉዋል” የተባሉ ሰዎች ስም ነው፡፡ የገላትያን ቤተክርስቲያን
የመሠረታት ቅዱስ ጳውሎስ ነበር፡፡ በመጀመሪያው ጉዞው እና በሦስተኛው ሐዋርያዊው ጉዞ ላይ ገብቶ
አስተምሮባታል፡፡ አስተምሮ ከወጣ በኋላ አይሁድ ገብተው ወንጌል ያለ ኦሪት ጥምቀት ያለግዝረት አትጠቅምም
ብለው ያወጁ ጀመር ለዚህ መልስ ይሆን ዘንድ መልዕክቱን ጽፎታል፡፡ ከዚህም ሌላ ቅዱስ ጳውሎስን “እንደ ሌሎች
ሐዋርያት ጌታን አላየምና ክብሩ ያነሰ ነው ከክርስቶስ ሐዋርያት አይቆጠርም ስለዚህ ትምህርቱን ልትቀበሉ
አይገባም” ይሉ ስለነበር በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደተጠራ ከዚህም ሌላ ጌታን እንዳየ ከሌሎቹ ሐዋርያትም
እንደማያንስ ካስረዳ በኋላ እነዚህን ሐሰተኞች መምህራን እንዳይቀበሉ በማዘዝ ጻፈላቸው፡፡ የገላትያ መልእክት
በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነትና ክብር በስፋት ስለምትናገር “የነፃነት መልእክት”
እየተባለች ትጠራለች፡፡ መጽሐፉ ስለተጻፈበት ዘመን የተለያየ አስተያየት ቢኖርም ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሁሉ
አስቅደማ በመጀመሪያ እስራቱ ላይ ሮም ሀገር እያለ በ48 ዓ.ም አካባቢ ተጽፋለች፡፡ መጽሐፉ 6 ምዕራፎች ሲኖሩት
አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-2 እውነተኛ ሐዋርያነቱን ያረጋገጠበት
 ከምዕራፍ 3-4 ከሕግ ባርነት ነፃ የወጡ መሆናቸውን
 ከምዕራፍ 5-6 ተገቢ የአኗኗር ሥርዓት ያላቸው ይሆኑ ዘንድ

222
2 Corinthians
223
Galatians
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 56
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

5 ወደ ኤፌሶን ሰዎች የተላከ መልእክት224


ኤፌሶን በታናሽ እስያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን ዛሬ የግሪክ ግዛት ናት፡፡ ይህች ጥንታዊ ከተማ በንግድ
ማዕከልነት ከመታወቋም ሌላ አርጤምስ ለምትባል ጣኦት በተሰራው ቤተ ጣዖት ትታወቃለች፡፡ ታላቁ
እስክንድር ዳርዮስን ድል አድርጐ የግሪክ ግዛት አደረጋት ሮማውያን በገነኑበት ዘመን ደግሞ የሮም ግዛት ሆና
ነበር፡፡ በዚህም ወቅት አይሁድ በስደትና በንግድ ምክንያት ሄደው ምኩራብ ሠርተውባት ይኖሩ ነበር፡፡ በ46
ዓ.ም ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያው ጉዞ እንዲሁም በ5ዐ ዓ.ም አስተምሮባታል፡፡ በኋላም የአርጤምስን አምልኮ
ለማስቀረት የሚያስችል ትምህርት እያስተማረ ብዙ ሰዎችን ሲመልስ የተመለከቱ የጣዖት ካህናትና የአርጤምስ
ምስል ቀራጮች ህዝቡን በማነሳሳት ቅዱስ ጳውሎስን አስወጥተውታል፡፡ ለቀሩትም ጢሞቴዎስን ሊቀጳጳስ
አድርጎ ሾሞላቸዉ ሄዷል፡፡ ኋላም ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ አስተምሮባታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በ58 ዓ.ም
ከኢሩሳሌም ወደ ሮም ተይዞ በሄደበት ጊዜ መልእክቱን ጽፎ በደቀመዝሙሩ በቲቶ እጅ ልኮላቸዋል፡፡ በምግባር
በሃይማናት መጽናታቸውን ሰምቶ ሊያመሰግናቸውና አህዛብም ሆኑ እስራኤል አንድ ሆነው የጸጋው ተካፋይ
በመሆናቸው እምነታቸውን አጠንክረው እንዲይዙ ለማበረታታት ከዚህም ሌላ ወደቀድሞ ኃጢአታቸው /አምልኮ
ጣዖታቸው/ የተመለሱትን ለመውቀስ በመጨረሻም መንፈሳዊ እንደመሆናቸው የሰይጣን ፈተና እንዳያሸንፋቸው
ሰይጣንን ድል የሚነሱበትን መንገድ ጽፎላቸዋል፡፡ የኤኤሶን መልእክት ከወቀሳና ከተግሳጽ ነፃ የሆነ ትምህርትን
ያዘለች ትምህርት ናት፡፡ በውስጡ የሥነ ምግባርና የሃይማኖት ትምህርት ያዘለ ነው፡፡ መጽሐፉ 6 ምዕራፎች
ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-3 እግዚአብሔር ለህዝቡ ያቀደው እቅድ
 ከምዕራፍ 4-6 ለምዕመናን የሚገባ ኑሮ

6 ወደ ፊልጵስዮስ ሰዎች የተላከ መልእክት225


ይህች ከተማ የተመሰረተችውም በታላቁ እስክንድር አባት በፊሊጶስ በ358 ዓ.ም ዳግመኛ የተቆረቆረች
የመቄዶንያ (ግሪክ) መዲና ናት፡፡ ሮማውያን ግሪካውያንን ባሸነፉ ጊዜ የሮም ከተማ ሆነች፡፡ ልድያ የተባለችው
የሐር ነጋዴ የወንጌልን ቃል ሰምታ ክርስትናን የተቀበለችው በዚች ከተማ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
በመጀመሪያ ጉዞው በዚች ከተማ ገብቶ አስተምሮ አፍሮዲጡን ሾሞላቸዋል እነሱም በ58 ዓ.ም በሮም እስር ቤት
ሳለ በአፈሮዲጡ እጅ ስጦታ ላኩለት በዚህም በመከራ ጊዜ የማይረሱት ልጆች ስላገኘ ተደስቶባቸዋል፡፡ መልእክቱንም
በሚከተሉት ምክንያቶች ጽፏል፡፡
 በአፍሮዲጡ እጅ ስለላኩት ስጦታ ምስጋና ለማቅረብ
 የቅዱስ ጳውሎስን መታሰር የሰሙ የሐሰት መምህራን ለአፎሮዲጡ አንታዘዝም ከማለታቸው
በተጨማሪ እኛ እራሳችን እናስተምራለን እናጠምቃለን እያሉ ስለአስቸገሩ ክርስቶስን አብነት
እንዲያደርጉ ስለ እውነት ብለው እንዲሰሩ ለማስተማር
 አይሁድም ላመጡት የኦሪት ትምህርት መልስ ለመስጠት
በመጨረሻም ጢሞቴዎስን እንደሚልክላቸውና እርሱም ስለሚፈታ በቶሎ እንደሚመጣ ገልጦ በዚያው
በእስር ቤት እያለ በ58 ዓ.ም ጽፎ በአፍሮዲጡ እጅ ልኮላቸዋል፡፡ መጽሐፉ 4 ምዕራፎች ያሉት ሲሆን አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ስለ ቤተክርስቲያን ፅናትና ስለ ሐውርያው ግላዊ ህይወት
 ከምዕራፍ 2፡1-18 አንድነታቸውን ያፀኑ ዘንድና ጌታን እንዲመስሉ መታዘዛቸው
 ከምዕራፍ 2፡19-30 ስለጢሞቲዋስና አፍሮዲጡ መላክ
 ምዕራፍ 3 ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ጌታ የስጋን ረብ ሁሉ መተው
 ከምዕራፍ 4፡1-7 ኤድያንና ሴንጤኪን በአንድ ሀሳብ እንዲስማሙ የጻፈው ምክር
 ከምዕራፍ 4፡8-23 ስለተላከለት ስጦታ

224
Ephesians
225
Philippians
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 57
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

7. ወደ ቆላስይስ ሰዎች የተላከ መልእክት226


ቆላስይስ በታናሽ እስያ ውስጥ የምትገኝ የፍርግያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ከተማዋ መንገድ ዳር ስለተመሰረተች
የምትታወቀው በንግድ ከተማነቷ ነው፡፡ በተለይም በበግ ጸጉር ንግድ በጣም ታዋቂ ከተማ ናት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ
ወደዚህች ከተማ ገብቶ አላስተማረም ነገር ግን ደቀመዝሙሩን “ኤጳፍራስን” ልኮ እንዲማሩ ቢያደርጋቸው አምነው
ተጠምቀዋል፡፡ ከዚህም ሌላ የፊልሞናና የአቅርጳስ አገር ስለሆነች እነዚህ ሰዎችም አስተምረውባታል፡፡ በፊልሞና
ርስት ላይም ቤተክርስቲያን ተሰርታ ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከፊልጵስዮስ ወጥቶ ሲሄድ ኤጳፍራስም ለቆላስይስ
ክርስቲያኖች አክርጳስን ሾሞላቸው ቅዱስ ጳውሎስን ተከትሎ ሄዷል፡፡ ከዚህ በኋላ የኤጳፍራንስ መሄድ ያዩ የሐሰት
መምህራን አይሁድ “እናንተ ከአክርጳስ ከአጳፍራስ ከጳውሎስ የተማራችሁት ትምህርት የቅጂ ቅጂ ስለሆነ
ሃይማኖታችሁ የቀና አይደለም ከዚህም ሌላ ወንጌል ያለ ኦሪት ጥምቀት ያለ ግዝረት አትረባም” እያሉ ያወኳቸው
ጀመር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ሰምቶ እርሱ ራሱ መምህራቸው እንደሆነ ለማወቅና ለአይሁድ የሐሰት ትምህርት
እንዳይንበረከኩ ለማዘዝ ጽፎላቸዋል፡፡ በተጨማሪም በመካከላቸው ለሚገኙ ፈላስፎች መልስ ተግሳጽ የሚሆን
የእግዚአብሔርን አዳኝነትና ማንነት ለመግለጽ ስለማህበራዊ ኑሮአቸውም ባልና ሚስት የልጆች በአጠቃላይ
የመንፈሳዊ ሰው ጠባያት ምን መሆን እንደሚገባው ጠቅሶ በሮም ወህኒ ቤት በመጀመሪያ እስሩ ላይ እያለ በ58
ዓ.ም ጽፎ በቲኪቶስና በአናሲሞስ እጅ ላከላቸው፡፡ የቆላስያስ መልእክት 4 ምዕራፎች ሲኖሯት አከፍፈሏም፡-
 ከምዕራፍ 1፡1-8 የመግቢያ ሰላምታ
 ከምዕራፍ 2፡8-23 በክርስቶስ ስም አታለው እንዳይማርኳቸው የጻፈው ማሳሰቢያ
 ከምዕራፍ 3፡1-17 ስለ ሥነ-ምግባር የጻፈላቸው ትምህርት
 ከምዕራፍ 4፡1-18 ማጠቃለያ

ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች የተላኩ መልእክታት


ተሰሎንቄ የቀድሞ ስሟ “ቩማር” ይባል ነበር፡፡ “ቩማር” ማለት ፍል-ውሀ ማለት ነው፡፡ በኋላም ክሳንደር
የተባለው ገዢ በሚስቱ በሰሎኒቃ ተሰሎንቄ ብሏታል፡፡ ሰሎኒቃ የታላቁ እስክንድር እህት ነች፡፡ ይህች ከተማ
የመቄዶንያ ወደብና የንግድ ቦታ ነበረች፡፡ በ5ዐ ዓ.ም ቅዱስ ጳውሎስ አስተምሮባታል፡፡ ነገር ግን የአይሁድ ምኩራብ
ውስጥ ሲያስተምር ኦሪታችንን ሊያሳልፍብን ነው በሚል ፍርሀት ተቃወሙት በዚህም ተሰሎንቄን ለቆ ወደ ቤርያ
ሄደ፡፡ በዚያ ሲያስተምር ተከትለው ተቃወሙት በዚህ ምክንያት ምዕመናን ወደ አቴና ላኩት፡፡ ከዚህ በኋላ
ጢሞቲዎስን እንዲጐበኛቸው ልኮታል፡፡

8. ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች የመጀመሪያው227


ይህች መልእክቱን በሚከተሉት ምክንያቶች ጽፏታል፡-
 ስለሞቱ ሰዎች እንደአረማውያን ተስፋ እንዳይቆርጡ እና ከሃይማኖት እንዳይወጡ ስለ እግዚአብሔር
ብለው የሞቱት እንኳን ተስፋ ትንሣኤ እንዳላቸው ለማስረዳት
 እርስ በርሳቸው የተፋቀሩ መስሏቸው ሚስት ይዋዋሉ ስለበር ከዚህ ክፉ የዝሙት ሥራ እንዲለዩ
ሊያስተመራቸው
 ያለን ይበቃናል ብለው ሥራ መስራት ስለተው ፈተና ውስጥ እንዳይገቡ ሥራ በመስራት እንዲኖሩ
 በሃይማኖታቸው በፍቅራቸው በመጽናናታቸው ደስታውን ለመግለጽ እና ለማጽናናት የጌታ አመጣጥ እንደ
ሌባ ድንገት ስለሆነ ከጨለማ ሥራቸው ተለይተው በመልካም ሥራ ጸንተው እንዲኖሩ ለማሳሰብ

ይህች መልእክት 5 ምዕራፎች ሲኖራት በአቴና ሳለ በ5ዐ ዓ.ም ጽፎ በስልዋኖስ እና በጢሞቴዎስ እጅ


ልኮላቸዋል አከፍፈሏም
 ምዕራፍ 1 ሐዋርያው ለቤተክርስቲያኒቱ ያቀረበው ምስጋና
 ከምዕራፍ 2-3 ለቤተክርስቲያኒቱ የነበረው ስጋትና ገድሉ
 ከምዕራፍ 4፡1-12 ስለ ምዕመናን ቅድስናና ፍቅር
 ከምዕራፍ 4፡13-5፡11 ስለ ጌታ ዳግም ምጽዓት

226
Colossians
227
1 Thessalonians
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 58
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ከምዕራፍ 5፡12-28 ስለ ምዕመናን በህብረት መኖርና ልዩ ልዩ ምክሮች

9. ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ሁለተኛው228


ይህች መልእክት የተላከችው በመጀመሪያይቱ መልእክት የተጠቀሰውን229 “እኛ ህያዋን ሆነን” የምትለውን
ቃል ይዘው ምጽአት በእነ ቅዱስ ጳውሎስ ዘንድ ይደረጋል፡፡ እያሉ በሐሰት ትምህርት ህዝብን የሚያሸብሩ ሰዎች
ስለ ነበሩ እነዚህ ሰዎች የሚሉት ሐሰት እንደሆነና ከምጽአት በፊት የሚደረጉ ትንቢቶች ሳይፈፀሙ ምጽአት
እንደማይደረግ ለማሳሰብ ነው፡፡ በተጨማሪም በመካከላቸው ሥራ ሳይሰሩ በሰው ላብ ሊመገቡ የሚያስቡ ሰነፎች
ሰዎች ስለ ነበሩ ከእነርሱ እንዲለዩ እነዚህም ሰዎች በራሣቸው ላብ ለፍተው እንዲኖሩ ለማሳሰብ ጽፎታል፡፡ ይህች
መልእክት ሦስት ምዕራፎች ሲኖራት በ51 ዓ.ም ጽፎ በጢሞቴዎስና በስልዋኖስ እጅ ልኮላቸዋል፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1፡1-4 የመግቢያ ሰላምታ
 ከምዕራፍ 1፡6-1ዐ ሰለ ዳግም ምጽአት
 ከምዕራፍ 2፡15-3፡14 ያስተማረውን ሥርዓት እንዲጠብቁ ለማሳሰብ
 ከምዕራፍ 3፡16-18 የማጠቃለያ ትምህርት

ወደ ጢሞቴዎስ የተላኩ መልእክታት


ጢሞቴዎስ አገሩ ደርቤን ልሰጥራ ሲሆን አባቱ ግሪካዊ እናቱ አይሁዳዊት ናቸው፡፡ በመጀመሪያ ወንጌልን
ከእናቱና ከዘመዶቼ እንዲሁም በደርቤን ይኖሩ ከነበሩ ክርስቲያኖች ተምሯል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም
ስለአይሁድ ፅናት ገዝሮ አስከትሎታል፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጳውሎስን በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ አብሮ ረድቶታል፡፡
ወንጌልን በማስተማር፣ መልእክት በማድረስ፣ በእስራቱ በችግሩ ጊዜ በመርዳት አገልግሎታል፡፡ ጢሞቴዎስ ቅዱስ
ጳውሎስ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ በቅርብ ሲያገለግለው ቆይቷል ቅዱስ ጳውሎስ ካረፈ በኋላ ወደ ሀገረ ስብከቱ ወደ
ኤፌሶን ተመልሶ ለ33 ዓመታት በአባትነት አገልግሎ በ97 ዓ.ም በአረማውያን እጅ ተደብድቦ በሰማዕትነት አርፏል፡፡

፲ የመጀመሪያይቱ መልእክት/1ኛ ጢሞቴዎስ/230


ቅዱስ ጳውሎስ በሕይወት እያለ ለጢሞቴዎስ ከጻፈለት መልእክት የመጀመሪያዋ የተጻፈችው ጢሞቴዎስን
የኤፌሶን ሊቀ ጳጳስ አድርጐ ሾመት ስለነበር ጳጳሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን የሚሾምበት ምዕመናንን
የሚመራበትና የሚያስተዳድርበት ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሚያስጠብቅበትን የክህነት ሥራ /ትምህርተ ኖሎት/
ለማስተማር ሲል ነው፡፡ ከዚህም ሌላ በዘመኑ ለተነሱ መናፍቃን /ግኖስቲኮች/ ትምህርት መቃወሚያ የሚሆን
ትምህርት ሊያመለክተው በአፌሶን ገብተው ከሚበጠብጡ የሐሰት መምህራን እንዲጠበቅ በአጠቃላይ ሊኖረው
ስለሚገባው መንፈሳዊ ሕይወት፣ ከምን ዓይነት ሰዎች ጋር መኖር እንዳለበት፣ እንዴት መኖር እንዳለበት እንዲሁም
ለምዕመናን ጥሩ ምሣሌ መሆን እንዳለበት ለማስተማር ሰፋ ያለ ምክር ጽፎለታል፡፡ ይህ መልእክት 6 ምዕራፎች
ሊኖሩት በ6ዐ ዓ.ም ተጽፎ በቲቶ እጅ ተልኮለታል፡፡ አከፋፈሉም፡፡
 ከምዕራፍ 1፡1-2 የመግቢያ ሰላምታ
 ከምዕራፍ 3፡1-6፡19 ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ትምህርተ /ኖሎት/ ስለ ቤተክርስቲያን አመራር
 ከምዕራፍ 6፡2ዐ-21 ማጠቃለያ

፲1. ሁለተኛይቱ መልእክት/2ኛ ጢሞቴዎስ/231


ይህችን መልእክት በ66 ዓ.ም ከሮም እስር ቤት /በ2ኛ እስሩ ላይ ሆኖ/ ጽፎ በአንክሮሎስ እጅ ሰዶለታል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ይህችን መልእክት የጻፈበት ምክንያት፡-
 ጢሞቴዎስ ለተማሪዎቹ በሃይማኖታቸው ምክንያት መከራ ይጸናባቸው ስለነበር ለማጽናናት ለመምከር
ለማበረታታት

228
2 Thessalonians
229
1ተሰ 4፡17
230
1 Timothy
231
2 Timothy
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 59
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ከምዕመናን ብዙዎቹ ትምህርቱን ሳይቀበሉ ወደ ክህደትና ወደ ቀድሞ ጣዖታቸው ስለተመለሱ


የመጣበትን ተስፋ መቁረጥ ለማራቅና ለማጽናናት
 ለራሱ በጎ ተጋድሎ እንዲጋደል ምዕመናንን ሳይፈራ እንዲያስተምር ምዕመናንም አረማውያን
ከማያመጡት መከራ የተነሳ እንዳይከፋፈሉ የመንግሥተ ሰማያትንም ተስፋ እየነገረ እንዲያጽናናቸው
ለማሳሰብ
 በመጨረሻም ቅዱስ ጳውሎስ ከእረፍቱ በፊት እርሱና ማርቆስን ሊያያቸው ስለናፈቀ እንዲመጡና
ሌሎችንም ነገሮች ለማሳሰብ ጽፎለታል፡፡
ይህ መልእክት 5 ምዕራፎች ያሉት አከፋፈሉም
 ከምዕራፍ 1፡1-7 የመግቢያ ሰላምታ
 ከምዕራፍ 1፡8-2፡7 ለጢሞቲዎስ የጻፈለት የአገልግሎት ትምህርት
 ከምዕራፍ 4፡6-13 ከመሞቱ በፊት እንዲመጣለት የጻፈው ቃል
 ከምዕራፍ 4፡19-22 ማጠቃለያ

፲2 ወደ ቲቶ የተላከ መልእክት232
ቲቶ የተወለደው በቆሮንቶስ ሲሆን አባቱና እናቱ ግሪካውያን ናቸው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን የተከተለው
በአንፆኪያ ነው፡፡ ከጢሞቴዎስ ጋር ቅዱስ ጳውሎስን በትምህርት፣ በመልእክተኛነት፣ በመከራው ጊዜ ሁሉ
ረድቶታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “በሃይማኖት ኀብረት እውነትኛ ልጄ” ብሎ ይጠራዋል፡፡233ብቃቱንም አይቶ የቀርጤስ
ሊቀ ጳጳስ አድርጐ ሾሞታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ካረፈ በኋላ ወደ ሀገረ ስብከቱ ተመልሶ ሲያገለግል ቆይቶ በ94
ዓመቱ አርፏል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ መልእክቱን የላከበት ምክንያት የቀርጤስ ሊቀ ጳጳስ አድርጎ ስለሾመው ካህናትን
የሚሾምበት፣ ሕዝቡን የሚመራበት፣ ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድርበት ሥርዓትን /ሥርዓተ ኖሎትን/
ለማስተማር ነው፡፡ የሀገሩን /የቀርጤስን/ ሰዎች ክፋት ሳይፈራ እንዲያስተምር እንዲገስፅ ለማበረታታት ኒቆጽልን
ከተባለች ቦታ በ63 ዓ.ም ጽፎ በደቀመዝሙሩ በአርጣማ እጅ ላከለት፡፡ ይህ መልእክት 3 ምዕራፎች ሲኖሩት
አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 የመግቢያ ሰላምታና በቀርጤስ ስላለችው የቤተክርስቲያን አስተዳደር
 ምዕራፍ 2 ቲቶን መሪ አድርጎት አርአያነቱን እንዲጠብቅ
 ምዕራፍ 3 ግብረ ገብነትን ማስተማር እንደሚገባው

፲3 ወደ ፊልሞና የተላከች መልእክት


ፊልሞና አገሩ ቆላስያስ የሆነና ባለጠጋ የሆነ ሰው ሲሆን በቅዱስ ጳውሎስ ስብከት አምኖ ክርስትናን
ተቀብሏል፡፡ ባለቤቱ አፉብያ ስትባል ልጁ ደግሞ የቆላስይስ ቤተክርስቲያን ኤጲስ ቆጶስ የነበረው አክርጳ ነው፡፡
ፊልሞና በጣም ደግና እንግዶችን ይቀበል የነበረ ሰው ነው፡፡ በዚህ የተነሳ በቤቱ ብዙ ክርስቲያኖች ይሰባሰቡ ነበር፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም “የማስተናገጃ ቤት አዘጋጅልኝ” በማለት በመልእክቱ ጽፎለታል፡፡234 ፊሊሞና አገልጋዩ የነበረው
አናሲሞስ የጌታውን ከብቶች ሲጠብቅ ይጠፉበታል፡፡ የሚከፍለውም ስላልነበረው ጠፍቶ ወደ ሮም ይሄዳል፡፡ እንደ
አጋጣሚ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እስር ላይ እያለ ይገናኛሉ፡፡ በእርሱ ትምህርት አምኖም ይጠመቃል፡፡ ከዛም ቅዱስ
ጳውሎስ አናሲሞስ የመጣበትን ሀገርና የመጣበትን ጉዳይ ጠይቆ ይረዳል፡፡ አናሲሞስም ቅዱስ ጳውሎስ ከጌታው
እንዲያስታርቀው በጠየቀው ሰዓት ፊልሞናን ያስተማረና ያሳመነ አባት እንደመሆኑ ለማስታረቅ ይህንን መልእክት
ይልካል፡፡ ከዚህም ሌላ በፊልሞና ቤት ባለች ቤተክርስቲያን አገልግሎት ለመስጠት ቦታ እንዲያዘጋጅለት ለመጠየቅ
ጽፎታል፡፡ ይህችን መልእክት ስለ አናሲሞስ ቅዱስ ጳውሎስ በእስር ላይ አያለ በ6ዐ ዓ.ም ጽፎ በአናሲሞስ እጅ
ልኮታል፡፡ ይህ መልእክት 1 ምዕራፍ ያለው ሲሆን አከፋፈሉም፡-
 ከቁጥር 1-7 የመግቢያ ሰላምታና ምስጋና
 ከቁጥር 8-21 ስለ አናሲሞስ የቀረበ ምልጃ
 ከቁጥር 22-25 የአደራ ሰላምታና ቡራኬ

232
Titus
233
ቲቶ 1፡4
234
ፊሊ 1፡22
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 60
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

፲4 ወደ እብራውያን ሰዎች የተላከ መልእክት235


እብራውያን የተባሉ አይሁድ ናቸው፡፡ በዔቦር /በአብርሃም ቅድመ አያት/ እብራውያን ተብለዋል፡፡ ቅዱስ
ጳውሎስ በዚህ መልእክት ስሙን አልጠቀሰም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት የእብራውያንን መልእክት የጻፈው ሌላ ነው፡፡
የሚል ግምት የሚገምቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ከሚሉባቸው ምክንያቶች መሐከል፡-
 በሌሎቹ መልእክታት ላይ እንዳደረገው በመልእክቱ መጀመሪያ ላይ ስሙን ባለመጥቀሱና የተለመደ
ሰላምታውን ባለመጠቀሙ
 መልእክቱ ለእብራውያን የተላከ እንደመሆኑ መጻፍ የነበረበት በእብራውያን ቋንቋ ነበር፡፡ መልእክቱ
ግን የተጻፈው በግሪክ ቋንቋና መጻፉ
 አጻጻፉና የመረጃ አቀራረቡ ከቅዱስ ጳውሎስ አጻጻፍና ማስረጃ አቀራረብ የተለየ በመሆኑ
 ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን የተቀበለው ከእግዚአብሔር መሆኑን በሌላ መልእክቱ ይገልፃል፡፡ በዚህ
መልእክት ላይ ግን ከሌላ ሰው እንደተቀበለው ይገልፃል፡፡
 በመልእክቱ ላይ የቅዱስ ጳውሎስ ፊርማ ስለሌለበት

የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ግን ጸሐፊው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ ይህን ሲያስረዱ በዕብ 13፡23
ላይ የተጠቀሰውን የጢሞቴዎስን ስም መነሻ በማድረግ ነው፡፡ ከእነዚህም አባቶች መካከል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ይገኝበታል፡፡ ሐዋርያው በዚህች መልእክቱ ስሙን ያልጠቀሰበት ምክንያት፡-
 አህዛብ ከአይሁድ ይልቅ ወንጌልን ለመቀበል ስለተዘጋጁ ቅዱስ ጳውሎስ አህዛበ ክርስቲያኖችን
ይወዳቸው ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት አይሁድ ይጠሉት ነበርና ገና ስሙን በመልእክቱ ሲያዩ
መልእክቲቱን አንቀበልም ብለው ሳያነቡ እንዳይቀሩ፡፡
 አጻጻፉ የግሪክ አጻጻፍን የመሰለው በመጀመሪያ ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ከጻፈው በኋላ
ወንጌላዊው ሉቃስ ወደ ግሪክ ቋንቋ በሚተረጉምበት ወቅት የአጻጻፉን ዘይቤ ለውጦታልና ነው፡፡
 ቅዱስ ጳውሎስ የኦሪት ሊቅ በመሆኑ ይህን መልእክት ለየት ባለ አገላለጽ የቤተመቅደስን
አገልግሎትና ሥርዓተ ኦሪትን በመጥቀስ ፍጻሜውን ለአይሁድ ፅፎላቸዋል፡፡
 በዕብ 2፡3 ላይ ወንጌልን የተቀበለው ከሌላ ሰው እንደሆነ የገለፀው ራሱን ከእብራውያን ጋር ቆጥሮት
ለትህትና እንጂ ወንጌሉን ከሌላ ሰው እንደተቀበለ ለማስረዳት ፈልጎ አይደለም
 ፊርማውንም ያላሰፈረው ጸሐፊው እርሱ መሆኑን ላለማሳወቅ ነው፡፡
ይህ መልእክት የተጻፈበት ምክንያት አይሁድ “ወንጌል ያለ ኦሪት ጥምቀት ያለ ግዝረት ክርስቶስ ያለ ሙሴ
አይጠቅሙም ኦሪትን ገንዘብ አድርጋችሁ ያዙ” እያሉ የክርስቲያኑን ልብ ከፍለው አንዳንዶቹ ወደ ኦሪት
እምነታቸው እየተመለሱ በመግባታቸው ወንጌል ከኦሪት፣ ጥምቀት ከግዝረት፣ ክርስቶስም ከሙሴ እንደሚበልጡ
ለማስረዳትና ከዚህ ጥፋት እንዲመለሱ ለማስተማር ከዚህም ሌላ አይሁድ ከሮማውያን አገዛዝ ነፃ ለመውጣት
ይታገሉ ነበር፡፡ በዚህ ትግላቸው ክርስቲያን አይሁድ ስላልተባበሩአቸው ይነቅፏቸውና ተጽእኖ ያደርጉባቸው ነበር፡፡
በዚህ ምክንያት ክርስቲያን አይሁድ ሊተባበሩአቸው ሲነሱ ክርስትናውን ትተው ወደ ኦሪት ገብተው ካልሆነ
አይሆንም ስላሏቸው ክርስትናውን እየተው ወደ አይሁድ ይቀላቀሉ ጀመር፡፡ ከዚህም ጥፋታቸው እንዲመለሱ
ለምመከርና የዳኑት መከራው የበዛባቸውን ለማጽናናት የቀድሞ አባቶችን እየጠቀሰ ለማበረታታት ጽፎላቸዋል፡፡
በመጨረሻም በብሉይ ኪዳን የነበሩ ሰዎችን ሥርዓቶችን ንዋየ ቅድሳትን እና ዘመነ ብሉይን እያነሳ ለዘመነ አዲስ
እንዴት ምሣሌ እንደሚሆን አስረድቷል፡፡ ይህ መልእክት 13 ምዕራፎች ሲኖሩት በሮም የመጀመሪያው እሥራቱ
ማብቂያ ላይ እያለ በ6ዐ ዓ.ም ጽፎ በጢሞቴዎስ እጅ ልኮላቸዋል፡፡አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1፡1-3 የመግቢያ ሰላምታ
 ከምዕራፍ 1፡4-4 ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና ከቅዱሳን መላእክትና ከቅዱሣን ነቢያት
እንደሚበልጥ
 ከምዕራፍ 5-1ዐ ሰለ ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለዓለም ክህነት
 ከምዕራፍ 11፡1-39 ስለ ሃይማኖት ታላቅነት
 ከምዕራፍ 13፡18-25 ማጠቃለያ

235
Hebrews
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 61
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ለ. ሰባቱ መልእክታት
በዚህ ክፍል ውስጥ የምናገኛቸው መጻሐፍት ብዛት 7 ሲሆኑ ጸሐፊያኑ ብዛታቸው 4 ናቸው፡፡ እነዚህም፡-
 ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ……………… 2 መልእታትን
 ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ……………….. 3 መልእክታትን
 ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ………………….. 1 መልእክትን
 ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ…………………… 1 መልእክትን ጽፈዋል፡፡

የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክታት


ጴጥሮስ ማለት በግሪክ ቋንቋ አለት መሠረት ማለት ሲሆን በዕብራይስጥ ቋንቋ ኬፋ ይባላል፡፡236 የመጀመሪያ
ስሙ ስምዖን ነበር አባቱ ዮና ይባላል፡፡ ትውልዱ ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተሳይዳ
ነው፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ሲያጠምድ ጌታ “ኑ ተከተሉኝ” ብሎ ጠርቷቸዋል፡፡237 ጴጥሮስ ለሐዋርያነት
ሲጠራ የ55 ዓመት ጎልማሳ እንዲሁም ባለትዳር ነበር ሚስቱም ጰርቴዋ ትባል ነበር፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ብዙ ጊዜ
ሐዋርያትን ወክሎ ስለሚናገር በእድሜው ትልቅነትና ጌታ በሰጠው ቃል መሠረት የሐዋርያት አለቃ የምዕመናን
አባት የቤተክርስቲያን ጠባቂ ነው፡፡238 ከዚህ በኋላ ዓለምን በወንጌል ለማዳረስ ሐዋርያት በእጣ ሲከፋፈሉ በደረሰው
እጣ መሠረት ሮም ሄዶ ለ25 ዓመታት ከማስተማሩም ሌላ ሐዋርያትን በየሀገረ ስብከታቸው በማድረስና
በማበረታታት ወንጌል እንድትስፋፋ ያደረገ አባት ነው፡፡ በተለይ በሮም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ወንጌል በመስበክ
አብዛኛው ሕዝብና የተወሰኑ የቤተመንግስት ሰዎች /የኔሮን ቄሣር ባለሟሎች ሳይቀሩ/ ወደ ክርስትናው
በመግባታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮባቸው በ67 ዓ.ም ሐምሌ 5 ቀን ቅዱስ ጴጥሮስ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በሮም
አደባባይ239 በሠማዕትነት በመስቀል ቁልቁል ተሰቅሎ አርፏል፡፡

1 መጀመሪያቱ የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት240


ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ እንደገለጠው ይህችን መልእክት የጻፈው በበዓለ ሃምሣ ዕለት
ላሳመናቸውና በእስጢፋኖስ አማካኝነት ይመሩ ለነበሩ ክርስቲያኖች ነው፡፡ በ35 ዓ.ም በቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት
ምክንያት እነዚህ ክርስቲያኖች በየሃገሩ ተበተኑ፡፡ ነገር ግን በሄዱበት ሀገር ወንጌልን እየሰበኩ ክርስትናን አስፋፉ፡፡
በዚህ ጊዜ የደረሱበት ሀገር ሕዝብ አይሁድም ሆኑ አህዛብ ብዙ መከራ ያደርሱባቸው ነበር በዚህም መከራ ሳይዘናጉ
ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን ጸጋ በመጠበቅ በምግባር በሃይማኖት እንዲጸኑ ሲመክራቸው፤ ከዚህም ሌላ በማያምኑ
ህዝቦች መካከል ሲኖሩ የእነርሱን መልካም ሥራ አይተው እግዚአብሔርን እንዲያምኑ በሃይማኖትና በምግባር
እንዲጸኑ መክሯቸዋል፡፡ ይህ መልእክት በ63 ዓ.ም ጽፎታል፡፡ መጽሐፉ 5 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1፡1-12 ስለተዘጋጀልን መዳን
 ከምዕራፍ 1፡13-2፡10 ስለተጠራንለት ቅድስና
 ከምዕራፍ 2፡11-4፡19 ስለታቀደልን መልካም ኑሮና ስለሚያገኘን መከራ
 ምዕራፍ 5 ልናደርገው ስለሚገባ ማህበራዊ ትጋት

2 ሁለተኛይቱ የቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት241


ይህች መልእክት የተጻፈችው ቅዱስ ጴጥሮስ የመጀመሪያይቱን መልእክት ለጻፈላቸው በእርሱ ስብከትና
በሌሎች ሐዋርያት በተለይም በቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ላመኑ ክርስቲያኖች ነው፡፡ ይኸውም ኔሮን ቄሳር
ክርስቲያኖች ለማጥፋት ባወጀው አዋጅ ተይዞ በታሰረ ጊዜ ነበር፡፡ መልእክቲቱ የተጻፈችበት ምክንያት በተለይ
በታናሽ እስያ ያሉ መናፍቃን፡- “ትንሣኤ ሙታን የለም”፣ “ለዚህ ዓለም ሠሪ መጋቢ የለውም”፣ “ሰማይና ምድር
አያልፍም”፣ “አንድ ጊዜ ካመኑ ምግባር አይጠቅምም” እያሉ ለሚያስተምሩት ክህደት በየምዕራፉ መልስ ለመስጠት

236
ዮሐ 1፡43
237
ማቴ 4፡18
238
ማቴ 16፡18፣ ዮሐ 21፡15-17፣ ሐዋ 2፡14-37
239
ኮሊሲየም በሚባል አደባባይ (የትያትር ቦታ)
240
1 Peter
241
2 Peter
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 62
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ነው፡፡ መጽሐፉ የተጻፈው በዛን ወቅት የነበሩ ክርስቲያኖች የትኛው ትምህርት እውነት እንደሆነ አውቀው
በክርስትና ሕይወታቸው ከበፊቱ ይበልጥ እንዲተጉ፣ ከሀሰት መምሕራን ተጠብቀው በእውነተኛ የሐዋርያት
እንዲመሩ ለማሳሰብ፣ የሚሞትበት ጊዜ ስለቀረበ ለሁልጊዜ የሚጠቀሙበትን ምክሩን ሊለግሳቸው የጻፈው ነው፡፡ይህ
መልእክት በ66 ዓ.ም አካባቢ የተጻፈ ሲሆን 3 ምዕራፎች አሉት፡፡ አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 ስለ ተላለፈላቸው የወንጌል እውነተኛነት
 ምዕራፍ 2 ስለ ሐሰተኛ መምህራን መነሳትና ጠቃሚ ትምህርት
 ምዕራፍ 3 ቃሉን በማሰብ ስለሚደረግ ጥንቃቄ

የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ መልእክት


ጌታችን በመጀመሪያ ካስከተላቸው ሐዋርያትና የጌታን ማንነት ከመጀመሪያ መምራቸው ከቅዱስ ዮሐንስ
ወጥምቅ ከተረዱት ሐዋርያት አንዱ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ከወንጌሉ ሌላ የጻፋቸው ሦስት መልእክታት አሉት፡፡
እንዚህን መልእክታት የጻፈው በ96 ዓ.ም አካባቢ ከፍጥሞ ደሴት በተመለሰ ጊዜ ሲሆን የተጻፈበት ቦታ ኤፌሶን
ነው፡፡
3 የመጀመሪያይቱ የቅዱስ ዮሐንስ መልእክት242
ይህ መልእክት የተጻፈበት ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስን መታሰር ያዩ መናፍቃን የተለያዩ የኑፋቄ ትምህርቶች
በማምጣታቸው ምዕመናን በእነርሱ ክህደት እንዳይተባበሩ ለማሳወቅና ትክክለኛውን ትምህርት ለማስረዳት ሲል
ነው፡፡ ከመናፍቃኑ ትምህርት መካከል፡-
 ሰው ከጥምቀት በኋላ ምግባር መስራት አይጠቅመውም ብለው ለሚያስተምሩ
 ትንሳኤ ሙታን የለም በመናገርና በመስራት የሚሰራውን ኃጢአት እንጂ በሐሳብ /በማሰብ/ የሚሰራውን
ኃጢአት እግዚአብሔር አያውቀውም በብርሃን እንጂ በጨለማ የሚሰራውን ኃጢአት አያውቀውም እያሉ
ለሚያሰተምሩ
 ከዚህ ጋር ተያይዞ ስለተለያዩ ምስጢራት እና ስለሥነ ምግባር መቅናት አስተምሯል፡፡

ይህ መልእክት የሚያበቃው ምዕመናን ከባዕድ አምልኮ ተለይተው በእውነተኛ አምልኮተ እግዚአብሔር


እንዲጸኑ በመምከር ነው፡፡ መጽሐፉ 5 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1፡14 ያየውንና የሰማውን የጌታ መገለጥ
 ከምዕራፍ 1፡5-2፡17 ስለ ጽናት
 ከምዕራፍ 2፡18-29 ስለ ተቃዋሚዎች ሐሰተኛ መምህራን
 ከምዕራፍ 3-4፡6 የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን የተገለጠበት
 ከምዕራፍ 4፡7-5፡5 የእግዚአብሔር ፍቅርና የእርስ በርስ ፍቅር
 ከምዕራፍ 5፡6-21 ስለጌታ እውነተኛ አምላክነትና ዘላለማዊ ሕይወት

2 ሁለተኛይቱ የቅዱስ ዮሐንስ መልእክት243


ቅዱስ ዮሐንስ ይህን መልእክት የጻፈው የተቸገሩ ሕፃናትን ሰብስባ ለምታሳድግ ሮምና ለምትባል ሴት
ነው፡፡ ይህቺ ሴት ከኤዥያን ባህር ደሴቶች በአንዷ ውስጥ ቀለብ እየተሰፈረላት የነገሠታት ልጆችን የመታሳድግ
ሞግዚት ነበረች ቅዱስ ዮሐንሰ ከደቀመዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ወደዚህች ደሴት መጥተው እንዴት ማስተማር
እንዳለባቸው ካሰቡ በኋላ ይህቺ ሮምና ውዳሴ ከንቱ የምትሻ መሆኗን ተረድተው “ቀድሞ የሮምና ባሮቿ ነበርን
አሁንም ወደ እርሷ ለመመለስ መጣን” አያሉ ያስወሩ ጀመር ያቺም ሴት እነዚህ ቅዱሳን አንዱን ውሃ ቀጂ
ሌላውን ማዕድ አዘጋጅ አድርጋ ስታሰራቸው ቆየች ከእለታት አንድ ቀን ወደ ጣዖት ቤት ይዛቸው ስትሄድ በጣዖት
ያደረ ርኩስ መንፈስ በእነርሱ ያደረውን መንፈስ ቅዱስ አይቶ የምታሳድገውን ልጅ ገድሎ ይሸሻል፡፡ እነርሱም
ያንን ሕፃን ከሞት አስነስተውት በዚህ ምክንያት አምና ተጠምቃለች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ወደ ሌላ ቦታ ለማስተማር
ሲሄድ ላለችበት ቦታ በምዕመናን ላይ አመምኔት አድርጐ ሾሟቸው ሄዷል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በታሰረበት ዘመን
መናፈቃን ይህቺን ማኀበረ ክርስቲያን ይከፋፍሏት ጀመር ከእስር በተፈታም ጊዜ ምዕመናን በመናፍቃን ትምህርት

242
1 John
243
2 John
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 63
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ሳይወናበዱ በፍቅር በአንድነት እንዲኖሩ ሮምናም በተሰጣት ጸጋ ጸንታ እንድትኖር ለመምከርና ለማበረታታት
እንዲሁም ስለመልካም ሥራዋ ለማመስገን ይህቺን መልእክት ጽፎ ልኮላታል፡፡ መጽሐፉ 1 ምዕራፍ ያለው ሲሆን
አከፋፈሉም፡-
 ከቁጥር 1-3 ሰላምታ
 ከቁጥር 4-6 አንድነታቸውን አጽንተው እንዲኖሩ
 ከቁጥር 7-11 የሐሰት ትምሕርትን መቃወም
 ከቁጥር 12-13 ለሌሎች የቀረበ ሰላምታ

3 ሦስተኛይቱ የቅዱስ ዮሐንስ መልእክት244


ይህን መልእክት የጻፈው ጋይዮስ ለተባለ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው በዘመነ ሐዋርያት በሃይማኖት ምክንያት
የሚሰደዱትን ክርስቲያኖች እየተቀበለ የሚያስተናግድ ደግ ሰው ነበር፡፡ በዚያ በአስፈሪው የመከራ ዘመን እንዲህ
ዓይነት ደግ በማገኘቱ እርሱን ለማበረታታትና በይበልጥ ደግሞ በአካል ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ሊያስተምረው
እንደሚፈልግ ለማስታወቅ ይህንን መልእክት ጽፎ ሰደደለት፡፡ መልእክቱ ባለ አንድ ምዕራፍ ሲሆን አከፋፈሉም፡-
 ቁጥር 1 የእምነቱን ጠንካራነት እና ምስጋና
 ከቁጥር 2-8 ስለ እንግዳ ተቀባይነቱ
 ከቁጥር 9-11 ለትዕቢተኛ ዲዮጥራጢስ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
 ከቁጥር 13-14 ስለ ድሜጥሮስ የተሰጠ ምስክርነት
 ቁጥር 15 ሰላምታ

4 የሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ መልእክት245


አባቱ እልፍዮስ ይባላል፡፡ ከጌታ ጋር አብረው ስላደጉ እና በሥጋ ዝምድና ሰለሚዛመድ “የጌታ ወንድም”
ተብሎ ተጠርቷል፡፡246 እንዲሁም ከያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ ለመለየት “ታናሹ ያዕቆብ” እየተባለ ይጠራል፡፡247
ቅዱስ ያዕቆብ ከገድል ጽናት የተነሳ እግሩ በሽተኛ ሆና እንደልቡ ተዘዋውሮ ለማስተማር ባለመቻሉ እንዲሁም
ምሁረ ኦሪት ስለነበረና የአይሁድን ጠባይ ስለሚያውቅ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ እንዲሆን ተመርጦ የእየሩሳሌም
ቤተክርስቲያንን ሲመራ ቆይቷል፡፡ በ5ዐ ዓ.ም በኢየሩሳሌም በተካሄደው የሐዋርያት ሲኖዶስ በሊቀመንበርነት
መርቷል፡፡ በአጠቃላይ በኢየሩሳሌም ለ28 ዓመት አገልግሏል፡፡ ያዕቆብ ተዓምራት እያደረገ ወንጌል እያስተማረ
ብዙ ሰው በማሳመኑ የቀኑበት አይሁድ ከቤተመቅአስ ጫፍ አውጥተው ክርስቶስን ክዶ እንዲያስተምር አስገደዱት
እርሱ ግን በይበልጥ የጌታን ጌትነት /አምላክነት/ በመመስከሩ ከቤተመቅደሱ ጫፍ ወርውረው በድጋይ ወግረው
ገድለውታል እረፍቱም የካቲት 1ዐ ቀን 62 ዓ.ም ነው፡፡መልእክቱ በ5ዐ ዓ.ም አካባቢ ተጽፏል፡፡ የተጻፈበት
ምክንያትም በቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ምክንያት በየሀገሩ በመበተናቸው መከራ ለሚደርስባቸው ከይሁዳነት
ለተመለከሱ ክርስቲያኖች መጽናኛ እንዲሆነ ነው፡፡በይዘቱም ምዕመናን ከሃይማኖት ጋር ምግባርን አጣምረው
እንዲይዙ መምከር፣ በኑሯቸው የሚገጥሟቸውን ፈተና እንዲቋቋሙ እንዲጸኑ ለማበረታታት፣ በአጠቃላይ
በኑሯቸው ሁሉ ስለሚገጥማቸው ነገሮች እያነሳ ጠቃሚ ትምህርት በዚህች መልእክት አስተምሯቸዋል፡፡መጽሐፉ
5 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ምዕራፍ 1 በመከራ ላሉ ሁሉ የሚያፅናና ቃል
 ከምዕራፍ 2-4 ልዩ ልዩ ስህተቶችን እርማት
 ምዕራፍ 5 ለትዕግስት እና ለፀሎት ይበረቱ ዘንድ ምክር

244
3 John
245
james
246
በኖቱ ገጽ 20 ላይ ያለውን በእስራኤላውያን የወንድም ትርጉምን ይመልከቱ፡፡
247
በኖቱ ገጽ 17 ላይ ያለውን ለሰዎች የሚሰጡ ቅጽል ስሞችን ይመልከቱ፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 64
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

5 የሐዋርያው የይሁዳ /የታዴዎስ/ መልእክት248


ይሁዳ ማለት ታማኝ ማለት ሲሆን የአረጋዊው ዮሴፍ ልጅ እንዲሁም የሐዋርያው ያዕቆብ ወንድም ነው፡፡
ጌታችን ከመረጣቸው ከ12 ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በማቴዎስና በማርቆስ ወንጌል ላይ “ታዴዮስ /ልብድዮስ/”
ተብሎ ተገልፆ እናገኛለን፡፡ እንዲሁም በሉቃስና በዮሐንሰ ወንጌል ላይ ደግሞ “የያዕቆብ ወንድም” ይሁዳ ብለው
ይጠሩታል፡፡ የጌታ ወንድሞች ከተባሉት መካከል አንዱ ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱ ሶሪያ ሲሆን ከዚህም ሌላ በዙሪያዋ
ባሉ አገሮች ሁሉ አስተምሯል፡፡ በሚያስተመርባቸው ቦታዎች ብዙ ተዓምራትን እያደረገ እያስተማረና ምዕመናንን
እያጠመቀ ቤተክርስቲያንን ሲየስፋፋ ቆይቷል፡፡ በመጨረሻም ፐርሺያ በምትባል ሀገር ሐምሌ 2 ቀን 68 ዓ.ም
አካባቢ አርፏል፡፡ ሐዋርያው መልእክቱን የጻፈበት ምክንያት በየቦታው በተለይ በታናሽ እስያ ተነስተው በኑፋቄ
ትምህርት ህዝቡን ለሚያውኩ ለግኖስቲኮች ሲሆን ምዕመናንን አንድ ጊዜ ለቅዱሣን ከእግዚአብሔር ለተሰጠች
ሃይማናት እንዲጸኑ ለመምከር ነው፡፡ ይህ ሐዋርያ የመናፍቃኑን የክህደት ትምህርት በማውገዝ የኃጥዓንን ክፋት
በኋላም የሚደርስባቸውን ቅጣት እያነሳ ያስተምራል፡፡ በመልዕክቱ ከገድለ ሙሴና ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሷል፡፡
ይህች መልእክት ከቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት በኋላ በ66 ዓ.ም ተጽፋለች ለዚህም በይሁዳ 1፡18 ላይ ሐዋርያው
በ2ጴጥ 3፡1 ላይ ያለውን መጥቀሱ ማስረጃ ነው፡፡

ክፍል አራት
የትንቢት መጻሕፍት
በዚህ ክፍል እንደ ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ብዙ የትንቢት መጻሕፍት አልተጻፈም አብዛኛው ትንቢተ
ነቢያት ፍፃሜ ያገኘው በዘመነ አዲስ ነውና፡፡249ይህ ሲባል ግን ምንም የትንቢት መፃሕፍት አልተጻፈም ማለት
አይደለም በወንጌላቱ በመልእክታቱ ከተነገሩት ትንቢቶች ሌላ በመደበኛነት የተጻፈ አንድ የትንቢት መጽሐፍ አለ፡፡
ይህም የዮሐንሰ ራዕይ ነው፡፡
የዮሐንስ ራዕይ250
እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሰዎች ምሥጢር ከሚገልጽበት መንግድ አንዱ ራዕይ ይባላል፡፡ በዚህ መንገድ
ቀደም ሲል ለክቡራን ነቢያት ብዙ ምስጢር ተገልጦላቸው በቃል አስተምረዋል በመጽሐፍቶቻቸውም ጽፈዋል፡፡
ቅዱሣን ሐዋርያትም ምሥጢር ተገልጦላቸው አስተምረዋል በየመጻሕፍቶቻቸውም ጽፈዋል፡፡ ከእነዚህም አንዱና
ዋነኛው ቅዱስ ዮሐንሰ ወንጌላዊ ነው፡፡ ይህ ሐዋርያ የሥላሴ ምስጢር ተገልጦለት ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስ፣
ንጽሐ ልቦና ተሰጥቶት ከጻፈው ድንቅ ወንጌል ሌላ እጅግ የሚያስደንቅ ብዙ ምስጢራትን ያዘለ ለጊዜው ለሰባቱ
የታናሽ እስያ አብያተ ቤተክርስቲያን ፍፃሜው ለምዕመናን ሁሉ ጠቃሚ የሆነ መጽሐፈ በራዕይ ተገልጦለት
ጽፏል፡፡ እነዚህ ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያን የተመሠረቱት በሰባቱ ዮናናውያን ሕዝቦች ውስጥ መካከል ነው፡፡
እነዚህ ህዝቦች የተገኙትም እስያ ከተባለ ሰው ነው፡፡ እስያም ከነገደ ያፌት የተወለደ ሲሆን ያፌት ደግመ የኖህ
ልጅ ነው፡፡ ሰባቱ ዮናናውያን የተባሉት ህዝቦች
1. ኤፌሶን 5. ፊልድልፍያ
2. ሰምርኔስ 6. ሰርዴስ
3. ጴርጋሞን 7. ሎዶቅያ ናቸው፡፡
4. ትርያጥሮን

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ከእመቤታችን እረፍት ከ49 ዓ.ም በኋላ ወደ ሐገረ ስብከቱ ወደ ኤፌሶንና አካባቢው
ወዳሉ ሀገሮች በመግባት እየተዘዋወረ ወንጌል በመስበኩ ሕዝቡ ያመልኩት ከነበረው አምልኮ ጣዖት ከአርጤምስና
ከዜውስ ጣዖታተ አምልኮና ከሰባቱ ከዋክብት አምልኮ ተላቀው ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኃጢአት ወደ
ገቢረ ጽድቅ ተመልሰው አምነው ተጠመቁ በሚቆጥሩባቸው በሚያመልኩባቸው ሰባት ከዋክብት አንፃር በብርሃነ
ትምህርታቸው የምዕመናን ልቦና ብሩህ የሚያደርጉ ሰባት መንፈሳውያን ከዋክብት /ኤጲስ ቆጶሳትን/ ሾመላቸው፡፡
የጣዖት ካህናትም ከንጉሡ ከድምጥያኖስ ዘንድ ከሰውት በፍልውሃ እንዲሰቃይ ካደረጉት በኋላ ወደ ፍጥሞ ደሴት
እንዲጋዝ አደረጉት በብዙ ስቃይ በኋላ ከደቀመዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር እዚች ደሴት ደረሰ፡፡ ከዚህ በኋላ ወንድሞቹ

248
Jude
249
ማቴ 5፡17
250
Revelation
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 65
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ሐዋርያት በየሐገረ ስብከታቸው ሲያስተምሩ እርሱ ባለማስተማሩ አዝኖ ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት


እግዚአብሔር የበለጠውን ምስጢር በራዕይ ገልጦለት ይህንን መጽሐፈ ሊጽፍ በቅቷል፡፡
ይህ መጽሐፈ የተጻበት ምክንያት ብዙ ነው ከእነዚህም መሐል፡-
 የካህናት ክብርን በሰማይ በመንበር ዙሪያ ባሉ ካህናት ለማስረዳት
 የሐሳዊ መሲህን ነገር ለማስረዳት
 የምፅዓትንና የመንግሥተ ሰማይን ምሥጢር ለመግለጥ
 አጲስ ቆጶሳቱና ምዕመናን ትምህርቱን ገድፈውበት ነበርና ለመገሠጽ “ነገር ግን የምነቅፍብህ ነገር
አለኝ” አንዲል251 የእንዳንዳንዳቸውን ስህተት ለየብቻ ጽፎ ምሥጢሩን በአንድ አድርጐ ልኮላቸዋል፡፡
 ይህንን ምስጢር ጌታ ለዮሐንስ ሲገልጥለት ሰባቱን አጲስ ቆጶሳት በሰባት ከዋክብት ሰባቱን
የቤተክርስቲያን ምዕመናን በሰባቱ መቅረዞች መስሎ ነግሮታል፡፡

በዚህ መጽሐፍ ከተለያዩ ምሣሌያዊ ምሥጢራት ሌላ ለሃይማኖትና ለሥነ ምግባር ጠቃሚ የሆኑ
ትምህርቶችና ምስክሮች ተካተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መጽሐፉ ስለፃድቃንና ሰማዕታት፣ ስለሐዋርያትና ስለ
ነቢያት፣ ስለመምህራንና ካህናት እንዲሁም ስለምዕመናን ክብር፣ ስለቅዱሣን መላእክት ማዕረግ ክብርና ተግባር
በስፋት ይገልፃል፡፡ ይህ መጽሐፍ በዘመነ ሰማዕታት /በዲዮቅልጢያኖስ የስደት ዘመን/ ምዕመናን በተሰደዱና በተደሉ
ጊዜ ጠፍቶ /ተቃጥሎ/ በርዕሱ ብቻ ሲታወስ የቆየ ሲሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በዚህ መጽሐፍ መጥፋት ታላቅ
የሆን መንፈሳዊ ቅንዓት ይዞት በደሴተ አጥራክያ በስደት እያለ ሱባዔ ይዞ እግዚአብሔርን ቢለምን የናቡከደነጾርን
ህልም ከነ ትርጓሜው ለነቢዩ ዳንኤል እንደተገለጠለት ሁሉ ለቅዱስ ዮሐንሰ አፈወርቅም ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ
ያየውን ራዕይ ከነትርጓሜው ተገልጦለት ጽፎታል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚነሱ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ
እንዳይጨምሩበትና ከተጻፈውም እንዳይቀንሱ ማስጠንቀቂያውን የጻፈው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው፡፡252
መጽሐፉ 22 ምዕራፎች ሲኖሩት አከፋፈሉም፡-
 ከምዕራፍ 1-3 ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት የተላከ
 ከምዕራፍ 4-5 በሰማያት ስላለው ኑሮ
 ከምዕራፍ 6-11 ስለ ሰባቱ ማህተሞችና መለከቶች
 ከምዕራፍ 12-13 ስለ ዘንዶው /ስለ ሐሳዊው መሲህ/
 ምዕራፍ 14 በሰማያት ስለሚሆኑ ነገሮች
 ከምዕራፍ 15-16 ስለ ሰባቱ ጽዋዎች
 ከምዕራፍ 17-19 ስለ ባቢሎን መፍረስ
 ከምዕራፍ 20-22 ስለ እግዚአብሔር መንግስት

ክፍል አምስት
የሥርዓት መጻሕፍት

ከ35ቱ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት መካከል ስምንቱ የአዲስ ኪዳን የቀኖና /የሥርዓት/ መጻሕፍት በመባል
ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ መጻሕፍት የተጻፉበት ቋንቋ የሶሪያ ቋንቋ በሆነው በሱርስት ቋንቋ ሲሆን አንዳንድ ሊቃውንት
ደግሞ በፅርዕ ቋንቋ እንደተጻፉ ይገልጻሉ፡፡ በኋላ የተነሱ ሊቃውንትም የሱርስትና የግሪኩን ቋንቋ መሰረት በማድረግ
ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች ተርጉመዋቸዋል፡፡253 የተጻፉበት ጊዜ ከትንሳዔ በኋላ ሲሆን በቅዱሳን ሐዋርያት ተጽፈዋል፡፡
እነዚህ መጻሕፍት በ3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-
ሀ. በቤተክርስቲያን አመሰራረት፡- የቤተክርስቲያን አወቃቀር፣ አጠቃላይ የአገልግሎት ሥርዓትና ትምህርት
ክፍል የሚያተኩሩ ናቸው፡፡ እነዚህም፡- ዲዲስቅልያና መጽሐፍተ ሲኖዶሳት /ትዕዛዝ፣ ግጽው፣አብጥሊስ፣ ሥርዓተ
ፅዮን/ ናቸው፡፡ እነዚህም ሐዋርያት በየጊዜው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እየተሰበሰቡ ያዘጋጁዋቸው መጻሕፍት
ናቸው፡፡

251
ራዕ 2፡1፣ 14
252
ራዕ 22፡18
253
ፍትሀ ነገስት መቅድም
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 66
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ለ. የኪዳን ክፍል፡- ይህ ክፍል ደግሞ 2 የኪዳን መጻሕፍትን የያዘ ነው፡፡ እነዚህም መጽሐፈ ኪዳን
ቀዳማዊና መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ ናቸው፡፡ ጌታ በመዋዕለ ሥጋዌው /ከትንሳዔው በፊት/ ያደረገቸው “ወንጌል” ሲባል
ከትንሳዔው በኃላ ያደረጋቸው ሁሉ ደግሞ “ኪዳን” ይባላል፡፡ በሁለት የኪዳን መጻሕፍት ተዘጋጅቶ ቤተክርስቲያን
በጠዋት፣ በሰርክ፣ በሌሊት፣ በሁሉም ሠዓታት ለአገልግሎት እግዚአብሔርን በማመስገን እየተጠቀመችበት
ትገኛለች፡፡
ሐ. በአጠቃላይ አገልጋዮች፡- አበው ነብያትን፣ ሐዋርያትንና አርድዕትን ወዘተ… የሚመለከት ክፍል ነው፡፡
በተለይም ከቅዱስ ጴጥሮስ ሥርዓትን የተማረው ቅዱስ ቀለሜንጦስ ስለ ራሱ፣ ስለ ምዕመናን በሥርዓት መሄድ
እንዲገባ በስፋት ይተነትናል፡፡ መጽሐፉ በቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር ስም በመሰየሙ መጻሕፍትን ሰፍረው
ቆጥረው ሲሰጡት ስምንት የሥርዓት መጻሕፍትንም ጨምረው እንደሰጡት ይነገራል፡፡ ውድ ተማሪዎች ከዚህ
ቀጥለን መጻሕፍቱን አንድ በአንድ እንመለከታለን፡፡ ተከተሉን፡-

መጻሕፈተ ኪዳን
ይህ መጽሐፍ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት
ያስተማራቸውን ትምህርቶች የያዘ ባለ ሁለት ክፍል መጽሐፍ ነው፡፡ ኪዳን መባሉም ጌታ በዚህ ትምህርቱ
ከክርስቲያኖች ሁሉ ጋር ቃል /ኪዳን/ የተገባባ ስለሆነ ነው፡፡ “ዘዐቀበ ቃል ዝንቱ ኪዳን ይሄሉ ወየሐዩ ከመ
መላእክት /የዚህን ኪዳን ቃል የተጠበቀ እንደ መላዕክት ህያው ሆኖ ይኖራል/” እንዲል መጽሐፈ ኪዳን ፡፡ ይህ
መጽሐፍ መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ እና መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ በመባል ይታወቃል፡፡ “ክልዔቱ ገበዋቲሃ ለመጽሐፍ”
እንዲል፡፡

1 መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ


ይህን መጽሐፍ የጻፉት ቅዱስ ዮሐንስ፣ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ማቴዎስ ናቸው፡፡ መጽሐፉ 59 የሚሆኑ
አንቀጾችን የያዘ ሲሆን በዚህ ክፍል ጌታ ስለ ቤተክርስቲያን መሪዎች /ስልጣነ ክህነት/ አሰጣጥና ደረጃ /ማዕረግ/
ሁኔታ የተናገረውን አብራርቶ የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ ከነዚህም ሌላ ስለ ቤተክርስቲያን የአምልኮ ሥርዓትና ስለ
ሥነ ምግባር ያስተማረው ትምህርት በተለያዩ ጊዜያት የሚጸለዩ ጸሎቶች ለምሣሌ የኪዳን ፀሎት፣ የጌታ ቅዳሴ
/ቅዳሴ እግዚዕ/፣ ትምህርት ሕቡዓት፣ በእንተ ቅድሣት፣ በሰማይ እግዚአብሔር ዘብርሃናትና የቁርባን ምሥጋና
/የቅዱስ ሥሉስ/ ወዘተ… የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ለዚህም ማስረጃ በእነዚህ ጸሎቶች መጀመሪያ ርእስ “እመጽሐፈ
ኪዳን ዘነገሮሙ እግዝእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱሁ ንጹሐን /ይህ ጸሎት ጌታችን መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ለንፁሐን ደቀመዛሙርቱ ካስተማራቸው መጽሐፈ ኪዳን የተገኘ ነው/ ይላል፡፡ የመጀመሪይው
የመጽሐፈ ክፍል አጠቃላይ ይዘቱ ይህንን ይመስላል፡፡

2 መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ


ይህ መጽሐፍ አጻጻፉ በስድ ንባብ መልክ ሲሆን ወደፊት የሚደረጉ ታሪኮች /የዓለም ምስጢሮች/ የተጻፈበት
መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህ የመጽሐፍ ክፍል ጌታ ስለነገረ ምጽዓቱ፣ ከምጽዓት አስቀድሞ ስለሚነሱ የዓለም ነገሥታት፣
ስለሐሣዊ መሲህ አነሳስ በአጠቃላይ ያስተማራቸው ትምህርቶች ይገኙበታል፡፡

መጻሕፈተ ሲኖዶስ
ሲኖዶስ ማለት ጉባኤ/ስብሰባ/ ማለት ሲሆን ቅዱሣን ሐዋርያት እነዚህን መጻሕፍት የጻፉት ለተለያዩ
የቤተክርስቲያን ጉዳዮች በተሰበሰቡ ጊዜ የወሰኗቸውን ውሳኔዎችን ለማሣወቅ ነው፡፡ በተለይ በ5ዐ ዓ.ም በኢየሩሳሌም
ከተማ በቅዱስ ያዕቆብ ሊቀመንበርነት ቅዱሣን ሐዋርያት /ቅዱስ ጳውሎስን ጨምሮ/ ባደረጉት ጉባዔ የተወሰኑ
ውሣኔዎችና የተሰሩ ሥርዓቶች ይገኙባቸዋል፡፡

3 ሥርዓተ ጽዮን
ፅዮን ማለት አንባ መጠጊያ ማለት ስለሆነ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት በማርቆስ እናት በማርያም ጽርሐ
ፅዮን በተባለው ቤት በመጻፉ ምክንያት የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡ መጽሐፉ ስለ ሥርዓተ ክህነት አገልግሎትና
ምግባር፣ ስለ በዓላትና አፅዋማት፣ ስለ ቅዱሳን ክብር በስፋት ይተነትናል፡፡

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 67
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

4 መጽሐፈ ትዕዛዝ
ትዕዛዝ ማለት በቁሙ ከስራ አስቀድሞ የሚሰጥና የሚነገር ህግ ወይም ሥርዓት እንዲሁም አድርግ
አታድርግ የሚል ፍቃድ ማለት ነው፡፡ መጽሐፉን ቅዱሳን ሐዋርያት በ1ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢየሩሳሌም
ጽፈውታል፡፡ ይኸውም ቅዱሳን ሐዋርያት በቀሌምንጦስ እጅ ለአህዛብ ህገ ቤተክርስቲያንን ለማሳወቅ እንደጻፉት
ይነገራል፡፡ በአጠቃላይ መጽሐፉ ስለ ሢመተ መላእክት፣ ስለ አስራት፣ መባዕ፣ ሥርዓተ ቁርባን በስፋት ያትታል፡፡

5 መጽሐፈ ግጽው
ግጽው ማለት የታየ፣የተገለፀ፣ ጉልህ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ስለ ሢመተ ክህነትና ስለ ህዝባውያን ተልዕኮ፣
ስለ ትህትና፣ ስለ 10ቱ ቃላት፣ ስለ አሥራት፣ ስለ ሰንበት፣ ስለ ሙታን ተዝካር፣ ስለ ቁርባንና ስለ ጋብቻ በስፋት
ይገልፃል፡፡
6 መጽሐፈ አብጥሊስ
አብጥሊስ ማለት ሐዋርያውያን ቀኖናት ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ቀለሜንጦስ በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን
ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት የቅዱስ ሲኖዶስን ድንጋጌዎች እንደጻፈ ይነገራል፡፡ መጽሐፉ ከ 81ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት
በዝርዝር ይገልፃል፡፡
7 መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
ቀሌምንጦስ ትውልዱ ሮማዊ የሆነ የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙርና የሮሜ የመጀመሪያው ሊቀጳጳስ
ነበር፡፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ እንደተጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተገልጧል፡፡254 ቅዱሣት
መጻሕፍት ቁጥራቸው 81 እንደሆነ ከቅዱሣን ሐዋርያት ተረድቶ የቅዱሣን መጻሕፍትን ዝርዝር ጽፎ ያዘጋጀ
አባት እንደሆነ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በመጽሐፍቶቻቸው ያትታሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ከ81 ቅዱሣን መጻሕፍት
የሚቆጠር ሲሆን የመጽሐፉን ምስጢር ከጌታ እየተነገረ የተረዳው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡ ቀሌምንጦስም ቅዱስ
ጴጥሮስ እየነገረው ይህንን መጽሐፍ በመጻፍ በጸሐፊው ስም መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ተብሏል፡፡ መጽሐፉ በውስጡ፡-
 ከሥነ ፍጥረት ታሪክ አንስቶ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮአታም ዘመን ያለውን ታሪክ
 ቅዱስ ጴጥሮስ ለቀሌምንጦስ የነገረውን ብዙ መንፈሳውያን ምሥጢራት
 ሰለ ሰው ልጅ የተደረገው ምህረት ሰዎች በምድር ላይ ሲኖሩ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጌታ
ለቅዱስ ጴጥሮስ የሰጠውን ትምህርት
 ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ ያስተማረውን ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
 ስለ ሙሴ በትር ታሪክና ስለ ስምዖን ካርዮ ራዕይ ወዘተ… የገለጡ ብዙ ታሪኮች ያሉበት ሰፊ
መጽሐፍ ሲሆን በሰባት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡፡

6 መጽሐፈ ዲድስቅልያ
ዲድስቅልያ ማለት ትምህርት ማለት ሲሆን ሐዋርያት ያስተማሩትና የሰሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓት
የተጻፈበት መጽሐፍ ነው የተጻፈውም ከ12ዐ ዓ.ም በፊት ነው፡፡ በ43 ምዕራፎች የተከፋፈለ መጽሐፍ ሲሆን
በይዘቱም
 ከምዕራፍ 1-7 ስለ ህይወትና ስለ ሞት
 ከምዕራፍ 7-15 ሰለ ጾም ጸሎት ስለ ቅዱስ ቁርባን ሥርዓት ስለ ነቢያትና ሐዋርያት ትምህርት
ተዛምዶ
 ሰለ ጥምቀት ሥርዓትና ጥምቀትን ሲያጠምቁ በስመ ስላሴ መሆን እንዳለበት
 ስለ ጸሎት ሥርዓት /ቢያንስ በቀን 3 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት መጸለይ እንደሚገባ/
 ጾመ ድህነት /የረቡዕና የዓርብ ጾም/ እንዲሆን የተወሰነ ውሣኔ
 ጥምቀት የፈጸሙ ሴቶች ቅዱስ ቁርባን መቀበል እንዳለባቸው ወዘተ... የመሳሰሉት የቤተክርስቲያን
ሥርዓቶችና ትምህርቶች የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ስምንት የአዲስ ኪዳን የቀኖና መጻሕፍት በይዘታቸው መመሪያ ሰጪና
ሥርዓትና መሪ /አስተማሪ/ ስለሆኑ ከትምህርት ክፍል መጻሕፍት ጋር ይቆጠራሉ፡፡

254
ፊሊ 4፡3
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 68
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

የምዕራፍ ሶስት የክለሳ ጥያቄዎች

ትዕዛዝ 1፡- ትክክለኛውን መልስ አብራሩ


1. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ምዕራፍ ያላቸውን መጻሕፍት ዘርዝሩ
2. ወንጌላት ከይዘታቸው አንጻር ለስንት ይከፈላሉ ዘርዝሩ
3. የብሉይ ኪዳን የጥበብ የቅኔ መጻሕፍት ብዛታቸው ስንት ነው ዘርዝሩ
4. ነብያት ከጻፏቸው መጻሕፍት ይዘት አንጻር ለስንት ይከፈላሉ ዘርዝሩ
5. ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በሴቶች ስም የተጠሩ መጻሕፍትን ዘርዝሩ
6. የአዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍትን ዘርዝሩ

ትዕዛዝ 2፡- በ”ሀ” ስር ያሉትን በ”ለ” ስር ካሉት ጋር አዛምዱ


ሀ ለ

1 መጽሐፈ ኩፋሌ ሀ. ወደ እብራውያን ሰዎች


2 የመልዕክታት ብዛት ለ. 81
3. የኦሪት መጻሕፍት ብዛት ሐ. አራተኛው የመቃብያን መጽሐፍ
4. ቅድስት ቤተክርስቲያን በቀኖናዋ የምትቀበላቸው መ. ወደ ፊልጵዮሲስ ሰዎች
መጻሕፍት ብዛት ሠ. 21
5 ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስሙን ያልጠቀሰበት ረ. ቅዱስ ጴጥሮስ
መጽሐፍ ሰ. 17

ምዕራፍ አራት
አዋልድ መጻሕፍት
41 የቃሉ ትርጉም ፡- አዋልድ መጻሕፍት ማለት የመጻሕፍት ልጆች ማለት ሲሆን ልጅነታቸውም
ለአስራው መጻሕፍት ነው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በቅርፃቸውም ሆነ በይዘታቸው ከአስራው መጻሕፍት ጋር
የሚመሳሰሉ በቤተክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖትን፣ ሥርዓትን፣ እምነትና ክርስቲያናዊ ትውፊትን መሰረታውያን
የሆኑትን ንባብ እንጂ ትርጓሜ ጥሬ ቃል እንጂ ትንታኔ የሌላቸው ቀጥራቸው ሰማንያ አንድ የሆኑትን መጻሕፍትን
(አስራው መጻሕፍትን) የሚተነትኑ፣ የሚተረጉሙ፣ ምስጢሩን የሚያራቅቁ255 ትርጓሜውንም የአቃንተው
የሚያቀርቡ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ይህም ማለት በቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት አተናተን መሰረት አስራው መጻሕፍት
ብሉያት ቅዱሳት መጻሕፍት256 ንባብ አዲሳት ቅዱሳት መጻሕፍት257 አዋልድ መጻሕፍት258 ደግሞ ትርጓሜ ናቸው፡፡

42 የአዋልድ መጻሕፍት አስፈላጊነት


አዋልድ መጻሕፍት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸው አስፈላጊነት እንዲህ በቀላሉ ተዘርዝሮ የማያልቅ እጅግ
የላቀና ከፍ ያለ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዋ ማለትም በጸሎቷ፣ በትምህርቷ፣ ምስጢራትን
ለመፈጸም እና ለምስጋናዋ የአዋልድ መጻሕፍትን በእጅጉ ትጠቀማለች፡፡ ለአብነትም፡-
 በቤተክርስቲያን ለሚካሄደው ጸሎት ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ ለጸሎተ ቅዳሴ፣ ለሰዓታት ጸሎት፣
ወዘተ...
 ለቤተክርስቲያን ለፈጣሪዋ ምስጋና የምታቀርበው በአብዛኛው በእነዚህ መጻሕፍት በመታገዝ ነው፡፡
 እነዚህ መጻሕፍተ ለቤተክርስቲያን ህግና ሥርዓት ለማስጠበቅ ዋነኛ ተጠቃሽ ናቸው
 በቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሰውን ጥቅስ ያብራራሉ

255
ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ በምስጢራዊ ትርጉም ስለሚተረጎም ያንን ትርጉም የሚተረጉሙ መጻሕፍት ናቸው፡፡
256
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት
257
የአዲስ ኪዳን መጻህፍት
258
በሌላ ስያሜያቸው መጻሕፍተ ሊቃውንት ይባላሉ፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 69
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 ብሉያትንና ሐዲሳትን አስማምተው ምስጢሩ የረቀቀውን አጉልተው ቃሉ መሰረቱን ሳይለቅ ለሰው


እንደሚገባ አድርገው በመተርጎም የሃይማኖትን ምስጢር የሥነ ምግባር ትሩፋት ነገርን መማሪያና
ማስተማሪያ መመከሪያና መምከሪያ በመሆኑ የጠለቀና የመጠቀ ጥቅም አላቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ መጻሕፍት በቀጥታ ለአምላክ ምስጋና ማቅረቢያ እና ለጸሎትም እንዲሆኑም
ታስበው በቅዱሳን አበው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የቅዱሳን መላእክትን ተልዕኮ፣ ባለሟልነት፣ ክብርና
ቅድስና የቅዱሳን ነብያትንና ሐዋርያትን፣ የጻድቃንና ሰማዕታትን ትሩፋታቸውን፣ ገድላቸውን፣ ቅድስናቸውን
ጸጋቸውን እና ከፈጣሪም የተቀበሉትን ቃል ኪዳን በሰፊው የሚገልጡ ለሌላውም መልካም ምሳሌነት በቀላሉ
የሚያሳውቁ የትምህርትና የጸሎት መጻሕፍት ናቸው፡፡
 “በመጽናትና መጻሕፍት የሚሰጡት መጽናናትና ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈ ሁሉ
ለትምህርታችን ተጽፏል” ሮሜ 15፡4
 “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ
ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ሁሉ
ይጠቅማል፡፡” 2ጢሞ 3፡116-17

43 የአዋልድ መጻሕፍት ጸሐፊዎች


እነዚህ መጻሕፍትን የጻፏቸው በተለያዩ ዘመናት የተነሱ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ናቸው፡፡ ሊቃውንቱም
መጻሕፍቱን ሲጽፏቸው ከራሳቸው ልብ አፍልቀውና አመንጭተው ሳይሆን አስቀድሞ ነብያቱንና ሐዋርያቱን
እንዲሁም አርድዕቱን ያጻፈ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሊቃውንቱም ላይ አድሮ ምስጢሩንና ጥበቡን
ገልጦላቸው በእርሱ እየተነዱ ጽፈውታል፡፡ መጻሕፍቱን ሲጽፏቸው የብሉይ ኪዳንና የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን
ጥቅስ በመያዝና እነርሱን መነሻና መሰረት በማድረግ ታሪኩን ሳይደመስሱ ምስጢሩን ሳያፋልሱ በታላቅ ጥንቃቄና
በፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲሁም በጥልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት በመነሳት ጽፈዋል፡፡ ሊቃውንቱ አበዛኞቹን
መጻሕፍት የጻፉበት ዘመን ወንጌል መስፋፋት ከጀመረችበት ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አንስቶ እስከ
በቤተክርስቲያን የተነሱ መናፍቃንን ድል እስከተነሱበት ዘመን ድረስ ነው፡፡

44 አዋልድ መጻሕፍት የአስራው መጻሕፍት ልጆች መሆናቸው በምን ይታወቃል/?/csjrfkl?


የተወደዳችሁ ተማሪዎች ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው አዋልድ መጻሕፍት የሚባሉት የአስራው ወይም
የሰማንያ አንዱ መጻሕፍት ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በይዘታቸው ከአስራው መጻሕፍት ጋር ተመሳሳይ
መሆን አለባቸው፡፡ በይዘታቸው ከአስራው መጻሕፍት የሚለዩ ከሆነ ከአዋልድ መጻሕፍት ሊመደቡ አይችሉም፡፡
እናም አዋልድ መጻሕፍት የአስራው መጻሕፍት ልጆች መሆናቸውን የምናውቅበት መንገዶች አሉ እነርሱም፡-

ሀ. በይዘታቸው፡- አስራው መጻሕፍት የተሰኙት ሰማንያ አንዱ መጻሕፍት በአይነታቸው የህግ፣


የታሪክ፣ የመዝሙር የጥበብና የቅኔ እንዲሁም የትንቢት ተብለው እንደሚከፈሉ ሁሉ የእነርሱ ልጆች የሆኑት
አዋልድ መጻሕፍትም በተመሳሳይ መልኩ ይከፈላሉ፡፡
 የሕግ መጻሕፍት የሚባሉት በይዘታቸው ስለቤተክርስቲያን እና ስለክርስቲያናዊ ኑሮ ሕግና ሥርዓት
የወጣባቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ፍትሐ ነገስት
 የታሪክ መጻሕፍት የሚባሉት የቅዱሳኑን ታሪክ እና ተጋድሎ የሚናገሩ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡-
ተዓምረ ማርያም፣ገድላት
 የጥበብ የቅኔ የመዝሙርና የጸሎት መጻሕፍት የሚባሉት ቅዱሳን አበው በተለያየ ጊዜ የጸለዩትና እኛም
ለጸሎት የምጠቀምባቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ ለአብነትም፡- ውዳሴ ማርያም፣ ወዳሴ አምላክ
 የትንቢት መጻሕፍት የሚባሉት ደግሞ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን አበው ላይ አድሮ ወደፊት
የሚሆነውን የገለጠባቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ ለአብነትም፡- ራዕየ ማርያም፣ ፉካሬ ኢየሱስ

ለ. በባለቤታቸው፡- እነዚህ መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ ነጂነት በመጻፋቸው ባለቤታቸው ቤተክርስቲያን


ናት፡፡ የብሉይም ሆነ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ባለቤት ቤተክርስቲያን እንደሆነች ሁሉ ይህም ማለት ቅዱሳን
ነብያት፣ ሐዋርያትና አርድዕት የጻፏቸውን መጻሕፍት ለቤተክርስቲያን አውርሰዋል፡፡ እንደዚሁ ሁሉ የአዋልድ
መጻሕፍት ጸሐፍያን የሆኑት አበው የቤተክርስቲያን ልጆች እንደመሆናቸው መጻሕፍቱን በመንፈስ ቅዱስ

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 70
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ነጂነት ከጻፉ በኋላ ለቤተክርስቲያን አውርሰዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህ መጻሕፈት የቤተክርስቲያን በመሆናቸው
ለትርጉማቸውና ለምስጢራቸው ጭምር መጠየቅ ያለባት ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት፡፡

ሐ. በቅድስናቸው፡- አስራውንም ሆነ አዋልድን መጻሕፍት ያጻፈው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡


አባትንም ልጅንም ያስገኘ መንፈስ ቅዱስ የአስራው መጻሕፍት ጸሐፊያንን እንደባረከ፣ እንደመረጠና ከስህተትም
እንደጠበቀ ሁሉ የአዋልድ መጻሕፍት ጸሐፍያንን መርጧል፣ ባርኳል እንዲሁም ቀድሷል በመሆኑም አስራውንና
አዋልድ መጻሕፍትን በአንድነት ቅዱሳት መጻሕፍት ብለን እንጠራቸዋለን፡፡
 “ከሕጻንነትህ ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ
የሚችሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን አውቀሃልና” 2ጢሞ 3፡15

45 የአዋልድ መጻሕፍት መሰረታቸው ምንድን ነው?


አዋልድ መጻሕፍት መሰረታቸውና አባታቸው አስራው መጻሕፍት ናቸው፡፡ ይህ በመሆኑ እነዚህ መጻሕፍት
ጠባያቸውንም የሚወርሱት ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በአይነት በአይነታቸው ተመድበው ሲጠሩ
ድርሳን፣ ተአምር፣ ገድል፣ መጽሐፈ ታሪክ ይባላሉ፡፡ ሆኖም ዋና ዋናዎቹን መመሳሰል ለአብነት ያክል
እነደሚከተለው እንጠቅሳለን፡-
 ወንጌልን የሚስለው ተኣምረ ኢየሱስ
 ግብረ ሐዋርያትን የሚመስለው ተኣምረ ማርያም
 ራዕየ ዮሐንስን የሚመስለው ራዕየ ማርያም ወዘተ... መጥቀሰ ይቻላል፡፡

46 የአዋልድ መጻሕፍት ዝርዝር


የተወደዳችሁ ተማሪዎች በዚህ ክፍለ ትምህርት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን
የተወሰኑትን አዋልድ መጻህፍትና የጸሐፊያኑን ማንነት፣ ሀገር እና ማዕረግ እንዲሁም የመጽሐፉን ይዘት በዝርዝር
በሠንጠረዥ አድርገን በዝርዝር ለመመልከት እንሞክራለን ተከተሉን፡-

ተ.ቁ የመጽሐፉ መጠሪያ ጸሐፊው ማዕረግ/ ሀገር የመጽሐፉ ይዘት


ስም
1. ማር ይስሐቅ ቅዱስ ማር ይስሐቅ መነኮስ/ ሶሪያ ሥጋዊ ፈተናን ስለማሸነፍ
2. ፊልክስዩስ ቅዱስ ፊልክስዩስ ኤጲስ ቆጶስ/ ሶሪያ ስለ ሥጋዊ ፈተናና አሸናፊዎች
3. አረጋዊ መንፈሳዊ ቅዱስ አረጋዊ መነኮስ/ ግብጽ ሥጋዊ ፈተናን በማሸነፍ ስለሚገኝ ክብር
4. ድጓ ቅዱስ ያሬድ ካህን/ ኢትዮጵያ በበዓላት የሚደረስ የዜማ መጽሐፍ
5. ጾመ ድጓ ቅዱስ ያሬድ ካህን/ ኢትዮጵያ በአብይ ጾም የሚዘመር የዜማ መጽሐፍ
6. ምዕራፍ ቅዱስ ያሬድ ካህን/ ኢትዮጵያ በወርኅ ጾም የሚዘመር የዜማ መጽሐፍ
7. ዝማሬ ቅዱስ ያሬድ ካህን/ ኢትዮጵያ ከቅዳሴ በኋላ የሚዘመር የዜማ መጽሐፍ
8. አንቀጸ ብርሃን ቅዱስ ያሬድ ካህን/ ኢትዮጵያ የእመቤታችን የምስጋና መጽሐፍ
9. መጽሐፈ ቄደር ቅዱስ ፊሊጶስ ካህን/ ኢትዮጵያ በንስሐ ጊዜ የሚጸለይ የጸሎት መጽሐፍ
10. መጽሐፈ ብርሃን ቅዱስ ዘርያቆብ259 ካህን/ ኢትዮጵያ ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንና ነገረ
ሃይማኖት የሚያትት
11. መጽሐፈ አርኬ ቅዱስ አርክ ሥሉስ ካህን/ ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ጥያቄዎችን እና መልሶችን
የያዘ መጽሐፍ
12. ርቱዐ ሃይማኖት ቅዱስ ርቱዐ ያዕቆብ መነኮስ/ ኢትዮጵያ ስለ ሥነ ፍጥረት የሚያትት
13. መጽሐፈ ተአቅቦ ቅዱስ ዘርዐ ያዕቆብ ካህን ኢትዮጵያ ስለ ከንቱ ወሬና ተርታ ንግግሮች
የሚያትት መጽሐፍ

259
ይህ ቅዱስ አባት ኢትዮጵያን በንግስና አስተዳድሯል፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 71
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

14. መጽሐፈ ሰዓታት ቅ/ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መነኮስ/ ኢትዮጵያ


በቤተክርስቲያን ለሊት በዜማ የሚጸለይ
15. መጽሐፈ አርጋኖን ቅ/ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መነኮስ/ ኢትዮጵያ
የእመቤታችን ምስጋና
16. መጽሐፈ ምስጢር ቅ/ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መነኮስ/ ኢትዮጵያ
የነገረ ሃይማኖት መጽሐፍ
17. መጽሐፈ ኖኅተ ብርሃን ቅ/ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መነኮስ/ ኢትዮጵያ
የእመቤታችን ምስጋና
18. ተአምኖ ቅዱሳን ቅ/ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መነኮስ/ ኢትዮጵያ
ስለ ቅዱሳን ምልጃ የሚያትት
19. መጽሐፈ ባሕርይ ቅ/ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መነኮስ/ ኢትዮጵያ
ስለ ምስጢረ ሥላሴና ምስጢረ ስጋዌ
የሚያትት
20. መጽሐፈ ቄርሎስ ቅዱስ ቄርሎስ ፓትርያርክ/ ግብጽ ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንና ሃይማኖት
የሚያስረዳ መጽሐፍ
21. መጽሐፈ ምዕዳን ቅዱስ ጢሞቲዎስ ፓትርያርክ/ ግብጽ ስለ ክርስቲያኖች ሐዘንና መከራ
የሚያትት
22. መጽሐፈ ጊዮርጊስ ቅዱስ ጊዮርጊስ መነኮስ/ ግብጽ የሥነ ፍጥረትን ታሪክ የሚናገር
ወአሚድ ወአሚድ መጽሐፍ
23. መጽሐፈ ባሕል ቅዱስ ገብርኤል መነኮስ/ ግብጽ በቤተክርስቲያን አባቶች የተሰበሰቡ
ወ/በሬክ ብሂሎችና የሥነ ምግባር መመሪያዎችን
የያዘ መጽሐፍ
24. መጽሐፈ አቡሻኸር ቅዱስ አቡሻኸር መነኮስ/ ግብጽ ስለ ዘመናት አቆጣጠር
25. ድርሳነ ማርያም ቅዱስ ሚናስ ኤጲስ ቆጶስ/ ስለ እመቤታችን አማላጅነትና ተኣምራት
ኢትዮጵያ የሚያትት
26. ድርሳነ ሚካኤል ቅዱስ ማቴዎስ ፓትርያርክ/ ግብጽ ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና
ተኣምራት የሚያትት
27. ድርሳነ ባስልዮስ ቅዱስ ባስልዮስ ፓትርያርክ/ ቂሳርያ ስለ ነገረ መላዕክት የሚያትት
ዘቂሳርያ
28. ድርሳነ ፍስለታ ቅዱስ ቄርሎስ ፓትርያርክ/ ግብጽ ስለ እመቤታችን ትንሳኤና ዕርገት
እንደዲሁም ስለ ነገረ ሃይማኖት
የሚያስረዳ
29. ገድለ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ ዮሐንስ እጨጌ/ ኢትዮጵያ ስለ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ተጋድሎ
፣ አማላጅነት እና ስላደረጉት ገቢረ
ተኣምራት የሚያትት መጽሐፍ
30. ገድለ ክርስቶስ ሰምራ ቅዱስ ፊሊጶስ እጨጌ/ ኢትዮጵያ ስለ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ተጋድሎ
አማላጅነትና ስለፈጸመቻቸው ገቢረ
ተኣምራት የሚያትት መጽሐፍ
31. ገድለ ጊዮርጊስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ ኤጲስ ቆጶስ/ ገላትያ ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋድሎ
አማላጅነትና፣ ስለ አደረጋቸው ገቢረ
ተኣምራት የሚያትት መጽሐፍ
32. ውዳሴ ማርያም ቅዱስ ኤፍሬም ካህን/ ሶሪያ የእመቤታችን ምስጋና
33. ቅዳሴ ማርያም ቅዱስ ሕርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ/ ግብጽ የቅዳሴ መጽሐፍ
34. ተኣምረ ማርያም ቅዱስ ደስቅዮስ ኤጲስ ቆጶስ/ ግብጽ ስለ እመቤታችን ተራዳኢነት የሚያትት
35. ራዕየ ማርያም ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ/ እስራኤል ስለእመቤታችን ተራዳኢነትና አማላጅነት
የሚናገር
36. መልክአ ማርያም ቅዱስ ዘርዐ ያዕቆብ ካህን/ ኢትዮጵያ የእመቤታችን ምስጋና የሚናገር የመልክዕ
ድርሰት
37. መልክአ ጊዮርጊስ ቅዱስ ዘርዐ ያዕቆብ ካህን/ ኢትዮጵያ የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ምስጋና
የሚናገር የመልክዕ ድርሰት

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 72
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

38. መልክአ ኢየሱስ ቅ/ ዓምደ ሐዋርያት መነኮስ/ ኢትዮጵያ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ
ክርስቶስን የማዳን ስራና ምስጋና
የሚናገር የመልክዕ ድርሰት
39. መልክአ ሥላሴ ቅዱስ ስብሐት ለአብ መነኮስ/ ኢትዮጵያ የቅድስት ሥላሴን ምስጋና የሚናገር
የመልክዕ ድርሰት
40. ባሕረ ሀሳብ ቅዱስ ድሜጥሮስ ፓትርያርክ/ ግብጽ የበዓላትና የአጽዋማት ዘመን መቁጠሪያ
መጽሐፍ
41. ራዕየ ፊቅጦር ቅዱስ ፊቅጦር መነኮስ/ ግብጽ ትንቢታዊ መጽሐፍ
42. ረድዕ እንጦስ ቅዱስ ጊዮርጊስ መነኮስ/ ግብጽ ስለ ነገረ ሃይማኖትና ስለ መነኮሳት
ተልሙድ ህይወት የሚያትት
43. ፈውስ መንፈሳዊ ቅዱስ ሚካኤል ኤጲስ ቆጶስ/ ስለ ንስሐ፣ ኃጢአት፣ ነገረ ሃይማኖትና
ኢትዮጵያ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሚያትት
44. ውዳሴ አምላክ ቅ/ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ፓትርያርክ/ ቂሳርያ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ
ክርስቶስ ምስጋና
45. መጽሐፈ አክሲማሮስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ኤጲስ ቆጶስ/ የሥነ ፍጥረትን ጥንተ ታሪክ የሚያትት
ቆጵሮስ
46. ምስጢረ ሰማይ ቅ/ አባ ኃይለ ሚካኤል መነኮስ/ ኢትዮጵያ ስለ ፈጣሪ ሥነ ፍጥረትና ራዕይ የሚናገር
ወምድር መጽሐፍ
47. ሥርዓተ ቤክርስቲያን ቅ/ ዮሐንስ አፈወርቅ ፓትርያሪክ/ ሶሪያ ስለቤተክርስቲያን ሥርዓት የሚያትት
መጽሐፍ
48. አዕማደ ምስጢር ቅ/ ዮሐንስ አፈወርቅ ፓትርያርክ/ ሶርያ ስለ አምስቱ አዕማደ ምስጢራት
የሚያትት መጽሐፍ
49. የቅዱስ ዮሐንስ ቅ/ ዮሐንስ አፈወርቅ ፓትርያርክ/ ሶርያ የነገረ ሃይማኖትና የሥነ ምግባር
ድርሳንና ተግሳጽ መጽሐፍ

ሠንጠረዥ 2፡- የቤተክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት

ውድ ተማሪዎች ከላይ በዝርዝር የተመለከትናቸው ቤተክርስቲያን ለተለያየ አገልግሎት የምትጠቀምባቸውን


አዋልድ መጻሕፍትን ነው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት ምዕመናን በተለያየ ጊዜ ለተለያየ አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው
ናቸው፡፡ ከዚህ የምንረዳው ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለሥርዓተ አምልኮቷ የምትጠቀምባቸው ቀጥራቸው በዛ ያሉ
አዋልድ መጻሕፍት እንዳሏት ነው፡፡ እናም እነዚህ መጻሕፍት በይዘታቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ ነገር ግን ዋና ዋናዎቹን
በዓይነት በዓይነት ስንመድባቸው እንደሚከተለው ነው፡-

ሀ. አንድምታ (የቤተክርስቲያን የትርጓሜ መጻሕፍት)


እነዚህ መጻሕፍት የቤተክርስቲያንን አስራው መጻሕፍትን ምስጢር የሚያብራሩ የራቀውን አቅርበው
የረቀቀውን አጉልተው የሚያሳዩ መጻሕፍት ናቸው፡፡ የተወደዳቸሁ ተማሪዎች በምዕራፍ 2 ትምህርታችን ላይ
መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት መተርጎም እንደሚገባው ተማምረናል በዛ ክፍል ውስጥ ካየናቸው የትርጓሜ ዘዴዎች
መካከል ምሳሌያዊ ትርጉም እና ምስጢራዊ ትርጉም ይገኙበታል፡፡ በትርጓሜ መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስን
ምስጢራዊም ሆነ ምሳሌያዊ ትርጉም እነረዳ ዘንድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በመራቸው ቅዱሳን አባቶች
(ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን) እነዚህ የትርጓሜ መጻሕፍት ተጽፈዋል፡፡ ከላይ ለመግለጥ እንደሞከርነው መጽሐፍ
ቅዱስ ንባብ በመሆኑ እርሱን በምናነብበት ጊዜ የግድ የነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት አጋዥነት ያስፈልገናል፡፡
በባሕርያቸውም ምስጢራትን የሚፈቱ የረቀቀውን የሚያጎሉ በመሆናቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ኃይለ ቃላት
ለመረዳትና ቃሉ ለማን፣ ለምን፣ እንዴት፣ወዘተ... እንደተነገረና እንደሁም ውስጡ ያዘለው ምሳሌም ሆነ ምስጢር
ለመረዳት የግድ የነዚህ መጻሕፍት አስፈላጊነት የጎላ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም መጻህፍትን በምናነብበት ወቅት
የራቀውን የሚያቀርቡልን የረቀቀውን የሚያጎሉልን አጋዦች እንደሚያስፈልጉን በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መረዳት

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 73
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

እንችላለን፡፡ እርሱም ቅዱስ ፊሊጶስ ወደ እርሱ ቀርቦ የሚያነበውን ነገር ምን ያህል እንደሚያስተውል በጠየቀው
ጊዜ የመለሰው መልስ ይህንኑ የሚያስዳ ነው፡፡
 “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል” ሐዋ 8፡31

እናም እኛም መጽሐፍ ቅዱስን በምናነብበት ወቅት የመጽሐፍ ቅዱሱን ሃሳብ በአግባቡ እንድንረዳ
የሚያደርጉንን የቤተክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍትን ልናነብ በእነርሱ ልንመራና ልንታገዝ ይገባል፡፡ ያለዚያ
መጻሕፍትን ያለእነርሱ አጋዥነት የማናነብ ከሆነ መጻሕፍትን በራሳችን መንገድ ባሻን አተረጓጎም እንተረጉማለን
ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የተከለከለ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ማንም መጻሕፍትን በራሱ መንገድ ሊተረጉም እንደማገባ
አስተምሮናል፡፡260 እናም መጽሐፍ ቅዱስን በእነዚህ መጻሕፍት አጋዥነት ልናነብ ያስፈልጋል፡፡ በቤተክርስቲያናችን
የተለያዩ የአንድምታ መጻሕፍት ይገኛሉ ለአብነትም፡- ትርጓሜ ወንጌል፣ የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክታት ንባቡና
ትርጓሜው፣ የትንቢተ ኢሳይያስ አንድምታ፣ ሰለስቱ ሐዲሳት ንባቡና ትርጓሜው፣ የመዝሙረ ዳዊት ንባቡና
ትርጓሜው፣ወዘተ.... መጥቀስ ይቻላል፡፡

ለ. ስንክሳር
ስንክሳር ማለት ስብስብ ማለት ሲሆን ከቃሉ እንደምንረዳው በይዘቱ የሥላሴን አንድነትና ሶስትነት፣
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን ከመግለጡም በተጨማሪ የቅዱሳን መላዕክትን፣ የቅዱሳን
ነብያትን፣ የቅዱሳን ሐዋርያትን፣ የቅዱሳን ጻድቃንና የቅዱሳን ሠማዕታትን፣ወዘተ.... ተጋድሎ፣ ተኣምራት፣
ትሩፋትና መታሰቢያ በየዕለታቱ የሚዘክር የታሪክ ይዘት ያለው መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ የተለያዩ ምንጮችን
መሰረት በማድረግ የተጻፈ ሲሆን በተለይም የብሉያትንና የሐዲሳት መጻሕፍትን መሰረት በማድረግ የተጻፈ
መጽሐፍ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ይህ መጽሐፍ የተለያዩ ቅዱሳን አባቶች በመንፈስ ቅዱስ በመመራት የጻፏቸው
መጻሕፍት ስብስብ ሲሆን አጻጻፉም በየዕለቱ እንዲነበብ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህንን መጽሐፍ በመንፈስ ቅዱስ
ነጂነት ያዘጋጁት የአትሪብ ኤጲስ ቆጶስ አባ ሚካኤል፣ የብሩልስ ኤጲስ ቆጶስ አባ ዮሐንስና ሌሎች ቅዱሳን አባቶች
ናቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ በዋናነት የቅዱሳንን ተጋድሎና ተኣምራት እንደመያዙ ምዕመናን ቅዱሳንን በመዘከር
የሚገኘውን ጸጋ261 ተካፋይ እንዲሆኑ የሚረዳ መጽሐፍ ከመሆኑም በተጨማሪ የእምነት ዋኖቻችንን በማሰብ
እነርሱ በሄዱበት ፍኖት እንድንጓዝ የሚረዳ መጽሐፍ ነው፡፡262

ሐ. የጸሎት መጻሕፍት
ለጸሎት የምንጠቀምባቸው መጻሕፍት ቅዱሳን አባቶች መጽሐፈ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመንፈስ ቅዱስ
መሪነት የጻፏቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት ቅዱሳኑ በተለያየ ጊዜ የጸለዮአቸው ጸሎቶች ሲሆኑ
እኛም በእነርሱ አንደበት የተመሰገነ እግዚአብሔርን ለማመስገን ለጸሎት የምንጠቀምባቸው ናቸው፡፡ በዋናነት
መጻሕፍቱ ለማኀበር የሚያገለግሉ፣ ለዘወትርና በተሠወኑ ዕለታት የምንጠቀምባቸው፣ ለካህናትና ለምዕመናን
ተብለው የተለዩ በንባብና በዜማ የሚደርሱ የምስጢር መፈጸሚያ እየልን ከፋፍለን ማየት እንችላለን፡፡

 ለግል ጸሎት የሚያገለግሉ የምንላቸው መጻሕፍት በየጊዜውና በየሰዓቱ ለግል ጸሎት የምንጠቀምባቸው
መጻሕፍት ሲሆኑ ለአብነትም ውዳሴ ማርያም፣ ውዳሴ አምላክ፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ወዘተ... ይጠቀሳሉ፡፡
 ለማህበር ጸሎት የሚያገለግሉ እነዚህ ምዕመናን በቤተክርስቲያን እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች
የሚጠቀሙባቸው ናቸው፡፡ ለምሣሌም መጽሐፈ ቅዳሴ (የ14ቱ ቅዳሴያት መጽሐፍ) ተጠቃሽ ነው፡፡
 ለዘወትር ጸሎት የሚየገለግሉ የምንላቸው ምዕመናን በዘወትር የጸሎት ሕይወታቸን ውስጥ በየዕለቱ
የሚጠቀሙባቸው ሲሆኑ ለአብነትም የዘወትር ጸሎት፣ ውዳሴ ማርያም፣ ውዳሴ አምላክ ወዘተ…
ይጠቀሳሉ

260
2ኛ ጴጥ 1፡20
261
ማቴ 10፡41-42
262
ዕብ 13፡7
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 74
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

 በተወሰኑ ዕለታትና በበዓላት የሚያገለግሉ መጻሕፍት የሚባሉት በንዑሳንና በአበይት በዓላት እንዲሁም
በተለያዩ ወቅቶች የሚያገለግሉ ሲሆኑ ለምሣሌም ግብረ ሕማማት፣ ማህሌተ ጽጌ፣ ፆመ ድጓ፣ ድጓ፣
ወዘተ … ተጠቃሽ ናቸው፡፡
 ለካህናትና ለምህመናን የሚያገለግሉ የምባሉት ደግሞ ለካህናት ኪዳን፣ ሊጦን፣ መስተብቁ፣ ዘይነግስ
እንዲሁም ለምዕመናን፡- ውዳሴ እግዚዕ፣ ውዳሴ ማርያም፣ ጸሎተ ሃይማኖት፣ መዝሙረ ዳዊት፣
ድርሳናት፣ ወዘተ... ናቸው፡፡
 ለምሥጢር መፈጸሚያ የሚያገለግሉ የሚባሉት ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ለመፈጸም የሚያገለግሉ ሲሆኑ
እነዚህም መጽሐፈ ተክሊል፣ መጽሐፈ ቅዳሴ፣ መጽሐፈ ክርስትና፣ መጽሐፈ ቀንዲል፣ መጽሐፈ ግንዘት
ናቸው፡፡
 በዜማ የሚደርሱ የምንላቸው መጽሐፈ ቅዳሴ፣ ኪዳን፣ ውዳሴ ማርያም፣ ማህሌተ ጽጌ፣ ጾመድጓ፣ ጽጓ፣
መጽሐፈ ግንዘት፣ ወዘተ….ናቸው

መ. ገድላትና ድርሳናት
ገድል ማለት ትግል፣ ፈተና፣ ውጊያ፣ ሰልፍ፣ ድልና አክሊል እስኪገኝ ድረስ የሚደክሙት ድካም፣
የሚሰሩት ሥራ፣ የሚቀበሉት መከራና ጸጋ እንዲሁም ተጋድሏቸውን የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ
ቅዱሳን ስለ ክርስቶስ ሲሉ የሚቀበሉትን መከራ፣ ስቃይ፣ ህማም እና የሚያሳዩትን ጽናት፣ ትዕግስት፣ወዘተ....
የሚያትት መጽሐፍ ነው፡፡ ይህም ቅዱሳን ሰማዕታት ስለክርስቶስ እጅ እግራቸውን ለስዕለት፣ አይናቸውን ለፍላት
ሰጥተው የፈጸሙትን መንፈሳዊ ተጋድሎ እና ቅዱሳን ጻድቃን የመዓልት ሐሩሩን የሌሊት ብርዱን ታግሰው፣ ዳዋ
ጥሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፣ ሌጦ ለብሰው፣ የአራዊቱን ግርማ ታግሰው በየዱሩና በየጢሻው እየኖሩ
ስለክርስቶስ ሲሉ መከራውን ሁሉ በመታገስ በጾም በጸሎት በመጽናት የፈጸሙትን ተጋድሎ የሚዘክር መጽሐፍ
ነው፡፡ በአጠቃላይ ገድል ማለት ቅዱሳን ጻድቃንና ቅዱሳን ሠማዕታት በሕይወት ዘመናቸው የሰሩትን ታላቅ ስራ
የሚገልጥ መጽሐፍ ነው፡፡263 በውስጡም የቅዱሳኑን ተጋድሎ ከማተቱም በተጨማሪ እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ
የገባውን ቃል ኪዳንና ክብራቸውን የሚያትት መጽሐፍ ነው፡፡264 በተዘዋዋሪ ገድላት የቅዱሳንን ተጋድሎ ብቻ
ሳይሆን እግዚአብሔር እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ሕይወት ውስጥ የሰራውን ታላቅ ሥራ የሚዘክርና የሚያትት
መጽሐፍ ነው፡፡
 “ስለ ቅዱሳን መናገር ማለት በእነርሱ ላይ ጸጋውን ስላሳደረው ስለ እግዚአብሔር መናገር
ማለት ነው፡፡” ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ

ድርሳናት የሚባሉት የቅዱሳን መላእክት ክብር፣ ተራዳኢነት፣ እና ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣቸውን ቃል


ኪዳን የሚያትት መጽሐፍ ሲሆን በዋናነት በውስጡ ስለ ቅዱሱ መልአክ ማንነት ክብሩንና ስራውን የሚገልጥ፣
ያደረገውን ተኣምራት፣ የመልአኩ ተራዳኢነቱን የሚያትት መጽሐፍ ነው፡፡
 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል”
መዝ 33(34)፡7
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም የመላእክትን ክብር፣ ታራዳኢነት፣ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ክብር
የሚገልጡ ክፍሎች ይገኛሉ ለአብነትም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይመልከቱ፡- መሳ 13፡19፣ ዳን
3፡24፣ 6፡22፣ ሀዋ 12፡6፣ ወዘተ.... መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሠ. ተኣምራት
እነዚህ መጻሕፍት በዋናነት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፈው
የማናገኛቸውን ድንቅ ድንቅ ገቢረ ተኣምራት265፣ ጌታችንም ለቅዱሳኑ ይህች ተኣምር ትከተላቸዋለች ሲል በሰጠው

263
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ገጽ 301
264
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም የተለያዩ ቅዱሳን ተጋድሎዎች ተመዝግበው ይገኛሉ ለአብነትም በብሉይ ኪዳን የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ፣ የዳዊት፣ የነብዩ
ኤልያስ በአዲስ ኪዳን ደግሞ የቅዱሳን ሐዋርያት ተጋድሎዎች ተመዝግበው ይገኛል፡፡
265
በዮሐ 20፡30 ላይ “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ ተብሎ እንደተገለጸ ጌታችን በመዋዕለ ስጋዌው
ያደረጋቸው ድንቅ ተኣምራት ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ አይገኙም፡፡
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 75
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ተስፋ መሰረት ጻድቃን ሰማዕታት በሕይወተ ስጋ ሳሉ ከሞቱም በኋላ ስማቸው ከተጠራበት፣ ደመ ትረሩፋታቸው
በፈሰሰበት፣ ሥጋቸው በተቀበረበት፣ አጽማቸው በተከሰከሰበት፣ መታሰቢያቸው በሚደረግበት ሁሉ ሀይማኖታቸውን
ለመግለጥና ድንቅ ድንቅ ተኣምራት መስራታቸውን የሚያትት መጽሐፍ ነው፡፡

47 የአዋልድ መጻሕፍት ስናነብ ልንላቸው የሚገቡ ነጥቦች

 በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን የተገለጡ መሰረታዊ የሃይማኖት እና የሥነ ምግባር ትምህርቶችን ጠንቅቆ
ማወቅ
 የእግዚአብሔርን ከሃሊነትና ቸርነት ያለምንም ጥርጥር ማመን
 ለቅዱሳን የተሰጠውን ክብርና ሥልጣን መረዳት
 ከሥጋዊ ፍልስፍና ጋር ቀላቅሎ ለመረዳት አለመሞከር
 መጽሐፉ የተጻፈበትን ዘመን የነበሩትን ሁኔታዎች በማገናዘብ ማንበብ
 ከእምነት፣ ከዕውቀት፣ ከሕሊና በላይ የሆኑ ሥራዎች በእግዚአብሔር ረዳትነትና አከናዋኝነት እንደሚሰሩ
ማመን ወዘተ... ይጠቀሳሉ፡፡

48 የምዕራፍ አራት የክለሳ ጥያቄዎች

1. የሚከተሉትን መጻሕፍት ምንነት አስረዱ?


 ድርሳናት
 ገድላት
 ተኣምራት
 ስንክሳር
 አንድምታ
2. የአዋልድ መጻሕፍትን ጥቅም አስረዱ?
3. የሚከተሉትን አዋልድ መጻሕፍት ጸሐፊዎች ማንነት ግለጹ?
 ውዳሴ ማርያም
 መጽሐፈ አክሲማሮስ
 አንቀጸ ብርሐን
 ተኣምረ ማርያም
 ተኣምረ ኢየሱስ
 መልክአ ማርያም
 መልክአ ኢየሱስ
4. አዋልድ መጻሕፍት የአስራው መጻሕፍት ልጆች መሆናቸው በምን ይታወቃል በዝርዝር አስረዱ?
5. ለጸሎት ከምንጠቀምባቸው አዋልድ መጻሕፍት መካከል 5ቱን ጥቀሱ?

ማጠቃለያ
መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ወይም መሪነት የተጻፈ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ
መጽሐፍ በአስገኚው ቅድስና፣ በጸሐፊዎቹ ቅድስና እንዲሁም አንባቢያኑም እርሱን በማንበባቸው፣ በመስማታቸው
እንዲሁም በመከተላቸው ወደ ቅደስና ስለሚመራቸው ቅዱስ መጽሐፍ ይባላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ
ከመጽሐፍት ሁሉ ቀደምት፣ የሚያነቡትንና የሚሰሙትን የሚያንጽ እንዲሁም ስላለፈውና ወደፊት ስለሚመጣው
ነገር በእርግጠኝነት የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡ እናም ሰዎች አምላካቸው እግዚአብሔር ያስተላለፈላቸውን መልዕክት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያገኙታል፡፡ ስለዚህ ይህንን መጽሐፍ ማንበብ ተገቢ ነው፡፡ በምናነብበትም ወቅት
እንደሌሎች ተራ መጻሕፍት ሳይሆን የራሱ የሆኑትን የአነባበብ ዘዴዎች በመጠቀም ማንበብ ከዚያም አልፎ
መመርመር ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህንን ድንቅና ጥልቅ መጽሐፍ ያለበቂ እውቀትና ያለ ፈሪሃ እግዚአብሔር
ብዙዎች በድፍረት በተሳሳተ አተረጓጎም እና አገላለጽ ስለተረጎሙት ነው፡፡ ስለዚህ እኛ ራሳችንን ከነዚህ የስህተት

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 76
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ትርጉሞች ለመጠበቅ የመጽሐፍ ቅዱስን የአተረጓጎም ዘዴዎች ማወቅ ይህም ማለት የመጽሐፍ ቅዱስን የአጻጻፍ
ባሕል ጠንቅቆ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ቅዱሳን ሐዋርያትና ከእነርሱ
በኋላ የተነሱ ቅዱሳን አባቶች የጻፉልንን የአንድምታ መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማጣመር ልናጠና
ያስፈልጋል፡፡ ይህን የምናደርግ ከሆነ መናፍቃን ከሚያነሷቸው ትኛውም አይነት የምንፍቅና መርዞች ራሳችንን
ከዚያም አልፎ ተርፎ ሌሎች እህትና ወንድሞቻችንን መጠበቅ እንችላለን፡፡ በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስን ዘወትር
በምናነብበት ወቅት ወደ ስህተት እንዳናመራ ተገቢውን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ምስጢር
ለመረዳትና ለማወቅ ከዚያም አልፎ ለጸሎት፣ የቅዱሳንን ትሩፋት ለመዘከርና ከእነርሱ ጸጋ ተካፋይ ለመሆን፣
ለትምህርትና ለተግሳጽ፣ ወዘተ.... ወዘተ የሚረዱ የአስራው ቅዱሳት መጻሕፍት ልጆች የሆኑ አዋልድ መጻሕፍት
አሉ እነዚህ መጻሕፍፍ ቅዱሳን ሊቃውንት በመንፈስ ቅዱስ ነጂነት የጻፏቸው ሲሆኑ በይዘታቸውና በቅድስናቸው
ከአስራው መጻሕፍት ጋር ፍጹም ተመሳሳይ በመሆናቸው ከአስራው መጻሕፍት ልጆች መሆናቸው ይረጋገጣል፡፡
ከአዋልድ መጻሕፍት ለአብነትም አንድምታዎች፣ የጸሎት መጻሕፍት እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ለመረጣቸው መጻሕፍትን ይመረምሩ ዘንድ አዕምሯቸውን የከፈተላቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ


ለእኛም ለባሪያዎቹ ምስጢሩን ይገልጥልን ዘንድ ልክ እንደቤሪያ ሰዎች መጻህፍትን እንድንመረምር ጸጋውን
ያበዛልን ዘንድ የእርሱ የአምላካችን በጎ ፈቃድ ይሁንልን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

በደ/ፍ/መ/ሰ/ቅ/ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ው/ብ/ሰ/ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ

የግዕዝ ቁጥሮች
1.. ......... አንድ ፳........... ሀያ
2 ........ ሁለት #........... ሰላሳ
3 .......... ሶስት $.......... አርባ
4 .......... አራት %.......... ሃምሳ
5.......... አምስት 8......... ስልሳ
6..............ስድስት &.../ ........ ሰባ
7............ ሰባት . ...... ሰማንያ
*
8........... ስምንት (........... ዘጠና
9........... ዘጠኝ ).......... መቶ
፲........... አስር
በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 77
ለበጋ ኮርሠኞች የተዘጋጀ
[ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማስተማሪያ ኖት

ዋቢ መጻሕፍት
 መጽሐፍ ቅዱስ/ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር
 የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት/ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር
 የትንቢተ ኢሳይያስ አንድምታ ትርጓሜ
 የትንቢተ ሚክያስ አንድምታ ትርጓሜ
 መጽሐፈ ሰዋሰው ወግ/ በአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
 መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ዘዴ/ በመምህር ቸርነት አበበ
 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት/ በአባይነህ ካሴ
 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት /የደብረ /ፍ/መ/ሰ/ቅቂ/ቤ/ያን/ዉ/ብ/ሠ/ት/ቤት የርቀት መማሪያ መጽሐፍ/
 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት/ የማህበረ ቅዱሳን ጊቢ ጉባኤያት ማስተማሪያ መጽሐ
 ጉዞ ወደ እግዚአብሔር/ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነሺኖዳ
 የክፍሉ የበፊት የማስተማሪያ ኖቶች እና የተለያዩ ማስታወሻዎች

በደብረ ፍስሐ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ዉሉደ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ ትምህርት ክፍል| 78

You might also like