You are on page 1of 23

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦

www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
ማኅበረ ቅዱሳን

አምስቱ አዕማደ ምሥጢር

መ/ር ምሥጢረሥላሴ ማናዬ


ምዕራፍ ሁለት
ምሥጢረ ሥላሴ
❑ የምሥጢረ ሥላሴ ምንነት

❑ ምሥጢረ ሥላሴን የሚያስረዱ ተፈጥሮአዊ ምሳሌዎች

❑ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
2.3 ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች

❖ የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት አፈ ታሪክ (Legend) ሳይሆን በቅዱሳን መጻሕፍት ምስክርነት ላይ


የተመሠረተ፣ በራሱ በልዑል እግዚአብሔር የተገለጠ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት ነው፡፡

❖ ይህንንም ለማስረገጥ፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎችን በሦስት ከፍለን እናያለን፦


✓ ብሉይ ኪዳን
✓ ሐዲስ ኪዳን
✓ መጻሕፍተ ሊቃውንት

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሀ፣ የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች
❖ “... እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር።” ዘፍ 1፡26
➢ ይህ ጥቅስ በራሱ በእግዚአብሔር ባሕርይ አንድነትና ሦስትነት እንዳለ ይነግረናል።
✓ “...እግዚአብሔርም አለ...” የሚለው አንድነቱን፣
✓ “... ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር።” የሚለው ደግሞ ሦስትነቱን
ያመላክታል።
❖ በተመሳሳይ መልኩ የሚከተሉትን ጥቅሶችን እንመልከት ...
➢ “... እግዚአብሔር አምላክ አለ እነሆ አዳም መልካሙንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ
ሆነ።” ዘፍ.3÷22

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሀ፣ የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች ...
➢ “... ኑ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።”
ዘፍ.11፡7

➢ “... እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን


ሞልቶት ነበር፡፡ ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤
በሁለቱም ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበረ፤ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበረ፤ በሁለቱም ክንፍ
ይበር ነበር፤ ... አንዱም ለአንዱ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ
ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር፡፡ ...” ኢሳ 6፡1- 3

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሀ፣ የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ ከላይ የተዘረዘሩት አራቱ ጥቅሶች፣ እግዚአብሔር ከአንድነቱ ጋር ብዝኃነት እንዳለው
እንጂ ሦስትነቱን በግልጽ አልገለጡም።

❖ በብሉይ ኪዳን፣ አንድነቱና ሦስትነቱ በአንፃራዊነት ግልጽ በሆነ መንገድ የተገለጠው


እግዚአብሔር በአባታችን በአብርሃም ቤት በእንግድነት በተገለጠበት ጊዜ ነው።

❖ ዘፍ.18፥1-33 ያለውን ልብ ብለው ይመልከቱ።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሀ፣ የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ “በቀትርም ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ ዛፍ
ሥር ተገለጠለት። ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፣ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤
ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤
እንዲህም አለ፣ ‘አቤቱ በፊትህስ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈው፤
ውኃ እናምጣላችሁ፤ እግራችሁንም እንጠባችሁ።...’ እነርሱም፣ ‘እንዳልህ እንዲሁ
አድርግ’ አሉት። ... እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤
እነርሱም በሉ። ...” ዘፍ.18፥1-8
✓ በቀይ የተቀለሙት አንድነቱን ሲገልጡ፣ በወይን ጠጅ ያሉት ሦስትነቱን የሚገልጡ ናቸው።
✓ ቀሪውን ገጸ ንባብ (ዘፍ.18፥9-33) እያነበቡ ከላይ ባለው መሠረት ለመለየት
ይሞክሩ።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሀ፣ የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች ...
አንድነቱን የሚያመለክቱ ሦስትነቱን የሚያመለክቱ
“...እርሱም ‘ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?’ አለው። ...” “... አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፣ ‘ሦስት
ዘፍ.18፥9 መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ ለውሺ፤...’አላት።...”ዘፍ.18፥6
“... እርሱም፣ ‘የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመልሼ “...እርጎና መዓር፣ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፣ በፊታቸውም
እመጣለሁ፤...’...” ዘፍ.18፥10 አቀረበው፤...”ዘፍ.18፥8
“...እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፣ ‘ሣራን ለብቻዋ “... እነዚያም ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶምና ገሞራ አቀኑ፤
በልብዋ ምን አሳቃት?...’..”ዘፍ18፥14-15 አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ...” ዘፍ.18፥16
“...እግዚአብሔርም አለ፣ ‘እኔ የማደርገውን ከወዳጄ “... ሰዎቹም ከዚያ በተመለሱ ጊዜ ወደ ሰዶም መጡ፤ ...” ዘፍ.18፥22
አብርሃም አልሰውርም፤...’...”ዘፍ18፥17
“...እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ
ሄደ፤ ...” ዘፍ.18፥33

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ለ፣ የሐዲስ ኪዳን ማስረጃዎች
❖ በብሉይ ኪዳን፣ የአንድነቱና የሦስትነቱ ምሥጢር ለህዝብ ሁሉ ግልጽ በሆነ ሁኔታ
አልተገለጠም።

❖ የሥላሴ ምሥጢር በገሃድ(በግልጽ)፣ በታወቀና በተረዳ መልኩ ለህዝብ ሁሉ


የተገለጠው በሐዲስ ኪዳን ነው።
❖ በሐዲስ ኪዳን ምሥጢረ ሥላሴን የሚያስረዱ ማስረጃዎች እጅግ ብዙ ናቸው።
➢ ጥቂቶቹን ብቻ ለመዳሰስ እንሞክራለን...

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ለ፣ የሐዲስ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ “...ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ
የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤እነሆም
ድምጽ ከሰማያት መጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ...”
ማቴ.3÷16-17
➢ በዚህ ገጸ ንባብ ላይ ሦስቱ አካላት ከነ ግብራቸው በግልጽ ተጠቅሰዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ለ፣ የሐዲስ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ “...እንግዲህ ሒዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ፣በወልድ፣በመንፈስ ቅዱስ ስም
እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ
መዛሙርት አድርጓቸው...” ማቴ.28÷19
➢ ሦስት አካላት በስማቸው በግልጽ ተጠቅሰዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ለ፣ የሐዲስ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ “...የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም ግን እሱ
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ
ይነግራችኋል፡፡ እሱ ያከብረኛል ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና፡፡ ለአብ ያለው
ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ...” ማቴ.16፥12-15

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ለ፣ የሐዲስ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር
ነበረ። ይህም በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉም በእርሱ ሆነ፤
ከሆነውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም። ...” ዮሐ.1፥1-3
❖ “ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛም አደረ፤ ለአባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብሩን
አየን፤ ...” ዮሐ.1፥14

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ለ፣ የሐዲስ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ “... እኔን ያየ አብን አየ፤ እንግዲህ እንዴት አብን አሳየን ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ፣
አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? ...” ዮሐ.14፥8-14

❖ “እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት


መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።” ዮሐ.15፥26

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ለ፣ የሐዲስ ኪዳን ማስረጃዎች ...
❖ “...በመንግሥተ ሰማያት የሚመሰክሩት ሦስቱ ናቸው፡፡ አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ
እነዚህም ሦስቱ አንድ ናቸው...” 1ኛዮሐ5፥7
❖ “… For there are three that bear record in heaven; The
Father, The Word, and The Holy Ghost. And they are one.”
(the holy Bible the British and Foreign Bible Society
1611ዓ.ም.ዕትም)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሐ፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንት ማስረጃዎች
❖ ከዘመነ ሐዋርያት በኋላ የተነሱ ሊቃውንት አባቶቻችን፣ የትምህርተ ሃይማኖት
መሠረት ስለሆነው ምሥጢረ ሥላሴ ከሐዋርያት የተረከቡትን አጽንተው፣
አምልተውና አብራርተው አስተምረዋል።

❖ ለአብነት ያህል የተወሰኑትን እንመለከታለን።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሐ፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንት ማስረጃዎች ...
❖ “ከሥራው ሁሉ አስቀድሞ ሦስት አካላት ባሉት በአንድ መለኮት እንመን፤ በባሕርይ
አንድ፤ በአካል ሦስት የሚሆኑ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ፤ አንድ ሲሆኑ ሦስት
ናቸው፤ ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው።”
ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ (ሃይማኖተ አበው ምዕ.33 ቁ.2)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሐ፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንት ማስረጃዎች ...
❖ “አብ ወላዲ ነው እንጂ ተወላዲ አይደለም፡፡ ወልድ ግን ተቀዳሚ ተከታይ ሳይኖረው
ቅድመ ዓለም ከብቻው ከአብ ተወለደ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ሠረጸ፤ በቀዳማዊነት፣
በአገዛዝ፣ በሥልጣን፣ በከሀሊነት፣ ፍጥረትን ሁሉ በመፍጠር ከአብ ከወልድ ጋር
አንድ ነው፡፡ በመለኮት አንድ የሚሆኑ ሦስት አካላት ከመወሰን፣ ከቁጥር ሕግ ሁሉ
የራቁ ናቸው።” ቅዱስ ዘካርያስ ዘእስክንድርያ (ሃይማኖተ አበው ምዕ.108 ቁ.2)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሐ፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንት ማስረጃዎች ...
❖ “አብ አዳምን እንደፈጠረ ወልድም በአርያውና በአምሳሉ ፈጥሮታል፤ ወልድ አዳምን
በአርያውና በአምሳሉ እንደፈጠረው መንፈስ ቅዱስም በራሱ መልክ ፈጥሮታል።”
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምስጢር ገጽ39)

❖ “የሚሰገድላቸው ሦስት ስሞች የማይቀላቀሉ ሦስት አካላት በአንድ ፈቃድ፣በአንድ


ጌትነት፣በአንድ ሥልጣን፣ በአንድ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ እንደሆኑ እንታመናለን።”
ቅዱስ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘአንጾኪያ (ሃይማኖተ አበው ምዕ.92 ቁ.2)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሐ፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንት ማስረጃዎች ...
❖ “አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ በአካል ሦስት እንደሆኑ በባሕርይ ሦስት ብለን የምናምን
አይደለንም፡፡ በአካል ሦስት ብለን በባሕርይ አንድ ብለን እናምናለን እንጂ፡፡
አሐዱም(አንድ) ስላልን ከፍጥረት ሁሉ አስቀድሞ የነበረ አዳም በአካል አንድ
እንደሆነ በአካል አንድ ብለን የምናምን አይደለም፡፡ በባሕርይ አንድ ብለን በአካል
ሦስት ብለን እናምናለን እንጂ።” ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ? (ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ማጠቃለያ
❖ ምሥጢረ ሥላሴ ከሙሉ በከፊሉ፣ ከብዙ በጥቂቱ በዚህ ተፈጸመ!
➢ የሩቁን ለማቅረብ፣ የረቀቀውን ለማጉላት አበው ሊቃውንት የተጠቀሟቸውን ተፈጥሮአዊ
ምሳሌዎች ለመዳሰስ ሞክረናል።

❖ እንግዲህ የሃይማኖት መሠረት የሆነውን ምሥጢረ ሥላሴን ከተማሩ በኋላ


ምሥጢረ ሥጋዌን መማር ይገባል።

➢ ይህንን ምሥጢር ሳይማሩና ሳይረዱ ምሥጢረ ሥጋዌን ለመማር መሞከር ግን በክህደት


ቁልቁለት ላይ ሆኖ እንደመጫወት ይቆጠራል።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ይቆየን !

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org

You might also like