You are on page 1of 56

የአዲስ አበባ ዓመታዊ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ይህንን ሪፖርት ለማዘጋጀት የተሳተፉ ተቋማት
ይዘት
ddddd

1. መልዕክት……………….……………………………………………………....... ii

2. ምስጋና ………………..…………………………………………………… iii

3. የቃላት መፍቻ…..…………………………………………… iv

4. የትራፊክ አደጋ ማጠቃለያ …..…………………………………………......1

5. መግቢያ ……………………………………………. …………..................... 2

6. ስለ አዲስ አበባ…….…………………………………………………………….3

7. የሪፖርቱ ዓላማ……….…………………………………………………………4

8. የመረጃ ምንጭ………………..……………………………................. 5

9. የአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ አደጋ.…………………..................6

10. አደገኛ የመንገድ ባሕሪያት በአዲስ አባባ……………................26

11. የመንገድ ደህንነት ተግባራት በአዲስ አበባ..………………………31

12. ማጣቀሻ………………………………………………………………………….43
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት ii

የት/ማ/ኤ/ ዋና ዳይሬክተር መልዕከት

ኢንጂነር ጅሬኛ ሂርጳ


የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

በአለም ላይ በየቀኑ አማካኝ 3,700 ሰዎች በአመት ደግሞ 1.35 ሚንየን የሚሆኑ ሰዎችን መከላከል በሚቻለው የመንገድ ትራፊክ

አደጋ በሞት እናጣለን:: ከ 50 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የአካል ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ በዚህ ሪፖርት መሠረት በአዲስ

አበባ በቀን አንድ ሰው በአመት ደግሞ በአማካኝ 480 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ፡፡ ከሞት እና ጉዳቶች ጀርባ ከዚህ በጣም

ትልቅ ቁጥር በኢኮኖሚያዊ፣ስነልቦና እና የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ሊገባ ይችላል ፡፡

ከ 2008 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ በ 13 ዓመታት የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ

እና የ 3 ዓመት የመንገድ ደህንነት ትግበራ እቅድን በመቅረፅ የመንገድ ትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ልዩ ትኩረት ተሰቶ

እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የመንገድ ደህንነት ትግበራ ውጤት ማየት እንደጀመረች መሆኑን ሪፖርቱ

ያሳያል ፡፡ ይህ ደግሞ አበረታች ለውጥ ነው ፡፡ እነዚህ አበረታች ለውጦች የባለሞያዎች ትብብር እና የተቋማት ጠንካራ ቅንጅት

ውጤት ነው።

ይህን ሪፖርት ውጤታማ ለማድረግ አስተዋፆ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና አቀርባለው፡፡


iii አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ምስጋና
ይህ ሪፖርት የአዲስ አበባ ከተማ አራተኛ ዓመታዊ የመንገድ ደህንነት ሪፖርት ሲሆን የከተማውን የትራፊክ ደህንነት ሁኔታ ለማሻሻል

፣ ችግር ፈቺ ማሻሻያ ስራዎችን ለማቀድ እና ለመገምገም እንዲሁም ተከታታይ ዓመታዊ የመንገድ ደህንነት ሪፖርት እንዲኖረን ነው ፡፡

ይህንን ሪፖርት ለማዘጋጀት የተለያየ ድጋፍ ላደረጉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ፣ አዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ብሉምበርግ ፊላንትሮፒ በBIGRS ላደረገው የገንዘብ እርዳታ ቫይታል ስትራቴጂ(VS) የመንገድ ደህንነት ሰርቬላንሲን በማስተባበር

ቀልፍ ድጋፎች ላደረጉ አጋር ድርጅቶች በጆን ሆፕኪንስ አለምአቀፍ የጉዳት ጥናት ክፍል የአለም ሪሶርስ ተቋም (ደብሊው አር አይ)

አለምአቀፍ የመንገድ ግምገማ ፕሮግራም (አይ ራፕ) የአለም ባንክ እና ብሔራዊ የከተማ ማጓጓዣ ኦፊሻሎች ማህበር - የግሎባል

ዲዛይኒንግ ሲቲስ ኢኒሼቲቭ ( ናክቶ) ልዩ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

ሜሮን ጌታቸው የብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ ሰርቪላንስ አስተባባሪ የፖሊስ የትራፊክ አደጋ ሞት እና አካል ጉዳቶች መረጃ ማሰባሰብ ላይ

እና መረጃን ወደ ኮምፒውተር ማስገባት በትራንስፖርት ቢሮ መረጃ አስገቢዎች ጋር በመተባበር ሀላፊነት ነበራቸው፡፡ እንዲሁም በመረጃ

ትንታኔ እና ፅሁፍ ላይ ከሳራ ዋይቴድ ጋር በመተባበር የተከናወነ ሲሆን የአዲስ አበባ BIGRS ቢድን በህግ ማስከበር ፣ስትራቴጂክ

ኮሚኒኬሽን እና መንገድ ደህንነት እና እንቅስቃሴ ላይ የተተገበሩ ስራዎችን አቀናጅቶ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች ፡- በመንገድ አደጋ መረጃን በማቅረብ ተባብሯል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ፡- የገንዘብ ድጋፍ መረጃ አሰባሰብ ላይ በፖሊስ መምሪያዎች ፣መረጃን ወደ ኮምፒውተር

ማስገባት እና ጂኦ ሎኬሽን አደጋ ቦታን ለመለየት ትብብር አድርገዋል፡፡

አዲስ አበባ የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፡- በከተማዋ በ2011 ዓ.ም በመንገድ ደህንነት ላይ የተተገበሩ ስራዎችን መረጃ አቀናጅተው

አቅርበዋል፡፡
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት iV

የቃላት መፍቻ

AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

BIGRS ብሉምበርግ ፊላንትሮፒ ኢኒሼቲቭ የግሎባል ሮድ ሴፍቲ

DD ጠጥቶ ማሽከርከር

JHUIIRU ጆን ሆፕኪን ዩኒቨርስቲ አለም አቀፍ የጥናት መአከል

NACTO-GDCI ናሽናል አሶሴሽን ኦፍ ሲቲ ትራንስፖርት ኦፊሻል ግሎባለ ዲዛይን ሲቲ ኢኒሼቲቭ

RTI መንገድ ትራፊክ አደጋ

TMA አዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

WHO የአለም ጤና ድርጅት

WRI ወርልድ ሪሶርስ ኢኒስቲቲዩት


1 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

የትራፊክ አደጋ ማጠቃለያ


2011 ዓ.ም

ትራንስፖርት በኢኮኖሚው ግብአት እያንዳንዱ መልካም አገልግሎት ውስጥ የተካተተ ሲሆን ለዕለት ተዕለት ኑሮ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

ነገር ግን ጥቅሞቹን በብር እንደሚገመተው ሁሉ ጉዳቱ በሞትና በአካል ጎዳት ይለካል (10)

አጠቃላይ የትራፊክ አደጋ

30,427

458 2,991 26,019


የሞት አደጋ ብዛት የአካል ጉዳት ግጭቶች ብዛት የንብረት ጉዳት ብዛት

480 3,440
የሞቱ ሰዎች ብዛት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 2

መግቢያ
የመንገድ ትራፊክ ጉዳቶች ዋነኛ ግን የተዘነጉ የዓለም የጤና ችግሮች ናቸው፡፡ ውጤታማ እና ዘላቂነት ባለው መልኩ

ለመከላከል የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል፡፡ [1], በመንገድ ትራፊክ አደጋ ላይ የሚደርሰው ሞት እና የአካል ጉዳት አሁንም

ዋነኛው የህዝብ ጤና ችግር ነው ፡፡የዓለም የመንገድ ትራፊክ አደጋ በ 2018 እ.ኤ.አ የመንገድ ትራፊክ ሞት 1.35 ሚሊዮን

አካባቢ የደረሰ ሲሆን፣ 8 ኛ ዋነኛ በአለማችን ሞት የሚያስከትል የጤና ችግር ነው፡፡ችግሩን በጣም አስከፊ የሚያደርገው

አምራች እና ወጣት የማህበረሰብ ከ15 እስከ 29 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ዋነኛ ገዳይ መሆኑ ነው፡፡

በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ በየቀኑ በአማካይ 13 ሰዎች ሲሞቱ ፣ 37 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ሰለባዎች ይሆናሉ፡፡ ከዚህ

ውስጥ አዲስ አበባ 10% የሚሆነውን የሞት እና 26% የሚሆኑት የአካል ጉዳት ከሀገር አቀፍ ደረጃ ትሸፍናለች [2]

በአዲስ አበባ ውስጥ የትራፊክ አደጋ ሳይከሰት የሚውልበት ቀን የለም፡፡ ቢያንስ በአማካኝ በከተማዋ አንድ ሰው ይሞታል ፣

10 ሰው የአካል ጉዳት ይደርስበታል እንዲሁም 72 የንብረት ጉዳት በየቀኑ በከተማዋ መንገዶች ላይ ይከሰታል፡፡

እ.ኤ.አ 2016 የዓለም ጤና ድርጅን ግምት መሰረት በአጠቃላይ በኢትዩጵያ 27,326 ሰዎች ህይወታቸው ያልፋል [3], ነገር

ግን የፖሊስ መረጃ በዛው አመት 4,597 ያሳያል፡፡ ይህ ልዩነት የሚያሳየው የፖሊስ ሪፖርት በሀገር ውስጥ ምን ያህል ከግምት

በታች መሆኑን ነው፡፡ሁለት የቅርብ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፖሊስ መረጃ 57 እና 82 በመቶ ከጠቅላላው ከሚደርሰው

የትራፊክ አደጋ መረጃ ይፋ እንደሚያደርግ ያሳያል ፡ [4] [5]

ይህ ሪፖርት የአዲስ አበባ ከተማ አራተኛ ዓመታዊ የመንገድ ደህንነት ሪፖርት ሲሆን ፣ የቀደሙት ሪፖርቶች ከተማዋ የመንገድ

ደህንነት ስትራቴጂ እና የትግበራ ዕቅድን እንድትቀርፅ እና የመንገድ ደህንነት የተተገበሩ ተግባራትን ለማቀድ እና ለመከታተል

ረድተዋል፡፡

የሪፖርቱ ዋና አላማ በ2011ዓ.ም የፖሊስ መረጃ መሠረት የመንገድ ትራፊክ አደጋዎችን ፣ ጉዳቶችን እና የሞት ሁኔታዎችን

በአዲስ አበባ ለማሳየት ነው ፡፡ የሪፖርቱ ባለፈው ዓመት ውስጥ የተተገበሩ የመንገድ ደህንነት ትግበራ ውጤቶች ያሳዩትን

ለውጦች እና 8ኛ ዙር የአደጋ መንስኤዎች ቁጥጥር እና ክትትል ሪፐርት ያሳያል ፡፡

13 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ፡፡

37 ሰዎች በትራፊክ አደጋ አካል ጉዳት ይደርስባቸዋል::


3 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

አደስ አበባ

የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች: - 596,084 [8]


የህዝብ ብዛት: - 3,600,810 [7]

አዲስ አበባ የኢትዮጲያ ዋና ከተማ እና በአገሪቱ ትልቋ ከተማ ስትሆን በ 2011 ዓ.ም ወደ 3.6 ሚሊዮን አማካኝ ህዝብ ብዛት

ያለው ነው ፡፡ ከተማዋ 596,938 የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች ያላት ሲሆን ከጠቅላላ የኢትዮጲያ ተሽከርካሪዎች (1,071,345 )

ሀምሳ ስድስት በመቶ ይይዛል ፡፡ ከተማዋ የቆዳ ስፋት በአማካኝ 540 ካሬ ኪ.ሜ.
.
ምስል 1 :- እስከ 2011 ዓ.ም የተመዘገቡ ተሸከርካሪዎች ብዛት

ሌላOther
29,219
አንቡላንስ
Ambulance 253
ተሽከርካሪ በህዝብ ሪሾ

Construction
የኮንስትክሽን መኪናCar 2,235
1:6
Motorcycle
ሞተር ሳይክል 24,700

አውቶቡስBus 44,055

ከባድ ጭነት
Heavy Vehicle 195,509
የቤት መኪና
Car 300,110
0 50,000 100,000 150,000 200,000 250,000 300,000 350,000
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 4

የሪፖርቱ ዓላማ

የህብረተሰብ ሰርቬላንስ ሲስተም በተገቢው ጊዜ ከተተገበረ እንዲሁም ተአማኒነት ያለው መረጃን በመጠቀም ውጤታማ ፕሮግራሞችን
ለማቀድ ክትትልና ግምገማ ለማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው [9].

ከዚህ በፊት በተከታታይ የተዘጋጁ ዓመታዊ የመንገድ ደህንነት ሪፖርቶች የአዲስ አበባ ከተማ አሥራ ሦስት ዓመት የመንገድ ደህንነት
ስትራቴጂዎችን እና የሦስት ዓመት የትግበራ ዕቅድ ለማዳበር፣ የመንገድ ትራፊክ አደጋን እና ጉዳቶችን አዝማሚያ ለመከታተል እና የመንገድ
ደህንነት ማሻሻያ ተግባራትን ለመቆጣጠር እና ለመገምገም ረድቷል፡፡

የመንገድ ትራፊክ
የመንገድ አደጋዎች
ትራፊክ ያስከተሉትን
አደጋዎች ሞት እና
ሞት እና የአካል የአካልሁኔታ
ጉዳቶችን ጉዳትለመከታተል
መከታተል

በመንገድ ትራፊክ አደጋ ሳቢያ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች


ማህበራዊና ስነሕዝባዊ እና የመንገድ ተጠቃሚ ባህርያትን ያብራራል

የተተገበሩ መፍትሔ እርምጃዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል

በትራፊክ አደጋአደጋ
ለትራፊክ በተደጋጋሚ ተጋላጭ
አደጋ ቦታን የሆኑይረዳል
ለመለየት ቦታዎች ለመለየት ይረዳል
5 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

የመረጃ ምንጭ
የፖሊስ ሪፖርት አሁንም የአዲስ አባባ ዋና የትራፊክ አደጋ የመረጃ ምንጭ ነው ፡፡
ይህንን ሪፖርት ለማዘጋጀት የፖሊስ የአደጋ መመዝገቢያ ፎርም በሰርቪላንስ አስተባባሪ
የትራፈክ ሞትና የአካል ጉዳት ተለይቶ፣ ምስል ተነስቶ በ ኢፒኢፎ በተዘጋጀ የመረጃ
ወደ ኮምፖውተር ማስገቢያ በትራንስፖርት ቢሮ መረጃ አስገቢዎች ወደ ኮምፒውተር
እንዲገባ ተደርጓል፡፡

ይህ ሪፖርት ከፖሊስ ከአደጋ መረጃ በተጨማሪ በ2011 ዓ.ም በመንገድ

ደህንነት የተተገበሩ ተግባራትን ከህግ ማስከበር ፣ ከስራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ፣

ደህንነቱን ከጠበቀ መንገድ እንቅስቃሴ ፣ከመረጃ አያያዝ ከBIGRS እና

ከአዲሰ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው፡፡

በተጨማሪም ሪፖርቱ 8ኛ ዙር የአደጋ መንስኤዎች ቁጥጥር እና ክትትል በአዲስ


አበባ ዩኒቨርስቲ ፐብሊክ ኸልዝ ዲፓርትመንት እና በጆን ሆፕኪን ዩኒቨርስቲ
የቅርብ ሪፖርት ያሳያል፡፡

በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መረጃ ወደ ኮምፒውተር በማስገባት ላይ


አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 6

ምዕራፍ 1

የአዲስ አበባ የመንገድ


ትራፊክ አደጋዎች
2011 ዓ.ም
7 Aአዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

የትራፊክ አደጋ ሞት እና የአካል ጉዳት በአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ በተከታታይ እየጨመረ ሲሄድ የነበረው የመንገድ ትራፊክ ሞት ካለፈው ሶስት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ

መሻሻል አሳይቷል፡፡ በ2011 ዓ.ም 480 ተመዝግቧል፡፡ (ምስል 2).

ምንም እንኳን የሞት ቁጥር መረጋጋት ቢያሳይም የአካል ጉዳት ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ9 በመቶ ጨምሯል፡፡

ምስል 2 :- የመንገድ ትራፊክ አደጋ ሞት ሁኔታ በአዲስ አበባ 2011 ዓ.ም


የሞት ብዛት
600
478 480
433 463 477
443
382 463 458
400 439 456
418
391
362 የሞት አደጋ ብዛት

200

2004
2012/13 2005
2013/14 2006
2014/15 2007
2015/16 2009
2016/17 2010
2017/18 2011
2018/19
ምስል 3:- የመንገድ ትራፊክ የአካል ጉዳት ሁኔታ በአዲስ አበባ

የአካል ጉዳት ብዛት

4000 3589 3576 3317 3133 3440


2995
2773
3000
2762 3089
2669 2991
2000 2599 2612 2605

1000 የአካል ጉዳት አደጋ ብዛት

0
2004
2012/13 2005
2013/14 2006
2014/15 2007
2015/16 2009
2016/17 2010
2017/18 2011
2018/19
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 8

የመንገድ ትራፊክ አደጋ ሞት እና የአካል ጉዳት

ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

ምስል 4 :- የመንገድ ትራፊክ አደጋ ሞት እና የአካል ጉዳት ሁኔታ በኢትዮጵያ

18000 የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች


16000 15529
14000 14543
13957
13356
12000 11927 12426
11355 የአካል ጉዳት አደጋ ብዛት
10000
8000 6807 7813
6606 7032 7607
6914 6911
6000 የሞቱ ሰዎች ብዛት
5118 4597
4000 3847 4352 4257
3362 3331
2000 3475 3820 3738
3170
2575 2664 3172 የሞት አደጋ ብዛት
0
2004
2012/13 2005
2013/14 2006
2014/15 2007
2015/16 2009
2016/17 2010
2017/18 2011
2018/19

በ2011 ዓ.ም ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ስታቲስቲክስ ሪፖርት መሠረት በኢትዮጵያ የመንገድ ትራፊክ ሞት እና የአካል ጉዳቶች በመቶኛ ካለፈው

ዓመት ሲነፃፀር በ 10 እና 13 በመቶ ቀንሷል ፡፡


9 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

በ 100,000 ህዝብ ሞት እና አካል ጉዳት


ምስል 5 የሚያሳየው ሞት እና የአካል ጉዳት በ100,000 ህዝብ ነው ፡፡ በ2011 ዓ.ም የትራፊክ አደጋ ሞት በመቶ ሺህ ህዝብ
ሲሰላ ከባለፈው ዓመት 13.6 ወደ 13.3 ወርዷል፡፡ የአካል ጉዳት ብዛት ደግሞ 89 ወደ 96 /በ 100,000 ህዝብ መጨመር
ያስያል በ10,000 ተሽከርካሪ ሲነፃፀር ሞት ከ9 ወደ 8 በአስር ሺህ የተመዘገቡ ተሽከርካሪች መውረዱን ያሳያል፡፡

ምስል 5:- ሞት እና የአካል ጉዳት በ100,000 ህዝብ

120
112.3 የአካል ጉዳት በ100,000 ህዝብ
106.7
100 96.6 95.8
91.5 89.1
80

60
ሞት 100,000 ህዘብ
40
13.5 13.5 13.8 13.9 13.6 13.3
20

0
2005
2013/14 2006
2014/15 2007
2015/16 2009
2016/17 2010
2017/18 2011
2018/19

ምስል 6 :- የትራፊክ አደጋ ሞት እና የአካል ጉዳት በ 10,0000 የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች

160 150
128
120
የአካል ጉዳት በ10,000 የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች

79 ve
80 63
56 57
40
18 ሞት በ10,000 የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች
19 10
20 9 9 8
ve

2005
2013/14 2006
2014/15 2007
2015/16 2009
2016/17 2010
2017/18 2011
2018/19
0
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 10

ሞት እና የአካል ጉዳት በመንገድ ተጠቃሚዎች

በአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ላይ አብዛኛውን የጉዳት መጠን የሚይዙት እግረኞች ሲሆኑ በአማካኝ ከጠቅላላ ሞት 84 በመቶ

እና ከአካል ጉዳት 67 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡

ምንም እንኳን የመንገድ ደህንነት አብዛኛዎቹ መፍትሄ እርምጃዎች እግረኛ ላይ ቢያተኩሩም ፣ አሁንም የእግረኛ ሞት ከጠቅላላው የመንገድ
ትራፊክ አደጋ ከ5 ሞት አራቱን ይይዛል ፡፡

ምስል 7:- ሞት በመንገድ ተጠቃሚዎች 2011 ዓ.ም

እግረኞች
84%

9% ተሳፋሪዎች

4% አሽከርካሪዎች

1% ሞተረኞች

ምስል 8:- አካል ጉዳት በመንገድ ተጠቃሚዎች 2011 ዓ.ም

67% እግረኞች

23% ተሳፋሪዎች

5% አሽከርካሪዎች

4% ሞተረኞች
11 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ሞት እና የአካል ጉዳት በመንገድ ተጠቃሚ ያለው ሂደት

ሰንጠረዥ 1:- የትራፊክ አደጋ ሞት በመንገድ ተጠቃሚዎች 2009 -2011 ዓ.ም

2009 2010 2011


እግረኛ 393(82%) 76%(363) 84%(401)
ተሳፋሪ (49) 10% 57(12%) 44(9%)
አሽከርካሪ 28(6%) 33(7%) 20(4%)
ሞተረኛ (6) 1% (22) 5% 14(1%)
ሳይክሊስት 1 3 1

ምስል 9:- የትራፊክ አደጋ ሞት ሂደት በመንገዱ ተጠቃሚዎች

500
401 እግረኛ ሞት
400 393
363
300

200

100

0
2009 ዓ.ም
2016/17 2010 ዓ.ም
2017/18 2011 ዓ.ም
2018/19

57
60 49
44 ተሳፊሪ ሞት
50
33
40 28
30 22 20 አሽከርካሪ ሞት
6
20 14 ሞተርሳይክል
1 3 1 ሳይክሊስት
10
2016/17
2009 ዓ.ም 2017/18
2010 ዓ.ም 2018/19
2011 ዓ.ም
0
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 12

ሰንጠረዥ 1:- የትራፊክ አደጋ አካል ጉዳት ሂደት በመንገዱ ተጠቃሚዎች

2010 ዓ.ም 2011 ዓ.ም


እግረኛ 2163(67%) 1958(63)
ተሳፋሪ 693(22%) 580(23%)
አሽከርካሪ 174(6%) 169(5%)
ሞተረኛ 89(3%) 122(4%)
ሳይክሊስት 12(0%) 17(1%)

ምስል 10:- የትራፊክ አደጋ አካል ጉዳት ሂደት በመንገዱ ተጠቃሚዎች

2500
2000
2163 1958 እግረኛ ጉዳት
1500
1000
500
0
2010 ዓ.ም
2017/18 2011 ዓ.ም
2018/19

800
700 693 ተሳፋሪ ጉዳት
600 580
500
400
300
አሽከርካሪ ጉዳት
200
174 169
100 89 122 ሞተርሳይክል ጉዳት
0 12 17 ሳይክሊስት ጉዳት
2010 ዓ.ም
2017/18 2011 ዓ.ም
2018/19
13 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

የትራፊክ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት በፆታ እና በእድሜ


በመንገድ ትራፊክ አደጋ ሞት እና አካል ጉዳት ወንዶች ዋነኛ ተጠቂ ናቸው ፡፡ 78 በመቶ የሚሆነውን ሞት እና 77 በመቶ
የሚሆነውን የአካል ጉዳት ድርሻ ይይዛሉ፡፡ .ይህ ማለት ሴቶችን ሶስት እጥፍ በላይ ለትራፊክ አደጋ ሞት የመጋለጥ እድል
አላቸው ማለት ነው፡፡

አምራች እና ወጣቶች እድሜያቸው ከ18-59 ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች በ2011 ዓ.ም 60 በመቶ የሞት እና 80 በመቶ
የአካል ጉዳት ተጎጂዎች ናቸው ፡፡

ምስል 11 :- ሞት እና የአካል ጉዳት በፆታ

ሞት ፡ 78% ወንዶች

የአካል ጉዳት ፡ 78% ወንዶች

ምስል 12:- ሞት እና የአካል ጉዳት በእድሜ ፣ 2011 ዓ.ም

60%

50% 48%
43% ሞት
40% 37%
31%
30% የአካል ጉዳት

20%
14%
9% 10%
10% 7%

0%
<17 18-29 30-59 >60
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 14

ሞት እና የአካል ጉዳት በሰዓታት

ምስል 13 እንደሚያሳየው ሞት እና የአካል ጉዳት ጠዎት ማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ መጨመር ሲያሳይ ወደ እኩለ ለሊት ሲደርስ
መውረድ ያሳያል፡፡ ይህ መረጃ ባለፊት 3 አመታት ተመሳሳይ ሂደት ነበረው፡፡ በሳምንቱ ቀናት ደግሞ ሲታይ ብዙ ሞት
ቅዳሜ እና የአካል ጉዳት ደግሞ ሀሙስ ቀን በ2011 ዓ.ም መብዛቱን ያሳያል፡፡

. ምስል 13:- ሞት በሰዓት በ2011 ዓ.ም

400
373
350 337
300 305 321
280 289 የአካል ጉዳት
250 252 266
200
150
109 119
100
81 80 66 77 ሞት
50 44
18 17 30 31 28 30 28 31 32
0 Deaths

ምስል 14 :- የአካል ጉዳት በሳምንቱ ቀናት በ2011 ዓ.ም

450 412 398


400 368 359 364
347
350 313
300
አካል ጉዳት
250
200
150
100 58 59 58 72 70
46 49
50
ሞት
0
ሰኞ ማክሰኞ እሮብ ሐሙስ አርብ ቅዳሜ እሁድ
15 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

የትራፊክ አደጋ ሞት በሰአት እና በሳምንቱ ቀናት


ከዚህ በታች ያለው ምስል በሰዓት እና በሳምንቱ ቀናት ያለውን የአደጋ ሂደት ያሳያል፡፡ ቅዳሜና እሁድ ከምሽቱ 12 እስከ 4 ሰዓት አብዛኛው
የሞት አደጋ ሚደርስበት ሲሆን ፡፡ የዚህ አይነቱ የመረጃ ትንተና ለህግ አስከባሪዎች አደጋ ሚደርስባቸውን ሰአታት በመለየት እቅድ
ለማውጣት ይጠቅማል ፡፡

ሰንጠረዥ 3:- ሞት በሰአት እና በሳምንት ቀናት 2011 ዓ.ም

ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ሀሙስ አርብ ቅዳሜ ዕሁድ አጠቃላይ


00:00-02:00 3 1 4 4 1 2 2 17
02:01-04:00 2 1 1 0 5 3 3 15
04:01-06:00 2 2 8 7 4 2 2 27
06:01-08:00 2 8 6 7 2 8 7 40
08:01-10:00 7 3 5 2 3 2 7 29
10:01-12:00 4 3 2 7 5 4 1 26
12:01-14:00 5 2 3 2 2 8 5 27
14:01-16:00 6 4 6 2 2 3 2 25
16:01-18:00 6 3 2 5 5 3 4 28
18:01-20:00 7 9 11 6 6 18 8 65
20:01-22:00 8 3 8 9 11 13 20 72
22:01-24:00 4 4 1 4 3 4 7 27
58 45 59 58 49 72 70 411

<05 ሞት አደጋ 6-10 ሞት አደጋ


crashes
10-15 ሞት አደጋ 15-20 ሞት አደጋ
crashes

34% የሚሆነው የሞት አደጋ በእረፍት ቀናት ነው የተከሰተው


አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 16

አካል ጉዳት በሰዓት እና በሳምንቱ ቀናት

የአካል ጉዳት ከሞት አደጋ ጋር በሰአት እና በቀናት ሲነፃፀር የተወሰነ ልዩነት ያሳያል ፡፡ ብዙ ያካል ጉዳት የደረሰው ሀሙስ ሲሆን በሰዓት
ደግሞ ጠዋት ከ2 እስከ 4 እና ምሽት 12 – 4 ሰእት መጨመር ያሳያል፡፡

ሰንጠዛዥ 4:- የአካል ጉዳት በሰአት እና በሳምንቱ ቀናት ፤ 2011 ዓ.ም

ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ሀሙስ አርብ ቅዳሜ ዕሁድ አጠቃላይ


00:00-02:00 8 6 12 12 9 9 12 68
02:01-04:00 9 7 8 5 11 11 10 61
04:01-06:00 12 12 6 13 18 16 15 92
06:01-08:00 36 34 42 52 51 27 30 272
08:01-10:00 57 43 40 53 57 37 47 334
10:01-12:00 36 36 42 42 40 49 41 286
12:01-14:00 35 28 29 33 25 35 35 220
14:01-16:00 42 31 34 47 29 27 42 252
16:01-18:00 45 34 38 44 30 39 30 260
18:01-20:00 35 43 47 41 38 40 61 305
20:01-22:00 29 21 31 36 34 46 49 246
22:01-24:00 13 10 8 24 13 22 17 107
368 313 347 412 359 364 398 2561

<15 አካል ጉዳት 30-45 አካል ጉዳት


crashes
45-61 አካል ጉዳት
15-30 አካል ጉዳት

2011 ዓ.ም ብዙ ቁጥር ያለው የአካል ጉዳት የተመዘገበው ሀሙስ ነው ፡፡


17 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ሞት እና የአካል ጉዳት በወራት


ከዚህ በታች ያለው ምስል እንደሚያሳየው በነሀሴ ወር ሞት ጉዳት ብዙውን ጊዜ የሚደጋገምበት ነበር ይህ ቀጥር ከፍ ያለው በዚህ የመረጃ
ትንተና ጳግሜ 6 ቀን ነሀሴ ላይ ስለተደመረ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የአካል ጉዳት ሁኔታ በወራት ሲታይ ከሞት የተለየ ሂደት ነው፡፡
ያለው ብዙ የአካል ጉዳት የደረሰው በታህሳስ ወር ላይ ነው ፡፡

ምስል 15፡ ሞት እና የአካል ጉዳት በወራት በ2011 ዓ.ም


አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 18

ሞት እና አካል ጉዳት በክፍለ ከተማዎች


ይህ ካርታ በአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች የደረሰውን ሞት እና የአካል ጉዳት አጠቃላይ ቁጥር ያሳያል፡፡ የክፍለ ከተሞቹ የመሬት ስፋት
የመንገድ ርዝመት የተለያየ ቢሆንም ሁሉም ክፍለ ከተማ ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭነቱን ያሳያል፡፡

ምስል 16 :- ሞት እና አካል ጉዳት በክፍለ ከተማ 2011 ዓ.ም

ቦሌ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የትራፊክ አደጋ ሞት ጉዳትን 32 በመቶ ይይዛሉ፡፡
19 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

የአሽከርካሪ የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ


ምስል 19 እና 20 የፖሊስ ሪፖርት ሞት እና የአካል ጉዳት በአሽከርካሪ የትምህርት ደረጃ እና የማሽከርከር ልምድ ያሳያል፡፡

ምስል 17፡- ሞት እና የአካል ጉዳት በአሽከርካሪ ትምህርት ደረጃ

60%
54%

50% 47%

40%
32%
30% 26% አካል ጉዳት
21% 20%
20%

10%
ሞት
0%
አንደኛ primery
ደረጃ
Primary ሁለተኛ ደረጃ
secondary ከሁለተኛ ደረጃ በላይ
post secondary

ምስል 18 :- ሞት እና አካል ጉዳት በአሽከርካሪ የማሽከርከር ልምድ 2011 ዓ.ም

60%

44%
38%
40%

24% 26%
20% 18%
20% 17%
11%

0%
ሞት
Death የአካል ጉዳት
Injuries
<1
< 1year
ዓመት 1 to
1 – 55ዓመት
year 6 6to 10ዓመት
– 10 year >10
> 10 year
ዓመት
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 20

ሞት እና አካል ጉዳት አደጋ ባስከተለው ተሽከርካሪ

ለሞት እና የአካል ጉዳት በተደጋጋሚ የሚያስከትሉ የመኪና አይነቶች ታክሲዎች ናቸው (27 በመቶ ሞት እና 31 በመቶ አካል ጉዳት
ሲያስከትሉ የቤት መኪና በተከታይነት አደጋ አድራሽ ነው) ፡፡ ይህ የሚያሳየው የታክሲ ብዛት መጨመሩን እና የታክሲ አሽከርካሪዎች
በማሽከርከር ረጅም ሰዓት ማሳለፋቸውን ነው፡፡

ምሰል 19 :- ሞት እና አካል ጉዳት አደጋ ባስከተለው ተሽከርካሪዎች ፤ 2011 ዓ.ም

35% 35%
31%
29% 29% 30%
30% 27% 26%
ሞት አካል ጉዳት
25% 25%

20% 20%

15% 12% 15%


10% 10% 10% 10%
10% 10% 8%
5% 4%
5% 3% 5% 2% 2%
0% 0%
ታክሲ ቤት ከባድ ቀላል ባስ ሞተር ባጃጅ ሌላ ታክሲ ቤት ከባድ ቀላል ባስ ሞተር ባጃጅ ሌላ
መኪና ጭነት ጭነት ሳይክል መኪና ጭነት ጭነት ሳይክል

ሞት እና የአካል ጉዳት በእግረኛ እንቅስቃሴዎች


68 በመቶ የእግረኛ ሞት እና 54 በመቶ አካል ጉዳት የተከሰተው መንገድ በመሻገር ላይ እያሉ ሲሆን 26 በመቶ ሞት እና 42 በመቶ
ጉዳት በመንገድ ዳር በመሄድ ላይ እና ቆመው የተከሰቱ ናቸው፡፡

ሰንጠረዥ :- ሞት እና አካል ጉዳት በእግረኛ እንቅስዋሴዎች ፤ 2011

በመሻገር ላይ በመንገድ ላይ በመሄድ /ቆመው መንገድ ላይ ተኝተው U ያልታወቀ


/ተቀምጠው

?
ሞት 68% 26% 6% 1%

አካል ጉዳት 54% 42% 3% 1%


ሞት እና አካል ጉዳት በተሽከርካሪ እና በመንገዱ ተጠቃሚ አይነት

ከታች ያለው ምስል እንደሚያሳየው የእግረኛ ሞትን በአብዛኛው ያስከተለው ታክሲ(ላዳና ሚኒባስ) ሲሆን ከባድ ጭነት እና የቤት መኪናዎች
በተከታይ የሞት ጉዳት ያደርሳሉ፡፡ በእግረኛ አካል ጉዳት ሲታይ ደግሞ ታክሲ የመጀመሪያው ጉዳት አድራሽ ሲሆን የቤት መኪና በመከተል
በተደጋጋሚ ጉዳት ያደርሳል፡፡

ሰንጠረዥ 6፡- ሞት በአደጋ አድራሽ ተሽከርካሪ እና ተጎጂዎች 2011 ዓ.ም

እግረኞች ተሳፋሪዎች አሽከርካሪዎች ሞተረኞች


ታክሲ 85 10 4 0
የቤት መኪና 57 6 8 0
ባጃጅ 11 3 1 0
አውቶቡስ 34 2 1 1
ሳይክል 3 0 0 0
የኮንስትራክሽን መኪና 6 1 1 0
ከባድ ጭነት 58 10 2 2
ቀላል ጭነት 38 3 2 0
ሞተርሳይክል 11 0 0 9
218 25 15 12

ሰንጠረዥ 7 :- የአካል ጉዳት በአደጋ አድራሽ ተሽከርካሪ ፣2011 ዓ.ም

እግረኞች ተሳፋሪዎች አሽከርካሪዎች ሞተረኞች ሳይክሊሰት


ታክሲ 485 109 22 17 5
የቤት መኪና 380 75 40 30 4

ባጃጅ 105 93 12 0 0
ሳይክል 16 0 0 0 5
ባስ 37 7 2 1 0
ከባድ ጭነት 125 55 21 2 1

ቀላል ጭነት 103 28 9 12 2


ሞተርሳይክል 156 12 4 33 0

ሌላ 25 5 1 0 0
1432 384 111 73 17
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 22

ካርታ 1: የሞት አደጋ ቦታ ሂት ማፕ


2011 ዓ.ም

ማሳሰቢያ:- በካርታው ላይ ስማቸው የተሰየመው የአደጋ ቦታዎች በ2011 ዓ.ም ከ4 ሞት በላይ ያስከተሉ ናቸው፡፡
23 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ካርታ 2፡ የእግረኛ የሞት አደጋ ቦታ ሂት ማፕ


2011 ዓ.ም

ማሳሰቢያ:- በካርታው ላይ ስማቸው የተሰየመው የአደጋ ቦታዎች በ2011 ዓ.ም ከ4 በላይ የእግረኛ ሞት ያስከተሉ
ናቸው፡፡
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 24

የ 3 አመት የትራፊክ አደጋ ሞት በአዲስ አበባ


የቦታ ስም 2009 2010 2011 አማካኝ ሞት አደጋ /በ3 አመት
ሀይሌ ጋርመንት 6 1 10 6
ዘነበወርቅ 5 4 6 5
ሳሪስ አቦ 4 5 5 5
ወሰን ግሮሰሪ 5 4 4 4
ጉርድ ሾላ 3 5 4 4
ኪዳነ ምህረት 4 5 3 4
አየር ጤና 6 2 3 4
ሀና ማሪያም 6 5 0 4
18 ማዞሪያ 5 1 4 3
ቦሌ ሚካኤል 3 2 5 3
አዲሱ ገበያ 4 3 2 3
ዳርማር 3 6 0 3
ገላን ኮንዶሚኒየም 0 4 5 3
አለማየሁ ህንፃ 6 1 0 2
ቦሌ አራብሳ 2 3 2 2
ቡልጋሪያ 2 4 1 2
ኮከብ ፅብሀ 2 2 3 2
መካኒሳ 3 3 1 2
አብነት አደባባይ 3 1 2 2
ጎሮ 3 1 2 2
ላምበረት 2 0 4 2
ልደታ ቤተ-ክርስቲያን 2 1 3 2
መገናኛ 5 1 0 2
ቆሼ 0 4 2 2
ሳሊተ ምህረት 3 1 2 2
ቻይና ካምፕ 1 3 1 2
ደንበል 2 1 2 2
ኮዬ ፈች 2 1 2 2
ጦር ሀይሎች 1 1 3 2
ቱሉዲምቱ 0 1 4 2
ባምቢስ 0 1 3 1
ጀርመን አደባባይ 0 1 3 1
የሺ ደበሌ 2 0 2 1
ፈረንሳይ ኤንባሲ 0 0 3 1
25 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ካርታ 3: የሞት አደጋ ቦታ ሂት ማፕ


2009 -2011 ዓ.ም

ማሳሰቢያ:- በካርታው ላይ ስማቸው የተሰየመው የአደጋ ቦታዎች በ2009-2011 ዓ.ም ከ 10 ሞት በላይ ያስከተሉ
ናቸው፡፡
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 26

ምዕራፍ 2

አደገኛ የመንገድ አጠቃቀም


ባህሪያት
አዲስ አበባ
27 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

8ኛ ዙር ክትትልና ግምገማ ሪፖርት


አደገኛ ባህሪያት በእይታ ዳሰሳ ጥናት አዲስ አበባ, ሰኔ /2007 - መጋቢት / 2011 Round 8 Report,
February – March 2019 City: Addis Ababa, Ethiopia

ይህ ሪፖርት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በ JHU-IIRU የተዘጋጀ ነው፡፡. የሪፖርቱ አጠቃላይ አላማ በሰኔ 2007
እስከ መጋቢት 2011 መካከል አዲስ አበባ ውስጥ የተስተዋሉ የሄልሜት አጠቃቀምን ፣ ደህንነት ቀበቶ እና የሕፃናትን
ደህንነት መጠበቂያ ወንበር ፣ ፍጥነት እና ጠጥቶ ማሽከርከር ሂደት ነው፡፡
ይህ ሪፖርት የ BIGRS የእይታ ጥናት በዝርዝር ያሳያል፡፡እንዲሁም ከ 8 ዙር የጥናት ውጤቶች በአደጋኛ የመንገድ አጠቃቀም
በአዲስ አበባ ያለውን ሁኔታ ያሳያል፡፡

የጥናቱ ጊዜ ማጣቀሻ

ዙር 1 ዙር 2 ዙር 3 ዙር 4 ዙር 5 ዙር 6 ዙር 7 ዙር 8

ሰኔ -ሀምሌ /2007 የካቲት - ሚያዚያ/2008 ሀምሌ-ነሀሴ/2008 ጥር- የካቲት/2009 ነሀሴ - መስከ/2010 መጋቢት- ሚያዚያ ነሀሴ- የካቲት -
/ 2011 መስከ/2011 መጋቢት/ 2011

ጠጥቶ ማሽከርከር
ምስል 25 :- አሽከርካሪዎች ከአልኮል መጠን በላይ በመፈተሻ ቦታዎች

በአዲስ አበባ ጠጥቶ


12.0% ማሽከርከር በ89 በመቶ
ቀንሷል፡፡
10.0%
9.7%
8.0%

5.9%
6.0%

3.3%
4.0% 4.5% 2.7% 2.7%
2.4%
2.0% 1.1%

0.0%
ዙር 1 1 Round
Round ዙር 22 Round
ዙር 33 Round
ዙር 44 Round
ዙር 55 Round
ዙር 66 Round
ዙር 77 Round
ዙር88

ጠጥቶ ማሽከርከር ቋሚ እና ቀጣይነት ያለው የመቀነስ ሁኔታ ነበረው፡፡ በ8ኛው ዙር 1.1 % አሽከርካሪዎች ጠጥተው ያሽከረከሩ ሲሆን 1 %
የሚሆኑት ከተፈቀደው የአልኮል መጠን በላይ 0.04g/dL ነበር፡፡ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲነፃፀር የበለጠ ጠጥቶ ሲያሽከረክሩ ተገኝተዋል፡፡
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 28

ፍጥነት 50

ምስል 26 :- ከተፈቀደው ፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ ተሽከርካሪዎች በመቶኛ


00,
60%
51% 48% 51% ከፍጥነት ወሰን በላይ
49%
50%
43% 43% 43%
39%
40% 5km/hr ከፍጥነት ወሰን በላይ
30% 30% 30% 32% 33%
30% 27% 26%
24% 25%
20% 10km/hr ከፍጥነት ወሰን በላይ
23% 22% 22% 24% 15%
15%
10% 4% 5%
11% 20km/hr ከፍጥነት ወሰን በላይ
10% 11% 11% 11% 6% 4%
0% .
ዙር11 Round
Round ዙር2 2 Round
ዙር3 3 Round
ዙር4 4 Roundዙር
5 5Round
ዙር6 6 Round
ዙር7 7 Round
ዙር8 8

ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር የተለመደ እና በጥናቱ አነስተኛ መሻሻል እያሳየ የመጣ አደገኛ የመንገድ አጠቃቀም ባህሪ ነው፡፡ በአጠቃላይ 43%
የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ እንዳሽከረከሩ መረጃው ያሳያል፡፡
29 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ሔልሜት

ምስል 27:- የሔልሜት አጠቃቀም በፐርሰንት

ሔልሚት ያጠለቁ አሽከርካሪዎች


90%
81% 77%
80% 73% 72%
65%
70% 63% 64%
70%
60% ሔልሚት ያጠለቁ ሞተርሳይክል ተሳፋሪዎች
50% 41% 43%
37%
34% 38%
40% 32% 28%
31%
30% 28%
19% 24%
20% በትክክል ሔልሚት ያጠለቁ አሽከርካሪዎች
4% 4% 8%
10% 5% 5% 10% 13%
8%
በትክክል ሔልሚት ያጠለቁ ሞተርሳይክል ተሳፋሪዎች
0% 2% 3% 3% 3% 5%
Round
ዙር 1 1 Round
ዙር 2 Round
ዙር 33 Round
ዙር 44 Round
ዙር 55 Round
ዙር 66 Round
ዙር 7 Round
ዙር8 8

በአጠቃላይ በ8ኛው ዙር ጥናት በአዲስ አበባ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች በትክክል ሔልሜት ያደረጉት 24% ነበሩ፡፡.
ከመጀመሪያው ዙር ጋር ሲነፃፀር ሔልሜት በትክክል ያደረጉት ቋሚ የሆነ ለውጥ ያሳያል፡፡ (28% in ዙር 8 vs. 41% in ዙር 1). በሁሉም ዙር ላይ ትክክለኛ
የተሳፋሪዎች ሔልሚት ያደረጉ ተሳፋሪዎች ቀስ በቀስ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
(13% in ዙር 8, ከዙር 1 2% ).
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 30

የደህንነት ቀበቶ እና የህፃናት የደህንነት መቀመጫ ወንበር

ምስል 28 :- የደህንነት ቀበቶ እና የህጻናት ደህንነት መቀመጫ ወንበር በመቶኛ

110%
97% 99% 100% 99% 99% 99% 99%
100%
98%
90%
80% የደህንነት ቀበቶ ያሰሩ አሽከርካሪዎች
70%
60%
50%
40% ‹5 አመት በታች የሆኑ ተሳፋሪዎች በህፃናት የደህንነት መቀመጫ የተጠቀሙ
30% 13%
8% 9%
20% 5% 7% 7% 3% 6%
10% 6% 14%
6% 7% 7% 6% 5% 7%
0%
ዙር 1 1 Round
Round ዙር 2 2 Round
ዙር 3 3 Round
ዙር 44 Round
ዙር 55 Round
ዙር 66 Round
ዙር 7 7 ዙር 8 8
Round
የደህንነት ቀበቶ ያሰሩ ተሳፋሪዎች

ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ አሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶ ቢጠቀሙም የፊት መቀመጫ የሚቀመጡ ተሳፋሪዎች የደህንነት
ቀበቶ ለብሰው የታዩት በጣም አነስተኛ ነበሩ (9%) የጀርባ መቀመጫ ላይ የሚቀመጡ ተሳፋሪዎች በአጠቃላይ የደህንነት
ቀበቶ አርገው አልታየም ነበር (1%):: የህፃናት የደህንነት መቀመጫ ቀበቶ አጠቃቀምን በተመለከተ , 6% የሚሆኑት ከ5
አመት በታች እና 2% የሚሆኑት ከ12 አመት በታች የልጆች የደህንት ቀበቶ ተጠቅመዋል፡፡
x
31 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ምዕራፍ 3

የመንገድ ደህንነት ለማሻሻል


የተተገበሩ ተግባራት
አዲስ አበባ
2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 32

ስትራቴጂክ ኮሚኒዩኬሽን
2011 ዓ.ም

የፀረ_ጠጥቶ ማሽከርከር የመገናኛ ብዙሃን ዘመቻ

ከዚህ ቀደም በተካሄደው የመገናኛ ብዙሃን ዘመቻ እና የተጠናከረ የህግ ማስከበር ስራ የጠጥቶ ማሽከርከር የአደጋ መንስኤ በከፍተኛ
ደረጃ በመቀነሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋውን መንስኤ መቀነሱን እንዲቀጥል ለሶስተኛ ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን ዘመቻ
አካሂዷል:: ከተማውም ከዚህ በፊት የተሰራውን እና የአደጋ መንስኤውን ጉዳት አጉልቶ በማሳየት እና የህዝቡን ግንዛቤ ከመጨመር አንፃር
ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበውን “ እናትዬዋ” የተሰኘውን እና የህግ ማስከበሩን የስራ ሂደት የሚያሳየውን “ህግ ማስከበር” የተሰኘውን
የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያዎች እንደገና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንዲተላለፍ ሰርቷል:: ወደ 3 ሚልዮን ብር በመመደብም የህዝብ
አገልግሎት ማስታወቂያዎቹ በተለያዩ ዋና ዋና በሚባሉ የቴሌቭዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለተከታታይ 4 ሳምንታት እንዲተላለፉ
ተደርጓል:: በአማካኝ በከተማዋ ብቻ ወደ 4 ሚልዮን የሚሆን ህዝብ እና በአገራችን የሚገኙ ብዙ ሚልዮኖች ተደራሽ ተደርገዋል ተብሎ
ይገመታል:: በተጨማሪም በተለያዩ ሚድያዎች የሚዘጋጁ የተለያዩ የመንገድ ደህንነት ፕሮግራሞች ስለጠጥቶ ማሽከርከር የአደጋ መንስኤ
ውይይት እንዲያደርጉበት በመስራት መንገድ ተጠቃሚው ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያገኝ በማድረግ የባህሪ ለውጥ እንዲመጣ ለማስቻል
ተሰርቷል::

ምስል 29: “ እናትዬዋ” የተሰኘው የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ


33 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር የአደጋ መንስኤን ለመቀነስ የተዘጋጀ


የመገናኛ ብዙሃን ዘመቻ

ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር የአደጋ መንስኤ በከተማዋ በአደጋ መንስኤነቱ አሁንም ከፍተኛውን ደረጃ ይዟል:: የከተማዋ አስተዳደር፣
በብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ ኢንሽዬቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲ ቫይታል ስትራቴጂስ እና ፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በመተባበር ከዚህ
ቀደም የተሰራውን እና ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር የአደጋ መንስኤ ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበውን “ ዶክተሩ”
የተሰኘውን የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ በኦሮምኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለህዝቡ ተደረሽ እንዲሆን ሰርተዋል:: የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያው
በዋና ዋና አገር አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እና በተለያዩ በትምህርት ቤት ውስጥ በሚገኙ ስክሪኖች ላይ እንዲተላለፉ ተደርጓል:: ከመገናኛ ብዙሃኑ
ዘመቻ በተጓዳኝ ሀገር አቀፍ የተጠናከረ የህግ ማስከበር ስራ ተከናውኗል::

በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የሚገኙ 45 የህግ አስከባሪዎችን በማሰልጠን ለተማሪዎች የመንገድ
ደህንነት ስልጠና እንዲሰጧቸው ተደርጓል::

ህግ ማስከበር
2011ዓ.ም M&E Round

. በአደገኛ የመንገድ ባህሪያት የተካሄደ ወርክሾፕ

ምስል 30:- በአደገኛ የመንገድ ባህሪያት የተሰጡ ስልጠናዎች

 45 የትራፊክ ማኔጅመንት ኢጀንሲ ህግ ማስከበር ባለሞያዎች በአደገኛ የመንገድ ባህሪያት ላይ ስልጠና ወስደዋል፡፡

 ፍጥነት
 ጠጥቶ ማሽከርከር
 የደህንነት ቀበቶ
 የህጻናት የደህንነት መቀመጫ
 የሞተር ሳይክል ሔልሜት
 ትኩረት ሳይሰጡ ማሽከርከር
 የህግ ጥሰቶች
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 34

የሔልሜት የማድረግ ህግ ማስከበር ፖሊሲ ዎርክሾፕ

 70 ትራፊክ ፖሊሶች በሔልሜት አደራረግ ህግ ማስከበር ላይ ስልጠና ወስደዋል (ግንቦት 23 እና 24 2011 ዓ.ም)

ምስል 31 :- በሔልሜት ህግ ማስከበር ላይ ስልጠና

የመረጃ አያያዝ እና የአሠራር እቅድ አውደ ጥናት በቀጣይ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ


ለአንድ ቀን ተካሂዷል

 መረጃ አያያዝ ትንተና እና ስርጭት

 ስትራቴጂ ማሻሻል – የትራፊክ መረጃ መለኪያዎች

 የትራፊክ ሕግ አፈፃፀም ተግበራት


 የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ

 የመንገድ ፖሊሲ ስትራቴጂ እቅድ

 የመንገድ ፖሊሲ ስትራቴጂ አላማ

 የመንገድ ላይ የፖሊሲ ስትራቴጂ ዕቅድ ደረጃዎች


 የመንገድ ላይ የፖሊሲ ሥራ ዕቅድ

 ክትትል እና ቁጥጥር
35 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

መረጃ አያያዝ እና ክትትል


2011 ዓ.ም&E Round 8 Report March 2019
City: Addis Ababa, Ethiopia

የመንገድ ደህንነት ሪፖርቶች

 ይህ ሪፖርት 4ኛው የመንገድ ደህንነት ሪፖርት ሲሆን የበፊቶቹ ሪፖርቶች የተዘጋጁት በከተማዋ እና BIGRS
ኢኒሼቲቭ ትብብር ነው ፡፡

ምስል 32 :-የመንገድ ደህንነት ሪፖርቶች

የተሻሻለ የፖሊስ አደጋ መመዝገቢያ ቅጽ

 BIGRS ኢኒሼቲቭ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት የትራፊክ አደጋ መመዝገቢያ ቅጹን ተገምግሞ
መመዝገቢያው እንዲቀል እና ከኤሌክትሮኒክ መመዝገቢያው ጋር እንዲናበብ ተደርጏል፡፡

አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 36

ምስል 33 :-የተሻሻለው የአደጋ መመዝገቢያ ቅፅ

በአደጋ መመዝገቢያ ቅፅ ስልጠና

 120 የትራፊክ አደጋ መርማሪ ፖሊሶች በተሻሻለ የትራፊክ አደጋ መመዝገቢያ ቅፅ ላይ ስልጠና ተሰቷል፡፡

ምስል 34:- በአደጋ መመዝገቢያ ቅፅ ስልጠና


37 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ እና እንቅስቃሴ


2011 ዓ.ም: Addis Ababa, Ethiopia

ምስል 35:-BRT B2 የመንገድ ደህንነት ኦዲት


የፈጣን አውቶቡስ ትራንስፖርት መንገድ ደህንነት ኦዲት
በአዲስ አበባን የመጀመሪያው የፈጣን አውቶቡስ ትራንስፖርት
መንገድ ደህንነት ኦዲት ኦዲት ተደርጓል፡፡ 17.4 ኪሜ በሚረዝመው የ
B2 ኮሪደር የመንገድ ደህንነት ኦዲት ዋና የደህንነት ተግዳሮቶች
አጉልቶ አሳይቷል ፡፡ የ “WRI” ዋና ምክሮች መካከል መሳፈሪያዎች
ለእግረኞች ያላቸውን ተደራሽነትን ማሻሻል ፣ የእግረኞች መሻገሪያን
ደህንነት ማሻሻል ፣ ወድ አደባባይ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በትራፊክ
መብራት እንዲስተናገዱ ማድረግ፣ በ “LRT” ጋር የሚኖረውን ቅንጅት
ማሻሻል ፣ ተርሚናሎችን ከመጋቢ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶ
አማራጭ ጋር ማስተሳሰር ይገኙበታል። በ WRI የቀረቡት የማሻሻያ
ደህንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት ትራንስፖርት
ምክረ ሃሳቦች በዲዛይን ላይ የተካተቱ ሲሆን ቀሪ ማሻሻያዎችም
በግንባታው ወቅት የሚካተቱ ይሆናል። በ”WRI” ደህንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት ትራንስፖርት ለማጎልበት
ዝርዝር ተግባራት ያካተተ ፕላን ዝግጅት ላይ ድጋፍ ተደርጓል ።
በተጨማሪም ከብስክሌት ትራንስፖርት ጋር የተያያዙ
ውይይቶችን በማድረግ እና የዳሰሳ ጥናቶች ግኝት በማዳበር
ለደህንነቱ የተጠበቀ የብስክሌትዲዛይን ማንዋል ከ ITDP እና
WRI የ በአዲስ አበባ ረቂቅ የትራንስፖርት ስትራቴጂ ዝግጅት TUMI ጋር በመሆን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡ በመጨረሻም
WRI በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ስትራቴጂ ለማዘጋጀት WRI በ 3 የሙከራ ኮሪደሮች ላይ ኦዲት ያደረገ ሲሆን ለብስክሌት
ከተዋቀረው ግብረሃይል አካል ነው። WRI በአጠቃላይ ስልጠና ቦታዎችን የመጀመሪያ ንድፍ አዘጋጅቷል ፡፡
በስትራቴጂው ዝግጅት ግብዐት ከማቅረብ ባሻገር የመሬት
አጠቃቀምን እና የትራንስፖርት ዕቅድን ፣ የህዝብ ትራንስፖርት እና
የመንገድ ደህንነትን ላይ የትኩረት አቅጣጫ አዘጋጅቷል ፡፡
ለስትራቴጆውም ከዋና ዋና ባለድርሻ አካላት ግብረመልስ
ምስል 36:- ደህንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት ትራንስፖርት
ለመሰብሰብ እና በመጨረሻው ሰነድ ላይ ለማካተት ሶስት
ወርክሾፖች ተዘጋጅተዋል። WRI የመጨረሻውን ግብረመልስ
እያካተተ ሲሆን ረቂቅ ስትራቴጂውን ለሁሉም ባለድርሻ አካላት
የሚያስተላልፍ ይሆናል።
አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 38

ሴቶች እና ትራንስፖርት የውይይት መድረክ ምስል 37:- ሴቶች እና ትራንስፖርት የውይይት መድረክ
WRI ከትራንስፖርትና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሴቶች እና ትራንስፖርት
በአፍሪካ በሚል ርዕስ የ3 ቀናት የውይይት መድረክ አዘጋጅተዋል።
በመድረኩ ከ 150 በላይ ፖሊሶች ፣ ተመራማሪዎችን ፣ ባለሙያዎችን እና
ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎች ሴቶች እና
ሌሎች ተጋላጭ የሆኑ የመንገድ ተጠቃሚዎች የሚያጋጥሟቸውን
CS
የትራንስፖርት ችግሮች ለመቅረፍ አዳዲስ መፍትሄዎችን ለማቅረብ በሦስት
ዋና ዋና ዘርፎች ላይ መክረዋል። እናዚህም 1) ተደራሽነት እና ደህንነት ፣
2) የስራ እድል እና 3) አካባቢ ጥበቃ ናቸው ፡፡ WRI በሥርዓተ-ፆታ ላይ
የተመሠረተ የትራንስፖርት ፖሊሲዎችን እና ፕሮጄክቶችን ለማሳወቅ
በስብሰባው ላይ የቀረቡትን ምርምርና ጥናቶችን አጠናቅሮ የሚያቀርብ
ይሆናል፡፡

የተሻሻሉ መጋጠሚያዎች
2011 ዓ.ም

አንበሳ ግቢ

ለገሀር

18 ማዞሪያ
39 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

23 መጋጠሚያዎች የትራፊክ መብራት ተተክሎላቸዋል


2011 ዓ.ም

151 የፍጥነት ማብረጃ ጉብታዎች


አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 40

5,847 ተቀባሪ አንፀባራቂ ተከላ

15 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መተላለፊያ አጥር እና 35 ኪሎ ሜትር


የIRAP ውጤት ትግበራ
341 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

3989 ቦላርድ ተከላ


አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት 42

የበጎ ፍቃድ ትራፊክ አስተባባሪዎች ስልጠና


43 አዲስ አበባ መንገድ ደህንነት ሪፖርት

References

[1] World Health Organization (WHO), "World report on road traffic injury prevention," WHO, Geneva,
2004.

[2] Federal Police commission, "Police Annual crash statistics report," Federal Police Commission,
Ethiopia, 2018-2019.

[3] World Health Organization (WHO), "Global Status Report on Road Safety, 2018" Geneva, 2019.

[4] Transport Programs Management Office (TPMO), "Annual Road Safety Report," TPMO, Addis
Ababa, 2017-2018.

[5] Abegaz T, Berhane Y, Worku A, Assrat A, Assefa A,, "Road Traffic Deaths and Injuries Are Under-
Reported in Ethiopia: A Capture-Recapture Method," PlosOne 97(7).
doi:10.1371/journal.pone.0103001, 2014
[6] World Health Organization (WHO), "Fatal injury surveillance in mortuaries and hospitals," WHO,
Geneva, 2012.

[7] Central Statistics Agency (CSA), "Population Projection of Ethiopia for all woreda levels," CSA,
Ethiopia, 2013.

[8] Fedreral Transport Authority, "Registered vehicles in Ethiopia," FTA, Ethiopia, 2019.

[9] World Health Organization (WHO), "Fatal injuries Surveillance in mortualities and hospital," WHO,
Geneva, 2012.

[10] Greene DL, Jones, DW. "The full costs and benefits of transportation: Contributions to theory,
method and measurement" Springer Science and Business Media, p. 1, 1997.
ግራፊክስ ዲዛይን እና ሌይአውት
በሜሮን ጌታቸው

You might also like