You are on page 1of 3

እውነት ምንድን ነው?

/ ክፍል ፩ /

📜📜📜📜

በአንዳንድ መመዘኛዎች አብዛኛው ሰው እውነት ብሎ የተስማማበት ነገር ነገር ከሞላ ጎደል እውነትነት አለው ተብሎ
ይታሰባል ። ይሁንና ይሄ ብያኔ ከብዙ የእውነታ ማረጋገጫ መንገዶች መንገዶች አንዱ እንጂ የመጨረሻ ማጠቃለያው
እንዳልሆነ ልብ ማለት ይገባል ። ስለዚህ አንተም ሆንክ የሀዲስ ኪዳኑ ጲላጦስ " እውነት ምንድር ነው? " ስትሉ
ለጠየቃችሁት የጓደኞችህ መደምደሚያ አርኪ ምላሽ አይሆንም ።

📜📜📜

ከሁሉም በፊት ውሸት እንድንናገር የሚገፋፉን ነገሮች ምንድን ናቸው ብለን መነሳት የእውነትን ተፈጥሮ መርምሮ
ለማግኘት ይረዳናል ። አንድ ሰው እንደማያፈቅራት ልቡናው የሚያውቀውን ሴት አፈቅርሻለሁ ቢል ውሸት ተናግሯል
ማለት ነው ። ወይም አንድ ልጅ የብስኩት ማስቀመጫውን አድፋፍቶ እያለ እናቱ ስትጠይቀው << አላደረኩም >> ቢል
ዋሽቷል ። ውሸት ማለት የምታውቀውን የምታስበውንና የሚሰማህን ክደህ መናገር ነው ። እንዲህ ያለው ድርጊት
በየዋህነት ወይም በስህተት ከሚፈጸመው የተለየ ነው ። ለምሳሌ አንድ የእግር ኳስ ዳኛ በአጠራጣሪ ሁኔታ የገባን ጎል
ቢሽር ማለት ነው ።

📜📜📜

የቅርብ ጊዜው አሜሪካዊው ታላቁ ፈላስፋ ጆሲያህ ሮይስ (Josiah Royce) ለውሸት ትርጓሜ " ሲሰጥ የሰው ልጅ ይሁነኝ
ብሎ የድርጊት መወከያ ቃላቱን በማቀያየር የሚያውቀውን እውነታ ሲቃረን ነው " ይላል ። "አይደለም" መባል
የሚገባውን "ነው" በሚልበት ጊዜ ፤ ወይም "ነው" ማለት ሲገባው "አይደለም" ለማለት ሲደፍር ። ሮይስ ውሸትን
የፈታበት መንገድ ወደ ጥንታዊ የእውነት ትርጓሜ ይመራናል ። ከ 2 ሺህ 5 መቶ አመታት በፊት ፕሎቶና አርስቶትል
በዚሁ መንገድ ለእውነትና ውሸት ብያኔ ሰጥተው ነበር ።...

ይቀጥላል....

እውነት ምንድን ነው?

/ ክፍል ፪ /

📜📜📜📜📜

… የቀጠለ

ፕሌቶና አርስቶትል እንደሚሉት የጨበጥነው አስተያየት ትክክለኛ መሆኑ የሚረጋገጠው "

ነው" መባል ያለበት "ነው" ተብሎ ሲገኝ ወይም "አይደለም" መባል የሚገባው "አይደለም" ሲባል ነው ። በአንፃሩ
አስተያየታችን ሐሰት ሆኖ የሚገኘው ደግሞ የተገላቢጦሽ "ነው" መባል ያለበት "አይደለም" በሚል ተለውጦ ሲገኝ
ወይም "አይደለም" በ"ነው" ተተክቶ ስናገኘው ነው ።
📜📜📜

ፕሌቶና አርስቶትል እንደሚሉት የአስተያየታችን እውነትነት የሚረጋገጠው ከገሃዱ ዓለም ተጨባጭ ሁኔታና ከተፈጥሮ
ህግ ጋር እየተመሳከረ ይሆናል ። አስተያየታችን ከገሃዱ ዓለም ሆነ ከተፈጥሮ ህግ ጋር የተስማማ ሆኖ ከተገኘ እውነትነት
ሲኖረው በአንፃሩ ከተጣረሰ ደግሞ ስህተት ተናግረናል ማለት ይቻላል ይላሉ ።

📜📜📜

ስለዚህ ከላይ እንደተመለከትነው የእውነታን ምንነት አንጥሮ ማውጣት በጣም ቀላል ነው ። ፍቺውንም መረዳት ያን
ያህል አዳጋች አይደለም ። ጲላጦስ ኢየሱስን ስለእውነት ምንነት ሲጠይቅ ምናልባትም ምላሹ በኋላ ለሌላ ጥያቄ እራሱን
አዘጋጅቶ ነበር "የተነገረን እውነት ይሁን ሐሰት እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?"

📜📜📜

ለዚህ ጥያቄ ሶስት ዋና ዋና ምላሾች አሉ ። አንዳንዱ ጉዳይ በራሳችን ተጨባጭ እውነታ የምንዳኘው ነው ። "ድፍኑ
ከቁራሹ ይበልጣል" ይሄ እውነት በራሳችን አይተን ያረጋገጥነው በመሆኑ በየትኛውም አግባብ ተቀይሮ ቢመጣ ልንቀበለው
የሚያዳግተን ነው ። ድፍኑን እናውቃለን ቁራሹንም እንረዳለን ። ስለዚህ ቁራሹ ከድፍኑ ሊበልጥ የሚችልበት አንድም
መንገድ የለም ። የአንዳንድ ነገር እውነትነት የምናረጋግጥበት አግባብ ቁራሹ ከድፍኑ የአለመብለጡ እውነታን መመዘኛ
አድርገን ነው ። ...

ይቀጥላል...

እውነት ምንድን ነው?

/ ክፍል ፫ /

📜📜📜📜📜

...የቀጠለ

ሁለተኛው እውነታን የማረጋገጫ መንገድ ደግሞ ልምድ ወይም ምልከታን መሰረት ያደረገ ነው ። አንድ ሰው ያለፈው
አንድ ወር ሙሉ ቺካጎ ውስጥ አለመዝነቡን ቢነግረን ሜትሮሎጂ ያዘጋጀውን የአየር ንብረት ሁኔታ መዝገብ በመመልከት
ማረጋገጥ እንችላለን ። ወይም ስለመዋኛው ገንዳ ውሃ ሙቀት ቢነግረን አንድ እግራችንን ሰደድ አድርገን ማረጋገጥ ነው
። እዚህ ላይ ሳይንስ ነክ ማጠቃለያዎች እንደ እውነታ የሚወሰዱት ተቃራኒ ሃሳብ እስካላጋጠማቸው ጊዜ ድረስ ብቻ ነው

📜📜📜

ሶስተኛው መንገድ በራሳችን ተጨባጭ እውነታ ሆነ በሶስተኛ ወገን ማረጋገጫነት የምንዳኘው እውነታ ሲያጋጥመን
የምንጠቀምበት ዘዴ ነው ። ለምሳሌ ስለአንድ ሰው ባህርይ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ስለአንድ ምርት ውጤታማ
አገልግሎት እንዲህ ያለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው ድምፅ በማሰባሰብ ሂደት አብላጫ ተቀባይነት ያለውን በመለየት ነው
። ብዙ ግዜ አብላጫ ድምፅ ያገኘ ነገር እንደ እውነት የመቆጠር እድሉ እጅግ በጣም ሰፊ ነው ።

📜📜📜
...ነገር ግን አብዛኛው ሰው በደፈናው የተስማማበት ነገር " እውነት ምንድነው " ለሚለው ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ ሰጪ
አይሆንም ። የዚያኑ ያህል የተሟላ ምላሽም ሊሆን አይችልም ። እውነትን መግለጽ ቀላል ነገር ነው ። የሚነገረንን
እውነት ይሁን አይሁን ለይቶ ማወቁ የበለጠ ከብዶ ይገኛል ። ከእነዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የራስን እውነት ለሌሎች
ለማስረዳት መሞከር ዋነኛው አዳጋች ጉዳይ ነው ።

❇ ተፈፀመ ❇

ምንጭ የፍልስፍና አፅናፍ

✍ ዶክተር ሞርቲመር ጄሮም ✍

ትርጉም ዓለማየሁ ገላጋይ

ከፍልስፍና አለም እንዲሁም ንባብ ለሕይወት የቴሌግራም ቻናል ዝግጅት ክፍል

@filsfina

@books4all32

You might also like