Ethiopian Reporter Amharic

You might also like

You are on page 1of 10

24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

ሪፖርተር ማህደር ሪፖርተር ስራ Reporter English Reporter Tenders 

 (https://www.facebook.com/EThReporter/)  (https://twitter.com/ethioreporter) 
(https://www.linkedin.com/in/%E1%88%AA%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-
%E1%88%AA%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-12341514)

(/)

(https://metropolitanaddis.com/)

መነሻ ገጽ (/index.php/) / እኔ የምለዉ (/index.php/ine-yemilewu) / የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና

እኔ የምለዉ (/INDEX.PHP/INE-YEMILEWU)

የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና


23 February 2020
አንባቢ (/index.php/author/anebabi)

በሀላሌ ሲዳማ
የሲዳማ ብሔር አሁን በሚኖርበት አካባቢ የሰፈረው በ16ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበረ የተለያዩ ጸሐፊዎች ያነሳሉ (Brogger 1986፣ 26፣ Hamer
1987፣ Braukamper 1977, Haileyesus Seba 2003)። የሲዳማ ብሔር በዚህ አካባቢ ከሠፈረበት ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ከነበሩ ሌሎች
ማኅበረሰቦች ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው። ሆኖም በ17ኛው ክፍለ ዘመን የራሱን የአስተዳደርና የአምልኮ ሥርዓት ለማከናወን በተደጋጋሚ
ሙከራ ቢያደርግም፣ በአከባቢው ይኖሩ የነበሩ ማኅበረሰቦች አዎንታዊ ምላሽ ባለመስጠታቸው ምክንያት ወደ ትግል ሊገባ ተገልዷል።
ባደረገው ትግልም በአሸናፊነት በመውጣት የራሱን የአስተዳደር ሥርዓት መመሥረቱ ይነገራል (ቤታና ሆጤሳ 2013፣ 63)።
በዚያን ጊዜ በትግሉ ግንባር ቀደም ነን ያሉና ትውልዳቸውን ከቡሼ የዘር ሐረግ የሚመዙት የሼቤዲኖ፣ ያናሴ፣ ዊጋ፣ ማልጋ፣ ሆሎ፣ ጋርብቾና
ሃርቤጎና ጎሳዎች “የመሬቾ” የተባለና በአንጋ (Anga) የመንፃት (Wolapho) ፍልስፍና የሚመራ የባህል፣ የሃይማኖትና የአስተዳደር ሥርዓት
እንደ መሠረቱ ይነገራል (Hamer 1987፣ 32)። በዚህ ሥርዓት ያልታቀፉ “የአለታ” ቡድን አባላት ይህን አደረጃጀት ተቃውመው የተሠለፉ ሲሆን፣
በሁለቱም ቡድን ያልተሳተፉ ሌሎች የሲዳማ ጎሳዎች በሦስተኛ ቡድንነት በመፈረጃቸው ምክንያት፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በሲዳማ ውስጥ የሦስት
ቡድኖች ክፍፍል እንደ ተመሠረተ ይነገራል።
የየመሬቾ ኃይል በሲዳማ ውስጥ የባህል፣ የሃይማኖትና የአስተዳደር ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ሚና የነበረው ቢሆንም በአለታ ቡድን ሊሸነፍ ችሏል።
ይህም ለሁለቱም ቡድኖች መፍረስና በፍልስፍናው ስም ለሚጠራ የወላዊቾ (Wolawichcho) ቡድን መመሥረት ምክንያት በመሆን የኃይል
አሠላለፉን ከሦስት ወደ ሁለት ማውረድ እንዳስቻለ ይነገራል። በዚህ መሠረት ወላዊቾ (Wolawichcho) ቡድን የገዥነቱን ቦታ ሲረከብ ሌሎች
የሲዳማ ጎሳዎች የተገዥነት ደረጃ እንዲይዙ ተደርጓል (Hamer 1987፣ 32)።

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 1/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

በዚህ መሠረት የመሬቾ ቡድን ጎሳዎች ቀደም ብሎ ሲዳማ በሠፈረበት አከባቢ ይኖር የነበረ የሆፋ ማኅበረሰብ መሸነፍ በኋላ የተገኘውን መሬት

ለራሳቸው የተከፋፈሉ ሲሆን፣ በኋላ ወደ ጥምረቱ የተቀላቀለው ወገን (በአለታ ስም የተሰየመው) ጋር እኩል የሲዳማ የአምልኮና የባህል ሥርዓት
(ለሞቱት ቅድመ አያቶች የሚቀርብ መስዋዕት “Xorishi’ra” ሥነ ሥርዓት) አስፈጻሚ መሆን ችለዋል። የአስተዳደር ሥርዓቱ ሁሉንም ጎሳ በጋራ
ማስተባበር ባይችልም፣ እያንዳንዱ ጎሳ የራሱ ሞቴ እንዲኖረው አድርጓል። የጎሳው የአስተዳደር ሥርዓት የሚመራው በሞቴ (Moote) ሲሆን፣
ቀጥሎ ያለው በምክትል (Ja’laawa) እና አስተዳዳሪ (Gashsho) ነበር።
በዚህ መሠረት የሲዳማ ባህላዊ አስተዳደር የፖለቲካ መዘውሩ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በወላዊቾ ቡድን ስም በጋራ የሚመራ ሲሆን፣ ከዚህ
የሚለዩ ጉዳዮች ሲያጋጥሙም በመሬቾ የገዥ ቡድን ይዘወሩ ነበር። በዚህ ጽሑፍ በዋነኛነት ለመመልከት የተፈለገው የዚህን ቡድን ታሪካዊ
አመጣጥ ሳይሆን፣ ይህ ቡድን በሲዳማ ፖለቲካ ላይ ያለውን ሚናና በመልካም አስተዳደር ሥርዓት ግንባታ ላይ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ
አስተዋጽኦ ነው።
ይህ ቡድን ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በአሁኑ ጊዜ በሲዳማ ውስጥ የሚታዩትን ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና አስተዳደራዊ (ፖለቲካዊ) ሥርዓቶችን
ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየ ነው። የሥርዓቱ ፍልስፍና መነሻ የሚያደርገው “የአንጋ” (Anga) ሥርዓት ሲሆን፣ አንጋ ማለት የመንፃት ሥርዓት ነው።
ፍልስፍናው የየመሬቾ ምሥረታን ተከትሎ የተገኘውን መሬት ንፁህ ለተባሉ (Wolawichcho) ጎሳዎች ያከፋፈለ ሲሆን፣ በኋላም መሬት ብቻ
ሳይሆን የሃይማኖትና ባህላዊ ሥርዓቱም በእነዚሁ ጎሳዎች ብቻ እንዲመራ የሚያስገድድ ነበር።
ይህ ፍልስፍና በሒደት ወደ ባህላዊ አስተዳደር አድጎ የእያንዳንዱ ንፁህ ጎሳ የአስተዳደር ሥርዓት በዚሁ ፍልስፍና እንዲቃኝ አድርጓል። በኋላም
የተመሠረተው የወላዊቾ ቡድን ስያሜውን የወሰደው ከራሱ መንፃት (Wolapho) ከሚለው ከሲዳምኛ ቃል ሲሆን፣ በዚህ ፍልስፍና ራሱን በአዲስ
መልክ እንዲያደራጅ ተደርጓል።
ሆኖም ይህ የወላዊቾ (Wolawichcho) ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ፣ ከዚህ በፊት እንደነበረው መቀጠል
አልቻለም። ምክንያቱም የመሬት ባለቤት የነበረው ወላዊቾ ቡድን መሬቱ እየተቀማ ለምኒልክ ጦር አበጋዞች በመሰጠቱና በኋላም በንጉሡ
ሥርዓት መሬት በፊውዳሉ እጅ በመውደቁ ምክንያት ወላዊቾ የነበረውን ገዥነት አጥቶ፣ እንደ ሌሎቹ የሲዳማ ጎሳዎች ጭሰኛ እንዲሆን
አስገድዶታል።
የመንፃት አስተሳሰብ በሲአን (ሲዳማ አርነት ንቅናቄ)
የፊውዳል ሥርዓት ጭቆና እየበዛ በመጣበት ወቅት የሲዳማ ሕዝብ አዲስ የትግል ሥልት ነድፎ ወደ ትግል እንዲገባ አድርጎታል። በዚህም
መሠረት ‹‹ሲዳማ አርነት ንቅናቄ›› (Sidaamu Wolaphote Millimmo) በሚል የፖለቲካ ፓርቲ መሥርቶ ወደ ትግል እንደገባ ይነገራል።
ንቅናቄው በደርግ ዘመን በዚህ ስያሜ ለበርካታ ዓመታት ትግል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አገር ውስጥ ገብቶ በመታገል ላይ
ይገኛል።
በዋነኛነት ለመመልከት የተፈለገው የፖለቲካ ፓርቲ መመሥረትን ሳይሆን የፓርቲውን ስያሜ ነው። ከስሙ እንደምንረዳው “Wolapho” ወይም
“መንፃት” የሚል ስያሜ የሲዳማን ነፃነት ለማረጋገጥ የሚደረግ ትግል አይመስልም። ይህ ስያሜ ከላይ እንዳነሳነው የሲዳማ ገዥው ኃይል
የነበረው የመሬቾ ቡድን ከሆፋ መሸነፍ በኋላ የተገኘውን መሬት በብቸኝነት ለመቆጣጠር፣ ሲዳማን በሦስት ቦታ ለመክፈል የፈለሰፈውን የአንጋ
ሥርዓት ለማስፈጸም የተጠቀመው ስያሜ ነው። ይህንን የመሬቾ ፈርሶ ወደ ወላዊቾ ሲቀየር በቀጥታ የአንጋ ሥርዓት ማስፈጸሚያ የነበረውን
የነፁ (Wolapho) የሚል ስም በመውሰድ ያቋቋመው የቡድኑ መጠሪያ የነፁ (Wolawicho) የሚል ነበር። በዚህ መሠረት መንፃት (Wolapho)
የሚለው ስያሜ በቀጥታ የሚገናኘው የሲዳማ ብሔር ከባርነት ማላቀቅ ወይም ከአርነት ማውጣት ሳይሆን ይህንን የየመሬቾ/የወላዊቾ ቡድን
ፍልስፍናን መልሶ ለማረጋገጥ የሚደረግ ትግል መሆኑን ነው።
በዚህ በመንፃት (Wolapho) ስያሜ ባለፉት 27 ዓመታት በሲዳማ ውስጥ መንግሥት ለመመሥረት ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ሊሳካ
አልቻለም። ሲአን በሲዳማ ሥልጣን እንዳይዝ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ ፓርቲው የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም መነሻ ነው። ከስሙ
እንደምንረዳው መንፃት (Wolapho) የሚለው ስያሜ የመላው ሲዳማ ሕዝብ ሳይሆን፣ ከዚህ በፊት ከ17ኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ 20ኛው
ክፍለ ዘመን የተሸጋገረና ሲዳማን ሦስት ቦታ የከፈለ የየመሬቾ ቡድን አስተሳሰብ በመሆኑ ነው። በዚህ መሠረት ኢሕአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ
በኋላ ይህ አስተሳሰብ በሲዳማ ውስጥ ጎልቶ በመምጣቱ፣ መላው የሲዳማ ሕዝብ ባደረገው ጥረት ፓርቲው ሲዳማን መምራት ሳይችል
ቀርቷል።
በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም ሲዳማን ለማሳመንና ወደ ሥልጣን መጥተው ርዕዮተ ዓለማቸውን ለማስፈጸም እንዲያስችለው
በሲዳማ ክልል ጥያቄ መነሻ በሰፊው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በአሁኑ ጊዜ ፓርቲው በሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ የሁለቱም ፓርቲዎች መሠረታዊ
ዓላማቸው በሲዳማ ውስጥ መንፃት (Wolapho) የሚለውን የየመሬቾ አስተሳሰብ ለመተግበር እንደሆነ ከሚያደርጉት የፖለቲካ እንቅስቃሴ
መረዳት ይቻላል። የዚህ ፓርቲ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም የ17ኛው ክፍለ ዘመን የሲዳማ ገዥ ኃይል አስተሳሰብን በ21 ክፍለ ዘመን ለማምጣት
የሚደረግ ትግል በመሆኑ፣ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በየትኛው መመዘኛ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
የመንፃት አስተሳሰብ በኢሕአዴግ ፓርቲ

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 2/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

በኢሕአዴግ ውስጥ የሲዳማን ይወክል የነበረው ሲሕዴድ ነበር። ይህ ፓርቲ በርዕዮተ ዓለም ደረጃ ሲአንን በመቃወምና በሲዳማ ውስጥ

የነበረውን ክፍፍል በማጥበብ አንድ ሲዳማ ለመመሥረት የተቋቋመና ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲዳማን የመራ ፓርቲ ነው። ከጅምሩ ይህ ፓርቲ
የመንፃት አስተሳሰብን የሚቃወምና አንድ ሲዳማን ለመፍጠር የሚደረገውን ትግል የሚደግፍ ነበር።
ሆኖም ይህ የሲሕዴድ አስተሳሰብ ብዙም መጓዝ አልቻለም። በኢሕአዴግም ሆነ በሕገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጠውን ራስን በራስ የማስተዳደር
መብት በመጠቀም፣ ሲዳማ ራሱን የመምራት ወይም የማስተዳደር ሚናውን እንዲወጣ የተሰጠውን ተልዕኮ ወደ ጎን በመተው፣ የሲዳማ አመራር
ወደ መንፃት ፍልስፍና በመግባቱ የመሬቾ ሲያራምድ የነበረውን አስተሳሰብ ተግባራዊ አድርጎታል እየተባለ ይታማል። በዚህ ምክንያት ዳግም
በኢሕአዴግ ዘመን ተመልሶ ሲዳማ ወደ ሦስት ቦታ እንዲከፈል ምክንያት እንደሆነ ይነሳል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ (Lovise Aalen) በ2010 ዓ.ም. ባደረጉት ጥናትና (The politics of ethnicity in Ethiopia actor power and
mobilization under ethnic federalism) በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 137 ላይ እንዲህ ብለው አስቀምጠዋል። በሲዳማ ውስጥ በባህላዊ
አስተዳደር የተቀዳጁትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁለቱ የየመሬቾ ቡድንና የአለታ ቡድን እየተፎካከሩ መሆኑን ሲያስረዳ፣ አቶ አባተ ኪሾ የክልሉ
ፕሬዚዳንት ሆኖ በቆየበት አሥር ዓመት የመሬቾ ቡድን አባል ለሆኑ ግለሰቦች የትምህርት ዕድል በማመቻቸትና በተለያዩ ጥቅም በሚኖራቸው
ቦታዎች በመሾም መጥቀሙን በማንሳት አለታዎች እየተቃወሙ መሆኑን አውስቷል።
አባተ ኪሾ ከሥልጣን ከወረደ በኋላ የመሬቾ ቡድን አባል የሆኑና በሥልጣን ላይ ያሉ እንደተገፉ ባደረገው ቃለ መጠይቅ ማረጋገጡን
አሥፍሯል። በተመሳሳይ በዚህ ጊዜ በመጀመርያ ሲሕዴድ ሲመሠረት መሥራች የነበሩ የሃዲቾና ሌሎች የሲዳማ ጎሳዎች በአንዳንድ የመንግሥት
ሥልጣን ቦታዎች እንዳይሳተፉ እንደተደረገ ይነሳል። በተለይ የሃዲቾ ጎሳ አባላት በየአከባቢው በሚደርስባቸው በደል መነሻ የሃዲቾ ጎሳ የራሱን
ፖለቲካ ፓርቲ ያቋቋመበት ጊዜ መኖሩን (Lovise Aalen) በተጨማሪ ገጽ 155 ላይ አስፍሮ እንመለከታለን።
በዚህ መሠረት በኢሕአዴግ ዘመን
መንግሥት የየመሬቾ አስተሳሰብ በፓርቲ ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ተሿሚዎች በኩል የመንፃት አስተሳሰብና አመለካከት በሲዳማ ውስጥ
ተግባራዊ በመደረጉ ምክንያት፣ ሲዳማ ዳግም ወደ ክፍፍል እንደገባ መመልከት ይቻላል። በዚህም በሲዳማ ውስጥ ያለው ባህላዊ አስተሳሰብ
ወደ መንግሥታዊ አስተሳሰብ ያደገ ሲሆን፣ የትኛው ጎሳ የዞን አስተዳዳሪ እንደሚሆን ለይቶ እስከማስቀመጥ የደረሰበትንና ጎሳዎች ደረጃ
የወጣላቸው ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል።
በዚህም ምክንያት በፍትሕ ሥርዓት፣ በፖሊስና በአስተዳደራዊ ሥርዓት የመብት ረገጣ በቡድን የሚፈጸምበት፣ ተጠያቂነት የሌለበት ሥርዓት
እንዲፈጠርና ሥርዓት አልበኝነት እንዲሰፍን ምክንያት በመሆን ላይ ይገኛል። የመንፃት ፍልስፍና እንደማይሳካ የተረዱ የእዚህ ፍልስፍና
አቀንቃኞች በኢሕአዴግ ዘመነ መንግሥት በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች ተሹመው ሥራቸውን ሲከውኑ ኖረዋል። እነዚህ ግለሰቦች የተሾሙት
የሲዳማ ሕዝብ የነበረበትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ፣ ልማት እንዲያረጋግጡና በሕዝቦች መካከል አንድነትና መቀራረብ
እንዲፈጥሩ ቢሆንም፣ በተግባር ልዩነቶች እየሰፉና ወደ 17ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ እየተመለሱ መምጣታቸው ታይቷል።
የመንፃት አስተሳሰብ በብልፅግና ፓርቲ
ይህ ፓርቲ ቀድሞ የነበረው ኢሕአዴግን በማክሰም እንደ አዲስ የተመሠረተ ነው። በፓርቲው ደረጃ ሊመዘን የሚገባው ፓርቲው የመደመር
ፍልስፍና የያዘ መሆኑ ነው። የመደመር ፍልስፍና አሁን ባለበት ደረጃ ለሲዳማ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ኢትዮጵያ ጠቃሚ መሆኑን ብዙዎች
ያነሳሉ። መደመር የሚለው አንድነትን የሚያጎላ በመሆኑ፣ በተለይ ሲዳማ ውስጥ ያለውን ክፍፍል የሚያጠብ በመሆኑ ለሲዳማም ጠቃሚ
መሆኑን ማመን አይከብድም። ከዚህም ባለፈ ከሲዳማ ብሔር ውጪ በአካባቢው የሚኖሩ ሌሎች ጭቁን ሕዝቦች ለሚኖራቸው አብሮነት
ጠቃሚ መሆኑም ይነሳል። ይህ የመደመር ዕሳቤ ለመንፃት ቦታ የማይሰጥ በመሆኑ፣ በአሁኑ ጊዜ ብዙዎች የመንፃት አስተሳሰብ አራማጆች
ይህንን ፓርቲ ሲቃወሙ ይሰማል። የመቃወማቸው ሚስጥር ሌላ ሳይሆን በሲዳማ ውስጥ ያለውንና የኖረውን የ17ኛው ክፍለ ዘመን የመንፃት
አስተሳሰብ የመናድ አቅም እንዳለው መረዳታቸውን ያሳያል።
በሲዳማ ውስጥ አንዳንድ አካላት እያራመዱት ያለውን ያረጀ አስተሳሰብ መናድ የሚቻለው፣ በመደመር ዕሳቤ የሚያምንና አንድ ሲዳማን ሊፈጥር
የሚችል ርዕዮተ ዓለምን ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችል የፖለቲካ ፓርቲ ሲኖር ብቻ ነው ብሎ የእዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ያምናል። ለሲዳማ
የሚያስፈልገውን አንድነት ተግባራዊ ለማድረግ ከመደመር ጽንሰ ሐሳብና ከብልፅግና ፓርቲ ጋር በመሥራት በቀጣይ ሲዳማዊና ኢትዮጵያዊ
አስተሳሰብ የተላበሰ ዜጋ መፍጠር የሚያስችል መደላደል ሊመቻች ይገባል።
በመሆኑም አሁን ያለውን ክፍፍል ማስቀረት የሁሉም ሲዳማ ግዴታ ነው። በአሁኑ ጊዜ በየቦታው የሚታዩ የጎሳ ፖለቲካ አስተሳሰብን በመናድ
ሲዳማን አንድ በማድረግ ጠንካራ ኢትዮጵያን ሊገነባ የሚችል በአመለካከቱ፣ በአስተሳሰቡና በድርጊቱ የተደመረ የሲዳማ ማኅበረሰብ መፍጠር
ያስፈልጋል። ከእዚህ ጋር በተያያዘ ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባው የ17ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ በምንም መልኩ መቀጠል እንደሌለበት ነው።
የመንፃት አስተሳሰብ በሲሕዴድ ፓርቲ
ይህ ፓርቲ የአንድ ጎሳ አስተሳሰብ ይዞ የተመሠረተ ሲሆን ዋናው በሲሕዴድ/ኢሕአዴግ አመራር በኩል የሚደርስበትን በደል ለመታገል የተቋቋመ
ድርጅት ነው። በወቅቱ በሃዲቾ ጎሳ አባላት ላይ የሚደርሰው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና አስተዳደራዊ በደል እያየለ ሲመጣ ይህንን
በተደራጀ አግባብ ለመከላከል ሰፊ ትግል በማድረግ ላይ የቆመ ሲሆን፣ በ1992 ዓ.ም. በተደረገው ምርጫ በዳራ ወረዳ አሸናፊ ፓርቲ ሆኖ

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 3/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

የነበረ ፓርቲ ነው።



ይህ ፓርቲ እንደሌሎቹ የመንፃት አስተሳሰብ ይዞ የሚታገል ሳይሆን፣ መንፃት በሃድቾና በሌሎች ጎሳዎች ላይ ያደረሰውን በደል የሚታገል
ቢሆንም፣ ሲዳማን አንድ ከማድረግ አንፃር የራሱ አሉታዊ ጎን ያለው ነው። በዚህ መሠረት በ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የኃይል አሠላለፉ
በሦስተኛ ደረጃ የተገለጸውን ደረጃ ይዞ የሚታገል በመሆኑ ለሲዳማ አንድነት ጠቃሚ አይደለም።
የመንፃት አስተሳሰብ በኤጄቲማ ፌዴራሊስት ፓርቲ
ኤጄቶ የሚለው ስያሜ ጀግንነትን የሚገልጽ ነው። የሲዳማ ጀግኖችም ኤጄቶ ይባላሉ። ይህን ስያሜ እንደ ማሰባሰቢያ ኃይል በመጠቀም
የክልል ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደርጓል። በየትኛውም አካባቢ ያለው የሲዳማ ሕዝብ ኤጄቶ ለክልል ጥያቄ ያደረገውን ትግል ደግፏል።
በአሁኑ ጊዜ ኤጄቶ የክልል ጥያቄ ካጠናቀቀ በኋላ ለምን ኤጄቲማ ፌዴራሊስት ፖለቲካ ፓርቲ ወደመሆን ተሸጋገረ የሚለውን ጥያቄ በአሁኑ ጊዜ
ብዙ ሲዳማዎች ያነሳሉ። ኤጄቶ የክልሉ ጥያቄ ወደ ውጤት እስከሚሸጋገር ትግሉን መቀጠል አለበት እንጂ፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሆኑ ተገቢ
አይደለም ይላሉ። የፖለቲካ ፓርቲ ምሥረታ መላው ሲዳማ ተነጋግሮና ተወያይተው የፈጠሩት ሳይሆን፣ የተወሰነ ቡድን የፈጠረው ነው ብለው
አብዛኞቹ ሲዳማዎች ያውሳሉ። በዚህም መነሻ ከኤጄቶ ጀርባ ያሉ ግለሰቦች ፍላጎት በተገቢው መንገድ መፈተሽ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከሆነ ማን ፈጠረው የሚለውን ጥያቄ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። የኤጄቶ እንቅስቃሴ በሲዳማ ፖለቲካ ላይ አንድ መሠረታዊ ለውጥ
ማምጣቱ ይታመናል። ይህም የክልል ጥያቄ ይዞ ውጤታማ ለማድረግ ያለውን ተነሳሽነት አንዳንድ ግለሰቦች ለፖለቲካቸው ማስፈጸሚያ
ለማድረግ እንደሆነ ይወሳል። በሲዳማ ውስጥ ተቀባይነት ያጣው የ17ኛው ክፍለ ዘመን የመንፃት አስተሳሰብ ወይም ርዕዮተ ዓለም በኤጄቶ
በኩል ለማስፈጸም የሚደረግ እንቅስቃሴ መሆኑን በጥርጣሬ የሚያነሱ አካላት አሉ። ይህ ደግሞ መላውን ሲዳማ አንድ ከማድረግ ይልቅ፣
እንደተለመደው የ17ኛው ክፍለ ዘመን የገዥው መደብ ርዕዮተ ዓለምን በሌላው ላይ ለመጫን የሚደረገውን ትግል ቀጣይ ክፍል ሊሆን
ስለሚችል፣ መላው ሲዳማ ነገሩን ቆም ብሎ መፈተሽ ይኖርበታል።
የመንፃት አስተሳሰብ በሌሎች አገር አቀፍ ፓርቲዎች
የሲዳማ ፖለቲካን ስንመለከት ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሁሉንም በየራሳቸው ጎሳ የተደራጁ በመሆናቸው፣ የአቀአፊነት ችግር ይታይባቸዋል።
በዚህ መሠረት ወደ ሲዳማ የሚመጡ ፓርቲዎች አንድነት ሊያመጣ የሚችል የፖለቲካ ፕሮግራም ከሌላቸው በመንፃት ፖለቲካ አስተሳሰብ
ተጠልፈው መውደቃቸው አይቀርም። በዚህ ዕሳቤ ወደ ሲዳማ የሚሄዱ ማናቸውም አገር አቀፍ ፓርቲዎች፣ ይህንን እውነታ ተረድተው ሲዳማን
ማቀፍ የሚያስችል ፕሮግራም ያላቸው ሊሆኑ ይገባል።
ማጠቃለያ
የሲዳማ ፖለቲካ በአሁኑ ደረጃ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን የተለየ አይደለም። መንፃት የሚለው አስተሳሰብ በየትኛው ደረጃ የሚገኝ የገዥው ሲዳማ
ማኅበረሰብ ቃሉን ሲጠቀም ይሰማል። ቃሉ የነፃ ወይም ከባርነት የወጣ የሚለውን ትርጉም የያዘ ቢሆንም፣ በማኅበረሰቡ የሚታወቀው
ትክክለኛው ትርጉም ይህ አይደለም። መንፃት የሚለው ሲያሜ ከላይ እንደተገለጸው ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ቃል ነው።
ትክክለኛ ትርጉሙ ከሌሎች ሲዳማ ጎሳዎች የተለየ የነፃ (Wolaphino) የሚል ትርጉም ይይዛል። ይህ ማለት ሌሎች የሲዳማ ጎሳዎችን
የማያካትት ቃል ነው።
በዚህ መሠረት የሲዳማ ፖለቲካ በአንድ በኩል በነፁ (Wolawicho) ገዥ ጎሳዎች በሌላ በኩል ያልነፁ ተገዥ ጎሳዎች የተደራጀ በመሆኑ፣ ሁል
ጊዜ ከግጭት የጠራ አይደለም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚቻለው ይህንን የመንፃት አስተሳሰብ በመናድ እኩልነት ሊያሰፍን የሚችል
የመንግሥት አሠራር ተግባራዊ ሲደረግ ነው። በመሆኑም ይህንን ለማድረግ የመጀመርያው ፓርቲዎች ከእዚህ አስተሳሰብ የፀዱ መሆን
የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ ፓርቲዎችም የሚሾሟቸው ግለሰቦች ከእዚህ አስተሳሰብ የፀዱና የራሴ ለሚሉት ጎሳ ወገንተኝነት የሌላቸው መሆኑን
ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል ከግለሰቦች አንፃር ፓርቲዎች መከተል የሚገባቸው የሚሾሙትን ግለሰብ ጎሳቸው ባለበት አካባቢ ከመሾም
ይልቅ፣ ወደ ሌላ አካባቢ በመውሰድ ቢሾሙ በተወሰነ ደረጃ በሕዝቡ ውስጥ የሚኖረውን የተሳሳተ አስተሳሰብ ለማረም የሚያግዝ ሊሆን
ይችላል። በዚሁ መነሻ የሲዳማ ሕዝብ እያንዳንዱ ፓርቲ የሚያራምደውን ርዕዮተ ዓለም በትክክል ተረድቶ መደገፍ የሚገባው ሲሆን፣ ይህም
ለአካባቢው መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ በኢሜይል አድራሻቸው bissaremelese109@gmail.com
(mailto:bissaremelese109@gmail.com) ማግኘት ይቻላል፡፡

(/#facebook) (/#twitter) (/#linkedin)

(https://www.addtoany.com/share#url=http%3A%2F%2

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 4/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

ተጨማሪ ጽሑፎች

Feb 23, 2020


ለግብፅና ለሱዳን 31 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ በየዓመቱ እንለቅላችኋለን ብለን እንዳንስማማ “ኡኡታ” እናሰማ!
(/index.php/article/18165)

Feb 16, 2020


ክቡር ምክትል ከንቲባ ከተማዋን በአግባቡ እየመራሁ ነው ብለው ያስቡ ይሆን? (/index.php/article/18107)

Feb 16, 2020


የዓብይ አህመድ ‹‹መደመር›› (/index.php/article/18106)

Feb 02, 2020


ኢኮኖሚያዊ ዕድገትንና የአገር ውስጥ ገቢን ምን አገናኛቸው? (/index.php/article/17994)

Feb 02, 2020


የተፈጥሮ ጋዝ ኢንዱስትሪ ለመመሥረት ምን ያግደናል? (/index.php/article/17993)

Jan 26, 2020


ከአሜሪካና ከኢራን ግጭት ጀርባ በጨረፍታ. . . (/index.php/article/17934)

ማስታወቂያ

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 5/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

(https://www.ethiopianreporter.com/node/17612)

ማስታወቂያ

(http://www.amisoft.et/index.php?refer=reporter)

ማስታወቂያ

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 6/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic


ለዜና መጽሔታችን ደንበኝነት ይመዝገቡ

የኢሜል አድራሻ

ዜና መጽሔት

ሳምንታዊ ዜና መጽሔት

ሰበር ዜና

ይመዝገቡ

ማስታወቂያ

ማስታወቂያ

ማስታወቂያ

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 7/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

የቅርብ ዜና

‹‹የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ላይ ከፖለቲካ ሴራ እስከ ተዋጊ ጦር በመላክ ወደ ውጊያ እንድንገባ እየተፈታተነን ነው››
01 ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሕወሓት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር (/article/18159)

02 የሁሉም ስኳር ፋብሪካዎች ዕዳ ወለዱን ሳይጨምር 149 ቢሊዮን ብር ደርሷል (/article/18158)

03 በመንፈቅ ዓመቱ 94 ቢሊዮን ብር ያህል ቃል የተገባና የተለቀቀ ብድር ተመዘገበ (/article/18157)

04 ሲኖዶስ ሁለት ወጣቶች ሕይወታቸው ያለፈበት ቦታ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራበት ጠየቀ (/article/18155)

የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ለአካባቢዎች በተተመነ ምጣኔ እንዲከፈል የሚያስገድድ መመርያ ወጣ


05 (/article/18154)

መንግሥት በባለቤትነት በያዛቸው ድርጅቶች ቦርዶች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ 50 በመቶ እንዲሆን ተጠየቀ
06 (/article/18152)

ማስታወቂያ

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 8/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

ብዙ የተነበቡ

ፖለቲካ (/poletika) | Feb 19


ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያበሳጨው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቀባበል (/article/18124)

(/article/18124)

ፖለቲካ (/poletika) | Feb 23


‹‹የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ላይ ከፖለቲካ ሴራ እስከ ተዋጊ ጦር በመላክ ወደ ውጊያ እንድንገባ
እየተፈታተነን ነው›› ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሕወሓት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል
(/article/18159)

ፖለቲካ (/poletika) | Feb 19


የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ጫና እንደነበረባቸው በውይይት መድረክ ላይ ገለጹ (/article/18122)

ፖለቲካ (/poletika) | Feb 19


‹‹በዚች አገር ፍፁም ፀረ ዴሞክራሲ አፈና ነግሷል›› ሕወሓት (/article/18123)

(/article/18123)

ፖለቲካ (/poletika) | Feb 23


የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ለአካባቢዎች በተተመነ ምጣኔ እንዲከፈል የሚያስገድድ መመርያ
ወጣ (/article/18154)

ክቡር ሚኒስትር (/kibur-minisiter) | Feb 12


ለክቡር ሚኒስትሩ የቀድሞ ሚኒስትር ስልክ ደወሉላቸው (/article/18056)

(/article/18056)

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 9/10
24/02/2020 የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic

የሪፖርተር አድራሻ

ሪፖርተር
ሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የሪፖርተር አገልግሎት

Reporter Tenders
https://www.reportertenders.com (https://www.reportertenders.com)
Reporter Jobs

https:\\www.ethiopianreporterjobs.com (https:\\www.ethiopianreporterjobs.com)
Goalgoogle
http://goalgoole.com/ (http://goalgoole.com/)

የሪፖርተር የሥራ ሰአት

ከሰኞ እስከ አርብ: ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽት 11 ሰዓት

የቅጂ መብት © 2019 ሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር (https://www.ethiopianreporter.com/)፡፡ ሁሉም


መብቶች የተጠበቁለት፡፡

https://www.ethiopianreporter.com/index.php/article/18166?fbclid=IwAR08d0-BDwXcf3wT8BGBdIHD-zVa51X2TSLuo_di9KErGjry05l12FDTWfY 10/10

You might also like