You are on page 1of 2

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነሮች የተከበራችሁ የፊልም ባለሙያዎች በጣም አመሰግናለሁ፡፡

ዓላማችን ሰብዓዊ መብቶችን ባህል ማድረግ ነው በማለት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ እንዲዳብር
ከሚሰራቸው ስራዊች አንዱ ነው፡፡ በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ላይ በቀላሉ ተደራሽ የሆነው የፊልም ሙያ
ነው፡፡ በዚህ ዓመት የሰራቸው ፊልሞች ኪነ-ጥበብ ለሰብዓዊ መብቶች የሚሰራ፣ ለሰብዓዊ መብቶች
መከበር ድምፅ የመሆን ጉዳዮቹን ሰብዓዊ ክብር፣ነፃነት፣ ፍትህ ናእኩልነት ላይ ያተኮረ ቢሆንም በዚህ
ዙሪያ ላይ ያተኮረ ፊልም ለመስራት መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር፡፡ (በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ላይ
ያለው ነባራዊ ሁኔታ) ፊልሞችን ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ናበአውንታዊ መንገድ የሚያሰሩ ሲባል
ከቀረቡት በርካታ የሀገር ውስጥ ና የሀገር ውጪ ፊልሞች የተመረጡ ናቸው፡፡ የመዓዛ ፊልም
ፕሮዳክሽን እና Art concentancy ፊልሞችን ለእይታ አቅርቧል፡፡ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽኑ 8
የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎችን መድቦ ለውይይት ያገዛሉ ያላቸውን ፊልሞች እንዲመረጡ
አድርጓል፡፡ ይህም ማለት ፊልሞችን በመምረጥ ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር ለፊልሙ ዘርፍ ከፍ ያለ
ጠቀሜታ አለው፡፡ ስለፊልም እንዲዎራ ፊልምም ጠንካራ ጉዳይ ላይ እንዲያዎራ በአጠቃላል ጥሩ
እና ሰዋዊ ፊልሞች እንዲሰሩ ምክንያት ሆኗል፡፡በአንደኛው እና ሁለተኛው የፊልም ፌስቲቫል
ዝግጅት ብቻ 8 አዳዲስ ፊልሞች ተሰርተዋል፡፡ እነዚህ ፊልሞች በሰብዓዊ መብት ጉዳይ ትምህርት
መስጠትባስፈለገ ጊዜ ዋና ግብዓት ሆነው አገልግለዋል፡፡ በየዓመቱ በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ላይ
የሚሰሩ ፊልሞች ቁጥር እየጨመረ እንደሚመጣ ደግሞ እምነት አለን፡፡ በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ
የፊልም ባለሙያ እና አዘጋጆች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ በዚህ ፌስቲቫል በኦሮሚያ 105፣ በሱማለያ
ክልል 133፣ በሐዋሳ 28፣ በባህርዳር 26፣ በአዲስ አበባ 30፣ በድምሩ 340 ባለሙያዎች
አንቀሳቅሷል፡፡ ለወደፊቱም ይህ ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ሀሳባቸውን በነፃነት ለመግለፅየሚፈልጉ
ታዳሚያን ፊልሞች በብዙ ቁጥር የመወያያ መድረኮችም ሰፊ እንደሚሆኑላቸው ተስፋ
እናደርጋለን፡፡ ይህ ፊስቲቫል ከሰጣቸው እድሎች መካከል ለሌላው ደግሞ ፊልም ሰሪዎች በራሳቸው
ቋንቋ እንዲሰሩ ማስቻሉ ነው፡፡ተመልካቾችም ከሀሳብ ሳይርቁ የራሳቸውን ሀሳብ በራሳቸው ቋንቋ
የክልል ቋንቋ እንዲገልፁ ምቹ ተደርጎ ቀርቧል፡፡ በሶማሌ ክልል በራሳቸው ቋንቋ ለክልሉ ሰዎች
አጭር ፊልም እና ዘጋቢ ተሰርቷል፡፡ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ በአማርኛ እና በኢንግሊዘኛ
ቋንቋዎች በተሰሩ ፊልሞች ደግሞ በአምርኛ sub title ወይም አጋዣ ፅሑፍ እንዲታከልባቸው
ተደርጓል፡፡ በኦሮምያ እንደዚሁ ፊልሞቹ በአንድ ክልል ብቻ ታጥረው እንዳይቀሩ በሊላ ቋንቋ
በመተርጎም አንዳችን የአንዳችንን ታሪክ እንድንሰማ እና እንድናይ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ መዓዛ
ፊልም ፕሮዳክሽን እና Art concentancy ፕሮግራሙን የማስተባበር ድርሻ ይኑረው እንጂ በየክልሉ
ተባባሪ ግለሰቦች ነበሩ፡፡ በሁሉም ክልሎች ስንዘዋወር ከፍተኛ ድጋፋችሁ ላልተለየን ባለሙያዎቸ እና
ተመልካቾች ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡፡ ወልቂጤ፣ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር፣ ቴያትር እና ሥነ-
ጥበባት ትምህርት ክፍል በጣም እናመሰግናለን፡፡ ፊልማቸው በፊልም ፌስቲቫሉ ላይ እንዲቀርብ
መልካም ፈቃዳቸው ለሆነው ባለሙያዎች ከልብ እናመሰግናለን! የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት

1
ኮሚሽን በዋናነት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በሆነው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርምር
በመሆኑ ይህ ስራ ይሳካ ዘንድ ፊልምን እንደመሳሪያ ለመጠቀም የፊልም ፌስቲቫል ሃሳብን
ከማምጣት ጀምሮ ፊልሞችን በማሰባሰብ እና ባለሙዎችን መመደብን ጨምሮ ለኪነ-ጥበብ
ለሰጠው ትኩረት በትልቁ መመስገን አለበት፡፡ በመጨረሻም ይህ ፊልም ፌስቲቫል በየዓመቱ እየሰፋና
እየተሻሻለ እንዲመጣ ሰፊ ጥሪ ለፊልም ባለሙያዎች እንዲደረግ ፊልሞች ለውድድር እንዲመጡ
ዘላቂነት እንዲኖራቸው የአቅማችሁን ታደርጋላችሁ የሚል እምነት አለኝ፡፡ አመሰግናለሁ!

You might also like