You are on page 1of 1

ዓምድ ፦የዚህ ወር በዓለት

የታህሳስ ወር

ሀ,ርእስ ፦ታህሳስ 3 ፦በዓታ ለእግዚእትነ ውስተ ቤተ መቅደስ

እመቤታችን አባቷ ኢያቄም እናቷ ሐና ይባላሉ ። በብስራተ መልአክ ወልደዋታል። የብፅዐት ልጅ ናትና ሦስት ዓመት
ሲሆናት ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔርም ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ ምግብ
ሳይለምድ ወስደን እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት ሄዱ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ መጥቅዕ መቶ
ህዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ አለ ። ወዲያው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ
ይዞ ረቦ ታየ። ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሳ ።መልአኩ ወደ
ላይ ራቀበት ። የርሱ ተወራጅም ስምዖንም እንኪያስ ለኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ ራቀበት ። ካህናቱም ሕዝቡም በተራ
ቢቀርቡ ራቀባቸው ። ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ብለው ለዚህች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እናቷ ሐና
ትተሻት እልፍ በይ አሏት ትታት እልፍ አለች። ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን
አንጥፎ አንድ ክንፍን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ ። የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ
እንጂ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት ። "ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ
ነበርኪ ዐሠርተ ወ ክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት " ይላል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየተመገበች
መላእክት እየጎበኟት 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች

ለ, ርእስ ፦ ዕረፍቱ ለአቡነ ዜና ማርቆስ

ሀገራቸው ዘረሬ(ድላልሽ) ነው ። አባታቸው ዮሐንስ ይባላል ። የአቡነ ጸጋ ዘአብ ወንድም ነው ። እናታቸው ዲቦራ
(ማርያም ዘመደ) ትባላለች ፤ የአቡነ ቀውስጦስ እህት ናት ። በብስራተ ማርቆስ ወንጌላዊ የካቲት 24 ተጸንሰው ህዳር 24
ቀን ተወልደዋል ። በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ጭን ወርደው እሰግድ ለአብ ወእሰግድ ለወልድ ወእሰግድ
ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ሦስት ጊዜ ሰግደዋል ። አርባ ቀን ሲሞላቸው ሊያስጠምቋቸው ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዷቸው
ካህናቱ በመጽሐፍ የሚያደርሱትን እሳቸው በቃላቸው አድርሰውታል ። ከውሃውም ሲከቷቸው ቆመው እሰግድ ለአብ
ወእሰግድ ለወልድ ወእሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ሦስት ጊዜ ሰግደዋል ውሃው ፈላ ካህኑ እንድርያስ የአቡነ ጸጋ ዘአብ
ወንድም ነው ። የሰባ ሁለት ዓመት አረጋዊ ፣ ነበረ ፈርቶ ወደ መቅደስ ሮጠ ። ቅዱስ ሩፋኤል ምን አስፈራህ ? መላጣህን
ተቀብተኸው ቢሆን ጸጉር ባበቀልክ ነበር ። ተጽናንቶ ሄደ ከውሃው ጨልፎ መላጣውን ቢቀባው ጸጉር አብቅሎለታል።

አምስት ዓመት ሲሆናቸው ወስደው ለመምህር ሰጧቸው በሦስት አመት ብሉይና ሐዲስ አጥንተዋል ። በስምንት
ዓመታቸው መዓርገ ዲቁና ለመቀበል ወደ አባ ኔርሎስ ሄዱ ። ተቀብለው ሲመለሱ ሳይንት ላይ ሽፍታዎች አግኝተዋቸው
የእጃቸውን በትር ሳይቀር ነጥቋቸው ። ወደ ጌታ ቢያመለክቱ በትሮቻቸው እባብ ሆነው ነድፈው ገድሏቸዋል ። እንዲህ
እያሉ አድገው 30 ዓመት ሲሆናቸው ማርያም ክብራ የምትባል ደግ ሴት አጋቧቸው ። ልምደ መርዓዊ መርዓት ያድርሱ
ብለው መጋረጃ ሲጥሉባቸው አንቺ እህቴ ይህ ዓለም አላፊ ጠፊ ነው ። ምን ይረባናል ብለን እናደርገዋለን ? አላት ። እኔ
ብንተወው እወዳለሁ አለቻቸው ። በሌሊት ወጥተው ሄዱ። እሷን መላእክት በጌቴሴማኒ አድርሰዋት 7 ዓመት ኖራ ጥር
21 ቀን አርፋለች ። አናብስቱ ቀብረዋታል ። ጌታም ስለ ንጽሕናዋ ስለ ምናኔዋ እና ስለ ተጋድሎዋ ሦስት አክሊላት
አቀዳጅቷታል

እሳቸው መልአኩ ሀገረ ምሑር አድርሷቸው መስፍነ ብሔሩ አውጋትን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ራበኝ አብላኝ አሉት
ኢየሱስ ክርስቶስ የምትለው እርሱ ማነው አለ አንተንም እኔንም የፈጠረ አምላክ ነዋ አሉት። ያንተ ይሆናል እንጂ የኔ
አምላክ ማኮስ ነው አሏቸው

You might also like