You are on page 1of 7

የቅድስት አርሴማ ሥዕል

በቤተክርስቲያን
ትክክለኛው ሥዕል የቱ ነው?

ስም፦ ሚኪያስ ሸዋታጠቅ

ቀን ፦ 28/03/2016
ቅድስት አርሴማ ማን ናት?

እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለገሉ ከነበሩት ካህናት ወገን የሆነ ፣ ቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ከቅድስት አትናስያ በስእለት ተወለደች።
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ከአዲስ ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትር በጸሎት ትተጋ ነበር: ትውልዷ ሮም ቢሆንም
በሰማዕትነት ያረፈችው በአርመን ነው፡፡ እኛ አርሴማ ስንላት እነርሱ Saint Hripsime ይሏታል፡፡ የዚህች ወጣት ሰማዕት ታሪክ በስንክሳር በመስከረም 29
ቀን ተጽፏል፡፡

የቅድስት አርሴማ ሥዕሏ የትኛው ነው?

በሀገራችን ያሉ ክርስቲያኖች ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ያላቸውን ትልቅ ፍቅር በመመልከት አንዳንድ ሰዎች የተለያዩ ቅዱሳት አንስትን በእርሷ ስም ሥዕሉን
ለብቻው አሊያም የገጽ ሽፋን በማድረግ በውስጥ ገድሏን ወይም አጭር የሕይወት ታሪኳን በማካተት ይሸጣሉ። ከዚህ በተጨማሪም በመረጃ መረብና
ማኅበራዊ ድረገጾች ሰማዕቷን የሚዘክሩ ሥዕሎችም በዚህ የተሳሳተ መረጃ ሰለባ የሰማዕቷን ትክክለኛ ያልሆነ ሥዕል ሲጠቀሙ ይታያል።

እነኚህን ሥዕላት ለመጠቀማቸው ምክንያታቸው ደግሞ ለቅድስት አርሴማ የተሰጣትን ፀጋ ይኸውም

 ጽዋ [ማንኛውም ሰማዕት የሰማዕትነቱን ጽዋ (የሞትን ጽዋ) መቀበሉን ያመለክታል ማቴ 26፡39]፣


 ዘንባባ ዝንጣፊ [የድል፣ የሰማያዊት ኢየሩሳሌም እና የሕይወት ምልክት] እና
 መስቀል [መከራውን ያሸነፉበት ኃይል ምልክት] መሠረት በማድረግ ነው።

ሆኖም ግን በሥዕሎቿ ላይ የሚገኙት እነኚህ ምልክቶች የቅድስት አርሴማ ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ቅዱሳት አንስትም ጭምር ናቸው እንጂ። ለምሳሌ ለመጥቀስ
ያህል፦ቅድስት በርብራ፣ ቅድስት ማሪና ዘአንጾኪያ፣ ቅድስት ኢየሉጣና ልጇ ቅቂርቆስ፣ ቅድስት ድሚያ፣ ቅድስት ሙሕራኤል እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው።

ነገር ግን ቅድስት አርሴማ ተብለው ተሰራጭተው ከሚሸጡት አሊያም በየድረገጹ ሰማዕቷን ከሚዘክሩ ሥዕሎች በአብዛኛው በሚያስብል መልኩ
የእርሷ ሥዕሎች አይደሉም፡፡ በመሆኑም ከሥር ቅድስት አርሴማ ተብለው የሚገለጹ ሥዕሎች አንድ በአንድ የማን ሥዕል እንደሆኑ እንመልከት፡

1. ቅድስት በርበራ (Saint Barbara)


2. ቅድስት ሉሲያ (Saint Lucia)
3. ቅድስት ኪይሪያኬ (Η ΑΓΙΑ KYPIAKH Saint Kyriake)
4. ቅድስት ካትሪን ዘአሌክሳንድርያ (Η ΑΓΙΑ AIKATEPINH Saint Catherine)
1. ቅድስት በርበራ

ቅዴስት በርብራ በማክሲምያኖስ ዘመን (305-311) የተነሣች ታላቅ ሰማእት ስትሆን አባቷ ዱዮስቆሮስ የተባለ ሀብታም እና ዝነኛ ጣዖት
አምሊኪ ሰው ነበር፡፡ ይህ ዲዮስቆሮስ ባለቤቱ ካረፈች በኋላ ሕይወቱን ለልጁ ለቅድስት በርብራ ማሰብ ጀመረ፡፡ የቅድስት በርብራን ደምግባቷንና
ውበቷን ተመልክቶ ከሰዎች ዓይን እንድትጠበቅና ከውጪው ዓለም እዳትግናኝ እርሷን ለመከላከል ሲል ዲዮስቆሮስ በትልቅ ቤተ መንግሥት
አስቆልፎባት ነበር፡፡ ወደ ክፍሏም መግባት የሚችለት የጣዖት አምላኪ መምህራኖቹ ብቻ ነበሩ፡፡

ቅድሰት በርብራም አባቷ ባሰራላት ቤተ መንግሥት ማማ ላይ ሳለች ቀን ቀን ላይ ሜዲው ሊይ የሚታየው ውብ መልክአ ምድር፣ የአበቦችን
ውበት የፀሐይን ብርሃን የወንዞችን አወራራድ፤ ማታ ማታ ላይ ደግሞ በሰማይ የሚታየው የከዋክብት ሥርዓት ውብ የሆነውን የእግዚአብሔር
ሥራ ስትመሇከት አባቷና ጣዖት አምላኪ መምህራኑ የሚመኩባቸው ጣዖቶች ይህንን ድንቅ ሥራ አንዲልፈጠሩ ተገነዘበች፡፡ በዚህን ወቀትም
ራሷን በድንግልና ጠብቃ ለመኖር ወሰነች፡፡

አባቷም በሀገሩ የውበቷን ነገር ሰምተው የጋብቻ ጥያቄ ለልጁ የሚያቀርቡትን ይዞ በልመና ቢጠይቅም ሰማእቷ ግን የአንዳቸውንም ሀሳብ
ሳትቀበል ቀረች፡፡ በዚህም ወቅት አባቷ ለብቻዋ በመኖሯ ነው ይህ ሊከሰት የቻለው ብሎ ከቤተ መንግሥቱ እንድትወጣ እና ከፈለገችው ሰው ጋር
እንድትገኛኝ እና ጓደኝነት እንድትመሠርት ፈቀደ፡፡ በዚህም ወቅት ወጣት ክርስቲያን የሆኑ አገልጋዮችን በከተማ ውስጥ አግኝታ ስለዓለም ፈጣሪ፣
ስለ ምስጢረ ሥሊሴ እና ክርስትና በአጠቃላይ እስተማሯት፡፡ ከእስክንድርያም በነጋዴ ተመስሎ በመጣ ቄስ የእግዙአብሔር ልጅነት በጥምቀት
ገንዘብ አደረገች፡፡

ይህ በሚሆንበት ወቅትም አባቷ ጉዞ አጋጥሞት ከመሄዱ በፊት እርሷ ከምትገኝበት ስፍራ አካባቢ ውብ የሆነ የመታጠቢያ ክፍል እንዲሠራላት
አዝዞ ወድ ጉዞው ይሄዳል፡፡ የክፍሉ ደቡብ ገጽ ላይ አባቷ ሁለት መስኮቶችን እንዲሠራ አዝዞ የሄደ ቢሆንም የእርሱን አለመኖር ተጠቅማ ቅድስት
በርብራ አንድ መስኮት ምስጢረ ሥሊሴን እንዲወክል በማሰብ አሰጨምራ አሰራች፡፡ በመጣጠቢያው ክፍሉ የእብነበረድ ግድግዳ ላይም በጣቶቿ
የመስቀልን ቅርጽ ፍቃ ሳለችበት፡፡ የመስቀል አፋፋቅና ጥልቀቱ በብረት የተሠራ የሚመስል የነበር ሲሆን ታሪኳም በስንክሳር በተጻፈበት ወቅትም
ይህ የእብነ በረድ መታጠቢያ ክፍልና የመስቀለ ቅርጽ ይታይ ነበር፡፡

አባቷም ከጉዝው ሲመለስ በመታጠቢያው ክፍል የሆነውን በተመለከት ጊዜ ምክንያቱን ከሰማዕቷ ሲጠይቃት ስለ ምስጢረ ሥሊሴ እና ነገረ
እግዙአብሔር ነገረችው፡፡ በዚህም ወቅት ክርስትናን እንድትክድና ጣዖት እንድታመልክ በጠየቃት ወቅት ፈቃደኛ አለመሆኗን ተከትሎ በንዴት
በሰይፍ ሊመታት ሲል ቅድስቷ ከአባቷ በፍጥነት አመለጠች፡፡ አንድ ኮረብታ በደረሰች ጊዜ ኮረብቷዋ በተአምራት መልኩ ተከፍታ ዋጠቻት
በተቃራኒው የኮረብታው በኩልም ከአባቷ ራሷን ደበቀች፡፡ በዚህን ወቅትም በአካባቢው ሁለት እረኞች ይህንን የተመለከቱ ነበር፡፡

አባቷም ከብዙ ልፋት በኋላ በኮረብታው አከባቢ እነዚያን እረኞች አገኛቸው፡፡ አንደኛው እረኛ አባቷ ስለ ቅድስት በርብራ በጠየቀው ጊዜ
አሳፈረው ምንም አልነገረውም፤ ሆኖም ግን ሊላኛው እረኛ ሰማዕቷን በመካዴ ያለችበትን ቦታ ለዱዮስቆሮስ ነገረው፡፡ እርሱም ወደ ድንጋይነት
የሚጠብቃቸው ከብቶችም ወደ አንበጣነት ተቀየሩ፡፡

ዱዮስቆሮስም ቅድስት በርበራ ያለችበትን ቦታ ሄዶ ከያዛት በኋላ ብዙ መከራን በመደብደብ አደረሰባት፡፡ ዳግመኛም በጠባቂዎች በረሃብ
እንዱቀጧት አስረከባት፡፡ ከዚህን በኋላ በአካባቢው አስተዳዳሪ ማርጢያነስ አሳልፎ ሰጣት፡፡ አብዝተው ቅድስት በርብራን መቷት፤ ባልለፋም ቆዳ
እየገረፉና ሕመሙ የበለጠ እንዲሰማት በልብስ ቁስሎን እየፈተጉ መከራውን አጸኑባት፡፡ በምሽት ግን ቅድስት በርብራ ይህ ሁለ መከራ
ቢደርስባትም አብዝታ ወደ ክርስቶስ ትጸልይ ነበር፡፡ ጌታም ወደ እርሷ በአካል ተገልጦ በመምጣት ከቁስሎ ይፈውሳት ነበር፡፡ በሚቀጥለው ቀንም
ደግሞ አዲስ በሆነ መንገድ መከራ ማጽናታቸው ይቀጥል ነበር፡፡
ኡልያና የምትባል በከተማው የምትኖር አንድ ደግ ክርስቲያን ሴት ነበረች፤ እርሷም በቅድስት
በርብራ ላይ የሚፈጸመውን ግፍና እንግልት ተመልክታ ስህተትነቱን በአደባባይ ተናገረች፡፡
ክርስቲያን መሆኗንም ለሁለም ገለጸች፡፡ እነርሱም ቅድስት ኡልያናን ይዘው ከቅዴስት በርብራ ጋር
አብረው ለብዙ ጊዚያት መከራ አጸኑባቸው፡፡ ብዙ መከራ ካደረጉባቸው በኋላ በአደባባይ ለሳቅና
ፌዝ እንዲሆን ዕርቃናቸው አወጧቸው፡፡ ሆኖም ግን በቅድስት በርብራ ጸሎት ልዑል
እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ውብ በሆነ ልብስ ቅዱስ አካላቸውን ሸፈነላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ
ለሁቱ ቅዱሳን የሰማእትነት አክሊሉን ተቀዳጁ፡፡ ቅድስት በርብራም በአባቷ እጅ አንገቷ ተሰይፎ
የሰማእትነት አክሊል ተቀበለች፡፡

(የታህሳስ 8 ስንክሳርን እንዱሁም መምህር እንግዲ መርጊያ። የኒቆሞዱያዋ ኮከብ ሰማዕት ቅዴስት
በርብራ መጽሐፍን በተጨማሪ ማብራሪያ ያንብቡ)። የክርስቶስ ሙሽራና ሰማዕታት የሆናችሁ
ቅዴስት በርብራ እና ቅዴስት ኡሌያና ሇእኛ ጸሌዩሌን፡፡ ለአባቷ እና ለማርጢያነስ ግን
ፍጻሚያቸው አላማረም ምክንያቱም ሁለቱም በመብረቅ ተመትተው ሞተዋልና፡፡ የቅድስት
በርብራና ቅዴስት ኡልያና በረከትና ምልጃቸው ይድረሰን፡፡

በቅብጥ ቤተክርስቲያን አሣሣል የተሣለ የቅድስት በርብራ እና ቅድስት ኡልያና ሥዕል

2. ቅድስት ሉሲያ

ቅድስት ሉሲያ (283-304) በሲራከስ የተወለችና በዲዮቅልጢያኖስ ዘመነ ሰማዕታት ወቅት የሰማዕትነት አክሊልን በ 304 ዓ.ም. አካባቢ
የተቀበለች ቅድስት እናት ነበረች፡፡ ሉሲያ የሚለው ቃል ከላቲኑ ሉሲያስ ወይም ለክስ ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ይህ ደግሞ በትውፊት ቅድስት ሉሲያ ሰማዕትነት ከመቀበሏ በፊት ዓይኖቿን እንደወጡ ካለው ትውፊት ጋር ይገናዘባል፡፡ ይህንንም ተከትሎ
ስትሣሎ በሰሀን ላይ ዓይኖችን ይዛ ትሣላለች፤ ምሳሊነቱም የዓይነ ብርሃን እና የዓይነ ሥውራን ረዲት እና ጠባቂነቷን ያመለክታል፡፡
ቅድስት ሉሲያ ከሀብታምና ከመኳንት ወገን ከሆኑ ወላጆች በ 283 ገደማ ተወለደች፡፡ አባቷ
በልጅነቷ የሞተ ስለነበር እናቷ አውጣኪያ ለብቻዋ አሰደገቻት፡፡ እናቷ በተቅማጥ በሽታ
ለ 4 ዓመታት ስትሰቃይ የነበረ ሲሆን በወቅቱ ቅድስት አጋታ ዘፓሌርሞ የተባለችን ጻደቅ
ታሪክ በመስማቷ እና በወንጌል የጌታን ልብስ ነክታ የዳነችውን ሴት ታሪክ በማመን ለእናቷ
ወደ ጸድቋ መቃብር ሄዯው እንዱጸሌዩ አደረገች፡፡

ሌሉቱንም ሲጸልዩ ከቆዩ በኋላ እንቅልፍ አሸለባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በራዕይ ቅድስት
አጋታ ተገልጣላት “ እኔ ለካታኒያ እንዯሆንሁ አንቺም በቅርቡ ለሲራከስ ክብር ትሆኛለሽ”
አለቻት፡፡ በዚያን ወቅትም እናቷ ከሕመሟ ዳነች፤ ቅድስት ሉሲያም ከዙያን ወቅት ጀምሮ
በድብቅ ራሷንና ድንግልናዋን ለእግዚአብሔር ሰጠች፡፡ ሀብቷንም ለድሆች ታከፋፍል
ጀመረች፡፡

በወቅቱ የነበረውን ጣዖት አምሊኪ የጋብቻ ጥያቄ ባለመቀበሏ ለአካባቢው ገዢ


ክርስቲያንነቷን ገለጠባት እርሷም በሃይማኖቷ ምክንያት ተያዘች፡፡ በመጀመሪያ ጣዖት
አምሊኪዎቹ እርሷን ለማዋረድ ወድ ሴተኛ አዲሪዎች ቦታ ሊዋሰዶት ቢጥሩ በኃይል
እግዚአብሔር ከቆመችበት ስፍራ ማንቀሳቀስ ተሳናቸው፤ በዚህም ድንግልናዋ ተጠበቀ፡፡
ዳግመኛም ወደ ነበረችበት ስፍራ ትላልቅ እንጨቶች ከምረው በእሳት ሉያቃጥሏት
ቢሞክሩም እግዙአብሔር ግን አዳናት፡፡ በመጨረሻም ሰማዕቷ ነፍሷን ለእግዙአብሔር
አሳልፋ ሰጥታ በሰይፍ ሰማዕትነትን ተቀበለች፡፡ ቅድስት ሉሲያ ሰማዕትነት ከመቀበሎ በፊት
ዓይኖቿን ወጥተው የነበሩ ሲሆን ቅዱስ አካሏን በክብር ለመቅበር ሲዘጋጁ ቅደሳን ዓይኖቿ
በተአምራታዊ መልኩ ተመልሰው ተገኝተዋል፡፡ መታሰቢያዋም በታህሳስ 4 ቀን ነው፡፡
የቅድስት ሉሲያ በረከትናምልጃዋ ይድረሰን፡፡
3. ቅድስት ኪርያኬ

ቅዴስት ኪርያኬ ከግሪካውያን ድሮተስ እና አውሳብያ ከተባሉት ደግና ባለጠጎች ክርስቲያኖች በስለት የተገኘች ቅድስት እና ሰማዕት ነበረች፡፡ እናት
እና አባቷ ልጅ ስላልነበራቸው ያለማቋረጥ በጸሎት እግዙአብሔርን ቢለምኑት ቅደስቷን እግዙአብሔር ልጅ ትሆናቸው ዘንድ ሰጣቸው፡፡

ቅድስት ኪርያኬም መንፈሳዊ ሕይወትን ገንዘብ በማድረግ ከልጅነቷ ጀምሮ ራሷን ለእግዚአብሔር ቀደሰች፡፡ ባደገችም ወቅት በሥጋ እና በነፍስ
ውብ በመሆኗ ብዙ ሰዎች እርሷን ሊያጩ ይመጡ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ሰማዕቷ በፈቃዷ የክርስቶስ ሙሽራ ለመሆንና በድንግልና ለመኖር
ስለወሰነች የጋብቻ ጥያቄያቸውን ባለመቀበል ትመልሳቸው ነበር፡፡

ወላጆቿ ባለጠጎች መሆናቸውን ተከትሎ በኒቆሞድያ የነበረ አንድ ዳኛም ለልጁ ሊድራት ከፈለጉት ሰዎች አንዱ ነበር ነገር ግን ጥያቄውን
አለመቀበሏን ተመልክቶ ለዲዮቅልጢያኖስ ወላጆቿ ክርስቲያን መሆናቸውን ገለጠ፡፡ ዲዮቅሌጢያኖስም ወላጆቿን እንዲሰቃዩ አስደረገ፡፡ በዚያም
ሜሊተን ወደ ምትባል ስፍራ እንዱጋዙ አስደረገ በዚያም ስፍራ ስለ ክርስቶስ ብዙ መከራን ተቀብለው አረፉ፡፡

ዱዮቅልጢያኖስ ቅድስት ኪርያኬንም ወድ ማክስምያኖስ ላካት፡፡ ማክስምያኖስም ክርስቶስን ክዲ ጣዖቶችን ብታመለክ ከዱዮቅሌጥያኖስ
ሀብታምና የቅርብ ዘመድች ጋር እንደሚያጋባት ነገራት፡፡ ነገር ግን ሃይማኖቷን እንደማትቀይር እንዲሁም የዚህን ዓለም አብረቅራቂ ገንዘብ
እንደማትመኝ ስትገልጽለት በንዴት እንድተገረፍ ማክስምያኖስ አዘዘ፡፡ ወታደሮቹም በቻሉበት መንገድ እርሷን መከራ አጸኑባት ሆኖም ግን
ሃይማኖቷን አልካደችም ነበር፡፡ እንዱያውም ወታዯሮቹ ከድካም የተነሳ ሦስት ጊዜ እንዲቀያየሩ ሆነ፡፡ በአንዴ ምሽትም እግዚአብሔር ተገልጦ
“ኪርያኬ መከራና ስቃዩን አትፍሪ፣ መንፈሴ ካንቺ ጋር ነው፡፡” አላት፡፡ ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ቅድስት ኪርያኬን ሀሳቧን ለማስቀየር
ባለመቻሉ ማክስምያኖስ አፍሮ ለሑራሌዮን በኬሌቄድን በምተገኘው የቢታንያ ገዢ ሃሳቧን እንዱያስቀይር ላካት፡፡

እርሱም ቀድሞ እንደነበሩት በማባበል እንዲሁም በማስፈራራት ክርስቶስን


እንድትክድ ቢጠይቃት ሰማዕቷ ግን በእምነቷ ጸናች፡፡ እንዱያውም የተቻለውን
ያህል መከራ እንዱያጸናባት ተገዳደረችው፡፡ እርሱም ለብዘ ሰዓታት በፀጉሯ
ተንጠልጥላ ከሥር ወታደሮች አካሏን እንዱያቃጥሉ አደረገ፡፡ ነገር ግን በዚህ
መከራ ውስጥ ሆና ይበልጥ ጥንካሬና ብርታትን ማግኘት ቻለች፡፡ በዚያም ምሽት
በወህኒ ሳለች ክርስቶስ ከቁስሏ ሁሉ ፈወሳት፤ ብዙ ጣዖት አምላኪዎች ይህንን
ተመልክተው በእግዚአብሔር አመኑ፡፡

በነጋታውም ሒላርዮን መፈወሷን ተመልክቶ ጣዖቶቹ ለእርሷ አዝነው እንዳዳኗት


ገለጸላት፡፡ ሒላርዮንም ወደ ቤተ ጣዖቶቹ እንዱሔደና ምስጋና እንዱያቀርቡ
አጥብቆ ለመናት፡፡ በክርስቶስ እንደተፈወሰች ነግራው ግን አብራው ወደ ቤተ
ጣዖቱ እንደምትሔድ ነገረችው፡፡ ሒላርዮንም ያሸነፈ መስሎት ተደሰተ፡፡ በቤተ
ጣዖቱ ሳለም ቅድስት ኪያርኬ ሕይወት የሌላቸውን እነዚያን ጣዖቶች
እግዚአብሔር እንዲያጠፋቸው ለመነች፡፡ በዚህም ጊዜ ታላቅ የምድር መናወጥ
ሆነ፤ ጣዖቶቹም ወደ ምድር ወደቀው ተሰባበሩ፡፡ ሁለም ጥለው ሸሹ፤ ሒላርዮንም
በተደረገው ተአምር ክርስቶስን እንደማመን ጣዖቶቹን ስለወዳደሙ ተሳደበ፡፡
እርሱም ወዲያውኑ በመብረቅ ተመትቶ ሞተ፡፡

ከሒላርዮን በመቀጠል የተተካው አፖሊዮን ሰማዕቷ ላይ ብዙ መከራን አጸናባት፡፡


ወደ እሳት እንድትጨመር ቢያደርግ እሳቱ ይጠፋል፣ ወደ ምድር አውሬዎች
ብትጣል ለማዳ ይሆናሉ፡፡ በዚህን ወቅት ሰማዕቷን በሰይፍ እንድትሰዋ አፖሊዮን
አዘዘ፤ ሰማዕቷ ቅድስት ኪያርኬ አንድ ጊዜ ከመሰየፏ በፊት ጸሎት እንድታደርግ
ጠየቀች፡፡ በጸሎትም ነፍሷን እንዲቀበሉና ሰማዕትነቷን የዘከሩትን እንዲያስባቸው
ጠየቀች፡፡ ወታደሮቹም በሰይፍ አንገቷን ከመቁረጣቸው በፊት ቅዱሳን መላእክት
ነፍሷን ከሥጋዋ ለዩት፤ ቅደስቷም በሰማዕትነት አረፈች፡፡ መታሰቢያዋ ሰኔ 30
የቅድስት ኪያርኬ በረከትና ምልጃዋ ይድረሰን፡፡
4. ቅድስት ካትሪን ዘአሌክሳንድሪያ

የቅድስት አርሴማ ተብለው ከሚታዩት ሥዕልች ከቅድስት በርብራ፣ ቅድስት ሉሲያ እና ቅድስት ኪርያኬ በተጨማሪ በስፋት ባይሆንም አንዳንድ
ጊዜ የሚታየው የቅድስት ካትሪን ዘአሌክሳንድሪያ ሥዕል ሲሆን፤ የእርሷ ታሪክ በአጭሩ ይህንን ይመስላል፡፡ ቅድስት ካትሪን በአሌክሳንድርያ
ኮንስታስ ከተባለ ሰው የተወለደች ንጹሕ፣ የተማረችና ውብ እመቤት ነበረች፡፡ በጽኑ የማያወላውል እምነቷ ፈጽማ የማክሲሚነስ ስሜታዊ እና
ያልተገታ ነፍስ ደላ አደረገች፡፡ በአንደበተ ርቱእነቷ ደግሞ ከእርሷ ጋር ሊከራከሩ የመጡትን የዘመኑ ፈላስፋዎችን አፍ አዘጋች፡፡ በ 305 ዓ.ም.
የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች፡፡

ቅደስ አካሏ ወደ ሲና በርሃ በመላእክት የተወሰደ ሲሆን ከብዘ ዘመናት በኋላም ሲገኝ ቀደሞ በጌታ ደብረ ታቦረ ቤተክርስቲያንና የሲና ሐመልማል
አሁን በሰማዕቷ በተሰየመው ቤተክርስቲያን ተወሰደ፡፡ መታሰቢያዋ ሕዳር 16 የቅድስት ካትሪን በረከትና ምልጃዋ ይድረሰን፡፡
የኢትዮጵያውያን ሠዓሊያን ቅድስት አርሴማን ሥለዋት ያውቃሉ?

በተለያዩ ጊዜያት ከላይ የተገለጸውን እውነታ ለሰዎች ለማስረዳት ስሞከር የገጠመኝ ፈተና
«እነኚህ ሥዕላት የቅድስት አርሴማ ካልሆነ ኢትዮጵያውያን ቅድስት አርሴማን ከዚህ በፊት ሥለዋት ያውቃሉ?» የሚ
ለው ጥያቄ ነበር። ለዚህ ጥያቄ መለስ የሚሆነኝን መረጃ ያገኘሁት ደግሞ ከመቐለ ከተማ ወጣ ብላ
በምትገኘው ኮኽሎ የሐንስ ተብላ በምትጠራው ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው ጥንታዊ የብራና «ገድለ ሰማዕታት»
የተሰኘ መጽሐፍ ላይ ነበር። ይህ አስደናቂ መጽሐፍ ሲሆን በውስጡ የመላእክትን ሥዕላት እንዲሁም የብዙ
ሰማዕታት ሥዕላትን እንዲሁም በተለያዩ መንገድ የተሠሩ ሐረጋት የያዘ ገድል ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ
በጥንታዊው የአሣሣል ዘይቤ ቅድስት አርሴማ ተሥላ ትገኛለች። የዚህ መጽሐፍን ዕድሜ በእርግጠኛነት መረጃው
የሌለኝ ቢሆንም ከአሣሣል ዘይቤው በመነሣት ግን በ 15 ኛው መ.ክ.ዘ. የነበረውን የአሣሣል ዘይቤ የያዘ ይመስላል።

ከዚህ በተጨማሪ በመጀመሪያው የጎንደር አሣሣል ዘይቤ የተሳለ የገበታ ሥዕል ላይ የቅድስት አርሴማ ሥዕል በስስ
ቅጂ ለማግኘት ችያለሁ፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ሥዕል የሚገኝበት ቦታና መቼ እንደተሠራ መረጃው እስከአሁን የለኝም፤
ይሁን እንጂ ከአሣሣል ዘይቤው በመነሳት ሥዕሉ በ 17 ኛው መ.ክ.ዘ. እንደተሠራ መገመት ይቻላል፡፡

በዘመናችንም ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትንና ገደሏን መሠረት በማድረግ የተሠራ ሥዕል በአ.አ. ቦሌ ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ
እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን በሴቶች መግቢያ በር ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ በማኀበረ ቅዱሳን ንዋየ ቅዱሳት
መሸጫ መደብርም (አምስትኪሎ ቅርንጫፍ ሕንጻው ላይ) ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ምንጭ፦ https://ethioicons.wordpress.com/

You might also like