You are on page 1of 4

5/3/22, 7:01 PM ቅድስት አርሴማ ድንግል ማን ናት?

- አትሮንስ ዘተዋሕዶ


May 3, 2022           Home About Contact

(አትሮንስ ዘተዋሕዶ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ/ር ቀሲስ ንጋ
እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው)

ስብኩ ወንጌለ ለኩሉ ፍጥረት ማቴ 16፤15

በተጨማሪም አትሮንስ ዘተዋሕዶ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችና የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችንና ዜናዎችን ያቀርባል።

 ቀዳሚ ገጽ ኪነጥበብ  የጽሑፎች ቋት ትምህርተ ሃይማኖት  አጽዋማት  ዜና ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ተዋሕዶ ፊልሞች 

 በቅርብ የተጻፉ ልዩ ልዩ ግማደ መስቀሉን ወደ ኢትዮጵያ ማን አመጣው ? እንዴት ? ልዩ ልዩ “መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ” ልዩ ልዩ መስቀል አትሮንስ መልእክት

Home 
ነገረ ቅዱሳን
 ቅድስት አርሴማ ድንግል ማን ናት? አትሮንስ ዘተዋሕዶን የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድ
SUBSCRIBE OUR YOU TUBE CHANNEL
ቅድስት አርሴማ ድንግል ማን ናት?

አትሮንስ ዘተዋሕዶ

3 years ago

ነገረ ቅዱሳን,

እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን ከሆኑ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት
ተወለደች፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ሐዲስን ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትርም በጸሎት ትተጋ እንደነበር ገድሏ ይተርካል፡፡ በዚህ
ዘመን ድርጣድስ የሚባል በአርመን የነገሠ አረማዊ ንጉሥ ለጣዖት የሚሰግድ' ፀሐይንም የሚያመልክ' ክርስቲያኖችንም እኔ ለማመልከው አምላክ መስገድ
አለባችሁ በማለት መከራ ያጸናባቸው ነበር፡፡

እናታችን ቅድስት አርሴማም ተጋድሎዋን የጀመረችው የዚህ ጨካኝ ንጉሥ አገልጋይ ወይም ሹም ፳፯ ክርስቲያኖችን እንደልማዱ እየደበደበ' እየገረፈና ልዩ ልዩ
ስቃይ እያደረሰባቸው ሲወስዳቸው በማየቷ ነበር፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘‘ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን ስለኔ ወደገዢዎችና ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ፡፡’’ (ማቴ. ፲፡፲፮፡፲፱)፡፡
ያለውን በማሰብ ቅድስት አርሴማም ገና በሃያ ዓመቷ የዚህን ዓለም ንጉሥ እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ወገኖቿ ጋር ግንባር ቀደም በመሆን
ትመሰክር ጀመር፡፡ የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ልትሠዋ በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ
ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና FACEBOOK
ፍላጎቱ ተመኛት፡፡ ለእርሱም ሙሽራ እንድትሆን ብዙ ወተወታት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን ናቀችው ‘‘እኔ የሰማያዊው ንጉሥ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን
ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም፡፡’’ በማለትም መለሰችለት፡፡

ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ፤ በመናቁም ተበሳጨ፤ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሰሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ፡፡
አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር፡፡ በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው፡፡ ንጉሡ ይበልጥ ነደደው
ክርስቲያኖቹ በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሰሩ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ
ከሰማይ አወረደላቸው፡፡ ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን የጠበቀ አምላክ እነርሱንም አዳናቸው፡፡
በሌላም በብዙ መንገድ ሊያጠፋቸው እንደሞከረ ገድሏ ይተርካል፡፡ በመጨረሻም ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ በሰይፍ እንዲያልቁ ይወስናሉ፡፡

እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው ቅድስት አርሴማ ለሚሰየፉት ሁሉ የድል አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት
 

https://www.atronsmedia.com/2019/06/blog-post_7.html 1/4
5/3/22, 7:01 PM ቅድስት አርሴማ ድንግል ማን ናት? - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

ትጠብቀው ነበር፡፡ በመደሰቷም እየጸለየች አይዟችሁ ጽኑ ትላቸው ነበር፡፡

በመጨረሻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽናቷን ተመልክቶ ቃል ኪዳን ይገባላታል፡፡ ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ
እየጮኸ አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም ስቃይሽን አጸናብሻለሁ ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት አይኗን አስወጥቶ በእጇ ያሲዛታል፤ ጡቷን
ያስቆርጣል፤ በኋላም አንገቷን ያሰይፋታል በዚሁ ሁኔታ እናታችን ሰማዕትነትን ተቀበለች፡፡

ይህንን ሁሉ መከራ ስለአምላኳ ስትል እራሷን አሳልፋ የሰጠች ድንቅ ሰማዕት ናት፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ‘‘ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ’’
(መዝ.) እንዳለ ለእናታችንም የገባላት ቃል ኪዳን ‘‘በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል፤
የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ፤ በዓልሽን ያከበረ፤ ዝክርሽን የዘከረ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ፤ የሰማና ያሰማም እስከ ፲፪ ትውልድ ድረስ
እምርልሻለሁ’’ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ እገዳሟም ሄዶ በጸሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ
እንደሚመለስ እሙን ነው፡፡ የቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከት ጸሎትና ምልጃ ከእኛ ጋር ይኑር፡፡

 አሜን አሜን አሜን

ስንክሳር  " ታኅሣሥ 6 "

<<< እንኩዋን "ለድንግልና ሰማዕት ቅድስት አርሴማ" : "አባ አብርሃም" እና "ቅዱስ ስምዖን ጫማ ሰፊው" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ >>>

RECENT P O PU L A R COMM
+*" ቅድስት አርሴማ ድንግል "*+

=>እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው “መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ”
"በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" (ማቴ. 5:11) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::
 አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021
*ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::

*ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::

መስቀል
*ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::  አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021
*ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::

*ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::

በመስቀል እንመካለን።
¤ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:

 አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021


+አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቁዋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን
ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:-

የመስቀል ደመራ በዓል ታሪክና አከባበር


1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት

 አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021


2.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት

3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::

ግማደ መስቀሉን ወደ ኢትዮጵያ ማን አመጣው


+ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው
 አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021
ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::

+ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በሁዋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኩዋ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ
ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::

ARCHIVE
+በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ:: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ
ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::

June (12)
+በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ
አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::

+ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: TAGS
ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::

ልዩ ልዩ መዝሙር መ ጽ ሐፍ ቅ ዱ ስ ጥ ና ት ማስታ
+አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ::
በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ቃለ መጠ

+ከነገር ሁሉ በሁዋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው::
ቅዱሳን ሊቃውንት ቅዱሳን መላእክት ቅዱሳን መካ

+የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን-ጐርጐርዮስን
በዐላት ብሂለ አበው ተ ዋ ሕ ዶ ፊ ልሞ ች
ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::

ት ም ህ ር ተ ሃይ ማ ኖ ት ነገረ ማርያም ነገረ ቅዱሳን


+ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው::

ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::


ነ ገ ረ ተ ሀድ ሶ አትሮንስ መልእክት አጽዋማት ኪ

+የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮዽያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ ክብረ በዓል ዐውደ ስብከት ዜና ቤተ ክርስቲያን
እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ : ስባ : ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተራበት ሁሉ ኃይልን
የሰርግ ሥነ ሥርዓት የጉባኤ መዝሙር ጉባኤያት
ታደርጋለችና::

+ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ
እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::" (መዝ. 75:5)
 

https://www.atronsmedia.com/2019/06/blog-post_7.html 2/4
5/3/22, 7:01 PM ቅድስት አርሴማ ድንግል ማን ናት? - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

+በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት
ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::

+ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት:

Tags
# ነገረ ቅዱሳን

Share This 

https://www.atronsmedia.com/2019/06/blog-post_7.html

About አትሮንስ ዘተዋሕዶ

Templatesyard is a blogger resources site is a provider of high quality blogger template with
premium looking layout and robust design. The main mission of templatesyard is to provide the
best quality blogger templates which are professionally designed and perfectlly seo optimized
to deliver best result for your blog.

     

 Newer Article Older Article 


ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቃለ መጠይቅ (በሊቁ እንደስራቸው አግማሴ እስር ጉዳይ ከአባ ሙሉ ሽታነህ
ጋር )

RELATED POST  View More

ነገረ ቅዱሳን  ነገረ ቅዱሳን  ነገረ ቅዱሳን 

መስከረም ፲፬ በዚች ዕለት ታላቁ ቅዱስ አባ አጋቶን መስከረም ፲፫ በዚች ዕለት አባ ባስልዮስ ቅዳሴ የመስከረም ፲ የቅዱሳን በዓላት ጼዴንያ ማርያም
እና ሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ ቀን ባስሊዮስን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ጽፏ
 አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021
 አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021  አትሮንስ ዘተዋሕዶ  Oct 02, 2021

BLOGGER DISQUS FACEBOOK

NO COMMENTS:

POST A COMMENT

 

https://www.atronsmedia.com/2019/06/blog-post_7.html 3/4
5/3/22, 7:01 PM ቅድስት አርሴማ ድንግል ማን ናት? - አትሮንስ ዘተዋሕዶ

Pages        

HOME

ABOUT ME

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብን የጠበቁ ጽሑፎችና ምስሎች በመ


ቀሲስ ንጋቱ አበበ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው

CRAFTED WITH  BY TEMPLATESYARD | DISTRIBUTED BY GOOYAABI TEMPLATES

 

https://www.atronsmedia.com/2019/06/blog-post_7.html 4/4

You might also like