You are on page 1of 2

" ወድሰኒ " በይኝ

አባቶችሽና ልጆችሽ አሟጠው ምስጋናሽን በሉ


የልጅ ልጆችሽስ የክብርሽን ነገር የፍቅርሽን ነገር በምን ይመስሉ ?
ገና ሳትወለጅ በትንቢት ምስጋና
አባቶችሽ ክብርን ሰጥተዉሻልና
አካል ባልመጣበት በዘመነ ጥላ
ዳዊት ምስጋናሽን በትንቢት ሲበላ
ጌዲዎን ሳያውቅሽ ተስፋሽን በፀምር
አንዴ ይድረቅ ብሎ አንዴ ይርጠብልኝ ብሎ ሲያመሰጥር
ዘለዓለማዊ ድንግል መኾንሽን
በምስራቅ መስሎ ሕዝቅኤል ደጃፍሽን
ሁሉ ላንቺ ክብር ምሳሌ እንዳሠሠ
በዘመነ ጥላ ባባቶችሽ ዘመን ምግቡ ተጋመሰ
ቀድሶ እሚቀደስ ስምሽን የሚጠብቅ
ህየንተ አበውኪ ተወልዱለኪ ደቂቅ
ባባቶችሽ ፈንታ ልጆችሽ ተተኩ
ከኦሪት-ራዕይ የዘመኑን ቁመት በምስጋናሽ ለኩ
"ተፈስሒ "አሉ በመላዕኩ ልሳን
ልጆችሽ ተቀኙ ወርሰው ኪዳንሽን
" ተፈስሒ ፍስሕት ኦ ምልዕይተ ፀጋ"
በስጋም በነፍስም መቼ ወድቆ ያውቃል አንቺን የተጠጋ
" ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ"
"ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ"
"ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ"
" ወአናአእድ ቅዳሴሐ ለማርያም"
በማሳነስ እንጂ በማብዛት አይደለም
እህተ መላእክት፤ እመ ሰማዕታት አለ በተመስጦ
አባ ሕርያቆስ ክብርሽን ከፍጥረት ሁሉ አስበልጦ
እህተ መላእክት ወእመ ኩሉ ሕዝብ ከጥፋት ማምለጫ
አለ በዉዳሴ አባታችን ጊዮርጊስ ብሔረ ጋስጫ
ዘመኑ አለፈ የልጆችሽ ልጆች ቃላት ነጠፉብን
አባቶችሽና ልጆችሽ ተቋድሰው የበሉት ምስጋናሽ ራበን !
ራበን ምስጋና ራበን ዉዳሴ
ራበን ድርሳንሽ ራበን ቅዳሴ
አባቶች ያልበሉት ልጆች ያልቀመሱት የክብር መግለጫ
የልቦናን ፍቅር ዉዳሴን መወጪያ
ድንግል ነጥፎብናል አዲስ አይነት ቅኔ አዲስ አይነት ቃና
እንዳባቶቻችን እንደልጆቻቸው
በአዲስ ኳኳታ ደጅሽን ልንጠና
ወዳሴ አትሚብን ያልተሰማ ዜማ ያልታየ ምስጋና
የስምሽን ሕብስት አባቶችሽና ልጆችሽ አሟጠው በልተዉታልና

You might also like