You are on page 1of 36

በደ/ብ/ብ/ክ/መንግስት/ ቴ/ሙ ት/ሥ/ በሮ

በሆልና ቱሪዚም በደረቅና ባልቲና ዝግጅት አጫጭር ሥልጠና


ለመስጠት የተዘጋጄ የሥለጠና ሞጁል/መንዋል፡፡

ሚያዝያ 2008

አጫጫር ሥልጠናዉ የሚካተትበት የብቃት አሀዶች ዝርዝር

1
የሙያ ዓይነት-- ሆቴል ክቺን ኦፔረሽ /ምግብ ዝገጅት

የብቃት አሀድ ስም የብቃት አሀድ ኮድ ተሰጠዉ ሰዓት ምርመራ

1 ባልቲናና ቅመማ ቅመም

1- Use Basic Methods of Cookery CST HKO1 M01 0412 20

2- Prepare Basic Ethiopian Cultural Dishes CST HKO1 M03 0412 60

3- Clean and Maintain Kitchen Premises CST HKO1 M07 0412 15

4- Follow Health, Safety and Security Procedures CST HKO1 M012 0412 15

5- Follow Workplace Hygiene Procedure CST HKO1 M013 0412 15

6- Apply 5’s Procedure CST HKO1 M020 0412 5

Total 130

ሥልጠናዉ የሚፈጀዉ ጊዜ ------------------------


130

ይዘት፤ ገጽ

1. አጫጫር ሥልጠናዉ የሚካተትበት የብቃት አሀዶች ዝርዝር ---------------------- 2


2. ምግብና የምግብ ሳይንስ ---------------------------------------------------- 4

2
1. የምግብ ደህንነት አጠባበቅ ----------------------------------------------------- 4
2. የምግብ አበሳሰል ዘዴዎችና ምግብ ማቀናበር ---------------------------------- 6
3. የቅሜማ ቅሜሞች አዘገጃጀትና አሰተሸሻጋችዉ----------------------9
4.1 በተናጠል የሚዘጋጁ----------------------------------------------- 9
1.ቁንዶ በርበሬ----------------------------------------------------------- 10
 ጥቁር .ቁንዶ በርበሬ-------------------------------------------- 10
 ነጭ ቁንዶ በርበሬ----------------------------------------------- 11

2. ኮረርማ-------------------------------------------------------------- 12

3. ገዉዝ---------------------------------------------------------------- 19

4. ከመን---------------------------------------------------------------- 19

5. አብሽ----------------------------------------------------------------- 20

6. ጥቁር አዝሙድ----------------------------------------------------------------- 21
7. ነጭ አዝሙድ-------------------------------------------------------------------- 21

4.2 በመቀላቀል/በጥምረት/ የሚዘጋጁ--------------------------------------------22

1.አብሽና ኩርንፉድ-----------------------------------------------------------------22

2.ዲብልቅ የባህር ቅመም----------------------------------------------------------22

5.በዱቀት መልከ የሚዘጋጁ የባልትና ዉጤቶች------------------------------------------ 23

3
5.1.የአጥሚት ምጢን---------------------------------------------------------------- 23

5. 2. የገብስ ዱቀት------------------------------------------------------------------ 25

5. 3. የበሶ ዱቀትና ---------------------------------------------------------------- 27

5. 4.የቡላ ዱቀት-------------------------------------------------------------------- 28

5. 5.ነጭ ሽሮ----------------------------------------------------------------------- 29

5. 6. ምጥን ሽሮ------------------------------------------------------------------ 30

5. 7.የሽምብራ ሽሮ--------------------------------------------------------------- 30

5. 8.የባቄላ ዱቀት ለስልጆ------------------------------------------------------ 30

5. 9.የገብስ ቆሎ------------------------------------------------------------------ 32

5. 10.ዳቦ ቆሎ-------------------------------------------------------------------- 33

5.11.ፈንድሻ------------------------------------------------------------------------ 34

5.12.ቃንጣ ------------------------------------------------------------------------ 34

5. 13.ቺፒስ------------------------------------------------------------------------ 35

5.14.ንጥር ቅቤ------------------------------------------------------------------- 37

5.15.ጩኮ-------------------------------------------------------------------------- 38

መግቢያ

ምገብ ዝግጅት በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ይከፈላል

ይሄዉም፤-

1. ምግብ ማቀነቀበር ቅድሜ ምግብ ዝግጅት /የባልቲና ዉጤቶች አዘገጃጀት/

4
2. ባሕላዊና ዘመናዊ የምግብ ዝግጅት ሲሁን የዝህ ማንዋል ዝግጅት የእነጀራን አዘገጃጀት በዝርዘር የያዘ
ነዉ

አጠቃላይ ዓላማ

በፓኬጅ ለታቀፉ የሥራ መስኮች ለሚሳተፉ አንቀሳቃሾች በቴክኒኪና ሙያ መስክ ያለባችዉን የክህሎት
ክፍተት መሙላት

ዝርዝር ዓላማ

 ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ የምግብ አዘገጃጀት ፤ምግብን ለረዥም ጊዜ የማቆያ ዜዴዎችንና የአስተሸሸግ
ጭዉቀት ማጠናከር
 ምግብን ከብክለት መከላከልና በምግብ መበከል ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችንና ኪሳራን መከላከል
 በመሰኩ የተሰማሩትን የሕብረተሰብ ክፍሎች በምግብ አየያዝ አዘገጃጀትና አስተሸሸግ በኩል ያለዉን
የክህሎት ክፍተት በመሙላት ጥራቱን የጠበቀ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ አቅራቢ በገበያ ላይ ብቁ
ተወዳዳሪ ማድረግ፡፡

1. ምግብና የምግብ ሳይንስ

ትርጉም

የምግብ ሳይንስ ማለት ስለ ምግብ ምንጮች፣ ስለንጥረ ምግቦችና ጥቅማቸው፣ ስለ ምግብ ደህነነት
አጠባበበቅ፣ የምግብ መበከል ከምን እንደሚመጣና መከላከያውን፣ ምግብ ሳይበላሽ ለረዥም ጊዜ የማቆያ
ዘዴዎችን፣ የአካባቢና የግል ንፅህና አጠባበቅን ስለምግቦችን አዘገጃጀት አያያዝና አስተሻሸግ የምናጠናበት
ሳይንስ ነው፡፡

5
a. ንጥረ ምግቦችና ጥቅማቸው

ንጥረ ምግቦች ማለት በምግብ ውስጥ የሚገኙና ለሰውነታቸን የተለያየ ጥቅሞች የሚሠጡ የምግብ ክፍሎች
ናቸው፡፡ እነሱም፡- ፕሮቲን፣ ካርቦሃይድሬት፣ ቫይታሚን፣ ማዕድንናት፣ ቅባትና ውሃ ናቸው፡፡

1. ፕሮቲን

ፕሮቲን እጅግ ጠቃሚ የሆነ አልሚ ምግብ ነው፡፡ ለዕድገት ጡንቻዎችን ለማዳበር፣ አጥንቶችንና ጥርሶችን
ለማጠንከር ሰውነታችን በየዕለቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን

ያስፈልገዋል፡፡ ፕሮቲን የሚገኝባቸው የምግብ አይነቶች ሥጋ፣ ዓሣ፣ ወተትና የወተት ውጤቶች ከቂቤ
በስተቀር፣ አተር፣ ሽንብራ፣ እንቁላል፣ ባቄላና ምስር እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

2. ቅባትና ካርቦሃይድሬት

ለሰው ልጅ ሰውነት ኃይልን ይሰጣል፡፡ የሚገኘውም ከድንች፣ ከስኳር፣ ከማር፣ ከቂቤ፣ ከዘይት፣ ከጤፍ፣ ከበቆሎ፣
ከማሽላ፣ ከዳጉሳ፣ ከአጃና ከመሳሰሉት ነው፡፡

3. ማዕድናት

እንደ ብረት፣ ካልሺየም፣ እና የመሳሰሉት በምግብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ብረት ለቀይ ደም ሴሎች
የሚያገለግል ከፍተኛ ንጥረ ምግብ ነው፡፡ ካልሺየም አጥንትንና ጥርስን ለማጠንከር የሚጠቅም ነው፡፡
የካልሺየም ምንጭ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች ወተትና የወተት ውጤቶች ጤፍ፣ ቦለቄ፣ ዳጉሳ፣ እንሰት፣ ሽንብራ
ወዘተ ናቸው፡፡

4. ቫይታሚን

የቫይታሚን ይዘት ያላቸው የምግብ አይነቶች

 ሰውነትን ከበሽታ የመከላከል

6
 የሰውነትን ቆዳ ጤንነት ለመጠበቅና
 የሰውነት ክፍል በትክክል ሥራውን እንዲያከናውን ለማድረግ ይረዱናል

የቫይታሚን ምንጭ የሆኑ የምግብ አይነቶች ወተት፣ ቂቤ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንቁላል እና የመሳሰሉትን
ይይዛል፡፡

የእነዚህ ንጥረ ምግቦች በሰውነታችን ውስጥ በበቂ ሁኔታ ተሟልቶ አለመገኘት ሰውነታችንን ለተለያዩ
በሽታዎች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

2. . የምግብ ደህንነት አጠባበቅ

የምግብ ደህንት አጠባበቅ ማለት ምግብ በተለያዩ መንገዶች ሳይበላሹ የማቆየት ዘዴ ነው፡፡ ምግብ ለብዙ ጊዜ
ሲቆይ ለብልሽት የሚዳረግባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 2

ሀ/ በተፈጥሮ ባሉት ንጥረነገሮች ላይ በሚመጣ ለውጥ


ለ/ በልዩ ልዩ ተባዮች፡- (አይጥ፣ ዝንብ፣ ነቀዝ፣ ወዘተ…)
ሐ/ በልዩ ልዩ ጥቃቅን ሕዋሳት፡- ባክቴሪያ እንደ ሻጋታ፣ እርሾ፣ ወዘተ ….

ምግብን ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ማቆያ ዘዴዎች

ምግብን የሚያበላሹ ልዩ ልዩ ሕዋሳቶችን ለመራባት እርጥበት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ሀ/ ስለዚህ ምግብ ውስጥ ያለውን እርጥበት ወይም ውሃ በማስወገድ፣

ለ/ ምግብን አብስሎ በውስጡ የሚገኙትን ሕዋሳት በማጥፋ ማቆየት ይቻላል፡፡

ሐ/ ምግብን አቀዝቅዞ ያሉትን ሕዋሳትን እንዳይበዙ በማድረግ

መ/ በምግብ ውስጥ ቅመማ ቅመም በመጨመር

ለምሳሌ፡- ጨው፣ ስኳር፣ ኮምጣጤ እና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች

 የአካባቢና የግል ንፅህና አጠባበቅ

7
ምግብ ከምርት አንስቶ ለሰው ልጅ ፍጆታ እስከሚውል ድረስ ልዩ እንክብካቤ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ምግብ
በሚዘጋጅበት ቦታና ለማዘጋጀት የሚውሉ ዕቃዎችን ንፅህና መጠበቅ አለበት፡፡ እንደዚሁም ከምግብ ጋራ ንክኪ
ያለው ሰው የግል ንፅህናውና ጤንነቱን ጭምር በደንብ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

ንጽህና የጎደለው አካባቢ የዝንብና የተላላፊ በሽታ መንስኤ ሲሆኑ የሚችሉ ጥቃቅን ሕዋሳት መራቢያ
ይሆናል፡፡ የግል ንጽህና በተለይም የእጅና የሌሎች የአካል ክፍሎች ንጽህና ጉድለት፣ በሚዘጋጀው ምግብ ዙሪያ
ማስነጠስና ማሳል የመሳሰሉት፣ የምግብ ማዘጋጃ ዕቃዎች አጠቃቀምና ንፅህና ጉድለት፣ ተገቢውን ዕቃ
በተገቢው አገልግሎት ላይ አለማዋል የምግብን መበከል ያስከትላል፡፡

የምግብ መበከል ተመጋቢውን መመረዝና በሽታ ላይ መጣል ብሎም ሞትን ሊያስከትል ሲችል በአቅርቦትም
በኩል ሲታይ የጥራትን ማነስና፣ ተፈላጊነትን ማጣት እና ባጠቃላይ ኪሣራን በግልና በሀገር ደረጃ ያስከትላል፡፡
አንድ ምግብን የሚያዘጋጅ ሰው የግል ንጽህናውን መጠበቅ አለበት፡፡ ይኸውም፡
3

 ፀጉርን በንጽህና መያዝና ፀጉርን መሸፈን

 እጆችን መታጠብ
 ጥፍር መቁረጥ
 ገላ መታጠብ
 ንፁህ ልብስና ሽርጥ መልበስ
 ጥርስ መፋቅ
 በምግብና በምግብ ዙሪያ አለመሳልና አለማስነጠስ
 በተላላፊ በሽታ የተያዘን ሰው እስኪድን ድረስ በምግብ ሥራ እንዳይሳተፍ ማድረግ
 የምግብ ሠራተኛ ወደ ምግብ ሥራ ከመግባቱ በፊት መታከም እንዲሁም በሥራ ላይ ያለ ሠራተኛ
በየጊዜው የሕክምና ምርመራ ማድረግ አለበት
 እርጥብና ደረቅ ምግቦችን ለይቶ ማስቀመጥ
 እርጥብ ምግቦችን በፀሀይ በምናሰጣበት ጊዜ የፀሐይ ብርሃን ማስተላለፍ በሚችል ስስ ጨርቅ መሸፈን
 የሚታሸጉ ምግቦችን በወቅቱ ማሸግ
3. የምግብ አበሳሰል ዘዴዎች

መሠረታዊ የምግብ አበሳሰል ዘዴዎች በሁለት ይከፈላሉ

8
1. በፈሳሽ የማብሰል
ሀ. መቀቀል
ለ. ማገንፈል
ሐ. ወጥ መሥራት
መ. ፖች በማደረግ ፤በምንተከተክ ዉሀ ላይ ማብሰል
ሰ. በሬይዝ በማደረግ ጣዕሙን በዋጠ ማብሰል
2. በደረቁ ማብሰል
ሀ. መጥበስ 1 ኛ፡ በትንሽ ዘይት ማብሰል 2 ኛ. በብዙ ዘይት ማብሰል
ለ. አሮስቶ
ሐ. ማይክሮ ዌቭ

3.የተዘጋጁ ምግቦች አስተሻሸግ

ምግቦችን በምናሽግበት ጊዜ እንደየ ምግቡ አይነት የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን መጠቀም የምንችል ሲሆን
በጠቅላላው ምግቦችን ለረዥም ጊዜ እንዲቆዩ በምናሽግበት ጊዜ የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች፡-

 ለደረቅ ምግብ ጠንካራ ፕላስቲኮችን መጠቀም


 ለእርጥብ ምግቦች የሚገጥም ክዳን ያላቸውን ብርጭቆ ነክ ማሸጊያዎችን መጠቀም

ምግብን በምናሽግበት ጊዜ በማሸጊያው ላይ ስያሜ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ፡- የምርቱ አይነት፣


የተመረተበት ቀን፣ ለምርቱ የተጠቀምንባቸው ግብዓቶች፣ የድርጅቱ ስም (ምርቱን የሚያመርተው)፣ ቢቻል
የምረቱ አጠቃቀምና የመሳሰሉትን በማካተት ስያሜ ከሰጠን በኋላ ለገበያ ማቅረብ ይቻላል፡፡
ምገብ ማቀናበር
ምገብ ማቀናበር ማለት ቅሜማ ቅሜሞችን ማዘጋለትና ጥረእቃዎችን በማቀናጀት
ቅድሜዝግጅት ማድረግና ምግብ ለመመገብ አስከሚመች ድረስ የማዘጋጀት ሂደት ነዉ

የቅሜማ ቅሜሞች አዘገጃጀትና አሰተሸሻጋችዉ


የቅሜማ ቅሜሞች ጥቅም ምግብን ማጣፈጥ ምግብ ሳይበላሽ ለረዥም ጊዜ ማቆየት
ለብቻና በጥምረት ተዘጋጅተዉ የታሸጉ ቅሜማ ቅሜሞች ገበያ ላይ ሲቀርቡ የገቢ መስገኛና አንዳንድ
ቅሜማ ቅሜሞች ለጤንነት አስፈላጊ ናቸዉ ለምሳሌ ነጭ ሽንኩርት ዝንጅብል አብሽ ጥቁር
አዝሙድ ወ ዘተ

9
በርበሬ በተለያየ መልክ ሊዘጋጅ ይችላል ለምሳሌ ዛላዉ በርበሬ ተቀመምሞ የተፈጨ፤
አፍርንጅ፤አዋዜ ፤ዳታና ሚጥሚጣ ለመሳሰሉት ስሆን የምግብነት ጥቅሙም ለወጥ መልክ መስጠትና
፤ማባያነት የምግብነትና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

4. የአምስቱ ማዎች አሠራር ሥርዕት መከተል


1. ማጣራት
2. ማስቀመጥ
3. ማጽዳት
4. ማላመድ
5. መዝለቅ

 ማጣራት /መለየት/፡- የሚሠራና የማይሠራ ፤የሚወገድ፤የሚጠግን፤ንጹህና የቆሸሸ መለየት


 ማስቀመጥ መሆን የሚገባዉን ቦታ መስጠት /መሰየም
 ማጽዳት ፡- መታጠብ የሚገባዉን ማጠብ መጠረግ የሚገባዉን መጥረግ መጠገን የሚገባዉን
መጠገን መወገድ የሚገባዉን ማስወገድ
 ማላመድ፡- ስሙን ጽፎ መለያ በመሥራት ማነኛዉንም ነገር ከተጠቀሙ በኃላ
ወደ ተለመደዉ ቦታ በመመለስ እነደለመድ ማድረግ
ደረጃዉን የጠበቀ አሰራር እነድሆን ማድረግ
መዝለቅ፡- ይህን ደረጃዉን የጠበቀ አሰራር ቀጣይነት ያለዉ ማድረግ

10
የቅሜማ ቅሜሞች በሁለት ዓይነት መንገድ ይዘጋጃሉ እነሱም
ሀ/በተናጠል
ለ/ በመቀላቀል

በተናጠል የሚዘጋጁ
1.ቁንዶ በርበሬ
 ጥቁር .ቁንዶ በርበሬ
 ነጭ ቁንዶ በርበሬ
2. ኮ
3. ረርማ

3. ገዉዝ

4. ከመን

5. አብሽ

6. ጥቁር አዝሙድ
7. ነጭ አዝሙድ

በመቀላቀል/በጥምረት/ የሚዘጋጁ

1.አብሽና ኩርንፉድ

2.ዲብልቅ የባህር ቅመም

ሀ/ቀረፋ

ለ/ ቁሪንፉድ

ሐ/ገዉዝ

11
መ/ ኮረሪማ

ሠ/ ጥምዝ

ረ/ ቁንዶ በርበሬ

ሰ/ ነጭ አዝሙድ

2.1 የቀየ ወጥ ቅመም

የሚደለዝ፤-

ሀ/ ጥቁር አዝሙድ
ለ/ ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅቢል

ሐ/ በሶቢላ

መ/ የጠናአዳም ፍሬ

ከደረቀ በኃላ አብሮ የሚፈጭ

ሀ/ ኮረርማ

ለ/ ቁንዶ በርበሬ ትንሽ

ሐ/ ነጭ አዝሙድ እዳስፈላጊነቱ

2.2 . የሻይ ቅመም

ሀ/ ቀረፋ

ለ/ ቁርንፉድ

ሐ/ ሔል ናቸዉ፡፡

12
የቁንዶ በርበሬ አዘገጃጀት

ሀ/ ለቅሞ ማጠብ

ለ/ በፀሐይ ማድረቅ

ሐ/የደረቀዉን መዉቀጥ

በምንወቅጥበት ጊዜ ጥቁሩን ቁንዶ በርበረ ለመለየት በተደጋጋሚ ከ 1 እስከ 3 ጊዜ በመዉቀጥና


በማንቀርቀብ ተለይቶ ለየብቻ በማድቀቅ ጥቁርና ነጭ ቁንዶ በረበሬ ይሆናል ይህም ታሽጎ
ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙም፡- ጥቁሩ ለቀይ ወጥና በርበሬ ለሚገባበቸዉ ማባያዎች

ለዘመናዊ ምግብ ዝግጅቶች ማጣፈጫነት

ነጩ ለዱቀትና በርበሬ ለማየገባበቸዉ ማባያዎች

ለዘመናዊ ምግብ ዝግጅቶች ማጣፈጫነት

2.4 የኮረሪማ አዘገጃጀት

ሀ/ ሽፋኑን መለየት

ለ/ በማሸት ፍረዉን ከገለባዉ መሌየት ገለባዉን ለበርበሬ ቀመምነት መጠቀም

ሐ/ ማመስ አድቅቆ መውቀጥ

መ/ የደቀቀዉነ የኮረርማ ፍሬ በማሸግ ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ


ይዉላል፡፡

13
ረ/ ወይም ፍረዉን ኮረርማ በማሸግ ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ
ይዉላል፡፡

ሰ/ እንዳስፈላጊነቱ በማነኛዉም ምግብ እግጅት መጠቀም

2.5. የገወዝ አዘገጃጀት

 ቅርፈቱን ከፍሬዉ መለየት


 የዉስጠኛዉነ ፍሬ አደርቆ ማመስና መዉቀጥ
 የተወቀጠዉን በወንፍት በመለየት የደቀቀዉን ማሸግና

ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙ

 ለፓስታል ፉርኖ
 ለመከለሻ ቅመም መቀየጫ

2.6. የከሙን አዘገጃጀት

 ቆሻሻዉነ መልቀም
 ማጠብና ማድረቅ

14
 ማመስ
 መዉቀጥ
 በወነፊት ማጣራት
 ማሸግና ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡
 በሌላ መልኩ ታጥቦ የደረቀዉን ከሙን ፍሬ ማሸግና

ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙ

 በአብዘኛዉ ለሩዝ
 ለመከለሻ ቅመም መቀየጫ

2.7 . ነጭ አዝሙድ አዘገጃጀት

 ቆሻሻዉነ ለቅሞ ማጠብ


 ማድረቅና ማመስ
 መዉቀጥ
 በወነፊት ማጣራት
 ማሸግና ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡
 በሌላ መልኩ ታጥቦ የደረቀዉን ነጭ አዝሙድ ፍሬ ማሸግና

ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙ

በጨዉ ለሚዘጋጅ ኩኪስና እንዳስፈላጊነቱ ለተለያዩ ምግብ ዝግጅቶቸተ መጠቀም


ይቻላል፡፡

15
2.8. የጥቁር አዝሙድ አዘገጃጀት

 ቆሻሻዉን ለቅሞ ማጠብ


 ማድረቅ /በፀሐይ ብቻ/
 መዉቀጥ
 በወነፊት ማጣራት
 ማሸግና ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡
 በሌላ መልኩ ታጥቦ የደረቀዉን ጥቁር አዝሙድ ፍሬ ማሸግና

ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙ
 ለቀይ ወጥ ማጣፈጫነት
 ለበርበሬ ቅመምነት

2.9. የጦስኝ አዘገጃጀት

 ቆሻሻዉን ለቅሞ ማጠብ


 ማድረቅ /በፀሐይ ብቻ/
 ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙ
 ለፒዛ
 ለበርበሬ ቅመምነት
 ለሻይ እንዳስፈላጊነቱ

16
2.10. የአብሽ አዘገጃጀት

አብሽ በሁለት ዓይነት መንገድ ልዘጋጅ ይችላል

ሀ/ ለምግብነት

 ቆሻሻዉን ለቅሞ ማጠብ


 አገንፍሎ ወይም አብቅሎ ቦቆልቱን ማድረቅ
 መስፈጨት በወነፊት ማጣራት
 ማሸግና ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙ
 የዉስጥ ዴዌ ላለባአዉ ሰዎች ለምግብነትና ለፈዉስ
 ለቆዳ ጥራት
 በጥምረት ለሚዘጋጁ ቅሜማ ቅሜሞች መቀየጫነት

ለ/ አብሽ በቅሜም መልክ ይዘጋጃል

 ለቄይ ወጥ ማቁለያነት
 ለበርበሬ ለቅቤና ለተለያዩ ቅሜማ ቅመሞች መቀየጫነት..ወዘተ

2.11. አብሽና ቁሪንፉድ አዘገጃጀት

 ቆሻሻዉነ ለቅሞ ማጠብ

17
 ማድረቅና ገባ እስከምል ደረስ መቁላት
 ቁሪንፉዱን ቆሻሻዉነ ለቅሞ ማጠብ ማድረቅና ማሞቅ

 አንድ ለይ መዉቀጥ
 በወንፊት ማጣራት
 ማሸግና ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡
 በሌላ መልኩ ታጥቦ የደረቀዉን ፍሬ ማሸግና

ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡

ጥቅሙ

 ለቅቤና ለማቁላያ ቅሜምነት

2.12. ድብልቅ የባህር ቅሜም/መከለሻ/

 ቀረፋ
 ቁሪንፉድ
 ገዉዝ
 ኮሪማ
 ጥምዝ
 ቁንዶ በርበረ

አዘገጃጀቱ

 እያንዳንዱ ቅመም ተለቅሞ ታጥቦ ገዉዝና ኮረርማ ቀርፊቱ ተወገዶ ደርቆ ተምሶ
ደባልቆ መዉቀጥ
 በወንፊት ማጣራት
 ማሸግና ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡
 በሌላ መልኩ ታጥቦ የደረቀዉን ፍሬ ማሸግና ለገበያ ማቅረብ

ጥቅሙ

 ለተለያዩ ማባያዎች ማጣፈጫነት

18
2፣13. የሚደለዝ የቀይ ወጥ ቅመም

 ጥቁር አዝሙድ
 በሶብላ
 ነጭ ሽንኩርትናዝንጅብል
 ትንሽየጤናዳም ፍሬ

አዘገጃጀቱ

 ታጥቦ ንጹህ የሆኑትን ቀመሞች በመደባለቅ አንድ ላይ መደለዝ


 ከደረቀ በኃላ ተንሽኮሪማ ቁንዶ በርበሬና ነጭ አዝሙድ መጨመርና መዉቀጥ
 በወንፊት ማጣራት
 ማሸግና ሥሙንና የተዘጋጀበትን ቀን ጽፎ በመለጠፍ ገበያ ላይ ይዉላል፡፡
 በሌላ መልኩ ታጥቦ የደረቀዉን ማሸግና ለገበያ ማቅረብ

2.14. የሻይ ቅመም

 ቀረፋ
 ቁርንፉድ
 ሔል

አዘገጃጀቱ

 አጥቦ ማድረቀና ስሙን ጽፎ ለገበያ ማቅረብ፡፡

2.15. የበርበሬ አዘገጃጀት

19
2.15. 1. የወጥ በርበሬ አዘገጃጀት

5 ኪሎ ታጥቦ የደረቀ በርበሬ

የመደለዣ ቅመሞች

 1 ኪሎ ነጭ ሽንኩርት
 1/2 ከኪሎ ዝንጅብል
 1 ከኪሎቀይ ሽንኩርት
 1 ስኒ ጤናዳም ፍሬ
 1 ስኒ እርጥብ የበሶብላ ፍሬ

ተደልዞ ከደረቀ በኃላ አብሮ የሚፈጭ

 1 ሲኒ ንጹህ ጦስኝ
 1 ሲኒ የበሶብላ ፍሬ
 1/2 ሰሲኒ ጥቁር አዝሙድ
 1/2 ሰሲኒ ነጭ እሙደ
 1/2 ሰሲኒ ኮረርማ
 1/2 ሰሲኒ ቁሪንፉድ
 1/2 ሰሲኒ ድንብላል
 1/2 ሰሲኒ ቀረፋ
 2 ሲኒ ጨዉ

አዘገጃጀቱ

1. በጣም ቀይ በርበሬ መምረጥና መቀንጠስ


2. ማጠብ ማድረቅና መሸክሸክ
3. ከመደለዣ ቅመም ጋር አብሮ መደለዝና ደምድሞ ከርኖ ለአንድ ቀን ማሳደር
4. በሁለተኛዉ ቀን እንድደርቅ በፀሐይ ላይ ማስጣት
5. ታጥቦ የደረቀዉን ቅመምና ጩዉ ማመስ
6. ቅመምና በርበሬዉን አደባልቆ ማስፈጨት
7. በወንፍት በማጣራት ማሸግና ስሙን ከምን እነደተዘጋጀና ቀኑን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ
ማቅረብ

20
2.15. 2. ሚጥሚጣ

ለሚጥሚጣ ዝግጅት የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

 3 ኪሎ ገራም ሚጥሚጣ
 3 ሲኒ የኮረሪማ
 ፍሬ
 ጨዉ ለጣዕም ½ ሲኒ እነስላል
 1/2 ሰሲኒ ኮሰረት
 1 ሲኒ ነጭ አዝሙድ

አዘገጃጀቱ

1. ታጥቦ የደረቀዉን ሚጥሚጣ ከቅመሞች ጋር አንድ ለይ አደባልቆ መዉቀጥ


2. በወንፊት አጣርቶ መዉቀጥ
3. ስሙን ከምን እነደተዘጋጀና ቀኑን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ ማቅረብ
ጥቅሙ
ለማባያነትና ለማጣፈጫነት …ወዘተ

21
2.15.3. አፍርንጅ /የበርበሬ ፍሬ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

 3 ኪሎ ገራም የተበጠረና የታጠበ ደረቅ የበርበረ ፍሬ


 ሲኒ ኮረርማ ፍሬ
 ጨዉ ለጣዕም
 ½ ሲኒ እንስላል
 1/2 ሰሲኒ ደረቅ ዝንጅብል
 1/2 ሰሲኒ ነጭ አዝሙድ

አዘገጃጀቱ

1. ከጨዉ በስተቀር ከሁሉም ቅመም ጋር የነበረዉን ፍሬ መዉቀጥ


2. እነደገና ከጨዉ ጋር መዉቀጥ በወንፊት ማጣራተና ማሽገ
3. ስሙን ከምን እነደተዘጋጀና ቀኑን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ ማቅረብ
ጥቅሙ
ለማባያነትና ለማጣፈጫነት …ወዘተ

2.15. 4. አዋዜ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

 3 ኪሎ ገራም ፍረዉ ወጥቶ የታጠበ ዛላ በርበሬ


 3 ሲኒ ኮረሪማ
 ½ ሰኒ ቀረፋ
 ½ ሲኒ ቁሪንፉድ

አዘገጃጀቱ

1. መዉቀጥ/ማስፈጨት/

22
2. በወንፍት ማጣራት
3. በሎሚ ዉሀ/ወይም በቭኖ/በፈረንጅ አረቄ /መለወስ
4. በሚገጥም ክዳን ባለዉ ጠርሙዝ ማሸግ
5. ስሙን ከምን እነደተዘጋጀና ቀኑን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ ማቅረብ

ጥቅሙ
ለማባያነትና ለማጣፈጫነት …ወዘተ

ማሳሰቢያ

 ይህ አዋዜ መቀዝቀዣ በለለበት አከባቢሊበላሸሰለምችል ተንሽ ትንሽ በማዘጋጀት


ለአጭር ቀናት መጠቀም

2፣15.5. የሰናፍጭ አዋዜ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

 1 ኪሎ ሰናፍጭ
 ግመሽ ኪሎ ዘይት
 1/4 ሰሲኒ ቁንዶ በርበሬ
 ዉሀ እንዳስፈላዲነቱ
 ጨዉ ለጣዕም

አዘገጃጀቱ

23
1. መልቀም ፤ማጠብ ፤ማድረቅ፤መዉቀጥ /መፍጨት
2. በወንፊት መለየት
3. ሰናፍጩን ሞቅ ባለዉሀ ጨዉና ቁንዶበርበሬ ጨምሮ ማዋሁድ
4. የሚገጥም ኪዳን ባለዉ ጣርሙስ ዉስጥ ማድረግ
5. በትንሽ ዘይት በመሸፈን ማሸግ

ስሙን ከምን እነደተዘጋጀና ቀኑን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ ማቅረብ

ጥቅሙ

መዮኔዝ ለማዘጋጀት ና ለማባያነት

2.15. 6. ዳታ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

 3 ከሎ እሽት በለርበሬ ወይንም ቃሪያ


 1 ኪሎ ነጭ ሽንኩርት ተልጦ ገንፈል ያለ
 ½ ሲሲ ዝንጅብል
 ½ ሲኒ ድንድላል
 1/4 ሲኒ ጥቁር አዝሙድ
 ½ ሲኒ ኮረሪማ

አዘገጃጀቱ

1. ቀዩን ሆነ አሮንጋዴዉን ቃሪያ መክተፍ


2. ከተዘጋጀዉ ቅመማ ቅመምና ጨዉ ጋር ማደባለቅ
3. መፍጨትና ክዳን ባለዉ ጠርሙስ ዉስጥ ዘየት በመሸፍን ማሸግ
4. ስሙን ከምን እነደተዘጋጀና ቀኑን ጽፎ በመለጠፍ ለገበያ ማቅረብ

ጥቅሙ

ለማባያነት

24
 መቀዝቀዣ በለለበት አከባቢሊበላሸሰለምችል ተንሽ ትንሽ በማዘጋጀት ለአጭር ቀናት
መጠቀም

5. በዱቀት መልከ የሚዘጋጁ የባልትና ዉጤቶች

5.1. አጥሚት ምጢን

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

 10 ኪሎ ገብሰ
 1 ሲኒ አብሽ
 ግማሽሲኒ ደረቅ ነጭ ሽንኩርት
 ግማሽሲኒ ደረቅ ዝንጅብል
 ቸዉ ለጣዕም
 2 ፍረ ኮረሪማ
 5 ከሎ አጃ
 ግመሽ ኪሎ የተከካ አተር
 ግመሽ ኪሎ የተከካ ሽንብራ
 ግመሽ ኪሎ ስንዴ
 ግመሽ ኪሎ ጤፍ
 ሩብ ኪሎ የተከካ ምስር
 1 ኪሎ ነጭ ማሽላ
 ግመሽ ኪሎ የተከካ ቦቆሎ
 ግመሽኪሎ ሩዝ

አዘገጃጀት

ሀ/ ጥራይሬዎቹን መልቀም

ለ/ ገብሱን ለአንድ ቀን መዘፍዘፍ ዉሀዉን አጥልሎ ፀሐይ ላይ ማድረቅ

ሐ/ገብሱን ማመስ

መ/በወፍጮ ቤት ማስከካትና ማበጠር

ሠ/ ስንዴ አብሽ እና ሌሎች ጥራጥሬዎችን ማመስ

ረ/ ሁሉንም በመቀላቀል ማስፈጨት

25
ሰ/ በወንፍት ማጣራት

ሸ/ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ


5.2. የገንፎ ምጥን
የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 10 ኪሎ ገብስ
 5 ኪሎ አጃ
 2 ከሎ ስንዴ
 1 ኪሎ ማሽላ
 1 ኪሎ በቆሎ
 1 ኪሎ ነጭ ሩዝ

አዘገጃጀቱ

1. ታጥቦ ደርቆ ሁሉም ይታመሳል


2. ተፈጭቶ በወንፍት በማጣራት ይሸጋል
3. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
5. 3. የገብስ ዱቀት

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 10 ኪሎ ገብስ
 1 ሰኒ አብሽ
 ½ ሲኒ ደረቅ ነጭ ሽንኩረት
 ½ ግማሽ ሺኒ ደረቅ ዝንጅብል

አዘገጃጀቱ

1. ማበጠርና መልቀም
2. ገብሱን በወሀ ዘፍዝፎ ማሳደር
3. በማገስቱ ዉሀዉን አጠንፍፎ ማድረቅ
4. ማመስ ማስከካት ወይም ሸክሽኮ ማበጠርና ማስፈጨት
5. በወንፍት አጣርቶ ማሸግ
6. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
ጥቅሙ

 ለእንጀራ ለብቻዉም ሆነ በቅይጥ መልክ ያገለግላል


 ለዳቦ

26
5.4. የበሶ ዱቀት

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 10 ኪሎ ገብስ
 ጨዉ ለጠዕም
 3 ፈሬ ኮረሪማ
 2 ማንኪያ ነጭ አዝሙድ
 1 ማኒኪያ ድንብላል

አዘገጃጀቱ

1. ማበጠርና መልቀም
2. ገብሱን በወሀ ዘፍዝፎ ማሳደር
3. በማገስቱ ዉሀዉን አጠንፍፎ ማድረቅ
4. መቁላትና በሙቀጫ ሆነ በወፍጮ ገለባዉን መለየት
5. ከቅመም ጋር በመደባለቅ ማስፈጨትና በወንፍት ማጣራት
6. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
ጥቅሙ
 ለስንቅ ለረዢም ጊዜ ለመጠቀም
 በጁስ መልከ ለመጠቀም
 ለጭኮ ዝግጅት

4. 5.የቡላ ዱቀት

አዘገጃጀቱ

1. ቡላዉን በብዙ ዉሀ በጥብጦ በወንፍት ማጣራት


2. ቡላዉን ከወሀ ጋር በማሳደር ቡላዉ ወደ ሥር እነድዘቅጥ ማድረግ
3. ነጩን የቡላ ክፍል ለማግኘት ደጋግሞ ሶስት ጊዜ ያክል ዉሀ በመጨመር ማጥለል
4. የዘቀጠዉን ንፁ ቡላ በፀሐይ ላይ እያገላበጡ መድረቅ
5. ስደርቅ ወድያዉኑ በወንፍት አሳልፎ ሳይነፍስበት ቶሎ ማሸግ
6. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ

27
ጥቅሙ
 በምግብነት ሰዉነትን የመጠገን ባሕሪይ አለዉ
 በቀላሉ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር/ለማጋጋዝ
 ለዉጪ ሚኒዛሪ

5. 6.ነጭ ሽሮ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 10 ከሎ አተር
 5 ከሎ በቀላ
 1 ሲኒ በሶብላ
 ½ ሲኒ የጠናዳም ፈሬ
 1 ሲኒ የተከተፌ ዝንጂብል
 1 ሲኒ የተከተፌ ነጭ ሽንኩርት
 1/2 ሰሲኒ ኮረሪማ ፍሬ
 1 ሲኒ ጦሲኝ
 ¼ ሲኒ አብሽ
 1 ሲኒ ቀይ ሽንኩረት
 ጨዉ ለጣዕም

አዘገጃጀቱ

1. ጥራጥረዎቹን ለቅሞ ማጠብና ማገንፈል


2. ወሀዉነን አጠንፍፎ መቁላትና መከካት
3. ማበጠርና መልቀም
4. ቅመማ ቀመሞቹን ማመስ
5. ቀይ ሽንኩርቱንና ዝንጅብሉን ከትፎ መዉቀጥና ማድረቅ
6. ሁሉንም ቅመማ ቅመሞች ና ጥራጥሬዎች ደባልቆ ማስፈጨት
7. በወንፍት በመለየት ማሸግ
8. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ

28
ጥቅሙ
 ለቀይ ሆነ ለአልጫ ወጥ
 ለሽሮ ፍትፍት

5. 7. ምጥን ሽሮ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 6 ኪሎ አተር የተከካ
 3 ኪሎ ባቄላ የተከካ
 3 ኪሎ ሽንብራ የተከካ
 1 ኪሎ የተደለዘ በርበሬ
 1 ኪሎ ነጭ ሽንኩረት
 1 ኪሎ ነጭ ቀይ ሽንኩረት
 1/2 ከኪሎ ዝንጅብል
 1 ሲኒ ድንብላል
 1 ሲኒ ጦስኝ
 2 የሾርባ ማኒኪያ ቀረፋ
 2 የሾርባ ማኒኪያ ቁሪንፉድ
 1 የሾርባ ማኒኪያ ጤናዳም ፍሬ
 ጨዉ ለጣዕም
 2 ሲኒ ዉሀ ወይም ወይን የተደለዘዉን በርበሬ ለማዋሄድ

አዘገጃጀቱ

1. አተሩን ባቄላዉን ሽንብራዉነ ለቅሞ አጥቦ ማድረቅ መቄላት መከካት ማበጠር


2. .ከተደለዘ በርበሬ ቀላቅሎ ለአንድ ቀን ማሳደር
3. ከደረቀ በኃላ ከደረቅ ቅመሞች ጋር ቀላቅሎ መሰፈጨትና በወንፊት የተጣራዉን ማሸግ
4. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
ጥቅሙ
እንደ ቀይ ሽሮ ወጥ በአጭር ጊዜ አዘጋጅቶ ለመጠቀም

5. 8.የሽምብራ ሽሮ

አዘገጃጀቱ

29
1. ሽነብራዉ ተለቅሞ ታጥቦ ደርቆ ይቆላል
2. ይከካል ይበጠራል ንጡህ ሆኖ የፈጫል
3. በወንፍት ተጣርቶ ይታሸጋል
4. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
ጥቅሙ ፤-ለወጥ

5.8.1.የሽምብራ ዱቄት

አዘገጃጀቱ

1. ሽንብራዉ ተለቅሞ ታጠቦ ይደርቃል


2. ይከካል ይበጠራል ንጡህ ሆኖ የፈጫል
3. በወንፍት ተጣርቶ ይታሸጋል
4. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
ጥቅሙ
 የሽንብራ አሳ ለማዘጋጀት
5. 9.የባቄላ ዱቀት ለስልጆ

አዘገጃጀቱ
1. ባቄላዉን ለቅሞ ለአንድ ቀን መዘፍዘፍ
2. መድረቅ ማመስና መስከካት
3. ከደረቀዉ ዝንጅብልና ነጭ ሽንኩርት ጋር መስፈጨት
4. በወንፍት ተጣርቶ ይታሸጋል
5. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
5. ጥቅሙ፤-
 ለስልጆ

6. 10.የገብስ ቆሎ
የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 ገብስ
 ለዉዝ
 ሱፍ

30
አዘገጃጀቱ

1. ገብሱን አበጥሮ መልቀም


2. በፈላ ዉሀ ነዘፍዘፍ ከዉሀ ለይቶ መፈተግ
3. ለአንድ ቀን ሸፍኖ ማሳደር
4. አበጥሮ እንዳይቃጠል ከአሸዋ ጋር መቁላት አሸዋዉ የታጠበና በወንፍት መለየት የምችል ሞን
አለበት
5. መሸክሸክና ማበጠር መልቀም
6. በዘይት አሽቶ ንጹህ ከሆነ ለዉዘና ሱፍ ገር ማቀላቀልና ማሸግ
ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ

5.11.ዳቦ ቆሎ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 1 ኪሎ ፉርኖ ዱቀት
 1 የቡና ሰኒ ዘይት
 1 የቡና ሰኒ ስካር
 ጨዉ ለጣዕም

አዘገጃጀቱ

1. ዉሀ ሳይበዛበት በደረቁ በዘይት በስካር አሽቶ አድቦልቡሎ በተለያየ ቅርጽ መቆራረጥ


2. በእንጀራ ምጣድ መቁላት ሲበርድ በአይት አሽቶ ማሸግ
3. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ

5.12.ፈንድሻ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 ለፈንድሻ የሚሆን በቆሎ ወይም ማሽላ
 ዘይት

31
ጨዉ ወይም ስካር ለጣዕም

አዘገጃጀቱ

 መልቀምና ማሸት
 በጋለ ዘይት ፈንድሻዉ እስከሚፈካ ድረስ ድስተን ከድኖመቁላት
 ፈክቶ ስያበቃ በንጹህ ዕቃ ላይ በማዉጣት ትንሽ ስካር ወይም ጨዉ ለጣዕም መነስነስ
 ስቀዘቅዝ ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ

5.13.ቃንጣ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 ቀይ ለስላሳ ስጋ ወይም አሳ ሰጋ
 ጨዉ
 ሚጥሚጣ
 ቁንዶ በርበሬ

አዘገጃጀቱ

1. በስሱ መዘላዘል
2. ሚጥሚጣ ቁንዶበርበሬ በመነስነስ በመስቀያ ገመድ መደርደር
3. ስቀዘቅዝ ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ
4. የአሣ ቃንጣ ለማዘጋጀት በቅድሚያ የአሣዉ ሥጋ በደንብ መታጠብ ይኖርበታል
ጥቅሙ
 ሳይበላሽ ለረዢም ጊዜ ለማቆየት
 በቀላሉ ከቦታ ወደ ቦታ ለማጋጋዝ አመቺ እንድሆን

32
5. 14.የድንች ቺፒስ ድንች

ድንች በተለያየ ቅረጽ ለምሳሌ በክብ ፤በክብሪት ቅርጽ፤ወዘተ..ተሰነጣጥሮ ሊዘጋጅ ይችላል

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 ድንች
 ዘይት
 ጨዉ
 ዉሃ

አዘገጃጀቱ

1. ተመሳሳይ መጠን ያለዉን ደድንች አጥቦ መላጥ


2. የተላጠዉን ድንች በዉሀ ማለቅለቅና በክብ በከብሪት እንጨት መልክና በተበታተነ
ክር መልክ ወዘተ ቅርጽ በመሽጠት መሰነጣጠር

በቁመት መቁረጥ
በክብ

መቁረጥ

በዳይስ ካት በአራት ማዕዘን እኩል

3. ጨዉ ተጨምሮ በፈላ ዉሀ ለሁለት ደቅቃ ማገንፈል አዉጥቶ ዉሀዉን በማጠንፈፍ በንጡህ


አቦጃዲ ጨርቅ ማድረቅ
4. በፈላ በምሸፍን ዘይት መጥበስ ዲፕ ፈራይ ማድረግ
5. ከመጥበሻ ላይ ላይ ዘይቱን በማጥልለል ድንቹን እያወጡ በንጹሕ ወረቀት በማድረግ
ማቀዝቀዝ
6. በንጹህ ፒላስቲክ ማሸግ
7. ስሙን ቀኑና ይዘቱን ጽፎ በመለየጠፍ ለገበያ ማቅረብ

5.15.ንጥር ቅቤ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
 ሶስት ኪሎ ቅቤ

33
 አንድ የሾርባ ማኒኪያ ቀረፋ
 አንድ የሾርባ ማኒኪያ ቁርንፉድ
 ½ ሲኒ ኮረሪማ

አዘገጃጀቱ

1. ቅመሞቹን ሳያደቁ መዉቀጥ


2. ከቅቤዉ ገር ማንተክተክ
3. ቅቤዉ አረፋዉን ስጨርስ ጠብቆ ማዉጣት
4. በረድስል ማጥለል
5. ስቀዘቅዝ በየገራሙ ከፋፍሎ ማሸግ
በምን እንደተነጠረ ለጋ ወየም በሳል መሆኑን ቀኑንና ስሙን ጽፎ በመለጠፍ በማቀዝቀዣ
በማስቀመጥ ለገበያ ማቅረብ

ቅቤ

ንጥር ቅቤ

ንጥር ቅቤ

5.16.ጩኮ

የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች

 ፍረሽየበሶ ዱቀት
 የተነጠረ ቅቤ

34
 ጨዉ
 ትንሽ ኮረርማ
አዘገጃጀቱ

1. ዱቀቱን ቅቤዉን ጨዉና ኮረሪማወን ማዋሄድ


2. በሚፈለገዉ መጠን ማሸግ
3. ስሙን ከምን እንደተዘጋጀና ቀኑን ጽፎ በመለጠፍ ቀዘቃዛ ቦታ አስቀምጦ ለገበያ
ማቅረብ

ምስጋና

ይህ በወቅቱ ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና ለመስጠት ተፈልጊ የሆነዉን የዘርፉም እቅድ የነበረዉን
በተገባር ላየ በማዋል የሠልጠና መርጃ መሣሪያ ለማዘጋጀት ቅድ ሁነታዎችን በማመቻቼት
ዉጠት ተኮር ሥራ እንድሰራ የረዳንን የደቡብ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ብሮና አቶ ሽመልስ በኔና በሙያ
አጋሮቼ ስም አመሰግናለሁ፡፡

35
አዘጋጅ ተዋበች ጴጥሮስ

36

You might also like