You are on page 1of 24

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ቴ/ክ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ

የፀጉርና ውበት ሥራ ሙያ የአጫጭር ግዜ ሥልጠና ማሰልጠኛ


ማንዋል

ሚያዚያ/2008

ሀዋሳ
Table of Contents
መግቢያ.........................................................................................................................3
የብቃት አሀድ ዝርዝር........................................................................................................3
የአላቂእቃ ዝርዘር.............................................................................................................4
ምዕራፍ 1......................................................................................................................6
ሣሎን ማለት እ ና የሳሎንስራ ደንብና መመሪያ.......................................................................6
የፀጉር አጠቃለል ዘዴዎች................................................................................................8
ምዕራፍ 2......................................................................................................................9
ፀጉራ ንዕህና....................................................................................................................9
የፀጉር ይዘትና ዓይነቶች.................................................................................................10
የፀጉር አሰተጣጠብ......................................................................................................10
አንድን ደንበኛ ፀጉሩን ከማጠባችን በፊት ማድረግ የሚገባን ቅድመ ዝግጅት...............................12
ምዕራፍ 3....................................................................................................................13
ካውያ Iron..................................................................................................................13
ካውያ ስንሰራ ማወቅ ያለብን ነገሮች.................................................................................13
የሚያስፈልገዉ ጥሬ እቃ አጠቃቀም ለሀረጉ የሚገቡ ጥንቃቄ...................................................13
ምዕራፍ-5....................................................................................................................14
ፒየስትራ እና ፎን...........................................................................................................14
ምዕራፍ 6....................................................................................................................14
ፐርም.........................................................................................................................14
ምዕራፍ 7....................................................................................................................15
ፀጉር አቆራረጥ...............................................................................................................15
ምዕራፍ 8....................................................................................................................15
ቀለም..........................................................................................................................15
የቀለም አይነቶች.........................................................................................................16
ምዕራፍ 10..................................................................................................................17
ሚካአፕ.......................................................................................................................17
ማጠቃለያ:...................................................................................................................18
መግቢያ

የዚህ ማኑዋል ዓላማ የተለያዩ ሥራ አጥ የሆኑ የህብረተሰበ ከፍሎች በመደራጀት ሥራ እንድፈጥሩና እንዲሰማሩ ደግሞም
በዚህ በጸጉር ስራ ሙያ በማህበር ተደራጅተው ለሚሰሩ ማህበራት ያለባቸውን የከህሎት ከፍተት ለመሙላት እና በሥራ ቦታ
ደረጃውን የጠበቀ ስራ እንዲሰሩ ተብሎ የተዘጋጀ ማኑዋል ሲሆን፡የሚይዛቸውም ሥራዎች

1. የጸጉር አጠባ/ SHAMPOOING /


2. ጥቅለላ/ SETTING/
3. ካዉያ/IRONING/
4. ፓይስትራ፡ የቀለምና የፐርም አቀባብ
5. የሜካፐ ሥራን ያካትታል
ለተለያዩ የፀጉር አይነት ማጠቢያ የተለያዩ ሻምፖ እና ኮነድሼነሮች አለ

ለምሳሌ

የሻምፖ አይነቶች
1. Cream shampoo :- ለደረቅ ለተሠባበረ ብሊች ለተደረገበትና ቀለም ለተሰረገበት ፀጉር እንጠቀምበታለን
2. Oily shampoo; ለደረቅ ብሊችና ቀለም ለተደረገበትና ፐርም ላለው ፀጉር ይናል
3. Medicated shampoo:- መድኃኒትነት ያለው ሻምፖ ሲሆን ፎረፎር ለማጥፈት ይናል
4. Egg shampoo :- (ለሴንሲቲቭ scalp) ወይም በተፈጥሮ ምንም አይነት ነገር ለማይችል እና ለልጆች የሚሆን
shampoo ነው፡፡
5. Beer shampoo :- ለቀጭንና ለሰላሳ ፀጉር የሚሆን ነው
6. Lemon shampoo :- የፀጉራችንን የ PH (የአሲድ መጠን) የሚያስተካክል shampoo ነው
7. Protein shampoo:- በኬሚካል ለተጎዳ ፀጉር ይሆናል
8. Herbal shampoo :- ከአነትክልትና ከፍራፍሬ የተሰራ shampoo ሲሆን ፀጉሩ ሻይን እንዲያርግ ይጠቅማል
9. የ ph balance shampoo :- የፀጉራችንን የ ph መጠንን ከ 4 -6 እንዲሆን ያደርግልና በተለይ ኬሚካል ላለው ፀጉር
10.Pawder shampoo:- ለተቀደደ ለቆሰለ scale የሚሆን shampoo
11.Colour shampoo:- ቴምፓራሪ (ጊዜያዊ) ቀለም ለተቀባ ለተቀባ ፀጉር ይጠቅማል፡፡
ምዕራፍ 1

አንድ የውበት ሳሎን ሊኖሩት የሚገቡ ነገሮች

1. በሙያው የሰለጠነ (professional) የፀጉር ሙያ ሠራኛ መኖር አለበት


2. ንዕህናው የተሟላ መሆን አለበት
3. ደንበኛን የሚስብና የሚያዝናና ሣሎን መሆን አለበት
4. Reception ወይም የእንግዳ መቀበያ መኖር አለበት

በመጀመሪያ አንድ ሰውን ማስዋብ ከመጀመራች በፊት የራሣችንን ንዕህና አጠባበቅ ማወቀ አለብን ማለትም ጥፍራችንን
ፀጉራችንን ቆዳችንን ጥርሳችንን ልብሳችን ማንኛውም አላስፈላጊ ጠረን ባጠቃላይ ሠውነታችን ንዑህ መሆን አለበት፡፡

በተጨማሪም ማወቅ ያለብን የሣሎን ስርዓት


1. ደንበኛ ማክበር
2. የቤቱን ንዕህና መጠበቅ
3. ዕቃዎችን በንዕህና መያዝ
4. የአነጋገር ስርዓት ማወቅ አለብን
5. ታማኝ መሆን፡፡

ፀጉር
ፀጉር ማለት ቆዳቸን ላይ የሚገኝ ሆኖ ለሰው ልጅ እንደ ውበት የሚገለገልበት ሆኖ እንዲሁም ፀጉራችን
የተሠራው ከማይሟሟ (protein) ሆኖ ስሙም (kertatin ) ኬራቲን ተብሎ ይጠራል ፡፡

በፀጉራችንም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች


1. Carbon
2. Nitrogen
3. Hydrogen
4. Sulpher
5. Phosphorous
6. Chlorine ናቸው

የጭንቅላታችን ቆዳ (scalp) ሰካልፕ ሲባል እዚሁ scalp ላይ ቀዳዳዎች አሉ፡፡


እነዚህም ቀዳዳዎች ፀጉር የሚያድግባቸው ሲሆን (hair follicle) ሂር ፎሊክል ተብለው ይጠራሉ፡፡

የ hair follicle ጥቅም ለፀጉራችን oxygen እና ምግብ ያቀብላል፡፡

በአንዷ ነጠላ ፀጉራችን ላይ ሦስት የተለያዩ ነገሮች ተደረራርበው ይገኛሉ፡፡ እነርሱም፡-

1. Cuticle (ኩቲክል) የፀጉራችን የውጪኛው ክፍል ንጣፍ ሲሆን


2. Medulla (ኮርቴክስ)የፀጉራችን መሀከለኛው ክፍል ንጣፍ ሲሆን

3. Medulla (ሜዱላ) የፀጉራችን የውስጠኛው ክፍል ንጣፍ ነው

የተለያየ መጠን ያለው መጠቅለያ የሚያስፈለግበት ምክንያት

1.ትልቁ መጠቅለያ ለረጅም ፀጉር ሲሆን


2. መካከለኛው መጠቅለያ ለመካከለኛ ቁመት ያለው ፀጉር ይጠቅማል

3.ትንሽ መጠቅለያ ለአጭር ፀጉር እንጠቀምበታለን

በደረቁ ለመጠቅለል የሚያስፈልጉን መሣሪያዎችን ጥቅማቸው

1. የተለያየ መጠን ያለው መጠቅለያ፡-ፀጉሩን በመጠኑ ጠጥቅልሎ ለማስያዝ


2. የጸጉር ዳንቴል /hair net / ጠቅልለን ካበቃን በኋላ መጠቅለያው እንዳይፈታና ወደ ላይ የቆሙትን ፀጉሮች ለማስያዝ
3. ማበጠሪያ ፡- ፀጉራችንን አለስልሶ ለማበጠር እና በ በምናጥርበት ጊዜ ፀጉራችንን ለጥ አድርጎ ለማበጠር፡፡መክፈያ፡-
ለመክፈል እንዲሁም ለመገሸን ይጠቅማል፡፡
4. መክፈያ/ tail comp/ - ለመክፈል እንዲሁም ለመፈሸን እና ብሩሽ

በደረቁ ለመጠቅለል የምንከተላቸው ስርዓቶች በቅደም ተከተል፡፡

1. ስራ ከመጀመራችን በፊት የደንበኛችንን ጌጣ ጌጦች አውልቆ በክብር ማስቀመጥ


2. ፎጣ ማልበስ

3. የፀጉሩን ይዘት ማየት ምክንያቱም በምን ዓይነት መንገድ መጠቅለል እንደሚገባን ለማወቅ እና ጤንነቱን ለማረጋገጥ
4. በዘርዛራ ማበጠሪያ ፀጉርን ማፍታታት
5. በመክፊያ እየከፈልን በጠቅጣቃ ማበጠሪያ ማበጠርና መጠቅለል
6. ሻሹን ማሰር
7. መጠቀለያውን ከፊታን በኋላ ጭንቅላቱን በጣታችን መዳፍ ማሻሸት (massage) ማድረግ ምክንያቱም የተከፈለው
እንዲጠፉ እንዲሁም ሰውነት እንዲዝናና ለማድረግ
8. በዘርዛራ ማበጠሪያ ፀጉርን ማፍታታት
9. እንደ አሰፈላጊነት ማጠር
የአንድ ሰው የተፈጥሮ የፀጉር ዕድገቱ መጠን ምንም አይነት ኬሚካል ያልነካው ከሆነ 1.25 ሳ.ሜ ነው፡፡

ምዕራፍ 2

የፀጉር ንዕህና

የፀጉር ንዕህና አስፈላጊነቱ


1. ጤናችንን ለመጠበቅ
2. ውበታችንን ለመጠበቅና ለማማር ነው፡፡

ዋናው የጤና ጉዳይ በመሆኑ ጤነኞች ልንሆን የምንችለው ንዕህና ስንጠብቅ ብቻ ነው፡፡ንዕህናችንን ጠብቀን ጤነኞች
ከሆንን ደግሞ ውበታችን ጎልቶ ይታያል እንዲሁም በአግባቡ ለመጠቀም እንችላለን
የፀጉር ይዘትና ዓይነቶች
የፀጉር ይዘት በሁለት ሲከፈል የፀጉር አይነት ግን በ 6 ይከፊላል፡፡
የፀጉር ዓይነቶች (Nature)
1. Cursive በጣም ወፍራም ፀጉር
2. Medium ቀጭን ያልሆነ ወፍራምም ያልሆን መካከለኛ ፀጉር
3. Fine :- ቀጭን ፀጉር
4. Oily :- ቅባት የበዛበት ፀጉር
5. Dry :- ቅባት የሌለው ደረቅ ፀጉር
6. Normal:- ቅባት ያልዛበት ያሳነሰው ልከኛ የሆነ ፀጉር ናቸው፡፡

ስድስት የፀጉር ዓይነቶች ከላይ የጠቀሰናቸው ሲሆን እነሱም በሁለት ይከፈላሉ


- Medium conursive fine ስንል ሰለ ፀጉሩ ውፍረትና አፈጣጠር ሲሆን
- Normal, oil, Dry ደግሞ ስለ ፀጉሩ ቅባት መጠን የሚገልፅ ነው፡፡

ውበታችን በአግባቡ ለመጠበቅም ሆነ ወይንም ተውበን ለመታየት ጤነኞች መሆን አለብን፡፡ እንዳልነው ጤነኞች መሆን ያለብን
ደግሞ ለፅጉር አይነት የሚሆን ማጠቢያ shampoo እንዲዑም ፀጉሩን በደንብ ለማበጠር ብሎም ለመሥራት እንዲያመቸን
የሚያለሰልለ conditioner መጠቀም ይኖርብናል

የፀጉር አሰተጣጠብ

1. ፀጉር ስናጥብ በመዳፍ ማጠብና በተቻለን መጠን በተለያዩ ማጠቢያ ዘዴዎች ማጠብ
2. ንጽህ እስከሚሆን በሻመፖ ማጠብ
3. ኮንዲሽነር/ conditioner / አርገን ፀጉሩን ማፍታታት.
4. በብሩሽ መቦረሽ
 የሁለት ቅንጅት ያላቸው ፀጉሮች

የሁለት ቅንጅት ያለቸው ማለት በአንድ ሠው ላይ ሁለት አይነት የፀጉ አይነት መኖር ማለት ሲሆን እንዲሁም ሶስት የፀጉር አይነት
ያለ፤ቸው አሉ

ለምሣሌ፡- የሁለት ቅንጅት ያላቸው ፀጉሮች ስንል

1. Medium to coursive
2. Dry to medium
3. Fine to oily
4. Dry to fine
5. Normal to coursive
6. Fine to normal እያለ ይቀጥላል፡፡

ለምሳሌ፡- የሦስት ቅንጅት ያላቸው ፀጉሮች ስንል


1. Medium coursive, to normal
2. Fine medium to oily -------- ወዘተ ናቸው
ከዚህ በተረፈ shampoo ይሁን conditioner እንደ የፀጉራችን አይነት እንደሚሰሩ ማወቅ ይኖርብናል፡፡
 በጭራሽ የማይቀናጁ የፀጉር አይነቶች እነሱም፡፡
1. Corusive to fine
2. Dry to oily የሚባል ቅንጅት እንደሌለ ማወቅ አለብን፡፡

- የፀጉራችን የአሲድ መጠን መለኪያ P.H. ይባሳል


- የፀጉራችን የ P.H. መጠን (ከ 4-6) መሆን አለበት፡፡

የጸጉራችንን ጤንነት የሚያወኩ

 ፎረፎር

ፎርፎር የቆዳ ድርቀት ሲሆን ሲሆን መንስዔውም በየጊዜው ካለመታጠብና ቆዳችን የሚያስፈልግውን ቅባት ባለመቀባት
የሚመጣ በሽታ ሲሆን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሻምፖ እና ኮንድሽነር ማጠብ ያስፈልጋል፡፡

 ቆረቆር

ቆረቆር ማለት ፈንገስ የሚያመጣው በሽታ ሲሆን በቀላሉም የሚተላለፍ በሕክምና እርዳታ ብቻ የሚድን የቆዳ በሽታ ነው፡፡

ጸጉርን ለማጠብ የሚያስፈልጉ ነገሮች

1. ሙቅውሃ ፡- ፀጉርን አጽድቶ ለማጠብ


2. ቀዝቃዛ ውሃ ፡- ቅባት ያለውን ፀጉር ለማጠብ
3. ፎጣዎች፡- አንደኛው ትከሻ ላይ በማልበስ ከፀጉር የሚወርደውን የውሃ እንጥፍጣፊ ልብስን እንዳያበላሽ ለመከላከል ሲሆን
ሌላው ደግሞ ፀጉርን አጥበን ከጨረሰን በኋላ ጠቅልለን ውሃውን ለማድረግ ይጠቅማል
4. Shampoo:- ፀጉሩን አዕድቶ ለማጠብ
5. Conditioner:- ስናጥብ የተረበሸውን ፀጉር በቀላሉ እንድናበጥረው እንዲያፍታታ እና ፀጉሩን ልስላሴ እንዲያገኝ ይረዳል፡፡
6. ሞራ ሳሙና፡- ቅባት ያለውን የበዛበትን ፀጉር ቅባቱን አስለቅቆ ለማጠብ ይጠቅማል፡፡
7. ብሩሽ፡- ኮንዲሽነር ከቀባን በኋላ ፀጉሩን በሚገባ ለማፍታታት የሚረዳን እንዲሁም ፀጉሩን አጥበን ከጨረስን በኋላ ሽንጠቀልል
ፀጉሩን እናፍታታበታለን
8. ዘርዛራ ማበጠሪያ፡- ፀጉሩን አፍታተን ለማዘጠር እንጠቀምበታለን
9. ጨርቅ ካባ፡- ፀጉሩ በሚታበጠበት ጊዜ ልብሱን እንዲያበላሽ ለመከላከል
10. ማጠቢያ ሳህን፡- የሰውን ምቾት ጠብቆ ውሃ ሳናፈስባቸው ለማጠብ ይረዳል
11. መክፊያ የሚጠቅመን ፀጉሩን ስነሰራ ለመክፈል ነው፡፡

አንድን ደንበኛ ፀጉሩን ከማጠባችን በፊት ማድረግ የሚገባን ቅድመ ዝግጅት


1. ሙቅና ቀዝቃዛ ውሃ ማዘጋጀት
2. ንዑህ ፎጣዎችን ማዘጋጀት
3. ሻመፖ ማዘጋጀት
4. ብሩሽ ማዘጋጀት
5. ለተለያየ የፀጉር ዓይነት የሚሆነ ሻምፖና ኮንዲሽነር ማዘጋጀት
6. ንጹህ የማጠበያ /ሲንክ/ ማዘጋጀት

ፀጉርን ስናጥብ የምንከተላቸው ሥርዓቶች በቅደም ተከተላቸው


1. አስፈላጊውን ጌጥ ማውለቅ
2. ፎጣ ማልበስ
3. የፀጉሩን ይዘት በደንብ ማወቅ (ዓይነቱን)
4. ፀጉሩን በደንብ ማበጠር
5. ቅባት ያለው ጠጉር ከሆነ በሳሙናና በቀዝቃዛ ውሃ ቅባቱ እስኪለቅ ድረስ ደጋግሞ ማጠብ
6. እንደ ፀጉሩ አይት ተገቢውን ሻምፖ አደርገን ቆሻሻው እስኪለቅ እየደጋገሙ ማጠብ ከዚያም ማለቅለት
7. ክሬም ሻምፖ ከሆነ ቆዳውን በደንብ ማዳረስ
8. ኮንዲሽነሩን በመቀባት ጸጉሩን መቦረሽ
9. ከ 5-10 ደቂቃ ቆይቶ በደንብ ማለቅለቅ
10. በንጹሀ ፎጣ ጠቅለልሎ ወደ መጠቅለያ ቦታ መውሰድ
11. አስፈላጊ ከሆነ ተገቢውን አይነት ቅባት መቀባት

5 ቱ ማዎች ለውበት ሳሎን ያገለግላሉ

1. መለየት
2. ማስቀመጥ
3. ማጽዳት
4. ማላመድ
5. ማዝለቅ ናቸው
ምዕራፍ 3

ካውያ /Iron/
ካውያ ፀጉራችንን ከምናስወብበት መሳሪያ አንዱ ነው፡፡ ሉጫ ፀጉር በካውያ ስንሰራው ከሌላው ፀጉር ያነሱ ውጤት
ይሰጠናል ማለት ይህም ማለት ፀጉሩ እሳት ስለማይችል ልጥፍ ብሎ ቅርፅ ቢስ ይሆናል፡፡

ካውያ ስንሰራ ማወቅ ያለብን ነገሮች


1. ምድጃው እሳት ተሎክሶ አልኮል አለመጨመር ምክንያቱም እሳቱ ይፈነዳል፡፡
2. ስንሰራ ድንገት ቆዳቸውን ካውያ ካስነካን በእጅ ቆዳቸውን ሳነካ ወዲያውኑ ባዝሊን መቀባት ግንባራቸውንና
አንገታቸውን ካውያ ከነዳቸው ኮልጌት በማድረግ ጠባሳውን ማጥፋት ይቻላል፡፡
3. ሰርተን እንደጨረስን ወዲያውን ማጥፋት
4. ምድጃውን ጥጥ መሙላት
5. ፐርም ያው ፀጉር በካውያ አለመስራት
6. እንደ ፀጉሩ ቁመት ካውያ መምረጥ ማለትም ለረጅም ፀጉር ትልቅ ካውያ፤ ለመካከለኛ ፀጉር መሀከለኛ ካውያና
ለአጭር ፀጉር ቀጭን ካውያ መሆን አለበት፡፡
የሚያስፈልገዉ ጥሬ እቃ አጠቃቀም ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄ

የእቃዎች አጠቃቀም

 ለካክስ ማድረቂያ ሲሆን በመጠነኛ ሙቀት መጠቀም


 ሶኬትን በመንቀል አለማፅዳት
 እስቲመር በደረቁ አለማስቀመጥ
 ካዉያ ምድጃ እየነደደ አልኮል አለመጨመር ይህ ፍጂታን ያስከትላል
 ስለታማ ነገሮችን sterilize ማድረግ ይህም ተላላፊ በሺታዎችን ይከላከላል
 በካዉያ ሰአት ሲሰራ ፀጉር እንዳይቃጠል መጠንቀቅ
 ለፀጉር አይነቶች ሻፖና ኮንድሺነር መምረጥ

Hazardous የሚባሉ ነገሮች (haccp}

1. የኬሚካል (ቀለም ፐርም በአግባቡ አለመጠቀም)


2. በባዕድ ነገሮች (ምላጭ መቀስ መቀንደቢያ ያሉትን ነገሮች ለአንድ ጊዜ ብቻ ያለመጠቀም)
3. ባዮሎጂካል ችግር በአይን የማናያቸውን ሕይወት ያላቸው ነገሮች ወደ ሰው ጸጉር ወይም ቆዳ እንዳይተላለፍ
አለማድረግ ለምሳሌ ባክቴሪያና ፈንገስ የሚመጡ በሽታዎችን የሳሎን ንጽህናን ባለመጠበቅ

ምዕራፍ-4
ፒየስትራ እና ፎን

ፎን ስንሰራ ኤልክትሪክ ሰክተን ፀጉሩን ከፍለን ማድረቂያ ነው፡፡ ከዚያም ፒየስትራ ሰክትን ፀጉረን ከፋፍለን
በኖርማል ፣በአበባ ስራ ፣ከርል ወይም በግልብጥ መስራት፤

ፒየስትራ ስንሰራ ቅባት በእጃችን ላይ በማድረግ እየቀባን መተኮስ ነው፡፡

ምዕራፍ 5

ፐርም

ሁለት አይነት ፐርም አለ፡፡ 1 ኛ ከርል የሚሰራ

2 ኛ ቀጥ የሚያደርግ / go back/

ፐርም ስንቀባ ማወቅ ያለብን ነገሮች፤

1 ኛ/ ፀጉሩን አራት ቦታ እንከፍለዋለን

2 ኛ/ ባዝሊን ቤዝ/ የፀጉሩን ቆዳ እንቀባለን

3 ኛ/ ማበጠሪያ ገልብጠን እንቦርሸዋለን፤

4 ኛ/ ያልተዳረሰበትን አዳርሰን ፀጉሩን በእጃችን እንስበዋለን፡፡


5 ኛ/ ኒውትራላይዝ ሻንፖ ኬሚካሉን ማምከኛ እንጠቀማለን፡፡

6 ኛ/ በሙቅ ውሃ ፀጉሩን በደንብ እናለቀልቃለን፤

7 ኛ/ ፐርም ከቀባን በኋላ የተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ ትሪትመንት መቀባት አለብን፡፡

ማስጠንቀቂያ፡- አሳከከኝ ለሚል ደንበኛ ቶሎ አቋርጠን እናጥበዋለን፡፡

- ፐርም የነካው ፀጉር የተጎዳ ስለሆነ ቀለም ከሶስት ወር በፊት አንቀባውም

ምዕራፍ 6

ፀጉር አቆራረጥ

ፀጉር ስንቆርጥ የምንጠቀማቸው ቅደም ተከተሎች፡-

1. መጀመሪያ በካውያ መስራት


2. መሪ (ጋይድ) ማውጣት
3. በፊት ቅርጽ መሰረት በደንበኛው ትዕዛዝ መቁረጥ
4 ሁልግዜበመሀል ጣትይዞመቁረጥ
ምዕራፍ 7

ቀለም

ቀለም ስንቀባ የምንከተላቸው መመሪያዎች

1. ከመቀባቱ በፊት በደንብ በሻምፖ መታጠብ አለበት፡፡


2. ፀጉሩን ኮንድሽነር ፣ቅባት ወይም ትሪትመንት መቀባት የለብንም ፡፡
3. ፐርም ላይ ቀለም ከሶስት ወር በፊት መቀባት የለብንም፡፡
4. ስንቀባ ከኋላ መጀመር አለብን፡፡
5. አራት ቦታ ፀጉሩን መክፈል አለብን፡፡
6. ያልያዘ ፀጉር ከሆነ በእጃችን ማሞቅ አለብን፡፡
ማሰሰቢያ፡- ጥቁር ቀለም የተቀባ ፀጉር ሌላ የቀለም አይነት ቶሎ አይቀበልም፡፡
በኑትራላይዝ ሻንፖ በደንብ ማጠብ አለብን፡፡
የቀለም መበጥበጫ ዕቃ ፕላስቲክ ወይም ከእንጨት የተሰራ መሆን አለበት፡፡
በብረት መበጥበጥ ቀለሙን መርዛማ ያደርገዋል፡፡
የቀለም አይነቶች

1. ጊዜአዊ ቀለም
2. ቋሚ ቀለም
3. እስከ ሶስት ወር የሚቆይ ቀለም
ምዕራብ 8
የጥፍር አሰራር
ጥፍር ስንሰራ የምንከተላቸው መመሪያዎች
1. የተጠቀምንበትን መሳሪያ መቀቀል፤
2. ጥፍሩን በሻምቦ መዘፍዘፍ እና ክሬም መቀባት
3. ዩቲክል እና ቆሻሻ ማውጣት
4. ኦቫል ሼፕ እስኬር ፣ ከርቭ ጥፍሬን መቆረጥ

ቀለመስንቀባ መገመርያየጥፍር ቀለም ማስለቀቅ ፤ጥፍሮቹን መቁረጥ፤ጥፍሩንስሞርዱ ለእግሮጣቶች የሚስማማቅርዕ ክብ


አድርገዉ ቁረጡ፤የእጅጥፍርከሆነጣቶን ፣ለብ ባለ ወሃ እና በፈሳሳ ሣሙና ለአምስት ደቂቃ መዘፍዘፍ፤ቆሳሳ
ማዉጣት፤ካደረቁ በሓላትን የፈለጉትን ቀለም መቀባተ፣
ምዕራፍ 9

ሚካአፕ

ሚካአፕ ስንሰራ የምንከተላቸው መመሪያዎች


1. የቆዳውን አይነት ማየት
2. ክሬም ሳሙና ክሊሰር በመጠቀም ማጽዳት
3. እስቲም ማስገባት
4. ማጽዳት
ለሜካፕ የሚያገለግሉ አላቂ ዕቃዎች

1. ክሊንሰር የፊትቆዳን ለማጽዳት


2. ቶነር ፡-
3. ፋውንዴሽን
4. ፓውደር
5. ኩል
6. ማስካራ
7. ሻዶ ፡- የተለያየ ቀለማት በፊት ላይ ማምጣት
8. ሊፕስቲክ ከንፈርን ማስዋብያ
9. ቻፕስቲክ ፡- ለማለስለስ
10. እስክራፐር ፡- ጥቅሙ ሻካራን ነገር ከፍት ላይ ማንሳት
11. ሞስቸራይዝድ ክሬም፡- የፊት ቆዳን ለማለስለስ

ማጠቃለያ:

ይህ ሞጁል ለአጫጭር ጊዜ ሰልጣኝ ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ -የሚያካትታቸው

 አጠባ (shampooing)
 ካዉያ (Ironing)`
 ፓይስትራ
 የፀጉር አቆራረጥ
 የቀለም አጠቃቀም ያካተተ ሲሆን

ይህ ሰልጠና በምዘና ስርዐት ዉስጥ እንድያልፍና ደረጃዉን የጠበቀ መሆን አለበት

አዘጋጆች

1.ታሪካየሁ ገ/ስላሴ

2.ከበቡሽ ከፍአለ

You might also like