Professional Documents
Culture Documents
2011 e
2011 e
የ 2011 በጀት
የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን
ዓመት
የልማት ቡድን እቅድ
ሰኔ 2010
ገንዳ ውሃ
መግቢያ
በአጠቃላይ ይህ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2011 በጀት ዓመት የልማት ቡድኑ እቅድ ውስጥ
የእቅዱ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች፣ መርሆች፣ ዓላማ፣ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ስጋቶች፣ መፍትሔዎችና
የልማት ቡድኑ አባላትን ስም ዝርዝር አካቶ የታቀደ ነው፡፡
ተልዕኮ፡- በቡድኑ ቀልጣፋና ዉጤታማ አደረጃጀት አሰራርና የሰዉ ሀይል በመገንባት ተጨባጭ
ለውጥ
ተፈጥሮ ማየት ፡፡
እሴቶች
መርሆች
የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ስኬት በተሻለ ፣በተፋጠነ፣ ተደራሽ በሆነና ዘላቂነት
ባለዉ መንገድ ለማስቀጠል በቡድን መሪውና በባለሙያዉ በኩል እየታየ ያለዉን የአፈፃፀም
ክፍተት በማስወገድ የሚፈለገዉን ለዉጥ ለማምጣት በተደራጀና ወጥነት ባለዉ መንገድ
መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑ ነዉ ፡፡ ዉጤት የሚመዘግቡት ባላዉ የስራ ህብረት እንጂ
በተናጠል እንዳልሆነ ሁሉም የቡድኑ አባላት በመተማመን ነው፡፡ በቡድናችን የምናከናዉናቸዉ
ተግባራት ዉጤታማ የሚሆኑት በቡድኑ ዉስጥ ያለነዉ ሰራተኞች በምናደርገዉ የሥራ
እንቅስቃሴ በመሆኑ የልማት ቡድን አደረጃጀት አስፈላጊ ነዉ ፡፡
በቡድኑ ዉስጥ የቡድን መሪዉን ጨምሮ አራት /4/ ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ
ሰራተኞች በአንድ የስራ ቡድን ተደራጅተዋል ፡፡ ስለሆነም ይህ የስራ ቡድን በቡድን
መሪዉ የሚመራ ሆኖ በአንድ የልማት ቡድን የተደራጀ ነዉ ፡፡
አንድን ተግባር የባለሙያው ሳይሆን የቡድኑ ተግባር አድርጎ በመረዳት በልማት ቡድን መፈፀም
በወረዳችን የትምህርት ተቋማቶች ውስጥ እየታዩ ያሉ ጥንካሬዎችንና እጥረቶችን እየለዩ የጋራ
በማድረግ ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ስርዓት በማምጣት ትግል ማድረግ
የልማት ቡድን ውይይት ዓርብ ከ 11፡30 ስዓት ጀምሮ በሳምንቱ የተሰሩና ያልተሰሩ ስራዎችን
ግምገማ ማድረግ የቀጣይ ሳምንት ተግባራትን ለይቶ ማስቀመጥ
እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ርዕሶችን በመምረጥ መወያየት ፡፡
የልማት ቡድን ውይይት በዓመት ውስጥ 48 ጊዜ ውይይት ማድረግ