You are on page 1of 2

አብርሃም

 አንድ ቀን እግዚአብሔር አብራምን ወደአዲስ ምድር እንዲሄድ አዘዘው። ሚስቱን


ሳራይንና የአጎቱን ልጅ ሎጥን ይዞ ወደ ከነአን ምድር ሄደ።

 አብራምና ሎጥ ሁለቱም ሀብታሞችና ብዙ የከብት መንጋዎች ነበሯቸው።


እንስሶቻቸውን ይጠብቁ የነበሩ እረኞቻቸው እርስ በርስ ስለተጣሉ የነበሯቸውን
መንጎች ለመከፋፈልና ለመለያየት ወሰኑ። አብርሃም የመጀመሪያውን ምርጫ
ለሎጥ ተወለት። ሎጥም ምርጥ የሆነውን አካባቢ መርጦ ወደዚያው ሄደ።
አብርሃም ደግሞ ከሎጥ ምርጫ የተረፈውን አካባቢ ወሰደ።

 እግዚአብሔርም የአብራምን ስም አብርሃም ብሎ ቀየረለት። እግዚአብሔር


በተጨማሪም አብርሃምን እንደሚባርከውና ትልቅ ቤተሰብ እንደሚሰጠው ቃል
ገባለት።
 አንድ ቀን ሶስት ሰዎች አብርሃም ሊጎበኙት መጡ። ሳራ በቅርብ ጊዜ
እንደምትወልድ ነገሩት። በዚያን ጊዜ ሳራ እድሜዋ 90 ዓመት ሲሆን አብርሃም
ደግሞ የ100 ዓመት የዕደሜ ባለጠጋ ነበር።

 ይስሐቅም ልክ ሶሰቱ ሰዎች እንደተናገሩት ተወለደ። አንድ ቀን እግዚአብሔር


አብርሃም ይስሐቅን እንዲሰዋ አዘዘው። እግዚአብሔር የእውነት ይስሐቅን
እንዲሰዋው አስቦ ሳይሆን እምነቱን ሊፈትነው ፈልጎ ነበር ይህን ያለው። አንድ
መልአክም የይስሐቅን ሕይወት አዳነ።
የአብርሃም ታሪክ በዘፍጥረት ምዕራፍ 13፣18፣21 እና 22 ውስጥ ይገኛል።

http://gardenofpraise.com

You might also like