Professional Documents
Culture Documents
እንለይ
እንለይ
ተለይ፥
ዘፍጥረት 12
¹ እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።
² ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤
³ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።
⁴ አብራምም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ሄደ፤ ሎጥም ከእርሱ ጋር ሄደ፤ አብራምም ከካራን በወጣ ጊዜ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበረ።
* በዚህ ክፍል እግዚአብሔር አብርሃምን ተለይተህ ውጣ የሚልባቸው ዝርዝር ሁነቶችን ስንመለከት፥ ከምን ከምንድነው የወጣው ?
# አብረሃም እንግዲህ እነዚህን ነገሮች በፍጹም መታመን ተግባራዊ ካደረገ እግዚአብሔርም ህይወቱን ኑሮውን ስራውን ሁሉም ነገሩን
እንደሚቀይርለት ቃልኪዳን ስገባ በዚህ ክፍል እናያለን ፥
እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ለመባረክ የነበረው የመጀመሪያው ሀሳብ እንደገና በአብርሃምና በዘሮቹ ፍጻሜ እንደሚያገኝ ያመለክታል ።
አብረሃም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወጣ ይህ የሕዝቦች አባት ከእምነት የተነሳ ለእግዚአብሔር ያሳየው ታዛዥነት በህይወቱ ሁሉ የሚታይ ልዩ
ባህሪይ ነው ።
አብረሃም ከሎጥ ተለየ ፥
# አብራምም ዘወትር ቸር ስለነበር ደስ ያሰኘውን መርጦ እንድወስድ ምርጫውን ለሎጥ ሰጠ ፤ ይህንንም ያደረገው እግዚአብሔር ካልባረከው
በቀር ሰው ሀብትም ሆነ ደስታ ሠላምም ማግኘት እንደማይችል ስለተረዳ ነው ።
ኦ/ዘፍጥረት 14:22-24
ሎጥና አብራም የተለያየ አመለካከት ያላቸው ዘመዳሞች ግን የተለያዩ ሰዎች ናቸው ። ሎጥ ስስታም እና የራሱን ፍላጎት ብቻ ለሟሟላት
የሚሯሯጥ የነበረ ስሆን ፤ አብራም ደግሞ በእግዚአብሔር ፍቃድና ምርት የሚመላለስ የተባረከ ሰው ነበረ ።
ከዚህ ቀጥሎ ከሎጥ መለየትና ከሁለተኛ ቃልኪዳን እስከ ሦስተኛው መለየትና ቃልኪዳን ድረስ ያለው ፦
ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብረሃምን ፈተነው ፥ እንዲህም አለው ፦ አብረሃም ሆይ ። አብረሃምም እነሆ አለሁ አለ። የሚትወደውን
አንድ ልጅህን ይዘህ ወደ ሞሪያ ተራራ ሂድ ። እኔም በሚነግርህ በአአድ ተራራ ላይ በዚያ መስዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ ። አብረሃምም በማለዳ
ተነስቶ አህያውን ጫነ ፤ ሁለቱን ሎሌዎችና ልጁን ይስሐቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ እንጨትም ተሰነጠቀ ፤ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ
በሶስተኛውም ቀን አብረሃም አይኑን አነሳና ቦታውን ከሩቅ አየ ። አብረሃምም ሎሌዎቹን አላቸው አህያውን ይዛችሁ እዚህ ቆዩ ። እኔና ልጄ ወደዚያ
ሄደን እንሰግዳለን ወደ እናንተም እንመለሳለን ።
ኦ/ዘፍጥረት 22:2-5
ስለዚህ በእነዚህ ምክንያቶች መስዋዕት እንዳይስተጓጎል አብረሃም ከእነዚህ ሰዎች ተለይቶ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም ኪዳኑን ወይም
የተስፋውን ቃል ማረጋገጥ አለበት ።
ቃልኪዳን/በረከት/(3)
$ እኛስ ዛሬ የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ወይም አገልጋዮች ከየት ወዴት እንውጣ ወይም ከምን እንለይ ?
""ከማያምኑት ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ ፤ ጽድቅ ከአመጽ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና ? ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለውና ?
ክርስቶስ ከበልሆር ጋር ምን መስማማት አለው ? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው ? ለእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ከጣዖት ጋር
ምን መጋጠም አለው ?
እኛ የሕያው የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህም ሲል፦
በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ ፤ አምላካቸው እሆናለሁ እነርሱም ህዝቤ ይሆናሉ ።
ስለዚህ ጌታ ፦ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ረኩስንም ነገር አትንኩ ይላል ፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ ፦ እኔም እቀበላችኋለሁ አባት
እሆናለሁ እናም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ"" ። 2ቆሮንቶስ 6:14-18
በመጨረሻም እግዚአብሔር በዚህ በእላቅው ዘመን ከእኛ የሚፈልገው ነገር ብኖር በቅድስናና በጽድቅ ህይወት እንድንመላለስ ነው ። ሐዋርያው
ጳውሎስ በሮሜ ለነበሩት ቅዱሳን መልዕክት ስጽፍ እንዲህ ይላል ፦
''እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ህያው ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ ፥
በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ ። እርሱም ለአዕምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው ። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ
ፍጹምም የሆነ ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህንን አለም አትምሰሉ
። ሮሜ 12:1-2