You are on page 1of 2

እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ ወዴት ነህ?

አለው።
(ዘፍጥረት 3 : 9)
ሰበዓ ሰገል የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? እያሉ
መጡ። (የማቴዎስ ወንጌል 2 : 2)
በመጀመሪያው ጥቅስ እግዚአብሄር አምላክ አዳምን ወዴት ነህ ያለበት ክፍል ስንመለከት ይህ የሰውን ልጅ ለመዋጀትና የሰው
ልጅ ከተያዘበት የሃጢያት ባርነት ለሞት ፍርሃት ከተሰጠ ህይወት ነጻ ሊያወጣን የኛን ስጋ ለብሶ በበረት ተወለደ፡፤ ይህንን
'ወዴት ነህ?' የሚለውን ጥያቄውን ራሱ ሊመልስ ከርሱ የጠፋነውን ጠላቶች የሆንነውን ሊዋጀን በበረት ተወለደ። መወለዱን
ከምስራቅ ለሆኑ ጠቢባን ገልጦላቸው ይህ የአይሁድ ንጉስ የተባለለት ሕጻን ወደሚገኝበት በኮከብ እየመራ ከሩቅ ምድር
መጥተዋል። ከማቴዋስ ወንጌል ምእራፍ ሁለት እንደምንረዳው ወደሁለት አመት ያህል ሆኖአቸዋል ይህንን ኮከብ ካዩ ማለት
የዚህ ሕጻን መወለድ ከሰሙ። ይህንን ኮከብ እየተከተሉ ረጅም መንገድ፡ተጉዘዋል ። በዚህ በማቴዎስ 2:2 ላይ ግን እነዚህ
በኮከብ በድንቅ ያለምንም ጥርጥር እየተመሩ የነበሩ ጠቢባን የራሳቸው በሰው ስሌት የሚያስበው አእምሮአቸው ቀድሞ
የኮከቡን ምሪት የት ደረጃ ላይ እንደጣሉት ባናውቅም የተወለደው ሕጻን የአይሁድ ንጉስ ነው በሚል የአይሁድ ከተማ ውስጥ
ገብተው 'ወዴት ነው?" ብለው መጠየቅ ጀመሩ።
ለረጅም ጊዚ ሲመራቸው ከነበረው ምሪት ወጥተው በአእምሮ በመመራት ይህንን ጥያቄ ሲያነሱ በከተማው ግራ መጋባትን
መናወጥን አስከትለዋል። እነዚህን ከነበረው ከሚመራቸው ኮከብ ሕጻኑ እስካለበት ድረስ የሚመራቸው ኮከብ ጋር በድጋሚ
የተገናኙት በትንቢት ተጽፎ በተገኘው መሰረት ሄሮድስ ወደቤቴልሄም መሄጃውን መንገድ ሲያሳቸው ነው፡
"እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው
ነበር።ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።(ቁ.9-10)

‘ወዴት ነህ?’ ብሎ ፈላጊ አምላክ ወደምድር መጥቶ ለነዚህ ሰዎች በአስተማማኝ የሚመራ ኮከብ አዘጋጅቶ ወደሚፈልጋቸው
ጌታ ሊያደርሳቸው እንደሚችል የብዙ ቀናትና ሌሊቶች ልምድ ያላቸው ቢሆንም በድንገት በአእምሮ ጉልበት ከምሪቱ ውጪ
ወጥተው ባልተላኩበት መስክ በከተማ ገብተው እስከቤተመንግስት ድረስ ጥያቄያቸው ቢደርስም በናፍቆት ሊያዩት ቀርቶ
ወይም ደስታቸውንና ጉጉታቸውን የሚጋራ ሳይሆን መወለዱን ምንም ያላወቀ ጭራሽ ሕጻኑን ለመግደል የሚፈልግ ጠላት
እንዲንቀሳቀስ ምክንያት ሆኑ።
በራሳቸው ስሌት የጠፋባቸው ምሪት እንደገና የተገኘው ተወለደ የተባለውን ሕጻን ለመግደል የሚፈልገው ሄሮድስ ራሱ
ጠቢባንን ሰብስቦ መጻሕፍት መርምረው በተገኘው ትንቢት ነበር። ይህ የቃሉ ብርሃን መሪ ሆኖ ራሱ ክፉው ሄሮድስ
የቤተልሄም መንገድ አመላከታቸው። ያ ጠፍቶባቸው የነበረው ኮከብ እንደገና ባዩ ጊዜ “በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው”።
እስከመጨረሻ ሊመራቸው የቻለ እሱ ነው። ደግሞም መራቸው አደረሳቸው።
በዚህ ዘመን በኛ ሁናቴ እንዲህ እማራለሁ፡
• ወዴት ነህ ብሎ ፈላጊ አምላክ ዛሬም ይፈልገናል።
• በእርግጥ እስከፍጻሜ ሊመራን መንፈሱን ሰጥቶናል እሱ ወደእውነት ሁሉ የሚመራን አምላክ መንፈስ ቅዱስ አለ።
• አእምሮአችን በጣም አደገኛ የመንፈስ ቅዱስ ምሪት እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል እና ሁልጊዜ ሊታደስ
እንደሚገባው
• እግዚአብሄር ቸር ስለሆነ ጠላት የተባለውን እንኳ እኛ ያጠፋነውን ምሪት እንደገና እንድናገኝ ለበጎ ሊለውጠው
እኛንም ወደትክክለኛውና ፈቀቅ ካልንበት አካሄድ ወደመንፈሱ ምሪት ሊመልሰን እንደሚራራልን ተምሪያለሁ።
በመጨረሻ ግን እነሱ ከተነሱበት ምሪት ወጥተው በከተማ ስለተወለደው የአይሁድ ንጉስ ሲጠይቁ በቤተልሄም ላይ ትልቅ
አደጋ በቁጠር 19 እንደተጻፈው ይህ ክፉ ነገር ሄርድስ አደረገ፡ -
‘’ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ
ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥
ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።’’
ይህ የሆነው እነሱ ከምሪቱ ወጥተው የነበራቸውን መረዳት ለማይገባው በማይገባው ስለተናገሩ ነው። ምናልባት ኮከቡን
እየተከተሉ ሆነው ቢሆን ይሄ ሁሉ ሕጻን ባላለቀ ነበር። በኛ ዘመን -
• ለብዙ አመታት ሲመራን ከነበረው ከመንፈስ ቅዱስ ምሪት ወጥተን እሱ በሌለበት ‘ወዴት ነው?” እያልን
የምንጠይቅ በንስሃ ወደሱ እንመለስ። ዳግም ሊመራን በቃሉና በመንፈሱ ቢያስፈልግ ጠላት የሆኑ ሰዎችን መሳሪያ
እያደረገ አስተማማኝ ወደሆነው ወደምሪቱ ሊመልሰን የታመነ ነው።
• እኛ የከበረው የእግዚአብሄር ነገር መነገር የሌለበትና መስማት በሌለባቸው ሰዎች ፊት በሶሻል ሚዲያ ሁሉ ሳይቀር
አውጥተን ያዝረከረክነው የከበረው ምስጢር በሕዝብ ላይ መከራ እንዲመጣ ምክንያት የሆንን ንስሃ እንግባ።
የነዚህ ከሁለት አመት በታች ያሉ ሕጻናት መሞት እነዚህ ጠቢባን ማለትም እግዚአብሄር ከሰጣቸው ምሪት
ወጥተው በሳቱት ስህተት ነው።

Berhe Woldu Gebru


03 January 2022
London UK

You might also like