You are on page 1of 2

አላህ፣ መሃመድ እና እርግማን

እኛ ክርስቲያኖች የምንኖርበት አዲሱ ኪዳን ከአፋችን ከንቱ ነገር እንዳይወጣና በአንደበታችን ተራግመን እንዳንረክስ መጽሃፍ ቅዱስ
ያዘናል (ኤፌ 4፡29፣ ያዕ 3፡9-10)። ኢየሱስም ሰዎች ባልተቀበሉት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ከአፋቸው “እሳት ይውረድባችሁ” የሚል
እርግማን ለማውጣት ሲጋበዙ እንደገሰጻቸው ሉቃ 9፡55 ላይ እናነባለን። ከዚህም ባለፈ “የሚያሳድዷችሁን መርቁ እንጂ አትርገሙ”
በማለት መጽሃፍ ቅዱስ ቀጥተኛ መመሪያ ይሰጣል። ስለዚህ ክርስቲያን ቢራገም ሃጢአት ይሆንበታል።

እስልምና ግን ለመሃመድና ለአላህ ያልተገደበ የመራገም መብት ሰጥቶአቸዋል። መሃመድ ቤተሰቦቿ የሞቱባትን ትንሽ ልጅ ጨምሮ ሰዎችን
ይራገም እንደነበረ፤ ከመራገሙም በላይ በስህተት ቢራገም እንኳን ይቅርታ መጠየቅ እንደማይጠበቅበት እስልምና ያስተምራል። እስቲ
አብረን እንዝለቅ፡

አይሻ እንደተረከችው በአንድ ወቅት ሁለት ሰዎች ወደ መሃመድ መጥተው ምን እንደሆነ ያልተረዳችውን ወሬ ማውራት ሲጀምሩ
መሃመድ በብስጭት ሰዎቹን ረግሞ ያባርራቸዋል።

Aisha reported that two persons visited Allah’s Messenger (may peace be upon him) and both of them
talked about a thing, of which I am not aware, but that annoyed him and he invoked curse upon both of
them and hurled malediction, and when they went out I said: Allah’s Messenger, the good would reach
everyone but it would not reach these two. He said: Why so? I said: Because you have invoked curse and
hurled malediction upon both of them. He said: Don’t you know that I have made condition with my
Lord saying thus: O Allah, I am a human being and that for a Muslim upon whom I invoke curse or hurl
malediction make it a source of purity and reward.
(Sahih Muslim Book 32, Hadith Number 6285.)

ለምን እንደተራገመ ያልገባት አይሻም ወደ መሃመድ ገብታ ብትጠይቀው እንዲህ የሚል መልስ ሰጣት፡

“ከአላህ ጋር እንዲህ የሚል ቃል እንዳለኝ አታውቂምን?፡ አላህ ሆይ እኔ ሰው ነኝና በሙስሊም ላይ የማይገባውን እርግማን ከተራገምኩ
የንጽህና እና የሽልማት ምክንያት አድርገው”

ተመልከቱ! ተሳስቶ ቢራገም እንኳን አላህ ወደ ባርኮት እንዲቀይረው ከአላህ ጋር ቃል ስላለው መሃመድ ተሳስቶ የማይገባውን ሰው
ቢራገም እንኳን ይቅርታ መጠየቅና ንሰሃ መግባት አይጠብቅበትም፤ የመራገም ያልተገደበ ነጻነት ይሏል ይህ ነው። ይህ ነጻነቱ ደግሞ
ቤተሰቧ የሞተባትን ትንሽ ልጅ እድሜሽ ይጠር ብሎ እስከመራገም አድርሶታል፤ እነሆ ማስረጃው፡

በሌላ ሃዲስ ላይ መሃመድ አንዲት ወላጇን በሞት ያጣች ትንሽ ልጅ አግኝቶ “አትደጊ” ብሎ እንደረገማትና ልጅቷም እያለቀሰች በመሄድ
ለሱለይም እናት “የአላህ መልእክተኛ አትደጊ ብለው ረግመውኛልና ከዚህ በኋላ አላድግም” ብላ እንደተናገረች፤ ሴትየዋም ነገሩን
ለማጣራት እንደሄደች እናነባለን። ይህች ሴት መሃመድን “ልጄ እንደረገሟት ነገረቺኝ” ብላ ስትጠይቅ ያገኘችው መልስ ግን
ሳያስደነግጣት አልቀረም፤ መሃመድ የመለሰው ልክ እንደላይኛው ሁሉ በሚከተለው መልኩ ነበር፡

“ጌታዬ ሆይ ሰው በመሆኔ እንደሰው እደሰታለሁ፣ እንደ ሰውም እበሳጫለሁና ከኡማዬ መሃል ሳይገባው የምረግመውን ሰው በትንሳኤ ቀን
የንጽህና እና ወደ አንተ የመቅረቢያ ምክንያት አድርግለት የሚል ቃል ከአላህ ጋር እንዳለኝ አታውቂምን?” (ሳሂህ ሙስሊም 2603)

እንግዲህ መሃመድ ተሳስቶ ሙስሊሞችን (ትንንሽ ልጆችን ጨምሮ) ቢራገም ሃጢአት የለበትም፤ አላህ ዋስ ይሆንለታልና የተረገመውን
ሰው ይቅርታ መጠየቅ እንኳን አይጠበቅበትም። በርግጥ መሃመድ በሞት አፋፍ ላይ ሳለ እንኳን ከአፉ የወጣው ቃል ክርስቲያኖችን እና
አይሁድን እየተራገመና አላህም እንዲረግምለት እየተመኘ ነበር።

When the last moment of the life of Allah's Messenger (‫ )ﷺ‬came he started
putting his 'Khamisa' on his face and when he felt hot and short of breath he
took it off his face and said, "May Allah curse the Jews and Christians for
they built the places of worship at the graves of their Prophets." The Prophet
(‫ )ﷺ‬was warning (Muslims) of what those had done. (Sahih al-Bukhari 435,
436)

መሃመድ ለእርግማን የአላህን ትብብር የጠራው ለምንድነው? ብትሉ አላህም በተመሳሳይ የመራገም ባህርይ ስላለው ነበር። ይህንን
ለምሳሌ ሱራ 4፡155 ላይ አይሁዳውያንን ሲራገም እናገኘዋለን፤ በቀጣይም ሱራ 2፡65 ላይ አላህ አይሁዳውያንን ሰንበትን
ባለመጠበቃቸው ዝንጀሮ እስከሚሆኑ ድረስ እንደረገማቸው እንመለከታለን። ይህ ደግሞ እርግማን የመሃመድና የአላህ የወል ባህርይ
መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

የኛ ጌታ ኢየሱስ ግን በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሰቃዮቹን ከመራገም ይልቅ “የሚያደርጉትን አያውቅምና ይቅር በላቸው” ብሎ የጮኸ፣
ይህንን ምሳሌነቱን እንከተል ዘንድ “የሚረግሟችሁን መርቁ” ብሎ ያስተማረ፣ ደግሞም ስለ አሳዳጆቹ ሳይቀር ራሱን አሳልፎ የሰጠ ድንቅ
ጌታ ነው። ሙስሊሞች ሆይ ወደዚህ ጌታ መጥታችሁ ህይወታችሁን ታተርፉ ዘንድ ግብዣዬ ነው።

✍️ሞኖጌኔስ

You might also like