You are on page 1of 71

፡-

0
ማ ው ጫ

ምዕራፍ አንድ ........................................................................................................................................... 5


የወንጀል ህግ ምንነት፣ ዓላማውና ህገ መንግስቱ.............................................................................................. 5
የምዕራፉ አላማዎች ....................................................................................................................................... 5
1. የወንጀል ህግ ምንነት እና አላማው .......................................................................................................... 5
ወንጀል ምን ማለት ነው? ................................................................................................................................ 6
የወንጀል ህግ አላማና ግብ ............................................................................................................................... 7
የወንጀል ህግ አላማ......................................................................................................................................... 8
የወንጀል ህጉ ግብ............................................................................................................................................ 8
የወንጀል ህግ ከሌሎች ህጐችና ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች የሚለይበት ሁኔታ ............................................... 10
የወንጀል ህግ ከሌሎች ህጐች የሚለይበት ሁኔታ .................................................................................... 10
1. በወንጀል ህግ ውስጥ ተዘርዝረው የሚገኙ የወንጀል አይነቶች ................................................... 10
2. በሁለቱም ህጐች የሚሰጠው ውሣኔ ................................................................................................. 11
የወንጀል ህግ ንፅፅር በኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች ........................................................................................... 11
የወንጀል ህጉ አላማና ግብ ከህገ - መንግስቱ ጋር ያለው ቁርኝት ........................................................... 12
የህይወት መብት .......................................................................................................................................... 13
የአካል ደህንነት መብት .............................................................................................................................. 13
የነፃነት መብት ............................................................................................................................................ 14

ምዕራፍ ሁለት .............................................................................................................................. 17


2. የወንጀል ህግ መሠረታዊ መርሆዎች ................................................................................................... 17
የምዕራፉ አላማዎች ................................................................................................................................... 17
2.1. የህጋዊነት መርህ .............................................................................................................................. 17
2.1.1. ህገ-ወጥ የተባሉ ድርጊቶች፣ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ግልፅነት፣.............................. 18
2.1.2. ፍርድ ቤት ህጉን የመተርጐም ስልጣን ...................................................................................... 19
2.2.3. አንድ ሰው በአንድ ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም............................................. 20
1
የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑ............................................................................ 21
ልዩነቶች (Exceptions) ................................................................................................................................. 23
ለተከሣሹ የሚጠቅም ከሆነ .......................................................................................................................... 23
የጥንቃቄ እርምጃዎች አፈፃፀም................................................................................................................... 25
የይረጋ ዘመን አፈፃፀም............................................................................................................................... 26
የፍርዶች አፈፃፀም...................................................................................................................................... 27
የእኩልነት መርህ ....................................................................................................................................... 29
ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ ብቻ ተጠያቂ ስለመሆኑ ............................................................................ 31

ምዕራፍ ሶስት ..................................................................................................................................... 33


በወንጀል ህግ ተጠያቂነት ....................................................................................................................... 33
የምዕራፉ አላማዎች ................................................................................................................................. 33
በወንጀል ህግ ተጠያቂነት ቅድመ ሁኔታ ............................................................................................... 33
ህጋዊ ፍሬ ነገር ..................................................................................................................................... 34
ግዙፉዊ ፍሬ ነገር .................................................................................................................................... 34
ድርጊት..................................................................................................................................................... 35
አለማድረግ ............................................................................................................................................... 35
የምክንያትና ውጤት ግንኙነት ............................................................................................................... 36
ምክንያትና ውጤትን ሊያቋርጡ የሚችሉ ጉዳዮች ............................................................................... 38
ሀ. አስቀድሞ የደረሰ (ይህ አዲስ ነው)..................................................................................................... 39
ለ. ተደራራቢ ምክንያት ........................................................................................................................... 39
ሐ. ጣልቃ የገባ ምክንያት ....................................................................................................................... 40
የሃሣብ ክፍል ......................................................................................................................................... 41
አስቦ ወንጀል ማድረግ ........................................................................................................................... 42
ቀጥተኛ የሆነ አጥፊነት ........................................................................................................................... 42
እውቀት.................................................................................................................................................... 42
ፍላጐት .................................................................................................................................................... 44
ቀጥተኛ ያልሆነ አጥፊነት ....................................................................................................................... 44
በችልተኝነት ወንጀል ማድረግ ................................................................................................................. 44
የታወቀ ቸልተኝነት .................................................................................................................................. 45
ያልታወቀ ቸልተኝነት .............................................................................................................................. 45
2
ቸልተኝነት እና ቅጣት ............................................................................................................................ 46
በህግ ሰውነት የተሰጠው አካል በወንጀል ተጠያቂነት ........................................................................... 47
የመሠናዳት ተግባሮች.............................................................................................................................. 48
የወንጀል ሙከራ ..................................................................................................................................... 49
ሀ. ፍፃሜ ያላገኘ ...................................................................................................................................... 51
ለ. ፍፃሜ ያገኘ .......................................................................................................................................... 52
የወንጀል ሙከራ ተጠያቲነት ................................................................................................................. 52
ሊፈፀም የማይቻል ወንጀል ................................................................................................................... 53

ምዕራፍ አራት ...................................................................................................................................... 55


የምዕራፉ አላማዎች ................................................................................................................................... 55
በወንጀል አፈፃፀም ላይ ተካፋይ መሆን ...................................................................................................... 55
በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ መሆን .................................................................................................. 55
ወንጀልን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መፈፀም ....................................................................................... 56
በሞላ ሃሳብና አድራጐቱ መሣተፍ ............................................................................................................. 57
በሌላ ሰው ወንጀሉን መፈፀም ..................................................................................................................... 58
በዋና ወንጀል አድራጊነት መካፈል እና ቅጣቱ ....................................................................................... 58
ሌሎች ተካፋይነት ........................................................................................................................................ 60
በልዩ ወንጀል ተካፋይ መሆን...................................................................................................................... 60
ማነሣሣት ..................................................................................................................................................... 60
የወንጀል ፈፃሚው መነሣሣት .................................................................................................................... 61
የሃሣብ ክፍል ............................................................................................................................................. 62
ወንጀሉ ቢያንስ መሞከር አለበት ................................................................................................................. 62
አባሪነት ........................................................................................................................................................ 62
የሃሣብ ክፍል ............................................................................................................................................. 63
የአባሪነት ጊዜ .............................................................................................................................................. 63
የእርዳታ አይነቶች ....................................................................................................................................... 64
የአባሪነት ውጤት ........................................................................................................................................ 64
በሰው ህይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች............................................................................................... 65
ሰው መግደል .............................................................................................................................................. 65
የዘር ማጥፋት ወንጀል .................................................................................................................................. 69
3
4
ምዕራፍ አንድ

የወንጀል ህግ ምንነት፣ ዓላማውና ህገ መንግስቱ

የምዕራፉ አላማዎች
 የወንጀል ህግ ምንነት፣ አላማውን ግቡን ይረዳሉ፣

 የወንጀል ህግ ከሌሎች ህጐች እና ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች ያለውን ልዩነት ግነዛቤ፣


ይጨብጣሉ ፣

 የወንጀል ህጉ ከህገ መንግስቱ ጋር ያለውን ትስስር ይለያሉ፣

1. የወንጀል ህግ ምንነት እና አላማው

የሰው ልጅ ሠላማዊ ህይወትን ለመምራት ከወንጀል የፀዳ ህብረተሠብ መፍጠር አለበት፡፡ ለዚህ
ደግሞ ያለው አማራጭ የወንጀል ፍትህ አስተዳደርን መዘርጋት ነው፡፡ ይህ የወንጀል ፍትህ
አስተዳደር እንዲኖር ህግ አውጭ፣ ህግ ተርጓሚና አስፈፃሚ አካላት መኖር አለባቸው፡፡ በዚሁ
መሠረት ህግ አውጪው እንደ ወንጀል አድርጐ የሚቆጥራቸው ድርጊቶች እና ተገቢ ብሎ
ያመነባቸውን ቅጣቶች ዘርዝሮ በህግ ያወጣል፤ ህግ ተርጓሚው ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው
የተከሰሱ ሠዎችን ሲቀርቡለት ማስረጃውን አዳምጦ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጣል፡፡ አስፈፃሚው
አካል በፖሊስ አማካኝነት ወንጀል እንዳይፈፀም ይከላከላል ተፈፅሞም ከሆነ ተጠርጣሪዎች ይዞ
ለፍርድ ያቀርባል፡፡ ዓቃቤ ህግ መንግስትን በመወከል ክስ ያቀርባል፡፡ ማረሚያ ቤቶች ቅጣት
የተወሰነባቸውን ጥፋተኞች ተቀብለው ያሰራሉ ሌሎች ቅጣቶችም ተወስነው ከሆነ ያስፈፅማሉ፡፡

ስለሆነም የወንጀል ህግና የወንጀል የፍትህ አስተዳደር መሠረታዊ አላማዎች የወንጀል


አይነቶችን አስቀድሞ በማሣወቅ የአንድ ህብረተሠብ አባላት ይህንን አውቀው ከጥፋት
እንዲታቀቡ ማድረግና ይህን ማስጠንቀቂያ በማይከተሉ ላይ ቅጣት መፈፀም ናቸው፡፡ በዚህም
መሠረት የወንጀል ህግ የተለያዩ የህብረተሠብ አባላት ማለትም ሰዎች ከሠዎች ወይም
ከቡድኖች ወይም ከመንግስት ጋር ያላው ግንኙነት ይወስናል፡፡ በህግ እውቅና በተሠጠው

5
ግንኙነት መሠረት ድርጊታቸውን ማስተካከል የሚችሉ ህጉ ተፈፃሚ የማይሆንባቸው ሲሆን
ይህን ማድረግ የማይቻላቻው በህጉ መሠረት ይዳኛሉ፡፡

ኢትዮጵያ ከላይ የተጠቀሰውን አላማ ለማሣካት በተለያዩ ጊዜያት የወንጀል ህጐች ድንግጋ
በተግባር ላይ አውላለች፡፡ በ1923 ዓ.ም የተደነገገው ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ የዋለው
የወንጀል ህግ ነው፡፡ 1949 ዓ.ም የወጣው ደግሞ ሁለተኛውና ከ40 ዓመት በላይ በስራ ላይ
የነበረ የወንጀል ህግ ነው፡፡ በየመሃሉም ተጨማሪና ያለውን ከፍተት ሊሞሉ የሚችሉ ህጐች
በስራ ላይ ነበሩ፡፡

ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ ከ1949 ዓ.ም ጀሞሮ በስራ ላይ


የነበረውን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ በመተካት ከግንቦት 1 ቀን 1997 ዓ. ም ጀምሮ በተግባር ላይ
ውሏል፡፡ በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 52(5) ላይ በተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት መሠረት
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣ ነው፡፡ ይህ የወንጀል ህግ ህብረተሠቡን በጉዳት ለመጠበቅ
የወጣና እንደ ወንጀል የሚቆጠሩ ድርጊቶችና ለነዚህ የተከለከሉ ድርጊቶች ተገቢ ተብለው
የተዘረዘሩ ቅጣቶችን የሚዘረዝር ህግ ነው፡፡ ስለሆነም ቅጣት እና ወንጀል ሁለቱ የወንጀል ህግ
መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ወንጀል ምን ማለት ነው?

ወንጀል ምን ምን አይነት ባህሪያትን ያካትታል ብሎ ቋሚና አለም አቀፋዊ ትርጉም ለመስጠት


ያስቸግራል፡፡ ወንጀል የሚባሉት ባህሪያት ከማህበረሠብ ማህበረሰብ ይለያያሉ፡፡ ማህበረሠቡ
ሲያድግ ይለወጣሉ፡፡ ስለሆነም በዛሬ ጊዜ ወንጀል ተብሎ የተደነገገ ድርጊት ወይም ያለማድረግ
ከዚህ በፊት ወንጀል ላይሆን ይችላል፡፡ ወይም ከዚህ በፊት ወንጀል ተብሎ የተደነገገ ጉዳይ ዛሬ
ወንጀል ላይሆን ይችላል፡፡

የወንጀል ህግ ህግ እና ቅጣቶቹ በአብዛኛው የአለማችን ሃገሮች በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ


ተመሣሣይነት ቢኖራቸውም በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ሊለያዩ ይችላሉ፡፡ እንዲህ አይነት ልዩነት
ሊፈጠር የሚችለው የተለያዩ ሃገሮች ህዝቦች በተወሰኑ ጉዳዮች ያላቸው የአመለካከት ልዩነት
ነው፡፡ ይህ ልዩነት ሃይማኖት ከባህል በስልጣኔ እድገት በሰው ልጆች መብት አጠባበቅ ብለው
አስተሣሠብ ሊመነጨ ይችላል፡፡ በዚሁም መሠረት የአልኮል መጠጦችን ማዘዋወር፣ ዝሙት
6
አዳሪዎች፣ ግብረሰዶም፣ ፅንስ ማስወረድ የመሣሠሉት ድርጊቶች በአንዳንድ ሃገሮች የወንጀል
ድርጌት ተብለው ክልከላ ተደርጐባቸው ግርፋት ወይም የሞት ቅጣት የመሣሠሉትን
ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ በሌሎች ሃገሮች ግን ይሄንኑ ተመሣሣይ ድርጊቶች ያልተከተሉ ወይንም
በወንጀል ህግ የማያስጠይቁ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ሆኖም ግን በሠፊው ተቀባይነት ያገኘው
ትርጉም የሚከተለውን ይመስላል

ወንጀል ማለት ፡- በወንጀል ህግ የተከለከሉ ድትጊቶችን መፈፀም ወይም እንዲፈፀሙ ትዕዛዝ


ወይም ግዴታ የተጣለበቸውን ድርጊቶች አለመፈፀም ነው፡፡

በዚህ መሠረት የወንጀል ህጉ ኃላፊነትን የማያስከትል ተግባር የፈፀሙ ሠዎች በወንጀል


እንዳይጠቁ ማድረጊያና ወንጀል የፈፀሙ ቢሆንም እንኳን በህጉ ላይ ከተመለከተው ቅጣት
ውጪ በዘፈቀደና ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንግድ እንዳይቀጡ መከላከያ መሣራያ ነው፡፡

የወንጀል ህግ አላማና ግብ

የወንጀል ህጉ አንቀፅ 1 ሁለት ፓራግራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው አላማውን ሲገልፅ


ሁለተኛው ግቡን ያብራራል፡፡

አ ንቀ ፅ 1

የወንጀል ሕግ ዓላማ፣ ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግሥት፣ የሕዝቦቹን፣


የነዋሪዎቹን፣ ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው፡፡

የወንጀል ሕግ ግብ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው


ስለወንጀሎችና፣ ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ ማስጠንቀቂያነቱ
በቂ ባልሆነበት ጊዜ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም
እንዲቆጠቡና ለሌሎች ማስተማሪያ እንዲሆኑ ወይም እንዲታረሙ በማድረግ ወይም
ተጨማሪ ወንጀሎች እንዳይፈፅሙ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው በማድረግ ነው፡፡

7
የወንጀል ህግ አላማ

የወንጀል ህግ አላማ ከፍ ብሎ በተቀመጠው አን ቀ ፅ 1 የመጀመሪያው ፓራግራፍ


እንደተመለከተው የሃገሪቱ መንግስት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን፣ ሰላም ደህንነት ስርዓት
መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ ነው ይላል፡፡ ይህ ህጉ በመጨረሻ ሊደረስበት ያስበውን
አላማ ያመለክታል ስለዚህም የወንጀል ህጉ አላማ አጠቃላይ ህብረተሠቡን ከወንጀል ድርጊቶች
መጠበቅና ሰላምን ማረጋገጥ ነው፡፡

በአንቀፁ የተገለፀው “ህዝቦች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ህገ መንግስቱ ለብሔር


ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ከፍተኛ ጥበ ቃ ያደረገላቸው በመሆኑ የወንጀል ህጉ ይህንን
ሊያንፀባርቅና ህጉ ነዋሪዎቹ በግለሰብነታቸው ብቻ ሣይሆን በልዩ ልዩ ህብረት በተቋቋሙበት
ሁኔታ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ነው፡፡ በተጨማሪም ዜጐቹንም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ
የሚገኙትን የውጭ ሃገር ሰዎች ስለሚያጠቃልልና ወንጀል ህግ ጥብቃ የሚያደርገው ለሰዎች
ሁሉ ስለሆነ “ዜጐች” ተብሎ በቅድሞው ህግ ተገልፆ የነበረው ነዋሪዎች በሚለው ተተክቷል፡፡

የወንጀል ህጉ አላማ የነዋሪዎቹን ሰላም ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህ በግልፅ የሚያመለክተው


ከግለሰቦች መብት ይልቅ የህዝቦች መብት ቅድሚያ እንደተሠጠው ነው፡፡ ስለሆነም አንድ
የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም በህብረተሠቡ አጠቃላይ ጥቅም ላይ ጉዳት ደርሷል ተብሎ
ይገመታል፡፡ በዚህም መሠረት የህዝብ ስርዓት ፣ ሰላምና ፀጥታ ሊጠበቅ የሚችለው የግለሰቦች
መብት ሲጠበቅ በመሆኑ በእነዚህ መብቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት በህዝብ ጥቅም ወይም መብት
ላይ እንደተፈፀመ ወንጀል ይቆጠራል፡፡

የወንጀል ህጉ ግብ

በአንቀፅ 1 ፓራግራፍ ሁለት ላይ እንደተመለከተው ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል የወንጀል


ህጉ ግብ ነው፡፡ ይህንን ለማሣካትም የተለያዩ ስልቶችን በተግባር ያውላል፡፡ በዚህም ህብረተሠቡ
የተለያዩ መብቶቹ ይጐዳሉ ብሎ የሚያምንባቸውን ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ወንጀሎችንና
ቅጣታቸውን በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡

የወንጀል ህጉ እንዱ ግብ ማስጠንቀቅ የሆነበት ምክንያት ህግ በሌለበት ቅጣት ስለማይኖር


አስቀድሞ ህጉን በማውጣት ማስጠንቀቅ ይገባል፡፡ የወንጀል ህግ መሠረታዊ መርህ ስንመለከት
8
በአንቀፅ 2 ላይ በህጉ ተለይቶ ወንጀል ነው የልተባለ ጉዳይ እንደ ማያስቀጣና በወንጀል ህጉ
አንቀፅ 5 ደግሞ የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ሄዶ እንደማይሰራ መግለፁ ማስጠንቀቅ የወንጀል ህግ
ግብ መሆኑን ያስረዳል፡፡

ማስጠንቀቂያ ብቻውን የህጉን አላማ ማሣካት ካልቻለ አጥፊው በጥፋቱ ልክ እና ህጉ


ባስቀመጠው መሠረት ይቀጣል፡፡ የህጉ ግብ አጥፊዎቹን ማረምና ሌላውን ማስተማር ነው፡፡
“አጥፊ ሲቀጣ የሚያየው ብልህ የሆናል”፡፡ እንደተባለው ሁሉ ለሌላው አጥፊ ትምህርት
እንዲሆነው ነው፡፡

አንቀፅ አንድ ፓራግራፍ ሁለት ላይ የተመለከተው “ወንጀል መከላከል” የሚለው ቃል


የሚያመለክተው የሚከተሉትን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ነው፡፡

 የመንግስት የአገርና የአለም አቀፍ ጥቅሞች (ሶስተኛ መፅሃፍ አንቀፅ 238-374)

 የህዝብና የማህበረሰብ ጥቅም (አራተኛ መፅሃፍ አንቀፅ 375-537)

 የሰው ህይወት አካል እና ጤንነት፣ ነፃነት እና ክብር (አምስተኛ መፅሃፍ አንቀፅ 538-
661)

 የንብረት መብት ጥቅም (ስድስተኛ መፅሃፍ አንቀፅ 662-733)

በተጨማሪም የወንጀል ህጉ ሶስተኛ ታላቅ ክፈል የደንብ መተላለፍ ወንጀሎችን እና


ቅጣታቸውን ይዘረዝራል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ጥበቃ የተደረገላቸው

 የህዝብና ማህበሪዊ ጥቅሞች (መፅሃፍ ስምንት አንቀፅ 776-837)

 የሰዎች እና የንብረት ጥቅሞች እና መብቶች ናቸው ( 838-865)

ስለሆነም የወንጀል ህጉ አላማውን ለማሣካት ሁለት አይነት ስልቶችን እንደሚከተል ያሣየናል፡፡


በመጀመሪያ ወንጀል እንዳይፈፀም ማስጠንቀቂያ መስጠት ይህም ማለት ከላይ እንደታየው
ጥበቃ የተደረገላቸውን መብቶችና ጥቅሞች ዘርዝሮ ማስቀመጥ፡፡ ይህ ካልተሣካ አጥፊውን ህጉ
በሚያዘው መሠረት መቅጣት ናቸው፡፡

9
የወንጀል ህግ ከሌሎች ህጐችና ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች የሚለይበት ሁኔታ

የወንጀል ህግ ከሌሎች ህጐች የሚለይበት ሁኔታ

ማንኛውም ግለሰብ በህግ ሠውነት የተሰጠው አካልም ሆነ የተፈጥሮ ሰው በህግ የተከለከለን


ድርጊት ከፈፀመ ወይም ህግ እንዲፈፅም ግዴታ የጣለበትን ጉዳይ ካልፈፀመ የሌሎች
ግለሰቦች ወይም በአጠቃላይ የማህበረሰቡን መብት ሊጐዳ ይችላል፡፡፡ እነኝህ ግድፈቶች ወይም
ስህተቶች በግለሰብ ወይም በአጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ቢታወቅም
የወንጀል ድንጋጌዎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ስህተቶችና እና የሚያስከትሉ አደጋ አጠቃላይ
በህብረተሰቡ ላይ እንደተፈፀሙ ይታሰባል፡፡ ይህ ከላይ እንደተገለፀው የወንጀል ህግ ከሌሎች
ህጐች የሚለይበት መሠረታዊ ባህሪይ ነው፡፡ ይሄንንና ሌሎች ልዩነቶቹን ቀጥለን ዘርዘር
አድርገን እንመለከታለን፡፡

1. በወንጀል ህግ ውስጥ ተዘርዝረው የሚገኙ የወንጀል አይነቶች

ቢፈፀሙ ወይም ቢሞክሩ ህብረተሠቡን የሚጐዱና አንድን ህብረተሠብ በህበረተሠብነት


እንዳይቀጥል ስለሚያደርጉት መንግስት የህዝቡን ሠላምና መረጋጋት የመጠበቅ ሃላፊነት
ስላለበት አጥፊውን በዐቃቤ ህግ በኩል ክስ መስረቶ ማስረጃ አቅርቦ አጥፊውን ያስቀጣል፡፡ ይህ
ሂደት የተጐጂ ቤተሠቦች ወይም ተጐጂው ራሱ ለደረሰበት ጉዳት ካሣ ቢሰጠውም የሚቀጥል
ነው፡፡ ለምሣሌ፡- ግድያና አስገድዶ መድፈር ዘረፉ የመሣሠሉት በወንጀል ህጉ መሠረት
የተከለከለና ተፈፅመው ከተገኙ ፈፃሚው ተጠያቂ እንደሚሆን በግልፅ ተቀምጧል፡፡ እነኚህ
ድርጊቶች ያደረሱት ጉዳት በግለሰብ ላይ ቢሆንም በወንጀል ህጉ መሠረት ህብረተሰቡን የሚጐዱ
ተደርገው ይታያሉ፡፡ ዓቃቤ ህግም የወንጀል ህጉ በግልፅ አቤቱታ የማቅረብ መብቱን ለግል
ተበዳዩ ካልሰጠ በስተቀር ተገቢውን ማስረጃ አስባስቦ ወንጀል የፈፀመውን ሰው ፍርድ ቤት
አቅረቦ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡

1. በፍትሐብሔር ህግ መሠረት ግን ተከራካሪዎች ወይም በህጉ መሠረት የተቀመጠልኝ


መብት ተጥሷል የሚል ግለሰብ ጉዳዩን ወደ ህግ ያቀርባል እንጂ መንግስት በወንጀል

10
እንዳየነው ግለሰብን ወክሎ በፍትሐብሔር ጉዳይ አይከራከርም፡፡ ምክንያቱም የፍትሐብሔር
ክርክር በግለሰቦች መከላከል የተፈጠረ አለመግባባት ነው፡፡

2. በሁለቱም ህጐች የሚሰጠው ውሣኔ

በወንጀል ህግ የተደነገገውን ተላልፎ የተገኘ ሰው የሚጣልበት ቅጣት የተለያዩ መሠረታዊ


መብቶቹን ሊነኩ ይችላሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ በዓቃቤ ህግ በኩል የቀረበለትን ማስረጃ ከሠማ
በኋላ ጥፋተኛ ሆኖ ካገኘው ቅጣት ይጥላል፡፡ እነኝህ ቅጣቶች የመንቀሣቀስ እና በነፃ
የመዘዋዋር መብትን የሚቃረኑ ሊሆኑ ይችላሉ ለምሣሌ እስር ወይም በህይወት የመኖር
መብትን ሊጥሱ ይችላሉ፡፡ ጥፋተኛው የሞት ቅጣት ቢጣልበት ትልቁና ዋጋ የሌለውን
መብቱን ያጣል፡፡ በፍትሐብሔር ክርክር የመጨረሻው ውሣኔ ግን የወሰደው ንብረት
እንዲመልስ ወይም ካሣ እንዴከፈል ማድረግ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከንብረት ጋር የሚያያዝ
እንጂ የተከሣሹን መሠረታዊ መብቶች የሚነኩ አይደሉም፡፡ ሰለሆነም በወንጀል ተጠያቂነት
የሚወሰኑ ቅጦቶች ከባድና ምናልባትም እጅግ አስከፊ ሲሆኑ በፍትሐብሔር የሚወሰኑት
ግን በተነፃፃሪነት ቀላል ናቸው፡፡

የወንጀል ህግ ንፅፅር በኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አንድ ድርጊት ወይም ያለማድረግ እንደ ወንጀል የሚቆጠረው
ህግ አውጭው በግልፅ ጉዳዩን ወንጀል መሆኑን ሲደነግግ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን ጥሩም ሆነ
መጥፎ ሞራላዊ እሴቶች ምንጫቸው ሃይማኖት ወይም ከውስጥ በሚመነጭ የማክበር ሰሜት
ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሃይማኖታዊ ግበረ-ገብነት ሊመነጭ የሚችለው ግለሰቡ ለሃይማኖቱ መርሆች
ያለው መንፈሣዊ አመለካከት ነው፡፡ ግብረ-ገብነት ቤተሠብን፣ ታላላቆችን፣ አለቆችን እና
አመለካከቶችን በማክበር ሊመነጭ ይችላል፡፡ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እንዳሚታየው
የቤተሠብ አመለካከትን ማክበር፣ ታላላቆች የሚሉትን መፈፀም ምንጩ ለጉዳዩ የሚሰጠው
ጥልቅ ስሜት ነው፡፡

መሠረታዊ ልዩነታቸው የሚታየው ሁለቱ በተግባር በሚውልበት ጊዜ ነው፡፡ የወንጀል


ተጠያቂነት የህግ አውጭው አሣብና አላማ መሠረት ያደረገ ጠንካራና መደበኛ ቅጣት አለው፡፡

11
የግብረገብ ወይም ሞራላዊ እሴቶች ሊኖሩና ሊቀጥሉ የሚችሉት ህብረተሠቡ የሚሰጣቸው
ክብር እና ጥልቅ ስሜት እንጂ መደበኛ ተጠያቂነትን ስለማያስከትሉ አይደሉም፡፡

ለምሳሌ፡- በወንጀል ህጉ ያስቀጣል ተብሎ የተደነገገውን የተላለፈ ቅጣት ይከተለዋል፡፡ ሆኖም


ግን በህብረተሠቡ ውስጥ የታላቅን ምክር መስማት ወይም ሠላምታ ከጐረቤት ጋር መወዋወጥ
እንደ ጥሩ ባ ህሪ መለኪያ ቢቆጠርና አንድ ሰው እነኚህን ቢተላለፍ መደበኛ ቅጣት
አይከተለውም፡፡ ሞራላዊ አሴቶች በተግባር የሚውሉት በግለሰቡ መልካም ፍቃድ ነው፡፡ መደበኛ
ቅጣት የላቸውም፡፡

የወንጀል ህጉ አላማና ግብ ከህገ - መንግስቱ ጋር ያለው ቁርኝት

ህገ - መንግስት በዜጐችና በመንግስት መካከል የሚኖረውን ግንኙነት የሚወስን ህግ ነው፡፡ ህገ


መንግስት የመንግስትን ስልጣንና የዜጐችን መብትና ነፃነት ለይቶ የሚደነግግ ሰነድ ነው፡፡
በአንቀፅ 9 (ዘጠኝ) ላይ እንደተመለከተው ህገ መንግስቱን የሚቃረን ማንኛውም ህግ ልማድ
እንዲሁም መንግስታዊ ውሣኔ ተፈፃሚነት የለውም፡፡ የአንድ አገር ዜጐች በአንድ መንግስት
ጥላ ስር ሲተዳደሩ ምን መብት ምንስ ግዴታ ይኖራቸዋል? የመንግስትስ ስልጣንና ተግባር
ምንድን ነው? መንግስትስ ስልጣንና ተግባሩን የሚያከናውነው በምን አኳኋን ነው? እነዚህን
አበይት ጉዳዮች በህገ መንግስቱ ተለይተው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ህገ መንግስት በበታች ህጐች
ልማዷች ወይም አሰራሮች የሚጣስ ከሆነ የዜጐች መብትና ግዴታ የመንግስት የሰልጣን ገደብና
የአሰራር ዋስትና አጡ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ (1) “ህገ መንግስት
የበላይ ህግ ነው” በማለት የደነገገው፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወንጀል ህግ እንዲያወጣ በህገ መንግስቱ


ስልጣን በተሠጠው የመንግስት አካል ፀድቆ ከግንባት 1 ቀን 1997 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ላይ
የዋለ ህግ ነው፡፡ ይህ ህግ የህጐች ሁሉ የበላይ የሆነው ህገ መንግስት መሠረት አድርጐ
የተዘጋጀ ነው፡፡ የወንጀል ህጉ አለማና ግብ በህገ መንግስቱ ላይ የደነገጉትን የሰብአዊና
ዲሞክራሲያዊ መብቶች በማስከበር ዙሪያ ከፍተኛ ሚና አለው እያንዳንዱ ዜጋ ወይም
የመንግስት አካል በህገ መንግስቱ ላይ የተጣለውን ግዴታ ካልተወጣ እና ከጣሰ የወንጀል ህጉ
አስፈላጊውን ምላሽ ይሰጣል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ህገ መንግስቱ እና የወንጀል ህጉ ያላቸውን ትስሰር
በዝርዝር እንመልከታለን፡፡
12
የህይወት መብት

በህገ መንግስቱ አንቀፅ 15 መሠረት ማንም ሰው በህይወት የመኖር መብት አለው ማንኛውም
ሰው የሌላውን ሰው ህይወት ያጠፋ እንደሆነ በወንጀለኛ ህግ ይቀጣል፡፡ በአንቀፅ 15 ስር
የተደነገገው በህይወት የመኖር መብት አለው ሲል መንግስት በማናቸውም ምክንያት የሰውን
ህይወት ሊያጠፋ አይችልም፡፡ ይህ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ሰው ህይወቱን ሊያጣ የሚችልበት
ሁኔታ ይኖራል መንግስት የሰው ህይወት ሊያጠፋ የሚችለው የሚከተሉትን መሠረት አድርጐ
ነው፡፡

ሀ. ሰውዬው ከባድ የወንጀል ጥፋት የፈፀመ እንደሆነ፣

ለ. የፈፀመው ወንጀል የሞት ቅጣት የሚያስከተል መሆኑ በህግ የተደነገገ ከሆነ እና

ሐ. ጥፋቱ በህግ በተቋቋመ ነፃ አካል በማስረጃ የተረጋገጠ ከሆነ ነው፡፡

በዚህ መሠረት አንድ ሰው ለሞት ቅጣት የሚያደርሰው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ


ሪፐብሉክ የወንጀል ህግ የተደነገገ ከባድ የወንጀል ጥፋት ሠርቶ ሲገኝ እና ሲረጋገጥ ሰልጣን
የተሰጠው ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት እርምጃ ይወስዳል፡፡

የአካል ደህንነት መብት

ከላይ በተመለከትነው አንቀፅ 15 መሠረት ሰው በህግ ድንጋጌና በፍርድ ቤት ውሣኔ መሠረት


በህይወት የመኖር መብቱን የሚያጣበት ሁኔታ አለ፡፡ ከታች በ አን ቀ ፅ 17 መሠረት
እንደምናየው ሰው በህግ መሠረት የነፃነት መብት ሊገደብ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በአንቀፅ 16
መሠረት ሁሉም ሰው በማንኛውም ህግ መሰረት የአካለ ደህንነት መብቱ ሊደፈር አይችልም፡፡
ማንኛውም ሰው በቅጣት ይሁን በምርመራ በሰውነቱ ላይ ማናቸውም ቅጣት ሊደርስበት
አይችልም፡፡ ይህ ፈፅሞ የሚከለከል ነው፡፡ በቀድሞዎቹ የወንጀል መቅጫ ህግ ላይ ከተቀመጡት
የቅጣት አይነቶች አንዱ ግርፋት ነበር፡፡ ይህ ድርጊት የአካል ደህንነት ላይ አደጋ ሰለሚያስከተል
13
እና ከህገ መንግስቱ ጋር ስለሚቃረን በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ የተሻረ ድንጋጌ
ነበር፡፡

የአካል ደህንነት መብት የተላለፈ ማንኛውም የመንግስት አካል ወይም ግለሰብ ህገ መንግስቱን
እንደጣሰ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ሰው የወንጀል ድርጊት መፈፀሙ ከተረጋገጠበት
እንደነገሩ ሁኔታ ወይ በእስራት ወይም በሞት ሊቀጣ ይችላል እንጂ አካሉን በማሰቃየት ሊቀጣ
አይችልም፡፡ እንዲሁም አንድ ሰው ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ በበቂ ምክንያት ተጠርጥሮ እያለ
ማስረጃው ግን በበቂ ሁኔታ ካልተገኘ ተጠርጣሪው ይለቀቃል እንጂ ወንጀሉን እንዲያምን
አይደበደብም፡፡ በማናቸውም ሁኔታ የሰው አካል ደህንነት መብት የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንን
የፈፀመ ካለ በወንጀል ህጉ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

የነፃነት መብት

በህገ መንግስስቱ አንቀፅ 17 መሠረት ማንኛውም ሰው የነፃነተ መብት እንዳለው ተቀምጧል፡፡


ይህ መብት የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

 ከቦታ ቦታ መዘዋወር

 በመረጡት ስፍራ መኖር

 በፈለጉት ጊዜ ወጥቶ በፈለጉት ጊዜ መግባት

 ከመረጡት ሰው፣ ቤተሠብ ወይም ህብረተሠብ ጋር መቀላቀል

 ቢፈልጉም በብቸኝነት መኖር

 በማናቸውም ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ተሣታፊ ለመሆን መቻል እና የመሣሠሉት


ናቸው፡፡

እነዚህ እውቅና የተሠጣቸው መብቶች ፈፅሞ አይደሉም፡፡ ህገ መንግስቱ አንቀፅ 17(1)


መሠረት በህግ መሠረት ማንኛውም ሰው ነፃነቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ በወንጀል ህጉ ተለይተው
ከተቀመጡት ቅጣቶች አንዱ ማገድና መለየት ነው፡፡ የዚህ ቅጣት አላማ ወንጀለኞችን

14
ከህብረተሠቡ ነጥሎ በማስቀመጥ ሌሎች ወንጀሎች እንዳይፈፅሙ መከላከል ነው፡፡ በዚህም
መሠረት አንድ ወንጀለኛ እሰራት ቢፈረድበት እስሩን እስኪጨረሰ ድረስ ሌላ ወንጀል በመፈፀም
የህብረተሠቡን ሠላም አያናጋም የሚል ግምት ስላለ በህገ መንግስቱ እውቅና የተሠጠው
የነፃነት መብት ሊያጣ ይችላል፡፡

በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጡትን ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በወንጀል ህጉ ጋር


ያላቸውን ቁርኝት ሙሉ በሙሉ መዘርዘር የዚህ ፅሁፍ ዋና አላማ ባይሆንም ከላየ የተዳሰሱት
የህገ መነግስቱ አንቀፆች ህገ መንግስቱ እና የወንጀል ህጉ በቀጥታ ትስስር እንዳላቸው
ያመለክታሉ፡፡

መንግስት የህብረተሰብን ሠላምና ፀጥታ እንዲሁም የግለሰብን መብትና ነፃነት የማስከበር


ሃላፊነት አለው፡፡ ይሄንን ሃላፊነት ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው እና በሚያዘው መሠረት
ተገባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡ ከእነዚህ እርምጃዎች አንዱ የወንጀል
ህግ መደንገግ እና ይህንን ህግ የተላለፉ ሰዎች ወደ ህግ ማቅረብ ይጨምራል፡፡ በነዚህ
የወንጀል ህግ ድንጋጌዎች ንፁህ ግለሰቦች ሣይጐዱ የመንግስትና የህዝብ ጥቅም ሣይስተጓሎል
ጥፋተኞች እንዲቀጡና ከጥፋታቸው እንዲማሩ ማድረግ የመንግስት ሃላፊነት ነው፡፡ በሌላ
በኩል ደግሞ የእነዚህ ህገ መንግስታዊ መርሆች ዋና አላማ መንግስት ከለይ የተገለፀውን
ሃላፊነት ሲወጣ ሊያልፈ የማይችለውን ገደብ ማበጀት ነው፡፡ በአጠቃላይ ህገ መንግስት
በባህሪው መብቶችና ግዴታዎችን በጥቅል መልኩ የሚያስቀምጥ ሰነድ ነው፡፡ የወንጀል ህግ
ደግሞ በህገ መንግስቱ ውስጥ ጥበቃ የተደረገላቸውን መብቶችና ነፃነቶች ተግባራዊ ማድረጊያ
መንገድ ነው፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. የኢትዮጵያ ወንጀል ህግ አንቀፅ 1 የህዝቦቹን የነዋሪዎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ


የህጉ አላማ መሆኑን ይገልፃል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ከግለሰብ መብት ይልቅ ለጋራ
መብት ቅድሚያ እንደተሰጠው ነው፡፡

 የጋራ መብት ለምን ቅድሚያ ተሠጠው?

15
 የጋራ መብት ቅድሚያ መሠጠቱ የግለሰብ መብት በወንጀል ህጉ ጥበቃ
አይደረግለትም ማለት ነው?

2. አንቀፅ 1 ላይ የመጀመሪያው ፓራግራፍ ላይ የተቀመጡትን

 “ሰላም”

 “ደህንነት”

 “ስርዓት”

 “መብት”

 “ጥቅም” ትርጉማቸውን፣ ልዩነታቸውን እናትስስራቸውን በጋራ ተወያዩ

3. በወንጀል ህግ እና በፍትሐብሔር ህጐች መካከል ያሉ ልዩነቶችን ግለፅ/ግለጭ(እዚህ


ፅሁፍ ላይ ከተዘረዘሩት ውጭ)

16
ምዕራፍ ሁለት

2. የወንጀል ህግ መሠረታዊ መርሆዎች

የምዕራፉ አላማዎች
1. የህጋዊነት መርህን ምንነት በዝርዝር ይረዳሉ፣

2. የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ሄዶ የማይሰራ መሆኑንና ተገቢውን የወንጀለኛ ህጉንና የህገ


መንግስቱን አንቀፆች በመጥቀስ ያመለከታሉ፣

3. የወንጀል ህግ ወደኋላ ሄዶ ተግባራዊ የማይሆንበትን ምክንያት በዝርዝር ይገነዘባሉ፣

4. አንቀፅ 5 ላይ የተቀመጠውን መሠረታዊ መርህ ወደ ጐን በመተው ህጉ ከፀናበት ጊዜ


በፊት ያሉትን ጉዳዮች ለመሸፈን ወደ ኋላ ተመልሶ የሚሠራባቸውን ድንጋጌዎች
ያብራራሉ

5. የእኩልነት መርህ ምንነት ይረዳሉ

6. የእኩልነት መርህ ከህገ መንግስቱ ጋር ያለውን ቁርኝት ይገነዘባሉ፡፡

2.1. የህጋዊነት መርህ

ይህ መሰረታዊ የወንጀል ህግ መርህ በአንቀፅ 2 ላይ የተመለከተ ሲሆን የተለያዩ ጉዳዮችን


በስሩ አካቶ ይዟል፡፡

አ ንቀ ፅ ሁለ ት

1. የወንጀል ሕግ ስለ ልዩ ልዩ ወንጀሎችና ወንጀል አድራጊዎች ላይ ስለፈፀሙት


ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች በዝርዝር ይደነግጋል፡፡

17
2. ፍርድ ቤት ሕገወጥነቱ በሕግ ያልተደነገገን ድርጊት ወይም ግድፈት እንደወንጀል
ሊቆጥረው እና ቅጣት ሊወስንበት አይችልም፡፡

ፍርድ ቤቱ በሕግ ከተደነገጉት በቀር ሌሎች ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን


መወሰን አይችልም፡፡

3. በሕግ ላይ ከተደነገጉት ወንጀሎች ጋር ይመሳሰላል በማለት ወንጀልነቱ በግልፅ


ያልተደነገገን ድርጊት ወይም ግድፈት ፍርድ ቤት እንደወንጀል ሊቆጥር አይችልም፡፡

4. ከላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች፣ ፍርደ ቤት ሕጉን እንዳይተረጉም አያግዱትም፡፡ የሕጉ


አነጋገር አሻሚ በሚሆንበት ጊዜ ሕጉ ሊደርስበት ያስበውን ግብ ለማረጋገጥ እንዲቻል
ሕግ አውጪው ባቀደው ትርጉምና በሕግ መንፈስ መሠረት ፍርድ ቤቱ መተርጐም
አለበት፡፡

5. ማንም ሰው በሕግ መሠረት የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኛናነቱ ተረጋግጦ ከዚህ


ቀደም በተቀጣበት ወይም ሌላ ሕጋዊ እርምጃ በተወሰደበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት
ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም፡፡

2.1.1. ህገ-ወጥ የተባሉ ድርጊቶች፣ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ግልፅነት፣

በወንጀል ህጉ የሚያስቀጡ የተባሉ ድርጊቶ ቅጣታቸው እና ሊወሰድ የታሰበው የጥንቃቄ


እርምጃዎች በሙሉ በማያሻማ መለኩ በግልፅ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ይህ ግልፅነት ካለ ህጉ
ስለወንጀሎች እና ቅጣታቸው በቅድሚያ ለህብረተሰቡ ማስጠንቀቂያ መስጠት ቀላል ነው፡፡
በተጨማሪም በዘፈቀደ የሚሰሩ ስራዎች ያሰግዳል፤ ፍርድ ቤቶች በህጉ ብቻ እንዲመሩ
ያደርጋል፡፡ በፍትህ ስርዓት ውስጥ ያሉ ሁሉም ባለሞያዎች ስራቸውን በአግባቡ ህጉ
ባስቀመጠው መንገድ እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል፡፡ በዚህ መርህ መሰረት

ሀ. በህግ በግልፅ ካልተደነገገ በስተቀር ወንጀል የለም፡፡ በአንቀፅ 2(1) እንደተቀመጠው ወንጀል
መሆኑ በግልፅ ካልተቀመጠ ማንኛውም ሰው ለፈፀመው ድርጊት ምንም እንኳን ድርጊቱ
ግብረ-ገብነት የጐደለው ቢሆን ተጠያቂ አይደለም፡፡

18
ለ. በህጉ በግልፅ የተቀመጠውን ወንጀል ድርጊት የፈፀመው ሰው የሚቀጣው ህጉ ባስቀመጠው
መሠረት ነው፡፡ ለተላለፈው ድርጊት የተቀመጠው ቅጣት ብቻ ይቀጣል፡፡ ሁለት አባባሎች
በአጭር ሲቀመጡ፡-

 ህግ በግልፅ ካልተደነገገ ወንጀል የለም፣

 ህግ በግልፅ ካስቀመጠው በስተቀር ቅጣት የለም የሚሉ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ህግ አውጨው በአንድ አገር ውስጥ ያለ ህዝቦች የሚተዳደሩበትንና ግንኙነታቸውን


የሚመሠረቱበትን ህጐች የማውጣት ስልጣን ሲኖረው ህግ ተርጓሚው አካል ወይም ፍርድ
ቤቶች የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች ህጉ በደነገጋቸው ብቻ ውሣኔ ይሰጣሉ፡፡ ይህ የሚያስረዳው
አስቀድሞ በህግ ያልተመለከተን ጥፋት ፍርድ ቤት በራሱ አነሣሽነት አንደ ህግ መጣስ
ሊቆጥረው አይቻልም፡፡ በወንጀል ህጉ ም ከተወሰኑት ቅ ጣ ቶች በስተቀር ሌላ መፈፀም
አይቻልም፡፡ በተመሣሣይ በወንጀል ህጉ ከተዘረዘሩት የጥንቃቄ እርምጃዎች ውጭ ሌላ መፈፀም
አይቻልም፡፡

2.1.2. ፍርድ ቤት ህጉን የመተርጐም ስልጣን

በአንቀፅ 2(3)(4) ላይ እንደተገለፀው ፍርድ ቤቶች የወንጀል ህግን ህግ አውጪው ባቀረበው


ትርጉምና በህጉ መንፈስ መሠረት መተርጐም እንደሚችሉ ይገልፃል፡፡ ትርጉም በህግ እውቀት
ውስጥ ትልቁን ስፍራ የሚይዝ ነው፡፡ ህግ የሚወጣው መሠረታዊ የሆነውን ጠቅላላ መርህ
በመከተል ነው፡፡ በሠዎች ማሃከል ያለውን ማህበራዊ ህይወት እያደገ ሲመጣ ውስብስብ
ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ህጉን ከእነዚሀ ሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም ከሚረዱት መንገዶች አንዱ
ህጉን ከተፈጠሩት አዲስ ጉዳዮች ጋር በማጣጣም መተርጐም ነው፡፡

የህግ አውጭው ህጐች ሲደነግግ በተቻለ መጠን ግልፅና የማያሻማ መሆን አለበት፡፡ ሆኖም ግን
በተለያዩ ምክንያቶች የተዘጋጁት ህጐች ግልፅነት ሊጐድላቸው ይችላል፡፡ በዚህም መሠረት
አንዳንድ ቃላቶች ግልፅነት ሊጐድላቸው ይችላል ወይም የተለያዩ አሻሚ ትርጐም ይሰጣሉ፡፡

ለምሳሌ ፡- አንድ በወንጀል ህጉ ጥበቃ የተደረገለት መብት ወይም ጥቅም ላይ ጉዳት


ቢደርስና የደረሰው ጉዳት ህጉ ባላስቀመጠው ዘዴና አካሄድ ከሆነ ፍርድ ቤቱ
19
የተባለው ወንጀል መፈፀሙን ለማረጋገጥ የወንጀል ህጉ ን መተርጐም
ይገባዋል፡፡

ህጉ የሚተረጉመው ግልፅነት ሲጐድለው አሻሚነት ሲፈጠር እና ክፍተት ሲኖር ነው፡፡ ከዚህ


ውጭ ህጉ በተሟላበት ግልፅ በሆነበት የሚያሻማ ባልሆነበት ሁኔታ የህግ ትርጉም አይነሣም፡፡

2.2.3. አንድ ሰው በአንድ ወንጀል እንደገና አይከሰስም ወይም አይቀጣም

ይህ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 23 መሠረት አንድ ሰው በአንድ ወንጀል ሁለት ጊዜ


እንደማይቀጣ እንደማይከሰስና የሚደነግገውን የሚያጠናክር ነው፡፡ በዚህ መርህ መሰረት አንድ
ሰው በፈፀመው ወንጀል ሊቀጣ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ህይ ብቻ ሣይሆን በዚህ
ወንጀል ሊከሰስ የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ዐቃቤ ህጉ ክስ አዘጋጅቶ ያቀረበው ማስረጃ
ክሱን የሚያስረዳ ከሆነ ተጠርጣሪው ይለቀቃል፡፡ በዚህ መርህ መሠረት የመጨረሻ ነው፡፡ ዐቃቤ
ህጉ ሌላ ጊዜ አዲስ ማስረጃ ቢያገኝም መክሰስ አይችልም፡፡

ስለዚህ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 2(5) መሠረት

ሀ. ማንም ሰው በአንድ የወንጀል ስራ ሁለት ጊዜ አይከሰስም፣

ለ. ማንም ሰው በአንድ የወንጀል ስራ ሁለት ጊዜ አይቀጣም፣

በ(ለ) ስር የተመለከተው ድንጋጌ አንድ ሰው ለፈፀመው ለተቀጣበት ጥፋት ደግመኛ እንዳይቀጣ


ይከለክላል፡፡ ፍርድ ቤቱ የሰጠው የቅጣት ውሣኔ እንደነገሩ ሁኔታ ወዲያው ሊፈፀም ወይም
በገደብ ሊተላለፍ ይቻላል፡፡ ተከሣሹ በማንኛውም መንገድ ቅጣቱን ጨርሶ የወጣ እንደሆነ ያንኑ
ቅጣት ድጋሚ እንዲፈፀምበት አይደረግም፡፡ ይህ ሊሆን የሚቻለው ግን የጠፋተኝነት ውሣኔ
የተረጋገጠበት እንደሆነ ብቻ ሣይሆን በውሣኔው መሠረት ቅጣቱን የፈፀመ እንደሆነ ጭምር
ነው፡፡ የቅጣት ውሣኔ ከተበየነበት በኋላ ህግ በሚፈቅደው መሠረት ይቅርታ የተደረገለት ወይም
ቅጣት የተቀነሰለት ሰው በማናቸውም ጊዜ በይቅርታ ወይም በቀናሽ የተነሣለትን ቅጣት
እንዲፈፅም አይደረግም፡፡

20
የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራ ስለመሆኑ

አንቀፅ አምስት

1. በዚህና በተሻረው የወንጀል ሕግ እንደወንጀል የተቆጠረ ድርጊት የተፈፀመው ይህ ሕግ


ከመፅናቱ በፊት ከሆነ፣ ጉዳዩ የሚታየው በተሻረው የወንጀል ሕግ መሠረት ነው፡፡

2. ድርጊቱ በዚህ ሕግ መሠረት ወንጀል ሆኖ በተሻረው የወንጀል ሕግ ግን እንደወንጀል


ካልቆጠረና የተፈፀመው ይህ ሕግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ ሊያስቀጣ አይችልም፡፡

3. የተሻረው ሕግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈፀመ ወንጀል ሲኖርና በዚህ ሕግ ግን


እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስሰም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም፤ ክሱም ተጀምሮ
እንደሆነ ይቋረጣል፡፡

የወንጀል ህጉ አንቀፅ 5 እና የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 22 የወንጀል ህግ ወደ ኋላ


ተመልሶ የማይሰራ መሆኑን ይደነግጋሉ፡፡ በዚህ መሰረት አንድ ድርጊት ወይም አለማድረግ
ወንጀል ተብሎ ሊያስጠይቅ የሚችለው ወንጀል ነው ተብሎ ከተደነገገበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
መሠረታዊና በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው መርህ ነው፡፡ አንድ ሰው ላሣየው ባህሪ
ጥፋተኛ ለማድረግ መጀመሪያ ባህሪው ያልተፈቀደ እና ወንጀል እንደሆነ ማ ስ ጠ ንቀ ቅ
መሠረታዊ ስራ እንደሆነ አንቀፅ 2 ላይ የተቀመጠው ህጋዊነት መርህ ያስረዳል፡፡ ጥፋት
መሆኑን ሳይነግረው ወይም ማስጠንቀቂያ ሣይሰጠው ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም፡፡ አንቀፅ 5
ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ ከህጋዊነት መርህ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው፡፡

ማንኛውም ህግ የተጨባጭነት ባህሪይ ሊኖረው ይገባል፡፡ በተለይም የወንጀል ህግ፡፡ ሰዎች


ህግን ከመጣስ እንዲቆጠቡ ቢጥሱም የሚከተላቸውን ቅጣት አውቀው አነዲገቡበት የተወሰነ
የታወቀና የተጨበጠ ህግ መኖር አለበት፡፡ አንድ ህግ ይህኛውን ወይም ያኛውን ሰው ለመቅጣት
ብሎ የሚወጣ ከሆነ ሁሉን አቀፍ ባህሪዩን አጣ ማለት ነው፡፡ አንድ ህግ እንዲፀና ከመደረጉ
በፊት የተሠራ ስራ ሲኖርና ህግን እንደመጣስ ያልተቆጠረ ሲሆን አዲስ በወጣው ህግ
ሊያስቀጣ አይችልም፡፡ እንዲሁም የህግ መጣስ ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜ ባልተፃፈ ቅጣት
ሊፈርድ አይችልም፡፡

21
አንድ ድርጊት ከተፈፀመበት ጊዜ በፊት “ወንጀል ሆኖ ያስቀጣል” ተብሎ ቀደም ሲል ተደንግጐ
ካልቆየና ተከሣሹም ለፍርድ የሚቀርብበት ህግ በድርጊቱ ፍፃሜ በፊት በህግ መልስ ተቀርፆ
ካልቆየና ድርጊቱን ከፈፀመ በኋላ አድሪጊውን ለመቅጣት ሲባል ሌላ ህግ ከወጣ በህገ መንግስቱ
መሠረት ተፈፃሚነት የለውም፡፡

አንድ ህግ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ ማንም ሰው ህግን የጣሠ እንደሆነ የሚፈርደው በዚያው ህግ


መሠረት ነው፡፡ ነገር ግን ወንጀሉ የተሠራው የቀድሞው ህግ ይሰራበት በነበረ ጊዜ እንደሆነ
ፍርዱ የሚፈፀመው በቀድሞው ህግ መሠረት ነው፡፡

ስለዚህ የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ተመልሶ የማይሰራባቸው ድንጋጌች ሁለት አይነት ናቸው፡፡


አንደኛው አንድ ቅጣት ህግ ከመውጣቱ በፊት እንድ ወንጀል ይቆጠር ያልነበረ ድርጊት ቢፈፀም
ሆኖም ግን በአዲሱ ህግ መሠረት እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚያስቀጣ ቢሆን አድሪጊው ህጉ
ከመፅናቱ በፊት ለፈፀመው ተግባር በወንጀል ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ሁለተኛው አንድ የቆየ
የቅጣት ህግ በአዲስ ቢተካ አዲሱ ህገ ከመውጣቱ በፊት የተፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶች
የሚዳኙት በተሻረው ህግ ድንጋጌዎች እንጂ በኋለኛው ህግ አይደለም፡፡ በማንኛውም መልኩ
ህግ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ድንጋጌዎች ላይ እንጂ ባለፉት ላይ ተፈፃሚነት ሃይል
የለውም፡፡ ይህ መሠረታዊ ድንጋጌ ሰዎች ከአሁን በፊት የሚያውቁት ህግ ብቻ የመዳኘት
መብት ይሰጣቸዋል፤ ካልተጠበቀና ካልተሳበ ቅጣት ያድናቸዋል፡፡ ህጉ ሁሌም አብሮአቸው
እንዲኖር እንዲያውቁትና እንዲጠነቀቁበት ካልሆነም ደግሞ የሚደርስባቸውን የቅጣት ደረጃ
ለመገመት እንዲችሉ ይረዳቸዋል፡፡

ህግ በአጠቃላይ እንደጊዜው ሁኔታ ያለፈውን ድርጊት ባለፈው ህግ የአሁኑንና የወደፊቱን


ደግሞ በአሁኑ ህግ እንዲታይ እድል ይሰጣል፡፡

አንድ ድርጊት በቀድሞው ህግ ስር ያስከትል የነበረው የቅጣት ክብደት በሌላ አዲስ ህግ


የተጨመረ እንደሆነ ጥፋተኛው የሚቀጣው ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ ለወንጀሉ ተፈፃሚ
በነበረው ቅጣት ነው፡፡ ወንጀሎን በፈፀመበት ጊዜ ለወንጀሉ ተፈፃሚ ከነበረው ቅጣት ጣራ
በላይም አይፈፀመበትም፡፡ ይህ የወንጀል ቅጣት በተከሣሽ ላይ የከበደ ቅጣት ለማስፈረድ
በየጊዜው እንደ ገበያ ዋጋ ከፍና ዝቅ የሚል አለመሆኑን ያመለክታል፡፡ ዋናው ጥያቄ አንድ
ሰው ወንጀል በሚፈፅምበት ጊዜ የነበረው ህግ የሚደነገገው የቅጣት ጣሪያ የት ድረስ ነው?

22
የሚለው እንጂ ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ የወጣ (አዲስ) ህግ የሚደነገገው የቅጣት ጣሪያ የት
ድረስ ነው? የሚለው አይደለም፡፡

ስለሆነም አሁን በሰራ ላይ ያለው የወንጀል ህግ በተግባር የሚውለው ከግንቦት 1 ቀን 1997


ዓ.ም ጀምሮ ለተፈፀመ ድርጊቶች ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ግን ወደ ኋላ ተመልሶ የሚሰራበት
ልዩነቶች እንዳሉ ከአንቀፅ 6 ጀምሮ ተዘርዝሯል፡፡ ይህንን ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

ልዩነቶች (Exceptions)

ከነዚህ ልዩነቶች የወንጀል ህጉ አንቀፅ 5 ላይ ያስቀመጠውን መሠረታዊ መርህ ወደ ጐን


በመተው ህጉ ከፀናበት ጊዜ በፊት ያሉት ጉዳዮች ለመሸፈን ወደ ኋላ ተመልሶ የሚሰራባቸው
ድንጋጌዎች ናቸው፡፡

ለተከሣሹ የሚጠቅም ከሆነ

አንቀፅ ስድስት

ይህ ህግ እንዲፀና ከተደረገ በኋላ አድራጊው ሕጉ ከመፅናቱ በፊት ላደረገው ወንጀል


ሲፈረድበት ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ በሥራ ላይ ከነበረው ሕግ ይልቅ ይሄኛው ሕግ
ቅጣት የሚያቃልለት ሲሆን በዚህ ሕገ ላይ ተመለከተው ቅጣት ይፈፀምበታል፡፡

ፍርድ ቤቱ ይህ ሕግ የተሻለ መሆኑን የሚወስነው በእያንዳንዱ ጉዳይ አግባብነት


ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች በማመዛዘን ነው፡፡

ተከሣሹ ድርጊቱን የፈፀመው የቀድሞው ወንጀል ህግ በሰራ ላይ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ


ድርጊትም በሁለቱም የወንጀል ህጐች የተከለከለና የማያስቀጣ እንደሁነ ተገልፆል፡፡ ሆኖም ግን
ቅጣን በሚመለከት አዲሱ ህግ በፊት ከነበረው የተሻለ እና ቀለል ያለ ድግጋጌ አስቀምጧል፡፡
ተከሣሹን ለመጥቀም ሲባል በአዲሱ ህግ ላይ የተቀመጠውን ቅጣት ይፈፀሙበታል ይህ
የሚያሣየው የወንጀል ህጉ በስራ ላይ ባልነበረበት ወቅት የተፈፀመን ድርጊት ወደ ኋላ ተመልሶ
እንዲሰራ የሚደረግበት ልዩነት ነው፡፡

23
ለምሳሌ፡- አንድ ሰው በቀድሞው ህግ መሠረት በ6 አመት ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ
ወንጀል ቢፈፅምና በአሁኑ ህግ መሠረት ይሄው ተመሣሣይ ወንጀል በ6
አመት ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ቢሆን ምንም እንኳን ወንጀሉ የተፈፀመው
የቀድሞው ህግ በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ቢሆንም አዲሱ ህግ መሠረት የ6
አመት ቀላል እስራት ተፈፃሚ ይሆንበታል፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. አቶ “ሀ” በሰሩት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ ሰርዓት


ድንጋጌዎችን በስህተት በመተለለፍ ጉዳዩን ስልጣን ለሌለው ፍርድ ቤት አቀረበ፡፡ ፍርድ
ቤቱም ስልጣን የለኝም በማለት መዝገቡን በመዝጋት ተከሣሹን አሥናበተ፡፡ ከዚህ በኋላ
ዐቃቤ ህግ የሠራውን የስነ ስርዓት ስህተት በማስተካከል በተመሣሣይ ወንጀል አቶ
”ሀ”ን ጉዳዩን የማየት ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይከሣል፡፡ ተከሣሹም አቶ ”ሀ” ከዚህ
በፊት በተከሠስኩበት ጉዳይ እንደገና አልከሰስም፡፡ ህገ መንግስታዊ መብቴን የተላለፈ
አካሄድ ስለሆነ በነፃ ልሰናበት ብለው አመለከቱ፡፡ አና ን ተ ዳኛ ብትሆኑ ምን
ትወስናላችሁ? በቡድን ተወያዩ፡፡

2. አቶ ”ለ” ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ዐቃቤ ህግ ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ


ቤት ክስ ያቀርባል፡፡ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸው ምስክሮች አቅረቦ ካሠማ በኋላ ፍርድ
ቤቱ የቀረበው ማስረጃ እንደ ክሱ ያላስረዳ ስለሆነ ተከሣሹ በነፃ ይስናበቱ በማለት
ይወስናል፡፡ ዐቃቤ ህግም በዚህ ቅር በመሠኘት ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ
ይጠይቃል፡፡ ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቶ ተከሣሽ አቶ “ለ” ጥሪ ሲደረግላቸው በዚህ
ጉዳይ ተከስሼ ነፃ ስለወጣሁ ድጋሚ ልጠየቅ አይገባኝ በማለት መልስ አቀረቡ፡፡
የተከሣሽ መልስ ተቀባይነት አለው? ተቀባይነት ካለው ለምን? ከሌለውስ ለምን?

3. የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 6 አንድ ወንጀል ህጉ ከመፅናቱ በፊት ላደረገው ወንጀል


ሲፈርድበት ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ በስራ ላይ ከነበረው ህግ ይልቅ ይሄኛው ቅጣት
የሚያቃልልለት ከሆነ በዚህ ህግ መሠረት ቅጣት ይፈፀመበታል ይላል፡፡ ይህ አባባል
ከዋናው የወንጀል ህግ መርህ “የወንጀል ህግ ወደ ኃላ ተመልሶ አይሰራም” ከሚለው
24
በልዩነት የተቀመጠ ነው፡፡ ሆኖም ግን አንቀፅ 2 ላይ የተቀመጠው የህጋዊነት መርህ
ህግ በግልፅ ካልተደነገገ በስተቀር ወንጀልም ቅጣትም የለም ይላል፡፡ በዚህ መሠረት
ለወንጀለኛው ይጠቅማል በማለት ቀደም ያልነበረ ቅጣት መፈፀም የህጋዊነት መርህን
አይቃረንም?

የጥንቃቄ እርምጃዎች አፈፃፀም

አንቀፅ ሰባት

የተሻረው ሕግ በሥራ ላይ በነበረበት ጊዜ በተፈፀሙ ወንጀሎች ላይ ይህ ሕግ ከፀና


በኋላ በሚሰጡ ፍርዶች ላይ የጥንቃቄ እርምጃዎችን አወሳሰን በሚመለከት የዚህ ሕግ
ድንጋጌዎች (አንቀፅ 129-163) ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አንቀፅ 7 ላይ በተገለፀው መሠረት ከ129 -165 የተቀመጡት የጥንቃቄ እርምጃዎች በዚህ ህግ


መሠረት ይፈፀማው፡፡ ይህ የሚሆነው ወንጀሉ የተፈፀመው በቀድሞው ህግ በስራ ላይ
በነበረበት ጊዜ ቢሆንና የተሠጠውም ፍርድ በቀድሞ ህግ መሠረት ሆኖ በተጨማሪ የጥንቃቄ
እርምጃ ፍርድ ቤቱ ካዘዘ ተግበራዊ የሚሆኑት በአዲሱ የወንጀል ህግ መሰረት ነው፡፡

ለምሣሌ፡- አንድ “X” የተባለ የንግድ ድርጅት ሰራውን በሚያካሂዱበት ወቅት በወንጀል
ህጉ የተከለከለ እና የሚያስጠይቅ ድርጊት ከፈፀመ ጉዳዩን ያየው ፍርድ ቤት
ሁለት አይነት ውሣኔ ይሰጣል፡፡

1. ለፈፀሙት ወንጀል በቀድሞው ህግ መሠረት ይቀጣል (ወንጀሉን የፈፀሙት


በቀድሞው ህግ በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ ነው ብለን እናስብ)

2. በአንቀፅ 143 በአዲሱ ህግ መሠረት የንግድ ተቋሙን መዘጋት

25
የይረጋ ዘመን አፈፃፀም

አንቀፅ ስምንት

1. የተሻረው ሕግ በስራ ላይ በነበረበት ጊዜ በተፈፀሙ ወንጀሎች ረገድ፣ የክስ


አቀራረብና የቅጣት አፈፃፀም የይርጋ ዘመን ይህ ሕግ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ
ሕግ መሠረት ይመራል፡፡

ቢሆንም ይህ ሕግ ከመፅናቱ በፊት ያለፈው ጊዜ ለይርጋ ዘመን መታሰብ አለበት፡፡

2. በግል አቤቱታ አቅሪቢነት ብቻ ያስቀጣ የነበረ ወንጀል በዘህ ሕግ መሠረት ያለግል


አቤቱታ የሚያስቀጣ ሲሆን፣ ይህ ሕግ ከፀናበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ውሰጥ
አቤቱታ አቅሪቢው የግል አቤቱታ የማቅረብ መብቱን ካለተጠቀመበት ቀሪ ይሆናል፡፡

እንደሚታወቀው የክስ አቤቱታን ለማቅረብ ሃላፊነት የተሰጠው ዐቃቤ ህግ ወይም የግል


አቤቱታን የማቅረብ መብት ያለው ግለሰብ ይህንኑ መብት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ሲገለገልበት
ይገባል፡፡ ይህ ክስ የማቅረብ መብት ዘላለማዊ ሣይሆን በተወሰነ ጊዜ የተገደበ ነው፡፡
በተጨማሪም በአንድ ወንጀለኛ ላይ የተወሰነ ቅጣት መፈፀም ያለበት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ
ነው፡፡ ስለሆነም በህግ የተቀመጠው ጊዜ ካለፈ ክስ ማቅረብም ሆነ ውሣኔ ማስፈፀም
አይቻልም፡፡ ይርጋው ክስንም ሆነ ቅጣትን ያስቀራል፡፡ የዚህ የይርጋ ዘመን ስሌት ደግሞ
በአዲሱ ህግ ይመራል፡፡

በህጉ አንቀፅ 8 መሠረት የክስ አቀራረብና የቅጣት አፈፃፀም ይርጋ ዘመን በዚህ ህግ
እንደሚመራ ይገልፃል፡፡ ይህ ማለት ወንጀሉ የተፈፀመው የቀድሞው ህግ በስራ ላይ በነበረበት
ጊዜ ይሁን ወይም በአሁኑ ህግ ይርጋ የሚሳራው እና የሚፈፀመው በአዲሱ ህግ መሰረት ብቻ
ነው፡፡

26
የፍርዶች አፈፃፀም

አንቀፅ ዘጠኝ

ፍርዱ በተሻረው የወንጀል ሕግ መሠረት ተሰጥቶ እንደሆነ፣ አፈፃፀሙ የሚመራው


ከዚህ በታች ባሉት መርሆች ነው፡፡

1. ቀድሞ ቅጣት ተወስኖበት የነበረው ድርጊት በአዲሱ ሕግ የሚያስጣ እንደሆነ፣


ቅጣቱ ሊፈፀም አይችልም፤ የተጀመረው ቅጣትም ወዲያውኑ ይቋረጣል፡፡

2. ለአንድ ለተወሰነ ጊዜና አላፊ ለሆኑ ምክንያቶች ሕግ የደነገገውን ግዴታ በመጣስ


የወንጀል ፍርድ ተሰጥቶ እንደሆነ፣ የተባለው ጊዜ ማለፍ ምክንያት ሆኖ
የተወሰነውን ቅጣት ሊያቆመው አይችልም፤ የተባለው ጊዜ ማለፉ ክስ
ማቅረብንም አያግድም፡፡

3. ይህ ሕግ ከመፅናቱ በፊትም ሆነ በኋላ በተሰጠ ወይም በሚሰጡ ፍርዶች


የተወሰኑ ቅጣቶች አፈፃፀም፣ በዚሁ ሕግ በተመለከተው ድንጋጌ መሠት
ይሆናል፡፡ እንዲሁም የተጣለውን መቀጮ ስለማስገባት፣ አስቀድሞ በገደብ
ሰለመልቀቅ እና ስለአመክሮ የሚደረገው የ ሥር ዓ ቱ አፈፃፀም በዚህ ህግ
እንደተመለከተው ነው፡፡

4. ይህ ሕግ ከፀናበት ጊዜ፣ የተወሰነበትን ቅጣት በመፈፀም ላይ የሚገን እስረኛ


ቀደም ሲል ነፃነትን በማሳጣት የሚያስቀጣ ሌላ ወንጀል ፈፅሞ ሳይደረስበት የቀረ
መሆኑ ሲታወቀ፣ ፍርዱን የሚወስንበት ፍርድ ቤት ለተቀጪው የተሻለለውን
የሕግ ድንጋጌ /አንቀፅ 6/ መሠረት አድርጐ በመያዝ፣ ስለተደራራቢ ወንጀሎች
በተወሰኑ ድንጋጌዎች /አንቀጽ 186/ መሠረት ይወስናል፡፡

ቢሆንም በቀድሞ ፍርድ መሠረት የፈፀመው የእስራት ቅጣት ጊዜ ይቀነስለታል፡፡

27
አንቀፅ 9 የሚያመለክተው በተሻረው ህግ መሠረት የተሰጡ ፍርዶች አፈፃፀማቸው የሚመራው
በስራ ላይ ባለው ህግ መሠረት ይመራል፡፡ ይህ አንቀፅ በስሩ የተለያዩ ድንገጌዎችን ስለያዘ
ዝርዝር አድርገን እንመለከተው፡፡

 9(1) መሠረት አንድ ግለሰብ በቀድሞው ህግ የወንጀል ድርጊት ፈፅሟል ተብሎ 10


አመት ቢፈረድበትና አምስት አመቱን ከፈፀመ በኋላ ግንቦት 1 ቀን 1997 ዓ.ም
የተቀጣበት ድርጊት በአዲሱ ህግ ወንጀል መሆኑ ቢቀር ቅጣቱ እንዲቋረጥ እና ግለሰቡ
እንዲለቀቅ ያዛል፡፡

 9(2) የሚያመለክተው ለተወሰነ ጊዜ በተለያዩ ምከንያቶች እንደ ጦርነት ረሃብ የተፈጥሮ


አደጋ ሲከሰት የሚወጡ ህጐችን ነው፡፡ እነኚህ ህጐችን ሲወጡ ለአምስት አመት ወይም
የተፈጠረው ችግር እስኪጠፋ ድረስ ተብለው ሊዘጋጅ ይችላል፡፡

ለምሳሌ፡- ድሬዳዋ በደረሰው የጐርፍ አደጋ ምክንያት የተሠባሰበውን አስቸኮይ ጊዜ


እና እርዳታ የማሰባሰቢያ አዋጅ ቢወጣና የተሠበሰበውን እርዳታ አንድ የስራ
ሃላፊ ለግል ጥቅሙ አውሎት 5 አመት ፅኑ እስራት ቢፈረድበት

ሀ. የጐርፉ አደጋ በማለፉ ምክንያት ቅጣቱን አያስቀርም

ለ. የጐርፉ አደጋ ቢያልፍም ዐቃቤ ህግ ከላይ የተጠቀሰውን አዋጅ የተላለፉ


ሰዎችን ከመክሰስ አያግደውም፡፡

 9(3) የቀድሞው ህግ በስራ ላይ እያለ የተሰጠ ፍርድ በተለያዩ ምክንያቶች ሣይፈፀም


ቢቀርና እስከ ግንቦት 1 ቀን 1997 ዓ.ም ከቆየ አፈፃፀሙ በዚህ ህግ መሠረት
ይሆናል፡፡

ለምሳሌ፡- አንድ ግለሰብ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት በቀድሞው


ህግ መሠረት ቢወሰንበትና በተለያዩ ምክንያቶች ሣይፈፀም እስከ ግንቦት 1
ቀን 1997 ዓ.ም ቢቆይ አፈፃፀሙ በአንቀፅ 117 መሠረት ሰብአዊ በሆነ
መንገድ ይፈፀማል፡፡ በስቅላት አይፈፀምበትም፡፡

28
የእኩልነት መርህ

አንቀፅ አራት

የወንጀል ሕግ የሰውን፣ የማህበራዊ ኑሮ ደረጃን፣ የዘርን፣ የብሔርን፣ የብሔረሰብን፣


የቀለምን፣ የጾታን፣ የቋንቋን፣ የሃይማኖትን፣ የፖለቲካን ወይም የሌላ አስተሳሰብን፣
በሐብትን፣ የትውልድን ወይም የሌላ አቋምን ልዩነት ሳያደርግ በሁሉም ላይ በእኩልነት
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

በወንጀል አድራጊዎች መሐከል ልዩነት የሚደረገው ምንጩ የዓለም አቀፍ ሕግ ወይም


ሕገመንግሥት ሆኖ በዚህ ሕግ የተደነገገ መሠረታዊ መብት ሲኖር፣ ወይም የወንጀሉ
ከባድነት፣ የጥፋቱ ደረጃ ወይም የአድራጊው ዕድሜ፣ ሁኔታዎች ወይም ልዩ ግላዊ
ጠባዩ ወይም ወንጀሉ በሕብረተሰቡ ላይ ያስከተለው አደጋ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ይህ
ሕግ ሲደነግግ ነው፡፡

ሰዎች በህግ ፊት እኩል መሆናቸው በአብዛኛው በፍርድ ቤትና በአስተዳደራዊ ውሣኔዎች ላይ


ነው፡፡ ሰዎች በዳኛው ወይም በአስተዳደራዊ ፊት በተወላጅነታቸው ወይም በአቅማቸው
ተመዝነው የሚገባቸውን የሚያጡ ወይም የማይገባቸውን የሚያገኙ ከሆነ በ ህግ ፊት
የእኩልነት መብታቸው አልተከበረም፡፡ ሰዎች በህግ ፊት እኩል መሆናቸው የሚረጋገጥው
የበደለው ሲከስ የተበደለው ሲከስ ነው፡፡ የዚህ መርህ አንድ አላማም ሚዛን በመጠበቅ በሰዎች
በኩል የሚኖረው ግንኙነት አንዱ በአመፅ የሌለውን መብት ሣይጋፉ ተፈጥሮአዊ ሂደትን ጠብቆ
እንዲጓዝ መቆጣጠር ነው፡፡

ከዚህ መርህ ለማየት እንደሚቻለው በህግ ፊት እኩል የመሆን መብት ሚዛናዊና ፍትሐዊ
ፍርድ የማግኘት መብት ከሌሎች ነገሮች መሃል ዘርንና ቀለምን ሣይለይ ሰዎች በአጠቃላይ
የሚጐናፀፉት ነው፡፡ ህገ መንግስቱ አንቀፅ 25 ላይ እንደተገለፀው ህጉ ”ዜጐች ሁሉ” ሣይሆን
“ሰዎች ሁሉ” በማለት ይጀምራል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንድ ኢትዮጵያዊና በአንድ የውጭ
አገር ዜጋ መካከል የወንጀል ወይም የፍትሐብሔር (የብድር፣ የውል፣ የጋብቻ፣ የንብረት
ወዘተ) ክርክር ሲነሣና ህግ ፊት (ፍርድ ቤት ወይም አስተዳደር) ቢቀርብ ኢትዮጵያዊው
ተከራካሪ ከዜግነቱ የሚመነጭ አንዳች የተለየ ፍርድ አያገኝም፡፡ የውጭ አገር ዜጋም ለእርሱ
ሲባል ከህግ ውጭ የተለየ ፍርድ አይሰጠውም፡፡ ፍትህ የሰዎችን ዜግነት አትለይም ዓለም
29
አቀፋዊ ናት፡፡ ይህ ህግ የአለም መንግስታት የተቀበሉት በመሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ
ኢትዮጰያዊያንም የዚህ መብት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

“እኩል የህግ ጥበቃ” ስንል ምን ማለታችን ነው? ከላይ እንደጠቀስነው በህግ ፊት እኩል
የመሆን መብት የሚረጋገጠው በትክክለኛ ዳኝነት ወይም የአስተዳደር ስርዓት ነው፡፡ እኩል
የህግ ጥበቃ የሚረጋገጠው ደግሞ ህጉ ተረቶ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ሰዎች ሁሉ በህግ
ፊት እኩል መሆናቸው የሚረጋገጠው የፍትህ አካላት ህግ አስፈፃሚው ህግን
በሚተረጉሙበትና በስራ ላይ በሚያውሉበት ጊዜ ሲሆን ሁሉም ሰዎች እኩል የህግ ጥበቃ
የሚያደርግላቸው ደግሞ ህግ አውጭው የመንግስት አካል ነው፡፡ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ
ህግ ይሄን መሠረታዊ መርሀ በአንቀፅ አራት ላይ በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ሁሉም ሰዎች በህግ
እንደምን እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል?

የህግ ዋንኛ አላማ የህብረተሠቡን የሀብት የአስተሣሠብ የእምነትና የሃይል ሚዛን በመቆጣጠር
ሰዎች እለታዊ ኑሮአቸው ያለ ሰጋት እንዲያካሂዱ ማድረግ ነው፡፡ የህግ ትልቁ ዓላማ ሠላምን
መፍጠረና ሠላምን ማረጋገጥ ነው ማናቸውም ህግ ሲወጣ የእያንዳንዱን ሰው ህይወት
በአጠላይ ደግሞ የህብረተሠቡን ህይወት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንካቱ አይቀርም፡፡ የህግ
አይነተኛ ጠባይ ደግሞ ሁሉን አቀፍነት ነው፡፡ የሃገሪቱን ህዝቦች በአጠቃላይ የሚነካ ህግ
ሊወጣ ይችላል፤ ወይም የአገሪቱ አጠቃላይ ህብረተሠብ የተወሰነውን ክፍል ብቻ የሚነካ ሊሆን
ይችላል፤ ወይም በአንድ በተወሰነ ሞያ የተሠባሠቡ ሰዎችን ብቻ የሚነካ ሊሆንም ይችላል፡፡
ለአንድ ሰው ወይም ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ ተብሎ የሚሰራ ህግ የለም፡፡

ህግ አውጭው አካለ አንድን ህግ የሚያወጣበት ጊዜ መጀመሪያ ህጉ የትኛው የህብረተሠብ


ክፍል አንደሚነካ ከዚያም የዚያን ህብረተሠብ አባላት ጥቅምና ፈላጐት እንዴት በተጠጋጋ
መንገድ ማስማማት አንደሚቻል ማጤን አለበት፡፡ የሰዎች አኩል ህጋዊ ጥበቃ የሚረጋገጠው
ህጉ ጥቅማቸውን በየፈርጅ ሲያስጠብቅላቸው ነው፡፡ ማንኛውም ሰው የሚውልበት የስራ
መስክ፤ በሚያራምደው የፖለቲካ መስመር፤ የሚያምንበት ሃይማኖት አድሎ እንደማይደረግበት
የወንጀለኛ ህጉ አንቀፅ 4 እና ህገ መንግስቱ አንቀፅ 25 ዋስትና ይሰጣሉ፡፡

ሆኖም ግን የወንጀል ህጉ አንቀፅ አራት ፓራግራፍ ሁለት ላይ በወንጀል አድራጊዎች መሃከል


ልዩነት እንደሚደረግ ይገልፃል፡፡

30
ይህ ከዚህ በላይ ከተገለፀው የእኩልነት መርህ ጋር ይቃረናል? መልሱ አይቃረንም ነው፡፡
ምክንያቱም ሁለት ወንጀል አድሪጊዎች በህግ ፊት እኩል ናቸው ማለት ሁለቱም በአንድ
አይነት የህግ ስነ ስርዓት አካሄድ መሠረት ይዳኛሉ ወይም ይቀጣሉ ማለት አይደለም፡፡ ይህ
ጉዳይ የክስ አቀራረብ፣ የፍርድ ቤት ነገሩን የማየት ስልጣንና የመሣሠሉት የህግ ስነ ስርዓት
ጉዳዮች ናቸው፡፡ እንዴት እንደሆነ ቀጥለን እንመልከት

1. በአብዛኛው የአላማችን ክፍል ኢትዮጵያንም ጨምሮ የፓርላማ አባላት በብዙ ሺህ


የሚቆጠር ህዝብ ወክለው የህግ አውጭውን ወንበር ስለሚይዙ የተወሰነ የስነ ስርዓት
ህግ ከለላ አላቸው፡፡ አንድ ወንጀል አድራጊ የሚያዝበት ስርዓት እና አንድ የፓርላማ
አባል የሚያዝበት ስነርዓት የተለያየ ነው፡፡ ይሀ ማለት ግን የፓርላማ አባል ወንጀል
አድራጊ ሆኖ ከተገኘ ከቅጣት ነፃ ነው ማለት አይደለም፡፡ ፓርላማው ህግን ተከትሎ
የአባሉን ያለመከሰስ መብት ካነሣው በኋላ እንደማንኛም ዜጋ ይከሠሣል ይቀጣልም፡፡

2. ሁለተኛው እና ወንጀል አድራጊዎች ባደረጉት ወንጀል በፈፀሙበት ቦታ የማይጠየቁበት


የህግ ስነ ስርዓት ደግሞ የዲፕሎማቲክ የህግ ከለላ የሚባለው ነው፡፡ ይህ ሁለት
አገሮች የሚስማሙት አለም አቀፍ ስምምነት ወይም በአለም አቀፍ ህግ መሠረት
ሊሆን ይችላል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው ይሄም ግለሰብ ያለመከሰስ መብት የተሰጠው
ወንጀል በፈፀመው ቦታ ብቻ ነው፡፡

ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ ብቻ ተጠያቂ ስለመሆኑ

በዚህ መሠረታዊ የወንጀል ህግ መርህ መሠረት አንድ ሰው በወንጀል ሊጠየቅና ሊቀጣ


የሚችለው ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ ብቻ ነው፡፡ በወንጀል ድርጊት እስካልተሣተፈ
ድረስ የወንጀል አድሪጊው ጓደኛ ወይም ዘመድ ስለሆነ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ የወንጀል
ተጠያቂነት በባህሪው ፈፃሚውን ወይም ፈፃሚዎቹን ብቻ የሚመለከት ነው፡፡ ይህ
በሌሎች የፍትሐብሔር ህጐች የሚሠራ አይደለም፡፡ ማንኛውም ሰው በውል ያልገባውን
ግዴታ እንዲፈፅም ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ አባት በውል ሊፈፀም የገባውን ግዴታ
ሣይፈፅም ቢሞት ወራሹች እንዲፈፅሙ ሊገደድ ይችላሉ፡፡ እዚህ ላይ ውሉን

31
የተዋዋለው አባታቸው ቢሆንም እንኳን ወራሾች ባለተዋዋሉት ውል በወረሱት ልክ
እንዲፈፅሙ ሊጠሩ ይችላሉ፡፡ የዚህ አይነቱ አሰራር በወንጀል ህግ ተነባራዊ ማድረግ
አይቻልም፡፡ ተጠየቂው ፈፃሚው ብቻ ነው፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. የወንጀል ህግ ይርጋ ለምን አስፈለገ? በቡድን ተወያዩ

2. “ሀ” የተባለው ግለሰብ ሰኔ 30 ቀን 1992 ዓ.ም ክስ ለማቅረብ የይርጋ ዘመኑ አመስት


አመት የሆነ ወንጀል ቢፈፅም

ሀ. ሊከሰስ ይችላል? (ግንቦት 1 ቀን 1997 ዓ.ም አዲስ የወንጀል ህግ መውጣቱን


አስታውሱ)

ለ. ግንቦት 1 ቀን 1997 በወጣው ህግ መሠረት “ሀ” የፈፀመው የስርቆት ወንጀል የክስ


ይርጋ ዘመኑ አመስት አመት መሆኑን ቀርቶ ወደ ስድስት አመት ቢራዘም ሊከሰስ
ይችላል?

3. አንቀፅ 9(3) መሠረት ይህ ህግ በመፅናቱም ሆነ በፊት የተሠጡ ቅጣቶች የሚፈፅሙት


በአዲሱ የወንጀል ህግ ነው፡፡ ይሄንን አፈፃፀም በአዲሱ ህግ ማድረጉ ለምን አስፈለገ?
ጠቀሜታ አለው? ካለው ያብራሩ፡፡

4. አንቀፅ 10 ላይ የተመለከተው የወንጀለኞችን ሪከርድ መሠረዝ እና መሰየም ማለት ምን


ማለት ነው? በቡድን ተወያዩ

32
ምዕራፍ ሶስት
በወንጀል ህግ ተጠያቂነት

የምዕራፉ አላማዎች
1. የወንጀል ህግ ተጠያቂ የሚያደርጉትን ቅድመ ሁኔታዎች ይገነዘባሉ፣

2. የምክንያትና ውጤት ግንኙነት ምንነትና አላማውን ይረዳሉ፣

3. ምክንያትና ውጤት ግንኙነት ሊያቋርጡ የሚቻሉ ምክንያቶችንና ህጋዊ ውጤታቸውን


ይዘርዝራሉ፣

4. በህግ ሰውነት የተሰጠው አካል የወንጀል ተጠያቂነትን ከወንጀል ቅድመ ሁኔታዎች ጋር


ያለውን ልዩነት ያያሉ፣

5. መሠናዳትና ሙከራ በወንጀል ህጉ የላቸውን ህጋዊ ውጤት ይገነዘባሉ፣

በወንጀል ህግ ተጠያቂነት ቅድመ ሁኔታ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት የወንጀል ህግ የተለያዩ የተከለከሉ


ድርጊቶችንና እንዲፈፀሙ የታዘዙ ግዴታዎችን ይዘረዝራል፡፡ እነኚህ ድንጋጌዎች
የሚጠብቁት የመብት አይነት ቢለያይም በወንጀል ህግ ተጠያቂ ለማድረግ ግን አንድ አይነት
ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 23 መሠረት
አንድ ሰው ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ ተጠያቂነት ሊከተል የሚችለው ሶስት ቅድመ ሁኔታዎች
ሲሟሉ ነው፡፡ እነኝህም ፡-

ሀ. ህጋዊ ፍሬ ነገር

ለ. ግዙፋዊ ፍሬ ነገር

33
ሐ ሞራላዊ ፍሬ ነገር በአንድ ላይ ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው አንድ
ሰው ወንጀል አድርጓል ተብሎ ተጠያቂ የሚሆነው ሁሉንም ተራ
በተራ እንመልከታቸው፡፡

አ ንቀ ፅ 2 3 (2 )

አንድ ወንጀል ተደረገ የሚባለው ወንጀሉን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፣ ገዙፋዊ እና ሞራላዊ


ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ብቻ ነው፡፡

ህጋዊ ፍሬ ነገር

አ ንቀ ፅ 2 3 (1 )

ሕገ ወጥነቱና አስቀጪነቱ በሕግ የተደነገገውን ድርጊት መፈፀም ወንጀል ነው፡፡ በዚህ


ሕግ ውስጥ ድርጊት ማለት በሕግ የተከለከለውን ማድረግ ወይም በሕግ የታዘዘውን
አለማድረግ ነው፡፡

አንድ ድርጊት ወይም ያለማድረግ በወንጀል ህግ ያስቀጣል ተብሎ በግልፅ እስካልተደነገገ


ድረስ ኃላፊነትን አያስከትልም፡፡ ይህ ድንጋጌ ከሌለ የተፈፀመው ድርጊት ለሞራል ተቃራኒ
ቢሆንም እንኳን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ኃላፊነትን አያስከትልም፡፡ ይህ ድንጋጌ የወንጀል
ህግ መሠረታዊ ከሆነው የህጋዊነት መርህ ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው፡፡ ስለሆነም
ማንኛውም ፍርድ ቤት ህገ ወጥነቱ በህግ ያልተደነገገን ድርጊት ወይም ግድፈት እንደ
ወንጀል ሊቆጥረው አይቻልም፡፡ ባለፈው አንዳየነው አንድ ሰው አጥፋተሃል ብሎ ከመቅጣት
በፊት ማስጠንቀቂያ መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ ማስጠንቀቂያ የሚሆነው ደግሞ በወንጀል ህጉ
የተከለከለ ድርጊት መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ሊቻል ነው፡፡

ግዙፉዊ ፍሬ ነገር

በዚህ ቅድመ ሁኔታ መሠረት አንድ ሰው ወንጀል የመፈፀም ሃሣብ ካለው በድርጊት
እስካልተገለፀ ድረስ ተጠያቂነትን አያስከትልም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ወንጀል የመፈፀም
ሃሣብ ኖሮት በድርጊት አስካልገደጸው ድረስ ማንም ሊያውቀው አይችልም፡፡ አንድ ሰው
ወንጀል ለመስራት አስቦ በድርጊት ካልገለፀው አይቀጣም የሚለው ድንጋጌ መሠረታዊ የሆነ
34
የወንጀል መርህ ነው፡፡ ወንጀል በድርጊት ወይም ከሃሣብ በመነጨ አካላዊ እንቅስቃሴ
መፈፀም መቻል አለበት፡፡ ሃሣብ በሚታይ አካላዊ እንቅስቃሴ ካልተደገፈ ወንጀል ፈፃሚው
ያሠበውን ነገር ራሱ ብቻ ስለሚያውቀው ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም፡፡

ለምሣሌ፡- አንድ ሁል ጊዜ ጐረቤቱን ለመግደል የሚያስብ ሰው ሃሣቡን


ለመፈፀም መወሰኑን በተግባር ካላሠየን ማ ንም ሊያወቅ
አይችልም፡፡

ግዙፋዊ ቅድመ ሁኔታ የሚባለው ፍሬ ነገር በስሩ የተለያዩ ጉዳዮችን የያዘ ነው፡፡

ድርጊት
በድርጊት የተፈፀመ ወንጀል ማለት አንድ እንዳይፈፀም ክልከላ ወይም እገዳ የተደረገበትን
ድርጊት መፈፀም ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በአንቀፅ 538 መሠረት ማንም ሰው አሳቦ ወይም
በቸልተኝነት በማናቸውም አይነት መሣሪያ ወይም ዘዴ ሌላውን ሰው የገደለ እንደሆነ
ነፍስ ገዳይ እንደሆነና ተጠያቂ እንደሚሆን ይገልፃል፡፡ በዚህም መሠረት አንድ ሰው ለብዙ
ጊዜ ለመግደል ሲያስብ የቆየውን ጐረቤቱን ጠመንጃ ገዝቶ በጥይት መቶ ቢገድለው ወይም
በሴንጢ ወግቶ ቢገድለው የወንጀል ህጉ እንዳይፈፀም ክልከላ ያደረገበትን ነገር ስለፈፀመ
ይቀጣል፡፡

አለማድረግ
ይህ ከላይ ከተገለፀው ጋር ተቃራኒ ነው አለማድረግ ማለት በወንጀል ህጉ ላይ እንዲያደረግ
የታዘዘውን ነገር አለመፈፀም ማለት ነው፡፡ በርግጥ በህጉ ከተዘረዘሩት የወንጀል አይነቶች
አብዛኛዎቹ በድርጊት አማካኘነት የሚፈፀሙ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን እንዳንዶቹ የሚፈፀሙት
በህጉ የታዘዘን ጉዳይ ባለመፈፀማቸው ነው፡፡

ለምሳሌ፡- አንቀፅ 443(1) ማንም ሰው በቂ ምክንያት ሳይኖረው፡-

35
ሀ. በሞት ወይም በዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት የሚያስቀጣ ወንጀል
መፈፀሙን ወይም የወንጀለኛውን ማንነት እየወቀ ለሚመለከታቸው
ባለሥልጣኖች ሳያስታውቅ የቀረ እንደሆነ፤ ወይም

ለ. በሕግ ወይም በመያው ደንቦች ለህዝብ ደህንነት ወይም ሰላምና


ሥር ዓ ት ሲባል አንዳንድ ወንጀሎችን ወይም አንዳንድ ከ ባድ
ሁኔታዎችን ለሚመለከታቸው ባለሥልጣኖች የማስታወቅ ግዴታ
እያለበት ይህን ግዴታውን ሳይፈፅም የቀረ እንደሆነ፤

ከብር አንድ ሽህ በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከስድሰት ወር


በማይበልጥ ቀላል አሥራት ይቀጣል፡፡

በአንቀፅ 443 መሠረት አንድ ሰው በህጉ መሠረት የተገለፀውን ወንጀል ሲፈፀም ካየ


ለሚመለከተው አካል ማስታወቅ አለበት፡፡ በዚህ ህግ መሠረት አንድ ሰው ሊቀጣ
የሚችለው እንዲፈፅም የታዘዘውን ግዴታ ባለመፈፀሙ ብቻ ነው፡፡

የምክንያትና ውጤት ግንኙነት

አንድ የወንጀል ድርጊት ጉዳት ወይም አደጋ አስከትሎ ከሆነ በድርጊቱና በውጤት መሃከል
የምክንያትና የውጤት ግንኙነት አለ ማለት ይቻላል፡፡ ይሄን የምክንያትና ውጤት ግንኙነት
ማረጋገጥ ከተቻለ ድርጊቱን የፈፀመው ሰው ለደረሰው ጉዳት በወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡
ሆኖም ግን ለውጤቱ ምክንያት የሆነው ጉዳይ ግልፅ ካለሆነ እጅግ ውስብስብ ችግሮች
ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡

በዚህ ዙሪያ በተለያዩ ሙህራኖች ሁለት አይነት የምክንያትና ውጤት ንድፈ ሃሣብ
ያቀርባሉ፡፡ የመጀመሪያው በርቀት ያለ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ንድፈ ሃሣብ መሠረት “ይህ
ባይሆን ኖሮ” ውጤት አይከተልም ነበር በሚል ውጤቱ ከመከሠቱ በፊት ያሉ ድርጊቶች
ወይም ክስተቶችን በሙሉ ምክንያት አድርጐ የሚወስድ ነው

36
ለምሳሌ ፡- “ሀ” በቅርብ የሚያውቀው ጓደኛው “ለ”ን የልደት በአሉ ላይ እንዲገኝ ጥሪ
አድርጐለት በቀጠሮው መሠረት ልደቱ ላይ ለመገኘት “ለ” መኪናውን
እያሽከረከረ ሲሄድ አደጋ አጋጥሞት ቢሞት ለሞቱ ምክንያት “ሀ” ነው፡፡

በዚህ ንድፈ ሃሢብ መሠረት “ሀ” “ለ”ን የልደት በዓሉ ላይ እንዲገኝ ጥሪ ባያደርግለት ኖሮ
መኪና አያሽከረክርም ነበር ቢያሽከረክር ደግሞ አይሞትም ነበር በማለት ከውጤቱ በፊት
የተፈጠሩ ክስተቶች በሙሉ ምክንያት አድርገው ይቆጠራሉ፡፡

ሁለተኛው የምክንያትና ውጤት ንድፈ ሃሣብ የቅርብ ወይም በቂ የሚባለው ምክንያት


ነው፡፡ በዚህም መሠረት አንድ ምክንያት ሁሌም ባይሆን በአብዛኛው አንድን ውጤት
የሚያስከትል ከሆነ በቂ ምክንያት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይሄንን ንድፈ ሃሣብ ከግምት
ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ የሚለውን ቀጥለን እንመለከት

አ ንቀ ፅ 2 4 (1 )

አንድ ወንጀል አፈፃፀም አንድ የተወሰነ ውጤት እንደሚያመጣ የታወቀ በሆነበት


ጊዜ ሁሉ፣ ውጤቱን ያስገኘው ተከሳሽ የተከሰሰበት ድርጊት መሆኑ ካልተረጋገጠ
በቀር ወንጀሉ እንደተደረገ አይቆጠርም፡፡

ምክንያቱና በውጤቱ መካከል ግንኙነት አለ የሚባለውን በነገሮች የታወቀ ወይም


የተለመደ ሂደት የተከሳሽ ድርጊት ውጤቱን ለማስገኘት የሚችል ሆኖ ሲገኝ
ነው፡፡

በዚህ አንቀፅ መሰረት አንድ ወንጀል ድር ጊ ት ተፈፅሟል ለማለት ከሚያስፈልጉት


መሠረታዊ ጉዳዩች የምክንያትና ውጤት ግንኙነት መኖር ነው፡፡ የወንጀል ህጉ ጥበቃ
የሚያደርግለት በአንድ መብት ላይ አደጋ ደርሶ ከሆነ ለውጤቱ መድረስ ምክንያት የሆነ
ድርጊት ወይም ያለማድረግ ጉዳት አስከትሎ ከሆነ በሁለቱ መካከል የምክንያትና ውጤት
ግንኙነት አለ ማለት ይቻላል፡፡

ለምሳሌ፡- 494 እንመልከት በዚህ አንቀፅ መሠረት የእሳት ቃጠሎ ማድረስ ወንጀል
እንዲኖር አንድ ሰው በንብረት ላይ አደጋ ለማድርስ አስቦ በንብርቶቹ ላይ
ከሣት መለኮስ አለበት፡፡ ግለሰቡ እሣቱን በንብርቱ ላይ መለኮሱ ምክንያት
37
ሲሆን የንብረቱ ቃጠሎ ደግሞ ውጤት ነው፡፡ በዚህም መሠረት በአደጋውና
በድርጊቱ መካከል የምክንያትና ውጤት ግንኙነት አለ ማለት ይቻላል፡፡

ጥያቄ፡- አንድ ድርጊት ወይም አለማድረግ ለውጤቱ ምክንያት ነው የሚባለው እንዴት


ነው?

1. “ሀ” ተማሪው “ሐ” ያልተገባ ባህሪ ስላናደደው በጥፊ መታው፤ ተማሪው ወዲያው
ሞተ፡፡

2. “ለ” ጐረቤቱ “መ” ለመግደል አስቦ በየዘው ጠመንጃ ተኩሶ ቅልጠሙ ላይ


መታው፡፡ “መ” ወዲያው ሞተ፡፡

3. “ለ” ጐረቤቱ “መ”ን ለመግደል አስቦ በየዘው ጠመንጃ ተኩሶ ጭንቅላቱ ላይ


መታው፡፡ “መ” ህክመና ለመከታተል ሆስፒታል እንዳለ ሞተ፡፡

ጥያቄ ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ በአንቀፅ 24(1) መሠረት የምክንያትና


ውጤት ግንኙነት መኖሩን አስረዳ?

ጥያቄ አንድ በህግ ጥብቃ የተደረገለት መብት ወንጀል ሲፈፀም ፈፃሚውን


ተጠያቂ ለማድረግ ሁል ጊዜ የምክንያትና ውጤት ግንኙነት መኖር
አለበት?

ምክንያትና ውጤትን ሊያቋርጡ የሚችሉ ጉዳዮች

በኑሮ እጅግ ውስብስብ በሆነበት በአሁኑ ዘመን ብዙ ምክንያቶች በሚያጋጡበት ጊዜ


ማለትም የተደራረቡና ጣልቃ ገብ ምክንያቶች በመፈጠራቸው የመጀመሪያው ምክንያት
የተከሳሹ ድርጊት ላይሆን ይችላል፡፡ ከአንዱ ድርጊት በኋላ ውጤቱን ማስከተል የሚችል
ጣልቃ ገብ ምክንያት ሊኖር የመቻሉን ያህል ካለው ድርጊት አስቀድሞ የደረሰ የሌላ ሰው
ድርጊት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በዚህን ጊዜ በተከሳሹ ድርጊትና በውጤቱ መካከል ሊኖር
ይችል የነበረው ግንኙነት ይቋረጣል በአንቀፅ 24(2) መሠረት ሶስት እንግዳ ምክንያቶች
የምክንያትና ውጤት ግንኙነት ያቋርጣሉ፡፡

38
አ ንቀ ፅ 2 4 (2 )

ለተከሳሹ እንግዳ ከሆነ የሌላ ሰው አድራጐት፣ ፍጥረታዊ ነገር ወይም አጋጣሚ


ሁኔታ የተነሳ አስቀድሞ የደረሰ፣ የተደረበ ወይም ጣለቃ የገባ ምክንያት በተገኘ
ጊዜ ይህ እንግዳ ምክንያት ራሱን ችሎ አንድን ውጤት ያስከተለ ሲሆን በተከሳሹ
ድርጊትና በውጤቱ መካከል ሊኖር ይችል የነበረው ግንኙነት ይቋረጣል፡፡

ሀ. አስቀድሞ የደረሰ (ይህ አዲስ ነው)

ተከሳሹ ከፈፀመው ድርጊት በፊት እንግዳ የሆነ የሌላ ሰው አድራጐት፣ ፍጥረታዊ ነገር ወይም
አጋጣሚ ሁኔታ የተነሣ በህግ ጥበቃ የተደረገለት መብት ጉዳት ሲደርስበት ነው፡፡

ለምሣሌ፡-

“ሀ” “ለ” በተባለ ባላጋራው ክፉኛ በጥይት ቢመታና በድጋሚ “ሐ” በተባለ ሰው በጥይት
ተመቶ ቢቆስልና ቢሞት “ሐ” የተኮሰው ጥይት በህክምና ለሞት የማያደርስ መሆኑ
ከተረጋገጠ “ሀ” ለሞት ያበቃው ምክንያት የመጀመሪያው በ”ለ” የተተኮሰው ጥይት
ይሆናል፡፡ ስለሆነም በ”ሐ” ተመስርቶ የነበረው ሰው የመግደል ወንጀል ተጠያቂነት ወደ
መግደል መከራ ይቀየራል፡፡

ለ. ተደራራቢ ምክንያት
በዚህ መሠረት ለአንድ ውጤት መድረስ ከአንድ በላይ የሆኑ ምክንያቶች ሲኖሩና እነዚህም
ምክንያቶች በአንድ ጊዜ የተፈፀሙ ድርጊቶች ከሆኑ ነው፡፡

ለ ምሣ ሌ

“ሀ” “ለ” መንገድ ላይ ያገኙትን ነጋዴ ለመዝረፍ አስበው በአንድ ጊዜ በጥይት ተኩሰው
ቢገድሉት ለሞቱ ተደራራቢ ምክንያት እንዳለ ይገመታል፡፡

ጥያቄ፡- ሁለቱም በሰው መግደል ወንጀል መጠየቅ አለባቸው? እንዴት?


39
ሐ. ጣልቃ የገባ ምክንያት
እዚህም እንደሌሎቹ ሁሉ ከአንድ በላይ የሆኑ ምክንያቶች ኖረው ሆኖም ግን በተለያየ ጊዜ
የተፈፀሙ ድርጊቶች ናቸው፡፡ በፊት ከተፈፀመው ድርጊቶች በማስከተል የተፈፀሙት ጣልቃ
ገብ በመባል ይታወቃሉ፡፡

ለምሳሌ፡- “ሀ” “ለ”ን በጥይት ከመታው በኋላ መብረቅ ቢመታውና ቢሞት ጣልቃ የገባው
መብረቅ በ”ሀ” ድርጊት እና በ”ለ” መሞት መካከል ያለውን የምክንያት ውጤጥት
ግንኙነት ያቋርጣል፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. ጣልቃ ከገባው ምክንያት በፊት የነበረው ድርጊት በራሱ ውጤቱን ቢያስከትል


የምክንያትና ውጤት ግንኙት ይቋረጣል?

2. 24(3) አዲስ የገባ አንቀፅ ነው፡፡ በዚህ አንቀፅ መሠረት የተለያዩ ምክንያቶች
እያንዳንዳቸው ራሣቸውን ችለው አንድ ውጤት ማምጣት ባይችሉም ተደምረው
ውጤት ካስገኙ ሁሉም ለውጤቱ ምክንያቶች ናቸው ይላል ምን ማለት ነው?
በምሣሌ አብራራ፡፡

3. “ሀ” እና ጓደኛው “ለ” የሣምንቱን መጨረሻ ከአዲስ አበባ ውጭ ለማሣለፍ


ይወስናሉ፡፡ በዚህም መሠረት ትናንት ጧት “ለ” በሚያሽከረክረው መኪና ከከተማው
ለመውጣት ትንሽ ሲቀራቸው መኪናው ባፈናጠረው ድንጋይ አንድ መንገደኛ “ሐ”
ይቆስልና ይሞታል፡፡ ይሄንን የተመለከተው የ”ሐ” ጓደኛ “መ” በያዘው ሽጉጥ
ለመግደል “ለ” ላይ ሲያነጣጥር “ለ” በነበረበት የልብ ድካም ምክንያት ደንገጦ
ይሞታል፡፡ የጓደኛው መሞት ያበሣጨው “ሀ” እቤት ገብቶ ራሱን ያጠፋል፡፡

40
ጥያቄ ፡- በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ የምክንያትና ውጤት ግንኙነት መኖሩን
አለመኖሩን በዝርዝር አስረዳ

ሀ. በ “ለ” መኪና ማሽከረከርና (ድርጊት)በ “ሐ” ሞት (ውጤት)

ለ. በ “መ” ሽጉጥ ማነጣጠርና (ድርጊት) በ “ለ” ሞት (ውጤት)

ሐ. በ”መ” ሽጉጥ ማነጣጠርና (ድርጊት) በ “ሀ” ሞት (ውጤ)

የሃሣብ ክፍል

ይህ ሶስተኛው ከዚህ በፊት ከተዘረዘሩት በአንድ ጋር መገኘት ያለበት የወንጀል ቅድመ ሁኔታ
ነው፡፡ በዚህ መሠረት አንድ ሰው በህግ ጥበቃ የተደረገለት መብት ላይ ድርጊቱን የፈፀመው
በወንጀል አጥፊነት መንፈስ መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው የደረሰውን ጉዳት አስቦ ወይም
በቸልተኝነት መፈፀሙ ካልተረጋገጠ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ
ነገር የተፈፀመ ተደርጐ ስለሚታይ በወንጀል ህግ ሊፈርድበት እንደማይገባ አንቀፅ 57
ያሣያል፡፡ ስለሆነም ይህ ቅድመ ሁኔታ እንዲሟላ በወንጀል አጥፊነት መንፈስ ድርጊቱ
መፈፀሙን ማረጋገጥ አለብን፡፡

አ ንቀ ፅ 5 7 (1 ) (2 )

1. በሕጉ መሰረት ጥፋተኛነቱ ካልተረጋገጠ በቀር ማንም ሰው ሊቀጣ አይችልም፡፡

ለድርጊቱ ኃላፊ ሊሆን የሚገባው ሰው አስቦ ወይም በቸልተኛነት አንድ ወንጀል


ካላደረገ በቀር በወንጀል ጥፋተኛ አይሆንም፡፡

2. ማንም ሰው የፈፀመው ድርጊት በሕገ የሚያስቀጣ ቢሆንም ምንም ጥፋት ሳያደርግ


ወይም ከአቅም በላይ በሆነ ኃይል መክንያት ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ ነገር
የተፈፀመ ወይም የደረሰ ሆኖ ሲገኝ በወንጀል ሕግ ሊፈረድበት አይገባውም፡፡

41
በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ መሠረት የሃሣብ ክፍል ለሁለት ይከፈላል፡፡ እነዚህም አስቦ ወንጀል
ማድረግ እና በቸልተኝነት ወንጀል ማድረግ ተብለው የራሣቸውን ንኡሣን ክፍል ይዘው
ይገኛሉ፡፡

አስቦ ወንጀል ማድረግ

በአንቀፅ 58 መሠረት አንድ ሰው ወንጀል አስቦ አድርጓል ሊባል የሚችልበትን የተለያዩ


ቅርፆች ያሣያል፡፡

ቀጥተኛ የሆነ አጥፊነት


አንቀፅ 58(1) (ሀ)

አንድ የተወሰነን ውጤት ለማግኘት ብሎ ሕገ ወጥና የሚያስቀጣን


ድርጊት እያወቀ በራሱ ፍላጐት ያደረገ እንደሆነ፣

በአንቀፅ 58(1)(ሀ) መሠረት እውቀትና ፍላጐት ሁለት የቀጥተኛ የሆነ አጥፊነት ቅድመ
ሁኔታዎች እንደሆኑ ያሣያል፡፡

እውቀት

አንድ ሰው ወንጀሉን አውቆ ፈፅሟል ለማለት ድርጊቱን የሚፈፀምበት ሁኔታ እና ውጤቱን


በተመለከተ እውቀት ወይም ግንዛቤ እንደነበረው ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ማንም ሰው
ያዉቃቸዋል ተበለው የሚገመቱ ሁኔታዎች በወንጀል ፈፃሚው ይታወቃሉ ተብሎ ይገመታል፡፡
ጥይት ሰው እንደሚገድል አልኮል እንደሚያሰክር ወዘተ በሁሉም ሰው የሚታወቅ ተራ ጉዳይ
ነው፡፡

ለምሳሌ “ሀ” የተባለው የአዲስ አበባ ነዋሪ የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደሙ ውስጥ እንዳለ
እያወቀና ሆን ብሎ የፍቅር ጓደኛውን ለመጉዳት አስቦ ያለጥንቃቄ የግብረ ስጋ
ግንኙነት ቢፈጽምና ጓደኛው የኤች አይ ቪ ቫይረስ ቢገኝባት “ሀ” የኤች አይ ቪ
42
ቫይረስ በግብረ ስጋ ግንኙነት እንደሚተላለፍ አላውቅም ብሎ ሊከራከር
አይችልም፡፡ ይህ በተለይ አዲስ አበባን በመሰለና የመገናኛ ብዙሃን በየቀኑ ስለ
በሽታው መተላለፊያ መንገድ በሚሰብኩበት ከተማ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

43
ፍላጐት

አንድ ወንጀል አድራጊ ፍላጐት ነበረው ለማለት የድርጊቱን መፈፀም ወይም በድርጊቱ ምክንያት
የሚገኘውን ውጤት ፈልጐ በፍቃደኝነት ሲፈፅም ነው በዚህም መሰረት ከወንጀል ድርጊቱ
የተነሳ የደረሱት ውጤቶች አስቀድመው የታዩ እና የተፈለጉ ናቸው፡፡

ቀጥተኛ ያልሆነ አጥፊነት


አ ንቀ ፅ 5 8 (1 ) (ለ )

ድርጊቱ ሕገ ወጥና የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል እያወቀ


የሆነው ይሁን ብሎ ውጤቱን በመቀበል ድርጊቱን ያደረገ እንደሆነ፤ ነው፡፡

በአንቀፅ 58(1)(ለ) መሠረት ወንጀል የፈፀመ ሰው ድርጊቱ የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከተል


እንደሚችል እያወቀ እሱ የፈለገውን ውጤት ወይም መድረስ ያሰበበት አላማ መድረስ እስከቻለ
ድረስ የሆነው ይሁን ብሎ ውጤቱን በመቀበል ድርጊቱን ያደረገ እንደ ሆነ ነው፡፡

ቀጥተኛ ባልሆነ አውቆ አጥፊነት ወንጀል የሚፈፅም ሰው ድርጊቱ ጉዳት እንደሚያስከትል


በእርግጠኝነት በተቃረበ ሁኔታ አያውቅም ሆኖም ግን ድርጊቱ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል
ይገምታል ከዚህ በተጨማሪ ቀጥተኛ ያልሆነ አጥፊነት መለያ ባህሪው ውጤትን መቀበል
ነው፡፡ ወንጀል አድራጊው ከድርጊቱ የተነሳ የሚደርሰውን ውጤት ፈልጐታል ባይባልም
መድረሱን ግን አይቃወምም ውጤቱ ቢደርስም ባይደርስም ግድ አይሰጠውም፡፡ ውጤቱን
መቀበልና ያለመቀበል ሁለቱን የወንጀለኛነት የሃሳብ ክፍሎች ለይቶ ለማወቅ በመጥቀሙም
በተጨማሪ የወንጀል አድራጊውን ሃላፊነት ለመወሰን ይጠቅማል፡፡

በችልተኝነት ወንጀል ማድረግ

ቸልተኝነት ከስሙ እንደምንረዳው አንድ ሰው ጥንቃቄ ማድረግ ሲገባው ሣያደርግ ሲቀር ነው፡፡
በዚህም የጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት ያልተፈለገ እና ሊወገድ የሚችል ጉዳት ሲደርስ ነው፡፡
አንቀፅ 59(1) የቸልተኝነት አይነት ሁለት ናቸው፡፡

44
የታወቀ ቸልተኝነት

አንቀፅ 59(1) (ሀ)

ሀ. ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል እያወቀ


እይደርስም የሚል ግምት ወይም ባለማመዛዘን፣

በ59 (1) (ሀ) መሠረት አንድ ሠው በታወቀ ቸልተኝነት ሊቀጣ የሚችለው ድርጊቱ በወንጀል
የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚቻል እያወቀ አይደርስም በሚል ግምት ወይም
ባለማመዛዘን የፈፀመ እንደ ሆነ ነው፡፡ በሌላ አነጋግር ድርጊቱ ጉዳትን እንደሚያስከትል
ያውቃል ሆኖም ግን የድርጊቱን ውጤት አይቀበልም፡፡ ምክንያቱም ድርጊቱ ጉዳት ያደርሣል
ብሎ አያምንም ወይም ጉዳት ለመከላከል እያደረገ ያለው ጥንቃቄ በቂ በመሆኑ ጉዳት
አይደርስም የሚል ግምት አለው፡፡

አንድ የታከሲ ሹፌር ባለቤቱ ስልክ ደውላ ስታናግረው የመኪናውን መፍጠን ተረድታ “ረጋ
ብለህ ሂድ” ብላ ብትጠይቀውና እሱም፡፡ 15 አመት መኪና የመንዳት ልምድ አለኝ አታሰቢ
ቢል” እና ከ2 ደቂቃ በኋላ ሰው ገጭቶ ቢገድል በዚህ አንቀፅ ይታያል

ያልታወቀ ቸልተኝነት

አ ንቀ ፅ 5 9 (1 ) (ለ )

ድርጊቱ በወንጀል የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ እያለበት ወይም


እየቻለ፣ ባለመገመት ወይም ባለማሰብ፤ ድርጊቱን የፈፀመ እንደሆነ ነው፡፡

የወንጀል ቸልተኝነት አለ የሚባለው የአድራጊው የግል ሁኔታ፣ በተለይም ዕድሜው፣


ያለው የኑሮ ልምድ፣ የትምህርት ደረጃው፣ ሥራው እና የማኅበራዊ ኑሮ ደረጃው
ሲመዘን በጉዳዩ ሁኔታዎች ሊደረጉ ይገባል ተብሎ በአግባቡ የሚጠበቁትን ጥንቃቄዎች
ያላደረገ እንደሆነ ነው፡፡

45
በአንቀፅ 59(1) (ለ) መሠረት ያልታወቀ ቸልተኝነት የሚባለው ወንጀል ፈፃሚው ድርጊቱ
ጉዳት እንደሚያስከትል ሳያውቅ ሲቀር ወይም ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ባለመገንዘቡ
ጉዳት ሲያደርስ ነው፡፡

ቸልተኝነት እና ቅጣት
አ ንቀ ፅ 5 9 (2 )

በተደረገው ጥፋት ዓይነት ወይም ከባድነት ወይም በሕብረተሰቡ ላይ ሊያደርስ


በሚችለው አደጋ ምክንያት በሕጉ ላይ በተለይ ያስቀጣል ተብሎ ካልተደነገገ በቀር
በቸልተኛነት የተፈፀመ ድርጊት አያስቀጣም፡፡

ፍርድ ቤት በወንጀል አድራጊው ላይ ቅጣት የሚወስነው፣ ድርጊቱ ሊያስከትል


የሚችለውን ውጤት፣ አድራጊው በኅሉናው እየተረዳው ወይም መረዳት ሲገባው
ካለማመዛዘኑ የተነሳ ያደረገውን የጥፋት ደረጃና የአደገኛነት ባሕሪውን በመመርመር
ነው፡፡

በዚህ በአንቀፅ መሠረት ቸልተኝነት በህጉ ላይ በተለይ ያስቀጣል ተብሎ ካልተደነገገ በቀር
በቸልተኝነት የተፈፀመ ወንጀል አያስቀጣም ስለሆነም አንድ ድርጊት ወይም ያለማድረግ
በቸልተኝነት ቢፈፀሙ ሊያስቀጡ የሚችሉት ህጉ በግልፅ የወንጀል ተጠያቂነት መኖሩን
ካስቀመጠ ነው፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በቸልተኝነት ሲፈፀሙ ሊያስጠይቁ የሚችሉ ወንጀሎችን ጥቄቶቹን ጥቀስ?

2. በቸልተኝነት በህጉ ላይ ተለይቶ ያስቀጣል ተብሎ ካልተደነገገ በቸልተኝነት የሚፈፀም


ወንጀል አያስቀጣም ተብሎ ለምን ተደነገገ?

3. አብዛኛው የወንጀል ድንጋጌዎች የሃሣብ ክፍሉን በግልፅ ሲያስቀምጡ ሌሎች ደግሞ


ወንጀሉ የሚፈፀምበት የሃሣብ ክፍል ማለትም ታስቦ ይሁን ወይንም በቸልተኝነት

46
ሲፈፀም የሚያስቀጣ እንደሆነ አይገልፁም፡፡ እነዚህ በግልፅ የሃሣብ ክፍሉን
የማይገልፁ አንቀፆች ቢያጋጥምህ/ሽ በየትኛው መመደብ አለበት?

 ታስቦ በሚደረግ ወንጀል?

 በቸልተኝነት በሚደረግ ወንጀል?

 ሌላ?

4. በአንቀፅ 58(1)(ለ) እና በአንቀፅ 59(1)(ሀ) መካከለ ያለውን ልዩነት አስረዳ

5. በአንቀፅ 59(1)(ሀ) እና በአንቀፅ 59(1)(ለ) መካከል ያለውን ልዩነት አስረዳ

በህግ ሰውነት የተሰጠው አካል በወንጀል ተጠያቂነት

አ ንቀ ፅ 3 4 (1 )

የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት የመንግሥት አስተዳደር አካላትን ሳይጨምር በሕግ


ላይ በግልፅ በተደነገገ ጊዜ በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት
በወንጀል ሊቀጣ ይችላል፡፡

አንድ ድርጅት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጥሮ የሚቀጣውም በኃላፊዎቹ ወይም ከሠራተኞቹ


አንዱ ከድርጅት ሥራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ የድርጅቱን ጥቅም በህገ ወጥ መንገድ
ለማራመድ በማሰብ፣ ወይም የድርጅቱን ህጋዊ ግዴታ በመጣስ፣ ወይም ድርጅቱን
በመሣሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሣሽነት ወይም
በአባሪነት ወንጀል ሲያደርግ ነው፡፡

በዚህ አንቀፅ መሠረት በህግ የሰውነት መብት ያላቸው ድርጅቶች የመንግስት አስተዳደር
አካላትን ሣይጨምር ወንጀል ፈፅመው በተገኙ ጊዜ እንደሚከሰሱና እንደሚቀጡ በአዲስ መልክ
እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ይህ እስከአሁን የተመለከትነውን ሦስቱ የወንጀል ቅድመ ሁኔታዎች ጋር
በልዩነት የተቀመጠ ድንጋጌ ነው፡፡ ስለሆነም በአንቀፅ 513፣ 716፣ 777 መሠረት በህግ

47
የሰውነት መብት ያላቸው ድርጅቶች የተፈፀመ ወንጀል አንቀፅ 23(3) ላይ የተጠቀሰው የሃሣብ
ክፍል በቅድመ ሁኔታነት አይታይም፡፡

ጥያቄዎች፡-

1. በህግ ሰውነት የተሰጠው አካል ወንጀል ፈፅሞ ቢገኘና ለዚህ ለፈፀመው ወንጀል
በህጉ ላይ የተቀመጠው ቅጣት እሰራት ቢሆን ምን ማድረግ አለበት?

2. በአንቀፅ 34(3) መሠረት የድርጅቱ መቀጣት የድርጅቱ ሃላፊዎች ወይም


ሠራተኞችን ቅጣት እንደሚያስቀረው ይገለፃል፡፡ አንድ ድርጅት ላጠፋው ጥፋት
በወቅቱ የነበረውን ሃላፊ ወይም ሠራትኛ ከተቀጣ ለምን በድጋሚ ድርጅቱ ይቀጣል?
አላማው ምንድን ነው?

የመሠናዳት ተግባሮች

አንቀፅ 26(ሀ) እና (ለ)

ሀ. ራሳቸው ወንጀል ሆነው የሚያስቀጡ መሆናቸው በሕግ የተደነገገ እንደሆነ፤ ወይም

ለ. ከወንጀሎቹ ከባድነትና በአጠቃላይ ከሚያደርሱት አደጋ መጠን የተነሳ ልዩ ወንጀል


መሆናቸው በሕግ በግልፅ የተደነገገ እንደሆነ፤ ያስቀጣሉ

ወንጀል ተጀምሮ እስከጨረሰ የተለያዩ ደረጀዎች ሊኖሩት ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ ወንጀል ወደ


ቁሣዊ ደረጃ ለመለወጥ ሃሣባዊ ውሣኔ ማለፍ አለበት፡፡ ለምሳሌ ሰው ለመግደል ያሰበ

 ማንን መግደል እንዳለበት?

 መቼ መግደል እንዳለበት?

 ለምን መግደለ እንዳለበት ?

 የት መግደል እንዳለበት? የመሣሠሉትን ብቻውን በሃሣብ ያቅዳል፡፡ ይህ


በድርጊት ካልተገለፀ በስተቀር የፈለገውን ቢያስብ አና ቢወስን የወንጀል
ተጠየቂነት አይከተለውም፡፡
48
ለምሳሌ፡- አቶ “ሀ” በአካባቢው የሚገኘውን የልብስ መሸጫ ሱቅ ማታ ለመዝረፍ ያስብና
ልብስ የሚገዛ በመምሰል ሱቁ ውስጥ ገብቶ ከሻጮቹ ጋር በዋጋ እየተከራከረ
የበሩን ቁልፍና የመሳሰሉትን ቢመለከትና እንዴት መግባት እንደሚችል
ቢያጠና ከክሱ በስተቀር ማንም ስላሰበው ነገር መናገር አይችልም፡፡ የሰው ልጅ
ምን እንዳሰበ ራሱ ካልተናገረ በስተቀር ማንም ሊያውቅ አይችልም፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ የመሰናዳት ተግባሮች ከውጤት የራቁ ናቸው፡፡ የመጨረሻውን
የወንጀል ድርጊት በመፈፀም መካከል ሰፊ የሆነ ስነ ልቦናዊና ቁሳዊ ርቀት
አለ፡፡ የተሰናዳ ሁሉ ያሰበውን ወንጀል ይፈጽማል ማለት አይችልም፡፡ ወንጀል
ለመፈፀም የተሰናዳ ሰው ያሰበውን ወንጀል ተግባር ሊተው ይችላል፡፡ በዚህም
መሰረት የመሰናዳት ተግባሮችን የሚያስቀጡ ማድረግ የድርጊቱ ፈፅሚዎች
“መቀጣታችን ካልቀረ ለምን የወንጀሉን ሐሳብ ከግብ አናደርስም” የሚል ውሳኔ
ላይ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው የወንጀል ህጉ የመሰናዳት ተግባሮችን
ከተጠያቂነት ነፃ ያደርገው፡፡

ከዚያም አለፎ ያስበውን ለመፈፀም መሣሪያዎችን ቢገዛ ወይም ሌሎች ምቹ ሁኔታዎች ቢፈጥር
በአንቀፅ 26 መሠረት አያስቀጣም፡፡

ሆኖም ግን የመሠናዳት ተግባሮች እንደወንጀል ተቆጥረው ሊያስቀጡ የሚችሉት በአንቀፅ


26(ሀ) እና (ለ) ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የወንጀል ሙከራ

የወንጀል ሙከራ ያልተሣካና የተቋረጠ የወንጀል ድርጊት ነው ሙከራ ሃሣባዊ ውሣኔና


መሠናዳት ደረጃዎች አልፈው ሆኖም ግን ታስበው የነበሩት ውጠቶች ወይም ጉዳቶች ያላስገኘ
የወንጀል አፈፃፀም ደረጀ ነው፡፡

አ ንቀ ፅ 2 7 (1 )

ማንም ሰው አስቦ ወንጀልን ለማድረግ ጀምሮ የወንጀሉን ድርጊት እስከ መጨረሻው


ያልተከታተለ ወይም ለመከታተል ያልቻለ ወይም የወንጀሉ ድርጊት እንዲፈጸም እስከ

49
መጨሻው ተከታትሎ አስፈላጊ የሆነውን ውጤት ያላገኘ ቢሆንም በመሞከሩ ብቻ
ጥፋተኛ ይሆናል፡፡

ወንጀሉ እንደተጀመረ የሚቆጠረው የተደረገው ተግባር በማያጠራጥር ሁኔታና በቀጥታ


ወንጀሉን ለመፈፀም ወደ ታሰበበት ግብ ለማድረስ የተደረገ በሆነበት ጊዜ ነው፡፡

በአንቀፅ 27 መሠረት አንድ የወንጀል ድርጊት ሙከራ ነው የሚባለው የሚከተሉትን ቅድመ


ሁኔታዎች ሲያሟላ ነው፡፡

ሀ . ሃ ሣብ

ለ. የወንጀሉ ድርጊት መጀመር አለበት

ሐ. የወንጀሉ ድርጊት መፈፀም የለበትም

አንድ የወንጀል ድርጊት ተጀመረ የሚባለው መቼ ነው? ለምሣሌ “ሀ” በግጦሽ መሬት ምክንያት
ከ”ለ” ጋር ስለተጣላ ለመግደል ወስኖ ህገ ወጥ ጠመንጃ ከዘመዱ ላይ ገዛ፡፡ ያስበውን ለመፈፀም
ዛሬ ከምሽቱ 12 ሠዓት ሲሆን ወደ “ለ” ቤት አመራ በዚህ ምሣሌ መሠረት”ሀ” የወንጀለ
ድርጊቱን የጀመረው መቼ ነው

 ጠመንጃ ሲገዛ?

 “ለ” ጊቢ ውስጥ ሲገባ?

 “ለ”ን ሲያየው?

 ጠመንጃውን በ”ለ” ላይ ሲያነጣጥር

 ሲተኩስ?

 ወይስ ሌላ?

ወንጀሉን የተጀመረበትን ጊዜ ማወቅ ተጠርጣሪውን የፈፀመው ድርጊት ዝግጅት ነው ወይንስ


ሌላ? የሚለውን ጥያቄ ይመልስልናል ይሄንን ጊዜ በትክክል መወሰን ካልቻልን የወንጀል
ተጠያቂነትን መመስረት ያስቸግረናል፡፡ የወንጀል አጀማመር ጊዜ ከወንጀል ወንጀል ይለያያል፡፡

50
አንድ ሊሰርቅ ያሰበ ሰው እና ሰው ለመግደል ያሰበ ሰው ወንጀሉን ጀመረ የሚባልበት ጊዜ
የተለያየ ነው፡፡ የወንጀል አጀማመር ከጉዳይ ጉዳይ ይለያያል፡፡ ይሄንን ለመመለስ የቀረበልንን
ጉዳይ በጥንቃቄ ማየት ይጠይቃል፡፡ ጊዜውን መለየት ከቻልን ተጠርጣሪው በዝግጅት ላይ ነው
ወይንስ በሙከራ የሚለው መልስ ያገኛል፡፡

ሌላው መታየት ያለበት ጉዳይ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀም የለበትም፡፡ የታሰበው ወንጀል
ከተፈፀመ ሙከራ ሳይሆን ፍፃሜ ያገኘ ወንጀል ነው፡፡ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 27(1) ላይ
እንደተመለከተው ሙከራ ሁለት አይነቶች ናቸው፡፡

ሀ. ፍፃሜ ያላገኘ

ይህ ወንጀል አድራጊው ያሰበውን ወንጀል ጀምሮ ሆኖም ግን እስከ መጨረሻው ያልተከታተለ


ወይም ለመከታተል ያልቻለ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በሁለት ምከንያቶች ነው፡፡
የመጀመሪያው በራሱ ፍላጐት ማንም ሳያስገድደው የጀመረውን የወንጀል ድርጊት ለሶስተኛ ሰው
ጣልቃ ገብነት ሲያቋርጥ ነው፡፡

ለምሳሌ፡- “ሀ” ብዙ ጊዜ ለመግደል ሲሰናዳበት የነበረው “ለ” ከሩቅ ሲመጣ ያየዋል


የገዛውን ጠመንጃ ካነጣጠረ በኋላ የ “ለ” ሚስት በቅርብ መሞቷ ትዝ
ይለውና ልጆቹን ለምን ያላሣዳጊ አስቀራለሁ ብሎ ተፀፅቶ ይታዋል፡፡

ይህ ምሣሌ የሚያሣየን አቶ “ሀ” ወንጀል መፈፀሙን ያቋረጠው ያለማንም ግፊትና ጣልቃ


ገብነት በራሱ ወስኖ ነው፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ያለው ሌላው ፈፅሜ ያላገኘው ሙከራ ወንጀል አድራጊው እስከ መጨረሻው
ለመከታተል ያልቻለው ነው፡፡ ይህ ሙከራ ፍፃሜ ያለገኘው በራሱ ፈቃድ ሣይሆን በሌላ
ውጫዊ ምክንያት ነው፡፡ ወንጀል ፈፃሚው ያሰበውን ለመፈፀም ፈቃደኛ ሰለሆነ ጀምሮታል፡፡
ሆኖም ግን እንቅፋት አጋጠመው፡፡ በቅድሙ ምሣሌ መሠረት “ሀ” ወንጀሉን ለመፈፀም
ጠመንጃውን ካነጣጠረ በኋላ በአከባቢው የሚያልፍ ሰው ስላየው አቋረጠ፤ ይህ ከራሱ ፍላጐት
የመጣ አይደለም፡፡ ሰው ባያየው ንኖ ወንጀሎን መጨረሻ የማድረስ እቅድ ነበረው፡፡

51
ለ. ፍፃሜ ያገኘ

ይህ የወንጀሉን ድርጊት እንዲፈፀም እስከ መጨረሻው ተከታትሎ አስፈላጊውን ውጤት


አላገኘም፡፡ ውጤት ያስገኛል ብሎ ያስበውን ድርጊት ሙሉ በሙሉ ፈፅሟል፡፡ ሆኖም ግን
የታሰበው ውጤት አልተገኘም፡፡ ምክንያቶቹ በሁለት መንገድ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው
በሞካሪው ነፃ ውሣኔ ምክንያት ውጤት ካላስገኘ ነው፡፡ በቅድሙ ምሣሌ “ሀ” ለመግደል አስቦ
“ለ” ተኩሶ ከመታው በኋላ ወደ ሆስፒታል ወስዶት በህክምና እንዲድን ካደረገው አስፈላጊው
ውጤት አልተገኘም፡፡ ሁለተኛው ፍፃሜ ያላገኘው ሙከራ በፈፃሚው ነፃ ፍላጐት ሣይሆን
በሶስተኛ ወገን ጣሊቃ ገብነት የተሳበው ውጤት ሣይገኝ ነው፡፡ “ለ” በጥይት ከተመታ በኋላ
መንገደኛ ደርሶ ወደ ሆሰፒታል በመውሰድ ህክመና እንዲያገኝ በማድድረግ ህይወቱን ካተረፈው
የተሳበው ውጤት አልተገኘም፡፡ ሊከሽፍ የቻለው በሌላ ሰው ተሣትፎ ነው፡፡

የወንጀል ሙከራ ተጠያቲነት

በአንቀፅ 27(2) መሠረት በህጉ ላይ ተቃራኒ ድንጋጌ ከሌለ በስተቀር የወንጀል ሙከራ ሁል
ጊዜም የሚያስቀጣ ነው፡፡ አድራጊው በመደቡ ለመፈፀም በፈለገው ወንጀል የተደነገገውን ቅጣት
ይቀጣል፡፡ ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ ሙከራው የተፈለገውን ውጤት ያላስገኘበትን ምክንያት
ከርምት ውሰጥ በማስገባት ቅጣቱን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ቅጣቱ ሊ ቀ ንስ የሚቻልበባቸው
ምክንያቶች አንቀፅ 28 ላይ ተዘርዝረዋል፡፡

አ ንቀ ፅ 2 8 (1 )

አድራጊው ሊፈጽመው የነበረውን የወንጀል ድረጊት በገዛ ፍቃዱ የተወ እንደሆነ፤ የነገሩ
ሁኔታዎች የሚገቡ ምክንያቶችን ሲያስገኙ ፍርድ ቤት በሕግ በተፈቀደው ወሰን
መሠረት (አንቀፅ 179) ወይም እንደመሰለው (አንቀፅ 180) ቅጣቱ ያቃልልለታል፡፡
የወንጀል ድርጊቱን የተወው በሐቀኝነት ወይም ከፍ ባለ የሕሊና ስሜት በመነሳሳት
ምክንያት እንደሆነ፤ ፍርድ ቤቱ ከቅጣት ነፃ ያደርጋዋል፡፡

52
ሊፈፀም የማይቻል ወንጀል

አ ንቀ ፅ 2 9

በማናቸውም ዘዴና መሣሪያ ወይም በማናቸውም ነገር ላይ ምንም ቢሆን ሊፈፀም


የማይቻል ወንጀልን ለማድረግ ለሞከረ ሰው ፍርድ ቤቱ እንደመሰለው ቅጣቱን
ያቃልልለታል /አንቀፅ 180/፡፡

አድራጊው ጉዳት ለማድረስ በማይችል በማናቸውም ዘዴ ወይም መሣሪያ፣ በአምልኮ


ሥራ፣ በሞኝነት ወይም በመንፈስ ልልነት የወንጀል ድርጊት ሙከራ ባደረገ ጊዜ ፍርድ
ቤቱ ከቅጣቱ ነፃ ያደርገዋል፡፡

ከዚህ በላይ የተመለከቱት የአንቀጽ ድንጋጌዎች ለወንጀል አነሳሽ ወይም አባሪ


በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ይህ ወንጀል ሊፈፀም ያልቻለው በሁለት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው ወንጀል ሊፈፀምበት


የታሰበው መሣሪያ የትፈለገውን ውጤት የማያመጣ ሰለሆነ ነው፡፡

ለምሣሌ፡- “ሀ” “ለ”ን ለመግደል አስብ መረዝ በመስጠት ፋንታ ተሣስቶ ስኳር

ቢሰጠው የታሰበው ውጤት አላገኘም፡፡ ምክንያቱም ስ ኳር ሰው


አይገድልም፡፡

ወንጀሉ ሊፈፀም ያልቻለበት ሁለተኛው ምክንያት ወንጀል ሊፈፀምበት የተሳበው ነገር ወይም
ጣባይ ነው፡፡ ለረጅም ጊዜ ጐረቤቱን ለመግደል ሲያስብ የነበረ ሰው ከለታት አንድ ቀን መንገድ
ላይ ሞቶ ቢያገኘውና በጥይት ቢመታው ያሰበውን ውጤት ማግኘት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም
የሞተን ሰው መግደል ማሰብ ሊፈፀም የማይቻል ወንጀል ስለሆነ ነው፡፡

53
የመወያያ ጥያቄዎች

1. አንቀፅ 26(ለ) ላይ የተጠቀሱት የመሰናዳት ተግባሮች የሚያስቀጡ ተብለው


መከልከላቸው በምንድን ነው? በምሣሌ አብራራ

2. አንቀፅ 26 ላይ የተገለፀው የመሠናዳት ተግባር አንቀፅ 27 ላይ ከተገለፀው መኩራ


ያለውን ልዩነቶች አበራራ፡፡

3. አንድ የወንጀል ሙከራ የፈፀመ ሰው በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ መሠረት ቅጣት


ሊቀነስለት የሚቻለው የሞከረው የወንጀል ድርጊት ስላልተሣካለት ሣይሆን እንዳይሣካ
ያደረጉት ምከንያቶች ናቸው፡፡ አብራራ

54
ምዕራፍ አራት

የምዕራፉ አላማዎች

1. ስለ ዋና ወንጀል አድራጊ ምንነት ይገነዘባሉ

2. ዋና ወንጀል አድራጊነት መካፈልና ቅጣቱን ይገነዘባሉ

3. ሌሎች የወንጀል ተካፋይነት ምንነት (እንደ ማነሣሣት እና ህጋዊ ውጤቱ፣


አባሪነትና ህጋዊ ውጤቱን ይረዳሉ

4. ሰው ህይወት ላይ ልጆች ስለሚፈፀሙ ወንጀሎች ምንነት ይገነዘባሉ

 የዘር ማጥፋት ወንጀል ምንነት እና በኢትዮጰያ የወንጀል ህግ ያለው


ትርጉም ከህገ መንግስቱ አንፃር ምን እንደሚመስል ያያሉ

በወንጀል አፈፃፀም ላይ ተካፋይ መሆን

በወንጀል አፈፃፀም ላይ ተከፋይ መሆን ማለት በአንድ የወንጀል ድርጊት ከአንድ ሰው በላይ
ከአጀማመሩ እስከ ፍፃሜው ባለ ው ሂደት ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች መሣተፋቸውን
ያመለክታል፡፡ ወንጀል በአንድ ሰው የወንጀል ሃሣብ ጠንሣሽነት ተጀምሮ በዚሁ ሰው ድርጊቶች
ፍፃሜ ሊያገኝ እንደሚችል ሁሉ የሌሎች ሠዎች የተለያየ ችሎታና ተሣትፎ ተጨምሮበት
ሊጠናቀቅ ይችላል፡፡

በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ መሆን

በ1949 ዓ.ም በወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 32 ስያሜ “ስለዋና ወንጀል አድራጊው
እና ግብረአበሮቹ” የሚል የነበረው በአሁኑ ስያሜ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሚል ተቀይሯል፡፡
ይህ አሁን በስራ ላይ ያለው የወንጀል ህግ አንዱና መሠረታዊ ለውጥ ነው፡፡ ይህ የሆነበትን
55
ምክንያት ፍትህ ሚኒስቴር ባተመው ሃተታ ዘምክንያት ላይ እንደተገለፀው የቀድሞው ህግ
ድንጋጌ ስያሜ አንድ ቀንደኛ ወንጀል አድራጊ እንዳለና ሌሎቹ ግን ከርሱ ያነሰ ሚና ያላቸው
ረዳቶች እንደሆኑ ያሳያል፡፡ ከዚህም ሌላ ሁለት ወንጀል አድራጊዎች በወንጀል አድሪጊዎች
በወንጀሉ አፈፃፀም ላይ በግብር ወይም በድርጊት ላይሣተፉ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ በቀጥታ
በድርጊት ተካፋይ ቢሆኑም ሌሎቹ ሀሣብ ወይም መመሪያ በመስጠት ብቻ ተሣታፊ ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ግብረ አበሮች የሚለው ግን በግብር ወይም በድርጊት ተካፋይ የሆኑትን ብቻ
ያመለክታል ሆኖም ይሄንንና ሌሎች በንዑስ ቁጥር አንድ መግቢያ እንደሚያስረዳው በፊደል
ከ(ሀ)(ለ) እና (ሐ) የተዘረዘሩት ወንጀል አድራጊዎች ሁሉ እንደ ዋና ወንጀል አድራጊ እንጂ
አንዱን እንደ አብይ ወንጀለኛ ሌሎቹን እንደ አነስተኛ ወንጀለኞች የሚቆጥረውን በማሶገድ
በስያሜውም ሆነ በይዘቱ እንዲስተካከል ተደርጓል፡፡ ዋና ወንጀል አድራጊነት በተለያዩ ገፅታዎች
ሊከሰት ይቻላል፡፡

ወንጀልን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መፈፀም

አንቀፅ 32(1) (ሀ)

በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር በተለይም በእንስሳ ወይም በተፈጥሮ ኃይል አማካይነት
በእርግጥ ወንጀሉን አድርጐ እንደሆነ፤

በአንቀፅ 32(1)(ሀ) መሠረት ማንም ሠው በዋና ወንጀል አድራጊነት ወንጀል እንዳደረገ ተቆጠሮ
የሚቀጣው በቀጥታ ወይም በእጅ አዙር በተለይም በእንሰሣ ወይም በተፈጥሮ ኃይል አማካኝነት
በርግጥ ወንጀሉን አድርጐ እንደሆነ ነው ይላል፡፡ የዚህ ዋና ወንጀል አድራጊነት ገፅታዎች
ሁለት ናቸው፡፡ እነኚህም በቀጥታ የሚለው በግል ድርጊት ወይም አካላዊ እንቅስቃሴ በቀጥታ
መፈፀም እና በተዘዋዋሪ ተብለው የተቀመጡት በእንሰሳና በተፈጥሮ አማካኝነት መፈፀም ናቸው

ለምሳሌ ፡-

o “ሀ” የተጣላውን ሰው በጥይት ተኩሶ ቢገድል በቀጥታ በግሉ አካላዊ እንቅስቃሴ


ወይም ድርጊት ወንጀሉን ፈፅሟል እንላለን

56
o በተመሣሣይ “ሀ” “ለ”ን ለመግደል አሰቦ “ሀ” በቤት ውስጥ መተኛቱን እያወቀ
እሣት ለኩሶ ቢያቃጥለውና በእሣቱ ምክንያቱ “ለ” ቢሞት አሁንም “ሀ”
ወንጀሉን በቀጥታ ፈፅሞታል፡፡

በሞላ ሃሳብና አድራጐቱ መሣተፍ

አ ንቀ ፅ 3 2 (1 ) ( ለ )

ወንጀሉን እሱ ራሱ በቀጥታ ባያደርግም እንኳን በመላ አሳቡና አድራጐቱ በወንጀሉ


ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን ድርጊቱን የራሱ ያደርገ ሲሆን፤

በአንቀፅ 32(1)(ለ) መሠረት ሁለተኛው ወንጀል አድራጊ የሚባለው ወንጀሉን እሱ ራሱ በቀጥታ


ባያደርግም እንኳን በመላ ሀሣቡና አድራጐቱ በወንጀሉ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙሉ
ተካፋይ በመሆን ድርጊቱን እራሱ ያደረገ ሲሆን ነው፡፡ እዚህ ላይ ወንጀለኛው ድርጊቱን
የፈፀመው በግል ድርጊት ወይም በአካላዊ እንቅስቃሴ ሣይሆን ወንጀሉ የሚፈፀምበት እቅድ
በማውጣትና ወንጀሉ የሚፈፀምበት ስልት በመንደፍ ነው፡፡ እነኝህ የወንጀሉ ዋና አንቀሣቃሾች
ወይም ተቆጣጣሪ ጭንቅላቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡

ለምሳሌ ፡-

 “ሀ” በአካባቢው የታወቀውን ባለሃብት ቤት እንዲዘረፍ የተለያዩ እቅዶችን አወጣ፡፡


በዚህም መሠረት

 በስንት ሰዓት እንደሚዘርፍ ወሰነ

 ማን በዘራፊነት እንደሚሰማራ መለመለ

 ምን እንደሚዘርፍ አቀደ

 ለመዝረፊያ የሚሆን መሣሪያ አዘጋጀ የመሣሰሉት በተቆጣጣሪ


ጭንቅላቶች የሚዘጋጅ ስልቶች ናቸው፡፡

57
በሌላ ሰው ወንጀሉን መፈፀም
አንቀፅ 32(1) (ሐ)

ሕፃንን ወይም አእምሮው ያልተስተካከለውን ወይም ሁኔታውን ያልተገነዘበውን ሰው


ወንጀል ለማድረግ መሣሪያ ያደረገ፣ ወይም ሌላውን ሰው ወንጀል እንዲያደርግ ያስገደደ
ሲሆን ነው፡፡

በአንቀፅ 32(1)(ሐ) መሠረት ሌላ ሰው መሣሪያ በማድረግ ወይም ሌላውን ሰው ወንጀል


እንዲያደርግ በማስገደድ ወንጀል የፈፀመ ሰው ዋና ወንጀል አድራጊ ነው፡፡ በ1949 ዓ.ም
በነበረው የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ላይ ያልነበረና አሁን በስራ ላይ ባለው የወንጀል ህግ ውስጥ
በተካተቱ ግለሰቦች በኩል ወንጀል መፈፀምም እንደ ዋና ወንጀል አድራጊ ያስቆጥራል፡፡ በልዩ
ልዩ ምክንያት ወንጀሉን ሣይገነዘብ ወይም ሣያውቅ መሣሪያ ሊሆን ስለሚቻል እና ህፃናትም
በመሣሪያነት ሊያገለግሉ ስለሚችሉ በእነዚህም በኩል ወንጀሉን የፈፀመ ሠው እንደ ዋና
ወንጀል እንዲቆጠር በአዲስ መልክ ተቀርፆ ገብቷል፡፡

በዋና ወንጀል አድራጊነት መካፈል እና ቅጣቱ

አ ንቀ ፅ 3 2 (2 )

የተደረገው ወንጀል ከአድሪጊው አሳብ በላይ ያለፈ እንደሆነ፤ ጉዳዩ የሚታየው በአንቀጽ
58(3) በተመለከተው መሰረት ነው፡፡

እነዚህ አንቀፆች እንደሚያሣዩት በዋና ወንጀል አድሪጊነት የተሣተፉት ሁለት ሰዎች ምንም
እንኳን ማናቸው የተለያየ ቢሆንም ተጠየቂነታቸው እኩል ነው፡፡ በዚህ ረገድ በሞራል
ወንጀለኛው እና ቀጥታ በአካል ወንጀሉን በፈፀመው ሰው መካከል ምንም ልዩነት አይደረግም፡፡
ሆኖም ግን ቅጣቱ የሚላከው እያንዳንዱ ወንጀለኛ ሊፈፅም ባሰበው ልክ ነው፡፡ በአንቀፅ 58(3)
መሠረት አንድ ሰው በላወቀው ባልፈለገው ወይም በቀጥታ ወይም በአጋጣሚ ከሃሣቡ በላይ
በሆነው ነገር ሊፈረድበት አይቻልም፡፡
58
ለምሣሌ፡- “ሀ” የተባለው የሞራል ወንጀለኛ “ለ” እና “ሐ” ባንክ እንዲዘረፉ ሁሉንም
አቅድ አውጥቶ ቢልካቸውና ሆኖም ግን “ለ” የባንኩ ዘበኛ አላስገባ ሲለው
በጥይት ዘበኛውን ቢገድል፤ በግድያው ለይ “ሀ” ተጠያቂ አይደለም፡፡
ምክንያቱም በእቅዱ የሌለ እና ያላሰበው ስለሆነ ነው፡፡ በዘበኛው መሞት
ያልፈለገው እና ከሃሣቡ በላይ ነው፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በአንቀፅ 32(1)(ሀ) ላይ በተዘዋዋሪ ወንጀልን መፈፀም ተብሎ የተጠቀሰው እና በዚሁ


አንቀፅ (ሐ) ላይ በተጠቀሰው መካከል ልዩነት አለ? አብራራ?

2. በአንቀፅ 32(1) (ሐ) ላይ “ሁኔታውን ያልተገነዘበውን ሰው” ተብሎ የተጠቀሰው ምን


አይነት ነው?

3. በአንቀፅ 32(1) (ሐ) ላይ “ህፃንን” ተብሎ የተገለፀው እድሜው ስንት አመት የሆነውን
ነው?

4. በአንቀፅ 32(1)(ሐ) ላይ በተመለከተው ወንጀል የሚፈፅም ሰው እሱ የሚፈልገውን


የወንጀል ድርጊት አንድ ቦታ ቁጭ ብሎ ስለሚያስፈፅም ለምን ተቆጣጣሪ ጭንቅላት
ተብሎ 32(1)(ለ) ላይ አልተካተተም?

5. “ሀ” አንድ የመንግስት ባንክ እንዲዘርፍ እቅድ ያወጣና መሣሪያ ይገዛል፣ ጊዜ ይወስንና
ለጓደኞቹ ለ “ሐ” እና “መ” ያዋያቸዋል፡፡ እነሱም ሃሣቡን ይቀበሉና ትናንት ምሽት
ዘረፋውን ለማከናወን “መ” እና “ሐ” ወደ ባንኩ በ “ሀ” እቅድ መሠረት ይሄዳሉ፡፡
የባንኩን በር ሰብረው ወደ ጊቢው ከገቡ በኋላ “መ” እኔ በዚህ ሃሣብ አልስማማም ወደ
ቤቴ እሄዳለሁ ብሎ “ሐ” እዛው ትቶት ይሄዳል፡፡ “ሐ” በወጣለት እቅድ መሠረት
ዘረፋውን አከናውኖ ይመለሣል፡፡ ሁሉም ዋና ወንጀል አድራጊ ናቸው? እኩልስ
ይጠየቃሉ፡፡

59
ሌሎች ተካፋይነት

በልዩ ወንጀል ተካፋይ መሆን


አ ንቀ ፅ 3 3

የተለዩ ሰዎች ብቻ ሊፈፅሙት የሚቻል ወንጀል ሲያጋጥም፣ በተለይም ወታደራዊ


ወንጀሎችን በሚመለከት ወታደር፣ ከመንግሥት ሥራ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን
በሚመለከት የመንግሥት ሠራተኛ ወይም ሴትን አስገድዶ ለመድፈር ወንድ መሆን
የሚያሻ ሲሆን ወንጀል አድራጊው የተባለው ልዩነት ባይኖረውም፣ በሙሉ ፈቃዱና
ዕውቀቱ የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ እንደሆነ፤ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተጠያቂ ከመሆን
አይድንም፡፡

ወንጀሎች ከፀባያቸው የተነሣ በሁሉም ሰዎች ሊፈፀሙ አይችሉም፡፡ አንድ አንድ ወንጀሎች
የተለዩ ሰዎች ብቻ ይፈፀማሉ፡፡ በአንቀፅ 33 መሠረት ወታደራዊ ወንጀሎችን ለመፈፀም
ወታደር መሆንን ይጠይቃል፡፡ ከመንግስት ስራ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ለመፈፀም
የመንግስት ሠራተኛ ብቻ መሆንን ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ወንጀል አድራጊው የተባለው
ልዩነት ባይኖረውም በሙሉ ፈቃድና እውቀቱ የወንጀሉ ተካፋይ ከሆነ በዋና ወንጀል አድራጊነት
ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ለምሳሌ፡- አንድ ሰው ወታደር ሣይሆን በሞራል ወንጀለኛነት ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ


የመክዳት ወንጀል እንዲፈፀም ካደረገ በዋና ወንጀል አድራጊነት ሊጠየቅ ይችላል፡፡

ማነሣሣት

አ ንቀ ፅ 3 6 (1 )

ማንም ሰው ወንጀል እንዲደረግ አነሳሳ የሚባለው አስቦ ሌላውን ሰው በመጐትጐት፣


ተስፋ በመስጠት፣ በገንዘብ፣ በስጦታ፣ በማስፈራራት ወይም በማናቸውም ሌላ ዘዴ
አንድ ወንጀል እንዲያደርግ ያግባባ እንደሆነ ነው፡፡

60
ለወንጀል ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ከሚችሉ ተሣታፊዎች አንዱ አነሣሽ
ነው፡፡ አንድ ሰው ወንጀሉን ራሱ በተለያየ መልኩ በቀጥታ ተሣትፎ ባይፈፅመውም ሌሎች
እንዲፈፅሙት እና የተፈለገውን ውጤት እንዲገኝ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በአንቀፅ 36 መሠረት
ሌሎች ሰዎችን በመሣሪያነት በመጠቀም ወንጀል ሊፈፀም ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ
ወንጀልን በአካል የሚፈፅመው ሰው ማነሣሣት ነው ሆኖም ግን አንድ ሰው ሌላውን በተለያዩ
ዘዴዎች ወንጀል እንዲፈፅም አነሣስቷል ከማለታችን በፊት የሚከተሉትን ነጥቦች በጥንቃቄ
ማየት ይገባል፡፡

የወንጀል ፈፃሚው መነሣሣት

አንድ ሰው ለሌላው ሰው ወንጀል ለመፈፀም የሚያስችል ሀሣብ ስለሰጠ ብቻ አነሣሽ ነው


አይባልም፡፡ ስለሆነም አነሣሹ ፈፃሚውን ወንጀል እንዲፈፅም ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ እንዲደረስ
ካደረገው ብቻ አነሣስቷል ሊባል የሚችለው፡፡ ይህ በአንጭሩ ሲገለፅ አነሣሹ ወንጀል ፈፃሚውን
ባያነሣሣው ኖሮ ወንጀል አይፈፅምም ነበር የሚል ድምዳሜ መድረስ ስንችል ነው፡፡ በዚህም
መሠረት በአነሣሹ የመነሣሣት ድርጊት እና በተነሣሹ የወንጀል ድርጊት መካከል በቂ የሆነ
የምክንያትና ውጤት ግንኙነት ሊኖር ይገባዋል፡፡

ለምሳሌ ፡- “ሀ” በግጦሽ መሬት ጉዳይ ሁል ጊዜ የሚጨቃጨቀውን “መ” ለመግደል


ሁሌ ያስባል፡፡ ከለታት አንድ ቀን የ “ሀ” ጓደኛ “ለ” እቤት መጥቶ ከ “መ”
ጋር እንደተጋጨና የሚገድልለት ሰው ካገኘ 10000 ብር ለመክፈል ዝግጁ
መሆኑን ይገልፅለታል፡፡ “ሀ” ብሩን ከሰጠኸኝ ራሲ ፈፅመዋለሁ በማለት
ገንዘቡን ተቀብሎ “መ” ን ይገድላል፡፡

ከዚህ ምሣሌ እንደምንረደው “ሀ” መጀመሪያ “መ” ን ለመግደል ሁሌ ያስባል ያውጠነጥናል፡፡


ሆኖም ግን ለመግደል ወስኖ አያውቅም፡፡ ውሣኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገው የ “ለ” ማነሣሣት
ተግባር ነው”” በማነሣሣቱ ተግባርና በ “መ” መሞት ቀጥተኛ የሆነ የምክንያትና ውጤት
ግንኙነት እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ በተመሣሣይ ምሣሌ “ሀ” “መ” ን ለመግደል አስቦ አውጥቶ
አውርዶ ከወሰነ በኋላ ማንም ሰው “ሀ” አነሣሰቷል ሊባል አይቻልም ምክንያቱም በፊት የነበረና
የተወሰነ ጉዳይ ስለሆነ የምክንያትና ውጤት ግንኙነት የለም፡፡
61
የሃሣብ ክፍል

ማነሣሣት ምን ጊዜም በአውቆ አጥፊነት መፈፀም ያለበት ወንጀል ነው፡፡ ሰለሆነም አነሣሹ
የማነሣሣት ድርጊቱን የሚፈፅመው አውቆ ፈልጐና ውጤት እንዲገኝ በማሰብ ነው፡፡

ለምሳሌ አንድ የህክምና ባለሞያ ከጓደኛው ጋር በሻይ ሰዓት ሲወያይ ስለተማረው ትምህርት
እና ለሞት የሚያበቁ የመድሃኒት አይነቶች ቢያጫውተው እና ሠው ለመግደል ሃሣብ
የነበረው ጓደኛው ውሣኔ ላይ ደርሶ የግድያ ወንጀል ቢፈፅም የህክምና ባለሞያው ድርጊቱን
በአውቆ አጥፊነት ስላልፈፀመው ወይም ድርጊቱ እንዲፈፀም ፍላጐት ስላልነበረው በአነሣሽነቱ
ሊጠየቅ አይገባውም፡፡

ወንጀሉ ቢያንስ መሞከር አለበት

አ ንቀ ፅ 3 6 (2 )

አነሳሹ የሚቀጣው ወንጀሉ ቢያንስ ተሞክሮ እንደሆነ ነው፡፡

በአንቀፅ 36(2) መሠረት አነሣሹ ለአነሣሣው ወንጀል የሚቃጣው ቢያንስ ተሞክሮ እንደሆነ
ነው፡፡ ሊነሣሣ የታሰበው ሰው ወንጀሉን ካልሞከረ ወይም ካልፈፀመ በስተቀር ስለማይቀጣ
የማነሣሣት ተግባር የፈፀመውም ሰው አይቀጣም፡፡ ቅጣቱም የሚወሰነው ሊደረግ ለታሰበው
ወንጀል ህጉ በተደነገገው ቅጣት ልክ ነው፡፡

አባሪነት

አ ንቀ ፅ 3 7 (1 )

ማንም ሰው በወንጀል ድርጊት አባሪ ነው ተብሎ የሚቆጠረው ዋና ወንጀል አድራጊው


ወንጀል ከማድረጉ በፊትም ሆነ ወይም በሚያደርግበት ጊዜ ወሬ በማቀበል፣ በመምከር፣

62
ወንጀል የሚያደርግበትን ዘዴ ወይም መሣሪያ ወይም ግዙፋዊ እርዳታ በመስጠት
ወይም ለወንጀሉ አፈፃፀም በሚጠቅም በማናቸውም ሌላ ዓይነት መንገድ አስቦ የረዳው
እንደሆነ ነው፡፡

አባሪነት የወንጀል ተሣትፎ አንድ ገፅታ ሲሆን ዋናው ወንጀል አድራጊ በተለያየ ጊዜ ከሌሎች
ሰዎች የሚያገኘው እገዛ ነው፡፡ የአባሪነት እርዳታ በተለያየ መልክ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
እርዳታዎቹ ቁሣዊ ወይም ሞራላዊ ወይም አካላዊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወንጀሉን የሚፈፅምበት
መሣሪያ መስጠት ቁሣዊ እርዳታ ነው፤ ስለወንጀሉ አፈፃፀም የሚመለከት መረጃ መስጠት
ሞራላዊ ድጋፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ወንጀሉ በሚፈፀምበት አከባቢ ሰዎች እንዳይደርሱ ማድረግ
አካላዊ እርዳታ ነው ማንም ሰው በሰጠው እርዳታ በወንጀል ድርጊት አባሪ ነው ተብሎ ተጠያቂ
የሚሆነው የሚከተሉትን ግርምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡

የሃሣብ ክፍል

አባሪነት ምን ጊዜም ቢሮን በአወቆ አጥፊነት የሚፈፀም ወንጀል ነው፡፡ አንድ አባሪ የሚሰጠው
እርዳታ የወንጀሉ ስራ እንዲቃና በማሰብ የተሰጠ መሆን አለበት፡፡ ስለሆነም እርዳታ
በቸልተኝነት ከተሠጠ አባሪነት የለም፡፡

የአባሪነት ጊዜ

የአባሪነት እርዳታ ወንጀሉ ከመፈፀም በፊት ወይም በመፈፀም ላይ እንዳለ የተሰጠ መሆን
አለበት፡፡ ስለሆነም ወንጀሉ ከተፈፀመ በኋላ የሚሰጥ እርዳታ የአባሪነት እርዳታ ሊሆን
አይችልም፡፡ ወንጀሉ ከመፈፀሙ በፊት እርዳታ የሚሰጥ ሰው ዋና ወንጀል አድራጊ ወይም
አነሳሽ አድርጐ መመደብ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ማንንም እንዲወሰን አላነሣሣም፡፡ ያደረገው
ነገር ቢኖር ወንጀል ለመስራት ወስነው የመጡ ሰዎችን የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ ማቅረብ
ነው፡፡

63
የእርዳታ አይነቶች

እርዳታው በተለያዩ መልኩ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ቁሣዊ ሊሆን ይችላል ለምሣሌ የሚዘረፈውን ቤት
ቁልፍ፡፡ ሞራላዊ ሊሆን ይችላለ ለምሣሌ ምክር መለገስ እና የተለያዩ መረጃዎችን ማቀበል፡፡
በአካል ተኝቶ መርዳትም ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሣሌ ወንጀሉ በሚፈፀምበት አከባቢ የሚያልፍ
ሰው መኖሩን እና አለመኖሩን መከታተል፡፡ ሆኖም ግን ሁል ጊዜ የሚያከራክሩ ጉዳዮች
በአባሪነት ላይ ይነሣሉ

 እርዳታው እስከምን ድረስ ነው?

 የተሰጠው እርዳታ ለታሰበው የወንጀል ድርጊት ባይረዳስ? የመሣሠሉትን ማየት


ይገባል፡፡ ለምሣሌ አንድ እርዳታ ሰጭ ወንጀል አድራጊው ለዘረፋ ቤቱን ሰብሮ አስኪገባ
እና እስከሚወጣ ድረስ ሰው መምጣቱንና አለመምጣቱን ለማረጋገጥ በር ላይ ቆሞ
ሲጠብቅ ቆይቶ ማንም ሰው ባይመጣ ረዳ ሊባል ይችላል?

በተጨማሪ አንድ የቤት ሠራተኛ የምትሰራበትን ቤት ጓኛዎ እንዲዘረፈው የቤቱን ቁልፍ


ሰጥታው ሆኖም ግን ጓደኛዋ ለዘረፋ ሲሄድ የቤቱ በር ክፍት ሆ-ኖ ቢያገኘው የቤት
ሠራተኛዋን አባሪ ማድረግ ይችላል?

የአባሪነት ውጤት

አ ንቀ ፅ 3 7 (2 ) ( 3 )

2. ታስቦ ለሚደረግ ወንጀል አባሪ መሆን ሁል ጊዜም የሚያስቀጣ ነው፡፡

3. አባሪው የሚቀጣው ወንጀሉ ቢያንስ የተሞከረ እንደሆነ ነው፡፡

በዚህ አንቀፅ መሠረት አባሪ በተሞከረው ወንጀል ልክ ይቀጣል፤ ከላይ ስለአነሣሽነት በቀረበው
ማብራሪያ ላይ አነሣሽነት እንደሚያስቀጣና የተነሣሣው ሰው ቢያንስ ወንጀሉን መሞከር
እንደለበት አነሣሹ ለተሞከረው ወይም ለተፈፀመው ወንጀል በተደነገገው ቅጣት አንደሚቀጣ
ተገለፆል፡፡ ተመሣሣይ ስለሆነ መንግድም አያስፈልግም፤ ሆኖም ግን በህጉ ልዩ ክፍል ውስጥ

64
በግልፅ ያስቀጣል ተብሎ ከተደነገገ እርዳታ የሰጠው ሰው አባሪ ሣይሆን ዋናው ወንጀል
አድራጊ ይሆናል፡፡

የመወያያ ጥያቄዎች

1. በወንጀል ህጉ አንቀፅ 274 መሠረት ማንም ሰው ወንጀል እንዲሰራ ማነሣሣትና መገፋፋት


ያስቀጣል ይላል (አንቀፁ አመልከቷል) ፡፡ ይሀ አንቀፅ እስካሁን የተወያየንበትን አንቀፅ 36
ጋር ያለውን ልዩነት ምንድን ነው? ለምንስ ማነሣሣት የሚል ሌላ አንቀፅ አስፈለገ?

2. ማነሣሣት በስልክና በደብዳቤ ይቻላል? በሶስተኛ ወገንሰ? ለምሣሌ “ሀ” “ለ”ን በአካል ወይም
በስልክ አግኝቶ ማነሣሣት ስላልቻለ “መ” የተባለ ጓደኛውን እንዲያነሣሣለት ጠይቆ
የማነሣሣቱ ስራ ተሣካለት፡፡ ማነው አነሣሽ? ተወያዩ

በሰው ህይወት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች

ሰው መግደል

የወንጀል ድርጊቶች ከሚያደርሱት ጉዳት አንፃር ደረጃ ይውጣላቸው ከተባለ በመጀመሪያ ደረጃ
የሚመደበው ወይም መመደብ ያለበት በሰው ህይወት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ነው፡፡ በሌሎች
ወንጀሎች የተጐዳ ሰው ሊያጣ የሚችለው የተወሰነ ነገር ሲሆን ህይወቱ የጠፋ ሰው ግን
የሚያጣው ሁሉንም ነገሩን ነው፡፡

በህይወት መኖር የሰው ልጅ ሰብአዊ መብቱ ነው፤ ሰብዓዊ መብት ስንል ሰው ሰብዓዊ ፍጡር
በመሆኑ ብቻ የሚኖረው መብት ነው፡፡ የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 10(1) ላይ “ከሠው
ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ” ሲል ሰው ሰው ሆኖ በመወለዱ ብቻ ማናቸውም ቅድም ሁኔታ
ሣያስፈልግ የሚኖሩት መብቶች ለማለት ነው፡፡

የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ይሄንን መሠረታዊ የሰው ልጆች መብት ጥበቃ ለማድረግ አምስተኛ
መፅሃፍ ላይ ከአንቀፅ 538 ጀምሮ ደረጃ በደረጃ አስቀምጧል፡፡ እነዚህም እንደ ቅደም

65
ተከተላቸው ከባድ አገዳደል ተራ የሆነ አገዳደል እና ቅጣትን የማያቀል አገዳደል ተብለው
ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡ አንቀፅ 539 ቅጣትን የሚያከብዱ ምክንያቶች የየዘ ሲሆን አንቀፅ
541 ደግሞ የማቅለያ ምክንያቶችን ይዟል፡፡ ሆን ተብሎ የሚፈፀም የሰው መግደል ወንጀል
በአንቀፅ 539 ከተገለፀው የቅጣት ማክበጃ ወይም በህጉ አንቀፅ 541 ከተገለፀው የቅጣት ማቅለያ
ውጭ ከሆነ ደግሞ ድርጊቱ የሚሸፈነው በአንቀፅ 540 ነው፡፡

አንቀፅ 539 (1) (ሀ)(ለ)(ሐ) እና (2)

1. ማንም ሰው፡-

ሀ. ሰውን ለመግደል አስቀድሞ የነበረው አሳብ፣ ወይም ምክንያት፣ ለመግደል


የተጠቀመበት መሣሪያ ወይም ዘዴ፣ ያገዳደሉ ሁኔታ ወይም ግድያው
የተፈፀመበት ቅጣትን የሚያከብድ ጠቅላላ ምክንያት (አንቀፅ 84) ወይም
ሌላ ምክንያት (አንቀፅ 86) ሲታይ ገደዩ በተለይ ጨካኝ፣ ነውረኛ ወይም
አደገኛ መሆኑን የሚገልጽ ሁኔታ፤ ወይም

ለ. ሰውን ለመግደል ወይም የውንብድና ወንጀልን ለመፈጸም የተደራጀ የወንበዴ


ቡድን አባል በመሆን፤ ወይም

ሐ. ሌላ ወንጀልን ለመፈጸም እንዲመቸው ወይም የተፈፀመ ወንጀል እንዳይገለጽ


ለማድረግ ሲል፤

አስቦ ሰውን የገደለ እንደሆነ፤

2. ወንጀለኛው የዕድሜ ልክ ፅኑ እሥራት ተፈርዶበት ቅጣቱን በመፈፀም ላይ ሳለ


ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ (1) በተመለከተው ሁኔታ ሰውን የገደለ እንደሆነ፤

በሞት ይቀጣል፡፡

በዚህ አንቀፅ መሠረት ከባድ ስለሆነ የሰው ግድያ ይዘረዘራል፡፡ ሰዎች በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ
ከሚፈፅሟቸው ተግባራት ጨካኝ ነውረኛ አደገኛ የሚያሰኛቸው ሰው ከገደሉ ነው፡፡ ሆኖም ግን
በአንቀፅ 539 መሠረት ጨካኝ ነውረኛ የሚያሰኘው ሰውን መግደል ብቻ ሣይሆን በአፈፃፀሙ
ረገድ የሚደረገው ክንውን ለማሳየት ይመስላል፡፡ ስለሆነም ጨካኝነት፣ ነውረኛነት እና አደገኛነት

66
ለማቋቋም ሊኖር የሚገባው መመዘኛ መሠረት የሚደረገው ምክንያት ምንድን ነው? ይህ
የህብረተሠቡን ማህበራዊ እድገትና ባህላዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ አስገብቶ ትርጉም ለማስጠት
መሻት አስቸጋሪ ነው፡፡ እንቁላል ሌባን በሚኮንነው እና የአባትን ገዳይ መግደል በሚያሞግሰው
ህብረተሠብ ባህል ውስጥ በተፈጠረ ስነ ልቦና የነውረኛነት መስፈሪያ መነሻ የሚያደርገው
ምንድን ነወ? ይህ በጥንቃቄ መታየት የሚገባውና የህጉ መንፈስ እና አላማን ከግምት ወስጥ
ያስገባ ትርጉም መስጠት አሰአላጊ ነው፡፡

በንኡስ አንቀፅ ቁጥር 2 መሠረት ግድያ የፈፀመ ሰው የሞት ቅጣት የሚፈረድበት አስቀድሞ
ለፈፀመው ወንጀል የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት የተፈረደበት ወንጀለኛ ሁሉ ሣይሆን የእድሜ ልክ
ጽኑ እስራት ተፈርዶበት ቅጣቱን በመፈፀም ላይ እያለ ከባድ የግድያ ወንጀል የፈፀመ ብቻ
ነው፡፡ የዚህ አይነቱን ወንጀለኛ በሞት እንዳይቀጣ የሚያደርግ ምንም ማቀለያ ምክንያት
የሌለው በመሆኑ ምንጊዜም ቢሆን የሞት ቅጣት ሊፈርድበት ይገባል፡፡ የእድሜ ልክ ፅኑ
እስራት ቢፈረድበትም ቅጣቱን በመፈፀም ላይ ያልሆነ ወንጀለኛ ግን ሰው በሚገድልበት ጊዜ
የእድሜ ልክ አስራት በመፈፀም ላይ የሚገኘውን ወንጀለኛ ያህል አደገኛ ነው የማይባልበት ጊዜ
ሊኖር ይችላል፡፡ ሁኔታው እየታየ የሞት ቅጣት ወይም የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ሊፈረድበት
ይችላል፡፡

ለምሣሌ ፡- ጥፋተኛው በመጀመሪያ ከተፈረደበት የእድሜ ልክ እሰራት ውስጥ ምንም


ሣይቀጣ ይቅርታ ወይም ምህረት ተደረጐለት ይሆናል ወይም የእድሜ ልክ
አስራት የተፈረደበት በሌለበት ሊሆን ይችላል፡፡ የዚህ አይነቱ ጥፋተኛ ከባድ
ግድያ ቢፈጽም የእድሜ ልክ እስራት እየፈፀመ ባለበት ጊዜ ከባድ ግድያ
የሚፈፅመውን ጥፋተኛ ያህል ቅጣቱ ላይከብድበት ይችላል፡፡ ምክንያቱም
ቅጣት ስላልደረሰበትና ከቅጣት ያገኘው ትምህርት ስለሌለ ነው፡፡

ሆኖም ግን የእድሜ ልከ እሰራት ተፈርዶበት ቅጣቱን በመፈፀም ላይ እያለ በንዑስ ቁጥር አንድ
ለይ የተመለከተው ከባድ ግድያ ብቻ ሲፈፅም፤ የሞት ቅጣት ይፈረድበታል እንጂ ከዚህ ውጭ
አስቦም ይሁን በቸልተኝነት ወይም በህጋዊ መከልከል በሚገድልበት ጊዜ መሆን ያለበትም፡፡

67
በአንቀፅ 540 ላይ ስለ ተራ የሆነ የሰው ግድያ ተመልክቷል “ተራ” የሚለው ቃሉ የግድያውን
ቀላልነት የሚያሣይ ሣይሆን በከባድ ግድያ በቀላል ግድያ መካከል የሚገኘውን የግድያ አይነት
ነው፤ ምን አይነት ናቸው፡፡

በአንቀፅ 541 ላይ ቀላል ስለሆነው የሰው ግድያ ተመልክቷል፡፡ ይህ አንቀፅ በቅድሞው 524
ላይ በተደነገገው መሠረት ቀላል ግድያ የሚባለው በመኖሪያ ቤቱ ወይም በአጥሩ ግቢ ሌላ ሰው
ከገባ በተንኮል የገባውን ሰው ሊያስግድል በሚጥርበት ጊዜ ሰው የገደለ እንደሆነ ነበር፡፡

ሆኖም ግን ህጋዊ መከልከልን ከመጠን በማሣለፍ የግድያው ቅጣት መቅለል የሚገባው ወደ


መኖሪያ ቤቱ ወይም ወደ አጥር ጊቢው በኃይል ወይም በተንኮል የገባውን ሰው በሚያስገድልበት
ጊዜ ብቻ መሆኑ ትክክል ስላልነበር ተቀይሯል፡፡ ምክንያቱም ከተባለው ሁኔታ ውጭ በራሱ
ወይም በሌላ ሰው ህይወት ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ሲመለስ ወይም በሌላ ሁኔታ መብቱን
ሲያስከብር ህጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሣለፍ ሰውን ሲገድልም ድንጋጌው ተፈፃሚነት
ሊኖረው ይገባል፡፡

ግድያው የተፈፀመው ያስገዳጅ ሁኔታን ወይም የአልሞት ባይ ተጋዳይነት መስፈርት በመጣስ


ወይም በማለፍ እስከ ሆነ ድርስ ግድያው የተፈፀመው በማናቸውም ቦታ፣ ጊዜ ወይም ሁኔታ
ቢሆንም አንቀፅ አጠቃላይ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ተደርጐ መቀረፁን ፍትህ ሚኒስቴር
ያዘጋጀው ሃተታ ዘምክንያት ይገልፃል፡፡

የወንጀል ህግ አንቀፅ 542 ላይ የተገለፀው ራስን ማጥፋት ወይም (Suicide)ነው፡፡ በዚህ


ድንጋጌ ተጠያቂ የሚሆነው ድርጊቱን ፈፃሚው ሣይሆን ድርጊቱ እንዲፈፀም ያነሣሣ ነው፡፡
ድርጊት ፈፃሚው የሚያጠፋው የራሱን ህይወት በመሆኑ የማይጠየቅበት ምክንያት ግልፅ ነው፡፡
በወንጀል ህጉ ላይ ራስን ማጥፋት ወንጀል ነው ተብሎ አልተደነገገም፡፡ በህጉ ተለይቶ ወንጀል
ነው የልተባለ ነገር ደግሞ እንደሚያስጠይቅ በወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ቁጥር 2 ላይ ተገልፆል፡፡
ከዚህም አንፃር ዋናው ድርጊት ወንጀል ነው ባልተባለበት ሁኔታ ማነሣሣት ወንጀል ይሆናል
ከተባለ ከህጉ መሠረታዊ መርህ ጋር ይጣጣማል?

አንቀፅ 543 ላይ በቸልተኝነት ሰው መግደል የሚለው ድንጋጌ ቀድሞ ከነበረው የወንጀለኛ


መቅጫ ህግ ጠንከር ያለ ቅጣት በማስቀመጥ ተዘጋጅቷል፡፡ በቀድሞው ህግ ላይ የሰው ህይወት

68
ማጥፋቱ እየታወቀ ቀላል የእስራቱ መነሻ እስር ቀን የመቀጫውን ደግሞ አንድ ብር ብሎ
መደንገጉ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነበር፡፡

ንዑስ አንቀፅ (2) መሠረት የሚያስቀጣው ሙያዊ ሆኖ ጥንቃቄ መውሰድ ሲገባው በከባድ
ቸልተኝነት ሰው የገደለ እንደሆነ ነው፡፡ ለዚህ አይነቱ ወንጀል የቅጣት መነሻው ከፋ ቢል ሰው
ተጠንቅቆ የሞያ ግዲታውን ይወጣል ተብሎ ስለሚገመት ቅጣቱ ከፍ ተደርጐ ተደንግጓል፡፡

ንዑስ አንቀፅ (3) መሠረት ብዙ ጊዜ ከአንድ በላይ በሆነ ሰዎች ላይ በጠንቃቄ ጉድለት የተነሣ
ስለሚደርስባቸው ጉዳት ነው፡፡

ለምሣሌ፡-የመኪና አደጋ ብዙ ሠዎችን ያለ አግባብ በመጫንና በፍጥነት ማሽከርከር


ይመጣል በተጨማሪም የሚያሰክሩ ወይም የሚያፈዙ ንጥረ ነገሮችን ወይም
መጠጦችን በመውሰድ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል እንዲቻል ቅጣቱ
ከፍ ያለ ሆኖ ከአምስት አመት እስከ 15 አመት ፅኑ እስራት እና ከ10000 ብር
እስከ 15000 ብር ተደንግጓል፡፡

የዘር ማጥፋት ወንጀል

ኢትዮጵያ ባፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶችና በወንጀለኛ መቅጫ ህግ የተደነገጉ “በሰው


ልጆች ላይ የሚሰሩ ወንጀሎች” ተብለው የሚታወቁት የጥፋት ድርጊቶች አንድ የዘር ማጥፋት
ወንጀል ነው፡፡

አ ንቀ ፅ 2 6 9

ማንም ሰው በሠላምም ሆነ በጦርንት ጊዜ በብሔር፣ በብሔረሰብ፣ በጐሣ፣ በዘር፣


በዜግነት፣ በቀለም፣ በሃይማኖት ወይም በፖለቲካ አንድ የሆነን ቡድን በመላ ወይም
በከፊል ለማጥፋት በማሰብ የጥፋቱን ድርጊት በማደራጀት፣ ትዕዛዝ በመስጠት ወይም
ድርጊቱን በመፈፀም፡-

ሀ. በማናቸውም ሁኔታ የማኅበረሰቡን አባት የገደለ፣ አካላዊ ወይም ሕሊናዊ ጤንነት


የጐዳ፣ ወይም የአካል ጉዳት ያደረሰ ወይም ያጠፋ እንደሆነ፤ ወይም

69
ለ. የማኅበረሰብቡ አባላት በዘር እንዳይራቡ ወይም በሕይወት እንዳይኖሩ ለማድረግ
ማናቸውንም ዘዴ በሥራ ላይ ያዋለ እንደሆነ፤ ወይም

ሐ. በማህበረሰቡን አባላት ወይም ሕፃናት በግዴታ ከሥፍራ ወደ ሥፍራ ያዛወረ ወይም


የበተነ ወይም ሊሞቱ ወይም ሊጠፉ በሚችሉበት የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ ያደረገ
እንደሆነ፤

ከአመሰት ዓመት እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ የሚችል ፅኑ እስራት፤


ወይም ነገሩ ከባድ በሆነ ጊዜ በዕድሜ ልክ ፅኑ እሰራት ወይም በሞት ይቀጣል፡፡

ይህ አንቀፅ በአጭሩ የሚገልፀው በሠላም ሆነ በጦርነት ጊዜ በሃይማኖት፣ በዘር፣ በፖለቲካና


በመሣሠሉት ምክንያቶች ሰላማዊ ሰዎችን ህፀናትን አረጋውያንን ሴቶችን አቅመ ደካሞችን
የጦር ምርኮኞችን ቁስለኞችን የጨፈጨፉ ያሰቃየ የገደለ ያጋዘ ወይም በከፊልም ሆነ በሙሉ
ከምድረ ገፅ ያጠፋ ወይም በድርጊቱ የተሣተፈ ሰው በሠው ልጆች መብት ላይ የሚፈፀመው
ወንጀሎች ተጠያቂ ይሆናል፡፡

በሁለተኛው የአለም ጦርነት ካስከተለው ወታደሪዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በተጨማሪ


የጀርመን ናዚዎችና የጣሊያን ፋሽስቶች ታሪክ አሣዛኝ አድርጐታል፡፡ ከጦርነቱ በኋላ የቀድሞው
ጥፋት እንዳይፈፀም በተግባር ላይ አውሏል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱና ዋንኛው የሰው ልጆች
ሠብአዊ አጠባበቅ የሚመለከት ነው፡፡ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከሁሉም የላቀ በመሆኑ ይህንን
ለመከላከል የተደረገው ስምምነት አለም አቀፍ ግዴታዎችን በሁሉም ወገኖች ላይ የጣለ ነው፡፡

ከዚህም አንፃር የዘር ማጥፋት ተግባር አለም አቀፋዊ ወንጀል በመሆኑ በአገራችን የወንጀለኛ
መቅጫ ህግ ውስጥ አቀማመጡ ይህን ይዘት በሚያካትት መልክ ነው፡፡

በእንደዚህ አይነት ከባድ የወንጀል ድርጊቶች የሚጠየቁ ግለሰቦች በህግ ፊት ስለሚቀርቡበት


ስነስርዓትና ስለሚወሰንባቸው ቅጣት በዝርዝር ህግ የሚታይ ሆኖ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 28
እንደተመለከተው በሠብአዊ ፍጥረት ላይ የሚፈፀም የወንጀል ድርጊት በይርጋ አይታገድም፡፡
በህግ አውጭው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግስት አካል ውሣኔዎች በምህረት ወይም
በይቅርታ አይታለፍም፡፡

70

You might also like