You are on page 1of 87

1

ኦርቶዶክሳዊነት
ምንድን ነው?

2
ባይኖር ሕዝብ መረን
 “ራእይ
ይሆናል፡፡”
ምሳ. 29፡18
“እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ
መልካም ነበረ። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ
ቀን።”
ዘፍ. 1፡31
“What is true by lamplight is not always true by
sunlight.” Joseph Joubert
“Be careful how you interpret the world: It is like
that.” Erich Heller 3
 Orthos (right) and
 doxa (teaching or worship)

ኦርቶዶክስ -
 እውነተኛ አስተምህሮ (right teaching)፣
 እውነተኛ አምልኮ (right worship) ማለት ነው፡፡
 በጥንቱ የክርስትና ዘመን ክርስቲያን ነን የሚሉ
የስህተትና የኑፋቄ ትምህርቶች እየበዙና የቤ/ክንን
አንድነትና ንጽሕና ሊሸፍኑ ስለ ደረሱ ሐዋርያዊት
የሆነችውን እምነትና አስተምህሮ ከሌሎቹ ለመለየት
“ኦርቶዶክስ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ዋለ፡፡

4
 ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ከጌታና ከሐዋርያት
የተቀበለችውን እውነት በፍጹም ጥንቃቄ
ትጠብቃለች፣ ይህም መንጋዋን ለመጠበቅ እና
እርሷ አካሉ የሆነችለትን ራሷን ክርስቶስን
ለማክበር ነው፡፡

5
 የቤ/ክ አስተምህሮ ከሁለት ምንጮች የተገኙ ናቸው፡-
እነዚህም፡-
 ቅዱሳት መጻሕፍት (Holy Scripttures) እና
 ቅዱስ ትውፊት (Sacred Tradition) ናቸው፡፡
 የመጨረሻውና ከፍተኛው መገለጥ የኢየሱስ ክርስቶስ
ሥጋዌ ነው፤
 ቅዱሳት መጻሕፍት ደግሞ የዚህ የሥጋዌ ምሥጢር
እውነተኛና ትክክለኛ ገላጮች ናቸው፡፡
 ቅዱስ ትውፊት ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት የተገኙበት
እንዲሁም የሚተረጎሙበትና የምንረዳበት ዐውድና
መሠረት ነው፡፡ 6
 “ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ
ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን
ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ
ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት
ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል።” ዮሐ. 20፡29-30

 በትውፊት የመጡልን ብዙ ትምህርቶች አሉ፤


ሆኖም የትውፊት መመዘኛውና መለኪያው
በመጽሐፍ ቅዱስ ያለው ትምህርት ነው፤ “ኢትጻኡ
እም ቃለ መጻሕፍት - ከተጻፈው አትለፉ”
ተብሏልና፡፡ 1 ቆሮ. 4፡6
7
“Concerning . . . the superessential and hidden
Deity, it is not permitted to speak or even to
think beyond the things divinely revealed to us
in the sacred Oracles. For even as Itself has
taught in the Oracles, the science and
contemplation of Itself in Its essential Nature is
beyond the reach of all created things, as
towering superessentially above all.”
(St. Dionysisus, Section II)

8
 ኦርቶዶክሳዊነት እውነት ነው፣ ኦርቶዶክሳዊት
ቤ/ክም የእውነት ቤት ናት፡፡ በእርሷ ውስጥ ውሸት
(ሐሰት) ቦታም ተቀባይነትም የለውም፡፡
 “ብዘገይ ግን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር
እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤
ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፣ የሕያው
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።” 1 ጢሞ. 3፡15
 አገልጋዮቿ ካህናት ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም አካሏ የሆኑ
ልጆቿ ሁሉ ሐሰትን መጸየፍ ይኖርባቸዋል፤ “ስለዚህ ውሸትን
አስወግዳችሁ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ
ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።” ኤፌ. 4፡25
9
 “እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ” ቆላ. 3፡9
 “ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፣ ሐሰተኛ
የሐሰትም አባት ነውና።” ዮሐ. 8፡44
 ኦርቶዶክሳዊነት መንፈስ ነው፤

 “እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው፣


ሕይወትም ነው።” ዮሐ. 6፡63

10
 በዘመናችን ኦርቶዶክሳዊነትን በትክክል የሚረዱት
ስንቶቹ ይሆኑ?
 “የተማሩ” ከሚባሉት መካከል፣ ከካህናትና ከቤ/ክ
በአገልግሎት እርከን ውስጥ ካሉት መካከል
ኦርቶዶክሳዊነትን ምንነቱንና ጭብጡን በትክክል
የተረዱት ስንቶቹ ይሆኑ?
 ብዙዎች ጥልቀቱንና ስፋቱን ተረድተውት ሳይሆን
አፍኣዊና ጥራዝ ነጠቅ በሆነ ሁኔታ ነው የሚረዱት፡፡
 ኦርቶዶክሳዊነት በክርስትና ስም ካሉት ብዙ
ዲኖሚኔሽኖች አንዱ አይደለም፣ ከሃይማኖቶች
መካከል አንዱም አይደለም፡፡
11
 ኦርቶዶክሳዊነት ጌታ የሰጠው፣ ሐዋርያት
ያስተማሩት፣ አበው የጠበቁት ነው፡፡
 ኦርቶዶክሳዊነት እውነተኛው ያልተበረዘውና በሰዎች
ፍልስፍናዊ እርሾ ያልተበከለውና ያልተከለሰው
እምነትና አስተምህሮ ነው፡፡
 ኦርቶዶክሳዊነት “ኦርቶዶክስ” በምትባለው ቤ/ክ ውስጥ
ያለችው የፓትርያርክ፣ የጳጰሳት፣ የካህናትና የምእመናን
የተዋቀረችውና በዚህ ዓለም ያለችው ምድራዊ ተቋም
ብቻ አይደለችም፡፡
 ኦርቶዶክሳዊነት ረቂቅ የክርስቶስ አካል ናት (the mystical
"Body of Christ)፣ አካላቶቿም ካህናት ብቻ ሳይሆኑ
በክርስቶስ በእውነት ያመኑ ሁሉ፣ በጥምቀት የእርሱ አካል
12
 “ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም
ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርሷም
አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።”
ኤፌ. 1፡22-23

 ቤተ ክርስቲያን - አቅሌስያ - ጉባኤ፣ አንድነት (ዮሐ.


10፡15-16፤ 17፡22-23፤ 1 ቆሮ. 1፡9)

“ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፣ የእግዚአብሔርም መላእክት


ተገናኙት፡፡ ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፡- እነዚህ የእግዚአብሔር
ሠራዊት ናቸው አለ፤ የዚያንም ስፍራ ስም መሃናይም
ብሎ ጠራው፡፡”
ዘፍ. 32፡1-2
13
መሃናይም = ሁለት ሠራዊት
1) የመላእክት እና የሰዎች አንድነት

2) የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳን ምእመናን አንድነት፣

3) በዓለመ ነፍስ ያሉ (Church Triumphant) እና


በዚህ ዓለም ያሉ (Church Militant) አንድነት፣

4) የስውራንና በግልጽ ያሉ ምእመናን አንድነት

14
 “ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው
እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም
ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ
አእላፋት መላእክት፣ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ
በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ
እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን
መንፈሶች፣ . . . ደርሳችኋል።”
ዕብ. 12፡22-24

15
 “እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው. .
. ስለ አካሉም ማለት ስለ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዬ
በክርስቶስ መከራ የጐደለውን እፈጽማለሁ።” ቆላ.
1፡18፣24
 ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ የካህናት ሞኖፖሊ ወይም
ተቋም አይደለችም፡፡
 በዚህ ዓለም ያለችው ቤ/ክ በዚህ ዓለም እስካለች
ድረስ በአወቃቀሯና በአሠራሯ፣ በአባላቶቿ
እንዲሁም በአፍኣዊ አደረጃጀቷ “ምድራዊ” ከሆኑ
ነገሮች ሙሉ በሙሉ ነጻ ልትሆን አትችልም፡፡

16
 የሆነ ሆኖ ይህ “ምድራዊ” ቅሬት መንፈሳዊ የሆነውን
ማንነቷን ሊሸፍነው አይገባም፣ ከዓላማዋም
እንዳያስታት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ቤ/ክ
የተመሠረተችውም፣ የምትኖረውም ነፍሳት የዘለዓለምን
ሕይወት ያገኙ ዘንድ ነውና ይህ ዓላማዋ ምን ጊዜም
መጠበቅና መቅደም ይኖርበታል፡፡
 “ . . . ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ
የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም
እንዲሁ ነው።” ገላ. 4፡28-30
 “ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም
በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ
አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ
17
ኦርቶዶክሳዊነት
 አተያይ ነው፣ እይታ ነው፣ አመለካከት ነው፣
 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስን
የምንረዳበት መንገድ ነው፣
 ዓለምንና በዓለሙ ያለውንና የሚሆነውን ነገር
ሁሉ የምናይበት መነጽርና የምንረዳበት
መንገድ ነው፡፡
 መጽሐፍ ቅዱሳዊና በአበው የተመሠረተ ነው፡፡

18
 መጽሐፍ ቅዱስን በምልዓት ማመንና
መቀበል ላይ የተመሠረተ ነው፣
 የጥቅሶች ስብስብ አይደለም፣
 የመረጃ ጥርቅም ወይም የእውቀት ክምችት
አይደለም፤ ሰዎች አዋቂዎች ሆነው
ኦርቶዶክሳዊ እይታ ላይኖራቸው ይችላል፡፡

19
፩. ነገረ ድኅነታዊ
፪. ነገረ መለኮታዊ
፫. ምንታዌ - ምልአታዊ እይታ
፬. እምነት እና እውቀት
፭. የቤተ ክርስቲያን አንድነት መሠረት
፮. ሥራና ገንዘብ
፯. አክባሪነት - አቃላይነት

20
1. ኃጢአት ካመጣው ፍዳ ከሞትና
ከቅጣት መዳን፣
2. ፈጣሪውን እንዲያውቅ መሆን፣
3. ሐዲስ ተፈጥሮ፣ እና
4. በቅድስና (እግዚአብሔርን በመምሰል)
ማደግ ናቸው፡፡

21
 “በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ” ዘፍ. 2፡17
 “… ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፣ እኛም
እንለወጣለን፡፡ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን
ሊለብስ፣ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ
ይገባዋልና፡፡ ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው
የማይበሰብሰውን ሲለብስ፣ ይህም የሚሞተው
የማይሞተውን ሲለብስ በዚያን ጊዜ፡- ሞት ድል
በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል፡፡”
1 ቆሮ. 15:51-55
22
 በኃጢአት ምክንያት የዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ
ነበር፡፡ ጌታችን ያን ባርነት አስወግዶ የልጅነትን
ጸጋ ሰጠን፡፡
 “የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ
መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል”
እንዳለ፡፡ ሮሜ. 8:16
 ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት
ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ
ውስጥ ላከ፡፡ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ
ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ
ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ
23
 “እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ
ናችሁ። ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ
ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን
ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ
አስታውቄአችኋለሁና።” ዮሐ. 15፡14-15
 “የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፡፡” ኤፌ. 1:9

24
 “የዝግባን፣
የዞጲንን፣ የኮምቦልንና የጥድን ዛፍ
ይተክላል፣ ዝናብም ያበቅለዋል፡፡ ለሰውም
ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፣
አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም
አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፣ የተቀረጸውንም
ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል፡፡
ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፣ ሥጋም
ይጠብስበትና ይበላል . . . የቀረውንም
እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤
በፊቱም ተጎንብሶ ይሰግዳል፣ ወደ እርሱም
25
 “እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች
በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ
የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤
እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር
ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።
የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ
ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ
ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም
እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን
ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤
ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም
ልባቸው ጨለመ።”
26
 “ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች
በስብከት በሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን
የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኗልና” 1 ቆሮ. 1:21
“ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤
እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም
መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም
ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ።
በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።”
ማቴ.3፡16-17
 “መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ
የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ
ተረከው፡፡” ዮሐ. 1:18 27
 “ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ
ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ
ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ
ይመጣል።” ዮሐ. 6፡45

 “ሌላሰው ያላደረገውን ሥራ
በመካከላቸው ባላደረግሁ፥ ኃጢአት
ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም
አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል።”
ዮሐ. 15፡24 28
 “ፊልጶስጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል
አለው። ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥
ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር
አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤
እንዴትስ አንተ አብን አሳየን ትላለህ? እኔ
በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ
አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ
አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ
እርሱ ሥራውን ይሠራል። እኔ በአብ እንዳለሁ
አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ
ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።” ዮሐ. 14፡8-11 29
 “እኛናፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ
መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር
ነው? ብለው በጠየቁት ጊዜ “በአረጀ ልብስ አዲስ
እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን
ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል።
በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር
የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥
የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤
ነገር ግን አዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም
ይጠባበቃሉ” በማለት የመለሰላቸው ለዚህ
ነበር። ማቴ. 9፡16-17 30
 “እርሱሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ
በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ
በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው
ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን
ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ
ዘንድ” እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ኤፌ. 2፡14-
15

ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ


 “ስለዚህ
ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፏል፤ እነሆ
ሁሉም አዲስ ሆኗል” ሮሜ 6፡4 31
 ይህን ሐዲስ ተፈጥሮ እያንዳንዱ ገንዘብ
ሊያደርገው የሚገባ ስለመሆኑም ሲናገር፡-
 “በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን
ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም
አለመገረዝ አይጠቅምምና” ገላ. 6፡15
 “ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ
እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን
ሰው ልበሱ፡፡” ኤፌ. 4፡24
 “ለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ
ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥
ሁሉም አዲስ ሆኖአል።” 2 ቆሮ. 5፡17 32
 “ከአንግዲህስወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ
የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን
ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን”
በማለት የገለጸው ይህን ነው፡፡ እንዲሁም
 “አሁንግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ
ለእግዚአብሔር ተገዝታችሁ ልትቀደሱ
ፍሬ አላችሁ፡፡” ሮሜ. 6:6 ፣ 20-22 ፣
7:4-6

33
 “እምይእዜሰ ኢኮንክሙ ነግደ ወፈላሴ
አላ አንትሙ ሰብአ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን
ወሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር -
 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን
ጋር ባላገሮች እና የእግዚአብሔር ቤተ
ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች
አይደላችሁም፡፡” ኤፌ. 2:19
34
 “ወደ
ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው
እግዚአብሔር ተራራ ደርሳችኋል፣ ወደ
ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፣ በደስታም ወደ
ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፣
በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት
ማኅበር፣ የሁሉም ዳኛ ወደ ሆነ ወደ
እግዚአብሔር፣ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ
ጻድቃን መንፈሶች፣ የአዲስ ኪዳንም
መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ …
35
 ሱታፌ አምላካዊ (Theosis or Divinization)
 “ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ
ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል
እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና
እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን”2 ጴጥ. 1፡4

 የእግዚአብሔር ባሕርይ (ουσια - God’s essence)


 የእግዚአብሔር ባሕርይ መገለጫዎች (ενεργια -
divine energies) - ቅድስና፣ ቸርነት፣ ደግነት፣
ጥበብ፣ እውነተኛነት፣ ገዢነት፣ . . .
36
 “እኔ ግን አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም
የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ” የተባለውና
ጌታችንም ይህን በማጽናት
 “እኔ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ
የተጻፈ አይደለምን?” በማለት የተናገረው
ይህን ለሰው ልጅ የተዘጋጀውን ጸጋ ሲያስረዳ
ነው፡፡ መዝ. 81፡6 ፤ ዮሐ. 10፡34

37
 “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን
ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ
እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኗልና፡፡” ሮሜ
8፡29
 “እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት
የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን
መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ
እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር
እንለወጣለን።” 2 ቆሮ. 3፡18

38
 “እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ
እናንተ ፍጹማን ሁኑ፡፡” ማቴ. 5፡48
 ይህ የማይቻል ቢሆን ኖሮ ጌታችን ሊሆን
የማይችል ነገር አይናገርም ነበር፡፡
 “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤
ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን
እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥
በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን
መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ፡፡” ፊል.
3፡13-14
39
 “እርሱ ሰው የሆነው እኛን አማልክት ዘበጸጋ
ያደርገን ዘንድ ነው፤ ከሴት፣ ከድንግል የተወለደው
በስህተት ላይ የነበረውን ትውልዳችንን ያስቀርልንና
ከዚያ ወዲህ የተቀደስን ዘሮች እና የመለኮታዊ
ባሕርይ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ ነው፡፡” ቅዱስ
አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
 “ቃል ሰው የሆነው ሰዎች የጸጋ አማልክት ይሆኑ
ዘንድ ነው፡፡” ቅዱስ ሄሬኔዎስ

 “እኔ የጸጋ አምላክ ልሆን የተጠራሁ ፍጡር ነኝ፡፡”


ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
40
 “በመፈጠሬ የእግዚአብሔር መልክ (አርአያ
እግዚአብሔር - the image of God) አለኝ፣ ነጻ
ፈቃዴን በመጠቀም ደግሞ በእግዚአብሔርን ምሳሌ
(in the likeness of God) እሆናለሁ፡፡” ቅዱስ
ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
 “አምላክ ሰው የሆነበት (ሥጋዌ) ዓላማ ሰውን
አምላክ ለማድረግና የሰማያዊ ክብርና ሐሤት
ተካፋይ ለማድረግ ነው፡፡ . . . የጸጋ አምላክነት እርሾ
የሰውን ሰውነት አዲስ ፍጥረት አድርጎታል፣ ይህን
እርሾ በመቀበልም የሰው ባሕርይ ከመለኮታዊ ባሕር
ጋር በተዋሕዶ አንድ ሆኗል፣ በመለኮት ተዋሕዶም
የጸጋ አምላክነትን አግኝቷል፡፡” ቅዱስ ጎርርዮስ 41
 በምዕራባውያንና በምሥራቃውያን ነገረ መለኮታዊ
አተያየቶች መካከል መሠረታዊ የሆነ ልዩነቶች አሉ፡፡
 The Western approach is called Cataphatic,
 The Eastern approach is called Apophatic.

42
 This approach is also known as positive or
affirmative theology.
 In general, the western approach in theology from the
early times is more rigid and legalistic.
 The west attempted to express theological truths using
hard and fast definitions and principles. They followed
a more legalistic approach in theologization.
 Later in the medieval period empirical philosophies
brought more rigidity to the western theology and it
expressed the traits of monotonous and academic
nature.
43
 Thomas Aquinas (1225-1274), an Italian scholastic
philosopher and theologian of 13th century, prepared a
more cataphatic and academic platform for the western
theology.
 Thus the medieval western theology became an
intellectual and philosophical exercise standing far
from the pastoral tasks of the Church.
 All the works of Aquinas are thoroughly sealed with
scholastic approach to learning.
 The whole of the western theological world continued
to be in the Thomistic legacy until the emergence of
Protestantism

44
 Protestantism emerged as a breakthrough in the milieu
of legalistic mediaeval theology of the Catholic
Church.
 The movement of reformation in the Catholic Church
has successfully identified some of the problems of
then Catholic Church, but pathetically failed in
introducing a balanced approach to rectify the serious
issues in the theological standpoint of the western
theological world.
 It seems to be an un-thoughtful emotional reaction
towards the rigidity of the catholic administrative
structure, the over philosophized theology and
ritualistic and superstitious piety promoted by the
Catholic Church in the mediaeval period. 45
 The Cataphatic way tries to define the theological
truths using logical and rational theories.
 It tries to define the divine self-revelation using
human language and knowledge and to affirm the
definitions and ideas as if they are perfect
conclusions on theological affairs.
 Such a trend prevents the understanding of theology
as an enquiry everlasting. It will rather end up in
conclusions within the limits of human
intelligence and reasoning capacity.
46
 It also tries to get an answer for every question
regarding theology.
 It is rather speculative and philosophical than
spiritual and mystical

 Following the footsteps of the medieval


western theology, the modern theologians use
techniques of scientific and logical enquiry to
reach in objective conclusions in Theology.

47
 Brian Daly, one of the scholars of the Catholic
Church, comments on the critical approach of the
western Biblical theology:
 “. . . modern historical criticism including the
criticism of Biblical texts is methodologically
atheistic; even if what it studies is some form
or facet of religious belief, and even if it is
practiced by believers. ... explanations that
could be acceptable to believers and
unbelievers alike, are taken as historically
admissible”.
48
 This is an attempt to highlight historical
criticism as a way to explore the real
Christianity by passing over the understanding
of whole generations of faithful.

 It attempts to move into diverse directions


without stability of faith and following the trial
and error system while spirituality identified its
own path free from intellectual traits and
logical quests. So there we see distinct traits of
lifeless theology and shallow spirituality.
49
 It is the theological methodology of the Eastern
ecclesiastical tradition.
 This approach is also called negative theology.
 The basic principle behind this approach is that the
divine mysteries are beyond human perception and
we cannot make definitions or theories regarding
them.
 It explains the faith in a mystical way and makes a
series of negations while learning theology.
 According to the apophatic theologians, rational
theories and logical definitions are quite irrelevant in
explaining the divine mysteries.
50
 In general we can say that Theology of the Eastern
tradition is grounded on the sources of faith namely
scriptures, tradition, liturgies, Patristic writings,
monasticism, asceticism, mysticism, spiritual literature,
and all sort of spiritual expressions.

 Theology in the Oriental, especially Semitic, traditions


is not an academic exercise supported by a rational
enquiry, but it is the conviction of the Church naturally
developed out of prayer, meditation, contemplation,
fasting, abstinence and ascetical life deep-rooted in her
commitment to God.

51
 The most fundamental tenet of Theology of the
Eastern tradition in general and that of Semitic
traditions in particular is its scriptural
rootedness.
 The eastern approach in theology never
completely denies the role of logic or
philosophy in theology, but limit it to the level
of a tool or method to explore the real
meanings of the revealed truth.

52
◦ “Reason, in its speculative thrust, is free to go
where ever it wants, where as for the Christian,
reason has to be controlled by the category of
the Intent of Scripture.”

◦ “We make the Holy Scripture the standard and


rule of all teaching; we are bound, therefore, to
have in view that and only that is which is in
harmony with the intention of Scripture”.
St. Gregory of Nyssa, On the Soul and Resurrection.

53
 Theology is understood by the Oriental fathers as
necessarily and intimately a pastoral task. They
developed the theology profoundly pastoral in its tenor,
purpose and execution.

54
አንዳንድ የልዩነቱ ማሳያዎች

55
 ...
 According to it, the elements will be consecrated at
the moment of pronunciation of the ‘Words of
Institution’ by the celebrant.
 They declare the ‘Words of Institution’ as Consecratory
formula. Importance of the rest of the Anaphora is
totally neglected. The role of Holy Spirit in the
Eucharist is also ignored. For them the power of the
‘Words of Institution’ is more important than the
working of the Holy Spirit. They call it consecratory
formula.
 56
 In the Orthodox understanding the whole
Anaphora is consecratory. We do not attribute a
special consecratory effect to a particular prayer
or formula.
 Eucharist is the utmost act of the Church, which
makes her the body of Christ. In the Eucharist
the bread and wine become the body and blood
of Christ. It is divine mystery realised by the
working of the Holy Spirit. We cannot explain
it using any theory like ‘transubstantiation’ and
specify any moment of consecration.
57
 According to the Catholic understanding,
marriage is a contract between bridegroom and
bride. The role of Church in the marriage is that
of a witness and to communicate divine
blessings to them. There the celebrant of the
Sacrament is the couple, not the Church. The
priest witnesses and blesses their union as
representing the Church.

58
 According to the Orthodox understanding, in
the Sacrament of Marriage, the Church unites
two of her children to constitute a Christian
family. There the priest as the representative of
the Church serves as the celebrant of the
Sacrament. The couple is recipient and
participant of the Sacrament.

 So for us marriage is not a mutual contract


between two persons but a sacramental mystery
executed by God through the Church.
59
 The Catholic Church separate sins into
different grades like mortal, venial etc. Such
kind of gradation is not in the Orthodox
tradition.
 For them, the right to remit some sins is
reserved to Bishops or the Pope. The prayer of
absolution in the Catholic Church is different
from the same in the Orthodox Churches.
 In catholic tradition the priest says, “...by the
authority given to me I absolve your sins.”
60
 Whereas the in Eastern traditions the prayer of
absolution is in a passive grammatical
structure, “... let God absolve your sins.”

 Cataphatic and Apophatic approaches are


clearly visible in these prayers. Catholics do
not call it prayer but ‘formulae of absolution’.
The Catholic approach has the influence of
Roman legalism.
61
 The Catholic Church developed certain laws
regarding the validity of the Sacraments and
time of Consecration of the elements used in
it.
 The Orthodox Tradition considers the
Sacraments as the acts of the Church entering
into the eternal salvific mysteries of God.

62
 “If you see the world in black and white,
you're missing important grey matter.”
Jack Fyock
 ጸጋና ሥራ (grace vs work)
 የእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነትና የሰው ነጻ ፈቃድ
(Free will vs Foreknowledge)
 ነፍስና ሥጋ (Body vs Spirit)
 እምነትና ሥራ (Faith vs works)
...

63
 ኦርቶዶክሳዊነት የተቀበልነውና የምናምነው
አስተምህሮ ብቻ አይደለም፣ አስተሳሰብ ብቻ
አይደለም፣ ሕይወትም ነው እንጂ፡፡ ንድፈ ሃሳብ ብቻ
አይደለም፣ ተግባርም ነው እንጂ፡፡
 እውነተኛውና ቀጥተኛው እምነት ብቻ ሳይሆን
በሁሉም መንገድ ከእምነቱ ጋር የሚስማማ ሕይወትም
ነው ነው፡፡
 እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ በሆነ
መንገድ የሚያስብ ብቻ አይደለም፣ በኦርቶዶክሳዊነት
ሁኔታ የሚሰማውና ኦርቶዶክሳዊነትን በተግባርም
የሚኖር ነው እንጂ፡፡ የክርስቶስን እውነተኛ ትምህርት 64
 ዛሬ ቀላሉን የክርስቶስን ቀንበር “እናለዝባለን” የሚሉ፣
መንፈሳዊነትን ከኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ለማስወጣት
የሚታገሉ፣ የቤ/ክንን ገዳማዊና ምናኔያዊ ጠባይ የሚጠሉና
ለማጥፋት የሚጥሩ፣ ኃጢአትን ጽድቅ ወይም ሥልጣኔ
መስሎ እንዲታይ ለማድረግ የሚጥሩ፣ ግን “ኦርቶዶክስ”
ነን የሚሉ ሰዎችን በውስጥም ሳይቀር ማየት እንግዳ
አይደለም፡፡ ይህ ከኦርቶዶክሳዊነት ጋር መቸም መች
ሊስማማ የማይችል ነገር ነው፡፡
 ማንኛውም ዓይነት ነገር ሕጋዊና መብት ማስመሰል፣
ኃጢአት “ኃጢአት” ነው ከማይባልበት ደረጃ እየደረስን
እንገኛለንና ይህ ሊያሳስበን ይገባል፡፡
 ቤ/ክንን ከመንፈሳዊነት ዓላማዋ ለማውጣትና ወደ ሌላ
ለመጎተት ያለው ሁኔታም እንዲሁ፡፡
65
 በኦርቶዶክሳዊነት ጸሎትና ጾም እጅግ በጣም ታላቅ
የሆነ ቦታ አላቸው፡፡ ከመዳናችን ጠላቶች ጋር
የምንዋጋባቸው ረቂቅ መሣሪያዎች እነዚህ ናቸውና
ቤ/ክ እነዚህን ልትተው አይቻላትም፡፡
 ነፍሳችን ብርህት የምትሆነውም በእነዚህ ነው፡፡
 “ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር
አይወጣም አላቸው።”
ማቴ. 17፡20-21

66
 “ጸሎትና ጾም በሌለበት ሰው ውስጥ ሰይጣን አለ ብለን ማሰብ
እንችላለንን?” ብሎ ይጠይቅና ሲመልስ “ አዎ፣ አጋንንት ወደ
ሰው ውስጥ ሲገቡ መግባታቸውን በገሀድ አያሳውቁም፣
መግባታቸው እንዳይታወቅባቸው ለማድረግ ሲሉ ራሳቸውን
ይደብቃሉ እንጂ፤ ሆኖም የገቡበትን ያን ሰው ክፉውን ነገር
ሁሉ በስውር ከውስጥ ያስተምሩታል፣ መልካም የሆነውን ነገር
ደግሞ ያስጠሉታል፡፡ ያ ሰው የሚፈጽመው የጠላትን ፈቃድ
ሆኖ ሳለ እርሱ ግን እርሱ ራሱ እያደረገው እንደሆነ ያስባል፡፡
ጠላት ትቶህ የሚወጣውና ሌላ መመለሻ አጋጣሚ እሰኪያገኝ
ድረስ ከአንተ ርቆ የሚጠባበቀው ጸሎትና ጾምን ስትታጠቅ
ብቻ ነው፡፡ ጸሎትና ጾም ከተተው ግን እንደገና ተመልሶ
ይመጣል፡፡”
(Theophan the Recluse, Thoughts for Each Day of the
Year, pp. 245-246) 67
 ስለሆነም ጾምና ጸሎት በተተውበትና በሌሉበት
ሕይወት ዘንድ ኦርቶዶክሳዊነት ሽታውም አለ ማለት
አይቻልም፤ የአጋንንት መሥሪያ ቤት እንጂ
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይኖርም፡፡
 “ዘመነኛ” ወይም “ሊበራል” በሚል ሽፋን ሰይጣን
የሚሰብከውን “ጾም የለሽ” ክርስትና ወይም እምነት
ልብ እንበል፣ እንወቅበት!
 ኦርቶዶክሳዊነት በባሕርዩ ትህርምታዊ ነው፡፡

 “ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ


እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ
ቢኖር ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ
ይከተለኝ።” ማር. 8፡34 68
 “የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና
ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ
እንመላለስ።” ገላ. 5፡24-25
 ጊዜውንና ሕይወቱን በተድላና በደስታ ለማሳለፍ
የሚፈልግና ራስን ስለ መካድና ራስን ስለ መግዛት
የማያስብ ሰው፣ ሥጋዊ ደስታንና ምኖትን ብቻ የሚከተል
ሰው ኢኦርቶዶክሳዊ ነው፣ ኢክርስቲያናዊ ነው፡፡
 “የእግዚአብሔር መንገድ በየዕለቱ የሚሆን መስቀል ነው፡፡
ያለ ውጣ ውረድና ተጋድሎ፣ እንዲሁ ተዘልሎ የሚኖር
ማንም ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት ሊወጣ አይችልም፡፡
እንዲህ ያለው ተዘልሎ የመቀመጥ ሕይወት መንገድም
የት እንደሚያደርስ እናነውቃለን፡፡ ይህም ራሱ ጌታችን
ፍጻሜው ጥፋት ነው ብሎናልና፡፡” 69
 «What is the difference, in your opinion, between the
Roman and the Orthodox Church?'»
 He said: «In the Roman Church I met many good
people. But I have never found a really spiritual
person».

 Fr. Gabriel Pataci was a man of a «deep» heart. His


thirst was a thirst for the unification of mind and heart.
He intensely felt —both in himself and in the world
around him— the schismatic disunity between mind
and heart, knowledge and faith, action and existence.

70
 በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ የአንድነቱ መሠረት ሃይማኖት ነው፣
መገለጫው ደግሞ በምሥጢራት አንድነት (ሱታፌ) ነው፡
 በምዕራባውያን (ካቶሊኮች) ዘንድ የአንድነቱ መሠረት ለሮማው
ፓፓ መታዘዝና በእርሱ የአስተዳደር የእዝ ሠንሰለት ሥር መሆን
ነው፡፡
 በፕሮቴስታንቶች ዘንድ ደግሞ ቤ/ክ ማለት የግለሰቦች ስብስብ
(Congregation) ብቻ ነው፡፡
 “Denominationalism might not be the ideal, but in a world
of sin and misery, God in his providence can use each
faithful denominational stone who hold to the once for all
faith delivered to the saints that is articulated in the
Apostles Creed to build his holy temple.” (Protestants’ view
71
 “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም
ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።” ዘፍ. 2፡15
 ገነትን እንዲጠብቃትና እንዲንከባከባት ያዘዘው በገነት የጎደለ
ነገር ኖሮ አዳም ያን እንዲያሟላ አልነበረም፤ ምክንያቱም
በገነት ውስጥ ለሰው የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ነበረና፡፡
 እግዚአብሔር ሥራን ገንዘብ ከማግኘትና ከትርፍና ከኪሳራ
ስሌት ጋር ብቻ እንዲተሳሰር ያላደረገበትና ሥራ በራሱ ያለው
አስፈላጊነት ጎላ ብሎ እንዲታይ ያደረገበት ምክንያት ነበረው፡፡
እንዲያ ቢሆን ኖሮ ሰው ያን ጊዜ የጎደለበት ነገር ስላልነበረ
ለመሥራት የሚነሣሳበት ምክንያት አልነበረውም፡፡

72
 በመቀጠልም አዳም ከገነት ከተባረረ በኋላ በራሱ ድካም ሠርቶ
በሚያገኘው ነገር ራሱን እንዲያኖር ተነግሮታል፤ “አዳምንም
አለው፣ . . . በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርሷ
ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፣ የምድርንም
ቡቃያ ትበላለህ። ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ
በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፣ አፈር ነህና፣ ወደ አፈርም
ትመለሳለህና።” ዘፍ. 3፡17-19
 አሁን የተለወጠው ሥራ ማስፈለጉ ሳይሆን ሥራ ለመኖር የግድ
አስፈላጊ መሆኑና ከዚያም ላይ አድካሚና በውጣ ውረድ
የታጀበ መሆኑ ነበር፡፡
 ሥራው ገነትን ማበጃጀትና መጠበቅ መሆኑ ቀርቶ ምድርን
ማረስና መውዛት አስፈለገው፡፡ “በፊትህ ወዝ” የሚለው
መድከምን፣ መውጣትንና መውረድን፣ በአጠቃላይ በዚህ
ዓለም ያለውን የኑሮ ውጣ ውረድና ትግል የሚያመለክት ነው፡፡
73
 ይልቁንም ስንፍና በራሱ ታላቅ ቅጣት መሆኑን መጽሐፍ
ቅዱስ “ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው” በማለት ይናገራል፡፡
ምሳ. 16፡22
 እንዲሁም “ወኢትኑም ከመ ኢትንዲ ክሥት አዕይንቲከ
ወጽገብ ኅብስተ - ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፤
ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ” ይላል። ምሳ. 20፡13
 ሥራን ጠልተው ስንፍናንና ዕለታዊ ተድላ ደስታን ብቻ
የሚያሳድዱ ሰዎች ደግሞ ምን እንደሚያገኛቸው ሲናገር
“ተድላን የሚወድድ ድሀ ይሆናል፥ የወይን ጠጅንና ዘይትንም
የሚወድድ ባለጠጋ አይሆንም” ይላል፡፡ ምሳ. 21፡17
 ስንፍና ምን ያህል ሰውን የሚያበላሽ ነገር መሆኑንም “የሞቱ
ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፣ እንዲሁም
ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል” ይላል። መክ. 10፡1
74
 ስንፍና ከዚያም ባለፈ እብደት መሆኑን ሲናገር፡- “አውቅና
እመረምር ዘንድ፣ ጥበብንና የነገሩን ሁሉ መደምደሚያ
እፈልግ ዘንድ፣ ኃጢአትም ስንፍና፣ ስንፍናም እብደት እንደ
ሆነች አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ” ይላል። መክ. 7፡25
 ሥራ ፈትነት ምን ያህል ጥፋትን የሚያስከትል መሆኑንም
“እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፡- ትዕቢት፣
እንጀራን መጥገብ፣ መዝለል እና ሥራ መፍታት በእርሷና
በሴቶች ልጆቿ ነበረ” ይላል፡፡ ሕዝ. 16፡49
 አምስት ከተሞች የነበሩባቸውን ሰዶምንና ገሞራን እጅግ
አስነዋሪ በሆነ ኃጢአት እንዲመላለሱና በድኝ እሳት እንዲጠፉ
ካደረጋቸው ነገር አንዱ “ሥራ መፍታትና መዝለል” ነበረ
ማለት ነው፡፡

75
 እንዲሁም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን
የሚያረክሱት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ከዘረዘራቸው ነገሮች
መካከል አንዱ ስንፍና መሆኑን ተናግሯል፤ እንዲህ ሲል፡-
 “ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። ከውስጥ
ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥
ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥
ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው
ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።” ማር. 7፡20-23

 እንዲሁም ጊዜያቸውን ለሥራ ማዋል ትተው ሥራ ፈትነትን


የሚያስተምሩና ሥራን የሚያዳክሙትን እንዲህ ሲል በጽኑ
ይወቅሳቸዋል፤ “ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን
መፍታት ደግሞ ይማራሉ፥ የማይገባውንም እየተናገሩ
ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ ሥራ ፈቶች ብቻ
አይደሉም።” 1 ጢሞ. 5፡13 76
 ቤተ ክርስቲያን ሥራ አስፈላጊ ስለ መሆኑ ከጥንት ጀምሮ
አስተምራለች፡፡ መሥራት የታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ
ተፈጥሯዊ ግዴታ ተደርጎ ይታሰብ በነበረበትና መሳፍንቱና
ወይዛዝርቱ ግን ከዚህ ጉዳይ ነጻ እንደሆኑ ተደርጎ
ይታሰበብበት በነበረውና ያን ዓይነት አስተሳሰብ መቃወም
ሥርዓተ ማኅበረሰቡን እንደ መቃወም ተደርጎ ይቆጠር
በነበረበት በዚያን ዘመን “ሊሠራ የማይወድ አይብላ”
በማለት ስታስተምርና ስትናገር ነበር፡፡ 2 ተሰ. 3፡10

 እንዲህ ብዙ የተደከመበት ዓለም አሁን ከደረሰበት ዘመን


ላይ ሆኖ ስለ ሥራ ክቡርነትና አስፈላጊነት በግልጽና በጠራ
ሁኔታ ሲያስተምር የነበረውን ክርስትናን ለመተቸት መነሣት
ወይ ታሪክ አለማወቅ ነው፣ አለዚያም ደግሞ ሆን ብሎ
ጥላሸት የመቀባት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር መሠረት የለሽ 77
 እግዚአብሔር ለተልእኮ የጠራቸውን ሰዎች ሁሉንም
ማለት በሚቻል መልኩ የጠራቸው ከሥራ ላይ ነው፡፡
 ታዲያ “ያለኝ ይበቃኛል” ወይም “ኑሮዬ ይበቃኛል”
ማለት ምን ማለት ነው? ለምንስ ተባለ? እንዲህ
መባሉስ ጠቃሚ ነው ወይ? ፊል. 4፡9-13
 “ስግብግብ ሰው ዓይኖቹም ከባለጠግነት
አይጠግቡም” ተብሏልና፡፡ መክ. 4፡9 ፤ ሢራ. 14፡9
ስለዚህ “እንደነዚህ ካሉት ራቅ” በማለት ቅዱስ
ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩን ጢሞቴዎስን መከረው፡፡

78
 ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና ፈተና የሚሆነውም ባለ ጸጋ
መሆን ሳይሆን ባለ ጸጋ የመሆን ምኞት ነው፤ “ዳሩ ግን
ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን
በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና
በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ” በማለት ሁለቱ (ባለ
ጸጋነትና ባለ ጸጋ የመሆን ምኞት) የተለያዩ ነገሮች
መሆናቸውን በግልጽ አስረዳ፡፡ ቁ. 9
 ሰው ሀብት ሊኖረውና ሀብቱንም በአግባቡ በመጠቀም
ለራሱም ለሌላውም የሚጠቅም ሰው ሊሆን ይችላል፡፡
በአንጻሩ ደግሞ ሀብትን ለሀብትነቱ ሲሉ ብቻ አጥብቀው
የሚፈልጉትና የሚመኙት ሰዎች ደግሞ ያን ገንዘብ
ለማግኘት ሲሉ ብዙ አስቸጋሪና ከእግዚአብሔር የሚለዩ፣
ሊፈጸሙ የማይገቡ ነገሮችን ወደ ማድረግ ሊሄዱ 79
 ከእያንዳንዱ ሀብት በስተ ጀርባ የሆነ ታሪክ አለ
እንደሚባለው ባለ ጸጋ በመሆን ምኞት ምክንያት ተስበው
እንደ ፉላ ቀሲስ ከራሳቸውም ከእግዚአብሔርም ሳይሆኑ
የቀሩ ብዙዎች አሉ፡፡
 ሰዎች ልጆቻቸውን እንኳ ሳይቀር ለመተትና ለሟርት፣
ለሰይጣን መጫወቻነት አሳልፈው እስከ መስጠትና
በቤታቸው ውስጥ በሽተኞች ሆነው እንዲቀመጡ እስከ
ማድረግ ያደረሳቸው ባለ ጸጋ የመሆን ምኞት አይደለምን?
ብዙ ሰዎች ለጠንቋይ የሚሰግዱት፣ ባልንጀራቸውን
የሚክዱት፣ አምኖ በተጠጋቸው ሰው ላይ አሰቃቂ ነገሮችን
የሚያደርጉት በገንዘብ ፍቅር ተነድተው እንጂ ሌላ ምን አገኝ
ብለው ይሆን? ለዚህ ነው “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ
ሥር ነው” ያለው፡፡
80
 በዚህ በፍቅረ ነዋይ ምክንያት በሰዎች ላይ ምን እንደ
ደረሰባቸው ሲናገር “አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት
ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ” ይላል።1 ጢሞ.
6:10-12
 አዎ፣ ብዙ ሰዎች ከሃይማኖት የወጡት በገንዘብ ምክንያት
ነው፣ ገንዘብ ለማግኘት ወይም ያገኙትን ላለማጣት ሲሉ
ከሃይማኖት ወደ መናፍቅነትና ወደ ክህደት የገቡ ብዙዎች
ናቸው፡፡
 ምድራዊ ሀብት፣ ሥልጣን፣ ሹመት፣ ሽልማት፣ ዝና፣ ክብር፣
ወዘተ እናገኛለን በማለት ክርስቶስን የካዱ ለጣዖት (ለሀብት፣
ለሥልጣን . . . ) የሰገዱ ብዙ ናቸው፡፡ ቀን ከደኅና ወንበር
ከትልቅ መንበር ተቀምጠው እየዋሉ ሌሊቱን ደግሞ “ሌላ
ቦታ” በ “አገልግሎት” ተጠምደው የሚያሳልፉትን ቤት
ይቁጠራቸው፡፡ 81
 የገንዘብ ፍቅር ከልብ ውስጥ ከገባ ለራስም ለማኅበረሰብም
ብዙ ጉዳት ያደርሳል፡፡ የታላቁ የኤልሳዕ ደቀ መዝሙር
የነበረው ግያዝ በንዕማን ሶርያዊ ሰውነት ላይ የነበረው
ለምጽ በእርሱ ላይ ተገልብጦ ያደረበት ገንዘብን በመውደዱ
ምክንያት ነበር፡፡ 2 ነገ. 5፡18-27

 አካን የተባለው እስራኤላዊ “እርም ነው አትንኩ” የተባለውን


የኢያሪኮን ወርቅ በመንካቱ ሕዝበ እስራኤላውያን
በጠላቶቻቸው እንዲሸነፉና ከመካከላቸው ብዙዎች
እንዲገደሉ ምክንያት ሆኗል፡፡

 በእርሱም ምክንያት መላው ሕዝብ አምላካችን ትቶናል


ብለው በእጅጉ ተጨንቀዋል፡፡ ኢያ. 7 ዲያብሎስ ገንዘብ
ሰውን እንደሚያጓጓውና ልቡን እንደሚያማልለው ካየ በዚያ
ቀዳዳ በኩል ገብቶ ይፈትነዋል፣ በቀላሉም ይጥለዋል፡፡ 82
 ስለዚህ የዚህን ዓለም ሕይወት በጣም አድርገው
ለማጣጣም የሚፈልጉ ሰዎች ያንኑ የተመኙትን የዚህ
ዓለም ሕይወት የሚሰጠውን ተድላ ደስታ እንኳ በቅጡ
አያገኙትም፡፡

 በአንጻሩ ተስፋቸውን በዚህ ዓለም ሕይወት ሳይሆን


በሚመጣው በዘለዓለማዊው ሕይወት የሚያደርጉ ሰዎች
ደግሞ በዚህ ዓለም ያለውንም ነገር በአግባቡ
ይጠቀሙበታል፣ ደስታ ጣዕም ያለው ደግሞ አንድ ነገር
ስላለ ብቻ ሳይሆን ያንን ነገር የምንቀበልበት ሥነ
ልቡናዊና ውስጣዊ ስሜት ስለሆነ የሚያገኙትን ነገር ሁሉ
በምስጋናና በሐሤት ስለሚቀበሉት ጣዕሙ በእጅጉ
የጣፈጠ ይሆንላቸዋል፡፡
83
 በዚህ ዓለም በሉ ክፉ ነገሮች ሁሉ ከጀርባቸው ገንዘብ
የሌለባቸው ነገሮች ይኖሩ ይሆን? ጥላቻዎች፣ የእርስ በርስ
ሽኩቻዎች፣ ጦርነቶች፣ ጭካኔዎች፣ መገዳደሎች፣ መከዳዳቶች፣
ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው ክፉ ነገሮች መሠረታዊ
መንሥዔያቸው ስግብብነት አይደለምን?
 ጥበበኛው ሰሎሞን “ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤
ድኅነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ፣ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን
እንጀራ ስጠኝ፥ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም፣ እግዚአብሔርስ
ማን ነው? እንዳልል፣ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥
በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል” በማለት ፈጣሪውን
የለመነው ለዚህ ነበር። ምሳ. 30፡8-9
 ለገንዘብ ብቻ የሚስገበገብ ሰው ጓደኛ ወይም ዘመድ የሚባል
ነገር አያውቅም፡፡ እግዚአብሔርንም አያውቅም፡፡ ገንዘብ
ያስገኝልኛል ከመሰለው የማያፈርሰው የእግዚአብሔር ሕግ
84
 እንዲህ ያሉ ሰዎች ቋሚ ወዳጃቸው ገንዘብ እንጂ ማንም
ሰው አይደለም፡፡ በዓለም ያለው ውጥንቅጥና መከራ፣
ስቃይና ጭንቅ በአብዛኛው እንደዚህ ካሉ ሰዎች ስውር እጆች
የሚመነጭ ነው፡፡ ይህን ለመረዳት ብዙ የዓለም ታሪኮችንና
ዛሬም እየተደረጉ ያሉ ድርጊቶችን፣ በተለይ ደግሞ
ከድርጊቶቹ ጀርባ ያሉትን መሠረታዊ እጆች ማወቅ የግድ
ይላል፡፡ የሚያሳዝነው ግን ብዙው ሰው እንዲሁ የሚፈጸሙ
ክስተቶችን (ድርጊቶችን) ብቻ እንጂ ከጀርባ ሆነው እነዚያን
ነገሮች የሚጠነስሷቸውንና እንዲሆኑ የሚያመቻቿቸውን
ሰዎችና ቡድኖች አያስባቸውም ወይም አያውቃቸውም፤
እንደዚያ አድርጎ እንዲያስብም አይፈለግም፡፡

85
 ኦርቶዶክሳዊነት አክባሪነት ነው፡፡
 እግዚአብሔር አክባሪ ነውና፤
 ታቦትን ከግራር እንጨት፣ ነቢያትን ከተራ ሰውነት፣
ዳዊትን ከእረኝነት፣ ሐዋርያትን ከዓሣ አጥማጅነት፣
ከቀራጭነት፣ ወዘተ
 አቃላይነት ኦርቶዶክሳዊነት አይደለም፡፡
የምንቃወመውና የማንቀበለው ነገር ሲሆን እንኳ
አክብሮታዊነት ሊርቀን አይገባም፡፡

86
ስብሐት ለእግዚአብሔር

87

You might also like