Professional Documents
Culture Documents
ስደት እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ Ppt
ስደት እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ Ppt
ወንጀልን ለመከላከል
ለሀይማኖት አባቶች፤ ለሀገር ሽማግሌዎችና ለሚመለከታቸው
አካላት ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ሰነድ
በዞናችን በሁሉም አካባቢዎች በሰዎች መነገድ፣ በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልና
መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት የሚስተዋል ቢሆንም በተለይ ወደ ዉጪ በሚደረገዉ ፍልሰት
ከፍተኛ ዝውውር ያለባቸው ወልቂጤ፤ አበሽጌ፤ እኖር፤ቸሀ፤ጌታ፤እንደጋኝ፤ ገ/ጉ/ወለኔ፤
እ/ኤ/መገር፤ ጉንችሬ ሲሆኑ ይብዛ ይነስ እንጂ ፤በሌሎችም የዞናችን ወረዳዎችና ከተማዎች
ዝውውሩ እንዳለ በተለያየ ጊዜ በምንቀበላቸው መረጃዎች ማረጋገጥ ችለናል፡፡
ከክልሉ በተለይ ዞናችን በተመሳሳይ በአገር ዉስጥም በተለይ ህጻናት እና ወጣት ሴቶች
ትምህርታቸዉን እያቋረጡ ከገጠር ወደ ከተሞች፣ ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ወደ ሌሎች
የክልሎች ከተማ በመፍለስ በተለያዩ መደበኛ ባልሆኑ የሥራ ዘርፎች ( በሎተሪ አዟሪነት፣
በእርሻ፣ በማዕድን ቁፋሮ፣ በልመና፣ በጀብሎ፣ በቆሻሻ ማጓጓዝ፣ በሱቅ በደረቴ፣ በሊስትሮ፣
በሆቴሎች እና በመንገድ ላይ ሴተኛ አዳሪነት) ተሰማርተው ለጉልበት ብዝበዛና ለተለያዩ
ጉዳቶች ሰለባ ሆነዋል፡፡
…… የቀጠለ (ገጽታና መንስኤዎቹ)
• የተሻለ ኑሮ እና ህይወት ይገኛል በሚል ቀቢጸ ተስፋና ሰበብ ለሰዎች
መነገድ ወንጀል ተጋላጭም እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
• ይህ ተግባር ለጥቂቶች የብልጽግና ምንጭ፣ ለብዙሀኑ ህዝባችን መርዶና
ሃዘን እንዲሁም ለዞናችን የማንነት ገጽታ ችግር ወደ መሆን ደረጃ
ደርሷል፡፡
• የዞናችን ተወላጆች በኢ-መደበኛ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት
የሚሰደዱባቸው መስመሮችና መነሻ አካባቢዎች ተለይተው
ይታወቃሉ፡፡ እነዚህም፡-
• በደቡባዊ መስመር፡-በዚህ መስመር እንደዞናችን በጣም ውስን የሆኑ
ከሃድያ ድበር አካባቢ ያሉና በተለያየ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው በሌላ ዞን
የሚኖሩ በቁጥር የሚፈልሱ ካልሆነ በስተቀረ በትክክል ከዞናችን
ተነስተው የሚሄዱ መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡
…… የቀጠለ (ገጽታና መንስኤዎቹ)
• በምስራቃዊና ሰሜን ምዕራብ መስመር፡- ከዞናችን በአብዛኛው
ወልቂጤ እና አበሽጌ ወረዳዎች (በተለይም ሴቶች) መነሻ አድርገው
ወደ አረብ ሀገራት፣ ሱዳን፤ ሊቢያና አውሮፓ መዳረሻ
የሚያደርጉበት መስመር ነው፡፡
• አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፡- በዚህ መስመር
እንደ ዞናችን በአብዛኛው ደቡብ አፍሪካና አረብ ሀገራትን መዳረሻ
የሚያደርጉ የኢ-መደበኛ ፍልሰተኞች የሚሄዱበት መስመር ሲሆን
በዚህ መስመር ሰለባ የሆኑ መዋቅሮች በወረዳዎች ተለይተው
ሲታዩ የሚከተለውን ገጽታ እናገኛልን፡፡
የቀጠለ
• አበሽጌ፣ ቸሃ፣ ወልቂጤ ከተማ፤ገ/ጉ/ወለኔ፤እኖር፤ ጉመር፤ጌታ፤
እንደጋኝ እና እዣ ወረዳዎች ሲሆኑ በተወሰነ መልኩ ሌሎችም
ወረዳዎች ላይ መኖሩ መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡
• በዞናችን የስደቱ ገጽታና እያስከተለ ያለው ጉዳት ለመረዳት ያስችለን
ዘንድ ከወንጀሉ ውስብስብነት አንጻር የተሟላ ዞናዊ መረጃ ማቅረብ
አዳጋች ቢሆንም በተለያዩ ጊዜያት ከክልሉ፤መንግስታዊና መንግስታዊ
ካልሆኑ ተቋማት እና በራሳቸው መንገድ የመጡትን የተሰበሰቡ የህገ-
ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጋላጮች የተገኘው መረጃ እንደሚከተለው
ለመዳሰስ ተሞክራል፡፡
የቀጠለ
ለዚህም አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ሌሎች አጎራባች ክልሎች በደላላ ግፊት፣ በግንዛቤ
ችግርና በመሳሰሉት ምክንያቶች የሚፈልሱ የህጻናት ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መሆኑን
በየከተሞቹ በጎዳና ተዳዳሪነትና በሴተኛ አዳሪነት ህይወት እየገፉ ያሉትን ህፃናትን ብቻ
ማየት ለጉዳዩ በቂ አስረጂ ነው፡፡
የኢ-መደበኛ ፍልሰት መንስዔዎች
ሰብአዊ ቀውስ
ሞት (በባህር ላይ፣ በየበረሀው)፣
ከፍተኛ የአካል እና የሰውነት ክፍል ጉዳት፣
ስነ-ልቦናዊ ቀውስ
ማህበራዊ ቀውስ
የልማት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ይፈታተናል፤
ተዘዋውሮ በመሥራት ላይ የተዛባ አስተሳሰብ እንዲያዝ የሚያደርግ ወንጀል መሆኑ፣
የቀጠለ
እንደ አገር ያለንን የሰው ኃይል ተጠቅመን የፀረ-ድህነት ትግላችንን በማጠናከር ልማታችንን
እንዳናረጋግጥ የሚፈታተን መሆኑ፣
የትምህርትና ሥልጠናን እሴት በማሳነስ የማስፈፀም አቅማችንን በሂደት የሚያዳክምና የልማትና
የመልካም አስተዳደር ሥራችንን የሚያደናቅፍ መሆኑ፣
ፖለቲካዊ ቀውስ
በሄዱባቸው አገራት በሕገወጥ ተግባራት (በአሸባሪነት፣ በአደንዛዥ ዕፅና የጦር መሣሪያ
አዘዋዋሪነት፣ በሴተኛ አዳሪነት…ወ.ዘ.ተ) በመሳተፍ
የአገር ገጽታን የሚያጠፉ
በህገዊ መንገድ ለሚሄዱ ዜጎች እንቅፋት መሆን
በአገር ውስጥ ከሕጋዊነት ይልቅ ሕገ-ወጥነትን ማስፋፋት፤ የሕግ የበላይነትን መናድ፣ የዴሞክራሲ
ሥርዓት ግንባታን ለመሸርሸር አመቺ ሁኔታ መፍጠር፣
ዜጎች በአገሪቱ ውስጥ ባሉት ሕጋዊ ተቋማት ላይ እምነት እንዲያጡ በማድረግ ሥርዓት
አልበኝነትን ማስፈን፣
ከውጭ አገር ተቋማት ጋር በመሻረክ ዜጎች በሌሎች አገሮች ላይ እምነት እንዲጥሉ ማድረግ፣
በአጠቃላይ ዜጎች ብሔራዊ ስሜት እንዲያጡ የሚያደርግ መሆኑ
የቀጠለ
ኢኮኖሚያዊ ቀውስ
ከህጋዊ ኤጀንሲዎች መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ግብርና ታክስ በመደበቅ
የግል ጥቅም ላይ ማዋልና የልማት ሥራዎችን መጉዳት፣
አምራች የሆነው ወጣት ክፍል (Youth Labour Force) መፍለሱ
በኢኮኖሚ ዕድገታችን ያለዉ አሉታዊ ተጽእኖ፣
ፍልሰተኞችና ቤተሰቦቻቸው ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሣራና ውድቀት
እያደረሰ መሆኑ፣
ከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛ (ለረጅም ሰዓታት መሥራት)
እንደ አገር ዋና ዋና የፍልሰት መውጫ በሮች (Major migration routes)
ለ. ሞያሌ መውጫ በር
ሐ. መተማ መውጫ በር
መ. ጅጅጋ መውጫ በር
ሠ. ሚሌ/ጋላፊ መውጫ በር
ረ. ኩምሩክ መውጫ በር
ዜጎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ ወደ ዉጭ ሲፈልሱ የሚያወጡት ወጪ
• 1. በሰዎች መነገድና ህገ-ወጥ ድንበር ማሻገር ወንጀል ወይም በሌላ ስያሜው ህገ-ወጥ
የሰዎች ዝውውር መከላከል ተግባር ስንመለከት በአሁኑ ወቅት እጅግ በተራቀቀና
በተደራጀ መልክ የሚከናወን ዓለም አቀፋዊ ወንጀል በመሆኑ የችግሩ ውስብስብነትና
አሳሳቢነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ዜጐች ከሀገር ሀገር በመዘዋወር
መስራት ህጋዊ መብት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች በተለይም በህገ-ወጥና በአቋራጭ
መንገድ ለመክበር በሚሯሯጡ ስግብግብ ደላሎች በመታለል በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር
ለመውጣት በሚደረግ እንቅስቃሴ በርካታ ዜጐች ለከፋ ችግር እንግልትና ሞት
ተዳርገዋል፤ሴት እህቶቻችን ተደፍረዋል፣ ጉልበታቸው ተበዝብዘዋል ፣ የጤነኛ
ወጣቶችን ብልታቸው ወጥቶ ተሸጠዋል፣ወላጅ እናት አባት ለዘመናት ደክመው ያፈሩት
ቋሚ ሀብት ንብረታቸው ተዘርፈዋል፣ ሰብዓዊ መብታቸውና ክብራቸው
ተጥሰዋል፤በበረሀ በረሃብና በጥም ወድቀዋል፤በርካታ ዜጎቻችን በዚህ ህገ-ወጥ ስደት
ይኑሩ ወይም ይሙቱ ጭምር የደረሱበት አይታወቅም፡፡
የቀጠለ
• ችግሩ በዚህ አያበቃም ገንዘብ ይልክልኛል በሚል ባልተጨበጠ ተስፋ ያለውን
ጥሪት ሀብትና ንብረት አወድመው የላኩ ቤተሰቦች ያልጠበቁት ነገር ይከሰትና
አጠቃላይ ቤተሰብ ለክፍተኛ ማህበራዊ ተጋላጭነት ለቤተሰብ መፍረስና
መበታተን ምክነያት እየሆነ ይገኛል፡፡ ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ወደ መዳረሻ
ሀገር የገቡትም ቢሆን ህጋዊው መስመር ተከትለው ባለመውጣታቸው ወደ
ውጭ ሳይወጡ ከአንድ ቤት በላይ በዘመድ አዝማድ ጉልበታቸው
እየተበዘበዙና ከአቅም በላይ የሆነ ስራ እየሰሩ የፈለጉትን ሳያሳኩ የሄዱበትን
የደላላውን ብር እየከፈሉ ለከፍተኛ የአእምሮ ጭንቀትና ህመም የሚጋለጡም
ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ከአቅም በላይ ስራ ሰርተው ከቆይታ በኋላ ደምና
ስጋቸው አልቆ፤ብዙዎቹ መውለድ የማይችሉ ሆነው ስለሚመለሱ ትዳር
አጥተው ያለ ዘር አና የአእምሮ ዘገምተኛ ሆነው ህይወታቸው ከንቱ ሆኖ
ይቀራል፡፡ ታድያ ለዚህ ሁሉ ችግር በቀጥታ ሰለባ የሚሆኑት ወጣቶች
በመሆናቸው ህገ-ወጥ ድርጊቱን ለመከላከል ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም
ከችግሩ አሳሳቢነትና ስፋት አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ፡፡
የቀጠለ
• እስካሁን ድረስ በዞኑ ፣በክልሉና ከአለም አቀፍ ፍልሰት ድርጅት
(IOM) ጋር በመቀናጀት በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች 108
ቀበሌያት ላይ ስልጠና በመስጠት የማ/ሰብ ውይይት
በማቋቋም ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ከኮቪድ መምጣት ጋር
ተያይዞ በአሁን ወቅት የተቀዛቀዘ ቢሆንም በቀበሌ የማ/ሰብ
ውይይት በማድረግ ስደት የሚጸየፍ ማህበረሰብ በመፍጠር
ከክልሉ አንደኛ በመውጣት በፌደራል ደረጃ ምርጥ ተሞክሮ
የተቀመረበት እንደነበርም አይተናል፡፡
የቀጠለ
• ሌላው ችግሩ በከፋባቸው አካባቢዎች ከተማሪዎች መጠነ-
ማቋረጥ ጋር በቀጥታ ስለሚያያዝ ስደት በሚበዛባቸው
አካባቢዎች ባሉ በ30-ት/ቤቶች አመቻቾች በማሰልጠን የአቻ
ለአቻ ክበብ በማቋቋም የውይይት ፕሮግራሞችን በማስጀመር
በሰለጠኑ አመቻቾች አማካይነት ከት/ቤቱ ተማሪዎች በማቀፍ
በክበቡ፣ በወመህ፣ በት/ቤቱ ሚኒሚዲያ በበዓላትና በሰልፍ
ፕሮግራሞች ሰፋፊ የግንዛቤ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፤ በዚህም
ድጋፍና ክትትል ተደርጎ ግብረ-መልስ ሲወርድ የነበረና እምርታዊ
ለውጥ የታየበት እንደነበር የሚታወቅ ቢሆንም አሁን ባለው
ሁኔታ ከኮቪድ መከሰት በኋላ ባብዛኛው ት/ት ቤት ውይይቱ
ተቃርጦና በከፍተኛ ሁኔታ ተቀዛቅዞ ይገኛል፡፡
በሰዎች መነገድን፣ በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎችንና ኢ-መደበኛ ፍልሰትን
ለመከላከል የተደረጉ ጥረቶችና ተግዳሮቶች
በዞናችን እስከ 2015 ግማሽ የበጀት ዓመት ድረስ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ
ኢ-መደበኛ የሰዎች ፍልሰት ተጋላጭ መዋቅሮች ውስጥ በአለም አቀፍ ፍልሰት ድርጅት
(IOM)፤በክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና በዞን ሠ/ማ/ጉ/መምሪያ በጥቅሉ
108 ተጋላጭ ቀበሌያት በማህበረሰብ ዉይይት ፕሮግራም እንዲታቀፉ ተደርጓል፡፡
በ30 ትምህርት ቤቶች የአቻ ለአቻ ዉይይት ክበባት ተቋቁመዉ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ
ተደርጓል፡፡