Professional Documents
Culture Documents
4 5926872628722664811 PDF
4 5926872628722664811 PDF
1
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
(1969-1970)
ሚያዚያ 2006
አዲስ አበባ
2
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ለመግቢያ ያህል
ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከሀምሌ 1969 እስከ መጋቢት 1970 ባለው ጊዜ በዘመናዊው የአፍሪቃ
ታሪክ ከታዩት ታላላቅ ጦርነቶች መካከል አንዱን አካሂደዋል፡፡ የጦርነቱ መከሰት የኢትዮጵያንም
ሆነ የአፍሪቃ ቀንድን ጂኦ-ፖለቲካ ከስረ መሰረቱ ቀይሮታል፡፡ ይሁንና በሁለቱም ወገን ከፍተኛ
መስዋዕትነት የተከፈለበት የዚያ ታላቅ ጦርነት ታሪክ በአግባቡ አልተመዘገበም፡፡ ጊዜ በሄደ
ቁጥር በጦርነቱ ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው የጦር መሪዎችና ተዋጊዎች ከምድራዊው
ህይወት በመሰናበታቸው የጦርነቱ ውሎ በመረሳት ላይ ይገኛል፡፡ በቅርብ ዓመታት የታሪክ
ማስታወሻዎቻቸውን የጻፉ የጦር ጄኔራሎችና የፖለቲካ መሪዎችም ደግሞ ለኢትዮ-ሶማሊያ
ጦርነት ተገቢውን ሽፋን አልሰጡትም፡፡
ይህ ድርሳን የጦርነቱን ታሪክ ሙሉ በሙሉ ይተርካል የሚል እምነት ፈጽሞ የለኝም፡፡ ነገር
ግን ስለያኔው ታሪክ ለማወቅ ለሚፈልጉ አንባቢያን የዐይን መግለጫ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡
ስለጦርነቱ መጻፍ ለሚፈልጉትም እንደ አቅጣጫ ጠቋሚ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡
*****
በዚህ ድርሳን ውስጥ የምታነቧቸው ጽሑፎቹ የቀረቡት በፌስቡክ ላይ በተነበቡበት አኳኋን
ነው፡፡ በጽሑፎቹ ውስጥ የመረጃ መፋለስ እንዳይኖርም ጥረት አድርጌአለሁ፡፡ ታሪኩን ስጽፍ
እስከመጨረሻው ድረስ የገለልተኝነት መርህን ለመጠበቅ ብሞክርም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ
ለሀገሬ (ለኢትዮጵያ) ማድላቴን አልደብቃችሁም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በሚመለከት ግን
ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ ሆኜ ነው የጻፍኩት (የደርግ፤ የኢህአፓ፣ የምዕራብ ሶማሌ፣ የህወሐትም
ሆነ የኦነግ ደጋፊ አይደለሁም)፡፡
*****
ይህ ድርሳን የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ለሆኑ ወገኖቻችን ነው የተዘጋጀው፡፡
ሁኔታዎች የሚያመቹ ከሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያነበውን አንድ መጽሐፍ በኢትዮ-ሶማሊያ
ጦርነት ዙሪያ ለማዘጋጀት እሞክራለሁ፡፡ እስከዚያው ግን ወዳጆቻችን በዚህች አነስተኛ
ሙከራችን እንዲያዘግሙ በአክብሮት እንጠይቃቸዋለን፡፡ በድርሳኑ ላይ ሃሳብና ትችት ለመሰንዘር
የሚፈልግ ካለ ደግሞ ከታች ባሉት የኢ-ሜይል እና የፌስቡክ አድራሻዎች መጠቀም ይችላል፡፡
መልካም ንባብ!!
አፈንዲ ሙተቂ
ሚያዚያ 15/2006
አዲስ አበባ
ኢ-ሜይል፡- afandimutaqi2012@gmail.com
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/afendi.muteki.7
4
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል አንድ
===የልጅነት ትዝታ===
እነኝህ መዝሙሮች ከነፍስ ካወቅኩ በኋላም ይዘመሩ ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ቆይታዬ የሙዚቃ
ክፍለ ጊዜአችንን ከሚያደምቁልን ዋነኛ ሙዝሙሮቻችን መካከልም ነበሩ፡፡
*****
የሀብሮ አውራጃ የኢሰፓ ኮሚቴ ጽ/ቤት የሚገኘው የገለምሶ ከተማን ከሰሜናዊ አቅጣጫ
ከሚያዋስነው የካምቦ ተራራ ጥግ ነው፡፡ ከዚህ ጽ/ቤት አጠገብ “ቱታ በሪሳ” የሚባል አነስተኛ
ኳስ ሜዳ አለ፡፡ በልጅነታችን ለኳስ ጨዋታ ከምንሄድባቸው ስፍራዎች አንዱ ይህ “ቱታ በሪሳ”
ነው፡፡ ታዲያ “ቱታ በሪሳ” ስንሄድ ሁል ጊዜ ኳስ አንጫወትም፡፡ አንዳንድ ቀን የኳስ ጨዋታውን
የሚያስጥለን ሌላ አስገራሚ መጫወቻ ነበረን!! ነገሩ እንዲህ ነው፡፡
5
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ከሀብሮ አውራጃ የኢሰፓ ጽ/ቤት አጠገብ ከቆርቆሮ የተሰራ አንድ አውሮፕላን ነበረ፡፡ ይህ
አውሮፕላን በመጠኑ ከአንድ መለስተኛ አውቶቡስ ጋር ይስተካከላል፡፡ ነገር ግን ጎማም ሆነ
ክንፍ የለውም፡፡ ምንም ነገር ሳይደግፈው ከመሬት ላይ “ዧ” ብሎ ተዘርግቷል፡፡ እኛም “ዛሬ
በሰማይ ላይ ስበርር ነው የዋልኩት” ማለቱ ስለሚያስደስተን የኢሰፓ ዘበኞች በማይደርሱበት
በኩል እየሾለክን ወደ አጸደ ግቢው እንገባና ተአምር እንሰራለን፡፡ ይህም ከአውሮፕላኑ ሆድ
ገብቶ መጨፈር ነው፡፡
“ከኢሰፓ ጽ/ቤት አጠገብ ያለው አውሮፕላን የእውነት ጢያራ ሳይሆን ሞዴል አውሮፕላን
ነው፤ በ1970 በካራ ማራ የተገኘውን ድል ለመዘከር ከተዘጋጀው የጅጅጋ ፌስቲቫል በጨረታ
የተገዛ ነው፤ የሀብሮ አውራጃ ከአስራ ሶስቱ የሀረርጌ አውራጃዎች የበለጠ ዋጋ ስላቀረበ ነው
ጨረታውን ያሸነፈው”
ሄደ በረሃ ሚሊሻው
ፊቱ ደም መስሏል ተቆጥቷል
ሶማሊያ ዛሬ ፈርዶባታል፡፡
የሶማሊያ ጦር እርቦት
ዳቦ ነው ብላ ስትሻማ
6
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ተቀጣጠለች እንደ ሻማ፡፡
*****
በምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ “ካራ ማራ” የሚል ስያሜ ያላቸው ሆቴሎችና ሻይ ቤቶች
በብዛት ይገኛሉ፡፡ በኔዋ ገለምሶም “ካራ ማራ” ሆቴል አለ፡፡ ሆኖም “ካራ ማራ” አኩሪ ጀግንነት
የተፈጸመበት የድል ሜዳ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስረዱን ጋሽ ደመቀ ነበሩ፡፡
===ቅድመ-ታሪክ===
የእንግሊዝ ሶማሊላንድ የምትባለው ግዛት በ1952 ነጻነቷን ተቀዳጀች፡፡ ከአራት ቀናት በኋላ
ደግሞ የ“ኢጣሊያ ሶማሊያ” የምትባለው ምድር ነጻ ሆነች፡፡ በወቅቱ “የተበታተኑትን የሶማሊ
ግዛቶች አንድ ላይ ሰብስቦ ታላቋ ሶማሊያን መፍጠር” የሚል እሳቤ ይንቀለቀል ሰለነበር የሁለቱ
ግዛቶች ፖለቲከኞችም የጉዞ መስመራቸውን በዚህ ፈር ለመቀየስ ወሰኑ፡፡ በመሆኑም ሁለቱ
የሶማሊ ግዛቶች ከስድስት ወር በኋላ በመቀላቀል “የሶማሊ ሪፐብሊክ”ን መሰረቱ፡፡
እነዚያ የሶማሊያ መሪዎች በያዙት መሬት ሳይብቃቁ “እያንዳንዱ የሶማሊ መሬት በአዲሲቷ
ሶማሊያ ስር መግባት አለበት” የሚል አቋም እንደ መርህ ያዙ፡፡ በመሆኑም “ኢትዮጵያ፣ ኬንያ
እና ጅቡቲ የያዙትን መሬቶቻችንን እንፈልጋለን” የሚል ሰበካ ጀመሩ፡፡ በዚያ ወቅት ጅቡቲና
ኬኒያ ነጻነታቸውን አልተጎናጸፉም፡፡ ስለዚህ ሶማሊዎቹ ከቅኝ ገዥዎቹ ፈረንሳይና እንግሊዝ ጋር
መጋጠም እንደማያዋጣቸው ስላወቁ ትኩረታቸውን በኢትዮጵያ ላይ አደረጉ፡፡ ከአንድ ዓመት
በኋላም አነስተኛ የሰርጎ ገብ ሃይል በማደራጀት በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለውን ቆላማውን
የኦጋዴንን ክልል ለመውረር ሞከሩ፡፡ ነገር ግን በጄኔራል አማን ሚካኤል አንዶም የሚመራው
ሶስተኛ ክፍለ ጦር በአስር ቀናት ውስጥ ሶማሊዎቹን አባረራቸው፡፡
7
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
በይፋ በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት አወጀች፡፡ ይሁንና ጦርነቱ ረጅም ጊዜ ሳይቆይ በኢትዮጵያ
አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
ጄኔራል ሙሐመድ ዚያድ ባሬ ጥቅምት 1962 በመንፈቅለ መንግሥት ስልጣን ሲይዙ ደግሞ
ሁሉም ነገር ከመሰረቱ ተቀየረ፡፡ “ሶማሊያ ከኢትዮጵያ የምትፈልገው ኦጋዴንን ብቻ አይደለም”
ተባለ፡፡ “በኢትዮጵያ የተወሰደብን መሬት የሀረርጌ፣ ባሌ እና ሲዳሞ ክፍለ ሀገራትን
የሚያጠቃልል ነው” የሚል አዋጅ ታወጀ፡፡ ይህ ሰፊ ግዛት በጥቅሉ “ሶማሊ ገልቤድ” (ምዕራብ
ሶማሊያ) ተብሎ ተሰየመ፡፡ “በውስጡ የሚኖሩት ሶማሊ ያልሆኑ ህዝቦችም ከጊዜ ብዛት
ቋንቋቸው ቢቀየርም ጥንተ ማንነታቸው ሶማሊ ነው” ተብሎ ተነገረ፡፡ በሶማሊያ የሚገኙ
ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ስደተኞችም አዲሱን መርህ እንዲያቀነቅኑ ተገደዱ፡፡ “እምቢ” ያሉት ደግሞ
ወደ እስር ቤት ተወረወሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በባሌና በሲዳሞ ክፍለ ሀገራት የሚደረገውን
ውጊያ የሚያስተባብር “የሶማሊ አቦ ነጻነት ግንባር” (ሶ.አ.ነ.ግ) የተባለ ድርጅት ተመሰረተ፡፡
በጥቅሉ የሶማሊያ መንግሥት “ከአዋሽ ወንዝ በታች ያለው መሬት በሙሉ የኔ ነው” የሚል
አቋም ማራመድ ጀመረ፡፡
*****
ሚያዚያ 4/2006 ተጻፈ፡፡
8
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል ሁለት
====የይፋ ወረራ===
የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል የሶማሊያ ባለጋራውን በዐይነ ቁራኛ ሲጠብቅ የነበረው በኦጋዴን
መስመር ነበር፡፡ በመሆኑም ከበለድወይን የተነሳው የሶማሊያ ሰራዊት የኦጋዴን አውራጃዎችን
በቀላሉ ለመቆጣጠር አልቻለም፡፡ የኢትዮጵያ ተዋጊዎች ኦጋዴንን ላለማስነጠቅ እስከ
10
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
መጨረሻው ተሟሙተዋል፡፡ በተለይም በሐምሌ አጋማሽ (1969) ማብቂያ ላይ የቀብሪደሃር
ከተማን ላለማስለቀቅ በተደረገው ትግል በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ተሰውተዋል፡፡
*****
ሚያዚያ 5/2006 ተጻፈ፡፡
11
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል ሶስት
13
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
14
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የለባቸውም የሚለውን የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔን ተከትሎ” ነው ትላለች፡፡
*****
ሚያዚያ 6/2006
15
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል አራት
ሚያዚያ ወር/ 1969፡፡ በዚህ ወር የኢትዮጵያ መሪዎች አንድ ያልታሰበ ፖለቲካዊ እርምጃ
ወሰዱ፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊና ሲቪል ተቋማት እንዲዘጉ
ማድረጋቸው ነው፡፡ በዚህ መሰረት በአስመራ የሚገኘው የቃኘው ወታደራዊ መረጃ ጣቢያ
(ቃኘው ሰቴሽን)፣ በምጽዋ የነበረው የአሜሪካ የባህር ሀይል መደብ (በተለምዶ “ናምሩ”
የሚባለው)፣ በአዲስ አበባ የነበረው የአሜሪካ ወታደራዊ አማካሪ ቡድን (ማግ-MAG)፣
የአሜሪካ የማስታወቂያ አገልግሎት (USIS) ተዘጉ፡፡ በማስከተልም በአሜሪካ የሰብዓዊ እርዳታ
አገልግሎት ድርጅቶች ላይ ገደብ ተጣለ፡፡
17
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ሀይል ከፍተኛ የውጊያ ስልጠና ያስፈልገው ነበር፡፡
የኢትዮጵያ መሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ካጤኑ በኋላ ሁለት ውሳኔዎችን ወሰኑ፡፡
አንደኛው መደበኛ ሰራዊቱን ለማጠናከር የሚረዳ ተጨማሪ ሀይል በብዛት ተመልምሎ በስልጠና
ላይ እንዲቆይ የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው በታጠቅ ካምፕ ሲሰለጥን የነበረው የሚሊሻ ሰራዊት
በቶሎ ወደ ግንባር ተልኮ ወረራውን በመከላከል ላይ የነበረውን ሰራዊት እንዲያግዝ የሚል ነው፡
፡ በተጨማሪም ሚሊሻውን የማሰልጠኑ ተግባር በየክፍለ ሀገሩ እንዲጀመር ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ መሪዎች የወሰዱት እርምጃ ከወታደራዊ ስልት አንጻር ሲታይ በጣም ትክክል ነው
ተብሎ ተወድሷል፡፡ ከላይ እንደተገለጸው የኢትዮጵያ መደበኛ ሰራዊት በብዙ እጥፍ
የሚበልጠውን የሶማሊያ ሰራዊት ከሀገሩ ለማባረር የተጠናከረ ስልጠና ይፈልጋል፡፡ የውጊያ
ስልጠናውን ካጠናቀቀ በኋላም ከሶቪየት ሰራሽ መሳሪያዎች ጋር እስኪተዋወቅ ድረስ በቂ
ልምምድ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ለዚህ ደግሞ በቂ ጊዜ ይሰጠው ዘንድ የግድ ይላል፡፡ በተለይ
የከባድ መሳሪያ ተኳሾችንና የአውሮፕላን አብራሪዎችን በአጭር ጊዜ ለውጤት ማብቃት
አይቻልም፡፡ ስለዚህ እነርሱ እስኪሰለጥኑ ድረስ የነርሱን ቦታ ሸፍኖ የሚዋጋ ሀይል መኖር
ነበረበት፡፡ ይህንን ለማድረግ የተሻለው አማራጭም የሚሊሻ ሰራዊቱን በፍጥነት አሰልጥኖ ወደ
ግንባር ማሰማራት ነው፡፡
በክፍል ሁለት እንደተገለጸው ሶማሊያ አደገኛ ወረራ ያደረገችው በሀርጌሳ ግንባር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሰራዊትም በዚህ ግንባር ተጠቃልሎ በመግባት ከፍተኛ የመከላከል ውጊያ ሲያደርግ
ነበር፡፡ በወቅቱ ለኢትዮጵያ መሪዎች ያስቸገረው የሶማሊያ ጦር የስምሪት አቅጣጫዎችንና
የመጨረሻ ዒላማዎችን ማወቁ ነው፡፡ ቀደም ሲል በነበረው ግምት የሶማሊያ ሰራዊት ጅጅጋን
ከያዘ በኋላ በማስከተል ወደ ሀረር ይመጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡ ነገር ግን የሶማሊያ ሰራዊት
በነሀሴ አጋማሽ ላይ ጅጅጋንም ሆነ ሀረርን ሳይነካ ከጭናክሰን ከተማ ጀርባ ወደ ሰሜን ምዕራብ
መጓዝ ጀመረ፡፡
የኢትዮ የኢትዮጵያ የጦር መሪዎች የሶማሊያ ሰራዊት በጉርሱም አውራጃ ውስጥ በማሳበር
ወደ ሀረር ከተማ የሚያመራ ነበር የመሰላቸው፡፡ በመሆኑም በሀረር ዙሪያ የነበረውን ጥበቃ
አጠናከሩ፡፡ የሶማሊ ሀይሎች በቀጥታ ወደ ድሬ ዳዋ እየገሰገሱ መሆናቸው ታወቀ፡፡ በዚህም ጊዜ
በኢትዮጵያ መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጠረ፡፡ “ለድሬ ዳዋ የሚረባ መከላከያ
አልተደረገም” በሚል መወቃቀስ ተጀመረ፡፡
የኢትዮጵያ ሰራዊት የመከላከያ ጣቢያውን “ጀልዴሳ” በተባለ ስፍራ ላይ መሰረተ (ይህ ስፍራ
ከድሬ ዳዋ በደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ በ50 ኪሎ ሜትር ላይ ነው የሚገኘው)፡፡ ነሀሴ 5 ቀን
1969 ወደ ድሬ ዳዋ የሚያመራው የሶማሊያ ሰራዊት “ጀልዴሳ” ሲደርስ ያልጠበቀው ውጊያ
ገጠመው፡፡ ሶስት ቀናት ሙሉ ቢዋጋም ጀልዴሳን ማለፍ አቃተው፡፡ በመሆኑም ተጨማሪ ጦር
አስመጥቶ እንደገና ሌላ ጥቃት ከፈተ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ሀይሎችን አንበርክኮ ለማለፍ
ሳይችል ቀረ፡፡ የሶማሊያ ሰራዊት በዚህ ተስፋ ሳይቆርጥ ለሶስተኛ ጊዜ ሀይለኛ የሜካናይዝ ውጊያ
ከፈተ፡፡
*****
በመከረም 1970 የሶማሊያ ጦር ጅጅጋን ለመያዝ ውጊያ ከፈተ፡፡ በከተማዋ የቀረው
የኢትዮጵያ ሀይል ባለው አቅም ሁሉ ከተማዋን ላለማስነጠቅ ተከላከለ፡፡ ይሁንና የሶማሊያ ጦር
በሰው ሀይልም ሆነ በመሳሪያ ብዛት ስለሚበልጥ በያዘው መሳሪያ ስለሚበልጥ ሁለት ብርጌድ
ብቻ ይዞ በሚዋጋው የኢትዮጵያ ጦር የሚመለስ አልሆነም፡፡ በተጨማሪም የሶማሊያ አየር
ሀይል በውጊያው ላይ በከፍተኛ ደረጃ ተሳትፎ ነበር፡፡ ስለዚህ ጳጉሜ 5/1969 የኢትዮጵያ ጦር
በስልታዊ ማፈግፈግ ጅጅጋን እንዲለቅ ታዘዘ፡፡
19
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
በዚሁ መሰረት ጦሩ ከከተማዋ ወጥቶ በጅጅጋና በሀረር መሀል ካለችው አነስተኛዋ የቆሬ
ከተማ አቅራቢያ (ከጅጅጋ በስተምዕራብ በኩል በ40 ኪሎ ሜትር ላይ) የመከላከያ ጣቢያውን
መሰረተ፡፡ ከኦጋዴን ያፈገፈገው ጦርም በዚህ ግንባር ተሰልፎ የሶማሊያ ጦር ወደ ሀረር ከተማ
እንዳይገፋ ገትሮ እንዲይዝ ተደረገ፡፡
*****
ሚያዚያ 6/2006 ተጻፈ፡፡
20
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል አምስት
የሶማሊያ ሰራዊት ከምስራቅና የደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች መካከል ከፍተኛ ትኩረት ያደረገው
በሀረር ላይ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያት አለው፡፡ ሀረር ረጅምና ጥንታዊ ታሪክ ያላት ከተማ
በመሆኗ የሶማሊያ መሪዎች የኛ ከተማ ናት ይሏት ነበር፡፡ በተለይም ሀረርን ከኢማም አህመድ
ኢብራሂም አል-ጋዚ ታሪክ ጋር በማያያዝ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ይነዙላት ነበር፡፡ በሁለተኛ ደረጃ
ሀረር የዘመኑ ትልቁና ሐብታሙ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገር የነበረው የሀረርጌ ዋና ከተማ ነበረች፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ኢትዮጵያ ከነበሯት አራት ክፍለ ጦሮች መካከል በጣም ግዙፍ የሆነው የሶስተኛ
ክፍለ ጦሮች ዋና የማዘዣ ጣቢያ የሚገኝባት ከተማ ነበረች፡፡ በአራተኛ ደረጃ ሀረር ብቸኛው
የአትዮጵያ የጦር አካዳሚ የሚገኝባት ከተማ ነበረች፡፡ የሶማሊያ መሪዎች ይህንን ሁሉ
በማመዛዘን ነው ሀረርን የትልቋ የድል ብስራት ማወጃ ማዕከል በማድረግ ያተኮሩባት፡፡
21
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ከተማ ከተነሳ በኋላ ወደ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ እየገሰገሰ “ፊቅ” ከተማ ደረሰ፡፡ እነዚህ ሁለት
ሀይሎች አንድ ላይ በመጣመር በቀድሞው የሀረር ዙሪያ አውራጃ ውስጥ ካለው የፈዲስ ወረዳ
ከገቡ በኋላ ለሁለት ተከፈሉ፡፡ አንደኛው ሀይል የሰሜን ምስራቅ አቅጣጫን በመያዝ ሀረርን
በደቡብ ምስራቅ የሚያዋስነውን የሀኪም ጋራ እንዲቆጣጠር ግዳጅ ተሰጠው፡፡ ሁለተኛው ሀይል
ቀጥታ ወደ ሰሜን እየተጓዘ የሀረር ከተማ ምዕራባዊ ድንበር የሆነውን የአቦከር ተራራን እንዲይዝ
ታዘዘ፡፡
ባለፉት ክፍሎች እንደገለጽኩት የኢትዮጵያ አየር ሀይል በወቅቱ ጥቂት የጦር አውሮፕላኖች
ናቸው የነበሩት፡፡ ከሶቪየት የተገኙት አውሮፕላኖችም በዚያን ጊዜ ወደ ሀገር ቤት አልገቡም፡፡
ነገር ግን የአየር ሀይሉ አብራሪዎች በጣም የተዋጣላቸው በመሆናቸው ዒላማቸውን ሳይስቱ
ይመቱ ነበር፡፡ በድሬ ዳዋ (ጀልዴሳ) ግንባር በርካታ ታንኮችን ከጥቅም ውጪ እንዳደረጉት ሁሉ
በዚህም ግንባር የሶማሊያ መድፎችንና ሞርታሮችን በመደምሰስ ከዒላማቸው አሰናክለዋል፡፡
ታዋቂው የኢትዮጵያ አየር ሀይል አብራሪና የህብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሜዳይ ተሸላሚ
ብርጋዴር ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ብቃቱን ካሳየባቸው ግዳጆች አንዱ ያ ሀረርን ለመከላከል
የተደረገው ውጊያ ነው፡፡
22
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
በነገራችን ላይ የሶማሊያ ሰራዊት ሀረርን ለመያዝ በተደረገው ዘመቻ መድፍና የቢ ኤም
ሮኬቶችን እንጂ ታንክ መጠቀሙ አልተዘገበም፡፡ ይህም የአካባቢው ተራራማነት ለሜካናይዝድ
ውጊያ የማያመች በመሆኑ ይመስለኛል፡፡
ሶቪየት ህብረት የምድር ጦር ሀይሏ ምክትል አዛዥ የነበሩትን ሜጀር ጄኔራል (በኋላ ፊልድ
ማርሻል) ቫሰሊ ፔትሮቭን የዓለም አቀፉ ቡድን ሃላፊ አድርጋ መድባለች፡፡ የጄኔራሉ ሃላፊነት
የኢትዮጵያን ሰራዊት ማማከርና በኢትዮጵያ መሪዎችና ሞስኮ በሚገኘው የሶቪየት ህብረት የጦር
ሀይሎች ጠቅላይ መምሪያ መካከል እንደ አገናኝ ሆኖ ማገልገል ነው፡፡ ከጄኔራል ፔትሮቭ
በተጨማሪ ሶቪየት ህብረት
23
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
መረጃዎችን (ስታቲስቲክስ፣ ካርታ ወዘተ) ለኢትዮጵያ ሰጥታለች፡፡
ለጦር ቁስለኞች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታና የቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጡ ሀኪሞችን
መድባለች፡፡
ከዚህ ሌላ ሶቪየት ህብረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አጋር ሆና ቆይታለች፡፡
ሆኖም ሶቪየቶች ድጋፍ ሰጪ ከመሆን ባሻገር ተዋጊ የጦር ሀይል አልመደቡም፡፡
ለ./. ኩባ
በቆዳ ስፋቷ ትንሽ የሆነችው የኩባ ሶሻሊስት ሪፐብሊክ በጦርነቱ ሂደት በቀጥታ ከተሳተፉት
ሁለት ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በወቅቱ ኩባ ያስመጣችው የተዋጊ ብዛት ከ16, 000 እስከ 20, 000
ይገመታል፡፡ ከዚህ ሀይል መካከል ሁለቱ ሜካናይዝ ብርጌድ ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው
የኩባ ጦር የሚመራው የሀሪቱ ም/የመከላከያ ሚኒስትር በነበሩት በጄኔራል አርናልዶ ኦቾዋ
ሲሆን በዘመኑ በአንጎላ ተመድቦ የነበረውንም የኩባ የጦር ሀይል የሚያዙት እርሳቸው ናቸው፡፡
ኩባ ከወታደሮቿ በተጨማሪ የህክምና ሰራተኞችን ልካለች፡፡
ደቡብ የመን ለጦርነቱ የመደበችው 2000 መድፈኞችን ነው፡፡ እነዚያ መድፈኛ የመኒዎች
በቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆኑም አልሞ-ተኳሽ መሆናቸው በብዙዎች ዘንድ ተደንቆላቸዋል፡፡
ከዚህ በፊት እንደለገጽትም ደቡብ የመን ለኢትዮጵያ 30 ታንኮችን ሰጥታለች፡፡
*****
ሶስቱ ሀገራት ለረጅም ጊዜ የሶማሊያ አጋር ነበሩ፡፡ ሶማሊያ የመሬት ጥያቄዋን ባነሳችበት
ጊዜም ሀሳቧን እንድትቀይር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ከዚህም አልፎ ፕሬዚዳንት
ካስትሮ “ሶማሊያ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ የመን በኮንፌዴሬሽን ተያይዘው አንድ ታላቅ ህብረት
መመስረት አለባቸው” የሚል ሃሳብ እስከ ማቀንቀን ደርሰዋል፡፡ የሶማሊያ ወረራ ገፍቶ ሲመጣ
ግን ከኢትዮጵያ ጋር ተሰልፈዋል፡፡
ባለፈው ክፍል እንደገለጽኩት ሌሎች የሶሻሊስት ሀገራት በጦርነቱ ሂደት በቀጥታ ባይሳተፉም
ለኢትዮጵያ የመሳሪያ ድጋፍ አበርክተዋል፡፡ ሶማሊያ በግልጽ የሶሻሊዝምን ካባ ወርውራ ወደ
ምዕራቡ ዓለም መጓዝ የጀመረችው በዚያን ጊዜ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ብሎም ቢሆን
ከምዕራባዊያን ጋር ድብቅ ግንኙነቶችን ማድረግ እንደ ጀመረች አንዳንድ ምንጮች ያወሳሉ፡፡
ለምሳሌ ከአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ካለው አንድ ተቋም የተገኘ ጥናታዊ
ጽሑፍ አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ለሶማሊያ የጦር መሳሪያዎችን ለመሸጥ በድብቅ
24
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የተስማሙት ወረራው በተጀመረበት የሀምሌ ወር (1969) መሆኑን ይገልጻል፡፡ ከዐረብ ሊግ
ሀገራት መካከል ግብጽና ሳዑዲ ዐረቢያ በድብቅ ሶማሊያን ይረዷት ነበር፡፡ ሊቢያና አልጄሪያ
ግን የኢትዮጵያ ደጋፊ ነበሩ፡፡
*****
ሚያዚያ 8/2006 ተጻፈ፡፡
25
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል ስድስት
ዋናው ነጥብ ያለው እዚያ ላይ ነው! የኢትዮጵያ ህዝብ በጦርነቱ ሙሉ በሙሉ መንግሥትን
በመደገፉ ነው ኢትዮጵያ ድል ለማድረግ የቻለችው፡፡ በአምስት ወር ውስጥ 80,000 መደበኛ
ሰራዊትና እና 220,000 ሚሊሺያ ሰራዊት ለመመልመል የተቻለው ከግዳጅ ነጻ በሆነ ሂደት
ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወታደር ዲሲፕሊን ጠባቂና የተመደበበትን ግዳጅ ለመወጣት ቁርጠኛ
ሆኖ መገኘቱም ሌላ ነጥብ ነው፡፡ ህዝቡ በየቀበሌው የተመደበበትን ግዳጅ ሲወጣ የነበረ
መሆኑም ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡ ለምሳሌ የሰራዊቱ ቀለብ በአብዛኛው በህዝቡ ነበር
የሚዘጋጀው፡፡ ታዲያ ብዙዎች የሚደነቁበት አንድ ነጥብ አለ፡፡ ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገርንና
መንግሥትን ለያይቶ የሚያይበት ሚዛን ነው፡፡ የደርግ መንግሥት ከየካቲት 1969-እስከ ህዳር
26
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
1970 ድረስ በቀይ ሽብር ልጆቹን ሲጨርስበት ነበር፡፡ ጦርነቱ እየተካሄደ እንኳ ቀይ ሽብር ሙሉ
በሙሉ አላቆመም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቹ በደርግ ታጣቂዎች የጥይት እራት ቢሆኑበትም
በመንግሥቱ ላይ አላቄመም፡፡ በድንቁርናና በድህነት ሲማቅቅ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገርን
ከጊዜያዊ መንግሥት ነጥሎ ማየትን ያውቅበታል፡፡ ለዚህም የያኔው የኢትዮጵያ ህዝብ የሶማሊያ
ወረራን በልበሙሉነት ለመከላከል የቻለው፡፡ ህዝቡ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ ሶማሊያ እንደ ምኞቷ
በአዋሽ ብቻ ሳትገታ አዲስ አበባንም ጠቅልላ ትወስድ ነበር፡፡
መኢሶን እርምጃውን “የትግል ስልት ለውጥ ነው” ይለዋል፡፡ “ይህንንም ያደረግኩት ደርግ
ከኢህአፓ ቀጥሎ እኔን ሊያጠፋኝ በሚስጢር ሲያደባ በማየቴ ነው” ይላል፡፡ ደርግ ግን ኩነቱን
“ፍርጠጣ ነው” ይለዋል፡፡ የመኢሶንንም እርምጃ ከሶማሊያ ወረራ ጋር ያዛምደዋል፡፡ ሊቀመንበር
መንግሥቱ ኃይለማሪያም ከጋዜጠኛ ገነት አየለ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “መኢሶን የስልጣን
ጥመኛ ነው፤ ከኛ ጋር ቆይተው ስልጣን ለመቆናጠጥ አመቺ ጊዜ በመጠበቅ ላይ እያሉ ሶማሊያ
ወረረችን፤ በመሆኑም ሶማሊዎቹ በጥቂት ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ የሚገቡ ስለመሰላቸው ከዚህ
ከደከመ መንግሥት ጋር ምን እንሰራለን በማለት ፈርጥጠዋል” ብለዋል፡፡
27
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
በጣም አወዛጋቢው ኢህአፓ የወሰደው አቋም ነው፡፡ የደርግ መንግሥት ባለስልጣኖች
“ኢህአፓ እኛን በማውገዝ ከሶማሊያ ጋር በግልጽ ቆሟል” ይላሉ፡፡ ከዚህም አልፎ በቆሬ ግንባር
በሰራዊታችን ውስጥ በሰገሰጋቸው ሰርጎ ገቦቹ አማካኝነት “ሳቦታጅ” በመስራት በረቀቀ ዘዴ
ወግቶናል በማለትም ያከሳሉ፡፡ ለምሳሌ ኮሎኔል መንግሥቱ ሀይለማሪያም በቆሬ ግንባር
የተሰማሩት የኢህአፓ ሰርጎ ገቦች “ድሬ ዳዋ በሶማሊያ ጦር ተይዟል፤ የቆሬ ምሽግም ከባቢሌ
በኩል በመጣ ሀይል ተቆርጧል፤ የኢትዮጵያ ሰራዊት አልቆለታል፤ ጉድጓድ ውስጥ ተቀምጠን
ጠላት እስኪመታን ድረስ መጠበቅ የለብንም፤ እጅ መስጠት ይሻለናል” እያሉ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ
ይነዙ ነበር” በማለት ጽፈዋል፡፡ በደርግ ወገን ሆነው የያኔውን ታሪክ ጻፉት አቶ ገስጥ ተጫኔም
(በብዕር ስማቸው “ዘነበ ፈለቀ”) “ነበር” በተሰኘው መጽሐፋቸው እንዲህ ይሉናል፡፡
*****
28
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
በዚያ ዘመን አነስተኛ ሀይል የነበራቸው ህወሐትና ኦነግ በሶማሊያ ወረራ ላይ የወሰዱትን
አቋም በማስረጃ አስረግጦ መተንተን አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁንና ድርጅቶቹ በጦርነቱ ወቅት
ከሶማሊያ መንግሥት ጥቅሻ ያላገኙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የዚያድ ባሬ መንግሥት ሁለቱን
ድርጅቶች ወደ ሞቃዲሾ የጠራው ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ነው፡፡ ጀብሃና ሻዕቢያ ደግሞ ወረራውን
ደግፈዋል፡፡
የሶማሊያ ሰራዊት ሀረርን ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረት ከከፈሸበት በኋላ ይዞታውን ለማስፋት
አልሞከረም፡፡ ሶቪየት ህብረት፣ ኩባ እና የመን ኢትዮጵያን በመደገፍ በጦርነቱ ውስጥ
መግባታቸውን ሲረዳ በያዛቸው አካባቢዎች መከላከያውን ማጠናከሩን ነው የመረጠው፡፡
ኢትዮጵያ በበኩሏ የመልሶ ማጥቃት ዝግጅቷን አጧጧፈች፡፡
ሶቪየት ህብረት በቃሏ መሰረት በታህሳስ ወር 1970 (ስድሳ ሰባት) የሚግ ተዋጊ ጄቶችን
ለኢትዮጵያ ሰጠች፡፡ 600 ታንኮች፣ ከ200 በላይ ብረት ለበሶች፣ 150 ያህል መድፎች፣ 100
የቢ.ኤም ሮኬት ማስወንጨፊያዎች፣ ዙ-23 የአየር መቃወሚያዎች፣ ቀላልና ከባድ መትረየሶች፣
ቦምቦች፤ ሮኬቶች፣ ወዘተ… ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ዘመናዊ የሆኑ ሶቪየት ሰራሽ ዋዝ ጂፖች፣
ሽፍን ወታደራዊ መኪናዎች፣ “ኦራል”፣ “አይፋ” እና “ካማዝ” የሚባሉ ከባድ መኪናዎችም
ለኢትዮጵያ ተሰጡ፡፡ የአውሮፕላንና የሂሊኮፕተር አብራሪዎች፣ ወታደራዊ መኮንኖችና የውጊያ
አሰልጣኞች፣ የፈንጂ መሐንዲሶች፣ ወዘተ…. በአስቸኳይ ወደ ሶቪየት ህብረት እየተላኩ ተጨማሪ
ስልጠና እንዲወስዱ ተደረገ፡፡ በሀገር ውስጥ ደግሞ ቀደም ብለው የተጀመሩት የፓራ-ኮማንዶ፣
የአየር ወለድ፣ የባህር ወለድ፣ የከባድ መሳሪያ ተኳሾች፣ የበታች አዛዦች፣ የመደበኛ ተዋጊዎች
እና የሚሊሻ ወታደሮች ስልጠናዎች ተጠናክረው ቀጠሉ፡፡
“ታጠቅ የጦር ሰፈር”፡- በሸዋ ክፍለ ሀገር ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ (20 ኪሜ ) የሚገኝ
ሲሆን ኢትዮጵያ በታሪኳ የገነባችው ትልቁ የጦር ማሰልጠኛ ማዕከል ነው፡፡ በኢትዮ-ሶማሊያ
ጦርነት ወቅት በታጠቅ ይሰለጥኑ የነበሩት ሚሊሻዎች ናቸው፡፡ ይህ ማዕከል በአንድ ጊዜ መቶ
ሺህ ሰልጣኞችን ለመቀበል ይችላል፡፡
1. “ኩሃ የጦር ሰፈር”፡- በትግራይ ክፍለ ሀገር የሚገኝ የጦር ማሰልጠኛ ነው፡፡ በዚህ
ማዕከል የሰጠለኑት የመደበኛ ጦር አባላት ናቸው፡፡
2. “አዘዞ ጦር ሰፈር”፡- በጎንደር ክፍለ ሀገር ነው የሚገኘው፡፡ በዚህኛውም ማዕከል
የሰለጠኑት የመደበኛ ጦር አባላት ናቸው፡፡
29
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
3. “ለምለም ጦር ሰፈር” (ለምለም ግቢ)፡- በሸዋ ክፍለ ሀገር በደብረ ዘይት ከተማ
የሚገኝ የጦር ማሰልጠኛ ነው፡፡ በዚህ ማዕከል የሰለጠኑት መደበኛ ተዋጊዎችና አየር
ወለዶች ናቸው፡፡
4. ዝዋይ ጦር ሰፈር፡- በሸዋ ክፍለ ሀገር ነው የሚገኘው፡፡ በዚህ ማዕከል የሰለጠኑት
ፓራኮማንዶዎች ናቸው፡፡
5. አዋሳ የጦር ሰፈር፡- በሲዳሞ ክፍለ ሀገር ከአዋሳ ሀይቅ ዳር ነው የሚገኘው፡፡
በዚህኛውም የጦር ሰፈር የሰለጠኑት የፓራኮማንዶ ተዋጊዎች ናቸው፡፡
6. ለገዳዲ የጦር ማሰልጠኛ፡- ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ በ20 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ
ነው የሚገኘው፡፡ በዚህኛውም ማዕከል የሰለጠኑት ፓራኮማንዶዎች ነበሩ፡፡
7. አዋሽ አርባ የጦር ትምህርት ቤት፡- በሸዋ እና በሀረርጌ ድንበር አቅራቢያ (ከአዋሽ
ሰባት ኪሎ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ) ነው የሚገኘው፡፡ በዚህ ማዕከል የሰለጠኑት
በአብዛኛው የታንክ፣ የመድፍና የሌሎች ከባድ መሳሪያ ተኳሾች ሲሆኑ አንድ
የፓራኮማንዶ ብርጌድም በማዕከሉ ሰልጥኗል፡፡
*****
ሚያዚያ 10/2006 ተጻፈ፡፡
30
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል ሰባት
31
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
3. በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላይ ያነጣጠረ ፕሮፓጋንዳ
*****
በሌላ በኩል የዘመኑ የኢትዮጵያ መሪዎች በዓለም ዙሪያ ሰፊ የዲፕሎማሲ ስራ ሰርተዋል፡፡
በውጤቱም የሶሻሊስቱ ካምፕ በየሶማሊያን ወረራ ሊያወግዝ በቅቷል፡፡ የአፍሪቃ አንድነት
ድርጅትም የሶማሊያን ወረራ በማውገዝ ከኢትዮጵያ ጋር ቆሟል፡፡ የምዕራብ ሀገራት ግን
ሶማሊያ ወራሪ መሆኗን እያወቁ እንኳ ሊያወግዟት አልፈቀዱም፡፡ ይህም የሆነው ሶቪየት
ህብረት የኢትዮጵያ አጋር ሆና በመገኘቷ ነው፡፡
1. በምስራቅ ግንባር
አራት ታንከኛ ብርጌድ
ሁለት መድፈኛ ብርጌድ
ሁለት የከባድ መሳሪያ (ቢ.ኤም) ተኳሽ ብርጌድ
ሁለት መደበኛ ክፍለ ጦር
አራት ህዝባዊ ሚሊሻ ክፍለ ጦር
2. በደቡብ ግንባር
ሁለት ህዝባዊ ሚሊሻ ክፍለ ጦር
አንድ መድፈኛ ሻለቃ
3. አየር ሀይል
የኢትዮጵያ አየር ሀይል በጠቅላላው ከታጠቃቸው 75 አውሮፕላኖች
መካከል 40 የሚሆኑትን ለግዳጅ አሰልፏል፡፡
32
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮጵያ ጦር ካሰለፈው ሀይል በተጨማሪ ቀደም ሲል የጠቀስኳቸው አንድ ክፍለ ጦር
የሚሆን የኩባ ሰራዊትና አንድ የደቡብ የመን መድፈኛ ብርጌድም በምስራቁ ግንባር ተሰልፈዋል፡
፡ (የኢትዮጵያ ሰራዊት ለረጅም ጊዜ ሲከላከል የቆየው በሁለት መደበኛ ክፍለ ጦሮች፤ ሶስት
ሚሊሻ ክፍለ ጦሮች፣ ሁለት ሜካናይዝድ ብርጌድና ሁለት ነበልባል ብርጌድ ብቻ ነው)፡፡
*****
የኢትዮጵያ ሰራዊት የማጥቃት ዘመቻውን በሚከተለው ሁኔታ ለመፈጸም ነበር ያቀደው፡፡
ኮሎኔል መንግሥቱ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ይህንን የውጊያ እቅድ ያወጣችው የሶቪየትና የኩባ
አማካሪዎች ከመምጣታቸውና ኢትዮጵያ ከሶቪየት ያኘችውን የመሳሪያ ድጋፍ ከመረከቧ በፊት
ነበር፡፡ በዚያ ዕቅድ መሰረት የታንክና የመድፍ ተኳሾች በአሰብ ላይ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ
በኋላ ታንካቸውን ይዘው ወደ ጦርነቱ ቦታ እንዲሄዱ ነበር የተፈለገው፡፡ የውጊያው የመጨረሻ
ፕላን ላይ ውይይት በሚደረግበት ወቅት የሶቪየት አማካሪዎች “ዕቅዱ ሶማሊያን ለመውረር
የተዘጋጀ ይመስላል” በማለታቸው ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ውጥን ለመከለስ ተገዳለች፡፡
33
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ሶቪየቶች ይህንን እንዲሉ ያደረጋቸው ኢትዮጵያ ካደራጀችው ሜካናይዝድ ጦር ውስጥ ሰማኒያ
በመቶ የሚሆነው ለሰሜን ሶማሊያ ቅርብ በሆነችው የጅጅጋ መስመር እንዲሰለፍ በመደረጉ
ይመስላል (ሀርጌሳ ከጅጅጋ በቅርብ ርቀት ላይ ያለች መሆኗን ልብ በሉ)፡፡
*****
የካቲት 23/1970፡፡ የኢትዮጵያ ጦር በጭናክሰን እና በቆሬ በኩል በጅጅጋ ላይ የተጠናከረ
ጥቃት ከፈተ፡፡ የሶማሊያ ጦር ጥቃት ይመጣብኛል ብሎ ባልጠበቀው አቅጣጫ በመወጋቱ
ተደናገጠ፡፡ ጅጅጋን ላለመልቀቅ መሟሟት ጀመረ፡፡ ሶማሊዎች በዚህ ውዥንብር ውስጥ
እያሉ በጀልዴሳ ግንባር ሌላ ጥቃት ገጠማቸው፡፡ የኢትዮጵያ አየር ሀይልም እስከ ሶማሊያ
ድንበር እየገባ የሶማሊያ ሰራዊትን የአቅርቦትና የእደላ መስመሮችን በመደብደብ ከጥቅም
ውጪ አደረጋቸው፡፡
34
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ኩባ-የመን ጥምር ጦር በጀልዴሳ የተከማቸውን የሶማሊያ ሰራዊት ለሶስት
ተከታታይ ቀናት ወጋ፡፡ ይህ ውጊያ ታንክ ከታንክ ጋር የተፋጨበት በመሆኑ በርካታ የጦር
መሪዎች “የጦርነት ፊልም ይመስል ነበር” እያሉ አድናቆታቸውን ሰጥተውታል፡፡ የሶስቱ ሀገራት
ጥምር ጦር ከሶስት ቀን በኋላ ግዳጁን በማጠናቀቅ በቆላው ምድር ላይ ገሰገሰ፡፡ የካቲት
30/1970 ግዳጁን በማጠናቀቅ ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር በስተደቡብ ያሉ ከተሞችን
ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡ ከሀረር የተንቀሳቀሰው ጦር ደግሞ በሰሜን በኩል ግዳጁን በቀላሉ
በመወጣት ኮምቦልቻን አልፎ እስከ ኤጀርሳ ጎሮ ድረስ ገስግሷል፡፡ ከሀረር በስተደቡብ
የተነቃነቀው ግብረ ሀይል ግን ከሶማሊያ ሰራዊት ከፍተኛ የሆነ መከላከል ገጥሞታል፡፡
የኢትዮጵያ ጦር የካቲት 29/1970 ፈዲስን የተቆጣጠረው ከባድ መስዋዕትነት ከከፈለ በኋላ
ነው፡፡ በባሌ እና በነጌሌ ቦረና ግንባር የተሰለፈው ጦር ግን ጠንካራ መከላከል ሳያጋጥመው
እስከ ጠረፍ ድረስ እየገሰገሰ የኢትዮጵያ ከተሞችን ሁሉ በቀላሉ ለመቆጣጠር ችሏል፡፡
*****
ሚያዚያ 11/2006 ተጻፈ፡፡
35
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል ስምንት
===የጦርነቱ ውጤት===
በጦርነቱ የደረሰው ጉዳት በልዩ ልዩ ወገኖች በተለያየ መንገድ ተገልጿል፡፡ ለምሳሌ ኮሎኔል
መንግሥቱ ኃይለማሪያም የጦርነቱን ጉዳት በሚከተለው ሁኔታ ጽፈውታል፡፡
ከዊኪፒዲያ የተገኘው መረጃ አንድ ተቃርኖ አለው፡፡ ይኸውም “1/3ኛ የሚሆን “የሶማሊያ
ሰራዊት ከጥቅም ውጪ ሆነ” እያለ በሶማሊዎች ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን አሳንሶ
የሚያቀርብ መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም በጦርነቱ በሶማሊያ ሰራዊት ላይ የደረሰው ጉዳት በሁለቱ
ምንጮች ከቀረበው የሚበልጥ እንደሆነ እሙን ነው፡፡ ኢትዮጵያን ለመርዳት ከመጡት የውጪ
ዜጎች መካከል 400 ኩባዊያን፤ 100 የመናዊያንና 33 የሶቪየት ህብረት ዜጎች ሞተዋል፡፡
36
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ሁለቱ ሀገራት ለጦርነቱ ካሰለፏቸው ከባድ መሳሪያዎች መካከል ብዙዎችን አጥተዋል፡፡ በዚህ
ረገድ በሶማሊያ ጦር ላይ የደረሰው ጉዳት ከበድ ይላል፡፡ ሶማሊያ ለጦርነቱ ካሰለፈቻቸው
ታንኮች መካከል 200 የሚሆኑትን አጥታለች፡፡ ኢትዮጵያም 100 ታንክ ተደምስሶባታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ሀይል 15 ያህል አውሮፕላኖች ወድመውበታል፡፡ ሶማሊያ ግን 35 ጢያራዎችን
አጥታለች፡፡ (የሚገርመው ነገር የኢትዮጵያ የአየር ሀይል ብዙ አውሮፕላኖችን የደመሰሰው
በአየር በአየር ውጊያ ነው)፡፡
የኢትዮጵያ ጦርም ኦጋዴንን መልሶ ከያዘ በኋላ የሶማሊያን ሰራዊት ደግፈዋል ባላቸው ላይ
የግድያና የዘረፋ እርምጃ መውሰዱ ይነገራል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት የደረሰው በፊቅ፤ ጎዴ፣
ደጋሃቡርና ቀብሪ ደሃር አካባቢዎች ነው፡፡ አንዳንድ የጦር መሪዎች ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆኑ
ሶማሊዎችን ከሶማሊያ ጦር ባለመለየት ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ውርጅብኝ ሲያካሄዱባቸው ነበር
ይባላል፡፡ በዚህም የተነሳ ከአንድ ሚሊዮን ያላነሱ ኢትዮጵያዊ ሶማሊዎች ሀገር ጥለው
ተሰደዋል፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ድንበር ገብቶ ሲቪሎችን ምርኮኛ አላደረገም፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ እጅ የወደቁ የጦር ምርኮኞች ሰብዓዊ ክብራቸውን በማይነካ መልኩ
ነው የተያዙት፡፡
37
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
“ኢትዮጵያ ሀገራችንን ልትወርር ስለሆነ እያንዳንዱ ዜጋ ለውጊያው ይሰለፍ” የሚል አዋጅ
አስነግረዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር የተባበሩት የሶቪየት አማካሪዎችም “ሶማሊያን ልትወርሩ ነው
እንዴ?” እያሉ መጨቅጨቅ ጀምረው ነበር፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ ጦር ኦጋዴንን ሙሉ በሙሉ
ከተቆጣጠረ በኋላ በድንበሩ ላይ ቆሟል፡፡
*****
ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማሪያም ሶማሊያን ማሸነፋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ
የድሉን ብስራት በድምቀት እንዲያከብር አዋጅ አስነገሩ፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ ጦር
ስትራቴጂካዊውን የካራማራ ተራራን የተቆጣጠረበት ውጊያ የድሉን ቁልፍ ያስጨበጠ በመሆኑ
በብሄራዊ ደረጃ መዘከር እንዳለበት ተነገረ፡፡ በመሆኑም መላው ኢትዮጵያ ህዝብ የካራማራውን
ድል በቅድሚያ በአውራጃ ደረጃ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች አማካኝነት በየአካባቢው አከበረ፡፡
በማስከተልም ድሉ በጅጅጋ ከተማ በብሄራዊ ደረጃ በተዘጋጀው ታሪካዊ ክብረ-በዓል ተከበረ፡፡
*****
ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከጦርነቱ በኋላም በጠላትነት መፈላለጋቸውን አላቆሙም፡፡ በ1972
የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ባደረገው ጥረት የተኩስ ማቆሚያ ስምምነት ቢፈራረሙም እስከ
1983 ድረስ በእጅ አዙር ሲዋጉ ነው የሰነበቱት፡፡ ሁለቱ መንግሥታት በጋራ የፈጸሙት መልካም
ነገር ቢኖር በ1980-1981 የእስረኛ ልውውጥ ማድረጋቸው ብቻ ነው፡፡ ያ ታሪካዊ ጦርነት ሙሉ
ፍጻሜውን ያገኘው በጥር/1983 የዚያድ ባሬ መንግሥት ከስልጣን በተወገደበት ጊዜ ነው
39
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
(ይህንን የምለው ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ አይደለም፤ ጦርነቱ ሲለኮስ የነበረው የዚያድ ባሬ
መንግሥት በዓለም አቀፍ መድረክ እውቅና የተሰጠውን የኢትዮጵያ ህጋዊ ድንበርን የማያከብር
በመሆኑ ነው)፡፡
*****
ሚያዚያ 12/2006 ተጻፈ፡፡
40
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት
ክፍል ዘጠኝ
41
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ነበር፡፡ የውዝግቡ መነሻ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላኖች ሶማሊያ
ድንበር ውስጥ ገብተው ጥቃት መፈጸማቸው ነው፡፡ማርሻል ፔትሮቭ አውሮፕላኖቹ
ሶማሊያ መግባታቸውን ይቃወማል፡፡ ኮሎኔል ፋንታ ደግሞ “መሬታችንን የያዘብንን
ጠላት እስከ ሞቃዲሾ ድረስ ሄደን የመውጋት መብት አለን” ባይ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ
ማርሻል ፔትሮቭ ክሱን ለሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማሪያም አሰማ፡፡ መንጌም “ፋንታ
ያደረገው ትክክል ነው” በማለት ፈረዱበት፡፡ በዚህም አኩርፎአፋቸው ነበር ይባላል፡፡
ማርሻል ፔትሮቭ ባለፈው የካቲት ወር ውስጥ በ97 ዓመቱ አርፏል፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የኩባ ጦር አዛዥ ነው፡፡ ይህም ጄኔራል ግሩም የሆነ ወታደራዊ
ችሎታ የነበረው ሲሆን ከኢትዮጵያ የጦር መኮንኖችም ጋር ተግባብቶ በመስራት
ተደናቂነትን አትርፏል፡፡ እርሱ ያዘመተው ጦር ለፈጸመው ጀብዱ መታሰቢያ ይሆነው
ዘንድ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ኒሻን ተሸልሟል፡፡
ጄኔራል ኦቾዋ ወደ አንጎላ የዘመተውንም የኩባ ጦር ይመራ ነበር፡፡ ነገር ግን በአንጎላ
ምድር በለስ ሊቀናው አልቻለም፡፡ በደቡብ አንጎላ በተደረገ አንድ ውጊያ ብዙ የኩባ
ወታደሮች ሲሞቱ “ለውድቀቱ ተጠያቂው አንተ ነህ” የሚል ወቀሳ ከፕሬዚዳንት ፊደል
ካስትሮ ቀርቦበታል፡፡ በዚሁ ጦስ ከስልጣኑ ወርዶ በቁም እስር ላይ እያለ “በአደንዛዥ እጽ
እና በህገ-ወጥ የአልማዝ ንግድ ውስጥ እጁን ነክሯል” የሚል ክስ ቀረበበት፡፡ ክሱ በዝግ
ችሎት ከታየ በኋላም የሞት ፍርድ ተፈረደበት፡፡ ሀምሌ 7/1981 በጥይት ተደብድቦ
ተገደለ፡፡
4. ብ/ጄኔራል ለገሠ ተፈራ (የህብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጀግና)፡
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ካፈራቸው ምርጥ አብራሪዎች አንዱ ነው፡፡ በአየር በአየር ውጊያ
ስድስት የሶማሊያ ሚግ ጄቶችን በማጋየት ጀብዱ የፈጸመ ተዋጊም ነው፡፡ ሆኖም
በመጨረሻው ዙር ባደረገው በረራ በሶማሊያ ድንበር ውስጥ ጥቃት አድርሶ ሲመለስ
አውሮፕላኑ በመመታቱ ሊማረክ በቅቷል፡፡
ሶማሊዎቹ ጄኔራል ለገሠን ለአስራ አንድ ዓመታት ካሰሩት በኋላ በ1981 ለቀውታል፡፡
ጄኔራሉ በእስር ቤት ሳለ ከፍተኛ ስቃይ ስለደረሰበት ከእስር ተፈትቶ ወደ አዲስ አበባ
በመጣበት ጊዜ ሰውነቱ አልቆ ከሞት የተነሳ አጽም ይመስል ነበር፡፡ ሊቀመንበር
መንግሥቱ ጄኔራል ለገሠን በልዩ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ከተቀበሉት በኋላ የሀገሪቱ
የመጨረሻ ደረጃ ኒሻን የሆነውን “የህብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ”
ሸልመውታል፡፡ ከጄኔራል ለገሰ ሌላ ይህንን ሜዳይ የተሸለሙት ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው
(አንደኛው ሊቀመንበር መንግሥቱ ራሳቸው ሲሆኑ ሁለተኛው ብ/ጄኔራል ተስፋዬ
ሀብተማሪያም ናቸው)፡፡
5. ሌ/ኮ/ ፋንታ በላይ
42
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሲሆን አየር ሀይሉ በሶማሊያ ባለጋራው ላይ የበላይነት
እንዲቀዳጅ ያስቻለውን ወታደራዊ ስልት የነደፈ እውቅ መኮንን ነው፡፡ በተለይም
የኢትዮጵያ አየር ሀይል በሶማሊያ ድንበር ውስጥ እየገባ የሶማሊያ ሰራዊት የእደላና
የስምሪት መስመሮችን እንዲደበድብ የሚለውን ሃሳብ ያመነጨው እርሱ ነው፡፡ በዚህም
ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል፡፡
ሌ/ኮ/ ፋንታ በላይ በአየር ሀይል አዛዥነቱ እስከ 1979 አገልግሏል፡፡ በማዕረጉም እስከ
ሜጀር ጄኔራል ደረጃ ደርሷል፡፡ በ1981 ተሞክሮ የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ዋነኛ
ጠንሳሽ እርሱ እንደነበረም ይነገራል፡፡ መፈንቅለ መንግሥቱ ከከሸፈ ከሁለት ወር በኋላ
ግን እስከ ዛሬ ድረስ እንቆቅልሽ በሆነ ሁኔታ ተገድሏል፡፡
*****
ሚያዚያ 13/2006 ተጻፈ፡፡
43
የኢትየ-ሶማሊያ ጦርነት (1969-1970) ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ
ጠቃሚ የመረጃ ምንጮች
1. Evil Days, Thirty Years of War and Famine in Ethiopia: An Africa Watch
Report, New York , September 1991
2. Gebru Tareke, “The Ethiopia-Somalia War of 1977 Revisited, Journal of
African Historical Studies, pp-635-667
3. Gebru Tareke, The Ethiopian Revolution: War in the Horn of Africa,
New Haven CT, Yale University Press, 2009
4. Kenneth G. Weiss, “The Soviet Involvement in the Ogaden War”, Center
for Naval Analysis, Alexandria, Virginia, February 1980
5. Mesfin Wolde-Mariam: Somalia: A Problem Child of Africa, 1978
6. Tibebe Eshete, The Root Cause of Ogadeni Problem, Journal of North
African Studies, Vol 13, Number 1, 1991
7. ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም፣ “ትግላችን”-የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ የትግል
ታሪክ፡ ጸሐይ አሳታሚና አከፋፋይ ድርጅት፡ ሎስ አንጀለስ፡ 2004
8. ብ/ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ፡ የጦር ሜዳ ውሎዎች ከምስራቅ እስከ ሰሜን፡ አዲስ አበባ፣
2000
9. ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ሀብተማሪያም፣ የጦር ሜዳ ውሎ፣ አዲስ አበባ፣ 1996
10. ዘነበ ፈለቀ፣ “ነበር”፣ አዲስ አበባ፣ 1996
11. ገነት አየለ አንበሴ፣ የሌ/ኮ/ መንግሥቱ ኃይለማሪያም ትዝታዎች፣ ሜጋ አሳታሚ
ድርጅት፣ 1994
44