You are on page 1of 1

ትዕይንተ ጎንደር


ይህ በ öó ው መ.ክ.ዘ፣ አዛዥ ሲኖዳ በተባለ የጎንደር ሊቅ፣ጸሐፌ ትዕዛዝ የተዘጋጀ፡መጽሐፍ ነው፡፡ አዛዥ ሲኖዳ በማበብ
ላይ ስለነበረችው፣ የጎንደር ከተማ የጻፈው መጽሐፍ ነው፡፡ አዛዥ ሲኖዳ የዐፄ በካፋ (መሲሕሰገድ) ጸሐፌ ትዕዛዝና ታሪክ
ጸሐፊ ሲሆን፣ የአድያም ሰገድ ኢያሱ የልጅ ልጅ ነው፡፡ ደራሲ፣ ፈላስፋና ባለ ራዕይ መሆኑ ይነገርለታል፡፡ ሲኖዳ ከዚህም
ሌላ፣ እስካሁን ድረስ ያላገኘናቸውንና በለሳ ተክለኃይማኖት በሚገኘው መጽሐፈ ቄርሎስ የመጨረሻ ገጽ ላይ የተጻፉትን
መርሥኤ ኀዘን፣ ምዝባሬ ቤተ መንግሥት፣ ተፍጻሜተ መንግሥት፣ ምዝባሬ ቤተ መቅደስ፣ምሳሌ መምህራን፣ መጽሐፈ
ሰዋስው እና ማኅለቅተ ዘመን የሚሰኙ ድርሰቶችንም ጽፏል፡፡

You might also like