You are on page 1of 28

ማረጋገጫ (Declaration)

“በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ፤ በዳባት ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት በዘጠነኛ ክፍልተ ማሪዎች ተተኳሪነት” በሚል ርእስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብዕ
ኮሌጅ፣ የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች)ና ስነጽሁፍ አማርኛ ትምህርት ክፍል በተግባራዊ ስነ-ልሳን አማርኛን ማስተማር
ለማስተርስ ዲግሪ ማሟያነት ያቀረብኩት ይህ ጥናት ከዚህ በፊት በማንኛውም አካል ያልተሰራ የራሴ ወጥስራ መሆኑንና
የተጠቀምኩባቸው ድርሳናትም በትክክል ዋቢዎች የሆኑና ጎንደር ዩኒቨርሲቲም የጥናቱ ህጋዊ ባለቤትነት ያለው መሆኑን
በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

ስም ----------------------------------------------

ፊርማ -------------------------------------------

ቀን--------------------------------------------------

ምዕራፍ አንድ
መግቢያ
1.1 የጥናቱ ዳራ
ማንበብ የተጻፈን ነገር ቀጥተኛ ትርጉም መረዳት ብቻ ሳይሆን፣ በጽሁፍ ውስጥ በተዘዋዋሪ መንገድ የተገለጸን
ሃሳብንም የመረዳት ሂደት ነው (ቤከር፣ 2008)፡፡ እንደቲየርኔይ (2005) ገለጻ ለማንበብ መማር ቃላትን ለማወቅ ወይም
ለማስታወስ መማር ብቻ ሳይሆን የምንባብን አጠቃላይ ትርጉም ለመረዳት መማርንም ያካትታል፡፡ ማንበብ የአራት
ጉዳዮች መስተጋብር ውጤት ነው፡፡ አንደርሰን (2003) እንደገለጹት ማንበብ የአንባቢ፣ የውህድአሃድ፣ የአቀላጥፎ
ማንበብ (በተገቢ ፍጥነት በትክክል አንብቦ የመረዳት ችሎታ) እና የብልሃታዊ ማንብበ (የማንበብ አላማ ለማሳካት
የአንባቢው የተለያዩ የማንበብ ብልሃቶችን የመጠቀም ችሎታ) መስተጋብር ያካትታል፡፡ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት
በተለያዩ ንድፈሃሳቦች ስለማንበብ የተለያዩ ዕይታዎች ሲንጸባረቁ ቆይቷል፡፡ ከ 1950 ዎቹ እስከ 1960 ዎቹ የነበረውና
የባህርያውያን ንድፈሃሳብ ስነ-ልቦና ተጽዕኖ ያረፈበት የማንበብ ትምህርት ዕይታ ታህታይ-ላዕላይ ዕይታ ነው፡፡ በዚህ
ዘመን የነበሩት ተመራማሪዎችና የትምህርት ባለሙያዎች ማንበብን እንደታህታይ-ላዕላይ ሂደት አድርገው ያስቡ ነበር፡፡
ታህታይ-ላዕላይ የማንበብ ሂደትን ያስተዋወቁት ጎፍ (1972)፣ ላበርግና ሳሙኤልስ (1974) ናቸው፡፡ ይህ የማንበብ ዕይታ
የልየታ (decoding) ንድፈሃሳብ በመባልም ይታወቃል፡፡ በዚህ የማንበብ ዕይታ ለማንበብ አስፈላጊው ነገር ውህድአሃዱ
ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም በዚህ ዕይታ ትርጉም ያለው በተጻፈው ነገር ወይም በወረቀት ላይ ብቻነው፤ ተብሎ ይታሰባል፡፡
ማካርቲ (1999) እንደሚሉት ይህ ዕይታ ከውጭ ወደውስጥ ሂደት (Outside-in processing) ነው፤ ምክንያቱም
ትርጉም ያለው በተጻፈው ነገር ላይ እንደሆነና በአንባቢው እንደሚተረጎም ስለሚታሰብ ነው፡፡ ኑናን (1991)
እንደሚያስረዱት አንብቦ መረዳት በጽሁፍ ውስጥ ያሉ ምልክቶችን በተናጠል የመለየት ጉዳይ ሲሆን፣ አንባቢው
ውህድአሃዱን በመመልከት መጀመሪያ በቃል ውስጥ የሚገኙ ፊደላትን በተናጠል ከለየ በኋላ ወደ ውስብስብ ቅንጣቶች
ይሸጋገራል፡፡ በሌላ አገላለጽ በመጀመሪያ ፊደላቱን ይለያል፣ ከዚያም ከፊደላት የተዋቀሩትን ቃላት ይለያል፤ ከቃላት ወደ
ሃረጋት ልየታ ይሸጋገራል፤ ከዚያም ወደ ዐረፍተነገር ልየታ ይሸጋገራል፤ በእነዚህ ሁሉ ሂደቶች ትርጉም ይረዳል፡፡ አንባቢው
የውህድአሃዱን ትርጉም የሚረዳው ግን የልየታ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ነው(ሃሪስ፣ 2005)፡፡ በአጠቃላይ በዚህ የማንብብ ዕይታ
ማንበብ አንድ አቅጣጫን የሚከተል (ከውህድአሃዱ ወደአንባቢው የሆነ) ሂደት ነው፡፡ ውጤታማ ማንበብ ማለት
አንባቢው ጸሃፊው በውህድአሃዱ ያሰፈረውን መልዕክት የመረዳት ችሎታ ካለው የማንበብ ተግባሩ ውጤታማ ይሆናል
ተብሎ የሚታሰብበት ነው፡፡ አንባቢው የቀረበውን ውህድአሃድ በመገንዘብ ብቻ እንዲገደብ የሚያደርግ ነው፡፡ አንባቢው
በማንበብ ሂደቱ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የማይሆንበት የማንበብ ሂደት ስለሆነ፣ አመለካከቱ አሉዊይሆናል፡፡ በ 1970 ዎቹ
የነበረውና በአዕምሯውያን ንድፈሃሳብ ላይ የተመሰረተው የማንበብ ትምህርት እይታ ደግሞ ላዕላይ-ታህታይ ሂደትነው፡፡
ይህንን የማንበብ ሂደት ያስተዋወቁት ስሚዝ (1978) እና ጉድማን (1976) ናቸው፡፡ ይህ የማንበብ ሂደት በ 1970 ዎቹ
በአዕምሯዊ ሳይንስ ረገድ የአመለካከት ለውጥ ከመከሰቱ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ዘመኑም የባህርያውያን የማንበብ
ዕይታ በአዕምሯውያን የማንበብ ዕይታ የተተካበት ነው፡፡ ይህ ዘመን መማር እንዲከሰት የአዕምሮ አስተዋጽኦ ከፍተኛ
እንደሆነ የታሰበበት ጊዜ ነበር፡፡ የታህታይ-ላዕላይ የማንበብ ሂደት በላዕላይ-ታህታይ ሂደት የተተካበት ነበር፡፡ የማንበብ
ሂደቱመሰረት ድምጸልሳናትን ማደራጀት ወይም የፊደላትና የቃላት ልየታ አስፈላጊ ቢሆንም ለተሳካ ማንባብ ግን በቂ
አይሆንም የሚል ነበር፡፡ በመሆኑም በላዕላይ-ታህታይ ሂደት አንብቦ መረዳት ሁልጊዜም ቢሆን አንባቢው ስለውህድአሃዱ
ርዕስ በሚኖረው የቀደመ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ የማንበብ ሂደት የሚጀምረው በአንባቢው ጭንቅላት
ውስጥ ነው፡፡ በመሆኑም በላዕላይ-ታህታይ ዕይታ ትኩረት የሚሰጠው ለትርጉም ምስረታ የአንባቢው ዳራዊ ዕውቀትና
የውህድአሃድ መስተጋብር ነው (ሀሪስ፣ 2005)፡፡ ላዕላይ-ታህታይ ሂደት ተማሪዎች ለማንበብ የሚማሩባቸውን መንገዶች
ጽንሰ ሃሳብ አሳይቷል (ስሚዝ፣ 1994)፡፡ በማንበብ ሂደት ዳራዊ ዕውቀት መጠቀም፣ ከመረጃ በመነሳት የራስ ውሳኔ ላይ
ወይም ማጠቃለያ ላይ መድረስ፣ አንብቦ መረዳትን መቆጣጠር፣ ለመሳሰሉት ጉዳዮች ትኩረት ይሰጣል፡፡ ላዕላይ-ታህተይ
ሂደት ተማሪው ዝም ብሎ መረጃ ተቀባይ ሳይሆን፣ በትርጉምና በዕውቀት ምስረታ ሂደት ውስጥ በንቃት ሲሳተፍ ነው
መማር የሚከሰተው የሚለውን የግንባታውያን ዕይታ ይቀበላል፡፡ የግንባታውያን ዕይታ ተማሪው አዲስ መረጃን ወይም
ተመክሮን ለመረዳት የማሰብና የአዕምሮ ሂደቶችን ይጠቀማል፤ አዳዲስ ነገሮችንም ይማራል (ሮቢንሰን
ሞሌንዳናሬዛቤክ፣ 2008)፡፡ በቅድመ ማንበብ፣ በማንበብና በድህረ ማንበብ አንባቢው በጭንቅላቱ ውስጥ የሚያስበውን
ነገር ያካትታል (ኦርምሮድ፣ 2008)፡፡ በግንባታውያን ንድፈሃሳብ አንባቢው በመማር ሂደት ውስጥ እንደንቁ ተሳታፊ
የሚታይበት ብቻ ሳይሆን የአንባቢው ውህድአሃድን መረዳትም እንደትርጉም ምስረታ ሂደት የሚታይበት ነው(ግሬቭና
ሌሎች፣ 1998)፡፡ ይህም ማለት ተማሪው ከውህድአሃዱ ዝምብሎ ትርጉም የሚቀበልበት ወይም የሚያገኝበት ሳይሆን
እያነበበ እያለ ትርጉም የሚመሰርትበት ሂደት ነው፡፡ አንድ አንባቢ ከውህድአሃዱ የሚመሰርተው ትርጉም በንባብ አውዱ፣
በአንባቢው ተመክሮ፣ በአንባቢው ችሎታና በሌሎችም ምክንያቶች ተጽዕኖ ስለሚደርስበት ሌላው አንባቢ
ከሚመሰርተው ትርጉም ይለያል (ካምቦርኔ፣ 2004)፡፡ ስለሆነም ሁለት አንባቢዎች ከአንድ ውህድአሃድ አንድ አይነት
ትርጉም ይመሰርታሉ ማለት አይቻልም(ግሬቭና ሌሎች፣ 1998) ፡፡ ምክንያቱም አንባቢዎች በማንበብ ሂደቱ ውስጥ ንቁ
ተሳታፊዎች ስለሚሆኑ በራሳቸው ትርጉም ስለሚመሰርቱ ነው፡፡ ንድፈሃሳቦቹ እንዳሉ ሆነው ሰለንባብ ልምድና አንብቦ
መረዳት ችሎታ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ የዘርፉ ምሁራን የራሳቸውን ብያኔ ሰጥተዋል፡፡ ቴንድል(2003) ማንበብ ከተፃፈ
ነገር ላይ ትርጉምን መረዳትና መረጃን በአግባቡ የመውሰድ ደረጃና ከቋንቋ ክሂሎች ውስጥ በመማር ብቻ የሚገኝ
ከማዳመጥና ከመናገር ቀጥሎ የሚመጣ ክሂል ነው፤ ሲሉ አያይዘውም ስለንባብ ማንበብ ከዝቅተኛ የክፍል ደረጃ ጀምሮ
ወደከፍተኛ የክፍል ደረጃ በሚሄድበት ጊዜ ልምዱም ሆነ የመረዳት ችሎታው አብሮ እያደገ እንደሚመጣ ያሰረዳሉ፡፡
በሌላ በኩል አልደርሰን (2003) ማንበብ ከተፃፈ ጹሁፍ ላይ መረጃ መውሰድ ብቻ ነው ብሎ ወስኖ ማስቀመጥ
ያስቸግራል፡፡ ይኽውም አንድ አንባቢ የሚያነበው ለተለያየ አላማ በመሆኑ ከአላማው አንፃርም የተለያዩ ውህድ
ክሂሎችንና ብልሀቶችን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ሰለዚህ ንባብ ለእውቀት (ለመረዳት) ተብሎ ብቻ የሚተገበር ሳይሆን እንደ
አንባቢው አላማ ለተለያዩ ተግባራት የሚፈፀም በመሆኑ በውስጡ ሌሎች ንዑሳን ክሂሎችን አካቶ የያዘ ክሂል ነው
በማለት ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ኒልሰን (1963) ንባብ በየእለቱ በሚደረግ ተከታታይነት ያለው ልምምድ እያደገና
እየጎለበተ የሚመጣ ክሂል መሆኑን ገልፀው ለተማሪዎች ያለውን ጠቀሜታ ሲያስረዱ ንባብ በተማሪዎች ውጤት ላይ
በየጊዜው የሚታይ የራሱ አሻራ ያለው የቋንቋ ክህሎት ነውይላሉ፡፡ እንደስሚዝ (1978)፣ ኑናን (1982) እና ኮንሌፍ
(1992) አገላለጽ ደግሞ፣ ማንበብ ማለት ደራሲው ለተደራሲው ሊያስተላልፍ የፈለገውን መልዕክት የመረዳት ሂደት
ነው፡፡ በሌላ በኩል ንባብ የደራሲውና የአንባቢው የሁለት ወገን ግንኙነት እንደሆነና ግንኙነቱም ቀስ በቀስ እያደገ
እንደሚሄድ ሚች (1997) ይገልጻሉ፡፡ ብራነስ (1984) የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለሁለተኛ ቋንቋም
ሆነ ለአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት አስፈላጊና ወሳኝ እንደሆነ ያሰረዳሉ፡፡ ኦሁሹ አችዋ (2014) በበኩላቸው የማንበብ
ልምድ ተማሪዎች ፊደል መቁጠር ከሚጀምሩበት ጊዜ ጀምሮ እየሰፋና እየጎለበተ የሚመጣ ችሎታ እንደሆነና ተማሪዎች
አንድን ርዕሰ ጉዳይ ወይም የትምህርት ይዘት አንብበው ከተረዱ በኋላ ለመመለስ፣ አካባቢያቸውን ተረድተው እንዲኖሩ፣
የእውቀት አድማሳቸው እንዲሰፋ ከክፍል ወደ ክፍል እንዲዘዋወሩ ለማድረግ ቁልፍ ሚና የሚጫዎት፡፡ የተማሪዎችን
የትምህርት ውጤት በመወሰን በኩልም ትልቅ ሚና ያለው እንደሆነ ያሰረዳሉ፡፡ በመሆኑም አንብቦ የመረዳት ችሎታ
ለአንድ ለተወሰነ የክፍል ደረጃ የሚዘጋጅ ንባብን በክፍል ደረጃው የተመደቡ ተማሪዎች ያለምንም ችግር ማንበብና
የምንባቡን ሀሳብ መረዳት መቻልን ያመለክታል፡፡ በድሉ(1988) ጋሪሌት (1981)ን በመጥቀስ እንደገለፁት አንድን ምንባብ
መረዳት ማለት ምንባቡ የያዘውን አስፈላጊ መረጃ በሚቻለው መጠን መገንዘብ ነው፡፡ በምንባቡ ውስጥ ተፈላጊውን
መረጃ የመገንዘብ ሂደት የተለያየ ሲሆን ልዩነቱ የሚመነጨው ከሚነበበው የጹሑፍ ይዘት ፣ ከሚነበብበት አላማና
ከማንበቢያ ዘዴው የተነሳ ነው፡፡ ሃይማኖት (በ 2005) ለሁለተኛ ድግሪ መመረቂያ በሰራችው ጥናት ተማሪዎች በክፍል
ውስጥ ከሚሰጧቸው ምንባቦች በተጨማሪ በሕይዎት ዘመናቸው ሊያውቋቸውና ሊረዷቸው የሚፈልጉ የምርምር
ስራዎችንም ጭምር ሊያስቡ የሚችሉት በቀደመ የማንበብ ልምዳቸውና አረዳዳቸው ነው በማለት ገልፃለች፡፡
በመሆኑም አንድን ርእሰ ጉዳይ በውል ለመረዳት ማንበብና የማንበብ ልምድን ማዳበር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አያይዛ
ታስረዳለች፡፡ ግሪን (2001) በበኩላቸው የማንበብ ልምድ የሰው ልጆችን አዕምሮ ሚዛናዊ በማድረግ አንባቢዎች
በሕይዎት ዘመናቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል በማለት ይገልፃሉ፡፡ ባሸርናማቶ (2012) ፓላኒ (2012)ን በመጥቀስ
የማንበብ ልምድ ተማሪዎች ለወደፊቱ የሰነጽሁፍ ጸሐፊዎች እንዲሆኑ ከማድርጉም በላይ አንባቢዎች በመረጃ
ተመስርተው የተደራጀ ሀሳብ እንዲይዙና እንዲያፈልቁ ይረዳቸዋል ይላሉ፡፡ ምሁራኑ አያይዘውም የማንበብ ልምድና
አንብቦ የመረዳት ችሎታ አብዛኛውን ጊዜ የማይለያዩ ሲሆን የማንበብ ልምድ ያላቸው ተማሪዎች በትምህርታቸውም
ውጤታማ ሲሆኑ የማንበብ ልምድ የሌላቸው ተማሪዎች በትምህርታቸው የሚያሰመዘግቡት ወጤትም ዝቅተኛ መሆኑ
የተለመደ እንደሆነ ያሰረዳሉ፡፡ ግርሃም (1987) ተማሪዎች በትምህርት አለም የተሻለ ውጤት አስመዝግበው ለመቀጠል
ከሚያስችሏቸው የትምህርት ሂደቶች ውስጥ የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ዋናው ነው ይላሉ::

ኒልስን (1984) እና ሃይላንድ (1990) በበኩላቸው ስለማንበብ ልምድ ሲያሰረዱ የማንበብ ልምድና አንብቦ
የመረዳት ችሎታ ከሌሎቹ ችሎታዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም በትምህርት አለም ያሉ ሰዎች
በየእለቱ ከሚነበቡ በርካታ ነገሮች ጋር የመገናኘት ዕድል አላቸው፡፡ ነገር ግን የማንበብ ልምዳቸውና አንብቦ የመረዳት
ችሎታቸው በአግባቡ ከጽሁፎች ተገቢውን እውቀት ለመቅሰም ያስችላቸዋል ለማለት አያስደፍርም ይላሉ፡፡ ቪክቶሪያ
እና ሌሎች (1989) በትምህርት ቤትም ይሁን ከትምህርት ቤት ውጪ ትምህርት የሚገኘው ተማሪዎች ባላቸው
የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ መጠን ነው፡፡ እውቀታቸውም የሚጐለብተው በጽሁፍ በቀረበ ሃሳብ
አማካኝነት ነው፡፡ የትምህርቱም ዋና ግብ ተማሪዎች ከንባብ በቂ የሆነሃሳብና መረጃ እንዲያገኙ መርዳት ነው፡፡
በመሆኑም በመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በንባብ ፕሮግራም ለተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ
የመረዳት ችሎታ ማደግ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ይላሉ፡፡ ምክንያቱም በአብዛኛው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ
ተማሪዎች እውቀትን የሚያገኙት በማንበብ አማካኝነት ነው፡፡ ውጤታማ የሆነ የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያላቸው
ተማሪዎች በማንበብ ሂደት መሠረታቸውን የሚጥሉት አንብቦ ለመረዳት በሚያደርጉት ጥረት፣ በንባብ ዳራቸውና
ሃሳቡን ከቀዳሚ እውቀታቸው ጋር በማዛመድ ነው (አርምብሩስተር፣ አንደርሰን፣ አስታርግ 1987፣ ቪክቶሪያ እና ሌሎች
1989፣ ካሬል 1984፣ ኤጅ 1994፣ ናታል 1996)፡፡ ይሁንና ኮንለይ (1992) እና ዳይሞክስ (2007) እንደሚያስረዱት
ዘወትር እንደሚታየው ተማሪዎች ከንባብ ጋር ሳይተዋወቁ፣ የማንበብ ልምድ አናሳ በሆነበትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ
ሳይኖራቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡ በመሆኑም በርካታ ተማሪዎች የማንበብ ልምዳቸውና
አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ደካማ ነው፡፡ የዳበረ አንብቦ የመረዳት ችሎታና ልምድ ስለሌላቸው የሚያነቡትን ምንባብ
በሰፊው እንዳይመለከቱ ከማድረግ ባለፈ በትምህርት ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል ይላሉ፡፡ ከዚህ ጋር
በተያያዘ ቤንትዝ (1997) በአንብቦ መረዳት ዙሪያ ከመቶ በላይ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ የሚያስተምሩ 6 መምህራንን
ጠይቀው በሰበሰቡት መረጃ መሠረት ሁሉም መምህራን የተማሪዎቻቸው አንብቦ የመረዳት ችሎታ ያልዳበረ መሆኑን
መግለፃቸውን በጥናታቸው አመላክተዋል፡፡ አርምቢስተርና ሊሎች (1987፣1989) በሁለተኛ ደረጃ ያሉ ተማሪዎች ብዙ
ጊዜ የሚገጥማቸው ችግር ለትምህርት የሚቀርቡ ጽሁፎችን አንብቦ መረዳት አለመቻል ነው፡፡ ችግሮቹ በየትኛውም
ጊዜ እና ቦታ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ጽሁፉን ካነበቡ በኋላ ጠቃሚ ነጥቦችን የመለየት ዋናውን ሃሳብ የማውጣትና
የማጠቃለያ ሃሳብን የመጻፍ ችግሮች ይገጥማቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጽሁፍ ውስጥ ስላለው ሃሳብ የቀደመ እውቀት
አለመኖር፣ ፍላጐት ማጣት፣ አለመነሳሳት በጥቅሉ የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው አናሳ የመሆን
ችግሮች ይታይባቸዋል፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የዳበረ የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ አለመኖር
እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

1.2 የጥናቱ ችግር


ባለፉት ጥቂት አመታት የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለማሳደግ በተመራማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ፍላጐት እያደገ
በመምጣቱ ተማሪዎች ንግግራዊም ይሁን ጽሁፋዊ ሃሳብን ለመረዳት ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን ለማወቅ
ተመራማሪዎች ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ በዘርፉ ምርምር እያደረጉ የሚገኙ ተመራማሪዎችን (ለምሳሌ፣ ሊናና
ካሪም፣ 2007፤ ግራቢስ፣ ሊበርግና ኩኪ፣ 1983፤ ናንሲ፣ 1989፤ ክርስቲናና ጆናታን፣ 2011)ን መጥቀስ ይቻላል፡፡
እንደተመራማሪዎቹ ጥናት የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታን ለማጐልበት የሚረዱ ወቅታዊ የማስተማር
ዘዴዎችን በተግባር ላይ በማዋል የተማሪዎችን የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታን ማጐልበት ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ በትምህርት ቤት ብቻ ተወስኖ የሚቀር ባለመሆኑ በማንኛውም
ጊዜ እና ቦታ የማንበብ አቅም የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ስልቶችን ተጠቅሞ ማንበብ ከእያንዳንዱ አንባቢ እንደሚጠበቅ
ባድራዊ (1992) ያብራራሉ፡፡ በሌላ በኩል የተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ እንዳያድግ ተጽዕኖ
ከሚያሳድሩ ምክንያቶች መካከል ተማሪዎች የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀንን የመጠቀም ልምዳቸው እየሰፋ መምጣቱ
እንደሆነ (ፓላሲን፣ 2012) ያሰረዳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከመረጃ መረብ እድገቱ ጋር በተያያዘ በሞባይል የሚደረጉ
ምልልሶች፣ የፌስቡክ፣ ቲዩተርና የመሳሰሉት ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሀን የሚሰጧቸው አገልግሎቶች የተማሪዎችን
ስነልቦና የሚስቡና የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች የሚቀርቡበት በመሆኑ ተማሪዎች ጥልቅ ንባብ እንዳያነቡና የሚያነቡትን ነገር
እንዳይረዱ አድርገዋቸዋል በማለት ፓላሲ (2012)ን ይገልጻሉ ፡፡ ኢሳብ (2012) በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ ያሉ ተማሪዎች
አንብቦ ከመረዳት ይልቅ በቴሌቨዝን የሚተላለፉ ፊልሞችን በጆሮ ተሰክተው የሚደመጡ ሙዚቃዎችን (ዘፈኖችን) እና
ወቅታዊ መዝናናትን የሚሰጡ የተለያዩ ጨዋታዎችን የሚመርጡና ለሌሎች የማንበብ ተግባራት ደንታ የሌላቸው
እንደሆኑ በጥናታቸው ገልዋል፡፡ ለተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው መዳከም ምክንያት
እንደሆኑ በውጭ ጥናቶች ላይ የተጠቀሱ የጥናት ውጤቶች የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀንና እና ድህረ ገጾች እንደሆኑ
ተመላክቷል፡፡ ይህም በሀገራችን ባሉ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ ችግር
እንደሆነ አሁን አሁን የሚስተዋል ሆኖአል፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አንብቦ የመረዳት ችሎታ አስቸጋሪ የሚሆነው
በተጠቀሱት ወቅታዊ የማንበብ ልምድ በሚቀንሱ ምክንያቶች ብቻ ሳይሆን ተማሪዎች የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ዝቅ
አድርገው ስለሚመለከቱና ጊዜ ሰጥተውም ስለማያነቡት እንደሆነ በሀገር ውስጥ ከዚህ የጥናት ርዕስ ጋር በከፊል
በሚዛመዱ ጥናቶች ተመላክቷል፡፡ ለአብነትም የተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ
ሀሰን (2004) ያጠኑት ጥናት ውጤት እንደሚያመለክተው የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ
የላቸውም፡፡ የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት አንብቦ መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ጉልህ ድርሻም የለውም፤
የሚል ሲሆን ለዚህም ሀሰን በምክኒያትነት የሚጠቅሱት የአንብቦ መረዳት ችሎታ እንዳይጎለብት የሚያደርጉት
ምክንያቶች አዎንታዊ የማንበብ አመለካከት እንዲዳብር ትኩረት ባለመሰጠቱ መምህራን የበርካታ ተማሪዎቻቸውን
የማንበብ አመለካከትና ዝንባሌ ግምት ውስጥ ሳያስገቡ የዕለት ከዕለት ተግባራቸውን መከናዎናቸው እንዲሁም ወላጆች
ማንበብን የትርፍ ጊዜ ተግባር አድርገው መቁጠራቸው እንደሆኑ በጥናታቸው ገልፀዋል፡፡ ዘላለም (2010) በበኩላቸው
ባደረጉት ጥናት የተማሪዎች የማንበብ ልምድ፣ አመለካከትና ምርጫን ቃኝተዋል በጥናቱ ውጤት ግኝት መሰረት
የተማሪዎች የማንበብ ልምድ ጥሩ ሆኖ አልተገኘም፡፡ የማንበብ አመለካከታቸው አዎንታዊ ነው፡፡ ከወንዶች ይልቅ
የሴቶች የማንበብ አመለካከት የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ደምሰው(1995) የመማሪያ መጻህፍት ምንባቦች የተማሪዎችን
የማንበብ ፍላጎት ለመያዝ ያላቸውን ብቃት በሚመለከት ጥናት ያጠኑ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መሰረት የማንበብ ፍላጎት
ምንባብን ለማንበብ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው፣ በመማሪያ መጽሀፍ ውስጥ ያሉት ምንባቦች የተማሪዎችን ፈላጎት
ለመያዝ አቅም ያላቸው መሆናቸውንና ምንባቦቹ በአብዛኛው በፍላጎት ላይ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ መስፈርቶች አንጻር
በአመዛኙ ሰኬታማ ለመሆን የቻሉ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡ ገደፋው (1993) ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን ለመማር ያላቸው
ተነሳሽነትና የትምህርት ውጤት ተዛምዶ የመረመሩ ሲሆን፣ ውጤት እንደተመላከተው ፍላጎትና የትምህርት ውጤት
ተዛምዶ አላቸው ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን ለመማር ያላቸው ፍላጎትና ተነሳሽነት ከፍ ሲል የትምህርት ውጤታቸው
ከፍተኛ ሆኗል በተቃራኒው ፍላጎታቸው ሲቀንስ የትምህርት ውጤታቸውም ዝቅ ብሎአል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ
በመማሪያ መፃህፍቱ ውስጥ የተካተቱት ምንባቦች የተማሪዎችን ፍላጎት መሰረት አለማድረጋቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል
ደግሞ የመማር ፍላጎት ከቀነሰ የትምህርት ውጤቱ እንደሚቀንስ በጥናቱ ተረጋግጦአል፡፡ ሌላው በውጭ አገር
የተማሪዎች የማንበብ ልምድ በተማሪዎች የትምህርት ውጤት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመመርመር በጋና በሚገኝ
አንድ የፖሊቴክኒክ የትምህርት ኮሌጅ በሚካኤል ኦሁሹ አችዋ (2014) በተጠና ጥናት የጥናቱ ተተኳሪ ከሆኑ ተጠኝዎች
መካካል 75 በመቶ የሚሆኑት የሚያነቡት ፈተና ለማለፍ ብቻ ሲሆን ወደ ቤተመጽሀፍት ከመጡ 62 በመቶ የሚሆኑት
በትምህርት ጊዜ የያዙትን ማሰታዎሻ ለማንበብ ፣25 በመቶ የሚሆኑት የመማሪያ መፃህፍታቸውን ለማንበብ የገቡ ሲሆን
3 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ልቦለድ ለማንብብ እንደገቡ ጥናቱ አረጋግጧአል፡፡ የዚህን ጥናት መጠይቅ የሞሉ አብዛኛዎቹ
ተተኳሪዎች በሰጡት መረጃ የማንበብ ልምድ ከትምህርት ውጤታማነት ጋርና የትምህርት ውጤታማነት ከማንበብ
ልምድ ጋር በቀጥታ እንደሚገናኙ ጥናቱ አረጋግጧአል፡፡ ተማሪዎች ያላቸውን አጠቃላይ የማንበብ ልምድና አንብቦ
የመረዳት ችሎታን አስመልክቶ ቤንጃሚን (2010) የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የማንበብ ልምድ በሚል ጥናታዊ ጹሑፍ
በአማራ ክልል 49 ፐርሰንት ያክሉ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎችና አንድ ሶስተኛው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች
የሚያነቡትን ፁሁፍ ለመረዳት ይቸገራሉ ይላል፡፡የዚህ ጥናት አቅራቢም በትምህርት ቤት ቆይታዋና ከስራ ልምዴ
የታዘብኩትመምህራን ለተማሪዎች የንባብ ልምዳቸውን የሚያዳብሩ ተግባራት በማይሰጡበት፣ ተማሪዎችም የማንበብ
ተግባራትን በማይከውኑበት ሁኔታ ተማሪዎች ከክፍል ክፍል ሲዛወሩ ይታያል በተጨማሪም አጥኝዋ ከመምህራንና
ከተማሪዎች ጋር ባደረገቸው ኢመደበኛ ውይይት በአሁኑ ጊዜ የተማሪዎች የማንበብ ልምድና በደረጃቸው የቀረበውን
ንባብ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ይህ ነው፤ ብሎ ወጥ የሆነ ደረጃ ማሰቀመጥ እንደማይቻል፣የተማሪዎች የማንበብ
ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ አንዴ የመውጣት አንዴ የመውረድ ችግር እንዳለበት ተገንዘባለች፡፡ በመሆኑም
ተማሪዎች በማንበብ ልምድና አንብቦ በመረዳት ችሎታቸው መካከል ያለውን ዝምድና በመመርመር የተማሪዎችን
የንባብ ልምድ መዳበርና ከማንበብ የሚገኘውን ሙሉ የሆነ እውቀት ለተማሪዎች መሰጠት የሚቻልበትን ስራ ለመሰራት
የተጨበጠ መረጃ ሰለሚያሰፈልግ ነው፡፡ በመሆኑም በሁለተኛ ደረጃ በሚገኙ ተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ
የመረዳት ችሎታቸው መካከል ያለውን ዝምድና ለመመርመር ጥናትና ምርምር ማድረግ ያሰፈልጋል፡፡ ከላይ ከዚህ የጥናት
ዓላማ ጋር በከፊል የሚዛመዱ ጥናቶችን ብንመለከትም፣ ሁሉም አጥኝዎች ግን በአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድና
በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል የለውን ተዛምዶ አልተመለከቱም፡፡ መሐመድ (1992) የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች
የአማርኛ ቋንቋ ለመማር ባላቸው አመለካከት ላይ ባደረጉት ጥናት የተማሪዎቹ አመለካከት አወንታዊ መሆኑን
አረጋግጠዋል፡፡ ለዚህም በምክንያትነት የተጠቀሱት (በተማሪዎች የመማር አመለካከት ላይ ተፅዕኖ የሚያስከትሉ
ጉዳዬች) ቤተሰብ፣ ማህበረሰብ፣ የመምህራን የማስተማር ዕውቀትና ዘዴ፣ የተማሪዎቹ ግላዊ ችሎታና የመማሪያ
መፃህፍት ተፅዕኖ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ታዛሽ (1992) የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ
አጥንተዋል፡፡ በጥናቱም የተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ምን ያህል እንደሚመሳሰልና በአንድ የክፍል ደረጃ ላይ
የሚገኙ ተማሪዎች በደረጃቸው የሚጠበቅባቸው የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያላቸው መሆንና አለመሆኑን መርምረዋል፡፡
በትንተናው ውጤት መሰረትም ተማሪዎች መካከለኛ የሆነ አንብቦ የመረዳት ችሎታ ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም ተማሪዎቹ በደረጃቸው የሚጠበቅባቸውን የአንብቦ መረዳት ችሎታ አካብተው ያልተገኙ ሲሆን፣ ለዚህም
ምክንያቱ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን ለማጎልበት የሚያግዝ በቂ የሆነ ትምህርት ስለማይሰጣቸው
ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ በተለያዩ ተለዋዋጮች አማካኝነት የማንበብ አመለካከትን በሚመለከት ከተለያዩ ጉዳዮች ጋር


በማዛመድ የተደረጉ ጥናቶችም አሉ (ደምሰው 1995፣ ገደፋው 1993)፡፡ ደምሰው (1995) የመማሪያ መፅሐፍ ምንባቦች
የተማሪዎችን የማንበብ ፍላጎት ለመያዝ ያላቸውን ብቃት በሚመለከት አጥንተዋል፡፡ በጥናቱ ውጤት መሰረት የማንበብ
ፍላጎት ምንባብን ለማንበብ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ ተማሪዎች በመማሪያ መጽሐፍ ውስጥ ላሉት ምንባቦች ፍላጎት
አላቸው፡፡ የመማሪያ መፀሐፉ ምንባቦች የተማሪዎቹን ፍላጎት የመያዝ አቅም አላቸው፡፡ በተጨማሪም ምንባቦቹ
በአብዛኛው በፍላጎት ላይ ተፅእኖ ከሚያሳድሩ መስፈርቶች አንፃር በአመዛኙ ስኬታማ ለመሆን የቻሉ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር እንደቀረበው በውጭ ሐገር በተደረጉት ጥናቶች በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና አንብቦ
የመረዳት ችሎታ መካከል ልዩነቱን ያመላከቱ የመኖራቸውን ያህል፣ ተዛምዶ አለመኖሩንም ያሳዩ አሉ፡፡ አንዳንዶቹ
ተመራማሪዎች በጥናታቸው የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታን ተዛምዶ ከተፈጥሮ፣ ከአካባቢ፣ ከፆታና
ከትምህርት ደረጃ ጋር ለማዛመድ ሞክረዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ከማንበብ ውጤትና ከማንበብ ብቃት ጋር እያገናኙ
ዝምድናውን ፈትሸዋል፡፡ ለምሳሌ ዱቢንና ዞርካኢያ (2010)፣ ሊን (2010)፣ ያኮቭ (2010)፣ ኩሽና ዋትኪንስ (1996)፣
ዌብ (2009) መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም በሐገር ውስጥ ጥናቶች የታየው ክፍተት የማንበብ አመለካከት ከሌሎች
ተለዋዋጮች ጋር እየተመሳከረ አልተጠናም፣ አመለካከትን ብቻውን ወይም አንብቦ የመረዳት ችሎታን በአንድ አቅጣጫ
ብቻ በመመልከት የተሰሩ ጥናቶች ናቸው፣ አንዳንዶቹ ጥናቶች ደግሞ በማንበብ ፍላጎትና በመማሪያ መፀሐፍ የንባብ
ችሎታን ከተነሳሽነት ጋር እያዛመዱ አጥንተዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ የተማሪዎችን የማንበብ አመለካከት ከማንበብ
ምርጫቸውና ከማንበብ ልምዳቸው ጋር በማነፃፀር ብቻ ቃኝተዋል፡፡ ለዚህም የሐሰን (2004)፣ የመሐመድ (1992) እና
የታፈረ (2000) የዘላለም (2010) ጥናትን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚህም መሰረትየሁለተኛ ደረጃ
ተማሪዎችንበአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ ማጥናቱ አስፈላጊ በመሆኑና
ጥቅሙም የጎላ ሰለሆነ ጥናቱን በዳባት በሚገነኝ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማጥናት አጥኝዋን ከላይ
የተገለጹት ምክንያቶች አነሳስተዋታል፡፡ ጥናቱ የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድና አንብቦ 11
በመረዳት ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ የሚመረምር ሲሆን ጥናቱ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ይሞክራል ፡፡

1. በተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ተዛምዶ አለ? 2. የተማሪዎች የማንበብ
ልምድ የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ድርሻው ምን ያህል ነው?
3. በተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት ያሳያለል?

1.3 የጥናቱ ዓላማ


የዚህ ጥናት ዋና አላማ በተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር
ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጥናቱ የሚከተሉት ዝርዝር አላማዎች አሉት፡፡

1. በተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ተዛምዶ መኖር አለመኖሩን መመርመር፤
2. የተማሪዎች የማንበብ ልምድ የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ድርሻው ምን ያህል እንደሆነ መላከት፣
3. በተማሪዎች የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት እንዳለው መመርመር
የሚሉ ናቸው፡፡
1.4 የጥናቱ አስፈላጊነት
ይህ ጥናት በተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ የሚያተኩር
በመሆኑ ከጥናቱ የሚገኘው ውጤት ለመምህራን፣ ለተማሪዎች እና ለስርዓተ ትምህርት አዘጋጆች የሚከተሉት
ጠቀሜታዎች ያስገኛል ተብሎ ይታመናል፤

1. ለመምህራንና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ
ምን እንደሚመስል መረጃ ይሰጣል ፡፡ 2. በአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች የማንበብ
ልምድበአንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ላይ ይተነብይ እንደሆን ፍንጭ በመስጠት የቋንቋ ትምህርቱ በተማሪዎች
የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ እንዲያተኩር ያደርጋል፡፡
3. የተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድ በአንብቦ መረዳት ችሎታቸውላይ ያለውን ጠቀሜታ ያመላክታል፡፡
የተማሪዎች የማንበብ ልምድ በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ያለውን የትንበያ መጠን ለመገንዘብ ስለሚያስችል፤ ይህንን
መሠረት በማድረግ የመማሪያ ክፍል የትምህርት አቀራረብ የማንበብ ልምድን እንዲሚያጎለብት መምህራን
እንዲገነዘቡት ያደርጋል፡፡ 4. በተማሪዎች የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ
መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት እንዳለውና እንደሌለው ስለሚያሳይ ወላጆች የልጆቻቸውን የማንበብ ልምድ
አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን በመገንዘብ ለችግሮቻቸው ከመምህራን ጋር በመተባበር መፍትሄ እንዲፈልጉ ያግዛል፡፡
5. የትምህርት ባለሙያዎች በጥናቱ ግኝቶች መረጃ መሠረት የተማሪዎችን የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት
ችሎታን በመገንዘብ መምህራን የትምህርት ዕቅድ፣ መርሐትምህርትና የንባብ ትምህርት መርሐግብር ሲያዘጋጁ
የተማሪዎቹን የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ከማጎልበት አንፃር እንዲመለከቱት ይረዳቸዋል፡፡

1.5 የጥናቱ ወሰን


ጥናቱ በ ሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ በዳባት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙ በ 2010 ዓ.ም የሚማሩ
የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎችን ብቻ ትኩርት አድርጓል። ጥናቱም በማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት መካከል ያለውን
ተዛምዶ የሚመረምር ነው።

1.6 የጥናቱ ውስንነት


ጥናቱ የተማሪዎችን የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ የሚመረምር ነው፡፡ በመሆኑም
ጥናቱ በዳባት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ ተተኳሪ በማድረጉ ጥናቱን በአንጻራዊነት ውስንነት
እንዲኖረው ያደርጋል፤ በተጨማሪም ተዛምዶን እንጅ የክፍል ውስጥ ክንውን ስለማያሳይ ውስንነት ይኖርበታል፡፡

1.7 የቁልፍ የፅንሰ ሃሳቦች አጠቃቀም ተግባራዊ ብያኔ


የጥናቱ ቁልፍ ቃላት የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ሲሆኑ፣ አጠቃቀማቸውም ቀጥሎ በቀረበው
ብያኔ መሠረት ነው፡፡ የማንበብ ልምድ፤ ተማሪዎች ፊደል መቁጠር ከሚጀምሩበት ጊዜ ጀምሮ እየሰፋና እየጎለበተ
የሚመጣ ችሎታ ሲሆን፣ አንድን ርእሰጉዳይ ወይም የትምህርት ይዘት አንብበው ከተረዱ በኋላ ለመመለስ፣
አካባቢያቸውን ተረድተው እንዲኖሩ፣ የእውቀት አድማሳቸው እንዲሰፋ የሚያድርግ ነው፡፡ አንድን ውህድአሃድ
በሚያነቡበት ወቅት ተፈላጊውን መልእክት እንዲረዱ የሚያደርግ ቀዳሚ የንባብ እውቀት ሲሆን፣ ተማሪዎች ከዚህ
በፊት ያካባቱትና ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ለንባብ ስራቸው መሰረታዊ የሆነ እውቀት ነው፡፡ ተማሪዎች ሰለቀረበላቸው
ውህድአሃድ ወይም የቋንቋ አወቃቀርና ይዘት ከትምርት ቤት ውጭም ሆነ በትምህርት ቤት ውስጥ እውቀት
የሚያገኙበት መንገድ ነው፡፡ ይህም በፅሁፍ መጠይቅ ተፈትሿል፡፡ የአንብቦ መረዳት ችሎታ፤ የአንብቦ መረዳት ችሎታ፤
የአንብቦ መረዳት ችሎታ (Reading comprhansion ability)፣ የምንባቡን ጥቅል መልእክት መረዳትን፣ ከፅሁፍ
ቀጥተኛና ኢቀጥተኛ መረጃዎችን መለየትን፣ አንድምታዊ ሀሳቦችን የመገንዘብ ችሎታ ድምር ውጤት ሲሆን፣
ተመራማሪዋ በምታዘጋጀው አንብቦ የመረዳት ፈተና ተፈትሿል፡፡ ተዛምዶ (correlation(correlation)፤ በተማዎች
የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው መካከል የሚኖርን አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ግንኙነት ይመለከታል፡፡

ምዕራፍ ሁለት
ክለሳ ድርሳናት

2.1 የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ


የማንበብ ልምድ ተማሪዎች ፊደል መቁጠር ከሚጀምሩበት ጊዜ ጀምሮ እየሰፋና አየጎለበተ የሚመጣ ችሎታ
ነው፡፡ የማንበብ ልምድ ተማሪዎች አንድን ርእሰ ጉዳይ ወይም የትምህርት ይዘት አንብበው ከተረዱ በኋላ ለመመለስ፣
አካባቢያቸውን ተረድተው እንዲኖሩ፣ የእውቀት አድማሳቸው እንዲሰፋ ከክፍል ወደ ክፍል እንዲዘዋዋሩ ለማድረግ ቁልፍ
ሚና ይጫዋታል፡፡ የተማሪዎችን ውጤት በመወሰን በኩልም ትልቅ ሚና አለው በማለት ያስረዳሉ (አችዋ፣ 2014)፡፡
የማንበብ ልምድ አንባቢያን አንድን ምንባብ በሚያነቡበት ወቅት ተፈላጊውን መልእክት እንዲረዱ የሚያደርግ ቀዳሚ
የንባብ እውቀት ነው፡፡ እንደሄጅ (1990) እና እስትሮንግማንና ሆል (2004) ማብራሪያ የማንበብ ልምድ በንባብ ሂደት
የምንባቡን ዋና ሀሳብ ለማወቅ የሚያስችል የተማሪዎች የቆየ ከልምድ የተገኘ እውቀት ነው፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች
የተደራጁ ግንኙነቶች ያላቸውን ፅንሰ ሀሳቦች ያሰባሰበ ረዥም ጊዜ የተከማቸ ዕውቀት ሊባልም እንደሚችል ጨምረው
ያሰረዳሉ፡፡ ኮንለይ (1992) በበኩላቸው የንባብ ልምድ ተማሪዎች ከዚህ በፊት ያካባቱትና ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ
ለንባብ ስራቸው መሰረታዊ የሆነ እውቀት የሚሰጥ ነው፡፡ ተማሪዎች ሰለቀረበላቸው ቴክስት ወይም የቋንቋ አወቃቀርና
ይዘት ከትምርት ቤት ውጭም ሆነ በትምህርት ቤት ውስጥ እውቀት የሚያገኙት ከንባብ ልምድ እንደሆነ ያስገነዝባሉ፡፡
ይህም የተማሪዎች ህይዎት ውጤታማ በሆነ መንገድ ወደሚፈለገው ግብ እንዲያመራ ለተማሪዎች ቀጣይና ዘላቂ የሆኑ
ስልቶችን የሚያዳብሩ መልመጃዎች ሊዘጋጁ እንደሚጋባ ያሳስባሉ፡፡ ዋልከር (1988) የተማሪዎች የንባብ ልምድ ወይም
የቀደመ እውቀት ከሚያነቡት ፅሁፍ የሚያገኙትን ሀሳብ የሚረዱበት፣ ለቃላት ተስማሚ ትርጉም የሚሰጡበት ትልቅ
ቅርስ፣ አንብቦ የመረዳት ችሎታን የሚያፋጥንና የሚያጠናክር አቅም እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ ርዕስ ጉዳዮችን
ለመረዳት እና ተጠየቃዊ አካሂድን ለመከተል አጋዥ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

በአንድ ጉዳይ ዙሪያ የቀደመ የንባብ ዳራ፣ ግንዛቤ፣ ዕውቀት፣ ወ.ዘ.ተ. መኖር ያለው ጠቀሜታ በቀላል የሚገመት
አይደለም፡፡ ተማሪዎች ሰለሚያነቡት ቴክስት የቆየ የንባብ ልምድ ሲኖራቸው በቀላሉ አንብበው መረዳት ይችላሉ፡፡
በመሆኑም አንድን ምንባብ ውጤታማ በሆነ መልኩ አንብቦ ለመረዳት የንባብ ልምድን መጠቀም ግድ ይላል፡፡ ለዚህም
ሲልበስትሪንና(1994) እና ኡር (1999) ተማሪዎች በሚያነቡበት ወቅት የሚያነቡት ቴክስት ከአሁን በፊት የሚያውቁት
ከሆነ ያለምንም ድካም በቀላሉ ሊረዱት ይችላሉ፡፡ይህም እውቀት በተለያየ መንገድ ለምሳሌ በመምህራን፣ በወላጅ፣
በመማሪያ ቴክስቶች እና በተማሪዎች የማንበብ ልምድ ሊገኝ እንደሚችል ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ካሬ (1983)
ያስገነዝባሉ፡፡ የንባብ ልምድ በተማሪዎች ኑሮ ደረጃ የተለያየ ከሆነ አንብቦ የመረዳት ችሎታም በዚያው መጠን ሊለያይ
ይችላል፡፡ ይህም ሲባል ሰለሚነበበው ቴክስትትንሽ እውቀት ካላቸው ተማሪዎች ወይም አንባቢያን ይልቅ ሰፊ የማንበብ
ልምድ ያላቸው ተማሪዎች ወይም አንባቢያን ቴክስቱን በተሻለ መልኩ ይረዳሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት ጆንሰን (2000) የንባብ
ልምድ ያለቸው ተማሪዎች የንባብ ልምድ ከሌላቸው ተማሪዎች በተሻለ የሚያነቡትን ቴክስት ይዘትና ቅንጅት መረዳት
እንደሚችሉ ያብራሩት፡፡ ይህን ሀሳብ ፍሎይድና ሌሎች (1987) ሁለት ምርምሮችን ሰርተው ባገኙት ውጤት የማንበብ
ልምድ ያላቸው ተማሪዎች የንባብ ልምድ ከሌላቸው ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀሩ የማንበብ ልምድ ያላቸው ተማሪዎች
ሰለሚነቡት ቴክስት በተሻለ ሁኔታ መረጃውን ለማጠናከር ለመተርጎምና ለመረዳት እንደቻሉ በጥናት ውጤታቸው
ታይቷል፡፡ ንባብ ውስብስብ ሂደት ሲሆን አንብቦ መረዳት ደግሞ አንዱ የንባብ ችሎታ መገለጫ ነው፡፡ የተለያዩ ምሁራን
በስነ ልቦና አንደ ብሉም(1963) እንዲሁም በቋንቋ ስነ ትምህርት መስክ የሚሰሩ እንደ ፐርፊት(1985) ያሉት አንብቦ
መረዳት አዕምሯዊ ሂደት መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ለምሳሌ በትምህርት አላማዎች አመዳደብ ብሉም(1963)፣ ቻለሀምና
ክላርክ(1988) አንብቦ መረዳት በአዕምሮታዊ ምድብ ከዕውቀት ቀጥሎ የሚመጣው ዋናው የአዕምሮታዊ
ክፍል(cognitive domains) መሆኑን ይገልፃሉ፡ ፕርፊት (1985) እንዲሁ ሲገልፅ ‹‹ንባብ የበርካታ አዕምሮታዊ ሂደት
ውጤት ነው፡፡ በተለይም አንብቦ መረዳት በአዕምሮታዊ ተግባር ውስጥ፣ ማንበብን የሚወሰነው በአንባቢው እውቀትና
የሚነበበውን ነገር ከመረዳት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ሲል፣ ቢችና ኮል(1987) ይህንን ሃሳብ ሲገልፁ ማንበብ፣ የተለያዩ ቃላትና
ሐረጋትን መገንዘብና መረዳትን ያካትታል፡፡ዋናው የጥሩ አንባቢ ችሎታ በቃላትመደበኛ ትርጉምና አግባባዊ ትርጉም
መካከል ያለውን ግንኙነት ከአሀዱ በመነሳት አስቦ መድረስ ወይም መረዳት 16 ነው፡፡ በሌላ በኩል ጋርሌት(1996)
እንደሚያብራሩት አንብቦ መረዳት ውህድአሃድ የያዘውን መልዕክት በአግባቡ መርምሮ መገንዘብ የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ
የሚያመለክት ነው፡፡ አንብቦ መረዳት ማለት በተቻለ መጠን በጽሁፉ ውስጥ ያለውን መረጃ በአግባቡ መገንዘብ መቻል
ማለት ነው፡፡ እንደፓንግና ሌሎች(2003) የምናነበው ነገር ማስታወቂያ፣ የጋዜጣ ርዕስ አንቀፅ፣ የሳይንሳዊ ጆርናል
መጣጥፍ ወዘተ.ሊሆን ይችላል፡፡ በመሆኑም አንድን ማስታወቂያ ማንበብና አንድን የሳይንስ ጆርናል መጣጥፍ ማንበብ
አላማው ይለያያል፡፡ይሁን እንጅ አንደ አላማው መለያየት ሁሉንም በተገቢው መንገድ አንብቦ ውጤታማ መረጃ ማግኘት
ወይም ግንዛቤ መውሰድ መቻል አንብቦ መረዳት ነው፡፡ ሌላው ከዚህ ጋር የምናየው አንደኛው ነገር ውጤታማ አንባቢ
በፍጥነት በማንበብ በአሀዱ ውስጥ ያለውን ጠቃሚውንና የማይጠቅመውን መረጃ ይለያል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ፣
ጠቃሚውን መለየት ብቻ በራሱ በቂ ስላልሆነ በጥልቀት ገብቶ በመመርመር ትልቅ ግንዛቤ ይወስዳል፡፡ ይህም አንብቦ
መረዳት ይባላል፤ በማለት ይገልፃሉ፡፡ አንቶኒና ሌሎች (2004) ማሶን(1984)ን ጠቅሰው እንደሚያስረዱት አንብቦ
መረዳት የአንባቢው በቴክስት መልክ የቀረበ መረጃን ከቀደመ እውቀቱ ጋር ውጤታማና ትርጉም አዘል በሆነ መልኩ
የማቀናጀት ችሎታ ነው፡፡ ኮንልን (1990) ጠቅሰው አንቶኒና ሌሎች (2004) እንደሚያሰረዱት አንብቦ መረዳት ቃላዊ
ከሆነ ክሂል በተፃራሪ መልኩ የቃላቱን ትርጉም የመረዳት፣ ከዳራዊ እውቀትና ተማሪው ከተማረው ትምህርት ጋር
የማያያዝ አይነት በርካታ ችሎታዎች ይጠይቃል፡፡ ጃኔትና ቤቲ (1988) ስፒሮ(1980)ን ጠቅሰው እንደሚገልፁት አንብቦ
መረዳት አንባቢው ያገኘውን አዲስ መረጃ በውስጡ ካለው ዳራዊ እውቀት ጋር እንዲያስተሳሰር የሚያግዘው ገንቢ
ተግባር ነው ተግባሩን እንዲያከናውን የሚያስችለው ደግሞ የማንበብ ልምዱ ነው፡፡ በአንብቦ መረዳት ሂደት የቃላት
ትርጉም እውቀት አረፍተ ነገርና የቴክስት መዋቅር እውቀት እንዲሁም የህይዎት ልምድ (ዳራዊ እውቀት) የየራሳቸው
አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ ዋግነር፣ መሴና ታነንቡዋ (2007) እንደሚያሰረዱትም አንብቦ መረዳት አንድ ሰው የሚያነበውን
ፅሁፍ የመተርጎምና የመረዳት ችሎታ ውጤት ነው፡፡ እንደፓንግና ሌሎች (2003) የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት
ችሎታ ተማሪዎች አካባቢያቸውን በሚገባ እንዲያውቁና ቀጣይ እድላቸውን እንዲተነብዪ በር ይከፍትላቸዋል፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ አዲስ እውቀት እንዲገበዩ፣ በሰነፅሁፍ ራሳቸውን እንዲያዝናኑና ከዘመናዊው ሕይዎት ጋር የተያያዙ የእለት
ከእለት ተግባራትን በልበ ሙሉነት እንዲፈፅሙ ያስችላቸዋል፡፡ ባለሙያዎቹ እንደሚያስረዱት ማንበብ በፁሁፍ የቀረበን
አሀድ መረዳት ነው፡፡ የማንበብ ኪሂል ውስጣዊ ግንዛቤን እና እሳቤን የሚጠይቅ ውስብስብ ተግባር ነው፡፡ ኪሂሉ ሁለት
የተያያዙ ሂደቶችን ቃላትን መለየትንና መረዳትን ያካትታል፡፡ቃላትን መለየት የሚባለው የፅሁፉ ወኪል የሆኑ ቃላት
እንዴት ከንግግር ቋንቋ ጋር እንደሚገናኙ መለየት ሂደት ሲሆን ቃላትን መረዳት ደግሞ ቃላቱ ስሜት እንዲሰጡ የማድረግ
ሂደት ነው ይህ ደግሞ በዳበረ የማንበብ ልምድ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡ አልደርሰን ናፒርሶንን (1988) ጠቅሶ ኮንለይ
(1992) እንደሚያብራሩት የማንበብ ልምድ አንብቦ ለመረዳት የተለያዩ ቅድመ እውቀቶች ከአዲሱ ንባብ ጋር
የሚዋሃዱበትን ሂደት የሚያፋጥን ነው፡፡ ይኸውም የተማሪው ቅድመ ዕውቀት፣የሚነበበው ነገር ዕውቀት (የርዕሰ ጉዳዩ
ዕውቀት)፣ ለቋንቋው ያለው ቀረቤታ፣ ስለርዕሰ ጉዳዩ ያለው አስተሳሰብና የሚነበበው ፅንሰ ሐሳብ አንድ ላይ
የሚገናኙበትን ሂደት ተግባራዊ ለማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም በማንበብ ልምድ የዳበረ አንብቦ የመረዳት
ችሎታ በርካታ ክሂሎችንና ዕውቀቶችን ባንድ ላይ በማዋሃድ አንድን ጹሁፍ ለመገንዘብም እንደሚያስችል ይገልጻሉ፡፡
በተመሳሳይ ሂትልማን(1988) ሲገልፁ፤ በንባብ ጊዜ መረዳት የሚባለው በአውድ ውስጥ ያሉትንና ከአውድ ውጭ ያሉትን
ተላውጦች መሰረት አድርጎ የቃላትንና የአርፍተ ነገርን ሃሳብ መገንዘብ መቻል ሲሆን፣ የሚነበበውን ቴክስት ፅንሰ ሐሳብ
ለማደራጀት፣ ለመተርጎምና ለማጠቃለል ልምድ ከፈተኛ ሚና አለው፡፡ በተጨማሪም አንብቦ መረዳት፣ ተማሪዎች
የሚያነቡትን ጽሁፍ ካላቸው ዕውቀትና ልምድ ጋር በማስተሳሰር በማደራጀት፣ በመተርጎምና በማጠቃለል እንዲሁም
ከደራሲው ሃሳብ ጋር በማዋሃድ የራሳቸውን ግላዊ ግንዘቤ የሚያጠናክሩበት(የሚፈጥሩበት) ክሂል ነው፡፡ ቢችና
ኮል(1987)፣ ሆሪባ(1996) እና ሻንግ (2000) በአጠቃላይ እንደሚስማሙበት አንብቦ መረዳት አንዱ ከሌላውጋር
የተዛመዱና ደረጃቸውን የጠበቁ በዙ አዕምሯታዊ ሂደቶች(multiple cognitive processes) ይካተቱበታል፡፡ ምሁራን
ይህንን ሃሳብ ሲያረጋግጡ አንብቦ መረዳት መረጃን በተለያየ መንገድ ማቀነባበርና መረዳት ይፈልጋል፡፡ ይህ መረጃን
የማቀነባበር ሂደት በአንባቢው የቀደመ የማንበብ ልምድ እያንዳንዱን ቃል ከመረዳት ጀምሮ በአንባቢው ዳራዊ እውቀት
መሰረት አወድፍችተኮር(ከምናነበው ፀሁፍ) ወይም አውድፍች ተኮር ያልሆነ(ከቅድመ ዕውቀታችን) ስርፀተ ሃሰብ
ተጠቅሞ አስከ መተርጎም የሚደርስ ሂደት በውስጡ ያካትታል፡፡ ስለዚህ በማንበብ ልምዳችን የታገዘ አንብቦ መረዳት
የተሰጠንን ጹሁፍ በማንበብ በግልፅ የቀረበውንና ያልቀረበውን መረጃ መረዳት የሚያስችል ነው በማለት ያብራራሉ፡፡
ይሁን እንጅ እንደሻንግ(2000) ገለጻየ ተወሰኑ ትምህርት ቤቶች አንብቦ መረዳትን የማስተማር የምንባቡ ላዕላይ መዋቅር
ላይ ብቻ ላይ የተመሰረተና ልምድን የዘነጋ በመሆኑ፣ አንባቢው ግልብ በሆነ መልኩ የጹሁፉን ላዕላይ ትርጉም ከማንበብ
በሰተቀር በደራሲው ወይም በጻሐፊው ሐሳብ ላይ የመመራመርና ከልምዱ ጋር የማስተሳሰር ክፍተት ይታይበታል፡፡
ይህም ልምዱን መሰረት አድረጎ በፅሁፉ ውስጥ ሊተላለፉ የተፈለጉትን ቀጥተኛና ተጓዳኝ መልዕከቶች የመተርጎም ስራ
ላይ ትኩረት አይሰጡም፡፡ በተለይእንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት የተማሪዎች የንባብ ልምዳቸውን ተጠቅሞ አንብቦ
መረዳትን የመማር ችግር መኖሩን አስረስ (2008) በጥናታቸው ጠቁመዋል፡፡ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን
የሚያጠናቅቁት የማንበብ ልምዳቸው ዝቅተኛ ሆኖና በክፍል ደረጃቸው ሰለንባብ የሚገባቸውን ያህል እውቀት ሰይዙ
በክፍል ደረጃቸው የቀረበውን ምንባብ ሀሳብ ለመረዳት፣ ለመተርጎምና ፀሀፊው ሊያስተላልፍ የፈለገውን ሀሳብ
ለመረዳት ተቸግረው እንደሆነ የአገር ውስጥ ጥናቶች (ለምሳሌ፣ ገደፈው፣ 1993፤ ሀሰን፣2004) ጠቁመዋል፡፡ እንደናታል
(1982) የተማሪዎችን የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታን ለመገምገም(ለመፈተን) የችሎታው
መገለጫዎችን በተለይም የንባብ ፍጥነትን በሚከተለውመንገድ መለካት ይቻላል፡፡ ፍጥነታቸውን ስንለካ የምንመርጠው
ምንባብ ለተማሪዎች እንግዳ የሆነና አስቸጋሪ መሆን የለበትም፤በመቀጠልም የተመረጠው ምንባብ የያዘውን የቃላት
ቁጥር መቁጠር፤ አስከትሎም ለእያንዳንዱ ተማሪ የምንባቡን አንዳንድ ቅጅ ማዘጋጀት፤ ቀጥሎም ምንባቡ ምንም
ግድፈት የሌለውና በግልፅ የሚነበብ መሆኑን ማረጋገጥ፤ ከዚህ በኋላ ለተማሪዎች በራሳቸው ችሎታና አቅም እንዲያነቡ
ገለፃ ማድረግ፤ የማታለል ስራ እንዳይሰሩ በግልፅ መንገርና፤በመጨረሻም የንባቡን አተገባበር በሚከተለው መልኩ
ማደራጀት ያስፈልጋል፡፡ የተማሪዎችን አንብቦ መረዳት ለመለካት የተለያዩ የጥያቄ አይነቶችን በማዘጋጀት መለካት
ይቻላል፡፡ አንብቦ መረዳትን ለመለካት የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ሲዘጋጁ ለተማሪው በቀላሉ የሚረዱና የተለያዩ
አይነት መሆን አለባቸው፡፡ ጥያቄዎችም ከተዘጋጀው ጽሁፍ ጋር ጥበቅ ዝምድና ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ይህ ትልቅ
ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጥያቄው ሲዘጋጅ የደራሲው አመለካከት፣ትኩረትና ድምፀት ሙሉ
ግንዛቤ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ጥያቄውም በሚከተሉት አይነቶች ማለትም በክፍት ጥያቄዎች፣ በምርጫ፣ በእውነት ሐሰት፣
ወዘተ. ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩም ጽሁፋዊ ያልሆኑ አጠያየቆችም መጠየቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ካርታዎችን
ማገናኘት፣ ፎቶግራፎችን ማዛመድና በአንቀፅ (ከተለያየ ፅሁፍ ላይ የተወሰዱ ፅሁፎችን በታትኖ በመስጠት እንዲያገናኙ
በማድረግ) ሊዘጋጅ ይችላል (ጋርሌት፣1996)፡፡

2.2 አንብቦ የመረዳት ችሎታና ጾታ


ወላጆች የልጆችን የማንበብ ልምድ ለማሳደግና ለማጠናከር በመኖሪያቤት ውስጥ ሁለት ሚናዎችን
ይጫወታሉ፡፡ የመጀመሪያው ሚና ማንበብን ባህላቸው አድርገው የሚነበቡ ነገሮችን በመኖሪቤት ውስጥ ማስቀመጣቸው
ሲሆን፣ ሁለተኛው ሚና በማንበብ ልምዳቸው አማካኝነት ለልጆቻቸው አዝናኝና አስተማሪ ድርሳናትን እያነበቡላቸው
ተፅዕኖ ማሳደራቸው ናቸው፡፡ ወላጆች የማንበብ ልምዳቸውን በማዳበር ለልጆቻቸውም አርአያ ከሆኑ ልጆቻቸው
በመኖሪያ ቤት ውስጥ እንዲያነቡ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ (ስፓይገል 1994)፡፡ ሊናና ካሪም (2007) የማንበብ ልምድ፣
ቤተሰባዊ ቅድመሁኔታና በራስ ጥረት መማር አንብቦ በመረዳት ችሎታ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በሚመከለከት ጥናት
አድርገዋል፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በ 4018 የጥናቱ ተሳታፊ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ መጠይቅና አንብቦ የመረዳት
ፈተና በማቅረብ ነው፡፡ ከጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደጠቆመው የአጠቃላይ ትምህርት በራስ ጥረት መረዳት (verbal
General academic self concept) ከፍተኛ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም የፆታ ልዩነት በማንበብ ልምድ ላይ ተፅዕኖ እንዳለውና
እንደሌለው ተፈትሻል፡፡ በጥናቱ ውጤቱ መሰረት ሴት ተማሪዎች ከወንድ ተማሪዎች የተሻለ ጥሩ የማንበብ ልምድ
አላቸው፡፡ ወንድ ተማሪዎች የተሻሉ ሆነው የተገኙት ትምህርትን በራስ ጥረት በመረዳት፣ በራስ ውጤታማነት፣
በማስታወስ፣ በማብራራትና በመነሳሳት ናቸው፡፡ በተጨማሪ የማንበብ ልምድ፣ አንብቦ የመረዳትና ማስታወስ ችሎታ
ለመመርመር ግራቢስ፣ ሊበርግና ኩኪ (1983) ጥናት አድርገው ነበር፡፡ በጥናቱ ተሳታፊ 72 ተማሪዎች በደረጃቸው አንብቦ
ለመረዳት ቀላልና አስቸጋሪ አጫጭር የንባብ ታሪኮችን በማቅረብ ጥናቱ ተካሂዶአል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው
አንብቦ ለመረዳት ቀላል ለሆኑት ታሪኮች የተማሪዎች የማንበብ ልምድ አዎንታዊ (የዳበረ) ሲሆን የመረዳትና
የማስታወስ ችሎታቸውም ከ 13% እስከ 38% ጨምሯል በሌላ በኩል ክርስቲናና ጆናታን(2011) የታላቋ እንግሊዝ
ወጣት ተማሪዎች የንባብ ልምድ ለምን እንደቀነሰ ለማወቅ ጥረት አድርገዋል፡፡ በጥናቱ 17000 ተማሪዎች ላይ የማንበብ
ልምዳቸው መቀነስ ምክንያት የትምህርት ቤት የማንበብ ልምድ፣ የጾታ ወይም የጎሳ ልዩነት ምክንያት እንደሆነ ቅኝት
በማድረግ ባህሪያቸውን ለመመርመር ጥረት ተደርጓል፡፡ በጥናቱ የተገኘው ውጤት እንዳመለከተው የተማሪዎቹ የማንበብ
ልምድ ከ 2005 እስከ 2009 ባሉት አምስት አመታት ቀንሶ ተገኝቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ፣ ወጣት ተማሪዎቹ በማንበብ
ሰለማይደሰቱ ማንበብን በማቆማቸው ነው፡፡ ናንሲ (1989) ከአንደኛ እስከስምንተኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን
የማንበብ አመለካከትና የማንባብ ችሎታ ተዛምዶ አጥንተዋል፡፡ በጥናቱ የተሳተፉ 876 ተማሪዎች ከሞሉት የማንበብ
አመለካከት መለኪያ መጠይቅና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ፈተና የተገኘው ውጤት 1. በተማሪዎች
የማንበብ አመለካከትና የንባብ ውጤት መካከል ተዛምዶው ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቶአል፤
2. የማንበብ ችሎታ ውጤታቸው ደረጃው መካከለኛ ሆኗል፤ 3. እስከስምንተኛ ክፍል
ባሉ የትምህርት ደረጃዎች የሚማሩ ተማሪዎች የማንበብ አመለካከት ቀንሷል፣
4. ከወንዶቹ ተማሪዎች በተሻለ የሴት ተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና የንባብ ችሎታ ውጤት ተዛምዶ ከፍተኛ
ሆኗል፤ 5. የሰባተኛና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች የማንበብ
አመለካከት አዎንታዊ እንደነበር ተጠቁሟል፤ 6. በሴትና በወንድ ተማሪዎች መካከል የማንበብ ብቃትን በሚመለከት
ጉልህ ልዩነት አልታየም፤ 7. ዝቅተኛ የማበብ ችሎታ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች አመለካከታቸውም ቀንሷል፡፡
ከዚህ ሌላ የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ በጾታ ልዩነት ተዛምዶ እንዳለውና እንደሌለው
ለመመርመር የተደረጉ ጥናቶች አሉ፡፡ ዊዊ (2009) በቻይና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የፆታ ልዩነት ከአንብቦ
መረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ መርምረዋል፡፡ በመጠይቅና በክለሳ ድርሳን የተሰበሰቡት መረጃዎች እንዳመለከቱት
ሴት ተማሪዎች ከወንድ ተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ ብልሀቶችን በመጠቀም፣ የንባብ ጭንቀቶችን በመቋቋም እንዲሁም
አንብቦ በመረዳት ችሎታ የተሻሉ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

2.3 የቀደምት ጥናቶች የአጠናን ስልቶች


ጃጎብስና ሰዊንርድ (1999) መምህራን በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለተማሪዎቻቸው የሚያነቡላቸው ግላዊ
የመዝናኛ ንባብ የተማሪዎችን የማንበብ ልምድ ለማሳደግ ያለውን ፋይዳ በሚመለከት ጥናት ያጠኑ ሲሆን በመጠይቅ
ከተሰበሰበው የማስተማርና የግላዊ ንባብ ልምድ መረጃ ከተገኘው ውጤት ለመረዳት እንደተቻለው መምህራን
በአብዛኛው የሚያነቡት የሚያስተምሩትን ትምህርት ምንባቦችን ብቻ ነው፡፡ በዚህ ምክኒያት ተማሪዎች ማንበብን
መሰረት በማድረግ እየተዝናኑ ስለማይማሩ ለንበብ ያላቸው ልምድ ዝቅተኛ ወደ መሆን አዘንብሎአል፡፡ በተመሳሳይ
አፕልጌት (2004) ባደረጉት ጥናት የመምህራን የማንበብ ልምዶችና አመለካከቶች የመረመሩ ሲሆን በልቅ መጠይቅ
አማካኝነት በመምህራን ላይ በተደረገው ቅኝት 54% የሚሆኑ መምህራን ማንበብ ልምድ የሌላቸው መሆናቸውን ጥናቱ
አመልክቶአል፡፡ በጥናቱ ማጠቃለያ ላይ እንደሰፈረው የመምህራን የማንበብ ልምድ አለመዳበር የተማሪዎችን የማንበብ
ልምድ በእጅጉ እንደሚጎዳው ተገልጧል፡፡ ሌላው ተመራማሪ ብላክ (2006) ያጠኑት ጥናት ከአፕሊጌት (2004) በተለየ
መልኩ በተማሪዎች የማንበብ ልምድ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ጉዳዮች ተማሪዎች የሚኖሩበት አካባቢና የሚማሩበት ሁኔታ
በማንበብ ልምዳቸው ላይ ለተጽእኖ ያጋልጣቸዋል የሚል ነው፡፡ አያይዘውም በተማሪዎች የማንበብ ልምድ ላይ ተፅእኖ
ለማድረስ ምክኒያት የሚሆኑት ጉዳዪች ተፈጥሮ፣ ቤተሰብና ትምህርት ቤት ናቸው፡፡ እነዚህ የተጽዕኖ ምክኒያቶች
ለተማሪዎች የማንበብ ልምድ መዳበር በሚነሳሱበት ወቅትና ራሳቸውን እንደ አንባቢ መቁጠር በሚጀምሩበት ጊዜ
ማንበብን ልማዳቸው እንዲያደርጉ ወይም እንዳያደርጉ የሚያስችሉ ናቸው፡፡ እንደብላክ (2006) ማብራሪያ ቤተሰብ
በማንበብ ልምድ ላይ አንዳዳንድ ተፅዕኖዎችን ያሳድራል፡፡ ማህበራዊ መደቦችእና የቤተሰብ ባህል የተማሪዎች ማንነት
ላይ ጫና በመፍጠር ተጽዕኖ የሚያሳድሩት በማንበብ ተግባራትና በማንበብ ልምዳቸው ላይ ነው፡፡ ተማሪዎች በማንበብ
ባህል ውስጥ ባለ ቤተሰብ የሚያድጉ ከሆነ የማንበብና የመጻፍ ችሎታቸው ሲያድግየማንበብ ልምዳቸውም አብሮ
ይዳብራል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ምንም አይነት የማንበብ ልምድ በሌለውና ልጆችን ለንባብ ተግባራት በማያነሳሳ ቤተሰብ
ውስጥ የሚያድጉ ልጆች የንባብ ልምዳቸው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚርፍበት ብላክ በጥናታቸው ገልፀዋል፡፡ ሞሮውና
ያንግ (1997) በተመሳሳይ እንዳጠኑት ወላጆች በመኖሪያ ቤት ልምዶቻቸው በልጆቻቸው ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ
ያምናሉ ይህ ተጽዕኖም በተማሪዎች የማበብልምድ ላይ ያርፋል፡፡አሁን አሁን የመረጃ መረብ እድገቱ የተማሪዎች
የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳት ችሎታ እንዳያድግ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳረፈ መጥቷል፡፡ ፓላሲን (2012) ከዚህ
በተጨማሪ ከመረጃ መረብ እድገቱ ጋር በተያያዘ በሞባይል የሚደረጉ ምልልሶች፣የፌስቡክ፣ የቲውተርና የመሳሰሉት
ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሀን የሚሰጡት አገልግሎቶች የተማሪዎችን ሰነልቦና የሚስቡ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች
የሚቀርቡበት በመሆኑ ተማሪዎች ጥልቅ ንባብ እንዳያነቡና የሚያነቡትን ነገር እንዳይረዱ ከፍተኛ ተፅእኖ አሳርፎአል
በማለት ይገልጻሉ፡፡ ኢሳብ (2012) በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ ላሉ ተማሪዎች አንብቦ ከመረዳት ይልቅ በቴሌብዥን
የሚተላለፉ ፊልሞችን በጆሮ ተሰክተው የሚደመጡ ሙዚቃዎችን (ዘፈኖችን) እና ዎቅታዊ መዝናናትን የሚሰጡ
የተለያዩ ጨዋታዎች ከፍተኛ ተፅእኖ በመፍጠር ተማሪዎች ለሌሎች የማንበብ ተግባራት ደንታ የሌላቸው እንዲሆኑ
እንዳደረጉ በጥናታቸው አመላክተዋል፡፡
ምዕራፍ ሶስት

የአጠናን ዘዴ

3.1 የጥናቱ ንድፍ


የዚህ ጥናት ዐቢይ አላማ የተማሪዎች የማንበብ ልምድ ከአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ጋር ያለውን ተዛምዶ
መመርመር ነው፡፡ በመሆኑም ጥናቱ በአይነቱ መጠናዊ ሆኖ ተዛምዷዊ የምርምር ስልትን ተከትሎ ተከናውኗል፡፡ የጥናቱ
ተሳታፊዎች የማንበብ ልምድ በፅሁፍ መጠይቅ ተለይቷል፡፡ የአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ደግሞ፣ በፈተና ተለክቷል፡፡
ለጥናቱ የተሰበሰቡት መረጃዎችም መጠናዊ በሆነ መንገድ ተተንትነው በተማሪዎች የማንበብ ልምድ በአንብቦ መረዳት
ችሎታቸው መካከል ያለው ተዛምዶ ተለይቷል፡፡ በፆታ ያለው ልዩነትም ተፈትሿል፡፡ በመጨረሻም የተደረሰበት
ማጠቃለያና መደምደሚያ ቀርቧል፡፡

3.2 የጥናቱ ተሳታፊዎች


ጥናቱ የተካሄደው በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በዳባት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ነው፡፡ ይህ ትምህርት ቤት ለአጥኚዋ ቅርብ በመሆኑና መረጃውን ተከታትሎ ለመሰብሰብ አመች በመሆኑ በዞኑ ከሚገኙ
ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአመቺ የንሞና ዘዴ (convinance sampling) ተመርጧል፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት
አጥኚዋ የምታስተምረው በዚሁ ትምህርት ቤት በመሆኑ፣ ጥናቱን ለማካሄድ ሊገጥማት ከሚችለው የጊዜና የገንዘብ
እጥረት አንፃር አመቺ በመሆኑና አስተማኝኝነት ያለው መረጃ በቅርበት ለማግኘት የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡
ተጠኝዎቹ በ 2010 በዚሁ ትምህርት ቤት በመማር ላይ የሚገኙ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ፣ የናሙና አመራረጡን
በተመለከተ ዞልታን ዶርኒ(2007)፣ ኮትሪል(2004) እና ያለው(1998) የምርምሩ ስልት ተዛምዶዊና የጥናቱ አካላይ በርካታ
አባላት ያቀፈ ከሆነ በጥናቱ መሳተፍ ያለባቸው የናሙና አባላት ብዛት ከ 30% ማነስ እንደሌለባቸውና በቡድን
አስራአምስት አባላት እንደሚካተቱ የገለጹትን መሰረት በማድረግ ከትምህርት ቤቱ ከአጠቃላይ 348 (210 ሴት፣ ወንድ
138) ውስጥ 120 ተማሪዎች በእጣ ንሞና ተመርጠዋል፡፡ በዚህ የናሙና ዘዴ ሁሉም ተማሪዎች እኩል የመመረጥ እድል
ስለሚያገኙ በጥናቱ ውስጥ የሚሳተፉት ተማሪዎች በተለያየ ችሎታ ላይ ሆነው እንዲካተቱ ለማድረግ አስችሏል፡፡

3.3 የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች


የጥናቱ ዓላማ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸውን የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ
መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡ በመሆኑም የጽሁፍ መጠይቅና ፈተና በመረጃ መሰብሰቢያነት ውለዋል፡፡

3.3.1 የጽሁፍ መጠይቅ


የጽሁፍ መጠይቁ የተዘጋጀው ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸውን የማንበብ ልምድ ለመመርመር
ነው፡፡ መጠይቁ 32 ሃሳቦችን የያዘ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ ሃሳብ አምስት አምስት የመልስ መወሰኛ አማራጮች (rating
scales) ቀርበውለታል፡፡ እነሱም፣ ከዝቅተኛ ወደከፍተኛ (1) በጭራሽ አልስማማም (2) አልስማማም (3) በመጠኑ
እስማማለሁ (4) እስማማለሁ (5) በጣም እስማማለሁ፣ የሚሉ ናቸው፡፡ እነዚህ 1 እስከ 5 የቀረቡ መለያዎች
በተቀመጡበት ቅደም ተከተል ነው፡፡ መጠይቁ የተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸውን የማንበብ ልምድ
እንዲሁም የማንበብ ልምድ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን ይተነብያል? የሚሉ ጉዳዩችን ሊያሳይ በሚችል መልኩ
ምንውየለት (2005) በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የሰብዕና አይነቶችና የማንበብ ልምድ ተዛምዶን ለመመርመር
(www.surveymonky.coms/pmgNF86) ጠቅሶ የተጠቀመውን ከምርምሬ ሀሳብ ጋር በሚስማማ መንገድ ሀሳቡን፣
ሀረጋትንና ሰዋሰስዋዊ መዋቅሮችን በማስተካከል፣ የትምህርት ባለሙያዎችና የቋንቋ መምህራን እንዲገመግሙት
ከተደረገ በኋላ ባለሙያዎቹ የሰጡትን ግብዓት በማካተት መጠይቁ በአግባቡ ተዘጋጅቶ በጥናቱ ባልተካተተ ሌላ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት በሚማሩ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የሙከራ ጥናት ተካሂዶአል፡፡ አስተማማኝነቱም በክሮንባሰ
አልፋ (cronbach alpha) ቀመር ተሰልቶ የተገኘው ውጤት 0.87 ሆኗል፡፡ በዚህ መሰረትም ለዋናው ጥናት ተፈላጊው
መረጃ ተሰብስቦበታል፡፡ አተገባበሩም ለጥናቱ የተመረጡ ተማሪዎችን በአንድ ላይ በመሰብሰብ ሰለመጠይቁ አላማ፣
ሰለአሞላሉና በመጠይቆቹ ላይ የቀረበውን ሀሳብ አንብበው ግልፅ ያልሆነውን እንዲጠይቁ እድል የሰጠ መግለጫ
ከተሰጣቸው በኋላ መጠይቁን በማደል መረጃውን ከ 116 ተማሪዎችም መረጃዎችን ሳያዛንፉና በትክክል ሞልተው
መልሰዋል፡፡ አራት ተማሪዎች በትክክል ባለመሙላታቸው ከጥናቱ ተወግደዋል፡፡

3.3.2 ፈተና
ሁለተኛው የመረጃ መሰብሰቢያ አንብቦ የመረዳት ፈተና ነው፡፡ ፈተናው አጥኝዋ ለተመረጡ ተጠኝ ተማሪዎች
አንብቦ የመረዳት ፈተና አዘጋጅታለች፡፡ ለአንብቦ መረዳት ፈተና የሚያገለገሉ ምንባቦች ሂተን (1990) እና
ማድሰን(1983) ከተማሪዎች ማህበረ ባህላዊ አውድ ጋር የሚጣጣም ይዘት ያላቸው፣ የደራሲውን አመለካከት ከራሳቸው
እንዲያወዳድሩ የሚያግዝ፣ አንድን ጉዳይ በጥልቀት ለመመርመር እንዲነሳሱ የሚገፋፋ፣ የድምር ሀሳቦችን ፍጻሜ
ለማዎቅ የሚያጓጉ (ለምሳሌ፣ ከልቦለዶች ጋር የተቀነጨቡ)፣ ከእውቀት አድማሳቸውጋር የሚጣጣም ይዘት ያላቸው፣
ለየደረጃው የሚመጥኑ የተወሰኑ እንግዳ ቃላት ያካተቱና ፍቻቸውንም ከአውድ ለመገመት የሚያስችሉና መሆን
አለባቸው፤ በሚሉት መሰረት የተዘጋጀ ነው፡፡ በተጨማሪ ማረው (1998) እንደሚገልጹት ከንበብ በኋላ የሚጠየቁ
ጥያቄዎች የተማሪዎችን ግንዛቤ ለመረዳት የሚረዱ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለምሰሌ፣ ተማሪዎች ያላቸውን ክፍተት
ለመሙላት፣ ያነበቡትን ለማጠቃለል፣ ያነበቡትን አዲስ መረጃ ከነበራቸው እውቀት ጋር ለማዛመድ የሚያስችሉ፣
ምክኒያታቸውን የሚገልፁበት፣ የንባቦችን ይዘት የሚተነትኑበት፣ ትርጉምና ማጠቃለያ የሚሰጡበት፣ ሊሆኑ ይገባል፤
ያሉትንና ናታል (1996) እና ማድሰን (1983) የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች በማዛመድ፣ ትንበያ እንዲሰጡ በማድረግ፣
በአጭር መልስ ስጥ፣ በፃፍ፣ በክፍት ቦታ ሙላ መጠየቅ እንደሚቻል የሚያሰረዱትን ግምት ውሰጥ በማሰገባት ሁለት
ምንባቦችን በመጠቀም ፈተና ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ሆኗል የመጀመሪያው ምንባብ ከሲሳይ ንጉሱ (1999፣1-2) ሲዎሰድ
ሁለተኛው ምንባብ ከከበደ ሚካኤል (ዓ.ም ያልተጠቀሰ፣ 23-25) ተወስዷል፡፡ በመጀመሪያው ምንባብ ከተካተቱት ሀያ
ሁለት ጥያቄዎች አስራ ሁለቱ የባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎች፣ አምስቱ የአዛምድ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ሁሉም መልስ
አስመራጭ እንዲሆኑ የተደረገበት ምክንያትም ለአስተማማኝነት ትከረት ለመስጠት ነው፡፡ በተጨማረሪም በአብዛኛው
ተማሪዎች የለመዷቸው በመሆናቸው አስቸጋሪ ሁኔታን ሰለማይፈጥሩባቸው ነው፡፡ እንዲሁም ሂተን (1990) እና
ማድሰን (1983) ባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎች በበርካታ ተፈታኞች ዘንድ በማንኛውም የክፍል ደረጃ የሚመረጡና
የሚሰሩባቸው ከመሆኑ ባሻገር በተለያየ መንገድ ከምንባቡ ውስጥ በተካተቱ ቃላት አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን
ለመለካት የተሻሉ መሆናቸውን ሰለሚመሰክሩ ነው፡፡ ሁለተኛው ምንባብ ደግሞ ስምንት ጥያቄዎችን የያዘ ነው
በአንቀፅ(ምንባቡ) ውስጥ ገብተው የተሟላ ትርጓሜ የሚሰጡ አማራጮች ቀድመው ተካተዋል፡፡ እነዚህ አማራጮች
በምንባቡ ውስጥ በቁጥር በተወከሉት ቦታዎች እንዲያስገቡ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ የፈተና ክፍል ተማሪዎች
አጠቃላይ የምንባቡን ሀሳብ እንዲተነብዩ ብሎም በቅርብና በሩቅ አውድ በመታገዝ መልሱን እንዲገምቱ የማድረግ ብቃቱ
ከፍተኛ ነው፡፡ እያንዳንዱ መልስ በቅርብና በሩቅ አውድ የታገዘ በመሆኑ በጥንቃቄ አንብቦ የተረዳን ተማሪ ለመለየት
ያስችላል፡፡ ሂተን (1990) እና ማድሰን (1983) ዝግ ጥያቄዎች ተማሪዎች ከግላቸው ሰሜት ተነሳስተው በትክክል
እንዲመልሱ የሚደረግበት ሂደት ሳይሆን ቃላቱ ወይም ሀረጋቱ የሚተውት ሰልታዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ ተማሪዎች
በስልት ታግዘው እንዲንደረደሩ ይረዳቸዋል፤ በሚሉት መሰረት የተዘጋጀ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ሁለቱም ምንባቦች ከተዘጋጁ
በኋላ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚያሰተምሩና ለጥናቱ በተመረጠው
የክፍል ደረጃ በሚያሰተምሩ የቋንቋ መምህራን ተገምግሞና አስተያየታቸው ተካቶ የጥያቄዎችን አመላለስ
የሚያመለክት መመሪያ ታክሎበት ፈተናው በጥናቱ ሌላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚማሩ የዘጠነኛ ክፍል
ተማሪዎች የሙከራ ጥናት ተካሂዷል፡፡ አስተማማኝነቱም በክሮንባህ አልፍ (cronbach alpha) ቀመር ተሰልቶ የተገኘው
ወጤት 0.74 ሆኗል፡፡ በሙከራ ጥናቱ የፈተናው አስተማማኝነት በመረጋገጡ ለዋናው ጥናት ፈተናው በተጠኝዎች ቁጥር
ልክ ተባዝቶና ለተማሪዎች ኮድ ተሰጥቶ የመረጃዎችን አስተማማኝነት ለመጠበቅ በአንድ ትልቀ አዳራሽ በሶስት
የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ተራርቀው በአንድ ጠረጵዛና ወንበር አንድ ተማሪ በማሰቀመጥ ፈተናውን እንዲሰሩ
ተደርጓል፡፡ ለፈተና የተሰጠው ሰአት ሲያልቅ የፈተና ወረቀቶቹ በአጥኝዋና በረዳቶቿ ተሰብስበዋል፡፡

3.4 የመረጃ አተናተን


የጥናቱ ዋና አላማ የተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ መካከል
ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነበር፡፡ በተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳት
ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ ደረጃ ለማወቅ የፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ ቀመር (Pearson Correlation
Cofficient) ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም የተማሪዎቹ የማንበብ ልምድ አንብቦ የመረዳት ችሎታን የመተንበይ ጉልህ
ድርሻ እንዳለው ለማረጋገጥ በቀላል ድህረት ትንተና (Simple Regression Analysis) ተተንትኗል፡፡ በተጨማሪም
በሴትና በወንድ ተማሪዎች መካከል በተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ልዩነት መኖር አለመኖሩን
ለመፈተሸ የተሰበሰበው መረጃ በነጻ ናሙናዎች ቲ-ቴስት (Independent Samples T-test) ተሰልቷል፡፡

ምዕራፍ አራት

የጥናቱ ትንተና ማብራሪያ

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳት ችሎታ
መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነበር፡፡ ለዚህም እንዲረዳ በፅሁፍ መጠይቅና በፈተና አማካይነት የተማሪዎች
የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ውጤት በመረጃነት ተሰብስቧል፡፡ በዚህ ምዕራፍ በፅሁፍ መጠይቅና በፈተና
የተገኙትን መረጃዎች መሠረት በማድረግ የጥናቱ ውጤት ትንተናና ማብራሪያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

4.1 የጥናቱ ውጤት ትንተና


የጥናቱ የመጀመሪያው ጥያቄ ተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው መካከል ተዛምዶ
መኖሩን መፈተሽ ሲሆን፣ የተለዋዋጮችን ዝምድና ለማወቅ የፒርሰን የተዛምዶ (Pearson product-moment
correlation) መጠን መለኪያ ቀመር በመጠቀም ውጤቱ ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡ ሰንጠረዥ 4.1፤
በተማሪዎች የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ ተላውጦ የተጠኝዎቸ ብዛት አማካይ ውጤት መደበኛ
ልይይት ተዛምዶ የማንበብ ልምድ አንብቦ የመረዳት ችሎታ የማንበብ ልምድ 116 89.47 7.79 1 አንብቦ የመረዳት
ችሎታ 116 69.15 14.73 0.711* 1

we got to create data carefully here.

4.2 የጥናቱ ማብራሪያ


የዚህ ጥናት ዓላማ ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸው የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳት ችሎታ
መካከል ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነው፡፡ የማንበብ ልምድ የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ጉልህ ድርሻ
እንዳለውና በፆታ ልዩነት ያሳይ ወይም አያሳይ እንደሆነ ለመፈተሽ በተለያዩ ገላጭና ተንባይ ስታትስቲክሶች ተተንትኗል፡፡
ለዚህም በመጠይቅና በፈተና በተሰበሰቡ መረጃዎች አማካኝነት የተማሪዎች የማንበብ ልምድ ከአንብቦ መረዳት
ችሎታቸው ጋር ያለውን ተዛምዶ በንፅፅር ታይቷል፡፡ በሰንጠረዥ 1 እንደታየው በተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ
የመረዳት ችሎታ መካከል ተዛምዶው በፒርሰን ተዛምዶ መለኪያ (persn correltion coefficient) ተለክቶ በተማሪዎች
የማንበብ ልምድና አንብቦ በመረዳት ችሎታ መካከል ስታትሰቲካዊ ጉልህ አዎንታዊ ተዛምዶ መኖሩን የጥናቱ ውጤት
አሳይቷ፡፡ ይህም ማለት የተማሪዎች የማንበብ ልምድ ሲጨምር አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውም ይጨምራል፤ በዚህም
የተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳታቸው በእጅጉ የተቆራኘ ይሆናል፡፡ የተማሪዎቹ አማካይ የማንበብ ልምድ
ውጤት መጠን (89.47) ከአንበቦ መረዳት ውጤታቸው አማካይ ውጤት (69.15) አንፃር ሲታይ (r=0.711፣ P>0.05)
ተለዋዋጮቹ የሚጋሩት የጋራ ባሕሪ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ በማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት መካከል ጉልህ ተዛምዶ
አለ፡፡ ከዚህ በመነሳት ተማሪዎቹ ከፍተኛ የሆነ የማንበብ ልምድ ሲኖራቸው የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውም ከፍተኛ
ነው፡፡ ተማሪዎቹ ከፍተኛ የሆነ የማንበብ ልምድ ስላላቸው በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ከፍተኛ ውጤት
አስመዝግበዋል፡ ፡ ይህም የማንበብ ልምድ መኖር ምንባቦችን አንብቦ ለመረዳት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ያሳያል፡፡ በዚህም
ጥናት ብላክ (2006)፣ ፓላሲ (2012)፣ ኦሁሹኦችዋ (2014) እና ደምስው (1995) ጥናት ውጤት ጋር ተመሳሳይ ሲሆን፣
ከናንሲ (1989) እና ሃሰን (2004) የጥናት ውጤት ጋር ደግሞ ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የዚህ ጥናት ሁለተኛ አላማ
የተማሪዎች የማንበብ ልምድ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን ይተነብያል ወይ የሚል ሲሆን፣ ለዚህም ትንተና ይረዳ
ዘንድ ቀላል ድህረት (Regression Analysis) ትንተና ጥናቱ ተጠቅሟል፡፡ ወጤቱም በሰንጠረዥ 2 ተመላክቷል፡፡
በሰንጠረዥ 2 የተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታን የሚያሳይ ቀላል ደህረት ስታትሰቲክ ውጤት
እንደሚያሳየው የማንበብ ልምድ አንብቦ የመረዳት ችሎታን በማጉላት ረገድ ጉልህ ድርሻ መኖሩን ውጤቱ ያሳያል፡፡
ይህም ማለት የተማሪዎች የማንበብ ልምድ ከዳበረ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን በጉልህ ደረጃ ይተነብያል ማለት
ነው፡፡ የማንበብ ልምድ በአንብቦ መረዳት ችሎታ የቀጥታ ተፅዕኖ (Beta coefficient) ሲለካ (B= 1.344, t=10.789,
p<0.05) ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም የሚያሳየው የማንበብ ልምድ በ 0.711 ሲጨምር አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው እንደሁ
0.711 ዩኒት ይጨምራል ማለት ነው፡፡ የማንበብ ልምድ በተማሪዎች አንብቦ መረዳት ነፃ ድርሻ ተሰልቷል፡፡ ይህም
የማንበብ ልምድ የተማሪዎች አንብቦ መረዳት ችሎታን በ 50.5% ከጠቅላላው R2 መጠን ድርሻ እንዳለው ጥናቱ
አመልክቷል፡፡ የዚህ ጥናት ውጤትም አችዋ(2014)፣ ደምሰው(1995) ከራንስበሪ(1973)፣ ከሒዚግነቶንና አሌክሳንደር
(1984)፣ ከማናናማይሽፍ (1987)፣ ከሪሰን፣ ጃኮብስና ስዊንያርድ (1999)፣ ከአፕሊጌትና አፕሊጌት(2004)፣ ከስችማይት
(2009) የምርምር ግኝቶች ጋር ተደ ጋገፊነት ሲሆን ከዴይና ባምፎርድ(1982)፣ ከኮንሊ(1992)፣ ከአሌክሳንደርና ፊለር
(1992)፣ ከሮኢና ስሚዝ (2005) ፣ ናንሲ (1989) እና ሀሰን (2004) ጥናቶች ውጤት ጋር የሚቃረን ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ሶስተኛው የጥናቱ ዓላማ በማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ጉልህ ልዩነት እንደሌለው
የጥናቱ ውጤት አሳይቷል፡፡ ይህም በሠንጠረዥ 3 እንደተመለከተው የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ በፆታ
ልዩነት እንዳለውና እንደሌለው የተደረገው የጥናት ውጤት ትንተና እንዳመለከተው በማንበብ ልምድ ሴት ተማሪዎች
ከወንድ ተማሪዎች ተመሳሳይ ልምድ እንዳላቸው ያሳያል፡፡ በተመሳሳይም የሴት ተማሪዎች አንብቦ መረዳት ችሎታ
ከወንድ አቻዎቻቸው ተመሳሳይ መሆኑን ያሳያል፡፡ በመጠይቅና በፈተና የተገኘው የጥናት ውጤት ከሊናና ካሪም (2007)፣
ከክሪስቲናና ጆናታን (2011)፣ ከዊዊ (2009) እና ሀሰን (2004) የጥናት ውጤት ጋር ሲደጋገፍ፤ ከሳላበስ (2008)፣ ከባስ
(2012) እና ከተራቪስ (2010)፣ የጥናት ውጤት ጋር አይደጋገፍም፡፡ በአጠቃላይ ከጥናቱ ውጤት ለመረዳት
እንደሚቻለው የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ጉልህ ተዛምዶ አላቸው፡፡ የተማሪዎች የማንበብ ልምድ
አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ ነገር ግን በማንበብ ልምድ ረገድ በጾታ ልዩነት አልታየም፡፡

ምዕራፍ አምስት

ማጠቃለያ
5.1 የጥናቱ ዐቢይ አላማ
የጥናቱ ዐቢይ አላማ በተማሪዎች የማንበብ ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ
መመርመር ነበር፡፡ በዚህ መሰረትምበጥናቱ በቀዳሚነት መልስ እንዲገኝባቸው የተነሱት መሰረታዊጥያቄዎች
የሚከተሉት ነበሩ፡፡

1. በተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶምንይመስላል?


2. የተማሪዎች የማንበብ ልምድ የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻቸው ምንያህል ነው? 3. የተማሪዎች
ማንበብ ልምድ በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት ያሳያል?

የጥናቱን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻልም የፅሁፍ መጠይቅና ፈተና ለመረጃ መሰብበሰቢያነት
ውለዋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በዳባት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በ 2010 ዓ.ም በዘጠነኛ ክፍል ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዚህ የክፍል ደረጃ ከሚማሩ
(ወንድ =56፣ ሴት =60) ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጭ የንሙና ዘዴ የተመረጡ 116 ተማሪዎች የጥናቱ ተሳታፊዎች
ሆነዋል፡፡ የጥናቱ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የፅሁፍ መጠይቅ ሲሆን፣ የተማሪዎቹ የአንብቦ መረዳት ችሎታ ውጤትም
በፈተና አማካይነት ተሰብስቧል፡፡ በፅሁፍ መጠይቁና በአንብቦ መረዳት ፈተና የተሰበሰቡት መረጃዎች ገላጭና ተንባይ
ስታትስቲካዊ የቅመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረትም የተማሪዎችን የማንበብ
ልምድና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶን ለማየት ተሞክሯል፡፡ በዚህም የተማሪዎች የማንበብ ልምድ ከአንብቦ
መረዳት ችሎታ ጋር ጉልህ አዎንታዊ ተዛምዶ እንዳላቸው የጥናቱ ውጤት አመልክቷል፡፡

የተማሪዎች የማንበብ ልምድ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን መተንበይ አለመተንበዩን መመርመር ሲሆን፣
ለዚህም ትንተና ይረዳ ዘንድ የድህረት ትንተና ተከናውኗል፡፡ ውጤቱም የማንበብ ልምድ የአንብቦ መረዳት ችሎታን
በማጎልበት ረገድ ጉልህ ድርሻ መኖሩን አሳይቷል፡፡ ይህም ማለት የማንበብ ልምድ ከዳበረ የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን
በጉልህ ደረጃ ይተነብያል፡፡ የማንበብ ልምድ አንብቦ መረዳት ችሎታን የቀጥታ ተጽእኖ በቤታ ቀመር(beta coefficient)
ሲለካ ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም የሚያሳየዉ የማንበብ ሲጨምር አንብቦ የመረዳት ችሎታ አብሮ ይጨምራል፡፡
በተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ያለውን ልዩነት ለመፈተሸ
ተሞክሯል፡፡ በሴትና በወንድ ተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ በመረዳት ችሎታ መካከል ልዩነት እንደሌለ የውጤት
ትንተናው አሳይቷል፡፡ በመሆኑም በማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ
ተመሳሳይ መሆኑ ውጤቱ አሳይቷል፡፡

5.2 መደምደሚያ
የጥናቱን ውጤትና ማብራሪያ መሰረት በማድረግ ከሚከተሉት መደምደሚዎች ላይ ተደርሷል፡፡

1. በተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ በመረዳት ችሎታ መካከል ጉልህ ዝምድና አለ፡ 2.
የተማሪዎች የማንበብ ልምድ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን በጉልህ ይተነብያል፡፡ ይህም የማንበብ ልምዳቸው
ሲጨምር አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውም በተመሳሳይ ይጨምራል፡፡ የተማሪዎች የማንበብ ልምድ ከዳበረ አንብቦ
የመረዳት ችሎታቸውን ውጤት በጉልህ ደረጃ ስለሚጨምር፣ የማንበብ ልምድ የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ
ይተነብያል፡፡ 3. ፆታ በማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታ ምንም ልዩነት የለውም፡፡ ወይም
በሴትና በወንድ ተማሪዎች መካከል ያለው የማንበብ ልምድ ተመሳሳይ ነው፤ የሚል አንድምታ አለው፡፡

5.3 የመፍትሔ ሀሳብ


የጥናቱ አላማ አድርጎ የተነሳው የተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው
መካከል ያለው ዝምድና ምን እንዲመስል መመርመር ነበር፡፡ በመሆኑም ጥናቱ የተደረሰባቸውን ውጤቶች ተግባራዊ
ለማድረግ እንዲቻል የሚከተሉት መፍትሔዎች ተጠቁመዋል፡፡

1. መምህራን በተማሪዎች የማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው መካከል ዝምድና መኖሩን ተገንዝበው
የበለጠ የተማሪዎችን የማንበብ ልምድ የሚያዳብሩ የትምህርት ዘዴዎችን ተጠቅመው የቋንቋ ትምህርቱን ቢሰጡ
በጥናቱ ውጤት የታየው አበረታች የተማሪዎች ማንበብ ልምድ የበለጠ ሊዳብር ይችላል፡፡
2. ሁሉም ባለድርሻ አካላት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳት ላይ ትኩረት አድረገው ቢሰሩ
በተማሪዎች የማንበብ ልምድና አንብቦ መረደት ላይ የሚታየውን አበረታች ለውጥ ማሳደግ ይቻላል፡፡
3. የስርዓተትምህርት ቀራጮች፣ ተመራማሪዎች፣ የትምህርት ፖሊሲና ዕቅድ አውጭዎች የአንብቦ መረዳትን
ትምህርት መርሀግብር ሲያዘጋጁ የተማሪዎችን የማንበብ ልምድ የሚያዳብሩ የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የበለጠ
ልምዱን ለማሳደግ ቢሰሩ፡፡ የሚሉት በአጥኝዋ የቀረቡ የመፍትሄ ሀሳቦች ናቸው፡፡
4. በጥናቱ በማንበብ ልምድና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት አላሳየም፡፡ መምህራን
ይህን ከግምት በማስገባት ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ተማሪዎች በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ፤
የማንበብ ልምዳቸውን ሊያዳብሩ በሚችሉ ልዩ ልዩ ክበቦች (ለምሳሌ፣ በቤተመፅሐፍት፣ የስነጽሁፍ ክበባት) ቢሳተፉ፡፡
5. የትምህርት ባለሙያዎች በጥናቱ ግኝቶች መረጃ መሠረት የተማሪዎችን የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ
በመገንዘብ መምህራን የትምህርት ዕቅድ፣ መርሐ ትምህርትና የንባብ ትምህርት መርሐግብር ሲያዘጋጁ የተማሪዎቹን
የማንበብ ልምድና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ከማጎልበት አንፃር እንዲመለከቱት ቢጠቁሙ፡፡
6. በርዕሱ ዙሪያ ተጨማሪ ጥናት የሚያደርጉ ተመራማሪዎች ይህንን ጥናት እንደመነሻ በማድረግ ከዚህ የተሻለ ጥናት
ለማካሄድ ጥረት ቢያደርጉ፤ የሚሉት በአጥኝዋ የቀረቡ የመፍትሄ ሐሳቦች ናቸው፡፡

ዋቢዎች

ሀሰን መሐመድ (2004)፡፡

በህርዳር ከተማ በፋሲሎ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ 10 ኛ ክፍልተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ፡፡

ለ 2 ኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጽሁፍ ባህርዳር ዩኒበርስቲ (ያልታተመ) ሀይማኖት ደመላሽ (2005)፡፡

የቃላት እውቀት ችሎታና አንብቦ መረዳት ውጤት ተዛምዶ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለድህረ ምረቃ የቀረበ ያልታተመ
መሐመድ ዓሊ (1992 )፡፡

‘‘በባሕርዳር ከተማ የግዩን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋን ለመማር
ያላቸው አመለካከት፡፡''
ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ)፡፡ መሐመድ ዓሊ፡፡ (1992 ዓ.ም)፡፡

‘‘በባሕር ዳር ከተማ የግዩን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋን ለመማር
ያላቸው አመለካከት፡፡'' ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ)፡፡ መስፍን
ኃብተማሪያም(2001)፡፡

የቡና ቤት ስዕሎችና ሌሎችም ወጐች (1976-1999)፡፡

ኤማይ ፕሪንተርስ ኃ.የተ.የግ.ማ፡፡ አዲስ አበባ፡፡ማረው ዓለሙ (1998)፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ማሰተማሪያ ዘዴ፡፡ አዲስአበባ፤
ንግድ ማተሚያ ቤት፡፡

ምንው የለት መብራቱ (2005)፡፡

የተማሪዎች የስብዕና አይነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ፤ ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕርዳር
ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ) ፡፡ በድሉ ዋቅጅራ (1988)፡፡

ተሳታፊነት፣ ጭምትነት፣ ስብዕና አይነት ከድርሰት መጻፍከ አንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ፡፡ አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት አዲስአበባ፣ ያልታተመ፡፡ ታዛሽ ሰይፉ (1992 ዓ.ም)፡፡

የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች የአንብቦ መረዳትችሎታ፡፡'' ለመጀመሪያ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ፡፡
(ያልታተመ)፡፡ ታፈረ ወርቁ (2000)፡፡

በዳንግላ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ 9 ኛ ክፍልተማሪዎች የንባብ ዳራና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ፡፡
ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባህርዳር ዩንቨርሲቲ (ያልታተመ)፡፡ያለው እንግዳወርቅ (1998)፡፡

የምርምር መሰረታዊ መርሆዎችና አተገባበር ባህርዳር ዩንበርሲቲ ደምሰው አሰፋ (1995)፡፡

የ 10 ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጽሀፍ ውስጥ የሚገኙምንባቦች የተማሪዎችን የማንበብ ፍላጎት ለመያዝ ያላቸው
ብቃት፡፡ለመጀመሪያ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጽሁፍ፡፡ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ (ያልታተመ) ገደፈው አምሳሉ (1993)፡፡

የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን ለመማር ያላቸው ተነሳሽነትና የትምህርት ውጤት ተዛምዶ፡፡ ባህርዳር
ዩኒበርስቲ (ያልታተመ)፡

Abu-Rabia, S. (1996). Attitudes and cultural background and their relationship to reading comprehension
in a second language: a comparison of three different social contexts.

International Journal of Applied Linguistics, 6: 81–105. Doi: 10.1111/j.1473-4192.

1996.tb00090.x Aebersold, J.A., and Field, M.A. (1997). From Reader to Reading Teacher: Issues and
strategies for second language classrooms.Cambridge Universty Press.

Alexander, J.E., and Filler, R.C. (1976). Attitudes and Reading. Newark., DE. International Reading
Association.

Aliderson.M.J.(2003) Beginninge to Read: thinking and learning about print.


Cambrige.M.A.M/T Press.

Ambrusster, B.B. Anderson. T.H. And Osterag.j.(1987) Dase Test Structral Sammarization Institution
Facilitate learning from Exposi Tory Text? ReadingResearch Quarterly.22.331.346.

Anderson, N.J. (2003). Metacognitive reading strategies increase L2 performance. The Language Teacher
Online, 27(7).

Anderson, V. (1992).A teacher development project in Transactional Strategy Instruction for teachers of
severely reading-disabled adolescents.Teaching and Teacher Education,8, 391-403.

Appllegate, A.J. and Appllegate, M.D. (2004). The Peter Effect: Reading Habits and Attitudes of
Preservice Teachers. The Reading teacher, 57, 554-563.

Appllegate, A.j.and Appllegate, M.D. (2004). The peter effect Reading Habits and Attitudes of preservice
Teachers.The Reading Teachers the Reading Teacher, (57). 554_563.

Bas, G. (2012). Correlation between elementary students’ reading attitudes and their writing dispositions.
IJGE: International Journal of Global Education - 2012, volume 1 issue 2. Konya University.Graduate
School of Education Sciences. Konya, Turkey

Bas, G (2012). Coreiation between.elementry studntes reading attitude and their writing dispositions.
IJGE; International Jornal of Giobal of Global Education Science.Konya, Jurkey.

Basir, I. Mattoo, N.H. (2012) A study on study Habits and AcademicPerformance among Adolescent (14-
19) year. International Journal of social Sciencetomorrow. Vol.1, No.5, pp.1-5.

Benjamin, p(ed.) (2010). “Ethiopian Elementry Scool Grad Reding assessment” Data Ll Task
Number7.Publication USAID/ETHIOPA.

Blackb, A. (2006) << Attitudes to Readnge: An Inyestigation across the Primary years.>>this Master of
education. School of Education, Australlan CatholicUniversty.

Blackb, A. (2006). Attitudes to Reading: An Investigation across the Primary Years.

Thesis.Master of Education, School of Education, Australian Catholic Universty.

Block, C.C. (1997), Teaching the Language Arits: Expanding Thinking Through student Centerd
Instruction, Boston Allyn and Bacon.

Bloom, B.S.(ed.) (1963). Taxonomy of Educatinal Objecitve: The Classification of Educational Goals.
New York Longman, Green and co.

Bokhorst-Heng, W. and Pereira, D. (2008), Non-at-risk adolescents' attitudes towards reading in a


Singapore secondary school. Journal of Research in Reading, 31: 285–301.

Doi: 10.1111/j.1467-9817.2008. 00369.x Burns, p.c. (1984) Teaching) Reading in Todays Elementary
school Boston: Houghton, Mifflin company.
Kothar C.R. (2004) Resarch MItedologe-Methdes and Techiques Former Principals, College of
commerce University of Raiasthan, jaipur (india).

Carrel.P.L.et al (1989) Interactive Approaches to second Language Readnge.cambridge:

Cambridge University Press.

Christina, (2011).young people Reading and Writing: An-Depth study Focusingon Enjoyment, Behavior,
Attitudes and Attaimhent.2011-00-00.

Christina, C. and Jonathan D. (2011). Young People's Reading and Writing: An In-Depth Study Focusing
on Enjoyment, Behavior, Attitudes and Attainment. 2011-00-00.

Conely, m.w. (1992). Content Reading Instruction: A communicative Approach. New York:

MC Graw Hill lnc.

Cramer, M. (1994). Fosternig the Love of reading: The Affective Domain in Reading Education (PP.74-
87). Newyork, DE: International reading Association.

Day, R and Bamford. (1998), Eytensive Reading in the second language Classroom U.S.A.:

Cambridge Uniuersty press.

Day, R. and Bamford. (1998). Extensive Readng and in The Second Language Classroom. U.S.A:
Cambridge Universty Press.

Dishiner.E.K. et.al.(1980) Readinge Strategies and practice: Guide for Improving Instruction.

Boston: Allyan and Bacon, Inc.

Dornyei, Z. (2001). Motivational Strategies in the Language Classroom. Cambridge: Cambridge


Universty Press.

Dubin, B.V, and Zorkaia, N.A (2010). The changes in the attitude of Russia's Reading public interms of
frequency and intensiveness. Russian Education and Society, v52n7 P16-51 Jul. 2010.

Eiser, J. R., (1994). Social Psychology.Attitudes, cognition and social behavior. Cambridge University
Press.

Estes, T. H. (1971). A Scale to Measure Attitudes Toward Reading. Journal of reading. 15, 135-138.

Evans, K.M., (1965). Attitudes and Interests in Education. Routlege and Kegan private limited.

Feldman, R.S (1999). Understanding Psychology.(5th Ed). McGraw-Hill, Inc.

Feldman, R.S., (1996). Understanding Psychology.(4th Ed). McGraw-Hill, Inc.

Flood J., and Lapp, D., (1983). Teaching Reading to Every Child (2ed ed). Macmillan Publishing Co.,
Inc.
Frankel, J.R., and Wallen.(2000). How to design and Evaluate Research in education. (4th Ed).Mcgraw
Hill. Gambrell, l.B., (1996). Creating Classroom cuitures that Foster ReadingMotivation, the Reading
Teachers 50,14.25.

Gambrell, L.B., (1996). Creating Classroom Cultures That Foster Reading Motivation. The Reading
Teacher, 50, 14-25.

Graves, MF., Laberge, M.J.and Cooke c. (1983). Efects of previeng difficults short Stories on low ability
junior higy school students Compration, realland Attitudes,18(3), Greaney, V. and Hegarty, M. (1987).
Correlates of leisure-time reading. Journal of Research in Reading, 10: 3–20. Doi: 10.1111/j.1467-9817.
1987.tb00278.x Greene, B. (2001) “Testing Reading Comprehension of Theoretical Discourse with
Close” Journal of Research in Reading. Owusu-Acheaw, Micheal, ‘’Reading Habits Among Students and
its Effect On Academic Performance A study of students.

Heatan, J.B. (1990) writing English anguge Tests, Landon: Long man Heathington, B.S. and Alexander,
J.E. (1984). Do Classroom Teachers Emphasize Attitudes Toward Reading? The Reading Teacher, 37,
484-488.

Heaton, J.B. (1990). Writing English Language Test. London: Longman.

Heilman, A.W. Blair, T.R., and Ruphley W.H. (1998). Principles and Practices of Teacing Reading.(9th
Ed.). New Jersy prints Hall Inc.

Hittle man, D.R. (1988) Developmntal Reading.k-8; Teaching from a Whole Language Prespective.
Columbus: Merrill publishing company.

http://digital commons.unl.edu/libphilpral/1130.

Issa. A. O., Aliyu, M. B., Akangbel, R.B.& Adedeji, A.F. (2012) Reading Interest and Habits of the
Federal Polytechnic Students, International of Learninge & Development.vol.2, No.1.pp 470-486.

Kulik, A.J. and Kulik C.C. (1982). Effects of Ability Grouping on Secondary School Students: A Meta-
analysis of Evaluation Findings.American Educational Research Journalaer.sagepub.com. Doi:
10.3102/00028312019003415. Am Educ Res J September 21, 1982 vol. 19 no. 3 415-428 University of
Michigan.

Kush, J.C, and Watkins, M.W. (1996). Long –Term Stability of Children's Attitudes Toward Reading.
[Eelectronic Version]. The Journal of Educational Reserch.

Lena S.and, Karin T. ( 2007). Influences of Family Based Prerequisites, Reading Attitudes, and Self-
Regulation onReading Ability.Contemporary Educational Psychology, v32 n2 p206-230 Apr 2007
Journal of Atricles; Reports – Research.

Lenas.s.and T. (2007). Infiuences of family Based prerequisites, Reading Attitudes, and Self-Regulation
on Reading Ability. Contemporary Educational psychology,32 (2),206-230 JOrnal of Atricels; Reports-
Research.

Logna, S., and Johnston, R. (2009). Gender Differences in Reading Ability and Attitudes:
Examining where these differences Lie. Jornal of Research in Reading, V32 n2 P199-214 May 2009.

Lorene, W.C., (2010). ‘‘Secondary Students' Reading Attitudes and Achievement in a scaffold Silent
Reading Program Versus Traditional Sustained Silent Reading.’’ProQuest LLC, Ph.D. Dsessertaion,
Auburn University.

Lynn, H.W. (2010). Difference between third, forth, and fifth Grade students' attitudes to ward reading in
relation to community size. Master of education (MED), Bowling Green state Universty, reading 2010.

Madsons, H.S. (1983).Teachniques in Testing. Newyork: Oxford Universty Press.

Martinez, R.S., Tolga, A.o, and Jermy, J. (2008). Influence of Reading Attitude on Reading Achievement:
A Test of the Temporal Interaction Model. Psychology in the schools, v45 n10 P1010-1022.Dec.2008.

May, B.F. (1990). Reading as Communication: An Interactive Approach. (3rd Ed.). U.S.A:

Macmillan Publishing Company.

McCarthy, C. (1999). Reading theory as a microcosm of the four skills.The Internet TESL Journal, 5(5).

Mckenna, M.C., Kear, D.J., and Ellsworth, R.A., (1995). Children’s attitudes to woard reading.A national
survey.Reading research quarterly.Retrieved on 01/08/2011 09:59.From http:// WWW.jstor.Org
/stable/748205.

Muller, D.L., (1973). Teacher Attitude Towards reading.Journal of Reading. 17, 202-205.

Myers, G.D. (1999). Social Psychology.(6th Ed).The McGraw-Hill Componies, Inc.

Nancy, W. (1989).Developmental relationships between Students’ attitudes Toward reading and Reading
Achivement in Grades 1 through 8. Page 95, Education Specialist Thesis, Universty of Northen Iowa.

Nelson, H. (1963). ‹‹ overcoming Reading Deficiencies at the college level.’’Journal of Developmental


Reding Vol.6, pp .238.

Norton, D.E. (1997). The Effective Teaching of Language Arts. (5th Ed.). New Jersy: Prentice Hall Inc.
Nunan, D. (1991). Language teaching methodology: A textbook for teachers. Prentice Hall Nuttall, c
(1982).Teaching Reading skill in foreign language London: Heinemann Educational Book Ltd.

Ormrod, J.E. (2008). Human learning.Fifth Edition. New Jersey: Upper Saddle River.

OWUSU-Achewa, Micheal<<Reading Habits Among Students and its Effecton Acadeic Performance:
AstudyOf Students of Konforidua poly technic>> /2014/. Library Philosophy and Practice (e-
Journal).paper 1130.

Palani, K.K. (2012) Promising Reading Habits and Creating Literate Social.International Reference
Research Journal.vol. (1) Issue2(1) pp1.

Perfetti.C.A. (1985).Reading Ability. Oxford: oxford University press.

Ransbury, M.K. (1973). An Assesment of Reading Attitude. Journal of Reading, 17,25-28.


Rasinski, T., and Padak, N, (1996). Holistic Reading Strategies Teaching Children Who Find Reading
Difficult. Prentice Hall, Inc.

Roe, B.D., and Smith, S.H., (2005). Teaching reading in today's middle schools, Houghton Mifflin
Company.

Rrowell, G.C., (1972). An Investigation of Factors Related to Change in Attitude Toward Reading. 972-
73* Vol.5, No.4, Fall.

Sallabas, M.E., (2008). Relationship between 8th Grade Secondary School Students' Reading Attitudes
and Reading Comprehension skills. Journal of the Faculty of Education.V01, 9, Issue.16 (fall 2008).141-
155. Retrived on http://WWW.web. Inonu. Edu.tr/ efdergi/ sayi 16/08-Rn.pdf.

Schmitt, E. (2009). ‘‘Four Case studies: The reading Attituds and Practices of Teachers and students
Grade’’.Thesis, Master of Education in Reading, The graduate College of Bowling Green State Universty.

Sheng, H.S. (2000). ``Acognitive Model for Teaching Reading comprehension`` English Teaching
forum.Vol.38, No.4, October.

Simith, f. (1978) Reading Cambridge: Cambridghe Unviersity press.

Skinner, C.E., (1998). Educational Psychology.(4th Ed). Prentice-Hall, Inc.

Spiegel, D.L. (1994). A Portrait of Parents of successful readers. In E.H. NewYork, DE:

International Reading association.

Steven, A. (1993) Assessing EFL Reading Comprehension.

Teremotit, J. (1995) ‘’Improving Junior College Reading Programs.’’ Theodore S.K. (2010). Reading
Achievement, Attitudes towards, Reading and Reading Self-Esteem of Historically Low Achieving
Students Journal of Instructional Psychology, v37 n2 p184-188 Jun 2010.Journal Articls; Reports –
Research.

Thraves, P., (2010). "An Investigation into Students' Reading Attitudes and Habits Using a Children's
Literature Intervention Programme" CPUT Thesis and Dissertations.Paper 296.
http://dk.cput.ac.za/td_cput/296 Tindale j.c. (2003) Assessing Reading.cambridge Unviersity Cambridge
university press.

Vacca, R.T. And Vacca, J.L., (1999). Content Area Reading Literacy and Learning across the
Curriculum. (6th Ed). Long Man.

Webb, H.L., (2009). The Relationship between African American Middle School Students' attitudes
toward Reading and their Reading Comprehension Level’’. Proquest LLC, Ed.D. Unpublished
Dissertation, the University of Memphis.

Wie (2006) Gender Difference in Reading Comprehension for Chinese Secondary School Students.
Aseminar Paper Resarch Retraved on 20-05-2012, fromhttp://mindsMaster of science in
education.unpublisher theis, the faculityUniversity of wis consin-piatteville.
Wie (Veronica) (2009). Gender Difference in Reading Comprehension for Chinese Secondary School
Students.A Seminar Paper Research.Master of Science in Education.Unpublished Thesis.The Graduate
Faculty Universty of Wisconsin-Platteville.

Wigfield, A., Guthrie, J. T., Tonks, S., & Perencevich, K. C. (2004). Children's motivation forreading:
Domain specificity and instructional influences. Journalof Educational Research, 97, 299-309.

Yaacov, P. (2010). A Meta- Analysis of the Relationship between Student Attitudes towards Reading and
Achievement in Reading. Journal of Research in Reading, v33 n4 P335-355 Nov 2010.

Zelalem Berhanu. (2010). The Reading Attitudes Preferences and Habits of First Year Bahir Dar
Universty Studentes with Particular Reference to The faculty of Humanities.Unpublished Master’s
Thesis. Humanities Faculty, Bahir Dar Universty.

Zoitan Dorney. (2001). Resrch methods Applied Linguistics. Oxford Universty press.

አባሪ

የዘጠነኛ ክፍል ተማዎችን የማንበብ ልምድ ለመለካት የቀረበ መጠይቅ

ውድ ተማሪዎች፤ የዚህ መጠይቅ ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ልምድና አንብቦ መረዳት ችሎታ
መካከል ያለውን ተዛምዶ በመርመር ለሚሰራ ጥናት መረጃ ማስገኘት ነው፡፡ በመሆኑም ከመጠይቁ የሚገኘው መረጃ
ለጥናቱ ግብ መምታትወሳኝ በመሆኑ መጠይቁን በጥንቃቄ በመሙላት እንድትተባበሩኝ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
ሰለትብብራቸሁ ከልብ አመሰግናለሁ!

መመሪያ፣ ከዚህ በታች የተሰጡት ዓረፍተ-ነገሮች እያንዳንዳቸው አራት አራት አማራጮች አሏቸው፡፡ ከተሰጡት
አማራጮች መካከል የምትስማሙበትን የ(X) ምልክት በማድረግ አመልክቱ፡፡ መግለጫዎቹ ከ 1-5 ባሉ ቁጥሮች
ተወክለዋል፡፡ የማንበብ ልምድን የሚመለከቱ መግለጫዎችን ታገኛላችሁ የቀረቡትን ዝርዝር መግለጫዎች
አንብባችሁየምትስማሙበትን ከቀረቡት አማራጭ መልሶች ግርጌ ይህን (X) ምልክት በማድረግ አመልክቱ፡፡ ከ 1-5
የተመለከቱት ቁጥሮች ውክልና ቀጥሎ በቀረበው መሰረት አማራጮቹም፤

1.በጭራሽ አልስማማም 2.አልስማማም


3. በመጠኑ እስማማለሁ 4. እስማማለሁ
5.በጣም እስማማለሁ

ሃሳቦች የስምምነት ደረጃዎች 1 2 3 4 5

1 ጥሩ የማንበብ ልምድ ስላለኝ በማንበቤ እደሰታለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)


2 ጥሩ የማንበብ ልምድ አለኝ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
3 የሚያዝናናኝን መጽሀፍ ለመምረጥ ባለኝ ልምድ እተማመናለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
4 የማነበውን መጽሀፍ ለመምረጥ የማንበብ ልምዴ ለኔ አስፈላጊ ነው፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
5 የማንበብ ልምዴን የቤት ስራየ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
6 ወላጆቸ በማንበብ ልምዴ ይደሰታሉ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
7 ቤተሰቦቼ የማንበብ ልምዴን ያበረታታሉ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
8 ሰለአነበብኩት ነገር ከቤተሰቦቸ ጋር እወያየለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
9 በየትኛውም የክፍል ደረጃ የማንበብ ልምድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
10 ለአማርኛ ትምህርት የማንበብ ልምድ አስፈላጊ ነው፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
11 ትምህርት ቤት የተማሪዎች የንባብ ልምድ ለመምህራን ጠቃሚ እንደሆነ (1) (2) (3) ( 4) (5)
አምናለሁ፡፡
12 በትምህርት ቤት ያለ የተማሪዎች የንባብ ልምድ ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር (1) (2) (3) ( 4) (5)
ጠቃሚ ነው ብየ አምናለሁ፡፡
13 በልጅነቴ በነበረኝ የማንበብ ልምድ እደሰት ነበር፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
14 በእድሜ ከፍ እያልሁ ሰሄድ ለንባብ ያለኝ አመለካከትና ፍላጎት እያደገ መጥቶአል፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
15 መምህራን የእኔ የማንበብ ልምድ እንዲያድግና እንዲዳብር ጥሩ ስራ ሰርተዋል፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
16 አብዛኞቹ ጓደኞቸ የአማርኛ መፃሀፍትን በማንበቤ ይደሰታሉ ብየ አምናለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
17 የማንበብ ልምዴ ከአመት እስከ አመት እያደገ መጥቶአል፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
18 ለንባብ ልምድ የምሰጠው አስተያየት በጣም አነስተኛ ነው፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
19 በአማርኛ የተፃፉ መጽሀፍትን ለማንበብ ሁልጊዜ የምነሳሳው በቤተሰቦቸ ግፊት (1) (2) (3) ( 4) (5)
ነው፡፡
20 ከማንበብ ልምዴ አንፃር ብዙ ጊዜ ለማንበብ የምመርጣቸው መፃሀፍት ሳይንሰ (1) (2) (3) ( 4) (5)
ነክ ናቸው፡፡
21 ለንባብ የምመርጠው መጽሀፍ የለም፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
22 አንድን ርእስ ማንበብ ጀምሬ ንባቤን ሳልጨርስ አላቋርጥም፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
23 ያነበብኳቸውን መጻሀፎች ታሪክ ለጓደኞቸ መነገር ያስደስተኛል፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
24 ሌሎች በአማርኛ ሰለተፃፉ መፃህፍት በሚያወሩበት ጊዜ በአማርኛ የተጻፉ (1) (2) (3) ( 4) (5)
መጽሀፍትን የማንበብ ፈላጎት ያድርበኛል፡፡
25 ሁሉም ሰው ስለምንባብ የፈለገውን ቢናገር ለንባብ ያለኝ ፍላጎት አይነሳሳም፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
26 መፅሀፍ ለማንበብ ያለኝ ፍላጎት ከፍተኛ ነው፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
27 ንባብን ተግባራዊ የማደርገው በመምህሬ ትዕዛዝ ብቻ ነው፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
28 በክፍል ውስጥ ንባብ ሲኖር ቀድሜ ማንበብ እወዳለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
29 ንባብ ከማንበብ ይልቅ የሌሎችን ወሬ ማዳመጥ እመርጣለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
30 ማንበብ የማዘወትረው በርካታ ችግሮች ለማምለጥ ነው፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
31 መፅሀፍ ባይኖረኝም ከጓደኞቸ ተውሸ አነባለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)
32 አንብቤ የጨረስኩትን መጽሐፍ እደግማለሁ፡፡ (1) (2) (3) ( 4) (5)

You might also like