You are on page 1of 3

አንድ ሽ ማዕልት

የአመጋገብ የክትተል ተግባር ውጤት


ለእድሜ ዘመን ብሩህ ህይዎት
ወሳኝ ጊዜ ወሳኝ እለት
አንድ ሽ ማዕልት ወለሊት፡፡
በፈጣሪ የአፈጣጠር ጥበብ ኡደት፤
ካለመኖር ወደ መኖር ህያውነት፤
በዘጠኝ ወር መቃረብያ በማህጸን አለምነት፤

የአባት እናት ዘር ፍንካች፤


ሲጠነሰስ የሰውነት ውጥን ሂደት፤
ከስጋዋ ስጋ ከአየር እስትንፋሷ፤
ከእለተ መቁንኗ ከማዕደ ህብስቷ፤
ከሴትነት ወጓ ከእናትነት ጥጓ፤
አጋርታ እና አካፍላ በገመደ እትብቷ፡፡

በጊዜ ባለቤት በዘመን አለቃ በዘመናት ዳኛው፤


ቀናት ተሰድረው ሳምንት ሳምንት ሁነው፤
ሰንብተው ሰንብተው - ቆይተው ቆይተው ወራት አስቆጥረው፤
በማህጸን ውስጥ እድሜ - ጽንስን አሳድጎ፤
የሰውነት ቅርጼን እንድይዝ አድርጎ፡፡

የወራተ ዘጠኝ የእናት ሆድ ኩንትራት፤


ደርሶ ሲጠናቀቅ የማህጸን ጫጉላ የውል ስምምነት፤
ሲቀየር ሂደቷ የተፈጥሮ ህጓ፤
የምጥ ጣር ህመሟ የፅኑ ድካሟ፡፡
የልጅ መሽራዋን የአለም ላይ ንጉሷን፤
የብስራት አዋጁን ስሰማው ልቅሶየን፤
እረሳቸው ምጧን አነሳች ህጻኗን፤
ስታየው በአየኗ አይኔን፤
የወራት ድካሟን የስቃይ ደስታዋን፤
ለአምላኳ አቀረበች የእነባ መሥዋዕቷን፡፡
የተፈጥሮ ምጥን ወተት - ከጋቷ ምንጭ ከሚፈልቀው፤
ሳትጨምር ሳትሳንስ ሳትሰልስው፤
በእናትነት ፍቅሯ አቅፋ፤ደግፋ ፤
በማይነጥፈው ወዟ አውዳ አቅፋ፤
እስከ ጊዜ መንፈቅ ጡቷን ብቻ አጥብታ፤

ከእንቁላል ከስጋው ከምጥን አጥሚቱ፤


ከሴሪፋም ፋፋው ከእንጀራ ፍትፍቱ፤
ከስጋ ቅጠሉ ከማር ከወተቱ፤
ከጥሬ ዶቄቱ ከገንፎ አትክልቱ፡፡

ከጓሮ ሸምጥጣ ከገብያ ሸምታ ቀምማ አዘጋጅታ፤


ጨመራ ሰልሳ አብስላ አሰናድታ፤
በደቂቃ ክፍተት በስዓት ልዩነት፤
መግባ መግባ አብልታ አጠጥታ፤
በሥርዓተ ጾታ በአባትነት ድጋፍ፤
በእናትነት ጥረት ድካምና ልፋት፡፡
በእለታት ጥርቅም፤ በዕለታት ስብስብ፤
በሰቆጣ ኪዳን - በተቀመጠው ግብ በቀናተ
ገደብ፤
በሽ ቀናት ማዕልት ወለሊት፤
ይሄው በቃሁ ለአካል እና አእምሮ እድገት፤
ለእድሜ ዘመን ብሩህ ህይዎት፡፡

እማ…… አንቺ……….
አንቺ የኔ አካፋይ - ከነፍስ ከስጋሽ፤
እኔ የአንቺ - የአንድ ሽ ቀን ግንባታሽ፡፡
የእድሜ ዘመን ትሩፋትሽ - ሞልቶ ይፍሰስልኝ፤
ሽ አመት ኑሪልኝ - ሽ እንደገነባሽኝ፡፡
ከእንዳለ ደጉ
በንጹህ ኢትዮጲያ
የሰሜን እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞናል አድቫዘር ፤ ሚያዚያ 17/2011 ዓ.ም

You might also like