You are on page 1of 1

ነገረ ሃይማኖት

1. ነገረ ሃይማኖትን የማጥናት ዓላማ እና ጥቅም


2. ሃይማኖት ምንድን ነው
 ሃይማኖት እግዚአብሔር ራሱን ለሰው ልጅ የገለጠው መግለጥ ነው
 እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ያሳየበት መንገድ፣ የሰው ልጅ ሊቀበለው በሚችለው መጠን ስለ ራሱ
ማንነት ለእኛ የገለጠው እውነታ ነው
 “የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። ግን እርሱ የእውነት
መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል” እንዳለ፡፡ ዮሐ. 16፡12-13
 እግዚአብሔር አንድ ስለ ሆነ፣ ባሕርዩም የማይለወጥ ስለ ሆነ፣ ሃይማኖት (ይህ አምላክ ስለ ራሱ
የገለጠው መግለጥ) አንድና የማይለዋወጥ ነው፡፡ ስለዚህም ሊኖር የሚችለው እውነተኛ ሃይማኖት
አንድ ብቻ ነው፡፡
 እግዚአብሔር የሚገልጠው እውነት (ሃይማኖት) በሰው መቀበል ወይም አለመቀበል ላይ
የተመሠረተ አይደለም፤ ምን ጊዜም እውነት ነውና፡፡“ባናምነው እርሱ የታመነ ሆኖ
ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና” እንዳለ፡፡ 1 ጢሞ. 2፡13
 “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ለዚህ ነው፡፡ ኤፌ. 4፡5
 ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ
ግድ ሆነብኝ” በማለት ሃይማኖት አንድ ጊዜ ከእግዚአብሔር ለቅዱሳን የተሰጠ መሆኑን በአጽንዖት
ገልጿል፡፡ይሁዳ 3
 “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፣ ሩጫዬን ጨርሼያለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄያለሁ”
በማለት፤ እንደዚሁም “እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር
ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ” በማለት ሃይማኖትን መጠበቅ
እንደሚገባ በጽኑ አሳስቧል፡፡ 2 ጢሞ. 4፡7 ዕብ. 4፡14
እምነት
 እምነት እግዚአብሔር የገለጠውን እውነት (ሃይማኖት) አዎ፣ እውነት ነው፣ ትክክል ነው
ብሎ “አሜን” ብሎ መቀበል ነው፡፡

3. ሀልወተ ፈጣሪ
4. ሥነ ፍጥረት
5. የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ምንጮች

You might also like