You are on page 1of 1

ስራ ፍለጋ

በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ
ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። ልትድን ትወዳለህን? አለው።
ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም
ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ኢየሱስ፦ ተነሣና
አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ወዲያውም ሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።

አንድ ቤተክርስትያን ቁጭ ብዬ በስብከት ሰዓት የዕለቱ ተረኛ ሰባኪ ይህን ክፍል ሲናገር
እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ከስራ ፍለጋ ጋር ተያያዘብኝ፡፡ እስኪ ክፍሉን የታመመውን ሰውዬ
አውጥተን ስራ ፈላጊ ሰውዬ እናስገባበት፡፡ ምናልባት ግን ሌላ ወንጌል እየሰበኩ ከሆነ መልሱኝ፡

ይቅርታ ግን ካጠፋው፤ አንድ ቤተክርስትያን ቁጭ ብዬ የመጣልኝ ሀሳብ ነው የማካፍላችሁ፤


ታሪኩ በዩሀንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ላይ ያለው ሰው ታሪክ ነው፡፡ እኔና ሌሎች ተመራቂዎች
ባለሁበት ሁኔታ ሲቀየር

“በዚያም ከሆነ ጊዜ ጀምሮ ስራ ያልያዘ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥
እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ። “ስራ ልትይዝ ትወዳለህን? አለው” ።
ስራ ዕጡም “ጌታ ሆይ፥ መንግስትና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ በሀገሪቱ ላይ ባናወጡ
ጊዜ በድርጅታቸው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው (ዘመድ) የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ
ሌላው ቀድሞኝ ይቀጠራል” ብሎ መለሰለት። ኢየሱስ፦ ተነሣና ሲቪህን ተሸክመህ ሂድ አለው።
ወዲያውም ሰውዬው ተነሳ ሲቪውንም ተሸክሞ ሄደ።”

በዚህ ጊዜ ያለ ዘመድ ስራ ማግኘት እጅግ ከባድ ነው፡፡ ካንተ በውጤት የሚያንስ፤ ግቢ


በነበራችሁ ቆይታ አንተ ላይብረሪ ስትመላለስ እሱ ግን ፈታ ሲል የነበረ እና ደግሞ ስንት ጊዜ
አጥና ብለሀ የመከርከው ሰው፤ በግሬድ ጭራሽ የማትገናኙ ሆናችሁ ሳላችሁ እሱ በወጣ
በጥቂት ጊዜው ስራ ሲይዝ አንተ ግን እስካሁን ሲቪ ኮፒ እያደረክ ላይ ታች እየዳከርህ ስራ
እየፈለክ ነው፡፡ ዘመድ ካለህ በመስሪያ ቤቶች ሆነ በድርጅቶች መንገድ አለ፤ ካልሆነ ላም አለኝ
በሰማይ እያልክ መኖር ነው፡፡ ግና ክርስትያንም እንደ ዓለማውያን በዘመድ አለኝ ወይስ የለኝም
ጭንቀት መወጠር የለበትም፡፡ ኢየሱስ ከዘመድ በላይ ነው፡፡

You might also like