Professional Documents
Culture Documents
(Repaired Final)
(Repaired Final)
1 የሰውነት ልክ መውሰድ
/Take Body Measurements/ TXT BAP1 02 0311 15 hrs
2
መሰረታዊ የልብስ ፓተረን ማዘጋጀት፣ጨርቅ
TXT BAP1 02-04 70 hrs
ማንጠፍ፣ምልክት ማረግ፣መቁረጥ እና መቀንጨብ
0315
/ Prepare Basic Pattern for Apparels, Lay,
Mark, Cut and Bundle Simple Fabrics /
3 የስፌት ማሽን ማዘጋጀት እና መጠገን
/Prepare and Maintain Sewing Machines/ TXT BAP1 06 0315 30 hrs
1. ለደህንነት የጥንቃቄ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ ሳጥን - ግራሶ
የማሽን ዘይትና ቅባት - መጥረጊያ
መወለልወያ - ሳሙና እና ሌሎች
2. ለፓተርን ሥራ የሚያስፈልጉ
የፓተርን ወረቀት - እስፒልና የስፒል ማስቀመጫ
A3 ወረቀት - መረሰሻ (tracing wheel)
A4 ወረቀት - እርሳስ፣ ላጵስና መቅረጫ
ማስመሪያዎች - ማርከር የተለያ ቀለም
ፍሬንች ከርቭ - ማግነት
የዳሌ (ጎባጣ) ማመሪያ - ነጭ ሠሌዳ (የማይበን ጠመኔ)
ሴት ስኩዊርስ - ጠረጴዛ
ባለ 50 ሳ.ሜ እና ባለ 1 ሜትር ማመሪያ - መቀስ የወረቀት መቁረጫ
ማታወሻደብተር
3- ለስፌት የሚያስፈልጉ
የስፌት ማሽን
ባለ አንድ መርፌ የስፌት ማሽን (Single needle m/c
ኦቨር ሎክ ማሽን (Over lock sewing m/c)
መዘምዘሚያ - መርፌ የእጅና የማሽን
ቁልፍ መትከያና መቁረጫ - ክር የጥልፍና የስፌት
ልዩ ልዩ መፍቻ - ቀፎና እንዝርት
ፒንሳ - መተርተሪያ
ጨርቅ - ቁልፍ
ምልክት ማድረጊያ የተለያየ ቀለም ያላቸው የልብስ ጠመኔዎች
ልዩ ልዩ መቀሶች (መቁረጫ፣ ቅርፅ ማውጫ፣ መቀንጨቢያ)
ባለ 150 ሳ.ሜ ፕላስቲክ ሜትር (tape measure)
ስታንዳርድ የሰውነት ልክ ሠንጠረዥ (standard chart)
የሰውነት ሞዴል (dummy) - እስፒል - ዚፕ
ገበር (lining) - የልብስ መስቀያና የቁም ሳጥን
ማድረቂያ (enter lining) - የፊት መስተዋት/ሙሉ ቁመት ያለው/
ካውያና መተኮሻ ጠረጴዛ (iron/Steam Iron and ironing board)
3- የጥንቃቄ ደህንነት ሕግጋት
የአሰራር ጉድለት
የስራ ቦታ ምቹ አለመሆን ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በአደጋው መንስኤ ሠራተኛው /ግለሠቡ/ ከአካለ ጐደሎነት እስከ ህይወት ማጣት የሚያደርስ ሊሆን
ይችላል፡፡ አደጋው በራሱ፣ በቤተሰቡም ሆነ በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ በአደጋው ከሚከሰቱ
ችግሮች ጥቂቶቹ፣
የቤተሰብ መበተን፣
አምራች ኃይል /ዜጋ/ ማጣት፣
የንብረት ውድመት እና ፣
የስራ ውጤት ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡
በኢንዱስትሪ ውስጥ አደጋ የሚደርሰው በአብዛኛው ሥራ የሚሠራው በዘመናዊ መሣሪያ እየታገዘ ቢሆንም
በጥንቅቄ ጉድለት የከፋ አደጋ ሊደርስ ይችላል፡፡ ያም በስራ ወቅት በሚፈጠር ቸልተኝነት ወይም
መዘናጋት በቀላሉ ለአደጋ የሚያጋልጡ በኤሌትሪክ የሚሰሩ ማሽነሪዎች ላይ ጥንቃቄ ካለመድረግና ትኩረት
ማነስ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ይሻል፡፡ ለአደጋ ከሚያጋልጡ መንገዶች ጥቂቶቹ፣
የስራ ቦታ አጠባበቅና አያያዝ ጉድለት
የአሰራር ዘዴ ጉድለት
የስራተኛው ስህተት /የግል ጥንቃቄ ጉድለት/
መሣሪያው በሚገባ አለማወቅና የአጠቃቀም ችግር ናቸው፡፡
ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በመደርደሪያችን ከታችኛው ክፍል ቀላል የሆኑትን ደግሞ ከላይኛው
የመደርደሪያ ክፍል በማስቀመጥ፣
የኤሌክትሪክ መስመር በኮርኒስ ውስጥ ወይም በመሬት ውስጥ ለውስጥ መዘርጋት ይኖርበታል፣
የደንበኛ ፍላጐት መግለጫ ደንበኛ ልብስ ለማሰፋት መጥቶ የሠጠው ትዕዛዝ መሰረት ተመዝግቦ
መሰራት አለበት፡፡
የጨርቅ ዓይነት - ለምሣሌ የጥጥ፣ የሱፍ ወዘተ… በደንበኛው ምርጫና አቅም መሠረት
መወሰን፣
በየቀኑ ሳይሆን በተወሰነ ወቅት ግራሶ የሚያስፈልግበት ቦታ መቀባባት፡፡ ለምሣሌ የእግር ፔዳል
ወዘተ
ሀ/ ለሸሚዝ ለ/ ለኮት
1. ሜትር (Tape Measure):- ይህ የመገልገያ መሣሪያ የሚሠጠን ጥቅም የምንሠራው ሥራ የራሱ የሆነ
መጠን ስለሚኖረው ያንን መጠን መያዘ አለመያዙን ለመለካት የሚረዳን የመሣሪያ አይነት ነው፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
የሚያገለግለው ሰውነትን ለመለካት ሴሆን፡፡ የሚሰራው ጠንከር ካለ ሴንቴቲክ ፋይበር ሲሆን ርዝመቱ
150 ሴሜ ርዝመት ወይም 60 ኢንች ነው፡፡
3. ኮምፓስ (Compass)፡- ይህ መሣሪያ ሁለት እግሮች ሲኖሩት በአንደኛው እግር ላይ ለእርሳስ መያዣ
የሚሆን ቀዳዳ ያለው እና በሁለተኛው ላይ ሹል ቀጨን መርፌ መሳይ ብረት አለው፡፡ ይህ
የሚያገለግለውም ክብ የሆኑ ሥዕሎችን ለመሥራት ነው፡፡
4.
ማከፈፋፈያ (Divider)፡- ይህ መሣሪያ እንደ ኮምፓስ ሁለት እግሮች ያሉት ሲሆን የሚለይበትም
በሁለቱ እግሮች ጫፍ ላይ ሹል የሆኑ ብረቶች ስለአሉት ብቻ ነው፡፡ የሚያገለግለውም ርቀቶችን
ለክቶ ወደ ሌላ ቦታ ለማስተላለፍ መስመሮችን ወይም አንግሎች እኩል ለማከፋፈል ነው፡፡
5. ሦስት መዕዘን ቅርጽ ያለው መሣሪያ (Try-Square):- ይህ መሣሪያ ሦስት ቀጥታ በሆኑ
መስመሮች የተገጣጠመና ሦስት አንግል ያለው ሆኖ ሁለት ዓይነት አለው፡፡ አንደኛው 90 ዲግሪ፣60
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
ዲግሪና 30 ዲግሪ የሆኑ አንግሎች ሲኖሩት ሁለተኛው ደግሞ 90 ዲግሪና 45 ዲግሪ ያለው ነው፡፡
መሣሪያው የሚያገለግለው ከላይ የተገለጹትን አንግሎችንና ቀጥታ መስመሮች ለመሥራት ነው፡፡
7. ጠመዝማዛ ቅርጽ ያለው ማስመሪያ(French Curve)፡- የዚህ ዓይነት መሣሪያ የተሠራው ክብና፣
የተለያየ ቅርጽ ያላቸውና ጠመዝማዛ የሆኑ መስመሮች ለመለካትመሳል ያገለግላል፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
8. የተጣመመ ቅርጽ ያለው ማስመሪያ (Curved Stick)፡- ይህ መሣሪያ ከፕላስቲክ ወይም ከእንጨት
የተሠራ ሲሆን የሚያገለግለው ብዙ ከርቭ በሚያስፈልገው ቦታ ላይ ለማስመር ይጠቅማል፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
10. ማስመሪ (Transparent Ruler)፡- ከፕላስቲክ ወይም ከእንጨት የተሠራ ሊሆን ይችላል፡፡ አገልግሎቱም
ቀጥ ያሉ መስመሮችን ለማስመር ይጠቅማል፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
11. T - ቅርጽ ያለው ማስመሪያ (T_Square) ፡- ከእንጨት ወይም ከፕላስቲክ የተሰራ ሆኖ ቀጥተኛ የሆነ
መስመር ያለውና በ 90 ዲግሪ ከሌላ ቀጥተኛ ከሆነ እንጨት (ፓላስቲክ) ጋር በብሎን የተገጣጠመ ነው፡፡
የሚገለግለውም ቀጥታና (አግድመት ) ትይዩ መስመሮችን ለማስመር ነው፡፡
12. መቀስ (Siscors) :- መቀስ በልብስ ስፌት ስራ ለፓተርን ወረቀት መቁረጫ፣ የሚሰፉ ጨርቆችን
ለመቁረጥ፣ ዝግዛግ በመቁረጥ ለማስገጥ እና ከስፌት በኋላ ትርፍ ክሮችን በመቁረጥ ጥራቱን ለማስጠበቅ
ያገለግላል፡፡
የልጆች ልብሶች አንድ ሱሪና ሸሚዝ ለወንድም ለሴትም በአንድ ዓይነት መስራት ሲቻል የቁልፍ መትከያና የቁልፍ ቀዳዳ መስሪያዎችን ብቻ
ማለዋወጥ በቂ ነው፡፡ ስለዚህ ለወንድና ለሴት ብሎ መከፋፈል አስፈላጊ አይደለም፡፡
የተሰራው የሰዓት ክፍፍል በቀን 7 የስራ ሰዓታት ታሳቢ በማድረግ ስለሆነ ማሳጠርም ሆነ ማስረዘም የሚወሰነው በጊዜ አጠቃቀም ይወሰናል፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
1. የመርፌ ዘንግ (Needle bar)፡- በጭንቅላቱ በስተግራ በኩል የሚገኝና ወደላይና ወደታች የሚል መርፌውን
የሚይዝ ነው፡፡
2. የመርገጫ ዘንግ ማሽን (Knee lift)፡- ከመኪናው ጠረጴዛ በታች (በሥር) በኩል የሚገኝና በጉልበት
በመጠቀም የመርገጫውን ተሸካሚ ብረት (ዘንግ) ለማንሳት የሚያገለግል ነው፡፡
3. የክር ማስገቢያዎች (Thread guids)፡- ክሩ ወደ መርፌው በትክክለኛ አቅጣጫ ተስተካክሎ እንዲሄድ
የሚረዱ ክብ ቀዳዳና ጠፍጣፋ ሆነው የተሠሩ ብረቶች ናቸው፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
4. የክር አቀባይ መወጠሪያ ሊቨር (Thread Take-up lever)፡- ወደላይና ወደታች የሚንቀሳቀስ በጭንቅላቱ
ላይ በስተግራ በኩል የሚገኝና ለመርፌው ክር በማቀበልና በመወጠር የሚያገለግል ነው፡፡
5. የእጅ ፑሊ (Hand wheel)፡- በመኪናው ጭንቅላት ላይ በስተቀኝ በኩል የሚገኝና በችንጋ አማካኝነት
የተላለፈውን እንቅስቃሴ በመቀበል ወደ ሌሎች የመኪናው ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሚያስተላልፍ ነው፡፡
6. መወጠሪያና ማስተካከያ ዳዶ (Tension regulating nut)፡- በመወጠሪያዎቹ ፊት ለፊት የሚገኝ ክብ
ብረትና በውስጡ ጥርስ ያለው ሲሆን ሞላውን በመጫንና በመዘርጋት መወጠሪያዎቹ ላይ ግፊትን
ለማስተካከል የሚረዳ ነው፡፡
7. የእንዝርት ማጠንጠኛ (Bobbin thread winder)፡- በጭንቅላቱ በስተቀኝ በኩል ከመኪናው ጠረጴዛ ላይ ወይም
ከጭንቅላቱ ጋር በቢቴ (ብሎን) የተገጣጠመ ሲሆን ትንሽ የሚሽከረከር ፑሊ አለበት፡፡ ከፑሊ ጋር አንድ ላይ የሚሽከረከር
እንዝርት እንዲያስገባ ሆኖ የተሠራ ዘንግ አለው፡፡ በእንዝርቱ ላይ ለማጠንጠን በመጀመሪያ የክሩን ጫፍ በእጅ
መጠምጠም ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ፑሊውን ወደችንጋው በመግፋት ወይም በማስጠጋት እንዲያጠነጥን
ያደርገዋል፡፡
8. ችንጋ (Belt)፡- ከትልቁ ፑሊ ወይንም ከሞተሩ ጋር ከተያያዘው ፑሊ የሚወጣውን ወይም የሚገኘውን
እንቅስቃሴ ወደላይኛው (የእጅ ፑሊ) የሚያስተላልፍ ነው፡፡
9. እንዝርት (Bobbin)፡- ከታች በኩል ለሚወጣው ክር መጠቅለያ የሚሆን አነስተኛ አካል ነው፡፡
10. የእንዝርት ቀፎ አቃፊ (bobbin case holder)፡- በመኪናው ጭንቅላት ላይ በታች በኩል በሚገኘው
አግዳሚ ተሽከርካሪ ዘንግ (Shaft) ላይ የሚገኝ ቀፎውን የሚይዝ ነው፡፡
11. የእንዝርት ቀፎ (Bobbin case)፡- እንዝርቱን የሚይዝና የተጠቀለለውን ክር ጫፉን በስንጥቁ በኩል
ለማውጣት እንዲችል ተደርጐ የተሠራ ነው፡፡
12. መጋቢ ጥርስ (Feed deg)፡- በጭንቅላቱ መሠረት ላይ (Bed of the machine) የሚገኝ ክፍል ሲሆን
መኪናው በሚንቀሳቀስበት ጊዜ የሚሠፋውን ጨርቅ ለመጐተት የሚረዳ ነው፡፡
13. የመርፌ መያዣ ብሎን (Needle clamp screw)፡- በመርፌ ዘንግ ላይ የሚገኝና መርፌውን ከመርፌ ዘንግ
ጋር ለማሰር የሚያገለግል ነው፡፡
14. የመርገጫ መያዣ ዘንግ (Presser bar)፡- በጭንቅላቱ በስተግራ በኩል የሚገኝ መርገጫውን እንዲይዝ ሆኖ
የተሠራ ነው፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
15. የመርገጫ መያዣ ዘንግ ማንሻ (Presser bar hand lifter)፡- በጭንቅላቱ በስተግራ በኩል የሚገኝ
የመርገጫ መያዣ ዘንጉን በእጅ ለማንሳት የሚያገለግል አነስተኛ አካል ነው፡፡
16. መርገጫ (Presser foot)፡- ጨርቁን ከመኪናው ጭንቅላት መሠረት ጋር ተጭኖ የሚይዝ አካል
ነው፡፡
17. የስፌት ርዝመት መቆጣጠሪያ (Stitch regulator)፡- የመጋዝ መሰል ጥርሱን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር
የመርፌውን ውግ ርዝመት ለማስተካከል የሚችል አካል ነው፡፡
18. የመጋቢ ጥርስ መስታወት (Needle plate)፡- ከመኪናው ጭንቅላት መሠረት ጋር አንድ ላይ በብሎን
የሚያያዝና ለመጋቢ ጥርስና ለመርፌ ማለፊያ ቀዳዳ ወይም ስንጥቅ ያለው ነው፡፡
19. መወጠሪያዎች (Tension disc)፡- ሁለት ክብ ሆነው የተሠሩ ጠፍጣፋ ብረቶች ሲሆኑ በመካከላቸው
የመርፌው ክር በሚያልፍበት ጊዜ ለመወጠር የሚረዱ ናቸው፡፡
20. የእግር መርገጫ (Pedal)፡- ጠፍጣፋ ሆኖ የተሠራ ብረት ሲሆን እግርን በላዩ ላይ በማስቀመጥ በሰው ኃይል
ወይም በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀሰውን መኪና ፑሊዎች እንዲንቀሳቀሱ የሚረዳ ነው፡፡
21. የክር ማስቀመጫ ዘንግ (Thread stand)፡- የብረት ዘንግ ከመኪና ጭንቅላት በስተቀኝ በኩል የሚገኝና
ጠረጴዛው ላይ በብሎን የታሠረና ክር ለማስቀመጥ እንዲያገለግሉ ሆነው የተሠሩ ብረቶች ናቸው፡፡
ቀጥታ መስመር
1 2 3 4 6 7 8 9
5 10
ዚግዛግ መስመር
1 2 3 4 5
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
3 1.5
0.5 ቁመት 70
ደ+2 4 ወገብ 68
ደ 6
9 10 ዳሌ 100 10 9
ደደደደደደደደ
3 3
1. የጉርድቁመት ስንሰራ የጉርድ ቁመት ሲቀነስ 3 ሲደመር 1 እንወስዳለን
2. የዳሌ ቁመት ለማግኘት ዳሌ ሲካፈል ለ 6 ሲደመር 2 (ዳ/6 + 2)ይሆናል
2 2
3. ወገብ ለማግኘት ወገብ ሲካፈል ለ 4 (ወ/4) + 1 ፔንስ ለፊትም ለኋላም እንጠቀማለን
4. የዳሌ ስፋት ለማግኘት ዳሌ ሲካፈል ለ 4 ሲደመር 1 (ዳ/4 + 1)
5. ከታች ጉርድ እንዲጠብ ከተፈለገ ከዋንወው ስፋት 2 ሳ.ሜ ገብተን ወደ ዳሌ ማስመር
6. የኋላ የዚፕ ሽፋን ከ 1-1.5 ሳ.ሜ ይሆነል፡፡
የስፌት ሥራ
1. ጉርዱን ጠርዝ ኦቨርሎክ ማድረግ
2. የፊትና የኋላ ፔንስ መስፋት መተኮስ
3. የዚፐር መትከያ ቦታ በመተዉ መስፋት
4. መተኮስ
5. ዚፐር መትከል
6. የጎን ስፌት ማጋጠም መተኮስ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
7. ወገብ ማዘጋጀት / ማድረቂያ ከዉስጥ መተኮስ
8. የተዘጋጀዉን ወገብ ጉርዱ ጋር ማጋጠም መተኮስ
9. ግርጌ ማጠፍና መተኮስ
10. የተተኮሰዉን ግርጌ እጥፋት በማሽን ወይም የእጅ ስራ መስራት
11. አግራፍ መትከል እና ሌብል መለጠፍ
12. የተበጣጠሱ ክሮችን ማጽዳት
13. ሙሉዉን አጠቃላይ በደንብ መተኮስ
14. ማጠፍና ማሸግ
ወ/4 ወ/4
ወ/4
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
ምስል ሀ/
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
ምስል ለ/
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
2.5 አ/5
1. የደረት ዙሪያ 100 ደ/5=8 3
2. ትከሻ 40
3. አንገት 38
ደ/5 + 4
4. የፊት ሽንጥ 40 ደ/5 + 1
5. የኋላ ሽንጥ 38 21
ደ/5 + 1
ትከሻ ትከሻ + 1
የአንገት ቁመት ቁመት + 1 የአንገት
ስፋት አንገት/5
በመጀመሪያ ለገበር 5 ለቁልፍ 2 ይሰጣል
የግርጌው ስፋት ከብብት ስፋት ጋር እኩል
ነው፡፡
ከትከሻና ከአንገት ጫፍ ወደታች 2.5 ሳ.ሜ እንወርድና የኋላ የትከሻ ቦታ ላይ ቀንሰን እናስቀምጣለን፡፡
የደረት ኪስ ለመስራት የደረት ስፋትን ለሁለት አካፍለን ከእኩሌታው ወደ ብብት 1 ሳ.ሜ በመግባት የኪሱን ስፋት ደ/10
እና የኪሱን ቁመት ደ/10 + 3 በማድረግ ከደረት መስመር 3 ሳ.ሜ ወደላይ በመውጣት እንሰራለን፡፡
የኋላ የሸሚዝ ሞዴል አሰራር
ስፋቱን ደ/4 + 2 እና ቁመቱ የፊት ሞዴል ተመሳሳይ በማድረግ ጀርባ ላይ ሁለት እጥፋት ከፈለግን የኋላውን የደረት ስፋት
ለሁለት በማካፈል ለእጥፋት መጨመሪያ 5 ሳ.ሜ በመስጠት ከእኩሌታው ወደ ብብት 1.5 ሳ.ሜ በመጠጋት እጥፋት
እናሳያለን፡፡
የፊት የአንገት ቁመት 2.5 + 2.5 = 5 ሳ.ሜ ሲሆን የኋላ አንገት 2.5 ሳ.ሜ ይሆናል፡፡
ለተደራቢ በአንገት በኩል ከ 2.5 ሳ.ሜ በኋላ 9 ሳ.ሜ ለክተን በቀጥታ መስመር ካስቀመጥን በኋላ ከደረቱ ስፋት ወደ
ውጭ 5 ሳሜ እንወጣለን፡፡ ይህም ለእጥፋት የጨመርነውን ለመተካት ነው፡፡
እጅጌ 2 የእጅጌ ክፈፍ
1 1.5
1.5 6
ደ/5 + 4
ደ/10 + 2 1 1 11
ኮሌታ
1
1
4 4
ቁ-6+2
ቁ-6+2
ደ/5 +በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/
1 መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
ደ/5 + 1 አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
2 0.5
2
3 0.5
አ/2 + 1 አ/2 + 1 2
SIZE
የሴት ሸሚዝ
1. የዮክ ተደራቢ ከጀርባ ጋር መግጠምና መሰወር
2. የፊትና የኋላ ክፍል መስፋትና መሰወር
3. ኪስ ማዘጋጀትና መለጠፍ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
4. ፕላነኬት ማድረቂያ መተኮስ ማጠፍና መስፋት
5. ፕላንኬት የቁልፍ ቦታ መስራት
6. ማድረቂያ መተኮስ ኮሌታ ማዘጋጀት
7. የተዘጋጀ ኮሌታ ከሸሚዝ አንገት መትከል ሌብል ማስገባት
8. ፔንስ እጅጌዉ ላይ መስራት
9. እጅጌዉን መትከል
10. ቁልፍ ቀዳዳ መስራትና መትከሌ
11. ከግርጌ በመነሳት እስከ እጅጌዉ አንድ ወጥ ስፌት ማጋጠም ከላይ መደረዝ
12. አምባር ማጋጀትና አምባሩን እጅጌ ላይ መትከል
13. ግርጌዉን መስራት
14. ማፅዳትና መተኮስ
15. ማጠፍና ማሸግ
ምስል ለ/
የፊት ሱሪ ክፍል
የሱሪ ቁመት ቁ - 3 + 1
የመቀመጫ መስመር ለማግኘት ዳሌ ዳ/4 – 1
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
የኋላ ሱሪ ክፍል
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
ለአንድ ሰልጣኝ
በልብስ ስፌት ስልጠና
የሚያስፈልገው ግብዓት
ተ.ቁ የእቃው ዓይነት ብዛት
1
አቡጀዴ 10 ሜትር
2 ክር 2 በቁጥር
3 ማድረቂያ 1 ሜትር
4 ሜትር 1 በቁጥር
5 ባለቆብ እስፒል 1 ፓኬት
6 መተርተሪያ 1 በቁጥር
7 የሸሚዝ ቁልፍ 1 ፓኬት
8 ቀፎ ከነእንዝርቱ 1 በቁጥር
9 መቀንጨቢያ 1 በቁጥር
10 የመኪና መርፊ 14 1 ፓኬት
11 አግራፍ 4 በቁጥር
12 የእጅ መርፌ 1 ፓኬት
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
40 400C ለብ ባለ ውሃ የሚታጠብ
በቀዝቃዛ ውሃ የሚታጠብ ነው
በእጅ የሚታጠብ ነው
በበረኪና የሚታጠብ
በበረኪና የማይተጠብ
የመሳሰሉት ናቸው፡፡
8. ማጠቃለያ
ይህ ማንዋል በግልም ሆነ በቡድን ተደራጅተው ለሚመጡ ሰልጣኞች በቂ የሆነ
ዕውቀት፣ክህሎትና አመለካከት እንዲኖራቸው በማድረግ ከስልጠና በኋላ ስልጣኞች
ደረጃውን የጠበቀና ሳይንሳዊ ዘዴን በተከተለ መንገድ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ
ሲሆን በተጨማሪ በሙያዉ ከሰለጠኑ በኋላ በቃት አሀዱ መሰረት በምዘና ብቁ ከሆኑ
በኋላ ተደራጅተዉ ስራ በመፍጠር ገቢ ሰለሚየገኙ ለሀገራቸዉ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ
አስተዋጽኦ እንዲየደርጉ ይረዳቸዋል፡፡
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ የተዘጋጀ መሰረታዊ የልብስ ስፌት
አጫጭር ሥልጠና መስጫ ማኑዋል
አዘጋጆች