You are on page 1of 10

በኢፌዴሪ ህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል

ህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም የአስተምህሮ ስራ እንዲያከናውኑ ለመገናኛ ብዙሃን


ሙያተኞች የተሰጠ ስልጠና የተግባር ክንዋኔ ላይ የቀረበ ሪፖርት

ሰኔ 2015

አዲስ አበባ

ክፍል አንድ

1. መግቢያ
የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በ 2014 ዓም የበጀት አመት በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ለመገናኛ ብዙሃን አስተምህሮ ስራ ማከናወን የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና ለ 206 የመገናኛ
ብዙሃን ሙያተኞች እና አመራሮች በ 4 ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥተዋል። የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም
አስተምህሮ ማዕከል ከሚሰጣቸው ስልጠናዎች ጎን ለጎን ስልጣኞች ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ ወደ ተግባር
መቀየራቸውን ወይም ወደ ተግባር ያልገቡትን ደግሞ በመለየት የክትትልና ድጋፍ ማድረግ የተቋሙ ሌላኛው
ተግባር ነው። በመሆኑም አጠቃላይ ስልጠናውን የወሰዱ ሙያተኞችና አመራሮች የሚሰሩበትን ዘርፎች
በመከፋፈል የድህረ ስልጠና ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ተችሏል። በዚሁ መሰረት አጠቃላይ ስልጠናውን
የወሰዱ የሚዲያ ባለሙያዎች 206 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 135 ፈፃሚ የሚዲያ ባለሙያ የተቀሩት 71 ደግሞ
የሚዲያ አመራሮች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የድህረ ስልጠና ክትትልና ድጋፍ የበለጠ ውጤታማና ታዓማኒነት
ያለው መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ተቋማት የሚገኙበትን ደረጃ ለመለየት እንዲቻል የቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣
ህትመትና በየነ መረብ … ወዘተ በመከፋፈል ተቋማቱ የሚገኙበትን አሁናዊ ሁኔታ ለመግለፅ ተችሏል።

ዓላማ
የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በ 2014 ዓም በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ለ 206
ለሚሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች የሰጠውን የአስልጣኞች ስልጠና መሰረት አድርጎ የተግባር ክንዋኔ
ደረጃ መለየትና ድጋፍና ክትትል ማድረግ ነው።

የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች


የድህረ ስልጠና ክትትልና ድጋፍ መረጃ ለመሰብሰብና ለመተንተን የመረጥነው ዘዴ አይነታዊ (Qualitative) ና
በመጠን የሚገለፅ (quantitative) አንድ ላይ በማዋሀድ ነዉ፡፡ አይነታዊ የጥናት ዘዴ ለጥናቱ የሚረዱ
መረጃዎችን አይነታዊና ገላጭ በሆነ መልኩ ለማሰባሰብም ሆነ መረጃዎችን አይነታዊ በሆነ መልኩ ለመተንተን
የሚያስችል ዘዴ ሲሆን መጠናዊ ደግሞ በተደራጁ የቃልና የፅሁፍ መጠይቆች የተሰባሰቡ መረጃዎችን በቁጥር
ለመግለፅ የሚረዳ ነው፡፡የድህረ ስልጠና ክትትልና ድጋፍ መረጃ ለማሰባሰብ በመንግስት፣ በግልና ማህበረሰብ
አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ተቋማት የተመረጡ ናቸው፡፡ መረጃ ለማሰባሰብም የፅሁፍና የቃል መጠይቅ የተዘጋጀ
ሲሆን መጠይቁም ዓይነታዊና መጠናዊ የሆኑ መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅተዋል
የማዕከሉ ሙያተኞች በአካል ወደቦታዎች በግል በመንቀሳቀስ እንዲሞሉ ተደርጓል፡፡ የመገናኛ ብዙኃን
ስርጭትም በፌዴራል፣በክልሎችና በዞን ተደራሽ ለማድረግ አላማ መር (purposive) የናሙና ዘዴ ተግባራዊ
ተደርጓል፡፡ ከእነዚህ 22 ተቋማት ተሳታፊዎች ሲሆን ከእያንዳንዱ ተቋም ምላሽ እንዲሰጡ የተደረገ ሲሆን
በአጠቃላይ 118 በላይ ባለሞያዎች እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡በተቋማቱ ምርጫ ላይም የቴሌቪዥን፣የራዲዮና
የበየነ መረብ እንዲሁም የህትመት ሚዲያዎች ስብጥር በመጠበቀ መልኩ በናሙናዉ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡
በናሙናዉ ከተመረጡ ተቋማትም ምላሽ እንዲሰጡ የተመረጡ ተሳታፊዎች በፌዴራሊዝም ህገ-መንግስት
አስተምህሮ ፕሮግራም የሚሳታፉ ጋዜጠኞችና አመራሮች ናቸው። በመጨረሻም በተሰበሰበው መረጃ
ትንተና የተገኙ ውጤቶችን በመጠቀም ድምዳሜዎች ላይ ለመድረስ ተችሏል፡፡

1.4.የጥናቱ አደረጃጀት
የድህረ ስልጠና ክትትልና ድጋፉ ሶስት ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡የመጀመሪያዉ ክፍል
መግቢያ፣የፕሮግራሙ ዓላማና የመረጃ መሰባሰቢያ ዘዴዎች የተካተቱበት ነዉ፡፡ሁለተኛው ክፍል የመረጃዎች
ትንተና የተካሄደበት ሲሆን ሶስተኛዉ ክፍል የተገኙ ውጤቶችንና ድምዳሜዎችን የያዘ ነዉ፡፡

ክፍል ሁለት

አጠቃላይ የመረጃ ትንተና


2.1 የመገናኛ ብዙሃን ተቋሙ የባለቤትነት ሁኔታ

ተ.ቁጥር የተቋሙ ባለቤትነት ሁኔታ ብዛት በመቶኛ ምርመራ


1 የመንግስት 16 72.7%
2 የግል 3 13.6%
3 የማህበረሰብ 3 13.6%
4 ድምር 22 100

ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት 72.7% የሚሆኑ የሚዲያ ተቋማት የመንግስት ይዞታ ሲሆኑ 13.6% የሚሆኑ
የሚዲያ ተቋማት ደግሞ በግል ይዞታ ስር ያሉ ናቸው። 13.6% የሚሆኑ ደግሞ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት
የሚሰጡ የሚዲያ ተቋማት ናቸው። ምንም እንኳን የማህበረሰብ አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ቁጥራቸው
አነስተኛ ቢሆኑም መረጃን ከመስጠት አንፃር ለአካባቢ ማህበረሰብ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸው።
2.2 ተቋሙ የሚገኝበትን ቦታ በተመለከተ

ተ.ቁጥር ተቋሙ የሚገኝበት ቦታ ብዛት በመቶኛ


1 በፌዴራል 2 9.09%
2 በክልል 13 59.0%
3 በዞን ወይም በማህበረሰብ 7 31.8%
4 ድምር 22 100

ከላይ በቀረበው ሰንጠረዥ ለመረዳት እንደሚቻለው 9.09% የሚሆኑ የሚዲያ ተቋማት በፌዴራል ደረጃ
የሚገኙ ሲሆኑ 59.0% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ በክልል ደረጃ የሚገኙ ናቸው። እነዚህም
በኦሮሚያ፣ በአማራ፣በሲዳማ ክልልና በደቡብ ክልል ስር የሚገኙ ናቸው። 31.8% የሚሆኑ ደግሞ በዞን ወይም
በማህበረሰብ ደረጃ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ናቸው።

2.3 ከፆታ አንፃር

ተ.ቁጥር የፆታ ሁኔታ ብዛት በመቶኛ


1 ወንድ 12 54.5%
2 ሴት 10 45.4%
3 ድምር 22 100

ከላይ ከቀረበው መረጃ ለመረዳት እንደሚቻለው 54.5% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች ወንዶች ናቸው። 45.4%
የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ሴቶች ናቸው። ይህም ሴቶች ቁጥር ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው
ወደፊት ተቋሙ ለሚሰራው ስራ የፆታ ምጥጥንን ታሳቢ ቢያደርግ ጥሩ ነው።

2.4 የሚዲያ ተቋሙ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ በተመለከተ

ተ.ቁጥር ተቋሙ የሚንቀሳቀስበት ዘርፍ ብዛት በመቶኛ


1 የቲቪና ሬድዮ ጣቢያ 8 38.0%
2 የሬድዮ አገልግሎት 7 33.3%
3 የህትመት ሚዲያ - -
4 የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት 6 28.5%
5 የበየነ መረብ አገልግሎት - -
6 ድምር 21 100

የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ለሚዲያ ተቋማት በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ
ስልጠና ሰጥቷል። የድህረ ስልጠና ክትትልና ድጋፍ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሚዲያ ተቋማትን በተለያዩ
ዘርፎች መከፋፈል አስፈላጊ ሆናል። በዚህም መሰረት 38.0% የሚሆኑ የሚዲያ ተቋማት በቲቪና ራዲዮ
ሁለቱንም ተቋማት በአንድ ላይ አጣምረው የያዙ ናቸው። 33.3% የሚሆኑ ተቋማት ደግሞ ሬዲዮ ብቻ
የሚጠቀሙ ናቸው። 28.5% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች የማህበረሰብ አቀፍ በሚለው አገልግሎት ውስጥ
የተሰማሩ ናቸው። በአጠቃላይ የመረጃ ምንጮችን ታማኝነት ለማረጋገጥ የሚዲያ ተቋማት በእንደዚህ
ዓይነት ሁኔታ መከፋፈሉ ተገቢ ነው።

2.5 ሙያተኞች የሚሰሩበት ዘርፍ በተመለከተ

ተ.ቁጥር ሙያተኛው የሚሰራበት ዘርፍ ብዛት በመቶኛ


1 ፕሮግራም አዘጋጅ 10 52.6%
2 ሪፖርተር 8 42.1%
3 የሚዲያ አመራር 1 5.26%
4 ኤዲተር - -
5 ድምር 19 100

ከላይ በቀረበው መረጃ መሰረት 42.1% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በሪፖርተርነት ወይም በዘጋቢነት እንዲሁም
በዜና አንባቢነት የሚሰሩ ባለሞያዎች ሲሆኑ ይህም ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ሪፖርት አዘጋጅነት ተሳታፊ
ሆነዋል። 52.6%የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ፕሮግራም አዘጋጆች ናቸው። 5.26%
የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ የሚዲያ አመራሮች ናቸው።

2.6 ተቋማት የሚገኙበትን የተግባር ክንዋኔ ደረጃ በተመለከተ

ተ.ቁጥር የክንዋኔ ሁኔታ ብዛት በመቶኛ


1 ወደ ተግባር የገቡ ተቋማት 20 90.9%
2 ወደ ተግባር ያልገቡ ተቋማት 2 9.09%
3 ድምር 22 100

የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በ 2014 ዓም የበጀት ዓመት ለ 206 የሚዲያ ባለሞያዎችና
አመራሮች በ 4 ዙር ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል። ከእነዚህ ውስጥ ለሁለተኛ ዙር ለክትትልና ድጋፍ ለማድረግ
የተመረጡ ተቋማት 22 ናቸው። 90.9% የሚሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎች የህገ መንግስታና ፌዴራሊዝም
ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ወደ ተግባር የገቡና በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ሲሆን። 9.09% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች
ደግሞ ምንም ዓይነት የተግባር ክንዋኔ ያልጀመሩ ናቸው።እነዚህም ተቋማት ደቡብ መገናኛ ቴሌቪዥን ፣አዳማ
ብሮድካስት ሰርቪስ።ወደ ተግባር ያልገቡ የሚዲያ ተቋማትም ምክንያታቸውንም እንደሚከተለው
ዘርዝረዋል።የወሰድነው ስልጠና ወደ ተግባር እንድንሸጋገር የሚረዳ አይደለም፣ የበጀትና የባለሙያ እጥረት፣
ተቋሙ በቂ ሰራተኛ ስሌለንና የስራ መደራረብ፣የቋንቋ ችግርን በዋናነት ጠቅሰዋል። ሌላው ከላይ በቀረበው
መረጃ መሰረት አብዛኛው የሚዲያ ባለሞያዎች ወደ ስራ የገቡና ለማህበረሰቡም በህገ መንግስትና
ፌዴራሊዝም ላይ ንቃት ለመጨመር እየሰሩ ይገኛሉ። ለአብነት ያህል የፌዴራሊዝምን ፅንሰ ሀሳብና
ተግባራዊነት ፕሮግራም በማዘጋጀት ያልጠሩ ሃሳቦችን ባለሞያ በመጋበዝ ሃሳቦችን እንዲሸራሸሩ ለማድረግ
ተችሏል። ይህ ማለት የሚሰራው ስራ በቂ ነው ለማለትና በማህበረሰቡ ውስጥ ሰፊ ግንዛቤ አለ ለማለት
አያስደፍርም።

2.7 በሚዲያ ተቋማት የተዘጋጀ የፕሮግራም አምድ ብዛትና የፈጀው ሰዓት በተመለከተ

ተ.ቁጥር የተዘጋጁ ፕሮግራም ብዛት ብዛት የፈጀው ሰዓትና ብዛት በመቶኛ


1 ፕሮግራም ብዛት 1 - 1 ሰዓት ብዛት 10 58.8%
2 ፕሮግራም ብዛት 2 2 2 ሰዓት ብዛት 2 11.7%
3 ፕሮግራም ብዛት 3 3 3 ሰዓት ብዛት 3 17.6%
4 ፕሮግራም ብዛት 4 2 30 ደቂቃ ብዛት 4 23.5%
5 ፕራግራም ብዛት 5 1 -
6 ፕሮግራም ብዛት ከ 5 በላይ 9
7 ድምር 17 100

የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ለሚዲያ ተቋማት በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ
የሰጠውን የአሰልጣኞች ስልጠና ከወሰዱት ውስጥ አብዛኛዎቹ ወደ ተግባር የገቡ መሆኑን ከላይ ለመግለፅ
ሞክራለሁ። አሁን ደግሞ የተዘጋጁ ፕሮግራሞች ወይም አምዶች ብዛታቸውና የፈጁትን የአየር ሰዕት
እንመለከታለን። 52.9% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ያዘጋጁት ፕሮግራም ብዛት ከ 5 በላይ ነው። ይህም
ትልቁን ድርሻ ይይዛል። 5.88% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ 5 ፕሮግራሞችን አዘጋጅተዋል።41.2%
የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ያዘጋጁት ፕሮግራም ብዛት ከ 4 ና ከዚያ በታች ነው።በዚህ ረገድ የአስተምህሮ
ተቋሙ የሚፈለገውን መረጃ ለማህበረሰቡ ለማድረስ የሚዲያ ባለሙያዎች እየሰሩ ያሉትን ስራ እውቅና
በመስጠትና ማበረታቻ በማድረግ ከዚህ የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል።ሌሎች የግንኙነት
አማራጮችን መጠቀም ይኖርበታል።

2.8 የፕሮግራም ይዘት አቀራረብ በተመለከተ

ተ.ቁጥር የፕሮግራም አቀራረብ ብዛት በመቶኛ


1 ፅሁፍ በማንበብ 3 15.7%
2 የውይይት መድረክ በማዘጋጀት 2 10.5%
3 ባለሞያ በመጋበዝ 10 52.6%
4 1 ና 2 ዘዴዎችን በማጣመር 4 21.0%
5 ድምር 19 100

ከላይ በቀረበላቸው መረጃ መሰረት 15.7% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች የሚዘጋጁ ፕሮግራሞች አቀራረባቸው
ፅሁፍ በማንበብ ለምሳሌ ዜና በማንበብ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። 10.5% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ
የውይይት መድረክ በማዘጋጀት በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።52.6% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ ባለሞያ
በመጋበዝ ፕሮግራም እንደሚያዘጋጁ ምላሽ ሰጥተዋል። የተቀሩት 21.0% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ
የተለያዩ አቀራረቦችን በመጠቀም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

2.9 የአድማጭ ተመልካች ና አንባቢ ተሳትፎ አስተያየት በተመለከተ

አብዛኞቹ የማህበረሰብ ክፍሎች በሚዘጋጁት ፕሮግራሞች ላይ ይለው አስተያየት ጥሩና ገንቢ የሚባል
ቢሆንም አሁንም ህዝቡ ፌዴራሊዝምን የሚረዳበት መንገድ የጠራ አለመሆኑና ይህንን ችግር ለመፍታት
የሚዲያ ባለሞያዎች በፌዴራሊዝም ላይ የሰለጠነ ባለሞያ ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ ከባለሙያዎች
በቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ለመረዳት ይቻላል።

2.10 የሚዲያ ተቋማት ፕሮግራም ሲያዘጋጁ ያጋጠማቸው ችግሮች

ይህ መጠይቅ ከቀረበላቸው ባለሞያዎች መካከል አብዛኛዎቹ የሚከተሉትን ዋና ዋና ችግሮች አጋጥሞቸዋል።


 አንዳንድ ሙሁራና ፖለቲከኞች በዘርፉ ገለፃ ለማድረግ ፍላጎት አለመኖር እንዲሁም የአመለካከት
ችግሮች ተስተውሏ
 የበጀት፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ችግሮች፣
 በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ቁጥራቸው አነስተኛ መሆንና መረጃ
ማጣት በዚህ ረገድ የመንግስት ሃላፊዎች መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸው ነው በማለት
ምላሽ ሰጥተዋል
 የቋንቋ ችግር ህዝቡ በሚገባው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ስልጠና አለማግኘት… ወዘተ ዋና ዋና ያጋጠሙ
ችግሮች ናቸው።

2.11 ከአስተምህሮ ማዕከሉ የሚፈለጉ ድጋፍ ወይም እገዛ

የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ከአስተምህሮ ማዕከሉ የሚፈልጓቸው ድጋፍና እገዛ እንደሚከተለው ይቀርባል።
ሙያዊ ትንታኔዎችን በተፈለገው ስዓት ብትሰጡን፣ በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ላይ አትኩረው ለሚሰሩ
ባለሞያዎችና መገናኛ ብዙሃን እውቅና ብትሰጡ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤና አባላቱም በውይይት
መድረኩ እንዲሳተፉ ቢደረግ፣ በግል ሚዲያዎች ጋር ስፖንሰር በማድረግ ድጋፍ ብታደርጉ፣ ከመገናኛ ብዙሃን
ጋር ሳምንታዊ ፕሮግራም በህገ መንግስት ዙሪያ ቢዘጋጅ፣ አጫጭር ማስታወሻና መፀሃፍት ቢዘጋጅና ቢሰጥ
ከዚህ ጋር ተያይዞ እንድ ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው ባለሞያ እንዲህ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል የአስተምህሮ
ማዕከሉ በቂ ሰነዶችና መፀሃፍት ቢያዘጋጅ በማለት መልሰዋል … ወዘተ እነዚህንና ሌሎች ድጋፎችን
ጠቅሰዋል።

2.12 የግንኙነት ሁኔታ በተመለከተ

ተ.ቁጥር የግንኙነት ሁኔታ በተመለከተ ብዛት በመቶኛ


1 የገፅ ለገፅ ግንኙነት 7 36.8%
2 ሪፖርት በማቅረብ 1 5.26
3 በቴሌ ግራምና ኢ ሜይል 11 57.8%
4 ሌላ ዘዴ 1 5.26%
5 ድምር 19 100

36.8% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ከህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ
ማዕከል ጋር አብሮ ለመስራት የገፅ ለገፅ ግንኙነትን የመረጡ ሲሆን 5.26% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች ደግሞ
ሪፖርት በማቅረብ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።57.8%በቴሌ ግራም ቻናል ወይም በኢ ሜይል የግንኙነት
መስመር መርጠዋል። 5.26% የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች የተለያዩ ዘዴዎችን ማለትም የገፅ ለገፅ ና
በኤሌክትሮኒስ በመጠቀም ከአስተምህሮ ማዕክል ጋር አብሮ ለመስራት ወስነዋል። ይህም የአስተምህሮ
ማዕከሉ በቀጣይ ለሚሰራቸው ስራዎች ከሚዲያ ተቋማት ጋር ዘላቂ ግንኙነት ለመፍጠር ያስችለዋል።

2.13 የአድማጭ ወይም የተመልካች ብዛት በተመለከተ

ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የመገናኛ ተቋማት በሚያስተላልፉት ፕሮግራም የአድማጭ ተመልካች ብዛት ምን
ያህል እንደሆነ በጥናት ባይገልፁም ከቃለ መጠይቁና ከፁሁፍ መጠይቁ ለመረዳት እንደሚቻለው የህገ
መንግስትና ፌዴራሊዝም እስተምህሮ ማዕከል ለሰጣቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና
ወስደው በህገ መንገግስትና ፌዴራሊዝም ጋር በተያያዙ ከ 20 ሚሊዩን በላይ ለሚሆኑ የማህበረሰቡ ክፍሎች
መረጃ ተደራሽ ተደርጓል።
2.14 ምርጥ ተሞክሮችንና አስተያየቶችን በተመለከተ

የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ካከናወናቸው ምርጥ ተሞክሮችና የተሰጡ አስተያየቶች
የሚከተሉት ናቸው።

 የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝምን አተገባበርንና የማህበረሰቡ እይታን አድማስን ማሰፋት ላይ መስራቱ፣


 የተለያዩ ስልጠናዎችን ማዘጋጀቱ የተጠቀሱ ተሞክሮች ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ ለአስተምህሮ
ማዕከሉ የተሰጡ አስተያየቶች የሚከተሉት ናቸው።
 የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት፣ የውጪ ሀገር ተማክሮችን የሚገኝበት ሁኔታ ቢመቻች፣ዲጅታል
ሲስተሞችን በመጠቀም ስልጠና መስጠት ቢቻልና የአየር ሰዓት በመግዛት ፕሮግራሞች ቢተላለፉ…
ወዘተ በዋናነት ይጠቀሳሉ።

ክፍል ሦስት
የተለዩ ችግሮች

 በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ ለሚዲያ
ባለሞያዎችና አመራሮች የተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ከወሰዱ በኋላ አብዛኛዎቹ ወደ ስራ የገቡ
ቢሆንም የተሰሩ ስራዎች ከማህበረሰቡ የግንዛቤ ክፍተት አንፃር እጅግ ዝቅተኛ ነው። ይህ ማለት
የሚዲያ ባለሞያዎችም ሆኑ የስራ አመራሮች በተደራጀና ቁርጠኛ በሆነ መንገድ ፕሮግራሞችን
አለማዘጋጀት ለዚህም እንደምክንያት የተቀረቡት የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፍቃደኛና ትብብር
አለመኖር፣የበጀት ችግርና የባለሞያ እጥረት በዋናነት ተጠቅሰዋል።
 የሚዲያ ተቋማት ለማህበረሰቡ መረጃን ማስተላለፊያ አንዱ ቻናል እንደመሆናቸው መጠን ከተለያዩ
የመንግስት ተቋማት የስራ ሃላፊዎች በህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም ዙሪያ በቂ መረጃ ለማግኘት
አስቸጋሪ መሆን አንዱ ችግር ሲሆን በዚህም ምክንያት ሚዲያ ተቋማት በቂ ዜናና ፕሮግራም
ለማዘጋጀት እንቅፋት ሆኖባቸዋል።
 የአስተምህሮ ማዕከሉ ለሚዲያ ተቋማት የሰጠው ስልጠና አንድም በሰለጠኑት ስልጠና መሰረት
ለማህበረሰቡ በህገመንግስትም ሆነ በፌዴራሊዝም ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ሲሆን በዚህ ረገድ የተሰሩ
ስራዎች እንደጀማሪ ጥሩ ቢሆኑም ለማህበረሰቡ መረጃ ተደራሽነት ላይ ክፍተት አለ። ከዚህ
በተጨማሪም ስልጠናውን የወሰዱ የሚዲያ ባለሞያዎች በሚሰሩበት መ/ቤት የሚሰሩ ሰራተኞችን
ማሰልጠን ሲሆን በዚህ ረገድ በተደረገው ዳሰሳ ከ 19 ተቋማት ውስጥ አንድም የሚዲያ ተቋም
ለሰራተኞች ስልጠና የሰጠ የለም።
 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል
ዓላማውን ራዕዩንና የሚሰራቸውን ስራዎችና መረጃ ለህዝብ ተደራሽ አለሞሆን እንዲሁም ተቋሙ
ራሱ የህገ መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ተቋሙ ፌዴራሊያዊ
አወቃቀር አለመከተል።ማለትም በክልልሎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አለመክፍትና ዜጎች በአፍ መፍቻ
ቋንቋቸው ስልጠና ያለማግኘት።

መፍትሄ

 አስተምህሮ ማዕከሉ በቀጣይ ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና የፖለቲካ ሃላፊዎች በተቋሙ


ስራዎችና ተልዕኮች ላይ ስልጠና ቢሰጥ ይህም ሚዲያ ተቋማት ላይ የሚሰተዋለውን የመረጃ እጦት
በከፍተኛ ደረጃ የመፍታት አቅም ይኖረዋል።
 ለአስተምህሮ ማዕከሉ ሃላፊና አሰልጣኞች ማዕከሉ የሚሰጠው የስልጠና አካሄድ መቀየር። ይህ ማለት
አስተምህሮ ማዕከሉ በዚህ የስልጠና አካሄድ ተደራሽ የመሆን አቅሙ በጣም ዝቅተኛ ነው። ስለሆነም
ከመደበኛ የስልጠና አካሄድ ጎን ለጎን ኢ መደበኛ የሆኑ የስልጠና አካሄድ ቢከተል ጥሩ ነው። ለምሳሌ
ዲጂታል ሚዲያ ሲስተሞችን መጠቀም፣ የማህበረሰብ አንቂዎችን በመምረጥና ስልጠና በመስጠት
ፕሮግራም እንዲያዘጋጁ ማድረግ፣ የማህበረሰብ ሚዲያዎችን መጠቀም፣ የክርክርና ውይይት
መድረኮችን ማዘጋጀት፣ ለህዝብ ተደራሽ የሚሆኑ በራሪ ፅሁፎችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት።
 የአስተምህሮ ማዕከሉ አመራርና ሰራተኞች የውስጥ ገቢ በማሳደግ ወይም የውስጥ ፈንድ ማግኛ
ዘዴዎችን በመጠቀም በቲቪ፣ በሬድዮ እንዲሁም በጋዜጦች ላይ ቋሚ የአየር ሰዓት መግዛት
ተቋሙን ማስተዋወቅና ፕሮግራም ማቅረብ።
 የአስተምህሮ ማዕከሉ ከሌሎች የዴሞክራቲክ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት በተለይ የእምባ
ጠባቂ ተቋም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ና የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ወዘተ ጋር
በትብብር መስራትና ፈንድ ማፈላለግ ያስፈልጋል።
 ለማዕከሉ የስራ ሃላፊ ዘመኑ የዲጂታልና የመረጃ ዘመን እንደመሆኑ መጠን ለአስተምህሮ ማዕከሉ
የአይቲ ባለሞያዎች ቢቀጠሩና ማዕከሉ በዚህ ረገድ ቢጠናከር።
 ለማዕከሉ የሃላፊ የአስተምህሮ ማዕከሉ በክልሎች ተመሳሳይ አደረጃጀት ቢከፍትና ሰስራዎቹ
ለሰፊው ህዝብ ተደራሽ ቢሆን ይመረጣል ።

ማጠቃሊያ
የህገ መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል አዲስ የተቋቋመ ተቋም እንደመሆኑ መጠን
አጀማመሩ ጥሩ ቢሆንም ተቋሙ ከተነሳበት ዓላማና ራዕይ አንፃር ግን ከፍተኛ የሆነ ስራዎች መስራት
ያስፈልጋል። በተለይ የተቋሙን የውስጥ አደረጃጀት በሰው ሃይልና በፋይናንስ ማስፋትና በክልሎች
ተመሳሳይ ተቋማትን ማደራጀትን ይጠይቃል።

You might also like