You are on page 1of 68

መፍጠንና መፍጠር

የወል እውነቶችን የማጽናት ቀጣይ


የትግል ምእራፍ

ሰኔ 2015 ዓ.ም
ብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
ማውጫ
መግቢያ ...................................................................................................................................... 1
ክፍል አንድ...................................................................................................................... 3
I. ተለዋዋጭ ዓለም፤ሥር የሰደዱ ሀገራዊ ችግሮች ..................................................................... 3
1.1 ከባለ አንድ ዋልታ ወደ ብዝኃ ዋልታ እየተቀየረ ያለ የዓለም የኃይል አሰላለፍ ........... 3
1.2 የመንግሥታት ኃይል መሸርሸር.................................................................................. 5
1.3 የድኅረ እውነት ፖለቲካዊ ሐሳዊነት ........................................................................... 7
1.4 የሃይማኖት፣ የብሔርና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ጥምረት አደጋ ..................................... 11
1.5 ድህነት እንደ ታላቁ ተግዳሮት ................................................................................. 14
1.6 በእንጥልጥል ላይ ያለ የሀገር ግንባታ........................................................................ 17
ክፍል ሁለት ................................................................................................................... 20
II. የፈጠራና ፍጥነት አስፈላጊነት ............................................................................................ 20
2.1 ኋላ ከቀረንበት ወጥተን ከፊት ለመገኘት .................................................................. 20
2.2 ጊዜና የምርጫ ቃል ኪዳን ....................................................................................... 22
2.3 ቃልን ማጠፍ እና ቃልን ማክበር ............................................................................. 23
ክፍል ሦስት ................................................................................................................... 24
III. የመፍጠን ጅማሮ ስኬቶች ............................................................................................... 24
3.1 ብልጽግናዊ መንግሥት እና ኢኮኖሚያዊ ፍጥነት ..................................................... 24
3.2 ከተናጠል ወደ ወል እውነት ..................................................................................... 30
3.3 የታደሰው የዓለም አቀፍ ግኑኘነትና ዲፕሎማሲ ........................................................ 44
ክፍል አራት ................................................................................................................... 48
IV. ከፍጥነት የሚገቱን .......................................................................................................... 48
4.1 የሠርጎ ገብ ፖለቲካ፡ ራእይን መንጠቅ፤ ዕይታን መስረቅ ......................................... 50
4.2 የተናጠል እውነት እና አንጻራዊ ጥቅም .................................................................... 51
4.3 ያልተገባ ክብርና ሀብት ፍለጋ .................................................................................. 52
4.4 ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን አለመላመድ፡ ጠባቂነት እና መርሕ አልባነት .................. 53
ክፍል አምስት ................................................................................................................ 54
V. ይበልጥ መፍጠር፤ ይበልጥ መፍጠን................................................................................... 54
5.1 “የብልጽግና አጣዳፊነት” ዕሳቤ ................................................................................. 54
5.2 ነገርን ከሥሩ ........................................................................................................... 55
5.3 አዳዲሶቹን ወደ ትግበራ ነባሮቹን ወደ ሥራ ገበታ _ ለትውልድ .............................. 56
5.4 በክረምት፣ እራትና መብራት .................................................................................... 57
5.5 የወል እውነትን የማጽናት ቀጣይ የፖለቲካ አቅጣጫ ................................................ 58
VI. ማጠቃለያ ....................................................................................................................... 62
መግቢያ

ብልጽግናን ማረጋገጥ ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው ጉዞንና ጥረትን የሚጠይቅ ነው። ለውጡ
የነበረውን ሁኔታ በመለወጥ በመለወጥ ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መደላድል
ወይም ምሕዋር ውስጥ እየተጓዘ ነው።

የለውጡ የመጀመሪያ ምእራፍ ብዙ ተስፋ፣ ብዙ ሙቀትና መደበላለቅ የበዛበት ነበር። በዚህ


መደበላለቅና ሙቀት የተነሣ መርሕና መርሕ አልባነት፣ ዲሲፕሊንና ዲሲፕሊን አልባነት፣
ደጋፊነትና ተቃዋሚነት፣ ተደበላልቀው እስከ ተወሰኑ ወቅቶች ተጉዘዋል። የመጀመሪያዎቹ
ሁለት ዓመታት የዚህ መገለጫዎች ነበሩ። ሁለተኛው ምእራፍ ደግሞ ለውጡ በመደመር
መንገድ መጓዝ የጀመረበት፣ የለውጡን ጉዞ ወደ ራሳቸው መሳብና መጥለፍ ያልቻሉ አካላት
እየተለዩ የመጡበት፣ መጥለፍ ያልተቻለውን ለውጥ ለማደናቀፍ ብርቱ ጦርነት የተከፈተበት
ወቅት ነው። ያለፉት ሦስት ዓመታት የዚህ ማሳያዎች ናቸው።

ይህ ጉዟችን ነገሮች ጠርተው ያልወጡበት፤ ከመንገዳችን መለስ ቀለስ _ የበዛበት እና ወደኋላ


ጎታቾች በዝተው የታዩበት ነበር። ቀጣይ ምእራፋችን ግን የማጥሪያ ምእራፍ መሆን
ይገባዋል። በለውጡ የተጣለውን መሠረት ተጠቅሞ የጉዞውን ፍጥነት እና ቀጣይነት
የምናሣልጥበት ምእራፍ ነው። የፓርቲ አባላትም በቅተው፣ ጠርተውና ነጥረው የሚወጡበት
ምእራፍ ነው።

ፍጥነት ማለት በቶሎ በቶሎ ነገሮችን በመማርና በማሻሻል፣ ነገሮች በተፈጥሯዊ መንገድ
ከሚወስዱት ጊዜ በተሻለ ጊዜ፣ በወቅቱ የተፈጠሩ ዕድሎችን በቶሎና አማጥጦ በመጠቀም፣
ነገሮችን ከግብ ለማድረስ መቻል ነው። በለውጥ ያመጣናቸውን ስኬቶች ለማላቅ፣ የተፈጠሩ
እንከኖችን ለማረም ጥራት ያለው ፍጥነት ወሳኝ ነው። ጥራት ያለው ፍጥነት ማለት ‹የነ
ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ› ከሚለው የተለየ፤ ለፍጥነት ሲባል ጥራትን፣ ለጥራትም
ሲባል ፍጥነትን ሳያስተጓጉሉ፣ ለውጥን መምራት ነው። ብልጽግና ለማረጋገጥ ጥራት ያለው
ፍጥነትን መጨመር ያስፈልገናል።

የብልጽግና መነሻችን ወለል ዝቅተኛ ነው:: በዕድገትም ከኋላ ቀርተናል። ስለዚህም ውድድር
በበዛበት ዓለም ለማሸነፍ አንዱ መሣሪያችን ፍጥነት ነው። ወደ ኋላ መቅረት ለተለያዩ
ጫናዎች ይዳርጋል። ከዚህ ጫና ተላቅቆ ከሌሎቹ ጋር በእኩል ደረጃ ለመታየት መፍጠን
አለብን። ከመነሻ እስከ መዳረሻችን ያለው ጉዞ ሩቅ ስለሆነ፣ በለውጥ ጎዳና ላይ መጓዝ ብቻ

1
ሳይሆን የግድ ፍጥነት መጨመር ያስፈልጋል። ከዚህም በተጨማሪ መፍጠን ነገሮችን በቶሎ
ለማጠናቀቅ እና ሌሎች ሥራዎችን ለመጀመር ዕድል ይሰጣል። እንጦጦን በቶሎ
መጨረሳችን፣ ኮይሻን እንድንጅምር አድርጎናል። ኮይሻን መጨረሳችን ገበታ ለትውልድን
እንድንጀምር አድርጎናል። ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን እንድንሠራ የጊዜ ነጻነት ሰጥቶናል።
በመሆኑም የፍጥነትን ዋጋ ተገንዝበን ለመፍጠን የሚያስፈልገውን ሥርዓታዊ ጥንካሬ
ማምጣት ይኖርብናል።

ፓርቲያችን ሁለንተናዊ የወል እውነቶች ገዥ ሐሳብ ሆነው እንዲጸኑ ለማድረግ የጀመራቸውን


መሠረተ ሰፊ ሥራዎች ፈጠራ እና ፍጥነትን በማከል በትጋት ይሠራል፤ ሀገራዊ አንድነታችን
በኅብረ ብሔራዊ መሠረት ላይ እንዲገነባ ያደርጋል፤ የሁሉም ሕዝቦች የወል እውነቶች ገዥ
ሐሳብ ማዕከላዊ ሥርዓቷ የሆነ ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ይሠራል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ፓርቲያችን ኢትዮጵያ ሀገራችን በወል እውነቶች ገዥ ሐሳብ
የምትመራ እንደትሆን የሚያስችሉ በሁሉም ዕድገት ተኮር ተግባሮች ላይ የሚጨበጡ
ድሎችን እያስመዘገበ ይገኛል። ድሎችን በማስቀጠል፣ በአፈጻጸም በደከምንባቸው ተግባራት
ላይ ፈጠራ እና ፍጥነታችንን በመጨመር፣ ኅብረ ብሔራዊነትን ማጽናት ይገባናል።
የአመለካከት ጥራት የአሰላለፍ ግልጽነት ጠርቶ፣ አደረጃጀቶቻችንን በሙሉ ዐቅማቸው
ካስገባናቸው ሁለንተናዊ ብልጽግናዋ የተረጋገጠ መፍጠራችን አይቀሬ ይሆናል።

2
ክፍል አንድ

I. ተለዋዋጭ ዓለም፤ሥር የሰደዱ ሀገራዊ ችግሮች

1.1 ከባለ አንድ ዋልታ ወደ ብዝኃ ዋልታ እየተቀየረ ያለ የዓለም የኃይል አሰላለፍ

ብዙ ጊዜ ሚዛናችንን የሚያስቱ ነገሮች የሚገጥሙን ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ነው። ውስጣዊ


አንድነትና አስተማማኝ ሰላም ሚዛን ጠብቆ ለሚደረገው ዓለም አቀፍ ግንኙነት የጀርባ
አጥንት ነው። በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለ የዓለም ሥርዓት ውስጥ እንደ ሀገር ለመቀጠል
ያለን ዕድል የውስጥ ሰላምንና አንድነታችንን ማረጋገጥና በጋራ መቆም ነው። ይህም የውጭ
ግንኙነቱን ሚዛን ያጸናዋል።

ከሉላዊ ትሩፋቶች እንደ መቋደሳችን ዓለም ስትታመም መታመማችን አይቀርም። የኃያላኑ


ጦርነት በአዳጊ ሀገራት የኢኮኖሚና የምግብ ቀውስ ፈጥሯል። ችግሮች በሚከሠቱ ጊዜ
በአፋጣኝ ችግር ፈቺ መፍትሔዎችን መፍጠር ያስፈልጋል። የዘረጋነው የብልጽግና ሥርዓት
በዓለም አቀፍ ክሥተቶች ሁለት ጊዜ ተፈትኖ አልፏል። በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት
የሎጀስቲክስ መቆራረጥ የዓለም ኢኮኖሚ ሲፈትነው ተቋቁመነዋል። ችግሩን ወደ ዕድል
ቀይረን የኢኮኖሚ ዕድገታችንን ለማስቀጠል እንደቻልን ይታወሳል። ስንዴ ተቀባይ ሀገራት
በስንዴ ፖለቲካ ሲታመሱ ሀገራችን ከስንዴ ቀውስ ተሻግራ ለጎረቤቶቻችን መፍትሔ
ሆነናል።

ሉላዊ ዓለምን የመረዳት ፍጥነትና የፈጠራ መፍትሔዎችን በማፍለቅ ብልጽግናችንን


ለማረጋገጥ ዓለም አቀፍዊ ሁነትን መረዳትና መተንበይ ይገባል። ከዚህ ጋር ተያይዞ
የምንገኝበት ቀጣና ጂኦፖለቲካዊ ተጽዕኖው ከፍ ያለ ነው። ስለሆነም የዓለም አቀፍ ሁኔታ
ተለዋዋጭነትን ከቀጣናችን ጂኦፖለቲካ ጋር አስተሣሥሮ መመልከት ይሻል።

የአፍሪካ ቀንድን ሰላም፣ ደኅንነትና ብልጽግና ከቀይ ባሕርና ከመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት
ጋር አጣምሮ ማየት ይገባል። የኃያላኑ ዕይታም በዚህ ልክ በመሆኑ፣ የቀንዱ ሀገራትን ጥቅምና
ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚያስችለው በዚህ ልክ መመልከትና መረዳት ስንችል ነው። በርግጥ
የቀንዱ ሀገራት ቀጥታ ግንኙነት በዚህ ክበብ ሳይወሰን ሰሜን አፍሪካ ድረስ ይደርሳል።
አውታረ ሰፊ ግንኙነቶች ቀጣናውን ተለዋዋጭ ክሥተቶችን የሚያስተናግድ አድርገውታል።
በመሆኑም በንቃት መከታተልና ዝግጁነትን ማረገገጥ የሠርክ ተግባር መሆን ይገባዋል።

3
የየሀገራቱ የውስጥ ጉዳይ አለመርጋትና ጣልቃ የሚገቡ ሀገራት ፍላጎት መበራከት፣ በድንበር
ተገድቦ የሚቀር የውስጥ ጉዳይ እንደሌለ ያሳያል።

የእርስ በርስ ጦርነት ሳይበቃን የቀንዱ ሀገራትን ተፈጥሮ ትፈትነናለች። የኮቪድ ወረርሽኝ
ያቀዛቀዘው ኢኮኖሚ እያገገመ ሳለ የአየር ንብረት ለውጥ በምሥራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ድርቅ
አስከተለ፤ ከዚህ ጋር እየታገልን የአንበጣ ወረርሽኝ መጣ። እርሱንም ስንቋቋመው ዩክሬን
ጦርነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን የሩሲያ እንድናስተናግድ አደረገን። በቀጣናው
ጂኦፖለቲካዊ ውድድር ውስጥ ታላላቆቹ ኃያላን አሜሪካ፣ ቻይና፣ የአውሮፓ ኅብረትና ሩሲያ
እየተፎካከሩ ናቸው። እንዲሁም ወደ ኃያልነት የሚንደረደሩት ቱርክ፣ ጃፓንና የባሕረ
ሰላጤው ሀገራት በአካባቢው እያማተሩ ይገኛሉ።

የእኛ አፍሪካውያን የችግሮቻችን ምንጭ፣ የጸና ሰላም ማጣታችን ነው። የጸና ሰላም ማለት
ለረዥም ዓመታት የዘለቀ፣ ሁለንተናዊ የሆነ፣ ከውስጥና ከውጭ ግጭት የጸዳ ሰላም ማለት
ነው። በአራቱም የአፍሪካ ማዕዘናት መትረየስ _ ያጓራል። የአፍሪካ ኅብረት በ2060 በአፍሪካ
የመሣሪያ አርምሞን ለማሳካት እየሠራ ቢሆንም፣ ያስቀመጠውን ግብ እውን ማድረግ ከባድ
እንደሆነ በርካታ አመላካቾች ይታያሉ። በ2022/2023 ከ54 ሀገራት ውስጥ ከ35 በላይ
የሚሆኑት በጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። ይሄንን መሰል ችግሮቻችንን ተሸክመን ኃያላኑ ይዘውት
የመጡትን ዕድል በአግባብ ልንጠቀም አንችልም። ኬክን በጥይት፣ ፍቅርን በግጭት እየቀየርን
ትውልድ የማይገፋውን ድህነት መሻገር ፈጽሞ አይቻልም።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ምልክት ናት። ከቀንዱ ሀገራት መካከል ሰፊ የቆዳ ስፋት አላት፤
በሕዝብ ብዛት ትልቋ ናት ፤ በታሪክ፣ በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በሰላም ማስከበር ትታወቃለች፤
የአፍረካ ኅብረት መቀመጫ ናት። ከዐሥሩ የቀንዱ ሀገራት መካከል ከሰባቱ ጋር ድንበር
ትጋራለች። ይህ ሁሉ ስለ ቀንዱ ሲነሣ የኢትዮጵያን ድርሻ እንዲገዝፍ አድርጎታል። ድንበር
ከምንጋራቸው ሀገራት በዘለለ መነሻውን ኢትዮጵያ ያደረገው ዓባይ ከዐሥር ሀገራት ጋር
ያገናኘናል። ከዐሥሩ ሀገራት መካከል ከአራቱ ጋር ድንበር ስንጋራ፣ ከተቀሩት ስድስቱ ጋር
ደግሞ ድንበር ሳይሆን ውኃ እንጋራለን። በድምሩ ከኢትዮጵያ ጋር በድንበርና በውኃ
ግንኙነት ያላቸው 13 አፍሪካ ሀገራት ናቸው። ሀገራችን ከእነዚህ ሀገራት ጋር ጂኦፖለቲዊና
የጂኦ ኢኮኖሚያዊ ትሥሥሮች አሏት።

ኢትዮጵያ የምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና የቀይ ባሕር አዋሳኝ መሆኑና ቀጣናው የብዙ
ዓለም አቀፍ ኃይሎች መሻኮቻ መሆኑ፣ ቀይ ባሕርን ከኢትዮጵያ ህልውናና ጥቅም ጋር

4
በእጅጉ የተቆራኘ አድርጎታል። ቀይ ባሕር የዓለም ወሳኝ የንግድ ማሳለጫ መሥመር ነው።
ከዚያም ባሻገር ውቅያኖሶችን አቋርጦ ለሚደረግ ማናቸውም ዓይነት የባሕር ኃይል
እንቅስቃሴ እጅግ አስፈላጊ ሥፍራ ነው። በሀገራት መካከል የሚደረጉ ኢኮኖሚያዊም ሆነ
ወታደራዊ ግብግቦች በቀይ ባሕርና በቀጣናው በሚኖረው የኃይል ሚዛን ላይ የተመሠረተ
ነው።

ኢትዮጵያና የቀንዱ ሀገራት በአጠቃላይ ባላቸው የጂኦ ፖለቲካ ሥፍራ፣ በለም መሬታቸው
እና በሕዝብ ብዛታቸው ብቻ ሰፊ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉበት ዕድል በፊትም አሁንም
ክፍት ነው። ሆኖም ቀጣናው ለብዙ ኃያላን ሀገራት መናኸሪያ በመሆኑ በቀጣናው ሀገራት
ውስጣዊ ፖለቲካ እጁን ሰድዶ የሚፈተፍተውና ሀገራቱ ጠንክረው እንዳይወጡ የሚያሤረው
ኃይል ብዛት የትየለሌ ነው። ይህን ሤራና የጂኦፖለቲካ ግብግብ መቋቋምና ብሔራዊ ጥቅምን
ማስከበር የሚቻለው ውስጣዊ አንድነታችንን አጠንክረን ከጎረቤቶቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት
በማሣለጥ ከቀጣናው የሚገኘውን ጥቅም ለማረጋገጥ ስንችል ነው። የቀጣናው ሽኩቻ
ውስብስብ፣ ብዙ ኃይሎች ያሉበት፣ ተለዋዋጭ፣ እና በሥጋት የተከበበ ነው። ይህን ሁኔታ
አልፎ በብቃት ዘላቂ ጥቅምን ለማስከበር ውስጣዊ የፖለቲካ መረጋጋትና ጠንካራ አንድነት
ያስፈልጋል። ሌላው ቀርቶ ጊዜያዊ የኢኮኖሚ ማስተንፈሻ ድጋፎችን ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ
ሀገራት ለማግኘት እንኳን፣ በቀጣናው ያለን ይዞታ መጠንከር፣ በቀይ ባሕር ላይ የሚኖረን
ሚናም መጨመር አለበት።

አፍሪካ ብሎም ሀገራችን ያለችበት የአፍሪካ ቀንድ የኃያላኑ ትኩረት ማረፊያ መሆኑን ወደ
ጥቅም ለመቀየር የቀንዱ ሀገራት ትብርርና ሰላም በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ይሄን ማድረግ
አለመቻል ውሻ በቀደደው ጅብ እንዲገባ ያደርገዋል። ቀዳዳችንን ደፍነን የግንኙነት
ሚዛናችንን ጠብቀን መጓዝ እስከቻልን ዕድሉ መልካም ነው። ይሁንና ዕድሉን በፍጥነትና
ፈጠራ አክለን ወደጥቅም ካልቀየርነው፣ ዕድሉ በተለዋዋጭ ክሥተቶች ምክንያት
ያመልጠናል።

1.2 የመንግሥታት ኃይል መሸርሸር

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከመቶ ዓመት በፊት የነበረ አንድ መንግሥት እና በዚህ በ21ኛው
ክፍለ ዘመን ያለ መንግሥት ያላቸው ኃይልና ሥልጣን ሲወዳደር፣ የዚህ ዘመን መንግሥታት
ኃይልና ሥልጣን እጅጉን ቀንሷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ሥርዓት የተሣሠረ
ሆኗል፤ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው ፤ የዲጂታል ሉዓላዊነት
5
ትርጉም አልባ ሆኗ፤ የትላልቅ ኩባንያዎች ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ አይሏል፤ የዴሞክራሲ
ሥርዓት ያልተማከለ ኃይልና ሥልጣንን እየፈጠረ ነው፤ እነዚህ ሁሉ ተደምረው በፈጠሩት
ጫና የሀገረ መንግሥታት ኃይልና ሥልጣን እጅጉን አሽቆልቁሏል።

ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አሁን ድንበር ተሻጋሪ የፖለቲካ


እንቅስቃሴዎችን እና ዘመቻዎችን ያስተባብራሉ። የመረጃ ጠላፊዎች (ሐከሮችና ክራከሮች)
የመንግሥት ተቋማትን ሥርዓቶች ጊዜና ቦታ ሳይገድባቸው በቀላሉ ያስተጓጉላሉ። ሀብት
ለመዝረፍና ለማዛባት ይችላሉ። አሸባሪዎች መቶ ዶላር ባልሞላ ወጪ ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን
በመሥራት የሽብር ድርጊትን ይፈጽማሉ። በቀላሉ ገንዘብ ያሰባስባሉ፤ አባላትን
ይመለምላሉ፤ ዐመጽ ይቀሰቅሳሉ፤ በጥቅሉ በሕግና በሥርዓት ሕዝብን የሚያስተዳድረው
መንግሥት ሕግ የማውጣት እና የማስፈጸም ዐቅሙ እጅጉን አደጋ ውስጥ ገብቷል፡
በተቃራኒው በአስገዳጅ ሕግና ሥርዓት የማይገዙ የግል ተቋማት እና ኢ-መደበኛ
አደረጃጀቶች ኃይልና ጉልበት የሚያገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ፣ የኃይል መበተን የገጠመው መንግሥት ብቻ


አይደለም። የጦር ኃይሎች፣ ሚዲያዎችና የእምነት ተቋማትም ጭምር ናቸው። በመሆኑም
የኃይል መቀያየር ለጠንካራ የፖለቲካ ሥርዓት ግንባታ ፈተና ሆኖ መጥቷል። ይህ ለውጥ
ምን ዓይነት ማኅበራዊ ለውጥ ያመጣል? የኃይል ዐቅሙ የላላ መንግሥት ምን ሊከተለው
ይችላል? ዓለምስ በቀጣይ ምን ዓይነት መልክ ይኖረዋል? እነዚህን የመሰሉ ጥያቄዎችን
ከነባራዊ ክሥተቶች ጋር እያሰናሠልን መመልከት የተቀየረውን ዓለም ለመመልከትና
መውጫ መንገድ ለመተለም ይረዳናል።

የዴሞክራሲ ሥርዓት መስፋፋት የዜጎችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደጉና በውሳኔ ላይ ያላቸውን


ድርሻ መጨመሩ የመንግሥትን የኃይል መላላት ፈጥሯል። መንግሥታት በየአምስት ዓመቱ
ምርጫ ያደርጋሉ። ዜጎችም ከምርጫው ጊዜ ባልተናነሰ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ትኩረታቸውን
ሰጥተው በቅድመና ድኅረ ምርጫ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፋሉ። ይሄም ማን ይምራን?
የሚለውን መወሰንን ጨምሮ በበርካታ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ዜጎች በድምፃቸው ተጽዕኖ
እንዲያሳድሩ አድርጓቸዋል፡ የዜጎች ተሳትፎ መብዛትና ወሳኝ የሥልጣን መገኛ ምንጭ
መሆናቸው ፖለቲከኞች የሕዝብን ቀልብ የሚገዙበት ሩጫ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

በዚህ ኑባሬ ውስጥ የወል እውነት መገንባት ታላቅ ፈተና ነው። የተለያዩ ቡድኖች
የየራሳቸውን እውነት በማራገብ ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅ፣ ከመደጋገፍ ይልቅ መገፋፋትን

6
የህልውናቸው መሠረት አድርገው ስለሚወስዱ የውጥረት ፖለቲካ መለያቸው ነው። በዚህ
ውጥረት መካከል የወል እውነትን ግንባታ በፈተና ውስጥ የሚከወን ይሆናል።

ባለፉት ዐሠርት ዓመታት ውስጥ የቴክኖሎጂ ልህቀት በመንግሥትና በሕዝብ መካከል


ያለውን መሥመር አደብዝዞታል። ማንኛውም ሰው በፖለቲካ ምኅዳር ውስጥ ያለአንዳች
ገደብ መግባት የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ለፖለቲካ ተሳትፎ ተቋማዊና ባህላዊ
አሠራሮች ተጥሰው አዲስ ዐውድ ተፈጥሯል። ዛሬ ዛሬ የመንግሥትን፣ የፓርቲዎችንና
ተቋማትን ምሥጢር በቀላሉ ዐደባባይ ላይ የሚያሰጡ መኖራቸው ብቻ ሳይሆን ማስጫ
መንገዱ ፈጣን ተደራሽ መሆኑም አንዱ የዘመናችን ክሥተት ነው። የፔንታጎንን የጦር
ዕቅድ፣ ግምገማና የስለላ መረጃ የያዘ አንድ ሰነድ ማፈትለክ ብዙዎችን ያስገርም ይሆናል።
ከዚህ በላይ ግን ያፈተለከው ሰነድ በዓለም ላይ የሚዳረስበት ፍጥነት ግለሰቦች ያላቸውን
የኃይል ድርሻ ያገዝፈዋል። በመንግሥታት የአሠራር ግልጽነትም ሆነ እንደዚህ አፈትልከው
በሚወጡ መረጃዎች የተነሣ፣ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ያለ የእውነት ገመድ ሰልሏል።
በዚህ ሳቢያ የፖለቲካ መሪዎች ለሚከሠቱ ችግሮች ትክክለኛውን ርምጃ ለመውሰድ የነጻነት
እጦት ክበብ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል። በመሆኑም የመሪነት ሚናን በማሣነስ የአመራር
ብቁነት ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።

በአዲሱ ዓለም የሚዲያ ዓይነቶችና ባለቤቶቹ በዝተዋል። ይህም ‹ሚዲያን የያዘ ኃይልን ያዘ
የሚለውን አባባል ከአንድ ኃይል እጅ አውጥቶ ወደ ብዙዎች እጅ እንዲገባ አደረገው። በዚህ
የተነሣም የአንድ ኃይል የበላይነት እያከተመ የኃይል መከፋፈል ተፈጥሯል። በመሆኑም ዛሬ
የሕዝብን አስተሳስብ የሚቀርጹ ብዙ ኃይሎች አሉ። ነገሩ እንደ መንግሥት የኃይል መሸርሸር
ሲፈጥር፣ እንደ ሕዝብ ደግሞ ግራ መጋባት የፈጠረ ዘመን ሆኗል። የመንግሥት ሥልጣን
ከሕዝብ በሚመነጭበት ሥርዓት ውስጥ፣ የሕዝቡን ሐሳብ የሚቀርጹ ኃይሎች መብዛታቸው፣
የወል እውነቶችን መገንባት እጅግ ከባድ እንዲሆን ያደርገዋል።

1.3 የድኅረ እውነት ፖለቲካዊ ሐሳዊነት

የድኅረ እውነት ፖለቲካ ሰዎች ከሐቅ ይልቅ በስሜት የሚመሩበት፣ ከእውነትና ከማስረጃ
ይልቅ ወሬን ማናፈስና ስሜትን መያዝ የበላይነት የያዘበት፣ እንዲሁም የሤራ ትንተና
የብዙዎችን ቀልብና አስተሳሰብ የሚገራበት ጊዜ ነው። በመሆኑም የድኅረ እውነት ፖለቲካ
እውነትን በውሸት የቀየረ ብቻ ተብሎ ሊበየን የሚችል ሳይሆን፣ ውስብስብ የአመለካከት፣
የአስተሳሰብና የባህሪ ለውጥን ያመጣ ኑባሬ ሆኗል። ይህ ኑባሬ እውነትንና ምክንያታዊነትን
7
በመያዝ ብቻ የሰውን ሐሳብና ዕይታ መቅረጽ የማይቻልበት፣ ከሐሳብ ጥራት ይልቅ
የሥርጭት ዐቅሙና ስሜት ኮርኳሪነቱ የበለጠ ተጽዕኖ የሚፈጥርበት ዓለም ነው።

ድኅረ እውነት ስንል የውሸት ዜና (fake news) ማለትም ያልተከሠተን ነገር ተከሥቷል ብሎ
መዘገብ፣ ፈጥሮ ማውራት እና ማጋነን፣ ሆን ተብሎ የተዛባ መረጃ ማቅረብ (dis-information)
የተለመደበትን ዘመን ነው። ሰዎች እውነታዉን እንዳያውቁ በማድረግ ውሸት፣ ሤራ እና
ፕሮፖጋንዳ በመንዛት በሌሎች ላይ ጉዳት እንዲደርስባቸው ማድረግ፣ የተሳሳተ መረጃ (mis-
information) ሆን ተብሎ ጉዳት ለማድረስ ሳይሆን ባለ ማወቅ የሚተላለፍ የሐሰት መረጃ
መልቀቅ፤ እንዲሁም ያልተገባ መረጃ( mal- infommation) ማለትም ሆን ተብሎ የሆነን
አካል ስም ለማጥፋት እውነትን ከውሸት ጋር እንደ መርዝ በመቀላቀል የሚደረግ ጎጂ ድርጊት
የሚካሄድበትን ዘመን ነው።

ዘመንን እንደ ዘመን ‹ድኅረ እውነት› ብሎ መፈረጅ በጣም አስደንጋጭ ነው። በዙሪያችንን
ያለውን ሁሉ ነገር እንድንጠራጠር የሚያደርግ እና ለትውልዱም አእምሮ እጅግ ከባድ አባባል
ነው። ይህ ማለት ግን በዘመናችን ምንም ዓይነት እውነት የለም፤ ወይም እውነትን የሚናገሩ
አካላት የሉም ለማለት ተፈልጎ አይደለም። ነገር ግን እንደ ማዕበል ከዓለም ጫፍ ወደ
ሌላኛው ጫፍ እውነትን እየደፈጠጠ ያለው ውሸት እና የሤራ ዜና መበራከት፣ ጊዜውን ድኅረ
እውነት አስብሎታል። ይህ የፈጠረው ደግሞ ብዙ የመረጃ ምንጮች በመኖራቸው ምክንያት
ሰዎች የትኛውን መረጃ ማመን እንዳለባቸው ስለሚቸገሩ ነው።

በድኅረ እውነት - ዓለም ውስጥ፣ ስለ እውነት የጋራ መሥፈሪያ፣ ልኬትና ብያኔ ማግኘት
አዳጋች ሆኗል። በእውነትና በአማራጭ እውነት፣ በዕውቀትና በአስተያየት፣ በእምነትና በሐቅ
መካከል ያሉ ዕይታዎች ዓለምን ግራ መጋባትና ወዥንብር ውስጥ ጥሏታል። በድኅረ እውነት
በተጠየቅ ያልተፈተሹና በሳይንሳዊ ሂደት ያልተረጋገጡ እውነቶች የሚሠራጩበትና በቀላሉ
የሰፊውን ሕዝብ አእምሮና ልቡና የሚማርኩበት ዕድል አግኝተዋል። በድኅረ እውነት
ከተጨባጭ እውነቶች ይልቅ የሰዎችን ስሜት የሚኮረኩሩ ንግግሮችና መረጃዎች ገዥና
ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆነዋል።

ይህንን ፈተና የማኅበራዊ ሚዲያ አብዮት ቢያባብሰውም፣ የሐሰት ወሬ አጥፊነት ግን ዛሬ


የተፈጠረ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ጉዳቶችን ያስከተለ እና የብዙዎችን ሕይወት
የቀጠፈ ጉዳይ ነው። በሃይማኖት መጻሕፍት እንኳን ከሺ ዘመናት በፊት በሐሰተኛ መረጃ

8
ምክንያት የጠፉ ሕዝቦች ታሪክ በብዛት ተጽፎ ይገኛል። ከጆን ኤፍ. ኬኔዲ እስከ ሩዋንዳ
የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም ላይ የውሸት ዘገባ ብዙ ጉዳት አስከትሏል።

ምን እንደ ተፈጠረ እንኳ የማያውቁ ንጹሐን በቤታቸውና በቀያቸው በተቀመጡበት በውሸት


የጥላቻ ዜና እና ዘመቻ አሰቃቂ ወንጀሎች ተፈጽመውባቸዋል። ሰዎች መረጃውን ግራ እና
ቀኝ ከማረጋገጥ ይልቅ በስሜት በመነዳታቸው፣ ከፍተኛ የሆነ እልቂት እንዲፈጸም ምክንያት
ሆኗል። የትናንቱን መረጃ ዛሬ እንደተደረገ፤ አንድ አካባቢ ያለን ነገር ሌላ አካባቢ እንደሆነ፤
ሆን ብሎ ተቀናብሮ የተሠራን ነገር በእውነታው ዓለም እንደተከወነ ተደርገው የሚቀርቡት
መረጃዎች፣ ሰዎችን ከአእምሯቸው ይልቅ ለስሜታቸው ቅርቦች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

በሀገራችን ያለው እውነታ ደግሞ ከሀገሪቱ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ


ብዝኃነት ጋር ተያይዞ ቡድንተኝነቱን አወሳስቦታል። ሰዎች በቀላሉ በማኅበራዊ ሚዲያ
ተቧድነው አንዱ ሌላውን ብሔር፣ ሃይማኖት እና ታሪካዊ ይዘት መተቸት፣ ማንቋሸሽና
ማጥቃት የተለመደ ተግባር ሆኗል። ፌደራሊዝም የተሰጠው ትርጉም በአንዳንዶቹ ዘንድ
ትናንሽ ሀገራትን መመሥረት እስከ ደርሷል። የአካባቢ ጌቶች እኛ ካልፈቀድን ፌዴራል
መንግሥት በሠፈራችን አያልፍም እስከ ማለት ደርሰዋል። ራስን እንደ ዋና ኃይል ቆጥሮ
የሀገር አንድነትን እና ሉዓላዊነትን የሚገዳደር አመለካከት ተይዟል።

የውሸት ዜና አሠራጮች በሁለት መልኩ ተጠቃሚ እየሆኑ መጥተዋል። አንደኛው


እንታገልለታለን የሚሉትን ዓላማ ማሳካት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ይህንን ዓላማቸውን
ለማሳካት የሚያሠራጩበት አውታር የገቢ ምንጫቸው እየሆነ መምጣቱ ነው። በዚህ በኩል
ሕዝብን ከሕዝብ በውሸት ዜና ያፋጃሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የዩቲዩብ ዶላር ይሰበስባሉ።
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት መደበኛ፣ ሰላማዊ እና ልማታዊ ዘገባዎችን ሽፋን ከሚሰጡ የሚዲያ
አውታሮች ይልቅ፤ የግጭት፣ የነውጥ እና የጥላቻ መረጃዎችን የሚያሠራጩ አካላት የበለጠ
ተቀባይነት አግኝተው በርካታ ተከታይ አፍርተዋል።

በሀገራችን ታሪክም ጥቂት የመንግሥት ሚዲያዎች በነበሩበት ጊዜ መንግሥት ሐሳቡን


ያለተቀናቃኝ በቀላሉ ወደ ሕዝብ ያደርስ ነበር። የሚዲያዎች መበራከትና የማኅበራዊ ሚዲያ
መምጣት መንግሥታት ይህንን የሚዲያና የመረጃ የበላይነት እንዲያጡ አድርጓቸዋል።
ስለሆነም መንግሥታት ከሚዲያዎችና ከማኅበራዊ ሚዲያዎች ጋር በመረጃ ምንጭነትና _
አድራሽነት ትንቅንቅ ውስጥ መግባታቸው የተለመደ ክሥተት ሆኗል።

9
በዚህ ጉዳይ የተከናወኑ በርካታ ጥናቶች መፍትሔውን በአጭር ጊዜ እና በረጅም ጊዜ
ከፋፍሎ ማየት ጠቃሚ እንደሆነ ይገልጻሉ። አሠራጮች የሚያደርሱትን ጉዳት
የመጀመሪያው የአጭር ጊዜ የመፍትሔ መንገድ የሐሰት መረጃ በመመዘን፣ አስቸኳይ እና
አሳሳቢዎችን ቅድሚያ በመስጠት፣ አስፈላጊውን የመመከት እና የመልሶ ማጥቃት
ርምጃዎችን መውሰድ ነው። እንደ ዘለፋ፣ ቁም ነገር አዘል ቀልዶች፣ የተፈበረኩ መረጃዎች፣
ግነት የታከለበት መረጃ፤ የተዛባ ሪፖርት ፤ የዘር ማጥፋት፣ ብጥብጥ፣ ወደ ፀብ የሚገፋፉ
ሚዲያዎችን እና የሚዲያ ውጤቶችን በመለየት እንደየ ችግሩ አሳሳቢነት ደረጃ መስጠት
እና ፈጣን ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።

የመንግሥትና የፓርቲ ኃላፊዎች በዲጅታል ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች ዙሪያ በቂ ዕውቀትና


ክሂሎት ሊኖራቸው ይገባል። ትክክለኛ መረጃዎችን ለማዘጋጀትና ለማድረስ ዘወትር የተጉ
መሆን አለባቸው። እንደ ጥንቱ እነርሱ የመረጃ ሥርጭቱን ሥራ ባይሠሩት ሥራው
አይጠብቃቸውም። ሌሎች በተዛባና በአፍራሽ መልኩ ይሠሩታል እንጂ። በስማቸው ወይም
በሚመሩት ተቋም ስም የሚለቀቁ የውሸት መረጃዎች የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ፣
ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋቸዋል። የማኅበራዊ ሚዲያ አካውታቸውን ከሚዲያ ባለቤቶች
ጋር ትክክለኛነቱን (ቬሪፋይድ) በማረጋገጥ፣ በትክከለኛ አካውንት ብቻ ለሕዝብ መረጃ
ማቅረብ አለባቸው። አመራሮች የሐሰት አካውንቶችን ከማጋለጥ በተጨማሪ የሚያጋሯቸውን
መረጃዎች ተአማኒነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።

ከረጅም ጊዜ የመፍትሔ አቅጣጫ አንጻር ተአማኒነት ያለው፣ ጠንካራ፣ ተደራሽ እና የተደራጀ


የሚዲያ ተቋም ግንባታ ወሳኝ ነው። ይሄም ኅብረተሰቡ በቀላሉ እውነተኛውን እና በውሸት
ያልተበረዘውን መረጃ ለማግኘት ያስችለዋል። የሚዲያ ተቋማት እንዲኖራቸው የሚያስችል
ተቋማዊ ቁመና፣ በሕዝብ ተቀባይነት መርሕ እና ዐቅም ሊኖራቸው ይገባል። በማኅበራዊ
ሚዲያ አማካኝነት በሐሰት ትርክት የምትናጠውን ሀገር ለመታደግ እውነተኛውን መረጃ
ቀድሞ ተደራሽ የሚያደርግ ሚዲያ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ሚዲያዎቻችን (በተለይም የፌዴራልና የክልል ሚዲያዎች) ለአንድ ዓላማ፣ ነገር ግን በየዘርፉ


በሚኖራቸው ልዩ ዐቅም የሚሠማሩ መሆን አለባቸው። ራሳቸውን ከተለዋዋጩ ዓለም ጋር
አብረው የሚያስኬዱ፣ የኢትዮጵያን አጀንዳዎች ለመሸፈን ዐቅም የሚኖራቸው፣ ሕዝብ
በሚፈልጋቸው ልዩ ልዩ መልኮች ስፔሻላይዝ አድርገው የሚሠሩ፣ ብዝኃ መልክ የተላበሱ፣
ሀብትን በማያባክን መልኩ የሚሠሩ መሆን አለባቸው። ለዚህ ደግሞ በማዕከል ክትትልና
ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል።
10
1.4 የሃይማኖት፣ የብሔርና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ጥምረት አደጋ

የሀገራችን ፖለቲካ አንዱ ጉድለት የጋራ አጀንዳን በመፍጠር ሕዝብን ለጋራ ግብ ማሰባሰብ
አለመቻሉ ነው። ከዚያ ይልቅ ዋልታ ረገጥነት እና እስከ ታችኛው ቅንጣት ድረስ መከፋፋል
የፖለቲካችን አንዱ ገጽታ ነው። ሁሉም ራሱን የእውነት ብቸኛ ባለቤት አድርጎ
ስለሚመለከት በተለያዩ አስተሳሰቦች፣ አመለካከቶችና ማንነቶች መካከል መስተጋብርን
አለመፍጠር እና የጋራ አጀንዳን ይዞ መታገል የፖለቲካችን አንዱ ትልቅ ክፍተት ሆኖ
ሲፈትነን ቆይቷል።

ከኔ ምልከታ ውጭ ያሉት ሐሳቦች በሙሉ ከእውነት ተፃራሪ እና አጥፊ በመሆናቸው


በሚቻለው መንገድ ሁሉ በመታገል ማጥፋት አለብኝ ብሎ የሚንቀሳቀስ ነው። በመሆኑም
ከሌላው ጋር በአብሮነት፣ በመደራደርና በመነጋገር ነገሮችን ከመፍታት ይልቅ ጉልበትን እና
ጥቃትን እንደ መፍትሔ አድርጎ ይጠቀማል። በአክራሪነት ውስጥ ልዩነትን _ ማቀራረብና
ማስታረቅ የሚባል ነገር _ የለም። ያለው የበላይነትን ማስፈን ነው። ስለሆነም ደም አፋሳሽነት
ሁነኛ መገለጫው ነው።

በሀገራት ፖለቲካ ዕድገት ውስጥ አንዱና ትልቁ ጥያቄ ልዩነት የሚስተናገድበት መንገድ
ምን ያህል የሠለጠነ ነው? የሚለው ነው። በየሀገራቱ የተለያዩ የአመለካከትና የማንነት
ልዩነቶች አሉ። ልዩነቶቹ የሚታዩበትና የሚስተናገዱበት መንገድ ለሀገራት ፖለቲካዊ
መረጋጋት እጅግ አስፈላጊ ነው። የሀገራችን የፖለቲካ ባህል ልዩነትን ከልክ በላይ ለጥጦ
የሚያይ እና ለማቀራረብም ምን ዓይነት በር ለመክፈት የማይሞክር ነው። አክራሪነት
ልዩነትን ያለ አግባብ ለጥጦ በመመልከት፣ ማናቸውንም ዓይነት ሌሎች ሐሳቦችን
ለማድመጥም ይሁን ለማክበር ፍላጎት የሌለው የፖለቲካ አካሄድ ነው።

አክራሪነት ሰፍኗል ልንል የምንችለው ሁለት ጉዳዮች መንታ ሆነው ሲመጡ ነው። አንዱ
ልዩነቶችን አላግባብ በመለጠጥ እውነት የእኔ ብቻ ነው በሚል ስለሌላው ያለው ዕይታ
ማቻቻል የሌለበት፤ የበላይነትን መፍጠር እና ማጥፋት የሚተልም ሲሆን ነው። ሁለተኛው
ደግሞ ሐሰት የሚሉትን ከእነርሱ ውጭ ያለውን አመለካከት ለማጥፋት ማንኛውንም ዓይነት
ኃይል እና ማጥቃትን እንደ መንገድ የሚጠቀም ሲሆን ነው። የእኛ እና የእነርሱ ወገን ብሎ
በመለየት የአንዱን ወገን በሌላው ላይ መቀስቀስ፣ ማነሣሣት እና ማስጠቃት እንደ
ማስፈጸሚያ መንገድ ይጠቀማል።

11
በሀገራችን አክራሪነት ዋነኛው የፖለቲካ ችግር እንደሆነ ለመጥቀስ ሁለቱ መገለጫዎችን
እንመለከታቸው። የሀገራችን ፖለቲካ ‹እውነት የእኔ ብቻ ነው› የሚል ዋልታ ረገጥ
አመለካከቶች የሰፈነበት ነው፡ ጫፍና ጫፍ ያሉ አመለካከቶችን ወደ አማካይና ወደ
አስታራቂው መሥመር ለመምጣት ፍላጎት የሌለው የፖለቲካ ምልከታና እና አካሄድ
የሀገራችን ፖለቲካ መገለጫ ነው። የማይታረቁ ልዩነቶች አሉ የሚለው ገዥ መርሑ ነው።
ለውይይት፣ ለክርክር እና ለመቀራረብ ቦታ አይሰጥም። የኔን ብቻ የሚተልም በመሆኑ
ጥቃቅን የቃላት ልዩነቶች ሳይቀሩ ጎልተው ይታያሉ። ይህን ተከተሎም መጠፋፋትን
መሠረት ያደረጉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ሀገራችንን ሲያቆራቁዙ ኖረዋል።

ይህ ዓይነቱ ፖለቲካ በሀገራችን ሥር የሰደደ ችግር ነው። በየዘመናቱ ለተፈጠሩ ጥፋቶች


ዋነኛው ምክንያትም ነው። በትናንሽ ነጥቦች እና ቃላት ስንጠቃዎች ሀገርን ወደ ኋላ የጎተቱ
ብዙ ጥፋቶችን የፈጠረ፣ አሁን ድረስ የተጣባን ፖለቲካዊ ችግር ነው። በነባራዊ ዓለም አቀፋዊ
ሁኔታዎች ውስጥ አዲስ መልክ ለብሶ የሀገርን ህልውና ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከባዱ ፈተና
ሆኗል። አክራሪነት ዋነኛ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥቅምን ማጋበሻ መሣሪያ ሆኖ የወጣ
ሲሆን፣ የሤራ ትንታኔ እና ዐመጽ መገለጫዎቹ ናቸው።

ይህ የፖለቲካ አመለካከትና አካሄድ ሥር የሰደደ የሀገራችን ችግር ነው። አሁን ላይ ተለዋዋጭ


ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ውስጥ አዲስ መልክ ተላብሶ ከባድ ፈተናን ደቅኗል።
የመጀመሪያው ሀገራዊ ለውጥን ተከትሎ በተፈጠረው የዴሞክራሲ ምኅዳር ለዘመናት ተዘርቶ
የቆየው ጥላቻ ተገልብጦ ወደ ዐደባባይ ወጥቷል።

ሁለተኛው ፈተና ደግሞ የጥላቻ ትርክት በፍጥነትና በብዛት ታች ድረስ እንዲሠራጭ ምቹ


ሁኔታ መፍጠሩ ነው። ሦስተኛው ይህ የአክራሪነት ሽኩቻ ዓለም አቀፍ ተዋንያን በቀላሉ
የሚሳተፉበት መሆኑ ነው።

በአዲሱ ነባራዊ ሁኔታ አሉታዊ ትርክትና ጽንፈኝነት በቀላሉ እና ከየትኛውም ቦታ በፍጥነት


የሚስፋፉ ሆነዋል። ይህም ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት ትርክት እና ለመሐል ፖለቲካ ትልቅ
ጫናን ፈጥሯል። አዎንታዊና አቀራራቢ ትርክቶችን ለማስፋፋት ከአሉታዊ ትርክቶች ጋር
የግድ አድርጎታል። ከዚህ ቀደም ሀገራት ተገዳድሮ ማሸነፍን የሚፈልጉትን ትርክት
ለማሠራጭት የሚዲያና መዋቅራዊ ዕድል ነበራቸው። ማኅበራዊ ሚዲያ ግን ይህንን የሚዲያ
ኃይል የተበታተነ እና ቁጥጥር የማይደረግበት እንዲሆን አድርጎታል።

12
እየጨመረ የመጣው አክራሪነት ሁሉንም ነገር በማንነት መነጽር ውስጥ የሚዳኝ አድርጎታል።
ሁሉንም ነገር በብሔርና በሃይማኖት ሚዛን የሚያስቀምጠው ፖለቲካ፣ ለሐሳብ ውድድር
ክፍተትን አይሰጥም᎓᎓

አክራሪነትን የከፋ ያደረገው በማንነት ላይ በተመሠረተ የጥቅም ትሥሥር ሥልጣንን እና


ሀብትን ለመቀራመት የሚደረገው ውድድር ነው። በተለያየ ወገን የመንግሥት ባለሥልጣናት፣
ባለ ሀብቶች፣ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች የጥቅም ትሥሥር ፈጥረው፣ የማንነት ሽፋን
በለበሱ የተለያዩ ጎራዎች ውስጥ ተሰልፈው፣ የሚያደርጉት ፍልሚያ ለሀገር አደጋ የደቀነ
ነው። ይህ የአክራሪነት መሥመር፣ ሥልጣን እና ጥቅም ማግኛ እና ማስጠበቂያ ዋነኛው
መንገድ ሆኖ ሥልጣን እና ሀብትን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ለማግኘትና ለማስጠበቅ
ለሚፈልጉ ኃይላት ዋነኛ የመጨዋቻ ካርዳቸው ነው። በአጠቃላይ የፖለቲካ ሥርዓታችንን
የተለያዩ ኃይላት ለፖለቲካና ለኢኮኖሚ ትርፍ ወደሚንቀሳቀሱበት የፖለቲካ ገበያነት
ይቀይረዋል።

በአጠቃላይ አክራሪነት የሀገረ መንግሥትን ጥንካሬ የሚፈትኑ የተለያዩ ችግሮችን


ያስከትላል። እነዚህም፡-

የወል እውነት (የጋራ ግብ) መላላት፡- የጋራ ግብ የሕዝብን የጋራ ዕጣ ፈንታ የተሻለ ማድረግ
ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖር ሕዝብ የጋራ ዕጣ ፈንታ ይኖረዋል። ይህ የጋራ ዕጣ
ፈንታ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖር ሕዝብ ባስቀመጠው ግብ እና በግቡ ዙሪያ ተሰባስቦ
ለስኬቱ በሠራው ሥራ ላይ ይንጠላጠላል። በኅብረትና በጥንካሬ በጋራ ግብ ዙሪያ የሠራ
ሕዝብ ነገውን የተሻለ ያደርጋል። ከዚህ በተቃራኒ ለጋራ ግብ በጋራ መቆም ካልተቻለ ዕጣ
ፈንታችን የከፋ ይሆናል።

አግላይ የሆነ የልዩነት ፖለቲካ በሰፈነበት ሥርዓት ውስጥ፣ ፖለቲካኞች ራሳቸውን በተናጠል
የአንድ ማንነት ተወካይ አድርገው ይቆጥራሉ። ሥልጣን የሚታየው የአንድ ብሔር፣
ሃይማኖት ወይም የሌሎች ማንነቶች ጉዳይ ማስፈጸሚያ ተደርጎ ነው። በመሆኑም ሁሉም
እወክለዋለሁ የሚሉትን አካል ተናጠላዊ ፍላጎት አስጠባቂ አድርጎ በሚወስድበት የፖለቲካ
ሥርዓት ውስጥ የጋራ ግብ ቦታ እያጣ ይመጣል። ሁሉም አነስ ሲል ግለሰባዊ ፍላጎቱን፣ ከፍ
ሲል ቡድናዊ ፍላጎቶችን የሚያስፈጽም እንጂ ለሀገራዊ ጉዳዮች ቁብ የሚስጥ አይሆንም።
ይልቁንም በሌሎች ፍላጎቶች ወይም በጋራ ፍላጎት ላይ ተንተርሶ ግለሰባዊና ቡድናዊ
ፍላጎትን ለማርካት ሩጫዎች ይበዛሉ።

13
ማኅበረሰባዊ ትሥሥር መላላትና አለመረጋጋት፡- አንድ የፖለቲካ ስርዓት የተለያዩ
የማህበረሰብ ክፍሎች ውቅር ነው። ጥቁር ነጭ፣ሀብታም ድኻው፣ ሴት ወንዱ፣ የተለያየ ብሔር
በአንድ ላይ የሚኖሩበት ነው። አንድን ሥርዓት ሥርዓት የሚያደርገውም በእነዚህ
ማኅበረሰቦች መካከል የሚኖር ትሥሥር ነው። አክራሪነት ልዩነትን በማጉላት በአንድ
ማኅበረሰብ ውስጥ ያለን ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ያናጋዋል።

በተናጠላዊ የቡድን ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ አክራሪነት ለዘመናት የቆየና የተሠራ


የማኅበረሰብ ትሥሥርን ከሚሸረሽሩ ጉዳዮች መካከል ነው። ማንነትን መሠረት ባደረገ በእኛ
እና እነሱ፣ በወዳጅና ጠላት፣ የሤራ ትንታኔ የተመሠረተው ፖለቲካ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ
መተማመንን ይሸረሽራል። በተለያዩ ማኅበረሰቦች፣ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል
የሚኖረውን መተማመን በመሸርሸር፣ የሥርዓቱን መረጋጋት ጥያቄ ውስጥ ይከትታል።

የሕግ የበላይነት እና የፖለቲካ ተጠያቂነት መሸርሸር፡- ሥራዎችና ውጤቶች የሚዳኙት


በሕግ ሳይሆን በማንነት መሠረት በመሆኑ የፖለቲካ ተጠያቂነት ይሸረሸራል። ከሕዝብ ጋር
የሚኖር ግንኙነት ግለሰባዊ ስለሆነ ሕጋዊና ተቋማዊ በሆነ መንገድ ተጠያቂነትን ለማምጣት
ያስቸግራል። የማኅበረሰቡ ተወካይ አድርገው ራሳቸውን የሚቆጥሩ ግለሰቦችና ቡድኖች
ንግግራቸውንም ይሁን ድርጊታቸውን የማንነት ሽፋን ስለሚሰጡት ማንኛውም ተጠያቂነትን
ለማስፈን የሚደረግ ጥረት በማንነቱ ላይ እንደተቃጣ ጥቃት ይወሰዳል። በዚህም ተጠያቂነትን
አጣብቂኝ ውስጥ ይከተዋል።

ለውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት በር መክፈት፡- እጅግ አደገኛው ውጤት ሀገራችንን ለውጭ
የፖለቲካ ነጋዴዎች አሳልፎ መስጠቱ ነው። በኢኮኖሚያዊም ይሁን በፖለቲካዊ ዐቅም
ጠንካራ የሆኑ ሀገራት በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በረቀቀ መንገድ ገብተው የፖለቲካ ገበያውን
ለመዘወር ዕድል ያገኛሉ።

1.5 ድህነት እንደ ታላቁ ተግዳሮት

የሀገራት ዋነኛ ግብ ህልውናቸውን የሚያስጠብቅ ሀገራዊ ጥንካሬን መፍጠር እና የዜጎቻቸውን


ፍላጎት ማሟላት ነው። ሁለቱ ጉዳዮች የሚያያዙ ናቸው። ዜጎች ለአንድ ሀገር ህልውና
የሚኖራቸው ቅቡልነት የሚመነጨው ሀገረ መንግሥቱ ምን ያህል ፍላጎቴን ሊያስጠብቅልኝ
ይችላል ከሚለው በመነሣት ነው። ለአንድ ሀገር ቀጣይነት የሕዝብ ፍላጎት መሟላት እና
የሕዝብ የማያቋርጥ ድጋፍ መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው። ሕዝብ ፍላጎቱ ሲሟላለት ድጋፉን
ይሰጣል፤ ይህም ለሀገረ መንግሥቱ ቀጣይነት መሠረት ነው። ድህነት ለሀገረ መንግሥት
14
ህልውና በብዙ መልኩ ፈተናን የሚደቅነው የሕዝብን መሠረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት
ስለማያስችል ነው።

ድህነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ሲሆን የዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና


ማኅበራዊ ጉዳዮች ውጤት ነው። ያልተሟሉ የዜጎች መሠረታዊ ፍላጎቶች እና የአንድ
ማኅበረሰብ ኋላ ቀርነት እና መሻሻል አለመቻል ማሳያ ነው:: በሀገራችን ዕድገትና መሻሻልን
ለመፍጠር በተደረገው ጥረት እና በተከታታይ ዓመታት በተመዘገበው ስኬት ብዙ ሕዝብ
ከድህነት እንዲወጣ ለማድረግ ቢቻልም አሁንም በዘርፈ ብዙ በድህነት የሚማቅቀው ሕዝብ
ቁጥሩ ከፍተኛ ነው። ምግብ፣ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ፣ መብራት እና ሌሎች ጉዳዮች ጥያቄ
የሆኑበት የኅብረተሰብ ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው። የምንኖርበት የድህነት እና የኋላ ቀርነት
ደረጃ ከፍተኛ ሲሆን እንደ ሀገር የዘርፈ ብዙ ችግሮች ውጤት እና የተለያዩ ፈተናዎች
ምክንያት ነው። ድህነት የፖለቲካ አለመስከን፣ የሀገር አለመረጋጋት፣ የሰላም እጦት፣ ወዘተ.
ምክንያቶች ውጤት ሲሆን መልሶ ለሰላም እጦትና ለግጭት ምክንያት ይሆናል::

ድህነት ማለት የሚፈጠሩ የተለያዩ ፈተናዎችን ለመመለስ ኢኮኖሚያዊ ዐቅም አለመኖር


ነው። አንድ ማኅበረሰብ እንደ ማኅበረሰብ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ
ዐቅም ከሌለው የሚኖረው በድህነት ውስጥ ይሆናል። ሀገራት እንደ ሀገር ቀጣይነታቸውን
ለማረጋገጥ ከሚያስፈልጋቸው ኃይል መካከል ኢኮኖሚያዊ ኃይል ቀዳሚው ነው:: አንዳንድ
የዓረብ ሀገራት ነዳጅ የፈጠረላቸው ኢኮኖሚያዊ ዐቅም እንደ ሀገር ላላቸው ጥንካሬ መሠረት
ነው::

ኢኮኖሚያዊ ዐቅም የማኅበረሰብ ፍላጎትን ለመመለስ፤ ሀገርን ከአደጋ ያስችላል።


በተጨማሪም ለመከላከል እና ጥቅምን ለማስከበር የሚያስችሉ ኃይሎችን ለመፍጠር ዓለም
አቀፍ ተጽዕኖን ለመቋቋም ና ያዳግተዋል። ፍላጎቱ ያልተሟላለት ለመፍጠር ያስችላል።
ደካማ ሥርዓት የማኅበረሰቡን ፍላጎት ማሟላት ማኅበረሰብ አለመረጋጋትን ይፈጥራል።
አለመረጋጋት ደግሞ ደካማ ሥርዓትን ያመጣል። እንዲህ እያለ ማብቂያ የሌለው አዙሪት
ውስጥ ይከትታል፡ ልማት የተሻለ ሥርዓት ውጤት ነው። እንዲሁም የተሻለ ሥርዓትን
ለመገንባት መንሥኤ ሆኖ አስተዋጽዖ የሚያደርግ ነው። ድህነት በተቃራኒው የደካማ ሥርዓት
ውጤት ሲሆን ለደካማ ሀገርነትም አስተዋጽዖ ያደርጋል። ለዚህም ነው ድህነት የሀገራችን
ችግሮች ማጣፊያ እና ታላቁ ተግዳሮት የሆነው። ድህነትን ማቃለል ለሁሉም ችግሮቻችን
መፍትሔ ይሆናል ባንልም ለብዙ ችግሮቻችን መቃለል በር ይከፍታል።

15
የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ዋነኛ ፈተና ሥር የሰደደ ድህነት ከሚፈጥረው አዙሪት
የሚመነጭ ነው። ድህነት የሀገራችንን ህልውና ለሚፈትኑ ከውስጥና ከውጪ ለሚነሡ
ጫናዎች ይዳርጋል። በሀገራችን የውጭ ተጽዕኖዎች እንዲያይሉ፣ የብሔርና የሃይማኖት
ግጭት ዘላቂ መፍትሔ እንዳያገኝ እንዲሁም የተረጋጋ የሀገር ግንባታ እንዳይኖር ትልቅ
ተግዳሮት ሆኖ ለዘመናት የዘለቀው ድህነትና ኋላ ቀርነት ነው። ኢትዮጵያ ከዓለም ድኻ
ሀገሮች ተርታ የምትሰለፍ ናት። ይህ ድህነት ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት እንዳትችል
አድርጓታል። ድህነት፣ ሥራ አጥነት እና በቂ የመሠረተ ልማት አውታሮች አለመሟላት
በሀገራችን በቂ የመንግሥት ሥርዓት ግንባታ እንዳይኖር አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ናቸው።
ሕዝቡ ካለበት ድህነት ወጥቶ ወደ ዕድገት እንዳያመራ ራሱን ችሎ የሚቆም መንግሥት
ያስፈልገዋል። ድህነት ተደጋፊ መንግሥት እንዲኖር የበኩሉን ድርሻ ይወስዳል።

ከእነዚህ ተግዳሮቶች እና ማነቆዎች በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥነት ችግር


በኢኮኖሚው ላይ ብቻ ሳይሆን በሥርዓት አልበኝነት ላይ ለለውጥ፣ ለአዲስ ለአዲስ የራሱን
አሉታዊ ዐሻራ እያሳረፈ ይገኛል። ወጣትነት ለሥራ፣ ለትግል፣ ነገር ተነሣሽነት ጎልቶ
የሚታይበት የሚታይበት ዕድሜ እንደመሆኑ፣ የአንዲት ሀገር ዕድገትም ሆነ ውድቀት
በየዘመኑ ባለው ወጣት ትውልድ እንቅስቃሴ ላይ የተመረኮዘ ነው። ሥራ ፍለጋ ከገጠር ወደ
ትናንሽ ከተሞች የሚፈልሱ እንዲሁም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪ
የደረሱ፣ በተለያያ ደረጃ ከቴክኒክና ሞያ ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶችን ማስተናገድ
የሚችል የሥራ ዕድል ባለመፈጠሩ፣ የሥራ አጥ ወጣቶች መጠን ከፍተኛ እየሆነ ይገኛል።
የሀገሪቱን ከተሞች ያጨናነቁ፣ ከዓመት ዓመት ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄድ ሥራ ፈላጊ
ወጣቶች የተስፋ መቁረጥ ስሜት አድሮባቸዋል። በሀገራቸው ሥራ አግኝተው የተሻለ ሕይወት
የመኖር ተስፋ የራቃቸው ወጣቶች፣ ባልፈለጉት መሥመር ወደ ውጭ ለመጓዝ ይገደዳሉ።
በየዓመቱም ሁለት ሚልዮን አዳዲስ ሥራ ፈላጊዎች ገበያውን ይቀላቀላሉ። ከዐርባ በላይ
ከሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎችም በየዓመቱ ከ150 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይመረቃሉ። እነዚህ ሁሉ
ሀገራችን ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር እንዳለባት የሚያሳዩ ናቸው። ነገሩን ከድጡ
ወደ ማጡ የሚያደርገው ደግሞ እግሮች ሁሉ ወደ አዲስ አበባ መትመማቸው ነው። ከሀገራችን
የሕዝብ ቁጥር ከግማሽ በላይ የሚይዙት ወጣቶች ለልማት አስቻይ ዐቅሞች የመሆናቸውን
ያክል ወደ አጥፊነት የመቀየር ዕድል አላቸው። ወጣትነት በተስፋና በትዕግሥት ማጣት
የሚናጡበት የእድሜ ምእራፍ እንደ መሆኑ ወጣቶችን የሚያስተናግዱ መሠረተ ሰፊ የልማት

16
ሥራዎች ካልተሠሩና ወጣቶች ተስፋቸው ካልለመለመ ወደ ጥፋት ኃይልነት ለመቀየር
ቅርብ ናቸው።

ያለፉት አራት እና አምስት ዓመታት በኮቪድ ወረርሽኝ፣ በዓለም አቀፉ ውጥረት፣ እንዲሁም
በሰሜኑ ጦርነት ውስጥ ብታልፍም፣ ኢትዮጵያ ከየትኞቹም የአፍሪካ ሀገራት የተሻለ
የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች። በዚህ የዕድገት ጉዞ ውስጥ ወጣቶችን ፈጠራ በታከለበት
መልኩ በማሳተፍ፣ የዕድገት ምጣኔውንና ፍጥነቱን እንዲጨምሩት በማድረግ፣ ወጣቶችን
ከጥፋት ጎዳና ማዳን ይገባናል። የመንግሥትና የግል ዘርፉን ትብብር በማሳደግ በበለጸገች
ኢትዮጵያ ውስጥ የወጣቶች ቦታ እንደቁጥራቸው መጠን እንዲሆን መሥራት ይገባናል።
የተጀመሩ ልማቶችን በየክልሉ በማስፋፋት እና አንዱን ክልል ከሌላኛው ጋር የጥቅም
ትሥሥር እንዲፈጥር በማስቻል፣ ሁሉም ክልሎች ተቀራራቢ የሆነ ዕድገት እንዲኖራቸው
መሥራት ይገባል።

1.6 በእንጥልጥል ላይ ያለ የሀገር ግንባታ

ሀገራችንን ወደ ብልጽግና ለመምራት ያለብን የቤት ሥራ ዘርፈ ብዙ እና እንደ ሀገር


ከቆምንባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች የሚጀምር ነው። ሀገራችን የረዥም ጊዜ የሀገርነት ታሪክ
ቢኖራትም ለአንድ ሀገር ጥንካሬ መሠረት የሆኑ መሠረታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ከማሟላት
አንጻር ሰፊ ክፍተት አለባት። የሀገር ግንባታ ሂደት የማይቆምና የማያቋርጥ ሂደት ቢሆንም
ገና ሥራቸውን ባላጠናቀቁና ሥራቸውን በአብዛኛው በአጠናቀቁ ሀገራት መካከል የሚጭነው
ዕዳ እኩል ዕዳ እኩል አይደለም። ቀድመው የቤት ሥራቸውን የጨረሱ ሀገራት የዘወትር
ተግባራቸው ቤቱን እያስተካከሉና እየወለወሉ ማሣመር ነው። የቤት ሥራቸው ያልጨረሱ
ሀገራት ግን ለዘመናት ሳይመለሱ የቀሩ ብዙ ችግሮች አሉባቸው፤ መሠረታዊ የሆኑ የነጻ
ተቋማት ግንባታ እና የጋራ ማንነት ግንባታ ገና ብዙ ያደክማቸዋል። የሀገራችንም ትልቁ
ፈተና ባልተጠናቀቀ የሀገር ግንባታ ላይ እየሠሩ፣ ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም አቀፍ አካባቢ
ውስጥ የሚፈጠሩ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ድህነትን መቅረፍ ነው። ድህነት የሕዝብን ፍላጎት
ለማርካት የሚያስችል ዐቅም የሌላቸው ደካማ ተቋማት ውጤት ነው። እርሱም መልሶ ለደካማ
ሀገር መፈጠር ምክንያት ይሆናል። የሀገር ግንባታችን ያልተጠናቀቀና በእንጥልጥል ላይ
የሚገኝ ነው።

ይህም ሲባል ነጻ፣ ገለልተኛና ጠንካራ ተቋማት ለመገንባት አሁንም ሰፊ ሥራን ይጠይቃል
ማለት ነው። በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያሉ መግባባቶች፣ መጻኢውን ትውልድ
17
በኢትዮጵያዊነት የመቀረጽና የማነጽ እንዲሁም የጋራ ማንነትን የመፍጠር ሥራ አሁንም
ትልቅ ጥያቄ ነው። በተጨማሪም የፖለቲካ ሥርዓቱን የጨዋታ ሕግጋት ሰላማዊ፣ መርሕ
ተኮር፣ በሐሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ እና ዴሞክራሲያዊ የማድረግ ሥራ ገና በጅምር
ላይ የሚገኝ ነው። ከድህነት ተላቅቀን ትርጉም ያለው ሕይወትን የሚያጣጥም የበለጸገ
ማኅበረሰብ የመፍጠር ትልማችን ብዙ ርቀት መጓዝን ይጠይቃል።

በሀገራችን የፖለቲካ ኃይሎች መካከል በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ማለትም በታሪክ፣ በሕገ
መንግሥት፣ በሰንደቅ ዓላማ፣ በፌደራሊዝም፣ በወሰንና በማንነት፣ ወዘተ. ጉዳዮች ዙሪያ
መግባባት የለም። በመሆኑም ጠንካራ የፖለቲካ ሥርዓት በሀገራችን ዘላቂ፣ አስተማማኝና
አለመገንባቱ ብቻ ሳይሆን የሀገራችን ህልውናም አደጋ ውስጥ እንዲገባ ሆኗል። ስለዚህም
ይሄንን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት ዕርቀ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር
መንግሥትና ፓርቲያችን በድኅረ ምርጫ ለእነዚህ ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት እንደሚሠራ
አቅጣጫ ተቀምጧል።

ያልተሟላ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ግንባታ ሲኖር ብዙ ጊዜ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እምነት


ያጣል። አንድ ሀገር ውጤታማ የአስተዳደር መዋቅሮችን እና ተቋማትን ማቋቋም ሲያቅተው
የጸጥታ እጦት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ውሱንነት እና የፖለቲካ አለመረጋጋትን ያስከትላል።
ይህም ሕዝብ መንግሥትን ወደ አለማመን እንዲያመራ ያደርገዋል:: ዜጎች መንግሥት
መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም ትምህርት፣ ፍትሕ፣ ወይም ደኅንነትን ማረጋገጥ መቻሉን
ይጠራጠራሉ። እንዲሁም መንግሥትን ሙሰኛ እንደሆነ፣ ውጤታማ እንዳልሆነ ወይም
ለፍላጎታቸው ምላሽ እንደማይሰጥ አድርገው ሊያዩ ይችላሉ። ይህ የመተማመን ጉድለት
ዜጎች በመንግሥት ተቋሞቻቸው የማይወከሉ ወይም የማይከበሩ ስለሚመስላቸው
ለመንግሥት ሥርዓት ቅቡልነትን ይነፍጋሉ።

በመሆኑም ለረጅም ጊዜ እየተንከባለሉ የመጡና በቂ ትኩረትና ውይይት ያልተደረገባቸውን


ጉዳዮች ማኅበራዊ ውላችንን ለማደስ ወይም ለማሻሻል በሚያስችል፣ እንዲሁም የከረሙ
ጥያቄዎችን ለመፍታትና የጋራ መግባባታችንን ለማጠናከር በሚያግዝ መልኩ መፍታት
ይኖርብናል። የሀገር ግንባታ ሂደቱን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም የሚያስችሉ በርካታ
ሥራዎችን በመሥራት፣ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር ያስፈልጋል። ይህም ሂደት ማኅበራዊ
ውላችንን ለማደስና ለማሻሻል የምንችልበትን፣ በአዲስ ውል የሀገር ግንባታ ሂደቱን
የምናጠናክርበትን አጋጣሚ የሚፈጥር ነው።

18
በጥቅሉ የሀገር ግንባታ እና መጠናከር የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። ሀገርን ለማጠናከር
የሚደረገው ጥረት ለዘመናት ሥር የሰደዱ ችግሮችን እና ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም አቀፍ
ሁኔታ የሚፈጠሩ ፈተናዎችን መመከትን ይጠይቃል። ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ
አዝማሚዎች የሚፈጥሩትን ዕድል ለመጠቀምና ተግዳሮቶችን ለመግታት፣ ተቋማትን
ለመገንባት፣ ብሔራዊ መግባባትን ለማስፈን፣ ዴሞክራሲን ለማጎልበትና ብልጽግናን
ለማረጋግጥ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ያስፈልጋል።

የሀገር ግንባታ መሠረታዊ ጉድለቶች የሆኑትን የተቋማት አለመጠናከር እና የጋራ ማንነት


ግንባታ ክፍተቶችን እየደፈንን መሄድ ካልቻልን፣ የሚፈጠሩ ተለዋዋጭ ፈተናዎችን መመከት
አንችልም። እነዚህን ፈተናዎች መመከት ካልቻልን ደግሞ ጠንካራ ሀገር የመፍጠር
ትልማችን ሊሳካ አይችልም።

19
ክፍል ሁለት

II. የፈጠራና ፍጥነት አስፈላጊነት

2.1 ኋላ ከቀረንበት ወጥተን ከፊት ለመገኘት

በለውጥ ጉዟችን ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎች እና


ለቀጣይ ጉዟችን ያላቸውን አንድምታ ስንመለከት የተለያዩ ጉዳዮችን እንረዳለን።
የመጀመሪያው ሀገራዊ ችግሮቻችን ሥር የሰደዱ፣ አንዱ ከአንዱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው፣
የችግር አዙሪትን የሚፈጥሩ መሆናቸው ነው።

ሁለተኛው በፍጥነት እየተለዋወጠ የመጣው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ዕድሎችን እና አደጋዎችን


ይዞ መምጣቱ ነው። ይሄም ሥር ለሰደዱ ሀገራዊ ችግሮቻችን አዲስ መልክና ገጽታ
እየሰጣቸው ከመሆኑ በላይ ተለዋዋጭ አድርጓቸዋል። አክራሪነትን የድኅረ እውነት ፖለቲካ
ሌላ መልክ ሰጥቶታል፤ ዓለም አቀፍ ሽኩቻዎች እና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተጨማሪ እና
አዳዲስ ኢኮኖሚያዊ ጫናን በመፍጠር ድህነትን ለመቀነስ ለሚደረገው ጥረት ሌላ መልክ
ሰጥተውታል። የሀገረ መንግሥት ግንባታ ባልተጠናቀቀበት ሁኔታ የመንግሥታት ኃይል
መሸርሸር የሚፈጥረው ጫና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደቱ ተጨማሪ ፈተና ፈጥሮበታል።
በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታው ይዞት የመጣው ዕድል ቢኖርም ሥር የሰደዱት
ሀገራዊ ችግሮች ተለዋዋጭ፣ አዲስ መልክ የተላበሱና ይበልጥ ፈታኝ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል::

በሀገራችን እንዴት ይሄ ኖሮን እንዴት በዚህ ችግር ውስጥ ልንገኝ እንችላለን? የሚሉ
ጥያቄዎች በዝተው ይነሣሉ። ለዚህም ዋነኛው ችግር ዐቅሞቻችንን የምንጠቀምባቸውና እና
ችግሮቻችን የምንፈታባቸው አዳዲስ ሐሳቦችን የማመንጨት እና የማደረግ ክፍተት መኖሩ
ነው። ችግሮችንን የምንፈታበት መንገድ አዲስነት እና ፍጥነት የሚጎድለው በመሆኑ ለረዥም
ጊዜ ከችግሮች ሳንላቀቅ ኖረናል። ከችግር ለመላቀቅና የሕዝብን ሐሴት የሚፈጠር ዕሴት
ለመፍጠር ያደረግነው ጥረት ፈጠራና ፍጥነት የሚጎድለው ሲሆን ችግር ፈቺ አዳዲስ
ሐሳቦችን ባለማምጣታችን እና ችግሮቻችንን ለመፍታት በፍጥነት ባለመጓዛችን ወደ ኋላ
ቀርተናል። ችግሮች በችግሮች ላይ እየተደራረቡ ከአንድ የዕድገት ደረጃ ወደ ሌላ የዕድገት
ደረጃ ሳንሸጋገር ከችግሮቻችን እና ከዓለም ኋላ ቀርተናል።

20
በአንድ በኩል ተደራራቢ የሆኑ ችግሮችን እየመለሱ፣ በሌላ በኩል ከዓለም የፖለቲካ እና
የኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ ተወዳዳሪ እየሆኑ ለመሄድ የሚያስችል ፍጥነት ያስፈልገናል።
ፈጠራ ፈጠራ ከችግሮቻችን መላቀቅ እንድንችል የሚያደረግ መሻሻል ለማምጣት እንዲሁም
በዓለም ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት የሚያስችል ዕድል ይሰጠናል። ፈጠራና ፍጥነት
ውዝፍ ችግሮችን ለመቅረፍ እና በለውጥ ውስጥ የሚፈጠሩ አዳዲስ ፈተናዎችን ለመቋቋም፤
ዕምቅ ዐቅሞችን እና በነባራዊ ሁኔታ ውስጥ የሚከፈቱ ዕድሎችን መጠቀም የሚያስችል ነው።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ መዘግየት ብልጽግናን ለማረጋገጥ ያለንን ውሱን ሀብትና ጊዜ እንዲባክን
እና ዓለም አቀፍ ጫናዎች እንዲበረቱ ያደርጋል። በመዘግየታችን ሀገራችንን ለመለወጥ እና
የተሻለ የብልጽግና ደረጃ ላይ ለማስቀመጥ የሚያስችሉ ብዙ ዕድሎች መክነዋል። በዚያው
ልክ ብዙ ችግሮች እየተወሳሰቡ እና እየጠነከሩ መጥተዋል። ጫናዎችም በርትተዋል።
አንዳንዴ በሀገራችን ትልልቅ ሐሳቦች እና አጓጊ ውጥኖች ቢነሡም እነዚህን ውጥኖች
ለማሳካት አንፈጥንም። ይህ አዝጋሚ ጉዟችን ከሐሳቦቹ ውጤት እና ከጅምሮቹ ፍጻሜ
ሳንደርስ ባክነን እንድንቀር ያደርገናል። አልያም ብዙ ፈተና ይበዛብናል።

ለአዝጋሚ ጉዟችን አንዱ ማሳያ የሕዳሴ ግድብ ግንባታችን ነው። የሕዳሴ ግድብ ትልቅ
ውጥን እና ሐሳብ ቢሆንም በአዝጋሚ ጉዟችን ምክንያት ብዙ ፈተናዎች ውስጥ ገብቷል።
የሕዳሴ ግድብ ከተጀመረ _ ጀምሮ ያሉ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች በግድቡ ላይ ያሳረፉት ጫና
ቀላል አይደለም። ከሚገባው በላይ በመዘግየቱ የተነሣ የዋጋ ጭማሪ ፈትኖናል፤ ዓለም አቀፍ
ፖለቲካው ተቀያይሯል፤ ለዲፕሎማሲያዊ ጫና እንድንጋለጥ አድርጎናል፤ የዓለም የኢኮኖሚ
ፈተና ጨምሯል።

ይህ ሁሉ የመጣው ግድቡ በመዘግየቱ ነው። ከኢኮኖሚ እና ከዋጋ አንጻር ስንመለከተው


ግድቡ በጊዜው ባለመጠናቀቁ በአንድ በኩል እየተለዋወጠ ከሚመጣው ዋጋ ጋር ተያይዞ
ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዲፈጠር ሆኗል። በሌላ በኩል አልቆ ሊገኘ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ
ጥቅም ሀገር ሳታገኝ ቀርታለች። እስካሁን ሊጨምረው የሚችለውን ዕሴት ሀገር አላገኘችም።
ከዓለም አቀፍ ፖለቲካና ከዲፕሎማሲ አንጻር ግድቡ ሲጀመር የነበረው ምቹ ዓለም አቀፋዊ
ሁኔታ ተለውጦ የግድቡን የውኃ ሙሌት ፈታኝ እውነታዎች በነበሩበት ጊዜ ለማካሄድ ግድ
ሆኗል::

ፈጠራና ፍጥነት በሰው ልጆች ውስጥ ያሉ ዕምቅ ዐቅሞች ናቸው። በየተሠማራንበት መስክ
እነዚህን ዕምቅ ዐቅሞችን ወደ ተግባር ከቀየርን ዕጣ ፈንታችንን ራሳችን እንድንጽፍ

21
ያስችሉናል። በፓርቲና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ፈጠራና ፍጥነት እንደ ግልና እንደ
ቡድን ምን ያክል አለን? ለአንድ ራእይ የተሰለፉ ባለ ራእዮች ወደ ራእያቸው ለመድረስ
ፍጥነትና ፈጠራ ያስፈልጋቸዋል። ፍጥነት በውስጡ ጊዜና ርቀትን ይይዛል። ከታለመው
ርቀት(ራእይ) በጊዜ ለመድረስ ፈጠራ ያስፈልጋል። ፈጠራ በእግር ከመሄድ በፈረስ፤ ከፈረስ
ወደ ሳይክል፣ ከሳይክል ወደ መኪና፣ ከመኪና ወደ ፈጣን ባቡር፣ ከእነዚህ በበለጠ ፍጥነት
ለመጓዝና ካሰብንበት ለመድረስ አውሮፕላን የበለጠ አማራጭ ነው::

ፈጠራ ከራእያችን ለመድረስ አማራጭ የሚያቀርብ መሣሪያ ነው። በርካታ የፈጠራ ሐሳብ
ኖሮ የአድራሹ ፍጥነት ከዘገየ ፈጠራዎቹ ከመዳረሻቸው ሳይደርሱ በሌላ ይተካሉ። እያዘገሙ
ፈጠራን መተግበር በጦርነት መሐል ፈረስን እንደ መቀየር ነው። የሚያስከትለው አደጋ
የሕይወት እንደሆነ ሁሉ መዘግየት ከመድረስ ጋር ፍጹም የራቀ እንደገና እንደ መጀመር
ነው። ለዚህ ነው እንደ ግለሰብም እንደ ሀገርም አንድ ጊዜ ያደናቀፈን ድንጋይ፣ ሺ ጊዜ
የሚደጋግመን።

2.2 ጊዜና የምርጫ ቃል ኪዳን

‹የምርጫ ቃል ኪዳን› ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚበየንበትና የሚጸናበት ቁልፍ ፖለቲካዊ


ውል ነው። በውክልና ዴሞክራሲ ውስጥ ተመራጩ መራጩን ውክልና የሚሰጠው በምርጫ
ቃል ኪዳኑ ላይ የተቀመጡትን ግቦች እንዲያሳካለት ነው። ተመራጩ እነዚህን ግቦች ማሳካት
ካልቻለ ውክልናውን ጥሷል ወይም የውክልና ውሉን አፍርሷል ተጠያቂነት ማለት ተመራጩ
ማለት ነው። ይህም የቃል ኪዳን ተጠያቂነትን ያመጣል። የቃል ኪዳን በምርጫ ቃል ኪዳኑ
መሠረት ተልእኮውን ካልፈጸመ፣ በቀጣዩ ምርጫ በመራጩ የሚቀጣበት ሁኔታ ነው።
ተመራጩ ቃል ኪዳኑን በማፍረሱ ወይም ለማሳካት ባለመቻሉ ምክንያት፣ በቀጣዩ ምርጫ
ካልተጠየቀና ካልተቀጣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ሊሆን አይችልም።

ማዝገም ማስተዋል ተደርጎ ከሚቆጠርበት ሀገራዊ ድባብና ባህል እየተላቀቅን ስለመምጣታችን


የሚያስረዱንን ብዙ ምሳሌዎች መጥቀስ ይቻላል። ነገር ግን ከራሳችን ቃል፣ ከብልጽግና
ግባችን፣ ካስቀመጥነው ዕቅድ አንጻር አፈጻጸማችንን ስንለካው፣ ፍጥነት መጨመር
እንደሚገባን በግልጽ እንገነዘባለን። አሁን ያለብን ዋናው ጥያቄ የፍጥነት ጥያቄ ነው።
ጅምሮቻችን አጓጊ ናቸው ፤ ግን መፍጠን አለብን። ርምጃዎቻችን ተስፋን የሚያለመልሙ
ናቸው፤ ግን መፍጠን አለብን። የዘገዩ ሀገራት ዋነኛው የስኬት መለኪያ ነገሮችን
ማከናወናቸው ብቻ ሳይሆን ያከናወነበት ፍጥነት ጭምር ነው። ስኬታችን እንደ አትሌት
22
ባስመዘገብነው የሰዓት ሪኮርድ ልክ የሚወሰን ነው። ዋናው ቁም ነገር ያከናወነው ነገር ብዛት
ሳይሆን በምን ያክል ጊዜ አከናውነነዋል? የሚለው ጉዳይ ነው።

2.3 ቃልን ማጠፍ እና ቃልን ማክበር

ቃልን ማጠፍ በማንኛውም ኅብረተሰብ ውስጥ እምነትን የሚሸረሽር፣ እንደ ከሐዲ የሚያስቆጥርና
የፖለቲካ ባሕልን የሚጎዳ ጉዳይ ነው። ቃላቸውን የሚያጥፉ ፖለቲከኞች በበዙበት ሀገር _ ውስጥ፣
ዜጎች _ እምነታቸውን ሰጥተው የሚያዳምጡት፣ የሚመርጡትና የሚደግፉት ፖለቲከኛ ወይም
የፖለቲካ ፓርቲ ማግኘት ፈታኝ ነው። በዚህ ሁኔታ ደግሞ የውክልና ዴሞክራሲን መገንባትና
ማጽናት ዴሞክራሲን የተላመጠ የሸንኮራ አገዳ ያደርገዋል፤ ጣዕሙን ያጣ ባዶ እንጨት።
ዴሞክራሲ ማለት የሕዝብ አስተዳደር በመሆኑ የሕዝብን ቃል የሚበሉ ፖለቲከኞች ባለበትና
የውክልና ውሉ በፈረሰበት ሁኔታ ሕዝብ ራሱን በራሱ አስተዳደረ ሊባል አይችልም።

የምርጫ ቃል ኪዳንን በመጠበቅ ረገድ አራት የቢሆን ሁኔታዎች ሊከሠቱ ይችላሉ። አንደኛው
የቢሆን ሁኔታ ቃልን ጠብቆ በአፈጻጸም ግን ዝቅተኛ መሆን ነው። ይህ ሁኔታ የፖለቲከኞችን
የመፈጸም ፍላጎትና ለቃላቸው ያላቸውን ታማኝነት የሚያሳይ ቢሆንም ቃላቸውን ግን መፈጸም
አለመቻላቸውን ያመለክታል። ለሕዝቡ የገቡትን ቃልና የፖሊሲ አቅጣጫ ቢከተሉም በውጤቱ
ግን አስፈላጊውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግብ ማሳካት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሠት የቢሆን ሁኔታ
ነው። ሁለተኛው የቢሆን ሁኔታ ቃላቸውን አጥፈውና ከቃላቸው ውጭ ሌላ የፖሊሲ አቅጣጫና
አስተሳሰብ ተከትለው፣ ነገር ግን በተግባራዊ አፈጻጸማቸው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስኬት
ሲያስመዘግቡ የሚከሠት ነው። በዚህኛው የቢሆን ሁኔታ፣ ፖለቲከኞች በእነርሱ ጥንካሬም ይሁን
በተለያዩ ውጫዊ ምክንያቶች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዕድገት ቢያስመዘግቡም፣ የተከተሉት
መንገድ ግን ለሕዝቡ ከገቡት ቃል የተለየ ነው። ሦስተኛው የቢሆን ሁኔታ ቃላቸውን አጥፈው፣
በአፈጻጸማቸውም ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሠት ነው።

ሆኖም ይህ የቢሆን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እውን የሚሆነው ቃል የገባናቸውን ነገሮች በታቀደላቸው


ጊዜና ከዚያም ባጠሩ ዓመታት ውስጥ እውን ሆነው ማሳየት ስንችል ነው። ለእዚህ ደግሞ
የርምጃችን ልክነት ብቻ ሳይሆን የርምጃችን ፍጥነት እጅግ ወሳኝ ነው። እያንዳንዱ ድርጊታችን
ከምርጫ ቃል ኪዳኖቻችን የጊዜ ልኬት አንጻር ተለክቶ በተሰጠን ጊዜ ውስጥ መከናወን
ይኖርበታል። ሰዓቱን እያየን በፍጥነት መሮጥ ይኖርብናል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ብልጽግናን
እውን ለማድረግ የምርጫ ቃል ኪዳንን እያስታወሱ መሮጥ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።

23
ክፍል ሦስት

III. የመፍጠን ጅማሮ ስኬቶች

3.1 ብልጽግናዊ መንግሥት እና ኢኮኖሚያዊ ፍጥነት

የአንድ ማኅበረሰብ ዕድገትና ለውጥ ማኅበረሰቡ ባለው ዕምቅ ዐቅምና በፈጠረው ሥርዓት
ላይ ይመሠረታል። ትላልቅ ሥልጣኔዎች የተፈጠሩት እነዚህ ዕምቅ ዐቅሞች ባሉበት አካባቢ
ሰዎች ተሰባስበው ዕምቅ ዐቅሞችን በሰላም እና የራሳቸውን ፍላጎት ለማሳካት በሚያስችል
መልኩ ለመጠቀም በፈጠሩት ሥርዓት ነው። ማኅበረሰቦች ለማደግና ለመለወጥ ሁለቱ ድምር
ነገሮች እጅግ አስፈላጊ ሲሆን ከሁለት አንዱ በተጓደሉባቸው አካባቢዎች ዕድገት ፈታኝ
ነው። አያሌ የአፍሪካ ሀገሮች ብዙ ዕምቅ ዐቅም አሏቸው። ነገር ግን የፈጠሩት ሥርዓት
ዕምቅ ዐቅሞቹን ተጠቅሞ ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲሁም ፍትሐዊ
ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አልቻለም። በመሆኑም የአፍሪካ ሕዝቦች በሀብት ላይ ተኝተው
የሚራቡ እና በብዙ ችግሮች ውስጥ የሚሰቃዩ ናቸው። በሌላ በኩል ዕምቅ ዐቅም እምብዛም
የሌላቸው ወይም ለዕድገት ምቹ ባልሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦች ለማደግ እጅግ
ፈታኝ ሁኔታ እንደሚያጋጥማቸው የታወቀ ነው።

ነገን የተሻለ ለማድረግ ተልመናል። ትልማችንን ለማሳካት ዘረፈ ብዙ ግቦችን ነድፈናል።


መካከለኛ ገቢ ላይ መድረስ፣ በምግብ ራስን መቻል፣ ከቀዳሚዎቹ የአፍሪካ ኢኮኖሚዎች
ተርታ ለመሰለፍ እና ሌሎች ግቦቻችን ለማሳካት ተደራራቢ እና ዘርፈ ብዙ የሆኑ ችግሮችን
መቅረፍ እና ተለዋዋጭ በሆነው ከባቢ ውስጥ የሚፈጠሩ አዳዲስ ጫናዎችን መቋቋም
ያስፈልጋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተደራራቢ ችግሮቻችንን ለመቅረፍ እና ሌሎች ጫናዎችን
ለመቋቋም ዐቅሞቻችንን እና ዕድሎችን አሟጦ መጠቀም ያስፈልጋል። በመሆኑም
ለመበልጸግ የሚያስችሉ ዕምቅ ዐቅሞቻችንን በመጠቀም ግቦቻችንን ለመድረስ
ኢትዮጵያውያንን በተድላና በሐሴት ለማኖር ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ለትውልድ
የሚሆን ሀብት ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎች ተሠርተዋል። እነዚህ ጥረቶች ተለዋዋጭ
በሆነው ዓለም ውስጥ የሚፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን በመቋቋም ተወዳዳሪነትን
ለመፍጠርም የተለሙ ናቸው። ተደራራቢ የሆኑ ችግሮችን በመቅረፍ፣ አዳዲስ ዓለም
አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታዎች የፈጠሩትን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቋቋም እና ተወዳዳሪ የሆነ
ኢኮኖሚን ለመፍጠር የሚያስችል ተገኝቷል። ይህም እንዲሆን ኢኮኖሚው በመሠረታዊነት
24
ውጤት በሁለት ጉዳዮች ተለውጧል። የመጀመሪያው በሐሳብ ደረጃ ሲሆን ሁለተኛው እነዚህን
ሐሳቦች ተግባራዊ ለማደረግ በምንወስደው ፍጥነት ነው።

በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ሽግግርን ለማምጣት እና ከፍተኛ


የዕድገት ስኬት ለመፍጠር ቀድመው ያላቸውን ዐቅም አሟጥጠው መጠቀም አለባቸው᎓᎓
ለዚህም ያላቸውን ዐቅም በሚገባ መገንዘብና የሚመለከቱበት መንገድ ወሳኝ ለውጥ
የሚያመጣ ነው:: በሀገራችን አንደኛው መሠረታዊ ችግር ዐቅሞቻችንን በሚገባ
አለመረዳታችን ነው። ሊሰጡ የሚችሉትንም ጥቅም በቅጡ አናውቀውም። በመሆኑም
ብልጽግናን ለማረጋገጥ ከፈለግን ዐቅሞቻችንን በቅጡ መገንዘብ እና ማወቅ እንዲሁም ከፍ
ያለ ውጤት ሊሰጡበት የሚችሉበት አዲስ ምልከታ ያስፈልገናል። የአዲስ ምልከታና ከፍ
ያለ ምናብ ውጤት የሆኑ አዳዲስ ፈጠራዎች አንዱ የአዲሱ ገጽታ ነው᎓᎓ በየጊዜው አዳዲስ
ችግር ፈቺ እና ለመፍጠር የሚያስችሉ ሐሳቦችን በማምጣት መሬት ላይ እንዲወርዱ
ያደርጋል።

ሁለተኛው ለውጥ ፍጥነት ነው። በፍጥነት ማሰብ፣ በቶሎ መተግበር እና ማጠናቀቅ የሥራዎች
ዋና ገጽታ ነው። ትላልቅ ሐሳቦች በፍጥነት ተተግብረው እና እውን ሆነው ሀብት ማመንጨት
ሲጀምሩ ማየት እየተለመደ ነው። ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ውጤቶችን ለማስመዝግብ
ዕድል የሰጠ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ፣ ሸገርን ማስዋብ፣ ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር፣ የሕዳሴ
ግድብ እና መሰል ስኬቶች ከፍ ያለ ሐሳብን በፍጥነት የመከወን ውጤቶች ናቸው።

እነዚህ ውጤቶች ትላልቅ ሐሳቦችን በሚያስብ እና በፍጥነት በሚከውን መንግሥት ቀዳሚ


ጥረት፣ በግሉ ዘርፍ ትብብር እና በአጠቃላይ በኅብረተሰቡ ንቅናቄ የመጡ ውጤቶች ናቸው᎓᎓

ኢኮኖሚው የመፍጠን እና የመፍጠር ዐቅሙ እያደገ በመምጣቱ ችግሮችን ተቋቁሞ ለማለፍ


ብቻ ሳይሆን ሥጋቶችን ወደ ዕድል ለመቀየር አስችሏል። ሀገራችን ለውጡ ከመጣበት ዓመት
ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ ጫናን በፈጠሩ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ቀውሶች ውስጥ ብታልፍም
ከዕድገት ሂደቷ አልተገታችም። ከዚህ ጋር ተያይዞ ለዐሥር ዓመት ባዘጋጀነው የኢኮኖሚ
ዕድገት ፕሮግራም ባለፈው አምስት የለውጥ ዓመታት ውስጥ ብቻ የሀገራችን የኢኮኖሚ
ምርታማነት መጠን ጨምሯል። በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት(GDP) በጊዜው በነበረው የገበያ
ዋጋ ሲገለጽ በ50 በመቶ በመጨመር በ2010 በጀት ዓመት ከነበረበት 84.3 ቢልዮን
የአሜሪካን ዶላር አድጎ፣ በ2014 የበጀት ዓመት ወደ 126.8 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር ዕድገት
አስመዝግቧል። በሀገር ውስጥ ብር ሲገለጽ 180 በመቶ ጨምሯል። በ2010 በጀት ዓመት

25
ከነበረበት 2.2 ትሪልዮን ብር በ2014 በጀት ዓመት ወደ 6.2 ትሪልዮን ብር እንዲያድግ
ለማድረግ ተችሏል።

ለጠቅላላ የምርት ዕድገቱ የግብርና ዘርፍ በአማካይ የ33 በመቶ ድርሻ ነበረው። ከዚህም
ውስጥ የዋና ዋና ሰብሎች ንዑስ ዘርፍ 65.4 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል። የኢንዱስትሪ
ዘርፉም በአማካይ የ28 _ በመቶ ድርሻ አለው። ለዚህም የኮንስትራክሽን እና የማኑፋክቸሪንግ
ንዑስ ዘርፎች በቅደም ተከተል የ66 በመቶ እና የ19 በመቶ ድርሻ ነበራቸው። በሌላ በኩል
የአገልግሎት ዘርፍ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የ39 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን፣ ከዚህም
ውስጥ የጅምላና የችርቻሮ ንግድ ንዑስ ዘርፍ 35 በመቶ ድርሻ ይይዛል። ይህም ማለት
የምርት ዕድገታችን በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች እንደተመዘገበ ያመለክታል። በውሱን
ዘርፎች ጥገኛ ከመሆን ወደ ብዝኃ ዘርፍ ያደረገነው ሽግግር ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ
እንደሆነም ያሳየናል።

ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ዋና ዋና የማክሮ
ኢኮኖሚ ማነቆዎቹን ለመለየት ተችሏል። ማነቆዎቹን ለመፍታት የሚያስፈልጉ የፖሊሲ
አቅጣጫዎችን በማመላከት ሰፊ ርብርቦች ሲደረጉ ቆይቷል። በተጨማሪም በዐሥር ዓመቱ
የልማት ዕቅድ ኢኮኖሚውን ከረዥም ጊዜ ዕይታ አኳያ በመቃኘት ብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ
ዕድገት ስትራቴጂን ተከትለናል። የግብርናና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን ጨምሮ ማዕድን፣
ቱሪዝምና የከተማን ዕድገት መሠረት ያደረገ የአይ.ሲ.ቲ. ዘርፍ እንደ ተጨማሪ የዕድገት እና
የሥራ ዕድል ምንጮች ተለይተዋል። በዚህም የኢኮኖሚ ዕድገቱን ከአንድ የገቢና የዕድገት
ምንጭ ይልቅ በብዝኃ ዘርፍ የዕድገት ምንጮች ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጦ
ሥራዎች ተሠርተዋል፤ እየተሠሩም ይገኛሉ።

በዚህም እንደ ሀገር ከገጠሙን በተጨማሪ እንደ አንድ የዓለም ማኅበረሰብ የተጋፈጥናቸውን
የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመቋቋም፣ ኢኮኖሚው ባለፉት አራት ዓመታት በአማካይ በ7.1
በመቶ ዕድገት አስመዝገቧል። ለዚህም ዕድገት ግብርና በ4.6 በመቶ የኢንዱስትሪ ዘርፍ
በ9.4 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፉ በ7.8 በመቶ በአማካይ አድጓል። ከግብርናው
ክፍለ ኢኮኖሚ ንዑስ ዘርፎች መካከል የዋና ዋና ሰብል ምርትና ምርታማነት ለዘርፉ ዕድገት
ከፍ ያለ አስተዋጽዖ አበርክቷል። _ በባለፉት አምስት ዓመታት አጠቃላይ ኢኮኖሚው
ላስመዘገበው ዕድገት በአማካይ ግብርና የ16.2 በመቶ ድርሻ ነበረው። ሌላው ከግብርና
ዘርፎች ውስጥ የሚጠቀሰው የእንስሳት ልማት ንዑስ ዘርፍ ሲሆን ይህም ለአጠቃላይ
ኢኮኖሚው ዕድገት የ5.2 በመቶ ድርሻ አስተዋጽዖ አድርጓል።
26
የኢኮኖሚ ሥርዓታችን ወደ ብዝኃ ዘርፍ በመቀየሩ ሁሉንም የምርታማነት ዘርፎች
የኢኮኖሚው ጥቅል ምርታማት እና የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት እንዲሆኑ አድርገናል። ይህ
የአስተሳሰብ ለውጥ ቀላል አይደለም። በነጠላ ቡድናዊ ተጠቃሚነት የበላይነት ሲዘወር
የነበረን ኢኮኖሚ፣ ለሁሉም ፍትሐዊ እና እኩል ተጠቃሚነትን እንዲያረጋግጥ ለማድረግ
ታግለናል።

ፓርቲያችን ይህን የአስተሳሰብ ፓራዳይም የሚቀይር አዲስ ታሪክ ጽፏል። ከገጠመን ችግር
ተነሥተን ችግርን እንደ ዕድል ተጠቅመን በአምስት ዓመት ውስጥ ጥቅል ሀገራዊ የምርት
ዕድገትን 6.2 ትሪልዮን ብር ለማድረስ ተችሏል። ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት በአማካይ 7.1
በመቶ ዕድገት ተመዝግቧል። በዓመት ለሁለት ጊዜ ከማምረት በላይ ስንዴን ወደ ወጭ
መላክ ተችሏል። ከሃምሳ ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ምንም ዓይነት የውጭ ምንዛሬ
ለስንዴ ግዢ ሳናውል ቀርተናል። እንዲያውም በተቃራኒው ከስንዴ ምርት የውጭ ምንዛሬ
ወዳገኘንበት አዲስ ምእራፍ ላይ ደርሰናል።

ኢኮኖሚያችን አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ ነው። ከሥርዓት ጥገኝነት እየተላቀቀ ገበያ መር


እየሆነ፤ ከነጠላ ዘርፍ ዕድገት ተኮርነት ወደ ብዝኃ ዘርፍ ተኮርነት እየተሸጋገረ ነው።
መሠረቱን ብዝኃ ኢኮኖሚ በማድረግ የሕዝቦችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዓይነተ
ብዙ ፈተናዎች ተፈትኖ በጽናት ተሻግሯል። ኢኮኖሚያችን ከዳግም ስብራት ወደ ላቀ
የዕድገት ምሕዋር እየተጓዘ ይገኛል። በዚህም ምክንያት በዐሥር ዓመት ውስጥ እናሳካቸዋለን
ብለን ዐቅደን እየሠራንባቸው ያሉት ሀገራዊ የምርታማነት እና የኢኮኖሚ ዕድገት ትልሞች፣
በአጭር ጊዜ እየተሳኩ ይገኛሉ::

የኢኮኖሚ ዕድገታችን በቀጣዮቹ ዐሥር ዓመታት ውስጥ ከአፍሪካ አምስት ጠንካራ ኢኮኖሚ
ካላቸው ሀገራት ተርታ የሚሰለፍ እንዲሆን ፓርቲያችን በመሥራት ላይ ነው። ዓለም አቀፉ
የገንዘብ ተቋም አይ.ኤም.ኤፍ. ባወጣው የ2023 የኢኮኖሚ ምጣኔያዊ ሪፖርት መሠረት
የሀገራችን GDP 156.08 ቢልዮን ዶላር ይሆናል። በዚህም ከአፍሪካ አምስተኛ ከፍተኛ
ኢኮኖሚ፤ ከምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚው ኢኮኖሚ፤ እንዲሁም ከዓለም ሃምሳ ዘጠኛ ደረጃ ያየዘ
ግዙፍ ኢኮኖሚ ሆኗል። ይህ ውጤት በውስጣዊ እና በውጫዊ ጫናዎች፤ በሰው ሠራሽ እና
በተፈጥሯዊ ፈተናዎች ሳንበገር በጽናት በመትጋት ፓርቲያችን ያስመዘገበው ውጤት ነው።
የአስተሳሰብ ውጤታችንንም ፍሬ ያየንበት ድል ነው።

27
ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝባችን የነፍስ ወከፍ ገቢ በአማካይ በ 38 በመቶ ጨምሯል።
በ2010 በጀት ዓመት ከነበረበት 882 የአሜሪካን ዶላር በ2014 በጀት ዓመት ወደ 1,218
የአሜሪካን ዶላር ደርሷል። በሀገር ውስጥ ብር ሲገለጽ በ157 በመቶ በመጨመር በ2010
በጀት ዓመት ከነበረበት 23,038 ብር፣ በ2014 በጀት ዓመት ወደ 59,169 ብር ደርሷል። ይህ
ውጤት የወል ውጤት የወል ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በፍትሐዊነት መታየት መጀመሩን
ያየንበት ነው። የኢኮኖሚ ፖሊሲያችን ሁለንተናዊ የወል እውነታችንን የሚያረጋግጥ መሆኑን
በውጤት የተገለጠበት ተጨባጭ ማሳያ ነው።

የውጭ ንግድ ባለፉት 5 የለውጥ ዓመታት ትልቅ እመርታ ከታየባቸው ዘርፎች ውስጥ
በዋነኝነት ይጠቀሳል። የሸቀጦች የወጪ ንግድ በ2010 በጀት ዓመት ከነበረበት 2.84 ቢልዮን
ዶላር በ2014 ወደ 4.1 ቢልዮን ዶላር ደርሷል። ይህም ከ2010 በጀት ዓመት በፊት በነበሩት
5 ተከታታይ ዓመታት ቅናሽ ሲያሳይ ከነበረበት በመነሣት መሆኑ አፈጻጸሙን የላቀ
ያደርገዋል። በተለይም የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ በተደረገባቸው ባለፉት 3
ዓመታት የሸቀጦች ወጪ ንግድ አፈጻጸም በአማካይ 136 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ኢኮኖሚያችን እመርታዊ ዕድገት እያስመዘገበ ያለው፤ ‹ይቻላል› ብለን በአዲስ የአስተሳሰብ


ቅኝት በመሥራታችን ነው። ባለፉት ዓመታት ብዙ ሀገራት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ስብራት
ሲገጥማቸው፣ እኛ በ ‹ይቻላል› መንፈስ በተሻለ ምርታማነት ዕድገታችንን ጠብቀን ለመጓዝ
በመብቃታችን ነው።

ዲጂታል ኢኮኖሚን በዕድገት ምንጭነት መጠቀምና ቴክኖሎጂን ለተከታታይ የምርታማነትና


የተወዳዳሪነት ማሻሻያነት ማዋል፤ የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ ተሳትፎ ሚና ማሳደግ
ለዕድገታችን ጎልሕ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውስጥ፣
የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት እና የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርፕራይዞች የኢ-ኮሜርስ
ሥራዎችን በውጤታማነት ሠርተዋል። በተለይም በዘመናዊ የክፍያ ዘዴ የተላለፈው የገንዘብ
መጠን በ2011 ከነበረበት ብር 51.1 ቢልዮን ወደ 596.8 ቢልዮን ብር ለመድረስ ችሏል።
ለሞባይል መኒ አገልግሎት የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ቁጥር 59 ሚልዮን ሲደርስ፣ ከ200
ቢልዮን ብር በላይ ግብይት ተፈጽሟል። የኢኮኖሚ ዕድገቱ በ2015 በጀት ዓመት በ7.5
በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል። ለዚህም የግብርና ዘርፍ ዕድገት ትንበያ 63 በመቶ
(ከግብርና ዘርፍ ውስጥ የሰብል ምርት ዕድገት ትንበያ 67 በመቶ፣ የእንስሳት ምርት ዕድገት
ትንበያ 57 በመቶ እንደሚሆን ይገመታል፤ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ዕድገት ትንበያ 8.2 በመቶ
(ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ የአምራች ኢንዱስትሪ (ማኑፋክቸሪንግ) ዕድገት ትንበያ 10.6
28
በመቶ እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕድገት ትንበያ 7.1 በመቶ እንደሚሆን ይገመታል)፣
የአገልግሎት ዘርፍ ዕድገት ትንበያ 75 በመቶ (የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ዕድገት ትንበያ 8.1
በመቶ) በማደግ ለተተነበየው የ7.5 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽዖ እንዲሚያደርጉ
ካለፉት ጊዜያት ውጤት አንጻር ይጠበቃል።

በዚህ በጀት ዓመት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ የግድቡን ግራና ቀኝ 634 ሜትር ከባሕር
ጠለል በላይ ለማድረስ ታቅዷል። የግድቡን መካከለኛ አካል ከባሕር ጠለል በላይ ወደ 620
ሜትር ለማድረስ ታቅዶ እየተሠራ ነው። ከቀሪ ዩኒቶች በቀጣይ ዓመት ቢያንስ በ5
ጄነሬተሮች ኃይል ለማመንጨትን የተርባይኖች እና የጀነሬተሮች ተከላ እየተከናወነ
ይገኛል። በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 66.2 በመቶ (ከለዉጡ በፊት) ከነበረበት ወደ
90.7 በመቶ ከፍ ብሎ ኃይል ለማመንጨት ተደርሷል። የግድቡም ሥራ በመጪዉ ዓመት
እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው። 13ቱም ጀነሬተሮች በ2017 ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀዉ በሙሉ
ዐቅማቸዉ ኃይል የሚያመነጩበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። በዚህም ፕሮጀክቱን በድል
ለማጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየሠራን እንገኛለን።

የሸቀጦች የወጪ ንግድ አፈጻጸም በ2015 በጀት ዓመት ስድስት ወራት 2.285 ቢልዮን
የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 1.76 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል።
ይሄም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 7 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል። ከግብርና
ምርቶች 1,607 ሚልዮን ዶላር ታቅዶ 1,359.78 (84.59 በመቶ) ሚልዮን ዶላር ተገኝቷል።
ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 36.34 ሚልዮን ዶላር ጭማሪ
አሳይቷል። በሌላ በኩል ከማኑፋክቸሪንግ ምርቶች 308.89 ሚልዮን ዶላር ታቅዶ 227,61
ሚልዮን ዶላር ተገኝቷል። ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 10.65
(4.89 በመቶ) ሚልዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል። በተመሳሳይ ከማዕድን ምርቶች 324.67
ሚልዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 116.54 ሚልዮን ዶላር ተገኝቷል። ከባለፈው ዓመት
ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 28152 ሚልዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር 164,97 ቅናሽ አሳይቷል።

በማኅበራዊ ልማት ዘርፍ በተለይም በትምህርት ዘርፍ የተሠሩ ሥራዎች ነገን አመላካች
ናቸው። ባለፈው ዓመት የተመዘገበው አስደንጋጭ የ12ኛ ክፍል የማጠናቀቂያ ውጤት
የዘርፉን ስብራት አሳይቶናል። በቀጣይ ውጤታማ ትውልድ የሚያፈራ እንዲሆን አዲሱን
የትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ የትምህርት ዘርፉ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ
የሆነውን ምክንያታዊ ትውልድ የሚያፈራ ተቋም እንዲሆን ተደርጎ እየተሠራበት ይገኛል።
ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንጻር በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ለ1.83 ሚልዮን ዜጎች ቋሚ
29
የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ1,49 ሚልዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።
ይሄም የዕቅዱ 81 በመቶ ነው።

ዕድገት ሲመዘገብ ጉድለት ሁሌም ከጎን ይኖራል። በመሆኑም የዋጋ ንረትን እና የኑሮ
ውድነትን ለማርገብ ብዙ ሥራዎች ቢሠሩም ለማስቀጠል በዋጋ ፈተናነቱ ገና አልቀነሰም።
ሁለንተናዊ ዕድገቱን ማረጋጋት ላይ በትኩረት መሥራት ይጠበቅብናል።

ኢኮኖሚያችን እመርታዊ ለውጥ እያመጣ ነው ስንል ፈተና አልቦ ነው ማለታችን አይደለም።


ባለፉት አምስት ዓመታት ያሳለፍነው ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ተጨምሮረውበት ፤
አንዳንድ አካባቢዎች በተከታታይ አራት ዓመታት በዝናብ እጥረት ተፈትነው፤ የአቅርቦት
እና የፍላጎት አለመጣጣም የዋጋ ንረቱን አሻቅቦት፤ የኑሮ ውድነቱ የሕዝባችን ፈተና
እንዲሆን አድርጎታል። የዋጋ ግሽበት የቅርብ ጊዜ ክሥተት አይደለም። ባለፉት ሃያ ዓመታት
መቀዛቀዝ ሳይታይበት እያሻቀበ የመጣ ሂደት ውጤት ነው። ባለፉት አምስት ዓመታት ደግሞ
በድርብርብ ፈተናዎች ታጅቦ በዝቅተኛ የኑሮ ላይ የሚገኘውን ሕዝባችንን እየፈተነው
ይገኛል።

3.2 ከተናጠል ወደ ወል እውነት

እውነት ምንድነው? ሲሉ ከጥንት እስከ ዛሬ ፈላስፎች ይጠይቃሉ። አያሌ ፈላስፎች እስከ


ዛሬ ድረስ በብዙ ፍልስፍናዊ ዕይታ እውነትን ለመበየን ሞክረዋል። በዘመናዊ የፍልስፍና
ብያኔ እውነት በፍጹማዊ፤ በአንጻራዊ እና በተጨባጭ ጽንሰ ሐሳባዊ ዐውድ ይበየናል።
እውነት ፍጹማዊ ሲሆን ንጽጽር አልባ፤ አንጻራዊ ሲሆን ከሌሎች ነገሮች ጋር የሚነጻጸር፣
ተጨባጭ ሲሆን ከምናባዊነት ይልቅ በአካል የሚጨበጥ እንደሆነ ይታመናል። በመሆኑም
ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች እውነትን ከሦስቱ ጽንሰ ሐሳባዊ ዐውዶች በአንዱ ወይም ከሌላ
ጽንሰ ሐሳብ በመነሣት ብያኔ ሊሰጡ ይችላሉ። የሰው ልጅ በሥርዓተ መንግሥት መተዳደር
ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የተናጠል እና የወል እውነቶችን ገዥ ሐሳብ ለማድረግ በቀጥታም
ይሁን በተዘዋዋሪ ትግል ያደርጋል።

የተናጠል ቡድናዊ እውነት ይዞ የተነሣ ኃይል የቡድኑን እውነት ልክነት ለማሳየት ካመነበት
እውነት በተቃራኒ በቆሙ ኃይሎች ላይ ሁሉንም የማስተግበሪያ ዐቅሞች ተጠቅሞ በኃይል
ይጭናል። በጊዜ ሂደት ያላመነበት እውነት በላዩ ላይ የተጫነበት ቡድን ደግሞ የራሱን
የተናጠል እውነት ገዥ እውነት ለማድረግ ትግል ያደርጋል። ይህ ዓለም ላይ የምናየው
ተጨባጭ እውነት ነው። በምድራችን ላይ የተደረጉ እልፍ ጦርነቶች የተናጠል እውነትን
30
ልክነት በአሸናፊነት ለማጽናት የተደረጉ ናቸው። የተናጠል ቡድናዊ እውነት የቡድኑን
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እውነቶችን ለማሳካት በሚደረግ ትግል፣ በተናጠል
ቡድናዊ ፍላጎት ልኬት የበላይነት የሚቃኝ ነው። ይሄውም ከህገር እስከ ዓለም ሥርዓታዊ
የበላይነት ድረስ ሊይዝ ይችላል።

ገዥ ትርክት መፍጠር የተናጠል ቡድናዊ እውነትን ገዥ ለማድረግ የሚሠራ ቡድን ዋነኛ


መሣሪያው ነው። ቡድናዊ እውነቱን በሌላው ላይ ለመጫን የራሱን ትርክት ያዘጋጃል።
ዓላማው የተናጠል እውነትን ማንገሥ ስለሆነ ሌላውን ማግለል መፈረጅ እና ማጥላላት
ስትራቴጂው ያደርገዋል። ፍላጎቱ ቡድናዊ የበላይነቱን ማጽናት በመሆኑ የቡድኑ ትርክት
ቅቡል ሲሆን ሥርዓት የሚቀጥል፣ ትርክቱ ቅቡል ካልሆነ ሥርዓት የሚያፈርስ ዕሳቤ ይዞ
ይንቀሳቀሳል።

ከጭቆና ለመላቀቅ እና የተናጠል ቡድናዊ እውነትን ገዥ ዕሳቤ እንዲሆን ለማድረግ


በሚኖረው ሂደት የራስ እውነት መጨቆኑን ብቻ ማዕከል ስለሚያደርግ ሌሎች በጭቆና ውስጥ
ያለፉ ቡድኖችን እውነት እንኳን ለማካተት ፍላጎት አይኖርም። በዚህ ምክንያት እውነቱ
ያልተደመጠለት ቡድን ደግሞ ሌላ ዙር የራስን እውነት ገዥ የማድረግ እንቅስቃሴ ውስጥ
ይገባል። በዚህም ምክንያት የነጠላ እውነት ሐሳቦች ገዥ እና ተገዥ ለመሆን በሚያደርጉት
ጉተታ፣ ፍትሐዊነት፣ እኩልነት እና ሀገራዊ አንድነት እየተዳከሙ ይሄዳሉ። የነጠላ ቡድኖች
እውነት በየዘመኑ እያሸነፈ የታሪክ ዑደት ሆኖ ይቀጥላል። ሀገር እና ሕዝብም ዋጋ ይከፍላሉ።

የሀገራችን ኢትዮጵያ እውነታም ተመሳሳይ ነው። የተናጠል ቡድናዊ እውነቶችን ገዥ ሐሳብ


በማድረግ ሥርዓታዊ ዕሳቤ እየሆኑ ዛሬ ላይ ደርሰናል። ምንም እንኳን ዘለግ ያለ የሀገረ
መንግሥት ታሪክ ቢኖረንም የተናጠል ቡድናዊ እውነትን ማዕከል ያደረጉ ሥርዓቶች
በመብዛታቸው የሥርዓት መተካካቶቹ ብዙ ደም አፋሳሽ ጦርነቶችን ያስከትሉ ነበር። በዚህም
ምክንያት የብዝኃ ማንነቶች ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ የተናጠል ቡድናዊ እውነት እሥረኞች
በሆኑ ፍላጎቶች እየቃተተች የሀገረ መንግሥት ግንባታዋን ዳር ሳታደርስ ዛሬ ላይ ደርሳለች።

ከተናጠል ቡድናዊ እውነት ወደ ወል እውነት እንሸጋገር ሲባል ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ


ከሰሜን እስከ ደቡብ በሁሉም የኢትዮጵያ አከባቢዎች የሚገኙ የሁሉም ኢትዮጵያውያን
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እውነቶች ገዥ ሐሳብ የሚሆኑበትን ሥርዓት እንገንባ
ማለታችን ነው። የመደመር ዕሳቤ የተናጠል የተናጠል ቡድናዊ እውነት የፈጠሯቸው
ሥርዓቶች የፈጸሙትን ስሕተት በማረም ለሁለንተናዊ የወል እውነት መሠረት የሚጥል

31
አዲስ ሥርአት ለመገንባት ያለመ ነው። በዚህም በጅምር ላይ ያለውን የሀገረ መንግሥት
ግንባታ ሂደት ዳር በማድረስ፣ ለመጪው ትውልድ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የወል እውነት
ገዥ የሆነባት ሀገር ማስረከብ ነው።

በመደመር ዕሳቤ ከነጠላ ቡድናዊ እውነት የበላይነት ወደ ወል እውነት መሻገር ይቻላል።


ወንድማማችነትን ማዕከል ያደረገ፣ ያለፉ በደሎችን በይቅርታ ቀጣይ ተስፋችንን ደሞ
በመደመር በአብሮነት መዝለቅ ነው ዓላማችን። ሁሉም ዜጎች ክብራቸው የሚጠበቅባት፤
እኩልነት እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የተረጋገጠበባት የቤተኛ እና የባይተዋር ዕሳቤ
የተገፈፈባት፤ ሁሉም ዜጎች ባለቤት የሆነባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ፓርቲያችን ሰፋፊ
ሥራዎች ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት እየተገበረ ይገኛል። በዋነኛነት አካታች የፖለቲካ
ሥርዓት በመገንባት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ፤ ቅድሚያ ለዜጎች
ክብር የሚሰጥ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን ወደ ተግባር በማስገባት፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን
የጋራ እውነት ምላሽ እንዲያገኝ በመሥራት ላይ ነው።

ከነጠላ ቡድናዊ እውነት የበላይነት ወደ ሁለንተናዊ የወል እውነት የበላይነት እያደረግን


ያለው ሥርዓታዊ ሽግግር ሥርዓታዊ ሽግግር አልጋ በአልጋ አይደለም። በዘርፈ ብዙ
ፈተናዎች የተሞላ ነው። በዋነኛነት በቀደመው የነጠላ ቡድናዊ እውነት ገዥ ሐሳብ የበላይነት
ሲዘወር የነበረው የሀገራችን የፖለቲካ ኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ሥርዓት ተጠቃሚዎች
የሚያደርሱት ፈተና ከባድ ነው። እነዚህ ወገኖች የነጠላ እውነታቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ
እንዲችሉ በኃይል ወደ ሥልጣን ለመመለስ ጦርነት እስከ መግጠም ደርሰው ነበር። ነገር
ግን ዓላማቸው ሳይመታ መክኖ ቀርቷል። በሌላ በኩል በነጠላ ቡድናዊ እውነት የበላይነት
በጭቆና ያሳለፉ ቡድኖች ወደ ሁለንተናዊ የወል እውነት በምናደርገውን ሽግግር ከትብብር
ይልቅ ፉክክር ላይ በመጠመዳቸው ሌላ ፈተና ገጥሞናል። በዚህም አዲሲቷ ኢትዮጵያ
የሁሉም ብሔር እና ብሔረሰቦች እውነት ገዥ ሐሳብ የሚሆንባት ቤት ሆና እንዳትወለድ
እየፈተኗት ይገኛሉ።

ይሁን እንጂ እልፍ ፈተናዎች ቢኖሩም ድሉ ጣፋጭ ስለሚሆን የምንገነባው ሥርዓት


ሁለንተናዊ ሀገራዊ የወል እውነቶችን ገዥ ሐሳቡ የሚያደርግ ሥርዓት እንጂ በተለመደው
መንገድ የነጠላ እውነት ገዥ ሐሳብ የሚሆንበት ሥርዓት አይደለም።

32
3.2.1 የወል እውነቶችን የማጽናት ፖለቲካዊ እመርታችን

ከቀደምት ነገሥታት እስከ ቅርብ ጊዜዎቹ የሀገራችን የፖለቲካ ሥርዓቶች ድረስ የነጠላ
ቡድናዊ እውነቶች የበላይነት ዓይነተኛ መገለጫቸው ነው። የሺ ዘመናት የሀገረ መንግሥት
ታሪክ ቢኖረንም የፖለቲካ ሥርዓቶቻችን በነጠላ ቡድናዊ እውነቶች ዕሳቤ ላይ ብቻ
በመመራታቸው፤ ከነጠላ ቡድን ወደ ሌላ ነጠላ ቡድን የፖለቲካ የበላይነት በሚደረግ ሽግግር፤
የወል እውነቶች የሚገባቸውን ቦታ በፖለቲካ ሥርዓቶቹ አላገኙም። በዚህም ምክንያት ቀድሞ
መጠናቀቅ የነበረበት የሀገረ መንግሥት ግንባታችን ሳይጠናቀቅ ዛሬ ላይ ደርሷል። ይህ
ክሥተት ከዓለም ቀዳሚ ሥልጣኔዎች ውስጥ ተጠቃሽ ለሆነችው ሀገራችን የማይመጥን፤
ከሥልጣኔ ፈር ቀዳጅነት እና ከነጻነት ቀንዲልነት ታሪካችን ጋር የማይጣጣም ነው። ታላቋን
ሀገር በአግባቡ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ዑደቷን ያላጠናቀቀች ሀገር እንድትሆን
አድርጓታል።

ሐሳብ ሽጠው ፖለቲካዊ ሥልጣን ማግኘት ያልቻሉ የነጠላ ቡድናዊ ፍላጎት አቀንቃኞች፣
ከዴሞክራሲያዊ መንገድ ባፈነገጠ መልኩ፤ ጅምሩን የፖለቲካ ጉዟችንን ወደ ኋላ የሚመልስ
ተግባር ላይ ሲረባረቡ ይስተዋላሉ። ይህም የጥላቻ እና የፍረጃ ፖለቲካን ተጠቅመው ሥልጣን
ለመቆናጠጥ የሚያደርጉት ሩጫ ነው። የጥላቻ ፖለቲካ ከግለሰብ እስከ ማኅበረሰብ ይረጫል።
በዚህ የጥላቻ ፖለቲካ ዘመቻ አይነኬ የሚባሉ ማኅበረሰባዊ የሞራል ዕሴቶች ጭምር
በአደባባይ እንዲዋረዱ ይደረጋሉ። ጥላቻው ከፖለቲካኛው አልፎ የሕዝብ አጀንዳ ሆኖ
እልቂት እንዲፈጠር በብርቱ ይሠራል። ጥፋቱን ያቀጣጠሉት ዳር ሆነው እሳቱን እየሞቁ
የድኻውን ልጅ ማግደው ሥልጣን ለማግኘት ይቋምጣሉ።

በሕጋዊ መንገድ ሥልጣን ማግኘት ያልቻሉ የነጠላ ቡድን ፍላጎት አስፈጻሚዎች እንችላለን
ያሉት በጦርነት አሸንፈው ሥልጣን ለማግኘት ሞክረው አልቻሉም። የጥላቻ ፖለቲካ
አራምደው ሥልጣን ለመያዝ እየሞከሩ ያሉ ኃይሎች ደግሞ እጅግ አደገኛ እና አክሳሪውን
መንገድ መርጠው እየሠሩ ይገኛሉ። ድል ቀንቷቸው ባይችሉ እንኳን ወደ ሕዝብ እየወረደ
ያለው ሥልጣን ለማግኘት የጥላቻ መርዝ ወደተግባር ተቀይሮ ጥፋት ሊያደርስ የሚችልበት
ዕድል ዝግ አይደለም። በመሆኑም ፓርቲያችን ይህን አደገኛ አካሄድ በብስለት በማስተዳደር
መርዙን የማርከስ (ኖርማላይዝ የማድረግ) ቁልፍ ተግባር ይጠብቀዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት የዘመናት የሕዝቦች ፍላጎት የነበረውን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ
ዴሞክራሲያዊ መብት በሚገባ ለማስተናገድ ፓርቲያችን ብዙ ሥራ ሠርቷል፤ እየሠራም _

33
ይገኛል። ሕጎችን ከማሻሻል፤ የጸጥታ ተቋማትን ሪፎርም ለማድረግ፣ የሰብአዊ መብት
ኮሚሽንንና የምርጫ ቦርድን ነጻና ገለልተኛ ለማድረግ፣ የፍትሕ ሥርዓታችን የዜጎችን
አመኔታ እንዲያገኝ ለማድረግ ተሞክሯል። በሌላ በኩል የትብብር ዴሞክራሲ ልምድ
እንዲዳብር ፓርቲያችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተፎካካሪ ፓርቲዎች በምርጫ ድምፅ አግኝተው
ባይመረጡ እንኳን ከሚኒስትር እስከ ቀበሌ አመራር ሥልጣን ተሰጥቷቸው ሕዝባቸውን
እንዲያገለግሉ ሆነዋል። ዴሞክራሲን በትብብር እና በፉክክር ሚዛን ጠብቆ እንዲሄድ መነሻ
የሚሆን ሥራ እየሠራን ነው።

3.2.2 ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ርምጃችን

ሀገራዊ ለውጡን ስንጀምር የሰላም፣ የአንድነትና የአብሮነት በሮችን በመክፈት፤ ከጥላቻ


ከሤራ እና የራስን የነጠላ ቡድናዊ እውነትን ገዥ ከማድረግ ፍላጎቶች በመውጣት፤
አካታችነትና የሌላውን እውነትና የፍትሕ ጥማት የማድመጥ ባህል እንዲመጣ ፓርቲያችን
ተግባራዊ ሥራዎችን ሠርቷል።

በተለይም በሕወሐትና በሌሎች ተመሳሳይ የነጠላ ቡድናዊ እውነታቸውን ብቻ ይዘው ወደ


ሥልጣን ለመምጣት በሚፈልጉ ኃይሎች በኩል የተሰነዘሩ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን በመቋቋም
የፖለቲካ ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሰፊ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

የፓርቲያችን የሰላም ፍላጎት፤ በነጠላ ቡድናዊ እውነት አራማጆች ዘንድ ሽንፈት እና


ደካማነት ተደርጎ ተወሰደ። እኛ በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር ስንል የነጠላ ቡድናዊ
እውነታቸውን ገዥ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች የይዋጣልን የጦርነት ጉሰማዎች ማሰማት
መደበኛ ሥራቸው አደርገው ቀጠሉ። ጥቅል ሀገራዊ ሰላማችን ለማደፍረስ በአራቱም አቅጣጫ
ግጭት እየጠመቁ ወደ ሙሉ ሙሉ ሀገራዊ ቀውስ እንድንገባ በማድረግ ከቀውስ ፍርስራሽ
ውስጥ ዳግም የነጠላ እውነታቸውን ገዥ ሥርዓት ለማድረግ በሀገራዊ ለውጡ የመጀመሪያ
ሁለት ዓመት ቢጥሩም ለድል ስላልበቁ ሰሜን ዕዝን በማጥቃት በአጭር ጊዜ ማዕከላዊ
መንግሥትን መያዝ ዓላማው ያደረገ ጦርነት ቢጀምሩም በፓርቲያችን እና በሕዝባችንን
የተባበረ ክንድ ባጠረ ጊዜ ድል ነሥተናቸዋል።

ገዥነታቸውን ሊጭኑብን የመጡ የወል እውነቶቻችን ዳግም እንዳይሰበሩ በኃይል የነጠላ


ቡድናዊ ኃይሎችን በኃይል ፈጽሞ እንደማይቻል አስመስክረን፤ ወደገፉት የሰላም መድረክ
እንዲመለሱ ሆነዋል። ይህን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ብዙ ዋጋ ከፍለናል። ቢሆንም
ለሀገራችን የፖለቲካ ሥርዓት አዲስ ባህል እንዲመጣ አድርገናል። ለሰላም ሁሌም ዝግጁ
34
በመሆን፤ በኃይል የሚፈጸም ነጠላ ቡድናዊ ፍላጎት እንደማይኖር ትምህርት ሰጥተናል። ጊዜ
ጠብቆ የሚዘጋ የሰላም በር ስለሌለን _ በወታደራዊ መስክ ያገኘነውን ድል በሰላማዊ ድርድር
ደግመናል። በዚህም ድሎቻችንን ሁለንተናዊ በማድረግ የወል እውነቶቻችን ገዥ ሥርዓታዊ
ዕሳቤ ሆነው እንዲቀጥሉ አደርገናል። እንዲሁም ‹የአፍሪካ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች›
የሚለውን መርሕ ትርጉም አልባ እና ባዶ መፈክር አድርገው የሚመለከቱትን፣ የአፍሪካ
ተቋማትን እና መሪዎችን በንቀት ዓይን የሚያዩትን ያሳፈረ ነበር። በመርሕ ላይ
የተመሠረተው አቋማችን ለመላው አፍሪካ የኩራት ምንጭ ሆኗል።

የሰላም ስምምነቱ የመተማመን ደረጃ ዝቅተኛ ከነበረበት ከፕሪቶሪያ፤ መካከለኛ መተማመን


ወደተገኘበት ናይሮቢ፤ ከፍ ወዳለ ደረጃ ደርሶ ተግባራዊ ሥራዎች ወደ ተጀመሩበት የመቀሌ
ስምምነት ተሸጋገረ። በስምምነቱ መሰረት የሀገራችንን ግዛት አንድነት የማስከበር ሥራ
ተከናወነ፤ ሕወሐትን ትጥቅ ማስፈታት በተግባር የተጀመረበት ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቋመ።
ከዚያም መልሶ ግንባታ ተገብቶ ቃል በተግባር እየተተገበረ የሰላም ስምምነቱ በሙሉ
መተማማን ደረጃ ላይ ደረሰ። በመጨረሻም አዲስ አበባ ላይ ለስምምነቱ መሳካት አስተዋጽዖ
ላደረጉ ወገኖች ዕውቅና በመስጠት መሠረት እንዲይዝ ተደረገ።

ሰላማችንን ዘላቂ ለማድረግ፤ ቂምን በመሻር፤ ከሂሳብ ማወራረድ የጥላቻ መንገድ ለመውጣት
የሚያስችል ፍትሕን ማረጋገጥ ይገባናል። በመሆኑም የሽግግር ፍትሕ ማሕቀፍ ተግባራዊ
እንዲሆን በሕግ እና በመመሪያ ተደግፎ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ስምምነት ተደርሶ፣
የዝግጅት ምእራፍ ተጠናቆ ወደ ትግበራ ምእራፍ ይገባል። በዚህ ሂደት በሙሉ መተማመን
ወደ ትግበራ የገባውን ሀገራዊ ሰላም ዘላቂ የማድረግ ውጥናችን ይበልጥ የሚጸናበት፤ ፍትሕን
የማረጋገጥ እና የተጎጂዎችን የፍትሕ ፍላጎት የማርካት ዓላማን እንዳይስት በማድረግ፣
ሰላማችንን አስቀጣይ የሽግግር ፍትሕ ተፈጻሚ እንዲሆን እናደርጋለን።

3.2.3 የሕግ የበላይነት ለፖለቲካዊ እመርታችን ቀጣይነት

የፖለቲካ ሥርዓታችን ተገዳዳሪዎች እና በውስጣችን የሚገኙ የውስጥ ባንዳዎች፣ ነጠላ


ቡድናዊ እውነታቸውን ከቻሉ ወደ ሥልጣን ለማምጣት፣ ካልቻሉ ሥርዓት አልበኝነት
የበላይነትን ይዞ ደካማ ሀገር እንዲኖረን ለማድረግ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት ብዙ ጥረቶችን
አደርገዋል። በየአካባቢው የታቀደባቸውን ግጭቶች ማስነሣት፣ ኢኮኖሚውን ማዛባት፤
ወንጀሎች እንዲስፋፉ ማድረግ፤ ሌብነት እንዲበራከት ማድረግ ስልቶቻቸው ናቸው። ይሄንን
ለማስፈጸም ፖለቲካዊም ኢኮኖሚያዊም ዓላማ ያላቸው የተደራጁ ጠላቶች በሥርዓት

35
አልበኝነት ተግባር ላይ ተሠማርተዋል። ፓርቲያችን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የጸጥታ
እና የሕግ አስከባሪ ተቋማትን ለማሻሻል ረጅም ርቀት ሄዷል።

የጸጥታና የሕግ ማስከበር ተቋማቱን ሕጎችና ዶክትሪኖች አሻሽለናል። ሞያዊ ቁመና


እንዲላበሱ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታጠቁ አድገናል። የአሠራር ማሻሻያዎችን በማድረግ
ብቃታቸውን ከፍ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል። በዚህም የተሻለ ዐቅም እና ብቃት ለመፍጠር
አስችሏል። ሆኖም፣ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እስካሁን የተሠራው ሥራ እና የተገኘው
ውጤት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እየገጠመን ካለው ፈተና እና ተግዳሮት አንፃር ገና ብዙ ሥራ
ይቀረናል።

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ኢ-ዴሞክራሲያዊ ከሆኑ የጥፋት ኃይሎች ራሱን መጠበቁ እና


መከለላከሉ የግድ እና አስፈላጊ ነው። ራሱን ከጥፋት እና ከጥቃት የማይጠብቅ
ዴሞክራሲ፣ዴሞራሲያዊ ሥርዓት ሆኖ ሊቀጥል አይችልም። ምክንያቱም፣ በዴሞክራሲያዊ
ፉክክር የተሸነፉ የነጠላ ቡድናዊ ፍላጎት አስጠባቂዎች፣ የወል እውነታችን ላይ ፈቃዳቸውን
በኃይል ለመጫን ጥረት ማድረጋቸው አይቀርም። እንዲህ ያሉ ዝንባሌዎችን ጠንካራ በሆኑ
የሕግ ማስከበር እና ተጓዳኝ ርምጃዎች መግታት ካልተቻለ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን
ለመገንባት አይቻልም።

ዴሞክራሲ የሀገር ህልውና አደጋ ውስጥ እየወደቀ ሊገነባ አይችልም። ዴሞክራሲ ሀገር ካፈረሰ
መቆሚያውን አጥቷል ማለት ነው። የሕግ የበላይነት እየተረጋገጠ ሲሄድ ሚዛን በመጠበቅ
በሂደት ዴሞክራሲ ይገነባል። በጥላቻ ፖለቲካ በተገኘው አጀንዳ የነጠላ ቡድናዊ የበላይነትን
ለመያዝ የሚደረግን ተግባር፣ በሕግ እና በሥርዓት መግራት ይገባል። በእንጭጩ ያልገራነው
የጥላቻ ፖለቲካ መሥመር ካልያዘ፣ ሶሪያ እና ሊቢያን የሚያስንቅ ጥፋት ያመጣል።

የወንጀል አፈጻጸም እየረቀቀ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያው ፍላጎቶች እየተቆራኙ፣ ድንበር


ተሻጋሪ የሆኑ ትሥሥሮች እየተፈጠሩ፣ የወንጀል አድራጊዎች ተደራጅተው እና ተቀናጅተው
ጡንቻቸው ሲፈርጥም፣ በተለመደው እና ዘመን ባስቆጠረው አካሄድ ውጤታማ የሕግ ማስከበር
ሥራ ልንሠራ አንችልም። አዳዲስ አሠራር፣ አስተሳሰብ፣ ቁርጠኝነት እና መሰጠት፣ ብቃት
እና ዐቅም ያለው ዘመናዊ አካሄድ ልንከተል ይገባል። የጀመርነውን የሪፎርም ሥራ
በማጠናከር፣ ውጤታማ የሕግ ማስከበር ሥራ በመሥራት፣ ውስጣዊ ሰላም እና ደኅንነታችንን
የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። የሕግ ማስከበር ዐቅማችንን አጠናክረን፣ ለወንጀለኞች
ፈጽሞ የማይመች ሁኔታ፣ በወንጀለኞች የሚፈሩ፣ ለሕግ አክባሪ ዜጎች ደግሞ ጥላ የሆኑ የሕግ

36
አስከባሪ ተቋማትን እንፈጥራለን። ይህን ግብ እውን ማድረግ ለብልጽግና ጉዟችን የግድ
ነው።

ፓርቲያችን በፍርድ ቤቶች ላይ እየተስተዋለ ያለውን በተለይም ዳኞች በፍትሕ ሥርዓቱ


ላይ ከፍተኛ የሥነ ምግባር ብልሽት እየፈጠሩ እንደሆነ ተመልክቷል። በዋነኝነት ፍትሕን
በገንዘብ የሚሸጡ ዳኞች አሉ። ሌሎቹ ደግሞ ለሕግ የበላይነት መከበር ዕንቅፋት በመሆን
የዳኝነት ነጻነትን ለሕግ የበላይነት ማዳከሚያነት እየተጠቀሙበት ነው።

ለሕዝብ ጸጥታ እና ደኅንነት ተገቢ ትኩረት በመስጠት የሕግ የበላይነት እንዲከበር ዐቅም
ከመሆን ይልቅ ሰብአዊ መብቶችን ሽፋን በማድረግ ፍትሕን የማዛባት ሁኔታ ይታያል።
ፍትሕን መንግሥትን ለማጥቂያ የመጠቀም አዝማሚያም አለ። መንግሥት የሚከስሳቸውን
በመልቀቅ ግላዊ ጀግና የመሆንና ራስን ታላቅ አድርጎ የማሳየት አካሄድ እየተስተዋለ ነው።
በተጨማሪም በጽንፈኝነት አመለካከቶች መወሰድ እና የግል እምነትን በፍትሕ ወንበር ላይ
መጫን ይታያል። እነዚህ አደገኛ አዝማሚያዎች ዋና ዋና ችግሮች መሆናቸው ተለይተዋል።
በመሆኑም በፍርድ ቤቶች ላይ የተጀመረው ሪፎርም እክል እንደገጠመው ታይቷል።
የገጠመውን ችግር ሥር ሳይሰድ የማስተካከያ ርምጃዎች ተወስደዋል። በሁሉም ደረጃ የሚገኙ
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አመራሮችን የመለወጥ ሥራዎች እየተሠራ ነው። በቀጣይነት
ሪፎርሙ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን ይሆናል።

በፓርቲ ደረጃ ከማዕከል እስከ ታችኛው ርከን አመራርም ይሁን አባላችን የሌብነት ተግባር
ላይ የግድ ተጨባጭ መረጃ ባይገኝበት እንኳን ከመጠቃቃት በጸዳ መልኩ አዝማሚያውን
እያየን ፖለቲካዊ እርምት መውሰድ ይጠበቅብናል። በፓርቲ ደረጃ የተደራጀ የሙስና ትግል
አድርገን ሌላውን ካላታገልን በቀር ትግላችን ግብ አይመታም። ፓርቲያችን ራሱን ንጽሕ
በማድረግ ከሙስና የነጻች ሀገር የመገንባት ትግል መምራት አለበት። የፓርቲ እጅ ሳይነጻ
የሀገር እጅ አይነጻም።

በመሆኑም በፓርቲ መሪነት የፀረ ሙስና መሪነት የፀረ ሙስና ትግላችን መፋፋም
ይኖርበታል። ነጠላ ቡድናዊ እውነታቸው የተሸነፈባቸው ኃይሎች ሥርዓት አልበኝነት
አንግሠው የጥላቻ ፖለቲካ ቸርችረው፤ በቻሉት ዐቅም እጃችን ጠምዝዘው ሥልጣን ለመያዝ
እየደሚሠሩ አይተናል። በመሆኑም የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የግድ ነው። የነጻነት
አስተዳደር እና አጠቃቀም በሕግ አግባብ ሚዛን እንዲጠብቅ አድርገን ሌብነትን በተቀናጀ

37
የፓርቲ እና የሕዝብ ዐቅም እየገታን መሄድ የሕግ የበላይነት ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው
ቀይ መሥመራችን መሆኑን በተጨባጭ ርምጃዎች ማረጋገጥ አለብን።

3.2.4 የኃይል አጠቃቀም ማዕከላዊነት

በዘመናዊ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ መንግሥት በብቸኝነት
ኃይልን የመጠቀም መብቱን ማስከበሩ ነው። መንግሥት በብቸኝነት ኃይል የመጠቀም
ሥልጣኑን ሥራ ላይ የሚያውለው በመሠረታዊነት ለሁለት ዓላማዎች ነው። የመጀመሪያው
ዓላማ በሀገር ውስጥ ሕግ እና ሥርዓትን ለማስከበር ነው። ይህ ብዙውን ጊዜ በፖሊስ ኃይል
የሚሠራ የወንጀል መከላከል እና የምርመራ ሥራ ነው። ሁለተኛው መንግሥት ኃይልን
የሚጠቀምበት ዓላማ ሀገርን ከወረራና ከውጭ ጠላት ለመከላከል እና አስፈላጊ በሆነ ወቅት
ወታደራዊ ኃይልን በመጠቀም ሀገራዊ ጥቅምን ለማስከበር ነው።

ግለሰብ ዜጎች ውሱን በሆነ እና በሕግ በተፈቀደ ልዩ ሁኔታ ራስን ለመከላከል ኃይል
ለመጠቀም መብት አላቸው። ቢሆንም፣ በመርሕ ደረጃ ኃይልን በብቸኛነት የመጠቀም መብት
የመንግሥት ሥልጣን ነው:: በፌደራል ሥርዓት ውስጥ፣ በሀገር ውስጥ ሕግ እና ሥርዓት
የማስጠበቅ ኃላፊነትን የፌደራል መንግሥት እና የክልል አስተዳደሮች የሚካፈሉበት አሠራር
የተለመደ ነው። ሆኖም ለዚሁ ዓላማ በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ የሚደራጀው የፖሊስ
ኃይል በፖሊሳዊ የሞያ መሥፈርት የተደራጀ የሲቪል ተቋም ነው። ሥልጠናው፣
የሚታጠቀው መሣሪያ፣ አጠቃላይ አደረጃጀቱ እና ቅኝቱ ለውጊያ ወይም ለጦርነት ሳይሆን
የውስጥ ጸጥታን እና ሕግን ለማስከበር የተዘጋጀ ነው።

ሀገርን ለመከላከል እና ሀገራዊ ጥቅምን ጥቅምን በኃይል ለማስክበር የሚደራጀው ሠራዊት


ደግሞ፣ የሀገር ዐቅም በፈቀደው ልክ የተቻለውን ያህል መሣሪያ ይታጠቃል። ከፍተኛ ብቃት
ኖሮት በወታደራዊ ሳይንስ እና መርሖች መሠረት በተማከለ ሁኔታ ይደራጃል። ይህ መርሕ
እውን ያልሆነባቸው ሀገራት፣ እንደ ሀገረ መንግሥት ያላቸው ህልውና አጠያያቂ ነው᎓᎓

ተፎካካሪ ፓርቲዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሀገራዊ ለውጡ ጀምሮ በነበሩ የሕዝብ
ውይይቶች እና በምርጫ ክርክሮች ላይ የልዩ ኃይል አደረጃጀትና አላስፈላጊነት ዋነኛ አጀንዳ
አድርገው ሲያነሡት ነበር። በእነዚህ ውይይቶች ጊዜ የልዩ ኃይል አደረጃጀት ለሀገረ
መንግሥት ቀጣይነት ቀጣይ ፈተና ሆኖ እንደሚመጣ ተነሥቶ ነበር። የኃይል አጠቃቀም
በሕገ መንግሥቱ መሠረት ለፖሊስ እና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት መሆን እንዳለበት ሲያነሡ
ነበር። ፓርቲያችን በጉዳዩ ላይ ክልሎችን ያሳተፈ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ ከጥቂት
38
ዓመታት በፊት ምክረ ሐሳብ አቅርቦ ነበር። ነገር ግን በወቅቱ ከነበርንበት ሀገራዊ ሁኔታ
የተነሣ ምክረ ሐሳቡን ተግባራዊ ለማድረግ አልተቻለም። ስለዚህ ጉዳዩ በይደር እንዲቆይ
የተደረገ፣ የዘገየ ግን የግድ አስፈላጊ የሆነ የቤት ሥራ ነው።

የወል እውነቶቻችን ገዥ የሆነበት ሥርዓት ሊገነባ እንደሚፈልግ ፓርቲ፤ ለዘመናት ሳይቋጭ


ሲንከባለል ቆይቶ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የወል እውነት ገዥነት እንዲመሠረት
ለምንፈልገው ሀገረ መንግሥት ማዕከላዊነቱ የተጠበቀ እና በተልዕኮ ልክ የሚደራጅ የጸጥታ
ኃይል አደረጃጀት ወሳኝ ይሆናል። ባለፉት አምስት ዓመታት ነጠላ ቡድናዊ እውነታቸውን
ገዥ ሥርዓት ለማድረግ እየታገሉን ያሉ ኃይሎች፤ በተላላኪ እና በሽፋን ሲያደርጉት
የነበረውን ሀገረ የማፍረስ ተግባር አልሳካ ሲላቸው፣ በግልጽ ጦርነት የገጠሙን፣ የልዩ ኃይል
አደረጃጀታቸውን በመጠቀም ነው። በቀጣይም ነጠላ ቡድናዊ እውነቱን ገዥ ሐሳብ ለማድረግ
የሚፈልግ ሌላ ኃይል ዓላማውን ለማሳካት ይህን ኃይል መጠቀሙ አይቀርም። በመሆኑም
የወል እውነቶቻችን ገዥ ሥርዓት እንዲሆኑ የኃይል የኃይል አጠቃቀም መዛባቶችን
ማስተካከል ያስፈልጋል።

ሌላው ኢመደበኛ አደረጃጀት የሚባል ነገር በማንኛውም ክልል አያስፈልግም። ይህም ኃይል
ወደ መደበኛ ሕይወቱ እንዲመለስ የማድረግ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ። የኃይል
አጠቃቀምን የማስተካከል ጉዳይ፣ የሀገረ መንግሥት ቀጣይነትና የሕዝቦችን ሁንተናዊ የወል
እውነት የማጽናት ጉዳይ ነው። የጸጥታ ኃይላችንን ይበልጥ በማጠናከር፤ የሀገር ውስጥ
ሰላማችንን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ባልተረጋጋው ባልተረጋጋው የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናችን
ላይ ብሔራዊ ጥቅማችንን በዲፕሎማሲም፤ በወታደራዊ መስክም ይበልጥ የምናስከብርበት፣
ከውስጣዊ ፍላጎቶቻችን የውጭ ጉዳያችንን የምናስፈጽምበት ዐቅም የምንፈጥርበት መንገድም
ነው።

3.2.5 የሕገ መንግሥት ቅቡልነት - የወል እውነትን ማጽኛ መሠረት

በዘመናዊ የሀገረ መንግሥት እና የፖለቲካ ሥርዓት፣ ሕገ መንግሥት ትልቅ ቦታ አለው።


ቀደም ባሉ ዘመናት፣ በተለይም ዘመናዊ የሀገረ መንግሥት ሥርዓት በስፋት በሥራ ላይ
ሳይውል በፊት ሕገ መንግሥት ሳይኖር ሀገራት እና የፖለቲካ ማኅበረሰቦች ይኖሩ ነበር።
የዘመናዊ ሕገ መንግሥቶች ታሪክ ግፋ ቢል የአራት ምዕተ ዓመታት ታሪክ ያለው ነው።
በአሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን በሀገረ አሜሪካ፣ ቀጥሎም በፈረንሳይ የተከሠቱት አብዮቶች
እና ከእነዚህ አብዮቶች ቀደም ብለው የተስፋፉት የማኀበራዊ ውል” የፖለቲካ ፍልስፍና

39
ዕይታዎች፣ በአንድ ሰነድ የተጠናቀረ፣ የአንድን ሀገረ መንግሥት አወቃቀር፣ ቅርጽ እና
በሀገረ መንግሥቱ ሥልጣን የሚያዝበትንና እንዲሁም ሥራ ላይ የሚውልበትን መንገድ፣
የሚከፋፈልበትን፣ እንዲሁም ሥራ ከዚያም አልፎ መሠረታዊ የዜጎችን መብቶች የያዘ የሕግ
ማሕቀፍን ለዓለም አስተዋውቀዋል። ይህ ተሞክሮ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ እየተስፋፋ
በላቲን አሜሪካ፣ በእስያ እና በአፍሪካም በተለያየ መልኩ ተተግብሯል።

በአህጉራችን አፍሪካ የዘመናዊ ሕገ መንግሥቶችን ታሪክ ስንቃኝ ከቅኝ ግዛት ዐውድ ውጪ


የተጻፈ ወይም የተሰነደ አንድ ወጥ ሕገ መንግሥት በማውጣት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀደምት
ከሚባሉት ሀገራት አንዷ መሆኗን እንመለከታለን። አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት
ነጻ ሲወጡ የቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸውን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በመውረስ የዘመናዊ ሕገ
መንግሥት ታሪካቸውን ጀምረዋል። እነዚህ የውርስ ሕገ መንግሥቶች ብዙም ሳይበረክቱ
ተለውጠዋል። በዓለም አቀፍ እና በአህጉሪቱ ካጋጠሙ የተለያዩ የፖለቲካ ክሥተቶች ጋር
በተገናኘ ሕገ መንግሥትን አስመልክቶ ያሉ ዕይታዎች እየተለዋወጡ መጥተው ዛሬ ላይ
ደርሰናል። በአሁኑ ወቅት ሕገ መንግሥትን አስመልክቶ በስፋት የሚንፀባረቀው አስተሳሰብ
የሚከተሉት መገለጫዎች አሉት።

ሕገ መንግሥት ከሞላ ጎደል የሕዝቦችን የወል እውነቶች መግለጫ እንዲሆን ይጠበቃል።


ይሁን እንጂ በተጻፈ ሕገ መንግሥት መተዳደር ከጀመረች መቶ ዓመት እየተጠጋች ያለችው
ሀገራችን ነጠላ ቡድናዊ እውነቶችን ሥርዓታዊ የበላይነት እንዲይዙ ያደረጉ አራት ሕገ
መንግሥቶችን አውጥታለች። ከእነዚህ ሁለቱ ንጉሣዊ ሕገ መንግሥቶች ናቸው (የ1923 እና
1948ዓም)። በደርግ መጀመሪያ ዘመን ከንጉሣዊ ሥርዓት ሀገሪቷን ወደ ሕገ ወደ ሕገ
መንግሥታዊ መንግሥታዊ ሥርዓት ያሸጋግራል ተብሎ የተዘጋጀ ሦስተኛው ሕገ
መንግሥታዊ ረቂቅ በአብዮቱ ማዕበል በረቂቅ ደረጃ እንዳለ መክኖ ቀርቷል። በኢትዮጵያ
ታሪክ አራተኛው ሕገ መንግሥት በ1980 ዓም የኢሕዲሪ ሕገመንግሥት ታውጆ ነበር።

የኢሕአዴግን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ፣ እስካሁን ድረስ በሥራ ላይ ያለውና


አምስተኛው ሕገ መንግሥት ታውጇል። ይህ ሕገ መንግሥት የወል እውነቶችን የማካተት
ሙከራዎች ቢኖሩበትም፤ የቅቡልነት ፈተናዎች ከገጠሙት ሰነባብቷል። በወቅቱ የሕገ
መንግሥት ዝግጅት ውስጥ ከመገባቱ ቀደም ብሎ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ
ምክክር አልተደረገም። የቀደሙ በደሎች በይቅርታ እና በካሣ ተሽረው የበለጠ ሀገራዊ
አንድነት አልተፈጠረም፡ እነዚህ ተደርገው ወደ ሕገ መንግሥት ዝግጅት ቢገባ ኖሮ ዛሬ ላይ

40
የምናያቸው በሕገ መንግሥቱ ላይ የሚነሡ የቅቡልነት ፈተናዎች የመቅረት ዕድል
ይኖራቸው ነበር።

ሕገ መንግሥቱ ገዥ የሆኑ የወል እውነቶችን ከማካተት አንጻር ባለበት ክፍተት የተነሣ፣


ከአተገባበሩ፣ ከንድፉም ሆነ ከይዘቱ አኳያ ለተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮች ተጋላጭ ሆኗል። ይህ
እውነታ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ማኅበረሰቡ ውስጥ ሲንፀባረቁ ከምናያቸው አቋሞች፣
ከሚንሸራሸሩ ሐሳቦች፣ በመደበኛ ሚዲያዎች በማኅበራዊ እና በተጨማሪም በዚህ ጉዳይ ላይ
ከተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች በበቂ ሁኔታ የሚታይ ነው።

ሕገ መንግሥቱ እና በሕገ መንግሥቱ የተካተቱት መሠረታዊ ይዘቶችን በተመለከተ በተለያዩ


የነጠላ ቡድናዊ እውነት አለን በሚሉ ኃይሎች መካከል ሰፊ የሐሳብ ልዩነቶች ይንፀባረቃሉ።
እነዚህ የሐሳብ ልዩነቶች እና ተቃርኖዎች ከፖለቲካ ልሂቃኑ አልፈው ወደ ማኅበረሰቡ
ዘልቀዋል። አንደኛው ወገን የነጠላ ቡድናዊ እውነት አቀንቃኝ ኃይሎች ሕገ መንግሥቱ
የህልውናዬ ዋስትና እና በአጠቃላይ በጎ የሆነ ሰነድ ነው ብለው ያምናሉ፣ ከሞላ ጎደል ሕገ
መንግሥቱ ባለበት እንዲቀጥል ይፈልጋሉ። በሌላኛዎቹ የነጠላ ቡድናዊ እውነት አቀንቃኝ
ኃይሎች ደግሞ ሕገ መንግሥቱ ለህልውናዬ አደጋ ነው ብለው ያስባሉ፣ እኩይ የሆነ የጥፋት
ሰነድ ነው በማለት ሕገ መንግሥቱን መሉ በሙሉ መሻር እና በሌላ መተካት ያስፈልጋል
ያስባሉ።

ሁለት የተቃረኑ ሐሳቦችን በሚያራምዱ የነጠላ ቡድናዊ እውነት ብቻ አስጠባቂ ኃይሎች እና


እነርሱን በሚከተሉ ዜጎች መካከል ያለው አለመተማመን እና ውጥረት ከፍተኛ ነው። ይሄም
ለሀገራችን ትልቅ ፈተና እየሆነ መጥቷል። ይህ ልዩነት የተረጋጋ እና የሰከነ የፖለቲካ ድባብ
በሀገሪቱ እንዳይኖር፤ ከውጥረት፣ ከነውጥ እና ከግጭት አረንቋ እንዳንወጣ አድርጎናል። ይሄ
ሁኔታ ደግሞ በፖለቲካም፣ በኢኮኖሚም ሆነ በማኅበራዊው መስክ እንደ ሀገር ለማሳካት
የምንፈልጋቸውን ግቦች እንዳናሳካ ትልቅ መሰናክል ሆኗል። ሆኗል። ዴሞክራሲያዊ
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት፣ የሀገርን ዕድገት በማሣለጥ፣ ሀብት እና ሥራ በመፍጠር
የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ሕዝብና መንግሥት ተገቢውን እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ይሄ
መሠረታዊ ተቃርኖ ዕንቅፋት ሆኗል።

በሕገ መንግሥቱ ላይ የሚነሡ ውዝግቦች ካልተፈቱ በሀገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግናን


ማረጋገጥ አዳጋች ነው። የወል እውነቶቻችን ገዥ የሚሆኑበት ጠንካራ ሀገረ መንግሥት
ለመገንባትም አይቻልም። የሀገሪቱ ዜጎች ሙሉ በሙሉ በሕገ መንግሥቱ ላይ ፍጹም የሆነ

41
ስምምነት እንዲኖራቸው ማድረግ የሚቻል ባይሆንም፣ ምልዓተ ሕዝቡ በአብዛኛው የሕገ
መንግሥቱ ይዘቶች ላይ ይዘቶች ላይ እንዲግባባ ማድረግ ያስፈልጋል። ሕገ መንግሥቱን
የእኔም ነው ብሎ እንዲቀበለው ማድረግ ለሀገራዊ አንድነት እና ሰላም ትልቅ ግብአት ነው።
በሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያለን ተቃርኖ፣ ከታሪክ ምልከታችን ጋር ተሣሥሮ ወደፊት
መራመድን አስቸጋሪ አድርጎታል።

ፓርቲያችን ሕገ መንግሥቱ የሁላችን የሆነ የወል እውነቶች ገዥ ሐሳቦች ያደረገ፤ ያደረገ፤


በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው፣ የሀገራችንን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ታሳቢ ያደረገ
ሰነድ መሆን እንዳለበት ያምናል። ሕገ መንግሥቶች የሥርዓቶች የአሸናፊነት ማጽኛ
ማኅተም መሆን አለባቸው ብሎ ፓርቲያችን አያምንም። ነገር ግን ሕገ መንግሥቱ ጫፉ
አይነካም፤ ሕገ መንግሥቱ ሙሉ በሙሉ ተቀዶ ይጣል በሚሉ፤ በሁለቱም የነጠላ ቡድናዊ
እውነት ፍላጎት አስጠባቂዎች በሚያነሣው ዋልታ ረገጥ ሐሳብ አይስማማም። ሕገ
መንግሥት የነጠላ ቡድናዊ እውነት ብቻ አስተናግዶ ሀገር አያጸናም። በመሆኑም የሁሉንም
ፍላጎት ያሟላ እንኳን ባይባልም የብዙኃኑን የወል እውነቶች ገዥ ሐሳቡ ያደረገ ሕገ
መንግሥት ሊኖረን እንደሚገባ እናምናለን። ምክንያቱም በአንድ ሀገር ውስጥ መሠረታዊ
ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች እልባት አግኝተው፣ በሀገራዊ መግባባት በበቂ ሁኔታ የተደገፉ
ሲሆኑ፣ ሕገ መንግሥታዊነት ይሰፍናል፤ የፖለቲካ እና የአስተዳደር ትኩረት የሀገርን
ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት ማሣለጥ ላይ ያተኮሩ የፖሊሲ አማራጮች ላይ
የሚያጠነጥን ይሆናል፡ ሕገ መንግሥታዊነትን ለማጎልበት በጋራ ሁላችንም የምንገዛበት እና
የምንመራበት፣ የኔ ብለን የምንቀበለው፣ ለፖለቲካ እና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎቻችን
ማሕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግለን ሕገ መንግሥት ሊኖረን ይገባል። ይህ እንዲሆን ደግሞ በሕገ
መንግሥቱ ዙሪያ የጋራ አመለካከትና ሀገራዊ መግባባትን መገንባት ያስፈልጋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት መሠረተ ብዙ ሥራዎችን ፓርቲያችን


እየሠራ ይገኛል። ባለፉት አምስት ዓመታት የተፈተንባቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና
ማኀበራዊ ጉዳዮች አብዛኛውን በድል እየተሻገርን አሁን ላይ ደርሰናል። ሀገራዊ የውርስ
የቤት ሥራዎችን ለማጠናቀቅ መሣሪያ የሚሆነን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር
ይገባል። ይሄም ሕገ መንግሥቱን ጨምሮ ያልተቋጨውን የሀገረ መንግሥት ግንባታችንን
መሥመር የምናስይዝበት ነው። በምክክር ኮሚሽኑ ዓላማዎቻችንን ማሳካት፣ በብዙ ፈተናዎች
ተፈትነን ያስመዘገብናቸውን ሀገራዊ ድሎች ማጽናት እና የወል እውነቶቻችን ገዥ ሆነው
ሕገ መንግሥታዊ ድጋፍ እንዲኖራቸው መሥራት ቀዳሚ አጀንዳዎቻችን ናቸው።
42
3.2.6 የውስጠ ፓርቲ አንድነት ለርእያችን ስኬት

የብልጽግና ፓርቲ መመሥረት የወል እውነታችን ገዥ ሥርዓት እንዲሆን የማድረግ


ፍላጎታችን ውጤት ነው። የሀገራዊ የወል እውነታችን ተግባራዊ መገለጫ ብልጽግና ፓርቲ
ነው። የሁሉም የሀገራችን ሕዝቦች ውክልና ያለበት፤ የሁሉንም ሕዝቦች ኢኮኖሚያዊ፣
ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ፍላጎት የመመለስ ዐቅም ያለው ብቸኛ ፓርቲ ብልጽግና ብቻ ነው።
ሌሎች ፓርቲዎች አብዛኞቹ የነጠላ ቡድናዊ እውነት አራማጆች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የወል
እውነትን ሽፋን አድርገው ነጠላ ቡድናዊ ፍላጎቶችን ለማስፈጸም የሚሠሩ ናቸው። ለዚህ
ነው አሁን ላይ ከብልጽግና ፓርቲ ውጭ እውነቶችን ሀገራዊ ሁለንተናዊ የወል ማዕከል
አድርጎ የሚሠራ ፓርቲ የለም የምንለው። ፓርቲያችን በአንድ ወጥ ፓርቲነት ዳግም
ተደራጅቶ ሀገራዊ ለውጡን መምራት ከጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያ የወል እውነቶቻችን ገዥ
ዕሳቤ የሆኑባት እንድትሆን ዘርፈ ብዙ ትግሎችን እያደረገ ይገኛል።

የውስጠ ፓርቲ አንድነትን ለማስጠበቅ አበረታች ሥራዎች ተሠርተዋል። ነገር ግን


እያለፍንበት ካሉት ሀገራዊ ሁኔታዎች እና ለመገንባት ከምንፈልገው የወል እውነታችን ገዥ
ዕሳቤ የሆነበት ማኅበረ ፖለቲካ ፍላጎት አንጻር፤ ብዙ ሥራዎች ይቀሩናል። በዋነኝነት የውስጠ
ፓርቲ አንድነት ፈተና የሆነው፣ የነጠላ ቡድናዊ እውነታቸው ገዥ ዕሳቤ እንዲሆን የሚፈልጉ
ኃይሎች በውስጣችን መኖራቸው ነው። ይሄም የወል እውነቶቻችንን ገዥ እውነቶቻችንን
ገዥ ሥርዓታዊ ዕሳቤ ዕሳቤ ለማድረግ አድርጎታል። የምናደርገውን ጥረት ከውስጥም
ከውጪም ፈተና እንዲገጥመው አድርጎታል።

የነጠላ ቡድናዊ እውነታቸውን ወደ ሥልጣን ለማምጣት የሚሠሩ ኃይሎች አሁን ላይ ብሔር


ከብሔር የሚያጋጭ ከፍተኛ የጥላቻ ዘመቻ ላይ ይገኛሉ። ከፓርቲ እና ከግለሰብ አልፈው
ወደ ሕዝቦች የወረደ የጥላቻ ሰበካ ላይ ተጠምደዋል። የራሳቸውን ቡድን ሀገር አዳኝ አድርገው
ከሀገር ውስጥ እስከ ውጪ ሀገር በተደራጀ መልኩ በስሕተት እና በጭፍን ጥላቻ የታጀለውን
ዘመቻቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ። ይህ አክሳሪ መንገድ ዳፋው ለሕዝባችን እንዳይተርፍ፤
የተቀናጀ የአጀንዳ ሰጪነት አዲስ ስትራቴጂ አዘጋጅተን፣ ሙሉ አደረጃጀታችንን በመጠቀም፣
የማኮላሸት ተልዕኮ ላይ መሰለፍ አለብን። ከአመለካከት ጥራት እስከ አጀንዳ ሰጪነት
የተደራጀ ተልዕኮ የውስጠ ፓርቲ አንድነትን ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው። ግቡን እንዲመታ
ለምንፈልገው የወል እውነቶቻችን ገዥ የሆኑበት ሥርዓት የመፈጠር ጉዳይ ወሳኝ በመሆኑ
ሁሉንም ዐቅሞቻችንን አስተባብረን የምንሠራበት ይሆናል።

43
3.3 የታደሰው የዓለም አቀፍ ግኑኘነትና ዲፕሎማሲ
ኢትዮጵያ እንደሚታወቀው የውጭ ግንኙነቷ በገለልተኝነት (non- ሉዓላዊነት በማከብር፣
በሀገራት የውስጥ aligned) መርሕ ላይ የቆመ ነው። ይህም በዋናነት የሌሎች ሀገራትን ጉዳይ
ላይ ጣልቃባለመግባት፣ በሁለትዮሽ ከሀገራት ጋርም ሆነ በባለ ብዙ ወገኖች የግንኙነት
መድረኮች ላይ (multilateral platforms) ዓለም አቀፋዊ የሰላምና የኢኮኖሚያዊ ዕድገት
ትብብሮችን በማጠናከር ላይ የተመሠረተ መንገድን ታራምዳለች። በዚህም ሰላሟን
ለማጽናትና ከድህነት በመላቀቅ ለመልማት ከሚተባበሯት ሀገራት ጋር በሙሉ በትብብር
ትሠራለች::

ኢትዮጵያ በበኩሏ ከቀጣናዋና ከዓለም አቀፍ ሀገራትና ከባለብዙ ወገን መድረኮች


ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷንና ነጻነቷን ያከበረ፣ በሰጥቶ መቀበል ላይ የተመሠረተ የእርስ
በርስ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲኖር ትጠብቃለች።

3.3.1 የሰሜኑ ግጭትና የዲፕሎማሲያችን ፈተና

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከሕወሐት ጋር የፈነዳው ጦርነት በሀገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን


መፍጠሩ ይታወቃል። በሪፎርሙ የሠመረውን ዲፕሎማሲ ወደ ኋላ የመለሰ ብቻ ሳይሆን
የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ጭምር ፈተና ውስጥ የከተተ ክሥተት ነበር።
ግጭቱ በተለይ ለዴሞክራሲና ለሰብአዊነት “ጠበቆች ነን” በሚሉት የምዕራቡ ዓለም ሀገራት
ዘንድ ከፍ ያለ ጫናን ያስከተለብን ነበር። ግጭቱ ዲፕሎማሲያችንን ክፉኛ ጎድቶታል ማለት
ይቻላል።

የውጭ ግንኙነት ሪፎርሙ ገና በሁለት እግሩ ሳይቆም በተከፈተብን የመረጃ ጦርነት የተነሣ
ብልጫው ተወሰደብን። የመረጃ ጦርነቱ ሀገሪቷን አጠልሽቶ ማሳየት ጀመረ። የግጭቱ ጠባይ
የውጭ ኃይሎችን ጭምር የጋበዘ በመሆኑና ይህም ከፍ ያለ የውጭ ጫናን በማስከተሉ ከፍ
ያለ ሰብአዊ ሰብአዊ ጉዳትና የሀብት ውድመት አስከትሎብናል። በውጤቱም በዓለም አቀፉ
ማኅበረሰብ ዘንድ፣ በተለይም በምዕራባውያኑና ከፍተኛ ተጽዕኖ ባላቸው እንደ የዓለም ገንዘብ
ተቋም (IMF)፣ የዓለም ባንክ (World Bank)፣ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ
ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) አማካይነት ከፍ ያለ ሆነ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ጫናና
ክልከላዎችን ጭምር አስተናግደናል።

የውጭ ኃይሎች በተዘዋዋሪ መንገድ ከመንግሥት በተቃራኒ በመሰለፍና ለወደረኞቻችን


ድጋፍ በማድረግ፣ የሀገሪቷን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መፈታተናቸው፤ ተጠቃሽ
44
የጦርነቱ ጉዳቶች ነበሩ። ሆኖም ይህ ሁሉ ሁኔታ በሀገሩ ሉዓላዊነትና ነጻነት ተደራድሮ
የማያውቀውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አላንበረከከውም። ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ፣ የፖለቲካ
ውስጣዊ ልዩነቱን ወደጎን በመተው፣ በአንድነት ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረጉ፣ የጦርነቱ
ምእራፍ ተዘግቶ ወደ ቀጣዩ ምእራፍ ለመሸጋገር ተችሏል።

3.3.2 የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አዲስ ምእራፍ

በመንግሥትና በሕወሐት መካከል ግጭቱን ለማስቆም የተደረሰው ስምምነት(agreement on


cessation of hostilities) ሀገራችን እንደገና ወደ ሰላሟ እንድትመለስ ከማድረጉ ባሻገር
ጀምራው የነበረውን ሪፎርሙን ተከትሎ እየተካሄደ የነበረውን ውጤታማ የውጭ ግንኙነትና
ዲፕሎማሲው መንገድ እንድትገባ አስችሏታል። የግጭት ማቆም ስምምነቱ ሂደት ሚዛን
የሳተ አቋም የነበራቸው ምዕራባዊ ሀገራት ተጽዕኖ አላረፈበትም። “ለአፍሪካዊ ችግሮች
አፍሪካዊ መፍትሔዎች” በሚል የመንግሥት የፈረጠመ አቋም በአፍሪካ ኅብረት መሪነት
በወዳጅ የአፍሪካ ሀገራትና ሰብእናዎች ዋና አደራዳሪነትና በሌሎቹም ድጋፍ ሰጪነትና
ታዛቢነት የተከናወነ ነበር። በዚህም ኢትዮጵያ ግጭቱን ለማቆምና ወደ ሰላማዊ መንገዶች
ለመግባት ችላለች።

3.3.3 ማስገንዘብና ማለዘብ (reengagement) የውጭ ግንኙነታችንንና


ዲፕሎማሲያችንን ማደስ

በስምምነት ፈራሚዎቹ ዘንድ ቁርጠኝነት የታየበትን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ


መንግሥት በጦርነቱ ወቅት የታዩትን የዲፕሎማሲ ስብራቶች ለመጠገንና ለማለዘብ ሥራ
ተጀምሯል። ከግጭቱ ጋር ተያይዞ የተካረረ አቋም ውስጥ ከገባንባቸው ሀገራት ጋር ሁኔታውን
ለማርገብ እየተሠራ ነው (እዚህ ላይ አየርላንድን ከመሳሰሉ ሀገራት ጋር ኢትዮጵያ ይፋዊ
የዲፕሎማሲ ግንኙነትን እስከ ማቋረጥ የደረሰ ውሳኔ መውሰዷን ማስታወስ ግድ ይሏል)።
በግጭቱ ወቅት በመረጃ ጦርነት ተፈጥረውብን የነበሩትንና ለሀገራት የተሳሳተ ውሳኔ ግብአት
የነበሩትን ስሑት ትርክቶች የማስተካከል ሥራ ተሠርቷል። በዚህ መንገድም ኢትዮጵያ
በርካታ አዎንታዊ ውጤቶችን አግኝታለች እያገኘችም ነው።

እንደማሳያም፦ የዩናይትድ ስቴትስ - አፍሪካ ሁለተኛው ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ የልዑካን


ቡድን የሠራቸው ጠንካራ ሥራዎችና የተገኙ አዎንታዊ ውጤቶች ተጠቃሽ ናቸው። በዚህም
የአሜሪካ መንግሥት “ለጊዜው ይዟቸው” የነበሩትን የልማት ድጋፎች መልቀቅ ጀምሯል።
የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ300 ሚልዮን ዶላር ድጋፍን ማስለቀቅ
45
ተችሏል። ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም መሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ በቅርቡ
አመራሮቹ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላቸውን አዎንታዊ
ግምገማቸውን አካሂደዋል።

3.3.4 ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ - የኢትዮጵያ ተግባራዊ ድል

ኢትዮጵያ ከቀኝ ግዛት ነጻ ሆና የቆየችው በቅኝ ገዥነት የመጡባትን ሀገራት በጦርነት ገጥማ
አስደናቂ ድል በማስመዝገብ ነጻነቷን ጠብቃ ስለቆየች ነው። ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን በዕጣ
ተከፋፍለው ሕዝቦቿን በባርነት አሰቃይተዋል። የተፈጥሮ ሀብቷን በመዝረፍ ለዘመናት
የጨለማ አህጉር እንድትባል አድርገዋል። ኢትዮጵያ የነጻነትን ዋጋ ታውቃለች። በክንዷ
ነጻነቷን አስጠብቃ አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ወደ ነጻነት እንዲመጡ ከማንዴላ እስከ
ሮበርት ሙጋቤ ድረስ ዐቅሟ የቻለውን ሁሉ ድጋፍ አደርጋለች።

የነጻነት ጎሕ እየቀደደ ሲመጣ አፍሪካውያን በአንድ ጥላ ሥር እንዲሰባሰቡ የሚያስችል አንድ


አፍሪካዊ ተቋም እንዲቋቋም የመሪነትን ሚና ተወጥታለች። በዚህም የአፍሪካ አንድነት
ድርጅት እንዲቋቋም በማድረግ አፍሪካዊ አንድነትን እንዲጠናከር ሠርታለች። ከቅኝ
ገዥዎች ነጻ ያልወጡ የአፍሪካ ሀገራት ነጻ እንዲወጡ በማድረግ ተቋሙ እንዲጠነክር ጉልህ
ሚና ተጫውታለች። የአፍሪካ አንድነት ደርጅት ዓላማውና ተልዕኮውን ከፍ በማድረግ ወደ
አፍሪካ ኅብረት ሲሸጋገር ያኔም ግንባር ቀደም የመሪነት ሚናዋን ተወጥታለች። ሁሌም
አፍሪካዊ ጉዳይ በአፍሪካውያን ሊፈታ እንደሚችል ኢትዮጵያ የምታምነው ዛሬ ችግር
ሲገጥማት ብቻ ሳይሆን ትናንት ከምሥረታው ጀምሮ ሰላም በማስከበር
በኮንጎ፤በሩዋንዳ፤በቡሩንዲ፤በሶማልያ፣በሱዳን እና በላይቤሪያ ወታደሮቿን በማሠማራት
ጭምር ለአፍሪካ ሰላም መረጋገጥ በተግባር ያላትን ቁርጠኝነት አሳይታ ነው።

ፓርቲያችን በሰሜኑን ጦርነት በጦር ሜዳ ሜዳ የተገኘነውን ድል በዲፕሎማሲው መስክ


የደገመበት መንገድ ኃያላን ሀገራት እና ታሪካዊ ጠላቶቻችን እንደሚፈልጉት የጠጓዘ
አልነበረም። ‹ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ይገኛል የሚለውን የቀደመ አቋም፣
በተለይም በሕዳሴ ግድብ ላይ ሲደረግ የነበረውን የሦስትዮች ድርድር የአፍሪካ ኅብረት
እንዲመራ በመወሰን ያሳየነውን አቋም ያጸናንበት ነበር።

46
3.3.5 የጋራ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ቀጣናዊ ትሥሥር

የፓርቲያችን የውጭ ጉዳይ ሌላኛው መርሕ ለጎረቤት ሀገራት ትኩረት የሚሰጥ መሆኑ ነው።
ይህንንም ተከትሎ በውጭ ግንኙነታችን ውስጥ የመጀመሪያው ትኩረት ከጎረቤት ሀገራት ጋር
በመተባበርና በመነጋገር ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መመሥረትና ማጠናከር ነው። የኛ እና
የጎረቤት ሀገሮቻችን ዕጣ ፈንታ የተሣሠረ ስለሆነ የጋራ ጥቅማችንን መሠረት ያደረገ
መተጋገዝና ትብብር ያስፈልጋል ብለን አናምናለን። በመሆኑም ከጎረቤት ሀገራት ጋር
በሚኖረን ግንኙነት ብሔራዊ ጥቅም በአብዛኛው በፍጹማዊ የጋራ ጥቅም ላይ ተመሥርቶ
ሊበየን ይገባዋል። ስለሆነም በቀጣናው ካሉ ሀገሮች ጋር የጋራ ጥቅሞቻችንን መሠረት
ያደረገ፣ አካባቢያዊ የልማት፣ የኢኮኖሚ እና የሰላም ዲፕሎማሲ ትሥሥር እንዲፈጠር
በማድረግ፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ጥምረት እንዲገነባ ከሀገራዊ ለውጡ ጀምሮ እየሠራን
እንገኛለን።

47
ክፍል አራት

IV. ከፍጥነት የሚገቱን

በመሠረቱ ፍጥነታችንን የሚገቱት ምንድን ናቸው? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የመኪና


ፍጥነትን የሚገድቡ ምክንያቶችን በምሳሌነት ብንመለከት ለነገራችን አስረጂ ይሆናል።
በሰዓት 360 ኪ.ሜ የሚነዳ መኪና ሲሠራ ከፍተኛ የፍጥነት ወሰኑ እንደ ዕምቅ ዐቅም
ይወሰዳል። ቢቻልና ሁሉ ቢስተካከል መኪናውን የተቀመጠለት የፍጥነት ወሰን ድረስ
መንዳት ይቻላል። እንዲሁም የሰው ልጅ የፍጥነትና ፈጠራ ዕምቅ ዐቅም አለው። ይሄን
ዐቅም _ ለመጠቀም _ አስቻይና ገዳቢ ሁኔታዎች ግን አሉ። አንድ መኪና ያለውን ዕምቅ
ዐቅም የሚገድበው ሞተሩ ያለውን ኃይል ወደ ፍጥነት በመቀየር ረገድ ያሉ ልዩነቶች ናቸው።
ያለንን ኃይል ወደ ፍጥነት ለመቀየር ምን አደረግን? ልንጠይቅ ይገባናል። የኃይል
አጠቃቀምና አከፋፈል በማርሽ የሚደለደል ሲሆን የሞተርን ብቃት አልቆ ለመጠቀም
ያስችላል።

ኃይልን አከፋፍሎ መጠቀም ከፊት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እየገመገምን ወደ መዳረሻችን


በፍጥነት ለመድረስ ይረዳናል። ከፊታችን ያለውን ተስማሚ መንገድ በከፍተኛ ፍጥነት
ብናቀጣጥለው፣ ተራራማ መንገድ ስንደርስ ግን የሚጠይቀን ፍጥነት ብቻ ሳይሆን ኃይልም
(ጉልበትም) ጭምር ነው። የውስጥና የውጭ ችግሮች መዳረሻችን (ራእያችንን) ጠብቀን
የፍጥነትና የኃይል ድልድላችንን አስተካክለን በመጓዝ ረገድ ያለብንን ክፍተት መርምረን
ማረም ፍጥነታችን ተጠብቆ ከመዳረሻችን ለመድረስ ይረዳናል።

ሸክም ፍጥነትን ይገድባል። ተመሳሳይ ዕምቅ ዐቅም ያላቸው መኪናዎች ፍጥነታቸው


በሸክማቸው ይገደባል። ተቀጽላ ሸክሞች መብዛታቸው ፍጥነታችንን ገድበውታል። የሥነ
ምግባር፣ ኢዲሲፕሊናዊነትና አጀንዳ ተሸካሚነት ዕምቅ ፍጥነታችንን በልኩ እንዳንጠቀም
አድርገውናል።

የጎማችን መሬት ነክሶ የመያዝ ዐቅም ፍጥነታችንን ይወስነዋል። መንሸራተት ፍጥነትን


ይገድባል መሥመር ያስታል። የጎማችን መንሸራተት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያመራ
ያደርጋል። መንሸራተት መሥመራችን በማሳት ካለምንበት ዓላማ በተቃራኒ ያስጉዘናል።
ከዚያም አልፎ ከዚያም አልፎ የከፋ አደጋ ውስጥ ይገለብጠናል፤ ያጋጨናል። ፍጥነታችንን
ገትተው መሥመራችንን የሚያስቱ ክሥተቶችን ልንታገላቸው ይገባል። ጥርስ ያለው ጎማ
48
የመንገዱን ላይ ንግ እንደሚያጠብቅ ሁሉ ድርጅታዊና መንግሥታዊ መዋቅሮቻችን ጥርስ
ሊኖራቸው ይገባል።

ሁሉም ነገር የተገናኘ ነው። በግንኙነቶች ውስጥ መጣጣምና መላተም ፍጥነትን ይወስነዋል።
የመኪናችን መዋቅራዊ ንድፍ(ዲዛይን) ከንፋስ ጋር ያለው ግንኙነት የፍጥነት መጠንን
ይወስነዋል። በመደበኛ መኪናዎችና በስፖርት መኪናዎች መካከል አንዱ ልዩነት ለነፋስ
ያላቸው የተጋላጭነት መጠን ነው። መዋቅራችን በውዥንብር መረጃና በአሉባልታ ነፋስ
እየተፈተነ ይገኛል። ይሄም ፍጥነታችንን እየገደበው ነው።

በዩኒቨርስ ውስጥ ሁሉም ነገር የተገናኘ ነው። ሁሉም ከአንዱ ጋር አንዱም ከሁሉም ጋር
ተጣጥሞ ይኖራል። አንዱ ቦታ የሚፈጠር እንከን መላ ሥርዓቱን ይመለከተዋል። የጣት
መቁሰል የሳንባን ተግባር ባይገታም በሰውነት ሥርዓት ውስጥ በአንድ አካልነቱ ጉዳቱ
ለሁሉም ይደርሳል። በዚህ የሰውነት ሥርዓት ውስጥ ለጉዳት የሚሰጠው ምላሽ ፍጠነትና
ፈጠራ የተሞላበት ነው። ጉዳቱን ለመላ አካል የማድረስ ፍጥነትና የተቀናጀ ምላሽ አሰጣጥ
ተፈጥሮዊ ፈጠራን ያሳያል።

ሰዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ጤነኛም፣ንቁና ዝግጁም መሆን አለባቸው። ለዚህም አካላዊ፣


አእምሯዊና መንፈሳዊ ኃይላቸው በአንድ ፍስት ውስጥ መግባት ይኖርበታል። የሦስቱ
ኃይሎች መዳበር ለአንድ ሰው ስኬት በተናጠልና በጋራ ሚና ይኖራቸዋል። አንዱ ቢጎደል
ወይም ቢዳከም በሁለቱ ላይ መዛባት ይፈጠራል። የሦስቱ መዛባት በሰው ልጅ ፍጥነትና
ፈጠራ ላይ እንከን ይፈጥራል።

እኔ አይተኬ ነኝ፤ እኔ መነካት የለብኝም፤ ከኔ በላይ ላሳር፤ የሚሉ አመለካከቶች


የሚወልዱዋቸው ኩርፊያ፣ ልግመኝትና ዳተኝነት ይስተዋላሉ። የወረቀት ሠራተኞችና
የፋይበር ሠራተኞች የቀንና የማታን ያህል ቢለያዩም ኢንዱስትሪውን ለማንቀሳቀስ ሁለቱም
አስፈላጊ ናቸው። የሰው ልጅ በሕይወት ለመኖር ቀን ነው ወይስ ማታ? የሚል ምርጫ
እንደማይሰጠው ሁሉ፣ የነዚህ ሁለት አካላት ሥርዓታዊ አስፈላጊ ናቸው። ቅንጅት በፍጥነት
ተሣልጦ፣ በፈጠራ ታጅቦ፣ የላቀ ምርት ለማምጣት የአንዱ መዘግየት (መንተፋተፍ) በቀጣዩ
ሥርዓት ላይ ያለው አሉታዊ ውጤት ስለሚጨምር በሂደቱ ሥርዓቱ ይረበሻል። የሥርዓቱ
መረበሽ ምርት ስለሚቀንስ፣ ከሚሠራበት ጊዜ የማይሠራበት ጊዜ እየበለጠ ይመጣል። በዚህ
የመገታት ሂደት የኢንዱስትሪው ሥርዓት መዛግ፣ መበስበስና መሰባበር ዕጣ ፈንታው
ይሆናል።

49
በፓርቲና በመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ፍጥነትና ፈጠራን ለማረጋገጥ የሥርዓቱ አካላት
ጤናማነት መረጋጥ ቀዳሚው አጀንዳ ነው። በሥርዓት ውስጥ የኃይሎች ግንኙነትና የነገሮች
ግንኙነት እንዳለ ሁሉ መገፋፋትም አለ። በሥርዓት ውስጥ በሚደረግ ትግል ፍጥነት በሦስት
ይከፈላል፤

1) መሳሳብ ፍጥነትን ሲያቅበው እንዲቆም ያደርገዋል (ከታሪ ኃይል)


2) ፍጥነት ጎታች ኃይል ፍጥነቱን ከሚመራው የበለጠ ኃይል ሲያበዛ፣ ወደኋላ መመለስ
ይሆናል (አንሸራታች ኃይል)፤
3) ፍጥነቱን የሚመራው ኃይል በዝቶ በቁጥር የሚያንሱትን ይዞ በፍጥነት ወደፊት ሲጓዝ
ይስፈነጠራል (አስወንጫፊ ኃይል)።

በዚህ ረገድ የፓርቲና የመንግሥትን ፍጥነት የሚስቡ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት አሉ።
የፍጥነት ትግላችን ውጫዊና ውስጣዊ ኃይሎችን ጠርምሶ የሚያልፍ አስወንጫፊ ኃይል
መብዛት አለበት። ፍጥነታችንን የምናስጠብቀውና ተገዳዳሪ ኃይሎችን ድል የምንነሣው
የፈጠራ ዐቅማችንን አሟጠን በመጠቀም ነው። በፖርቲና በመንግሥት መዋቅር ውስጥ
ፈጠራና ፍጥነት የሚያሣልጥ ሥርዓት ዘርግተናል። ፍጥነትና ፈጠራ በሥርዓት ውስጥ
ይገኛሉ። አንድ ሥርዓት በፍጥነትና በፈጠራ ውስጥ መሆኑ የሚወሰነው የዕምቅ ዐቅሙን
በገለጠበት ልክ ነው። ተያያዥነት ባለው ሥርዓት ውስጥ ፈጠራና ፍጥነት አይነጣጠሉም።

በዚህ ክፍል በሥርዓታችን ውስጥ ፍጥነትን እና ፈጠራን እንዳናረጋግጥ ያደረጉን ከታሪ እና


አንሸራታች ኃይሎች በዝርዝር ቀርበዋል።

4.1 የሠርጎ ገብ ፖለቲካ፡ ራእይን መንጠቅ፤ ዕይታን መስረቅ

የፓርቲያችን መሠረታዊ ፈተና ሠርጎ ገብነት እና ሠርጎ ገቦች ናቸው᎓᎓ ሠርጎ ገብነት
የአንድን ፓርቲ ወይም መንግሥት መዋቅር ወይም አባላትን በመጥለፍ የራስን ግብ
ለማስፈጸም ወይም ፓርቲውንና መንግሥትን ለማዳከም የሚደረግ ጥረት ነው። ሠርጎ ገቦች
የሌላን ቡድን ወይም ዓላማ ይዘው ከእነርሱ ተቃራኒ ወይም ተገዳዳሪ ነው ብለው በሚያስቡት
ፓርቲ ወይም መንግሥት ውስጥ በመግባት ያንን ፓርቲ ወይም መንግሥት የሚሰልሉና እና
ለማዳከም የሚሠሩ ናቸው።

የፓርቲውን ዓላማ የሚገነዘቡ ቁርጠኛ አመራሮችና አባላት ለተመዘገበው ዕድገት ትልቁን


ድርሻ ይወስዳሉ። በፍጥነት ከግብ ለመድረስ ዓላማውን ተረድቶ የሚንቀሳቀስ አመራር እጅግ

50
አስፈላጊ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ተለጣፊነት እና ተጠላፊነት ከፍጥነታችን ይገቱናል።
ተለጣፊዎች ማለት ፖለቲካዊ ዓላማና ግብ ሳይኖራቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማጋበስ ሲሉ
ፓርቲውን ተለጥፈው የሚኖሩ ናቸው። ተለጣፊዎችን ተሸክሞ መጓዝ የጉዟችን ፍጥነት
ይገታዋል። ስለዚህም ማራገፍ አለብን።

ርእዩ የተነጠቀ እና ዕይታው የተሰረቀ መዳረሻውን አያውቅም፤ ጉዞውም የዕውር ድንብር


ነው። ነገሮችን ከፓርቲያችን ግብ አንጻር የሚመለከት ሳይሆን ሌሎች በሠሩለት መነጽር
የሚመለከት ነው። እንደዚህ ዓይነት አመራር ፓርቲያችንን በማደናቀፍ ሥልጣን እና ሀብት
ለመቆጣጠር የሚፈልጉ አካላት ሠርገው እንዲገቡ በሩን ይከፍታል።

ሌላው ርእይን ለመንጠቅ የሚደረገው ጥረት ባለ ርእዮችን በመንጠቅ ላይ ትኩረት የሚያደርግ


ነው። በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሆነው ብልጽግናን የማረጋገጥ ትልማችንን ለማሳካት የቆሙ
አመራሮቻችን በማሸማቀቅና በመግደል ርእይን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሙከራዎች አሉ።
ይሄም ርእይን የመንጠቅና ዕይታን የመስረቅ አንዱ ገጽታ ነው። የመሐሉን መንገድ የመረጡ
ግርማ የሺጥላን የመሰሉ በዕሳቤያችን ላይ የጠራ አመለካከት እና ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት
ያላቸው አመራሮችን በመግደል ከጉዟችን ለመግታት ሙከራዎችን አድርገዋል። በወለጋ
ከጽንፈኝነት ይልቅ በመሐሉ መንገድ ላይ የቆረጡ አመራሮችን በተደጋጋሚ በመግደል
ርእይን ለመንጠቅ ተሞክሯል። ነገር ግን እነዚህ ጉዳዮች ዕይታችንን የሚሰርቁን እንዲሁም
ጉዟችንን የሚያስቀሩን አይደሉም። እንዲያውም በዓላማቸው የተሠዉ አመራሮቻችንን አደራ
ተቀብለን የኢትዮጵያን ብልጽግና በማረጋገጥ፣ ብልጽናዋን የስማቸው መታሰቢያ ለማድረግ
በቁርጠኝነት እንድንተጋ የሚያደርጉን ናቸው።

4.2 የተናጠል እውነት እና አንጻራዊ ጥቅም

ብልጽግና የጋራ እውነታችን ነው። አንዳችን ያለአንዳችን ቀጣይነታችንን ልናረጋግጥ


አንችልም። ይህ የጋራ እውነታችን ነው። ህልውናችን የተጋመደ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ
የሁላችንም ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ይህንን የጋራ እውነታችንን በማጽናት ወይም ባለማጽናት
ነው። ከዚህ በተቃራኒ ለተናጠል እውነት የሚደረግ ሽኩቻ እና የበላይነትን ለማረጋገጥ
የሚደረግ ትግል አንጻራዊና ጊዜያዊ ጥቅም ቢያስገኝ እንጂ ዘላቂ የሆነ ከፍታን
ሊያረጋግጥልን አይችልም:: በመሆኑም በጋራ ልንደርስበት ከምንችለው ከፍታ ይልቅ
አነስተኛ አንጻራዊ እና ጊዜያዊ ጥቅምን ለማግኘት የሚደረገው ትግል ዋነኛ ፈተናችን ነው።
የተናጠል እውነት እኔ ላይ የተመሠረተ በአንጻራዊነት መነጽር ነገሮችን የሚመለከት ነው።
51
ሥር የሰደደ አክራሪነት እና የድኅረ እውነት ፖለቲካ ፖለቲካ የተለያዩ ቡድኖችና ኃይሎች
በጋራ ከመቆም ይልቅ አጥር ፈጥረው በአጥራቸው ውስጥ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። ሁሉም
በአጥሩ ውስጥ ሆኖ የሚያደርገው ሽኩቻ ከፍጥነት የሚያንቀራፍፈን አንደኛው ጉዳይ ነው።
ሌብነትን እና ሀብት ቅርመታን ግቡ ያደረገ ነው። በአካሄድ ደረጃም መርሕን እና ሕግን
የማይከተል ሲሆን ሥልጣን እና ሀብትን ለማግኘት ሲባል ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ
ነው።

ብልጽግናን ማረጋገጥ በጋራ መሰባሰብና በጋራ መቆምን ይጠይቃል። ይሄንን የጋራ መሰባሰብ
ለመፍጠር የጋራ ስምምነትን መፍጠር ይሻል። ፈጣን ለውጥና ዕድገት አረጋግጠዋል
በሚባሉት ሀገራት ውስጥ ልማት ሊረጋገጥ የቻለው ለጋራ ከፍታ በጋራ መቆም በቻሉ ሕዝቦች
ነው። በተቃራኒ ተናጠላዊ ፍላጎትን ለማሳካት እና አንጻራዊ ጥቅምን ለማግኘት የሚደረግ
ሽኩቻ የጋራ ከፍታን ሳይሆን የጋራ ድቀትን የሚፈጥር ነው። የተናጠል እውነት ይዞ የሚደረግ
ሩጫ ግጭትን እንጂ ስኬትን አይፈጥርም።

ጊዜያዊ ችግሮችን በመመልከት ብቻ ዘላቂ ግብን ያላማከለ መፍትሔ ፍለጋ ለችግሮች


መወሳሰብ ዕድል ይሰጣል እንጂ ከችግሮች አያላቅቅም። ያለፈውን ያተበላሸ መንገድ ለጊዜያዊ
ፖለቲካ በሚል የማስቀጠልና የመድገም ፍላጎት የተፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አያስችልም።

4.3 ያልተገባ ክብርና ሀብት ፍለጋ

ለብልጽግና ደንቃራ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ የመሪዎች ያልተገባ ክብር እና ሀብት
ፍለጋ ውስጥ መግባት ነው። ይህ የመሪዎች ያልተገባ ውዳሴን እና ጥቅም ፍለጋ በዋነኝነት
በሞቅታ የዓላማ መሳትን ይፈጥራል። በተጨማሪም ሂደቶችን በማወሳሰብ ቅልጥፍና እና
ውጤታማነትን ያጠፋል። መሪዎች ያልተገባ ክብርና ጭብጨባ ለማግኘት ሲሉ የፓርቲና
የመንግሥትን ዓላማ ይስታሉ። ባልተገባና በሕዝባዊ አጀንዳዎች ይወሰዳሉ። ለዓላማና
ለመርሕ ከመሥራት ይልቅ ለመወደድና ለመደነቅ ይሠራሉ። እንደዚህ ዓይነት አመራሮች
ጉዟቸው ወደ ዓላማና ወደ ግባቸው ሳይሆን ገንዘብና ጭብጨባ ወዳለበት ሜዳ ነው።

መንገዶች ሲጠለፉ እና አቅጣጫ ሲስቱ መፍጠን አዳጋች ይሆናል። ብልጽግናን ለማረጋገጥ


ኃላፊነት ያለባቸው መሪዎች መሪዎች መንገዳቸው ሲጠለፍ እና አቅጣጫ ሲስት ብልጽግናን
ማረጋገጥ አዳጋች ይሆናል።

52
4.4 ውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን አለመላመድ፡ ጠባቂነት እና መርሕ አልባነት

ለመፍጠን እና ለመፍጠር ፈተና ከፈጠሩብን ጉዳዮች አንዱ አዲስ ሐሳብ እና አዲስ ባህል
ለመላመድ ያለን ዝግጁነት አዝጋሚ መሆኑ ነው። ብልጽግና አዲስ ሐሳብ እና አዲስ ባህልን
እያስተዋወቀ ያለ ፓርቲ ነው᎓᎓ አዲስ ሐሳብ እና አዲስ ባህልን ማሥረጽ ፈታኝ እና ጊዜ
የሚወስድ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም በሀገራችን አዲስ ሐሳብን እና አዲስ ባህልን ለመቀበል
ያለው ዝግጁነት ደካማ በመሆኑ ፈተናውን ያከብደዋል። ይህ ፈተና ደግሞ የሚጀመረው
የአዲሱ ሐሳብ አስፈጻሚ ከሆኑት ከፓርቲያችን አባላት በመሆኑ ችግሩን ከባድ ያደርገዋል።

ፓርቲያችን እንደ ፓርቲ ከቀደመው የተለየ የአሠራር ሥርዓትና አዲስ የፖለቲካ ልምምድ
ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው። ነገር ግን አዲሱን ባህል ተዋውቆ በፍጥነት ለዚያ ባህል ተገዥ
የመሆን ችግር አለ። ከዚህ መካከል ቀዳሚ ሆኖ የሚታየው ዴሞክራሲያዊ መርሐዊነት እና
የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን የመላመድ እና ለዚያ ተገዥ የመሆን ፓርቲዎች ከቀደሙትን
የሀገራችን ፓርቲያችን ችግር ነው።

ማርክሲስታዊ ልማድ ከዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የወጣ መሆኑ ይታወቃል። ይሄንንም


በውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲ ተክቶታል። ይሄን ባህል ለመላመድ ባለመቻሉ ሁለት ፈተናዎች
ገጥመውናል። አንዱ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የለም ማለት ልቅነት እንዲሰፍን ተፈቅዷል
ማለት ነው ብሎ የማሰብ አካሄድ ነው። በዚህ አካሄድ የፓርቲን መርሕ፣ የተግባርና የዓላማ
አንድነት የሚሸረሽር ልቅነት ተፈጥሯል።

ሁለተኛው ደግሞ አዲሱን ዴሞክራሲያዊ ባህል ቶሎ ተላምዶ በዚያ መሠረት የመንቀሳቀስ


ችግሮች ይታያሉ።

ዴሞክራሲያዊ መርሐዊነት የሁለት ነገሮች ውቅር ነው። የሐሳብ ብዝኃነት እና መርሕን


ያቀፈ ነው። የሐሳብ ብዝኃነት ሲባል የትኛውም ሐሳብ በፓርቲ መዋቅር ውስጥ ለውይይትና
ለክርክር ክፍት መሆን አለባቸው ማለት ነው። መርሐዊነት ማለት ደግሞ እነዚህ ውይይቶችና
ክርክሮች እንዲሁም ሐሳቦች ተፈጻሚነታቸው የፓርቲውን ሥነ ሥርዓት እና የዴሞክራሲ
መርሖች የተከተለ መሆን አለበት፡ ማለት ነው። የፓርቲ ሥነ ሥርዓት የፓርቲ አባላት
ፍላጎት ነጸብራቅ ሲሆን ማንኛውም የብልጽግና ፓርቲ አባል የሆነ ሰው ሊገዛባቸው የግድ
ይለዋል።

53
ክፍል አምስት

V. ይበልጥ መፍጠር፤ ይበልጥ መፍጠን

የገጠመንን ፈተና መሻገር የምንችለው ይበልጥ በመፍጠር እና ይበልጥ በመፍጠን ነው᎓᎓


ፍጥነት ጎታች የሆኑ ክፍተቶቻችንን እየቀረፍን ተጨማሪ ችግር ፈቺ ሐሳቦችን ማመንጨት
እና እነሱን በፍጥነት እየተገበሩ ወደ ብልጽግና መጓዝ ይገባል። በመሆኑም ፍጥነትን
ለመጨመር እና ፈጠራን ለማጠናከር ቀጣይ አቅጣጫችን ከሥር የተዘረዘሩት ናቸው። እነዚህ
ጉዳዮች በአንድ በኩል ለመፍጠን ያሉብንን ክፍተቶች በማረም ለመፍጠን የሚያስችል ዐቅም
ለማዳበር የሚጠቅሙ ሲሆነ፣ በሌላ በኩል በመፍጠር እና በመፍጠን የጀመርነውን ውጤት
የሚያሰፉ አመላካቾች ናቸው።

ከችግሮቻችንን ልንሻገር የምንችለው ከችግሮቻችን እየራቅን በሄድን ቁጥር ነው። ይበልጥ


እየጠነከርን የምንሄደው ተደራራቢ ችግሮቻችንን ከጫንቃችን እያቀለልን እና ዓለምን
እየቀረብን ስንሄድ ነው። ይህን ለማድረግ ጊዜያችንን እየበሉ፣ውጤታችንን እያኮሰመኑ፣
ካለንበት እንዳንሻገር እና እንዳንፈጥን እያደረጉ ያሉ ፈተናዎቻችንን መሻገር አለብን።
ችግሮቻችንን የሚበልጥ ውጤት፣ የባከነውን ጊዜ የሚያካክስ ስኬት፣ ተወዳዳሪነትን
የሚያረጋግጥ ውጤት ማምጣት ያስፈልጋል።

5.1 “የብልጽግና አጣዳፊነት” ዕሳቤ

የብልጽግናን አስፈላጊነት ግንዛቤ በመፍጠር መልካም መልካም ውጤቶች ተመዝግበዋል።


ፍጥነትን ለመጨመር የብልጽግናን አጣዳፊነት እና አንገብጋቢነት ግንዛቤ መፍጠር
ያስፈልጋል። እንዴት ጦርነት እያለ ፓርክ ይሠራል? እንዴት ሰዎች እየሞቱ ችግኝ
ይተከላል? የሚሉ ጉዳዮች የብልጽግናን አጣዳፊነት ካለመገንዘብ የሚመነጩ ናቸው።
የምናደርገው ጉዞ ረዥም፤ ያለን ጊዜ አነስተኛ ነው።

ብልጽግናን ባረጋገጡ የትኞቹም ሀገራት ውስጥ የአመራር ሚና እጅግ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው


ነው። ፍጥነትን ለመጨመር የአመራሩ የብልጽግና ምልከታ እጅግ ወሳኝ ነው። አመራሩ
ነባራዊ ሁኔታውን ተገንዝቦ እና ያለችውን ውሱን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ወደ ውጤት
ለመቀየር መሥራት አለበት። ውጤትን ለማረጋገጥ ከተፈለገ ሥራን ለነገ መተው ሳይሆን
በጊዜ የለም ስሜት መሥራት ያስፈልጋል።

54
ብልጽግናዊ መንግሥት ብልጽግናን ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ የሚንቀሳቀስ አመራር
ይፈልጋል። ያለንን ትኩረት፣ ዐቅም እና ጊዜ ብልጽግናን እውን ለማድረግ ማዋልና መጠቀም
ያስፈልጋል። ይህ ሲሆን ፍጥነትን መጨመር ይቻላል። ምክንያቱም ለተጓዳኝ አጀንዳዎች
የሚውል ትኩረት፣ በፍትጊያ የሚጠፋ ዐቅም እና ትኩረት በሙሉ ብልጽግናን ወደ ማረጋገጥ
ሲውል፣ ፍጥነትን መጨመር እና ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይቻላል።

5.2 ነገርን ከሥሩ

“የአሉ” ድኅረ እውነት ፖለቲካ፡- የፖለቲካችን መሠረታዊ ችግር ነገርን በቅጡ እና ከሥሩ
አለመረዳት ነው። አሉባልታ ለማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ዕድገታችን ትልቅ እንቅፋት ነው።
ብዙ ሀገር ሊለውጡ የሚችሉ ዕሳቤዎችና ሰዎች የደረቁት በአሉባልታ ነው። አንድ ወሬ ከየት
መጣ? እንዴት ተነሣ? እና ምክንያቱ ምንድነው? ሳይባል በጋራ ይፈረጃል፣ በማኅበር
ይጠላል፤ በማኅበር ይደነቃል፣ በጋራ ይወደዳል። “በአሉ” ብቻ ፍርድ ይሰጣል፣ ሰው ይቀጣል፣
ብዙ ነገሮች ይደረጋሉ። “በአሉ” ብቻ ብዙ ጥፋት ደርሷል።

ፖለቲካችን አንዱ የሚያስፈልገው ትልቅ ለውጥ ነገርን ከሥሩ መመልከት ነው። ወቅቱ
ደግሞ ከምንም በላይ በጥልቀት መመልከት እና ከሥሩ መመርመር የሚፈልግበት ነው።

አመክንዮአዊ አሰሳ፡- “አሉ” ከጓዳ ወጥቶ ዐደባባይ በዋለበት እና መረጃ ሆን ተብሎ


በሚምታታበት ዘመን ፖለቲከኞች ከቀደመው በላቀ ነገሮችን በአንክሮ የሚመለከቱ መሆን
አለባቸው። እንደ ደራሽ ጎርፍ ደራሽ መረጃ አጥፊ ነው። ዘመናችን ደራሽ መረጃ የበዛበት
ነው። የሆነ መረጃ ከሆነ ቦታ ይነሣል፤ ያገኘውን ሁሉ አጥለቅልቆ ይወስዳል። ውሳኔን
ያስቀይራል፤ አቅጣጫን ያስታል፤ በማዕበል ውስጥ መወዛወዝን ይፈጥራል። በእንደዚህ
ዓይነት ዓለም አቀፍ ሁኔታ ውስጥ ነገርን ከሥሩ አለመረዳት ለፍጥነት ዕንቅፋት ነው።
ጉዟችን መለስ ቀለስ እያለ እንዲዋልል ያደርገዋል። በመንገዳችን መጓዝ ሳይሆን መረጃ
በሚያወዛውዘን መንገድ እየሄድን ወደ መዳረሻችን ሳይሆን ወደ ጥፋት እንጓዛለን።

እውነትን ለማግኘት አመክንዮአዊ ፍለጋ አስፈላጊ ነገር ነው። ከተለያዩ አቅጣጫዎች


የሚመጡልንን መረጃዎች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የለምንም ማገላበጥ የምንቀበል ከሆነ
ካለምነው መዳረሻ ሳይሆን ካላሰብነው አጣብቂኝ ውስጥ ይከቱናል። ምክንያቱም በዚህ
የፖለቲካ ጦርነት ዘመን የሚሠራጩ መረጃዎች የኛን ሳይሆን ያሠራጨውን እነርሱን
የሚገልጹ ናቸውና እያንዳንዱ የሚቀርብልንን በስሜት መከተል ሳይሆን በምክንያት
መመርመር ያስፈልጋል። ነገርን ከሥሩ ማጤን እና መመለክት ይገባል። ለሚከሠቱ ነገሮች
55
ቅርንጫፉን ብቻ በማየት ከመወሰን ይልቅ ከሥሩ ማጥራት አለብን። ችግሮችን ከመነሻው
ወይም ማጤን (root cause analysis) እና የሚሠራጩ ከምንጩ ማጤን መረጃዎችን
በጥልቀት መነጽር(critical thinking) እያንዳንዷን ነገር ሰባብሮ መመልከት ያስፈልጋል።

መሪ ነገሮችን በጥልቁ የሚመለከት እና ከምንጩ የሚያጤን መሆን አለበት። በጉዳዩ ላይ


የተለያዩ ጥያቄዎችን ማንሣት፣ ጥያቄዎችን ለመመለስ መረጃን መሰብስብ፤ ጉዳዩ ሊያስከትል
የሚችለውን ነገር አርቆ መመለከት እና የተለያዩ አመለካከቶችን ማማተር የመሪ ክሂሎት
ነው። እንደዚህ ስናደርግ በተሳሳተ ውሳኔ ምክንያት የሚመጣውን ጥፋት መከላከል
እንችላለን።

5.3 አዳዲሶቹን ወደ ትግበራ ነባሮቹን ወደ ሥራ ገበታ _ ለትውልድ

ፓርቲያችን የዛሬን እና የነገን ትውልድ የሚጠቅሙ ዐሻራዎችን ማስቀመጥ ከጀመረ አምስት


ዓመታት ተቆጠሩ። የአፍሪካና የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የምትባለው አዲስ አበባ ከሀገራዊ
ለውጡ በኋላ ያለችበት ሁለንተናዊ ዕድገት ብልጽግናችንን አመላካች ነው። የአንድነት
ፓርክ፤ የወዳጅነት ፓርክ አንድ እና ሁለት ፤ እንጦጦ ፓርክ፣ የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት፤
የአዲስ አበባ መዘጋጃ-ቸርቸል ጎዳና- መስቀል ዐደባባይ፤ የፈጠራ ማዕከል የሆነው የሳይንስ
ሙዝየም፤ ዘመናዊ ግራንድ ፓላስ የመኪና ማቆሚያ፣ በጥቂት ዓመታት ውስጥ የተጠናቀቁ
ናቸው።

ተጠናቅቀው ወደ ሥራ ከገቡት በተጨማሪ የትናንት አኩሪ ታሪካችንን ጠብቆ ከማቆየት


አንጻር ለትውልዱ የጀግንነት ምሳሌ የሆነው የዐድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት እና ሌሎች ሜጋ
ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ስሟን የምትመጥን ብቻ ሳይሆን ከስሟ የላቀች ዓለም አቀፍ ደረጃን
ያሟላች ከተማ ወደ መሆን እያሸጋገራት ነው።

ገበታ ለሀገር ብለን ከአዲስ አበባ ውጪ በአማራ ክልል በጎርጎራ ላይ አስገራሚ የቱሪስት
መዳረሻ በመጠናቀቅ ላይ ነው። የጎርጎራ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ታሪክ ጠገብ የቱሪዝም መዳረሻ
ያለው የአማራ ክልል ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናል። ሌላኛው በደቡብ ክልል እየተሠራ
ያለው የኮይሻ ፕሮጀክት እና በኦሮሚያ ክልል እየተሠራ ያለው የወንጪ ፕሮጀክትም
ከተፈጥሮ ጋር የተስማሙ ሆነው እየተገነቡ ይገኛሉ። ቦታዎቹ ሲጠናቀቁ ሀገራችንን በቱሪስት
ተመራጭነቷን የሚያልቁ፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኙ የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻዎች
ጋር መወዳደር የሚችሉ፣ የሰው እና የተፈጥሮን መስተጋብር የጠበቁ ውብ የቱሪስት
መዳረሻዎች እንደሚሆኑ ይታመናል። መጀመር ብቻ ሳይሆን ጨርሰን ማሳየት እንደምንችል
56
አረጋግጠናል። ሲጀመር የሚነሡ አቧራዎች እየተነኑ የሥራ ዐሻራ ብቻ መመዘኛ እንደሚሆን
ባለፉት አምስት ዓመታት አይተናል። ይህ የሚያሳየን ፓርቲያችን ትውልድ አስቀጣይ
ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በመደመር ትውልድ ተጀምሮ የሚፈጸም እንጂ ተጀምሮ የሚቆም
ተግባር አለመኖሩን ለማስመስከር መቻሉን ነው።

ገበታ ለትውልድ የብልጽግና ዐሻራችንን በሁሉም የሀገራችን ክልሎች የምናሳርፍበት ነው።


የሁሉንም የሀገራችን የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች በማልማት የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች በስፋት
እንዲጎበኙ በማድረግ፣ ኢትዮጵያን ከራስ መንደር አንጻር ብቻ የመመልከት የጎዶሎ ዕይታን
የሚቀርፍ ነው። ይሄም ትውልዱ ወደ ሙሉ ዕይታ እንዲሸጋገር በማድረግ ከነጠላ ቡድናዊ
እውነት ወደ ወል እውነት ዕሳቤ እንዲመጣ እጅግ ጠቃሚ ተግባራዊ መሣሪያ ይሆነናል።
በመሆኑም ይህ ዓይነተ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ፕሮጀክት ለውጤት እንዲበቃ በሁሉም ደረጃ
ያለው የፓርቲያችን አመራር እና አባል ድጋፍ ማድረግና ዐሻራውን ለትውልዱ በተግባር
ማሳረፍ አለበት።

5.4 በክረምት፣ እራትና መብራት

ክረምቱ በጊዜ የለም ስሜት የምንሠራበት እና የጀመርናቸውን ዘርፈ ብዙ ውጤቶች


የምናጠናክርበት ነው። ክረምትን ተከትሎ እራትን የምናዘጋጀበት እንዲሁም
መብራታችንንም ከዳር የማድረስ ወሳኝ መርሐ ግብሮች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ አንደኛው
የግብርና ምርታማነታችንን የምናጠናክርበት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ሲሆን ሌላኛ
የሕዳሴ ግድብ አራተኛው ዙር የውኃ ሙሌት የሚካሄድበት ነው።

የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬትን ማስቀጠል በአረንጓዴ ዐሻራ ዓመታዊ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር፣
በስንዴ ምርታማነት እና በአጠቃላይ በግብርና ምርታማነት ላይ የታየውን ስኬት ማስቀጠል
_ አለብን። በምርት ዘመኑ በመኸር ወቅት በስንዴ ዘር ከተሸፈነው 2.82 ሚልዮን 02013/14
ምርት ሄ/ር ከ112 ሚልዮን ኩንታል በላይ ስንዴ የተመረተ ሲሆን ይህ ዘመን በማዕከላዊ
ስታትስቲክስ አገልግሎት ከተገመተው 52.13 ሚልዮን ኩንታል ምርት በ52.6 በመቶ ብልጫ
ያለው ምርት እንደተመረተ የሚያመለክት ነው። በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 1.32
ሚልዮን ሄክታር ለመሸፈን ታቅዶ 1.33 ሚልዮን ሄክታር በዘር ተሸፍኗል። ከዚህም 52
ሚልዮን ኩንታል እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል። በመሆኑም አሁንም የታቀደውን ግብ ለማድረስ
መሥራት አለብን። በስንዴ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የግብርና ምርቶች እየታየ ያለውን ውጤት
ክረምቱን በአግባቡ በመጠቀም በፍጥነት ማጠናከር ያስፈልጋል።
57
ባለፉት አራት ዓመታት ከፍተኛ ውጤት ያገኘንበት ዓመታዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ
መትከል መርሐ ግብር ወርዶ የነበረውን ሀገራዊ የደን ሽፋናችንን ወደ 17 በመቶ እንዲያድግ
ያደረግንበት ነው። በጥቅሉ በአራት ዓመት ውስጥ ከ25 ቢልዮን በላይ ተክለናል። ለዘንድሮ
በጀት ዓመት ቅድመ ዝግጅት የተጀመረ ሲሆን 6.3 ቢልዮን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ አሁን
ላይ 5.4 ቢልዮን ተዘጋጅቷል። ስለዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ የታቀደውን ችግኝ ያህል
ማድረስ ይጠበቅብናል።

የሌማት ትሩፋት ጅምሮችን ማስፋት- የወተት ምርት (የላም፣ የግመል፣ የፍየል) ባለፉት
ወራት 4.1 ቢልዮን ሊትር አፈጻም ነበረው። ዓመታዊ ዕቅዱ 75 ቢልዮን ሊትር ነው፤ ባለፉት
ወራት የሥጋ ምርት ከዳልጋ ከብት፣ ከበግ፣ ከፍየል እና ከግመል 237ሺ ቶን ተገኝቷል።
ዓመታዊ ዕቅዱ 505 ሺህ ቶን የሥጋ ምርት ነው፤ የዶሮ ዕንቁላል ምርትን በበጀት ዓመቱ
ወደ 3.47 ቢልዮን ለማድረስ ታቅዶ ባለፉ ወራት1.8 ቢልዮን ለማምረት ተችሏል።
በተጨማሪም ባለፉት ወራት የዶሮ ሥጋ ምርት 48 ሺቶን የተገኘ ሲሆን ዓመታዊ ዕቅዱ
95990 ቶን ነው የዓሣ ምርት ባለፉት ወራት 45.41 ሺ ቶን ሲመረት ዓመታዊ ዕቅዱ
106190 ሺህ ቶን ነው። በመሆኑም በቀሪ ጊዜያት ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ በፍጥነትና
በትጋት መሠራት አለበት።

5.5 የወል እውነትን የማጽናት ቀጣይ የፖለቲካ አቅጣጫ

የሀገር ግንባታ ገንቢዎቿ ለግንባታዋ መክፈል እንደሚፈልጉት የዋጋ ዓይነት ይወሰናል።


የተናጠል ቡድናዊ እውነታቸውን ገዥ ሥርዓት ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ይህን
ፍላጎታቸውን ለማሳካት በእጃቸው ላይ የነበራቸውን ሁሉንም አማራጮች ተጠቅመው
በቡድንም ይሁን በግለሰብ ደረጃ በነበራቸው ቁርጠኝነት ሦስት ዙር ጦርነት ገጥመውናል።
በዚህ ሂደት ላመኑበት ዓላማ ነፍሳቸውን ጭምር በዋጋነት ከፍለዋል። ሌሎች ኃይሎችም
ብረት አንሥተው የባዕድ ሀገራትን ፍላጎት በእናት ሀገራቸው ላይ ለመፈጸም የሀገር ማፍረሻ
ዋጋ እስከ ሕይወት መሥዋዕትነት ሲከፍሉ እያየን ነው። ይህ የሚያሳየን ቡድኖችም ይሁኑ
ግለሰቦች ዓላማ ብለው ለቆሙለት ጉዳይ ከየት እስከ የት ዋጋ እንደሚከፍሉ ነው።

የአፍራሾች እና የገንቢዎች የማድረግ ዐቅም የሚለካው ለዓላማቸው ለመክፈል እንደተዘጋጁት


ዋጋ ነው። የአፍራሾች መሰባሰቢያ በጥላቻ ላይ የተመሠረተ የነጠላ ቡድናዊ እውነትን
መሸቀጥ ነው፤ እውነታቸው ገዥ እስኪሆን፣ ሀገር እና ሕዝብ እንዳይረጋጉ ፋታ በመንሣት፣
የመናጆ ፖለቲካን ዋነኛ የመታገያ ስልት በማድረግ፣ ከአጀንዳ ወደ አጀንዳ እያካለቡ
58
የገንቢዎችን ዐቅም በማዳከም፣ ፍላጎታቸውን ማሳካት ነው። ዓላማቸው እስኪሳካ ድረስ ከቀውስ
ወደ ቀውስ ከመዝለል አይቆጠቡም። መሻታቸው እስኪሟላ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ሽፋን
አድርገው ጥላቻን በሁሉም የሚዲያ አማራጮች ሲቸረችሩ ይገኛሉ። ዓላማቸው ማፍረስ
ስለሆነ ለመክፈል የተዘጋጁት ዋጋ የማፍረስ ዋጋ ነው። የሀገር ሰላምና የሕዝቦች አንድነት
አይገዳቸውም። የፈጀውን ፈጅቶ ነጠላ ቡድናዊ እውነታችን ማሽንፍ አለበት የሚል ነው
አቋማቸው።

አፍራሾች ገንቢዎች የሚሠሯቸውን ሁሉንም ሥራዎች መቃረን መደበኛ ተግባራቸው ነው።


ከትንሽ እስከ ትልቅ ቀውስ ባለበት ሁሉ አሉ፤ የተገኘውን አጀንዳ ሁሉ ለማፍረሻ
ይጠቀሙበታል። ገንቢዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ አሉ፤ ለመገንባት ገና መሠረት መጣል
ሲጀመር መፍረሻ መዶሻቸውን ይዘው በሁሉም የማፍረሻ አማራጮች ይዘምቱብናል።
ከእውነት ጋር ጠበኞች ስለሆኑ የተለመደውን የሤራ ፖለቲካ መርዝ ሲረጩ ትንሽም እንኳን
በሕዝቦች መካከል አብሮነት መስተጋብራችንን ማኅበራዊ መዶሻቸውን አድርገው እንዳይኖር
ለመበጣጠስ ይጠቀሙበታል። በጥቅሉ ጥላቻን በችርቻሮ እና በጅምላ በመሸቀጥ አፍራሾች
አሁን ላይ እየሄዱበት ያለው መንገድ አደገኛ እየሆነ መጥቷል።

ይህን ሀገር የሚገዘግዝ አደገኛ አካሄድ መከላከል የኛ የገንቢዎቹ ወሳኙ ዓላማችን ነው። ለዚህ
የሚከፈለው መሥዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁዎች መሆን አለብን። አፍራሾ የሚሸነፉት
ገንቢዎች ከአፍራሾች ከጠነከሩ፤ ከአፍራሾች በላይ ከወሰኑ ከአፍራሾች በላይ መሥዋዕትነት
ከከፈሉ ብቻ ነው። በምንገነባት ኢትዮጵያ የሁላችንም በላይ የወል እውነት ገዥ ሐሳብ
እንዲሆን፣ ለምንፈልጋት ሀገር ለመክፈል የተዘጋጀነው የገንቢነት ዋጋ ይወስነዋል።

ማፍረስ እንደ መገንባት ከባድ ባለመሆኑ አፍራሾች ለመናጆነት የሚሰበስቡት የሚነዳ ኃይል
በቀላሉ ማሰባሰብ ይችላሉ። መገንባት አድካሚ ነው፤ ደምም ላብም ስለሚፈልግ ጊዜ
ይወስዳል፤ ያደክማል፤ በቀላሉ ኃይል ለማሰባሰብም ይፈትናል። ትውልድ ግንባታ፤ ሀገር
ማስቀጠል፤ ብልጽግናን ማረጋገጥ ወሳኝ ሥራዎቹ የሆነ ፓርቲ ውስጥ ነን። የመናጆ ፖለቲካ
ሳይፈታን፤ ለሕዝብ በመቆርቆር ሽፋን በተለወሰው ሀገር በታኝ የጥላቻ ፖለቲካ ሳንሸነፍ፤
አሰላለፋችን ሳይደበላለቅብን፤ በአመለካከት ሳንሰለብ፤ የወል እውነታችን አሸናፊነትን ወደ
ምናረጋግጥበት ረጅሙ የብልጽግና ጉዞ እስከ መዳረሻው ለመድረስ በትክክለኛው ባቡር ላይ
ተሳፍረናል ወይ? የሚለው የአመራሩና አባሉ ወሳኝ ጥያቄ ነው።

59
በመሆኑም ቀጣይ የፖለቲካ ሥራችን የወል እውነቶቻችን መሠረት የሆኑትን የፍትሕ፤
የነጻነት እና የእኩልነት ፍላጎቶች ምላሽ እንዲያገኙ የሚከተሉት ቁልፍ ፖለቲካዊ
ሥራዎቻችንን በትኩረት የምንሠራባቸው ይሆናሉ።

 የውስጠ ፓርቲ አንድነትን ማጎልበት:- የወል እውነቶቻችን ገዥ ዕሳቤ እንዲሆኑ


የፓርቲያችንን የውስጠ ፓርቲ አንድነት የጠነከረ መሆን አለበት። አስተሳሰባችን፤
አሰላለፋችን፤ አደረጃጀታችን የተሰናኘ ሲሆን ተግባራችን በውጤት የታጀበ ይሆናል።
ውስጣዊ አንድነታችን ሲጠነክር ተቀናቃኞቻችን ቀዳዳ ያጣሉ፤ የሚለያየንን ቀዳዳ
በከፈትን ቁጥር የበለጠ ሊለያዩን ይሠራሉ። ውስጠ ፓርቲ አንድነት ስንል የሐሳብ
ልዩነቶች የማይስተናገዱበት፣ ፀረ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሐሳብ የሚታፈንበት
አካሄድ አይደለም። በዴሞክራሲያዊ መርሐዊነት ውስጣዊ ችግሮቻችንን እየፈታን፤
በመሠረታዊ ተልኮዎቻችን ላይ የጠራ ዐቋም ይዘን፤ በሚፈጠሩ አጀንዳዎች ሁሉ
ሳንጠለፍ ፤ በመንገዳችን ላይ ጸንተን በመቆም፤ የወል እውነቶቻችን ገዥ
የሚሆኑበትን ሥርዓት እየገነባን፤ የውስጠ ፓርቲ አንድነታችንን እያጎለበትን፤
መዳረሻችን ወደሆነው ሁለንተናዊ ብልጽግና መጓዝ ነው።
 ከአንጻራዊ ሰላም ወደ ተሟላ ሰላም መሸጋገር:- ባለፉት አምስት ዓመታት የነጠላ
ቡድናዊ እውነታቸው ከሥርዓታዊ ገዥነት የወደቀባቸው እና አዲስ ነጠላዊ
እውነታቸውን ገዥ ሥርዓት ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች እና የታሪካዊ ጠላቶቻችን
በጋራ ተነሥተውብን ነበር። ተልዕኮ ተቀብለው ሰላማችንን ሲያደፈርሱ የነበሩ
ኃይሎችን በብዙ መልኩ ቢፈትኑንም በተባበረ ክንዳችን ሀገራችንን ከታሰበላት
የመበታተን አደጋ አትርፈናታል። አስገራሚ የልማት ድሎችን እያስመዘገብን
አንጻራዊ የሚባል ሀገራዊ ሰላም እንዲሰፍን አደርገናል። አሁንም ሀገራዊ ሰላማችንን
ለማጽናት መሥመር የያዙት ወደ ኋላ እንዳይመለሱ በማድረግ ወደ ሰላም
ያልመጡትን ኃይሎች ወደ ሰላም ማምጣት አለብን።
 ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳካ መደገፍ:- ሕገ መንግሥታዊነት ለሀገረ መንግሥት ቀጣይነት
መሠረት ነው። የሀገራት ሰላምም ይሁን ብልጽግና የሚወሰነው ዜጎቻቸው በሕገ
መንግሥታቸው ላይ በሚኖራቸው የቅቡልነት ደረጃ ነው። _ ሀገራችን ሕገ
መንግሥታዊነትን መለማመድ ከጀመረች ብትሰነብትም የሕገ መንግሥቶቹ ሥሪት
የሥርዓታት መገለጫ እና ማጽኛ እየሆነ ስለሚዘጋጅ ሥርዓታት ሲቀየሩ አብሮ
እየተቀያየረ አሁን እስካለው ሕገ መንግሥት ላይ ደርሰናል። አሁን ያለን ሕገ

60
መንግሥት እንደ ቀዳሚዎቹ በሥርዓት መቀያየር የመሻር ዕጣ አልገጠመውም።
የመታደስ እና ሁሉንም አካታች የመሆን ዕድል ደርሶታል። ሕገ መንግሥታችን
የሁላችንን የወል እውነት እንዲካተትበት ተደርጎ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ገዥ ሰነድ
እንዲሆን ለማድረግ መሥራት ይገባናል። በመሆኑ ዘላቂ ስላም፤ ኢኮኖሚያዊ እና
ፖለቲካዊ ድሎች የሚጸኑት ቅቡልነት ባለው ሕገ መንግሥት በመሆኑ፣ ሕገ
መንግሥታዊ ቅቡልነት እንዲረጋገጥ በልዩ ትኩረት ፓርቲያችን ይሠራል።
ሀገራዊ ምክክሩ ሰላማችንን ማዝለቂያ፤ ልዩነቶቻችንን ማጥበቢያ፤ የወል እውነቶቻችን
የበለጠ ገዥ ሐሳብ ማድረጊያ፤ ጅምሩ የሀገረ መንግሥት ግንባታን ማጠናቀቂያ
እንዲሆን እንሠራለን። ዛሬም ድረስ ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን መፍቻ መሣሪያ መሣሪያ
ሆኖ ፈተና የሆኑብን በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት ተግባሩን የምንደግፍ
ይሆናል።
 የነጻነት አስተዳደር እና አጠቃቀም ሚዛን መጠበቅ:- ሀገራዊ ለውጡ ከአፈና ወደ
ነጻነት ያደረገው ሽግግር ነጻነትን በአግባቡ የመጠቀም ፈተና እየገጠመው ነው። ነጻነት
እና ተጠያቂነት ትውውቅ የሌላቸው ትውውቅ የሌላቸው በሚመስል መልኩ የሀገር
አንድነት መሠረቶችን ወደ ሚነቀንቅ መሣሪያነት እየተሻገረ ነው።
በመሆኑም ነጻነት ያለ ኃላፊነት ሥርአት አልበኝነት በመሆኑ፣ የአጠቃቀም መዛነፎችን
የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ መሥመር ማስያዝ ያስፈልጋል። የመብት እና
የተጠያቂነትን ሚዛን ሚዛን ስንጠብቅ ስንጠብቅ ዴሞክራሲን ልቅነት አድርገው
ለሚመለከቱ ኃይሎች፣ ዴሞክራሲ ከተጠያቂነት ጋር እኩል ካልተጓዘ ችግር እንዳለው
ማሳየት ይገባል። በመሆኑም በነጻነት ስም የሀገረ መንግሥታችን አደጋ የሚሆኑ
ኃይሎችን በሕግ አግባብ መግራት አለብን። ሀገር ማስቀጠል የፓርቲም፣ የአመራር፣
የዜግነትም ግዴታችን በመሆኑ ሚዛን ያልሳተ ሕግ የማስከበር ዘርፈ ብዙ ሥራ
የምንሠራ ይሆናል።
 የተማከለ የኃይል አጠቃቀም ትግበራን ዳር ማድረስ:- ፓርቲያችን ለመገንባት
የሚያስበው እና እየሠራበት ያለው የሁላችንም የወል እውነቶች ገዥ ሐሳቡ የሆነ
ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ነው። በዚህም የሀገረ መንግሥት ግንባታችን እንዲፋጠን
የኃይል አጠቃቀም ሥርዓት ሀገር በሚያስቀጥል መልኩ መደራጀት አለበት። በዚህም
ምክንያት ሕገ መንግሥታዊ ባልሆነ መልኩ ክልሎች ልዩ ኃይል በሚል ያደራጇቸው
ወታደራዊ ኃይሎች ነጠላ ቡድናዊ እውነታችን ገዥ ሥርዓት ለማድረግ ሲሞክሩ
በተግባር ከትግራይ ክልል አይተናል። ሌሎችም ክልሎች ይህን ሕገ መንግሥታዊ
61
ያልሆነ አደረጃጀት የነጠላ ቡድናዊ እውነታቸው ማስከበሪያ ለማድረግ ሲሠሩ እያየን
ነው። አሁን ላይ ሀገራችን በተግባር ተፈትነው የተደራጁ የፌዴራል የጸጥታ ተቋማት
እየገነባች ናት።
ክልሎች በሕገ መንግሥቱ በተሰጣቸው ሥልጣን መሠረት የክልል ፖሊስ እና ሚሊሻ
ብቻ እንዲያደራጁ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል። የወል እውነቶቻችን ገዥ የሆኑበትን
ሥርዓት ለመገንባት የኃይል አጠቃቀም ሥርዓት መያዝ የግድ የሚልበት ወቅት ላይ
እንገኛለን። በመሆኑም በተወሰነው ውሳኔ መሠረት የክልል ልዩ ኃይሎችን በማፍረስ
ወጥ የሆነ የኃይል አጠቃቀም ተግባራዊ ማድረግ በምንም ምድራዊ ኃይልም ሆነ
ምክንያት ወደኋላ የምንመልሰው ተግባር አይደለም። ባስቀመጥነው አቅጣጫ
መሠረት በአጭር ጊዜ ተፈጻሚ እንዲሆን መረባረብ ይኖርብናል።
 የተደራጁ ወንጀሎችን መከላከል:- የፀረ ሙስና ትግል እንደ ሀገር ከጀመርን ወዲህ
አንዳንድ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ። ነገር ግን ከችግሩ ስፋት አንጻር በቂ
አይደሉም። ሌብነት ግለሰቦችን እና ቡድኖች ብቻ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎ
የሚያቆም ጉዳይ አይደለም። በጊዜ ሂደት በሌብነት የተሰባሰበ ኃይል ወደ ሥርዓት
ነጠቃ በመግባት ለሀገረ መንግሥት ጠንቅ የመሆን ዕድል ሊፈጥር ይችላል።
በተጨማሪም ሙሰኞች የተንሰራፉበት ሀገር እና ሥርዓት የነጠላ ቡድናዊ እውነቶች
የበላይ እንዲሆነ ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ይፈጥራሉ። ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዐቅሙን
ያጠናከረ ቡድናዊ ኃይል ፍላጎቱን የሥርዓቱ ገዥ ሐሳብ ለማድረግ መታገሉ
አይቀርም። ስለዚህም የፀረ ሙስና ትግላችንን ኢኮኖሚያዊ ብቻ አድርገን ሳንመለከት
የሀገረ መንግሥታችን ፈተና እንዳይሆን ልንሠራበት ይገባል።

VI. ማጠቃለያ

የለውጡ ተስፋ ሀገራችንን ወደ ተረጋጋ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የብልጽግና ሥርዓት


ለመውሰድ ጉዞ ከጀመረ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል። በእነዚህ የለውጥ ዓመታት ለውጡ
ይቅር ባይነትንና ወደፊት መመልከትን መርሑ በማድረግ፣ በታሪክ በታሪክ ላይ
የመንጠልጠልንና የመጠፋፋትን ፖለቲካ በመተው፤ ፉክክርንና ትብርን በሚዛን በመምራት፤
ውይይትንና ድርድርን በመጠቀም የሰከነ ፖለቲካ ለማካሄድ ሞክሯል። ሆኖም ማንኛውም
ነባራዊ ሁኔታን በመቀየር አዲስ የተሻለ ሥርዓትን ለመፍጠር የሚደረግ ጥረት ከነጠላ
ቡድናዊ የበላይነት ሥርዓት ሲጠቀሙ ከነበሩ ቡድኖች ተግዳሮት ይከሠትበታል። ይህንን

62
የለውጥ መሠረታዊ ባህርይ በመረዳት ግጭትን ለማስቀረት የተደረገው ይቅር ባይነት
ደካማነት መስሎ የታያቸው ኃይሎች አሉ። እነዚህ ኃይሎች ዓይነት ብዙ ቀውሶች በመጥመቅ
የነጠላ ቡድናዊ የበላይነታቸውን ለመመለስ ጥረት አድርገዋል።

ባለፉት አምስት ዓመታት የገጠሙን ፈተናዎች ዋነኞቹ የአስተሳሰብ ለውጣችንን (ፓራዳይም


ሺፍት) ለመቀልበስ የተደረጉ ናቸው። በአንድ በኩል ነባሩን የነጠላ ቡድናዊ እውነት
ገዥነትን ባለበት ለማቆየት ፤ በሌላ በኩል አዲሱን የሁሉም የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች
እና ሕዝቦች ሁለንተናዊ የወል እውነቶች ገዥ ሥርዓታዊ ዕሳቤ ለማድረግ የሚካሄድ ትንቅንቅ
ነው። ይህ ትግል ለዘመናት የሀገራችን ሥርዓተ መንግሥታት መለያ የሆነውን የነጠላ
ቡድናዊ የበላይነትን የማስጠበቅ እና የፍትሐዊ ተጠቃሚነት እና የእኩልነት የከረመ ጥያቄ
ያላቸው ሕዝቦችን ፍላጎት በወል እውነት ምላሽ እንዲያገኝ የማድረግ ትግል ነው።

ባለፋት ወራት በነበረው የፀረ ሙስና ትግላችን የሚታዩ ክፍተቶችን የሚሞላ የድርጊት
መርሐ ግብር በድጋሚ ማዘጋጀት አለብን። በሁሉም ክልሎች ወጥነት ያለውና ገዘፍ ያሉ
ሌብነቶችን የሚይዝ መሆን አለበት። በስፋት በቅንጅታዊ አሠራር በታገዘ መልኩ ውጤቶችን
ለማስመዝገብ መሥራት ይኖርብናል። በግራም በቀኝም ያሉ ሌቦች ሲነኩ የብሔር
ከረጢታቸው ውስጥ ለመወሸቅ ጥረት ማድረጋቸው አይቀርም፤ ነገር ግን ሥራችን በመረጃና
በማስረጃ የተረጋገጠ እንዲሆን በማድረግ ሌቦችን መደበቂያ ዋሻ ማሳጠት ያስፈልጋል።
ሂደቱን በሚገባ ግልጽ በማድረግና ሌቦቹን በማጋለጥ ሌብነትን ከልባችን ተጸይፈን ሌቦችን
የምንታገል ስብስቦች እንደሆንን በማስመስከር ሕዝባዊ ቅቡልነታችንን ማሳደግ ይገባል። ይህ
ሲደረግ ግን ጉዳዩ ከግለሰብ እስከ ቡድን የመጠቃቂያ፤ ንጹሐንን የመበቀያ መሣሪያ አድርጎ
የመጠቀም ዕድሎች እንዳይኖሩ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ዲስፕሊን ሊመራ ይገባዋል።

የወል እውነታችን ሥርዓታዊ መሪነት እንዳይኖረው፣ ዘላቂ ቀውስ ውስጥ እንድንገባና ነጠላ
ቡድናዊ የበላይነታቸውን ዳግም ለማንገሥ ጦርነት የገጠሙን ኃይሎች ድል ሆነዋል።
በደማችን ያገኘነውን ድል ዘላቂ ለማድረግ በላባችን ትርጉም ወዳለው የሰላም ስምምነት
ተሸጋግረናል። በየክልሎች ነፍጥ አንሥተው ከሚታገሉ ኃይሎች ጋር ችግሮችን በንግግር
እየፈታን ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ የተሐድሶ ኮሚሽን አቋቋመን እየሠራን ነው።
ከታጣቂ ኃይሎች ጋር የተጀመረው የሰላም ንግግር በውጤት እንዲጠናቀቅ በማድረግ ዘላቂ
ሀገራዊ ሰላም የምናሰፍን ይሆናል። የወል እውነቶቻችን መሠረት እንዲይዙ፤ የሕግ
የበላይነትን ማረጋገጥ፤ የተማከለ የኃይል አጠቃቀም ማስፈን፤ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን

63
ተግባራትን ማሳለጥ፤ ቅቡል የሆነ ሕገ መንግሥታዊነት መፍጠር፤ ቀጣይ ተግባሮቻችን
ናቸው።

በበሰሜኑ ጦርነት እንድንሸነፍ፣ በተፈጥሮ ሀብታችንም እንዳንጠቀም ግንኙነታችን ተግዳሮት


ኃይሎች የተነሣ የውጭ በሚፈልጉ እንዲገጥመው ሆኗል። የቀደመው ዕሳቤያችን የሆነውን
‹ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ የማምጣት አቋማችንን በሰላም ስምምነቱ ተጨባጭ
ውጤት አይተንበታል።

የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ያልተሻገርናቸው ፈተናዎች ናቸው። በድርብርብ ጫናዎች


ውስጥ ሆነን፣ ጠላቶቻችን ኢኮኖሚያችንን በመስበር፣ እንደ ሀገር ሊያዳክሙን ቢሠሩም፤
እንዳሰቡት ሳይሆን ተጨባጭ እመርታዊ ውጤት ኢኮኖሚያችን አስመዝግቧል። ነገር ግን
ከኮሮና እስከ ዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ያሉ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በኢኮኖሚያዊ ምኅዳሩ
ላይ ብዙ መናጋቶች እንዲፈጠር አደርገዋል። ሀገራችንም ችግሩን ለመቋቋም እየሠራች
ቢሆንም፤ ተጽዕኖ መፍጠሩ ግን አልቀረም። በተለይም ከተሞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ
ላይ የሚገኙ ዜጎች የችግሩ ቀዳሚ ተጎጂ ሆነዋል።

በጥቅሉ የቀጣይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትኩረቶቻችን ማዕከሎች ማስቀጠል፤ ማምረት


እና ማስተዳደር ይሆናሉ፤

ማስቀጠል፡- በብዝኃ ኢኮኖሚ ፖሊሲያችን ያስመዘገብነውን ጥቅል ኢኮኖሚያዊ ዕድገት


በዚህ ዓመትም መድገም ይጠበቅብናል።

በፖለቲካዊ የማስቀጠል ተልዕኳችን ሰላምን ዘላቂ የማድረግ ሥራችንን ወደ ተሟላ ሀገራዊ


ሰላም በማንኛውም አማራጭ ማረጋገጥ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይሆንም።

ማምረት፡- ኢኮኖሚያዊ ዕድገታችንን ለማስጠበቅ ምርታማነት ወሳኝ ነው። የብዝኃ ዘርፍ


ምርታማነት በተለይም የስንዴ ምርታማነት ዓመታዊ ግባችንን ማሳካት፤ የኑሮ ውድነት ዋነኛ
ማረጋጊያ የሆነውን ሥራዎቻችንን ያለምንም መንገራገጭ ወደ የሌማት ትሩፋት
ውጤታማነት እንዲቀየሩ በልዩ ትኩረት መሥራት ይጠበቅብናል።

በፖለቲካዊ ምርታማነታችን ቀጣይ ተልዕኳችን የመድብለ ፓርቲ ጅምር ሥራዎችን


ማስፋት፤ በውስጠ ፓርቲ ምርታማነታችን የአባላት ምልመላ እና የአመራር ብቃት ከቁጥር
የተሻገረ ማድረግ፤ ብልጽግናዊ ዕሳቤን ተላብሶ ቃሉ ከተግባሩ የተሰናኘ አመራር ማምረት
ቁልፍ ተግባራችን ነው።

64
ማስተዳደር፡- ኢኮኖሚያዊ ኢኮኖሚውን ማስተዳደር ዋና ችግራችን ነው። በመሆኑም
የተመረተን ምርት ደረጃውን ጠብቆ ተጠቃሚው ጋር እስኪደርስ ያለው በደላላ የሚመራ
የንግድ ሰንሰለት ለዋጋ ንረት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ ነው። በመሆኑም የንግድ ቁጥጥር
ሥርዓታችንን ከፌዴራል እስከ ቀበሌ በመፈተሽ ጉድለቶችን መሙላትና ገበያውን ከደላላ
መዳፍ ማውጣት ይገባናል። ኢኮኖሚያዊ አሻጥር፣ ኮንትሮባንድ፣ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር
እና ምርት ሥወራ ኢኮኖሚ የማስተዳዳር ተግዳሮቶች ናቸው። በዚህም ምክንያት የገበያ
አለመረጋጋት አሁን ካለበት እንዲያድግ እንዲያድግ በር ይከፍታል። በመሆኑም በጥናት
ላይ የተመሠረተ ሥር ነቀል አስተማሪ ርምጃዎች እንወስዳለን።

ፖለቲካዊ ማስተዳደርን በተመለከተ፣ ከቀጣይ ተልዕኳችን መካከል የነጻነት አስተዳደር እና


አጠቃቀምን ሚዛን ማስጠበቅ አንዱ ነው። በጥላቻ ፖለቲካ የሀገር ቀጣይነት ፈተና ውስጥ
እንዳይገባ ሕገ መንግሥታዊ የሕግ የበላይነት፣የሀገራዊ ሰላም ዘላቂነት፣ ዴሞክራሲያዊ እና
እና ሰብአዊ መብቶችን በሚዛኑ ሀገር በሚያስቀጥል አግባብ ማስተዳዳር ይገባል። የማኅበራዊ
ሚዲያም የብሮድካስት ሚዲያዎችም የነጠላ ቡድናዊ የበላይነት አጀንዳ ሸቃጮች መጠቀሚያ
እንዳይሆኑ ሕጋዊ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ መግራት ይገባል።

የውስጠ ፓርቲ ምርታማነትን በማስጠበቅ ሠርጎ ገቦችን በማጥራት ፓርቲያችንን ከውስጥ


የመጥለፍ ተልዕኮ አንግበው የሚንቀሳቀሱ የውስጥ ባንዳዎችን የማጽዳት ሥራ ይሠራል።
የፖለቲካ አጀንዳ መሸጫ ሚዲያዎች ላይ ስኬቶቻችን መሸጥ፤ አጀንዳ መስጠት፤ ማሳካት
ለምንፈልገው ጉዳይ የትርክት የበላይነት ለማያዝ መሥራት ዋነኛ ሥራችን ይሆናል።

ፖለቲካን የማስተዳዳር ሥራችን የሁላችን የሆነውን የወል እውነታችን ገዥ ሥርዓታዊ ዕሳቤ


እንዲሆን ለማድረግ መሥራት ነው። የወል ገዥ እውነታችን የተጋረጡበትን አደጋዎች
መከላከል፣ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ የበላይነት ይዘን ኅብረ ኅብረ ብሔራዊ
አብሮነታችን ቀጣይነቱ እንዲሠምር ማድረግ፤ የወል እውነቶቻችን አሸናፊ ሆነው፣ የነጠላ
ቡድናዊ ፍላጎታቸውን የበላይነት ለማስያዝ በሚሠሩ ኃይሎች ላይ የአጀንዳ እና የትርክት
አስተዳዳር የበላይነት እንዲኖረን መሥራት ይገባናል።

በፍጥነት እና በፈጠራ ሁለንተናዊ ምርታማነታችንን ለማስቀጠል መትጋት አለብን። በቀረን


የምርጫ ዘመን ለሕዝባችን ቃል የገባናቸውን ተግባሮች የምንፈጽምበት ጅምር
ፈጠራዎቻችንን ለማሰናከል ከታሪ የሆኑ ኃይሎችን የምንፋለምበት ነው። ይበልጥ በመፍጠን
እና በመፍጠር በቅንጅት ወደ ምናልመው ድል የምንገሠግሥበት ነው። ብልጽግና የሐሳብ

65
ፓርቲ ነው። ሁሌ ያስባል። ያሰበውን በፍጥነት ይተገብራል። የተገበረውን ዘላቂ ሀገራዊ
ብልጽግና አረጋጋጭ ዐቅም እንዲሆን ይሠራል። ሁሌም መፍጠን፤ሁሌም መፍጠር ከጊዜያዊ
ችግሮች በላይ ከፍ ብሎ መጓዝ ይገባናል። እንደ ተራራ የገዘፉ ችግሮችን ያለፈ ፓርቲ
በቋጥኞች አይደናቀፍም። በመሆኑም በፍጥነት እና በፈጠራ ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና
መጓዝ ቋሚ ርእያችን ነው። በጋራ ትግላችን ከርእያችን ለመድረስ የሚያግደን ምድራዊ
ኃይል አይኖርም።

ሀገር የትውልድ ቅብብሎሽ ውጤት ነች። ሁሉም ትውልድ በጊዜ፣ በቦታ እና በሁኔታ
ምሕዋርነት ከነጉድለቱ እና ሙላቱ ሲቀባበላት እኛ እጅ ላይ ደርሳለች። በመሆኑም
ሀገራችንን ጉድለቷን ሞልተን፣ ብልጽግናዋን እውን ለማድረግ እየተጋን እንገኛለን። ጉድለት
ስንሞላ የትናንትን ስብራት ለመጠገን እንጂ ዳግም ለመስበር አይደለም። ለዚህ ነው የሥርዓት
ስብራቷ መገለጫ የሆነውን ዘመናትን ያስቆጠረውን የነጠላ ቡድናዊ እውነት ሥርዓታዊ
የበላይነት በማስወገድ ፤ የሁላችን እውነት ገዥ ሥርዓታዊ ዕሳቤ እንዲሆን የምንሠራው።
ይህ አካሄዳችን የነጠላ ቡድናዊ የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ በሚፈልጉ ኃይሎች ተፈትኗል።
ከባድ የሆኑ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ተጋፍጠናል። ዓላማችን ሐቀኛ በመሆኑ
በድል አልፈናቸዋል።

66

You might also like