You are on page 1of 38

የጥናትና ምርምር ምክረ ሐሳብ

አዘገጃጀት
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስትያን ማኀበረ ቅዱሳን የጥናትና
ምርምር ማእከል
የሥልጠናዉ ዓላማ
• ሠልጣኞች ስለ ምክረ ሐሳብ አዘገጃጀት ያላቸውን ግንዛቤ
ለመጨመር

• ሠልጣኞች የተለያዩ ምክረ ሐሳቦችን በማዘጋጀት


ጥናትና ምርምር አካሂደዉ የቤተ ክርስትያንን ችግር
እንዲፈቱ ለማገዝ
መግቢያ፡ ምርምር
ትርጉም
• ምርምር ለሰው ልጆች አልተከለከለም። ኹሎ አመክሩ ወዘሠናየ
አጽንኡ፡ ኹሉን መርምሩ መልካሙን ያዙ ፩ ተሰ ፭: ፳

• ሥርዓት ያለው በቁጥጥር ሥር የዋለ ሳይንሳዊ የመላምቶች ፍተሻ ነው


፡፡

• ጥናትና ምርምር በሳይንሳዊ ዘዴ ለችግር መፍትሔ ለማፈላለግ፣


አዳዲስ ግኝቶችን ለመፍጠር፣ ተጨማሪ ዕውቀትን ለማግኘት፣
አስፈላጊውን ዉህብ (data) ይዞ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት
የሚያስችል ዐቢይ ተግባር ነው ፤
መግቢያ.....
• ምርምር ለምን
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያላትን
እምቅ ሀብት በአግባቡ ጠብቆ ለመያዝ፤

• ለቤተ ክርስቲያን ውሳጣዊና ውጫዊ ችግሮች መፍትሔ


ለመሻት፣

• ቤተ ክርስቲያኗን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን


ለማስቻል ፡፡
ምርምር ከዐላማ/ግብ አንጻር በሦስት
ይከፈላል
አ. ተግባራዊ ምርምር(Applied Research)
• የገጠመን ችግር ለመፍታት ወይም ለአንድ ለተወሰነ
ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት
• ለተከሰተ ችግር መፍትሔ መሻት
• ችግር ምርምር መፍትሔ
• ድርጊታዊ ምርምር (Action Research)፡ በሥራ
ሒደት ለሚጋጥሙ ችግሮች ባሉት ባለሙያዎች
መፍትሔ መፈለግ.
የቀጠለ …
• ችግሩ መኖሩን ማወቅ ችግሩን ማብራራት
ለችግሩ ምክንያት ሊኾኑ የሚችሉ ነገሮች ውህብ
መሰብሰብ የመፍትሔ ሐሳቦችን መለየት
የመፍትሔ ሐሳቦችን ተግባራዊ ማድረግ
ውጤታማነታቸውን መገምገም የተገኘውን
ውጤት መተርጐም ንድፈ ሐሳብ
በ. መሠረታዊ/ንድፈ ሐሳባዊ ምርምር
Basic/Fundamental/Pure/Theoretical Research
• የዕውቀት ጥማት ለማርካት፤ በአእምሮ ውስጥ ለሚጉላሉ
ጥያቄዎች መልስ መሻት
• ዐዲስ ንድፈ ሐሳብ ለማፍለቅ
• እስካኹን የሰው ልጅ ያልተረዳቸውን
• ተግባራዊ ምርምር ንድፈ ሐሳብ/ዐዲስ ዕውቀት
• ከተገኘው ዐዲስ ዕውቀት/ንድፈ ሐሳብ ተመሥርቶ
ችግሮችን ለመፍታት ይችላል
ምሳሌ፡ ምእመናን እንዴት ቢማሩ ሥጋ ወደሙ ሊቀበሉ
ይችላሉ?
ገ.ገምጋሚ ምርምር (Evaluation Research)

• በአንድ በተወሰነ ቦታ የሚከናወን/ተግባራዊ በመደረግ


ላይ ያለ መርሐ ግብር፤ ፖሊሲ፤ መሥሪያ ቤት
ውጤታማ መኾኑ አለመኾኑ
ምሳሌ፡ የቃለ ዐዋዲ በአጥቢያዎች አተገባበር ምን
ይመስላል?
• ግቢ ጉባኤያት በመሰጠት ያለው ሥርዐተ ትምህርት
እንዴት እየተተገበረ ነው? ሰንበት ት/ቤት፤ ጥናትና
ምርምር ማእከል፤ ማኅበረ ቅዱሳን በሚፈለገው ዐላማ
እየሔደ ነው ወይስ?
የቀጠለ …ዐላማዎችና ተግባራት
• ዐዲስ መርሐ ግብር ለመጀመር የሚያስችል መረጃ
ለማግኘት
• በሒደት ላይ ስላለ መርሐ ግብር ለውጥ
ለማድረግ/ለማሻሻል የሚያስችል መረጃ ለማግኘት
• ቀጣይነትን፤ማስፋፋትን እንደ አስፈላጊነቱም አንድን
መርሐ ግብር ለመንቀፍም ኾነ ለመደገፍ
• ውጫዊ ተፅዕኖዎችን ለመረዳት
ለምሳሌ፡ የክህነት አሠጣጥ ምን ይመስላል?
የቀጠለ …
• ከሒደት እና ከሚሰበሰቡት የውህብ ዐይነቶች ገምጋሚ
ምርምር በኹለት ይከፈላል።
አ. ሒደታዊ ግምገማ (Formative Evaluation)
• በየዕለቱ የሚካሔደውን ለውጥ ለመረዳት
• የናሙና አመራረጡ ዐላማ ተኮር (purposive)
በ. ማጠቃለያ ግምገማ (Summative Evaluation)
• መርሐ ግብሩ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ከኾነ በኃላ
• ለምሳሌ፡ የግቢ ጉባኤ ሥርዐተ ትምህርት
• የአንድን መርሐ ግብር ብቃት (effectiveness) ለማረጋገጥ
Cont…
• On the basis of how deep they go in their
investigative power
• A. Exploratory
• B. Descriptive
• C. Explanatory
ከሚሰበሰበው የውህብ ዐይነቶች እና
የአተናተን ዘዴዎች
• ከሚሰበሰበው የውህብ ዐይነት ምርምር በኹለት ዐበይት
ክፍሎች ይከፈላል
1. መጠናዊ/አኀዛዊ ምርምር (Quantitative Research)
• መጠን ገላጭ፤ በቊጥር የሚገልጽ
• በአብዛኛው ውህብ የሚተነተነው ስታቲስቲካዊ በኾነ
መንገድ ነው
• በተለዋዋጭ መካከል ምክንያታዊ ተዛምዶና ተፅዕኖ
ለምሳሌ፡ ሥጋ ወደሙ እንዳንቀበል ተፅዕኖ የሚያደርጉብን
ተለዋዋጮች
2. ዐይነታዊ ምርምር (Qualitative Research)
• በዐይነት የሚገለጽ
• ትረካዊ/ገላጫዊ መንገድ ይጠቀመል
• በጥልቀትና በስፋት ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመዳሠሥ
• የተመራማርውን አርቆ አሳቢነት/አስተዋይነት ይጠይቃል
• ትክክለነቱ ከመጠናዊ ምርምር አንጻር አናሳ ነው
• ተፈጥሯዊ ምልክ ያለው ነው፤
– ምልከታ ማከሔድ፡
– ያዩትን መገንዘብ፡
– የተገነዘቡትን በተገቢ መንገድ መግለጽ
• ማጠቃለያ ለመስጠት ያስቸግራል
• ዐላማ፡ ችግር ፈች፤ የውሳኔ ሐሳብ ለማግኘት
ይዘት
፩. ርእስ አመራረጥ (Title Selection)
፪. ጥናታዊ ዳራ (Background)
፫. የችግሩ ትንታኔ (Statement of the problem)
፬. የጥናቱ ዓላማ (Objectives)
፭. የጥናቱ አስፈላጊነት (Significance)
፮. የተዛማጅ ጽሑፍ ዳሠሣ ማካሄድ (Literature Review)
፯. ናሙና መምረጥ (Sample Selection)
፰. የተለያዩ የዉህብ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን መምረጥና ማዘጋጀት
(Data Collection Methods)
፱. የዉህብ የትንተና ዘዴ (Data Analysis Methods)
፲. የድርጊት መርሐግብር (Work plan)
፲ ፩. የጥናቱ በጀት (Budget)
፲፪. የማጣቀሻ (ዋቢ) ዝርዝር (References)
. ርእስ አመራረጥ (Title Selection)
• ችግር ወይም ጉድለቶች ናቸዉ
• የጥናት መነሻ ችግሮች ምሳሌዎች
– የካህናት እጥረት
– የፋይናንስ እጥረት
– የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት
– የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ጫና
– የሰንበት ትምህርት ቤቶች ግጭት ወዘተ
የርእስ አመራረጥ…
• ርእሱ ግልጽ መሆን አለበት
• ሊደረስበት የሚችል መሆን አለበት
• ችግር ፈች መሆን አለበት
ምሳሌ
– የሰ/ት/ቤቶቻችን ችግሮች ከየት ወደ የት
– የስብከተ ወንጌል አሠጣጥ ጉድለቶች
. ጥናታዊ ዳራ (Background)

 እንደመነሻ ሐሳብ የጥናቱን ርእስ አስፈላጊነት ለምን


እንደ ተመረጠ ማስቀመጥ
 ነባር መዛግብትን (documents) መዳሰስ
(literature review)
ጥናታዊ ዳራ…. ምሳሌዎች
• ሰ/ት ቤቶቻችን ባለፉት አምስት ዓመታት ዉስጥ  %
አባላት ቀንሰዋል

 / የሰ/ት ቤት አባላት መንፈሳዊ ሥርዐተ ትመህርት


(Course) አልወሰዱም

  % የሚሆኑ አድባራትና ገዳማት መተዳደሪያ


የላቸዉም ወዘተ
. የችግሩ ትንታኔ (Statement of the problem)

• የችግሩን ምንነት
• የችግሩን መንስኤ
• የችግሩን ጉዳት ግዝፈት
• ችግሩ ያስከተለዉን ጉዳት ማስረዳት
. የጥናቱ ዓላማ (Objectives)
• ዓላማ ማለት የጥናቱ ዉጤት መድረሻ ነዉ

• ይህም በሁለት መልኩ ሊቀመጥ ይችላል

– ጥቅል ዓላማ (general objective)

– ዝርዝር ዓላማዎች (specific objectives)

• ብዛቱ እንደየጥናቱ ቢለያይም የዝርዝር ዓላማ


ከሶስትባይበልጥ ባለሙያዎች ይስማሙበታል
የዓላማ ምሳሌዎች
• ጥቅል ዓላማ (general objective)
• የሰንበት ትምህርት ቤቶቻችንን ችግሮች በመረዳት
የመፍትሔ ሐሳቦችን ማመንጨት

• ዝርዝር ዓላማዎች (specific objectives)


• የሰ/ት/ት ቤቶችን ችግሮች መለየት
• የሰ/ት/ቤቶቻችንን ግጭቶች መንስኤ መገንዘብ
• የመፍትሔ ሐሳቦችን መዘርዘር
. የጥናቱ አስፈላጊነት (Significance)
• በዚህ ሥር ጥናቱ ለምን እንደሚጠቅም

• ለነማን እንደሚጠቅም መዘርዘር ነዉ

ምሳሌ
– ሰንበት ት/ቤቶቻችን ከነበረባቸዉ ችግሮች እንዲላቀቁ መንገድ ይከፍታል

– በቤተ ክርስትያን ሓላፊዎችና ሰንበት ት/ቤቶች መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዲኖር


ዕድል ይፈጥራል ወዘተ
፮. የተዛማጅ ጽሑፍ ዳሠሣ ማካሄድ
• ከምርምሩ ርእስ ጋር ተዛማጂነት ያላቸውን
መዛግብት መምረጥ
• ከርእሱ ጋር በምን መንገድ እንደሚዛመዱ በተገቢው
መልክ ሂስ ወይም ትችት ማካሄድ
• ለጥናቱ ቁልፍ የሆኑ ምነጮች ምንድን ናቸው?
መጻሕፍት፡ የመርምር መጽሔትና ዘገባ
• ዐቢይ ጉዳዮችና ተመራማሪዎች ትኩረት
የሚሰጡባቸው ነጥቦች
የተዛማጅ ጽሑፍ ዳሠሣ ጠቀሜታዎች
• የምርመሩን ርእስ ለመወሰንና ለማብራራት
• ያልታሰበና አላስፈላጊ ድግግሞሽ ለማስቀረት
• ምርምሩ ቀድመው ከተካሄዱ የምርምር ሥራዎች
የሚኖረው ግንኙነት
• ምርምሩን ለማካሄድ የሚያስችሉና ለመረጃ
መሰብሰቢያ የሚሆኑ ዘዴዎችን ለመምረጥ፡
ለማዘጋጀትና ለመወሰን
፯. ናሙና መምረጥ
• የናሙና ዘዴ…...ናሙናና እክብ
• ፪ ዐበይት ዓይነት የናሙና ዘዴ
– እድል ሰጪ ናሙና
– ወሳኝ ናሙና
፰. የተለያዩ የዉህብ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን
መምረጥና ማዘጋጀት (Data Collection
Methods)
• የጽሑፍ መጠይቅ
• የቃል መጠይቅ
• ምልከታ
• መዛግብት
• የተለያዩ ፈተናዎች
• ቡድን ተኮር ውይይት
የመጠይቅ አዘገጃጀት
• መጠይቅ ዋነኛ የዉህብ ማሰባሰቢያ መሣሪያ ነዉ
• መጠይቅን በመበተን ወይንም ይዞ ፊትለፊት
በመጠየቅ የምንፈልገዉን ዉህብ መሰብሰብ
እንችላለን
 ዓይነት መጤጠቅ አለ
.ክፍት የሆነ ምላሽ የሚሻ (Open Ended)
. ክፍትና የተሰናዳ ምላሽ ያለዉ (Semi
Structured)
. ዝግና ምርጫዎችን ያቀረበ (Closed Ended)
.ክፍት የሆነ ምላሽ የሚሻ (Open
Ended)
• ምሳሌ
• የሰ/ትቤቱ አባላት ብዛት ስንት ነዉ?
• የሰንበት ት/ቤቱና የቤተ ክርስትያን አሰተዳዳሪዎች
ግንኙነት ምን ይመስላል?
. ክፍትና የተሰናዳ ምላሽ ያለዉ (Semi
Structured)
• ሰንበት ት/ቤቱ መቼ ተነሠረተ?
• ከተመሠረተ ጀምሮ በየዓመቱ የአባላት ብዛት ምን
ይመስላል?
• ሰንበት ት/ቤቱ ከአስተዳዳሪዎች ጋር ያለዉ ግንኙነት
. መልካም ነዉ . መጥፎ ነዉ . አንስማማም
. ዝግና ምርጫዎችን ያቀረበ (Closed
Ended)
• ይህ ምርረጫን ብቻ ማቅረብ ነዉ
• የሰ/ት ቤቱ መሠረታዊ ችግሮች ምን ምን ናቸዉ?
. የአባላት መቀነስ
. የገንዘብ እጥረት
. የእርስ በርስ ግጭት
. የመማሪያ ቦታ እጦት
ቃለ መጠይቁን ለማካሄድ
• ማንን ቃለ መጠይቅ ለመጠየቅ እንደሚፈልጉ አስቀድመው
መወሰን

• የጥያቄዎችን ዝርዝር ያዘገጁ

• ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉበት ቦታ ይምረጡ

• ቃለ መጠይቅ ማድረግና ሐሳቦችን መመዝገብ

• በመሐል የሚጋጩ ሐሳቦችን ለይቶ መጠየቅ


፱. ዉህብ ትንተና ዘዴዎች (Data
Analysis Methods)
• ቅድመ … ተግባራት
– የምላሽ ማጣራት
– ውሁቡን በአኀዝ መሰየም
• ድኅረ…. ዘዴዎች
– ስታቲስቲካዊ ውህብ መተንተኛ (ገላጭና ድምዳሚ)
– ዓይነታዊ ውህብ መተንተኛ
የጥናትና ምርምር ዉህብ(data) አሰባሰብ
ዘዴ
. ምልከታ (direct observation)

. መጠይቅ (questionnaire)

. ቃለ መጠየቅ (interview)

. በዉይይት /discussion/focus group discussion)

. በዳሰሳ (review of documents)


. የድርጊት መርሐግብር
• የሥራዉን ዝርዝር በክንዉን ጊዜ መበጀት ነዉ
ተ.ቁ የሥራዉ ዝርዝር የክንዉን ጊዜ ምርመ

 ምክረ ሐሳቡን ማጽደቅ መስ  ዓ.ም
 ከባለድርሻ አካላት ጋር ጥቅ  ዓ.ም
መወያየት
. የጥናቱ በጀት (Budget)
በዚህ ሥር
• የሰዉ ኃይል፡
• የቁሳቁስ ግዥ፡
• የትራንስፖርትና መሰል ወጪዎች ይቀመጣሉ
• ግምታቸዉ ትክክል መሆን አለበት
• መጠባበቂያ ከ - በመቶ ይያዛል
የበጀት ቅጽ
ተ. ዓይነት መለኪያ መጠን ያንዱ ጠ/ዋጋ
ቁ ዋጋ
 ወረቀት ደስጣ   

 መጓጓዣ ኪ.ሜ   

 አበል ቀን   

 መጠባበቂያ %
. የማጣቀሻ (ዋቢ) ዝርዝር
(References)
• የተጠቀምናቸዉን መዛግብት (Documents)፤
መጽሔቶችና መጻሕፍት በዝርዝር ማስቀመጥ
አለብን
• የጽሑፉን ርእስ፤ ደራሲዉን (ድርጂቱን)፤ዓመቱንና
አሳታሚዉን መግለጽ ያስፈልጋል
ምሳሌ፡
– ሐመረ ተዋሕዶ ቁ.  ገጽ ፵፳-፶፷፣ ማኅበረ ቅዱሳን  ዓ.ም
ዐዲስ አበባ
ማጠቃለያ
• ምርምር የቤተ ክርስቲያናችንን ችግሮች ለመፍታት ያግዛል

• እያንዳንዳችን ድርሻችንን እንወጣ

• ለሚቀጥለዉ  ቀናት አንዳንድ ምክረ ሐሳብ አዘጋጅታችሁ


አስረክቡ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

You might also like