Professional Documents
Culture Documents
የአብክመ ከተማና መስረተ ልማት ቢሮ
የአብክመ ከተማና መስረተ ልማት ቢሮ
ዋና ዋና መልዕክቶች
ነሐሴ 2014 ዓ.ም
ባህር ዳር -ኢትዮጵያ
አሸባሪው ህወሃት የከፈተብንን ጦርነት አስመልክቶ
ለህዝቡ ማስጨበጥ ያለብን
ዋና ዋና መልዕክቶች
ያዳነ ነበር
➢ በዚህ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ህወሃት ዋነኛ ተሳታፊና የትግራይ ህዝብም የለውጡ ተጠቃሚ
እንዲሆን ያልተደረገ ጥረት የለም፣
የቀጠለ…..
የቀጠለ……
ይሁን እንጂ አሸባሪው ህወሃት ከለውጡ መነሻ ጀምሮ የማደናቀፍና አገር የማፍረስ
ተልዕኮ ይዞ ሲንቀሳቀስ ነበር፣
➢ ከጅምሩ ለውጡ እንዳይሳካና እንዲደናቀፍ የተለያዩ መሰናክሎችን ሲፈጥር
ቆይቷል፡፡
➢ ለውጡን በተመለከተ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ህዝቡ በለውጡ ላይ
ጥርጣሬ እንዲያድርበት የቻለውን ሁሉ ቢሞክርም አልተሳካለትም፣
➢ የሽግግር መንግሥት መቋቋም አለበት በሚል በግራ በቀኝ ቢወተውትም ሰሚ
ሳያገኝ ቀርቷል፣
➢ ቡድኑ መቀሌ መሽጎ የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠል
ሙሉ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል፣
➢ ከፌደራል መንግሥቱ ተነጥሎ የራሱን ህገወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ
ለማድረግም ሞክሯል፣
➢ በአገሪቱ ጽንፈኛና አክራሪ ሀይሎችን በማደራጀት፣ በማሰልጠን፣ በሎጀስቲክስ
በመደገፍና በማሰማራት በመላው አገሪቱ ህይወት እንዲጠፋ፣ ንብረት
የቀጠለ……
ዜጎች እንዲፈናቀሉና የህዝብ ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ሲያደርግ
ቆይቷል፣
በተለያዩ አካባቢዎች የተቀናጀ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፈጸም የአገሪቱን ኢኮኖሚ
ለማሽመድመድ በርካታ ጥረቶችን አድርጓል፣
ከላይ ከተገለጹት ከፍ ባለ ሁኔታ በአገሪቱ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለመፈጸም እቅድ
አዘጋጅቶ የሰው ሀይል አሰልጥኖ፣ ከቀላል እስከ ከባድ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የጥላቻ
ፕሮፓጋንዳ በህዝቡ ውስጥ አሰራጭቶ በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለመፈጸም
ሙሉ ዝግጅት ሲያደርግ ነበር፣
በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሌም ለሰላም እጁን እንደዘረጋ፣ ቡድኑ
ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጣ አሉ የተባሉ አማራጮችን ሁሉ ያለመታከት ሲያቀርብ
ነበር፡፡
መንግሥት ከጅምሩ ለአንድ ደቂቃም የሰላም እጁን ከመዘርጋት ቦዝኖ አያውቅም
በለውጡ ወቅት የተዘረጉ የሰላም እጆች ሁሉ ግን በአሸባሪው ቡድን ተነክሰዋል፡፡
2. የአሸባሪው ህወሃት የመጀመሪያ ዙር ጥቃት
አሻባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን ማፈራረስና አ ማ ራ ን ቅ ስ ሙ ን መ ስ በ ር አቅዶ
አስቦበት የሚያከናውነው እኩይ ተግባር ነው፣
ከለውጦ እለት ጀምሮ እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት በሚል እኩይ ሀሳብ ነው
የጥፋት ተልዕኮውን ሲፈጽም የነበረው፣
ጥቅምት 24 ቀን 2 0 1 3 ዓ.ም በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው
ታሪክ የማይረሳው ጥቃት የቡድኑን የጭካኔ ልክ ያሳየ ነው፡፡
ህብረ-ብሄራዊ የአገር መከላከያ ሰራዊታችን የኢትዮጵያዊነት አርማ በመሆኑ እሱን ቀድሞ
ለማፈራረስ አቀደ፡፡
አገራዊ ክብራችንን ያስጠበቀ ሰራዊትን በለሊት በጭካኔ ጨፈጨፈ
በታሪክ ዉስጥ አንገታችንን ቀና አድርገን በአለም ፊት እንድንታይ ያደረገ የሉዓላዊነታችን
መገለጫን የኔ ብሄር ከሚለው ውጭ ያለውን ለይቶ አረደ፣
የትግራይን ህዝብ በሰላሙም በልማቱም ሲደግፍ ከ20 ዓመት በላይ አብሮት የኖረን ሰራዊት
በተኛበት በበርካታ ምሽጎች በአንድ ጊዜ ተኩስ ከፍቶ ወታደሩን ከነሲቪል ሚስቶቹና ልጆቹ
ጨፈጨፈ
የቀጠለ…..
➢ በዚያች ለሊት በሰሜን ዕዝ ካምፖች የተፈጠረዉ አሳዛኝ ጭካኔ ተጽፎ የዚህ ት ዉልድ ታሪክ ሆኖ
ተቀምጧል፡፡ አሁን ያለዉም ቀጣዩም ትዉልድ ይማርበታል፡፡
➢ መከላከያችን ጀግና በመሆኑ መስዋዕትነት ከፍሎ ጥቃቱን መቋቋምና እንደ አገር
አለኝታ ተቋም ተጠናክሮ መቀጠል ችሏል፣
➢ የተከፈተበትን ጥቃት ተከትሎ መንግሥት በወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ አሸባሪ ቡድኑ
አከርካሪው ተመቶ ተንቤን ዋሻ ሊገባ ችሏል፡፡
➢ መንግሥት የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ከምንም በላይ የትግራይ ህዝብ የሰላም አማራጭ
ተጠቃሚ እንዲሆን በማሰብ ሁለተኛ ዙር የሰላም እጁን ለቡድኑ ዘረጋ፣
➢ ለዚህ እንዲመችም የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ በመወሰን ከትግራይ ክልል ወጣ፣ ዓላማው
ለቡድኑና ለትግራይ ህዝብ የጥሞና ጊዜ በመስጠት ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱና የትግራይ
ህዝብም እፎይ እንዲል ነበር፣
➢ በዚህ ጊዜ የተዘረጋው የሰላም እጅም ለሁለተኛ ጊዜ ተነከሰ፣ አሻባሪው የሰላም አማራጭ የሚባል
ነገር መስማት አይፈልግም፣ ጦርነትና ደም መፋሰስ ብቻ ነው ስሪቱ፣
3. የአሸባሪው ህወሃት ሁለተኛ ዙር ጥቃት