You are on page 1of 1

አድዋን ያለ ምኒሊክ ማሰብ እንደማይሆን ሁሉ በዘር ተጥልለህ አድዋን ለማክበር የመጣህ የመንግስት ክፍልም ታዳሚም

አድዋን ከዘር በላይ አስበው! አድዋ የአለም ታሪክ እንጂ ያንተ ወይም ያንቺ ያደባባይ የዘር ቅርሻት መትፊያ አይደለም።

የዛሬውን የአድዋ ክብረ በአል ለመታደምም ለመዘገብም በታሪክ አጋጣሚ ተገኝቼ ነበር። እኔ አድዋን ታሪክ ሳነበው እና
ስረዳው የድላችን ቀን እንጂ የነፃነታችን ቀን አይደለም። እናም የተሰዉትን በማሰብ፣ ታሪክን በማስታወስ እና ጀግኖችን
በማወደስ ነው አድዋ ሊከበር የሚገባው። በቅርበት አብረውኝ የሚሰሩ ጓደኞቼ ኢትዮጵያዊነትን በለሊቱ ነበር የሰበኩኝ።
እኔም ኢትዮጵያዊነቴን ኮርቼበት እና ተደስቼበት ነው ምኒሊክ አደባባይ ስወጣ። ከደቂቃ በኋላ ክርክር በመሀከላችን
ተነሳ። እኔ ብዙ ግዜ ክርክር ላለመግጠም እና ለማዳመጥ ነው የምጥረው። በክርክሩ መሃል ስለዘማቾች ታሪክ ተነሳ።
እከሌ እኮ ከእንትን ነው የዘመተው እከሌ እኮ ከኛ ትውልድ ሀገር ትንሽ ራቅ ብሎ ባለችው እንትን ነው የተወለደው የሚል
የዘማች ታሪከኞች ዘር ቆጠራ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ከኔ በላይ ያለውን ሰውዬ በዘር ጥላ አስተዋልኩት። ይሄኔ በውስጤ
አንድ ጥያቄ ተፈጠረ። መንግስትን መጥላት አንድ ነገር ነው። እኔ ለምሳሌ ህውሃትን አምርሬ ጠልቼዋለሁ ያቅሜንም
ታግያለሁ። ነገር ግን ትግሬን ልጠላ አልችልም። ትግሬ ከሌለ የኢትዮጵያ አካል ጎዶሎ ይሆናል። ዛሬም ድረስ ለትግራይ
ወገኖች አዝናለሁ። አብይ አህመድን ስደበው ጥላው። ግን ኦሮሞ በታሪክ ምንም ክፍል እንደሌለው አድርገህ ስትስል ምን
እያረከው ነው??? በዚህስ ኢትዮጵያ ትቀጥላለች? እንዴት ሙሉ ኦሮሚያን ህዝብ ንቀን ጠልተን እንዘልቃለን? አመራር
ሁሉ ዘርህን የሚወክል ከሆነማ በትግራይ የተደረገውን ጦርነት እሰይ እንኳን እንዳውም ለምን ቆመ ማለት አለብን ማለት
ነው። ፖለቲካን ጥላ። መሪን ጥላ። እንዴት ህዝብ ትጠላለህ? በዚህ ሁኔታ ኢትዮጵያን አቆማለሁ ብሎ የሚያስብ
የትኛውም ፖለቲከኛ፣የትኛውም መሪ፣የትኛውም ሰው ገደል መግባት ይችላል። ለኔ አማራ የሌለበት ትግሬ ጉራጌ ስልጤ
ኦሮሞ አፋር ኩናማ፣ሀረሬ°°° ጎዶሎ ነው። ትክክል ነውም ብዬ አላምንም። የዘር ፖለቲካን እግድ የምደግፈው ለዛ ነው።
ወደ ዛሬው ክስተት ስመለስ ሁለት ጎራ ጥርት ብሎ ታይቶኛል። አምና የኔ ተስፋ ዘንድሮ አንድ ቦታ በአንድ ልብ
እንድናከብር ነው። ከሁሉ በፊት የመንግስት ግዙፍ ጥፋትን ላስቀድም መንግስት ለራሱ የፖለቲካ አጀንዳ ሲል ክብረ በአሉ
በአጭሩ ተጠናቆ እንዲየልቅ ፈልጓል። ይሄ ትልቅ ስህተት ነው ህፃን የማይሰራው። ሁለት ሰአት ሳይሞላ መንገድ ክፍት
ተደረገ። ይሄ ያናድዳል። ከሁሉ በላይ መከላከያ ሀላፊነቱን ሲወስድ ቢያንስ በብሄራዊ ደረጃ ከፍ ይላል ብዬ ገምቻለሁ።
በእርግጥ የነበረውን ትርኢት ምኒሊክ አደባባይ እንደማይችለው አያጠያይቅም። ግን ቢያንስ ሰዉ ነፃ እንዲሆን ቢሆን ጥሩ
ይሆናል። ከዛ በኋላ አድማ በታኝ ተሰማራ። ይህም ትክክል አይደለም። ሰው ታፍኗል ይተንፍስ። ኑሮው ትምህርቱ እና
የቤት ክራይ ያጨለለው ስንት አለ መሰልህ ይህንን አጋጣሚ በጥብቅ የሚፈልግ። በእርግጥ በሰላም መግባት የማይፈልግ
እንደሚቀላቀል ግልፅ ነው። እና ሰው ይጩህ፣ይተንፍስ፣ይዝፈን ይሸልል ይፎክር ይቅረፅ ምን ጨነቀህ መንግስቱ ዝም
አትልም? ግን ጭስ ለቀቅክ። ይሄ ደሞ ሰውን ይበልጥ እልክ ይከተዋል። ከሁሉ በላይ ጉዳት ያመጣል። እኔ ሁሌም ፀሎቴ
ሰው እንዳይጎዳ ነው። ሌላው ይተካል። ሐበሻ ደሞ ሄዋን ነው። የተከለከለውን ነገር ብሶበት ታገኘዋለህ። ስለዚ ዝም
ቢልስ ኖሮ ይሄ ሁሉ ግርግር ይከሰታል?

ህዝብ ሁሌ ትክክል ነው አይሳሳትም የምትባል ጨዋታ እኔ ጋር አትሰራም። እግዚአብሔር ፈጣሪያችን እንጂ ሌላው
ይሳሳታል። እና አንዳንድ ቃላት ውርወራ በጊዮርጊስ ወደ አቡነ ጴጥሮስ መሄጃው ካሉ አንዳንድ ሰዎች ምናልባትም አስር
ከማይሞሉ ሰዎች መወርወር ጀመሩ። ቃላቱን መድገም አያስፈልግም። የጥላቻ ነውና። ትንሽ ቆይቶ ብሽሽቅ ተጀመረ።
ይሄም ሁሉንም አይወክልም። ጥቂት! ለምሳሌ ወታደሮች ሰዎች ናቸው ስሜት አላቸው ልክ እንደኛ። ቆሻሻ ብለህ
ሰደብካቸው። ቀጥሎ ደሞ ህግ አስከብር ብለህ ነብሱን ታስበላዋለህ እና ክላሽ አያረግም? በዛ ላይ ከበላይ
የሚያጣድፋቸው ትዕዛዝ አለ። ልብ በል እነሱን ሰድበን ስናበቃ ምን የሚከሰት ይመስልሃል? እኔ እንኳን መሳሪያ የሌለኝ
ሰውዬ ሆድ አደር ብሎ ሲሞልጨኝ ደሜ ይፈላል። ዛሬ ስራ ለቅቄ ሜዳ ላይ ብወድቅ እና ቤተሰብ ብበትን ማንም ዞር
ብሎ አያየኝም አሳሬን ነው ብቻዬን የምበላው። ግን ይሁን ብዬ መልስም አልሰጠሁ የሰውን ስሜት ተረድቼ አለፍኩ።
ስለዚ ህዝባችን ሊያስብ የሚገባው አንደኛ ሌላን ዘር በማጥላላት አድዋን ማክበር እንደማይቻል። ሁለተኛ በፍፁም
ፖለቲካ እና ክብረ በአሉን መለየት ይገባናል። መንግስት ደሞ ማሳለፍን መቻልን ሀላፊነትን ባግባቡ መወጣትን ይልመድ።
ከሁሉም ግን አድዋ የኢትዮጵያውያን የኩራት ልክ እንጂ የጉልበተኛ ሁሉ መድረክ አይደለምና ስርአት ይበጅለት!

You might also like