You are on page 1of 87

የማሽላ አመራረት ቴክኖሎጅ ፓኬጅ

የካቲት 2012 ዓ.ም.


ማውጫ
1.መግቢያ
 የሰብሉ አጠቃላይ ሁኔታ /በሃገር አቀፍና በክልል/
o የመሬት ሽፋን
o ምርትና ምርታማነት
 የሠብሉ ጠቀሜታ ከስነ ምግብ ይዘት አኳያ
 ተስማሚ ስነ ምህዳር
2.በሰብሉ አመራረት ላይ የሚታዩ ችግሮች
o በማሳ መረጣና ዝግጅት የታዩ ችግሮች መፍትሄዎች
o በዘር መረጣ፤የዘር ወቅት፤መጠንና የአዘራር ዘዴ የታዩ ችግሮችና መፍትሄዎች
3.የሰብል አመራረት ስርአት
o ሰብል ፈረቃ
o ሰብል ስብጥር
o ዳግም ሰብል
4.በሰብል ጥበቃ የታዩ ችግሮችና መፍትሄዎች
5.የምርት አሰባሰብ ክምችት ችግሮችና መፍትሄዎች
6.ዘር ብዜት
1.መግቢያ
 ማሽላ (Sorghum: Sorghum bicolor (L.) Moench)
ከአገዳና ብዕር ሰብሎች የሚመደብ የሰብል አይነት ነው፡፡
 የማሽላ መገኛ፤ ስብጥርና ስርጭት (origin, diversity and
distribution)፡- የሰብሉ መገኛ ማዕከልና ከፍተኛ የሆነ ብዝሃነት
የሚገኘው በሰሜን ምስራቅ ሐሩራማ (tropical) የአፍሪካ ክፍል
ሲሆን የተላመደውም በኢትዮጵያ ነው ተብሎ በሰፊው ይታመናል፡፡
 ኢትዮጵያ ማሽላ የተላመደበት ቦታ ብቻ ሳትሆን የማሽላ መገኛና
ቀዳማዊ የስብጥር ማዕከልም (origin and center of
diversity) እንደሆነችም ይታወቃል፡፡ ማሽላ የተላመደው
ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1000 ዓዓ አካባቢ እንደሆነ በስፋት
ይገመታል፡፡
የማሽላ ብዛህነት (sorghum genetic diversity)
መግቢያ የቀጠለ….

• በዓለም ማሽላን በስፋት በማመረት የሚታወቁ 5 ሀገራት አሜሪካ 25% ፤ሕንድ 21.5% ፤ሜክሲኮ 11%
፤ቻይና 9% ፤ እና ናይጄሪያ 7% ናቸው::

 እንደ ሀገር በአጠቃላይ በ2011/12 ምርት ዘመን በመኸር የተሸፈነው መሬት 12,773,911.58 ሄ/መሬት ውስጥ

ማሽላ 1,785,227.99 ሄ/ር (14% ) ሽፋን የነበረው ሲሆን በጠቅላላ ከተመረተው 329,281,366.98

ኩ/ል ውስጥ ማሽላ የተገኘ ምርት 51,077,960.6 ኩ/ል (15.5% ) ነው፡፡ (CSA 2019/20)

 በክልላችን በ2011/12 ምርት ዘመን ከተሸፈነው 4,518,123.625 ሄ/ር መሬት ውስጥ ማሽላ

688,144.09 ሄ/ር (15.23% ) ሽፋን የነበረው ሲሆን በአጠቃላይ ከተመረተው 106,137,996.73

ኩ/ል ውስጥ 18,831,823.38ኩ/ል (17.74% ) የምርት ድርሻ አለው፡፡ ፡፡ (CSA 2019/20)


መግቢያ የቀጠለ….

 ምርታማነቱም በ2010/11 ምርት ዘመን 26.5 ኩንታል በሄክታር ሲሆን በ2011/12 ምርት ዘመን

27.37 ኩንታል በሄክታር በ0.73 ኩ/ል በሄ/ር ጭማሪ ያሳያል፡፡ ፡፡ (CSA 2019/20)
 በ2011/12 ምርት ዘመን በክልላችን በሰብል ከተሸፈነው 4.5 ሚ/ሄር መሬት ውስጥ በመሬት ሽፋን ከጤፍ ቀጥሎ ማሽላ በሁለተኛ
ደረጃ ሲገኝ በምርት ደግሞ ከጤፍና ከበቆሎ ቀጥሎ ይገኛል፡፡ (CSA 2019/20) የ2010/11 እና የ2011/12 የአራት
ዋናዋና ሰብሎች መሬትና ምርት (CSA 2019/20)

የሰብል በ2010/11 በ2011/12


ዓይነት
መሬት ምርታ ምርት መሬት ምርታ ምርት
ማነት ማነት

ጤፍ 1200986.74 18 21614861.85 1201283.74 18.8 22582406


በቆሎ 559981.55 40.8 22844483.11 534007.8 41.12 21958807.3
ማሽላ 643170 26.5 17040820.52 688114.09 27.37 18831823.38

ስንዴ 570742.91 25.97 14820433.79 575015.31 27.1 15583799.9


2.የሰብሉ ጠቀሜታ ከስነ
ምግብ አኳያ
ማሽላ ከግሉቲን ነጻ ሲሆን በንጥረ ነገር ይዘቱ ከስንዴ
ጋር ሲነጻጸር ተመሳሳይነት አለዉ፡፡

ከጤና አኳያ ማሽላ ለጤናማ የሰዉነት እንቅስቃሴ


(ሜታቦሊዝም)፣ በነርቭ ጥገና፣ በቆዳ እና በፀጉር ጤና
የማሽላ ፈንዲሻ ከማሽላ የተሰራ ከማሽላ የተሰራ ቢራ
ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ቪታሚኖችን (ቫይታሚን
እንጀራ
ቢ1፣ ቢ3፣ ቢ6) የያዘ ነዉ፡፡

ማሽላ ከፍተኛ ቁጥር ላለው የህብረተሰብ ክፍል


በእንጀራ፣ በንፍሮ፣ በቂጣ፣ በገንፎ መልኩ ጥቅም ላይ
የሚውል ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለኢንዱስትሪ
ጥሬቃነት ማለትም ፡ ለኢታኖል፣ ለቢራ፤ ለጠላ፣
ወይንና ሽሮፕ አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡

አዝመራ ቢራ ለእንስሳት መኖነት


2.የሰብሉ ጠቀሜታ የቀጠለ…
• በ100 ግራም ማሽላ የሚገኝ ንጥረ ምግብ ይዘት
ንጥረ ምግቦች መጠን
ካሎሪ 319
ጠቅላላ ሃይል ሰጭ (ካርቦ ሃይድሬት) (በግራም) 72
ፕሮቲን (ግራም) 11
ጠቅላላ ስብ (በግራም) 3.5

ያልተጣራ ስብ (በግራም) 0.6


የአመጋገብ ፋይበር (በግራም) 6.7
ስኳር (በግራም) 2.5
ሶዴየም (ሚሊ ግራም) 2
ካልሴየም (ሚሊ ግራም) 13.
ብረትሚሊ ግራም 3.36
ፖታሲየም (ሚሊ ግራም) 363
የማሽላ ሰብል ተስማሚ ሥነ ምህዳር፡-

 በአራቱ ዋና ዋና ሥነ-ምህዳሮች ማለትም በደረቅ ቆላ (1600 ሜትር በታች ከፍታ ያላቸው አካባቢዎች)፤ እርጥብ

ቆላ (1600 ሜትር በታች ከፍታ ከበቂ እርጥበት ጋር) ፤ ወይና ደጋ (1600-1900 ሜትር ከፍታ) እና ደጋ

(ከ1900-2700 ሜትር ከፍታ) ይበቅላል፡፡

 ማሽላ ከቀላል አሽዋማ አፈር ጀምሮ እስከ ከባድ ደቃቅ አፈር ድረስ በአብዛኛው የአፈር ዓይነቶች ላይ የተጠነፈፉ

እስከሆነ ድረስ ይበቅላል፡፡

 የአፈር ጣዕም (pH) ከ5.5-8.5 ቢሆን ይመረጣል፡፡ በተወሰነ ደረጃ ጨዋማነትንና አልካሊነትንም ይቋቋማል::

 ማሽላ በእድገት ጊዜው ከ500 ሚሜ የዝናብ መጠን በላይ ባላቸው አካባቢዎች የተሻለ ምርት የሚሰጥ ቢሆንም፣

ከ500 ሚሜ በታች የዝናብ መጠን በሚያገኙ አካባቢዎች በማሳ ላይ ታይሪጅ በማዘጋጀት ውሃ ማቆር ፣ የጎርፍ

ውሃ ወደ ማሳ ውስጥ ማስገባትና ሌሎች ባህላዊና ዘመናዊ ዘዴዎችን በጠቀም ማምረት ይቻላል፡፡

 ሆኖም ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ250-1170 ሚሊ ሜትር ከተስተካከለ ስርጭት ጋር እንዲያገኝ ይፈልጋል፡፡

እንዲሁም ከ270c -320c ተስማሚ የአየር ሙቀት ሲሆን ከ100c ማነስና ከፍተኛው ከ410c መብለጥ

እንደሌለበት ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡


2.በሰብሉ አመራረት ላይ የሚታዩ ዋናዋና ችግሮች
1. የማሳ መረጣና ዝግጅት ችግሮች
1.1 ለማሽላ ሰብል ተስማሚ ማሳ አለመለየት እና ተገቢ የማሳ ዝግጅት
አለማከናወን፣
1.2 ማሳንና አ/አደሮችን በወቅቱ ለይቶ በክላስተር አለማደራጀት
1.3 ተስማሚ የአፈር ዓይነት አለመጠቀም (ውሃ የሚተኛበት ማሳ ኮትቻ አፈር
አጠንፍፎ አለመዝራት)፣
1.4 ትክክለኛውን የሰብል ፈረቃ ጠብቆ አለመዝራት (ለተከታታይ ዓመታት
ማሽላን መዝራት፤ ማሽላን እና በቆሎ ማፈራረቅ)፣
1.5 ተስማሚ ከፍታን ጠብቆ አለመዝራት፣
1.6 የመጀመሪያ እርሻ ሰብሉ እንደተነሳ እርጥበቱን ሳይለቅ አለማረስ፣
1.7 የሚፈለገውን የእርሻ ድግግሞሽ አለማከናወን፣
1.8 የወቅቱን የዝናብ ሁኔታ መሰረት አድርጎ አለማረስ፣
1.9 ተገቢውን የእርሻ መሳሪያ አለመጠቀም (ገልባጭ ማረሻ፤ ጠንካራ ክንድ)፣
መፍትሄዎች
 ደለላማና መካከለኛ የሸክላ ይዘት ያላቸው ማሣዎችን መጠቀም፣
 ከአቀንጭራና ከሌሎች አረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት፣
 ሰብሉን ከጥራጥሬና ቅባት ሰብሎች ጋር አፈራርቆ መጠቀም
(ቦሎቄ፣ሽምብራ፣ ማሾ፣የእርግብ አተር)፣
 ከተባይ ነጻ ሆኖ የከረመን ማሳ የሰብሉን ቅሪት ሙሉ በሙሉ አለማንሳት፣
 የማሳ ዝግጅትን በአማካኝ ከ2-3 ጊዜ የእርሻ ድግግሞሽ ማከናወን፣
• አንደኛ እርሻ ሰብሉ እንደተሰበሰበና ማሳው እርጥበቱን ሳያጣ ፣
• ሁለተኛው እርሻ ዝናብ እንደጣለና አረም ሲያወጣ ፣
• የመጨረሻውን እርሻ በዘር ወቅት በማካሄድ ማሳው ከአረም፣ ከጓል አፈር
እና ከሰብል ቃርሚያ የፀዳ እንዲሆን ማድረግ፣
• ገልባጭ ማረሻን መጠቀም፣
2.የዘር መረጣ፤ የዘር ወቅት እና አዘራር ዘዴ ችግሮች

2.1 የተሻሻሉ ዝርያዎችን አለመጠቀም፣

2.2 ዘርን በኬሚካል አሽቶ አለመጠቀም፣

2.3 የአገዳ ቆርቁርን በመፍራት/ለመከላከል ደህና አቋም ያለውን ቡቃያ ደጋግሞ የመገልበጥ

ችግር፣

2.4 የሚፈለገውን የዘር መጠን አለመጠቀም፣

2.5 በመስመር አለመዝራት እና የተዘራውንም አለማሳሳት

2.6 በጣም በደረቀ ወይም በጨቀዬ አፈር ላይ መዝራት

2.7 የእርጥበት ዕቀባ (ጎርፍን ወደ ማሳ ማሰገባት፤ ታይሬጅንግ) ስራዎችን አቀናጅቶ አለመስራት፣

2.8 የኮትቻ አፈርን አጠንፍፎ አለመዝራት


መፍትሄዎች
• የዘር መረጣ
ሀ. የተሻሻሉ ዝርያዎች

 በበቂ እርጥበትም ሆነ በእርጥበት አጠር አካባቢዎች የተሻሻሉ የማሽላ ዝርያዎች


ቢኖሩም አርሶ አደሩ እነዚህን ዝርያዎች ተጠቅሞ በቂ ምርት እያመረተ አይደለም።
ስለዚህ ባለሙያዎች የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በማሳደግ ዝርያዎቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ

ማድረግ ያስፈልጋል።

 የተሻሻሉ ዝርያዎች ከእርጥበት ማቆያ ዘዴዎች ጋር አቀናጅቶ መጠቀም የማሽላ


ምርታማነት በአማካይ በ145% እንደሚጨምር በመልካሳና ቆቦ የተሞከሩ የምርምር
ውጤቶች ያሳያሉ፡፡
. ለማሽላ ፓኬጅ የተመረጡ ዝርያዎች

ተ.ቁ ዝርያዎች የተለቀቁበት ዓ.ም. ለመድረስ ለማበብ የሚፈጅበት የተክሉ ቁመት(ሳ.ሜ ተስማሚ ከፍታ (ሜ) ምርታማነት ኩ/ል የዘር ቀለም የለቀቀው
የሚፈጅበት ቀናት ቀናት በሄ/ር
ማዕከል

1 ጋምቤላ 1107 1968 115-150 80-90 150-200 1600-1900 30-50 ነጭ መልካሳ

2 76T1# 23 1968 90-120 60-70 120-140 <1600 25-45 ነጭ መልካሳ


3 መኮ-1 1990 108 61-92 132 <1600 22-33 ነጭ መልካሳ
4 አብሽር 1992 100-120 83 120-135 <1600 15-25 ነጭ መልካሳ
5 ጎብዬ 1992 100-120 80 110-140 <1600 19-27 ነጭ መልካሳ
6 ተሻለ 1994 108 65-76 196 <1850 26-52 ነጭ መልካሳ
7 ማሺያ 1999 113-130 55-60 120-145 <1600 42-44 ነጭ መልካሳ
8 ሬድ ስዋዚ 1999 106-112 55-60 120-135 <1600 30-33 ቡና መልካሳ
9 መልካም 2001 118 76-82 151 <1600 37-58 ነጭ መልካሳ
10 ESH-1 2001 118 71-78 179 <1600 50-55 ነጭ መልካሳ
11 ESH-2 2001 120 61-75 167 <1600 42-60 ነጭ መልካሳ
12 ደቀባ 2004 119 75 119 <1600 37-45 ነጭ መልካሳ
13 ESH-3 2006 103-121 62-78 <1600 43-53 ነጭ መልካሳ
14 የጁ 1994 68 172 <1600 50.9 ነጭ ሲሪንቃ
ፈጣን
15 ብርሃን 1994 101 63 106-167 <1850 40 ቡናማ ሲሪንቃ
16 አቡዋሬ 1995 102-157 67-80 134-156 <1850 26-57 ነጭ ሲሪንቃ
17 ሆርማት 1997 71 161-171 1450-1850 23.3 ነጭ ሲሪንቃ
ፈጣን
18 ራያ 1999 129 82 185.7 <1600 37.68 ነጭ ሲሪንቃ
19 ምስክር 1999 126 76 123-191 1450-1850 40.73 ነጭ ሲሪንቃ

20 ጊራና-1 1999 122 75 135-305 1450-1850 40.86 ነጭ ሲሪንቃ


21 ገዶ 1999 75 116-138 1450-1850 34 ነጭ ሲሪንቃ
ፈጣን
22 መሳይ 2003 106-134 65-79 137-231 <1850 38-62 ነጭ ሲሪንቃ
23 ጫሬ 2003 120 73 192 <1600 42 ነጭ ደ/ብርሃን
24 ESH4 2008 110 67 120 <1600 42 ቀይ መልካሳ
25 አርጊቲ 2009 124 79 192 <1600 38 ቀይ መልካሳ
መፍትሄዎች የቀጠለ…
ለ. የአካባቢ ዝርያዎች
 የተሻሻሉ የማሽላ ዝርያዎችን በበቂ መጠን ማቅረብ የተሻለ ምርት የሚሰጡ የአካባቢ
ዝርያዎችን መርጦ እና አበጥሮ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
 ማሽላ በኮትቻ አፈር በሚለማባቸው አካባቢዎች (ጣቁሳ፣ ጎንደር ዙሪያ፣ ደንቢያ ወዘተ)
አርሶ አደሮች ትርፍ ውሃን በቢቢኤም እና አይባር ቢቤኤም በመሳሰሉት ቴክኖሎጂዎች
በመጠቀም ከማሳ ውስጥ በማጠንፈፍ ማምረት ይገባል፡፡
 በክረምቱ መጨረሻ አካባቢ የሚከሰተውን የእርጥበት እጥረት ለመቅረፍ የማጠንፈፊያ
ቦዮችን አልፎ አልፎ በመከተር የዝናብ ውሃውን/እርጥበቱን በማሳ ውስጥ እንዲቆይ
ማድረግ፣
ማሽላ ድርቅን የሚቋቋም ሰብል ቢሆንም የእርጥበት እጥረት ወይንም ድርቅ በከፍተኛ ደረጃ ምርቱን የሚቀንሰው መሆኑ
መፍትሄዎች የቀጠለ…
• በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ለጎንደር ዙሪያ ማሽላ አምራችና ተመሳሳይ
አካባቢዎች ምክረ-ሃሳብ መሠረት ማሽላ ከተዘራ በሦስተኛው ሳምንት ቦይ በማውጣት
ትርፍ ውሃን ማፋሰስና በዘጠነኛው ሳምንት ላይ ደግሞ የውሃ እጥረት ለመከላከል ቦዩን
በማሰር የ38.5 ኩ/ል በሄ/ር ሲያስገኝ ከአካባቢያዊ አሠራር ጋር ሲነጻጸር የ20 ኩ/ል
ምርት ጭማሪና የመድረሻ ጊዜውን ከዘጠኝ ወራት ወደ አምስት ወራት መቀነስ
አስችሏል።
• የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ማዳበሪያ አቀናጅቶ በመጠቀም የአፈር ለምነትን ማሻሻል
ይገባል፡፡
• ፈጥኖ ደራሽ የሆኑ የማሽላ ዝርያዎች በመጠቀም ይመከራል፡፡
መፍትሄዎች የቀጠለ…
የዘር ወቅት
የዘር ወቅት እንደዝናቡ አጀማመር የሚለያይ ቢሆንም በትክክለኛው የዘር
ወቅት መዝራት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
 በደጋ የማሽላ አብቃይ አካባቢዎች፡- ከመጋቢት አጋማሽ እስከ ሚያዝያ መጀመሪያ
ሳምንት
 በወይናደጋ አካባቢዎች ከሚያዚያ መጨረሻ እስከ ግንቦት መጀመሪያ ሣምንት፣
 በእርጥብ ቆላማ አካባቢዎች ከሰኔ መጀመሪያ- ሃምሌ መጀመሪያ ሣምንት
 (በሰኔ ወር የሚዘሩ ዝርያዎች ፈጥኖ ደራሽ መሆን ያለባቸው ሲሆን እንደ ጎብየ፣ አብሸር
፣ብርሃን ፣ሆርማት ዝርያዎች ፈጥኖ የመድረስ ባህሪ ስላላቸው አስተማማኝ የመኸር
ዝናብ ከጣለ በኋላ ቢዘሩ ይመከራል፡፡
መፍትሄዎች የቀጠለ…
• የዘር መጠንና የአዘራር ዘዴ
ሀ/ የዘር መጠን
 የዘር መጠን የሚወሰነው እንደ ዝርያው የፍሬ ክብደት፣ የአፈሩ የዕርጥበት ይዘትና
በአፈሩ ለምነት ቢሆንም በመስመር ሲዘራ 10-12 ኪ/ግ ዘር በሄክታር መጠቀም
ለ/ የአዘራር ዘዴ
 ማሽላ በመስመር መካከል 75 ሳ.ሜ እና በተክሎች መካከል 15-20 ሳ.ሜ ርቀት
መዝራት፣
o ከፍተኛና መካከለኛ ከፍታ ለላቸው ቦታዎች አ/አደሮች የአካባቢያቸውን ዘር (ቁመታቸው
ረዣዥምና ቅጠለ ሰፋፊ) የሚጠቀሙ ከሆነ በመስመር መካከል 75 ሳ.ሜ እና በተክሎች መካከል 20
ሳ.ሜ ርቀት እንዲጠቀሙ ይመከራል፣
o ለቆላማ አካባቢዎች ደግሞ በመስመር መካከል 75 ሳ.ሜ እና በተክሎች መካከል 15 ሳ.ሜ ርቀት
እንዲጠቀሙ ይመከራል፣
 በመስመር ለመዝራት በማረሻ በሚወጣው ፈሰስ ላይ ዘሩን መጥኖ በማንጠባጠብ የዘር ጥልቀቱን ከ4
ሳ.ሜ በላይ እንዳይቀበር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
በመስመር መዝራትና ዘሩን መጥኖ በፈሰሱ ማንጠባጠብ
መፍትሄዎች የቀጠለ…
o ማሽላ ተዘርቶ ከ2 እስከ 3 ቅጠል በሚያወጣበት ጊዜ ለዝናብ አጠር ቆላማ
አካባቢዎች በየ15 ሣ.ሜ እና
o ለከፍተኛና መካከለኛ ከፍታ ላላቸው ቦታዎችና በቂ እርጥበት ለሚያገኙ አካባቢዎች
ግን በየ20 ሣ.ሜ ርቀት ላይ 1 ተክል በመተው ማሳሳት አስፈላጊ ነው፡፡
o ለእህል(grain) ለሚመረት ማሽላ በማሳሳት ወቅት እንደየመሬቱ እርጥበት እየታየ
ማዛመት ሲቻል፣
o ለዘር(seed) በሚመረት ማሽላ ግን ማዛመት አይመከርም፡፡

o በየተክሎቹ መካከል በየ15 ሣ.ሜ. ርቀት ላይ የሳሳና በየመስመሮቹ መካከል ያለ


75ሳ.ሜ. የሆነ ማሽላ በአንድ ሄክታር ውስጥ 88,887 የተክሎች ብዛት ይኖረዋል
መፍትሄዎች የቀጠለ…
 የኮትቻ አፈርን አጠንፍፎ መዝራት
 የዝናብ መቆራረጥ በሚኖርበት ወቅት የእርጥበት ዕቀባ ስራዎችን አቀናጅቶ መስራት
(በታይሬጀር ታይ ማድረግ፤ ጎርፍን ወደ ማሳ ማሰገባት፤ የማሳ ውስጥ እና የማሳ አናት
ትሬንች መስራት፤ ደጋፊ መስኖ መጠቀም፤ ጉዝጓዝ፤ ኮምፖስት ወዘተ አቀናጅቶ
መጠቀም)፣ ማሳሳት እና ችግኝ አዘጋጅቶ መጠቀም
የማሳ ዝግጅትና የእርጥበት እቀባ ስራዎች
3. የማዳበሪያ መጠን እና አጠቃቀም ችግሮች

 የተፈጥሮ ማዳበሪያ በሚፈለገው መጠን እና ጥራት አለማዘጋጀትና አለመጠቀም፣


 የኬሚካል ማዳበሪያ (ኤንፒኤስ ዝርያ፤ ዩሪያ) በትክክለኛው ወቅትና መጠን
አለመጠቀም፣
መፍትሄዎች
ሀ/ የሰው ሰራሸ ማዳበሪያ መጠን እና አጠቃቀም
 ምክረ-ሃሳብ ላልወጣላቸው አካባቢዎች የማሽላ ስብል በሁሉም የአፈር አይነቶች
100 ኪ/ግ ኤንፒኤስ እና 100 ኪ/ግ ዩሪያ በሄክታር ሂሳብ መጠቀም፣
 በሚዘራበት ወቅት 1ኩ/ል ኤንፒኤስ ሙሉ በሙሉ በዘር ወቅት ለ100 ሜትር
መስመር 0.75ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ 7.5 ግራም ወይም 2 ሙሉ ቆርኪ)
በማንጠባጠብ አፈር ማልበስና ሰብሉ ከበቀለ ከ35-40 ባሉት ቀናት ውስጥ 100
ኪ/ግራም ዩሪያ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለ 100 ሜትር መስመር 0.75 ኪ.ግ
(በየአንድ ሜትሩ 7.5 ግራም ወይም 2 ሙሉ ቆርኪ) ማዳበሪያ መጥኖ ከተክሉ ጎን 5
ሳ.ሜ ራቅ በማድረግ ማፍስስና አፈር ማልበስ፣
የማዳበሪያ አጠቃቀም መፍትሄ የቀጠለ…
o በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክረ- ሃሳብ ለወጣላቸው አካባቢዎች ፡

 በቆቦ እና ጨፋ ወረዳዎችና አካባቢዎች 60 ኪ.ግ ኤንፒኤስ 125 ኪ.ግ ዩሪያ መጠቀም


ይመከራል፡፡ አጠቃቀሙን በተመለከተ በዘር ወቅት 60ኪ.ግ ኤንፒኤስ ሙሉ በሙሉ እና
ግማሹን የዩሪያ መጠን (62.5ኪ.ግ) ለ100 ሜትር መስመር 0.92ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ
9.2 ግራም ወይም 2.3 ቆርኪ) በማንጠባጠብ አፈር ማልበስና የሰብሉ ቁመት በጉልበት
ደረጃ ሲደርስ ቀሪዉን 62.5 ኪ/ግ ዩሪያ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለ100 ሜትር መስመር
0.47 ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ 4.7 ግራም ወይም 1.2 ቆርኪ) ማዳበሪያ መጥኖ ከተክሉ ጎን 5

ሳ.ሜ ራቅ በማድረግ ማፍስስና አፈር ማልበስ፣

 በተጨማሪም በቆቦና አካባቢው የማሽላ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚወስነው ናይትሮጂን


በመሆኑ አርሶ አደሩ ሰዉ ሰራሽ ማዳበሪያን ከተፈጥሮ ማዳበሪያ ጋር አቀናጅቶ ቢጨምር
የተሻለ እንደሆነ የጥናቱ ውጤት ያስረዳል፡፡
የማዳበሪያ አጠቃቀም መፍትሄ የቀጠለ…
• በቀወት፣ ኤፍራታና ግድም፣ አንጾኪያ እና እንሳሮ ወረዳዎች 60 ኪ.ግ ኤንፒኤስ
100ኪ.ግ ዩሪያ መጠቀም ይመከራል፡፡ አጠቃቀሙን በተመለከተ በዘር ወቅት 60ኪ.ግ
ኤንፒኤስ ሙሉ በሙሉ እና ግማሹን የዩሪያ መጠን (50ኪ.ግ) ለ100 ሜትር መስመር
0.75ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ 7.5 ግራም ወይም 2.ሙሉ ቆርኪ) በማንጠባጠብ አፈር
ማልበስና የሰብሉ ቁመት በጉልበት ደረጃ ሲደርስ ቀሪዉን 50ኪ/ግ ዩሪያ መጠቀም
የሚቻል ሲሆን ለ100 ሜትር መስመር 0.375ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ3.75ግራም
ወይም አንድ ቆርኪ) ማዳበሪያ መጥኖ ከተክሉ ጎን 5 ሳ.ሜ ራቅ በማድረግ ማፍስስና
አፈር ማልበስ፣
• ለሰቆጣና አካባቢው ለማሽላ 100 ኪ.ግ ዩሪያና 50 ኪ.ግ ኤንፒኤስ በሄ/ር መጠቀም
ይመከራል፡፡
የማዳበሪያ አጠቃቀም መፍትሄ የቀጠለ…

• አጠቃቀሙን በተመለከተ በዘር ወቅት 50ኪ.ግ ኤንፒኤስ ሙሉ በሙሉ


እና ግማሹን የዩሪያ መጠን (50ኪ.ግ) ለ100 ሜትር መስመር 0.75 ኪ.ግ
(በየአንድ ሜትሩ 7.5ግራም ወይም 2 ቆርኪ) በማንጠባጠብ አፈር
ማልበስና የሰብሉ ቁመት በጉልበት ደረጃ ሲደርስ ቀሪዉን 50ኪ/ግ ዩሪያ
መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለ100 ሜትር መስመር 0.38ኪ.ግ (በየአንድ
ሜትሩ 3.8 ግራም ወይም አንድ ቆርኪ) ማዳበሪያ መጥኖ ከተክሉ ጎን 5
ሳ.ሜ ራቅ በማድረግ ማፍስስና አፈር ማልበስ፣
• ላሊበላና አካባቢው ደግሞ 50 ኪ.ግ ዩሪያና 60.5 ኪ.ግ ኤንፒኤስ በሄ/ር
መጠቀም ይመከራል፡
የማዳበሪያ አጠቃቀም መፍትሄ የቀጠለ…

• አጠቃቀሙን በተመለከተ በዘር ወቅት 60.5ኪ.ግ ኤንፒኤስ ሙሉ በሙሉ እና ግማሹን


የዩሪያ መጠን (25ኪ.ግ) ለ100 ሜትር መስመር 0.64ኪ.ግ (በየአንድ ሜትር
6.4ግራም ወይም አንድ ቆርኪ ከድርበብ) በማንጠባጠብ አፈር ማልበስና የሰብሉ
ቁመት በጉልበት ደረጃ ሲደርስ ቀሪዉን 25ኪ/ግ ዩሪያ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለ100
ሜትር መስመር 0.2ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ 2 ግራም ወይም ግማሽ ቆርኪ) ማዳበሪያ
መጥኖ ከተክሉ ጎን 5 ሳ.ሜ ራቅ በማድረግ ማፍስስና አፈር ማልበስ፣
• በታች አርማጭሆና በመተማ ወረዳዎች 114 ኪ.ግ ዩሪያና 60.5 ኪ.ግ ኤንፒኤስ በሄ/ር
መጠቀም ይመከራል፡፡
የማዳበሪያ አጠቃቀም መፍትሄ የቀጠለ…

• አጠቃቀሙን በተመለከተ በዘር ወቅት 60.5ኪ.ግ ኤንፒኤስ ሙሉ በሙሉ እና ግማሹን


የዩሪያ መጠን (57 ኪ.ግ) ለ100 ሜትር መስመር 0.88ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ
8.8ግራም ወይም 2 ሙሉ ቆርኪ) በማንጠባጠብ አፈር ማልበስና የሰብሉ ቁመት
በጉልበት ደረጃ ሲደርስ ቀሪዉን 57 ኪ/ግ ዩሪያ መጠቀም የሚቻል ሲሆን ለ100
ሜትር መስመር 0.42ኪ.ግ (በየአንድ ሜትሩ 4.2 ግራም ወይም አንድ ቆርኪ)
ማዳበሪያ መጥኖ ከተክሉ ጎን 5 ሳ.ሜ ራቅ በማድረግ ማፍስስና አፈር ማልበስ፣
• ለማሽላ የተሠራው የፎስፈረስ አስፈላጊነት ማረጋገጫ ጥናት ከአበርገሌ በስተቀር
ለሰቆጣና ለላስታ ናይትሮጅን ማዳበሪያን ብቻ ከመጨመር ናይትሮጂንን ከፎስፈረስ ጋር
መጨመር ከፍተኛ ምርት እንደሚያስገኝ ታይቷል፡፡ ስለዚህ የተሻለ ስሌት ለሰብሉ
እስከሚሠራ ድረስ 50 ኪ.ግ ኤንፒኤስና 80 ኪ.ግ ዩሪያ ለሄ/ር መጨመር የማሽላ
ምርትን እንደመጨምር ታይቷል፡፡
ለ/ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መጠን

• ጥራቱን የጠበቀ ኮምፖስት እያዘጋጁ ማሽላን ለሚያለሙ አካባቢዎች 120 ኩ/ል


ኮምፖስት ከዘር በፊት 1 ወር ቀደም ብሎ ማሳ ላይ ከተጨመረ በኋላ በዘር ወቅት 100
ኪ/ግ ኤንፒኤስ ማዳበሪያ ይጨመራል። 50 ኪ/ግ ዩሪያ ደግሞ ሰብሉ ከበቀለ ከ35-40
ቀናት ውስጥ እንዲጨመር ይመከራል፡፡
• ይህ የሚሆነው የኮምፖስቱ ጥራት በባለሙያ የተረጋገጠ ሲሆን ብቻ ነው ። ነገር ግን
የሚዘጋጀው ኮምፖስት ጥራቱን የጠበቀ ካልሆነ ለሄ/ር የታዘዘውን ሰው ሰራሽ
የማዳበሪያ መጠን ሙሉ በሙሉ መጠቀም ይገባል፡፡
• በደንቢያ ወረዳ በኮትቻ አፈር ላይ 80ኩ/ል ኮምፖስት 50 ኪ.ግ ኤንፒኤስ እና 50
ኪ.ግ ዩሪያ ማዳበሪያ ጋር መጠቀም ይመከራል፡፡
የሰብል አመራረት ስርዓት/cropping system/

የሰብል ፈረቃ ጠቀሜታ (Crop rotation)


 ማሽላን ከጥራጥሬና ቅባት ሰብሎች ጋር ማፈራረቁ የሚደገፍ ሲሆን እንደየአካባቢው
ሁኔታ ማሽላ ከጥጥ፣ ከለውዝ፣ ከዴዝሞዲዬም፣ ከእርግብ አተር (pigeon pea)፣
ከደገራ (cowpea) ዝርያዎች ወዘተ ጋር ማፈራረቁ ይደገፋል፡፡
የሰብል ስብጥር (Inter cropping)
 ከማሽላ ጋር ለስብጥር የሚያገለግሉ ሰብሎች እንደ አካባቢው የዝናብ መጠንና እንደ
አምራቹ ፍላጎት የሚለያዩ ናቸው፣
 ለእርጥበት አጠር የማሽላ አብቃይ አካባቢዎች ለውዝ፣ የርግብ አተር (pigeon pea)፣
ደገራ(cowpea)፣ ቦሎቄ፣ ማሾ ከማሽላ ጋር ለማሰባጠር የተመረጡ ናቸው
 ማሽላ ከማሾ (mung bean) ጋር በማሰባጠር ተጨማሪ 4.95 ኩ/ል በሄ/ር የማሽላ
ምርት ካልተሰባጠረው ጋር ሲነፃፀር መገኘቱ የምርምር ውጤቶች ያሳያሉ ፡፡
የሰብል ስብጥር አሰራር

 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 1 መስመር ቦለቄ (Haricot bean)


 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 1 መስመር የእርግብ አተር (pigeon
pea)
 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 1 መስመር ማሾ (mung bean)
ለበለሳ ዝናብ አጠር አካባቢ
 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 2 መስመር ማሾ ለሰ/ሸዋ አካባቢዎች
ይመከራል
የሰብል ስብጥር አሰራር የቀጠለ…

 ሰስፓንያ ሰስፓን፤ ሊውኪኒያ ወይንም የእርግብ አተር የተባሉትን ቁጥቋጧማ ተክሎች


ከ4-6 ሜትር አራርቆ በማሽላ ማሳ ውስጥ በረድፍ መትከል በማሽላ ምርት ላይ አሉታዊ
ተጽዕኖ ሳያሳድር ተጨማሪ የመኖ፣ የአረጓዴ ማዳበሪያ ወይንም የገንዘብ ምንጭ ሊሆን
ከመቻሉ በተጨማሪ የአፈር ለምነትን ያሻሽላሉ፤ የአፈር መሽርሸርንም ይቀንሳሉ፡፡
 በማሽላ መስመሮች መካከል ዲስሞድየም የተባለውን የእንስሳት መኖ መዝራትና
በማሣው ዙሪያ ደግሞ 3 ዙር ናፒር ወይም የሱዳን ሳር መትከል 70% የሚሆኑት የእሳት
ራቶች እንቁላላቸውን በሣሩ ላይ እንዲጥሉና ከተክሉ በሚወጣው ማጣበቂያ ፈሳሽ
ተጣብቀው እንዳይፈለፈሉ ያደርጋል ዲስሞድየሙ ደግሞ የእሳትራቶቹን ወደ ማሣው
እንዳይገቡ ከማድረጉም በተጨማሪ አቀንጭራ አረምን ለመከላከል በአጣማጅነት
እንደሚያገለግል የምርምር ውጤቶች ያሳያሉ(Push-Pull System)፡፡
Push-Pull System
ዳግም ሰብል (Double cropping) ለምዕራብ አማራዎች

• በመጋቢት ወር ላይ ለአጭር ጊዜ የሚዘንበው ዝናብ ተጠቅሞ በአጭር ጊዜ የሚደርሱ


የቆላ ጥራጥሬ ሰብሎች መጠቀም ይገባል፡፡ ለምሳሌ ማሾ፣ የላም አተር(ደገራ)፣ ቦሎቄ፣
ላብላብ በዋናው የአዝመራ ወቅት ፈጥነው የሚደርሱ ሰብሎች ናቸው፡፡
• በዳግም ሰብል የአመራረት ዘዴ መጠቀም የሚገባን ፈጣንና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ
የማሽላ ዝርያዎች፣ የእህልና የመኖ ጥራጥሬዎች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
በሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ አራዳም ቀበሌ በ2011/12 የተዘራ የማሽላ ማሳ
• በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ረሳ ቀበሌ በ2011/12 የተዘራ የማሽላ ማሳ
4.ሰብል ጥበቃና እንክብካቤ ችግሮች
3.1 አረም መከላከል
 ጥገኛና መደበኛ የሆኑ የማሽላ አረሞችን ተከታትሎ አለማስወገድ

 አረም በወቅቱና በሚፈለገው ድግግሞሽ መጠን መሰረት አለመተግበር፣

 የኬሚካል አጠቃቀም ችግር (በወቅት፤ በመጠን እና በዓይነት)፣

 ተገቢ የመርጫ መሳሪያና የመርጫ ጫፍ ለይቶ አለመጠቀም፣

3.2 መደበኛና የወረርሽኝ ነፍሳት ተባይ እና በሽታ


 መደበኛና የወረርሽኝ ተባዮችን ለመለየት የሚያስችል ወቅታዊ የማሳ አሰሳ አለማካሄድ

 የተከሰቱ ተባዮችን መለየት አለመቻልና በወቅቱ ሪፖርት አለማድረግ

 ለተከሰቱ ተባዮች የተቀናጀ የተባይ መከላከል ዘዴዎችን አለመጠቀም


 የኬሚካል አጠቃቀም ችግር (በወቅት ፤ በመጠን እና በዓይነት)

 ተገቢ የመርጫ መሳሪያና የመርጫ ጫፍ ለይቶ አለመጠቀም ፣


መፍትሄዎች

 አረም መከላከል

ሀ. በባህላዊ መከላከል

በእጅ ማረም:-
 1ኛ አረም ማሽላው ከበቀለ ከ18-20 ቀናት (ስብሉ ከ5-6 ቅጠል እንዳወጣ የመጀመሪያ አረም
በሚታረምበት ወቅት በ15-20 ሳ.ሜ ርቀት ብቻ ያሉትን ጠንካራ ተክሎችን በመተው
ሌሎችን መንቀል ያስፈልጋል፡፡ የማሳሳት ሥራ የሚከናወነው አፈሩ በቂ እርጥበት ሲኖረው
ነው።
 2ኛውን አረም ማሽላው ከበቀለ ከ35-40 ቀናት ማከናወን ተገቢ ነው፣

 የአረም ሥራን ከኩትኳቶ ጋር አቀናጅቶ መፈፀም፣ አረሞችን ዘር ከማፍራታቸው በፊት


በማረም በሰብሉ ስር መጎዝጎዝ (mulching) አረምን ከመቆጣጠሩ በተጨማሪ የማሳ ላይ
እርጥበትን ይጠብቃል፡፡
የአዘራርና የእንክብካቤ ችግር የሌለበትና ያለበት ማሳ
መፍትሄዎች የቀጠለ…

የአቀንጭራ ቁጥጥር
o የተቀናጀ የአቀንጭራ መከላከል (Integrated Striga Management) ስትራቴጂዎች

 አቀንጭራን የሚቋቋሙ የማሽላ ዝርያዎችን መጠቀም ( ጎብዬ፣ አብሽር፣ ሆርማት፣ ብርሃን እና ገዶ) ፣
 ፍግ፣ ኮምፖስትና ስው ሰራሽ ማዳበሪያ በመጠቀም የአፈር ለምነትን ማሻሻል፣
 የውሃ ዕቀባ ዘዴዎችን መጠቀም
o ሌሎች የመከላከያ ዘዴዎች

 ከአቀንጭራ የፀዳ ንጹህ ዘር መጠቀም


 ሰብልን ማፈራረቅ (በቆሎ፣ ማሽላና ዳጉሳን አለመዝራት)
 አቀንጭራው ከአበበ በኃላ ፍሬ ከማፍራቱ በፊት እየነቀሉ ማቃጠል
በአቀንጭራ የተጎዳ የማሽላ ማሳ
በአቀንጭራ የተጎዳና ያልተጎዳ የማሽላ ማሳ
• በአቀንጭራ አረም (ስትራይጋ ሄርሞንቲካ) የተወረረ የማሽላ ማሳ ቆቦ
የአቀንጭራ ቁጥጥር የቀጠለ …

 ዘሩ በእርሻ መሳሪያዎች፣ በከብቶችና በሌሎች መንገዶች ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት ማድረግ

 የጥራጥሬ ሰብሎችን አሰባጥሮ መዝራት


o እንደ አካባቢው የዝናብ መጠንና እንደ አምራቹ ፍላጎት የሚከተሉትን በአገር ውስጥና በውጭ
አገር በምርምር የተደገፉ የስብጥር ዓይነቶች መጠቀም የአቀንጭራ አረምን ለመከላከልና
መቆጣጠር ያግዛል፡፡
 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 1 መስመር ቦለቄ (Haricot bean)

 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 1 መስመር የርግብ አተር

 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 4 መስመር አኩሪ አተር

 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 4 መስመር ለውዝ

 በሁለት ማሽላ መስመር መካከል 2 መስመር የፈረንጅ ሱፍ


ለ. በኬሚካል መከላከል

ለ1ሄ/ር መጠቀም የሚረጭበት የሰብሉ የሚቆጣጠራቸው የአረም ሊደረጉ የሚገባ ጥንቃቄዎች


የፀረ አረሙ ስም ያለብን መጠን (ሊትር) የእድገት ደረጃ አይነቶች

2 ፎርዲ (2,4-D) 0.5 - 0.8 ስብሉ በቅሎ ከ10- 30 አብዛኞች ዓመታዊ ቅጠለ ሰፋፊ ቅጠለ ሰፋፊ ስብሎችን ሊጎዳ
ሳ.ሜ ከፍታ ሲደርስ አረሞች ስለሚችል ሲረጭ በንፋስ
እንዳይሄድ መጠንቀቅ

አትራዚን 50 ኤስሲ 4 ስብሉ በቅሎ ከ3- 4 ቅጠለ ሰፋፊ አረሞችና በአሽዋማ አፈር ላይ ዝቅተኛ
ቅጠል ደረጃ ሲደርስ በመብቀል ላይ ያሉ የሳር መጠን መጠቀም
አረሞችን

ማሳሰቢያ:-ለአትራዚን ከ 200-300 ሊትር እና ለቱ ፎርዲ ደግሞ 150 ሊትር ውሃ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡


ከዚህ በተጨማሪ በአገራችን የተመዘገቡ ሌሎች ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መሰረት
መተግበር ይቻላል፡፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር

o አገዳ ቆርቁር
 የበቆሎ አገዳ ቆርቁር አሰሳ/ቅኝት/
• ከሰብሉ የቡቃያ ወቅት ጀምሮ የተባዩን እንቁላል አሰሳ ማካሄድ ያስፈልጋል።
• ትሉን ለማሰስም ሰብሉ በመስመር የተዘራ ከሆነ በየ10 ወይም በየ 5 መስመሮች ርቀት
ላይ ከግራና ቀኝ አምስት አምስት ተክሎችን በማሰስ ውጤቱን ማወቅና የተጠቃው
የተክል ብዛት 5% ከደረሰ የመከላከል ዕርምጃ ሊወሰድ ይገባል።
• ሀ/ በባህላዊ ዘዴ መከላከል
• በአገዳ ቆርቁር የተጠቃ የማሽላ አገዳን ወደ መሬት ዝቅ አድርጎ ማጨድና አገዳውን
ከመከመር በፊት ፀሐይ ላይ ለ4 ሳምንት ተጋድሞ እንዲቆይ ማድረግ፣
• ተባዩ በበጋ ወራት በአማራጭነት ሊራባባቸው የሚችሉ ወፍራም አገዳ ያላቸው የሳር
ዝርያዎችን (ሰምበሌጥ፤የሱዳን ሳር ወዘተ) ሰብሉ ከመዘራቱ ቀደም ብሎ ማስወገድ፣
• ዝናብ እንደጀመረ በአንድ አካባቢ ያሉ አርሶአደሮች በተመሳሳይ ወቅት እንዲዘሩ
ማድረግ፣
• ሰብሉ በተዘራ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ሳምንታት በተባዬ ጥቃት በጣም የተጎዱ
ቡቃያዎችን (dead hearts) ነቅሎ በማስወገድ መቅበር፣
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

• በማሽላ መስመሮች መካከል ዲስሞድየም የተባለውን የእንስሳት መኖ መዝራትና በማሣው


ዙሪያ ደግሞ 3 ዙር ናፒር ሣር ወይም የሱዳን ሳር መትከል 70% የሚሆኑት የእሳት
እራቶች እንቁላላቸውን በሣሩ ላይ እንዲጥሉና ከተክሉ በሚወጣው ማጣበቂያ ፈሳሽ
ተጣብቀው ሳይፈለፈሉ እንዲቀሩ ያደርጋል። ዲስሞድየሙ ደግሞ የእሳት እራቶቹን ወደ
ማሣው እንዳይገቡ (እንዲሸሹ) ከማድረጉም በተጨማሪ አቀንጭራ አረምን ለመከላከል
በአጥማጅነት እንደሚያገለግል የኬንያ አርሶአደሮች ተሞክሮ ያሳያል።
• አይደርቄ (Jatropha) ዘሩን በመፍጨትና ዱቄቱን 2 ቁንጥር (Pinch) በተክሉ አናት ላይ
መጨመር 93% የአገዳ ቆርቁር ትሎችን እንደሚገድል በኮምቦልቻ አዝርዕት ጥበቃ ክሊኒክ
ተረጋግጣôል'
• በመስመር መዝራት ትሎቹ ከአንዱ ተክል ወደ ሌላ ተክል በቀላሉ መሸጋገር
ስለሚያስቸግራቸዉ አብዛኛዎቹ ይሞታሉ፡፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

ለ/ በኬሚካል መከላከል
• የተባይ ወረራው 5% እንደደረሰ የሚከተሉትን ኬሚካሎች በመጠቀም መከላከልና
መቆጣጠር ይገባል።
• ዲያዚኖን (ኢትዮዚኖን) 10% ሽርክት 2.5-5 (ኪ.ግ/ በሄ/ር ወይም ተባዩን በርጭት
መከላከል ካስፈለገ ወደ ሙሽራው ውስጥ ከመግባቱ በፊት ወይም ቡቃያው ከጉልበት
ከፍታ በላይ ሳያልፍ-
• ሄሊራት ወይም ካራቴ 5% ኢሲ 300 ሚ.ሊትር

• ካርባሪል 85% ደብልዩ.ፒ 1.5 ኪ/ግ በሄ/ር በ200 ሊትር ውሃ በመበጥበጥ ሙሽራው
ውስጥ መርጨት ያስፈልጋል።
• አኪቶ 2.5% ኢሲ፣ ብራቮ 5% ኢሲ (ደብሊው/ቪ)፣ ዲያዝኖን 60% ኢሲ እና ሌሎችም
ኬሚካሎችን በአምራቹ ምክረ-ሃሳብ መሰረት መጠቀም ይቻላል፡፡
ለአገዳ ቆርቁር መፈጠር ምክንያት የሆኑ ነገሮችን በምክረ ሀሳቡ መሰረት ማስወገድ
የቅጠል መስኮት
በከፍተኛ ደረጃ የተጎዳ ቅጠል
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

o መጤ ተምች/Fall Army Worm/ ለመከላከል


ሀ/ በባህላዊ ዘዴ መከላከል
• ማሳን በበጋ ወራት ደጋግሞ በማረስ ለፀሃይ ማጋለጥ፣
• ተባዩ በበጋ ወራት በአማራጭነት ሊራባባቸው የሚችሉ ወፍራም አገዳ
ያላቸው የሳር ዝርያዎችን ማስወገድ፣
• ሰብሉ በተዘራ በመጀመሪያዎቹ ስድስት ሳምንታት በተባይ ጥቃት በጣም
የተጎዱ ቡቃያዎችን (dead hearts) ነቅሎ በማስወገድ መቅበር፣
• ተባዩ የተከሰተ ማሳ አነስተኛ ከሆነና የተባይ ክስተት አነስተኛ ከሆነ ለቅሞ
ማስወገድ/መግድል/፣
• ሰብልን አፈራርቆ መዝራት፣
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

ለ/ በኬሚካል መከላከል

• ተባዩን በባህላዊ ለመከላከል ከቁጥጥር ውጭ ከሆነና በተባይ አሰሳ ወቅት በአንድ ተክል ላይ ከ2-3 ትሎች
ከተመዘገቡ ወይም ከ100 ተክሎች 20 ተክሎች በተባዩ ከተያዙ የሚከተሉትን ኬሚካሎች መጠቀም
ያስፈልጋል፡፡

• አቫዉንት 150 ኤስሲ 450ሚሊ ሊትር/ሄ/ር

• አግሮላባሲን ሱፐር315 ኢሲ 400 ሚሊ ሊትር/ሄ/ር

• ትሬሰር 480 ኤሲ150 ሚሊ ሊትር/ሄ/ር

• ፕሮቨን 44% ኢሲ 1 ሊትር/ሄ/ር

• ሴቪን 80% WP በውሃ የሚበጠበጥ ዱቄት 1.5ኪ. ግ /ሄ/ር.

• ዱርስባን 48% EC በውሃ የሚበጠበጥ ፈሳሽ 1.0 ሊትር/ሄ/ር.

• ማላታዩን 50% EC በውሃ የሚበጠበጥ ፈሳሽ 1-2ሊትር/ሄ/ር.

• ካራቴ 5% EC በውሃ የሚበጠበጥ ፈሳሽ 300 ሚ.ሊ/ሄ/ር.


የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

o ጓይትል
ሀ) በባህላዊ ዘዴዎች መከላከል (Cultural practice)
 መሬቱ ሲታረስ በጥልቀት በማረስ አፈር ውስጥ የተደበቁትን ትሎችና ፑፓዎች
ለፀሐይና ለተመጋቢ ጠላቶቻቸው ማጋለጥ፣
 ለነፍሳት ተባዩ መራቢያ የሚሆኑና በማሳው አካባቢ የሚገኙ አረሞችን ማስወገድ፣

 ነፍሳት ተባዩ በተደጋጋሚ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ብትን ራስ ያላቸውን


የማሽላ ዝርያዎች መጠቀም፣
 ለነፍሳት ተባዩ የክስተት መጠን አነስተኛ ከሆነ በእጅ መልቀም፣

 ሌሎችም በየአካባቢው ጠቃሚ የሆኑ ባህላዊ የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም


የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

ጓይ ትል
ለ) በኬሚካል መከላከል

ጓይትልን በተለይም ረዣዥም ለሆኑ ዝርያዎች በኬሚካል መከላከል አስቸጋሪ ስለሚሆን በማሳው ውስጥ
እየተዘዋወሩ በከፍታ ቦታ ላይ ሆኖ ፀረ-ተባዩን ለመርጨት እንዲያመች ተንቀሳቃሽ ማማ ማዘጋጀት
ያስፈልጋል። ይህን ካዘጋጀን በኋላ ከሚከተሉት ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች ውስጥ አንዱን-
• ካርባሪል (ሴቪን) 85% ደብልዩ. ፒ 1.5 ኪ.ግ፣

• ሄሌራት ወይም ካራቴ 5% ኢሲ 300 ሚሊ.ሊትር፣

• ፕሮፊት 72% ኢሲ 0.5-1 ሊትር፣

• ዲያዚኖን (ባሱዲን) 60% ኢሲ 1 ሊትር በሄ/ር በ200 ሊትር ውሃ በርዞ ቢቻል በሞተር መርጫ መሳሪያ
መጠቀም ውጤታማ ያደርጋል፡፡
• በተጨማሪም በአገራችን የተመዘገቡ ሌሎች ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም መመሪያ መሰረት
መተግበር ይቻላል፡፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

 የማሽላ ሙሽራ ዝንብ

ሀ/ ባህላዊ የመከላከያ ዘዴዎች (Cultural practice) ፡-

• የሰብል ፈረቃን መጠቀም፣

• ማሳውን ጠለቅ አድርጎ ማረስ፣

ለ/ በኬሚካል የመከላከያ ዘዴዎች፡-

• ካራቴ 5 % ኢ.ሲ 0.4ሊትር ለ1ሄ/ር ወይም

• ዱርስባን 48% ኢ.ሲ 1-2 ሊትር ለ1 ሄ/ር ሁለት ጊዜ በሰባት ቀን ልዩነት ወይም

• ዲያዚኖን (ባሱዲን) 60% ኢ.ሲ 1ሊትር ለ1ሄ/ር ወይም

• ሮገር (ዳይሜቶት) 40% ኢ.ሲ 1ሊትር ለ1ሄ/ር ወይም

• ማላታዮን 50% ኢ.ሲ 2ሊትር ለ1ሄ/ር በ200ሊትር ውሃ በጥብጦ በመርጨት ተባዩን መከላከል
ይቻላል፡፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

 ቆራጭ ትል (Cut worm)

• ዘር ከበቀለና ከበቀለ በኋላ በየ3 ቀኑ ወካይ በሆኑ ስፍራዎች ላይ 0.25ሜ2 ኳድራንት እየጣሉ በኳድራንቱ

ውስጥ የበቀሉትን ቡቃያዎች ብዛትና ከእነዚህ መካከል በቆራጭ ትል የተቆረጡትን ብዛት መመዝገብ፤

• ኳድራንት ውስጥ በአጠቃላይ በተክሉ ላይ ያሉትንና አፈሩን እየጫሩ የሚገኙትን ትሎች ቁጥራቸውን

መመዝገብ፣

• በድንበሮች አካባቢም መረጃው መወሰድ ይኖርበታል፡፡

ሀ/ በባህላዊ መከላከል (Cultural practice)

• በበጋ ወራት ማሳውን ጠለቅ አድርጐ በማረስ ኩብኩባውን ለፀሀይና ለሌሎች የተፈጥሮ ጠላቶች ማጋለጥ፤

• አረሞች ለተባዩ እንቁላል መጣያና ለሚፈለፈሉት ትሎች የመጀመሪያ ምግብና መጠለያ ሆነው ለመራባት ምቹ

ሁኔታ ስለሚፈጥሩ ከማሳውና ከማሳው ዙሪያ ማስወገድ፣


ለ/ በኬሚካል መከላከል
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

• ዘሩን በኬሚካል በማሸት መከላከል፡- ክሩዘር 350 FS ከ100-200 ግራም በ1 ሊትር ውሃ


በጥብጦ 1 ኩ/ል ዘር አሽቶ መዝራት፣

በአጣማጅ መከላከል (Baiting)፡-

• 25 ኪ/ግ የጤፍ ብጣሪ (የስንዴ ወይም የሩዝ) ወይም ፉርሽካ፣ ሳጋቱራ (የእንጨት ፍቅፋቂ)
በሚገባ በውሃ በማርጠብ ከ1 ኪ/ግ ሴቪን 85% ደብልዩ ፒ ኬሚካል ጋር በበርሜል ወይም
ፕላስቲክ ጆንያ በመጠቀም ማዋሀድ፡፡ በዚህ ስሌት መሠረት የተዘጋጀውን 25 ኪ/ግ አጥማጅ
ቆራጭ ትሉ እንደታየና መቁረጥ እንደጀመረ በምሽት ወቅት በማሣው ውስጥ መበተን፣

• ሴቪን 85% ደብልዩ ፒ 100 ግራም ከ10 ኪ/ግ ፉርሽካ፣ 500 ግራም ስኳርና 10 ሊትር
ውሃ ጋር በትክክል አደባልቆ ለሩብ ሄ/ር ማሳ በምሽት (ማታ) መበተን ውጤታማ ነው፡፡
በመስመር የተዘራ ሰብል ከሆነ በመስመሩ አስጠግቶ መነስነስ ጠቃሚ ነው፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

በርጭት መከላከል፡-

• ሰብሉ ከበቀለና ከበቀለ በኋላ አሰሳ በማካሄድ የተባዩ የጉዳት መጠን ኬሚካል
የሚያስረጭ ሆኖ ከተገኘ የሚከተሉትን ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች መጠቀም ይቻላል፡

• ዱርስባን 48% ኢሲ 1ሊትር

• ዲያዚኖን 60% ኢሲ 1ሊትር

• ካርባሪል 85% ደብልዩ. ፒ 1.5ኪ/ግ ለአንድ ሄ/ር ሂሳብ እስከ 1000 ሊትር
በሚደርስ ውሃ በርዞ በምሽት ወቅት መርጨት ተባዩን ለመከላከል ያስችላል፡፡

• ሌሎች በአገራችን የተመዘገቡ ፀረ-ነፍሳት ኬሚካሎችን በአምራቹ የአጠቃቀም


መመሪያ መሰረት መጠቀም ይቻላል፡፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

ምስጥን (Termite) ለመከላከል፡-


• ሀ/ በባህላዊ መከላከል (Cultural practice) ፡-

• የሰብል ቅሪቶችን ከማሳው ላይ ቶሎ ማንሳት፣


• ሰብሉ እንደታጨደ ማሳውን ወዲያውኑ ማረስ፣
• ኩይሳውን ቆፍሮ ንግስቷን አውጥቶ መግደል፣
• የተብላላ የከብት ሽንት በኩይሳው ዉስጥ መጨመር፣
• መርዛማ ፀረ-ተባይ እጽዋትን መጠቀም
– የአሳ ባቄላ (Fish bean) ቴፍሮዚያ (Tephrosia vogelli) የተባለውን እጽዋት
ቅጠሉን ጨቅጭቆ በውሃ በመበጥበጥ በኩይሳው ውስጥ መልቀቅ፤
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

– ቅጠሉን አድርቆና ፈጭቶ /ወቅጦ/ በዛፎችና በሌሎች ምስጥ አዘውትሮ


በሚታይባቸው አካባቢዎችና በሰብል ክምር ስር መነስነስ፤
– ከሰብሉ ስር ቅጠሉን መጉዝጎዝ (Mulching)፣

ለ/ በኬሚካል መከላከል፡-
• ኩይሳው ባለበት ቦታ በመቆፈር ለአንድ ኩይሳ ዱርስባን 48% ኢ.ሲ
ወይም ዲያዚኖን 60% ኢ.ሲ ከ20-30ሚ.ሊትር ከ15-20 ሊትር ውሃ
እየበረዙ መጨመር፣
• ሌሎች በአገራችን የተመዘገቡ ፀረ-ነፍሳት ኬሚካሎችን በአምራቹ
የአጠቃቀም መመሪያ መሰረት መጠቀም ይቻላል፡፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

o ነቀዝ፣ ጥንዚዛና እሳት እራት ዝርያዎች ፡-

ሀ) ባህላዊ ዘዴዎች መከላከል

 የጎተራውን ንጽህና መጠበቅ፣

 የሚሰራው ጎተራ ነፋሻማ ቦታ ላይ እንዲሆን ማድረግ፣

 የሚከማቸው እህል በሚገባ መድረቁን ማረጋገጥ፣

 ማሽላውን ትንንሽ ዘር ካላቸው (ጤፍና ዳጉሳ) ሰብሎች ጋር አደባልቆ


ማስቀመጥ
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

ለ) በኬሚካል መከላከል

 ፀረ-ተባይ ኬሚካል መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ:-

 በተባይ ላልተወረረ 25 ግራም (በክብሪት መያዣ ሙሉ) አክቴሊክ 2%


ዱቄት ለ1 ኩ/ል መጠቀም ወይም፣

 በተባይ ለተወረረ 50 ግራም አክቴሊክ 2% ዱቄት ለ1 ኩ/ል መጠቀም


ያስፈልጋል፡፡

 እህሉን ለመርጨት ካስፈለገ አክትሊክ 25% E.C ለ10 ኩ/ል ከ16-40


ሚሊ ሊትር በ1ሊትር ወይም 2 ሊትር ውሃ በጥብጦ መርጨት ያስፈልጋል፡፡
የነፍሳት ተባይ ቁጥጥር የቀጠለ…

ማሳሰቢያ፦
• ከላይ የተገለፁትን የጎተራ ተባይ ኬሚካል ከተጠቀምን ከ2 ሳምንት በኃላ እህሉን
ለምግብነት ብናውለው ችግር እንደማያመጣ ሊታወቅ ይገባል፡፡
• በአንጻሩ ግን ለነቀዝ መከላከያነት ዲዲቲ 75% እና ማላታዮን 50% ኢ.ሲ መጠቀሙ
በጤና ላይ ችግር ስለሚያስከትል አ/አደሩ እንዳይጠቀም የተጠናከረ የምክር አገልግሎት
መስጠት ያስፈልጋል።
የበሽታ ቁጥጥር

• አረማሞ
ሀ.ባህላዊ መከላከያ ዘዴዎች፡-

 የስብል ፈረቃ መጠቀም፣

 በአረማሞ የተጠቃውን የማሽላ ራስ ነቅሎ


ማቃጠል፣
 የከብት ሽንት አጠራቅሞ ለ7 ቀን ፀሃይ
እንዲያገኘው ሆኖ ከተብላላ በኋላ አንድ እጅ ብትን አረማሞ
(Loose smut)
የከብት ሽንትና 1እጅ ውሃ (1፡1 ምጥጥን)
በማቀላቀል 500 ግራም የማሽላ ዘር በአንድ
ሊትር የተቀላቀለ የከብት ሽንት ሂሳብ በመዘፍዘፍ
ለ20 ደቂቃ በማቆየትና የተዘፈዘፈውን ዘር
አጠንፍፎ ከ1-2 ቀን በማድረቅ መዝራት ሽፍንና
ብትን አረማሞን መከላከል ያስችላል፡፡
ሽፍን አረማሞ (Covered smut)
የበሽታ ቁጥጥር የቀጠለ…

ለ. በኬሚካል መከላከል
 አፕሮን ስታር 42 ደብልዩ ኤስ (Wettable solution) 250 ግራም በ650 ሚሊ
ሊትር ውሃ በመበጥበጥ 100 ኪ/ግ ዘር አሽቶ መዝራት ያስፈልጋል።

 በማሽላ ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ የቅጠል በሽታዎችን ለመከላከል በበቆሎ ላይ

የተጠቀሱትን የመከላከያ ዘዴዎች መጠቀም ያስፈልጋል።


5.ምርት አሰባሰብና ክምችት ችግሮች

 የሰብል አሰባሰብና የድህረ-ምርት አያያዝ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ አለመጠቀም፣


 የማሽላ ሰብል የሚታጨድበትን የእርጥበት መጠን ባለመጠበቅ ብክነት መኖር
 የማሽላ ሰብል አከማመር ለዝናብ የተጋለጠ መሆን
 ሰብሉን በማጓጓዝ የሚደርስ ብክነት መኖር
መፍትሄዎች
 ማሽላ በሚታጨድበት ጊዜ ከመሬት ከ20-30 ሴ.ሜትር ከፍ ብሎ በእጅ ማጨድና
መሰብሰብ አስፈላጊ ነው፡፡
 ማሽላን ለመውቃት በንጹህ አውድማ በከብት በማበራየትና ሸራ በማንጠፍ በዱላ
መውቃት
ምርት አሰባሰብ መፍትሄዎች የቀጠለ…

• ማሽላ ከፍሬው አናት ላይ ጥቁር ነጥብ ካሳየ ወይም የጭንቅላቱ (panicle) የታችኞቹ
ዘሮች ደረቅ ሲሉ ሊሰበሰብ ይችላል፡፡ በሚሰበሰብበት ጊዜ ከመሬት ከፍ ባለ ቦታ ላይ
ጉዝጓዝ በማድረግ መከመርና ሲደርቅ መውቃት ይገባል።
• ከማሳ ወደ ቤት ወይም ከቤት ወደ ገበያ በማጓጓዝ የሚደርስውን የሰብል፤ የጊዜና
የጉልበት ብክነት ለማስቀረት በእንሰሳት የሚጎተቱ ጋሪዎችን መጠቀም ያስፈልጋል።

የድህረ- ምርት አያያዝ

 የተሰበሰበውን ዘር በአግባቡ ማበጠርና የተፈቀደው የእርጥበት ደረጃ (12.5%)


እስኪደርስ ድረስ ማድረቅ
 የተሰባበሩ፣ በበሽታ ወይም በተባይ የተጎዱ ዘሮችን እንዲሁም ከዘሩ ጋር የተቀላቀሉ
ባዕድ አካላትን ማስወገድ
 የጎተራ ተባዮችን ጉዳት ሊቀንስ የሚችሉ የተሻሻሉ የእህል ማከማቻ ቴክኖሎጂዎችን
(የብረት ጎተራዎችንና የተሻሻሉ ጆንያዎችን) መጠቀም፡
Metal silo and pics bag
ዘር ብዜት
o በዘር አመራረት የሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮች
• ግልጽ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የዘር ስርዓት አለመኖሩ፣
• የመነሻ ዘር የጥራት ችግርና የአቅርቦት እጥረት፣
• በተሳለጠና በተቀናጀ መንገድ ዝርያዎችን አለማስተዋወቅ፣
• በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በየቦታው የሚቀርበው የመነሻ ዘር
በመደበኛ የዘር ስርዓት ውስጥ የማያልፍ በመሆኑ በዘር ጥራትና አጠቃቀም ላይ አሉታዊ ተጽኖ
ማሳደር፣
• በተበታተነ መንገድ ዘር ማምረት/በኩታ-ገጠም አለማምረት፣
• የኮንትራት ዘር አመራረት ውል ስምምነት አሰገዳጅ ባለመሆኑ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች የገቡትን
ውል አለማክበር፣
• ብዙ ዋጋ ተከፍሎበት የተመረተውን ዘር አ/አደሮች አለማስረከብ፣
• የዘር ጥራትን በከፍተኛ ሁኔታ ማጓደል፣
• የተጠናከረ የዘር ብዜት እና የኤክስቴንሽን የድጋፍ አገልግሎት አለመኖር፣
• ከዘር ማምረት እስከ ግብይት የሚውል የብድር አቅርቦት ውስንነት፣
• ደካማ የዘር የግብይት ስርዓት መኖር፣
• ፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነታቸውን አውቀው በአግባቡ አለመወጣት ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡፡
የዘር አመራረት መፍትሄዎች
• በክልሉ የዘር ስርዓት እንዲጠና በማድረግ ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች
ተለይተው ተቀምጠዋል፣
• የኮንትራት ዘር አመራረት ስርዓትን ተግባራዊ በማደርግ አምራችና አስመራች ቀድመው
ውል እንዲይዙ በማድረግ የመነሻ ዘር ጥራትን ማስጠበቅ፣ የአቅርቦት እጥረትን
መቅረፍና በወቅቱ ማቅረብ፣
• ክልሉ በመነሻ ዘር እራሱን እንዲችል ማድረግ፣
• አዳዲስ የሚለቀቁ ዝርያዎችን ተከታትሎ በየደረጃው ማስተዋወቅ፣
• በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በየቦታው የሚቀርበውን የመነሻ
ዘር በመደበኛ የዘር ስርዓት ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ የዘር ጥራትና አጠቃቀምን
ማሻሻል፣
• የኩታ- ገጠም የዘር አመራረት ስርዓትን በተሟላ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ፣
• የተጠናከረ የዘር ብዜት እና የኤክስቴንሽን ስርዓት መፍጠር፣
• በዘር አምራችና አስመራች መካከል የተገባው የውል ስምምነት ተፈጻሚነት እንዲኖረው
ማድረግ፣
መፍትሄዎች የቀጠለ…
• ክልሉ ለዘር ማምረት የሚውል መሬት እንዲኖረው በየደረጃው ግፊት
ማድረግ፣
• ለዘር ብዜት ለሚሳተፉ አካላት የብድር ስርዓት እንዲፈጠር ማድረግ፣
• የግብይት ስርዓቱን ዘመናዊና ቀልጣፋ ማድረግ፣
• ፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት ተግባርና ኃላፊነታቸውን አውቀው
እንዲፈጽሙ ማድረግ፣
የዘር አመራረት ዋና ዋና ተግባራት

• አካባቢው ለዘር ብዜት ያለው ምቹነት

• የአ/አደሩ የዘር ፍላጎት

• ለአካባቢው ተመራጭ ዝርያ መሆኑ

• ከፍተኛ የሆነ መነሻ ዘር/መስራች ዘር/ መኖሩ

• የዘር ብዜት አቅምና በብጠራ ወቅት የሚቀንሰው መጠን ግምት ውስጥ መግባት

አለበት፡፡ ምሳሌ ማሽላ በብጠራ ወቅት 15% ይቀንሳል

ማሣ መረጣ

• ለዝርያው ተስማሚውን አካባቢ በጥንቃቄ መምረጥ

• ማሣዎችን በክላስተር/በኩታ-ገጠም/ መለየት፣


ዋና ዋና ተግባራት የቀጠለ…

• ለዘር ማምረት የሚመረጠው ማሳ የሰብል ፈረቃን የጠበቀ ስለመሆኑ ማረጋገጥ፣

• የግለላ ርቀትን/isolation distance/ የጠበቀ፣

የዘር ማሳ በሚመረጥበት ወቅት ድቃይ በቆሎና ከድቃይ በቆሎ ውጪ ያሉ የሰብል

ዝርያዎችን በተቀመጠላቸው የግለላ ርቀት መስፈርት መሰረት እንዲፈጸም ማድረግ

ያስፈልጋል፡፡

• ለክትትልና ድጋፍ አመቺ የሆነ፣

ማሣዎችን በክላስተር /ኩታ-ገጠም/ የማደራጀት ጠቀሜታ፤-

• የዘር ማሳዎችን በቀላሉ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ፣

• የዘር ጥራት ቁጥጥር ሥራ ለማካሄድ ምቹ በመሆኑ፣


ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

• ዘሩ ከተመረተ በኋላ በቀላሉ ለማሰባሰብና ግብይት ሥራን ለማካሄድ፣


• ቀጣይነት ያለው የዘር ማምረትና ግብይት ሥርዓን ለመፍጠር
ስለሚያስችል ፣
• ዘር አምራች አ/አደር እና አካባቢን ለመፍጠር፣
• ለነፍሳት ተባይ፣ ለበሽታ እና ለአረም ቁጥጥር ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥር፣
ማሣ ዝግጅት/Land preparation/
• የማሣ ዝግጅት ድግግሞሽ እንደአፈሩ አይነት፣ እንደዝናቡ ሁኔታና
እንደማሣው ጽዳት ይለያያል፡፡ ጥራቱን የጠበቀ ዘር ለማምረት ማሣን
በወቅቱና በተገቢው ድግግሞሽ ማዘጋጀትና ማለስለስ ይገባል/ለበለጠ
መረጃ የእያንዳንዱን ሰብል ፓኬጅ ይመልከቱ/::
ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

ግለላ ርቀት/isolation distance/


• የግለላ ርቀት ሲባል በዘረ-መል፣ በንክኪና በሽታ የሚፈጠርውን ብክለትና ዝርያ መቀላቀልን
ለመከላከል በሁለት ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ የሰብል አይነቶች መካከል የሚኖረው
ዝቅተኛ የርቀት መጠን ማለት ነው፡፡
• የሚባዛው ሰብል በአበባ ዱቄት አማካይነት ጥራቱ እንዳይጓደል ጥንቃቄ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡
• ግለላ በርቀት /distance/ እና በጊዜ/time/ መጠበቅ የሚቻል ሲሆን በተለይ በጊዜ ግለላን
ለማስጠበቅ አስቸጋሪ በመሆኑ የሰብሉን የእያንዳንዱን የዕድገት ደረጃና ፊዚዬሎጂካዊ
ባህሪን ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል፡፡
• በርቀት ግለላን ማስጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆን አለበት፡፡
• በአብዛኛው ድቃይ ባልሆኑ ሰብሎች እንደዘር ደረጃው ግለላ ርቀት ከ3-5 ሜትር የሚርቅ
ሲሆን ሰሊጥ ከ50-100ሜትር፤ ሱፍ ከ800-1000ሜ፤ ማሽላ ከ200-250ሜትር መራቅ
ይኖርባቸዋል፡፡
የዘር አመራረት ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

የዘር ወቅትና አዘራር

የዘር ወቅት

• የዘር ወቅት እንደ ሰብሉ ዓይነት፣እንደዝርያውና እንደዝናቡ አጀማመር ሁኔታ ይወሰናል፣

• የዘር ወቅትን ለመወሰን የአካባቢውን ሁኔታና የአ/አደሩን ልምድ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

• የዘር ወቅት ከተዛባ የነፍሳት ተባይ፣ የበሽታ እና የአረም ሥጋት ሊፈጥር ይችላል፡፡

• በሰብሉ መካከል የአየር፣የውሃና የንጥረነገር ሽሚያ ለማስወገድና ጥራቱን የጠበቀ ዘር ለማምረት


ተገቢውን የዘር መጠን፣ የዘር ወቅት፣ የዘር ጥልቀትና የአዘራር ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ ወሣኝነት
ይኖረዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ የሰብል ፓኬጁን ይመልከቱ፡፡

የዘር መጠን

• የዘር መጠን እንደዝርያው ባህሪ፣እንደአፈሩ ለምነትና እንደ አፈሩ እርጥበት መጠን ይወሰናል፡፡
የዘር አመራረት ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

የዘር ጥልቀት
• የዘር ጥልቀት በአፈሩ እርጥበትና በዝርያዎች ተፈጥሮአዊ ባህሪ ይወሰናል፡፡ የዘር ጥልቀት በሰብል
ፓኬጅ ምክረ-ሃሳብ የታዘዘውን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡
የአዘራር ዘዴ
• የአዘራር ዘዴ በብተና /broad casting/ እና በመስመር/Row planting/ የሚዘራ ሲሆን
በመስመር መዝራት የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡
ዘርን በመስመር የመዝራት ጠቀሜታው
• ሊባክን የሚችለውን የዘር መጠን ለመቀነስ፣
• በዘር ወቅት ተመሣሣይ የዘር ሥርጭት እንዲኖር ለማስቻል፣
• ለሁሉም ተክሎች እኩል የፀሃይ ብርሃንና የአየር ዝውውር ሰለሚኖረው የተሻለ የምግብ ዝግጅት
እንዲኖረው ያግዛል፣
• ለዘር ጥራት ቁጥጥር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
• ሊገኝ የሚችለዉ ምርት ከፍተኛ መሆኑ፣
• ለሰብል እንክብካቤ /ለአረም፣ለበሽታ፣ ለሰብል አሰባሰብ ወዘተ/ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፣
የዘር አመራረት ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

የማዳበሪያ አጠቃቀም

የማዳበሪያ አይነት
• የማዳበሪያ አይነት (NPS, NPSB, NPSZn, NPSZnB, NPSBCU,
NPSZnBCU ,kc etc) የአፈር ጥናትን መሠረት ያደረገ ይሆናል፡

የማዳበሪያ መጠን /ኩ/ል/ ሄ/ር/


• በሰብል ፓኬጁ በተወሰነው ምክረ ሃሳብ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ማዳበሪያ የሚጨመርበት ወቅት


• ኤንፒኤስ ሙሉ በሙሉ በዘር ወቅት የምንጠቀም ሲሆን ዩሪያ ማዳበሪያውን ደግሞ
እንደየሰብሉ አይነት በዘር ወቅትና ከዘር በኃላ የምንጠቀም ይሆናል(በሰብል ፓኬጁ
የተቀመጠው ምክረ-ሃሳብ ተግባራዊ ይሆናል)፡፡
የዘር አመራረት ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…
• NPS/NPSZN/NPSZNB ማዳበሪያ በበቂ መጠን ካልተገኘ
– በቡቃያ ወቅትና ፍሬ በሚይዝበት ወቅት የምርት መጠንን ይቀንሣል፣የዘር ጥራትን ያጓድላል፡፡

አረም ቁጥጥር
• ለዘር ጥራት መጓደል ዋነኛ መንስኤ ከሆኑት አረም በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ በመሆኑ የዘር ማባዥ
ማሣ ከአደገኛ አረም /አቀንጭራ፣ ቦረን፣ የጅብ ራስ፣ ፓርቲኒየም/ እና ከመደበኛ አረም ነፃ መሆን
አለበት፡፡ የመከላከል ስራው በሰብል ፓኬጁ በተቀመጠው መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር


• የተለያዩ ሰብሎች በተለያዩ ነፍሳት ተባዬችና በሽታዎች /አገዳ ቆርቁር፣ ክሽክሽ፣ አረማሞ፣ ቢጫ ዋግ/
የሚጠቁ በመሆኑ የተቀናጀ የተባይ መከላከል ኘሮግራምን ቅድሚያ በመስጠት መከላከል የሚቻል
ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ኬሚካሎችን መጠቀም ይገባል፡፡ ለበለጠ መረጃ በሰብል ፓኬጁ የተቀመጠውን
መክረ-ሃሳብ መተግበር ይገባል፡፡
የዘር አመራረት ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

ነቀሣ /Rouging/
• በዘር ማባዥ ማሣ ውስጥ ከሚባዛው ሰብል ባህሪ ውጪ የሆነ፣ ተመሣሣይ
ወይም የሌላ ሰብል ዝርያ በነቀሣ ማስወገድ የዘሩን ጥራት ከመጠበቅ አንፃር
በትኩረት መከናወን ያለበት ተግባር ነው፡፡
• የነቀሣ ተመራጭ ወቅት ሰብሉ ጭንቅላት በሚያወጣበት ወይም
በሚያዘረዝርበት ወቅት ቢሆን በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡
• በነቀሣ ወቅት እንደ አርማሞ/smut/ባሉ በሽታዎች የተያዙ ሰብሎችን
የአርማሞ ዱቄት ከመበተናቸው በፊት ከስራቸው መንቀልና መቅበር
አስፈላጊ ነው፡፡
የዘር አመራረት ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

አጨዳ
• የአጨዳ ወቅቶችን ለመወሰን የሰብሉን ድርቀትና ለአጨዳ መድረሱን መከታተል አሰፈላጊ
ነው፡፡
• ሰብሉ ለአጨዳ መድረሱን ለመለየት የሚቻለው በቀለሙ፣ በጥፍር፣ በእይታ፣ በጥርስ ወጋ
ሲደረግ ጠንከር ያለና በቀላሉ የማይሰበር ከሆነ እና በእርጥበት መለኪያ መለየት ይቻላል፡፡
• በአጨዳ ወቅት የዘር ጥራትን ሊያጓድሉ የሚችሉ የተሳቱ አረሞችና ሌሎች ባዕድ ዝርያዎችን
በጥንቃቄ ማስወገድ ይገባል፡፡ ሰብሉ በተገቢው መንገድ ተገላብጦ መድረቅ ይኖርበታል፡፡
ክመራ
• ሰብሉ ከታጨደና በሚገባ ተገላብጦ እንዲደርቅ ከተደረገ በኋላ በጥንቃቄ መከመር
ይኖርበታል ፡፡
• በተመረጠው ቦታ ዙሪያ የጎርፍ ማፋሰሻ ማዘጋጀት፣ ከማሣ ውሰጥ /ጉብታ/ ቦታዎችን
መምረጥ፣ በአካባቢው ያሉ ቁጥቋጦዎችን ማፅዳትና የአይጥ ጥቃትን መከላከል፣ ከተቻለ
በእንጨት በተሰራ ማማ /አልጋ/ላይ መከመር ጠቃሚ ነው፡፡
የዘር አመራረት ዋናዋና ተግባራት የቀጠለ…

የአውድማ ዝግጅትና ውቂያ

• አውድማው የሚዘጋጅበት ቦታ ተዳፋት ያልሆነ፣አፈሩ አሸዋማ ያልሆነ፣ ብክለትን የሚጋብዙና ጥራትን


የሚቀንሱ ነገሮች የሌሉበት፣ ምርቱን ለመለየት ነፋሻማ የሆነ፣ ሌሎች ሰብሎችን ያልተወቁበት፣ ሰብሉ
ከገለባ፣ ግርድ፣ እብቅና፣ሌሎች ባዕድ ነገሮች በሚገባ ከተለየ በኋላ ለዚሁ በተዘጋጀው ጆንያ መቋጠርና
ንፁህ ቦታ ላይ በጥንቃቄ ማስቀመጥ ይገባል፡፡

ዘር ርክክብ

• በዘር ብዜት የተሣተፉ አ/አደሮች ከአመረቱ በኋላ በገቡት ውልና ስምምነት መሠረት ዘር አምራቹ
በሚያቀርበው ጆንያ በማድረግ የተመረተውንና ጥራትና ደረጃው በባለሙያው የተመሰከረለትን ዘር
በጥንቃቄ በማጓጓዝ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡ የተመረተው ዘር የሚከማች ከሆነ ለዚሁ በተዘጋጀ
ጆንያ ብቻ ተሞልቶ የዝርያውን አይነት ለመለያ የሚሆን ጽሑፍ ከጆንያው ውስጥና ውጭ በማድረግ
ወደ ማከማቻ መጋዘን ማጓገጓዝ ይኖርበታል፡፡
የዘር ብዜት የጥራት ቁጥጥር
ከዘር በፊት የማሣ ጥራት ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን
• ከዘር በፊት የሚደረግ የማሳ ላይ ጥራት ቁጥጥር ማሟላት ያለበት ተስማሚና ለም የሆነ አፈር፣ ውሃ
የማይተኛበት፣ በክላስተር የተደራጀ፣ ከአደገኛ አረም ነፃ፣ የማሣ ፈረቃን የጠበቀ፣ የግለላ ርቀትን ያሟላ፣
ከአካባቢ ተጽዕኖ የነፃ (ከወፍ፣ የዱር አራዊት)፣ ለክትትልና ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን አመቺ የሆነ ሊሆን ይገባል፡፡

በዘር ወቅት የሚደረግ ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን


• ዘሩ በዕቅዱ የተያዘና የተመዘገበ ሰለመሆኑ ማረጋገጥ፣ የዝርያውን ዘረ-መል /Genetically
pure seed/ ባህሪይ የያዘ ስለመሆኑ፣ ወቅቱን ጠብቆ ስለመዘራቱ፣ ማሣው ካለፈው የዘር
ቅሬት ነፃ ሰለመሆኑ፣ የእርሻ መሣሪያዎች ንፁህ ሰለመሆናቸው፣ የዘር መጠን ትክክለኛ
ሰለመሆኑ፣ ሌሎች ግብዓቶችን/ ማዳበሪያ/በትክክል ስለመጠቀሙ ቁጥጥር ይደረጋል፡፡
በሰብሉ የዕድገት ወቅት የሚደረግ ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን
• አረም፣ ተባይና በሸታ ቁጥጥር፣ የማሣ ዙሪያ ጥራትን መቆጣጠር፣ ባዕድ ዝርያዎችን
ማስወገድ ሲሆን ባዕድ ዝርያ ሲባል ተመሣሣይ ሆነው በባህሪይ ልዩ የሆኑ ፣ ከዋናው
ዘር ቀድመው ወይም ዘግይተው የሚያብቡ፣ በቅጠልና ግንድ ልዩ የሆኑ፣
በቁመታቸውና በቀለማቸው የተለዩት ተለይተው ይወገዳሉ፡፡
የጥራት ቁጥጥር የቀጠለ…
በዋና አበባ ወቅት የሚደረግ የዘር ጥራት ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን
• በዚህ ወቅት accepted/ rejected የሚደረግበት፣ የዘር ማሣውን ዙሮ እይታ
የሚደረግበት ( አደገኛ አረም ስለመኖር፣ የማሣው መጋሸብ፣ የበሸታ ክስተት ስለመኖሩ፣
የግለላ ርቀት ሰለመጠበቁ)፣ የማሣው አጠቃላይ ገጽታ ወጥነት/uniformity/
የሚታይበት የጥራት ቁጥጥር ወቅት ነው፡፡
• ከአበባ በኋላ ዘግይተው የሚከሰቱ ችግሮችን መቆጣጠር
– የዝናብ መብዛት/ በረዶ/ ችግሮች
– ባልታሰቡ ሁኔታ የሚፈጠሩ ነገሮች/ ተባይ፣ በሸታ አረም ወዘተ/
በሰብል ሰብሰባ ጊዜ የሚካሄድ ኢንስፔክሽን /ቁጥጥር/
• ትክክለኛ የእርጥበት መጠን፣ የግለላ ንክኪ በአጨዳ አለመኖሩን/ ከዲቃላ ሰብሎች
ውጪ ባሉ ሰብሎች 3 ሜትር ገባ ብሎ ማጨድ /የሚሰበሰበው ሰብል ከትክክለኛው
ማሳ መሆኑን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡
የጥራት ቁጥጥር የቀጠለ…
በውቂያ፣ ክምችትና ማጓጓዝ ወቅት የሚካሄድ ቁጥጥር
• የአውድማ ሰብል ቅሬትን ለማረጋገጥ፣ አዲስና ንፁህ ጆንያ ስለመሆኑ/if there is
smut -danger/፣ እሰከ ርክክብ ልዩና ንፁህ ቦታ ስለመሆኑ፣ ተበጥሮ ደረጃ
መውጣቱን የማረጋገጥ ሥራ ይሠራል፡፡
• Note:-ከክምችት በኋላ የዘር ናሙና ተወስዶ ለሰርጭት ዝግጁ መሆኑ ይረጋገጣል፡፡
በስርጭት ወቅት የሚደረግ ቁጥጥር
– በአያያዝ/ በአቀማመጥ ጉድለት/ የሚመጡ ችግሮችን መለየት፣
– በከረሙ ዘሮች እንዳይበከል ማረጋገጥ፣
– ከሌላ አካባቢ በሚመጡ ዘሮች እንዳይበከል ማረጋገጥ፣
– በዝናብ፣ በሙቀት ወዘተ በመሳሰሉት ችግሮች እዳይበከል ማረጋገጥ፣
• በላብራቶሪ ፍተሻ የወደቀ ዘር ሌላውን ንፁህ ዘር እንዳይበክል የማስወገድ ሥራ
የሚሰራ ሲሆን አወጋገዱ በሚሰጠው ውሳኔ ይሆናል፡፡
አመሰግናለሁ

You might also like