You are on page 1of 2

የምንመካባቸው ነገሮች

በመጀመሪያ ሮሜ 5:1_11 ይነበባል

ይህ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል ክርስቲያኖች ሊመኩበት የሚገቡ ሶስት ቁም ነገሮች እንዳሉ ይናገራል።በሮሜ 5:10

1):እንግዲህ በእምነት ከፀደቅን በእግዚአብሄር ዘንድ በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ በእርሱ ደግሞ
ወደቆምንበት ወደዚህ ፅጋ በእምነት አግኝተናል በእግዚአብሄር ክብር እና ተስፋ እናደርጋለን።

በሮሜ 3:23 ደግሞ ሁሉ ሀጢያትን ሰርቷል እና የእግዚአብሄር ክብር ጎድሏቸዋል ይላል።ስለሆነ በሁሉቱ ምዕራፎች
ይህን ያክል ልዩነት ሊፈጥር ያስቻለው ምንድነው?

ልዩነቱ የመጣው በስራችን ሳይሆን እግዚአብሄር አለምን ከመፍጠሩ በፊት ሃጢያታችን የሚያፅድቅ ቅባት መንገድ
ስለፈጠረ ነው።ይኽውም የህያው የእግዚአብሄር ልጅ ስለሀጢያታችን ለመስቀል ሞት ተሰጠ ስለፅድቃችንም
ከሙታን ተነሳ ሮሜ 4:25 አማኝን ወደ እግዚአብሄር ክብር እንዳይገባ ከልክሎት የነበረ ሁሉ በክርስቶስ እየሱስ
ትንሳኤ ተወገድ እውነት በሆነው በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ ይፀድቃሉ ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም አላቸው ወደ
እግዚአብሄር ህልውና በእምነት ይገባሉ።

በተስፋ የምንጠብቀው አንድ ነገር አለ ይኸውም በእግዚአብሄር ክብር እንድንሆን ነው።በሐዋሪያት ስራ ምዕራፍ 7
እስጢፋኖስ ዜታ እየሱስን በአብ ቀኝ አየው።ክርስቶስ እየሱስ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ዕብ 6:20 ስለኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ
እኛም ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በተገኘበት እንገኛለን።ጌታ ሲመጣ ይህን ሃጥያት የሞላ በቅን አለም ትተን ወደ
እግዚአብሄር ማደሪያው ወደ መጋረጃ ውስጥ ወደ እግዚአብሄር ክብር እንገባለን።

2): ይህም ብቻ አይለም ነገር ግን መከራ ትዕግስት እንዲያደርግ ትዕግስትም ፈተናን እንዲያደርግ እያወቅን
በመከራችን ደግሞ እንመካለን በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር ፍቅር በልባችን ስለፈሰሰ ተስፋ
አያሳፍርም።

ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እስኪመጣ ህይወታችንን ከጭቆናና 2መንከራተት የምንድን የሚመስለን ሰዎች እንኖር
ይሆናል አይምሰላችሁ አንድ አንጥረኛ ለብረት የፈለገውን ቅርስ ለመስጠት በእሳት ያገለግለዋል።እንዲሁም የሰማይ
አባታችን ልጁን እንመስል ዘንድ በህይዎታችን ጫና(መከራ)ይጠቀምብናል።ሮሜ 8:28_29

እግዚአብሄር አምላካችን በዚህ አለም ጫናዎች እንዲያጋጥሙን የሚያደርገው ስለ ሶስት ምክኒያቶች ነው።

1)ትዕግስት ዕብ 12:2 ጌታ እየሱስ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግዞ በእግዚአብሄር በዙፋኑ
ላይ ተቀምጧልና እናም መከራን ሁሉ ብንታገስ በቀኙ መቀመጥ ይሆንልናል።

2)ምስክርነት በመከራ ስናልፍ እግዚአብሄር የምንፈልገውን ሊያደርግ ታማኝ መሆኑን ለመመስከር በእርሱ
መደገፍን እንማራለን።
3)ተስፋ መዝ 41(42)፡5 ነፍሴ ሆይ ለምን ታዝኛለሽ ለምንስ ታውኪኛለሽ?የፊቴን መዳህኒት አምላኬን
አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሄር ታመኝ ተስፋሽ እርሱ ብቻ ይሁን።

መከራን መሸከም ስንማር የአባታችን ታማኝነት ስናውቅና ስንረዳ ተስፋችን በእግዚአብሄር ላይ እንጥላለን እርሱም
ታማኝ ስለሆነ ይህ ተስፋ ሳይሆን የቀረበት ጊዜ የለም።

3ኛ መመካታችን ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን አሁን መታረቅን ባገኘንበት በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ በኩል
በእግዚአብሄር ደግሞ እንመካለን ሮሜ 5:11

በዚህ ሰላም

You might also like