You are on page 1of 2

1

ምዕራፍ፩፡ ሰው እና ምድራዊው ዓለም


1.1 የሰው ልጅ እና ምድራዊው ዓለም

ሰው በምድር ላይ የተፈጠረ ሕይወታዊ ፍጥረትይኹን እንጅ የሰማያዊው ዓለም ፍጥረታት


ነፍሳዊ አካል እና ባሕርይ በሥጋው ውስጥ አለ1፡፡ ሰብዓዊ አካላት (ሰዎች) ወደ ሰማየ-
ሰማያት ወጥተው የወደቁ መላዕክትን አቤቱታ ለሰው ልጅ (ፈጣሪ) አቅርበዋል፤
እንዲኹም ሰዎች በነፍሳዊ አካላቸው ሰማያትና ምስጢራትን መርምረዋል፡፡ከምድራዊው
ዓለም በተጨማሪ ገነት፣ ሲኦል፣ ብሔረ ሕያዋን፣ ብሔረ ብጹዓን በሚባሉት የምድራዊ
ሰማያት2 ዓለማት በነጻነት የሚንቀሳቀሱ ሰዋስወ ጽድቅ የሚባሉ ቅዱሳን ሰብዓውያን አሉ፡
፡ ቅዱሳን ሰብዓውያን በፈጣሪ ፈቃድ ከዓለመ መላእክት በላይ አርባዕቱ እንስሳት ያሉበትን
ሰማያዊ ክበብ አልፈው ፈጣሪ ማደሪያ ገብተው ሰማያዊ ሥርዐትን ተምረው በምድራዊው
ዓለም ቤተ-መቅደስ እንዲተገበር አድርገዋል፡፡ በዚህም ሥርዐት ሰማያዊና ምድራዊ
ምስጢራትን በመመርመር ታላቅ ኾነው ኖረዋል፡፡

ምንም እንኳ የሰው ልጆች ከመላእክት የተሰወረውን ሰማያዊ ምስጢራትና ጥበብን


ማግኘት የቻሉ እና የተገበሩ ይኹኑ እንጅ፣ ሰማያዊ ኀይላት በሰዎች እና በሚኖሩባት
ምድር ላይ የተለያዩ ፈተናዎችን አምጥተውባቸዋል፡፡ በቅዱሳን መጽሐፍት
እንደተጠቀሰው፣ በቅዱስ ኖኅ ዘመን የተከሰተው የጥፋት ውሃ መላእክት ከሰው ልጅ ሴት
ልጆች ጋር ጋብቻ በመመሥረታቸውና የወለዷቸውም ልጆች አዲስ ፍጥረታት
በመኾናቸው ነው፡፡ እነዚኽ ግዙፍ ፍጥረታት መሬት ለምግብነት የለገሰቻቸውን ነገሮች
ኹሉ ቢመገቡም፤ መጥገብ የሚችሉ አልነበሩም፡፡ ስለዚህ የመሬት አካላትን ኹሉ
መብላት ጀመሩ፡፡ ያም አልበቃቸው ብሎ በሕይወት ለመቆየት እርስ በእርስ መበላላት
ጀመሩ፡፡ ይኽ የተፈጥሮ መዛባት እና ጥፋት በሰው ልጆችም ሆነ በሌሎች መሬታዊ
ሕይወታውያን ላይ ትልቅ ችግር አስከተለ፡፡ በዚኽ የተነሳ፣ በተፈጥሮ መዛባት ምክንያት
ምድር ልትጠፋ ስትቃረብ፣ ፍጥረታቱ በሰማያዊ ሥልጣናት በንፍር ውሃ እንዲጠፉ
ተደረገ፡፡ ይኽን ተከትሎ፣ መሬት ቀደም ብሎ የነበራትን የኀይል ጸጋ አጣች፣ የጊዜና
የግዝፈት መጠኗም ተቀየረ፤ በውስጧ ያሉ ሕይወታውያን ሥነ-ፍጥረታዊ ሥርዐትም
በእጅጉ ተለወጠ፡፡ ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረው ሰማያዊ ሥርዐትም እንዲኹ ተዳፈነ፡፡

1
ቅዳሴ ማርያም ንባብና ትጓሜው ምዕራፍ 5፡ ቁ 50
2
ምድራዊ ሰማያት ማለት ነባራዊው (ፊዚካል) ዓለም ማለት ነው፡ በሌላ ቋንቋ በፀሓይ
ሥርዐት የተጠቃለለው ዓለም ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ ሰማየ-ሰማያት ማለት ከፊዚካሉ
ዓለም በተለየ መንፈሳውያን ፍጥረታት የሚኖሩበት ዓለም ማለት ነው፡፡
2

ከአዳም ውድቀት በኋላ የነበረው የቤተ መቅደስ ሥርዐት፣ ለዐሥር ትውልድ ያኽል
ሰዎችን የጥበብ ባለቤት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በመሬት ላይ (በተለይም አኹን አፍሪካ እና
እስያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ) በሰማያዊ ሥልጣናት ጣልቃብነት በደረሰው ጥፋት
ሳቢያ፣ በሰዎች ንቃት እና ጥበብ የተገነባው ሥልጣኔ ሙሉ በሙሉ ፈራረሰ፡፡
የተከለከሉ ምስጢራትን ለሰው ልጆች ያስተማሩት የወደቁ አማልክት ናቸው፡፡ ለምሳሌ
ለሴቶች የምንዝር ጌጥን፣ማለትም ቅንድብን መቀንደብን፣ ሰውነትን በመብሳት ብረት
ማጥለቅን፤ ንቅሳትን፤ ሰውነትን አራቁቶ መኼድን አስተምረዋል፡፡ እንዲሁም አውዳሚ
የጦር መሳሪያዎችን፣ ጥንቆላንና ሟርትን፣ ቂም በቀልን የመሳሰሉትን አስጠንተዋል፡፡
ለአማልክት መወለድ ምክንያት የሆኑት መላእክትን፣ ቅዱሳን መላእክት በመሬት ውስጥ
ባሉ የእሳት ባሕሮች እና በተራሮች ከርስ እንዲሁም በጥልቅ የውሃ አካላት ውስጥ
ቀብረዋቸዋል፡፡ ከዚያ የውሃ ሙላት እና የመሬት ነውጥ በኋላ፣ ቀደሞ የነበረው መልክዐ
ምድር ተለውጧል፡፡ የዕፀዋትና እንስሳት ብዛትም ኾነ ዓይነት ቀንሷል፡፡ ከዚያ ክሥተት
በኋላ የሰው ልጆች ከጥበባዊው ሥርዐት በመንፈስም ኾነ በዕውቀት ርቀው ኖሩ፡፡
የወደቁ መላእክት ጣልቃ ገብነት የእግዚአብሔር ልጆች ይኖሩባት የነበረችውን ኢትዮጵያ
ለጥፋት ዳርጓታል፡፡ ከማየ-አይኅ በኋላ ኢትዮጵያ ኦና ሐገር ሆነች፡፡ ማዕከላዊው
ኢትዮጵያም በቀይ ባሕር አማካኝነት ከእስያ ጋር ተለያየ፡፡ተለያየ፡፡በኋላኛው ዘመን የኖኅ
ልጆች ምድርን ሲከፋፈሉ ባዶ በነበረችው ኢትዮጵያ፣ የተለያዩ ሕዝቦች በመንፈስ ቅዱስ
ፈቃድ እየመጡ በፍቅር እና በሰላም ይኖሩባት ጀመር፡፡ እነዚኽን ሕዝቦች ካህኑ መልከ
ጼዴቅ (በቀደመው የእግዚአብሔር ልጆች ርስት ሐገር በሚኖሩበት ጊዜ የአዳምን አጽም
እንደ መሰዊያ በመጠቀም ከእግዚአብሔር ጋር ይገናኝ የነበረው) እየተገለጸ ይባርካቸውና
የቀደመውን ሥርዐት ያስተምራቸው ጀመር፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ የጥንታዊው የሰው ልጅ
የእምነት ቦታ ኾነች፡፡
የግብፅ የታላላቅ ፒራሚዶች ግንባታ እና ሌሎች የዓለም ድንቃ ድንቅ እየተባሉ የሚጠሩት
የሰው ልጅ የሥልጣኔ አሻራዎች ምንጫቸው የዛሬው የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ሐገራትና
ሕዝቦች ሲኾኑ፣ የሥልጣኔዎቹ አዕምሮና ልብ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ የእነዚህ ሕዝቦች
የቀደመ ማኅበረ-ፖለቲካ እና ሥርዐተ-መንግሥት የሚመራው በካህን ንጉሥ እንደነበር
አፈታሪኮች ይመሰክራሉ፡፡
በኋላ ላይ ግን መንፈሳዊው ሥርዐት በሃይማኖታዊ ሥርዐት በመተካቱ ሕዝቦች
ተከባብረው በራሳቸው ሥርዐት ከመኖር ይልቅ አንዱ የአንዱን ሥርዐት በመገርሰስ የራስን
የበላይነት በሌሎች ላይ ለመጫን መሯሯጥ ተጀመረ፡፡ ይኽም የሰው ልጆች የእርስ
በእርስ ጦርነትን እንደ ባሕል በመቁጠር ከፍ ሲልም እንደ ተፈጥሮ ሥርዐት በመውሰድ
እስካለንበት ዘመን ቀጠሉበት፡፡የመንፈሳዊ መንግሥት ሥርዐት ጀማሪ ተብሎ
የሚታወቀው የዘላላም ክህነት ያለው መልከ ጸዴቅ ተከባብረው በራሳቸው ሥርዐት ከ::

You might also like