You are on page 1of 2

12/31/2020 የክልሎች ሕገመንግሥት የዜጎችን በአገራቸው የመኖር መብት የነፈገ መሆኑ ተገለጸ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

የክልሎች ሕገመንግሥት የዜጎችን በአገራቸው የመኖር መብት የነፈገ መሆኑ


ተገለጸ
December 31, 2020

በሀገሪቱ እየተፈጠሩ ላሉ ግጭቶች መሰረት መሆኑም ተጠቆመ

ጽጌረዳ ጫንያለው

አዲስ አበባ፡- የክልሎች ሕገመንግሥት የዜጎች በአገራቸው የመኖር መብት የነፈገ በመሆኑ በየቦታው ግጭቶች እንዲበራከቱ ማድረጉን የሕግና የፖለቲካ ሳይንስ
ምሁራን ገለጹ።

በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የሕግና ታሪክ መምህሩ ዶክተር አልማው ክፍሌ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ የኢትዮጵያ ሕገመንግስት መልካም ነገሮች እንዳሉት
ሁሉ ክፋት ያዘሉ ሕጎችም የተካተቱበት ነው። በተለይም ከክልሎች አወቃቀር ጀምሮ ያለው የብሔር፣ የቋንቋ አስተሳሰብ ብዙ ነገሮችን አዛብቷል።

ከእነዚህ መካከል ክልሎች ሕገመንግስት ሲያረቁ አግላይ እንጂ አቃፊና አሳታፊ እንዲሆን አድርገው እንዳልሆነ ያመለከቱት ዶክተር አልማው ፣ ልዩነቱ ገዝፎ አንድ
ብሔር በአንድ ክልል ላይ ፈላጭ ቆራጭ እንዲሆን ማድረጉን አስታውቀዋል ።

አገሪቱ ስትሰራ በሕዝቦች መስተጋብር፣ በሕዝቦች ትግል፣ በሕዝቦች ተሳትፎ እንጂ በአንድ ብሔር ማንነትና ብልጽግና እንዳልሆነ የሚያነሱት ዶክተር አልማው፤
የክልሎች ሕገመንግሥት አቀራረጽ ግን ከዚህ የተለየ እንደሆነ አመልክተዋል ።

“የክልሎች ሕገመንግሥት ሲቀረጽ ልዩነቶችን አግዝፎ ሕብረ ብሔራዊነትን አክስቶ ያቀርባል። በሕግ የተሰጠን የባለቤትነት መብት የእኛ ብቻ ነው በሚል
በውጣልኝ አስተሳሰብ ተገንብቷል። ይህ ደግሞ ዜጎች በፈለጋቸው ቦታ የመኖር መብታቸውን ከመንፈጉም በላይ ያፈሩትን ሀብት ጭምር ለዚያ ክልል
እንዲያስረክቡና ባዷቸውን እንዲሰደዱ ያደርጋል። ግጭቶችም ቢሆኑ የአገር ይገባኛል ባይነት ጥያቄዎች የፈጠሯቸው ናቸው” ብለዋል።

የፌዴራሉ ሕገ መንግሥትም ቢሆን በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መልኩ የተቀረጸ እንደሆነ የሚያነሱት ዶክተር አልማው፤ አስተሳሰቡ አንዱን ገዳይ አንዱን ተገዳይ፣
አንዱን ባለቤት ሌላውን ጥገኛ፣ አንዱን ሰዳጅ ሌላውን ተሰዳጅ አድርጎም የፈረጀ ነው። ጨቋኝህን አጥፋ የሚል ሕጋዊ መብትም የሚያጎናጽፍ መልክ አለው
ብለዋል ። ስለሆነም ክልሎች በህግ የተሰጣቸውን መብት እንዲጠቀሙና የአንተ አይደለም እንዲሉ እንዳደረጋቸው ጠቁመዋል ።

https://www.press.et/Ama/?p=38522 1/2
12/31/2020 የክልሎች ሕገመንግሥት የዜጎችን በአገራቸው የመኖር መብት የነፈገ መሆኑ ተገለጸ | የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

እንደ ዶክተር አልማው ገለጻ፤ የክልሎች ሕገ መንግስት በውስጥህ የሚገኙ አካላትን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የመኖር መብትን ከልክላቸው የሚል ነው። በዚህም
በክልሎቹ ተጠቃሚነታቸው የተረጋገጠላቸው ተወላጆች ከኖሩበት ውጪ አገራቸውን እንዳያዩ፤ የሌሎችን ቋንቋ እንዳይሰሙና እንዳይናገሩ፣ ባህላቸውን
እንዳይኖሩት አድርጓቸዋል።

የክልል አመራሮችም ተወላጁን እንጂ የሌሎች ዜጎችን ሉዓላዊነት እንዳያረጋግጡ ገድቧቸዋል። ስለዚህ ሕገ መንግስቱ ብሔር እንጂ ዜግነት ዋጋ እንዳይሰጠው
አድርጓል።

የክልሎች ሕገ መንግሥት ከመሰረቱ የተጣመመ መሆኑ መፈናቀል ብቻ ሳይሆን ሞትን በስፋት እንድናስተናግድ እንዳደረገ የሚገልጹት ዶክተር አልማው፤ ሕገ
መንግሥቱ የማሳደድና የመግደል፣ የሀብትና የስልጣን መብት መንጠቅ፣ ልዩነትን ያለማስተናገድ መብት የሰጠ መሆኑ ይበልጥ አደጋ ውስጥ እንድንገባ አድርጓል
ብለዋል።

አገሪቱ የተገነባችበትን ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ባህሉንና ሀይማኖትን የጣሰ ሆኗል ያሉት ዶክተር አልማው፤ ሕዝቦችም ባላመኑት ነገር እንዲገዙ ጫና ፈጥሯል፤
ስለዚህም ሕገመንግስቱ የጭቅጭቅ፣ የግጭት፣ የመገዳደል መሰረታዊ ግብዓት ሆኖ የማገልገሉ ሁኔታው መስፋቱንም አብራርተዋል።

አሁን ያለው ሕገመንግሥት በሕዝባዊ ተሳትፎ አገራዊ ማንነቱን ይዞ በባህልና ታሪኩ ተቃኝቶ በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሕገመንግስት እስካልተቀየረ ድረስ አሁንም
አገራዊ ስሜትን ማምጣት እንዲሁም ግጭቶችን ማስቆም እንደማይቻል የሚያነሱት ዶክተር አልማው፤ ሕዝቦች በራሳቸው ራዕይ መዳኘት እንዲችሉ መሰራት
እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ በበኩላቸው የዶክተር አልማውን ሀሳብ ይጋራሉ።
የኢፌዴሪ ሕገመንግስት መግቢያው ላይ ‹‹የተዛባ ግንኙነታችን›› በሚል በህዝብ መካከል የተዛባ ግንኙነት እንዳለ በግልጽ ሰብኳል ይላሉ።

ይህ ደግሞ ክልሎች የተዛባውን ለማካካስ የእኔ ብቻ በሚል ሕገመንግስት ቀርጸው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓቸዋል። ለዚህም የድሬዳዋና የቤኒሻንጉልን ሕገ
መንግስቶች ማየት በቂ እንደሆነ ተናግረዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አርባ ለኦሮሞና አርባ ለሶማሌ ብሔረሰቦች ባለቤትነት መብት ሰጥቶ 20 በመቶ የሚሆነውን ለሌሎች ብሎ ያስቀምጣል። ይህ
የሚያሳየው ደግሞ ምንም እንኳን አርባውን ከወሰዱት ሌሎች ብሔረሰቦች ቢበልጡም የባለቤትነት መብታቸው አይኖራቸውም።

በተመሳሳይ የቤኒሻንጉል ክልል ጉዳይም ለበርታ ፣ ለሽናሻ፣ ለጉምዝ፣ ለኦሞና ማኦ ብሔረሰቦች ብቻ ሁሉንም መብት ያጎናጸፈ ነው። ሌላውን አገር አልባ ያደረገ
ነው። ስለዚህም ግጭቶችን በሕገ መንግስት አስደግፎ የማንቀሳቀስ ተግባር እንዲከወን የሆነው ለዚህ ነው ብለዋል።

ነውረኛ ሕገመንግስት ከተቋቋመ ነውረኛ ሥራ ይጠበቃል የሚሉት ረዳት ፕሮፌሰሩ፤ በቤኒሻንጉል ውስጥ የአማራና የኦሮሞ ማህበረሰብ ጥገኛ ሆኖ በሕግ
ስለተደነገገ የፈለገውን ማድረግ ቀርቶ የመኖርም መብት የለውም። በዚህም መሬት ቢነጠቅ ቢፈናቀል አያስገርምም።

አመራሩ በራሱ በሞግዚት እንዲተዳደር ተደርጎ የተመሰረተ በመሆኑ የሚጻፍለትን “አጤሬራ” እየተቀበለ ያስፈጽማል። ስለዚህም ህወሓት መራሹ ሕገመንግስት
አገርን እየፈተነ ያለው በክልሎች አማካኝነት እንደሆነ አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ሕግ ከክልል ክልል መስፈር አለመቻሉም ሌላው ፈተና ነው። አንዱ ክልል ላይ ሄዶ መስራት እንዳይቻል ያደርጋል። ለተወሰኑ ቡድኖችም ክልሉ
አገልጋይ እንዲሆን እድል ይሰጣል።

አንድ ክልል አንድ ብሔር ሆኖ እስከመጨረሻው ይቀጥልና አገር አልባ ሰዎች እንዲኖሩ ይሆናል። ስለዚህም ሕጎች አገርን ገንቢ እንጂ አገርን ከፋፋይ እንዳይሆኑ
ተደርገው ከእንደገና መታየት አለባቸው ብለዋል።

አዲስ ዘመን ታህሳስ 22/2013

https://www.press.et/Ama/?p=38522 2/2

You might also like