You are on page 1of 6

ጥቂቷን አትናቅ

እናት አንድ ጊዜ ልጇን ጠየቀችው

ተስፈኛ ተማሪ ሆኖ ያገኘችውን እንደዚህ አለችው

“ማሙሽዬ ልጄ ትልቅ ስትሆንልኝ

ኮሌጅ ተመርቀህ ሥራ ስትይዝልኝ

ሀገር ምታኮራ ምን ሆነህ ነው ልጄ

ምን ላይ ነው ማገኝህ በዛ ዘመን ሄጄ”

ማሙሽም እናቱን ሰምቷት ተደስቶ

የሚነግራትን መልስ ቀድሞኑ አስልቶ

ፍላጎቱን ገፍታ ስለጠየቀችው

እሱም መለሰላት እያደመጠችው

“እማዬ እናቴ የኔ አስተማሪ

እኔን በጥያቄሽ ስትመረምሪ

ደስ ይለኛል በጣም ምኞቴ ቢሰምርር

ሳድግ የምፈልገው መሆን ነው ዶክተር”

እናቱም ነገሩን በጥንቃቄ ዓይታ

ልጇን አስተዋለች ምኞቱን በርጋታ

“ልጄ ወዳጄ ሆይ አንተ የኔ ጉጉ

ምንድን ነው ምክንያትህ ዶክተር መፈለጉ”

“ውዲቷ እናቴ ዶክተር መፈለጌ

ጋወን ከስቴቶኮፕ አንድ ላይ ሰንጌ

የዶክተሩ ሙያ በግልጽ ይታወቃል

ሰው ማከም መሆኑ ምን ያጠያይቃል”

“አዎን ማሙሽዬ ልክ ብለኻልል

ከኑሮ ኑሮ ግን ሔደህ ስትዘልል


ሕልምህን ማጤኑ ያስፈልግሃል

ሰው መርዳቱ በጄ መልካም ነው ሀሳቡ

ሐኪም የመሆኑ በጎ ነው ጥበቡ

በሽታው ካንጀት ነው ወይንስ ከልቡ

ብሎ የመጠየቅ ተሰጥቶታል ሐኪም

ፈጣሪ በሰጠው በማዳን ከንፈሩ ድውያንን እንዲስም

ነገር ግን ፍላጎት ግብን አያሳካም

ብቻውን ከሆነ ምኞት አያረካም

በተስፋ እንጀራ መኖር ከንቱ ድካም

ጊዜ ስትሰጥ ነው የሚሆነው መልካም”

“እማዬ አልገባኝም ምን ትይኛለሽ

ግራ አገብቶኛል ይህ ንግግርሽ

ረዥም ጊዜ ነው ይህን ስሰማሽ

ልቤ ታወከብኝ አልኩኝ ርብሽብሽ”

“አታስብ ልጄ ሆይ ምንም አትከፋ

በነገርኩህ ቃላት ተው አትቁረጥ ተስፋ

እኔስ የመከርኩህ ነው እንድትለፋ

ምኞትህ ከምኞት ዳበር ይበል ይስፋ

ጥበብን እንድታውቅ እንድትመረምር

ትኬቱን እንድትቆርጥ ለመሆን ዶክተር

በል ልጄ ተነሣ ካሁኑ ጀምር

ከቅድሙ ትንሽ ቢሰማው እፎይታ

እናት በሰጠችው የቃላት ጋጋታ

አሁንም ግን ልቡ አልቻለም ሊገታ

ዶክተር አልሆንም ወይ እያለ ሲመታ

አሰናሰነና ነገሩን በርጋታ


አሁንም ሳብ አርጎ የጥያቄ ቃታ

“እናቴ እምዬ፣ ምኞቴ በልኬ እንደምን ይሰፋ

ዶክተር ለመሆኔ ብለፋ ብለፋ

ምንድን ነው መፍትሔው ከኔ ሚጠበቀው

ንገሪኝ እናቴ ምንድን ነው ማረገው”

ትንሽ ልጅ እናቱን እንዲህ ቢጠይቃት

ቢጨንቀው ቢጠበው ሕልሙን ለማሳካት

እናትም ተረድታ

የቃላቱን ነገር እርግፍ አርጋ ትታ

በምሣሌ ጥበብ አስመለከተችው

ቃሏን በተግባር ላይ እንዲህ አዋለችው

ያጋጣሚ ነገር የማሙሽ እጆችች

የጀርም ባክቴሪያ መጫወቻዎችች

ሆነው ነበርና በጣም ቆሻሾችች

እናቱም ነገሯን በዚህ ገለጸችች

የጣፋጭ ምግቦችን ልዩ ስብጥርር

ሁሉንም ወዳፉ እንዲወረውር

ምኑንም ምኑንም አምጥታ ብትሰጠው

ማሙዬ ማሙካ አንስቶ ገመጠው

አወየው ማሙሺ የመድኃኒት ጀግና

የወደፊት ሐኪም ትንሽ ብላቴና

በዋዛ መስሎታል ሚገኝ ዱክትርና

እናቱም ማሙሽን “አይ ማሙሽ አይ ማሙሽ

ይኼኔ ነው ሚያመው ሆድህ የሚረበሽ

ከመብላትህ በፊት እጅህን ታጥበሃል?

ከሐኪም ክልከላ መቼ ታቅበሃል


ግን ትፈልጋለህ መሆኑን ሐኪም

ትንሹን ትዕዛዝ በቅጥ ሳትፈጽም”

ይኼነዜ ማሙሽ ነገሩ ገብቶታል

እጅ ሳይታጠቡ ዱክትርና የታል?

ማሙሽስ ሕጻን ነው እኛ ትልቆቹስ

አንዱ አገር ሲመራ ወይ መንገድ ሲቀይስ

አንደኛው አዝናንቶ ሒወቱን ሲቀልስ

ወይም እንዳክሊሉ መባሉ ዶክተር

አልያም ደግሞ አብራሪ አልያም መምህር

ወይ ከምበጡር ሠሪ ወይ ደሞ ነጋዴ

ምን እንፈልጋለን ሌላስ ይኖር እንዴ

ፍላጎትህ እኮ ይሆናል ሩጫ

ይኼኔ ቅልጥማም ትሆናለህ ቢጫ

ነገር ግን ወንድሜ፣ ሲርሮጥ ተመልክተህ አምስትሺ አሥር ሺ

እነሱ እየሮጡ አንት ወንበር ስታሺ

ዱብ ዱብ ካላልክ፣ ሯጭ የሚኮነው በምንድነው እሺ

ለረዣዥም መንገድ ለትልቅ መሄጃ

ጅማሮው መሆኑን ዕወቅ አንድ እርምጃ

አንዱን ካልተራመድክ መሄድህን እንጃ

ፈጣሪም ነቢዩን ሲመርጠው ሙሴን

በአመራረጡ አየሁ ራሴን

ሙሴ በ፳ኤል ላይ ከፍ ብሎ የተሾመው

ምን ጥበብ አድርጎ ምን ምታት ሠርቶ ነው?

ወይስ በጣም ሀብታም በጣም ባለጠጋ


ግን ለዛ ነው እንዴ የተሰጠው ዋጋ

የንጉሥነት ዘውድ የንግሥና ፀጋ

እንዲ እንዳይመስላችሁ ስሙኝ ወንድሞቼ

መለስ ላርጋችሁ ወይ እሱን ጎትቼ

ላምጣላችሁ መሠል ሙሴን ላሳያችሁ

እንድትማሩበት ጉዱን ላጫውታችሁ

እንዲህ ነው……

ሙሴ ምንም ቢሆን በፈርዖን ተወዳጅ

ሳይነካ ያደገ የቤተመንግሥት ልጅ

አሳዳጊዎቹ ግብጻዊያን ቢሆኑ

ልቡ ግን ነበረ ለዕብራውያኑ

ሁሌ ይቆጨዋል የነሱ ግርፋት

ይከፋል ይነድዳል በግብጻውያን ቅጣት

ከለታት ባንድ ቀን፣ ግብጻዊው ሲቀጥል የቀድሞ ተግባሩን

ሲቀጣ አስተውሎ ዕብራዊ ወንድሙን

ታዲያ ሙሴ መልካም ለወገኑ አግዞ

የቁጣ ቅጣቱን ግብጻዊው ላይ መዞ

ለምን መታህ ብሎ ግብጻዊውን ጣለው

ያም ግፈኛ ሞተ ሙሴ ሳያስበው

ዋናው ግን መግደሉ አይደለም ወገኔ

መተጋገዙ ነው የሙሴ እንኳ ወኔ

ፈጣሪም ይኸን ሰው ስለተረዳ ነው

በረዳው ወገኑ በ፳ኤል ላይ የሾመው

ሙሴን ተመልከቱት ትንሽ አደረገ

ከብዙ ዕብራዊ አንድ ወንድም ታደገ

ታዲያ ይኼኮ ነው መታመን በጥቂት

ብዙ ላይ መድረሱ ከትንሽ ልቃቂት


እኔ እነግርሃለሁ አንተ ግን ተገንዘብ

ነገሩን በማጤን ልብ ብለህ አስብ

ትልቅ ምኞትህን ለማሳካት ካሰብህ

የማይሆን ነውና ትንሽ ነገር ንቀህ

እግዚአብሔር ፈጣሪ በብዙ እንዲሾመን

በጥቂቷ ነገር ይገባል መታመን

ስላነበባችሀሁ አመሠግናለሁ

ይገረም ብሥራት ነኝ ሁሌም እጽፋለሁ

You might also like