Professional Documents
Culture Documents
ክዋኔ ሪፖርት
ክዋኔ ሪፖርት
አዲስ አበባ
ክፍል አንድ
መግቢያ፡-
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 1151/2011 እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ዓላማው በመገናኛ ብዙኃን በፕሬስና
በሌሎች አግባብ ባላቸው ሕጐች መሠረት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚፈፀመው አበይትና ወቅታዊ ጉዳዮች
እንዲሁም ትምህርታዊና አዝናኝ ዝግጅቶችን ለሕዝብ ማቅረብ ሲሆን የድርጅቱ በጀት በመንግሥት ከሚመደብለት
የድጋፍ በጀት እና በዚህ አዋጅ መሠረት ከሚሰበሰብ የአገልግሎት ክፍያ እንዲሁም ከሌሎች ምንጮች ናቸው፡፡
የኦዲቱ አላማ
በድርጅቱ የሚከናወኑ ግዥዎች እኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ የሚከናወኑ መሆኑና የግዥ ሥርአቱም በመመሪያና
በደንብ እንደዚሁም በመንግስት አዋጅ የተደገፈ መሆኑን፣ የግዥ አፈፃፀም ለመከታተል የሚያስችል ብቃት
ያለዉ የግዥ ሥርአት የተዘረጋና ስራ ላይ የዋለ መሆኑን በመገምገም የድርጅቱ ግዥ ሂደት ላይ የሚታዩ ድክመቶችን
እና መንስኤዎቻቸዉን በመለየት የማሻሻያ ሀሳብ ለማቅረብ ነው፡፡
ከላይ የተገለጸውን የኦዲት ዓላማ ለማሳካት አ ን ድ የኦዲት የትኩረት አቅጣጫ ተለይቷል፡፡ እሱም፡-
1. የድርጅቱ የግዥ ሥርዓት ወጪ ቆጣቢ ብቃት ያለው እና ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጥ፣
የኦዲት መመዘኛ መስፈርቶች
ለዝርዝር ኦዲቱ ለተመረጡት አንድ የኦዲት የትኩረት አቅጣጫዎች 28 መመዘኛ መስፈርቶች የተዘጋጁ ሲሆን፣
መመዘኛ መስፈርቶቹ ከዚህ ሪፖርት ጋር (በአባሪ 1) ተያይዘዋል፡፡
የኦዲቱ ወሰን
ዝርዝር ኦዲቱ የሚሸፍነዉ ከ 2013 ሐምሌ- መጋቢት 2013 ዓ.ም ያለውን የዘኝ ወራት የግዥ አፈፃፀም
ሥርዓት ነዉ፡፡
የኦዲቱ ዘዴ
ዝርዝር ኦዲቱ የተከናወነው፣ በድርጅቱ በተከናወኑ የግዥዎች አፈፃፀምን በናሙና በመምረጥ
ከሚመለከታቸው ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ጋር ጥያቄዎችን በማቅረብ እናቃለ መጠይቅ በማድረግ
ተከናውኗል፡፡
ክፍል ሁለት
የኦዲት ግኝቶች
1-የኦዲቱ ግኝቶች የድርጅቱ የግዥ መመሪያ ወቅታዊ አለመደረጉን በተመለከተ፡-
ድርጅቱ እንደገና በተቋቋመዉ አዋጅ ቁጥር 1151/2011 መሰረት ለሚያከናዉነዉ የቋሚና አላቂ ዕቃዎች እንዲሁም
ያአግልገሎት ግዥ የሚያገለግል ወቅታዊ የሆነ የግዥ መመሪያ ሊኖረዉና በሚወጣዉ መመሪያ መሰረት ሊፈፀም ይገባል፡፡
ነገር ግን የድርጅቱ የ 2013 በጀት አመት እስከ መጋቢት ወር የግዥ አፈፃፀም ሲታይ በአዋጁ መሰረት የወጣ
መመሪያ አለመኖሩን በተሰጠዉ ቃለ መጠይቅ የተረጋገጠ ሲሆን እንደዚሁም አብዛኛው የግዥ ክንዉን ሲታይ
የመንግስት የግዥ አዋጅ ቁጥር 649/2001 መሰረትም ያልተፈፀመ መሆኑን በቀረቡት ሰነዶች ሳምፕል
መሠረት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ይሁን እንጂ የበላይ አመራሩ መመሪያዉ ተዘጋጅቷል ነገር ግን ለቦርድ ቀርቦ አልፀደቀም፡፡ ይሄ ግኝት በ 2012
የዋና ኦዲት ግኝት ላይም ቀርቧል፡፡ስለዚህ ማኔጅመንቱ አስተያየት ሰጥቶበት መመሪያዉን ቶሎ ቦርዱ
እንዲያፀድቀዉ ማድረግ ይገባል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
የፌደራል መንግሥት የግዥ መመሪያ አንቀጽ 25 (7) (ሀ) ላይ የመንግስት መ/ቤት ዕቅድ ውስጥ ያልተካተቱ ዋጋቸው
ከብር 5,000.00(አምስት ሺ) ያልበለጠ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ወይም በጉዞ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከመፍታት ጋር
የተያያዙ የቀጥታ ግዥዎችን ከማናቸውም ሻጭ ድርጅት መፈፀም ይችላል፡፡ ሆኖም በዚህ ዓይነት የሚፈፀሙ ጥቃቅን ግዥዎች
ድምር በአንድ የበጀት ዓመት ውሰጥ ከብር 75,000.00 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) መብለጥ አይኖርበትም ይላል፡፡
ነገር ግን ከታች በሰንጠረዡ እንተዘረዘረው በ 2013 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር የቁጥቁጥ ግዥ አፈፃፀም ሲታይ በድምሩ
ብር 111,419.78 ሲሆን አመት ሳይ ሞላዉ(በ 9 ወር ውስጥ) ለአመቱ ከተፈቀደው በላይ በድምር ብር 36,419.78
በብልጫ ተፈፅሞ መገኘቱን በቀረቡት ሰነዶች ሳምፕል መሠርት የተረጋገጠ መሆኑ እንዲሁም በ 2013 በጀት ዓ.ም
በግልፅ ጨረታ ይገዛሉ ተብሎ የታቀዱት ሁሉ በቁጥቁጥ ግዥ ተፈፀሞ መገኘቱ፡፡
ይሁን እንጂ የበላይ አመራሩ የሰጠዉ መልስ የመስሪያቤቱ አሰራር የተለየ በመሆኑ አብሮ የሚህድ የድርጅቱ
የግዥ መመሪያ ባለመፅደቁ ከድርጅቱ የሥራ ሁኔታ ጋር የሚመጡ ችግሮችን መፍትሄ ማግኝት አልተቻለም፡፡
እንደዚሁም የ 2014 እቅድ አልፀደቀም አመራሩ እጅ ላይ ነዉ ያለዉ እንደ አመራር ተቀብለን የበላይ አመራሩ
መመሪያዉን እና እቅዱን ቶሎ ቢያፀድቅ ጥሩ ነዉ በማለት ሃሳባቸዉን ተናገረዋል፡፡
ተ.ቁ የግዥዉ ምክንያት የደረሰኝ ቁጥር ቀን የብር መጠን በዓመቱ የግዥ ዕቅድ ላይ
መኖሩ
1 የጠጠርና የብሎኬት ግዥ 8139 14/4/2013 7,240.00
2 የሆቴል አገልገሎት ግዥ 9132 30/07/2013 7,574.22
3 የአሸዋ ግዥ 9070 1 4/07/2013 8,510.00
የለቀማ ግዥ(ከህንፃመሳሪያ
4 የሚገኝ) 8926 2/7/2013 10,000.00
5 የአንድ መኪና ድንጋይና አሸዋ ግዥ 8076 9/4/2013 12,095.01
6 የመኪና መፍቻ ዕቃዎች ግዥ 7891 24/03/2013 16,617.50
7 የአዳራሽ ኪራይ ግዥ 8908 1/7/2013 17,250.00
8 የናፍጣና የዘይት ፊልትሮ ግዥ 7863 21/03/2013 17,435.01
9 የእምነ በረድ ግዥ 9156 18/07/2013 65,000.00
10 የመኪና እስፔር ፓርት 8784 22/06/2013 879.12
11 የኬብል ግዥ 8751 17/06/2013 850.00
12 የሰርትፍከት ህትመት ግዥ 8808 22/06/2013 3,125.13
13 የፎቶግራፍ ህትመት ግዥ 10503 22/7/2013 600.00
ድምር 167,175.99
የበላይ አመራሩ አንዳንድ ግዥዎችን በተመለከተ በፕሮፎርማ ማግኘት አይቻልም ምክንያቱም አብዛኛዎቹ
አቅረቢዎች ፕሮፎርማ ለመስጠት ፍቃደኛ ስላልሆኑ ችግሩን ለመፍታት ተነጋግረን በቃለጉበኤ በመወሰን ግዥው
በቀጥታ ግዥ እንዲፈፀም ተደርጓል የሚል ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
ሆኖም ግን የበላይ አመራሩ ህግን ብቻ ጠብቆ መሄድ ስራዉ እንዲጓተት ስለሚያደርግ አመራሩ ስራ ተጓተተ
ማለት የለበትም፡፡ ቢሆንም ግን አመራሩ ብልሹ አሰራር እንዳይፈጠር የቁጥጥር ስረዓቱን ማጠናከር አለብን፡፡
ቀጣይ በሚፀድቀዉ መመሪያ ዉስጥ የፕሮፎርማ ግዥ ለምን አላማ እንደሚዉል በመመሪያዉ ዉስጥ ማካተት
አለበት በማለት ተናግረዋል፡፡
የ ፌ ደ ራ ል መ ን ግ ስ ት የ ግዥ አፈፃፀም መመሪያ አንቀፅ 24.3 ፊደል (ሀ) መሰረት በዋጋ ማቅረቢያ የሚፈፀም ግዥ መፈፀም
የሚቻለዉ የመንግስት መ/ቤቱ በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡት ሁሉም ተሳታፊዎች በዙር የመወዳደር እድል ማግኘታቸዉን እና
ለመ/ቤቱ ጠቃሚ የሆነ የተለየ ሁኔታ መኖሩ ካልተረጋገጠ በስተቀር አንድ ወይም የተወሰኑ አቅራቢዎችን ብቻ በተደጋጋሚ መጋበዝ
አይኖርባቸዉም ይላል፡፡
ነግር ግን ከታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ግዥዎች እና ተንቀሳቃሽ የፅህፈትና የጋዜጣ
መደርደሪያ የሁለቱም ለየብቻ በጠቅላላ ድምር ከ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ስለሆነ በጨረታ መግዛት
ሲቻል ከፋፍሎ በፕሮፎርማ ከመገዛቱም በላይ ለሌሎች አቅራቢዎች እድል ሳይሰጥ ከአራት አቅራቢዎች ብቻ ተለይቶ
ከኤልሳቤጥ ፈለቀች የመኪና እቃ መለዋወጫ፤ ኳሊቲ የመኪና እቃ መለዋወጫ፤ ፤ሞኤንኮ፤የሺዋስ አሰፋ እና ሳስኮ
ኢንዱስተሪያል ንግድና ትራንስፖርት በተደጋጋሚ አወዳድሮ ግዥ ተፈፅሞ የተገኘ መሆኑ፡፡
ሰነጠረዥ(1)
ተ.ቁ የግዥዉ ምክንያት የደረሰኝ ቁጥር ቀን የብር መጠን በዓመቱ የግዥ ዕቅድ ላይ መኖሩ
ድምር 254,226.72
ሰነጠረዥ(2)
አራት ተመሳሳይ አቅራቢዎች ሶስት ጊዜ ተወዳድረዉ ሶስት ጊዜም ከይስሃቅ ዘላለም ንግድ ድርጅት ብቻ
በድምሩ 588,052.50(አምስት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺህ ሃምሳ ሁለት ከ 50/100) ብር የተገዛ መሆኑ፡፡
ተ.ቁ የግዥዉ ምክንያት የደረሰኝ ቁጥር ቀን የብር መጠን በዓመቱ የግዥ ዕቅድ ላይ መኖሩ
1 ተንቀሳቃሽ የፅህፈትና የጋዜጣ መደርደሪያ 8115 13/06/2013 196,017.50
2 ተንቀሳቃሽ የፅህፈትና የጋዜጣ መደርደሪያ 8013 05/04/2013 196,017.50
3 ተንቀሳቃሽ የፅህፈትና የጋዜጣ መደርደሪያ 7926 28/03/2013 196,017.50
ድምር 588,052.50
6. የጨረታ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዶች የታሸጉባቸዉ ፖስታዎች ሲከፈቱ የታሸጉባቸዉ ፖስታዎች ላይ ቢያንስ ሶስት የግዥ ኮሚቴዎች
ሳይፈርሙ የተገዙ ዕቃዎች፡፡
የጨረታ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዶች አቀባበልና አከፋፈት ግልጽና ተጠያቂነትን ለመወጣት እንዲያስችሉ የጨረታ እና የዋጋ
ማወዳደሪያ ግዥ ሠነዶች ታሽገው የሚመጡባቸው ፖስታዎች ከሶስት ባላነሱ የግዥ ኮሚቴዎች ተፈርሞባቸው ከተከፈቱ
በኋላ በመረጃነት ከግዥ ሠነዶቹ ጋር ተያይዘው ሊቀመጡ ይገባል፡፡ በተጨማሪም የ ፌ ደ ራ ል መ ን ግ ስ ት የ ግዥ አፈፃፀም
መመሪያ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ 13 መሰረት የግዥ ማወዳደሪያ ሰነዶችን በቡድን በመሆን መገምገም እንዳለበት ይገልፃል፡፡
ነግር ግን በእያንዳንዱ የግዥ ክፍያ ሰነዶች ላይ ሙሉ የጨረታ ሰነዶች ተያይዘዉ የማይገኙ እና ለዋጋ
ማወዳደሪያ ግዥ ለቀረቡት የማወዳደሪያ ፖስታዎች ላይ ያልተፈረሙ እንዲሁም በአንድ ሰዉ ብቻ
ተፈርሞ ግዥ የተፈፅመ መሆኑ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፀ ሲሆን ይህ ደግሞ በቡድን ያላወዳደሩት
መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ መገኘቱ፡፡
በመሆኑም የበላይ አመራሩ በስራ ክፍሉ የሰዉ ሃይል እጥረት ምክንያት የተፈጠረ ነዉ በማለት
ቀጣይ የሚስተካከል ነዉ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በዚህ አመት የማወዳደሪያ ሰነዶች ከክፍያ ሰነድ
ጋር አብሮ እንዲቀርብ የተስተካከለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ይሁን እንጂ የበላይ አመራሩ ከተቀጠሩት የጉልበት ሰራተኞች አቅም በላይ ሲሆን የበላይ አመራሩ
መፍቀድ እንዳለበት አቅጣጫ የተቀመጠ ቢሆንም አንዳነዴ እቃዎቹ ከስራ ሰዓት ዉጪ
ሰለሚመጡ ይሄ ችግር ሊፈጠር የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ገልፀዉ ቀጣይ ከበላይ አመራሩ እና
ከስራ ክፍሉ ኃላፊ ማን መፍቀድ እንዳለበት ማስቀመጥ አለብን የሚል ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
ሆኖም ግን የበላይ አመራር ተቋሙ ሚዲያ እንደመሆኑ መጠን ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ለማኔጅመነት ፕሮፖዛል
በማቅረብ ተወስኖ የተፈፀመ ግዥ መሆኑን ገልፀዉ ለቀጣይ ተቋሙ መመሪያ ተዘጋጅቶ በቦርድ ስላፀደቀ ቀጣይ
በመመሪያዉ መሰረት የሚከናወን ይሆናል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
የግዥአዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀፅ 22 ንዑስ አነቀፅ 2 መሰረት የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ በዓመቱ የሚፈፀመዉን የግዥ
ዕቅድ አፅድቆ እሰከ ሐምሌ 30 ለመ/ቤቱ የስራ ክፍሎች እና ለኤጀንሲዉ መላክ ይኖርበታል ይላል፡፡ እንደዚሁም
የፌደራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ክፍል ሶስት አንቀፅ 7 ተራቁጥር 1 ማናኛዉም የመንግስት መ/ቤት በሰሩ
የተደራጁ አካላት የታቀዱ የሰራ ፕሮግራሞቻቸዉን ተግባራዊ ለማድረግ የሚስፈልጋቸዉን ግዥ በወቅቱ ለመፈፀም
የሚያስችል በመርሃግብር የተደገፈ የግዥ ዕቅድ ማዘጋጀት አለባቸዉ ይላል፡፡እንደዚሁም ዕቅዱ የመንግስት ግዥ መረሆችን
(ቁጠባ ፤ብቃት እና ዉጤታማነትን)መከተል ይገባል፡፡ በተጨማሪም የግዥ አፈፃፀም ሪፖርት በመርሃ ግብሩ መሰረት
በየጊዜዉ መቅረብ ይገባ ነበር፡፡
ነገር ግን የ 2013 በጀት ዓ.ም የግዥ ዕቅድ ፀድቆ ለስራ ክፍሎች የደረሰዉ የካቲት 04/2013 ዓ.ም መሆኑ፤ እቅዱ
በመርሃ ግብር ያለተደገፈ እና የመንግስትን የግዥ መርሆችን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም የቁጥቁጥ ግዥን
ለመከላከል የሚስችል ሆኖ አልተገኘም፡፡ እንደዚሁም የስራ ክፍሉ በየጊዜዉ የግዥ አፈፃፀም ሪፖረት የሌለዉ ሆኖ
ተግኝቷል፡፡
ይሁን እንጂ የበላይ አመራሩ የ 2013 ዕቅድን በተመለከተ በጊዜው አልታቀደም አሁንም ይሄ ችግር እየተደገመ ስለሆነ የ 2014
የግዥ ዕቅድ ማኔጅመንቱ ቶሎ አይቶ ማፅደቅ አለበት በማለት አስተያየት የሰጡ ሲሆን የግዥ አፈፃፀም ሪፖርት ግን
በየጊዜዉ ለሚመለከተዉ የስራ ኃላፊዎች መቅረብ አለበት ብለዋል፡፡
የበላይ አመራሩ ኮፒ ሰነዶቹ ታሽገዉ ነዉ የሚሰጣቸዉ ይሄን የፈጠረዉ የኢትዮጵያ የንግድ ስርዓቱ መሆኑን ገልፀዉ ለወደፊቱ
የሚሰተካከል ይሆናል በማለት ገልፀዋል፡፡
የግዥ አዋጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 51 ላይ ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ተጨማሪ ግዥ ለመፈፀም እና ተጨማሪ
ውል ለመግባት ቀደም ሲል በጨረታ ለተገዛው ግዥዎች ብቻ የተፈቀደ ሲሆን በዋጋ ማወዳደሪያ ለሚፈፀም ግዥዎች
ተጨማሪ ግዥ እና ዉል ማራዘም የሚፈቅድ ሆኖ አልተገኝም፡፡
ነገር ግን ለአሮጌ ህንፃ እድሳት የአገልግሎት ግዥ በመመሪያው መሠረት በፕርፎርማ መግዛት አግባብ ባይሆንም
ተፈፅሞ የተገኘ እንዲሁም በዋጋ ማቅረቢያ ግዥ ላይ ተጨማሪ ግዥ ተፈፅሞ ተጨማሪ ውል መግባት
ያልተፈቀደ ቢሆንም ተፈፅሞ የተገኝ ሆኖ
ምሳሌ፡- ገዛኽኝ በሱፍቃድና ጓደኛቻቸው ህንፃ ኮ/ስ/ተ/ህ/ሽ/ማ ፕሮፎርማ ተወዳደድሮ አሸናፊ ሆኖ ውል የፈረመው በቀን
1/4/2013 ዓ.ም ሲሆን ውሉ የሚቆይበት ጊዜ ከታህሳስ 1-2013 ዓ.ም እስከ ጥር 1/05/2013 ዓ.ም ሲሆን ተጨማሪ ውል በቀን
20/4/2013 የተፈረመ ሲሆን ውሉ የሚቆይበት ጊዜ ከታህሳስ 20-2013 ዓ.ም እስከ ጥር 5/05/2013 ዓ.ም የሆነ እና
ለመጀመሪያ ውል ብር 181,499.79 የተከፈለ ሲሆን ለሁለተኛ ውል ለመጀመሪያ ብር 23,920.00 የተከፈለ ሆኖ መገኘቱ፡፡
ሆኖም ግን የበላይ አመራሩ ለመስሪያ ቤቱ ጥቅም ሲባል በዚህ መንገድ ቢሰራ አዋጪ መሆኑ ታይቶ
የተሰራ ስራ ነዉ በማለት ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
ክፍል ሶስት
የመደምደምያ ሃሳብ
በተመረጠው አንድ የኦዲት የትኩረት አቅጣጫዎች አንፃር የድርጅቱ የግዥ ሥርዓት ወጪ ቆጣቢ ብቃት ያለው እና ውጤታማ
መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ፣ ኦዲት ተደርጎ በዝርዝር የኦዲት ግኝቶች ላይ የተመለከቱት ጉልህ የሆኑ የአሠራር እና የአፈፃፀም ችግሮች
ታይተዋል፡፡ ዋና ዋናዎቹም፣
ድርጅቱ እንደገና በተቋቋመዉ አዋጅ ቁጥር 1151/2011 መሰረት ለሚያከናዉነዉ የቋሚና አላቂ ዕቃዎች እንዲሁም የአግልገሎት
ግዥ የሚያገለግል መመሪያ ወቅታዊ አለመደረጉ፡፡
የቁጥቁጥ ግዥን በተመለከተ ከተፈቀደለት ገደብ በላይ ተፈፅሞ ስለ መገኘቱ፡፡
ከአንድ አቅራቢ የተፈፀመ ግዥ ከመመሪያው ውጪ ተፈፅሞ ስለመገኘቱ፡
ድርጅቱ የጥቅል (bulk) ግዥ ( በጨረታ)ስ ለማያከናውን የዋጋ የቅናሽ ተጠቃሚ ስላለመሆኑ
በተደጋጋሚ ከተወሰኑ ድርጅት ብቻ በፕሮፎርማ የተፈፀመ ግዥን ስለመፈፀም፡-
የጨረታ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዶች የታሸጉባቸዉ ፖስታዎች ላይ በቡድን ያለመፈረም ወይም ምንም ፍርማ ስላለመኖር፡፡
በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የጉልበት ሰራተኞች እያሉ በእነሱ መሰራት እየተቻለ በበላይ ኃላፊ ሳይፈቀድ በውጪ
የጉልበት ሰራተኞች የጉልበት ግዥ ስለመፈፀሙ፡፡
የሙያ ፍቃድ ሳይኖረዉ ያለዉድድር የተፈፀመ የአገልግሎት ግዥን ስለመፈፀሙ
የ 2013 በጀት ዓመት የግዥ ዕቅድ እና የግዥ አፈፃፀም ሪፖርት በመንግስት የግዥ መሪሆች ስላለመዘጋጀቱ፡፡
የአሮጌ ህንፃ እድሳት የአገልግሎት ግዥ በፕርፈፐርማ ስለ መገዛቱ እና የፕርፎርማ ተጨማሪ ግዥ
ተፈፅሞ ስለመገኝቱ፡፡
ክፍል አራት
የማሻሻያ ሃሳብ
ድርጅቱ እንደገና በተቋቋመዉ አዋጅ ቁጥር 1151/2011 መሰረት ለሚያከናዉነዉ የቋሚና አላቂ ዕቃዎች እንዲሁም
ያአግልገሎት ግዥ የሚያገለግል ወቅታዊ የሆነ የግዥ መመሪያ በአዋጅ ቁጥር 649/2001
መሠረት ያደረገ መመሪያ ሊኖረዉና ይገባል፡፡
በቁጥቁጥ ግዥ የሚከናወኑ ግዥዎች መመሪያውን መሠረት ባደረገ የአፈፃፀም ዜዴን በመጠቀም ለአመቱ የተፈቀደውን የግዥ
የገንዘብ ጣሪያ ሳይበልጥ ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ የሆነ የግዥ አፈፃፀም ሊያከናወን ይገባል፡፡-
ከአንድ አቅራቢ የሚፈፀም ግዥ አቅራቢው ብቸኛ አቅራቢ መሆኑ በመስረጃ ሲረጋገጥ መንግስት ባወጣው መመሪያ
መሠረት ግዥው ሊፈፀም ይገባል፡፡
ድርጅቱ የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ እንዲሆን እንዲሁም ቁጠባን የአፈፃፀም ብቃትን እና ዉጤታማነትን ለማረጋገጥ ግዥዎችን
አ ስቀድሞ ማቀድ እስከተቻለ ድረስ ግዥን በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ መፈፀም አለባቸው፡፡ሆኖም ሊታቀዱ ያልቻሉና
ወዲያውኑ ጥቅም ላይ የሚውሉ ወይም በጅምላ ሊገዙ ያልቻሉ የገበያ ዋጋ መሆኑን በጥናት በማረጋገጥ ግዥዎችን
በዋጋ ማቅረቢያ ግዥ መፈፀም የሚችል በመሆኑን አውቆ ግዥን ሊያከናውን ይገባዋል፡፡
በዋጋ ማቅረቢያ የሚፈፀም ግዥን ለመፈፀም በመመሪያው የፈቀደ መሆኑን በማረጋገጥ ከአንድ ወይም የተወሰኑ
አቅራቢዎችን ብቻ በተደጋጋሚ በመጋበዝ ግዥ ከመፈፀም የመንግስት መ/ቤቱ በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡት
ሁሉም ተሳታፊዎች በዙር የመወዳደር እድል ማግኘታቸዉን እና ለመ/ቤቱ ጠቃሚ የሆነ የተለየ ሁኔታ መኖሩ በማረጋገጥ ግዥው
ሊተገበር ይገባል፡፡
በተደጋጋሚ ከተወሰኑ ድርጅቶች ብቻ በፕሮፎርማ ግዥ መፈፀም በመመሪያዉ መሰረት አግባብ ባለ መሆኑ ግዥ
ሲፈፀም በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡት ሁሉም ተሳታፊዎች በዙር የመወዳደር እድል ማግኘታቸዉን እና ለመ/ቤቱ
ጠቃሚ የሆነ የተለየ ሁኔታ መኖሩ በማረጋገጥ መተገበር አለበት፡፡
የጨረታ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዶች አቀባበልና አከፋፈት ግልጽና ተጠያቂነትን ለመወጣት እንዲያስችሉ የጨረታ
እና የዋጋ ማወዳደሪያ ግዥ ሠነዶች ታሽገው የሚመጡባቸው ፖስታዎች ከሶስት ባላነሱ የግዥ ኮሚቴዎች
ተፈርሞባቸው ከተከፈቱ በኋላ በመረጃነት ከግዥ ሠነዶቹ ጋር ተያይዘው ሊቀመጡ ይገባል፡፡
የጉልበት አገልግሎት ግዥን በተመለከተ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ተቀጥረው የጉልበት ስራ የሚሰሩ
የጉልበት ሰራተኞች መሰራት ይገባል፡፡ሆኖም ከእነሱ አቅም በላይ ሆኖ ተጨማሪ የጉልበት ሥራ ማሰራት
ከተፈለገ የገንዘብ ብክነት ለመከላከል በበላይ ሃላፊ እየተፈቀደ ማሰራት ይገባዋል፡፡
የሙያ ፍቃድ ሳይኖረዉ ያለዉድድር የተፈፀመ የአገልግሎት ግዥን በተመለከተ ማንኛዉም ግዥ ሲፈፀም
ኢኮኖሚን ብቃትን እና ዉጤታማነትን ያገናዘበ ሆኖ መንግስት ያወጣዉን ህግ እና መመሪያ መሰረት መፈፀም
ይገባል፡፡
መ/ቤት በሰሩ የተደራጁ የሥራ ክፍሎችን የታቀዱ የሰራ ፕሮግራሞቻቸዉን ተግባራዊ ለማድረግ
የሚስፈልጋቸዉን ግዥ በወቅቱ ለመፈፀም የሚያስችል በመርሃግብር የተደገፈ የግዥ ዕቅድ ማዘጋጀት
አለባቸዉ ፡፡እንደዚሁም ዕቅዱ የመንግስት ግዥ መረሆችን (ቁጠባ ፤ብቃት እና ዉጤታማነትን)መከተል ይገባል፡፡
በተጨማሪም የግዥ አፈፃፀም ሪፖርት በመርሃ ግብሩ መሰረት በየጊዜዉ መቅረብ ይገባል፡፡
በዋጋ ማቅረቢያ ግዥ የሚፈፀም የአገልግሎት ግዥ በመመሪያው መሠረት በፕርፎርማ መግዛት የሚገባቸው ብቻ
መገዛት ያለበት ሲሆን በዚህ የግዥ ሂደት ተጨማሪ ግዥ መፈፀምና ዉል ማራዘም አይገባም፡፡
ክፍል አምስት
በአባሪ 1
1.2 የድርጅቱ የግዥ 5. የግዥ ውሎች ሲዘጋጁ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግና ለአገልግሎትም
ሂደት የመንግሰትን የግዢ
ደንብ እና መመሪያ ተከትሎ ሆነ ለዕቃ ግዢ ተፈላጊው መስፈርትና ሊጠናቀቅ የሚችልበት ወራት በግልጽ
የተፈጸመ መሆኑን ሊቀመጥ ይገባል፡፡
6. የአቅራቢዎች ዝርዝር እና የአቅርቦት ታሪክ በአግባቡ እየተመዘገበ
ማጣራት፡፡
ሊያዝ ይገባል፡፡
7. በግዥ ሂደቶች ላይ መጓተት እንዳይደርስ የግዥ ጥያቄዎች
መሰረት ሥልጣኑሰነድ
10. የጨረታ የተሰጣቸው
አቀባበልናሃላፊዎች
አከፋፈትሊሆኑ ይገባል፡፡
ግልጽና ተጠያቂነትን
1.3 በድርጅቱ የተፈፀሙ 20. ዕቃ አቅራቢዎች በግዥ ውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ
ከሰላምታ ጋር