You are on page 1of 5

ሞደል የግብርና ቴክኖሎጂዎች መንደር መቋቋሚያ ምቹ ሁኔታ ደሳሰ ትናት

መግቢያ
የግብርና ቴክኖሎጂ መንደር ሰፋ ያለ አከባቢ ላይ ሰፋ ያሉ ዘመናዊ እና የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎች
ለአርሶ አደሩን ማህበረሰብ በሳይንሳዊና በተቀናጃ መልኩ ለማሳየት እና ለማስተዋወቅ ተሊሞ የሚቋቋም ነው፡፡
በዚህ ቴክኖሎጂ መንደር ሁሉም ዓይነት የግብርና ቴክኖሎጂዎች የሚተዋወቁበት እና የሚታዩበት መንደር ነው
፡፡

የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ይህንን በማረዳት በስሩ በሉሁት ማዕከላት ዙሪያ የቴክኖሎጂ መንደር
ለማቋቋም በ AGP-2 በጀት በመታገዝ ግብርና ዕድገትን መሠረት ያደረገ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመንዳር
ለማስተዋወቅ መስፈሪቱን የሚያሟሉ የአርሶ አዳር መሰልጠኛ መዕከላትን ለመለየት ይህ ደሳሰ ጥናት
አስፈልጓል፡፡ በዚህም መሰራት ጥናቱ በጎፋ ዞን ከመሎኮዘ ወረዳ እና በባስኬቶ ልዩ ወረዳ ከተመረጡ 6 ቀበሌያት
መረጃዎች ተሰብስቧል፡፡

የተገኘዉ ዉጤቶች

የግብርና የማምራት አቅምና ተግዳሮቶች

ጥናቱ በተደረገበት ቦታዎች (በመሎኮዛ እና ባስኬቶ ልዩ ወረደ) የተለያዩ ሰብሎች በቆላ፤ በደጋ እና በወይና ደጋ
አየር ፀባይ ላይ ሁሉም የሰብል ዓይናቶች ይመራታሉ፡፡ ከዋና ዋና ሰብሎች ምርት የበቆሎ፤ ጤፍ እና ማሽላ
ሽፋኖች በቅደም ተከተል 85.9%፣ 25.1% እና 11.5% ናቸው ፡፡ በዳሰሳ ጥናት ወቅት በተደረገው የቡድን
ውይይት መሠረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እና እንደ የገንዘብ ሰብሎች በቆሎ ያመርታሉ ፡፡ የተቀሩት ሰብሎች
ሰሊጥ ፣ ኮሮርማ እና ቡና እንደ ገንዘብ ሰብሎች ያገለግላሉ ፡፡

በጥናቱ በተደራገበት አካባቢ የሚገኙት የእንስሳት እርባታ ቴክኖሎጂዎች መከካል፡-ከብቶች (አከባቢ) ፣ በግ


(አከባቢ) ፣ ፍየል (አከባቢ) ፣ ዶሮ እርባታ (አከባቢና ሳሶ) ፣ ንብ (በህላዊ እና በጥቅቱ የተሻሻሉ ቀፎዎች)
ናቸዉ፡፡ ዋና የከብት መኖ ምንጮች የተፈጥሮ ግጦሽ፤ የሰብል ምርታቸውን ከሰበሰቡ በኋላ የሰብል ተረፈ-
ምረት ለከብት መኖ ይጠቀመሉ፡፡ በተጨማርም አነስተኛ መጠን ባለ ማሳ የዴሾ እና የዝሆን ሣር የመኖ
ዝርያዎች ጥቂት አርሶ አደሮች የሚጠቀመቸዉ ናቸው ፡፡

ሌለኛዉ የእንስሳት ዘርፍ ያለተጠቀምነዉ የዓሳ እርባታ ቴክኖሎጂ ነዉ፡፡ ከእነዚህም ዉስጥ በትናንሽ ኩሬዎች
ውስጥ ዓሳና አትክልት ማምረት ዋናኛዉ ነዉ፡፡ በአንዳንድ ደጋ አካባቢዎች የአነስታኛ አመዣክዎችን በተላይም
በግ እርባታ በጣም ውጤታማ መሆኑን በደሳሰ ጥናቱ ተለይቷል፡፡
የሰብል ምርታማነት ዋና ዋና ተግደሮቶች

ጥናቱ በተደረገበት አከባቢ የሰብል ምርታማነትን ከሚቀንሱ ተግደሮቶች ወስጥ በሽታዎች እና ተምች(Fall
army worm) ዋና ዋና ናቸዉ፡፡ የዳሰሳ ጥናት ውጤት እንዳረጋገጠው 56% የሚሆኑት ምላሽ ሰጭዎች የሰብል
ምርትን እና ምርታማነትን የሚያደናቅፍ በተለይም የበቆሎ እና የሰሊጥ ሰብልን ከሚቀንሱት ዉስጥ ተምች
ዋናኛዉ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሰሊጥ በሽታ መከሰት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የመጣዉ የሰልጥ ዋጋ
ገበሬዎች ወደ ሌሎች ሰብሎች እንዲቀይሩ ከሚያደርጋቸዉ ችግር ዋናኛዉ ነዉ፡፡

የተሻሻሉ ሰብል ዘሮች እጥረት፣ ዝቅተኛ ጥራት ያለው ዘር፣ ከፍተኛ የግብዓት ዋጋ እና የግብአት (ማዳበሪያ፣
ዘሮች፣ ኬሚካሎች) ወቅት ማዘግየት፣ ደካማ የድህረ ምርት አያያዝ እና የማምረቻ ቴክኖሎጂዎች እጥረት እና
ከፍተኛ የአፈር አሲድማነት በጥናቱ የተላዩ ችግሮች ናቸው ፡፡

በመሎኮዛ እና በባስቶ ልዩ ወረዳ ቆላማ መሬት ክፍሎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ሰዎች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች
በሰፋረ መልክ የሰፈሩ በመሆናቸው የመንገድ እና ትራንስፖርት ችግር የሰብል ምርታቸውን ለመሸጥ እንደ ዋና
ችግሮች ተጠቅሰዋል፡፡ በተላይህም የፀጥታ ችግር በጣም አሳሳቢ እና በአከባቢው የመጀመሪያ ችግር ነው፡፡
የበቆሎ ድህረ ምርት አያያዝ (በመሳ)
ምስጥ በበቆሎ መሳ

የእንስሳት እርባታ ምርታማነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ በርካታ ችግሮች መከካል የተሻሻሉ የከብት ዝርያዎች
እጥረት፡ የተሻሻሉ የመኖ ቴክኖሎጂዎች እጥረት እና በሽታዎች እና ሌሎች ያልታወቁ ችግሮች ናቸው፡፡ የዳሰሳ
ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው 92 በመቶዎቹ መልስ ሰጭዎች የእንስሳትን በሽታ ቅሬታ እያሰሙ ነበር፡፡
ምንም እንኳን በአካባቢው የተሻሻለ የሳሶ ዶሮ ዝርያ ቢኖርም በሽታዎችን እና ሌሎች የውጭ ተጋላጭነቶችን
አይቋቋምም፡፡ ስለዚህ አሁን ላለው የግብርና ሥነ ምህዳሩ በሚገባ የሚያከናውን አዲስ የዶሮ ዝርያ
ማስተዋወቅ ይፈልጋል፡፡

በጥናቱ በተደረገበት አከባቢዎች ያሉት ሌጦ እና ቆዳ በጭራሽ ገቢያ የለም፡፡ ስለዚህ የድህረ ምርት አያያዝ
በማስተዋወቅ ረገድ እና የገቢያ ትስስሮችን ልዩ ትኩረት መስጠት ግዴታ ነው፡፡

የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብቶች አያያዝ ችግሮች መከካል ደን መጨፍጨፍ፣ በአፈር መሸርሸር (በነፋስ፣ በውሃ
(የመሬት አቀማመጥ) ምክንያት የአፈር ለምነት ከጊዜ ወደ ጊዜ መቀነስ፤ ማዳበሪያ አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ
እጥረት መኖሩ የተሻሻሉ ችግኞችን ማልማት የሚያስችል የተሻሻሉ ችግኞች አለመኖር ዋና ዋና ችግሮች
ናቸዉ፡፡

የግብርና ቴክኖሎጅዎችን ፍላጎት

የሰብል ቴክኖሎጂ ፍላጎት መከካል የተሻሉ የብዕር ሰብል ሆነዉ ምረታማነተቸዉ ከፍተኛ እና በሽታን
የሚቋቋሙ የበቆሎ፣ ስንዴ እና ገብስ ዘሮች ናቸው፡፡ ከቅመማ ቅመም መከካል ዝንጅብል (በሽታ የሚቋቋም)
የጥራጥሬ ሰብሎች ዉስጥ ሰሊጥ (በሽታ የሚቋቋም)፣ ባቄላ (ቀላ ያለ ቀይ ባቄላ); ፍራፍሬዎች እና
አትክልቶች አፕል (ፍሬው ልዩ የሆነ ቡናማ)፣ ቲማቲም (የዚዌይ) እና ሥረ-ሥር (ቦሎሶ-1)፡፡

በእንስሳት እርባታ ቴክኖሎጂ ዉስጥ የተሻሻሉ የከብት ዝርያዎችን (ጀርሲ እና ሆስተስቲን ፍሬሪስ)፤ በሰዉ
ሰራሽ ዘር መደቀልን ማስተዋወቅ እና ቦረና ዝርያ (በቆላ አከበቢ በሽታ እና ድርቅን የሚቋቋሙ)፤ የዶሮ ዝሪያ
(dual purpose) እና ለእንስሳቱ በሽታ እና ለጥገኛ ተወሳያን ሕክምና ቴክኖሎጂዎች፤ የተሻሻሉ ንብ ቀፎዎችን
(ጀርሜን እና ኬንያ ቶፒ በር) ማስተዋወቅ እና የአገር በቀል የሆኑ በጎችን በማህበረሰቡ ላይ የተመሠረተ የዘር
መሻሻል ስርዓት በተለይም ደጋ እና ወይናደጋ አካባቢዎች መዘርገት ዋና ዋና በአርሶአደሮቹ የተነሱ ፍላጎቶች
ናቸወ፡፡

የተፈጥሮ ሀብትን ቴክኖሎጂ ፍላጎት በተመለከተ የኖራ ቴክኖሎጂን ማስተዋወቅ፤የተሻሻሉ የተለያዩ የአግሮ-
ፎሬስትሪ አሰራሮችን ማስተዋወቅ፣ በማህበረሰብ ላይ የተመሰረቱ የደን አስተዳደር አሰራሮች ላይ ማተኮር፤
በተመጣጣኝ ዋጋ የውሃ ፓምፕ ማስተዋወቅ፤ ለተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ልምዶች ጠንካራ ትኩረት መስጠት፣
ልዩ የሆኑ ዛፎችን ማስተዋወቅ፣ የአፈርን ለምነት ለማሳደግ ከተለያዩ የአካባቢዎች ቁሳቁሶች የተሻሻለ
የማዳበሪያ ዝግጅት ማሳያት ዋና ዋና ናቸዉ።

የአርሶ አደሮችና ባለሙያዎች አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ማሳያ አቀራረቦች ላይ ያለው አመለካት

በአሁኑ ወቅት መንግሥት ለአርሶ አደሩ ማህበረሰብ አዳዲስ የተለቀቁና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን
ለማስተላለፍና ለማሳየት የተለያዩ አሰራሮችን አውጥቷል፡፡ ከእነዝህም መካከል ቅድመ-ማስፋት(PED)፣
የገበሬዎች ማሠልጠኛ ማዕከል፣ የሞዴል ገበሬ ፣ አርሶ አደሮች ምርምር ቡድን እና አሳታፊ የዘር መረጣ(pvs)
ናቸዉ። ሆኖም በእነዚህ ጥናቶች ላይ አርሶ አደሮች የሚያደርጉት ተሳትፎ በጥናቱ ውስጥ ለተለያዩ አርሶ
አደሮች የሚለያይ ነው ፡፡ ጥናት እንደሚያሳየው እያንዳንዱ የመስታዋወቅ መንገድ የራሱ የሆነ አዎንታዊ እና
ደካማ ጎኖች አሉት ፡፡ ለምሳሌ ፣ አርሶ አደሮች ማሠልጠኛ ማዕከል (FTC) ወደ 88 በመቶ የሚሆኑት አርሶ
አደሮች ይሳተፋሉ፡፡ እንደ መልስ ሰጪዎች አመለካከት FTC ለሁሉም አርሶ አደሮች በማንኛውም መንገድ
ለመሳተፍ ክፍት እና የመሳ ስፋት ስላለው ብዙ (ከአንድ) በላይ ቴክኖሎጂ በአንድ ወቅት ሊታይ ስለሚቸል
FTC ከሌሎች መንገዶች የተሻለ ነው ፡፡ ቢሆኑም አብዛኛዎቹ FTCs ተልእኮዎቻቸውን እየሰሩ አይደሉም፡፡
ለምሳሌ ምንም ሙከራ ወይም ማሳያ ስራ የለም፡፡ የቀበሌ በለሙያዎች የተለያዩ ሰብሎችን ለስረቶ ማሳያ
ሳሆን ለገቢ መሰጋኛ ነዉ፡፡ የባለሙያዎች እጥረት፣ በተለይም የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች፣ መደበኛ ክትትል
አለመኖር እንደ ችግር ይነሰል፡፡ ምንም እንኳን የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩትም አብዛኛዎቹ (64%) ምላሽ
ሰጪዎች FTC እንደ ቴክኖሎጂ ማሳያ ይመርጣሉ፡፡

የኩታ ገጣም (ክላስተር) የሰብል አዘራር መንገድ ደግሞ ብዙ ትናንሽ እርሻዎችን በማዋሃድ እና አነስተኛ
ገበሬዎች ለምርታቸው ጥሩ ትርፍ እንዲያገኙ የሚያስችል ነዉ፡፡ ጥናቱ እንደሚያሳየው የኩታ ገጣም ከ FTC
በጣም የተሻለ እንደሆነ ለመወቅ ተችሎዎል፡፡ ምክንያቱም አርሶ አደሮቹ አንዳቸው ከሌላኛው ተሞክሮ
ለመማር ወይም ለመጋራት ያስችላቸዋል፡፡ ሆኖም አርሶ አደሮችን በቅብብሎሽ አካሄድ ውስጥ እንዲሳተፉ
ለመምረጥ ግልፅ መመዘኛ የለም፡፡ እንዲሁም ለሁሉም ግብዓቶች (ዘር፣ ማዳበሪያ፣ ኬሚካሎች) ለአርሶ
አደሮች ነፃ መገኘቱ በአርሶ አደሮች መካከል ጥገኝነት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ግብዓቶቹ
ለተወሰነ አርሶ አደሩ ክፍል ሲሰጡ ለሌሎችም የማይሰጡ ሲሆኑ በአርሶ አደሮች እና በመንግስት መከከል
ቅሬታ ይፋጥራል፡፡ ምንም እንኳን ሌሎች መንገዶች (የአርሶ አደሮች ምርምር ቡድን፣ አሳታፊ ዝሪያ ማረጠ
እና ቅድመ-መስፋት የበለጠ ሳይንሳዊ ቢሆኑም አብዛኛዉ አርሶ አደር FTC እና ክላስተር ይመረጣሉ፡፡
መጠቃለያ

ዋና ዋና የግብርና ምርትና ምርታመነት መናቆ የሆነሉ ተብሎ የተለዩ በሽታ፣ ተምች እና የተሸሸሉ የግብርና
ቴክኖሎጂወች እጥራት ነቸዉ፡፡ አርሶ አደሮች በተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ላይ ፍላጎት አላቸው፣
በዋነኝነት በሽታን የመቋቋም የሰብል ዝርያዎችን፣ የተሻሻሉ የከብት ዝርያዎችን መስተዋውቅ (ጀርሲ እና
ሆልስቴይን ፍሪስያን)፤ የቦረና ዝርያ ፣ የዶሮ ዝርያ (cockock)፤ የተሻሻሉ መኖዎች፣ ሁለገብ የዛፍ ችግኞችን
ማስተዋወቅ፣ ዘመናዊ የመስኖን መገንባት እና የተሻሻሉ የጥምር ደን ልማትን ማሳየት ግንበር ቀድመም
ፍለጎቶች ናቸዉ፡፡

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ማንኛውንም የግብርና ቴክኖሎጅዎች (የሰብሎች፣ የእንሰሳትና ተፈጥሮ ሀብት
አያያዝ) ለማሳየት የሚያስችል የቴክኖሎጂ መንደር መለየትና ማቋቋም ነዉ፡፡ ይህም የሚለየዉ ለቴክኖሎጂ
መንደሩ የተመረተዉ መሬት መጠን (FTC፣ የግል፣ ተቋም)፣ተደራሽነት (መንገድ)፣ የአግሮ-ኢኮሎጂ
ማእከልነት እና የቴክኖሎጂ አቃበበል ልምድን መሠረት በመድረግ ነዉ፡፡
በዚህም መሰራት፡- ከመሎኮዛ፡ ጣፈ (1 ኛ) እና ሳላይሽ መንደር 03 (2 ኛ) ፤ ከባስኬቶ፡ አንግለ 03 (1 ኛ) እና
ሞቲኬሳ አርዘካ (2 ኛ) የተመረጡ ቀበሌያት ናቸዉ፡፡ ስለሆነም አቅም ከፈቀደ ሁለቱንም መንደሮች መጠቀሙ
ይመከራል፡፡ ሆኖም ፣ የሀብት ዉስንናት ካለ ጥቅም ላይ የሚውለው በመጀመሪያ ደረጃ የተቀመጠው አማራጭ
የተሻለ ነው፡፡

You might also like