You are on page 1of 1

ስርም በኢ-አቻነት የሂዩመር መፍጠሪያ ዘዴዎች የተዋቀሩ ሂዩመሮችን ፣ በአራት ክፍሎች በመከፋፈል ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ

ሂዩመሮችን ከየወጉቹ ውስጥ እየወጡ ይቀርባሉ ፡፡


4.2.1.1 ማግዘፍ
በዚህ የሂዩመር መፈጠሪያ ዘዴ ፣ ተነፃፃሪዎቹ ነገሮች በእውኑ ያለው እና ተጋኖ የቀረበው ነገር ናቸው ፡፡ በተለይ የግነቱ ደረጃ
ከፍ ያለ እና ጥበብ የታከለበት ከሆነ ፣ አንባሲ ከነባሩ (ከእውነታው) ጋር እያነፃፀረ ፈገግታውን ይቀጥላል ። ለዚህ ማሳያ
ከሚሆኑት ሂዩመሮች አንዱ በሶስና አሽናፊ ከራስ ሽሽት (1996) ወግ
ላይ ይገኛል ፡፡ በዚህ ወግ ውስጥ ሶስና የቀብር ቦታ ላይ የሚነበቡ የህይወት ታሪክ አይነቶችን ትደረድራለች ፡፡ በወጓ መሀል
አንዳንዱ ሟች “ አቶ እገሌ ተወዳዳሪ
የጠፋለት የጦር መሪ ፣ እግዜር ባይቀድመው ጠፈር ለመሄድ የቅርብ ጊዜ እቅድ የነበረው ተመራማሪ ...” (ገጽ 39)
እንደሚባልለት ትጠቅሳለች ፡፡ በዚህ ሰግነት በቀረበ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ጭራሽ የጠፈር ምርምር በሌለባት ሀገር ጠፈር ለመሄድ
እቅድ የነበረው ሰው ይገኛል ፡፡ በእርግጥ ሰመቃብር ላይ የሚነገሩት ታሪኮች ፣ ጭራሽ ክፉ የማይሰማባቸው ናቸውና ፣ የሶስና
ግነት ከእውነታው እምብዛም የራቀ አይደለም ፡፡ በመሆኑም ሂዩመሩም ያን ያህል የጠነከረ አይደለም ማለት ይቻላል ፡፡
ስብሃትም “ የአበላል ሥርዓት” በሚለው ወጉ ላይ “ አሁን ይሄ የነአያ እገሌ ወንድም ሰው ነው? ጅብ እንኳ እንደዚያ
አይበላም ፡፡ አንዱን የጠገበ ጠብደል እንጀራ በሶስት ጉርሻ ይጨርሰዋል” (ገጽ 7) ይላል ፡፡ እዚህም ላይ ግነቱ ሂዩመራዊ ነው
፡፡ አንድም የበላተኛው አጐራረስ ከጅብ በላይ አድጓል ። በእርግጥ ‹‹ ሆዳም ›› ለማለት ብዙ ሰው የሚጠቀመው ‹‹ ጅብ
›› የሚለውን ቃል በመሆኑ ግነቱ እምብዛም አዲስነት የሌለው ይመስላል ፡፡ ግን ገለፃው በዚህ ብቻ አላበቃም ፡፡ ሲቀጥልም
እንጀራው የጠገበ ጠብደል ሆኗል ፤ ይህንኑ እንጀራም በላተኛው በሶስት ጉርሻ ይጨርሰዋል ፡፡ ግነቱ ሂዩመራዊ ነው የተባለውም
እነዚህን ሁሉ በመደማመር ነው ፡፡ ኤፍሬም እንዳለ (1994) “ ብድር ጩቤ አይደለም” የሚለው ወጉ ውስጥም ፣ ሰርዙልኝ
ማለት ስለሚቻል ለመበደር አገር መሆን እንደሚሻል ይገልፃል ፡፡ ይሄ እውነት እንጂ ፣ ግነትም ፣ ሂዩመርም አይደለም ሊባል
ይችላል ፡፡ ሂዩመራዊ ግነቱ የሚመጣው “ እስቲ ሁለት መቶ ብር ያበደረዎትን ሰው እዳ ሰርዝልኝ በሉት” ካለ በኋላ
ባስቀመጠው አባባል ላይ ነው ፤ አባባሉ “ አይደለም ወለንጪቲና ሞጆ ያሉ ዘመዶቹን በስደት ማዳጋስካር የሄዱ ጓደኞቹን
ሊሰበስብ ምንም አይቀረው 11 (ገጽ 7) የሚል ነው ፡፡
61

You might also like