You are on page 1of 2

ትንቢተ ኢሳይያስ

ጸሃፊውና ተደራሲያኑ

መጽሃፉ በመግቢያው ላይ እንደሚያሳየን የትንቢቱ ጸሃፊ ራሱ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ነው (ኢሳ 1፡1)። ጸሃፊው ስለራሱ እንደሚናገረው
በእግዚአብሄር ነቢይ ይሆን ዘንድ በተጠራ ጊዜ ራሱን እንደ ሃጢአተኛ በመቁጠር የፈራ ቢሆንም በራእይ ከተመለከተው እንግዳ ክስተት
በኋላ ራሱን ለተልዕኮ አዘጋጀ (ኢሳ 6፡5-10)። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ለጠራው አምላክ ታማኝ በመሆን እንዳገለገለ መጽሃፉን ስናነብ
እንረዳለን። ነቢዩ ኢሳይያስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 8 ኛው ክ/ዘ በይሁዳ ያገለገለ ሲሆን እርሱ ባገለገለበት ዘመን የነበሩት ነገስታት
ዖዝያን (783-742 ዓ.ዓ)፣ ኢዮአታም (742-735 ዓ.ዓ)፣ አካዝ (735-715 ዓ.ዓ)፣ እና ሕዝቅያስ (715-687 ዓ.ዓ) ነበሩ።[1]
የመጽሃፉ ተደራሲያን ደግሞ በዘመኑ የነበሩት ነገስታት፣ የይሁዳ ህዝብና የአህዛብ ነገስታትም ጭምር ነበሩ።

የተጻፈበት ዘመንና ሁኔታ

የኢሳይያስ ትንቢት የተጻፈው ከ 740 እስከ 680 ዓ.ዓ ድረስ ባሉት ጊዜያት እንደሆነ ይታመናል። በዚህ ዘመን ይሁዳ ከውጪ በዙሪያዋ
በነበሩ አህዛብ ነገስታት ምክንያት በከባድ ፍርሃት ውስጥ ስትገባ ከውስጥ ደግሞ ነገስታቱ፣ አገልጋዮቹና ህዝቡ በሚሰሩት ሃጢአት
ምክንያት የእግዚአብሄር ቁጣ ክፉኛ የቀሰቀሱበት ወቅት ነበር።

ነቢዩ ይህንን ትንቢት በጻፈበት ዘመን የይሁዳ በገስታት እየጨመረ በመጣው የአሦራውያን ወረራ ፍርሃት ውስጥ ነበሩ። በ 2 ነገ 18 እና
19 እንደምናነበው ሕዝቅያስ በአሦር ሰራዊት ምክንያት በተረበሸና ወደ እግዚአብሔር በጮኸ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያጽናና ምላሽ
የሰጠው በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ነበር፤ ይህንኑ ታሪክ ኢሳ 37 ላይ ተዘግቦ እናገኘዋለን።

በተጨማሪም

የመጽሃፉ አላማ

ለዛሬዎቹ አንባቢዎች ምን ያስተምረናል?


[1] Marvin A. Sweeney; The Prophetic literature; Abingdon press: 2005; 46

You might also like